text
stringlengths 0
84.2k
|
---|
የተላከው ወታደርም ለሊት የተኩስ ድምፅ በተሰማበት በኩል ፍለጋውን ቀጠለ ። |
በተለይ ለመጀመሪያ ጊዜ በወርልድ ቴኮንዶ እና በብስክሌት ስፖርቶች ሜዳሊያዎች በዚሁ አህጉራዊ የውድድር መድረክ መገኘቱ ፈርቀዳጅ ታሪክ ነው ። |
ከእርሷ ጋር ቁጭ ብዬ ወሬዋን ለመስማት እንኳን ይከብደኝ የነበርኩ እኔ ፣ በጥቂት ሳምንታት እጄን አንስቼ ከእርሷ ጋር እስከመላፋት ባደረሰኝ አስማተኛ የለውጥ ዋሻ ውስጥ መራችኝ ። |
እንዲህ ዓይነቶቹ ሰዎች ወዳጅ ጓደኛ ብቻ ሳይሆን ዘመድም ቢሆን ፣ በኋላ የተጣሉትና የተቆራረጡት ከሆነ ፣ " ደሞ የሱ ዘር ነኝ ሲል አጠገቤ ቆሟል ፣ በል ዓይኔ እንዳያየው ቅደድልኝ " ማለት ይቀናቸዋል ። |
አቶ ሞቱማ ባሕላዊ አምራቾች ላይ የገበያ ትስስር ለመፍጠር ጥረት ይደረጋል ። |
ወንበር እኮ ነው … " ብሎ ያ ማባባስ ። " |
ለሁለተኛ ጊዜ በሮም ኦሊምፒክ በብስክሌት የተሳተፉት ገረመው ፣ ከአልአዛር ክፍሉ ፣ ተሰማ አሞሳና መንግሥቱ ንጉሤ ጋር በመሆን በቡድን በተደረገው የ100 ኪ.ሜ ግልቢያ በ2 ሰዓት 38 ደቂቃ 34.08 ሰከንድ 28ኛ ደረጃን ተቀዳጅተዋል ። |
በዚሁ መሠረት ምክር ቤቱም ከሶስቱ በሁለቱ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ የሰጠ ሲሆን ፤ አንዱ ጉዳይ ላይ በስፋት ውይይት ተደርጎ ተጨማሪ መረጃዎች እንዲካተቱበት አዟል ። |
እሺ ተይው የሳቸውስ ይቅር " ለሀጥዓን የመጣ ለፃድቃን ይተርፋል " አሉ እስቲ ሌሎቹንስ በዚህ ርካሽ ሰውየው አይን ከመታየት ምን ይከልላቸዋል ? |
በሚል የኤሽያው ዴስክ ባቀረበው ዘገባ ፤ አገሪቱን አደጋ ያንዣበባት አገር ብሏታል ። |
2.4 ሚሊዮን ። |
በአዲስ አበባ ለ60 ዓመት ጠንካራና ልዩ ሱስ የሚያስይዝ ግሩም የማሽን ቡና ለደንበኞቹ በማቅረብ የሚታወቀው ቶሞካ ፣ ሳር ቤት አካባቢ " ጋለሪያ ቶሞካ " የተባለ ቡናና ስዕል የሚቀርብበት የጥበብ እልፍኝ እንደከፈተ አስታወቀ ። |
እንባ ጠባቂ ተቋም በሰጠው ውሳኔ መሠረትም አቤቱታ አቅራቢዎቹ ያቀረቡት ጥያቄ የሕግ መሠረት ካለው ተጣርቶ ምላሽ እንዲሰጣቸው በድጋሚ አሳስቧል ። |
ያሳለፉትን መልካምና ጣፋጭ ዘመን እሰከወዲያኛው ላለማሰብ ቆረጡ ፣ የሞቱትን አባወራ ባፈቀሩበት ልባቸው በጥልቀት ምሰው ለመቅበር ። |
ይህ ቀላል ነገር አልነበረም ። |
የአገሪቱ ጦር ሠራዊት በዓለም አቀፍ ሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች መልካም ዝና እንዳለው አይካድም ። |
ዘመናይ " ማለት ትርጉሙ ምን እንደሆነ ማወቅ ስለነበረብኝ ማለቴ ነው ። |
