doc_no
int64
1
12.6k
doc_text
stringlengths
81
395k
relevant_topic_nos
sequencelengths
0
1
relevant_topic_titles
sequencelengths
0
1
relevant_topic_descriptions
sequencelengths
0
1
relevant_topic_narratives
sequencelengths
0
1
12,501
7  ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ አንተን ለፈርዖን እንደ አምላክ አድርጌሃለሁ፤ የገዛ ወንድምህ አሮን ደግሞ የአንተ ነቢይ ይሆናል። 2  አንተም የማዝህን ሁሉ ደግመህ ትናገራለህ፤ ወንድምህ አሮንም ለፈርዖን ይነግረዋል፤ እሱም እስራኤላውያን ከምድሩ እንዲወጡ ይለቃቸዋል። 3  እኔ ደግሞ የፈርዖን ልብ እንዲደነድን እፈቅዳለሁ፤ በግብፅ ምድርም ምልክቶቼንና ተአምራቴን አበዛለሁ። 4  ፈርዖን ግን አይሰማችሁም፤ እኔም በግብፅ ምድር ላይ እጄን አሳርፋለሁ፤ ሠራዊቴን ይኸውም ሕዝቤ የሆኑትን እስራኤላውያንን በታላቅ ፍርድ ከግብፅ ምድር አወጣቸዋለሁ። 5  በግብፅ ላይ እጄን ስዘረጋና እስራኤላውያንን ከመካከላቸው ሳወጣ ግብፃውያን እኔ ይሖዋ መሆኔን በእርግጥ ያውቃሉ።” 6  ሙሴና አሮን ይሖዋ እንዳዘዛቸው አደረጉ፤ ልክ እንደተባሉት አደረጉ። 7  ከፈርዖን ጋር በተነጋገሩበት ጊዜ ሙሴ የ80 ዓመት ሰው፣ አሮን ደግሞ የ83 ዓመት ሰው ነበር። 8  በዚህ ጊዜ ይሖዋ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፦ 9  “ምናልባት ፈርዖን ‘እስቲ ተአምር አሳዩ’ ቢላችሁ አሮንን ‘በትርህን ወስደህ በፈርዖን ፊት ጣለው’ በለው። በትሩም ትልቅ እባብ ይሆናል።” 10  ስለሆነም ሙሴና አሮን ወደ ፈርዖን ገብተው ልክ ይሖዋ እንዳዘዛቸው አደረጉ። አሮንም በትሩን በፈርዖንና በአገልጋዮቹ ፊት ጣለው፤ በትሩም ትልቅ እባብ ሆነ። 11  ይሁንና ፈርዖን ጠቢባኑንና መተተኞቹን ጠራ፤ አስማት የሚሠሩ የግብፅ ካህናትም በአስማታቸው ተመሳሳይ ነገር አደረጉ። 12  እያንዳንዳቸውም በትራቸውን ጣሉ፤ በትሮቹም ትላልቅ እባቦች ሆኑ፤ ይሁን እንጂ የአሮን በትር የእነሱን በትሮች ዋጠ። 13  ያም ሆኖ የፈርዖን ልብ ደነደነ፤ ልክ ይሖዋ እንዳለውም ያሉትን ነገር አልሰማቸውም። 14  ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “የፈርዖን ልብ ደንድኗል። እሱም ሕዝቡን ለመልቀቅ እንቢተኛ ሆኗል። 15  በማለዳ ወደ ፈርዖን ሂድ። እሱም ወደ ውኃው ይወርዳል! አንተም እሱን ለማግኘት በአባይ ወንዝ ዳር ቁም፤ ወደ እባብ ተለውጦ የነበረውንም በትር በእጅህ ያዝ። 16  እንዲህም በለው፦ ‘የዕብራውያን አምላክ ይሖዋ ወደ አንተ ልኮኛል፤ እሱም “በምድረ በዳ እንዲያገለግለኝ ሕዝቤን ልቀቅ” ብሎሃል፤ ይኸው አንተ ግን እስካሁን ድረስ አልታዘዝክም። 17  እንግዲህ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ በዚህ ታውቃለህ። ይኸው በበትሬ በአባይ ወንዝ ውስጥ ያለውን ውኃ እመታለሁ፤ ውኃውም ወደ ደም ይለወጣል። 18  በአባይ ውስጥ ያሉት ዓሣዎች ይሞታሉ፤ አባይም ይከረፋል፤ ግብፃውያንም ከአባይ ወንዝ ውኃ መጠጣት አይችሉም።”’” 19  ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “አሮንን እንዲህ በለው፦ ‘የግብፅ ውኃዎች ይኸውም ወንዞቿ፣ የመስኖ ቦዮቿ፣ ረግረጋማ ቦታዎቿና የተጠራቀሙት ውኃዎቿ ሁሉ ወደ ደም እንዲለወጡ በትርህን ወስደህ በእነሱ ላይ እጅህን ዘርጋ።’ በመላው የግብፅ ምድር ላይ ሌላው ቀርቶ ከእንጨትና ከድንጋይ በተሠሩ ዕቃዎች ውስጥ ደም ይሆናል።” 20  ሙሴና አሮን ወዲያውኑ ልክ ይሖዋ እንዳዘዛቸው አደረጉ። እሱም ፈርዖንና አገልጋዮቹ እያዩ በትሩን አንስቶ በአባይ ወንዝ ውስጥ ያለውን ውኃ መታ፤ በወንዙ ውስጥ የነበረውም ውኃ በሙሉ ወደ ደም ተለወጠ። 21  በወንዙ ውስጥ የነበሩት ዓሣዎች ሞቱ፤ ወንዙም መከርፋት ጀመረ፤ ግብፃውያንም ከአባይ ወንዝ ውኃ መጠጣት አልቻሉም፤ በመላው የግብፅ ምድር ላይም ደም ነበር። 22  ይሁንና አስማት የሚሠሩ የግብፅ ካህናትም በሚስጥራዊ ጥበባቸው ተመሳሳይ ነገር አደረጉ፤ በመሆኑም የፈርዖን ልብ ደነደነ፤ ልክ ይሖዋ እንዳለውም እነሱን ለመስማት እንቢተኛ ሆነ። 23  ከዚያም ፈርዖን ተመልሶ ወደ ቤቱ ሄደ፤ ይህን ከቁም ነገር አልቆጠረውም። 24  ግብፃውያን ሁሉ ከአባይ ወንዝ ውኃ መጠጣት ስላልቻሉ የሚጠጣ ውኃ ለማግኘት የአባይን ዳርቻ ተከትለው ጉድጓዶችን ይቆፍሩ ነበር። 25  ይሖዋ አባይን ከመታ ሰባት ቀን አለፈ።
[]
[]
[]
[]
12,502
8  ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ወደ ፈርዖን ገብተህ እንዲህ በለው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እንዲያገለግለኝ ሕዝቤን ልቀቅ። 2  እነሱን ለመልቀቅ አሁንም ፈቃደኛ የማትሆን ከሆነ ምድርህን በሙሉ በእንቁራሪት መቅሰፍት እመታለሁ። 3  የአባይም ወንዝ በእንቁራሪቶች ይሞላል፤ እነሱም ወጥተው ወደ ቤትህ፣ ወደ መኝታ ክፍልህ ይገባሉ፤ አልጋህም ላይ ይወጣሉ፤ እንዲሁም ወደ አገልጋዮችህ ቤቶች ይገባሉ፤ ሕዝብህም ላይ ይወጣሉ፤ መጋገሪያ ምድጃዎችህና ቡሃቃዎችህም ውስጥ ይገባሉ። 4  እንቁራሪቶቹ በአንተ፣ በሕዝብህና በአገልጋዮችህ ሁሉ ላይ ይወጡባችኋል።”’” 5  በኋላም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “አሮንን እንዲህ በለው፦ ‘እጅህን ሰንዝረህ ወንዞቹን፣ የአባይ ወንዝ የመስኖ ቦዮቹንና ረግረጋማ ቦታዎቹን በበትርህ በመምታት እንቁራሪቶቹ በግብፅ ምድር ላይ እንዲወጡ አድርግ።’” 6  ስለዚህ አሮን በግብፅ ውኃዎች ላይ እጁን ሰነዘረ፤ እንቁራሪቶቹም እየወጡ የግብፅን ምድር መውረር ጀመሩ። 7  ይሁን እንጂ አስማተኞቹ ካህናትም በሚስጥራዊ ጥበባቸው ተመሳሳይ ነገር ፈጸሙ፤ እነሱም እንቁራሪቶች በግብፅ ምድር ላይ እንዲወጡ አደረጉ። 8  ከዚያም ፈርዖን ሙሴንና አሮንን ጠርቶ “ሕዝቡ ለይሖዋ መሥዋዕት እንዲያቀርብ መልቀቅ ስለምፈልግ እንቁራሪቶቹን ከእኔም ሆነ ከሕዝቤ ላይ እንዲያስወግድ ይሖዋን ለምኑልኝ” አላቸው። 9  ከዚያም ሙሴ ፈርዖንን እንዲህ አለው፦ “እንቁራሪቶቹ ከአንተ፣ ከአገልጋዮችህ፣ ከሕዝብህና ከቤቶችህ ይወገዱ ዘንድ አምላክን እንድለምንልህ የምትፈልገው መቼ እንደሆነ የመወሰኑን ጉዳይ ለአንተ ትቼዋለሁ። እንቁራሪቶቹ በአባይ ወንዝ ውስጥ ብቻ ተወስነው ይቀራሉ።” 10  እሱም “ነገ ይሁን” አለው። በመሆኑም ሙሴ እንዲህ አለው፦ “እንደ አምላካችን እንደ ይሖዋ ያለ ማንም እንደሌለ እንድታውቅ ልክ እንዳልከው ይሆናል። 11  እንቁራሪቶቹ ከአንተ፣ ከቤቶችህ፣ ከአገልጋዮችህና ከሕዝቦችህ ይወገዳሉ። በአባይ ወንዝ ውስጥ ብቻ ተወስነው ይቀራሉ።” 12  ሙሴና አሮንም ከፈርዖን ፊት ወጥተው ሄዱ፤ ሙሴም ይሖዋ በፈርዖን ላይ ያመጣቸውን እንቁራሪቶች አስመልክቶ ወደ እሱ ጮኸ። 13  ይሖዋም ሙሴ እንደጠየቀው አደረገ፤ እንቁራሪቶቹም በየቤቱ፣ በየግቢውና በየሜዳው መሞት ጀመሩ። 14  እነሱም እንቁራሪቶቹን በየቦታው ከመሯቸው፤ ምድሪቱም መግማት ጀመረች። 15  ፈርዖንም ችግሩ ጋብ ማለቱን ባየ ጊዜ ልቡን አደነደነ፤ ልክ ይሖዋ እንደተናገረውም እነሱን ለመስማት ፈቃደኛ አልሆነም። 16  በዚህ ጊዜ ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “አሮንን እንዲህ በለው፦ ‘በትርህን ሰንዝረህ የምድርን አቧራ ምታ፤ አቧራውም በመላው የግብፅ ምድር ላይ ትንኝ ይሆናል።’” 17  እነሱም እንዲሁ አደረጉ። አሮን በእጁ የያዘውን በትር ሰንዝሮ የምድርን አቧራ መታ፤ ትንኞቹም ሰዉንም እንስሳውንም ወረሩ። በምድሪቱ ያለው አቧራ ሁሉ በመላው የግብፅ ምድር ላይ ትንኝ ሆነ። 18  አስማተኞቹ ካህናትም ተመሳሳይ ነገር ለመፈጸምና በሚስጥራዊ ጥበባቸው ትንኞች እንዲፈሉ ለማድረግ ሞከሩ፤ ሆኖም አልቻሉም። ትንኞቹ ሰዉንም እንስሳውንም ወርረው ነበር። 19  በመሆኑም አስማተኞቹ ካህናት ፈርዖንን “ይህ የአምላክ ጣት ነው!” አሉት። የፈርዖን ልብ ግን ደነደነ፤ ልክ ይሖዋ እንዳለውም እነሱን አልሰማቸውም። 20  ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “በማለዳ ተነስተህ ፈርዖን ፊት ቁም። እሱም ወደ ውኃው ይወርዳል! አንተም እንዲህ በለው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እንዲያገለግለኝ ሕዝቤን ልቀቅ። 21  ሕዝቤን የማትለቅ ከሆነ ግን በአንተ፣ በአገልጋዮችህና በሕዝብህ ላይ እንዲሁም በቤቶችህ ውስጥ ተናካሽ ዝንብ እለቃለሁ፤ ዝንቦቹም በግብፅ ያሉትን ቤቶች ይሞላሉ፤ አልፎ ተርፎም የቆሙበትን መሬት ይሸፍናሉ። 22  በዚያ ቀን ሕዝቤ የሚኖርበትን የጎሸንን ምድር እለያለሁ። በዚያ ምንም ተናካሽ ዝንብ አይኖርም፤ ይህን በማድረጌም እኔ ይሖዋ በምድሪቱ መካከል እንዳለሁ ታውቃለህ። 23  እኔም በሕዝቤና በሕዝብህ መካከል ልዩነት እንዲኖር አደርጋለሁ። ይህ ምልክት ነገ ይፈጸማል።”’” 24  ይሖዋም እንዳለው አደረገ፤ የተናካሽ ዝንብ መንጋም የፈርዖንን ቤትና የአገልጋዮቹን ቤቶች እንዲሁም መላውን የግብፅ ምድር መውረር ጀመረ። በተናካሽ ዝንቦቹም የተነሳ ምድሪቱ ክፉኛ ተበላሸች። 25  በመጨረሻም ፈርዖን ሙሴንና አሮንን ጠርቶ “ሂዱ፤ በምድሪቱም ለአምላካችሁ መሥዋዕት ሠዉ” አላቸው። 26  ሙሴ ግን እንዲህ አለው፦ “ይሄማ ተገቢ አይደለም፤ ምክንያቱም እኛ ለአምላካችን ለይሖዋ መሥዋዕት የምናደርገው ነገር ለግብፃውያን አስጸያፊ ነው። ታዲያ ግብፃውያን የሚጸየፉትን መሥዋዕት እዚያው እነሱ እያዩን ብናቀርብ አይወግሩንም? 27  ስለዚህ ወደ ምድረ በዳው የሦስት ቀን መንገድ እንጓዛለን፤ በዚያም አምላካችን ይሖዋ ባለን መሠረት ለእሱ መሥዋዕት እናቀርባለን።” 28  በዚህ ጊዜ ፈርዖን እንዲህ አለ፦ “በምድረ በዳ ለአምላካችሁ ለይሖዋ መሥዋዕት እንድታቀርቡ እለቃችኋለሁ። ብቻ ብዙ ርቃችሁ መሄድ የለባችሁም። ስለ እኔም ለምኑልኝ።” 29  ከዚያም ሙሴ እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ አሁን ከአንተ ተለይቼ እወጣለሁ፤ ይሖዋንም እለምናለሁ፤ ተናካሽ ዝንቦቹም በነገው ዕለት ከፈርዖን፣ ከአገልጋዮቹና ከሕዝቡ ይወገዳሉ። ሆኖም ፈርዖን፣ ሕዝቡ ለይሖዋ መሥዋዕት ለማቅረብ እንዳይሄድ በመከልከል ሊያታልለን መሞከሩን ይተው።” 30  ከዚያም ሙሴ ከፈርዖን ፊት ወጥቶ በመሄድ ይሖዋን ለመነ። 31  ይሖዋም ሙሴ እንዳለው አደረገ፤ ተናካሽ ዝንቦቹም ከፈርዖን፣ ከአገልጋዮቹና ከሕዝቡ ተወገዱ። አንድም ዝንብ አልቀረም። 32  ሆኖም ፈርዖን እንደገና ልቡን አደነደነ፤ ሕዝቡንም ለመልቀቅ ፈቃደኛ አልሆነም።
[]
[]
[]
[]
12,503
9  ስለሆነም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ወደ ፈርዖን ገብተህ እንዲህ በለው፦ ‘የዕብራውያን አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እንዲያገለግለኝ ሕዝቤን ልቀቅ። 2  እነሱን ለመልቀቅ እንቢተኛ የምትሆንና እንዳይሄዱ የምትከለክላቸው ከሆነ 3  የይሖዋ እጅ በመስክ ያሉትን ከብቶችህን ይመታል። በፈረሶች፣ በአህዮች፣ በግመሎች፣ በበሬዎች፣ በላሞችና በመንጎች ላይ አጥፊ መቅሰፍት ይወርዳል። 4  ይሖዋም በእስራኤል ከብቶችና በግብፅ ከብቶች መካከል ልዩነት እንዲኖር ያደርጋል፤ ከእስራኤላውያን ከብቶች መካከል አንድ እንኳ አይሞትም።”’” 5  ከዚህም በላይ ይሖዋ “በነገው ዕለት እኔ ይሖዋ በምድሪቱ ላይ ይህን አደርጋለሁ” በማለት ቀን ቆርጧል። 6  ይሖዋም በማግስቱ ይህን አደረገ፤ የግብፅ ከብት ሁሉ ይሞት ጀመር፤ ከእስራኤላውያን ከብቶች መካከል ግን አንድ እንኳ አልሞተም። 7  ፈርዖንም ሁኔታውን ሲያጣራ ከእስራኤላውያን ከብቶች መካከል አንድ እንኳ አለመሞቱን ተገነዘበ። ያም ሆኖ ግን የፈርዖን ልብ ደነደነ፤ ሕዝቡንም አለቀቀም። 8  ከዚያም ይሖዋ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፦ “ከሸክላ መተኮሻ ምድጃ እፍኝ ሙሉ ጥቀርሻ ውሰዱ፤ ሙሴም ጥቀርሻውን በፈርዖን ፊት ወደ ሰማይ ይበትነው። 9  ጥቀርሻውም በመላው የግብፅ ምድር ላይ አቧራ ይሆናል፤ ከዚያም በመላው የግብፅ ምድር ባለ ሰውና እንስሳ ላይ መግል የያዘ እባጭ ሆኖ ይወጣል።” 10  እነሱም ከሸክላ መተኮሻ ምድጃ ጥቀርሻ ወስደው ፈርዖን ፊት ቆሙ፤ ሙሴም ጥቀርሻውን ወደ ሰማይ በተነው፤ ጥቀርሻውም በሰውና በእንስሳ ላይ መግል የያዘ እባጭ ሆኖ ወጣ። 11  አስማተኞቹ ካህናት በእባጩ የተነሳ ሙሴ ፊት ሊቆሙ አልቻሉም፤ ምክንያቱም እባጩ በአስማተኞቹ ካህናትና በሁሉም ግብፃውያን ላይ ወጥቶ ነበር። 12  ሆኖም ይሖዋ የፈርዖን ልብ እንዲደነድን ፈቀደ፤ ፈርዖንም ልክ ይሖዋ ለሙሴ እንደነገረው እነሱን አልሰማቸውም። 13  ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “በማለዳ ተነስተህ ፈርዖን ፊት ቁም፤ እንዲህም በለው፦ ‘የዕብራውያን አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እንዲያገለግለኝ ሕዝቤን ልቀቅ። 14  ምክንያቱም በመላው ምድር ላይ እንደ እኔ ያለ ማንም እንደሌለ እንድታውቅ ልብህን፣ አገልጋዮችህንና ሕዝብህን ለመምታት መቅሰፍቴን በሙሉ አሁን አወርዳለሁ። 15  እስካሁን እጄን ዘርግቼ አንተንም ሆነ ሕዝብህን አጥፊ በሆነ መቅሰፍት በመታኋችሁ ነበር፤ አንተም ከምድር ገጽ ተጠራርገህ በጠፋህ ነበር። 16  ሆኖም ኃይሌን እንዳሳይህና ስሜ በመላው ምድር እንዲታወጅ ስል በሕይወት አቆይቼሃለሁ። 17  ሕዝቤን አለቅም በማለት አሁንም በእነሱ ላይ እንደታበይክ ነህ? 18  እንግዲህ በነገው ዕለት በዚህ ሰዓት ገደማ ግብፅ ከተመሠረተችበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ ሆኖ የማያውቅ እጅግ ታላቅ የበረዶ ውርጅብኝ አዘንባለሁ። 19  ስለዚህ አሁን መልእክት ልከህ በመስክ ላይ የተሰማሩትን ከብቶችህንና የአንተ የሆኑትን ሁሉ ወደ መጠለያ እንዲገቡ አድርግ። በመስክ የተገኘና ወደ ቤት ያልገባ ማንኛውም ሰውና እንስሳ በረዶው ይወርድበትና ይሞታል።”’” 20  ከፈርዖን አገልጋዮች መካከል የይሖዋን ቃል የፈሩ ሁሉ አገልጋዮቻቸውንና ከብቶቻቸውን በፍጥነት ወደ ቤት አስገቡ፤ 21  ሆኖም የይሖዋን ቃል ከቁም ነገር ያልቆጠሩት ሁሉ አገልጋዮቻቸውንና ከብቶቻቸውን እዚያው መስክ ላይ እንዳሉ ተዉአቸው። 22  በዚህ ጊዜ ይሖዋ ሙሴን “በመላው የግብፅ ምድር ላይ ይኸውም በሰው፣ በእንስሳና በግብፅ ምድር ላይ በበቀለው ተክል ሁሉ ላይ በረዶ እንዲወርድ እጅህን ወደ ሰማይ ዘርጋ” አለው። 23  በመሆኑም ሙሴ በትሩን ወደ ሰማይ አነሳ፤ ይሖዋም ነጎድጓድና በረዶ ላከ፤ እሳትም በምድር ላይ ወረደ፤ ይሖዋ በግብፅ ምድር ላይ ያለማቋረጥ በረዶ እንዲወርድ አደረገ። 24  በረዶም ወረደ፤ በበረዶውም መካከል የእሳት ብልጭታ ነበር። በረዶውም እጅግ ከባድ ነበር፤ ግብፅ እንደ አገር ሆና ከተመሠረተችበት ጊዜ አንስቶ በዚያች ምድር ላይ እንዲህ ያለ በረዶ ተከስቶ አያውቅም። 25  በረዶው ከሰው አንስቶ እስከ እንስሳ ድረስ በግብፅ ምድር በመስክ ላይ የነበረውን ማንኛውንም ነገር መታ፤ ዕፀዋቱን ሁሉና በሜዳ ላይ ያለውን ዛፍ በሙሉ አወደመ። 26  በረዶ ያልወረደው እስራኤላውያን በሚኖሩበት በጎሸን ምድር ብቻ ነበር። 27  ስለሆነም ፈርዖን ሙሴንና አሮንን አስጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “አሁንስ በድያለሁ። ይሖዋ ጻድቅ ነው፤ ጥፋተኞቹ እኔና ሕዝቤ ነን። 28  አምላክ ያመጣው ነጎድጓድና በረዶ እንዲቆም ይሖዋን ለምኑልኝ። እኔም እናንተን ለመልቀቅ ፈቃደኛ እሆናለሁ፤ ከአሁን በኋላ እዚህ አትቆዩም።” 29  በመሆኑም ሙሴ እንዲህ አለው፦ “ልክ ከከተማዋ እንደወጣሁ እጆቼን በይሖዋ ፊት እዘረጋለሁ። ምድር የይሖዋ እንደሆነች እንድታውቅም ነጎድጓዱ ይቆማል፤ በረዶውም ከዚያ በኋላ አይወርድም። 30  ሆኖም አንተም ሆንክ አገልጋዮችህ ይህ ከሆነ በኋላም እንኳ ይሖዋ አምላክን እንደማትፈሩ አውቃለሁ።” 31  በዚህ ጊዜ ገብሱ አሽቶ፣ ተልባውም አብቦ ስለነበር ተልባውና ገብሱ ከጥቅም ውጭ ሆኑ። 32  ስንዴውና አጃው ግን ወቅታቸው ገና ስለነበር ጉዳት አልደረሰባቸውም። 33  ሙሴም ከፈርዖን ተለይቶ ከከተማዋ ወጣ፤ እጆቹንም በይሖዋ ፊት ዘረጋ፤ ነጎድጓዱና በረዶውም ቆመ፤ ዝናቡም በምድር ላይ መዝነቡን አቆመ። 34  ፈርዖንም ዝናቡ፣ በረዶውና ነጎድጓዱ መቆሙን ባየ ጊዜ እንደገና ኃጢአት ሠራ፤ እሱም ሆነ አገልጋዮቹ ልባቸውን አደነደኑ። 35  የፈርዖን ልብ ደነደነ፤ ልክ ይሖዋ በሙሴ አማካኝነት እንደተናገረውም እስራኤላውያንን አለቀቀም።
[]
[]
[]
[]
12,504
1  በመጀመሪያ አምላክ ሰማያትንና ምድርን ፈጠረ። 2  ምድርም ቅርጽ አልባና ባድማ ነበረች፤ ጥልቁም ውኃ በጨለማ ተሸፍኖ ነበር፤ የአምላክም ኃይል በውኃው ላይ ይንቀሳቀስ ነበር። 3  አምላክም “ብርሃን ይሁን” አለ። ብርሃንም ሆነ። 4  ከዚህ በኋላ አምላክ ብርሃኑ መልካም እንደሆነ አየ፤ አምላክም ብርሃኑን ከጨለማው ለየ። 5  አምላክም ብርሃኑን ‘ቀን’ ብሎ ጠራው፤ ጨለማውን ግን ‘ሌሊት’ ብሎ ጠራው። መሸ፣ ነጋም፤ የመጀመሪያ ቀን። 6  ከዚያም አምላክ “በውኃዎቹ መካከል ጠፈር ይሁን፣ ውኃዎቹም ከውኃዎቹ ይከፈሉ” አለ። 7  ከዚያም አምላክ ጠፈርን ሠራ፤ ከጠፈሩ በታች ያሉትንም ውኃዎች ከጠፈሩ በላይ ካሉት ውኃዎች ለየ። እንዳለውም ሆነ። 8  አምላክ ጠፈሩን ‘ሰማይ’ ብሎ ጠራው። መሸ፣ ነጋም፤ ሁለተኛ ቀን። 9  በመቀጠልም አምላክ “ከሰማያት በታች ያሉት ውኃዎች አንድ ቦታ ላይ ይሰብሰቡና ደረቁ መሬት ይገለጥ” አለ። እንዳለውም ሆነ። 10  አምላክ ደረቁን መሬት ‘የብስ’ ብሎ ጠራው፤ አንድ ላይ የተሰበሰቡትን ውኃዎች ግን ‘ባሕር’ ብሎ ጠራቸው። አምላክም ይህ መልካም እንደሆነ አየ። 11  ቀጥሎም አምላክ “ምድር ሣርን፣ ዘር የሚሰጡ ተክሎችን እንዲሁም ዘር ያለው ፍሬ የሚያፈሩ ዛፎችን እንደየወገናቸው ታብቅል” አለ። እንዳለውም ሆነ። 12  ምድርም ሣርን፣ ዘር የሚሰጡ ተክሎችን እንዲሁም ዘር ያለው ፍሬ የሚያፈሩ ዛፎችን እንደየወገናቸው ማብቀል ጀመረች። ከዚያም አምላክ ይህ መልካም እንደሆነ አየ። 13  መሸ፣ ነጋም፤ ሦስተኛ ቀን። 14  አምላክም እንዲህ አለ፦ “ቀኑና ሌሊቱ እንዲለይ በሰማያት ጠፈር ላይ ብርሃን ሰጪ አካላት ይኑሩ፤ እነሱም ወቅቶችን፣ ቀናትንና ዓመታትን የሚጠቁሙ ምልክቶች ሆነው ያገለግላሉ። 15  በምድርም ላይ እንዲያበሩ በሰማያት ጠፈር ላይ ያሉ ብርሃን ሰጪ አካላት ሆነው ያገለግላሉ።” እንዳለውም ሆነ። 16  አምላክም ሁለቱን ታላላቅ ብርሃን ሰጪ አካላት ሠራ፤ ታላቁ ብርሃን ሰጪ አካል በቀን እንዲያይል፣ ታናሹ ብርሃን ሰጪ አካል ደግሞ በሌሊት እንዲያይል አደረገ፤ ከዋክብትንም ሠራ። 17  በዚህ መንገድ አምላክ በምድር ላይ እንዲያበሩ በሰማያት ጠፈር ላይ አስቀመጣቸው፤ 18  በተጨማሪም በቀንና በሌሊት እንዲያይሉ እንዲሁም ብርሃኑን ከጨለማው እንዲለዩ አደረገ። አምላክም ይህ መልካም እንደሆነ አየ። 19  መሸ፣ ነጋም፤ አራተኛ ቀን። 20  ከዚያም አምላክ “ውኃዎቹ በሚርመሰመሱ ሕያዋን ፍጥረታት ይሞሉ፤ እንዲሁም የሚበርሩ ፍጥረታት ከምድር በላይ በሰማያት ጠፈር ላይ ይብረሩ” አለ። 21  አምላክም ግዙፍ የባሕር ፍጥረታትን እንዲሁም በውኃዎቹ ውስጥ የሚንቀሳቀሱና የሚርመሰመሱ ሕያዋን ፍጥረታትን ሁሉ እንደየወገናቸው ብሎም ክንፍ ያለውን እያንዳንዱን የሚበር ፍጥረት እንደየወገኑ ፈጠረ። አምላክም ይህ መልካም እንደሆነ አየ። 22  ከዚያም አምላክ “ብዙ ተባዙ፤ የባሕሩንም ውኃ ሙሉት፤ የሚበርሩ ፍጥረታትም በምድር ላይ ይብዙ” ብሎ ባረካቸው። 23  መሸ፣ ነጋም፤ አምስተኛ ቀን። 24  ቀጥሎም አምላክ “ምድር ሕያዋን ፍጥረታትን እንደየወገናቸው እንዲሁም የቤት እንስሳትን፣ መሬት ለመሬት የሚሄዱ እንስሳትንና የዱር እንስሳትን እንደየወገናቸው ታውጣ” አለ። እንዳለውም ሆነ። 25  አምላክም በምድር ላይ ያሉ የዱር እንስሳትን እንደየወገናቸው፣ የቤት እንስሳትን እንደየወገናቸው እንዲሁም መሬት ለመሬት የሚሄዱ ፍጥረታትን ሁሉ እንደየወገናቸው ሠራ። አምላክም ይህ መልካም እንደሆነ አየ። 26  ከዚያም አምላክ “ሰውን በመልካችን እንደ አምሳላችን እንሥራ፤ እሱም በባሕር ዓሣዎች፣ በሰማያት ላይ በሚበርሩ ፍጥረታት፣ በቤት እንስሳትና በምድር ሁሉ እንዲሁም በምድር ላይ በሚንቀሳቀሱ መሬት ለመሬት የሚሄዱ እንስሳት ሁሉ ላይ ሥልጣን ይኑረው” አለ። 27  አምላክም ሰውን በራሱ መልክ ፈጠረው፤ በአምላክ መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው። 28  በተጨማሪም አምላክ ባረካቸው፤ እንዲህም አላቸው፦ “ብዙ ተባዙ፤ ምድርንም ሙሏት፤ ግዟትም። እንዲሁም የባሕር ዓሣዎችን፣ በሰማያት ላይ የሚበርሩ ፍጥረታትንና በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱ ፍጥረታትን በሙሉ ግዟቸው።” 29  ቀጥሎም አምላክ እንዲህ አለ፦ “በመላው ምድር ላይ ያሉ ዘር የሚሰጡ ተክሎችን በሙሉ እንዲሁም ዘር ያለው ፍሬ የሚያፈሩ ዛፎችን በሙሉ ይኸው ሰጥቻችኋለሁ። ምግብ ይሁኗችሁ። 30  በምድር ላይ ላለው የዱር እንስሳ ሁሉ፣ በሰማያት ላይ ለሚበር ፍጥረት ሁሉ እንዲሁም ሕይወት ላለው በምድር ላይ ለሚንቀሳቀስ ነገር ሁሉ አረንጓዴ ተክሎችን በሙሉ ምግብ እንዲሆኗቸው ሰጥቻቸዋለሁ።” እንዳለውም ሆነ። 31  ከዚያ በኋላ አምላክ የሠራውን እያንዳንዱን ነገር ተመለከተ፤ እነሆ፣ እጅግ መልካም ነበር! መሸ፣ ነጋም፤ ስድስተኛ ቀን።
[]
[]
[]
[]
12,505
10  የኖኅ ወንዶች ልጆች የሆኑት የሴም፣ የካም እና የያፌት ታሪክ ይህ ነው። ከጥፋት ውኃ በኋላ ወንዶች ልጆች ወለዱ። 2  የያፌት ወንዶች ልጆች ጎሜር፣ ማጎግ፣ ማዳይ፣ ያዋን፣ ቱባል፣ መሼቅ እና ቲራስ ነበሩ። 3  የጎሜር ወንዶች ልጆች አሽከናዝ፣ ሪፋት እና ቶጋርማ ነበሩ። 4  የያዋን ወንዶች ልጆች ኤሊሻ፣ ተርሴስ፣ ኪቲም እና ዶዳኒም ነበሩ። 5  በደሴቶች ላይ የሚኖሩ ሕዝቦች እንደየቋንቋቸውና እንደየቤተሰባቸው በየብሔራቸው በመሆን ወደየምድራቸው የተሰራጩት ከእነዚህ ነው። 6  የካም ወንዶች ልጆች ኩሽ፣ ሚጽራይም፣ ፑጥ እና ከነአን ነበሩ። 7  የኩሽ ወንዶች ልጆች ሴባ፣ ሃዊላ፣ ሳብታ፣ ራአማ እና ሳብተካ ነበሩ። የራአማ ወንዶች ልጆች ሳባ እና ዴዳን ነበሩ። 8  ኩሽ ናምሩድን ወለደ። እሱም በምድር ላይ የመጀመሪያው ኃያል ሰው ነበር። 9  እሱም ይሖዋን የሚቃወም ኃያል አዳኝ ሆነ። በዚህም የተነሳ “እንደ ናምሩድ ያለ ይሖዋን የሚቃወም ኃያል አዳኝ” ይባል ነበር። 10  የግዛቱ መጀመሪያም በሰናኦር ምድር የሚገኙት ባቤል፣ ኤሬክ፣ አካድ እና ካልኔ ነበሩ። 11  ከዚያ ምድር ተነስቶም ወደ አሦር በመሄድ ነነዌን፣ ረሆቦትኢርን እና ካላህን ቆረቆረ፤ 12  እንዲሁም በነነዌና በካላህ መካከል የምትገኘውን ረሰንን ቆረቆረ፤ እሷም ታላቋ ከተማ ናት። 13  ሚጽራይም ሉድን፣ አናሚምን፣ ለሃቢምን፣ ናፊቱሂምን፣ 14  ጳትሩሲምን፣ ካስሉሂምን (ፍልስጤማውያን የተገኙት ከእሱ ነው) እንዲሁም ካፍቶሪምን ወለደ። 15  ከነአን የበኩር ልጁን ሲዶናን፣ ሄትን 16  እንዲሁም ኢያቡሳዊውን፣ አሞራዊውን፣ ገርጌሻዊውን፣ 17  ሂዋዊውን፣ አርቃዊውን፣ ሲናዊውን፣ 18  አርዋዳዊውን፣ ጸማራዊውን እና ሃማታዊውን ወለደ። ከዚያ በኋላ የከነአናውያን ቤተሰቦች ተበተኑ። 19  በመሆኑም የከነአናውያን ወሰን ከሲዶና አንስቶ በጋዛ አቅራቢያ እስካለችው እስከ ጌራራ እንዲሁም እስከ ሰዶም፣ ገሞራ፣ አድማህ እና በላሻ አቅራቢያ እስካለችው እስከ ጸቦይም ድረስ ያለው ነበር። 20  የካም ወንዶች ልጆች እንደየቤተሰባቸውና እንደየቋንቋቸው በየአገራቸውና በየብሔራቸው እነዚህ ነበሩ። 21  የኤቤር ወንዶች ልጆች ሁሉ ቅድመ አያትና የታላቅየው የያፌት ወንድም የሆነው ሴምም ልጆች ወለደ። 22  የሴም ወንዶች ልጆች ኤላም፣ አሹር፣ አርፋክስድ፣ ሉድ እና አራም ነበሩ። 23  የአራም ወንዶች ልጆች ዑጽ፣ ሁል፣ ጌተር እና ማሽ ነበሩ። 24  አርፋክስድ ሴሎምን ወለደ፤ ሴሎምም ኤቤርን ወለደ። 25  ኤቤር ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ። የአንደኛው ስም ፋሌቅ ነበር፤ ምክንያቱም በእሱ የሕይወት ዘመን ምድር ተከፋፍላ ነበር። የወንድሙ ስም ደግሞ ዮቅጣን ነበር። 26  ዮቅጣን አልሞዳድን፣ ሸሌፍን፣ ሃጻርማዌትን፣ ያራህን፣ 27  ሃዶራምን፣ ዑዛልን፣ ዲቅላን፣ 28  ኦባልን፣ አቢማዔልን፣ ሳባን፣ 29  ኦፊርን፣ ሃዊላን እና ዮባብን ወለደ፤ እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ወንዶች ልጆች ነበሩ። 30  መኖሪያ ስፍራቸውም ከሜሻ አንስቶ እስከ ሰፋር ይኸውም እስከ ምሥራቅ ተራራማ አካባቢ ድረስ ይዘልቃል። 31  የሴም ወንዶች ልጆች እንደየቤተሰባቸውና እንደየቋንቋቸው በየአገራቸውና በየብሔራቸው እነዚህ ነበሩ። 32  የኖኅ ወንዶች ልጆች ቤተሰቦች እንደየዘር ሐረጋቸው በየብሔራቸው እነዚህ ነበሩ። ከጥፋት ውኃው በኋላ ብሔራት ሁሉ በምድር ላይ የተሰራጩት ከእነዚህ ነበር።
[]
[]
[]
[]
12,506
11  በዚህ ጊዜ፣ ምድር ሁሉ አንድ ቋንቋና ተመሳሳይ ቃላት ትጠቀም ነበር። 2  ወደ ምሥራቅ ሲጓዙም በሰናኦር ምድር ወደሚገኝ አንድ ሸለቋማ ሜዳ ደረሱ፤ በዚያም መኖር ጀመሩ። 3  እርስ በርሳቸውም “ኑ! ጡብ እንሥራ፤ በእሳትም እንተኩሰው” ይባባሉ ጀመር። በመሆኑም በድንጋይ ፋንታ ጡብ፣ ለማያያዣም ቅጥራን ተጠቀሙ። 4  ከዚያም “ኑ! በመላው ምድር ላይ እንዳንበተን ከተማና ጫፉ ሰማይ የሚደርስ ግንብ ለራሳችን እንገንባ፤ ስማችንንም እናስጠራ” ተባባሉ። 5  ከዚያም ይሖዋ ሰዎች የሠሩትን ከተማና ግንብ ለማየት ወረደ። 6  ይሖዋም እንዲህ አለ፦ “እነዚህ ሰዎች አንድ ቋንቋ የሚናገሩ አንድ ሕዝብ ናቸው፤ ይኸው አሁን ደግሞ ይህን መሥራት ጀምረዋል። በዚህ ከቀጠሉ ያሰቡትን ሁሉ ከማከናወን የሚያግዳቸው ምንም ነገር አይኖርም። 7  ና! እንውረድና በቋንቋ እርስ በርስ እንዳይግባቡ ቋንቋቸውን እናዘበራርቅ።” 8  በመሆኑም ይሖዋ ከዚያ ቦታ ተነስተው በመላው ምድር ላይ እንዲበተኑ አደረገ፤ እነሱም ቀስ በቀስ ከተማዋን መገንባታቸውን አቆሙ። 9  የከተማዋ ስም ባቤል የተባለውም በዚህ የተነሳ ነው፤ ምክንያቱም ይሖዋ በዚያ የምድርን ሁሉ ቋንቋ አዘበራርቋል፤ እንዲሁም ይሖዋ ሰዎቹ ከዚያ ቦታ ተነስተው በመላው ምድር ላይ እንዲበተኑ አድርጓል። 10  የሴም ታሪክ ይህ ነው። ሴም የጥፋት ውኃ ከተከሰተ ከሁለት ዓመት በኋላ አርፋክስድን ሲወልድ የ100 ዓመት ሰው ነበር። 11  ሴም አርፋክስድን ከወለደ በኋላ 500 ዓመት ኖረ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። 12  አርፋክስድ 35 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ሴሎምን ወለደ። 13  አርፋክስድ ሴሎምን ከወለደ በኋላ 403 ዓመት ኖረ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። 14  ሴሎም 30 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ኤቤርን ወለደ። 15  ሴሎም ኤቤርን ከወለደ በኋላ 403 ዓመት ኖረ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። 16  ኤቤር 34 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ፋሌቅን ወለደ። 17  ኤቤርም ፋሌቅን ከወለደ በኋላ 430 ዓመት ኖረ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። 18  ፋሌቅ 30 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ረኡን ወለደ። 19  ፋሌቅ ረኡን ከወለደ በኋላ 209 ዓመት ኖረ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። 20  ረኡ 32 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ሴሮህን ወለደ። 21  ረኡ ሴሮህን ከወለደ በኋላ 207 ዓመት ኖረ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። 22  ሴሮህ 30 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ናኮርን ወለደ። 23  ሴሮህ ናኮርን ከወለደ በኋላ 200 ዓመት ኖረ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። 24  ናኮር 29 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ታራን ወለደ። 25  ናኮር ታራን ከወለደ በኋላ 119 ዓመት ኖረ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። 26  ታራ 70 ዓመት ከኖረ በኋላ አብራምን፣ ናኮርን እና ካራንን ወለደ። 27  የታራ ታሪክ ይህ ነው። ታራ አብራምን፣ ናኮርን እና ካራንን ወለደ፤ ካራን ደግሞ ሎጥን ወለደ። 28  ካራንም አባቱ ታራ ገና በሕይወት እያለ፣ በተወለደበት አገር በከለዳውያን ዑር ሞተ። 29  አብራምና ናኮር ሚስት አገቡ። የአብራም ሚስት ስሟ ሦራ ሲሆን የናኮር ሚስት ደግሞ ስሟ ሚልካ ነበር፤ እሷም የሚልካ እና የዪስካ አባት የሆነው የካራን ልጅ ናት። 30  በዚህ ጊዜ ሦራ መሃን ነበረች፤ ልጅም አልነበራትም። 31  ከዚያም ታራ ልጁን አብራምንና የልጁ ልጅ የሆነውን የካራንን ልጅ ሎጥን እንዲሁም የልጁ የአብራም ሚስት የሆነችውን ምራቱን ሦራን ይዞ ወደ ከነአን ምድር ለመሄድ ከከለዳውያን ዑር ተነሳ። ከጊዜ በኋላም ወደ ካራን መጡ፤ በዚያም መኖር ጀመሩ። 32  ታራም 205 ዓመት ኖረ። ከዚያም በካራን ሞተ።
[]
[]
[]
[]
12,507
12  ይሖዋም አብራምን እንዲህ አለው፦ “ከአገርህ፣ ከዘመዶችህና ከአባትህ ቤት ወጥተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ሂድ። 2  አንተን ታላቅ ብሔር አደርግሃለሁ፤ እንዲሁም እባርክሃለሁ፤ ስምህንም ታላቅ አደርገዋለሁ፤ አንተም በረከት ትሆናለህ። 3  የሚባርኩህን እባርካለሁ፤ የሚረግምህንም እረግማለሁ፤ የምድር ሕዝቦችም ሁሉ በአንተ አማካኝነት ይባረካሉ።” 4  ስለዚህ አብራም ልክ ይሖዋ በነገረው መሠረት ወጣ፤ ሎጥም አብሮት ሄደ። አብራም ከካራን በወጣበት ጊዜ ዕድሜው 75 ዓመት ነበር። 5  አብራም ሚስቱን ሦራን፣ የወንድሙን ልጅ ሎጥን እንዲሁም ያፈሩትን ንብረት ሁሉና በካራን አብረዋቸው የነበሩትን ሰዎች በሙሉ ይዞ ተነሳ፤ እነሱም ወደ ከነአን ምድር አቀኑ። ከነአን ምድር በደረሱም ጊዜ 6  አብራም በሞሬ ትላልቅ ዛፎች አቅራቢያ እስከሚገኘው ሴኬም እስከሚባለው አካባቢ ድረስ ወደ ምድሪቱ ዘልቆ ገባ። በዚያን ጊዜ ከነአናውያን በምድሪቱ ይኖሩ ነበር። 7  ይሖዋም ለአብራም ተገለጠለትና “ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ” አለው። ስለዚህ አብራም ተገልጦለት ለነበረው ለይሖዋ በዚያ መሠዊያ ሠራ። 8  በኋላም ከዚያ ተነስቶ ከቤቴል በስተ ምሥራቅ ወደሚገኘው ተራራማ አካባቢ ተጓዘ፤ እሱም ቤቴልን በስተ ምዕራብ፣ ጋይን ደግሞ በስተ ምሥራቅ አድርጎ ድንኳኑን ተከለ። በዚያም ለይሖዋ መሠዊያ ሠራ፤ የይሖዋንም ስም ጠራ። 9  ከዚያ በኋላ አብራም ድንኳኑን ነቅሎ በየቦታው እየሰፈረ ወደ ኔጌብ ተጓዘ። 10  በምድሪቱም ላይ ረሃብ ተከሰተ፤ ረሃቡ በጣም አስከፊ ስለነበር አብራም ለተወሰነ ጊዜ በግብፅ ለመኖር ወደዚያ ወረደ። 11  ወደ ግብፅ ለመግባት ሲቃረብም ሚስቱን ሦራን እንዲህ አላት፦ “እባክሽ ስሚኝ፤ አንቺ በጣም ውብ ሴት ነሽ። 12  ስለሆነም ግብፃውያን አንቺን ሲያዩ ‘ይህች ሚስቱ ናት’ ማለታቸው አይቀርም። ከዚያም እኔን ይገድሉኛል፤ አንቺን ግን ይተዉሻል። 13  በአንቺ የተነሳ መልካም እንዲሆንልኝ እባክሽ፣ እህቴ እንደሆንሽ አድርገሽ ተናገሪ፤ እንዲህ ካደረግሽ ሕይወቴ ይተርፋል።” 14  አብራምም ግብፅ እንደደረሰ ግብፃውያኑ ሴቲቱ እጅግ ውብ እንደሆነች ተመለከቱ። 15  የፈርዖንም መኳንንት ሴቲቱን አዩአት፤ ስለ እሷም ለፈርዖን በአድናቆት ነገሩት። በመሆኑም ሴቲቱ ወደ ፈርዖን ቤት ተወሰደች። 16  ፈርዖንም በእሷ ምክንያት አብራምን ተንከባከበው፤ በጎችን፣ ከብቶችን፣ ተባዕትና እንስት አህዮችን፣ ግመሎችን እንዲሁም ወንድና ሴት አገልጋዮችን ሰጠው። 17  ከዚያም ይሖዋ በአብራም ሚስት በሦራ የተነሳ ፈርዖንንና ቤተሰቡን በታላቅ መቅሰፍት መታ። 18  በመሆኑም ፈርዖን አብራምን ጠርቶ እንዲህ አለው፦ “ይህ ያደረግክብኝ ነገር ምንድን ነው? ሚስትህ እንደሆነች ያልነገርከኝ ለምንድን ነው? 19  ‘እህቴ ናት’ ያልከውስ ለምንድን ነው? እኔ እኮ ወስጄ ሚስቴ ላደርጋት ነበር። በል፣ ሚስትህ ይችውልህ፤ ይዘሃት ሂድ!” 20  ስለዚህ ፈርዖን አብራምን በተመለከተ ለአገልጋዮቹ ትእዛዝ አስተላለፈ፤ እነሱም አብራምን ከሚስቱና ከንብረቱ ሁሉ ጋር አሰናበቱት።
[]
[]
[]
[]
12,508
13  ከዚያም አብራም ሚስቱንና ያለውን ንብረት ሁሉ ይዞ ከሎጥ ጋር በመሆን ከግብፅ ወጥቶ ወደ ኔጌብ ሄደ። 2  አብራም በከብት፣ በብርና በወርቅ እጅግ በልጽጎ ነበር። 3  እሱም ከኔጌብ ተነስቶ ወደ ቤቴል በሚጓዝበት ጊዜ ድንኳኑን ተክሎበት ወደነበረው በቤቴልና በጋይ መካከል ወደሚገኘው ስፍራ እስኪደርስ ድረስ በየቦታው ይሰፍር ነበር፤ 4  ይህም ቀደም ሲል መሠዊያ ሠርቶበት የነበረው ስፍራ ነው። በዚያም አብራም የይሖዋን ስም ጠራ። 5  ከአብራም ጋር ይጓዝ የነበረው ሎጥም በጎች፣ ከብቶችና ድንኳኖች ነበሩት። 6  በመሆኑም ሁሉም አንድ ላይ ለመኖር ምድሪቱ አልበቃቻቸውም፤ ንብረታቸው በጣም እየበዛ ስለመጣ አብረው መኖር አልቻሉም። 7  በዚህም ምክንያት በአብራም እረኞችና በሎጥ እረኞች መካከል ጠብ ተነሳ። (በወቅቱ ከነአናውያንና ፈሪዛውያን በምድሪቱ ይኖሩ ነበር።) 8  ስለዚህ አብራም ሎጥን እንዲህ አለው፦ “እባክህ በእኔና በአንተ እንዲሁም በእኔ እረኞችና በአንተ እረኞች መካከል ምንም ዓይነት ጠብ አይኑር፤ እኛ እኮ ወንድማማቾች ነን። 9  ምድሪቱ ሁሉ በእጅህ አይደለችም? እባክህ ከእኔ ተለይ። አንተ ወደ ግራ ብትሄድ እኔ ወደ ቀኝ እሄዳለሁ፤ አንተ ወደ ቀኝ ብትሄድ ደግሞ እኔ ወደ ግራ እሄዳለሁ።” 10  ሎጥም ዓይኑን አቅንቶ መላውን የዮርዳኖስ አውራጃ እስከ ዞአር ድረስ ተመለከተ፤ (ይሖዋ ሰዶምንና ገሞራን ከማጥፋቱ በፊት) አካባቢው ልክ እንደ ይሖዋ የአትክልት ስፍራ፣ ልክ እንደ ግብፅ ምድር ውኃ የጠገበ ነበር። 11  ከዚያም ሎጥ መላውን የዮርዳኖስ አውራጃ ለራሱ መረጠ፤ ሎጥም ወደ ምሥራቅ ሄዶ ሰፈረ። በዚህ መንገድ አንዳቸው ከሌላው ተለዩ። 12  አብራም በከነአን ምድር ኖረ፤ ሎጥ ግን በአውራጃው በሚገኙ ከተሞች አቅራቢያ ኖረ። በመጨረሻም በሰዶም አቅራቢያ ድንኳን ተከለ። 13  የሰዶም ሰዎች በይሖዋ ፊት ከባድ ኃጢአት የሚፈጽሙ ክፉ ሰዎች ነበሩ። 14  ሎጥ ከአብራም ከተለየ በኋላ ይሖዋ አብራምን እንዲህ አለው፦ “እባክህ ካለህበት ቦታ ሆነህ ዓይንህን አቅንተህ ወደ ሰሜን፣ ወደ ደቡብ፣ ወደ ምሥራቅና ወደ ምዕራብ ተመልከት፤ 15  ምክንያቱም የምታየውን ምድር ሁሉ ለአንተና ለዘርህ ለዘለቄታው ርስት አድርጌ እሰጣለሁ። 16  ዘርህን እንደ ምድር አፈር አበዛዋለሁ፤ ማንም ሰው የምድርን አፈር መቁጠር ከቻለ የአንተም ዘር ሊቆጠር ይችላል። 17  ተነሳ፣ ይህችን ምድር ልሰጥህ ስለሆነ በምድሪቱ ስፋትና ርዝመት ሂድ።” 18  በመሆኑም አብራም ሄደ፤ በድንኳን መኖሩንም ቀጠለ። ከጊዜ በኋላም በኬብሮን ወደሚገኙት የማምሬ ትላልቅ ዛፎች መጥቶ መኖር ጀመረ፤ በዚያም ለይሖዋ መሠዊያ ሠራ።
[]
[]
[]
[]
12,509
14  በዚያን ጊዜ የሰናኦር ንጉሥ አምራፌል፣ የኤላሳር ንጉሥ አርዮክ፣ የኤላም ንጉሥ ኮሎዶጎምር እና የጎይም ንጉሥ ቲድአል 2  ከሰዶም ንጉሥ ከቤራ፣ ከገሞራ ንጉሥ ከቢርሻ፣ ከአድማህ ንጉሥ ከሺንአብ፣ ከጸቦይም ንጉሥ ከሸሜበር እና ከቤላ ማለትም ከዞአር ንጉሥ ጋር ጦርነት ገጠሙ። 3  እነዚህ ሁሉ በሲዲም ሸለቆ ማለትም በጨው ባሕር ሠራዊታቸውን አሰባሰቡ። 4  እነሱም ኮሎዶጎምርን 12 ዓመት አገለገሉት፤ በ13ኛው ዓመት ግን ዓመፁ። 5  ስለሆነም በ14ኛው ዓመት ኮሎዶጎምርና አብረውት የነበሩት ነገሥታት መጥተው ረፋይምን በአስተሮትቃርናይም፣ ዙዚምን በሃም፣ ኤሚምን በሻዌቂሪያታይም፣ 6  ሆራውያንን ደግሞ ሴይር ከሚባለው ተራራቸው አንስቶ በምድረ በዳ እስከሚገኘው እስከ ኤልጳራን ድረስ በሚዘልቀው ስፍራ ድል አደረጓቸው። 7  ከዚያም ቃዴስ ወደምትባለው ወደ ኤንሚሽጳጥ ተመልሰው በመምጣት መላውን የአማሌቃውያን ግዛትና በሃጻጾንታማር ይኖሩ የነበሩትን አሞራውያንን ድል አደረጉ። 8  በዚህ ጊዜ የሰዶም ንጉሥ፣ የገሞራ ንጉሥ፣ የአድማህ ንጉሥ፣ የጸቦይም ንጉሥ እንዲሁም የቤላ ማለትም የዞአር ንጉሥ ከእነሱ ጋር ለመዋጋት ሠራዊታቸውን አስተባብረው በሲዲም ሸለቆ ውስጥ ለጦርነት ተሰለፉ፤ 9  የኤላምን ንጉሥ ኮሎዶጎምርን፣ የጎይምን ንጉሥ ቲድአልን፣ የሰናኦርን ንጉሥ አምራፌልን እንዲሁም የኤላሳርን ንጉሥ አርዮክን ለመውጋት ተነሱ፤ አራቱ ነገሥታት ከአምስቱ ጋር ተዋጉ። 10  የሲዲም ሸለቆ በቅጥራን ጉድጓዶች የተሞላ ነበር፤ የሰዶምና የገሞራ ነገሥታት ሸሽተው ለማምለጥ ሲሞክሩ እነዚህ ጉድጓዶች ውስጥ ወደቁ፤ የቀሩት ደግሞ ወደ ተራራማው አካባቢ ሸሹ። 11  ከዚያም ድል አድራጊዎቹ የሰዶምንና የገሞራን ንብረት በሙሉ እንዲሁም ምግባቸውን ሁሉ ይዘው ሄዱ። 12  በተጨማሪም በሰዶም ይኖር የነበረውን የአብራምን የወንድም ልጅ ሎጥን ከነንብረቱ ይዘውት ሄዱ። 13  ከዚያም አንድ ያመለጠ ሰው መጥቶ ለዕብራዊው ለአብራም ነገረው። በዚያን ጊዜ አብራም የኤሽኮል እና የአኔር ወንድም በሆነው በአሞራዊው በማምሬ ትላልቅ ዛፎች አጠገብ ይኖር ነበር። እነዚህ ሰዎች የአብራም አጋሮች ነበሩ። 14  በዚህ መንገድ አብራም ዘመዱ በምርኮ መወሰዱን ሰማ። ስለሆነም በቤቱ የተወለዱትን 318 የሠለጠኑ አገልጋዮች ሰብስቦ ተነሳ፤ ወራሪዎቹንም ተከትሎ እስከ ዳን ድረስ ሄደ። 15  በሌሊትም ሠራዊቱን ከፋፈለ፤ እሱና አገልጋዮቹም በወራሪዎቹ ላይ ጥቃት በመሰንዘር ድል አደረጓቸው። እሱም ከደማስቆ በስተ ሰሜን እስከምትገኘው እስከ ሆባ ድረስ አሳደዳቸው። 16  የወሰዷቸውን ንብረቶችም ሁሉ አስመለሰ፤ በተጨማሪም ዘመዱን ሎጥንና ንብረቶቹን እንዲሁም ሴቶቹንና ሌሎቹን ሰዎች አስመለሰ። 17  አብራም ኮሎዶጎምርንና ከእሱ ጋር የነበሩትን ነገሥታት ድል አድርጎ ከተመለሰ በኋላ የሰዶም ንጉሥ ከአብራም ጋር ለመገናኘት ወደ ሻዌ ሸለቆ ማለትም ወደ ንጉሡ ሸለቆ ወጣ። 18  የሳሌም ንጉሥ መልከጼዴቅም ምግብና የወይን ጠጅ ይዞ ወጣ፤ እሱም የልዑሉ አምላክ ካህን ነበር። 19  አብራምንም ባረከው፤ እንዲህም አለው፦ “ሰማይንና ምድርን የሠራውልዑሉ አምላክ አብራምን ይባርክ፤ 20  የሚጨቁኑህን በእጅህ አሳልፎ የሰጠህ፣ልዑሉ አምላክ ይወደስ!” አብራምም ከሁሉም ነገር ላይ አንድ አሥረኛውን ሰጠው። 21  ከዚያም የሰዶም ንጉሥ አብራምን “ሰዎቹን ስጠኝ፤ ንብረቶቹን ግን ለራስህ ውሰድ” አለው። 22  አብራም ግን የሰዶምን ንጉሥ እንዲህ አለው፦ “ሰማይንና ምድርን ወደሠራው ወደ ልዑሉ አምላክ ወደ ይሖዋ እጄን አንስቼ እምላለሁ፣ 23  ‘አብራምን አበለጸግኩት’ እንዳትል የአንተ ከሆነው ነገር ምንም አልወስድም፤ ሌላው ቀርቶ ብጣሽ ክርም ሆነ የጫማ ማሰሪያ አልወስድም። 24  ወጣቶቹ ከበሉት ምግብ በስተቀር ምንም ነገር አልወስድም። ከእኔ ጋር የዘመቱት አኔር፣ ኤሽኮልና ማምሬ ግን ድርሻቸውን ይውሰዱ።”
[]
[]
[]
[]
12,510
15  ከዚህ በኋላ የይሖዋ ቃል በራእይ ወደ አብራም መጥቶ “አብራም አትፍራ። እኔ ጋሻ እሆንሃለሁ። የምታገኘውም ሽልማት እጅግ ታላቅ ይሆናል” አለው። 2  አብራምም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ያለልጅ እንደቀረሁና ቤቴን የሚወርሰው የደማስቆ ሰው የሆነው ኤሊዔዘር እንደሆነ ታያለህ፤ ታዲያ ምን ትሰጠኛለህ?” 3  በተጨማሪም አብራም “እንግዲህ ዘር አልሰጠኸኝም፤ ደግሞም ወራሼ የሚሆነው በቤቴ ያለው አገልጋይ ነው” አለ። 4  ሆኖም እንዲህ የሚል የይሖዋ ቃል ወደ እሱ መጣ፦ “ይህ ሰው ወራሽህ አይሆንም፤ ከዚህ ይልቅ የገዛ ልጅህ ወራሽህ ይሆናል።” 5  ወደ ውጭም ካወጣው በኋላ “እባክህ ቀና ብለህ ወደ ሰማይ ተመልከት፤ እስቲ መቁጠር ከቻልክ ከዋክብቱን ቁጠራቸው” አለው። ከዚያም “የአንተም ዘር እንዲሁ ይሆናል” አለው። 6  አብራምም በይሖዋ አመነ፤ አምላክም ይህን ጽድቅ አድርጎ ቆጠረለት። 7  ደግሞም እንዲህ አለው፦ “ይህችን ምድር ርስት አድርጌ ልሰጥህ ከከለዳውያን ዑር ያወጣሁህ እኔ ይሖዋ ነኝ።” 8  አብራምም “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ይህችን ምድር ርስት አድርጌ እንደምወርስ እንዴት አውቃለሁ?” አለ። 9  እሱም መልሶ “አንዲት የሦስት ዓመት ጊደር፣ አንዲት የሦስት ዓመት ፍየል፣ አንድ የሦስት ዓመት አውራ በግ እንዲሁም አንድ ዋኖስና አንድ የርግብ ጫጩት ውሰድ” አለው። 10  እሱም እነዚህን እንስሳት ሁሉ ወስዶ ለሁለት ሰነጠቃቸው፤ ከዚያም አንዱን ግማሽ ከሌላኛው ግማሽ ትይዩ አድርጎ አስቀመጠ። ወፎቹን ግን አልሰነጠቃቸውም። 11  አሞሮችም በበድኖቹ ላይ መውረድ ጀመሩ፤ አብራም ግን ያባርራቸው ነበር። 12  ፀሐይ ልትጠልቅ ስትቃረብም አብራም ከባድ እንቅልፍ ወሰደው፤ ታላቅና የሚያስፈራ ጨለማም ወረደበት። 13  አምላክም አብራምን እንዲህ አለው፦ “ዘሮችህ በባዕድ አገር ባዕዳን ሆነው እንደሚኖሩ እንዲሁም በዚያ ያሉት ሰዎች ለ400 ዓመት በባርነት እንደሚገዟቸውና እንደሚያጎሳቁሏቸው በእርግጥ እወቅ። 14  ይሁንና በባርነት በሚገዛቸው ብሔር ላይ እፈርዳለሁ፤ እነሱም ብዙ ንብረት ይዘው ይወጣሉ። 15  አንተ ግን ወደ አባቶችህ በሰላም ትሄዳለህ፤ ዕድሜ ጠግበህም ወደ መቃብር ትወርዳለህ። 16  ሆኖም በአራተኛው ትውልድ ወደዚህ ይመለሳሉ፤ ምክንያቱም የአሞራውያን በደል ጽዋው ገና አልሞላም።” 17  ፀሐይዋ ከጠለቀችና ድቅድቅ ጨለማ አካባቢውን ከዋጠው በኋላ የሚጨስ ምድጃ ታየ፤ ለሁለት በተከፈለውም ሥጋ መካከል የሚንቦገቦግ ችቦ አለፈ። 18  በዚያ ቀን ይሖዋ እንዲህ ሲል ከአብራም ጋር ቃል ኪዳን ገባ፦ “ከግብፅ ወንዝ አንስቶ እስከ ታላቁ የኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ያለውን ይህን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ፤ 19  የቄናውያንን፣ የቀኒዛውያንን፣ የቃድሞናውያንን፣ 20  የሂታውያንን፣ የፈሪዛውያንን፣ የረፋይምን፣ 21  የአሞራውያንን፣ የከነአናውያንን፣ የገርጌሻውያንንና የኢያቡሳውያንን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ።”
[]
[]
[]
[]
12,511
16  የአብራም ሚስት ሦራ ለአብራም ልጆች አልወለደችለትም ነበር፤ ይሁንና አጋር የምትባል አንዲት ግብፃዊት አገልጋይ ነበረቻት። 2  በመሆኑም ሦራ አብራምን እንዲህ አለችው፦ “እንግዲህ እንደምታየው ይሖዋ ልጆች እንዳልወልድ አድርጎኛል። እባክህ ከአገልጋዬ ጋር ግንኙነት ፈጽም። ምናልባትም በእሷ አማካኝነት ልጆች ላገኝ እችላለሁ።” ስለሆነም አብራም የሦራን ቃል ሰማ። 3  አብራም በከነአን ምድር ለአሥር ዓመት ያህል ከኖረ በኋላ የአብራም ሚስት ሦራ ግብፃዊት አገልጋይዋን አጋርን ወስዳ ሚስት እንድትሆነው ለባሏ ለአብራም ሰጠችው። 4  በመሆኑም አብራም ከአጋር ጋር ግንኙነት ፈጸመ፤ እሷም ፀነሰች። መፀነሷን ባወቀች ጊዜም እመቤቷን መናቅ ጀመረች። 5  በዚህ ጊዜ ሦራ አብራምን እንዲህ አለችው፦ “ለደረሰብኝ በደል ተጠያቂው አንተ ነህ። አገልጋዬን በእቅፍህ ያደረግኩልህ እኔው ራሴ ነበርኩ፤ እሷ ግን መፀነሷን ባወቀች ጊዜ ትንቀኝ ጀመር። ይሖዋ በእኔና በአንተ መካከል ይፍረድ።” 6  በመሆኑም አብራም ሦራን “እንግዲህ አገልጋይሽ እንደሆነች በእጅሽ ናት። መልካም መስሎ የታየሽን ነገር አድርጊባት” አላት። ከዚያም ሦራ አገልጋይዋን አዋረደቻት፤ ስለዚህም ጥላት ኮበለለች። 7  በኋላም የይሖዋ መልአክ አጋርን በምድረ በዳ በሚገኝ አንድ የውኃ ምንጭ አጠገብ ማለትም ወደ ሹር በሚወስደው መንገድ ላይ ባለው ምንጭ አጠገብ አገኛት። 8  እሱም “የሦራ አገልጋይ አጋር፣ ለመሆኑ የመጣሽው ከየት ነው? ወዴትስ እየሄድሽ ነው?” አላት። እሷም መልሳ “ከእመቤቴ ከሦራ ኮብልዬ እየሄድኩ ነው” አለች። 9  የይሖዋም መልአክ “ወደ እመቤትሽ ተመለሽ፤ ለእሷም በትሕትና ተገዢላት” አላት። 10  ከዚያም የይሖዋ መልአክ “ከብዛቱ የተነሳ የማይቆጠር እስኪሆን ድረስ ዘርሽን እጅግ አበዛዋለሁ” አላት። 11  በተጨማሪም የይሖዋ መልአክ እንዲህ አላት፦ “እንግዲህ ይኸው ፀንሰሻል፤ ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ። ስሙንም እስማኤል ትይዋለሽ፤ ምክንያቱም ይሖዋ የሥቃይ ጩኸትሽን ሰምቷል። 12  እሱም እንደ ዱር አህያ ይሆናል። ባገኘው ሰው ሁሉ ላይ እጁን ያነሳል፤ ያገኘውም ሰው ሁሉ እጁን ያነሳበታል፤ ከወንድሞቹም ሁሉ ፊት ለፊት ይኖራል።” 13  ከዚያም አጋር “የሚያየኝን አሁን በእርግጥ አየሁት ማለት ነው?” ብላ ስላሰበች እያነጋገራት የነበረውን ይሖዋን ስሙን ጠርታ “አንተ የምታይ አምላክ ነህ” አለች። 14  የውኃ ጉድጓዱ ብኤርላሃይሮዒ ተብሎ የተጠራው በዚህ የተነሳ ነው። (ጉድጓዱም በቃዴስና በቤሬድ መካከል ይገኛል።) 15  ስለዚህ አጋር ለአብራም ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ አብራምም አጋር የወለደችለትን ልጅ እስማኤል ብሎ ስም አወጣለት። 16  አጋር ለአብራም እስማኤልን በወለደችለት ጊዜ አብራም የ86 ዓመት ሰው ነበር።
[]
[]
[]
[]
12,512
17  አብራም ዕድሜው 99 ዓመት ሲሆን ይሖዋ ተገለጠለትና እንዲህ አለው፦ “እኔ ሁሉን ቻይ አምላክ ነኝ። በፊቴ ተመላለስ፤ እንከን የሌለብህ መሆንህንም አስመሥክር። 2  ከአንተ ጋር ቃል ኪዳኔን እመሠርታለሁ፤ አንተንም እጅግ አበዛሃለሁ።” 3  በዚህ ጊዜ አብራም በግንባሩ ተደፋ፤ አምላክም እንዲህ በማለት እሱን ማነጋገሩን ቀጠለ፦ 4  “በእኔ በኩል ከአንተ ጋር የገባሁት ቃል ኪዳኔ እንደጸና ነው፤ አንተም በእርግጥ የብዙ ብሔር አባት ትሆናለህ። 5  ከእንግዲህ ስምህ አብራም አይባልም፤ የብዙ ብሔር አባት ስለማደርግህ ስምህ አብርሃም ይሆናል። 6  እጅግ አበዛሃለሁ፤ ብዙ ብሔርም አደርግሃለሁ፤ ነገሥታትም ከአንተ ይወጣሉ። 7  “ለአንተም ሆነ ከአንተ በኋላ ለሚመጡት ዘሮችህ አምላክ እሆን ዘንድ በእኔና በአንተ እንዲሁም መጪዎቹን ትውልዶቻቸውን ሁሉ ጨምሮ ከአንተ በኋላ በሚመጡት ዘሮችህ መካከል ያለውን ቃል ኪዳኔን ዘላለማዊ ቃል ኪዳን አድርጌ እጠብቀዋለሁ። 8  ባዕድ ሆነህ የኖርክበትን አገር ይኸውም መላውን የከነአን ምድር ለአንተና ከአንተ በኋላ ለሚመጡት ዘሮችህ ዘላቂ ርስት አድርጌ እሰጣለሁ፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ።” 9  በተጨማሪም አምላክ አብርሃምን እንዲህ አለው፦ “በአንተ በኩል፣ አንተም ሆንክ ከአንተ በኋላ የሚመጡት ዘሮችህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ቃል ኪዳኔን መጠበቅ አለባችሁ። 10  እናንተም ሆናችሁ ከእናንተ በኋላ የሚመጡት ዘሮቻችሁ ልትጠብቁት የሚገባው በእኔና በእናንተ መካከል ያለው ቃል ኪዳኔ ይህ ነው፦ በእናንተ መካከል ያለ ወንድ ሁሉ መገረዝ አለበት። 11  ሸለፈታችሁን መገረዝ አለባችሁ፤ ይህም በእኔና በእናንተ መካከል ላለው ቃል ኪዳን እንደ ምልክት ሆኖ ያገለግላል። 12  በትውልዶቻችሁ ሁሉ በመካከላችሁ ያለ ስምንት ቀን የሞላው ማንኛውም ወንድ መገረዝ አለበት፤ በቤት የተወለደም ሆነ ዘርህ ያልሆነ ወይም ደግሞ ከባዕድ ሰው ላይ በገንዘብ የተገዛ ማንኛውም ወንድ ሁሉ ይገረዝ። 13  በቤትህ የተወለደ ማንኛውም ወንድ እንዲሁም በገንዘብህ የተገዛ ማንኛውም ወንድ መገረዝ አለበት፤ በሥጋችሁ ላይ ያለው ይህ ምልክት ከእናንተ ጋር ለገባሁት ዘላቂ ቃል ኪዳን ማስረጃ ሆኖ ያገለግላል። 14  ሸለፈቱ እንዲገረዝ የማያደርግ ያልተገረዘ ወንድ ካለ ያ ሰው ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ ይደረግ። ይህ ሰው ቃል ኪዳኔን አፍርሷል።” 15  ከዚያም አምላክ አብርሃምን እንዲህ አለው፦ “ሚስትህን ሦራን በተመለከተ ሦራ ብለህ አትጥራት፤ ምክንያቱም ከእንግዲህ ስሟ ሣራ ይሆናል። 16  እኔም እባርካታለሁ፤ ከእሷም ወንድ ልጅ እሰጥሃለሁ። እባርካታለሁ፤ እሷም ብዙ ብሔር ትሆናለች፤ የሕዝቦች ነገሥታትም ከእሷ ይወጣሉ።” 17  በዚህ ጊዜ አብርሃም በግንባሩ ተደፋ፤ እየሳቀም በልቡ እንዲህ አለ፦ “እንዲያው ምንስ ቢሆን 100 ዓመት የሆነው ሰው የልጅ አባት ሊሆን ይችላል? ዘጠና ዓመት የሆናት ሣራስ ብትሆን ልጅ ልትወልድ ትችላለች?” 18  ስለዚህ አብርሃም እውነተኛውን አምላክ “ምነው እስማኤልን ብቻ በባረክልኝ!” አለው። 19  አምላክም እንዲህ አለው፦ “ሚስትህ ሣራ በእርግጥ ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ይስሐቅ ትለዋለህ። እኔም ከእሱ በኋላ ለሚመጡት ዘሮቹ ጭምር ዘላለማዊ ቃል ኪዳን እንዲሆን ከእሱ ጋር ቃል ኪዳኔን እመሠርታለሁ። 20  እስማኤልን በተመለከተም ልመናህን ሰምቻለሁ። እሱንም ቢሆን እባርከዋለሁ፤ ፍሬያማ አደርገዋለሁ፤ እጅግም አበዛዋለሁ። ደግሞም 12 አለቆች ከእሱ ይወጣሉ፤ ታላቅ ብሔርም አደርገዋለሁ። 21  ሆኖም የዛሬ ዓመት በዚሁ ጊዜ ሣራ ከምትወልድልህ ከይስሐቅ ጋር ቃል ኪዳኔን እመሠርታለሁ።” 22  አምላክ ከአብርሃም ጋር ተነጋግሮ ሲያበቃ ከእሱ ተለይቶ ወደ ላይ ወጣ። 23  ከዚያም አብርሃም ልጁን እስማኤልን፣ በቤቱ የተወለዱትንና በገንዘቡ የገዛቸውን ወንዶች ሁሉ እንዲሁም በአብርሃም ቤት የሚገኙትን ወንዶች ሁሉ ወስዶ ልክ አምላክ በነገረው መሠረት በዚያኑ ዕለት ሸለፈታቸውን ገረዘ። 24  አብርሃም ሸለፈቱን ሲገረዝ የ99 ዓመት ሰው ነበር። 25  ልጁ እስማኤል ሸለፈቱን በተገረዘበት ጊዜ ደግሞ 13 ዓመቱ ነበር። 26  በዚሁ ዕለት አብርሃም ተገረዘ፤ ልጁ እስማኤልም ተገረዘ። 27  በተጨማሪም በቤቱ የሚገኙ ወንዶች ሁሉ፣ በቤት የተወለዱ ሁሉ እንዲሁም ከባዕድ ሰው በገንዘብ የተገዙ ሁሉ ከእሱ ጋር ተገረዙ።
[]
[]
[]
[]
12,513
18  ከዚያም አብርሃም በጣም ሞቃታማ በሆነው የቀኑ ክፍለ ጊዜ ድንኳኑ ደጃፍ ላይ ተቀምጦ ሳለ ይሖዋ በማምሬ ትላልቅ ዛፎች አጠገብ ተገለጠለት። 2  ቀና ብሎም ሲመለከት እሱ ካለበት ትንሽ ራቅ ብሎ ሦስት ሰዎች ቆመው አየ። ሰዎቹን ባያቸው ጊዜም ከድንኳኑ ደጃፍ ተነስቶ ወደ እነሱ እየሮጠ ሄደ፤ ወደ መሬት ዝቅ ብሎም ሰገደ። 3  ከዚያም እንዲህ አለ፦ “ይሖዋ፣ እንግዲህ በፊትህ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ እባክህ አገልጋይህን አልፈኸው አትሂድ። 4  እባካችሁ ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁና እግራችሁን ታጠቡ፤ ከዚያም ከዛፉ ሥር አረፍ በሉ። 5  ወደ አገልጋያችሁ ከመጣችሁ አይቀር፣ ብርታት እንድታገኙ ትንሽ እህል ላምጣላችሁና ቅመሱ፤ ከዚያም ጉዟችሁን ትቀጥላላችሁ።” በዚህ ጊዜ እነሱ “እሺ፣ እንዳልከው አድርግ” አሉት። 6  በመሆኑም አብርሃም ሣራ ወዳለችበት ወደ ድንኳኑ በፍጥነት ሄዶ “ቶሎ በይ! ሦስት መስፈሪያ የላመ ዱቄት ወስደሽ አቡኪና ቂጣ ጋግሪ” አላት። 7  በመቀጠልም አብርሃም ወደ መንጋው ሮጦ በመሄድ ሥጋው ገር የሆነ ፍርጥም ያለ ወይፈን መረጠ። ለአገልጋዩም ሰጠው፤ እሱም ለማዘጋጀት ተጣደፈ። 8  ከዚያም ቅቤና ወተት እንዲሁም ያዘጋጀውን ወይፈን ወስዶ ምግቡን አቀረበላቸው። እየበሉ ሳሉም ዛፉ ሥር አጠገባቸው ቆሞ ነበር። 9  እነሱም “ሚስትህ ሣራ የት አለች?” አሉት። እሱም “እዚህ ድንኳኑ ውስጥ ናት” አላቸው። 10  ከመካከላቸውም አንዱ ንግግሩን በመቀጠል “የዛሬ ዓመት በዚሁ ጊዜ በእርግጥ ወደ አንተ እመለሳለሁ፤ ሚስትህ ሣራም ወንድ ልጅ ትወልዳለች” አለ። በዚህ ጊዜ ሣራ ከሰውየው በስተ ጀርባ ባለው በድንኳኑ ደጃፍ ላይ ሆና ታዳምጥ ነበር። 11  አብርሃምና ሣራ አርጅተው፣ ዕድሜያቸውም ገፍቶ ነበር። ሣራ ልጅ የመውለጃዋ ዕድሜ አልፎ ነበር። 12  በመሆኑም ሣራ “አሁን እንዲህ አርጅቼ ጌታዬም ዕድሜው ገፍቶ እያለ በእርግጥ እንዲህ ዓይነት ደስታ ላገኝ እችላለሁ?” ብላ በማሰብ በልቧ ሳቀች። 13  ከዚያም ይሖዋ አብርሃምን እንዲህ አለው፦ “ሣራ ‘እንዲህ ካረጀሁ በኋላም እንኳ ልወልድ ነው ማለት ነው?’ በማለት የሳቀችው ለምንድን ነው? 14  ለይሖዋ የሚሳነው ነገር አለ? የዛሬ ዓመት በዚሁ በተወሰነው ጊዜ ወደ አንተ እመለሳለሁ፤ ሣራም ወንድ ልጅ ትወልዳለች።” 15  ሣራ ግን ስለፈራች “ኧረ አልሳቅኩም!” ስትል ካደች። በዚህ ጊዜ “እንዴ! ሳቅሽ እንጂ” አላት። 16  ሰዎቹም ለመሄድ በተነሱና ቁልቁል ወደ ሰዶም በተመለከቱ ጊዜ አብርሃም ሊሸኛቸው አብሯቸው ሄደ። 17  ይሖዋ እንዲህ አለ፦ “እኔ ላደርገው ያሰብኩትን ነገር ከአብርሃም ደብቄ አውቃለሁ? 18  አብርሃም በእርግጥ ታላቅና ኃያል ብሔር ይሆናል፤ የምድር ብሔራትም ሁሉ በእሱ አማካኝነት ይባረካሉ። 19  እኔ ከአብርሃም ጋር የተዋወቅኩት ትክክለኛና ተገቢ የሆነውን ነገር በማድረግ የይሖዋን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቹንና ከእሱ በኋላ የሚመጣውን ቤተሰቡን እንዲያዝዝ ነው፤ እንዲህ ካደረገ ይሖዋ አብርሃምን አስመልክቶ ቃል የገባውን ነገር ይፈጽምለታል።” 20  ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለ፦ “በሰዶምና በገሞራ ላይ የሚሰማው ጩኸት በእርግጥም ታላቅ ነው፤ ኃጢአታቸውም እጅግ ከባድ ሆኗል። 21  ድርጊታቸው እኔ ዘንድ እንደደረሰው ጩኸት መሆን አለመሆኑን ለማየት ወደዚያ እወርዳለሁ። ነገሩ እንደዚያ ካልሆነም ማወቅ እችላለሁ።” 22  ሰዎቹም ከዚያ ተነስተው ወደ ሰዶም አቀኑ፤ ይሖዋ ግን እዚያው ከአብርሃም ጋር ቀረ። 23  ከዚያም አብርሃም ቀረብ ብሎ እንዲህ አለ፦ “በእርግጥ ጻድቁን ከኃጢአተኛው ጋር አብረህ ታጠፋለህ? 24  እስቲ በከተማዋ ውስጥ 50 ጻድቅ ሰዎች አሉ እንበል። ታዲያ ሁሉንም ዝም ብለህ ታጠፋቸዋለህ? በውስጧ ስለሚኖሩት 50 ጻድቃን ስትል ስፍራውን አትምርም? 25  በጻድቁም ሆነ በኃጢአተኛው ላይ ተመሳሳይ ነገር እንዲደርስ የሚያደርግ እንዲህ ዓይነት እርምጃ በመውሰድ ጻድቁን ከኃጢአተኛው ጋር አንድ ላይ ትገድላለህ ብሎ ማሰብ ፈጽሞ የማይሆን ነገር ነው! ይህ በአንተ ዘንድ ፈጽሞ የማይታሰብ ነገር ነው። የምድር ሁሉ ዳኛ ትክክል የሆነውን ነገር አያደርግም?” 26  ከዚያም ይሖዋ “በሰዶም ከተማ ውስጥ 50 ጻድቅ ሰዎች ባገኝ ስለ እነሱ ስል ስፍራውን በሙሉ እምራለሁ” አለ። 27  አብርሃም ግን እንደገና እንዲህ ሲል መለሰ፦ “መቼም እኔ ትቢያና አመድ ሆኜ ሳለሁ አንዴ ደፍሬ ከይሖዋ ጋር መነጋገር ጀምሬያለሁ። 28  ከ50ዎቹ ጻድቃን መካከል አምስት ጎደሉ እንበል። ታዲያ በአምስቱ የተነሳ መላዋን ከተማ ታጠፋለህ?” እሱም “በዚያ 45 ባገኝ ከተማዋን አላጠፋም” አለ። 29  አብርሃም ግን በድጋሚ “በዚያ 40 ተገኙ እንበል” አለው። እሱም መልሶ “ስለ 40ዎቹ ስል አላደርገውም” አለ። 30  አብርሃም ግን በመቀጠል “ይሖዋ እባክህ፣ አትቆጣና አሁንም ልናገር፤ እንደው በዚያ 30 ብቻ ቢገኙስ?” አለ። እሱም “በዚያ 30 ካገኘሁ አላደርገውም” ሲል መለሰ። 31  አብርሃም ግን እንዲህ በማለት ቀጠለ፦ “መቼም አንዴ ደፍሬ ከይሖዋ ጋር መነጋገር ጀምሬያለሁ፤ እንደው በዚያ 20 ብቻ ቢገኙስ?” እሱም መልሶ “ስለ 20ዎቹ ስል አላጠፋትም” አለ። 32  በመጨረሻም አብርሃም እንዲህ አለ፦ “ይሖዋ እባክህ፣ አትቆጣና አንድ ጊዜ ብቻ ልናገር፤ በዚያ አሥር ብቻ ቢገኙስ?” እሱም መልሶ “ስለ አሥሩ ስል አላጠፋትም” አለ። 33  ይሖዋም ከአብርሃም ጋር ተነጋግሮ ሲጨርስ ጉዞውን ቀጠለ፤ አብርሃም ደግሞ ወደ ስፍራው ተመለሰ።
