text
stringlengths
0
2.31k
በሁለተኛነት በተመሰረተባቸው ክስም በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢፌዴሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 32(1)(ሀ)ና539(1) (ሀ)ስር የተደነገገውን መተላለፉ ነው፡፡ በዚህ ክስ ስር ከባድ የሰው መግደል ወንጀል የተረጋገጠበት ግለሰብ በእድሜ ልክ ጽኑ እስራት ወይም በሞት እንደሚቀጣ ተደንግጓል፡፡
«በ16 ዓመቷ ታዳጊ ሃና ላላንጎ ላይ የመድፈር ወንጀል በመፈፀም ለሞት አብቅተዋታል» የተባሉት አምስት ተጠርጣሪዎች ሳምሶን ስለሺ፣ በዛብህ ገብረማርያም፣ በቃሉ ገብረመድህን፣ ኤፍሬም አየለና ተመስገን ጸጋዬ ሲሆኑ፤ ታህሳስ 7 ቀን 2007 ዓ.ም በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበዋል፡፡
ችሎቱም የተከሳሾችን ማንነት አጣርቶ የተመሰረተባቸው ክስ እንዲደርሳቸውና ጉዳያቸውን በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲከታተሉ አዝዟል፣ «ጠበቃ የማቆም አቅም የለንም» ባሉት መሰረት መንግሥት ጠበቃ እንዲመደብላቸው አዝዟል፡፡ ክሱን ለማንበብም ለታህሳስ 30 ቀን 2007 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
ዐቃቤ ህግ የመሰረተው ክስ እንደሚያስረዳው መስከረም 20 ቀን 2007ዓ.ም በግምት 11፡00ሲሆን ሃና ላላንጎ ጦር ኃይሎች አካባቢ ታክሲ ስትጠብቅ ነበር፡፡ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን የግብረ ሥጋ ግንኙነት ለመፈጸም አስበው ታክሲ ከምትጠብቅበት ስፍራ አንደኛ ተከሳሽ ሳምሶን ስለሺ በሚያሽከረክረው ሚኒ ባስ በማስገባት ቀራንዮ አደባባይ አካባቢ ተጉዘው አብረው እስከ ምሽቱ ሁለት ተኩል ከቆዩ በኋላ ሁለተኛ ተከሳሽ በዛብህ ገብረማርያምን በስልክ ደውሎ ጠርቶታል፡፡
በዛብህ ገብረማርያምም በሚያሽከረክረው ሚኒባስ ታክሲ አራተኛና አምስተኛ ተከሳሾችን ኤፍሬም አየለንና ተመስገን ጸጋዬን ይዞ ከሳምሶን ስለሺ ጋር በመገናኘት ሟችን ወደ ቤቱ ወስዷታል፡፡ የሚያሽከረክረውን ታክሲ አቁሞ እንደሚመለስ ተነጋግሮ መለየቱንም ይገልጻል፡፡ ኤፍሬምም በዛብህና ሶስተኛው ተከሳሽ በቃሉ ገብረመድህን መኖሪያ ቤት ወስደዋታል፡፡ በግምትም ከምሽቱ አራት ሰዓት ጀምሮ ሌሊቱን በሙሉ ሁሉም ተከሳሾች እየተፈራረቁ በአሰቃቂ ሁኔታ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ሲፈፅሙባት እንዳደሩ ነው መዝገቡ የሚያትተው፡፡ በዚህም 18 ዓመት ባልሞላቸው ልጆች ላይ የሚፈፀም የግብረ ሥጋ ድፍረት በደል ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡
ከዚያም ከአምስት ቀናት በኋላ በዛብህ ገብረማርያም በበቃሉ ገብረመድህን አማካኝነት ሟችን ልዩ ቦታው ጦር ኃይሎች ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን አካባቢ ወስዶ ጥሏታል፡፡ ሟች በደረሰባት ጉዳት የሰውነት ክፍሎቿ ሥራ በማቆማቸውና ብዛት ያለው ደም ስለፈሰሳት ከቀናት በኋላ ህይወቷ በማለፉ በፈፀሙት ከባድ የሰው መግደል ወንጀል ተከስሰዋል፡፡
ምንጭ: ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ
«ለሃና ፈጣን እርዳታ አልተደረገም» ሲሉ አባቷ ተናገሩ
አላህ ፍቱን ቅጣት ያውርድባቸው!!
