label
class label
4 classes
headline
stringlengths
17
80
text
stringlengths
1
16.8k
headline_text
stringlengths
28
16.8k
url
stringlengths
36
49
5sports
በቅጣት ከቼልሲ ጨዋታ ውጪ የሆነው ሮናልዶ ምላሽ ሰጠ
በዲስፕሊን ምክንያት ማንቸስተር ዩናይትድ ከቼልሲ ከሚያደርገው ጨዋታ ውጭ የታደገው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ምላሽ ሰጠ። ሮናልዶ ከትናንት በስቲያ ጨዋታ ሳይጠናቀቅ ስታዲየም ለቅቆ የወጣው “በወቅቱ በነበረው ሁኔታ” ምክንያት ነው ብሏል። የማንችስተር ዩናይትዱ የፊት መስመር ተጫዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ ቡድኑ ረቡዕ ምሽት የነበረው ጨዋታ ሳይጠናቀቅ ስታዲየሙን ለቆ መሄዱ ይታወቃል። ሮናልዶ በወቅቱ የነበረው ሁኔታ ስታዲየም ጥሎ እንዲወጣ እንዳደረገው ኢንስታግራም ገጹ ላይ ባሰፈረው ጽሑፍ አመላክቷል። በተቀያሪ ወንበር ላይ የነበረው ፖርቹጋላዊ ቡድኑ ማንቸስተር ዩናይትድ ቶተነሃምን 2-0 እየመራ 89ኛው ደቂቃ ላይ ከተቀያሪ ወንበር ተነስቶ ሲወጣ ታይቷል። ሮናልዶ ከተቀያሪ ወንበር ተነስቶ በቀጥታ ወደ ልብስ መቀየሪያ ከሄደ በኋላ ከስታዲየሙ መውጣቱ ተገልጿል። "በወከልኳቸው ቡድኖች ውስጥ ላሉ ወጣቶች ራሴን አርአያ ለማድረግ ሁልጊዜ እሞክራለሁ" ሲል ሃሙስ ምሽት በኢንስታግራም ገጹ አስፍሯል። "ይህ ግን ሁል ጊዜም የሚቻል አይደለም። . . . አንዳንድ ጊዜ የወቅቱ ሁኔታ ያሸንፈናል” ሲል አክሏል። “በካርሪንግተን (የዩናይትድ የልምምድ ቦታ) ጠንክሬ መሥራት እንዳለብኝ ይሰማኛል፣ የቡድን አጋሮቼን መደገፍ እና በማንኛውም ጨዋታ ዝግጁ መሆን እንዳለብኝ ይሰማኛል።" "ለግፊቱ መልስ መሰጠት አማራጭ አይደለም፤ በጭራሽ አልነበረምም። ይህ ማንቸስተር ዩናይትድ ነው። እናም ሁሌም አንድ ሆነን መቆም አለብን። በቅርቡ እንደገና አብረን እንሆናለን።" ብሏል የዩናይትድ የፊት መምመር ተጫዋቹ። ማንችስተር ዩናይትድ የ37 ዓመቱ ተጫዋች አሁንም የቡድኑ ወሳኝ አባል እንደሆነ ገልጿል። ተጫዋቹ ከቼልሲው ጨዋታ ውጭ የሆነው በዲሲፕሊን ጉዳይ መሆኑን ጠቁሟል። በስታምፎርድ ብሪጅ የማይሳተፍበት ጨዋታ ትልቅ ሲሆን ዩናይትድ አራተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው ቼልሲ በአንድ ነጥብ ብቻ ዝቅ ብሎ ይገኛል። በስፐርስ ጨዋታ በመጠናቀቂያ ደቂቃዎች ተቀይሮ እንዲገባ ቢጠየቅም ፈቃደኛ አለመሆኑን በርካታ መገናኛ ብዙሃን እየዘገቡ ነው። ዩናይትዶች ከተፈቀደላቸው 5 ቅያሬዎች ውስጥ ሦስቱን ብቻ ቢያደርጉም  በ89ኛው ደቂቃ ሮናልዶ ከተቀያሪ ወንበር ተነስቶ ወደ መልሻ ክፍል አቅንቷል። ቀጥሎም በፍጥነት ከስታዲየም መውጣቱ ታውቋል። አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃግ ሐሙስ ዕለት ጉዳዩን "እንደሚፈቱት” ተናግረው ነበር። ሮናልዶ ማንቸስተር እሑድ ዕለት በሜዳው ከኒውካስትል ጋር 0 - 0 ሲለያይ ተቀይሮ በመውጣቱ የተሰማውን ቅሬታ አሳይቷል። የቀድሞው የእንግሊዝ አጥቂ ጋሪ ሊንክከር የሮናልዶ ባህሪ ዩናይትድ በስፐርስ ላይ ያሳየውን አስደናቂ ብቃት ትኩረት እንዳሳጣ ተናግሯል። "ይህ ተቀባይነት የሌለው ነው።  በጣም ደካማ ነው" ሲልም ሊንከር በቢቢሲ ማች ኦፍ ዘ ዴይ ፕሮግራም ላይ ተናግሯል። የቀድሞው የዌልስ አምበል አሽሊ ዊሊያምስ “ለማንቸስተር ዩናይትድ ታላቅ ምሽት ነበር። ተሰልፎ ባይጫወትም አሁንም ስለ ክርስቲያኖ ሮናልዶ እንናገራለን” ብሏል። የቀድሞ የእንግሊዝ ተከላካይ ሚካህ ሪቻርድስ “ቡድንህ ሲያሸንፍ ከስፖርቱ ታላላቆች አንዱ ይህን ማድረጉ ተስፋ አስቆራጭ ነው” ብሏል። ሪቻርድስ አክሎም የሮናልዶ ባህሪ "አክብሮት የጎደለው ነው" እና በጥር የዝውውር መስኮትም እንዲለቅ ሊፈቀድለት ይገባል ብሏል። ሪቻርድስ ለቢቢሲ ሬድዮ 4 እንደተናገረው “አሰልጣኙ በውድድር ዘመኑ መጀመሪያ ከእሱ ጋር ችግር ውስጥ ገባ። በቅድመ-ውድድር ዘመንም ቀጠለ።  አሁንም ያው ነው። እኔ እንደማስበው ይህ መፈታት ያለበት በአንድ መንገድ ብቻ ነው” ብሏል። "በጥር የዝውውር መስኮት ሊለቁት ይገባል።  የአሰልጣኙን ሥራ እያበላሸ በመሆኑ መለያየቱ  ጥሩ ይመስለኛል።" ብሏል። የቀድሞው የዩናይትድ ግብ ጠባቂ ፒተር ሽሚሼል ሮናልዶ እንደዚህ አይነት ባህሪው “ርዕሰ ዜና" እንደሚሆን ያውቅ ነበር ብሏል። "በእሱ ቅር እንደተሰኘሁ መናገር የምችልበት የመጀመሪያ አጋጣሚ ነው። ስደግፈው ቆይቻለሁ። ያለበትንም ሁኔታ ተረድቻለሁ" ሲል ሽማይክል ለቢቢሲ ሬዲዮ 5 ቀጥታ ስርጭት ወቅት ተናግሯል። "እኛ በሽግግር ላይ ነን። ማንቸስተር ዩናይትድ ከአሌክስ ፈርጉሰን መልቀቅ በኋላ አምስት አሰልጣኞች ቀያይሯል።” "እኛ እንደዚህ አይነት ትኩረት የሚከፋፍሉ ነገሮች አያስፈልጉንም። ይህ ተስፋ አስቆራጭ ነው” ብሏል።
በቅጣት ከቼልሲ ጨዋታ ውጪ የሆነው ሮናልዶ ምላሽ ሰጠ በዲስፕሊን ምክንያት ማንቸስተር ዩናይትድ ከቼልሲ ከሚያደርገው ጨዋታ ውጭ የታደገው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ምላሽ ሰጠ። ሮናልዶ ከትናንት በስቲያ ጨዋታ ሳይጠናቀቅ ስታዲየም ለቅቆ የወጣው “በወቅቱ በነበረው ሁኔታ” ምክንያት ነው ብሏል። የማንችስተር ዩናይትዱ የፊት መስመር ተጫዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ ቡድኑ ረቡዕ ምሽት የነበረው ጨዋታ ሳይጠናቀቅ ስታዲየሙን ለቆ መሄዱ ይታወቃል። ሮናልዶ በወቅቱ የነበረው ሁኔታ ስታዲየም ጥሎ እንዲወጣ እንዳደረገው ኢንስታግራም ገጹ ላይ ባሰፈረው ጽሑፍ አመላክቷል። በተቀያሪ ወንበር ላይ የነበረው ፖርቹጋላዊ ቡድኑ ማንቸስተር ዩናይትድ ቶተነሃምን 2-0 እየመራ 89ኛው ደቂቃ ላይ ከተቀያሪ ወንበር ተነስቶ ሲወጣ ታይቷል። ሮናልዶ ከተቀያሪ ወንበር ተነስቶ በቀጥታ ወደ ልብስ መቀየሪያ ከሄደ በኋላ ከስታዲየሙ መውጣቱ ተገልጿል። "በወከልኳቸው ቡድኖች ውስጥ ላሉ ወጣቶች ራሴን አርአያ ለማድረግ ሁልጊዜ እሞክራለሁ" ሲል ሃሙስ ምሽት በኢንስታግራም ገጹ አስፍሯል። "ይህ ግን ሁል ጊዜም የሚቻል አይደለም። . . . አንዳንድ ጊዜ የወቅቱ ሁኔታ ያሸንፈናል” ሲል አክሏል። “በካርሪንግተን (የዩናይትድ የልምምድ ቦታ) ጠንክሬ መሥራት እንዳለብኝ ይሰማኛል፣ የቡድን አጋሮቼን መደገፍ እና በማንኛውም ጨዋታ ዝግጁ መሆን እንዳለብኝ ይሰማኛል።" "ለግፊቱ መልስ መሰጠት አማራጭ አይደለም፤ በጭራሽ አልነበረምም። ይህ ማንቸስተር ዩናይትድ ነው። እናም ሁሌም አንድ ሆነን መቆም አለብን። በቅርቡ እንደገና አብረን እንሆናለን።" ብሏል የዩናይትድ የፊት መምመር ተጫዋቹ። ማንችስተር ዩናይትድ የ37 ዓመቱ ተጫዋች አሁንም የቡድኑ ወሳኝ አባል እንደሆነ ገልጿል። ተጫዋቹ ከቼልሲው ጨዋታ ውጭ የሆነው በዲሲፕሊን ጉዳይ መሆኑን ጠቁሟል። በስታምፎርድ ብሪጅ የማይሳተፍበት ጨዋታ ትልቅ ሲሆን ዩናይትድ አራተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው ቼልሲ በአንድ ነጥብ ብቻ ዝቅ ብሎ ይገኛል። በስፐርስ ጨዋታ በመጠናቀቂያ ደቂቃዎች ተቀይሮ እንዲገባ ቢጠየቅም ፈቃደኛ አለመሆኑን በርካታ መገናኛ ብዙሃን እየዘገቡ ነው። ዩናይትዶች ከተፈቀደላቸው 5 ቅያሬዎች ውስጥ ሦስቱን ብቻ ቢያደርጉም  በ89ኛው ደቂቃ ሮናልዶ ከተቀያሪ ወንበር ተነስቶ ወደ መልሻ ክፍል አቅንቷል። ቀጥሎም በፍጥነት ከስታዲየም መውጣቱ ታውቋል። አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃግ ሐሙስ ዕለት ጉዳዩን "እንደሚፈቱት” ተናግረው ነበር። ሮናልዶ ማንቸስተር እሑድ ዕለት በሜዳው ከኒውካስትል ጋር 0 - 0 ሲለያይ ተቀይሮ በመውጣቱ የተሰማውን ቅሬታ አሳይቷል። የቀድሞው የእንግሊዝ አጥቂ ጋሪ ሊንክከር የሮናልዶ ባህሪ ዩናይትድ በስፐርስ ላይ ያሳየውን አስደናቂ ብቃት ትኩረት እንዳሳጣ ተናግሯል። "ይህ ተቀባይነት የሌለው ነው።  በጣም ደካማ ነው" ሲልም ሊንከር በቢቢሲ ማች ኦፍ ዘ ዴይ ፕሮግራም ላይ ተናግሯል። የቀድሞው የዌልስ አምበል አሽሊ ዊሊያምስ “ለማንቸስተር ዩናይትድ ታላቅ ምሽት ነበር። ተሰልፎ ባይጫወትም አሁንም ስለ ክርስቲያኖ ሮናልዶ እንናገራለን” ብሏል። የቀድሞ የእንግሊዝ ተከላካይ ሚካህ ሪቻርድስ “ቡድንህ ሲያሸንፍ ከስፖርቱ ታላላቆች አንዱ ይህን ማድረጉ ተስፋ አስቆራጭ ነው” ብሏል። ሪቻርድስ አክሎም የሮናልዶ ባህሪ "አክብሮት የጎደለው ነው" እና በጥር የዝውውር መስኮትም እንዲለቅ ሊፈቀድለት ይገባል ብሏል። ሪቻርድስ ለቢቢሲ ሬድዮ 4 እንደተናገረው “አሰልጣኙ በውድድር ዘመኑ መጀመሪያ ከእሱ ጋር ችግር ውስጥ ገባ። በቅድመ-ውድድር ዘመንም ቀጠለ።  አሁንም ያው ነው። እኔ እንደማስበው ይህ መፈታት ያለበት በአንድ መንገድ ብቻ ነው” ብሏል። "በጥር የዝውውር መስኮት ሊለቁት ይገባል።  የአሰልጣኙን ሥራ እያበላሸ በመሆኑ መለያየቱ  ጥሩ ይመስለኛል።" ብሏል። የቀድሞው የዩናይትድ ግብ ጠባቂ ፒተር ሽሚሼል ሮናልዶ እንደዚህ አይነት ባህሪው “ርዕሰ ዜና" እንደሚሆን ያውቅ ነበር ብሏል። "በእሱ ቅር እንደተሰኘሁ መናገር የምችልበት የመጀመሪያ አጋጣሚ ነው። ስደግፈው ቆይቻለሁ። ያለበትንም ሁኔታ ተረድቻለሁ" ሲል ሽማይክል ለቢቢሲ ሬዲዮ 5 ቀጥታ ስርጭት ወቅት ተናግሯል። "እኛ በሽግግር ላይ ነን። ማንቸስተር ዩናይትድ ከአሌክስ ፈርጉሰን መልቀቅ በኋላ አምስት አሰልጣኞች ቀያይሯል።” "እኛ እንደዚህ አይነት ትኩረት የሚከፋፍሉ ነገሮች አያስፈልጉንም። ይህ ተስፋ አስቆራጭ ነው” ብሏል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cgeg92p8epdo
2health
ኢትዮጵያ የምታከናውነው ድንበር ተሻጋሪ የእንስሳት ክትባት ምንድነው?
በኢትዮጵያና በኬንያ ድንበር አካባቢዎች ድንበር ተሻጋሪ ተዛማች የእንስሳት በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ሁለተኛው ዙር የእንስሳት ክትባት ዘመቻ እየተካሄደ ይገኛል። የክትባት ዘመቻው በኢትዮጵያ በኩል በቦረና ዞን፣ ሞያሌ ወረዳ የተለያዩ እንስሳትን በመከተብ የተጀመረ ሲሆን በመቀጠል ደግሞ በኬንያ በኩል ይካሄዳል። ይህ ከአጎራባች አገራት ጋር በመቀናጀት የሚካሄደው ድንበር ተሻጋሪ የክትባት ዘመቻ በደቡብ ኦሞ ዞን፣ በሀመር ወረዳም በይፋ ተጀምሯል። አርብቶ አደሮች ግጦሽና ውሃ ፍለጋ ከቦታ ወደ ቦታ መንቀሳቀሳቸውን ተከትሎ አጎራባች አገራት ተቀናጅተው ድንበር ተሻጋሪ በሽታዎችን በጋራ መከላከልና መቆጣጠር ካልቻሉ በድንገት የሚከሰቱ በሽታዎች የእንስሳትን ምርታማነት ከመቀነሰ አልፎ ቁጥራቸውንም በጊዜ ብዛት ይቀንሰዋል። የኢትዮጵያ ግብርና ሚኒስቴር እንደሚለው የእንስሳት ሀብት ልማት ውጤታማ ሊሆን የሚችለው ዝሪያን በማሻሻል፣ በቂ መኖን በማቅረብ እና ገበያን በማመቻቸት ብቻ ሳይሆን ከጤናማ እንስሳት ጤናማ ምርት ማቅረብ ሲቻል ነው። በአርብቶ አደሩ አካባቢ የእንስሳት በሽታዎችን በመካለከል እና በመቆጣጠር ጥራት ያለውን የእንስሳት ምርት በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ በሆነ መልኩ ማቅረብ ዋነኛ አላማው ነው። የድንበር ዘለል የእንስሳት በሽታ ክትባትን በጋራ የመተግበር ሥራ በተለይ በአራት ዋና ዋና በሽታዎች ላይ ያተኮረ እንደሆነ በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ዘርፍ ሚኒትር ዴኤታ አማካሪ የሆኑት ዮሐንስ ግርማ (ዶ/ር) ለቢቢሲ ገልጸዋል። "ከኬንያ ጋር በተለይ አራት ድንበር ተሻጋሪ በሽታዎችን ለመቆጣጠር ስምምነት ላይ ደርሰናል። የመጀመሪያው የበጎችና የፍየሎች ደስታ መሰል በሽታ ክትባት ነው። ሁለተኛው ደግሞ የበጎችና የፍየሎች የሳምባ በሽታ ክትባት፣ የከብቶች የሳምባ በሽታ እንዲሁም በግመሎች ላይ የሚከሰቱ ዋና ዋና በሽታዎችን ነው አንድ ላይ የምንከትበው" ይላሉ። በአውሮፓውያኑ 2019 የተጀመረው ይህ ድንበር ተሻጋሪ በሽታዎችን በጋራ የመከላከል ሥራ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦ የነበረ ሲሆን፤ በያዝነው ዓመት ደግሞ በአዲስ መልኩ ነው እየተሠራ የሚገኘው። ምንም እንኳን የግብርና ሚኒስቴር በተለይ ከኬንያ መንግሥት ጋር ባደረገው ስምምነት መሠረት ከሁለት ዓመት በፊት የድንበር ተሻጋሪ በሽታዎችን ክትባት መስጠት ቢጀምርም፤ ባለፈው ዓመት ግን ከወረርሽኙ ጋር ተያይዞ በተጣሉ የእንቅስቃሴ ገደቦች ምክንያት ሥራውን ማስቀጠል አልተቻለም። ነገር ግን በያዝነው ዓመት ሚኒስቴሩ በኢትዮጵያ በኩል በቦረና ዞን፣ ሞያሌ ወረዳ ክትባቱን ያካሄደ ሲሆን በኬንያ በኩል ደግሞ በመርሳቢት ካውንቲ ተካሂዷል። በመቀጠል በደቡብ ኦሞ ዞን፣ በሐመር ወረዳ እንዲሁም በሰሜን ኦሞ ዞን የእንስሳት ክትባቱ ተካሂዷል። በኢትዮጵያና በኬንያ መካከል ካለው የንግድ ትስስር አንጻር እና በሁለቱም አገራት የሚገኙ አርብቶ አደሮች ከብቶቻቸውን ይዘው መንቀሳቀሳቸው እንስሳቱን ለድንበር ተሻጋሪ በሽታዎች ተጋላጭ ያደርጋቸዋል። ዮሐንስ (ዶ/ር) እንደሚሉት፤ "ምናልባት እኛ በራሳችን በኩል ያሉትን እንስሳት ብቻ ከትበን ብንተውና በሌላኛው በኩል በተመሳሳይ እንስሳቱን ባይከትቡ የበሽታዎቹን ስርጭት መቆጣጠር አንችልም።" ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ እንስሳቱ ከአንዱ አገር ወደሌላኛው መንቀሳቀሳቸው ነው። ይህ የክትባት ስምምነት የተደረገው ከኬንያ ጋር ብቻ ሳይሆን ከጅቡቲ፣ ከሶማሊያ እና ከሱዳን ጋር ነው። ከዚህ በፊት በተደረጉ ድንበር ተሻጋሪ ተዛማች የእንስሳት ክትባት ዘመቻዎች በርካታ እንስሳት መከተባቸውን የገለጹት ዶ/ር ዮሐንስ፤ በዚህኛውም ዙር የተሻለ ውጤት እንደሚጠብቁ ገልጸዋል። "በዋነኛነት የምናተኩረው እነዚህ በሽታዎች በድንገት እንዳይከሰቱ ማድረግ ላይ ነው። አብዛኞቹ በሽታዎች በወረርሽኝ መልክም ሆነ በሌላ መልኩ የሚከሰቱባቸው ወቅቶች አሉ። እነሱን ተንተርሰን ከመከሰታቸው ቀደም ብለን ዘመቻዎች እናደርጋለን። አሁን ካለው የድርቅ ክስተት ጋር ተያይዞ እንስሳት ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሱ ቢሆንም የበሽታዎች ክስተት ግን በብዛት እየታየ አይደለም" ይላሉ። በአጠቃላይ በዚህ ዓመት ኢትዮጵያን በሚያዋስኑና ስምምነት ካደረጉ አገራት ጋር አጎራባች በሆኑ አካባቢዎቸ እስከ 5.4 ሚሊየን እንስሳትን ለመከተብ ዕቅድ መያዛቸውን አማካሪው ይናገራሉ። በያዝነው ዓመት የሴንትራል ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ በሠራው ጥናት መሠረት ኢትዮጵያ ወደ 61 ሚሊየን የሚጠጉ የቀንድ ከብቶች አሏት። ከ40 ሚሊየን በላይ ፍየሎችና ከ50 ሚሊየን በላይ በጎች እንዲሁም 8 ሚሊየን የሚደርሱ ግመሎችም አሏት። አርብቶ አደሩ የሚያረባቸውና የሚጠቀማቸው አብዛኛዎቹ የእንስሳት ዝርያዎች በተፈጥሯቸው በሽታን የመቋቋምና አስቸጋሪ የአየር ፀባይን መቋቋም የሚችሉ ናቸው። የግብርና ሚኒስቴር እንደሚለው እነዚህ ዝርያዎች በሽታና አስቸጋሪ ሁኔታዎችን መቋቋም ቢችሉም ምርትና ምርታማነት ላይ ግን ችግር አለባቸው። ይህንኑ ከግምት ውስጥ በማስገባትም ሚኒስቴሩ ከክትባቶች በተጨማሪ በአርብቶ አደር አካባቢዎች የሚገኙት እንስሳት ላይ ማሻሻያ በማድረግ የተሻለ ምርት መስጠት እንዲችሉ እየሠራ መሆኑን ዮሐንስ (ዶ/ር) ይናገራሉ። "በቦረና ዞን የሚገኘው የዝርያ ማሻሻያ ማዕከል ውስጥ የቦረና ዝርያዎችን በማባዛት፣ በማሻሻልና በመጠበቅ ሥራዎችን ይሠራል። ቁጥራቸው ሲበዛ ደግሞ ለአካባቢው ማኅበረሰብ እንዲከፋፈሉ ይደረጋል። ወደሌሎች የአገሪቱ አርብቶ አደር አካባቢዎችም እንዲደርሱ ይደረጋል" ብለዋል። በድንበር አካባቢዎች ላይ ከሚደረገው የክትባት ዘመቻ በተጨማሪ በመላው አገሪቱ የሚገኙ እንስሳት ላይ ክትባቱ ይቀጥላል። ነገር ግን በድንበር አካባቢዎች ላይ የሚገኙ እንስሳት ቁጥራቸው ላቅ ያለ መሆኑ እና ከቦታ ቦታ ስለሚንቀሳቀሱ ቅድሚያ ተሰጥቶ ይከተባሉ። እነዚህ በሽታዎች ቀስ በቀስ ሲጠፉና የእንስሳቱን ደኅንነት መጠበቅ ከተቻለ በዓለም አቀፍ ደረጃ የገበያ ተወዳዳሪነትን ለመጨመር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል። "እነዚህ በሽታዎች በኢትዮጵያ አሉ ተብሎ ከታሰበ ምርታችንን ማንም አይገዛም፤ አልያም ቁጥሩ ዝቅተኛ ይሆናል። በተለይ በርካታ ያደጉ አገራት እነዚህን በሽታዎች ማጥፋት በመቻላቸው በከፍተኛ ሁኔታ ተጠቃሚ ሆነዋል። እኛም እነዚህም በሽታዎች ማጥፋት ስላልቻልን ወደ አውሮፓ እና እስያ ገበያዎች መድረስ አልቻለንም" ሲሉ ያስረዳሉ። ዓለም አቀፍ የእንስሳት ጤና ድርጅት የሚባለውና 182 አባል አገራት ያሉት ተቋም በየጊዜው የአገራትን የእንስሳት ጤና የሚከታተልና የአገራቱን ደረጃ የሚያወጣ ነው። ኢትዮጵያም የዚህ ድርጅት አባል እንደመሆኗ የእንስሳቶቿን ጤንነት ከጠበቀች የምታገኘው ተቀባይነት ከፍተኛ እንደሆነም ይናገራሉ። ይህ ክትባት የዓለም አቀፍ ገበያውን ከመድረስ ባለፈም አርብቶ አደሮች በበቂ ሁኔታ ከእንስሳቶቻቸው ተገቢውን ምርት እንዲያገኙ እና የምግብ ዋስትናቸውን እንዲያረጋግጡም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።
ኢትዮጵያ የምታከናውነው ድንበር ተሻጋሪ የእንስሳት ክትባት ምንድነው? በኢትዮጵያና በኬንያ ድንበር አካባቢዎች ድንበር ተሻጋሪ ተዛማች የእንስሳት በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ሁለተኛው ዙር የእንስሳት ክትባት ዘመቻ እየተካሄደ ይገኛል። የክትባት ዘመቻው በኢትዮጵያ በኩል በቦረና ዞን፣ ሞያሌ ወረዳ የተለያዩ እንስሳትን በመከተብ የተጀመረ ሲሆን በመቀጠል ደግሞ በኬንያ በኩል ይካሄዳል። ይህ ከአጎራባች አገራት ጋር በመቀናጀት የሚካሄደው ድንበር ተሻጋሪ የክትባት ዘመቻ በደቡብ ኦሞ ዞን፣ በሀመር ወረዳም በይፋ ተጀምሯል። አርብቶ አደሮች ግጦሽና ውሃ ፍለጋ ከቦታ ወደ ቦታ መንቀሳቀሳቸውን ተከትሎ አጎራባች አገራት ተቀናጅተው ድንበር ተሻጋሪ በሽታዎችን በጋራ መከላከልና መቆጣጠር ካልቻሉ በድንገት የሚከሰቱ በሽታዎች የእንስሳትን ምርታማነት ከመቀነሰ አልፎ ቁጥራቸውንም በጊዜ ብዛት ይቀንሰዋል። የኢትዮጵያ ግብርና ሚኒስቴር እንደሚለው የእንስሳት ሀብት ልማት ውጤታማ ሊሆን የሚችለው ዝሪያን በማሻሻል፣ በቂ መኖን በማቅረብ እና ገበያን በማመቻቸት ብቻ ሳይሆን ከጤናማ እንስሳት ጤናማ ምርት ማቅረብ ሲቻል ነው። በአርብቶ አደሩ አካባቢ የእንስሳት በሽታዎችን በመካለከል እና በመቆጣጠር ጥራት ያለውን የእንስሳት ምርት በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ በሆነ መልኩ ማቅረብ ዋነኛ አላማው ነው። የድንበር ዘለል የእንስሳት በሽታ ክትባትን በጋራ የመተግበር ሥራ በተለይ በአራት ዋና ዋና በሽታዎች ላይ ያተኮረ እንደሆነ በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ዘርፍ ሚኒትር ዴኤታ አማካሪ የሆኑት ዮሐንስ ግርማ (ዶ/ር) ለቢቢሲ ገልጸዋል። "ከኬንያ ጋር በተለይ አራት ድንበር ተሻጋሪ በሽታዎችን ለመቆጣጠር ስምምነት ላይ ደርሰናል። የመጀመሪያው የበጎችና የፍየሎች ደስታ መሰል በሽታ ክትባት ነው። ሁለተኛው ደግሞ የበጎችና የፍየሎች የሳምባ በሽታ ክትባት፣ የከብቶች የሳምባ በሽታ እንዲሁም በግመሎች ላይ የሚከሰቱ ዋና ዋና በሽታዎችን ነው አንድ ላይ የምንከትበው" ይላሉ። በአውሮፓውያኑ 2019 የተጀመረው ይህ ድንበር ተሻጋሪ በሽታዎችን በጋራ የመከላከል ሥራ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦ የነበረ ሲሆን፤ በያዝነው ዓመት ደግሞ በአዲስ መልኩ ነው እየተሠራ የሚገኘው። ምንም እንኳን የግብርና ሚኒስቴር በተለይ ከኬንያ መንግሥት ጋር ባደረገው ስምምነት መሠረት ከሁለት ዓመት በፊት የድንበር ተሻጋሪ በሽታዎችን ክትባት መስጠት ቢጀምርም፤ ባለፈው ዓመት ግን ከወረርሽኙ ጋር ተያይዞ በተጣሉ የእንቅስቃሴ ገደቦች ምክንያት ሥራውን ማስቀጠል አልተቻለም። ነገር ግን በያዝነው ዓመት ሚኒስቴሩ በኢትዮጵያ በኩል በቦረና ዞን፣ ሞያሌ ወረዳ ክትባቱን ያካሄደ ሲሆን በኬንያ በኩል ደግሞ በመርሳቢት ካውንቲ ተካሂዷል። በመቀጠል በደቡብ ኦሞ ዞን፣ በሐመር ወረዳ እንዲሁም በሰሜን ኦሞ ዞን የእንስሳት ክትባቱ ተካሂዷል። በኢትዮጵያና በኬንያ መካከል ካለው የንግድ ትስስር አንጻር እና በሁለቱም አገራት የሚገኙ አርብቶ አደሮች ከብቶቻቸውን ይዘው መንቀሳቀሳቸው እንስሳቱን ለድንበር ተሻጋሪ በሽታዎች ተጋላጭ ያደርጋቸዋል። ዮሐንስ (ዶ/ር) እንደሚሉት፤ "ምናልባት እኛ በራሳችን በኩል ያሉትን እንስሳት ብቻ ከትበን ብንተውና በሌላኛው በኩል በተመሳሳይ እንስሳቱን ባይከትቡ የበሽታዎቹን ስርጭት መቆጣጠር አንችልም።" ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ እንስሳቱ ከአንዱ አገር ወደሌላኛው መንቀሳቀሳቸው ነው። ይህ የክትባት ስምምነት የተደረገው ከኬንያ ጋር ብቻ ሳይሆን ከጅቡቲ፣ ከሶማሊያ እና ከሱዳን ጋር ነው። ከዚህ በፊት በተደረጉ ድንበር ተሻጋሪ ተዛማች የእንስሳት ክትባት ዘመቻዎች በርካታ እንስሳት መከተባቸውን የገለጹት ዶ/ር ዮሐንስ፤ በዚህኛውም ዙር የተሻለ ውጤት እንደሚጠብቁ ገልጸዋል። "በዋነኛነት የምናተኩረው እነዚህ በሽታዎች በድንገት እንዳይከሰቱ ማድረግ ላይ ነው። አብዛኞቹ በሽታዎች በወረርሽኝ መልክም ሆነ በሌላ መልኩ የሚከሰቱባቸው ወቅቶች አሉ። እነሱን ተንተርሰን ከመከሰታቸው ቀደም ብለን ዘመቻዎች እናደርጋለን። አሁን ካለው የድርቅ ክስተት ጋር ተያይዞ እንስሳት ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሱ ቢሆንም የበሽታዎች ክስተት ግን በብዛት እየታየ አይደለም" ይላሉ። በአጠቃላይ በዚህ ዓመት ኢትዮጵያን በሚያዋስኑና ስምምነት ካደረጉ አገራት ጋር አጎራባች በሆኑ አካባቢዎቸ እስከ 5.4 ሚሊየን እንስሳትን ለመከተብ ዕቅድ መያዛቸውን አማካሪው ይናገራሉ። በያዝነው ዓመት የሴንትራል ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ በሠራው ጥናት መሠረት ኢትዮጵያ ወደ 61 ሚሊየን የሚጠጉ የቀንድ ከብቶች አሏት። ከ40 ሚሊየን በላይ ፍየሎችና ከ50 ሚሊየን በላይ በጎች እንዲሁም 8 ሚሊየን የሚደርሱ ግመሎችም አሏት። አርብቶ አደሩ የሚያረባቸውና የሚጠቀማቸው አብዛኛዎቹ የእንስሳት ዝርያዎች በተፈጥሯቸው በሽታን የመቋቋምና አስቸጋሪ የአየር ፀባይን መቋቋም የሚችሉ ናቸው። የግብርና ሚኒስቴር እንደሚለው እነዚህ ዝርያዎች በሽታና አስቸጋሪ ሁኔታዎችን መቋቋም ቢችሉም ምርትና ምርታማነት ላይ ግን ችግር አለባቸው። ይህንኑ ከግምት ውስጥ በማስገባትም ሚኒስቴሩ ከክትባቶች በተጨማሪ በአርብቶ አደር አካባቢዎች የሚገኙት እንስሳት ላይ ማሻሻያ በማድረግ የተሻለ ምርት መስጠት እንዲችሉ እየሠራ መሆኑን ዮሐንስ (ዶ/ር) ይናገራሉ። "በቦረና ዞን የሚገኘው የዝርያ ማሻሻያ ማዕከል ውስጥ የቦረና ዝርያዎችን በማባዛት፣ በማሻሻልና በመጠበቅ ሥራዎችን ይሠራል። ቁጥራቸው ሲበዛ ደግሞ ለአካባቢው ማኅበረሰብ እንዲከፋፈሉ ይደረጋል። ወደሌሎች የአገሪቱ አርብቶ አደር አካባቢዎችም እንዲደርሱ ይደረጋል" ብለዋል። በድንበር አካባቢዎች ላይ ከሚደረገው የክትባት ዘመቻ በተጨማሪ በመላው አገሪቱ የሚገኙ እንስሳት ላይ ክትባቱ ይቀጥላል። ነገር ግን በድንበር አካባቢዎች ላይ የሚገኙ እንስሳት ቁጥራቸው ላቅ ያለ መሆኑ እና ከቦታ ቦታ ስለሚንቀሳቀሱ ቅድሚያ ተሰጥቶ ይከተባሉ። እነዚህ በሽታዎች ቀስ በቀስ ሲጠፉና የእንስሳቱን ደኅንነት መጠበቅ ከተቻለ በዓለም አቀፍ ደረጃ የገበያ ተወዳዳሪነትን ለመጨመር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል። "እነዚህ በሽታዎች በኢትዮጵያ አሉ ተብሎ ከታሰበ ምርታችንን ማንም አይገዛም፤ አልያም ቁጥሩ ዝቅተኛ ይሆናል። በተለይ በርካታ ያደጉ አገራት እነዚህን በሽታዎች ማጥፋት በመቻላቸው በከፍተኛ ሁኔታ ተጠቃሚ ሆነዋል። እኛም እነዚህም በሽታዎች ማጥፋት ስላልቻልን ወደ አውሮፓ እና እስያ ገበያዎች መድረስ አልቻለንም" ሲሉ ያስረዳሉ። ዓለም አቀፍ የእንስሳት ጤና ድርጅት የሚባለውና 182 አባል አገራት ያሉት ተቋም በየጊዜው የአገራትን የእንስሳት ጤና የሚከታተልና የአገራቱን ደረጃ የሚያወጣ ነው። ኢትዮጵያም የዚህ ድርጅት አባል እንደመሆኗ የእንስሳቶቿን ጤንነት ከጠበቀች የምታገኘው ተቀባይነት ከፍተኛ እንደሆነም ይናገራሉ። ይህ ክትባት የዓለም አቀፍ ገበያውን ከመድረስ ባለፈም አርብቶ አደሮች በበቂ ሁኔታ ከእንስሳቶቻቸው ተገቢውን ምርት እንዲያገኙ እና የምግብ ዋስትናቸውን እንዲያረጋግጡም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።
https://www.bbc.com/amharic/59252309
0business
አውሮፓ በሩሲያ ላይ በጣለችው ማዕቀብ ከ400 ቢሊየን ዶላር በላይ ታጣለች፡ ፑቲን
የአውሮፓ ሕብረት በሩሲያ ላይ ማዕቀብ በመጣሉ ምክንያት በመቶ ቢሊዮኖች የሚገመት ኪሳራ ሊያጋጥመው እንደሚችል የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ተናገሩ። ሩሲያ ሴንት ፒተርስበርግ ውስጥ በተዘጋጀ ዓመታዊው ዓለም አቀፍ የምጣኔ ሀብት መድረክ ላይ ፑቲን እንዳሉት አገራቸው ላይ በተጣለው ማዕቀብ ሳቢያ የአውሮፓ ሕብረት ከ400 ቢሊየን ዶላር በላይ ምጣኔ ሀብታዊ ኪሳራ ሊገጥመው ይችላል ብለዋል። በ27ቱ የአውሮፓ ሕብረት አባል አገራት ውስጥ የዋጋ ግሽበት እየጨመረ መሆኑንና ቡድኑ በሩሲያ ላይ ማዕቀብ በሚጥልበት ጊዜ የአገራቱን ዜጎች ትክክለኛውን ጥቅም ወደጎን ገፍቷል ሲሉ ፑቲን ወቅሰዋል። ጨምረውም የምጣኔ ሀብት ጫናው ዕቀባው ከተጣለባት ሩሲያ ይልቅ፣ ዕቀባውን በጣሉት አገራት ላይ “የበለጠ ጉዳትን ያስከትላል” ሲሉም ተናግረዋል። ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው "በሩሲያ ላይ እየተካሄደ ያለው ምጣኔ ሀብታዊ ዕቀባ ከመነሻው አንስቶ ምንም አይነት የመሳካት እድል የለውም” ብለዋል። ምዕራባውያን ከዩክሬን ወረራ በኋላ በሩሲያ ላይ የጣሏቸው ማዕቀቦች “እብደትና የሚያስከትሉትን ጉዳት ያላገናዘቡ ናቸው” ሲሉም ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ተችተዋል። ምዕራባውያን መንግሥታት የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ አንስቶ ሩሲያ ላይ ጫናን በመፍጠር እና የራሳቸውን የምጣኔ ሀብት ጥቅም በማስጠበቅ መካከል ሚዛን ለመጠበቅ ሲጥሩ ቆይተዋል። ነገር ግን አንድ የሩሲያ ባለሥልጣን በአገራቸው ላይ የተጣሉት ማዕቀቦች በምጣኔ ሀብቷ ላይ ከባድ ጉዳት እያስከተለ መሆኑን አመልክተዋል። የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ ገዢ ኤልቪራ ናቡሊና ሐሙስ ዕለት እንደተናገሩት “የአገሪቱ 15 በመቶ አገራዊ ምርት” በማዕቀቦቹ ምክንያት ስጋት ላይ ወድቋል። የጦርነቱን መቀስቀስ ተከትሎ በርካታ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች በሩሲያ ያሏቸውን ተቋማት እየለቀቁ ቢወጡም ፑቲን ግን በራቸው ለመዋዕለ ነዋይ አፍሳሾች አሁንም ክፍት እንደሆነ ጥሪ አቅርበዋል። ፑቲን በተጨማሪም ዩክሬን ውስጥ በቀጠለው ጦርነት ምክንያት የተፈጠረውን ዓለም አቀፋዊ የምግብ አቅርቦት ቀውስን በተመለከተም፣ ሩሲያ ለዓለም ገበያ የሚቀርበውን የእህል ምርትና ማዳበሪያ በከፍተኛ ደረጃ ልትጨምር እንደምትችል ተናግረዋል። በዚህም አገራቸው የእህል ምርት አቅርቦቷን በ50 ሚሊዮን ቶን ከፍ ለማድግ አቅሙ አላት ብለዋል። ዩክሬን እና ሩሲያ ለዓለም ከፍተኛውን የእህል ምርት የሚያቀርቡ አገራት ሲሆኑ ከወራት በፊት በተቀሰቀሰው ጦርነት ምክንያት የጥቁር ባሕር ወደቦቿ በመዘጋታቸው ዩክሬን ምርቷን ለዓለም ገበያ ማቅረብ አልቻለችም። አሁንም በተለያዩ የዩክሬን አካባቢዎች ከፍተኛ ውጊያዎች እየተካሄዱ ሲሆን ምዕራባውያንም በሩሲያ ላይ ከጣሏቸው ምጣኔ ሀብታዊ ዕቀባዎች በተጨማሪ፣ ዩክሬን እራሷን እንድትከላከልና በጦርነቱ አሸናፊ እንድትሆን ቢሊዮን ዶላሮችን የሚያወጡ ዘመናዊ የጦር ማሳሪያ ድጋፍ እያደረጉላት ይገኛሉ።
አውሮፓ በሩሲያ ላይ በጣለችው ማዕቀብ ከ400 ቢሊየን ዶላር በላይ ታጣለች፡ ፑቲን የአውሮፓ ሕብረት በሩሲያ ላይ ማዕቀብ በመጣሉ ምክንያት በመቶ ቢሊዮኖች የሚገመት ኪሳራ ሊያጋጥመው እንደሚችል የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ተናገሩ። ሩሲያ ሴንት ፒተርስበርግ ውስጥ በተዘጋጀ ዓመታዊው ዓለም አቀፍ የምጣኔ ሀብት መድረክ ላይ ፑቲን እንዳሉት አገራቸው ላይ በተጣለው ማዕቀብ ሳቢያ የአውሮፓ ሕብረት ከ400 ቢሊየን ዶላር በላይ ምጣኔ ሀብታዊ ኪሳራ ሊገጥመው ይችላል ብለዋል። በ27ቱ የአውሮፓ ሕብረት አባል አገራት ውስጥ የዋጋ ግሽበት እየጨመረ መሆኑንና ቡድኑ በሩሲያ ላይ ማዕቀብ በሚጥልበት ጊዜ የአገራቱን ዜጎች ትክክለኛውን ጥቅም ወደጎን ገፍቷል ሲሉ ፑቲን ወቅሰዋል። ጨምረውም የምጣኔ ሀብት ጫናው ዕቀባው ከተጣለባት ሩሲያ ይልቅ፣ ዕቀባውን በጣሉት አገራት ላይ “የበለጠ ጉዳትን ያስከትላል” ሲሉም ተናግረዋል። ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው "በሩሲያ ላይ እየተካሄደ ያለው ምጣኔ ሀብታዊ ዕቀባ ከመነሻው አንስቶ ምንም አይነት የመሳካት እድል የለውም” ብለዋል። ምዕራባውያን ከዩክሬን ወረራ በኋላ በሩሲያ ላይ የጣሏቸው ማዕቀቦች “እብደትና የሚያስከትሉትን ጉዳት ያላገናዘቡ ናቸው” ሲሉም ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ተችተዋል። ምዕራባውያን መንግሥታት የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ አንስቶ ሩሲያ ላይ ጫናን በመፍጠር እና የራሳቸውን የምጣኔ ሀብት ጥቅም በማስጠበቅ መካከል ሚዛን ለመጠበቅ ሲጥሩ ቆይተዋል። ነገር ግን አንድ የሩሲያ ባለሥልጣን በአገራቸው ላይ የተጣሉት ማዕቀቦች በምጣኔ ሀብቷ ላይ ከባድ ጉዳት እያስከተለ መሆኑን አመልክተዋል። የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ ገዢ ኤልቪራ ናቡሊና ሐሙስ ዕለት እንደተናገሩት “የአገሪቱ 15 በመቶ አገራዊ ምርት” በማዕቀቦቹ ምክንያት ስጋት ላይ ወድቋል። የጦርነቱን መቀስቀስ ተከትሎ በርካታ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች በሩሲያ ያሏቸውን ተቋማት እየለቀቁ ቢወጡም ፑቲን ግን በራቸው ለመዋዕለ ነዋይ አፍሳሾች አሁንም ክፍት እንደሆነ ጥሪ አቅርበዋል። ፑቲን በተጨማሪም ዩክሬን ውስጥ በቀጠለው ጦርነት ምክንያት የተፈጠረውን ዓለም አቀፋዊ የምግብ አቅርቦት ቀውስን በተመለከተም፣ ሩሲያ ለዓለም ገበያ የሚቀርበውን የእህል ምርትና ማዳበሪያ በከፍተኛ ደረጃ ልትጨምር እንደምትችል ተናግረዋል። በዚህም አገራቸው የእህል ምርት አቅርቦቷን በ50 ሚሊዮን ቶን ከፍ ለማድግ አቅሙ አላት ብለዋል። ዩክሬን እና ሩሲያ ለዓለም ከፍተኛውን የእህል ምርት የሚያቀርቡ አገራት ሲሆኑ ከወራት በፊት በተቀሰቀሰው ጦርነት ምክንያት የጥቁር ባሕር ወደቦቿ በመዘጋታቸው ዩክሬን ምርቷን ለዓለም ገበያ ማቅረብ አልቻለችም። አሁንም በተለያዩ የዩክሬን አካባቢዎች ከፍተኛ ውጊያዎች እየተካሄዱ ሲሆን ምዕራባውያንም በሩሲያ ላይ ከጣሏቸው ምጣኔ ሀብታዊ ዕቀባዎች በተጨማሪ፣ ዩክሬን እራሷን እንድትከላከልና በጦርነቱ አሸናፊ እንድትሆን ቢሊዮን ዶላሮችን የሚያወጡ ዘመናዊ የጦር ማሳሪያ ድጋፍ እያደረጉላት ይገኛሉ።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cm5vy3ejd3no
3politics
ፑቲን ቅንጡ ቤተ መንግሥት ማስገንባታቸውን 'የሚያጋልጠው' ቪድዮ
የሩስያው ፕሬዘዳንት ቭላድሚር ፑቲን ቅንጡ ቤተ መንግሥት ለመገንባት በሕገ ወጥ መንገድ ገንዘብ ማፍሰሳቸውን የሚያሳየው የምርመራ ቪድዮ በተለቀቀ በጥቂት ቀናት ውስጥ ከ20 ሚሊዮን በላይ ተመልካች አግኝቷል። ቪድዮው የተለቀቀው በሩስያዊው ተቃዋሚ አሌክሴ ናቫልኒ ቡድን ነው። ናቫልኒ ሩስያ፣ ሞስኮ ሲደርስ በቁጥጥር ስር የዋለው ከቀናት በፊት ነበር። የምርመራ ቪድዮው እንደሚያሳየው፤ ቤተ መንግሥቱ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር ወጥቶበታል። "በታሪክ ትልቁ ጉቦ ነው" በማለት በቪድዮው ተገልጿል። ክሬምሊን ቤተ መንግሥቱ የፑቲን አይደለም ብሏል። በደቡብ ሩስያ ብላክ ሲ አካባቢ የሚገኘው ቤተ መንግሥት የሞኖኮ 39 እጥፍ ስፋት እንዳለው ተገልጿል። ቪድዮው የተለቀቀው ናቫልኒ ከጀርመን ወደ ሩስያ ከሄደ ከሁለት ቀን በኋላ ነበር። ናቫልኒ በቅድመ ምርመራ ለ30 ቀናት የታሰረ ሲሆን፤ ገንዘብ በመበዝበር የቀረበበትን ክስ በመጣሱ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል። እሱ ግን እስሩ ፖለቲካዊ ነው ይላል። የ44 ዓመቱ ተቃዋሚ ባለፈው ነሐሴ ተመርዞ ለሞት ተቃርቦ ነበር። ለመመረዙ ተጠያቂው ፑቲን እንደሆኑ ቢናገርም፤ የሩስያ መንግሥት እጁ እንደሌለበት አስታውቋል። ቪድዮው ምን ያሳያል? የምርመራ ቪድዮው እንደሚያሳው ቤተ መንግሥቱ የተሠራው በፑቲን የቅርብ ሰዎች ሕገ ወጥ የገንዘብ ድጋፍ ነው። የነዳጅ ምርት ባለሥልጣኖች እና ቢሊየነሮች ከነዚህ መካከል ናቸውም ተብሏል። ናቫንሊ በቪድዮው "በዚህ ገንዘብ ለአለቃቸው ቤተ መንግሥት ሠርተዋል" ብሏል። የሩስያ ብሔራዊ የምርመራ ተቋም ቤተ መንግሥቱ ዙርያ ያለው 27 ስኩዌር ማይል መሬት ባለቤት እንደሆነም በቪድዮው ተጠቁሟል። ሕንጻው ውስጥ ካዚኖ (መቆመሪያ)፣ የበረዶ ሆኪ መጫወቻና ወይን ማቀነባበሪያ ይገኛል ተብሏል። "ለመጣስ የሚከብድ አጥር አለው። ራሱን የቻለ ወደብና ቤተ ክርስቲያን አለው። በረራ ማድረግ ክልክል ነው። የድንበር ላይ ጥበቃ ኃይልም አለው። ሩስያ ውስጥ ያለ ራሱን የቻለ አገር ነው" ሲል ናቫንሊ ተናግሯል። ናቫንሊ በጸረ ሙስና ንቅናቄው ይታወቃል። እአአ 2018 ላይ ፑቲን ተቀናቃኝ ሆኖ ምርጫ ሊወዳደር ሲል ገንዘብ የመበዝበዝ ክስ ተመስርቶበታል። ታዋቂው ሩስያዊ ተቃዋሚ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተከታዮች አሉት። የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፐስኮቭ በቪድዮው ላይ የተባሉት ነገሮች "ሐሰት ናቸው" ብለዋል። ፕሬዘዳንቱ "ምንም ቤተ መንግሥት የላቸውም" ሲሉም ቃል አቀባዩ አስተባብለዋል። 22 ሚሊዮን ተመልካቾች ያገኘው የምርመራ ቪድዮ የሚገባደደው፤ ሕዝቡ ተቃውሞውን በአደባባይ እንዲገልጽ በማሳሰብ ነው። "ከተበሳጩ ሰዎች 10 በመቶው እንኳን የተቃውሞ ሰልፍ ቢያደርጉ መንግሥት ምርጫውን ለማጭበርበር አይደፍርም" ሲል ናቫንሊ ተናግሯል። ናቫንሊ የተመረዝኩት በፑቲን ነው ብሎ ወደ ሩስያ መመለሱ በርካቶችን አስገርሟል። ሆኖም ግን ማረሚያ ቤት ሆኖ ቪድዮው ከተለቀቀ በኋላ ደጋፊዎቹ ተቃውሞ እንዲካሄድ እያነሳሱ ነው። የናቫንሊ እጣ ፈንታ ምን ይሆናል? የካቲት 2 ናቫንሊ ፍርድ ቤት ይቀርባል። 2014 ላይ በፍርድ ቤት የተወሰነበት የሦስት ዓመት ተኩል እስር ስለመጽናቱም ውሳኔ ይተላለፋል። ከሦስት ቀናት በኋላ በድጋሚ ፍርድ ቤት ቀርቦ የሁለተኛው ዓለም ጦርነት ጀግኖችን ስም የማጥፋት ክሱ ይታያል። ናቫንሊ ከተመረዘ በኋላ ጀርመን ውስጥ ህክምና ሲከታተል ነበር። ወደ ሩስያ ከተመለሰ እንደሚታሰር ማስጠንቀቂያ ቢሰጠውም ወደ አገሩ ከመመለስ ወደኋላ አላለም። የቀረበበትን ክስ "ፍትሕ ላይ መቀለድ ነው። ሕገ ወጥነት መንሰራፋቱን ያሳያል" ሲል ተችቷል። 2018 ላይ የአውሮፓ የሰብአዊ መብት ፍርድ ቤት፤ የናቫንሊ ክስ "የዘፈቀደ ነው" ብሎ ነበር። መታሰሩ ከዚህ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ጋር የሚቃረን ነው የሚል ጥያቄ ተነስቷል።
ፑቲን ቅንጡ ቤተ መንግሥት ማስገንባታቸውን 'የሚያጋልጠው' ቪድዮ የሩስያው ፕሬዘዳንት ቭላድሚር ፑቲን ቅንጡ ቤተ መንግሥት ለመገንባት በሕገ ወጥ መንገድ ገንዘብ ማፍሰሳቸውን የሚያሳየው የምርመራ ቪድዮ በተለቀቀ በጥቂት ቀናት ውስጥ ከ20 ሚሊዮን በላይ ተመልካች አግኝቷል። ቪድዮው የተለቀቀው በሩስያዊው ተቃዋሚ አሌክሴ ናቫልኒ ቡድን ነው። ናቫልኒ ሩስያ፣ ሞስኮ ሲደርስ በቁጥጥር ስር የዋለው ከቀናት በፊት ነበር። የምርመራ ቪድዮው እንደሚያሳየው፤ ቤተ መንግሥቱ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር ወጥቶበታል። "በታሪክ ትልቁ ጉቦ ነው" በማለት በቪድዮው ተገልጿል። ክሬምሊን ቤተ መንግሥቱ የፑቲን አይደለም ብሏል። በደቡብ ሩስያ ብላክ ሲ አካባቢ የሚገኘው ቤተ መንግሥት የሞኖኮ 39 እጥፍ ስፋት እንዳለው ተገልጿል። ቪድዮው የተለቀቀው ናቫልኒ ከጀርመን ወደ ሩስያ ከሄደ ከሁለት ቀን በኋላ ነበር። ናቫልኒ በቅድመ ምርመራ ለ30 ቀናት የታሰረ ሲሆን፤ ገንዘብ በመበዝበር የቀረበበትን ክስ በመጣሱ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል። እሱ ግን እስሩ ፖለቲካዊ ነው ይላል። የ44 ዓመቱ ተቃዋሚ ባለፈው ነሐሴ ተመርዞ ለሞት ተቃርቦ ነበር። ለመመረዙ ተጠያቂው ፑቲን እንደሆኑ ቢናገርም፤ የሩስያ መንግሥት እጁ እንደሌለበት አስታውቋል። ቪድዮው ምን ያሳያል? የምርመራ ቪድዮው እንደሚያሳው ቤተ መንግሥቱ የተሠራው በፑቲን የቅርብ ሰዎች ሕገ ወጥ የገንዘብ ድጋፍ ነው። የነዳጅ ምርት ባለሥልጣኖች እና ቢሊየነሮች ከነዚህ መካከል ናቸውም ተብሏል። ናቫንሊ በቪድዮው "በዚህ ገንዘብ ለአለቃቸው ቤተ መንግሥት ሠርተዋል" ብሏል። የሩስያ ብሔራዊ የምርመራ ተቋም ቤተ መንግሥቱ ዙርያ ያለው 27 ስኩዌር ማይል መሬት ባለቤት እንደሆነም በቪድዮው ተጠቁሟል። ሕንጻው ውስጥ ካዚኖ (መቆመሪያ)፣ የበረዶ ሆኪ መጫወቻና ወይን ማቀነባበሪያ ይገኛል ተብሏል። "ለመጣስ የሚከብድ አጥር አለው። ራሱን የቻለ ወደብና ቤተ ክርስቲያን አለው። በረራ ማድረግ ክልክል ነው። የድንበር ላይ ጥበቃ ኃይልም አለው። ሩስያ ውስጥ ያለ ራሱን የቻለ አገር ነው" ሲል ናቫንሊ ተናግሯል። ናቫንሊ በጸረ ሙስና ንቅናቄው ይታወቃል። እአአ 2018 ላይ ፑቲን ተቀናቃኝ ሆኖ ምርጫ ሊወዳደር ሲል ገንዘብ የመበዝበዝ ክስ ተመስርቶበታል። ታዋቂው ሩስያዊ ተቃዋሚ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተከታዮች አሉት። የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፐስኮቭ በቪድዮው ላይ የተባሉት ነገሮች "ሐሰት ናቸው" ብለዋል። ፕሬዘዳንቱ "ምንም ቤተ መንግሥት የላቸውም" ሲሉም ቃል አቀባዩ አስተባብለዋል። 22 ሚሊዮን ተመልካቾች ያገኘው የምርመራ ቪድዮ የሚገባደደው፤ ሕዝቡ ተቃውሞውን በአደባባይ እንዲገልጽ በማሳሰብ ነው። "ከተበሳጩ ሰዎች 10 በመቶው እንኳን የተቃውሞ ሰልፍ ቢያደርጉ መንግሥት ምርጫውን ለማጭበርበር አይደፍርም" ሲል ናቫንሊ ተናግሯል። ናቫንሊ የተመረዝኩት በፑቲን ነው ብሎ ወደ ሩስያ መመለሱ በርካቶችን አስገርሟል። ሆኖም ግን ማረሚያ ቤት ሆኖ ቪድዮው ከተለቀቀ በኋላ ደጋፊዎቹ ተቃውሞ እንዲካሄድ እያነሳሱ ነው። የናቫንሊ እጣ ፈንታ ምን ይሆናል? የካቲት 2 ናቫንሊ ፍርድ ቤት ይቀርባል። 2014 ላይ በፍርድ ቤት የተወሰነበት የሦስት ዓመት ተኩል እስር ስለመጽናቱም ውሳኔ ይተላለፋል። ከሦስት ቀናት በኋላ በድጋሚ ፍርድ ቤት ቀርቦ የሁለተኛው ዓለም ጦርነት ጀግኖችን ስም የማጥፋት ክሱ ይታያል። ናቫንሊ ከተመረዘ በኋላ ጀርመን ውስጥ ህክምና ሲከታተል ነበር። ወደ ሩስያ ከተመለሰ እንደሚታሰር ማስጠንቀቂያ ቢሰጠውም ወደ አገሩ ከመመለስ ወደኋላ አላለም። የቀረበበትን ክስ "ፍትሕ ላይ መቀለድ ነው። ሕገ ወጥነት መንሰራፋቱን ያሳያል" ሲል ተችቷል። 2018 ላይ የአውሮፓ የሰብአዊ መብት ፍርድ ቤት፤ የናቫንሊ ክስ "የዘፈቀደ ነው" ብሎ ነበር። መታሰሩ ከዚህ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ጋር የሚቃረን ነው የሚል ጥያቄ ተነስቷል።
https://www.bbc.com/amharic/55735400
5sports
ሲፈን ሐሰን፡ "ፈይሳ ሌሊሳ የእኔ ጀግና ነው''
ሲፈን ሐሰን፡ "ፈይሳ ሌሊሳ የእኔ ጀግና ነው''
ሲፈን ሐሰን፡ "ፈይሳ ሌሊሳ የእኔ ጀግና ነው'' ሲፈን ሐሰን፡ "ፈይሳ ሌሊሳ የእኔ ጀግና ነው''
https://www.bbc.com/amharic/50697605
3politics
የውጭ ጣልቃ ገብነትን በመቃወም በአዲስ አበባ ነዋሪዎች ድምጻቸውን አሰሙ
በአዲስ አበባ "ብሔራዊ ክብር በሕብር" በሚል በአገሪቱ የውስጥ ጉዳይ የውጭ ጣልቃ ገብነትን በመቃወም ኢትዮጵያውያን በያሉበት ድምጻቸውን አሰሙ። በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች "እጃችሁን ከኢትዮጵያ ላይ አንሱ" ፣ "ምዕራባውያን በኢትዮጵያ ጉዳይ ጣልቃ እየገቡ የሚያሳድሩት ተጽዕኖ የአገርን ሉዓላዊነት የሚጥስ ነው"፣ "ግድቡ የኔ ነው" የሚሉና መሰል መልዕክቶች በመኪናዎች ላይ በመለጠፍና በእጃቸው በመያዝ ተቃውሟቸውን ገልጸዋል። ከአስተባባሪዎቹ አንዷ የሆኑት ክብሬ ተስፋዬ ድምጽ የማሰማቱ መርሃ ግብር ዓላማ በቀጥታ ጣልቃ ገብነትን የሚመለከቱ መግለጫዎችን ለሚያወጡ አካላት 'እጃቸውን ከኢትዮጵያ ላይ እንዲያነሱ' ለመጠየቅ መሆኑን ለቢቢሲ ገልጸዋል። "የሕዳሴ ግድብ፣ በትግራይ ክልል የሕግ ማስከበር ዘመቻ ጋር የሚነሱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና ምርጫን ተከትሎ የውጭ ተጽዕኖ ኢትዮጵያ ላይ እየበረታ ነው" ያሉት አስተባባሪዋ፤ የውጭ አካላት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነት እንዲያቆሙ ለመጠየቅ መርሃ ግብሩ መካሄዱን ተናግረዋል። "'ለኢትዮጵያ እናውቅላታለን' የሚል የውጭ ኃይል ሲመጣ፤ እኛ ደግሞ የኢትዮጵያን ሕዝብ እናውቀዋለን፤ ስለዚህ እጃችሁን አንሱልን ነው ያልነው" ብለዋል አስተባባሪዋ። የሰብዓዊ መብት ጥሰት አለ ማለት ምን ያስቆጣል ተብለው የተጠየቁት አስተባባሪዋ፤ ተቃውሟቸው 'ለእናንተ እኛ እናውቅላችኋለን' ብለው ውሳኔና መፍትሔ ካልፈለግን ለሚሉት እንደሆነ ተናግረዋል። "የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችም መንግሥትም ያመናቸው እንዳሉና እኛም እያለቀስንበት ያለ ጉዳይ ነው" በማለት "የውስጥ ጉዳይን መፍታት ያለብን እኛው ነን" ብለዋል። አስተባባሪዋ አክለውም ዛሬ በነበረው የመርሃ ግብሩ ማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት "በቀጥታ ጣልቃ ገብነትን የሚመለከቱ መግለጫዎችን ለሚያወጡት እጃቸውን እንዲያነሱ፤ አብረውን ለቆሙ ለተረዱን አገራት ደግሞ የምስጋና ደብዳቤ የማስገባት እቅድ ነበረን" ብለዋል። ይሁን እንጂ አንዳንድ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅቶች 'የጸጥታ ስጋት' በሚል መሥሪያ ቤታቸውን በመዝጋታቸው ይህንን ማድረግ እንዳልቻሉ አስረድተዋል። ድምጽ የማሰማት መርሃ ግብሩ አዲስ አበባ በሚገኘው ከአሜሪካ ኤምባሲ ውጪ ተቃውሞ እንደሚካሄድ ቀደም ብሎ የተገለጸ ቢሆንም በዛሬው ዕለት ይህ እንዳልተከናወነ የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ገልጿል። ከሲቪክ ማኅበራት፣ ከሐይማኖት ተቋማት፣ እንዲሁም መንግሥታዊ ካልሆኑ አካላት የተዘጋጀ የተቃውሞ ደብዳቤ ወደ ኤምባሲዎች ለማስገባት ታቅዶ እንደነበርና ዛሬ ኤምባሲዎቹ ዝግ በመሆናቸው አለመሳካቱን ከመርሃ ግብሩ አስተባባሪዎች አንዱ የሆኑት አቶ ዐብይ ታደለ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ተናግረዋል። ኮሚቴው ኤምባሲዎቹን ቀጠሮ እንዲሰጠው መጠየቁንና ቀጠሮውን በሚሰጣቸው ጊዜ ደብዳቤውን በአካል እንደሚያቀርቡ አስተባባሪው አክለዋል። የአሜሪካ ኤምባሲ ትናንት ባወጣው መግለጫ በማኅበራዊ የትስስር ገጾች በኤምባሲው አካባቢ ተቃውሞ ሊኖር እንደሚችል በመግለጽ አርብ መሥሪያ ቤቱ ዝግ መሆኑን ማስታወቁ ይታወሳል። በትግራይ ውስጥ የህወሓት ኃይሎች በፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ላይ የፈጸሙትን ጥቃት ተከትሎ በተቀሰቀሰው ግጭት ሳቢያ እንዲሁም በታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ዙሪያ ምዕራባዊያንና ዓለም አቀፍ ተቋማት በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማሳደር እየሞከሩ ነው ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት ቅሬታውን ሲያሰማ ቆይቷል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ ሌሎች የአገሪቱ ባለሥልጣናት በተለያዩ መድረኮች ላይ ምዕራባዊያን በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ ለመግባት እየሞከሩ መሆናቸውን፤ ነገር ግን ይህ ተቀባይነት እንደሌለው ሲናገሩ ተደምጠዋል። ይህ "ብሔራዊ ክብር በሕብር" የተሰኘው በታዋቂ ሰዎች የተዘጋጀው እንቅስቃሴም ዜጎች የውጭ አገር መንግሥታት በኢትዮጵያ ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ ለመግባት እያደረጉ ነው ያሉትን ጥረት ለመቃወም የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።
የውጭ ጣልቃ ገብነትን በመቃወም በአዲስ አበባ ነዋሪዎች ድምጻቸውን አሰሙ በአዲስ አበባ "ብሔራዊ ክብር በሕብር" በሚል በአገሪቱ የውስጥ ጉዳይ የውጭ ጣልቃ ገብነትን በመቃወም ኢትዮጵያውያን በያሉበት ድምጻቸውን አሰሙ። በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች "እጃችሁን ከኢትዮጵያ ላይ አንሱ" ፣ "ምዕራባውያን በኢትዮጵያ ጉዳይ ጣልቃ እየገቡ የሚያሳድሩት ተጽዕኖ የአገርን ሉዓላዊነት የሚጥስ ነው"፣ "ግድቡ የኔ ነው" የሚሉና መሰል መልዕክቶች በመኪናዎች ላይ በመለጠፍና በእጃቸው በመያዝ ተቃውሟቸውን ገልጸዋል። ከአስተባባሪዎቹ አንዷ የሆኑት ክብሬ ተስፋዬ ድምጽ የማሰማቱ መርሃ ግብር ዓላማ በቀጥታ ጣልቃ ገብነትን የሚመለከቱ መግለጫዎችን ለሚያወጡ አካላት 'እጃቸውን ከኢትዮጵያ ላይ እንዲያነሱ' ለመጠየቅ መሆኑን ለቢቢሲ ገልጸዋል። "የሕዳሴ ግድብ፣ በትግራይ ክልል የሕግ ማስከበር ዘመቻ ጋር የሚነሱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና ምርጫን ተከትሎ የውጭ ተጽዕኖ ኢትዮጵያ ላይ እየበረታ ነው" ያሉት አስተባባሪዋ፤ የውጭ አካላት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነት እንዲያቆሙ ለመጠየቅ መርሃ ግብሩ መካሄዱን ተናግረዋል። "'ለኢትዮጵያ እናውቅላታለን' የሚል የውጭ ኃይል ሲመጣ፤ እኛ ደግሞ የኢትዮጵያን ሕዝብ እናውቀዋለን፤ ስለዚህ እጃችሁን አንሱልን ነው ያልነው" ብለዋል አስተባባሪዋ። የሰብዓዊ መብት ጥሰት አለ ማለት ምን ያስቆጣል ተብለው የተጠየቁት አስተባባሪዋ፤ ተቃውሟቸው 'ለእናንተ እኛ እናውቅላችኋለን' ብለው ውሳኔና መፍትሔ ካልፈለግን ለሚሉት እንደሆነ ተናግረዋል። "የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችም መንግሥትም ያመናቸው እንዳሉና እኛም እያለቀስንበት ያለ ጉዳይ ነው" በማለት "የውስጥ ጉዳይን መፍታት ያለብን እኛው ነን" ብለዋል። አስተባባሪዋ አክለውም ዛሬ በነበረው የመርሃ ግብሩ ማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት "በቀጥታ ጣልቃ ገብነትን የሚመለከቱ መግለጫዎችን ለሚያወጡት እጃቸውን እንዲያነሱ፤ አብረውን ለቆሙ ለተረዱን አገራት ደግሞ የምስጋና ደብዳቤ የማስገባት እቅድ ነበረን" ብለዋል። ይሁን እንጂ አንዳንድ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅቶች 'የጸጥታ ስጋት' በሚል መሥሪያ ቤታቸውን በመዝጋታቸው ይህንን ማድረግ እንዳልቻሉ አስረድተዋል። ድምጽ የማሰማት መርሃ ግብሩ አዲስ አበባ በሚገኘው ከአሜሪካ ኤምባሲ ውጪ ተቃውሞ እንደሚካሄድ ቀደም ብሎ የተገለጸ ቢሆንም በዛሬው ዕለት ይህ እንዳልተከናወነ የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ገልጿል። ከሲቪክ ማኅበራት፣ ከሐይማኖት ተቋማት፣ እንዲሁም መንግሥታዊ ካልሆኑ አካላት የተዘጋጀ የተቃውሞ ደብዳቤ ወደ ኤምባሲዎች ለማስገባት ታቅዶ እንደነበርና ዛሬ ኤምባሲዎቹ ዝግ በመሆናቸው አለመሳካቱን ከመርሃ ግብሩ አስተባባሪዎች አንዱ የሆኑት አቶ ዐብይ ታደለ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ተናግረዋል። ኮሚቴው ኤምባሲዎቹን ቀጠሮ እንዲሰጠው መጠየቁንና ቀጠሮውን በሚሰጣቸው ጊዜ ደብዳቤውን በአካል እንደሚያቀርቡ አስተባባሪው አክለዋል። የአሜሪካ ኤምባሲ ትናንት ባወጣው መግለጫ በማኅበራዊ የትስስር ገጾች በኤምባሲው አካባቢ ተቃውሞ ሊኖር እንደሚችል በመግለጽ አርብ መሥሪያ ቤቱ ዝግ መሆኑን ማስታወቁ ይታወሳል። በትግራይ ውስጥ የህወሓት ኃይሎች በፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ላይ የፈጸሙትን ጥቃት ተከትሎ በተቀሰቀሰው ግጭት ሳቢያ እንዲሁም በታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ዙሪያ ምዕራባዊያንና ዓለም አቀፍ ተቋማት በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማሳደር እየሞከሩ ነው ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት ቅሬታውን ሲያሰማ ቆይቷል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ ሌሎች የአገሪቱ ባለሥልጣናት በተለያዩ መድረኮች ላይ ምዕራባዊያን በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ ለመግባት እየሞከሩ መሆናቸውን፤ ነገር ግን ይህ ተቀባይነት እንደሌለው ሲናገሩ ተደምጠዋል። ይህ "ብሔራዊ ክብር በሕብር" የተሰኘው በታዋቂ ሰዎች የተዘጋጀው እንቅስቃሴም ዜጎች የውጭ አገር መንግሥታት በኢትዮጵያ ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ ለመግባት እያደረጉ ነው ያሉትን ጥረት ለመቃወም የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።
https://www.bbc.com/amharic/news-57184359
5sports
የሳዑዲ አረቢያ የሴቶች እግር ኳስ ሊግ ተጀመረ
በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ ተጓትቶ የነበረው የሳዑዲ አረቢያ የሴቶች እግር ኳስ ሊግ ተጀምሯል። 600 እግር ኳስ ተጫዋቾች በ24 ቡድኖች ተከፍለው በሪያድ፣ ጅዳና ዳማም ከተሞች ለቻምፒየንሺፕ ዋንጫ ይፋለማሉ። ማክሰኞ አመሻሹን የተደረገው የመጀመሪያው ጨዋታ በቴሌቪዥን ባይተላለፍም የሳዑዲ መገናኛ ብዙሃን የሊጉ መጀመር ለሴቶች ተሳትፎ እመርታ ነው ሲሉ ተደምጠዋል። ሳዑዲ፤ ሴቶች ስታድየም ገብተው እግር ኳስ ጨዋታዎችን እንዲመለከቱ የፈቀደችው በፈረንጆቹ 2018 ነበር። ለዘመናት የሃገሪቱ ባለሥልጣናት ባሕላዊና ኃይማኖታዊ እሴቶችን በማጣቀስ ሴቶች በስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች እንዳይሳተፉ ሲከለክሉ ቆይተዋል። ወግ አጥባቂዎች ሴቶች በስፖርት ጨዋታዎች መሳተፋቸው ወደ ኢ-ሞራላዊነት ይመራል ይላሉ። በመክፈቻው ቀን የሳዑዲ ሴቶች እግር ኳስ ሊግ ጨዋታዎች በዋና ከተማዋ ሪያድና በቀይ ባህሯ ጅዳ ከተማዋ ተከናውነዋል። ታይገርስ ጅዳ ቻለንጅን 11 ለባዶ፤ አል ሪያድ ዩናይትድ ናጅድ ሪያዲን 10 ለ 1 ያሸነፉበት ጨዋታ በርካታ ጎሎች የተቆጠሩበት ሆኗል። አሸናፊዋ ቡድን 500 ሺህ የሳዑዲ ሪያል ወይም 133 ሺህ ዶላር ተሸላሚ ትሆናለች። የሳዑዲ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሊጉን ያስጀመረው ሴቶች በስፖርትና ሌሎች ማሕበራዊ እንቅስቃሴዎች የጎላ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ነው ብሏል። አረብ ኒውስ ለሰተኘው ጣቢያ ድምጿን የሰጠችው የ16 ዓመቷ ናጂላ አሕመድ በፈረንጆቹ 2021 ከትምህርት ቤት አልፋ ለሊጉ ቡድን ለመጫወት እንደምትሻ ተናግራለች። "የዚያኔ 17 ዓመት ይሆነኛል። ለመጫወት ብቁ እሆናለሁ ማለት ነው። ማን እንደሚያቆመኝ አያለሁ።" በተያያዘ በዓለም የመጀመሪያው የሴቶች የጎልፍ ጨዋታ ሳዑዲ አራቢያ የተካሄደው በዚህ ሳምንት ነው። የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ተቺዎች ግን ሃገሪቱ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በመሰል ክንውኖች እየሸፋፈነች ነው ሲሉ ይተቻሉ። በርካታ የሴቶች መብት ተሟጋቾች አሁንም በሳዑዲ እሥር ቤቶች ይገኛሉ።
የሳዑዲ አረቢያ የሴቶች እግር ኳስ ሊግ ተጀመረ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ ተጓትቶ የነበረው የሳዑዲ አረቢያ የሴቶች እግር ኳስ ሊግ ተጀምሯል። 600 እግር ኳስ ተጫዋቾች በ24 ቡድኖች ተከፍለው በሪያድ፣ ጅዳና ዳማም ከተሞች ለቻምፒየንሺፕ ዋንጫ ይፋለማሉ። ማክሰኞ አመሻሹን የተደረገው የመጀመሪያው ጨዋታ በቴሌቪዥን ባይተላለፍም የሳዑዲ መገናኛ ብዙሃን የሊጉ መጀመር ለሴቶች ተሳትፎ እመርታ ነው ሲሉ ተደምጠዋል። ሳዑዲ፤ ሴቶች ስታድየም ገብተው እግር ኳስ ጨዋታዎችን እንዲመለከቱ የፈቀደችው በፈረንጆቹ 2018 ነበር። ለዘመናት የሃገሪቱ ባለሥልጣናት ባሕላዊና ኃይማኖታዊ እሴቶችን በማጣቀስ ሴቶች በስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች እንዳይሳተፉ ሲከለክሉ ቆይተዋል። ወግ አጥባቂዎች ሴቶች በስፖርት ጨዋታዎች መሳተፋቸው ወደ ኢ-ሞራላዊነት ይመራል ይላሉ። በመክፈቻው ቀን የሳዑዲ ሴቶች እግር ኳስ ሊግ ጨዋታዎች በዋና ከተማዋ ሪያድና በቀይ ባህሯ ጅዳ ከተማዋ ተከናውነዋል። ታይገርስ ጅዳ ቻለንጅን 11 ለባዶ፤ አል ሪያድ ዩናይትድ ናጅድ ሪያዲን 10 ለ 1 ያሸነፉበት ጨዋታ በርካታ ጎሎች የተቆጠሩበት ሆኗል። አሸናፊዋ ቡድን 500 ሺህ የሳዑዲ ሪያል ወይም 133 ሺህ ዶላር ተሸላሚ ትሆናለች። የሳዑዲ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሊጉን ያስጀመረው ሴቶች በስፖርትና ሌሎች ማሕበራዊ እንቅስቃሴዎች የጎላ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ነው ብሏል። አረብ ኒውስ ለሰተኘው ጣቢያ ድምጿን የሰጠችው የ16 ዓመቷ ናጂላ አሕመድ በፈረንጆቹ 2021 ከትምህርት ቤት አልፋ ለሊጉ ቡድን ለመጫወት እንደምትሻ ተናግራለች። "የዚያኔ 17 ዓመት ይሆነኛል። ለመጫወት ብቁ እሆናለሁ ማለት ነው። ማን እንደሚያቆመኝ አያለሁ።" በተያያዘ በዓለም የመጀመሪያው የሴቶች የጎልፍ ጨዋታ ሳዑዲ አራቢያ የተካሄደው በዚህ ሳምንት ነው። የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ተቺዎች ግን ሃገሪቱ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በመሰል ክንውኖች እየሸፋፈነች ነው ሲሉ ይተቻሉ። በርካታ የሴቶች መብት ተሟጋቾች አሁንም በሳዑዲ እሥር ቤቶች ይገኛሉ።
https://www.bbc.com/amharic/news-54993325
2health
"በረሃብ ምክንያት ከሥራ ገበታቸው የሚቀሩ የጤና ባለሙያዎች አሉ" አይደር ሪፈራል ሆስፒታል
በትግራይ ክልል መቀለ ከተማ የሚገኘው ዋነኛ የሕክምና ተቋም አይደር ሪፈራል ሆስፒታል በቀን ከ4 እስከ 6 አስክሬኖች የሚሸኝበት ደረጃ እንደደረሰ ለቢቢሲ ገለጸ። በመድኃኒትና ሕክምና አገልግሎት እጥረት ከሞቱት መካከል የሆስፒታሉ የጤና ባለሙያዎች እንደሚገኙበትም አስታውቋል። ቢቢሲ ያነጋገረው የሆስፒታሉ የነርሲንግ አገልግሎት ኃላፊ ቴዎድሮስ ካህሳይ ከጦርነቱ በፊት ከትግራይ፣ አማራና አፋር ክልሎች ለሚመጡ ታካሚዎች አገልግሎት ይሰጥ የነበረው ሆስፒታል አሁን ግን እጅግ መዳከሙን ገልጿል። ከአንድ ዓመት በላይ በሆነው የሰሜኑ ጦርነት ከሌላው የኢትዮጵያ ክፍል እና ከዓለም ተቆራርጣ ባለችው ትግራይ ክልል በሕክምና ቁሳቁሶች፣ መድሃኒቶችን እና የሰብዓዊ እርዳታዎች እጥረት በርካቶች ለከፋ ችግር መዳረጋቸው ሲዘገብ ቆይቷል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በትግራይ የጤና ማዕከላት በአስፈላጊ መድኃኒት እጥረት ሳቢያ ሥራ ማቆማቸውን ያስታወቀ ሲሆን በትግራይ ክልል የሚገኙ የሕክምና ባለሙያዎች በበኩላቸው ህፃናትን ጨምሮ ህሙማን በከፍተኛ መድኃኒት እጥረት ምክንያት እየሞቱ መሆናቸውን መግለጻቸው ይታወሳል። ከጥቂት ሳምንታት በፊት የፌደራሉ መንግሥት በትግራይ ክልል ሰብዓዊ እርዳታን በተቀላጠፈ ሁኔታ ለማድረስ ሲባል ግጭት ለማቆም መወሰኑን አስታውቆ፤ የትግራይ ኃይሎች ከማንኛውም ጥቃት እንዲታቀቡና በኃይል ከያዟቸው የአጎራባች አፋር ክልል አካባቢዎች እንዲወጡ ጠይቆ ነበር። ይህንን ተከትሎም የትግራይ ኃይሎች የተኩስ አቁም እንዳደረጉና ከአፋር ክልል ኤረብቲ መውጣታቸውን ገልጸዋል። በዚህ ሳምንት ደግሞ የህወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ህወሓት ከአፋር ክልል ሙሉ ለሙሉ ለመውጣት ዘላቂ፣ ያልተገደበ፣ ወቅታዊ እና በቂ የሆነ እርዳታ ማቅረብን ጨምሮ ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጠዋል። ቀደም ሲል የተደረገውን ስምምነት ተከትሎም ከሁለት ሳምንት በፊት የዓለም ምግብ ፕሮግራም 47 ምግብና ነዳጅን ጨምሮ የተለያዩ ሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ትግራይ ማድረሱን ገልጿል። አለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ መድኃኒቶች፣ የህክምና መገልገያዎችና የምግብ እርዳታ የጫኑ መኪኖቹ ከስድስት ወራት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሜ መጋቢት 24፣ 2014 ወደ ትግራይ መግባታቸውን አስታውቋል። አሜሪካም በሰሜን ኢትዮጵያ ለተከሰተው ችግር የሚውል 313 ሚሊየን ዶላር የሚገመት የሰብዓዊ እርዳታ ማድረጓን ከትናንት በስቲያ አስታውቃለች። የአይደር ሪፈራል ሆስፒታል የነርሲንግ አገልግሎት ኃላፊው ቴዎድሮስ ካለፉት አራት ዓመታት ጀምሮ ለሆስፒታሉ ሲሰጥ የነበረው ድጎማ እና የሕክምና ቁሳቁስ አነስተኛ እንደነበር አስታውሰው ላለፈው አንድ ዓመት ግን ሆስፒታሉ ካለምንም በጀት እየሠራ እንደሆነ ተናግሯል። " በአሁኑ ሰዓት 30 በመቶ በሚሆን አቅም ነው አገልግሎት እየሰጠን ያለነው፤የመድሃኒት ክምችታችን ወደ 10 በመቶ ወርዶ ነበር። ከዓለም ጤና ድርጅት የመጣ እርዳታ ተጨምሮበት ክምችቱ ወደ 20 በመቶ ደርሶ ነበር። ነገር ግን ይህ ለሆስፒታሉ የተሰጠው መድሃኒት ያለቀው በሁለት ሳምንት ውስጥ ነው" ይላል። ኃላፊው እንደሚሉት ድጋፍ የተደረጉላቸው መድሃኒቶች በዓይነትም እጅግ አነስተኛ እንደነበር ጠቁመዋል። ኃላፊው እንደ ካንሰር፣ ደም ግፊት ላሉ ስር የሰደዱ በሽታዎች ምንም ዓይነት መድሃኒት አለመግባቱን በመግለፅም ለሳንታት ታይቶ የነበረው የሆስፒታሉ አገልግሎት መሻሻል ተመልሶ መውረዱን አክለዋል። ለላብራቶሪ የሚውሉ ግብዓቶች ፣ መድሃኒቶች፣ ማሽኖችን ማንቀሳቀሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ፣ ተኝተው ለሚታከሙ የሚቀርብ ምግብ ፣ ለሠራተኞች የሚከፈል በሌለበት መስራትም አስቸጋሪ አንደሆነ ቴዎድሮስ ገልጿል። "በረሃብ ምክንያት ከሥራ ገበታቸው የሚቀሩ ባልደረቦቻችን አሉ" በሆስፒታሉ ድንገተኛ ክፍል ውስጥ ነርስ የሆነው ገብረይ አቢዩ " ሰዎች ለሕክምና መጥተው እያየናቸው ሕይወታቸውን ሲያጡ እጅግ እናዝናለን" ይላል። የሆስፒታሉ ሠራተኞች በዚህ ሁሉ ፈተና ውስጥ ሆነው እየሠሩ እንደሆነ የሚናገረው አቶ ገብረይ "በረሃብ ምክንያት ከሥራ ገበታቸው የሚቀሩ ባልደረቦቻችን ግን አሉ" ይላል። "ከባድ ሁኔታ ላይ ነው ያለነው ሰዎች ሙያዊ ድጋፍ ፈልገው ሲመጡ ምንም ሳይደረግላቸው ሲቀር ሥራ ቦታ ብቻ ሳይሆን ቤት ሄደህም ሰላም አታገኝም። ለሊት ተኝተህ ወደ ህሊናህ የሚመጣ ብዙ ነገር አለ። ሕጻናት መጥተው በኦአርኤስ ወይም በሌላ ትንሽ ነገር ሕይወታቸውን ማትረፍ እየተቻለ ይህ ባለመኖሩ ስታጣቸው በጣም ከባድ ነው። እጆችህን አጣጥፈህ ነው ቆመህ የምታየው። ልብህን የሚያደማ እንጂ ደስ ብሎህ የምትሠራው ሥራ አይደለም።" ሲሉ በሆስፒታሉ ያለውን ችግር ያስረዳሉ። ችግሩ ይህ ብቻ አይደለም፤ ድርብርብ ነው። የትራንስፖርት አገልግሎት ባለመኖሩም ለ11 ወራት ደሞዝ ያልተከፈላቸው ሠራተኞች እስከ 2 ሰዓት የሚወስድ መንገድ በእግር ተጉዘው ሆስፒታሉ እንደሚደርሱ ቢቢሲ ያነጋገራቸው የጤና ባለሙያዎች ይገልጻሉ። "የጤና ባለሙያዎችም በሕክምና አገልግሎት እጦት ሕይወታቸው አልፏል" ቴዎድሮስ እንደሚለው የመድኃኒትና የሕክምና አገልግሎት እጥረት የታካሚዎችን ሕይወት ብቻ ሳይሆን የጤና ባለሙያዎችንም ሕይወት እየቀጠፈ ነው። "በዚህ ሁለት ወር 2 ነርሶች ሞተውብናል። መዳን ይችሉ ነበር፤ ግን መድኃኒት ማግኘት አልቻሉም። በተለይ አንደኛዋ ነርስ ኤምአርአይ ማሽኑ እየሠራ ስላልሆነ በሽታዋን በግልጽ ማወቅ አልተቻለም። በዚህ ምክንያት ሕመሟ ጸንቶ ሞታለች። ሁለተኛው ነርስ ደግሞ ሊወስደው የሚገባ መድኃኒት እዚህ ሆስፒታል ስለሌለ ያጣነው ባልደረባችን ነው። አሁን በቀን እስከ 4 አልፎም እስከ 6 አስክሬን ከዚህ ሆስፒታል ይሸኛል። ከዚህ በፊት ግን በሁለት ወይም ሦስት ቀን አንድ ሬሳ ነበር የሚወጣው" ይላል። በሕክምና እጦት ምክንያት ሕይወታቸው ከሚያልፍ የጤና ባለሙያዎች መካከል አብዛኞቹ የክሮኒክ በሽታዎች ተጠቂ መሆናቸውንም ኃላፊው ገልጿል። ትግራይ ባለው የጥሬ ገንዘብ እጥረት ምክንያት ሆስፒታሉ ለሚሰጠው አግልግሎት ከታካሚዎች የሚጠይቀው ገንዘብም እጅግ ዝቅተኛ ክፍያ [ከቀድሞው ከ90 በመቶ ያነሰ) ነው። "በሆስፒታሉ የማይገኙ መድኃኒቶችን ከውጭ ለመግዛት የተቸገሩ ሰዎች፣ ከሩቅ የትግራይ አካባቢ መጥተው መመለሻ ያጡ ሰዎች፣ የሞቱ ቤተሰቦቻቸውን አስክሬን ለመውሰድ የሚቸገሩ ሰዎችን ማየት የሠራተኞቹን ልብ በሐዘን ይሰብራል" ብሏል። ለታካሚዎችና ለተወሰኑ ሠራተኞች ይቀርብ የነበረ ምግብ ላለፉት 10 ቀናት ውስጥ ስለተቋረጠ እስከ 240 ታካሚዎች ወደ ቤታቸው እንደተሸኙም አክሏል። ከዚህ ቀደምም የአይደር ሆስፒታል የህክምና ባለሙያዎች ባወጡት መግለጫ በቀዶ ህክምና ወቅት የሚያስፈልጉ በደም ስር የሚሰጡ (intravenous fluids) እና የሰመመን መስጫ መድኃኒቶች ባለመኖራቸው ቀዶ ህክምና ማድረግ አለመቻላቸውን ነው። በተደጋጋሚ የሚከሰተው የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ እና ያልተሟላ የኦክስጂን አቅርቦት ለታካሚዎች ሞት ምክንያት ነው ብለዋል። ከጦርነቱ ጋር ተያይዞ በትግራይ ክልል መሰረታዊ የሚባሉ አገልግሎቶች መብራት፣ ውሃ፣ ስልክ፣ ትራንስፖርትና የባንክ አገልግሎቶች ተቋርጠው ይገኛሉ። ባለፈው ዓመት ጥቅምት መጨረሻ ላይ ትግራይ ውስጥ ተከስቶ ወደ አማራና አፋር ክልሎች የተዛመተው ደም አፋሳሽ ጦርነት ሺዎችን በመቅጠፍና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን በማፈናቀል መጠነ ሰፊ ሰብዓዊ ቀውስ አድርሷል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንደሚለው ወደ 10 ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ በሰሜን ኢትዮጵያ የሰብአዊ እርዳታ የሚያስፈልገው ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በትግራይ ክልል ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውን ገልጿል። አስራ ስምንት ወራት ያስቆጠረው ይህ ጦርነት እንዲቋጭ አሜሪካን ጨምሮ የአፍሪካ ሕብረትና ሌሎች አጋሮች ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ። ከሰሞኑ የኢትዮጵያ መንግሥትና የትግራይ ኃይሎች ለሰብዓዊነት ሲባል የተኩስ አቁም ያወጁ ሲሆን ይህም ለሰላም በር ሊከፈትና ደም አፋሳሽ ጦርነት ለማብቃት ወደሚያስችል ውይይት መሄድ እንደሚችል ተስፋ ተጥሎበታል።
"በረሃብ ምክንያት ከሥራ ገበታቸው የሚቀሩ የጤና ባለሙያዎች አሉ" አይደር ሪፈራል ሆስፒታል በትግራይ ክልል መቀለ ከተማ የሚገኘው ዋነኛ የሕክምና ተቋም አይደር ሪፈራል ሆስፒታል በቀን ከ4 እስከ 6 አስክሬኖች የሚሸኝበት ደረጃ እንደደረሰ ለቢቢሲ ገለጸ። በመድኃኒትና ሕክምና አገልግሎት እጥረት ከሞቱት መካከል የሆስፒታሉ የጤና ባለሙያዎች እንደሚገኙበትም አስታውቋል። ቢቢሲ ያነጋገረው የሆስፒታሉ የነርሲንግ አገልግሎት ኃላፊ ቴዎድሮስ ካህሳይ ከጦርነቱ በፊት ከትግራይ፣ አማራና አፋር ክልሎች ለሚመጡ ታካሚዎች አገልግሎት ይሰጥ የነበረው ሆስፒታል አሁን ግን እጅግ መዳከሙን ገልጿል። ከአንድ ዓመት በላይ በሆነው የሰሜኑ ጦርነት ከሌላው የኢትዮጵያ ክፍል እና ከዓለም ተቆራርጣ ባለችው ትግራይ ክልል በሕክምና ቁሳቁሶች፣ መድሃኒቶችን እና የሰብዓዊ እርዳታዎች እጥረት በርካቶች ለከፋ ችግር መዳረጋቸው ሲዘገብ ቆይቷል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በትግራይ የጤና ማዕከላት በአስፈላጊ መድኃኒት እጥረት ሳቢያ ሥራ ማቆማቸውን ያስታወቀ ሲሆን በትግራይ ክልል የሚገኙ የሕክምና ባለሙያዎች በበኩላቸው ህፃናትን ጨምሮ ህሙማን በከፍተኛ መድኃኒት እጥረት ምክንያት እየሞቱ መሆናቸውን መግለጻቸው ይታወሳል። ከጥቂት ሳምንታት በፊት የፌደራሉ መንግሥት በትግራይ ክልል ሰብዓዊ እርዳታን በተቀላጠፈ ሁኔታ ለማድረስ ሲባል ግጭት ለማቆም መወሰኑን አስታውቆ፤ የትግራይ ኃይሎች ከማንኛውም ጥቃት እንዲታቀቡና በኃይል ከያዟቸው የአጎራባች አፋር ክልል አካባቢዎች እንዲወጡ ጠይቆ ነበር። ይህንን ተከትሎም የትግራይ ኃይሎች የተኩስ አቁም እንዳደረጉና ከአፋር ክልል ኤረብቲ መውጣታቸውን ገልጸዋል። በዚህ ሳምንት ደግሞ የህወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ህወሓት ከአፋር ክልል ሙሉ ለሙሉ ለመውጣት ዘላቂ፣ ያልተገደበ፣ ወቅታዊ እና በቂ የሆነ እርዳታ ማቅረብን ጨምሮ ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጠዋል። ቀደም ሲል የተደረገውን ስምምነት ተከትሎም ከሁለት ሳምንት በፊት የዓለም ምግብ ፕሮግራም 47 ምግብና ነዳጅን ጨምሮ የተለያዩ ሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ትግራይ ማድረሱን ገልጿል። አለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ መድኃኒቶች፣ የህክምና መገልገያዎችና የምግብ እርዳታ የጫኑ መኪኖቹ ከስድስት ወራት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሜ መጋቢት 24፣ 2014 ወደ ትግራይ መግባታቸውን አስታውቋል። አሜሪካም በሰሜን ኢትዮጵያ ለተከሰተው ችግር የሚውል 313 ሚሊየን ዶላር የሚገመት የሰብዓዊ እርዳታ ማድረጓን ከትናንት በስቲያ አስታውቃለች። የአይደር ሪፈራል ሆስፒታል የነርሲንግ አገልግሎት ኃላፊው ቴዎድሮስ ካለፉት አራት ዓመታት ጀምሮ ለሆስፒታሉ ሲሰጥ የነበረው ድጎማ እና የሕክምና ቁሳቁስ አነስተኛ እንደነበር አስታውሰው ላለፈው አንድ ዓመት ግን ሆስፒታሉ ካለምንም በጀት እየሠራ እንደሆነ ተናግሯል። " በአሁኑ ሰዓት 30 በመቶ በሚሆን አቅም ነው አገልግሎት እየሰጠን ያለነው፤የመድሃኒት ክምችታችን ወደ 10 በመቶ ወርዶ ነበር። ከዓለም ጤና ድርጅት የመጣ እርዳታ ተጨምሮበት ክምችቱ ወደ 20 በመቶ ደርሶ ነበር። ነገር ግን ይህ ለሆስፒታሉ የተሰጠው መድሃኒት ያለቀው በሁለት ሳምንት ውስጥ ነው" ይላል። ኃላፊው እንደሚሉት ድጋፍ የተደረጉላቸው መድሃኒቶች በዓይነትም እጅግ አነስተኛ እንደነበር ጠቁመዋል። ኃላፊው እንደ ካንሰር፣ ደም ግፊት ላሉ ስር የሰደዱ በሽታዎች ምንም ዓይነት መድሃኒት አለመግባቱን በመግለፅም ለሳንታት ታይቶ የነበረው የሆስፒታሉ አገልግሎት መሻሻል ተመልሶ መውረዱን አክለዋል። ለላብራቶሪ የሚውሉ ግብዓቶች ፣ መድሃኒቶች፣ ማሽኖችን ማንቀሳቀሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ፣ ተኝተው ለሚታከሙ የሚቀርብ ምግብ ፣ ለሠራተኞች የሚከፈል በሌለበት መስራትም አስቸጋሪ አንደሆነ ቴዎድሮስ ገልጿል። "በረሃብ ምክንያት ከሥራ ገበታቸው የሚቀሩ ባልደረቦቻችን አሉ" በሆስፒታሉ ድንገተኛ ክፍል ውስጥ ነርስ የሆነው ገብረይ አቢዩ " ሰዎች ለሕክምና መጥተው እያየናቸው ሕይወታቸውን ሲያጡ እጅግ እናዝናለን" ይላል። የሆስፒታሉ ሠራተኞች በዚህ ሁሉ ፈተና ውስጥ ሆነው እየሠሩ እንደሆነ የሚናገረው አቶ ገብረይ "በረሃብ ምክንያት ከሥራ ገበታቸው የሚቀሩ ባልደረቦቻችን ግን አሉ" ይላል። "ከባድ ሁኔታ ላይ ነው ያለነው ሰዎች ሙያዊ ድጋፍ ፈልገው ሲመጡ ምንም ሳይደረግላቸው ሲቀር ሥራ ቦታ ብቻ ሳይሆን ቤት ሄደህም ሰላም አታገኝም። ለሊት ተኝተህ ወደ ህሊናህ የሚመጣ ብዙ ነገር አለ። ሕጻናት መጥተው በኦአርኤስ ወይም በሌላ ትንሽ ነገር ሕይወታቸውን ማትረፍ እየተቻለ ይህ ባለመኖሩ ስታጣቸው በጣም ከባድ ነው። እጆችህን አጣጥፈህ ነው ቆመህ የምታየው። ልብህን የሚያደማ እንጂ ደስ ብሎህ የምትሠራው ሥራ አይደለም።" ሲሉ በሆስፒታሉ ያለውን ችግር ያስረዳሉ። ችግሩ ይህ ብቻ አይደለም፤ ድርብርብ ነው። የትራንስፖርት አገልግሎት ባለመኖሩም ለ11 ወራት ደሞዝ ያልተከፈላቸው ሠራተኞች እስከ 2 ሰዓት የሚወስድ መንገድ በእግር ተጉዘው ሆስፒታሉ እንደሚደርሱ ቢቢሲ ያነጋገራቸው የጤና ባለሙያዎች ይገልጻሉ። "የጤና ባለሙያዎችም በሕክምና አገልግሎት እጦት ሕይወታቸው አልፏል" ቴዎድሮስ እንደሚለው የመድኃኒትና የሕክምና አገልግሎት እጥረት የታካሚዎችን ሕይወት ብቻ ሳይሆን የጤና ባለሙያዎችንም ሕይወት እየቀጠፈ ነው። "በዚህ ሁለት ወር 2 ነርሶች ሞተውብናል። መዳን ይችሉ ነበር፤ ግን መድኃኒት ማግኘት አልቻሉም። በተለይ አንደኛዋ ነርስ ኤምአርአይ ማሽኑ እየሠራ ስላልሆነ በሽታዋን በግልጽ ማወቅ አልተቻለም። በዚህ ምክንያት ሕመሟ ጸንቶ ሞታለች። ሁለተኛው ነርስ ደግሞ ሊወስደው የሚገባ መድኃኒት እዚህ ሆስፒታል ስለሌለ ያጣነው ባልደረባችን ነው። አሁን በቀን እስከ 4 አልፎም እስከ 6 አስክሬን ከዚህ ሆስፒታል ይሸኛል። ከዚህ በፊት ግን በሁለት ወይም ሦስት ቀን አንድ ሬሳ ነበር የሚወጣው" ይላል። በሕክምና እጦት ምክንያት ሕይወታቸው ከሚያልፍ የጤና ባለሙያዎች መካከል አብዛኞቹ የክሮኒክ በሽታዎች ተጠቂ መሆናቸውንም ኃላፊው ገልጿል። ትግራይ ባለው የጥሬ ገንዘብ እጥረት ምክንያት ሆስፒታሉ ለሚሰጠው አግልግሎት ከታካሚዎች የሚጠይቀው ገንዘብም እጅግ ዝቅተኛ ክፍያ [ከቀድሞው ከ90 በመቶ ያነሰ) ነው። "በሆስፒታሉ የማይገኙ መድኃኒቶችን ከውጭ ለመግዛት የተቸገሩ ሰዎች፣ ከሩቅ የትግራይ አካባቢ መጥተው መመለሻ ያጡ ሰዎች፣ የሞቱ ቤተሰቦቻቸውን አስክሬን ለመውሰድ የሚቸገሩ ሰዎችን ማየት የሠራተኞቹን ልብ በሐዘን ይሰብራል" ብሏል። ለታካሚዎችና ለተወሰኑ ሠራተኞች ይቀርብ የነበረ ምግብ ላለፉት 10 ቀናት ውስጥ ስለተቋረጠ እስከ 240 ታካሚዎች ወደ ቤታቸው እንደተሸኙም አክሏል። ከዚህ ቀደምም የአይደር ሆስፒታል የህክምና ባለሙያዎች ባወጡት መግለጫ በቀዶ ህክምና ወቅት የሚያስፈልጉ በደም ስር የሚሰጡ (intravenous fluids) እና የሰመመን መስጫ መድኃኒቶች ባለመኖራቸው ቀዶ ህክምና ማድረግ አለመቻላቸውን ነው። በተደጋጋሚ የሚከሰተው የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ እና ያልተሟላ የኦክስጂን አቅርቦት ለታካሚዎች ሞት ምክንያት ነው ብለዋል። ከጦርነቱ ጋር ተያይዞ በትግራይ ክልል መሰረታዊ የሚባሉ አገልግሎቶች መብራት፣ ውሃ፣ ስልክ፣ ትራንስፖርትና የባንክ አገልግሎቶች ተቋርጠው ይገኛሉ። ባለፈው ዓመት ጥቅምት መጨረሻ ላይ ትግራይ ውስጥ ተከስቶ ወደ አማራና አፋር ክልሎች የተዛመተው ደም አፋሳሽ ጦርነት ሺዎችን በመቅጠፍና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን በማፈናቀል መጠነ ሰፊ ሰብዓዊ ቀውስ አድርሷል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንደሚለው ወደ 10 ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ በሰሜን ኢትዮጵያ የሰብአዊ እርዳታ የሚያስፈልገው ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በትግራይ ክልል ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውን ገልጿል። አስራ ስምንት ወራት ያስቆጠረው ይህ ጦርነት እንዲቋጭ አሜሪካን ጨምሮ የአፍሪካ ሕብረትና ሌሎች አጋሮች ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ። ከሰሞኑ የኢትዮጵያ መንግሥትና የትግራይ ኃይሎች ለሰብዓዊነት ሲባል የተኩስ አቁም ያወጁ ሲሆን ይህም ለሰላም በር ሊከፈትና ደም አፋሳሽ ጦርነት ለማብቃት ወደሚያስችል ውይይት መሄድ እንደሚችል ተስፋ ተጥሎበታል።
https://www.bbc.com/amharic/news-61132952
2health
ከበርካታ ሕጻናት ሞት በኋላ በ4 የሕንድ ምርት በሆኑ ሽሮፖች ላይ ማስጠንቀቂያ ወጣ
በርካታ ቁጥር ያላቸው ሕጻናት ሕይወታቸው ካለፈ በኋላ የሕንድ ምርት በሆኑ አራት የሽሮፕ አይነቶች ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ማስጠንቀቂያ ተሰጠ። የዓለም ጤና ድርጅት ዓለም አቀፍ ማስጠንቀቂያውን ያወጣው በአፍሪካዊቷ ጋምቢያ የ66 ሕጸናት ሕልፈት ከሽሮፖቹ ጋር ሳይገናኝ አይቀርም ከተባለ በኋላ ነው። ሽሮፖቹ ለከፍተኛ የኩላሊት ጉዳት እና ለ66 የሕጻናት ሞት ምክንያት ሳይሆኑ አይቀርም ብሏል የዓለም ጤና ድርጅት። የዓለም ጤና ድርጅት ወላጆች ለልጆቻቸው ከመስጠት መቆጠብ አለባቸው ያላቸው ሽሮፖች ፕሮመታዚን ኦራል ሶሉሽን (Promethazine Oral Solution)፣ ኮፌክስማሊን ቤቢ ካፍ ሲረፕ (Kofexmalin Baby Cough Syrup)፣ ማኮፍ ቤቢ ካፍ ሲረፕ (Makoff Baby Cough Syrup) እና ማግሪፕ ኤን ኮልድ ሲረፕ (Magrip N Cold Syrup) የሚባሉት ናቸው። እነዚህ የሕጻናት ሽሮፖችን ያመረተው ማይደን ፋርማሱቲካልስ የሚባል የሕንድ ኩባንያ ሲሆን፤ ለሽሮፖቹ የደኅንነት ማስረጃ ማቅረብ አለመቻሉን የዓለም ጤና ድርጅት ጨምሮ አስታውቋል። አምራቹ ኩባንያ በጉዳዩ ላይ እስካሁን ያለው ነገር የለም። ቢቢሲም ላቀረበው ጥያቄ ምላሽ አልሰጠም። የሕንድ ባለሥልጣናት በበኩላቸው ሽሮፖቹ ለሕጻናቱ ሞት ምክንያት መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ እንዲሰጣቸው የዓለም ጤና ድርጅትን መጠየቃቸው ተገልጿል። ሽሮፖቹን መጠቀም በተለይ በሕጻናት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ወይም ሞትን ሊያስከትል እንደሚችል የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። የዓለም ጤና ድርጅት ሽሮፖቹ የጤና ጉዳት እንደሚያስከትሉ ማወቅ የቻለው የጎብኚዎች መዳረሻ በሆነችው በጋምቢያ በተለይ ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ከፍተኛ የኩላሊት ጉዳት የሚያጋጥማቸው ሕጻናት ቁጥር መጨምሩን ተከትሎ ነው። ይህን ተከትሎ የአገሪቱ መንግሥት ዜጎች ፓራሲታሞል ሽሮፖችን መጠቀም በማቆም በምትኩ የሚዋጥ ኪኒኒ እንዲጠቀሙ አሳስቧል። የጋምቢያ ጤና ኃላፊዎች ባለፈው ወር ትክክለኛውን ቁጥር ሳይጠቅሱ በርካታ ሕጻናት ሕይወታቸው አልፏል ብለው ነበር። የዓለም ጤና ድርጅት በሽሮፖቹ ላይ በተደገረ ምርመራ ዳይታይለን ግላይኮል እና ኢታይለን ግላይኮል የተሰኙ ከፍተኛ መጠን ያላቸው ንጥረ ነገሮች ተገኝተዋል። እነዚህ ንጥረ ነገሮች መርዛማ ሲሆኑ የሆድ ሕመም፣ ትውከት፣ ተቅማጥ፣ ራስ ምታት እና ለሞት የሚዳርግ ከፍተኛ የኩላሊት ጉዳት ሊያስከትሉ ይችላሉ። የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ረቡዕ መስከረም 25/2015 ዓ.ም. በጄኔቭ ንግግር ሲያደርጉ፤ “የእነዚህ ጨቅላ ሕጻናት ሕልፈት ለወላጆቻቸው ልብ የሚሰብር ነው” ብለዋል። የሕንድ ማዕከላዊ የመድኃኒት ጥራት ተቆጣጣሪ ድርጅት ሽሮፖቹ ለጋምቢያ ብቻ መላካቸውን ለዓለም ጤና ድርጅት መግለጹን ኤአፍፒ የዜና ወኪል ዘግቧል። ምንም እንኳ እነዚህ አራት የሕጻናት ሽሮፕ አይነቶች የተሰራጩት በጋምቢያ ብቻ ነው ቢባልም መደበኛ ባልሆነ የገበያ ስንሰለት ወደ ተቀሩት ጎረቤት አገራትም ሳይሰራጩ አይቀርም ተብሏል። ከዚህ በተጨማሪም የዓለም ጤና ድርጅት አምራቹ ሽሮፖቹ ውስጥ የተገኙትን መርዛማ ኬሚካሎች በሌሎች ምርቶቹ ላይ በመጠቀም ሕንድ ውስጥ እና ወደተቀረው ዓለም ልኮ ሊይሆን ይችላል ብሏል።
ከበርካታ ሕጻናት ሞት በኋላ በ4 የሕንድ ምርት በሆኑ ሽሮፖች ላይ ማስጠንቀቂያ ወጣ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሕጻናት ሕይወታቸው ካለፈ በኋላ የሕንድ ምርት በሆኑ አራት የሽሮፕ አይነቶች ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ማስጠንቀቂያ ተሰጠ። የዓለም ጤና ድርጅት ዓለም አቀፍ ማስጠንቀቂያውን ያወጣው በአፍሪካዊቷ ጋምቢያ የ66 ሕጸናት ሕልፈት ከሽሮፖቹ ጋር ሳይገናኝ አይቀርም ከተባለ በኋላ ነው። ሽሮፖቹ ለከፍተኛ የኩላሊት ጉዳት እና ለ66 የሕጻናት ሞት ምክንያት ሳይሆኑ አይቀርም ብሏል የዓለም ጤና ድርጅት። የዓለም ጤና ድርጅት ወላጆች ለልጆቻቸው ከመስጠት መቆጠብ አለባቸው ያላቸው ሽሮፖች ፕሮመታዚን ኦራል ሶሉሽን (Promethazine Oral Solution)፣ ኮፌክስማሊን ቤቢ ካፍ ሲረፕ (Kofexmalin Baby Cough Syrup)፣ ማኮፍ ቤቢ ካፍ ሲረፕ (Makoff Baby Cough Syrup) እና ማግሪፕ ኤን ኮልድ ሲረፕ (Magrip N Cold Syrup) የሚባሉት ናቸው። እነዚህ የሕጻናት ሽሮፖችን ያመረተው ማይደን ፋርማሱቲካልስ የሚባል የሕንድ ኩባንያ ሲሆን፤ ለሽሮፖቹ የደኅንነት ማስረጃ ማቅረብ አለመቻሉን የዓለም ጤና ድርጅት ጨምሮ አስታውቋል። አምራቹ ኩባንያ በጉዳዩ ላይ እስካሁን ያለው ነገር የለም። ቢቢሲም ላቀረበው ጥያቄ ምላሽ አልሰጠም። የሕንድ ባለሥልጣናት በበኩላቸው ሽሮፖቹ ለሕጻናቱ ሞት ምክንያት መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ እንዲሰጣቸው የዓለም ጤና ድርጅትን መጠየቃቸው ተገልጿል። ሽሮፖቹን መጠቀም በተለይ በሕጻናት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ወይም ሞትን ሊያስከትል እንደሚችል የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። የዓለም ጤና ድርጅት ሽሮፖቹ የጤና ጉዳት እንደሚያስከትሉ ማወቅ የቻለው የጎብኚዎች መዳረሻ በሆነችው በጋምቢያ በተለይ ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ከፍተኛ የኩላሊት ጉዳት የሚያጋጥማቸው ሕጻናት ቁጥር መጨምሩን ተከትሎ ነው። ይህን ተከትሎ የአገሪቱ መንግሥት ዜጎች ፓራሲታሞል ሽሮፖችን መጠቀም በማቆም በምትኩ የሚዋጥ ኪኒኒ እንዲጠቀሙ አሳስቧል። የጋምቢያ ጤና ኃላፊዎች ባለፈው ወር ትክክለኛውን ቁጥር ሳይጠቅሱ በርካታ ሕጻናት ሕይወታቸው አልፏል ብለው ነበር። የዓለም ጤና ድርጅት በሽሮፖቹ ላይ በተደገረ ምርመራ ዳይታይለን ግላይኮል እና ኢታይለን ግላይኮል የተሰኙ ከፍተኛ መጠን ያላቸው ንጥረ ነገሮች ተገኝተዋል። እነዚህ ንጥረ ነገሮች መርዛማ ሲሆኑ የሆድ ሕመም፣ ትውከት፣ ተቅማጥ፣ ራስ ምታት እና ለሞት የሚዳርግ ከፍተኛ የኩላሊት ጉዳት ሊያስከትሉ ይችላሉ። የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ረቡዕ መስከረም 25/2015 ዓ.ም. በጄኔቭ ንግግር ሲያደርጉ፤ “የእነዚህ ጨቅላ ሕጻናት ሕልፈት ለወላጆቻቸው ልብ የሚሰብር ነው” ብለዋል። የሕንድ ማዕከላዊ የመድኃኒት ጥራት ተቆጣጣሪ ድርጅት ሽሮፖቹ ለጋምቢያ ብቻ መላካቸውን ለዓለም ጤና ድርጅት መግለጹን ኤአፍፒ የዜና ወኪል ዘግቧል። ምንም እንኳ እነዚህ አራት የሕጻናት ሽሮፕ አይነቶች የተሰራጩት በጋምቢያ ብቻ ነው ቢባልም መደበኛ ባልሆነ የገበያ ስንሰለት ወደ ተቀሩት ጎረቤት አገራትም ሳይሰራጩ አይቀርም ተብሏል። ከዚህ በተጨማሪም የዓለም ጤና ድርጅት አምራቹ ሽሮፖቹ ውስጥ የተገኙትን መርዛማ ኬሚካሎች በሌሎች ምርቶቹ ላይ በመጠቀም ሕንድ ውስጥ እና ወደተቀረው ዓለም ልኮ ሊይሆን ይችላል ብሏል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c29eg84k0gko
5sports
ባሎንዶር፡ እውን ሜሲ የዘንድሮው ሽልማት አይገባውም?
