text
stringlengths
0
2.31k
የኢትዮጵያን የድርቅ ማዕበል ለመታደግ የሚያስችሉ 4 መንገዶች ቀጥለው ቀርበዋል፡፡
1.ቀጣይነት ያለው ድርጊትና ትኩረት
የተገኘውን ልማት ለመጠበቅና ከፍተኛ ሰብዓዊ አደጋ እንዳይከሰት ለማድረግ፤ ለጋሾች ድርቁን ለመቋቋም የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው መቀጠል ይኖርባቸዋል፡፡ አሜሪካ እስከአሁን ድረስ ከግማሽ ቢሊዮን ዶላር በላይ የአስቸኳይ የድርቅ ድጋፍ ያደረገች ሲሆን፤ በቅርቡም ተጨማሪ ድጋፍ ታደርጋለች፡፡ ሌሎች ለጋሾችም የበለጠ ድጋፍ እንዲያደርጉ የዘውትር ጥሪያችንን ማድረግ እንቀጥላልን፡፡
በተጨባጭ እየተሰጠ ያለው ምላሽ በፈጣን ሁኔታ ካልተሻሻለ፤ የምግብ ዕርዳታ የሚፈልገው ሕዝብ ቁጥር ይበልጥ ሊጨምርና ሕይወትም ሊጥፋ እንደሚችል ሊታወቅ ይገባል፡፡ የተገኘው ልማት ከተቀለበሰ መልሶ ለማገገም ረጅም መንገዱ መጓዝን ይጠይቃል፡፡
ቀጣዩ ጊዜ አስከፊው ድርቅ የሚከሰትበት ሊሆን ይችላል፡፡ የበጋው ወቅት እየተቃረበ ነው፡፡ ይህም ማለት እርዳታ ለማቅረብ ያለው ጊዜ በፈጣን ሁኔታ እያበቃ ነው ፡፡ በጉዞዬ በዩ ኤስ ኤ አይ ዲ በሚደገፍ የዕርዳታ ምግብ ማደያ ጣብያ የተሰለፉ ሰዎችን አነጋግሬ ነበር፡፡ ሁሉም ባለፉት ሁለት አመታት ዝናብ ባለመዝነቡ ምክንያት ምርት ማምረት ያልቻሉ ገበሬዎች ነበሩ፡፡ ሁሉም ገበሬዎች እንደጎረቤቶቻቸው ሁሉ በዕርዳታ ምግብ ላይ ጥገኞች ናቸው፡፡
አሜሪካ ላደረገችው የዕርዳታ ምግብ ድጋፍ ምስጋና ቢቸሩም ፤የራሳቸውን ምርት ለማምረት ግን በእጅጉ ጓጉተዋል፡፡ የሰኔ ወር ዝናብ ከመጀመሩ በፊት በአስቸኳይ ዘር እንዲቀርብላቸው ይፈልጋሉ፡፡ ዝናቡን መቆጣጠር አንችልም ፤ ዝግጅት ማድረግ ግን እንችላለን፡፡ 1.7 ሚሊዮን ገበሬዎች ራሳቸውን እንዲችሉ ለማድረግ በአስአቸኳይ ዘር ልናቀርብላቸው ይገባል፡፡
ድጋፍ የሚያደርግ ተጨማሪ የሰው ኃይል
ተገቢውን ዕርዳታ ውጤታማ በሆነ መንገድ ለተረጂዎች ለማድረስ ፤ ዓለም አቀፍ ለጋሾችና የልማት ድርጅቶች በቂ የሰው ኃይል ማንቀሳቀስ ይገባቸዋል፡፡ ሰፊ ጥረት እየተደረገ ቢሆንም፤ ለተረጂው ወገን በፈጣን ሁኔታ እርዳታ እየደረሰ አይደለም፡፡ በዚህም የተነሳ የጤና ማዕከላት በተመጣጠነ ምግብ እጥረት በተጎዱ ሕጻናት ተጨናንቀዋል፡፡
አንድ የጤና ባለሙያ በተመጣጠነ ምግብ እጥረት የተገዱ ሕጻናትን የያዙ 88 እናቶችን ለመርዳት ጥረት የሚያደርግበትን ማዕከል ጎብኝቻለሁ፡፡ እያንዳንዱን ሕጻን የመመዝገብ፤ የመመርመር ፤አልሚ ምግብ የመስጠት፤ የመመዘንና ቁመቱን የመለካት ሥራ በአንድ የጤና ባለሙያ ብቻ ይከናወናል፡፡ እኛ ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ማዕከሉ ስንደርስ ፤የሕጻናቱ ወላጆች ለሰዓታት ሲጠብቁ የቆዩ ሲሆን የጤና ባለሙያው ከመምሸቱ በፊት ለልጆቻቸው ድጋፍ የማድረጉ ዕድልም ጠባብ ነበር፡፡
ተጨማሪ ድጋፍ ከኢትዮጵያ መንግሥት