Amharic News _ አማርኛ ዜና
Ethiopian News, Sunday, July 22 , 2018 _ የዕለቱ ዜና በአማርኛ
በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ቦታዎች አዲሱ ዓመት ለመቀበል ያለውን ዝግጅት የሚያስቃኝ.
1ዐ ሚሊየን ዶላር በህገ-ወጥ መንገድ ከሃገር ሊወጣ ሲል በቁጥጥር ሥር ዋለ
ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አብይ አህመድ እና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሀዋሳ ያደረጉት ጉብኝት
የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ወደ ኤርትራ ዛሬ በተጓዘው ልዑክ ዙሪያ የተናገሩት ንግግር
Ethiopian News: የአክሱም ጽዮን ማርያም በዓል በድምቀት ተከበረ
Amharic News _ ዜና በአማርኛ
የአክሱም ጽዮን ማርያም በዓል በድምቀት ተከበረ
(Dec, 01, 2014, (አዲስ አበባ))--አክሱም ህዳር 21/2007 የአክሱም ጽዮን ማርያም የንግስ በአል ከግማሽ ሚሊዮን ህዝብ በላይ በተገኘበት ዛሬ ተከበረ ። አቡነ ማቲያስ ርእሳነ ሊቃነ ጳጳሳት ዘ ኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወኢጨጌ ዘ መንበረ ተክለሀይማኖት በዓሉን ለማክበር ለተሰበሰበው ህዝብ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅርና የደስታ እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡
የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርእሰ መስተዳድር አቶ አባይ ወልዱ እንደተናገሩት በአሉ በአክሱም ከተማ የሚገኙ ታሪካዊና ተፈጥሮአዊ ቅርሶችን በማስተዋወቅ ልናከብረው ይገባል ብለዋል ። በተጨማሪም በአክሱምና አከባቢው የሚገኙ ቅርሶችን በማልማት የቱሪስት መዳረሻዎችን ማስፋት እንደሚገባ ገልፀው በዚህም ባለሀብቶችና የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በርትተው ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
የአክሱም ጽዮን ማርያምን ለማክበር ከጀርመንና እስራኤል የመጡ ዶክተር አልያን ደቢድና ሚስ ዮላአነዳ ዲሎሰ እንደተናገሩት በርካታ ህዝብ በአንድ ላይ ተሰባስቦ በዓሉን በፍቅር ማክበሩ በጣም ደስ የሚል ትእይንት እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
በበዓሉ አከባበር ላይ የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ የሃይማኖት አባቶችና ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ምእምናን ተገንተዋል፡፡
Amharic News _ አማርኛ ዜና
Ethiopian News, Sunday, July 22 , 2018 _ የዕለቱ ዜና በአማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አብይ አህመድ እና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሀዋሳ ያደረጉት ጉብኝት
በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ቦታዎች አዲሱ ዓመት ለመቀበል ያለውን ዝግጅት የሚያስቃኝ.