( ሐ ) ያዕቆብ ያደረገው ምን የተለመደ የሐዘን መግለጫ ነው ? |
ያህዌ ከሁሉ የላቀ ቢሆንም እንኳ ወደ እሱ በጸሎት እንድንቀርብ ያበረታታናል ፤ እንዲሁም ጸሎታችንን እንደሚሰማ ማረጋገጫ ሰጥቶናል ። |
የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ኢዴፓ/ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ኤርሚያስ ባልከው እንዳሉት " የግድብ ግንባታ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ኢዴፓ ድጋፉን እየሰጠ ነው " ። |
በአፋምቦ ወረዳ የአለሳቦሎ ቀበሌ ነዋሪ ወይዘሮ ሀሎ ሁመድ እንደገለፁት ፣ መንግስት ካለፈዉ ክረምት ጀምሮ በድርቁ ሳቢያ ጉዳት እንዳይደርስባቸው የምግብና ዘይት ድጋፍ እያደረገላቸው ይገኛል ። |
( ከበቂ በላይ ጠላት እኮ ነው ያለን ! ) እኔ እንደውም … . መንግሥት በኢትዮጵያ ምድር ከድህነት ውጭ ጠላት ባይኖረው እመርጣለሁ ። |
[ በገጽ 159 ላይ የሚገኝ ሥዕል ] |
በዚህም ኬንያን ፣ ኡጋንዳን ፣ አንጎላንና ቶጎን ጨምሮ በርካታ አገራት ከኢትዮጵያ ልምድ የወሰዱ ሲሆን እንደ ናይጄሪያ ፣ ሌሴቶና ሌሎች አገራትም ልምዱን ለመውሰድ ጥያቄ ማቅረባቸውን ነው የገለጹት ። |
በዚህ ወቅት ብሪታንያ ናይጄሪያን በሰሜን ፣ በምዕራብና በምሥራቅ በመከፋፈል የተለያዩ የአስተዳደር ዘዴዎችን በማስፈን ቆይታ ነበር ። |
ይህም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ26 በመቶ ብልጫ እንዳለው ነው ያስረዱት ። |
ስለዚህ መድሃኒቱን የተላመደ ቲቢ በኤችአይቪ/ ኤድስ ህሙማን ላይ የሚያደርሰውን ተጽእኖ ስንመለከት በሁለቱም በሽታዎች የሚሰጡ አንዳንድ መድሃኒቶች አርስ በርስ በመቃረን ለበሽታው የሚደረገውን ሕክምና ውስብስብ ወይም አስቸጋሪ ሊያደርጉት ይችላሉ ፤ ኤችአይቪ እንዲባባስና ህሙማኑ በሌሎች ተጓዳኝ በሽታዎች እንዲጠቁ ምክንያት ሊሆንም ይችላል ። |
ተደጋጋሚ ስብሰባን ፣ ረጅም ቀጠሮን ይጠይቃል ። |
ስለዚህ ትኩረት ከችግሮች ለመውጣት እንላለን ። |
በሉቺያኖ ነበር የምንሰለጥነው ። |
/ለ/ ለምክትል ዋና ኦዲተር ብር 4 ) |
በንግድ አሠራር ሬጉላቶሪ ዘርፍ ሥር ደግሞ የኤንስፔክሽንና ሪጉላቶሪ ፣ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ እንዲሁም የወጪና ገቢ ዕቃዎች ቁጥጥር ዳይሬክቶሬቶችን ይዞ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል ። |
የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ቲሸርት ደግሞ ይህንኑ የሚገልጽ ነው ። |
