input
stringlengths
1
130k
የመብት ተሟጋች ሜሮን እስጢፋኖስ በበኩሏ ኤርትራዉያን ለሐገር ነፃነት ታግለናል ትላለች።
ይሁን እንጂ በእነኝህ ዓመታት አልፎ አልፎ በታጠቁ ቡድኖች ሲያጋጥማቸው ከነበረው የከብት ዘረፋ በስተቀር የግብርና ሥራቸውን በሰላም ሲያከናውኑ መቆየታቸውን ያስታውሳሉ፡፡
ሆኖም ካለፉት ሁለት ሳምንታት ወዲህ ባልተለመደ መልኩ በታጠቁ ቡድኖች የሚፈጸሙ የግድያና የዘረፋ ተግባራት እየተባባሱ በመምጣቸው አካባቢውን ጥለው መውጣታቸውን ገልጸዋል፡፡
አሁን የሚታየውን መፈናቀል ለማስቆምና በቀጣይ መደረግ ያለበትን ሁኔታ ለመገምገም ከተለያዩ አካላት የተውጣጣ ቡድንም ወደ አካባቢው መንቀሳቀሱን አመልክተዋል፡፡
በደቡብ ክልል የሰፈራ ፕሮግራም በተካሄደባቸው የቤንች ማጂና የከፋ ዞኖች በሠፋሪ አርሶአደሮች ላይ የመፈናቀል አደጋ ሲያጋጥም የአሁኑ መጀመሪያው አይደለም፡፡
ባለፈው ዓመት በነበረው ዝቅተኛ ዝናብ የተነሳ ከዞኑ ነዋሪዎች ገሚሱ አስቸኳይ ርዳታ የሚያሻው ነው ተብሏል።
የችግሩን መነሻ ባለፈው ዓመት በአካባቢው በቂ ዝናብ በለመኖሩ ድርቅ በመከሰቱ እንደሆነ አቶ መልካሙ አብራርተዋል፡፡
አንድ የዝቋላ ወረዳ አርሶአደር በበኩላቸው ችግሩ አሳሳቢና አፋጣኝ መፍትሔ የሚሻ ነው ነው ያሉት፡፡
የምግብ እርዳታው በፍጥነት ወደ አካባቢው ካልደረሰ ከፍተኛ ሰብዓዊ ቀውስ እንደሚፈጠር አቶ መልክሙ ስጋታቸውን አስቀምተዋል፡፡
የዋግኽምራ ብሔረሰብ ዞን አስተዳደር ዝናብ አጠር ከሆኑ የአማራ ክልል አካባቢዎች አንዱ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ኢትዮጵያ ጠ ሚ ዐቢይ አህመድ የዓለም የሰላም ኖቤል አሸነፉ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ የዘንድሮውን የዓለም የሰላም ኖቤል አሸነፉ።
ጠ ሚ ዐቢይ ለዚህ የበቁት በዋናነት ሃያ ዓመታት በዘለቀው የኢትዮጵያና ኤርትራ የድንበር ውዝግብ ሰላም እንዲወርድ ላበረከቱት አስተዋጽኦ መኾኑ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ የዘንድሮውን የዓለም የሰላም ኖቤል አሸነፉ።
በሱዳን ወታደራዊ ኃይሉን ከተቃዋሚዎች ጋር ማስማማታቸውም ሽልማቱን እንዲያሸንፉ ረድቷቸዋል ነው የተባለው።
አብይ አህመድ ኛው የዓለም የሰላም ኖቤል ተሸላሚ ሲሆኑ የአሜሪካን ዶላርም ይበረከትላቸዋል።
አፍሪቃ ጀርመን በዘር ማጥፋት ተከሰሰች ሁለት የናሚቢያ ጎሳዎች የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽማለች የሚሏት ጀርመን ላይ በኒው ዮርክ ክስ መስርተዋል።
ጀርመን በዘር ማጥፋት ተከሰሰች የታሪክ ታዛቢዎች የ ኛው ክ ዘ የመጀመሪያው የዘር ማጥፋት ወንጀል ይሉታል።
ወደ የሔሬሮ እና ናማ ጎሳ አባላት በዛሬዋ ናሚቢያ ከጎርጎሮሳዊው እስከ ዓ ም ባሉት ዓመታት በጀርመን ቅኝ ገዢዎች እጅ ማለቃቸው ይታመናል።