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የ2011 ለዳያስፖራው ያስተላለፉት መልዕክት
ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አሁን በቤተ-መንግስት ያደረጉት ታሪካዊ ንግግር
Featured / አርዕስተ ዜና
በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በተካሄደውና እየተካሄደ ባለው ሕዝባዊ ተቃውሞ ምክንያት የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ለተቃውሞ በወጡ ዜጎች ላይ በወሰዱት ከመጠን ያለፈ የኃይል ዕርምጃ 103 ሰዎች መሞታቸውን፣ 59 ሰዎች መቁሰላቸውን፣ 22 ሰዎች ድብደባና ስቃይ እንደተፈጸመባቸው፣ 226 ሰዎች ከሕግ ውጪ መታሰራቸውን፣ 12 ሰዎች የደረሱበት አለመታወቁን፣ 800 ሰዎች መፈናቀላቸውንና 892 መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸውን የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ሰመጉ) ባወጣው ሪፖርት ይፋ አደረገ፡፡
ሰመጉ ሰኞ መጋቢት 5 ቀን 2008 ዓ.ም. በዋና ጽሕፈት ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት፣ በሪፖርቱ የሰፈረው በክልሉ ከሚገኙ 342 ወረዳዎች ውስጥ በ33 ወረዳዎች ከኅዳር 2 እስከ የካቲት 12 ቀን 2008 ዓ.ም. ውስጥ ባካሄደው የመስክ ምርመራ አማካይነት የተገኘ ውጤት መሆኑን አስታውቋል፡፡
በዚህም መሠረት በምዕራብ ሸዋ፣ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ በፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን፣ በምዕራብና በምሥራቅ ወለጋ፣ በሆሮ ጉድሩ፣ በምዕራብና በምሥራቅ ሐረርጌ፣ በባሌ፣ በአርሲ ዞኖች የሚገኙ 33 ወረዳዎች ውስጥ የመስክ ምርመራ መካሄዱ ተገልጿል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ከተቀሰቀሰው ሕዝባዊ ተቃውሞ ጋር በተያያዘ የተለያዩ የመንግሥትና የሕዝብ ንብረት መውደሙ የተገለጸ ሲሆን፣ ‹‹ከክልሉ መስተዳድር አካላት ባገኘነው መረጃ መሠረት በርካታ የገበሬ ማኅበር ጽሕፈት ቤቶች፣ ንዑስ ፖሊስ ጣቢያዎች፣ የገበሬዎች ማሠልጠኛ አዳራሾችና ንብረትነታቸው የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ የሆኑ ከአሥር በላይ መኪናዎች ተቃጥለዋል፡፡ አንድ ሚሊዮን ሰባት መቶ ሺሕ ብር የሚገመት አንድ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስም ተቃጥሏል፤›› በማለት የሰመጉ ሪፖርት የጉዳቱን መጠን ይጠቁማል፡፡
‹‹የመንግሥት ታጣቂ ኃይሎች በአምቦ፣ በጀልዱና በግንደበረት አስገድዶ መድፈር መፈጸማቸውን ከነዋሪዎች ለማወቅ ችለናል፤›› የሚለው የሰመጉ ሪፖርት በተጨማሪም በአንዳንድ ቦታዎች የመንግሥት ታጣቂዎች ሕገወጥ የቤት ለቤት አሰሳ ሌሊት ላይ ማድረጋቸውን፣ በፍተሻ ወቅት የሚያገኙትን ንብረት መውሰዳቸውን፣ በዜጎች ላይ ከፍተኛ የሆነ ድብደባ መፈጸማቸውንና ዛቻ፣ ማስፈራሪያና ስድብ መሰንዘራቸውን ያትታል፡፡ በተቃውሞ እንቅስቃሴው የተነሳ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን አመያ ወረዳ ኩኖ ቁሊታ (ቀረሳ ቁሊት)፣ ወረወገሪ (በሬዳ) እንዲሁም አብሌ መድኃኔዓለም በተባሉ ቀበሌዎች ከ30 ዓመታት በላይ በአካባቢው የሚኖሩ የአማራ ብሔር ተወላጆች መኖሪያ ቤት ከነሙሉ ንብረቱ ማስተር ፕላኑን በመቃወም ሰልፍ በወጡ ጥቂቶች አማካይነት ታኅሳስ 2 ቀን 2008 ዓ.ም. መቃጠሉም በሪፖርቱ ሰፍሯል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም በቤት ውስጥ የነበረ ለሽያጭ የተዘጋጀ በርበሬና የተለያዩ የእህል ዓይነቶች ምርት መውደሙን፣ ማሳ ላይ የነበረ እህል መቃጠሉንና በዚህም ምክንያት ቁጥራቸው ከ500 የማያንስ ተፈናቃዮች በድንኳን ውስጥ መጠለላቸውን የሰመጉ ባለሙያዎች ማረጋገጣቸውን ሪፖርቱ ያብራራል፡፡