የዘንድሮው የባሎን ዶር ሽልማት አከርካሪ ሆኗል። ሽልማቱ ለፖላንዳዊው ሌቫንዶቭስኪ ነው የሚገባው ከሚለው ወቀሳ ጀምሮ ሞሐመድ ሳላህ ሰባተኛ መውጣቱ አግባብ አይደለም የሚሉ ደምፆች እየተሰሙ ነው። አርጀንቲናዊው ሊዮኔል አንድሬስ ሜሲ ሽልማቱን ለሰባተኛ ጊዜ በማንሳት ታሪክ ፅፏል። ነገር ግን እንደዚህ ቀደሙ የይገባዋል ድምፅ ሳይሆን ሌቫንዶቭስኪ እያለ እንዴት በሚሉ ትችቶች የታጀበ ሆኗል። እርግጥ ነው የ34 ዓመቱ ሜሲ ያሳለፈው የውድድር ዘመን የከፋ የሚባል አልነበረም። ሜሲ በ2021 40 ጎሎች አስቆጥሯል። 28 ለባርሴሎና፤ 4 ለፒኤስጂ እንዲሁም 8 ለሃገሩ አርጀንቲና። ሜሲ በእግር ኳስ ሕይወቱ ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር የመጀመሪያውን ዓለም አቀፍ ዋንጫ ያነሳው በዚህ ዓመት አርጀንቲና የኮፓ አሜሪካ ዋንጫ አሸናፊ ስትሆን ነው። እና ለምን ሽልማቱ አይገባውም የሚሉ ድምፆች በረከቱ? በርካታ የእግር ኳስ ተንታኞች የባየር ሚዩኒክና ፖላንድ የፊት መስመር ተጫዋች የሆነው ሮበርት ሌቫንዶቭስኪ የዘንድሮው ባለን ዶር ሽልማት አሸናፊ ሊሆን በተገባ ነበር ይላሉ። የ33 ዓመቱ አጥቂ ዘንድሮ ለባየርን በሁሉም ውድድሮች 53 ጎሎች በማስቆጠሩ የዓመቱ ምርጥ አጥቂ የተሰኘ ሽልማት ተበርክቶለታል። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የተሰረዘው የባለፈው ዓመት የባለን ዶር ሽልማት ተዘጋጅቶ ቢሆን ኖሮ አሸናፊው ሌቫንዶስኪ እንጂ ሌላ ማንም ሊሆን አይችልም የሚሉ ብዙዎች ናቸው። ሌቫንዶቭስኪ ከባየርን ጋር ባለፈው ዓመት የጀርመን ዋንጫ፣ ቡንደስሊጋ እንዲሁም ቻምፒዮንስ ሊግ ማንሳት ችሏል። በ2021 ባየርን ቡንደስሊጋ ለዘጠነኛ ተከታታይ ጊዜ ሲያነሳ ሌቪ በቡንደስሊጋው በአንድ የውድድር ዘመን በርካታ ጎሎች በማግባት በ41 ጎሎች የገርድ ሙለርን ክብረ ወሰን መስበር ችሎ ነበር። እግር ኳስ ተጨዋቾች፣ አሠልጣኞች እንዲሁም ተንታኞች ትላንት አመሻሹን ከተከናወነው የባለን ዶር ሽልማት በኋላ ሐሳባቸውን ሰጥተዋል። የሪያል ማድሪዱ አማካይ ቶኒ ክሩስ "ሜሲ ሽልማቱ በጭራሽ አይገባውም" ብሏል። ሜሲና ሮናልዶ ያለፈውን 10 ዓመት በበላይነት መያዛቸው የማያከራክር ቢሆንም ዘንድሮ ግን ሽልማቱ የሚገባው ለሌላ ሰው ነበር። ሌላው ቀርቶ ሜሲ እንኳ ሳይቀር ሽልማቱን ሲቀበል ሌቪ ባለን ዶር ይገባው እንደነበር ተናግሯል። በሌላ በኩል የወቅቱ የዓለማችን ድንቅ ተጫዋች እየተባለ እየተሞካሸ ያለው ግብፃዊው የሊቨርፑል አጥቂ ሞ ሳላህ ሰባተኛ መውጣቱ ብዙዎችን አስከፍቷል። የሊቨርፑል አሠልጣኝ ዩርገን ክሎፕ ሞ ሳላህ የተሻለ ድምፅ ማግኘት በተገባ ነበር ሲሉ ማክሰኞ ዕለት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። ክሎፕ አክለው ሜሲ የሕይወት ዘመን ሽልማት ቢሆን ኖሮ ወርቃማው ኳስ ይገባው ነበር ሲሉ የሽልማቱን አዘጋጆች ሸንቆጥ አድርገዋል።
ባሎንዶር፡ እውን ሜሲ የዘንድሮው ሽልማት አይገባውም? የዘንድሮው የባሎን ዶር ሽልማት አከርካሪ ሆኗል። ሽልማቱ ለፖላንዳዊው ሌቫንዶቭስኪ ነው የሚገባው ከሚለው ወቀሳ ጀምሮ ሞሐመድ ሳላህ ሰባተኛ መውጣቱ አግባብ አይደለም የሚሉ ደምፆች እየተሰሙ ነው። አርጀንቲናዊው ሊዮኔል አንድሬስ ሜሲ ሽልማቱን ለሰባተኛ ጊዜ በማንሳት ታሪክ ፅፏል። ነገር ግን እንደዚህ ቀደሙ የይገባዋል ድምፅ ሳይሆን ሌቫንዶቭስኪ እያለ እንዴት በሚሉ ትችቶች የታጀበ ሆኗል። እርግጥ ነው የ34 ዓመቱ ሜሲ ያሳለፈው የውድድር ዘመን የከፋ የሚባል አልነበረም። ሜሲ በ2021 40 ጎሎች አስቆጥሯል። 28 ለባርሴሎና፤ 4 ለፒኤስጂ እንዲሁም 8 ለሃገሩ አርጀንቲና። ሜሲ በእግር ኳስ ሕይወቱ ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር የመጀመሪያውን ዓለም አቀፍ ዋንጫ ያነሳው በዚህ ዓመት አርጀንቲና የኮፓ አሜሪካ ዋንጫ አሸናፊ ስትሆን ነው። እና ለምን ሽልማቱ አይገባውም የሚሉ ድምፆች በረከቱ? በርካታ የእግር ኳስ ተንታኞች የባየር ሚዩኒክና ፖላንድ የፊት መስመር ተጫዋች የሆነው ሮበርት ሌቫንዶቭስኪ የዘንድሮው ባለን ዶር ሽልማት አሸናፊ ሊሆን በተገባ ነበር ይላሉ። የ33 ዓመቱ አጥቂ ዘንድሮ ለባየርን በሁሉም ውድድሮች 53 ጎሎች በማስቆጠሩ የዓመቱ ምርጥ አጥቂ የተሰኘ ሽልማት ተበርክቶለታል። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የተሰረዘው የባለፈው ዓመት የባለን ዶር ሽልማት ተዘጋጅቶ ቢሆን ኖሮ አሸናፊው ሌቫንዶስኪ እንጂ ሌላ ማንም ሊሆን አይችልም የሚሉ ብዙዎች ናቸው። ሌቫንዶቭስኪ ከባየርን ጋር ባለፈው ዓመት የጀርመን ዋንጫ፣ ቡንደስሊጋ እንዲሁም ቻምፒዮንስ ሊግ ማንሳት ችሏል። በ2021 ባየርን ቡንደስሊጋ ለዘጠነኛ ተከታታይ ጊዜ ሲያነሳ ሌቪ በቡንደስሊጋው በአንድ የውድድር ዘመን በርካታ ጎሎች በማግባት በ41 ጎሎች የገርድ ሙለርን ክብረ ወሰን መስበር ችሎ ነበር። እግር ኳስ ተጨዋቾች፣ አሠልጣኞች እንዲሁም ተንታኞች ትላንት አመሻሹን ከተከናወነው የባለን ዶር ሽልማት በኋላ ሐሳባቸውን ሰጥተዋል። የሪያል ማድሪዱ አማካይ ቶኒ ክሩስ "ሜሲ ሽልማቱ በጭራሽ አይገባውም" ብሏል። ሜሲና ሮናልዶ ያለፈውን 10 ዓመት በበላይነት መያዛቸው የማያከራክር ቢሆንም ዘንድሮ ግን ሽልማቱ የሚገባው ለሌላ ሰው ነበር። ሌላው ቀርቶ ሜሲ እንኳ ሳይቀር ሽልማቱን ሲቀበል ሌቪ ባለን ዶር ይገባው እንደነበር ተናግሯል። በሌላ በኩል የወቅቱ የዓለማችን ድንቅ ተጫዋች እየተባለ እየተሞካሸ ያለው ግብፃዊው የሊቨርፑል አጥቂ ሞ ሳላህ ሰባተኛ መውጣቱ ብዙዎችን አስከፍቷል። የሊቨርፑል አሠልጣኝ ዩርገን ክሎፕ ሞ ሳላህ የተሻለ ድምፅ ማግኘት በተገባ ነበር ሲሉ ማክሰኞ ዕለት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። ክሎፕ አክለው ሜሲ የሕይወት ዘመን ሽልማት ቢሆን ኖሮ ወርቃማው ኳስ ይገባው ነበር ሲሉ የሽልማቱን አዘጋጆች ሸንቆጥ አድርገዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-59483014
0business
በቅርቡ ከወጣው ኮንዶሚኒየም ዕጣ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነገረ
አዲስ አበባ ውስጥ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለማግኘት ለተመዘገቡ ሰዎች በተካሄደው የዕጣ ሂደት ላይ ከታዩ ጉድለቶች ጋር በተያያዘ የከተማው አስተዳደር ኃላፊዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነገረ። ባለፈው ሳምንት አርብ ሐምሌ 01/2014 ዓ.ም. 25ሺህ 491 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በ20/80 እና የ40/60 የቁጠባ መርሃ ግብር አማካይነት ለባለ ዕድሎች እንዲደርስ ዕጣ መውጣቱ አስታውቆ ነበር። ይህንን ሂደት ተከትሎም የተለያዩ ወገኖች በዕጣ አወጣጡና በዕጣው ውስጥ በተካተቱ ሰዎች ላይ የተለያዩ ጥያቄዎችን ሲያነሱ ቆይተው፣ የከተማው አስተዳደር አደረግኩት ባለው ማጣራት ችግሮች እንዳሉ አረጋግጧል። በከተማ አስተዳደሩ ውስጥ ያሉ ምንጮች ለቢቢሲ እንደገለጹት ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ቢያንስ ሁለት ኃላፊዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸዋል። ሰኞ ዕለት የከተማው አስተዳደር ባወጣው መግለጫ ላይም ቤቶቹን ለማስተላለፍ ከተከናወነው የዕጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓት በኋላ የተለያዩ ጥቆማዎች መቅረባቸውን አመልክቷል። ይህንንም ተከትሎ በዕጣው ውስጥ በተካተተው መረጃ ላይ በተደረገው ማጣራት “በባንክ የተላከውና ለዕጣ እንዲውል ወደ ኮምፒውተር የተጫነው ዳታ ላይ ልዩነቶች ተግኝተዋል” ሲል ተፈጠረ ያለውን ችግር አመልክቷል። ጨምሮም ባለፈው አርብ በወጣው የቤቶች ማስተላለፍ የዕታ ሂደት ላይ በተደረገው ማጣራት “ላልቆጠቡ ሰዎች ዕጣ መውጣትን ጨምሮ የተለያዩ የተዓማኒነት ጉድለቶች ታይተዋል” ሲል ገልጿል። የከተማው አስተዳደር የተዓማኒነት ጉድለቶች ያላቸውን ጉዳዮች ዝርዝር እንዲሁም ጉድለቱ የታየው ምን ያህል ቤቶች ላይ መሆኑን አላሳወቀም። በዚህም ምክንያት የቤት ማስተላለፍ ሂደቱ ላይ ተከስተዋል የተባሉ “የተዓማኒነት ጉድለቶች” ገለልተኛ በሆኑ በሚመለከታቸው ተቋማት ተጨማሪ የማጣራት ሥራ በመከናወን ላይ ነው ብሏል የከተማው አስተዳደር ባወጣው መግለጫ። ከተከሰተው የአሰራር መዛባት ጋር በተያያዘም “የተጠረጠሩ ባለሙያዎች እና አመራር በቁጥጥር ሥር ሆነው ምርመራ እየተደረገባቸው” እንደሚገኝም አረጋግጧል። ምርመራው ስለደረሰበትም ሂደት ሆነ ስለተጠረጠሩ አመራሮችን በተመለከተ ቢቢሲ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የሚመለከታቸውን የአስተደዳሩን ኃላፊዎች ለማግኘት በተደጋጋሚ ቢሞክርም ምላሽ ማግኘት አልቻለም። የከተማዋ ነዋሪዎችን ባለቤት ለማድረግ በማቀድ በ1997 ዓ.ም. የተጀመረው የጋራ መኖሪያ ቤት ከዓመት ወደ ዓመት እየናረ ያለውን የቤት ኪራይ ጫናንም ለበርካቶች ያቃልላል የሚል ተስፋ ተሰንቆበት ነበር። ነዋሪዎች የተወሰነውን ቆጥበው በዓመታት ይከፍሉታል በተባለው 20/80 እንዲሁም 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ፕሮጀክት እንደታሰበው የግንባታው ሥራ ሊከናወን አልቻለም። ለዓመታት በርካቶች ቆጥበው ቤቶች እንዳልደረሳቸው የሚናገሩ ሲሆን በተጨማሪም ሳይወረራዱ የቀሩ ብሮች፣ ሕገወጥ የመሬት ይዞታዎችና የሌሎች ውዝግቦች ምንጮች ሆነዋል። በባለፈው ዓመት ጥር ወር ላይ በአዲስ አበባ 21 ሺህ 695 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በሕገ-ወጥ ተይዘው መገኘታቸውን ከንቲባዋ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ማስታወቃቸው ይታወሳል።
በቅርቡ ከወጣው ኮንዶሚኒየም ዕጣ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነገረ አዲስ አበባ ውስጥ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለማግኘት ለተመዘገቡ ሰዎች በተካሄደው የዕጣ ሂደት ላይ ከታዩ ጉድለቶች ጋር በተያያዘ የከተማው አስተዳደር ኃላፊዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነገረ። ባለፈው ሳምንት አርብ ሐምሌ 01/2014 ዓ.ም. 25ሺህ 491 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በ20/80 እና የ40/60 የቁጠባ መርሃ ግብር አማካይነት ለባለ ዕድሎች እንዲደርስ ዕጣ መውጣቱ አስታውቆ ነበር። ይህንን ሂደት ተከትሎም የተለያዩ ወገኖች በዕጣ አወጣጡና በዕጣው ውስጥ በተካተቱ ሰዎች ላይ የተለያዩ ጥያቄዎችን ሲያነሱ ቆይተው፣ የከተማው አስተዳደር አደረግኩት ባለው ማጣራት ችግሮች እንዳሉ አረጋግጧል። በከተማ አስተዳደሩ ውስጥ ያሉ ምንጮች ለቢቢሲ እንደገለጹት ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ቢያንስ ሁለት ኃላፊዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸዋል። ሰኞ ዕለት የከተማው አስተዳደር ባወጣው መግለጫ ላይም ቤቶቹን ለማስተላለፍ ከተከናወነው የዕጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓት በኋላ የተለያዩ ጥቆማዎች መቅረባቸውን አመልክቷል። ይህንንም ተከትሎ በዕጣው ውስጥ በተካተተው መረጃ ላይ በተደረገው ማጣራት “በባንክ የተላከውና ለዕጣ እንዲውል ወደ ኮምፒውተር የተጫነው ዳታ ላይ ልዩነቶች ተግኝተዋል” ሲል ተፈጠረ ያለውን ችግር አመልክቷል። ጨምሮም ባለፈው አርብ በወጣው የቤቶች ማስተላለፍ የዕታ ሂደት ላይ በተደረገው ማጣራት “ላልቆጠቡ ሰዎች ዕጣ መውጣትን ጨምሮ የተለያዩ የተዓማኒነት ጉድለቶች ታይተዋል” ሲል ገልጿል። የከተማው አስተዳደር የተዓማኒነት ጉድለቶች ያላቸውን ጉዳዮች ዝርዝር እንዲሁም ጉድለቱ የታየው ምን ያህል ቤቶች ላይ መሆኑን አላሳወቀም። በዚህም ምክንያት የቤት ማስተላለፍ ሂደቱ ላይ ተከስተዋል የተባሉ “የተዓማኒነት ጉድለቶች” ገለልተኛ በሆኑ በሚመለከታቸው ተቋማት ተጨማሪ የማጣራት ሥራ በመከናወን ላይ ነው ብሏል የከተማው አስተዳደር ባወጣው መግለጫ። ከተከሰተው የአሰራር መዛባት ጋር በተያያዘም “የተጠረጠሩ ባለሙያዎች እና አመራር በቁጥጥር ሥር ሆነው ምርመራ እየተደረገባቸው” እንደሚገኝም አረጋግጧል። ምርመራው ስለደረሰበትም ሂደት ሆነ ስለተጠረጠሩ አመራሮችን በተመለከተ ቢቢሲ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የሚመለከታቸውን የአስተደዳሩን ኃላፊዎች ለማግኘት በተደጋጋሚ ቢሞክርም ምላሽ ማግኘት አልቻለም። የከተማዋ ነዋሪዎችን ባለቤት ለማድረግ በማቀድ በ1997 ዓ.ም. የተጀመረው የጋራ መኖሪያ ቤት ከዓመት ወደ ዓመት እየናረ ያለውን የቤት ኪራይ ጫናንም ለበርካቶች ያቃልላል የሚል ተስፋ ተሰንቆበት ነበር። ነዋሪዎች የተወሰነውን ቆጥበው በዓመታት ይከፍሉታል በተባለው 20/80 እንዲሁም 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ፕሮጀክት እንደታሰበው የግንባታው ሥራ ሊከናወን አልቻለም። ለዓመታት በርካቶች ቆጥበው ቤቶች እንዳልደረሳቸው የሚናገሩ ሲሆን በተጨማሪም ሳይወረራዱ የቀሩ ብሮች፣ ሕገወጥ የመሬት ይዞታዎችና የሌሎች ውዝግቦች ምንጮች ሆነዋል። በባለፈው ዓመት ጥር ወር ላይ በአዲስ አበባ 21 ሺህ 695 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በሕገ-ወጥ ተይዘው መገኘታቸውን ከንቲባዋ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ማስታወቃቸው ይታወሳል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cw53zpx3wx3o
0business
ከአዲስ አበባ ኮምቦልቻ ተቋርጦ የነበረው በረራ ሊጀመር ነው
ከአዲስ አበባ ወደ ኮምቦልቻ/ደሴ ተቋርጦ የነበረው በረራ ከታኅሣሥ 27/2014 ዓ.ም ሊጀመር መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ። አየር መንገዱ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አክሎ እንዳሰፈረው ከተጠቀሰው ዕለት ጀምሮ በየቀኑ በረራዎች እንደሚኖሩ ነው። የደቡብ ወሎ ከተሞች የሆኑት ደሴና ኮምቦልቻ በህወሓት ኃይሎች ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተከትሎ ነበር አየር መንገዱ ወደ ኮምቦልቻ የሚያደርገውንና ሁለቱን ከተሞች የሚያገለግለውን በረራ አቋርጦ የነበረው። አየር መንገዱ በኮምቦልቻ አየር ማረፊያ የሚያደርጋቸውን የየቀኑ በረራዎች ለሁለት ወራት ያህል አቋርጦ ነበር። ከኮምቦልቻ በተጨማሪ በላሊበላ ለወራት ተቋርጦ የነበረው በረራም በትናንትናው ዕለት ታኅሣሥ 25/2014 ዓ.ም መጀመሩን አየር መንገዱ በተጨማሪ ገልጿል። በህወሓት ቁጥጥር ስር በነበሩ ከተሞች የመብራት፣ ውሃና ስልክ አገልግሎት ተቋርጦ የነበረ ሲሆን መንግሥት እነዚህን ከተሞች በስሩ ማድረጉን ተከትሎ የመብራትና፣ ውሃና ስልክ አገልግሎት ተመልሷል። በበርካታ የአማራ ክልል ከተሞችም እንዲሁ ተቋርጦ የነበረው ኢንተርኔት አገልግሎት (ዳታ) መመለሱንም ነዋሪዎች ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪም የባንክ አገልግሎቶች በበርካታ የአማራ ክልል ከተሞች የተመለሱ ሲሆን ትራንስፖርት በአንዳንድ አካቢዎች መጀመሩም ተነግሯል። የመንግሥት መስሪያ ቤቶችን ጨምሮ ትምህርት ቤቶች መከፈታቸውንም ቢቢሲ ከነዋሪዎች በሰበሰው መረጃ መረዳት ችሏል። ከጦርነቱና ትራንስፖርት መገደብ ጋር ተያይዞ በከፍተኛ ሁኔታ ንሮ የነበሩ መሰረታዊ ሸቀጣሸቀጦች ዋጋም በተወሰነ መልኩ መቀነስ እንዳሳየም ነዋሪዎች ገልጸዋል። ሆኖም በአሁኑ ወቅትም በአማራ ክልል አንዳንድ ከተሞች ለምሳሌ በሰቆጣ ከተማና አካባቢው የመብራትና ውሃ አገልግሎት አሁንም እንዳልተመለሰ ነዋሪዎች ይናገራሉ። ከጦርነቱ ጋር ተያይዞ በትግራይ ክልል መሰረታዊ የሚባሉ አገልግሎቶች መብራት፣ ውሃ፣ ስልክና የባንክ አገልግሎቶች አሁንም እንደተቋረጡ ናቸው። ባለፈው ዓመት ጥቅምት መጨረሻ ላይ ትግራይ ውስጥ ተከስቶ ወደ አማራና አፋር ክልሎች የተዛመተው ደም አፋሳሽ ጦርነት ሺዎችን በመቅጠፍና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን በማፈናቀል መጠነ ሰፊ ሰብዓዊ ቀውስ አድርሷል። በኢትዮጵያ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ያሉ ሁሉም ወገኖች በተለያየ ደረጃ እንደ ጦር ወንጀል ሊቆጠሩ የሚችሉ ከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ሕግና የስደተኛ ሕግ ጥሰቶችን መፈፀማቸውን የመብት ተቆርቋሪዎች ያወጧቸው ሪፖርቶች ያመለክታሉ። ከአስራ አራት ወራት በላይ ያስቆጠረው ይህ ጦርነት እንዲቋጭ አሜሪካን ጨምሮ የአፍሪካ ሕብረት እንዲሁም የሕብረቱ የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጎን ኦባሳንጆ እና ሌሎች አጋሮች ጥረት ቢያደርጉም ፍሬ አላፈራም።
ከአዲስ አበባ ኮምቦልቻ ተቋርጦ የነበረው በረራ ሊጀመር ነው ከአዲስ አበባ ወደ ኮምቦልቻ/ደሴ ተቋርጦ የነበረው በረራ ከታኅሣሥ 27/2014 ዓ.ም ሊጀመር መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ። አየር መንገዱ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አክሎ እንዳሰፈረው ከተጠቀሰው ዕለት ጀምሮ በየቀኑ በረራዎች እንደሚኖሩ ነው። የደቡብ ወሎ ከተሞች የሆኑት ደሴና ኮምቦልቻ በህወሓት ኃይሎች ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተከትሎ ነበር አየር መንገዱ ወደ ኮምቦልቻ የሚያደርገውንና ሁለቱን ከተሞች የሚያገለግለውን በረራ አቋርጦ የነበረው። አየር መንገዱ በኮምቦልቻ አየር ማረፊያ የሚያደርጋቸውን የየቀኑ በረራዎች ለሁለት ወራት ያህል አቋርጦ ነበር። ከኮምቦልቻ በተጨማሪ በላሊበላ ለወራት ተቋርጦ የነበረው በረራም በትናንትናው ዕለት ታኅሣሥ 25/2014 ዓ.ም መጀመሩን አየር መንገዱ በተጨማሪ ገልጿል። በህወሓት ቁጥጥር ስር በነበሩ ከተሞች የመብራት፣ ውሃና ስልክ አገልግሎት ተቋርጦ የነበረ ሲሆን መንግሥት እነዚህን ከተሞች በስሩ ማድረጉን ተከትሎ የመብራትና፣ ውሃና ስልክ አገልግሎት ተመልሷል። በበርካታ የአማራ ክልል ከተሞችም እንዲሁ ተቋርጦ የነበረው ኢንተርኔት አገልግሎት (ዳታ) መመለሱንም ነዋሪዎች ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪም የባንክ አገልግሎቶች በበርካታ የአማራ ክልል ከተሞች የተመለሱ ሲሆን ትራንስፖርት በአንዳንድ አካቢዎች መጀመሩም ተነግሯል። የመንግሥት መስሪያ ቤቶችን ጨምሮ ትምህርት ቤቶች መከፈታቸውንም ቢቢሲ ከነዋሪዎች በሰበሰው መረጃ መረዳት ችሏል። ከጦርነቱና ትራንስፖርት መገደብ ጋር ተያይዞ በከፍተኛ ሁኔታ ንሮ የነበሩ መሰረታዊ ሸቀጣሸቀጦች ዋጋም በተወሰነ መልኩ መቀነስ እንዳሳየም ነዋሪዎች ገልጸዋል። ሆኖም በአሁኑ ወቅትም በአማራ ክልል አንዳንድ ከተሞች ለምሳሌ በሰቆጣ ከተማና አካባቢው የመብራትና ውሃ አገልግሎት አሁንም እንዳልተመለሰ ነዋሪዎች ይናገራሉ። ከጦርነቱ ጋር ተያይዞ በትግራይ ክልል መሰረታዊ የሚባሉ አገልግሎቶች መብራት፣ ውሃ፣ ስልክና የባንክ አገልግሎቶች አሁንም እንደተቋረጡ ናቸው። ባለፈው ዓመት ጥቅምት መጨረሻ ላይ ትግራይ ውስጥ ተከስቶ ወደ አማራና አፋር ክልሎች የተዛመተው ደም አፋሳሽ ጦርነት ሺዎችን በመቅጠፍና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን በማፈናቀል መጠነ ሰፊ ሰብዓዊ ቀውስ አድርሷል። በኢትዮጵያ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ያሉ ሁሉም ወገኖች በተለያየ ደረጃ እንደ ጦር ወንጀል ሊቆጠሩ የሚችሉ ከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ሕግና የስደተኛ ሕግ ጥሰቶችን መፈፀማቸውን የመብት ተቆርቋሪዎች ያወጧቸው ሪፖርቶች ያመለክታሉ። ከአስራ አራት ወራት በላይ ያስቆጠረው ይህ ጦርነት እንዲቋጭ አሜሪካን ጨምሮ የአፍሪካ ሕብረት እንዲሁም የሕብረቱ የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጎን ኦባሳንጆ እና ሌሎች አጋሮች ጥረት ቢያደርጉም ፍሬ አላፈራም።
https://www.bbc.com/amharic/news-59864724
2health
በሽታን በሚከላከሉ ክትባቶች መካከል ለምን ልዩነት ተፈጠረ?
የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባት አንድን ሰው እስከ ምን ያህል ጊዜ ከበሽታው ሊከላከል እንደሚችል ማንም እርግጠኛ አይደለም። አንዳንድ ክትባቶች እስከ እድሜ ልክ በሽታን የመከላከል አቅም ሲኖራቸው ሌሎች ደግሞ በተወሰነ ጊዜ የተገደበ የመከላከል አቅምን ያዳብራሉ። ይህ ልዩነት እንዴት ሊፈጠር ቻለ? ይህ ቪዲዮ ምላሽ አለው።
በሽታን በሚከላከሉ ክትባቶች መካከል ለምን ልዩነት ተፈጠረ? የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባት አንድን ሰው እስከ ምን ያህል ጊዜ ከበሽታው ሊከላከል እንደሚችል ማንም እርግጠኛ አይደለም። አንዳንድ ክትባቶች እስከ እድሜ ልክ በሽታን የመከላከል አቅም ሲኖራቸው ሌሎች ደግሞ በተወሰነ ጊዜ የተገደበ የመከላከል አቅምን ያዳብራሉ። ይህ ልዩነት እንዴት ሊፈጠር ቻለ? ይህ ቪዲዮ ምላሽ አለው።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cyrdrpjd6d2o
3politics
መሪዋን ከቀናት በፊት በድምጽ ብልጫ ያነሳችው ፓኪስታን አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር መረጠች
የፓኪስታኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካን እሁድ ዕለት ያለመተማመን ድምጽ [አንድ በሥልጣን ላይ ያለ ግለሰብ በኃላፊነቱ ለመቀጠል ብቁ ነው ወይስ አይደለም በሚል የሚሰጥ ድምጽ] ብልጫ ከሥልጣናቸው ከተነሱ በኋላ የፓኪስታን ፓርላማ ሼህባዝ ሻሪፍን የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ መረጠ። ካንን ከሥልጣን ለማውረድ ሲሰሩ የነበሩ የተቃዋሚዎች ጥምረት መሪ የፓርላማውን አብላጫ ድጋፍ ማግኘት ችለዋል። በመሆኑም ሼህባዝ ሻሪፍ ነሐሴ 2023 ምርጫ እስከሚደረግ ድረስ ሥልጣን ላይ የሚቆይ አዲስ መንግሥት ይመሰርታሉ። የ69 ዓመቱ ካን ከሥልጣናቸው የተነሱት ቀናትን ካስቆጠረና ከብዙ የፖለቲካ ድራማ በኋላ አነስተኛ ድምጽ በማግኘት ነበር። ካን ከዚህ ቀደም ፓርላማውን በመበተን እና በአስቸኳይ ምርጫ እንዲካሄድ በመጠየቅ በእርሳቸው ላይ ሊካሄድ የነበረውን ያለመተማመን ድምጽ አሰጣጥ እንዲዘገይ ሙከራ አድርገው ነበር። ይሁን እንጂ የአገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ድርጊቱ ከሕገ መንግሥቱ ጋር ይቃረናል በማለት የተቃዋሚዎችን አቤቱታ በማጽደቅ ያለመተማመን ድምጽ አሰጣጡ እንዲቀጥል አዝዟል። በመሆኑም ሰኞ ዕለት ሻሪፍ ያለምንም ተቀናቃኝ በፓርላማው የተመረጡ ሲሆን የፓኪስታን 23ኛው ጠቅላይ ሚኒስትር ይሆናሉ። የተቀናቃኝ እጩ ሸህ ማህሙድ ቁረይሺ በካን የሚመራው የፓኪስታን 'ተህሪክ ኢ ኢንሳፍ' ፓርቲ የፓርላማውን ድምጽ እንደማይቀበለው በመግለጽ አዳራሹን ጥሎ መውጣቱን አስታውቀዋል። የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የፓርቲያቸው አብዛኞቹ የምክርቤት አባላት ከድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ ቀደም ብሎ ከምክር ቤት አባልነታቸው ለቀዋል።
መሪዋን ከቀናት በፊት በድምጽ ብልጫ ያነሳችው ፓኪስታን አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር መረጠች የፓኪስታኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካን እሁድ ዕለት ያለመተማመን ድምጽ [አንድ በሥልጣን ላይ ያለ ግለሰብ በኃላፊነቱ ለመቀጠል ብቁ ነው ወይስ አይደለም በሚል የሚሰጥ ድምጽ] ብልጫ ከሥልጣናቸው ከተነሱ በኋላ የፓኪስታን ፓርላማ ሼህባዝ ሻሪፍን የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ መረጠ። ካንን ከሥልጣን ለማውረድ ሲሰሩ የነበሩ የተቃዋሚዎች ጥምረት መሪ የፓርላማውን አብላጫ ድጋፍ ማግኘት ችለዋል። በመሆኑም ሼህባዝ ሻሪፍ ነሐሴ 2023 ምርጫ እስከሚደረግ ድረስ ሥልጣን ላይ የሚቆይ አዲስ መንግሥት ይመሰርታሉ። የ69 ዓመቱ ካን ከሥልጣናቸው የተነሱት ቀናትን ካስቆጠረና ከብዙ የፖለቲካ ድራማ በኋላ አነስተኛ ድምጽ በማግኘት ነበር። ካን ከዚህ ቀደም ፓርላማውን በመበተን እና በአስቸኳይ ምርጫ እንዲካሄድ በመጠየቅ በእርሳቸው ላይ ሊካሄድ የነበረውን ያለመተማመን ድምጽ አሰጣጥ እንዲዘገይ ሙከራ አድርገው ነበር። ይሁን እንጂ የአገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ድርጊቱ ከሕገ መንግሥቱ ጋር ይቃረናል በማለት የተቃዋሚዎችን አቤቱታ በማጽደቅ ያለመተማመን ድምጽ አሰጣጡ እንዲቀጥል አዝዟል። በመሆኑም ሰኞ ዕለት ሻሪፍ ያለምንም ተቀናቃኝ በፓርላማው የተመረጡ ሲሆን የፓኪስታን 23ኛው ጠቅላይ ሚኒስትር ይሆናሉ። የተቀናቃኝ እጩ ሸህ ማህሙድ ቁረይሺ በካን የሚመራው የፓኪስታን 'ተህሪክ ኢ ኢንሳፍ' ፓርቲ የፓርላማውን ድምጽ እንደማይቀበለው በመግለጽ አዳራሹን ጥሎ መውጣቱን አስታውቀዋል። የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የፓርቲያቸው አብዛኞቹ የምክርቤት አባላት ከድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ ቀደም ብሎ ከምክር ቤት አባልነታቸው ለቀዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-61020768
5sports
ፈረንሳይ እና እንግሊዝ ተጋጣሚዎቻቸውን በብቃት በመርታት ሩብ ፍጻሜን ተቀላቀሉ
ኳታር እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም ዋንጫ ትናንት የጥሎ ማለፍ ጨዋታቸውን ያደረጉት ፈረንሳይ እና እንግሊዝ ተጋጣሚዎቻቸውን በመርታት ወደ ቀጣይ ዙር አለፈዋል። ፈረንሳይ ከፖላንድ ተገናኝታ 3 ለ 1 ያሸነፈች ሲሆን እንግሊዝ ደግሞ ሴኔጋልን 3 ለ 0 ረትታለች። ትናንት ታጋጣሚዎቻቸውን በብቃት ያሸነፉት ሁለቱ ቡድኖች በሩብ ፍጻሜው እርስ በርስ የሚገናኙ ሲሆን ገና ከአሁኑ በርካቶች ጨዋታውን ከፍጻሜ በፊት ለዋንጫ የሚደረግ ጨዋታ ነው እያሉት ይገኛል። የፈረንሳይ እና እንግሊዝ ግጥሚያ የፊታችን ቅዳሜ ምሽት 4 ሰዓት ይካሄዳል። 12 ሰዓት ላይ ቀድሞ በተካሄደው ጨዋታ ኦሊቪዬ ጂሩድ ቡድኑን ቀዳሚ ያደረገች ጎል ሲያስቆጥር ጎሏ ደግሞ ለእርሱ የምንግዜም የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ አድርገዋለች። የቀድሞ የአርሰናል እና ቼልሲ የአሁን የኤሲ ሚላን አጥቂው የ36 ዓመቱ ጂሩድ ለአገሩ እስካሁን ድረስ 52 ጎሎችን አስቆጥሯል። ከጁሩድ ጎል በኋላ ትናንት ድንቅ ሆኖ ያመሸው ካሊያን ምባፔ ሁለቱ ቀሪ ጎሎችን አስቆጥሯል። ምባፔ ትናንት ያስቆጠራቸውን ሁለት ጎሎች ጨምሮ በውድድሩ አምስት ጎሎችን በማስቆጠር እየመራ ይገኛል። በምድብ ጨዋታቸው ኳታር እና ኤኳዶርን አሸንፈው ወደ ጥሎ ማለፉ የገቡት ሴኔጋሎች፤ እንግሊዝ ላይ ያልተጠበቀ ውጤት ሊያስመዘግቡ ይችላሉ የሚል ግምት ነበር። ሆኖም ግን ሴኔጋሎች አንድ ግዜ ብቻ ዒላማውን የጠበቀ ሙከራ አድርገው ከተሸነፉ በኋላ ከውድድሩ ተሰናብተዋል። በአሁኑ ወቅት በውድድሩ ላይ ያለችው አፍሪካዊት አገር ሞሮኮ ብቻ ናት። ሞሮኮ ነገ ኃያሏን ስፔንን ትገጥማለች። እንግሊዞች ሴኔጋልን 3 ለ 0 ያሸነፉት ከፍጽም የበላይነት ጋር ነበር። የእንግሊዝን የማሸነፊያ ጎሎች ጆርዳን ሄንደርሰን፣ ሃሪ ኬን እና ቡካዮ ሳካ ሲያስቆጥሩ ኮከብ ሆኖ ያመሸው ግን አማካዩ ጁድ ቤሊንግሃም ነበር። የቦሪሺያ ዶርትመንዱ አማካይ የመጀመሪያውን ጎል አመቻችቶ ከመስጠቱም በላይ እንግሊዝ ሁለተኛውን ጎል ማስቆጠር እንድትችል የመልሶ ማጥቃት ሥራ በበላይነት ሲከወን የነበረው ይህ የ19 ዓመት ወጣት ነበር።
ፈረንሳይ እና እንግሊዝ ተጋጣሚዎቻቸውን በብቃት በመርታት ሩብ ፍጻሜን ተቀላቀሉ ኳታር እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም ዋንጫ ትናንት የጥሎ ማለፍ ጨዋታቸውን ያደረጉት ፈረንሳይ እና እንግሊዝ ተጋጣሚዎቻቸውን በመርታት ወደ ቀጣይ ዙር አለፈዋል። ፈረንሳይ ከፖላንድ ተገናኝታ 3 ለ 1 ያሸነፈች ሲሆን እንግሊዝ ደግሞ ሴኔጋልን 3 ለ 0 ረትታለች። ትናንት ታጋጣሚዎቻቸውን በብቃት ያሸነፉት ሁለቱ ቡድኖች በሩብ ፍጻሜው እርስ በርስ የሚገናኙ ሲሆን ገና ከአሁኑ በርካቶች ጨዋታውን ከፍጻሜ በፊት ለዋንጫ የሚደረግ ጨዋታ ነው እያሉት ይገኛል። የፈረንሳይ እና እንግሊዝ ግጥሚያ የፊታችን ቅዳሜ ምሽት 4 ሰዓት ይካሄዳል። 12 ሰዓት ላይ ቀድሞ በተካሄደው ጨዋታ ኦሊቪዬ ጂሩድ ቡድኑን ቀዳሚ ያደረገች ጎል ሲያስቆጥር ጎሏ ደግሞ ለእርሱ የምንግዜም የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ አድርገዋለች። የቀድሞ የአርሰናል እና ቼልሲ የአሁን የኤሲ ሚላን አጥቂው የ36 ዓመቱ ጂሩድ ለአገሩ እስካሁን ድረስ 52 ጎሎችን አስቆጥሯል። ከጁሩድ ጎል በኋላ ትናንት ድንቅ ሆኖ ያመሸው ካሊያን ምባፔ ሁለቱ ቀሪ ጎሎችን አስቆጥሯል። ምባፔ ትናንት ያስቆጠራቸውን ሁለት ጎሎች ጨምሮ በውድድሩ አምስት ጎሎችን በማስቆጠር እየመራ ይገኛል። በምድብ ጨዋታቸው ኳታር እና ኤኳዶርን አሸንፈው ወደ ጥሎ ማለፉ የገቡት ሴኔጋሎች፤ እንግሊዝ ላይ ያልተጠበቀ ውጤት ሊያስመዘግቡ ይችላሉ የሚል ግምት ነበር። ሆኖም ግን ሴኔጋሎች አንድ ግዜ ብቻ ዒላማውን የጠበቀ ሙከራ አድርገው ከተሸነፉ በኋላ ከውድድሩ ተሰናብተዋል። በአሁኑ ወቅት በውድድሩ ላይ ያለችው አፍሪካዊት አገር ሞሮኮ ብቻ ናት። ሞሮኮ ነገ ኃያሏን ስፔንን ትገጥማለች። እንግሊዞች ሴኔጋልን 3 ለ 0 ያሸነፉት ከፍጽም የበላይነት ጋር ነበር። የእንግሊዝን የማሸነፊያ ጎሎች ጆርዳን ሄንደርሰን፣ ሃሪ ኬን እና ቡካዮ ሳካ ሲያስቆጥሩ ኮከብ ሆኖ ያመሸው ግን አማካዩ ጁድ ቤሊንግሃም ነበር። የቦሪሺያ ዶርትመንዱ አማካይ የመጀመሪያውን ጎል አመቻችቶ ከመስጠቱም በላይ እንግሊዝ ሁለተኛውን ጎል ማስቆጠር እንድትችል የመልሶ ማጥቃት ሥራ በበላይነት ሲከወን የነበረው ይህ የ19 ዓመት ወጣት ነበር።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cnlgk9zex0ro
5sports
የአየር ትራንስፖርት፡ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ የአየር ትራንስፖርተ ዘርፍ ሥራዎች አሁንም አደጋ ላይ ናቸው ተባለ
በኮሮናቫይረስ ምክንያት በመቶ ሺዎቹ የሚቆጠሩ የአየር መጓጓዣ ሥራዎች አሁንም አደጋ ላይ እንደሚገኙ ዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማኅበር አስታወቀ። 290 አየር መንገዶችን የሚወክለው ዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማኅበር የአየር ትራፊክ በ2019 ከነበረው ከ2020 ጋር ሲነጻጸር በ66 በመቶ ይቀንሳል ሲል ተንበያውን አሳውቋል። በማኅበሩ ቅድመ ግምት መሠረት ከወረርሽኙ በኋላ የአየር ትራንስፖርት ዘርፍ ወደቀደመ ደረጃው የሚመለሰው ከአራት ዓመታት በኋላ በ2024 ይሆናል ብሏል። በበርካታ አገራት የኮሮናቫይረስ ሁለተኛ ዙር ስርጭት መከሰቱ እና መንግሥታት አሁንም የጉዞ ክልከላዎችን መጣላቸው ኢንዱስትሪ የሚፈለገውን ያክል ለውጥ እንዳያስመዘግብ ምክንያት ሆኗል ተብሏል። ኮሮናቫይረስ ወደ ወረርሽኝ ደረጃ ከፍ ባለበት ወቅት የአቪዬሽን ኢንዱስትሪው በከፍተኛ መጠን መጎዳቱ ይታወሳል። ግዙፍ አየር መንገዶች፣ አየር ማረፊያዎች እና አስጎብኚ ደርጅቶች በሺህዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞቻቸውን ለመቀነስ መገደዳቸውን አሳውቀው ነበር። "አየር መንገዶች ከመንግሥት ድጋፍ አለማግኘታቸው እና ደንበሮች ዝግ ሆነው መቆየታቸው በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሥራቸውን እንዲያጡ ምክንያት ይሆናል" ብለዋል የማኅበሩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አሌክሳንደር ዲ ጁኒአካ። "መንገደኞች ያለ ስጋት እንዲጓዙ፤ መንግሥታት ደግሞ ደንበሮቻቸውን እንዲከፍቱ ለማበረታታት አየር መንገዶች ተጓዦች ከኮቪድ-19 ነጻ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሰርተፊኬት ይዘው እንዲቀርቡ ማደረግ ይኖርባቸዋል" ብለዋል ዋና ሥራ አስፈጻሚው። ከዚህ ቀደም 3 ሺህ 500 ሠራተኞቹን የቀነሰው ቨርጅን አትላንቲክ አሁንም ተጨማሪ 1 ሺህ 150 ሰዎችን ሊቀንስ መሆኑን አስታውቋል። አየር መንገዱ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው በሥራ ላይ የሚቆይበትን ጊዜ በ18 ወራት ለማራዘም አቅዶ ነው ተብሏል። የዓለማችን ግዙፉ አየር መንገድ አሜሪካን ኤርላይንስ በበኩሉ ባለፈው ወር 19 ሺህ ሠራተኞቹን እንደሚቀንስ አስታውቆ ነበር። አየር መንደጉ በወረርሽኙ ሳቢያ 30 በመቶ ሠራተኞቹን እንዲቀንስ መገደዱ ተጠቅሷል። ሌላኛው የአሜሪካ ግዙፍ አየር መንገድ ዩናይትድ ኤርላይንስ በበኩሉ 36 ሺህ ሠራተኞቹ ሊቀንስ እንደሚችል አስታውቆ ነበር። የጀርመኑ ሉፍታንዛ 22 ሺህ ሠራተኞችን ሊቀንስ እንደሚችል አስታውቋል። ብሪቲሽ ኤርዌይስ ደግሞ 13 ሺህ ሠራተኞችን ቀንሷል።
የአየር ትራንስፖርት፡ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ የአየር ትራንስፖርተ ዘርፍ ሥራዎች አሁንም አደጋ ላይ ናቸው ተባለ በኮሮናቫይረስ ምክንያት በመቶ ሺዎቹ የሚቆጠሩ የአየር መጓጓዣ ሥራዎች አሁንም አደጋ ላይ እንደሚገኙ ዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማኅበር አስታወቀ። 290 አየር መንገዶችን የሚወክለው ዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማኅበር የአየር ትራፊክ በ2019 ከነበረው ከ2020 ጋር ሲነጻጸር በ66 በመቶ ይቀንሳል ሲል ተንበያውን አሳውቋል። በማኅበሩ ቅድመ ግምት መሠረት ከወረርሽኙ በኋላ የአየር ትራንስፖርት ዘርፍ ወደቀደመ ደረጃው የሚመለሰው ከአራት ዓመታት በኋላ በ2024 ይሆናል ብሏል። በበርካታ አገራት የኮሮናቫይረስ ሁለተኛ ዙር ስርጭት መከሰቱ እና መንግሥታት አሁንም የጉዞ ክልከላዎችን መጣላቸው ኢንዱስትሪ የሚፈለገውን ያክል ለውጥ እንዳያስመዘግብ ምክንያት ሆኗል ተብሏል። ኮሮናቫይረስ ወደ ወረርሽኝ ደረጃ ከፍ ባለበት ወቅት የአቪዬሽን ኢንዱስትሪው በከፍተኛ መጠን መጎዳቱ ይታወሳል። ግዙፍ አየር መንገዶች፣ አየር ማረፊያዎች እና አስጎብኚ ደርጅቶች በሺህዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞቻቸውን ለመቀነስ መገደዳቸውን አሳውቀው ነበር። "አየር መንገዶች ከመንግሥት ድጋፍ አለማግኘታቸው እና ደንበሮች ዝግ ሆነው መቆየታቸው በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሥራቸውን እንዲያጡ ምክንያት ይሆናል" ብለዋል የማኅበሩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አሌክሳንደር ዲ ጁኒአካ። "መንገደኞች ያለ ስጋት እንዲጓዙ፤ መንግሥታት ደግሞ ደንበሮቻቸውን እንዲከፍቱ ለማበረታታት አየር መንገዶች ተጓዦች ከኮቪድ-19 ነጻ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሰርተፊኬት ይዘው እንዲቀርቡ ማደረግ ይኖርባቸዋል" ብለዋል ዋና ሥራ አስፈጻሚው። ከዚህ ቀደም 3 ሺህ 500 ሠራተኞቹን የቀነሰው ቨርጅን አትላንቲክ አሁንም ተጨማሪ 1 ሺህ 150 ሰዎችን ሊቀንስ መሆኑን አስታውቋል። አየር መንገዱ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው በሥራ ላይ የሚቆይበትን ጊዜ በ18 ወራት ለማራዘም አቅዶ ነው ተብሏል። የዓለማችን ግዙፉ አየር መንገድ አሜሪካን ኤርላይንስ በበኩሉ ባለፈው ወር 19 ሺህ ሠራተኞቹን እንደሚቀንስ አስታውቆ ነበር። አየር መንደጉ በወረርሽኙ ሳቢያ 30 በመቶ ሠራተኞቹን እንዲቀንስ መገደዱ ተጠቅሷል። ሌላኛው የአሜሪካ ግዙፍ አየር መንገድ ዩናይትድ ኤርላይንስ በበኩሉ 36 ሺህ ሠራተኞቹ ሊቀንስ እንደሚችል አስታውቆ ነበር። የጀርመኑ ሉፍታንዛ 22 ሺህ ሠራተኞችን ሊቀንስ እንደሚችል አስታውቋል። ብሪቲሽ ኤርዌይስ ደግሞ 13 ሺህ ሠራተኞችን ቀንሷል።
https://www.bbc.com/amharic/news-54351583
2health
በኢትዮጵያ በአንድ ቀን ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ተመዘገቡ
በኢትዮጵያ በ24 ሰዓታት ውስጥ በተደረጉ የኮሮናቫይረስ ምርመራዎች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች መገኘታቸው ተገለጸ። በየዕለቱ የሚደረጉ የኮሮናቫይረስ ምርመራዎችን መሠረት በማድረግ ማክሰኞ ታኅሣሥ 13/2014 ዓ. ም በጤና ሚኒስቴር በኩል የወጣው መረጃ እንዳመለከተው 2,323 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል። ይህ አሐዝም ከዚህ በፊት በአንድ ቀን ከተመዘገቡት በጣም ከፍተኛው ነው። በየዕለቱ በ24 ሰዓት ይፋ የተደረጉ ቀደም ያሉ ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት ቫይረሱ የሚገኝባቸው ሰዎች ዕለታዊ አሐዝ ከ500 እስከ 1000 ባለው መካከል የቆየ ነበር። የማክሰኞ ዕለቱ ሪፖርት እንዳመለከተው 2,323 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው በዕለቱ ምርመራ ካደረጉ 10,016 ሰዎች መካከል ነው። እስካሁን በአገሪቱ በወረርሽኙ መያዛቸው በምርመራ የተረጋገጠ ሰዎች አጠቃላይ ቁጥር 379,379 የደረሰ ሲሆን፣ ትናንት ለተመዘገበው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ከፍተኛ ቁጥር ምክንያቱ ምን እንደሆነ የጤና ሚኒስቴር እስካሁን የሰጠው መረጃ የለም። እስካሁን በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ ተይዘው ከነበሩ መካከል 351,168 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን፤ 6,877 ሰዎች በወረርሽኙ ሳቢያ ሕይወታቸው አልፏል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል በዓለም ዙሪያ ክትባት እየተሰጠ ቢሆንም፤ በቅርቡ የተከሰተው ኦሚክሮን የተባለው አዲስ ዓይነት ዝርያ የበሽታውን የመስፋፋት ፍጥነትና አደገኝነት እንዳባባሰው የዓለም ጤና ድርጅት ገልጿል። ይህ መጀመሪያ ላይ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ መገኘቱ የተነገረው ኦሚክሮን በርካታ ሰዎች ላይ እየተገኘ ሲሆን አገራት በሽታውን ለመቆጣጠር ጥብቅ እርምጃ እየወሰዱ ነው። ይህ የወረርሽኙ ዝርያ ኢትዮጵያ ውስጥ ስለመገኘቱ በጤና ባለሥልጣናት በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም።
በኢትዮጵያ በአንድ ቀን ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ተመዘገቡ በኢትዮጵያ በ24 ሰዓታት ውስጥ በተደረጉ የኮሮናቫይረስ ምርመራዎች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች መገኘታቸው ተገለጸ። በየዕለቱ የሚደረጉ የኮሮናቫይረስ ምርመራዎችን መሠረት በማድረግ ማክሰኞ ታኅሣሥ 13/2014 ዓ. ም በጤና ሚኒስቴር በኩል የወጣው መረጃ እንዳመለከተው 2,323 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል። ይህ አሐዝም ከዚህ በፊት በአንድ ቀን ከተመዘገቡት በጣም ከፍተኛው ነው። በየዕለቱ በ24 ሰዓት ይፋ የተደረጉ ቀደም ያሉ ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት ቫይረሱ የሚገኝባቸው ሰዎች ዕለታዊ አሐዝ ከ500 እስከ 1000 ባለው መካከል የቆየ ነበር። የማክሰኞ ዕለቱ ሪፖርት እንዳመለከተው 2,323 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው በዕለቱ ምርመራ ካደረጉ 10,016 ሰዎች መካከል ነው። እስካሁን በአገሪቱ በወረርሽኙ መያዛቸው በምርመራ የተረጋገጠ ሰዎች አጠቃላይ ቁጥር 379,379 የደረሰ ሲሆን፣ ትናንት ለተመዘገበው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ከፍተኛ ቁጥር ምክንያቱ ምን እንደሆነ የጤና ሚኒስቴር እስካሁን የሰጠው መረጃ የለም። እስካሁን በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ ተይዘው ከነበሩ መካከል 351,168 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን፤ 6,877 ሰዎች በወረርሽኙ ሳቢያ ሕይወታቸው አልፏል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል በዓለም ዙሪያ ክትባት እየተሰጠ ቢሆንም፤ በቅርቡ የተከሰተው ኦሚክሮን የተባለው አዲስ ዓይነት ዝርያ የበሽታውን የመስፋፋት ፍጥነትና አደገኝነት እንዳባባሰው የዓለም ጤና ድርጅት ገልጿል። ይህ መጀመሪያ ላይ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ መገኘቱ የተነገረው ኦሚክሮን በርካታ ሰዎች ላይ እየተገኘ ሲሆን አገራት በሽታውን ለመቆጣጠር ጥብቅ እርምጃ እየወሰዱ ነው። ይህ የወረርሽኙ ዝርያ ኢትዮጵያ ውስጥ ስለመገኘቱ በጤና ባለሥልጣናት በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም።
https://www.bbc.com/amharic/news-59730317
3politics
የናንሲ ፔሎሲ ባለቤት ጠጥቶ በማሽከርከር ጥፋተኛ ተባሉ
የአሜሪካ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ ባለቤት ጠጥተው መኪና በማሽከርከር ብሎም ጉዳት በማድረስ ጥፋተኛ ተበለው የአምስት ቀን እስር ተፈረደባቸው። የ82 ዓመቱ ፖል ፔሎሲ በግንቦት ወር ካሊፎርኒያ ናፓ ካውንቲ ውስጥ በመጠጥ ኃይል ውስጥ ሆነው ፖርሽ መኪናቸውን ማጋጨታቸውን እና ጉዳት ማድረሳቸውን አምነዋል። ሚሊየነሩ ፖል ከዐቃቤ ሕግ ጋር በሚደረግ ድርድር አነስተኛ ፍርድ ይቀበሉ እንጂ ወንጀሉ ከዚህም ለከፋ ጥፋት ይዳርጋቸው ነበር። በአሜሪካ ኮንግረስ ውስጥ የዴሞክራቲክ ፓርቲ ከፍተኛ  መሪ የሆኑት ናንሲ ፔሎሲ እ.ኤ.አ. ከ1963 ጀምሮ ከፖል ፔሎሲ ጋር በትዳር ቆይተዋል። ፖል ከዐቃቤ ሕግ ጋር ባደረጉት ድርድር መሠረት ከአምስት ቀኑ በተጨማሪ ሌላ የእስር ቅጣት አይጠብቃቸውም። ከአደጋውበኋላ በእስር ቤት ሁለት ምሽት አሳልፈው መውጣታቸውም ታውቋል። ይህንንም ተከትሎ ከአምስት ቀኑ ቅጣት ላይ የሚቀነስ ይሆናል። ለመልካም ሥነ ምግባር ሁለት ተጨማሪ ቀናት የተቀነሰላቸው ሲሆን የመጨረሻው አንድ ቀን የማኅበረሰብ አገልግሎት በመስጠት ይካካሳል። በፋይናንስ ሥራ ላይ የተሰማሩት ፖል ሌሎች ቅጣቶችም ይጠብቃቸዋል። ለሦስት ዓመት በዕግድ ላይ የሚቆዩ ሲሆን ለሦስት ወር የሚቆይ እና ስለጠጥቶ ማሽከርከር የሚያስተምር ትምህርት ወስደው ማጠናቀቅ ይጠበቅባቸዋል። እንዲሁም 7,000 ዶላር የገንዘብ ቅጣትም ይጠብቃቸዋል። ፖል መንጃ ፈቃዳቸውን ባይነጠቁም የመኪናቸው ሞተር ከመነሳቱ በፊት በትንፋሽ የአልኮል መጠናቸውን የሚለከውን መሳሪያ መጠቀም ይኖርባቸዋል። ናንሲ ፔሎሲ ባለቤታቸው ላይ የቅጣት ውሳኔ በተላለፈበት ወቅት በችሎት አልተገኙም። ፖል ፔሎሲ ኦክቪል ካሊፎርኒያ ውስጥ የረዥም ጊዜ ጓደኛቸው እና የዴሞክራቲክ ፓርቲ ለጋሽ ከሆኑት ግለሰብ ቤት ለቀው በወጡበት ወቅት ነበር አደጋው ያጋጠመው። የፖሊስ መዝገብ እንደሚያመለክተው የ2021 ሞዴል የሆነው ጥቁር ፖርሽ መኪናቸውን በቤታቸው አቅራቢያ ከሚገኝ ጂፕ መኪና ጋር አጋጭተዋል። ሁለቱም ተሽከርካሪዎች ውድመት ደርሶባቸዋል። ፖል ፔሎሲ የካሊፎርኒያ ሀይዌይ ጠባቂ የፖሊስ መኮንኖችን የሚደግፍ የበጎ አድራጎት ድርጅት አባል መሆናቸውን የሚያሳይ ካርድ አደጋውን ተከትሎ በስፍራው ለተገኙ መኮንኖች አሳይተዋል ሲል ፖሊስ ቅሬታውን አቅርቧል። ናንሲ ፔሎሲ በወቅቱ በሌላኛው የአሜሪካ ጥግ ሮድ አይላንድ ውስጥ ብራውን ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የምረቃ ንግግር ለማቅረብ ተጉዘው ነበር። ጽሕፈት ቤታቸውም ይህ “የግል ጉዳይ ነው” በማለት ተጨማሪ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል።
የናንሲ ፔሎሲ ባለቤት ጠጥቶ በማሽከርከር ጥፋተኛ ተባሉ የአሜሪካ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ ባለቤት ጠጥተው መኪና በማሽከርከር ብሎም ጉዳት በማድረስ ጥፋተኛ ተበለው የአምስት ቀን እስር ተፈረደባቸው። የ82 ዓመቱ ፖል ፔሎሲ በግንቦት ወር ካሊፎርኒያ ናፓ ካውንቲ ውስጥ በመጠጥ ኃይል ውስጥ ሆነው ፖርሽ መኪናቸውን ማጋጨታቸውን እና ጉዳት ማድረሳቸውን አምነዋል። ሚሊየነሩ ፖል ከዐቃቤ ሕግ ጋር በሚደረግ ድርድር አነስተኛ ፍርድ ይቀበሉ እንጂ ወንጀሉ ከዚህም ለከፋ ጥፋት ይዳርጋቸው ነበር። በአሜሪካ ኮንግረስ ውስጥ የዴሞክራቲክ ፓርቲ ከፍተኛ  መሪ የሆኑት ናንሲ ፔሎሲ እ.ኤ.አ. ከ1963 ጀምሮ ከፖል ፔሎሲ ጋር በትዳር ቆይተዋል። ፖል ከዐቃቤ ሕግ ጋር ባደረጉት ድርድር መሠረት ከአምስት ቀኑ በተጨማሪ ሌላ የእስር ቅጣት አይጠብቃቸውም። ከአደጋውበኋላ በእስር ቤት ሁለት ምሽት አሳልፈው መውጣታቸውም ታውቋል። ይህንንም ተከትሎ ከአምስት ቀኑ ቅጣት ላይ የሚቀነስ ይሆናል። ለመልካም ሥነ ምግባር ሁለት ተጨማሪ ቀናት የተቀነሰላቸው ሲሆን የመጨረሻው አንድ ቀን የማኅበረሰብ አገልግሎት በመስጠት ይካካሳል። በፋይናንስ ሥራ ላይ የተሰማሩት ፖል ሌሎች ቅጣቶችም ይጠብቃቸዋል። ለሦስት ዓመት በዕግድ ላይ የሚቆዩ ሲሆን ለሦስት ወር የሚቆይ እና ስለጠጥቶ ማሽከርከር የሚያስተምር ትምህርት ወስደው ማጠናቀቅ ይጠበቅባቸዋል። እንዲሁም 7,000 ዶላር የገንዘብ ቅጣትም ይጠብቃቸዋል። ፖል መንጃ ፈቃዳቸውን ባይነጠቁም የመኪናቸው ሞተር ከመነሳቱ በፊት በትንፋሽ የአልኮል መጠናቸውን የሚለከውን መሳሪያ መጠቀም ይኖርባቸዋል። ናንሲ ፔሎሲ ባለቤታቸው ላይ የቅጣት ውሳኔ በተላለፈበት ወቅት በችሎት አልተገኙም። ፖል ፔሎሲ ኦክቪል ካሊፎርኒያ ውስጥ የረዥም ጊዜ ጓደኛቸው እና የዴሞክራቲክ ፓርቲ ለጋሽ ከሆኑት ግለሰብ ቤት ለቀው በወጡበት ወቅት ነበር አደጋው ያጋጠመው። የፖሊስ መዝገብ እንደሚያመለክተው የ2021 ሞዴል የሆነው ጥቁር ፖርሽ መኪናቸውን በቤታቸው አቅራቢያ ከሚገኝ ጂፕ መኪና ጋር አጋጭተዋል። ሁለቱም ተሽከርካሪዎች ውድመት ደርሶባቸዋል። ፖል ፔሎሲ የካሊፎርኒያ ሀይዌይ ጠባቂ የፖሊስ መኮንኖችን የሚደግፍ የበጎ አድራጎት ድርጅት አባል መሆናቸውን የሚያሳይ ካርድ አደጋውን ተከትሎ በስፍራው ለተገኙ መኮንኖች አሳይተዋል ሲል ፖሊስ ቅሬታውን አቅርቧል። ናንሲ ፔሎሲ በወቅቱ በሌላኛው የአሜሪካ ጥግ ሮድ አይላንድ ውስጥ ብራውን ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የምረቃ ንግግር ለማቅረብ ተጉዘው ነበር። ጽሕፈት ቤታቸውም ይህ “የግል ጉዳይ ነው” በማለት ተጨማሪ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cprlrv7q9geo
2health
ኮሮናቫይረስ፡ አንዳንድ ሰዎች ለምን ቶሎ ከኮቪድ-19 አያገግሙም?
ብዙዎች ከኮሮናቫይረስ በቀላሉ፣ በአጭር ጊዜ ያገግማሉ። አንዳንዶች ላይ ግን በሽታው ይበረታል። ለወራት መተንፈስ የሚቸገሩ፣ የሚደክማቸውም አሉ። አጭር ርቀት ተጉዘው በጣም እንደሚደክማቸው የተናገሩ ሰዎች አሉ። በሽታው ዘለግ ላለ ጊዜም ይቆይባቸዋል። ኮቪድ-19 አንዳንዶች ላይ ለወራት የሚቆይ ተጽዕኖ የሚያሳድረው ለምንድን ነው? ለሚለው ገና ግልጽ መልስ አልተገኘም። ኮሮናቫይረስ ለምን ረዥም ጊዜ ይቆያል? በሽታው ረዥም ጊዜ የቆየባቸው ሰዎች በአጠቃላይ ተመሳሳይ ምልክት አያሳዩም። ሆኖም ሁሉም እንደሚደክማቸው ይናገራሉ። ትንፋሽ ማጠር፣ ሳል፣ የጡንቻ ህመም፣ የስሜት ህዋሳት ህመም፣ ራስ ምታት እንዲሁም የልብ፣ ኩላሊት፣ አንጀት እና ሳምባ በሽታ የሚገጥማቸውም አሉ። በተጨማሪም ድብርት፣ ጭንቀት እና በግልጽ ለማሰብ መቸገር ይስተዋላል። ጄድ ግሬይ ክርስቲ “እንዲህ አይነት ድካም ተሰምቶኝ አያውቅም” ስትል ስሜቱን ገልጻለች። ፕ/ር ዴቪድ ስትሬይን “በሽታው አንዳንዶች ላይ እንደሚቆይ አንጠራጠርም” ብለዋል። በሮም ሆስፒታል 143 ታማሚዎች ላይ የተሠራ ጥናት፤ 87 በመቶ የሚሆኑት ከሁል ወራት በኋላ ከምልክቶቹ ቢያንስ ሁለቱ እንደታዩባቸው ይጠቁማል። ከግማሽ በላዩ ይደክማቸዋል። ዩኬ ውስጥ የሚሠራ መተግበሪያ እንደሚያሳየው፤ 12 በመቶ ህሙማን ከ30 ቀናት በኋላ የበሽታው ምልክት ታይቶባቸዋል። ከ50 ሰዎች አንዱ ከ90 ቀናት በኋላ ምልክት አሳይተዋል። ዘለግ ላለ ጊዜ የሚታመሙት በሽታው ከመጀመሪያውም የበረታባቸው ሰዎች ብቻ አይደሉም። ደብሊን ውስጥ የተሠራ ጥናት በበሽታው ከተያዙ ከአሥር ሳምንት በኋላ ድካም የገጠማቸው እንዳሉ ያሳያል። አንድ ሦስተኛው ወደ ሥራ ገበታቸው መመለስ አልቻሉም። ፕ/ር ክሪስ ብራይትሊንግ እንደሚናገሩት፤ ሳምባቸው የተጎዳ ሰዎች ለኒሞኒያ ተጋልጠዋል። ቫይረሱ ከሰውነት ቢወጣም አንዳንድ አካል ላይ እንደሚቀር ባለሙያዎች ያስረዳሉ። ፕ/ር ቲም ስፔክተር “ዘለግ ላለ ጊዜ ተቅማጥ ከተከሰተ ቫይረሱ አንጀት ውስጥ ቀርቷል ማለት ነው። ማሽተት ካቀተ ደግሞ ቫይረሱ በህዋሳት ውስጥ ቀርቷል” ይላሉ። ቫይረሱ ህዋሳትን ሲያጠቃ፤ ሰውነት በሽታውን ለመከላከል ከመጠን በላይ ሲሞክር፤ አካላችን ይጎዳል። በሽታው የሰውነታችንን እንቅስቃሴም ያስተጓጉላል። የደም ዝውውር ላይ ተጽዕኖ ስለሚያሳድር የስኳር መጠናቸውን ለመቆጣጠር የተቸገሩ ህሙማን አሉ። የአንጎል መዋቅር ላይ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል የሚጠቁም መረጃ ቢኖርም እስካሁን አልተረጋገጠም። ህመሙ የተለመደ ነው? በቫይረስ ከተያዙ በኋላ መድከም ወይም ማሳል የተለመደ ነው። ከአሥር ሰዎች አንዱ ለወራት የሚቆይ የህዋሳት ህመም ሊገጥመው ይችላል። እአአ በ1918 ከተከሰተው ወረርሽኝ ወዲህ ጉንፋን የፓርኪንሰን በሽታን የሚመስል ምልክት ያለው ህመም እንደሚያስከትል ታይቷል። ኮቪድ-19ን ተከትሎ የተለያዩ የህመም ምልክቶች ሊስተዋሉ እንደሚችሉ ፕ/ር ክሪስ ያስረዳሉ። “ቫይረሱ የተለያዩ ሰዎችን በተለያየ መንገድ ይጎዳል። ህዋሳት ላይ የሚያስከትለው ችግርም ይለያያል። አንዳንዶች ላይ ሲበረታ፣ ለሌሎች ይቀላል” ይላሉ። ሙሉ በሙሉ ማገገም ይቻላል? ኮሮናቫይረስ ለረዥም ጊዜ የሚቆይባቸው ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ ይመስላል። ሆኖም ግን በሂደት የሚከሰተው አይታወቅም። ፕ/ር ክሪስ ሰዎችን ለ25 ዓመታት ለመከታተል እንደወሰኑና ህመሙ ከአንድ ዓመት በላይ ይቆይባቸዋል ብለው እንደማያምኑ ይናገራሉ። ሆኖም ግን ሰዎች አሁን ቢያገግሙም በሽታው ዘላቂ ተጽዕኖ ሊያሳድርባቸው የሚችልበት እድል አለ። በጣም የሚደክማቸው ሰዎች ስሜቱ ዘለግ ላለ ጊዜ ሊቆይባቸው ይችላል። የዓለም ጤና ድርጅት እንደሚለው ወጣቶችም ሳይቀር ለልብ ህመም ሊጋለጡ ይችላሉ። ስለዚህም ከኮሮናቫይረስ በማገገም ላይ ያሉ ሰዎች ራሳቸው ላይ ጫና እንዳያሳድሩና እንዲያርፉ ይመከራል። አድካሚ ሥራ ካለባቸው በተከታታይ ከማከናወን ይልቅ በተለያየ ሰዓት መተግበር አለባቸው። በተጨማሪም በጠበቁት ፍጥነት ካላገገሙ ወደ ህክምና መስጫ መሄድ ይጠበቅባቸዋል።
ኮሮናቫይረስ፡ አንዳንድ ሰዎች ለምን ቶሎ ከኮቪድ-19 አያገግሙም? ብዙዎች ከኮሮናቫይረስ በቀላሉ፣ በአጭር ጊዜ ያገግማሉ። አንዳንዶች ላይ ግን በሽታው ይበረታል። ለወራት መተንፈስ የሚቸገሩ፣ የሚደክማቸውም አሉ። አጭር ርቀት ተጉዘው በጣም እንደሚደክማቸው የተናገሩ ሰዎች አሉ። በሽታው ዘለግ ላለ ጊዜም ይቆይባቸዋል። ኮቪድ-19 አንዳንዶች ላይ ለወራት የሚቆይ ተጽዕኖ የሚያሳድረው ለምንድን ነው? ለሚለው ገና ግልጽ መልስ አልተገኘም። ኮሮናቫይረስ ለምን ረዥም ጊዜ ይቆያል? በሽታው ረዥም ጊዜ የቆየባቸው ሰዎች በአጠቃላይ ተመሳሳይ ምልክት አያሳዩም። ሆኖም ሁሉም እንደሚደክማቸው ይናገራሉ። ትንፋሽ ማጠር፣ ሳል፣ የጡንቻ ህመም፣ የስሜት ህዋሳት ህመም፣ ራስ ምታት እንዲሁም የልብ፣ ኩላሊት፣ አንጀት እና ሳምባ በሽታ የሚገጥማቸውም አሉ። በተጨማሪም ድብርት፣ ጭንቀት እና በግልጽ ለማሰብ መቸገር ይስተዋላል። ጄድ ግሬይ ክርስቲ “እንዲህ አይነት ድካም ተሰምቶኝ አያውቅም” ስትል ስሜቱን ገልጻለች። ፕ/ር ዴቪድ ስትሬይን “በሽታው አንዳንዶች ላይ እንደሚቆይ አንጠራጠርም” ብለዋል። በሮም ሆስፒታል 143 ታማሚዎች ላይ የተሠራ ጥናት፤ 87 በመቶ የሚሆኑት ከሁል ወራት በኋላ ከምልክቶቹ ቢያንስ ሁለቱ እንደታዩባቸው ይጠቁማል። ከግማሽ በላዩ ይደክማቸዋል። ዩኬ ውስጥ የሚሠራ መተግበሪያ እንደሚያሳየው፤ 12 በመቶ ህሙማን ከ30 ቀናት በኋላ የበሽታው ምልክት ታይቶባቸዋል። ከ50 ሰዎች አንዱ ከ90 ቀናት በኋላ ምልክት አሳይተዋል። ዘለግ ላለ ጊዜ የሚታመሙት በሽታው ከመጀመሪያውም የበረታባቸው ሰዎች ብቻ አይደሉም። ደብሊን ውስጥ የተሠራ ጥናት በበሽታው ከተያዙ ከአሥር ሳምንት በኋላ ድካም የገጠማቸው እንዳሉ ያሳያል። አንድ ሦስተኛው ወደ ሥራ ገበታቸው መመለስ አልቻሉም። ፕ/ር ክሪስ ብራይትሊንግ እንደሚናገሩት፤ ሳምባቸው የተጎዳ ሰዎች ለኒሞኒያ ተጋልጠዋል። ቫይረሱ ከሰውነት ቢወጣም አንዳንድ አካል ላይ እንደሚቀር ባለሙያዎች ያስረዳሉ። ፕ/ር ቲም ስፔክተር “ዘለግ ላለ ጊዜ ተቅማጥ ከተከሰተ ቫይረሱ አንጀት ውስጥ ቀርቷል ማለት ነው። ማሽተት ካቀተ ደግሞ ቫይረሱ በህዋሳት ውስጥ ቀርቷል” ይላሉ። ቫይረሱ ህዋሳትን ሲያጠቃ፤ ሰውነት በሽታውን ለመከላከል ከመጠን በላይ ሲሞክር፤ አካላችን ይጎዳል። በሽታው የሰውነታችንን እንቅስቃሴም ያስተጓጉላል። የደም ዝውውር ላይ ተጽዕኖ ስለሚያሳድር የስኳር መጠናቸውን ለመቆጣጠር የተቸገሩ ህሙማን አሉ። የአንጎል መዋቅር ላይ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል የሚጠቁም መረጃ ቢኖርም እስካሁን አልተረጋገጠም። ህመሙ የተለመደ ነው? በቫይረስ ከተያዙ በኋላ መድከም ወይም ማሳል የተለመደ ነው። ከአሥር ሰዎች አንዱ ለወራት የሚቆይ የህዋሳት ህመም ሊገጥመው ይችላል። እአአ በ1918 ከተከሰተው ወረርሽኝ ወዲህ ጉንፋን የፓርኪንሰን በሽታን የሚመስል ምልክት ያለው ህመም እንደሚያስከትል ታይቷል። ኮቪድ-19ን ተከትሎ የተለያዩ የህመም ምልክቶች ሊስተዋሉ እንደሚችሉ ፕ/ር ክሪስ ያስረዳሉ። “ቫይረሱ የተለያዩ ሰዎችን በተለያየ መንገድ ይጎዳል። ህዋሳት ላይ የሚያስከትለው ችግርም ይለያያል። አንዳንዶች ላይ ሲበረታ፣ ለሌሎች ይቀላል” ይላሉ። ሙሉ በሙሉ ማገገም ይቻላል? ኮሮናቫይረስ ለረዥም ጊዜ የሚቆይባቸው ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ ይመስላል። ሆኖም ግን በሂደት የሚከሰተው አይታወቅም። ፕ/ር ክሪስ ሰዎችን ለ25 ዓመታት ለመከታተል እንደወሰኑና ህመሙ ከአንድ ዓመት በላይ ይቆይባቸዋል ብለው እንደማያምኑ ይናገራሉ። ሆኖም ግን ሰዎች አሁን ቢያገግሙም በሽታው ዘላቂ ተጽዕኖ ሊያሳድርባቸው የሚችልበት እድል አለ። በጣም የሚደክማቸው ሰዎች ስሜቱ ዘለግ ላለ ጊዜ ሊቆይባቸው ይችላል። የዓለም ጤና ድርጅት እንደሚለው ወጣቶችም ሳይቀር ለልብ ህመም ሊጋለጡ ይችላሉ። ስለዚህም ከኮሮናቫይረስ በማገገም ላይ ያሉ ሰዎች ራሳቸው ላይ ጫና እንዳያሳድሩና እንዲያርፉ ይመከራል። አድካሚ ሥራ ካለባቸው በተከታታይ ከማከናወን ይልቅ በተለያየ ሰዓት መተግበር አለባቸው። በተጨማሪም በጠበቁት ፍጥነት ካላገገሙ ወደ ህክምና መስጫ መሄድ ይጠበቅባቸዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-54441793
5sports
91 ለ 1 በማሸነፍ የታገደው የአፍሪካ እግር ኳስ ክለብ ወደ ውድድር እንዲገባ ተፈቀደለት
በሴራሊዮን የሚገኘው የሁለተኛ ደረጃ የእግር ኳስ ክለብ፣ ገልፍ ኮኖ 91 ለ 1 በሆነ ውጤት በተጠናቀቀው የእግር ኳስ ጨዋታ የማጭበርበር  ወንጀል ምርመራ እየተደረገበት ቢሆንም ወደ አገሪቱ ፕሪሚየር ሊግ ለማለፍ በሚደረገው ውድድር እንዲሳተፍ ተፈቀደለት። ገልፍ ኮኖ የተሰኘው ክለብ ኮኪማ ሌባኖን በማሸነፍ ወደ ሱፐር 10 የፕሪሚየር ሊግ ምዕራፍ ማለፉን ሲያረጋግጥ የቅርብ ተፎካካሪው ካሁንላ ሬንጀርስ እሁድ በተደረገው የመልስ ጨዋታ በሉምቤቡ ዩናይትድ 1 ለ 0 ተሸንፏል። ባለፈው ወር ካሁንላ ሌንጀርስ ሉምቤቤ ዩናይትድን 95 ለ0 በማሸነፍ ገልፍ ኮኖ ደግሞ ኮኪማ ሌባኖንን 91 ለ 1 በማሸነፍ አለም አቀፍ መነጋገሪያ ሆነው ነበር። በነዚህ ሁለት ጨዋታዎች 187 ጎሎች በመቆጠራቸው የሴራሊዮን እግር ኳስ ማህበር በጨዋታ ማጭበርበር ክስ ሰርዟቸዋል እንዲሁም ምርመራም ተከፍቷባቸዋል። ሁለቱ ቡድኖች ከፍተኛ ወደሆነው የአገሪቱ ፕሪሚየር ሊግ ለማለፍ ተጋጣሚዎቻቸውን ማመን በማይቻል ውጤት ቢያሸንፉም የሁለቱም ጨዋታ ውጤቶች ተሰርዘዋል። በነዚህ ጨዋታዎች የተሳተፉት አራት ቡድኖች በጨዋታዎቹ አዘጋጆች አካላት ታግደው ነበር። ይሁንና እገዳው የጨዋታው አዘጋጅ የሆነውና የሴራሊዮን እግር ኳስ ማህበር አካል የሆነው የምስራቃዊ ክልል የእግር ኳስ ማህበር ባለፈው ሳምንት ሐሙስ የተነሳ ሲሆን ይህም የዲሲፒሊን ኮሚቴው ያደረገው ጥናት ተከትሎ ነው። ጥናቱ እስካሁን ለህዝብ ይፋ አልሆነም። “ከምስራቃዊ ክልል የእግር ኳስ ማህበር ባገኘነው ሪፖርት መሰረት የፕሪሚየር ሊጉን የጊዜ ሰሌዳ እንዳያልፍ ግጥሚያዎቹ እንዲደገሙ ፈቅደናል” ሲሉ የሴራሊዮን እግር ኳስ ማህበር ፕሬዝዳንት ቶማስ ዳዲ ብሪማ ለቢቢሲ ስፖርት አፍሪካ ተናግረዋል። “ነገር ግን ይህ ማለት ምርመራውን ዘግተነዋል ማለት አይደለም። ፊፋ እና ካፍ (የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን) እንዲመለከቱት እና በዚያም መሰረት እንዲመክሩበት ልከናል” ብለዋል። “ ገልፍ በሱፐር 10 ውስጥ እንዲሳተፍ መፈቀዱን አረጋግጣለሁ” ብለዋል ሆኖም ማህበሩ የቀደመ ውጤቱን በተግባር የማይቻል እንደሆነም በዚህ ወቅት አስምሯል። “ማንም ሰው ቢሆን ይህንን ውጤት ከቁም ነገር አይወስደውም። በማንኛውም መስፈርት በ90 ደቂቃ ውስጥ 90 ግቦች ሊቆጠሩ አይችሉም ብሏል። ማህበሩ ከአራቱም ክለቦች የተውጣጡ ተጫዎቾችን እንዲሁም ኃላፊዎችን እንደሚመረምሩ ተናግረዋል። ሆኖም ገልፍ በሚቀጥለው የውድድር ዘመን በምዕራብ አፍሪካ ፕሪሚየር ሊግ ውስጥ ለመግባት ቅዳሜ በሱፐር 10 የመጀመሪያ ግጥሚያው ላምቦይን ይገጥማል።
91 ለ 1 በማሸነፍ የታገደው የአፍሪካ እግር ኳስ ክለብ ወደ ውድድር እንዲገባ ተፈቀደለት በሴራሊዮን የሚገኘው የሁለተኛ ደረጃ የእግር ኳስ ክለብ፣ ገልፍ ኮኖ 91 ለ 1 በሆነ ውጤት በተጠናቀቀው የእግር ኳስ ጨዋታ የማጭበርበር  ወንጀል ምርመራ እየተደረገበት ቢሆንም ወደ አገሪቱ ፕሪሚየር ሊግ ለማለፍ በሚደረገው ውድድር እንዲሳተፍ ተፈቀደለት። ገልፍ ኮኖ የተሰኘው ክለብ ኮኪማ ሌባኖን በማሸነፍ ወደ ሱፐር 10 የፕሪሚየር ሊግ ምዕራፍ ማለፉን ሲያረጋግጥ የቅርብ ተፎካካሪው ካሁንላ ሬንጀርስ እሁድ በተደረገው የመልስ ጨዋታ በሉምቤቡ ዩናይትድ 1 ለ 0 ተሸንፏል። ባለፈው ወር ካሁንላ ሌንጀርስ ሉምቤቤ ዩናይትድን 95 ለ0 በማሸነፍ ገልፍ ኮኖ ደግሞ ኮኪማ ሌባኖንን 91 ለ 1 በማሸነፍ አለም አቀፍ መነጋገሪያ ሆነው ነበር። በነዚህ ሁለት ጨዋታዎች 187 ጎሎች በመቆጠራቸው የሴራሊዮን እግር ኳስ ማህበር በጨዋታ ማጭበርበር ክስ ሰርዟቸዋል እንዲሁም ምርመራም ተከፍቷባቸዋል። ሁለቱ ቡድኖች ከፍተኛ ወደሆነው የአገሪቱ ፕሪሚየር ሊግ ለማለፍ ተጋጣሚዎቻቸውን ማመን በማይቻል ውጤት ቢያሸንፉም የሁለቱም ጨዋታ ውጤቶች ተሰርዘዋል። በነዚህ ጨዋታዎች የተሳተፉት አራት ቡድኖች በጨዋታዎቹ አዘጋጆች አካላት ታግደው ነበር። ይሁንና እገዳው የጨዋታው አዘጋጅ የሆነውና የሴራሊዮን እግር ኳስ ማህበር አካል የሆነው የምስራቃዊ ክልል የእግር ኳስ ማህበር ባለፈው ሳምንት ሐሙስ የተነሳ ሲሆን ይህም የዲሲፒሊን ኮሚቴው ያደረገው ጥናት ተከትሎ ነው። ጥናቱ እስካሁን ለህዝብ ይፋ አልሆነም። “ከምስራቃዊ ክልል የእግር ኳስ ማህበር ባገኘነው ሪፖርት መሰረት የፕሪሚየር ሊጉን የጊዜ ሰሌዳ እንዳያልፍ ግጥሚያዎቹ እንዲደገሙ ፈቅደናል” ሲሉ የሴራሊዮን እግር ኳስ ማህበር ፕሬዝዳንት ቶማስ ዳዲ ብሪማ ለቢቢሲ ስፖርት አፍሪካ ተናግረዋል። “ነገር ግን ይህ ማለት ምርመራውን ዘግተነዋል ማለት አይደለም። ፊፋ እና ካፍ (የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን) እንዲመለከቱት እና በዚያም መሰረት እንዲመክሩበት ልከናል” ብለዋል። “ ገልፍ በሱፐር 10 ውስጥ እንዲሳተፍ መፈቀዱን አረጋግጣለሁ” ብለዋል ሆኖም ማህበሩ የቀደመ ውጤቱን በተግባር የማይቻል እንደሆነም በዚህ ወቅት አስምሯል። “ማንም ሰው ቢሆን ይህንን ውጤት ከቁም ነገር አይወስደውም። በማንኛውም መስፈርት በ90 ደቂቃ ውስጥ 90 ግቦች ሊቆጠሩ አይችሉም ብሏል። ማህበሩ ከአራቱም ክለቦች የተውጣጡ ተጫዎቾችን እንዲሁም ኃላፊዎችን እንደሚመረምሩ ተናግረዋል። ሆኖም ገልፍ በሚቀጥለው የውድድር ዘመን በምዕራብ አፍሪካ ፕሪሚየር ሊግ ውስጥ ለመግባት ቅዳሜ በሱፐር 10 የመጀመሪያ ግጥሚያው ላምቦይን ይገጥማል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cyxk9pwnklro
0business
ለወንዶች የተተወ የሚመስለውን ሥራ የደፈረችው ሴት
የታክሲ ረዳትነት እየሰራች መንጃ ፈቃድ አወጣች። እንዳሰበችው ስራ ስላላገኘች በቀን ሰራተኝነት ተቀጠረች። በኋላም የከባድ መኪና አሽከርካሪ በመሆን በየበረሃው ሰርታለች።
ለወንዶች የተተወ የሚመስለውን ሥራ የደፈረችው ሴት የታክሲ ረዳትነት እየሰራች መንጃ ፈቃድ አወጣች። እንዳሰበችው ስራ ስላላገኘች በቀን ሰራተኝነት ተቀጠረች። በኋላም የከባድ መኪና አሽከርካሪ በመሆን በየበረሃው ሰርታለች።
https://www.bbc.com/amharic/50832947
2health
የወባ በሽታ መከላከያ ክትባት ላይ የተደረገ ሙከራ ከፍተኛ ውጤት አሳየ
በኦክስፎርድ የኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች እና በቡርኪናፋሶ ሳይንቲስቶች በጋራ የተሰራ አዲስ የወባ በሽታ መከላከያ ክትባት በተደረገለት ሙከራ ውጤታማ መሆነ ተገለጸ። በክትባቱ ላይ በተደረጉት መጀመሪያ ሙከራዎች 77 በመቶ በሆነ ውጤት ስኬታማ መሆኑ የተነገረ ሲሆን፤ ይህም አሁን ለህክምና ከሚውሉ መድኃኒቶች አንጻር ውጤታማነቱ በእጅጉ የላቀ ነው ተብሏል። የህክምና ጉዳዮች መጽሔት በሆነው 'ላንሴት' ላይ የታተመው የጥናቱ ውጤት 450 ከቡርኪናፋሶ የተወጣጡ ህጻናት የተሳተፉበት ሲሆን ከዚህ በኋላ በርከት ያሉ ሰዎች የሚሳተፉበት ሙከራ ይደረግበታል። በቀጣዩ የሙከራ ሂደትም 4,800 ህጻናት የሚሳተፉ ሲሆን እነዚህም ከቡርኪናፋሶ፣ ከማሊ እና ከኬንያ ናቸው። "ይህ ሙከራ በጣም አስደሳች የሆነ ውጤታማነት ነው ያሳየው። ክትባቱ ከዚህ በፊት ከነበሩ ህክምናዊች አንጻር የተሻለ የመከላከል ብቃት አሳይቷል። "በመቀጠል የምናካሂዳቸውን ሁለተኛና ሦስተኛ ዙር ሙከራዎች እየተጠባበቅን ነው። በእነዚህ ሙከራዎች በርከት ያሉ ሰዎች የሚሳተፉ ሲሆን በስፋት ቢመረት ምን አይነት ውጤት እንደሚኖረው ለማወቅ ይረዳናል" ብለዋል በቡርኪናፋሶ የጤና ሳይንስ ተቋም ዳይሬክተር የሆኑት ሃሊዶ ቲንቶ። ለወባ በሽታ የሚሆን ክትባት ማግኘት በህክምና ምርምር ውስጥ እግጅ ትልቅ ዜና ነው የሚሆነው። ሙከራው በስኬት የሚጠናቀቅ ከሆነ ትልቅ ግኝት እንደሚሆን ይጠበቃል። የወባ በሽታ በዓመት ከ400 ሺህ በላይ ሰዎችን የሚገድል ሲሆን አብዛኛዎቹ ከሰሀራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ አገራት ውስጥ የሚኖሩ ህጻናት ናቸው። በአሁኑ ጊዜ ለወባ በሽታ የሚሆን አንድ ክትባት ያለ ሲሆን ውጤታማነቱ ደግሞ 50 በመቶ ብቻ ነው። በአዲሱ ክትባት የመጀመሪያ ዙር ሙከራ ላይ 77 በመቶ ውጤታማነት የታየ ሲሆን በሌሎች አገራትም ላይ ለመሞከር ታቅዷል። በጊዜ ብዛት ደግሞ ቢያንስ በአራት የአፍሪካ አገራት ውስጥ ይሞከራል። በሙከራው የሚሳተፉት 5 ሺህ የሚሆኑ ህጻናት ደግሞ እድሜያቸው ከሦስት ዓመት በታች የሆኑ ናቸው። አሁን በሙከራ ላይ የሚገኘው አዲሱ ክትባት ሙሉ ፈቃድ አላገኘም። ነገር ግን ውጤታማነቱ በሙከራዎች በተገቢ ሁኔታ የሚረጋገጥ ከሆነ የበርካቶችን ህይወት የማትረፍ ትልቅ አቅም አለው ተብሏል።
የወባ በሽታ መከላከያ ክትባት ላይ የተደረገ ሙከራ ከፍተኛ ውጤት አሳየ በኦክስፎርድ የኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች እና በቡርኪናፋሶ ሳይንቲስቶች በጋራ የተሰራ አዲስ የወባ በሽታ መከላከያ ክትባት በተደረገለት ሙከራ ውጤታማ መሆነ ተገለጸ። በክትባቱ ላይ በተደረጉት መጀመሪያ ሙከራዎች 77 በመቶ በሆነ ውጤት ስኬታማ መሆኑ የተነገረ ሲሆን፤ ይህም አሁን ለህክምና ከሚውሉ መድኃኒቶች አንጻር ውጤታማነቱ በእጅጉ የላቀ ነው ተብሏል። የህክምና ጉዳዮች መጽሔት በሆነው 'ላንሴት' ላይ የታተመው የጥናቱ ውጤት 450 ከቡርኪናፋሶ የተወጣጡ ህጻናት የተሳተፉበት ሲሆን ከዚህ በኋላ በርከት ያሉ ሰዎች የሚሳተፉበት ሙከራ ይደረግበታል። በቀጣዩ የሙከራ ሂደትም 4,800 ህጻናት የሚሳተፉ ሲሆን እነዚህም ከቡርኪናፋሶ፣ ከማሊ እና ከኬንያ ናቸው። "ይህ ሙከራ በጣም አስደሳች የሆነ ውጤታማነት ነው ያሳየው። ክትባቱ ከዚህ በፊት ከነበሩ ህክምናዊች አንጻር የተሻለ የመከላከል ብቃት አሳይቷል። "በመቀጠል የምናካሂዳቸውን ሁለተኛና ሦስተኛ ዙር ሙከራዎች እየተጠባበቅን ነው። በእነዚህ ሙከራዎች በርከት ያሉ ሰዎች የሚሳተፉ ሲሆን በስፋት ቢመረት ምን አይነት ውጤት እንደሚኖረው ለማወቅ ይረዳናል" ብለዋል በቡርኪናፋሶ የጤና ሳይንስ ተቋም ዳይሬክተር የሆኑት ሃሊዶ ቲንቶ። ለወባ በሽታ የሚሆን ክትባት ማግኘት በህክምና ምርምር ውስጥ እግጅ ትልቅ ዜና ነው የሚሆነው። ሙከራው በስኬት የሚጠናቀቅ ከሆነ ትልቅ ግኝት እንደሚሆን ይጠበቃል። የወባ በሽታ በዓመት ከ400 ሺህ በላይ ሰዎችን የሚገድል ሲሆን አብዛኛዎቹ ከሰሀራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ አገራት ውስጥ የሚኖሩ ህጻናት ናቸው። በአሁኑ ጊዜ ለወባ በሽታ የሚሆን አንድ ክትባት ያለ ሲሆን ውጤታማነቱ ደግሞ 50 በመቶ ብቻ ነው። በአዲሱ ክትባት የመጀመሪያ ዙር ሙከራ ላይ 77 በመቶ ውጤታማነት የታየ ሲሆን በሌሎች አገራትም ላይ ለመሞከር ታቅዷል። በጊዜ ብዛት ደግሞ ቢያንስ በአራት የአፍሪካ አገራት ውስጥ ይሞከራል። በሙከራው የሚሳተፉት 5 ሺህ የሚሆኑ ህጻናት ደግሞ እድሜያቸው ከሦስት ዓመት በታች የሆኑ ናቸው። አሁን በሙከራ ላይ የሚገኘው አዲሱ ክትባት ሙሉ ፈቃድ አላገኘም። ነገር ግን ውጤታማነቱ በሙከራዎች በተገቢ ሁኔታ የሚረጋገጥ ከሆነ የበርካቶችን ህይወት የማትረፍ ትልቅ አቅም አለው ተብሏል።
https://www.bbc.com/amharic/news-56827450
3politics
ምርጫ 2013 ፡ ኦፌኮ እና ባልደራስ በመጪው ምርጫ የመሳተፋቸው ነገር እንደሚያሳስባቸው ገለጹ
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) እና የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) አመራሮች አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ወደ ምርጫ መግባት ያሳስበናል ሲሉ ለቢቢሲ ተናገሩ። ሁለቱ ፓርቲዎች ይህንን ያሉት ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዚህ ዓመት ለሚካሄደው አገራዊና ክልላዊ ምርጫ ማስፈጸሚያ የሚሆን ረቂቅ የጊዜ ሠሌዳን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ነው። የኦፌኮ የጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጥሩነህ ገምታ፤ "ከከፍተኛ እስከ መካከለኛ የፓርቲያችን አመራሮች መታሰር እና የአገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ ለምርጫ የምናደርገውን ዝግጅት አስቸጋሪ ያደርገዋል" ሲሉ ተናግረዋል። በተመሳሳይ የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ቢሮ ኃላፊ አቶ ገለታው ዘለቀ፤ የባልደራስ አመራሮች በተራዘመ የፍርድ ቤት ቀጠሮ ላይ እንዳሉ በመጥቀስ "የምንገባበት ምርጫ እጅግ አሳስቦናል" ብለዋል። የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቃል አቀባይ ሶሊያና ሽመልስ ከቀናት በፊት ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ "ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ምርጫው መካሄድ አለበት ነው ያሉት። ምርጫው ከመካሄዱ በፊት ስጋት ይሆናል ያሉት ሁለት ነገር ነው። አንዱ የአገሪቱ የጸጥታ ችግር ነው። አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች ደግሞ ቢሯቸው እንደሚዘጋ እና አባሎቻቸው ችግር እንደሚደርስባቸው ተናግረዋል" ብለዋል። ፓርቲዎች ለሚያነሷቸው መሰል ችግሮች መፍትሄ መስጠት የሚችለው የመንግሥት ሥራ አስፈጻሚ አካል እንጂ ምርጫ ቦርድ አለመሆኑንም ተናግረዋል። የምርጫ ቦርድ ረቂቅ የምርጫ የጊዜ ሠሌዳውን አርብ እለት ይፋ ባደረገበት መድረክ ላይ የብልጽግና ፓርቲን ወክለው የተሳተፉት አቶ ዛዲግ አብረሃ ተፎካካሪ ፓርቲዎች እየደረሰብን ነው ያሉት ጫናን በተመለከተ ምላሽ ሰጥተው ነበር። በዚህም መሰረት የቀረቡ ቅሬታዎች ላይ ማጣራት እንደተደረገና አንዳንዶቹ የተጋነኑ መሆናቸውን ገልጸው፤ የቀረቡትን አቤቱታዎችን ፓርቲያቸው እንደማያጣጥላቸውና ለማረም አስፈላጊውን ነገሮች ሁሉ እንደማያደርግ እንዲሁም ቀጣዩ ምርጫ ትክክለኛ ፉክክር የሚደረግበት እንዲሆን እንደሚሰሩ ተናግረዋል። በዚህ ዓመት ለሚካሄደው ስድስተኛው ዙር አገራዊና ክልላዊ አጠቃላይ ምርጫ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ በተደረገው ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት የድምጽ መስጫው ቀን ግንቦት 28 እና ሰኔ 5 መሆኑ ገልጿል። አቶ ጥሩነህ በርካታ አባሎቻቸው መታሰራቸውን፣ የቀሩትም ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው መሆኑን እና በዞንና በወረዳ ደረጃ ያሉ ጽህፈት ቤቶቻቸው መዘጋታቸውን በመጥቀስ፤ "በምርጫው ለመሳተፍ ፍላጎት ቢኖረንም በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንገኛለን" ብለዋል። ይህንንም ስጋታቸውን ከዚህ ቀደም መግለጫ በማውጣት ማስታወቃቸውን አስታውሰዋል። ትናንት ምርጫ ቦርድ ባካሄደው ስብሰባ ላይም ተገኝተው ይህንኑ ስጋታቸውን ማስረዳታቸውን የተናገሩት አቶ ጥሩነህ፤ "ችግሮችን ለማስተካከል ጥረት እናደርጋለን" የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል። "ነገር ግን አንዳንድ ከአቅማቸው በላይ የሆኑ ነገሮች መኖራቸውንም ተገንዝበናል" ብለዋል አቶ ጥሩነህ። እንደ ኦፌኮ እስካሁን በምርጫው አንሳተፍም የሚል ውሳኔ ላይ ባይደርሱም፤ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ በሚያስችል አቅም ላይ አለመሆናቸውን ግን አስረግጠው ተናግረዋል። ለዚህም የጽህፈት ቤቶቻቸው መዘጋት፣ የአባላቶቻቸው እስር፣ ስደትና ማስፈራሪያ እንዲሁም በአገሪቷ በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ችግሮችን እንደ ምክንያት ጠቅሰዋል። "በዚህ ሁኔታስ መንግሥትና ምርጫ ቦርድ ምርጫ ማካሄድ ይችላሉ ወይ?" ሲሉም ጠይቀዋል። የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሕገ መንግሥትና ጸረ ሽብር ጉዳዮች ወንጀል ችሎት የባልደራስ ፓርቲ ሊቀመንበር በሆኑት በአቶ እስክንድር ነጋ ላይ ዐቃቤ ሕግ ምስክር እንዲያሰማ ለመጋቢት 29 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል። በትናንቱ የፍርድ ቤት ውሎ ማዘናቸውን የገለፁት የፓርቲው ቢሮ ኃላፊ አቶ ገለታው፤ "በእነአቶ እስክንድር ነጋ ላይ የተሰጠው ቀጠሮ ተሰሚነት ያላቸው ሰዎች በውድድሩ ውስጥ ሳይገቡ መንግሥት ብቻውን ሮጦ 'አሸናፊ ነኝ' ለማለት የተደረገ ይመስላል" ሲሉ ኮንነዋል። አቶ ገለታው "ምርጫው በህወሓት ዘመን የተለመደ የምርጫ ዓይነት ሊሆን ነው" በማለትም በእነርሱ በኩል ተስፋ እየታያቸው እንዳልሆነ ተናግረዋል። "አባላቶቻችን ወከባ አለባቸው። መንግሥት በየጊዜው ምህዳሩን እያጠበበ ነው፤ ባልሰፋ ምህዳር ውስጥ ታሪካዊ ምርጫ ሊደረግ እንደማይችል እያረጋገጠ ነው" ሲሉም ወቅሰዋል። ይህ እንደ ፓርቲ ብቻም ሳይሆን እንደ አንድ ግለሰብ እንደሚያሳስባቸውም አልሸሸጉም። አቶ ገለታው "ይህ ምርጫ እንደ በፊቱ ተጭበርብሮ እንራመድ ቢባል የማያራምድ ሕዝብ የተነሳበት ወቅት ስለሆነ፤ ድህረ ምርጫ አገሪቷን ወደ ብጥብጥ እንዳይወስዳት ያሳስባል" ብለዋል። መንግሥት ሁኔታዎችን በፍጥነት ማስተካከል ካልቻለም ምርጫው ታሪካዊ መሆኑ ቀርቶ፤ አደጋዎችን ይዞ ሊመጣ እንደሚችል ስጋታቸውን ገልፀዋል። የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቃል አቀባይ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ "ፓርቲዎች ችግር ገጥሞናል ባሉት ጉዳይ ላይ ለክልል አስተዳደር፣ ለፖሊስ ኮሚሽን ወይም ሌላ ጉዳዩ ለሚመለከተው አካል ቦርዱ ያሳውቃል" በማለት የመሥሪያ ቤታቸው የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት የሚያደርገውን ጥረት አስረድተዋል። በዚህም መሰረት ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች አቤቱታ ካላቸው ለቦርዱ በጽሑፍ እንዲያቀርቡ ተጠይቆ፤ 11 ፓርቲዎች የሚገጥማቸውን ችግር ለቦርዱ ማሳወቃቸውን የጠቀሱት ሶሊያና፤ ቦርዱም ለእነዚህ ችግሮች መፍትሔ ያስፈልጋል ብሎ ለመንግሥት ማሳወቁን ገልጸዋል። በየክልሉ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች የሚገጥማቸውን ችግር በተመለከተ ከገዢው ፓርቲ፣ መንግሥትና ምርጫ ቦርድ ጋር የሦስትዮሽ ውይይት የሚካሄድበት አሠራር መዘርጋቱንም ዳይሬክተሯ ተናግረዋል። የኦፌኮ እና ባልደራስ ፓርቲዎች አመራር እና አባላት የሆኑት ጀዋር መሐመድ፣ በቀለ ገርባ እንዲሁም እስክንድር ነጋ፣ አስቴር ስዩምና ስንታሁ ቸኮል በሽብር ወንጀል ተከሰው በእስር እንደሚገኙ ይታወቃል። ምርጫ ቦርድ ፓርቲዎች ከየካቲት 8 ጀምሮ የእጩዎች ምዝገባ እንደሚያከናውኑ እና የምረጡኝ ቅስቀሳ እንደሚያደርጉ በትናንትናው ዕለት ገልጿል። ከየካቲት 22 እስከ መጋቢት 21 ድረስ ደግሞ የመራጮች ምዝገባ የሚከናወን ይሆናል። ከዚህ በተጨማሪም የአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች የድምጽ መስጫ ቀን በአንድ ሳምንት ዘግይቶ ሰኔ 5/2013 ዓ.ም እንደሚከናወን አስታውቋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቀጣዩ አገራዊ ምርጫ እስከ 50 ሚሊዮን የሚደርሱ መራጮች ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠብቅ ማስታወቁ ይታወሳል።
ምርጫ 2013 ፡ ኦፌኮ እና ባልደራስ በመጪው ምርጫ የመሳተፋቸው ነገር እንደሚያሳስባቸው ገለጹ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) እና የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) አመራሮች አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ወደ ምርጫ መግባት ያሳስበናል ሲሉ ለቢቢሲ ተናገሩ። ሁለቱ ፓርቲዎች ይህንን ያሉት ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዚህ ዓመት ለሚካሄደው አገራዊና ክልላዊ ምርጫ ማስፈጸሚያ የሚሆን ረቂቅ የጊዜ ሠሌዳን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ነው። የኦፌኮ የጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጥሩነህ ገምታ፤ "ከከፍተኛ እስከ መካከለኛ የፓርቲያችን አመራሮች መታሰር እና የአገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ ለምርጫ የምናደርገውን ዝግጅት አስቸጋሪ ያደርገዋል" ሲሉ ተናግረዋል። በተመሳሳይ የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ቢሮ ኃላፊ አቶ ገለታው ዘለቀ፤ የባልደራስ አመራሮች በተራዘመ የፍርድ ቤት ቀጠሮ ላይ እንዳሉ በመጥቀስ "የምንገባበት ምርጫ እጅግ አሳስቦናል" ብለዋል። የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቃል አቀባይ ሶሊያና ሽመልስ ከቀናት በፊት ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ "ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ምርጫው መካሄድ አለበት ነው ያሉት። ምርጫው ከመካሄዱ በፊት ስጋት ይሆናል ያሉት ሁለት ነገር ነው። አንዱ የአገሪቱ የጸጥታ ችግር ነው። አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች ደግሞ ቢሯቸው እንደሚዘጋ እና አባሎቻቸው ችግር እንደሚደርስባቸው ተናግረዋል" ብለዋል። ፓርቲዎች ለሚያነሷቸው መሰል ችግሮች መፍትሄ መስጠት የሚችለው የመንግሥት ሥራ አስፈጻሚ አካል እንጂ ምርጫ ቦርድ አለመሆኑንም ተናግረዋል። የምርጫ ቦርድ ረቂቅ የምርጫ የጊዜ ሠሌዳውን አርብ እለት ይፋ ባደረገበት መድረክ ላይ የብልጽግና ፓርቲን ወክለው የተሳተፉት አቶ ዛዲግ አብረሃ ተፎካካሪ ፓርቲዎች እየደረሰብን ነው ያሉት ጫናን በተመለከተ ምላሽ ሰጥተው ነበር። በዚህም መሰረት የቀረቡ ቅሬታዎች ላይ ማጣራት እንደተደረገና አንዳንዶቹ የተጋነኑ መሆናቸውን ገልጸው፤ የቀረቡትን አቤቱታዎችን ፓርቲያቸው እንደማያጣጥላቸውና ለማረም አስፈላጊውን ነገሮች ሁሉ እንደማያደርግ እንዲሁም ቀጣዩ ምርጫ ትክክለኛ ፉክክር የሚደረግበት እንዲሆን እንደሚሰሩ ተናግረዋል። በዚህ ዓመት ለሚካሄደው ስድስተኛው ዙር አገራዊና ክልላዊ አጠቃላይ ምርጫ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ በተደረገው ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት የድምጽ መስጫው ቀን ግንቦት 28 እና ሰኔ 5 መሆኑ ገልጿል። አቶ ጥሩነህ በርካታ አባሎቻቸው መታሰራቸውን፣ የቀሩትም ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው መሆኑን እና በዞንና በወረዳ ደረጃ ያሉ ጽህፈት ቤቶቻቸው መዘጋታቸውን በመጥቀስ፤ "በምርጫው ለመሳተፍ ፍላጎት ቢኖረንም በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንገኛለን" ብለዋል። ይህንንም ስጋታቸውን ከዚህ ቀደም መግለጫ በማውጣት ማስታወቃቸውን አስታውሰዋል። ትናንት ምርጫ ቦርድ ባካሄደው ስብሰባ ላይም ተገኝተው ይህንኑ ስጋታቸውን ማስረዳታቸውን የተናገሩት አቶ ጥሩነህ፤ "ችግሮችን ለማስተካከል ጥረት እናደርጋለን" የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል። "ነገር ግን አንዳንድ ከአቅማቸው በላይ የሆኑ ነገሮች መኖራቸውንም ተገንዝበናል" ብለዋል አቶ ጥሩነህ። እንደ ኦፌኮ እስካሁን በምርጫው አንሳተፍም የሚል ውሳኔ ላይ ባይደርሱም፤ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ በሚያስችል አቅም ላይ አለመሆናቸውን ግን አስረግጠው ተናግረዋል። ለዚህም የጽህፈት ቤቶቻቸው መዘጋት፣ የአባላቶቻቸው እስር፣ ስደትና ማስፈራሪያ እንዲሁም በአገሪቷ በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ችግሮችን እንደ ምክንያት ጠቅሰዋል። "በዚህ ሁኔታስ መንግሥትና ምርጫ ቦርድ ምርጫ ማካሄድ ይችላሉ ወይ?" ሲሉም ጠይቀዋል። የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሕገ መንግሥትና ጸረ ሽብር ጉዳዮች ወንጀል ችሎት የባልደራስ ፓርቲ ሊቀመንበር በሆኑት በአቶ እስክንድር ነጋ ላይ ዐቃቤ ሕግ ምስክር እንዲያሰማ ለመጋቢት 29 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል። በትናንቱ የፍርድ ቤት ውሎ ማዘናቸውን የገለፁት የፓርቲው ቢሮ ኃላፊ አቶ ገለታው፤ "በእነአቶ እስክንድር ነጋ ላይ የተሰጠው ቀጠሮ ተሰሚነት ያላቸው ሰዎች በውድድሩ ውስጥ ሳይገቡ መንግሥት ብቻውን ሮጦ 'አሸናፊ ነኝ' ለማለት የተደረገ ይመስላል" ሲሉ ኮንነዋል። አቶ ገለታው "ምርጫው በህወሓት ዘመን የተለመደ የምርጫ ዓይነት ሊሆን ነው" በማለትም በእነርሱ በኩል ተስፋ እየታያቸው እንዳልሆነ ተናግረዋል። "አባላቶቻችን ወከባ አለባቸው። መንግሥት በየጊዜው ምህዳሩን እያጠበበ ነው፤ ባልሰፋ ምህዳር ውስጥ ታሪካዊ ምርጫ ሊደረግ እንደማይችል እያረጋገጠ ነው" ሲሉም ወቅሰዋል። ይህ እንደ ፓርቲ ብቻም ሳይሆን እንደ አንድ ግለሰብ እንደሚያሳስባቸውም አልሸሸጉም። አቶ ገለታው "ይህ ምርጫ እንደ በፊቱ ተጭበርብሮ እንራመድ ቢባል የማያራምድ ሕዝብ የተነሳበት ወቅት ስለሆነ፤ ድህረ ምርጫ አገሪቷን ወደ ብጥብጥ እንዳይወስዳት ያሳስባል" ብለዋል። መንግሥት ሁኔታዎችን በፍጥነት ማስተካከል ካልቻለም ምርጫው ታሪካዊ መሆኑ ቀርቶ፤ አደጋዎችን ይዞ ሊመጣ እንደሚችል ስጋታቸውን ገልፀዋል። የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቃል አቀባይ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ "ፓርቲዎች ችግር ገጥሞናል ባሉት ጉዳይ ላይ ለክልል አስተዳደር፣ ለፖሊስ ኮሚሽን ወይም ሌላ ጉዳዩ ለሚመለከተው አካል ቦርዱ ያሳውቃል" በማለት የመሥሪያ ቤታቸው የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት የሚያደርገውን ጥረት አስረድተዋል። በዚህም መሰረት ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች አቤቱታ ካላቸው ለቦርዱ በጽሑፍ እንዲያቀርቡ ተጠይቆ፤ 11 ፓርቲዎች የሚገጥማቸውን ችግር ለቦርዱ ማሳወቃቸውን የጠቀሱት ሶሊያና፤ ቦርዱም ለእነዚህ ችግሮች መፍትሔ ያስፈልጋል ብሎ ለመንግሥት ማሳወቁን ገልጸዋል። በየክልሉ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች የሚገጥማቸውን ችግር በተመለከተ ከገዢው ፓርቲ፣ መንግሥትና ምርጫ ቦርድ ጋር የሦስትዮሽ ውይይት የሚካሄድበት አሠራር መዘርጋቱንም ዳይሬክተሯ ተናግረዋል። የኦፌኮ እና ባልደራስ ፓርቲዎች አመራር እና አባላት የሆኑት ጀዋር መሐመድ፣ በቀለ ገርባ እንዲሁም እስክንድር ነጋ፣ አስቴር ስዩምና ስንታሁ ቸኮል በሽብር ወንጀል ተከሰው በእስር እንደሚገኙ ይታወቃል። ምርጫ ቦርድ ፓርቲዎች ከየካቲት 8 ጀምሮ የእጩዎች ምዝገባ እንደሚያከናውኑ እና የምረጡኝ ቅስቀሳ እንደሚያደርጉ በትናንትናው ዕለት ገልጿል። ከየካቲት 22 እስከ መጋቢት 21 ድረስ ደግሞ የመራጮች ምዝገባ የሚከናወን ይሆናል። ከዚህ በተጨማሪም የአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች የድምጽ መስጫ ቀን በአንድ ሳምንት ዘግይቶ ሰኔ 5/2013 ዓ.ም እንደሚከናወን አስታውቋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቀጣዩ አገራዊ ምርጫ እስከ 50 ሚሊዮን የሚደርሱ መራጮች ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠብቅ ማስታወቁ ይታወሳል።
https://www.bbc.com/amharic/news-55447033
5sports
አትሌት ሲፋን ሐሰን ለኢትዮጵያ ባለመሮጤ ፀፀት አይሰማኝም አለች
በቶኪዮ ኦሎምፒክ የሜዳሊያ "ሦስታ" በመሥራት ዓለምን ያስደነቀችው ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ የኔዘርላንድስ ሯጭ ሲፋን ሐሰን ኢትዮጵያን ወክላ ባለመሮጧ አንዳችም ፀፀት እንደማይሰማት ተናገረች፡፡ አትሌት ሲፋን አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ጦርነት አገሪቱን ድምጥማጧን እያጠፋት ነው ብላለች፡፡ በፖለቲካ ሥልጣን መጋራት የተሻለ ሁኔታ ሊያመጣ እንደሚችልና ይህም ሌሎች በርካታ ሯጮች ወደፊት ለሌሎች አገሮች መሮጥ ትተው ለኢትዮጵያ እንዲሮጡ መፍትሄ ሊሆን እንደሚችልም ጠቁማለች፡፡ አትሌት ሲፋን ለኔዘርላንድስ በ5ሺህ እና በ10ሺህ ወርቅ አስገኝታለች፡፡ በ1ሺ 500 ደግሞ ነሐስ አግኝታለች፡፡ አትሌት ሲፋን ከኢትዮጵያ ወደ ኔዘርላንድስ የወጣችው ገና በ14 ዓመቷ ነበር፡፡ የ28 ዓመቷ ሲፋን በኦሮሚያ ክልል ነው ያደገችው፡፡ በወቅቱ የራስ ገዝ ጥያቄ ይነሳ የነበረበት ሲሆን ለነጻነት የሚዋጉ ኃይሎች ጥቃት ይፈጽሙ ነበር ብላለች፡፡ ሲፋን በ10ሺህ ሜትር ያሸነፈቻት በርቀቱ የዓለም ክብረ ወሰን ያላትን ኢትዮጵያዊቷን ለተሰንበት ግደይን ጭምር በመምራት ነው፡፡ ለተሰንበት የተገኘችው ደግሞ አሁን በጦርነት እየታመሰች ከምትገኘው ትግራይ ነው፡፡ ለቢቢሲ ስፖርት አፍሪካ ሐሳቧን የሰጠችው ሲፋን ሐሰን ያን ወቅት በኦሮሚያ የነበረው የሰዎች ግድያ ልብ የሚሰብር እንደነበር አስታውሳለች፡፡ ‹‹ከዚያች አገር በመሰደዴ አንዳች ቅሬታ የለኝም፡፡ መመለስም አልፈልግም፡፡ ማሰቡ ራሱ ያመኛል፡፡›› ብላለች፡፡ ሲፋን በፈረንጆቹ እስከ 2007 ደስ የሚል የልጅነት ጊዜ እንዳሳለፈችና ከዚያ በኋላ ግን በኦሮሚያ በነበረው ውጊያ ነገሮች እየተበላሹ መምጣታቸውን አስታውሳለች፡፡ በቶኪዮ የ10ሺህ ሜትር የሜዳሊያ አሸናፊዎች ሥነ ሥርዓት መድረኩ በትውልደ ኢትዮጵያዊያን ነበር የተሞላው፡፡ሆኖም ለተሰንበት ብቻ ናት ኢትዮጵያን የወከለችው፡፡ የብር ሜዳሊያ ያገኘችው ቃልኪዳን ገዛኸኝ ባህሬንን ትወክል እንጂ ትውልደ ኢትዮጵያዊት ናት፡፡ በሕዝብ ብዛት ከአፍሪካ ሁለተኛ የሆነችው ኢትዮጵያ በብሔር ግጭት ውጥረት ስሟ የሚነሳ ሲሆን ይህ ሁኔታ አገሪቱ በርካታ አትሌቶችን እንድታጣ ምክንያት ሆኗል ብላለች ሲፋን ሐሰን፡፡ ‹‹ትዝ ይለኛል በፊት ወጣቱ እርስ በእርስ ይዋደድ ነበር፡፡ አሁን ግን እርስ በእርሱ የሚጠላላ ሆኗል፡፡ በፊት ሁሉም ራሱን ኢትዮጵያዊ ብሎ ይጠራ ነበር፡፡ አሁን ግን እርግጠኛ ነኝ ብዙ ትግራዊያን ራሳቸውን ኢትዮጵያዊ ብለው አይጠሩም›› ብላለች ሲፋን፡፡ በሰኔ ወር ለተሰንበት በ10ሺህ ሜትር ሁለት ቀናት ብቻ የቆየውን የሲፋንን የዓለም ክብረ ወሰን በርቀቱ ስትወስድ በርካታ የስፖርት ወዳጆች ወደ ዓለም አቀፉ የትሌቲክስ ማኅበር ማኅበራዊ ሚዲያ ገጽ በመሄድ ክብረ ወሰኑ የትግራዋይት እንጂ የኢትዮጵያ አይደለም ሲሉ ይጽፉ ነበር፡፡ በዚህ ወር መጀመርያ የተባበሩት መንግሥታት አፋጣኝ የሰብአዊ እርዳታ በኦሮሚያ እንደሚያስፈልግ የጠቀሰ ሲሆን በትግራይ ደግሞ አራት ሚሊዮን ሰዎች አስቸኳይ እርዳታን ይሻሉ ሲሉ መግለጫ አውጥቶ ነበር፡፡ ‹‹ለተሰንበት ድንቅ አትሌት ናት፡፡ የመጣችበት ቦታ ግን ሕጻናት ይደፈራሉ፤ አስቀያሚ ሁኔታ ነው ያለው፤ ያሳዝናል›› ብላለች ሲፋን ለቢቢሲ፡፡ "አስበሽዋል! ልክ እንደኔው ሕልም የነበራቸው ስንትና ስንት ሴቶች እንደተደፈሩ?" ስትል ሁኔታውን ምን ያህል እንደሚያውክ አብራርታለች፡፡ ከኦሮሚያ የተገኙት የአሁን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ተቺዎች ለክልሎች የራስ ገዝ አስተዳደርን ከመስጠት ይልቅ ማዕከላዊ መንግሥትን አጠናክሮ አሀዳዊ መንግሥት ለመፍጠር ይሞክራሉ ሲሉ ይወቅሷቸዋል፡፡ ‹‹እኔ እሱን ብሆን ዘወር እል ነበር፡፡ ሥልጣኑን ለሕዝቦች እሰጥ ነበር፣ የሚፈልጉትን እንደሚርጡ አደርግ ነበር፡፡›› ብላለች ሲፋን ሐሰን፡፡