[]
[]
[]
[]
12,514
19  ሁለቱ መላእክት ምሽት ላይ ሰዶም ደረሱ፤ ሎጥም በሰዶም በር ተቀምጦ ነበር። እሱም ባያቸው ጊዜ ተነስቶ ወደ እነሱ ሄደ፤ በግንባሩም መሬት ላይ ተደፋ። 2  እንዲህም አለ፦ “ጌቶቼ፣ እባካችሁ ወደ አገልጋያችሁ ቤት ጎራ በሉና እደሩ፤ እግራችሁንም ታጠቡ። ከዚያም በማለዳ ተነስታችሁ ጉዟችሁን ትቀጥላላችሁ።” እነሱም መልሰው “አይሆንም፣ አደባባዩ ላይ እናድራለን” አሉ። 3  እሱ ግን አጥብቆ ስለለመናቸው አብረውት ወደ ቤቱ ሄዱ። ከዚያም ግብዣ አደረገላቸው። ቂጣም ጋገረላቸው፤ እነሱም በሉ። 4  ከመተኛታቸውም በፊት የከተማዋ ሰዎች ማለትም በሰዶም ያሉ ወንዶች ሁሉ ከልጅ እስከ አዋቂ ድረስ ግልብጥ ብለው በመውጣት ቤቱን ከበቡት። 5  ሎጥንም ደጋግመው በመጥራት “በዚህ ምሽት ወደ አንተ የመጡት ሰዎች የት አሉ? ከእነሱ ጋር የፆታ ግንኙነት እንድንፈጽም ወደ ውጭ አውጣልን” ይሉት ጀመር። 6  ከዚያም ሎጥ ወደ እነሱ ወደ ውጭ ወጣ፤ በሩንም ከኋላው ዘጋው። 7  እንዲህም አላቸው፦ “እባካችሁ ወንድሞቼ፣ እንዲህ ያለ ክፉ ድርጊት አትፈጽሙ። 8  እባካችሁ፣ ከወንድ ጋር የፆታ ግንኙነት ፈጽመው የማያውቁ ሁለት ሴቶች ልጆች አሉኝ። እባካችሁ፣ እነሱን ላውጣላችሁና መልካም መስሎ የታያችሁን አድርጉባቸው። እነዚህ ሰዎች ግን በጣሪያዬ ጥላ ሥር ስለተጠለሉ በእነሱ ላይ ምንም ነገር አታድርጉ።” 9  በዚህ ጊዜ ሰዎቹ “ዞር በል!” አሉት። ከዚያም “ይህ ወገን የሌለው መጤ፣ ደግሞ በእኛ ላይ ዳኛ ልሁን ይላል እንዴ! በእነሱ ላይ ልናደርግ ካሰብነው የከፋ ነገር እንዳናደርግብህ” አሉት። ሎጥንም በኃይል ገፉት፤ በሩንም ሊሰብሩት ተቃረቡ። 10  ስለሆነም ውስጥ የነበሩት ሰዎች እጃቸውን ወደ ውጭ ዘርግተው ሎጥን እነሱ ወዳሉበት ወደ ቤት አስገቡት፤ በሩንም ዘጉት። 11  ሆኖም በቤቱ ደጃፍ ላይ የነበሩትን ሰዎች ከትንሹ አንስቶ እስከ ትልቁ ድረስ አሳወሯቸው፤ በዚህም የተነሳ ሰዎቹ በሩን ለማግኘት ሲዳክሩ ደከሙ። 12  ከዚያም ሰዎቹ ሎጥን እንዲህ አሉት፦ “እዚህ የሚኖሩ ሌሎች ዘመዶች አሉህ? አማቾችህን፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህን እንዲሁም በከተማዋ ውስጥ የሚኖር ዘመድ አዝማድህን በሙሉ ከዚህ ስፍራ ይዘህ ውጣ! 13  ይህን ስፍራ ልናጠፋው ነው፤ ምክንያቱም ሕዝቦቿን በተመለከተ የሚሰማው ጩኸት በይሖዋ ፊት እየጨመረ ስለመጣ ይሖዋ ከተማዋን እንድናጠፋት ልኮናል።” 14  በመሆኑም ሎጥ ወጥቶ የሴት ልጆቹ እጮኛ የሆኑትን አማቾቹን “ተነሱ! ይሖዋ ከተማዋን ሊያጠፋት ስለሆነ ከዚህ ስፍራ ውጡ!” አላቸው። አማቾቹ ግን የሚያሾፍ መሰላቸው። 15  ጎህ ሲቀድ መላእክቱ ሎጥን “ተነስ! በከተማዋ በደል የተነሳ እንዳትጠፋ ከአንተ ጋር ያሉትን ሚስትህንና ሁለቱን ሴቶች ልጆችህን ይዘህ ውጣ!” በማለት አቻኮሉት። 16  ሎጥ በዘገየ ጊዜ ይሖዋ ስለራራለት ሰዎቹ የእሱን እጅ፣ የሚስቱን እጅና የሁለቱን ሴቶች ልጆቹን እጅ ይዘው ከከተማዋ አስወጡት። 17  ልክ ከተማዋ ዳርቻ ላይ እንዳደረሷቸውም ከእነሱ አንዱ እንዲህ አለ፦ “ሕይወትህን ለማትረፍ ሽሽ! ወደ ኋላህ እንዳትመለከት፤ አውራጃውንም ለቀህ እስክትወጣ ድረስ የትኛውም ቦታ ላይ እንዳትቆም! እንዳትጠፋ ወደ ተራራማው አካባቢ ሽሽ!” 18  ከዚያም ሎጥ እንዲህ አላቸው፦ “እባክህ ይሖዋ፣ ወደዚያስ አልሂድ! 19  መቼም አገልጋይህ በፊትህ ሞገስ አግኝቷል፤ ሕይወቴን በማትረፍ ታላቅ ደግነት አሳይተኸኛል፤ ሆኖም አደጋ እንዳይደርስብኝና እንዳልሞት ስለምፈራ ወደ ተራራማው አካባቢ ሸሽቼ ማምለጥ አልችልም። 20  እባክህ ይህች ከተማ ቅርብ ነች፤ ወደዚያ መሸሽ እችላለሁ፤ ትንሽ ስፍራ እኮ ናት። እባክህ፣ ወደዚያ መሸሽ እችላለሁ? ትንሽ ስፍራ እኮ ናት። እንደዚያ ከሆነ እተርፋለሁ።” 21  እሱም እንዲህ አለው፦ “እሺ ይሁን፣ ያልካትን ከተማ ባለማጥፋት አሁንም አሳቢነት አሳይሃለሁ። 22  ፍጠን! አንተ እዚያ እስክትደርስ ድረስ ምንም ነገር ማድረግ ስለማልችል ወደዚያ ሽሽ!” ከተማዋን ዞአር ብሎ የሰየማት ለዚህ ነው። 23  ሎጥ ዞአር ሲደርስ ፀሐይ በምድሩ ላይ ወጥታ ነበር። 24  ከዚያም ይሖዋ በሰዶምና በገሞራ ላይ እሳትና ድኝ አዘነበ፤ ይህም የመጣው ከሰማይ ከይሖዋ ዘንድ ነው። 25  እሱም እነዚህን ከተሞች ገለባበጠ፤ አዎ፣ የከተሞቹን ነዋሪዎችና የምድሪቱን ተክል ሁሉ ጨምሮ መላውን አውራጃ ገለባበጠ። 26  ሆኖም ከሎጥ በስተ ኋላ የነበረችው የሎጥ ሚስት ወደ ኋላ ዞራ መመልከት ጀመረች፤ እሷም የጨው ዓምድ ሆነች። 27  አብርሃምም በማለዳ ተነሳ፤ ቀደም ሲል በይሖዋ ፊት ቆሞ ወደነበረበትም ስፍራ ሄደ። 28  ወደ ሰዶምና ወደ ገሞራ እንዲሁም በአውራጃው ውስጥ ወዳሉት ከተሞች በሙሉ ቁልቁል ሲያይም የሚያስገርም ነገር ተመለከተ። ከእቶን እንደሚወጣ ያለ የሚትጎለጎል ጭስ ከምድሩ እየተትጎለጎለ ይወጣ ነበር! 29  አምላክ የአውራጃውን ከተሞች ባጠፋበት ጊዜ ሎጥ ይኖርባቸው ከነበሩትና አምላክ ካጠፋቸው ከተሞች ውስጥ ሎጥን በማውጣት አብርሃምን አሰበው። 30  በኋላም ሎጥ በዞአር መኖር ስለፈራ ከዞአር ወጥቶ ከሁለቱ ሴቶች ልጆቹ ጋር በተራራማው አካባቢ መኖር ጀመረ። ስለዚህ ከሁለቱ ሴቶች ልጆቹ ጋር በዋሻ ውስጥ መኖር ጀመረ። 31  የመጀመሪያዋ ልጅ ታናሿን እንዲህ አለቻት፦ “አባታችን አርጅቷል፤ በመላው ምድር ላይ ባለው ልማድ መሠረት ከእኛ ጋር ግንኙነት የሚፈጽም ወንድ በዚህ አካባቢ የለም። 32  ነይ፣ አባታችንን የወይን ጠጅ እናጠጣውና ከእሱ ጋር እንተኛ፤ እንዲህ በማድረግ ከአባታችን ዘር እናስቀር።” 33  በመሆኑም በዚያ ምሽት አባታቸውን ደጋግመው የወይን ጠጅ አጠጡት፤ ከዚያም የመጀመሪያዋ ልጅ ገብታ ከአባቷ ጋር ተኛች። እሱ ግን ስትተኛም ሆነ ስትነሣ አላወቀም። 34  በማግስቱም የመጀመሪያዋ ልጅ ታናሿን እንዲህ አለቻት፦ “ይኸው እኔ ትናንት ሌሊት ከአባቴ ጋር ተኝቻለሁ። ዛሬ ማታም የወይን ጠጅ እናጠጣው። ከዚያም አንቺ ገብተሽ ከእሱ ጋር ትተኚያለሽ። እንዲህ በማድረግ ከአባታችን ዘር እናስቀር።” 35  በመሆኑም በዚያ ምሽትም አባታቸውን ደጋግመው የወይን ጠጅ አጠጡት፤ ከዚያም ታናሽየዋ ልጅ ሄዳ ከአባቷ ጋር ተኛች። እሱ ግን ስትተኛም ሆነ ስትነሳ አላወቀም። 36  ስለሆነም ሁለቱም የሎጥ ሴቶች ልጆች ከአባታቸው ፀነሱ። 37  ታላቅየዋም ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሞዓብ አለችው፤ እሱም ዛሬ ያሉት ሞዓባውያን አባት ነው። 38  ታናሽየዋም ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ቤንአሚ አለችው፤ እሱም ዛሬ ያሉት አሞናውያን አባት ነው።
[]
[]
[]
[]
12,515
2  በዚህ መንገድ ሰማያትንና ምድርን እንዲሁም በውስጣቸው ያለውን ነገር ሁሉ የመፍጠሩ ሥራ ተጠናቀቀ። 2  በሰባተኛውም ቀን አምላክ ይሠራው የነበረውን ሥራ አጠናቀቀ፤ በሰባተኛውም ቀን ይሠራው ከነበረው ሥራ ሁሉ ማረፍ ጀመረ። 3  አምላክም ሰባተኛውን ቀን ባረከው እንዲሁም ቀደሰው፤ ምክንያቱም አምላክ ከመፍጠር ሥራው ሁሉ፣ ሊሠራ ካሰበው ነገር ሁሉ ያረፈው ከዚያ ቀን አንስቶ ነው። 4  ሰማያትና ምድር በተፈጠሩበት ጊዜ፣ ይሖዋ አምላክ ምድርንና ሰማይን በሠራበት ቀን የተከናወነው ነገር ይህ ነው። 5  በዚህ ጊዜ በምድር ላይ ምንም ዓይነት የሜዳ ቁጥቋጦ አልነበረም፤ እንዲሁም በሜዳ ላይ ምንም ዓይነት ተክል አልበቀለም፤ ምክንያቱም ይሖዋ አምላክ በምድር ላይ ዝናብ እንዲዘንብ አላደረገም ነበር፤ መሬቱን የሚያለማም ሰው አልነበረም። 6  ይሁንና ተን ከምድር እየተነሳ መላውን መሬት ያጠጣ ነበር። 7  ይሖዋ አምላክም ሰውን ከምድር አፈር ሠራው፤ በአፍንጫውም የሕይወትን እስትንፋስ እፍ አለበት፤ ሰውየውም ሕያው ሰው ሆነ። 8  በተጨማሪም ይሖዋ አምላክ በስተ ምሥራቅ፣ በኤደን የአትክልት ስፍራ ተከለ፤ የሠራውንም ሰው በዚያ አስቀመጠው። 9  ከዚያም ይሖዋ አምላክ ለማየት የሚያስደስተውንና ለምግብነት መልካም የሆነውን ዛፍ ሁሉ ከመሬት አበቀለ። በተጨማሪም በአትክልቱ ስፍራ መካከል የሕይወት ዛፍ እንዲሁም የመልካምና ክፉ እውቀት ዛፍ አበቀለ። 10  የአትክልቱን ስፍራ የሚያጠጣ ወንዝ ከኤደን ወጥቶ ይፈስ ነበር፤ ከዚያም ተከፋፍሎ አራት ወንዝ ሆነ። 11  የመጀመሪያው ወንዝ ስም ፊሶን ነው፤ ይህ ወንዝ ወርቅ የሚገኝበትን መላውን የሃዊላ ምድር የሚከብ ነው። 12  የዚያ አገር ወርቅ ምርጥ ነው። በተጨማሪም በዚያ ጥሩ መዓዛ ያለው ሙጫና የኦኒክስ ድንጋዮች ይገኛሉ። 13  የሁለተኛው ወንዝ ስም ግዮን ነው፤ ይህ ወንዝ መላውን የኢትዮጵያ ምድር የሚከብ ነው። 14  የሦስተኛው ወንዝ ስም ጤግሮስ ነው፤ ይህ ወንዝ ከአሦር በስተ ምሥራቅ የሚፈስ ነው። አራተኛው ወንዝ ደግሞ ኤፍራጥስ ነው። 15  ይሖዋ አምላክ ሰውየውን ወስዶ እንዲያለማውና እንዲንከባከበው በኤደን የአትክልት ስፍራ አስቀመጠው። 16  በተጨማሪም ይሖዋ አምላክ ለሰውየው ይህን ትእዛዝ ሰጠው፦ “በአትክልቱ ስፍራ ውስጥ ከሚገኘው ዛፍ ሁሉ እስክትረካ ድረስ መብላት ትችላለህ። 17  ከመልካምና ክፉ እውቀት ዛፍ ግን አትብላ፤ ምክንያቱም ከዚህ ዛፍ በበላህ ቀን በእርግጥ ትሞታለህ።” 18  ከዚያም ይሖዋ አምላክ “ሰውየው ብቻውን መሆኑ መልካም አይደለም። ማሟያ የምትሆነውን ረዳት እሠራለታለሁ” አለ። 19  ይሖዋ አምላክም እያንዳንዱን የዱር እንስሳ እንዲሁም በሰማያት ላይ የሚበረውን እያንዳንዱን ፍጥረት ከአፈር ሠርቶ ነበር፤ ከዚያም ሰውየው እያንዳንዳቸውን ምን ብሎ እንደሚጠራቸው ለማየት ሁሉንም ወደ እሱ አመጣቸው፤ ሰውየው ለእያንዳንዱ ሕያው ፍጡር የሰጠው መጠሪያም የዚያ ፍጡር ስም ሆነ። 20  በመሆኑም ሰውየው ለቤት እንስሳት በሙሉ፣ በሰማያት ላይ ለሚበርሩ ፍጥረታት እንዲሁም ለዱር እንስሳት ሁሉ ስም አወጣላቸው፤ ለሰው ግን ማሟያ የሚሆን ረዳት አልነበረውም። 21  ስለሆነም ይሖዋ አምላክ በሰውየው ላይ ከባድ እንቅልፍ ጣለበት፤ እንቅልፍ ወስዶት ሳለም ከጎድን አጥንቶቹ አንዷን ወሰደ፤ ቦታውንም በሥጋ ደፈነው። 22  ይሖዋ አምላክም ከሰውየው የወሰዳትን የጎድን አጥንት ሴት አድርጎ ሠራት፤ ሴቲቱንም ወደ ሰውየው አመጣት። 23  በዚህ ጊዜ ሰውየው እንዲህ አለ፦ “እንግዲህ እሷ የአጥንቶቼ አጥንት፣የሥጋዬም ሥጋ ናት። እሷ ከወንድ ስለተገኘች‘ሴት’ ትባላለች።” 24  በዚህም ምክንያት ሰው ከአባቱና ከእናቱ ይለያል፤ ከሚስቱም ጋር ይጣበቃል። ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ። 25  ሰውየውም ሆነ ሚስቱ ራቁታቸውን ነበሩ፤ እንደዚያም ሆኖ ኀፍረት አይሰማቸውም ነበር።
[]
[]
[]
[]
12,516
20  አብርሃም ድንኳኑን ከዚያ ነቅሎ ወደ ኔጌብ ምድር ሄደ፤ በቃዴስና በሹር መካከልም መኖር ጀመረ። በጌራራ እየኖረ ሳለ 2  በድጋሚ ሚስቱን ሣራን “እህቴ ናት” አለ። በመሆኑም የጌራራ ንጉሥ አቢሜሌክ ሰዎችን ልኮ ሣራን አስመጣት፤ ከዚያም ወሰዳት። 3  ከዚያም አምላክ ለአቢሜሌክ ሌሊት በሕልም ተገልጦለት “በወሰድካት ሴት የተነሳ ትሞታለህ፤ ምክንያቱም እሷ ያገባችና ባለቤት ያላት ሴት ናት” አለው። 4  ሆኖም አቢሜሌክ ወደ እሷ አልቀረበም ነበር። በመሆኑም እንዲህ አለ፦ “ይሖዋ፣ ምንም በደል ያልፈጸመን ብሔር ታጠፋለህ? 5  እሱ ‘እህቴ ናት’ አላለኝም? እሷስ ብትሆን ‘ወንድሜ ነው’ አላለችም? ይህን ያደረግኩት በቅን ልቦናና በንጹሕ እጅ ነው።” 6  ከዚያም እውነተኛው አምላክ በሕልም ተገልጦለት እንዲህ አለው፦ “ይህን ያደረግከው በቅን ልቦና ተነሳስተህ እንደሆነ አውቃለሁ፤ በእኔም ላይ ኃጢአት እንዳትሠራ ጠብቄሃለሁ። እንድትነካት ያልፈቀድኩልህም ለዚህ ነው። 7  በል አሁን የሰውየውን ሚስት መልስ፤ እሱ ነቢይ ነውና፤ ስለ አንተም ልመና ያቀርባል፤ አንተም በሕይወት ትኖራለህ። እሷን ባትመልስ ግን በእርግጥ እንደምትሞት እወቅ፤ አንተም ሆንክ የአንተ የሆነው ሁሉ ትሞታላችሁ።” 8  አቢሜሌክ በማለዳ ተነሳ፤ አገልጋዮቹንም በሙሉ ጠርቶ የሆነውን ሁሉ ነገራቸው፤ እነሱም በጣም ፈሩ። 9  ከዚያም አቢሜሌክ አብርሃምን ጠርቶ እንዲህ አለው፦ “ይህ ያደረግክብን ነገር ምንድን ነው? በእኔም ሆነ በግዛቴ ላይ እንዲህ ያለውን ታላቅ ኃጢአት ያመጣህብን ለመሆኑ ምን በድዬህ ነው? ያደረግክብኝ ነገር ትክክል አይደለም።” 10  በመቀጠልም አቢሜሌክ አብርሃምን “ለመሆኑ ይህን ያደረግከው ምን አስበህ ነው?” አለው። 11  አብርሃምም እንዲህ አለው፦ “ይህን ያደረግኩት ‘በዚህ ስፍራ እንደሆነ ፈሪሃ አምላክ የሚባል ነገር የለም፤ ሰዎቹ ለሚስቴ ሲሉ ሊገድሉኝ ይችላሉ’ ብዬ ስለሰጋሁ ነው። 12  ደግሞም እኮ በእርግጥ እህቴ ናት፤ የእናቴ ልጅ ባትሆንም የአባቴ ልጅ ናት፤ እሷም ሚስቴ ሆነች። 13  በመሆኑም አምላክ ከአባቴ ቤት ወጥቼ ከአገር አገር እየዞርኩ እንድኖር በነገረኝ ጊዜ ‘በምንሄድበት ስፍራ ሁሉ “ወንድሜ ነው” ብለሽ በመናገር ታማኝ ፍቅር አሳዪኝ’ ብያት ነበር።” 14  ከዚያም አቢሜሌክ በጎችን፣ ከብቶችን እንዲሁም ወንድና ሴት አገልጋዮችን ለአብርሃም ሰጠው፤ ሚስቱን ሣራንም መለሰለት። 15  በተጨማሪም አቢሜሌክ “አገሬ አገርህ ናት፤ ደስ ባለህ ቦታ መኖር ትችላለህ” አለው። 16  ሣራንም እንዲህ አላት፦ “ይኸው ለወንድምሽ 1,000 የብር ሰቅል እሰጠዋለሁ። ይህም አንቺ ንጹሕ ሰው መሆንሽን ከአንቺ ጋር ባሉት ሰዎች ሁሉ ፊትም ሆነ በሌሎች ሰዎች ፊት የሚያሳውቅ ምልክት ነው፤ አንቺም ከማንኛውም ነቀፋ ነፃ ነሽ።” 17  አብርሃምም ወደ እውነተኛው አምላክ ልመና አቀረበ፤ አምላክም አቢሜሌክን፣ ሚስቱንና ሴት ባሪያዎቹን ፈወሳቸው፤ እነሱም ልጆች መውለድ ጀመሩ፤ 18  ምክንያቱም ይሖዋ በአብርሃም ሚስት በሣራ የተነሳ በአቢሜሌክ ቤት ያሉትን ሴቶች ሁሉ መሃን አድርጎ ነበር።
[]
[]
[]
[]
12,517
21  ይሖዋ ልክ በተናገረው መሠረት ሣራን አሰባት፤ ይሖዋም ለሣራ ቃል የገባላትን አደረገላት። 2  በመሆኑም ሣራ ፀነሰች፤ ለአብርሃምም አምላክ ቃል በገባለት በተወሰነው ጊዜ ላይ በስተርጅናው ወንድ ልጅ ወለደችለት። 3  አብርሃም ሣራ የወለደችለትን ልጅ ይስሐቅ ብሎ ጠራው። 4  አብርሃምም ልክ አምላክ ባዘዘው መሠረት ልጁ ይስሐቅ ስምንት ቀን ሲሆነው ገረዘው። 5  አብርሃም ልጁ ይስሐቅ ሲወለድ ዕድሜው 100 ዓመት ነበር። 6  ከዚያም ሣራ “አምላክ በደስታ እንድስቅ አድርጎኛል፤ ይህን የሰማም ሁሉ ከእኔ ጋር አብሮ ይስቃል” አለች። 7  አክላም “ለመሆኑ ለአብርሃም ‘ሣራ ልጆች ታጠባለች’ ማን ብሎት ያውቃል? እኔ ግን ይኸው በስተርጅናው ወንድ ልጅ ወለድኩለት” አለች። 8  ልጁም አደገ፤ ጡትም ጣለ፤ አብርሃምም ይስሐቅ ጡት በጣለበት ቀን ትልቅ ግብዣ አደረገ። 9  ሣራም ግብፃዊቷ አጋር ለአብርሃም የወለደችለት ልጅ በይስሐቅ ላይ እንደሚያፌዝበት በተደጋጋሚ አስተዋለች። 10  ስለዚህ አብርሃምን “ይህችን ባሪያና ልጇን ከዚህ አባር፤ ምክንያቱም የዚህች ባሪያ ልጅ ከልጄ ከይስሐቅ ጋር ወራሽ አይሆንም!” አለችው። 11  አብርሃም ግን ሣራ ስለ ልጁ የተናገረችው ነገር በጣም ቅር አሰኘው። 12  ከዚያም አምላክ አብርሃምን እንዲህ አለው፦ “ሣራ ስለ ልጁና ስለ ባሪያህ እየነገረችህ ያለው ነገር ምንም ቅር አያሰኝህ። ዘርህ የሚጠራልህ በይስሐቅ በኩል ስለሆነ የምትልህን ስማ። 13  የባሪያይቱም ልጅ ቢሆን ልጅህ ስለሆነ ከእሱ አንድ ብሔር እንዲገኝ አደርጋለሁ።” 14  ስለዚህ አብርሃም በማለዳ ተነሳ፤ ለአጋርም ምግብና የውኃ አቁማዳ ሰጣት። እነዚህንም በትከሻዋ አሸከማት፤ ከዚያም ከልጁ ጋር አሰናበታት። እሷም ሄደች፤ በቤርሳቤህ ምድረ በዳም ትንከራተት ጀመር። 15  በመጨረሻም በአቁማዳው ውስጥ የነበረው ውኃ አለቀ፤ እሷም ልጁን አንዱ ቁጥቋጦ ሥር ጣለችው። 16  ከዚያም “ልጁ ሲሞት ማየት አልፈልግም” ብላ የቀስት ውርወራ ያህል ርቃ ተቀመጠች። እሷም ትጮኽና ታለቅስ ጀመር። 17  በዚህ ጊዜ አምላክ የልጁን ድምፅ ሰማ፤ የአምላክም መልአክ ከሰማይ አጋርን ጠርቶ እንዲህ አላት፦ “አጋር፣ ምን ሆነሻል? ልጁ ካለበት ቦታ ሆኖ ሲያለቅስ አምላክ ስለሰማ አይዞሽ አትፍሪ። 18  ተነሽ፣ ልጁንም አንስተሽ በእጅሽ ያዢው፤ ምክንያቱም እኔ ታላቅ ብሔር አደርገዋለሁ።” 19  ከዚያም አምላክ ዓይኖቿን ከፈተላት፤ የውኃ ጉድጓድም ተመለከተች። ወደዚያም ሄዳ በአቁማዳው ውኃ ሞላች፤ ልጁንም አጠጣችው። 20  ልጁም እያደገ ሄደ፤ አምላክም ከልጁ ጋር ነበር። እሱም የሚኖረው በምድረ በዳ ነበር፤ ቀስተኛም ሆነ። 21  እሱም በፋራን ምድረ በዳ ኖረ፤ እናቱም ከግብፅ ምድር ሚስት አመጣችለት። 22  በዚያን ጊዜ አቢሜሌክ ከሠራዊቱ አዛዥ ከፊኮል ጋር ሆኖ አብርሃምን እንዲህ አለው፦ “በምታደርገው ነገር ሁሉ አምላክ ከአንተ ጋር ነው። 23  ስለዚህ እኔንም ሆነ ልጆቼንና ዘሮቼን እንደማትክድ እንዲሁም ለእኔም ሆነ ለምትኖርባት ምድር እኔ ያሳየሁህ ዓይነት ታማኝ ፍቅር እንደምታሳይ በአምላክ ስም ማልልኝ።” 24  አብርሃምም “እሺ፣ እምላለሁ” አለ። 25  ሆኖም አብርሃም የአቢሜሌክ አገልጋዮች በጉልበት ስለወሰዱት የውኃ ጉድጓድ ለአቢሜሌክ ቅሬታውን ገለጸለት። 26  አቢሜሌክም መልሶ “ይህን ያደረገው ማን እንደሆነ አላውቅም፤ አንተም ብትሆን ስለዚህ ጉዳይ አልነገርከኝም፤ ስለዚህ ነገር ያለዛሬ አልሰማሁም” አለው። 27  በዚህ ጊዜ አብርሃም በጎችንና ከብቶችን ወስዶ ለአቢሜሌክ ሰጠው፤ ሁለቱም ቃል ኪዳን ገቡ። 28  አብርሃም ሰባት እንስት በጎችን ከመንጋው ለይቶ ለብቻቸው እንዲሆኑ ባደረገ ጊዜ 29  አቢሜሌክ አብርሃምን “እነዚህን ሰባት እንስት በጎች ለብቻቸው የለየኸው ለምንድን ነው?” አለው። 30  እሱም “ይህን ጉድጓድ የቆፈርኩት እኔ ለመሆኔ ምሥክር እንዲሆን እነዚህን ሰባት እንስት በጎች ከእጄ ውሰድ” አለው። 31  የቦታውን ስም ቤርሳቤህ ብሎ የጠራው በዚህ የተነሳ ነው፤ ምክንያቱም በዚያ ሁለቱ ተማምለዋል። 32  ስለዚህ በቤርሳቤህ ቃል ኪዳን ገቡ፤ ከዚያም አቢሜሌክ ከሠራዊቱ አዛዥ ከፊኮል ጋር ሆኖ ወደ ፍልስጤማውያን ምድር ተመለሰ። 33  ከዚያም በኋላ አብርሃም በቤርሳቤህ የታማሪስክ ዛፍ ተከለ፤ በዚያም የዘላለማዊውን አምላክ የይሖዋን ስም ጠራ። 34  አብርሃምም በፍልስጤማውያን ምድር ረዘም ላለ ጊዜ ኖረ።
[]
[]
[]
[]
12,518
22  ከዚህ በኋላ እውነተኛው አምላክ አብርሃምን ፈተነው፤ “አብርሃም!” ሲል ጠራው፤ እሱም መልሶ “አቤት!” አለ። 2  ከዚያም አምላክ እንዲህ አለው፦ “እባክህ ልጅህን፣ በጣም የምትወደውን አንድ ልጅህን ይስሐቅን ይዘህ ወደ ሞሪያ ምድር ሂድ፤ በዚያም እኔ በማሳይህ በአንዱ ተራራ ላይ የሚቃጠል መባ አድርገህ አቅርበው።” 3  ስለዚህ አብርሃም በማለዳ ተነስቶ አህያውን ከጫነ በኋላ ከአገልጋዮቹ መካከል ሁለቱን ከልጁ ከይስሐቅ ጋር ይዞ ለመሄድ ተነሳ። ለሚቃጠል መባ የሚሆን እንጨትም ፈለጠ፤ ከዚያም ተነስቶ እውነተኛው አምላክ ወዳሳየው ስፍራ ተጓዘ። 4  በሦስተኛውም ቀን አብርሃም ቀና ብሎ ቦታውን ከሩቅ ተመለከተ። 5  በዚህ ጊዜ አብርሃም አገልጋዮቹን “እናንተ አህያውን ይዛችሁ እዚህ ቆዩ፤ እኔና ልጄ ግን ወደዚያ በመሄድ በአምላክ ፊት ሰግደን ወደ እናንተ እንመለሳለን” አላቸው። 6  ስለዚህ አብርሃም ለሚቃጠል መባ የሚሆነውን እንጨት ወስዶ ልጁን ይስሐቅን አሸከመው። እሱ ደግሞ እሳቱንና ቢላውን ያዘ፤ ሁለቱም አብረው ሄዱ። 7  ይስሐቅም አባቱን አብርሃምን “አባዬ!” ሲል ጠራው። እሱም መልሶ “አቤት ልጄ!” አለው። ይስሐቅም “እሳቱና እንጨቱ ይኸውና፤ ለሚቃጠል መባ የሚሆነው በግ ግን የት አለ?” አለው። 8  በዚህ ጊዜ አብርሃም “ልጄ፣ ለሚቃጠል መባ የሚሆነውን በግ አምላክ ራሱ ያዘጋጃል” አለው። ሁለቱም አብረው ጉዟቸውን ቀጠሉ። 9  በመጨረሻም እውነተኛው አምላክ ወዳሳየው ስፍራ ደረሱ፤ አብርሃምም በዚያ መሠዊያ ሠርቶ እንጨቱን ረበረበበት። ልጁን ይስሐቅንም እጁንና እግሩን አስሮ በመሠዊያው ላይ በተረበረበው እንጨት ላይ አጋደመው። 10  ከዚያም አብርሃም ልጁን ለማረድ እጁን ዘርግቶ ቢላውን አነሳ። 11  ሆኖም የይሖዋ መልአክ ከሰማይ ጠርቶት “አብርሃም፣ አብርሃም!” አለው፤ እሱም መልሶ “አቤት!” አለ። 12  መልአኩም እንዲህ አለው፦ “በልጁ ላይ እጅህን አታሳርፍበት፤ ምንም ነገር አታድርግበት፤ ምክንያቱም ልጅህን፣ አንድ ልጅህን ለእኔ ለመስጠት ስላልሳሳህ አምላክን የምትፈራ ሰው እንደሆንክ አሁን በእርግጥ አውቄአለሁ።” 13  በዚህ ጊዜ አብርሃም ቀና ብሎ ሲመለከት ከእሱ ትንሽ እልፍ ብሎ ቀንዶቹ በጥሻ የተያዙ አውራ በግ አየ። በመሆኑም አብርሃም አውራውን በግ ካመጣ በኋላ በልጁ ምትክ የሚቃጠል መባ አድርጎ አቀረበው። 14  አብርሃምም ያን ስፍራ ይሖዋ ይርኤ ብሎ ጠራው። እስከ ዛሬም ድረስ “ይሖዋ በተራራው ላይ የሚያስፈልጉትን ነገሮች ያቀርባል” የሚባለው በዚህ የተነሳ ነው። 15  የይሖዋም መልአክ ከሰማይ ለሁለተኛ ጊዜ አብርሃምን ጠራው፤ 16  እንዲህም አለው፦ “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በራሴ እምላለሁ፤ ይህን ስላደረግክ እንዲሁም ልጅህን፣ አንድ ልጅህን ለመስጠት ስላልሳሳህ 17  በእርግጥ እባርክሃለሁ፤ ዘርህንም በሰማያት ላይ እንዳሉ ከዋክብትና በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ በእርግጥ አበዛዋለሁ፤ ዘርህም የጠላቶቹን በር ይወርሳል። 18  ቃሌን ስለሰማህ የምድር ብሔራት ሁሉ በዘርህ አማካኝነት ለራሳቸው በረከት ያገኛሉ።’” 19  ከዚያ በኋላ አብርሃም ወደ አገልጋዮቹ ተመለሰ፤ ተነስተውም አብረው ወደ ቤርሳቤህ ተመለሱ፤ አብርሃምም በቤርሳቤህ መኖሩን ቀጠለ። 20  ከዚህ በኋላ ለአብርሃም እንዲህ ተብሎ ተነገረው፦ “ሚልካም ለወንድምህ ለናኮር ወንዶች ልጆችን ወልዳለታለች፤ 21  እነሱም የበኩር ልጁ ዑጽ፣ ወንድሙ ቡዝ፣ የአራም አባት የሆነው ቀሙኤል፣ 22  ኬሰድ፣ ሃዞ፣ ፒልዳሽ፣ ይድላፍ እና ባቱኤል ናቸው።” 23  ባቱኤልም ርብቃን ወለደ። ሚልካ ለአብርሃም ወንድም ለናኮር እነዚህን ስምንቱን ወለደችለት። 24  ቁባቱ የሆነችው ረኡማም ተባህ፣ ጋሃም፣ ታሃሽ እና ማአካ የተባሉ ወንዶች ልጆችን ወለደች።
[]
[]
[]
[]
12,519
23  ሣራም 127 ዓመት ኖረች፤ ሣራ በሕይወት የኖረችው ይህን ያህል ዓመት ነበር። 2  ሣራም በቂርያትአርባ ይኸውም በከነአን ምድር በሚገኘው በኬብሮን ሞተች፤ አብርሃምም በሣራ ሞት ያዝንና ያለቅስ ጀመር። 3  ከዚያም አብርሃም ከሚስቱ አስከሬን አጠገብ ተነሳ፤ የሄትንም ወንዶች ልጆች እንዲህ አላቸው፦ 4  “እኔ በመካከላችሁ የምኖር የባዕድ አገር ሰውና ሰፋሪ ነኝ። አስከሬኔን ወስጄ እንድቀብር በመካከላችሁ የመቃብር ቦታ የሚሆን መሬት ስጡኝ።” 5  በዚህ ጊዜ የሄት ወንዶች ልጆች ለአብርሃም እንዲህ ሲሉ መለሱለት፦ 6  “ስማን ጌታዬ። አንተ እኮ በመካከላችን አምላክ የመረጠህ አለቃ ነህ። ካሉን የመቃብር ስፍራዎች ምርጥ በሆነው ቦታ አስከሬንህን መቅበር ትችላለህ። ከእኛ መካከል አስከሬንህን እንዳትቀብር የመቃብር ቦታውን የሚከለክልህ ማንም የለም።” 7  በመሆኑም አብርሃም ተነሳ፤ ለዚያ አገር ሰዎች ይኸውም ለሄት ወንዶች ልጆች ሰገደ፤ 8  እንዲህም አላቸው፦ “አስከሬኔን ወስጄ እንድቀብር ከፈቀዳችሁልኝ አንዴ ስሙኝ፤ የጾሃር ልጅ የሆነውን ኤፍሮንን 9  በእርሻ ቦታው ዳርቻ ላይ የሚገኘውን የእሱ ንብረት የሆነውን የማክፈላ ዋሻ እንዲሸጥልኝ ለምኑልኝ። የመቃብር ስፍራ የሚሆን ርስት እንዲኖረኝ ቦታው የሚያወጣውን ብር በሙሉ ልስጠውና በእናንተ ፊት ይሽጥልኝ።” 10  ኤፍሮን በሄት ወንዶች ልጆች መካከል ተቀምጦ ነበር። ስለሆነም ሂታዊው ኤፍሮን የሄት ወንዶች ልጆች እየሰሙ በከተማው በር በሚገቡት ሰዎች ሁሉ ፊት ለአብርሃም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ 11  “የለም ጌታዬ! አዳምጠኝ። የእርሻ ቦታውንም ሆነ በውስጡ ያለውን ዋሻ ሰጥቼሃለሁ። የሕዝቤ ልጆች በተገኙበት ለአንተ ሰጥቼሃለሁ። አስከሬንህን በዚያ ቅበር።” 12  በዚህ ጊዜ አብርሃም በአገሩ ሰዎች ፊት ሰገደ፤ 13  የአገሩ ሰዎችም እየሰሙ ኤፍሮንን እንዲህ አለው፦ “ፈቃድህ ከሆነ ስማኝ! የእርሻ ቦታው የሚያወጣውን ብር በሙሉ እሰጥሃለሁ። አስከሬኔን በዚያ እንድቀብር ብሩን ተቀበለኝ።” 14  ከዚያም ኤፍሮን ለአብርሃም እንዲህ ሲል መለሰ፦ 15  “ጌታዬ እኔ የምልህን ስማኝ። የዚህ መሬት ዋጋ 400 የብር ሰቅል ነው፤ ታዲያ ይህ በእኔና በአንተ መካከል ያን ያህል ትልቅ ነገር ሆኖ ነው? ይልቁንስ አስከሬንህን በዚያ ቅበር።” 16  አብርሃም፣ ኤፍሮን ያለውን ሰማ፤ አብርሃምም ኤፍሮን በሄት ወንዶች ልጆች ፊት የተናገረውን የብር መጠን ሰጠው፤ በነጋዴዎቹ ዘንድ ተቀባይነት ባለው ሚዛን መሠረት 400 ሰቅል ብር ለኤፍሮን መዘነለት። 17  በዚህ መንገድ በማምሬ ፊት ለፊት የነበረው በማክፈላ የሚገኘው የኤፍሮን የእርሻ ቦታ ይኸውም የእርሻ ቦታው፣ በውስጡ ያለው ዋሻና በእርሻ ቦታው ክልል ውስጥ የሚገኙት ዛፎች በሙሉ 18  አብርሃም የገዛቸው ንብረቶች መሆናቸው የሄት ወንዶች ልጆች በተገኙበት በከተማው በር በሚገቡት ሰዎች ሁሉ ፊት ተረጋገጠ። 19  ከዚያ በኋላ አብርሃም ሚስቱን ሣራን በማምሬ ይኸውም በከነአን ምድር ባለው በኬብሮን ፊት ለፊት በሚገኘው በማክፈላ የእርሻ ቦታ ውስጥ ባለው ዋሻ ቀበራት። 20  በዚህ መንገድ የእርሻ ቦታውና በውስጡ የሚገኘው ዋሻ የመቃብር ቦታ እንዲሆን ከሄት ወንዶች ልጆች ለአብርሃም በርስትነት ተሰጠ።
[]
[]
[]
[]
12,520
24  አብርሃምም አረጀ፤ ዕድሜውም ገፋ፤ ይሖዋም አብርሃምን በሁሉ ነገር ባረከው። 2  አብርሃም ንብረቱን በሙሉ የሚያስተዳድርለትንና በቤቱ ውስጥ ካሉት አገልጋዮች ሁሉ አንጋፋ የሆነውን አገልጋዩን እንዲህ አለው፦ “እባክህ እጅህን ከጭኔ ሥር አድርግ፤ 3  በመካከላቸው ከምኖረው ከከነአናውያን ሴቶች ልጆች ለልጄ ሚስት እንዳታመጣለት የሰማይና የምድር አምላክ በሆነው በይሖዋ አስምልሃለሁ። 4  ከዚህ ይልቅ ወደ አገሬና ወደ ዘመዶቼ ሄደህ ለልጄ ለይስሐቅ ሚስት አምጣለት።” 5  ይሁንና አገልጋዩ “ሴቲቱ ከእኔ ጋር ወደዚህ ምድር ለመምጣት ፈቃደኛ ባትሆንስ? ልጅህን አንተ ወደመጣህበት አገር መመለስ ይኖርብኛል?” አለው። 6  በዚህ ጊዜ አብርሃም እንዲህ አለው፦ “ልጄን ወደዚያ እንዳትወስደው ተጠንቀቅ። 7  ከአባቴ ቤትና ከዘመዶቼ አገር ያወጣኝ እንዲሁም ‘ይህን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ’ ብሎ የነገረኝና የማለልኝ የሰማይ አምላክ ይሖዋ መልአኩን ከፊትህ ይልካል፤ አንተም ከዚያ አገር ለልጄ ሚስት ታመጣለታለህ። 8  ሆኖም ሴቲቱ ከአንተ ጋር ለመምጣት ፈቃደኛ ሳትሆን ብትቀር ከዚህ መሐላ ነፃ ትሆናለህ። ልጄን ግን በምንም ዓይነት ወደዚያ እንዳትወስደው።” 9  ከዚያም አገልጋዩ እጁን ከጌታው ከአብርሃም ጭን ሥር አደረገ፤ ስለዚህ ጉዳይም ማለለት። 10  በመሆኑም አገልጋዩ ከጌታው ግመሎች መካከል አሥሩን ወሰደ፤ ከጌታውም ንብረት ምርጥ ምርጡን ሁሉ ይዞ ተነሳ። ከዚያም ከናኮር ከተማ ወደ ሜሶጶጣሚያ ጉዞ ጀመረ። 11  ከከተማዋ ውጭ ባለ አንድ የውኃ ጉድጓድ አጠገብም ግመሎቹን አንበረከከ። ጊዜውም ወደ ማምሻው አካባቢ ነበር፤ ይህ ጊዜ ደግሞ ሴቶች ውኃ ለመቅዳት የሚወጡበት ነው። 12  ከዚያም እንዲህ አለ፦ “የጌታዬ የአብርሃም አምላክ ይሖዋ፣ እባክህ በዚህ ዕለት ጉዳዬን አሳካልኝ፤ ለጌታዬ ለአብርሃምም ታማኝ ፍቅርህን አሳየው። 13  ይኸው እኔ እዚህ የውኃ ምንጭ አጠገብ ቆሜአለሁ፤ የከተማዋ ሴቶች ልጆች ውኃ ለመቅዳት እየመጡ ነው። 14  እንግዲህ ‘እባክሽ፣ ውኃ እንድጠጣ እንስራሽን አውርጂልኝ’ ስላት ‘እንካ ጠጣ፤ ግመሎችህንም አጠጣልሃለሁ’ የምትለኝ ወጣት ለአገልጋይህ ለይስሐቅ የመረጥካት ትሁን፤ እንዲህ ካደረግክልኝ ለጌታዬ ታማኝ ፍቅር እንዳሳየኸው አውቃለሁ።” 15  እሱም ገና ንግግሩን ሳይጨርስ የባቱኤል ልጅ ርብቃ እንስራዋን በትከሻዋ ተሸክማ ብቅ አለች፤ ባቱኤል የአብርሃም ወንድም የናኮር ሚስት ሚልካ የወለደችው ነው። 16  ወጣቷም በጣም ቆንጆና ከወንድ ጋር የፆታ ግንኙነት ፈጽማ የማታውቅ ድንግል ነበረች። እሷም ወደ ምንጩ ወርዳ በእንስራዋ ውኃ ሞልታ ተመለሰች። 17  አገልጋዩም ወዲያውኑ ወደ እሷ ሮጦ በመሄድ “እባክሽ ከእንስራሽ ውኃ ልጎንጭ” አላት። 18  እሷም መልሳ “ጌታዬ ጠጣ” አለችው። ከዚያም ፈጠን ብላ እንስራዋን ወደ እጇ በማውረድ የሚጠጣው ውኃ ሰጠችው። 19  ለእሱ ሰጥታው ከጠጣ በኋላ “ግመሎችህም ጠጥተው እስኪጠግቡ ድረስ ውኃ እቀዳላቸዋለሁ” አለችው። 20  በእንስራዋ ውስጥ የነበረውን ውኃም በፍጥነት ገንዳ ውስጥ ገለበጠች፤ ከዚያም በሩጫ እየተመላለሰች ከጉድጓዱ ውኃ ትቀዳ ጀመር፤ ለግመሎቹም ሁሉ ቀዳች። 21  ይህ ሁሉ ሲሆን ሰውየው ይሖዋ ጉዞውን አሳክቶለት እንደሆነና እንዳልሆነ በማሰብ ዝም ብሎ በመገረም ይመለከታት ነበር። 22  ግመሎቹም ጠጥተው ሲጨርሱ ሰውየው ግማሽ ሰቅል የሚመዝን የወርቅ የአፍንጫ ቀለበት እንዲሁም አሥር ሰቅል የሚመዝኑ ሁለት የወርቅ አምባሮች አውጥቶ ሰጣት፤ 23  እንዲህም አላት፦ “እስቲ ንገሪኝ፣ ለመሆኑ የማን ልጅ ነሽ? በአባትሽ ቤት የምናድርበት ቦታ ይኖር ይሆን?” 24  እሷም መልሳ “ሚልካ ለናኮር የወለደችለት የባቱኤል ልጅ ነኝ” አለችው። 25  አክላም “ገለባና ብዙ ገፈራ እንዲሁም ለማደሪያ የሚሆን ስፍራ አለን” አለችው። 26  በዚህ ጊዜ ሰውየው በይሖዋ ፊት ተደፍቶ ሰገደ፤ 27  እንዲህም አለ፦ “ለጌታዬ ታማኝ ፍቅሩንና ታማኝነቱን ያልነፈገው የጌታዬ የአብርሃም አምላክ ይወደስ። ይሖዋ ወደ ጌታዬ ወንድሞች ቤት መራኝ።” 28  ወጣቷም የሆነውን ሁሉ ለእናቷ ቤተሰቦች ለመንገር እየሮጠች ሄደች። 29  ርብቃ፣ ላባ የሚባል ወንድም ነበራት። ላባም ከከተማዋ ውጭ በምንጩ አጠገብ ወዳለው ሰው እየሮጠ ሄደ። 30  የአፍንጫ ቀለበቱንና አምባሮቹን በእህቱ እጆች ላይ ሲመለከት እንዲሁም እህቱ ርብቃ “ሰውየው እንዲህ እንዲህ አለኝ” ብላ ስትናገር ሲሰማ በምንጩ አጠገብ ከግመሎቹ ጋር ቆሞ የነበረውን ሰው ለማግኘት ወደ እሱ ሄደ። 31  እሱም ሰውየውን እንዳገኘው “አንተ ይሖዋ የባረከህ ሰው፣ ና እንጂ። ውጭ የቆምከው ለምንድን ነው? ቤቱን አዘጋጅቻለሁ፤ ለግመሎቹም ማደሪያ አለ” አለው። 32  ስለዚህ ሰውየው ወደ ቤት ገባ፤ እሱም የግመሎቹን ጭነት አራገፈለት፤ ለግመሎቹም ገለባና ገፈራ ሰጣቸው። እንዲሁም ሰውየውና አብረውት የነበሩት ሰዎች እግራቸውን የሚታጠቡበት ውኃ አቀረበላቸው። 33  ሆኖም ሰውየው የሚበላ ነገር ሲቀርብለት “የመጣሁበትን ጉዳይ ሳልናገር እህል አልቀምስም” አለ። በመሆኑም ላባ “እሺ፣ ተናገር!” አለው። 34  እሱም እንዲህ አለ፦ “እኔ የአብርሃም አገልጋይ ነኝ። 35  ይሖዋ ጌታዬን እጅግ ባርኮታል፤ በጎች፣ ከብቶች፣ ብር፣ ወርቅ፣ ወንድና ሴት አገልጋዮች እንዲሁም ግመሎችና አህዮች በመስጠት በጣም አበልጽጎታል። 36  በተጨማሪም የጌታዬ ሚስት ሣራ በስተርጅናዋ ለጌታዬ ወንድ ልጅ ወልዳለታለች፤ ጌታዬም ያለውን ሁሉ ለእሱ ይሰጠዋል። 37  በመሆኑም ጌታዬ እንዲህ በማለት አስማለኝ፦ ‘በአገራቸው ከምኖረው ከከነአናውያን ሴቶች ልጆች መካከል ለልጄ ሚስት እንዳታመጣለት። 38  ፈጽሞ እንዲህ እንዳታደርግ፤ ከዚህ ይልቅ ወደ አባቴ ቤትና ወደ ቤተሰቦቼ ሄደህ ለልጄ ሚስት አምጣለት።’ 39  እኔ ግን ጌታዬን ‘ሴቲቱ ከእኔ ጋር ለመምጣት ፈቃደኛ ባትሆንስ?’ አልኩት። 40  እሱም እንዲህ አለኝ፦ ‘አካሄዴን በፊቱ ያደረግኩት ይሖዋ መልአኩን ከአንተ ጋር ይልካል፤ ጉዞህን ያሳካልሃል፤ አንተም ከቤተሰቦቼና ከአባቴ ቤት ለልጄ ሚስት ታመጣለታለህ። 41  ወደ ቤተሰቦቼ ከሄድክና እነሱም ልጅቷን ለመስጠት ፈቃደኛ ካልሆኑ ከማልክልኝ መሐላ ነፃ ትሆናለህ። እንዲህ ካደረግክ ከመሐላህ ነፃ ትሆናለህ።’ 42  “እኔም ዛሬ ምንጩ አጠገብ ስደርስ እንዲህ አልኩ፦ ‘የጌታዬ የአብርሃም አምላክ ይሖዋ፣ ጉዞዬን የምታሳካልኝ ከሆነ 43  ይኸው እዚህ የውኃ ምንጭ አጠገብ ቆሜአለሁ። አንዲት ወጣት ሴት ውኃ ለመቅዳት ስትመጣ “እባክሽ፣ ከእንስራሽ ትንሽ ውኃ አጠጪኝ” እላታለሁ፤ 44  እሷም “አንተም ጠጣ፤ ለግመሎችህም እቀዳላቸዋለሁ” ካለችኝ ይህች ሴት ይሖዋ ለጌታዬ ልጅ የመረጣት ትሁን።’ 45  “እኔም ገና በልቤ ተናግሬ ሳልጨርስ ርብቃ እንስራዋን በትከሻዋ ተሸክማ ብቅ አለች፤ እሷም ወደ ምንጩ ወርዳ ውኃ ቀዳች። ከዚያም እኔ ‘እባክሽ፣ ውኃ አጠጪኝ’ አልኳት። 46  እሷም ፈጠን ብላ እንስራዋን ከትከሻዋ በማውረድ ‘ጠጣ፤ ግመሎችህንም አጠጣልሃለሁ’ አለችኝ። እኔም ጠጣሁ፤ ግመሎቹንም አጠጣች። 47  ከዚያም ‘ለመሆኑ የማን ልጅ ነሽ?’ ስል ጠየቅኳት፤ እሷም ‘ሚልካ ለናኮር የወለደችለት የባቱኤል ልጅ ነኝ’ አለችኝ። ስለዚህ ቀለበቱን በአፍንጫዋ ላይ፣ አምባሮቹን ደግሞ በእጆቿ ላይ አደረግኩላት። 48  እኔም በይሖዋ ፊት ተደፍቼ ሰገድኩ፤ የጌታዬን ወንድም ሴት ልጅ ለጌታዬ ልጅ እንድወስድለት በትክክለኛው መንገድ የመራኝን የጌታዬን የአብርሃምን አምላክ ይሖዋን አወደስኩ። 49  እንግዲህ አሁን ለጌታዬ ታማኝ ፍቅርና ታማኝነት ማሳየት የምትፈልጉ ከሆነ ንገሩኝ፤ ካልሆነ ግን ማድረግ ያለብኝን ነገር እንድወስን ቁርጡን አሳውቁኝ።” 50  ከዚያም ላባና ባቱኤል እንዲህ ሲሉ መለሱለት፦ “ይህ ነገር ከይሖዋ የመጣ ነው። እኛ እሺም ሆነ እንቢ ልንልህ አንችልም። 51  ርብቃ ይቻትልህ። ይዘሃት ሂድ፤ ልክ ይሖዋ እንደተናገረውም ለጌታህ ልጅ ሚስት ትሁን።” 52  የአብርሃም አገልጋይም ያሉትን ሲሰማ ወዲያውኑ በይሖዋ ፊት መሬት ላይ ተደፍቶ ሰገደ። 53   ከዚያም አገልጋዩ የብርና የወርቅ ጌጣጌጦችን እንዲሁም ልብሶችን እያወጣ ለርብቃ ይሰጣት ጀመር፤ ለወንድሟና ለእናቷም ውድ የሆኑ ዕቃዎችን ሰጣቸው። 54  ከዚህ በኋላ እሱና ከእሱ ጋር ያሉት ሰዎች በሉ፣ ጠጡም፤ እዚያም አደሩ። እሱም ጠዋት ሲነሳ “በሉ እንግዲህ ወደ ጌታዬ እንድንሄድ አሰናብቱን” አላቸው። 55  በዚህ ጊዜ ወንድሟና እናቷ “ልጅቷ ከእኛ ጋር ቢያንስ ለአሥር ቀን ትቆይ። ከዚያ በኋላ መሄድ ትችላለች” አሉት። 56  እሱ ግን “ይሖዋ ጉዞዬን እንዳሳካልኝ እያያችሁ አታዘግዩኝ። ወደ ጌታዬ እንድሄድ አሰናብቱኝ” አላቸው። 57   እነሱም “ልጅቷን እንጥራና እንጠይቃት” አሉት። 58  ርብቃን ጠርተውም “ከዚህ ሰው ጋር ትሄጃለሽ?” አሏት። እሷም “አዎ፣ እሄዳለሁ” አለች። 59  ስለዚህ እህታቸውን ርብቃንና ሞግዚቷን እንዲሁም የአብርሃምን አገልጋይና አብረውት የነበሩትን ሰዎች አሰናበቷቸው። 60  ርብቃንም “እህታችን ሆይ፣ ሺዎች ጊዜ አሥር ሺህ ሁኚ፤ ዘርሽም የጠላቶቹን በር ይውረስ” ብለው መረቋት። 61  ከዚያም ርብቃና ሴት አገልጋዮቿ ተነሱ፤ በግመሎች ላይ ተቀምጠው ሰውየውን ተከተሉት። አገልጋዩም ርብቃን ይዞ ጉዞውን ቀጠለ። 62  ይስሐቅም በኔጌብ ምድር ይኖር ስለነበር ከብኤርላሃይሮዒ አቅጣጫ መጣ። 63  ይስሐቅም አመሻሹ ላይ ለማሰላሰል ወደ ሜዳ ወጥቶ ነበር። ቀና ብሎ ሲመለከትም ግመሎች ሲመጡ አየ! 64  ርብቃም ቀና ብላ ስትመለከት ይስሐቅን አየችው፤ ከዚያም ከግመሉ ላይ በፍጥነት ወረደች። 65  አገልጋዩንም “ከእኛ ጋር ለመገናኘት ሜዳውን አቋርጦ የሚመጣው ያ ሰው ማን ነው?” ስትል ጠየቀችው። አገልጋዩም “ጌታዬ ነው” አላት። በመሆኑም ዓይነ ርግቧን ወስዳ ራሷን ሸፈነች። 66  አገልጋዩም ያደረገውን ሁሉ ለይስሐቅ ነገረው። 67  ከዚያም ይስሐቅ ርብቃን ወደ እናቱ ወደ ሣራ ድንኳን ይዟት ገባ። በዚህ መንገድ ሚስቱ አድርጎ ወሰዳት፤ እሱም ወደዳት፤ ከእናቱም ሞት ተጽናና።
[]
[]
[]
[]
12,521
25  አብርሃም ኬጡራ የምትባል ሌላ ሚስት አገባ። 2  እሷም ከጊዜ በኋላ ዚምራንን፣ ዮቅሻንን፣ ሚዳንን፣ ምድያምን፣ ይሽባቅን እና ሹሃን ወለደችለት። 3  ዮቅሻንም ሳባን እና ዴዳንን ወለደ። የዴዳን ወንዶች ልጆች ደግሞ አሹሪም፣ ለጡሺም እና ለኡሚም ነበሩ። 4  የምድያም ወንዶች ልጆች ኤፋ፣ ኤፌር፣ ሃኖክ፣ አቢዳዕ እና ኤልዳዓ ነበሩ። እነዚህ ሁሉ የኬጡራ ወንዶች ልጆች ነበሩ። 5  በኋላም አብርሃም ያለውን ሁሉ ለይስሐቅ ሰጠው፤ 6  ከቁባቶቹ ለወለዳቸው ወንዶች ልጆቹ ግን ስጦታ ሰጣቸው። ከዚያም ገና በሕይወት እያለ ከልጁ ከይስሐቅ እንዲርቁ በስተ ምሥራቅ አቅጣጫ ወደ ምሥራቅ ምድር ላካቸው። 7  አብርሃም በሕይወት የኖረበት ዘመን 175 ዓመት ነበር። 8  ከዚያም አብርሃም እስትንፋሱ ቀጥ አለ፤ ሸምግሎ፣ በሕይወቱ ረክቶና ዕድሜ ጠግቦ ሞተ፤ ወደ ወገኖቹም ተሰበሰበ። 9  ልጆቹ ይስሐቅና እስማኤልም የሂታዊው የጾሃር ልጅ በሆነው በኤፍሮን የእርሻ ቦታ ውስጥ ባለው በማምሬ ፊት ለፊት በሚገኘው በማክፈላ ዋሻ ቀበሩት፤ 10  ይህ የእርሻ ቦታ አብርሃም ከሄት ወንዶች ልጆች የገዛው ነው። አብርሃምም ከሚስቱ ከሣራ ጋር በዚያ ስፍራ ተቀበረ። 11  አብርሃም ከሞተ በኋላም አምላክ የአብርሃምን ልጅ ይስሐቅን መባረኩን ቀጠለ፤ ይስሐቅ በብኤርላሃይሮዒ አቅራቢያ ይኖር ነበር። 12  የሣራ አገልጋይ የነበረችው ግብፃዊቷ አጋር ለአብርሃም የወለደችለት የአብርሃም ልጅ የእስማኤል ታሪክ ይህ ነው። 13  የእስማኤል ወንዶች ልጆች ስም በየስማቸውና በየቤተሰብ የዘር ሐረጋቸው ሲዘረዘር የሚከተለው ነው፦ የእስማኤል የበኩር ልጅ ነባዮት ከዚያም ቄዳር፣ አድበዔል፣ ሚብሳም፣ 14  ሚሽማ፣ ዱማ፣ ማሳ፣ 15  ሃዳድ፣ ቴማ፣ የጡር፣ ናፊሽ እና ቄድማ። 16  የእስማኤል ወንዶች ልጆች በየመንደራቸውና በየሰፈራቸው ሲዘረዘሩ ስማቸው ይህ ነው፤ እነሱም በየነገዳቸው 12 የነገድ አለቆች ናቸው። 17  እስማኤል 137 ዓመት ኖረ። ከዚያም እስትንፋሱ ቀጥ አለና ሞተ፤ ወደ ወገኖቹም ተሰበሰበ። 18  እነሱም ከግብፅ አጠገብ በሹር አቅራቢያ ከምትገኘው ከሃዊላ አንስቶ እስከ አሦር ድረስ ባለው አካባቢ ሰፍረው ነበር። በወንድሞቹም ሁሉ አቅራቢያ ሰፈረ። 19  የአብርሃም ልጅ የይስሐቅ ታሪክ ይህ ነው። አብርሃም ይስሐቅን ወለደ። 20  ይስሐቅ በጳዳንአራም የሚኖረውን የአራማዊውን የባቱኤልን ሴት ልጅ ማለትም የአራማዊውን የላባን እህት ርብቃን ሲያገባ ዕድሜው 40 ዓመት ነበር። 21  ይስሐቅ ሚስቱ መሃን ስለነበረች ስለ እሷ አዘውትሮ ይሖዋን ይለምን ነበር፤ ይሖዋም ልመናውን ሰማው፤ ሚስቱ ርብቃም ፀነሰች። 22  በሆዷ ውስጥ ያሉት ልጆችም እርስ በርስ ይታገሉ ጀመር፤ በመሆኑም “እንዲህ ከሆነስ ብሞት ይሻለኛል” አለች። ስለዚህ ይሖዋን ጠየቀች። 23  ይሖዋም እንዲህ አላት፦ “በማህፀንሽ ውስጥ ሁለት ብሔራት አሉ፤ ከውስጥሽም ሁለት ሕዝቦች ተለያይተው ይወጣሉ። አንደኛው ብሔር ከሌላኛው ብሔር ይበረታል፤ ታላቁም ታናሹን ያገለግላል።” 24  የመውለጃዋም ጊዜ ሲደርስ በማህፀኗ ውስጥ መንታ ልጆች ነበሩ። 25  መጀመሪያ የወጣው መልኩ ቀይ ሲሆን ፀጉራም ካባ የለበሰ ይመስል ሰውነቱ በሙሉ በፀጉር የተሸፈነ ነበር፤ በመሆኑም ስሙን ኤሳው አሉት። 26  ከዚያም ወንድሙ ወጣ፤ በእጁም የኤሳውን ተረከዝ ይዞ ነበር፤ በዚህም የተነሳ ስሙን ያዕቆብ አለው። ርብቃ እነሱን ስትወልድ ይስሐቅ 60 ዓመቱ ነበር። 27  ልጆቹም እያደጉ ሲሄዱ ኤሳው ውጭ መዋል የሚወድ የተዋጣለት አዳኝ ሆነ፤ ያዕቆብ ግን አብዛኛውን ጊዜውን በድንኳን የሚያሳልፍ ነቀፋ የሌለበት ሰው ነበር። 28  ይስሐቅ ኤሳውን ይወደው ነበር፤ ምክንያቱም እያደነ ያበላው ነበር፤ ርብቃ ግን ያዕቆብን ትወደው ነበር። 29  አንድ ቀን ኤሳው ውጭ ውሎ በጣም ደክሞት ሲመጣ ያዕቆብ ወጥ እየሠራ ነበር። 30  በመሆኑም ኤሳው ያዕቆብን “ቶሎ በል እባክህ፣ በጣም ስለደከመኝ ከዚያ ከቀዩ ወጥ የተወሰነ ስጠኝ!” አለው። ስሙ ኤዶም የተባለውም በዚህ የተነሳ ነው። 31  በዚህ ጊዜ ያዕቆብ “በመጀመሪያ የብኩርና መብትህን ሽጥልኝ!” አለው። 32  ኤሳውም “እኔ ለራሴ ልሞት ደርሻለሁ! ታዲያ የብኩርና መብት ምን ይጠቅመኛል?” አለው። 33  ያዕቆብም “በመጀመሪያ ማልልኝ!” አለው። እሱም ማለለት፤ የብኩርና መብቱንም ለያዕቆብ ሸጠለት። 34  ከዚያም ያዕቆብ ለኤሳው ዳቦና ምስር ወጥ ሰጠው፤ እሱም በላ፣ ጠጣም፤ ተነሥቶም ሄደ። በዚህ መንገድ ኤሳው የብኩርና መብቱን አቃለለ።
[]
[]
[]
[]
12,522
26  በአብርሃም ዘመን ከተከሰተው ከመጀመሪያው ረሃብ ሌላ በምድሪቱ ላይ ረሃብ ተከሰተ፤ ስለዚህ ይስሐቅ በጌራራ ወደሚገኘው ወደ ፍልስጤማውያን ንጉሥ ወደ አቢሜሌክ ሄደ። 2  ከዚያም ይሖዋ ተገለጠለትና እንዲህ አለው፦ “ወደ ግብፅ አትውረድ። እኔ በማሳይህ ምድር ተቀመጥ። 3  በዚህ ምድር እንደ ባዕድ አገር ሰው ሆነህ ተቀመጥ፤ እኔም ከአንተ ጋር መሆኔን እቀጥላለሁ፤ እንዲሁም እባርክሃለሁ። ምክንያቱም ይህችን ምድር በሙሉ ለአንተና ለዘሮችህ እሰጣለሁ፤ ደግሞም ለአባትህ ለአብርሃም እንዲህ ስል የማልሁለትን መሐላ እፈጽማለሁ፦ 4  ‘ዘርህን በሰማያት ላይ እንዳሉ ከዋክብት አበዛዋለሁ፤ ይህችንም ምድር በሙሉ ለዘርህ እሰጣለሁ፤ የምድርም ብሔራት ሁሉ በዘርህ አማካኝነት ለራሳቸው በረከት ያገኛሉ።’ 5  ይህን የማደርገውም አብርሃም ቃሌን ስለሰማ እንዲሁም ሥርዓቶቼን፣ ትእዛዛቴን፣ ደንቦቼንና ሕጎቼን ጠብቆ ስለኖረ ነው።” 6  በመሆኑም ይስሐቅ በጌራራ መኖሩን ቀጠለ። 7  የዚያ አገር ሰዎች ስለ ሚስቱ በተደጋጋሚ ሲጠይቁት “እህቴ ናት” ይላቸው ነበር። “የዚህ አገር ሰዎች በርብቃ የተነሳ ሊገድሉኝ ይችላሉ” ብሎ ስላሰበ “ሚስቴ ናት” ለማለት ፈርቶ ነበር፤ ምክንያቱም ርብቃ ቆንጆ ነበረች። 8  ከተወሰነ ጊዜ በኋላም የፍልስጤማውያን ንጉሥ አቢሜሌክ በመስኮት ወደ ውጭ ሲመለከት ይስሐቅ ለሚስቱ ለርብቃ ፍቅሩን ሲገልጽላት አየ። 9  አቢሜሌክም ወዲያው ይስሐቅን ጠርቶ “መቼም እሷ ሚስትህ እንደሆነች ግልጽ ነው! ታዲያ ‘እህቴ ናት’ ያልከው ለምንድን ነው?” አለው። በዚህ ጊዜ ይስሐቅ “እንዲህ ያልኩት በእሷ የተነሳ ሕይወቴን እንዳላጣ ስለፈራሁ ነው” አለው። 10  አቢሜሌክ ግን “እንዴት እንዲህ ያለ ነገር ታደርግብናለህ? ከእኛ ሰዎች አንዱ ከሚስትህ ጋር ሊተኛ ይችል ነበር፤ እኛንም በደለኞች አድርገህ ታስቆጥረን ነበር!” አለው። 11  ከዚያም አቢሜሌክ “ይህን ሰውም ሆነ ሚስቱን የነካ ማንኛውም ሰው ያለምንም ጥርጥር ይገደላል!” በማለት ለሕዝቡ ሁሉ ትእዛዝ አስተላለፈ። 12  ይስሐቅም በዚያ ምድር ዘር መዝራት ጀመረ፤ ይሖዋም ስለባረከው በዚያ ዓመት፣ የዘራውን 100 እጥፍ አመረተ። 13  ሰውየውም ባለጸጋ ሆነ፤ እጅግ ባለጸጋ እስኪሆንም ድረስ በሀብት ላይ ሀብት እየጨመረ ሄደ። 14  የበግና የከብት መንጋው በዛለት፤ አገልጋዮቹም ብዙ ሆኑ፤ ፍልስጤማውያንም ይቀኑበት ጀመር። 15  በመሆኑም ፍልስጤማውያን የአባቱ አገልጋዮች በአብርሃም ዘመን የቆፈሯቸውን የውኃ ጉድጓዶች በሙሉ አፈር በመሙላት ደፈኗቸው። 16  ከዚያም አቢሜሌክ ይስሐቅን “ከእኛ ይልቅ እየበረታህ ስለመጣህ አካባቢያችንን ለቅቀህ ሂድልን” አለው። 17  በመሆኑም ይስሐቅ ከዚያ ተነስቶ በመሄድ በጌራራ ሸለቆ ሰፈረ፤ በዚያም መኖር ጀመረ። 18  ይስሐቅም በአባቱ በአብርሃም ዘመን ተቆፍረው የነበሩትንና አብርሃም ከሞተ በኋላ ፍልስጤማውያን የደፈኗቸውን የውኃ ጉድጓዶች እንደገና ቆፈረ፤ ቀደም ሲል አባቱ ባወጣላቸው ስምም ጠራቸው። 19  የይስሐቅ አገልጋዮችም በሸለቆው ውስጥ ሲቆፍሩ ለመጠጥ የሚሆን ውኃ ያለበት አንድ ጉድጓድ አገኙ። 20  የጌራራ እረኞች “ውኃው የእኛ ነው!” በማለት ከይስሐቅ እረኞች ጋር ጠብ አነሱ። ከእሱ ጋር ስለተጣሉም የውኃ ጉድጓዱን ስም ኤሴቅ አለው። 21  እነሱም ሌላ የውኃ ጉድጓድ ቆፈሩ፤ በዚህም ጉድጓድ ጠብ አነሱ። በመሆኑም የጉድጓዱን ስም ሲጥና አለው። 22  ከዚያም ያን ቦታ ትቶ በመሄድ ሌላ የውኃ ጉድጓድ ቆፈረ፤ እነሱም በዚህ ጉድጓድ ጠብ አላነሱበትም። በመሆኑም “አሁን ይሖዋ ሰፊ ቦታ ሰጥቶናል፤ በምድርም ላይ እንድንበዛ አድርጎናል” በማለት የጉድጓዱን ስም ረሆቦት አለው። 23  በኋላም ከዚያ ተነስቶ ወደ ቤርሳቤህ ወጣ። 24  ይሖዋም በዚያ ሌሊት ተገለጠለትና እንዲህ አለው፦ “እኔ የአባትህ የአብርሃም አምላክ ነኝ። እኔ ከአንተ ጋር ስለሆንኩ አትፍራ፤ ስለ አገልጋዬ ስለ አብርሃም ስል እባርክሃለሁ እንዲሁም ዘርህን አበዛዋለሁ።” 25  በመሆኑም በዚያ መሠዊያ ሠራ፤ የይሖዋንም ስም ጠራ። እንዲሁም ይስሐቅ ድንኳኑን በዚያ ተከለ፤ አገልጋዮቹም በዚያ የውኃ ጉድጓድ ቆፈሩ። 26  ከተወሰነ ጊዜ በኋላ አቢሜሌክ የግል አማካሪው ከሆነው ከአሁዛትና ከሠራዊቱ አዛዥ ከፊኮል ጋር በመሆን ከጌራራ ተነስቶ ወደ ይስሐቅ መጣ። 27  በዚህ ጊዜ ይስሐቅ “ጠልታችሁኝ ከአካባቢያችሁ ካባረራችሁኝ በኋላ አሁን ለምን ወደ እኔ መጣችሁ?” አላቸው። 28  እነሱም እንዲህ አሉት፦ “ይሖዋ ከአንተ ጋር እንደሆነ በግልጽ ማየት ችለናል። በመሆኑም እንዲህ አልን፦ ‘በእኛና በአንተ መካከል በመሐላ የጸና ስምምነት ይኑር፤ ከአንተም ጋር ቃል ኪዳን እንጋባ። 29  በአንተ ላይ ምንም ጉዳት እንዳላደረስንብህ ከዚህ ይልቅ በሰላም በማሰናበት መልካም እንዳደረግንልህ ሁሉ አንተም በእኛ ላይ ምንም መጥፎ ነገር እንደማታደርግብን ማልልን። አንተ አሁን ይሖዋ የባረከህ ሰው ነህ።’” 30  እሱም ግብዣ አዘጋጀላቸው፤ እነሱም በሉ፣ ጠጡም። 31  በማግስቱም በማለዳ ተነስተው እርስ በርሳቸው ተማማሉ። ከዚያም ይስሐቅ አሰናበታቸው፤ እነሱም ከእሱ ዘንድ በሰላም ሄዱ። 32  በዚያኑ ዕለት የይስሐቅ አገልጋዮች መጥተው ስለቆፈሩት የውኃ ጉድጓድ ነገሩት፤ እነሱም “ውኃ እኮ አገኘን!” አሉት። 33  በመሆኑም የጉድጓዱን ስም ሳቤህ አለው። የከተማዋ ስም እስከ ዛሬ ድረስ ቤርሳቤህ ተብሎ የሚጠራው በዚህ የተነሳ ነው። 34  ኤሳው 40 ዓመት ሲሆነው የሂታዊውን የቤኤሪን ልጅ ዮዲትን እንዲሁም የሂታዊውን የኤሎንን ልጅ ባሴማትን አገባ። 35  እነሱም ይስሐቅንና ርብቃን ለከፍተኛ ሐዘን ዳረጓቸው።
[]
[]
[]
[]
12,523
27  ይስሐቅ ባረጀና ዓይኖቹ ደክመው ማየት በተሳናቸው ጊዜ ታላቁን ልጁን ኤሳውን ወደ እሱ ጠርቶ “ልጄ ሆይ!” አለው። እሱም “አቤት!” አለው። 2  ይስሐቅም እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ አሁን አርጅቻለሁ። የምሞትበትንም ቀን አላውቅም። 3  ስለሆነም አሁን መሣሪያዎችህን፣ የቀስት ኮሮጆህንና ደጋንህን ይዘህ ወደ ዱር ሂድ፤ አድነህም አምጣልኝ። 4  እኔ የምወደው ዓይነት ጣፋጭ ምግብ ሠርተህ አቅርብልኝ። ከመሞቴም በፊት እንድባርክህ ልብላው።” 5  ይሁን እንጂ ይስሐቅ፣ ልጁን ኤሳውን ሲያነጋግረው ርብቃ ታዳምጥ ነበር። ኤሳው አደን አድኖ ለማምጣት ወደ ዱር ወጣ። 6  ርብቃም ልጇን ያዕቆብን እንዲህ አለችው፦ “አባትህ ወንድምህን ኤሳውን እንዲህ ሲለው ሰምቻለሁ፦ 7  ‘እስቲ አደን አድነህ አምጣልኝና ጣፋጭ ምግብ ሥራልኝ። እኔም ሳልሞት በይሖዋ ፊት እንድባርክህ ልብላ።’ 8  እንግዲህ ልጄ፣ አሁን የምልህን በጥሞና አዳምጥ፤ የማዝህንም አድርግ። 9  አባትህ የሚወደው ዓይነት ጣፋጭ ምግብ እንዳዘጋጅለት እባክህ ወደ መንጋው ሂድና ፍርጥም ያሉ ሁለት የፍየል ጠቦቶች አምጣልኝ። 10  ከዚያም ከመሞቱ በፊት እንዲባርክህ ምግቡን ለአባትህ ታቀርብለትና ይበላል።” 11  ያዕቆብ እናቱን ርብቃን እንዲህ አላት፦ “ወንድሜ ኤሳው ሰውነቱ ፀጉራም ነው፤ የእኔ ሰውነት ግን ለስላሳ ነው። 12  አባቴ ቢዳብሰኝስ? በእሱ ላይ እያሾፍኩበት ያለሁ ሊመስል ይችላል፤ ይህ ከሆነ ደግሞ በረከት ሳይሆን እርግማን አተርፋለሁ።” 13  በዚህ ጊዜ እናቱ “ልጄ፣ ለአንተ የታሰበው እርግማን ለእኔ ይሁን። ብቻ እኔ የምልህን አድርግ፤ ሄደህ ጠቦቶቹን አምጣልኝ” አለችው። 14  ስለዚህ ሄዶ ጠቦቶቹን አመጣ፤ ለእናቱም ሰጣት፤ እናቱም አባቱ የሚወደው ዓይነት ጣፋጭ ምግብ ሠራች። 15  ከዚያም ርብቃ ቤት ውስጥ ያስቀመጠችውን የታላቁን ልጇን የኤሳውን ምርጥ ልብስ ወስዳ ታናሹን ልጇን ያዕቆብን አለበሰችው። 16  በተጨማሪም የፍየል ጠቦቶቹን ቆዳ በእጆቹና ፀጉር በሌለው የአንገቱ ክፍል ላይ አደረገች። 17  ከዚያም የሠራችውን ጣፋጭ ምግብና ዳቦ ለልጇ ለያዕቆብ ሰጠችው። 18  እሱም ወደ አባቱ ገብቶ “አባቴ ሆይ!” አለው። እሱም መልሶ “አቤት! ለመሆኑ አንተ ማነህ ልጄ?” አለው። 19  ያዕቆብም አባቱን “እኔ የበኩር ልጅህ ኤሳው ነኝ። ልክ እንዳልከኝ አድርጌአለሁ። እንድትባርከኝ እባክህ ቀና ብለህ ተቀመጥና አድኜ ካመጣሁት ብላ” አለው። 20  በዚህ ጊዜ ይስሐቅ ልጁን “እንዴት እንዲህ ቶሎ ቀናህ ልጄ?” አለው። እሱም መልሶ “አምላክህ ይሖዋ አምጥቶ እጄ ላይ ስለጣለልኝ ነው” አለው። 21  ከዚያም ይስሐቅ ያዕቆብን “ልጄ ሆይ፣ አንተ በእርግጥ ልጄ ኤሳው መሆንህን እንዳውቅ እስቲ ቀረብ በልና ልዳብስህ” አለው። 22  በመሆኑም ያዕቆብ ወደ አባቱ ወደ ይስሐቅ ቀረበ። እሱም ዳበሰውና “ድምፁ የያዕቆብ ድምፅ ነው፤ እጆቹ ግን የኤሳው እጆች ናቸው” አለ። 23  እጆቹ እንደ ወንድሙ እንደ ኤሳው እጆች ፀጉራም ስለነበሩ ማንነቱን አልለየውም። ስለዚህ ባረከው። 24  ከዚያም “በእርግጥ አንተ ልጄ ኤሳው ነህ?” ሲል ጠየቀው። እሱም “አዎ፣ ነኝ” አለው። 25  በመቀጠልም “በል እንግዲህ ልጄ፣ አድነህ ያመጣህልኝን እንድበላ አቅርብልኝ፤ ከዚያም እባርክሃለሁ” አለው። እሱም አቀረበለትና በላ፤ እንዲሁም የወይን ጠጅ አመጣለትና ጠጣ። 26  ከዚያም አባቱ ይስሐቅ “ልጄ፣ እስቲ ቀረብ በልና ሳመኝ” አለው። 27  ስለዚህ ወደ እሱ ቀረበና ሳመው፤ ይስሐቅም የልጁን ልብስ ጠረን አሸተተ። ከዚያም ባረከው፤ እንዲህም አለው፦ “አቤት፣ የልጄ ጠረን ይሖዋ እንደባረከው መስክ መዓዛ ነው። 28  እውነተኛው አምላክ የሰማያትን ጠል፣ የምድርን ለም አፈር እንዲሁም የተትረፈረፈ እህልና አዲስ የወይን ጠጅ ይስጥህ። 29  ሕዝቦች ያገልግሉህ፤ ብሔራትም ይስገዱልህ። የወንድሞችህ ጌታ ሁን፤ የእናትህም ወንዶች ልጆች ይስገዱልህ። የሚረግሙህ ሁሉ የተረገሙ ይሁኑ፤ የሚባርኩህም ሁሉ የተባረኩ ይሁኑ።” 30  ይስሐቅ ያዕቆብን ባርኮ እንዳበቃና ያዕቆብ ከአባቱ ከይስሐቅ ፊት እግሩ እንደወጣ ወንድሙ ኤሳው ከአደን ተመለሰ። 31  እሱም ደግሞ ጣፋጭ ምግብ አዘጋጅቶ ለአባቱ አቀረበለት፤ አባቱንም “እስቲ እንድትባርከኝ አባቴ ይነሳና ልጁ አድኖ ካመጣለት ይብላ” አለው። 32  በዚህ ጊዜ አባቱ ይስሐቅ “አንተ ደግሞ ማን ነህ?” አለው። እሱም መልሶ “ልጅህ ነኛ! የበኩር ልጅህ ኤሳው” አለው። 33  ይስሐቅም በኃይል እየተንቀጠቀጠ “አደን አድኖ ያመጣልኝና ያቀረበልኝ ታዲያ ማን ነበር? እኔ እኮ አንተ ከመምጣትህ በፊት በላሁ፤ እንዲሁም ባረክሁት፤ ደግሞም የተባረከ ይሆናል!” አለው። 34  ኤሳው አባቱ የተናገረውን ሲሰማ ከፍ ባለ ድምፅ ምርር ብሎ እያለቀሰ አባቱን “አባቴ ባርከኝ፤ እኔንም ባርከኝ እንጂ!” አለው። 35  ይስሐቅ ግን “ወንድምህ ለአንተ የታሰበውን በረከት ለማግኘት አንድ ተንኮል ሠርቷል” አለው። 36  ኤሳውም እንዲህ አለ፦ “ስሙ ያዕቆብ የተባለው መቼ ያለምክንያት ሆነ! የኔ የሆነውን ሲወስድብኝ ይህ ሁለተኛ ጊዜው ነው። የብኩርና መብቴን መውሰዱ ሳያንሰው አሁን ደግሞ በረከቴን ቀማኝ!” ከዚያም “ለእኔ ምንም በረከት አላስቀረህልኝም?” አለው። 37  ይስሐቅ ግን ኤሳውን እንዲህ አለው፦ “በአንተ ላይ ጌታ አድርጌ ሾሜዋለሁ፤ እንዲሁም ወንድሞቹን ሁሉ አገልጋዮቹ እንዲሆኑ ሰጥቼዋለሁ። እህልና አዲስ የወይን ጠጅ እንዲበዛለት ባርኬዋለሁ፤ ታዲያ ለአንተ ላደርግልህ የምችለው ምን የቀረ ነገር አለ ልጄ?” 38  ኤሳውም አባቱን “አባቴ ሆይ፣ ለእኔ የምትሆን አንዲት በረከት እንኳ የለችህም? አባቴ ባርከኝ። እኔንም ባርከኝ እንጂ!” አለው። ኤሳውም ከፍ ባለ ድምፅ ምርር ብሎ አለቀሰ። 39  ስለዚህ አባቱ ይስሐቅ እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ መኖሪያህ ለም ከሆነው የምድር አፈር እንዲሁም በላይ ካሉት ሰማያት ጠል የራቀ ይሆናል። 40  በሰይፍህ ትኖራለህ፤ ወንድምህንም ታገለግላለህ። ይሁንና እየተቅበጠበጥክ ባስቸገርክ ጊዜ ቀንበሩን ከጫንቃህ ላይ ሰብረህ ትጥላለህ።” 41  ይሁን እንጂ ኤሳው አባቱ ያዕቆብን ስለባረከው ለያዕቆብ ከፍተኛ ጥላቻ አደረበት። ኤሳውም በልቡ “ለአባቴ ሐዘን የምንቀመጥበት ቀን ሩቅ አይደለም። ከዚያ በኋላ ወንድሜን ያዕቆብን እገድለዋለሁ” ይል ነበር። 42  ርብቃ ታላቁ ልጇ ኤሳው ያለው ነገር ሲነገራት ወዲያውኑ ለታናሹ ልጇ ለያዕቆብ እንዲህ የሚል መልእክት ላከችበት፦ “ወንድምህ ኤሳው አንተን በመግደል ሊበቀልህ እያሰበ ነው። 43  እንግዲህ ልጄ እኔ የምልህን አድርግ። ተነስተህ በካራን ወደሚገኘው ወደ ወንድሜ ወደ ላባ ሽሽ። 44  የወንድምህ ቁጣ እስኪበርድ ድረስ ለተወሰነ ጊዜ እሱ ጋ ተቀመጥ፤ 45  ወንድምህ ንዴቱ እስኪበርድለትና ያደረግክበትን እስኪረሳ ድረስ እዚያ ቆይ። እኔም እልክብህና አስጠራሃለሁ። ሁለታችሁንም በአንድ ቀን ለምን ልጣ?” 46  ከዚያ በኋላ ርብቃ ይስሐቅን እንዲህ ትለው ጀመር፦ “በሄት ሴቶች ልጆች የተነሳ ሕይወቴን ጠልቻለሁ። ያዕቆብም በዚህ አገር የሚገኙትን እንደነዚህ ያሉትን የሄት ሴቶች ልጆች የሚያገባ ከሆነ በሕይወት መኖር ለእኔ ምን ያደርግልኛል?”