የኢትዮጵያ መንግሥት እስከአሁን ድረስ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ኢንቨስት ያደረገ ሲሆን ፤ በቀጣይም ተጨማሪ ገንዘብ መመደብ ይኖርበታል፡፡ መንግሥት የቢሮክራሲ ማንቆዎችን በማቃለልና የምግብ ሥርጭቱ እንዲፋጠን የሚያግዙ አሰራሮች በመፍቀድ፤ ለዓለም ዓቀፍ ማኅበረሰቡ ድጋፍ ማድረግ ይችላል፡፡ ለተረጂዎች በቀጥታ ድጋፍ የሚያደርግ የሰው ኃይል መጨመርና ዓለም ዓቀፍ ኤጀንሲዎች ያላቸውን ብቃት ለማሳደግና የሰው ኃይላቸውን ለመጨመር የሚያደርጉትን ድጋፍ የኢትዮጵያ መንግሥት መቀበል ይኖርበታል፡፡
እነዚህ እርምጃዎች አሁን ላለው ቀውስ ምላሽ ለመስጠት የሚያግዙ ቢሆንም፤ የረጅም ጊዜ ዕቅድ ሊኖረን ይገባል ፡፡ እ.ኤ.አ. በ2012 የአፍሪካ ቀንድ በመሳሰሉ አካባቢዎች በአየር ጠባይ መለዋወጥ ሳቢያ የሚከሰቱ ችግሮችን ለመቋቋም በዩ ኤስ ኤ አይ ዲ ስር የተመሰረተው የችግር መቋቋም አመራር ምክር ቤት ዓባልነቴ፣ የችግር መቋቋም አቅም ግንባታ ( Resilience ) በተግባር ምን እንደሚመስል ለማየት ጓጉቼ ነበረ፡፡
ፋጡማን የመሳሰሉ ቤተሰቦች ያስመዘገቡት ስኬት ፤ በከፊል በዩ ኤስ ኤ አይ ዲ የጀመረው ዘላቂ ልማትን እውን ለማድረግ ችግርን የመቋቋም አቅም ማሳደግ ፕሮግራም ውጤት ነው፡፡ ፕሮግራሙ በዩ ኤስ ኤ አይ ዲ ድጋፍና በኢትዮጵያ መንግሥት በሚመራው የምግብ ለሥራ ፕሮግራም ታቅፈው የምግብ ዕርዳታ የሚደረግላቸው ቤተሶቦችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው፡፡ እንዲሁም ፕሮግራሙ በቂ ሀብት አፍርተው ራሳቸውን እንዲችሉ የሚያግዝ ነው፡፡
ፕሮግራሙ ሩቅ በሆኑ አካባቢዎች የሚገኙ ቤተሰቦችን በማኅበር በማደራጀት ፤ ከእርሻና ከእርሻ ውጭ በሆኑ እንቅስቃሴዎች ገቢ ማፍራት እንዲችሉና የብድር አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያሥችል ስልጠና ይሰጣል፡፡ የተሻለ ዘር ፣ ማዳበሪያና የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከዘመናዊ ግብይት ጋር ያስተሳስራቸዋል፡፡
ምንም እንኳ ባለፉት አራት ዓመታት በፕሮግራሙ ከተሳተፉት ከ 33,000 በላይ ቤተሰቦች፤ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ከምግብ ዕርዳታ የተላቀቁ ቢሆንም ፤ የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ ደረጃ ላይ ያልተደረሰ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡ ወደ 8 ሚሊዮን የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን በምግብ ለሥራ ፕሮግራም ታቀፈው በየወሩ የምግብ ዕርዳታ ይቀበላሉ፡፡
የሚያሳይ አቅም እየገነባን ቢሆንም፤ ያጋጠመን ቀውስ ከስኬታችን የላቀ ነው፡፡
ከኢትዮጵያ ጉብኝቴ ስመለስ ፤ በመዘንጋታቸው ምክንያት የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ ያልቻሉ የኅበረተሰብ ክፍሎች ፤ ችግርን የመቋቋም አቅም እንዲፈጥሩና ከድህነት እንዲወጡ ለማድረግ ከለጋሾችና ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ተባብረን መስራት እንደሚገባን ተግንዝቢያለሁ፡፡
