text
stringlengths 0
2.31k
|
---|
ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ስራቸውን እየሰሩ ነው ማለት ነው! |
ሰሞኑን ከኢህአዴግ ጋር የስጋ ዘመድና አላቸው እየተባሉ የሚጠረጠሩ ወዳጆቻችን ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ከአንዳች ሀይል ኢህአዴግን ለመገዳደሪያ የሚሆን ገንዘብ እንዳገኙ የሚያሰማ ድምፅ አጋርተውናል፡፡ ችግሩ ግን ይህ ገንዘብ ከየት እንደተገኘ እርስ በርሳቸው ስምምነት ላይ አልደረሱም፡፡ አንዳቸው ከኤርትራ ነው ሲሉ ሌላኛው ደግሞ ከግብፅ ነው ይላሉ፡፡ በደንብ ጆሮ ጣል ብናደርግ ከኢህአዴግ መንግስት ነው የሚልም አይጠፋም፡፡ |
ወዳጆቻችን ያጋሩን ድምፅ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ከሆነ ቦታ የተገኘውን ብር፤ ለእንትን ይሄን ያህል፣ ለእንትና ይሄን ያህል እያሉ ሲናገሩ ያስደምጣል፡፡ በዚህ ላይ ያስደነቀኝን ልናገር እና እመለሳለሁ ቆይ አዲስ መስመር ላይ እንገናኝ፡፡ |
ዶክተሩ የሆነውን ብር እዛው ለመከላከያ እና ደህንነቱ የተበጀተ ነው፤ ሲሉ ሰማናቸው፡፡ ይሄኔ በተለይ እንደኔ በኢህአዴግዬ ፍቅር የተለከፈ ሰው ክው!!! ማለቱ አይቀርም፡፡ ደህነነት እና መከላከያችን ከመንግስት ከሚመደብለት በጀት ውጪ በግንቦት 7 ደግሞ ሌላ በጀት አለው ማለት ነው፡፡ ይቺን ነው መፍራት፤ ዶክተሩ ስራቸውን ቀጥ ለጥ አድርገው እየሰሩ ነው ማለት ነው፡፡ |
ታድያ ለዚህ ነዋ የኢህአዴግዬ ገመናዋ ሁሉ ቀድሞ አደባባይ የሚሰጣው!!! እኔ ልሰጣ … ልበል ወይስ አልበል! (በቅንፍም ይቅርብኝ እነ እንትና ሳይሉ እኔ ቀድሜ ልሰጣ… ብል እነሱን ማሳጣት ሆንብኛል!) ከቅንፍ ስንወጣም ለኢሳትም የሆነ ብር ይሰጣል ሲሉ ዶክተሩ መናገራቸውን አዳመጥኩ፡፡ በእውነት ዶክተርዬ የተባረኩ ኖት፡፡ … እንዴ… በአሁኑ ጊዜ ማን እንደዚህ ያደርጋል… የምር እኮ ኢሳትን ሁሉም መርዳት አለበት፡፡ ግንቦት 7 ከረዳው በጣም ጥሩ ጅምር ነው፡፡ እንኳን ሌላ ቀርቶ ግንቦት 20 ም ራሷ ኢሳትን መርዳት አለባት፡፡ እንዴ ኢቲቪ የማይሰራውን በሙሉ የሚሰራው ኢሳት አይደለ እንዴ…! ታድያ እንዲህ እንዲተጋገዙ ሁሉም የአቅሙን ቢያዋጣ ምን ችግር አለበት! |
ወደ ዋናው መስመር ስመለስ ወዳጆቻችን “ፈልፍለው” ይፋ ባደረጉት መረጃ ዶክተሩ ለካስ አልተኙም ብለናል፡፡ እና ይበርቱ ልንላቸው ይገባል፡፡ |
ገንዘቡ ከግብጽ ነው፤ |
ግብፅ የምር ለኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ገንዘብ የምትረዳ ከሆነ ተጃጅላለች ማለት ነው፡፡ ሌላ ቀርቶ ኢህአዴግ እንኳ ያንን ሁላ አድርጋለት አልተመለሰላትም፡፡ በእውኑ ሌሎቹማ ከኢህአዴግ የበለጠ ለሀገራቸው ተቆርቋሪ አይደሉምን…! |
ገንዘቡ ከኤርትራ ነው፤ |
ወይ…. ኤርትራ….!!! አሁን ማን ይሙት ኤርትራዬ ከራሷ አልፋ ለሌላ ሰው ይሄንን ያክል ብር መስጠት ትችላለች…! ይሄንን ሃሳብ የሰነዘሩ ሰዎች በእርግጠኝነት ኤርትራዊያን ናቸው፡፡ አላማውም የኤርትራም መልካም ገፅታ ለመገንባት ሳይሆን አይቀርም ብለን እኛ ጠርጣሮቹ እንጠረጥራለን! |
የትም ፍጪው ኢህአዴግን አስወጪው፤ |
ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ግንቦት 7 የሚባል ተቃዋሚ ፓርቲ መስርተው ሁለገብ በሆነ ዘዴ ኢህአዴግን ወግድ እለዋለሁ ብለውናል፡፡ ግንቦት 7 ይህ ከሆነለት የዘመናት ብሶት የወለዳቸው ሁሉ ተሰባሰበው ዋንጫ እንደበላ ሰው “የእርግብ አሞራ” እያሉ የሚጨፍሩለት ደስታ የሚሆን ይመስለኛል፡፡ ታድያ ለዚህ አላማ ገንዘብ ከየትስ ቢያመጡ እኛ ምን አገባን…!? |