በጊዜው የዛሬዋ ናሚቢያ የጀርመን ደቡብ ምዕራብ አፍሪቃ ተብላ የምትጠራ ቅኝ ግዛት ነበረች።
በ ዓ ም በቅኝ ገዚዎቻቸው ላይ ለተቃውሞ የወጡት የሔሬሮ እና የናማ ጎሳዎች በጀርመን ወታደሮች ወደ በረሐ ተባረሩ።
በቅኝ ገዢዎቹ እርምጃ በመቶ የሔሬሮ ጎሳ አባላት እንዲሁም ከናማ ጎሳ ግማሽ ያክሉ አለቁ።
ይኸ ሁሉ ግን ለበርካታ አመታት ለአውሮጳም ሆነ ለአፍሪቃ ተዘንግቶ የቆየ የሰቆቃ ታሪክ ነው።
ወንጀሉ የተፈፀመባቸዉ የሁለቱ የናሚቢያ ጎሳዎች ተወካዮች ካሳ ሊከፈለን ይገባል በማለት ሲሟገቱ አመታት አስቆጥረዋል።
አሁን ክስ የመሰረቱት የፖለቲካዉ ሙግት ዉጤት አላመጣ ስላለ ይመስላል።
የድርድሩን ሒደት አጥብቀው ከሚተቹት መካከል አንዷ የሆኑት የሔሬሮ ጎሳ ተወካይ ኤስተር ሙይንጃንጉዌ ለእኛ ሒደቱ በሕፀጽ የተሞላ ነው።
በጉዳዩ ላይ የሚደራደሩት ወገኖች ሁለቱ ልዩ ልዑኮች እንዲሆኑ የወሰነው ማን ነው
ከጎርጎሮሳዊው ዓ ም የተፈጸመውን ጭፍጨፋ ጀርመን ዘር ማጥፋት ተብሎ መጠራቱን ባትክድም ካሳ ለመክፈል ግን ስታንገራግር ቆይታለች።
ፍርድ ቤቱ ለበርካታ ዓመታት ሲንከባለል የቆየውን ጉዳይ ለመዳኘት ሥልጣኑ እንዳለው ገና አልታወቀም።
ማንኛውም ፍርድ ቤት የቀረበለትን ክስ የመዳኘት ሥልጣን እንዳለው ይመረምራል።
መመርመር ብቻም ሳይሆን ጉዳዩ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ሕጋዊ መሰረት መኖሩንም ያጤናል።
አንድ የጀርመን ፖለቲከኞች በበኩላቸው አገራቸው ጉዳዩን የያዘችበት መንገድ ተገቢ አይደለም ሲሉ ይተቻሉ።
ይፋዊ በሆነ መልኩ ዘር ማጥፋት ነው ብሎ መቀበሉ በርግጥም አንዳች እርምጃ ነው።
ሆኖም ግን ሁልጊዜም ከሔሬሮ እና ከናማዎች ጋር የቀጥታ ድርድር ማድረግ እንደሚገባቸው ሲናገሩ አይደመጥም።
ዛሬ ሥልጠናው ይፋ በተደረገበት መርሐ ግብር እንደተገለጸው በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ስልጠናዎች በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች ይሰጣሉ።
አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ እና ጆን ሖፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ በምርጫ ላይ ያተኮረ ሥልጠና መስጠት ጀመሩ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአገሪቱ ፖለቲከኞች ዘንድ ዛሬም ድረስ የክርክር መነሾ የሆነው አገራዊ ምርጫ ነሐሴ ቀን ዓ ም እንዲካሔድ ወስኗል።
ቦርዱ ይፋ ባደረገው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ከሚያዝያ እስከ ግንቦት ቀን ዓ ም ድረስ የመራጮች ምዝገባ ይከናወናል።
ከግንቦት እስከ ግንቦት ባሉት ቀናት ደግሞ የእጩዎች ምዝገባ ይካሔዳል።