ወጣቶች ጉልበታቸውን ለመንግሥቱ አገልግሎት ማዋል የሚችሉት እንዴት ነው ? |
ያቺ በር ከተዘጋች ሌባም ሆነ ኮንትሮባንድ ማለፍ አይችልም ። |
የረጅም እና የአጭር ግጥም የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤቶች ናቸው ። |
ህጉ ይሄንን ያህል ክፍል ይከራያል የሚል አይመስለኝም ፤ እንደሚበቃው መጠን ነው የሚለው ፤ ቤተሰቤ ሃያ ቢሆን የሚበቃኝ ሃያ ክፍል ነው ማለት ነው ። |
በፊፋ የእግር ኳስ ደረጃ ዋልያዎቹ የተሰኘው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ባፋና ባፋና ከሚባለው የደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ ቡድን በ71 ደረጃዎች ዝቅ ብሎ 138ኛ ላይ የሚገኝ ነው ። |
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከመለስ ዜናዊና ከኦሮሚያ መንግስት አመራር አካዳሚዎች ጋር በመተባበር ለቀጣዮቹ 36 ቀናት ባዘጋጀው የተሀድሶ ስልጠና ላይ ከመላ ሀገሪቱ የተውጣጡ 1 ሺህ 500 የመንግስት የልማት ድርጅቶች አመራሮችና ሰራተኞች በሁለት ዙር ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል ። |
የስታዲየሙ " ካታንጋ " መቀመጫ የአፈር መደብ ሳር እየተተከለበት ነው ። |
አርዕስቱ ራሱ የተአምር ባህርይ አለው ። |
ኮኛክ ተቀድቶ ሁሉም አንዳንድ መለኪያ ከጠጡ በሁዋላ ሌሊቱ ተገባድዶ ስለ ነበረ አዝማሪው ውቤና በሻህ ተሰናብተው ሲወጡ ፣ ጌጤና ደመቀች አዛዥን አስነስተው ወዳልጋቸው ወሰዱዋቸው ። |
አሁን የምንጨነቀው ኤክስፖርት ስለማድረግ እንጂ ከውጭ ስለማስገባት አይደለም ። |
ይህም መንግስት ያስቀመጠውን የነጠላ አሀዝ የዋጋ ግሽበት ሊያሳድገው ይችላል ። |
ዘቢዳር አካባቢ ያለው መሬት በጸጥታ ችግር ምክንያት ፤ በዳባ እና ቀጭን አዋሳኝ መሬት ላይ ባለው ደግሞ " መሬቱ ያንተ ስለመሆኑ መረጃ ባለመኖሩ ማልማት አትችልም " በሚል በወረዳው አስተዳደር በመከልከላቸው ምክንያት አለማልማታቸውን ያሰባሰብነው መረጃ ያሳያል ። |
ቤት ይኑሩው አይኑረው ፣ ማደሪያው በየፔንሲዮኑ ይሁን ወይም አይሁን ፣ ተከራይቶ ይሁን ሠርቶ መሆኑ አይታወቅም እንጂ በአለባበሱና በዘመኑ የፀጉር አበጣጠር " ሄር ስታይል " ማንም አይደርስበትም ። |
ኤልሳዕ ፣ ቤንሃዳድና ሃዛኤል ( 7 15 ) |
መቅዳት ማለት ነው ። |
ህዝቡም ይህን ህገወጥ ድርጊት አልሸከምም ይበል ። |
ግብፅ ራሷን ካገለለችበት የዓባይ ቀን ክብረ በዓል ተመልሳለች |