መንግሥት በክልሉ አሸባሪዎችና የታጠቁ አካላት የሕዝቡን ጥያቄ ተገን አድርገው በአገር ንብረትና በሰው ሕይወት ላይ ጉዳት እያደረሱ ነው የሚል ወቀሳ የሚሰነዝር ሲሆን፣ የሰመጉ ሪፖርት ግን ምርመራ ባካሄደባቸው አካባቢዎች እንዲህ ያለ ነገር አለመመልከቱን አስታውቋል፡፡
‹‹ማጣራት ባደረግንበት ሥፍራና ጊዜ ውስጥ በዓለም አቀፍ ብያኔ መሠረት አሸባሪዎች የምንላቸው ክፍሎች የአሸባሪነት ጥቃት ማድረሳቸውን አላየንም፡፡ እንዲሁም የታጠቁ ኃይሎች ከመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ጋር ተኩስ ሲያደርጉ አላስተዋልንም፤›› በማለት የሰመጉ ዋና ዳይሬክተር አቶ ብፅአተ ተረፈ አስረድተዋል፡፡
በክልሉ የተለያዩ ሥፍራዎች እየተካሄዱ ያሉ ተቃውሞዎች አሁንም በመካሄድ ላይ ያሉ በመሆናቸው በተቃውሞው የተገደሉ፣ የተጎዱ፣ የታሰሩና የወደሙ ንብረቶች ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል ሰመጉ አስገንዝቧል፡፡
በዚህም የተነሳ ተቃውሞው በተካሄደበት ወቅት በምዕራብ አርሲ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ የሃይማኖት ተቋማት ማለትም የኦርቶዶክስ፣ የፕሮቴስታንትና የካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት መቃጠላቸው በሪፖርቱ ከተካተቱ ጉዳዮች አንዱ ነው፡፡
ሰመጉ ከዚህ ቀደም በዚህ ጉዳይ ላይ ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ ከተቃውሞ እንቅስቃሴው ጋር በተያያዘ የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን መንግሥት በገለልተኛ አካል እንዲያጣራ፣ ለጥሰቱ ተጠያቂ የሆኑ አካላትን ለፍርድ እንዲያቀርብ፣ በግጭቱ ሳቢያ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ተገቢው ካሳ እንዲከፈል፣ እንዲሁም ቤቶቻቸው ለተቃጠሉባቸው፣ ንብረት ለወደመባቸውና ከኑሮአቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች መልሶ የማቋቋም ሥራ እንዲከናወን ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡
ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ
ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተከታታይ ትምህርት መርሃ-ግብር(CEP) በ2007 ዓ.ም በአዲስና ነባር የትምህርት ዘርፎች ተማዎችን ተቀብሎ በድግሪ መርሃ-ግብር ማስተማር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ማንኛውም አመልካች እስከ መስከረም 25 ቀን 2007 ዓ.ም በየመርሃ-ግብሩ ማዕከላት (ሐረር፤ድሬዳዋ፤ጅግግጋ እና ጭሮ) ቀርቦ ማመልካት የሚቻል ሲሆን የትምህርት ዘርፎች ዝርዝር እንዲሚከተለው ይሆናል፡፡
በሥራ አመራር (Management)
በኮምፕዩተር ሳይንስ (Computer Science)
አፋን ኦሮሞ፤ሥነ ጽሑፍና ተግባቦት (Afan Oromo, Literature & Communication
አመልካቾች ከግንቦት 10/2006 ጀምሮ እስከ መስከረም 25/2007 በሥራ ሰዓት ማመልከት የምትችሉ መሆኑን በደስታ እንገልጻለን፡፡
የምታመለክቱበት ቦታዎች፡-
የሚቻል መሆኑን በደስታ እንገልጻለን፡፡
ክቕይሮ ዝደሊ ብዙሕ ነገር'ዩ። ኣነ ኣብ ገዛ'የ ዝሰርሕ። እዚ ድማ ኣብ ዓደይ ኮይነ ክገብሮ እንተዝኽእል ክንደይ ምፈተኹን ወትሩ ዝምነዮን'ዩ።
ኣብ'ዚ ዓዲ ብዙሕ ዘማርር ነገር'ዃ እንተዘየጋጠመኒ እቲ ዝዓበየ ማሕለኻ ኮይኑኒ ዘሎን ዝነበረን ቋንቋ'ዩ።
Goolgule.com: የጌታቸው አሰፋ ሌጋሲ እና ቀጣይ አቅጣጫዎች!