[]
[]
[]
[]
12,524
28  በመሆኑም ይስሐቅ ያዕቆብን ጠርቶ ባረከውና እንዲህ ሲል አዘዘው፦ “ከከነአን ሴቶች ልጆች ሚስት እንዳታገባ። 2  በጳዳንአራም ወደሚገኘው ወደ እናትህ አባት ወደ ባቱኤል ቤት ሂድና ከእናትህ ወንድም ከላባ ሴቶች ልጆች መካከል አንዷን አግባ። 3  ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ ይባርክሃል፤ ፍሬያማም ያደርግሃል፤ እንዲሁም ያበዛሃል፤ አንተም በእርግጥ ብዙ ሕዝብ ያቀፈ ጉባኤ ትሆናለህ። 4  አምላክ ለአብርሃም የሰጠውን፣ አንተም እንደ ባዕድ አገር ሰው ሆነህ የምትኖርበትን ምድር እንድትወርስ የአብርሃምን በረከት ለአንተና ከአንተ ጋር ላለው ዘርህ ይሰጣል።” 5  ስለሆነም ይስሐቅ ያዕቆብን አሰናበተው፤ እሱም የያዕቆብና የኤሳው እናት የርብቃ ወንድም እንዲሁም የአራማዊው የባቱኤል ልጅ ወደሆነው ወደ ላባ ለመሄድ ወደ ጳዳንአራም ጉዞ ጀመረ። 6  ኤሳው፣ ይስሐቅ ያዕቆብን እንደባረከውና ሚስት እንዲያገባ ወደ ጳዳንአራም እንደላከው እንዲሁም በባረከው ጊዜ “ከከነአን ሴቶች ልጆች ሚስት እንዳታገባ” ብሎ እንዳዘዘውና 7  ያዕቆብም አባቱንና እናቱን በመታዘዝ ወደ ጳዳንአራም እንደሄደ አወቀ። 8  በዚህ ጊዜ ኤሳው የከነአን ሴቶች ልጆች በአባቱ በይስሐቅ ዘንድ የተጠሉ መሆናቸውን ተገነዘበ፤ 9  ስለዚህ ኤሳው ወደ እስማኤል ሄደ፤ ካሉትም ሚስቶች በተጨማሪ የአብርሃም ልጅ እስማኤል የወለዳትን የነባዮትን እህት ማሃላትን አገባ። 10  ያዕቆብ ከቤርሳቤህ ተነስቶ ወደ ካራን አቀና። 11  ከዚያም ወደ አንድ ስፍራ ደረሰ፤ ፀሐይ ጠልቃ ስለነበረም እዚያ ለማደር አሰበ። በመሆኑም በአካባቢው ካሉት ድንጋዮች አንዱን አንስቶ በመንተራስ እዚያው ተኛ። 12  እሱም ሕልም አለመ፤ በሕልሙም በምድር ላይ የተተከለ ደረጃ አየ፤ የደረጃውም ጫፍ እስከ ሰማያት ይደርስ ነበር፤ በላዩም ላይ የአምላክ መላእክት ይወጡና ይወርዱ ነበር። 13  ከደረጃውም በላይ ይሖዋ ነበር፤ እሱም እንዲህ አለ፦ “እኔ የአባትህ የአብርሃም አምላክና የይስሐቅ አምላክ ይሖዋ ነኝ። የተኛህበትን ምድር ለአንተና ለዘርህ እሰጣለሁ። 14  ዘርህም በእርግጥ እንደ ምድር አፈር ብዙ ይሆናል፤ ወደ ምዕራብ፣ ወደ ምሥራቅ፣ ወደ ሰሜንና ወደ ደቡብ ትስፋፋለህ። የምድር ቤተሰቦች ሁሉ በአንተና በዘርህ አማካኝነት በእርግጥ ይባረካሉ። 15  እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፤ በምትሄድበት ሁሉ እጠብቅሃለሁ፤ ወደዚህችም ምድር እመልስሃለሁ። የገባሁልህን ቃል እስክፈጽምልህ ድረስ አልተውህም።” 16  ከዚያም ያዕቆብ ከእንቅልፉ ነቅቶ “በእርግጥም በዚህ ስፍራ ይሖዋ አለ፤ እኔ ግን ይህን አላወቅኩም ነበር” አለ። 17  እሱም በፍርሃት ተዋጠ፤ እንዲህም አለ፦ “ይህ ስፍራ እንዴት የሚያስፈራ ነው! ይህ የአምላክ ቤት እንጂ ሌላ ሊሆን አይችልም፤ ይህ የሰማያት በር ነው።” 18  በመሆኑም ያዕቆብ በማለዳ ተነሳ፤ ተንተርሶት የነበረውን ድንጋይ ወስዶ እንደ ዓምድ አቆመው፤ በአናቱም ላይ ዘይት አፈሰሰበት። 19  ስለዚህ ያን ቦታ ቤቴል አለው፤ የከተማዋ የቀድሞ ስም ግን ሎዛ ነበር። 20  ከዚያም ያዕቆብ እንዲህ ሲል ስእለት ተሳለ፦ “አምላክ ከእኔ ባይለይና በመንገዴ ቢጠብቀኝ እንዲሁም የምበላው ምግብና የምለብሰው ልብስ ቢሰጠኝ፣ 21  ወደ አባቴም ቤት በሰላም ብመለስ ይሖዋ አምላኬ መሆኑን አስመሠከረ ማለት ነው። 22  እንደ ዓምድ ያቆምኩት ይህ ድንጋይም የአምላክ ቤት ይሆናል፤ አምላክ ሆይ፣ እኔም ከምትሰጠኝ ከማንኛውም ነገር አንድ አሥረኛውን ለአንተ እሰጣለሁ።”
[]
[]
[]
[]
12,525
29  ከዚያ በኋላ ያዕቆብ ጉዞውን ቀጠለ፤ ወደ ምሥራቅ ሰዎች ምድርም ሄደ። 2  እዚያም በሜዳ ላይ አንድ የውኃ ጉድጓድ ተመለከተ፤ እረኞች የበግ መንጎቻቸውን ሁልጊዜ የሚያጠጡት ከዚያ የውኃ ጉድጓድ ስለነበር በአቅራቢያው ሦስት የበግ መንጎች ተኝተው አየ። በጉድጓዱም አፍ ላይ ትልቅ ድንጋይ ነበር። 3  መንጎቹ በሙሉ እዚያ ከተሰበሰቡ በኋላ እረኞቹ በውኃ ጉድጓዱ አፍ ላይ ያለውን ድንጋይ ያንከባልሉና መንጎቹን ያጠጣሉ፤ ከዚያም ድንጋዩን ወደ ቦታው በመመለስ የጉድጓዱን አፍ ይገጥሙታል። 4  ያዕቆብም “ወንድሞቼ፣ ከየት ነው የመጣችሁት?” ብሎ ጠየቃቸው፤ እነሱም “ከካራን ነው የመጣነው” አሉት። 5  እሱም “የናኮርን የልጅ ልጅ ላባን ታውቁታላችሁ?” አላቸው፤ እነሱም “አዎ፣ እናውቀዋለን” አሉት። 6  እሱም “ለመሆኑ ደህና ነው?” አላቸው። እነሱም “አዎ፣ ደህና ነው። እንዲያውም ልጁ ራሔል ይኸው በጎች ይዛ እየመጣች ነው!” አሉት። 7  ከዚያም እሱ “እንደምታዩት ገና እኩለ ቀን ነው። አሁን እኮ መንጎች የሚገቡበት ሰዓት አይደለም፤ በጎቹን አጠጧቸውና ወደ ግጦሽ አሰማሯቸው” አላቸው። 8  እነሱም “መንጎቹ ሁሉ ካልተሰባሰቡና እረኞቹ ድንጋዩን ከጉድጓዱ አፍ ላይ ካላንከባለሉት እንዲህ ማድረግ አንችልም፤ በጎቹን ማጠጣት የምንችለው ከዚያ በኋላ ነው” አሉት። 9  እሱም ገና ከእነሱ ጋር እየተነጋገረ ሳለ ራሔል እረኛ ስለነበረች የአባቷን በጎች እየነዳች መጣች። 10  ያዕቆብ የእናቱን ወንድም የላባን ልጅ ራሔልንና የላባን በጎች ሲያይ ወዲያውኑ ወደ ጉድጓዱ ሄዶ ድንጋዩን ከጉድጓዱ አፍ ላይ አንከባለለ፤ የእናቱን ወንድም የላባን በጎችም አጠጣ። 11  ከዚያም ያዕቆብ ራሔልን ሳማት፤ ጮክ ብሎም አለቀሰ። 12  ያዕቆብም ለራሔል የአባቷ ዘመድና የርብቃ ልጅ መሆኑን ነገራት። እሷም እየሮጠች ሄዳ ለአባቷ ነገረችው። 13  ላባም የእህቱ ልጅ ስለሆነው ስለ ያዕቆብ ሲሰማ ወደ እሱ እየሮጠ ሄዶ አቅፎ ሳመው፤ ወደ ቤቱም አስገባው። ያዕቆብም ሁኔታውን ሁሉ ለላባ ነገረው። 14  ላባም “በእርግጥም አንተ የአጥንቴ ፍላጭ የሥጋዬ ቁራጭ ነህ” አለው። በመሆኑም ያዕቆብ ከእሱ ጋር አንድ ወር ሙሉ ተቀመጠ። 15  ከዚያም ላባ ያዕቆብን “ዘመዴ ስለሆንክ ብቻ እኔን በነፃ ልታገለግለኝ ይገባል? ንገረኝ፣ ደሞዝህ ምንድን ነው?” አለው። 16  ላባ ሁለት ሴቶች ልጆች ነበሩት። የታላቋ ስም ሊያ ሲሆን የታናሿ ስም ደግሞ ራሔል ነበር። 17  ሊያ ዓይነ ልም ነበረች፤ ራሔል ግን ዓይን የምትማርክ ውብ ሴት ነበረች። 18  ያዕቆብ ራሔልን ይወዳት ስለነበር “ለታናሿ ልጅህ ለራሔል ስል ሰባት ዓመት ላገለግልህ ፈቃደኛ ነኝ” አለው። 19  ላባም “ለሌላ ሰው ከምሰጣት ለአንተ ብሰጥህ ይሻለኛል፤ አብረኸኝ ተቀመጥ” አለው። 20  ያዕቆብም ለራሔል ሲል ሰባት ዓመት አገለገለ፤ ይሁንና ራሔልን ይወዳት ስለነበር ሰባቱ ዓመታት ለእሱ እንደ ጥቂት ቀናት ነበሩ። 21  ከዚያም ያዕቆብ ላባን “እንግዲህ የተባባልነው ጊዜ ስላበቃ ሚስቴን ስጠኝ፤ ከእሷም ጋር ልተኛ” አለው። 22  ስለዚህ ላባ የአካባቢውን ሰዎች በሙሉ ጠራ፤ ግብዣም አደረገ። 23  ሆኖም ሲመሽ ላባ ልጁን ሊያን ወስዶ ከእሷ ጋር እንዲተኛ ለያዕቆብ ሰጠው። 24  በተጨማሪም ላባ የእሱ አገልጋይ የሆነችውን ዚልጳን አገልጋይዋ እንድትሆን ለልጁ ለሊያ ሰጣት። 25  በማግስቱ ጠዋት ያዕቆብ አብራው ያደረችው ሊያ መሆኗን አወቀ! በመሆኑም ያዕቆብ ላባን “ያደረግክብኝ ነገር ምንድን ነው? ያገለገልኩህ ለራሔል ስል አልነበረም? ታዲያ ለምን አታለልከኝ?” አለው። 26  ላባም እንዲህ አለው፦ “በአካባቢያችን በኩሯ እያለች ታናሺቱን መዳር የተለመደ አይደለም። 27  ሳምንቱን ከዚህችኛዋ ጋር ተሞሸር። ከዚያም ለምታገለግለኝ ተጨማሪ ሰባት ዓመታት ሌላኛዋን ደግሞ እሰጥሃለሁ።” 28  ያዕቆብም እንደተባለው አደረገ፤ ሳምንቱን ከዚህችኛዋ ጋር ተሞሸረ። ከዚያም ላባ ልጁን ራሔልን ሚስት እንድትሆነው ሰጠው። 29  በተጨማሪም ላባ አገልጋዩ የሆነችውን ባላን አገልጋይዋ እንድትሆን ለልጁ ለራሔል ሰጣት። 30  ከዚያም ያዕቆብ ከራሔል ጋር ተኛ፤ ራሔልንም ከሊያ ይልቅ ወደዳት። ላባንም ሌላ ሰባት ዓመት አገለገለው። 31  ይሖዋም ሊያ እንዳልተወደደች ሲመለከት መፀነስ እንድትችል አደረጋት፤ ራሔል ግን መሃን ነበረች። 32  ሊያም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች። እሷም “ይህ የሆነው ይሖዋ መከራዬን ስላየልኝ ነው፤ ከእንግዲህ ባሌ ይወደኛል” ስትል ስሙን ሮቤል አለችው። 33  ዳግመኛም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች። እሷም “ይሖዋ እንዳልተወደድኩ ስለሰማ ይሄኛውንም ልጅ ሰጠኝ” አለች። ስሙንም ስምዖን አለችው። 34  አሁንም ደግሞ ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች። እሷም “ሦስት ወንዶች ልጆች ስለወለድኩለት አሁን ባሌ ይቀርበኛል” አለች። በዚህም የተነሳ ሌዊ ተባለ። 35  አሁንም እንደገና ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች። እሷም “አሁን ይሖዋን አወድሰዋለሁ” አለች። ስለሆነም ይሁዳ አለችው። ከዚያ በኋላ መውለድ አቆመች።
[]
[]
[]
[]
12,526
3  እባብም ይሖዋ አምላክ ከሠራቸው የዱር እንስሳት ሁሉ እጅግ ጠንቃቃ ነበር። በመሆኑም ሴቲቱን “በእርግጥ አምላክ ‘በአትክልቱ ስፍራ ካለው ከማንኛውም ዛፍ አትብሉ’ ብሏችኋል?” ሲል ጠየቃት። 2  በዚህ ጊዜ ሴቲቱ እባቡን እንዲህ አለችው፦ “በአትክልቱ ስፍራ ካሉት ዛፎች ፍሬ መብላት እንችላለን። 3  ይሁንና በአትክልቱ ስፍራ መካከል የሚገኘውን ዛፍ ፍሬ በተመለከተ አምላክ ‘ከእሱ አትብሉ፤ ፈጽሞም አትንኩት፤ አለዚያ ትሞታላችሁ’ ብሏል።” 4  በዚህ ጊዜ እባቡ ሴቲቱን እንዲህ አላት፦ “መሞት እንኳ ፈጽሞ አትሞቱም። 5  አምላክ ከዛፉ በበላችሁ ቀን ዓይኖቻችሁ እንደሚገለጡና መልካምና ክፉን በማወቅ ረገድ እንደ አምላክ እንደምትሆኑ ስለሚያውቅ ነው።” 6  በዚህም የተነሳ ሴቲቱ ዛፉ ለመብል መልካም፣ ሲያዩትም የሚያጓጓ እንደሆነ ተመለከተች፤ ዛፉ ለዓይን የሚማርክ ነበር። ስለሆነም ከዛፉ ፍሬ ወስዳ በላች። ባሏም አብሯት ሲሆን ለእሱም ሰጠችው፤ እሱም በላ። 7  ከዚያም የሁለቱም ዓይኖች ተገለጡ፤ ራቁታቸውን መሆናቸውንም አስተዋሉ። በመሆኑም የበለስ ቅጠል በመስፋት የሚያሸርጡት ነገር ለራሳቸው ሠሩ። 8  በኋላም ሰውየውና ሚስቱ ቀኑ ነፋሻማ በሆነበት ጊዜ ላይ ይሖዋ አምላክ በአትክልቱ ስፍራ ውስጥ ሲሄድ ድምፁን ሰሙ፤ እነሱም በአትክልቱ ስፍራ ባሉት ዛፎች መካከል በመግባት ከይሖዋ አምላክ ፊት ተደበቁ። 9  ይሖዋ አምላክም ሰውየውን በተደጋጋሚ በመጣራት “የት ነህ?” አለው። 10  በመጨረሻም ሰውየው “በአትክልቱ ስፍራ ድምፅህን ሰማሁ፤ ሆኖም ራቁቴን ስለነበርኩ ፈራሁ፤ ስለሆነም ተደበቅኩ” አለ። 11  እሱም “ራቁትህን እንደሆንክ ማን ነገረህ? እንዳትበላ ብዬ ካዘዝኩህ ዛፍ በላህ?” አለው። 12  ሰውየውም “ከእኔ ጋር እንድትሆን የሰጠኸኝ ይህች ሴት ከዛፉ ፍሬ ሰጠችኝና በላሁ” አለ። 13  ከዚያም ይሖዋ አምላክ ሴቲቱን “ለመሆኑ ይህ ያደረግሽው ነገር ምንድን ነው?” አላት። ሴቲቱም “እባቡ አታለለኝና በላሁ” ስትል መለሰች። 14  ከዚያም ይሖዋ አምላክ እባቡን እንዲህ አለው፦ “ይህን ስላደረግክ ከቤት እንስሳት ሁሉ እንዲሁም ከዱር እንስሳት ሁሉ የተረገምክ ትሆናለህ። በሕይወትህ ዘመን ሁሉ በሆድህ እየተሳብክ ትሄዳለህ፤ እንዲሁም አፈር ትበላለህ። 15  በአንተና በሴቲቱ መካከል እንዲሁም በዘርህና በዘሯ መካከል ጠላትነት እንዲኖር አደርጋለሁ፤ እሱ ራስህን ይጨፈልቃል፤ አንተም ተረከዙን ታቆስላለህ።” 16  ሴቲቱንም እንዲህ አላት፦ “በእርግዝናሽ ወቅት የሚሰማሽን ሕመም በእጅጉ አበዛለሁ፤ ልጆች የምትወልጂውም በሥቃይ ይሆናል፤ ምኞትሽ ሁሉ ባልሽ ይሆናል፤ እሱ ደግሞ ይገዛሻል።” 17  አዳምንም እንዲህ አለው፦ “የሚስትህን ቃል ስለሰማህና ‘ከእሱ አትብላ’ ብዬ ካዘዝኩህ ዛፍ ወስደህ ስለበላህ በአንተ የተነሳ ምድር የተረገመች ትሁን። በሕይወትህ ዘመን ሁሉ የምድርን ፍሬ በሥቃይ ትበላለህ። 18  ምድርም እሾህና አሜኬላ ታበቅልብሃለች፤ አንተም በሜዳ ላይ የሚበቅለውን ተክል ትበላለህ። 19  ከመሬት ስለተገኘህ ወደ መሬት እስክትመለስ ድረስ ላብህን እያንጠፈጠፍክ ምግብ ትበላለህ። አፈር ስለሆንክ ወደ አፈር ትመለሳለህ።” 20  ከዚህ በኋላ አዳም ሚስቱን ሔዋን ብሎ ጠራት፤ ምክንያቱም እሷ የሕያዋን ሁሉ እናት ትሆናለች። 21  ይሖዋ አምላክም ረጅም ልብስ ከቆዳ ሠርቶ አዳምንና ሚስቱን አለበሳቸው። 22  ከዚያም ይሖዋ አምላክ እንዲህ አለ፦ “እንግዲህ ሰውየው መልካምና ክፉን በማወቅ ረገድ ከእኛ እንደ አንዱ ሆኗል። አሁን ደግሞ እጁን በመዘርጋት ከሕይወት ዛፍ ፍሬ ወስዶ እንዳይበላና ለዘላለም እንዳይኖር አንድ ነገር ማድረግ አለብኝ።” 23  ስለሆነም የተገኘበትን መሬት እንዲያርስ፣ ይሖዋ አምላክ አዳምን ከኤደን የአትክልት ስፍራ አባረረው። 24  ሰውየውንም አስወጣው፤ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም መንገድ ለመጠበቅ በኤደን የአትክልት ስፍራ በስተ ምሥራቅ በኩል ኪሩቤልና ያለማቋረጥ የሚሽከረከር የነበልባል ሰይፍ አስቀመጠ።
[]
[]
[]
[]
12,527
30  ራሔል ለያዕቆብ ምንም ልጅ እንዳልወለደችለት ባየች ጊዜ በእህቷ ቀናች፤ ያዕቆብንም “ልጆች ስጠኝ፤ አለዚያ እሞታለሁ” ትለው ጀመር። 2  በዚህ ጊዜ ያዕቆብ ራሔልን በጣም ተቆጥቶ “እኔ፣ እንዳትወልጂ ያደረገሽን አምላክ መሰልኩሽ እንዴ?” አላት። 3  እሷም በዚህ ጊዜ “ባሪያዬ ባላ ይችውልህ፤ ልጆች እንድትወልድልኝና እኔም በእሷ አማካኝነት ልጆች እንዳገኝ ከእሷ ጋር ግንኙነት ፈጽም” አለችው። 4  በዚህ መሠረት አገልጋይዋን ባላን ሚስት እንድትሆነው ሰጠችው፤ ያዕቆብም ከእሷ ጋር ግንኙነት ፈጸመ። 5  ባላም ፀነሰች፤ ከዚያም ለያዕቆብ ወንድ ልጅ ወለደችለት። 6  ራሔልም “አምላክ ዳኛ ሆነልኝ፤ ቃሌንም ሰማ። በመሆኑም ወንድ ልጅ ሰጠኝ” አለች። በዚህም የተነሳ ስሙን ዳን አለችው። 7  የራሔል አገልጋይ ባላ በድጋሚ ፀነሰች፤ ከዚያም ለያዕቆብ ሁለተኛ ወንድ ልጅ ወለደችለት። 8  ራሔልም “ከእህቴ ጋር ብርቱ ትግል ገጠምኩ፤ አሸናፊም ሆንኩ!” አለች። በመሆኑም ስሙን ንፍታሌም አለችው። 9  ሊያ ልጅ መውለድ እንዳቆመች ስትረዳ አገልጋይዋን ዚልጳን ለያዕቆብ ሚስት እንድትሆነው ሰጠችው። 10  የሊያም አገልጋይ ዚልጳ ለያዕቆብ ወንድ ልጅ ወለደችለት። 11  ከዚያም ሊያ “ምንኛ መታደል ነው!” አለች። በመሆኑም ስሙን ጋድ አለችው። 12  ከዚያ በኋላ የሊያ አገልጋይ ዚልጳ ለያዕቆብ ሁለተኛ ወንድ ልጅ ወለደችለት። 13  ከዚያም ሊያ “ምንኛ ደስተኛ ነኝ! በእርግጥም ከእንግዲህ ሴቶች ደስተኛ ይሉኛል” አለች። በመሆኑም ስሙን አሴር አለችው። 14  የስንዴ መከር በሚሰበሰብበት ወቅት ሮቤል ወደ ሜዳ ወጣ፤ ከሜዳውም ላይ ፍሬ ለቀመ። ለእናቱ ለሊያም አመጣላት። ከዚያም ራሔል ሊያን “እባክሽ፣ ልጅሽ ካመጣው ፍሬ የተወሰነ ስጪኝ” አለቻት። 15  በዚህ ጊዜ ሊያ “ባሌን የወሰድሽብኝ አነሰሽና አሁን ደግሞ ልጄ ያመጣውን ፍሬ መውሰድ ትፈልጊያለሽ?” አለቻት። በመሆኑም ራሔል “እሺ፣ ልጅሽ ባመጣው ፍሬ ፋንታ ዛሬ ማታ ከአንቺ ጋር ይደር” አለቻት። 16  ያዕቆብ የዚያን ቀን ምሽት ከእርሻ ሲመለስ ሊያ ወጥታ ተቀበለችውና “ልጄ ባመጣው ፍሬ ስለተከራየሁህ ዛሬ የምትተኛው ከእኔ ጋር ነው” አለችው። ስለሆነም በዚያ ሌሊት ከእሷ ጋር አደረ። 17  አምላክም ሊያን ሰማት፤ መልስም ሰጣት፤ እሷም ፀነሰች፤ ከዚያም ለያዕቆብ አምስተኛ ወንድ ልጅ ወለደችለት። 18  ሊያም “አገልጋዬን ለባሌ ስለሰጠሁ አምላክ ደሞዜን ከፈለኝ” አለች። በመሆኑም ስሙን ይሳኮር አለችው። 19  ሊያም በድጋሚ ፀነሰች፤ ከዚያም ለያዕቆብ ስድስተኛ ወንድ ልጅ ወለደችለት። 20  ሊያም “አምላክ አድሎኛል፤ አዎ፣ መልካም ስጦታ ሰጥቶኛል። ለባሌ ስድስት ወንዶች ልጆች ስለወለድኩለት ከእንግዲህ ይታገሠኛል” አለች። በመሆኑም ስሙን ዛብሎን አለችው። 21  ከዚያ በኋላ ሴት ልጅ ወለደች፤ ስሟንም ዲና አለቻት። 22  በመጨረሻም አምላክ ራሔልን አሰባት፤ ልመናዋንም ሰምቶ መፀነስ እንድትችል በማድረግ ጸሎቷን መለሰላት። 23  እሷም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች። ከዚያም “አምላክ ነቀፋዬን አስወገደልኝ!” አለች። 24  በመሆኑም “ይሖዋ ሌላ ወንድ ልጅ ጨመረልኝ” በማለት ስሙን ዮሴፍ አለችው። 25  ራሔል ዮሴፍን ከወለደች በኋላ ብዙም ሳይቆይ ያዕቆብ ላባን እንዲህ አለው፦ “ወደ ስፍራዬና ወደ ምድሬ እንድመለስ አሰናብተኝ። 26  ለእነሱ ስል ያገለገልኩህን ሚስቶቼንና ልጆቼን ስጠኝና ልሂድ፤ ምን ያህል እንዳገለገልኩህ በሚገባ ታውቃለህ።” 27  ከዚያም ላባ “በፊትህ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ እባክህ ከእኔ ጋር ተቀመጥ፤ ይሖዋ እየባረከኝ ያለው በአንተ የተነሳ መሆኑን በንግርት ተረድቻለሁ” አለው። 28  ከዚያም “ደሞዝህን አሳውቀኝና እሰጥሃለሁ” አለው። 29  በመሆኑም ያዕቆብ እንዲህ አለው፦ “እንዴት እንዳገለገልኩህና መንጋህም ምን ያህል እየበዛልህ እንዳለ ታውቃለህ፤ 30  እኔ ከመምጣቴ በፊት የነበረህ ነገር ጥቂት እንደሆነና እኔ ከመጣሁ በኋላ ግን ከብቶችህ በጣም እየበዙ እንደሄዱ፣ ይሖዋም እንደባረከህ ታውቃለህ። ታዲያ ለራሴ ቤት አንድ ነገር የማደርገው መቼ ነው?” 31  ከዚያም ላባ “ምን እንድሰጥህ ትፈልጋለህ?” አለው። ያዕቆብም እንዲህ አለ፦ “እኔ ምንም ነገር እንድትሰጠኝ አልፈልግም! የምጠይቅህን አንድ ነገር ብቻ የምታደርግልኝ ከሆነ መንጋህን መጠበቄንና መንከባከቤን እቀጥላለሁ። 32  ዛሬ በመንጎችህ ሁሉ መካከል እዘዋወራለሁ። አንተም ከመንጋው መካከል ጠቃጠቆ ያለባቸውንና ዥጉርጉር የሆኑትን በጎች ሁሉ፣ ከጠቦቶቹም መካከል ጥቁር ቡናማ የሆኑትን በጎች ሁሉ እንዲሁም ዥጉርጉር የሆኑትንና ጠቃጠቆ ያለባቸውን እንስት ፍየሎች ሁሉ ለይ። ከዚህ በኋላ እንዲህ ዓይነቶቹ የእኔ ደሞዝ ይሆናሉ። 33  ወደፊት ደሞዜን ለመመልከት በምትመጣበት ጊዜ ጽድቄ ስለ እኔ ይናገራል፤ ከእንስት ፍየሎቹ መካከል ጠቃጠቆ የሌለበትና ዥጉርጉር ያልሆነ እንዲሁም ከጠቦቶቹ መካከል ጥቁር ቡናማ ያልሆነ በእኔ ዘንድ ከተገኘ ያ የተሰረቀ እንደሆነ ይቆጠራል።” 34  በዚህ ጊዜ ላባ “ይሄማ ጥሩ ነው! እንዳልከው ይሁን” አለው። 35  ከዚያም በዚያኑ ቀን ሽንትር ያለባቸውንና ዥጉርጉር የሆኑትን ተባዕት ፍየሎች ሁሉ፣ ጠቃጠቆ ያለባቸውንና ዥጉርጉር የሆኑትን እንስት ፍየሎች ሁሉ፣ ነጭ የሚባል ነገር ያለበትን ሁሉ እንዲሁም ከጠቦቶቹ መካከል ጥቁር ቡናማ የሆኑትን ሁሉ ለየ፤ እነዚህንም ወንዶች ልጆቹ እንዲጠብቋቸው ሰጣቸው። 36  ከዚህ በኋላ በእሱና በያዕቆብ መካከል የሦስት ቀን መንገድ ያህል ርቀት እንዲኖር አደረገ፤ ያዕቆብም የቀሩትን የላባን መንጎች ይጠብቅ ጀመር። 37  ከዚያም ያዕቆብ ከሊብነህ፣ ከአልሞንድና ከአርሞን ዛፎች ላይ የተቆረጡ እርጥብ በትሮችን ወሰደ፤ በመቀጠልም በትሮቹን አለፍ አለፍ ብሎ በመላጥና ነጩ እንዲታይ በማድረግ ዥጉርጉር እንዲሆኑ አደረገ። 38  ከዚያም የላጣቸውን በትሮች ወስዶ መንጎቹ ውኃ ለመጠጣት ሲመጡ እንዲያዩአቸው በመንጎቹ ፊት ለፊት በቦዮቹ ማለትም ውኃ በሚጠጡባቸው ገንዳዎች ውስጥ አስቀመጣቸው፤ ይህን ያደረገውም መንጎቹ ውኃ ለመጠጣት ሲመጡ በበትሮቹ ፊት ለስሪያ እንዲነሳሱ ለማድረግ ነው። 39  ስለዚህ መንጎቹ በበትሮቹ ፊት ለስሪያ ይነሳሱ ነበር፤ መንጎቹም ሽንትርና ጠቃጠቆ ያለባቸውን እንዲሁም ዥጉርጉር የሆኑ ግልገሎችን ይወልዱ ነበር። 40  ከዚያም ያዕቆብ ጠቦቶቹን ለየ፤ ከዚያም መንጎቹ በላባ መንጎች መካከል ወዳሉት ሽንትር ወዳለባቸውና ጥቁር ቡናማ ወደሆኑት ሁሉ እንዲመለከቱ አደረገ። ከዚያም የራሱን መንጎች ለየ፤ ከላባ መንጎች ጋር አልቀላቀላቸውም። 41  ያዕቆብም ብርቱ የሆኑት እንስሳት ለስሪያ በተነሳሱ ቁጥር በትሮቹን በመንጎቹ ፊት ለፊት ገንዳዎቹ ውስጥ ያስቀምጣቸው ነበር፤ እንዲህ የሚያደርገው መንጎቹ በበትሮቹ አማካኝነት ለስሪያ እንዲነሳሱ ለማድረግ ነበር። 42  እንስሶቹ ደካማ ሲሆኑ ግን በትሮቹን ገንዳዎቹ ውስጥ አያስቀምጥም ነበር። ስለሆነም ደካማ ደካማዎቹ ለላባ ሲሆኑ ብርቱ ብርቱዎቹ ግን ለያዕቆብ ሆኑ። 43  በዚህ መንገድ ይህ ሰው እጅግ ባለጸጋ እየሆነ ሄደ፤ የብዙ መንጎች፣ የወንድና የሴት አገልጋዮች፣ የግመሎች እንዲሁም የአህዮች ባለቤት ሆነ።
[]
[]
[]
[]
12,528
31  ከጊዜ በኋላ ያዕቆብ፣ የላባ ልጆች “ያዕቆብ የአባታችንን ንብረት እንዳለ ወስዷል፤ ይህን ሁሉ ሀብት ያካበተው እኮ ከአባታችን ንብረት ነው” ሲሉ ሰማ። 2  ያዕቆብ የላባን ፊት ሲመለከት ፊቱ እንደተለወጠበት አስተዋለ። 3  በመጨረሻም ይሖዋ ያዕቆብን “ወደ አባቶችህና ወደ ዘመዶችህ አገር ተመለስ፤ እኔም ከአንተ ጋር እሆናለሁ” አለው። 4  ከዚያም ያዕቆብ ራሔልና ሊያ መንጎቹን ወዳሰማራበት መስክ እንዲመጡ መልእክት ላከባቸው፤ 5  እንዲህም አላቸው፦ “አባታችሁን ሳየው ፊቱ ተለውጦብኛል፤ የአባቴ አምላክ ግን ከእኔ አልተለየም። 6  መቼም አባታችሁን ባለኝ አቅም ሁሉ እንዳገለገልኩት እናንተ ራሳችሁ በሚገባ ታውቃላችሁ። 7  አባታችሁ ሊያጭበረብረኝ ሞክሯል፤ ደሞዜንም አሥር ጊዜ ቀያይሮብኛል፤ አምላክ ግን ጉዳት እንዲያደርስብኝ አልፈቀደለትም። 8  ‘ደሞዝህ ዥጉርጉር የሆኑት ይሆናሉ’ ሲለኝ መንጎቹ ሁሉ ዥጉርጉር ወለዱ፤ ‘ደሞዝህ ሽንትር ያለባቸው ይሆናሉ’ ሲለኝ ደግሞ መንጎቹ ሁሉ ሽንትር ያለባቸው ወለዱ። 9  ስለዚህ አምላክ የአባታችሁን ከብቶች ከእሱ እየወሰደ ለእኔ ይሰጠኝ ነበር። 10  በአንድ ወቅት፣ መንጎቹ ለስሪያ በሚነሳሱበት ጊዜ እንስቶቹን የሚያጠቁት አውራ ፍየሎች ሽንትር ያለባቸው፣ ዥጉርጉር የሆኑና ጠቃጠቆ ያለባቸው መሆናቸውን በሕልሜ አየሁ። 11  ከዚያም የእውነተኛው አምላክ መልአክ በሕልሜ ‘ያዕቆብ!’ ሲል ጠራኝ፤ እኔም ‘አቤት’ አልኩት። 12  እሱም እንዲህ አለኝ፦ ‘እንስቶቹን የሚያጠቁት አውራ ፍየሎች ሁሉ ሽንትር ያለባቸው፣ ዥጉርጉር የሆኑና ጠቃጠቆ ያለባቸው መሆናቸውን እባክህ ቀና ብለህ ተመልከት፤ ምክንያቱም ላባ እየፈጸመብህ ያለውን ነገር ሁሉ ተመልክቻለሁ። 13  ዓምድ አቁመህ የቀባህበትና በዚያም ለእኔ ስእለት የተሳልክበት የቤቴል እውነተኛው አምላክ እኔ ነኝ። በል አሁን ተነስተህ ከዚህ ምድር ውጣ፤ ወደተወለድክበትም ምድር ተመለስ።’” 14  በዚህ ጊዜ ራሔልና ሊያ እንዲህ ሲሉ መለሱለት፦ “እንደው ለመሆኑ በአባታችን ቤት ልንወርሰው የምንችለው የቀረ ነገር ይኖራል? 15  እሱ እኛን የሸጠንና ለእኛ የተሰጠውን ገንዘብ የበላው እንደ ባዕድ ስለሚያየን አይደለም? 16  አምላክ ከአባታችን ላይ የወሰደበት ሀብት ሁሉ የእኛና የልጆቻችን ነው። ስለሆነም አምላክ አድርግ ያለህን ነገር ሁሉ አድርግ።” 17  ከዚያም ያዕቆብ ተነሳ፤ ልጆቹንና ሚስቶቹን ግመል ላይ አስቀመጣቸው፤ 18  እንዲሁም መንጎቹን ሁሉና ያከማቸውን ንብረት ሁሉ፣ በጳዳንአራም ሳለ ያገኛቸውንም ከብቶች ሁሉ እየነዳ በከነአን ምድር ወደሚገኘው ወደ አባቱ ወደ ይስሐቅ ለመሄድ ጉዞ ጀመረ። 19  በዚህ ጊዜ ላባ በጎቹን ለመሸለት ሄዶ ነበር፤ ራሔልም የአባቷን የተራፊም ቅርጻ ቅርጾች ሰረቀች። 20  ያዕቆብም ቢሆን ለአራማዊው ለላባ ሳይነግረው ሊኮበልል በመነሳቱ አታሎታል። 21  ያዕቆብም ያለውን ሁሉ ይዞ ኮበለለ፤ ወንዙንም ተሻግሮ ሄደ። ከዚያም ጊልያድ ወደተባለው ተራራማ አካባቢ አቀና። 22  በሦስተኛውም ቀን የያዕቆብ መኮብለል ለላባ ተነገረው። 23  በመሆኑም ላባ ያዕቆብ ላይ ለመድረስ ወንድሞቹን አስከትሎ የሰባት ቀን መንገድ ተጓዘ፤ ከዚያም ጊልያድ በተባለው ተራራማ አካባቢ ደረሰበት። 24  ከዚያም አምላክ ለአራማዊው ለላባ ሌሊት በሕልም ተገልጦለት “ክፉም ሆነ ደግ ያዕቆብን ስለምትናገረው ነገር ተጠንቀቅ” አለው። 25  ያዕቆብ በተራራው ላይ ድንኳኑን ተክሎ ሳለ ላባ ወደ ያዕቆብ ቀረበ፤ ላባም ከወንድሞቹ ጋር ጊልያድ በተባለው ተራራማ አካባቢ ሰፈረ። 26  ከዚያም ላባ ያዕቆብን እንዲህ አለው፦ “ይህ ያደረግከው ነገር ምንድን ነው? እኔን ለማታለል የተነሳሳኸውና ሴት ልጆቼን በሰይፍ እንደተማረከ ምርኮኛ አስገድደህ የወሰድካቸው ለምንድን ነው? 27  ምንም ሳትነግረኝ ተደብቀህ የሸሸኸውና ያታለልከኝስ ለምንድን ነው? ነግረኸኝ ቢሆን ኖሮ በደስታና በዘፈን፣ በአታሞና በበገና እሸኝህ ነበር። 28  አንተ ግን የልጅ ልጆቼንና ሴቶች ልጆቼን ስሜ እንድሰናበት እንኳ ዕድል አልሰጠኸኝም። የሠራኸው የሞኝነት ሥራ ነው። 29  እናንተን መጉዳት እችል ነበር፤ ሆኖም ትናንት ሌሊት የአባታችሁ አምላክ ‘ክፉም ሆነ ደግ ያዕቆብን ስለምትናገረው ነገር ተጠንቀቅ’ አለኝ። 30  እሺ፣ አንተ ለመሄድ የተነሳኸው ወደ አባትህ ቤት ለመመለስ ስለናፈቅክ ነው፤ ሆኖም አማልክቴን የሰረቅከው ለምንድን ነው?” 31  ያዕቆብ ለላባ እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “እንዲህ ያደረግኩት ‘ሴቶች ልጆችህን በኃይል ነጥቀህ ታስቀርብኛለህ’ ብዬ ስለፈራሁ ነው። 32  አማልክትህን ያገኘህበት ማንኛውም ሰው ይገደል። በወንድሞቻችን ፊት ንብረቴን ፈትሽና የእኔ ነው የምትለውን ውሰድ።” ይሁንና ያዕቆብ ራሔል ጣዖቶቹን እንደሰረቀች አላወቀም ነበር። 33  በመሆኑም ላባ ወደ ያዕቆብ ድንኳን ገባ፤ ከዚያም ወደ ሊያ ድንኳን እንዲሁም ወደ ሁለቱ ሴት ባሪያዎች ድንኳን ገባ፤ ሆኖም ምንም አላገኘም። ከዚያም ከሊያ ድንኳን ወጥቶ ወደ ራሔል ድንኳን ገባ። 34  በዚህ ጊዜ ራሔል የተራፊም ቅርጻ ቅርጾቹን በግመል ኮርቻ ላይ በሚገኘው የሴቶች ዕቃ ማስቀመጫ ውስጥ ከትታ በላያቸው ላይ ተቀምጣ ነበር። በመሆኑም ላባ ድንኳኑን በሙሉ በረበረ፤ ሆኖም ምንም አላገኘም። 35  ከዚያም ራሔል አባቷን “ጌታዬ፣ ስላልተነሳሁልህ አትቆጣ፤ የሴቶች ልማድ ደርሶብኝ ነው” አለችው። ስለዚህ ላባ በጥንቃቄ ፈተሸ፤ ይሁንና የተራፊም ቅርጻ ቅርጾቹን አላገኘም። 36  በዚህ ጊዜ ያዕቆብ ተቆጣ፤ ላባንም ወቀሰው። ከዚያም ላባን እንዲህ አለው፦ “እስቲ የፈጸምኩት በደል ምንድን ነው? እንደዚህ በቁጣ ገንፍለህ የምታሳድደኝ ምን ኃጢአት ሠርቼ ነው? 37  ይኸው ዕቃዬን ሁሉ ፈትሸሃል፤ ታዲያ የቤትህ ንብረት የሆነ ምን ነገር አገኘህ? እስቲ በወንድሞቼና በወንድሞችህ ፊት አስቀምጠውና እነሱ በሁለታችን መካከል ይፍረዱ። 38  ከአንተ ጋር አብሬ በኖርኩባቸው በእነዚህ 20 ዓመታት ውስጥ በጎችህና ፍየሎችህ ጨንግፈው አያውቁም፤ እኔም ከመንጋህ መካከል አንዲት በግ እንኳ አልበላሁም። 39  አውሬ የቦጫጨቀውን እንስሳ አምጥቼልህ አላውቅም። ኪሳራውን በራሴ ላይ ቆጥሬ እከፍልህ ነበር። በቀንም ይሁን በሌሊት አንድ እንስሳ ቢሰረቅ ታስከፍለኝ ነበር። 40  ቀን በሐሩር፣ ሌሊት ደግሞ በቁር ስሠቃይ ኖሬአለሁ፤ እንቅልፍም በዓይኔ አይዞርም ነበር። 41  እንግዲህ 20 ዓመት ሙሉ በቤትህ የኖርኩት በዚህ ሁኔታ ነበር። ለሁለት ሴቶች ልጆችህ ስል 14 ዓመት፣ ለመንጋህ ስል ደግሞ 6 ዓመት አገለገልኩህ። አንተ ግን ደሞዜን አሥር ጊዜ ትቀያይርብኝ ነበር። 42  የአባቴ አምላክ፣ የአብርሃም አምላክና ይስሐቅ የሚፈራው አምላክ ከእኔ ጋር ባይሆን ኖሮ ባዶ እጄን ታሰናብተኝ ነበር። አምላክ ጉስቁልናዬንና ልፋቴን አየ፤ ትናንት ሌሊት የገሠጸህም ለዚህ ነው።” 43  ከዚያም ላባ ለያዕቆብ እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ሴቶቹ የገዛ ልጆቼ ናቸው፤ ልጆቹም ቢሆኑ ልጆቼ ናቸው፤ መንጋውም ቢሆን የእኔው መንጋ ነው፤ የምታየው ነገር ሁሉ የእኔና የሴት ልጆቼ ነው። ታዲያ ዛሬ በእነዚህም ሆነ በወለዷቸው ልጆቻቸው ላይ ምን ማድረግ እችላለሁ? 44  በል አሁን ና፣ እኔና አንተ ቃል ኪዳን እንጋባ፤ ይህም በእኔና በአንተ መካከል ምሥክር ሆኖ ያገለግላል።” 45  ስለዚህ ያዕቆብ ድንጋይ ወስዶ እንደ ዓምድ አቆመው። 46  ከዚያም ያዕቆብ ወንድሞቹን “ድንጋይ ሰብስቡ!” አላቸው። እነሱም ድንጋይ እያመጡ ከመሩ። በኋላም እዚያው ድንጋዩ ክምር ላይ በሉ። 47  ላባም የድንጋዩን ክምር ያጋርሳሃዱታ አለው፤ ያዕቆብ ግን ጋልኢድ ሲል ጠራው። 48  ከዚያም ላባ “ይህ የድንጋይ ክምር ዛሬ በእኔና በአንተ መካከል ምሥክር ነው” አለ። ከዚህም የተነሳ ያዕቆብ ጋልኢድ 49  እና መጠበቂያ ግንብ የሚል ስም አወጣለት፤ ምክንያቱም ላባ እንዲህ ብሎ ነበር፦ “እርስ በርስ በማንተያይበት ጊዜ ይሖዋ በእኔና በአንተ መካከል ጠባቂ ይሁን። 50  ልጆቼን ብትበድላቸውና በእነሱ ላይ ሌሎች ሚስቶችን ብታገባ ማንም ሰው ባያይም እንኳ አምላክ በእኔና በአንተ መካከል ምሥክር እንደሆነ አትርሳ።” 51  ላባም ያዕቆብን እንዲህ አለው፦ “የድንጋይ ክምሩ ይኸው፤ በእኔና በአንተ መካከል ያቆምኩት ዓምድም ይኸው። 52  እኔ አንተን ለመጉዳት ይህን የድንጋይ ክምር አልፌ ላልመጣ፣ አንተም እኔን ለመጉዳት ይህን የድንጋይ ክምርና ይህን ዓምድ አልፈህ ላትመጣ ይህ የድንጋይ ክምር ምሥክር ነው፤ ዓምዱም ቢሆን ምሥክር ይሆናል። 53   የአብርሃም አምላክና የናኮር አምላክ የሆነው የአባታቸው አምላክ በእኛ መካከል ይፍረድ።” ያዕቆብም አባቱ ይስሐቅ በሚፈራው አምላክ ማለ። 54  ከዚያ በኋላ ያዕቆብ በተራራው ላይ መሥዋዕት አቀረበ። ወንድሞቹንም ምግብ እንዲበሉ ጋበዛቸው። እነሱም ምግብ በሉ፤ በተራራውም ላይ አደሩ። 55  ላባም በማግስቱ ጠዋት ተነስቶ የልጅ ልጆቹንና ሴቶች ልጆቹን ስሞ መረቃቸው። ተነስቶም ወደ ቤቱ ተመለሰ።
[]
[]
[]
[]
12,529
32  ከዚያም ያዕቆብ ጉዞውን ቀጠለ፤ የአምላክ መላእክትም አገኙት። 2  ያዕቆብም ልክ እንዳያቸው “ይህ የአምላክ ሰፈር ነው!” አለ። በመሆኑም የቦታውን ስም ማሃናይም አለው። 3  ከዚያም ያዕቆብ በኤዶም ክልል ሴይር በተባለው ምድር ወደሚኖረው ወንድሙ ወደ ኤሳው መልእክተኞችን አስቀድሞ ላከ፤ 4  እንዲህም ብሎ አዘዛቸው፦ “ጌታዬን ኤሳውን እንዲህ በሉት፦ ‘አገልጋይህ ያዕቆብ እንዲህ ይላል፦ “ከላባ ጋር እስካሁን ድረስ ለረጅም ጊዜ ኖሬአለሁ። 5  አሁን በሬዎች፣ አህዮች፣ በጎች እንዲሁም ወንድና ሴት አገልጋዮች አሉኝ፤ ይህን መልእክት ለጌታዬ የላክሁት በፊትህ ሞገስ እንዳገኝ ለመጠየቅ ነው።”’” 6  ከተወሰነ ጊዜ በኋላም መልእክተኞቹ ወደ ያዕቆብ ተመልሰው በመምጣት እንዲህ አሉት፦ “ወንድምህን ኤሳውን አግኝተነው ነበር፤ እሱም ከአንተ ጋር ለመገናኘት ወደዚህ እየመጣ ነው፤ ከእሱም ጋር 400 ሰዎች አሉ።” 7  ያዕቆብም እጅግ ፈራ፤ በጭንቀትም ተዋጠ። በመሆኑም አብረውት ያሉትን ሰዎች፣ መንጎቹን፣ ከብቶቹንና ግመሎቹን በሁለት ቡድን ከፈላቸው። 8  እሱም “ምናልባት ኤሳው በአንደኛው ቡድን ላይ ጥቃት ቢሰነዝር፣ ሌላኛው ቡድን ሊያመልጥ ይችላል” አለ። 9  ከዚህ በኋላ ያዕቆብ እንዲህ አለ፦ “‘ወደ አገርህና ወደ ዘመዶችህ ተመለስ፤ እኔም መልካም ነገር አደርግልሃለሁ’ ያልከኝ የአባቴ የአብርሃም አምላክና የአባቴ የይስሐቅ አምላክ የሆንከው ይሖዋ ሆይ፣ 10  እኔ ባሪያህ ይህን ያህል ታማኝ ፍቅርና ታማኝነት ልታሳየኝ የሚገባኝ ሰው አልነበርኩም፤ ዮርዳኖስን ስሻገር ከበትር ሌላ ምንም አልነበረኝም፤ አሁን ግን ይኸው ሁለት ቡድን ሆኛለሁ። 11  ከወንድሜ ከኤሳው እጅ እንድታድነኝ እለምንሃለሁ፤ ምክንያቱም መጥቶ በእኔም ሆነ በእነዚህ እናቶችና በልጆቻቸው ላይ ጥቃት እንዳይሰነዝር ፈርቻለሁ። 12  አንተው ራስህ ‘በእርግጥ መልካም አደርግልሃለሁ፤ ዘርህንም ከብዛቱ የተነሳ ሊቆጠር እንደማይችል የባሕር አሸዋ አደርገዋለሁ’ ብለኸኛል።” 13  እሱም በዚያ ሌሊት እዚያው አደረ። ከንብረቱም መካከል የተወሰነውን ወስዶ ለወንድሙ ለኤሳው ስጦታ አዘጋጀ፤ 14  ስጦታውም የሚከተለው ነበር፦ 200 እንስት ፍየሎች፣ 20 ተባዕት ፍየሎች፣ 200 እንስት በጎች፣ 20 አውራ በጎች 15  እንዲሁም 30 የሚያጠቡ ግመሎች፣ 40 ላሞች፣ 10 በሬዎች፣ 20 እንስት አህዮችና 10 ተባዕት አህዮች። 16  እሱም በመንጋ በመንጋ ለይቶ ለአገልጋዮቹ ሰጣቸው። አገልጋዮቹንም “ቀድማችሁኝ ተሻገሩ፤ አንዱን መንጋ ከሌላው መንጋ አራርቁት” አላቸው። 17  በተጨማሪም የመጀመሪያውን እንዲህ ሲል አዘዘው፦ “ወንድሜ ኤሳው ቢያገኝህና ‘ለመሆኑ አንተ የማን ነህ? የምትሄደው ወዴት ነው? እነዚህ የምትነዳቸው እንስሳትስ የማን ናቸው?’ ብሎ ቢጠይቅህ፣ 18  ‘የአገልጋይህ የያዕቆብ ናቸው። ይህ ለጌታዬ ለኤሳው የተላከ ስጦታ ነው፤ እንዲያውም እሱ ራሱ ከኋላችን እየመጣ ነው’ በለው።” 19  እንዲሁም ሁለተኛውን፣ ሦስተኛውንና መንጎቹን የሚነዱትን በሙሉ እንዲህ ሲል አዘዛቸው፦ “ኤሳውን ስታገኙት ይህንኑ ንገሩት። 20  ‘አገልጋይህ ያዕቆብ ከኋላችን እየመጣ ነው’ ማለት እንዳለባችሁም አትዘንጉ።” ይህን ያላቸው ‘ስጦታውን አስቀድሜ በመላክ ቁጣው እንዲበርድለት ካደረግኩ ከእሱ ጋር ስገናኝ በጥሩ ሁኔታ ይቀበለኝ ይሆናል’ ብሎ ስላሰበ ነው። 21  በመሆኑም ስጦታው ከእሱ ቀድሞ ተሻገረ፤ እሱ ግን እዚያው የሰፈረበት ቦታ አደረ። 22  በኋላም በዚያው ሌሊት ተነሳ፤ ሁለቱን ሚስቶቹን፣ ሁለቱን ሴት አገልጋዮቹንና 11ዱን ወንዶች ልጆቹን ይዞ በያቦቅ መልካ ተሻገረ። 23  እነሱንም ወስዶ ወንዙን አሻገራቸው፤ ያለውንም ነገር ሁሉ አሻገረ። 24  በመጨረሻም ያዕቆብ ብቻውን ቀረ። ከዚያም አንድ ሰው ጎህ እስኪቀድ ድረስ ሲታገለው ቆየ። 25  ሰውየውም ሊያሸንፈው እንዳልቻለ ሲያይ የጭኑን መጋጠሚያ ነካው፤ ያዕቆብም ከእሱ ጋር በሚታገልበት ጊዜ የጭኑ መጋጠሚያ ከቦታው ተናጋ። 26  በኋላም ሰውየው “ጎህ እየቀደደ ስለሆነ ልቀቀኝና ልሂድ” አለው። እሱም “ካልባረክኸኝ አለቅህም” አለው። 27  በመሆኑም ሰውየው “ስምህ ማን ነው?” አለው፤ እሱም “ያዕቆብ” ሲል መለሰለት። 28  ሰውየውም “ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ እስራኤል እንጂ ያዕቆብ አይባልም፤ ምክንያቱም ከአምላክም ሆነ ከሰዎች ጋር ታግለህ በመጨረሻ አሸንፈሃል” አለው። 29  ያዕቆብም መልሶ “እባክህ ስምህን ንገረኝ” አለው። እሱ ግን “ስሜን የምትጠይቀኝ ለምንድን ነው?” አለው። እንዲህ ካለው በኋላም በዚያ ስፍራ ባረከው። 30  በመሆኑም ያዕቆብ “አምላክን ፊት ለፊት አይቼ እንኳ ሕይወቴ ተርፏል” በማለት የቦታውን ስም ጰኒኤል አለው። 31  ያዕቆብ ጰኑኤልን እንዳለፈ ፀሐይ ወጣችበት፤ እሱም ጭኑ በመጎዳቱ ምክንያት ያነክስ ነበር። 32  የእስራኤል ልጆች እስከ ዛሬ ድረስ በጭን መጋጠሚያ ላይ ያለውን ጅማት የማይበሉት ለዚህ ነው፤ ምክንያቱም ሰውየው በያዕቆብ ጭን መጋጠሚያ ላይ ያለውን ጅማት ነክቶ ነበር።
[]
[]
[]
[]
12,530
33  ያዕቆብም ቀና ብሎ ሲመለከት ኤሳው ሲመጣ አየ፤ ከእሱም ጋር 400 ሰዎች ነበሩ። በመሆኑም ልጆቹን ለሊያ፣ ለራሔልና ለሁለቱ ሴት አገልጋዮች አከፋፈላቸው። 2  እሱም ሴት አገልጋዮቹንና ልጆቻቸውን ከፊት፣ ሊያንና ልጆቿን ከእነሱ ቀጥሎ፣ ራሔልንና ዮሴፍን ደግሞ ከእነሱ በኋላ እንዲሆኑ አደረገ። 3  ከዚያም እሱ ቀድሟቸው ሄደ፤ ወደ ወንድሙ ሲቀርብም ሰባት ጊዜ ወደ መሬት ዝቅ ብሎ ሰገደ። 4  ሆኖም ኤሳው ወደ እሱ እየሮጠ በመሄድ አንገቱ ላይ ተጠምጥሞ ሳመው፤ ሁለቱም ተላቀሱ። 5  ኤሳውም ቀና ብሎ ሴቶቹንና ልጆቹን ሲያይ እንዲህ አለ፦ “እነዚህ አብረውህ ያሉት እነማን ናቸው?” እሱም “አምላክ በቸርነቱ ለአገልጋይህ የሰጣቸው ልጆች ናቸው” አለው። 6  በዚህ ጊዜ ሴት አገልጋዮቹ ከልጆቻቸው ጋር ወደ ፊት ቀርበው ሰገዱ፤ 7  ሊያና ልጆቿም ወደ ፊት ቀርበው ሰገዱ። ከዚያም ዮሴፍና ራሔል ወደ ፊት ቀርበው ሰገዱ። 8  ኤሳውም “ቀደም ሲል ያገኘኋቸውን ሰዎችና እንስሳት የላክሃቸው ለምንድን ነው?” አለው። እሱም “በጌታዬ ፊት ሞገስ ባገኝ ብዬ ነው” አለው። 9  ከዚያም ኤሳው “ወንድሜ ሆይ፣ እኔ ከበቂ በላይ አለኝ። የአንተ የሆነው ለራስህ ይሁን” አለው። 10  ያዕቆብ ግን እንዲህ አለው፦ “የለም፣ እንዲህማ አይሆንም። በፊትህ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ ስጦታዬን ከእጄ መውሰድ አለብህ፤ ምክንያቱም ስጦታውን የላክሁት ፊትህን እንዳይ ብዬ ነው። እንዲህ በደስታ ተቀብለኸኝ የአንተን ፊት ማየቴ ራሱ ለእኔ የአምላክን ፊት የማየት ያህል ነው። 11  አምላክ ሞገስ ስላሳየኝና የሚያስፈልገኝ ነገር ሁሉ ስላለኝ የመልካም ምኞት መግለጫ እንዲሆን ያመጣሁልህን ይህን ስጦታ እባክህ ተቀበለኝ።” ያዕቆብም አጥብቆ ለመነው፤ ስለዚህ ስጦታውን ወሰደ። 12  በኋላም ኤሳው “በል እንነሳና ጉዟችንን እንቀጥል፤ እኔም ከፊት ከፊትህ እሄዳለሁ” አለው። 13  እሱ ግን እንዲህ አለው፦ “ልጆቹ አቅም እንደሌላቸው እንዲሁም የሚያጠቡ በጎችና ከብቶች እንዳሉኝ ጌታዬ ያውቃል። እንስሳቱ ለአንድ ቀን እንኳ በጥድፊያ ቢነዱ መንጋው በሙሉ ያልቃል። 14  ስለዚህ ጌታዬ ከአገልጋዩ ቀድሞ ይሂድ፤ እኔ ግን ከጌታዬ ጋር እዚያው ሴይር እስከምንገናኝ ድረስ በምነዳቸው ከብቶች ፍጥነትና እንደ ልጆቹ እርምጃ ቀስ እያልኩ ላዝግም።” 15  ኤሳውም “እባክህ ከእኔ ጋር ካሉት ሰዎች መካከል ጥቂቶቹን ልተውልህ” አለው። እሱም “ለምን ብለህ? በጌታዬ ፊት ሞገስ ማግኘቴ ብቻ ይበቃኛል” አለው። 16  በመሆኑም በዚያ ቀን ኤሳው ወደ ሴይር ለመመለስ ጉዞ ጀመረ። 17  ያዕቆብም ወደ ሱኮት ሄደ፤ በዚያም ለራሱ ቤት፣ ለመንጎቹም ዳስ ሠራ። የቦታውንም ስም ሱኮት ያለው ለዚህ ነበር። 18  ያዕቆብ ከጳዳንአራም ተነስቶ በመጓዝ በከነአን ምድር ወደምትገኘው ወደ ሴኬም ከተማ በሰላም ደረሰ፤ በከተማዋም አቅራቢያ ሰፈረ። 19  ከዚያም ድንኳኑን የተከለበትን ቦታ ከሴኬም አባት ከኤሞር ወንዶች ልጆች እጅ በ100 ጥሬ ገንዘብ ገዛ። 20  በዚያም መሠዊያ አቆመ፤ መሠዊያውንም አምላክ፣ የእስራኤል አምላክ ብሎ ጠራው።
[]
[]
[]
[]
12,531
34  ያዕቆብ ከሊያ የወለዳት ዲና የተባለችው ልጅ እዚያ አገር ካሉ ወጣት ሴቶች ጋር ጊዜ ለማሳለፍ ትወጣ ነበር። 2  የአገሩ አለቃ የሆነው የሂዋዊው የኤሞር ልጅ ሴኬም ዲናን አያት፤ ከዚያም ወሰዳትና አብሯት ተኛ፤ አስገድዶም ደፈራት። 3  እሱም ልቡ በያዕቆብ ልጅ በዲና ተማረከ፤ ወጣቷንም አፈቀራት፤ በሚያባብሉ ቃላትም አነጋገራት። 4  በመጨረሻም ሴኬም አባቱን ኤሞርን “ከዚህች ልጅ ጋር አጋባኝ” አለው። 5  ያዕቆብ፣ ሴኬም ልጁን ዲናን እንዳስነወራት በሰማ ጊዜ ወንዶች ልጆቹ በመስክ መንጎቹን እየጠበቁ ነበር። በመሆኑም ያዕቆብ ልጆቹ እስኪመለሱ ድረስ ዝም አለ። 6  በኋላም የሴኬም አባት ኤሞር ከያዕቆብ ጋር ለመነጋገር ወጣ። 7  ሆኖም የያዕቆብ ወንዶች ልጆች ስለ ሁኔታው ሰሙ፤ ወዲያውኑም ከመስክ መጡ። ሴኬም የያዕቆብን ሴት ልጅ በመድፈር ፈጽሞ መደረግ የማይገባውን ድርጊት ስለፈጸመና በዚህም እስራኤልን ስላዋረደ በጣም ተበሳጩ፤ እጅግም ተቆጡ። 8  ኤሞርም እንዲህ አላቸው፦ “ልጄ ሴኬም ልጃችሁን በጣም ወዷታል። እባካችሁ ሚስት እንድትሆነው ስጡት፤ 9  በጋብቻም እንዛመድ። ሴቶች ልጆቻችሁን ዳሩልን፤ የእኛንም ሴቶች ልጆች አግቡ። 10  አብራችሁንም መኖር ትችላላችሁ፤ አገራችን አገራችሁ ናት። ኑሩባት፤ ነግዱባት፤ ሀብትም አፍሩባት።” 11  ከዚያም ሴኬም አባቷንና ወንድሞቿን እንዲህ አላቸው፦ “በፊታችሁ ሞገስ ላግኝ እንጂ የምትጠይቁኝን ሁሉ እሰጣለሁ። 12  ብዙ ጥሎሽና ስጦታ ልትጠይቁኝ ትችላላችሁ። እኔ የጠየቃችሁኝን ሁሉ ለመስጠት ፈቃደኛ ነኝ። ብቻ ይህችን ወጣት ሚስቴ እንድትሆን ስጡኝ።” 13  የያዕቆብ ወንዶች ልጆችም ሴኬም እህታቸውን ዲናን ስላስነወረ ለእሱና ለአባቱ ለኤሞር ተንኮል ያዘለ መልስ ሰጧቸው። 14  እንዲህም አሏቸው፦ “እንዲህ ያለ ነገር ፈጽሞ አናደርግም፤ እህታችንን ላልተገረዘ ሰው አንሰጥም፤ ምክንያቱም ይህ ለእኛ ውርደት ነው። 15  በሐሳባችሁ የምንስማማው እኛን ከመሰላችሁና የእናንተ የሆነው ወንድ ሁሉ እንዲገረዝ ካደረጋችሁ ብቻ ነው። 16  ከዚያም ሴቶች ልጆቻችንን እንድርላችኋለን፤ እኛም ሴቶች ልጆቻችሁን እናገባለን፤ አብረናችሁም እንኖራለን፤ አንድ ሕዝብም እንሆናለን። 17  የምንላችሁን የማትሰሙና ለመገረዝ ፈቃደኛ የማትሆኑ ከሆነ ግን ልጃችንን ይዘን እንሄዳለን።” 18  የተናገሩትም ነገር ኤሞርንና ልጁን ሴኬምን ደስ አሰኛቸው። 19  ወጣቱም ያሉትን ነገር ለማድረግ ጊዜ አልወሰደበትም፤ ምክንያቱም የያዕቆብን ልጅ ወዷት ነበር፤ ደግሞም በአባቱ ቤት ካሉት ሰዎች ሁሉ እጅግ የተከበረ ነበር። 20  በመሆኑም ኤሞርና ልጁ ሴኬም ወደ ከተማዋ በር በመሄድ በከተማቸው የሚኖሩትን ወንዶች እንዲህ አሏቸው፦ 21  “እነዚህ ሰዎች ከእኛ ጋር በሰላም መኖር ይፈልጋሉ። ምድሪቱ ለእነሱም ስለምትበቃ በምድሪቱ ይኑሩ፤ እንዲሁም ይነግዱ። ሴቶች ልጆቻቸውን ማግባት፣ የእኛንም ሴቶች ልጆች ለእነሱ መዳር እንችላለን። 22  ሆኖም ሰዎቹ ከእኛ ጋር አንድ ሕዝብ በመሆን አብረውን ለመኖር የሚስማሙት፣ ልክ እነሱ እንደተገረዙት የእኛ የሆኑ ወንዶች ሁሉ የሚገረዙ ከሆነ ብቻ ነው። 23  እንዲህ ብናደርግ ንብረታቸው፣ ሀብታቸውና ከብቶቻቸው ሁሉ የእኛ ሆኑ ማለት አይደለም? በመሆኑም ከእኛ ጋር ለመኖር ባቀረቡት ሐሳብ እንስማማ።” 24  በከተማው በር የሚወጡ ሁሉ ኤሞርና ልጁ ሴኬም ያሏቸውን ሰሙ፤ በከተማዋም በር የሚወጡ ወንዶች በሙሉ ተገረዙ። 25  ሆኖም በሦስተኛው ቀን፣ ሰዎቹ ገና ቆስለው እያሉ የዲና ወንድሞች የሆኑት ሁለቱ የያዕቆብ ልጆች ማለትም ስምዖንና ሌዊ ማንም ሳይጠረጥራቸው ሰይፋቸውን ይዘው ወደ ከተማዋ በመግባት ወንዶቹን ሁሉ ገደሉ። 26  ኤሞርንና ልጁን ሴኬምን በሰይፍ ገደሏቸው፤ ከዚያም ዲናን ከሴኬም ቤት ይዘው ሄዱ። 27  ሌሎቹ የያዕቆብ ወንዶች ልጆችም በሬሳ ላይ እየተረማመዱ ከተማዋን ዘረፉ፤ ይህን ያደረጉትም እህታቸው ስለተነወረች ነው። 28  እነሱም መንጎቻቸውን፣ ከብቶቻቸውን፣ አህዮቻቸውን እንዲሁም በከተማዋ ውስጥና በመስክ ያገኙትን ሁሉ ወሰዱ። 29  በተጨማሪም ንብረቶቻቸውን በሙሉ ወሰዱ፤ እንዲሁም ትናንሽ ልጆቻቸውንና ሚስቶቻቸውን ማረኩ፤ በየቤቱ ያገኙትን ሁሉ ዘረፉ። 30  በዚህ ጊዜ ያዕቆብ፣ ስምዖንንና ሌዊን እንዲህ አላቸው፦ “በዚህች አገር በሚኖሩት በከነአናውያንና በፈሪዛውያን ዘንድ እንደ ጥምብ እንድቆጠር በማድረግ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ከተታችሁኝ። እኔ እንግዲህ በቁጥር አነስተኛ ነኝ፤ እነሱም በእኔ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ግንባር ፈጥረው መምጣታቸው አይቀርም፤ በዚህም የተነሳ እኔም ሆንኩ ቤቴ እንጠፋለን።” 31  እነሱ ግን “ታዲያ ማንም እህታችንን እንደ ዝሙት አዳሪ ቆጥሮ እንዲህ ያለ ድርጊት ይፈጽምባት?” አሉ።
[]
[]
[]
[]
12,532
35  ከዚያ በኋላ አምላክ ያዕቆብን እንዲህ አለው፦ “ተነስተህ ወደ ቤቴል ውጣ፤ በዚያም ኑር፤ ከወንድምህ ከኤሳው እየሸሸህ ሳለህ ለተገለጠልህ ለእውነተኛው አምላክ በዚያ መሠዊያ ሥራ።” 2  ከዚያም ያዕቆብ ቤተሰቡንና አብረውት የነበሩትን ሰዎች ሁሉ እንዲህ አላቸው፦ “በመካከላችሁ ያሉትን ባዕዳን አማልክት አስወግዱ፤ ራሳችሁን አንጹ፤ ልብሳችሁንም ቀይሩ፤ 3  ተነስተንም ወደ ቤቴል እንውጣ። በዚያም በጭንቀቴ ጊዜ ለሰማኝና በሄድኩበት ሁሉ ከእኔ ላልተለየው ለእውነተኛው አምላክ መሠዊያ እሠራለሁ።” 4  በመሆኑም ባዕዳን አማልክታቸውን በሙሉ እንዲሁም በጆሯቸው ላይ ያደረጓቸውን ጉትቻዎች ለያዕቆብ ሰጡት፤ ያዕቆብም በሴኬም አቅራቢያ ባለው ትልቅ ዛፍ ሥር ቀበራቸው። 5  በሚጓዙበት ጊዜም አምላክ በዙሪያቸው ባሉት ከተሞች ላይ ሽብር ይለቅባቸው ስለነበር የያዕቆብን ልጆች አላሳደዷቸውም። 6  በመጨረሻም ያዕቆብና አብረውት ያሉት ሰዎች በሙሉ በከነአን ምድር ወደምትገኘው ወደ ሎዛ ማለትም ወደ ቤቴል መጡ። 7  እሱም በዚያ መሠዊያ ሠራ፤ የቦታውንም ስም ኤልቤቴል አለው፤ ምክንያቱም ከወንድሙ በሸሸበት ጊዜ እውነተኛው አምላክ በዚያ ራሱን ገልጦለት ነበር። 8  በኋላም የርብቃ ሞግዚት ዲቦራ ሞተች፤ በቤቴል አቅራቢያ በሚገኝ የባሉጥ ዛፍ ሥርም ተቀበረች። በመሆኑም ስሙን አሎንባኩት አለው። 9  ያዕቆብ ከጳዳንአራም እየተመለሰ ሳለ አምላክ ዳግመኛ ተገለጠለትና ባረከው። 10  አምላክም “ስምህ ያዕቆብ ነው። ከእንግዲህ ያዕቆብ ተብለህ አትጠራም፤ ከዚህ ይልቅ ስምህ እስራኤል ይባላል” አለው። ስለዚህ እስራኤል ብሎ ጠራው። 11  በተጨማሪም አምላክ እንዲህ አለው፦ “እኔ ሁሉን ቻይ አምላክ ነኝ። ብዛ፣ ተባዛ። ብሔራትና ብዙ ብሔራትን ያቀፈ ጉባኤ ከአንተ ይገኛሉ፤ ነገሥታትም ከአንተ ይወጣሉ። 12  ለአብርሃምና ለይስሐቅ የሰጠኋትን ምድር ለአንተ እሰጥሃለሁ፤ ከአንተ በኋላ ለሚመጡት ዘሮችህም ይህችን ምድር እሰጣለሁ።” 13  ከዚያም አምላክ ከእሱ ጋር ሲነጋገርበት ከነበረው ስፍራ ወደ ላይ ወጣ። 14  ስለዚህ ያዕቆብ ከአምላክ ጋር ሲነጋገር በነበረበት ስፍራ ላይ የድንጋይ ዓምድ አቆመ፤ ባቆመውም ዓምድ ላይ የመጠጥ መባና ዘይት አፈሰሰበት። 15  ያዕቆብም ከአምላክ ጋር የተነጋገረበትን ስፍራ ቤቴል በሚለው በዚያው ስም ጠራው። 16  ከዚያም ከቤቴል ተነስተው ሄዱ። ኤፍራታ ለመድረስ የተወሰነ ርቀት ሲቀራቸው ራሔል ምጥ ያዛት፤ ምጡም እጅግ ጠናባት። 17  ምጡ እጅግ አስጨንቋት ሳለም አዋላጇ “አይዞሽ አትፍሪ፤ ሌላ ወንድ ልጅ ልትገላገዪ ነው” አለቻት። 18  እሷ ግን ሕይወቷ ሊያልፍ በማጣጣር ላይ ሳለች (ሞት አፋፍ ላይ ስለነበረች) የልጁን ስም ቤንኦኒ አለችው፤ አባቱ ግን ስሙን ቢንያም አለው። 19  ራሔልም ሞተች፤ ወደ ኤፍራታ ይኸውም ወደ ቤተልሔም በሚወስደው መንገድ ላይ ተቀበረች። 20  ያዕቆብም በመቃብሯ ላይ ዓምድ አቆመ፤ ይህ የራሔል መቃብር ዓምድ እስከ ዛሬ ድረስ አለ። 21  ከዚያ በኋላ እስራኤል ከዚያ ተነስቶ በመሄድ ከኤዴር ማማ አለፍ ብሎ ድንኳኑን ተከለ። 22  አንድ ቀን፣ እስራኤል በዚያ ምድር ሰፍሮ ሳለ ሮቤል ከአባቱ ቁባት ከባላ ጋር ተኛ፤ እስራኤልም ይህን ሰማ። ያዕቆብ 12 ወንዶች ልጆች ነበሩት። 23  ከሊያ የወለዳቸው ወንዶች ልጆቹ የበኩር ልጁ ሮቤል ከዚያም ስምዖን፣ ሌዊ፣ ይሁዳ፣ ይሳኮር እና ዛብሎን ነበሩ። 24  ከራሔል የወለዳቸው ወንዶች ልጆቹ ዮሴፍና ቢንያም ነበሩ። 25  ከራሔል አገልጋይ ከባላ የወለዳቸው ወንዶች ልጆቹ ዳንና ንፍታሌም ነበሩ። 26  ከሊያ አገልጋይ ከዚልጳ የወለዳቸው ወንዶች ልጆቹ ደግሞ ጋድና አሴር ነበሩ። እነዚህ ያዕቆብ በጳዳንአራም ሳለ የወለዳቸው ወንዶች ልጆቹ ናቸው። 27  ከጊዜ በኋላ ያዕቆብ አባቱ ይስሐቅ ወደነበረበት፣ አብርሃምና ይስሐቅ የባዕድ አገር ሰው ሆነው ወደኖሩበት በቂርያትአርባ ይኸውም በኬብሮን አካባቢ ወደሚገኘው ወደ ማምሬ መጣ። 28  ይስሐቅ 180 ዓመት ኖረ። 29  ከዚያም ይስሐቅ የመጨረሻ እስትንፋሱን ተነፈሰ፤ ዕድሜ ጠግቦና በሕይወቱ ረክቶ ሞተ፤ ወደ ወገኖቹም ተሰበሰበ፤ ልጆቹ ኤሳውና ያዕቆብም ቀበሩት።
[]
[]
[]
[]
12,533
36  የኤሳው ማለትም የኤዶም ታሪክ ይህ ነው። 2  ኤሳው ከከነአን ሴቶች ልጆች ሚስቶችን አገባ፤ እነሱም የሂታዊው የኤሎን ልጅ አዳ እንዲሁም የአና ልጅና የሂዋዊው የጺብኦን የልጅ ልጅ የሆነችው ኦሆሊባማ ናቸው፤ 3  በተጨማሪም የእስማኤል ልጅ የሆነችውን የነባዮትን እህት ባሴማትን አገባ። 4  አዳ ለኤሳው ኤሊፋዝን ወለደችለት፤ ባሴማት ደግሞ ረኡዔልን ወለደች፤ 5  ኦሆሊባማ የኡሽን፣ ያላምን እና ቆሬን ወለደች። እነዚህ ኤሳው በከነአን ምድር ሳለ የተወለዱለት ልጆች ናቸው። 6  ከዚያም ኤሳው ሚስቶቹን፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቹን፣ የቤተሰቡን አባላት ሁሉ፣ መንጋውን፣ ሌሎቹን እንስሳት ሁሉና በከነአን ምድር ያፈራውን ሀብት ሁሉ ይዞ ከወንድሙ ከያዕቆብ ርቆ ወደ ሌላ ምድር ሄደ። 7  ምክንያቱም ንብረታቸው በጣም ስለበዛ አብረው መኖር አልቻሉም፤ እንዲሁም ከመንጋቸው ብዛት የተነሳ ይኖሩበት የነበረው ምድር ሊበቃቸው አልቻለም። 8  በመሆኑም ኤሳው በሴይር ተራራማ አካባቢ መኖር ጀመረ። ኤሳው ኤዶም ተብሎም ይጠራል። 9  በሴይር ተራራማ አካባቢ የሚኖረው የኤዶማውያን አባት የኤሳው ታሪክ ይህ ነው። 10  የኤሳው ወንዶች ልጆች ስም የሚከተለው ነው፦ የኤሳው ሚስት የአዳ ልጅ ኤሊፋዝና የኤሳው ሚስት የባሴማት ልጅ ረኡዔል ናቸው። 11  የኤሊፋዝ ወንዶች ልጆች ደግሞ ቴማን፣ ኦማር፣ ጸፎ፣ ጋታም እና ቀናዝ ናቸው። 12  ቲምና የኤሳው ልጅ የኤሊፋዝ ቁባት ሆነች። ከጊዜ በኋላም ለኤሊፋዝ አማሌቅን ወለደችለት። የኤሳው ሚስት የአዳ ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው። 13  የረኡዔል ወንዶች ልጆች ናሃት፣ ዛራ፣ ሻማህ እና ሚዛህ ናቸው። እነዚህም የኤሳው ሚስት የባሴማት ልጆች ነበሩ። 14  የአና ልጅና የጺብኦን የልጅ ልጅ የሆነችው የኤሳው ሚስት ኦሆሊባማ ለኤሳው የወለደቻቸው ወንዶች ልጆች የኡሽ፣ ያላም እና ቆሬ ናቸው። 15  የነገድ አለቆች የሆኑት የኤሳው ወንዶች ልጆች የሚከተሉት ናቸው፦ የኤሳው የበኩር ልጅ የኤሊፋዝ ወንዶች ልጆችም አለቃ ቴማን፣ አለቃ ኦማር፣ አለቃ ጸፎ፣ አለቃ ቀናዝ፣ 16  አለቃ ቆሬ፣ አለቃ ጋታም እና አለቃ አማሌቅ ናቸው። እነዚህ በኤዶም ምድር የነገድ አለቆች የሆኑት የኤሊፋዝ ልጆች ነበሩ። እነዚህ የአዳ ወንዶች ልጆች ናቸው። 17  የኤሳው ልጅ የረኡዔል ወንዶች ልጆች፣ አለቃ ናሃት፣ አለቃ ዛራ፣ አለቃ ሻማህ እና አለቃ ሚዛህ ናቸው። እነዚህ በኤዶም ምድር የነገድ አለቆች የሆኑት የረኡዔል ልጆች ናቸው። እነዚህ የኤሳው ሚስት የባሴማት ወንዶች ልጆች ናቸው። 18  በመጨረሻም የኤሳው ሚስት የኦሆሊባማ ወንዶች ልጆች፣ አለቃ የኡሽ፣ አለቃ ያላም እና አለቃ ቆሬ ናቸው። እነዚህ የነገድ አለቆች የአና ልጅ የሆነችው የኤሳው ሚስት የኦሆሊባማ ልጆች ናቸው። 19  የኤሳው ማለትም የኤዶም ወንዶች ልጆችና አለቆቻቸው እነዚህ ናቸው። 20  በዚያ ምድር የሚኖሩት የሆራዊው የሴይር ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው፦ ሎጣን፣ ሾባል፣ ጺብኦን፣ አና፣ 21  ዲሾን፣ ኤጼር እና ዲሻን። እነዚህ በኤዶም ምድር የሆራውያን የነገድ አለቆች የሆኑት የሴይር ወንዶች ልጆች ናቸው። 22  የሎጣን ወንዶች ልጆች ሆሪ እና ሄማም ናቸው፤ የሎጣን እህት ቲምና ትባላለች። 23  የሾባል ወንዶች ልጆች አልዋን፣ ማናሃት፣ ኤባል፣ ሼፎ እና ኦናም ናቸው። 24  የጺብኦን ወንዶች ልጆች አያ እና አና ናቸው። ይህ አና የአባቱን የጺብኦንን አህዮች ሲጠብቅ በምድረ በዳ የፍል ውኃ ምንጮችን ያገኘው ነው። 25  የአና ልጆች ዲሾን እና የአና ሴት ልጅ ኦሆሊባማ ናቸው። 26  የዲሾን ወንዶች ልጆች ሄምዳን፣ ኤሽባን፣ ይትራን እና ኬራን ናቸው። 27  የኤጼር ወንዶች ልጆች ቢልሃን፣ ዛአዋን እና አቃን ናቸው። 28  የዲሻን ወንዶች ልጆች ዑጽ እና አራን ናቸው። 29  የሆራውያን የነገድ አለቆች እነዚህ ናቸው፦ አለቃ ሎጣን፣ አለቃ ሾባል፣ አለቃ ጺብኦን፣ አለቃ አና፣ 30  አለቃ ዲሾን፣ አለቃ ኤጼር እና አለቃ ዲሻን። በሴይር ምድር የሆራውያን የነገድ አለቆች በየአለቆቻቸው ሲዘረዘሩ እነዚህ ናቸው። 31  እነዚህ በእስራኤላውያን ላይ የትኛውም ንጉሥ መግዛት ከመጀመሩ በፊት በኤዶም ምድር ይገዙ የነበሩ ነገሥታት ናቸው። 32  የቢዖር ልጅ ቤላ በኤዶም ይገዛ ነበር፤ የከተማውም ስም ዲንሃባ ይባል ነበር። 33  ቤላ ሲሞት የቦስራው የዛራ ልጅ ዮባብ በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ። 34  ዮባብ ሲሞት ከቴማናውያን ምድር የመጣው ሁሻም በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ። 35  ሁሻም ሲሞት ምድያማውያንን በሞዓብ ክልል ድል ያደረጋቸው የቤዳድ ልጅ ሃዳድ በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ፤ የከተማውም ስም አዊት ይባል ነበር። 36  ሃዳድ ሲሞት የማስረቃው ሳምላ በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ። 37  ሳምላ ሲሞት በወንዙ አጠገብ ያለው የረሆቦቱ ሻኡል በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ። 38  ሻኡል ሲሞት የአክቦር ልጅ ባአልሀናን በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ። 39  የአክቦር ልጅ ባአልሀናን ሲሞት ሃዳር በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ። የከተማው ስም ጳኡ ነበር፤ የሚስቱም ስም መሄጣቤል ሲሆን እሷም የመዛሃብ ሴት ልጅ የማጥሬድ ልጅ ናት። 40  እንግዲህ የኤሳው ልጆች የሆኑ የነገድ አለቆች በየቤተሰባቸው፣ በየስፍራቸውና በየስማቸው ሲዘረዘሩ ስማቸው ይህ ነው፦ አለቃ ቲምና፣ አለቃ አልዋህ፣ አለቃ የቴት፣ 41  አለቃ ኦሆሊባማ፣ አለቃ ኤላህ፣ አለቃ ፒኖን፣ 42  አለቃ ቀናዝ፣ አለቃ ቴማን፣ አለቃ ሚብጻር፣ 43  አለቃ ማግዲኤል እና አለቃ ኢራም። ከኤዶም የተገኙት የነገድ አለቆች ርስት አድርገው በያዙት ምድር እንደየመኖሪያቸው ሲዘረዘሩ እነዚህ ናቸው። የኤዶማውያን አባት ኤሳው ይህ ነው።