አትሌት ሲፋን ሐሰን ለኢትዮጵያ ባለመሮጤ ፀፀት አይሰማኝም አለች በቶኪዮ ኦሎምፒክ የሜዳሊያ "ሦስታ" በመሥራት ዓለምን ያስደነቀችው ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ የኔዘርላንድስ ሯጭ ሲፋን ሐሰን ኢትዮጵያን ወክላ ባለመሮጧ አንዳችም ፀፀት እንደማይሰማት ተናገረች፡፡ አትሌት ሲፋን አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ጦርነት አገሪቱን ድምጥማጧን እያጠፋት ነው ብላለች፡፡ በፖለቲካ ሥልጣን መጋራት የተሻለ ሁኔታ ሊያመጣ እንደሚችልና ይህም ሌሎች በርካታ ሯጮች ወደፊት ለሌሎች አገሮች መሮጥ ትተው ለኢትዮጵያ እንዲሮጡ መፍትሄ ሊሆን እንደሚችልም ጠቁማለች፡፡ አትሌት ሲፋን ለኔዘርላንድስ በ5ሺህ እና በ10ሺህ ወርቅ አስገኝታለች፡፡ በ1ሺ 500 ደግሞ ነሐስ አግኝታለች፡፡ አትሌት ሲፋን ከኢትዮጵያ ወደ ኔዘርላንድስ የወጣችው ገና በ14 ዓመቷ ነበር፡፡ የ28 ዓመቷ ሲፋን በኦሮሚያ ክልል ነው ያደገችው፡፡ በወቅቱ የራስ ገዝ ጥያቄ ይነሳ የነበረበት ሲሆን ለነጻነት የሚዋጉ ኃይሎች ጥቃት ይፈጽሙ ነበር ብላለች፡፡ ሲፋን በ10ሺህ ሜትር ያሸነፈቻት በርቀቱ የዓለም ክብረ ወሰን ያላትን ኢትዮጵያዊቷን ለተሰንበት ግደይን ጭምር በመምራት ነው፡፡ ለተሰንበት የተገኘችው ደግሞ አሁን በጦርነት እየታመሰች ከምትገኘው ትግራይ ነው፡፡ ለቢቢሲ ስፖርት አፍሪካ ሐሳቧን የሰጠችው ሲፋን ሐሰን ያን ወቅት በኦሮሚያ የነበረው የሰዎች ግድያ ልብ የሚሰብር እንደነበር አስታውሳለች፡፡ ‹‹ከዚያች አገር በመሰደዴ አንዳች ቅሬታ የለኝም፡፡ መመለስም አልፈልግም፡፡ ማሰቡ ራሱ ያመኛል፡፡›› ብላለች፡፡ ሲፋን በፈረንጆቹ እስከ 2007 ደስ የሚል የልጅነት ጊዜ እንዳሳለፈችና ከዚያ በኋላ ግን በኦሮሚያ በነበረው ውጊያ ነገሮች እየተበላሹ መምጣታቸውን አስታውሳለች፡፡ በቶኪዮ የ10ሺህ ሜትር የሜዳሊያ አሸናፊዎች ሥነ ሥርዓት መድረኩ በትውልደ ኢትዮጵያዊያን ነበር የተሞላው፡፡ሆኖም ለተሰንበት ብቻ ናት ኢትዮጵያን የወከለችው፡፡ የብር ሜዳሊያ ያገኘችው ቃልኪዳን ገዛኸኝ ባህሬንን ትወክል እንጂ ትውልደ ኢትዮጵያዊት ናት፡፡ በሕዝብ ብዛት ከአፍሪካ ሁለተኛ የሆነችው ኢትዮጵያ በብሔር ግጭት ውጥረት ስሟ የሚነሳ ሲሆን ይህ ሁኔታ አገሪቱ በርካታ አትሌቶችን እንድታጣ ምክንያት ሆኗል ብላለች ሲፋን ሐሰን፡፡ ‹‹ትዝ ይለኛል በፊት ወጣቱ እርስ በእርስ ይዋደድ ነበር፡፡ አሁን ግን እርስ በእርሱ የሚጠላላ ሆኗል፡፡ በፊት ሁሉም ራሱን ኢትዮጵያዊ ብሎ ይጠራ ነበር፡፡ አሁን ግን እርግጠኛ ነኝ ብዙ ትግራዊያን ራሳቸውን ኢትዮጵያዊ ብለው አይጠሩም›› ብላለች ሲፋን፡፡ በሰኔ ወር ለተሰንበት በ10ሺህ ሜትር ሁለት ቀናት ብቻ የቆየውን የሲፋንን የዓለም ክብረ ወሰን በርቀቱ ስትወስድ በርካታ የስፖርት ወዳጆች ወደ ዓለም አቀፉ የትሌቲክስ ማኅበር ማኅበራዊ ሚዲያ ገጽ በመሄድ ክብረ ወሰኑ የትግራዋይት እንጂ የኢትዮጵያ አይደለም ሲሉ ይጽፉ ነበር፡፡ በዚህ ወር መጀመርያ የተባበሩት መንግሥታት አፋጣኝ የሰብአዊ እርዳታ በኦሮሚያ እንደሚያስፈልግ የጠቀሰ ሲሆን በትግራይ ደግሞ አራት ሚሊዮን ሰዎች አስቸኳይ እርዳታን ይሻሉ ሲሉ መግለጫ አውጥቶ ነበር፡፡ ‹‹ለተሰንበት ድንቅ አትሌት ናት፡፡ የመጣችበት ቦታ ግን ሕጻናት ይደፈራሉ፤ አስቀያሚ ሁኔታ ነው ያለው፤ ያሳዝናል›› ብላለች ሲፋን ለቢቢሲ፡፡ "አስበሽዋል! ልክ እንደኔው ሕልም የነበራቸው ስንትና ስንት ሴቶች እንደተደፈሩ?" ስትል ሁኔታውን ምን ያህል እንደሚያውክ አብራርታለች፡፡ ከኦሮሚያ የተገኙት የአሁን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ተቺዎች ለክልሎች የራስ ገዝ አስተዳደርን ከመስጠት ይልቅ ማዕከላዊ መንግሥትን አጠናክሮ አሀዳዊ መንግሥት ለመፍጠር ይሞክራሉ ሲሉ ይወቅሷቸዋል፡፡ ‹‹እኔ እሱን ብሆን ዘወር እል ነበር፡፡ ሥልጣኑን ለሕዝቦች እሰጥ ነበር፣ የሚፈልጉትን እንደሚርጡ አደርግ ነበር፡፡›› ብላለች ሲፋን ሐሰን፡፡
https://www.bbc.com/amharic/news-58176592
3politics
ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት አሜሪካን ተጠያቂ አደረጉ
የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የኤርትራ 31ኛው የነጻነት በዓልን አስመልክቶ ባደረጉት ንግግር ለሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት አሜሪካን ተጠያቂ አድርገዋል። በእርሳቸው አገላለጽ፣ ከቀዝቃዛው ጦርነት ማክተም በኋላ "በአሜሪካ የሚመራው የምዕራባውያን ኃይል፣ የአሜሪካ ሕዝብንም ይሁን የምዕራቡ ዓለምን የማይወክል አደገኛ አካሄድ ጀምሯል።" "ዓለም የኛ ይሆናል፣ በሁሉም ዘርፍ ያለን ኃያልነት ተገዳዳሪ አይኖረውም" ብለው ምዕራባውያኑ እንደተነሱ ጠቅሰው በዚህም ኤርትራ ላይ የተጣሉ ማዕቀቦችን ከመተቸት አልፈው ለሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት አሜሪካን ተጠያቂ እስከማድረግ ደርሰዋል። በተባበሩት መንግሥታት ውይይት ሩሲያ ዩክሬንን በመውረሯ ማዕቀቦች እንዲጣሉ የተነሱ ሐሳቦችን ከተቃወሙ አገራት አንዷ ኤርትራ እንደሆነች አይዘነጋም። ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ባደረጉት ንግግር በዋነኛነት አሜሪካ ሊገዳደሯት የሚችሉ ኃይሎች ላይ "የአፈና ፖሊስ" እንደምትከተልና፣ ይህንን ፖሊሲዋን ሩሲያን "ለመቆጣጠር" እንዳዋለችው ጠቅሰዋል። የሩሲያ የቅርብ ጎረቤቶች የሆኑ የምሥራቅ አውሮፓ አገራት "እንደ እጅ አዙር መጠቀሚያ" እንደዋሉ በንግግራቸው ጠቅሰዋል። የዩክሬን እና ሩሲያ ጦርነት ይህ "የአፈና ፖሊሲ" እንደሆነ ገልጸው፣ የዩክሬን ሕዝብ የዚህ ሰለባ ሆኗል ሲሉ ተችተዋል። ፕሬዝዳንቱ ባለፉት 30 ዓመታት ይህ አካሄድ "አልሠራም" ሲሉም አክለዋል። "ማስፋራራት፣ መቅጣት፣ መውረር፣ ስም ማጠልሸት፣ ማዕቀብ መጣል፣ ሰብአዊ መብትን እንደ መሣሪያ መጠቀም አልሠራም።" በእጅ አዙር የምጣኔ ሀብት ጫና ለማሳደር ከሩሲያ በተጨማሪ ቻይና ላይም "እንደተቃጣ" ገልጸዋል። "ታይዋን እና ሆንግ ኮንግን እንዲሁም በአጠቃላይ እስያ ያሉ አገራትን እንደ መሣሪያ ለመጠቀም ተሞክሯል። ይህም ከሩሲያ ቢበልጥ እንጂ የማይተናነስ ቀውስ ያስከትላል።" ጠቅለል አድርገውም ዓለም አቀፍ ሕግጋት የሚከበሩበት፣ ማዕቀቦች የሚቀለበሱበት፣ ዓለም አቀፍ ፍትሐዊ የሀብት ክፍፍል የሚረጋገጥበት፣ ሉዓላዊ አገሮች የማይገረሰሱበት እንዲሁም አገራዊ፣ ቀጠናዊና አህጉራዊ ትብብር የሚደረጅበት ዓለም መገንባትን እንደ አማራጭ አቅርበዋል።የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለኤርትራ 31ኛው የነጻነት በዓል ባደረጉት ንግግር፣ የአፍሪካ ቀንድን "መረጋጋት ማረጋጋጥ" የኤርትራ አገረ ግንባታ ዋነኛ ማጠንጠኛ እንደሆነ ተናግረዋል። በንግግራቸው ካነሷቸው ነጥቦች መካከል የአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት፣ የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት እንዲሁም "የምዕራባውያን ጫና" ይገኙበታል። "የቀጠናውን መረጋጋት ማስጠበቅ፣ የጋራ ትብብርን ማጠናከር እና በሉዓላዊ አገራት መካከል ትስስርና እድገትን ማረጋገጥ የአገር ግንባታው ዋነኛ ማጠንጠኛ ነው፣ ሆኖም ይቀጥል" ብለዋል። "የውስጥ እና የውጭ አፍራሽ አጀንዳዎች" ባሏቸው ጉዳዮች "የጎረቤት አገራት ዜጎች" እንደሚፈተኑም አያይዘው ጠቅሰዋል። ከቀጠናው ባለፈ አፍሪካን እንደ አህጉር ቀጠናዊ ትስስሮችን ማጠናከር እንዳለባት ጠቅሰው "ይህ የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን እጅግ አስፈላጊ ነው" ሲሉ አጽንኦት ሰጥተውታል። የኤርትራ መንግሥት "ለቀጠናዊ ትስስር ግብዓት እንዳፈሰሰ" ከዚህ ባሻገርም ለጋራ የምጣኔ ሀብት እድገት፣ ለጸረ ሽብር ትግል እና ብሔራዊ ደኅንነት ስጋትን ለመቀልበስም "እንደሚታጋ" ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል። ለ30 ዓመታት የተካሄደውን የትጥቅ ትግል የመራው የኤርትራ ነጻ አውጪ ግንባር (ሻዕቢያ) የኤርትራ መዲና አሥመራን የተቆጣጠረበት ቀን በኤርትራ ተከብሮ ውሏል። የነጻነት ቀንን አስመልክተው ንግግር ያደረጉት ፕሬዝዳንት ኢሳያስ፣ በዓሉ የአገሪቱ "አሁናዊ፣ የቀድሞ እና የወደፊት ሁኔታ የሚቃኝበት" ብለውታል። በቀጠናውና በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉ "ሁኔታዎችን ከግምት በማስገባት" የኤርትራን ሉዓላዊነት እና ነጻነት ለመጠበቅ የተደረገው ትግል አልፎም አገሪቱ ለወደፊት ማሳካት የምትሻው የሚቃኝበት ዓመት እንደሆነም ጠቅሰዋል። ስለ ኤርትራ ፕሬዝዳንቱ የኤርትራ ሕዝብ ነጻነቱን ለመቀዳጀት ለ50 ዓመታት ያደረገውን ትግል አሞግሰዋል። ኤርትራን በሃይማኖት ለመከፋፈል፣ በምጣኔ ሀብት ለማዳከም እንዲሁም የተለያዩ አሉታዊ ሙከራዎች ቢደረጉም የኤርትራን ሕዝብ "ፖለቲካዊ ንቃተ ሕሊና ያዳበሩ" እንጂ ያወኩ አለመሆናቸውን ተናግረዋል። "ለ50 ዓመታት ከተደረገው ትግል የተገኘው ተሞክሮና ትምህርት" ከትውልድ ወደ ትውልድ እንደተሸጋገረ በንግገራቸው ጠቅሰዋል። ኤርትራ "ሽብርን ትደግፋለች" በሚል ሽፋን የተጣሉባትን ማዕቀቦች ሳይኮንኑም አላለፉም። ኤርትራ ውስጥ የመገናኛ ብዙኃን፣ የሃይማኖት፣ የፖለቲካ ነጻነት እንደተሸረሸረ እና ሰብአዊ መብትን የሚጥሱ አፈናዎች በመንግሥት እንደሚፈጸሙ የተባበሩት መንግሥታትን ጨምሮ የተለያዩ የመብት ተሟጋቾች ቢተቹም፣ የኤርትራ መንግሥት ግን እነዚህን ውንጀላዎች አይቀበላቸውም።
ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት አሜሪካን ተጠያቂ አደረጉ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የኤርትራ 31ኛው የነጻነት በዓልን አስመልክቶ ባደረጉት ንግግር ለሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት አሜሪካን ተጠያቂ አድርገዋል። በእርሳቸው አገላለጽ፣ ከቀዝቃዛው ጦርነት ማክተም በኋላ "በአሜሪካ የሚመራው የምዕራባውያን ኃይል፣ የአሜሪካ ሕዝብንም ይሁን የምዕራቡ ዓለምን የማይወክል አደገኛ አካሄድ ጀምሯል።" "ዓለም የኛ ይሆናል፣ በሁሉም ዘርፍ ያለን ኃያልነት ተገዳዳሪ አይኖረውም" ብለው ምዕራባውያኑ እንደተነሱ ጠቅሰው በዚህም ኤርትራ ላይ የተጣሉ ማዕቀቦችን ከመተቸት አልፈው ለሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት አሜሪካን ተጠያቂ እስከማድረግ ደርሰዋል። በተባበሩት መንግሥታት ውይይት ሩሲያ ዩክሬንን በመውረሯ ማዕቀቦች እንዲጣሉ የተነሱ ሐሳቦችን ከተቃወሙ አገራት አንዷ ኤርትራ እንደሆነች አይዘነጋም። ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ባደረጉት ንግግር በዋነኛነት አሜሪካ ሊገዳደሯት የሚችሉ ኃይሎች ላይ "የአፈና ፖሊስ" እንደምትከተልና፣ ይህንን ፖሊሲዋን ሩሲያን "ለመቆጣጠር" እንዳዋለችው ጠቅሰዋል። የሩሲያ የቅርብ ጎረቤቶች የሆኑ የምሥራቅ አውሮፓ አገራት "እንደ እጅ አዙር መጠቀሚያ" እንደዋሉ በንግግራቸው ጠቅሰዋል። የዩክሬን እና ሩሲያ ጦርነት ይህ "የአፈና ፖሊሲ" እንደሆነ ገልጸው፣ የዩክሬን ሕዝብ የዚህ ሰለባ ሆኗል ሲሉ ተችተዋል። ፕሬዝዳንቱ ባለፉት 30 ዓመታት ይህ አካሄድ "አልሠራም" ሲሉም አክለዋል። "ማስፋራራት፣ መቅጣት፣ መውረር፣ ስም ማጠልሸት፣ ማዕቀብ መጣል፣ ሰብአዊ መብትን እንደ መሣሪያ መጠቀም አልሠራም።" በእጅ አዙር የምጣኔ ሀብት ጫና ለማሳደር ከሩሲያ በተጨማሪ ቻይና ላይም "እንደተቃጣ" ገልጸዋል። "ታይዋን እና ሆንግ ኮንግን እንዲሁም በአጠቃላይ እስያ ያሉ አገራትን እንደ መሣሪያ ለመጠቀም ተሞክሯል። ይህም ከሩሲያ ቢበልጥ እንጂ የማይተናነስ ቀውስ ያስከትላል።" ጠቅለል አድርገውም ዓለም አቀፍ ሕግጋት የሚከበሩበት፣ ማዕቀቦች የሚቀለበሱበት፣ ዓለም አቀፍ ፍትሐዊ የሀብት ክፍፍል የሚረጋገጥበት፣ ሉዓላዊ አገሮች የማይገረሰሱበት እንዲሁም አገራዊ፣ ቀጠናዊና አህጉራዊ ትብብር የሚደረጅበት ዓለም መገንባትን እንደ አማራጭ አቅርበዋል።የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለኤርትራ 31ኛው የነጻነት በዓል ባደረጉት ንግግር፣ የአፍሪካ ቀንድን "መረጋጋት ማረጋጋጥ" የኤርትራ አገረ ግንባታ ዋነኛ ማጠንጠኛ እንደሆነ ተናግረዋል። በንግግራቸው ካነሷቸው ነጥቦች መካከል የአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት፣ የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት እንዲሁም "የምዕራባውያን ጫና" ይገኙበታል። "የቀጠናውን መረጋጋት ማስጠበቅ፣ የጋራ ትብብርን ማጠናከር እና በሉዓላዊ አገራት መካከል ትስስርና እድገትን ማረጋገጥ የአገር ግንባታው ዋነኛ ማጠንጠኛ ነው፣ ሆኖም ይቀጥል" ብለዋል። "የውስጥ እና የውጭ አፍራሽ አጀንዳዎች" ባሏቸው ጉዳዮች "የጎረቤት አገራት ዜጎች" እንደሚፈተኑም አያይዘው ጠቅሰዋል። ከቀጠናው ባለፈ አፍሪካን እንደ አህጉር ቀጠናዊ ትስስሮችን ማጠናከር እንዳለባት ጠቅሰው "ይህ የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን እጅግ አስፈላጊ ነው" ሲሉ አጽንኦት ሰጥተውታል። የኤርትራ መንግሥት "ለቀጠናዊ ትስስር ግብዓት እንዳፈሰሰ" ከዚህ ባሻገርም ለጋራ የምጣኔ ሀብት እድገት፣ ለጸረ ሽብር ትግል እና ብሔራዊ ደኅንነት ስጋትን ለመቀልበስም "እንደሚታጋ" ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል። ለ30 ዓመታት የተካሄደውን የትጥቅ ትግል የመራው የኤርትራ ነጻ አውጪ ግንባር (ሻዕቢያ) የኤርትራ መዲና አሥመራን የተቆጣጠረበት ቀን በኤርትራ ተከብሮ ውሏል። የነጻነት ቀንን አስመልክተው ንግግር ያደረጉት ፕሬዝዳንት ኢሳያስ፣ በዓሉ የአገሪቱ "አሁናዊ፣ የቀድሞ እና የወደፊት ሁኔታ የሚቃኝበት" ብለውታል። በቀጠናውና በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉ "ሁኔታዎችን ከግምት በማስገባት" የኤርትራን ሉዓላዊነት እና ነጻነት ለመጠበቅ የተደረገው ትግል አልፎም አገሪቱ ለወደፊት ማሳካት የምትሻው የሚቃኝበት ዓመት እንደሆነም ጠቅሰዋል። ስለ ኤርትራ ፕሬዝዳንቱ የኤርትራ ሕዝብ ነጻነቱን ለመቀዳጀት ለ50 ዓመታት ያደረገውን ትግል አሞግሰዋል። ኤርትራን በሃይማኖት ለመከፋፈል፣ በምጣኔ ሀብት ለማዳከም እንዲሁም የተለያዩ አሉታዊ ሙከራዎች ቢደረጉም የኤርትራን ሕዝብ "ፖለቲካዊ ንቃተ ሕሊና ያዳበሩ" እንጂ ያወኩ አለመሆናቸውን ተናግረዋል። "ለ50 ዓመታት ከተደረገው ትግል የተገኘው ተሞክሮና ትምህርት" ከትውልድ ወደ ትውልድ እንደተሸጋገረ በንግገራቸው ጠቅሰዋል። ኤርትራ "ሽብርን ትደግፋለች" በሚል ሽፋን የተጣሉባትን ማዕቀቦች ሳይኮንኑም አላለፉም። ኤርትራ ውስጥ የመገናኛ ብዙኃን፣ የሃይማኖት፣ የፖለቲካ ነጻነት እንደተሸረሸረ እና ሰብአዊ መብትን የሚጥሱ አፈናዎች በመንግሥት እንደሚፈጸሙ የተባበሩት መንግሥታትን ጨምሮ የተለያዩ የመብት ተሟጋቾች ቢተቹም፣ የኤርትራ መንግሥት ግን እነዚህን ውንጀላዎች አይቀበላቸውም።
https://www.bbc.com/amharic/news-61579468
2health
በኢንዶኔዥያ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ የኮቪድ ናሙና መሰብሰቢያዎችን በድጋሚ የተጠቀሙ ግለሰቦች ተያዙ
በኢንዶኔዥያ የሚገኝ የመድኃኒት አምራች ኩባንያ ሠራተኞች ያገለገሉ የኮቪድ መመርመሪያ መሣሪያዎችን አጥበው ድጋሚ በመሸጥ ወንጀል በቁጥጥር ስር ውለዋል። በሜዳን በሚገኘው አውሮፕላን ማረፊያ በኩል የተጓጓዙ እስከ 9000 የሚደርሱ መንገደኞች እንደገና ጥቅም ላይ በዋሉት መሣሪያዎች ተመርምረው ሊሆን እንደሚችል ፖሊስ ገልጿል። በመንግሥት የሚተዳደረው ኪሚያ ፋርማ በተጓዦቹ ስም በተመሠረተ ክስ ፍርድ ቤት ሊቆም እንደሚችል ተዘገቧል፡፡ በኮቪድ ወረርሽኝ በተጠቁ በርካታ አገሮች ውስጥ ከአፍንጫ ፈሳሽ በመውሰድ መመርመር የተለመደ ሆኗል፡፡ ካለፈው ታህሳስ ጀምሮ በሰሜን ሱማትራ ሜዳን በሚገኘው ኳላናሙ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ማጭበርበሩ ሲፈጸም እንደነበር ይታመናል ብሏል ፖሊስ፡፡ ተሳፋሪዎች ለመብረር ከፈለጉ ከተህዋሲው ነጻ መሆን ይጠበቅባቸዋል። አየር ማረፊያው ፈጣን ውጤት ለሚፈልጉ በቦታው የምርመራ አማራጭ ይሰጣል። የአውሮፕላን ማረፊያው ባለሥልጣናት ኪሚያ ፋርማ የሚያቀርበውን አንቲጂን ፈጣን የመመርመሪያ መሣሪያዎችን ይጠቀሙ ነበር ተብሏል፡፡ በስህተት ተህዋሲው እንዳለባቸው የሚያሳይ የምርመራ ውጤት ማግኘታቸውን ተከትሎ ከተሳፋሪዎች ቅሬታ ቀርቧል። ባለፈው ሳምንት ፖሊስ ተሳፋሪ አስመስሎ በህቡዕ መኮንኑን በመላክ ጉዳዩን ማጣራቱን ዴቲክ የተሰኘው የአካባቢው የዜና አውታር ዘግቧል፡፡ ፖሊሱ ከአፍንጫው ናሙናው ተወስዶ ተህዋሲው እንዳለበት ሲነገረው ሌሎች ባልደረቦቹ ወደ ላቦራቶሪው በመግባት እንደገና ጥቅም ላይ የዋሉ የመመርመሪያ መሣሪያ አግኝተዋል፡፡ ባለፈው ሳምንት የሜዳንን ሥራ አስኪያጅ ጨምሮ አምስት የኪሚያ ፋርማ ሠራተኞች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ከአፍንጫ ናሙና መውሰጃ የጥጥ ዘንጎችን በማጠብ እና በማሸግ ለሽያጭ አቅርበዋል በሚል የጤና እና የሸማቾች ህጎችን በመጣስ ወንጀል ተከሰዋል፡፡ የአካባቢው መገናኛ ብዙሃን ባለሥልጣናት ከ 23 ምስክሮች ሪፖርቶችን አጠናቅረዋል ብለው ዘግበዋል። በጉዳዩ የተጠረጠረው አንዱ ግለሰብ በ124,800 ዶላር ገደማ የገነባው ቅንጡ ቤት ገንዘብ የዚሁ የማጭበርበር የውጤት ስለመሆኑ እየመረመሩ ነው። መቀመጫውን በዋና መዲናዋ ጃካርታ ያደረገው ኪሚያ ፋርማ በድርጊቱ የተሳተፉ ሠራተኞችን ያባረረ ሲሆን አሠራሩን እንደሚያጠብቅ ቃል ገብቷል፡፡ ባለፉት ወራት በኳላናሙ አውሮፕላን ማረፊያ በተደጋጋሚ በረራ ያደረጉ ሁለት ጠበቆች ኪሚያ ፋራማን ለመክሰስ ማቀዳቸውን የደቡብ ቻይና ሞርኒንግ ፖስት ዘግቧል፡፡ በጋራ ክስ በመመስረት ለእያንዳንዱ ተጎጂ ተሳፋሪ 1 ቢሊዮን ሩፒያ እንደሚያገኙ ተስፋ አድርገዋል፡፡ የኢንዶኔዥያ ባለሥልጣናት በዚህ ሳምንት መጀመሪያ በሕንድ የታየው አዲሱ የኮቪድ ዝርያ በሁለት ሰዎች ላይ መገኘቱን ገልጸው ነበር፡፡
በኢንዶኔዥያ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ የኮቪድ ናሙና መሰብሰቢያዎችን በድጋሚ የተጠቀሙ ግለሰቦች ተያዙ በኢንዶኔዥያ የሚገኝ የመድኃኒት አምራች ኩባንያ ሠራተኞች ያገለገሉ የኮቪድ መመርመሪያ መሣሪያዎችን አጥበው ድጋሚ በመሸጥ ወንጀል በቁጥጥር ስር ውለዋል። በሜዳን በሚገኘው አውሮፕላን ማረፊያ በኩል የተጓጓዙ እስከ 9000 የሚደርሱ መንገደኞች እንደገና ጥቅም ላይ በዋሉት መሣሪያዎች ተመርምረው ሊሆን እንደሚችል ፖሊስ ገልጿል። በመንግሥት የሚተዳደረው ኪሚያ ፋርማ በተጓዦቹ ስም በተመሠረተ ክስ ፍርድ ቤት ሊቆም እንደሚችል ተዘገቧል፡፡ በኮቪድ ወረርሽኝ በተጠቁ በርካታ አገሮች ውስጥ ከአፍንጫ ፈሳሽ በመውሰድ መመርመር የተለመደ ሆኗል፡፡ ካለፈው ታህሳስ ጀምሮ በሰሜን ሱማትራ ሜዳን በሚገኘው ኳላናሙ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ማጭበርበሩ ሲፈጸም እንደነበር ይታመናል ብሏል ፖሊስ፡፡ ተሳፋሪዎች ለመብረር ከፈለጉ ከተህዋሲው ነጻ መሆን ይጠበቅባቸዋል። አየር ማረፊያው ፈጣን ውጤት ለሚፈልጉ በቦታው የምርመራ አማራጭ ይሰጣል። የአውሮፕላን ማረፊያው ባለሥልጣናት ኪሚያ ፋርማ የሚያቀርበውን አንቲጂን ፈጣን የመመርመሪያ መሣሪያዎችን ይጠቀሙ ነበር ተብሏል፡፡ በስህተት ተህዋሲው እንዳለባቸው የሚያሳይ የምርመራ ውጤት ማግኘታቸውን ተከትሎ ከተሳፋሪዎች ቅሬታ ቀርቧል። ባለፈው ሳምንት ፖሊስ ተሳፋሪ አስመስሎ በህቡዕ መኮንኑን በመላክ ጉዳዩን ማጣራቱን ዴቲክ የተሰኘው የአካባቢው የዜና አውታር ዘግቧል፡፡ ፖሊሱ ከአፍንጫው ናሙናው ተወስዶ ተህዋሲው እንዳለበት ሲነገረው ሌሎች ባልደረቦቹ ወደ ላቦራቶሪው በመግባት እንደገና ጥቅም ላይ የዋሉ የመመርመሪያ መሣሪያ አግኝተዋል፡፡ ባለፈው ሳምንት የሜዳንን ሥራ አስኪያጅ ጨምሮ አምስት የኪሚያ ፋርማ ሠራተኞች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ከአፍንጫ ናሙና መውሰጃ የጥጥ ዘንጎችን በማጠብ እና በማሸግ ለሽያጭ አቅርበዋል በሚል የጤና እና የሸማቾች ህጎችን በመጣስ ወንጀል ተከሰዋል፡፡ የአካባቢው መገናኛ ብዙሃን ባለሥልጣናት ከ 23 ምስክሮች ሪፖርቶችን አጠናቅረዋል ብለው ዘግበዋል። በጉዳዩ የተጠረጠረው አንዱ ግለሰብ በ124,800 ዶላር ገደማ የገነባው ቅንጡ ቤት ገንዘብ የዚሁ የማጭበርበር የውጤት ስለመሆኑ እየመረመሩ ነው። መቀመጫውን በዋና መዲናዋ ጃካርታ ያደረገው ኪሚያ ፋርማ በድርጊቱ የተሳተፉ ሠራተኞችን ያባረረ ሲሆን አሠራሩን እንደሚያጠብቅ ቃል ገብቷል፡፡ ባለፉት ወራት በኳላናሙ አውሮፕላን ማረፊያ በተደጋጋሚ በረራ ያደረጉ ሁለት ጠበቆች ኪሚያ ፋራማን ለመክሰስ ማቀዳቸውን የደቡብ ቻይና ሞርኒንግ ፖስት ዘግቧል፡፡ በጋራ ክስ በመመስረት ለእያንዳንዱ ተጎጂ ተሳፋሪ 1 ቢሊዮን ሩፒያ እንደሚያገኙ ተስፋ አድርገዋል፡፡ የኢንዶኔዥያ ባለሥልጣናት በዚህ ሳምንት መጀመሪያ በሕንድ የታየው አዲሱ የኮቪድ ዝርያ በሁለት ሰዎች ላይ መገኘቱን ገልጸው ነበር፡፡
https://www.bbc.com/amharic/news-56980753
0business
በአዲስ አበባና አካባቢዋ ባለፉት 9 ወራት በደረሰ ድንገተኛ አደጋ ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ ውድመት መድረሱ ተገለጸ
ባለፉት 9 ወራት ብቻ በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ በደረሰ የእሳትና ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት የንብረት ውድመት መድረሱ ተገለጸ። የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ለቢቢሲ እንደገለጸው ባለፉት 9 ወራት በመዲናዋ እና አካባቢዋ በደረሱ 377 ድንገተኛ አደጋዎች 511 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል። የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ በተከሰቱት ድንገተኛ አደጋዎችም የ104 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በ154 ሰዎች ላይ ድግሞ ከባድና ቀላል ጉዳት መድረሱን ገልጸው፣ ከ90 በመቶ በላይ የሚሆነው ድንገተኛ አደጋ የእሳት አደጋ መሆኑን ተናግረዋል። እንደ ኮሚሽኑ መረጃ ከሟቾቹ ውስጥ በእሳት አደጋ የሞቱት 13 ሲሆኑ ሌሎቹ በጎርፍ፣ በኤሌክትሪክ አደጋ፣ ጉድጓድ ውስጥ በመግባት እና በኮንስትራክሽን ሥራ ላይ በደረሰ አደጋ ሕይወታቸው ያለፉ ናቸው። አቶ ንጋቱ፣ በመዲናዋ እና አካባቢዋ በደረሰው አደጋ የደረሰው ጉዳት ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ጭማሬ አሳይቷል ብለዋል። አደጋዎቹን በመቆጣጠር ሂደት ላይ ጉዳት የደረሰባቸው የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ቢኖሩም የተጠቀሰው አሃዝ ይህንን እንደማያካትት አክለዋል። ከዚህ ቀደም በአደጋ ሕይወታቸውን ያጡ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች መኖራቸውንም ባለሙያው አስታውሰዋል። ባለፉት ዘጠኝ ወራትም 47 የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች የተለያየ መጠን ያለው ጉዳት አጋጥሟቸዋል። የአደጋ ጊዜ ሠራተኞቹ በ55 ሰዎች ላይ ሊደርስ የሚችልን አደጋ ማስቀረታቸውንና 3.7 ቢሊየን ብር የሚገመት የንብረት ውድመትን ማዳን ችለዋል ብለዋል። ለመሆኑ እዚህም እዚያም እየተከሰቱ ላሉ የእሳት አደጋዎች ምክንያቱ ምንድን ነው? በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ድንገተኛ አደጋዎች አጋጥመዋል። በዚህም የሰዎች ሕይወት አልፏል፤ በንብረት ላይም ከፍተኛ ውድመት ደርሷል። ባለፉት ዘጠኝ ወራት በመዲናዋ አዲስ አበባ መካኒሳ አካባቢ የደረሰው የጎርፍ አደጋ የቤተሰብ አባላት ሕይወት አልፏል። በኦሮሚያ ልዩ ዞን ቡራዩ አካባቢ ተለኩሶ በተረሳ ሻማ ሳቢያ የተነሳ የእሳት አደጋ አባትን ከአራት ልጆቹ ጋር በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሏል። ቦሌ ቡልቡላ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የጋዝ ሲሊንደር ፈንድቶ የ10 እና የ6 ህጻናት ሕይወት አልፏል። በቅርቡም በአዲስ አበባ ቃሊቲ ኢንደስትሪ መንደር ኤሊያስ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ ከ350 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወድሟል። በመዲናዋ እና አካባቢዋ ለተከሰቱ እነዚህ ድንገተኛ አደጋዎች ዋነኛ ምክንያቶች የከተሞች እያደገ መምጣት እና የሕዝብ ቁጥር መጨመር እንዲሁም የጥንቃቄ ጉድለት ናቸው ይላሉ ባለሙያው። በከተሞች ያለው የሕዝብ ቁጥር መጨመር በእሳትና በኤሌክትሪክ የሚገለገሉ ሰዎች ቁጥር እንዲጨምር ምክንያት ነው ያሉት ባለሙያው፣ ነዋሪው ለመረጃ ቅርብ የሆነ ዘመናዊ የአኗኗር ዘይቤ ቢከተልም ለጥንቃቄ የሚሰጠው ዋጋ ግን አነስተኛ ነው ብለዋል። ባለፉት ዘጠኝ ወራት ካጋጠሙት የእሳት አደጋዎች ውስጥም ከ90 በመቶ በላይ ለሚሆኑት መነሻው የጥንቃቄ ጉድለት ሲሆን 10 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ከአቅም በላይ በሆነ ችግር የተከሰቱ መሆናቸውን ባለሙያው ጠቅሰዋል። በጥንቃቄ ጉድለት ከተፈጠሩት ውስጥ ደግሞ ወደ 85.5 በመቶ የሚሆኑት ከኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ጋር የተያያዙ ናቸው። ወደ ኮሚሽኑ ሪፖርት ያልተደረጉ አደጋዎች እንደሚኖሩ የተናገሩት ባለሙያው፣ እነዚህ አሃዞች ያልተሰሙና ሪፖርት ያልተደረጉ አደጋዎችን አያካትትም ብለዋል። እነዚህ ቢካተቱ በአደጋው የደረሰው ጉዳት ከተጠቀሰው ከፍ ሊል እንደሚችል ተናግረዋል። ኮሚሽኑ የእሳት አደጋን ለመቆጣጠር ምን ያህል ብቁ ነው? ኮሚሽኑ በመዲናዋ እና አካባቢዋ የሚደርሱ ድንገተኛ አደጋዎችን ለመቆጣጠር ፈጥኖ ባለመድረስ እና የሰዎችን ሕይወትና ንብረትን ለማታደግ አስፈላጊ መሳሪያዎች እና ማሽኖች ባለመኖሩ ይተቻል። ለዚህም በከተማው ውስጥ ቤቶች ተጠጋግተው መሰራት፣ የመንገዶች ምቹ አለመሆን፣ የህንጻዎችና የመኖሪያ ቤቶች ድንገተኛ አደጋዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ምቹ ተደርገው አለመሰራታቸው፣ ስለድንገተኛ አደጋዎች በቂ ግንዛቤ አለመኖር አፋጣኝ ምላሽ ላለመስጠቱም እንደ ምክንያትነት ይጠቀሳሉ። ይህንኑ ያነሳንላቸው ባለሙያው፣ ኮሚሽኑ በዘጠኝ ቅርንጫፍ ጣቢያዎችና በአንድ ማዕከል እንደሚመራና በእያንዳንዱ ጣቢያ አራት የእሳት አደጋ ተሽከርካሪዎች መኖራቸውን ገልጸው፣ ይህ ግን እየተስፋፋ ላለው ከተማ በቂ አይደለም ብለዋል። ባለሙያው እንዳሉት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ህንጻ ላይ እሳት ቢነሳ ኮሚሽኑ ይህንን ለመቆጣጠር የሚያስችል መሳሪያ የለውም። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት ህንጻ በመዲናዋ ከሚገኙ ረጃጅም ህንጻዎች አንዱ ሲሆን ከመሬት 209 ነጥብ 15 ሜትር ከፍታ እና 53 ወለሎች አሉት። "ህንጻዎች ከፍታቸው እየጨመረ በመጣ ቁጥር ለእንዲህ ዓይነት አደጋዎች የመጋለጥ እድላቸውን የሚቀንሱበትና የሚቆጣጠሩበት መንገድ መዘርጋት ህንጻዎቹን የሚገነቡት ግለሰቦች፣ ተቋማት፣ ድርጅቶች እና መንግሥት ኃላፊነት ነው" ይላሉ። በመሆኑም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት ህንጻ አደጋ ከመድረሱ በፊት መረጃ የሚሰጥና በቀላሉ ለመቆጣጠር የሚያስችል ቴክኖሎጂ በመጠቀም የተገነባ መሆኑን ይናገራሉ። ሆኖም በከተማዋ የሚሰሩ የመኖሪያ ህንጻዎች ፣ የንግድ ተቋማት፣ የአደጋ ጊዜ መውጫ እና ድንገተኛ አደጋዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሚያስችል መልኩ የተገነቡ አለመሆናቸውን ባለሙያው ይተቻሉ። በህንጻዎቹ ላይ የእሳት ማጥፊያ መሣሪያ የተገጠመላቸው ቢኖሩም አብዛኞቹ አገልግሎት የሚሰጡ እንዳልሆኑና ባለሙያም እንደሌላቸው ጠቁመዋል። አዲስ አበባ ከተማ የእሳት ማጥፊያ ሄሊኮፕተር ለምን የላትም? የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ዋና መሥሪያ ቤት ሲገነባ ሁለት ሄሊኮፕተር እንዲያሳርፍ ተደርጎ የተሰራ ቢሆንም አንድም ሄሊኮፕተር የለውም ይላሉ። በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በርካታ ጥብቅ ፓርኮች እንዳሉና በመዲናዋም የጉለሌ የእፅዋት ማዕከል እና የእንጦጦ ፓርክ መኖራቸውን ያነሱት ባለሙያው፣ በእነዚህ ፓርኮች እሳት ቢነሳ በከተማ ባሉ የእሳት አደጋ መቆጣጠሪያ ተሽከርካሪዎችን ብቻ በመጠቀም ሊጠፋ እንደማይችል ይናገራሉ። በመሆኑም ለዚሁ ተብሎ የተዘጋጀ የእሳት ማጥፊያ ሄሊኮፕተር መኖሩ የግድ ነው ይላሉ። ባለፉት ዓመታት በርካታ የደን ቃጠሎዎች አጋጥመው አቻ ከሆኑ የአፍሪካ ከተሞች ማለትም ከኬንያ ፣ ደቡብ አፍሪካ ድጋፍ መጠየቁንና በሌሎች አገራት ድጋፍ እሳቱን ለማጥፋት መሞከሩን ባለሙያው አስታውሰዋል። ከዚህም በተጨማሪ የጎርፍ አደጋ ሲያጋጥም የሰዎችን ሕይወት ለመታደግ ጀልባዎች እንደሚያስፈልጉም ጠቁመዋል። ክልሎች የራሳቸውን የእሳት አደጋ ተሽከርካሪዎች ለማሟላት ቢሞክሩም ብዙም የተጠናከረ አቅም ስለሌላቸው በርካታ ጉዳቶች ደርሰዋል። ምንም እንኳን ኢንደስትሪ ፓርኮች ባሉበት አልፎ አልፎ የእሳት አደጋ ማጥፊያዎች በተሻለ ሁኔታ ቢኖሩም፣ በፌደራል ደረጃ የእሳት አደጋ መከለከያና መቆጣጠሪያ ተቋም ቢዋቀር ለሕብረተሰቡ የቀረበ አገልግሎት መስጠት እንደሚቻል ባለሙያው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። የእሳት አደጋ ከመድረሱ በፊትና ከደረሰ በኋላ ምን ማድረግ አለብን? በኮሚሽኑ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ማካተትና ትግበራ ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት እመቤት ኃይለሚካኤል፣ የእሳት አደጋን ለመከላከል በመኖሪያ መንደርም፣ በተቋምም ደረጃ በሕብረተሰቡ ዘንድ ግንዛቤ መፍጠር ቀዳሚው ነው ይላሉ። ከዚህም ባሻገር እያንዳንዱ ተቋም ከሚሠራው ሥራ አንጻር አደጋ የሚከላከልበትን ጥንቃቄዎችና እርምጃዎችን ሊወስድ ይገባል። ይህንን ለማድረግ እንዲያስችልም በዓለም አቀፍ ደረጃ የተቀመጡና ህንጻዎች ከሚሰጡት አገልግሎት አንጻር አደጋን ለመከላከል የሚያስችል የሚሰጣቸው መለያ (ኮድ) አለ። በዚህም መሠረት አደጋን የመከላከል ሥራው ህንጻዎች ከሚሰጡት አገልግሎት አንጻር የሚገነቡበትን ጥሬ እቃ ከመምረጥ ይጀምራል። ምክንያቱም ህንጻዎቹ የሚገነቡበት ጥሬ እቃ እሳትን የመቋቋም አቅማቸው ተመሳሳይ ስለማይሆን ነው። በመሆኑም ፋብሪካዎች ፣ ባንኮችና ሌሎች ተቋማት የሚገነቡበት ጥሬ እቃ ከሚሰጡት አገልግሎት አንጻር የተለያየ መሆን አለበት። ከዚህም በተጨማሪ ህንጻዎች በሚገነቡበት ጊዜም የእሳት ማጥፊያ ሥርዓት ዝርጋታ፣ የእሳት ማጥፊያ፣ የእሳት ሃይድራንት፣ አደጋ አነፍናፊ መሣሪያዎች [ሴንሰር] መገጠም አለባቸው። የጭስ፣ የሙቀት፣ የጋዝ እና የጨረር አነፍናፊ መሣሪያዎችን መግጠም፣ በተገቢው ሁኔታ እንዲሰሩ ማድረግ እና የሰለጠኑ ባለሙያዎችን ማዘጋጀትና በየጊዜው መስራታቸውን መከታተል ያስፈልጋል። የአደጋ ጊዜ መውጫ ቦታዎችን ማለትም በሮችን፣ መንገዶችንና ኮሪደሮችን መገንባት ማዘጋጀት፣ ተንቀሳቃሽ የእሳት ማጥፊያ መሣሪያዎችን ማደራጀት እና እሳትን መቋቋም የሚችሉ በሮችን መግጠም ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባም ባለሙያዋ ይመክራሉ። ይህም ብቻ ሳይሆን የአደጋ ጊዜ መውጫ በሮች አዘጋግና አከፋፈታቸውን ለመውጣት አመቺ እንዲሆኑ ማድረግ ወሳኝ ነው። በመጋዘኖች አሊያም በቤት ውስጥ እቃዎችን ስናስቀምጥ በዓይነት በዓይነታቸው እንዲቀመጡ ማድረግ፣ በእቃዎቹ መካከል ክፍተት እንዲኖረው ማድረግ፣ ተቀጣጣይ ነገሮች ካሉ ርቀታቸውን ጠብቀው እንዲከማቹ ማድረግም ሊደርስ የሚችልን አደጋ በመከላከልና አደጋውን በመቀነስ ረገድ አስተዋጽኦ አለው። በመኖሪያ ቤቶች አካባቢ ያለውን ጥግግት ማስቀረት ፣ የኤሌክትሪክ ዝርጋታን በባለሙያ ማከናወንና የጋዝ ሲሊንደር አጠቃቀምን ጥንቃቄ የተሞላበት ማድረግ፣ ያረጁትን መቀየር፣ የኤሌክትሪክ መሳሪያዎችን ከተጠቀሙ በኋላ መንቀል፣ የኤሌክትሪክ ገመዶችን በእቃዎች ሥር እና ህጻናት በሚደርሱበት ቦታ አለማስቀመጥ፣ የጋዝ ሲሊንደርን ሙቀት ካለበት ቦታ ማራቅ፣ የማያገለግሉ እቃዎችንና ደረቅ ተቀጣጣይ ነገሮችን ግቢ ውስጥ አለማከማቸት የእሳት አደጋ እንዳይከሰት ለማድረግ ወሳኝ እርምጃዎች ናቸው። አደጋ ከደረሰ በኋላስ ምን መደረግ አለበት? የእሳት አደጋ ከደረሰ በኋላ እሳቱን በተገኘው ነገር ለማጥፋት ከመሞከር በፊት እሳቱ የተነሳበትን መንስዔ ማወቅ አስፈላጊ ነው። በትልልቅ ተቋማት የተገጠሙ የእሳት ማጥፊያ መሣሪያዎች ህንጻዎቹ በሚሰጡት አገልግሎት ላይ የተመሰረቱ በመሆናቸው እሳት ሲከሰት መሣሪያዎቹን በተገቢው መንገድ በባለሙያ በመጠቀም ማጥፋት ወሳኙ እርምጃ ነው። "የተከሰተ አደጋ ሁሉ ተመሳሳይ የእሳት አደጋ አይደለም" የሚሉት ባለሙያዋ፣ ሁሉንም እሳት በተመሳሳይ የእሳት ማጥፊያ መሣሪያ ማጥፋት አይቻልም ይላሉ። የእሳት ማጥፊያ መንገዶች ውሃ፣ ፎም፣ ካርቦንዳኦክሳይድ እና ደረቅ ኬሚካል ዱቄት ናቸው። እነዚህ የእሳት ማጥፊያ መሣሪያዎችን የምንጠቀመውም እንደ የእሳት አደጋው መንስኤ ነው። ለምሳሌ የነዳጅ ዴፖ፣ የአልኮል መጠጦች፣ የኮስሞቲክስ፣ ዘይት ፣ ቀለም የሚመረቱበትና የሚሸጡበት ቦታ ላይ የተነሳን የእሳት አደጋ በውሃ ለማጥፋት መሞከር እሳቱን ያባብሰዋል። በመሆኑም ተቀጣጣይ ፈሳሾች ባሉበት ቦታ የተነሳን እሳት ማጥፋት የሚቻለው በፎም ነው። ፎም 90 በመቶው ውሃ ሲሆን 10 በመቶው ውሃ ነው። ደረቅ ተቀጣጣይ ነገሮች ባሉበት ደግሞ ውሃን መጠቀም አስፈላጊ ነው። የፋይናንስ ተቋሞች፣ ባንኮች ፣ ቤተ መጽሐፍት ፣ ቤተ መዛግብት፣ ሙዚየም እና የሰነዶች መቀመጫ ቦታዎች ደግሞ በውሃ ቢረጩ ሊበላሹ ስለሚችሉ እሳት ቢነሳ ካርቦንዳ ኦክሳይድን በመጠቀም ማጥፋት ይቻላል። እሳትን ማጥፋት ያለበት ማን ነው? የእሳት አደጋ ሲከሰት ማንኛውም ሰው እሳቱን ለማጥፋት መረባረብ አለበት? በምን ዓይነት ደረጃ ላይ ያለ እሳት ነው ያለ ባለሙያ ድጋፍ ሊጠፋ የሚችለው? እሳቱ የተነሳበት ተቋም ወይም ቤት ውስጥ ያሉ ሰዎችስ ምን ማድረግ አለባቸው? ባለሙያዋ እንደሚሉት ሦስት የእሳት ደረጃዎች አሉ። አንደኛው ጅምር ሲባል ቀሪዎቹ በማደግ ላይ ያለ እና የሞተ እሳት ይባላል። በመሆኑም በተቋም ወይም በመኖሪያ ቤት ያሉ ሰዎች ሊያጠፉት የሚችሉት ጅምር በተባለው ደረጃ ላይ ያለን እሳት ነው። እሳቱ በማደግ ላይ ወይም በመስፋፋት ላይ ካለ ግን ሰዎች ቤቱንም ሆነ ህንጻውን ለቀው በመውጣትና በአንድ ላይ በመሰባሰብ ለአደጋ መቆጣጠሪያ ተቋም መደወል ነው የሚጠበቅባቸው። በዚህ ደረጃ ላይ ያለ እሳት መጥፋት የሚችለው በተሽከርካሪ በታገዘ የእሳት ማጥፊያ መሣሪያ አማካይነት ነው። ሰዎች እንዲህ ዓይነት አደጋ በሚያጋጥም ጊዜም ወደ ቤቱ የሚገባውን የኦክስጅን መጠን ለመቀነስ እና ወደ ውጭ እሳቱ እንዳይስፋፋ ለማድረግ በርና መስኮት ዘግቶ መውጣትም ይመከራል። አደጋ በሚከሰትበት ሰዓት ሰዎች በድንጋጤ ይዋጣሉ። ምን አልባት የሚያደርጉት ሊጠፋቸው ይችላል። በዚህም ጊዜ ሕይወታቸውን አደጋ ላይ የሚጥል ውሳኔ ሊወስኑ ይችላሉ። በዚህ ጊዜ ግን ሰዎች ማድረግ ያለባቸው ቤታቸውን ወይም ተቋሙን ወዲያውኑ ለቀው በመውጣት ለአደጋ ጊዜ ሠራተኞች መደወል እንዳለባቸው ባለሙያዋ ይመክራሉ። " በአደጋ ጊዜ ለሰው ሕይወት ነው ቅድሚያ መሰጠት ያለበት" የሚሉት ባለሙያዋ፣ ተቀጣጣይ ነገሮች የሚለቁት መርዛማ ጋዞች ስላሉ ለእርሱ ሊጋለጡ ስለሚችሉ ቤት ውስጥ የቀረ ሰው ቢኖርም እንኳን ለባለሙያዎች መተው አስፈላጊ መሆኑን ባለሙያዋ ይመክራሉ። አደጋው የተከሰተበት ቦታ የቀረ ሰው ካለም መረጃዎች በመስጠት፣ የቤቱን ወይም የተቋሙን መግቢያ መውጫ በማመላከት የአደጋ ጊዜ ሠራተኞችን ማገዝ እንደሚገባም ባለሙያዋ ተናግረዋል። አሁን አሁን በተለይ በከተሞች አካባቢ የሚገነቡ ህንጻዎች እና የመኖሪያ መንደሮች እየተበራከቱ ነው። ይሁን እንጂ በርካታ ማሕበረሰብ የሚኖርባቸውን የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ጨምሮ መንግሥት ህንጻዎች ሲገነቡ ለደህንነት ጥንቃቄ የሚያስፈልጉ ጉዳዮችን ከግምት አያስገቡም። አብዛኞቹ የአደጋ መውጫ ጊዜ መውጫ ኮሪደርና በሮች የሏቸውም። የተገጠመላቸው የእሳት ማጥፊያ መሣሪያዎችም እንዲሁ የተገጠመላቸው አይደሉም። በተለይ ዝቅተኛ የገቢ ምንጭ ያላቸው ነዋሪዎች የሚኖሩባቸው መንደሮች የተጠጋጉና አደጋን ለመቆጣጠር የሚያመቹ የውስጥ ለውስጥ መንገድ የላቸውም። አንድ ህንጻ ሲገነባ ከዲዛይኑ ጀምሮ ደህንነት ለመጠበቅ የሚያስችሉ ደንቦችን ተግባራዊ እንዲያደርጉ የሚያስችል ሕግ ቢኖርም አፈጻፀም ላይ ግን ችግር እንዳለ ባለሙያዋ ይናገራሉ። ይህም በሰው ሕይወት እና በንብረት ላይ የሚደርሰውን ጉዳት እንዲባባስ አድርጎታል። አንዳንድ ህንጻዎችና ተቋማት ቁሳቁሶቹን ለደንቡ ቢያሟሉም ባለሙያ የሌላቸውና በየጊዜው ፍተሻ እንደማይደረግላቸውም ባለሙያዋ ተችተዋል። አሁን ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተሳሰር ይህንን ክፍተት ለመሙላት እየተሰራ ቢሆንም ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ባለሙያዋ አሳስበዋል።
በአዲስ አበባና አካባቢዋ ባለፉት 9 ወራት በደረሰ ድንገተኛ አደጋ ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ ውድመት መድረሱ ተገለጸ ባለፉት 9 ወራት ብቻ በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ በደረሰ የእሳትና ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት የንብረት ውድመት መድረሱ ተገለጸ። የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ለቢቢሲ እንደገለጸው ባለፉት 9 ወራት በመዲናዋ እና አካባቢዋ በደረሱ 377 ድንገተኛ አደጋዎች 511 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል። የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ በተከሰቱት ድንገተኛ አደጋዎችም የ104 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በ154 ሰዎች ላይ ድግሞ ከባድና ቀላል ጉዳት መድረሱን ገልጸው፣ ከ90 በመቶ በላይ የሚሆነው ድንገተኛ አደጋ የእሳት አደጋ መሆኑን ተናግረዋል። እንደ ኮሚሽኑ መረጃ ከሟቾቹ ውስጥ በእሳት አደጋ የሞቱት 13 ሲሆኑ ሌሎቹ በጎርፍ፣ በኤሌክትሪክ አደጋ፣ ጉድጓድ ውስጥ በመግባት እና በኮንስትራክሽን ሥራ ላይ በደረሰ አደጋ ሕይወታቸው ያለፉ ናቸው። አቶ ንጋቱ፣ በመዲናዋ እና አካባቢዋ በደረሰው አደጋ የደረሰው ጉዳት ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ጭማሬ አሳይቷል ብለዋል። አደጋዎቹን በመቆጣጠር ሂደት ላይ ጉዳት የደረሰባቸው የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ቢኖሩም የተጠቀሰው አሃዝ ይህንን እንደማያካትት አክለዋል። ከዚህ ቀደም በአደጋ ሕይወታቸውን ያጡ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች መኖራቸውንም ባለሙያው አስታውሰዋል። ባለፉት ዘጠኝ ወራትም 47 የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች የተለያየ መጠን ያለው ጉዳት አጋጥሟቸዋል። የአደጋ ጊዜ ሠራተኞቹ በ55 ሰዎች ላይ ሊደርስ የሚችልን አደጋ ማስቀረታቸውንና 3.7 ቢሊየን ብር የሚገመት የንብረት ውድመትን ማዳን ችለዋል ብለዋል። ለመሆኑ እዚህም እዚያም እየተከሰቱ ላሉ የእሳት አደጋዎች ምክንያቱ ምንድን ነው? በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ድንገተኛ አደጋዎች አጋጥመዋል። በዚህም የሰዎች ሕይወት አልፏል፤ በንብረት ላይም ከፍተኛ ውድመት ደርሷል። ባለፉት ዘጠኝ ወራት በመዲናዋ አዲስ አበባ መካኒሳ አካባቢ የደረሰው የጎርፍ አደጋ የቤተሰብ አባላት ሕይወት አልፏል። በኦሮሚያ ልዩ ዞን ቡራዩ አካባቢ ተለኩሶ በተረሳ ሻማ ሳቢያ የተነሳ የእሳት አደጋ አባትን ከአራት ልጆቹ ጋር በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሏል። ቦሌ ቡልቡላ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የጋዝ ሲሊንደር ፈንድቶ የ10 እና የ6 ህጻናት ሕይወት አልፏል። በቅርቡም በአዲስ አበባ ቃሊቲ ኢንደስትሪ መንደር ኤሊያስ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ ከ350 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወድሟል። በመዲናዋ እና አካባቢዋ ለተከሰቱ እነዚህ ድንገተኛ አደጋዎች ዋነኛ ምክንያቶች የከተሞች እያደገ መምጣት እና የሕዝብ ቁጥር መጨመር እንዲሁም የጥንቃቄ ጉድለት ናቸው ይላሉ ባለሙያው። በከተሞች ያለው የሕዝብ ቁጥር መጨመር በእሳትና በኤሌክትሪክ የሚገለገሉ ሰዎች ቁጥር እንዲጨምር ምክንያት ነው ያሉት ባለሙያው፣ ነዋሪው ለመረጃ ቅርብ የሆነ ዘመናዊ የአኗኗር ዘይቤ ቢከተልም ለጥንቃቄ የሚሰጠው ዋጋ ግን አነስተኛ ነው ብለዋል። ባለፉት ዘጠኝ ወራት ካጋጠሙት የእሳት አደጋዎች ውስጥም ከ90 በመቶ በላይ ለሚሆኑት መነሻው የጥንቃቄ ጉድለት ሲሆን 10 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ከአቅም በላይ በሆነ ችግር የተከሰቱ መሆናቸውን ባለሙያው ጠቅሰዋል። በጥንቃቄ ጉድለት ከተፈጠሩት ውስጥ ደግሞ ወደ 85.5 በመቶ የሚሆኑት ከኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ጋር የተያያዙ ናቸው። ወደ ኮሚሽኑ ሪፖርት ያልተደረጉ አደጋዎች እንደሚኖሩ የተናገሩት ባለሙያው፣ እነዚህ አሃዞች ያልተሰሙና ሪፖርት ያልተደረጉ አደጋዎችን አያካትትም ብለዋል። እነዚህ ቢካተቱ በአደጋው የደረሰው ጉዳት ከተጠቀሰው ከፍ ሊል እንደሚችል ተናግረዋል። ኮሚሽኑ የእሳት አደጋን ለመቆጣጠር ምን ያህል ብቁ ነው? ኮሚሽኑ በመዲናዋ እና አካባቢዋ የሚደርሱ ድንገተኛ አደጋዎችን ለመቆጣጠር ፈጥኖ ባለመድረስ እና የሰዎችን ሕይወትና ንብረትን ለማታደግ አስፈላጊ መሳሪያዎች እና ማሽኖች ባለመኖሩ ይተቻል። ለዚህም በከተማው ውስጥ ቤቶች ተጠጋግተው መሰራት፣ የመንገዶች ምቹ አለመሆን፣ የህንጻዎችና የመኖሪያ ቤቶች ድንገተኛ አደጋዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ምቹ ተደርገው አለመሰራታቸው፣ ስለድንገተኛ አደጋዎች በቂ ግንዛቤ አለመኖር አፋጣኝ ምላሽ ላለመስጠቱም እንደ ምክንያትነት ይጠቀሳሉ። ይህንኑ ያነሳንላቸው ባለሙያው፣ ኮሚሽኑ በዘጠኝ ቅርንጫፍ ጣቢያዎችና በአንድ ማዕከል እንደሚመራና በእያንዳንዱ ጣቢያ አራት የእሳት አደጋ ተሽከርካሪዎች መኖራቸውን ገልጸው፣ ይህ ግን እየተስፋፋ ላለው ከተማ በቂ አይደለም ብለዋል። ባለሙያው እንዳሉት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ህንጻ ላይ እሳት ቢነሳ ኮሚሽኑ ይህንን ለመቆጣጠር የሚያስችል መሳሪያ የለውም። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት ህንጻ በመዲናዋ ከሚገኙ ረጃጅም ህንጻዎች አንዱ ሲሆን ከመሬት 209 ነጥብ 15 ሜትር ከፍታ እና 53 ወለሎች አሉት። "ህንጻዎች ከፍታቸው እየጨመረ በመጣ ቁጥር ለእንዲህ ዓይነት አደጋዎች የመጋለጥ እድላቸውን የሚቀንሱበትና የሚቆጣጠሩበት መንገድ መዘርጋት ህንጻዎቹን የሚገነቡት ግለሰቦች፣ ተቋማት፣ ድርጅቶች እና መንግሥት ኃላፊነት ነው" ይላሉ። በመሆኑም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት ህንጻ አደጋ ከመድረሱ በፊት መረጃ የሚሰጥና በቀላሉ ለመቆጣጠር የሚያስችል ቴክኖሎጂ በመጠቀም የተገነባ መሆኑን ይናገራሉ። ሆኖም በከተማዋ የሚሰሩ የመኖሪያ ህንጻዎች ፣ የንግድ ተቋማት፣ የአደጋ ጊዜ መውጫ እና ድንገተኛ አደጋዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሚያስችል መልኩ የተገነቡ አለመሆናቸውን ባለሙያው ይተቻሉ። በህንጻዎቹ ላይ የእሳት ማጥፊያ መሣሪያ የተገጠመላቸው ቢኖሩም አብዛኞቹ አገልግሎት የሚሰጡ እንዳልሆኑና ባለሙያም እንደሌላቸው ጠቁመዋል። አዲስ አበባ ከተማ የእሳት ማጥፊያ ሄሊኮፕተር ለምን የላትም? የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ዋና መሥሪያ ቤት ሲገነባ ሁለት ሄሊኮፕተር እንዲያሳርፍ ተደርጎ የተሰራ ቢሆንም አንድም ሄሊኮፕተር የለውም ይላሉ። በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በርካታ ጥብቅ ፓርኮች እንዳሉና በመዲናዋም የጉለሌ የእፅዋት ማዕከል እና የእንጦጦ ፓርክ መኖራቸውን ያነሱት ባለሙያው፣ በእነዚህ ፓርኮች እሳት ቢነሳ በከተማ ባሉ የእሳት አደጋ መቆጣጠሪያ ተሽከርካሪዎችን ብቻ በመጠቀም ሊጠፋ እንደማይችል ይናገራሉ። በመሆኑም ለዚሁ ተብሎ የተዘጋጀ የእሳት ማጥፊያ ሄሊኮፕተር መኖሩ የግድ ነው ይላሉ። ባለፉት ዓመታት በርካታ የደን ቃጠሎዎች አጋጥመው አቻ ከሆኑ የአፍሪካ ከተሞች ማለትም ከኬንያ ፣ ደቡብ አፍሪካ ድጋፍ መጠየቁንና በሌሎች አገራት ድጋፍ እሳቱን ለማጥፋት መሞከሩን ባለሙያው አስታውሰዋል። ከዚህም በተጨማሪ የጎርፍ አደጋ ሲያጋጥም የሰዎችን ሕይወት ለመታደግ ጀልባዎች እንደሚያስፈልጉም ጠቁመዋል። ክልሎች የራሳቸውን የእሳት አደጋ ተሽከርካሪዎች ለማሟላት ቢሞክሩም ብዙም የተጠናከረ አቅም ስለሌላቸው በርካታ ጉዳቶች ደርሰዋል። ምንም እንኳን ኢንደስትሪ ፓርኮች ባሉበት አልፎ አልፎ የእሳት አደጋ ማጥፊያዎች በተሻለ ሁኔታ ቢኖሩም፣ በፌደራል ደረጃ የእሳት አደጋ መከለከያና መቆጣጠሪያ ተቋም ቢዋቀር ለሕብረተሰቡ የቀረበ አገልግሎት መስጠት እንደሚቻል ባለሙያው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። የእሳት አደጋ ከመድረሱ በፊትና ከደረሰ በኋላ ምን ማድረግ አለብን? በኮሚሽኑ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ማካተትና ትግበራ ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት እመቤት ኃይለሚካኤል፣ የእሳት አደጋን ለመከላከል በመኖሪያ መንደርም፣ በተቋምም ደረጃ በሕብረተሰቡ ዘንድ ግንዛቤ መፍጠር ቀዳሚው ነው ይላሉ። ከዚህም ባሻገር እያንዳንዱ ተቋም ከሚሠራው ሥራ አንጻር አደጋ የሚከላከልበትን ጥንቃቄዎችና እርምጃዎችን ሊወስድ ይገባል። ይህንን ለማድረግ እንዲያስችልም በዓለም አቀፍ ደረጃ የተቀመጡና ህንጻዎች ከሚሰጡት አገልግሎት አንጻር አደጋን ለመከላከል የሚያስችል የሚሰጣቸው መለያ (ኮድ) አለ። በዚህም መሠረት አደጋን የመከላከል ሥራው ህንጻዎች ከሚሰጡት አገልግሎት አንጻር የሚገነቡበትን ጥሬ እቃ ከመምረጥ ይጀምራል። ምክንያቱም ህንጻዎቹ የሚገነቡበት ጥሬ እቃ እሳትን የመቋቋም አቅማቸው ተመሳሳይ ስለማይሆን ነው። በመሆኑም ፋብሪካዎች ፣ ባንኮችና ሌሎች ተቋማት የሚገነቡበት ጥሬ እቃ ከሚሰጡት አገልግሎት አንጻር የተለያየ መሆን አለበት። ከዚህም በተጨማሪ ህንጻዎች በሚገነቡበት ጊዜም የእሳት ማጥፊያ ሥርዓት ዝርጋታ፣ የእሳት ማጥፊያ፣ የእሳት ሃይድራንት፣ አደጋ አነፍናፊ መሣሪያዎች [ሴንሰር] መገጠም አለባቸው። የጭስ፣ የሙቀት፣ የጋዝ እና የጨረር አነፍናፊ መሣሪያዎችን መግጠም፣ በተገቢው ሁኔታ እንዲሰሩ ማድረግ እና የሰለጠኑ ባለሙያዎችን ማዘጋጀትና በየጊዜው መስራታቸውን መከታተል ያስፈልጋል። የአደጋ ጊዜ መውጫ ቦታዎችን ማለትም በሮችን፣ መንገዶችንና ኮሪደሮችን መገንባት ማዘጋጀት፣ ተንቀሳቃሽ የእሳት ማጥፊያ መሣሪያዎችን ማደራጀት እና እሳትን መቋቋም የሚችሉ በሮችን መግጠም ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባም ባለሙያዋ ይመክራሉ። ይህም ብቻ ሳይሆን የአደጋ ጊዜ መውጫ በሮች አዘጋግና አከፋፈታቸውን ለመውጣት አመቺ እንዲሆኑ ማድረግ ወሳኝ ነው። በመጋዘኖች አሊያም በቤት ውስጥ እቃዎችን ስናስቀምጥ በዓይነት በዓይነታቸው እንዲቀመጡ ማድረግ፣ በእቃዎቹ መካከል ክፍተት እንዲኖረው ማድረግ፣ ተቀጣጣይ ነገሮች ካሉ ርቀታቸውን ጠብቀው እንዲከማቹ ማድረግም ሊደርስ የሚችልን አደጋ በመከላከልና አደጋውን በመቀነስ ረገድ አስተዋጽኦ አለው። በመኖሪያ ቤቶች አካባቢ ያለውን ጥግግት ማስቀረት ፣ የኤሌክትሪክ ዝርጋታን በባለሙያ ማከናወንና የጋዝ ሲሊንደር አጠቃቀምን ጥንቃቄ የተሞላበት ማድረግ፣ ያረጁትን መቀየር፣ የኤሌክትሪክ መሳሪያዎችን ከተጠቀሙ በኋላ መንቀል፣ የኤሌክትሪክ ገመዶችን በእቃዎች ሥር እና ህጻናት በሚደርሱበት ቦታ አለማስቀመጥ፣ የጋዝ ሲሊንደርን ሙቀት ካለበት ቦታ ማራቅ፣ የማያገለግሉ እቃዎችንና ደረቅ ተቀጣጣይ ነገሮችን ግቢ ውስጥ አለማከማቸት የእሳት አደጋ እንዳይከሰት ለማድረግ ወሳኝ እርምጃዎች ናቸው። አደጋ ከደረሰ በኋላስ ምን መደረግ አለበት? የእሳት አደጋ ከደረሰ በኋላ እሳቱን በተገኘው ነገር ለማጥፋት ከመሞከር በፊት እሳቱ የተነሳበትን መንስዔ ማወቅ አስፈላጊ ነው። በትልልቅ ተቋማት የተገጠሙ የእሳት ማጥፊያ መሣሪያዎች ህንጻዎቹ በሚሰጡት አገልግሎት ላይ የተመሰረቱ በመሆናቸው እሳት ሲከሰት መሣሪያዎቹን በተገቢው መንገድ በባለሙያ በመጠቀም ማጥፋት ወሳኙ እርምጃ ነው። "የተከሰተ አደጋ ሁሉ ተመሳሳይ የእሳት አደጋ አይደለም" የሚሉት ባለሙያዋ፣ ሁሉንም እሳት በተመሳሳይ የእሳት ማጥፊያ መሣሪያ ማጥፋት አይቻልም ይላሉ። የእሳት ማጥፊያ መንገዶች ውሃ፣ ፎም፣ ካርቦንዳኦክሳይድ እና ደረቅ ኬሚካል ዱቄት ናቸው። እነዚህ የእሳት ማጥፊያ መሣሪያዎችን የምንጠቀመውም እንደ የእሳት አደጋው መንስኤ ነው። ለምሳሌ የነዳጅ ዴፖ፣ የአልኮል መጠጦች፣ የኮስሞቲክስ፣ ዘይት ፣ ቀለም የሚመረቱበትና የሚሸጡበት ቦታ ላይ የተነሳን የእሳት አደጋ በውሃ ለማጥፋት መሞከር እሳቱን ያባብሰዋል። በመሆኑም ተቀጣጣይ ፈሳሾች ባሉበት ቦታ የተነሳን እሳት ማጥፋት የሚቻለው በፎም ነው። ፎም 90 በመቶው ውሃ ሲሆን 10 በመቶው ውሃ ነው። ደረቅ ተቀጣጣይ ነገሮች ባሉበት ደግሞ ውሃን መጠቀም አስፈላጊ ነው። የፋይናንስ ተቋሞች፣ ባንኮች ፣ ቤተ መጽሐፍት ፣ ቤተ መዛግብት፣ ሙዚየም እና የሰነዶች መቀመጫ ቦታዎች ደግሞ በውሃ ቢረጩ ሊበላሹ ስለሚችሉ እሳት ቢነሳ ካርቦንዳ ኦክሳይድን በመጠቀም ማጥፋት ይቻላል። እሳትን ማጥፋት ያለበት ማን ነው? የእሳት አደጋ ሲከሰት ማንኛውም ሰው እሳቱን ለማጥፋት መረባረብ አለበት? በምን ዓይነት ደረጃ ላይ ያለ እሳት ነው ያለ ባለሙያ ድጋፍ ሊጠፋ የሚችለው? እሳቱ የተነሳበት ተቋም ወይም ቤት ውስጥ ያሉ ሰዎችስ ምን ማድረግ አለባቸው? ባለሙያዋ እንደሚሉት ሦስት የእሳት ደረጃዎች አሉ። አንደኛው ጅምር ሲባል ቀሪዎቹ በማደግ ላይ ያለ እና የሞተ እሳት ይባላል። በመሆኑም በተቋም ወይም በመኖሪያ ቤት ያሉ ሰዎች ሊያጠፉት የሚችሉት ጅምር በተባለው ደረጃ ላይ ያለን እሳት ነው። እሳቱ በማደግ ላይ ወይም በመስፋፋት ላይ ካለ ግን ሰዎች ቤቱንም ሆነ ህንጻውን ለቀው በመውጣትና በአንድ ላይ በመሰባሰብ ለአደጋ መቆጣጠሪያ ተቋም መደወል ነው የሚጠበቅባቸው። በዚህ ደረጃ ላይ ያለ እሳት መጥፋት የሚችለው በተሽከርካሪ በታገዘ የእሳት ማጥፊያ መሣሪያ አማካይነት ነው። ሰዎች እንዲህ ዓይነት አደጋ በሚያጋጥም ጊዜም ወደ ቤቱ የሚገባውን የኦክስጅን መጠን ለመቀነስ እና ወደ ውጭ እሳቱ እንዳይስፋፋ ለማድረግ በርና መስኮት ዘግቶ መውጣትም ይመከራል። አደጋ በሚከሰትበት ሰዓት ሰዎች በድንጋጤ ይዋጣሉ። ምን አልባት የሚያደርጉት ሊጠፋቸው ይችላል። በዚህም ጊዜ ሕይወታቸውን አደጋ ላይ የሚጥል ውሳኔ ሊወስኑ ይችላሉ። በዚህ ጊዜ ግን ሰዎች ማድረግ ያለባቸው ቤታቸውን ወይም ተቋሙን ወዲያውኑ ለቀው በመውጣት ለአደጋ ጊዜ ሠራተኞች መደወል እንዳለባቸው ባለሙያዋ ይመክራሉ። " በአደጋ ጊዜ ለሰው ሕይወት ነው ቅድሚያ መሰጠት ያለበት" የሚሉት ባለሙያዋ፣ ተቀጣጣይ ነገሮች የሚለቁት መርዛማ ጋዞች ስላሉ ለእርሱ ሊጋለጡ ስለሚችሉ ቤት ውስጥ የቀረ ሰው ቢኖርም እንኳን ለባለሙያዎች መተው አስፈላጊ መሆኑን ባለሙያዋ ይመክራሉ። አደጋው የተከሰተበት ቦታ የቀረ ሰው ካለም መረጃዎች በመስጠት፣ የቤቱን ወይም የተቋሙን መግቢያ መውጫ በማመላከት የአደጋ ጊዜ ሠራተኞችን ማገዝ እንደሚገባም ባለሙያዋ ተናግረዋል። አሁን አሁን በተለይ በከተሞች አካባቢ የሚገነቡ ህንጻዎች እና የመኖሪያ መንደሮች እየተበራከቱ ነው። ይሁን እንጂ በርካታ ማሕበረሰብ የሚኖርባቸውን የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ጨምሮ መንግሥት ህንጻዎች ሲገነቡ ለደህንነት ጥንቃቄ የሚያስፈልጉ ጉዳዮችን ከግምት አያስገቡም። አብዛኞቹ የአደጋ መውጫ ጊዜ መውጫ ኮሪደርና በሮች የሏቸውም። የተገጠመላቸው የእሳት ማጥፊያ መሣሪያዎችም እንዲሁ የተገጠመላቸው አይደሉም። በተለይ ዝቅተኛ የገቢ ምንጭ ያላቸው ነዋሪዎች የሚኖሩባቸው መንደሮች የተጠጋጉና አደጋን ለመቆጣጠር የሚያመቹ የውስጥ ለውስጥ መንገድ የላቸውም። አንድ ህንጻ ሲገነባ ከዲዛይኑ ጀምሮ ደህንነት ለመጠበቅ የሚያስችሉ ደንቦችን ተግባራዊ እንዲያደርጉ የሚያስችል ሕግ ቢኖርም አፈጻፀም ላይ ግን ችግር እንዳለ ባለሙያዋ ይናገራሉ። ይህም በሰው ሕይወት እና በንብረት ላይ የሚደርሰውን ጉዳት እንዲባባስ አድርጎታል። አንዳንድ ህንጻዎችና ተቋማት ቁሳቁሶቹን ለደንቡ ቢያሟሉም ባለሙያ የሌላቸውና በየጊዜው ፍተሻ እንደማይደረግላቸውም ባለሙያዋ ተችተዋል። አሁን ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተሳሰር ይህንን ክፍተት ለመሙላት እየተሰራ ቢሆንም ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ባለሙያዋ አሳስበዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-61435709
2health
በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከአምስት ሺህ ተሻገረ
በኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት ቀናት ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ከ70 በላይ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ተመዘገበ። ከጤና ሚንስቴር እና ከሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የተገኙ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከሆነ ማክሰኞ መስከረም 4/2014 ዓ.ም. ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ የ34 ሰው ሕይወት አልፏል። ሰኞ መስከረም 3/2014 ዓ.ም. ደግሞ ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ የ38 ሰዎች ሕይወት አልፎ፤ በሁለቱ ቀናት ውስጥ ብቻ 72 ሰዎች ለሞት ተዳርገዋል። በወረርሽኙ ምክንያት ሕይወታቸው ከሚያልፍ ሰዎች በተጨማሪ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እንዲሁ በከፍተኛ ሁኔታ ጭማሪ እያሳየ ነው። ከሰሞኑ በቫይረሱ ምክንያት የሚሞቱ እና የሚያዙ ሰዎች ቁጥር የጨመረው 'ዴልታ' በተባለው አዲስ አይነት የቫይረሱ ዝርያ ስርጭት ምክንያት መሆኑን የጤና ሚንስትር ዲኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማን ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል። ሦስተኛ ዙር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ እንደተከሰተ መልክት በታየባት ኢትዮጵያ፤ "ዴልታ" የተሰኘው አዲስ የኮቪድ ዝርያ መገኘቱንም የጤና ሚንስቴር ባለፈው ሳምንት አስታውቆ ነበር። የአሜሪካ በሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል እንደሚለው ይህ 'ዴልታ' የኮቪድ ዝርያ ከሌላው የቫይረሱ ዝረያ ሁለት እጥፍ የመስፋፋት አቅም ያለው ሲሆን የሚያስከትለው ህመምም ከፍ ያለ ነው። 'ዴልታ' የተባለው ይህ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ሁሉንም የዕድሜ ክልል የሚያጠቃ፣ ለከባድ ህመምና ሞት የሚዳርግ በተለይም ባልተከተቡ ሰዎች ላይ የሚበረታ መሆኑ ተነግሯል። የጤና ሚንስቴር ዲኤታው እንዳሉት በአሁኑ ጊዜ 'ዴልታ' በተሰኘው የቫይረሱ ዝርያ የሚያዙ፣ ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል የሚገቡ እና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ ነው። ሕብረተሰቡ የኮቪድ-19 ቅድመ ጥንቃቄ መመሪያዎችን አለመከበር የቫይረሱ ስርጭት እንዲስፋፋ ካደረጉ ምክንያቶች አንዱ እንደሆነ በተደጋጋሚ ሲገለጽ ቆይቷል። ከዚህ ቀደም ለመጨረሻ ጊዜ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ከ30 በላይ የሞት መጠን የተመዘገበው ባለፈው ዓመት 2013 ሚያዝያ ወር የመጨረሻ ሳምንታት ላይ ነበር። ሚያዝያ 19 ላይ 35 ሰዎች፣ ሚያዝያ 20 ላይ 34 ሰዎች እንዲሁም ሚያዝያ 25 እና 30/2013 ዓ.ም. ላይ ከበሽታው ጋር በተያያዘ 31 ሰዎች መሞታቸውን የጤና ሚንቴር አስታውቆ ነበር። አዲሱ የኮቪድ-19 ዝርያ 'ዴልታ' ከቀናት በፊት የጤና ጥበቃ ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ አዲሱ የኮቪድ-19 ዝርያ ቀደሞ ካለው የከፋ መሆኑን ተናግረዋል። 'ዴልታ' የተሰኘው የኮሮናቫይረስ ዝርያ የኮቪድ-19 ክትባት በወሰዱ ሰዎች ላይ የሚኖረው ጉዳት ዝቅተኛ ስለሆነ ሰዎች የኮቪድ-19 ክትባቶችን እንዲወስዱ ይመከራሉ። መንግሥት የኮሮናቫይረስ በሽታ በከፍተኛ ሁኔታ መስፋፋት በመቀጠሉ የጤና ሚኒስቴር ከጥቂት ሳምንት በፊት በሽታውን ለመከላከል መወስድ ስላለባቸው የጥንቃቄ እርምጃዎች ያወጣውን መመሪያ በማሻሻል በጥብቅ ተግባራዊ እንዲሆን አዟል። ከዚህ በተጨማሪም የኮቪድ-19 ክትባት የሚሰጣቸው ዜጎች የዕድሜ ገደብ ዝቅ ከመደረጉ በተጨማሪ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች እንዲካተቱ ተደርጓል። የኮሮናቫይረስ ክትባት በኢትዮጵያ መሰጠት ሲጀምር ክትባቱ በቀዳሚነት ለጤና ባለሙያዎች፣ ዕድሜያቸው ከ65 ዓመት በላይ ለሆኑ እንዲሁም ዕድሜያቸው ከ50 እስከ 60 ሆኖ ተጓዳኝ ህመም ላለባቸው እንዲሰጥ ቅድሚያ ተሰጥቶ ነበር። በአሁኑ ወቅት ደግሞ በሽታው በከፍተኛ ሁኔታ በተስፋፋባት በመዲናዋ በአዲስ አበባ ውስጥ ያሉ እድሜያቸው ከ35 ዓመት በላይ ለሆኑ ነዋሪዎች እንዲሁም በሌሎች የአገሪቱ ክልሎችና የከተማ አስተዳደር እድሜያቸዉ ከ55 ዓመት በላይ ለሆኑ ዜጎች እንደሚሰጥ የጤና ሚኒስተሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ አስታውቀው ነበር። በኢትዮጵያ የወረርሽኙ መከላከያ ክትባት መሰጠት ከጀመረ አንስቶ አስከ ትናንት መስከረም 4 2014 ዓ.ም. ድረስ 2.3 ሚሊዮን ሕዝብ ክትባት ወስዷል። የአሜሪካ የበሽታ መከላከል እና መቆጣጠር ማዕከል በኮቪድ ስርጭት ምክንያት ኢትዮጵያን "ደረጃ ሦስት" በሚል የጉዞ ማስጠንቀቂያ ከሰጠባቸው አገራት ውስጥ ትናንት አካቷል። የአሜሪካ መንግሥት ዜጎቹ "ደረጃ ሦስት" ውስጥ ወደ ተመደቡ አገራት አስገዳጅ ያልሆነ ጉዞ እንዳያደርጉ ይመክራል። የኮቪድ-19 የበለጠ የከፋባቸው አገራት ደግሞ "ደረጃ አራት" ውስጥ የሚካተቱ ሲሆን፤ የአሜሪካ መንግሥት ዜጎቹ ወደነዚህ አገራት እንዳይጓዙ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል። የክትባት ፍትሐዊነት የዓለም ጤና ድርጅት አፍሪካ ከቀሪው ዓለም ጋር ስትነጻጸር በኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባት አቅርቦት "ወደኋላ ቀርታለች" ሲል አስጠነቀቀ። የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት የዓለም ጤና ድርጅት ባስቀመው ግብ መሠረት ባለንበት የፈረንጆች ዓመት 40 በመቶ የሚሆነውን ሕዝባቸውን መከተብ የሚችሉት የአፍሪካ አገራት ሁለት ብቻ ናቸው። ይህም ከሌሎች የዓለም አህጉራት ሁሉ በጣሙን ዝቅተኛው ነው ብለዋል፤ ዶ/ር ቴድሮስ። ዳይሬክተሩ እንዳሉት እስካሁን በዓለም ዙሪያ ከ5.7 ቢሊየን በላይ የኮሮናቫይረስ ክትባቶች የተሰጡ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ለአፍሪካ የደረሰው ግን 2 በመቶው ብቻ ነው። ዶ/ር ቴድሮስ ጨምረውም ክትባቶቹ በፍትሐዊ ሁኔታ ካልተከፋፈለ ቫይረሱ ባህሪዩን እንዲቀይር የሚያደርግ ከፍተኛ ዕድል እንዳለ አስጠንቅቀዋል።
በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከአምስት ሺህ ተሻገረ በኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት ቀናት ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ከ70 በላይ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ተመዘገበ። ከጤና ሚንስቴር እና ከሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የተገኙ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከሆነ ማክሰኞ መስከረም 4/2014 ዓ.ም. ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ የ34 ሰው ሕይወት አልፏል። ሰኞ መስከረም 3/2014 ዓ.ም. ደግሞ ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ የ38 ሰዎች ሕይወት አልፎ፤ በሁለቱ ቀናት ውስጥ ብቻ 72 ሰዎች ለሞት ተዳርገዋል። በወረርሽኙ ምክንያት ሕይወታቸው ከሚያልፍ ሰዎች በተጨማሪ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እንዲሁ በከፍተኛ ሁኔታ ጭማሪ እያሳየ ነው። ከሰሞኑ በቫይረሱ ምክንያት የሚሞቱ እና የሚያዙ ሰዎች ቁጥር የጨመረው 'ዴልታ' በተባለው አዲስ አይነት የቫይረሱ ዝርያ ስርጭት ምክንያት መሆኑን የጤና ሚንስትር ዲኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማን ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል። ሦስተኛ ዙር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ እንደተከሰተ መልክት በታየባት ኢትዮጵያ፤ "ዴልታ" የተሰኘው አዲስ የኮቪድ ዝርያ መገኘቱንም የጤና ሚንስቴር ባለፈው ሳምንት አስታውቆ ነበር። የአሜሪካ በሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል እንደሚለው ይህ 'ዴልታ' የኮቪድ ዝርያ ከሌላው የቫይረሱ ዝረያ ሁለት እጥፍ የመስፋፋት አቅም ያለው ሲሆን የሚያስከትለው ህመምም ከፍ ያለ ነው። 'ዴልታ' የተባለው ይህ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ሁሉንም የዕድሜ ክልል የሚያጠቃ፣ ለከባድ ህመምና ሞት የሚዳርግ በተለይም ባልተከተቡ ሰዎች ላይ የሚበረታ መሆኑ ተነግሯል። የጤና ሚንስቴር ዲኤታው እንዳሉት በአሁኑ ጊዜ 'ዴልታ' በተሰኘው የቫይረሱ ዝርያ የሚያዙ፣ ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል የሚገቡ እና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ ነው። ሕብረተሰቡ የኮቪድ-19 ቅድመ ጥንቃቄ መመሪያዎችን አለመከበር የቫይረሱ ስርጭት እንዲስፋፋ ካደረጉ ምክንያቶች አንዱ እንደሆነ በተደጋጋሚ ሲገለጽ ቆይቷል። ከዚህ ቀደም ለመጨረሻ ጊዜ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ከ30 በላይ የሞት መጠን የተመዘገበው ባለፈው ዓመት 2013 ሚያዝያ ወር የመጨረሻ ሳምንታት ላይ ነበር። ሚያዝያ 19 ላይ 35 ሰዎች፣ ሚያዝያ 20 ላይ 34 ሰዎች እንዲሁም ሚያዝያ 25 እና 30/2013 ዓ.ም. ላይ ከበሽታው ጋር በተያያዘ 31 ሰዎች መሞታቸውን የጤና ሚንቴር አስታውቆ ነበር። አዲሱ የኮቪድ-19 ዝርያ 'ዴልታ' ከቀናት በፊት የጤና ጥበቃ ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ አዲሱ የኮቪድ-19 ዝርያ ቀደሞ ካለው የከፋ መሆኑን ተናግረዋል። 'ዴልታ' የተሰኘው የኮሮናቫይረስ ዝርያ የኮቪድ-19 ክትባት በወሰዱ ሰዎች ላይ የሚኖረው ጉዳት ዝቅተኛ ስለሆነ ሰዎች የኮቪድ-19 ክትባቶችን እንዲወስዱ ይመከራሉ። መንግሥት የኮሮናቫይረስ በሽታ በከፍተኛ ሁኔታ መስፋፋት በመቀጠሉ የጤና ሚኒስቴር ከጥቂት ሳምንት በፊት በሽታውን ለመከላከል መወስድ ስላለባቸው የጥንቃቄ እርምጃዎች ያወጣውን መመሪያ በማሻሻል በጥብቅ ተግባራዊ እንዲሆን አዟል። ከዚህ በተጨማሪም የኮቪድ-19 ክትባት የሚሰጣቸው ዜጎች የዕድሜ ገደብ ዝቅ ከመደረጉ በተጨማሪ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች እንዲካተቱ ተደርጓል። የኮሮናቫይረስ ክትባት በኢትዮጵያ መሰጠት ሲጀምር ክትባቱ በቀዳሚነት ለጤና ባለሙያዎች፣ ዕድሜያቸው ከ65 ዓመት በላይ ለሆኑ እንዲሁም ዕድሜያቸው ከ50 እስከ 60 ሆኖ ተጓዳኝ ህመም ላለባቸው እንዲሰጥ ቅድሚያ ተሰጥቶ ነበር። በአሁኑ ወቅት ደግሞ በሽታው በከፍተኛ ሁኔታ በተስፋፋባት በመዲናዋ በአዲስ አበባ ውስጥ ያሉ እድሜያቸው ከ35 ዓመት በላይ ለሆኑ ነዋሪዎች እንዲሁም በሌሎች የአገሪቱ ክልሎችና የከተማ አስተዳደር እድሜያቸዉ ከ55 ዓመት በላይ ለሆኑ ዜጎች እንደሚሰጥ የጤና ሚኒስተሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ አስታውቀው ነበር። በኢትዮጵያ የወረርሽኙ መከላከያ ክትባት መሰጠት ከጀመረ አንስቶ አስከ ትናንት መስከረም 4 2014 ዓ.ም. ድረስ 2.3 ሚሊዮን ሕዝብ ክትባት ወስዷል። የአሜሪካ የበሽታ መከላከል እና መቆጣጠር ማዕከል በኮቪድ ስርጭት ምክንያት ኢትዮጵያን "ደረጃ ሦስት" በሚል የጉዞ ማስጠንቀቂያ ከሰጠባቸው አገራት ውስጥ ትናንት አካቷል። የአሜሪካ መንግሥት ዜጎቹ "ደረጃ ሦስት" ውስጥ ወደ ተመደቡ አገራት አስገዳጅ ያልሆነ ጉዞ እንዳያደርጉ ይመክራል። የኮቪድ-19 የበለጠ የከፋባቸው አገራት ደግሞ "ደረጃ አራት" ውስጥ የሚካተቱ ሲሆን፤ የአሜሪካ መንግሥት ዜጎቹ ወደነዚህ አገራት እንዳይጓዙ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል። የክትባት ፍትሐዊነት የዓለም ጤና ድርጅት አፍሪካ ከቀሪው ዓለም ጋር ስትነጻጸር በኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባት አቅርቦት "ወደኋላ ቀርታለች" ሲል አስጠነቀቀ። የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት የዓለም ጤና ድርጅት ባስቀመው ግብ መሠረት ባለንበት የፈረንጆች ዓመት 40 በመቶ የሚሆነውን ሕዝባቸውን መከተብ የሚችሉት የአፍሪካ አገራት ሁለት ብቻ ናቸው። ይህም ከሌሎች የዓለም አህጉራት ሁሉ በጣሙን ዝቅተኛው ነው ብለዋል፤ ዶ/ር ቴድሮስ። ዳይሬክተሩ እንዳሉት እስካሁን በዓለም ዙሪያ ከ5.7 ቢሊየን በላይ የኮሮናቫይረስ ክትባቶች የተሰጡ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ለአፍሪካ የደረሰው ግን 2 በመቶው ብቻ ነው። ዶ/ር ቴድሮስ ጨምረውም ክትባቶቹ በፍትሐዊ ሁኔታ ካልተከፋፈለ ቫይረሱ ባህሪዩን እንዲቀይር የሚያደርግ ከፍተኛ ዕድል እንዳለ አስጠንቅቀዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-58567895
0business
"አገሪቷ ስለተረጋጋች ኢንተርኔቱ በሚቀጥለው ሳምንት እንደሚከፈት ተስፋ አደርጋለሁ"-ቢልለኔ ስዩም
በአገሪቱ ከተቋረጠ ቀናት የተቆጠሩት የኢንትርኔት አገልግሎት በቀጣይ ሳምንት ሊመለስ እንደሚችል በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት የሆኑት ቢልለኔ ስዩም ለቢቢሲ ኒውስዴይ ተናገሩ። ቢልለኔ እንዳሉት የኢንተርኔት አገልግሎት የብሔር ጥላቻን ለማስፋፋት ጥቅም ላይ በመዋሉ መንግሥት አገሪቱንና ሕዝቡን የመጠበቅ ኃላፊነት ስላለበት ለማቋረጥ መገደዱን ተናግረዋል። ኢንተርኔት መቼ ይለቀቃል ተብለው ሲጠየቁ ነገሮች ወደ ቀደመው ሁኔታ እየተመለሱ መሆኑን ገልጸው በሚቀጥለው ሳምንት ውስጥ ሊሆን እንደሚችል ግምታቸውን ተናግረዋል። ቃል አቀባይዋ ለኒውስዴይ እንደተናገሩት በአሁኑ ሰዓት በአዲስ አበባም ሆነ በኦሮሚያ ውስጥ ሁኔታዎች ወደ ቀደሞው መረጋጋታቸው መመለሳቸውን ገልጸዋል። ቢልለኔ ስዩም የሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ በተቀሰቀሰ ግጭት 80 ሰዎች መገደላቸውን ተናግረዋው፤ አንዳንድ ሰዎች የቀብር ሥነ ሥርዓቱን በማስተጓጎል ችግር ለመፍጠር ቢሞክሩም ፖሊስ ግን በሰዎች ላይ አልተኮሰም ብለዋል። ጨምረውም ካለመረጋጋት ታሪክ ውስጥ እየወጣች ያለችውን አገር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ወደ ዲሞክራሲ ለመውሰድ ቁርጠኛ መሆናቸውን በመግለጽ ከጥቂት ዓመታት በፊት የማይቻል የነበረው በአሁኑ ሰዓት በርካታ ወገኖች ድምጻቸውን ማሰማት ችለዋል ሲሉም ተናግረዋል። ከሃጫሉ ሁንዴሳ ሞት ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው የተያዙ ሰሰዎች መኖራቸውን የተናገሩት ቃል አቀባይዋ፤ ነገር ግን ጉዳዩ በምርመራ ላይ ያለ በመሆኑ አስተያየት መስጠት እንደማይችሉ አስታውቀዋል። በተያያዘ ዜና የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በአዲስ አበባ ቢሯቸውን ከፍተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሦስት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ላይ ምርመራ እያደረገ መሆኑን አስታወቋል። እነዚህም የቴሌቪዥን ጣቢያዎች አስራት፣ ድምጺ ወያኔ እንዲሁም ኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ (ኦኤምኤን) ሲሆኑ ኦኤምኤን የአዲስ አበባ ቢሮው መዘጋቱ ታውቋል። የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን እንዳለው ለድምጺ ወያኔ እና ለትግራይ ቲቪ ጠንከር ያለ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ መጻፉን ገልጿል። ቢቢሲ ስማቸው ከተጠቀሱት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ከእራሳቸው ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እየሞከረ ቢሆንም እስካሁን አልተሳካም። ምላሻቸውን ለማግኘት ጥረታችን ይቀጥላል። የድምጺ ወያኔ ዋና ቢሮ መቀሌ የሚገኝ ሲሆን አስራትና ኦኤምኤን የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ደግሞ ዋና ስቱዲዮዋቸው በአሜሪካ መሆኑ ይታወቃል። በትናንትናው ዕለት ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ በሰጡት መግለጫ የከተማ አስተዳደሩ ከጥምር የፀጥታ ኃይል ጋር በመሆን የከተማዋን ሰላምና ሥርዓት ማስከበር መጀመሩንም ተናግረው ነበር። "ማናችንም ብንሆን ከአገር በታች ነን፣ ከሕግ በታች ነን" በማለት አገርንና ትውልድን ቅድሚያ እንደሚሰጣቸው ጠቅሰው፤ አገር የማስተዳደር ሂደትን ለማደናቀፍ የሚሞክር የትኛውም አካልን "ትዕግስት ልክ አለው" በማለት "ከዚህ በኋላ በየትኛውም ሚዲያ፤ በየትኛውም ጽሁፍ ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጭ፤ ግለሰብን ማዕከል ያደረገ፤ ሕዝብን ማዕከል ያደረገ የጥላቻ፤ የፕሮፖጋንዳ ሥራ አንታገስም" ማለታቸው ይታወሳል። ሲፒጄ በበኩሉ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ መዘጋቱ ከተሰማ በኋላ ባወጣው መግለጫ "የመንግሥት ባለስልጣናት በአስቸኳይ ኢንተርኔቱን እንዲመልሱት" ጠይቆ ነበር።
"አገሪቷ ስለተረጋጋች ኢንተርኔቱ በሚቀጥለው ሳምንት እንደሚከፈት ተስፋ አደርጋለሁ"-ቢልለኔ ስዩም በአገሪቱ ከተቋረጠ ቀናት የተቆጠሩት የኢንትርኔት አገልግሎት በቀጣይ ሳምንት ሊመለስ እንደሚችል በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት የሆኑት ቢልለኔ ስዩም ለቢቢሲ ኒውስዴይ ተናገሩ። ቢልለኔ እንዳሉት የኢንተርኔት አገልግሎት የብሔር ጥላቻን ለማስፋፋት ጥቅም ላይ በመዋሉ መንግሥት አገሪቱንና ሕዝቡን የመጠበቅ ኃላፊነት ስላለበት ለማቋረጥ መገደዱን ተናግረዋል። ኢንተርኔት መቼ ይለቀቃል ተብለው ሲጠየቁ ነገሮች ወደ ቀደመው ሁኔታ እየተመለሱ መሆኑን ገልጸው በሚቀጥለው ሳምንት ውስጥ ሊሆን እንደሚችል ግምታቸውን ተናግረዋል። ቃል አቀባይዋ ለኒውስዴይ እንደተናገሩት በአሁኑ ሰዓት በአዲስ አበባም ሆነ በኦሮሚያ ውስጥ ሁኔታዎች ወደ ቀደሞው መረጋጋታቸው መመለሳቸውን ገልጸዋል። ቢልለኔ ስዩም የሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ በተቀሰቀሰ ግጭት 80 ሰዎች መገደላቸውን ተናግረዋው፤ አንዳንድ ሰዎች የቀብር ሥነ ሥርዓቱን በማስተጓጎል ችግር ለመፍጠር ቢሞክሩም ፖሊስ ግን በሰዎች ላይ አልተኮሰም ብለዋል። ጨምረውም ካለመረጋጋት ታሪክ ውስጥ እየወጣች ያለችውን አገር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ወደ ዲሞክራሲ ለመውሰድ ቁርጠኛ መሆናቸውን በመግለጽ ከጥቂት ዓመታት በፊት የማይቻል የነበረው በአሁኑ ሰዓት በርካታ ወገኖች ድምጻቸውን ማሰማት ችለዋል ሲሉም ተናግረዋል። ከሃጫሉ ሁንዴሳ ሞት ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው የተያዙ ሰሰዎች መኖራቸውን የተናገሩት ቃል አቀባይዋ፤ ነገር ግን ጉዳዩ በምርመራ ላይ ያለ በመሆኑ አስተያየት መስጠት እንደማይችሉ አስታውቀዋል። በተያያዘ ዜና የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በአዲስ አበባ ቢሯቸውን ከፍተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሦስት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ላይ ምርመራ እያደረገ መሆኑን አስታወቋል። እነዚህም የቴሌቪዥን ጣቢያዎች አስራት፣ ድምጺ ወያኔ እንዲሁም ኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ (ኦኤምኤን) ሲሆኑ ኦኤምኤን የአዲስ አበባ ቢሮው መዘጋቱ ታውቋል። የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን እንዳለው ለድምጺ ወያኔ እና ለትግራይ ቲቪ ጠንከር ያለ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ መጻፉን ገልጿል። ቢቢሲ ስማቸው ከተጠቀሱት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ከእራሳቸው ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እየሞከረ ቢሆንም እስካሁን አልተሳካም። ምላሻቸውን ለማግኘት ጥረታችን ይቀጥላል። የድምጺ ወያኔ ዋና ቢሮ መቀሌ የሚገኝ ሲሆን አስራትና ኦኤምኤን የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ደግሞ ዋና ስቱዲዮዋቸው በአሜሪካ መሆኑ ይታወቃል። በትናንትናው ዕለት ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ በሰጡት መግለጫ የከተማ አስተዳደሩ ከጥምር የፀጥታ ኃይል ጋር በመሆን የከተማዋን ሰላምና ሥርዓት ማስከበር መጀመሩንም ተናግረው ነበር። "ማናችንም ብንሆን ከአገር በታች ነን፣ ከሕግ በታች ነን" በማለት አገርንና ትውልድን ቅድሚያ እንደሚሰጣቸው ጠቅሰው፤ አገር የማስተዳደር ሂደትን ለማደናቀፍ የሚሞክር የትኛውም አካልን "ትዕግስት ልክ አለው" በማለት "ከዚህ በኋላ በየትኛውም ሚዲያ፤ በየትኛውም ጽሁፍ ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጭ፤ ግለሰብን ማዕከል ያደረገ፤ ሕዝብን ማዕከል ያደረገ የጥላቻ፤ የፕሮፖጋንዳ ሥራ አንታገስም" ማለታቸው ይታወሳል። ሲፒጄ በበኩሉ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ መዘጋቱ ከተሰማ በኋላ ባወጣው መግለጫ "የመንግሥት ባለስልጣናት በአስቸኳይ ኢንተርኔቱን እንዲመልሱት" ጠይቆ ነበር።
https://www.bbc.com/amharic/53274906
3politics
በርካቶች ስፔናውያን ለካታላን ተገንጣዮች የሚሰጥ ምህረትን በመቃወም አደባባይ ወጡ
በእስር ላይ ለሚገኙት የካታላን ተገንጣዮች ለማድረግ የታሰበውን አከራካሪ የይቅርታ ዕቅድ በመቃወም በአስር ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች በስፔን ዋና ከተማ ማድሪድ የተቃውሞ ሰልፎችን አካሄዱ። የስፔን የቀኝ ክንፍ ፓርቲ አመራሮች እአአ በ2017 ያልተሳካውን የነጻነት ሙከራ የመሩ 12 ተገንጣዮች ምህረትን በመቃወም ሰልፉን ተቀላቅለዋል። በሶሻሊስት ፓርቲ የሚመራው የስፔን መንግሥት ዕቅዱን የፖለቲካ ድጋፉን ለማጎልበት ተጠቅሞበታል ሲሉ ሰልፈኞቹ ይከሳሉ። መንግሥት በበኩሉ በምህረቱ በካታሎኒያ ላይ የተፈጠረውን አለመረጋጋት ለማርገብ ይረዳል ብሏል። የከፊል ራስ ገዟ ክልል ካታሎኒያ የእአአ 2017 የነፃነት እንቅስቃሴ ስፔንን በ40 ዓመታት ውስጥ ትልቁ ወደ ተባለው የፖለቲካ ቀውስ ከቷታል። ዘጠኝ የካታላን ተገንጣይ መሪዎች በሕገወጥ የነፃነት ሪፈረንደም ውስጥ ከነበራቸው ሚና ጋር ተያይዞ ጥፋተኛ ተብለዋል። ሌሎች ሦስት ሰዎች ደግሞ ጥፋተኛ ሆነው ቢገኙም በቁጥጥር ስር አልዋሉም። እንደሰልፈኞቹ ከሆነ ይቅርታው ለብሔራዊ አንድነት አደጋ ነው። በማዕከላዊ ማድሪድ ኮሎን አደባባይ ሲሰበሰቡ ብዙዎች ቀይ እና ቢጫ ብሔራዊ ባንዲራዎችን ያውለበለቡ ነበር። ካርሎስ ባንዴቻ የተባሉ ሰልፈኛ ለሮይተርስ የዜና ወኪል እንደተናገሩት "ይህንን ማስቆም አለብ። ምክንያቱም ይቅር ለማለት ይቅርታ መጠየቅ አለበት። ተገንጣዮቹ ግን ያን አያሳዩም።" የስፔን ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ እርምጃውን ካታሎኖችን እና ስፔናውያንን ይበልጥ ያቀራርባል በሚል ውሳኔውን ተከላክለዋል። ሳንቼዝ ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ "የስፔን ማኅበረሰብ ካለፈው መጥፎ ታሪክ ወደ ተሻለ የወደፊት ኑሮ መሸጋገር ይኖርበታል" ብለዋል። የስፔኑ 'ኤል ሙንዶ' ጋዜጣ ባደረገው አንድ ጥናት መሠረት 61 በመቶ የሚሆኑት ስፔናውያን በይቅርታው አይስማሙም፣ 29.5 በመቶዎቹ ደግሞ ደግፈውታል። የስፔን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ካርመን ካልቮ ይቅርታው "ቅርብ" መሆኑን ጠቁመዋል። የአገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባለፈው ወር አስገዳጅ ባልሆነው ሪፖርት ለካታላን ተገንጣይ መሪዎች መንግሥት ሊሰጥ የሚችለውን ይቅርታ እንደሚቃወም ገልጿል።
በርካቶች ስፔናውያን ለካታላን ተገንጣዮች የሚሰጥ ምህረትን በመቃወም አደባባይ ወጡ በእስር ላይ ለሚገኙት የካታላን ተገንጣዮች ለማድረግ የታሰበውን አከራካሪ የይቅርታ ዕቅድ በመቃወም በአስር ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች በስፔን ዋና ከተማ ማድሪድ የተቃውሞ ሰልፎችን አካሄዱ። የስፔን የቀኝ ክንፍ ፓርቲ አመራሮች እአአ በ2017 ያልተሳካውን የነጻነት ሙከራ የመሩ 12 ተገንጣዮች ምህረትን በመቃወም ሰልፉን ተቀላቅለዋል። በሶሻሊስት ፓርቲ የሚመራው የስፔን መንግሥት ዕቅዱን የፖለቲካ ድጋፉን ለማጎልበት ተጠቅሞበታል ሲሉ ሰልፈኞቹ ይከሳሉ። መንግሥት በበኩሉ በምህረቱ በካታሎኒያ ላይ የተፈጠረውን አለመረጋጋት ለማርገብ ይረዳል ብሏል። የከፊል ራስ ገዟ ክልል ካታሎኒያ የእአአ 2017 የነፃነት እንቅስቃሴ ስፔንን በ40 ዓመታት ውስጥ ትልቁ ወደ ተባለው የፖለቲካ ቀውስ ከቷታል። ዘጠኝ የካታላን ተገንጣይ መሪዎች በሕገወጥ የነፃነት ሪፈረንደም ውስጥ ከነበራቸው ሚና ጋር ተያይዞ ጥፋተኛ ተብለዋል። ሌሎች ሦስት ሰዎች ደግሞ ጥፋተኛ ሆነው ቢገኙም በቁጥጥር ስር አልዋሉም። እንደሰልፈኞቹ ከሆነ ይቅርታው ለብሔራዊ አንድነት አደጋ ነው። በማዕከላዊ ማድሪድ ኮሎን አደባባይ ሲሰበሰቡ ብዙዎች ቀይ እና ቢጫ ብሔራዊ ባንዲራዎችን ያውለበለቡ ነበር። ካርሎስ ባንዴቻ የተባሉ ሰልፈኛ ለሮይተርስ የዜና ወኪል እንደተናገሩት "ይህንን ማስቆም አለብ። ምክንያቱም ይቅር ለማለት ይቅርታ መጠየቅ አለበት። ተገንጣዮቹ ግን ያን አያሳዩም።" የስፔን ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ እርምጃውን ካታሎኖችን እና ስፔናውያንን ይበልጥ ያቀራርባል በሚል ውሳኔውን ተከላክለዋል። ሳንቼዝ ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ "የስፔን ማኅበረሰብ ካለፈው መጥፎ ታሪክ ወደ ተሻለ የወደፊት ኑሮ መሸጋገር ይኖርበታል" ብለዋል። የስፔኑ 'ኤል ሙንዶ' ጋዜጣ ባደረገው አንድ ጥናት መሠረት 61 በመቶ የሚሆኑት ስፔናውያን በይቅርታው አይስማሙም፣ 29.5 በመቶዎቹ ደግሞ ደግፈውታል። የስፔን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ካርመን ካልቮ ይቅርታው "ቅርብ" መሆኑን ጠቁመዋል። የአገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባለፈው ወር አስገዳጅ ባልሆነው ሪፖርት ለካታላን ተገንጣይ መሪዎች መንግሥት ሊሰጥ የሚችለውን ይቅርታ እንደሚቃወም ገልጿል።
https://www.bbc.com/amharic/news-57455831
3politics
ሺንዞ አቤ እና አበበ ቢቂላ