ዲና እስፖሲቶ በዩ ኤስ ኤ አይ ዲ የዲሞክራሲ፣ ግጭትና የሰብዓዊ ዕርዳታ ተጠባበቂ ምክትል አስተዳዳሪ ናቸው፡፡
መጋቢት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በግለሰቦች እና ቡድኖች ላይ በፕሬስ የሚካሄዱ የስም ማጥፋትን ለመዳኘት የወንጀል ሕጉን ለማሻሻል መታቀዱ ተጠቆመ፡፡
ከ2005-2007 የሚቆየውና እስካሁን ሳይጸድቅ በውይይት ላይ የሚገኘው ብሔራዊ የሰብዓዊ መብት የድርጊት መርሃግብር ሰነድ ላይ እንደተመለከተው በመገኛኛ ብዙሃን አማካይነት የሚካሄዱና በተለይ በግለሰቦች እና ቡድኖች ላይ ያነጣጠሩ የሰም ማጥፋት ዘመቻዎችን ለማስቆም የወንጀል ሕጉን ለማሻሻል ጥናት ይካሄዳል፡፡
ይህው ሰነድ በመገናኛ ብዙሃን የሚቀርብ የስም ማጥፋት ክስ በሕገመንግስቱ በተቋቋሙ የህግ አውጪ፣የህግ አስፈጻሚወይም የፍርድ ቤት ባለስልጣኖች ላይ ካልሆነ በስተቀር በግለሰቦችና የግል ድርጅቶች ላይ ሲሆን፣ በአቃቤ ሕግ ሳይሆን በግል ተበዳይ ክስ ቀርቦ የሚታይበት ስርዓት ተዘርግቷል ሲል ስርዓቱን ያሞካሻል፡፡
ቢበዛ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ውሳኔ እንዲሰጥ በማድረግ እንዲሁም በመገናኛ ብዙሃን ላይ ሊቀርብ የሚችል ማንኛውም
በማድረግ ኀሳባቸውን የመግለጽ ነጻነታቸው እንዲጠበቅላቸው ሆኗል ሲል ምስክርነቱን ይሰጣል፡፡
ይረቀቃል ሲል በሰነዱ ላይ ቢያሰፍርም፣ አሁን በስራ ላይ ያለው ሕግ ምን እንደጎደለበት በግልጽ ያመለከተው ነገር
የለም፡፡ሆኖም ግን ሰነዱ መንግስት አሁንም ፕሬሱን በስም ማጥፋት ስም ለማሳደድ ያለውን ቁርጠኛ አቋም የሚጠቁም
በኢትዮጵያ በመንግስት ላይ ጠንካራ ትችት የሚያቀርቡ ጋዜጦች ሙሉ በሙሉ ከገበያ እንዲጠፉ መደረጉ ይታወሳል።
← የአቶ መለስ ምስሎች አሁን ከአዲስአበባ ጎዳናዎች ላይ አልተነሱም
ወቅታዊ አገር የማዳን ጥሪ አርበኞች ግንቦት 7 የኖርዲክ ሐገራት የገቢ ማሰባሰቢያ እና የውይይት ፕሮግራም በኖርዌይ ኦስሎ !!
(Breaking News – ሰበር ዜና) አቡነ ሕዝቅኤል የሥልጣን መልቀቂያ ደብዳቤ አቀረቡ
የ255ቱን የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚዎች ስም ዝርዝር ይመልከቱ
በፌስቡክ ያግኙን – “like” የሚለውን ይጫኑ
#Ethiopia የግንቦት 20 በዓል በመቐለ ከተማ በፓናል ውይይት ሲከበር በአዲስ አበባ የግንቦት 7ን መሪ በደማቅ አቀባበል እየተከበረ ይገኛልfollow@dagmaw_tewodros 2 weeks ago
ወደ ፈተና አለመግባት ይቻላል →
በህይወቴ ካገኘሁዋቸው ሰዎች ሁሉ ህይወቱን መለወጥ የማይፈልግ ሰው አጋጥሞኝ አያውቅም፡፡ ሁሉም ሰው ህይወቱን ወደተሻለ መለወጥ ይፈልጋል፡፡
ታዲያ ህይወታችንን መለወጥ እየፈለግን ህይወታችንን እንደፈለግነው መለወጥ ያልቻልነው ለምንድነው የሚለው ጥያቄ ወሳኝ ጥያቁ ነው፡፡
ለዚህ የተለያዩ ምክኒያቶችም ቢኖሩ በአገልግሎት ህይወቴ የተመከትኩትን ዋና ምክኒያት ላካፍላችሁ፡፡ ብዙ ሰዎች መለወጥ ይፈልጋሉ ነገር ግን ስለህይወታቸው ሃላፊነት መውሰድ በፍፁም አይፈልጉም፡፡