የፕሮፌሰሩ ፅሁፍ አልገባኝም…. ማስፈራራቴ አይደለም ይላሉ…… ጦር ህይልን ያነፃፅራሉ…….. ኢትዮጵያ ብቻዋን ናት ይላሉ ተሳሳቱ ብቻዋን አይደለችም አግዚአብሄር አለላት፡፡ ድሮስ ግን ማን ነበራት….. እና አያሥፈራሩን፡፡ እጅና እግራችችንን አጣምረን ድህነትን የሙጥኝ እንበል? አልፈራንም ለወደፊቱም አንፈራም ትእቢትም አይደለም. |
ቀናኹብዎ! [ታዲያ “ቅንዑ ለእንተ ተዐቢ ጸጋ” ባለው መንገድ ነው።] በእውነቱ በርስዎ ያልተቀና በማን ይቀናል? ያስተያየትዎ ስፋት፤ የምርምርዎ ጥልቀት! |
Pingback: ዓባይና የአሜሪካ ጨዋታ _ yabedew / ያ - በደው |
Pingback: ዓባይና የአሜሪካ ጨዋታ _ Time for change |
እንደተለመደው በጣም ጥሩ ግንዛቤ የሚሰጥ ትንታኔ ነው። ታዲያ ከዚህ ዓለማቀፍ ሁኔታ አትራፊ ሆኖ ለመውጣት ምን መደረግ አለበት ይላሉ? |
ፕሮፌሰር፣ አምላክ ረጅም ዕድሜ ከጤንነት ጋር ለእርሰዎ ይስጥልን፡፡ |
ዶር. ዓቢይና አቶ ለማ |
የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ እሁድ ይመረቃል – New Business Ethiopia |
የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ እሁድ ይመረቃል |
የኦሞ ወንዝን በሚያዋስኑ በካፋና ቤንች ማጂ ዞኖች የሚገኘው የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ እሁድ በይፋ እንደሚመረቅ ተገለጸ፡፡ |
በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ይገኛሉ ተብሏል፡፡ |
የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ስር ከሚገነቡት አራት ስኳር ፋብሪካዎች አንዱ ነው፡፡ |
ኮምፕላንት በተባለ የቻይና ኩባንያ የተገነባው ይህ ፋብሪካ በቀን ከ8 ሺህ አስከ 10 ሺህ ኩንታል ስኳር የማምረት አቅም እንዳለው የተገለጸ ሲሆን ጥሬ ስኳር፣ ነጭ ስኳር እና የተጣራ ስኳር ያመርታል ተብሏል፡፡ |
የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ መመረቅ ስኳር የሚያመርቱት ፋብሪካዎችን ቁጥር ወደ ስምንት ያደርሰዋል፡፡ |
የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 የግንባታ ሥራው በይፋ የተጀመረው በመጋቢት ወር 2008 ዓመተ ምህረት ከቻይና ልማት ባንክ በተገኘ ከ8 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር ነው፡፡ |
ለአራቱም ስኳር ፋብሪካዎች የሚውል በ100 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ሸንኮራ አገዳ ለማልማት በኦሞ ወንዝ ላይ የመስኖ መሰረተ ልማት ግንባታ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ |
በጥቅሉ 30 ሺህ ሄክታር መሬት ውሃ ገብ ማድረግ የተቻለ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 16 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ሸንኮራ አገዳ መተከሉን ከስኳር ኮርፖሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ |
እስከ አሁን በቋሚ፣ በኮንትራትና ጊዜያዊነት ከ110 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የአካባቢው ወጣቶችና ዜጎች የሥራ ዕድል የተፈጠረ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ከ300 በላይ የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማትን አደራጅቶ ወደ ሥራ መግባቱን አስታውቀዋል፡፡ |
የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ ከመጋቢት 2009 ጀምሮ ወደ ሥራ መግባቱ የሚታወስ ነው፡፡ |
ኦነግ ትጥቅ መፍታት አለበት- መንግስት |
በቡራዩ ግጭት ተጠርጥረው በተያዙ ግለሰቦች የባንክ ሂሳብ ውስጥ 8 ሚሊየን ብር ተገኝቷል |
ግፍ ሠርቶ መደበቅ፣ ዘርፎ መንደላቀቅ አይቻልም |
በ7 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር የሚገመቱ 17 የአጋርነት ፕሮጀክቶች ይፋ ሆኑ |
የኢትዮጵያ ፕሬስ ከድጡ ወደ ማጡ እንዳይሆን |
December 14, 2018 Comments Off on የኢትዮጵያ ፕሬስ ከድጡ ወደ ማጡ እንዳይሆን |
በጠቅላይ አቃቤ ህግ እስካሁን በቁጥጥር ስር የዋሉ ግለሰቦች ዝርዝር |
November 14, 2018 Comments Off on በጠቅላይ አቃቤ ህግ እስካሁን በቁጥጥር ስር የዋሉ ግለሰቦች ዝርዝር |
የአዲስ አበባ-ሞያሌ-ናይሮቢ-ሞምባሳ መንገድ ግንባታ ተጎበኘ |
November 13, 2018 November 13, 2018 Comments Off on የአዲስ አበባ-ሞያሌ-ናይሮቢ-ሞምባሳ መንገድ ግንባታ ተጎበኘ |
ከጥቂት ጊዜያት በፌት አንድ የመጽሐፍ ዳሰሳ ዝግጅት ላይ ተገኝቼ ነበር፡፡ መጽሐፉ “ፌኒክሷ ዛሬም፣ ሞታም ታንቀላፋለች” ሲሆን ጸሐፊዋ የቀድሞው የሕወሓት አባልና አመራር የአቶ ገብሩ አስራት ባለቤት ወ/ሮ ውብማር ናቸው፡፡ በዳሰሳው ወቅት በትግል ጊዜ ለምን መጽሐፉ ላይ የተጠቀሱትን ችግሮች እንዳልፈቱ ሲጠየቁ ወይዘሮዋ እንዲህ ብለው መልሰው ነበር፡፡ |
“ደርግን የሚያህል ጠላት ከፊት ለፊታችን እያለ እንዴት እርስ በርስ በመጣላት ጊዜ እናባክናለን? ነጻ ስንወጣ የሕወሓት ፖሊሲና ፕሮግራም ሁሉንም ነገር ይፈታዋል::” ብለን ተውነው ይላሉ፡፡ |
በኋላ ላይ ደግሞ ሕወሓትን ስለመለወጥ ሲጠየቁ ‹‹ሕወሓት ከዚህ በኋላ የሚለወጥ ድርጅት አይደለም አርጅቷል፡፡ 40 ዓመት በኋላ የድርጅት ባሕሪይ አይቀየርም›› ሲሉ ይከራከራሉ፡፡ |
የትኛው ጠላት? የትኛው ትልቁ ዓላማ? |
አሁንም ሕወሓት ሥልጣን ከያዘ ከ20 ዓመት በኋላም ቢሆን የዋናው ጠላት ወይም “ትልቁ ዓላማ” ክርክር እንደ መተባበርያ እና እነደመቻቻያ ሰበብ እንዲሁም እንደአለመተቺያ ምክንያት ይነሳል፡፡ ተቃዋሚዎች እንዲተባበሩ የሚጠየቁት “ዋናውን ጠላት” ለማንበርከክ ነው፡፡ የትልቁ ጠላት መኖር አገራዊ የፖለቲካ ክርክራችንንም ሆነ የፓርቲ ፖለቲካችንን የሚበጠብጥ ትልቅ ችግራችን እየመሰለኝ መጥቷል፡፡ መንግሥት/ገዥው ፓርቲ የተሰኘውን ይህንን ጠላት ለማባረር በሚደረገው ጥረት ውስጥ ለትልቁ ዓላማ ተብሎ የምናጣቸውን ነገሮች ሳናስተውል የምናልፍበት ጊዜ ብዙ ነው፡፡ ምሳሌ እናንሳ ብንል ለትልቁ ዓላማ ሲባል የማይተች ጋዜጠኛ አለን፣ ለትልቁ ዓላማ ሲባል የተቃዋሚ ፓርቲ አይነካም፣ ለትልቁ ዓላማ ሲባል ውስጠ ፓርቲ ልዩነቶች ይታፈናሉ (ሲፈነዱ የሚያመጡት አደጋ መባሱ ላይቀር)፡፡ ለትልቁ ዓላማ ሲባል ሐሳብን በነጻነት መግለጽ መብትን የሚያፍኑ ሌሎች ትንንሽ ጨቋኞችን ማበረታታት የተለመደ ሆኗል፡፡ ለትልቁ ዓላማ ሰበብ ሲባል ጋዜጠኞች ላይ የጥላቻ ፓሮፖጋንዳ ይነዛል፡፡ ትልቁ ዓላማ ሁላችንም ስህተቶቻችንን የምንሸፍንበት አገራዊ የተቃውሞ ሰበብ ሆኖልናል፡፡ |