በቀዳሚ፡ገብረ፡እግዚኣብሔር፡ሰማየ፡ወምድረ።
ትምህርቱ በጣም በጥሩ ሁኔታ ተፅፏል፣ በጣም ግልፅ ነው፣ ሆኖም ግን ለያንዳንዱ ቃልና ፊደል አጠራር በተጨማሪ በኦዲዮ ቢዘጋጅ በጣም ቆንጆ ነው፣ ምክንያቱም ግዕዝ የራሱ አክሰንት ስላለው፣ አናባቢው ቢሳሳት የሚያርመው ሰው የለም። ስለዚህ በቪዲዮና ኦዲዮ ቀረፃ ሙያ የሚተባበር ሰው ካስፈለገ የኢሜል ወይም የቴሌፎን አድራሻችሁን ብትልኩልኝ በኦዲዮና በቪዲዮ ቀርፃው ልተባበራችሁ እችላለሁ!
ኢሜል አድራሻየ crossage@gmail.com ነው!
የምኖረው ካናዳ ነው።
በሲያትል የሰሜን አሜሪካ ስፖርትና ባህል ሳምንት በድምቀት ተጠናቀቀ _ Ethiopia Nege
በሲያትል የሰሜን አሜሪካ ስፖርትና ባህል ሳምንት በድምቀት ተጠናቀቀ
– ሲያትል በኢትዮጵያ ቀን አሸብርቃ ነበር
– ሃመልማል አባተ የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ ያድርግልኝ አለች
– ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ እና ሻምበል በላይነህ ተጋባዥ ነበሩ
/Ethiopia Nege News/:- በኢትዮጵያዊያን ስፖርትና ባህል ፌስቲቫል ታሪክ ከመክፈቻው ጀምሮ ሙሉ ሳምንት በድምቀት የተከበረበት የመጀመሪያው ነው የተባለለትና በርካታ ኢትዮጵያዊያን የተሰባሰቡበት ክብረ በአል በድምቀት ተጠናቀቀ፡፡
በመክፈቻው የኢትዮጵያ ባንዲራ ወደ ስቴድዮሙ በፓራሹት ሲወርድ ታዳሚውን ያስደመመው የሲያትሉ የስፖርትና ባህል በአል ልዩ ልዩ ዝግጅቶችን አካቶ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡
በምግብ ሽያጭ፡ የተለያዩ ሃገራዊ እቃወችና ቅርሳቅርሶች በመገበያያ ድንኳኖች ውስጥ ልዩ ልዩ እቃዎች ሲቸበቸቡ ከመሰንበታችውም በላይ የኢትዮጵያ ባንድራ የታተሙባቸው ቲሸርቶች፡ ቦርሳዎች፡ ጃኬቶችና የቁልፍ መያዣዎች የገበያውን አጣበውት ነበር፡፡ በተጨማሪ እየወጣና እየገባ ይርመሰመስ የነበረው ህዝብ ወደ 30 ሺህ ይደርሳል የሚል ግምት የተሰጠው ሲሆን በርካታ ታዳሚዎች የኢትዮጵያ ባንዲራን ለብሰውና በጃቸው ይዘው ተስተውለዋል፡፡
ከተመሰረተ 34ኛ አመቱን ያከበረው ኢ.ኤስ.ኤፍ.ኤን.ኤ በተለያዩ ጊዜያት ራሱን እያሳደገ እንደመጣ የሚታወቅ ሲሆን ላለፉት ጥቂት አመታት በሃብታሙ ሼክ ሙሃመድ አላሙዲንና አብነት ባቋቋሙት ተለጣፊ ድርጅት ውድድር ውስጥ ገብቶ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ኢ.ኤስ.ኤፍ.ኤን.ኤ ላለፉት ጥቂት አመታት ከፍተኛ ህዝባዊ ተቀባይነትን በማግኝቱ ተለጣፊው በእነ አብነት ተቋም በዘንድሮው አመት ምንም አይነት ዝግጅት ሳያደርግ ቀርቷል፡፡
የዘንድሮው በአል ተመልካች እጅግ በርካታ ከመሆኑም ባሻገር በተለያዩ መገናኛ ብዙሃንና ማህበራዊ ድረገጾች በቪድዩ የተመለከቱ ኢትዮጵያዊያን ቁጥርም እጅግ በርካታ እንደነበር ለመረዳት ተችሏል፡፡