ስላልተለወጠው ህይወታቸው የሚያሳብቡበት ነገር አለ፡፡ እከሊት ነች ፡ እከሌ ነው ፡ ወላጆቼ ናቸው አገሩ ነው ፡ አለቃዬ ነው ለዚህ ያበቃኝ ስለሚሉና ጥፋቱን በሌላው ላይ ስለሚያላክኩ ተስፋ ቆርጠዋል፡፡
ወደፊትም መለወጥ የማይችሉበትን ምክኒያቶችን ይዘረዝራሉ፡፡ የማልለወጥበት ምክኒያት ጊዜው ነው ፡ አገሩ ነው ፡ ሰዉ ከፍቶ ነው በማለት ለህይወት ለውጣቸው ሃላፊነቱን ከመውሰድ ይልቅ በቀላሉ ጥፋቱን ወደሌላ በማላከክ ጥሩ ሰበብ አግኝተው ተስፋ ይቆርጣሉ፡፡
እነዚህ ሁሉ አሉታዊ ነገሮች እያሉ ሌሎች ሰዎች ህይወታቸውን ይለውጣሉ፡፡ እነዚህ የተለወጡት የተሸነፉ ሰዎች የሚያከብሩዋቸው ምክኒያቶች ህይወታቸውን ሊያስቆም የሚችል በቂ ምክኒያት እንደሆነ አልተቀበሉትም፡፡
ህይወት ጥቂቱ በመቶ በውጭ ሁኔታ ለምሳሌ ሰዎች በእኛ ላይ በሚያደርጉት ሲወሰን አብዛኛው በመቶው ግን የሚወሰነው እኛ ለዚያ ነገር በምንሰጠው ምላሽ ነው፡፡ ምርጫው የእኛ ነው፡፡ በሁኔታው ተስፋ ልንቆርጥ ወይም ብንወድቅ እንኳን ወድቀን እንደ ማንቀር በማመን መነሳታችንን ማየት እንችላለን፡፡
ሁላችንም ብዙ ነገሮች እንዳናደርግ ብዙ ምክኒያቶች ነበሩን፡፡ ነገር ግን የቀጠልነው ምክኒያቶቹ በህይወት ተስፋ ለመቁረጥ በፊታችን በቁ ስላልሆኑ ነው፡፡ ከእነዚህ ያነሱ ምክኒያቶች እንኳን ብዙ ሰዎችን ከእርምጃቸው አሰናክለዋል፡፡
አንተ በህይወትህ ተስፋ ከቆረጥክ ሌላ ማንም ሰው ሊረዳህ አይችልም፡፡ አንተ ግን ከተነሳህ ሌላ ሰው ቢረዳህም ባይረዳህም ህይወትህን ይለወጣል፡፡
ያንተ ህይወት እንዲለወጥ ያንተ አስተዋፅኦ እጅግ ወሳኝና አብዛኛው ማጆሪቲ /majority/ ነው፡፡ ያንተ ህይወት ያንተ ነው፡፡ ሰዎች ህይወትህን ሊለውጡ በፍፁም አይችሉም፡፡ ለህይወትህ መለወጥ ጥቂት አስተዋፅኦ ብቻ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡
ህይወትህ እንዲለወጥ ሃላፊነትን ውሰድ፡፡
ከዚህ ሁሉ በላይ እግዚአበሄር መልካም እንደሆነና ከሃጢያትህ ሊያድንህ ልጁን በመስቀል ላይ የከፈለልህ ስለሚወድህ መሆኑን አውቀህ በእርሱ ታመን፡፡
በአዲስ አበባ ውስጥ የሚታየውን የሃይል እጥረት ለመቅርፍ ረጅም ጊዜ ሊወስድ እንደሚችል ባለሙያዎች ገለጹ
ዘጠኝ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አንድ የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል።
← እየነጋ ነው! (እስከመቼ)
በሃገሪቱ ሰሜናዊ እና ስሜን ምስራቅ ድንበር ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል
በሃገሪቱ ሰሜናዊ እና ስሜን ምስራቅ ድንበር ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል። #Ethiopia የወያኔ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እና ከባድ መሳሪያዎች ተወልውለው በድንበሩ ዙሪያ ተኮልኩለዋል።