አብዛኛው ተቃዋሚ ፓርቲዎች/ግለሰቦች ዓላማቸው ቢጠየቁ ሃገሪትዋ አሁን ካለችበት ሁኔታ በሁሉም መልኩ ተሻሽላ እንድትገኝ ማድረግ እንደሆነ ቢያንስ በግርድፉ ይናገራሉ ብዬ እገምታለሁ፡፡ አሁን ላለን የፖለቲካዊ ሁኔታ ትኩረት እንሰጣለን የምንል ቡድኖችም ሆነ ግለሰቦች በቋንቋ ብንለያይም፣ ብንጠየቅ የምንናገረው ሐሳብም ከዚህ የተለየ አይሆንም የሚል ግምት አለኝ፡፡ (የገዥው ፓርቲ ደጋፊዎች አሁን ባለችው ኢትዮጵያ እንደሚስማሙና እንደማይመለከታቸው ባስብም ኢሕአዴግም ራሱ በተቃዋሚዎች ቦታ ቢሆን የተሻለ አቅም እንደማይኖረው በመገመት ይህንን ውይይት ወደራሳቸው ቢተረጉሙት አልጠላም፡፡) ነገር ግን አሁን ያለውን ነባራዊ የፓለቲካ ሁኔታ ከመቀየር ረገድ እየሠራን ነው የሚሉት አካላት ሁሉ የሚስማሙበት የሚመስለው ሌላው ነገር ሥልጣን ላይ ያለውን መንግሥት መቀየር የሚለውን አካሄድ ነው፡፡ ይህ እንግዲህ ሠላማዊዎቹንም ነፍጥ ያነሱ ቡድኖችንም የሚያስማማ ሁለተኛው የጋራ ሐሳብ መሆኑ ነው፡፡ እንግዲህ ከላይ በተጠቀሱት ጉዳዮች ላይ የሚስማሙት ተቃዋሚዎች በተመሳሳይ ሁኔታ መንግሥት ለመቀየር የሚያደርጉትን ጥረት ባለማስተባበር ሲታሙ ኖረዋል፡፡ “ተባበሩ ወይ ተሰባበሩ” ተብለው ሲተቹ ከርመው ቢተባበሩም ደግሞው በአጭር ጊዜ ውስጥ ከመሰባበር አላመለጡም፡፡ |
እኔ እንዳስተዋልኩት ተቃውሞው ጎራ ያሉ አብዛኛው ቡድኖች ከሚስማሙባቸው ጉዳዮች አንዱ መንግሥት ማንኛውንም ተቃራኒ ድምፅ ለማፈን ጥረት ማድረጉን ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ይህንን ስርዓት ለመቀየር (ትልቁ ዓላማ) ሲባል እርስበርስ የሚፈጠሩ ክፍተቶችን መተው/ማለፍ እንደሚገባ ነው፡፡ ይህ ያልተጻፈ የመግባቢያ ሐሳብ በሕዝቡም በፓርቲዎችም በግለሰቦችም ውስጥ ሰርፆ በተቃውሞ ቡድኖች መካከል ልዩነቶች በተፈጠሩ ቁጥር ሕዝቡንም የሚያስከፋው “እነዚህ እርስ በርስ መስማማት ያልቻሉ እንዴት ነገ መንግሥት ይሆናሉ?” “ እንዴት በዚህ ጊዜ እንኳን ለትልቁ ዓላማቸው ሲሉ ችግሮቻቸውን አያመቻምቹም?” የሚሉት ጥያቄዎች ናቸው፡፡ ጉዳዩን ከላይ ከላይ ያየነው እንደሆነ የሚረባ ጠንካራ ፓርቲ አለማግኘት የማንኛውም ሕዝብ የተስፋ መቁረጥ ምንጭ ሊሆንበት ይችላል፡፡ ስለዚህ ጠንካራ ፓርቲዎችን ለማየት መመኘትና ደካማ የሚያስመስሉ ችግሮችን መሸሽም ተገቢ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን መጀመሪያ ትልቁ ዓላማችን አገራችንን ዴሞክራያዊ የተሻለች አገር ማድረግ ነው ወይስ መንግሥትን መቀየር ብቻ? መንግሥትን መቀየር የተሻለ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለማምጣት አስፈላጊ ነው ብዬ ባምንም ይህንን የምናደርገው ለወደፊትዋ ዴምክራሲያዊት ኢትዮጵያ የሚስፈልጉ እሴቶችን በመሸርሸር መሆኑ ግን ያሳስበኛል፡፡ ከነዚህ መሸርሸሮች አንዱ ደግሞ ልዩነትን እንደአማራጭ ያለመቀበል አዝማሚያ ነው፡፡ በመሆኑም አሁን ባለን የተዛባ የመቻቻልና ተስፋ ያለማስቆረጥ ጽንሰ ሐሳብ ከቀጠልን እንደአገር በዴሞክራሲያዊ ስርዓቱ ውስጥ የምናጣው ነገር ከመብዛቱም በተጨማሪ የሚመጣው ስርዓት የተሻለ ለመሆኑ ማረጋገጫ አይኖረንም ብዬ እከራከራለሁ፡፡ |