[]
[]
[]
[]
12,534
37  ያዕቆብ አባቱ የባዕድ አገር ሰው ሆኖ ይኖርበት በነበረው በከነአን ምድር ኖረ። 2  የያዕቆብ ታሪክ ይህ ነው። ዮሴፍ የ17 ዓመት ወጣት ሳለ ከአባቱ ሚስቶች ከባላና ከዚልጳ ወንዶች ልጆች ጋር በጎች ይጠብቅ ነበር። እሱም ስለ ወንድሞቹ መጥፎ ድርጊት የሚገልጽ ወሬ ለአባታቸው ይዞለት መጣ። 3  እስራኤል ዮሴፍን የወለደው በስተርጅናው ስለነበር ከሌሎቹ ወንዶች ልጆቹ ሁሉ ይበልጥ ይወደው ነበር፤ ለእሱም ልዩ የሆነ ቀሚስ አሠራለት። 4  ወንድሞቹም አባታቸው ከእነሱ አስበልጦ እንደሚወደው ሲያዩ ይጠሉት ጀመር፤ በሰላምም ሊያናግሩት አልቻሉም። 5  በኋላም ዮሴፍ ሕልም አለመ፤ ሕልሙንም ለወንድሞቹ ነገራቸው፤ እነሱም እሱን የሚጠሉበት ተጨማሪ ምክንያት አገኙ። 6  እሱም እንዲህ አላቸው፦ “እባካችሁ ያየሁትን ሕልም ልንገራችሁ፣ ስሙኝ። 7  በእርሻ መካከል ነዶ እያሰርን ነበር፤ ከዚያም የእኔ ነዶ ተነስታ ቀጥ ብላ ስትቆም የእናንተ ነዶዎች ደግሞ የእኔን ነዶ ከበው ሰገዱላት።” 8  ወንድሞቹም “በእኛ ላይ ንጉሥ ልትሆንና ልትገዛን ታስባለህ ማለት ነው?” አሉት። በመሆኑም ያየው ሕልምና የተናገረው ነገር እሱን ይበልጥ እንዲጠሉት አደረጋቸው። 9  ከዚያም ሌላ ሕልም አለመ፤ ሕልሙንም ለወንድሞቹ እንዲህ ሲል ነገራቸው፦ “ሌላም ሕልም አለምኩ። አሁን ደግሞ ፀሐይ፣ ጨረቃና 11 ከዋክብት ሲሰግዱልኝ አየሁ።” 10  ሕልሙንም ለአባቱና ለወንድሞቹ ነገራቸው፤ አባቱም ገሠጸው፤ እንዲህም አለው፦ “ይህ ያለምከው ሕልም ፍቺ ምንድን ነው? እኔም ሆንኩ እናትህና ወንድሞችህ መጥተን መሬት ላይ ተደፍተን እንድንሰግድልህ ታስባለህ?” 11  ወንድሞቹም ይበልጥ ቀኑበት፤ አባቱ ግን ነገሩን በልቡ ያዘው። 12  ወንድሞቹ የአባታቸውን መንጋ ለማሰማራት ሴኬም አቅራቢያ ወደሚገኝ ቦታ ሄደው ነበር። 13  በኋላም እስራኤል ዮሴፍን “ወንድሞችህ በሴኬም አቅራቢያ መንጎቹን እየጠበቁ እንዳሉ አውቀሃል አይደል? በል ና፣ ወደ እነሱ ልላክህ” አለው። እሱም “እሺ፣ እሄዳለሁ!” አለ። 14  በመሆኑም “እባክህ ሂድና ወንድሞችህ ደህና መሆናቸውን እይ። መንጋውም ደህና መሆኑን እይና መጥተህ ትነግረኛለህ” አለው። በዚህም መሠረት ከኬብሮን ሸለቆ ወደዚያ ላከው፤ ዮሴፍም ወደ ሴኬም ሄደ። 15  በኋላም ዮሴፍ በሜዳ ላይ ሲባዝን አንድ ሰው አገኘው። ሰውየውም “ምን ፈልገህ ነው?” ሲል ጠየቀው። 16  እሱም “ወንድሞቼን እየፈለግኩ ነው። መንጎቹን እየጠበቁ ያሉት የት እንደሆነ እባክህ ንገረኝ” አለው። 17  ሰውየውም “ከዚህ ሄደዋል፤ ምክንያቱም ‘ወደ ዶታን እንሂድ’ ሲባባሉ ሰምቻቸዋለሁ” አለው። ስለዚህ ዮሴፍ ወንድሞቹን ፍለጋ ሄደ፤ ዶታን ላይም አገኛቸው። 18  እነሱም ከሩቅ ሲመጣ ተመለከቱት፤ አጠገባቸውም ከመድረሱ በፊት እሱን እንዴት እንደሚገድሉት ይመካከሩ ጀመር። 19  እነሱም እንዲህ ተባባሉ፦ “ያውና! ያ ሕልም አላሚ መጣ። 20  ኑ፣ እንግደለውና ከውኃ ጉድጓዶቹ በአንዱ ውስጥ እንጣለው፤ ከዚያም ኃይለኛ አውሬ በልቶታል እንላለን። እስቲ የሕልሞቹን መጨረሻ እናያለን።” 21  ሮቤል ይህን ሲሰማ ከእነሱ ሊያስጥለው አሰበ፤ በመሆኑም “ሕይወቱን እንኳ አናጥፋ” አለ። 22  ከዚያም እንዲህ አላቸው፦ “ደም አታፍስሱ። በምድረ በዳ በሚገኘው በዚህ የውኃ ጉድጓድ ውስጥ ጣሉት እንጂ ጉዳት አታድርሱበት።” ይህን ያላቸው ከእነሱ ሊያስጥለውና ወደ አባቱ ሊመልሰው አስቦ ነበር። 23  ዮሴፍ ወደ ወንድሞቹ እንደደረሰም የለበሰውን ያን ልዩ ቀሚስ ገፈፉት፤ 24  ወስደውም የውኃ ጉድጓዱ ውስጥ ጣሉት። ጉድጓዱም ባዶ ነበር፤ ውኃም አልነበረበትም። 25  ከዚያም ሊበሉ ተቀመጡ። ቀና ብለው ሲመለከቱም እስማኤላውያን ነጋዴዎች ግመሎቻቸውን አግተልትለው ከጊልያድ ሲመጡ አዩ። እነሱም በግመሎቻቸው ላይ ጥሩ መዓዛ ያለው ሙጫ፣ በለሳንና ከርቤ ጭነው ወደ ግብፅ እየወረዱ ነበር። 26  በዚህ ጊዜ ይሁዳ ወንድሞቹን እንዲህ አላቸው፦ “ወንድማችንን ብንገድለውና ደሙን ብንሸሽግ ምን እንጠቀማለን? 27  ኑ፣ ለእስማኤላውያን እንሽጠው፤ እጃችንን አንሰንዝርበት። ደግሞም እኮ እሱ ወንድማችን፣ የገዛ ሥጋችን ነው።” እነሱም በወንድማቸው ሐሳብ ተስማሙ። 28  ምድያማውያን ነጋዴዎች በአጠገባቸው ሲያልፉም ዮሴፍን ከውኃ ጉድጓዱ አውጥተው በ20 የብር ሰቅል ለእስማኤላውያን ሸጡት። እነሱም ዮሴፍን ወደ ግብፅ ወሰዱት። 29  በኋላም ሮቤል ወደ ውኃ ጉድጓዱ ተመልሶ ዮሴፍ በዚያ አለመኖሩን ሲመለከት ልብሱን ቀደደ። 30  ወደ ወንድሞቹም ተመልሶ “ልጁ የለም! እንግዲህ ምንድን ነው የማደርገው?” አላቸው። 31  ስለዚህ የዮሴፍን ቀሚስ ወሰዱ፤ አንድ ፍየል ካረዱ በኋላም ቀሚሱን ደሙ ውስጥ ነከሩት። 32  ከዚያም ያን ልዩ ቀሚስ እንዲህ ከሚል መልእክት ጋር ወደ አባታቸው ላኩት፦ “ይህን አገኘን፤ እባክህ ይህ የልጅህ ቀሚስ መሆን አለመሆኑን እስቲ እየው።” 33  እሱም ልብሱን አገላብጦ ካየው በኋላ “ይሄማ የልጄ ቀሚስ ነው! ኃይለኛ አውሬ በልቶት መሆን አለበት! በቃ ዮሴፍን አውሬ ቦጫጭቆታል ማለት ነው!” አለ። 34  ከዚያም ያዕቆብ ልብሱን ቀደደ፤ በወገቡም ላይ ማቅ ታጥቆ ለብዙ ቀናት ለልጁ አለቀሰ። 35  ወንዶችና ሴቶች ልጆቹ ሁሉ ሊያጽናኑት ሞከሩ፤ እሱ ግን ፈጽሞ ሊጽናና አልቻለም፤ “በልጄ ሐዘን እንደተቆራመድኩ ወደ መቃብር እወርዳለሁ!” ይል ነበር። አባቱም ለልጁ ማልቀሱን አላቋረጠም። 36  በዚህ ጊዜ ምድያማውያን ዮሴፍን ግብፅ ውስጥ ጶጢፋር ለተባለ ሰው ሸጡት፤ ይህ ሰው የፈርዖን የቤተ መንግሥት ባለሥልጣንና የዘቦች አለቃ ነበር።
[]
[]
[]
[]
12,535
38  በዚሁ ጊዜ አካባቢ ይሁዳ ከወንድሞቹ ተለይቶ በመውረድ ሂራ በሚባል አዱላማዊ ሰው አቅራቢያ ድንኳኑን ተከለ። 2  በዚያም ሹአ የሚባል የአንድ ከነአናዊ ሰው ሴት ልጅ አየ። እሷንም አገባትና ከእሷ ጋር ግንኙነት ፈጸመ፤ 3  እሷም ፀነሰች። ወንድ ልጅም ወለደች፤ ስሙንም ኤር አለው። 4  ዳግመኛም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች፤ ስሙንም ኦናን አለችው። 5  በድጋሚም ሌላ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሴሎም አለችው። እሱም ልጅ በወለደችለት ጊዜ አክዚብ በሚባል ቦታ ነበር። 6  ከጊዜ በኋላ ይሁዳ ለበኩር ልጁ ለኤር ሚስት አመጣለት፤ ስሟም ትዕማር ይባል ነበር። 7  ይሁንና የይሁዳ የበኩር ልጅ ኤር ይሖዋ ያዘነበት ሰው ነበር፤ በመሆኑም ይሖዋ በሞት ቀሰፈው። 8  በዚህ የተነሳ ይሁዳ ኦናንን “ከወንድምህ ሚስት ጋር ግንኙነት በመፈጸም የዋርሳነት ግዴታህን ተወጣ፤ ለወንድምህም ዘር ተካለት” አለው። 9  ኦናን ግን የሚወለደው ልጅ የእሱ ልጅ እንደሆነ ተደርጎ እንደማይቆጠር ያውቅ ነበር። በመሆኑም ለወንድሙ ዘር ላለመተካት ሲል ከወንድሙ ሚስት ጋር ግንኙነት በሚፈጽምበት ጊዜ ዘሩን መሬት ላይ ያፈስ ነበር። 10  እሱም ያደረገው ነገር በይሖዋ ፊት መጥፎ ስለነበር አምላክ በሞት ቀሰፈው። 11  ይሁዳ ምራቱን ትዕማርን “ልጄ ሴሎም እስኪያድግ ድረስ በአባትሽ ቤት መበለት ሆነሽ ተቀመጪ” አላት፤ ይህን ያላት ‘እሱም እንደ ወንድሞቹ ሊሞትብኝ ይችላል’ ብሎ ስላሰበ ነው። ስለዚህ ትዕማር ሄዳ በአባቷ ቤት መኖር ጀመረች። 12  የተወሰነ ጊዜ ካለፈ በኋላም የሹአ ልጅ የሆነችው የይሁዳ ሚስት ሞተች። ይሁዳም ሐዘን ተቀምጦ ተነሳ፤ ከዚያም ከአዱላማዊው ወዳጁ ከሂራ ጋር በመሆን በጎቹን የሚሸልቱለት ሰዎች ወዳሉበት ወደ ቲምና ሄደ። 13  ትዕማርም “አማትሽ በጎቹን ለመሸለት ወደ ቲምና እየወጣ ነው” ተብሎ ተነገራት። 14  በዚህ ጊዜ የመበለትነት ልብሷን በማውለቅ የአንገት ልብስ ተከናንባና ፊቷን ተሸፍና ወደ ቲምና በሚወስደው መንገድ ላይ በምትገኘው በኤናይም መግቢያ ላይ ተቀመጠች፤ ይህን ያደረገችው ሴሎም ቢያድግም ለእሱ እንዳልተዳረች ስላየች ነው። 15  ይሁዳም ባያት ጊዜ ዝሙት አዳሪ መሰለችው፤ ምክንያቱም ፊቷን ሸፍና ነበር። 16  ስለሆነም ከመንገዱ ወጣ በማለት ወደ እሷ ጠጋ ብሎ “እባክሽ አብሬሽ እንድተኛ ፍቀጂልኝ” አላት፤ ይህን ያደረገውም ምራቱ መሆኗን ስላላወቀ ነው። ሆኖም እሷ “አብሬህ ብተኛ ምን ትሰጠኛለህ?” አለችው። 17  እሱም “ከመንጋዬ መካከል አንድ የፍየል ጠቦት እልክልሻለሁ” አላት። እሷ ግን “ጠቦቱን እስክትልክልኝ ድረስ መያዣ ትሰጠኛለህ?” አለችው። 18  እሱም “ምን መያዣ ልስጥሽ?” አላት። እሷም “የማኅተም ቀለበትህን ከነማንጠልጠያ ክሩ እንዲሁም በእጅህ የያዝከውን በትርህን ስጠኝ” አለችው። ከዚያም እነዚህን ነገሮች ሰጣት፤ ከእሷም ጋር ተኛ፤ ከእሱም ፀነሰች። 19  ከዚያ በኋላ ተነስታ ሄደች፤ የአንገት ልብሷንም አውልቃ የመበለትነት ልብሷን ለበሰች። 20  ይሁዳም መያዣውን ከሴቲቱ እጅ ለማስመለስ አዱላማዊ ወዳጁን የፍየል ጠቦት አስይዞ ወደ እሷ ላከው፤ እሱ ግን ፈጽሞ ሊያገኛት አልቻለም። 21  እሱም የአካባቢውን ሰዎች “ያቺ መንገድ ዳር የምትቀመጠው በኤናይም ያለች የቤተ መቅደስ ዝሙት አዳሪ የት አለች?” በማለት ጠየቀ። እነሱ ግን “ኧረ በዚህ አካባቢ የቤተ መቅደስ ዝሙት አዳሪ ታይታ አትታወቅም” አሉት። 22  በመጨረሻም ወደ ይሁዳ ተመልሶ እንዲህ አለው፦ “ሴቲቱን በፍጹም ላገኛት አልቻልኩም፤ ደግሞም የአካባቢው ሰዎች ‘በዚህ አካባቢ የቤተ መቅደስ ዝሙት አዳሪ ታይታ አትታወቅም’ አሉኝ።” 23  በመሆኑም ይሁዳ “በኋላ እኛ መሳለቂያ እንዳንሆን መያዣውን ትውሰደው። እኔ እንደሆነ ይህን ጠቦት ልኬላት ነበር፤ አንተ ግን ፈጽሞ ልታገኛት አልቻልክም” አለው። 24  ይሁን እንጂ ከሦስት ወር በኋላ ለይሁዳ “ምራትህ ትዕማር ዝሙት አዳሪ ሆናለች፤ ዝሙት በመፈጸሟም ፀንሳለች” ተብሎ ተነገረው። በዚህ ጊዜ ይሁዳ “አውጧትና በእሳት ትቃጠል” አለ። 25  እሷም ይዘዋት እየሄዱ ሳሉ ለአማቷ “የፀነስኩት የእነዚህ ዕቃዎች ባለቤት ከሆነ ሰው ነው” የሚል መልእክት ላከችበት። በተጨማሪም “ይህ የማኅተም ቀለበትና ማንጠልጠያ ክሩ እንዲሁም ይህ በትር የማን እንደሆነ እስቲ አጣራ” አለችው። 26  ይሁዳም ዕቃዎቹን ከተመለከተ በኋላ “እሷ ከእኔ ይልቅ ጻድቅ ናት፤ ምክንያቱም ለልጄ ለሴሎም ልድራት ይገባኝ ነበር” አለ። ከእሷም ጋር ዳግመኛ የፆታ ግንኙነት አልፈጸመም። 27  የመውለጃዋም ጊዜ ሲደርስ በሆዷ ውስጥ መንታ ልጆች እንዳሉ ታወቀ። 28  በምትወልድበት ጊዜም አንደኛው ልጅ እጁን አወጣ፤ አዋላጇም “መጀመሪያ የወጣው ይህ ነው” በማለት ወዲያውኑ በእጁ ላይ ቀይ ክር አሰረችለት። 29  ይሁን እንጂ ልጁ እጁን በመለሰ ጊዜ ወንድሙ ቀድሞት ወጣ፤ በመሆኑም አዋላጇ “አንተ እንዴት ጥሰህ ወጣህ?” አለች። በመሆኑም ስሙ ፋሬስ ተባለ። 30  በኋላም እጁ ላይ ቀይ ክር የታሰረለት ወንድሙ ወጣ፤ ስሙም ዛራ ተባለ።
[]
[]
[]
[]
12,536
39  ዮሴፍም ወደ ግብፅ ተወሰደ፤ የፈርዖን የቤተ መንግሥት ባለሥልጣንና የዘቦች አለቃ የሆነ ጶጢፋር የሚባል አንድ ግብፃዊ ወደዚያ ይዘውት ከወረዱት እስማኤላውያን እጅ ዮሴፍን ገዛው። 2  ሆኖም ይሖዋ ከዮሴፍ ጋር ነበር። በዚህም የተነሳ ስኬታማ ሆነ፤ በግብፃዊው ጌታው ቤትም ላይ ኃላፊ ሆኖ ተሾመ። 3  ጌታውም ይሖዋ ከዮሴፍ ጋር እንደሆነና የሚሠራውንም ነገር ሁሉ ይሖዋ እንደሚያሳካለት አየ። 4  ዮሴፍም በፊቱ ሞገስ እያገኘ ሄደ፤ የቅርብ አገልጋዩም ሆነ። በመሆኑም በቤቱ ላይ ሾመው፤ የእሱ የሆነውንም ነገር ሁሉ በኃላፊነት ሰጠው። 5  በቤቱና ባለው ነገር ሁሉ ላይ ከሾመው ጊዜ አንስቶ ይሖዋ በዮሴፍ ምክንያት የግብፃዊውን ቤት ባረከ፤ ይሖዋም በቤትና በመስክ ያለውን ነገር ሁሉ ባረከለት። 6  ከጊዜ በኋላም ያለውን ነገር ሁሉ ለዮሴፍ በኃላፊነት ሰጠው፤ እሱም ከሚመገበው ምግብ በስተቀር ስለሌላው ነገር ምንም አይጨነቅም ነበር። ደግሞም ዮሴፍ ሰውነቱ እየዳበረና መልኩ እያማረ ሄደ። 7  በኋላም የጌታው ሚስት በዮሴፍ ላይ ዓይኗን ጣለችበት፤ እሷም “ከእኔ ጋር ተኛ” ትለው ጀመር። 8  እሱ ግን ፈቃደኛ አለመሆኑን በመግለጽ የጌታውን ሚስት እንዲህ አላት፦ “ጌታዬ በዚህ ቤት በእኔ እጅ ስላለው ነገር ምንም የሚያውቀው ነገር የለም፤ ያለውንም ነገር ሁሉ በአደራ ሰጥቶኛል። 9  በዚህ ቤት ውስጥ ከእኔ የሚበልጥ ሰው የለም፤ ጌታዬ ከአንቺ በስተቀር ምንም ያልሰጠኝ ነገር የለም፤ ይህን ያደረገውም ሚስቱ ስለሆንሽ ነው። ታዲያ እንዲህ ያለውን እጅግ መጥፎ ድርጊት በመፈጸም በአምላክ ላይ እንዴት ኃጢአት እሠራለሁ?” 10  እሷም ዮሴፍን በየቀኑ ትወተውተው ነበር፤ እሱ ግን ከእሷ ጋር ለመተኛትም ሆነ አብሯት ለመሆን ፈጽሞ ፈቃደኛ አልሆነም። 11  ይሁንና አንድ ቀን ዮሴፍ ሥራውን ለማከናወን ወደ ቤት ሲገባ ከቤቱ አገልጋዮች መካከል አንዳቸውም በዚያ አልነበሩም። 12  እሷም ልብሱን አፈፍ አድርጋ ይዛ “አብረኸኝ ተኛ!” አለችው። እሱ ግን ልብሱን እጇ ላይ ጥሎ ወደ ውጭ ሸሽቶ ወጣ። 13  እሷም ልብሱን እጇ ላይ ጥሎ ወደ ውጭ እንደሸሸ ባየች ጊዜ 14  የቤቷን ሰዎች ጮኻ በመጣራት እንዲህ አለቻቸው፦ “አያችሁ! ባለቤቴ ያመጣው ይህ ዕብራዊ መሳለቂያ ሊያደርገን ነው። መጥቶ አብሬሽ ካልተኛሁ አለኝ፤ እኔ ግን ጩኸቴን አቀለጥኩት። 15  ድምፄን ከፍ አድርጌ ስጮኽ ልብሱን አጠገቤ ጥሎ ወደ ውጭ ሸሽቶ ወጣ።” 16  ከዚያም ጌታው ወደ ቤቱ እስኪመለስ ድረስ ልብሱን አጠገቧ አቆየችው። 17  ከዚያም እንዲህ ስትል ያንኑ ነገር ነገረችው፦ “ይህ ያመጣህብን ዕብራዊ አገልጋይ እኔ ወዳለሁበት ገብቶ መሳለቂያ ሊያደርገኝ ነበር። 18  ሆኖም ድምፄን ከፍ አድርጌ ስጮኽ ልብሱን አጠገቤ ጥሎ ወደ ውጭ ሸሽቶ ወጣ።” 19  ጌታውም “ይኸውልህ፣ አገልጋይህ እንዲህ አደረገኝ” ብላ ሚስቱ የነገረችውን ሲሰማ ቁጣው ነደደ። 20  በመሆኑም የዮሴፍ ጌታ ዮሴፍን ወስዶ የንጉሡ እስረኞች የታሰሩበት እስር ቤት አስገባው፤ ዮሴፍም እዚያው እስር ቤት ውስጥ ቆየ። 21  ይሁን እንጂ ይሖዋ ከዮሴፍ አልተለየም፤ እንደወትሮው ሁሉ ለእሱ ታማኝ ፍቅር ከማሳየት ወደኋላ አላለም፤ በእስር ቤቱ አለቃም ፊት ሞገስ ሰጠው። 22  በመሆኑም የእስር ቤቱ አለቃ ዮሴፍን በእስር ቤቱ ውስጥ ባሉት እስረኞች ሁሉ ላይ ኃላፊ አደረገው፤ በእስር ቤቱ ውስጥ እስረኞቹ የሚያከናውኑትን ማንኛውንም ሥራ የሚቆጣጠረው እሱ ነበር። 23  ይሖዋ ከዮሴፍ ጋር ስለነበርና የሚያደርገውን ነገር ሁሉ ይሖዋ ስለሚያሳካለት የእስር ቤቱ አለቃ በዮሴፍ ኃላፊነት ሥር ስላለው ስለ ማንኛውም ነገር ምንም አይጨነቅም ነበር።
[]
[]
[]
[]
12,537
4  አዳምም ከሚስቱ ከሔዋን ጋር የፆታ ግንኙነት ፈጸመ፤ እሷም ፀነሰች። ቃየንንም በወለደች ጊዜ “በይሖዋ እርዳታ ወንድ ልጅ አፈራሁ” አለች። 2  በኋላም ወንድሙን አቤልን ወለደች። አቤል የበግ እረኛ ሆነ፤ ቃየን ግን አራሽ ሆነ። 3  ከጊዜ በኋላም ቃየን የተወሰኑ የምድር ፍሬዎችን ለይሖዋ መባ አድርጎ አቀረበ። 4  አቤል ግን ከመንጋው በኩራት መካከል የተወሰኑትን ከነስባቸው አቀረበ። ይሖዋ አቤልንና ያቀረበውን መባ በጥሩ ፊት ሲመለከት 5  ቃየንንና ያቀረበውን መባ ግን በጥሩ ፊት አልተመለከተም። በመሆኑም ቃየን በጣም ተናደደ፤ እጅግ አዘነ። 6  ከዚያም ይሖዋ ቃየንን እንዲህ አለው፦ “ለምን ተናደድክ? ለምንስ አዘንክ? 7  መልካም ወደ ማድረግ ብታዘነብል ኖሮ ሞገስ አታገኝም ነበር? መልካም ወደ ማድረግ ካላዘነበልክ ግን ኃጢአት በደጅህ እያደባ ነው፤ ሊቆጣጠርህም ይፈልጋል፤ ታዲያ አንተ ትቆጣጠረው ይሆን?” 8  ከዚያ በኋላ ቃየን ወንድሙን አቤልን “ና ወደ ሜዳ እንሂድ” አለው። በሜዳው ላይ ሳሉም ቃየን ወንድሙን አቤልን ደብድቦ ገደለው። 9  በኋላም ይሖዋ ቃየንን “ወንድምህ አቤል የት ነው?” አለው፤ እሱም “እኔ አላውቅም። እኔ የወንድሜ ጠባቂ ነኝ?” አለ። 10  በዚህ ጊዜ እንዲህ አለው፦ “ያደረግከው ነገር ምንድን ነው? ስማ! የወንድምህ ደም ከምድር ወደ እኔ እየጮኸ ነው። 11  እንግዲህ የወንድምህን ደም ከእጅህ ለመቀበል አፏን ከከፈተችው ምድር እንድትሰደድ ተረግመሃል። 12  ምድርን በምታርስበትም ጊዜ ምርቷን አትሰጥህም። በምድር ላይ ተንከራታችና ስደተኛ ትሆናለህ።” 13  በዚህ ጊዜ ቃየን ይሖዋን እንዲህ አለው፦ “ለሠራሁት ጥፋት የምቀበለው ቅጣት ልሸከመው ከምችለው በላይ ነው። 14  ይኸው በዚህ ቀን ከምድሪቱ ልታባርረኝ ነው፤ ከፊትህም እሰወራለሁ፤ እንዲሁም በምድር ላይ ተንከራታችና ስደተኛ እሆናለሁ፤ እንግዲህ በቃ፣ ያገኘኝ ሁሉ ይገድለኛል።” 15  ስለሆነም ይሖዋ “እንግዲያው ቃየንን የሚገድል ማንኛውም ሰው ሰባት እጥፍ የበቀል ቅጣት ይቀበላል” አለው። በመሆኑም ያገኘው ማንም እንዳይገድለው ይሖዋ ለቃየን ምልክት አደረገለት። 16  ከዚያም ቃየን ከይሖዋ ፊት ርቆ ሄደ፤ ከኤደን በስተ ምሥራቅ በሚገኘው በግዞት ምድር መኖር ጀመረ። 17  ከዚህ በኋላ ቃየን ከሚስቱ ጋር የፆታ ግንኙነት ፈጸመ፤ እሷም ፀነሰች፤ ሄኖክንም ወለደች። ከዚያም ቃየን ከተማ መገንባት ጀመረ፤ ከተማዋንም በልጁ በሄኖክ ስም ሰየማት። 18  ከጊዜ በኋላም ሄኖክ ኢራድን ወለደ። ኢራድም መሁያኤልን ወለደ፤ መሁያኤልም መቱሻኤልን ወለደ፤ መቱሻኤል ደግሞ ላሜህን ወለደ። 19  ላሜህም ሁለት ሚስቶች አገባ፤ የመጀመሪያዋ ስም አዳ ሲሆን የሁለተኛዋ ስም ደግሞ ጺላ ነበር። 20  አዳ ያባልን ወለደች። ያባል በድንኳን የሚኖሩና ከብት የሚያረቡ ሰዎች አባት ነበር። 21  የወንድሙ ስም ዩባል ነበር። እሱም የበገና ደርዳሪዎችና የእምቢልታ ነፊዎች አባት ነበር። 22  ጺላ ደግሞ ቱባልቃይንን ወለደች፤ እሱም መዳብና ብረት እየቀጠቀጠ የተለያዩ መሣሪያዎችን ይሠራ ነበር። የቱባልቃይን እህት ናዕማ ትባል ነበር። 23  ከዚያም ላሜህ ለሚስቶቹ ለአዳና ለጺላ የሚከተለውን ተቀኘ፦ “እናንተ የላሜህ ሚስቶች፣ ቃሌን ስሙ፤የምላችሁንም አዳምጡ፦ አንድ ሰው ስላቆሰለኝ፣አዎ፣ አንድ ወጣት ስለመታኝ ገደልኩት። 24  ቃየንን የሚገድል 7 እጥፍ የበቀል ቅጣት የሚደርስበት ከሆነላሜህን የገደለማ 77 ጊዜ የበቀል ቅጣት ይደርስበታል።” 25  አዳም ከሚስቱ ጋር በድጋሚ የፆታ ግንኙነት ፈጸመ፤ እሷም ወንድ ልጅ ወለደች። ስሙንም “ቃየን አቤልን ስለገደለው በእሱ ፋንታ አምላክ ሌላ ዘር ተክቶልኛል” በማለት ሴት አለችው። 26  ሴት ደግሞ ወንድ ልጅ ወለደ፤ ስሙንም ሄኖስ አለው። በዚያን ዘመን ሰዎች የይሖዋን ስም መጥራት ጀመሩ።
[]
[]
[]
[]
12,538
40  ይህ ከሆነ በኋላ የግብፁ ንጉሥ የመጠጥ አሳላፊዎች አለቃና የዳቦ ጋጋሪዎች አለቃ ጌታቸውን የግብፁን ንጉሥ በደሉ። 2  በመሆኑም ፈርዖን በሁለቱ ሹማምንቱ ማለትም በመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃና በዳቦ ጋጋሪዎቹ አለቃ ላይ እጅግ ተቆጣ፤ 3  እሱም በዘቦች አለቃ ቤት በሚገኘው ወህኒ ቤት ይኸውም ዮሴፍ በታሰረበት እስር ቤት ውስጥ እንዲታሰሩ አደረገ። 4  ከዚያም የዘቦቹ አለቃ፣ ዮሴፍ ከእነሱ ጋር እንዲሆንና እንዲረዳቸው መደበው፤ እነሱም ለተወሰነ ጊዜ ወህኒ ቤት ውስጥ ቆዩ። 5  እስር ቤት ውስጥ ታስረው የነበሩት የግብፁ ንጉሥ መጠጥ አሳላፊና ዳቦ ጋጋሪ በአንድ ሌሊት ሕልም አለሙ፤ የእያንዳንዳቸውም ሕልም የተለያየ ፍቺ ነበረው። 6  በማግስቱ ጠዋት ዮሴፍ ገብቶ ሲያያቸው ተክዘው አገኛቸው። 7  በመሆኑም በጌታው ቤት ከእሱ ጋር የታሰሩትን የፈርዖንን ሹማምንት “ምነው ዛሬ ፊታችሁ በሐዘን ጠቆረ?” ሲል ጠየቃቸው። 8  እነሱም “ሁለታችንም ሕልም አልመን ነበር፤ ሕልማችንን የሚፈታልን ሰው ግን አላገኘንም” አሉት። ዮሴፍም “ሕልምን የሚፈታው አምላክ አይደለም? እስቲ ያያችሁትን ሕልም ንገሩኝ” አላቸው። 9  በመሆኑም የመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃ እንዲህ ሲል ሕልሙን ለዮሴፍ ነገረው፦ “በሕልሜ ከፊት ለፊቴ አንድ የወይን ተክል አየሁ። 10  በወይኑም ተክል ላይ ሦስት ቀንበጦች ነበሩ፤ ተክሉም በማቆጥቆጥ ላይ እያለ አበባ አወጣ፤ በዘለላዎቹም ላይ ያሉት ፍሬዎች በሰሉ። 11  እኔም የፈርዖንን ጽዋ በእጄ ይዤ ነበር፤ የወይን ፍሬዎቹንም ወስጄ በፈርዖን ጽዋ ውስጥ ጨመቅኳቸው። ከዚያም ጽዋውን ለፈርዖን በእጁ ሰጠሁት።” 12  በዚህ ጊዜ ዮሴፍ እንዲህ አለው፦ “የሕልሙ ፍቺ ይህ ነው፦ ሦስቱ ቀንበጦች ሦስት ቀናት ናቸው። 13  ከሦስት ቀን በኋላ ፈርዖን ከእስር ቤት ያስወጣሃል፤ ወደ ቀድሞ ሹመትህም ይመልስሃል። አንተም የመጠጥ አሳላፊው በነበርክበት ጊዜ ታደርግ እንደነበረው ሁሉ የፈርዖንን ጽዋ በእጁ ትሰጠዋለህ። 14  ይሁንና ሁኔታዎች ሲስተካከሉልህ እኔን እንዳትረሳኝ። እባክህ ታማኝ ፍቅር አሳየኝ፤ ከዚህ እስር ቤት እንዲያስፈታኝም ስለ እኔ ለፈርዖን ንገረው። 15  በመሠረቱ እኔ ከዕብራውያን ምድር ወደዚህ የመጣሁት ተገድጄ ነው፤ አሁንም ቢሆን እዚህ እስር ቤት ውስጥ የጣሉኝ ያለምንም ጥፋት ነው።” 16  የዳቦ ጋጋሪዎቹ አለቃም ዮሴፍ የተናገረው የሕልሙ ፍቺ መልካም መሆኑን ሲያይ እሱም እንዲህ አለው፦ “እኔም ሕልም አይቼ ነበር፤ በሕልሜም ነጭ ዳቦዎች የያዙ ሦስት ቅርጫቶች በራሴ ላይ ተሸክሜ ነበር፤ 17  ከላይ ባለው ቅርጫት ውስጥ ለፈርዖን የሚቀርቡ የተለያዩ የተጋገሩ ምግቦች ነበሩ፤ ወፎችም በራሴ ላይ ከተሸከምኩት ቅርጫት ውስጥ ይበሉ ነበር።” 18  ከዚያም ዮሴፍ እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “የሕልሙ ፍቺ ይህ ነው፦ ሦስቱ ቅርጫቶች ሦስት ቀናት ናቸው። 19  ከሦስት ቀን በኋላ ፈርዖን ከእስር ቤት ያስወጣሃል፤ ራስህንም ቆርጦ በእንጨት ላይ ይሰቅልሃል፤ ወፎችም ሥጋህን ይበላሉ።” 20  ሦስተኛው ቀን ደግሞ ፈርዖን የልደት በዓሉን የሚያከብርበት ዕለት ነበር፤ እሱም ለአገልጋዮቹ በሙሉ ግብዣ አዘጋጀ። አገልጋዮቹ ባሉበትም የመጠጥ አሳላፊዎቹን አለቃና የዳቦ ጋጋሪዎቹን አለቃ ከእስር ቤት አስወጣቸው። 21  የመጠጥ አሳላፊዎቹንም አለቃ ወደ መጠጥ አሳላፊነት ሹመቱ መለሰው፤ እሱም እንደቀድሞው ለፈርዖን ጽዋውን ይሰጠው ጀመር። 22  የዳቦ ጋጋሪዎቹን አለቃ ግን ዮሴፍ ሕልማቸውን በፈታላቸው መሠረት ሰቀለው። 23  ይሁንና የመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃ ዮሴፍን አላስታወሰውም፤ ጨርሶም ረሳው።
[]
[]
[]
[]
12,539
41  ሁለት ድፍን ዓመታት ካለፉ በኋላ ፈርዖን በሕልሙ አባይ ወንዝ ዳር ቆሞ አየ። 2  ከዚያም ቁመናቸው ያማረ ሰባት የሰቡ ላሞች ከአባይ ወንዝ ሲወጡ አየ፤ እነሱም አባይ ወንዝ ዳር ያለውን ሣር ይበሉ ነበር። 3  ከእነሱም ቀጥሎ አስቀያሚ መልክ ያላቸውና ከሲታ የሆኑ ሌሎች ሰባት ላሞች ከአባይ ወንዝ ወጡ፤ እነሱም አባይ ወንዝ ዳር ከነበሩት የሰቡ ላሞች አጠገብ ቆሙ። 4  ከዚያም አስቀያሚ መልክ ያላቸው ከሲታ የሆኑት ላሞች ያማረ ቁመና ያላቸውን የሰቡትን ሰባት ላሞች በሏቸው። በዚህ ጊዜ ፈርዖን ከእንቅልፉ ባነነ። 5  ከዚያም ፈርዖን በድጋሚ እንቅልፍ ወሰደው፤ ለሁለተኛ ጊዜም ሕልም አለመ። በሕልሙም በአንድ አገዳ ላይ የተንዠረገጉና ያማሩ ሰባት የእህል ዛላዎች ሲወጡ አየ። 6  ከእነሱም በኋላ የቀጨጩና በምሥራቅ ነፋስ የተመቱ ሰባት የእህል ዛላዎች በቀሉ። 7  የቀጨጩት የእህል ዛላዎች የተንዠረገጉትንና የፋፉትን ሰባት የእህል ዛላዎች ዋጧቸው። በዚህ ጊዜ ፈርዖን ከእንቅልፉ ባነነ፤ ሕልም እንደሆነም ተገነዘበ። 8  በነጋም ጊዜ መንፈሱ ተረበሸ። በመሆኑም በግብፅ የሚገኙ አስማተኛ ካህናትን በሙሉ እንዲሁም ጥበበኞቿን በሙሉ አስጠራ። ፈርዖንም ያያቸውን ሕልሞች ነገራቸው፤ ሆኖም ለፈርዖን ሕልሞቹን ሊፈታለት የቻለ አንድም ሰው አልነበረም። 9  በዚህ ጊዜ የመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃ ፈርዖንን እንዲህ አለው፦ “ኃጢአቴን ዛሬ ልናዘዝ። 10  ፈርዖን በአገልጋዮቹ ተቆጥቶ ነበር። በመሆኑም እኔንና የዳቦ ጋጋሪዎቹን አለቃ በዘቦቹ አለቃ ቤት በሚገኘው ወህኒ ቤት ውስጥ አስሮን ነበር። 11  ከዚያም ሁለታችንም በአንድ ሌሊት ሕልም አለምን። እኔም ሆንኩ እሱ ያለምነው ሕልም የተለያየ ፍቺ ነበረው። 12  ከእኛም ጋር የዘቦቹ አለቃ አገልጋይ የሆነ አንድ ወጣት ዕብራዊ ነበር። ያየናቸውንም ሕልሞች በነገርነው ጊዜ የእያንዳንዳችንን ሕልም ፈታልን። 13  ነገሩ ሁሉ ልክ እሱ እንደፈታልን ሆነ። እኔ ወደ ሹመቴ ተመለስኩ፤ ሌላኛው ሰው ግን ተሰቀለ።” 14  ስለሆነም ፈርዖን ዮሴፍን እንዲያመጡት ሰዎች ላከ፤ እነሱም ከእስር ቤቱ በፍጥነት ይዘውት መጡ። እሱም ተላጭቶና ልብሱን ለውጦ ወደ ፈርዖን ገባ። 15  ከዚያም ፈርዖን ዮሴፍን እንዲህ አለው፦ “ሕልም አይቼ ነበር፤ የሚፈታልኝ ሰው ግን አልተገኘም። አንተ ሕልም ሰምተህ መፍታት እንደምትችል ሰማሁ።” 16  በዚህ ጊዜ ዮሴፍ ለፈርዖን “ኧረ እኔ እዚህ ግባ የምባል ሰው አይደለሁም! ለፈርዖን መልካም የሆነውን ነገር የሚያሳውቀው አምላክ ነው” ሲል መለሰለት። 17  ፈርዖንም ለዮሴፍ እንዲህ ሲል ነገረው፦ “በሕልሜ አባይ ወንዝ ዳር ቆሜ ነበር። 18  ከዚያም ቁመናቸው ያማረ የሰቡ ሰባት ላሞች ከአባይ ወንዝ ሲወጡ አየሁ፤ እነሱም አባይ ወንዝ ዳር ያለውን ሣር ይበሉ ጀመር። 19  ከእነሱ ቀጥሎም የተጎሳቆሉ እንዲሁም አስቀያሚ ቁመና ያላቸውና ከሲታ የሆኑ ሌሎች ሰባት ላሞች ወጡ፤ በመላው የግብፅ ምድር እንደ እነሱ ያሉ አስቀያሚ ላሞች ፈጽሞ አይቼ አላውቅም። 20  ከዚያም ከሲታ የሆኑት አስቀያሚ ላሞች የመጀመሪያዎቹን ሰባት የሰቡ ላሞች በሏቸው። 21  ከበሏቸው በኋላም ግን ቁመናቸው ልክ እንደቀድሞው አስቀያሚ ስለነበር ማንም ሰው እንደበሏቸው እንኳ ሊያውቅ አይችልም ነበር። በዚህ ጊዜ ከእንቅልፌ ባነንኩ። 22  “ከዚያ በኋላ የፋፉና ያማሩ ሰባት የእህል ዛላዎች በአንድ አገዳ ላይ ሲወጡ በሕልሜ አየሁ። 23  ከእነሱም በኋላ የቀጨጩና በምሥራቅ ነፋስ የተመቱ ሰባት የጠወለጉ የእህል ዛላዎች በቀሉ። 24  ከዚያም የቀጨጩት የእህል ዛላዎች ያማሩትን ሰባት የእህል ዛላዎች ዋጧቸው። እኔም ሕልሜን አስማተኛ ለሆኑት ካህናት ነገርኳቸው፤ ሆኖም ሊያብራራልኝ የቻለ አንድም ሰው አልተገኘም።” 25  ከዚያም ዮሴፍ ፈርዖንን እንዲህ አለው፦ “ሁለቱም የፈርዖን ሕልሞች አንድ ዓይነትና ተመሳሳይ ናቸው። እውነተኛው አምላክ ወደፊት የሚያደርገውን ነገር ለፈርዖን አሳውቆታል። 26  ሰባቱ ያማሩ ላሞች ሰባት ዓመታት ናቸው። በተመሳሳይም ሰባቱ ያማሩ የእህል ዛላዎች ሰባት ዓመታት ናቸው። ሕልሞቹ አንድ ዓይነትና ተመሳሳይ ናቸው። 27  ከእነሱ በኋላ የመጡት ሰባቱ ከሲታና አስቀያሚ ላሞች ሰባት ዓመታት ናቸው፤ በምሥራቅ ነፋስ የተመቱት ሰባቱ ፍሬ አልባ የእህል ዛላዎች ረሃብ የሚከሰትባቸው ሰባት ዓመታት ይሆናሉ። 28  ቀደም ብዬ ለፈርዖን እንደተናገርኩት እውነተኛው አምላክ ወደፊት የሚያደርገውን ነገር ለፈርዖን አሳይቶታል። 29  “በመላው የግብፅ ምድር እህል እጅግ የሚትረፈረፍባቸው ሰባት ዓመታት ይመጣሉ። 30  ከዚያ በኋላ ግን ረሃብ የሚከሰትባቸው ሰባት ዓመታት ይመጣሉ። በግብፅ ምድር እህል የተትረፈረፈበት ዘመን ፈጽሞ ይረሳል፤ ረሃቡም ምድሪቱን በእጅጉ ይጎዳል። 31  ከዚያ በኋላ በሚከሰተው ረሃብ የተነሳ በምድሪቱ እህል የተትረፈረፈበት ጊዜ ፈጽሞ አይታወስም፤ ምክንያቱም ረሃቡ በጣም አስከፊ ይሆናል። 32  ሕልሙ ለፈርዖን ሁለት ጊዜ መታየቱ ነገሩ በእውነተኛው አምላክ ዘንድ የተቆረጠ መሆኑን ያሳያል፤ እውነተኛውም አምላክ ይህን በቅርቡ ይፈጽመዋል። 33  “ስለሆነም አሁን ፈርዖን ልባምና ጠቢብ የሆነ ሰው ይፈልግና በግብፅ ምድር ላይ ይሹም። 34  ፈርዖን በምድሪቱ ላይ የበላይ ተመልካቾችን በመሾም እርምጃ ይውሰድ፤ እህል በሚትረፈረፍባቸው ሰባት ዓመታትም በግብፅ ምድር ከሚገኘው ምርት አንድ አምስተኛውን ያከማች። 35  እነሱም በመጪዎቹ መልካም ዓመታት የሚገኘውን እህል በሙሉ ይሰብስቡ፤ ለምግብነት የሚሆነውንም እህል በፈርዖን ሥልጣን ሥር በየከተማው ያከማቹ፤ የተከማቸውንም እህል ይጠብቁት። 36  በግብፅ ምድር ረሃብ በሚከሰትባቸው ሰባት ዓመታት ምድሪቱ በረሃቡ እንዳትጠፋ የተከማቸው እህል ለአገሪቱ ነዋሪዎች ይሰጣል።” 37  ፈርዖንና አገልጋዮቹ በሙሉ ይህን ሐሳብ መልካም ሆኖ አገኙት። 38  በመሆኑም ፈርዖን አገልጋዮቹን “ታዲያ የአምላክ መንፈስ ያለበት እንዲህ ያለ ሌላ ሰው ሊገኝ ይችላል?” አላቸው። 39  ከዚያም ፈርዖን ዮሴፍን እንዲህ አለው፦ “አምላክ ይህን ሁሉ እንድታውቅ ስላደረገህ እንደ አንተ ያለ ልባምና ጠቢብ ሰው የለም። 40  አንተው ራስህ በቤቴ ላይ ትሾማለህ፤ ሕዝቤም ሁሉ ያላንዳች ማንገራገር ይታዘዝልሃል። እኔ ከአንተ የምበልጠው ንጉሥ በመሆኔ ብቻ ይሆናል።” 41  በመቀጠልም ፈርዖን ዮሴፍን “ይኸው በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ሾሜሃለሁ” አለው። 42  ከዚያም ፈርዖን የማኅተም ቀለበቱን ከእጁ ላይ አውልቆ በዮሴፍ እጅ ላይ አደረገለት፤ ከጥሩ የተልባ እግር የተሠራ ልብስም አለበሰው፤ በአንገቱም ላይ የወርቅ ሐብል አጠለቀለት። 43  ከዚህም በላይ ከእሱ ቀጥሎ ባለው የክብር ሠረገላው ላይ አስቀመጠው፤ ሰዎችም ከፊት ከፊቱ እየሄዱ “አቭሬክ!” እያሉ ይጮኹ ነበር። በዚህ መንገድ በመላው የግብፅ ምድር ላይ ሾመው። 44  በተጨማሪም ፈርዖን ዮሴፍን “እኔ ፈርዖን ነኝ፤ ሆኖም ያለአንተ ፈቃድ ማንም ሰው በመላው የግብፅ ምድር ላይ ምንም ነገር ማድረግ አይችልም” አለው። 45  ከዚያም ፈርዖን ለዮሴፍ ጸፍናትፓነህ የሚል ስም አወጣለት፤ የኦን ካህን የሆነውን የጶጥፌራን ልጅ አስናትንም አጋባው። ዮሴፍም መላውን የግብፅ ምድር መቃኘት ጀመረ። 46  ዮሴፍ በግብፁ ንጉሥ በፈርዖን ፊት በቆመ ጊዜ ዕድሜው 30 ዓመት ነበር። ከዚያም ዮሴፍ ከፈርዖን ፊት ወጣ፤ መላውን የግብፅ ምድርም ተዘዋውሮ ተመለከተ። 47  እህል ይትረፈረፍባቸዋል በተባሉት ሰባት ዓመታት ምድሪቱ የተትረፈረፈ ምርት ሰጠች። 48  በእነዚያ ሰባት ዓመታት በግብፅ ምድር የተገኘውንም እህል በሙሉ እየሰበሰበ በየከተሞቹ ያከማች ነበር። በእያንዳንዱ ከተማ ዙሪያ ከሚገኘው እርሻ የተሰበሰበውን እህል በየከተማው ያከማች ነበር። 49  በመጨረሻም ሰዎቹ እህሉን መስፈር አቅቷቸው መስፈራቸውን እስኪተዉ ድረስ ዮሴፍ እንደ ባሕር አሸዋ በጣም ብዙ የሆነ እህል አከማቸ። 50  ዮሴፍ የረሃቡ ዓመት ከመጀመሩ በፊት የኦን ካህን ከሆነው ከጶጥፌራ ልጅ ከአስናት ሁለት ወንዶች ልጆች ወለደ። 51  ዮሴፍም “አምላክ የደረሰብኝን ችግር ሁሉና የአባቴን ቤት በሙሉ እንድረሳ አደረገኝ” በማለት ለበኩር ልጁ ምናሴ የሚል ስም አወጣለት። 52  ሁለተኛውን ልጁን ደግሞ “መከራዬን ባየሁበት ምድር አምላክ ፍሬያማ አደረገኝ” በማለት ኤፍሬም የሚል ስም አወጣለት። 53   ከዚያም በግብፅ ምድር እህል የተትረፈረፈባቸው ሰባት ዓመታት አበቁ፤ 54  ልክ ዮሴፍ እንደተናገረውም ሰባቱ የረሃብ ዓመታት ጀመሩ። ረሃቡም በምድር ሁሉ ላይ እየሰፋ ሄደ፤ በመላው የግብፅ ምድር ግን ምግብ ነበር። 55  በመጨረሻም መላው የግብፅ ምድር በረሃቡ ተጠቃ፤ ሕዝቡም ምግብ ለማግኘት ወደ ፈርዖን ይጮኽ ጀመር። ፈርዖንም ግብፃውያንን ሁሉ “ወደ ዮሴፍ ሂዱ፤ የሚላችሁንም ሁሉ አድርጉ” ይላቸው ነበር። 56  ረሃቡም በመላው ምድር ላይ እየተስፋፋ ሄደ። ረሃቡ በግብፅ ምድር ላይ እየጸና ስለሄደ ዮሴፍ በመካከላቸው ያሉትን የእህል ጎተራዎች በሙሉ በመክፈት ለግብፃውያን እህል ይሸጥላቸው ጀመር። 57   በተጨማሪም ረሃቡ በመላው ምድር ላይ ክፉኛ ጸንቶ ስለነበር በመላው ምድር የሚኖሩ ሰዎች ከዮሴፍ እህል ለመግዛት ወደ ግብፅ ይመጡ ነበር።
[]
[]
[]
[]
12,540
42  ያዕቆብ በግብፅ እህል መኖሩን ባወቀ ጊዜ ወንዶች ልጆቹን “ለምን ዝም ብላችሁ እርስ በርስ ትተያያላችሁ?” አላቸው። 2  ከዚያም “በግብፅ እህል እንዳለ ሰምቻለሁ። በሕይወት እንድንኖር ወደዚያ ወርዳችሁ እህል ግዙልን፤ አለዚያ ማለቃችን ነው” አላቸው። 3  ስለሆነም አሥሩ የዮሴፍ ወንድሞች እህል ለመግዛት ወደ ግብፅ ወረዱ። 4  ሆኖም ያዕቆብ የዮሴፍን ወንድም ቢንያምን “ምናልባት አደጋ ሊደርስበትና ሊሞትብኝ ይችላል” ብሎ ስላሰበ ከሌሎቹ ወንድሞቹ ጋር አላከውም። 5  ረሃቡ እስከ ከነአን ምድር ድረስ ተስፋፍቶ ስለነበር የእስራኤል ወንዶች ልጆች እህል ለመግዛት ወደ ግብፅ ከሚመጡት ሰዎች ጋር አብረው መጡ። 6  በዚያን ጊዜ በምድሩ ላይ አስተዳዳሪ የነበረውና ለምድር ሕዝቦች ሁሉ እህል የሚሸጠው ዮሴፍ ነበር። በመሆኑም የዮሴፍ ወንድሞች መጥተው መሬት ላይ በመደፋት ሰገዱለት። 7  ዮሴፍም ወንድሞቹን ሲያያቸው ወዲያውኑ አወቃቸው፤ እሱ ግን ማንነቱን ከእነሱ ደበቀ። በመሆኑም “የመጣችሁት ከየት ነው?” በማለት በቁጣ ተናገራቸው፤ እነሱም “እህል ለመግዛት ከከነአን ምድር ነው የመጣነው” አሉት። 8  ዮሴፍ ወንድሞቹን ያወቃቸው ቢሆንም እነሱ ግን አላወቁትም። 9  ዮሴፍም ስለ እነሱ ያያቸው ሕልሞች ወዲያው ትዝ አሉት፤ እሱም “እናንተ ሰላዮች ናችሁ! የመጣችሁት ምድሪቱ በየት በኩል ለጥቃት እንደተጋለጠች ለማየት ነው!” አላቸው። 10  እነሱም እንዲህ አሉት፦ “ኧረ እንደዚያ አይደለም ጌታዬ፤ እኛ አገልጋዮችህ የመጣነው እህል ለመግዛት ነው። 11  ሁላችንም የአንድ ሰው ልጆች ነን። እኛ ንጹሐን ሰዎች ነን። አገልጋዮችህ ሰላዮች አይደለንም።” 12  እሱ ግን “በፍጹም አይደለም! የመጣችሁት ምድሪቱ በየት በኩል ለጥቃት እንደተጋለጠች ለማየት ነው!” አላቸው። 13  በዚህ ጊዜ እንዲህ አሉት፦ “እኛ አገልጋዮችህ 12 ወንድማማቾች ነን። በከነአን ምድር የሚኖር የአንድ ሰው ልጆች ነን፤ ትንሹ ወንድማችን አሁን ከአባታችን ጋር ነው፤ አንደኛው ግን የለም።” 14  ይሁን እንጂ ዮሴፍ እንዲህ አላቸው፦ “‘እናንተ ሰላዮች ናችሁ!’ አልኳችሁ እኮ፤ 15  እንግዲህ ሰላዮች መሆን አለመሆናችሁ በዚህ ይረጋገጣል፤ በፈርዖን ሕይወት እምላለሁ፣ ትንሹ ወንድማችሁ ወደዚህ ካልመጣ በስተቀር ከዚህች ንቅንቅ አትሉም። 16  እናንተ እዚሁ ታስራችሁ እያላችሁ ከመካከላችሁ አንዱን ላኩትና ወንድማችሁን ይዞት ይምጣ። በዚህ መንገድ የተናገራችሁት ነገር እውነት መሆን አለመሆኑ ይረጋገጣል። አለዚያ ግን በፈርዖን ሕይወት እምላለሁ፣ እናንተ ሰላዮች ናችሁ።” 17  ከዚያም ለሦስት ቀን አንድ ላይ እስር ቤት አቆያቸው። 18  በሦስተኛውም ቀን ዮሴፍ እንዲህ አላቸው፦ “እንግዲህ እኔ አምላክን ስለምፈራ እንዲህ በማድረግ ሕይወታችሁን አትርፉ። 19  እንዳላችሁት ንጹሐን ሰዎች ከሆናችሁ ከመካከላችሁ አንዱ ወንድማችሁ እዚሁ እስር ቤት ውስጥ ይቆይ፤ የቀራችሁት ግን ለተራቡት ቤተሰቦቻችሁ እህል ይዛችሁ መሄድ ትችላላችሁ። 20  የተናገራችሁት ቃል እውነት መሆኑ እንዲረጋገጥና ከሞት እንድትተርፉ ትንሹን ወንድማችሁን ወደ እኔ ይዛችሁት ኑ።” እነሱም እንደተባሉት አደረጉ። 21  ከዚያም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፦ “ይህ ሁሉ እየደረሰብን ያለው በወንድማችን ላይ በፈጸምነው ግፍ የተነሳ እንደሆነ ምንም ጥርጥር የለውም፤ ምክንያቱም ተጨንቆ እንድንራራለት ሲማጸነን እኛ ግን አልሰማነውም። ይህ ሁሉ መከራ እየደረሰብን ያለው በዚህ ምክንያት ነው።” 22  በዚህ ጊዜ ሮቤል እንዲህ አላቸው፦ “‘በዚህ ልጅ ላይ ክፉ ነገር አታድርጉ’ ብያችሁ አልነበረም? እናንተ ግን አልሰማችሁኝም። ይኸው አሁን ደሙ ከእጃችን እየተፈለገ ነው።” 23  ይሁንና ዮሴፍ ያነጋገራቸው በአስተርጓሚ ስለነበር ምን እየተባባሉ እንዳለ እንደሚሰማ አላወቁም ነበር። 24  በመሆኑም ከፊታቸው ዞር ብሎ አለቀሰ። ከዚያም ወደ እነሱ ተመልሶ በመምጣት በድጋሚ ካነጋገራቸው በኋላ ስምዖንን ከእነሱ ለይቶ በመውሰድ ዓይናቸው እያየ አሰረው። 25  በኋላም ዮሴፍ በየከረጢቶቻቸው እህል እንዲሞሉላቸው አዘዘ፤ በተጨማሪም የእያንዳንዳቸውን ገንዘብ በየከረጢቶቻቸው መልሰው እንዲያስቀምጡና ለጉዟቸው የሚሆን ስንቅ እንዲሰጧቸው ትእዛዝ አስተላለፈ። ልክ እንዳለውም ተደረገላቸው። 26  እነሱም እህላቸውን በአህዮቻቸው ላይ ጭነው ጉዞ ጀመሩ። 27  ከእነሱ መካከል አንዱ ባረፉበት ቦታ ለአህያው መኖ ለመስጠት ከረጢቱን ሲፈታ ገንዘቡን ከረጢቱ አፍ ላይ አገኘው። 28  እሱም በዚህ ጊዜ ወንድሞቹን “ኧረ ገንዘቤ ተመልሶልኛል፤ ይኸው እዚህ ከረጢቴ ውስጥ አገኘሁት!” አላቸው። እነሱም ልባቸው በፍርሃት ራደ፤ እየተንቀጠቀጡም እርስ በርሳቸው “አምላክ ያደረገብን ይህ ነገር ምንድን ነው?” ተባባሉ። 29  በከነአን ምድር ወዳለው ወደ አባታቸው ወደ ያዕቆብ በደረሱም ጊዜ ያጋጠማቸውን ሁሉ እንዲህ በማለት ነገሩት፦ 30  “የአገሩ ጌታ የሆነው ሰው በቁጣ ተናገረን፤ አገሪቱን ለመሰለል እንደሄድን አድርጎም ቆጠረን። 31  እኛ ግን እንዲህ አልነው፦ ‘እኛ ንጹሐን ሰዎች ነን። ሰላዮች አይደለንም። 32  እኛ የአንድ አባት ልጆች የሆን 12 ወንድማማቾች ነን። አንዱ የለም፤ ትንሹ ወንድማችን ደግሞ አሁን ከአባታችን ጋር በከነአን ምድር ይገኛል’፤ 33  ሆኖም የአገሩ ጌታ የሆነው ሰው እንዲህ አለን፦ ‘እንግዲህ ንጹሐን ሰዎች መሆን አለመሆናችሁን በዚህ አውቃለሁ፤ አንዱ ወንድማችሁ እዚህ እኔ ጋ እንዲቆይ አድርጉ። የቀራችሁት ግን ለተራቡት ቤተሰቦቻችሁ የሆነ ነገር ይዛችሁ ሂዱ። 34  ንጹሐን ሰዎች እንጂ ሰላዮች አለመሆናችሁንም እንዳውቅ ትንሹን ወንድማችሁን ወደ እኔ ይዛችሁት ኑ። ወንድማችሁንም መልሼ እሰጣችኋለሁ፤ እናንተም በምድሪቱ መነገድ ትችላላችሁ።’” 35  እያንዳንዳቸውም ከረጢታቸውን ሲያራግፉ ገንዘባቸውን እንደተቋጠረ በከረጢታቸው ውስጥ አገኙት። እነሱም ሆኑ አባታቸው የተቋጠረውን ገንዘብ ሲያዩ ደነገጡ። 36  አባታቸው ያዕቆብም “ለሐዘን የዳረጋችሁት እኔን ነው! ዮሴፍ የለም፤ ስምዖንም የለም፤ አሁን ደግሞ ቢንያምን ልትወስዱት ነው! ኧረ ምን ጉድ ነው የመጣብኝ!” አላቸው። 37  ሮቤል ግን አባቱን “ልጁን መልሼ ባላመጣልህ ሁለቱን ወንዶች ልጆቼን ግደላቸው። ለእኔ በኃላፊነት ስጠኝ፤ እኔ ራሴ መልሼ አስረክብሃለሁ” አለው። 38  እሱ ግን እንዲህ አለ፦ “ልጄ ከእናንተ ጋር ወደዚያ አይወርድም። ምክንያቱም ወንድሙ ሞቷል፤ አሁን የቀረው እሱ ብቻ ነው። ከእናንተ ጋር አብሮ ሲሄድ መንገድ ላይ አደጋ ቢደርስበትና ቢሞት ሽበቴን በሐዘን ወደ መቃብር ታወርዱታላችሁ።”
[]
[]
[]
[]
12,541
43  ረሃቡ በምድሪቱ ላይ በርትቶ ነበር። 2  ስለሆነም ከግብፅ ያመጡትን እህል በልተው ሲጨርሱ አባታቸው “ተመልሳችሁ ሂዱና ጥቂት እህል ግዙልን” አላቸው። 3  በዚህ ጊዜ ይሁዳ እንዲህ አለው፦ “ሰውየው ‘ወንድማችሁን ይዛችሁት ካልመጣችሁ በምንም ዓይነት ዳግመኛ ፊቴን አታዩም’ በማለት በግልጽ አስጠንቅቆናል። 4  ወንድማችንን ከእኛ ጋር የምትልከው ከሆነ ወደዚያ ወርደን እህል እንገዛልሃለን። 5  እሱን የማትልከው ከሆነ ግን ወደዚያ አንወርድም፤ ምክንያቱም ሰውየው ‘ወንድማችሁን ይዛችሁት ካልመጣችሁ በምንም ዓይነት ዳግመኛ ፊቴን አታዩም’ ብሎናል።” 6  እስራኤልም “ምነው እንዲህ ላለ ችግር ዳረጋችሁኝ? ሌላ ወንድም እንዳላችሁ ለምን ለሰውየው ነገራችሁት?” አላቸው። 7  እነሱም እንዲህ አሉት፦ “ሰውየው ‘አባታችሁ አሁንም በሕይወት አለ? ሌላስ ወንድም አላችሁ?’ በማለት በቀጥታ ስለ እኛና ስለ ዘመዶቻችን ጠየቀን፤ እኛም ለጥያቄው መልስ ሰጠነው። ታዲያ ‘ወንድማችሁን ይዛችሁ ኑ’ ይለናል ብለን እንዴት ልንጠረጥር እንችላለን?” 8  ከዚያም ይሁዳ አባቱን እስራኤልን እንዲህ በማለት ለመነው፦ “እኛም ሆን አንተ እንዲሁም ትናንሽ ልጆቻችን በረሃብ ከምናልቅ፣ በሕይወት እንድንተርፍ ልጁ ከእኔ ጋር እንዲሄድ ፍቀድና ተነስተን ወደዚያ እንሂድ። 9  የልጁን ደህንነት በተመለከተ ኃላፊነቱን እኔ እወስዳለሁ። አንድ ነገር ቢሆን እኔን ተጠያቂ ልታደርገኝ ትችላለህ። ልጁን ወደ አንተ መልሼ ባላመጣውና ባላስረክብህ በሕይወቴ ሙሉ በፊትህ በደለኛ ልሁን። 10  ዝም ብለን ጊዜ ባናጠፋ ኖሮ እስካሁን ሁለት ጊዜ እዚያ ደርሰን በተመለስን ነበር።” 11  በመሆኑም አባታቸው እስራኤል እንዲህ አላቸው፦ “እንግዲህ ሌላ አማራጭ ከጠፋ እንዲህ አድርጉ፦ ምድሪቱ ከምታፈራቸው ምርጥ ነገሮች መካከል ጥቂት በለሳን፣ ጥቂት ማር፣ ጥሩ መዓዛ ያለው ሙጫ፣ ከርቤ፣ ለውዝና አልሞንድ ለሰውየው ስጦታ እንዲሆን በከረጢቶቻችሁ ይዛችሁ ውረዱ። 12  በተጨማሪም እጥፍ ገንዘብ ያዙ፤ በከረጢቶቻችሁ አፍ ላይ ተደርጎ የተመለሰላችሁንም ገንዘብ ይዛችሁ ሂዱ። ምናልባት በስህተት የመጣ ሊሆን ይችላል። 13  በሉ ተነሱና ወንድማችሁን ይዛችሁ ወደ ሰውየው ሂዱ። 14  ሌላውን ወንድማችሁንና ቢንያምን እንዲለቅላችሁ ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ የሰውየውን ልብ ያራራላችሁ። እንግዲህ ልጆቼን አጥቼ ለሐዘን ከተዳረግኩም ምን አደርጋለሁ፤ የመጣውን እቀበላለሁ!” 15  ስለዚህ ሰዎቹ ይህን ስጦታና እጥፍ ገንዘብ እንዲሁም ቢንያምን ይዘው ተነሱ። ወደ ግብፅም ወረዱ፤ እንደገናም ዮሴፍ ፊት ቀረቡ። 16  ዮሴፍ ቢንያምን ከእነሱ ጋር ሲያየው የቤቱ ኃላፊ የሆነውን ሰው ወዲያውኑ እንዲህ አለው፦ “ሰዎቹን ወደ ቤት ውሰዳቸው፤ አብረውኝ ምሳ ስለሚበሉ እንስሳ አርደህ ምግብ አዘጋጅ።” 17  ሰውየውም ወዲያውኑ ልክ ዮሴፍ እንዳለው አደረገ፤ ሰዎቹንም ወደ ዮሴፍ ቤት ወሰዳቸው። 18  ሰዎቹ ግን ወደ ዮሴፍ ቤት ሲወሰዱ ፈሩ፤ እንዲህም ይሉ ጀመር፦ “ወደዚህ ያመጡን ባለፈው ጊዜ በከረጢቶቻችን ውስጥ በተመለሰው ገንዘብ የተነሳ ነው። በቃ አሁን ያሠቃዩናል፤ ባሪያ ያደርጉናል፤ አህዮቻችንንም ይቀሙናል!” 19  በመሆኑም የዮሴፍ ቤት ኃላፊ ወደሆነው ሰው ቀርበው በቤቱ በራፍ ላይ አነጋገሩት። 20  እነሱም እንዲህ አሉት፦ “ይቅርታ ጌታዬ! እኛ ባለፈው ጊዜ ወደዚህ የመጣነው እህል ለመግዛት ነበር። 21  ሆኖም የምናርፍበት ቦታ ደርሰን ከረጢቶቻችንን ስንከፍት የእያንዳንዳችንን ገንዘብ ምንም ሳይጎድል በየከረጢታችን አፍ ላይ አገኘነው። ስለዚህ ራሳችን ገንዘቡን መመለስ እንፈልጋለን። 22  እህል ለመግዛት ተጨማሪ ገንዘብ ይዘናል። ገንዘባችንን በከረጢታችን ውስጥ መልሶ ያስቀመጠው ማን እንደሆነ አናውቅም።” 23  እሱም “አይዟችሁ፣ አትፍሩ። ይህን ገንዘብ በከረጢቶቻችሁ ውስጥ ያስቀመጠላችሁ የእናንተ አምላክና የአባታችሁ አምላክ ነው። እኔ እንደሆነ ገንዘባችሁ ደርሶኛል” አላቸው። ከዚያም ስምዖንን አውጥቶ ወደ እነሱ አመጣው። 24  ከዚያም ሰውየው ሰዎቹን ወደ ዮሴፍ ቤት አስገባቸው፤ እግራቸውን እንዲታጠቡም ውኃ አቀረበላቸው፤ እንዲሁም ለአህዮቻቸው ገፈራ ሰጣቸው። 25  እነሱም እዚያው ምሳ እንደሚበሉ ስለሰሙ ዮሴፍ ቀትር ላይ ሲመጣ የሚሰጡትን ስጦታ ማዘገጃጀት ጀመሩ። 26  ዮሴፍ ወደ ቤት ሲገባ፣ ያዘጋጁትን ስጦታ ይዘው ወደ እሱ በመግባት አበረከቱለት፤ መሬት ላይም ተደፍተው ሰገዱለት። 27  ከዚያም ስለ ደህንነታቸው ጠየቃቸው፤ እንዲህም አላቸው፦ “ባለፈው ጊዜ የነገራችሁኝ አረጋዊ አባታችሁ ደህና ነው? አሁንም በሕይወት አለ?” 28  እነሱም “አገልጋይህ አባታችን ደህና ነው። አሁንም በሕይወት አለ” አሉት። ከዚያም መሬት ላይ ተደፍተው ሰገዱ። 29  ዮሴፍም ቀና ብሎ ሲመለከት የእናቱን ልጅ ወንድሙን ቢንያምን አየ፤ እሱም “ባለፈው ጊዜ ስለ እሱ የነገራችሁኝ ትንሹ ወንድማችሁ ይሄ ነው?” አላቸው። ቢንያምንም “የእኔ ልጅ፣ አምላክ ሞገሱን ያሳይህ” አለው። 30  ዮሴፍ ወንድሙን ሲያይ ስሜቱን መቆጣጠር ስላቃተው በፍጥነት ወጣ፤ የሚያለቅስበትንም ቦታ ፈለገ። ብቻውን ወደ አንድ ክፍል ገብቶም አለቀሰ። 31  ከዚያም ፊቱን ተጣጥቦ ወጣ፤ እንደ ምንም ስሜቱን ተቆጣጥሮም “ምግብ ይቅረብ” አለ። 32  እነሱም ለዮሴፍ ለብቻው አቀረቡለት፤ ለእነሱም ለብቻቸው አቀረቡላቸው። እንዲሁም በቤቱ ለሚበሉት ግብፃውያን ለብቻቸው አቀረቡላቸው። ይህን ያደረጉት ግብፃውያን ከዕብራውያን ጋር አብረው ምግብ ስለማይበሉ ነው፤ ምክንያቱም ይህ ለግብፃውያን አስጸያፊ ነገር ነው። 33  ወንድማማቾቹም የበኩሩ እንደ ብኩርና መብቱ፣ ታናሹም እንደ ታናሽነቱ በፊቱ ተቀመጡ፤ እርስ በርሳቸውም በመገረም ይተያዩ ነበር። 34  እሱም ፊቱ ከቀረበው ምግብ እየተነሳ ለእነሱ እንዲሰጣቸው ያደርግ ነበር፤ የቢንያም ድርሻ ግን ከሌሎቹ አምስት እጥፍ እንዲበልጥ ያደርግ ነበር። እነሱም እስኪጠግቡ ድረስ አብረውት በሉ፣ ጠጡም።
[]
[]
[]
[]
12,542
44  ከዚህ በኋላ ዮሴፍ የቤቱ ኃላፊ የሆነውን ሰው እንዲህ ሲል አዘዘው፦ “የቻሉትን ያህል እህል በየከረጢቶቻቸው ሙላላቸው፤ የእያንዳንዳቸውንም ገንዘብ በየከረጢቶቻቸው አፍ ላይ አድርገው። 2  ሆኖም የእኔን ጽዋ ይኸውም የብር ጽዋዬን ውሰድና እህል ለመግዛት ካመጣው ገንዘብ ጋር አድርገህ በትንሹ ወንድማቸው ከረጢት አፍ ላይ አድርገው።” እሱም ልክ ዮሴፍ እንዳዘዘው አደረገ። 3  ሰዎቹም ማለዳ ላይ ጎህ ሲቀድ ከነአህዮቻቸው ተሸኙ። 4  እነሱም ከከተማዋ ብዙም ርቀው ሳይሄዱ ዮሴፍ የቤቱ ኃላፊ የሆነውን ሰው እንዲህ አለው፦ “ተነስ! ሰዎቹን ተከታተላቸው! ስትደርስባቸውም እንዲህ በላቸው፦ ‘ለተደረገላችሁ መልካም ነገር ክፉ የመለሳችሁት ለምንድን ነው? 5  ይህ ጌታዬ የሚጠጣበትና የሚጠነቁልበት ጽዋ አይደለም? የፈጸማችሁት ድርጊት በጣም አሳፋሪ ነው።’” 6  እሱም ተከታትሎ ደረሰባቸውና ልክ እንደተባለው አላቸው። 7  እነሱ ግን እንዲህ አሉት፦ “ጌታዬ እንዲህ ያለ ነገር የሚናገረው ለምንድን ነው? አገልጋዮችህ እንዲህ ያለ ነገር ያደርጋሉ ማለት ፈጽሞ የማይታሰብ ነው። 8  በከረጢቶቻችን አፍ ላይ ያገኘነውን ገንዘብ እንኳ ከከነአን ምድር ድረስ ይዘን ወደ አንተ መጥተን የለም? ታዲያ ከጌታህ ቤት ብር ወይም ወርቅ እንዴት እንሰርቃለን? 9  ከእኛ ከባሪያዎችህ መካከል የተገኘበት ቢኖር ያ ሰው ይገደል፤ የቀረነውም ለጌታዬ ባሪያዎች እንሆናለን።” 10  እሱም “እሺ፣ እንዳላችሁት ይሁን፤ ጽዋው የተገኘበት ሰው ባሪያዬ ይሆናል፤ የቀራችሁት ግን ነፃ ትሆናላችሁ” አላቸው። 11  ከዚያም እያንዳንዳቸው ወዲያውኑ ከረጢታቸውን መሬት አውርደው መፍታት ጀመሩ። 12  እሱም ከታላቁ ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ በጥንቃቄ ፈተሸ። በመጨረሻም ጽዋው በቢንያም ከረጢት ውስጥ ተገኘ። 13  በዚህ ጊዜ ልብሳቸውን ቀደዱ፤ እያንዳንዳቸውም ጓዛቸውን መልሰው በአህዮቻቸው ላይ በመጫን ወደ ከተማዋ ተመለሱ። 14  ይሁዳና ወንድሞቹ ወደ ዮሴፍ ቤት ሲገቡ ዮሴፍ ገና ከቤት አልወጣም ነበር፤ እነሱም በፊቱ መሬት ላይ ተደፉ። 15  ዮሴፍም “ይህ ያደረጋችሁት ነገር ምንድን ነው? እንደ እኔ ያለ ሰው ማንኛውንም ነገር በጥንቆላ የማወቅ ችሎታ እንዳለው አታውቁም?” አላቸው። 16  በዚህ ጊዜ ይሁዳ እንዲህ አለ፦ “እንግዲህ ለጌታዬ ምን ማለት እንችላለን? ምንስ አፍ አለን? ጻድቅ መሆናችንን እንዴት ማረጋገጥ እንችላለን? እውነተኛው አምላክ ባሪያዎችህ የፈጸሙትን ስህተት አጋልጧል። እንግዲህ እኛም ሆን ጽዋው የተገኘበት ሰው ለጌታዬ ባሪያዎች እንሆናለን!” 17  እሱ ግን እንዲህ አላቸው፦ “ይህንማ ፈጽሞ አላደርገውም! ባሪያዬ የሚሆነው ጽዋው የተገኘበት ሰው ነው። የቀራችሁት ግን ወደ አባታችሁ በሰላም ሂዱ።” 18  ይሁዳም ወደ እሱ ቀርቦ እንዲህ አለው፦ “እባክህ ጌታዬ እማጸንሃለሁ፤ ባሪያህ አንዲት ቃል ብቻ ይናገር፤ ጌታዬም ይስማው፤ እባክህ በባሪያህ ላይ አትቆጣ፤ ምክንያቱም አንተ ልክ እንደ ፈርዖን ነህ። 19  ጌታዬ እኛን ባሪያዎቹን ‘አባት ወይም ወንድም አላችሁ?’ በማለት ጠይቆን ነበር። 20  እኛም ለጌታዬ እንዲህ ስንል መለስንለት፦ ‘አረጋዊ አባት አለን፤ እንዲሁም በስተርጅናው የወለደው የሁላችንም ታናሽ የሆነ ወንድም አለን። ወንድሙ ግን ሞቷል፤ በመሆኑም ከአንድ እናት ከተወለዱት መካከል የቀረው እሱ ብቻ ነው፤ አባቱም በጣም ይወደዋል።’ 21  ከዚያም አንተ እኛን ባሪያዎችህን ‘እንዳየው ወደ እኔ አምጡት’ አልከን። 22  እኛ ግን ጌታዬን ‘ልጁ ከአባቱ ሊለይ አይችልም። ከተለየው ደግሞ አባቱ ያለጥርጥር ይሞታል’ አልነው። 23  አንተም እኛን ባሪያዎችህን ‘ትንሹን ወንድማችሁን ይዛችሁት ካልመጣችሁ ከእንግዲህ ፊቴን አታዩም’ አልከን። 24  “በመሆኑም ወደ ባሪያህ ወደ አባታችን ሄደን የጌታዬን ቃል ነገርነው። 25  ከጊዜ በኋላም አባታችን ‘ተመልሳችሁ ሂዱና ጥቂት እህል ግዙልን’ አለን። 26  እኛ ግን እንዲህ አልነው፦ ‘ወደዚያ መሄድ አንችልም። ትንሹ ወንድማችን ከእኛ ጋር ካልሄደ የሰውየውን ፊት ማየት ስለማንችል ትንሹ ወንድማችን አብሮን የሚሄድ ከሆነ ወደዚያ እንወርዳለን።’ 27  በዚህ ጊዜ ባሪያህ አባታችን እንዲህ አለን፦ ‘ሚስቴ ከሁለት ወንዶች ልጆች ሌላ ምንም እንዳልወለደችልኝ እናንተ ራሳችሁ በሚገባ ታውቃላችሁ። 28  ሆኖም አንዱ እንደወጣ በመቅረቱ “መቼም አውሬ ቦጫጭቆት መሆን አለበት!” አልኩ፤ ይኸው ከዚያን ጊዜ ወዲህ አይቼው አላውቅም። 29  ይሄኛውንም ልጅ ከእኔ ለይታችሁ ብትወስዱትና አደጋ ደርሶበት ቢሞት ሽበቴን በሥቃይ ወደ መቃብር ታወርዱታላችሁ።’ 30  “እንግዲህ ወደ ባሪያህ ወደ አባቴ ስመለስ ልጁ ከእኛ ጋር ከሌለ፣ የአባታችን ሕይወት ከልጁ ሕይወት ጋር በጥብቅ የተቆራኘ ስለሆነ 31  አባታችን ልጁ አብሮን አለመኖሩን ሲያይ ይሞታል፤ ባሪያዎችህም የባሪያህን የአባታችንን ሽበት በሐዘን ወደ መቃብር ያወርዱታል። 32  እኔ ባሪያህ ‘ልጁን ወደ አንተ መልሼ ባላመጣው በአባቴ ፊት ለዘላለም በደለኛ ልሁን’ ብዬ ለአባቴ ቃል ገብቻለሁ። 33  ስለዚህ እባክህ ልጁ ከወንድሞቹ ጋር እንዲሄድ እኔ ባሪያህ በልጁ ፋንታ እዚሁ ቀርቼ ለጌታዬ ባሪያ ልሁን። 34  ልጁን ሳልይዝ እንዴት ወደ አባቴ እመለሳለሁ? በአባቴ ላይ እንዲህ ያለ መከራ ሲደርስ ማየት አልችልም!”