ምክንያቱም ልማትን ማፋጠንና ዕድገትን ዘላቂ ማድረግ የሚቻለው በአገሮቹ መካከል እርስ በርስ መተሳሰርና መደጋገፍ የሚያስችል ውህደትና ቅንጅት በመፍጠር ነው ። |
( ማቴዎስ 7 12 ) ይሁን እንጂ እውነተኛው ሃይማኖት በጎ ዓላማን በማራመድ ብቻ የተወሰነ ነው ? |
የአውሮፓ ኅብረት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2009 ጀምሮ የክዋሜ ንክሩማህን ክብር የሚዘክር " የክዋሜ ንክሩማህ ሳይንሳዊ ሽልማት " ሲያበረክት መቆየቱ ይታወሳል ። |
ታኅሣሥ 15 ቀን 1922ዓ.ም ከአባታቸው ለማ አሰግድ እና ከእናታቸው ወይዘሮ ላቀች አድምቄ በአማራ ክልል ተጉለትና ቡልጋ አውራጃ በሞረትና ጅሩ ወረዳ ልዩ ስሙ ጅሁር መድሃኒዓለም እንቡስ አምባ መንደር ለቤተሰባቸው የመጀመሪያ ልጅ ሆነው ይህችን ምድር ተቀላቀሉ አርበኛ አስረሳኸኝ ለማ ። |
ከዚያ ይልቅም በመልክዓምድራዊ አቀማመጥ ቢከለል አሁን እዚህም እዚያም የሚስተዋሉትን ግጭቶችና ቅሬታዎች መፍታት ያስችላል ። |
እርስ በርስ እየተያዩ ከንፈራቸውን ያንቀሳቅሳሉ ። |
" የነ ቶሎ ቶሎ ቤት ግድግዳው ሰንበሌጥ " እንዲሉ ይሆናል ማለትህ ነው አይደል ? |
መናደዴ ገብቷታል ። |
ለዚህ ችግር መከሰት ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረግ የሚታወቀው በህክምና ቁጥጥር ሥር ያልዋለ የደም ግፊት በሽታ ነው ። |
የክልሉ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አብረሀ ኪሮስ በመድረኩ ላይ ያቀረቡት ጥናታዊ ጽሁፍ እንዳመለከተው በክልሉ ከ150 ሺህ የሚበልጡ ሕጻናት በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ቢገኙም በሚፈለገው ደረጃ ስለመብታቸው የሚሰራ ግለሰብም ሆነ ተቋም አልተፈጠረም ። |
መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን ፣ ፍትሕ በእኩልነት ተደራሽ እንዲሆን ፣ የአገርና የሕዝብ ጠንቅ የሆነው ሙስና እንዲጠፋ ፣ ፀረ ዴሞክራሲያዊና አምባገነናዊ አስተሳሰቦች ቦታ እንዳይኖራቸው ከእያንዳንዱ ዜጋ እስከ አገር መሪዎች ድረስ የመስጠትና የማካፈል መንፈስ ሊያድርባቸው ይገባል ። |
መውጫ በሌለው የድህነት አዙሪት ውስጥ በመግባት ተስፋ ቆራጭነትና ጨለምተኝነት የሚያስከትሉትን ፋይዳ የለሸ ጦርነትና እልቂት ለመከላከልም ከቀደመውም በላይ መስራት ያስፈልጋል ። |
አላህ ጀዛህን ይክፈልህ … በረካ ሁን … ያሳድግህ … ከውስል ድረስ … ዑምርህን ያስረዝመው … . " እያሉ ከሱቁ እስከሚርቁ ድረስ ምርቃት ሲያዘንቡበት ዘካርያስ ገረመው ። |
መልሱ የእኛ ይሁን የሌላ እያጣራ ይሆናላ ፤ " መጨረሻ ባለመነጽሯ ታብራራለች ። " |