ሺንዞ አቤ ኢትዮጵያ መጥተው ነበር። የዛሬ ሰባት ዓመት ገደማ። በወርሃ ጥር 2007 ዓ.ም. ኢትዮጵያ መጥተው ምን አደረጉ? ከአበበ ቢቂላ ልጅ የትናየት አበበ ጋር ተገኛኙ። የትናየት የአባቱን የአበበ ቢቂላን ፎቶ አበረከተላቸው። ለመሆኑ አበበ ቢቂላና ሺንዞ አቤ ምንና ምን ናቸው? ከሟቹ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አንደበት እንደተሰማው ከሆነ እሳቸው አበበ ቢቂላን አይረሱትም። አበበ ከ58 ዓመት ገደማ በፊት በቶኪዮ ማራቶን በባዶ እግሩ ሮጦ ድል ሲያደርግ እሳቸው ትንሽ ልጅ ነበሩ። ተማሪ ቤት ነበሩ። የአበበ ቢቂላ ስምና ዝና ደግሞ በመላዋ ጃፓን እጅግ ናኝቶ ነበር። ሺንዞ አቤ ደግሞ መጠሪያ ስማቸው አቤ ነው። ‘አቤ’ በሰሜን ጃፓን ሆካይዶ ደሴት ውስጥ ከሚነገር ‘አይኑ’ ቋንቋ የተገኘ ስያሜ ነው። አቤ በጃፓን ውስጥ የበርካታ ሰዎች መጠሪያ ስም ከመሆኑ በተጨማሪ ብዙ ቦታዎችም ይህንን ስያሜ ይጋራሉ። በዚህም የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ከዝነኛው አበበ ቢቂላ ጋር ባላቸው የስም ምስስሎሽ ትምህርት ቤት መቆሚያ መቀመጫ አጡ። የክፍል ልጆች አስቸገሯቸው። አበበ እያሉም ይጠሯቸው ነበር። በአበበ ቢቂላ በባዶ እግሩ የቶኪዮ ማራቶንን ባሸነፈበት ወቅት እሳቸው ገና 10 ዓመታቸው ነበር። ቢሆንም የአበበ ቢቂላ ድል ልክ ትናንት የሆነ ያህል ትዝ ይለኛል፣ ሲሉ ነበር ወደ ኢትዮጵያ ለጉብኝት በመጡበት ጊዜ የተናገሩት። በጉዟቸው አቤ የስመ ጥሩ ሞክሺያቸውን ፍቅር ለመግለጽ፣ የልጅነት ጊዜያቸው ጀግና ወደ ሆነው ሰው አገር ከመጡ አይቀር ቤተሰቡን እና አትሌቶችን አግኝተዋል። የአበበ ቢቂላን የሙያ ልጆች ፈለጉ አስፈለጉ። ደራርቱን፣ ኢብራሂም ጀይላንን፣ ቲኪ ገላና እና መሰረት ደፋርን አገኙ ኤኤፍፒ በወቅቱ እንደዘገበው። የአበበ ቢቂላ ልጅ የትናየት አበበም ለሺንዞ አቤ አባቱ ከ50 ዓመት በፊት ቶኪዮ ላይ ታሪክ ሰርቶ የመጨረሻውን የማራቶን መስመር በማለፍ ድል ያደረገበትን ጊዜ የሚያስታውስ ፎቶ በስጦታ አበረከተላቸው። ሺንዞ አቤ አበበ ቢቂላ ቶኪዮ ላይ ሲያሸንፍ የነበረውን ሁኔታ እያስታወሱ ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅት አድናቆታቸውን ገልጸው ነበር። “በርካታ ጃፓናውያን ተወዳዳሪዎች ሩጫውን ጨርሰው ተዘርረው ሲወድቁ፣ አበበ ግን ከባዱን ሩጫ ጨርሶ እዚው ሰውነቱን ያፍታታ ዱብ፣ ዱብ ይል ነበር” በማለት የ10 ዓመት ልጅ ሳሉ ያዩትን አበበን አስታውሰዋል። አበበ ቢቂላ በኦሊምፒክ ታሪክ ስሙ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በዓለም በደማቁ የተጻፈ አትሌት ነው። በተጨማሪ ደግሞ ሺንዞ አቤን ጨምሮ አሁን ድረስ በበርካታ ጃፓናውያን የሚጠቀስ ኮከብ ሯጭ ነው። ሐሙስ ዕለት የዓለም መገናኛ ብዙኃን በብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ላይ ዐይኑን ጥሎ ነበር። አርብ ዕለት ከማለዳው ጀምሮ ደግሞ ዓለም በሺንዞ አቤ በጥይት መመታት ከዚያም መሞት በእጅጉ ደንግጧል። እሳቸው ሥልጣን በቃኝ ካሉ ዓመታት ተቆጥረዋል። ነገር ግን ለጃፓን የላይኛው ምክር ቤት የሚወዳደር ዕጩን ወክለው ቅስቀሳ እያደረጉ ነበር። በኋላ ላይ የተመረመሩ ፎቶግራፎች እንዳሳዩት ተጠርጣሪው ገዳይ ከአቤ ኋላ በቅርብ ርቀት ቆሞ ንግግራቸውን ያዳምጥ ነበረ። ከዚያም ከጀርባቸው አከታትሎ ተኮሰባቸው። በቀኝ በኩል አንገታቸውና ጀርባቸው ላይ በጥይት ተመቱ። ተዝለፍልፈው ወደቁ። ደም ፈሰሳቸው። ሄሌኮፕተር ተጠራ። ሆስፒታል ገቡ። የጃፓን ስመጥር ሐኪሞች ነፍስ ለማዳን የቻሉትን ሁሉ አደረጉ። አልተሳካም። እሳቸው ይቺን ምድር ሲሰናበቱ ገና 67 ዓመታቸው ነበር። ረጅም ዕድሜን ለሚኖሩት ጃፓኖች ይህ ዕድሜ በአጭር የመቀጨት ያህል ነው። የጦር መሣሪያ ጥቃት እምብዛም ባልተለመደባት ጃፓን ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ የሚለው ብዙዎችን እያነጋገረ ነው። ጃፓን ጥብቅ የጦር መሣሪያ ቁጥጥር ያለባት አገር ነች። እንደ አሜሪካ ጃፓን ውስጥ የጦር መሣሪያ ከሱቅ እንደሸቀጥ እንደልብ አይገዛም። በአውሮፓውያኑ 2014 አሜሪካ ውስጥ 33,599 የጦር መሣሪያ ጥቃቶች ሲፈጸሙ፣ ጃፓን ውስጥ ግን ስድስት ብቻ ነበረ። መሣሪያ ለመታጠቅ የሚፈለግ ጃፓናዊ በመንግሥት የሚሰጥን ጥብቅ ፈተና እና የአእምሮ ጤና ምርመራን በብቃት ማለፍ ይጠበቅበታል። ለዚህም በጃፓን የጦር መሣሪያ ፍቃድ ለማግኘት ከመሞከር መሣሪያ መፈብረክ ይቀላል። ጃፓኖች ደግሞ ቁስ በማምረት ማን አህሏቸው፤ ከወዳደቀ ቁሳቁስም ቢሆን የጦር መሣሪያ ሊፈበርኩ ይችላሉ። በቁጥጥር ሥር የዋለው ገዳያቸው መሣሪያውን ቤቱ ውስጥ ራሱ ጠፍጥፎ እንደሰራው እየተዘገበ ነው። ፖሊስ የአቤ ገዳይ ለምን ግድያውን እንደፈጸመና ለድርጊቱ ተባባሪ እንዳለው ለማወቅ ምርመራ እያደረገ ነው። ቤቱ ላይ በተደረገው ፍተሻም ከጦር መሳሪያ በተጨማሪ ፈንጂዎች መገኘታው ተነግሯል። ሺንዞ አቤን በመግፈል ተጠርጥሮ በቁጥጥር ሥር የዋለው ቴተሱያ ያማጋሚ የሚባል ሥራ አጥ የ41 ዓመት ጎልማሳ መሆኑን የአካባቢው ፖሊስ አስታውቋል። ያማጋሚ ጡረተኛውን ጠቅላይ ሚኒስርት ለመግደል ምክንያቱ ምን እንደሆነ ከግምት በስተቀር የተነገረ ጉዳይ የለም። ሺንዞ አቤ፣ የአበበ ቢቂላ አድናቂና ሞክሼ፣ 20 ሺህ ጃፓናውያንን የጨረሰውን ሱናሚ አልፈው፣ እንደ መሪ የሚደረገውን ሁሉ አድርገው በአንድ ግለሰብ በተተኮሰ ቤት ሠራሽ ጥይት ላይመሱ አሸልበዋል። የፈሩት የአንጀት ቁስለት፣ ሥልጣን የለቀቁለት በሽታ ሳይገድላቸው፤ በቤት ሠራሽ ጥይት እስከወዲያኛው አሸልበዋል። ዓለም በተለይም ጃፓናውያን በእጅጉ ደንግጠዋል፣ ግድያውን ተከትሎም “ዴሞክራሲ እንጂ ፖለቲካዊ ጥቃትን አንፈልግም” የሚል የማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻን ከፍተዋል።
ሺንዞ አቤ እና አበበ ቢቂላ ሺንዞ አቤ ኢትዮጵያ መጥተው ነበር። የዛሬ ሰባት ዓመት ገደማ። በወርሃ ጥር 2007 ዓ.ም. ኢትዮጵያ መጥተው ምን አደረጉ? ከአበበ ቢቂላ ልጅ የትናየት አበበ ጋር ተገኛኙ። የትናየት የአባቱን የአበበ ቢቂላን ፎቶ አበረከተላቸው። ለመሆኑ አበበ ቢቂላና ሺንዞ አቤ ምንና ምን ናቸው? ከሟቹ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አንደበት እንደተሰማው ከሆነ እሳቸው አበበ ቢቂላን አይረሱትም። አበበ ከ58 ዓመት ገደማ በፊት በቶኪዮ ማራቶን በባዶ እግሩ ሮጦ ድል ሲያደርግ እሳቸው ትንሽ ልጅ ነበሩ። ተማሪ ቤት ነበሩ። የአበበ ቢቂላ ስምና ዝና ደግሞ በመላዋ ጃፓን እጅግ ናኝቶ ነበር። ሺንዞ አቤ ደግሞ መጠሪያ ስማቸው አቤ ነው። ‘አቤ’ በሰሜን ጃፓን ሆካይዶ ደሴት ውስጥ ከሚነገር ‘አይኑ’ ቋንቋ የተገኘ ስያሜ ነው። አቤ በጃፓን ውስጥ የበርካታ ሰዎች መጠሪያ ስም ከመሆኑ በተጨማሪ ብዙ ቦታዎችም ይህንን ስያሜ ይጋራሉ። በዚህም የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ከዝነኛው አበበ ቢቂላ ጋር ባላቸው የስም ምስስሎሽ ትምህርት ቤት መቆሚያ መቀመጫ አጡ። የክፍል ልጆች አስቸገሯቸው። አበበ እያሉም ይጠሯቸው ነበር። በአበበ ቢቂላ በባዶ እግሩ የቶኪዮ ማራቶንን ባሸነፈበት ወቅት እሳቸው ገና 10 ዓመታቸው ነበር። ቢሆንም የአበበ ቢቂላ ድል ልክ ትናንት የሆነ ያህል ትዝ ይለኛል፣ ሲሉ ነበር ወደ ኢትዮጵያ ለጉብኝት በመጡበት ጊዜ የተናገሩት። በጉዟቸው አቤ የስመ ጥሩ ሞክሺያቸውን ፍቅር ለመግለጽ፣ የልጅነት ጊዜያቸው ጀግና ወደ ሆነው ሰው አገር ከመጡ አይቀር ቤተሰቡን እና አትሌቶችን አግኝተዋል። የአበበ ቢቂላን የሙያ ልጆች ፈለጉ አስፈለጉ። ደራርቱን፣ ኢብራሂም ጀይላንን፣ ቲኪ ገላና እና መሰረት ደፋርን አገኙ ኤኤፍፒ በወቅቱ እንደዘገበው። የአበበ ቢቂላ ልጅ የትናየት አበበም ለሺንዞ አቤ አባቱ ከ50 ዓመት በፊት ቶኪዮ ላይ ታሪክ ሰርቶ የመጨረሻውን የማራቶን መስመር በማለፍ ድል ያደረገበትን ጊዜ የሚያስታውስ ፎቶ በስጦታ አበረከተላቸው። ሺንዞ አቤ አበበ ቢቂላ ቶኪዮ ላይ ሲያሸንፍ የነበረውን ሁኔታ እያስታወሱ ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅት አድናቆታቸውን ገልጸው ነበር። “በርካታ ጃፓናውያን ተወዳዳሪዎች ሩጫውን ጨርሰው ተዘርረው ሲወድቁ፣ አበበ ግን ከባዱን ሩጫ ጨርሶ እዚው ሰውነቱን ያፍታታ ዱብ፣ ዱብ ይል ነበር” በማለት የ10 ዓመት ልጅ ሳሉ ያዩትን አበበን አስታውሰዋል። አበበ ቢቂላ በኦሊምፒክ ታሪክ ስሙ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በዓለም በደማቁ የተጻፈ አትሌት ነው። በተጨማሪ ደግሞ ሺንዞ አቤን ጨምሮ አሁን ድረስ በበርካታ ጃፓናውያን የሚጠቀስ ኮከብ ሯጭ ነው። ሐሙስ ዕለት የዓለም መገናኛ ብዙኃን በብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ላይ ዐይኑን ጥሎ ነበር። አርብ ዕለት ከማለዳው ጀምሮ ደግሞ ዓለም በሺንዞ አቤ በጥይት መመታት ከዚያም መሞት በእጅጉ ደንግጧል። እሳቸው ሥልጣን በቃኝ ካሉ ዓመታት ተቆጥረዋል። ነገር ግን ለጃፓን የላይኛው ምክር ቤት የሚወዳደር ዕጩን ወክለው ቅስቀሳ እያደረጉ ነበር። በኋላ ላይ የተመረመሩ ፎቶግራፎች እንዳሳዩት ተጠርጣሪው ገዳይ ከአቤ ኋላ በቅርብ ርቀት ቆሞ ንግግራቸውን ያዳምጥ ነበረ። ከዚያም ከጀርባቸው አከታትሎ ተኮሰባቸው። በቀኝ በኩል አንገታቸውና ጀርባቸው ላይ በጥይት ተመቱ። ተዝለፍልፈው ወደቁ። ደም ፈሰሳቸው። ሄሌኮፕተር ተጠራ። ሆስፒታል ገቡ። የጃፓን ስመጥር ሐኪሞች ነፍስ ለማዳን የቻሉትን ሁሉ አደረጉ። አልተሳካም። እሳቸው ይቺን ምድር ሲሰናበቱ ገና 67 ዓመታቸው ነበር። ረጅም ዕድሜን ለሚኖሩት ጃፓኖች ይህ ዕድሜ በአጭር የመቀጨት ያህል ነው። የጦር መሣሪያ ጥቃት እምብዛም ባልተለመደባት ጃፓን ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ የሚለው ብዙዎችን እያነጋገረ ነው። ጃፓን ጥብቅ የጦር መሣሪያ ቁጥጥር ያለባት አገር ነች። እንደ አሜሪካ ጃፓን ውስጥ የጦር መሣሪያ ከሱቅ እንደሸቀጥ እንደልብ አይገዛም። በአውሮፓውያኑ 2014 አሜሪካ ውስጥ 33,599 የጦር መሣሪያ ጥቃቶች ሲፈጸሙ፣ ጃፓን ውስጥ ግን ስድስት ብቻ ነበረ። መሣሪያ ለመታጠቅ የሚፈለግ ጃፓናዊ በመንግሥት የሚሰጥን ጥብቅ ፈተና እና የአእምሮ ጤና ምርመራን በብቃት ማለፍ ይጠበቅበታል። ለዚህም በጃፓን የጦር መሣሪያ ፍቃድ ለማግኘት ከመሞከር መሣሪያ መፈብረክ ይቀላል። ጃፓኖች ደግሞ ቁስ በማምረት ማን አህሏቸው፤ ከወዳደቀ ቁሳቁስም ቢሆን የጦር መሣሪያ ሊፈበርኩ ይችላሉ። በቁጥጥር ሥር የዋለው ገዳያቸው መሣሪያውን ቤቱ ውስጥ ራሱ ጠፍጥፎ እንደሰራው እየተዘገበ ነው። ፖሊስ የአቤ ገዳይ ለምን ግድያውን እንደፈጸመና ለድርጊቱ ተባባሪ እንዳለው ለማወቅ ምርመራ እያደረገ ነው። ቤቱ ላይ በተደረገው ፍተሻም ከጦር መሳሪያ በተጨማሪ ፈንጂዎች መገኘታው ተነግሯል። ሺንዞ አቤን በመግፈል ተጠርጥሮ በቁጥጥር ሥር የዋለው ቴተሱያ ያማጋሚ የሚባል ሥራ አጥ የ41 ዓመት ጎልማሳ መሆኑን የአካባቢው ፖሊስ አስታውቋል። ያማጋሚ ጡረተኛውን ጠቅላይ ሚኒስርት ለመግደል ምክንያቱ ምን እንደሆነ ከግምት በስተቀር የተነገረ ጉዳይ የለም። ሺንዞ አቤ፣ የአበበ ቢቂላ አድናቂና ሞክሼ፣ 20 ሺህ ጃፓናውያንን የጨረሰውን ሱናሚ አልፈው፣ እንደ መሪ የሚደረገውን ሁሉ አድርገው በአንድ ግለሰብ በተተኮሰ ቤት ሠራሽ ጥይት ላይመሱ አሸልበዋል። የፈሩት የአንጀት ቁስለት፣ ሥልጣን የለቀቁለት በሽታ ሳይገድላቸው፤ በቤት ሠራሽ ጥይት እስከወዲያኛው አሸልበዋል። ዓለም በተለይም ጃፓናውያን በእጅጉ ደንግጠዋል፣ ግድያውን ተከትሎም “ዴሞክራሲ እንጂ ፖለቲካዊ ጥቃትን አንፈልግም” የሚል የማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻን ከፍተዋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cv29dpr543go
0business
ከ1600 በላይ የኢትዮጵያ ምርቶች ከቀረጥ ነጻ ወደ አገሯ እንዲገቡ ቻይና ፈቀደች
ኢትዮጵያ ምርታቸውን ወደ ቻይና ከቀረጥ እና ከኮታ ነጻ እንዲያስገቡ የገበያ ዕድል ከተፈቀደላቸው አገራት መካከል አንዷ መሆኗን የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገለጸ። የቻይና መንግሥት አብዛኞቹ ከአፍሪካ ከሆኑ አገራት ጋር ያለውን የንግድ ትስስር ለማጠናከር በሚል ባቀደው መርሃ ግብር መሠረት ነው ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ ምርቶች ያለ ቀረጥ እንዲገቡ የፈቀደው። ኢትዮጵያ በዚህ ነጻ ዕድል ለመጠቀም የሚያስፈልጉትን መረጃዎችን በወቅቱ ሳታሟላ በመቅረቷ በመርሃ ግብሩ ውስጥ ሳትካተት ቀርታለች ተብሎ ነበር። ነገር ግን በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ዋና ዳይሬክተር ቁምነገር እውነቱ፣ የኢትዮጵያ ምርቶች ከቀረጥ ነጻ ወደ ቻይና እንዲገቡ መፍቀዱን ለቢቢሲ ተናግረዋል። በዚህም መሠረት ቻይና ከ1600 በላይ የኢትዮጵያ ምርቶች ከቀረጥ ነጻ ወደ አገሯ እንዲገቡ መፍቀዷን ገልጸዋል። ይህም አሐዝ በአጠቃላይ የንግድ ልውውጥ ከሚደረግባቸው 6,422 ምርቶች መካከል 1,644ቱን ምርቶች ከቀረጥ እና ከኮታ ነጻ ማስገባት እንደሚቻል ተገልጿል፡፡ የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እንዳለው ይህ የገበያ ዕድል ከቻይና በኩል ብቻ የተሠጠ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ በዚህ ዕድል ተጠቃሚ ስትሆን የሚጠበቅባት ምንም ዓይነት ግዴታ የለም። ከዚህ ቀደም ቻይና 10 አገራት ከቀረጥ ነጻ ወደ አገሯ ምርቶች እንዲያስገቡ ዕድል ስትሰጥ ኢትዮጵያ በዝርዝሩ ውስጥ አለመካተቷ ጥያቄ ሲያስነሳ እንደነበር የጠቀሱት ዋና ዳይሬክተሯ፣ አሁን 1644 ምርቶች ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡ መፈቀዱን ለቢቢሲ አስረድተዋል። “ኢትዮጵያ ብዙ ሀብትና ምርት እያላት እንዴት ልትገለል ቻለች? የሚሉ ጥያቄዎች በተደጋጋሚ ሲነሱ ነበር። እኛም ስንጠባበቅ ነበር። አሁን 1644 ምርቶች ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡ ተፈቅዷል” ሲሉ አብራርተዋል። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ እነዚህን ሁሉ ምርቶች በአጠቃላይ ወደ ቻይና ትልካለች ማለት ሳይሆን “ከዝርዝሮቹ መካከል በእጇ ላይ የሚገኙትን ምርቶች” እንደምትልክ አክለዋል። ለምሳሌ የብረታ ብረት እጥረት እያለ እንዴት ወደ ውጭ መላክ ይቻላል? የሚሉ ጥያቄዎች እየተነሱ እንደሆነ የጠቀሱት ዋና ዳይሬክተሯ፣ “ኢትዮጵያ ወደ ቻይና መላክ የምትችለው የታወቁ ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶች ይሆናል” ብለዋል። እነዚህም ኢትዮጵያ እስካሁን ለተለያዩ የዓለም ገበያዎች በማቅረብ የምትታወቅባቸው ከቁም እንስሳት፣ ከቅባት እህሎች እና ከግብርና ምርቶች ጋር የተያያዙ ሲሆኑ፣ በተጨማሪም በቻይና ፈቃድ ከተሰጣቸው ምርቶች ውስጥም ሌሎች ከኢትዮጵያ ወደ ቻይና የሚላኩ እንደሚኖሩ ኃላፊዋ ተናግረዋል። ቻይና ከቀረጥ ነጻ ወደ አገሯ እንዲገቡ ከፈቀደቻቸው በርካታ ዓይነት የምርቶች ዝርዝር ውስጥ አሁን ለመላክ የምትችላቸውን በቀዳሚነት የምታቀርብ መሆኑም ተገልጿል። ነገር ግን በሂደት ለኢትዮጵያ ከተፈቀዱት ምርቶች ውስጥ በስፋት አምርታ ለገበያ ማቅረብ ከቻለች የተሻለ የውጭ ምንዛሪ ለማስገባት ዕድል እንዳላት ዳይሬክተሯ አመልክተዋል። “በዚህም ወደ ውጭ ምርቶችን በላክን ቁጥር እኛም ከቻይና ምርት የማስገባታችን ዕድል ሰፊ ይሆናል” ሲሉ በአገሪቱ ምጣኔ ሀብት ላይ የሚያመጣውን አዎንታዊ ተጽዕኖ ተናግረዋል። ይህ ፈቃድ ከተሰጠበት ዕለት አንስቶ በቀረጥ ነጻ ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ ምርቶችን መላክ እንደሚቻልም አያይዘው ገልጸዋል። ቻይና ይህንን ነጻ የንግድ ዕድል እንዲጠቀሙ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለአስር አገራት ነው በአሁኑ ጊዜ ፈቃድ የሰጠችው። ቀደም ሲል ለረዥም ጊዜ የቆየ ተመሳሳይ ዕድልን አሜሪካ አጎዋ በሚል ስያሜ ኢትዮጵያም ለተካተተችባቸው በማደግ ላይ ላሉ አገራት ሰጥታ ምርቶችን ከቀረጥና ከታሪፍ ነጻ እያስገቡ ይገኛሉ። ነገር ግን ኢትዮጵያ በትግራይ ውስጥ ሲካሄድ ከነበረው ጦርነት ጋር በተያያዘ ከዚህ የነጻ ንግድ ዕድል ካለፈው ዓመት ጥር ጀምሮ መታገዷ ይታወሳል።
ከ1600 በላይ የኢትዮጵያ ምርቶች ከቀረጥ ነጻ ወደ አገሯ እንዲገቡ ቻይና ፈቀደች ኢትዮጵያ ምርታቸውን ወደ ቻይና ከቀረጥ እና ከኮታ ነጻ እንዲያስገቡ የገበያ ዕድል ከተፈቀደላቸው አገራት መካከል አንዷ መሆኗን የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገለጸ። የቻይና መንግሥት አብዛኞቹ ከአፍሪካ ከሆኑ አገራት ጋር ያለውን የንግድ ትስስር ለማጠናከር በሚል ባቀደው መርሃ ግብር መሠረት ነው ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ ምርቶች ያለ ቀረጥ እንዲገቡ የፈቀደው። ኢትዮጵያ በዚህ ነጻ ዕድል ለመጠቀም የሚያስፈልጉትን መረጃዎችን በወቅቱ ሳታሟላ በመቅረቷ በመርሃ ግብሩ ውስጥ ሳትካተት ቀርታለች ተብሎ ነበር። ነገር ግን በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ዋና ዳይሬክተር ቁምነገር እውነቱ፣ የኢትዮጵያ ምርቶች ከቀረጥ ነጻ ወደ ቻይና እንዲገቡ መፍቀዱን ለቢቢሲ ተናግረዋል። በዚህም መሠረት ቻይና ከ1600 በላይ የኢትዮጵያ ምርቶች ከቀረጥ ነጻ ወደ አገሯ እንዲገቡ መፍቀዷን ገልጸዋል። ይህም አሐዝ በአጠቃላይ የንግድ ልውውጥ ከሚደረግባቸው 6,422 ምርቶች መካከል 1,644ቱን ምርቶች ከቀረጥ እና ከኮታ ነጻ ማስገባት እንደሚቻል ተገልጿል፡፡ የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እንዳለው ይህ የገበያ ዕድል ከቻይና በኩል ብቻ የተሠጠ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ በዚህ ዕድል ተጠቃሚ ስትሆን የሚጠበቅባት ምንም ዓይነት ግዴታ የለም። ከዚህ ቀደም ቻይና 10 አገራት ከቀረጥ ነጻ ወደ አገሯ ምርቶች እንዲያስገቡ ዕድል ስትሰጥ ኢትዮጵያ በዝርዝሩ ውስጥ አለመካተቷ ጥያቄ ሲያስነሳ እንደነበር የጠቀሱት ዋና ዳይሬክተሯ፣ አሁን 1644 ምርቶች ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡ መፈቀዱን ለቢቢሲ አስረድተዋል። “ኢትዮጵያ ብዙ ሀብትና ምርት እያላት እንዴት ልትገለል ቻለች? የሚሉ ጥያቄዎች በተደጋጋሚ ሲነሱ ነበር። እኛም ስንጠባበቅ ነበር። አሁን 1644 ምርቶች ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡ ተፈቅዷል” ሲሉ አብራርተዋል። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ እነዚህን ሁሉ ምርቶች በአጠቃላይ ወደ ቻይና ትልካለች ማለት ሳይሆን “ከዝርዝሮቹ መካከል በእጇ ላይ የሚገኙትን ምርቶች” እንደምትልክ አክለዋል። ለምሳሌ የብረታ ብረት እጥረት እያለ እንዴት ወደ ውጭ መላክ ይቻላል? የሚሉ ጥያቄዎች እየተነሱ እንደሆነ የጠቀሱት ዋና ዳይሬክተሯ፣ “ኢትዮጵያ ወደ ቻይና መላክ የምትችለው የታወቁ ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶች ይሆናል” ብለዋል። እነዚህም ኢትዮጵያ እስካሁን ለተለያዩ የዓለም ገበያዎች በማቅረብ የምትታወቅባቸው ከቁም እንስሳት፣ ከቅባት እህሎች እና ከግብርና ምርቶች ጋር የተያያዙ ሲሆኑ፣ በተጨማሪም በቻይና ፈቃድ ከተሰጣቸው ምርቶች ውስጥም ሌሎች ከኢትዮጵያ ወደ ቻይና የሚላኩ እንደሚኖሩ ኃላፊዋ ተናግረዋል። ቻይና ከቀረጥ ነጻ ወደ አገሯ እንዲገቡ ከፈቀደቻቸው በርካታ ዓይነት የምርቶች ዝርዝር ውስጥ አሁን ለመላክ የምትችላቸውን በቀዳሚነት የምታቀርብ መሆኑም ተገልጿል። ነገር ግን በሂደት ለኢትዮጵያ ከተፈቀዱት ምርቶች ውስጥ በስፋት አምርታ ለገበያ ማቅረብ ከቻለች የተሻለ የውጭ ምንዛሪ ለማስገባት ዕድል እንዳላት ዳይሬክተሯ አመልክተዋል። “በዚህም ወደ ውጭ ምርቶችን በላክን ቁጥር እኛም ከቻይና ምርት የማስገባታችን ዕድል ሰፊ ይሆናል” ሲሉ በአገሪቱ ምጣኔ ሀብት ላይ የሚያመጣውን አዎንታዊ ተጽዕኖ ተናግረዋል። ይህ ፈቃድ ከተሰጠበት ዕለት አንስቶ በቀረጥ ነጻ ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ ምርቶችን መላክ እንደሚቻልም አያይዘው ገልጸዋል። ቻይና ይህንን ነጻ የንግድ ዕድል እንዲጠቀሙ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለአስር አገራት ነው በአሁኑ ጊዜ ፈቃድ የሰጠችው። ቀደም ሲል ለረዥም ጊዜ የቆየ ተመሳሳይ ዕድልን አሜሪካ አጎዋ በሚል ስያሜ ኢትዮጵያም ለተካተተችባቸው በማደግ ላይ ላሉ አገራት ሰጥታ ምርቶችን ከቀረጥና ከታሪፍ ነጻ እያስገቡ ይገኛሉ። ነገር ግን ኢትዮጵያ በትግራይ ውስጥ ሲካሄድ ከነበረው ጦርነት ጋር በተያያዘ ከዚህ የነጻ ንግድ ዕድል ካለፈው ዓመት ጥር ጀምሮ መታገዷ ይታወሳል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cpvnp01eyx9o
3politics
የሶማሊያ ፕሬዚዳንት አዲስ ጠቅላይ ሚንስትር ሾሙ
የሶሚሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ አዲስ ጠቅላይ ሚንስትር ሾሙ። የፕሬዝዳንቱ ፓርቲ አባል እና የህዝብ እንደራሴ የሆኑት ሐምዛ አብዲ ባሬ የጠቅላይ ሚኒስትርነቱ ሹመት ተሰጥቷቸዋል። ፕሬዝዳንቱ ምርጫውን ለማከናወን ጊዜ ወስደው መወሰናቸውን ገልጸው ባሬም ጥሩ ዕጩ ሆነው ማግኘታቸውን ገልጸዋል። ሹመቱን ተከትሎ አስተያየታቸውን የሰጡት አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር የሶማሊያን አንድነት በማስጠበቅ ሃገሪቱን የማዳን ተግባር ላይ እንደሚያተኩሩ አስረድተዋል። ሐምዛ አብዲ ባሬ በሶማሊያ መንግሥት ውስጥ የተለያዩ የስልጣን እርከኖች ላይ ሠርተዋል። እአአ ከ2019 እስከ 20220 ድረስ የጁባላንድ የምርጫ ኮሚሽን ሊቀመንበር ባገለገሉበትም ወቅት ነው ስማቸው የገነነው። እአአ ከ2014 እስከ 2015 የቤናዲር ክልል ርዕሰ መስተዳድር እና የሞቃዲሾ ከንቲባ ለሆኑት ሐሰን መሐመድ ሁሴን አማካሪ ሆነው አገልግለዋል። የሕገ መንግሥት ጉዳዮችና የፌደራሊዝም ጉዳዮች ሚኒስቴር ከፍተኛ አማካሪ ሆነውም አገልግለዋል። ከሠላሳ ቀናት በፊት ሶማሊያ ሐሰን ሼክ መሀመድን የሶማሊያ 11ኛው ፕሬዝዳንት አድርጋ መርጣለች።  ለረዥም ጊዜ ዘግይቶ የተካሄደው ምርጫ በቀድሞው ፕሬዝዳንት መሐመድ አብዱላሂ ፋርማጆ እና በጠቅላይ ሚኒስትራቸው መሀመድ ሁሴን ሮብሌ መካከል አለመግባባት ፈጥሮ መቆየቱ ይታወሳል። አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሹመታቸው በፓርላማው ከጸደቀ በኋላ መንግሥት ይመሰርታሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የሶማሊያ ፕሬዚዳንት አዲስ ጠቅላይ ሚንስትር ሾሙ የሶሚሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ አዲስ ጠቅላይ ሚንስትር ሾሙ። የፕሬዝዳንቱ ፓርቲ አባል እና የህዝብ እንደራሴ የሆኑት ሐምዛ አብዲ ባሬ የጠቅላይ ሚኒስትርነቱ ሹመት ተሰጥቷቸዋል። ፕሬዝዳንቱ ምርጫውን ለማከናወን ጊዜ ወስደው መወሰናቸውን ገልጸው ባሬም ጥሩ ዕጩ ሆነው ማግኘታቸውን ገልጸዋል። ሹመቱን ተከትሎ አስተያየታቸውን የሰጡት አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር የሶማሊያን አንድነት በማስጠበቅ ሃገሪቱን የማዳን ተግባር ላይ እንደሚያተኩሩ አስረድተዋል። ሐምዛ አብዲ ባሬ በሶማሊያ መንግሥት ውስጥ የተለያዩ የስልጣን እርከኖች ላይ ሠርተዋል። እአአ ከ2019 እስከ 20220 ድረስ የጁባላንድ የምርጫ ኮሚሽን ሊቀመንበር ባገለገሉበትም ወቅት ነው ስማቸው የገነነው። እአአ ከ2014 እስከ 2015 የቤናዲር ክልል ርዕሰ መስተዳድር እና የሞቃዲሾ ከንቲባ ለሆኑት ሐሰን መሐመድ ሁሴን አማካሪ ሆነው አገልግለዋል። የሕገ መንግሥት ጉዳዮችና የፌደራሊዝም ጉዳዮች ሚኒስቴር ከፍተኛ አማካሪ ሆነውም አገልግለዋል። ከሠላሳ ቀናት በፊት ሶማሊያ ሐሰን ሼክ መሀመድን የሶማሊያ 11ኛው ፕሬዝዳንት አድርጋ መርጣለች።  ለረዥም ጊዜ ዘግይቶ የተካሄደው ምርጫ በቀድሞው ፕሬዝዳንት መሐመድ አብዱላሂ ፋርማጆ እና በጠቅላይ ሚኒስትራቸው መሀመድ ሁሴን ሮብሌ መካከል አለመግባባት ፈጥሮ መቆየቱ ይታወሳል። አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሹመታቸው በፓርላማው ከጸደቀ በኋላ መንግሥት ይመሰርታሉ ተብሎ ይጠበቃል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c87j5lnjjmno
0business
ለቀናት ባሕር ላይ ቆመው የነበሩ መርከቦች በሱዊዝ ቦይ ማቋረጥ ጀመሩ
የዓለማችን ዋነኛው የንግድ መርከቦች መተላለፊያ የሆነው የሱዊዝ ቦይን ዘግታው የነበረችው ግዙፍ መርከብ እንድትነሳ ከተደረገ ከአንድ ቀን በኋላ ለቀናት ቆመው የነበሩ መርከቦች ጉዟቸውን ጀመሩ። በአሁኑ መተላለፊያው በተዘጋበት ጊዜ ወደ ማቋረጫው ገብተው ባሉበት ቆመው የነበሩ 37 የጭነት መርከቦች ቅድሚያውን አግኝተው እንዲያልፉ የተደረገ ሲሆን፤ ሌሎች 70 መርከቦች ደግሞ ዛሬ ማክሰኞ በሱዊዝ ቦይ በኩል ያልፋሉ ተብሏል። የመተላለፊያው ባለስልጣናት የባሕር መስመሩ በተዘጋባቸው ባለፉት ቀናት ውስጥ ባሉበት ቆመው ለመጠበቅ ተገድደው የነበሩትን ከ300 በላይ መርከቦች አስተላልፎ ለመጨረስ ሦስት ቀን ተኩል ይፈልጋል ብለዋል። ከእነዚህ መርከቦች መካከል ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ከሞሮኮ ማዳበሪያና ከቱርክ ደግሞ የተለያዩ ሸቀጦችን የጫኑ ሁለት መርከቦች በሜዲትራኒያን ላይ ቆመው እንደቆዩ የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ለቢቢሲ መግለጹ ይታወሳል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በመተላላፊያው የሚያቋርጡ መርከቦች ለባሕር ጉዞ ብቁ መሆናቸው በባለሙያዎች ይመረመራሉ ተብሏል። 400 ሜትር ርዝመትና 200 ሺህ ቶን የምትመዝነው ኤቨር ጊቭን የተባለችው መርከብ ባለፈው ማክሰኞ ጠዋት በመተላለፊያው በኩል እያቋረጠች ሳለ አሸዋ በቀላቀለ ከባድ ንፋስ ሳቢያ መስመሯን ስታ ነበር አግድም የባሕር ማቋረጫውን የዘጋችው። መስመሩ ከተዘጋ ከሰባት ቀናት በኋላ በአሸዋ መቆፈሪያ ከባድ መሳሪያዎችና በጎታች ጀልባዎች እየተረዳች ግዙፏ መርከብ ተቀርቅራበት ከነበረው የባሕሩ ዳርቻ አሸዋ ውስጥ ሰኞ ዕለት ለማውጣት ተችሏል። የሱዊዝ መተላለፊያ ቦይ በግብጽ ግዛት ውስጥ 193 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን፤ የዓለማችን 12 በመቶ የንግድ ጭነት የሚያልፍበት መስመር ነው። የባሕር ላይ መስመሩ የሜዲትራንያንና የቀይ ባሕርን በማገናኘት ከእስያ ወደ አውሮፓ የሚደረግን ጉዞ አጭር አድርጎታል። በመተላለፊያው ላይ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች እንዳሉት እስከ ማክሰኞ ጠዋት ድረስ 306 መርከቦች ለማለፍ እየተጠባበቁ ናቸው። ከእነዚህም ውስጥ 163 በቦዩ ደቡባዊ የቀይ ባሕር ክፍል ላይ ሲገኙ ቀሪዎቹ 137ቱ ደግሞ በሰሜን በኩል ሜዲትራኒያን ባሕር ላይ ይገኛሉ ተብሏል። በሱዊዝ መተላለፊያ ቦይ በኩል ለማለፍ ተሰልፈው እየተጠባበቁ ያሉትን መርከቦች በማስተናገድ እንዲያልፉ ለማድረግ ረጅም ሠዓት የሚጠይቅ ሲሆን ሁሉም አልፈው እስኪያበቁ ድረስ ከሦስት ቀን በላይ እንደሚፈጅ ይጠበቃል።
ለቀናት ባሕር ላይ ቆመው የነበሩ መርከቦች በሱዊዝ ቦይ ማቋረጥ ጀመሩ የዓለማችን ዋነኛው የንግድ መርከቦች መተላለፊያ የሆነው የሱዊዝ ቦይን ዘግታው የነበረችው ግዙፍ መርከብ እንድትነሳ ከተደረገ ከአንድ ቀን በኋላ ለቀናት ቆመው የነበሩ መርከቦች ጉዟቸውን ጀመሩ። በአሁኑ መተላለፊያው በተዘጋበት ጊዜ ወደ ማቋረጫው ገብተው ባሉበት ቆመው የነበሩ 37 የጭነት መርከቦች ቅድሚያውን አግኝተው እንዲያልፉ የተደረገ ሲሆን፤ ሌሎች 70 መርከቦች ደግሞ ዛሬ ማክሰኞ በሱዊዝ ቦይ በኩል ያልፋሉ ተብሏል። የመተላለፊያው ባለስልጣናት የባሕር መስመሩ በተዘጋባቸው ባለፉት ቀናት ውስጥ ባሉበት ቆመው ለመጠበቅ ተገድደው የነበሩትን ከ300 በላይ መርከቦች አስተላልፎ ለመጨረስ ሦስት ቀን ተኩል ይፈልጋል ብለዋል። ከእነዚህ መርከቦች መካከል ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ከሞሮኮ ማዳበሪያና ከቱርክ ደግሞ የተለያዩ ሸቀጦችን የጫኑ ሁለት መርከቦች በሜዲትራኒያን ላይ ቆመው እንደቆዩ የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ለቢቢሲ መግለጹ ይታወሳል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በመተላላፊያው የሚያቋርጡ መርከቦች ለባሕር ጉዞ ብቁ መሆናቸው በባለሙያዎች ይመረመራሉ ተብሏል። 400 ሜትር ርዝመትና 200 ሺህ ቶን የምትመዝነው ኤቨር ጊቭን የተባለችው መርከብ ባለፈው ማክሰኞ ጠዋት በመተላለፊያው በኩል እያቋረጠች ሳለ አሸዋ በቀላቀለ ከባድ ንፋስ ሳቢያ መስመሯን ስታ ነበር አግድም የባሕር ማቋረጫውን የዘጋችው። መስመሩ ከተዘጋ ከሰባት ቀናት በኋላ በአሸዋ መቆፈሪያ ከባድ መሳሪያዎችና በጎታች ጀልባዎች እየተረዳች ግዙፏ መርከብ ተቀርቅራበት ከነበረው የባሕሩ ዳርቻ አሸዋ ውስጥ ሰኞ ዕለት ለማውጣት ተችሏል። የሱዊዝ መተላለፊያ ቦይ በግብጽ ግዛት ውስጥ 193 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን፤ የዓለማችን 12 በመቶ የንግድ ጭነት የሚያልፍበት መስመር ነው። የባሕር ላይ መስመሩ የሜዲትራንያንና የቀይ ባሕርን በማገናኘት ከእስያ ወደ አውሮፓ የሚደረግን ጉዞ አጭር አድርጎታል። በመተላለፊያው ላይ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች እንዳሉት እስከ ማክሰኞ ጠዋት ድረስ 306 መርከቦች ለማለፍ እየተጠባበቁ ናቸው። ከእነዚህም ውስጥ 163 በቦዩ ደቡባዊ የቀይ ባሕር ክፍል ላይ ሲገኙ ቀሪዎቹ 137ቱ ደግሞ በሰሜን በኩል ሜዲትራኒያን ባሕር ላይ ይገኛሉ ተብሏል። በሱዊዝ መተላለፊያ ቦይ በኩል ለማለፍ ተሰልፈው እየተጠባበቁ ያሉትን መርከቦች በማስተናገድ እንዲያልፉ ለማድረግ ረጅም ሠዓት የሚጠይቅ ሲሆን ሁሉም አልፈው እስኪያበቁ ድረስ ከሦስት ቀን በላይ እንደሚፈጅ ይጠበቃል።
https://www.bbc.com/amharic/news-56569253
2health
ለሁለት ዓመት ድንበሯን ዘግታ የቆየችው ኒው ዚላንድ በሯን ልትከፍት ነው
በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ከሁለት ዓመታት በላይ ድንበሯን ዘግታ የቆየችው ኒው ዚላንድ በስተመጨረሻ በሮቿን ልትከፍት እንደሆነ ይፋ አድርጋለች። ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ አውስትራሊያዊያን ምንም ዓይነት በለይቶ ማቆያ መቆየት ሳያስፈልጋቸው በነፃነት መግባት ይችላሉ። ከ60 ሃገራት የሚመጡ ሙሉ በሙሉ የተከተቡ ሰዎች ደግሞ ከግንቦት ወር ጀምሮ መግባት እንዲችሉ ይፈቀድላቸዋል። ከእነዚህ ሃገራት መካከል ዩናይትድ ስቴትስ እና ዩናይት ኪንግደም ይገኙበታል። ሁሉም ወደ ኒው ዚላንድ የሚመጡ ተጓዦች ከኮቭድ ነፃ መሆናቸውን የሚያሳይ ወረቀት ማሳየት አለባቸው። ኒው ዚላንድ ድንበሯን ሙሉ በሙሉ ዝግ በፈረንጆቹ መጋቢት 2020 ነበር። ኒው ዚላንድ ለአውስትራሊያ ከሰጠችው ለአጭር ጊዜ የቆየ የጉዞ ፈቃድ ውጭ ድንበሯን ለማንም ሳትከፍት ቆይታለች። አሁን ላይ ወደ ሃገሪቱ መግባትና መውጣት የሚችሉት የኒው ዚላንድ ዜጎች ብቻ ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርደን እንዳሉት ኒው ዚላንድ "ዓለምን ለመቀበል ዝግጁ ናት።" "አሁን በተሰጠን መመሪያ መሠረት ድንብራችንን ለመክፈት ሁሉም ነገር ምቹ ይመስላል። ቱሪስቶቻችንም ይመለሳሉ" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሯ። ወደ ኒው ዚላንድ ለመግባት ቪዛ ቀድሞ ያላቸው ሰዎች ከግንቦት ወር ጀምሮ እንደልባቸው መንቀሳቀስ ይችላሉ። ኒው ዚላንድ ጠንካራ የሚባል የእንቅስቃሴ ገደብ በመጣሏ የኮቪድ-19 ስርጭትን በመቆጣጠር ስሟ በተደጋጋሚ ይነሳል። ከኒው ዚላንድ ነዋሪዎች 95 በመቶው ተከትበዋል። ወረርሽኙ ከጀመረ ወዲህ በኮቪድ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 115 ብቻ ነው። ያልተከተቡ ሰዎች ሥራ አያገኙም መባሉን ተከትሎ በዋና ከተማዋ ዌሊንግተን ተቃውሞ ተቀስቅሶ እንደነበር አይዘነጋም። ምንም እንኳ ኒው ዚላንድ ድንበሯን ከፍታ፤ እጇን ዘርግታ እንግዶች ለመቀበል ብትዘጋጅም አሁንም ቢሆን በርከት ብሎ መሰባሰብም ሆነ ያለጭንብል መንቀሳቀስ ክልክል ነው።
ለሁለት ዓመት ድንበሯን ዘግታ የቆየችው ኒው ዚላንድ በሯን ልትከፍት ነው በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ከሁለት ዓመታት በላይ ድንበሯን ዘግታ የቆየችው ኒው ዚላንድ በስተመጨረሻ በሮቿን ልትከፍት እንደሆነ ይፋ አድርጋለች። ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ አውስትራሊያዊያን ምንም ዓይነት በለይቶ ማቆያ መቆየት ሳያስፈልጋቸው በነፃነት መግባት ይችላሉ። ከ60 ሃገራት የሚመጡ ሙሉ በሙሉ የተከተቡ ሰዎች ደግሞ ከግንቦት ወር ጀምሮ መግባት እንዲችሉ ይፈቀድላቸዋል። ከእነዚህ ሃገራት መካከል ዩናይትድ ስቴትስ እና ዩናይት ኪንግደም ይገኙበታል። ሁሉም ወደ ኒው ዚላንድ የሚመጡ ተጓዦች ከኮቭድ ነፃ መሆናቸውን የሚያሳይ ወረቀት ማሳየት አለባቸው። ኒው ዚላንድ ድንበሯን ሙሉ በሙሉ ዝግ በፈረንጆቹ መጋቢት 2020 ነበር። ኒው ዚላንድ ለአውስትራሊያ ከሰጠችው ለአጭር ጊዜ የቆየ የጉዞ ፈቃድ ውጭ ድንበሯን ለማንም ሳትከፍት ቆይታለች። አሁን ላይ ወደ ሃገሪቱ መግባትና መውጣት የሚችሉት የኒው ዚላንድ ዜጎች ብቻ ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርደን እንዳሉት ኒው ዚላንድ "ዓለምን ለመቀበል ዝግጁ ናት።" "አሁን በተሰጠን መመሪያ መሠረት ድንብራችንን ለመክፈት ሁሉም ነገር ምቹ ይመስላል። ቱሪስቶቻችንም ይመለሳሉ" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሯ። ወደ ኒው ዚላንድ ለመግባት ቪዛ ቀድሞ ያላቸው ሰዎች ከግንቦት ወር ጀምሮ እንደልባቸው መንቀሳቀስ ይችላሉ። ኒው ዚላንድ ጠንካራ የሚባል የእንቅስቃሴ ገደብ በመጣሏ የኮቪድ-19 ስርጭትን በመቆጣጠር ስሟ በተደጋጋሚ ይነሳል። ከኒው ዚላንድ ነዋሪዎች 95 በመቶው ተከትበዋል። ወረርሽኙ ከጀመረ ወዲህ በኮቪድ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 115 ብቻ ነው። ያልተከተቡ ሰዎች ሥራ አያገኙም መባሉን ተከትሎ በዋና ከተማዋ ዌሊንግተን ተቃውሞ ተቀስቅሶ እንደነበር አይዘነጋም። ምንም እንኳ ኒው ዚላንድ ድንበሯን ከፍታ፤ እጇን ዘርግታ እንግዶች ለመቀበል ብትዘጋጅም አሁንም ቢሆን በርከት ብሎ መሰባሰብም ሆነ ያለጭንብል መንቀሳቀስ ክልክል ነው።
https://www.bbc.com/amharic/60761357
5sports
''በኳታር የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን በሙቀቱ ተቸግሯል'' የቡድኑ መሪ
በኳታር የሚገኘው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን በሀገር ቤት ከነበረው ቀዝቃዛ የአየር ጸባይና ከፍተኛ ዝናብ አንጻር ወደ ኳታር ሲሄድ በሙቀት ምክንያት መቸገሩን የቡድኑ መሪ የሆኑት ዶክተር በዛብህ ወልዴ ለቢቢሲ ገልጸዋል። ''ሙቀቱ ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል ገምተን ነበር፤ ነገር ግን የአየሩ ሁኔታ ከገመትነው በላይ ሆኖ እንኳን ለሩጫ ውድድር ቆሞ መራመድ አስቸጋሪ ሆኖ ነው ያገኘነው። በዚሁም ምክንያት የማራቶኑ ሃሳባችን አልተሳካም፤ የአስር ሺውም ቢሆን መጥፎ ባይባልም እንዳሰብነው አልሆነም።'' በማራቶን ውድድር ወቅት በሙቀቱ ምክንያት አቋርጠው የወጡት ሦስቱም ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በአሁኑ ሰዓት በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙም የቡድን መሪው አክለዋል። ''ሯጮቹ በሰውነታቸው ውስጥ የውሃ ማነስ ነበር ያጋጠማቸው፤ ይሄን ያህል ለአደጋ የሚሰጣቸው ግን አይደለም።" • በዶሃ የሴቶች ማራቶን ሦስት ኢትዮጵያውያን ሯጮች አቋርጠው ወጡ • ሁሌም አብሮን ያለው 'የመስቀል ወፍ' በኳታር ካለው ከፍተኛ ሙቀት አንጻር ቡድኑ ከፍተኛ ሙቀት ባለባቸው አካባቢዎች ሄዶ ልምምዱን እንዲሰራ ታስቦ የነበረ ቢሆንም በብዙ ምክንያቶች ሳይሳካ መቅረቱንም የቡድን መሪው ጨምረው አስረድተዋል። ''እንደዚህ አይነት ነገር ለመተግባር ከባድ ነው። ወደታች በወረድን ቁጥር ከሙቀቱ ጋር አብረው የሚመጡ ብዙ ነገሮች አሉ" ያሉት ዶ/ር በዛብህ ሙቀት ቦታ ልምምድ መስራት ለእንደዚህ አይነት ውድድሮች ጠቃሚ ቢሆንም ብዙ ጉዳቶችም እንዳሉት ጠቅሰዋል። አትሌቶች በምን አይነት ሁኔታ ልምምድ መስራት አለባቸው ለሚለው ጥያቄ አሰልጣኞች ወደፊት ብዙ መነጋገርና ሃሳብ ማቅረብ እንዳለባቸውም ዶክተር በዛብህ ወልዴ ጠቁመዋል። በካታር ዶሃ እየተካሄደ ባለው 17ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና ላይ ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ሜዳሊያ ከትራንስ ኢትዮጵያ ክለብ በተገኘቸው ለተሰንበት ጊደይ አማካይነት አግኝታለች። ለተሰንበት ጊደይ ውድድሩን 30 ደቂቃ ከ21 ሰከንድ ከ23 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰአት በማጠናቀቅ የሁለተኛ ደረጃን ይዛ መጨረስ ችላለች። ከፍተኛ ፉክክር በታየበት የ10 ሺህ ሜትር ውድድር ኔዘርላንድስን ወክላ የተወዳደረችው ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሲፈን ሃሰን የወርቅ ሜዳሊያውን ወስዳለች። በውድድሩ ኬንያዊቷ አትሌት አግኔስ ትሪፖ ሦስተኛ ደረጃን ስትይዝ፤ በውድድሩ የተሳተፈችው ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ሰንበሬ ተፈሪ ስድስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። ከቢቢሲ ጋር አጭር ቆይታ ያደረገችው ለተሰንበት ''ውድድሩ በጣም አሪፍ ነበረ፤ አየሩም ቢሆን ከውጪ ነው የሚሞቀው እንጂ ስታዲየም ውስጥ ብዙም አላስቸገረኝም'' ብላለች። በመጨረሻዎቹ ዙሮች አንደኛ ከወጣችው ሲፈን ሃሰን ጋር የነበረው ፉክክር ምን እንደሚመስልና እንዴት ልታሸንፋት እንደቻለች ስትጠየቅ ለተሰንበት ይህንን ብላለች። ''በዚህ ውድድር ሜዳሊያ አግንቼ ስለማላውቅ አዲስ ሆኖብኝ ነበር፤ በቀጣይ ብዙ የማስተካክለው ነው። እስከመጨረሻው ድረስ ሄጄ ነበር ግን እሷ በአቅም ትንሽ በልጣኛለች'' ስትል በቁጭት ተናግራለች። ውድድሩ ሲጀመርም ኢትዮጵያዊያን በቡድን ተጋግዘው ለማሸነፍ ተመካክረው እንደነበር የገለጸችው ለተሰንበት ''በመጀመሪያዎቹ ዙሮች ሌሎች አትሌቶች መምራት ሲጀምሩ ደስ ብሎን እየጠበቅናቸው ነበር'' ብላለች። ''ወደ መጨረሻ ላይ ግን እንዳሰብነው ሳይሆን ተበታተንን''። ውድድሩ በተካሄደበት ግዙፉ ካሊፋ ስታዲየም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሔራዊ ቡድንን ለመደገፍ በርካታ ኢትዮጵያዊያን የተገኙ ሲሆን ለአትሌቶቹ ሞቅ ያለ ድጋፍ በመስጠት ምሽቱን አድምቀውት እንደነበር የቢቢሲ ዘጋቢ ገልጿል። የኢትዮጵያ ደጋፊዎች ጎላ ብሎ የሚሰማ ዝማሬ ሌሎች ታዳሚዎችንም ጭምር ስቦ ነበር። በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ያጌጡት ደጋፊዎች ግዙፋ የስታድየም ስክሪን ላይም ተደጋግመው ሲታዩ አምሽተዋል።
''በኳታር የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን በሙቀቱ ተቸግሯል'' የቡድኑ መሪ በኳታር የሚገኘው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን በሀገር ቤት ከነበረው ቀዝቃዛ የአየር ጸባይና ከፍተኛ ዝናብ አንጻር ወደ ኳታር ሲሄድ በሙቀት ምክንያት መቸገሩን የቡድኑ መሪ የሆኑት ዶክተር በዛብህ ወልዴ ለቢቢሲ ገልጸዋል። ''ሙቀቱ ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል ገምተን ነበር፤ ነገር ግን የአየሩ ሁኔታ ከገመትነው በላይ ሆኖ እንኳን ለሩጫ ውድድር ቆሞ መራመድ አስቸጋሪ ሆኖ ነው ያገኘነው። በዚሁም ምክንያት የማራቶኑ ሃሳባችን አልተሳካም፤ የአስር ሺውም ቢሆን መጥፎ ባይባልም እንዳሰብነው አልሆነም።'' በማራቶን ውድድር ወቅት በሙቀቱ ምክንያት አቋርጠው የወጡት ሦስቱም ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በአሁኑ ሰዓት በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙም የቡድን መሪው አክለዋል። ''ሯጮቹ በሰውነታቸው ውስጥ የውሃ ማነስ ነበር ያጋጠማቸው፤ ይሄን ያህል ለአደጋ የሚሰጣቸው ግን አይደለም።" • በዶሃ የሴቶች ማራቶን ሦስት ኢትዮጵያውያን ሯጮች አቋርጠው ወጡ • ሁሌም አብሮን ያለው 'የመስቀል ወፍ' በኳታር ካለው ከፍተኛ ሙቀት አንጻር ቡድኑ ከፍተኛ ሙቀት ባለባቸው አካባቢዎች ሄዶ ልምምዱን እንዲሰራ ታስቦ የነበረ ቢሆንም በብዙ ምክንያቶች ሳይሳካ መቅረቱንም የቡድን መሪው ጨምረው አስረድተዋል። ''እንደዚህ አይነት ነገር ለመተግባር ከባድ ነው። ወደታች በወረድን ቁጥር ከሙቀቱ ጋር አብረው የሚመጡ ብዙ ነገሮች አሉ" ያሉት ዶ/ር በዛብህ ሙቀት ቦታ ልምምድ መስራት ለእንደዚህ አይነት ውድድሮች ጠቃሚ ቢሆንም ብዙ ጉዳቶችም እንዳሉት ጠቅሰዋል። አትሌቶች በምን አይነት ሁኔታ ልምምድ መስራት አለባቸው ለሚለው ጥያቄ አሰልጣኞች ወደፊት ብዙ መነጋገርና ሃሳብ ማቅረብ እንዳለባቸውም ዶክተር በዛብህ ወልዴ ጠቁመዋል። በካታር ዶሃ እየተካሄደ ባለው 17ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና ላይ ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ሜዳሊያ ከትራንስ ኢትዮጵያ ክለብ በተገኘቸው ለተሰንበት ጊደይ አማካይነት አግኝታለች። ለተሰንበት ጊደይ ውድድሩን 30 ደቂቃ ከ21 ሰከንድ ከ23 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰአት በማጠናቀቅ የሁለተኛ ደረጃን ይዛ መጨረስ ችላለች። ከፍተኛ ፉክክር በታየበት የ10 ሺህ ሜትር ውድድር ኔዘርላንድስን ወክላ የተወዳደረችው ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሲፈን ሃሰን የወርቅ ሜዳሊያውን ወስዳለች። በውድድሩ ኬንያዊቷ አትሌት አግኔስ ትሪፖ ሦስተኛ ደረጃን ስትይዝ፤ በውድድሩ የተሳተፈችው ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ሰንበሬ ተፈሪ ስድስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። ከቢቢሲ ጋር አጭር ቆይታ ያደረገችው ለተሰንበት ''ውድድሩ በጣም አሪፍ ነበረ፤ አየሩም ቢሆን ከውጪ ነው የሚሞቀው እንጂ ስታዲየም ውስጥ ብዙም አላስቸገረኝም'' ብላለች። በመጨረሻዎቹ ዙሮች አንደኛ ከወጣችው ሲፈን ሃሰን ጋር የነበረው ፉክክር ምን እንደሚመስልና እንዴት ልታሸንፋት እንደቻለች ስትጠየቅ ለተሰንበት ይህንን ብላለች። ''በዚህ ውድድር ሜዳሊያ አግንቼ ስለማላውቅ አዲስ ሆኖብኝ ነበር፤ በቀጣይ ብዙ የማስተካክለው ነው። እስከመጨረሻው ድረስ ሄጄ ነበር ግን እሷ በአቅም ትንሽ በልጣኛለች'' ስትል በቁጭት ተናግራለች። ውድድሩ ሲጀመርም ኢትዮጵያዊያን በቡድን ተጋግዘው ለማሸነፍ ተመካክረው እንደነበር የገለጸችው ለተሰንበት ''በመጀመሪያዎቹ ዙሮች ሌሎች አትሌቶች መምራት ሲጀምሩ ደስ ብሎን እየጠበቅናቸው ነበር'' ብላለች። ''ወደ መጨረሻ ላይ ግን እንዳሰብነው ሳይሆን ተበታተንን''። ውድድሩ በተካሄደበት ግዙፉ ካሊፋ ስታዲየም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሔራዊ ቡድንን ለመደገፍ በርካታ ኢትዮጵያዊያን የተገኙ ሲሆን ለአትሌቶቹ ሞቅ ያለ ድጋፍ በመስጠት ምሽቱን አድምቀውት እንደነበር የቢቢሲ ዘጋቢ ገልጿል። የኢትዮጵያ ደጋፊዎች ጎላ ብሎ የሚሰማ ዝማሬ ሌሎች ታዳሚዎችንም ጭምር ስቦ ነበር። በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ያጌጡት ደጋፊዎች ግዙፋ የስታድየም ስክሪን ላይም ተደጋግመው ሲታዩ አምሽተዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-49869494
2health
ኮሮናቫይረስ፡ በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተገለፀ
የህክምና አገልግሎት የሚሰጡ ባለሙያዎችና በተለያዩ መስኮች ላይ በእነዚህ ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ሰዎች ለኮሮናቫይረስ የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ እንደሆነ ይታመናል። ይህንን በተመለከተም ባለፈው ሐምሌ ወር ላይ የዓለም ጤና ድርጅት እንዳለው በዓለም ዙሪያ በኮቪድ-19 ከተያዙት ሰዎች መካከል 10 በመቶዎቹ የጤና ሠራተኞች ሲሆኑ በአፍሪካም ከ10 ሺህ በላይ የህክምና ባለሙያዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። በኢትዮጵያ ውስጥ ወረርሽኙ መኖሩ ከታወቀ ባለፉት አምስት ወራት ውስጥ በተለያዩ ተቋማት ውስጥ የጤና አገልግሎት የሚሰጡ ሠራተኞች ላይ ቫይረሱ እንደተገኘ ተነግሯል። ይህንን በተመለከተ ቢቢሲ በአገሪቱ ውስጥ አንዳንድ አካባቢዎች ያሉ የጤና ባለሙያዎች ስላሉበት ሁኔታ ለማወቅ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በትግራይ፣ በሲዳማ ክልሎችና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የዳሰሳ ቅኝት አድርጓል። በዚህም በሁሉም ክልሎች የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎች ለኮቪድ-19 ያላቸው ተጋላጭነት አሳሳቢ መሆኑን ተገንዝቧል። በተጨማሪም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በተለያዩ ክልሎች በሚገኙ የህክምና ባለሙያዎች ዘንድ እየተስፋፋ መሆኑን ያነጋገርናቸው ክልሎች የጤና ቢሮ ኃላፊዎች ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። የጤና ቢሮ ኃላፊዎቹ ለቢቢሲ እንዳሉት ባለሙያዎቹ በተለያየ ምክንያት ለቫይረሱ የተጋለጡ ሲሆን፤ ከእነዚህም መካከል ከጥንቃቄ ጉድለት፣ ለመከላከያነት የሚያገለግሉ የህክምና ቁሳቁስ አቅርቦት እጥረት መኖር እና በሌሎች ስፍራዎች በሚኖር የቫይረሱ ተጋላጭነት ምክንያት መያዛቸውን ተናግረዋል። በትግራይ ክልል እስካሁን ድረስ ከ30 በላይ በኮቪድ-19 የተያዙ የህክምና ባለሙያዎችና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች መኖራቸውን የክልሉ የኮሮናቫይረስ ሎጀስቲክስ አስተባባሪ አቶ ጣዕመ አረዶ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ባለሙያዎቹ ከሥራ ቦታ ውጪ በነበራቸው ተጋላጭነት፣ ከቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር በነበራቸው ንክኪ፣ በጤና ተቋማት ውስጥ የኮሮናቫይረስ መከላከያ በቂ አቅርቦት ባለመኖሩ ምክንያት መያዛቸውን ጨምረው ተናግረዋል። በማይጨው ለምለም ካርል ሆስፒታል ለይቶ ማቆያ የሚሰሩት ዶ/ር ሳምሶን ነጋሲ የቫይረሱ ስርጭት አሳሳቢ ደረጃ መድረሱን ለቢቢሲ ገልፀዋል። "በአላማጣ በላብራቶሪ ቴክኒሺያንነት የሚሰሩ ሰባት ባለሙያዎች በቫይረሱ ተይዘዋል" ያሉት ዶ/ር ሳምሶን፣ በአይደር ሆስፒታል ሦስት ከፍተኛ የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ በርካታ የህክምና ባለሙያዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል ሲሉ ይናገራሉ። በዚህም የተነሳ ሆስፒታሉ ከድንገተኛ፣ ማዋለጃ እና አንዳንድ ህክምናዎች ውጪ ሌላው ክፍል ህክምና እየሰጠ አለመሆኑን ገልፀዋል። ዶ/ር ሳምሶን በህክምና ማዕከላቱ የሕክምና እቃዎች አቅርቦት ችግር መኖሩንም ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ለክልሉም ሆነ ለፌደራል አካላት ያለባቸውን ችግር ቢያቀርቡም እስካሁን መፍትሄ አለማግኘታቸውን ጨምረው አስረድተዋል። በአማራ ክልል በአሁኑ ሰዓት በስፋት በኮሮናቫይረስ ከተያዙት የኅብረተሰብ ክፍሎች መካከል የህክምና ባለሙያዎች እንደሚገኙበት የገለፁት ደግሞ የክልሉ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኅብረተሰብ ጤና ኢመርጀንሲ ማኔጅመንት ተወካይ ዳይሬክተር አቶ አሌ አያል ናቸው። ጨምረውም ለወረርሽኙ ተጋላጭ ናቸው የሚባሉት የህክምና ባለሙያዎች በክልሉ በተለየ ሁኔታ ተጠቅተዋል ባይባልም፤ አሁን ግን ቁጥሩ እየጨመረ በመምጣት 23 ባለሙያዎች በቫይረሱ መያዛቸውን መረጋገጡን ለቢቢሲ ገልጸዋል። ከዚህ ቀደም በድሬዳዋ አስተዳደር 21 የሕክምና ባለሙያዎችና በጤና ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች በኮቪድ-19 መያዛቸውን የከተማዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ለቢቢሲ ማረጋገጡ ይታወሳል። የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የሕዝብ ግንኙነት አስተባባሪ ስንታየሁ ደበሳ እንደተናገሩት በሕክምና ዘርፍ ላይ ያሉ ባለሙያዎች በቫይረሱ መያዛቸው እተደረገ ያለውን ወረርሽኙን የመከላከል ሥራን ያዳክመዋል የሚል ስጋት አለ ብለዋል። የከተማ አስተዳደሩ የሕዝብ ግንኙነት አስተባባሪዋ ለቢቢሲ እንደተናገሩት የጤና ባለሙያዎቹና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞቹ ለኮሮናቫይረስ የተጋለጡት በሥራ ቦታቸው ላይ እያሉ ነው። "የጤና ባለሙያዎቻችን በቫይረሱ እየተያዙ መምጣት ወረርሽኙን ለመከላከል የምናደርገውን ጥረት ያዳክማል" ሲሉም በአስተዳደሩ በኩል ያለውን ስጋት ለቢቢሲ ተናግረዋል። የከተማ አስተዳደሩ የሕዝብ ግንኙነት አስተባባሪዋ ለቢቢሲ እንደተናገሩት የጤና ባለሙያዎቹና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞቹ ለኮሮናቫይረስ የተጋለጡት በሥራ ቦታቸው ላይ እያሉ ነው። በሽታውን ለመከላከል አስፈጊ የሆኑ አቅርቦቶችን አስተዳደሩ በበቂ ሁኔታ ማቅቡንና ገልጸው "እስካሁን ድረስ እጥረት የለብንም" ብለዋል። ነገር ግን በሕክምና ተቋማቱ የሚኖሩ ንክኪዎች ባለሙያዎቹን ለቫይረሱ ማጋለጡን የሚናገሩት አስተባባሪዋ፤ ከባለሙያዎቹ ጋር በተደረገ ውይይት ለቫይረሱ የተጋለጡት በየትኛው ጊዜ እንደሆነ ለማለየት እንደሚቸገሩ ገልፀዋል። በህክምና ተቋማቱ ያሉ ሁኔታዎች እንደሚያሳዩት ግን ይላሉ ባለሙያዋ "በሕክምና ሥራ ላይ እያሉ ተጋላጭ መሆናቸውን ነው" በማለት ባለሙያዎቹ እየወሰዱ ያሉትን የጥንቃቄ እርምጃዎችን መፈተሽ እንደሚያስፈልግም ለቢቢሲ ተናግረዋል። በኦሮሚያ ክልል በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ሲሆን በሁሉም የክልሉ ዞኖችና ከተሞች ቫይረሱ መከሰቱን የክልሉ ጤና ቢሮ ገልጿል። በክልሉ እስካሁን ድረስ 1827 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው በምርመራ የተረጋገጠ ሲሆን፤ ከእነዚህ መካከል 34 የሚሆኑት የጤና ባለሙያዎች መሆናቸውን የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ኃላፊ ምክትል ኃላፊ አቶ ደረጃ አብደና ለቢቢሲ ገልጸዋል። የጤና ባለሙያዎች በብዛት የተገኙት መደበኛ ህክምና በሚሰጡ ሆስፒታሎችና ጤና ጣብያዎች ውስጥ መሆናቸውን አቶ ደረጀ ጨምረው ተናግረዋል። የሲዳማ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ዶ/ር ማቴ መንገሻ በበኩላቸውእስከ ዛሬ ድረስ በሲዳማ ክልል 13 የሕክምና ባለሙያዎች እና ሁለት ድጋፍ ሰጭ ሠራተኞች በኮቪድ-19 መያዛቸውን ተናግረዋል። በኮቪድ-19 ከተያዙት የህክምና ባለሙያዎች መካከል ወደተለያየ ስፍራ ሄደው ራሳቸውን ለቫይረሱ ያጋለጡ፣ በሚሰሩባቸው ተቋማት አካባቢ ባለ የጥንቃቄ ጉድለት እንዲሁም የህክምና ቁሳቁስ እጥረት በመኖሩ የተነሳ የተጋለጡ እንደሚገኙበት አብራርተዋል።
ኮሮናቫይረስ፡ በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተገለፀ የህክምና አገልግሎት የሚሰጡ ባለሙያዎችና በተለያዩ መስኮች ላይ በእነዚህ ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ሰዎች ለኮሮናቫይረስ የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ እንደሆነ ይታመናል። ይህንን በተመለከተም ባለፈው ሐምሌ ወር ላይ የዓለም ጤና ድርጅት እንዳለው በዓለም ዙሪያ በኮቪድ-19 ከተያዙት ሰዎች መካከል 10 በመቶዎቹ የጤና ሠራተኞች ሲሆኑ በአፍሪካም ከ10 ሺህ በላይ የህክምና ባለሙያዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። በኢትዮጵያ ውስጥ ወረርሽኙ መኖሩ ከታወቀ ባለፉት አምስት ወራት ውስጥ በተለያዩ ተቋማት ውስጥ የጤና አገልግሎት የሚሰጡ ሠራተኞች ላይ ቫይረሱ እንደተገኘ ተነግሯል። ይህንን በተመለከተ ቢቢሲ በአገሪቱ ውስጥ አንዳንድ አካባቢዎች ያሉ የጤና ባለሙያዎች ስላሉበት ሁኔታ ለማወቅ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በትግራይ፣ በሲዳማ ክልሎችና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የዳሰሳ ቅኝት አድርጓል። በዚህም በሁሉም ክልሎች የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎች ለኮቪድ-19 ያላቸው ተጋላጭነት አሳሳቢ መሆኑን ተገንዝቧል። በተጨማሪም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በተለያዩ ክልሎች በሚገኙ የህክምና ባለሙያዎች ዘንድ እየተስፋፋ መሆኑን ያነጋገርናቸው ክልሎች የጤና ቢሮ ኃላፊዎች ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። የጤና ቢሮ ኃላፊዎቹ ለቢቢሲ እንዳሉት ባለሙያዎቹ በተለያየ ምክንያት ለቫይረሱ የተጋለጡ ሲሆን፤ ከእነዚህም መካከል ከጥንቃቄ ጉድለት፣ ለመከላከያነት የሚያገለግሉ የህክምና ቁሳቁስ አቅርቦት እጥረት መኖር እና በሌሎች ስፍራዎች በሚኖር የቫይረሱ ተጋላጭነት ምክንያት መያዛቸውን ተናግረዋል። በትግራይ ክልል እስካሁን ድረስ ከ30 በላይ በኮቪድ-19 የተያዙ የህክምና ባለሙያዎችና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች መኖራቸውን የክልሉ የኮሮናቫይረስ ሎጀስቲክስ አስተባባሪ አቶ ጣዕመ አረዶ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ባለሙያዎቹ ከሥራ ቦታ ውጪ በነበራቸው ተጋላጭነት፣ ከቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር በነበራቸው ንክኪ፣ በጤና ተቋማት ውስጥ የኮሮናቫይረስ መከላከያ በቂ አቅርቦት ባለመኖሩ ምክንያት መያዛቸውን ጨምረው ተናግረዋል። በማይጨው ለምለም ካርል ሆስፒታል ለይቶ ማቆያ የሚሰሩት ዶ/ር ሳምሶን ነጋሲ የቫይረሱ ስርጭት አሳሳቢ ደረጃ መድረሱን ለቢቢሲ ገልፀዋል። "በአላማጣ በላብራቶሪ ቴክኒሺያንነት የሚሰሩ ሰባት ባለሙያዎች በቫይረሱ ተይዘዋል" ያሉት ዶ/ር ሳምሶን፣ በአይደር ሆስፒታል ሦስት ከፍተኛ የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ በርካታ የህክምና ባለሙያዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል ሲሉ ይናገራሉ። በዚህም የተነሳ ሆስፒታሉ ከድንገተኛ፣ ማዋለጃ እና አንዳንድ ህክምናዎች ውጪ ሌላው ክፍል ህክምና እየሰጠ አለመሆኑን ገልፀዋል። ዶ/ር ሳምሶን በህክምና ማዕከላቱ የሕክምና እቃዎች አቅርቦት ችግር መኖሩንም ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ለክልሉም ሆነ ለፌደራል አካላት ያለባቸውን ችግር ቢያቀርቡም እስካሁን መፍትሄ አለማግኘታቸውን ጨምረው አስረድተዋል። በአማራ ክልል በአሁኑ ሰዓት በስፋት በኮሮናቫይረስ ከተያዙት የኅብረተሰብ ክፍሎች መካከል የህክምና ባለሙያዎች እንደሚገኙበት የገለፁት ደግሞ የክልሉ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኅብረተሰብ ጤና ኢመርጀንሲ ማኔጅመንት ተወካይ ዳይሬክተር አቶ አሌ አያል ናቸው። ጨምረውም ለወረርሽኙ ተጋላጭ ናቸው የሚባሉት የህክምና ባለሙያዎች በክልሉ በተለየ ሁኔታ ተጠቅተዋል ባይባልም፤ አሁን ግን ቁጥሩ እየጨመረ በመምጣት 23 ባለሙያዎች በቫይረሱ መያዛቸውን መረጋገጡን ለቢቢሲ ገልጸዋል። ከዚህ ቀደም በድሬዳዋ አስተዳደር 21 የሕክምና ባለሙያዎችና በጤና ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች በኮቪድ-19 መያዛቸውን የከተማዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ለቢቢሲ ማረጋገጡ ይታወሳል። የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የሕዝብ ግንኙነት አስተባባሪ ስንታየሁ ደበሳ እንደተናገሩት በሕክምና ዘርፍ ላይ ያሉ ባለሙያዎች በቫይረሱ መያዛቸው እተደረገ ያለውን ወረርሽኙን የመከላከል ሥራን ያዳክመዋል የሚል ስጋት አለ ብለዋል። የከተማ አስተዳደሩ የሕዝብ ግንኙነት አስተባባሪዋ ለቢቢሲ እንደተናገሩት የጤና ባለሙያዎቹና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞቹ ለኮሮናቫይረስ የተጋለጡት በሥራ ቦታቸው ላይ እያሉ ነው። "የጤና ባለሙያዎቻችን በቫይረሱ እየተያዙ መምጣት ወረርሽኙን ለመከላከል የምናደርገውን ጥረት ያዳክማል" ሲሉም በአስተዳደሩ በኩል ያለውን ስጋት ለቢቢሲ ተናግረዋል። የከተማ አስተዳደሩ የሕዝብ ግንኙነት አስተባባሪዋ ለቢቢሲ እንደተናገሩት የጤና ባለሙያዎቹና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞቹ ለኮሮናቫይረስ የተጋለጡት በሥራ ቦታቸው ላይ እያሉ ነው። በሽታውን ለመከላከል አስፈጊ የሆኑ አቅርቦቶችን አስተዳደሩ በበቂ ሁኔታ ማቅቡንና ገልጸው "እስካሁን ድረስ እጥረት የለብንም" ብለዋል። ነገር ግን በሕክምና ተቋማቱ የሚኖሩ ንክኪዎች ባለሙያዎቹን ለቫይረሱ ማጋለጡን የሚናገሩት አስተባባሪዋ፤ ከባለሙያዎቹ ጋር በተደረገ ውይይት ለቫይረሱ የተጋለጡት በየትኛው ጊዜ እንደሆነ ለማለየት እንደሚቸገሩ ገልፀዋል። በህክምና ተቋማቱ ያሉ ሁኔታዎች እንደሚያሳዩት ግን ይላሉ ባለሙያዋ "በሕክምና ሥራ ላይ እያሉ ተጋላጭ መሆናቸውን ነው" በማለት ባለሙያዎቹ እየወሰዱ ያሉትን የጥንቃቄ እርምጃዎችን መፈተሽ እንደሚያስፈልግም ለቢቢሲ ተናግረዋል። በኦሮሚያ ክልል በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ሲሆን በሁሉም የክልሉ ዞኖችና ከተሞች ቫይረሱ መከሰቱን የክልሉ ጤና ቢሮ ገልጿል። በክልሉ እስካሁን ድረስ 1827 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው በምርመራ የተረጋገጠ ሲሆን፤ ከእነዚህ መካከል 34 የሚሆኑት የጤና ባለሙያዎች መሆናቸውን የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ኃላፊ ምክትል ኃላፊ አቶ ደረጃ አብደና ለቢቢሲ ገልጸዋል። የጤና ባለሙያዎች በብዛት የተገኙት መደበኛ ህክምና በሚሰጡ ሆስፒታሎችና ጤና ጣብያዎች ውስጥ መሆናቸውን አቶ ደረጀ ጨምረው ተናግረዋል። የሲዳማ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ዶ/ር ማቴ መንገሻ በበኩላቸውእስከ ዛሬ ድረስ በሲዳማ ክልል 13 የሕክምና ባለሙያዎች እና ሁለት ድጋፍ ሰጭ ሠራተኞች በኮቪድ-19 መያዛቸውን ተናግረዋል። በኮቪድ-19 ከተያዙት የህክምና ባለሙያዎች መካከል ወደተለያየ ስፍራ ሄደው ራሳቸውን ለቫይረሱ ያጋለጡ፣ በሚሰሩባቸው ተቋማት አካባቢ ባለ የጥንቃቄ ጉድለት እንዲሁም የህክምና ቁሳቁስ እጥረት በመኖሩ የተነሳ የተጋለጡ እንደሚገኙበት አብራርተዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-53742959
0business
በምዕራብ ኦሮሚያ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ መስተጓጎሉን ነዋሪዎች ገለፁ
በምዕራብ ኦሮሚያ በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ምክንያት የትራንፖርት እንቅስቃሴ መስተጓጎሉን ነዋሪዎች እና የአካባቢው አስተዳዳሪዎች ለቢቢሲ ገለፁ። በቄለም ወለጋ እና በምዕራብ ወለጋ ዞኖች ውስጥ በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ምክንያት ዋና መንገዶች በመዘጋታቸው ከቦታ ቦታ ለመንቀሳቀስ መቸገራቸውን ነዋሪዎች ሲናገሩ የአካባቢዎቹ ባለሥልጣናት ደግሞ ችግሩ የተፈጠረው በስጋት ምክንያት ነው ብለዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ከዚህ በፊት አጋጥሞ በማያውቅ ሁኔታ ከግምቢ ነጆ፣ ከግምቢ ደምቢ ዶሎ፣ ከጊዳሚ አሶሳ የሚወስዱ መንገዶች መዘጋታቸውን ተናግረዋል። መንግሥት አሸባሪ ሲል የፈረጀው የሸኔ ጦር አዛዥ ኩምሳ ድሪባ ሰሞኑን ለቢቢሲ እንደተናገረው በምዕራብ ኦሮሚያ በርካታ የገጠር አካባቢ እና ትንንሽ ከተሞችን በእጃቸው ማስገባታቸውን ተናግሯል። የምዕራብ ወለጋ እና የቄለም ወለጋ ዞን አስተዳዳሪዎች በበኩላቸው የተዘጋ መንገድም ሆነ በአማጺያኑ ቁጥጥር ስር የገባ ስፍራ የለም ሲሉ አስተባብለዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የሁለቱ ዞኖች አስተዳዳሪዎች የትራንስፖርት መስተጓጎል የተፈጠረው ታጣቂዎች በኃይል ከሾፌሮች ላይ ቁልፍ እየተቀበሉ ተሽከርካሪዎችን እየወሰዱ ስለሆነ ነው ይላሉ። የምዕራብ ወለጋ አስተዳዳሪ አቶ ኤልያስ ኡመታ ባለፉት ቀናት የሸኔ ታጣቂዎች ወደ ዋና መንገድ በመውጣት ከሾፌሮች ቁልፍ እየተቀበሉ መኪና ከቀሙ በኋላ ወደ ጫካ እየተመለሱ በመሆኑ በአንዳንድ አካባቢዎች የትራንስፖርት መስተጓጎሎች ተፈጠረ እንጂ መንገድ ሙሉ በሙሉ አልተዘጋም ብለዋል። ቢቢሲ በሁለቱ የወለጋ ዞኖች የሚኖሩ ነዋሪዎችን ያነጋገረ ሲሆን፣ መንገድ ከመዘጋቱ ጋር ተያይዞ በወለጋ ዩኒቨርስቲ በሚካሄደው የተማሪዎች ምርቃት ላይ ለመገኘት አለመቻላቸውን ተናግረዋል። አቶ ኤልያስ ኡመታ "የተዘጋ መንገድ አናውቅም፤ በእኛ ትዕዛዝ የተዘጋ መንገድ የለም፤ አንዳንድ ቦታዎች የፀጥታ ችግር ስላለ ብቻ ይህንን መስመር ለማስያዝ የሚሰራ ሥራ ይኖራል እንጂ የተስተጓጎለ መንገድ የለም" ብለዋል። አስተዳዳሪው አክለውም፣ ኦነግ ሸኔ የሚሏቸው ታጣቂዎች ኋላ ቀር መሳሪያዎችን እንዲሁም ባዶ እጃቸውን በመሆን ሹፌሮችን በማስፈራራት ቁልፍ እየተቀበሉ እነደነበር ገልጸዋል። በዚህ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው መኪኖች መኖር አለመኖራቸው ለጊዜው እንዳልተጣራ ተናግረዋል። በዚህ ሳምንት ውስጥ በቄለም እና በምዕራብ ወለጋ ዞኖች ውስጥ ከፍተኛ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ሲካሄድ እንደነበር የአካባቢዎቹ ነዋሪዎች ይናገራሉ። የቄለም ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ገመቹ ጉርሜሳ በበኩላቸው ዞኑን አቋርጦ በሚያልፈው መንገድ፤ ትራንስፖርት የተስተጓጎበትን ምክንያት ሲያስረዱ "እነዚህ ታጣቂዎች ከሾፌሮች ቁልፍ እየተቀበሉ መኪኖችን እየወሰዱ ትራንስፖርት እንዲስተጓጎል ስላደረጉ እንጂ እንደ ከዚህ ቀደሙ መንገድ ተዘግቶ አይደለም" ብለዋል። ከሁለት ቀናት በፊት በሃዋ ገላን ወረዳ በተለምዶ የሱሲ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ታጣቂዎች ከሾፌሮች ቁልፍ በመንጠቅ ሦስት መኪኖችን እንደወሰዱ አቶ ገመቹ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። በዞኑ አንዳንድ ወረዳዎችም በድንጋይና በእንጨት መንገድ ለመዝጋት ተሞክሯል የሚሉት አስተዳዳሪው፣ ይህ ሙከራም በፍጥነት እንደከሸፈ እና በዚህ መልኩም የተዘጋ መንገድ እንደተከፈተም ገልጸዋል። የምዕራብ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ኤልያስ "በአሁኑ ወቅት የእነዚህን ታጣቂዎች እንቅስቃሴ ለማስቆም መፈተሽ ያለበት ስፍራ ተፍሾ፣ መታየት ያለበት ቦታ ታይቶ የኅብረተሰቡ እንቅሰቃሴ ወደ ቀድሞው ተመልሷል" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አንድ ቢቢሲ ያነጋገረው እና ስሙ እንዳይገለጽ የጠየቀ ነዋሪ በሳምንቱ መጨረሻ፣ ዘመድ ጥየቃ ከጊዳሚ ወደ ጊምቢ መምጣቱንና መንገድ በመዘጋቱ ምክንያት ወደ ቀየው ለመመለስ እንደተቸገረ ይናገራል። መንግሥት አሸባሪ በማለት የፈረጀውና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር በማለት የሚጠራው አማጺ ቡድን ምዕራብ ወለጋ ዞን የሚገኙ አውራ መንገዶችን መቆጣጠሩን ማክሰኞ ነሐሴ 10/2013 ዓ.ም በትዊተር ሰሌዳቸው ላይ አስፍሯል። የአማጺያኑ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ኃላፊ ኦዳ ተርቢ ከግምቢ ነጆ፣ ከግምቢ ደምቢ ዶሎ፣ ከነቀምቴ ባሕር ዳር እና ከግዳሚ አሶሳ የሚወስዱ መንገዶች በቁጥጥራቸው ስር መግባቱን አስፍሮ ነበር። ከነቀምት ባሕር ዳር ከሚወስደው መንገድ በስተቀር ሌሎቹ በእነዚህ ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር መግባቱን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። በእነዚህ ሁለት ዞኖች ውስጥ የተለየ ጦርነት አለ? ሁለቱ የወለጋ ዞኖች ውስጥ እንደከዚህ ቀደሙ ከአማፂያኑ ጋር ግጭት መኖሩን የሁለቱ ዞኖች አስተዳዳሪዎቹ ለቢቢሲ ተናግረዋል። መንግሥት አሸባሪ በማለት የፈረጀው ሸኔ፣ በቅርቡ ለገሰ ወጊ በሚል ስም የጥቃት ዘመቻ እያካሄደ መሆኑን እና ትልልቅ መንገዶች፣ የኢትዮጵያ ጦር ሠራዊት ካምፖችን እና አንዳንድ አካባቢዎችን መያዙን እየገለጸ ይገኛል። ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር በማለት የሚጠራው አማጺ አዛዥ፣ ኩምሳ ድሪባ ከቢቢሲ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ባለፉት ቀናት በምዕራብ እና ደቡብ ኦሮሚያ መጠነ ሰፊ የጥቃት ዘመቻ መክፈታቸውን ተናግሯል። "የኦሮሞ ነጻነት ጦር አንድም ቀን ጦርነት አቋርጦ አያውቅም፤ የአሁኑን ለየት የሚያደርገው በራሳችን በሦስት አቅጣጫ ጦርነት ከፍተን ነው ያለነው።" አክሎም በምዕራብ ኦሮሚያ ብዙ የገጠር አካባቢ እና ትንንሽ ከተሞች አማጺ ቡድኑ፣ ከዚህ ቀደምም በእጁ አስገብቶ እንዳለ ተናግሯል። በተጨማሪም "በአገሪቱ ሰሜን አቅጣጫ ትልቅ ጦርነት ስላለ የእኛ እንቅስቃሴ ትኩረት አልተሰጠውም እንጂ ብዙ ቦታዎችን ተቆጣጥረን ነው ያለነው" ሲል አክሏል። ይሁን እንጂ የቄለም እና የምዕራብ ወለጋ ዞኖች አስተዳዳሪዎች የሸኔ ታጣቂ ቡድኖች ቀበሌን እና ወረዳን ለመቆጣጠር የሚያስችል አቅም የላቸውም ሲሉ ይናገራሉ። ቦታዎችን በቁጥጥራችን ስር አውለናል የሚሉት "ውሸት ነው" ሲሉም አጣጥለውታል። አቶ ኤልያስ ጥቂት ኃይሎች የፀጥታ ችግርን ከመፍጠር ባለፈ፣ ቀበሌን እና ወረዳን ለመቆጣጠር የሚችል ኃይል በዞናችን ውስጥ የለም ሲሉ ይናገራሉ። የቄለም ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ገመቹ፣ የእነዚህ ታጣቂዎች እንቅስቃሴ አልፎ አልፎ አንዳንድ ወረዳ ውስጥ ይታያል ግን ከመንግሥት አቅም በላይ የሆነ እንቅስቃሴ የለም ሲሉ ያስረዳሉ። "ጦርነት የሚካሄድበት እና ገፍተው የሚወጡበት ስፍራን በሙሉ ተቆጣጥረናል ይላሉ እንጂ የተቆጣጠሩት አንድም ቀበሌ እና ወረዳ የለም። አይቻልምም" ይላሉ አቶ ገመቹ። በምዕራብ ኦሮሚያ እንደሚንሳቀስ የሚነገረው ታታቂ ቡድኑ በተለያዩ ወቅቶች በሰላማዊ ነዋሪዎች ላይ እና በአካባቢ ባለሥልጣናት ላይ ጥቃቶችን በመፈጸም ክስ ይቀርብበታል። በቅርቡ መንግሥት በሽብርተኛ ቡድንነት የፈረጃቸው ህወሓትና እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው ቡድን ከኢትዮጵያ መንግሥት አንጻር በወታደራዊ መስክ ለመተባበር መስማማታቸውን ይፋ አድርገዋል። ኦነግ-ሸኔ በሚል መንግሥት የሚጠራው ቡድንን ቀደም ሲል በምዕራብ ኃይል አዛዥ የነበረውና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የአጠቃላዩ የኦሮሞ ነጻነት ጦር መሪ እንደሆነ የሚነገረው ኩምሳ ድሪባ ወይም መሮ ለቢቢሲ "ሁለቱም ቡድኖች የጋራ ጠላት ስላለን በወታደራዊ ጉዳዮች ላይ ለመደጋገፍ ከስምምነት ላይ ደርሰናል" ብሏል።
በምዕራብ ኦሮሚያ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ መስተጓጎሉን ነዋሪዎች ገለፁ በምዕራብ ኦሮሚያ በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ምክንያት የትራንፖርት እንቅስቃሴ መስተጓጎሉን ነዋሪዎች እና የአካባቢው አስተዳዳሪዎች ለቢቢሲ ገለፁ። በቄለም ወለጋ እና በምዕራብ ወለጋ ዞኖች ውስጥ በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ምክንያት ዋና መንገዶች በመዘጋታቸው ከቦታ ቦታ ለመንቀሳቀስ መቸገራቸውን ነዋሪዎች ሲናገሩ የአካባቢዎቹ ባለሥልጣናት ደግሞ ችግሩ የተፈጠረው በስጋት ምክንያት ነው ብለዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ከዚህ በፊት አጋጥሞ በማያውቅ ሁኔታ ከግምቢ ነጆ፣ ከግምቢ ደምቢ ዶሎ፣ ከጊዳሚ አሶሳ የሚወስዱ መንገዶች መዘጋታቸውን ተናግረዋል። መንግሥት አሸባሪ ሲል የፈረጀው የሸኔ ጦር አዛዥ ኩምሳ ድሪባ ሰሞኑን ለቢቢሲ እንደተናገረው በምዕራብ ኦሮሚያ በርካታ የገጠር አካባቢ እና ትንንሽ ከተሞችን በእጃቸው ማስገባታቸውን ተናግሯል። የምዕራብ ወለጋ እና የቄለም ወለጋ ዞን አስተዳዳሪዎች በበኩላቸው የተዘጋ መንገድም ሆነ በአማጺያኑ ቁጥጥር ስር የገባ ስፍራ የለም ሲሉ አስተባብለዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የሁለቱ ዞኖች አስተዳዳሪዎች የትራንስፖርት መስተጓጎል የተፈጠረው ታጣቂዎች በኃይል ከሾፌሮች ላይ ቁልፍ እየተቀበሉ ተሽከርካሪዎችን እየወሰዱ ስለሆነ ነው ይላሉ። የምዕራብ ወለጋ አስተዳዳሪ አቶ ኤልያስ ኡመታ ባለፉት ቀናት የሸኔ ታጣቂዎች ወደ ዋና መንገድ በመውጣት ከሾፌሮች ቁልፍ እየተቀበሉ መኪና ከቀሙ በኋላ ወደ ጫካ እየተመለሱ በመሆኑ በአንዳንድ አካባቢዎች የትራንስፖርት መስተጓጎሎች ተፈጠረ እንጂ መንገድ ሙሉ በሙሉ አልተዘጋም ብለዋል። ቢቢሲ በሁለቱ የወለጋ ዞኖች የሚኖሩ ነዋሪዎችን ያነጋገረ ሲሆን፣ መንገድ ከመዘጋቱ ጋር ተያይዞ በወለጋ ዩኒቨርስቲ በሚካሄደው የተማሪዎች ምርቃት ላይ ለመገኘት አለመቻላቸውን ተናግረዋል። አቶ ኤልያስ ኡመታ "የተዘጋ መንገድ አናውቅም፤ በእኛ ትዕዛዝ የተዘጋ መንገድ የለም፤ አንዳንድ ቦታዎች የፀጥታ ችግር ስላለ ብቻ ይህንን መስመር ለማስያዝ የሚሰራ ሥራ ይኖራል እንጂ የተስተጓጎለ መንገድ የለም" ብለዋል። አስተዳዳሪው አክለውም፣ ኦነግ ሸኔ የሚሏቸው ታጣቂዎች ኋላ ቀር መሳሪያዎችን እንዲሁም ባዶ እጃቸውን በመሆን ሹፌሮችን በማስፈራራት ቁልፍ እየተቀበሉ እነደነበር ገልጸዋል። በዚህ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው መኪኖች መኖር አለመኖራቸው ለጊዜው እንዳልተጣራ ተናግረዋል። በዚህ ሳምንት ውስጥ በቄለም እና በምዕራብ ወለጋ ዞኖች ውስጥ ከፍተኛ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ሲካሄድ እንደነበር የአካባቢዎቹ ነዋሪዎች ይናገራሉ። የቄለም ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ገመቹ ጉርሜሳ በበኩላቸው ዞኑን አቋርጦ በሚያልፈው መንገድ፤ ትራንስፖርት የተስተጓጎበትን ምክንያት ሲያስረዱ "እነዚህ ታጣቂዎች ከሾፌሮች ቁልፍ እየተቀበሉ መኪኖችን እየወሰዱ ትራንስፖርት እንዲስተጓጎል ስላደረጉ እንጂ እንደ ከዚህ ቀደሙ መንገድ ተዘግቶ አይደለም" ብለዋል። ከሁለት ቀናት በፊት በሃዋ ገላን ወረዳ በተለምዶ የሱሲ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ታጣቂዎች ከሾፌሮች ቁልፍ በመንጠቅ ሦስት መኪኖችን እንደወሰዱ አቶ ገመቹ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። በዞኑ አንዳንድ ወረዳዎችም በድንጋይና በእንጨት መንገድ ለመዝጋት ተሞክሯል የሚሉት አስተዳዳሪው፣ ይህ ሙከራም በፍጥነት እንደከሸፈ እና በዚህ መልኩም የተዘጋ መንገድ እንደተከፈተም ገልጸዋል። የምዕራብ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ኤልያስ "በአሁኑ ወቅት የእነዚህን ታጣቂዎች እንቅስቃሴ ለማስቆም መፈተሽ ያለበት ስፍራ ተፍሾ፣ መታየት ያለበት ቦታ ታይቶ የኅብረተሰቡ እንቅሰቃሴ ወደ ቀድሞው ተመልሷል" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አንድ ቢቢሲ ያነጋገረው እና ስሙ እንዳይገለጽ የጠየቀ ነዋሪ በሳምንቱ መጨረሻ፣ ዘመድ ጥየቃ ከጊዳሚ ወደ ጊምቢ መምጣቱንና መንገድ በመዘጋቱ ምክንያት ወደ ቀየው ለመመለስ እንደተቸገረ ይናገራል። መንግሥት አሸባሪ በማለት የፈረጀውና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር በማለት የሚጠራው አማጺ ቡድን ምዕራብ ወለጋ ዞን የሚገኙ አውራ መንገዶችን መቆጣጠሩን ማክሰኞ ነሐሴ 10/2013 ዓ.ም በትዊተር ሰሌዳቸው ላይ አስፍሯል። የአማጺያኑ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ኃላፊ ኦዳ ተርቢ ከግምቢ ነጆ፣ ከግምቢ ደምቢ ዶሎ፣ ከነቀምቴ ባሕር ዳር እና ከግዳሚ አሶሳ የሚወስዱ መንገዶች በቁጥጥራቸው ስር መግባቱን አስፍሮ ነበር። ከነቀምት ባሕር ዳር ከሚወስደው መንገድ በስተቀር ሌሎቹ በእነዚህ ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር መግባቱን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። በእነዚህ ሁለት ዞኖች ውስጥ የተለየ ጦርነት አለ? ሁለቱ የወለጋ ዞኖች ውስጥ እንደከዚህ ቀደሙ ከአማፂያኑ ጋር ግጭት መኖሩን የሁለቱ ዞኖች አስተዳዳሪዎቹ ለቢቢሲ ተናግረዋል። መንግሥት አሸባሪ በማለት የፈረጀው ሸኔ፣ በቅርቡ ለገሰ ወጊ በሚል ስም የጥቃት ዘመቻ እያካሄደ መሆኑን እና ትልልቅ መንገዶች፣ የኢትዮጵያ ጦር ሠራዊት ካምፖችን እና አንዳንድ አካባቢዎችን መያዙን እየገለጸ ይገኛል። ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር በማለት የሚጠራው አማጺ አዛዥ፣ ኩምሳ ድሪባ ከቢቢሲ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ባለፉት ቀናት በምዕራብ እና ደቡብ ኦሮሚያ መጠነ ሰፊ የጥቃት ዘመቻ መክፈታቸውን ተናግሯል። "የኦሮሞ ነጻነት ጦር አንድም ቀን ጦርነት አቋርጦ አያውቅም፤ የአሁኑን ለየት የሚያደርገው በራሳችን በሦስት አቅጣጫ ጦርነት ከፍተን ነው ያለነው።" አክሎም በምዕራብ ኦሮሚያ ብዙ የገጠር አካባቢ እና ትንንሽ ከተሞች አማጺ ቡድኑ፣ ከዚህ ቀደምም በእጁ አስገብቶ እንዳለ ተናግሯል። በተጨማሪም "በአገሪቱ ሰሜን አቅጣጫ ትልቅ ጦርነት ስላለ የእኛ እንቅስቃሴ ትኩረት አልተሰጠውም እንጂ ብዙ ቦታዎችን ተቆጣጥረን ነው ያለነው" ሲል አክሏል። ይሁን እንጂ የቄለም እና የምዕራብ ወለጋ ዞኖች አስተዳዳሪዎች የሸኔ ታጣቂ ቡድኖች ቀበሌን እና ወረዳን ለመቆጣጠር የሚያስችል አቅም የላቸውም ሲሉ ይናገራሉ። ቦታዎችን በቁጥጥራችን ስር አውለናል የሚሉት "ውሸት ነው" ሲሉም አጣጥለውታል። አቶ ኤልያስ ጥቂት ኃይሎች የፀጥታ ችግርን ከመፍጠር ባለፈ፣ ቀበሌን እና ወረዳን ለመቆጣጠር የሚችል ኃይል በዞናችን ውስጥ የለም ሲሉ ይናገራሉ። የቄለም ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ገመቹ፣ የእነዚህ ታጣቂዎች እንቅስቃሴ አልፎ አልፎ አንዳንድ ወረዳ ውስጥ ይታያል ግን ከመንግሥት አቅም በላይ የሆነ እንቅስቃሴ የለም ሲሉ ያስረዳሉ። "ጦርነት የሚካሄድበት እና ገፍተው የሚወጡበት ስፍራን በሙሉ ተቆጣጥረናል ይላሉ እንጂ የተቆጣጠሩት አንድም ቀበሌ እና ወረዳ የለም። አይቻልምም" ይላሉ አቶ ገመቹ። በምዕራብ ኦሮሚያ እንደሚንሳቀስ የሚነገረው ታታቂ ቡድኑ በተለያዩ ወቅቶች በሰላማዊ ነዋሪዎች ላይ እና በአካባቢ ባለሥልጣናት ላይ ጥቃቶችን በመፈጸም ክስ ይቀርብበታል። በቅርቡ መንግሥት በሽብርተኛ ቡድንነት የፈረጃቸው ህወሓትና እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው ቡድን ከኢትዮጵያ መንግሥት አንጻር በወታደራዊ መስክ ለመተባበር መስማማታቸውን ይፋ አድርገዋል። ኦነግ-ሸኔ በሚል መንግሥት የሚጠራው ቡድንን ቀደም ሲል በምዕራብ ኃይል አዛዥ የነበረውና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የአጠቃላዩ የኦሮሞ ነጻነት ጦር መሪ እንደሆነ የሚነገረው ኩምሳ ድሪባ ወይም መሮ ለቢቢሲ "ሁለቱም ቡድኖች የጋራ ጠላት ስላለን በወታደራዊ ጉዳዮች ላይ ለመደጋገፍ ከስምምነት ላይ ደርሰናል" ብሏል።
https://www.bbc.com/amharic/news-58206435
0business
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላንን ወደ በረራ መለሰ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሦስት ዓመታት ለሚተጋ ጊዜ ከበረራ አግዶት የነበረውን ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ወደ አገልግሎት መለሰ። አየር መንገዱ ዛሬ ጥር 23/2014 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ ላይ አውሮፕላኑ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የቦይንግ እና የአየር መንገዱ ቦርድ አባላትን አሳፍሮ ወደ በረራ ተመልሷል ብሏል። አየር መንገዱ ባጋጠሙ አስከፊ አደጋ ምክንያት ከበረራ አግዷቸው የነበሩት አራት ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላኖቹን ወደ መደበኛ የመንገደኞች በረራ በያዝነው ሳምንት እንደሚመልስ አስታውቆ ነበር። ከአፍሪካ ትልቁ አየር መንገድ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያሉትን ዘመናዊ ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላኖች ከበረራ ውጪ ካደረገ ሁለት ዓመት አልፎታል። መጋቢት 01 ቀን 2011 ዓ.ም ጠዋት ከአዲስ አበባ ወደ ኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ 149 ሰዎችን ይዞ ይበር የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን የበረራ ቁጥር ET302 መከስከሱን ተከትሎ ነበር አውሮፕላኖቹ በመላው ዓለም ከበረራ ውጪ የሆኑት። በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ላይ ከደረሰው አደጋው ቀደም ብሎ በኢንዶኔዢያው ላየን ኤየር አየር መንገድ ተመሳሳይ ቦይንግ አውሮፕላን ላይ አደጋ አጋጥሞ የ181 ሰዎች ሕይወት ተቀጥፏል። ከሁለቱ አደጋዎች በኋላ በመላው ዓለም የሚገኙ በርካታ አየር መንገዶች ቦይንግ 737 ማክስን 8 አውሮፕላኖችን ማብረር አቁመው ነበር። አየር መንገዱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ላይ ከሁሉም በፊት ቅድሚያ የሚሰጠው ለደኅንነት ነው ብሏል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ ተወልደ ገብረማሪያም አየር መንገዱ አውሮፕላኑን ወደ አገልግሎት ለመመለስ ከውሳኔ ላይ የደረሰው በዓለም ዙሪያ ያሉ የበረራ ደኅንነት ተቆጣጠሪ አካላት አውሮፕላኑ አስተማማኝ መሆኑን አረጋግጠው አስፈላጊውን ፈቃድ መስጠታቸውን ተከትሎ ነው ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪም በዓለም ዙሪያ ያሉ ሌሎች 36 አየር መንገዶች አውሮፕላኑን ወደ በረራ መመለሳቸውን ተከትሎ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል። አየር መንገዱ አውሮፕላኑን ወደ መደበኛ አገልግሎት ከመመለሱ በፊት 'የሙከራ' ናቸው የተባሉ በራራዎችን አካሂዷል። አየር መንገዱ አውሮፕላኑን ወደ አገልግሎት ከመመለሱ በፊት ያደረጋቸውን የሙከራ በረራዎችን ከፍላይት ራዳር24 እና ፍላይት አዌር ድረ-ገጾች በተገኘው መረጃ መሠረት አውሮፕላኑ በቅርቡ ጥር 17 እና ዛሬ ጥር 24/2014 ዓ.ም በረራዎችን አድርጓል። እንደ ፍላይት አዌር ድረ-ገጽ ከሆነ ማክሰኞ ጥር 17 ረፋድ 5፡20 ላይ ለበረራ የተነሳው የበረራ ቁጥር ET9301 ለ53 ደቂቃዎች አየር ላይ ቆይቶ እኩለ ቀን 6፡13 ላይ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተመልሶ አርፏል። ፍላይት ራዳር24 ላይ እንደተመለከተው ደግሞ አየር መንገዱ ሌላ በቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኑ ዛሬ ማክሰኞ ከሰዓት በኋላ ሌላ የሙከራ በረራ አድርጓል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና በኢንዶኔዚያው አየር መንገድ ላይ አውሮፕላኖች ላይ በበረራ መቆጣጠሪያው እክል ገጥሞት ባስከተለው አደጋ ከበረራ ውጪ እንዲሆን የተደረገው ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን እጅግ ዘመናዊ ተብለው ከሚጠቀሱት መካከል አንዱ ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ አራት ቦይንግ 737 ማክስ 8 ያሉት ሲሆን ከአደጋው ቀደም ብሎ ተጨማሪ 25 ተመሳሳይ አውሮፕላኖችን ለመግዛት አዝዞ በያዝነው የፈረንጆች ዓመት ይረከባል ተብሎ ይጠበቃል። በአፍሪካ ግዙፉ አየር መንገድ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፤ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትን ተከትሎ በርካታ አየር መንገዶች ለኪሳራ ሲዳረጉ አየር መንገዱ ግን ትርፋማነቱን ስለማስቀጠሉ ብዙ ተብሎለታል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአምስት አህጉራት በመቶዎች ወደሚቆጠሩ መዳረሻዎች ያሉት ሲሆን 130 አውሮፕላኖች አሉት። እነዚህም እጅግ ዘመናዊ የሚባሉትን 16 ኤይርባስ ኤ350-900 እና 19 ቦይንግ ቢ787-8 ይጨምራሉ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላንን ወደ በረራ መለሰ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሦስት ዓመታት ለሚተጋ ጊዜ ከበረራ አግዶት የነበረውን ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ወደ አገልግሎት መለሰ። አየር መንገዱ ዛሬ ጥር 23/2014 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ ላይ አውሮፕላኑ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የቦይንግ እና የአየር መንገዱ ቦርድ አባላትን አሳፍሮ ወደ በረራ ተመልሷል ብሏል። አየር መንገዱ ባጋጠሙ አስከፊ አደጋ ምክንያት ከበረራ አግዷቸው የነበሩት አራት ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላኖቹን ወደ መደበኛ የመንገደኞች በረራ በያዝነው ሳምንት እንደሚመልስ አስታውቆ ነበር። ከአፍሪካ ትልቁ አየር መንገድ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያሉትን ዘመናዊ ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላኖች ከበረራ ውጪ ካደረገ ሁለት ዓመት አልፎታል። መጋቢት 01 ቀን 2011 ዓ.ም ጠዋት ከአዲስ አበባ ወደ ኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ 149 ሰዎችን ይዞ ይበር የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን የበረራ ቁጥር ET302 መከስከሱን ተከትሎ ነበር አውሮፕላኖቹ በመላው ዓለም ከበረራ ውጪ የሆኑት። በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ላይ ከደረሰው አደጋው ቀደም ብሎ በኢንዶኔዢያው ላየን ኤየር አየር መንገድ ተመሳሳይ ቦይንግ አውሮፕላን ላይ አደጋ አጋጥሞ የ181 ሰዎች ሕይወት ተቀጥፏል። ከሁለቱ አደጋዎች በኋላ በመላው ዓለም የሚገኙ በርካታ አየር መንገዶች ቦይንግ 737 ማክስን 8 አውሮፕላኖችን ማብረር አቁመው ነበር። አየር መንገዱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ላይ ከሁሉም በፊት ቅድሚያ የሚሰጠው ለደኅንነት ነው ብሏል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ ተወልደ ገብረማሪያም አየር መንገዱ አውሮፕላኑን ወደ አገልግሎት ለመመለስ ከውሳኔ ላይ የደረሰው በዓለም ዙሪያ ያሉ የበረራ ደኅንነት ተቆጣጠሪ አካላት አውሮፕላኑ አስተማማኝ መሆኑን አረጋግጠው አስፈላጊውን ፈቃድ መስጠታቸውን ተከትሎ ነው ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪም በዓለም ዙሪያ ያሉ ሌሎች 36 አየር መንገዶች አውሮፕላኑን ወደ በረራ መመለሳቸውን ተከትሎ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል። አየር መንገዱ አውሮፕላኑን ወደ መደበኛ አገልግሎት ከመመለሱ በፊት 'የሙከራ' ናቸው የተባሉ በራራዎችን አካሂዷል። አየር መንገዱ አውሮፕላኑን ወደ አገልግሎት ከመመለሱ በፊት ያደረጋቸውን የሙከራ በረራዎችን ከፍላይት ራዳር24 እና ፍላይት አዌር ድረ-ገጾች በተገኘው መረጃ መሠረት አውሮፕላኑ በቅርቡ ጥር 17 እና ዛሬ ጥር 24/2014 ዓ.ም በረራዎችን አድርጓል። እንደ ፍላይት አዌር ድረ-ገጽ ከሆነ ማክሰኞ ጥር 17 ረፋድ 5፡20 ላይ ለበረራ የተነሳው የበረራ ቁጥር ET9301 ለ53 ደቂቃዎች አየር ላይ ቆይቶ እኩለ ቀን 6፡13 ላይ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተመልሶ አርፏል። ፍላይት ራዳር24 ላይ እንደተመለከተው ደግሞ አየር መንገዱ ሌላ በቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኑ ዛሬ ማክሰኞ ከሰዓት በኋላ ሌላ የሙከራ በረራ አድርጓል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና በኢንዶኔዚያው አየር መንገድ ላይ አውሮፕላኖች ላይ በበረራ መቆጣጠሪያው እክል ገጥሞት ባስከተለው አደጋ ከበረራ ውጪ እንዲሆን የተደረገው ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን እጅግ ዘመናዊ ተብለው ከሚጠቀሱት መካከል አንዱ ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ አራት ቦይንግ 737 ማክስ 8 ያሉት ሲሆን ከአደጋው ቀደም ብሎ ተጨማሪ 25 ተመሳሳይ አውሮፕላኖችን ለመግዛት አዝዞ በያዝነው የፈረንጆች ዓመት ይረከባል ተብሎ ይጠበቃል። በአፍሪካ ግዙፉ አየር መንገድ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፤ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትን ተከትሎ በርካታ አየር መንገዶች ለኪሳራ ሲዳረጉ አየር መንገዱ ግን ትርፋማነቱን ስለማስቀጠሉ ብዙ ተብሎለታል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአምስት አህጉራት በመቶዎች ወደሚቆጠሩ መዳረሻዎች ያሉት ሲሆን 130 አውሮፕላኖች አሉት። እነዚህም እጅግ ዘመናዊ የሚባሉትን 16 ኤይርባስ ኤ350-900 እና 19 ቦይንግ ቢ787-8 ይጨምራሉ።
https://www.bbc.com/amharic/news-60218470
3politics
በአሜሪካ - አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ምን አይነት ጉዳዮች ይነሳሉ?
የኢትዮጵያውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የ49 አገራት መሪዎች የሚሳተፉበት ሁለተኛው የአሜሪካ- አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ ታኅሣሥ 04/2015 ዓ.ም. ይጀመራል። ከማክሰኞ ጀምሮ ለሦስት ቀናት የሚካሄደው የመሪዎች ጉባኤ ዓለማችንን እየፈተኗት ያሉ ተግዳሮቶች የአየር ንብረት ቀውስ፣ መልካም አስተዳደር፣ የምግብ ዋስትና እና የዓለም ጤናን የሚጨምር ሲሆን፣ እንዲሁም የአሜሪካ-አፍሪካ የንግድ እና የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማጠናከር ላይ ያተኩራል። “ጉባዔው… አፍሪካ ቁልፍ የጂኦፖለቲካል ተጫዋች እንደሆነች ዕውቅና በመስጠት ላይ የተመሠረተ ነው። አህጉሪቱ የአፍሪካን ህዝቦች ብቻ ሳይሆን የአለምን የወደፊት ሁኔታ ትቀርፃለች” ሲሉ የአሜሪካ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ጃክ ሱሊቫን ሰኞ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ መናገራቸው ተዘግቧል። በጉባኤው አርባ ዘጠኝ የአፍሪካ መሪዎች እንዲሁም የአፍሪካ ኅብረት ተጋብዘዋል ሲሉ ሱሊቫን በዚሁ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል። በዚህ ሳምንት በሚካሄደው የአሜሪካ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ፕሬዝዳንት ባይደን በቡድን 20 ውስጥ የአፍሪካ ኅብረት ቋሚ ቦታ እንዲያገኝ ድጋፍ እንደሚሰጡ ይጠበቃል ተብሏል። በተጫማሪም የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ ከአፍሪካ አገራት መካከል “ቋሚ አባል እንዲያካትት” ድጋፍ መስጠትን ጨምሮ ማሻሻያ እንዲያደርግ ፕሬዝዳንት ባይደን ቁርጠኛ ናቸው በማለት ሱሊቫን ተናግረዋል። የመሪዎቹ የመክፈቻ ጉባኤ የአፍሪካውያን እና የዲያስፖራ ወጣት መሪዎች ላይ የሚያጠነጥን ይሆናል። “ድምጾችን ማጉላት፡ ዘላቂ የሆነ ሽርክና መፍጠር” በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄደው ይህ ጉባኤ፣ ከአህጉሪቱ ጋር የጠበቀ ትስስር ያላቸው አፍሪካውያን እና ዲያስፖራዎች ከአሜሪካ ባለሥልጣናት ጋር ያላቸውን ግንኙነት የሚያጠናክር እንደሆነም ተገልጿል። የአሜሪካ-አፍሪካ ስትራቴጂያቸውን ይፋ ባደረጉበት ወቅት ፕሬዝዳንት ባይደን እንዳስታወቁት “የአፍሪካ ዲያስፖራች የጥንካሬያችን ምንጭ ናቸው” ብለዋል። አህጉሪቷን በመገንባት ከፍተኛ ሚና የተጫወቱትን በባርነት ከአህጉሪቷ ተግዛው አሜሪካ የደረሱ አፍሪካውያን የልጅ ልጆች፣ ከአፍሪካ ጋር የጠበቀ ቤተሰባዊ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ያላቸው ወደ ሁለት ሚሊዮን የሚጠጉ አፍሪካውያን ስደተኞችን ያጠቃልላል። የአፍሪካ እና የዲያስፖራ ወጣት መሪዎች ጉባኤ፣ በፈጠራ ኢንዱስትሪዎች እና በአካባቢ ፍትሃዊነት ላይ ያተኮረ እንደሆነም ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው ማስረጃ ያስረዳል። አሜሪካ ለአፍሪካውያን አገራት ከቀረጥ ነፃ ንግድ ተጠቃሚነት ዕድል (አጎዋ) ጋር በተያያዘ ከተጠቃሚ አገራቱ ንግድ ሚኒስትሮች ጋር የሚካሄደው ጉባኤም በዛሬው ዕለት ቀጠሮ ተይዞለታል። ። የአሜሪካ የንግድ ፖሊሲ ከፍተኛ ባለሥልጣን በሆኑት በአምባሳደር ካትሪን ታይ የሚመራው ይህ ጉባኤ፣ የአሜሪካ ምክር ቤት አባላት፣ የአሜሪካ መንግሥት እና የአፍሪካ ኅብረት ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ሴክሬታሪያት፣ የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን፣ የአፍሪካ ልማት ባንክ እና ክልላዊ የኢኮኖሚ ማኅበረሰቦችን የሚያሳትፍ ነው። በዚህ ጉባኤም በዋነኝነት የኢኮኖሚ ትብብርን ማጠናከር፣ የሁለትዮሽ ንግድ እና ኢንቨስትመንትን ማስፋፋት፣ ቀጣናዊ ኢኮኖሚያዊ ውህደትን መደገፍ እና የአሜሪካ-አፍሪካ ንግድን በሚመለከቱ ሌሎች የጋራ ተጠቃሚነት ጉዳዮች እና አጎዋ ትግበራ ላይ ይወያያል። አሜሪካ ከትግራዩ ጦርነት ጋር በተያያዘ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ተፈፅመዋል በሚል አጎዋ ከተሰኘው የቀረጥ ነፃ ንግድ ተጠቃሚነት ኢትዮጵያ መታገዷ ይታወሳል። ከኢትዮጵያ በተጨማሪም ከሰብዓዊ መብት እና ከዲሞክራሲ ስጋቶች ጋር በተያያዘም ማሊ እና ጊኒም እንዲወገዱ ተደርገዋል። በወቅቱም ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለአሜሪካ ኮንግረስ በጻፉት ደብዳቤ ኢትዮጵያ “በዓለም አቀፍ ደረጃ የታወቁ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ፈፅማለች” ማለታቸው ይታወሳል። ኢትዮጵያን ከቀረጥ ነፃ ንግድ ተጠቃሚነት እድል፣ አግዋ ማስወጣትም ከ200 ሺህ በላይ ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ቤተሰቦች ላይ ተፅእኖ እንደሚኖረው የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚነስቴር የገለጸ ሲሆን፣ በተለይም ከግጭቱ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው ሴቶች ላይ ጉዳቱ ይበረታል ብሎ ነበር። ከሰሞኑም ኢትዮጵያ ከቀረጥ ነጻ ንግድ አጎዋ እንድትመለስ በኢትዮጵያ የእርስ በርስ ጦርነት የተፈጸሙ ጥሰቶችን ለሚያጣረው የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት የሰብዓዊ ባለሙያዎች ቡድን ፍቃድ ስትሰጥ መሆኑ ተዘግቧል። ሪፖርተር እንግሊዝኛው ጋዜጣ እንደዘገበው የባለሙያዎቹ ቡድን ወደ አገር ውስጥ ገብተው መመርመር እንደ ቅድመ ሁኔታ መቀመጡን በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካን ኤምባሲ ባለሥልጣን መናገራቸውን ነው። ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም ባወጣው የ19 ገጽ ሪፖርት የጦር ወንጀሎች እና በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች መፈጸማቸውን አካቶ ጦርነቱ ወደተካሄደባቸው የትግራይ ክልል አካባባቢዎች እንዲሄዱ አለመፈቀዱን መግለጹ ይታወሳል። በተጨማሪም የሲቪል ማኅበረሰቦች፣ የአፍሪካ ጠፈር፣ የሰላም፣ የፀጥታ እና አስተዳደር፣ የጤና ትብብር ጉባኤዎች በዛሬው ዕለት ይካሄዳሉ። ታኅሣሥ 05/2015 ዓ.ም. የሚካሄዱት ጉባኤዎች  በአሜሪካ- አፍሪካ ቢዝነስ ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥኑ ይሆናል። በዚህም ጉባኤ ላይ ፕሬዚዳንት ባይደን ንግግር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። የአሜሪካ- የአፍሪካ የንግድ እና የኢንቨስትመንት ግንኙነት የወደፊት ዕጣፈንታ፣ ለአፍሪካ መሠረተ ልማት እና የኃይል ሽግግርን ለመገንባት ሽርክናን መፍጠር፣ የምግብ ዋስትናን የማጠናከር አጋርነት፣ የዲጂታል ግንኙነትን ማሳደግ እና በቴክኖሎጂ ሁሉን አቀፍ ዕድገት የማስቻል ትብብር የሚሉ ውይይቶችንም ያካተተ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በድረ-ገጹ አውጥቷል። በማጠቃለው ሐሙስ ታኅሣሥ 06/2015 ዓ.ም. የመሪዎች ጉባኤ ይካሄዳል። በዚህም  “መልካም አስተዳደር፣ ዲሞክራሲ የሰፈነባት፣ ሰብአዊ መብቶች የተከበሩባት፣ ፍትህ እና የሕግ የበላይነት የሰፈነባት አፍሪካ”፤ “ሰላምና አስተማማኝ የሰፈነባት አፍሪካ”፤ “በአካታች ዕድገት እና ዘላቂ ልማት ላይ በመመስረት የበለጸገች አፍሪካ” በሚልም በሦስት ክፍሎች ይካሄዳል። ጉባኤው አሜሪካ እንደ ዋና ዓለም አቀፍ ተፎካካሪዋ የምትመለከታት ቻይና በአፍሪካ ያላት ኢንቨስትመንቶች ከፍተኛ ብልጫ ባለበት ወቅት ነው። ከቻይና በተጨማሪ ሩሲያ በዩክሬን እያደረገችው ያለውን ጦርነት አህጉሪቷ ድጋፍ እንድትሰጣት እየጣረች ትገኛለች። በባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር የባይደን አስተዳደር ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ አገራትን በተመለከተ አዲስ የስትራቴጂ ሰነድ አውጥቷል። ይህም ሰነድ የአህጉሪቷን ጠቃሚነት በማጉላት የአሜሪካን እሳቤ ከሚጋሩ አገራትም ጋር የመከላከያ ትብብርንም አስፈላጊነት ጠቅሷል። ፕሬዝዳንት ባይደን አገራቸው የተባበሩት መንግሥታትን የመሳሰሉ ዓለም አቀፍ ተቋማትን ጨምሮ ከሌሎች አገራት ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለመገንባት እየጣሩ ይገኛሉ። በተለይም ከእሳቸው በፊት የነበሩት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የውጭ ፖሊሲያቸው “ቀዳሚዋ አሜሪካ” በማለት ላይ የተመሠረተ እና የአፍሪካ አገራትንም በመዝለፍና በማንቋሸሽ ለአራት አመታት መስራታቸውንም ተከትሎ ፕሬዚዳንት ባይደን ይህንን ለማስተካከል ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ። የመጀመሪያው የአሜሪካ አፍሪካ ጉባኤ የተካሄደው በፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የሥልጣን ዘመን ከስምንት ዓመታት በፊት ሲሆን ፕሬዚዳንት ትራምፕ ወደ ሥልጣን መምጣታቸውን ተከትሎ አሜሪካ በአፍሪካ ውስጥ ያላት ሚና ማሽቆልቆሉም ተነግሯል። የባይደን አስተዳደር ባለሥልጣናት በአፍሪካ ካሉ አገራት ጋር አሜሪካ ያላትን ግንኙነት ማጠናከርም እንደሚያስፈልግ ሲያሳስቡም ይሰማል። “ከኮንግረሱ (ምክር ቤቱ) ጋር በቅርበት በመሥራት አሜሪካ በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ውስጥ 55 ቢሊዮን ዶላር ለአፍሪካ ትሰጣለች” ሲል ሱሊቫን ሰኞ ዕለት ተናግረዋል።።
በአሜሪካ - አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ምን አይነት ጉዳዮች ይነሳሉ? የኢትዮጵያውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የ49 አገራት መሪዎች የሚሳተፉበት ሁለተኛው የአሜሪካ- አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ ታኅሣሥ 04/2015 ዓ.ም. ይጀመራል። ከማክሰኞ ጀምሮ ለሦስት ቀናት የሚካሄደው የመሪዎች ጉባኤ ዓለማችንን እየፈተኗት ያሉ ተግዳሮቶች የአየር ንብረት ቀውስ፣ መልካም አስተዳደር፣ የምግብ ዋስትና እና የዓለም ጤናን የሚጨምር ሲሆን፣ እንዲሁም የአሜሪካ-አፍሪካ የንግድ እና የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማጠናከር ላይ ያተኩራል። “ጉባዔው… አፍሪካ ቁልፍ የጂኦፖለቲካል ተጫዋች እንደሆነች ዕውቅና በመስጠት ላይ የተመሠረተ ነው። አህጉሪቱ የአፍሪካን ህዝቦች ብቻ ሳይሆን የአለምን የወደፊት ሁኔታ ትቀርፃለች” ሲሉ የአሜሪካ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ጃክ ሱሊቫን ሰኞ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ መናገራቸው ተዘግቧል። በጉባኤው አርባ ዘጠኝ የአፍሪካ መሪዎች እንዲሁም የአፍሪካ ኅብረት ተጋብዘዋል ሲሉ ሱሊቫን በዚሁ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል። በዚህ ሳምንት በሚካሄደው የአሜሪካ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ፕሬዝዳንት ባይደን በቡድን 20 ውስጥ የአፍሪካ ኅብረት ቋሚ ቦታ እንዲያገኝ ድጋፍ እንደሚሰጡ ይጠበቃል ተብሏል። በተጫማሪም የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ ከአፍሪካ አገራት መካከል “ቋሚ አባል እንዲያካትት” ድጋፍ መስጠትን ጨምሮ ማሻሻያ እንዲያደርግ ፕሬዝዳንት ባይደን ቁርጠኛ ናቸው በማለት ሱሊቫን ተናግረዋል። የመሪዎቹ የመክፈቻ ጉባኤ የአፍሪካውያን እና የዲያስፖራ ወጣት መሪዎች ላይ የሚያጠነጥን ይሆናል። “ድምጾችን ማጉላት፡ ዘላቂ የሆነ ሽርክና መፍጠር” በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄደው ይህ ጉባኤ፣ ከአህጉሪቱ ጋር የጠበቀ ትስስር ያላቸው አፍሪካውያን እና ዲያስፖራዎች ከአሜሪካ ባለሥልጣናት ጋር ያላቸውን ግንኙነት የሚያጠናክር እንደሆነም ተገልጿል። የአሜሪካ-አፍሪካ ስትራቴጂያቸውን ይፋ ባደረጉበት ወቅት ፕሬዝዳንት ባይደን እንዳስታወቁት “የአፍሪካ ዲያስፖራች የጥንካሬያችን ምንጭ ናቸው” ብለዋል። አህጉሪቷን በመገንባት ከፍተኛ ሚና የተጫወቱትን በባርነት ከአህጉሪቷ ተግዛው አሜሪካ የደረሱ አፍሪካውያን የልጅ ልጆች፣ ከአፍሪካ ጋር የጠበቀ ቤተሰባዊ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ያላቸው ወደ ሁለት ሚሊዮን የሚጠጉ አፍሪካውያን ስደተኞችን ያጠቃልላል። የአፍሪካ እና የዲያስፖራ ወጣት መሪዎች ጉባኤ፣ በፈጠራ ኢንዱስትሪዎች እና በአካባቢ ፍትሃዊነት ላይ ያተኮረ እንደሆነም ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው ማስረጃ ያስረዳል። አሜሪካ ለአፍሪካውያን አገራት ከቀረጥ ነፃ ንግድ ተጠቃሚነት ዕድል (አጎዋ) ጋር በተያያዘ ከተጠቃሚ አገራቱ ንግድ ሚኒስትሮች ጋር የሚካሄደው ጉባኤም በዛሬው ዕለት ቀጠሮ ተይዞለታል። ። የአሜሪካ የንግድ ፖሊሲ ከፍተኛ ባለሥልጣን በሆኑት በአምባሳደር ካትሪን ታይ የሚመራው ይህ ጉባኤ፣ የአሜሪካ ምክር ቤት አባላት፣ የአሜሪካ መንግሥት እና የአፍሪካ ኅብረት ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ሴክሬታሪያት፣ የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን፣ የአፍሪካ ልማት ባንክ እና ክልላዊ የኢኮኖሚ ማኅበረሰቦችን የሚያሳትፍ ነው። በዚህ ጉባኤም በዋነኝነት የኢኮኖሚ ትብብርን ማጠናከር፣ የሁለትዮሽ ንግድ እና ኢንቨስትመንትን ማስፋፋት፣ ቀጣናዊ ኢኮኖሚያዊ ውህደትን መደገፍ እና የአሜሪካ-አፍሪካ ንግድን በሚመለከቱ ሌሎች የጋራ ተጠቃሚነት ጉዳዮች እና አጎዋ ትግበራ ላይ ይወያያል። አሜሪካ ከትግራዩ ጦርነት ጋር በተያያዘ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ተፈፅመዋል በሚል አጎዋ ከተሰኘው የቀረጥ ነፃ ንግድ ተጠቃሚነት ኢትዮጵያ መታገዷ ይታወሳል። ከኢትዮጵያ በተጨማሪም ከሰብዓዊ መብት እና ከዲሞክራሲ ስጋቶች ጋር በተያያዘም ማሊ እና ጊኒም እንዲወገዱ ተደርገዋል። በወቅቱም ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለአሜሪካ ኮንግረስ በጻፉት ደብዳቤ ኢትዮጵያ “በዓለም አቀፍ ደረጃ የታወቁ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ፈፅማለች” ማለታቸው ይታወሳል። ኢትዮጵያን ከቀረጥ ነፃ ንግድ ተጠቃሚነት እድል፣ አግዋ ማስወጣትም ከ200 ሺህ በላይ ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ቤተሰቦች ላይ ተፅእኖ እንደሚኖረው የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚነስቴር የገለጸ ሲሆን፣ በተለይም ከግጭቱ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው ሴቶች ላይ ጉዳቱ ይበረታል ብሎ ነበር። ከሰሞኑም ኢትዮጵያ ከቀረጥ ነጻ ንግድ አጎዋ እንድትመለስ በኢትዮጵያ የእርስ በርስ ጦርነት የተፈጸሙ ጥሰቶችን ለሚያጣረው የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት የሰብዓዊ ባለሙያዎች ቡድን ፍቃድ ስትሰጥ መሆኑ ተዘግቧል። ሪፖርተር እንግሊዝኛው ጋዜጣ እንደዘገበው የባለሙያዎቹ ቡድን ወደ አገር ውስጥ ገብተው መመርመር እንደ ቅድመ ሁኔታ መቀመጡን በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካን ኤምባሲ ባለሥልጣን መናገራቸውን ነው። ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም ባወጣው የ19 ገጽ ሪፖርት የጦር ወንጀሎች እና በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች መፈጸማቸውን አካቶ ጦርነቱ ወደተካሄደባቸው የትግራይ ክልል አካባባቢዎች እንዲሄዱ አለመፈቀዱን መግለጹ ይታወሳል። በተጨማሪም የሲቪል ማኅበረሰቦች፣ የአፍሪካ ጠፈር፣ የሰላም፣ የፀጥታ እና አስተዳደር፣ የጤና ትብብር ጉባኤዎች በዛሬው ዕለት ይካሄዳሉ። ታኅሣሥ 05/2015 ዓ.ም. የሚካሄዱት ጉባኤዎች  በአሜሪካ- አፍሪካ ቢዝነስ ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥኑ ይሆናል። በዚህም ጉባኤ ላይ ፕሬዚዳንት ባይደን ንግግር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። የአሜሪካ- የአፍሪካ የንግድ እና የኢንቨስትመንት ግንኙነት የወደፊት ዕጣፈንታ፣ ለአፍሪካ መሠረተ ልማት እና የኃይል ሽግግርን ለመገንባት ሽርክናን መፍጠር፣ የምግብ ዋስትናን የማጠናከር አጋርነት፣ የዲጂታል ግንኙነትን ማሳደግ እና በቴክኖሎጂ ሁሉን አቀፍ ዕድገት የማስቻል ትብብር የሚሉ ውይይቶችንም ያካተተ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በድረ-ገጹ አውጥቷል። በማጠቃለው ሐሙስ ታኅሣሥ 06/2015 ዓ.ም. የመሪዎች ጉባኤ ይካሄዳል። በዚህም  “መልካም አስተዳደር፣ ዲሞክራሲ የሰፈነባት፣ ሰብአዊ መብቶች የተከበሩባት፣ ፍትህ እና የሕግ የበላይነት የሰፈነባት አፍሪካ”፤ “ሰላምና አስተማማኝ የሰፈነባት አፍሪካ”፤ “በአካታች ዕድገት እና ዘላቂ ልማት ላይ በመመስረት የበለጸገች አፍሪካ” በሚልም በሦስት ክፍሎች ይካሄዳል። ጉባኤው አሜሪካ እንደ ዋና ዓለም አቀፍ ተፎካካሪዋ የምትመለከታት ቻይና በአፍሪካ ያላት ኢንቨስትመንቶች ከፍተኛ ብልጫ ባለበት ወቅት ነው። ከቻይና በተጨማሪ ሩሲያ በዩክሬን እያደረገችው ያለውን ጦርነት አህጉሪቷ ድጋፍ እንድትሰጣት እየጣረች ትገኛለች። በባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር የባይደን አስተዳደር ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ አገራትን በተመለከተ አዲስ የስትራቴጂ ሰነድ አውጥቷል። ይህም ሰነድ የአህጉሪቷን ጠቃሚነት በማጉላት የአሜሪካን እሳቤ ከሚጋሩ አገራትም ጋር የመከላከያ ትብብርንም አስፈላጊነት ጠቅሷል። ፕሬዝዳንት ባይደን አገራቸው የተባበሩት መንግሥታትን የመሳሰሉ ዓለም አቀፍ ተቋማትን ጨምሮ ከሌሎች አገራት ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለመገንባት እየጣሩ ይገኛሉ። በተለይም ከእሳቸው በፊት የነበሩት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የውጭ ፖሊሲያቸው “ቀዳሚዋ አሜሪካ” በማለት ላይ የተመሠረተ እና የአፍሪካ አገራትንም በመዝለፍና በማንቋሸሽ ለአራት አመታት መስራታቸውንም ተከትሎ ፕሬዚዳንት ባይደን ይህንን ለማስተካከል ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ። የመጀመሪያው የአሜሪካ አፍሪካ ጉባኤ የተካሄደው በፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የሥልጣን ዘመን ከስምንት ዓመታት በፊት ሲሆን ፕሬዚዳንት ትራምፕ ወደ ሥልጣን መምጣታቸውን ተከትሎ አሜሪካ በአፍሪካ ውስጥ ያላት ሚና ማሽቆልቆሉም ተነግሯል። የባይደን አስተዳደር ባለሥልጣናት በአፍሪካ ካሉ አገራት ጋር አሜሪካ ያላትን ግንኙነት ማጠናከርም እንደሚያስፈልግ ሲያሳስቡም ይሰማል። “ከኮንግረሱ (ምክር ቤቱ) ጋር በቅርበት በመሥራት አሜሪካ በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ውስጥ 55 ቢሊዮን ዶላር ለአፍሪካ ትሰጣለች” ሲል ሱሊቫን ሰኞ ዕለት ተናግረዋል።።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cn3zk02kp0vo
0business
የቻይናዋ ቤይጂንግ አሽከርካሪ አልባ የታክሲ አገልግሎት መስጠት ጀመረች
የቻይናዋ ቤይጂንግ ከተማ ባለሥልጣናት ለመጀመሪያ ጊዜ አሽከርካሪ አልባ የታክሲ አገልግሎት እንዲሰጥ ፈቃድ ሰጥተዋል። ይህም በርካታ የሮቦት ታክሲዎች በቤይጂንግ ጎዳናዎች ላይ እንዲታዩ አድርጓል። ለጊዜው አሸከርካሪ አልባ ታክሲዎቹ በመዲናዋ ደቡባዊ ክፍል በ60 ኪሎ ሜትር ውስጥ ብቻ እንዲንቀሳቀሱ ተወስኗል። በሂደት ብዙ ቦታዎች ተደራሽ ይሆናሉ ተብሎ ይታሰባል።
የቻይናዋ ቤይጂንግ አሽከርካሪ አልባ የታክሲ አገልግሎት መስጠት ጀመረች የቻይናዋ ቤይጂንግ ከተማ ባለሥልጣናት ለመጀመሪያ ጊዜ አሽከርካሪ አልባ የታክሲ አገልግሎት እንዲሰጥ ፈቃድ ሰጥተዋል። ይህም በርካታ የሮቦት ታክሲዎች በቤይጂንግ ጎዳናዎች ላይ እንዲታዩ አድርጓል። ለጊዜው አሸከርካሪ አልባ ታክሲዎቹ በመዲናዋ ደቡባዊ ክፍል በ60 ኪሎ ሜትር ውስጥ ብቻ እንዲንቀሳቀሱ ተወስኗል። በሂደት ብዙ ቦታዎች ተደራሽ ይሆናሉ ተብሎ ይታሰባል።
https://www.bbc.com/amharic/news-59682113
5sports
የቶኪዮ 2020 የፓራሊምፒክ ሜዳሊያ ዝርዝር
በጃፓን ቶኪዮ የተካሄደው የኦሊምፒክ ውድድርን ማብቃት ተከትሎ ማክሰኞ ነሐሴ 18/2013 ዓ.ም ሌላኛው ውድድር ፓራሊምፒክ መካሄድ ጀምሯል። የአሁኑ የፓራሊምፒክ ከዚህ ቀደም ከነበሩት ተመሳሳይ ውድድሮች በበለጠ 4,400 ስፖርተኞች በ22 የስፖርት አይነቶች አማካይነት 540 ውድድሮች ይካሄዱበታል። ይህ የቢቢሲ አማርኛ ገጽም በፓራሊምፒክ ውድድር ላይ ስፖርተኞች የሚያገኟወቸውን የወርቅ፣ የብርና የነሐስ ሜዳሊያዎች ዝርዝር ወክለው ከተወዳደሩባቸው ብሔራዊ የፓራሊምፒክ ቡድን ጋር ያቀርባል። ይህ ገጽ በየ10 ደቂቃው የሚኖሩ በፓራሊምፒክ ውድድር የተገኙ የሜዳሊያ ለውጦችን እየተከታተለ ያቀርባል።
የቶኪዮ 2020 የፓራሊምፒክ ሜዳሊያ ዝርዝር በጃፓን ቶኪዮ የተካሄደው የኦሊምፒክ ውድድርን ማብቃት ተከትሎ ማክሰኞ ነሐሴ 18/2013 ዓ.ም ሌላኛው ውድድር ፓራሊምፒክ መካሄድ ጀምሯል። የአሁኑ የፓራሊምፒክ ከዚህ ቀደም ከነበሩት ተመሳሳይ ውድድሮች በበለጠ 4,400 ስፖርተኞች በ22 የስፖርት አይነቶች አማካይነት 540 ውድድሮች ይካሄዱበታል። ይህ የቢቢሲ አማርኛ ገጽም በፓራሊምፒክ ውድድር ላይ ስፖርተኞች የሚያገኟወቸውን የወርቅ፣ የብርና የነሐስ ሜዳሊያዎች ዝርዝር ወክለው ከተወዳደሩባቸው ብሔራዊ የፓራሊምፒክ ቡድን ጋር ያቀርባል። ይህ ገጽ በየ10 ደቂቃው የሚኖሩ በፓራሊምፒክ ውድድር የተገኙ የሜዳሊያ ለውጦችን እየተከታተለ ያቀርባል።
https://www.bbc.com/amharic/news-58328997
5sports
በፈረንሳይ ሊግ የውሃ ኮዳ ተጫዋች ላይ በመወርወሩ ጨዋታው ተቋረጠ
በፈረንሳይ ሊግ የውሃ ኮዳ ተጫዋች ላይ በመወርወሩ ኒስ እና ማርሴ ሲያደርጉት የነበረው ጨዋታ እንዲቋረጥ ሆነ። የማርሴ ተጫዋች ዲሚቲሪ ፓዬ በውሃ ኮዳ ተመትቶ ኮዳውን ወደ ደጋፊዎች መልሶ መወርወሩን ተከትሎ ደጋፊዎች ወደ ሜዳ በመግባታቸው ጨዋታ እንዲቋረጥ ተደርጓል። የማርሴው ፓዬ የማዕዘን ምት ሊመታ ሲሰሰናዳ በባለሜዳዎቹ ኒስ ደጋፊዎች በውሃ ኮዳ ጀርባውን ተመቷል። ተጫዋቹ ኮዳውን መልሶ መወርወሩን ተከትሎ ወደ ሜዳ የገቡ ደጋፊዎችን ጠባቂዎች እና ተጫዋቾች ሊያስቆሟቸው አልቻሉም። ከረዥም ቆይታ በኋላ የኒስ ተጫዋቾች ጨዋታውን ለመጨረስ ወደ ሜዳ ቢገቡም የማርሴይ ተጫዋቾች ግን ፍቃደኛ አልሆኑም። በዚህ ምክንያት ጨዋታው ተቋርጧል። በካሴፐር ዶልበርግ የመጀመሪያ አጋማሽ ግብ ባለ ሜዳው ኒስ 1-0 እየመራ ነበር። አንዳንድ የማርሴይ ተጫዋቾች በተፈጠረው ግርግር ምክንያት ጉዳት እንደደረሰባቸው ተነግሯል። የማርሴይ ፕሬዝዳንት ፓብሎ ሎኖሪያ "የእኛ ተጫዋቾች ጥቃት ደርሶባቸዋል" ብለዋል። "በሜዳ ወረራው ወቅት ጥቃት ለደረሰባቸው ተጫዋቾቻችን እና ለሌሎቹም ደህንነት ዋስትና ስላልነበረ ጨዋታው እንዳይቀጥል ወስነናል" ብለዋል። ትርምሱ ተጫዋቾች ከሜዳ ለመውጣት ሲሞክሩ ቀጥሏል። የማርሴይ አሰልጣኝ ጆርጅ ሳምፓሊ በሥራ ባልደረቦቻቸው ሲገላገሉ ታይተዋል። ጨዋታው እየተካሄደም የማርሴይ ተጫዋቾች በማዕዘን ምቱ መምቻ አካባቢ የውሃ ኮዳ ሲወረወርባቸው የነበረ ሲሆን አንዱ ፓዬን በመታቱ አማካዩ ወድቋል። ይህን ተከትሎ በተፈጠረው አለመግባባት የቡድን ባልደረቦቹ አልቫሮ ጎንዛሌዝ እና ማቲዮ ጉንዶዚ ደጋፊዎቹን ለመጋፈጥ ሲሮጡ የኒሱ ግብ ጠባቂ ዳንቴ ደግሞ ደጋፊዎቹን ለማረጋጋት ሲሞክር ታይቷል። ማርሴይ ከሁለት ሳምንት በፊት ሞንትፔሊየን 3-2 ባሸነፈችበት ጨዋታም ደጋፊዎች ወደ ሜዳው የውሃ ኮዳዎችን በተመሳሳይ ሲወረውሩ ታይተዋል። በስታዲየሙ ድምጽ ማጉያ ደጋፊዎች እንዲረጋጉ የጠየቁት የኒሱ ፕሬዝዳንት ዣን ፒዬር ሪቭሬ ለአንዳንድ ጥፋቶች ማርሴዮችን ተጠያቂ አድርገዋል። "ጨዋታው በዚህ መልኩ መጠናቀቁ ያሳዝናል" ብለዋል። "ሁሉም የተከሰተውን አይቷል። የውሃ ኮዳዎች እንደተወረወሩ መካድ አንችልም። ግጭቱን ያቀጣጠለው የበቀል እርምጃ በወሰዱት ሁለት የማርሴይ ተጫዋቾች ምላሽ ነበር። ከዚያ በኋላ የማርሴይ የደህንነት ሠራተኞች ጣልቃ ገብተው ተጫዋቾቻችንን መምታታቸው በጣም የሚያሳዝን ነው።" ሲሉ ተናግረዋል።
በፈረንሳይ ሊግ የውሃ ኮዳ ተጫዋች ላይ በመወርወሩ ጨዋታው ተቋረጠ በፈረንሳይ ሊግ የውሃ ኮዳ ተጫዋች ላይ በመወርወሩ ኒስ እና ማርሴ ሲያደርጉት የነበረው ጨዋታ እንዲቋረጥ ሆነ። የማርሴ ተጫዋች ዲሚቲሪ ፓዬ በውሃ ኮዳ ተመትቶ ኮዳውን ወደ ደጋፊዎች መልሶ መወርወሩን ተከትሎ ደጋፊዎች ወደ ሜዳ በመግባታቸው ጨዋታ እንዲቋረጥ ተደርጓል። የማርሴው ፓዬ የማዕዘን ምት ሊመታ ሲሰሰናዳ በባለሜዳዎቹ ኒስ ደጋፊዎች በውሃ ኮዳ ጀርባውን ተመቷል። ተጫዋቹ ኮዳውን መልሶ መወርወሩን ተከትሎ ወደ ሜዳ የገቡ ደጋፊዎችን ጠባቂዎች እና ተጫዋቾች ሊያስቆሟቸው አልቻሉም። ከረዥም ቆይታ በኋላ የኒስ ተጫዋቾች ጨዋታውን ለመጨረስ ወደ ሜዳ ቢገቡም የማርሴይ ተጫዋቾች ግን ፍቃደኛ አልሆኑም። በዚህ ምክንያት ጨዋታው ተቋርጧል። በካሴፐር ዶልበርግ የመጀመሪያ አጋማሽ ግብ ባለ ሜዳው ኒስ 1-0 እየመራ ነበር። አንዳንድ የማርሴይ ተጫዋቾች በተፈጠረው ግርግር ምክንያት ጉዳት እንደደረሰባቸው ተነግሯል። የማርሴይ ፕሬዝዳንት ፓብሎ ሎኖሪያ "የእኛ ተጫዋቾች ጥቃት ደርሶባቸዋል" ብለዋል። "በሜዳ ወረራው ወቅት ጥቃት ለደረሰባቸው ተጫዋቾቻችን እና ለሌሎቹም ደህንነት ዋስትና ስላልነበረ ጨዋታው እንዳይቀጥል ወስነናል" ብለዋል። ትርምሱ ተጫዋቾች ከሜዳ ለመውጣት ሲሞክሩ ቀጥሏል። የማርሴይ አሰልጣኝ ጆርጅ ሳምፓሊ በሥራ ባልደረቦቻቸው ሲገላገሉ ታይተዋል። ጨዋታው እየተካሄደም የማርሴይ ተጫዋቾች በማዕዘን ምቱ መምቻ አካባቢ የውሃ ኮዳ ሲወረወርባቸው የነበረ ሲሆን አንዱ ፓዬን በመታቱ አማካዩ ወድቋል። ይህን ተከትሎ በተፈጠረው አለመግባባት የቡድን ባልደረቦቹ አልቫሮ ጎንዛሌዝ እና ማቲዮ ጉንዶዚ ደጋፊዎቹን ለመጋፈጥ ሲሮጡ የኒሱ ግብ ጠባቂ ዳንቴ ደግሞ ደጋፊዎቹን ለማረጋጋት ሲሞክር ታይቷል። ማርሴይ ከሁለት ሳምንት በፊት ሞንትፔሊየን 3-2 ባሸነፈችበት ጨዋታም ደጋፊዎች ወደ ሜዳው የውሃ ኮዳዎችን በተመሳሳይ ሲወረውሩ ታይተዋል። በስታዲየሙ ድምጽ ማጉያ ደጋፊዎች እንዲረጋጉ የጠየቁት የኒሱ ፕሬዝዳንት ዣን ፒዬር ሪቭሬ ለአንዳንድ ጥፋቶች ማርሴዮችን ተጠያቂ አድርገዋል። "ጨዋታው በዚህ መልኩ መጠናቀቁ ያሳዝናል" ብለዋል። "ሁሉም የተከሰተውን አይቷል። የውሃ ኮዳዎች እንደተወረወሩ መካድ አንችልም። ግጭቱን ያቀጣጠለው የበቀል እርምጃ በወሰዱት ሁለት የማርሴይ ተጫዋቾች ምላሽ ነበር። ከዚያ በኋላ የማርሴይ የደህንነት ሠራተኞች ጣልቃ ገብተው ተጫዋቾቻችንን መምታታቸው በጣም የሚያሳዝን ነው።" ሲሉ ተናግረዋል።
https://www.bbc.com/amharic/58302235
2health
ኮሮናቫይረስ፡ ቫይታሚን ዲ ከኮቪድ-19 ይከላከለን ይሆን?
ተመራማሪዎች ቫይታሚን ዲ ሰውነታችን የበሽታ መከላከል ስርዓት ብርታትን በመስጠት ከኮቪድ-19 ጋር ለሚያደርገው ፍልሚያ እገዛ ያደርጋል ወይ? የሚለውን ለማረጋገጥ የሚያስችላቸውን ሙከራ ለማድረግ በጎ ፈቃደኞችን እየፈለጉ መሆኑ ተገልጿል። በጎ ፈቃደኞቹ ከጸሀይ ብርሀን የሚገኘው ቫይታሚን ዲ እጥረት ካለባቸው ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት በፖስታ ቤት በኩል የቫይታሚን ዲ እንክብሎች ወደቤታቸው ይላክላቸዋል። የዩናይትድ ኪንግደም ዜጎችና ነዋሪዎች ደግሞ የብርዱ ወቅት እየመጣ መሆኑን ተከትሎ የቫይታሚን ዲ እጥረት በሰውነታችሁ ውስጥ ሊፈጠር ስለሚችል እንክብሎቹን ብትወስዱ ጥሩ ነው ተብለዋል። የቫይታሚን ዲ እንክብሎቹ ከኮቪድ ጋር በተያያዘ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ በሽታ የመከላከል አቅምን ከፍ ለማድረግና ኢንፌክሽኖችን ለመቀነስም በእጅጉ ጠቃሚ ነው ተብሏል። የቫይታሚን ዲ እጥረት የሚታይባቸው ሰዎች አብዛኛዎቹ እድሜያቸው የገፋና የአፍሪካ አልያም የእሲያ ዝርያ ያለባቸው ሰዎች ሲሆኑ እነዚህ ሰዎች ለኮቪድ-19 ተጋላጭ መሆናቸውም ሌላ አሳሳቢ ነገር ነው። በለንደን ኩዊን ሜሪ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች እየተደረገ የሚገኘው ምርምር በባርትስ በጎ አድራጎት ድጋፍ ይደረግለታል። በምርምሩም የቫይታሚን ዲ እንክብሎች ለሰዎች ይታደላሉ። የምርምሩ መሪ የሆኑት ዴቪድ ጆሊፍ እንደሚሉት ''ሙከራው በዚህ ረገድ ጠንከር ያለ ምላሽ ይሰጠናል ብለን እናምናለን'' ብለዋል። አክለውም ''ቫይታሚን ዲ ኮቪድ-19ኝን የመከላከል አቅም ከፍ የሚያደርግ ከሆነ ትልቅ ዜና ይሆናል'' ብለዋል። ''የቫይታሚን ዲ እንክብሎች እጅግ ዝቅተኛ በሆነ ዋጋ የሚገኙ ናቸው፤ በተጨማሪም የጎንዮሽ ጉዳታቸው ዝቅተኛና በቀላሉ መገኘት የሚችሉ ናቸው። ወረርሽኙን ለመዋጋት እየተሰራ ያለው ዓለማ አቀፍ ሰራ በደንብ ሊያግዝ ይችላል'' ምንም እንኳን የቫይታሚን ዲ እንክብሎችን መውሰድ ለጤና ጠቃሚ ቢሆንም ከህክምና ባለሙያዎች ምክር ውጪ መውሰድ ግን የጎንዮሽ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል ባለሙያዎቹ ገልጸዋል።
ኮሮናቫይረስ፡ ቫይታሚን ዲ ከኮቪድ-19 ይከላከለን ይሆን? ተመራማሪዎች ቫይታሚን ዲ ሰውነታችን የበሽታ መከላከል ስርዓት ብርታትን በመስጠት ከኮቪድ-19 ጋር ለሚያደርገው ፍልሚያ እገዛ ያደርጋል ወይ? የሚለውን ለማረጋገጥ የሚያስችላቸውን ሙከራ ለማድረግ በጎ ፈቃደኞችን እየፈለጉ መሆኑ ተገልጿል። በጎ ፈቃደኞቹ ከጸሀይ ብርሀን የሚገኘው ቫይታሚን ዲ እጥረት ካለባቸው ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት በፖስታ ቤት በኩል የቫይታሚን ዲ እንክብሎች ወደቤታቸው ይላክላቸዋል። የዩናይትድ ኪንግደም ዜጎችና ነዋሪዎች ደግሞ የብርዱ ወቅት እየመጣ መሆኑን ተከትሎ የቫይታሚን ዲ እጥረት በሰውነታችሁ ውስጥ ሊፈጠር ስለሚችል እንክብሎቹን ብትወስዱ ጥሩ ነው ተብለዋል። የቫይታሚን ዲ እንክብሎቹ ከኮቪድ ጋር በተያያዘ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ በሽታ የመከላከል አቅምን ከፍ ለማድረግና ኢንፌክሽኖችን ለመቀነስም በእጅጉ ጠቃሚ ነው ተብሏል። የቫይታሚን ዲ እጥረት የሚታይባቸው ሰዎች አብዛኛዎቹ እድሜያቸው የገፋና የአፍሪካ አልያም የእሲያ ዝርያ ያለባቸው ሰዎች ሲሆኑ እነዚህ ሰዎች ለኮቪድ-19 ተጋላጭ መሆናቸውም ሌላ አሳሳቢ ነገር ነው። በለንደን ኩዊን ሜሪ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች እየተደረገ የሚገኘው ምርምር በባርትስ በጎ አድራጎት ድጋፍ ይደረግለታል። በምርምሩም የቫይታሚን ዲ እንክብሎች ለሰዎች ይታደላሉ። የምርምሩ መሪ የሆኑት ዴቪድ ጆሊፍ እንደሚሉት ''ሙከራው በዚህ ረገድ ጠንከር ያለ ምላሽ ይሰጠናል ብለን እናምናለን'' ብለዋል። አክለውም ''ቫይታሚን ዲ ኮቪድ-19ኝን የመከላከል አቅም ከፍ የሚያደርግ ከሆነ ትልቅ ዜና ይሆናል'' ብለዋል። ''የቫይታሚን ዲ እንክብሎች እጅግ ዝቅተኛ በሆነ ዋጋ የሚገኙ ናቸው፤ በተጨማሪም የጎንዮሽ ጉዳታቸው ዝቅተኛና በቀላሉ መገኘት የሚችሉ ናቸው። ወረርሽኙን ለመዋጋት እየተሰራ ያለው ዓለማ አቀፍ ሰራ በደንብ ሊያግዝ ይችላል'' ምንም እንኳን የቫይታሚን ዲ እንክብሎችን መውሰድ ለጤና ጠቃሚ ቢሆንም ከህክምና ባለሙያዎች ምክር ውጪ መውሰድ ግን የጎንዮሽ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል ባለሙያዎቹ ገልጸዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-54569305
3politics
ታጣቂዎች በሙገር ሲሚንቶ የሠራተኞች አውቶቡስ ላይ ተኩስ ከፍተው ሰዎች ተገደሉ
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ውስጥ ታጣቂዎች በሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ የሠራተኞች ማመላለሻ አውቶቡስ ላይ ተኩስ ከፍተው በፈጸሙጥ ጥቃት ቢያንስ ሁለት ሰዎችን ሲገደሉ በርካቶች ቆሰሉ። ቢቢሲ ከሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ሠራተኞች እና ከአካባቢው ነዋሪዎች እንዳረጋገጠው ጥቃቱ የተፈጸመው ዛሬ ሰኞ መስከረም 23/2015 ዓ.ም. ንጋት 12 ሰዓት አካባቢ ነው። ነዋሪዎችና ሠራተኞች እንዳሉት ጥቃቱን የፈጸመው መንግሥት በሽብርተኝነት የፈረጀውና በአካባቢው እንደሚንቀሳቀስ የሚነገረው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ወይም ሸኔ ነው። በሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ሠራተኞች ላይ ጥቃት የተፈጸመው የሠራተኞች ማመላለሻ አውቶቡስ የሲሚንቶ ግብዓት ወደሚወጣበት አካባቢ እየተጓዘ ሳለ በታጣቂዎች በተከፈተባቸው ተኩስ ነው። በዚህ ጥቃት ቢያንስ ሁለት ሰዎች የተገደሉ ሲሆን ከ12 ያላነሱ ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸው ተገልጿል። በአውቶብሱ ምን ያክል ሰዎች ተሳፍረው እንደነበረ ግን ግልጽ አይደለም። ቢቢሲ ጥቃቱን በማስመልከት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የኦሮሚያ ደኅንነት ቢሮ ኃላፊ ከፍያለው ተፈራን ቢጠይቅም መረጃ እንደሌላቸው ሲገልጹ፤ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ እና የኦሮሚያ ክልል ፀጥታ እና አስተዳደር ምክትል ቢሮ ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ መልሰን እንድንደውል ነግረውናል። በተጨማሪም ስለደረሰው ጉዳት ለመጠየቅ ተሽከርካሪው ላይ ጥቃት የተፈጸመበትን የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካን አስተያየት ለማካተት ያደረገው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል። ቢቢሲ ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ምንጮች እንደተረዳው ከሆነ ሠራተኞቹ በአውቶቡሱ እየተጓዙ ሳለ አድፍጠው ይጠብቁ የነበሩት ታጣቂዎች የተሸካርካሪውን ጎማ ጨምሮ የተለያየ የመኪናውን አካል በጥይት መትተዋል። ተሳፋሪዎች እና ተሸከርካሪው በጥይት ይደብደቡ እንጂ የአውቶብሱ አሸከርካሪ መኪናውን ሳያቆም የፊት ጎማው በጥይት የተመታ መኪናውን እያሸከረከረ የሲሚንቶ ግብዓት ከሚወጣበት ቦታ ላይ ደርሷል። ከተገደሉት ሰዎች በተጨማሪ በርካታ ሰዎች ከወገባቸው በታች ያለ የሰውነት ክፍላቸው በጥይት ተመትቶ መቁሰላቸውን እማኞች ለቢቢሲ ገልጸዋል። ቢቢሲ ከሲሚንቶ ፋብሪካው ሠራተኞች እንደተረዳው በአካባቢው ያሉ ሲሚንቶ ፋብሪካዎች ለምርታቸው ግብዓት የሚሆናቸውን ላይምስቶን የተሰኘ የድንጋይ አይነት ከፋብሪካው በጥቂት ኪሎ ሜትር ርቆ ከሚገኝ አካባቢ ይወስዳሉ። ለሲሚንቶ ምርት ግብዓት የሚወጣበት አካባቢ በመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች ጥበቃ እንደሚደረግ የተገለጸ ሲሆን፤ ከታጣቂዎች ተኩስ ያመለጠው የሠራተኞች ማመላለሻ አውቶብስ ከጥቃቱ በኋላ የፀጥታ አስከባሪዎች እስካሉበት ቦታ ድረስ በቸርኬ ተጉዞ መድረሱን ቢቢሲ ከፋብሪካው ሠራተኛ እና ከነዋሪዎች ለማውቅ ችሏል። መንግሥት ሸኔ የሚለውና እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው ቡድን በስፋት ከሚንቀሳቀስባቸው አካባቢዎች መካከል አንዱ በርካታ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች የሚገኙበት ምዕራብ ሸዋ አድአ በርጋ ወረዳ እና ዙሪያው ነው። በዚህ አካባቢ ታጣቂ ቡድኑ የፋብሪካ ሠራተኞች እና ነዋሪዎችን በማገት የማስለቀቂያ ገንዘብ መጠየቅ የተለመደ ይሁን እንጂ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ተኩስ መክፈት የተለመደ አይደለም። ይሁን እንጂ በዚህ አካባቢ ሰላማዊ ሰዎች ከመንግሥት ወይም ከታጣቂዎች ጋር ተባብራችኋላ በሚል ምክንያት በታጣቂዎች እና በመንግሥት ኃይሎች ጥቃት እንደሚፈጸምባቸው ነዋሪዎች ለቢቢሲ ገልጸዋል። ከዚህ ቀደም በዚሁ አደአ በርጋ ወረዳ የኦሮሚያ ፖሊስ አባላት በታጣቂዎች ከተገደሉ በኋላ አርብ ሚያዚያ 21/2014 ዓ.ም. የፖሊስ አባላቱ በወሰዱት እርምጃ በርካታ ንጹሃን ሰዎችን መግደላቸውን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። ነዋሪዎች በዚህ ጥቃት የተገደሉት ሰዎች ቁጥርን ከ21 እስከ 40 አድርሰውት ነበር። ከዚህ በተጨማሪ ለመንግሥት የፀጥታ ኃይል አባላት ወደውም ሆነ ተገደው የትራንስፖርት አገልግሎት የሰጡ ሰላማዊ ሰዎች ጥቃት ተፈጽሞባቸው ያውቃል። ከምዕራብ ሸዋ ባሻገር በሌሎች የወለጋ ዞኖች ባለፉት ወራት ውስጥ ተፈጽመው በመቶዎች ለሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰዎች ሞት ምክንያት የሆኑ ጥቃቶችን ፈጽሟል ተብሎ ታጣቂው ቡድን ይከሰሳል። ቡድኑ ግን እነዚህ ጥቃቶች አልፈጸምኩል በማለት ሲያስተባብል ቆይቷል። ዛሬ ስለተፈጸመው ጥቃት ግን አስካሁን በቡድኑ በኩል የተባለ ነገር የለም።
ታጣቂዎች በሙገር ሲሚንቶ የሠራተኞች አውቶቡስ ላይ ተኩስ ከፍተው ሰዎች ተገደሉ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ውስጥ ታጣቂዎች በሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ የሠራተኞች ማመላለሻ አውቶቡስ ላይ ተኩስ ከፍተው በፈጸሙጥ ጥቃት ቢያንስ ሁለት ሰዎችን ሲገደሉ በርካቶች ቆሰሉ። ቢቢሲ ከሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ሠራተኞች እና ከአካባቢው ነዋሪዎች እንዳረጋገጠው ጥቃቱ የተፈጸመው ዛሬ ሰኞ መስከረም 23/2015 ዓ.ም. ንጋት 12 ሰዓት አካባቢ ነው። ነዋሪዎችና ሠራተኞች እንዳሉት ጥቃቱን የፈጸመው መንግሥት በሽብርተኝነት የፈረጀውና በአካባቢው እንደሚንቀሳቀስ የሚነገረው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ወይም ሸኔ ነው። በሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ሠራተኞች ላይ ጥቃት የተፈጸመው የሠራተኞች ማመላለሻ አውቶቡስ የሲሚንቶ ግብዓት ወደሚወጣበት አካባቢ እየተጓዘ ሳለ በታጣቂዎች በተከፈተባቸው ተኩስ ነው። በዚህ ጥቃት ቢያንስ ሁለት ሰዎች የተገደሉ ሲሆን ከ12 ያላነሱ ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸው ተገልጿል። በአውቶብሱ ምን ያክል ሰዎች ተሳፍረው እንደነበረ ግን ግልጽ አይደለም። ቢቢሲ ጥቃቱን በማስመልከት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የኦሮሚያ ደኅንነት ቢሮ ኃላፊ ከፍያለው ተፈራን ቢጠይቅም መረጃ እንደሌላቸው ሲገልጹ፤ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ እና የኦሮሚያ ክልል ፀጥታ እና አስተዳደር ምክትል ቢሮ ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ መልሰን እንድንደውል ነግረውናል። በተጨማሪም ስለደረሰው ጉዳት ለመጠየቅ ተሽከርካሪው ላይ ጥቃት የተፈጸመበትን የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካን አስተያየት ለማካተት ያደረገው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል። ቢቢሲ ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ምንጮች እንደተረዳው ከሆነ ሠራተኞቹ በአውቶቡሱ እየተጓዙ ሳለ አድፍጠው ይጠብቁ የነበሩት ታጣቂዎች የተሸካርካሪውን ጎማ ጨምሮ የተለያየ የመኪናውን አካል በጥይት መትተዋል። ተሳፋሪዎች እና ተሸከርካሪው በጥይት ይደብደቡ እንጂ የአውቶብሱ አሸከርካሪ መኪናውን ሳያቆም የፊት ጎማው በጥይት የተመታ መኪናውን እያሸከረከረ የሲሚንቶ ግብዓት ከሚወጣበት ቦታ ላይ ደርሷል። ከተገደሉት ሰዎች በተጨማሪ በርካታ ሰዎች ከወገባቸው በታች ያለ የሰውነት ክፍላቸው በጥይት ተመትቶ መቁሰላቸውን እማኞች ለቢቢሲ ገልጸዋል። ቢቢሲ ከሲሚንቶ ፋብሪካው ሠራተኞች እንደተረዳው በአካባቢው ያሉ ሲሚንቶ ፋብሪካዎች ለምርታቸው ግብዓት የሚሆናቸውን ላይምስቶን የተሰኘ የድንጋይ አይነት ከፋብሪካው በጥቂት ኪሎ ሜትር ርቆ ከሚገኝ አካባቢ ይወስዳሉ። ለሲሚንቶ ምርት ግብዓት የሚወጣበት አካባቢ በመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች ጥበቃ እንደሚደረግ የተገለጸ ሲሆን፤ ከታጣቂዎች ተኩስ ያመለጠው የሠራተኞች ማመላለሻ አውቶብስ ከጥቃቱ በኋላ የፀጥታ አስከባሪዎች እስካሉበት ቦታ ድረስ በቸርኬ ተጉዞ መድረሱን ቢቢሲ ከፋብሪካው ሠራተኛ እና ከነዋሪዎች ለማውቅ ችሏል። መንግሥት ሸኔ የሚለውና እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው ቡድን በስፋት ከሚንቀሳቀስባቸው አካባቢዎች መካከል አንዱ በርካታ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች የሚገኙበት ምዕራብ ሸዋ አድአ በርጋ ወረዳ እና ዙሪያው ነው። በዚህ አካባቢ ታጣቂ ቡድኑ የፋብሪካ ሠራተኞች እና ነዋሪዎችን በማገት የማስለቀቂያ ገንዘብ መጠየቅ የተለመደ ይሁን እንጂ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ተኩስ መክፈት የተለመደ አይደለም። ይሁን እንጂ በዚህ አካባቢ ሰላማዊ ሰዎች ከመንግሥት ወይም ከታጣቂዎች ጋር ተባብራችኋላ በሚል ምክንያት በታጣቂዎች እና በመንግሥት ኃይሎች ጥቃት እንደሚፈጸምባቸው ነዋሪዎች ለቢቢሲ ገልጸዋል። ከዚህ ቀደም በዚሁ አደአ በርጋ ወረዳ የኦሮሚያ ፖሊስ አባላት በታጣቂዎች ከተገደሉ በኋላ አርብ ሚያዚያ 21/2014 ዓ.ም. የፖሊስ አባላቱ በወሰዱት እርምጃ በርካታ ንጹሃን ሰዎችን መግደላቸውን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። ነዋሪዎች በዚህ ጥቃት የተገደሉት ሰዎች ቁጥርን ከ21 እስከ 40 አድርሰውት ነበር። ከዚህ በተጨማሪ ለመንግሥት የፀጥታ ኃይል አባላት ወደውም ሆነ ተገደው የትራንስፖርት አገልግሎት የሰጡ ሰላማዊ ሰዎች ጥቃት ተፈጽሞባቸው ያውቃል። ከምዕራብ ሸዋ ባሻገር በሌሎች የወለጋ ዞኖች ባለፉት ወራት ውስጥ ተፈጽመው በመቶዎች ለሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰዎች ሞት ምክንያት የሆኑ ጥቃቶችን ፈጽሟል ተብሎ ታጣቂው ቡድን ይከሰሳል። ቡድኑ ግን እነዚህ ጥቃቶች አልፈጸምኩል በማለት ሲያስተባብል ቆይቷል። ዛሬ ስለተፈጸመው ጥቃት ግን አስካሁን በቡድኑ በኩል የተባለ ነገር የለም።
https://www.bbc.com/amharic/articles/ck5855y03gro
0business
ግብጽ ስዊዝ ቦይን ዘገቶ የነበረውን መርከብ ለመልቀቅ ተስማማች
ከመርከቡ ባለቤትና መድህን ሰጪ ጋር ከስምምነት ከደረሰች በኋላ ግብጽ ባለፈው መጋቢት ወር ላይ የስዊዝ ቦይ እንቅስቃሴ ለመስተጓጎሉ ምክንያት የነበረችውን መርከብ ለመልቀቅ ፍቃዷ ሆኗል። ግብጽ ለድርድር በመያዣነት ያቆያቻትና 'ኤቨር ጊቭን' የሚል ስያሜ ያላት መርከቧ ነገ [ረብዕ] ወራትን ከቆየችበት ቦዩ ለቃ እንደምትወጣ ከሁለቱም ወገን ተሰምቷል። በሁለቱ ወገኖች መካከል የተደረሰው ስምምነት ጭብጥ ባይታወቅም ግብጽ ግን 550 ሚሊዮን ዶላር ካሳ መጠየቋ ታውቋል። 400 ሜትር የምትረዝመው 'ኤቨር ጊቭን' በከፍተኛ ንፍስ ከተመታች በኋላ ነበር አቅጣጫዋን ስታ በመቀርቀር ቦዩን የዘጋችው። እናም መርከቧን ከተቀረቀረችበት በማላቀቅ ቦዩን ወደ መደበኛ ስራው ለመመለስ ስድስት ቀናትን የፈጀ ሲሆን በሂደቱ አንድ ሰው ሞቷል። 193 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው የሜዲትራንያንን ባህር ከቀይ ባህር ጋር የሚያገናኘው እና በእስያ እና በአውሮፓ መካከል አጭሩን የባህር ላይ መንገድ የሆነው ሲዊዝ ቦይ በተዘጋበት በመቶዎች የሚቆጠሩ መርከቦች ለመቆም በመገደዳቸው የዓለም ንግድ አስተጎጉሎት ነበር። የ'ኤቨር ጊቭን' ሶስተኛ ወገን መድህን ሰጪ የሆነውና 'ዩኬ ክለብ' የተባለው ኢንሹራንስ ባለቤት ሾይ ኪሰን ከሱዊዝ ቦይ ባለስልጣን ጋር በመነጋገር ጉዳዩን እልባት ለመስጠት "መደበኛ መፍትሄ" ላይ መደረሱን አስታውቋል ፡፡ መርከቡን ለመልቀቅ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነም አንስተዋል። የቦዩ አስተዳደር ስምምነቱ ረብዕ ይደረጋል ያለ ሲሆን በተመሳሳይ ቀን መርከቡ ሊወጣ እንደሚችል አስታውቋል። የትኛውም ወገን በ'ኤቨር ጊቭን' የተፈጠረውን መጉላላላትና ኪሳራ ለመተካት የሚቀርበውን የካሳ ክፍያ መጠን ይፋ ባያደርጉም የቦዩ አስተዳደር ሊቀመንበር ኦሳማ ራቢ የስምምነቱ አካል የሆነ ተጎታች ጀልባ ግብጽ እንደምታገኝ ተናግረዋል። የቦዩ አስተዳደር ቀደም ብሎ ከ900 ሚሊዮን ዶላር ባላይ ካሳ ጠይቆ እንደነበር ተሰምቷል።
ግብጽ ስዊዝ ቦይን ዘገቶ የነበረውን መርከብ ለመልቀቅ ተስማማች ከመርከቡ ባለቤትና መድህን ሰጪ ጋር ከስምምነት ከደረሰች በኋላ ግብጽ ባለፈው መጋቢት ወር ላይ የስዊዝ ቦይ እንቅስቃሴ ለመስተጓጎሉ ምክንያት የነበረችውን መርከብ ለመልቀቅ ፍቃዷ ሆኗል። ግብጽ ለድርድር በመያዣነት ያቆያቻትና 'ኤቨር ጊቭን' የሚል ስያሜ ያላት መርከቧ ነገ [ረብዕ] ወራትን ከቆየችበት ቦዩ ለቃ እንደምትወጣ ከሁለቱም ወገን ተሰምቷል። በሁለቱ ወገኖች መካከል የተደረሰው ስምምነት ጭብጥ ባይታወቅም ግብጽ ግን 550 ሚሊዮን ዶላር ካሳ መጠየቋ ታውቋል። 400 ሜትር የምትረዝመው 'ኤቨር ጊቭን' በከፍተኛ ንፍስ ከተመታች በኋላ ነበር አቅጣጫዋን ስታ በመቀርቀር ቦዩን የዘጋችው። እናም መርከቧን ከተቀረቀረችበት በማላቀቅ ቦዩን ወደ መደበኛ ስራው ለመመለስ ስድስት ቀናትን የፈጀ ሲሆን በሂደቱ አንድ ሰው ሞቷል። 193 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው የሜዲትራንያንን ባህር ከቀይ ባህር ጋር የሚያገናኘው እና በእስያ እና በአውሮፓ መካከል አጭሩን የባህር ላይ መንገድ የሆነው ሲዊዝ ቦይ በተዘጋበት በመቶዎች የሚቆጠሩ መርከቦች ለመቆም በመገደዳቸው የዓለም ንግድ አስተጎጉሎት ነበር። የ'ኤቨር ጊቭን' ሶስተኛ ወገን መድህን ሰጪ የሆነውና 'ዩኬ ክለብ' የተባለው ኢንሹራንስ ባለቤት ሾይ ኪሰን ከሱዊዝ ቦይ ባለስልጣን ጋር በመነጋገር ጉዳዩን እልባት ለመስጠት "መደበኛ መፍትሄ" ላይ መደረሱን አስታውቋል ፡፡ መርከቡን ለመልቀቅ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነም አንስተዋል። የቦዩ አስተዳደር ስምምነቱ ረብዕ ይደረጋል ያለ ሲሆን በተመሳሳይ ቀን መርከቡ ሊወጣ እንደሚችል አስታውቋል። የትኛውም ወገን በ'ኤቨር ጊቭን' የተፈጠረውን መጉላላላትና ኪሳራ ለመተካት የሚቀርበውን የካሳ ክፍያ መጠን ይፋ ባያደርጉም የቦዩ አስተዳደር ሊቀመንበር ኦሳማ ራቢ የስምምነቱ አካል የሆነ ተጎታች ጀልባ ግብጽ እንደምታገኝ ተናግረዋል። የቦዩ አስተዳደር ቀደም ብሎ ከ900 ሚሊዮን ዶላር ባላይ ካሳ ጠይቆ እንደነበር ተሰምቷል።
https://www.bbc.com/amharic/news-57731706
3politics
የንግሥቲቷን ሞት ተከትሎ አንቲጓ ሪፓብሊክ ለመሆን ሕዝበ ውሳኔ ልታደርግ ነው
የእንግሊዝ ቅኝ ግዛት የነበረችው አንቲጓ እና ባርቡዳ የንግሥት ዳግማዊት ኤልዛቤጥ ሞትን ተከትሎ ሪፓብሊክ ለመሆን ሕዝበ ውሳኔ ልታካሂድ ነው። የአገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ጋስቶን ብራዎን ሕዝበ ውሳኔው ከሦስት ዓመታት በኋላ እንደሚከናወን ገልጸው፤ ሕዝበ ውሳኔ የማካሄድ እቅዱ “የጠላትን ድርጊት አይደለም” ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ አገራቸው ሪፓብሊክ ብትሆን “ነጻ እና ሉዓላዊ” መሆናችንን የምናገረጋግጥበት የመጨረሻው እርምጃ ይሆናል ብለዋል። ንግሥት ዳግማዊት ኤልዛቤጥ እስከ ዕለተ ሞታቸው ድረስ የአንቲጓ እና ባርባዱ ርዕሰ ብሔር ነበሩ። የአገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር አንቲጓ ሕዝበ ውሳኔ እንደምታደርግ የተናገሩት ንጉስ ቻርልስ ሳልሳዊ  የካሪቢያኗ አገር አንቲጓ እና ባርባዱ ርዕሰ ብሔር መሆናቸውን ካረጋገጡ በኋላ ነው። ጋስቶን ብራዎን በቀጣይ ዓመት በሚካሄደው ምርጫ ካሸነፉ ሕዝበ ውሳኔውን እንደሚያስፈጽሙ ገልጸዋል። ንግስት ኤልዛቤጥ ከካረቢያኗ አገር በተጨማሪ አውስትራሊያ፣ ካናዳ እና ኒው ዚላንድን ጨምሮ የበርካታ የቀድሞ የእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ርዕሰ ብሔር ናቸው። የንግስቲቱ ሞት በአውስትራሊያ ሪፓብሊክ የመሆን እንቅስቃሴን ዳግም አጋግሎታል። በአሁኑ ወቅት ንጉስ ቻርልስ ሳልሳዊ ከዩናይትድ ኪንግደም በተጨማሪ የ14 አገራት ርዕሰ ብሔር ናቸው። እነዚህም አንቲጓ እና ባርባዱ፣ አውስትራሊያ፣ ባህማስ፣ ቤሊዝ፣ ካናዳ፣ ግሬናዳ፣ ጀማይካ፣ ኒው ዚላንድ፣ ፓፐዋ ኒው ጊኒ፣ ሴንት ኪትስ እና ኔቪስ፣ ሴንት ሉሺያ እና ዘ ግሬናዲኢስ፣ ሰለሞን ደሴቶች እና ቱቫሉ ናቸው። ከአንድ ዓመት በፊት ባርባዶስ ንግስት ኤልዛቤጥን ከርዕሰ ብሔርነት አንስታ ተመራጭ ፕሬዝዳንቷን ርዕሰ ብሔር በማድረግ ሪፓብሊክ መሆኗን አውጃ ነበር። ሌላኛዋ የካረቢያን አገር ጀማይካ ገዢ የሠራተኞች ፓርቲ ሕዝበ ውሳኔ አካሂዶ ሪፓብሊክ መሆኑን ለማወጅ ማቀዱን አስታውቋል።
የንግሥቲቷን ሞት ተከትሎ አንቲጓ ሪፓብሊክ ለመሆን ሕዝበ ውሳኔ ልታደርግ ነው የእንግሊዝ ቅኝ ግዛት የነበረችው አንቲጓ እና ባርቡዳ የንግሥት ዳግማዊት ኤልዛቤጥ ሞትን ተከትሎ ሪፓብሊክ ለመሆን ሕዝበ ውሳኔ ልታካሂድ ነው። የአገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ጋስቶን ብራዎን ሕዝበ ውሳኔው ከሦስት ዓመታት በኋላ እንደሚከናወን ገልጸው፤ ሕዝበ ውሳኔ የማካሄድ እቅዱ “የጠላትን ድርጊት አይደለም” ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ አገራቸው ሪፓብሊክ ብትሆን “ነጻ እና ሉዓላዊ” መሆናችንን የምናገረጋግጥበት የመጨረሻው እርምጃ ይሆናል ብለዋል። ንግሥት ዳግማዊት ኤልዛቤጥ እስከ ዕለተ ሞታቸው ድረስ የአንቲጓ እና ባርባዱ ርዕሰ ብሔር ነበሩ። የአገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር አንቲጓ ሕዝበ ውሳኔ እንደምታደርግ የተናገሩት ንጉስ ቻርልስ ሳልሳዊ  የካሪቢያኗ አገር አንቲጓ እና ባርባዱ ርዕሰ ብሔር መሆናቸውን ካረጋገጡ በኋላ ነው። ጋስቶን ብራዎን በቀጣይ ዓመት በሚካሄደው ምርጫ ካሸነፉ ሕዝበ ውሳኔውን እንደሚያስፈጽሙ ገልጸዋል። ንግስት ኤልዛቤጥ ከካረቢያኗ አገር በተጨማሪ አውስትራሊያ፣ ካናዳ እና ኒው ዚላንድን ጨምሮ የበርካታ የቀድሞ የእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ርዕሰ ብሔር ናቸው። የንግስቲቱ ሞት በአውስትራሊያ ሪፓብሊክ የመሆን እንቅስቃሴን ዳግም አጋግሎታል። በአሁኑ ወቅት ንጉስ ቻርልስ ሳልሳዊ ከዩናይትድ ኪንግደም በተጨማሪ የ14 አገራት ርዕሰ ብሔር ናቸው። እነዚህም አንቲጓ እና ባርባዱ፣ አውስትራሊያ፣ ባህማስ፣ ቤሊዝ፣ ካናዳ፣ ግሬናዳ፣ ጀማይካ፣ ኒው ዚላንድ፣ ፓፐዋ ኒው ጊኒ፣ ሴንት ኪትስ እና ኔቪስ፣ ሴንት ሉሺያ እና ዘ ግሬናዲኢስ፣ ሰለሞን ደሴቶች እና ቱቫሉ ናቸው። ከአንድ ዓመት በፊት ባርባዶስ ንግስት ኤልዛቤጥን ከርዕሰ ብሔርነት አንስታ ተመራጭ ፕሬዝዳንቷን ርዕሰ ብሔር በማድረግ ሪፓብሊክ መሆኗን አውጃ ነበር። ሌላኛዋ የካረቢያን አገር ጀማይካ ገዢ የሠራተኞች ፓርቲ ሕዝበ ውሳኔ አካሂዶ ሪፓብሊክ መሆኑን ለማወጅ ማቀዱን አስታውቋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cpr2v5rgq7ro
0business
ልዑል ሃሪና ሜጋን ከዚህ በኋላ የገቢ ምንጫቸው ምን ይሆናል?
ልዑል ሃሪ ንጉሣዊው ቤተሰቡ ለሱና ለባለቤቱ ይሰጡትን የነበረውን የገንዘብ ድጎማ ማቋረጣቸውን ይፋ አድርጓል። ይህ የሆነው ልዑሉና ባለቤቱ ሜጋን ከነባር የንጉሣዊያን ቤተሰብ አባልነት 'ራሳቸውን አግልለው' ወደ ካሊፎርኒያ በማቅናታቸው ነው። እና አሁን የገቢ ምንጫቸው ምን ይሆናል? ልዑል ሃሪና ሜጋን ከንጉሣዊው ቤሰተብ ገንዘብ የሚያገኙበት መንገድ ይኖር ይሆን? የሰሴክስ ዱክና ደችስ በመባል የሚታወቁት ሜጋንና ሃሪ ባለፈው ዓመት ጥር ነበር የንጉሣዊ ቤተሰብ አባልነት በቃን ብለው የወሰኑት። በወቅቱ ራሳቸውን በገንዘብ ለመቻል ቃል ገብተውም ነበር። ነገር ግን በጊዜው ጥንዶቹ በገቡት ስምምነት መሠረት ከሃሪ አባት የገንዘብ ድጎማ ይደረግላቸው እንደነበር ይነገራል። የሃሪ አባት የሆኑት ልዑል ቻርልስ የሒሳብ መዝገብ እንደሚያሳየው ሃሪና ሜጋንን ጨምሮ የካምብሪጅ ዱክና ደችስ ተብለው ለሚታወቁት ጥንዶች የሚሆን 5.6 ሚሊዮን ዩሮ ወጪ ተደርጓል። ይህ ወጪ እስከ መጋቢት 2020 ያለውን ጊዜ የሚያሳይ ነው። ነገር ግን ልዑል ሃሪ ከዚህ ወቅት ጀምሮ የገንዘብ ድጎማ ተቋርጦብኛል ሲል ለጉምቱዋ አሜሪካዊት ቃለ-ምልልስ አድርራጊ ኦፕራ ዊንፍሬይ ነግሯታል። ቢሆንም ልዑሉ እያወራ ያለው ከአባቱ ኪስ ስለሚሰጠው ገንዘብ ይሁን አሊያም ከግብር ከፋዩ ማሕበረሰብ ወይም ከሁለቱ ግልፅ አይደለም። ከመጋቢት ጀምሮ ያለው የልዑል ቻርልስ ሒሳብ ዝርዝር መረጃ ይፋ አልደተረገም። ቤተ-መንግሥቱም በዚህ ጉዳይ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል። ሃሪና ሜጋን ሃብታም ናቸው? የሰሴክስ ዱክና ደችስ በመባል የሚታወቁት ሃሪን ሜጋን የማይናቅ ሃብት አላቸው። ልዑል ዊሊያምና ልዑል ሃሪ በድምሩ 13 ሚሊዮን ዩሮ ከእናታቸው ልዕልት ዳያና ወርሰዋል። ጓዛቸውን ጠቅልለው ወደ አሜሪካ እንደመጡ ለኦፕራ የነገራት ሃሪ "እናቴ ትታልኝ የሄደችው ነገር ባይኖር ኖሮ ይሄን ማድረግ አንችልም ነበር" ብሏል። የቢቢሲው የንጉሣዊያን ቤተሰብ ተንታኝ ኒክ ዊቼል ደግሞ ልዑል ሃሪ ከአያቱ [ንግሥት ኤሊዛቤት] ሚሊዮን ፓውንዶች ወርሷል ይላል። በሌላ በኩል ሜጋን ተዋናይት በነበረችበት ወቅት ሱትስ በተሰኘው ተከታታይ ድራማ ላይ ስትተውን በአንድ ክፍል 50 ሺህ ዶላር ይከፈላት እንደነበር ይነገራል። ሜጋን ከዚህ በተጨማሪ 'የላይፍስታይል' መጦመሪያ [ብሎግ] እና ለአንድ የካናዳ ልብስ አምራች የሚሸጥ የፋሽን ዲዛይን አላት። ሌላ የገቢ ምንጫቸው ምንድነው? አሁን ጥንዶቹ ከንጉሣዊው ቤተሰብ ጋር ያላቸው ውል ስለተቀደደ ያሻቸውን ነገር መሥራት ይችላሉ። ጥንዶቹ ከኦፕራ ጋር ያደረጉት ቆይታ በክፍያ አልነበረም። ነገር ግን ኔትፍሊክስና ስፖቲፋይ ከተሰኙት ድርጅቶች ጋር ውል ገብተዋል። እነዚህ ስምምነቶች በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር እንደሚያስገቡላቸው ይታመናል። ሜጋንና ሃሪ አርችዌል የተሰኘ ተቋም አላቸው። ይህ ድርጅት ከአንድ ሌላ የእርዳታ ድርጅት ጋር ይሠራል። ጥንዶቹ ዩናይትድ ኪንግደም እያሉ ጥበቃ ይመድብላቸው ነበር። የጥበቃው ሒሳብ ምን ያክል እንደሆነ አይታወቅም። የካናዳ መንግሥት ለጥንዶቹ የሚያደርገውን ጥበቃ እንደሚያቆም ሲያሳውቅ ነው ሜጋንና ሃሪ ወደ አሜሪካ ያቀኑት። ይሄኔ አሜሪካዊው ቢሊየነር ታይለር ፔሪ እስኪደላደሉ ድረስ መኖሪያ ቤትና ጥበቃ እንዳበረከተላቸው ጥንዶቹ ተናግረዋል። "ለኔ ዋናው ነገር የቤተሰቤን ደህንነት ለመጠበቅ በቂ የሆነ ገንዘብ ማግኘት ነበር" ሲል ሃሪ ለኦፕራ ነግሯታል። ጥንዶቹ የንጉሣዊው ቤተሰብ ኃላፊነት ይብቃን ከማለታቸው በፊት 95 በመቶ የገቢያቸው ምንጭ የሃሪ አባት ልዑል ቻርልስ ነበሩ። ለምሳሌ በፈረንጆቹ 2018-19 ብቻ ለሜጋንና ሃሪ እንዲሁም ለካምብሪጅ ዱክና ደችስ ከ25 ሚሊዮን በላይ ዩሮ ፈሰስ ተደርጓል። ከግብር ከፋዩ የሚገኘው ገቢ ደግሞ 5 በመቶ የሚሆነው ወጪ ይሸንፋል። ጥንዶቹ ከቤተሰቡ በወጡ ጊዜ በታክስ ከፋዩ ገንዘብ አሳደሱት የተባለውን ቤት ወጪ 2.4 ሚሊዮን ዩሮ መመለሳቸው አይዘነጋም።
ልዑል ሃሪና ሜጋን ከዚህ በኋላ የገቢ ምንጫቸው ምን ይሆናል? ልዑል ሃሪ ንጉሣዊው ቤተሰቡ ለሱና ለባለቤቱ ይሰጡትን የነበረውን የገንዘብ ድጎማ ማቋረጣቸውን ይፋ አድርጓል። ይህ የሆነው ልዑሉና ባለቤቱ ሜጋን ከነባር የንጉሣዊያን ቤተሰብ አባልነት 'ራሳቸውን አግልለው' ወደ ካሊፎርኒያ በማቅናታቸው ነው። እና አሁን የገቢ ምንጫቸው ምን ይሆናል? ልዑል ሃሪና ሜጋን ከንጉሣዊው ቤሰተብ ገንዘብ የሚያገኙበት መንገድ ይኖር ይሆን? የሰሴክስ ዱክና ደችስ በመባል የሚታወቁት ሜጋንና ሃሪ ባለፈው ዓመት ጥር ነበር የንጉሣዊ ቤተሰብ አባልነት በቃን ብለው የወሰኑት። በወቅቱ ራሳቸውን በገንዘብ ለመቻል ቃል ገብተውም ነበር። ነገር ግን በጊዜው ጥንዶቹ በገቡት ስምምነት መሠረት ከሃሪ አባት የገንዘብ ድጎማ ይደረግላቸው እንደነበር ይነገራል። የሃሪ አባት የሆኑት ልዑል ቻርልስ የሒሳብ መዝገብ እንደሚያሳየው ሃሪና ሜጋንን ጨምሮ የካምብሪጅ ዱክና ደችስ ተብለው ለሚታወቁት ጥንዶች የሚሆን 5.6 ሚሊዮን ዩሮ ወጪ ተደርጓል። ይህ ወጪ እስከ መጋቢት 2020 ያለውን ጊዜ የሚያሳይ ነው። ነገር ግን ልዑል ሃሪ ከዚህ ወቅት ጀምሮ የገንዘብ ድጎማ ተቋርጦብኛል ሲል ለጉምቱዋ አሜሪካዊት ቃለ-ምልልስ አድርራጊ ኦፕራ ዊንፍሬይ ነግሯታል። ቢሆንም ልዑሉ እያወራ ያለው ከአባቱ ኪስ ስለሚሰጠው ገንዘብ ይሁን አሊያም ከግብር ከፋዩ ማሕበረሰብ ወይም ከሁለቱ ግልፅ አይደለም። ከመጋቢት ጀምሮ ያለው የልዑል ቻርልስ ሒሳብ ዝርዝር መረጃ ይፋ አልደተረገም። ቤተ-መንግሥቱም በዚህ ጉዳይ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል። ሃሪና ሜጋን ሃብታም ናቸው? የሰሴክስ ዱክና ደችስ በመባል የሚታወቁት ሃሪን ሜጋን የማይናቅ ሃብት አላቸው። ልዑል ዊሊያምና ልዑል ሃሪ በድምሩ 13 ሚሊዮን ዩሮ ከእናታቸው ልዕልት ዳያና ወርሰዋል። ጓዛቸውን ጠቅልለው ወደ አሜሪካ እንደመጡ ለኦፕራ የነገራት ሃሪ "እናቴ ትታልኝ የሄደችው ነገር ባይኖር ኖሮ ይሄን ማድረግ አንችልም ነበር" ብሏል። የቢቢሲው የንጉሣዊያን ቤተሰብ ተንታኝ ኒክ ዊቼል ደግሞ ልዑል ሃሪ ከአያቱ [ንግሥት ኤሊዛቤት] ሚሊዮን ፓውንዶች ወርሷል ይላል። በሌላ በኩል ሜጋን ተዋናይት በነበረችበት ወቅት ሱትስ በተሰኘው ተከታታይ ድራማ ላይ ስትተውን በአንድ ክፍል 50 ሺህ ዶላር ይከፈላት እንደነበር ይነገራል። ሜጋን ከዚህ በተጨማሪ 'የላይፍስታይል' መጦመሪያ [ብሎግ] እና ለአንድ የካናዳ ልብስ አምራች የሚሸጥ የፋሽን ዲዛይን አላት። ሌላ የገቢ ምንጫቸው ምንድነው? አሁን ጥንዶቹ ከንጉሣዊው ቤተሰብ ጋር ያላቸው ውል ስለተቀደደ ያሻቸውን ነገር መሥራት ይችላሉ። ጥንዶቹ ከኦፕራ ጋር ያደረጉት ቆይታ በክፍያ አልነበረም። ነገር ግን ኔትፍሊክስና ስፖቲፋይ ከተሰኙት ድርጅቶች ጋር ውል ገብተዋል። እነዚህ ስምምነቶች በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር እንደሚያስገቡላቸው ይታመናል። ሜጋንና ሃሪ አርችዌል የተሰኘ ተቋም አላቸው። ይህ ድርጅት ከአንድ ሌላ የእርዳታ ድርጅት ጋር ይሠራል። ጥንዶቹ ዩናይትድ ኪንግደም እያሉ ጥበቃ ይመድብላቸው ነበር። የጥበቃው ሒሳብ ምን ያክል እንደሆነ አይታወቅም። የካናዳ መንግሥት ለጥንዶቹ የሚያደርገውን ጥበቃ እንደሚያቆም ሲያሳውቅ ነው ሜጋንና ሃሪ ወደ አሜሪካ ያቀኑት። ይሄኔ አሜሪካዊው ቢሊየነር ታይለር ፔሪ እስኪደላደሉ ድረስ መኖሪያ ቤትና ጥበቃ እንዳበረከተላቸው ጥንዶቹ ተናግረዋል። "ለኔ ዋናው ነገር የቤተሰቤን ደህንነት ለመጠበቅ በቂ የሆነ ገንዘብ ማግኘት ነበር" ሲል ሃሪ ለኦፕራ ነግሯታል። ጥንዶቹ የንጉሣዊው ቤተሰብ ኃላፊነት ይብቃን ከማለታቸው በፊት 95 በመቶ የገቢያቸው ምንጭ የሃሪ አባት ልዑል ቻርልስ ነበሩ። ለምሳሌ በፈረንጆቹ 2018-19 ብቻ ለሜጋንና ሃሪ እንዲሁም ለካምብሪጅ ዱክና ደችስ ከ25 ሚሊዮን በላይ ዩሮ ፈሰስ ተደርጓል። ከግብር ከፋዩ የሚገኘው ገቢ ደግሞ 5 በመቶ የሚሆነው ወጪ ይሸንፋል። ጥንዶቹ ከቤተሰቡ በወጡ ጊዜ በታክስ ከፋዩ ገንዘብ አሳደሱት የተባለውን ቤት ወጪ 2.4 ሚሊዮን ዩሮ መመለሳቸው አይዘነጋም።
https://www.bbc.com/amharic/news-56356832
0business
''የአሰብና ምፅዋ ወደቦችን አገልግሎት ለማሻሻል እየሰራን ነው'' ፕሬዚዳንት ኢሳያስ
የምፅዋና የአሰብ ወደቦች የሚሰጡትን አገልግሎት የማሻሻል ስራዎች እየሰሩ እንደሆነ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በትናንትናው ዕለት ተናግረዋል። ፕሬዚዳንቱ ይህንን የተናገሩት ከኃገሪትዋ ውስጣዊ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ በትናንትናው ዕለት ከመንግስት መገናኛ ብዙኃን ጋር ባደረጉት ቆይታ ነው። የነዚህን ወደቦችን አገልግሎት ውጤታማነት ለመጨመር የማደስ፣ የማስፋትና የማሳደግ ስራዎች ለማከናወን እቅድ መያዙን ፕሬዚዳንቱ አብራርተዋል። • "የኤርትራ መሬት ያልተመለሰው በህወሓት እምቢታ ነው" ፕ/ት ኢሳያስ • ስለ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ምን ያህል ያውቃሉ? "ወደቦቹን ስናሻሽል ኢትዮጵያን ብቻ እያሰብን አይደለም፤ ዋነኛ ትኩረታችን ቀይባሕር በቀጠናው ላይ ያላትን ቦታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ሰፋ ያለ አገልግሎት እንዲሰጡ ያለመ እቅድ ነው" ብለዋል ፕሬዚዳንቱ "ከተጋገዝን የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ስለምንችል በአካባቢው ኢኮኖሚያዊ ውህደት መፍጠር" አንዱ የመንግስታቸው ዓላማ መሆኑን ገልጸዋል። ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ከወደቦች በተጨማሪ ከመንገድ ግንባታ ጋር የተያዙ እቅዶችም ላይ መረጃ የሰጡ ሲሆን፤ በዚህም ኢትዮጵያንና ኤርትራን የሚያገናኙ መንገዶችም የሚያስፈልጋቸውን ጥገናም ሆነ ግንባታ ለመስራት መንግሥታቸው አቅዷል ብለዋል። በዚህም መሰረት ከአሰብ በደባየሲማ ኢትዮጵያን የሚያገናኘውን መንገድ የማስፋት፤ ከምጽዋ በደቀመኃሪ አድርጎ ዛላምበሳ፤ ከአስመራ በመንደፈራ፣ ራማን የሚያገናኙት የአስፋልት መንገዶች ደግሞ የማሻሻል ስራዎች በዚህ አመት እንደሚጀመሩና፤ የተጀመሩትም እንደሚጠናቀቁ ገልፀዋል። ፕሬዚዳንቱ በሃገሪቱ ውስጥ ያሉ የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን፣ ኢንቨስትመንት፣ የኑሮ ውድነት እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮች ላይ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል። ከዚህም መካከል ለሁለት አስርት አመታት ሲንከባለል የመጣው የመንግሥት ሰራተኞች ደመወዝ ማስተካከያ ጥያቄ ላይ ምላሽ የሰጡት ፕሬዚዳንቱ ሰራተኞች አስፈላጊውን የኑሮ ወጪ የሚሸፍንላቸው በቂ ደመወዝ እንዳልነበራቸው አምነዋል። መንግሥታቸው ይህንን ችግር ለመፍታት ከሁለት አመታት በፊት የደመወዝ ማስተካከያ ማድረግ መጀመሩን ጠቁመው፤ በደመወዝ ማስተካከያው ሂደት እስከ አሁን ጭማሪው ያልደረሳቸው የመንግስት ሰራተኞች የሁለት ዓመት ድምር እንደሚደርሳቸው ፕሬዚዳንቱ ገልፀዋል። መንግሥት የደመወዝ ማስተካከያ አሰራሩንም ለመተግበር እክሎች እንደገጠሙት የገለፁት ፕሬዚዳንቱ ይህም በሃገሪትዋ "ተገቢ ባልሆኑ ምክንያቶች" የሸቀጦች ዋጋ ንረት በመፈጠሩ ነው ብለዋል። "መንግሥት ይህ ኢ-ምክንያታዊ የሆነ የዋጋ ንረትን በቸልታ አያልፈውም ፤ እርምት ይወስዳል" በማለት አስጠንቅቀዋል ያለውን የዋጋ ንረት ለማስተካከልም ባለፉት ዓመታት መንግሥት የቤት ኪራይ፣ ስጋ እና የታሸገ ውሀ ላይ የዋጋ ተመን ማድረግ እንደጀመረ ምንጮች ይገልጻሉ። የመኖርያ ቤቶች ግንባታ ዋነኛው የሀገሪትዋ ቁልፍ ችግር እንደሆነ ያወሱት ፕሬዚዳንቱ መንግሥት ይህንን ችግር ለመፍታት ብሎ የጀመራቸው የቤቶች ግንባታ ቢጀምርም፤ ያላለቁ ቤቶች ግን በርካታ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። • ወደ አሥመራ ለመጓዝ ማወቅ የሚገባዎ 6 ነጥቦች • ኤርትራ በዶይቼ ቬለ ዘገባ ሳቢያ የጀርመን አምባሳደር ማብራሪያ እንዲሰጡ ጠየቀች በሂደትም መንግሥት ጥናት አካሂዶ አዋጪ ሆኖ ከተገኘ በቤቶች ግንባታ የውጪ ተቋራጮች ጭምር ለማሳተፍ ሀሳብ እንዳለ የገለጹት ፕሬዝደንት ኢሳይያስ አፈወርቂ፤ ያላለቁ እቅዶች ስላሉ በዚህ አመት የሚሰሩ ስራዎችን ለማስቀመጥ ትንሽ ከባድ እንደሆነ በመጠቆም ዝርዝርም ሆነ ቀነ ገደብ ከማስቀመጥ ተቆጥበዋል። ፕሬዚዳንቱ አንዳንድ ሃገሪቷ ያሉባትን ችግሮች በግልፅ ከመናገር ወደኋላ ያላሉ ሲሆን በተለይም ባለፉት 20 ዓመታት "አክስሮናል" ያሉትን የትምህርት ዘርፍ ፖሊሲ ለሀገሪትዋ ኢኮኖሚ ዋነኛው ምሰሶ በመሆኑ ስር ነቀል ለውጥ ሊመጣ ይገባል ብለዋል። ከዚህም በተጨማሪ ከቀይ ባህር በዓመት እስከ 100 ሺ ቶን የአሳ ሀብት ማግኘት እየታቸለ ባለፉት 20 ዓመታት ግን አስር ሺ ቶን ብቻ እንደነበረ ገልጸዋል። ይህንን የአሳ ሀብት ለማሳደግም አስፈላጊውን የመሰረተ ልማት ስራዎች ለማከናወን እቅድ መያዙን አብራርተዋል። ፕሬዚዳንቱ መንግሥታቸው በዚህ አመት ከያዟቸው ሌሎች እቅዶች መካከል በአሰብ፣ ምጽዋ እና አስመራ ከተሞች 60 ሜጋ ዋት ኤሌትሪክ ከታዳሽ ኃይል ለማመንጨት የተለያየ መጠን ያላቸው የውሀ ግድቦች የሚገነቡ ሲሆን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴውን ለማበረታት አስፈላጊ የመሰረተ ልማት ስራዎች እንደሚሰሩም አስረድተዋል።
''የአሰብና ምፅዋ ወደቦችን አገልግሎት ለማሻሻል እየሰራን ነው'' ፕሬዚዳንት ኢሳያስ የምፅዋና የአሰብ ወደቦች የሚሰጡትን አገልግሎት የማሻሻል ስራዎች እየሰሩ እንደሆነ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በትናንትናው ዕለት ተናግረዋል። ፕሬዚዳንቱ ይህንን የተናገሩት ከኃገሪትዋ ውስጣዊ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ በትናንትናው ዕለት ከመንግስት መገናኛ ብዙኃን ጋር ባደረጉት ቆይታ ነው። የነዚህን ወደቦችን አገልግሎት ውጤታማነት ለመጨመር የማደስ፣ የማስፋትና የማሳደግ ስራዎች ለማከናወን እቅድ መያዙን ፕሬዚዳንቱ አብራርተዋል። • "የኤርትራ መሬት ያልተመለሰው በህወሓት እምቢታ ነው" ፕ/ት ኢሳያስ • ስለ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ምን ያህል ያውቃሉ? "ወደቦቹን ስናሻሽል ኢትዮጵያን ብቻ እያሰብን አይደለም፤ ዋነኛ ትኩረታችን ቀይባሕር በቀጠናው ላይ ያላትን ቦታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ሰፋ ያለ አገልግሎት እንዲሰጡ ያለመ እቅድ ነው" ብለዋል ፕሬዚዳንቱ "ከተጋገዝን የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ስለምንችል በአካባቢው ኢኮኖሚያዊ ውህደት መፍጠር" አንዱ የመንግስታቸው ዓላማ መሆኑን ገልጸዋል። ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ከወደቦች በተጨማሪ ከመንገድ ግንባታ ጋር የተያዙ እቅዶችም ላይ መረጃ የሰጡ ሲሆን፤ በዚህም ኢትዮጵያንና ኤርትራን የሚያገናኙ መንገዶችም የሚያስፈልጋቸውን ጥገናም ሆነ ግንባታ ለመስራት መንግሥታቸው አቅዷል ብለዋል። በዚህም መሰረት ከአሰብ በደባየሲማ ኢትዮጵያን የሚያገናኘውን መንገድ የማስፋት፤ ከምጽዋ በደቀመኃሪ አድርጎ ዛላምበሳ፤ ከአስመራ በመንደፈራ፣ ራማን የሚያገናኙት የአስፋልት መንገዶች ደግሞ የማሻሻል ስራዎች በዚህ አመት እንደሚጀመሩና፤ የተጀመሩትም እንደሚጠናቀቁ ገልፀዋል። ፕሬዚዳንቱ በሃገሪቱ ውስጥ ያሉ የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን፣ ኢንቨስትመንት፣ የኑሮ ውድነት እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮች ላይ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል። ከዚህም መካከል ለሁለት አስርት አመታት ሲንከባለል የመጣው የመንግሥት ሰራተኞች ደመወዝ ማስተካከያ ጥያቄ ላይ ምላሽ የሰጡት ፕሬዚዳንቱ ሰራተኞች አስፈላጊውን የኑሮ ወጪ የሚሸፍንላቸው በቂ ደመወዝ እንዳልነበራቸው አምነዋል። መንግሥታቸው ይህንን ችግር ለመፍታት ከሁለት አመታት በፊት የደመወዝ ማስተካከያ ማድረግ መጀመሩን ጠቁመው፤ በደመወዝ ማስተካከያው ሂደት እስከ አሁን ጭማሪው ያልደረሳቸው የመንግስት ሰራተኞች የሁለት ዓመት ድምር እንደሚደርሳቸው ፕሬዚዳንቱ ገልፀዋል። መንግሥት የደመወዝ ማስተካከያ አሰራሩንም ለመተግበር እክሎች እንደገጠሙት የገለፁት ፕሬዚዳንቱ ይህም በሃገሪትዋ "ተገቢ ባልሆኑ ምክንያቶች" የሸቀጦች ዋጋ ንረት በመፈጠሩ ነው ብለዋል። "መንግሥት ይህ ኢ-ምክንያታዊ የሆነ የዋጋ ንረትን በቸልታ አያልፈውም ፤ እርምት ይወስዳል" በማለት አስጠንቅቀዋል ያለውን የዋጋ ንረት ለማስተካከልም ባለፉት ዓመታት መንግሥት የቤት ኪራይ፣ ስጋ እና የታሸገ ውሀ ላይ የዋጋ ተመን ማድረግ እንደጀመረ ምንጮች ይገልጻሉ። የመኖርያ ቤቶች ግንባታ ዋነኛው የሀገሪትዋ ቁልፍ ችግር እንደሆነ ያወሱት ፕሬዚዳንቱ መንግሥት ይህንን ችግር ለመፍታት ብሎ የጀመራቸው የቤቶች ግንባታ ቢጀምርም፤ ያላለቁ ቤቶች ግን በርካታ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። • ወደ አሥመራ ለመጓዝ ማወቅ የሚገባዎ 6 ነጥቦች • ኤርትራ በዶይቼ ቬለ ዘገባ ሳቢያ የጀርመን አምባሳደር ማብራሪያ እንዲሰጡ ጠየቀች በሂደትም መንግሥት ጥናት አካሂዶ አዋጪ ሆኖ ከተገኘ በቤቶች ግንባታ የውጪ ተቋራጮች ጭምር ለማሳተፍ ሀሳብ እንዳለ የገለጹት ፕሬዝደንት ኢሳይያስ አፈወርቂ፤ ያላለቁ እቅዶች ስላሉ በዚህ አመት የሚሰሩ ስራዎችን ለማስቀመጥ ትንሽ ከባድ እንደሆነ በመጠቆም ዝርዝርም ሆነ ቀነ ገደብ ከማስቀመጥ ተቆጥበዋል። ፕሬዚዳንቱ አንዳንድ ሃገሪቷ ያሉባትን ችግሮች በግልፅ ከመናገር ወደኋላ ያላሉ ሲሆን በተለይም ባለፉት 20 ዓመታት "አክስሮናል" ያሉትን የትምህርት ዘርፍ ፖሊሲ ለሀገሪትዋ ኢኮኖሚ ዋነኛው ምሰሶ በመሆኑ ስር ነቀል ለውጥ ሊመጣ ይገባል ብለዋል። ከዚህም በተጨማሪ ከቀይ ባህር በዓመት እስከ 100 ሺ ቶን የአሳ ሀብት ማግኘት እየታቸለ ባለፉት 20 ዓመታት ግን አስር ሺ ቶን ብቻ እንደነበረ ገልጸዋል። ይህንን የአሳ ሀብት ለማሳደግም አስፈላጊውን የመሰረተ ልማት ስራዎች ለማከናወን እቅድ መያዙን አብራርተዋል። ፕሬዚዳንቱ መንግሥታቸው በዚህ አመት ከያዟቸው ሌሎች እቅዶች መካከል በአሰብ፣ ምጽዋ እና አስመራ ከተሞች 60 ሜጋ ዋት ኤሌትሪክ ከታዳሽ ኃይል ለማመንጨት የተለያየ መጠን ያላቸው የውሀ ግድቦች የሚገነቡ ሲሆን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴውን ለማበረታት አስፈላጊ የመሰረተ ልማት ስራዎች እንደሚሰሩም አስረድተዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-51440267
3politics
የማሊው ወታደራዊ መሪ ከፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር መነጋገራቸውን ገለጹ
የማሊ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ኮሎኔል አሲሚ ጎኢታ ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በስልክ መነጋገራቸውን ገለጹ። በወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ሥልጣን የያዘው ጁንታ መሪ የሆኑት ኮሎኔሉ፤ ከፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር በስልክ የተነጋገሩት ትናንት ረቡዕ ነሐሴ 04/2014 ዓ.ም. መሆኑን አመልክተዋል። “ለማሊ ፖለቲካዊ ሽግግር የሩሲያ ፌዴሬሽን ድጋፍ ላይ ተነጋግረናል” ያሉት ኮሎኔል ጎኢታ፤ የማሊን ሉዓላዊነት ያከበረ እና የሕዝቡን ፍላጎት የሚረዳ የሁለቱ አገራት ወዳጅነት ጠንካራ መሆኑን ለፕሬዝዳንት ፑቲን መገለጻቸውን በትዊተር ገጻቸው አስፈረዋል። ከትናንት በስቲያ ማክሰኞ ኮሎኔል አሲሚ ጎኢታ በተገኙበት ሥነ ሥርዓት ላይ ማሊ ከሩሲያ የተረከበቻቸውን በርካታ ተዋጊ አውሮፕላኖችን በዋና ከተማዋ ባማኮ አየር ማረፊያ ለዕይታ አቅርባ ነበር። ሞስኮ በመፈንቅለ መንግሥት ሥልጣን ከጨበጠው ከማሊ ጦር ሠራዊት ጋር ያላንትን የጠበቀ ወዳጅነት ለማሳየት በሶቪየት ሕብረት የተመረቱ የጦር አውሮፕላኖችን ለማሊ ሰጥታለች። ከመፈንቅለ መንግሥቱ በኀወላ የማሊ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት ከምዕራባውያን አገራት በተለይ ደግሞ ከፈረንሳይ ጋር የነበረው ግንኙነት በእጅጉ ሻክሯል። ፈረንሳይ የሩሲያው ቅጥረኛ ተዋጊ ቡድን ዋግነር በምዕራባ አፍሪካዊቷ አገር መገኘቱን ከተቃወመች በኋላ ከጊዜያዊው ወታደራዊ መንግሥት ጋር ያላት ግንኙነት ተበላሽቶ ወደታደሮቿን ከአገሪቱ አስወጥታለች። የፈረንሳይ እና ሌሎች የአውሮፓ አገራት ጥምር ጦር ወታደሮች በማሊ ተሰማርተው ጸንፈኛ እስላማዊ ቡድኖችን ሲወጋ ቆይቷል። ለምዕራባውያን ጀርባዋን ሰጥታ ፊቷን ወደ ሩሲያ ባዞረችው ማሊ፣ በጽንፈኛ ቡድኖች የሚፈጸሙ ጥቃቶች ተበራክተዋል። ከጥቂት ቀናት በፊት በእስማላዊ ታጣቂ ቡድን በተፈጸመ ጥቃት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 42 መድረሱ ተገልጿል። ባለፈው እሁድ ነሐሴ 01/2014 ዓ.ም. ከኢስላሚክ ስቴትስ (አይኤስ) ጋር ግንኙነት አለው የተባለ ቡድን በፈጸመው ጥቃት በርካታ ወታደሮች መገደላቸው እና መቁሰላቸው ተዘግቦ ነበር። ቡድኑ ማሊ፣ ቡርኪና ፋሶ እና ኒጀር በሚዋሰኑበት የማሊ ግዛት ውስጥ በፈጸመው ጥቃት የሟቾች ቁጥር 42 መድረሱን እና በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ደግሞ መኖሪያቸውን ጥለው መሰደዳቸውን የአካባቢው ባለሥልጣናት ገልጸዋል።
የማሊው ወታደራዊ መሪ ከፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር መነጋገራቸውን ገለጹ የማሊ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ኮሎኔል አሲሚ ጎኢታ ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በስልክ መነጋገራቸውን ገለጹ። በወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ሥልጣን የያዘው ጁንታ መሪ የሆኑት ኮሎኔሉ፤ ከፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር በስልክ የተነጋገሩት ትናንት ረቡዕ ነሐሴ 04/2014 ዓ.ም. መሆኑን አመልክተዋል። “ለማሊ ፖለቲካዊ ሽግግር የሩሲያ ፌዴሬሽን ድጋፍ ላይ ተነጋግረናል” ያሉት ኮሎኔል ጎኢታ፤ የማሊን ሉዓላዊነት ያከበረ እና የሕዝቡን ፍላጎት የሚረዳ የሁለቱ አገራት ወዳጅነት ጠንካራ መሆኑን ለፕሬዝዳንት ፑቲን መገለጻቸውን በትዊተር ገጻቸው አስፈረዋል። ከትናንት በስቲያ ማክሰኞ ኮሎኔል አሲሚ ጎኢታ በተገኙበት ሥነ ሥርዓት ላይ ማሊ ከሩሲያ የተረከበቻቸውን በርካታ ተዋጊ አውሮፕላኖችን በዋና ከተማዋ ባማኮ አየር ማረፊያ ለዕይታ አቅርባ ነበር። ሞስኮ በመፈንቅለ መንግሥት ሥልጣን ከጨበጠው ከማሊ ጦር ሠራዊት ጋር ያላንትን የጠበቀ ወዳጅነት ለማሳየት በሶቪየት ሕብረት የተመረቱ የጦር አውሮፕላኖችን ለማሊ ሰጥታለች። ከመፈንቅለ መንግሥቱ በኀወላ የማሊ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት ከምዕራባውያን አገራት በተለይ ደግሞ ከፈረንሳይ ጋር የነበረው ግንኙነት በእጅጉ ሻክሯል። ፈረንሳይ የሩሲያው ቅጥረኛ ተዋጊ ቡድን ዋግነር በምዕራባ አፍሪካዊቷ አገር መገኘቱን ከተቃወመች በኋላ ከጊዜያዊው ወታደራዊ መንግሥት ጋር ያላት ግንኙነት ተበላሽቶ ወደታደሮቿን ከአገሪቱ አስወጥታለች። የፈረንሳይ እና ሌሎች የአውሮፓ አገራት ጥምር ጦር ወታደሮች በማሊ ተሰማርተው ጸንፈኛ እስላማዊ ቡድኖችን ሲወጋ ቆይቷል። ለምዕራባውያን ጀርባዋን ሰጥታ ፊቷን ወደ ሩሲያ ባዞረችው ማሊ፣ በጽንፈኛ ቡድኖች የሚፈጸሙ ጥቃቶች ተበራክተዋል። ከጥቂት ቀናት በፊት በእስማላዊ ታጣቂ ቡድን በተፈጸመ ጥቃት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 42 መድረሱ ተገልጿል። ባለፈው እሁድ ነሐሴ 01/2014 ዓ.ም. ከኢስላሚክ ስቴትስ (አይኤስ) ጋር ግንኙነት አለው የተባለ ቡድን በፈጸመው ጥቃት በርካታ ወታደሮች መገደላቸው እና መቁሰላቸው ተዘግቦ ነበር። ቡድኑ ማሊ፣ ቡርኪና ፋሶ እና ኒጀር በሚዋሰኑበት የማሊ ግዛት ውስጥ በፈጸመው ጥቃት የሟቾች ቁጥር 42 መድረሱን እና በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ደግሞ መኖሪያቸውን ጥለው መሰደዳቸውን የአካባቢው ባለሥልጣናት ገልጸዋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cnl1z2e1lk9o
5sports
የሳዑዲ አረቢያን ቡድን ለመደገፍ 1600 ኪሎ ሜትር በእግሩ የተጓዘው ደጋፊ
የዘንድሮው የዓለም ዋንጫ በውድድሩ ታሪክ በአረብ አገር አስተናጋጅነት ሲካሄድ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። በዚህም ትንሽየዋ ነገር ግን ባለፀጋዋ አገር ኳታር ቢሊዮኖችን አፍስሳ ውድድሩን እያካሄደች ነው። ይህ በኳታር የሚካሄደው የዓለም ዋንጫ በአረብ የእግር ኳስ አፍቃሪያን ዘንድ በልዩ ሁኔታ እየታየ ነው። ከመላው ዓለም ወደ አገሪቱ ካቀኑት በተጨማሪ በርካታ ሰዎች ከመካከለኛው ምሥራቅ እና ከባሕረ ሰላጤው አረብ አገራት ውድድሩን ለመታደም በተለያዩ መንገዶች ከስፍራው ደርሰዋል። ከእነዚህም መካከል አብዱላህ አል ሳልሚ ለዘመናት ሲያልመው የነበረውን ፍላጎቱን ለማሳካት በኳታር የሚስተናገደው የዓለም ዋንጫ ዕድሉን ፈጥሮለታል። አብዱላህ በመጀመሪያ ጨዋታው የእግር ኳስ ታላቅ አገር የሆነችውን አርጀንቲናን በማሸነፍ ዓለምን ያስደመመውን የአገሩን ቡድን  ለመደገፍ ከሳዑዲ አረቢያ ጅዳ እስከ ኳታር ዶሃ ያለውን 1600 ኪሎ ሜትር በእግሩ ተጉዟል። ጉዞው አስቸጋሪ ቢሆንም ኳታር ከደረሰ በኋላ ግን አብዱላህ ዝነኛ ሆኗል።
የሳዑዲ አረቢያን ቡድን ለመደገፍ 1600 ኪሎ ሜትር በእግሩ የተጓዘው ደጋፊ የዘንድሮው የዓለም ዋንጫ በውድድሩ ታሪክ በአረብ አገር አስተናጋጅነት ሲካሄድ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። በዚህም ትንሽየዋ ነገር ግን ባለፀጋዋ አገር ኳታር ቢሊዮኖችን አፍስሳ ውድድሩን እያካሄደች ነው። ይህ በኳታር የሚካሄደው የዓለም ዋንጫ በአረብ የእግር ኳስ አፍቃሪያን ዘንድ በልዩ ሁኔታ እየታየ ነው። ከመላው ዓለም ወደ አገሪቱ ካቀኑት በተጨማሪ በርካታ ሰዎች ከመካከለኛው ምሥራቅ እና ከባሕረ ሰላጤው አረብ አገራት ውድድሩን ለመታደም በተለያዩ መንገዶች ከስፍራው ደርሰዋል። ከእነዚህም መካከል አብዱላህ አል ሳልሚ ለዘመናት ሲያልመው የነበረውን ፍላጎቱን ለማሳካት በኳታር የሚስተናገደው የዓለም ዋንጫ ዕድሉን ፈጥሮለታል። አብዱላህ በመጀመሪያ ጨዋታው የእግር ኳስ ታላቅ አገር የሆነችውን አርጀንቲናን በማሸነፍ ዓለምን ያስደመመውን የአገሩን ቡድን  ለመደገፍ ከሳዑዲ አረቢያ ጅዳ እስከ ኳታር ዶሃ ያለውን 1600 ኪሎ ሜትር በእግሩ ተጉዟል። ጉዞው አስቸጋሪ ቢሆንም ኳታር ከደረሰ በኋላ ግን አብዱላህ ዝነኛ ሆኗል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cnd5438x5j9o
3politics
ጃዋር መሐመድ፡ በቢጫ ለባሾቹ ምክንያት የእነ ጃዋር ችሎት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠበት
ቢጫ ቀለም ልብስ በለበሱ ግለሰቦች ምክንያት የእነ አቶ ጃዋር መሐመድ የዛሬ ችሎት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠበት። የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የፀረ ሽብርና ሕገመንግሥታዊ አንደኛ ችሎት ዛሬ ማለዳ የተከሳሾችን የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሊቀበል ቀጠሮ ይዞ ነበር። ይህን ተከትሎ አቶ ጃዋር መሐመድ እና በቀለ ገርባን ጨምሮ በዚህ የክስ መዝገብ የተከሰሱ ተከሳሾች ፍርድ ቤትየቀረቡ ቢሆንም ችሎቱ ግን ተለዋጭ ቀጠሮ በመስጠት አሰናብቷቸዋል። ይሀህ ሊሆን ቻለው የፍርድ ሂደቱን ለመከታተል ቢጫ ልብስ ለብሰው በፍርድ ቤት የተገኙ ሰዎች ወደ ፍርድ ቤቱ እንዳይገቡ በፖሊስ መከልከላቸውን ተከትሎ ተከሳሾች እና ጠበቆች ባሰሙት አቤቱታ ነው። ከተከሳሾች መካከል አቶ ጃዋር መሐመድ፣ በቀለ ገርባ እና ሐምዛ አዳነ ሰዎች ቢጫ ቀለም ያለው ልብስ በመልበሳቸው ወደ ፍርድ ቤት እንዳይገቡ መደረጉ አግባብ አይደለም፤ ቢጫ ልብስ በመልበሳቸው ብቻ ለእስር የተዳረጉ አሉ ሲሉ ቅሬታቸውን ለፍርድ ቤት አቅርበዋል። ከሰሞኑ በማሕበራዊ ሚዲያዎች ላይ በርካቶች ቢጫ ልብስ የመልበስ ዘመቻ ሲያከናውኑ ቆይተዋል። ይህም ተከሳሾች በማረሚያ ቤት እና ፍርድ ቤት ሲቀርቡ የሚለብሱትን ባለ ቢጫ ቀለም ቱታ ለመወከል ነው። ተከሳሾች ፍርድ ቤት ሲቀርቡ፤ ለተከሳሾች የሞራል ድጋፍ ለመስጠት ቢጫ ቀለም ያላቸውን ልብሶች በመልበስ በፍርድ ቤት እንደሚገኙ የዘመቻው አካል የሆኑት ይናገራሉ። ባለፉት ሁለት ቀጠሮዎች በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ የክስ መዝገብ ሥራ የተከሰሱ ተከሳሾች ፍርድ ቤት በቀረቡብት ወቅት ቢጫ ቀለም ያለው ልብስ ለብሳ ከፍርድ ቤት የተገኘችው መሠረት ዳባ፤ ይህ ዘመቻችንን ለተከሳሾች የሞራል ብርታትን ለመስጠት ነው ትላለች። "እነሱ ከሚለብሱት የልብስ ቀለም ጋር ተመሳሳይ ልብስ በመልበስ 'እኛም ከእናንተ ጋር ነን'፣ 'ከእናንተ ጋር ታስረናል' የሚል መልዕክት ማስተላለፍ ፈልገን ነው" ስትል ለቢቢሲ ተናግራለች። ባለ ቢጫ ቀለም ልብስ የመልበስ ዘመቻ አስተባባሪ የሆነው ወቢ ቡርቃሳ የጀመሩት ዘመቻ በርካቶችን በማሳተፍ ከታሰበው በላይ ብዙ ሰዎች ጋር መድረሱን ይናገራል። በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ #oromoyellowmovement የሚል መሪ ቃል ሲጠቀሙ ቆይተዋል። በዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ ላይ አቶ ጃዋር መሐመድ፣ የቤተሰብ አባላቶቻቸው እና ሌሎች ሰዎች በለበሱት የልብስ ቀለም ሳቢያ ወደ ፍርድ ቤት እንዳይገቡ መደረጋቸውን እና ለእስር መዳረጋቸውን በመጥቀስ፤ በዚህ ምክንያት ሰዎች ወደ ፍርድ ቤት እንዳይገቡ ተደርጎ ባሉበት ሁኔታ ምንም ዓይነት አስተያየት መስጠት እንደማይችሉ ተናግረዋል። አቶ በቀለ ገርባ እና አቶ ሐመዛ አዳነ ሰዎች ወደ ፍርድ ቤት እንዳይገቡ መከልከላቸው እንዳሳዘናቸው እና ቢጫ በመልበሳቸው የታሰሩት ይፈቱ ሲሉ ጠይቀዋል። የተከሳሾች ጠበቆችም ችሎቱ ለሕዝብ ክፍት ሆኖ ሳለ ሰዎች በለበሱት የልብስ ቀለም ሳቢያ ወደ ችሎት እንዳይገቡ መከልከላቸው አግባብ አይደለም በማለት የተከሳሾችን የእምነት ክህደት ቃል ለመቀበል ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጥ ፍርድ ቤቱን ጠይዋል። ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ ሌላ ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠት የፍርድ ሂደቱን ያጓትታል ሲል ተከራክሯል። የግራ ቀኙን ክርክር ያደመጠው ፍርድ ቤቱ የተከሳሾችን የእምነት ክህደት ቃል ለመስማት ለጥር 27፣ 2013 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። ፍርድ ቤቱ ሰዎች በለበሱት የልብስ ቀለም ፍርድ ቤት እንዳይገቡ መደረጉ አግባብ አይደለም ያለ ሲሆን፤ ታዳሚዎች በሙሉ ግን ቢጫ ቀለም ያለው ልብስ ለብሰው በፍርድ ቤት የሚገኙ ከሆነ በችሎቱ ላይ ጫና ሊፈጥር እንደሚችል ከግምት ማስገባት አለበት ብሏል። በሰኔ ወር፣ 2012 ዓ.ም ከሙዚቀኛው ሃጫሉ ግድያ በኋላ በቁጥጥር ሥር የዋሉት አቶ ጃዋር መሐመድና በክስ መዝገባቸው ውስጥ የሚገኙ ሌሎች 24 ሰዎች ተደራራቢ አስር ክሶች እንደተመሰረተባቸው ይታወሳል። በእነ አቶ ጃዋር መሃመድ ከቀረቡ ተደራራቢ አስር ክሶች ስድስቱ እንዲቋረጡ ፍርድ ቤት ጥር 14/2013 ዓ.ም ውሳኔ አስተላልፏል። አቶ ደጀኔ ጉተማ፣ ዶ/ር ብርሃነ መስቀል አበበና ፀጋዬ ረጋሳ አገር ውስጥ የሌሉና በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ መዝገብ ውስጥ ከተከሰሱት መካከል ናቸው። የድምጻዊ ሃጫሉ ግድያን ተከትሎ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ተከስቶ ከነበረ ሁከት ጋር ተያይዞ ነበር እነ አቶ ጃዋር መሐመድ በቁጥጥር ሥር የዋሉት።
ጃዋር መሐመድ፡ በቢጫ ለባሾቹ ምክንያት የእነ ጃዋር ችሎት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠበት ቢጫ ቀለም ልብስ በለበሱ ግለሰቦች ምክንያት የእነ አቶ ጃዋር መሐመድ የዛሬ ችሎት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠበት። የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የፀረ ሽብርና ሕገመንግሥታዊ አንደኛ ችሎት ዛሬ ማለዳ የተከሳሾችን የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሊቀበል ቀጠሮ ይዞ ነበር። ይህን ተከትሎ አቶ ጃዋር መሐመድ እና በቀለ ገርባን ጨምሮ በዚህ የክስ መዝገብ የተከሰሱ ተከሳሾች ፍርድ ቤትየቀረቡ ቢሆንም ችሎቱ ግን ተለዋጭ ቀጠሮ በመስጠት አሰናብቷቸዋል። ይሀህ ሊሆን ቻለው የፍርድ ሂደቱን ለመከታተል ቢጫ ልብስ ለብሰው በፍርድ ቤት የተገኙ ሰዎች ወደ ፍርድ ቤቱ እንዳይገቡ በፖሊስ መከልከላቸውን ተከትሎ ተከሳሾች እና ጠበቆች ባሰሙት አቤቱታ ነው። ከተከሳሾች መካከል አቶ ጃዋር መሐመድ፣ በቀለ ገርባ እና ሐምዛ አዳነ ሰዎች ቢጫ ቀለም ያለው ልብስ በመልበሳቸው ወደ ፍርድ ቤት እንዳይገቡ መደረጉ አግባብ አይደለም፤ ቢጫ ልብስ በመልበሳቸው ብቻ ለእስር የተዳረጉ አሉ ሲሉ ቅሬታቸውን ለፍርድ ቤት አቅርበዋል። ከሰሞኑ በማሕበራዊ ሚዲያዎች ላይ በርካቶች ቢጫ ልብስ የመልበስ ዘመቻ ሲያከናውኑ ቆይተዋል። ይህም ተከሳሾች በማረሚያ ቤት እና ፍርድ ቤት ሲቀርቡ የሚለብሱትን ባለ ቢጫ ቀለም ቱታ ለመወከል ነው። ተከሳሾች ፍርድ ቤት ሲቀርቡ፤ ለተከሳሾች የሞራል ድጋፍ ለመስጠት ቢጫ ቀለም ያላቸውን ልብሶች በመልበስ በፍርድ ቤት እንደሚገኙ የዘመቻው አካል የሆኑት ይናገራሉ። ባለፉት ሁለት ቀጠሮዎች በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ የክስ መዝገብ ሥራ የተከሰሱ ተከሳሾች ፍርድ ቤት በቀረቡብት ወቅት ቢጫ ቀለም ያለው ልብስ ለብሳ ከፍርድ ቤት የተገኘችው መሠረት ዳባ፤ ይህ ዘመቻችንን ለተከሳሾች የሞራል ብርታትን ለመስጠት ነው ትላለች። "እነሱ ከሚለብሱት የልብስ ቀለም ጋር ተመሳሳይ ልብስ በመልበስ 'እኛም ከእናንተ ጋር ነን'፣ 'ከእናንተ ጋር ታስረናል' የሚል መልዕክት ማስተላለፍ ፈልገን ነው" ስትል ለቢቢሲ ተናግራለች። ባለ ቢጫ ቀለም ልብስ የመልበስ ዘመቻ አስተባባሪ የሆነው ወቢ ቡርቃሳ የጀመሩት ዘመቻ በርካቶችን በማሳተፍ ከታሰበው በላይ ብዙ ሰዎች ጋር መድረሱን ይናገራል። በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ #oromoyellowmovement የሚል መሪ ቃል ሲጠቀሙ ቆይተዋል። በዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ ላይ አቶ ጃዋር መሐመድ፣ የቤተሰብ አባላቶቻቸው እና ሌሎች ሰዎች በለበሱት የልብስ ቀለም ሳቢያ ወደ ፍርድ ቤት እንዳይገቡ መደረጋቸውን እና ለእስር መዳረጋቸውን በመጥቀስ፤ በዚህ ምክንያት ሰዎች ወደ ፍርድ ቤት እንዳይገቡ ተደርጎ ባሉበት ሁኔታ ምንም ዓይነት አስተያየት መስጠት እንደማይችሉ ተናግረዋል። አቶ በቀለ ገርባ እና አቶ ሐመዛ አዳነ ሰዎች ወደ ፍርድ ቤት እንዳይገቡ መከልከላቸው እንዳሳዘናቸው እና ቢጫ በመልበሳቸው የታሰሩት ይፈቱ ሲሉ ጠይቀዋል። የተከሳሾች ጠበቆችም ችሎቱ ለሕዝብ ክፍት ሆኖ ሳለ ሰዎች በለበሱት የልብስ ቀለም ሳቢያ ወደ ችሎት እንዳይገቡ መከልከላቸው አግባብ አይደለም በማለት የተከሳሾችን የእምነት ክህደት ቃል ለመቀበል ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጥ ፍርድ ቤቱን ጠይዋል። ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ ሌላ ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠት የፍርድ ሂደቱን ያጓትታል ሲል ተከራክሯል። የግራ ቀኙን ክርክር ያደመጠው ፍርድ ቤቱ የተከሳሾችን የእምነት ክህደት ቃል ለመስማት ለጥር 27፣ 2013 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። ፍርድ ቤቱ ሰዎች በለበሱት የልብስ ቀለም ፍርድ ቤት እንዳይገቡ መደረጉ አግባብ አይደለም ያለ ሲሆን፤ ታዳሚዎች በሙሉ ግን ቢጫ ቀለም ያለው ልብስ ለብሰው በፍርድ ቤት የሚገኙ ከሆነ በችሎቱ ላይ ጫና ሊፈጥር እንደሚችል ከግምት ማስገባት አለበት ብሏል። በሰኔ ወር፣ 2012 ዓ.ም ከሙዚቀኛው ሃጫሉ ግድያ በኋላ በቁጥጥር ሥር የዋሉት አቶ ጃዋር መሐመድና በክስ መዝገባቸው ውስጥ የሚገኙ ሌሎች 24 ሰዎች ተደራራቢ አስር ክሶች እንደተመሰረተባቸው ይታወሳል። በእነ አቶ ጃዋር መሃመድ ከቀረቡ ተደራራቢ አስር ክሶች ስድስቱ እንዲቋረጡ ፍርድ ቤት ጥር 14/2013 ዓ.ም ውሳኔ አስተላልፏል። አቶ ደጀኔ ጉተማ፣ ዶ/ር ብርሃነ መስቀል አበበና ፀጋዬ ረጋሳ አገር ውስጥ የሌሉና በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ መዝገብ ውስጥ ከተከሰሱት መካከል ናቸው። የድምጻዊ ሃጫሉ ግድያን ተከትሎ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ተከስቶ ከነበረ ሁከት ጋር ተያይዞ ነበር እነ አቶ ጃዋር መሐመድ በቁጥጥር ሥር የዋሉት።
https://www.bbc.com/amharic/news-55825409
5sports