አርብ እለት በሚደረገው የኢትዮጵያ ቀን ዝግጅት ተጋባዥ ከነበሩት መካከል ሻምበል /ራስ/ በላይነህንና ዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳን ጨምሮ የተለያዩ ድምጻዊያን ዝግጅታቸውን ያቀርውቡ ሲሆን ድምጻዊት ሀመልማል አባተ ከህዝብ ጉያ በመውጣቷ እንደተጸጸተች በመግለጽ የኢትዮጵያ ህዝብ ይቅርታ እንዲያደርግላት ጠይቃለች፡፡
Previous articleኢ.ኤስ.ኤፍ.ኤን.ኤ ሲያትል ጊዜያዊ መገበያያ ቦታ 2017
Next articleካልፎሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ (ታሪካዊ ልቦለድ) /‎በእውቀቱ ስዩም/
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ አለም አቀፍ ሽልማት አሸናፊ ሆነ
በአዲስ አበባ የታሰሩት የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች የዋስትና መብት በይግባኝ ታገደ
ሲጀመር ህዝቡ ጥፋተኛ ስለሆነ ይቅርታ ይጠይቀን ነው ያለችው እንጂ እኔ ስላጠፋሁ ይቅርታ ይደረግልኝ አላለችም ።
ሊያዳምጡት የሚገባ ቃለምልልስ /ተክለሚካኤል አበበ እና ጋዜጤኛ ዮሐንስ ደሳለኝ
የኢሕአዴግ መንግሥት አራት ፓርቲዎች መግለጫ /ክፍል ፪/
የኢሕአዴግ መንግሥት አራት ፓርቲዎች መግለጫ /ክፍል ፩/
የኦሮምኛ ሙዚቃ ድምጻዊ ሃጫሉ ሑንዴሳ በሚሊኒየም አዳራሽ የፖለቲካ እስረኞችን ያስበበት ሙዚቃ
ህብር ራዲዮ – ፊት ለፊት ውይይት ከፕሮፌሰር እዝቄኤል ጋቢሳ እና አቶ...
ሊያደምጡት የሚገባ-የዶ/ር ሃይሌ ፊዳ ፈረንሳዊት ባለቤት ወ/ሮ በርናዴት ሃይሌ ስለባልቤታቸው በደራው...
ፎረም 65፦ የኃይል እርምጃ መዘዝና መፍትሄ /ከቀይ ሽብር እስከ ኦሮሞ ተቃውሞ/
የጁምኣው አርበኛ! !!! መንግስቱ ዘገዬ
“ያን እኔን አፋልጉኝ!” /ወለላዬ ከስዊድን/
ጌታ ሆይ ! /መላኩ አላምረው/
እቶ አለኒ – ጥያቄ አለኝ? /ደረጀ ፍቅሩ/
ለአለም አቀፍ ንግድ የሚያግዙ መግቢያና መውጫ አማራጮቹን የማስፋት እንዲሁም ለምግብ ምርት ማምረቻ የሚሆኑ የእርሻ መሬቶች ወደ ክልሉ የማጠቃለል ስራዎች በዚህ የእቅዱ ክፍል ውስጥ ይገኛሉ። ትመጣለች ተብላ ለምትጠበቀው ሉአላዊ ትግራይ የኢንዱስትሪ ልማት መሰረት ለመጣል ሲል ገና በልቶ ካልጠገበው የኢትዮጵያ ህዝብ ጉሮሮ ላይ ካፒታልና ጥሬ እቃ ይዘርፋል፤ ይነጥቃልም።። ይህ እኔና አንተ/ቺ በእለት እለት ህይወታችን የምናየውና የሚሰማን ጸሀይ የሞቀው ሀቅ ነው። ማሳዎች ይቅረቡ ለሚል አካል እስኪ ምልከታችንን መረጃ አዘል እናድርገው፡፡
በአንድ መሬት ላይ እስከ ሶስት ሰዎች ብድር እንዲወስዱ መደረጉም ማስረጃነቱን ያጠናክረዋል። በቤኒሻንጉል ግሙዝ፣ አፋር እና ደቡብ ኦሞ ያለው የግብርና ኢንቨስትመንት ታሪክ ከዚህ የተለየ እንደማይሆን የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ። እንደ አንዳንድ ምንጮች ዘገባም ባለሃብት ተብዬ የትግራይ ተዋላጆች በቤኒሻንጉል ግሙዝ፣ አፋር እና ደቡብ ኦሞ ካለው መሬት ወሳጅ ባለሀብት አንጻር ሲታይ በትንሹ 75% በአንዳንድ ቦታዎች ደግሞ 90% ይደርሳሉ። የዚህ ጽሁፍ አቅራቢ ቤኒሻንጉል ግሙዝ ክልል ሰራተኛ በነበረበት ወቅት የተመለከተውም ሀቅም ነው። ይህም በሀገሩቱ ውስጥ ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል የለም የሚለውን ጩሀታችንን ያረጋግጥልናል።