የከብት ዕድሜና ጤና ይጨምራል ። |
የኢኮኖሚ ህይወቱ ያስመረረው ህዝብ ለብዙ ነገሮች ጆሮው ዝግ ይሆናል ። |
ጥ/ ( IUD ) ሉፕ የተባለው የእርግዝና መከላከያ አንዳንዴ እርግዝናን ሳይከላከል ከልጅ ጋር አብሮ ይወለዳል ? |
ሥራን ሳይንቅ ለመስራት ዝግጁ ከሆነ የማያሸንፍበት ምንም ምክንያት የለም ። |
የሚቸኩሉ ቱሪስቶች ሽሮ ሜዳ ፣ ጥቁር አንበሳ አካባቢ ወይም መርካቶ ለመዘዋወር ጊዜ አይኖራቸውም ። |
እኔም በቅርብ ጊዜ እጎበኛችኋለሁ ' በማለት ለፊልጵስዩስ ክርስቲያኖች ገልጾላቸዋል ። |
ከአንዱ ዕቃ ወደ ሌላው ዕቃ አልተገላበጡም ፤ በግዞትም ተወስደው አያውቁም ። |
ኅብረት ባንክ የዋና መሥሪያ ቤቱን ሕንፃ ግንባታ ለቻይናው ኩባንያ የሰጠው ግንባታውን ለማካሄድ ባንኩ አውጥቶት በነበረው ጨረታ ተሳትፎ በማሸነፉ ነው ። |
ብዙዎቹ ሱቆች በፍርግርግ ብረት በትላልቅ ጓጉንቸር ቁልፎች ይከረቻቸማሉ ። |
" እውነትዎን ነው እኛም ሰፈር እንዲሁ ነው ፤ ሰሞኑን ደህና ነበሩ ፤ ይህንን ሰሞን ደግሞ እንደገና እየተቸገርን ነው በአንድ ሳምንት ሶስት እና አራት ቀን በመደዳ እልም ይላል ፤ እንዴት ነው ነገሩ ሲባል ' የእንትን ችግር የለም ' ይባላል ፤ ግን ችግሩ ፤ ፊዩዝ ፤ ነፋስ ፤ መብረቅ ፤ ዛፍ ፤ … ምክንያቱ ብዙ ነው ! አውነት አሁን የችግሩ ፈጣሪዎች እነዚህ ብቻ ናቸው ? |
ልጃችሁ የተደበቁትን ነገሮች ማግኘት ይችላል ? |
ይህንንም ያረጋገጥኩት በራሴ ላይ በደረሰው በደል ነው ። |
በውድድሩ ላይ ሁለተኛ በመሆን የገባችው ኬንያዊቷ ቫዮላ ኪብዎት ስትሆን ፤ የገባችበት 14 29.50 የሆነ ሰዓትም ቀድሞ ከነበራት የአራት ሰከንዶች ብልጫ በማሳየቱ የግሏ ምርጥ ሰዓት ሆኖ ተመዝግቦላታል ። |
የኪነ ህንፃ ጥበብ ልክ እንደ ሙዚቃ የአለም ቋንቋ ነው ። |
ምክንያቱም የእነዚህ አገራት ስፖርት አፍቃሪያን ትንግርት የሚሆንባቸው ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፋቸው ሳይሆን የውድድሩ ሻምፒዮና መሆናቸው ነው ። |
ለዘብ ያሉ ተቃውሞዎችን ማስተናገድ ያቃተው ሥርዓት ሁሉንም ነገር ወዳልተገባ አቅጣጫ እየገፋ ነው ተብሎ በተደጋጋሚ ሲተች ፣ መንግሥት ቆም ብሎ ችግሮችን መመርመር አለበት ። |
በአካባቢው ያለው ይህ የውሀ ሀብት እና የመሬቱ ተራራማ አለመሆን ለመስኖ እርሻ ልማት አመቺ ያደርገዋል ። |
መቼና የት ቦታ ላይ መሸጥ አለበት ? |
በመንግሥትና በሕዝብ ይሰራሉ ያገለግላሉ ተብለው ታምኖባቸው የተቀምጡ ሹሞች ሕዝብ በምርጫ ድምጹን ሰጥቶ እንደመረጣቸው በመዘን ጋት ስለሚፈጽሙት በደልና ማንገላታት ፤ በመሬት ይዞታ ላይ ሲሰራ የነበረው ወንጀል ፤ የመንግሥትን ቤት የይዞታ ካርታ እያወጡ በግለሰቦች ስም እያዛወሩ መቸብቸባቸው ሁሉ በሕዝባዊ ንቅናቄው ተጋልጧል ። |