[]
[]
[]
[]
12,543
45  በዚህ ጊዜ ዮሴፍ አጠገቡ በነበሩት አገልጋዮቹ ፊት ስሜቱን መቆጣጠር አልቻለም። በመሆኑም “ሁሉንም ሰው አስወጡልኝ!” በማለት ጮኸ። ዮሴፍ ራሱን ለወንድሞቹ በገለጠበት ወቅት ከእሱ ጋር ማንም ሰው አልነበረም። 2  ከዚያም ጮክ ብሎ ማልቀስ ጀመረ፤ ግብፃውያንም ሰሙት፤ በፈርዖንም ቤት ተሰማ። 3  በመጨረሻም ዮሴፍ ወንድሞቹን “እኔ ዮሴፍ ነኝ። አባቴ እስካሁን በሕይወት አለ?” አላቸው። ወንድሞቹ ግን በሁኔታው በጣም ስለደነገጡ ምንም ሊመልሱለት አልቻሉም። 4  ስለሆነም ዮሴፍ ወንድሞቹን “እባካችሁ ወደ እኔ ቅረቡ” አላቸው። እነሱም ወደ እሱ ቀረቡ። ከዚያም እንዲህ አላቸው፦ “እኔ ወደ ግብፅ የሸጣችሁኝ ወንድማችሁ ዮሴፍ ነኝ። 5  አሁን ግን እኔን ወደዚህ በመሸጣችሁ አትዘኑ፤ እርስ በርሳችሁም አትወቃቀሱ፤ ምክንያቱም አምላክ ከእናንተ አስቀድሞ የላከኝ ሕይወት ለማዳን ሲል ነው። 6  ረሃቡ በምድር ላይ ከጀመረ ይህ ሁለተኛ ዓመቱ ነው፤ ምንም የማይታረስባቸውና አዝመራ የማይሰበሰብባቸው አምስት ዓመታት ገና ይቀራሉ። 7  አምላክ ግን በምድር ላይ ዘራችሁን ሊያስቀርና በታላቅ ማዳን ሕይወታችሁን ሊታደግ ከእናንተ አስቀድሞ ላከኝ። 8  ስለዚህ ለፈርዖን ዋና አማካሪ፣ በቤቱም ሁሉ ላይ ጌታ እንዲሁም በመላው የግብፅ ምድር ላይ ገዢ ሊያደርገኝ ወደዚህ የላከኝ እውነተኛው አምላክ እንጂ እናንተ አይደላችሁም። 9  “ቶሎ ብላችሁ ወደ አባቴ ሂዱና እንዲህ በሉት፦ ‘ልጅህ ዮሴፍ እንዲህ ይላል፦ “አምላክ በመላው ግብፅ ላይ ጌታ አድርጎኛል። ሳትዘገይ ወደ እኔ ና። 10  ወንዶች ልጆችህን፣ የልጅ ልጆችህን፣ መንጎችህን፣ ከብቶችህንና ያለህን ነገር በሙሉ ይዘህ በመምጣት በአቅራቢያዬ በጎሸን ምድር ትኖራለህ። 11  ረሃቡ ገና ለአምስት ዓመታት ስለሚቀጥል እኔ የሚያስፈልግህን ምግብ እሰጥሃለሁ። አለዚያ አንተም ሆንክ ቤትህ እንዲሁም የአንተ የሆነው ሁሉ ችግር ላይ ትወድቃላችሁ።”’ 12  እንግዲህ አሁን እያናገርኳችሁ ያለሁት እኔው ራሴ መሆኔን እናንተም ሆናችሁ ወንድሜ ቢንያም በገዛ ዓይናችሁ አይታችኋል። 13  በመሆኑም በግብፅ ስላለኝ ክብር ሁሉ እንዲሁም ስላያችሁት ስለ ማንኛውም ነገር ለአባቴ ንገሩት። አሁንም በፍጥነት ሄዳችሁ አባቴን ወደዚህ ይዛችሁት ኑ።” 14  ከዚያም በወንድሙ በቢንያም አንገት ላይ ተጠምጥሞ አለቀሰ፤ ቢንያምም አንገቱን አቅፎት አለቀሰ። 15  የቀሩትን ወንድሞቹንም አንድ በአንድ እየሳመ አለቀሰ፤ ከዚህ በኋላም ወንድሞቹ ከእሱ ጋር ማውራት ጀመሩ። 16  “የዮሴፍ ወንድሞች መጥተዋል!” የሚለው ወሬ በፈርዖን ቤት ተሰማ። ፈርዖንና አገልጋዮቹም ደስ አላቸው። 17  ስለዚህ ፈርዖን ዮሴፍን እንዲህ አለው፦ “ወንድሞችህን እንዲህ በላቸው፦ ‘እንዲህ አድርጉ፦ የጋማ ከብቶቻችሁን ጫኑና ወደ ከነአን ምድር ሂዱ። 18  የግብፅን ምድር መልካም ነገሮች እንድሰጣችሁ አባታችሁንና ቤተሰባችሁን ይዛችሁ ወደ እኔ ኑ፤ ከዚያም ለም ከሆነው የምድሪቱ ክፍል ትበላላችሁ።’ 19  አንተንም እንዲህ ብለህ እንድትነግራቸው አዝዤሃለሁ፦ ‘እንዲህ አድርጉ፦ ልጆቻችሁንና ሚስቶቻችሁን የምታጓጉዙባቸውን ሠረገሎች ከግብፅ ምድር ውሰዱ፤ አባታችሁንም በአንዱ ሠረገላ ላይ ጭናችሁ ወደዚህ ኑ። 20  ስለ ንብረታችሁ ምንም አትጨነቁ፤ ምክንያቱም በግብፅ ምድር ያለ ምርጥ ነገር ሁሉ የእናንተው ነው።’” 21  የእስራኤልም ወንዶች ልጆች እንደተባሉት አደረጉ፤ ዮሴፍ በፈርዖን ትእዛዝ መሠረት ሠረገሎችን ሰጣቸው፤ ለጉዟቸው የሚሆን ስንቅም አስያዛቸው። 22  ለእያንዳንዳቸው ቅያሪ ልብስ ሰጣቸው፤ ለቢንያም ግን 300 የብር ሰቅልና አምስት ቅያሪ ልብስ ሰጠው። 23  ለአባቱም የግብፅን ምድር መልካም ነገሮች የጫኑ አሥር አህዮችን እንዲሁም ለጉዞ ስንቅ እንዲሆነው እህል፣ ዳቦና ሌሎች ምግቦችን የጫኑ አሥር እንስት አህዮችን ላከ። 24  በዚህ መንገድ ወንድሞቹን ሸኛቸው፤ እነሱም ጉዞ ሲጀምሩ “ደግሞ በመንገድ ላይ እርስ በርስ እንዳትጣሉ” አላቸው። 25  እነሱም ከግብፅ ወጥተው ሄዱ፤ በከነአን ምድር ወዳለው ወደ አባታቸው ወደ ያዕቆብም መጡ። 26  ከዚያም “ዮሴፍ በሕይወት አለ፤ ደግሞም በመላው የግብፅ ምድር ላይ ገዢ ሆኗል!” ሲሉ ነገሩት። እሱ ግን ክው ብሎ ቀረ፤ ሊያምናቸውም አልቻለም። 27  ዮሴፍ የነገራቸውን ነገር በሙሉ ሲነግሩትና ዮሴፍ እሱን ለመውሰድ የላካቸውን ሠረገሎች ሲያይ የአባታቸው የያዕቆብ መንፈስ ታደሰ። 28  እስራኤልም “በቃ አምኛችኋለሁ! ልጄ ዮሴፍ በሕይወት አለ! እንግዲህ ከመሞቴ በፊት ሄጄ ዓይኑን ማየት አለብኝ!” አላቸው።
[]
[]
[]
[]
12,544
46  በመሆኑም እስራኤል ያለውን ሁሉ ይዞ ተነሳ። ቤርሳቤህ በደረሰ ጊዜም ለአባቱ ለይስሐቅ አምላክ መሥዋዕቶችን አቀረበ። 2  ከዚያም አምላክ ለእስራኤል ሌሊት በራእይ ተገልጦለት “ያዕቆብ፣ ያዕቆብ!” ሲል ጠራው፤ እሱም “አቤት!” አለ። 3  አምላክም እንዲህ አለው፦ “እኔ የአባትህ አምላክ የሆንኩት እውነተኛው አምላክ ነኝ። ወደ ግብፅ ለመውረድ አትፍራ፤ ምክንያቱም በዚያ ታላቅ ብሔር አደርግሃለሁ። 4  እኔ ራሴ ከአንተ ጋር ወደ ግብፅ እወርዳለሁ፤ ደግሞም እኔ ራሴ ከዚያ አወጣሃለሁ፤ ዮሴፍም ዓይኖችህን በእጁ ይከድናል።” 5  ከዚያ በኋላ ያዕቆብ ከቤርሳቤህ ተነሳ፤ የእስራኤል ወንዶች ልጆችም አባታቸውን ያዕቆብን፣ ልጆቻቸውንና ሚስቶቻቸውን ፈርዖን በላከለት ሠረገሎች ላይ አሳፍረው ጉዞ ጀመሩ። 6  እነሱም በከነአን ምድር ያፈሩትን ንብረትና መንጎቻቸውን ይዘው ሄዱ። ከዚያም ያዕቆብና ከእሱ ጋር የነበሩት ልጆቹ በሙሉ ወደ ግብፅ መጡ። 7  እሱም ወንዶች ልጆቹንና ወንዶች የልጅ ልጆቹን እንዲሁም ሴቶች ልጆቹንና ሴቶች የልጅ ልጆቹን ይኸውም ዘሮቹን ሁሉ ይዞ ወደ ግብፅ መጣ። 8  ወደ ግብፅ የመጡት የእስራኤል ማለትም የያዕቆብ ወንዶች ልጆች ስም ይህ ነው፦ የያዕቆብ የበኩር ልጅ ሮቤል። 9  የሮቤል ወንዶች ልጆች ሃኖክ፣ ፓሉ፣ ኤስሮን እና ካርሚ ነበሩ። 10  የስምዖን ወንዶች ልጆች የሙኤል፣ ያሚን፣ ኦሃድ፣ ያኪን፣ ጾሃር እንዲሁም ከአንዲት ከነአናዊት የወለደው ሻኡል ነበሩ። 11  የሌዊ ወንዶች ልጆች ጌድሶን፣ ቀአት እና ሜራሪ ነበሩ። 12  የይሁዳ ወንዶች ልጆች ኤር፣ ኦናን፣ ሴሎም፣ ፋሬስ እና ዛራ ነበሩ፤ ይሁንና ኤር እና ኦናን በከነአን ምድር ሞቱ። የፋሬስ ወንዶች ልጆች ኤስሮን እና ሃሙል ነበሩ። 13  የይሳኮር ወንዶች ልጆች ቶላ፣ ፑዋ፣ ዮብ እና ሺምሮን ነበሩ። 14  የዛብሎን ወንዶች ልጆች ሰሬድ፣ ኤሎን እና ያህልኤል ነበሩ። 15  ሴት ልጁን ዲናን ጨምሮ እነዚህ ሊያ በጳዳንአራም ለያዕቆብ የወለደችለት ልጆች ናቸው። በአጠቃላይ ወንዶች ልጆቹና ሴቶች ልጆቹ 33 ነበሩ። 16  የጋድ ወንዶች ልጆች ጺፍዮን፣ ሃጊ፣ ሹኒ፣ ኤጽቦን፣ ኤሪ፣ አሮድ እና አርዔላይ ነበሩ። 17  የአሴር ወንዶች ልጆች ይምናህ፣ ይሽዋ፣ ይሽዊ እና በሪአ ሲሆኑ እህታቸውም ሴራህ ትባላለች። የበሪአ ወንዶች ልጆች ሄቤር እና ማልኪኤል ነበሩ። 18  ላባ ለልጁ ለሊያ የሰጣት ዚልጳ የተባለችው አገልጋይ የወለደቻቸው ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው። እሷም ለያዕቆብ እነዚህን ወለደችለት፤ እነሱም በአጠቃላይ 16 ነበሩ። 19  የያዕቆብ ሚስት የራሔል ወንዶች ልጆች ዮሴፍና ቢንያም ነበሩ። 20  ዮሴፍ በግብፅ ምድር ሳለ ምናሴንና ኤፍሬምን ወለደ፤ እነዚህም የኦን ካህን የሆነው የጶጥፌራ ልጅ አስናት የወለደችለት ናቸው። 21  የቢንያም ወንዶች ልጆች ቤላ፣ ቤኬር፣ አሽቤል፣ ጌራ፣ ንዕማን፣ ኤሂ፣ ሮሽ፣ ሙጲም፣ ሁፒም እና አርድ ነበሩ። 22  እነዚህ ራሔል ለያዕቆብ የወለደችለት ወንዶች ልጆች ናቸው፤ እነሱም በአጠቃላይ 14 ነበሩ። 23  የዳን ልጅ ሁሺም ነበር። 24  የንፍታሌም ወንዶች ልጆች ያህጽኤል፣ ጉኒ፣ የጼር እና ሺሌም ነበሩ። 25  ላባ ለልጁ ለራሔል የሰጣት ባላ የተባለችው አገልጋይ የወለደቻቸው ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው። እሷም ለያዕቆብ እነዚህን ወለደችለት፤ እነሱም በአጠቃላይ ሰባት ነበሩ። 26  የያዕቆብ ዝርያዎች የሆኑትና ከእሱ ጋር ወደ ግብፅ የገቡት ሰዎች፣ የልጆቹን ሚስቶች ሳይጨምር በአጠቃላይ 66 ነበሩ። 27  ዮሴፍ በግብፅ የወለዳቸው ወንዶች ልጆች ሁለት ነበሩ። ወደ ግብፅ የገቡት የያዕቆብ ቤተሰቦች በአጠቃላይ 70 ነበሩ። 28  ያዕቆብ ወደ ጎሸን እየሄደ መሆኑን ለዮሴፍ እንዲነግረው ይሁዳን ከእሱ አስቀድሞ ላከው። ወደ ጎሸን ምድር በደረሱም ጊዜ 29  ዮሴፍ ሠረገላው እንዲዘጋጅለት ካደረገ በኋላ አባቱን እስራኤልን ለመቀበል ወደ ጎሸን ሄደ። ባገኘውም ጊዜ አንገቱ ላይ ተጠምጥሞ ረዘም ላለ ጊዜ አለቀሰ። 30  ከዚያም እስራኤል ዮሴፍን “ከእንግዲህ ብሞት አይቆጨኝም፤ ዓይንህን ለማየት በቅቻለሁ፤ በሕይወት መኖርህንም አረጋግጫለሁ” አለው። 31  ከዚያም ዮሴፍ ወንድሞቹንና የአባቱን ቤተሰቦች እንዲህ አላቸው፦ “ወደ ፈርዖን ወጥቼ ሁኔታውን ልንገረው፤ እንዲህም ልበለው፦ ‘በከነአን ምድር ይኖሩ የነበሩት ወንድሞቼና የአባቴ ቤተሰቦች ወደ እኔ መጥተዋል። 32  እነሱ እረኞችና ከብት አርቢዎች ናቸው፤ መንጎቻቸውን፣ ከብቶቻቸውንና ያላቸውን ሁሉ ይዘው መጥተዋል።’ 33  እንግዲህ ፈርዖን ጠርቶ ‘ሥራችሁ ምንድን ነው?’ ብሎ ሲጠይቃችሁ 34  ‘እኛ አገልጋዮችህም ሆን የቀድሞ አባቶቻችን ከልጅነታችን ጀምሮ ከብት አርቢዎች ነን’ በሉት። ግብፃውያን በግ ጠባቂዎችን ስለሚጸየፉ በጎሸን ምድር እንድትኖሩ ይፈቅድላችኋል።”
[]
[]
[]
[]
12,545
47  ስለዚህ ዮሴፍ ወደ ፈርዖን ሄዶ “አባቴና ወንድሞቼ እንዲሁም መንጎቻቸው፣ ከብቶቻቸውና የእነሱ የሆነው ሁሉ ከከነአን ምድር መጥተዋል፤ በጎሸን ምድር ይገኛሉ” አለው። 2  እሱም ከወንድሞቹ መካከል አምስቱን ወስዶ ፈርዖን ፊት አቀረባቸው። 3  ፈርዖንም የዮሴፍን ወንድሞች “ሥራችሁ ምንድን ነው?” ሲል ጠየቃቸው። እነሱም “እኛ አገልጋዮችህም ሆን የቀድሞ አባቶቻችን በግ አርቢዎች ነን” በማለት መለሱለት። 4  ከዚያም ፈርዖንን እንዲህ አሉት፦ “ወደዚህ የመጣነው በምድሪቱ ላይ እንደ ባዕድ አገር ሰው ሆነን ለመኖር ነው፤ ምክንያቱም በከነአን ምድር ረሃቡ በጣም ስለበረታ ለአገልጋዮችህ መንጋ የሚሆን የግጦሽ ቦታ የለም። ስለሆነም እባክህ አገልጋዮችህ በጎሸን ምድር እንዲኖሩ ፍቀድላቸው።” 5  በዚህ ጊዜ ፈርዖን ዮሴፍን እንዲህ አለው፦ “አባትህና ወንድሞችህ ወደ አንተ መጥተዋል። 6  የግብፅ ምድር እንደሆነ በእጅህ ነው። አባትህና ወንድሞችህ ምርጥ በሆነው የምድሪቱ ክፍል እንዲኖሩ አድርግ። በጎሸን ምድር ይኑሩ፤ ከእነሱ መካከል ጥሩ ችሎታ እንዳላቸው የምታውቃቸው ሰዎች ካሉ በከብቶቼ ላይ ኃላፊ አድርገህ ሹማቸው።” 7  ከዚያም ዮሴፍ አባቱን ያዕቆብን አስገብቶ ፈርዖን ፊት አቀረበው፤ ያዕቆብም ፈርዖንን ባረከው። 8  ፈርዖንም ያዕቆብን “ለመሆኑ ዕድሜህ ስንት ነው?” ሲል ጠየቀው። 9  ያዕቆብም ፈርዖንን እንዲህ አለው፦ “ከቦታ ወደ ቦታ በመንከራተት ያሳለፍኩት ዘመን 130 ዓመት ነው። የሕይወት ዘመኔ አጭርና ጭንቀት የበዛበት ነበር፤ ደግሞም አባቶቼ ከቦታ ወደ ቦታ በመንከራተት ያሳለፉትን ዘመን አያክልም።” 10  ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ፈርዖንን መረቀው፤ ከፊቱም ወጥቶ ሄደ። 11  በመሆኑም ዮሴፍ፣ አባቱና ወንድሞቹ እንዲሰፍሩ አደረገ፤ ፈርዖንም ባዘዘው መሠረት ምርጥ ከሆነው የግብፅ ምድር፣ የራምሴስን ምድር ርስት አድርጎ ሰጣቸው። 12  ዮሴፍም ለአባቱ፣ ለወንድሞቹና ለመላው የአባቱ ቤተሰብ በትናንሽ ልጆቻቸው ቁጥር ልክ ቀለብ ይሰፍርላቸው ነበር። 13  በዚህ ወቅት ረሃቡ እጅግ በርትቶ ስለነበር በመላው ምድር እህል አልነበረም፤ የግብፅም ምድር ሆነ የከነአን ምድር በረሃቡ የተነሳ በጣም ተጎድተው ነበር። 14  ዮሴፍም ሰዎች እህል ሲገዙ የከፈሉትን በግብፅ ምድርና በከነአን ምድር የሚገኘውን ገንዘብ በሙሉ እየሰበሰበ ወደ ፈርዖን ቤት ያስገባ ነበር። 15  ከጊዜ በኋላ በግብፅ ምድርና በከነአን ምድር ያለው ገንዘብ አለቀ፤ ግብፃውያንም በሙሉ ወደ ዮሴፍ በመምጣት “እህል ስጠን! ገንዘብ ስለጨረስን ብቻ እንዴት ዓይንህ እያየ እንለቅ?” ይሉት ጀመር። 16  ዮሴፍም “ገንዘባችሁ ካለቀ ከብቶቻችሁን አምጡ፤ እኔም በከብቶቻችሁ ምትክ እህል እሰጣችኋለሁ” አላቸው። 17  በመሆኑም ከብቶቻቸውን ወደ ዮሴፍ ያመጡ ጀመር፤ ዮሴፍም በፈረሶቻቸው፣ በመንጎቻቸው፣ በከብቶቻቸውና በአህዮቻቸው ምትክ እህል ይሰጣቸው ነበር፤ በዚያም ዓመት በከብቶቻቸው ሁሉ ምትክ እህል ሲሰጣቸው ከረመ። 18  ያም ዓመት ካለቀ በኋላ በቀጣዩ ዓመት ሕዝቡ ወደ እሱ በመምጣት እንዲህ ይለው ጀመር፦ “ከጌታዬ የምንደብቀው ምንም ነገር የለም፤ ገንዘባችንንም ሆነ ከብቶቻችንን ለጌታዬ አስረክበናል። ከእኛ ከራሳችንና ከመሬታችን በስተቀር በጌታዬ ፊት ምንም የቀረን ነገር የለም። 19  ዓይንህ እያየ ለምን እንለቅ? መሬታችንስ ለምን ጠፍ ሆኖ ይቅር? እኛንም ሆነ መሬታችንን በእህል ግዛን፤ እኛ ለፈርዖን ባሪያዎች እንሁን፤ መሬታችንም የእሱ ይሁን። በሕይወት እንድንኖርና እንዳንሞት እንዲሁም መሬታችን ጠፍ ሆኖ እንዳይቀር የምንዘራው እህል ስጠን።” 20  በመሆኑም ዮሴፍ የግብፃውያንን መሬት በሙሉ ለፈርዖን ገዛለት፤ ምክንያቱም ረሃቡ እጅግ ስለበረታባቸው ሁሉም ግብፃውያን መሬታቸውን ሸጠው ነበር፤ ስለዚህ ምድሪቱ የፈርዖን ሆነች። 21  ዮሴፍም በግብፅ ምድር ከዳር እስከ ዳር ያለው ሕዝብ ወደ ከተሞች እንዲገባ አደረገ። 22  ዮሴፍ ያልገዛው የካህናቱን መሬት ብቻ ነበር፤ ምክንያቱም ፈርዖን ለካህናቱ ቀለብ ይሰፍርላቸው ነበር፤ እነሱም የሚኖሩት ፈርዖን በሚሰፍርላቸው ቀለብ ነበር። መሬታቸውን ያልሸጡትም ለዚህ ነው። 23  ከዚያም ዮሴፍ ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፦ “ይኸው ዛሬ እናንተንም ሆነ መሬታችሁን ለፈርዖን ገዝቻለሁ። ዘር ይኸውላችሁ፤ እናንተም በመሬቱ ላይ ዝሩ። 24  ባፈራም ጊዜ አንድ አምስተኛውን ለፈርዖን ስጡ፤ አራቱ እጅ ግን ለመሬታችሁ ዘር እንዲሁም ለራሳችሁ፣ በቤታችሁ ላሉትና ለልጆቻችሁ ምግብ እንዲሆናችሁ የእናንተ ይሆናል።” 25  እነሱም “አንተ ሕይወታችንን አትርፈህልናል፤ በጌታዬ ፊት ሞገስ እናግኝ እንጂ እኛ ለፈርዖን ባሪያዎች እንሆናለን” አሉት። 26  ከዚያም ዮሴፍ አንድ አምስተኛው ለፈርዖን እንዲሰጥ የሚያዝ ሕግ አወጣ፤ ይህም ሕግ እስከ ዛሬ ድረስ በግብፅ ምድር ይሠራበታል። የፈርዖን ያልሆነው የካህናቱ መሬት ብቻ ነበር። 27  እስራኤላውያንም በግብፅ አገር፣ በጎሸን ምድር መኖራቸውን ቀጠሉ። በዚያም ተደላድለው ይኖሩ ጀመር፤ ፍሬያማም ሆኑ፤ ቁጥራቸውም እጅግ እየበዛ ሄደ። 28  ያዕቆብም በግብፅ ምድር ለ17 ዓመት ኖረ፤ በመሆኑም ያዕቆብ በሕይወት የኖረበት ዘመን 147 ዓመት ሆነ። 29  እስራኤልም የሚሞትበት ቀን ሲቃረብ ልጁን ዮሴፍን ጠርቶ እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ በፊትህ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ እባክህ እጅህን ከጭኔ በታች አድርግ፤ ለእኔም ታማኝ ፍቅርና ታማኝነት አሳየኝ። እባክህ በግብፅ አትቅበረኝ። 30  በምሞትበት ጊዜ ከግብፅ አውጥተህ በአባቶቼ መቃብር ቅበረኝ።” እሱም “እሺ፣ እንዳልከኝ አደርጋለሁ” አለው። 31  ያዕቆብም “በል ማልልኝ” አለው፤ እሱም ማለለት። በዚህ ጊዜ እስራኤል በአልጋው ራስጌ ላይ ሰገደ።
[]
[]
[]
[]
12,546
48  ይህ ከሆነ በኋላ ዮሴፍ “አባትህ ደክሟል” ተብሎ ተነገረው። ዮሴፍም ሁለቱን ወንዶች ልጆቹን ምናሴንና ኤፍሬምን ይዞ ሄደ። 2  ከዚያም ያዕቆብ “ልጅህ ዮሴፍ ወደ አንተ መጥቷል” ተብሎ ተነገረው። በመሆኑም እስራኤል እንደ ምንም ቀና ብሎ አልጋው ላይ ተቀመጠ። 3  ያዕቆብም ዮሴፍን እንዲህ አለው፦ “ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ በከነአን ምድር በምትገኘው በሎዛ ተገልጦልኝ ባረከኝ። 4  እሱም እንዲህ አለኝ፦ ‘ፍሬያማ እያደረግኩህ ነው፤ ደግሞም አበዛሃለሁ፤ ብዙ ሕዝብ ያቀፈ ጉባኤም አደርግሃለሁ፤ ይህችን ምድር ከአንተ በኋላ ለሚመጡት ዘሮችህ ዘላቂ ርስት አድርጌ እሰጣቸዋለሁ።’ 5  አንተ ወዳለህበት ወደ ግብፅ ከመምጣቴ በፊት በግብፅ ምድር የወለድካቸው ሁለት ወንዶች ልጆች የእኔ ናቸው። ሮቤልና ስምዖን የእኔ እንደሆኑ ሁሉ ኤፍሬምና ምናሴም የእኔ ይሆናሉ። 6  ከእነሱ በኋላ የምትወልዳቸው ልጆች ግን የአንተ ይሆናሉ። እነሱም ርስት በሚሰጣቸው ጊዜ በወንድሞቻቸው ስም ይጠራሉ። 7  እኔም ከጳዳን ስመጣ ኤፍራታ ለመድረስ ረዘም ያለ መንገድ ሲቀረኝ ራሔል በከነአን ምድር ሞተችብኝ። በመሆኑም ወደ ኤፍራታ ማለትም ወደ ቤተልሔም በሚወስደው መንገድ ላይ ቀበርኳት።” 8  ከዚያም እስራኤል የዮሴፍን ወንዶች ልጆች ሲያይ “እነዚህ እነማን ናቸው?” ሲል ጠየቀው። 9  ዮሴፍም አባቱን “እነዚህ አምላክ በዚህ ስፍራ የሰጠኝ ወንዶች ልጆቼ ናቸው” አለው። በዚህ ጊዜ “እባክህ እንድባርካቸው ወደ እኔ አቅርባቸው” አለው። 10  የእስራኤል ዓይኖች በእርጅና የተነሳ ደክመው ነበር፤ እሱም ማየት ተስኖት ነበር። ስለዚህ ዮሴፍ ልጆቹን ወደ እሱ አቀረባቸው። እሱም ሳማቸው፤ እንዲሁም አቀፋቸው። 11  እስራኤልም ዮሴፍን “ዓይንህን አያለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር፤ አምላክ ግን ልጆችህንም ጭምር ለማየት አበቃኝ” አለው። 12  ከዚያም ዮሴፍ ልጆቹን ከእስራኤል ጉልበቶች መካከል አውጥቶ ፈቀቅ ካደረጋቸው በኋላ በግንባሩ መሬት ላይ ተደፍቶ ሰገደ። 13  ዮሴፍም ሁለቱን ልጆች ወስዶ ኤፍሬምን ከራሱ በስተ ቀኝ ከእስራኤል በስተ ግራ፣ ምናሴን ደግሞ ከራሱ በስተ ግራ ከእስራኤል በስተ ቀኝ አድርጎ ወደ እሱ አቀረባቸው። 14  ይሁን እንጂ እስራኤል ታናሽየው ኤፍሬም ቢሆንም ቀኝ እጁን በእሱ ራስ ላይ አደረገ፤ ግራ እጁን ደግሞ በምናሴ ራስ ላይ አደረገ። እንዲህ ያደረገው ሆን ብሎ ነው፤ ምክንያቱም ምናሴ የበኩር ልጅ ነበር። 15  ከዚያም ዮሴፍን ባረከው፤ እንዲህም አለው፦ “አባቶቼ አብርሃምና ይስሐቅ በፊቱ የተመላለሱት እውነተኛው አምላክ፣እስከ ዛሬዋ ዕለት ድረስ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ እረኛ የሆነልኝ እውነተኛው አምላክ፣ 16  ከአደጋ ሁሉ ያዳነኝ መልአክ እነዚህን ልጆች ይባርክ። የእኔም ሆነ የአባቶቼ የአብርሃምና የይስሐቅ ስም በእነሱ ይጠራ። በምድርም ላይ ቁጥራቸው እየበዛ ይሂድ።” 17  ዮሴፍም አባቱ ቀኝ እጁን በኤፍሬም ራስ ላይ እንዳደረገ ሲያይ ቅር ተሰኘ፤ ስለዚህ የአባቱን እጅ ከኤፍሬም ራስ ላይ አንስቶ በምናሴ ራስ ላይ ሊያደርገው ሞከረ። 18  ዮሴፍም አባቱን “አባቴ፣ እንዲህ አይደለም፤ በኩሩ እኮ ይሄኛው ነው። ቀኝ እጅህን በእሱ ራስ ላይ አድርግ” አለው። 19  አባቱ ግን “አውቄአለሁ ልጄ፣ አውቄአለሁ። እሱም ቢሆን ሕዝብ ይሆናል፤ ታላቅም ይሆናል። ይሁን እንጂ ታናሽ ወንድሙ ከእሱ የበለጠ ይሆናል፤ ዘሩም በዝቶ ብዙ ብሔር ለመሆን ይበቃል” በማለት እንቢ አለው። 20  በመሆኑም በዚያው ቀን እንዲህ ሲል እነሱን መባረኩን ቀጠለ፦ “እስራኤል በአንተ ስም እንዲህ በማለት ይባርክ፦ ‘አምላክ እንደ ኤፍሬምና እንደ ምናሴ ያድርግህ።’” በዚህ ሁኔታ ኤፍሬምን ከምናሴ አስቀደመው። 21  ከዚያም እስራኤል ዮሴፍን እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ እኔ የምሞትበት ጊዜ ቀርቧል። አምላክ ግን ከእናንተ እንደማይለይ እንዲሁም ወደ አባቶቻችሁ ምድር እንደሚመልሳችሁ የተረጋገጠ ነው። 22  በእኔ በኩል ከአሞራውያን እጅ በሰይፌና በቀስቴ የወሰድኩትን መሬት ከወንድሞችህ አንድ ድርሻ መሬት አስበልጬ ለአንተ ሰጥቼሃለሁ።”
[]
[]
[]
[]
12,547
49  ያዕቆብም ወንዶች ልጆቹን ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “በኋለኞቹ ቀናት ምን እንደሚያጋጥማችሁ እንድነግራችሁ ተሰብሰቡ። 2  እናንተ የያዕቆብ ወንዶች ልጆች ተሰብሰቡና ስሙ፤ አዎ፣ አባታችሁን እስራኤልን አዳምጡ። 3  “ሮቤል፣ አንተ የበኩር ልጄ ነህ፤ ኃይሌና የብርታቴ የመጀመሪያ ፍሬ ነህ፤ የላቀ ክብርና የላቀ ኃይል ነበረህ። 4  እንደሚናወጥ ውኃ ስለምትዋልል የበላይ አትሆንም፤ ምክንያቱም አባትህ አልጋ ላይ ወጥተሃል። በዚያን ወቅት መኝታዬን አርክሰሃል። በእርግጥም አልጋዬ ላይ ወጥቷል! 5  “ስምዖንና ሌዊ ወንድማማቾች ናቸው። ሰይፎቻቸው የዓመፅ መሣሪያዎች ናቸው። 6  ነፍሴ ሆይ፣ ከእነሱ ጋር አትወዳጂ። ክብሬ ሆይ፣ ከእነሱ ማኅበር ጋር አትተባበር፤ ምክንያቱም በቁጣ ተነሳስተው ሰዎችን ገድለዋል፤ ደስ ስላላቸውም ብቻ የበሬዎችን ቋንጃ ቆርጠዋል። 7  ቁጣቸው ጨካኝ፣ ንዴታቸውም ምሕረት የለሽ ስለሆነ የተረገመ ይሁን። በያዕቆብ ልበትናቸው፤ በእስራኤልም ላሰራጫቸው። 8  “ይሁዳ ሆይ፣ ወንድሞችህ ያወድሱሃል። እጅህ የጠላቶችህን አንገት ያንቃል። የአባትህ ወንዶች ልጆች በፊትህ ይሰግዳሉ። 9  ይሁዳ የአንበሳ ደቦል ነው። ልጄ፣ በእርግጥም ያደንከውን በልተህ ትነሳለህ። እንደ አንበሳ ያደፍጣል፤ እንደ አንበሳ ይንጠራራል፤ ማንስ ሊያስነሳው ይደፍራል? 10  ሴሎ እስኪመጣ ድረስ በትረ መንግሥት ከይሁዳ፣ የአዛዥም በትር ከእግሮቹ መካከል አይወጣም፤ ለእሱም ሕዝቦች ይታዘዙለታል። 11  አህያውን በወይን ተክል ላይ፣ ውርንጭላውንም ምርጥ በሆነ የወይን ተክል ላይ ያስራል፤ ልብሱን በወይን ጠጅ፣ መጎናጸፊያውንም በወይን ፍሬ ጭማቂ ያጥባል። 12  ዓይኖቹ ከወይን ጠጅ የተነሳ የቀሉ፣ ጥርሶቹም ከወተት የተነሳ የነጡ ናቸው። 13  “የዛብሎን መኖሪያ በባሕር ዳርቻ፣ መርከቦች መልሕቅ ጥለው በሚቆሙበት ዳርቻ ይሆናል፤ የወሰኑም ጫፍ በሲዶና አቅጣጫ ይሆናል። 14  “ይሳኮር በመንታ ጭነት መካከል የሚተኛ አጥንተ ብርቱ አህያ ነው። 15  ማረፊያ ቦታው መልካም፣ ምድሩም አስደሳች መሆኑን ያያል። ሸክሙን ለመሸከም ትከሻውን ዝቅ ያደርጋል፤ ለግዳጅ ሥራ ይንበረከካል። 16  “ከእስራኤል ነገዶች አንዱ የሆነው ዳን በሕዝቡ ላይ ይፈርዳል። 17  ዳን፣ ጋላቢው ወደ ኋላ እንዲወድቅ የፈረሱን ሰኮና የሚነክስ በመንገድ ዳር ያለ እባብ፣ በመተላለፊያ ላይ ያለ ቀንዳም እባብ ይሁን። 18  ይሖዋ ሆይ፣ የአንተን ማዳን እጠባበቃለሁ። 19  “ጋድ ደግሞ የወራሪዎች ቡድን አደጋ ይጥልበታል፤ እሱ ግን ዱካውን ተከታትሎ ይመታዋል። 20  “የአሴር ምግብ የተትረፈረፈ ይሆናል፤ በንጉሥ ፊት የሚቀርብ ምግብ ያዘጋጃል። 21  “ንፍታሌም ሸንቃጣ የሜዳ ፍየል ነው። ከአፉም ያማሩ ቃላት ይወጣሉ። 22  “ዮሴፍ ፍሬያማ የሆነ ዛፍ ቀንበጥ ነው፤ ቅርንጫፎቹን በግንብ ላይ የሚሰድ በምንጭ ዳር ያለ ፍሬያማ የሆነ ዛፍ ቀንበጥ ነው። 23  ቀስተኞች ግን እረፍት ነሱት፤ ቀስታቸውንም ወረወሩበት፤ ለእሱም ጥላቻ አደረባቸው። 24  ሆኖም ቀስቱ ከቦታው ንቅንቅ አላለም፤ እጆቹም ብርቱና ቀልጣፋ ናቸው። ይህም ከያዕቆብ ኃያል አምላክ እጆች፣ ከእረኛው፣ ከእስራኤል ዓለት የተገኘ ነው። 25  እሱ ከአባትህ አምላክ የተገኘ ነው፤ አምላክም ይረዳሃል፤ እሱም ሁሉን ቻይ ከሆነው አምላክ ጋር ይሆናል። አምላክም ከላይ ከሰማያት በሚገኙ በረከቶች፣ ከታች ከጥልቁ በሚገኙ በረከቶች እንዲሁም ከጡትና ከማህፀን በሚገኙ በረከቶች ይባርክሃል። 26  የአባትህ በረከቶች ከዘላለማዊ ተራሮች ከሚመጡት በረከቶችና ጸንተው ከሚኖሩት ኮረብቶች ከሚገኙት መልካም ነገሮች የላቁ ይሆናሉ። በረከቶቹም በዮሴፍ ራስ ላይ፣ ከወንድሞቹ መካከል ተነጥሎ በወጣው በእሱ አናት ላይ ይሆናሉ። 27  “ቢንያም እንደ ተኩላ ይቦጫጭቃል። ያደነውን ጠዋት ላይ ይበላል፤ ምሽት ላይ ደግሞ ምርኮ ያከፋፍላል።” 28  እነዚህ ሁሉ 12ቱ የእስራኤል ነገዶች ናቸው፤ አባታቸው በባረካቸው ጊዜ የነገራቸው ነገር ይህ ነው። ለእያንዳንዳቸውም የሚገባቸውን በረከት ሰጣቸው። 29  ከዚህ በኋላ የሚከተሉትን ትእዛዛት ሰጣቸው፦ “እንግዲህ እኔ ወደ ወገኖቼ ልሰበሰብ ነው። በሂታዊው በኤፍሮን እርሻ ውስጥ በሚገኘው ዋሻ ከአባቶቼ ጋር ቅበሩኝ፤ 30  አብርሃም ለመቃብር ስፍራ ብሎ ከሂታዊው ከኤፍሮን በገዛው እርሻ ይኸውም በከነአን ምድር በማምሬ ፊት ለፊት በሚገኘው በማክፈላ እርሻ ውስጥ ባለው ዋሻ ቅበሩኝ። 31  አብርሃምንና ሚስቱን ሣራን የቀበሯቸው እዚያ ነው። ይስሐቅንና ሚስቱን ርብቃንም የቀበሯቸው እዚያ ነው፤ እኔም ብሆን ሊያን የቀበርኳት እዚያው ነው። 32  እርሻውም ሆነ በውስጡ ያለው ዋሻ የተገዛው ከሄት ወንዶች ልጆች ነው።” 33  በዚህ መንገድ ያዕቆብ ለወንዶች ልጆቹ እነዚህን መመሪያዎች ሰጥቶ ጨረሰ። ከዚያም እግሮቹን ወደ አልጋው አውጥቶ የመጨረሻ እስትንፋሱን ተነፈሰ፤ ወደ ወገኖቹም ተሰበሰበ።
[]
[]
[]
[]
12,548
5  የአዳምን ታሪክ የያዘው መጽሐፍ ይህ ነው። አምላክ አዳምን በፈጠረበት ቀን፣ በአምላክ አምሳል ሠራው። 2  ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው። በተፈጠሩበትም ቀን ባረካቸው፤ እንዲሁም ሰው ብሎ ጠራቸው። 3  አዳም 130 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም እሱን የሚመስል ወንድ ልጅ በራሱ አምሳያ ወለደ፤ ስሙንም ሴት አለው። 4  አዳም ሴትን ከወለደ በኋላ 800 ዓመት ኖረ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። 5  ስለዚህ አዳም በአጠቃላይ 930 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ሞተ። 6  ሴት 105 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ሄኖስን ወለደ። 7  ሴትም ሄኖስን ከወለደ በኋላ 807 ዓመት ኖረ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። 8  ስለዚህ ሴት በአጠቃላይ 912 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ሞተ። 9  ሄኖስ 90 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ቃይናንን ወለደ። 10  ሄኖስም ቃይናንን ከወለደ በኋላ 815 ዓመት ኖረ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። 11  ስለዚህ ሄኖስ በአጠቃላይ 905 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ሞተ። 12  ቃይናን 70 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም መላልኤልን ወለደ። 13  ቃይናንም መላልኤልን ከወለደ በኋላ 840 ዓመት ኖረ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። 14  ስለዚህ ቃይናን በአጠቃላይ 910 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ሞተ። 15  መላልኤል 65 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ያሬድን ወለደ። 16  መላልኤልም ያሬድን ከወለደ በኋላ 830 ዓመት ኖረ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። 17  ስለዚህ መላልኤል በአጠቃላይ 895 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ሞተ። 18  ያሬድ 162 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ሄኖክን ወለደ። 19  ያሬድም ሄኖክን ከወለደ በኋላ 800 ዓመት ኖረ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። 20  ስለዚህ ያሬድ በአጠቃላይ 962 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ሞተ። 21  ሄኖክ 65 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ማቱሳላን ወለደ። 22  ሄኖክ ማቱሳላን ከወለደ በኋላ ለ300 ዓመት ከእውነተኛው አምላክ ጋር መሄዱን ቀጠለ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። 23  ስለዚህ ሄኖክ በአጠቃላይ 365 ዓመት ኖረ። 24  ሄኖክ ከእውነተኛው አምላክ ጋር መሄዱን ቀጠለ። አምላክ ስለወሰደውም ከዚያ በኋላ አልተገኘም። 25  ማቱሳላ 187 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ላሜህን ወለደ። 26  ማቱሳላም ላሜህን ከወለደ በኋላ 782 ዓመት ኖረ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። 27  ስለዚህ ማቱሳላ በአጠቃላይ 969 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ሞተ። 28  ላሜህ 182 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ወንድ ልጅ ወለደ። 29  እሱም “ይህ ልጅ፣ ይሖዋ በረገማት ምድር የተነሳ ከምንለፋው ልፋትና ከምንደክመው ድካም በማሳረፍ ያጽናናናል” በማለት ስሙን ኖኅ ብሎ ጠራው። 30  ላሜህም ኖኅን ከወለደ በኋላ 595 ዓመት ኖረ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። 31  ስለዚህ ላሜህ በአጠቃላይ 777 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ሞተ። 32  ኖኅ 500 ዓመት ከሆነው በኋላ ሴምን፣ ካምንና ያፌትን ወለደ።
[]
[]
[]
[]
12,549
50  ከዚያም ዮሴፍ አባቱ ላይ ተደፍቶ አለቀሰ፤ አባቱንም ሳመው። 2  በኋላም ዮሴፍ መድኃኒት ቀማሚ የሆኑ አገልጋዮቹን የአባቱን አስከሬን መድኃኒት እንዲቀቡ አዘዛቸው። መድኃኒት ቀማሚዎቹም እስራኤልን መድኃኒት ቀቡት፤ 3  ይህም 40 ቀን ሙሉ ፈጀባቸው፤ ምክንያቱም አስከሬን መድኃኒት መቀባት ይህን ያህል ጊዜ ይወስድ ነበር፤ ግብፃውያንም 70 ቀን አለቀሱለት። 4  የሐዘኑም ጊዜ ሲያበቃ ዮሴፍ የፈርዖንን ቤተ መንግሥት ባለሥልጣናት እንዲህ አላቸው፦ “በፊታችሁ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ እባካችሁ ለፈርዖን ይህን መልእክት ንገሩልኝ፦ 5  ‘አባቴ “እንግዲህ እኔ የምሞትበት ጊዜ ቀርቧል። በመሆኑም በከነአን ምድር ባዘጋጀሁት የመቃብር ስፍራ ቅበረኝ” ሲል አስምሎኛል። ስለዚህ እባክህ ልውጣና አባቴን ልቅበር፤ ከዚያም እመለሳለሁ።’” 6  ፈርዖንም “እንግዲህ ባስማለህ መሠረት ሄደህ አባትህን ቅበር” አለው። 7  በመሆኑም ዮሴፍ አባቱን ለመቅበር ወጣ፤ ከእሱም ጋር የፈርዖን አገልጋዮች በሙሉ ሄዱ፤ በቤተ መንግሥቱም ያሉ ሽማግሌዎች፣ በግብፅ ምድር የሚገኙ ሽማግሌዎች በሙሉ፣ 8  በዮሴፍ ቤት ያሉ ሁሉ፣ ወንድሞቹና የአባቱ ቤተሰቦች ሄዱ። በጎሸን ምድር የቀሩት ትናንሽ ልጆቻቸው፣ መንጎቻቸውና ከብቶቻቸው ብቻ ነበሩ። 9  ሠረገሎችና ፈረሰኞችም አብረውት ወጡ፤ ያጀበውም ሰው እጅግ ብዙ ነበር። 10  ከዚያም በዮርዳኖስ ክልል ወደሚገኘው አጣድ የተባለ አውድማ ደረሱ፤ በዚያም እየጮኹ ምርር ብለው አለቀሱ፤ እሱም ለአባቱ ሰባት ቀን ለቅሶ ተቀመጠ። 11  በዚያ የሚኖሩ ከነአናውያንም ሰዎቹ በአጣድ አውድማ ሲያለቅሱ ሲመለከቱ “መቼም ይህ ለግብፃውያን ከባድ ሐዘን መሆን አለበት!” አሉ። በዮርዳኖስ ክልል የሚገኘው የዚህ ስፍራ ስም አቤልምጽራይም የተባለው በዚህ የተነሳ ነው። 12  በመሆኑም ልጆቹ ልክ በሰጣቸው መመሪያ መሠረት አደረጉለት። 13  ወንዶች ልጆቹም ወደ ከነአን ምድር ወስደው አብርሃም ለመቃብር ቦታ ብሎ ከሂታዊው ከኤፍሮን በገዛው ከማምሬ ፊት ለፊት በሚገኘው እርሻ ማለትም በማክፈላ እርሻ ውስጥ ባለው ዋሻ ቀበሩት። 14  ዮሴፍም አባቱን ከቀበረ በኋላ ከወንድሞቹና ለአባቱ ቀብር አብረውት ከሄዱት ሁሉ ጋር ወደ ግብፅ ተመለሰ። 15  የዮሴፍ ወንድሞች አባታቸው መሞቱን ባዩ ጊዜ “ምናልባት እኮ ዮሴፍ በፈጸምንበት በደል የተነሳ ቂም ይዞ ይበቀለን ይሆናል” አሉ። 16  ስለዚህ ለዮሴፍ እንዲህ የሚል መልእክት ላኩበት፦ “አባትህ ከመሞቱ በፊት እንዲህ የሚል ትእዛዝ አስተላልፎ ነበር፦ 17  ‘ዮሴፍን እንዲህ በሉት፦ “የወንድሞችህን በደል እንዲሁም በአንተ ላይ እንዲህ ያለ ጉዳት በማድረስ የሠሩትን ኃጢአት ይቅር እንድትል እማጸንሃለሁ።”’ እናም እባክህ የአባትህን አምላክ አገልጋዮች በደል ይቅር በል።” ዮሴፍም እንዲህ ሲሉት አለቀሰ። 18  ከዚያም ወንድሞቹ መጡ፤ በፊቱም ተደፍተው በመስገድ “እኛ የአንተ ባሪያዎች ነን!” አሉት። 19  ዮሴፍም እንዲህ አላቸው፦ “አይዟችሁ አትፍሩ። ለመሆኑ እኔን በአምላክ ቦታ ያስቀመጠኝ ማን ነው? 20  ምንም እንኳ እኔን ለመጉዳት አስባችሁ የነበረ ቢሆንም አምላክ ግን ይኸው ዛሬ እንደምታዩት ነገሩን ለመልካም አደረገው፤ የብዙ ሰዎችንም ሕይወት ለማዳን ተጠቀመበት። 21  ስለሆነም አትፍሩ። ለእናንተም ሆነ ለትናንሽ ልጆቻችሁ የሚያስፈልገውን እህል እሰጣችኋለሁ።” እሱም በዚህ መንገድ አጽናናቸው፤ እንዲሁም አረጋጋቸው። 22  ዮሴፍ ከአባቱ ቤተሰቦች ጋር በግብፅ መኖሩን ቀጠለ፤ ዮሴፍም 110 ዓመት ኖረ። 23  እሱም የኤፍሬምን ወንዶች ልጆች እስከ ሦስት ትውልድ ድረስ አየ፤ እንዲሁም የምናሴን ልጅ የማኪርን ወንዶች ልጆች አየ። እነዚህ የተወለዱት በዮሴፍ ጭን ላይ ነበር። 24  ከጊዜ በኋላ ዮሴፍ ወንድሞቹን እንዲህ አላቸው፦ “እንግዲህ እኔ የምሞትበት ጊዜ ቀርቧል፤ ይሁንና አምላክ ፊቱን ወደ እናንተ እንደሚመልስ የተረጋገጠ ነው፤ ደግሞም ያለጥርጥር ከዚህ ምድር አውጥቶ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ወደማለላቸው ምድር ያስገባችኋል።” 25  በመሆኑም ዮሴፍ የእስራኤልን ወንዶች ልጆች “አምላክ ፊቱን ወደ እናንተ እንደሚመልስ ጥርጥር የለውም። አደራ፣ በዚያን ጊዜ አፅሜን ከዚህ ይዛችሁ እንድትወጡ” በማለት አስማላቸው። 26  ዮሴፍም በ110 ዓመቱ ሞተ፤ እነሱም አስከሬኑን መድኃኒት ቀቡት፤ ከዚያም በሬሳ ሣጥን ውስጥ አድርገው በግብፅ አስቀመጡት።
[]
[]
[]
[]
12,550
6  ሰዎች በምድር ላይ ቁጥራቸው እየጨመረ ሲሄድ ሴቶች ልጆችን ወለዱ፤ 2  የእውነተኛው አምላክ ልጆችም የሰዎች ሴቶች ልጆች ውብ እንደሆኑ አስተዋሉ። በመሆኑም የመረጧቸውን ሁሉ ለራሳቸው ሚስቶች አድርገው ወሰዱ። 3  ከዚያም ይሖዋ “ሰው ሥጋ ስለሆነ መንፈሴ ሰውን ለዘላለም አይታገሥም። በመሆኑም ዘመኑ 120 ዓመት ይሆናል” አለ። 4  በዚያ ዘመንም ሆነ ከዚያ በኋላ ኔፍሊም በምድር ላይ ነበሩ። በዚያ ጊዜም የእውነተኛው አምላክ ልጆች ከሰዎች ሴቶች ልጆች ጋር ግንኙነት ፈጸሙ፤ ሴቶቹም ወንዶች ልጆችን ወለዱላቸው። እነሱም በጥንት ዘመን በኃያልነታቸው ዝና ያተረፉ ሰዎች ነበሩ። 5  በዚህም የተነሳ ይሖዋ የሰው ልጅ ክፋት በምድር ላይ እንደበዛና የልቡም ሐሳብ ሁሉ ምንጊዜም ወደ መጥፎ ብቻ ያዘነበለ እንደሆነ ተመለከተ። 6  ይሖዋም ሰዎችን በምድር ላይ በመፍጠሩ ተጸጸተ፤ ልቡም አዘነ። 7  በመሆኑም ይሖዋ እንዲህ አለ፦ “የፈጠርኳቸውን ሰዎች ከምድር ገጽ ጠራርጌ አጠፋለሁ፤ ሰውን ጨምሮ የቤት እንስሳትን እንዲሁም መሬት ለመሬት የሚሄዱ እንስሳትንና በሰማያት ላይ የሚበርሩ ፍጥረታትን አጠፋለሁ፤ ምክንያቱም እነሱን በመፍጠሬ ተጸጽቻለሁ።” 8  ኖኅ ግን በይሖዋ ፊት ሞገስ አገኘ። 9  የኖኅ ታሪክ ይህ ነው። ኖኅ ጻድቅ ሰው ነበር። በዘመኑ ከነበሩት ሰዎች መካከል እሱ እንከን የሌለበት ሰው ነበር። ኖኅ ከእውነተኛው አምላክ ጋር ይሄድ ነበር። 10  ኖኅ ከጊዜ በኋላ ሴም፣ ካምና ያፌት የተባሉ ሦስት ወንዶች ልጆች ወለደ። 11  ይሁንና ምድር በእውነተኛው አምላክ ፊት ተበላሽታ ነበር፤ እንዲሁም በዓመፅ ተሞልታ ነበር። 12  አዎ፣ አምላክ ምድርን ተመለከተ፤ ምድርም ተበላሽታ ነበር፤ ሰው ሁሉ በምድር ላይ መንገዱን አበላሽቶ ነበር። 13  ከዚህ በኋላ አምላክ ኖኅን እንዲህ አለው፦ “በእነሱ የተነሳ ምድር በዓመፅ ስለተሞላች ሥጋን ሁሉ ለማጥፋት ወስኛለሁ፤ ስለሆነም እነሱን ከምድር ጋር አጠፋቸዋለሁ። 14  አንተ ከጎፈር እንጨት ለራስህ መርከብ ሥራ። በመርከቡም ውስጥ የተለያዩ ክፍሎችን ሥራ፤ እንዲሁም መርከቡን ከውስጥም ሆነ ከውጭ ቅጥራን ለቅልቀው። 15  መርከቡንም የምትሠራው እንደሚከተለው ነው፦ የመርከቡ ርዝመት 300 ክንድ፣ ወርዱ 50 ክንድ እንዲሁም ከፍታው 30 ክንድ ይሁን። 16  በመርከቡም ላይ ከጣሪያው ሥር አንድ ክንድ ቁመት ያለው ብርሃን ማስገቢያ የሚሆን መስኮት ሥራ፤ የመርከቡንም በር በጎኑ በኩል አድርግ፤ መርከቡም ምድር ቤት እንዲሁም አንደኛና ሁለተኛ ፎቅ ይኑረው። 17  “እኔ ደግሞ ከሰማያት በታች የሕይወት እስትንፋስ ያለውን ሥጋ ሁሉ ለማጥፋት በምድር ላይ የጥፋት ውኃ አመጣለሁ። በምድር ላይ ያለ ነገር ሁሉ ይጠፋል። 18  እኔም ከአንተ ጋር ቃል ኪዳኔን እመሠርታለሁ፤ አንተም ወደ መርከቡ መግባት አለብህ፤ አንተ፣ ከአንተም ጋር ወንዶች ልጆችህ፣ ሚስትህና የልጆችህ ሚስቶች ወደ መርከቡ መግባት ይኖርባችኋል። 19  ከአንተ ጋር በሕይወት እንዲተርፉ ከሁሉም ዓይነት ሕያው ፍጡር ተባዕትና እንስት እያደረግክ ሁለት ሁለት ወደ መርከቡ አስገባ፤ 20  በሕይወት እንዲተርፉ የሚበርሩ ፍጥረታት እንደየወገናቸው፣ የቤት እንስሳት እንደየወገናቸው እንዲሁም በምድር ላይ ያሉ መሬት ለመሬት የሚሄዱ እንስሳት ሁሉ እንደየወገናቸው ሁለት ሁለት እየሆኑ ከአንተ ጋር ይግቡ። 21  ለአንተም ሆነ ለእንስሳቱ ምግብ እንዲሆን ማንኛውንም ዓይነት ምግብ ሰብስበህ ይዘህ ትገባለህ።” 22  ኖኅም አምላክ ያዘዘውን ሁሉ በተባለው መሠረት አከናወነ። ልክ እንደዚሁ አደረገ።
[]
[]
[]
[]
12,551
7  ከዚህ በኋላ ይሖዋ ኖኅን እንዲህ አለው፦ “በዚህ ትውልድ መካከል በፊቴ ጻድቅ ሆነህ ያገኘሁህ አንተን ስለሆነ አንተም ሆንክ መላው ቤተሰብህ ወደ መርከቡ ግቡ። 2  ከአንተም ጋር ንጹሕ ከሆነው ከእያንዳንዱ እንስሳ ሰባት ሰባት ትወስዳለህ፤ ተባዕትና እንስት ይሁኑ፤ ንጹሕ ካልሆነው ከእያንዳንዱ እንስሳ ደግሞ ሁለት ሁለት ውሰድ፤ ተባዕትና እንስት ይሁኑ፤ 3  በተጨማሪም በመላው ምድር ላይ ዘራቸው እንዲተርፍ በሰማይ ላይ ከሚበርሩ ፍጥረታት ሰባት ሰባት አስገባ፤ ተባዕትና እንስት ይሁኑ። 4  ከሰባት ቀን በኋላ በምድር ላይ 40 ቀንና 40 ሌሊት ዝናብ አዘንባለሁ፤ የሠራሁትንም ሕይወት ያለው ነገር ሁሉ ከምድር ገጽ ጠራርጌ አጠፋለሁ።” 5  ኖኅም ይሖዋ ያዘዘውን ሁሉ አደረገ። 6  የጥፋት ውኃው በምድር ላይ በወረደበት ወቅት ኖኅ 600 ዓመቱ ነበር። 7  ኖኅም የጥፋት ውኃው ከመጀመሩ በፊት ከወንዶች ልጆቹ፣ ከሚስቱና ከልጆቹ ሚስቶች ጋር በመሆን ወደ መርከቡ ገባ። 8  እያንዳንዱ ንጹሕ እንስሳ፣ እያንዳንዱ ንጹሕ ያልሆነ እንስሳ እንዲሁም የሚበርሩ ፍጥረታትና በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱ ነገሮች ሁሉ 9  አምላክ ኖኅን ባዘዘው መሠረት ተባዕትና እንስት በመሆን ጥንድ ጥንድ እየሆኑ ኖኅ ወዳለበት ወደ መርከቡ ገቡ። 10  ከሰባት ቀን በኋላም የጥፋት ውኃው በምድር ላይ ወረደ። 11  ኖኅ በተወለደ በ600ኛው ዓመት፣ በሁለተኛው ወር ከወሩም በ17ኛው ቀን፣ በዚያ ቀን፣ ተንጣሎ የሚገኘው ጥልቅ ውኃ ምንጮች ሁሉ ተነደሉ፤ የሰማያት የውኃ በሮችም ተከፈቱ። 12  ዝናቡም ለ40 ቀንና ለ40 ሌሊት በምድር ላይ ወረደ። 13  በዚያው ቀን ኖኅ ከወንዶች ልጆቹ ከሴም፣ ከካምና ከያፌት እንዲሁም ከሚስቱና ከሦስቱ የልጆቹ ሚስቶች ጋር ወደ መርከቡ ገባ። 14  ከእነሱም ጋር እያንዳንዱ የዱር እንስሳ እንደየወገኑ፣ እያንዳንዱ የቤት እንስሳ እንደየወገኑ፣ በምድር ላይ ያለ መሬት ለመሬት የሚሄድ እያንዳንዱ እንስሳ እንደየወገኑ፣ እያንዳንዱ የሚበር ፍጥረት እንደየወገኑ እንዲሁም እያንዳንዱ ወፍና እያንዳንዱ ክንፍ ያለው ፍጡር ወደ መርከቡ ገባ። 15  የሕይወት እስትንፋስ ያለው ሁሉም ዓይነት ሕያው ፍጡር ሁለት ሁለት ሆኖ ወደ ኖኅ በመምጣት መርከቡ ውስጥ ይገባ ጀመር። 16  በመሆኑም አምላክ ኖኅን ባዘዘው መሠረት ሁሉም ዓይነት ሕያው ፍጡር ተባዕትና እንስት እየሆነ ወደ መርከቡ ገባ። ከዚያም ይሖዋ ከበስተኋላው በሩን ዘጋበት። 17  የጥፋት ውኃው ለ40 ቀን በምድር ላይ ያለማቋረጥ ወረደ። ውኃው እየጨመረ ሲሄድ መርከቡን ወደ ላይ አነሳው፤ መርከቡም መሬቱን ለቆ መንሳፈፍ ጀመረ። 18  ውኃው በምድር ላይ እያየለና በእጅጉ እየጨመረ ሄደ፤ መርከቡ ግን በውኃው ላይ መንሳፈፉን ቀጠለ። 19  ውኃው በምድር ላይ በጣም እያየለ ከመሄዱ የተነሳ ከሰማይ በታች ያሉ ረጃጅም ተራሮች በሙሉ ተሸፈኑ። 20  ውኃው ከተራሮቹ በላይ 15 ክንድ ያህል ከፍ አለ። 21  በመሆኑም በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱ ሕያዋን ፍጥረታት በሙሉ ይኸውም የሚበርሩ ፍጥረታት፣ የቤት እንስሳት፣ የዱር እንስሳት፣ የሚርመሰመሱ ፍጥረታትና ሰዎች በሙሉ ጠፉ። 22  በአፍንጫው የሕይወት እስትንፋስ የነበረው በየብስ ላይ የሚኖር ፍጡር ሁሉ ሞተ። 23  እሱም ሰውን፣ እንስሳትን፣ መሬት ለመሬት የሚሄዱ እንስሳትንና በሰማይ ላይ የሚበርሩ ፍጥረታትን ጨምሮ ሕይወት ያለውን ነገር ሁሉ ከምድር ገጽ ጠራርጎ አጠፋ። ሁሉም ከምድር ላይ ተጠራርገው ጠፉ፤ ከጥፋቱ የተረፉት ኖኅና ከእሱ ጋር በመርከቡ ውስጥ የነበሩት ብቻ ናቸው። 24  ውኃውም በምድር ላይ እንዳየለ ለ150 ቀናት ቆየ።
[]
[]
[]
[]
12,552
8  ሆኖም አምላክ ኖኅን እንዲሁም ከእሱ ጋር በመርከቡ ውስጥ የነበሩትን የዱር እንስሳትና የቤት እንስሳት ሁሉ አሰበ። አምላክም ነፋስ በምድር ላይ እንዲነፍስ አደረገ፤ ውኃውም መጉደል ጀመረ። 2  የጥልቁ ውኃ ምንጮችና የሰማያት የውኃ በሮች ተደፈኑ፤ በመሆኑም ከሰማያት የሚወርደው ዝናብ መዝነቡን አቆመ። 3  ከዚያም ውኃው ቀስ በቀስ ከምድር ላይ እየቀነሰ ሄደ። ከ150 ቀናት በኋላም ውኃው ጎደለ። 4  በሰባተኛው ወር፣ ከወሩም በ17ኛው ቀን መርከቡ በአራራት ተራሮች ላይ አረፈ። 5  ውኃውም እስከ አሥረኛው ወር ድረስ ቀስ በቀስ እየቀነሰ ሄደ። በአሥረኛው ወር፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የተራሮቹ አናት ታየ። 6  ከ40 ቀንም በኋላ ኖኅ የሠራውን የመርከቡን መስኮት ከፍቶ 7  አንድ ቁራ ወደ ውጭ ላከ፤ ቁራው ከመርከቡ ውጭ ሲበር ይቆይና ተመልሶ ይመጣ ነበር፤ ውኃው ከምድር ላይ እስኪደርቅ ድረስ እንዲሁ ያደርግ ነበር። 8  በኋላም ውኃው ከምድር ላይ መጉደሉን ለማረጋገጥ አንዲት ርግብ ላከ። 9  ርግቧ ምንም የምታርፍበት ቦታ ስላላገኘች እሱ ወደነበረበት መርከብ ተመልሳ መጣች፤ ምክንያቱም ውኃው ገና መላውን ምድር እንደሸፈነው ነበር። በመሆኑም እጁን ወደ ውጭ ዘርግቶ ተቀበላትና ወደ መርከቡ አስገባት። 10  ከዚያም ሌላ ሰባት ቀን ከጠበቀ በኋላ ርግቧን በድጋሚ ከመርከቡ አውጥቶ ለቀቃት። 11  ርግቧም አመሻሹ ላይ ወደ እሱ በመጣች ጊዜ አዲስ የተቀጠፈ ለምለም የወይራ ቅጠል በአፏ እንደያዘች አየ! ስለዚህ ኖኅ ውኃው ከምድር ላይ መጉደሉን አወቀ። 12  እንደገና ሌላ ሰባት ቀን ጠበቀ። ከዚያም ርግቧን አውጥቶ ለቀቃት፤ በዚህ ጊዜ ግን ርግቧ ወደ እሱ ተመልሳ አልመጣችም። 13  ኖኅ በተወለደ በ601ኛው ዓመት፣ በመጀመሪያው ወር፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ውኃው ከመሬቱ ላይ ሸሸ፤ ኖኅም የመርከቡን ሽፋን አንስቶ ተመለከተ፤ በዚህ ጊዜ መሬቱ ደርቆ ነበር። 14  በሁለተኛው ወር፣ ከወሩም በ27ኛው ቀን ምድሪቱ ሙሉ በሙሉ ደረቀች። 15  ከዚያም አምላክ ኖኅን እንዲህ አለው፦ 16  “አንተ፣ ሚስትህ፣ ወንዶች ልጆችህና የልጆችህ ሚስቶች ከመርከቡ ውጡ። 17  በምድር ላይ እንዲዋለዱ፣ እንዲራቡና በምድር ላይ እንዲባዙ አብሮህ ያለውን እያንዳንዱን ዓይነት ሕያው ፍጡር ሁሉ ይኸውም የሚበርሩ ፍጥረታትን፣ እንስሳትን እንዲሁም በምድር ላይ መሬት ለመሬት የሚሄዱ እንስሳትን ይዘህ ውጣ።” 18  ስለዚህ ኖኅ ከወንዶች ልጆቹ፣ ከሚስቱና ከልጆቹ ሚስቶች ጋር አብሮ ወጣ። 19  እያንዳንዱ ሕያው ፍጡር፣ መሬት ለመሬት የሚሄድ እያንዳንዱ እንስሳና እያንዳንዱ የሚበር ፍጡር እንዲሁም በምድር ላይ የሚንቀሳቀስ ማንኛውም ነገር በወገን በወገኑ እየሆነ ከመርከቡ ወጣ። 20  ከዚያም ኖኅ ለይሖዋ መሠዊያ ሠራ፤ ንጹሕ ከሆኑት እንስሳት ሁሉ እንዲሁም ንጹሕ ከሆኑት የሚበርሩ ፍጥረታት ሁሉ የተወሰኑትን ወስዶ በመሠዊያው ላይ የሚቃጠል መባ አቀረበ። 21  ይሖዋም ደስ የሚያሰኘውን መዓዛ አሸተተ። ስለዚህ ይሖዋ በልቡ እንዲህ አለ፦ “በሰው የተነሳ ከእንግዲህ ወዲህ ፈጽሞ ምድርን አልረግምም፤ ምክንያቱም የሰው የልብ ዝንባሌ ከልጅነቱ ጀምሮ መጥፎ ነው፤ ደግሞም አሁን እንዳደረግኩት ሕያው ፍጡርን ሁሉ ፈጽሞ ዳግመኛ አላጠፋም። 22  ከአሁን ጀምሮ በምድር ላይ ዘር መዝራትና ማጨድ፣ ቅዝቃዜና ሙቀት፣ በጋና ክረምት እንዲሁም ቀንና ሌሊት ፈጽሞ አይቋረጡም።”
[]
[]
[]
[]
12,553
9  አምላክም ኖኅንና ወንዶች ልጆቹን ባረካቸው፤ እንዲህም አላቸው፦ “ብዙ ተባዙ፤ ምድርንም ሙሏት። 2  አስፈሪነታችሁና አስደንጋጭነታችሁ በምድር ላይ ባለ በእያንዳንዱ ሕያው ፍጡር፣ በሰማያት ላይ በሚበር በእያንዳንዱ ፍጡር እንዲሁም በመሬት ላይ በሚንቀሳቀስ ማንኛውም ፍጡርና በባሕር ውስጥ ባለ ዓሣ ሁሉ ላይ ይሁን። ይኸው ሁሉም በእጃችሁ ውስጥ እንዲሆኑ ተሰጥተዋል። 3  በሕይወት የሚንቀሳቀስ እያንዳንዱ እንስሳ ምግብ ይሁናችሁ። የለመለመውን ተክል እንደሰጠኋችሁ ሁሉ እነዚህን በሙሉ ሰጥቻችኋለሁ። 4  ሕይወቱ ማለትም ደሙ በውስጡ ያለበትን ሥጋ ብቻ አትብሉ። 5  ከዚህም በተጨማሪ ሕይወታችሁ የሆነውን ደማችሁን የሚያፈሰውን ሁሉ ተጠያቂ አደርገዋለሁ። እያንዳንዱን ሕያው ፍጡር ተጠያቂ አደርገዋለሁ፤ እያንዳንዱንም ሰው ለወንድሙ ሕይወት ተጠያቂ አደርገዋለሁ። 6  አምላክ ሰውን በአምሳሉ ስለሠራው የሰውን ደም የሚያፈስ ማንም ሰው የእሱም ደም በሰው እጅ ይፈስሳል። 7  እናንተ ግን ብዙ ተባዙ፤ ቁጥራችሁም በምድር ላይ እጅግ ይጨምር፤ ደግሞም ተባዙ።” 8  አምላክም ኖኅንና ከእሱ ጋር ያሉትን ወንዶች ልጆቹን እንዲህ አላቸው፦ 9  “እኔም አሁን፣ ከእናንተና ከእናንተ በኋላ ከሚመጡት ዘሮቻችሁ ጋር ቃል ኪዳኔን እመሠርታለሁ፤ 10  እንዲሁም ከእናንተ ጋር ካለው ከእያንዳንዱ ሕያው ፍጡር ማለትም ከወፎች፣ ከእንስሳት፣ አብረዋችሁ በምድር ላይ ከሚኖሩት ሕያዋን ፍጥረታት በሙሉ እንዲሁም ከመርከቡ ከወጡት ሁሉ ጋር ይኸውም በምድር ላይ ከሚገኝ ከእያንዳንዱ ሕያው ፍጡር ጋር ቃል ኪዳኔን እመሠርታለሁ። 11  አዎ፣ ከእንግዲህ ሥጋ ሁሉ በጥፋት ውኃ እንደማይጠፋ እንዲሁም የጥፋት ውኃ ከእንግዲህ ወዲህ ምድርን ፈጽሞ እንደማያጠፋት ከእናንተ ጋር ቃል ኪዳኔን እመሠርታለሁ።” 12  በተጨማሪም አምላክ እንዲህ አለ፦ “በእኔና በእናንተ እንዲሁም ከእናንተ ጋር ባለው በእያንዳንዱ ሕያው ፍጡር መካከል ለመሠረትኩት ቃል ኪዳን ምልክቱ ይህ ነው፤ ይህም ቃል ኪዳን በመጪዎቹ ትውልዶች ሁሉ ጸንቶ ይኖራል። 13  ቀስተ ደመናዬን በደመናው ላይ አደርጋለሁ፤ ይህም በእኔና በምድር መካከል ላለው ቃል ኪዳን ምልክት ሆኖ ያገለግላል። 14  ምድርን በደመና በጋረድኩ ጊዜ ሁሉ ቀስተ ደመናው በደመናው ላይ ይታያል። 15  እኔም ከእናንተ እንዲሁም ከማንኛውም ዓይነት ሕያው ፍጡር ሁሉ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን አስታውሳለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሥጋን ሁሉ ለማጥፋት የጥፋት ውኃ ፈጽሞ አይወርድም። 16  ቀስተ ደመናው በደመናው ላይ ይታያል፤ እኔም እሱን በማይበት ጊዜ በአምላክና በምድር ላይ በሚኖር በማንኛውም ዓይነት ሕያው ፍጡር መካከል ያለውን ዘላለማዊ ቃል ኪዳን አስታውሳለሁ።” 17  አምላክም “በእኔና በምድር ላይ በሚኖር ሥጋ ሁሉ መካከል ለመሠረትኩት ቃል ኪዳን ምልክቱ ይህ ነው” በማለት ለኖኅ በድጋሚ ነገረው። 18  ከመርከቡ የወጡት የኖኅ ወንዶች ልጆች ሴም፣ ካምና ያፌት ናቸው። ከጊዜ በኋላ ካም፣ ከነአንን ወለደ። 19  የኖኅ ወንዶች ልጆች እነዚህ ሦስቱ ነበሩ፤ የምድር ሕዝብ ሁሉ የተገኘው ከእነሱ ሲሆን በኋላም ወደተለያየ አካባቢ ተሰራጨ። 20  ኖኅም ገበሬ ሆነ፤ የወይን እርሻም አለማ። 21  አንድ ቀን ኖኅ የወይን ጠጅ ጠጥቶ ሰከረ፤ በድንኳኑም ውስጥ ራቁቱን ሆነ። 22  የከነአን አባት ካምም የአባቱን እርቃን አየ፤ ውጭ ላሉት ሁለት ወንድሞቹም ነገራቸው። 23  ስለዚህ ሴምና ያፌት ልብስ ወስደው ትከሻቸው ላይ በማድረግ የኋሊት እየተራመዱ ገቡ። በዚህ መንገድም ፊታቸውን ወደ አባታቸው ሳያዞሩ እርቃኑን ሸፈኑ፤ በመሆኑም የአባታቸውን እርቃን አላዩም። 24  ኖኅ ከወይን ጠጅ ስካሩ ሲነቃ ታናሽ ልጁ ያደረገበትን አወቀ፤ 25  እንዲህም አለ፦ “ከነአን የተረገመ ይሁን። ለወንድሞቹም የባሪያ ባሪያ ይሁን።” 26  በተጨማሪም እንዲህ አለ፦ “የሴም አምላክ ይሖዋ ይወደስ፤ከነአንም የእሱ ባሪያ ይሁን። 27  አምላክ ለያፌት ሰፊ መሬት ይስጠው፤በሴም ድንኳኖች ውስጥም ይኑር። ከነአን ለእሱም ጭምር ባሪያ ይሁን።” 28  ኖኅ ከጥፋት ውኃው በኋላ 350 ዓመት ኖረ። 29  በመሆኑም ኖኅ በአጠቃላይ 950 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ሞተ።
[]
[]
[]
[]
12,554
1  ሙሴ በዮርዳኖስ ክልል በሚገኘው ምድረ በዳ ይኸውም በፋራን፣ በጦፌል፣ በላባ፣ በሃጼሮት እና በዲዛሃብ መካከል ከሚገኘው ከሱፈ ፊት ለፊት ባለው በረሃማ ሜዳ ላይ ለነበሩት እስራኤላውያን በሙሉ የተናገረው ቃል ይህ ነው። 2  ወደ ሴይር ተራራ በሚወስደው መንገድ በኩል ከኮሬብ እስከ ቃዴስበርኔ የ11 ቀን መንገድ ነው። 3  በ40ኛው ዓመት፣ በ11ኛው ወር፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ሙሴ ለእስራኤላውያን እንዲነግራቸው ይሖዋ ባዘዘው መሠረት ነገራቸው። 4  ይህን ያደረገው በሃሽቦን ይኖር የነበረውን የአሞራውያንን ንጉሥ ሲሖንን ድል ካደረገና በአስታሮት ይኖር የነበረውን የባሳንን ንጉሥ ኦግን ኤድራይ ላይ ካሸነፈ በኋላ ነው። 5  በዮርዳኖስ ክልል፣ በሞዓብ ምድር ሙሴ ይህን ሕግ እንዲህ በማለት ያብራራ ጀመር፦ 6  “ይሖዋ አምላካችን በኮሬብ እንዲህ አለን፦ ‘በዚህ ተራራማ አካባቢ ለረጅም ጊዜ ቆይታችኋል። 7  ተነስታችሁ ወደ አሞራውያን ተራራማ አካባቢ እንዲሁም በአረባ፣ በተራራማው አካባቢ፣ በሸፌላ፣ በኔጌብ እና በባሕሩ ዳርቻ ወደሚገኙት ጎረቤቶቻቸው ሁሉ ብሎም ወደ ከነአናውያን ምድርና ወደ ሊባኖስ በመጓዝ እስከ ታላቁ ወንዝ ማለትም እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ሂዱ። 8  እነሆ በፊታችሁ ይህችን ምድር አስቀምጫለሁ። ይሖዋ ለአባቶቻችሁ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ እንዲሁም ከእነሱ በኋላ ለሚመጡት ዘሮቻቸው ሊሰጣቸው የማለላቸውን ምድር ገብታችሁ ውረሱ።’ 9  “እኔም በዚያን ጊዜ እንዲህ አልኳችሁ፦ ‘እኔ ብቻዬን እናንተን ልሸከማችሁ አልችልም። 10  ይሖዋ አምላካችሁ ቁጥራችሁን አብዝቶታል፤ ይኸው ዛሬ ከብዛታችሁ የተነሳ በሰማያት ላይ እንዳሉ ከዋክብት ሆናችኋል። 11  የአባቶቻችሁ አምላክ ይሖዋ ሺህ ጊዜ ያብዛችሁ፤ ደግሞም በገባላችሁ ቃል መሠረት ይባርካችሁ። 12  ይሁንና እኔ ብቻዬን የእናንተን ሸክምና ጫና እንዲሁም ጠብ እንዴት መሸከም እችላለሁ? 13  ከየነገዶቻችሁ ጥበበኛና አስተዋይ የሆኑ እንዲሁም ተሞክሮ ያካበቱ ወንዶችን ምረጡ፤ እኔም በእናንተ ላይ መሪ አድርጌ እሾማቸዋለሁ።’ 14  እናንተም ‘አድርጉ ያልከን ነገር መልካም ነው’ በማለት መለሳችሁልኝ። 15  እኔም ጥበበኛ የሆኑትንና ተሞክሮ ያካበቱትን የየነገዳችሁን መሪዎች ወስጄ የሺህ አለቆች፣ የመቶ አለቆች፣ የሃምሳ አለቆችና የአሥር አለቆች እንዲሁም የየነገዶቻችሁ ሹማምንት አድርጌ በእናንተ ላይ ሾምኳቸው። 16  “በዚያን ጊዜ ለዳኞቻችሁ ይህን መመሪያ ሰጠኋቸው፦ ‘በወንድሞቻችሁ መካከል የተፈጠረን አንድ ጉዳይ በምትሰሙበት ጊዜ በሰውየውና በወንድሙ ወይም በባዕድ አገሩ ሰው መካከል በጽድቅ ፍረዱ። 17  በምትፈርዱበት ጊዜ አታዳሉ። ትንሹንም ሆነ ትልቁን እኩል ስሙ። ፍርድ የአምላክ ስለሆነ ሰውን አትፍሩ፤ አንድ ጉዳይ ከከበዳችሁ ወደ እኔ አምጡት፤ እኔም እሰማዋለሁ።’ 18  በዚያን ጊዜ ማድረግ ስላለባችሁ ነገር ሁሉ መመሪያ ሰጠኋችሁ። 19  “ከዚያም ይሖዋ አምላካችን ባዘዘን መሠረት ከኮሬብ በመነሳት ያን ያያችሁትን ጭልጥ ያለና የሚያስፈራ ምድረ በዳ አቋርጠን ወደ አሞራውያን ተራራማ አካባቢዎች በሚወስደው መንገድ ተጓዝን፤ በመጨረሻም ቃዴስበርኔ ደረስን። 20  እኔም እንዲህ አልኳችሁ፦ ‘አምላካችን ይሖዋ ወደሚሰጠን ወደ አሞራውያን ተራራማ አካባቢዎች ደርሳችኋል። 21  ይኸው አምላካችሁ ይሖዋ ምድሪቱን ለእናንተ ሰጥቷችኋል። የአባቶቻችሁ አምላክ ይሖዋ በነገራችሁ መሠረት ተነሱና ውረሷት። አትፍሩ ወይም አትሸበሩ።’ 22  “ሆኖም እናንተ ሁላችሁም ወደ እኔ መጥታችሁ እንዲህ አላችሁኝ፦ ‘ምድሪቱን እንዲሰልሉልን እንዲሁም በየትኛው መንገድ መሄድ እንደሚኖርብንና ምን ዓይነት ከተሞች እንደሚያጋጥሙን አይተው እንዲነግሩን ሰዎችን አስቀድመን እንላክ።’ 23  ይህም ሐሳብ መልካም መስሎ ታየኝ፤ በመሆኑም ከእያንዳንዱ ነገድ አንድ አንድ ሰው ይኸውም ከመካከላችሁ 12 ሰዎችን መረጥኩ። 24  እነሱም ተነስተው ወደ ተራራማው አካባቢ ሄዱ፤ እስከ ኤሽኮል ሸለቆ ድረስ በመዝለቅም ምድሪቱን ሰለሉ። 25  ምድሪቱ ከምታፈራው ፍሬም የተወሰነ ይዘው ወደ እኛ መጡ፤ እንዲሁም ‘አምላካችን ይሖዋ የሚሰጠን ምድር መልካም ናት’ ብለው ነገሩን። 26  እናንተ ግን ወደዚያ ለመውጣት ፈቃደኞች አልሆናችሁም፤ በአምላካችሁ በይሖዋ ትእዛዝም ላይ ዓመፃችሁ። 27  በየድንኳኖቻችሁ ውስጥ ሆናችሁ እንዲህ በማለት አጉተመተማችሁ፦ ‘ይሖዋ ስለጠላን አሞራውያን እንዲያጠፉን ለእነሱ አሳልፎ ሊሰጠን ከግብፅ ምድር አወጣን። 28  ታዲያ የምንሄደው ወዴት ነው? ወንድሞቻችን “ሰዎቹ ከእኛ ይልቅ ብርቱና ረጃጅሞች ናቸው፤ ከተሞቻቸውም ቢሆኑ ታላላቅና እስከ ሰማይ በሚደርስ ቅጥር የታጠሩ ናቸው፤ እንዲያውም በዚያ የኤናቅን ልጆች አይተናል” በማለት ልባችን እንዲቀልጥ አድርገዋል።’ 29  “በመሆኑም እኔ እንዲህ አልኳችሁ፦ ‘በእነሱ የተነሳ በፍርሃት አትራዱ ወይም አትሸበሩ። 30  አምላካችሁ ይሖዋ በፊታችሁ ይሄዳል፤ የገዛ ዓይናችሁ እያየ በግብፅ እንዳደረገው ሁሉ አሁንም ይዋጋላችኋል። 31  በምድረ በዳም ተጉዛችሁ እዚህ እስክትደርሱ ድረስ አንድ አባት ልጁን እንደሚሸከም አምላካችሁ ይሖዋም በሄዳችሁበት ሁሉ እንዴት እንደተሸከማችሁ አይታችኋል።’ 32  እናንተ ግን ይህ ሁሉ ተደርጎላችሁም በአምላካችሁ በይሖዋ ላይ እምነት አላሳደራችሁም፤ 33  እሱ የምትሰፍሩበትን ቦታ ለመፈለግ ከፊት ከፊታችሁ ይሄድ ነበር። በየትኛው መንገድ መሄድ እንዳለባችሁ ለማሳየትም ሌሊት ሌሊት በእሳት፣ ቀን ቀን ደግሞ በደመና ይመራችሁ ነበር። 34  “በዚህ ጊዜ ይሖዋ ያላችሁትን ሰማ፤ ተቆጥቶም እንዲህ ሲል ማለ፦ 35  ‘ለአባቶቻችሁ ለመስጠት የማልኩላቸውን መልካሚቱን ምድር ከዚህ ክፉ ትውልድ መካከል አንድም ሰው አያያትም፤ 36  ከየፎኒ ልጅ ከካሌብ በስተቀር ማንም አያያትም። እሱ ያያታል፤ ይሖዋን በሙሉ ልቡ ስለተከተለም የረገጣትን ምድር ለእሱና ለልጆቹ እሰጣታለሁ። 37  (ይሖዋ በእናንተ የተነሳ በእኔም ላይ እንኳ ተቆጥቶ እንዲህ አለኝ፦ “አንተም ብትሆን ወደዚያ አትገባም። 38  ወደ ምድሪቱ የሚገባው በፊትህ የሚቆመው የነዌ ልጅ ኢያሱ ነው። እስራኤላውያን ምድሪቱን እንዲወርሱ የሚያደርገው እሱ ስለሆነ አበርታው።”) 39  በተጨማሪም ለምርኮ ይዳረጋሉ ያላችኋቸው ልጆቻችሁ እንዲሁም ዛሬ ክፉና ደጉን የማያውቁት ወንዶች ልጆቻችሁ ወደዚያ ይገባሉ፤ እኔም ምድሪቱን እንዲወርሷት ለእነሱ እሰጣታለሁ። 40  እናንተ ግን አቅጣጫ በመቀየር ወደ ቀይ ባሕር በሚወስደው መንገድ አድርጋችሁ ወደ ምድረ በዳው ሂዱ።’ 41  “እናንተም በዚህ ጊዜ እንዲህ አላችሁኝ፦ ‘በይሖዋ ላይ ኃጢአት ሠርተናል። በቃ፣ አምላካችን ይሖዋ ባዘዘን መሠረት ወጥተን እንዋጋለን!’ በመሆኑም እያንዳንዳችሁ የጦር መሣሪያዎቻችሁን ታጠቃችሁ፤ ወደ ተራራው መውጣት ቀላል መስሎ ታይቷችሁ ነበር። 42  ይሁንና ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ ‘እንዲህ በላቸው፦ “እኔ አብሬያችሁ ስለማልሆን ወጥታችሁ ውጊያ እንዳትገጥሙ። እንዲህ ብታደርጉ ግን ጠላቶቻችሁ ድል ያደርጓችኋል።”’ 43  እኔም ነገርኳችሁ፤ እናንተ ግን አልሰማችሁም። ከዚህ ይልቅ በይሖዋ ትእዛዝ ላይ በማመፅ በእብሪት ወደ ተራራው ለመውጣት ሞከራችሁ። 44  ከዚያም በተራራው ላይ ይኖሩ የነበሩት አሞራውያን እናንተን ለመግጠም ወጡ፤ እነሱም ልክ እንደ ንብ እየተከታተሉ አሳደዷችሁ፤ ከሴይር አንስቶ እስከ ሆርማ ድረስም በታተኗችሁ። 45  ስለሆነም ተመልሳችሁ በይሖዋ ፊት ማልቀስ ጀመራችሁ፤ ሆኖም ይሖዋ ጩኸታችሁን አልሰማም፤ ጆሮውንም አልሰጣችሁም። 46  እነዚያን ሁሉ ቀናት በቃዴስ የተቀመጣችሁትም ለዚህ ነው።