የአንዳርጋቸው ጽጌ መያዝ ፡ የግንቦት ሰባት ጥሪ እና የትሕዴን ሰራዊት መመረቅን ትከትሎ በሃገሪቱ ሰሜናዊ እና ሰሜን ምስራቅ ድንበር ላይ ከፍተኛ ውጥረት መንገሱን ለሰሜን እዝ ቅርብ የሆኑ የሰራዊቱ ምንጮቻችን በደረሱን መረጃ አስታውቀዋል።እንዲሁም በአፋር ክልል ውስጥ ክፍተኛ ደህንነቶች በማፍሰስ ሕዝቡን እየሰለሉት መሆኑ ሲታወቅ ከፍተኛ አመጽ በክልሉ እንዳይነሳ ወያኔ መስጋቱ ታውቋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በአዲስ መልክ በጎንደር በጎጃም እና በሰሜን ሸዋ ነዋሪዎችን መሳሪያ ማስፈታት ሊጀመር መሆኑ የታወቀ ሲሆን ይህም የሚያምለክተው አማራው ከግንቦት ሰባት ጋር ይሸፍታል የሚል ስጋት ስላላቸው መሆኑ ታውቋል። በዚህ ዙሪያ ተከታታይ መረጃዎችን ይቀርባሉ።
የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ሸንጎ በቅርቡ አዲስ አበባ ከተማን በተመለከተ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ በህዝብ ላይ እንዳይጫን ተከታታይ ስራ እንደሚሰራ አስታወቀ
አገራዊ ንቅናቄው የአገራችንን የፖለቲካ ችግር የሚመጥን መፍትሄ ለመፈለግ ጠቃሚ ነው – ፕ/ብርሃኑ ነጋ።የኢትዮጵያ ጉዳይ ከልብ ያሳስበኛል – አቶ ሌንጮ ለታ
አዲስ ነገር የለም ትግራይ የጉግማንጉጎች ምድር ከሆነ ሰነበተ – መስቀሉ አየለ
“የሰኔ አንድ ሰማዕታት አደራ በትግላችን እውን ይሆናል!!!” – ከአርበኞች ግንቦት 7 የተሰጠ መግለጫ
ዶ/ር መረራ ጉዲና በቀረበባቸው ክስ ላይ ያቀረቡት መቃወሚያ ብይን አልተሰራም
ድርቅ ርሃብና ችጋር ምንና ምን ናቸው? ኢትዮጵያስ ለምን የርሀብ ሀገር ሆነች? _ ፈቃደ ሸዋቀና _ The time for change
ድርቅ ርሃብና ችጋር ምንና ምን ናቸው? ኢትዮጵያስ ለምን የርሀብ ሀገር ሆነች? _ ፈቃደ ሸዋቀና
ተቃዋሚዎች ከራሳቸው ይልቅ ኢሕአዴግን ያምኑ ይሆን? (በፈቃዱ ዘ ሃይሉ) November 8, 2017
ንጉሠ ነገሥት የሌላቸው የኢትዮጵያ ንጉሦች – ይገረም አለሙ November 8, 2017
የመንግስትን ስልጣን ለመረከብ ዝግጁነት አለ ወይ? (ከሙሉቀን ገበየው) November 8, 2017
መሐመድ አል-አሙዲን ጨምሮ ሳዑዲ አረቢያ 38 ሰዎችን አሰረች November 8, 2017
የኛ ሰው በሄግ ችሎት – ክንፉ አሰፋ (ዘ ሄግ) November 8, 2017
የአማራና ኦሮሞ ትብብር ሕወሃቶችን ለቁጭትና ቅዠት የሚዳርገው ለምንድነው? – በስዩም ተሾመ November 8, 2017
የአገዛዙ ደኅንነቶች የኮሎኔል ደመቀን የ5 ዓመት ሕጻን ልጅ ለመጥለፍ ሙከራ አደረጉ _ በኮሎኔሉ ላይ 9 የሰለጠኑ ምስክሮች ቃላቸውን ሰጥተዋል July 13, 2017
በደ/ታቦር ኢየሱስ መናኝ ባሕታዊ በፖሊስ ታፍነው ተወሰዱ፤ – ሙሉቀን ተስፋው July 13, 2017
“እንኳን ኃይለማርያም ይቅርና ነባሮቹ የብአዴን መሪዎች እነበረከትና አዲሱ እንኳ ከኤርትራና ሱዳን ጉዳይ የተገለሉ ነበሩ” ያሬድ ጥበቡ
(ዘ-ሐበሻ) ትናንት አርብ በኢትዮጵያ ፓርላማ ቀርበው ስለኢትዮ-ሱዳን አወዛጋቢ የድንበር ማካለል ጉዳይ መግለጫ የሰጡት ሕወሓት የሚመራው መንግስት ጠቅላይ ሚ/ር ኃይለማርያም ደሳለኝ በድንበሩ ጉዳይ ያደረጉት ንግግር አነጋጋሪነቱ እንደቀጠለ ነው:: በርሳቸው ንግግር ዙሪያ የቀድሞው ኢህዲን (ብአዴን) ታጋይ የነበሩትና በአሁኑ ወቅት በሜሪላንድ አሜሪካ የሚገኙት ያሬድ ጥበቡ በፌስቡክ ገፃቸው ኃይለማርያም ዛሬ ካሰሙት ንግግር በኋላ ገስጸዋቸዋል::