ለ”ትልቁ ዓላማ” ሲባል ቅድሚያ የሚሰጣቸው የማይመስሉ ነገሮችን መሸፋፈን ባሕላችን እስከዛሬ ውጤታማ ሆኖ አላገኘነውም፡፡ ይህ የአለባብሶ የማረስ ትብብር በአረም ሲያስመልሰን ብዙ ጊዜ አስተውለናል፡፡ እየተሸፋፈኑ የማለፍ ፖለቲካ ከውስጥ ፓርቲ ጀምሮ እስከ አገሪትዋ ወሳኝ የፖለቲካ ጊዜያት ድረስ ብዙ ጊዜ ዋጋ ሲያስከፍለን ቆይቷል፡፡ እነዚህ ያልተተቹ ያልተፈተሹ እርስ በርስ መተባበሮች መካከል በተወሰነ መልኩም ቢሆን ለምርጫ 97 ውድቀት አስተዋእፆ ማድረጉ የሚታወስ ነው:: ለ”ትልቁ ዓላማ” ሲባል የሚደረጉ ያልተጠኑ መስማማቶች “ለትልቁ ዓላማ” ሲባል የታለፉ ልዩነቶች ምርጫ 97ትን የሚያህል ስኬት ለማጣት አስተዋፅዖ አድርገዋል፡፡ስለዚህ ለ”ትልቁ ዓላማ” ሲባል የሚታለፉ ልዩነቶቸ መጨረሻውን ውጤት ስኬታማነት ስለሚቀንሱት ለምንድነው የምንተባበረው? ከነማንጋር ነው አብረን መሥራት የምንችለው? የሚለውን ነገር ማጣራትና ልዩነትን በግልጽ ማስቀመጥ ከማይዘልቅ መተባር የተሻለ ለወደፊቱ ለፓለቲካ ባሕል ጥቅም ይኖረዋል፡፡ አሁን ባለን አካሄድ የመተባበር ሙከራዎቹ ችግሩንም ጭንቀቱንም ከመቀነስ አንጻር የሰጡት ጥቅም አይታየኝም፡፡ እነደውም ደካማ ተስፋ እየሰጡ እርሱንም በአጭሩ እያከሰሙት ብልጭ ድርግም የምትለው የተቃውሞ ፓለቲካ ላይ ተስፋ ለማሳጣት ዋነኞቹ ምክንያቶች ናቸው፡፡ |
የምናወርሰው የፖለቲካ ባሕል ምንድነው? |
በባሕል ደረጃ ሊገለጽ የሚችል የፖለቲካ ልምድ ባይኖረንም እነደአገር ለምናደርገው የመማር ሒደት መታሰብ ያለበት የምናሳድገውና የምናወርሰው የፖለቲካ ባሕል ምን ይሆናል የሚለውንም ጭምር ነው፡፡ አሁን ባለን ሁኔታ የፖለቲካ ባሕላችን በጠላትና በወዳጅ ልዩነት ብቻ የተወሰነ ሲሆን መሐል ላይ የሚቀመጥ ግራጫ ባሕሪይ የለውም፡፡ ይህ መሐል ያለመቀመጥ ችግር ፖለቲካ ፓርቲዋችን በግድም ቢሆን ወደተለባበሰ መተባበር ሲገፋቸው ይታያል፡፡ ልዮነቶችን የምናተናግድበት መንገድ የንግግር ባሕልን፣ ልዩነትን የማክበርን ሳይሆን ጎራ የመለየትን ከሆነ ለመጪው ትውልድም ቢሆን የምናወርሰው የፖለቲካ ባሕል ደካማ ይሆናል፡፡ |
እንደአገር ከ50 ዓመት በፌት የነበሩ ጥያቄዎችን መመለስ ያልቻልን ሕዝቦች ጥያቄዎቹን ለለመለስ የምንጠቀማቸው መንገዶች እንዲህ ደካማ መተባበሮች ላይ የተመሠረቱ ሆነው ከቀጠሉ ችግሮቹን ብቻ ሳይሆን ለመተባበር ሲባል ብቻ የሚነሱ ደካማ ውሕደቶችንም እንደ ባሕል አስተላልፈን ልናልፍ እንቸላለን የሚል ስጋት አለኝ፡፡ እነዚህን ኃላፊነቶች ከግምት ውስጥ ያላስገባ የፓለቲካ ተቃውሞም እስካሁን ውሕደት/አብሮ የመሥራት ችግሮች ምክያትን ሲያጠናም ሆነ ለመፍታት ሲሞክር አይታይም፡፡ የኅብረቶችን መፍረስ በሌላ ኅብረት በመተካት መፍታት የፓለቲካ ባሕሉ ሳይሻሻል እንዲቀጥል ከሚያደርጉት ጉዳዮች አንዱ ነው፡፡ ጥቃቅን ልምዶችን (መፍረስ መደራጀት) ችላ ማለት የተበላሸና ለማስተካከል ጊዜ የሚፈጅ የፖለቲካ ባሕል ይዘን እንድንቀር እንደማያደርገን እርግጠኛ መሆን አይቻልም፡፡ |
ልናመጣቸው የምንከራከርላቸው ሰው ልጆች መብት፣ ፍትሕ፣ እኩልነት እሴቶችን ራሳችን ለትልቁ ዓላማ በመቆርቆር ስያሜ እንደረምሳቸዋለን፡፡ ይህንን ለመረዳት ከፖለቲካ ፓርቲ እስከ ሚዲያ ከግለሰብ እስከ ብሎግና ማኅበረሰብ ሚዲያ አይቶ መመስከር ይቻላል፡፡ በዚህ ባህሪያች የተነሳ በየቀኑ የምንጥሳቸው እሴቶች ብዙ ሰዎችን ገፍተው ዓላማ ሲያስቱም አስተውለናል፡፡ (መቼም ትችቴን ተቹብኝ እንደሰበብ ተቀባይነት ባይኖረውም ተፅዕኖውን ዕውቅና መስጠቱ አስፈላጊ ነው) “ትልቁ ዓላማ” የሚባለው ሰበብም የእሴቶች እሴት ሆኖ ሁሉም ንግግር የመብት ጥያቄና ትችት ከሱ በታች ካልሆነ በስተቀር የማናተናግድበት ባሕል ፈጥረንና ብዛኛዎቻችን ተስማምተን ተቀምጠናል፡፡ ምን ነካት/ው? ለዚህ ሲል ምናለ ቢያልፈው? ይሄንን መናገሪያ ጊዜ አሁን ነው? የሚሉ ጥያቄዎች በተደጋጋሚ ይነሳሉ፡፡ |