[]
[]
[]
[]
12,555
10  “በዚያን ጊዜ ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ ‘እንደ መጀመሪያዎቹ ያሉ ሁለት የድንጋይ ጽላቶችን ጠርበህ ወደ እኔ ወደ ተራራው ውጣ፤ የእንጨት ታቦትም ለራስህ ሥራ። 2  እኔም በጽላቶቹ ላይ አንተ በሰበርካቸው በመጀመሪያዎቹ ጽላቶች ላይ የነበሩትን ቃላት እጽፋለሁ፤ አንተም ጽላቶቹን በታቦቱ ውስጥ አስቀምጣቸው።’ 3  ስለዚህ ከግራር እንጨት ታቦት ሠራሁ፤ ከዚያም እንደ መጀመሪያዎቹ ያሉ የድንጋይ ጽላቶችን ከቀረጽኩ በኋላ ሁለቱን ጽላቶች ይዤ ወደ ተራራው ወጣሁ። 4  እሱም በጽላቶቹ ላይ ቀደም ሲል ጽፏቸው የነበሩትን ቃላት ይኸውም ተሰብስባችሁ በነበረበት ቀን ይሖዋ በተራራው ላይ በእሳት ውስጥ ሆኖ ለእናንተ ነግሯችሁ የነበሩትን አሥርቱን ትእዛዛት ጻፈባቸው፤ ይሖዋም ጽላቶቹን ለእኔ ሰጠኝ። 5  እኔም ተመልሼ ከተራራው ወረድኩ፤ ይሖዋም ባዘዘኝ መሠረት ጽላቶቹን፣ በሠራሁት ታቦት ውስጥ አስቀመጥኳቸው። እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ ይገኛሉ። 6  “ከዚያም እስራኤላውያን ከበኤሮት ብኔያዕቃን ተነስተው ወደ ሞሴራ ሄዱ። አሮንም በዚያ ቦታ ሞቶ ተቀበረ፤ ልጁ አልዓዛርም በእሱ ምትክ ካህን ሆኖ ማገልገል ጀመረ። 7  ከዚያም ተነስተው ወደ ጉድጎዳ ተጓዙ፤ ከጉድጎዳም ተነስተው ጅረቶች ወደሚፈስሱባት ምድር ወደ ዮጥባታ ሄዱ። 8  “በዚያን ጊዜ ይሖዋ፣ የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት እንዲሸከም፣ ይሖዋን ለማገልገል በፊቱ እንዲቆምና እስከ ዛሬ እንደሚያደርገው በስሙ እንዲባርክ የሌዊን ነገድ ለየ። 9  ሌዊ ከወንድሞቹ ጋር ድርሻ ወይም ርስት የሌለው ለዚህ ነው። አምላክህ ይሖዋ በነገረው መሠረት ይሖዋ ርስቱ ነው። 10  እኔም እንደ መጀመሪያው ጊዜ ሁሉ በተራራው ላይ ለ40 ቀንና ለ40 ሌሊት ቆየሁ፤ በዚህ ጊዜም ደግሞ ይሖዋ ሰማኝ። ይሖዋ ሊያጠፋህ አልፈለገም። 11  ከዚያም ይሖዋ ‘ለአባቶቻቸው ለመስጠት የማልኩላቸውን ምድር ገብተው እንዲወርሱ ተነስና ከሕዝቡ ፊት ፊት ሂድ’ አለኝ። 12  “እንግዲህ እስራኤል ሆይ፣ አምላክህ ይሖዋ ከአንተ የሚፈልገው ምንድን ነው? አምላክህን ይሖዋን እንድትፈራው፣ በመንገዶቹ ሁሉ እንድትሄድ፣ እንድትወደው፣ አምላክህን ይሖዋን በሙሉ ልብህና በሙሉ ነፍስህ እንድታገለግለው 13  እንዲሁም ለገዛ ጥቅምህ ስትል እኔ ዛሬ የማዝህን የይሖዋን ትእዛዛትና ደንቦች እንድትጠብቅ ብቻ ነው። 14  እነሆ ሰማያት፣ ሌላው ቀርቶ ሰማየ ሰማያት እንዲሁም ምድርና በውስጧ ያለው ነገር ሁሉ የአምላክህ የይሖዋ ናቸው። 15  ይሁንና ይሖዋ የቀረበውና ፍቅሩን የገለጸው ለአባቶችህ ብቻ ነው፤ ስለሆነም ይኸው ዛሬ እንደሆነው የእነሱ ዘር የሆናችሁትን እናንተን ከሕዝቦች ሁሉ መካከል መረጠ። 16  ስለዚህ ልባችሁን አንጹ፤ ከእንግዲህም ወዲህ ግትር መሆናችሁን ተዉ። 17  ምክንያቱም አምላካችሁ ይሖዋ የአማልክት አምላክና የጌቶች ጌታ እንዲሁም ታላቅ፣ ኃያል፣ የሚያስፈራ፣ ለማንም የማያዳላና ጉቦ የማይቀበል አምላክ ነው። 18  አባት ለሌለው ልጅና ለመበለት ይፈርዳል፤ እንዲሁም የባዕድ አገሩን ሰው ይወደዋል፤ ምግብና ልብስም ይሰጠዋል። 19  እናንተም የባዕድ አገሩን ሰው ውደዱ፤ ምክንያቱም በግብፅ ምድር ሳላችሁ የባዕድ አገር ሰው ነበራችሁ። 20  “አምላክህን ይሖዋን ፍራ፤ አገልግለው፤ ከእሱም ጋር ተጣበቅ፤ በስሙም ማል። 21  ልታወድሰው የሚገባህ እሱን ነው። እሱ በዓይኖችህ ያየሃቸውን እነዚያን ታላላቅና አስፈሪ ነገሮች ሁሉ ያደረገልህ አምላክህ ነው። 22  አባቶችህ ወደ ግብፅ ሲወርዱ 70 ነበሩ፤ አሁን ግን አምላክህ ይሖዋ በሰማያት ላይ እንዳሉ ከዋክብት ቁጥርህን አብዝቶታል።
[]
[]
[]
[]
12,556
11  “አንተም አምላክህን ይሖዋን ውደድ፤ ለእሱ ያለብህንም ግዴታ ምንጊዜም ተወጣ፤ እንዲሁም ደንቦቹን፣ ድንጋጌዎቹንና ትእዛዛቱን ሁልጊዜ ጠብቅ። 2  ዛሬ እየተናገርኩ ያለሁት ለእናንተ እንጂ የአምላካችሁን የይሖዋን ተግሣጽ፣ የእሱን ታላቅነት፣ የእሱን ብርቱ እጅና የተዘረጋ ክንድ ላላወቁት ወይም ላላዩት ለልጆቻችሁ እንዳልሆነ ታውቃላችሁ። 3  እነሱ በግብፅ ይኸውም በግብፁ ንጉሥ በፈርዖን ፊትና በመላው ምድሩ ላይ ያሳየውን ተአምራዊ ምልክትም ሆነ ያደረገውን ነገር አልተመለከቱም፤ 4  ወይም እናንተን እያሳደዱ ሳሉ በቀይ ባሕር ውስጥ በሰጠሙት በግብፅ ሠራዊት፣ በፈርዖን ፈረሶችና የጦር ሠረገሎች ላይ ያደረገውን አላዩም፤ ይሖዋም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አጠፋቸው። 5  እናንተ እዚህ ቦታ እስክትደርሱ ድረስ በምድረ በዳ ያደረገላችሁን ነገር አልተመለከቱም፤ 6  ወይም ደግሞ የሮቤል ልጅ የኤልያብ ልጆች የሆኑትን ዳታንን እና አቤሮንን፣ ቤተሰቦቻቸውን፣ ድንኳኖቻቸውንና ከእነሱ ጋር ያበረውን ማንኛውንም ሕያው ፍጡር እስራኤላውያን ሁሉ እያዩ ምድር ተከፍታ በዋጠቻቸው ጊዜ በእነሱ ላይ ያደረገውን ነገር አልተመለከቱም። 7  እናንተ፣ ይሖዋ ያደረጋቸውን ታላላቅ ሥራዎች በሙሉ በገዛ ዓይናችሁ አይታችኋል። 8  “ብርታት እንድታገኙና ወደምትወርሷት ምድር ተሻግራችሁ እንድትገቡ ዛሬ የምሰጣችሁን ትእዛዛት በሙሉ ጠብቁ፤ 9  ይሖዋ ለአባቶቻችሁና ለዘሮቻቸው ለመስጠት በማለላቸው ወተትና ማር በምታፈሰው ምድር ላይ ዕድሜያችሁ እንዲረዝም እነዚህን ትእዛዛት በሙሉ ጠብቁ። 10  “የምትወርሳት ምድር ዘር ትዘራባት እንዲሁም ልክ እንደ አትክልት ስፍራ በእግርህ በመስኖ ታጠጣት እንደነበረችው እንደወጣህባት እንደ ግብፅ ምድር አይደለችም። 11  ከዚህ ይልቅ ተሻግራችሁ የምትወርሷት ምድር ተራሮችና ሸለቋማ ሜዳዎች ያሉባት ምድር ናት። የሰማይን ዝናብ የምትጠጣ ምድር ናት፤ 12  አምላክህ ይሖዋ የሚንከባከባት ምድር ናት። የአምላክህም የይሖዋ ዓይን ከዓመቱ መጀመሪያ እስከ መጨረሻው ድረስ ዘወትር በእሷ ላይ ነው። 13  “እኔ ዛሬ የማዛችሁን ትእዛዛቴን በትጋት ብትፈጽሙ፣ አምላካችሁን ይሖዋን ብትወዱት እንዲሁም በሙሉ ልባችሁና በሙሉ ነፍሳችሁ ብታገለግሉት፣ 14  እኔ ደግሞ ለምድራችሁ በወቅቱ ዝናብን ይኸውም የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ እሰጣለሁ፤ አንተም እህልህን፣ አዲስ የወይን ጠጅህንና ዘይትህን ትሰበስባለህ። 15  ለእንስሶችህም በሜዳህ ላይ ዕፀዋት አበቅልልሃለሁ፤ አንተም በልተህ ትጠግባለህ። 16  ልባችሁ እንዳይታለልና ዞር ብላችሁ ሌሎች አማልክትን እንዳታመልኩ እንዲሁም እንዳትሰግዱላቸው ተጠንቀቁ። 17  አለዚያ የይሖዋ ቁጣ በእናንተ ላይ ይነድዳል፤ ዝናብ ዘንቦ ምድሪቱ ምርት እንዳትሰጥ ሰማያትን ይዘጋል፤ እናንተም ይሖዋ ከሚሰጣችሁ መልካም ምድር ፈጥናችሁ ትጠፋላችሁ። 18  “እነዚህን ቃሎቼን በልባችሁና በነፍሳችሁ ላይ አትሟቸው፤ በእጃችሁም ላይ እንደ ማስታወሻ እሰሯቸው፤ በግንባራችሁም ላይ እንደታሰረ ነገር ይሁኑ። 19  በቤታችሁ ስትቀመጡ፣ በመንገድ ላይ ስትሄዱ፣ ስትተኙና ስትነሱ ስለ እነሱ በመናገር ለልጆቻችሁ አስተምሯቸው። 20  በቤታችሁ መቃኖችና በግቢያችሁ በሮች ላይ ጻፏቸው፤ 21  ይህን ካደረጋችሁ ሰማይ ከምድር በላይ እስካለ ድረስ ይሖዋ ለአባቶቻችሁ ለመስጠት በማለላቸው ምድር ላይ የእናንተም ሆነ የልጆቻችሁ ዕድሜ ይረዝማል። 22  “አምላካችሁን ይሖዋን እንድትወዱ፣ በመንገዶቹ ሁሉ እንድትሄዱና ከእሱ ጋር እንድትጣበቁ የሰጠኋችሁን እነዚህን ሁሉ ትእዛዛት በጥብቅ ብትከተሉና ብትፈጽሟቸው 23  ይሖዋም እነዚህን ሁሉ ብሔራት ከፊታችሁ ያባርራቸዋል፤ እናንተም ከእናንተ ይልቅ ታላቅ የሆኑትንና ብዙ ሕዝብ ያላቸውን ብሔራት ታስለቅቃላችሁ። 24  እግራችሁ የረገጠው ቦታ ሁሉ የእናንተ ይሆናል። ወሰናችሁም ከምድረ በዳው አንስቶ እስከ ሊባኖስ እንዲሁም ከወንዙ ይኸውም ከኤፍራጥስ ወንዝ አንስቶ በስተ ምዕራብ እስካለው ባሕር ድረስ ይሆናል። 25  ማንም ሰው ሊቋቋማችሁ አይችልም። አምላካችሁ ይሖዋም ቃል በገባላችሁ መሠረት በምትረግጡት ምድር ሁሉ ላይ ሽብርና ፍርሃት ይለቃል። 26  “እንግዲህ ዛሬ ይህን በረከትና እርግማን በፊታችሁ አስቀምጫለሁ፦ 27  እኔ ዛሬ የማዛችሁን የአምላካችሁን የይሖዋን ትእዛዛት ከፈጸማችሁ በረከቱን ታገኛላችሁ፤ 28  የአምላካችሁን የይሖዋን ትእዛዛት ካልፈጸማችሁና እኔ ዛሬ እንድትከተሉት ከማዛችሁ መንገድ ዞር በማለት የማታውቋቸውን አማልክት ከተከተላችሁ ግን እርግማኑ ይደርስባችኋል። 29  “አምላካችሁ ይሖዋ ርስት አድርጋችሁ ወደምትወርሷት ምድር በሚያስገባችሁ ጊዜ በረከቱን በገሪዛን ተራራ ላይ እርግማኑን ደግሞ በኤባል ተራራ ላይ ታውጃላችሁ። 30  እነዚህ ተራሮች የሚገኙት ከዮርዳኖስ በስተ ምዕራብ፣ በአረባ በሚኖሩት በከነአናውያን ምድር ከጊልጋል ትይዩ በሞሬ ትላልቅ ዛፎች አጠገብ አይደለም? 31  አሁን አምላካችሁ ይሖዋ የሚሰጣችሁን ምድር ገብታችሁ ለመውረስ ዮርዳኖስን ልትሻገሩ ነው። እንግዲህ ምድሪቱን ወርሳችሁ በእሷ ላይ ስትኖሩ 32  ዛሬ በፊታችሁ ያስቀመጥኳቸውን ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች በሙሉ በጥንቃቄ ፈጽሙ።
[]
[]
[]
[]
12,557
12  “የአባቶቻችሁ አምላክ ይሖዋ እንድትወርሷት በሚሰጣችሁ ምድር ላይ በሕይወት በምትኖሩበት ዘመን ሁሉ በጥንቃቄ ልትፈጽሟቸው የሚገቡ ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች እነዚህ ናቸው። 2  ከምድራቸው የምታስለቅቋቸው ብሔራት አማልክታቸውን ያመልኩባቸው የነበሩትን ቦታዎች በሙሉ፣ በረጃጅም ተራሮችም ሆነ በኮረብቶች ላይ ወይም በተንዠረገጉ ዛፎች ሥር ያሉትን ስፍራዎች ሙሉ በሙሉ አጥፉ። 3  መሠዊያዎቻቸውን አፈራርሱ፤ የማምለኪያ ዓምዶቻቸውን አድቅቁ፤ የማምለኪያ ግንዶቻቸውንም በእሳት አቃጥሉ፤ የአማልክታቸውን የተቀረጹ ምስሎች ሰባብራችሁ ጣሉ፤ ስማቸውንም ከዚያ ስፍራ ሙሉ በሙሉ ደምስሱ። 4  “እነሱ አማልክታቸውን በሚያመልኩበት መንገድ አምላካችሁን ይሖዋን አታምልኩ። 5  ከዚህ ይልቅ በነገዶቻችሁ ሁሉ መካከል ስሙን ሊያጸናበትና ማደሪያ ስፍራው ሊያደርገው በሚመርጠው በማንኛውም ቦታ አምላካችሁን ይሖዋን ፈልጉ፤ ወደዚያም ስፍራ ሂዱ። 6  የሚቃጠሉ መባዎቻችሁን፣ መሥዋዕቶቻችሁን፣ አሥራቶቻችሁን፣ ከእጃችሁ የሚዋጣውን መዋጮ፣ የስእለት መባዎቻችሁን፣ የፈቃደኝነት መባዎቻችሁን እንዲሁም የከብታችሁንና የመንጋችሁን በኩራት የምትወስዱት ወደዚያ ስፍራ ነው። 7  እናንተም ሆናችሁ ቤተሰቦቻችሁ በዚያ በአምላካችሁ በይሖዋ ፊት ብሉ፤ አምላካችሁ ይሖዋ ስለባረካችሁ በሥራችሁ ሁሉ ተደሰቱ። 8  “ዛሬ እዚህ እያደረግን እንዳለነው እያንዳንዳችሁ በራሳችሁ አመለካከት ትክክል መስሎ የታያችሁን ማድረግ የለባችሁም፤ 9  ምክንያቱም አሁን ይህን የምታደርጉት ወደምታርፉበት ቦታና አምላካችሁ ይሖዋ ወደሚሰጣችሁ ርስት ገና ስላልገባችሁ ነው። 10  ዮርዳኖስን በምትሻገሩበትና አምላካችሁ ይሖዋ ርስት አድርጎ በሚሰጣችሁ ምድር ላይ በምትኖሩበት ጊዜ በዙሪያችሁ ካሉ ጠላቶቻችሁ ሁሉ ያሳርፋችኋል፤ እናንተም ያለስጋት ትቀመጣላችሁ። 11  የማዛችሁንም ነገር በሙሉ ይኸውም የሚቃጠሉ መባዎቻችሁን፣ መሥዋዕቶቻችሁን፣ አሥራቶቻችሁን፣ የእጃችሁን መዋጮና ለይሖዋ የተሳላችሁትን ማንኛውንም የስእለት መባ አምላካችሁ ይሖዋ ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን ወደሚመርጠው ስፍራ ታመጣላችሁ። 12  እናንተ፣ ወንዶች ልጆቻችሁ፣ ሴቶች ልጆቻችሁ፣ ወንድ ባሪያዎቻችሁ፣ ሴት ባሪያዎቻችሁ እንዲሁም በከተሞቻችሁ ውስጥ የሚኖሩ ሌዋውያን በአምላካችሁ በይሖዋ ፊት ትደሰታላችሁ፤ ምክንያቱም ሌዋውያኑ በእናንተ መካከል ድርሻም ሆነ ውርሻ የላቸውም። 13  የሚቃጠሉ መባዎችህን በፈለግከው በየትኛውም ቦታ እንዳታቀርብ ተጠንቀቅ። 14  ከዚህ ይልቅ የሚቃጠሉ መባዎችህን ይሖዋ በሚመርጠው የነገዶችህ ይዞታ በሆነው ቦታ ብቻ አቅርብ፤ በዚያም እኔ የማዝህን ነገር ሁሉ አድርግ። 15  “አምላክህ ይሖዋ በሰጠህ በረከት መጠን በከተሞችህ ሁሉ አንተን ባሰኘህ በማንኛውም ጊዜ እንስሳትን አርደህ ሥጋ መብላት ትችላለህ። የሜዳ ፍየልና ርኤም እንደምትበላ ሁሉ ንጹሕ ያልሆነውም ሆነ ንጹሕ የሆነው ሰው ሊበላው ይችላል። 16  ደሙን ግን እንዳትበሉ፤ ከዚህ ይልቅ እንደ ውኃ መሬት ላይ አፍሱት። 17  የእህልህን፣ የአዲሱን የወይን ጠጅህንና የዘይትህን አንድ አሥረኛ፣ የከብትህንና የመንጋህን በኩር፣ የምትሳለውን ማንኛውንም የስእለት መባ፣ የፈቃደኝነት መባዎችህን ወይም የእጅህን መዋጮ በከተሞችህ ውስጥ እንድትበላ አይፈቀድልህም። 18  እነዚህንም አንተ፣ ወንድ ልጅህ፣ ሴት ልጅህ፣ ወንድ አገልጋይህ፣ ሴት አገልጋይህ እንዲሁም በከተሞችህ የሚኖሩ ሌዋውያን አምላክህ ይሖዋ በሚመርጠው ስፍራ በአምላክህ በይሖዋ ፊት ትበሏቸዋላችሁ፤ አንተም በሥራህ ሁሉ በአምላክህ በይሖዋ ፊት ትደሰታለህ። 19  በምድርህ ላይ በሕይወት እስካለህ ድረስ ሌዋውያንን ቸል እንዳትል ተጠንቀቅ። 20  “አምላክህ ይሖዋ ቃል በገባልህ መሠረት ግዛትህን በሚያሰፋልህ ጊዜ ሥጋ መብላት ፈልገህ ‘ሥጋ አማረኝ’ ብትል ባሰኘህ ጊዜ ሁሉ ሥጋ ብላ። 21  አምላክህ ይሖዋ ስሙ እንዲኖርበት የሚመርጠው ስፍራ አንተ ካለህበት የራቀ ከሆነ ይሖዋ ከሰጠህ ከከብትህ ወይም ከመንጋህ መካከል እኔ ባዘዝኩህ መሠረት አርደህ ባሰኘህ ጊዜ ሁሉ በከተሞችህ ውስጥ ብላ። 22  የሜዳ ፍየልንና ርኤምን እንደምትበላው ሁሉ ይህንም ልትበላው ትችላለህ፤ ንጹሕ ያልሆነውም ሆነ ንጹሕ የሆነው ሰው ሊበላው ይችላል። 23  ብቻ ደሙን እንዳትበሉ ተጠንቀቁ፤ ምክንያቱም ደም ሕይወት ነው፤ ሕይወትን ደግሞ ከሥጋ ጋር መብላት የለብህም። 24  ደሙን ፈጽሞ እንዳትበላ። ከዚህ ይልቅ እንደ ውኃ መሬት ላይ አፍስሰው። 25  ደሙን አትብላ፤ ምክንያቱም እንዲህ ስታደርግ በይሖዋ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር ትፈጽማለህ፤ ይህን የምታደርገው ለአንተም ሆነ ከአንተ በኋላ ለሚመጡት ልጆችህ መልካም እንዲሆንላችሁ ነው። 26  ይሖዋ ወደሚመርጠው ስፍራ ስትመጣ የአንተ የሆኑትን ቅዱስ ነገሮችና የስእለት መባዎችህን ብቻ መያዝ ይኖርብሃል። 27  የሚቃጠሉ መባዎችህን፣ ሥጋውንና ደሙን በአምላክህ በይሖዋ መሠዊያ ላይ ታቀርባለህ፤ የመሥዋዕቶችህም ደም በአምላክህ በይሖዋ መሠዊያ ላይ መፍሰስ ይኖርበታል፤ ሥጋውን ግን መብላት ትችላለህ። 28  “እኔ የማዝህን እነዚህን ቃላት በሙሉ በጥንቃቄ ፈጽም፤ ምክንያቱም እንዲህ ስታደርግ በአምላክህ በይሖዋ ፊት መልካምና ትክክል የሆነውን ትፈጽማለህ፤ ይህን የምታደርገው ለአንተም ሆነ ከአንተ በኋላ ለሚመጡት ልጆችህ ምንጊዜም መልካም እንዲሆንላችሁ ነው። 29  “ከምድራቸው የምታስለቅቃቸውን ብሔራት አምላክህ ይሖዋ ሲያጠፋቸውና በምድራቸው ላይ ስትኖር 30  እነሱ ከጠፉ በኋላ በእነሱ እንዳትጠመድ ተጠንቀቅ። ‘እነዚህ ብሔራት አማልክታቸውን ያመልኩ የነበረው እንዴት ነው? ቆይ እኔም እንደ እነሱ አደርጋለሁ’ ብለህ ስለ አማልክታቸው አትጠይቅ። 31  አንተ በአምላክህ በይሖዋ ላይ ይህን ማድረግ የለብህም፤ ምክንያቱም እነሱ ይሖዋ የሚጠላውን አስጸያፊ ነገር ሁሉ ለአማልክታቸው ያደርጋሉ፤ ሌላው ቀርቶ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ለአማልክታቸው በእሳት ያቃጥላሉ። 32  እናንተ እኔ የማዛችሁን እያንዳንዱን ነገር በጥንቃቄ ፈጽሙ። በእሱ ላይ ምንም አትጨምሩ፤ ከእሱም ላይ ምንም አትቀንሱ።
[]
[]
[]
[]
12,558
13  “አንድ ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ከመካከልህ ተነስቶ ተአምራዊ ምልክት ወይም ድንቅ ነገር እንደሚያሳይ ቢነግርህና 2  የነገረህ ተአምራዊ ምልክት ወይም ድንቅ ነገር ቢፈጸም፣ እሱም ‘ሌሎች አማልክትን ይኸውም አንተ የማታውቃቸውን አማልክት እንከተል፤ እናገልግላቸውም’ ቢልህ፣ 3  የዚያን ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ቃል እንዳትሰማ፤ ምክንያቱም አምላካችሁ ይሖዋ በሙሉ ልባችሁና በሙሉ ነፍሳችሁ አምላካችሁን ይሖዋን ትወዱት እንደሆነና እንዳልሆነ ለማወቅ እየፈተናችሁ ነው። 4  እናንተ አምላካችሁን ይሖዋን ተከተሉ፤ እሱን ፍሩ፤ ትእዛዛቱን ጠብቁ፤ ቃሉን ስሙ፤ እሱን አገልግሉ፤ እንዲሁም እሱን አጥብቃችሁ ያዙ። 5  ያ ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ግን ይገደል፤ ምክንያቱም አምላካችሁ ይሖዋ እንድትሄዱበት ካዘዛችሁ መንገድ ዞር እንድትሉ፣ ከግብፅ ምድር ባወጣችሁና ከባርነት ቤት በታደጋችሁ በአምላካችሁ በይሖዋ ላይ እንድታምፁ አበረታቷችኋል። አንተም ክፉውን ከመካከልህ አስወግድ። 6  “የእናትህ ልጅ ወንድምህ ወይም ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ አሊያም የምትወዳት ሚስትህ ወይም የቅርብ ጓደኛህ ‘ሌሎች አማልክትን እናምልክ’ በማለት በሚስጥር ሊያባብልህ ቢሞክርና እነዚህ አማልክት ደግሞ አንተም ሆንክ አባቶችህ የማታውቋቸው 7  እንዲሁም በቅርብም ሆነ በሩቅ፣ ከአንዱ የምድር ጫፍ እስከ ሌላኛው የምድር ጫፍ የሚገኙ በዙሪያህ ያሉ ሕዝቦች የሚያመልኳቸው አማልክት ቢሆኑ 8  እሺ አትበለው ወይም አትስማው አሊያም አትዘንለት ወይም ደግሞ አትራራለት፤ ከለላም አትሁነው፤ 9  ከዚህ ይልቅ ያለማመንታት ግደለው። እሱን ለመግደል መጀመሪያ እጅህን መሰንዘር ያለብህ አንተ ነህ፤ ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ እጁን ይሰንዝርበት። 10  ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ካወጣህ ከአምላክህ ከይሖዋ ዞር እንድትል ሊያደርግህ ስለሞከረ እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ውገረው። 11  ከዚያም እስራኤላውያን ሁሉ ሰምተው ይፈራሉ፤ በመካከልህም እንዲህ ያለ መጥፎ ነገር ዳግመኛ አያደርጉም። 12  “አምላክህ ይሖዋ እንድትኖርባቸው ከሚሰጥህ ከተሞች በአንዱ ውስጥ እንዲህ ሲባል ትሰማ ይሆናል፦ 13  ‘እናንተ የማታውቋቸውን “ሌሎች አማልክት ሄደን እናምልክ” እያሉ የከተማቸውን ነዋሪዎች ለማሳት የሚሞክሩ የማይረቡ ሰዎች ከመካከልህ ተነስተዋል’፤ 14  በዚህ ጊዜ ጉዳዩን በጥልቀት በመመርመርና በማጣራት ስለ ሁኔታው ማወቅ ይኖርብሃል፤ ይህ አስጸያፊ ነገር በመካከልህ ተፈጽሞ ከሆነና ነገሩ እውነት መሆኑ ከተረጋገጠ 15  የከተማዋን ነዋሪዎች በሰይፍ ግደላቸው። እንስሶቿን ጨምሮ ከተማዋንና በውስጧ ያለውን ነገር ሁሉ በሰይፍ ሙሉ በሙሉ አጥፋ። 16  ከዚያም በከተማዋ ውስጥ የተገኘውን ምርኮ በሙሉ በአደባባይዋ ላይ ሰብስብ፤ ከተማዋን በእሳት አቃጥል፤ በውስጧ የተገኘው ምርኮ ደግሞ ለአምላክህ ለይሖዋ ሙሉ በሙሉ የሚቀርብ መባ ይሆናል። እሷም ለዘላለም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች። ፈጽሞ ተመልሳ አትገነባም። 17  ይሖዋ ከሚነድ ቁጣው እንዲመለስ፣ ለአባቶችህ በማለላቸው መሠረት ምሕረት እንዲያደርግልህና እንዲራራልህ እንዲሁም እንዲያበዛህ ከፈለግክ፣ እንዲጠፉ ከተለዩት ነገሮች መካከል እጅህ ምንም አይውሰድ። 18  እኔ ዛሬ የምሰጥህን የእሱን ትእዛዛት በሙሉ በመጠበቅ አምላክህን ይሖዋን ታዘዝ፤ በዚህ መንገድ በአምላክህ በይሖዋ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር ታደርጋለህ።
[]
[]
[]
[]
12,559
14  “እናንተ የአምላካችሁ የይሖዋ ልጆች ናችሁ። ለሞተ ሰው ብላችሁ ሰውነታችሁን አትተልትሉ፤ ቅንድባችሁንም አትላጩ። 2  ምክንያቱም አንተ ለአምላክህ ለይሖዋ ቅዱስ ሕዝብ ነህ፤ ይሖዋም በምድር ላይ ካሉ ሕዝቦች ሁሉ መካከል አንተን የራሱ ሕዝብ፣ ልዩ ንብረቱ እንድትሆን መርጦሃል። 3  “ማንኛውንም አስጸያፊ ነገር አትብላ። 4  የምትበሏቸው እንስሳት እነዚህ ናቸው፦ በሬ፣ በግ፣ ፍየል፣ 5  ርኤም፣ የሜዳ ፍየል፣ ድኩላ፣ የዱር ፍየል፣ አጋዘን፣ የዱር በግ እና የተራራ በግ። 6  ለሁለት የተከፈለ የተሰነጠቀ ሰኮና ያለውን እንዲሁም የሚያመሰኳውን ማንኛውንም እንስሳ መብላት ትችላላችሁ። 7  ሆኖም ከሚያመሰኩት ወይም የተሰነጠቀ ሰኮና ካላቸው እንስሳት መካከል እነዚህን አትብሉ፦ ግመል፣ ጥንቸልና ሽኮኮ፤ ምክንያቱም እነዚህ እንስሳት ቢያመሰኩም ሰኮናቸው ስንጥቅ አይደለም። እነሱ ለእናንተ ርኩስ ናቸው። 8  አሳማም እንደዚሁ ነው፤ ምክንያቱም ሰኮናው ስንጥቅ ቢሆንም አያመሰኳም። ለእናንተ ርኩስ ነው። ሥጋቸውን መብላትም ሆነ በድናቸውን መንካት የለባችሁም። 9  “በውኃ ውስጥ ከሚኖሩ መካከል እነዚህን መብላት ትችላላችሁ፦ ክንፍና ቅርፊት ያላቸውን ሁሉ መብላት ትችላላችሁ። 10  ሆኖም ክንፍና ቅርፊት የሌለውን ማንኛውንም ነገር አትብሉ። ለእናንተ ርኩስ ነው። 11  “ንጹሕ የሆነውን ወፍ ሁሉ መብላት ትችላላችሁ። 12  እነዚህን ግን አትብሉ፦ ንስር፣ ዓሣ በል ጭላት፣ ጥቁር ጥምብ አንሳ፣ 13  ቀይ ጭልፊትም ሆነ ጥቁር ጭልፊት እንዲሁም ሁሉንም ዓይነት ሌሎች ጭልፊቶች፣ 14  ማንኛውንም ዓይነት ቁራ፣ 15  ሰጎን፣ ጉጉት፣ ዓሣ አዳኝ ወፍ፣ ማንኛውንም ዓይነት ሲላ፣ 16  ትንሿ ጉጉት፣ ባለ ረጅም ጆሮ ጉጉት፣ ዝይ፣ 17  ሻላ፣ ጥምብ አንሳ፣ ለማሚት፣ 18  ራዛ፣ ማንኛውንም ዓይነት ሽመላ፣ ጅንጅላቴና የሌሊት ወፍ። 19  በተጨማሪም ክንፍ ያላቸው የሚርመሰመሱ ፍጥረታት በሙሉ ለእናንተ ርኩስ ናቸው። መበላት የለባቸውም። 20  ንጹሕ የሆነን ማንኛውንም የሚበር ፍጥረት መብላት ትችላላችሁ። 21  “ሞቶ የተገኘን ማንኛውንም እንስሳ አትብሉ። ከዚህ ይልቅ በከተሞችህ ውስጥ ለሚኖር የባዕድ አገር ሰው ልትሰጠውና እሱ ሊበላው ይችላል፤ አሊያም ለባዕድ አገር ሰው ሊሸጥ ይችላል። ምክንያቱም አንተ ለአምላክህ ለይሖዋ ቅዱስ ሕዝብ ነህ። “የፍየልን ጠቦት በእናቱ ወተት አትቀቅል። 22  “በየዓመቱ ከእርሻህ ላይ ከምታገኘው ምርት ሁሉ አንድ አሥረኛውን መስጠት አለብህ። 23  ዘወትር አምላክህን ይሖዋን መፍራትን እንድትማር የእህልህን፣ የአዲስ የወይን ጠጅህንና የዘይትህን አንድ አሥረኛ እንዲሁም የከብትህንና የመንጋህን በኩራት በአምላክህ በይሖዋ ፊት ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን በሚመርጠው ስፍራ ብላ። 24  “ሆኖም አምላክህ ይሖዋ ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን የሚመርጠው ስፍራ አንተ ካለህበት ቦታ ሩቅ ከመሆኑ የተነሳ መንገዱ በጣም ቢረዝምብህና (አምላክህ ይሖዋ ስለባረከህ) እዚያ ድረስ ተሸክመኸው መሄድ ባትችል 25  ወደ ገንዘብ ልትቀይረው ትችላለህ፤ ገንዘቡንም ይዘህ አምላክህ ይሖዋ ወደሚመርጠው ስፍራ ሂድ። 26  ከዚያም በገንዘቡ የምትሻውን ነገር ይኸውም ከብት፣ በግ፣ ፍየል፣ የወይን ጠጅ፣ ሌላ የሚያሰክር መጠጥና የሚያስደስትህን ማንኛውንም ነገር መግዛት ትችላለህ፤ አንተና ቤተሰብህም በአምላክህ በይሖዋ ፊት በዚያ ብሉ፤ ተደሰቱም። 27  በከተሞችህ ውስጥ የሚኖረውን ሌዋዊ ችላ አትበለው፤ ምክንያቱም እሱ ከአንተ ጋር ድርሻም ሆነ ውርሻ የለውም። 28  “በየሦስት ዓመቱ መጨረሻ ላይ በዚያ ዓመት ያገኘኸውን ምርት አንድ አሥረኛ በሙሉ አምጥተህ በከተሞችህ ውስጥ አከማች። 29  አምላክህ ይሖዋ የእጅህን ሥራ ሁሉ እንዲባርክልህ ከአንተ ጋር ድርሻም ሆነ ውርሻ የሌለው ሌዋዊ እንዲሁም በከተሞችህ ውስጥ የሚኖሩት የባዕድ አገር ሰዎች፣ አባት የሌላቸው ልጆችና መበለቶች መጥተው እስኪጠግቡ ድረስ ይብሉ።
[]
[]
[]
[]
12,560
15  “በየሰባት ዓመቱ መጨረሻ የሌሎችን ዕዳ መሰረዝ ይኖርብሃል። 2  ዕዳ የሚሰረዘው በሚከተለው መንገድ ነው፦ እያንዳንዱ አበዳሪ ባልንጀራው ያለበትን ዕዳ ይሰርዝለታል። ከባልንጀራው ወይም ከወንድሙ ክፍያ መጠየቅ የለበትም፤ ምክንያቱም ለይሖዋ ሲባል ዕዳ እንዲሰረዝ ይታወጃል። 3  ከባዕድ አገር ሰው ክፍያ መጠየቅ ትችላለህ፤ ወንድምህ ለአንተ መመለስ ያለበትን ማንኛውንም ነገር ግን ተውለት። 4  ይሁንና አምላክህ ይሖዋ ርስት አድርገህ እንድትወርሳት በሚሰጥህ ምድር ላይ ይሖዋ ስለሚባርክህ ከእናንተ መካከል ማንም ድሃ አይሆንም፤ 5  ይህ የሚሆነው ግን የአምላክህን የይሖዋን ቃል በትኩረት የምትሰማና እኔ ዛሬ የምሰጥህን ትእዛዛት በሙሉ በጥንቃቄ የምትፈጽም ከሆነ ነው። 6  አምላክህ ይሖዋ በገባልህ ቃል መሠረት ይባርክሃልና፤ አንተም ለብዙ ብሔራት ታበድራለህ እንጂ አትበደርም፤ ብዙ ብሔራትን ትገዛለህ እንጂ አንተን አይገዙህም። 7  “ከወንድሞችህ መካከል አንዱ አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህ ምድር ከሚገኙት ከተሞች በአንዱ ውስጥ ድሃ ቢሆን በድሃው ወንድምህ ላይ ልብህ አይጨክንበት ወይም እጅህን አትጠፍበት። 8  ከዚህ ይልቅ በልግስና እጅህን ዘርጋለት፤ በተቻለ መጠን፣ የሚያስፈልገውን ወይም የጎደለውን ማንኛውንም ነገር አበድረው። 9  ‘ዕዳ የሚሰረዝበት ሰባተኛው ዓመት ቀርቧል’ የሚል ክፉ ሐሳብ በልብህ አድሮ ለድሃው ወንድምህ ከመለገስ ወደኋላ እንዳትልና ምንም ሳትሰጠው እንዳትቀር ተጠንቀቅ። እሱ በአንተ ላይ ቅር ተሰኝቶ ወደ ይሖዋ ቢጮኽ ኃጢአት ይሆንብሃል። 10  በልግስና ስጠው፤ ስትሰጠው ልብህ ቅር እያለው መሆን የለበትም፤ ምክንያቱም አምላክህ ይሖዋ በሥራህ ሁሉና በምታከናውነው በማንኛውም ነገር የሚባርክህ በዚህ የተነሳ ነው። 11  መቼም ቢሆን ከምድሪቱ ላይ ድሆች አይጠፉምና። ‘በምድርህ ላይ ለሚኖር ጎስቋላና ድሃ ወንድምህ በልግስና እጅህን ዘርጋለት’ በማለት ያዘዝኩህ ለዚህ ነው። 12  “ከወንድሞችህ አንዱ ይኸውም አንድ ዕብራዊ ወይም አንዲት ዕብራዊ፣ ለአንተ ቢሸጥና ስድስት ዓመት ቢያገለግልህ በሰባተኛው ዓመት ነፃ አውጣው። 13  ነፃ የምታወጣው ከሆነ ባዶ እጁን አትስደደው። 14  ከመንጋህና ከአውድማህ እንዲሁም ከዘይትና ከወይን መጭመቂያህ በልግስና ስጠው። አምላክህ ይሖዋ በባረከህ መጠን ስጠው። 15  አንተም በግብፅ ምድር ባሪያ እንደነበርክና አምላክህ ይሖዋ እንደተቤዠህ አስታውስ። እኔ ዛሬ ይህን እንድታደርግ የማዝህ ለዚህ ነው። 16  “ሆኖም ይህ ሰው ከአንተ ጋር በነበረበት ጊዜ ደስተኛ ስለነበር አንተንና ቤተሰብህን በመውደድ ‘ፈጽሞ ከአንተ አልለይም!’ ቢልህ 17  ጆሮውን በር ላይ አስደግፈህ በወስፌ ብሳው፤ እሱም ዕድሜ ልኩን የአንተ ባሪያ ይሆናል። ሴት ባሪያህንም በተመለከተ እንደዚሁ አድርግ። 18  ባሪያህን ነፃ አድርጎ ማሰናበት ሊከብድህ አይገባም፤ ምክንያቱም እሱ በስድስት ዓመት ውስጥ የሰጠህ አገልግሎት በቅጥር ሠራተኛ ደሞዝ ቢሰላ እጥፍ ዋጋ ያስወጣህ ነበር፤ ደግሞም አምላክህ ይሖዋ በምትሠራው ነገር ሁሉ ባርኮሃል። 19  “ከከብትህና ከመንጋህ መካከል በኩር የሆነውን ወንድ ሁሉ ለአምላክህ ለይሖዋ ቀድሰው። በከብትህ በኩር ምንም ሥራ አትሥራበት፤ የመንጋህንም በኩር አትሸልት። 20  አንተም ሆንክ ቤተሰብህ ይሖዋ በሚመርጠው ስፍራ በየዓመቱ በአምላክህ በይሖዋ ፊት ብሉት። 21  ይሁንና እንስሳው እንከን ካለበት ይኸውም አንካሳ ወይም ዕውር ከሆነ አሊያም ሌላ ዓይነት ከባድ ጉድለት ካለበት ለአምላክህ ለይሖዋ መሥዋዕት አድርገህ አታቅርበው። 22  በከተሞችህ ውስጥ ብላው፤ እንደ ሜዳ ፍየል ወይም እንደ ርኤም ሁሉ ንጹሕ ያልሆነውም ሆነ ንጹሕ የሆነው ሰው ሊበላው ይችላል። 23  ሆኖም ደሙን አትብላ፤ እንደ ውኃ መሬት ላይ አፍስሰው።
[]
[]
[]
[]
12,561
16  “አምላክህ ይሖዋ ከግብፅ በሌሊት ያወጣህ በአቢብ ወር ስለሆነ የአቢብን ወር አስብ፤ እንዲሁም ለአምላክህ ለይሖዋ ፋሲካን አክብር። 2  ይሖዋ ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን በመረጠው ስፍራ ከመንጋህና ከከብትህ ለአምላክህ ለይሖዋ የፋሲካን መባ ሠዋ። 3  ከእሱም ጋር እርሾ የገባበት ምንም ነገር አትብላ፤ ከግብፅ ምድር የወጣኸው በጥድፊያ ስለነበር ለሰባት ቀን ቂጣ ይኸውም የመከራ ቂጣ ብላ። ይህን የምታደርገው ከግብፅ ምድር የወጣህበትን ዕለት በሕይወት ዘመንህ ሁሉ እንድታስታውስ ነው። 4  ለሰባት ቀን በግዛትህ ሁሉ እርሾ አይገኝ፤ በመጀመሪያው ቀን ምሽት ላይ ከምታቀርበው መሥዋዕት ላይም ቢሆን ምንም ሥጋ ማደር የለበትም። 5  የፋሲካውን መባ አምላክህ ይሖዋ ከሚሰጥህ ከተሞች አንተ በፈለግከው በአንዱ ውስጥ መሠዋት አይገባህም። 6  ከዚህ ይልቅ አምላክህ ይሖዋ ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን በሚመርጠው ስፍራ መቅረብ ይኖርበታል። የፋሲካውን መባ ምሽት ላይ ፀሐይ እንደጠለቀች፣ ከግብፅ በወጣህበት በዚያው ጊዜ ሠዋው። 7  አምላክህ ይሖዋ በሚመርጠው ቦታ አብስለህ ብላው፤ ሲነጋም ተመልሰህ ወደ ድንኳንህ መሄድ ትችላለህ። 8  ለስድስት ቀን ቂጣ ብላ፤ በሰባተኛውም ቀን ለአምላክህ ለይሖዋ የተቀደሰ ጉባኤ ይሆናል። ምንም ሥራ አትሥራ። 9  “ሰባት ሳምንት ቁጠር። በማሳህ ላይ ያለውን እህል ለማጨድ ማጭድህን ካነሳህበት ጊዜ አንስቶ ሰባት ሳምንት ቁጠር። 10  ከዚያም አምላክህ ይሖዋ በባረከህ መጠን በምታቀርበው የፈቃደኝነት መባ አማካኝነት ለአምላክህ ለይሖዋ የሳምንታት በዓልን ታከብራለህ። 11  በአምላክህ በይሖዋ ፊት ደስ ይበልህ፤ አንተም ሆንክ ወንድ ልጅህ፣ ሴት ልጅህ፣ ወንድ ባሪያህ፣ ሴት ባሪያህ እንዲሁም በከተሞችህ ውስጥ የሚኖር ሌዋዊ፣ በመካከልህ የሚኖር የባዕድ አገር ሰው፣ አባት የሌለው ልጅና መበለቲቱ አምላክህ ይሖዋ ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን በመረጠው ስፍራ ደስ ይበላችሁ። 12  አንተም በግብፅ ባሪያ እንደነበርክ አስታውስ፤ እነዚህንም ሥርዓቶች ጠብቅ እንዲሁም ፈጽም። 13  “እህልህን ከአውድማህ፣ ዘይትህንና የወይን ጠጅህን ከመጭመቂያህ በምታስገባበት ጊዜ የዳስ በዓልን ለሰባት ቀን አክብር። 14  በዓልህን በምታከብርበት ወቅት ደስ ይበልህ፤ አንተም ሆንክ ወንድ ልጅህ፣ ሴት ልጅህ፣ ወንድ ባሪያህ፣ ሴት ባሪያህ እንዲሁም በከተሞችህ ውስጥ የሚኖር ሌዋዊ፣ የባዕድ አገር ሰው፣ አባት የሌለው ልጅና መበለቲቱ ደስ ይበላችሁ። 15  አምላክህ ይሖዋ ምርትህንና የእጅህን ሥራ ሁሉ ስለሚባርክልህ ይሖዋ በመረጠው ስፍራ ለአምላክህ ለይሖዋ ሰባት ቀን በዓሉን ታከብራለህ፤ አንተም እጅግ ትደሰታለህ። 16  “በመካከልህ ያሉ ወንዶች ሁሉ በዓመት ሦስት ጊዜ ይኸውም በቂጣ በዓል ቀን፣ በሳምንታት በዓል ቀን እንዲሁም በዳስ በዓል ቀን አምላክህ ይሖዋ በመረጠው ስፍራ ፊቱ ይቅረቡ፤ ማናቸውም ባዶ እጃቸውን ይሖዋ ፊት አይቅረቡ። 17  እያንዳንዱ ሰው የሚያመጣው ስጦታ አምላክህ ይሖዋ በባረከህ መጠን መሆን አለበት። 18  “አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህ ከተሞች ሁሉ ለእያንዳንዱ ነገድ ዳኞችንና አለቆችን ሹም፤ እነሱም ለሕዝቡ የጽድቅ ፍርድ ይፍረዱ። 19  ፍርድን አታዛባ፤ አድልዎ አትፈጽም ወይም ጉቦ አትቀበል፤ ምክንያቱም ጉቦ የጥበበኞችን ዓይን ያሳውራል፤ የጻድቃንንም ቃል ያጣምማል። 20  በሕይወት እንድትኖርና አምላክህ ይሖዋ የሚሰጥህን ምድር እንድትወርስ ፍትሕን፣ አዎ ፍትሕን ተከታተል። 21  “ለአምላክህ ለይሖዋ በምትሠራው መሠዊያ አጠገብ የማምለኪያ ግንድ እንዲሆን ማንኛውንም ዓይነት ዛፍ አትትከል። 22  “አምላክህ ይሖዋ አጥብቆ የሚጠላውን የማምለኪያ ዓምድ ለራስህ አታቁም።
[]
[]
[]
[]
12,562
17  “እንከን ወይም ማንኛውም ዓይነት ጉድለት ያለበትን በሬ ወይም በግ ለአምላክህ ለይሖዋ አትሠዋ፤ ምክንያቱም ይህ ለአምላክህ ለይሖዋ አስጸያፊ ነው። 2  “አምላክህ ይሖዋ ከሚሰጥህ ከተሞች በአንዱ ውስጥ በአምላክህ በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር የሚፈጽምና ቃል ኪዳኑን የሚያፈርስ ወንድ ወይም ሴት ቢገኝ 3  እሱም ሄዶ ሌሎች አማልክትን በማምለክ እንዲሁም ለእነሱ ወይም ለፀሐይ አሊያም ለጨረቃ ወይም ደግሞ ለሰማይ ሠራዊት በሙሉ በመስገድ እኔ ያላዘዝኩትን ነገር ቢያደርግ 4  አንተም ይህ ነገር ቢነገርህ ወይም ሁኔታውን ብትሰማ ጉዳዩን በጥንቃቄ አጣራ። ይህ አስጸያፊ ነገር በእስራኤል ውስጥ መፈጸሙ እውነት እንደሆነ ቢረጋገጥ 5  እንዲህ ያለ መጥፎ ድርጊት የፈጸመውን ያንን ሰው ወይም ያቺን ሴት ወደ ከተማዋ በር አውጣቸው፤ ከዚያም ሰውየው ወይም ሴትየዋ እስኪሞቱ ድረስ በድንጋይ ይወገሩ። 6  ሞት የሚገባው ሰው ሁለት ወይም ሦስት ሰዎች በሚሰጡት ምሥክርነት ይገደል። አንድ ምሥክር በሚሰጠው ቃል ብቻ መገደል የለበትም። 7  እሱን ለመግደል መጀመሪያ እጃቸውን የሚያነሱት ምሥክሮቹ መሆን ይኖርባቸዋል፤ ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ እጁን ያንሳበት። ክፉ የሆነውን ከመካከልህ አስወግድ። 8  “ከከተሞችህ በአንዱ ውስጥ ለመዳኘት አስቸጋሪ የሆነ ክርክር ቢነሳ ለምሳሌ፣ ጉዳዩ ደም ማፍሰስን የሚመለከትም ይሁን ለሕግ አቤቱታ ማቅረብን ወይም የዓመፅ ድርጊትን አሊያም ሌሎች አለመግባባቶችን የሚመለከት ቢሆን ተነስተህ አምላክህ ይሖዋ ወደሚመርጠው ስፍራ ውጣ። 9  ወደ ሌዋውያን ካህናትና በዚያን ጊዜ ዳኛ ሆኖ ወደሚያገለግለው ሰው ሄደህ ጠይቅ፤ እነሱም ውሳኔውን ይነግሩሃል። 10  አንተም እነዚህ ሰዎች ይሖዋ በሚመርጠው ስፍራ ሆነው በነገሩህ ውሳኔ መሠረት እርምጃ ውሰድ። የሰጡህንም መመሪያ በሙሉ በጥንቃቄ ፈጽም። 11  በሚሰጡህ ሕግና በሚነግሩህ ውሳኔ መሠረት እርምጃ ውሰድ። እነሱ ካሳለፉት ውሳኔ ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ ዞር አትበል። 12  አምላክህን ይሖዋን የሚያገለግለውን ካህን ወይም ዳኛውን ባለመስማት እብሪተኛ የሚሆን ሰው ካለ ይገደል። ክፉ የሆነውን ከእስራኤል መካከል አስወግድ። 13  ሕዝቡም ሁሉ ይህን ሲሰማ ይፈራል፤ ከእንግዲህም የእብሪት ድርጊት አይፈጽምም። 14  “አምላክህ ይሖዋ የሚሰጥህን ምድር ገብተህ ከወረስካት በኋላ በዚያ መኖር ስትጀምር ‘በዙሪያዬ እንዳሉት ብሔራት ሁሉ እኔም በላዬ ላይ ንጉሥ ላንግሥ’ ብትል 15  አምላክህ ይሖዋ የሚመርጠውን ንጉሥ ታነግሣለህ። የምታነግሠውም ንጉሥ ከወንድሞችህ መካከል መሆን ይኖርበታል። ወንድምህ ያልሆነን ባዕድ ሰው በላይህ ላይ ማንገሥ አይገባህም። 16  ይሁን እንጂ ንጉሡ ለራሱ ፈረሶች ማብዛት ወይም የፈረሶቹን ቁጥር ለመጨመር ሲል ሕዝቡ ወደ ግብፅ እንዲመለስ ማድረግ የለበትም፤ ምክንያቱም ይሖዋ ‘በዚህ መንገድ ፈጽሞ ዳግመኛ አንዳትመለሱ’ ብሏችኋል። 17  ልቡ ከትክክለኛው መንገድ ዞር እንዳይል ለራሱ ሚስቶች አያብዛ፤ ለራሱም ብርና ወርቅ አያከማች። 18  በመንግሥቱ ዙፋን ላይ በሚቀመጥበትም ጊዜ በሌዋውያን ካህናት እጅ ካለው ላይ ወስዶ የዚህን ሕግ ቅጂ ለራሱ በመጽሐፍ ላይ ይጻፍ። 19  “አምላኩን ይሖዋን መፍራትን እንዲማር እንዲሁም በዚህ ሕግና በእነዚህ ሥርዓቶች ላይ የሰፈሩትን ቃላት በሙሉ በመፈጸም እንዲጠብቃቸው ይህ መጽሐፍ ከእሱ ጋር ይሁን፤ በሕይወት ዘመኑም ሁሉ ያንብበው። 20  ይህን ካደረገ ልቡ በወንድሞቹ ላይ አይታበይም፤ ከትእዛዛቱም ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ ዞር አይልም፤ ይህም እሱም ሆነ ልጆቹ በእስራኤል መካከል በመንግሥቱ ላይ ረጅም ዘመን እንዲቆዩ ያስችላቸዋል።
[]
[]
[]
[]
12,563
18  “ሌዋውያኑ ካህናት አልፎ ተርፎም መላው የሌዊ ነገድ ከእስራኤል ጋር ድርሻም ሆነ ውርሻ አይኖራቸውም። የእሱ ድርሻ የሆኑትን ለይሖዋ በእሳት የሚቀርቡትን መባዎች ይበላሉ። 2  በመሆኑም በወንድሞቻቸው መካከል ውርሻ ሊኖራቸው አይገባም። አስቀድሞ በነገራቸው መሠረት ውርሻቸው ይሖዋ ነው። 3  “ካህናት ከሕዝቡ ሊያገኙ የሚገባቸው ድርሻ የሚከተለው ይሆናል፦ በሬም ሆነ በግ መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርብ ማንኛውም ሰው የእንስሳውን ወርች፣ መንገጭላውንና ሆድ ዕቃውን ለካህኑ ይስጥ። 4  የእህልህን በኩር፣ አዲስ የወይን ጠጅህንና ዘይትህን እንዲሁም ከመንጋህ በመጀመሪያ የተሸለተውን ፀጉር ስጠው። 5  አምላክህ ይሖዋ ከነገዶችህ ሁሉ መካከል በይሖዋ ስም ሁልጊዜ እንዲያገለግል የመረጠው እሱንና ወንዶች ልጆቹን ነው። 6  “ሆኖም አንድ ሌዋዊ ከሚኖርበት በእስራኤል ከሚገኙ ከተሞችህ ከአንዱ ወጥቶ ይሖዋ ወደሚመርጠው ስፍራ መሄድ ቢፈልግ 7  በይሖዋ ፊት ቆመው እንደሚያገለግሉት ሌዋውያን ወንድሞቹ ሁሉ እሱም በዚያ በአምላኩ በይሖዋ ስም ሊያገለግል ይችላል። 8  የአባቶቹን ርስት በመሸጥ ከሚያገኘው ገንዘብ በተጨማሪ ከእነሱ እኩል ምግብ ይሰጠዋል። 9  “አምላክህ ይሖዋ ወደሚሰጥህ ምድር በምትገባበት ጊዜ በዚያ የሚገኙ ብሔራት የሚፈጽሟቸውን አስጸያፊ ነገሮች አታድርግ። 10  ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን በእሳት የሚያሳልፍ፣ ሟርተኛ፣ አስማተኛ፣ ሞራ ገላጭ፣ ምትሃተኛ፣ 11  ድግምተኛ፣ መናፍስት ጠሪ፣ ጠንቋይ ወይም ሙታን አነጋጋሪ በመካከልህ አይገኝ። 12  ምክንያቱም እነዚህን ነገሮች የሚያደርግ ሰው ሁሉ በይሖዋ ፊት አስጸያፊ ነው፤ አምላክህ ይሖዋም እነሱን ከፊትህ የሚያባርራቸው በእነዚህ አስጸያፊ ነገሮች የተነሳ ነው። 13  በአምላክህ በይሖዋ ፊት እንከን የለሽ ሆነህ መገኘት አለብህ። 14  “አንተ ከምድራቸው የምታስለቅቃቸው እነዚህ ብሔራት አስማተኞችንና ሟርተኞችን ይሰማሉ፤ አንተ ግን እንዲህ እንድታደርግ አምላክህ ይሖዋ አልፈቀደልህም። 15  አምላክህ ይሖዋ ከወንድሞችህ መካከል እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሳልሃል። እናንተም እሱን ማዳመጥ ይኖርባችኋል። 16  ይህም የሚሆነው በኮሬብ ተሰብስባችሁ በነበረበት ዕለት ‘እንዳልሞት የአምላኬን የይሖዋን ድምፅ ከእንግዲህ አልስማ ወይም ይህን ታላቅ እሳት ከእንግዲህ አልይ’ በማለት አምላካችሁን ይሖዋን በጠየቃችሁት መሠረት ነው። 17  ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ ‘የተናገሩት ነገር መልካም ነው። 18  ከወንድሞቻቸው መካከል እንደ አንተ ያለ ነቢይ አስነሳላቸዋለሁ፤ ቃሌንም በአፉ ላይ አደርጋለሁ፤ እሱም እኔ የማዘውን ሁሉ ይነግራቸዋል። 19  በእኔ ስም የሚናገረውን ቃሌን የማይሰማውን ሰው በእርግጥ ተጠያቂ አደርገዋለሁ። 20  “‘እኔ እንዲናገር ያላዘዝኩትን ቃል በእብሪት ተነሳስቶ በስሜ የሚናገር ወይም በሌሎች አማልክት ስም የሚናገር ነቢይ ካለ ያ ነቢይ ይገደል። 21  ሆኖም አንተ በልብህ “ታዲያ ቃሉን ይሖዋ እንዳልተናገረው እንዴት እናውቃለን?” ብለህ ታስብ ይሆናል። 22  ነቢዩ በይሖዋ ስም ቢናገርና የተናገረው ቃል ባይፈጸም ወይም እውነት ሆኖ ባይገኝ ይህን ቃል የተናገረው ይሖዋ አይደለም። ይህ ቃል ነቢዩ በእብሪት ተነሳስቶ የተናገረው ነው። እሱን ልትፈራው አይገባም።’
[]
[]
[]
[]
12,564
19  “አምላክህ ይሖዋ ምድራቸውን ለአንተ የሚሰጥህን ብሔራት፣ ይሖዋ በሚያጠፋቸውና አንተም እነሱን አስለቅቀህ በከተሞቻቸውና በቤቶቻቸው መኖር በምትጀምርበት ጊዜ 2  አምላክህ ይሖዋ ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ውስጥ ሦስት ከተሞችን ለይ። 3  አምላክህ ይሖዋ እንድትወርሳት የሚሰጥህን ምድር ሦስት ቦታ ከፋፍላት፤ እንዲሁም ነፍስ ያጠፋ ማንኛውም ሰው ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዱ መሸሽ እንዲችል መንገድ አዘጋጅ። 4  “እዚያ ለመኖር ሸሽቶ የሄደን፣ ነፍስ ያጠፋ ሰው በተመለከተ መደረግ ያለበት ነገር ይህ ነው፦ ለባልንጀራው የቆየ ጥላቻ የሌለው አንድ ሰው ሳያስበው ባልንጀራውን መትቶ ቢገድለው፣ 5  ለምሳሌ ከባልንጀራው ጋር እንጨት ለመቁረጥ ወደ ጫካ ቢሄድ፣ ዛፉንም ለመቁረጥ መጥረቢያውን በሚሰነዝርበት ጊዜ ብረቱ ከእጀታው ላይ ወልቆ ባልንጀራውን ቢመታውና ቢገድለው ነፍሰ ገዳዩ ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዱ በመሸሽ ሕይወቱን ማትረፍ ይችላል። 6  አለዚያ በንዴት የበገነው ደም ተበቃይ ከተማዋ ሩቅ ከመሆኗ የተነሳ ነፍሰ ገዳዩን አሳዶ ሊደርስበትና ሊገድለው ይችላል። ይሁን እንጂ ይህ ሰው ለባልንጀራው የቆየ ጥላቻ ስለሌለው መሞት አይገባውም። 7  ‘ሦስት ከተሞችን ለይ’ በማለት ያዘዝኩህ ለዚህ ነው። 8  “አምላክህ ይሖዋ ለአባቶችህ በማለላቸው መሠረት ግዛትህን ሲያሰፋልህና ለእነሱ ለመስጠት ቃል የገባላቸውን ምድር በሙሉ ሲሰጥህ 9  ይኸውም አምላክህን ይሖዋን እንድትወድና ዘወትር በመንገዶቹ እንድትሄድ እኔ ዛሬ የማዝህን ይህን ትእዛዝ ሁሉ በመጠበቅህ ግዛትህን ሲያሰፋልህ ከእነዚህ ሦስት ከተሞች በተጨማሪ ሌሎች ሦስት ከተሞችን ትለያለህ። 10  ይህም አምላክህ ይሖዋ ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ላይ ንጹሕ ደም እንዳይፈስና በደም ዕዳ ተጠያቂ እንዳትሆን ነው። 11  “ይሁን እንጂ አንድ ሰው ባልንጀራውን ቢጠላው፣ አድብቶም ለሞት የሚያበቃ ጉዳት ቢያደርስበትና ሰውየው ቢሞት፣ ገዳዩም ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዱ ቢሸሽ 12  የሚኖርበት ከተማ ሽማግሌዎች ሰውየውን ከዚያ በማስመጣት ለደም ተበቃዩ አሳልፈው ይስጡት፤ ይህ ሰው ሞት ይገባዋል። 13  አትዘንለት፤ መልካም እንዲሆንልህ ንጹሕ ደም በማፍሰስ የሚመጣን በደል ከእስራኤል አስወግድ። 14  “አምላክህ ይሖዋ እንድትወርሳት በሚሰጥህ ምድር ውስጥ ርስትህን በምትቀበልበት ጊዜ የቀድሞ አባቶችህ የከለሉትን ወሰን በማለፍ የባልንጀራህን የድንበር ምልክት አትንካ። 15  “አንድ ሰው የትኛውንም ስህተት ወይም የትኛውንም ኃጢአት ቢፈጽም ግለሰቡን ጥፋተኛ ለማድረግ አንድ ምሥክር አይበቃም። ጉዳዩ የሚጸናው ሁለት ምሥክሮች ወይም ሦስት ምሥክሮች በሚሰጡት የምሥክርነት ቃል ነው። 16  ተንኮል ያሰበ አንድ ምሥክር አንድን ግለሰብ የሆነ በደል ፈጽሟል በማለት ቢመሠክርበት 17  ክርክር የገጠሙት ሁለቱ ሰዎች በይሖዋ ፊት፣ በካህናቱና በዚያን ጊዜ ዳኛ ሆነው በሚያገለግሉት ሰዎች ፊት ይቆማሉ። 18  ዳኞቹም ጉዳዩን በጥንቃቄ ይመረምራሉ፤ ምሥክሩ ሐሰተኛ ምሥክር ከሆነና ወንድሙን የወነጀለው በሐሰት ከሆነ 19  በወንድሙ ላይ ለማድረግ ያቀደውን ነገር በራሱ ላይ አድርጉበት፤ ክፉ የሆነውን ከመካከልህ አስወግድ። 20  ሌሎችም ይህን ሲሰሙ ይፈራሉ፤ በመካከልህም እንዲህ ያለ መጥፎ ነገር ፈጽሞ ዳግመኛ አያደርጉም። 21  አዘኔታ አታሳይ፤ ሕይወት ስለ ሕይወት፣ ዓይን ስለ ዓይን፣ ጥርስ ስለ ጥርስ፣ እጅ ስለ እጅ እንዲሁም እግር ስለ እግር ይሁን።
[]
[]
[]
[]
12,565
2  ከዚያም ልክ ይሖዋ በነገረኝ መሠረት ተመልሰን ወደ ቀይ ባሕር የሚወስደውን መንገድ በመከተል ወደ ምድረ በዳው ተጓዝን፤ በሴይር ተራራ አካባቢም ለብዙ ቀናት ተንከራተትን። 2  በመጨረሻም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ 3  ‘እንግዲህ በዚህ ተራራ አካባቢ ብዙ ተንከራታችኋል። አሁን ወደ ሰሜን አቅኑ። 4  ሕዝቡንም እንዲህ ብለህ እዘዝ፦ “እንግዲህ በሴይር በሚኖሩት በወንድሞቻችሁ በኤሳው ዘሮች ድንበር አልፋችሁ ልትሄዱ ነው፤ እነሱም ይፈሯችኋል፤ ቢሆንም ከፍተኛ ጥንቃቄ አድርጉ። 5  ከምድራቸው ላይ የእግር መርገጫ የምታክል መሬት እንኳ ስለማልሰጣችሁ ከእነሱ ጋር እንዳትጣሉ፤ ምክንያቱም የሴይርን ተራራ ለኤሳው ርስት አድርጌ ሰጥቼዋለሁ። 6  ለምትበሉት ምግብም ሆነ ለምትጠጡት ውኃ ገንዘብ ክፈሏቸው። 7  አምላክህ ይሖዋ የእጅህን ሥራ ሁሉ ባርኮልሃልና። በዚህ ጭልጥ ያለ ምድረ በዳ እንደተጓዝክ በሚገባ ያውቃል። በእነዚህ 40 ዓመታት አምላክህ ይሖዋ ከአንተ ጋር ስለነበር ምንም የጎደለብህ ነገር የለም።”’ 8  ስለዚህ በሴይር በሚኖሩት ወንድሞቻችን በኤሳው ዘሮች በኩል አልፈን ሄድን፤ ወደ አረባ ከሚወስደው መንገድ፣ ከኤላት እና ከዔጽዮንጋብር ርቀን ተጓዝን። “በመቀጠልም ተነስተን ወደ ሞዓብ ምድረ በዳ በሚወስደው መንገድ ተጓዝን። 9  ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ ‘ከሞዓብ ምድር የትኛውንም መሬት ርስት አድርጌ ስለማልሰጥህ ከእሱ ጋር አትጣላ ወይም ጦርነት አትግጠም፤ ምክንያቱም ኤርን ለሎጥ ዘሮች ርስት አድርጌ ሰጥቻቸዋለሁ። 10  (ታላቅና ብዙ እንዲሁም ልክ እንደ ኤናቃውያን ቁመተ ረጃጅም የሆኑት ኤሚማውያን ቀደም ሲል በዚያ ይኖሩ ነበር። 11  ረፋይማውያንም ልክ እንደ ኤናቃውያን ይቆጠሩ ነበር፤ ሞዓባውያንም ኤሚማውያን ብለው ይጠሯቸው ነበር። 12  ሆራውያን ቀደም ሲል በሴይር ይኖሩ ነበር፤ እስራኤላውያን ይሖዋ ርስት አድርጎ በሚሰጣቸው ምድር ላይ እንደሚያደርጉት ሁሉ የኤሳውም ዘሮች ሆራውያንን በማስለቀቅና በማጥፋት በምድራቸው ላይ መኖር ጀመሩ።) 13  በሉ አሁን ተነሱና የዘረድን ሸለቆ አቋርጣችሁ ሂዱ።’ ስለዚህ የዘረድን ሸለቆ አቋርጠን ሄድን። 14  ከቃዴስበርኔ ተነስተን የዘረድን ሸለቆ እስክናቋርጥ ድረስ 38 ዓመት ፈጅቶብናል፤ በዚህ ጊዜም ይሖዋ ለእነሱ በማለላቸው መሠረት ለጦርነት ብቁ የሆነው ትውልድ በሙሉ ከሕዝቡ መካከል አለቀ። 15  ሙሉ በሙሉ እስኪጠፉም ድረስ የይሖዋ እጅ ከሕዝቡ መካከል ሊያጠፋቸው በእነሱ ላይ ነበር። 16  “ለጦርነት ብቁ የሆኑት ወንዶች ሁሉ ከሕዝቡ መካከል ሞተው እንዳለቁ 17  ይሖዋ በድጋሚ እንዲህ አለኝ፦ 18  ‘ዛሬ በሞዓብ ክልል ይኸውም በኤር በኩል ታልፋለህ። 19  ወደ አሞናውያን በቀረብክ ጊዜ እነሱን አታስቆጣቸው ወይም አትተናኮላቸው፤ ምክንያቱም ምድሪቱን ለሎጥ ዘሮች ርስት አድርጌ ስለሰጠኋቸው ከአሞን ልጆች ምድር የትኛውንም መሬት ርስት አድርጌ አልሰጥህም። 20  ይህችም ምድር የረፋይማውያን ምድር ተደርጋ ትቆጠር ነበር። (ቀደም ሲል ረፋይማውያን በዚያ ይኖሩ ነበር፤ አሞናውያንም ዛምዙሚማውያን ብለው ይጠሯቸው ነበር። 21  እነሱም ታላቅና ቁጥራቸው የበዛ እንዲሁም ልክ እንደ ኤናቃውያን ቁመተ ረጃጅሞች ነበሩ፤ ይሖዋ ግን ከአሞናውያን ፊት አጠፋቸው፤ እነሱም ምድራቸውን አስለቅቀው በዚያ ሰፈሩ። 22  አሁን በሴይር ለሚኖሩት የኤሳው ዘሮች ሆራውያንን ከፊታቸው ባጠፋላቸው ጊዜ ያደረገላቸው ይህንኑ ነበር፤ በዚህም የተነሳ የኤሳው ዘሮች እነሱን አስለቅቀው እስከ ዛሬ ድረስ በምድራቸው ላይ እየኖሩ ነው። 23  አዊማውያን ደግሞ ከካፍቶር የተገኙት ካፍቶሪማውያን እነሱን አጥፍተው በምድራቸው ላይ መኖር እስከጀመሩበት ጊዜ ድረስ እስከ ጋዛ በሚገኙት መንደሮች ይኖሩ ነበር።) 24  “‘ተነሱና የአርኖንን ሸለቆ አቋርጣችሁ ሂዱ። ይኸው የሃሽቦንን ንጉሥ አሞራዊውን ሲሖንን በእጃችሁ ሰጥቻችኋለሁ። በመሆኑም ምድሩን መውረስ ጀምሩ፤ ከእሱም ጋር ጦርነት ግጠሙ። 25  በዚህች ዕለት፣ ስለ እናንተ የሰሙ ከሰማይ በታች ያሉ ሕዝቦች ሁሉ እንዲሸበሩና በፍርሃት እንዲርዱ አደርጋለሁ። በእናንተም የተነሳ ይታወካሉ፤ ምጥም ይይዛቸዋል።’ 26  “ከዚያም እኔ ከቀደሞት ምድረ በዳ ለሃሽቦን ንጉሥ ለሲሖን እንዲህ የሚል የሰላም መልእክት እንዲነግሩት መልእክተኞችን ላክሁበት፦ 27  ‘ምድርህን አቋርጬ እንዳልፍ ፍቀድልኝ። ከመንገዱ አልወጣም፤ ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ ዞር አልልም። 28  በገንዘብ የምትሸጥልኝን ምግብ ብቻ እበላለሁ፤ በገንዘብ የምትሰጠኝንም ውኃ ብቻ እጠጣለሁ። ምድሩን ረግጬ እንዳልፍ ብቻ ፍቀድልኝ፤ 29  አምላካችን ይሖዋ ወደሚሰጠን ምድር ለመግባት ዮርዳኖስን እስክሻገር ድረስ በሴይር የሚኖሩት የኤሳው ዘሮችና በኤር የሚኖሩት ሞዓባውያን እንዲሁ አድርገውልኛል።’ 30  የሃሽቦን ንጉሥ ሲሖን ግን በእሱ በኩል አቋርጠን እንድናልፍ አልፈቀደልንም፤ ምክንያቱም አምላክህ ይሖዋ ሐሳበ ግትር እንዲሆንና ልቡ እንዲደነድን ፈቅዶ ነበር፤ ይህን ያደረገው ይኸው ዛሬ እንደምታዩት እጃችሁ ላይ እንዲወድቅ ነው። 31  “ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ ‘እነሆ ሲሖንን እና ምድሩን በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼሃለሁ። እንግዲህ ምድሩን ለመውረስ ተነስ።’ 32  ሲሖንም ከመላው ሕዝቡ ጋር በመሆን ያሃጽ ላይ እኛን ለመውጋት በወጣ ጊዜ 33  አምላካችን ይሖዋ በእጃችን አሳልፎ ሰጠው፤ ስለዚህ እሱንም ሆነ ልጆቹን እንዲሁም ሕዝቡን በሙሉ ድል አደረግናቸው። 34  በዚያን ጊዜም ከተሞቹን ሁሉ ያዝን፤ ወንዶችን፣ ሴቶችንና ልጆችን ጨምሮ እያንዳንዱን ከተማ ሙሉ በሙሉ አጠፋን። ማንንም በሕይወት አላስተረፍንም። 35  ለራሳችን ማርከን የወሰድነው እንስሶችንና በያዝናቸው ከተሞች ውስጥ ያገኘነውን ንብረት ብቻ ነው። 36  በአርኖን ሸለቆ ዳርቻ ካለችው ከአሮዔር (በሸለቆው ውስጥ የምትገኘውን ከተማ ጨምሮ) እስከ ጊልያድ ድረስ ከእጃችን ያመለጠ አንድም ከተማ አልነበረም። አምላካችን ይሖዋ ሁሉንም በእጃችን አሳልፎ ሰጥቶን ነበር። 37  ሆኖም ወደ አሞናውያን ምድር፣ ወደ ያቦቅ ሸለቆ ዳርቻ ሁሉና በተራራማው አካባቢ ወደሚገኙት ከተሞች ወይም አምላካችን ይሖዋ ወደከለከለን ወደ ሌላ ማንኛውም ቦታ አልቀረባችሁም።
[]
[]
[]
[]
12,566
20  “ከጠላቶችህ ጋር ጦርነት ለመግጠም ብትሄድና ፈረሶቻቸው፣ ሠረገሎቻቸውና ሠራዊታቸው ከአንተ ይልቅ እጅግ ብዙ መሆናቸውን ብታይ አትፍራቸው፤ ምክንያቱም ከግብፅ ምድር ያወጣህ አምላክህ ይሖዋ ከአንተ ጋር ነው። 2  ወደ ውጊያው ለመግባት በምትቀርቡበትም ጊዜ ካህኑ መጥቶ ሕዝቡን ማነጋገር አለበት። 3  እንዲህም ይበላቸው፦ ‘እስራኤላውያን ሆይ፣ ስሙ፤ እንግዲህ ዛሬ ከጠላቶቻችሁ ጋር ጦርነት ልትገጥሙ ነው። ልባችሁ አይራድ። በእነሱ ምክንያት አትፍሩ፣ አትሸበሩ ወይም አትንቀጥቀጡ፤ 4  ምክንያቱም አምላካችሁ ይሖዋ ጠላቶቻችሁን ሊዋጋላችሁና ሊያድናችሁ አብሯችሁ ይወጣል።’ 5  “አለቆቹም ሕዝቡን እንዲህ ይበሉ፦ ‘ከመካከላችሁ አዲስ ቤት ሠርቶ ያላስመረቀ አለ? ወደ ቤቱ ይመለስ። አለዚያ በጦርነቱ ላይ ሊሞትና ቤቱን ሌላ ሰው ሊያስመርቀው ይችላል። 6  ወይን ተክሎ ገና ከዚያ ያልበላ አለ? ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ። አለዚያ በጦርነቱ ላይ ሊሞትና ሌላ ሰው ሊበላው ይችላል። 7  አንዲት ሴት አጭቶ ገና ያላገባት ሰው አለ? ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ። አለዚያ በጦርነቱ ላይ ሊሞትና ሌላ ሰው ሊያገባት ይችላል።’ 8  በተጨማሪም አለቆቹ ለሕዝቡ እንዲህ በማለት ይናገሩ፦ ‘ከመካከላችሁ የፈራና ልቡ የራደ አለ? ልክ እንደ ራሱ ልብ የወንድሞቹንም ልብ እንዳያቀልጥ ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ።’ 9  አለቆቹም ለሕዝቡ ተናግረው ሲጨርሱ ሕዝቡን እንዲመሩ የሠራዊቱን አለቆች ይሹሙ። 10  “አንዲትን ከተማ ለመውጋት ወደ እሷ ስትቀርብ ለከተማዋ የሰላም ጥሪ አስተላልፍ። 11  ከተማዋ የሰላም ጥሪህን ከተቀበለችና በሯን ከከፈተችልህ ነዋሪዎቿ ሁሉ የግዳጅ ሥራ የሚሠሩ ሕዝቦች ይሆኑልሃል፤ አንተንም ያገለግሉሃል። 12  ይሁን እንጂ የሰላም ጥሪህን ካልተቀበለችና ከአንተ ጋር ውጊያ ለመግጠም ከተነሳች ከተማዋን ክበባት፤ 13  አምላክህ ይሖዋ ከተማዋን በእጅህ አሳልፎ ይሰጥሃል፤ አንተም በውስጧ የሚኖሩትን ወንዶች ሁሉ በሰይፍ ግደላቸው። 14  ሆኖም ሴቶቹን፣ ትናንሽ ልጆቹን፣ እንስሳቱንና በከተማዋ ውስጥ የተገኘውን ነገር ሁሉ ማርከህ ለራስህ መውሰድ ትችላለህ፤ አምላክህ ይሖዋ በእጅህ አሳልፎ የሰጠህን ከጠላቶችህ ያገኘኸውን ምርኮም ትበላለህ። 15  “በአቅራቢያህ የሚገኙት ብሔራት ከተሞች ባልሆኑ ከአንተ ርቀው በሚገኙ ከተሞች ሁሉ ላይ የምታደርገው ይህንኑ ነው። 16  አምላክህ ይሖዋ ርስት አድርጎ በሚሰጥህ እነዚህ ሕዝቦች በሚኖሩባቸው ከተሞች ውስጥ ግን እስትንፋስ ያለውን ማንኛውንም ነገር በሕይወት አታስቀር። 17  ከዚህ ይልቅ አምላክህ ይሖዋ ባዘዘህ መሠረት ሂታውያንን፣ አሞራውያንን፣ ከነአናውያንን፣ ፈሪዛውያንን፣ ሂዋውያንንና ኢያቡሳውያንን ሙሉ በሙሉ አጥፋ፤ 18  ይህን የምታደርጉት ለአማልክታቸው የሚያደርጓቸውን አስጸያፊ ነገሮች በሙሉ እንዳያስተምሯችሁና በአምላካችሁ በይሖዋ ላይ ኃጢአት እንድትሠሩ እንዳያደርጓችሁ ነው። 19  “አንዲትን ከተማ ከበህ ከብዙ ቀናት ውጊያ በኋላ በቁጥጥርህ ሥር ብታውላት ዛፎቿን በመጥረቢያ አትጨፍጭፍ። ፍሬያቸውን ልትበላ ትችላለህ፤ ሆኖም አትቁረጣቸው። ደግሞስ ሰው ይመስል የሜዳን ዛፍ ከበህ ማጥፋት አለብህ? 20  ለምግብነት እንደማይሆን የምታውቀውን ዛፍ ብቻ ማጥፋት ትችላለህ። ዛፉንም ቆርጠህ ከአንተ ጋር ውጊያ የገጠመችው ከተማ እስክትወድቅ ድረስ ዙሪያዋን ልታጥርበት ትችላለህ።