“እንኳን እርሳቸው፣ ነባሮቹ የብአዴን መሪዎች እነበረከትና አዲሱ እንኳ ከኤርትራና ሱዳን ጉዳይ የተገለሉ ነበሩ” ያሉት አቶ ያሬድ ኃይለማርያም ከዚህ ጉዳይ እጃቸውን እንዲያወጡ መክረዋል::
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የሱዳን ኢትዮጵያን ወሰን ጉዳይ በታላቅ ጥንቃቄ ቢያዩትና፣ ምክርቤቱ ውስጥ የሰጡት አይነት የኢትዮጵያን አራሾች በድንበር ገፊነትና፣ በሽፍትነት የመሳል ምስክርነት ቢቆጠቡ ተመራጭ ነው ። አለመግባባቱ ወደፊት ወደአለምአቀፍ አርቢትሬሽን ቢላክ ይህ ቪዲዮ የሱዳኖችን የይገባኛል ጥያቄ የሚያጠናክርና ኢትዮጵያን የሚጎዳ በመሆኑ፣ ከዚህ መሰል ምስክርነት ቢቆጠቡ ተገቢ ነው ። በሁለተኛ ደረጃ፣ አቶ ኃይለማርያም ለኢህአዴግ መጤ መሆናቸውን መረዳት አለባቸው ። እንኳን እርሳቸው፣ ነባሮቹ የብአዴን መሪዎች እነበረከትና አዲሱ እንኳ ከኤርትራና ሱዳን ጉዳይ የተገለሉ ነበሩ። በወያኔ ፖሊትቢሮ ብቻ የተያዘ የውስጥ ጉዳይ ነበር ። በወያኔ 40ኛ አመት በአል ላይ መቀሌ ላይ ንግግር ያደረገው ሱዳናዊ፣ ” እኔም ወያኔ ነኝ” ብሎ ከፈከረ በኋላ፣ መለሰ ለመጨረሻው ከደርግ ጋር ድርድር ወደ ለንደን ከማቅናቱ በፊት፣ ካርቱም ላይ ፕሬዚደንቱ ቢሮ መሬት ላይ ፈርሸው ስላደረጓቸው ውይይቶች የነበረውን ትዝታ አካፍሏል ። በዚያ ወቅት፣ የጋራ ጠላታቸው የሆነውን የአማራ ህዝብ ለማዳከም መለስ የገባው ቃል ሊኖር ይችላል ። ምናልባትም አዲሱን መንግስት በማቋቋም ስም ወያኔ ከሱዳን የበላው መሃያ ሊኖርም ይችላል። ብዙ ያልተፈተሹና የማናውቃቸው ጉዳዮች ስላሉ፣ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያለኝ ምክር፣ እጃቸውን ከዚህ ጉዳይ ውስጥ ማውጣትና፣ የወሰን ድርድር ለማድረግ የሚያሰገድድ ሁኔታ ፈፅሞ ባለመኖሩ፣ ጉዳዩ ባለበት እንዲቀጥል መተው የተሻለ ነው ብዬ አስባለሁ ። ሃገራቸውን የሚጎዳ ነገር ውስጥ እጃቸውን ባያስገቡ ይመረጣል ።
ተቃዋሚዎች ከራሳቸው ይልቅ ኢሕአዴግን ያምኑ ይሆን? (በፈቃዱ ዘ ሃይሉ) November 8, 2017
ንጉሠ ነገሥት የሌላቸው የኢትዮጵያ ንጉሦች – ይገረም አለሙ November 8, 2017
የመንግስትን ስልጣን ለመረከብ ዝግጁነት አለ ወይ? (ከሙሉቀን ገበየው) November 8, 2017
መሐመድ አል-አሙዲን ጨምሮ ሳዑዲ አረቢያ 38 ሰዎችን አሰረች November 8, 2017
የኛ ሰው በሄግ ችሎት – ክንፉ አሰፋ (ዘ ሄግ) November 8, 2017
የአማራና ኦሮሞ ትብብር ሕወሃቶችን ለቁጭትና ቅዠት የሚዳርገው ለምንድነው? – በስዩም ተሾመ November 8, 2017
የአገዛዙ ደኅንነቶች የኮሎኔል ደመቀን የ5 ዓመት ሕጻን ልጅ ለመጥለፍ ሙከራ አደረጉ _ በኮሎኔሉ ላይ 9 የሰለጠኑ ምስክሮች ቃላቸውን ሰጥተዋል July 13, 2017
በደ/ታቦር ኢየሱስ መናኝ ባሕታዊ በፖሊስ ታፍነው ተወሰዱ፤ – ሙሉቀን ተስፋው July 13, 2017
እንዴት በይፋ ቅድሚያ አዳዲስ ግምገማዎች ቅድሚያ ይፈልጋል ቆሮንቶስ.