የአብዛኛዎቹ የዚህ ክርክር ደጋፊዎች የምናስቀድመው “ትልቁን ዓላማ” መሆን አለበት ከማለት በተጨማሪ ጊዜንና ቅድሚያ አሰጣጥን እንደተያያዥ ምክንያች ያነሳሉ፡፡ እነዚህ ምክንያቶች በቂ ሆነው ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት፣ የግለሰቦች መብት በቀላሉ ይጣሳል፡፡ ይህ ባሕል ደግሞ በየቦታው የምናነሳቸውን እሴቶች ተቃራኒ የመሆንን እና ተደራራቢ መመዘኛዎችን የመጠቀም ያጋልጠናል፡፡ የምንቆምላቸው እሴቶች ለእኛ ዓላማ ሲሆን የሚሸረፉ፣ ሌሎች ሲያደርጉት የሚያስወቅሱ ከሆነ ምኑን ቆምንላቸው? |
ዛሬ ለትልቁ ዓላማ ሲባል ዝምታን የምንመርጥባቸው ጥቃቅን መሳይ ጉዳዮች የምናፈራቸው መሪዎች ላይ የሚያሳድሩትን ተጽዕኖም መገመት ቀላል ሥራ አይደለም፡፡ ዛሬ እሴቶች እና መርሕዎቸ ሲሸራረፉ ዝም ማለታችን በትንሽ ሥልጣን ትንሽ አምባገነንነትን ሊያበረታታ ይችላል የሚል ስጋት አለኝ፡፡ ይህ ትንንሽ አምባገነኖችን የማበረታታት አዝማሚያ ነገ ትልቅ ሥልጣን ላይ ትልቅ አማባገነንነት ላለመፍጠሩ ምንም ማረጋገጫ የለም፡፡ የአመራር ብቃትና ባሕርይ ማጣት ችግር በሰፊው የሚታይበት የተቃውሞ ፓለቲካ ከገዥው ፓርቲ ከሚደርስበት ጫና በተጨማሪ የሚጋፉት ችግሮች አንዱ አመራሩ አለመገራቱ እና በገዥው ፓርቲ ስም ለስህተቶችቹ በቀላሉ የማርያም መንገድ ማግኘቱ ነው፡፡ ለ”ትልቁ ዓላማ” ሲባል የምናልፋቸው ስህተቶች ሌላ አምባገነን መሪዎችን መፍጠር አደጋ ውስጥ ገብተን እንዳይሆን አሁንም ቢሆን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ |
የዚህ ጽሑፍ ዓላማ የመንግሥት ተቃውሞውን የማዳከም ተፅዕኖ አሳንሶ ማየት አይደለም፡፡ እንደኽዝብ የምንፈልገውን በግልጽ ማወቅና ለዚያ መሽራትና መኖርንና መለማመድ እንደአንድ የክርክር ሐሳብ ለማቅረብ ብቻ ነው፡፡ ለ”ትልቁ ዓላማ” የሚደረጉ ማመቻመቾችም የት ድረስ መሄድ አለባቸው? የምናጥፋቸውና የማናጥፋቸው መርሕዎች የትኞቹ ናቸው? የትኛው ላይስ ማስተካከያ መውሰድ ይገባናል? የሚለውን ለመለየትና ከአሁኑ እርምጃ መውሰድ ካልቻልን “አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ” የሚለው የአበው ምሳሌ እንዳይደርስብን ከመጨነቅ የመነጨ ነው፡፡ የሐሳብ ልዩነታቸውን ተከትሎ ብቻ “ትልቁ ዓላማ” አልተከተላችሁም በሚል ሰበብ ያጣናቸውና የምናጣቸውን ሰዎችም እያሰብኩ እንደጻፍኩት ይታሰብልኝ፡፡ |
ማስታወሻ፡- “ትልቁ ዓላማ”- The bigger picture የሚለውን የእንግዘኛ ቃል ተክቶ የገባ ነው፡፡ |
በዘላለም ክብረት በሰዎች የእድገት መሰላል በተለምዶ ‹ሃያዎቹ› (twentysomethings) የሚባለው የዕድሜ ክልል እጅግ ወሳኝ እንደሆኑ ብዙ ጥናት መጥቀስ ይቻላል፡፡ ሰዎች ከልጅነት ጊዜያቸው ወደ ጉልምስና የሚ... |
“በአንድ ስርዓት ሥር ይህን ያህል ጊዜ መቆየት እጅግ ያንገበግባል” |
በ ወይንሸት ሞላ ወይንሸት ሞላ የ25 ዓመት ወጣት ስትሆን፤ በኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ ዘመን ተወልዳ አድጋለች፡፡ በሌላ አነጋገር ወይንሸት አንዳንዶቹ ‘The EPRDF Generation’ የሚሉት ትውልድ አባል ነች፡፡ ወይን... |
በዘላለም ክብረት አፍሪካ ከበደ ገና በአስራዎቹ የዕድሜ መጨረሻ ላይ ያለ ወጣት ነው፡፡ በጣም ተስፈኛ ነው፡፡ ሁሌም ለውጥ እንደሚመጣ መናገር ይወዳል፡፡ ለምን ስሙ ‹አፍሪካ› እንደተባለ ሲጠየቅ ደጋግሞ ወደ መምህር... |
በ ሶልያና ሽመልስ እና ማሕሌት ፋንታሁን እኛ ሴቶች በተወሰነ ጊዜ በቋሚነት የምንገናኝ ሴት ጓደኞች አይጠፉንም፡፡ የከተማዋ ካፌዎች ውስጥ የሚሆነው ይህ ቆይታችን በተለይ ወደ ሥራው ዓለም ከገባን ወዲ... |
የ365 ቀናት ፈተና እና ተስፋ - የአንድ ዓመት ማስታወሻ |