ደስታችሁ የተሟላ እንዲሆን ጠይቁ ፤ ትቀበላላችሁ ። " |
ፈላጊዎቹ የቀድሞ ክለቡ ኢንተር ሚላንና በልጅነቴ የምደግፈው ክለብ ያለው ኤሲ ሚላን ናቸው ። |
ባላት ፈጣን ሰዓት ባህሬናዊቷን ተከትላ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው አትሌት ሩቲ አጋ ስትሆን ፤ ያለፈው ዓመት የሊዝበን ግማሽ ማራቶን ውድድር አሸናፊ አትሌት ነበረች ። |
ሙች እውነቴን እኮ ነው " እላታለሁ " እኔ ሀብት ፣ ስልጣን ፣ ዕውቀት … ለፍቼ ፣ ደክሜ ላገኝ እችላለሁ ስል አስባለሁ ። |
( መዝ. 103 10 ) ያህዌ ግን ትኩረት ያደረገው በመልካም ጎናችን ላይ ነው ። |
የምግብ አለመስማማት በተለያዩ ምግቦች የተነሳ ሊከሰት ይችላል ፤ ከእነዚህ መካከል በጣም የተለመዱት ወተትና የወተት ተዋጽኦዎች ፣ ስንዴ ፣ ግሉተን ፣ አልኮልና እርሾ ናቸው ። |
ብሎ መጠየቅ ፖለቲከኛ ስለሚያስብል የግቢያችን ኮሚቴዎች አንድም ቀን በየሳምንቱ ሲሰበሰቡ አንስተው የተወያዩበት አይመስለኝም ። |
ዲሚያን በምሽቱ ኮንሰርት ወደ 14 የሚጠጉ የራሱን ስራዎች በላቀ ሀይልና ብቃት አቀንቅኗል ። |
በአሰቃቂ ሁኔታ የሚገደልበት ጊዜ በጣም እንደተቃረበ ተሰምቶታል ። |
ልክ ነዋ … ከዚህ መረጃ በኋላ የሚከተለው ጥያቄ … " ፀሐይ በስተምሥራቅ ከመውጣቷ ጀርባ የእነማን እጅ አለበት … " የሚል ይሆናላ ! ( ስሙኝማ … እዚሀ አገር መሀል ላይ ያለው ትልቅ ግራጫ ስፍራ ጠፍቶ … አለ አይደል … ሁሉም ነገር ' ወይ ጥቁር ፣ ወይ ነጭ ' ከሆነ ከራረመ ። " |
በደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል የሚገኘው የኮንሶ ወረዳ ከ234 ሺ በላይ ነዋሪዎች አሉት ። |
በባህሪያቸው ህዝባዊ የሆኑ መንግሥታት ፈጣንና መሠረታዊ ለውጥ የሚያስመዘግቡ ናቸው ። |
በመሆኑም በተለያዩ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የሚገኙ የ " ኤ " ( በሁለተኛ ዲግሪ ) ደረጃ ላይ ያሉ አሰልጣኞች እያሰለጠኗቸው ይገኛሉ ። |
የከተማዋ ምክትል ከንቲባና የአቅም ግንባታ ቢሮ ኃላፊ ከሃያ በላይ እህት ከተሞች በበዓሉ ላይ ይሣተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል |
የምንጠብቀው ጥበቃን ነው ። |
እነሱም ከጥቂት ጊዜ በኋላ ሥራውን ለቀው ሲሄዱ ይታያል ። |
በዚህ ድረ ገጽ ስለኤችአይቪ ኤይድስ አንዳንድ እውነታዎች በሚል ተመዝግቦአል ። |