← ለማሟላት. የሚሰጡዋቸውን ምዝገባ
ነፃ የሚሰጡዋቸውን. — (ነጻ ሙከራዎች) →
አድራሻችን ኮተቤ ወሰን አካባቢ ሕብረት ህንፃ ላይ ያገኙናል። Original victoria secret's body splash እኛ ጋር ያገኛሉ። 3 እና ከ3 በላይ ለሚወስዱ ልዩ ቅናሽ እናደርጋለን። ብዛት ለሚወስዱ ደግሞ በ 350 ብር እናስረክቦታለን። Telegram ቻናላችንን ይቀላቀሉን http://t.me/SAFEWAYMARKET
ምን እየሰሩ ነው?
በኅብረተሰብ ጤና ዘርፍ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የሚባል ለውጥ ካስመዘገቡ አገሮች ተርታ ትመደባለች፡፡ የጤና አገልግሎትን በቀበሌ ደረጃ ለማስፋፋት፣ በተለይም በዝቅተኛ የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ የሚገኘውን የኅብረተሰብ ክፍል ማዕከል ያደረገና በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና የተቸረውን የጤና ኤክስቴንሽን መርሐ ግብር ተግባራዊ በማድረግ፣ የዓለም መንግሥታት ድርጅትን የጤና የሚሊኒየም ግቦችን ለማሳካት ችላለች፡፡ እንደ አብዛኛው ታዳጊ አገሮች ሁሉ ባለፉት ዓመታት የመንግሥት የጤና ፕሮግራሞችና የአጋር ድርጅት ትኩረቶች ውስጥ ወባ፣ ኤችአይቪ/ኤድስና ሳንባ ነቀርሳ የመሳሰሉ ተላላፊ በሽታዎች የመከላከልና ቁጥጥር ሥራ፣ እንዲሁም የሕፃናትና እናቶች ጤናን ማሻሻል በዋናነት ይጠቀሳሉ፡፡ ሆኖም ግን ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ የአገሪቱ የበሽታዎች ሥርጭት ሁኔታ በለውጥ ሒደት ላይ ያለ ሲሆን፣ በተለይም በከተማዎችና በዙሪያቸው ባሉ ሥፍራዎች በመስፋፋት ላይ የሚገኙት የልብ፣ የመተንፈሻ አካላት፣ ስኳርና ካንሰርን የመሳሰሉ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ይጠቀሳሉ፡፡
ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች እየተስፋፉ በመምጣታቸው ምክንያት የጤና ጥበቃ ሚኒስቴርን የትኩረት አቅጣጫ የሚያሳይ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ብሔራዊ የድርጊት መርሐ ግብር ስትራቴጂ (National Strategic Action Plan (NSAP) for Prevention & Control of Non Communicable Diseases in Ethiopia) በ2007 ዓ.ም. ተዘጋጅቷል፡፡ ለእነዚህ በሽታዎች ወይም የጤና ሁኔታዎች ዋነኛ ምክንያቶች ተብለው ከተለዩት መካከልም ማንኛውንም ዓይነት የትምባሆ ምርት መጠቀም፣ ከመጠን በላይ የአልኮል መጠጦችን መውሰድ፣ በቂ የአካል እንቅስቃሴ አለማድረግና ለጤና ተስማሚ ያልሆኑ ምግቦችን ማዘውተር ይጠቀሳሉ፡፡
ከብሔራዊ የድርጊት መርሐ ግብር ስትራቴጂው በተጨማሪ በተመሳሳይ ዓመት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለተላላፊ ላልሆኑ በሽታዎች አጋላጭ ከሚባሉት ዋነኛ መንስዔዎች አንዱ የሆነውን የትምባሆ ምርትን በሚመለከት፣ በዓለም የጤና ድርጅት የወጣውን የትምባሆ ምርት ቁጥጥር ማዕቀፍ ኮንቬንሽን አፅድቋል፡፡ ተግባራዊነቱን የኢትዮጵያ የምግብ፣ መድኃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን እንዲከታተል ኃላፊነት በአዋጅ ቁጥር 822/2007 ሰጥቷል፡፡