ከዞን9 ጦማርያን እና ወዳጅ ጋዜጠኞች ጊዜው በጣም ይነጉዳል፡፡ ሀላፊነት የማይሰማው ስርዓት የገዛ ዜጎቹን ዕድሜ በእሳት ይማግዳል፡፡ ሚያዚያ 17/08/2006 ዓ.ም በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንድንውል የተደረግነው ስድስት ... |
" ከጥቂት ሰአታት በኋላ የእግር ኮቴ ስንሰማ ተሽቀዳድመን በቀዳዳ ስናይ ማህሌትን ወደ ሌላ ክፍል ሲያስገቧት አየሁ ፡፡ ያኔ ለመጀመሪያ ጊዜ አለቀስኩ " አርብ እለት መስሪያ ቤቴ ጎተራ ስ... |
‹‹ማዕከላዊ ነው እንዴ ያለነው?›› (ክፍል ፪) |
በናትናኤል ፈለቀ ( ካለፈው የቀጠለ) የማታው የመፀዳጃ ሰዓት አብቅቶ እስረኞችን ቆጥረው በሩን የሚቆልፉት ፖሊሶች መጡ፡፡ ሼህ ጀማል ዘወትር እንደሚያደርጉት የመጡት ፖሊሶችን ሰዓት ጠየቋቸው፡፡ አልፎ አልፎ... |
በ ሶልያና ሽመልስ እና በ በፍቃዱ ኃይሉ ‹‹ፍቅር ማወቅ እና አለማወቅ›› የሚባል ነገር አለ? ‹‹ፍቅር ማወቅ›› የሚባል ነገር ካለስ - ኢትዮጵያውያን ፍቅር ያውቃሉ? - የዛሬ የፍቅር (የቫለንታይን) ቀን... |
የዞን ዘጠኝ ጦማሪው ናትናኤል ፈለቀ ታሰረ |
የዞን ዘጠኝ ጦማሪው ናትናኤል ፈለቀ ትናንት ማክሰኞ መስከረም 24፣ 2009 ከስራ ሰዓት በኋላ ጸደቀ ድጋፌ እና አዲስአለም ሙሉጌታ ከተባሉ ሁለት የስራ ባልደረቦቹ ጋር በተለምዶ ‹ስታዲየም› ተብሎ የሚታወቀው አካባቢ ... |
በ አቤልዋበላ በዚህ በምህንድስናው የትምህርት ዘርፍ ልብን የሚሰቅዝ ህሊናን የሚቆጣጠር ርዕስ ብዙውን ጊዜ አይኖርም፡፡በተለይ እንደኔ መሐል አዲስ አበባ በሚገኙ የድሆች መንደር ተወልዶ ያደገ ሰው ለራሱም ሆነ ለማኀበረሰቡ... |
በጭቆናና በበደል የተፈተነ የፍትህ እና እኩልነት አባት - ዶ/ር ቢሂምራዎ ራምጂ... |
የኢትዮጵያ ፀረ ሽብር አዋጅ መሻሻል ለምን? |
ጦማሪያን በዚህ ሳምንት |
ዞን 9 የጦማሪያን ቡድን ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው ማኅበረሰባዊ እና ፖለቲካዊ ሁኔታ የተለየ እና ወገናዊ ያልሆነ ተረክ ለመፍጠር እየሠራ የሚገኝ የወጣቶች ስብስብ ነው፡፡ ዋናው ዓላማ ሁሉም ኢትዮጵያውያን የሀገሪቷ ጉዳይ ያገባኛል ብለው ውይይት የማድረግ ባሕል እንዲያሳድጉ መድረኩን በመፍጠር ሀገሪቷን በሁሉም መስኮች ወደተሻለ ደረጃ የሚያደርሱ ሐሳቦች እንዲወለዱ ለማመቻቸት ነው፡፡ |
በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች ሕዝባዊ እምቢተኝነቱ ዳግም አገረሸ! |
በአብዛኛው የምዕራብ ኦሮሚያ አከባቢዎች እና በአምቦ፣ ጊንጪ፣ ጉደር፣ ግንደበረት፣ በኮቴና ኩታዬ የስራ ማቆም አድማ እየተደረገ መሆኑ ታውቋል። |
ከአምቦ እስከ ነቀምት ሙሉ በሙሉ እንቢተኝነቱ ተጀምሮ ሕዝቡ ሱቁንና መንገድ በመዝጋት የሕወሃት አገዛዝ ያብቃ ጥያቄ ማሰማቱ ታውቋል። በሰንዳፋ፣ በኬና ሽኖ በተሰኙ አከባቢዎችም ህዝባዊ ተቃውሞ በመደረግ ላይ መሆኑን የሚወጡ መረጃዎች ያመላክታሉ። |
የሕወሃት ስርዓት የሕዝብን ጥያቄዎች ባለመመለስ እና ስልጣኑን በኃይል በወታደራዊ እና በደህንነት ጨፍልቆ ለመግዛት እንደወሰነ ታውቋል። በዜጎች ላይ እየፈፀመ ያለው ኢሰብዓዊ ድርጊት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰበት በመምጣቱ ዜጎችን በመከፋፈል እና በመግደል ጊዜውን ለማራዘም በመወሰን በአባላቱ ላይ እርምጃ ለመውሰድ መወሰኑም ተሰምቷል። |
አገር ወደ ጥፋት እያመራች ስለሆነ ከእኛ ጥቅም በላይ አገር ይበልጣል፤ ለግልና ለተወሰነ ቡድን ጥቅም ብለን ያልተፈለገ ውሳኔ መወሰን የለብንም ያሉትን የራሱን ሰዎች ለማጥፋት ወስኖ ተግባራዊ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ መሆኑም ታወቋል። |