ነሐሴ ቀን የሚካሔደው ምርጫ ውጤት ከነሐሴ እስከ ጳጉሜ ባሉት ቀናት ይፋ ይደረጋል።
የዶይቼ ቬለው ጌታቸው ተድላ ሥልጠናው ምን ይፈይዳል ሲል መርሐ ግብሩ ይፋ ሲደረግ የተገኙ አንድ ተሳታፊ ጠይቋል።
አባቶቻችን ጥለዉልን ያለፉትን የታሪክ አሻራ እኛ ልጆቻቸዉ ታሪኩን በሞያችን እናስተላፍ ብለን ነዉ።
የሟቾች ቁጥር በኢጣልያ ከ ሺህ በላይ በስፓኝ አስር ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰላሳ አምስት በአሜሪካን ሺህ በፈረንሳይ ደግሞ ሺህ ደርሶአል።
በዓለማችን በኮሮና የተያዙ ሰዎች ቁጥር ዛሬ እኩለ ቀን ላይ በወጣ ዘገባ መሠረት አንድ ሚሊዮን ሺህ ሶስት መቶ ሰማንያ ስድስት ደርሷል።
አንድ አራተኛው በአሜሪካን ሌሎቹ ደግሞ በተቀረው ዓለም ነው ያሉት።
በኮሮና ምክንያት ከዓለም ህዝብ ግማሹ ማለትም ከ ቢሊዮን በላይ የሚሆነው በ ሃገራት ከቤቱ እንዲሰራ ተገዷል።
ሜርክል ሐኪማቸው ተህዋሲው እንዳለባቸው ከታወቀ በኋላ ሦስት ጊዜ ምርመራ ተደርጎላቸው በሦስቱም ምርመራ ከተህዋሲው ነጻ መሆናቸው ተረጋግጧል።
ስደተኞቹና ለስደተኞቹ መብት እንከራከራለን የሚሉ ወገኖች እንደሚሉት ለስደተኞቹ ይሰጥ የነበረዉ የምግብ ርዳታዉ ከተቋረጠ ሁለት ወር አለፈዉ።
ረዥም ጊዜ የፈጀው የሁለቱ ሲኖዶሶች ዕርቀ ሰላም ውይይት በመጨረሻ ለፍፃሜ በቃ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከእንግዲህ አንድ ሲኖድስ ብቻ እንዳላትም ተገለጸ።
በእርቀ ሰላሙ መግለጫ ላይ የተገኙት ዶ ር ዐብይ አህመድ ዛሬ በኢትዮጵያውያን ላይ ተገንብቶ የቆየው የጥላቻ ግንብ ተናደ ብለዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚንሥቴር መሥሪያ ቤት በቃል አቀባዩ ነቢያት ጌታቸው አሰግድ አማካኝነት ዛሬ በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ።
አውሮጳ ጀርመን የአውሮጳ ህብረት እና የስደተኞች ጉዳይ የእሁዱ ጉባኤ ለጀርመን መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል እጅግ አስፈላጊ ነበር።
የአውሮጳ ህብረት የስደተኞች መርህ የአውሮጳ ህብረት በስደተኞች ጉዳይ ላይ በአባል ሀገራት መካከል የተፈጠረውን ልዩነት ለማጥበብ እየጣረ ነው።
በዚህ ሳምንት ሐሙስ ብራሰልስ ቤልጅየም የሚካሄደው የአባል ሀገራት መሪዎች ጉባኤ ከሚነጋገርባቸው ጉዳዮች አንዱ እና ዋነኛው ይኽው የስደተኞች ጉዳይ ነው።
ከዚህ ጉባኤ አስቀድሞ አባል ሀገራት ባለፈው እሁድ አስቸኳይ ስብሰባ አካሂደዋል።
የኮታ ስርዓቱን የተቃወሙት በተለይ ሀንጋሪ ፖላንድ ቼክ ሪፐብሊክ ስሎቫክያን የመሳሰሉ ሀገራት እስካሁንም በዚሁ አቋማቸው እንደጸኑ ነው።
አሁን ደግሞ ኢጣልያ እና ማልታን የመሳሰሉ ሀገራት በፈንታቸው የጀልባ ስደተኞች አናስገባም ማለት ጀምረዋል።