በዚህ አዋጅ መሠረት የትምባሆ ምርት ቁጥጥር ማዕቀፍ ኮንቬንሽን ማፅደቂያ በከፊል ለማስፈጸም ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ከሁለት ዓመት በፊት የትምባሆ ቁጥጥር መመርያ አውጥቷል፡፡ የትምባሆ ቁጥጥር መመርያው ከአፈጻጸም ጋር በተያያዘ የተለያዩ ክፍተቶች ቢኖሩበትም፣ ሕፃናትንና ታዳጊ ወጣቶችን በእጅጉ ሱስ አስያዥ የሆነው ኒኮቲክ ለሚባለው ንጥረ ነገር ተጋላጭነት ለመቀነስና ብዛት ባላቸው አገሮች እያደገ በመጣው የትምባሆን ምርት ጣዕም መቀየሪያ እንዳይጨመርበት በመከልከል፣ ሊመሰገን የሚገባው የሕግ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡ ተመሳሳይ የሆኑ ድንጋጌዎች የያዘ የትምባሆ ምርት ቁጥጥርን መመርያ በተወሰኑ ክልሎችና በከተማ አስተዳደር ደረጃ ጭምርም የወጣ ሲሆን፣ ይህን ዓይነት ምርት በክልሎች ውስጥ ለሽያጭ ማቅረብ፣ መሸጥና ማከፋፈል የተከለከለ ነው፡፡
የኢትዮጵያ የምግብ፣ መድኃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን ባወጣው የትምባሆ ምርት ቁጥጥር መመርያ ቁጥር 28/2007 መሠረት፣ የትምባሆ ምርት የሺሻ ትምባሆን ጨምሮ ማንኛውንም በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ከትምባሆ ቅጠል የተዘጋጀ በማጨስ፣ በመሳብ፣ በማኘክ፣ በማሽተት ወይም በሌላ መንገድ የሚወሰድ ንጥረ ነገርን እንዲያካትት ሆኖ ተተርጉሟል፡፡ ይህ ማለት ትምባሆ በስፋት በሚታወቀው የሲጋራ ምርት ብቻ ሳይወሰን የሚታኘክን፣ እንዲሁም የተለያዩ የማጨሻ መሣሪያዎችን በመጠቀም የሚጨስ እንደ ሺሻ ትምባሆ ያለን ምርት ያካትታል፡፡ ይህ የትምባሆ ምርት ትርጉም በተወካዮች ምክር ቤት በፀደቀው የትምባሆ ምርት ቁጥጥር ማዕቀፍ ኮንቬንሽን ጋር የተጣጣመ ሆኖ፣ የሺሻ ትምባሆን ወይም በባህላዊ መንገድ የሚዘጋጅ ጋያን በግልጽ እንዲያካትት ሆኖ ነው የተቀመጠው፡፡
ምንም እንኳን የሺሻ ትምባሆ ቁጥጥር የሚደረግበት ለጤና እጅግ አደገኛ የሆነ ሕጋዊ ምርት ቢሆንም፣ ሕገወጥ የሚያደርገውም ሁኔታ በትምባሆ ምርት ቁጥጥር መመርያ ቁጥር 28/2007 አንቀጽ 10 ሥር ተቀምጧል፡፡ በዚህ አንቀጽ መሠረት የሺሻ ትምባሆ ሳይቀጣጠል ወይም በሚጨስበት ጊዜ ከትምባሆ ጣዕም ውጪ እንደ ፍራፍሬ፣ ቸኮሌት፣ ቫኒላ፣ ማር፣ ከረሜላ፣ ካካዎ፣ ሜንቶል፣ ሚንት፣ የአልኮል መጠጥ፣ ዕፅዋት (Herbs) ወይም ቅመም (Spice) የመሳሰሉ የተለየ (Distinguishable) ጣዕም ወይም ቃና የሚሰጥ ይዘት ያለው ከሆነ ሕገወጥ እንደሆነ መመርያው ይደነግጋል፡፡ ይህንን ክልከላ ተፈጻሚ ለማድረግም ማንኛውም ሰው እንደዚህ ዓይነት ተጨማሪ ጣዕም ያለው ምርት (Flavored Tobacco Product) ወደ አገር ውስጥ ማስገባት፣ በጅምላ መሸጥ፣ ማከፋፈል፣ መሸጥ ወይም ለመሸጥ ማቅረብ እንደማይችል አስቀምጧል፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታ የትምባሆ ምርት ይዘቶች ለጤና የሚጠቅም ወይም ጤና ላይ የሚያስከትልን ጉዳት የሚቀንስ የማስመሰል ውጤት የሚፈጥሩ እንደ ቫይታሚን፣ ፍራፍሬና አትክልቶች፣ አሚኖ አሲድ፣ ጠቃሚ ፋቲ አሲዶችና ኃይልንና ጥንካሬን ከመስጠት ጋር የተያያዙ አነቃቂ ውህዶችን የያዘ የትምባሆ ምርት ወደ አገር ውስጥ ማስገባት፣ በጅምላ መሸጥ፣ ማከፋፈል፣ መሸጥ ወይም ለመሸጥ ማቅረብ እንደማይቻል በሌላ ንዑስ አንቀጽ ሥር ይደነግጋል፡፡