[]
[]
[]
[]
12,567
21  “አምላክህ ይሖዋ እንድትወርሳት በሚሰጥህ ምድር አንድ ሰው ሜዳ ላይ ተገድሎ ቢገኝና ማን እንደገደለው ባይታወቅ 2  ሽማግሌዎችህና ዳኞችህ ወጥተው የሞተው ሰው ከተገኘበት ስፍራ አንስቶ በዙሪያው እስከሚገኙት ከተሞች ድረስ ያለውን ርቀት ይለኩ። 3  ከዚያም የሞተው ሰው ለተገኘበት ስፍራ ቅርብ የሆነችው ከተማ ሽማግሌዎች ምንም ሥራ ያልተሠራባትንና ቀንበር ተጭኖባት የማያውቅን ጊደር ከከብቶች መካከል ይውሰዱ፤ 4  የከተማዋም ሽማግሌዎች ጊደሯን ከዚህ ቀደም ታርሶ ወይም ዘር ተዘርቶበት ወደማያውቅ ወራጅ ውኃ ወዳለበት ሸለቆ ይውሰዷት፤ በሸለቆውም ውስጥ የጊደሯን አንገት ይስበሩ። 5  “ካህናቱ፣ ሌዋውያኑ ይቅረቡ፤ ምክንያቱም አምላክህ ይሖዋ እሱን እንዲያገለግሉና በይሖዋ ስም እንዲባርኩ የመረጠው እነሱን ነው። ደግሞም የኃይል ጥቃትን በተመለከተ ለሚነሳ ለማንኛውም ክርክር እልባት የሚሰጡት እነሱ ናቸው። 6  ከዚያም የሞተው ሰው ለተገኘበት ስፍራ ቅርብ የሆኑት የከተማዋ ሽማግሌዎች በሙሉ በሸለቆው ውስጥ አንገቷ በተሰበረው ጊደር ላይ እጃቸውን ይታጠቡ፤ 7  እንዲህ ብለውም ይናገሩ፦ ‘እጆቻችን ይህን ደም አላፈሰሱም፤ ዓይኖቻችንም ይህ ደም ሲፈስ አላዩም። 8  ይሖዋ ሆይ፣ የታደግከውን ሕዝብህን እስራኤልን በዚህ ድርጊት ተጠያቂ አታድርገው፤ ንጹሕ ደም በማፍሰስ የተፈጸመ በደልም በሕዝብህ በእስራኤል መካከል እንዲኖር አትፍቀድ።’ እነሱም በደም ዕዳው ተጠያቂ አይሆኑም። 9  በዚህ መንገድ ንጹሕ ደም በማፍሰስ የተፈጸመን በደል ከመካከልህ በማስወገድ በይሖዋ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር አድርግ። 10  “ከጠላቶችህ ጋር ብትዋጋ፣ አምላክህ ይሖዋም እነሱን በእጅህ አሳልፎ ቢሰጥህ፣ አንተም ምርኮኛ አድርገህ ብትወስዳቸውና 11  ከምርኮኞቹ መካከል አንዲት የምታምር ሴት አይተህ ብትወዳት፣ ሚስትህም ልታደርጋት ብትፈልግ 12  ወደ ቤትህ ልትወስዳት ትችላለህ። እሷም ፀጉሯን ትላጭ፤ ጥፍሯንም ትቁረጥ፤ 13  የምርኮኛነት ልብሷን ታውልቅ፤ በቤትህም ትቀመጥ። ለአባቷና ለእናቷ አንድ ወር ሙሉ ታልቅስ፤ ከዚህ በኋላ ከእሷ ጋር ግንኙነት መፈጸም ትችላለህ፤ አንተ ባሏ ትሆናለህ፤ እሷም ሚስትህ ትሆናለች። 14  በእሷ ካልተደሰትክ ግን ወደፈለገችበት እንድትሄድ አሰናብታት። ሆኖም ለውርደት ስለዳረግካት በገንዘብ ልትሸጣት ወይም ግፍ ልትፈጽምባት አይገባም። 15  “አንድ ሰው ሁለት ሚስቶች ቢኖሩትና አንደኛዋን ከሌላኛዋ አስበልጦ የሚወዳት ቢሆን፣ ሁለቱም ወንዶች ልጆች ቢወልዱለትና በኩሩ የተወለደው ከማይወዳት ሚስቱ ቢሆን 16  ውርሱን ለወንዶች ልጆቹ በሚያስተላልፍበት ቀን ከማይወዳት ሚስቱ የተወለደውን በኩር የሆነውን ወንድ ልጅ ትቶ ከሚወዳት ሚስቱ የተወለደውን ወንድ ልጅ እንደ በኩር ልጁ አድርጎ መቁጠር የለበትም። 17  ከዚህ ይልቅ ከማይወዳት ሚስቱ ለተወለደው ወንድ ልጅ፣ ካለው ከማንኛውም ነገር ላይ ሁለት እጥፍ በመስጠት የልጁን ብኩርና መቀበል ይኖርበታል፤ ምክንያቱም የጎልማሳነቱ ብርታት መጀመሪያ ይህ ልጅ ነው። የብኩርና መብቱ የእሱ ነው። 18  “አንድ ሰው እልኸኛና ዓመፀኛ ልጅ ቢኖረው ልጁም አባቱንም ሆነ እናቱን ለመታዘዝ አሻፈረኝ ቢል፣ እነሱም እርማት ሊሰጡት ቢሞክሩና እሱ ግን ሊሰማቸው ፈቃደኛ ባይሆን 19  አባትና እናቱ እሱ ባለበት ከተማ በር ላይ ወዳሉት ሽማግሌዎች ያምጡት፤ 20  ሽማግሌዎቹንም ‘ይህ ልጃችን እልኸኛና ዓመፀኛ ነው፤ ሊታዘዘንም ፈቃደኛ አይደለም። ሆዳምና ሰካራም ነው’ ይበሏቸው። 21  ከዚያም የከተማዋ ሰዎች ሁሉ እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ይውገሩት። በዚህ መንገድ ክፉ የሆነውን ከመካከልህ አስወግድ፤ እስራኤላውያንም ሁሉ ይህን ሰምተው ይፈራሉ። 22  “አንድ ሰው ለሞት የሚያበቃ ኃጢአት ሠርቶ ቢገደልና በእንጨት ላይ ብትሰቅለው 23  በድኑ በእንጨቱ ላይ አይደር። ከዚህ ይልቅ በዚያው ዕለት ቅበረው፤ ምክንያቱም እንጨት ላይ የሚሰቀለው፣ አምላክ የረገመው ነው፤ አንተም አምላክህ ይሖዋ ርስት አድርጎ የሚሰጥህን ምድር አታርክስ።
[]
[]
[]
[]
12,568
22  “የወንድምህ በሬ ወይም በግ ጠፍቶ ሲባዝን ካየህ እንዳላየ ሆነህ አትለፍ። ከዚህ ይልቅ ወደ ወንድምህ መልሰህ ልትወስደው ይገባል። 2  ሆኖም ወንድምህ በአቅራቢያህ የማይኖር ወይም እሱን የማታውቀው ከሆነ እንስሳውን ወደ ቤትህ አምጣው፤ ወንድምህ እሱን ፈልጎ እስኪመጣም ድረስ አንተ ጋ ይቆይ። ከዚያም መልስለት። 3  አህያውንም ሆነ ልብሱን ወይም ወንድምህ ጠፍቶበት ያገኘኸውን ማንኛውንም ነገር በተመለከተ እንዲሁ ማድረግ ይኖርብሃል። አይተህ ዝም ብለህ ማለፍ የለብህም። 4  “የወንድምህ አህያ ወይም በሬ መንገድ ላይ ወድቆ ብታይ እንዳላየ ሆነህ አትለፍ። ከዚህ ይልቅ እንስሳው ተነስቶ እንዲቆም በማድረግ ሰውየውን ልትረዳው ይገባል። 5  “ሴት የወንድ ልብስ አትልበስ፤ ወንድ ደግሞ የሴት ልብስ አይልበስ። ምክንያቱም እነዚህን ነገሮች የሚያደርግ ማንኛውም ሰው በአምላክህ በይሖዋ ፊት አስጸያፊ ነው። 6  “መንገድ ላይ ስትሄድ ጫጩቶች ወይም እንቁላሎች ያሉበት የወፍ ጎጆ፣ ዛፍ ላይ ወይም መሬት ላይ ብታገኝና እናትየው ጫጩቶቹን ወይም እንቁላሎቹን ታቅፋ ቢሆን እናትየውን ከጫጩቶቿ ጋር አብረህ አትውሰድ። 7  እናትየውን ልቀቃት፤ ጫጩቶቹን ግን መውሰድ ትችላለህ። ይህን የምታደርገው መልካም እንዲሆንልህና ዕድሜህ እንዲረዝም ነው። 8  “አዲስ ቤት በምትሠራበት ጊዜ አንድ ሰው ከጣሪያህ ላይ ወድቆ በቤትህ ላይ የደም ዕዳ እንዳታመጣ በጣሪያህ ዙሪያ መከታ ሥራ። 9  “በወይን እርሻህ ላይ ሁለት ዓይነት ዘር አትዝራ። እንዲህ ካደረግክ ከዘራኸው ዘር የሚገኘው ምርትም ሆነ የወይን እርሻህ ምርት በሙሉ በቤተ መቅደሱ ተቀባይነት ያጣል። 10  “በሬና አህያ አንድ ላይ ጠምደህ አትረስ። 11  “ከሱፍና ከበፍታ ተቀላቅሎ የተሠራ ልብስ አትልበስ። 12  “በምትለብሰው ልብስ ላይ በአራቱም ማዕዘን ዘርፍ አድርግ። 13  “አንድ ሰው ሚስት አግብቶ ከእሷ ጋር ግንኙነት ከፈጸመ በኋላ ቢጠላት፣ 14  መጥፎ ምግባር እንዳላት አድርጎ ቢከሳትና ‘ይህችን ሴት አግብቼ ነበር፤ ሆኖም ከእሷ ጋር ግንኙነት ስፈጽም የድንግልናዋን ማስረጃ አላገኘሁም’ በማለት መጥፎ ስም ቢሰጣት 15  የልጅቷ አባትና እናት ድንግልናዋን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ይዘው በከተማዋ በር ወደሚገኙት ሽማግሌዎች ይምጡ። 16  የልጅቷም አባት ሽማግሌዎቹን እንዲህ ይበላቸው፦ ‘ልጄን ለዚህ ሰው ድሬለት ነበር፤ እሱ ግን ጠላት፤ 17  እንዲሁም “ልጅህን ከነድንግልናዋ አላገኘኋትም” በማለት መጥፎ ምግባር እንዳላት አድርጎ እየከሰሳት ነው። እንግዲህ የልጄ የድንግልና ማስረጃ ይኸውላችሁ።’ እነሱም ልብሱን በከተማዋ ሽማግሌዎች ፊት ይዘርጉት። 18  የዚያች ከተማ ሽማግሌዎችም ሰውየውን ወስደው ይቅጡት። 19  እነሱም 100 የብር ሰቅል ያስከፍሉታል፤ ከዚያም ገንዘቡን ለልጅቷ አባት ይስጡት፤ ምክንያቱም ይህ ሰው የአንዲትን እስራኤላዊት ድንግል ስም አጥፍቷል፤ እሷም ሚስቱ ሆና ትኖራለች። በሕይወት ዘመኑም ሁሉ እንዲፈታት አይፈቀድለትም። 20  “ሆኖም ክሱ እውነት ከሆነና ልጅቷ ድንግል እንደነበረች የሚያረጋግጥ ማስረጃ ካልተገኘ 21  ልጅቷን ወደ አባቷ ቤት ደጃፍ ያውጧት፤ በአባቷ ቤት የፆታ ብልግና በመፈጸም በእስራኤል ውስጥ አስነዋሪ ድርጊት ስለፈጸመች የከተማዋ ሰዎች እስክትሞት ድረስ በድንጋይ ይውገሯት። በዚህ መንገድ ክፉ የሆነውን ከመካከልህ አስወግድ። 22  “አንድ ሰው ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ተኝቶ ቢገኝ ከሴትየዋ ጋር የተኛው ሰውም ሆነ ሴትየዋ ሁለቱም ይገደሉ። በዚህ መንገድ ክፉ የሆነውን ከእስራኤል መካከል አስወግድ። 23  “አንድ ሰው ለሌላ ሰው የታጨችን አንዲት ድንግል ከተማ ውስጥ አግኝቶ ከእሷ ጋር ቢተኛ 24  ልጅቷ በከተማው ውስጥ ስላልጮኸች፣ ሰውየው ደግሞ የባልንጀራውን ሚስት ስላዋረደ ሁለቱንም ወደ ከተማዋ በር አውጥታችሁ እስኪሞቱ ድረስ በድንጋይ ውገሯቸው። በዚህ መንገድ ክፉ የሆነውን ከመካከልህ አስወግድ። 25  “ይሁንና ሰውየው የታጨችውን ልጃገረድ ያገኛት ሜዳ ላይ ቢሆንና በጉልበት አስገድዶ አብሯት ቢተኛ እሱ ብቻ ይገደል፤ 26  በልጅቷ ላይ ምንም አታድርግ። ልጅቷ ሞት የሚገባው ኃጢአት አልሠራችም። ይህ ጉዳይ በባልንጀራው ላይ ጥቃት ሰንዝሮ ከሚገድል ሰው ሁኔታ ጋር ተመሳሳይ ነው። 27  ምክንያቱም ሰውየው ልጅቷን ያገኛት ሜዳ ላይ ሲሆን የታጨችው ልጅ ብትጮኽም እንኳ ማንም አልደረሰላትም። 28  “አንድ ሰው ያልታጨችን አንዲት ድንግል አግኝቶ ቢይዛትና አብሯት ቢተኛ፣ በኋላም ቢጋለጡ 29  ሰውየው ለልጅቷ አባት 50 የብር ሰቅል ይስጥ፤ እሷም ሚስቱ ትሆናለች። ስላዋረዳትም በሕይወት ዘመኑ ሁሉ እንዲፈታት አይፈቀድለትም። 30  “ማንም ሰው አባቱን እንዳያዋርድ የአባቱን ሚስት አያግባ።
[]
[]
[]
[]
12,569
23  “የዘር ፍሬው ተቀጥቅጦ የተኮላሸ ወይም ብልቱ የተቆረጠ ማንኛውም ሰው ወደ ይሖዋ ጉባኤ አይግባ። 2  “ዲቃላ ወደ ይሖዋ ጉባኤ አይግባ። ሌላው ቀርቶ እስከ አሥረኛ ትውልድ ድረስ ዘሮቹ ወደ ይሖዋ ጉባኤ አይግቡ። 3  “አሞናውያንም ሆኑ ሞዓባውያን ወደ ይሖዋ ጉባኤ አይግቡ። ሌላው ቀርቶ እስከ አሥረኛ ትውልድ ድረስ ዘሮቻቸው ፈጽሞ ወደ ይሖዋ ጉባኤ አይግቡ፤ 4  ምክንያቱም እነሱ ከግብፅ ወጥታችሁ እየተጓዛችሁ በነበረበት ጊዜ ምግብና ውኃ በመስጠት አልረዷችሁም፤ ደግሞም በሜሶጶጣሚያ በምትገኘው በጰቶር የሚኖረው የቢዖር ልጅ በለዓም አንተን እንዲረግም በገንዘብ ቀጥረውት ነበር። 5  አምላክህ ይሖዋ ግን በለዓምን ለመስማት ፈቃደኛ አልሆነም። ከዚህ ይልቅ አምላክህ ይሖዋ ለአንተ ሲል እርግማኑን ወደ በረከት ለወጠው፤ ይህን ያደረገው አምላክህ ይሖዋ ስለወደደህ ነው። 6  በዘመንህ ሁሉ መቼም ቢሆን ለእነሱ ሰላምን ወይም ብልጽግናን አትመኝ። 7  “ወንድምህ ስለሆነ ኤዶማዊውን አትጥላው። “የባዕድ አገር ሰው ሆነህ በአገሩ ትኖር ስለነበር ግብፃዊውን አትጥላው። 8  ለእነሱ የሚወለዱላቸው የሦስተኛው ትውልድ ልጆች ወደ ይሖዋ ጉባኤ መግባት ይችላሉ። 9  “ጠላትህን ለመውጋት ወጥተህ በምትሰፍርበት ጊዜ ከማንኛውም መጥፎ ነገር መራቅ ይኖርብሃል። 10  አንድ ሰው ዘሩ በመፍሰሱ ምክንያት ቢረክስ ከሰፈሩ ውጭ ይውጣ፤ ወደ ሰፈሩም ተመልሶ አይግባ። 11  አመሻሹ ላይ በውኃ ይታጠብ፤ ከዚያም ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ወደ ሰፈሩ ተመልሶ መግባት ይችላል። 12  ለመጸዳጃ የሚሆን ቦታ ከሰፈሩ ውጭ አዘጋጅ፤ አንተም መሄድ ያለብህ ወደዚያ ነው። 13  ከመሣሪያዎችህም ጋር መቆፈሪያ ያዝ። ውጭ በምትጸዳዳበትም ጊዜ በመቆፈሪያው ጉድጓድ ቆፍር፤ ከዚያም በዓይነ ምድርህ ላይ አፈሩን መልስበት። 14  ምክንያቱም አምላክህ ይሖዋ ሊታደግህና ጠላቶችህን በእጅህ አሳልፎ ሊሰጥህ በሰፈሩ ውስጥ ይዘዋወራል፤ በመሆኑም ነውር የሆነ ምንም ነገር እንዳያይብህና ከአንተ ጋር መሄዱን እንዳይተው ሰፈርህ ቅዱስ መሆን አለበት። 15  “አንድ ባሪያ ከጌታው አምልጦ ወደ አንተ ቢመጣ መልሰህ ለጌታው አትስጠው። 16  ከከተሞችህ መካከል በመረጠውና ደስ ባለው ቦታ አብሮህ ሊኖር ይችላል። በደል አትፈጽምበት። 17  “ከእስራኤል ሴቶች ልጆች መካከል የትኛዋም የቤተ መቅደስ ዝሙት አዳሪ አትሁን፤ ከእስራኤል ወንዶች ልጆችም መካከል የትኛውም የቤተ መቅደስ ዝሙት አዳሪ አይሁን። 18  ለሴት ዝሙት አዳሪ የተከፈለን ዋጋም ሆነ ለወንድ ዝሙት አዳሪ የተከፈለን ዋጋ አንድን ስእለት ለመፈጸም ስትል ወደ አምላክህ ወደ ይሖዋ ቤት አታምጣ፤ ምክንያቱም አምላክህ ይሖዋ ሁለቱንም ይጸየፋቸዋል። 19  “ወንድምህን ወለድ አታስከፍለው፤ ከገንዘብም ሆነ ከእህል ወይም ወለድ ሊያስከፍል ከሚችል ከማንኛውም ነገር ወለድ አታስከፍለው። 20  ከባዕድ አገር ሰው ወለድ መጠየቅ ትችላለህ፤ ሆኖም አምላክህ ይሖዋ ገብተህ በምትወርሳት ምድር በሥራህ ሁሉ እንዲባርክህ ወንድምህን ወለድ አታስከፍለው። 21  “ለአምላክህ ለይሖዋ ስእለት ከተሳልክ ለመፈጸም አትዘግይ። ምክንያቱም አምላክህ ይሖዋ በእርግጥ ከአንተ ይፈልገዋል፤ አለዚያ ኃጢአት ይሆንብሃል። 22  ሳትሳል ከቀረህ ግን ኃጢአት አይሆንብህም። 23  ከአፍህ የወጣውን ቃል ጠብቅ፤ ለአምላክህ ለይሖዋ የፈቃደኝነት መባ አድርገህ ለማቅረብ በገዛ አንደበትህ የተሳልከውን ፈጽም። 24  “ወደ ባልንጀራህ የወይን እርሻ ከገባህ እስክትጠግብ ድረስ ወይን መብላት ትችላለህ፤ በዕቃህ ግን ምንም ይዘህ አትሂድ። 25  “ወደ ባልንጀራህ የእህል ማሳ ከገባህ እሸት ቀጥፈህ መብላት ትችላለህ፤ ሆኖም የባልንጀራህን እህል በማጭድ ማጨድ የለብህም።
[]
[]
[]
[]
12,570
24  “አንድ ሰው አንዲት ሴት ቢያገባ ሆኖም ነውር የሆነ ነገር አግኝቶባት ቅር ቢሰኝ የፍቺ የምሥክር ወረቀት ጽፎ በመስጠት ከቤቱ ያሰናብታት። 2  እሷም ከእሱ ቤት ከወጣች በኋላ የሌላ ሰው ሚስት መሆን ትችላለች። 3  በኋላ ያገባትም ሰው ቢጠላትና የፍቺ የምሥክር ወረቀት ጽፎ በመስጠት ከቤቱ ቢያሰናብታት ወይም አግብቷት የነበረው ሁለተኛው ሰው ቢሞት 4  ከቤቱ አሰናብቷት የነበረው የመጀመሪያው ባለቤቷ ከረከሰች በኋላ እንደገና ሚስቱ አድርጎ እንዲወስዳት አይፈቀድለትም፤ ምክንያቱም ይህ በይሖዋ ፊት አስጸያፊ ነው። አምላክህ ይሖዋ ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ላይ ኃጢአት አታምጣ። 5  “አንድ ሰው አዲስ ሙሽራ ከሆነ በሠራዊቱ ውስጥ ማገልገል የለበትም፤ ወይም ምንም ዓይነት ሌላ ሥራ ሊሰጠው አይገባም። ለአንድ ዓመት ያህል ከምንም ነገር ነፃ ሆኖ ይቆይ፤ በቤቱም ተቀምጦ ሚስቱን ያስደስታት። 6  “ማንም ሰው ወፍጮን ወይም መጅን የብድር መያዣ አድርጎ መውሰድ የለበትም፤ ምክንያቱም የሰውየውን መተዳደሪያ መያዣ አድርጎ መውሰድ ይሆንበታል። 7  “አንድ ሰው ከእስራኤላውያን ወንድሞቹ መካከል አንዱን አፍኖ በመውሰድ በደል ሲፈጽምበትና ሲሸጠው ቢገኝ አፍኖ የወሰደው ሰው ይገደል። ክፉ የሆነውን ከመካከልህ አስወግድ። 8  “የሥጋ ደዌ ቢከሰት ሌዋውያን ካህናት የሚሰጧችሁን መመሪያዎች ሁሉ በጥንቃቄ ተከተሉ። እኔ የሰጠኋቸውንም ትእዛዝ በጥንቃቄ ፈጽሙ። 9  ከግብፅ በወጣችሁ ጊዜ መንገድ ላይ ሳላችሁ አምላካችሁ ይሖዋ በሚርያም ላይ ያደረገውን አስታውሱ። 10  “ለባልንጀራህ ማንኛውንም ነገር ብታበድር መያዣ አድርጎ የሚሰጥህን ነገር ለመውሰድ ወደ ቤቱ አትግባ። 11  ውጭ ቆመህ ጠብቅ፤ ያበደርከውም ሰው መያዣ አድርጎ የሚሰጥህን ነገር ውጭ ድረስ ያምጣልህ። 12  ሰውየው ከተቸገረ መያዣ አድርጎ የሰጠህን ነገር አንተ ጋ አታሳድር። 13  ልክ ፀሐይ ስትጠልቅ መያዣውን ልትመልስለት ይገባል፤ እሱም ለብሶት ይተኛል፤ ደግሞም ይባርክሃል፤ በአምላክህም በይሖዋ ፊት እንደ ጽድቅ ይቆጠርልሃል። 14  “ከወንድሞችህም ሆነ በምድርህ ይኸውም በከተሞችህ ውስጥ ከሚኖሩ የባዕድ አገር ሰዎች መካከል የተቸገረውንና ድሃ የሆነውን ቅጥር ሠራተኛ አታታል። 15  ደሞዙን በዕለቱ ስጠው፤ ችግረኛ በመሆኑና ሕይወቱ የተመካው በደሞዙ ላይ ስለሆነ ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት ስጠው። አለዚያ በአንተ የተነሳ ወደ ይሖዋ ይጮኻል፤ አንተም በኃጢአት ትጠየቃለህ። 16  “አባቶች ልጆቻቸው በሠሩት ነገር መገደል የለባቸውም፤ ልጆችም አባቶቻቸው በሠሩት ነገር መገደል የለባቸውም። አንድ ሰው መገደል ያለበት በገዛ ኃጢአቱ ብቻ ነው። 17  “የባዕድ አገሩን ሰው ወይም አባት የሌለውን ልጅ ፍርድ አታዛባ፤ የመበለቲቱን ልብስ የብድር መያዣ አድርገህ አትውሰድ። 18  አንተም በግብፅ ባሪያ እንደነበርክና አምላክህ ይሖዋ ከዚያ እንደተቤዠህ አስታውስ። እኔም ይህን እንድታደርግ የማዝህ ለዚህ ነው። 19  “በማሳህ ላይ ያለውን እህል በምታጭድበት ጊዜ በማሳው ላይ ነዶ ብትረሳ ያን ለመውሰድ አትመለስ። አምላክህ ይሖዋ የእጅህን ሥራ ሁሉ እንዲባርክልህ ለባዕድ አገሩ ሰው፣ አባት ለሌለው ልጅና ለመበለቲቱ እንዲሆን እዚያው ተወው። 20  “የወይራ ዛፍህን በምታራግፍበት ጊዜ በየቅርንጫፉ ላይ የቀረውን ሙልጭ አድርገህ አታራግፈው። የቀረው ለባዕድ አገሩ ሰው፣ አባት ለሌለው ልጅና ለመበለቲቱ ይሁን። 21  “ከወይን እርሻህ ላይ የወይን ፍሬህን በምትሰበስብበት ጊዜ ተመልሰህ ቃርሚያውን አትልቀም። ለባዕድ አገሩ ሰው፣ አባት ለሌለው ልጅና ለመበለቲቱ መተው አለበት። 22  አንተም በግብፅ ምድር ባሪያ እንደነበርክ አስታውስ። እኔም ይህን እንድታደርግ የማዝህ ለዚህ ነው።
[]
[]
[]
[]
12,571
25  “በሰዎች መካከል አለመግባባት ቢፈጠር ሰዎቹ ዳኞች ፊት መቅረብ ይችላሉ፤ እነሱም ይዳኟቸዋል፤ ጻድቅ የሆነውን ንጹሕ፣ ጥፋተኛ የሆነውን ደግሞ በደለኛ ይሉታል። 2  ጥፋተኛው መገረፍ የሚገባው ሆኖ ከተገኘ ዳኛው መሬት ላይ እንዲያስተኙትና እሱ ባለበት እንዲገረፍ ያደርጋል። የግርፋቱም ቁጥር ከሠራው ጥፋት ጋር የሚመጣጠን ይሁን። 3  እስከ 40 ግርፋት ሊገርፈው ይችላል፤ ከዚያ ማስበለጥ ግን የለበትም። ከዚህ የበለጠ ብዙ ግርፋት ከገረፈው ግን ወንድምህ በፊትህ ይዋረዳል። 4  “እህል እያበራየ ያለውን በሬ አፉን አትሰር። 5  “ወንድማማቾች አንድ ላይ ሲኖሩ ቆይተው ከመካከላቸው አንዱ ወንድ ልጅ ሳይወልድ ቢሞት የሟቹ ሚስት ከቤተሰቡ ውጭ የሆነ ሰው ማግባት የለባትም። የባሏ ወንድም ወደ እሷ በመሄድ ሚስቱ አድርጎ ይውሰዳት፤ የዋርሳነት ግዴታውንም ይፈጽምላት። 6  መጀመሪያ የምትወልደው ልጅ በሟች ወንድሙ ስም ይጠራል፤ ይህ የሚሆነው የሟቹ ስም ከእስራኤል መካከል እንዳይጠፋ ነው። 7  “ሰውየው የሟች ወንድሙን ሚስት ለማግባት ፈቃደኛ ካልሆነ መበለት የሆነችው ሴት በከተማዋ በር ወደሚገኙት ሽማግሌዎች ሄዳ ‘የባሌ ወንድም የወንድሙ ስም ከእስራኤል መካከል እንዳይጠፋ ለማድረግ ፈቃደኛ አልሆነም። የዋርሳነት ግዴታውን ሊፈጽምልኝ አልተስማማም’ ትበላቸው። 8  የከተማዋ ሽማግሌዎችም ጠርተው ያናግሩት። እሱም ‘እኔ እሷን ማግባት አልፈልግም’ ብሎ በሐሳቡ ከጸና 9  የወንድሙ ሚስት በሽማግሌዎቹ ፊት ወደ እሱ ቀርባ ጫማውን ከእግሩ ላይ ታውልቅ፤ ከዚያም ፊቱ ላይ ትትፋበትና ‘የወንድሙን ቤት በማይሠራ ሰው ላይ የሚደረግበት እንዲህ ነው’ ትበል። 10  ከዚያ በኋላ የዚያ ሰው ቤተሰብ ስም በእስራኤል ውስጥ ‘ጫማው የወለቀበት ሰው ቤት’ ይባላል። 11  “ሁለት ሰዎች ቢደባደቡና የአንደኛው ሚስት ባሏን ከደብዳቢው እጅ ለማስጣል ስትል እጇን ዘርግታ ብልቱን ብትይዝ 12  እጇን ቁረጠው። ልታዝንላት አይገባም። 13  “በከረጢትህ ውስጥ ትልቅና ትንሽ የሆኑ ሁለት ዓይነት የሚዛን ድንጋዮች አይኑሩህ። 14  በቤትህም ውስጥ ትልቅና ትንሽ የሆኑ ሁለት ዓይነት መስፈሪያዎች አይኑሩህ። 15  አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝም ትክክለኛና ሐቀኛ ሚዛን እንዲሁም ትክክለኛና ሐቀኛ መስፈሪያ ይኑርህ። 16  ምክንያቱም እንዲህ ያሉ ነገሮችን በማድረግ ፍትሕ የጎደለው ድርጊት የሚፈጽም ሰው ሁሉ በአምላክህ በይሖዋ ፊት አስጸያፊ ነው። 17  “ከግብፅ በወጣችሁ ጊዜ መንገድ ላይ ሳላችሁ አማሌቃውያን ያደረጉባችሁን ነገር አስታውሱ፤ 18  በጉዞ ላይ ሳለህ ደክመህና ዝለህ በነበረበት ጊዜ አግኝተውህ ከኋላ ከኋላህ እያዘገሙ በነበሩት ሁሉ ላይ እንዴት ጥቃት እንደሰነዘሩ አስታውስ። አምላክንም አልፈሩም። 19  አምላክህ ይሖዋ ርስት አድርገህ እንድትወርሳት በሚሰጥህ ምድር ላይ አምላክህ ይሖዋ በዙሪያህ ካሉት ጠላቶችህ ሁሉ በሚያሳርፍህ ጊዜ አማሌቃውያንን ከሰማይ በታች ጨርሶ እንዳይታወሱ አድርገህ ጠራርገህ አጥፋቸው። ይህን አትርሳ።
[]
[]
[]
[]
12,572
26  “አምላክህ ይሖዋ ርስት አድርጎ የሚሰጥህን ምድር ገብተህ ስትወርስና በዚያ መኖር ስትጀምር 2  አምላክህ ይሖዋ ከሚሰጥህ ምድር ከምትሰበስበው ይኸውም ምድሪቱ ከምታፈራው ፍሬ ሁሉ በኩር የሆነውን ወስደህ በቅርጫት ውስጥ በማድረግ አምላክህ ይሖዋ ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን ወደሚመርጠው ስፍራ ይዘህ ሂድ። 3  በወቅቱ ወደሚያገለግለው ካህን ሄደህ ‘ይሖዋ ለእኛ ለመስጠት ለአባቶቻችን ወደማለላቸው ምድር መግባቴን ዛሬ ለአምላክህ ለይሖዋ አሳውቃለሁ’ በለው። 4  “ከዚያም ካህኑ ቅርጫቱን ከእጅህ ላይ ወስዶ በአምላክህ በይሖዋ መሠዊያ ፊት ያስቀምጠዋል። 5  አንተም በአምላክህ በይሖዋ ፊት እንዲህ ብለህ ተናገር፦ ‘አባቴ ዘላን አራማዊ ነበር፤ እሱም ወደ ግብፅ ወርዶ በቁጥር አነስተኛ ከሆነው ቤተሰቡ ጋር የባዕድ አገር ሰው ሆኖ መኖር ጀመረ። ሆኖም በዚያ ሲኖር ኃያልና ቁጥሩ የበዛ ታላቅ ብሔር ሆነ። 6  ግብፃውያንም ክፉኛ ያንገላቱንና ይጨቁኑን እንዲሁም በላያችን ላይ ከባድ የባርነት ቀንበር ይጭኑብን ነበር። 7  እኛም ወደ አባቶቻችን አምላክ ወደ ይሖዋ ጮኽን፤ ይሖዋም ጩኸታችንን ሰማ፤ ጉስቁልናችንን፣ መከራችንንና የደረሰብንን ጭቆናም ተመለከተ። 8  በመጨረሻም ይሖዋ በኃያል እጅና በተዘረጋ ክንድ፣ አስፈሪ ነገሮችን በማድረግ እንዲሁም ድንቅ ምልክቶችን በማሳየትና ተአምራትን በመፈጸም ከግብፅ አወጣን። 9  ከዚያም ወደዚህ ስፍራ አምጥቶ ይህችን ምድር ይኸውም ወተትና ማር የምታፈሰውን ምድር ሰጠን። 10  ይኸው አሁን ይሖዋ የሰጠኝ ምድር ካፈራችው ፍሬ በኩር የሆነውን አምጥቻለሁ።’ “ይህን በአምላክህ በይሖዋ ፊት አስቀምጠው፤ አንተም በአምላክህ በይሖዋ ፊት ስገድ። 11  ከዚያም አንተ፣ ሌዋዊውና በመካከልህ የሚኖረው የባዕድ አገር ሰው አምላክህ ይሖዋ ለአንተና ለቤተሰብህ በሰጠው መልካም ነገር ሁሉ ትደሰታላችሁ። 12  “የአሥራት ዓመት በሆነው በሦስተኛው ዓመት የምርትህን አንድ አሥረኛ አሥራት እንዲሆን ለይተህ ካስቀመጥክ በኋላ ለሌዋዊው፣ ለባዕድ አገሩ ሰው፣ አባት ለሌለው ልጅና ለመበለቲቱ ትሰጣለህ፤ እነሱም በከተሞችህ ውስጥ እስኪጠግቡ ድረስ ይበሉታል። 13  ከዚያም በአምላክህ በይሖዋ ፊት እንዲህ ትላለህ፦ ‘በሰጠኸኝ ትእዛዝ መሠረት ቅዱስ የሆነውን ነገር ከቤት አውጥቼ ለሌዋዊው፣ ለባዕድ አገሩ ሰው፣ አባት ለሌለው ልጅና ለመበለቲቱ ሰጥቻለሁ። ትእዛዛትህን አልጣስኩም ወይም ችላ አላልኩም። 14  ሐዘን ላይ በተቀመጥኩበት ጊዜ ከእሱ አልበላሁም፤ ወይም ረክሼ ባለሁበት ጊዜ ከእሱ ላይ ምንም ነገር አላነሳሁም፤ አሊያም ለሞተ ሰው ከእሱ ላይ ምንም ነገር አልሰጠሁም። የአምላኬን የይሖዋን ቃል ታዝዣለሁ፤ ያዘዝከኝንም ሁሉ ፈጽሜአለሁ። 15  እንግዲህ አሁን ከቅዱስ ማደሪያህ ከሰማያት ሆነህ ተመልከት፤ ሕዝብህን እስራኤልንና ለአባቶቻችን በማልክላቸው መሠረት የሰጠኸንን ምድር ይኸውም ወተትና ማር የምታፈሰውን ምድር ባርክ።’ 16  “አምላክህ ይሖዋ እነዚህን ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች እንድትጠብቅ ዛሬ ያዝሃል። አንተም በሙሉ ልብህና በሙሉ ነፍስህ ፈጽማቸው፤ ጠብቃቸውም። 17  ይሖዋ በመንገዶቹ ከሄድክ እንዲሁም ሥርዓቶቹን፣ ትእዛዛቱንና ድንጋጌዎቹን ከጠበቅክና ቃሉን ከሰማህ አምላክህ እንደሚሆን ዛሬ ነግሮሃል። 18  አንተም ይሖዋ ቃል በገባልህ መሠረት ሕዝቡ ማለትም ልዩ ንብረቱ እንደምትሆንና ትእዛዛቱን በሙሉ እንደምትጠብቅ የተናገርከውን ቃል በዛሬው ዕለት ሰምቷል፤ 19  አንተ ለአምላክህ ለይሖዋ ቅዱስ ሕዝብ ሆነህ ስትገኝ እሱ ደግሞ በገባው ቃል መሠረት ውዳሴ፣ ዝናና ክብር በማጎናጸፍ፣ ከፈጠራቸው ሌሎች ብሔራት ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያደርግሃል።”
[]
[]
[]
[]
12,573
27  ከዚያም ሙሴ ከእስራኤል ሽማግሌዎች ጋር በመሆን ሕዝቡን እንዲህ ሲል አዘዘ፦ “እኔ ዛሬ የምሰጣችሁን ትእዛዛት በሙሉ ጠብቁ። 2  አምላካችሁ ይሖዋ ወደሚሰጣችሁ ምድር ለመግባት ዮርዳኖስን በምትሻገሩበት ቀን ትላልቅ ድንጋዮችን አቁማችሁ ለስኗቸው። 3  ከዚያም የአባቶችህ አምላክ ይሖዋ ቃል በገባልህ መሠረት አምላክህ ይሖዋ ወደሚሰጥህ ምድር ይኸውም ወተትና ማር ወደምታፈሰው ምድር ለመግባት በምትሻገርበት ጊዜ የዚህን ሕግ ቃላት በሙሉ ጻፍባቸው። 4  ዮርዳኖስን ስትሻገሩ ዛሬ በሰጠኋችሁ ትእዛዝ መሠረት እነዚህን ድንጋዮች በኤባል ተራራ ላይ አቁሟቸው፤ ደግሞም ለስኗቸው። 5  በዚያም ለአምላክህ ለይሖዋ መሠዊያ ይኸውም የድንጋይ መሠዊያ ሥራ። ድንጋዮቹንም የብረት መሣሪያ አታስነካቸው። 6  የአምላክህን የይሖዋን መሠዊያ ካልተጠረበ ድንጋይ ሥራ፤ በላዩም ላይ ለአምላክህ ለይሖዋ የሚቃጠሉ መባዎችን አቅርብ። 7  የኅብረት መሥዋዕቶችንም አቅርብ፤ መሥዋዕቶቹንም እዚያው ብላቸው፤ አንተም በአምላክህ በይሖዋ ፊት ደስ ይልሃል። 8  በድንጋዮቹም ላይ የዚህን ሕግ ቃላት በሙሉ በግልጽ ጻፍባቸው።” 9  ከዚያም ሙሴና ሌዋውያኑ ካህናት እስራኤላውያንን በሙሉ እንዲህ አሏቸው፦ “እስራኤል ሆይ፣ ጸጥ ብለህ አዳምጥ። በዛሬው ቀን አንተ የአምላክህ የይሖዋ ሕዝብ ሆነሃል። 10  የአምላክህን የይሖዋን ቃል ስማ፤ እኔ ዛሬ የማዝህን የእሱን ትእዛዛትና ሥርዓቶች ፈጽም።” 11  ሙሴም በዚያ ቀን ሕዝቡን እንዲህ ሲል አዘዘ፦ 12  “ዮርዳኖስን በምትሻገሩበት ጊዜ በገሪዛን ተራራ ላይ ቆመው ሕዝቡን የሚባርኩት ነገዶች ስምዖን፣ ሌዊ፣ ይሁዳ፣ ይሳኮር፣ ዮሴፍ እና ቢንያም ናቸው። 13  እርግማኑን ለማሰማት በኤባል ተራራ ላይ የሚቆሙት ደግሞ ሮቤል፣ ጋድ፣ አሴር፣ ዛብሎን፣ ዳን እና ንፍታሌም ናቸው። 14  ሌዋውያኑም ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ ለእያንዳንዱ እስራኤላዊ እንዲህ ብለው ይናገራሉ፦ 15  “‘ይሖዋ የሚጠላውን አስጸያፊ ነገር ይኸውም የአንድ የእጅ ጥበብ ባለሙያ የእጅ ሥራ ውጤት የሆነውን የተቀረጸ ምስል ወይም ከብረት የተሠራ ሐውልት የሚሠራና በስውር የሚያስቀምጥ ሰው የተረገመ ይሁን።’ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ብሎ ይመልሳል።) 16  “‘አባቱን ወይም እናቱን የሚንቅ የተረገመ ይሁን።’ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይላል።) 17  “‘የጎረቤቱን የወሰን ምልክት የሚገፋ የተረገመ ይሁን።’ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይላል።) 18  “‘ዓይነ ስውሩን መንገድ የሚያሳስት የተረገመ ይሁን።’ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይላል።) 19  “‘የባዕድ አገሩን ሰው፣ አባት የሌለውን ልጅ ወይም የመበለቲቱን ፍርድ የሚያዛባ የተረገመ ይሁን።’ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይላል።) 20  “‘ከአባቱ ሚስት ጋር የሚተኛ አባቱን ስላዋረደ የተረገመ ይሁን።’ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይላል።) 21  “‘ከማንኛውም ዓይነት እንስሳ ጋር የሚተኛ የተረገመ ይሁን።’ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይላል።) 22  “‘የአባቱ ልጅ ወይም የእናቱ ልጅ ከሆነችው ከእህቱ ጋር የሚተኛ የተረገመ ይሁን።’ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይላል።) 23  “‘ከሚስቱ እናት ጋር የሚተኛ የተረገመ ይሁን።’ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይላል።) 24  “‘ጎረቤቱን አድብቶ በመጠበቅ የሚገድል የተረገመ ይሁን።’ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይላል።) 25  “‘ንጹሑን ሰው ለመግደል ሲል ጉቦ የሚቀበል የተረገመ ይሁን።’ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይላል።) 26  “‘የዚህን ሕግ ቃል ተግባራዊ በማድረግ የማይጠብቅ ሰው የተረገመ ይሁን።’ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይላል።)
[]
[]
[]
[]
12,574
28  “እኔ ዛሬ የማዝህን የአምላክህን የይሖዋን ትእዛዛት ሁሉ በጥንቃቄ በመፈጸም ቃሉን በእርግጥ ብትሰማ አምላክህ ይሖዋ በምድር ላይ ካሉ ብሔራት ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያደርግሃል። 2  የአምላክህን የይሖዋን ቃል ከሰማህ እነዚህ ሁሉ በረከቶች ይወርዱልሃል፤ ተከታትለውም ይደርሱብሃል፦ 3  “በከተማ የተባረክ ትሆናለህ፤ በእርሻም የተባረክ ትሆናለህ። 4  “የሆድህ ፍሬ፣ የመሬትህ ፍሬ፣ የቤት እንስሳህ ግልገል፣ ጥጃህና የበግህ ግልገል የተባረከ ይሆናል። 5  “ቅርጫትህና ቡሃቃህ የተባረከ ይሆናል። 6  “ስትገባ የተባረክ ትሆናለህ፤ ስትወጣም የተባረክ ትሆናለህ። 7  “ይሖዋ በአንተ ላይ የሚነሱ ጠላቶችህ በፊትህ ድል እንዲሆኑ ያደርጋል። ከአንድ አቅጣጫ ጥቃት ይሰነዝሩብሃል፤ ሆኖም በሰባት አቅጣጫ ከፊትህ ይሸሻሉ። 8  ይሖዋ በጎተራህና በምታከናውነው ሥራ ሁሉ ላይ በረከት እንዲፈስልህ ያዛል፤ አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህም ምድር ይባርክሃል። 9  የአምላክህን የይሖዋን ትእዛዛት ከጠበቅክና በመንገዶቹ ከሄድክ ይሖዋ በማለልህ መሠረት ለእሱ ቅዱስ ሕዝብ አድርጎ ያቆምሃል። 10  የምድር ሕዝቦች ሁሉ የይሖዋ ስም በአንተ አማካኝነት እንደሚጠራ ያያሉ፤ እነሱም ይፈሩሃል። 11  “ይሖዋ ለአንተ ለመስጠት ለአባቶችህ በማለላቸው ምድር ላይ ይሖዋ የሆድህ ፍሬ እንዲበዛ፣ የቤት እንስሶችህ እንዲረቡና መሬትህ ፍሬያማ እንዲሆን በማድረግ ያበለጽግሃል። 12  ይሖዋ በምድርህ ላይ በወቅቱ ዝናብን ለማዝነብና የእጅህን ሥራ ሁሉ ለመባረክ ሲል መልካም የሆነውን ጎተራውን ይኸውም ሰማይን ይከፍትልሃል። አንተም ለብዙ ብሔራት ታበድራለህ፤ አንተ ግን አትበደርም። 13  ይሖዋ ራስ እንጂ ጅራት አያደርግህም፤ ትጠብቃቸውና ትፈጽማቸው ዘንድ እኔ ዛሬ የማዝህን የአምላክህን የይሖዋን ትእዛዛት ከፈጸምክ መቼም ቢሆን ከላይ እንጂ ከታች አትሆንም። 14  ሌሎች አማልክትን ለማገልገል ብላችሁ እነሱን በመከተል እኔ ዛሬ ከምሰጣችሁ ትእዛዛት ሁሉ ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ ዞር አትበሉ። 15  “እኔ ዛሬ የማዝህን የእሱን ትእዛዛትና ደንቦች በሙሉ በጥንቃቄ የማትፈጽምና የአምላክህን የይሖዋን ቃል የማትሰማ ከሆነ ግን እነዚህ ሁሉ እርግማኖች ይወርዱብሃል፤ ተከታትለውም ይደርሱብሃል፦ 16  “በከተማ የተረገምክ ትሆናለህ፤ በእርሻም የተረገምክ ትሆናለህ። 17  “ቅርጫትህና ቡሃቃህ የተረገመ ይሆናል። 18  “የሆድህ ፍሬ፣ የመሬትህ ፍሬ፣ ጥጃህና የበግህ ግልገል የተረገመ ይሆናል። 19  “ስትገባ የተረገምክ ትሆናለህ፤ ስትወጣም የተረገምክ ትሆናለህ። 20  “ይሖዋ በፈጸምካቸው መጥፎ ድርጊቶችና እኔን በመተውህ የተነሳ ፈጥነህ እስክትደመሰስ እንዲሁም እስክትጠፋ ድረስ፣ በምታከናውነው በማንኛውም ሥራ ላይ እርግማንን፣ ግራ መጋባትንና ቅጣትን ያመጣብሃል። 21  ይሖዋ ከምትወርሳት ምድር ላይ ጨርሶ እስኪያጠፋህ ድረስ በሽታ እንዲጣበቅብህ ያደርጋል። 22  ይሖዋ በሳንባ በሽታ፣ በኃይለኛ ትኩሳት፣ ሰውነትን በሚያስቆጣ በሽታ፣ በሚያነድ ትኩሳት፣ በሰይፍ፣ ሰብል በሚለበልብ ነፋስና በዋግ ይመታሃል፤ እነሱም እስክትጠፋ ድረስ ያሳድዱሃል። 23  ከራስህ በላይ ያለው ሰማይ መዳብ፣ ከበታችህ ያለውም ምድር ብረት ይሆንብሃል። 24  ይሖዋ በምድርህ ላይ የሚዘንበውን ዝናብ ትቢያና አቧራ ያደርገዋል፤ ይህም እስክትጠፋ ድረስ ከሰማይ ይወርድብሃል። 25  ይሖዋ በጠላቶችህ ፊት እንድትሸነፍ ያደርግሃል። በአንድ አቅጣጫ ጥቃት ትሰነዝርባቸዋለህ፤ ሆኖም በሰባት አቅጣጫ ከፊታቸው ትሸሻለህ፤ የምድርም መንግሥታት ሁሉ በአንተ ላይ የደረሰውን ሲያዩ በፍርሃት ይርዳሉ። 26  ሬሳህ ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት ሁሉ ምግብ ይሆናል፤ አስፈራርቶ የሚያባርራቸውም አይኖርም። 27  “ይሖዋ ፈውስ ልታገኝ በማትችልበት የግብፅ እባጭ፣ ኪንታሮት፣ ችፌና ሽፍታ ይመታሃል። 28  ይሖዋ በእብደት፣ በዕውርነትና በግራ መጋባት ይመታሃል። 29  ጨለማ የዋጠው ዓይነ ስውር በዳበሳ እንደሚሄድ ሁሉ አንተም በእኩለ ቀን በዳበሳ ትሄዳለህ፤ የምታደርገው ነገር ሁሉ አይሳካልህም፤ ሁልጊዜ ትጭበረበራለህ፤ እንዲሁም ትዘረፋለህ፤ የሚያስጥልህም የለም። 30  አንዲትን ሴት ታጫለህ፤ ሆኖም ሌላ ሰው ይደፍራታል። ቤት ትሠራለህ፤ ሆኖም አትኖርበትም። ወይን ትተክላለህ፤ ግን አትበላውም። 31  በሬህ ዓይንህ እያየ ይታረዳል፤ ሆኖም ከእሱ ላይ ምንም አትቀምስም። አህያህም ከፊትህ ተዘርፎ ይወሰዳል፤ ሆኖም አይመለስልህም። በጎችህ ለጠላቶችህ ይሰጣሉ፤ የሚደርስልህ ግን የለም። 32  ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ ዓይንህ እያየ ለሌላ ሕዝብ ይሰጣሉ፤ አንተም ሁልጊዜ የእነሱን መመለስ ትናፍቃለህ፤ ሆኖም እጆችህ ምንም ኃይል አይኖራቸውም። 33  የምድርህን ፍሬና ያመረትከውን ሁሉ የማታውቀው ሕዝብ ይበላዋል፤ አንተም ሁልጊዜ ትጭበረበራለህ፤ ደግሞም ትረገጣለህ። 34  ዓይንህ የሚያየውም ነገር ያሳብድሃል። 35  “ይሖዋ በሚያሠቃይና ሊድን በማይችል እባጭ ጉልበቶችህንና እግሮችህን ይመታል፤ እባጩም ከእግር ጥፍርህ እስከ ራስ ቅልህ ድረስ ይወርስሃል። 36  ይሖዋ አንተንና በላይህ ያነገሥከውን ንጉሥ፣ አንተም ሆንክ አባቶችህ ወደማታውቁት ብሔር ይወስዳችኋል፤ እዚያም ሌሎች አማልክትን ይኸውም ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩ አማልክትን ታገለግላለህ። 37  ይሖዋ በሚያስገባህ ሕዝብ ሁሉ መካከል ማስፈራሪያ፣ መቀለጃና መሳለቂያ ትሆናለህ። 38  “ወደ እርሻህ ብዙ ዘር ይዘህ ትወጣለህ፤ የምትሰበስበው ግን ጥቂት ይሆናል፤ ምክንያቱም አንበጦች ያወድሙታል። 39  ወይን ትተክላለህ፤ ታለማለህም፤ ይሁንና ምንም ወይን አትጠጣም፤ እንዲሁም አንዳች አትሰበስብም፤ ምክንያቱም ትል ይበላዋል። 40  በግዛትህ ሁሉ የወይራ ዛፍ ይኖርሃል፤ ሰውነትህን የምትቀባው ዘይት ግን አይኖርህም፤ ምክንያቱም የወይራ ፍሬዎችህ ይረግፋሉ። 41  ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ትወልዳለህ፤ ሆኖም በምርኮ ስለሚወሰዱ የአንተ አይሆኑም። 42  ዛፎችህንና የምድርህን ፍሬ ሁሉ የሚርመሰመሱ ነፍሳት ይወሩታል። 43  አንተ ዝቅ ዝቅ እያልክ ስትሄድ በመካከልህ የሚኖረው የባዕድ አገር ሰው ግን በአንተ ላይ ከፍ ከፍ እያለ ይሄዳል። 44  እሱ ያበድርሃል እንጂ አንተ አታበድረውም። እሱ ራስ ይሆናል፤ አንተ ግን ጅራት ትሆናለህ። 45  “አምላክህ ይሖዋ ያዘዘህን የእሱን ትእዛዛትና ደንቦች ባለመጠበቅ ቃሉን ስላልሰማህ እነዚህ እርግማኖች ሁሉ እስክትጠፋ ድረስ ይወርዱብሃል፤ ያሳድዱሃል፤ ተከታትለውም ይደርሱብሃል። 46  እነሱም በአንተና በልጆችህ ላይ ለዘላለም ምልክትና ማስጠንቀቂያ ይሆናሉ፤ 47  ምክንያቱም ሁሉም ነገር ተትረፍርፎልህ ሳለ አምላክህን ይሖዋን በደስታና በሐሴት አላገለገልከውም። 48  ይሖዋ ጠላቶችህን በአንተ ላይ ያስነሳቸዋል፤ አንተም ተርበህ፣ ተጠምተህ፣ ተራቁተህና ሁሉን ነገር አጥተህ እያለ ታገለግላቸዋለህ። እሱም እስኪያጠፋህ ድረስ በአንገትህ ላይ የብረት ቀንበር ይጭንብሃል። 49  “ይሖዋ ቋንቋውን የማትረዳውን በሩቅ ያለን አንድ ብሔር ከምድር ጫፍ አስነስቶ ያመጣብሃል፤ እሱም እንደ ንስር ተምዘግዝጎ ይወርድብሃል፤ 50  ይህ ብሔር ለሽማግሌ የማያዝን ወይም ለወጣት የማይራራ ፊቱ የሚያስፈራ ብሔር ነው። 51  እስክትጠፋም ድረስ የእንስሶችህን ግልገልና የምድርህን ፍሬ ይበላሉ። አንተንም እስኪያጠፉህ ድረስ ምንም እህል፣ አዲስ የወይን ጠጅም ሆነ ዘይት፣ ጥጃም ሆነ የበግ ግልገል አያስተርፉልህም። 52  የምትተማመንባቸው ረጃጅምና የተመሸጉ ቅጥሮችህ እስኪወድቁም ድረስ በከተሞችህ ውስጥ እንዳለህ ዘግተውብህ ይከቡሃል። አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህም ምድር ሁሉ ላይ በከተሞችህ ውስጥ እንዳለህ ይከቡሃል። 53   ከሚያስጨንቀው ከበባና ጠላትህ በአንተ ላይ ከሚያደርሰው ሥቃይ የተነሳ አምላክህ ይሖዋ የሰጠህን የሆድህን ፍሬ ይኸውም የወንዶችና የሴቶች ልጆችህን ሥጋ ትበላለህ። 54  “ሌላው ቀርቶ በመካከልህ ያለ በምቾትና በቅምጥልነት ይኖር የነበረ ሰው እንኳ በወንድሙ፣ በሚወዳት ሚስቱ ወይም በተረፉት ልጆቹ ላይ ይጨክናል፤ 55  ከሚበላው የልጆቹ ሥጋ ላይ ምንም ነገር አያካፍላቸውም፤ ምክንያቱም ከሚያስጨንቀው ከበባና ጠላትህ በከተሞችህ ላይ ከሚያመጣው ሥቃይ የተነሳ የሚተርፈው ምንም ነገር አይኖረውም። 56  ከቅምጥልነቷ የተነሳ መሬት ለመርገጥ እንኳ ትጸየፍ የነበረች በመካከልህ ያለች ቅምጥልና በምቾት የምትኖር ሴትም በምትወደው ባሏ፣ በወንድ ልጇ ወይም በሴት ልጇ ላይ ትጨክናለች፤ 57   ሌላው ቀርቶ ከወሊድ በኋላ ከእግሮቿ መካከል በሚወጣው ነገር ሁሉና በምትወልዳቸው ልጆች ላይ ትጨክናለች፤ ምክንያቱም ከሚያስጨንቀው ከበባና ጠላትህ በከተሞችህ ላይ ከሚያመጣው ሥቃይ የተነሳ በድብቅ ትበላቸዋለች። 58  “በዚህ መጽሐፍ ላይ የተጻፈውን የዚህን ሕግ ቃላት ሁሉ በጥንቃቄ የማትጠብቅ እንዲሁም ክብራማና አስፈሪ የሆነውን የአምላክህን የይሖዋን ስም የማትፈራ ከሆነ 59  ይሖዋ በአንተና በልጆችህ ላይ ከባድ የሆኑ መቅሰፍቶችን ይኸውም ታላቅና ለረጅም ጊዜ የሚዘልቁ መቅሰፍቶችን እንዲሁም አስከፊና ለረጅም ጊዜ የሚቆዩ በሽታዎችን ያመጣል። 60  ትፈራቸው የነበሩትን የግብፅ በሽታዎች ሁሉ መልሶ ያመጣብሃል፤ እነሱም በአንተ ላይ ይጣበቃሉ። 61  በተጨማሪም ይሖዋ በዚህ የሕግ መጽሐፍ ውስጥ ያልተጻፉ በሽታዎችን ወይም መቅሰፍቶችን ሁሉ እስክትጠፋ ድረስ በአንተ ላይ ያመጣብሃል። 62  ብዛታችሁ በሰማያት ላይ እንዳሉ ከዋክብት የነበረ ቢሆንም የአምላካችሁን የይሖዋን ቃል ስላልሰማችሁ የምትቀሩት በጣም ጥቂት ትሆናላችሁ። 63  “ይሖዋ እናንተን በማበልጸግና በማብዛት እጅግ ይደሰት እንደነበረው ሁሉ ይሖዋ እናንተን በማጥፋትና በመደምሰስም እጅግ ይደሰታል፤ ገብታችሁ ከምትወርሷት ምድር ላይ ተጠራርጋችሁ ትጠፋላችሁ። 64  “ይሖዋ ከአንዱ የምድር ጫፍ እስከ ሌላኛው የምድር ጫፍ በብሔራት ሁሉ መካከል ይበትንሃል፤ እዚያም አንተም ሆንክ አባቶችህ የማታውቋቸውን ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩ አማልክት ታገለግላለህ። 65  በእነዚያም ብሔራት መካከል ሰላም አይኖርህም፤ ወይም ለእግርህ ማሳረፊያ የሚሆን ቦታ አታገኝም። ከዚህ ይልቅ ይሖዋ በዚያ ልብህ እንዲሸበር፣ ዓይንህ እንዲፈዝና በተስፋ መቁረጥ እንድትዋጥ ያደርጋል። 66  ሕይወትህ ለከፍተኛ አደጋ ይጋለጣል፤ ሌሊትና ቀንም በፍርሃት ትዋጣለህ፤ ለሕይወትህም ዋስትና ታጣለህ። 67  በልብህ ውስጥ ካለው ፍርሃትና በዓይንህ ከምታየው ነገር የተነሳ ጠዋት ላይ ‘ምነው በመሸ!’ ትላለህ፤ ምሽት ላይ ደግሞ ‘ምነው በነጋ!’ ትላለህ። 68  ‘ዳግመኛ አታያትም’ ባልኩህ መንገድ ይሖዋ ወደ ግብፅ በመርከቦች ይመልስሃል፤ በዚያም ራሳችሁን ለጠላቶቻችሁ ወንድ ባሪያዎችና ሴት ባሪያዎች አድርጋችሁ ለመሸጥ ትገደዳላችሁ፤ የሚገዛችሁ ግን አይኖርም።”
[]
[]
[]
[]
12,575
29  ይሖዋ በኮሬብ ከእስራኤል ሕዝብ ጋር ከገባው ቃል ኪዳን በተጨማሪ ሙሴ በሞዓብ ምድር ከእነሱ ጋር እንዲገባ ያዘዘው ቃል ኪዳን ቃላት እነዚህ ናቸው። 2  ከዚያም ሙሴ እስራኤላውያንን በሙሉ ሰብስቦ እንዲህ አላቸው፦ “ይሖዋ በግብፅ ምድር በፈርዖንና በአገልጋዮቹ ሁሉ እንዲሁም በመላ ምድሩ ላይ ያደረገውን ነገር ሁሉ በገዛ ዓይናችሁ ተመልክታችኋል፤ 3  ደግሞም እነዚያን ታላላቅ የፍርድ እርምጃዎች፣ ድንቅ ምልክቶችና ተአምራት በዓይናችሁ አይታችኋል። 4  ሆኖም ይሖዋ እስከ ዛሬ ድረስ የሚያስተውል ልብ፣ የሚያይ ዓይንና የሚሰማ ጆሮ አልሰጣችሁም። 5  ‘በምድረ በዳ ለ40 ዓመታት በመራኋችሁ ጊዜ ልብሳችሁ ላያችሁ ላይ አላለቀም፤ ጫማችሁም እግራችሁ ላይ አላለቀም። 6  እኔ አምላካችሁ ይሖዋ መሆኔን ታውቁ ዘንድ ዳቦ አልበላችሁም፤ የወይን ጠጅ ወይም ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አልጠጣችሁም።’ 7  በኋላም ወደዚህ ስፍራ መጣችሁ፤ የሃሽቦን ንጉሥ ሲሖን እና የባሳን ንጉሥ ኦግ ሊወጉን ወጡ፤ ሆኖም ድል አደረግናቸው። 8  ከዚያም ምድራቸውን ወስደን ለሮቤላውያን፣ ለጋዳውያንና ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ርስት አድርገን ሰጠናቸው። 9  በመሆኑም የምታደርጉት ነገር ሁሉ መልካም እንዲሆንላችሁ የዚህን ቃል ኪዳን ቃላት ጠብቁ፤ ደግሞም ታዘዙ። 10  “እናንተ ሁላችሁ ይኸውም የየነገዶቻችሁ መሪዎች፣ ሽማግሌዎቻችሁ፣ አለቆቻችሁና በእስራኤል ያለ ወንድ ሁሉ በዛሬው ዕለት በአምላካችሁ በይሖዋ ፊት ቆማችኋል፤ 11  እንዲሁም ልጆቻችሁ፣ ሚስቶቻችሁና ከእንጨት ለቃሚዎቻችሁ አንስቶ እስከ ውኃ ቀጂዎቻችሁ ድረስ፣ በሰፈራችሁ የሚኖሩ የባዕድ አገር ሰዎች ሁሉ በፊቱ ቆመዋል። 12  አሁን እዚህ የተገኘኸው አምላክህ ይሖዋ በዛሬው ዕለት ከአንተ ጋር ወደሚገባው ይኸውም በመሐላ ወደሚያጸናው ወደ አምላክህ ወደ ይሖዋ ቃል ኪዳን እንድትገባ ነው፤ 13  ይህም ለአንተ ቃል በገባውና ለአባቶችህ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ በማለላቸው መሠረት በዛሬው ዕለት አንተን ሕዝቡ አድርጎ ያጸናህ እንዲሁም አምላክህ ይሆን ዘንድ ነው። 14  “እኔ አሁን ይህን ቃል ኪዳን የምገባውም ሆነ ይህን መሐላ የምምለው ለእናንተ ብቻ አይደለም፤ 15  ከዚህ ይልቅ በዛሬው ዕለት በይሖዋ ፊት አብረውን ለቆሙትና በዚህ ዕለት ከእኛ ጋር ለሌሉት ጭምር ነው። 16  (በግብፅ እንዴት እንኖር እንደነበረና በጉዟችንም ላይ የተለያዩ ብሔራትን እንዴት አቋርጠን እንዳለፍን በሚገባ ታውቃላችሁና። 17  በመካከላቸው የነበሩትን የሚያስጠሉ ነገሮች እንዲሁም ከእንጨት፣ ከድንጋይ፣ ከብርና ከወርቅ የተሠሩ አስጸያፊ ጣዖቶቻቸውንም አይታችኋል።) 18  የእነዚያን ብሔራት አማልክት ለማገልገል ከአምላካችን ከይሖዋ ልቡ የሚሸፍት ወንድ ወይም ሴት ወይም ቤተሰብ አሊያም ነገድ በዛሬው ዕለት በመካከላችሁ እንዳይገኝ እንዲሁም መርዛማና መራራ ፍሬ የሚያፈራ ሥር በመካከላችሁ እንዳይኖር ተጠንቀቁ። 19  “አንድ ሰው ይህን የመሐላ ቃል ቢሰማና በመንገዱ ላይ ያገኘውን ሁሉ ጠራርጎ ለማጥፋት በማሰብ ‘እንዳሻኝ ብሆን እንኳ በሰላም እኖራለሁ’ እያለ በልቡ ቢኩራራ 20  ይሖዋ ይቅር ሊለው ፈቃደኛ አይሆንም። ከዚህ ይልቅ የይሖዋ ታላቅ ቁጣ በዚያ ሰው ላይ ይነድዳል፤ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የተጻፉት እርግማኖች በሙሉ ይወርዱበታል፤ ይሖዋም የዚህን ሰው ስም ከሰማይ በታች ይደመስሰዋል። 21  ከዚያም በዚህ የሕግ መጽሐፍ ውስጥ በተጻፈው በቃል ኪዳኑ እርግማን ሁሉ መሠረት ይሖዋ ከሌሎቹ የእስራኤል ነገዶች ሁሉ እሱን ለጥፋት ይለየዋል። 22  “መጪው የልጆቻችሁ ትውልድና ከሩቅ ምድር የሚመጡት የባዕድ አገር ሰዎች በምድሪቱ ላይ የወረዱትን መቅሰፍቶች ይኸውም ይሖዋ በላይዋ ላይ ያመጣውን በሽታ 23  እንዲሁም ይሖዋ በቁጣውና በመዓቱ ሰዶምንና ገሞራን፣ አድማህንና ጸቦይምን እንደገለባበጠ ሁሉ መላዋ ምድር እንዳይዘራባት፣ እንዳታቆጠቁጥ ወይም ምንም ዓይነት ተክል እንዳታበቅል የላከውን ድኝ፣ ጨውና እሳት ሲመለከቱ 24  እነሱም ሆኑ ሁሉም ብሔራት ‘ይሖዋ በዚህች ምድር ላይ እንዲህ ያደረገው ለምንድን ነው? ይህን ታላቅ ቁጣስ ምን አመጣው?’ ይላሉ። 25  ከዚያም እንዲህ ይላሉ፦ ‘ይህ የደረሰባቸው የአባቶቻቸው አምላክ ይሖዋ ከግብፅ ምድር ባወጣቸው ጊዜ ከእነሱ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን በማፍረሳቸው ነው። 26  ሄደውም ሌሎችን አማልክት ይኸውም የማያውቋቸውንና እሱ እንዲያመልኳቸው ያልፈቀደላቸውን አማልክት አገለገሉ፤ ደግሞም ሰገዱላቸው። 27  ይሖዋም በዚህ መጽሐፍ ላይ የተጻፉትን እርግማኖች በሙሉ እስኪያመጣባት ድረስ ቁጣው በምድሪቱ ላይ ነደደ። 28  በመሆኑም ይሖዋ በታላቅ ቁጣውና በኃይለኛው ንዴቱ ከምድራቸው ላይ ነቅሎ አሁን ወዳሉበት ሌላ ምድር አፈለሳቸው።’ 29  “የተሰወሩት ነገሮች የአምላካችን የይሖዋ ናቸው፤ የተገለጡት ነገሮች ግን በዚህ ሕግ ውስጥ ያሉትን ቃላት በሙሉ እንፈጽም ዘንድ ለዘላለም የእኛና የዘሮቻችን ናቸው።
[]
[]
[]
[]
12,576
3  “ከዚያም ተመልሰን ወደ ባሳን የሚወስደውን መንገድ ይዘን ወጣን። የባሳን ንጉሥ ኦግም ከሕዝቡ ሁሉ ጋር በመሆን ኤድራይ ላይ ጦርነት ሊገጥመን ወጣ። 2  በመሆኑም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ ‘እሱንም ሆነ ሕዝቡን ሁሉ እንዲሁም ምድሩን በእጅህ አሳልፌ ስለምሰጥህ አትፍራው፤ አንተም በሃሽቦን ይኖር በነበረው በአሞራውያን ንጉሥ በሲሖን ላይ እንዳደረግከው ሁሉ በእሱም ላይ ታደርግበታለህ።’ 3  ስለዚህ አምላካችን ይሖዋ የባሳንን ንጉሥ ኦግንና ሕዝቡን ሁሉ በእጃችን አሳልፎ ሰጠን፤ እኛም ከሕዝቡ መካከል አንድም ሰው ሳናስቀር ሁሉንም ደመሰስን። 4  ከዚያም ከተሞቹን በሙሉ ያዝን። ከእነሱ ያልወሰድነው አንድም ከተማ አልነበረም፤ በባሳን ባለው በኦግ መንግሥት ሥር የሚገኘውን የአርጎብን ክልል በሙሉ ይኸውም 60 ከተሞችን ወሰድን። 5  እነዚህ ከተሞች በሙሉ በረጃጅም ቅጥሮች የታጠሩ እንዲሁም በሮችና መቀርቀሪያዎች ያሏቸው ነበሩ፤ ከእነዚህም በተጨማሪ በጣም ብዙ የገጠር ከተሞች ነበሩ። 6  ሆኖም እያንዳንዱን ከተማ እንዲሁም ወንዶችን፣ ሴቶችንና ልጆችን በማጥፋት በሃሽቦን ንጉሥ በሲሖን ላይ እንዳደረግነው ሁሉ እነዚህንም ሙሉ በሙሉ ደመሰስናቸው። 7  ከብቶቹንና ከየከተማው የማረክናቸውን ነገሮች ሁሉ ለራሳችን ወሰድን። 8  “በዚያን ጊዜም ከአርኖን ሸለቆ አንስቶ እስከ ሄርሞን ተራራ ድረስ ባለው በዮርዳኖስ ክልል ከነበሩት ከሁለቱ የአሞራውያን ነገሥታት እጅ ምድራቸውን ወሰድን፤ 9  (ሲዶናውያን የሄርሞንን ተራራ ሲሪዮን ብለው ሲጠሩት አሞራውያን ደግሞ ሰኒር ብለው ይጠሩት ነበር፤) 10  በባሳን ባለው በኦግ መንግሥት ሥር የሚገኙትን ከተሞች ይኸውም በአምባው ላይ የሚገኙትን ከተሞች በሙሉ፣ ጊልያድን በሙሉ፣ ባሳንን በሙሉ እስከ ሳልካ ድረስ እንዲሁም ኤድራይን ወሰድን። 11  ከረፋይም ወገን የተረፈው የባሳን ንጉሥ ኦግ ብቻ ነበር። ቃሬዛው እንኳ የብረት ቃሬዛ ነበር፤ አሁንም የአሞናውያን ከተማ በሆነችው በራባ ይገኛል። በሰው ክንድ ሲለካ ርዝመቱ ዘጠኝ ክንድ ስፋቱ ደግሞ አራት ክንድ ነበር። 12  በዚያን ጊዜ ይህችን ምድር ወረስን፤ በአርኖን ሸለቆ አጠገብ ከምትገኘው ከአሮዔር አንስቶ ያለውን ምድር እንዲሁም የጊልያድን ተራራማ አካባቢ እኩሌታ ከነከተሞቹ ለሮቤላውያንና ለጋዳውያን ሰጠኋቸው። 13  የቀረውን የጊልያድን ክፍልና በኦግ ግዛት ሥር ያለውን ባሳንን በሙሉ ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ሰጠሁ። የባሳን ይዞታ የሆነው የአርጎብ አካባቢ በሙሉ የረፋይም ምድር ተብሎ ይጠራ ነበር። 14  “የምናሴ ልጅ ያኢር የአርጎብን ክልል በሙሉ እስከ ገሹራውያን እና እስከ ማአካታውያን ወሰን ድረስ ያለውን ወሰደ፤ በባሳን የሚገኙትን እነዚህን መንደሮች በራሱ ስም ሃዎትያኢር ብሎ ሰየማቸው፤ እስከ ዛሬም ድረስ የሚጠሩት በዚህ ስም ነው። 15  ጊልያድን ደግሞ ለማኪር ሰጠሁት። 16  ለሮቤላውያንና ለጋዳውያን የአርኖንን ሸለቆ መሃል ወሰን በማድረግ ከጊልያድ አንስቶ እስከ አርኖን ሸለቆ ድረስ እንዲሁም የአሞናውያን ወሰን እስከሆነው ሸለቆ ማለትም እስከ ያቦቅ ድረስ ሰጠኋቸው፤ 17  እንዲሁም ከኪኔሬት አንስቶ በአረባ እስከሚገኘው ባሕር ይኸውም በስተ ምሥራቅ አቅጣጫ በጲስጋ ሸንተረር ግርጌ እስከሚገኘው እስከ ጨው ባሕር ድረስ ያለውን አረባን፣ ዮርዳኖስንና ወሰኑን ሰጠኋቸው። 18  “ከዚያም ይህን ትእዛዝ ሰጠኋችሁ፦ ‘አምላካችሁ ይሖዋ ይህችን ምድር ርስት አድርጋችሁ እንድትወርሷት ሰጥቷችኋል። ብርቱ የሆናችሁት ወንዶች ሁሉ የጦር መሣሪያችሁን ታጥቃችሁ በወንድሞቻችሁ በእስራኤላውያን ፊት ትሻገራላችሁ። 19  ሚስቶቻችሁ፣ ልጆቻችሁና ከብቶቻችሁ ብቻ (መቼም ብዙ ከብቶች እንዳሏችሁ አውቃለሁ) በሰጠኋችሁ ከተሞች ውስጥ ይቀራሉ፤ 20  ይህም ይሖዋ ልክ ለእናንተ እንዳደረገላችሁ ሁሉ ለወንድሞቻችሁም እረፍት እስኪሰጣቸው እንዲሁም አምላካችሁ ይሖዋ ከዮርዳኖስ ማዶ የሚሰጣቸውን ምድር ርስት አድርገው እስኪወርሱ ድረስ ነው። ከዚያ በኋላ እያንዳንዳችሁ ወደሰጠኋችሁ ወደየራሳችሁ ርስት ትመለሳላችሁ።’ 21  “በዚያን ጊዜ ለኢያሱ ይህን ትእዛዝ ሰጠሁት፦ ‘አምላክህ ይሖዋ በእነዚህ ሁለት ነገሥታት ላይ ያደረገውን ሁሉ በገዛ ዓይንህ አይተሃል። ይሖዋ አልፈሃቸው በምትሄደው መንግሥታት ሁሉ ላይ እንዲሁ ያደርጋል። 22  ስለ እናንተ የሚዋጋው አምላካችሁ ይሖዋ ስለሆነ አትፍሯቸው።’ 23  “እኔም በዚያን ጊዜ ይሖዋን እንዲህ በማለት ተማጸንኩት፦ 24  ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ አገልጋይህ ታላቅነትህንና ብርቱ ክንድህን እንዲያይ አድርገሃል፤ አንተ እንደምታደርጋቸው ያሉ ታላላቅ ነገሮችን መፈጸም የሚችለው በሰማይም ሆነ በምድር ያለ የትኛው አምላክ ነው? 25  እባክህ ከዮርዳኖስ ማዶ ያለችውን መልካሚቱን ምድር፣ አዎ ውብ የሆነችውን ይህችን ተራራማ አካባቢና ሊባኖስን ተሻግሬ እንዳይ ፍቀድልኝ።’ 26  ይሖዋ ግን በእናንተ የተነሳ በጣም ተቆጥቶኝ ስለነበር አልሰማኝም። ከዚህ ይልቅ ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ ‘በቃ! ዳግመኛ ስለዚህ ጉዳይ እንዳታነሳብኝ። 27  ይህን ዮርዳኖስን ስለማትሻገር ወደ ጲስጋ አናት ውጣና ዓይንህን አቅንተህ ወደ ምዕራብ፣ ወደ ሰሜን፣ ወደ ደቡብና ወደ ምሥራቅ ተመልከት። 28  በዚህ ሕዝብ ፊት የሚሻገረውም ሆነ አንተ ያየሃትን ምድር እንዲወርሱ የሚያደርገው ኢያሱ ስለሆነ እሱን መሪ አድርገህ ሹመው፤ አደፋፍረው፤ አበረታታውም።’ 29  ይህ ሁሉ የሆነው በቤትጰኦር ፊት ለፊት በሚገኘው ሸለቆ ውስጥ በነበርንበት ጊዜ ነው።
[]
[]
[]
[]
12,577
30  “ይህ ቃል ሁሉ ይኸውም በፊትህ ያስቀመጥኩት በረከትና እርግማን በአንተ ላይ በሚመጣበትና አምላክህ ይሖዋ በመካከላቸው እንድትበተን ባደረገህ ብሔራት ምድር ሆነህ ይህን ቃል ሁሉ በምታስታውስበት ጊዜ 2  እንዲሁም አንተም ሆንክ ልጆችህ እኔ ዛሬ በማዝህ ትእዛዝ ሁሉ መሠረት በሙሉ ልባችሁና በሙሉ ነፍሳችሁ ወደ አምላካችሁ ወደ ይሖዋ በምትመለሱበትና ቃሉን በምትሰሙበት ጊዜ 3  አምላክህ ይሖዋ ተማርከው የተወሰዱብህን ይመልስልሃል፤ ምሕረትም ያሳይሃል፤ እንዲሁም አምላክህ ይሖዋ በመካከላቸው እንድትበተን ካደረገህ ሕዝቦች ምድር ሁሉ መልሶ ይሰበስብሃል። 4  ሕዝብህ እስከ ሰማያት ዳርቻ ድረስ ቢበተን እንኳ አምላክህ ይሖዋ ከዚያ ይሰበስብሃል፤ ከዚያም መልሶ ያመጣሃል። 5  አምላክህ ይሖዋ አባቶችህ ወርሰዋት ወደነበሩት ምድር ያስገባሃል፤ አንተም ትወርሳታለህ፤ እሱም ከአባቶችህ ይበልጥ ያበለጽግሃል፤ እንዲሁም ያበዛሃል። 6  በሕይወትም ትኖር ዘንድ አምላክህን ይሖዋን በሙሉ ልብህና በሙሉ ነፍስህ እንድትወደው አምላክህ ይሖዋ ልብህን እንዲሁም የልጆችህን ልብ ያነጻል። 7  ከዚያም አምላክህ ይሖዋ እነዚህን እርግማኖች ሁሉ በሚጠሉህና በሚያሳድዱህ ጠላቶችህ ላይ ያመጣል። 8  “አንተም ተመልሰህ የይሖዋን ቃል ትሰማለህ፤ እኔ ዛሬ የማዝህን ትእዛዛቱን ሁሉ ትፈጽማለህ። 9  አምላክህ ይሖዋ በአባቶችህ ደስ እንደተሰኘ ሁሉ ይሖዋ አንተንም በማበልጸግ ስለሚደሰት የሆድህን ፍሬ፣ እንስሶችህንና የምድርህን ፍሬ በማብዛት በእጅህ ሥራ ሁሉ እጅግ እንድትበለጽግ ያደርግሃል። 10  ይህም የሚሆነው የአምላክህን የይሖዋን ቃል ስለምትሰማ፣ በዚህ የሕግ መጽሐፍ የተጻፉትን ትእዛዛቱንና ደንቦቹን ስለምትጠብቅ እንዲሁም በሙሉ ልብህና በሙሉ ነፍስህ ወደ አምላክህ ወደ ይሖዋ ስለምትመለስ ነው። 11  “እኔ ዛሬ የማዝህ ይህ ትእዛዝ ለአንተ ያን ያህል ከባድ አይደለም፤ ከአንተም የራቀ አይደለም። 12  ‘ሰምተን እንድንፈጽመው ወደ ሰማይ ወጥቶ ማን ያምጣልን?’ እንዳትል ትእዛዙ ያለው በሰማይ አይደለም። 13  ደግሞም ‘ሰምተን እንድንፈጽመው ባሕሩን ተሻግሮ ማን ያምጣልን?’ እንዳትል ትእዛዙ ያለው ከባሕሩ ማዶ አይደለም። 14  ቃሉ ትፈጽመው ዘንድ ለአንተ በጣም ቅርብ ነውና፤ ደግሞም በአፍህና በልብህ ውስጥ ነው። 15  “እንግዲህ እኔ ዛሬ ሕይወትንና መልካም ነገርን እንዲሁም ሞትንና መጥፎ ነገርን በፊትህ አስቀምጫለሁ። 16  አምላክህን ይሖዋን በመውደድ፣ በመንገዶቹ በመሄድ እንዲሁም ትእዛዛቱን፣ ደንቦቹንና ድንጋጌዎቹን በመጠበቅ እኔ ዛሬ የማዝህን የአምላክህን የይሖዋን ትእዛዛት ብትሰማ በሕይወት ትኖራለህ፤ ደግሞም ትበዛለህ፤ አምላክህ ይሖዋም በምትወርሳት ምድር ውስጥ ይባርክሃል። 17  “ሆኖም ልብህ ቢሸፍትና ለመስማት ፈቃደኛ ባትሆን እንዲሁም ተታለህ ለሌሎች አማልክት ብትሰግድና ብታገለግላቸው 18  በእርግጥ እንደምትጠፉ በዛሬው ዕለት እነግራችኋለሁ። ደግሞም ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ በምትወርሷት ምድር ላይ ዕድሜያችሁ ያጥራል። 19  ሕይወትንና ሞትን፣ በረከትንና እርግማንን በፊታችሁ እንዳስቀመጥኩ ዛሬ ሰማይንና ምድርን ምሥክሮች አድርጌ እጠራባችኋለሁ፤ እንግዲህ አንተም ሆንክ ዘሮችህ በሕይወት እንድትኖሩ ሕይወትን ምረጥ፤ 20  ይህን የምታደርገው አምላክህን ይሖዋን በመውደድ፣ ቃሉን በመስማትና ከእሱ ጋር በመጣበቅ ነው፤ ምክንያቱም እሱ ሕይወትህ ነው፤ ይሖዋ ለአባቶችህ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ለመስጠት በማለላቸው ምድር ረጅም ዕድሜ የምትኖረውም በእሱ ነው።”