የሕወሃትን አካሄድ የተመለከቱ ስርዓቱ የማይማርና ለለውጥ አለመዘጋጀቱን በገሀድ እያሳየ ነው፤ የተጀመረውንም የነፃነት ትግል ምላሽ የሚያገኘው ይህ ዘረኛ ስርዓት ሲወገድ በመሆኑ ትግሉን አጠናክሮ መቀጠል ዋናውና ወሳኙ ሥራ ነው። ስለሆነም፣ ሕዝቡ ሕወሃትን ከሕዝብ የመነጠል፣ የማዳከም፣ የሕወሃትን ምርቶች ባለመጠቀም ይህን ዘረኛ ስርዓት የሁላችን ጠላት በመሆኑ ትግሉም የሁላችን ስለሆነ ሕዝባዊ እምቢተኝነቱን ሁላችንም ልንቀላቀለው ይገባል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ |
የኢትዮጵያ ሕዝብ አገዛዙ ሳይወርድ ትግሉን አያቆምም ተባለ! → |
የመለስ ዜናዊ ቤተስብ ኩባንያ ኦርኪድ የምርት ገበያን የአባልነት ወንበር በ1.6 ሚሊዮን ብር ገዛች |
የመሶቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ 313 ሚሊዮን ብር ትርፍ አገኘሁ አለ |
ደደቢት: የሕወሃት ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ከ416 ሚልዮን ብር በላይ ብድር ሰጠ |
‹‹ከኢትዮጵያ ጋር ከመደራደር ይልቅ ሌሎች አማራጮችን መውሰድ እንፈልጋለን›› የግብፅ የውኃ ሚኒስትር |
ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ አዳዲስ የገቢ ማስገኛ ፕሮጀክቶች ተዘጋጁ-የህዳሴ ግድብ ግንባታ ብሔራዊ ምክር ቤት |
ለታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ቃል ከተገባው ገንዘብ ከግማሽ በላይ ተሰብስቧል |
ኢትዮጵያ በአባይ የውሃ አጠቃቀም ላይ ያላት አቋም ለሌሎች ሀገራት ምሳሌ የሚሆን ነው … አቶ አለማየሁ ተገኑ |
የህዳሴ ግድብ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ይጠናቀቃል- የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር |
የህዳሴው ግድብ 23 በመቶ ወጪ በሕዝብ መሸፈኑ ተገለጸ |
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ 24 በመቶ ተጠናቀቀ |
ኢትዮጵያን ከድርቅ ለመታደግ የሚያስችሉ 4 መንገዶች |
ታሪካዊ ድርቅ ወደአጋጠመው የደቡብ ኢትዮጵያ ባድረኩት ጎዞ፤ በአስደናቂ ሁኔታ ራሷን የቻለች ፋጡማ የምትባል ሴት አግኝቼ ነበር፡፡ |
ምንም እንኳ ድርቁ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ቤተሰቦች መቋቋም ከሚችሉት በላይ ሆኖባቸው ለመኖር የሚያስችላቸውን የምግብ ዕርዳታ እንዲቀበሉ ቢያስገድዳቸውም፤ እንደፋጡማ ያሉ ቤተሰቦች ግን ቀውሱን ለመቋቋም ችለዋል፡፡ የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ኤጀንሲ (ዩ ኤስ ኤ አይ ዲ) ባደረገላቸው ድጋፍ ፤ በዝናብ ላይ ጥገኛ ከሆነ ግብርና ተላቀው ሕይወታቸውን በተለያዩ መንግዶች መምራት ችላዋል፡፡ |
ይህም ሆኖ ቤተሰቦች በምግብ ዕርደታ ላይ ያላቸውን ጥገኝነት እንዲቀንሱ እያደረግን ያለው ድጋፍ ቀውሱን ለመቋቋም በቂ አይደለም ፡፡ አምና ከነበረው ሶስት እጥፍ የሆነ 10 ሚሊዮን ሕዝብ አስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ ይፈልጋል፡፡ 6 ሚሊዮን ሕዝብ የውኃ፣ የንጽህናና የጽዳት አገልግሎት አቅርቦት ይፈልጋል፡፡ 2.6 ሚሊዮን ሕዝብ ከመካከለኛ እስከ ከፍተኛ በሚደርስ የተመጣጠና ምግብ እጥረት እየተቸገረ ሲሆን ህክምናም ይፈልጋል ፡፡ |