'ሴቶች ብዙ ያወራሉ' ያሉት የቶክዮ ኦሊምፒክ ኃላፊ ይቅርታ ጠየቁ
የቶክዮ ኦሊምፒክስ አዘጋጅ ኪሚቲ ኃላፊ የሆኑት ግለሰብ ሴቶችን አስመልክተው በሰጡት አስተያየት ምክንያት ሥልጣናቸውን ሊለቁ እንደሚችሉ ጠቁመዋል። የ83 ዓመቱ ዮሺሮ ሞሪ 'ምንም ሳያሰላስሉ' ለሰጡት አስተያየት ይቅር በሉኝ ብለዋል ሲሉ የጃፓን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የኮሚቲው ኃላፊ 'ሴቶች በጣም ብዙ ያወራሉ፤ ሴት የቦርድ ኃላፊዎች ያሉበት ስብሰባ በጣም ብዙ ጊዜ ይወስዳል' ሲሉ ተናግረዋል ተብለው ተወቅሰዋል። ሰውዬው ትላንት [ረቡዕ] በተካሄደው የጃፓን ኦሊምፒክ ኮሚቲ ስብሰባ ላይ ይህን ያሉት። የኦሊምፒክ ኮሚቲው በአሁኑ ወቅት 24 አባላት ያሉት ሲሆን አምስቱ ሴቶች ናቸው። የጃፖን ኦሊምፒክ ተሳታፊዎችን የመመረጥ ኃላፊነት ያለበት ይህ ኪሚቲ በፈረንጆቹ 2019 ሴት የቦርድ ኃላፊዎችን ድርሻ 40 በመቶ ለማድረስ ቃል ገብቶ ነበር። "ሴት የቦርድ አባላትን ቁጥር ለመጨመር ካሰብን ለሚያደርጉት ንግግር የሚሰጣቸው ሰዓት የተወሰነ ሊሆን ይገባል። እነሱ እንደሆነ ቶሎ ተናግሮ የመጨረስ ችግር አለባቸው። በጣም ያናድዳል" ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል በማለት አሳሂ ሺምቡን ጋዜጣ ዘግቧል። በፈረንጆቹ ከ2000 እስከ 2001 ለአንድ ዓመት ብቻ ጃፓን በጠቅላይ ሚኒስትርነት ያስተዳደሩት ዮሪ ዲፕሎማሲ በራቃቸው አስተያየቶቻቸው ይታወቃሉ። ሴቶችን በማስመልከት የሰጡት አስተያየትም ከማሕበራዊ ድር አምባ ተጠቃሚዎች ዘንድ ተቃውሞ አስነስቶባቸዋል። በርካታ የትዊተር ተጠቃሚዎች ዮሪ ሥልጣን ይልቀቁ በማለት ላይ ናቸው። ሰውዬው ቤት ሲገቡ ባለቤታቸው ጭምር በሰጡት አስተያየት እንደተቀየሟቸው መናገራቸውን አልደበቁም። "ትላንት ምሽት ቤት ስገባ ባለቤቴ፤ አሁን ደግሞ ሌላ የማይሆን ነገር ተናገርክ አይደል? ሴቶችን የሚያፀይፍ ነገር በመናገርህ እኔ ነኝ የምሳቀቀው" ብለዋል። "ዛሬ ጥዋት ደግሞ ሴት ልጄ፣ ሴት የልጅ ልጄ ወቀሳ ሰንዝረውብኛል" ብለዋል ሲል ጋዜጣው ዘግቧል። የቶኪዮ ኦሊምፒክስ አዘጋጅ ኮሚቲ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ለአንድ ዓመት የዘገየውን የቶኪዮ ኦሊምፒክና ፓራሊምፒክ በተሳካ ሁኔታ ለማዘጋጀት ደፋ ቀና እያለ ይገኛል። ኮሚቲው 36 ከፍተኛ የቦርድ አባላት ያሉት ሲሆን ከዚህ ቀድም ጃፓን ውስጥ በተለያዩ ኃላፊነቶች ላይ የሠሩ ናቸው።
'ሴቶች ብዙ ያወራሉ' ያሉት የቶክዮ ኦሊምፒክ ኃላፊ ይቅርታ ጠየቁ የቶክዮ ኦሊምፒክስ አዘጋጅ ኪሚቲ ኃላፊ የሆኑት ግለሰብ ሴቶችን አስመልክተው በሰጡት አስተያየት ምክንያት ሥልጣናቸውን ሊለቁ እንደሚችሉ ጠቁመዋል። የ83 ዓመቱ ዮሺሮ ሞሪ 'ምንም ሳያሰላስሉ' ለሰጡት አስተያየት ይቅር በሉኝ ብለዋል ሲሉ የጃፓን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የኮሚቲው ኃላፊ 'ሴቶች በጣም ብዙ ያወራሉ፤ ሴት የቦርድ ኃላፊዎች ያሉበት ስብሰባ በጣም ብዙ ጊዜ ይወስዳል' ሲሉ ተናግረዋል ተብለው ተወቅሰዋል። ሰውዬው ትላንት [ረቡዕ] በተካሄደው የጃፓን ኦሊምፒክ ኮሚቲ ስብሰባ ላይ ይህን ያሉት። የኦሊምፒክ ኮሚቲው በአሁኑ ወቅት 24 አባላት ያሉት ሲሆን አምስቱ ሴቶች ናቸው። የጃፖን ኦሊምፒክ ተሳታፊዎችን የመመረጥ ኃላፊነት ያለበት ይህ ኪሚቲ በፈረንጆቹ 2019 ሴት የቦርድ ኃላፊዎችን ድርሻ 40 በመቶ ለማድረስ ቃል ገብቶ ነበር። "ሴት የቦርድ አባላትን ቁጥር ለመጨመር ካሰብን ለሚያደርጉት ንግግር የሚሰጣቸው ሰዓት የተወሰነ ሊሆን ይገባል። እነሱ እንደሆነ ቶሎ ተናግሮ የመጨረስ ችግር አለባቸው። በጣም ያናድዳል" ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል በማለት አሳሂ ሺምቡን ጋዜጣ ዘግቧል። በፈረንጆቹ ከ2000 እስከ 2001 ለአንድ ዓመት ብቻ ጃፓን በጠቅላይ ሚኒስትርነት ያስተዳደሩት ዮሪ ዲፕሎማሲ በራቃቸው አስተያየቶቻቸው ይታወቃሉ። ሴቶችን በማስመልከት የሰጡት አስተያየትም ከማሕበራዊ ድር አምባ ተጠቃሚዎች ዘንድ ተቃውሞ አስነስቶባቸዋል። በርካታ የትዊተር ተጠቃሚዎች ዮሪ ሥልጣን ይልቀቁ በማለት ላይ ናቸው። ሰውዬው ቤት ሲገቡ ባለቤታቸው ጭምር በሰጡት አስተያየት እንደተቀየሟቸው መናገራቸውን አልደበቁም። "ትላንት ምሽት ቤት ስገባ ባለቤቴ፤ አሁን ደግሞ ሌላ የማይሆን ነገር ተናገርክ አይደል? ሴቶችን የሚያፀይፍ ነገር በመናገርህ እኔ ነኝ የምሳቀቀው" ብለዋል። "ዛሬ ጥዋት ደግሞ ሴት ልጄ፣ ሴት የልጅ ልጄ ወቀሳ ሰንዝረውብኛል" ብለዋል ሲል ጋዜጣው ዘግቧል። የቶኪዮ ኦሊምፒክስ አዘጋጅ ኮሚቲ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ለአንድ ዓመት የዘገየውን የቶኪዮ ኦሊምፒክና ፓራሊምፒክ በተሳካ ሁኔታ ለማዘጋጀት ደፋ ቀና እያለ ይገኛል። ኮሚቲው 36 ከፍተኛ የቦርድ አባላት ያሉት ሲሆን ከዚህ ቀድም ጃፓን ውስጥ በተለያዩ ኃላፊነቶች ላይ የሠሩ ናቸው።
https://www.bbc.com/amharic/55930694
5sports
ከካሜሩን ጋር በሚደረገው የዛሬው ጨዋታ "እስከ መጨረሻው ደቂቃ ድረስ ለመፋለም ዝግጁ ነን"- አሰልጣኝ ውበቱ
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ከአዘጋጇ ካሜሩን ጋር ለምታደርገው ለዛሬው ጨዋታ ቡድኑ ጥሩ ዝግጅት ማድረጉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ገልጸዋል። በአፍሪካ ውስጥ ስመ ጥር ከሆኑት ቡድኖች የሆነው የካሜሩን ቡድንም ጠንካራና ልምድ ያላቸው ተጫዋቾች እንደሆኑ እንደሚያውቁ በትናንትናው ዕለት በነበረ ጋዜጣዊ መግለጫ የተናገሩት አሰልጣኝ ውበቱ ሆኖም ቡድናቸው ከዚህ ጨዋታ አንድ ነገር ለማግኘት ዝግጁዎች ነን ብለዋል። ካሜሩን የዘንድሮው አፍሪካ ዋንጫ አዘጋጅ በመሆኗ በዛሬው ዕለትም ኢትዮጵያ የምታደርገው ጨዋታ በደጋፊዎቿ ፊት ከምትጫወት ሃገር ጋር ከመሆኑም ቀላል ባይሆንም "ጥቃቅን ስህተቶችን አስወግደን እስከ መጨረሻው ደቂቃ ድረስ ለመፋለም ዝግጁ ነን።" ይላሉ አሰልጣኙ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ መክፈቻ በነበራት ጨዋታ በኬፕቨርዴ አንድ ለምንም ተረታለች። በዚህ ጨዋታ አንድ ተጫዋች በቀይ ካርድ በመውጣቱ አብዛኛውን የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በአንድ ሰው ጎዶሎ እንደተጫወቱም የጠቀሱት አሰልጣኙ ይህም በዋልያዎቹ ላይ ተፅእኖ ፈጥሯል ብለዋል። "ይህ በተጨዋቾቻችን በአካልና በመንፈስ ጠንካራ እንዳይሆኑ ያደረገ ክስተት ነበር።" ያሉት አሰልጣኝ ውበቱ አክለውም ቡድኑ በጥሩ አቋም ላይ አለ ብለዋል። "ቢሆንም አሁን ወደ አቋማችን ተመልሰናል። ይህንንም በልምምድ ሜዳና በካምፕ ማየት ችለናል። ከዛሬው ጨዋታ የተሻለ ነገር እንደምናገኝ ተስፋ አለኝ።" በማለት አስረድተዋል። ውበቱ አክለው በካሜሩን ጋር በሚኖራቸው ጨዋታ ብሔራዊ ቡድኑ የሚታወቅበትን ጨዋታ ለማሳየት እንደሚሞክሩ ጠቁመዋል። የመጀመሪያው ጨዋታ ለቡድናቸው ፈታኝ እንደነበር ጠቁመው የተሸነፈውም በአንድ ጎል ነው ይላሉ። ቡድናቸው ጎል የተቆጠረበት በመጀመሪያ አጋማሽ መገባደጃ ላይ መሆኑንም ጠቅሰው "ይህ የሆነው በትኩረት ማነስ ሊሆን ይችላል።" ብለዋል። ለዚህም እንደ ማስረጃ የሚያቀርቡት ኢትዮጵያ ያደረገቻቸውን ያለፉትን ስድስ ሰባት ጨዋታዎችን በመጥቀስ ነው። "ያለፉትን ስድስት ሰባት የኢትዮጵያ ጨዋታዎች ብንመለከት ኳስን በመቆጣጠር ከተጋጣሚዎቻችን የተሻልን ነበርን። ጋናን ብናነሳ፣ ደቡብ አፍሪካ አሊያም ዚምባብዌ የተሻለ የኳስ ቁጥጥር ነበረን።" ይላሉ። በመጀመሪያው ጨዋታ ያሬድ ባየህ ቀይ ካርድ ከተመለከተ በኋላ ተቀይሮ የወጣው አማካዩ መሱድ ሞሐመድ ካሜሩንን ብናከብራትም ውጤት ለማግኘት መፋለማችን ግን አይቀርም ብሏል። "ካሜሩን ጠንካራ ቡድን እንደሆነች እናውቃለን። አፍሪካን ወክላ በዓለም ዋንጫ ስትጫወት እኛ ኢትዮጵያዊያን ስንደግፋት ነበር። አልፎም የሳሙዔል ኤቶ ሃገር በመሆኗ ክብር እንሰጣታለን። ነገር ግን ዛሬ ከፈጣሪ ጋር ጥሩ ፍልሚያ እንደምናደርግ አስባለሁ።" ብሏል መሱድ በትናንትናው ዕለት በነበረ ጋዜጣዊ መግለጫ ከቡድኑ አባላት በኮቪድ ምክንያት አሊያም በጉዳት የማይሰለፍ አለ ወይ ተብለው የተጠየቁት አሠልጣኙ ኮቪድን በተለመከተ ተጫዋቾችን ጨምሮ ሁሉም የብሔራዊ ቡድኑ አባላት ከኮቪድ-19 ነፃ መሆናቸውን ተናግረዋል። "ይህ ለኛ መልካም ዜና ነው" ብለዋል ጉዳትን በተመለከተ ለግብፅ ሊግ የሚጨዋተውና ልምድ አላቸው ከሚባሉት ተጫዋቾች አንዱ ሽመልስ በቀለ በጉዳት ምክንያት እንደማይሰለፍ ተናግረዋል። ከሃገር ውጭ ከሚጫወቱት ሁለት ተጫዋቾች አንዱ የሆነው ሽመልስ ከትናንት በስቲያ ጉዳት እንዳጋጠመው አሰልጣኝ ውበቱ ገልጸዋል። "ከሃገር ውጭ ከሚጫወቱ ሁሉት ተጫዎቾቻችን አንዱ ነው። ቢሆንም ልምዱን ልንጠቀምበት አልቻልንም። ከትናንት በስቲያ እንደገና ጉዳት አጋጥሞታል። ከሱ በቀር ሁሉም ተጫዋቾቻችን ለዛሬው ፍልሚያ ዝግጁ ናቸው።" ብለዋል።
ከካሜሩን ጋር በሚደረገው የዛሬው ጨዋታ "እስከ መጨረሻው ደቂቃ ድረስ ለመፋለም ዝግጁ ነን"- አሰልጣኝ ውበቱ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ከአዘጋጇ ካሜሩን ጋር ለምታደርገው ለዛሬው ጨዋታ ቡድኑ ጥሩ ዝግጅት ማድረጉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ገልጸዋል። በአፍሪካ ውስጥ ስመ ጥር ከሆኑት ቡድኖች የሆነው የካሜሩን ቡድንም ጠንካራና ልምድ ያላቸው ተጫዋቾች እንደሆኑ እንደሚያውቁ በትናንትናው ዕለት በነበረ ጋዜጣዊ መግለጫ የተናገሩት አሰልጣኝ ውበቱ ሆኖም ቡድናቸው ከዚህ ጨዋታ አንድ ነገር ለማግኘት ዝግጁዎች ነን ብለዋል። ካሜሩን የዘንድሮው አፍሪካ ዋንጫ አዘጋጅ በመሆኗ በዛሬው ዕለትም ኢትዮጵያ የምታደርገው ጨዋታ በደጋፊዎቿ ፊት ከምትጫወት ሃገር ጋር ከመሆኑም ቀላል ባይሆንም "ጥቃቅን ስህተቶችን አስወግደን እስከ መጨረሻው ደቂቃ ድረስ ለመፋለም ዝግጁ ነን።" ይላሉ አሰልጣኙ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ መክፈቻ በነበራት ጨዋታ በኬፕቨርዴ አንድ ለምንም ተረታለች። በዚህ ጨዋታ አንድ ተጫዋች በቀይ ካርድ በመውጣቱ አብዛኛውን የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በአንድ ሰው ጎዶሎ እንደተጫወቱም የጠቀሱት አሰልጣኙ ይህም በዋልያዎቹ ላይ ተፅእኖ ፈጥሯል ብለዋል። "ይህ በተጨዋቾቻችን በአካልና በመንፈስ ጠንካራ እንዳይሆኑ ያደረገ ክስተት ነበር።" ያሉት አሰልጣኝ ውበቱ አክለውም ቡድኑ በጥሩ አቋም ላይ አለ ብለዋል። "ቢሆንም አሁን ወደ አቋማችን ተመልሰናል። ይህንንም በልምምድ ሜዳና በካምፕ ማየት ችለናል። ከዛሬው ጨዋታ የተሻለ ነገር እንደምናገኝ ተስፋ አለኝ።" በማለት አስረድተዋል። ውበቱ አክለው በካሜሩን ጋር በሚኖራቸው ጨዋታ ብሔራዊ ቡድኑ የሚታወቅበትን ጨዋታ ለማሳየት እንደሚሞክሩ ጠቁመዋል። የመጀመሪያው ጨዋታ ለቡድናቸው ፈታኝ እንደነበር ጠቁመው የተሸነፈውም በአንድ ጎል ነው ይላሉ። ቡድናቸው ጎል የተቆጠረበት በመጀመሪያ አጋማሽ መገባደጃ ላይ መሆኑንም ጠቅሰው "ይህ የሆነው በትኩረት ማነስ ሊሆን ይችላል።" ብለዋል። ለዚህም እንደ ማስረጃ የሚያቀርቡት ኢትዮጵያ ያደረገቻቸውን ያለፉትን ስድስ ሰባት ጨዋታዎችን በመጥቀስ ነው። "ያለፉትን ስድስት ሰባት የኢትዮጵያ ጨዋታዎች ብንመለከት ኳስን በመቆጣጠር ከተጋጣሚዎቻችን የተሻልን ነበርን። ጋናን ብናነሳ፣ ደቡብ አፍሪካ አሊያም ዚምባብዌ የተሻለ የኳስ ቁጥጥር ነበረን።" ይላሉ። በመጀመሪያው ጨዋታ ያሬድ ባየህ ቀይ ካርድ ከተመለከተ በኋላ ተቀይሮ የወጣው አማካዩ መሱድ ሞሐመድ ካሜሩንን ብናከብራትም ውጤት ለማግኘት መፋለማችን ግን አይቀርም ብሏል። "ካሜሩን ጠንካራ ቡድን እንደሆነች እናውቃለን። አፍሪካን ወክላ በዓለም ዋንጫ ስትጫወት እኛ ኢትዮጵያዊያን ስንደግፋት ነበር። አልፎም የሳሙዔል ኤቶ ሃገር በመሆኗ ክብር እንሰጣታለን። ነገር ግን ዛሬ ከፈጣሪ ጋር ጥሩ ፍልሚያ እንደምናደርግ አስባለሁ።" ብሏል መሱድ በትናንትናው ዕለት በነበረ ጋዜጣዊ መግለጫ ከቡድኑ አባላት በኮቪድ ምክንያት አሊያም በጉዳት የማይሰለፍ አለ ወይ ተብለው የተጠየቁት አሠልጣኙ ኮቪድን በተለመከተ ተጫዋቾችን ጨምሮ ሁሉም የብሔራዊ ቡድኑ አባላት ከኮቪድ-19 ነፃ መሆናቸውን ተናግረዋል። "ይህ ለኛ መልካም ዜና ነው" ብለዋል ጉዳትን በተመለከተ ለግብፅ ሊግ የሚጨዋተውና ልምድ አላቸው ከሚባሉት ተጫዋቾች አንዱ ሽመልስ በቀለ በጉዳት ምክንያት እንደማይሰለፍ ተናግረዋል። ከሃገር ውጭ ከሚጫወቱት ሁለት ተጫዋቾች አንዱ የሆነው ሽመልስ ከትናንት በስቲያ ጉዳት እንዳጋጠመው አሰልጣኝ ውበቱ ገልጸዋል። "ከሃገር ውጭ ከሚጫወቱ ሁሉት ተጫዎቾቻችን አንዱ ነው። ቢሆንም ልምዱን ልንጠቀምበት አልቻልንም። ከትናንት በስቲያ እንደገና ጉዳት አጋጥሞታል። ከሱ በቀር ሁሉም ተጫዋቾቻችን ለዛሬው ፍልሚያ ዝግጁ ናቸው።" ብለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-59967701
2health
ኮሮናቫይረስ፡ የለንደን ፖሊስ ክልከላዎችን በመተላለፍ ሰልፍ የወጡ ሰዎችን አሰረ
በለንደን ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ የተጣለውን የእንቅስቃሴ ገደብ ለመቃወም ከወጡ ሰዎች መካካል 18 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ አስታወቀ። ውሳኔውን የተቃወሙ በርካታ ሰዎች ከዩናይትድ ኪንግደም ንጉሳውያን መኖሪያ በሆነው ባኪንግሃም ቤተ-መንግስት ፊትለፊት ተሰባስበው ነበር። በመቀጠል ተቃዋሚ ሰልፈኞች ወደ ትራፋልጋር አደባባይ አምርተዋል። ለተቃውሞ የወጡ ሰዎች በኮቪድ ምክንያት የተነጠቅነው ነጻነት ይመለስልን ሲሉ ድምጻቸውን አሰምተዋል። የሜትሮፖሊታን ፖሊስ ተቃዋሚ ሰልፈኞቹ እንዲበተኑ የተደረገ ቢሆንም ዜጎች ግን አሁንም ቢሆን አካላዊ ርቀታቸውን መጠበቅ እንዳለባቸው ማሳሰቢያ ተላልፏል። በዌስትሚኒስተር ድልድይ ላይ ደግሞ ፖሊስ ተቃዋሚ ሰልፈኞችን ለመበተን ጥረት በሚያደርግበት ወቅት አንዳንድ ችግሮች ተፈጥረው ነበር ተብሏል። የፖሊስ አባላት ቀላል የሚባል ጉዳት ደርሶባቸዋል። ፖሊስ ሰልፈኞቹ በቁጥጥር ሥር ያዋልኩት የተለያዩ ሕግጋቶችን በመተላለፍ ነው ብሏል። ከጥፋቶቹ መካከልም የኮሮረናቫይረስ ሕጎችን በመጣስ፣ የአደጋ ጊዜ ሰራተኛ ላይ ጉዳት ማድረስና ነውጠኝነት በዋነኛነት ተጠቃሽ ናቸው። ለንደን በያዝነው ሳምንት ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ ጠበቅ ያሉ ገደቦች ተጥለውባታል። ''ሰዎች በተቃውሞ ሰልፉ ላይ ሲገኙ አካላዊ ርቀታቸውን አለመጠበቃቸውና የተቀመጡ ሕግና ደንቦችን አለማክበራቸው በእጅጉ አሳስቦናል'' ብለዋል የሜርሮፖሊታን ፖሊስ አዛዡ ኮማንደር አዴ አዴሌካን። አክለውም ''የተቃውሞ ሰልፉ አዘጋጆች የሰዎችን ደህንነት ለመጠበቅ በቂ ዝግጅት አላደረጉም። በዚህ ሰአት ነው የህብረተሰቡን ደህንነት ለማረጋገጥ በማሰብ ፖሊሶች የተሰበሰቡትን ሰዎች ለመበተን የተንቀሳቀሱት'' ብለዋል። ''አብዛኛዎቹ የተሰበሰቡት ሰዎች የፖሊስ አባላቱ የነገሯቸውን በመስማታቸውና አካባቢውን ቶሎ በመልቀቃቸው ደስተኞች ነን። ነገር ግን ጥቂቶች ተባባሪ ለመሆን ፈቃደኛ አልነበሩም። ሆነ ብለው ፖሊሶች የሚነግሯቸው ነገር ችላ ሲሉ ነበር። ዌስትሚኒስተር ድልድይንም ዘግተው ነበር'' ብለዋል።
ኮሮናቫይረስ፡ የለንደን ፖሊስ ክልከላዎችን በመተላለፍ ሰልፍ የወጡ ሰዎችን አሰረ በለንደን ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ የተጣለውን የእንቅስቃሴ ገደብ ለመቃወም ከወጡ ሰዎች መካካል 18 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ አስታወቀ። ውሳኔውን የተቃወሙ በርካታ ሰዎች ከዩናይትድ ኪንግደም ንጉሳውያን መኖሪያ በሆነው ባኪንግሃም ቤተ-መንግስት ፊትለፊት ተሰባስበው ነበር። በመቀጠል ተቃዋሚ ሰልፈኞች ወደ ትራፋልጋር አደባባይ አምርተዋል። ለተቃውሞ የወጡ ሰዎች በኮቪድ ምክንያት የተነጠቅነው ነጻነት ይመለስልን ሲሉ ድምጻቸውን አሰምተዋል። የሜትሮፖሊታን ፖሊስ ተቃዋሚ ሰልፈኞቹ እንዲበተኑ የተደረገ ቢሆንም ዜጎች ግን አሁንም ቢሆን አካላዊ ርቀታቸውን መጠበቅ እንዳለባቸው ማሳሰቢያ ተላልፏል። በዌስትሚኒስተር ድልድይ ላይ ደግሞ ፖሊስ ተቃዋሚ ሰልፈኞችን ለመበተን ጥረት በሚያደርግበት ወቅት አንዳንድ ችግሮች ተፈጥረው ነበር ተብሏል። የፖሊስ አባላት ቀላል የሚባል ጉዳት ደርሶባቸዋል። ፖሊስ ሰልፈኞቹ በቁጥጥር ሥር ያዋልኩት የተለያዩ ሕግጋቶችን በመተላለፍ ነው ብሏል። ከጥፋቶቹ መካከልም የኮሮረናቫይረስ ሕጎችን በመጣስ፣ የአደጋ ጊዜ ሰራተኛ ላይ ጉዳት ማድረስና ነውጠኝነት በዋነኛነት ተጠቃሽ ናቸው። ለንደን በያዝነው ሳምንት ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ ጠበቅ ያሉ ገደቦች ተጥለውባታል። ''ሰዎች በተቃውሞ ሰልፉ ላይ ሲገኙ አካላዊ ርቀታቸውን አለመጠበቃቸውና የተቀመጡ ሕግና ደንቦችን አለማክበራቸው በእጅጉ አሳስቦናል'' ብለዋል የሜርሮፖሊታን ፖሊስ አዛዡ ኮማንደር አዴ አዴሌካን። አክለውም ''የተቃውሞ ሰልፉ አዘጋጆች የሰዎችን ደህንነት ለመጠበቅ በቂ ዝግጅት አላደረጉም። በዚህ ሰአት ነው የህብረተሰቡን ደህንነት ለማረጋገጥ በማሰብ ፖሊሶች የተሰበሰቡትን ሰዎች ለመበተን የተንቀሳቀሱት'' ብለዋል። ''አብዛኛዎቹ የተሰበሰቡት ሰዎች የፖሊስ አባላቱ የነገሯቸውን በመስማታቸውና አካባቢውን ቶሎ በመልቀቃቸው ደስተኞች ነን። ነገር ግን ጥቂቶች ተባባሪ ለመሆን ፈቃደኛ አልነበሩም። ሆነ ብለው ፖሊሶች የሚነግሯቸው ነገር ችላ ሲሉ ነበር። ዌስትሚኒስተር ድልድይንም ዘግተው ነበር'' ብለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-54681599
5sports
እንግሊዝ ከአለም ዋንጫ ውድድር ውጭ ስትሆን፣ ፈረንሳይ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፈች
ከፍተኛ ግምት የተሰጣት እንግሊዝ ከአለም ዋንጫ ውድድር ውጭ ሆነች። በኳታሩ አልባይት ስታዲየም ከፈረንሳይ ጋር ትናንት ታህሳስ 1፣ 2015 ዓ.ም ባደረገችው የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ እንግሊዝ ጥሩ እንቅስቃሴ ብታሳይም ወደቀጣዩ ዙር ለማለፍ ተስኗታል። በተለይም የሃሪ ኬን ፍጹም ቅጣት ምት መሳት የእንግሊዝን መሸነፍ ያመላከተ ነበር። ሃሪ ኬን በጨዋታው ላይ ስሪ ላየንስን እኩል ያደረገበትና ለእንግሊዝ 53 ጎሎች በማስቆጠር ክብረወሰን የያዘውን ዋይኒ ሩኒን የተስተካከለበትን ግብ በፍጹም ቅጣት ምት ማስቆጠር ችሎ ነበር። ፈረንሳይ በ17ኛው ደቂቃ በኦሬሊየን ቹአሚኒ ጎል የመሪነቱን ስፍራ ተቆጣጥራ ነበር። እንግሊዝ በጨዋታው የበላይነት ቢኖራትም የተሻሉ የጎል እድሎችን መፍጠር አልቻለችም። ኦሬሊዮን ቹአሚኒ በእንግሊዙ ተጫዋች ቡካዮ ሳካ ላይ ጥፋት በመፈጸሙ የተገኘችውንም የፍጹም ቅጣት ምት ሃሪ ኬን በመምታት ግብ በማስቆጠር እኩል መሆን ችለው ነበር። ጨዋታው ሊጠናቀቅ 12 ደቂቃ ሲቀረው አንትዋን ግሪዝማን ያሻገረለትን ኳስ ኦሊቪየር ጂሩድ በግንባሩ በመግጨት ባስቆጠራት ጎል ፈረንሳይ የመሪነቱን ቦታ ዳግም ተቆናጠጠች። ሆኖም እንግሊዝ ባገኘችው የፍጹም ቅጣት ምት እኩል የምሆንበትን እድል ብታገኝም አባክናዋለች። ፍጹም ቅጣት ምቱን የመታው ኬን ለሃገሩ ታሪክ ለማስመዝገብ እድሉን ቢያገኝም ነገር ግን ባልተለመደ መልኩን ኳሷን ወደላይ ጠልዟት ግቡን ስቷል። በዚህም የእንግሊዝ የአለም ዋንጫ ግስጋሴና ህልም የተገታ ሲሆን ፈረንሳይ ወደቀጣዩ የግማሽ ፍጻሜም አልፋለች። በቀጣዩም ፈረንሳይ ከሞሮኮ ጋር የምትፋለም ይሆናል። የሁለቱ አገራት ብሔራዊ ቡድኖች በተለያዩ የእግር ኳስ ውድድሮች ላይ ተሳታፊ የነበሩ ሲሆን ከዓለም ዋንጫ ውጪ በጥሎ ማለፍ ግጥሚያ ሲገናኙ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። በዓለም ዋንጫም ከአውሮፓውያኑ 1982 ወዲህ በጥሎ ማለፍ ውድድር የተገናኙት በዚህ ጨዋታ ነው።
እንግሊዝ ከአለም ዋንጫ ውድድር ውጭ ስትሆን፣ ፈረንሳይ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፈች ከፍተኛ ግምት የተሰጣት እንግሊዝ ከአለም ዋንጫ ውድድር ውጭ ሆነች። በኳታሩ አልባይት ስታዲየም ከፈረንሳይ ጋር ትናንት ታህሳስ 1፣ 2015 ዓ.ም ባደረገችው የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ እንግሊዝ ጥሩ እንቅስቃሴ ብታሳይም ወደቀጣዩ ዙር ለማለፍ ተስኗታል። በተለይም የሃሪ ኬን ፍጹም ቅጣት ምት መሳት የእንግሊዝን መሸነፍ ያመላከተ ነበር። ሃሪ ኬን በጨዋታው ላይ ስሪ ላየንስን እኩል ያደረገበትና ለእንግሊዝ 53 ጎሎች በማስቆጠር ክብረወሰን የያዘውን ዋይኒ ሩኒን የተስተካከለበትን ግብ በፍጹም ቅጣት ምት ማስቆጠር ችሎ ነበር። ፈረንሳይ በ17ኛው ደቂቃ በኦሬሊየን ቹአሚኒ ጎል የመሪነቱን ስፍራ ተቆጣጥራ ነበር። እንግሊዝ በጨዋታው የበላይነት ቢኖራትም የተሻሉ የጎል እድሎችን መፍጠር አልቻለችም። ኦሬሊዮን ቹአሚኒ በእንግሊዙ ተጫዋች ቡካዮ ሳካ ላይ ጥፋት በመፈጸሙ የተገኘችውንም የፍጹም ቅጣት ምት ሃሪ ኬን በመምታት ግብ በማስቆጠር እኩል መሆን ችለው ነበር። ጨዋታው ሊጠናቀቅ 12 ደቂቃ ሲቀረው አንትዋን ግሪዝማን ያሻገረለትን ኳስ ኦሊቪየር ጂሩድ በግንባሩ በመግጨት ባስቆጠራት ጎል ፈረንሳይ የመሪነቱን ቦታ ዳግም ተቆናጠጠች። ሆኖም እንግሊዝ ባገኘችው የፍጹም ቅጣት ምት እኩል የምሆንበትን እድል ብታገኝም አባክናዋለች። ፍጹም ቅጣት ምቱን የመታው ኬን ለሃገሩ ታሪክ ለማስመዝገብ እድሉን ቢያገኝም ነገር ግን ባልተለመደ መልኩን ኳሷን ወደላይ ጠልዟት ግቡን ስቷል። በዚህም የእንግሊዝ የአለም ዋንጫ ግስጋሴና ህልም የተገታ ሲሆን ፈረንሳይ ወደቀጣዩ የግማሽ ፍጻሜም አልፋለች። በቀጣዩም ፈረንሳይ ከሞሮኮ ጋር የምትፋለም ይሆናል። የሁለቱ አገራት ብሔራዊ ቡድኖች በተለያዩ የእግር ኳስ ውድድሮች ላይ ተሳታፊ የነበሩ ሲሆን ከዓለም ዋንጫ ውጪ በጥሎ ማለፍ ግጥሚያ ሲገናኙ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። በዓለም ዋንጫም ከአውሮፓውያኑ 1982 ወዲህ በጥሎ ማለፍ ውድድር የተገናኙት በዚህ ጨዋታ ነው።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c7215x0grmjo
3politics
የመንግሥት ጣልቃ ገብነት ካለ ከኃላፊነታቸው እንደሚለቁ ኮሚሽነሩ አሳሰቡ
መንግሥት በኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ላይ ጣልቃ የሚገባ ከሆነ ከኃላፊነታቸው በፈቃዳቸው እንደሚለቁ ከቀናት በፊት የኮሚሽኑ ዋና ሰብሳቢ ሆነው የተሰየሙት ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ተናገሩ። የኮሚሽኑ ዋና ሰብሳቢ ይህንን ያሉት የካቲት 16/2014 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን የሥራ መጀመሪያ ትውውቅ ፕሮግራም በተካሄደበት ወቅት መሆኑን ምክር ቤቱ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል። በዚህ ኮሚሽን አባል ሆነው እንዲሰሩ ኃላፊነት የሰጣቸው ሕዝቡ መሆኑን የተናገሩት ዋና ሰብሳቢው ኃላፊነት በተሞላው መንፈስ ለመስራትና ከሚዲያውና ከሌሎች አጋላት ጋር በጋራ እንደሚሰሩም መናገራቸው ተገልጿል። አክለውም ባደረጉት ንግግር የአስፈፃሚው አካል ወይም የመንግሥት ጣልቃ ገብነት እንደማይኖር እምነታቸው መሆኑን ጠቁመዋል። ሆኖም በኮሚሽኑ አሰራር ውስጥ የመንግሥት ጣልቃ ገብነት የሚኖር ከሆነ ግን ኃላፊነታቸውን በፈቃዳቸው እንደሚለቁ ማሳሰባቸውን ከምክር ቤቱ ካገኘነው መግለጫ መረዳት ተችሏል። በአገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ የትውውቅ ፕሮግራም ላይ ንግግር ያደረጉት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ በበኩላቸው ኮሚሽኑ ሥራውን በገለልተኝነት በመስራት የተሰጠውን ሕዝባዊ ኃላፊነት ሊወጣ እንደሚገባም አሳስበዋል። "ፖለቲካ ከአገር በላይ ስላልሆነ" ኮሚሽኑ በኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ መሰረት የተሰጠውን ኃላፊነት ገለልተኛ በመሆን ታሪካዊ ሥራ ሰርቶ ማለፍ እንደሚገባው ማስገንዘባቸው ተገልጿል። በምክክሩ የሚሳተፉት የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደ አንድ አካል ሊታዩ እንደሚገባ ያብራሩት አፈ ጉባኤው የምክክሩ ባለቤት ሕዝቡ በመሆኑም ትክክለኛ ውሳኔ የሚጠበቀውም ከሕዝብ ነው ማለታቸውም ሰፍሯል። በዚህ ትውውቅ ፕሮግራም ላይ ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች ተሞክሮዎችን በማካተት እና በሕዝቡ መካከል በርካታ የባህል ትስስሮች ስላሉ እድሉን ለሕዝቡ መስጠት ይገባል ሲሉ የኮሚሽኑ አባላት መናገራቸው ተገልጿል። በተጨማሪ ሕዝቡን በማወያየት በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ አለመግባባቶች በውይይት በሚፈቱበት ሁኔታም ላይ አበክረው እንደሚሰሩ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ መሠረታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር በማድረግና ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር የሚያስችል ሂደትን የሚመራና የሚያስተባብር አካል ለማቋቋም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አማካይነት ጥቆማ መካሄዱ ይታወሳል። ከጥቂት ወራት በፊት ለሕዝብ በቀረበ ጥሪ መሠረት 632 ዕጩዎች ለኮሚሽኑ አባልነት በተለያዩ ወገኖች ተጠቁመው ከእነዚህ መካከልም ኮሚሽኑን ለማቋቋም በወጣው አዋጅ መስፈርቶች መሠረት 42ቱ ተለይተው ኅብረተሰቡ አስተያየት እንዲሰጥባቸው ዝርዝራቸው ይፋ ሆኖ ነበር። ከዚህ ሂደት በኋላም በተጠቋሚ ዕጩዎቹ ላይ በተዘጋጀው መስፈርት መሠረት ከሕዝብ የሚቀርበው አስተያየት ተገምግሞ የመጨረሻዎቹ 11 ዕጩ ኮሚሽነሮች ተለይተው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቦ እንዲሾሙ አድርጓል። ኮሚሽኑ በአገሪቱ ለዘመናት የቆዩ ናቸው በተባሉ የተለያዩ አወዛጋቢና ጉዳዮች ላይ የሚመለከታቸው ወገኖችንና ኃይሎችን በማቀራረብ ውይይት ተደርጓ መግባባት ላይ እንዲደረስ ለማድረግ የሚያስችሉ ምክክሮችን ይመራል ተብሎ ይጠበቃል። ከሰሞኑ በአገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እንዲሁም የመንግሥታቸው የስድስት ወራት አፈጻጸም በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በበኩላቸው ብሔራዊ ውይይቱና ምክክሩ የሚደረገው በቆሰሉ ታሪኮችና ነገ በምንገነባት ኢትዮጵያ ላይ ፟እንደሆነ "የምንገነባው አገር ከሥልጣናችን በላይ ስለሆነ ነው፤ ለወደፊቱ ትውልድ ስለሆነ ነው" ሲሉም አስረድተዋል። የውይይቱ ሂደት በዋነኝት ሊያካትታቸው የሚገባ ጉዳዮች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህም ግልፅ፣ የሚገለል ማኅበረሰብ የሌለበትና ሁሉንም ሕዝብ አሳታፊ ሊሆን እንደሚገባም አንስተዋል። እንደ ምሳሌ የጠቀሱት በሕገ መንግሥቱ ላይ ያለውን አንቀፅ 39፣ በርካታ ጥያቄ የሚያነሱ ፓርቲዎችን ጉዳይ እንዲሁም የሰንደቅ አላማ ጉዳይን ሲሆን በአሁኑ ወቅት አገሪቱን የሚያከራክሩና የሚያጣሉ ጉዳዮች መቋጫ ሊያገኙ የሚችሉበት ነው ብለዋል። ውይይት የሚያስፈልገው ሽኩቻ፣ ጦርነትና የፖለቲካ ሽግግር ሲኖር መሆኑን ጠቅሰው አገሪቷ እያተዘጋጀችበት ያለችውም ምክክር አራት ምዕራፎች እንዳሉት ጠቅሰዋል። እስካሁን የተካሄደው ቅድመ ዝግጅት ሲሆን እስካሁን ያለው ብሔርና ፆታን ባሳተፈ መልኩ የተዋቀረ በመሆኑ ጥሩ ጅማሮ ነው ብለዋል። "በውይይትና በድርድር የሚፈታ ችግር ካለ መንግሥት ለማንም በሩ ክፍት ነው። እኛ የምንጠላው የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የሚነካ ሲሆን ነው" ብለዋል።
የመንግሥት ጣልቃ ገብነት ካለ ከኃላፊነታቸው እንደሚለቁ ኮሚሽነሩ አሳሰቡ መንግሥት በኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ላይ ጣልቃ የሚገባ ከሆነ ከኃላፊነታቸው በፈቃዳቸው እንደሚለቁ ከቀናት በፊት የኮሚሽኑ ዋና ሰብሳቢ ሆነው የተሰየሙት ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ተናገሩ። የኮሚሽኑ ዋና ሰብሳቢ ይህንን ያሉት የካቲት 16/2014 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን የሥራ መጀመሪያ ትውውቅ ፕሮግራም በተካሄደበት ወቅት መሆኑን ምክር ቤቱ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል። በዚህ ኮሚሽን አባል ሆነው እንዲሰሩ ኃላፊነት የሰጣቸው ሕዝቡ መሆኑን የተናገሩት ዋና ሰብሳቢው ኃላፊነት በተሞላው መንፈስ ለመስራትና ከሚዲያውና ከሌሎች አጋላት ጋር በጋራ እንደሚሰሩም መናገራቸው ተገልጿል። አክለውም ባደረጉት ንግግር የአስፈፃሚው አካል ወይም የመንግሥት ጣልቃ ገብነት እንደማይኖር እምነታቸው መሆኑን ጠቁመዋል። ሆኖም በኮሚሽኑ አሰራር ውስጥ የመንግሥት ጣልቃ ገብነት የሚኖር ከሆነ ግን ኃላፊነታቸውን በፈቃዳቸው እንደሚለቁ ማሳሰባቸውን ከምክር ቤቱ ካገኘነው መግለጫ መረዳት ተችሏል። በአገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ የትውውቅ ፕሮግራም ላይ ንግግር ያደረጉት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ በበኩላቸው ኮሚሽኑ ሥራውን በገለልተኝነት በመስራት የተሰጠውን ሕዝባዊ ኃላፊነት ሊወጣ እንደሚገባም አሳስበዋል። "ፖለቲካ ከአገር በላይ ስላልሆነ" ኮሚሽኑ በኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ መሰረት የተሰጠውን ኃላፊነት ገለልተኛ በመሆን ታሪካዊ ሥራ ሰርቶ ማለፍ እንደሚገባው ማስገንዘባቸው ተገልጿል። በምክክሩ የሚሳተፉት የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደ አንድ አካል ሊታዩ እንደሚገባ ያብራሩት አፈ ጉባኤው የምክክሩ ባለቤት ሕዝቡ በመሆኑም ትክክለኛ ውሳኔ የሚጠበቀውም ከሕዝብ ነው ማለታቸውም ሰፍሯል። በዚህ ትውውቅ ፕሮግራም ላይ ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች ተሞክሮዎችን በማካተት እና በሕዝቡ መካከል በርካታ የባህል ትስስሮች ስላሉ እድሉን ለሕዝቡ መስጠት ይገባል ሲሉ የኮሚሽኑ አባላት መናገራቸው ተገልጿል። በተጨማሪ ሕዝቡን በማወያየት በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ አለመግባባቶች በውይይት በሚፈቱበት ሁኔታም ላይ አበክረው እንደሚሰሩ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ መሠረታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር በማድረግና ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር የሚያስችል ሂደትን የሚመራና የሚያስተባብር አካል ለማቋቋም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አማካይነት ጥቆማ መካሄዱ ይታወሳል። ከጥቂት ወራት በፊት ለሕዝብ በቀረበ ጥሪ መሠረት 632 ዕጩዎች ለኮሚሽኑ አባልነት በተለያዩ ወገኖች ተጠቁመው ከእነዚህ መካከልም ኮሚሽኑን ለማቋቋም በወጣው አዋጅ መስፈርቶች መሠረት 42ቱ ተለይተው ኅብረተሰቡ አስተያየት እንዲሰጥባቸው ዝርዝራቸው ይፋ ሆኖ ነበር። ከዚህ ሂደት በኋላም በተጠቋሚ ዕጩዎቹ ላይ በተዘጋጀው መስፈርት መሠረት ከሕዝብ የሚቀርበው አስተያየት ተገምግሞ የመጨረሻዎቹ 11 ዕጩ ኮሚሽነሮች ተለይተው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቦ እንዲሾሙ አድርጓል። ኮሚሽኑ በአገሪቱ ለዘመናት የቆዩ ናቸው በተባሉ የተለያዩ አወዛጋቢና ጉዳዮች ላይ የሚመለከታቸው ወገኖችንና ኃይሎችን በማቀራረብ ውይይት ተደርጓ መግባባት ላይ እንዲደረስ ለማድረግ የሚያስችሉ ምክክሮችን ይመራል ተብሎ ይጠበቃል። ከሰሞኑ በአገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እንዲሁም የመንግሥታቸው የስድስት ወራት አፈጻጸም በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በበኩላቸው ብሔራዊ ውይይቱና ምክክሩ የሚደረገው በቆሰሉ ታሪኮችና ነገ በምንገነባት ኢትዮጵያ ላይ ፟እንደሆነ "የምንገነባው አገር ከሥልጣናችን በላይ ስለሆነ ነው፤ ለወደፊቱ ትውልድ ስለሆነ ነው" ሲሉም አስረድተዋል። የውይይቱ ሂደት በዋነኝት ሊያካትታቸው የሚገባ ጉዳዮች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህም ግልፅ፣ የሚገለል ማኅበረሰብ የሌለበትና ሁሉንም ሕዝብ አሳታፊ ሊሆን እንደሚገባም አንስተዋል። እንደ ምሳሌ የጠቀሱት በሕገ መንግሥቱ ላይ ያለውን አንቀፅ 39፣ በርካታ ጥያቄ የሚያነሱ ፓርቲዎችን ጉዳይ እንዲሁም የሰንደቅ አላማ ጉዳይን ሲሆን በአሁኑ ወቅት አገሪቱን የሚያከራክሩና የሚያጣሉ ጉዳዮች መቋጫ ሊያገኙ የሚችሉበት ነው ብለዋል። ውይይት የሚያስፈልገው ሽኩቻ፣ ጦርነትና የፖለቲካ ሽግግር ሲኖር መሆኑን ጠቅሰው አገሪቷ እያተዘጋጀችበት ያለችውም ምክክር አራት ምዕራፎች እንዳሉት ጠቅሰዋል። እስካሁን የተካሄደው ቅድመ ዝግጅት ሲሆን እስካሁን ያለው ብሔርና ፆታን ባሳተፈ መልኩ የተዋቀረ በመሆኑ ጥሩ ጅማሮ ነው ብለዋል። "በውይይትና በድርድር የሚፈታ ችግር ካለ መንግሥት ለማንም በሩ ክፍት ነው። እኛ የምንጠላው የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የሚነካ ሲሆን ነው" ብለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-60504072
5sports
ኢትዮጵያ ለአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ አለፈች
ኢትዮጵያ በዚህ ዓመት የምእራብ አፍሪካ አገሯ ካሜሮን ለምታዘጋጀው የአፍሪካ እግረ ኳስ ዋንጫ ማለፏ አረጋገጠች። ኢትዯጵያ ለአፍኮን 2021 ያለፈችው ከስምንት ዓመት በኋላ ነው። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የሚገኝበት ምድብ ወስጥ ያሉት የኒጀርና የማዳጋስካር አቻ መውጣታቸውን ተከትሎ ነው 9 ነጥብ በመያዝ ወደ አፍሪካ ዋንጫ መቀላቀሉን ያረጋገጠው። ዛሬ በምድብ ኬ የሚገኙት ኢትዮጵያ ኮትዲቯርና ማዳጋስካር ኒጀር የመጨረሻ ቀሪ ጨዋታቸውን አካሄደው ነበር። በዚህ ውጤት መሰረት ኢትዮጵያና ኮትዲቯር ባደረጉት ጨዋታ ኮትዲቯር ሦስት ለአንድ ኢትዮጵያን እየመራች ሳለ በዳኛው ሕመም ምክንያት ጨዋታው ተቋርጧል። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ማለፏን ያረጋገጠችው በተመሳሳይ ምድብ የሚገኙት ማዳጋስካርና ኒጀር ባዶ ለባዶ መለያየታቸውን ተከትሎ ነው። ሰባት ነጥብ የነበራት ማዳጋስካር ለአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ኒጀርን አሸንፋ 9 ነጥብ ያላትን ኢትዮጵያን መብለጥ ይጠበቅባት ነበር። የዋሊያዎቹን ድል ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድም የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። በሚቀጥለው ዓመት ታኅሣሥ ወር ላይ በካሜሮን አዘጋጅነት በሚካሄደው የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር ላይ 24 አገራት ተሳታፊ ይሆናሉ። እስካሁን ድረስ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ጊኒ፣ አልጄሪያ፣ ዚምባብዌ፣ ሴኔጋል፣ ቱኒዚያ፣ ማሊ፣ ግብጽ፣ ኮሞሮስ፣ ቡርኪናፋሶ፣ ማላዊ፣ጋና ፣ሱዳን ፣ጋምብቢ፣ ሞሮኮ እና ጋቦን ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።
ኢትዮጵያ ለአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ አለፈች ኢትዮጵያ በዚህ ዓመት የምእራብ አፍሪካ አገሯ ካሜሮን ለምታዘጋጀው የአፍሪካ እግረ ኳስ ዋንጫ ማለፏ አረጋገጠች። ኢትዯጵያ ለአፍኮን 2021 ያለፈችው ከስምንት ዓመት በኋላ ነው። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የሚገኝበት ምድብ ወስጥ ያሉት የኒጀርና የማዳጋስካር አቻ መውጣታቸውን ተከትሎ ነው 9 ነጥብ በመያዝ ወደ አፍሪካ ዋንጫ መቀላቀሉን ያረጋገጠው። ዛሬ በምድብ ኬ የሚገኙት ኢትዮጵያ ኮትዲቯርና ማዳጋስካር ኒጀር የመጨረሻ ቀሪ ጨዋታቸውን አካሄደው ነበር። በዚህ ውጤት መሰረት ኢትዮጵያና ኮትዲቯር ባደረጉት ጨዋታ ኮትዲቯር ሦስት ለአንድ ኢትዮጵያን እየመራች ሳለ በዳኛው ሕመም ምክንያት ጨዋታው ተቋርጧል። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ማለፏን ያረጋገጠችው በተመሳሳይ ምድብ የሚገኙት ማዳጋስካርና ኒጀር ባዶ ለባዶ መለያየታቸውን ተከትሎ ነው። ሰባት ነጥብ የነበራት ማዳጋስካር ለአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ኒጀርን አሸንፋ 9 ነጥብ ያላትን ኢትዮጵያን መብለጥ ይጠበቅባት ነበር። የዋሊያዎቹን ድል ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድም የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። በሚቀጥለው ዓመት ታኅሣሥ ወር ላይ በካሜሮን አዘጋጅነት በሚካሄደው የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር ላይ 24 አገራት ተሳታፊ ይሆናሉ። እስካሁን ድረስ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ጊኒ፣ አልጄሪያ፣ ዚምባብዌ፣ ሴኔጋል፣ ቱኒዚያ፣ ማሊ፣ ግብጽ፣ ኮሞሮስ፣ ቡርኪናፋሶ፣ ማላዊ፣ጋና ፣ሱዳን ፣ጋምብቢ፣ ሞሮኮ እና ጋቦን ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-56582175
2health
ቬትናም የመጀመሪያውን የኮቪድ-19 ሞት መዘገበች
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመቆጣጠር በምታደርገው ጥረት የምትመሰገነው እስያዊቷ አገር ቬትናም የመጀመሪያውን የኮቪድ -19 ሞት መዘገበች። ይህም እስካሁን በቫይረሱ ሳቢያ ሞት ላልመዘገበችው ቬትናም አሳዛኝ ክስተት ሆኗል። በበሽታው የሞቱት የ70 ዓመቱ ግለሰብ ከሆይ አን ከምትባል ግዛት መሆናቸውንም የአገሪቷ ሚዲያ ዘግቧል። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በዳ ናንግ ሪዞርት አቅራቢያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ከመመዝገባቸው በፊት ከሦስት ወራት ለሚበልጥ ጊዜ በአገሪቷ አዲስ በቫይረሱ የተያዘ ሰው አልነበረም። 95 ሚሊየን ሕዝብ ያላት ቬትናም፤ ወረርሽኙ ከጀመረ አንስቶ እስካሁን 509 በቫይረሱ ተይዘውባታል። ይህም ከሌሎች አገራት ጋር ሲነፃፀር ዝቅተኛ ቁጥር ነው። በእርግጥ አገሪቷ ከሌሎች አገራት በተለየ ቫይረሱን ለመከላከል እርምጃ መውሰድ የጀመረችው አንድም በቫይረሱ የተያዘ ሰው ሳይኖር ነበር። ድንበሮቿንም ወደ አገራቸው ከሚገቡ ዜጎቿ በስተቀር ለተጓዦች ዝግ ያደረገችው ቀድማ ነበር። ከዚህም ባሻገር ወደ አገሪቷ የሚገባ ማንኛውም ግለሰብ መንግሥት ባዘጋጀው ለይቶ ማቆያ ለ14 ቀናት መቆየትና መመርመር ግድ ነው። እነዚህ የጥንቃቄ እርምጃዎችም ውጤት አሳይተው ከሚያዚያ ወር አጋማሽ ጀምሮ በአገሪቷ አዲስ በቫይረሱ የተያዘ ሰው አልነበረም። በዚህ በወቅት በሽታውን ለመቆጣጠር ባደረገችው ጥረት እንዲሁም በቫይረሱ ተይዞ ሁለት ወራትን በሞት አፋፍ ላይ ሆኖ ላሳለፈው ስኮትላንዳዊ አብራሪ ላደረገችው እንክብካቤም አድናቆት ተችሯታል። ይሁን እንጂ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በታዋቂው ዳ ናንግ ሪዞርት አዳዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የመገኘታቸው አሳዛኝ ዜና ተሰምቷል። በዚህ ወቅትም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የአገሪቷ ጎብኝዎች በከተማዋ ውስጥ ነበሩ ተብሏል። መንግሥት ረቡዕ ዕለት በከተማዋ ሙሉ ለሙሉ የእንቅስቃሴ ገደብ ከመጣሉ በፊትም ከተማዋን ለጎብኝዎች ዝግ አድርጎ ነበር። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በዳ ናንግ የተከሰተውን ወረርሽኝ ተከትሎም ጠቅላይ ሚኒስተር ጉየን ዡዋን ፑክ "ወረርሽኙን ለመቆጣጠር በፍጥነትና በትጋት እርምጃ መውሰድ አለብን" በማለት በአገሪቷ ያሉ ግዛቶችና ከተሞችን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማስጠንቀቃቸውን የመንግሥት ሚዲያ ዘግቧል።
ቬትናም የመጀመሪያውን የኮቪድ-19 ሞት መዘገበች የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመቆጣጠር በምታደርገው ጥረት የምትመሰገነው እስያዊቷ አገር ቬትናም የመጀመሪያውን የኮቪድ -19 ሞት መዘገበች። ይህም እስካሁን በቫይረሱ ሳቢያ ሞት ላልመዘገበችው ቬትናም አሳዛኝ ክስተት ሆኗል። በበሽታው የሞቱት የ70 ዓመቱ ግለሰብ ከሆይ አን ከምትባል ግዛት መሆናቸውንም የአገሪቷ ሚዲያ ዘግቧል። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በዳ ናንግ ሪዞርት አቅራቢያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ከመመዝገባቸው በፊት ከሦስት ወራት ለሚበልጥ ጊዜ በአገሪቷ አዲስ በቫይረሱ የተያዘ ሰው አልነበረም። 95 ሚሊየን ሕዝብ ያላት ቬትናም፤ ወረርሽኙ ከጀመረ አንስቶ እስካሁን 509 በቫይረሱ ተይዘውባታል። ይህም ከሌሎች አገራት ጋር ሲነፃፀር ዝቅተኛ ቁጥር ነው። በእርግጥ አገሪቷ ከሌሎች አገራት በተለየ ቫይረሱን ለመከላከል እርምጃ መውሰድ የጀመረችው አንድም በቫይረሱ የተያዘ ሰው ሳይኖር ነበር። ድንበሮቿንም ወደ አገራቸው ከሚገቡ ዜጎቿ በስተቀር ለተጓዦች ዝግ ያደረገችው ቀድማ ነበር። ከዚህም ባሻገር ወደ አገሪቷ የሚገባ ማንኛውም ግለሰብ መንግሥት ባዘጋጀው ለይቶ ማቆያ ለ14 ቀናት መቆየትና መመርመር ግድ ነው። እነዚህ የጥንቃቄ እርምጃዎችም ውጤት አሳይተው ከሚያዚያ ወር አጋማሽ ጀምሮ በአገሪቷ አዲስ በቫይረሱ የተያዘ ሰው አልነበረም። በዚህ በወቅት በሽታውን ለመቆጣጠር ባደረገችው ጥረት እንዲሁም በቫይረሱ ተይዞ ሁለት ወራትን በሞት አፋፍ ላይ ሆኖ ላሳለፈው ስኮትላንዳዊ አብራሪ ላደረገችው እንክብካቤም አድናቆት ተችሯታል። ይሁን እንጂ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በታዋቂው ዳ ናንግ ሪዞርት አዳዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የመገኘታቸው አሳዛኝ ዜና ተሰምቷል። በዚህ ወቅትም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የአገሪቷ ጎብኝዎች በከተማዋ ውስጥ ነበሩ ተብሏል። መንግሥት ረቡዕ ዕለት በከተማዋ ሙሉ ለሙሉ የእንቅስቃሴ ገደብ ከመጣሉ በፊትም ከተማዋን ለጎብኝዎች ዝግ አድርጎ ነበር። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በዳ ናንግ የተከሰተውን ወረርሽኝ ተከትሎም ጠቅላይ ሚኒስተር ጉየን ዡዋን ፑክ "ወረርሽኙን ለመቆጣጠር በፍጥነትና በትጋት እርምጃ መውሰድ አለብን" በማለት በአገሪቷ ያሉ ግዛቶችና ከተሞችን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማስጠንቀቃቸውን የመንግሥት ሚዲያ ዘግቧል።
https://www.bbc.com/amharic/53610860
3politics
ሴኔቱ ዶናልድ ትራምፕ ላይ ክስ የመመስረቱ ሂደት ሕገ መንግሥታዊ ነው አለ
የአሜሪካ ሴኔት የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ላይ ክስ መመስረቱ ሕገ መንግሥታዊ ነው በማለት የክስ ሂደቱን አስቀጠለ። የትራምፕ ጠበቆች በበኩላቸው ዶናልድ ትራምፕ ዋይት ሃውስን ከለቀቁ በኋላ መሰል ክስ ሊቀርብባቸው አይችልም ሲሉ ተከራክረዋል። ይሁን እንጂ 56-44 በሆነ የድምጽ ብልጫ የቀድሞ ፕሬዝደንት ላይ ክስ የመመስረቱ ሂደት ድጋፍ አግኝቷል። ዶናልድ ትራምፕ ባሳለፍነው ወር ደጋፊዎቻቸው በካፒቶል ሂላ ላይ ጉዳት እንዲያደርሱ አመጽ ቀስቅሰዋል በሚል እየተወነጀሉ ነው። ትራምፕ ምንም አይነት ማረጋገጫ ሳያቀርቡ ምርጫው ተጭበርብሯል ሲሉ መቆየታቸው ይታወሳል። ትራምፕን እየከሰሱ የሚገኙት ዲሞክራቶች ሂድቱን በኤግዚቢትነት ያቀረቧቸውን ተንቀሳቃሽ ምስሎች በማሳየት ጀምረዋል። በተንቀሳቃሽ ምሰሉ ትራምፕ ደጋፊዎቻቸው ወደ ካፒቶል ሂል እንዲሄዱ 'ሲያነሳሱ' እና በሺዎች የሚቆጠሩ የትራምፕ ደጋፊዎች ካፒቶል ሂልን ሰብረው ሲገቡ፤ በንብረት እና በጸጥታ አስከባሪዎች ላይ ጉዳት ሲያደርሱ ያሳያል። ዴሞክራቶች ባቀረቡት ተንቀሳቃሽ ምስል ላይ ትራምፕ ደጋፊዎቻቸው 'እስከመጨረሻው እንዲታገሉ' መልዕክት ሲያስተላልፉ፤ ይህን ተከትሎም በካፒቶል ሂል ላይ ጉዳት ሲደርስ አስመልክተዋል። ዲሞክራቱ ጄሚ ራስኪን፤ ይህ ተግባር ትራምፕን በወንጀል ማስጠየቅ አለበት ብለው ተከራክረዋል። "ይህ የአሜሪካ የወደፊት እጣ መሆን የለበት። በመንግሥታችን ላይ አመጽ የሚቀሰቅስ ፕሬዝደንት ሊኖረን አይገባም" ብለዋል። የቀድሞ ፕሬዝደንት ትራምፕ ጠበቆች በበኩላቸው፤ ዶናልድ ትራምፕን በዚህ ሂደት ውስጥ ማሳለፍ ሕገ መንግሥታዊ አይደለም በማለት ተከራክረዋል። ዲሞክራቶችም ይህን እያደረጉ ያሉት ፖለቲካዊ ፍላጎታቸውን ለማሳካት ነው ብለዋል። 56-44 የሚለው የድምጽ ውጤት ስድስት የትራምፕ ፓርቲ አባላት የሆኑ ሪፐብሊካኖች ከዲሞክራቶች ጎን በመሆን ድምጽ መስጠታቸውን ያመላክታል። በትራምፕ ላይ ክስ ለመመስረት 100 መቀመጫ ባሉት ሴኔት ውስጥ 2/3ኛ ድጋፍ ያስፈልጋል። ትራምፕ ላይ ክስ እንዲመሰረት ከተወሰነ ዶናልድ ትራምፕ ወደፊት የፖለቲካ ተሳትፎ አድርገው ስልጣን እንዳይዙ ሊደረጉ ይችላሉ። በትራምፕ ላይ ክስ እንዲመሰረት የሚጠይቁት ዴሞክራቶችም ሆኑ የትራምፕ ጠበቆች ለአንድ ተጨማሪ ቀን መከራከሪያ ነጥቦቻቸውን ማቅረባቸውን ይቀጥላሉ። በሴናተሮች በኩል ለሚነሱ ጥያቄዎች ዴሞክራቶች እና የትራምፕ ጠበቆች ምላሽ ይሰጣሉ። ዴሞክራቶቹ የዓይን ምስክሮችንም ቃል ሊያሰሙ ይችላሉ። እስከ መጪው ሰኞ ድረስ ትራምፕ ክስ እንዲመሰረትባቸው አልያም ነጻ እንዲወጡ ሴኔቱ ውሳኔ ማስተላለፉ አይቀርም ተብሏል።
ሴኔቱ ዶናልድ ትራምፕ ላይ ክስ የመመስረቱ ሂደት ሕገ መንግሥታዊ ነው አለ የአሜሪካ ሴኔት የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ላይ ክስ መመስረቱ ሕገ መንግሥታዊ ነው በማለት የክስ ሂደቱን አስቀጠለ። የትራምፕ ጠበቆች በበኩላቸው ዶናልድ ትራምፕ ዋይት ሃውስን ከለቀቁ በኋላ መሰል ክስ ሊቀርብባቸው አይችልም ሲሉ ተከራክረዋል። ይሁን እንጂ 56-44 በሆነ የድምጽ ብልጫ የቀድሞ ፕሬዝደንት ላይ ክስ የመመስረቱ ሂደት ድጋፍ አግኝቷል። ዶናልድ ትራምፕ ባሳለፍነው ወር ደጋፊዎቻቸው በካፒቶል ሂላ ላይ ጉዳት እንዲያደርሱ አመጽ ቀስቅሰዋል በሚል እየተወነጀሉ ነው። ትራምፕ ምንም አይነት ማረጋገጫ ሳያቀርቡ ምርጫው ተጭበርብሯል ሲሉ መቆየታቸው ይታወሳል። ትራምፕን እየከሰሱ የሚገኙት ዲሞክራቶች ሂድቱን በኤግዚቢትነት ያቀረቧቸውን ተንቀሳቃሽ ምስሎች በማሳየት ጀምረዋል። በተንቀሳቃሽ ምሰሉ ትራምፕ ደጋፊዎቻቸው ወደ ካፒቶል ሂል እንዲሄዱ 'ሲያነሳሱ' እና በሺዎች የሚቆጠሩ የትራምፕ ደጋፊዎች ካፒቶል ሂልን ሰብረው ሲገቡ፤ በንብረት እና በጸጥታ አስከባሪዎች ላይ ጉዳት ሲያደርሱ ያሳያል። ዴሞክራቶች ባቀረቡት ተንቀሳቃሽ ምስል ላይ ትራምፕ ደጋፊዎቻቸው 'እስከመጨረሻው እንዲታገሉ' መልዕክት ሲያስተላልፉ፤ ይህን ተከትሎም በካፒቶል ሂል ላይ ጉዳት ሲደርስ አስመልክተዋል። ዲሞክራቱ ጄሚ ራስኪን፤ ይህ ተግባር ትራምፕን በወንጀል ማስጠየቅ አለበት ብለው ተከራክረዋል። "ይህ የአሜሪካ የወደፊት እጣ መሆን የለበት። በመንግሥታችን ላይ አመጽ የሚቀሰቅስ ፕሬዝደንት ሊኖረን አይገባም" ብለዋል። የቀድሞ ፕሬዝደንት ትራምፕ ጠበቆች በበኩላቸው፤ ዶናልድ ትራምፕን በዚህ ሂደት ውስጥ ማሳለፍ ሕገ መንግሥታዊ አይደለም በማለት ተከራክረዋል። ዲሞክራቶችም ይህን እያደረጉ ያሉት ፖለቲካዊ ፍላጎታቸውን ለማሳካት ነው ብለዋል። 56-44 የሚለው የድምጽ ውጤት ስድስት የትራምፕ ፓርቲ አባላት የሆኑ ሪፐብሊካኖች ከዲሞክራቶች ጎን በመሆን ድምጽ መስጠታቸውን ያመላክታል። በትራምፕ ላይ ክስ ለመመስረት 100 መቀመጫ ባሉት ሴኔት ውስጥ 2/3ኛ ድጋፍ ያስፈልጋል። ትራምፕ ላይ ክስ እንዲመሰረት ከተወሰነ ዶናልድ ትራምፕ ወደፊት የፖለቲካ ተሳትፎ አድርገው ስልጣን እንዳይዙ ሊደረጉ ይችላሉ። በትራምፕ ላይ ክስ እንዲመሰረት የሚጠይቁት ዴሞክራቶችም ሆኑ የትራምፕ ጠበቆች ለአንድ ተጨማሪ ቀን መከራከሪያ ነጥቦቻቸውን ማቅረባቸውን ይቀጥላሉ። በሴናተሮች በኩል ለሚነሱ ጥያቄዎች ዴሞክራቶች እና የትራምፕ ጠበቆች ምላሽ ይሰጣሉ። ዴሞክራቶቹ የዓይን ምስክሮችንም ቃል ሊያሰሙ ይችላሉ። እስከ መጪው ሰኞ ድረስ ትራምፕ ክስ እንዲመሰረትባቸው አልያም ነጻ እንዲወጡ ሴኔቱ ውሳኔ ማስተላለፉ አይቀርም ተብሏል።
https://www.bbc.com/amharic/news-55976634
3politics
የሚንስትሮች ምክር ቤት 'ሕወሓት እና ሸኔ' በሽብርተኛነት እንዲሰየሙ የውሳኔ ሐሳብ አስተላለፈ
የሚንስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) እና ሸኔ በሽብርተኛነት እንዲሰየሙ የውሳኔ ሐሳብ ማስተላለፉን የጠቅላይ ሚንስትሩ ጸ/ቤት አስታወቀ። ሁለቱ ቡድኖች ባለፉት ሦስት ዓመታት የመጣውን ለውጥ ለመቀልበስ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል በሰላማዊ ዜጎች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች ሲፈጸሙ ቆይተዋል ብሏል ጸ/ቤቱ። "በዚህም የበርካታ ዜጎች ሕይወት ጠፍቷል፣ አካላቸው ጎድሏል፤ ንብረታቸው ወድሟል፤ ከቀዬአቸውም ተፈናቅለዋል። ጥቃቶቹ ህብረተሰቡ ቀጣይነት ባለው ሥጋት እና ፍርሐት ውስጥ እንዲኖር በማድረግ በመንግሥት ላይ እምነት እንዲያጣ፣ ዜጎች እርስ በእርስ እንዳይተማመኑ አድርጓ።" "እነዚህ ሁሉ የሀገረ መንግሥቱን ህልውና አደጋ ላይ ለመጣል ታቅደው ሲፈጸሙ የነበሩ መሆኑን ከተለያዩ ማስረጃዎች ለመረዳት ተችሏል" ብሏል በመግለጫው። የጠቅላይ ሚንስቴሩ ጸ/ቤት በተለያዩ አካባቢዎች ሲፈጸሙ የቆዩት ጥቃቶች በተለያዩ አካላት ቢፈጸሙም "በዕቅድ፤ በገንዘብ፣ በሐሳብ እና በሰው ኃይል ሥልጠና በመደገፍ፤ የሚዲያ ሽፋን እና እገዛ በመስጠት ረገድ የመሪነት ሚናውን ሲጫወቱ የነበሩ ቡድኖች አሉ" ብሏል። "ኢትዮጵያን የማመሰቃቀል፤ የማዳከም እና የማፍረስ ፍላጎት ያላቸው" ናቸው ያላቸው 'የውጭ ኃይሎች' ቡድኖቹን እየተጠቀሙባቸው ነው ሲልም አስታውቋል። "ድርጅቶቹ ሲፈጸሙና ሲያስፈጽሙ የቆዩዋቸው የጥፋት ተግባራት የሽብር ወንጀል ተግባራት ናቸው። እነዚህ ተግባራት የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በወጣው አወጅ 1176/2012 አንቀጽ 3 ሥር ስለሽብር የወንጀል ድርጊት የተሰጠውን ትርጓሜ ሙሉ ለሙሉ የሚያሟሉ ተግባራት እንደሆኑ በቀላሉ ለመገንዘብ ይቻላል" ብሏል። የሽብር ተግባራቱን የፈጽሙ ድርጅቶች አባላትና እና ደጋፊዎቻቸውን በግለሰብ ደረጃ በተናጠል በሽብር ወንጀል ተጠያቂ ከማድረግ "ድርጅቶቹን የሽብርተኛ ድርጅት አድርጎ በመሰየም በሕጉ በተቀመጠው አግባብ የሽብር ወንጀል ድርጊትን በተሻለ ሁኔታ ለመቆጣጠር እና ለመከላከል ይችላል" ብሏል በመግለጫ። የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በወጣው አዋጅ ቁጥር 1176/2012 አንቀጽ 18 እና 19 በመጥቀስ "ሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕወሓት)" እና "ሸኔ" የሽብር ወንጀልን ዓላማቸው አድርገው የሚንቀሳቀሱ በመሆኑና የድርጅቶቹ የሥራ አመራር ወይም ውሳኔ ሰጭ አካላት ወንጀሉን አምነው የተቀበሉት ወይም አፈጻጸሙን እየመሩት በመሆኑ፤ የሽብር ተግባር መፈጸምም የድርጅቶቹ ጠቅላላ መገለጫ በመሆኑ፤ ድርጅቶቹ በሽብርተኛ ድርጅትነት እንዲሰየሙ የውሳኔ ሐሳብ ቀርቧል" ብሏል። የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በወጣው ዐዋጅ ቁጥር 1176/2012 አንቀጽ 23 መሠረትም "በተመሳሳይ ተግባር በተሰማሩ እና በዚህ ውሳኔ ሐሳብ መሠረት ከተሰየሙት የሽብርተኛ ድርጅቶች ጋር ትብብር፤ ትሥሥር ወይም የሐሳብ እና የተግባር ዝምድና ያላቸው ድርጅቶችና ግለሰቦች ላይም ይህ ውሳኔ ሐሳብ ተፈጻሚ ይሆናል" ሲል አጠናቋል።
የሚንስትሮች ምክር ቤት 'ሕወሓት እና ሸኔ' በሽብርተኛነት እንዲሰየሙ የውሳኔ ሐሳብ አስተላለፈ የሚንስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) እና ሸኔ በሽብርተኛነት እንዲሰየሙ የውሳኔ ሐሳብ ማስተላለፉን የጠቅላይ ሚንስትሩ ጸ/ቤት አስታወቀ። ሁለቱ ቡድኖች ባለፉት ሦስት ዓመታት የመጣውን ለውጥ ለመቀልበስ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል በሰላማዊ ዜጎች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች ሲፈጸሙ ቆይተዋል ብሏል ጸ/ቤቱ። "በዚህም የበርካታ ዜጎች ሕይወት ጠፍቷል፣ አካላቸው ጎድሏል፤ ንብረታቸው ወድሟል፤ ከቀዬአቸውም ተፈናቅለዋል። ጥቃቶቹ ህብረተሰቡ ቀጣይነት ባለው ሥጋት እና ፍርሐት ውስጥ እንዲኖር በማድረግ በመንግሥት ላይ እምነት እንዲያጣ፣ ዜጎች እርስ በእርስ እንዳይተማመኑ አድርጓ።" "እነዚህ ሁሉ የሀገረ መንግሥቱን ህልውና አደጋ ላይ ለመጣል ታቅደው ሲፈጸሙ የነበሩ መሆኑን ከተለያዩ ማስረጃዎች ለመረዳት ተችሏል" ብሏል በመግለጫው። የጠቅላይ ሚንስቴሩ ጸ/ቤት በተለያዩ አካባቢዎች ሲፈጸሙ የቆዩት ጥቃቶች በተለያዩ አካላት ቢፈጸሙም "በዕቅድ፤ በገንዘብ፣ በሐሳብ እና በሰው ኃይል ሥልጠና በመደገፍ፤ የሚዲያ ሽፋን እና እገዛ በመስጠት ረገድ የመሪነት ሚናውን ሲጫወቱ የነበሩ ቡድኖች አሉ" ብሏል። "ኢትዮጵያን የማመሰቃቀል፤ የማዳከም እና የማፍረስ ፍላጎት ያላቸው" ናቸው ያላቸው 'የውጭ ኃይሎች' ቡድኖቹን እየተጠቀሙባቸው ነው ሲልም አስታውቋል። "ድርጅቶቹ ሲፈጸሙና ሲያስፈጽሙ የቆዩዋቸው የጥፋት ተግባራት የሽብር ወንጀል ተግባራት ናቸው። እነዚህ ተግባራት የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በወጣው አወጅ 1176/2012 አንቀጽ 3 ሥር ስለሽብር የወንጀል ድርጊት የተሰጠውን ትርጓሜ ሙሉ ለሙሉ የሚያሟሉ ተግባራት እንደሆኑ በቀላሉ ለመገንዘብ ይቻላል" ብሏል። የሽብር ተግባራቱን የፈጽሙ ድርጅቶች አባላትና እና ደጋፊዎቻቸውን በግለሰብ ደረጃ በተናጠል በሽብር ወንጀል ተጠያቂ ከማድረግ "ድርጅቶቹን የሽብርተኛ ድርጅት አድርጎ በመሰየም በሕጉ በተቀመጠው አግባብ የሽብር ወንጀል ድርጊትን በተሻለ ሁኔታ ለመቆጣጠር እና ለመከላከል ይችላል" ብሏል በመግለጫ። የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በወጣው አዋጅ ቁጥር 1176/2012 አንቀጽ 18 እና 19 በመጥቀስ "ሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕወሓት)" እና "ሸኔ" የሽብር ወንጀልን ዓላማቸው አድርገው የሚንቀሳቀሱ በመሆኑና የድርጅቶቹ የሥራ አመራር ወይም ውሳኔ ሰጭ አካላት ወንጀሉን አምነው የተቀበሉት ወይም አፈጻጸሙን እየመሩት በመሆኑ፤ የሽብር ተግባር መፈጸምም የድርጅቶቹ ጠቅላላ መገለጫ በመሆኑ፤ ድርጅቶቹ በሽብርተኛ ድርጅትነት እንዲሰየሙ የውሳኔ ሐሳብ ቀርቧል" ብሏል። የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በወጣው ዐዋጅ ቁጥር 1176/2012 አንቀጽ 23 መሠረትም "በተመሳሳይ ተግባር በተሰማሩ እና በዚህ ውሳኔ ሐሳብ መሠረት ከተሰየሙት የሽብርተኛ ድርጅቶች ጋር ትብብር፤ ትሥሥር ወይም የሐሳብ እና የተግባር ዝምድና ያላቸው ድርጅቶችና ግለሰቦች ላይም ይህ ውሳኔ ሐሳብ ተፈጻሚ ይሆናል" ሲል አጠናቋል።
https://www.bbc.com/amharic/56954704
3politics
ሰሜን ኮሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ የባህር ድንበርን ያቋረጠ ሚሳኤል ተኮሰች
ሰሜን ኮሪያ ከጎረቤቷን ደቡብ ኮሪያ ጋር የሚለያትን የባህር ድንበር አቋርጣ ሚሳኤል ተኩሳለች። ይህም ሀገሪቱ ባህረ ገብ መሬቱን ከተካፈሉት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። የተተኮሰው የአጭር ርቀት ባለስቲክ ሚሳኤል በደቡብ ኮርያ ሶኮቾ ከተባለች ከተማ 60 ኪሎ ሜትር ርቆ በሚገኝ ስፍራ ላይ አርፏል። ይህም ደቡብ ኮሪያ ኡሌንጉዶ በተባለው ደሴቷ የሚገኘው አየር ሃይሏ በተጠንቀቅ እንዲቆም ያደረገ ነው። ደቡብ ኮሪያ በአጸፋው ሶስት ሚሳኤሎችን አከታትላ ተኩሳለች። የደቡብ ኮሪያው ፕሬዝዳንት ዩን ሱክይሉ የፒዮንግኣንግን ድርጊት “የድንበር ወረራ” ስትል ጠርታዋለች። ሰሜን ኮሪያ ዛሬ ጠዋት ቢያንስ 10 ሚሳኤሎችን እንደተኮሰች የደቡብ ኮሪያ ጦር አስታውቋል። ቀጥሎም ጦሩ ሶስት ከአየር ወደ ምድር የሚተኮሱ ሚሳኤሎችን ወደ ሰሜን በአጸፋ እንደተኮሰ አስታውቋል። ጦሩ “ በሰሜን ኮሪያ የሚፈጸሙ እንዲህ አይነት ጽብ አጫሪ ድርጊቶችን አይታገስም። በደቡብ ኮሪያ እና አሜሪካ መካከል ባለው ትብብር ጥብቅ ምላሽ ይሰጣል” ብሏል። የደቡብ ኮሪያው ፕሬዝዳንት ዩን ሱክይሉ ለተፈጸመው ጸብ አጫሪ ድርጊት ፈጣን ምላሽ እንዲሰጥ ማዘዛቸውም ተጠቁሟል። ሰሜን ኮሪያን ድርጊት ተከትሎ ደቡብ ኮሪያ እና ጃፓን ብሄራዊ የድህንነት ምክክር ጠርተዋል። ሁለቱ ሀገራት የድንበር ወሰን ያቋረጠውን ሚሳኤል ጨምሮ የተተኮሱ ሚሳኤሎችን መዝግበዋል። ወሰኑን ያቋረጠ ሌላ ሚሳኤል ከደቡብ ኮሪያዋ ምስራቃዊ ከተማ ሶኬቾ 57 ኪሎ ሜትር ርቀት እና በሰሜን ምዕራብ ከምትገኘው ኦልንጎዴ ደሴት 167 ኪሎ ሜትር ርቀት ውሃማ አካል ላይ አርፏል። ይህ ድርጊት “እጅግ ያልተለመደ እና ተቀባይነት የሌለው” ሲሉ የተናገሩት የጥምር ጦር ዘመቻው መሪ ካንግ ሺንቹል ባህረገብ መሬቱ ከተከፈለ በኋላ በግዛት ውስጥ ላለ የውሃ አካል የቀረበ ተኩስ መሆኑን ተናግረዋል። ሰሜን ኮሪያ ሚሳኤሎቹን ከማስወንጨፏ ቀድም ብሎ ፒዮንግያንግ አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ ከባህረ ገቡ መሬት አቅራቢያ የሚያደርጉትን የጋራ ልምምድ እንዲያቆሙ አስጠንቅቃ ነበር። ትላንትና ሰሜን ኮሪያ ጥምር ጦሩ ልምምዱን የማያቆም ከሆነ “ሃይለኛ” እርምጃ እንደምትወስድ ዝታ ነበር። ፒዮንግያንግ ባለፈው ወር አሜሪካ፥ ደቡብ ኮሪያ እና ጃፓን ላደረጉት የጋራ ወታደራዊ ልምምድ አጸፋ ሚሳኤል ተኩሳ ነበር። ይህ ተኩስ ወደ ደቡብ ኮሪያ የተደረገ የኒውክሌር ጥቃት “አምሳያ” ነው ትብሏል።
ሰሜን ኮሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ የባህር ድንበርን ያቋረጠ ሚሳኤል ተኮሰች ሰሜን ኮሪያ ከጎረቤቷን ደቡብ ኮሪያ ጋር የሚለያትን የባህር ድንበር አቋርጣ ሚሳኤል ተኩሳለች። ይህም ሀገሪቱ ባህረ ገብ መሬቱን ከተካፈሉት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። የተተኮሰው የአጭር ርቀት ባለስቲክ ሚሳኤል በደቡብ ኮርያ ሶኮቾ ከተባለች ከተማ 60 ኪሎ ሜትር ርቆ በሚገኝ ስፍራ ላይ አርፏል። ይህም ደቡብ ኮሪያ ኡሌንጉዶ በተባለው ደሴቷ የሚገኘው አየር ሃይሏ በተጠንቀቅ እንዲቆም ያደረገ ነው። ደቡብ ኮሪያ በአጸፋው ሶስት ሚሳኤሎችን አከታትላ ተኩሳለች። የደቡብ ኮሪያው ፕሬዝዳንት ዩን ሱክይሉ የፒዮንግኣንግን ድርጊት “የድንበር ወረራ” ስትል ጠርታዋለች። ሰሜን ኮሪያ ዛሬ ጠዋት ቢያንስ 10 ሚሳኤሎችን እንደተኮሰች የደቡብ ኮሪያ ጦር አስታውቋል። ቀጥሎም ጦሩ ሶስት ከአየር ወደ ምድር የሚተኮሱ ሚሳኤሎችን ወደ ሰሜን በአጸፋ እንደተኮሰ አስታውቋል። ጦሩ “ በሰሜን ኮሪያ የሚፈጸሙ እንዲህ አይነት ጽብ አጫሪ ድርጊቶችን አይታገስም። በደቡብ ኮሪያ እና አሜሪካ መካከል ባለው ትብብር ጥብቅ ምላሽ ይሰጣል” ብሏል። የደቡብ ኮሪያው ፕሬዝዳንት ዩን ሱክይሉ ለተፈጸመው ጸብ አጫሪ ድርጊት ፈጣን ምላሽ እንዲሰጥ ማዘዛቸውም ተጠቁሟል። ሰሜን ኮሪያን ድርጊት ተከትሎ ደቡብ ኮሪያ እና ጃፓን ብሄራዊ የድህንነት ምክክር ጠርተዋል። ሁለቱ ሀገራት የድንበር ወሰን ያቋረጠውን ሚሳኤል ጨምሮ የተተኮሱ ሚሳኤሎችን መዝግበዋል። ወሰኑን ያቋረጠ ሌላ ሚሳኤል ከደቡብ ኮሪያዋ ምስራቃዊ ከተማ ሶኬቾ 57 ኪሎ ሜትር ርቀት እና በሰሜን ምዕራብ ከምትገኘው ኦልንጎዴ ደሴት 167 ኪሎ ሜትር ርቀት ውሃማ አካል ላይ አርፏል። ይህ ድርጊት “እጅግ ያልተለመደ እና ተቀባይነት የሌለው” ሲሉ የተናገሩት የጥምር ጦር ዘመቻው መሪ ካንግ ሺንቹል ባህረገብ መሬቱ ከተከፈለ በኋላ በግዛት ውስጥ ላለ የውሃ አካል የቀረበ ተኩስ መሆኑን ተናግረዋል። ሰሜን ኮሪያ ሚሳኤሎቹን ከማስወንጨፏ ቀድም ብሎ ፒዮንግያንግ አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ ከባህረ ገቡ መሬት አቅራቢያ የሚያደርጉትን የጋራ ልምምድ እንዲያቆሙ አስጠንቅቃ ነበር። ትላንትና ሰሜን ኮሪያ ጥምር ጦሩ ልምምዱን የማያቆም ከሆነ “ሃይለኛ” እርምጃ እንደምትወስድ ዝታ ነበር። ፒዮንግያንግ ባለፈው ወር አሜሪካ፥ ደቡብ ኮሪያ እና ጃፓን ላደረጉት የጋራ ወታደራዊ ልምምድ አጸፋ ሚሳኤል ተኩሳ ነበር። ይህ ተኩስ ወደ ደቡብ ኮሪያ የተደረገ የኒውክሌር ጥቃት “አምሳያ” ነው ትብሏል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c2xz2z2n8m6o
2health
በቱርክ የድንጋይ ከሰል ማውጫ ላይ በተከሰተ ፍንዳታ 40 ሰዎች ሲሞቱ፣ 11 ቆሰሉ
በሰሜናዊ ቱርክ ውስጥ በሚገኝ አንድ የድንጋይ ከሰል ማውጫ ላይ በተከሰተ ፍንዳታ 40 ሰዎች መሞታቸውን የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ አስታወቁ። የቱርክ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሱሌይማን ሶይሉ እንዳሉት ከአደጋው ስፍራ 58 ሰዎችን በሕይወት ማትረፍ ሲቻል፣ 11 ደግሞ የመቁሰል አደጋ ሲደርስባቸው አንድ ሰው የደረሰበት አልታወቀም። በጥቁር ባሕር ዳርቻ በምትገኘው አምሳራ በምትባለው ስፍራ አርብ ዕለት በድንጋይ ከሰል ማውጫ ላይ ፍንዳታው ሲከሰት 110 ሰዎች በስፍራው ነበሩ። ሁሉም ቢያንስ ከምድር በታች 300 ሜትር ወርደው እየሠሩ ነበር። በፍንዳታው ከመሬት በታች የተቀበሩ ሰዎችን ከዋሻው ለማውጣት የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ሌሊቱን ሙሉ ቁፋሮ ሲያካሂዱ ነበር ያደሩት። የድንጋይ ከሰል አውጭ ሠራተኞች በጥቁር ጭስ ተሸፍነው እና ዐይናቸው ቀልቶ ወደ ሕክምና መስጫ ሲወሰዱ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምሥል ወጥቷል። የሠራተኞቹ ቤተሰቦች እና ወዳጆች ሠራተኞቹ ከዋሻው እስከሚወጡ በቦታው ሲጠባበቁም ታይቷል። የአገር ውስጥ ሚኒስትሩ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት፣ በተካሄደው ፍለጋ 40 አስከሬኖች የተገኙ ሲሆን 58 ሠራተኞች በራሳቸው እና በነፍስ አድን ሠራተኞች ከማዕድን ጉድጓዱ ወጥተዋል፤ በዚህም “ግዙፉ የነፍስ አድን ሥራ ወደ መጠናቀቁ ተቃርቧል” ብለዋል። ፍንዳታው ከመሬት 300 ሜትር ጥልቀት ላይ እንደተከሰተ ይታመናል። እስካሁን የፍንዳታው መንስኤ ምን እንደሆነ ባይታወቅም፣ የቱርክ ዐቃቤ ሕግ ቢሮ ምርመራ ጀምሯል። የቱርክ የኢነርጂ ሚኒስትር እንዳሉት፣ በድንጋይ ከሰል ማውጫ ውስጥ ተቀጣጣይ ኬሚካል በመፍጠር በሚታወቀው ፋየርዳምፕ ሳቢያ ፍንዳታው ተከስቶ ሊሆን ይችላል። ፍንዳታው የተከሰው አንድ ጊዜ እንደሆነም ገልጸዋል። ፕሬዝዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶዋን አደጋው የተከሰተበት ባርቲን ግዛትን ዛሬ ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። የአማስራ ግዛት ከንቲባ ሬሳይ ካኪር፣ ከፍንዳታው የተረፉ ሰዎች ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ገልጸዋል። አንድ ከፍንዳታው የተረፈ ሠራተኛ “ጭስ እና አቧራ አካባቢውን ሞልቶት ነበር። ምን እንደተከሰተ አልገባንም” ብሏል። የድንጋይ ከሰል ማውጫው በቱርክ መንግሥት የሚተዳደር ነው። በአገሪቱ የከፋ የድንጋይ ከሰል ማውጫ ቦታ አደጋ የተከሰተው እአአ በ2014 ሲሆን 301 ሰዎች ሞተዋል።
በቱርክ የድንጋይ ከሰል ማውጫ ላይ በተከሰተ ፍንዳታ 40 ሰዎች ሲሞቱ፣ 11 ቆሰሉ በሰሜናዊ ቱርክ ውስጥ በሚገኝ አንድ የድንጋይ ከሰል ማውጫ ላይ በተከሰተ ፍንዳታ 40 ሰዎች መሞታቸውን የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ አስታወቁ። የቱርክ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሱሌይማን ሶይሉ እንዳሉት ከአደጋው ስፍራ 58 ሰዎችን በሕይወት ማትረፍ ሲቻል፣ 11 ደግሞ የመቁሰል አደጋ ሲደርስባቸው አንድ ሰው የደረሰበት አልታወቀም። በጥቁር ባሕር ዳርቻ በምትገኘው አምሳራ በምትባለው ስፍራ አርብ ዕለት በድንጋይ ከሰል ማውጫ ላይ ፍንዳታው ሲከሰት 110 ሰዎች በስፍራው ነበሩ። ሁሉም ቢያንስ ከምድር በታች 300 ሜትር ወርደው እየሠሩ ነበር። በፍንዳታው ከመሬት በታች የተቀበሩ ሰዎችን ከዋሻው ለማውጣት የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ሌሊቱን ሙሉ ቁፋሮ ሲያካሂዱ ነበር ያደሩት። የድንጋይ ከሰል አውጭ ሠራተኞች በጥቁር ጭስ ተሸፍነው እና ዐይናቸው ቀልቶ ወደ ሕክምና መስጫ ሲወሰዱ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምሥል ወጥቷል። የሠራተኞቹ ቤተሰቦች እና ወዳጆች ሠራተኞቹ ከዋሻው እስከሚወጡ በቦታው ሲጠባበቁም ታይቷል። የአገር ውስጥ ሚኒስትሩ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት፣ በተካሄደው ፍለጋ 40 አስከሬኖች የተገኙ ሲሆን 58 ሠራተኞች በራሳቸው እና በነፍስ አድን ሠራተኞች ከማዕድን ጉድጓዱ ወጥተዋል፤ በዚህም “ግዙፉ የነፍስ አድን ሥራ ወደ መጠናቀቁ ተቃርቧል” ብለዋል። ፍንዳታው ከመሬት 300 ሜትር ጥልቀት ላይ እንደተከሰተ ይታመናል። እስካሁን የፍንዳታው መንስኤ ምን እንደሆነ ባይታወቅም፣ የቱርክ ዐቃቤ ሕግ ቢሮ ምርመራ ጀምሯል። የቱርክ የኢነርጂ ሚኒስትር እንዳሉት፣ በድንጋይ ከሰል ማውጫ ውስጥ ተቀጣጣይ ኬሚካል በመፍጠር በሚታወቀው ፋየርዳምፕ ሳቢያ ፍንዳታው ተከስቶ ሊሆን ይችላል። ፍንዳታው የተከሰው አንድ ጊዜ እንደሆነም ገልጸዋል። ፕሬዝዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶዋን አደጋው የተከሰተበት ባርቲን ግዛትን ዛሬ ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። የአማስራ ግዛት ከንቲባ ሬሳይ ካኪር፣ ከፍንዳታው የተረፉ ሰዎች ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ገልጸዋል። አንድ ከፍንዳታው የተረፈ ሠራተኛ “ጭስ እና አቧራ አካባቢውን ሞልቶት ነበር። ምን እንደተከሰተ አልገባንም” ብሏል። የድንጋይ ከሰል ማውጫው በቱርክ መንግሥት የሚተዳደር ነው። በአገሪቱ የከፋ የድንጋይ ከሰል ማውጫ ቦታ አደጋ የተከሰተው እአአ በ2014 ሲሆን 301 ሰዎች ሞተዋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c6pxz1ge16wo
3politics
ቻይና በኤርትራ ላይ የተጣለውን ማዕቀብ አወገዘች
በኤርትራ የሁለት ቀናት ጉብኝት ያደረጉት የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ በኤርትራ ላይ የተጣለውን ማዕቀብ አወገዙ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በአንድ ፓርቲ በብቸኝነት በምትተዳደረውና በምዕራባውያን ዘንድ በተገለለችው ኤርትራ ያደረጉትን ጉብኝታቸውን ረቡዕ ከሰዓት በኋላ አጠናቀዋል። ዋንግ ከኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር መወያየታቸውን እና "ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን" ለማጠናከር ፕሬዝዳንቱ በቻይና ጉብኝት እንዲያደርጉ መጋበዛቸውንም የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረ መስቀል በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል። የሁለቱ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ከስብሰባው በኋላ በጋራ በሰጡት መግለጫ "በዲሞክራሲና በሰብአዊ መብት ሰበብ በሌሎች አገራት የውስጥ ጉዳይ የሚደረግ ጣልቃገብነትን" አውግዘዋል። "ቻይና በኤርትራ ላይ የተጣለውን ማንኛውንም ማዕቀብ ትቃወማለች" ማለታቸውም ተገልጿል። በኢትዮጵያ ውስጥ ካለው ጦርነት ጋር በተያያዘ የአሜሪካ መንግሥት በአራት የኤርትራ ተቋማትና በሁለት ኤርትራውያን ላይ በያዝነው ዓመት ማዕቀብ ጥሏል። ማዕቀቡ የኢትዮጵያን መረጋጋትና አንድነት እያናጋ ነው ባለው ቀውስና ግጭት ውስጥ አስተዋጽኦ አላቸው ያላቸውን የኤርትራ ተቋማትና ዜጎችን ኢላማ ያደረገ መሆኑን የአሜሪካ የፌደራል ግምጃ ቤት በወቅቱ አመልክቷል። በዚህም መሠረት ዕቀባው የተጣለባቸው ተቋማት የኤርትራ መከላከያ ኃይል፣ የኤርትራ ገዢ ፓርቲ ህዝባዊ ግንባር ለዴሞክራሲና ለፍትህ፣ ህድሪ ትረስ እና ሬድ ሲ ትሬዲንግ ኮርፖሬሽን ሲሆኑ ግለሰቦቹ ደግሞ አብረሃ ካሳ ነማሪያም እና ሐጎስ ገብረሕይወት ወልደኪዳን የተባሉት ናቸው። ኅዳር ወር መጨረሻ አካባቢ በኢትዮጵያ ጉብኝት አድርገው የነበሩት የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በተመሳሳይ በኢትዮጵያ ላይ የሚደረግ ጣልቃ ገብነትን ተቃውመዋል። "ኢትዮጵያውያን ውስጣዊ ችግሮቻቸውን መፍታት ስለሚችሉ ቻይና በኢትዮጵያ ውስጣዊ ጉዳዮች ጣልቃ ገብነትን ትቃወማለች" ማለታቸውንም የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በወቅቱ አስታውቋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የአዲስ አበባ ጉብኝታቸውንም በተመለከተ ቻይና በኢትዮጵያ ላይ ያላትን መተማመን እንደሚያሳይ እና ቻይና ለጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት ያላትን ድጋፍ የሚገልጽ ነው ማለታቸውም የሚታወስ ነው። ቻይና በቅርብ ወራት በተለይ ደግሞ ከትግራዩ ጦርነት ጋር በተያያዘ ለኢትዮጵያ መንግሥት በተለያዩ መድረኮች ላይ ድጋፏን ስትገልጽ ቆይታለች። የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባል የሆነችው ቻይና፤ የፀጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ መክሮ የውሳኔ ሐሳብ እንዳያወጣ ሲቃወሙ ከነበሩ አገራት መካከል አንዷ ነች። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኤርትራው ጉብኝታቸው በተጨማሪ ቻይና ለአገሪቱ የምትሰጠውን የ100 ሚሊዮን ዩዋን ተጨማሪ ድጋፍ ማስታወቃቸውንም የማነ በትዊተር ገጻቸው ጠቅሰዋል። ፕሬዚዳንት ኢሳያስ በበኩላቸው ቻይና በባለፉት 100 ዓመታት ላስመዘገበችው ትልቅ እድገት እንዲሁም ለቻይና ሕዝቦች እና ለዓለም ሁሉ ያበረከተችውን አስተዋፅኦ አድንቀው መናገራቸውም ተገልጿል። ከዚህ በተጨማሪ ቻይና ዓለም አቀፍ ሕግን በማክበር ላይ የተመሰረተ ሚዛናዊ የሆነ ዓለም አቀፋዊ ሥርዓት እንዲመጣ ላበረከተችው ጉልህ ሚናም አመስግነዋል ተብሏል። የቻይናው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ከኤርትራ ጉዟቸው ተከትሎ ለሁለት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ረቡዕ ኬንያ ናይሮቢ የገቡ ሲሆን በቆይታቸው፣ ከአገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር በመገናኘት በተለያዩ መስኮች የትብብር ስምምነቶችን እንደሚፈርሙ ይጠበቃል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከኬንያ በኋላ ቀጣይ ጉብኝታቸውን ለማድረግ ወደ ሕንድ ውቅያኖሷ ደሴት ኮሞሮስ ያቀናሉ ተብሏል።
ቻይና በኤርትራ ላይ የተጣለውን ማዕቀብ አወገዘች በኤርትራ የሁለት ቀናት ጉብኝት ያደረጉት የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ በኤርትራ ላይ የተጣለውን ማዕቀብ አወገዙ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በአንድ ፓርቲ በብቸኝነት በምትተዳደረውና በምዕራባውያን ዘንድ በተገለለችው ኤርትራ ያደረጉትን ጉብኝታቸውን ረቡዕ ከሰዓት በኋላ አጠናቀዋል። ዋንግ ከኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር መወያየታቸውን እና "ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን" ለማጠናከር ፕሬዝዳንቱ በቻይና ጉብኝት እንዲያደርጉ መጋበዛቸውንም የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረ መስቀል በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል። የሁለቱ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ከስብሰባው በኋላ በጋራ በሰጡት መግለጫ "በዲሞክራሲና በሰብአዊ መብት ሰበብ በሌሎች አገራት የውስጥ ጉዳይ የሚደረግ ጣልቃገብነትን" አውግዘዋል። "ቻይና በኤርትራ ላይ የተጣለውን ማንኛውንም ማዕቀብ ትቃወማለች" ማለታቸውም ተገልጿል። በኢትዮጵያ ውስጥ ካለው ጦርነት ጋር በተያያዘ የአሜሪካ መንግሥት በአራት የኤርትራ ተቋማትና በሁለት ኤርትራውያን ላይ በያዝነው ዓመት ማዕቀብ ጥሏል። ማዕቀቡ የኢትዮጵያን መረጋጋትና አንድነት እያናጋ ነው ባለው ቀውስና ግጭት ውስጥ አስተዋጽኦ አላቸው ያላቸውን የኤርትራ ተቋማትና ዜጎችን ኢላማ ያደረገ መሆኑን የአሜሪካ የፌደራል ግምጃ ቤት በወቅቱ አመልክቷል። በዚህም መሠረት ዕቀባው የተጣለባቸው ተቋማት የኤርትራ መከላከያ ኃይል፣ የኤርትራ ገዢ ፓርቲ ህዝባዊ ግንባር ለዴሞክራሲና ለፍትህ፣ ህድሪ ትረስ እና ሬድ ሲ ትሬዲንግ ኮርፖሬሽን ሲሆኑ ግለሰቦቹ ደግሞ አብረሃ ካሳ ነማሪያም እና ሐጎስ ገብረሕይወት ወልደኪዳን የተባሉት ናቸው። ኅዳር ወር መጨረሻ አካባቢ በኢትዮጵያ ጉብኝት አድርገው የነበሩት የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በተመሳሳይ በኢትዮጵያ ላይ የሚደረግ ጣልቃ ገብነትን ተቃውመዋል። "ኢትዮጵያውያን ውስጣዊ ችግሮቻቸውን መፍታት ስለሚችሉ ቻይና በኢትዮጵያ ውስጣዊ ጉዳዮች ጣልቃ ገብነትን ትቃወማለች" ማለታቸውንም የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በወቅቱ አስታውቋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የአዲስ አበባ ጉብኝታቸውንም በተመለከተ ቻይና በኢትዮጵያ ላይ ያላትን መተማመን እንደሚያሳይ እና ቻይና ለጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት ያላትን ድጋፍ የሚገልጽ ነው ማለታቸውም የሚታወስ ነው። ቻይና በቅርብ ወራት በተለይ ደግሞ ከትግራዩ ጦርነት ጋር በተያያዘ ለኢትዮጵያ መንግሥት በተለያዩ መድረኮች ላይ ድጋፏን ስትገልጽ ቆይታለች። የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባል የሆነችው ቻይና፤ የፀጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ መክሮ የውሳኔ ሐሳብ እንዳያወጣ ሲቃወሙ ከነበሩ አገራት መካከል አንዷ ነች። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኤርትራው ጉብኝታቸው በተጨማሪ ቻይና ለአገሪቱ የምትሰጠውን የ100 ሚሊዮን ዩዋን ተጨማሪ ድጋፍ ማስታወቃቸውንም የማነ በትዊተር ገጻቸው ጠቅሰዋል። ፕሬዚዳንት ኢሳያስ በበኩላቸው ቻይና በባለፉት 100 ዓመታት ላስመዘገበችው ትልቅ እድገት እንዲሁም ለቻይና ሕዝቦች እና ለዓለም ሁሉ ያበረከተችውን አስተዋፅኦ አድንቀው መናገራቸውም ተገልጿል። ከዚህ በተጨማሪ ቻይና ዓለም አቀፍ ሕግን በማክበር ላይ የተመሰረተ ሚዛናዊ የሆነ ዓለም አቀፋዊ ሥርዓት እንዲመጣ ላበረከተችው ጉልህ ሚናም አመስግነዋል ተብሏል። የቻይናው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ከኤርትራ ጉዟቸው ተከትሎ ለሁለት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ረቡዕ ኬንያ ናይሮቢ የገቡ ሲሆን በቆይታቸው፣ ከአገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር በመገናኘት በተለያዩ መስኮች የትብብር ስምምነቶችን እንደሚፈርሙ ይጠበቃል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከኬንያ በኋላ ቀጣይ ጉብኝታቸውን ለማድረግ ወደ ሕንድ ውቅያኖሷ ደሴት ኮሞሮስ ያቀናሉ ተብሏል።
https://www.bbc.com/amharic/59884251
5sports
አሜሪካ የቅርጫት ኳስ ጀግናዋን ለማስፈታት ‘የሞት ነጋዴውን’ ከእስር ፈታች
ሩሲያና አሜሪካ ወራትን ባስቆጠረ ድርድር የተሳካ የእስረኛ ልውውጥ አድርገዋል። በቅርጫት ኳስ የኦሎምፒክ ጀግና የሆነችው አሜሪካዊቷ ብሪትኒ ግራይነር ላለፉት 9 ወራት በሩሲያ እስር ቤት ቆይታ ነበር። የአሜሪካ መንግሥት ይህችን ዝነኛ ለማስፈታት ከፍተኛ የደኅንነት ሰዎችን ያሳተፈ ድርድር ሲካሄድ ቆይቶ በመጨረሻ ተሳክቶለታል። ሩሲያ ይቺን የቅርጫት ኳስ ጀግና የምቀይረው በቪክቶር ቡት ብቻ ነው በማለቷ ይኸው ተፈጻሚ ሆኗል። ቪክቶር ቡት ሩሲያዊ ዜጋ ሲሆን እጅግ አደገኛ የተባለ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ ነጋዴና አዘዋዋሪ ነው። ሆሊውድ በርሱ ሕይወት ላይ ‘ሎርድ ኦፍ ዎር’ የተሰኘ ፊልም እስከመሥራት ደርሷል። ቪክተር ቡት ላለፉት 12 ዓመታት በአሜሪካ እስር ቤት ነበር። 25 ዓመታት ጽኑ እስር ተፈርዶበት የነበረው ይህ ዓለም አቀፍ የሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ ነጋዴ ቡት በመጨረሻ ዝነኛዋን ቅርጫት ኳስ ተጫዋች ብሪትኒ ግራይነርን ለማስፈታት ሲባል ተለቋል። ሁለቱ እስረኞችን ለማስፈታት ሁለት  የግል አውሮፕላኖች ከሞስኮና ከዋሺንግተን እስረኞችን ይዘው ወደ አቡ ዳቢ የበረሩ ሲሆን በአቡዳቢ አየር ማረፊያ እስረኞቹ ሲለዋወጡ የሚያሳይ ቪዲዮ ወጥቷል። የእስረኛ ልውውጡ እንዲሰምር የሳኡዲው ልዑል መሐመድ ቢን ሰልማንና የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ፕሬዝዳንት መሐመድ ቢን ዛይድ አል ነህያን ሁነኛ ሚና ተጫውተዋል ነው የተባለው። በተለይ ከፑቲን ጋር ጥብቅ ወዳጅ ናቸው የሚባሉት ልዑል ቢን ሰልማን ከዚህ የእስረⶉች ልውውጥ በሻገር የዩክሬንና የሩሲያ የጦር ምርኮኞችን ልውውጥ ያሳለጡ ሰው እንደሆኑ ይነገራል። ጆ ባይደን የእስረኛ ልውውጡ ተደርጎ ብሪትኒ ወደ አገሯ አሜሪካ በማቅናት ላይ ሳለች ከዋይት ሐውስ በሰጡት አጭር መግለጫ “ጀግኒትን በስልክ አወራኋት። ጥሩ ስሜት ላይ ናት። ለማገገም ጊዜ ያሻት ይሆናል’ ሲሉ ለአሜሪካዊያን እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል። የዚች ቅርጫት ኳስ ተጫዋች የፍቅር አጋር የሆነችው ቼሬል ግራይነር “ባለቤቴ በመፈታቷ ወደር የሌለው ደስታ ተሰምቶኛል’ ብላለች። በተመሳሳይ ‘የሞት ነጋዴው’ በሚል ቅጽል የሚታወቀው ቪክቶር ቦት ሞስኮ መድረሱ ተሰምቷል። ቦት ሞስኮ ሲደርስ ለሩሲያ ብሔራዊ ቴሌቪዥን እንደተናገረው፣ "ድንገት ሌሊት ላይ መጥተው ተነስ ሻንጣህን ሸክፍ አሉኝ፤ በቃ ይኸው ነው” ብሏል። ቦት ከአውሮፕላኑ ደረጃዎች ሲወርድ እቅፍ አበባ ለእናቱና ለባለቤቱ ሲያበረክት ታይቷል። ይህ ግለሰብ የዛሬ 12 ዓመት አካባቢ ነበር በአሜሪካ ደኅንነቶች ሲታደን ቆይቶ በታይላንድ ዋና ከተማ ባንኮክ በቁጥጥር ሥር የዋለው። ቦት ሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያን ለድሃ አገራትና ለአሸባሪዎች በማስተላለፍ የሩሲያ ቀኝ እጅ ነበር ትላለች አሜሪካ። ሩሲያ ይህ ሰው በአሜሪካ በቁጥጥር ሥር መዋሉ አበሳጭቷት ቆይቷል። የቅርጫት ኳስ ተጫዋቿ ግራይነር በበኩሏ በቁጥጥር ሥር የዋለችው በሞስኮ አየር መንገድ የካናቢስ ዘይት በሻንጣዋ ይዛ በመገኘቷ ነበር። ይህቺን አሜሪካዊት ለማስፈታት ድርድር ሲጀመር አሜሪካ የቀድሞውን የባሕር ኃይል ባልደረባ ፖል ዊላንን ከርሷ ጋር አብሮ እንዲፈታላት ጠይቃ ነበር። ነገር ግን ሩሲያ ይህን ሰው ለመልቀቅ አልፈቀደችም። ፖል የታሰረው በፈረንጆች 2008 ለአሜሪካ ሲሰልል በመገኘቱ ነው። የ32 ዓመቷ ብሪትኒ ግራይነር በቅርጫት ኳስ የሁለት ጊዜ የኦሎምፒክ አሸናፊ ለፊኒክስ ሜርኩሪ የምትጫወት ዕውቅ ስፖርተኛ ናት።
አሜሪካ የቅርጫት ኳስ ጀግናዋን ለማስፈታት ‘የሞት ነጋዴውን’ ከእስር ፈታች ሩሲያና አሜሪካ ወራትን ባስቆጠረ ድርድር የተሳካ የእስረኛ ልውውጥ አድርገዋል። በቅርጫት ኳስ የኦሎምፒክ ጀግና የሆነችው አሜሪካዊቷ ብሪትኒ ግራይነር ላለፉት 9 ወራት በሩሲያ እስር ቤት ቆይታ ነበር። የአሜሪካ መንግሥት ይህችን ዝነኛ ለማስፈታት ከፍተኛ የደኅንነት ሰዎችን ያሳተፈ ድርድር ሲካሄድ ቆይቶ በመጨረሻ ተሳክቶለታል። ሩሲያ ይቺን የቅርጫት ኳስ ጀግና የምቀይረው በቪክቶር ቡት ብቻ ነው በማለቷ ይኸው ተፈጻሚ ሆኗል። ቪክቶር ቡት ሩሲያዊ ዜጋ ሲሆን እጅግ አደገኛ የተባለ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ ነጋዴና አዘዋዋሪ ነው። ሆሊውድ በርሱ ሕይወት ላይ ‘ሎርድ ኦፍ ዎር’ የተሰኘ ፊልም እስከመሥራት ደርሷል። ቪክተር ቡት ላለፉት 12 ዓመታት በአሜሪካ እስር ቤት ነበር። 25 ዓመታት ጽኑ እስር ተፈርዶበት የነበረው ይህ ዓለም አቀፍ የሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ ነጋዴ ቡት በመጨረሻ ዝነኛዋን ቅርጫት ኳስ ተጫዋች ብሪትኒ ግራይነርን ለማስፈታት ሲባል ተለቋል። ሁለቱ እስረኞችን ለማስፈታት ሁለት  የግል አውሮፕላኖች ከሞስኮና ከዋሺንግተን እስረኞችን ይዘው ወደ አቡ ዳቢ የበረሩ ሲሆን በአቡዳቢ አየር ማረፊያ እስረኞቹ ሲለዋወጡ የሚያሳይ ቪዲዮ ወጥቷል። የእስረኛ ልውውጡ እንዲሰምር የሳኡዲው ልዑል መሐመድ ቢን ሰልማንና የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ፕሬዝዳንት መሐመድ ቢን ዛይድ አል ነህያን ሁነኛ ሚና ተጫውተዋል ነው የተባለው። በተለይ ከፑቲን ጋር ጥብቅ ወዳጅ ናቸው የሚባሉት ልዑል ቢን ሰልማን ከዚህ የእስረⶉች ልውውጥ በሻገር የዩክሬንና የሩሲያ የጦር ምርኮኞችን ልውውጥ ያሳለጡ ሰው እንደሆኑ ይነገራል። ጆ ባይደን የእስረኛ ልውውጡ ተደርጎ ብሪትኒ ወደ አገሯ አሜሪካ በማቅናት ላይ ሳለች ከዋይት ሐውስ በሰጡት አጭር መግለጫ “ጀግኒትን በስልክ አወራኋት። ጥሩ ስሜት ላይ ናት። ለማገገም ጊዜ ያሻት ይሆናል’ ሲሉ ለአሜሪካዊያን እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል። የዚች ቅርጫት ኳስ ተጫዋች የፍቅር አጋር የሆነችው ቼሬል ግራይነር “ባለቤቴ በመፈታቷ ወደር የሌለው ደስታ ተሰምቶኛል’ ብላለች። በተመሳሳይ ‘የሞት ነጋዴው’ በሚል ቅጽል የሚታወቀው ቪክቶር ቦት ሞስኮ መድረሱ ተሰምቷል። ቦት ሞስኮ ሲደርስ ለሩሲያ ብሔራዊ ቴሌቪዥን እንደተናገረው፣ "ድንገት ሌሊት ላይ መጥተው ተነስ ሻንጣህን ሸክፍ አሉኝ፤ በቃ ይኸው ነው” ብሏል። ቦት ከአውሮፕላኑ ደረጃዎች ሲወርድ እቅፍ አበባ ለእናቱና ለባለቤቱ ሲያበረክት ታይቷል። ይህ ግለሰብ የዛሬ 12 ዓመት አካባቢ ነበር በአሜሪካ ደኅንነቶች ሲታደን ቆይቶ በታይላንድ ዋና ከተማ ባንኮክ በቁጥጥር ሥር የዋለው። ቦት ሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያን ለድሃ አገራትና ለአሸባሪዎች በማስተላለፍ የሩሲያ ቀኝ እጅ ነበር ትላለች አሜሪካ። ሩሲያ ይህ ሰው በአሜሪካ በቁጥጥር ሥር መዋሉ አበሳጭቷት ቆይቷል። የቅርጫት ኳስ ተጫዋቿ ግራይነር በበኩሏ በቁጥጥር ሥር የዋለችው በሞስኮ አየር መንገድ የካናቢስ ዘይት በሻንጣዋ ይዛ በመገኘቷ ነበር። ይህቺን አሜሪካዊት ለማስፈታት ድርድር ሲጀመር አሜሪካ የቀድሞውን የባሕር ኃይል ባልደረባ ፖል ዊላንን ከርሷ ጋር አብሮ እንዲፈታላት ጠይቃ ነበር። ነገር ግን ሩሲያ ይህን ሰው ለመልቀቅ አልፈቀደችም። ፖል የታሰረው በፈረንጆች 2008 ለአሜሪካ ሲሰልል በመገኘቱ ነው። የ32 ዓመቷ ብሪትኒ ግራይነር በቅርጫት ኳስ የሁለት ጊዜ የኦሎምፒክ አሸናፊ ለፊኒክስ ሜርኩሪ የምትጫወት ዕውቅ ስፖርተኛ ናት።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c19vgxrgxreo
5sports
ናኦሚ ኦሳካ ለመገናኛ ብዙሃን አልናገርም በማለቷ ከውድድሮች ልትታገድ ትችላለች ተባለ
የዓለም ቁጥር ሁለቷ የሜዳ ቴኒስ ተጫዋች ናኦሚ ኦሳካ ለመገናኛ ብዙሃን ለመናገር ፈቃደኛ አለመሆኗን ከቀጠለች የፈረንሣይ ኦፕንን ጨምሮ ወደፊቱ ከሚደረጉ የግራንድ ስላም ውድድሮች እንደምትባረር አዘጋጆቹ ተናግሩ። ጃፓናዊቷ ኦሳካ ባለፈው ሳምንት የአዕምሮ ጤንነቷን ለመጠበቅ ስትል በሮላንድ ጋሮስ (የፈፈረንሳይ ኦፕን ሌላኛው ስም) ውድድር ወቅት ምንም ዓይነት መግለጫ እንደማትሰጥ ገልጻለች። እሑድ ሮማኒያዊቷን ፓትሪሺያ ማሪያ ቲግን በውድድሩ የመጀመሪያ ዙር አሸንፋ መግለጫ ባለመስጠቷ 15,000 ዶላር ተቀጥታለች፡፡ የዓለም ቁጥር ሁለቷ ውድድሩን 6-4 7-6 (7-4) አሸንፋለች፡፡ የአራቱ ግራንድ ስላም አዘጋጆች በጋራ በሰጡት መግለጫ ኦሳካ፤ “ተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት እና ወደፊቱ ከግራንድ ስላም ውድድሮች ልትታገድ ትችላለች” ብለዋል፡፡ ኦሳካ እሁድ ዕለት “ለውጥ ሰዎችን ምቾት እንዳይኖራቸው ያደርጋል” ስል በትዊተር ገጿ አስፍራለች። ኦሳካ ሃሳቧን ማስታወቋን ተከትሎ አዘጋጆቹ የ23 ዓመቷ የቴኒስ ተጫዋች ሃሳቧን እንደገና እንድታጤን የጠየቁ ሲሆን የጤንነቷን ሁኔታ ለመፈተሽ ያደረጉት ሙከራም አልተሳካም፡፡ ከኦሳካ “የምላሽ አለማግኘት” በኋላ ድጋፍ እንደሚሰጣት እና “ግዴታዋንም አስታሰውሰው” የጽሑፍ መልዕክት ሰደውላታል፡፡ “ከግራንድ ስላም ህጎች ዋነኛው ተጫዋቾች ምንም ውጤት ያስመዝግቡ ከሚዲያ ጋር የመሠራት ሃላፊነታቸው ነው። ይህም ተጫዋቾቹ ለስፖርቱ፣ ለደጋፊዎች እና ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ የሚወስዱት ሃላፊነት ነው” ብሏል መግለጫው፡፡ . “ናኦሚ ኦሳካ በውድድሩ ወቅት የሚዲያ ግዴታዎቿን ችላ ማለቷን ከቀጠለች ለተጨማሪ የሥነ ምግባር ጥሰት መዘዞች ራሷን ታጋልጣለች” ብሏል። “ተደጋጋሚ ጥሰቶች ከውድድሩ መታገድን ከባድ የወንጀል ምርመራን ጨምሮ ከፍተኛ ቅጣቶችን ያስከትላል። ለወደፊቱም ከግራንድ ስላም ውድድሮች እገዳን ሊያስከትል ይችላል።“ አክሎም ህጎች ያሉት “ሁሉም ተጫዋቾችን በአንድ ዓይን እንዲታዩ ለማድረግ” ነው ብሏል፡፡ እንዴት እዚህ ደረጃ ተደረሰ? የመገናኛ ብዙሃን መግለጫዎች በተጫዋቾች የአዕምሮ ጤንነት ላይ የሚያሳድሩትን ተጽዕኖ በመጥቀስ በፈረንሣይ ኦፕን ወቅት መግለጫ እንደማትሰጥ ኦሳካ ረቡዕ ዕለት አሳወቀች፡፡ ተጫዋቾች ከሽንፈት በኋላ ለጥያቄዎች መልስ እንዲሰጡ መጠበቁን “እየወደቀ ያለን ሰው ከኋላ የመርገጥ ያህል ነው” ስትል አስረድታለች፡፡ በማህበራዊ ድር አምባር ባስተላለፈችው መግለጫ “ብዙ ጊዜ ሰዎች ለአትሌቶች የአዕምሮ ጤንነት ምንም እንደማይጨነቁ ይሰማኛል። ይህ እውነት መሆኑን ጋዜጣዊ መግለጫ ስመለከት ወይም ስሳተፍ ያየሁት ነው” ብላለች፡፡ “ብዙ ጊዜ እዚያ ቁጭ ብለን ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ የተጠየቅነውን ጥያቄዎች ወይም በአዕምሯችን ጥርጣሬን የሚጭሩ ጥያቄዎችን እንጠየቃለን። እናም እኔ ለሚጠራጠሩኝ ሰዎች ራሴን አላስገዛም፡፡“ በግራንድ ስላም ህግ ተጫዋቾች የመገናኛ ብዙሃን ግዴታቸውን ባለመወጣታቸው እስከ 20,000 ዶላር ሊቀጡይችላሉ። የሴቶች ቴኒስ ማህበር እንደሚለው በውድድር ወቅት ተጫዋቾቹ ለመገናኛ ብዙሃን የመናገር “ስፖርታዊ እና የአድናቂዎቻቸው ኃላፊነት አለባቸው።" የቴኒስ ተጫዋቾችን ጨምሮ ሌሎች ስፖርተኞች ብዙዎቹ ለመገናኛ ብዙሃን መናገር “የሥራው አካል” መሆኑን ቢቀበሉም የኦሳካን አቋም አድንቀዋል። ኦሳካ ከድሏ በኋላ የተለመደውን የሜዳ ላይ ቃለ-መጠይቅ አድርጋለች፡፡ “በአሸዋ ሜዳ ያለኝ እንቅስቃሴ እየተሻሻለ ያለ ነው፡፡ ብዙ ግጥሚያዎችን ካደረኩኝ የተሻለ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ” ብላለች፡፡