የአውሮጳ ህብረት በወቅቱ ሁለቱም ሀገራት የሰዎችን ህይወት ለመታደግ ቅድሚያ እንዲሰጡ ቢጠይቅም ጥሪው ሰሚ አላገኘም ነበር።
ችግሩ ግን በስተመጨረሻ ስፓኝ ስደተኞቹን ለማስገባት ፈቃደኛ በመሆንዋ ተፈቷል።
እነዚህ እና ሌሎችንም የህብረቱን አባል ሀገራት የማያስማሟቸው ጉዳዮች በመካከላቸው ያለውን ልዩነት እያሰፋ ሄዷል።
ይህ መነሻ ሆኖም የፊታችን ሐሙስ እና አርብ ከሚካሄደው የአባል ሀገራት የመሪዎች ጉባኤ አስቀድሞ ባለፈው እሁድ አነስተኛ ጉባኤ ተካሂዷል።
ሁላችንም ህገ ወጥ ስደትን ለመቀነስ ድንበሮቻችንን ለመጠበቅ እንደምንፈልግ ተስማምተናል።
አንዳንዱ የመጀመሪያው የስደት ጉዳይ ተጋላጭ ሌሎች ደግሞ በሁለተኛ ደረጃ የችግሩ ተጋሪ መሆን የለባቸውም።
በማይቻልበት ጊዜ ደግሞ ፈቃደኛ የሆኑትን በአንድ ላይ አሰባስበን የጋራ የድጋፍ ማዕቀፍ እንፈልጋለን።
የእሁዱ ጉባኤ ለጀርመን መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል እጅግ አስፈላጊ ነበር።
ሜርክል ችግሩ በአጠቃላይ በአውሮጳ አቀፍ ደረጃ መፈታት አለበት የሚል አቋም ነው ያላቸው።
እንደ ሜርክል አውሮጳ አቀፍ የስደተኞች ፖሊሲ ሲነደፍ ነው የጀርመንም ችግር የሚወገደው።
እናም አባል ሀገራት በሙሉ የሚስማሙበትን የጋራ የስደተኞች መርህ ማምጣት እንዳልተቻለ በእሁዱ ጉባኤ ላይ መግባባት ላይ ተደርሷል።
ከእሁዱ ጉባኤ አስቀድሞ ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ሜርክልና የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮም በርሊን ውስጥ በጉዳዩ ላይ መክረው ነበር።
ማክሮ ሥልጣን እንደያዙ ያቀረቡትን የጋራ የስደተኞች ማዕከል የማቋቋም ሀሳብ በዚሁ ወቅት አንስተው ነበር።
ሃይማኖት እንደምትለው የአውሮጳ ህብረት አባል ሀገራት መንግሥታት ከሀገር ውስጥ የሚደርሱባቸው የተለያዩ ተጽእኖዎች አቋማቸውን እንዲቀያይሩ ምክንያት እየሆኑም ነው።
የአውሮጳ ህብረትን ለሁለት የከፈለ የሚመስለው የህብረቱ የስደተኞች መርህ በወደፊቱ ጉዞው ላይ ተጽእኖ እያሳደረ መሆኑ በግልጽ እየታየ ነው።
ያም ሆኖ በገበያው እምነት የህብረቱን አንድነት ያፈርሳል የሚል ስጋት የለም ።
ቁጥራቸው እና ዜግነታቸው በውል ያልታወቁት ቀሪ ስደተኞችም አስክሬን እንዲሁ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ የ ያህሉ መሰብሰቡ ተዘግቦ ነበር።
የሞሮኮ ባህር ኃይልም እንዲሁ ወደ ስፔን በጀልባ በጉዞ ላይ የነበሩ ስደተኞችን መታደጉን ገልጿል።
እንደ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከሆነ ባለፉት ሰባት ወራት የሚጠጉ ስደተኞችን በሜዲትራንያን ባህር በኩል አድርገው ወደ አውሮፓ ገብተዋል።