[]
[]
[]
[]
12,578
31  ከዚያም ሙሴ ወጥቶ እነዚህን ቃላት ለመላው እስራኤል ተናገረ፤ 2  እንዲህም አላቸው፦ “እንግዲህ እኔ አሁን 120 ዓመት ሆኖኛል። ይሖዋ ‘የዮርዳኖስን ወንዝ አትሻገርም’ ስላለኝ ከእንግዲህ ልመራችሁ አልችልም። 3  ከፊትህ የሚሻገረው አምላክህ ይሖዋ ነው፤ እሱ ራሱም እነዚህን ብሔራት ከፊትህ ያጠፋቸዋል፤ አንተም ታባርራቸዋለህ። ልክ ይሖዋ በተናገረውም መሠረት እየመራ የሚያሻግርህ ኢያሱ ነው። 4  ይሖዋ የአሞራውያንን ነገሥታት ሲሖንን እና ኦግን እንዲሁም ምድራቸውን ባጠፋ ጊዜ በእነሱ ላይ እንዳደረገው ሁሉ በእነዚህም ብሔራት ላይ እንዲሁ ያደርግባቸዋል። 5  ይሖዋ እነሱን ድል ያደርግላችኋል፤ እናንተም እኔ በሰጠኋችሁ ትእዛዝ ሁሉ መሠረት ታደርጉባቸዋላችሁ። 6  ደፋርና ብርቱ ሁኑ። ከእናንተ ጋር የሚሄደው አምላካችሁ ይሖዋ ስለሆነ አትፍሯቸው ወይም በፊታቸው አትሸበሩ። እሱ አይጥላችሁም ወይም አይተዋችሁም።” 7  ከዚያም ሙሴ ኢያሱን ጠርቶ በመላው እስራኤል ፊት እንዲህ አለው፦ “ደፋርና ብርቱ ሁን፤ ምክንያቱም ይህን ሕዝብ ይሖዋ ለአባቶቻቸው ሊሰጣቸው ወደማለላቸው ምድር የምታስገባው አንተ ነህ፤ ደግሞም ይህን ምድር ርስት አድርገህ ትሰጣቸዋለህ። 8  በፊትህ የሚሄደው ይሖዋ ነው፤ እሱ ምንጊዜም ከአንተ ጋር ይሆናል። አይጥልህም ወይም አይተውህም። አትፍራ ወይም አትሸበር።” 9  ከዚያም ሙሴ ይህን ሕግ ጽፎ የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት ለሚሸከሙት ሌዋውያን ካህናትና ለእስራኤል ሽማግሌዎች በሙሉ ሰጣቸው። 10  ሙሴ እንዲህ ሲል አዘዛቸው፦ “በየሰባት ዓመቱ መጨረሻ፣ በዓመቱ ውስጥ ዕዳ በሚሰረዝበት በተወሰነው ጊዜ ላይ ማለትም የዳስ በዓል ሲከበር 11  መላው እስራኤል አምላክህ ይሖዋ በሚመርጠው ስፍራ በፊቱ በሚሰበሰብበት ጊዜ ይህን ሕግ እስራኤላውያን በሙሉ እንዲሰሙት አንብብላቸው። 12  ስለ አምላካችሁ ስለ ይሖዋ ይሰሙና ይማሩ እንዲሁም እሱን ይፈሩ ዘንድ ብሎም የዚህን ሕግ ቃላት በሙሉ በጥንቃቄ እንዲፈጽሙ ሕዝቡን ማለትም ወንዶችን፣ ሴቶችን፣ ልጆችንና በከተሞችህ ውስጥ የሚኖረውን የባዕድ አገር ሰው ሰብስብ። 13  ከዚያም ይህን ሕግ የማያውቁት ልጆቻቸው ይሰማሉ፤ እንዲሁም ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ በምትወርሷት ምድር ላይ በምትኖሩበት ዘመን ሁሉ አምላካችሁን ይሖዋን መፍራት ይማራሉ።” 14  ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ የምትሞትበት ጊዜ ቀርቧል። ኢያሱን ጥራውና መሪ አድርጌ እንድሾመው በመገናኛ ድንኳኑ ተገኙ።” በመሆኑም ሙሴና ኢያሱ ሄደው በመገናኛ ድንኳኑ ተገኙ። 15  ከዚያም ይሖዋ በደመና ዓምድ ውስጥ ሆኖ በድንኳኑ ላይ ተገለጠ፤ የደመናውም ዓምድ በድንኳኑ መግቢያ ላይ ቆመ። 16  ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ አንተ መሞትህ ነው፤ ይህም ሕዝብ በሚሄድበት ምድር በዙሪያው ካሉ ባዕዳን አማልክት ጋር መንፈሳዊ ምንዝር ይፈጽማል። እኔንም ይተዉኛል፤ ከእነሱም ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን ያፈርሳሉ። 17  በዚያን ጊዜ ቁጣዬ በእነሱ ላይ ይነዳል፤ እኔም እተዋቸዋለሁ፤ ሙሉ በሙሉ እስኪደመሰሱም ድረስ ፊቴን ከእነሱ እሰውራለሁ። ከዚያም ብዙ መከራና ችግር ይደርስባቸዋል፤ እነሱም ‘ይህ ሁሉ መከራ የደረሰብን አምላካችን በመካከላችን ስለሌለ አይደል?’ ይላሉ። 18  ሆኖም ወደ ሌሎች አማልክት ዞር በማለት ከፈጸሙት መጥፎ ድርጊት ሁሉ የተነሳ በዚያ ቀን ፊቴን ከእነሱ እሰውራለሁ። 19  “እንግዲህ አሁን ይህን መዝሙር ለራሳችሁ ጻፉ፤ ለእስራኤላውያንም አስተምሯቸው። ይህ መዝሙር በእስራኤል ሕዝብ ላይ ምሥክሬ ሆኖ ያገለግል ዘንድ እንዲማሩት አድርጉ። 20  ምክንያቱም ለአባቶቻቸው ወደማልኩላቸው ወተትና ማር ወደምታፈሰው ምድር በማስገባቸው ጊዜ በልተው ሲጠግቡና ሲበለጽጉ ወደ ሌሎች አማልክት ዞር ይላሉ፤ እንዲሁም እነሱን ያገለግላሉ፤ እኔንም ይንቁኛል፤ ቃል ኪዳኔንም ያፈርሳሉ። 21  ብዙ መከራና ችግር በሚደርስባቸው ጊዜ ይህ መዝሙር ምሥክር ይሆንባቸዋል፤ (ምክንያቱም ዘሮቻቸው ይህን መዝሙር ሊዘነጉት አይገባም፤) እኔ እንደሆነ ወደማልኩላቸው ምድር ገና ሳላስገባቸው ምን ዓይነት ዝንባሌ እንዳዳበሩ አውቄአለሁ።” 22  ስለዚህ ሙሴ ይህን መዝሙር በዚያን ቀን ጻፈው፤ እስራኤላውያንንም አስተማራቸው። 23  እሱም የነዌን ልጅ ኢያሱን ሾመው፤ እንዲህም አለው፦ “ደፋርና ብርቱ ሁን፤ ምክንያቱም እስራኤላውያንን ወደማልኩላቸው ምድር የምታስገባቸው አንተ ነህ፤ እኔም ምንጊዜም ከአንተ ጋር እሆናለሁ።” 24  ሙሴም የዚህን ሕግ ቃላት በሙሉ በመጽሐፍ ላይ ጽፎ እንደጨረሰ 25  የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት የሚሸከሙትን ሌዋውያኑን እንዲህ ሲል አዘዛቸው፦ 26  “ይህን የሕግ መጽሐፍ ወስዳችሁ በአምላካችሁ በይሖዋ የቃል ኪዳን ታቦት አጠገብ አስቀምጡት፤ ይህም በዚያ በእናንተ ላይ ምሥክር ሆኖ ያገለግላል። 27  ምክንያቱም እናንተ ዓመፀኛና ግትር መሆናችሁን በሚገባ አውቃለሁ። እኔ ዛሬ ከእናንተ ጋር በሕይወት እያለሁ በይሖዋ ላይ እንዲህ ካመፃችሁ ከሞትኩ በኋላማ ምን ያህል ታምፁ! 28  የነገዶቻችሁን ሽማግሌዎችና አለቆቻችሁን በሙሉ ሰብስቡልኝ፤ እኔም ጆሯቸው እየሰማ እነዚህን ቃላት ልናገር፤ ሰማይንና ምድርንም በእነሱ ላይ ምሥክሮች አድርጌ ልጥራ። 29  ምክንያቱም እኔ ከሞትኩ በኋላ ክፉ ድርጊት እንደምትፈጽሙና ካዘዝኳችሁ መንገድ ዞር እንደምትሉ በሚገባ አውቃለሁ። በይሖዋም ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር ስለምትፈጽሙና በእጆቻችሁ ሥራ ስለምታስቆጡት ወደፊት መከራ ይደርስባችኋል።” 30  ከዚያም ሙሴ መላው የእስራኤል ጉባኤ እየሰማ የዚህን መዝሙር ቃላት ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ እንዲህ ሲል ተናገረ፦
[]
[]
[]
[]
12,579
32  “ሰማያት ሆይ፣ ጆሯችሁን ስጡኝ፤ እኔም እናገራለሁ፤ምድርም የአፌን ቃል ትስማ። 2  ትምህርቴ እንደ ዝናብ ይወርዳል፤ካፊያ ሣር ላይ እንደሚወርድ፣የሚያረሰርስ ዝናብም ተክልን እንደሚያጠጣ፣ቃሌም እንደ ጤዛ ይንጠባጠባል። 3  የይሖዋን ስም አውጃለሁና። ስለ አምላካችን ታላቅነት ተናገሩ! 4  እሱ ዓለት፣ የሚያደርገውም ነገር ሁሉ ፍጹም ነው፤መንገዶቹ ሁሉ ፍትሕ ናቸውና። እሱ ፈጽሞ ፍትሕን የማያጓድል ታማኝ አምላክ ነው፤ጻድቅና ትክክለኛ ነው። 5  ምግባረ ብልሹ የሆኑት እነሱ ናቸው። ልጆቹ አይደሉም፤ ጉድለቱ የራሳቸው ነው። ጠማማና ወልጋዳ ትውልድ ናቸው! 6  እናንተ ሞኞችና ጥበብ የጎደላችሁ ሰዎች ሆይ፣በይሖዋ ላይ እንዲህ ያለ ነገር ታደርጋላችሁ? ወደ ሕልውና ያመጣህ አባትህ እሱ አይደለም?የሠራህና አጽንቶ ያቆመህስ እሱ አይደለም? 7  የጥንቱን ዘመን አስታውስ፤ያለፉት ትውልዶች የኖሩባቸውን ዓመታት መለስ ብለህ አስብ። አባትህን ጠይቅ፤ ሊነግርህ ይችላል፤ሽማግሌዎችህንም ጠይቅ፤ ይነግሩሃል። 8  ልዑሉ ለብሔራት ርስታቸውን ሲሰጥ፣የአዳምን ልጆች አንዱን ከሌላው ሲለያይ፣በእስራኤል ልጆች ቁጥር ልክየሕዝቦችን ወሰን ደነገገ። 9  የይሖዋ ሕዝብ ድርሻው ነው፤ያዕቆብ ርስቱ ነው። 10  እሱን ምድረ በዳ በሆነ ምድር፣ነፋስ በሚያፏጭበት ጭው ያለ በረሃ አገኘው። ሊጠብቀውም ዙሪያውን ከበበው፤ ተንከባከበው፤እንደ ዓይኑም ብሌን ጠበቀው። 11  ንስር ጎጆዋን እንደምትነቀንቅናከጫጩቶቿ በላይ እንደምታንዣብብ፣ክንፎቿን ዘርግታ እንደምትይዛቸው፣በላባዎቿም እንደምትሸከማቸው ሁሉ 12  ይሖዋ ብቻውን መራው፤ከእሱም ጋር ምንም ባዕድ አምላክ አልነበረም። 13  በምድር ላይ በሚገኙ ከፍ ያሉ ቦታዎች እንዲሄድ አደረገው፤ስለሆነም የእርሻውን ምርት በላ። ከዓለት ማር አበላው፤ከባልጩትም ዘይት መገበው፤ 14  የላሞቹን ቅቤና የመንጋውን ወተትምርጥ ከሆነው በግ ጋር ሰጠው፤የባሳንን አውራ በጎችና አውራ ፍየሎችከምርጥ ስንዴ ጋር ሰጠው፤አንተም ከወይን ፍሬው ደም የወይን ጠጅ ጠጣህ። 15  የሹሩን ሲወፍር በዓመፀኝነት ተራገጠ። ሰባህ፤ ፈረጠምክ፤ ደለብክ። ስለሆነም የሠራውን አምላክ ተወ፤አዳኝ የሆነለትን ዓለት ናቀ። 16  በባዕዳን አማልክት አስቆጡት፤በአስጸያፊ ነገሮችም አሳዘኑት። 17  ለአምላክ ሳይሆን ለአጋንንት፣ለማያውቋቸው አማልክት፣በቅርቡ ለተነሱ ለአዲሶች፣አባቶቻችሁ ለማያውቋቸው አማልክት ይሠዉ ነበር። 18  አባት የሆነህን ዓለት ረሳኸው፤የወለደህንም አምላክ አላስታወስክም። 19  ይሖዋ ይህን ሲያይ ተዋቸው፤ወንዶችና ሴቶች ልጆቹ አሳዝነውት ነበርና። 20  ስለዚህ እንዲህ አለ፦ ‘ፊቴን ከእነሱ እሰውራለሁ፤ምን እንደሚሆኑም አያለሁ። ምክንያቱም እነሱ ጠማማ ትውልድ ናቸው፤ታማኝነት የሚባል ነገር የማያውቁ ልጆች ናቸው። 21  እነሱ አምላክ ባልሆነው አስቆጡኝ፤ከንቱ በሆኑ ጣዖቶቻቸው አሳዘኑኝ። በመሆኑም እኔ ሕዝብ ባልሆነው አስቀናቸዋለሁ፤ሞኝ በሆነ ብሔር አበሳጫቸዋለሁ። 22  ምክንያቱም ቁጣዬ እሳት አቀጣጥሏል፤እሱም እስከ መቃብር ጥልቀት ድረስ ዘልቆ ይነድዳል፤ምድርንና ምርቷን ይበላል፤የተራሮችንም መሠረት ያቃጥላል። 23  መከራቸውን አበዛዋለሁ፤ቀስቶቼን በእነሱ ላይ እጨርሳለሁ። 24  በረሃብ ይዳከማሉ፤በሚያቃጥል ትኩሳትና በመራራ ጥፋት ይበላሉ። የአራዊትን ጥርስ፣በምድር ላይ የሚሳቡ እንስሳትንም መርዝ እልክባቸዋለሁ። 25  ወጣቱንም ሆነ ልጃገረዲቱን፣ጨቅላውንም ሆነ ሽማግሌውን፣በውጭ፣ ሰይፍ ለሐዘን ይዳርጋቸዋል፤በቤት ውስጥ ደግሞ ሽብር አለ። 26  እኔም “እበትናቸዋለሁ፤መታሰቢያቸውም ከሰዎች ዘንድ እንዲጠፋ አደርጋለሁ” ባልኩ ነበር፤ 27  ነገር ግን የጠላትን ምላሽ ፈራሁ፤ምክንያቱም ባላጋራዎቼ በተሳሳተ መንገድ ሊረዱት ይችላሉ። “ክንዳችን የበላይ ሆነ፤ይህን ሁሉ ያደረገው ይሖዋ አይደለም” ሊሉ ይችላሉ። 28  እነሱ ማመዛዘን የጎደለው ብሔር ናቸው፤በመካከላቸውም ማስተዋል የሚባል ነገር የለም። 29  ምነው ጥበበኛ በሆኑ ኖሮ! ይህን ሁሉ ያሰላስሉ ነበር። የሚደርስባቸውንም ያስቡ ነበር። 30  ዓለታቸው ካልሸጣቸውናይሖዋ ለምርኮ ካልዳረጋቸው በስተቀር አንድ ሰው 1,000 ሊያሳድድ፣ሁለት ሰው ደግሞ 10,000 ሊያባርር እንዴት ይችላል? 31  የእነሱ ዓለት እንደ እኛ ዓለት አይደለም፤ጠላቶቻችንም እንኳ ይህን ተረድተዋል። 32  ወይናቸው ከሰዶም የወይን ተክልናከገሞራ የእርሻ ቦታ የተገኘ ነው። የወይን ፍሬያቸው መርዛማ የወይን ፍሬ ነው፤ዘለላቸው መራራ ነው። 33  ወይናቸው የእባቦች መርዝ፣የጉበናም ምሕረት የለሽ መርዝ ነው። 34  ይህ እኔ ጋ ያለ፣በግምጃ ቤቴ ውስጥ ማኅተም ታትሞበት የተቀመጠ አይደለም? 35  በቀልም ሆነ ቅጣት የእኔ ነው፤አስቀድሞ የተወሰነው ጊዜ ሲደርስ እግራቸው ይከዳቸዋል፤የሚጠፉበት ቀን ቀርቧልና፤የሚጠብቃቸውም ነገር በፍጥነት ይመጣል።’ 36  ይሖዋ ሕዝቡን ይዳኛል፤አገልጋዮቹ አቅም እንዳነሳቸው፣ረዳት የለሽና ደካማ የሆኑት ብቻ እንደቀሩ ሲያይለእነሱ ያዝንላቸዋል። 37  ከዚያም እንዲህ ይላል፦ ‘አማልክታቸው የት አሉ?መሸሸጊያ እንዲሆናቸው የተጠጉት ዓለትስ የት አለ? 38  የመሥዋዕቶቻቸውን ስብ ይበላ፣የመጠጥ መባዎቻቸውንም የወይን ጠጅ ይጠጣ የነበረው የት አለ? እስቲ ተነስተው ይርዷችሁ። እስቲ መሸሸጊያ ስፍራ ይሁኑላችሁ። 39  እንግዲህ እኔ እሱ እንደሆንኩ እዩ፤ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት የሉም። እኔ እገድላለሁ፤ እኔ ሕያው አደርጋለሁ። እኔ አቆስላለሁ፤ እኔው እፈውሳለሁ፤ከእጄም ማዳን የሚችል የለም። 40  እጄን ወደ ሰማይ አንስቼ፣“በዘላለማዊ ሕያውነቴ” ብዬ እምላለሁ፤ 41  የሚያብረቀርቅ ሰይፌን ከሳልኩናእጄን ለፍርድ ካዘጋጀሁ፣ተቃዋሚዎቼን እበቀላለሁ፤የሚጠሉኝንም እቀጣለሁ። 42  በታረዱና በተማረኩ ሰዎች ደም፣በጠላት መሪዎች ራስ፣ቀስቶቼን በደም አሰክራለሁ፤ሰይፌም ሥጋ ይበላል።’ 43  እናንተ ብሔራት ከሕዝቡ ጋር ደስ ይበላችሁ፤እሱ የአገልጋዮቹን ደም ይመልሳልና፤ተቃዋሚዎቹንም ይበቀላል፤ለሕዝቡም ምድር ያስተሰርይለታል።” 44  ሙሴም ከነዌ ልጅ ከሆሺአ ጋር መጥቶ የዚህን መዝሙር ቃላት በሙሉ ሕዝቡ እየሰማ ተናገረ። 45  ሙሴ እነዚህን ቃላት በሙሉ ለመላው እስራኤል ተናግሮ ከጨረሰ በኋላ 46  እንዲህ አላቸው፦ “የዚህን ሕግ ቃላት በሙሉ በጥንቃቄ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቻችሁን እንድታዟቸው እኔ በዛሬው ዕለት እናንተን ለማስጠንቀቅ የምነግራችሁን ቃል ሁሉ ልብ በሉ። 47  ይህ ቃል ለእናንተ ሕይወታችሁ እንጂ እንዲሁ ባዶ ቃል አይደለም፤ ይህ ቃል ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ በምትወርሷት ምድር ላይ ዕድሜያችሁን ሊያረዝምላችሁ ይችላል።” 48  ይሖዋ በዚያው ዕለት ሙሴን እንዲህ አለው፦ 49  “በኢያሪኮ ትይዩ በሞዓብ ምድር ወደሚገኘው ወደዚህ የአባሪም ተራራ ይኸውም ወደ ነቦ ተራራ ወጥተህ ለእስራኤላውያን ርስት አድርጌ የምሰጣትን የከነአንን ምድር ተመልከት። 50  ወንድምህ አሮን በሆር ተራራ ላይ ሞቶ ወደ ወገኖቹ እንደተሰበሰበ ሁሉ አንተም በምትወጣበት በዚህ ተራራ ላይ ትሞታለህ፤ ወደ ወገኖችህም ትሰበሰባለህ፤ 51  ምክንያቱም ሁለታችሁም በጺን ምድረ በዳ በሚገኘው በቃዴስ፣ በመሪባ ውኃዎች አጠገብ በእስራኤላውያን መካከል ለእኔ ታማኝ ሆናችሁ አልተገኛችሁም፤ እንዲሁም በእስራኤል ሕዝብ ፊት እኔን አልቀደሳችሁኝም። 52  ምድሪቱን ከሩቅ ታያታለህ፤ ሆኖም ለእስራኤል ሕዝብ ወደምሰጣት ምድር አትገባም።”
[]
[]
[]
[]
12,580
33  የእውነተኛው አምላክ ሰው ሙሴ ከመሞቱ በፊት እስራኤላውያንን የባረካቸው በረከት ይህ ነው። 2  እንዲህ አለ፦ “ይሖዋ ከሲና መጣ፤ከሴይርም ሆኖ አበራባቸው። ከፋራን ተራራማ አካባቢዎችም በክብር አበራ፤ከእሱም ጋር አእላፋት ቅዱሳን ነበሩ፤በቀኙም ተዋጊዎቹ አሉ። 3  እሱ ሕዝቡን ይወዳል፤ቅዱስ የሆነው ሕዝብ ሁሉ እጅህ ውስጥ ነው። እነሱም እግርህ ሥር ተቀምጠዋል፤ቃልህንም ይሰማሉ። 4  (ሙሴ ትእዛዝን ይኸውም ሕግን ሰጠን፤ይህም ለያዕቆብ ጉባኤ እንደ ርስት ነው።) 5  የሕዝቡ መሪዎች ከመላው የእስራኤል ነገድ ጋርአንድ ላይ በተሰበሰቡ ጊዜ፣አምላክ በየሹሩን ላይ ንጉሥ ሆነ። 6  ሮቤል በሕይወት ይኑር፣ አይሙት፤የወገኖቹም ቁጥር አይቀንስ።” 7  ይሁዳንም እንዲህ ሲል ባረከው፦ “ይሖዋ ሆይ፣ የይሁዳን ድምፅ ስማ፤ወደ ሕዝቦቹም መልሰህ አምጣው። እጆቹ የእሱ ለሆነው ይከላከላሉ፤አንተም ጠላቶቹን እንዲዋጋ እርዳው።” 8  ስለ ሌዊም እንዲህ አለ፦ “የአንተ ቱሚምና ኡሪም ለአንተ ታማኝ ለሆነ፣በማሳህ ለፈተንከው ሰው ይሆናል፤ በመሪባ ውኃዎች አጠገብ ተጣላኸው፤ 9  ሰውየው አባቱንና እናቱን በተመለከተ ‘ስለ እነሱ ግድ የለኝም’ አለ። ሌላው ቀርቶ ወንድሞቹን እንኳ አልተቀበለም፤የገዛ ልጆቹንም ችላ አለ። ቃልህን ታዘዋልና፤ቃል ኪዳንህንም ጠብቀዋል። 10  ለያዕቆብ ድንጋጌህን፣ለእስራኤልም ሕግህን ያስተምሩ። ደስ የሚያሰኝ መዓዛ እንዲሸትህ ዕጣን ያቅርቡልህ፤በመሠዊያህም ላይ ሙሉ በሙሉ የሚቀርብ መባ ይሠዉልህ። 11  ይሖዋ ሆይ፣ ጉልበቱን ባርክለት፤በእጆቹም ሥራ ደስ ይበልህ። እሱን የሚጠሉት ዳግመኛ እንዳያንሰራሩበእሱ ላይ የሚነሱትን እግራቸውን አድቅቅ።” 12  ስለ ቢንያም እንዲህ አለ፦ “ይሖዋ የወደደው ያለስጋት አብሮት ይኑር፤ቀኑን ሙሉ ይከልለዋልና፤በትከሻዎቹም መካከል ይኖራል።” 13  ስለ ዮሴፍ እንዲህ አለ፦ “ይሖዋ ከሰማይ በሚወርዱ ምርጥ ነገሮች፣በጤዛና ከታች በሚመነጩ ውኃዎችምድሩን ይባርክ፤ 14  እንዲሁም ፀሐይ በምታስገኛቸው ምርጥ ነገሮች፣በየወሩ በሚገኝ ምርጥ ፍሬ፣ 15  ጥንታዊ ከሆኑ ተራሮች በሚገኙ ምርጥ ነገሮች፣ጸንተው ከሚኖሩት ኮረብቶች በሚገኙ ምርጥ ነገሮች፣ 16  ከምድር በሚገኙ ምርጥ ነገሮችና ምድርን በሞሉ ምርጥ ነገሮች፣በቁጥቋጦው ውስጥ በተገለጠው በእሱ ሞገስ ይባርክ። እነዚህ ሁሉ በዮሴፍ ራስ ላይ፣ከወንድሞቹ መካከል ተነጥሎ በወጣው አናት ላይ ይውረዱ። 17  ግርማው እንደ በኩር በሬ ነው፤ቀንዶቹም የዱር በሬ ቀንድ ናቸው። በእነሱም ሰዎችን፣ሕዝቦችን ሁሉ እስከ ምድር ዳርቻ ይገፋል። እነሱ የኤፍሬም አሥር ሺዎች ናቸው፤የምናሴም ሺዎች ናቸው።” 18  ስለ ዛብሎን እንዲህ አለ፦ “ዛብሎን ሆይ፣ በመውጣትህ ደስ ይበልህ፤አንተም ይሳኮር፣ በድንኳኖችህ ውስጥ ደስ ይበልህ። 19  ሰዎችን ወደ ተራራው ይጠራሉ። በዚያም የጽድቅ መሥዋዕቶችን ያቀርባሉ። ምክንያቱም በባሕሮች ውስጥ ካለው የተትረፈረፈ ሀብት፣በአሸዋም ውስጥ ተሰውሮ ከተከማቸው ነገር ዝቀው ያወጣሉ።” 20  ስለ ጋድ እንዲህ አለ፦ “የጋድን ድንበሮች የሚያሰፋ የተባረከ ነው። በዚያ እንደ አንበሳ ይተኛል፤ክንድን፣ አዎ አናትን ለመዘነጣጠል ተዘጋጅቶ ይጠብቃል። 21  የመጀመሪያውን መርጦ ለራሱ ይወስዳል፤በዚያ የሕግ ሰጪው ድርሻ ተለይቶ ተቀምጧልና። የሕዝቡ መሪዎች አንድ ላይ ይሰበሰባሉ። የይሖዋን ጽድቅና ድንጋጌዎች፣በእስራኤል ያስፈጽማል።” 22  ስለ ዳን እንዲህ አለ፦ “ዳን የአንበሳ ደቦል ነው። ከባሳን ዘሎ ይወጣል።” 23  ስለ ንፍታሌም እንዲህ አለ፦ “ንፍታሌም በይሖዋ ሞገስ ረክቷል፤በእሱም በረከት ተሞልቷል። ምዕራቡንና ደቡቡን ውረስ።” 24  ስለ አሴር እንዲህ አለ፦ “አሴር በልጆች የተባረከ ነው። በወንድሞቹ ፊት ሞገስ ያግኝ፤እግሩንም ዘይት ውስጥ ይንከር። 25  የበርህ መቀርቀሪያ ብረትና መዳብ ናቸው፤በዘመንህ ሁሉ ያለስጋት ትኖራለህ። 26  አንተን ለመርዳት በሰማይ ውስጥ የሚጋልብ፣በግርማው በደመና ላይ የሚገሰግስ፣እንደ እውነተኛው የየሹሩን አምላክ ያለ ማንም የለም። 27  አምላክ ከጥንት ጀምሮ መሸሸጊያ ነው፤ዘላለማዊ ክንዶቹ ከበታችህ ናቸው። ጠላትን ከፊትህ ያባርራል፤እንዲሁም ‘አጥፋቸው!’ ይላል። 28  እህልና አዲስ ወይን ባለበት ምድር፣ሰማያቱ ጠል በሚያንጠባጥቡበትእስራኤል ያለስጋት ይቀመጣል፤የያዕቆብም ምንጭ የተገለለ ይሆናል። 29  እስራኤል ሆይ፣ ደስተኛ ነህ! የይሖዋን ማዳን ያየ፣እንደ አንተ ያለ ሕዝብ ማን አለ?እሱ የሚከልል ጋሻህናታላቅ ሰይፍህ ነው፤ ጠላቶችህ በፊትህ ይንቀጠቀጣሉ፤አንተም በጀርባቸው ላይ ትራመዳለህ።”
[]
[]
[]
[]
12,581
34  ከዚያም ሙሴ ከሞዓብ በረሃማ ሜዳ ተነስቶ ወደ ነቦ ተራራ ይኸውም በኢያሪኮ ትይዩ ወደሚገኘው ወደ ጲስጋ አናት ወጣ። ይሖዋም ምድሪቱን በሙሉ አሳየው፤ ይኸውም ከጊልያድ እስከ ዳን፣ 2  ንፍታሌምን በሙሉ፣ የኤፍሬምንና የምናሴን ምድር፣ በስተ ምዕራብ በኩል እስካለው ባሕር ድረስ ያለውን የይሁዳን ምድር በሙሉ፣ 3  ኔጌብን፣ የዮርዳኖስን አውራጃ እንዲሁም የዘንባባ ዛፍ ከተማ በሆነችው በኢያሪኮ ካለው ሸለቋማ ሜዳ አንስቶ እስከ ዞአር ድረስ አሳየው። 4  ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለው፦ “ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ‘ለዘርህ እሰጣታለሁ’ በማለት የማልኩላቸው ምድር ይህች ናት። በዓይንህ እንድታያት አድርጌሃለሁ፤ ነገር ግን ወደዚያ አትሻገርም።” 5  የይሖዋ አገልጋይ ሙሴም ልክ ይሖዋ እንደተናገረው በዚያው በሞዓብ ምድር ሞተ። 6  እሱም ከቤትጰኦር ትይዩ በሞዓብ ምድር በሚገኘው ሸለቆ ቀበረው፤ እስከ ዛሬም ድረስ መቃብሩ የት እንደሚገኝ የሚያውቅ የለም። 7  ሙሴ በሞተ ጊዜ ዕድሜው 120 ዓመት ነበር። ዓይኖቹ አልፈዘዙም፤ ጉልበቱም አልደከመም ነበር። 8  እስራኤላውያንም በሞዓብ በረሃማ ሜዳ ለሙሴ 30 ቀን አለቀሱለት። በመጨረሻም ለሙሴ የሚለቀስበትና የሚታዘንበት ጊዜ አበቃ። 9  የነዌ ልጅ ኢያሱ ሙሴ እጁን ስለጫነበት የጥበብ መንፈስ ተሞልቶ ነበር፤ እስራኤላውያንም እሱን ይሰሙት ጀመር፤ እንዲሁም ልክ ይሖዋ ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ። 10  ሆኖም ይሖዋ ፊት ለፊት እንዳወቀው እንደ ሙሴ ያለ ሌላ ነቢይ እስካሁን በእስራኤል ተነስቶ አያውቅም። 11  ይሖዋ በግብፅ ምድር በፈርዖን፣ በአገልጋዮቹ ሁሉና በምድሩ ሁሉ ፊት እንዲፈጽም የላከውን ምልክቶችና ተአምራት በሙሉ ፈጸመ፤ 12  ከዚህም በተጨማሪ ሙሴ በእስራኤላውያን ሁሉ ፊት በኃያል ክንድ ታላቅና አስፈሪ ድርጊት ፈጸመ።
[]
[]
[]
[]
12,582
4  “አሁንም እስራኤል ሆይ፣ በሕይወት እንድትኖሩና የአባቶቻችሁ አምላክ ይሖዋ የሚሰጣችሁን ምድር ገብታችሁ እንድትወርሱ፣ ትጠብቋቸው ዘንድ የማስተምራችሁን ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች አዳምጡ። 2  እኔ የማዛችሁን የአምላካችሁን የይሖዋን ትእዛዛት ጠብቁ፤ በምሰጣችሁ ትእዛዝ ላይ ምንም ነገር አትጨምሩ፤ ከዚያም ላይ ምንም አትቀንሱ። 3  “ይሖዋ ከፌጎር ባአል ጋር በተያያዘ ምን እንዳደረገ በገዛ ዓይናችሁ አይታችኋል፤ አምላክህ ይሖዋ የፌጎርን ባአል የተከተለውን እያንዳንዱን ሰው ከመካከልህ አጥፍቶታል። 4  አምላካችሁን ይሖዋን የሙጥኝ ያላችሁት እናንተ ሁላችሁ ግን ይኸው ዛሬም በሕይወት አላችሁ። 5  እኔም አምላኬ ይሖዋ ባዘዘኝ መሠረት ሥርዓቶችንና ድንጋጌዎችን ያስተማርኳችሁ በምትወርሷት ምድር ውስጥ እንድትጠብቋቸው ነው። 6  እነዚህንም በጥንቃቄ ጠብቋቸው፤ ፈጽሟቸውም፤ እንዲህ ብታደርጉ ስለ እነዚህ ሥርዓቶች ሁሉ በሚሰሙ ሕዝቦች ፊት እንደ ጥበበኞችና እንደ አስተዋዮች ትቆጠራላችሁ፤ እነሱም ‘ይህ ታላቅ ብሔር በእርግጥም ጥበበኛና አስተዋይ ሕዝብ ነው’ ይላሉ። 7  በምንጠራው ጊዜ ሁሉ ለእኛ ቅርብ እንደሆነው እንደ አምላካችን እንደ ይሖዋ፣ ለእሱ ቅርብ የሆኑ አማልክት ያሉት ታላቅ ብሔር የትኛው ነው? 8  ዛሬ በፊታችሁ እንዳስቀመጥኩት እንደዚህ ሕግ ያለ የጽድቅ ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች ያሉት የትኛው ታላቅ ብሔር ነው? 9  “ዓይኖቻችሁ ያዩአቸውን ነገሮች እንዳትረሱና በሕይወት ዘመናችሁ ሁሉ ከልባችሁ እንዳይጠፉ ተጠንቀቁ፤ ራሳችሁንም ጠብቁ። እነዚህንም ለልጆቻችሁና ለልጅ ልጆቻችሁ ንገሯቸው። 10  በኮሬብ በአምላካችሁ በይሖዋ ፊት በቆማችሁበት ቀን ይሖዋ ‘በምድር ላይ በሕይወት በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ እኔን መፍራት ይማሩና ልጆቻቸውንም ያስተምሩ ዘንድ ቃሌን እንዲሰሙ ሕዝቡን ወደ እኔ ሰብስብ’ ብሎኝ ነበር። 11  “በመሆኑም እናንተ መጥታችሁ በተራራው ግርጌ ቆማችሁ፤ ተራራውም እስከ ሰማያት ድረስ እየነደደ ነበር፤ ጨለማ፣ ደመናና ድቅድቅ ጨለማ ሆኖ ነበር። 12  ይሖዋም ከእሳቱ ውስጥ ያነጋግራችሁ ጀመር። እናንተም ድምፅ ከመስማት በስተቀር መልክ አላያችሁም፤ የሰማችሁት ድምፅ ብቻ ነበር። 13  እሱም እንድትጠብቁት ያዘዛችሁን ቃል ኪዳኑን ይኸውም አሥርቱን ትእዛዛት ገለጸላችሁ። ከዚያም በሁለት የድንጋይ ጽላቶች ላይ ጻፋቸው። 14  በዚያን ጊዜ ይሖዋ፣ ገብታችሁ በምትወርሷት ምድር የምትፈጽሟቸውን ሥርዓቶችና ደንቦች እንዳስተምራችሁ አዘዘኝ። 15  “በመሆኑም ይሖዋ በኮሬብ በእሳቱ መካከል ሆኖ ባነጋገራችሁ ቀን ምንም መልክ ስላላያችሁ ራሳችሁን ጠብቁ፤ 16  ይኸውም ምግባረ ብልሹ በመሆን በማንኛውም ነገር አምሳል የተቀረጸን የትኛውንም ዓይነት ምስል፣ የወንድ ወይም የሴት ምስል፣ 17  በምድር ላይ ያለን የማንኛውንም እንስሳ ምስል ወይም በሰማይ ላይ የሚበርን የማንኛውንም ወፍ ምስል፣ 18  መሬት ለመሬት የሚሄድን የማንኛውንም ነገር ምስል አሊያም ከምድር በታች በውኃ ውስጥ ያለን የማንኛውንም ዓሣ ምስል ለራሳችሁ እንዳትሠሩ ነው። 19  እንዲሁም ዓይኖችህን ወደ ሰማይ አቅንተህ ፀሐይን፣ ጨረቃንና ከዋክብትን ይኸውም የሰማይን ሠራዊት በሙሉ በምታይበት ጊዜ ተታለህ እንዳትሰግድላቸውና እንዳታገለግላቸው። እነዚህ አምላክህ ይሖዋ ከሰማይ በታች ላሉ ሕዝቦች ሁሉ የሰጣቸው ናቸው። 20  እናንተን ግን ልክ እንደ ዛሬው ሁሉ ይሖዋ የእሱ የግል ንብረት እንድትሆኑ የብረት ማቅለጫ ምድጃ ከሆነችው ከግብፅ አውጥቶ አመጣችሁ። 21  “ይሖዋ በእናንተ የተነሳ እኔን ተቆጣኝ፤ ዮርዳኖስን እንደማልሻገርም ሆነ አምላካችሁ ይሖዋ ርስት አድርጎ ወደሚሰጣችሁ ወደ መልካሚቱ ምድር እንደማልገባ ማለ። 22  እንግዲህ እኔ የምሞተው በዚህ አገር ነው፤ ዮርዳኖስን አልሻገርም፤ እናንተ ግን ተሻግራችሁ ይህችን መልካም ምድር ትወርሳላችሁ። 23  አምላካችሁ ይሖዋ ከእናንተ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን እንዳትረሱ እንዲሁም አምላካችሁ ይሖዋ የከለከላችሁን የማንኛውንም ነገር የተቀረጸ ምስል ለራሳችሁ እንዳትሠሩ ተጠንቀቁ። 24  ምክንያቱም አምላካችሁ ይሖዋ የሚባላ እሳት፣ እሱ ብቻ እንዲመለክ የሚፈልግ አምላክ ነው። 25  “ልጆችና የልጅ ልጆች ስታፈሩ፣ በምድሪቱም ላይ ረጅም ዘመን ስትኖሩ፣ የጥፋት ጎዳና ወደመከተል ዞር ብትሉና የማንኛውንም ነገር የተቀረጸ ምስል ብትሠሩ እንዲሁም በአምላካችሁ በይሖዋ ፊት ክፉ ነገር በመፈጸም እሱን ብታስቆጡት 26  ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ ከምትወርሷት ምድር ያለጥርጥር ወዲያውኑ እንደምትደመሰሱ በዚህ ቀን ሰማይንና ምድርን በእናንተ ላይ ምሥክር አድርጌ እጠራባችኋለሁ። በምድሪቱ ላይ ረጅም ዘመን ከመኖር ይልቅ ሙሉ በሙሉ ትደመሰሳላችሁ። 27  ይሖዋም በሕዝቦች መካከል ይበትናችኋል፤ ይሖዋ በሚበትናችሁ ብሔራትም መካከል ጥቂቶቻችሁ ብቻ ትተርፋላችሁ። 28  እዚያም ማየትም ሆነ መስማት፣ መብላትም ሆነ ማሽተት የማይችሉ በሰው እጅ የተሠሩ የእንጨትና የድንጋይ አማልክትን ታገለግላላችሁ። 29  “እዚያ ሆናችሁ አምላካችሁን ይሖዋን ብትፈልጉት፣ በሙሉ ልባችሁና በሙሉ ነፍሳችሁ ብትሹት በእርግጥ ታገኙታላችሁ። 30  ከጊዜ በኋላ ከባድ ጭንቀት ውስጥ ስትገባና እነዚህ ሁሉ ነገሮች በአንተ ላይ ሲደርሱ ያኔ ወደ አምላክህ ወደ ይሖዋ ትመለሳለህ፤ ድምፁንም ትሰማለህ። 31  ምክንያቱም አምላክህ ይሖዋ መሐሪ አምላክ ነው። አይተውህም፣ አያጠፋህም ወይም ለአባቶችህ በመሐላ ያጸናላቸውን ቃል ኪዳን አይረሳም። 32  “እንግዲህ ከአንተ ዘመን በፊት ስለነበሩት ስለ ቀደሙት ጊዜያት ይኸውም አምላክ ሰውን በምድር ላይ ከፈጠረበት ቀን አንስቶ ስላለው ዘመን ጠይቅ፤ ከአንዱ የሰማይ ጥግ እስከ ሌላኛው የሰማይ ጥግ ድረስ እስቲ መርምር። እንዲህ ያለ እጅግ ታላቅ ነገር ተደርጎ ወይም እንዲህ ያለ ነገር ተሰምቶ ያውቃል? 33  ልክ እንደ አንተ፣ አምላክ በእሳት ውስጥ ሆኖ ሲናገር የሰማና በሕይወት የኖረ ሌላ ሕዝብ አለ? 34  ወይስ አምላካችሁ ይሖዋ የገዛ ዓይኖቻችሁ እያዩ ለእናንተ በግብፅ እንዳደረገው ሁሉ በፍርድ እርምጃዎች፣ ድንቅ በሆኑ ምልክቶች፣ በተአምራት፣ በጦርነት፣ በብርቱ እጅ፣ በተዘረጋ ክንድና አስፈሪ በሆኑ ሥራዎች ከሌላ ብሔር መካከል ለራሱ ብሔር ለመውሰድ ሞክሯል? 35  እውነተኛው አምላክ፣ ይሖዋ መሆኑን ታውቅ ዘንድ እነዚህን ነገሮች እንድታይ ተደርገሃል፤ ከእሱ ሌላ ማንም የለም። 36  አንተን ለማረም ከሰማያት ድምፁን እንድትሰማ አደረገህ፤ በምድርም ላይ የእሱን ታላቅ እሳት እንድታይ አደረገህ፤ ድምፁንም ከእሳቱ ውስጥ ሰማህ። 37  “እሱ አባቶችህን ስለወደደና ከእነሱ በኋላ የሚመጣውን ዘራቸውን ስለመረጠ ከአንተ ጋር በመሆን በታላቅ ኃይሉ ከግብፅ አወጣህ። 38  እንዲሁም ዛሬ እንደሆነው ሁሉ ወደ ምድራቸው ሊያስገባህና ምድራቸውን ርስት አድርጎ ሊሰጥህ ከአንተ ይልቅ ታላቅና ኃያል የሆኑትን ብሔራት ከፊትህ አባረራቸው። 39  እንግዲህ በላይ በሰማይም ሆነ በታች በምድር እውነተኛው አምላክ፣ ይሖዋ እንደሆነ ዛሬ እወቅ፤ እንዲሁም ልብ በል። ሌላ ማንም የለም። 40  ለአንተም ሆነ ከአንተ በኋላ ለሚመጡት ልጆችህ መልካም እንዲሆንላችሁና አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህ ምድር ላይ ለረጅም ዘመን እንድትኖር እኔ ዛሬ የማዝህን የእሱን ሥርዓትና ትእዛዛት ጠብቅ።” 41  በዚያን ጊዜ ሙሴ ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ሦስት ከተሞችን ለየ። 42  ነፍስ ያጠፋ ማንኛውም ግለሰብ ባልንጀራውን የገደለው ሆን ብሎ ካልሆነና የቆየ ጥላቻ ካልነበረው ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዱ በመሸሽ በዚያ መኖር ይችላል። 43  ከተሞቹም ለሮቤላውያን በአምባው ላይ ባለው ምድረ በዳ የምትገኘው ቤጼር፣ ለጋዳውያን በጊልያድ የምትገኘው ራሞት እንዲሁም ለምናሴያውያን በባሳን ያለችው ጎላን ናቸው። 44  ሙሴ በእስራኤል ሕዝብ ፊት ያስቀመጠው ሕግ ይህ ነው። 45  እስራኤላውያን ከግብፅ ከወጡ በኋላ ሙሴ የሰጣቸው ማሳሰቢያዎች፣ ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች እነዚህ ናቸው፤ 46  ይህን የነገራቸው በዮርዳኖስ ክልል ከቤትጰኦር ባሻገር በሚገኘው ሸለቆ ይኸውም ሙሴና እስራኤላውያን ከግብፅ ከወጡ በኋላ ድል ባደረጉት በሃሽቦን ይኖር በነበረው በአሞራውያን ንጉሥ በሲሖን ምድር ነበር። 47  እነሱም ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ባለው ክልል የነበሩትን የሁለቱን የአሞራውያን ነገሥታት ምድር ማለትም የሲሖንን ምድርና የባሳንን ንጉሥ የኦግን ምድር ወረሱ፤ 48  ይህም ምድር በአርኖን ሸለቆ ዳርቻ ከሚገኘው ከአሮዔር አንስቶ እስከ ሲዎን ተራራ ይኸውም እስከ ሄርሞን ድረስ ያለውን አካባቢ ይሸፍናል፤ 49  እንዲሁም ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ የሚገኘውን የአረባን ምድርና በጲስጋ ሸንተረር ግርጌ እስከሚገኘው እስከ አረባ ባሕር ድረስ ያለውን አካባቢ ይጨምራል።
[]
[]
[]
[]
12,583
5  ከዚያም ሙሴ እስራኤላውያንን በሙሉ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ እስራኤላውያን፣ በዛሬው ዕለት የምነግራችሁን ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች ስሙ፤ እወቋቸው፤ በጥንቃቄም ፈጽሟቸው። 2  አምላካችን ይሖዋ በኮሬብ ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን ገብቷል። 3  ይሖዋ ይህን ቃል ኪዳን የገባው ከአባቶቻችን ጋር ሳይሆን ዛሬ በሕይወት እዚህ ካለነው ከእኛ ከሁላችን ጋር ነው። 4  ይሖዋ በተራራው ላይ በእሳት ውስጥ ሆኖ ከእናንተ ጋር ፊት ለፊት ተነጋገረ። 5  በዚያ ወቅት እኔ የይሖዋን ቃል ለእናንተ ለመንገር በይሖዋና በእናንተ መካከል ቆሜ ነበር፤ ምክንያቱም እናንተ ከእሳቱ የተነሳ ፈርታችሁ ወደ ተራራው አልወጣችሁም። እሱም እንዲህ አለ፦ 6  “‘ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ እኔ አምላክህ ይሖዋ ነኝ። 7  ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይኑሩህ። 8  “‘በላይ በሰማያት ወይም በታች በምድር አሊያም ከምድር በታች በውኃ ውስጥ ባለ በማንኛውም ነገር አምሳል የተቀረጸ ቅርጽም ሆነ የተሠራ ምስል ለራስህ አታብጅ። 9  ለእነሱ አትስገድ፤ አታገልግላቸውም፤ ምክንያቱም እኔ አምላክህ ይሖዋ እኔ ብቻ እንድመለክ የምፈልግና በሚጠሉኝ ሁሉ ላይ በአባቶች ስህተት የተነሳ በልጆቻቸው እንዲሁም በሦስተኛና በአራተኛ ትውልዶቻቸው ላይ ቅጣት የማመጣ አምላክ ነኝ፤ 10  ሆኖም ለሚወዱኝና ትእዛዛቴን ለሚጠብቁ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ታማኝ ፍቅር የማሳይ አምላክ ነኝ። 11  “‘የአምላክህን የይሖዋን ስም በከንቱ አታንሳ፤ ምክንያቱም ይሖዋ ስሙን በከንቱ የሚያነሳውን ሳይቀጣ አይተወውም። 12  “‘አምላክህ ይሖዋ ባዘዘህ መሠረት ቅዱስ አድርገህ ትጠብቀው ዘንድ የሰንበትን ቀን አክብር። 13  ሥራህን ሁሉ በስድስት ቀን ትሠራለህ፤ 14  ሰባተኛው ቀን ግን ለአምላክህ ለይሖዋ ሰንበት ነው። በዚህ ቀን አንተም ሆንክ ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ፣ ወንድ ባሪያህም ሆነ ሴት ባሪያህ፣ በሬህም ሆነ አህያህ ወይም ማንኛውም የቤት እንስሳህ አሊያም በከተሞችህ ውስጥ ያለ የባዕድ አገር ሰው ምንም ሥራ አትሥሩ፤ ይህም አንተ እንደምታርፈው ወንድ ባሪያህና ሴት ባሪያህ እንዲያርፉ ነው። 15  አንተም በግብፅ ምድር ባሪያ እንደነበርክና አምላክህ ይሖዋ በብርቱ እጅና በተዘረጋ ክንድ ከዚያ እንዳወጣህ አስታውስ። አምላክህ ይሖዋ የሰንበትን ቀን እንድታከብር ያዘዘህ ለዚህ ነው። 16  “‘አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝምና መልካም እንዲሆንልህ አምላክህ ይሖዋ ባዘዘህ መሠረት አባትህንና እናትህን አክብር። 17  “‘አትግደል። 18  “‘አታመንዝር። 19  “‘አትስረቅ። 20  “‘በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመሥክር። 21  “‘የባልንጀራህን ሚስት አትመኝ። የባልንጀራህን ቤት፣ እርሻውን፣ ወንድ ባሪያውን፣ ሴት ባሪያውን፣ በሬውን፣ አህያውን ወይም የባልንጀራህ የሆነውን ማንኛውንም ነገር አትመኝ።’ 22  “ይሖዋ በተራራው ላይ በእሳቱ መካከል በደመናውና በድቅድቅ ጨለማው ውስጥ ሆኖ እነዚህን ትእዛዛት ከፍ ባለ ድምፅ ለመላው ጉባኤያችሁ ተናገረ፤ ከእነዚህም ሌላ ምንም አልጨመረም፤ ከዚያም እነዚህን በሁለት የድንጋይ ጽላቶች ላይ ጽፎ ሰጠኝ። 23  “ይሁን እንጂ ተራራው በእሳት እየነደደ ሳለ ከጨለማው ውስጥ ድምፅ ሲወጣ ስትሰሙ የነገድ መሪዎቻችሁና ሽማግሌዎቹ በሙሉ ወደ እኔ መጡ። 24  ከዚያም እንዲህ አላችሁ፦ ‘ይኸው አምላካችን ይሖዋ ክብሩንና ታላቅነቱን አሳይቶናል፤ ድምፁንም ከእሳቱ ውስጥ ሰምተናል። አምላክ ከሰው ጋር መነጋገር እንደሚችልና ያም ሰው በሕይወት ሊኖር እንደሚችል በዛሬው ቀን አይተናል። 25  ታዲያ አሁን ለምን እንሙት? ምክንያቱም ይህ ታላቅ እሳት ሊበላን ይችላል። የአምላካችንን የይሖዋን ድምፅ መስማት ከቀጠልን እንደምንሞት የተረጋገጠ ነው። 26  ለመሆኑ ከሥጋ ሁሉ መካከል ልክ እኛ እንደሰማነው ሕያው የሆነው አምላክ በእሳት ውስጥ ሆኖ ሲናገር ሰምቶ በሕይወት የኖረ ማን አለ? 27  አንተው ራስህ ቀርበህ አምላካችን ይሖዋ የሚናገረውን ሁሉ ስማ፤ ከዚያም አምላካችን ይሖዋ የነገረህን ሁሉ ትነግረናለህ፤ እኛም እንሰማለን፤ ደግሞም የተባልነውን እናደርጋለን።’ 28  “ከዚያም ይሖዋ ያላችሁኝን ነገር ሰማ፤ ይሖዋም እንዲህ አለኝ፦ ‘ይህ ሕዝብ ምን እንዳለህ ሰምቻለሁ። የተናገሩት ነገር ሁሉ መልካም ነው። 29  ምንጊዜም እኔን የሚፈራና ትእዛዛቴን ሁሉ የሚጠብቅ ልብ ቢኖራቸው ምናለ፤ እንዲህ ቢሆን ለእነሱም ሆነ ለልጆቻቸው ለዘላለም መልካም ይሆንላቸው ነበር! 30  ሂድና “ወደየድንኳናችሁ ተመለሱ” በላቸው። 31  አንተ ግን እዚሁ እኔ ጋ ቆይ፤ እኔም ርስት አድርገው እንዲወርሷት በምሰጣቸው ምድር ውስጥ ይጠብቋቸው ዘንድ የምታስተምራቸውን ትእዛዛት፣ ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች በሙሉ እነግርሃለሁ።’ 32  እንግዲህ አምላካችሁ ይሖዋ ያዘዛችሁን በጥንቃቄ ፈጽሙ። ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ ዞር አትበሉ። 33  ርስት አድርጋችሁ በምትወርሷት ምድር በሕይወት እንድትኖሩ፣ እንድትበለጽጉና ዕድሜያችሁ እንዲረዝም አምላካችሁ ይሖዋ ባዘዛችሁ መንገድ ሁሉ ሂዱ።
[]
[]
[]
[]
12,584
6  “አምላካችሁ ይሖዋ ተሻግራችሁ በምትወርሷት ምድር ውስጥ ትጠብቋቸው ዘንድ እንዳስተምራችሁ የሰጠኝ ትእዛዛት፣ ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች እነዚህ ናቸው፤ 2  ይህም አንተ፣ ልጅህና የልጅ ልጅህ ዕድሜያችሁ ይረዝም ዘንድ በሕይወታችሁ ዘመን ሁሉ አምላካችሁን ይሖዋን እንድትፈሩ እንዲሁም እኔ የማዛችሁን የእሱን ደንቦችና ትእዛዛት ሁሉ እንድትጠብቁ ነው። 3  እስራኤል ሆይ፣ ስማ፤ የአባቶችህ አምላክ ይሖዋ በገባልህ ቃል መሠረት ወተትና ማር በምታፈሰው ምድር እንድትበለጽግና እጅግ እንድትበዛ እነዚህን በጥንቃቄ ጠብቅ። 4  “እስራኤል ሆይ ስማ፣ አምላካችን ይሖዋ አንድ ይሖዋ ነው። 5  አንተም አምላክህን ይሖዋን በሙሉ ልብህ፣ በሙሉ ነፍስህና በሙሉ ኃይልህ ውደድ። 6  እኔ ዛሬ የማዝህን እነዚህን ትእዛዛት በልብህ ያዝ፤ 7  በልጆችህም ውስጥ ቅረጻቸው፤ በቤትህ ስትቀመጥ፣ በመንገድ ላይ ስትሄድ፣ ስትተኛና ስትነሳ ስለ እነሱ ተናገር። 8  በእጅህም ላይ እንደ ማስታወሻ እሰራቸው፤ በግንባርህም ላይ እንደታሰረ ነገር ይሁኑ። 9  በቤትህ መቃኖችና በግቢህ በሮች ላይ ጻፋቸው። 10  “አምላክህ ይሖዋ ለአንተ ለመስጠት ለአባቶችህ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ወደማለላቸው ምድር ሲያስገባህና በዚያም አንተ ያልገነባሃቸውን ታላላቅና ያማሩ ከተሞች፣ 11  አንተ ባልደከምክባቸው የተለያዩ መልካም ነገሮች የተሞሉ ቤቶችን፣ አንተ ያልቦረቦርካቸውን የውኃ ማጠራቀሚያዎች እንዲሁም አንተ ያልተከልካቸውን የወይን ተክሎችና የወይራ ዛፎች ስታገኝ፣ በልተህም ስትጠግብ 12  ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣህን ይሖዋን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ። 13  ይሖዋ አምላክህን ፍራ፤ እሱን አገልግል፤ በስሙም ማል። 14  ሌሎች አማልክትን ይኸውም በዙሪያችሁ ያሉ ሕዝቦች የሚያመልኳቸውን የትኞቹንም አማልክት አትከተሉ፤ 15  ምክንያቱም በመካከልህ ያለው አምላክህ ይሖዋ እሱ ብቻ እንዲመለክ የሚፈልግ አምላክ ነው። አለዚያ የአምላክህ የይሖዋ ቁጣ በላይህ ይነድዳል፤ ከምድርም ገጽ ጠራርጎ ያጠፋሃል። 16  “በማሳህ እንደተፈታተናችሁት አምላካችሁን ይሖዋን አትፈታተኑት። 17  አምላካችሁ ይሖዋ እንድትጠብቋቸው ያዘዛችሁን ትእዛዛት እንዲሁም ማሳሰቢያዎቹንና ሥርዓቶቹን በጥንቃቄ ጠብቁ። 18  እንድትበለጽግና ይሖዋ ለአባቶችህ የማለላቸውን መልካሚቱን ምድር ገብተህ እንድትወርስ በይሖዋ ፊት ትክክልና መልካም የሆነውን አድርግ፤ 19  ይሖዋ በገባው ቃል መሠረት ጠላቶችህን ሁሉ ከፊትህ አባረህ አስወጣ። 20  “ወደፊት ልጅህ ‘አምላካችን ይሖዋ የሰጣችሁ ማሳሰቢያዎች፣ ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች ትርጉም ምንድን ነው?’ ብሎ ሲጠይቅህ 21  እንዲህ ትለዋለህ፦ ‘እኛ በግብፅ የፈርዖን ባሪያዎች ሆነን ነበር፤ ይሖዋ ግን በብርቱ ክንድ ከግብፅ አወጣን። 22  ይሖዋም በግብፅ፣ በፈርዖንና በቤተሰቡ ሁሉ ላይ ታላላቅና አጥፊ የሆኑ ድንቅ ምልክቶችንና ተአምራትን ዓይናችን እያየ ፈጸመ። 23  እኛንም ለአባቶቻችን የማለላቸውን ምድር ሊሰጠን ከዚያ አውጥቶ ወደዚህ አመጣን። 24  ከዚያም ይሖዋ ምንጊዜም መልካም ይሆንልን ዘንድ እነዚህን ሥርዓቶች ሁሉ እንድንፈጽምና አምላካችንን ይሖዋን እንድንፈራ አዘዘን፤ ይህም ዛሬ እንደሆነው ሁሉ በሕይወት እንድንኖር ነው። 25  አምላካችንን ይሖዋን በመታዘዝ ልክ እሱ በሰጠን መመሪያ መሠረት እነዚህን ትእዛዛት ሁሉ በጥንቃቄ ብንፈጽም ለእኛ ጽድቅ ይሆንልናል።’
[]
[]
[]
[]
12,585
7  “አምላክህ ይሖዋ ርስት አድርገህ ወደምትወርሳት ምድር ሲያመጣህ ብዙ ሕዝብ ያላቸውን ብሔራት ይኸውም ከአንተ ይልቅ ብዙ ሕዝብ ያላቸውንና ኃያላን የሆኑትን ሰባት ብሔራት ማለትም ሂታውያንን፣ ገርጌሻውያንን፣ አሞራውያንን፣ ከነአናውያንን፣ ፈሪዛውያንን፣ ሂዋውያንን እና ኢያቡሳውያንን ከፊትህ ያስወግድልሃል። 2  አምላክህ ይሖዋ እነሱን አሳልፎ ይሰጥሃል፤ ድልም ታደርጋቸዋለህ። አንተም ሙሉ በሙሉ ደምስሳቸው። ከእነሱ ጋር ምንም ዓይነት ቃል ኪዳን አትጋባ፤ አትራራላቸውም። 3  ከእነሱ ጋር በጋብቻ አትዛመድ። ሴቶች ልጆችህን ለወንዶች ልጆቻቸው አትዳር ወይም ሴቶች ልጆቻቸውን ለወንዶች ልጆችህ አትውሰድ። 4  ምክንያቱም ልጆችህ ሌሎች አማልክትን ያገለግሉ ዘንድ እኔን ከመከተል ዞር እንዲሉ ያደርጓቸዋል፤ ከዚያም የይሖዋ ቁጣ በእናንተ ላይ ይነድዳል፤ አንተንም ወዲያው ያጠፋሃል። 5  “ከዚህ ይልቅ እንዲህ አድርጉባቸው፦ መሠዊያዎቻቸውን አፈራርሱ፤ የማምለኪያ ዓምዶቻቸውን ሰባብሩ፤ የማምለኪያ ግንዶቻቸውን ቆራርጡ፤ የተቀረጹ ምስሎቻቸውንም በእሳት አቃጥሉ። 6  ምክንያቱም አንተ ለአምላክህ ለይሖዋ ቅዱስ ሕዝብ ነህ፤ አምላክህ ይሖዋ በምድር ላይ ካሉ ሕዝቦች ሁሉ መካከል አንተን የራሱ ሕዝብ፣ ልዩ ንብረቱ እንድትሆን መርጦሃል። 7  “ይሖዋ እናንተን የወደዳችሁና የመረጣችሁ ከሌሎች ሕዝቦች ሁሉ ይልቅ ቁጥራችሁ ስለበዛ አይደለም፤ ቁጥራችሁማ ከሌሎች ሕዝቦች ሁሉ አነስተኛ ነበር። 8  ከዚህ ይልቅ ይሖዋ እናንተን ከባርነት ቤት ይኸውም ከግብፅ ንጉሥ ከፈርዖን እጅ ይታደጋችሁ ዘንድ ይሖዋ በብርቱ እጅ ያወጣችሁ ስለወደዳችሁና ለአባቶቻችሁ የማለላቸውን መሐላ ስለጠበቀ ነው። 9  አንተም አምላክህ ይሖዋ እውነተኛ አምላክ፣ ታማኝ አምላክ እንዲሁም ለሚወዱትና ትእዛዛቱን ለሚጠብቁ ሁሉ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ቃል ኪዳኑን የሚጠብቅና ታማኝ ፍቅር የሚያሳይ መሆኑን በሚገባ ታውቃለህ። 10  የሚጠሉትን ግን በማጥፋት በግልጽ ይበቀላቸዋል። በሚጠሉት ላይ እርምጃ ለመውሰድ አይዘገይም፤ በግልጽ ይበቀላቸዋል። 11  ስለዚህ እኔ ዛሬ የማዝህን ትእዛዛት፣ ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች በማክበር በጥንቃቄ ጠብቃቸው። 12  “እነዚህን ድንጋጌዎች ብትሰሙና ብትጠብቋቸው እንዲሁም ብትፈጽሟቸው አምላካችሁ ይሖዋ ለአባቶቻችሁ በመሐላ የገባውን ቃል ኪዳንና ታማኝ ፍቅር ይጠብቃል። 13  ይወድሃል፣ ይባርክሃል እንዲሁም ያበዛሃል። አዎ፣ ለአንተ ሊሰጥህ ለአባቶችህ በማለላቸው ምድር ላይ የሆድህን ፍሬ፣ የመሬትህን ምርት፣ እህልህን፣ አዲሱን የወይን ጠጅህን፣ ዘይትህን፣ የከብቶችህን ጥጆችና የመንጋህን ግልገሎች ይባርክልሃል። 14  አንተም ከሕዝቦች ሁሉ ይበልጥ የተባረክ ትሆናለህ፤ በመካከልህ ልጅ የሌለው ወንድ ወይም ሴት አይገኝም፤ እንስሶችህም ግልገል የሌላቸው አይሆኑም። 15  ይሖዋ በሽታን ሁሉ ያስወግድልሃል፤ በግብፅ ሳለህ ታውቃቸው ከነበሩት አሰቃቂ በሽታዎች አንዱንም በአንተ ላይ አያመጣም። ከዚህ ይልቅ በሚጠሉህ ሁሉ ላይ ያመጣባቸዋል። 16  አምላክህ ይሖዋ አሳልፎ የሚሰጥህን ሕዝቦች ሁሉ ታጠፋለህ። አትዘንላቸው፤ አማልክታቸውንም አታገልግል፤ ምክንያቱም እንዲህ ማድረግህ ወጥመድ ይሆንብሃል። 17  “ምናልባት በልብህ ‘እነዚህ ብሔራት እኮ ከእኛ ይልቅ ብዙ ናቸው። ታዲያ እንዴት ላባርራቸው እችላለሁ?’ ትል ይሆናል፤ 18  ሆኖም አትፍራቸው። አምላክህ ይሖዋ በፈርዖንና በግብፅ ሁሉ ላይ ያደረገውን አስታውስ፤ 19  ዓይኖችህ ያዩአቸውን ታላላቅ የፍርድ እርምጃዎች እንዲሁም አምላክህ ይሖዋ አንተን ለማውጣት የተጠቀመባቸውን ድንቅ ምልክቶች፣ ተአምራት፣ ብርቱ እጅና የተዘረጋ ክንድ አስብ። አምላክህ ይሖዋ በምትፈራቸው ሕዝቦች ሁሉ ላይ የሚያደርገው ይህንኑ ነው። 20  አምላክህ ይሖዋ በሕይወት የተረፉትና ከፊትህ የተሸሸጉት እስኪጠፉ ድረስ ጭንቀት ይለቅባቸዋል። 21  ታላቅና የሚያስፈራ አምላክ የሆነው አምላክህ ይሖዋ ከአንተ ጋር ስለሆነ በእነሱ የተነሳ አትሸበር። 22  “አምላክህ ይሖዋ እነዚህን ብሔራት በጥቂት በጥቂቱ ከፊትህ ያባርራቸዋል። የዱር አራዊት እንዳይበዙብህ በአንድ ጊዜ ጠራርገህ እንድታጠፋቸው አይፈቀድልህም። 23  አምላክህ ይሖዋ እነሱን በእጅህ አሳልፎ ይሰጥሃል፤ እስኪጠፉም ድረስ ሙሉ በሙሉ ድል ታደርጋቸዋለህ። 24  እሱም ነገሥታታቸውን በእጅህ አሳልፎ ይሰጥሃል፤ አንተም ስማቸውን ከሰማይ በታች ትደመስሳለህ። ድምጥማጣቸውን እስክታጠፋ ድረስ ማንም አይቋቋምህም። 25  የአማልክታቸውን የተቀረጹ ምስሎች በእሳት አቃጥሉ። ወጥመድ ሊሆንብህ ስለሚችል በእነሱ ላይ ያለውን ብርም ሆነ ወርቅ አትመኝ ወይም ለራስህ አትውሰድ፤ ምክንያቱም ይህ በአምላክህ በይሖዋ ፊት አስጸያፊ ነገር ነው። 26  አስጸያፊ ነገር ወደ ቤትህ በማምጣት ልክ እንደ እሱ ራስህን ለጥፋት አትዳርግ። ለጥፋት የተለየ ነገር ስለሆነ ፈጽመህ ጥላው፤ ሙሉ በሙሉም ተጸየፈው።
[]
[]
[]
[]
12,586
8  “በሕይወት እንድትኖሩና እንድትበዙ እንዲሁም ይሖዋ ለአባቶቻችሁ የማለላቸውን ምድር ገብታችሁ እንድትወርሱ ዛሬ የማዛችሁን እያንዳንዱን ትእዛዝ በጥንቃቄ ጠብቁ። 2  አምላክህ ይሖዋ በልብህ ምን እንዳለ ይኸውም ትእዛዛቱን ትጠብቅ እንደሆነና እንዳልሆነ ለማወቅ ይፈትንህና ትሑት ያደርግህ ዘንድ በእነዚህ 40 ዓመታት በምድረ በዳ እንድትጓዝበት ያደረገህን ረጅሙን መንገድ አስታውስ። 3  ትሑት እንድትሆን አደረገህ፤ ካስራበህም በኋላ አንተ የማታውቀውን፣ አባቶችህም የማያውቁትን መና መገበህ፤ ይህን ያደረገው፣ ሰው ከይሖዋ አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በምግብ ብቻ ሊኖር እንደማይችል ሊያሳውቅህ ነው። 4  በእነዚህ 40 ዓመታት፣ የለበስከው ልብስ አላለቀም፤ እግርህም አላበጠም። 5  አንድ ሰው ለልጁ እርማት እንደሚሰጥ ሁሉ አምላክህ ይሖዋም እርማት ይሰጥህ እንደነበር ልብህ በሚገባ ያውቃል። 6  “እንግዲህ አንተ በመንገዶቹ በመሄድና እሱን በመፍራት የአምላክህን የይሖዋን ትእዛዛት ጠብቅ። 7  ምክንያቱም አምላክህ ይሖዋ መልካም ወደሆነች ምድር ሊያስገባህ ነው፤ ይህች ምድር ጅረቶች ያሏት፣ በሸለቋማ ሜዳዋና በተራራማ አካባቢዋ ምንጮች የሚፈልቁባትና ውኃዎች የሚንዶለዶሉባት፣ 8  ስንዴ፣ ገብስ፣ ወይን፣ በለስና ሮማን የሚበቅልባት፣ የወይራ ዘይትና ማር የሚገኝባት፣ 9  የምግብ እጥረት የሌለባት፣ ምንም ነገር የማታጣባት፣ ብረት ያለባቸው ድንጋዮች የሚገኙባት እንዲሁም ከተራሮቿ መዳብ ቆፍረህ የምታወጣባት ምድር ናት። 10  “በልተህ በምትጠግብበት ጊዜ ስለሰጠህ ስለ መልካሚቱ ምድር አምላክህን ይሖዋን አመስግነው። 11  እኔ ዛሬ የማዝህን የእሱን ትእዛዛት፣ ድንጋጌዎችና ደንቦች ችላ በማለት አምላክህን ይሖዋን እንዳትረሳው ተጠንቀቅ። 12  በልተህ ስትጠግብ፣ ጥሩ ጥሩ ቤቶችን ሠርተህ በዚያ መኖር ስትጀምር፣ 13  ከብትህና መንጋህ ሲበዛ፣ ብርህና ወርቅህ ሲበራከት እንዲሁም የአንተ የሆነው ሁሉ እየበዛ ሲሄድ 14  ልብህ እንዳይታበይና ከግብፅ ምድር ይኸውም ከባርነት ቤት ያወጣህን አምላክህን ይሖዋን እንዳያስረሳህ ተጠንቀቅ፤ 15  መርዛማ እባቦችና ጊንጦች በሞሉበት እንዲሁም ውኃ የተጠማ ደረቅ ምድር ባለበት በዚያ ጭልጥ ያለና የሚያስፈራ ምድረ በዳ አቋርጠህ እንድታልፍ ያደረገህን አምላክህን እንዳያስረሳህ ተጠንቀቅ። እሱ ከጠንካራ ዓለት ውኃ አፍልቆልሃል፤ 16  እንዲሁም ወደፊት መልካም እንዲሆንልህ አንተን ትሑት ለማድረግና ለመፈተን ሲል አባቶችህ የማያውቁትን መና በምድረ በዳ መግቦሃል። 17  በልብህም ‘ይህን ሀብት ያፈራሁት በራሴ ኃይልና በእጄ ብርታት ነው’ ብለህ ብታስብ 18  ሀብት እንድታፈራ ኃይል የሰጠህ አምላክህ ይሖዋ መሆኑን አስታውስ፤ ይህን ያደረገው ዛሬ እንደሆነው ሁሉ ለአባቶችህ በመሐላ የገባውን ቃል ኪዳን ለመፈጸም ነው። 19  “አምላክህን ይሖዋን ብትረሳና ሌሎች አማልክትን ብትከተል እንዲሁም እነሱን ብታገለግልና ለእነሱ ብትሰግድ፣ በእርግጥ እንደምትጠፉ እኔ ዛሬ እመሠክርባችኋለሁ። 20  የአምላካችሁን የይሖዋን ቃል ስላልሰማችሁ ይሖዋ ከፊታችሁ እንደሚያጠፋቸው ብሔራት እናንተም እንዲሁ ትጠፋላችሁ።
[]
[]
[]
[]
12,587
9  “እስራኤል ሆይ፣ ስማ፤ እንግዲህ ዛሬ ከአንተ ይልቅ ታላቅና ኃያል የሆኑ ብሔራትን እንዲሁም ታላላቅና እስከ ሰማያት የሚደርስ ቅጥር ያላቸውን ከተሞች በማስለቀቅ ወደ ምድሪቱ ለመግባት ዮርዳኖስን ልትሻገር ነው፤ 2  ‘የኤናቅን ልጆች ማን ሊቋቋማቸው ይችላል?’ ሲባልላቸው የሰማኸውን፣ አንተ ራስህ የምታውቃቸውን ታላቅ ሕዝብና ቁመተ ረጃጅም የሆኑትን የኤናቅን ልጆችም ልታስለቅቅ ነው። 3  ስለሆነም አምላክህ ይሖዋ ዛሬ ከአንተ ቀድሞ እንደሚሻገር እወቅ። እሱ የሚባላ እሳት ነው፤ ደግሞም ያጠፋቸዋል። ልክ ይሖዋ ቃል በገባልህ መሠረት በፍጥነት ታባርራቸውና ታጠፋቸው ዘንድ ዓይንህ እያየ ድል ያደርጋቸዋል። 4  “አምላክህ ይሖዋ እነሱን ከፊትህ በሚያባርራቸው ጊዜ በልብህ ‘ይሖዋ ይህችን ምድር እንድወርስ ወደዚህ ያመጣኝ እኮ በራሴ ጽድቅ ነው’ አትበል፤ ይሖዋ እነዚህን ብሔራት ከፊትህ የሚያባርራቸው በራሳቸው ክፋት የተነሳ ነው። 5  የእነሱን ምድር ገብተህ የምትወርሰው ከጽድቅህ ወይም ከልብህ ቅንነት የተነሳ አይደለም። ከዚህ ይልቅ አምላክህ ይሖዋ እነዚህን ብሔራት ከፊትህ የሚያባርራቸው ከራሳቸው ክፋት የተነሳ ነው፤ እንዲሁም ይሖዋ ለአባቶችህ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ የማለላቸውን ቃል ለመፈጸም ሲል ነው። 6  ስለዚህ አምላክህ ይሖዋ ይህችን መልካም ምድር እንድትወርሳት የሚሰጥህ ከጽድቅህ የተነሳ እንዳልሆነ እወቅ፤ ምክንያቱም አንተ ግትር ሕዝብ ነህ። 7  “በምድረ በዳ አምላክህን ይሖዋን እንዴት እንዳስቆጣኸው አስታውስ፤ ፈጽሞም አትርሳ። ከግብፅ ምድር ከወጣችሁበት ጊዜ አንስቶ እዚህ ቦታ እስክትደርሱ ድረስ በይሖዋ ላይ ዓምፃችኋል። 8  በኮሬብም እንኳ ይሖዋን አስቆጥታችሁት ነበር፤ ይሖዋም በእናንተ ላይ እጅግ ከመቆጣቱ የተነሳ እናንተን ለማጥፋት አስቦ ነበር። 9  እኔም የድንጋይ ጽላቶቹን ይኸውም ይሖዋ ከእናንተ ጋር የገባው ቃል ኪዳን የተጻፈባቸውን ጽላቶች ለመቀበል ወደ ተራራው በወጣሁ ጊዜ እህል ሳልበላና ውኃ ሳልጠጣ በተራራው ላይ 40 ቀንና 40 ሌሊት ቆይቼ ነበር። 10  ከዚያም ይሖዋ በአምላክ ጣት የተጻፈባቸውን ሁለቱን የድንጋይ ጽላቶች ሰጠኝ፤ በእነሱም ላይ ይሖዋ እዚያ ተሰብስባችሁ በነበረበት ቀን በተራራው ላይ በእሳት ውስጥ ሆኖ ለእናንተ የነገራችሁ ነገር ሁሉ ተጽፎባቸው ነበር። 11  ከ40 ቀንና ከ40 ሌሊት በኋላ ይሖዋ ሁለቱን የድንጋይ ጽላቶች ይኸውም የቃል ኪዳኑን ጽላቶች ሰጠኝ፤ 12  ይሖዋም እንዲህ አለኝ፦ ‘ተነስ፤ ቶሎ ብለህ ውረድ፤ ምክንያቱም ከግብፅ ያወጣኸው ሕዝብህ የጥፋት ጎዳና እየተከተለ ነው። እንዲከተሉት ካዘዝኳቸው መንገድ ፈጥነው ዞር ብለዋል። ከብረት የተሠራ ምስልም ለራሳቸው አበጅተዋል።’ 13  ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ ‘ይህን ሕዝብ አይቼዋለሁ፤ በእርግጥም ግትር ሕዝብ ነው። 14  አጠፋቸውና ስማቸውን ከሰማይ በታች እደመስሰው ዘንድ ተወኝ፤ አንተን ግን ከእነሱ ይልቅ ኃያልና ብዙ ሕዝብ ያቀፈ ብሔር አደርግሃለሁ።’ 15  “እኔም ተራራው በእሳት እየተቀጣጠለ እያለ ተመልሼ ከተራራው ወረድኩ፤ ሁለቱን የቃል ኪዳን ጽላቶችም በእጆቼ ይዤ ነበር። 16  ከዚያም ስመለከት በአምላካችሁ በይሖዋ ላይ ኃጢአት እንደፈጸማችሁ አየሁ! ለራሳችሁም የብረት ጥጃ ሠርታችሁ ነበር። ይሖዋ እንድትከተሉት ካዘዛችሁ መንገድ ፈጥናችሁ ዞር ብላችሁ ነበር። 17  ስለዚህ ሁለቱን ጽላቶች አሽቀንጥሬ በመወርወር ዓይናችሁ እያየ ሰባበርኳቸው። 18  ከዚያም እንደ መጀመሪያው ጊዜ ሁሉ ለ40 ቀንና ለ40 ሌሊት በይሖዋ ፊት ተደፋሁ። በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር በማድረግና እሱን በማስቆጣት በፈጸማችሁት ኃጢአት ሁሉ የተነሳ እህል አልቀመስኩም፤ ውኃም አልጠጣሁም። 19  ምክንያቱም ይሖዋ በእናንተ ላይ እጅግ ከመቆጣቱ የተነሳ ሊያጠፋችሁ ስለተዘጋጀ ፈርቼ ነበር። ይሁንና ይሖዋ በዚያን ጊዜም ሰማኝ። 20  “ይሖዋ አሮንን ለማጥፋት እስኪያስብ ድረስ በእሱ ላይ ተቆጥቶ ነበር፤ ሆኖም በዚያን ጊዜ ስለ አሮንም ምልጃ አቀረብኩ። 21  ከዚያም የኃጢአት ሥራችሁን ይኸውም ጥጃውን ወስጄ በእሳት አቃጠልኩት፤ ሰባበርኩት፤ እንደ አቧራ ብናኝ እስኪሆንም ድረስ ፈጨሁት፤ ብናኙንም ከተራራው በሚወርደው ጅረት ውስጥ በተንኩት። 22  “በተጨማሪም በታበራ፣ በማሳህ እና በቂብሮትሃታባ ይሖዋን አስቆጣችሁት። 23  ይሖዋ ከቃዴስበርኔ በላካችሁና ‘ውጡ፤ የምሰጣችሁንም ምድር ውረሱ!’ ባላችሁ ጊዜ በአምላካችሁ በይሖዋ ትእዛዝ ላይ በድጋሚ ዓመፃችሁ፤ በእሱ አልታመናችሁም፤ እንዲሁም አልታዘዛችሁትም። 24  እኔ እናንተን ካወቅኩበት ጊዜ አንስቶ በይሖዋ ላይ እንዳመፃችሁ ነው። 25  “በመሆኑም 40 ቀንና 40 ሌሊት በይሖዋ ፊት ተደፋሁ፤ እንዲህ በፊቱ የተደፋሁት፣ ይሖዋ እንደሚያጠፋችሁ ተናግሮ ስለነበር ነው። 26  ከዚያም እንዲህ በማለት ይሖዋን መማጸን ጀመርኩ፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ሕዝብህን አታጥፋ። እነሱ በታላቅነትህ የታደግካቸውና በኃያል ክንድህ ከግብፅ ያወጣሃቸው የግል ንብረቶችህ ናቸው። 27  አገልጋዮችህን አብርሃምን፣ ይስሐቅንና ያዕቆብን አስብ። የዚህን ሕዝብ ግትርነት፣ ክፋትና ኃጢአት አትመልከት። 28  አለዚያ እኛን ባወጣህበት ምድር የሚገኙ ሰዎች “ይሖዋ ቃል ወደገባላቸው ምድር ሊያስገባቸው ስላልቻለና ስለጠላቸው በምድረ በዳ ሊገድላቸው አወጣቸው” ሊሉ ይችላሉ። 29  እነሱ በታላቅ ኃይልህና በተዘረጋ ክንድህ ያወጣሃቸው ሕዝቦችህና የግል ንብረቶችህ ናቸው።’
[]
[]
[]
[]