ናኦሚ ኦሳካ ለመገናኛ ብዙሃን አልናገርም በማለቷ ከውድድሮች ልትታገድ ትችላለች ተባለ የዓለም ቁጥር ሁለቷ የሜዳ ቴኒስ ተጫዋች ናኦሚ ኦሳካ ለመገናኛ ብዙሃን ለመናገር ፈቃደኛ አለመሆኗን ከቀጠለች የፈረንሣይ ኦፕንን ጨምሮ ወደፊቱ ከሚደረጉ የግራንድ ስላም ውድድሮች እንደምትባረር አዘጋጆቹ ተናግሩ። ጃፓናዊቷ ኦሳካ ባለፈው ሳምንት የአዕምሮ ጤንነቷን ለመጠበቅ ስትል በሮላንድ ጋሮስ (የፈፈረንሳይ ኦፕን ሌላኛው ስም) ውድድር ወቅት ምንም ዓይነት መግለጫ እንደማትሰጥ ገልጻለች። እሑድ ሮማኒያዊቷን ፓትሪሺያ ማሪያ ቲግን በውድድሩ የመጀመሪያ ዙር አሸንፋ መግለጫ ባለመስጠቷ 15,000 ዶላር ተቀጥታለች፡፡ የዓለም ቁጥር ሁለቷ ውድድሩን 6-4 7-6 (7-4) አሸንፋለች፡፡ የአራቱ ግራንድ ስላም አዘጋጆች በጋራ በሰጡት መግለጫ ኦሳካ፤ “ተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት እና ወደፊቱ ከግራንድ ስላም ውድድሮች ልትታገድ ትችላለች” ብለዋል፡፡ ኦሳካ እሁድ ዕለት “ለውጥ ሰዎችን ምቾት እንዳይኖራቸው ያደርጋል” ስል በትዊተር ገጿ አስፍራለች። ኦሳካ ሃሳቧን ማስታወቋን ተከትሎ አዘጋጆቹ የ23 ዓመቷ የቴኒስ ተጫዋች ሃሳቧን እንደገና እንድታጤን የጠየቁ ሲሆን የጤንነቷን ሁኔታ ለመፈተሽ ያደረጉት ሙከራም አልተሳካም፡፡ ከኦሳካ “የምላሽ አለማግኘት” በኋላ ድጋፍ እንደሚሰጣት እና “ግዴታዋንም አስታሰውሰው” የጽሑፍ መልዕክት ሰደውላታል፡፡ “ከግራንድ ስላም ህጎች ዋነኛው ተጫዋቾች ምንም ውጤት ያስመዝግቡ ከሚዲያ ጋር የመሠራት ሃላፊነታቸው ነው። ይህም ተጫዋቾቹ ለስፖርቱ፣ ለደጋፊዎች እና ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ የሚወስዱት ሃላፊነት ነው” ብሏል መግለጫው፡፡ . “ናኦሚ ኦሳካ በውድድሩ ወቅት የሚዲያ ግዴታዎቿን ችላ ማለቷን ከቀጠለች ለተጨማሪ የሥነ ምግባር ጥሰት መዘዞች ራሷን ታጋልጣለች” ብሏል። “ተደጋጋሚ ጥሰቶች ከውድድሩ መታገድን ከባድ የወንጀል ምርመራን ጨምሮ ከፍተኛ ቅጣቶችን ያስከትላል። ለወደፊቱም ከግራንድ ስላም ውድድሮች እገዳን ሊያስከትል ይችላል።“ አክሎም ህጎች ያሉት “ሁሉም ተጫዋቾችን በአንድ ዓይን እንዲታዩ ለማድረግ” ነው ብሏል፡፡ እንዴት እዚህ ደረጃ ተደረሰ? የመገናኛ ብዙሃን መግለጫዎች በተጫዋቾች የአዕምሮ ጤንነት ላይ የሚያሳድሩትን ተጽዕኖ በመጥቀስ በፈረንሣይ ኦፕን ወቅት መግለጫ እንደማትሰጥ ኦሳካ ረቡዕ ዕለት አሳወቀች፡፡ ተጫዋቾች ከሽንፈት በኋላ ለጥያቄዎች መልስ እንዲሰጡ መጠበቁን “እየወደቀ ያለን ሰው ከኋላ የመርገጥ ያህል ነው” ስትል አስረድታለች፡፡ በማህበራዊ ድር አምባር ባስተላለፈችው መግለጫ “ብዙ ጊዜ ሰዎች ለአትሌቶች የአዕምሮ ጤንነት ምንም እንደማይጨነቁ ይሰማኛል። ይህ እውነት መሆኑን ጋዜጣዊ መግለጫ ስመለከት ወይም ስሳተፍ ያየሁት ነው” ብላለች፡፡ “ብዙ ጊዜ እዚያ ቁጭ ብለን ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ የተጠየቅነውን ጥያቄዎች ወይም በአዕምሯችን ጥርጣሬን የሚጭሩ ጥያቄዎችን እንጠየቃለን። እናም እኔ ለሚጠራጠሩኝ ሰዎች ራሴን አላስገዛም፡፡“ በግራንድ ስላም ህግ ተጫዋቾች የመገናኛ ብዙሃን ግዴታቸውን ባለመወጣታቸው እስከ 20,000 ዶላር ሊቀጡይችላሉ። የሴቶች ቴኒስ ማህበር እንደሚለው በውድድር ወቅት ተጫዋቾቹ ለመገናኛ ብዙሃን የመናገር “ስፖርታዊ እና የአድናቂዎቻቸው ኃላፊነት አለባቸው።" የቴኒስ ተጫዋቾችን ጨምሮ ሌሎች ስፖርተኞች ብዙዎቹ ለመገናኛ ብዙሃን መናገር “የሥራው አካል” መሆኑን ቢቀበሉም የኦሳካን አቋም አድንቀዋል። ኦሳካ ከድሏ በኋላ የተለመደውን የሜዳ ላይ ቃለ-መጠይቅ አድርጋለች፡፡ “በአሸዋ ሜዳ ያለኝ እንቅስቃሴ እየተሻሻለ ያለ ነው፡፡ ብዙ ግጥሚያዎችን ካደረኩኝ የተሻለ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ” ብላለች፡፡
https://www.bbc.com/amharic/news-57304051
3politics
የሰላም ስምምነቱ አፈጻጸምን በተመለከተ እየተሰሙ ያሉ ልዩነቶች
የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት የሰላም ስምምነቱ የሚጠይቀውን ሁሉ ተግባራዊ እያደረኩ ነው እያለ ባለበት በአሁኑ ወቅት፣ ከትግራይ በኩል ግን መንግሥት ቃሉን ሙሉ ለሙሉ እያከበረ አይደለም የሚል ወቀሳ እየተሰነዘረ ነው። መንግሥት ቅዳሜ ታኅሣሥ 08/2015 ዓ.ም. በኮሙኒኬሽን ጉዳዮች አገልግሎቱ በኩል ባወጣው መግለጫ ላይ የተደረሰውን ስምምነት ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን ገልጾ የነበረ ቢሆንም፣ በህወሓት በኩል ግን ከዚህ የሚቃረን ሃሳብ ተሰንዝሯል። መንግሥት በመግለጫው “ለአገር እና ለሕዝብ ሲባል በተደረሰው የሰላም ስምምነት የገባውን ቃል ሳይውል ሳያድር እና ሳያንጠባጥብ በመፈጸም ላይ ይገኛል” ብሏል። ነገር ግን የህወሓት ሊቀመንበር እና የክልሉ ፕሬዝዳንት ዶክተር ድብረጽዮን ገብረሚካኤል መቀለ በተካሄደ ጉባኤ ላይ ሲናገሩ የሚጠበቅባቸውን እየፈጸሙ ቢሆንም በመንግሥት በኩል የሚጠበቀው ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ እየሆነ አይደለም ማለታቸውን የትግራይ ክልል መገኛኛ ብዙኃን ዘግበዋል። ዕሁድ ታኅሣሥ 09/2015 ዓ.ም. ዶ/ር ደብረጽዮን በትግራይ ክልል ምክር ቤት በተደረገ አስቸኳይ ስብሰባ ላይ የሰላም ስምምነት የአንድ ወር አተገባበርን በተመለከተ አቀረቡት በተባለው ሪፖርት ላይ፣ ስምምነቱ በሚጠበቀው መጠን እየተተገበረ እንዳልሆነ ገልጸዋል። ደብረጽዮን (ዶ/ር) የሰላም ስምምነቱ ከተፈረመ ወዲህ በትግራይ በኩል ሁሉም የሰላም ስምምነቱ ጥያቄዎችን እየፈጸሙ መሆናቸውን ጠቅሰው “በፌደራል መንግሥት በኩል ከሰብአዊ እርዳታ አንፃር አበረታች ጉዳዮች ቢኖሩም በተቀሩት የሰላም ስምምነቱ ነጥቦች ዙርያ ግን መንግሥት በቃሉ መሠረት አልፈጸመም” ብለዋል። ሁለት ዓመት ያስቆጠረውን የእርስ በርስ ጦርነት ለማስቆም በመንግሥት እና በህወሓት አመራሮች መካከል በመጀመሪያ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የተደረገውን ድርድር ተከትሎ ዘላቂ ግጭት የሚያስቆም እና ትጥቅ የመፍታት ስምምነት ተደርሶ ነበር። በማስከተልም ኬንያ ውስጥ በሁለቱም ወገኖች ወታደራዊ አመራሮች መካከል የፕሪቶሪያውን ስምምነት ለመተግበር በሚያስችል አጠቃላይ የትግበራ ሰነድ ላይ ስምምነት መፈረማቸው ይታወሳል። በአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት በተደረሰው ስምምነት ግጭት ማቆም፣ የሰብአዊ እርዳታ እንዲቀርብ፣ መሠረታዊ አገልግሎቶች እንዲጀመሩ፣ የህወሓት ተዋጊዎች ትጥቅ እንዲፈቱ እና ከፌደራሉ ሠራዊት ውጪ የሆኑ ኃይሎች ከክልሉ እንዲወጡ ስምምነት ተደርሷል። ከሁለት ሳምንት በፊት ደግሞ የሰላም ስምምነቱን አፈጻጸም በተመለከተ በሁለቱም ወገኖች ወታደራዊ አመራሮች መካከል ትግራይ ሽረ ከተማ ውስጥ ውይይት መደረጉ እና የትግራይ ኃይሎች ከውጊያ ግንባሮች እየወጡ መሆናቸው ተዘግቧል። በተጨማሪም ሰላም ወርዶ ጦርነት ከቆመ በኋላ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ወደ ተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ያለችግር እየደረሰ መሆኑን የመንግሥታቱ ድርጅት እና ሌሎች የእርዳታ ተቋማት ገልጸዋል። ከዚህ ጎን ለጎን በጦርነቱ የተጎዱ መሠረተ ልማቶችን በመጠገን ጥቂት በማይባሉ የትግራይ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት መጀመሩ የተዘገበ ሲሆን፣ የስልክ አገልግሎትም የተመለሱባቸው ቦታዎች እንዳሉ፣ በሌሎቹም ቦታዎች አገልግሎት ለማስጀመር ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተነግሯል። በፌደራሉ መንግሥት እና በህወሓት ኃይሎች መካከል ከተፈረመ ከአንድ ወር በላይ የሆነውን ስምምነት አፈጻጸምን በተመለከተ እስካሁን ያለበትን ሂደት በተመለከተ ዝርዝር መረጃ ከአሸማጋዮቹም ሆነ ከሁለቱም ወገን በይፋ የተሰጠ መረጃ የለም። ከዚህ አንጻር ባለፉት ቀናት ሁለቱም ወገኖች በተናጠል የሰላም ስምምነቱን በተመለከተ ያለበትን ደረጃ በየበኩላቸው ገልጸዋል። የፌደራሉ መንግሥት በሰላም ስምምነቱ የሚጠበቅበትን ሁሉ ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን እየገለጸ ያለ ቢሆንም፣ ደብረጽዮን ባቀረቡት ሪፖርት ላይ ደግሞ ከእርዳታ አቅርቦት ውጪ ተግባራዊ ያልሆኑ ጉዳዮች እንዳሉ አንስተዋል። ዶክተር ደብረጽዮን ጨምረውም “በተደረሰው የሰላም ስምምነት ውል መሰረት የኤርትራ ሠራዊት እና የአማራ ታጣቂዎች በወረራ ከያዙት የትግራይ መሬት ለቀው ሊወጡ ሲገባ አሁንም በትግራይ መሬት ላይ ሆነው የትግራይ ሕዝብን እየጨፈጨፉ ይገኛሉ” ብለዋል። በሁለቱ ወገኖች መካከል በተደረሰው ስምምነት መሠረት በክልሉ ውስጥ ያሉ ከፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ውጪ የሆኑ ኃይሎች ለቀው እንዲወጡ እና የህወሓት ተዋጊዎችም ትጥቅ እንዲፈቱ ይጠበቃል። ነገር ግን ይህ ስምምነት ተግባራዊ ስለመሆኑ እስካሁን የተባለ ነገር የለም። ሁለት ዓመት የደፈነው የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ የኤርትራ ሠራዊት የፌደራል መንግሥቱን በመደገፍ በግጭቱ ውስጥ ሲሳተፍ መቆየቱ ሲዘገብ የቆየ ቢሆንም፣ በሁለቱ ወገኖች በተደረሰው ስምምነት ላይ ግን የኤርትራ ስም በግልጽ አልተጠቀሰም። ዝርዝር ጉዳዮችን የያዘው የሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ከፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ውጪ ያሉ ኃይሎች መውጣት በተጨማሪ የትግራይ ኃይሎች ትጥቅ እንዲፈቱ የሚጠበቅ ሲሆን፣ የፌደራሉ ሠራዊትም መቀለን ጨምሮ ወደ ሌሎች የትግራይ አካባቢዎች እንደሚገባ ያመለክታል። የፌደራል መንግሥቱ ከቀናት በፊት እንዳሳወቀው የመከላከያ ሠራዊት ባልደረሰባቸው መቀለን ጨምሮ በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች የተደራጀ የዝርፊያ ድርጊቶች እየተፈጸሙ መሆናቸውን በመግለጽ፣ መንግሥት የሕዝቡን ደኅንነት ለመጠበቅ ያለበትን ኃላፊነት ለመፈጸም አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ አመልክቷል። ይህንን በተመለከተ ደብረጽዮንም ሆኑ ህወሓት በይፋ የሰጡት ምላሽ ባይኖርም፣ ከህወሓት ከፍተኛ አመራሮች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ ግን የመንግሥት መግለጫን አያይዘው በትዊተር ገጻቸው አጭር አስተያየት አስፍረዋል። “እኛ ልንፈታው የማንችለው፣ ሕዝባችን ሊፈታው የማይችለው ምንም አይነት የደኅንነት ስጋት፣ ማንም ሊፈታው አይችልም” በማለት ጽፈዋል። በሁለቱም ወገኖች በኩል ስምምነት ተደርጎ አስካልተራዘመ ድረስ ስምምነቱ በአንድ ወር ውስጥ ወደ ተግባር እንደሚሸጋገር ተገልጾ ነበር። ነገር ግን ከእነዚህ ወሳኝ ጉዳዮች አንጻር የተደረጉ ተግባራዊ እርምጃዎች ስለመኖራቸው ከየትኛውም ወገን የተባለ ነገር የለም። ከባድ ሰብአዊ፣ ምጣኔ ሀብታዊ እና ፖለቲካዊ ቀውስን ያስከተለው የእርስ በእርስ ጦርነት ጥቅምት 23/2015 ዓ.ም. በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ፣ በኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት እና በህወሓት መሪዎች መካከል በተደረሰ ስምምነት ከቆመ ወደ ሁለት ወራት እየተቃረበ ነው።
የሰላም ስምምነቱ አፈጻጸምን በተመለከተ እየተሰሙ ያሉ ልዩነቶች የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት የሰላም ስምምነቱ የሚጠይቀውን ሁሉ ተግባራዊ እያደረኩ ነው እያለ ባለበት በአሁኑ ወቅት፣ ከትግራይ በኩል ግን መንግሥት ቃሉን ሙሉ ለሙሉ እያከበረ አይደለም የሚል ወቀሳ እየተሰነዘረ ነው። መንግሥት ቅዳሜ ታኅሣሥ 08/2015 ዓ.ም. በኮሙኒኬሽን ጉዳዮች አገልግሎቱ በኩል ባወጣው መግለጫ ላይ የተደረሰውን ስምምነት ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን ገልጾ የነበረ ቢሆንም፣ በህወሓት በኩል ግን ከዚህ የሚቃረን ሃሳብ ተሰንዝሯል። መንግሥት በመግለጫው “ለአገር እና ለሕዝብ ሲባል በተደረሰው የሰላም ስምምነት የገባውን ቃል ሳይውል ሳያድር እና ሳያንጠባጥብ በመፈጸም ላይ ይገኛል” ብሏል። ነገር ግን የህወሓት ሊቀመንበር እና የክልሉ ፕሬዝዳንት ዶክተር ድብረጽዮን ገብረሚካኤል መቀለ በተካሄደ ጉባኤ ላይ ሲናገሩ የሚጠበቅባቸውን እየፈጸሙ ቢሆንም በመንግሥት በኩል የሚጠበቀው ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ እየሆነ አይደለም ማለታቸውን የትግራይ ክልል መገኛኛ ብዙኃን ዘግበዋል። ዕሁድ ታኅሣሥ 09/2015 ዓ.ም. ዶ/ር ደብረጽዮን በትግራይ ክልል ምክር ቤት በተደረገ አስቸኳይ ስብሰባ ላይ የሰላም ስምምነት የአንድ ወር አተገባበርን በተመለከተ አቀረቡት በተባለው ሪፖርት ላይ፣ ስምምነቱ በሚጠበቀው መጠን እየተተገበረ እንዳልሆነ ገልጸዋል። ደብረጽዮን (ዶ/ር) የሰላም ስምምነቱ ከተፈረመ ወዲህ በትግራይ በኩል ሁሉም የሰላም ስምምነቱ ጥያቄዎችን እየፈጸሙ መሆናቸውን ጠቅሰው “በፌደራል መንግሥት በኩል ከሰብአዊ እርዳታ አንፃር አበረታች ጉዳዮች ቢኖሩም በተቀሩት የሰላም ስምምነቱ ነጥቦች ዙርያ ግን መንግሥት በቃሉ መሠረት አልፈጸመም” ብለዋል። ሁለት ዓመት ያስቆጠረውን የእርስ በርስ ጦርነት ለማስቆም በመንግሥት እና በህወሓት አመራሮች መካከል በመጀመሪያ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የተደረገውን ድርድር ተከትሎ ዘላቂ ግጭት የሚያስቆም እና ትጥቅ የመፍታት ስምምነት ተደርሶ ነበር። በማስከተልም ኬንያ ውስጥ በሁለቱም ወገኖች ወታደራዊ አመራሮች መካከል የፕሪቶሪያውን ስምምነት ለመተግበር በሚያስችል አጠቃላይ የትግበራ ሰነድ ላይ ስምምነት መፈረማቸው ይታወሳል። በአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት በተደረሰው ስምምነት ግጭት ማቆም፣ የሰብአዊ እርዳታ እንዲቀርብ፣ መሠረታዊ አገልግሎቶች እንዲጀመሩ፣ የህወሓት ተዋጊዎች ትጥቅ እንዲፈቱ እና ከፌደራሉ ሠራዊት ውጪ የሆኑ ኃይሎች ከክልሉ እንዲወጡ ስምምነት ተደርሷል። ከሁለት ሳምንት በፊት ደግሞ የሰላም ስምምነቱን አፈጻጸም በተመለከተ በሁለቱም ወገኖች ወታደራዊ አመራሮች መካከል ትግራይ ሽረ ከተማ ውስጥ ውይይት መደረጉ እና የትግራይ ኃይሎች ከውጊያ ግንባሮች እየወጡ መሆናቸው ተዘግቧል። በተጨማሪም ሰላም ወርዶ ጦርነት ከቆመ በኋላ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ወደ ተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ያለችግር እየደረሰ መሆኑን የመንግሥታቱ ድርጅት እና ሌሎች የእርዳታ ተቋማት ገልጸዋል። ከዚህ ጎን ለጎን በጦርነቱ የተጎዱ መሠረተ ልማቶችን በመጠገን ጥቂት በማይባሉ የትግራይ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት መጀመሩ የተዘገበ ሲሆን፣ የስልክ አገልግሎትም የተመለሱባቸው ቦታዎች እንዳሉ፣ በሌሎቹም ቦታዎች አገልግሎት ለማስጀመር ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተነግሯል። በፌደራሉ መንግሥት እና በህወሓት ኃይሎች መካከል ከተፈረመ ከአንድ ወር በላይ የሆነውን ስምምነት አፈጻጸምን በተመለከተ እስካሁን ያለበትን ሂደት በተመለከተ ዝርዝር መረጃ ከአሸማጋዮቹም ሆነ ከሁለቱም ወገን በይፋ የተሰጠ መረጃ የለም። ከዚህ አንጻር ባለፉት ቀናት ሁለቱም ወገኖች በተናጠል የሰላም ስምምነቱን በተመለከተ ያለበትን ደረጃ በየበኩላቸው ገልጸዋል። የፌደራሉ መንግሥት በሰላም ስምምነቱ የሚጠበቅበትን ሁሉ ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን እየገለጸ ያለ ቢሆንም፣ ደብረጽዮን ባቀረቡት ሪፖርት ላይ ደግሞ ከእርዳታ አቅርቦት ውጪ ተግባራዊ ያልሆኑ ጉዳዮች እንዳሉ አንስተዋል። ዶክተር ደብረጽዮን ጨምረውም “በተደረሰው የሰላም ስምምነት ውል መሰረት የኤርትራ ሠራዊት እና የአማራ ታጣቂዎች በወረራ ከያዙት የትግራይ መሬት ለቀው ሊወጡ ሲገባ አሁንም በትግራይ መሬት ላይ ሆነው የትግራይ ሕዝብን እየጨፈጨፉ ይገኛሉ” ብለዋል። በሁለቱ ወገኖች መካከል በተደረሰው ስምምነት መሠረት በክልሉ ውስጥ ያሉ ከፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ውጪ የሆኑ ኃይሎች ለቀው እንዲወጡ እና የህወሓት ተዋጊዎችም ትጥቅ እንዲፈቱ ይጠበቃል። ነገር ግን ይህ ስምምነት ተግባራዊ ስለመሆኑ እስካሁን የተባለ ነገር የለም። ሁለት ዓመት የደፈነው የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ የኤርትራ ሠራዊት የፌደራል መንግሥቱን በመደገፍ በግጭቱ ውስጥ ሲሳተፍ መቆየቱ ሲዘገብ የቆየ ቢሆንም፣ በሁለቱ ወገኖች በተደረሰው ስምምነት ላይ ግን የኤርትራ ስም በግልጽ አልተጠቀሰም። ዝርዝር ጉዳዮችን የያዘው የሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ከፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ውጪ ያሉ ኃይሎች መውጣት በተጨማሪ የትግራይ ኃይሎች ትጥቅ እንዲፈቱ የሚጠበቅ ሲሆን፣ የፌደራሉ ሠራዊትም መቀለን ጨምሮ ወደ ሌሎች የትግራይ አካባቢዎች እንደሚገባ ያመለክታል። የፌደራል መንግሥቱ ከቀናት በፊት እንዳሳወቀው የመከላከያ ሠራዊት ባልደረሰባቸው መቀለን ጨምሮ በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች የተደራጀ የዝርፊያ ድርጊቶች እየተፈጸሙ መሆናቸውን በመግለጽ፣ መንግሥት የሕዝቡን ደኅንነት ለመጠበቅ ያለበትን ኃላፊነት ለመፈጸም አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ አመልክቷል። ይህንን በተመለከተ ደብረጽዮንም ሆኑ ህወሓት በይፋ የሰጡት ምላሽ ባይኖርም፣ ከህወሓት ከፍተኛ አመራሮች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ ግን የመንግሥት መግለጫን አያይዘው በትዊተር ገጻቸው አጭር አስተያየት አስፍረዋል። “እኛ ልንፈታው የማንችለው፣ ሕዝባችን ሊፈታው የማይችለው ምንም አይነት የደኅንነት ስጋት፣ ማንም ሊፈታው አይችልም” በማለት ጽፈዋል። በሁለቱም ወገኖች በኩል ስምምነት ተደርጎ አስካልተራዘመ ድረስ ስምምነቱ በአንድ ወር ውስጥ ወደ ተግባር እንደሚሸጋገር ተገልጾ ነበር። ነገር ግን ከእነዚህ ወሳኝ ጉዳዮች አንጻር የተደረጉ ተግባራዊ እርምጃዎች ስለመኖራቸው ከየትኛውም ወገን የተባለ ነገር የለም። ከባድ ሰብአዊ፣ ምጣኔ ሀብታዊ እና ፖለቲካዊ ቀውስን ያስከተለው የእርስ በእርስ ጦርነት ጥቅምት 23/2015 ዓ.ም. በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ፣ በኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት እና በህወሓት መሪዎች መካከል በተደረሰ ስምምነት ከቆመ ወደ ሁለት ወራት እየተቃረበ ነው።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cj7zmyn3x44o
3politics
የአሜሪካ እና የታሊባን ስምምነት የአፍጋኒስታንን ውድቀት አፋጥኖታል ተባለ
የአሜሪካ የመከላከያ ባለሥልጣናት ታሊባን አፍጋኒስታንን በቁጥጥሩ ሥር ማድረጉ በቡድኑ እና በትራምፕ አስተዳደር መካከል በተደረገው ስምምነት ላይ የተመሠረተ ነው ሲሉ ገለጹ። የዶሃ ስምምነት ተብሎ የሚጠራው ውል እአአ የካቲት 2020 የተፈረመ ሲሆን አሜሪካ ወታደሮቿን ከአፍጋኒስታን የምታስወጣበትን ቀን አስቀምጧል። ጄነራል ፍራንክ ማክኬንዚ ስምምነቱ በአፍጋኒስታን መንግስት እና በወታደሮች ላይ "አስከፊ ውጤት" አለው ብለዋል። የመከላከያ ሚኒስትሩ ሎይድ ኦስቲንም በሃሳቡ ተስማምተው ስምምነቱ ታሊባን "እንዲጠናክር ረድቷል" ሲሉ ገልጸዋል። የዶሃው ስምምነት ቀን ገደብ ከማስወቀመጥ በተጨማሪ እንደ አልቃይዳ ያሉ ቡድኖች የአሜሪካን እና የአጋሮቿን ደህንነት አደጋ ላይ እንዳይጥሉ እርምጃዎችን እንዲወስድ ታሊባን ሰፊ ግዴታዎችን ተጥሎበታል። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን መንበሩን ከተቆጣጠሩ በኋላ የሠራዊቱን የማስውጣት ዕቅዱን ቀጥለውበታል። ቀነ ገደቡ ግን ከግንቦት ይልቅ ነሐሴ መጨረሻ ሆነ። የአሜሪካ የመከላከያ ባለሥልጣናት ሐሳባቸውን የተናገሩት ረቡዕ በተወካዮች ምክር ቤት የመከላከያ አገልግሎት ኮሚቴ ፊት ቀርበው ነበር። ባለስልጣናቱ ሐሳባቸውን የሰጡት የውጭ ኃይሎች ዜጎቻቸውን ሲያስወጡ እና በሺዎች የሚቆጠሩ ተስፋ የቆረጡ አፍጋኒስታኖች እንዲታደጓቸው ሲለምኑ በካቡል አውሮፕላን ማረፊያ ሁከት ከተነሳ ከሳምንታት በኋላ ነው። በወቅቱ በአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት 182 ሰዎች ተገድለዋል። የዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ ዕዝ መሪ የሆኑት ጄነራል ማክኬንዚ ከአፍጋኒስታን መውጣቱን በበላይነት ይቆጣጠሩ ነበር። ሥራው አሜሪካ በሃገሪቱ የነበራትን የ 20 ዓመታት ቆይታ እና ረዥሙ ጦርነት ያበቃበት ነበር። ጄነራል ማክኬንዚ ለኮሚቴው እንደገለጹት የዶሃው ስምምነት በአፍጋኒስታን መንግሥት ላይ "ሁሉም ዕርዳታ ይጠናቀቃል ብለው የሚጠብቁበትን ቀን" ያስቀመጠ ጠንካራ የስነ-ልቦና ተፅእኖ አሳድሯል። ዩናይትድ ስቴትስ በአፍጋኒስታን የሚገኙትን ወታደራዊ አማካሪዎቿን ከ 2500 በታች ዝቅ ካደረገች የአፍጋኒስታን መንግስት እና ወታደሩ መውደቃቸው የማይቀር መሆኑን ካመኑ "የተወሰነ ጊዜ" ማለፉን ገልጸዋል። ከዶሃ ስምምነት በኋላ በሚያዝያ ወር በፕሬዚዳንት ባይደን የታዘዘው የወታደራዊ ቅነሳ ችግሩን ያባባሰው ነው ብለዋል። ኦስቲን በበኩላቸው አሜሪካ በታሊባን ላይ የአየር ድብደባን ለማስቆም በዶሃው ስምምነት በመግባባታቸው "እስላማዊ ቡድኑ ተጠናከረ፣ በአፍጋኒስታን የጸጥታ ኃይሎች ላይ የማጥቃት ሥራቸውን ጨምሯል። አፍጋኒስታኖች በየሳምንቱ ብዙ ሰዎችን እያጡ ነበር።" የመከላከያ ባለሥልጣናቱ ማክሰኞ ከሴኔቱ የጦር መሣሪያ አገልግሎት ኮሚቴ ጋር ተነጋግረዋል። በወቅቱ ጄነራል ሚሌይ እና ጄኔራል ማክኬንዚ በነሐሴ ወር አሜሪካ ጦሯን ከማሰወውጣቷ በፊት በአፍጋኒስታን የ 2500 ወታደሮች እንዲቆዩ ምክረ ሃሳብ አቅርበው እንደነበር ገልጸዋል። ጄኔራል ሚሌይ አክለውም ቡድኑ አሁንም ከአልቃይዳ ጋር ያለውን ግንኙነት ያላቋረጠ አሸባሪ ድርጅት በመሆኑ አሜሪካውያንን ከአሸባሪ ጥቃቶች ለመጠበቅ ከባድ ያደርገዋል ብለዋል። የታሊባኑ ቃል አቀባይ ዛቢሁላህ ሙጃሂድ ረቡዕ ዕለት ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ታጣቂዎች "ከአፍጋኒስታን በመነሳት አሜሪካንን ጨምሮ ለማንኛውም ሃገር ምንም ዓይነት ስጋት እንደማይኖር ለዓለም ዋስትና ሰጥተዋል" ብለዋል። "በአፍጋኒስታን እስላማዊ ኢሚሬት እና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል በዶሃ ለተፈረመው ስምምነት መተግበር ቁርጠኛ ነን። አሜሪካና እና አጋሮቿም ለስምምነቱ ቁርጠኝነት እንዲሆኑ እንፈልጋለን። አሉታዊ አስተያየቶችን ከመስጠት ይልቅ የዲፕሎማሲን እና የትብብርን መንገድ ቢመርጡ ለእነሱ የተሻለ ይሆናል"ብለዋል።
የአሜሪካ እና የታሊባን ስምምነት የአፍጋኒስታንን ውድቀት አፋጥኖታል ተባለ የአሜሪካ የመከላከያ ባለሥልጣናት ታሊባን አፍጋኒስታንን በቁጥጥሩ ሥር ማድረጉ በቡድኑ እና በትራምፕ አስተዳደር መካከል በተደረገው ስምምነት ላይ የተመሠረተ ነው ሲሉ ገለጹ። የዶሃ ስምምነት ተብሎ የሚጠራው ውል እአአ የካቲት 2020 የተፈረመ ሲሆን አሜሪካ ወታደሮቿን ከአፍጋኒስታን የምታስወጣበትን ቀን አስቀምጧል። ጄነራል ፍራንክ ማክኬንዚ ስምምነቱ በአፍጋኒስታን መንግስት እና በወታደሮች ላይ "አስከፊ ውጤት" አለው ብለዋል። የመከላከያ ሚኒስትሩ ሎይድ ኦስቲንም በሃሳቡ ተስማምተው ስምምነቱ ታሊባን "እንዲጠናክር ረድቷል" ሲሉ ገልጸዋል። የዶሃው ስምምነት ቀን ገደብ ከማስወቀመጥ በተጨማሪ እንደ አልቃይዳ ያሉ ቡድኖች የአሜሪካን እና የአጋሮቿን ደህንነት አደጋ ላይ እንዳይጥሉ እርምጃዎችን እንዲወስድ ታሊባን ሰፊ ግዴታዎችን ተጥሎበታል። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን መንበሩን ከተቆጣጠሩ በኋላ የሠራዊቱን የማስውጣት ዕቅዱን ቀጥለውበታል። ቀነ ገደቡ ግን ከግንቦት ይልቅ ነሐሴ መጨረሻ ሆነ። የአሜሪካ የመከላከያ ባለሥልጣናት ሐሳባቸውን የተናገሩት ረቡዕ በተወካዮች ምክር ቤት የመከላከያ አገልግሎት ኮሚቴ ፊት ቀርበው ነበር። ባለስልጣናቱ ሐሳባቸውን የሰጡት የውጭ ኃይሎች ዜጎቻቸውን ሲያስወጡ እና በሺዎች የሚቆጠሩ ተስፋ የቆረጡ አፍጋኒስታኖች እንዲታደጓቸው ሲለምኑ በካቡል አውሮፕላን ማረፊያ ሁከት ከተነሳ ከሳምንታት በኋላ ነው። በወቅቱ በአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት 182 ሰዎች ተገድለዋል። የዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ ዕዝ መሪ የሆኑት ጄነራል ማክኬንዚ ከአፍጋኒስታን መውጣቱን በበላይነት ይቆጣጠሩ ነበር። ሥራው አሜሪካ በሃገሪቱ የነበራትን የ 20 ዓመታት ቆይታ እና ረዥሙ ጦርነት ያበቃበት ነበር። ጄነራል ማክኬንዚ ለኮሚቴው እንደገለጹት የዶሃው ስምምነት በአፍጋኒስታን መንግሥት ላይ "ሁሉም ዕርዳታ ይጠናቀቃል ብለው የሚጠብቁበትን ቀን" ያስቀመጠ ጠንካራ የስነ-ልቦና ተፅእኖ አሳድሯል። ዩናይትድ ስቴትስ በአፍጋኒስታን የሚገኙትን ወታደራዊ አማካሪዎቿን ከ 2500 በታች ዝቅ ካደረገች የአፍጋኒስታን መንግስት እና ወታደሩ መውደቃቸው የማይቀር መሆኑን ካመኑ "የተወሰነ ጊዜ" ማለፉን ገልጸዋል። ከዶሃ ስምምነት በኋላ በሚያዝያ ወር በፕሬዚዳንት ባይደን የታዘዘው የወታደራዊ ቅነሳ ችግሩን ያባባሰው ነው ብለዋል። ኦስቲን በበኩላቸው አሜሪካ በታሊባን ላይ የአየር ድብደባን ለማስቆም በዶሃው ስምምነት በመግባባታቸው "እስላማዊ ቡድኑ ተጠናከረ፣ በአፍጋኒስታን የጸጥታ ኃይሎች ላይ የማጥቃት ሥራቸውን ጨምሯል። አፍጋኒስታኖች በየሳምንቱ ብዙ ሰዎችን እያጡ ነበር።" የመከላከያ ባለሥልጣናቱ ማክሰኞ ከሴኔቱ የጦር መሣሪያ አገልግሎት ኮሚቴ ጋር ተነጋግረዋል። በወቅቱ ጄነራል ሚሌይ እና ጄኔራል ማክኬንዚ በነሐሴ ወር አሜሪካ ጦሯን ከማሰወውጣቷ በፊት በአፍጋኒስታን የ 2500 ወታደሮች እንዲቆዩ ምክረ ሃሳብ አቅርበው እንደነበር ገልጸዋል። ጄኔራል ሚሌይ አክለውም ቡድኑ አሁንም ከአልቃይዳ ጋር ያለውን ግንኙነት ያላቋረጠ አሸባሪ ድርጅት በመሆኑ አሜሪካውያንን ከአሸባሪ ጥቃቶች ለመጠበቅ ከባድ ያደርገዋል ብለዋል። የታሊባኑ ቃል አቀባይ ዛቢሁላህ ሙጃሂድ ረቡዕ ዕለት ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ታጣቂዎች "ከአፍጋኒስታን በመነሳት አሜሪካንን ጨምሮ ለማንኛውም ሃገር ምንም ዓይነት ስጋት እንደማይኖር ለዓለም ዋስትና ሰጥተዋል" ብለዋል። "በአፍጋኒስታን እስላማዊ ኢሚሬት እና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል በዶሃ ለተፈረመው ስምምነት መተግበር ቁርጠኛ ነን። አሜሪካና እና አጋሮቿም ለስምምነቱ ቁርጠኝነት እንዲሆኑ እንፈልጋለን። አሉታዊ አስተያየቶችን ከመስጠት ይልቅ የዲፕሎማሲን እና የትብብርን መንገድ ቢመርጡ ለእነሱ የተሻለ ይሆናል"ብለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-58716791
5sports
ሦስት የጂቡቲ እግር ኳስ ተጫዋቾች በፈረንሳይ ጥገኝነት ጠየቁ
ሦስት የጂቡቲ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን አባላት በፈረንሳይ ጥገኝነት የጠየቁ ሲሆን ከመካከላቸውም ለአንድ ሳምንት በአየር መንገድ ውስጥ የቆየው ተጫዋች በመጨረሻ መውጣት ችሏል። ነስረዲን አብዲ የተሰኘው ይህ ተጫዋች በፓሪስ በኩል በ2022 የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጉዞ ላይ ለመሳተፍ ሊሳፈር የሚገባውን አውሮፕላን በመተው እዚያው ጥገኝነት ጠይቋል። ሁለቱ የቡድን አጋሮቹ ቢላል ሐሰን እና አቦቡካሪ ኤልሚ ረቡዕ ከአውሮፕላን ማረፊያው የወጡ ሲሆን ጉዳያቸውን ለፈረንሳይ መንግሥት እንዲያቀርቡ ሦስት ወር ተሰጥቷቸዋል። ሦስቱም ተጫዋቾች በአውሮፕላን ማረፊያው ውስጥ ሳሉ በ72 ሰዓታት ውስጥ ጉዳያቸውን የሚያስረዳ ሰነድ እንዲያቀርቡ ጊዜ ተሰጥቷቸው ነበር። ተጫዋቾቹን በማገዝ ላይ የሚገኘው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅትም ለጂቡቲ መንግሥት የሚሠሩት ሐሰን እና ኤልሚ ጥገኝነት ተከልክለው ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ ከተገደዱ እስር ቤት ሊገቡ ይችላሉ የሚል ሥጋት እንዳለው ገልጾ ነበር። ኤልሚ በፖሊስ አገልግሎት ተቀጥሮ የሚሠራ ሲሆን፤ ሐሰን በጂቡቲ ሪፐብሊካን ዘብ ውስጥ በሚሠራበት ወቅት መፈጸም የማይፈልገውን ትዕዛዝ ለመከተል እንደሚገደድ ተናግሮ ጥገኝነት ጠይቋል ተብሏል። "ትክክል ያልሆነ ነገር በተናገሩ ቁጥር በመንግሥት ይዋከባሉ" ሲሉ የጂቡቲ የሰብአዊ መብቶች ማኅበር ፕሬዝዳንት ዣን-ሎፕ ሻል ተናግረዋል። "ሐሰን የቤተሰቡን አባላት እንዲያስር ይገደድ ነበር። ይህንን እያደረገ ለመቀጠል አልፈለገም" ሲሉ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል። የሁለቱም የትዳር አጋሮች አንዲሁም ቤተሰቦች በጂቡቲ ውስጥ ይገኛሉ ያሉት የማኅበሩ ፕሬዝዳንት የሐሰን ባለቤት በመጨረሻው የእርግዝናዋ ወራት ውስጥ እንደምትገኝም አስታውቀዋል። ቡድኑ ከአራት ቀናት በፊት በአፍሪካ ሻምፒዮና በኒጀር 8 ለ 0 ተሸንፎ ከአልጄሪያ ወደ ሞሮኮ በቀጥታ መብረር ባለመቻሉ በፓሪስ አድርጎ ለመጓዝ ወደ ፈረንሳይ ተጉዞ ነበር። ተጫዋቾቹ በቪዛ ብሎም በኮቪድ ሰነዶች መጓደል ምክንያት ከፓሪስ ወደ ሞሮኮ የሚሄደው በረራቸው አምልጧቸዋል። ቀጥሎም ጥገኝነት ስለሚጠይቁበት መንገድ እቅድ ማውጣታቸው ተነግሯል። ሌሎች የቡድን አባላቶቻቸው ፓሪስን ለቀው ሲበሩ ሦስቱ የቡድን አባላት ግን ተደብቀው ቀርተዋል። "በሰፊ የግብ ልዩነት ተሸንፈው ወደ አገራቸው መመለስ በጣም ፈርተዋል" ሲሉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ መሪ ተናግረዋል። ከቀናት በፊት የፈረንሳይ ችሎት ሐሰን እና ኤልሚ ከአውሮፕላን ማረፊያው እንዲወጡ እስከሚፈቅድበት ጊዜ ድረስ ሦስቱም የእግር ኳስ ተጫዋቾች በጣቢያው ትራንዚት ዞን ውስጥ ቆይተዋል። በምሽትም በዚያው በአየር ማረፊያው ውስጥ ባለ ሆቴል ውስጥ እንዲያርፉ ሲደረግ አንደነበረም ተገልጿል። የተጫዋቾቹ ጥያቄ በፈንሳይ የስደተኞች ተቋም መልስ ካገኘ በፈረንሳይ ውስጥ እንዲኖሩ ሊፈቀድላቸው ይችላል። ቢቢሲ ከጂቡቲ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን መልስ ለማግኘት ሞክሮ ሳይሳካ ቀርቷል።
ሦስት የጂቡቲ እግር ኳስ ተጫዋቾች በፈረንሳይ ጥገኝነት ጠየቁ ሦስት የጂቡቲ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን አባላት በፈረንሳይ ጥገኝነት የጠየቁ ሲሆን ከመካከላቸውም ለአንድ ሳምንት በአየር መንገድ ውስጥ የቆየው ተጫዋች በመጨረሻ መውጣት ችሏል። ነስረዲን አብዲ የተሰኘው ይህ ተጫዋች በፓሪስ በኩል በ2022 የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጉዞ ላይ ለመሳተፍ ሊሳፈር የሚገባውን አውሮፕላን በመተው እዚያው ጥገኝነት ጠይቋል። ሁለቱ የቡድን አጋሮቹ ቢላል ሐሰን እና አቦቡካሪ ኤልሚ ረቡዕ ከአውሮፕላን ማረፊያው የወጡ ሲሆን ጉዳያቸውን ለፈረንሳይ መንግሥት እንዲያቀርቡ ሦስት ወር ተሰጥቷቸዋል። ሦስቱም ተጫዋቾች በአውሮፕላን ማረፊያው ውስጥ ሳሉ በ72 ሰዓታት ውስጥ ጉዳያቸውን የሚያስረዳ ሰነድ እንዲያቀርቡ ጊዜ ተሰጥቷቸው ነበር። ተጫዋቾቹን በማገዝ ላይ የሚገኘው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅትም ለጂቡቲ መንግሥት የሚሠሩት ሐሰን እና ኤልሚ ጥገኝነት ተከልክለው ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ ከተገደዱ እስር ቤት ሊገቡ ይችላሉ የሚል ሥጋት እንዳለው ገልጾ ነበር። ኤልሚ በፖሊስ አገልግሎት ተቀጥሮ የሚሠራ ሲሆን፤ ሐሰን በጂቡቲ ሪፐብሊካን ዘብ ውስጥ በሚሠራበት ወቅት መፈጸም የማይፈልገውን ትዕዛዝ ለመከተል እንደሚገደድ ተናግሮ ጥገኝነት ጠይቋል ተብሏል። "ትክክል ያልሆነ ነገር በተናገሩ ቁጥር በመንግሥት ይዋከባሉ" ሲሉ የጂቡቲ የሰብአዊ መብቶች ማኅበር ፕሬዝዳንት ዣን-ሎፕ ሻል ተናግረዋል። "ሐሰን የቤተሰቡን አባላት እንዲያስር ይገደድ ነበር። ይህንን እያደረገ ለመቀጠል አልፈለገም" ሲሉ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል። የሁለቱም የትዳር አጋሮች አንዲሁም ቤተሰቦች በጂቡቲ ውስጥ ይገኛሉ ያሉት የማኅበሩ ፕሬዝዳንት የሐሰን ባለቤት በመጨረሻው የእርግዝናዋ ወራት ውስጥ እንደምትገኝም አስታውቀዋል። ቡድኑ ከአራት ቀናት በፊት በአፍሪካ ሻምፒዮና በኒጀር 8 ለ 0 ተሸንፎ ከአልጄሪያ ወደ ሞሮኮ በቀጥታ መብረር ባለመቻሉ በፓሪስ አድርጎ ለመጓዝ ወደ ፈረንሳይ ተጉዞ ነበር። ተጫዋቾቹ በቪዛ ብሎም በኮቪድ ሰነዶች መጓደል ምክንያት ከፓሪስ ወደ ሞሮኮ የሚሄደው በረራቸው አምልጧቸዋል። ቀጥሎም ጥገኝነት ስለሚጠይቁበት መንገድ እቅድ ማውጣታቸው ተነግሯል። ሌሎች የቡድን አባላቶቻቸው ፓሪስን ለቀው ሲበሩ ሦስቱ የቡድን አባላት ግን ተደብቀው ቀርተዋል። "በሰፊ የግብ ልዩነት ተሸንፈው ወደ አገራቸው መመለስ በጣም ፈርተዋል" ሲሉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ መሪ ተናግረዋል። ከቀናት በፊት የፈረንሳይ ችሎት ሐሰን እና ኤልሚ ከአውሮፕላን ማረፊያው እንዲወጡ እስከሚፈቅድበት ጊዜ ድረስ ሦስቱም የእግር ኳስ ተጫዋቾች በጣቢያው ትራንዚት ዞን ውስጥ ቆይተዋል። በምሽትም በዚያው በአየር ማረፊያው ውስጥ ባለ ሆቴል ውስጥ እንዲያርፉ ሲደረግ አንደነበረም ተገልጿል። የተጫዋቾቹ ጥያቄ በፈንሳይ የስደተኞች ተቋም መልስ ካገኘ በፈረንሳይ ውስጥ እንዲኖሩ ሊፈቀድላቸው ይችላል። ቢቢሲ ከጂቡቲ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን መልስ ለማግኘት ሞክሮ ሳይሳካ ቀርቷል።
https://www.bbc.com/amharic/news-58527743
2health
ኮሮናቫይረስ፡ሪፐብሊካኖች በሚያደርጉት እጩ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሚዲያዎች እንዳይሳተፉ ተወሰነ
የአሜሪካ የሪፐብሊካን ፓርቲ በዚህ ወር እጩ ፕሬዚዳንቱን በይፋ ለመምረጥ እቅድ ይዟል። ይህ ምርጫም ሚዲያዎች እንዳይሳተፉበትና በዝግም እንደሚካሄድ ተገልጿል። የሪፐብሊካን ቃለ አቀባይ እንደተናገሩት ሚዲያ እንዳይሳተፍ የተወሰነው ከኮሮናቫይረስ መመሪያዎች ጋር በተያያዘ መሆኑንም አሶሺየትድ ፕሬስ ዘግቧል። በሰሜን ካሮላይና የሪፐብሊካን ልዑካን ተሰባስበውም እጩ ፕሬዚዳንቱን ዶናልድ ትራምፕን በይፋ እንደገና ይመርጣሉ። 336 የሚሆኑ ልዑካን በሰሜን ካሮላይና ግዛት፣ ቻርሎቴ ከተማ በዚህ ወር ይሰባሰባሉ። እነዚህ ልዑካን በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ቁጥሩ በመገደቡ መገኘት ያልቻሉትን በሺዎች የሚቆጠሩ አባላትን ወክለው ይገኛሉ። ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የፓርቲያቸው ብቸኛ እጩ ተወዳዳሪ ሲሆኑ፤ እንደገና በይፋ መመረጣቸውም የምረጡኝ ቅስቀሳ ዘመቻቸውንም እንዲሁ በይፋ መጀመሩን የሚያበስር ነው ተብሏል። "ፓርቲያችን በፌደራል እንዲሁም በተለያዩ ግዛቶች የወጡ የኮሮናቫይረስ መመሪያዎችን በመከተልም ነው ስብሰባውን የሚሳተፉ ሰዎች ቁጥርን የወሰንነው" በማለት ቃለ አቀባይዋ ተናግረዋል። ይህ ውሳኔ ከዚህ በፊት ይደረጉ የነበሩ ስብሰባዎቸን አካሄድ የቀየረ ነው ተብሏል። ከዚህ ቀደም እንዲህ አይነቱ ስብሰባ የበርካታ ሚዲያዎችን ቀልብ የሚስብና ለህዝቡም መልዕክቶች ይፋ የሚሆኑበት ነበር። የሰሜን ካሮላይና አስተዳዳሪ በሚገኙት ሰዎች ብዛትና አካላዊ ርቀት ጋር ተያይዞ ስብሰባውን ወደ ሌላ ቦታ እንዲያደርጉት መጠየቀቻውን ተከትሎ ግንቦት ወር ላይ ወደ ጃክሰን፣ ፎሎሪዳ እንደሚደረግ ትራምፕ ተናግረው ነበር። ነገር ግን ወደ በኋላ ፍሎሪዳ ሊደረግ የነበረውን ስብሰባ በመሰረዝ ወደቀደመው እቅድ በመመለስ ሰሜን ካሮላይና እንዲካሄድ ተወስኗል።ግዛቲቷ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ያለምክንያት እያቀጣጠሉ ነው በማለት ወንጅለዋል።
ኮሮናቫይረስ፡ሪፐብሊካኖች በሚያደርጉት እጩ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሚዲያዎች እንዳይሳተፉ ተወሰነ የአሜሪካ የሪፐብሊካን ፓርቲ በዚህ ወር እጩ ፕሬዚዳንቱን በይፋ ለመምረጥ እቅድ ይዟል። ይህ ምርጫም ሚዲያዎች እንዳይሳተፉበትና በዝግም እንደሚካሄድ ተገልጿል። የሪፐብሊካን ቃለ አቀባይ እንደተናገሩት ሚዲያ እንዳይሳተፍ የተወሰነው ከኮሮናቫይረስ መመሪያዎች ጋር በተያያዘ መሆኑንም አሶሺየትድ ፕሬስ ዘግቧል። በሰሜን ካሮላይና የሪፐብሊካን ልዑካን ተሰባስበውም እጩ ፕሬዚዳንቱን ዶናልድ ትራምፕን በይፋ እንደገና ይመርጣሉ። 336 የሚሆኑ ልዑካን በሰሜን ካሮላይና ግዛት፣ ቻርሎቴ ከተማ በዚህ ወር ይሰባሰባሉ። እነዚህ ልዑካን በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ቁጥሩ በመገደቡ መገኘት ያልቻሉትን በሺዎች የሚቆጠሩ አባላትን ወክለው ይገኛሉ። ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የፓርቲያቸው ብቸኛ እጩ ተወዳዳሪ ሲሆኑ፤ እንደገና በይፋ መመረጣቸውም የምረጡኝ ቅስቀሳ ዘመቻቸውንም እንዲሁ በይፋ መጀመሩን የሚያበስር ነው ተብሏል። "ፓርቲያችን በፌደራል እንዲሁም በተለያዩ ግዛቶች የወጡ የኮሮናቫይረስ መመሪያዎችን በመከተልም ነው ስብሰባውን የሚሳተፉ ሰዎች ቁጥርን የወሰንነው" በማለት ቃለ አቀባይዋ ተናግረዋል። ይህ ውሳኔ ከዚህ በፊት ይደረጉ የነበሩ ስብሰባዎቸን አካሄድ የቀየረ ነው ተብሏል። ከዚህ ቀደም እንዲህ አይነቱ ስብሰባ የበርካታ ሚዲያዎችን ቀልብ የሚስብና ለህዝቡም መልዕክቶች ይፋ የሚሆኑበት ነበር። የሰሜን ካሮላይና አስተዳዳሪ በሚገኙት ሰዎች ብዛትና አካላዊ ርቀት ጋር ተያይዞ ስብሰባውን ወደ ሌላ ቦታ እንዲያደርጉት መጠየቀቻውን ተከትሎ ግንቦት ወር ላይ ወደ ጃክሰን፣ ፎሎሪዳ እንደሚደረግ ትራምፕ ተናግረው ነበር። ነገር ግን ወደ በኋላ ፍሎሪዳ ሊደረግ የነበረውን ስብሰባ በመሰረዝ ወደቀደመው እቅድ በመመለስ ሰሜን ካሮላይና እንዲካሄድ ተወስኗል።ግዛቲቷ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ያለምክንያት እያቀጣጠሉ ነው በማለት ወንጅለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-53627157
3politics
ባለፈው ሰኔ በጋምቤላ የፀጥታ ኃይሎች የአዕምሮ ህሙማንን ጨምሮ 50 ሰላማዊ ሰዎች መግደላቸው ተገለጸ
በጋምቤላ ከተማ ሰኔ 07/2014 ዓ.ም በክልሉ የፀጥታ ኃይሎች፣ በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና በጋምቤላ ነጻነት ግንባር የተደረገውን ውጊያ ተከትሎ ቢያንስ 50 ሰላማዊ ሰዎች በፀጥታ ኃይሎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሸን (ኢሰመኮ) አስታወቀ። በጋምቤላ ክልል ያጋጠመውን ቀውስ በተመለከተ ኢሰመኮ ዛሬ ረቡዕ መስከረም 18/2014 ዓ.ም. ባወጣው ሪፖርት በጋምቤላ ከተማ በሰላማዊ ነዋሪዎች ላይ ከሕግ ውጪ ግድያ የፈጸሙ ኃላፊዎች ላይ የሕግ ተጠያቂነት እንዲኖርም ጠይቋል። በከተማዋ በሰኔ ወር መጀመሪያ ላይ በክልሉ የፀጥታ ኃይሎች፣ እና በአማጺያኑ ታጣቂዎች መካከል የተደረገውን ውጊያ ተከትሎ የተፈጸሙ ግድያዎችን፣ የአካል ጉዳቶችን እና ዘረፋዎችን በተመለከተ ኢሰመኮ ምርመራ ማድረጉን ገልጿል። ይህንንም በተመለከተ ኮሚሽኑ ይፋ ባደረገው 13 ገፅ ሪፖርት ከሰኔ 07 እስከ 09 ቀን 2014 ዓ.ም. በሰላማዊ ሰዎች ላይ ከሕግ ውጪ ግድያ፣ የአካል ጉዳት እና የንብረት ዘረፋ  በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች እና በታጣቂ ኃይሎች መፈጸሙን አመልክቷል። እነዚህን አካላት ይፋ ያደረገው ኢሰመኮ የጋምቤላ ክልል ልዩ ኃይል፣ ፖሊስ፣ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ የጋምቤላ ነጻነት ግንባር፣ ሚሊሻዎች እና ተባባሪ ወጣቶች ድርጊቱን በመፈጸም፣ በመምራት እና በማስፈፀም ተሳትፈዋል ብሏል። በሦስቱ ቀናት ውስጥ የክልሉ የፀጥታ ኃይሎች ሴቶችና የአዕምሮ ህሙማንን ጨምሮ ቢያንስ 50 ሰላማዊ ሰዎችን በተናጠል እና በጅምላ ከፍርድ ውጪ መግደላቸውን ኮሚሽኑ አረጋግጧል። ታጣቂዎቹ ከተማዋን ለቀው ከወጡ እና ከተማው በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ከገባም በኋላ ግድያዎቹ የተፈፀሙ ሲሆን ለዚህ የክልሉ  የጸጥታ ኃይሎች ተጠያቂ መሆናቸው ሰፍሯል። ኮሚሽኑ የክልሉ የጸጥታ ኃይሎች ብሎ የጠራቸው የክልሉ ልዩ ኃይል፣ መደበኛ ፖሊሶች፣ ሚሊሻዎች ሲሆኑ ከጸጥታ ኃይሎች ጋር የተባበሩ የተወሰኑ ወጣቶች መኖራቸው ተጠቅሷል። የጸጥታ ኃይሎቹ ባደረጉት አሰሳ ቢያንስ 50 ሰዎችን በመኖሪያ ቤታቸው ግቢ እና ውጪ፣በመንገድ ላይ እና በህግ አስከባሪዎች ቁጥጥር ስር የነበሩ ሰዎችን ጭምር ከህግ አግባብ ውጭ መግደላቸውን ኮሚሽኑ በምርመራ አረጋግጫለሁ ብሏል። በተጨማሪ 25 በሚሆኑ ሰዎች ላይ ቀላል እና ከባድ የአካል ጉዳት፣ ቁጥራቸው ያልተጠቀሱ በርካቶች ላይ ደግሞ ድብደባ እና የማሰቃየት ተግባር መፈጸሙን የኢሰመኮ ሪፖርት ያስረዳል። ለዚህም የፀጥታ ኃይሎቹ “የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች እና መሳሪያ በቤታችሁ እንዳለ ተጠቁመናል፤ የደበቃችሁትን መሳሪያ አውጡ” የሚል ምክንያትም እየሰጡ ነበር ብሏል። በክልሉ የፀጥታ ኃይሎች የተገደሉ ሰላማዊ ነዋሪዎች አስከሬን በክልሉ ልዩ ኃይሎች እና ፖሊሶች አማካይነት በጭነት መኪና ተሰብስበው ወዳልታወቀ ቦታ እንደተወሰደና በጅምላ እንዲቀበሩ መደረጉን ኮሚሽኑ የተጎጂ ቤተሰቦችን፣ ነዋሪዎችና የዓይን እማኞችን ዋቢ አድርጎ አስፍሯል። በተጨማሪም አስከሬን እንዲሰጣቸው ጥያቄ ያቀረቡ የሟች ቤተሰቦችም መከልከላቸውን አረጋግጧል። የሟቾች አስከሬን ለምን ለቤተሰቦች እንዳልተሰጠና የተቀበሩበት ቦታ ለምን ለቤተሰቦች እንዳልተገለጸ ኢሰመኮ የክልሉን ፖሊስ ጠይቆ፣ አስከሬን እንዲሰጠው ያመለከተ የከተማው ነዋሪ የለም የሚል መልስ ማግኘቱን ገልጿል። የከተማው ማዘጋጃ በበኩሉ ፌደራል ፖሊስን እንዲያነጋግሩ ለኢሰመኮ ምላሽ የሰጠ ሲሆን፣ የፌደራል ፖሊስ በበኩሉ አስከሬኖች ተሰብስበው የተቀበሩት በማዘጋጃ ቤቱ መሆኑን መግለጹ ተጠቅሷል። ከክልሉ የፀጥታ ኃይሎች ሌላ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና የጋምቤላ ነጻነት ግንባር ታጣቂዎችም ውጊያው በተካሄደበት ዕለት “ተኩሳችሁብናል” በሚል ምክንያት በመንገድ ላይ ሲንቀሳቀሱ ያገኟቸውን ቢያንስ ሰባት ሰዎች መግደላቸውን ያትታል። ከግድያው በተጨማሪ በበርካታ ነዋሪዎች ላይ የንብረት ዘረፋ እና ውድመት ማድረሳቸውንም ተገልጿል። የፀጥታ ኃይሎቹና ታጣቂ ኃይሎቹ ከገደሏቸው በተጨማሪ በተኩስ ልውውጡ ወቅት በየትኛው አካል እንደተገደሉ ያልታወቁ ስድስት ሰዎች ሕይወታችው ማለፉንም ሪፖርቱ አመልክቷል። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንም በበኩሉ ከውጊያው በኋላ ባደረገው ማጣራት የክልሉ ልዩ ኃይሎች ሰኔ 8 እና ሰኔ 9/2014 ዓ.ም. በከተማዋ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን ገልጾ፣ በተጨማሪ መወሰድ ያለባቸውን ሕጋዊ እርምጃዎችም መጠቆማቸውን ገልጸዋል። “የመብት ጥሰቶችን የፈጸሙ ሰዎችና ቡድኖችን ተጠያቂነት ለማረጋገጥ የሚደረጉ ጥረቶችን ለማገዝ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ፣ ተጎጂዎች ፍትሕ እና ተገቢውን የካሳ እና መልሶ የመቋቋም ድጋፍ እንዲያገኙና” ተፈጻሚነቱንም እንደሚከታተል ኢሰመኮ አሳስቧል። ሰኔ 07 ከጥዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ መንግሥት በሽብርተኛነት የሰየመው የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት እና የጋምቤላ ነጻነት ግንባር በጋራ ወደ ጋምቤላ ከተማ ገብተው ጥቃት መፈጸማቸውን ተከትሎ ከክልሉ ልዩ ኃይሎች፣ ፖሊሶች፣ ሚሊሻዎች እና ፌደራል ፖሊስ ጋር ውጊያ ተደርጓል። ታጣቂዎቹ የከተማዋን የተወሰነ ክፍል ተቆጣጥረው የነበረ ሲሆን ውጊያውንም ተከትሎ  የመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች የጋምቤላን ከተማ መልሰው መቆጣጠራቸው ይታወሳል።
ባለፈው ሰኔ በጋምቤላ የፀጥታ ኃይሎች የአዕምሮ ህሙማንን ጨምሮ 50 ሰላማዊ ሰዎች መግደላቸው ተገለጸ በጋምቤላ ከተማ ሰኔ 07/2014 ዓ.ም በክልሉ የፀጥታ ኃይሎች፣ በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና በጋምቤላ ነጻነት ግንባር የተደረገውን ውጊያ ተከትሎ ቢያንስ 50 ሰላማዊ ሰዎች በፀጥታ ኃይሎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሸን (ኢሰመኮ) አስታወቀ። በጋምቤላ ክልል ያጋጠመውን ቀውስ በተመለከተ ኢሰመኮ ዛሬ ረቡዕ መስከረም 18/2014 ዓ.ም. ባወጣው ሪፖርት በጋምቤላ ከተማ በሰላማዊ ነዋሪዎች ላይ ከሕግ ውጪ ግድያ የፈጸሙ ኃላፊዎች ላይ የሕግ ተጠያቂነት እንዲኖርም ጠይቋል። በከተማዋ በሰኔ ወር መጀመሪያ ላይ በክልሉ የፀጥታ ኃይሎች፣ እና በአማጺያኑ ታጣቂዎች መካከል የተደረገውን ውጊያ ተከትሎ የተፈጸሙ ግድያዎችን፣ የአካል ጉዳቶችን እና ዘረፋዎችን በተመለከተ ኢሰመኮ ምርመራ ማድረጉን ገልጿል። ይህንንም በተመለከተ ኮሚሽኑ ይፋ ባደረገው 13 ገፅ ሪፖርት ከሰኔ 07 እስከ 09 ቀን 2014 ዓ.ም. በሰላማዊ ሰዎች ላይ ከሕግ ውጪ ግድያ፣ የአካል ጉዳት እና የንብረት ዘረፋ  በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች እና በታጣቂ ኃይሎች መፈጸሙን አመልክቷል። እነዚህን አካላት ይፋ ያደረገው ኢሰመኮ የጋምቤላ ክልል ልዩ ኃይል፣ ፖሊስ፣ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ የጋምቤላ ነጻነት ግንባር፣ ሚሊሻዎች እና ተባባሪ ወጣቶች ድርጊቱን በመፈጸም፣ በመምራት እና በማስፈፀም ተሳትፈዋል ብሏል። በሦስቱ ቀናት ውስጥ የክልሉ የፀጥታ ኃይሎች ሴቶችና የአዕምሮ ህሙማንን ጨምሮ ቢያንስ 50 ሰላማዊ ሰዎችን በተናጠል እና በጅምላ ከፍርድ ውጪ መግደላቸውን ኮሚሽኑ አረጋግጧል። ታጣቂዎቹ ከተማዋን ለቀው ከወጡ እና ከተማው በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ከገባም በኋላ ግድያዎቹ የተፈፀሙ ሲሆን ለዚህ የክልሉ  የጸጥታ ኃይሎች ተጠያቂ መሆናቸው ሰፍሯል። ኮሚሽኑ የክልሉ የጸጥታ ኃይሎች ብሎ የጠራቸው የክልሉ ልዩ ኃይል፣ መደበኛ ፖሊሶች፣ ሚሊሻዎች ሲሆኑ ከጸጥታ ኃይሎች ጋር የተባበሩ የተወሰኑ ወጣቶች መኖራቸው ተጠቅሷል። የጸጥታ ኃይሎቹ ባደረጉት አሰሳ ቢያንስ 50 ሰዎችን በመኖሪያ ቤታቸው ግቢ እና ውጪ፣በመንገድ ላይ እና በህግ አስከባሪዎች ቁጥጥር ስር የነበሩ ሰዎችን ጭምር ከህግ አግባብ ውጭ መግደላቸውን ኮሚሽኑ በምርመራ አረጋግጫለሁ ብሏል። በተጨማሪ 25 በሚሆኑ ሰዎች ላይ ቀላል እና ከባድ የአካል ጉዳት፣ ቁጥራቸው ያልተጠቀሱ በርካቶች ላይ ደግሞ ድብደባ እና የማሰቃየት ተግባር መፈጸሙን የኢሰመኮ ሪፖርት ያስረዳል። ለዚህም የፀጥታ ኃይሎቹ “የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች እና መሳሪያ በቤታችሁ እንዳለ ተጠቁመናል፤ የደበቃችሁትን መሳሪያ አውጡ” የሚል ምክንያትም እየሰጡ ነበር ብሏል። በክልሉ የፀጥታ ኃይሎች የተገደሉ ሰላማዊ ነዋሪዎች አስከሬን በክልሉ ልዩ ኃይሎች እና ፖሊሶች አማካይነት በጭነት መኪና ተሰብስበው ወዳልታወቀ ቦታ እንደተወሰደና በጅምላ እንዲቀበሩ መደረጉን ኮሚሽኑ የተጎጂ ቤተሰቦችን፣ ነዋሪዎችና የዓይን እማኞችን ዋቢ አድርጎ አስፍሯል። በተጨማሪም አስከሬን እንዲሰጣቸው ጥያቄ ያቀረቡ የሟች ቤተሰቦችም መከልከላቸውን አረጋግጧል። የሟቾች አስከሬን ለምን ለቤተሰቦች እንዳልተሰጠና የተቀበሩበት ቦታ ለምን ለቤተሰቦች እንዳልተገለጸ ኢሰመኮ የክልሉን ፖሊስ ጠይቆ፣ አስከሬን እንዲሰጠው ያመለከተ የከተማው ነዋሪ የለም የሚል መልስ ማግኘቱን ገልጿል። የከተማው ማዘጋጃ በበኩሉ ፌደራል ፖሊስን እንዲያነጋግሩ ለኢሰመኮ ምላሽ የሰጠ ሲሆን፣ የፌደራል ፖሊስ በበኩሉ አስከሬኖች ተሰብስበው የተቀበሩት በማዘጋጃ ቤቱ መሆኑን መግለጹ ተጠቅሷል። ከክልሉ የፀጥታ ኃይሎች ሌላ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና የጋምቤላ ነጻነት ግንባር ታጣቂዎችም ውጊያው በተካሄደበት ዕለት “ተኩሳችሁብናል” በሚል ምክንያት በመንገድ ላይ ሲንቀሳቀሱ ያገኟቸውን ቢያንስ ሰባት ሰዎች መግደላቸውን ያትታል። ከግድያው በተጨማሪ በበርካታ ነዋሪዎች ላይ የንብረት ዘረፋ እና ውድመት ማድረሳቸውንም ተገልጿል። የፀጥታ ኃይሎቹና ታጣቂ ኃይሎቹ ከገደሏቸው በተጨማሪ በተኩስ ልውውጡ ወቅት በየትኛው አካል እንደተገደሉ ያልታወቁ ስድስት ሰዎች ሕይወታችው ማለፉንም ሪፖርቱ አመልክቷል። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንም በበኩሉ ከውጊያው በኋላ ባደረገው ማጣራት የክልሉ ልዩ ኃይሎች ሰኔ 8 እና ሰኔ 9/2014 ዓ.ም. በከተማዋ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን ገልጾ፣ በተጨማሪ መወሰድ ያለባቸውን ሕጋዊ እርምጃዎችም መጠቆማቸውን ገልጸዋል። “የመብት ጥሰቶችን የፈጸሙ ሰዎችና ቡድኖችን ተጠያቂነት ለማረጋገጥ የሚደረጉ ጥረቶችን ለማገዝ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ፣ ተጎጂዎች ፍትሕ እና ተገቢውን የካሳ እና መልሶ የመቋቋም ድጋፍ እንዲያገኙና” ተፈጻሚነቱንም እንደሚከታተል ኢሰመኮ አሳስቧል። ሰኔ 07 ከጥዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ መንግሥት በሽብርተኛነት የሰየመው የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት እና የጋምቤላ ነጻነት ግንባር በጋራ ወደ ጋምቤላ ከተማ ገብተው ጥቃት መፈጸማቸውን ተከትሎ ከክልሉ ልዩ ኃይሎች፣ ፖሊሶች፣ ሚሊሻዎች እና ፌደራል ፖሊስ ጋር ውጊያ ተደርጓል። ታጣቂዎቹ የከተማዋን የተወሰነ ክፍል ተቆጣጥረው የነበረ ሲሆን ውጊያውንም ተከትሎ  የመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች የጋምቤላን ከተማ መልሰው መቆጣጠራቸው ይታወሳል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cy67z0d35q2o
2health
ኮሮናቫይረስ ፡ የ90 ዓመቷ አዛውንት የፋይዘር/ባዮንቴከ ክትባትን በመከተብ በዓለም የመጀመሪያዋ ሆኑ
ዩናይትድ ኪንግደም ለመጀመሪያ ጊዜ የኮሮናቫይረስ ክትባትን ዛሬ ለዜጎቿ መስጠት ስትጀምር የዘጠና ዓመቷ አዛውንት የፋይዘር/ባዮንቴክ ክትባትን በመውሰድ በዓለም የመጀመሪያዋ ሆኑ። በሰሜን አየርላንድ ኢኒስኪለን ነዋሪ ሆኑት የዘጠና ዓመቷ የእድሜ ባለጸጋ ማርግሬት ኪናን የፋይዘር/ባዮንቴክ የኮቪድ-19 ክትባትን ከሙከራ ውጪ በመውሰድ በምድራችን የመጀመሪያዋ ሰው ሆነዋል። አዛውንቷ ማርግሬት በመርፌ የሚሰጠውን ክትባት ዛሬ ማክሰኞ ማለዳ በኮቬንትሪ ዩኒቨርስቲ ውስጥ በሚገኘው የክትባት ማእከል ተገኝተው ነው የወሰዱት። አሁን መሰጠት የተጀመረው የኮቪድ-19 ክትባት በዋናነት ትኩረት ያደረገው ለበሽታው በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ የሆኑትን ሰዎች ሲሆን በቀጣይም ለሌሎች እንደሚዳረስ ተነግሯል። በመላው ዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) የሚገኙ ከ70 በላይ የሚሆኑ ሆስፒታሎች እድሜያቸው ከ80 ዓመት በላይ ለሆኑ አዛውንቶች እና ለጤና ባለሙያዎች ክትባቱን ለመስጠት መዘጋጀታቸው ተገልጿል። የአሜሪካ እና የጀርመን ኩባንያ የሆኑት ፋይዘር እና ባዮንቴክ ያበለጸጉት ክትባት ዩናይትድ ኪንግደም ለዜጎቿ እንዲሰጥ የመድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን መፍቀዱ ይታወሳል። በዚህም ዩኬ ይህን ክትባት በመጠቀም የመጀመሪያዋ አገር ሆናለች። ክትባቱን ዛሬ ከሚወስዱት መካከል የ87 ዓመቱ ዶ/ር ሃሪ ሹክላ አንዱ ናቸው። ዶ/ር ሃሪ ክትባቱን ከባለቤታቸው ጋር በመሆን ኒውካስትል በሚገኝ ሆስፒታል እንደሚወስዱ ገልጸው በዚህም ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ለቢቢሲ ገልጸዋል። የክትባት አሰጣጥ መረሃ ግብሩ ቅድሚያ ለበሽታው ተጋላጭ የሆኑትን በማስቀደም ሕይወት ወደቀደመ መልኩ እንድትመለስ ይረዳል ተብሏል። "ቪ-ዴይ" ወይም የድል ቀን የሚል ስያሜ በተሰጠው ዕለት የሚጀመረው የክትባቱ መርሃ ግብር፤ ዜጎች ክትባቱን የመከተብ ግዴታ አይኖርባቸውም ተብሏል። ጠቅላይ ሚንሰትር ቦሪስ ጆንሰን፤ "ዩናይትድ ኪንግደም ከኮሮናቫይረስ ጋር በምታደርገው ትግል የዛሬዋ ቀን ሌላ ምዕራፍ ከፍታለች" ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ክትባቱን ለዜጎች ለማዳረስ ወራትን ሊፈጅ እንደሚችል አስታውሰው እስከዚያው ድረስ ግን መንግሥት ያስተላለፋቸው የኮሮናቫይረስ መመሪያዎችን ዜጎች እንዲተገብሩ አስታውሰዋል። እስካሁን በዩናይትድ ኪንግደም ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ ከ60ሺህ በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። መንግሥት በአሁኑ ወቅት 800 ሺህ የክትባት ብልቃጦችን ዝግጁ ያደረገ ሲሆን ተጨማሪ 40 ሚሊዮን ክትባቶችንም አዟል። ይህም ለ20 ሚሊዮን ሕዝብ በቂ ነው። 95 በመቶ ቫይረሱን የመከላከል አቅምን ያጎለብታል የተባለለትን ክትባት ሰዎች በ21 ቀናት ልዩነት ሁለት ጊዜ መወጋት ይኖርባቸዋል። ሰዎች ከቫይረሱ እራሳቸውን መከላከያ የሚጀምሩት ሁለተኛውን ክትባት ከወሰዱ ከሰባተኛው ቀን በኋላ ነው ተብሏል። ባለፉት ሁለት ቀናት ክትባቱን የያዙ ማቀዝቀዣዎች ከሚመረቱበት ቤልጄየም ወደ ዩናይትድ ኪንግደም ሲገቡ ቆይተዋል። በቀጣይ ሦስት ሳምንታት ውስጥም ተጨማሪ 10 ሚሊዮን የክትባት ብልቃቶች ወደ ዩኬ ገብተው ወደ ተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ይሰራጫሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከሳምንታት በኋላ ደግሞ በስታዲየሞች እና በግዙፍ መሰብሰቢያ አዳራሾች ለበርካታ ሰዎች በአንድ ጊዜ ክትባት መስጠት ይጀመራል ተብሏል።
ኮሮናቫይረስ ፡ የ90 ዓመቷ አዛውንት የፋይዘር/ባዮንቴከ ክትባትን በመከተብ በዓለም የመጀመሪያዋ ሆኑ ዩናይትድ ኪንግደም ለመጀመሪያ ጊዜ የኮሮናቫይረስ ክትባትን ዛሬ ለዜጎቿ መስጠት ስትጀምር የዘጠና ዓመቷ አዛውንት የፋይዘር/ባዮንቴክ ክትባትን በመውሰድ በዓለም የመጀመሪያዋ ሆኑ። በሰሜን አየርላንድ ኢኒስኪለን ነዋሪ ሆኑት የዘጠና ዓመቷ የእድሜ ባለጸጋ ማርግሬት ኪናን የፋይዘር/ባዮንቴክ የኮቪድ-19 ክትባትን ከሙከራ ውጪ በመውሰድ በምድራችን የመጀመሪያዋ ሰው ሆነዋል። አዛውንቷ ማርግሬት በመርፌ የሚሰጠውን ክትባት ዛሬ ማክሰኞ ማለዳ በኮቬንትሪ ዩኒቨርስቲ ውስጥ በሚገኘው የክትባት ማእከል ተገኝተው ነው የወሰዱት። አሁን መሰጠት የተጀመረው የኮቪድ-19 ክትባት በዋናነት ትኩረት ያደረገው ለበሽታው በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ የሆኑትን ሰዎች ሲሆን በቀጣይም ለሌሎች እንደሚዳረስ ተነግሯል። በመላው ዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) የሚገኙ ከ70 በላይ የሚሆኑ ሆስፒታሎች እድሜያቸው ከ80 ዓመት በላይ ለሆኑ አዛውንቶች እና ለጤና ባለሙያዎች ክትባቱን ለመስጠት መዘጋጀታቸው ተገልጿል። የአሜሪካ እና የጀርመን ኩባንያ የሆኑት ፋይዘር እና ባዮንቴክ ያበለጸጉት ክትባት ዩናይትድ ኪንግደም ለዜጎቿ እንዲሰጥ የመድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን መፍቀዱ ይታወሳል። በዚህም ዩኬ ይህን ክትባት በመጠቀም የመጀመሪያዋ አገር ሆናለች። ክትባቱን ዛሬ ከሚወስዱት መካከል የ87 ዓመቱ ዶ/ር ሃሪ ሹክላ አንዱ ናቸው። ዶ/ር ሃሪ ክትባቱን ከባለቤታቸው ጋር በመሆን ኒውካስትል በሚገኝ ሆስፒታል እንደሚወስዱ ገልጸው በዚህም ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ለቢቢሲ ገልጸዋል። የክትባት አሰጣጥ መረሃ ግብሩ ቅድሚያ ለበሽታው ተጋላጭ የሆኑትን በማስቀደም ሕይወት ወደቀደመ መልኩ እንድትመለስ ይረዳል ተብሏል። "ቪ-ዴይ" ወይም የድል ቀን የሚል ስያሜ በተሰጠው ዕለት የሚጀመረው የክትባቱ መርሃ ግብር፤ ዜጎች ክትባቱን የመከተብ ግዴታ አይኖርባቸውም ተብሏል። ጠቅላይ ሚንሰትር ቦሪስ ጆንሰን፤ "ዩናይትድ ኪንግደም ከኮሮናቫይረስ ጋር በምታደርገው ትግል የዛሬዋ ቀን ሌላ ምዕራፍ ከፍታለች" ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ክትባቱን ለዜጎች ለማዳረስ ወራትን ሊፈጅ እንደሚችል አስታውሰው እስከዚያው ድረስ ግን መንግሥት ያስተላለፋቸው የኮሮናቫይረስ መመሪያዎችን ዜጎች እንዲተገብሩ አስታውሰዋል። እስካሁን በዩናይትድ ኪንግደም ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ ከ60ሺህ በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። መንግሥት በአሁኑ ወቅት 800 ሺህ የክትባት ብልቃጦችን ዝግጁ ያደረገ ሲሆን ተጨማሪ 40 ሚሊዮን ክትባቶችንም አዟል። ይህም ለ20 ሚሊዮን ሕዝብ በቂ ነው። 95 በመቶ ቫይረሱን የመከላከል አቅምን ያጎለብታል የተባለለትን ክትባት ሰዎች በ21 ቀናት ልዩነት ሁለት ጊዜ መወጋት ይኖርባቸዋል። ሰዎች ከቫይረሱ እራሳቸውን መከላከያ የሚጀምሩት ሁለተኛውን ክትባት ከወሰዱ ከሰባተኛው ቀን በኋላ ነው ተብሏል። ባለፉት ሁለት ቀናት ክትባቱን የያዙ ማቀዝቀዣዎች ከሚመረቱበት ቤልጄየም ወደ ዩናይትድ ኪንግደም ሲገቡ ቆይተዋል። በቀጣይ ሦስት ሳምንታት ውስጥም ተጨማሪ 10 ሚሊዮን የክትባት ብልቃቶች ወደ ዩኬ ገብተው ወደ ተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ይሰራጫሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከሳምንታት በኋላ ደግሞ በስታዲየሞች እና በግዙፍ መሰብሰቢያ አዳራሾች ለበርካታ ሰዎች በአንድ ጊዜ ክትባት መስጠት ይጀመራል ተብሏል።
https://www.bbc.com/amharic/news-55226540
5sports
የዓመቱ የአፍሪካ ምርጥ ስፖርተኛ ዕጩዎች ይፋ ሆኑ
በአፍሪካዊያን እና ዩናይትድ ኪንግደም በሚገኙ ጋዜጠኞች የተመለመሉት ስድስቱ የቢቢሲ የአፍሪካ የዓመቱ ምርጥ ስፖርተኞች ዝርዝር ይፋ ሆኗል። የጋዜጠኞቹ ጉባዔ ስድስት ዕጩዎችን ይፋ ያደረገ ሲሆን ስፖርተኞች በ2021 በዓለም አቀፍ መድረክ አፍሪካን ያስጠሩ ናቸው። እነሆ የዕጩዎቹ ዝርዝር፡ እርስዎም የዘንድሮው ሽልማት ይገባዋል ለሚሉት ዕጬ ድምፅዎን እዚህ መስጠት ይችላሉ። ድምፅ መስጫው ሰዓት የሚያበቃው ታኅሣሥ 11 ከሌሊቱ 9 ሰዓት ሲሆን የሽልማቱ አሸናፊ ታኅሣሥ 29 በፎከስ ኦን አፍሪካ ቴሌቪዥንና ራድዮ እንዲሁም በቢቢሲ ስፖርት ድረ-ገፅ ላይ ይፋ ይደረጋል። ዕጩዎቹን በዝርዝር ስንመለከት ኢሊዩድ ኪፕቾጌ አገር፡ ኬንያ ዕድሜ፡ 37 የሩጫ መስክ፡ ማራቶን ኪፕቾጌ በማራቶን ሩጫ እስከዛሬ ከታዩ አትሌቶች ምርጡ ነው ሲባል ይደመጣል። ኪፕቾጌ በሁለት ተከታታይ ኦሊምፒኮች በማራቶን ውድድር ወርቅ ማምጣት ችሏል። ኬንያዊው አትሌት በኦሊምፒክ ታሪክ በተከታታይ ማራቶን ያሸነፈ ሦስተኛው ሯጭ ሲሆን በዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ምርጥ ወንድ አትሌት ተብሎም ተመርጧል። በቶኪዮ ኦሊምፒክ ድል ያስመዘገበው ኪፕቾጌ 15 ጊዜ ማራቶን ሮጦ 13 ጊዜ ድል ማድረግ ችሏል። ከእነዚህ መካከል የርቀቱን ክብረ ወሰን በ2 ሰዓት ከ1 ደቂቃ ከ39 ሰከንድ የያዘበት የበርሊን ማራቶን ተጠቃሽ ነው። ፌይዝ ኪፕዬጎን አገር፡ ኬንያ ዕድሜ፡ 27 የሩጫ መስክ፡ መካከለኛ ርቀት ፌይዝ በቶኪዮ ኦሊምፒክስ በ1500 የውድድሩን ክብረ ወሰን መስበር ችላለች። በዚህ ርቀት በሪዮ የመጀመሪያዋን ወርቅ ማምጣቷም አይዘነጋም። በወሊድ ምክንያት ከ21 ወራት በኋላ ወደ ሩጫ መድረክ የተመለሰችው ፌይዝ ከወሊድ በኋላ በተመሳሳይ ርቀት ያሸነፈች በታሪክ ሦስተኛዋ አትሌት ሆናለች። ባለፈው ሐምሌ ሞናኮ በተረገ ውድድር በታሪክ አራተኛውን ፈጣን ሰዓት ማስመዝገቧ ይታወሳል። የፌይዝ ቀጣይ ዓላማዋ የርቀቱን የዓለም ክብረ ወሰን መጨበጥ ነው። ኡንታንዶ ማሽላንጉ አገር፡ ደቡብ አፍሪካዊ ዕድሜ፡ 19 የስፖርት መስክ፡ ዝላይና 200 ሜትር ሩጫ ማሽላንጉ በፓራሊምፒክ ውድድር የመጀመሪያውን ሜዳሊያ ያገኘው የ14 ታዳጊ ሳለ ነበር። በያዝነው ዓመት በ200 ሜትር [ቲ61] እና በዝላይ [ቲ63] ውድድሮች ወርቅ ማምጣት ችሏል። ደቡብ አፍሪካዊው አትሌት በ7.17 ሜትር ዝላይ የዓለም ክብረ ወሰንን ሰብሯል። ወደፊት ብዙ ስኬቶች የሚጠብቁት ወጣቱ አትሌት የ10 ዓመት ታዳጊ ሳለ ነበር እግሮቹን ያጣው። ማሽላንጉ ባለፈው ሚያዚያ በ22.94 ሰከንድ የ200 ሜትር የዓለም የወንዶች ክብረ ወሰንን ጨብጧል። ክሪስቲን ምቦማ አገር፡ ናሚቢያ ዕድሜ፡ 18 የስፖርት መስክ፡ አጭር ርቀት በ2020 የቶኪዮ ኦሊምፒክ ተሳታፊ የነበረችው ክሪስቲን በኦሊምፒክ የአሸናፊዎች መድረክ ላይ በመቆም የመጀመሪያዋ ናሚቢያዊት ሆናለች። በ25 ዓመታት የናሚቢያ ኦሊምፒክ ታሪክ የመጀመሪያውን ሜዳሊያ ያስገኘችው ክሪስቲን በ200 ሜትር ርቀት የጃማይካዋ ኦሊምፒክ ቻምፒዮን ኢለይን ቶምፕሰን-ሄራንን ተከትላ በመግባት ብር አግኝታለች። ክሪስቲን የገባችበት 21.81 ሰከንድ በርቀቱ ከ20 ዓመት በታች ፈጣኑ ሰዓት ሆኖ ተመዝግቦላታል። ባለፈው መስከረም ዙሪክ በተካሄደው ዳይመንድ ሊግ በ21.78 ሰከንድ ከማሸነፏም በላይ የአፍሪካ ክብረ ወሰንን ሰብራለች። የ18 ዓመቷ ታዳጊ በ400 ሜትር በዓለም አትሌቲክስ እንዳትሳተፍ የታገደች በተፈጥሮ ባላት ከፍተኝ ቴስቴስትሮን ምክንያት ነው። ኤድዋርዶ ሜንዲ አገር፡ ሴኔጋል ዕድሜ፡ 29 የስፖርት መስክ፡ እግር ኳስ ኤድዋርድ ሜንዲ ከፈረንሳዩ ክለብ ሬኔስ ወደ ቼልሲ ከተዛዋረ በኋላ በስታንፈርድ ብሪጅ ብቃቱን ማሳየት ችሏል። ባለፈው ግንቦት ደግሞ የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ በማንሳት ታሪክ ፅፏል። ወደ ቻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ ባደረገው ግስጋሴ ስምንት ጨዋታዎች ግብ ሳይቆጠርበት በመጠበቁ ታሪክ ተጋርቷል። ሜንዲ በቻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ የተጫወተ የመጀመሪያው ግብ ጠባቂም መሆን ችሏል። ከዚህ በፊት በአውሮፓ አህጉራዊ ዋንጫ ታሪክ በፍፃሜ የተሰለፈው የመጀመሪያው ግብ ጠባቂ ዚምባብዌያዊው ብሩስ ግሮብላር ሲሆን ይሄም በ1985 በአውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ የተጻፈ ታሪክ ነው። ሜንዲ ባለፈው ውድድር ዘመን በሁሉም ውድድሮች 19 ጨዋታዎች ግብ ሳይቆጠርበት በመጠበቁ የአውሮፓ የ2020-21 ምርጡ ግብ ጠባቂ ተብሎ ተሸልሟል። ሜንዲ በፍራንስ ፉትቦል የሚዘጋጀው የባለንዶር ሽልማት የያሺን ሽልማትን ባያገኘም ከዕጩዎቹ መካከል አንዱ ነበር። ታቲያና ስኩንማርከር አገር፡ ደቡብ አፍሪካ ዕድሜ፡ 24 የስፖርት መስክ፡ ውሃ ዋና ታቲያና በቶኪዮ ኦሊምፒክ በውሃ ዋና የወርቅና የብር ሜዳሊያ ለአገሯ ደቡብ አፍሪካ ከማስገኘቷም በላይ በ200 እና 100 ሜትር የዓለምና የኦሊምፒክ ክብረ ወሰንን መስበር ችላለች። ታቲያና በሪዮ ኦሊምፒክ ለመሳተፍ ባደረገችው ውድድር በሽራፊ ማይክሮሰከንድ ተሸንፋ በመውደቋ ከስፖርቱ ዓለም ራሷን ለማግለል ጫፍ ደርሳ ነበር። ነገር ግን ተስፋ ባለመቁረጥ ወደፊት በመግፋት በርካታ ዓለም አቀፍና አህጉራዊ ድሎችን ተጎናፅፋለች።
የዓመቱ የአፍሪካ ምርጥ ስፖርተኛ ዕጩዎች ይፋ ሆኑ በአፍሪካዊያን እና ዩናይትድ ኪንግደም በሚገኙ ጋዜጠኞች የተመለመሉት ስድስቱ የቢቢሲ የአፍሪካ የዓመቱ ምርጥ ስፖርተኞች ዝርዝር ይፋ ሆኗል። የጋዜጠኞቹ ጉባዔ ስድስት ዕጩዎችን ይፋ ያደረገ ሲሆን ስፖርተኞች በ2021 በዓለም አቀፍ መድረክ አፍሪካን ያስጠሩ ናቸው። እነሆ የዕጩዎቹ ዝርዝር፡ እርስዎም የዘንድሮው ሽልማት ይገባዋል ለሚሉት ዕጬ ድምፅዎን እዚህ መስጠት ይችላሉ። ድምፅ መስጫው ሰዓት የሚያበቃው ታኅሣሥ 11 ከሌሊቱ 9 ሰዓት ሲሆን የሽልማቱ አሸናፊ ታኅሣሥ 29 በፎከስ ኦን አፍሪካ ቴሌቪዥንና ራድዮ እንዲሁም በቢቢሲ ስፖርት ድረ-ገፅ ላይ ይፋ ይደረጋል። ዕጩዎቹን በዝርዝር ስንመለከት ኢሊዩድ ኪፕቾጌ አገር፡ ኬንያ ዕድሜ፡ 37 የሩጫ መስክ፡ ማራቶን ኪፕቾጌ በማራቶን ሩጫ እስከዛሬ ከታዩ አትሌቶች ምርጡ ነው ሲባል ይደመጣል። ኪፕቾጌ በሁለት ተከታታይ ኦሊምፒኮች በማራቶን ውድድር ወርቅ ማምጣት ችሏል። ኬንያዊው አትሌት በኦሊምፒክ ታሪክ በተከታታይ ማራቶን ያሸነፈ ሦስተኛው ሯጭ ሲሆን በዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ምርጥ ወንድ አትሌት ተብሎም ተመርጧል። በቶኪዮ ኦሊምፒክ ድል ያስመዘገበው ኪፕቾጌ 15 ጊዜ ማራቶን ሮጦ 13 ጊዜ ድል ማድረግ ችሏል። ከእነዚህ መካከል የርቀቱን ክብረ ወሰን በ2 ሰዓት ከ1 ደቂቃ ከ39 ሰከንድ የያዘበት የበርሊን ማራቶን ተጠቃሽ ነው። ፌይዝ ኪፕዬጎን አገር፡ ኬንያ ዕድሜ፡ 27 የሩጫ መስክ፡ መካከለኛ ርቀት ፌይዝ በቶኪዮ ኦሊምፒክስ በ1500 የውድድሩን ክብረ ወሰን መስበር ችላለች። በዚህ ርቀት በሪዮ የመጀመሪያዋን ወርቅ ማምጣቷም አይዘነጋም። በወሊድ ምክንያት ከ21 ወራት በኋላ ወደ ሩጫ መድረክ የተመለሰችው ፌይዝ ከወሊድ በኋላ በተመሳሳይ ርቀት ያሸነፈች በታሪክ ሦስተኛዋ አትሌት ሆናለች። ባለፈው ሐምሌ ሞናኮ በተረገ ውድድር በታሪክ አራተኛውን ፈጣን ሰዓት ማስመዝገቧ ይታወሳል። የፌይዝ ቀጣይ ዓላማዋ የርቀቱን የዓለም ክብረ ወሰን መጨበጥ ነው። ኡንታንዶ ማሽላንጉ አገር፡ ደቡብ አፍሪካዊ ዕድሜ፡ 19 የስፖርት መስክ፡ ዝላይና 200 ሜትር ሩጫ ማሽላንጉ በፓራሊምፒክ ውድድር የመጀመሪያውን ሜዳሊያ ያገኘው የ14 ታዳጊ ሳለ ነበር። በያዝነው ዓመት በ200 ሜትር [ቲ61] እና በዝላይ [ቲ63] ውድድሮች ወርቅ ማምጣት ችሏል። ደቡብ አፍሪካዊው አትሌት በ7.17 ሜትር ዝላይ የዓለም ክብረ ወሰንን ሰብሯል። ወደፊት ብዙ ስኬቶች የሚጠብቁት ወጣቱ አትሌት የ10 ዓመት ታዳጊ ሳለ ነበር እግሮቹን ያጣው። ማሽላንጉ ባለፈው ሚያዚያ በ22.94 ሰከንድ የ200 ሜትር የዓለም የወንዶች ክብረ ወሰንን ጨብጧል። ክሪስቲን ምቦማ አገር፡ ናሚቢያ ዕድሜ፡ 18 የስፖርት መስክ፡ አጭር ርቀት በ2020 የቶኪዮ ኦሊምፒክ ተሳታፊ የነበረችው ክሪስቲን በኦሊምፒክ የአሸናፊዎች መድረክ ላይ በመቆም የመጀመሪያዋ ናሚቢያዊት ሆናለች። በ25 ዓመታት የናሚቢያ ኦሊምፒክ ታሪክ የመጀመሪያውን ሜዳሊያ ያስገኘችው ክሪስቲን በ200 ሜትር ርቀት የጃማይካዋ ኦሊምፒክ ቻምፒዮን ኢለይን ቶምፕሰን-ሄራንን ተከትላ በመግባት ብር አግኝታለች። ክሪስቲን የገባችበት 21.81 ሰከንድ በርቀቱ ከ20 ዓመት በታች ፈጣኑ ሰዓት ሆኖ ተመዝግቦላታል። ባለፈው መስከረም ዙሪክ በተካሄደው ዳይመንድ ሊግ በ21.78 ሰከንድ ከማሸነፏም በላይ የአፍሪካ ክብረ ወሰንን ሰብራለች። የ18 ዓመቷ ታዳጊ በ400 ሜትር በዓለም አትሌቲክስ እንዳትሳተፍ የታገደች በተፈጥሮ ባላት ከፍተኝ ቴስቴስትሮን ምክንያት ነው። ኤድዋርዶ ሜንዲ አገር፡ ሴኔጋል ዕድሜ፡ 29 የስፖርት መስክ፡ እግር ኳስ ኤድዋርድ ሜንዲ ከፈረንሳዩ ክለብ ሬኔስ ወደ ቼልሲ ከተዛዋረ በኋላ በስታንፈርድ ብሪጅ ብቃቱን ማሳየት ችሏል። ባለፈው ግንቦት ደግሞ የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ በማንሳት ታሪክ ፅፏል። ወደ ቻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ ባደረገው ግስጋሴ ስምንት ጨዋታዎች ግብ ሳይቆጠርበት በመጠበቁ ታሪክ ተጋርቷል። ሜንዲ በቻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ የተጫወተ የመጀመሪያው ግብ ጠባቂም መሆን ችሏል። ከዚህ በፊት በአውሮፓ አህጉራዊ ዋንጫ ታሪክ በፍፃሜ የተሰለፈው የመጀመሪያው ግብ ጠባቂ ዚምባብዌያዊው ብሩስ ግሮብላር ሲሆን ይሄም በ1985 በአውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ የተጻፈ ታሪክ ነው። ሜንዲ ባለፈው ውድድር ዘመን በሁሉም ውድድሮች 19 ጨዋታዎች ግብ ሳይቆጠርበት በመጠበቁ የአውሮፓ የ2020-21 ምርጡ ግብ ጠባቂ ተብሎ ተሸልሟል። ሜንዲ በፍራንስ ፉትቦል የሚዘጋጀው የባለንዶር ሽልማት የያሺን ሽልማትን ባያገኘም ከዕጩዎቹ መካከል አንዱ ነበር። ታቲያና ስኩንማርከር አገር፡ ደቡብ አፍሪካ ዕድሜ፡ 24 የስፖርት መስክ፡ ውሃ ዋና ታቲያና በቶኪዮ ኦሊምፒክ በውሃ ዋና የወርቅና የብር ሜዳሊያ ለአገሯ ደቡብ አፍሪካ ከማስገኘቷም በላይ በ200 እና 100 ሜትር የዓለምና የኦሊምፒክ ክብረ ወሰንን መስበር ችላለች። ታቲያና በሪዮ ኦሊምፒክ ለመሳተፍ ባደረገችው ውድድር በሽራፊ ማይክሮሰከንድ ተሸንፋ በመውደቋ ከስፖርቱ ዓለም ራሷን ለማግለል ጫፍ ደርሳ ነበር። ነገር ግን ተስፋ ባለመቁረጥ ወደፊት በመግፋት በርካታ ዓለም አቀፍና አህጉራዊ ድሎችን ተጎናፅፋለች።
https://www.bbc.com/amharic/news-59546277
2health
ኮሮናቫይረስ፡ በኖርዌይ የአንዲት መርከብ ተሳፋሪዎችና ሠራተኞች በቫይረሱ ተያዙ
በኖርዌይ የመዝናኛ መርከብ ላይ ተሳፍረው የነበሩ ቢያንስ 40 መንገደኞችና ሠራተኞች በኮቪድ-19 መያዛቸውን ባለሥልጣናት አስታወቁ። ኤምኤስ ሮልስ አሙንድሰን በተባለችው መርከብ ላይ ተሳፍረው የነበሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሌሎች መንገደኞች ደግሞ ለይቶ ማቆያ ገብተው የምርመራ ውጤታቸውን እየተጠባበቁ እንደሆነ የመርከቧ ባለንብረት ተናግረዋል። ሁርቲግሩትን የተባለ የኖርዌይ ድርጅት ንብረት የሆነችው መርከብ በትሮምሶ ወደብ ያረፈችው ባሳለፍነው አርብ ነበር። በዚህም ሳቢያ ድርጅቱ ሁሉንም የመዝናኛ መርከቦቹን እንዳይንቀሳቀሱ አግዷል። የድርጅቱ ኃላፊ ዳንኤል ስካይልዳም "አሁን ትኩረት ያደረግነው ባልደረቦቻችንና እንግዶቻችንን ለመንከባከብ የምንችለውን ሁሉ በማድረግ ላይ ነው" ሲሉ በመግለጫቸው ተናግረዋል። አራት የመርከቡ ሠራተኞች የኮሮናቫይረስ ምልክት ታይቶባቸው አርብ ዕለት መርከቧ ወደብ ላይ ካረፈች በኋላ ሆስፒታል የገቡ ሲሆን በኋላ ላይ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ከ158 ሠራተኞች መካከልም ሌሎች 32ቱ በቫይረሱ መያዛቸው የምርመራ ውጤታቸው አመላክቷል። ይሁን እንጂ 180 የሚሆኑ መንገደኞች ከመርከቧ እንዲወጡ የተፈቀደላቸው ሲሆን በባለሥልጣናት ቁጥጥር እንዲመረመሩ ተደርጓል። ሁሉም መንገደኞች ራሳቸውን እንዲለዩ መደረጉንም የጤና ባለሥልጣናት ተናግረዋል። ከሐምሌ አጋማሽ ጀምሮ በመርከቧ ጉዞ ላይ ከነበሩ 387 ተሳፋሪዎች መካካልም እስካሁን በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠው አምስት እንደሆኑ ተገልጿል። የጤና ባለሥልጣን የሆኑት ሊን ቮልድ ለሮይተርስ የዜና ወኪል እንደተናገሩት አሁን ከተከሰተው የቫይረስ ሥርጭት ጋር ተያይዞ በርካታ ሰዎች ቫይረሱ ሊገኝባቸው እንደሚችል ገልፀዋል። መርከቧ በአርክቲክ በሚገኘው ስቫልባርድ ለአንድ ሳምንት የቆየች ሲሆን በኢንግላንድና ስኮትላንድ የሚገኙ ወደቦችን ደግሞ መስከረም ላይ ለመጎብኘት እቅድ ይዛ ነበር ተብሏል። ይሁን እንጂ ኢንዱስትሪው በወረርሽኙ በመመታቱ ሁሉም የወደፊት ጉዞዎች ስለመኖራቸው የታወቀ ነገር እንደሌለ ተገልጿል። በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ወረርሽኙ በመርከቦች ላይ በመዛመቱ በሺህዎች የሚቆጠሩ መንገደኞች በባሕር ላይ እንቅስቃሴያቸው ተገድቦ መቆየታቸው ይታወሳል።
ኮሮናቫይረስ፡ በኖርዌይ የአንዲት መርከብ ተሳፋሪዎችና ሠራተኞች በቫይረሱ ተያዙ በኖርዌይ የመዝናኛ መርከብ ላይ ተሳፍረው የነበሩ ቢያንስ 40 መንገደኞችና ሠራተኞች በኮቪድ-19 መያዛቸውን ባለሥልጣናት አስታወቁ። ኤምኤስ ሮልስ አሙንድሰን በተባለችው መርከብ ላይ ተሳፍረው የነበሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሌሎች መንገደኞች ደግሞ ለይቶ ማቆያ ገብተው የምርመራ ውጤታቸውን እየተጠባበቁ እንደሆነ የመርከቧ ባለንብረት ተናግረዋል። ሁርቲግሩትን የተባለ የኖርዌይ ድርጅት ንብረት የሆነችው መርከብ በትሮምሶ ወደብ ያረፈችው ባሳለፍነው አርብ ነበር። በዚህም ሳቢያ ድርጅቱ ሁሉንም የመዝናኛ መርከቦቹን እንዳይንቀሳቀሱ አግዷል። የድርጅቱ ኃላፊ ዳንኤል ስካይልዳም "አሁን ትኩረት ያደረግነው ባልደረቦቻችንና እንግዶቻችንን ለመንከባከብ የምንችለውን ሁሉ በማድረግ ላይ ነው" ሲሉ በመግለጫቸው ተናግረዋል። አራት የመርከቡ ሠራተኞች የኮሮናቫይረስ ምልክት ታይቶባቸው አርብ ዕለት መርከቧ ወደብ ላይ ካረፈች በኋላ ሆስፒታል የገቡ ሲሆን በኋላ ላይ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ከ158 ሠራተኞች መካከልም ሌሎች 32ቱ በቫይረሱ መያዛቸው የምርመራ ውጤታቸው አመላክቷል። ይሁን እንጂ 180 የሚሆኑ መንገደኞች ከመርከቧ እንዲወጡ የተፈቀደላቸው ሲሆን በባለሥልጣናት ቁጥጥር እንዲመረመሩ ተደርጓል። ሁሉም መንገደኞች ራሳቸውን እንዲለዩ መደረጉንም የጤና ባለሥልጣናት ተናግረዋል። ከሐምሌ አጋማሽ ጀምሮ በመርከቧ ጉዞ ላይ ከነበሩ 387 ተሳፋሪዎች መካካልም እስካሁን በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠው አምስት እንደሆኑ ተገልጿል። የጤና ባለሥልጣን የሆኑት ሊን ቮልድ ለሮይተርስ የዜና ወኪል እንደተናገሩት አሁን ከተከሰተው የቫይረስ ሥርጭት ጋር ተያይዞ በርካታ ሰዎች ቫይረሱ ሊገኝባቸው እንደሚችል ገልፀዋል። መርከቧ በአርክቲክ በሚገኘው ስቫልባርድ ለአንድ ሳምንት የቆየች ሲሆን በኢንግላንድና ስኮትላንድ የሚገኙ ወደቦችን ደግሞ መስከረም ላይ ለመጎብኘት እቅድ ይዛ ነበር ተብሏል። ይሁን እንጂ ኢንዱስትሪው በወረርሽኙ በመመታቱ ሁሉም የወደፊት ጉዞዎች ስለመኖራቸው የታወቀ ነገር እንደሌለ ተገልጿል። በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ወረርሽኙ በመርከቦች ላይ በመዛመቱ በሺህዎች የሚቆጠሩ መንገደኞች በባሕር ላይ እንቅስቃሴያቸው ተገድቦ መቆየታቸው ይታወሳል።
https://www.bbc.com/amharic/53640749
5sports
ስቴቨን ጄራርድ የአስተን ቪላ አሰልጣኝ ሆኖ ተሾመ
የቀድሞ የሊቨርፑል እና የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አማካይ ስቴቨን የአስቶን ቪላ ክለብ አሰልጣኝ ሆኖ ተሾመ። ጄራርድ ክለቡን ለሦስት ዓመት ተኩል ለማሰልጠን ውል መያዙ አስተን ቪላ ክለብ ይፋ አድርጓል። የ41 ዓመቱ ጄራርድ የአስተን ቪላ ክለብ ኃላፊነትን ከመቀበሉ በፊት ለሦስት ዓመታት የስኮትላንድ ክለብ የሆነውን ሬንጀርስን ሲያሰለጥን ቆይቷል። ጄራርድ ሬንጀርስ በባለፈው የውድድር ዘመን ከ10 ዓመታት በኋላ የሊጉን ዋንጫ እንዲያነሰ ረድቶ ነበር። ዕሁድ ዕለት አስተን ቪላ አምስት ዓመት በክለቡ የቆዩትን አሰልጣኝ ዲን ስሚዝን ከሥራ ማሰናበቱ ይታወሳል። አስተን ቪላ በአሁኑ ወቅት በፕሪሚየር ሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ላይ ከወራጅ ቀጠና በሁለት ነጥቦች ብቻ ርቀው 16ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። "አስተን ቪላ በእንግሊዝ እግር ኳስ ውስጥ ብዙ ታሪክ እና ባህል ያለው ክለብ ነው፤ አሰልጣኝ በመሆኔ ትልቅ ክብር ተሰምቶኛል" ብሏል ጄራርድ ከሹመቱ በኋል። ጄራርድ የበላይ የአሰልጣኝነት ሥራውን የጀመረው የኮቲሹን ሬንጀርስ ክለብ እአአ 2018 ላይ ማሰልጠን በጀመረበት ወቅት ነው። ጄራርድ ወደ ቪላ መሄዱን ተከትሎ አስተን ቪላ ለስኮትላንዱ ክለብ 4.5 ሚሊዮን ፓዎንድ ካሳ እንደሚከፍል ተዘግቧል። በእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን እና በሊቨርፑል ክለብ ውስጥ ትልቅ ስም የገነባው ጄራርድ፤ ለሊቨርፑል 710 ጊዜ ተሰልፎ ተጫውቷል። ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ደግሞ 114 ጊዜ ተሰልፎ ተጫውቷል። ጄራርድ የአስተን ቪላ አሰልጣኝነት ሥራውን ከተረከበ በኋላ ብራይተንን በሜዳው ያስተናግዳል። ቀጥሎም ኃያሎቹን ማንችስተር ሲቲ፣ ሊቨርፑል እና ቼልሲን ይገጥማል።
ስቴቨን ጄራርድ የአስተን ቪላ አሰልጣኝ ሆኖ ተሾመ የቀድሞ የሊቨርፑል እና የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አማካይ ስቴቨን የአስቶን ቪላ ክለብ አሰልጣኝ ሆኖ ተሾመ። ጄራርድ ክለቡን ለሦስት ዓመት ተኩል ለማሰልጠን ውል መያዙ አስተን ቪላ ክለብ ይፋ አድርጓል። የ41 ዓመቱ ጄራርድ የአስተን ቪላ ክለብ ኃላፊነትን ከመቀበሉ በፊት ለሦስት ዓመታት የስኮትላንድ ክለብ የሆነውን ሬንጀርስን ሲያሰለጥን ቆይቷል። ጄራርድ ሬንጀርስ በባለፈው የውድድር ዘመን ከ10 ዓመታት በኋላ የሊጉን ዋንጫ እንዲያነሰ ረድቶ ነበር። ዕሁድ ዕለት አስተን ቪላ አምስት ዓመት በክለቡ የቆዩትን አሰልጣኝ ዲን ስሚዝን ከሥራ ማሰናበቱ ይታወሳል። አስተን ቪላ በአሁኑ ወቅት በፕሪሚየር ሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ላይ ከወራጅ ቀጠና በሁለት ነጥቦች ብቻ ርቀው 16ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። "አስተን ቪላ በእንግሊዝ እግር ኳስ ውስጥ ብዙ ታሪክ እና ባህል ያለው ክለብ ነው፤ አሰልጣኝ በመሆኔ ትልቅ ክብር ተሰምቶኛል" ብሏል ጄራርድ ከሹመቱ በኋል። ጄራርድ የበላይ የአሰልጣኝነት ሥራውን የጀመረው የኮቲሹን ሬንጀርስ ክለብ እአአ 2018 ላይ ማሰልጠን በጀመረበት ወቅት ነው። ጄራርድ ወደ ቪላ መሄዱን ተከትሎ አስተን ቪላ ለስኮትላንዱ ክለብ 4.5 ሚሊዮን ፓዎንድ ካሳ እንደሚከፍል ተዘግቧል። በእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን እና በሊቨርፑል ክለብ ውስጥ ትልቅ ስም የገነባው ጄራርድ፤ ለሊቨርፑል 710 ጊዜ ተሰልፎ ተጫውቷል። ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ደግሞ 114 ጊዜ ተሰልፎ ተጫውቷል። ጄራርድ የአስተን ቪላ አሰልጣኝነት ሥራውን ከተረከበ በኋላ ብራይተንን በሜዳው ያስተናግዳል። ቀጥሎም ኃያሎቹን ማንችስተር ሲቲ፣ ሊቨርፑል እና ቼልሲን ይገጥማል።
https://www.bbc.com/amharic/news-59249764
2health
በኢትዮጵያ የጠፋ መድኃኒት የሚያፈላልገው መተግበሪያ
ቤዛዊት በዕድሜ የገፉ እናቷ የደም መርጋት በሽታ ያሰቃያቸዋል፡፡ በጤና እንዲቆዩ ሪቫሮክሳባን የሚባል መድኃኒት ሳያቋርጡ መውሰድ ነበረባቸው፡፡ ይህ መድኃኒት እየተገባደደ ሲመጣ ቤዛዊት እንደተለመደው ለመግዛት ወጣች፡፡ ወትሮ በቀላሉ ታገኘው የነበረው ሪቫሮክሳባን ከየት ይምጣ፡፡ ዮሐንስ-አራት መንታ-ሰባራ ባቡር አካባቢ ይገኛል አሏት፡፡ አልሆነም፡፡ ቀይ መስቀል ሞክሪ ተባለች፡፡ አልሆነም፡፡ ከነማ ተሰለፈች፡፡ አልሆነም፡፡ ወጣች ወረደች፡፡ ጠዋት ወጥታ፣ ማታ ገባች፡፡ አልሆነም፡፡ የመድኃኒት ደላሎችን ሳይቀር ተማጸነች፡፡ ከየትም ሊገኝ አልቻለም፡፡ መድኃኒቱ ግን የት ገባ? ምንም አማራጭ አልነበራት፤ አውስትራሊያ የሚገኝ የሩቅ ዘመድ ማስቸገር የግድ ሆነ፡፡ ለካንስ መድኃኒት ከውጭም ቢሆን ለማስገባት ቀላል አልነበረም፡፡ ዲኤችኤል፣ ፌዴክስ እና ሌሎች የጥቅል ዕቃ ተላላኪ ኩባንያዎች፣ በነርሱ በኩል መድኃኒት ለማስላክ ከመድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ደብዳቤ ይፈልጋሉ፡፡ ሌላ መከራ፡፡ ሌላ ስቃይ፡፡ ቀን እየገፋ ሲመጣ ቤዛዊት ተጨነቀች፡፡ ምክንያቱም መድኃኒቱ ከተገባደደ እናቷ ችግር ውስጥ ይወድቃሉ፡፡ መፍጠን አለባት፡፡ በመጨረሻ በሰው በሰው፣ ከብዙ የስልክ ልውውጦች በኋላ፣ ከብዙ ተማጽኖ በኋላ፣ ከኬንያ ወደ ኢትዮጵያ እየበረረች በነበረች አንዲት በጎ ፈቃደኛ በኩል መድኃኒቱ ደረሰላት፡፡ የእናቷን ሕይወትም ታደገች፡፡ ይህ የመድኃኒት ፍለጋ እሽክርክሪት የቤዛዊት ብቻ አይደለም፡፡ በርካቶች በየቀኑ ይኖሩታል፡፡ የሚሰወሩት መድኃኒቶች በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከውጭ ምንዛሬ መመናመን ጋር ተያይዞ መድኃኒቶች ድንገት ይሰውሩ ይዘዋል፡፡ መንግሥት ለምግብና መድኃኒት የውጭ ምንዛሬን አይሰስትም፡፡ ኾኖም ግን ይህ መድኃኒቶች እንደልብ እንዲገኙ አላስቻለም፡፡ ደላሎች ደብቀው አስወድደው ይሸጧቸዋል ይባላል፡፡ የጨነቀው ቤተሰብ የትኛውንም ዋጋ ከፍሎ እንደሚገዛቸው ያውቃሉ፡፡ በሰው ችግር ያተርፋሉ፡፡ አሁን አሁን የጠፉ መድኃኒቶች ብቻ አይደሉም፣ የሚገኙትም የት እንደሚገኙ ማወቅ ጊዜና ጉልበትን ይጠይቃል፡፡ በአዲስ አበባ ሺህ ፋርማሲዎች አሉ፡፡ የሚፈልጉት መድኃኒት ወይ ቦሌ ወይም ጉለሌ አንድ ፋርማሲ መደርደሪያ ላይ ቁጭ ብሎ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን ሁሉን ፋርማሲ አዳርሶ ይሆናል እንዴ? በዚህ ሕዝብ ጤፍ በሆነበት ከተማ ከጦር ኃይሎች-ሲኤምሲ፣ ከቦሌ-ሸጎሌ ለመድረስ ግማሽ ቀን አይበቃም፡፡ ይህን ችግር መነሻ አድርጎ ታዲያ አንድ የጤና ድርጅት መፍትሄ ፍለጋ ተነሳ፡፡ መድኃኒቶችን የሚያፈላልግ ድረ ገጽ ፀነሰ፡፡ ድረ ገጹ የስልክ መተግበሪያን ወለደ፡፡ የስልክ መተግበሪያው የጥሪ ማዕከልን ፈጠረ፡፡ ለምን ሁሉንም መድኃኒቶች ወደ አንድ ቋት አስገብተን የሕዝብን እንግልት አንታደግም ያለው ይህ ድርጅት ማን ነው? የመድኃኒት ዝርዝሮችን በስልክ ‹‹ጤናዎ›› የሞባይል መተግበሪያ የጤና ጥበቃ ከፍተኛ ተጠሪ በተገኙበት በሸራተን አዲስ የተመረቀው ከወራት በፊት ነበር፡፡ ኬ.ኤም.ኤስ ሄልዝ ትሬዲንግ ይባላል ድርጅቱ፡፡ ባለአክሲዮኖቹ በኢትዮጵያ፣ ካናዳ፣ እንግሊዝና አሜሪካ የሚገኙ ትውልደ ኢትዮያዊያን ናቸው፡፡ ገሚሶቹ የድርጅቱ መሥራቾች ታዲያ አገር ቤት በዚሁ የጤና ዘርፍ የተሠማሩ ባለሙያዎች መሆናቸው ለዚህ ትርምስምሱ ለወጣ የጤና ሥርዓት መፍትሄ እንዲሹ ሳይገፋፋቸው አልቀረም፡፡ ይህም ካለፉበትና በየቀኑ ከሚያስተውሉት ችግር ተነስተው ለማኅበረሰብ መፍትሄ ለመስጠት አግዟቸዋል፡፡ የዚህ ሐሳብ አፍላቂና የድርጅቱ መሥራች ዶ/ር ሲሳይ አበበ፣ በሠሩባቸው ሐኪም ቤቶች ሁሉ በተደጋጋሚ አንድ ነገር አስተዋሉ፡፡ ‹‹ታማሚዎች ተመልሰው መጥተው ያዘዝኩላቸውን መድኃኒት ማግኘት እንዳልቻሉ ይነግሩኝ ነበር›› ይላሉ፡፡ ይህ ሁኔታ መደጋገሙ ታዲያ ዶ/ር ሲሳይ የመተግበሪያውን ሐሳብ እንዲያብሰለስሉ ምክንያት ሆናቸው፡፡ ለመሆኑ የጤናዎ መተግበሪያ ተግባር ምንድነው? በአጭሩ ለማስቀመጥ ደንበኛው የሚፈልገው መድኃኒት የት እንዳለ ይጠቁመዋል፡፡ ይህን የሚያደርገው በስልክ መተግበሪያ በመጠቀም ነው፡፡ መተግበሪያው አሠራሩ ከነ ኡበር፣ ራይድ ወዘተ የታክሲ ማሰሻ መተግበሪያዎች ጋር ተመሳሳይ ይመስላል፡፡ መጀመርያ ለደንበኛው፣ ካለበት በ500 ሜትር ራዲየስ ያሉ መድኃኒት ቤቶችን ያሳየዋል፡፡ ወይም ደግሞ መድኃኒት ፈላጊዋ ካለችበት ሆና በከተማው ያሉ መድኃኒት ቤቶቹን እያማረጠች በመተግበሪያው በምናብ ፋርማሲዎች ውስጥ ትዘልቃለች፡፡ የመድኃኒት ዝርዝራቸውን መመልከት ትችላለች፡፡ የምትፈልገው መድኃኒት መኖሩን ስታረጋግጥ ደግሞ ዋጋቸውን ማመሳከር ይቻላታል፡፡ ይህ ነው ‹‹የጤናዎ የስልክ መተግበሪያ›› ተግባር፡፡ ይህ መተግበሪያ በከፊል ሥራ ጀምሯል፡፡ የመረጃ ቋቱን ብዛትና ጥራት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሳደገ ነው፡፡ ‹‹የተገልጋዩን ጊዜ፣ ጉልበትና ገንዘብ ከብክነት መታደግ ነው ቀዳሚው ፍላጎታችን›› ይላሉ ዶ/ር ሲሳይ አበበ፡፡ ዶ/ር ሲሳይ የኬ.ኤም.ሲ ሄልዝ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ናቸው፡፡ ጤናዎ መተግበሪያ ታዲያ በስልክ ብቻ የሚገኝ አገልግሎት አይደለም፡፡ ዘመናዊ ስልክ ላልታደሉና ከቴክኖሎጂ ላልተዋወቁ የማኅበረሰብ ክፍሎች ሌላ አማራጭ አለው፡፡ 24 ሰዓት አገልግሎት የሚሰጥ 9456 የጥሪ ማዕከል፡፡ ሐኪምና ታካሚን ማገናኘት የጤናዎ መተግበሪያ ዋናው ተግባሩ የትኞቹ መድኃኒቶች በየትኛው ፋርማሲ ውስጥ ይገኛሉ የሚለውን መጠቆም ይሁን እንጂ ሌሎች ተጓዳኝ አገልግሎቶችም አሉት፡፡ ለምሳሌ በግል ጤና ጣቢያ ለመታከም የሚፈልግ ተገልጋይ የት ሆስፒታል ማን የሚባል ስፔሻሊስት መቼ እንደሚገኝ ማወቅ ቢፈልግ ይህን መረጃ ከዚሁ ማግኘት ይችላል፡፡ በዚህ መተግበሪያ ውስጥ 80 የሚሆኑ ሐኪሞች፣ በተለያየ ስፔሻላይዜሽን ያሉ፣ ማንነታቸውና የሥራ ልምዳቸው ተካቷል፡፡ በቀጣይ ዓመታትም በርካታ ሐኪሞች የዚሁ መተግበሪያ አባል ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ይህ ማለት አንድ ታካሚ ሐኪሙን ከተገቢ ምክር ጋር የመምረጥ፣ ካለበት ሆኖ ቀጠሮ የማስያዝ ዕድልን ይሰጠዋል፡፡ ዶ/ር ሲሳይ እንደሚሉት በአሁኑ ጊዜ ድርጅታቸው በየትኛውም የግል ሆስፒታል የታካሚና የሐኪም ቀጠሮን የማስያዝ ተጨማሪ ሥራን ይሠራል፡፡ ‹‹ታካሚዎች የትኛውን ሐኪም፣ መቼ፣ የት ክሊኒክ ማግኘት እንደሚችሉ ማማከር ብቻ ሳይሆን ቀጠሮም እንይዝላቸዋለን፡፡ በሆስፒታል እየሄዱ ወረፋ መያዝ፣ መንገላታትን ለማስቀረት ነው እየሞከርን ያለነው›› ይላሉ፡፡ አገር ውስጥ የሌሉ መድኃኒቶችን ፍለጋ በቀድሞ ጊዜ የምሽት ተረኛ መድኃኒት ቤቶች በየቀኑ በብሔራዊ ራዲዮ ይነገሩ ነበር፡፡ ልክ ዛሬ የአየር ትንበያና ስፖርት ዘገባዎች ከዜና በኋላ እንደሚታወጁት ሁሉ፡፡ ዛሬ ይህ ነገር መኖሩን እንጃ፡፡ ዜጎች አጣዳፊ የመድኃኒት ጥያቄ ቢገጥማቸው እንግልታቸውን ለማስቀረት ያለመ ነበር ነገሩ፡፡ ያን ጊዜ ጥቂት ፋርማሲዎች ነበር በከተማው የነበሩት፡፡ አሁን መድኃኒት ቤቶች እንደ አሸን በፈሉበት ዘመን፣ ኮንዶሚንየም ግቢ ድረስ ዘልቀው የነዋሪዎች ጎረቤት መሆን በቻሉበት ዘመን ነገሩ ያን ያህልም አልተቃለለም፡፡ ለምን? መድኃኒት ቤቶችን እንጂ መድኃኒቶችን ማግኘት አልተቻለም፡፡ ይህ ሀቅ የጤናዎ መተግበሪያ ፈጣሪዎችም የሚክዱት አይደለም፡፡ በቂ መድኃኒቶች በሌሉበት ፋርማሲ መጠቆም ምን ይፈይዳል? በገበያ የሚገኙት መድኃኒት ቤቶችማ ወትሮም የትም የሚገኙ ናቸው፡፡ የማይገኙት ደግሞ የትም አይገኙም፡፡ ዶ/ር ሲሳይ ይህን ሁኔታ ድርጅታቸው እንደሚረዳ ለቢቢሲ አስረድተው ለዚህም ሲባል መድኃኒት ከውጭ የማስመጣት ፍቃድ መውሰዳቸውን አብራርተዋል፡፡ ለጊዜው ሰዎች ከገበያ ያጧቸውን መድኃኒቶች በተናጥል ጥያቄ ሲያቀርቡልን ከውጭ ለማስመጣት ዝግጅት ጨርሰናል ይላሉ፡፡ ዶ/ር ሲሳይ እንደሚሉት ታዲያ የጤና ድርጅቱ ሥራ በመድኃኒት አድራሻና ዋጋ ጥቆማ የሚቆም አይደለም፡፡ ለምሳሌ ኤምአርአይ ወይም ሌላ የኢሜጂንግ ወይም የላቦራቶሪ አገልግሎት የሚፈልግ ደንበኛ በአቅራቢያው ይህን አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም ስለመኖር አለመኖሩ፣ የዋጋ ዝርዝሩን እና ለአገልግሎቱ የሚጠየቀውን ተያያዥ መረጃ ሁሉ አቀናጅቶ አስቀድሞ መረጃ የማቀበል ተግባርም በመስጠት ላይ ናቸው፡፡ በጤና ሚኒስቴር የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ገመቺስ መልካሙ ይህ አዲስ የጤና መተግበሪያ የተገልጋይ እንግልትን፣ ጊዜና ጉልበትን በመቆጠብ ሁነኛ ሚና እንደሚጫወት መተግበሪያው በተመረቀበት ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተው አድናቆታቸውን ገልጠው ነበር፡፡ ይህ መተግበሪያ፣ የጥሪ ማዕከልና የጤና ድረ ገጽ ኅብረተሰብን በማገዝ ረገድ ሁነኛ ሚና ስላለው መሥሪያ ቤታቸው አስፈላጊውን ትብብር ሁሉ እንደሚያደርግም ቃል ገብተዋል፡፡ ከዚህ ቀደም ብቅ ጥልቅ እያሉም ቢሆን የጤና ዘርፉን ለማዘመን የተሞከሩ ሙከራዎች እንደነበሩ የጠቀሱት ዶ/ር ሲሳይ በበኩላቸው ጤናዎ መተግበሪያ አስተማማኝና ዘላቂ አገልግሎት ለመስጠት ከሐኪሞችና ከጤና ተቋማት ጋር መጠነ ሰፊ ግንኙነት መፍጠሩንና፣ በእስካሁኑ አጭር ተሞክሮም ተስፋ ሰጪ ሁኔታዎች እንዳዩም ለቢቢሲ ተናግረዋል፡፡ የዚህ አገልግሎት ልዩ ባህሪም የግል ዘርፉን የጤና አገልግሎት በአንድ ጥላ ጠቅልሎ መያዙ እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡ ይህም ማለት ሐኪም ቀጠሮ ከማስያዝ ጀምሮ እስከ መድኃኒት ዋጋ ድረስ ዲጂታል በሆነ አሠራር ቀላል ማድረግን፣ በዚህም የጤና ሥርዓቱን ማዘመንን ያካተተ ነው፡፡ የዲጂታል ነገር፣ እስኪዘልቅና ዘላቂነቱ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አዳዲስ ይበል የሚያሰኙ ሐሳቦች ይመነጫሉ፡፡ ወዲያው ይከስማሉ፡፡ አንዱ ምክንያት የኅብረተሰቡ ለውጡን ለመቀበል ዳተኛ መሆን ነው፡፡ ወደ ሕዝብ አይዘልቁም፡፡ ቢዘልቁም ዘላቂነት አይኖራቸውም፡፡ በዚህ ረገድ ጤናዎ መተግበሪያ የት ርቀት ይሄድ ይሆን? ዶ/ር ሲሳይ አንዱ ፈተና ይኸው መሆኑን አውስተዋል፡፡ ወደ ዲጂታል ሄልዝ ለመሸጋገር ለብዙ ሰዎች ቀላል እንዳልሆነ በዚህ አጭር ቆይታ ራሱ የተረዱት ዶ/ር ሲሳይ፣ ድርጅታቸው ታዲያ ሕዝቡን ከአግልግሎቱ ጋር በቀላሉ ለማስተዋወቅ በማሰብ ለጊዜው ማንኛውንም ክፍያ አየጠየቁ አለመሆኑን አብራርተዋል፡፡ ‹‹ለጊዜው ከመቶ በላይ መድኃኒት ቤቶች ከኛ ጋር ለመሥራት ተመዝግበዋል፡፡ እነዚህ መድኃኒት ቤቶች አዲስ መድኃኒት ሲያስገቡም ሆነ ነባር መድኃኒቶችን ሽጠው ሲጨርሱ በኛ ሲስተም እየገቡ አሁናዊ መረጃን ለኅብረተሰቡ ያቀብላሉ፡፡ ሌሎችንም ለማሳመን እየሞከርን ነው›› ይላሉ ዶ/ር ሲሳይ፡፡ በኢትዮጵያ ከ60 ሚሊዮን የሚልቅ ሞባይል ተጠቃሚ ቢኖርም፣ የኢንተርኔት ተደራሽነቱና ዘመናዊ ስልክ ተጠቃሚው ቁጥር የዚህ ሲሶውን እንኳ አይሞላም፡፡ እርግጥ በአሁን ዘመን ብዙ አገልግሎቶች ወደ ሞባይል እየገቡ ነው፡፡ ገንዘብ ዝውውርም ከወረቀት ወደ ሞባይል እየተሸጋገረ ነው፡፡ ይሁንና የሕዝብን እምነት ማግኘት በቀላል የሚገኝ እሴት አይደለም፡፡ ዶ/ር ሲሳይም ይህን አይክዱም፤ ‹‹ወደ ዲጂታል ሽግግር ጉዞው ቀላል እንደማይሆን አውቀን ነው የተነሳነው፤ በኛ አገር ዲጂታል ቴክኖሎጂ ገና እያደገ ነው፡፡ ሰዎች እምነት ገና አላዳበሩም፡፡ ይህ ነገር ጊዜ ሊወስድ ይችላል›› ብለዋል፡፡ ይህን ለማገዝም ነው የሚመሩት ድርጅት ለሁሉም አገልግሎቶቻቸው ለጊዜው ክፍያን ላለመጠየቅ የወሰነው፡፡ ፈውስን ፍለጋ ወጥቶ በሽታን መሸመት ወደ ዲጂታል ዓለም ለመግባት እዚያ እዚህም የሚታዩት ሙከራዎች ከብዙ በጥቂቱ ይሁንታን ያገኛሉ፡፡ በኢትዮጵያ ካየነው ሁሉ ለጊዜው በትራንስፖርት ዘርፍ የሰመረ ይመስላል፡፡ በፋይናንስ ዘርፍም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተስፋ ሰጪ ምልክቶች ታይተዋል፡፡ በጤና ዘርፍ ግን እምብዛም አይደለም፡፡ እርግጥ የሰዎች የጤና ሰነድ ከገንዘብም በላይ ከለላን ይሻል፡፡ ደኅንነቱ የተጠበቀ የመረጃ አያያዝን መከተል ይፈልጋል፡፡ በዚህ ረገድ ብዙ ከተሠራ ከብዙ ትዕግስት ጋር ወደፊት መንፏቀቅ ይቻል ይሆናል፡፡ በተለይ የኅብረተሰብን ችግር ለመፍታት ያለሙ፣ መፍትሄ ላይ መሠረት ያደረጉ መተግበሪያዎች ሲሳኩም የዛኑ ያህል ሕይወት ዘዋሪ ናቸው፡፡ የኬ.ኤም.ኤስ ሄልዝ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ሲሳይ አበበ ደጋግመው እንደሚሉት፣ ሰዎች ፈውስ ፍለጋ ወጥተው፣ በሽታን ሸምተው መመለስ የለባቸውም፡፡ ‹‹ጤናዎ ሁለገብ መተግበሪያ›› የጤናው ዘርፍ ዲጂታል ሽግግር ረዥሙ ጉዞ አንድ እርምጃ ይሆን?