ምናልባትም ስደተኞቹ ሌሎች የገጠማቸውን እጣ ፈንታ አገናዝበው ከጉዞ ተቆጥበው ይሆናል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በአሁኗ ሰዓት በአሁኗ ደቂቃ እጃቸው በህገ ወጥ ሰው አዘዋዋሪዎች ስር ያሉ ስደተኞች አሉ።
ታጋቾቹ እንደሚሉት ናስማህ በተባለው ቦታ ከአመት በላይ የታገቱ ሰዎች አሉ።
ቢሳካላቸው ሁሉም ወደ አውሮፓ በባህር ለመሰደድ ነበር አላማቸው ።
በአንድ ሊቢያዊ ታግተናል ከሚሉት መካከል አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያዊት ያለችበትን ሁኔታ እንዲህ ገልጻልናለች።
ከዚህም ሌላ በዚህ ዓመት ብቻ ከ በላይ ሰዎችን ወደ አውሮፓ እና ሌሎች ደህንነት የሚያገኙበት ቦታ ከተለያዩ የስደተኞች ማቆያ ለማስወጣት ችለናል።
የአለም አቀፉ ማህበረሰብ በህጋዊ መንገድ ስደተኞቹ ሊቢያን የሚለቁበትን መንገድ እንዲተባበረን እየጠየቅንም እንገኛለን።
ያም ሆኖ ታሪክ አርጋዝ እንደሚሉት በአሁኑ ሰዓት የሚጠጉ ስደተኞች በሊቢያ የተለያዩ የስደተኛ ማቆያዎች ይገኛሉ።
ይህ ቀደም ሲል ያነጋገርናቸውን በህገወጥ ሰው አዘዋዋሪዎች በየቤቱ ታግተው የሚገኙትን ሰዎች ሳይጨምር ነው።
ታሪክ አርጋዝ እነዚህን ታግተው የሚገኙ ስደተኞች ለመርዳት ስልጣን የለውም ይላሉ።
ይህ የሊቢያ ባለስልጣናት ኃላፊነት ነው ምክንያቱም ሰብዓዊ አገልግሎት የሚሰጥ ድርጅት ነው።
የአንድ ሀገር ፀጥታ እና የህብረተሰቡ ደህንነት ማስጠበቅ የሀገሪቱ ባለስልጣናት ሀላፊነት ነው።
የዶናልድ ያማማቶ ሹመት ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
የአፍሪቃውያንን ችግር በአፍሪቃውያን መፍታት ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
የድርቁ መዘዝ በተለይ በአርብቶ አደሮች ኑሮ ላይ ጫና አሳርፏል።
እንቦጭ የተሰኘው አረም በጣና ሐይቅ ላይ የደቀነው ስጋትም ሌላኛው ርእሳችን ነው።
ጣና ሐይቅ እምቦጭ በተሰኘ መጤ አረም የመወረሩ ዜና በርካቶችን አሳስቧል።
ከኢትዮጵያ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማዎች መካከል አንዱ የኾነው ዘመን ድራማ ባልደረቦች በምሥራቅ ኢትዮጵያ ሶማሌ ለቀረጻ ወጥተው እንግልት እንደደረሰባቸው በዚሁ መድረክ ገልጸዋል።
የድራማው ሠሪዎች የአካባቢው ፖሊስ በስህተት ላደረሰባቸው እንግልት ይቅርታ እንደጠየቃቸው በፌስቡክ ገጻቸዉ ተናግረዋል።
የለም ሌላ ተልዕኮ ነበራቸው ሲል በዛው በፌስቡክ ላይ የጻፈም አለ።
የድራማ ቀረጻው አባላት ስለ ስደተኞች ለመቅረጽ በሄዱበት ሥፍራ አጋጠመን ስላሉት እንግልት ሲገልጹ፥
አባላቱ ለተለየ ተልዕኮ በሥፍራው መከሰታቸውን በመግለጥ የሚከስ ጽሑፍም በዛው በማኅበራዊ መገናኛ አውታር ተነቧል።
የ ዘመን ድራማ ቀረጻ ወብርሃን መሪ ታሪኩ ደሳለኝ በወቅቱ ስለገጠማቸው በፌስቡክ ገጹ በዝርዝር ጽፏል።
የታሪኩ ጽሑፍ ዘለግ ያለ ቢሆንም በአካባቢው ደረሰብን ያሉትን በዝርዝር በዐይነ ኅሊና የሚያሳይ ነው።