በሌላ በኩል የተራ አባላቱን የስነልቦናና የኢኮኖሚ አቅም በማሳደግ ላይ የሰራው ስራም ቀላል የሚባል አይደለም። በሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦች የስነልቦናና የኢኮኖሚ ውድቀትና ዋጋ መክፈል ማለታችን ነው። በአንድ በኩል በኩል ለአባላቱ የአዲስ አበባን መሬት እና አነስተኛ ኪራይ የሚከፈልባቸው የመንግስት ቤቶች በማደል መጠመዱን ማንሳት ያስፈልጋል። ለነገዋ ትግራይ የእውቀትና አሰራር ሽግግር እንዲሁም ከጠቅላይነት በሽታው መነሻነት አባላቱ የስራ አመራር እውቀትና ክህሎታቸውን ኣያወደሙ አንዲያሳድጉ በፌደራልና አዲስ አበባ መስተዳድር ተቋማት ውስጥ ሰግስጎአል።
እስቲ በአካባቢዎቻችሁ ያሉ ወይም የነበሩ ልዩ ልዩ የተሻለ ጥቅማ ጥቅም ይገኝባቸዋል ተብሎ የሚታመኑ ተቋማትና አደረጃጀቶችን አስቡ። ማነው እየመራቸውና እየተጠቀመ ያለው? ከእድር ሊቀመንበር ጀምሩ፣ የቤተክርስትያን አስተዳዳሪዎች፡ የሙያ ማህበራት የሴቶችና እና ወጣቶች ማህበራት አመራሮች፣ የአረጋውያን፡ የልማትና ግብረሰናይ ድርጅቶች መሪዎች፣ ወጣት አስመጪና ላኪዎች እና ሌሎች ዘርፎችም በደጋፊዎቹ እንዲዋጡ ቀጥተኛ ባልሆኑ ስልቶች እየሰራ ይገኛል። ነባር አመራሮቹ እንዲለቁ በመግፋት የራሱን አባላት ወደ ቦታው እንዲደርሱ በተቀናጀ መልኩ በመርዳት። በ push and pull እስትራቴጂ ማለት ነው።
አየር መንገድ፡ ብሄራዊ ደህንነት፣ መከላከያ ሙሉ በሙሉ፣ የመከላከያ ብረታ ብረት ኮርፖሬሽን፣ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ተቋማት፣ የብሮድካስትና መረጃ ደህንነት መስሪያ ቤቶች፣ የግብር እና ግሙሩክ፣ የወሳኝ ተቋማት የቦርድ ሰብሳቢዎች እነማን ናቸው? ይህ በሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦች ዋጋ መክፈል የሚያካሂደውን የቀኝ ገዥነት ተግባር ሳያንሰው ነጻ ወጥታችሁአል፣ በዲሞክራሲ መንገድ ላይ ናችሁ ማለቱ ምን ይሉታል? መልሱ አንድ ነው። የንቀት ጥግ።
Previous articleእኔና አግባው በቂሊንጦ ዞን 2 ውስጥ …./ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ/
Next articleየዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ እናት ማን ናቸው? /አቻምየለህ ታምሩ/
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ አለም አቀፍ ሽልማት አሸናፊ ሆነ
በአዲስ አበባ የታሰሩት የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች የዋስትና መብት በይግባኝ ታገደ
ሊያዳምጡት የሚገባ ቃለምልልስ /ተክለሚካኤል አበበ እና ጋዜጤኛ ዮሐንስ ደሳለኝ
የኢሕአዴግ መንግሥት አራት ፓርቲዎች መግለጫ /ክፍል ፪/