በኢትዮጵያ የጠፋ መድኃኒት የሚያፈላልገው መተግበሪያ ቤዛዊት በዕድሜ የገፉ እናቷ የደም መርጋት በሽታ ያሰቃያቸዋል፡፡ በጤና እንዲቆዩ ሪቫሮክሳባን የሚባል መድኃኒት ሳያቋርጡ መውሰድ ነበረባቸው፡፡ ይህ መድኃኒት እየተገባደደ ሲመጣ ቤዛዊት እንደተለመደው ለመግዛት ወጣች፡፡ ወትሮ በቀላሉ ታገኘው የነበረው ሪቫሮክሳባን ከየት ይምጣ፡፡ ዮሐንስ-አራት መንታ-ሰባራ ባቡር አካባቢ ይገኛል አሏት፡፡ አልሆነም፡፡ ቀይ መስቀል ሞክሪ ተባለች፡፡ አልሆነም፡፡ ከነማ ተሰለፈች፡፡ አልሆነም፡፡ ወጣች ወረደች፡፡ ጠዋት ወጥታ፣ ማታ ገባች፡፡ አልሆነም፡፡ የመድኃኒት ደላሎችን ሳይቀር ተማጸነች፡፡ ከየትም ሊገኝ አልቻለም፡፡ መድኃኒቱ ግን የት ገባ? ምንም አማራጭ አልነበራት፤ አውስትራሊያ የሚገኝ የሩቅ ዘመድ ማስቸገር የግድ ሆነ፡፡ ለካንስ መድኃኒት ከውጭም ቢሆን ለማስገባት ቀላል አልነበረም፡፡ ዲኤችኤል፣ ፌዴክስ እና ሌሎች የጥቅል ዕቃ ተላላኪ ኩባንያዎች፣ በነርሱ በኩል መድኃኒት ለማስላክ ከመድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ደብዳቤ ይፈልጋሉ፡፡ ሌላ መከራ፡፡ ሌላ ስቃይ፡፡ ቀን እየገፋ ሲመጣ ቤዛዊት ተጨነቀች፡፡ ምክንያቱም መድኃኒቱ ከተገባደደ እናቷ ችግር ውስጥ ይወድቃሉ፡፡ መፍጠን አለባት፡፡ በመጨረሻ በሰው በሰው፣ ከብዙ የስልክ ልውውጦች በኋላ፣ ከብዙ ተማጽኖ በኋላ፣ ከኬንያ ወደ ኢትዮጵያ እየበረረች በነበረች አንዲት በጎ ፈቃደኛ በኩል መድኃኒቱ ደረሰላት፡፡ የእናቷን ሕይወትም ታደገች፡፡ ይህ የመድኃኒት ፍለጋ እሽክርክሪት የቤዛዊት ብቻ አይደለም፡፡ በርካቶች በየቀኑ ይኖሩታል፡፡ የሚሰወሩት መድኃኒቶች በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከውጭ ምንዛሬ መመናመን ጋር ተያይዞ መድኃኒቶች ድንገት ይሰውሩ ይዘዋል፡፡ መንግሥት ለምግብና መድኃኒት የውጭ ምንዛሬን አይሰስትም፡፡ ኾኖም ግን ይህ መድኃኒቶች እንደልብ እንዲገኙ አላስቻለም፡፡ ደላሎች ደብቀው አስወድደው ይሸጧቸዋል ይባላል፡፡ የጨነቀው ቤተሰብ የትኛውንም ዋጋ ከፍሎ እንደሚገዛቸው ያውቃሉ፡፡ በሰው ችግር ያተርፋሉ፡፡ አሁን አሁን የጠፉ መድኃኒቶች ብቻ አይደሉም፣ የሚገኙትም የት እንደሚገኙ ማወቅ ጊዜና ጉልበትን ይጠይቃል፡፡ በአዲስ አበባ ሺህ ፋርማሲዎች አሉ፡፡ የሚፈልጉት መድኃኒት ወይ ቦሌ ወይም ጉለሌ አንድ ፋርማሲ መደርደሪያ ላይ ቁጭ ብሎ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን ሁሉን ፋርማሲ አዳርሶ ይሆናል እንዴ? በዚህ ሕዝብ ጤፍ በሆነበት ከተማ ከጦር ኃይሎች-ሲኤምሲ፣ ከቦሌ-ሸጎሌ ለመድረስ ግማሽ ቀን አይበቃም፡፡ ይህን ችግር መነሻ አድርጎ ታዲያ አንድ የጤና ድርጅት መፍትሄ ፍለጋ ተነሳ፡፡ መድኃኒቶችን የሚያፈላልግ ድረ ገጽ ፀነሰ፡፡ ድረ ገጹ የስልክ መተግበሪያን ወለደ፡፡ የስልክ መተግበሪያው የጥሪ ማዕከልን ፈጠረ፡፡ ለምን ሁሉንም መድኃኒቶች ወደ አንድ ቋት አስገብተን የሕዝብን እንግልት አንታደግም ያለው ይህ ድርጅት ማን ነው? የመድኃኒት ዝርዝሮችን በስልክ ‹‹ጤናዎ›› የሞባይል መተግበሪያ የጤና ጥበቃ ከፍተኛ ተጠሪ በተገኙበት በሸራተን አዲስ የተመረቀው ከወራት በፊት ነበር፡፡ ኬ.ኤም.ኤስ ሄልዝ ትሬዲንግ ይባላል ድርጅቱ፡፡ ባለአክሲዮኖቹ በኢትዮጵያ፣ ካናዳ፣ እንግሊዝና አሜሪካ የሚገኙ ትውልደ ኢትዮያዊያን ናቸው፡፡ ገሚሶቹ የድርጅቱ መሥራቾች ታዲያ አገር ቤት በዚሁ የጤና ዘርፍ የተሠማሩ ባለሙያዎች መሆናቸው ለዚህ ትርምስምሱ ለወጣ የጤና ሥርዓት መፍትሄ እንዲሹ ሳይገፋፋቸው አልቀረም፡፡ ይህም ካለፉበትና በየቀኑ ከሚያስተውሉት ችግር ተነስተው ለማኅበረሰብ መፍትሄ ለመስጠት አግዟቸዋል፡፡ የዚህ ሐሳብ አፍላቂና የድርጅቱ መሥራች ዶ/ር ሲሳይ አበበ፣ በሠሩባቸው ሐኪም ቤቶች ሁሉ በተደጋጋሚ አንድ ነገር አስተዋሉ፡፡ ‹‹ታማሚዎች ተመልሰው መጥተው ያዘዝኩላቸውን መድኃኒት ማግኘት እንዳልቻሉ ይነግሩኝ ነበር›› ይላሉ፡፡ ይህ ሁኔታ መደጋገሙ ታዲያ ዶ/ር ሲሳይ የመተግበሪያውን ሐሳብ እንዲያብሰለስሉ ምክንያት ሆናቸው፡፡ ለመሆኑ የጤናዎ መተግበሪያ ተግባር ምንድነው? በአጭሩ ለማስቀመጥ ደንበኛው የሚፈልገው መድኃኒት የት እንዳለ ይጠቁመዋል፡፡ ይህን የሚያደርገው በስልክ መተግበሪያ በመጠቀም ነው፡፡ መተግበሪያው አሠራሩ ከነ ኡበር፣ ራይድ ወዘተ የታክሲ ማሰሻ መተግበሪያዎች ጋር ተመሳሳይ ይመስላል፡፡ መጀመርያ ለደንበኛው፣ ካለበት በ500 ሜትር ራዲየስ ያሉ መድኃኒት ቤቶችን ያሳየዋል፡፡ ወይም ደግሞ መድኃኒት ፈላጊዋ ካለችበት ሆና በከተማው ያሉ መድኃኒት ቤቶቹን እያማረጠች በመተግበሪያው በምናብ ፋርማሲዎች ውስጥ ትዘልቃለች፡፡ የመድኃኒት ዝርዝራቸውን መመልከት ትችላለች፡፡ የምትፈልገው መድኃኒት መኖሩን ስታረጋግጥ ደግሞ ዋጋቸውን ማመሳከር ይቻላታል፡፡ ይህ ነው ‹‹የጤናዎ የስልክ መተግበሪያ›› ተግባር፡፡ ይህ መተግበሪያ በከፊል ሥራ ጀምሯል፡፡ የመረጃ ቋቱን ብዛትና ጥራት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሳደገ ነው፡፡ ‹‹የተገልጋዩን ጊዜ፣ ጉልበትና ገንዘብ ከብክነት መታደግ ነው ቀዳሚው ፍላጎታችን›› ይላሉ ዶ/ር ሲሳይ አበበ፡፡ ዶ/ር ሲሳይ የኬ.ኤም.ሲ ሄልዝ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ናቸው፡፡ ጤናዎ መተግበሪያ ታዲያ በስልክ ብቻ የሚገኝ አገልግሎት አይደለም፡፡ ዘመናዊ ስልክ ላልታደሉና ከቴክኖሎጂ ላልተዋወቁ የማኅበረሰብ ክፍሎች ሌላ አማራጭ አለው፡፡ 24 ሰዓት አገልግሎት የሚሰጥ 9456 የጥሪ ማዕከል፡፡ ሐኪምና ታካሚን ማገናኘት የጤናዎ መተግበሪያ ዋናው ተግባሩ የትኞቹ መድኃኒቶች በየትኛው ፋርማሲ ውስጥ ይገኛሉ የሚለውን መጠቆም ይሁን እንጂ ሌሎች ተጓዳኝ አገልግሎቶችም አሉት፡፡ ለምሳሌ በግል ጤና ጣቢያ ለመታከም የሚፈልግ ተገልጋይ የት ሆስፒታል ማን የሚባል ስፔሻሊስት መቼ እንደሚገኝ ማወቅ ቢፈልግ ይህን መረጃ ከዚሁ ማግኘት ይችላል፡፡ በዚህ መተግበሪያ ውስጥ 80 የሚሆኑ ሐኪሞች፣ በተለያየ ስፔሻላይዜሽን ያሉ፣ ማንነታቸውና የሥራ ልምዳቸው ተካቷል፡፡ በቀጣይ ዓመታትም በርካታ ሐኪሞች የዚሁ መተግበሪያ አባል ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ይህ ማለት አንድ ታካሚ ሐኪሙን ከተገቢ ምክር ጋር የመምረጥ፣ ካለበት ሆኖ ቀጠሮ የማስያዝ ዕድልን ይሰጠዋል፡፡ ዶ/ር ሲሳይ እንደሚሉት በአሁኑ ጊዜ ድርጅታቸው በየትኛውም የግል ሆስፒታል የታካሚና የሐኪም ቀጠሮን የማስያዝ ተጨማሪ ሥራን ይሠራል፡፡ ‹‹ታካሚዎች የትኛውን ሐኪም፣ መቼ፣ የት ክሊኒክ ማግኘት እንደሚችሉ ማማከር ብቻ ሳይሆን ቀጠሮም እንይዝላቸዋለን፡፡ በሆስፒታል እየሄዱ ወረፋ መያዝ፣ መንገላታትን ለማስቀረት ነው እየሞከርን ያለነው›› ይላሉ፡፡ አገር ውስጥ የሌሉ መድኃኒቶችን ፍለጋ በቀድሞ ጊዜ የምሽት ተረኛ መድኃኒት ቤቶች በየቀኑ በብሔራዊ ራዲዮ ይነገሩ ነበር፡፡ ልክ ዛሬ የአየር ትንበያና ስፖርት ዘገባዎች ከዜና በኋላ እንደሚታወጁት ሁሉ፡፡ ዛሬ ይህ ነገር መኖሩን እንጃ፡፡ ዜጎች አጣዳፊ የመድኃኒት ጥያቄ ቢገጥማቸው እንግልታቸውን ለማስቀረት ያለመ ነበር ነገሩ፡፡ ያን ጊዜ ጥቂት ፋርማሲዎች ነበር በከተማው የነበሩት፡፡ አሁን መድኃኒት ቤቶች እንደ አሸን በፈሉበት ዘመን፣ ኮንዶሚንየም ግቢ ድረስ ዘልቀው የነዋሪዎች ጎረቤት መሆን በቻሉበት ዘመን ነገሩ ያን ያህልም አልተቃለለም፡፡ ለምን? መድኃኒት ቤቶችን እንጂ መድኃኒቶችን ማግኘት አልተቻለም፡፡ ይህ ሀቅ የጤናዎ መተግበሪያ ፈጣሪዎችም የሚክዱት አይደለም፡፡ በቂ መድኃኒቶች በሌሉበት ፋርማሲ መጠቆም ምን ይፈይዳል? በገበያ የሚገኙት መድኃኒት ቤቶችማ ወትሮም የትም የሚገኙ ናቸው፡፡ የማይገኙት ደግሞ የትም አይገኙም፡፡ ዶ/ር ሲሳይ ይህን ሁኔታ ድርጅታቸው እንደሚረዳ ለቢቢሲ አስረድተው ለዚህም ሲባል መድኃኒት ከውጭ የማስመጣት ፍቃድ መውሰዳቸውን አብራርተዋል፡፡ ለጊዜው ሰዎች ከገበያ ያጧቸውን መድኃኒቶች በተናጥል ጥያቄ ሲያቀርቡልን ከውጭ ለማስመጣት ዝግጅት ጨርሰናል ይላሉ፡፡ ዶ/ር ሲሳይ እንደሚሉት ታዲያ የጤና ድርጅቱ ሥራ በመድኃኒት አድራሻና ዋጋ ጥቆማ የሚቆም አይደለም፡፡ ለምሳሌ ኤምአርአይ ወይም ሌላ የኢሜጂንግ ወይም የላቦራቶሪ አገልግሎት የሚፈልግ ደንበኛ በአቅራቢያው ይህን አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም ስለመኖር አለመኖሩ፣ የዋጋ ዝርዝሩን እና ለአገልግሎቱ የሚጠየቀውን ተያያዥ መረጃ ሁሉ አቀናጅቶ አስቀድሞ መረጃ የማቀበል ተግባርም በመስጠት ላይ ናቸው፡፡ በጤና ሚኒስቴር የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ገመቺስ መልካሙ ይህ አዲስ የጤና መተግበሪያ የተገልጋይ እንግልትን፣ ጊዜና ጉልበትን በመቆጠብ ሁነኛ ሚና እንደሚጫወት መተግበሪያው በተመረቀበት ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተው አድናቆታቸውን ገልጠው ነበር፡፡ ይህ መተግበሪያ፣ የጥሪ ማዕከልና የጤና ድረ ገጽ ኅብረተሰብን በማገዝ ረገድ ሁነኛ ሚና ስላለው መሥሪያ ቤታቸው አስፈላጊውን ትብብር ሁሉ እንደሚያደርግም ቃል ገብተዋል፡፡ ከዚህ ቀደም ብቅ ጥልቅ እያሉም ቢሆን የጤና ዘርፉን ለማዘመን የተሞከሩ ሙከራዎች እንደነበሩ የጠቀሱት ዶ/ር ሲሳይ በበኩላቸው ጤናዎ መተግበሪያ አስተማማኝና ዘላቂ አገልግሎት ለመስጠት ከሐኪሞችና ከጤና ተቋማት ጋር መጠነ ሰፊ ግንኙነት መፍጠሩንና፣ በእስካሁኑ አጭር ተሞክሮም ተስፋ ሰጪ ሁኔታዎች እንዳዩም ለቢቢሲ ተናግረዋል፡፡ የዚህ አገልግሎት ልዩ ባህሪም የግል ዘርፉን የጤና አገልግሎት በአንድ ጥላ ጠቅልሎ መያዙ እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡ ይህም ማለት ሐኪም ቀጠሮ ከማስያዝ ጀምሮ እስከ መድኃኒት ዋጋ ድረስ ዲጂታል በሆነ አሠራር ቀላል ማድረግን፣ በዚህም የጤና ሥርዓቱን ማዘመንን ያካተተ ነው፡፡ የዲጂታል ነገር፣ እስኪዘልቅና ዘላቂነቱ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አዳዲስ ይበል የሚያሰኙ ሐሳቦች ይመነጫሉ፡፡ ወዲያው ይከስማሉ፡፡ አንዱ ምክንያት የኅብረተሰቡ ለውጡን ለመቀበል ዳተኛ መሆን ነው፡፡ ወደ ሕዝብ አይዘልቁም፡፡ ቢዘልቁም ዘላቂነት አይኖራቸውም፡፡ በዚህ ረገድ ጤናዎ መተግበሪያ የት ርቀት ይሄድ ይሆን? ዶ/ር ሲሳይ አንዱ ፈተና ይኸው መሆኑን አውስተዋል፡፡ ወደ ዲጂታል ሄልዝ ለመሸጋገር ለብዙ ሰዎች ቀላል እንዳልሆነ በዚህ አጭር ቆይታ ራሱ የተረዱት ዶ/ር ሲሳይ፣ ድርጅታቸው ታዲያ ሕዝቡን ከአግልግሎቱ ጋር በቀላሉ ለማስተዋወቅ በማሰብ ለጊዜው ማንኛውንም ክፍያ አየጠየቁ አለመሆኑን አብራርተዋል፡፡ ‹‹ለጊዜው ከመቶ በላይ መድኃኒት ቤቶች ከኛ ጋር ለመሥራት ተመዝግበዋል፡፡ እነዚህ መድኃኒት ቤቶች አዲስ መድኃኒት ሲያስገቡም ሆነ ነባር መድኃኒቶችን ሽጠው ሲጨርሱ በኛ ሲስተም እየገቡ አሁናዊ መረጃን ለኅብረተሰቡ ያቀብላሉ፡፡ ሌሎችንም ለማሳመን እየሞከርን ነው›› ይላሉ ዶ/ር ሲሳይ፡፡ በኢትዮጵያ ከ60 ሚሊዮን የሚልቅ ሞባይል ተጠቃሚ ቢኖርም፣ የኢንተርኔት ተደራሽነቱና ዘመናዊ ስልክ ተጠቃሚው ቁጥር የዚህ ሲሶውን እንኳ አይሞላም፡፡ እርግጥ በአሁን ዘመን ብዙ አገልግሎቶች ወደ ሞባይል እየገቡ ነው፡፡ ገንዘብ ዝውውርም ከወረቀት ወደ ሞባይል እየተሸጋገረ ነው፡፡ ይሁንና የሕዝብን እምነት ማግኘት በቀላል የሚገኝ እሴት አይደለም፡፡ ዶ/ር ሲሳይም ይህን አይክዱም፤ ‹‹ወደ ዲጂታል ሽግግር ጉዞው ቀላል እንደማይሆን አውቀን ነው የተነሳነው፤ በኛ አገር ዲጂታል ቴክኖሎጂ ገና እያደገ ነው፡፡ ሰዎች እምነት ገና አላዳበሩም፡፡ ይህ ነገር ጊዜ ሊወስድ ይችላል›› ብለዋል፡፡ ይህን ለማገዝም ነው የሚመሩት ድርጅት ለሁሉም አገልግሎቶቻቸው ለጊዜው ክፍያን ላለመጠየቅ የወሰነው፡፡ ፈውስን ፍለጋ ወጥቶ በሽታን መሸመት ወደ ዲጂታል ዓለም ለመግባት እዚያ እዚህም የሚታዩት ሙከራዎች ከብዙ በጥቂቱ ይሁንታን ያገኛሉ፡፡ በኢትዮጵያ ካየነው ሁሉ ለጊዜው በትራንስፖርት ዘርፍ የሰመረ ይመስላል፡፡ በፋይናንስ ዘርፍም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተስፋ ሰጪ ምልክቶች ታይተዋል፡፡ በጤና ዘርፍ ግን እምብዛም አይደለም፡፡ እርግጥ የሰዎች የጤና ሰነድ ከገንዘብም በላይ ከለላን ይሻል፡፡ ደኅንነቱ የተጠበቀ የመረጃ አያያዝን መከተል ይፈልጋል፡፡ በዚህ ረገድ ብዙ ከተሠራ ከብዙ ትዕግስት ጋር ወደፊት መንፏቀቅ ይቻል ይሆናል፡፡ በተለይ የኅብረተሰብን ችግር ለመፍታት ያለሙ፣ መፍትሄ ላይ መሠረት ያደረጉ መተግበሪያዎች ሲሳኩም የዛኑ ያህል ሕይወት ዘዋሪ ናቸው፡፡ የኬ.ኤም.ኤስ ሄልዝ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ሲሳይ አበበ ደጋግመው እንደሚሉት፣ ሰዎች ፈውስ ፍለጋ ወጥተው፣ በሽታን ሸምተው መመለስ የለባቸውም፡፡ ‹‹ጤናዎ ሁለገብ መተግበሪያ›› የጤናው ዘርፍ ዲጂታል ሽግግር ረዥሙ ጉዞ አንድ እርምጃ ይሆን?
https://www.bbc.com/amharic/61218340
3politics
የቀድሞ የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት በአንድ ጉባኤ ላይ 'ከሃዲ' ተባሉ
የቀድሞው የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት በአንድ ሃይማኖታዊ ጉባኤ ላይ በሚናገሩበት ወቅት ከተሳታፊዎች ስድብ ተወርውሮባቸዋል። አንዳንዶች "ከሃዲ" በሚል የሰደቧቸው ሲሆን "ነፃነት" የሚሉ ቃሎችም ተሰምተዋል። ፖለቲከኛው በያዝነው ሳምንት አርብ በኦርላንዶ ግዛት በነበረው የፌይዝ ኤንድ ፍሪደም ኮሊሸን ንግግር እያደረጉ በነበረ ወቅት ነው ይሄ የደረሰባቸው ተብሏል። የቀድሞው ምክትል ፕሬዚዳንት ለአሸናፊው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ዕውቅና መስጠታቸውንም ተከትሎ ነው ይህንን ያስተናገዱት ተብሏል። በተሳዳቢዎቹ ምክንያት ፖለቲከኛው ንግግራቸውን እንዳላቆሙና ለ28 ደቂቃም የቆየ ንግግርም አድርገዋል። ተሳዳቢዎቹም መሃል ላይ በፖሊስ እንዲወጡ ተደርገዋል። በዚህ ንግግግራቸው ወቅት የዲሞከራቱን ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ፖሊሲዎች በመተቸት የተሰናባቹን ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን አወድሰዋል። በጥር ወር ላይ ፕሬዚዳንት ትራምፕን ጨምሮ በርካታ ደጋፊዎቻቸው በወቅቱ የምክር ቤቱ የበላይ የነበሩትን ማይክ ፔንስን ፕሬዚዳንት ባይደን ያሸነፉበትን ሰርቲፊኬት በኮንግረሱ እውቅና እንዳይሰጡት ጠይቀዋቸው ነበር። ማይክ ፔንስ ይህንን ለማድረግ ስልጣኑ የለኝም ቢሉም በርካታ የትራምፕ ደጋፊዎች ተናደውባቸዋል። በምርጫው ውጤት የተናደዱ የትራምፕ ነውጠኛ ደጋፊዎች በጥር ወር ላይ በካፒቶል ህንፃ ሰብረው በመግባት ከፍተኛ ሁከት ማስከተላቸው ይታወሳል። ጥር 6፣ በተለምዶ "የካፒቶል ሒል ነውጥ" ተብሎ የሚጠራው የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች የሁለቱ ምክር ቤቶች መሰብሰብያና በርካታ የመንግሥት አስተዳደር ቢሮዎችን ሰብረው በመግባት የዲሞክራሲ ተምሳሌት ተደርጎ የሚታየውን ስፍራ እንዲሁም የአገሪቱን ስምና ክብር የሚያጎድፍ ተግባር የፈጸሙበት ዕለት ነው። በካፒቶል የደረሰውንም ጥቃት ተከትሎ ማይክ ፔንስ ከትራምፕ ራሳቸውን አግልለዋል። የካፒቶሉን ጥቃት ተከትሎ ትራምፕ በምክር ቤቱ ያለመከሰሰስ መብታቸው እንደተገፈፈ ይታወሳል። በአሜሪካ ታሪክ ለሁለተኛ ጊዜ በመከሰስ የመጀመርያ ሆነው የነበሩት ዶናልድ ትራምፕ አመጽን ቀስቅሶ ከመምራት ክስ ነጻ መደረጋቸው ይታወሳል። ማይክ ፔንስ ነውጠኞቹን የተቃወሙ ሲሆን የፕሬዚዳንት ጆ ባይደንን በዓለ ሲመት ላይ ተገኝተዋል። የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዓለ ሲመቱ ላይ አልተገኙም። ነገር ግን አርብ እለት በነበረው ንግግራቸው ማይክ ፔንስ የቀድሞ አለቃውን በስልጣን ላይ ያሳኩዋቸውን ነገሮች ተናግረዋል።
የቀድሞ የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት በአንድ ጉባኤ ላይ 'ከሃዲ' ተባሉ የቀድሞው የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት በአንድ ሃይማኖታዊ ጉባኤ ላይ በሚናገሩበት ወቅት ከተሳታፊዎች ስድብ ተወርውሮባቸዋል። አንዳንዶች "ከሃዲ" በሚል የሰደቧቸው ሲሆን "ነፃነት" የሚሉ ቃሎችም ተሰምተዋል። ፖለቲከኛው በያዝነው ሳምንት አርብ በኦርላንዶ ግዛት በነበረው የፌይዝ ኤንድ ፍሪደም ኮሊሸን ንግግር እያደረጉ በነበረ ወቅት ነው ይሄ የደረሰባቸው ተብሏል። የቀድሞው ምክትል ፕሬዚዳንት ለአሸናፊው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ዕውቅና መስጠታቸውንም ተከትሎ ነው ይህንን ያስተናገዱት ተብሏል። በተሳዳቢዎቹ ምክንያት ፖለቲከኛው ንግግራቸውን እንዳላቆሙና ለ28 ደቂቃም የቆየ ንግግርም አድርገዋል። ተሳዳቢዎቹም መሃል ላይ በፖሊስ እንዲወጡ ተደርገዋል። በዚህ ንግግግራቸው ወቅት የዲሞከራቱን ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ፖሊሲዎች በመተቸት የተሰናባቹን ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን አወድሰዋል። በጥር ወር ላይ ፕሬዚዳንት ትራምፕን ጨምሮ በርካታ ደጋፊዎቻቸው በወቅቱ የምክር ቤቱ የበላይ የነበሩትን ማይክ ፔንስን ፕሬዚዳንት ባይደን ያሸነፉበትን ሰርቲፊኬት በኮንግረሱ እውቅና እንዳይሰጡት ጠይቀዋቸው ነበር። ማይክ ፔንስ ይህንን ለማድረግ ስልጣኑ የለኝም ቢሉም በርካታ የትራምፕ ደጋፊዎች ተናደውባቸዋል። በምርጫው ውጤት የተናደዱ የትራምፕ ነውጠኛ ደጋፊዎች በጥር ወር ላይ በካፒቶል ህንፃ ሰብረው በመግባት ከፍተኛ ሁከት ማስከተላቸው ይታወሳል። ጥር 6፣ በተለምዶ "የካፒቶል ሒል ነውጥ" ተብሎ የሚጠራው የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች የሁለቱ ምክር ቤቶች መሰብሰብያና በርካታ የመንግሥት አስተዳደር ቢሮዎችን ሰብረው በመግባት የዲሞክራሲ ተምሳሌት ተደርጎ የሚታየውን ስፍራ እንዲሁም የአገሪቱን ስምና ክብር የሚያጎድፍ ተግባር የፈጸሙበት ዕለት ነው። በካፒቶል የደረሰውንም ጥቃት ተከትሎ ማይክ ፔንስ ከትራምፕ ራሳቸውን አግልለዋል። የካፒቶሉን ጥቃት ተከትሎ ትራምፕ በምክር ቤቱ ያለመከሰሰስ መብታቸው እንደተገፈፈ ይታወሳል። በአሜሪካ ታሪክ ለሁለተኛ ጊዜ በመከሰስ የመጀመርያ ሆነው የነበሩት ዶናልድ ትራምፕ አመጽን ቀስቅሶ ከመምራት ክስ ነጻ መደረጋቸው ይታወሳል። ማይክ ፔንስ ነውጠኞቹን የተቃወሙ ሲሆን የፕሬዚዳንት ጆ ባይደንን በዓለ ሲመት ላይ ተገኝተዋል። የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዓለ ሲመቱ ላይ አልተገኙም። ነገር ግን አርብ እለት በነበረው ንግግራቸው ማይክ ፔንስ የቀድሞ አለቃውን በስልጣን ላይ ያሳኩዋቸውን ነገሮች ተናግረዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-57534153
5sports
ዩሮ 2020፡ እግር ኳስ ተጫዋቾች በጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት የማስታወቂያ መጠጦችን ካነሱ ሊቀጡ ይችላሉ
በቅርቡ ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና ፖል ፖግባ እንዳደረጉት ተጫዋቾች በጋዜጣዊ መግለጫዎች ወቅት የስፖንሰሮችን መጠጦች ከጠረጴዛ አንስተው ከካሜራ ካራቁ በዩሮ 2020 የሚሳተፉ ቡድኖቻቸው የገንዘብ ቅጣት ሊጠብቃቸው ይችላል ተባለ። ሰኞ ዕለት የፖርቹጋሉ አምበል ክርስቲያኖ ሮናልዶ ሁለት የኮካ ኮላ ጠርሙሶችን ከፊቱ በማንሳት ሰዎች ውሃ እንዲጠጡ አበረታቷል። በቀጣዩ ቀን ደግሞ የእስልምና እምነት ተከታይ ሆነው ፈረንሳዊው አማካይ ፖግባ የሄኒከን ቢራ ጠርሙስን ከጠረጴዛው ላይ አንስቷል። ጣሊያናዊው ማኑዌል ሎካቴሊ ደግሞ ረቡዕ ዕለት ኮካ ኮላ አንስቶ በውሃ ተክቶታል። ሐሙስ ዕለት "የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር (ዩኤፋ) ተሳትፊ ቡድኖች ስፖንሰር አድራጊዎች ለውድድሩ መካሄድ ሚና እንዳላቸው አስታውሶ በመላው አውሮፓ ወጣቶችን እና ሴቶችን ጨምሮ የእግር ኳስ ዕድገትን ለማረጋገጥ ወሳኝ ናቸው" ብለዋል የውድድሩ አዘጋጆች። የዩኤፋ የዩሮ 2020 የውድድር ዳይሬክተር ማርቲን ካለን በበኩላቸው ተጫዋቾች "የውድድር ደንቦችን ለመጠበቅ በፌዴሬሽናቸው በኩል" የውል ግዴታቸው አለባቸው ብለዋል። ሆኖም እንደ ፖግባ ያሉ ተጫዋቾች በሐይማኖታዊ ምክንያቶች ያደረጉት በመሆኑ እንደሚረዱት ተናግረዋል። ቡድኖች የውል ደንቦቻቸውን እንዲያስታውሱ የተደረገ ሲሆን ካለን እንዳሉት ደግሞ የዲሲፕሊን እርምጃም ሌላው "አማራጭ" ነው። ዩኤፋ በቀጥታ ተጫዋቾችን የመቅጣት ፍላጎት የሌለው ሲሆን ማንኛውም ቅጣት የብሔራዊ ፌዴሬሽኖች ውሳኔ ነው። "ዩኤፋ ተጫዋቾችን በቀጥታ እየቀጣ አይደለም። ይህን ሁሌም በተሳታፊ ብሔራዊ ማኅበር በኩል ይከናወናል። ከዚያ በኋላ እነሱ ወደ ተጫዋቾቹ የሚሄዱ ከሆነ ማየት ይችላሉ። ለጊዜው በቀጥታ ወደ ተጫዋቾቹ አንሄድም" ብለዋል ካለን። "በተሳታፊ ፌደሬሽኖች የተፈረሙ ደንቦች አሉን" ብለዋል።
ዩሮ 2020፡ እግር ኳስ ተጫዋቾች በጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት የማስታወቂያ መጠጦችን ካነሱ ሊቀጡ ይችላሉ በቅርቡ ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና ፖል ፖግባ እንዳደረጉት ተጫዋቾች በጋዜጣዊ መግለጫዎች ወቅት የስፖንሰሮችን መጠጦች ከጠረጴዛ አንስተው ከካሜራ ካራቁ በዩሮ 2020 የሚሳተፉ ቡድኖቻቸው የገንዘብ ቅጣት ሊጠብቃቸው ይችላል ተባለ። ሰኞ ዕለት የፖርቹጋሉ አምበል ክርስቲያኖ ሮናልዶ ሁለት የኮካ ኮላ ጠርሙሶችን ከፊቱ በማንሳት ሰዎች ውሃ እንዲጠጡ አበረታቷል። በቀጣዩ ቀን ደግሞ የእስልምና እምነት ተከታይ ሆነው ፈረንሳዊው አማካይ ፖግባ የሄኒከን ቢራ ጠርሙስን ከጠረጴዛው ላይ አንስቷል። ጣሊያናዊው ማኑዌል ሎካቴሊ ደግሞ ረቡዕ ዕለት ኮካ ኮላ አንስቶ በውሃ ተክቶታል። ሐሙስ ዕለት "የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር (ዩኤፋ) ተሳትፊ ቡድኖች ስፖንሰር አድራጊዎች ለውድድሩ መካሄድ ሚና እንዳላቸው አስታውሶ በመላው አውሮፓ ወጣቶችን እና ሴቶችን ጨምሮ የእግር ኳስ ዕድገትን ለማረጋገጥ ወሳኝ ናቸው" ብለዋል የውድድሩ አዘጋጆች። የዩኤፋ የዩሮ 2020 የውድድር ዳይሬክተር ማርቲን ካለን በበኩላቸው ተጫዋቾች "የውድድር ደንቦችን ለመጠበቅ በፌዴሬሽናቸው በኩል" የውል ግዴታቸው አለባቸው ብለዋል። ሆኖም እንደ ፖግባ ያሉ ተጫዋቾች በሐይማኖታዊ ምክንያቶች ያደረጉት በመሆኑ እንደሚረዱት ተናግረዋል። ቡድኖች የውል ደንቦቻቸውን እንዲያስታውሱ የተደረገ ሲሆን ካለን እንዳሉት ደግሞ የዲሲፕሊን እርምጃም ሌላው "አማራጭ" ነው። ዩኤፋ በቀጥታ ተጫዋቾችን የመቅጣት ፍላጎት የሌለው ሲሆን ማንኛውም ቅጣት የብሔራዊ ፌዴሬሽኖች ውሳኔ ነው። "ዩኤፋ ተጫዋቾችን በቀጥታ እየቀጣ አይደለም። ይህን ሁሌም በተሳታፊ ብሔራዊ ማኅበር በኩል ይከናወናል። ከዚያ በኋላ እነሱ ወደ ተጫዋቾቹ የሚሄዱ ከሆነ ማየት ይችላሉ። ለጊዜው በቀጥታ ወደ ተጫዋቾቹ አንሄድም" ብለዋል ካለን። "በተሳታፊ ፌደሬሽኖች የተፈረሙ ደንቦች አሉን" ብለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-57519046
2health
በዓለማችን ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የመንትዮች ቁጥር ጨምሯል
ዓለማችን ከዚህ በፊት አይታው በማታውቀው መጠን በመንትዮች እየተሞላች እንደሆነ አጥኚዎች አረጋገጡ። በየዓመቱ 1.6 ሚሊዮን መንታ ልጆች ይወለዳሉ። ይህ ማለት ከ42 ሕፃናት መካከል መንታዎች አሉ ማለት ነው። ዘግይቶ ማርገዝና አንዳንድ የሕክምና መላዎች ከ1980ዎቹ በኋላ የመንታ ልጆች የውልደት መጠንን በሦስት እጥፍ እንዲያድግ አድርጎታል። ነገር ግን የመንታ ልጆች ውልደት መጠን ከዚህ በኋላ እንደሚቀንስ ይገመታል። ለዚህ ደግሞ ዋነኛው ምክንያት አንድ ልጅ ብቻ ወልዶ ማሳደግ አዲሱ የሕይወት ዘይቤ እየሆነ መምጣቱ ነው። ሂዩማን ሪፕሮዳክሽንስ የተሰኘው ጋዜጣ ላይ የወጣ ዘገባ እንደሚያሳየው ባለፉት 30 ዓመታት የመንታ ልጆች ዕድገት እስያ ውስጥ 32 በመቶ ሲጨምር ሰሜን አሜሪካ በ71 በመቶ ተመንድጓል። አጥኚዎቹ በፈረንጆቹ ከ2010-15 ባለው ጊዜ ከ165 አገራት የሰበሰቡትን ጥናት ከ1980-85 ካለው ጋር አነጻጽውታል። በአውሮፓና በሰሜን አሜሪካ ከአንድ ሺህ አዲስ የሚወለዱ ሕፃናት የመንታዎች ቁጥር ጨምሯል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ከአንድ ሺህ ሕፃናት መካከል 12 መንታዎች ይወለዳሉ። በአፍሪካ የሚወለዱ የመንታ ልጆች መጠን በፊትም ባለፉት 30 ዓመታት ከፍተኛ ነው፤ ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ የሕዝብ ብዛት ነው ይላሉ አጥኚዎች። አፍሪካና እስያ በዓለማችን ካሉ መንታዎች 80 በመቶውን በመያዝ ቀዳሚዎቹ አህጉራት ናቸው። የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር ክርስቲያን ሞንደን ለዚህ አንድ ምክንያት አሉ ይላሉ። "በአፍሪካ የመንታ ልጆች ቁጥር እየጨመረ ያለበት አንዱ ምክንያት ከሁለት የተለያዩ እንቁላሎች መወለዳቸው ነው።" "ይህ የሚሆንበት አንደኛው ምክንያት በአፍሪካ ሕዝብና በሌላው ሕዝብ መካከል ያለው የዘረ-መል (ጄኔቲክ) ልዩነት ሊሆን ይችላል።" የመንታ ልጆች ውልደት መጠን በአውሮፓ፣ ሰሜን አሜሪካና ኦሺኒክ አገራትም ከጊዜ ጊዜ እየጨመረ ነው። ለዚህ እንደምክንያት የሚቆጠረው ከ1970ዎቹ በኋላ እየተለመደ የመጡት ሳይንሳዊ መላዎችን ተጠቅሞ መንታ ልጆች መውለድ መለመዱ ነው። ሴቶች ዘግይተው ልጅ መውለዳቸው፣ የወሊድ መቆጣጠሪያዎች መበራከት፣ እንዲሁም የውልደት መጠን መቀነስ ለመንታ ልጆች ውልደት መጠን መጨመር አስተዋፅዖ እያበረከቱ ነው። ነገር ግን አሁኑ ትኩረቱ አንድ ልጅ ብቻ ወደማሳደግ እየዞረ መጥቷል፤ ይህ ተመራጭ ነው ይላሉ ፕሮፌሰር ሞንደን። ፕሮፌሰር አንድ ልጅ ብቻ ለመውለድ መሞከር መልካም ነው ብለው የሚያስቡት መንታ ልጆችን የሚያረግዙ እናቶች በእርግዝና ወቅት፣ በወሊድ ጊዜና እንዲሁም ከወሊድ በኋላ ብዙ ችግር እንደሚያጋጥማቸው ጥናቶች ስለሚጠቁሙ ነው። ከወሊድ በኋላም ቢሆን በተለይ ደግሞ በዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ባላቸው አገራት መንታ ልጆችን ማሳደግ ቀላል አይደለም። ለምሳሌ ከሰሃራ በታች የአፍሪካ ክፍል ውስጥ በርካታ መንታ ልጆች በመጀመሪያው ዓመት አብረዋቸው የተወደለዱ ልጆችን ያጣሉ። ወደፊት ለሚታየው የመንታ ልጆች ውልደት መጠን ቻይናና ሕንድ የበኩላቸውን ሊወጡ እንደሚችል ይታመናል።
በዓለማችን ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የመንትዮች ቁጥር ጨምሯል ዓለማችን ከዚህ በፊት አይታው በማታውቀው መጠን በመንትዮች እየተሞላች እንደሆነ አጥኚዎች አረጋገጡ። በየዓመቱ 1.6 ሚሊዮን መንታ ልጆች ይወለዳሉ። ይህ ማለት ከ42 ሕፃናት መካከል መንታዎች አሉ ማለት ነው። ዘግይቶ ማርገዝና አንዳንድ የሕክምና መላዎች ከ1980ዎቹ በኋላ የመንታ ልጆች የውልደት መጠንን በሦስት እጥፍ እንዲያድግ አድርጎታል። ነገር ግን የመንታ ልጆች ውልደት መጠን ከዚህ በኋላ እንደሚቀንስ ይገመታል። ለዚህ ደግሞ ዋነኛው ምክንያት አንድ ልጅ ብቻ ወልዶ ማሳደግ አዲሱ የሕይወት ዘይቤ እየሆነ መምጣቱ ነው። ሂዩማን ሪፕሮዳክሽንስ የተሰኘው ጋዜጣ ላይ የወጣ ዘገባ እንደሚያሳየው ባለፉት 30 ዓመታት የመንታ ልጆች ዕድገት እስያ ውስጥ 32 በመቶ ሲጨምር ሰሜን አሜሪካ በ71 በመቶ ተመንድጓል። አጥኚዎቹ በፈረንጆቹ ከ2010-15 ባለው ጊዜ ከ165 አገራት የሰበሰቡትን ጥናት ከ1980-85 ካለው ጋር አነጻጽውታል። በአውሮፓና በሰሜን አሜሪካ ከአንድ ሺህ አዲስ የሚወለዱ ሕፃናት የመንታዎች ቁጥር ጨምሯል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ከአንድ ሺህ ሕፃናት መካከል 12 መንታዎች ይወለዳሉ። በአፍሪካ የሚወለዱ የመንታ ልጆች መጠን በፊትም ባለፉት 30 ዓመታት ከፍተኛ ነው፤ ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ የሕዝብ ብዛት ነው ይላሉ አጥኚዎች። አፍሪካና እስያ በዓለማችን ካሉ መንታዎች 80 በመቶውን በመያዝ ቀዳሚዎቹ አህጉራት ናቸው። የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር ክርስቲያን ሞንደን ለዚህ አንድ ምክንያት አሉ ይላሉ። "በአፍሪካ የመንታ ልጆች ቁጥር እየጨመረ ያለበት አንዱ ምክንያት ከሁለት የተለያዩ እንቁላሎች መወለዳቸው ነው።" "ይህ የሚሆንበት አንደኛው ምክንያት በአፍሪካ ሕዝብና በሌላው ሕዝብ መካከል ያለው የዘረ-መል (ጄኔቲክ) ልዩነት ሊሆን ይችላል።" የመንታ ልጆች ውልደት መጠን በአውሮፓ፣ ሰሜን አሜሪካና ኦሺኒክ አገራትም ከጊዜ ጊዜ እየጨመረ ነው። ለዚህ እንደምክንያት የሚቆጠረው ከ1970ዎቹ በኋላ እየተለመደ የመጡት ሳይንሳዊ መላዎችን ተጠቅሞ መንታ ልጆች መውለድ መለመዱ ነው። ሴቶች ዘግይተው ልጅ መውለዳቸው፣ የወሊድ መቆጣጠሪያዎች መበራከት፣ እንዲሁም የውልደት መጠን መቀነስ ለመንታ ልጆች ውልደት መጠን መጨመር አስተዋፅዖ እያበረከቱ ነው። ነገር ግን አሁኑ ትኩረቱ አንድ ልጅ ብቻ ወደማሳደግ እየዞረ መጥቷል፤ ይህ ተመራጭ ነው ይላሉ ፕሮፌሰር ሞንደን። ፕሮፌሰር አንድ ልጅ ብቻ ለመውለድ መሞከር መልካም ነው ብለው የሚያስቡት መንታ ልጆችን የሚያረግዙ እናቶች በእርግዝና ወቅት፣ በወሊድ ጊዜና እንዲሁም ከወሊድ በኋላ ብዙ ችግር እንደሚያጋጥማቸው ጥናቶች ስለሚጠቁሙ ነው። ከወሊድ በኋላም ቢሆን በተለይ ደግሞ በዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ባላቸው አገራት መንታ ልጆችን ማሳደግ ቀላል አይደለም። ለምሳሌ ከሰሃራ በታች የአፍሪካ ክፍል ውስጥ በርካታ መንታ ልጆች በመጀመሪያው ዓመት አብረዋቸው የተወደለዱ ልጆችን ያጣሉ። ወደፊት ለሚታየው የመንታ ልጆች ውልደት መጠን ቻይናና ሕንድ የበኩላቸውን ሊወጡ እንደሚችል ይታመናል።
https://www.bbc.com/amharic/news-56372875
0business
የባንክና የኢንሹራንስ ዘርፍ ለኢትዮጵያዊያን ብቻ የተተዉ ይሆናል
ኢትዮጵያ የባንክና የኢንሹራንስ ተቋማትን ለውጪ ባለሃብቶች ተሳትፎ ክፍት እንደማታደርግ ሮይተርስ ጉዳዩን በሚመለከት የተዘጋጀን ረቂቅ ሕግን ዋቢ አድረጎ ዘገበ። ኢትዮጵያ የተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎችን ለውጪ ባለሃብቶች ክፍት ለማድረግ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነች ቢሆንም የባንክና የኢንሹራንስ ዘርፎች ግን አሁንም ዜጎቿ ብቻ የሚሳተፉባቸው መስኮች ሆነው እንዲቆዩ ልታደርግ መሆኑን ሮይተርስ አየሁት ባለው ረቂቅ ሕግ ላይ ሰፍሯል ብሏል። የተለያዩ የውጪ ባለሃብቶችና ተቋማት ኢትዮጵያ ክፍት ታደርጋቸዋለች ተብለው የሚጠበቁ ተቋማትን ለመግዛትና በመንግሥት እጅ ስር ብቻ ተይዘው በነበሩ ዘርፎች ላይ ለመሳተፍ ያላቸውን ፍላጎት እየገለጹ ነው። • እየበረታ በመሄድ ላይ ያለው የዋጋ ንረት አዙሪት • "ኢስላማዊ ባንክ ለኢትዮጵያ ምን ይፈይዳል?" የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድን ወደ ስልጣን መምጣትን ተከትሎ የአገሪቱን ኢኮኖሚ ለማሳደግና ኢትዮጵያን ወደ መካከለኛ ገቢ ለማሳደግ በመንግሥት ቁጥጥር ስር የነበሩ ዘርፎች ላይ የውጪ ባለሃብቶች ክፍት እንደሚሆኑ ተገልጾ ነበር። ሮይተርስ የጠቀሰው ረቂቅ የኢንቨስትመንት ሕግ ላይ እንዳመለከተው የባንክ፣ የኢንሹራንስ፣ አነስተኛ የቁጠባና የብድር የገንዘብ ተቋማት ለአገር ውስጥ ባለሃብቶች ብቻ የተተዉ ዘርፎች ይሆናሉ። የአገሪቱ የባንክ ዘርፍ በአፍሪካ በመንግሥት ከፍተኛ ቁጥጥር የሚደረግ ነው። ባለፈው ሐምሌ የአገሪቱ ምክር ቤት አምስት ሚሊዮን ለሚሆኑ የሌላ አገር ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የባንኮችን አክሲዮን ለመግዛት እንዲችሉ የሚፈቅድ ሕግ ሲያወጣ፤ በበርካቶች ዘንድ ቀስ በቀስ ዘርፉ ለውጪ ባለሃብቶችም ክፍት ሊደረግ ይችላል የሚል ተስፋን ፈጥሮ ነበር። • በስህተት የተሰጣቸውን 1 ሚሊየን ብር የመለሱት መምህር • እውን ድህነትን እየቀነስን ነው? በጠቅላይ ሚኒስትሩ እየተወሰዱ ካሉ የኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃዎች መካከል ትላልቆቹን የስኳር ማምረቻ ፋብሪካዎች ወደ ግል ይዞታነት የማዘዋወሩ እርምጃ ከወራት በኋላ ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል። በተጨማሪም መንግሥት ለሁለት የሞባይል ስልክ አገልግሎት አቅራቢ ድርጅቶች ፈቃድ ለመስጠትና የመንግሥት ንብረት ከሆነው ኢትዮ ቴሌኮም ላይ ደግሞ የተወሰነ ድርሻን ለባለሃብቶች ለመሸጥ ዕቅድ አለው። በሮይተርስ የተጠቀሰው ረቂቅ የኢንቨስትመንት ሕግ በቀጣዮቹ ሁለት ወይም ሦስት ሳምንታት ውስጥ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኋላ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል። ኢትዮጵያ በፍጥነት እየጨመረ የሚሄድና ወጣት ሕዝብ ያላት ሲሆን ኢኮኖሚዋም ከአስር ዓመታት በላይ በሁለት አሃዞች ሲያድግ ቆይቷል። ነገር ግን በአገሪቱ የሚስተዋለው ብሔርን መሰረት ያደረገ ውጥረትና ግጭት ኢኮኖሚው ላይ ስጋትን ፈጥሯል።
የባንክና የኢንሹራንስ ዘርፍ ለኢትዮጵያዊያን ብቻ የተተዉ ይሆናል ኢትዮጵያ የባንክና የኢንሹራንስ ተቋማትን ለውጪ ባለሃብቶች ተሳትፎ ክፍት እንደማታደርግ ሮይተርስ ጉዳዩን በሚመለከት የተዘጋጀን ረቂቅ ሕግን ዋቢ አድረጎ ዘገበ። ኢትዮጵያ የተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎችን ለውጪ ባለሃብቶች ክፍት ለማድረግ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነች ቢሆንም የባንክና የኢንሹራንስ ዘርፎች ግን አሁንም ዜጎቿ ብቻ የሚሳተፉባቸው መስኮች ሆነው እንዲቆዩ ልታደርግ መሆኑን ሮይተርስ አየሁት ባለው ረቂቅ ሕግ ላይ ሰፍሯል ብሏል። የተለያዩ የውጪ ባለሃብቶችና ተቋማት ኢትዮጵያ ክፍት ታደርጋቸዋለች ተብለው የሚጠበቁ ተቋማትን ለመግዛትና በመንግሥት እጅ ስር ብቻ ተይዘው በነበሩ ዘርፎች ላይ ለመሳተፍ ያላቸውን ፍላጎት እየገለጹ ነው። • እየበረታ በመሄድ ላይ ያለው የዋጋ ንረት አዙሪት • "ኢስላማዊ ባንክ ለኢትዮጵያ ምን ይፈይዳል?" የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድን ወደ ስልጣን መምጣትን ተከትሎ የአገሪቱን ኢኮኖሚ ለማሳደግና ኢትዮጵያን ወደ መካከለኛ ገቢ ለማሳደግ በመንግሥት ቁጥጥር ስር የነበሩ ዘርፎች ላይ የውጪ ባለሃብቶች ክፍት እንደሚሆኑ ተገልጾ ነበር። ሮይተርስ የጠቀሰው ረቂቅ የኢንቨስትመንት ሕግ ላይ እንዳመለከተው የባንክ፣ የኢንሹራንስ፣ አነስተኛ የቁጠባና የብድር የገንዘብ ተቋማት ለአገር ውስጥ ባለሃብቶች ብቻ የተተዉ ዘርፎች ይሆናሉ። የአገሪቱ የባንክ ዘርፍ በአፍሪካ በመንግሥት ከፍተኛ ቁጥጥር የሚደረግ ነው። ባለፈው ሐምሌ የአገሪቱ ምክር ቤት አምስት ሚሊዮን ለሚሆኑ የሌላ አገር ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የባንኮችን አክሲዮን ለመግዛት እንዲችሉ የሚፈቅድ ሕግ ሲያወጣ፤ በበርካቶች ዘንድ ቀስ በቀስ ዘርፉ ለውጪ ባለሃብቶችም ክፍት ሊደረግ ይችላል የሚል ተስፋን ፈጥሮ ነበር። • በስህተት የተሰጣቸውን 1 ሚሊየን ብር የመለሱት መምህር • እውን ድህነትን እየቀነስን ነው? በጠቅላይ ሚኒስትሩ እየተወሰዱ ካሉ የኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃዎች መካከል ትላልቆቹን የስኳር ማምረቻ ፋብሪካዎች ወደ ግል ይዞታነት የማዘዋወሩ እርምጃ ከወራት በኋላ ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል። በተጨማሪም መንግሥት ለሁለት የሞባይል ስልክ አገልግሎት አቅራቢ ድርጅቶች ፈቃድ ለመስጠትና የመንግሥት ንብረት ከሆነው ኢትዮ ቴሌኮም ላይ ደግሞ የተወሰነ ድርሻን ለባለሃብቶች ለመሸጥ ዕቅድ አለው። በሮይተርስ የተጠቀሰው ረቂቅ የኢንቨስትመንት ሕግ በቀጣዮቹ ሁለት ወይም ሦስት ሳምንታት ውስጥ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኋላ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል። ኢትዮጵያ በፍጥነት እየጨመረ የሚሄድና ወጣት ሕዝብ ያላት ሲሆን ኢኮኖሚዋም ከአስር ዓመታት በላይ በሁለት አሃዞች ሲያድግ ቆይቷል። ነገር ግን በአገሪቱ የሚስተዋለው ብሔርን መሰረት ያደረገ ውጥረትና ግጭት ኢኮኖሚው ላይ ስጋትን ፈጥሯል።
https://www.bbc.com/amharic/news-50641297
5sports
ሩሲያ ያሰረቻትን የቅርጫት ኳስ ተጫዋች አሜሪካ ባለእስረኛ የመለዋወጥ ፍላጎት እንዳላት ተነገረ
ሩሲያ ጉዳይዋ በፍርድ ቤት እየታየ የምትገኘውን ታዋቂ አሜሪካዊት የቅርጫት ኳስ ተጫዋችን አሜሪካ ውስጥ በሚገኝ እስረኛ ለመለዋወጥ ፍላጎት እንዳላት ተነገረ። አደንዛዥ ዕጽ ይዛ ተገኝታለች በሚል ከወራት በፊት ሩሲያ ውስጥ በእስር ላይ የምትገኘውን የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ብሪትኒ ግሪነር፣ በሕገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ተፈርደቦት አሜሪካ ውስጥ በሚገኘው ቪክቶር ባውት የመቀየር ፍላጎት በሩሲያ በኩል እንዳለ ስማቸው ያልተጠቀሰን ባለሥልጣን ጠቅሶ የሩሲያ የዜና ወኪል ዘግቧል። በቀጠሮ ፍርድ ቤት ቀርባ የነበረችው የቅርጫት ኳስ ተጨዋቿ ተጨማሪ የአንድ ወር የጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቶባታል። የ31 ዓመቷ ብሪትኒ ግሪነር በሩሲያ ከነበራት ጨዋታ በኋላ ወደ አገሯ ስትመለስ ካናቢስ የተባለ ዕጽ ሻንጣ ውስጥ ተግኝቶባታል በሚል ነበር በቁጥጥር ስር የዋለችው። የአሜሪካ ባለሥልጣናት የስፖርተኛዋ እስር ተገቢ አይደለም፤ መለቀቅ አለባት በማለት ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ቆይተዋል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ምርጥ ሴት የቅርጫት ኳስ ተጨዋች ከሚባሉት አንዷ የሆነችው ግሪነር በቀረበባት ክስ ጥፋተኛ ከተባለች እስከ 10 ዓመት የሚደርስ ቅጣት ይጠብቃታል ተብሏል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ተጨዋቿ ከሞስኮ ወጣ ብላ በምትገኝ ከተማ በነበራት ችሎት ላይ የቆንስላ ኃላፊዎች መታደማቸውን እና እርሷንም እንዳነጋገሯት ገልጿል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ሩሲያ በእስር ላይ ያለችውን ብሪትኒ ግሪነር አሜሪካ ውስጥ በሚገኝ እስር ቤት ባለ ሩሲያዊ ታሳሪ የመቀየር ፍላጎት እንዳላት ተሰምቷል። "የሞት ነጋዴው" በሚለው መጠሪያ በስፋት የሚታወቀው ቪክቶር ባውት በሕገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ነበር የተፈረደበት። ቦውት እንደ አውሮፓውያኑ በ2008 ታይላንድ ውስጥ በቁጥጥር ስር ውሎ ነው ለአሜሪካ ተላልፎ የተሰጠው። ግለሰቡ በኮሎምቢያ የሚገኙ አማጽያንን በማስታጠቅ የአሜሪካ ዜጎች ላይ ጥቃት እንዲያደርሱ አድርጓል የሚል ክስ ቀርቦበት ነበር እንደ አውሮፓውያኑ በ2012 በኒው ዮርክ ውስጥ የ25 ዓመታት እስር የተፈረደበት። ባለፈው የካቲት ወር ሩሲያ ውስጥ በተካሄደ የቅርጫት ኳስ ውድድር ላይ ተሳትፋ ወደ አገሯ ልትመለስ ስትል አየር ማረፊያ ውስጥ የተያዘችው አሜሪካዊቷ ግሪነር፣ ይዛው በነበረው ሻንጣዋ ውስጥ ቅባታማ ሃሺሽ በአነፍናፊ ውሻ እንደተለየ በወቅቱ የሩሲያ ባለሥልጣናት ገልጸው ነበር። ባለሥልጣናቱ የቅርጫት ኳስ ተጨዋቿን መታሰር ያረጋገጡትም ከሳምንታት በኋላ ነበር።
ሩሲያ ያሰረቻትን የቅርጫት ኳስ ተጫዋች አሜሪካ ባለእስረኛ የመለዋወጥ ፍላጎት እንዳላት ተነገረ ሩሲያ ጉዳይዋ በፍርድ ቤት እየታየ የምትገኘውን ታዋቂ አሜሪካዊት የቅርጫት ኳስ ተጫዋችን አሜሪካ ውስጥ በሚገኝ እስረኛ ለመለዋወጥ ፍላጎት እንዳላት ተነገረ። አደንዛዥ ዕጽ ይዛ ተገኝታለች በሚል ከወራት በፊት ሩሲያ ውስጥ በእስር ላይ የምትገኘውን የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ብሪትኒ ግሪነር፣ በሕገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ተፈርደቦት አሜሪካ ውስጥ በሚገኘው ቪክቶር ባውት የመቀየር ፍላጎት በሩሲያ በኩል እንዳለ ስማቸው ያልተጠቀሰን ባለሥልጣን ጠቅሶ የሩሲያ የዜና ወኪል ዘግቧል። በቀጠሮ ፍርድ ቤት ቀርባ የነበረችው የቅርጫት ኳስ ተጨዋቿ ተጨማሪ የአንድ ወር የጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቶባታል። የ31 ዓመቷ ብሪትኒ ግሪነር በሩሲያ ከነበራት ጨዋታ በኋላ ወደ አገሯ ስትመለስ ካናቢስ የተባለ ዕጽ ሻንጣ ውስጥ ተግኝቶባታል በሚል ነበር በቁጥጥር ስር የዋለችው። የአሜሪካ ባለሥልጣናት የስፖርተኛዋ እስር ተገቢ አይደለም፤ መለቀቅ አለባት በማለት ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ቆይተዋል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ምርጥ ሴት የቅርጫት ኳስ ተጨዋች ከሚባሉት አንዷ የሆነችው ግሪነር በቀረበባት ክስ ጥፋተኛ ከተባለች እስከ 10 ዓመት የሚደርስ ቅጣት ይጠብቃታል ተብሏል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ተጨዋቿ ከሞስኮ ወጣ ብላ በምትገኝ ከተማ በነበራት ችሎት ላይ የቆንስላ ኃላፊዎች መታደማቸውን እና እርሷንም እንዳነጋገሯት ገልጿል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ሩሲያ በእስር ላይ ያለችውን ብሪትኒ ግሪነር አሜሪካ ውስጥ በሚገኝ እስር ቤት ባለ ሩሲያዊ ታሳሪ የመቀየር ፍላጎት እንዳላት ተሰምቷል። "የሞት ነጋዴው" በሚለው መጠሪያ በስፋት የሚታወቀው ቪክቶር ባውት በሕገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ነበር የተፈረደበት። ቦውት እንደ አውሮፓውያኑ በ2008 ታይላንድ ውስጥ በቁጥጥር ስር ውሎ ነው ለአሜሪካ ተላልፎ የተሰጠው። ግለሰቡ በኮሎምቢያ የሚገኙ አማጽያንን በማስታጠቅ የአሜሪካ ዜጎች ላይ ጥቃት እንዲያደርሱ አድርጓል የሚል ክስ ቀርቦበት ነበር እንደ አውሮፓውያኑ በ2012 በኒው ዮርክ ውስጥ የ25 ዓመታት እስር የተፈረደበት። ባለፈው የካቲት ወር ሩሲያ ውስጥ በተካሄደ የቅርጫት ኳስ ውድድር ላይ ተሳትፋ ወደ አገሯ ልትመለስ ስትል አየር ማረፊያ ውስጥ የተያዘችው አሜሪካዊቷ ግሪነር፣ ይዛው በነበረው ሻንጣዋ ውስጥ ቅባታማ ሃሺሽ በአነፍናፊ ውሻ እንደተለየ በወቅቱ የሩሲያ ባለሥልጣናት ገልጸው ነበር። ባለሥልጣናቱ የቅርጫት ኳስ ተጨዋቿን መታሰር ያረጋገጡትም ከሳምንታት በኋላ ነበር።
https://www.bbc.com/amharic/news-61448051
2health
በርካቶች የኮቪድ-19 መከላከያ ላለመከተብ የሚያቀርቧቸው ምክንያቶችና መልሶቻቸው
በመላው ዓለም የኮቪድ ክትባት አሰጣጥ ላይ ትልቅ ልዩነት አለ። የክትባት አቅርቦት አሁንም በብዙ አገራት ትልቅ ችግር ነው። ነገር ግን ክትባቱ ኖሮም ብዙዎች ለመከተብ ያመነታሉ ወይም ፈቃደኛ አይደሉም። እርስዎ ተከትበዋል? ካልተከተቡ ምክንያትዎ ምንድን ነው? በበርካታ ሰዎች ዘንድ ላለመከተባቸው በስፋት እንደምክንያት የሚነሱ ነገሮችን በማንሳት ይህ ቪዲዮ ምላሽ ይሰጣል።
በርካቶች የኮቪድ-19 መከላከያ ላለመከተብ የሚያቀርቧቸው ምክንያቶችና መልሶቻቸው በመላው ዓለም የኮቪድ ክትባት አሰጣጥ ላይ ትልቅ ልዩነት አለ። የክትባት አቅርቦት አሁንም በብዙ አገራት ትልቅ ችግር ነው። ነገር ግን ክትባቱ ኖሮም ብዙዎች ለመከተብ ያመነታሉ ወይም ፈቃደኛ አይደሉም። እርስዎ ተከትበዋል? ካልተከተቡ ምክንያትዎ ምንድን ነው? በበርካታ ሰዎች ዘንድ ላለመከተባቸው በስፋት እንደምክንያት የሚነሱ ነገሮችን በማንሳት ይህ ቪዲዮ ምላሽ ይሰጣል።
https://www.bbc.com/amharic/news-60140221
3politics
"አን ሳን ሱቺ ጥሩ እንክብካቤ እያገኙ ነው"- የምያንማር ጦር
በመፈንቅለ መንግሥት ሥልጣን የጨበጠው የምያንማር ወታደራዊ መንግሥት አን ሳን ሱቺ በደል እየደረሰባቸው ነው መባሉን አስተባብሏል። የ76 ዓመቷ የቀድሞው የአገሪቱ መሪ፣ ወታደራዊው አገዛዝ ሥልጣን ከያዘበት ካለፈው ዓመት የካቲት ጀምሮ በአደባባይ አልታዩም። ከቢቢሲ ጋር ቆይታ ያደረጉት የወታደራዊው ኃይል ቃል አቀባይ ሜጀር ጄኔራል ዛው ሚን ቱን ናቸው ሱቺ ሰላም ናቸው ያሉት። የምያንማር መንግሥት አሜሪካዊውን ጋዜጠኛ ዳኒ ፎስተርን በ11 ዓመታት እሥር ከቀጣ በኋላ በቀናት ልዩነት በነፃ እንዲለቀቅ መወሰኑ ይታወሳል። ከመፈንቅለ መንግሥቱ ወዲህ በርካታ ጋዜጠኞችና በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች በአገሪቱ ለእሥር ተዳርገዋል። ሜጀር ጄኔራል ዛው ሚን ቱ እንደሚሉት አን ሳን ሱቺ ባሉበት እሥር ቤት እንክብካቤ እየተደረገላቸው ነው። "ከራሷ ሰዎች ጋር ቤት ውስጥ በአንድነት እንድትኖር እኮ ነው የፈቀድንላት። ነገር ግን የቁም እሥር ላይ ትገኛለች" የሚሉት ቃል አቀባዩ "የፈለገችውን እንድታገኝና የፈቀደችውን እንድትመገብ የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን" ሲሉ አክለዋል። ሳን ሱቺ በቅኝት ግዛት ዘመን ተግባራዊ ይደረግ በነበረ ሕግ ነው ተከሰው በቁም እሥር ላይ የሚገኙት። አልፎም የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል፤ ዋኪ ቶኪ የተሰኘውን የርቀት መነጋገሪያ ይዘው ተገኝተዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል። ምንም እንኳ ችሎት ፊት ይቅረቡ እንጂ ክሳቸውን በተለመከተ ያሉት ዘርዘር ያለ ነገር የለም። ለቢቢሲ ቃለ ምልልስ የሰጡት ሜጀር ጄኔራል ዛው ቱን ሚን ጨምረው ባለሥልጣናት አሜሪካዊውን ጋዜጠኛ ለመልቀቅ ሲያስቡ ነበር ብለዋል። ዳን ፌስተር፤ የኢሚግሬሽን ሕግን በመጣስ፣ ከሕገ-ወጥ ሰዎች ጋር በማበርና ወታደራዊው አገዛዝ ከሚያዘው ውጪ በመንቀሳቀስ የ11 ዓመት እሥር ከተጣለበት ከቀናት በኋላ ሰኞ ዕለት ተለቋል። በተጨማሪ ጋዜጠኛው በሽብር ወንጀልና ሥልጣን ላይ ያለን ኃይል ለመጣል በማሴር ተጠርጥሮ ፍርዱን እየተጠባበቀ ነበር። ጄኔራሉ፤ አሜሪካው ጋዜጠኛው ነፃ መሆኑን ተከትሎ ምያንማር በምትኩ የምታገኘው ነገር ይኖር ይሆን ተብለው ተጠይቀው "ምንም እንደሌለ" ተናግረዋል። ባለፈው ወር የምያንማር ወታደራዊ አገዛዝ መፈንቅለ መንግሥቱን በመቃወማቸው ምክንያት ለእሥር የተዳረጉ 5 ሺህ ሰዎችን ለመፍታት ቃል ገብቶ ነበር። ቢያንስ 7291 ሰዎች ለእሥር የተዳረጉ ሲሆን የተወሰኑት የተበየነባቸው የተቀሩት ደግሞ ክስ ያለባቸው ናቸው።
"አን ሳን ሱቺ ጥሩ እንክብካቤ እያገኙ ነው"- የምያንማር ጦር በመፈንቅለ መንግሥት ሥልጣን የጨበጠው የምያንማር ወታደራዊ መንግሥት አን ሳን ሱቺ በደል እየደረሰባቸው ነው መባሉን አስተባብሏል። የ76 ዓመቷ የቀድሞው የአገሪቱ መሪ፣ ወታደራዊው አገዛዝ ሥልጣን ከያዘበት ካለፈው ዓመት የካቲት ጀምሮ በአደባባይ አልታዩም። ከቢቢሲ ጋር ቆይታ ያደረጉት የወታደራዊው ኃይል ቃል አቀባይ ሜጀር ጄኔራል ዛው ሚን ቱን ናቸው ሱቺ ሰላም ናቸው ያሉት። የምያንማር መንግሥት አሜሪካዊውን ጋዜጠኛ ዳኒ ፎስተርን በ11 ዓመታት እሥር ከቀጣ በኋላ በቀናት ልዩነት በነፃ እንዲለቀቅ መወሰኑ ይታወሳል። ከመፈንቅለ መንግሥቱ ወዲህ በርካታ ጋዜጠኞችና በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች በአገሪቱ ለእሥር ተዳርገዋል። ሜጀር ጄኔራል ዛው ሚን ቱ እንደሚሉት አን ሳን ሱቺ ባሉበት እሥር ቤት እንክብካቤ እየተደረገላቸው ነው። "ከራሷ ሰዎች ጋር ቤት ውስጥ በአንድነት እንድትኖር እኮ ነው የፈቀድንላት። ነገር ግን የቁም እሥር ላይ ትገኛለች" የሚሉት ቃል አቀባዩ "የፈለገችውን እንድታገኝና የፈቀደችውን እንድትመገብ የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን" ሲሉ አክለዋል። ሳን ሱቺ በቅኝት ግዛት ዘመን ተግባራዊ ይደረግ በነበረ ሕግ ነው ተከሰው በቁም እሥር ላይ የሚገኙት። አልፎም የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል፤ ዋኪ ቶኪ የተሰኘውን የርቀት መነጋገሪያ ይዘው ተገኝተዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል። ምንም እንኳ ችሎት ፊት ይቅረቡ እንጂ ክሳቸውን በተለመከተ ያሉት ዘርዘር ያለ ነገር የለም። ለቢቢሲ ቃለ ምልልስ የሰጡት ሜጀር ጄኔራል ዛው ቱን ሚን ጨምረው ባለሥልጣናት አሜሪካዊውን ጋዜጠኛ ለመልቀቅ ሲያስቡ ነበር ብለዋል። ዳን ፌስተር፤ የኢሚግሬሽን ሕግን በመጣስ፣ ከሕገ-ወጥ ሰዎች ጋር በማበርና ወታደራዊው አገዛዝ ከሚያዘው ውጪ በመንቀሳቀስ የ11 ዓመት እሥር ከተጣለበት ከቀናት በኋላ ሰኞ ዕለት ተለቋል። በተጨማሪ ጋዜጠኛው በሽብር ወንጀልና ሥልጣን ላይ ያለን ኃይል ለመጣል በማሴር ተጠርጥሮ ፍርዱን እየተጠባበቀ ነበር። ጄኔራሉ፤ አሜሪካው ጋዜጠኛው ነፃ መሆኑን ተከትሎ ምያንማር በምትኩ የምታገኘው ነገር ይኖር ይሆን ተብለው ተጠይቀው "ምንም እንደሌለ" ተናግረዋል። ባለፈው ወር የምያንማር ወታደራዊ አገዛዝ መፈንቅለ መንግሥቱን በመቃወማቸው ምክንያት ለእሥር የተዳረጉ 5 ሺህ ሰዎችን ለመፍታት ቃል ገብቶ ነበር። ቢያንስ 7291 ሰዎች ለእሥር የተዳረጉ ሲሆን የተወሰኑት የተበየነባቸው የተቀሩት ደግሞ ክስ ያለባቸው ናቸው።
https://www.bbc.com/amharic/news-59284875
3politics
በቱኒዚያ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎ ጠቅላይ ሚንስትሩ ከስልጣናቸው ተነሱ
በመላው ቱኒዚያ የተቀሰቀሰውን ከፍተኛ አመጽ ተከትሎ ፕሬዝደንቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ከስልጣና አንስተው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን ደግሞ አገዱ። በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች መንግሥት ወረርሽኙን ለመግታት የወሰደውን እርምጃ በመቃወም አደባባይ ወጥተው ቁጣቸውን የገለጹ ሲሆን እሁድ ዕለት ደግሞ ከፖሊስ ጋር መጋጨታቸውም ተገልጿል። ፕሬዝደንት ካኢስ ሳኤድ በአገሪቱ መረጋጋትን ለመፍጠር እሰራለሁ ካሉ በኋላ አዲስ ጠቅላይ ሚንስትር እንደሚሾሙ ገልጸዋል። ይሁን እንጂ ተቃዋሚዎች ፕሬዝደንቱ ጠቅላይ ሚንሰትሩን ማሰናበታቸው እና ምክር ቤቱን ማገዳቸው ከመፈንቅለ መንግሥት ተይቶ አይታይም እያሉ ነው። "እነዚህን እርምጃዎች የወሰድነው በአገሪቱ ሰላም እስከሚመለስና አገሪቱን ማዳን እንድንችል በማሰብ ነው" ብለዋል ፕሬዝዳንቱ በቴሌቪዥን ባስተላለፉት መልዕክት። ትናንት ዕሁድ ምሽት ላይ የጠቅላይ ሚኒስትር ሂኬም ሚቺቺ ከኃላፊነታቸው የመነሳት ዜና ከተሰማ በኋላ ዜጎች አደባባይ ወጥተው ደስታቸውን የገለጹ ሲሆን በዋና ከተማዋ ቱኒዝ ደግሞ ፕሬዝዳንቱ ተቃዋሚዎችን ተቀላቅለው ታይተዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚ ሰልፈኞች በተለያዩ ከተሞች ዋና ዋና ጎዳናዎች በመሰባሰብ የገዢው ፓርቲ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ሲገልጹ ተስተውለዋል። በርካቶችም የፓርቲዎው አመራሮች ይውጡልን በማለት ፓርላማውም እንዲፈርስ ጠይቀዋል። የጸጥታ ኃይሎች ተቃዋሚዎች ወደ ፓርላማው ቅጥር ግቢ እንዳይጉ ሲከለክሉና ወደ 'ቦርጊባ' አደባባይ እንዳይሄዱ መንገድ ሲዘጉ ተስተውለዋል። ይህ ጎዳና በአውሮፓውያኑ 2011 ለተቀጣጠለው ጸረ መንግሥት ተቃውሞ ዋነኛ ማዕከል ሆኖ አገልግሎ ነበር። ፖሊስ ተቃዋሚ ሰልፈኞቹን ለመበተን አስለቃሽ ጭስ ጭምር የተጠቀመ ሲሆን አንዳንድ ሰዎችን ደግሞ በቁጥጥር ስር አውሏል። ይህን ተከትሎም ተቃውሞውም ወደ አብዛኛው የአገሪቱ ከተሞች ተስፋፍቷል። ተቃዋሚዎችም የገዢው ፓርቲ ቢሮዎችን ሰብረው በመግባት ንብረቶችን የሰባበሩ ሲሆን 'ቶውዙር' ውስጥ የሚገኘው ያርቲው አካባቢያዊ ዋና ቢሮም በእሳት አያይዘውታል። ፓርቲው በበኩሉ የሰልፈኞቹን ተግባር በማውገዝ ይህንን አጋጣሚ ወንጀለኛ ዘራፊዎች አገሪቱን ወደ ብጥብጥና መፈራረስ ለመውሰድ እየተጠቀሙበት ነው ብሏል። ምንም እንኳን በዋና ከተማዋ ወጥተው ከተቃዋሚ ሰልፈⶉች ጋር አብረው ቢታዩም ፕሬዝዳንቱ ከዚህ በኋላ አላስፈላጊ አመጽ የሚቀጥል ከሆነ መከላከያ ኃይል ጣልቃ እንደሚገባ አስጠንቅቀዋል። "ማንኛውም ዜጋ የጦር መሳሪያ የሚጠቀም ከሆነ፣ ጥይት የሚተኩስ ከሆነ የመከላከያ አባላት በጥይት ምላሽ ይሰጣሉ" ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ከአስር ዓመታት በፊት በቱኒዚያ የተቀሰቀሰው አብዮት ተስፋፍቶ የአረብ አገራትንም ያዳረሰ ሲሆን በወቅቱም ከለውጡ በኋላ በርካታ ነገሮች እንደሚቀየሩ ተስፋ ተደርጎ ነበር። ነገር ግን ቱኒዚያ አሁንም ድረስ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ውስጥ የምትገኝ ሲሆን በአፍሪካም በኮሮረናቫይረስ በእጅጉ ከተጠቁት አገራት መካከል ትገኝበታለች።
በቱኒዚያ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎ ጠቅላይ ሚንስትሩ ከስልጣናቸው ተነሱ በመላው ቱኒዚያ የተቀሰቀሰውን ከፍተኛ አመጽ ተከትሎ ፕሬዝደንቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ከስልጣና አንስተው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን ደግሞ አገዱ። በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች መንግሥት ወረርሽኙን ለመግታት የወሰደውን እርምጃ በመቃወም አደባባይ ወጥተው ቁጣቸውን የገለጹ ሲሆን እሁድ ዕለት ደግሞ ከፖሊስ ጋር መጋጨታቸውም ተገልጿል። ፕሬዝደንት ካኢስ ሳኤድ በአገሪቱ መረጋጋትን ለመፍጠር እሰራለሁ ካሉ በኋላ አዲስ ጠቅላይ ሚንስትር እንደሚሾሙ ገልጸዋል። ይሁን እንጂ ተቃዋሚዎች ፕሬዝደንቱ ጠቅላይ ሚንሰትሩን ማሰናበታቸው እና ምክር ቤቱን ማገዳቸው ከመፈንቅለ መንግሥት ተይቶ አይታይም እያሉ ነው። "እነዚህን እርምጃዎች የወሰድነው በአገሪቱ ሰላም እስከሚመለስና አገሪቱን ማዳን እንድንችል በማሰብ ነው" ብለዋል ፕሬዝዳንቱ በቴሌቪዥን ባስተላለፉት መልዕክት። ትናንት ዕሁድ ምሽት ላይ የጠቅላይ ሚኒስትር ሂኬም ሚቺቺ ከኃላፊነታቸው የመነሳት ዜና ከተሰማ በኋላ ዜጎች አደባባይ ወጥተው ደስታቸውን የገለጹ ሲሆን በዋና ከተማዋ ቱኒዝ ደግሞ ፕሬዝዳንቱ ተቃዋሚዎችን ተቀላቅለው ታይተዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚ ሰልፈኞች በተለያዩ ከተሞች ዋና ዋና ጎዳናዎች በመሰባሰብ የገዢው ፓርቲ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ሲገልጹ ተስተውለዋል። በርካቶችም የፓርቲዎው አመራሮች ይውጡልን በማለት ፓርላማውም እንዲፈርስ ጠይቀዋል። የጸጥታ ኃይሎች ተቃዋሚዎች ወደ ፓርላማው ቅጥር ግቢ እንዳይጉ ሲከለክሉና ወደ 'ቦርጊባ' አደባባይ እንዳይሄዱ መንገድ ሲዘጉ ተስተውለዋል። ይህ ጎዳና በአውሮፓውያኑ 2011 ለተቀጣጠለው ጸረ መንግሥት ተቃውሞ ዋነኛ ማዕከል ሆኖ አገልግሎ ነበር። ፖሊስ ተቃዋሚ ሰልፈኞቹን ለመበተን አስለቃሽ ጭስ ጭምር የተጠቀመ ሲሆን አንዳንድ ሰዎችን ደግሞ በቁጥጥር ስር አውሏል። ይህን ተከትሎም ተቃውሞውም ወደ አብዛኛው የአገሪቱ ከተሞች ተስፋፍቷል። ተቃዋሚዎችም የገዢው ፓርቲ ቢሮዎችን ሰብረው በመግባት ንብረቶችን የሰባበሩ ሲሆን 'ቶውዙር' ውስጥ የሚገኘው ያርቲው አካባቢያዊ ዋና ቢሮም በእሳት አያይዘውታል። ፓርቲው በበኩሉ የሰልፈኞቹን ተግባር በማውገዝ ይህንን አጋጣሚ ወንጀለኛ ዘራፊዎች አገሪቱን ወደ ብጥብጥና መፈራረስ ለመውሰድ እየተጠቀሙበት ነው ብሏል። ምንም እንኳን በዋና ከተማዋ ወጥተው ከተቃዋሚ ሰልፈⶉች ጋር አብረው ቢታዩም ፕሬዝዳንቱ ከዚህ በኋላ አላስፈላጊ አመጽ የሚቀጥል ከሆነ መከላከያ ኃይል ጣልቃ እንደሚገባ አስጠንቅቀዋል። "ማንኛውም ዜጋ የጦር መሳሪያ የሚጠቀም ከሆነ፣ ጥይት የሚተኩስ ከሆነ የመከላከያ አባላት በጥይት ምላሽ ይሰጣሉ" ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ከአስር ዓመታት በፊት በቱኒዚያ የተቀሰቀሰው አብዮት ተስፋፍቶ የአረብ አገራትንም ያዳረሰ ሲሆን በወቅቱም ከለውጡ በኋላ በርካታ ነገሮች እንደሚቀየሩ ተስፋ ተደርጎ ነበር። ነገር ግን ቱኒዚያ አሁንም ድረስ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ውስጥ የምትገኝ ሲሆን በአፍሪካም በኮሮረናቫይረስ በእጅጉ ከተጠቁት አገራት መካከል ትገኝበታለች።
https://www.bbc.com/amharic/news-57967516
3politics
የሕዳሴው ግድብ፡ ኢትዮጵያ ከሕዳሴው ግድብ ሙሌት የሚያደናቅፋት ኃይል እንደሌለ ገለጸች
ኢትዮጵያ በመጭው የክረምት ወራት በታላቁ ሕዳሴ ግድብ የሙከራ ኃይል ማመንጨት እንደምትጀምር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። ኢትዮጵያ ይህን ያለችው በመጭው ክረምት ለሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት እየተዘጋጀች ባለችበት ወቅት ነው። ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ ከግድቡ ሙሌት እና ግንባታ ጋር ተያይዞ የአሠራር ሂደቱን "ምንም ዓይነት ኃይል እንደማያደናቅፈው" ገልጿል። ኢትዮጵያ ትናንት ረቡዕ የግድቡ ግንባታ 80 በመቶ መድረሱን አስታውቃለች። የግድቡ ተደራዳሪዎች ቴክኒክ ቡድን አባል በለጠ ብርሃኑ (ዶ/ር) ለብሔራዊ ጣቢያው በሰጡት አስተያየት የግድቡ አጠቃላይ ግንባታ 80 በመቶ መድረሱን ገልጸዋል። የግድቡ የሲቪል ግንባታ 91.8፣ የኤሌክትሮ መካኒካል ግንባታው 54.5 በመቶ እንዲሁም የኃይድሮሊክ ስትራክቸር ሥራው ደግሞ 55.2 በመቶ መድረሱንም አስረድተዋል። በመሆኑም ግድቡን ለማጠናቀቅ የሚቀረው 20 በመቶ ግንባታ እንደሆነ ተናግረዋል። በሌላ በኩል የግብጽ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሽኩሪ በቀጣዩ ክረምት ኢትዮጵያ የምታከናውነው የውሃ ሙሌት አገራቸው ላይ የጎላ ተጽዕኖ እንደማይኖረው መናገራቸው የግብጽ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። ታላቁ የአስዋን ግድብ በቂ ውሃ በመያዙ የሕዳሴ ግድቡ በመጪው ክረምት ውሃ መያዙ ግብጽን አይጎዳም ሲሉ ነው ሳሚ ሽኩሪ የተናግሩት። የሕዳሴ ግድቡ በመጪው ክረምት ውሃ ከመያዝ በተጨማሪ በተያዘው ዓመት መገባደጃ ላይ ቅድመ ኃይል እንደሚያመነጭም በለጠ (ዶ/ር) ገልጸዋል። በተያዘው ዓመት የሕዳሴው ግድብ 13 ነጥብ 5 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ እንደሚይዘ መንግሥት የገለጸ ሲሆን ይህም ባለፈው ዓመት ካቆረው 4 ነጥብ 9 ቢሊዮን ኪዮቢክ ሜትር ውሃ ጋር በዓመቱ መጨረሻ የውሃውን መጠን ወደ 18 ቢሊዮን ከፍ ያደርገዋል። የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀ መንበርና የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዝዳንት ፊሊክስ ሴሸዴኪ በሕዳሴ ግድቡ ዙሪያ ሦስቱን አገራት ሊያግባባ የሚችል አዲስ ሃሳብ ማቅረባቸው ተስምቷል። የሦስቱን አገራት መሪዎች ተዘዋውረው ያነጋገሩት ፕሬዝዳንቱ ላመነጩት ሀሳብ ውጤታማነት የተባበሩት መንግሥታትና የአውሮፓ ሕብረት ድጋፋ እንደሚያደርጉ አል ሞኒተር የተባለ የዜና ተቋም ዘግቧል። ሀሳቡ በግድቡ ሙሊት ዙሪያ ኢትዮጵያ የጊዜ ሰሌዳዋንና የውሃውን መጠን መረጃ የምትሰጥበት ሆኖ አገራቱ ከሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት ላይ በአጭር ጊዜ ውስጥ ስምምነት ላይ እንዲደርሱ ያስችላል ነው የተባለው። በአባይ ወንዝ ላይ የተመሠረቱት ግብጽ እና ሱዳን የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ውሃ ሙሌትና ግንባታ በፊት በቅድሚያ ከስምምነት ላይ መደረስ እንደሚገባ በተደጋጋሚ አቋማቸውን ገልጸዋል። የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ከ10 ዓመታት በፊት ሲጀመር የጀመረው ይኸው የሕዳሴው ግድብ ድርድር ለበካታ ጊዜያት ያለስምምነት መቋረጡ በቀጠናው ስጋት ፈጥሯል።
የሕዳሴው ግድብ፡ ኢትዮጵያ ከሕዳሴው ግድብ ሙሌት የሚያደናቅፋት ኃይል እንደሌለ ገለጸች ኢትዮጵያ በመጭው የክረምት ወራት በታላቁ ሕዳሴ ግድብ የሙከራ ኃይል ማመንጨት እንደምትጀምር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። ኢትዮጵያ ይህን ያለችው በመጭው ክረምት ለሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት እየተዘጋጀች ባለችበት ወቅት ነው። ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ ከግድቡ ሙሌት እና ግንባታ ጋር ተያይዞ የአሠራር ሂደቱን "ምንም ዓይነት ኃይል እንደማያደናቅፈው" ገልጿል። ኢትዮጵያ ትናንት ረቡዕ የግድቡ ግንባታ 80 በመቶ መድረሱን አስታውቃለች። የግድቡ ተደራዳሪዎች ቴክኒክ ቡድን አባል በለጠ ብርሃኑ (ዶ/ር) ለብሔራዊ ጣቢያው በሰጡት አስተያየት የግድቡ አጠቃላይ ግንባታ 80 በመቶ መድረሱን ገልጸዋል። የግድቡ የሲቪል ግንባታ 91.8፣ የኤሌክትሮ መካኒካል ግንባታው 54.5 በመቶ እንዲሁም የኃይድሮሊክ ስትራክቸር ሥራው ደግሞ 55.2 በመቶ መድረሱንም አስረድተዋል። በመሆኑም ግድቡን ለማጠናቀቅ የሚቀረው 20 በመቶ ግንባታ እንደሆነ ተናግረዋል። በሌላ በኩል የግብጽ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሽኩሪ በቀጣዩ ክረምት ኢትዮጵያ የምታከናውነው የውሃ ሙሌት አገራቸው ላይ የጎላ ተጽዕኖ እንደማይኖረው መናገራቸው የግብጽ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። ታላቁ የአስዋን ግድብ በቂ ውሃ በመያዙ የሕዳሴ ግድቡ በመጪው ክረምት ውሃ መያዙ ግብጽን አይጎዳም ሲሉ ነው ሳሚ ሽኩሪ የተናግሩት። የሕዳሴ ግድቡ በመጪው ክረምት ውሃ ከመያዝ በተጨማሪ በተያዘው ዓመት መገባደጃ ላይ ቅድመ ኃይል እንደሚያመነጭም በለጠ (ዶ/ር) ገልጸዋል። በተያዘው ዓመት የሕዳሴው ግድብ 13 ነጥብ 5 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ እንደሚይዘ መንግሥት የገለጸ ሲሆን ይህም ባለፈው ዓመት ካቆረው 4 ነጥብ 9 ቢሊዮን ኪዮቢክ ሜትር ውሃ ጋር በዓመቱ መጨረሻ የውሃውን መጠን ወደ 18 ቢሊዮን ከፍ ያደርገዋል። የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀ መንበርና የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዝዳንት ፊሊክስ ሴሸዴኪ በሕዳሴ ግድቡ ዙሪያ ሦስቱን አገራት ሊያግባባ የሚችል አዲስ ሃሳብ ማቅረባቸው ተስምቷል። የሦስቱን አገራት መሪዎች ተዘዋውረው ያነጋገሩት ፕሬዝዳንቱ ላመነጩት ሀሳብ ውጤታማነት የተባበሩት መንግሥታትና የአውሮፓ ሕብረት ድጋፋ እንደሚያደርጉ አል ሞኒተር የተባለ የዜና ተቋም ዘግቧል። ሀሳቡ በግድቡ ሙሊት ዙሪያ ኢትዮጵያ የጊዜ ሰሌዳዋንና የውሃውን መጠን መረጃ የምትሰጥበት ሆኖ አገራቱ ከሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት ላይ በአጭር ጊዜ ውስጥ ስምምነት ላይ እንዲደርሱ ያስችላል ነው የተባለው። በአባይ ወንዝ ላይ የተመሠረቱት ግብጽ እና ሱዳን የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ውሃ ሙሌትና ግንባታ በፊት በቅድሚያ ከስምምነት ላይ መደረስ እንደሚገባ በተደጋጋሚ አቋማቸውን ገልጸዋል። የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ከ10 ዓመታት በፊት ሲጀመር የጀመረው ይኸው የሕዳሴው ግድብ ድርድር ለበካታ ጊዜያት ያለስምምነት መቋረጡ በቀጠናው ስጋት ፈጥሯል።
https://www.bbc.com/amharic/news-57167688
5sports
የእንግሊዝ ተጫዋቾች በድጋሚ የዘረኝነት ጥቃት ሰለባ ሆኑ
እንግሊዝ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ሀንጋሪን 4ለባዶ ባሸነፈችበት ጨዋታ ጥቁር ተጫዋቾች ላይ የደረሰውን የዘረኝነት ጥቃት እንደሚያወግዙ የቡድኑ አባላት አስታውቀዋል። ለማንችስተር ሲቲ የሚጫወተው ረሂም ስተርሊንግ እና ለጀርመኑ ዶርትመንድ የሚጫወተው ጁድ ቢሊንግሀም ናቸው የዘረንነት ጥቃት የደረሰባቸው። የሀንጋሪ ደጋፊዎች በአውሮፓ ዋንጫ ወቅት ያሳዩትን ተገቢ ያልሆነ ባህሪ ተከትሎ የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ብሄራዊ ቡድኑ በሜዳው የሚያደርጋቸውን ሶስት ጨዋታዎች ያለ ተመልካች በዝግ ስታዲየም እንዲያደርግ ውሳኔ አስተላልፎ ነበር። ነገር ግን ከእንግሊዝ ጋር በነበረው ጨዋታ 67 ሺ ተመልካቾችን ማስተናገድ በሚችለው የቡዳፔሽቱ ፑሽካሽ አሬና ውስጥ ጥቂት ተመልካቾች እንዲገቡ ተፈቅዶላቸው ነበር። ምከንያቱ ደግሞ ውድድሩን በበላይነት የሚቆጣጠረው ፊፋ ስለሆነ ነው። የእንግሊዝ ተጫዋቾች ገና ጨዋታው ሊጀመር ሲል ተንበርክከው ዘረኝነትን የሚቃወም መልእክት ሲያስተላልፉ የሀንጋሪ ደጋፊዎች በጩሀት ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ነበር። ምንም እንኳን የሀንጋሪ ተጫዋቾችና አሰልጣኙ ማርኮ ሪሲ ደጋፊዎቻቸው የአንግሊዝ ተጫዋቾች ማስተላለፍ የፈለጉትን መልእክት እንዲያከብሩ ቢጠይቁም የሚሰማቸው ግን አላገኙም። "ዘረኝነትን በመቃወም ተጫዋቾቹ ሲንበረከኩ ጀምሮ ተቃውሞ እንደሚገጥመን አውቀን ነበር። ነገር ግን ይህን ማድረግ ለእኛ ትክክለኛው ነገር ነው'' ብለዋል የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኙ ጋሬት ሳውዝጌት። የጨዋታው መጀመሪያ አጋማሽ ምንም ግብ ያልተቆጠረበት ሲሆን በሁለተኛው አጋማሽ ግን ራሂም ስተርሊንግ ለእንግሊዝ የመጀመሪያዋን ግብ ሲያስቆጥር የሀንጋሪ ደጋፊዎች በከፍተኛ ሁኔታ የፕላስቲክ ብርጭቆዎችን ጭምር ወርውረዋል። የማንችስተር ዩንይትዱ ተከላካይ ለእንግሊዝ ሶስተኛዋን ግብ ሲያስቆጥር ደግሞ የሀንጋሪ ደጋፊዎች ተቀጣጣይ ነገር ወደ ሜዳው ሲወረውሩ ተስተውለዋል። የእንግሊዙ አሰልጣኝ ጋሬት ሳውዝጌትም ቢሆን ከዚህ አላመለጠም ነበር። ከጨዋታው በኋላ አሰልጣኙ ለጋዜጠኞች መልስ በሚሰጥበት ወቅት የበረዶ ስባሪ ከተመልካቾች ተወርውሮበታል። "እንደ ቡድን ለየትኛው ጉዳይ አንድ ላይ መቆም እንዳለብን እናውቃለን። የተፈጠረው ነገር በየትኛውም መመዘኛ ተቀባይነት የለውም። የቡድናችን የደህንነት ኃላፊው ሁሉንም ተጨዋቾች አነጋግሮ መረጃ ሰብስቧል። ከዚህ በኋላ ማድረግ የሚገባንን ትክክለኛውን ነገር እናደርጋለን'' ብለዋል አሰልጣኙ። "አንዳንድ ተመልካቾች በተንቀሳቃሽ ስልክ ጭምር ተገቢ ያልሆነ ነገር ሲያደርጉ እና ሲናገሩ ተቀርጸዋል። በተገቢው መንገድ እንርምጃ እንደሚወሰድ ተስፋ አደርጋለው'' ሲሉም አክለዋል። የእንግሊዙ አምበል ሃሪ ኬን በበኩሉ ''ጓደኞቼን አነጋግራቸዋለሁ። በትክክል ሪፖርት እናደርገዋለን። በተገቢው መንገድ ጠንከር ያለ እርምጃ እንደሚወሰድ ተስፋ አደርጋለሁ'' ብሏል። የእንግሊዝ እግር ኳስ ማህበር ባወጣው መግለጫ ደግሞ "የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋቾች ቡዳፔሽት ውስጥ የዘረኝነት ሰለባ መሆናቸው በጣም አሳዝኖናል'' ብሏል። "ፊፋ ጉዳዩን በደንብ እንዲመረምረው እንጠይቃለን። ተጫዋቾቻችን እና የቡድ አባላት በሙሉ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል። እኛም ይህንኑ እናደርጋለን። ዘረኝነትንም እየተቃወምን እስከመጨረሻው ድረስ እንታገላለን።''
የእንግሊዝ ተጫዋቾች በድጋሚ የዘረኝነት ጥቃት ሰለባ ሆኑ እንግሊዝ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ሀንጋሪን 4ለባዶ ባሸነፈችበት ጨዋታ ጥቁር ተጫዋቾች ላይ የደረሰውን የዘረኝነት ጥቃት እንደሚያወግዙ የቡድኑ አባላት አስታውቀዋል። ለማንችስተር ሲቲ የሚጫወተው ረሂም ስተርሊንግ እና ለጀርመኑ ዶርትመንድ የሚጫወተው ጁድ ቢሊንግሀም ናቸው የዘረንነት ጥቃት የደረሰባቸው። የሀንጋሪ ደጋፊዎች በአውሮፓ ዋንጫ ወቅት ያሳዩትን ተገቢ ያልሆነ ባህሪ ተከትሎ የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ብሄራዊ ቡድኑ በሜዳው የሚያደርጋቸውን ሶስት ጨዋታዎች ያለ ተመልካች በዝግ ስታዲየም እንዲያደርግ ውሳኔ አስተላልፎ ነበር። ነገር ግን ከእንግሊዝ ጋር በነበረው ጨዋታ 67 ሺ ተመልካቾችን ማስተናገድ በሚችለው የቡዳፔሽቱ ፑሽካሽ አሬና ውስጥ ጥቂት ተመልካቾች እንዲገቡ ተፈቅዶላቸው ነበር። ምከንያቱ ደግሞ ውድድሩን በበላይነት የሚቆጣጠረው ፊፋ ስለሆነ ነው። የእንግሊዝ ተጫዋቾች ገና ጨዋታው ሊጀመር ሲል ተንበርክከው ዘረኝነትን የሚቃወም መልእክት ሲያስተላልፉ የሀንጋሪ ደጋፊዎች በጩሀት ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ነበር። ምንም እንኳን የሀንጋሪ ተጫዋቾችና አሰልጣኙ ማርኮ ሪሲ ደጋፊዎቻቸው የአንግሊዝ ተጫዋቾች ማስተላለፍ የፈለጉትን መልእክት እንዲያከብሩ ቢጠይቁም የሚሰማቸው ግን አላገኙም። "ዘረኝነትን በመቃወም ተጫዋቾቹ ሲንበረከኩ ጀምሮ ተቃውሞ እንደሚገጥመን አውቀን ነበር። ነገር ግን ይህን ማድረግ ለእኛ ትክክለኛው ነገር ነው'' ብለዋል የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኙ ጋሬት ሳውዝጌት። የጨዋታው መጀመሪያ አጋማሽ ምንም ግብ ያልተቆጠረበት ሲሆን በሁለተኛው አጋማሽ ግን ራሂም ስተርሊንግ ለእንግሊዝ የመጀመሪያዋን ግብ ሲያስቆጥር የሀንጋሪ ደጋፊዎች በከፍተኛ ሁኔታ የፕላስቲክ ብርጭቆዎችን ጭምር ወርውረዋል። የማንችስተር ዩንይትዱ ተከላካይ ለእንግሊዝ ሶስተኛዋን ግብ ሲያስቆጥር ደግሞ የሀንጋሪ ደጋፊዎች ተቀጣጣይ ነገር ወደ ሜዳው ሲወረውሩ ተስተውለዋል። የእንግሊዙ አሰልጣኝ ጋሬት ሳውዝጌትም ቢሆን ከዚህ አላመለጠም ነበር። ከጨዋታው በኋላ አሰልጣኙ ለጋዜጠኞች መልስ በሚሰጥበት ወቅት የበረዶ ስባሪ ከተመልካቾች ተወርውሮበታል። "እንደ ቡድን ለየትኛው ጉዳይ አንድ ላይ መቆም እንዳለብን እናውቃለን። የተፈጠረው ነገር በየትኛውም መመዘኛ ተቀባይነት የለውም። የቡድናችን የደህንነት ኃላፊው ሁሉንም ተጨዋቾች አነጋግሮ መረጃ ሰብስቧል። ከዚህ በኋላ ማድረግ የሚገባንን ትክክለኛውን ነገር እናደርጋለን'' ብለዋል አሰልጣኙ። "አንዳንድ ተመልካቾች በተንቀሳቃሽ ስልክ ጭምር ተገቢ ያልሆነ ነገር ሲያደርጉ እና ሲናገሩ ተቀርጸዋል። በተገቢው መንገድ እንርምጃ እንደሚወሰድ ተስፋ አደርጋለው'' ሲሉም አክለዋል። የእንግሊዙ አምበል ሃሪ ኬን በበኩሉ ''ጓደኞቼን አነጋግራቸዋለሁ። በትክክል ሪፖርት እናደርገዋለን። በተገቢው መንገድ ጠንከር ያለ እርምጃ እንደሚወሰድ ተስፋ አደርጋለሁ'' ብሏል። የእንግሊዝ እግር ኳስ ማህበር ባወጣው መግለጫ ደግሞ "የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋቾች ቡዳፔሽት ውስጥ የዘረኝነት ሰለባ መሆናቸው በጣም አሳዝኖናል'' ብሏል። "ፊፋ ጉዳዩን በደንብ እንዲመረምረው እንጠይቃለን። ተጫዋቾቻችን እና የቡድ አባላት በሙሉ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል። እኛም ይህንኑ እናደርጋለን። ዘረኝነትንም እየተቃወምን እስከመጨረሻው ድረስ እንታገላለን።''
https://www.bbc.com/amharic/news-58424831
0business
የዓለማችን ዋነኛ ቱጃር ጄፍ ቤዞስ ናሳን ሊከስ ነው
የጄፍ ቤዞስ የሕዋ ምርምር ተቋም ብሉ ኦሪጂን፤ ናሳ የተሰኘው የአሜሪካው የሕዋ ተቋምን ሊከስ እንደሆነ ተሰምቷል። ናሳ ሉናር ላንደር የተሰኘ ቴክኖሎጂ እንዲሠራለት ጨረታ አውጥቶ ለኢላን መስክ ድርጅት የ2.9 ቢሊዮን ብር ኮንትራት መስጠቱን ተከትሎ ነው ብሉ ኦሪጂን ክስ ሊመሠርት የተሰናዳው። የቤዞስ ብሉ ኦሪጂን በሁለቱ ድርጅቶች መካከል የተገባው ስምምነት "ችግሮች አሉበት"፤ አልፎም ፍትሃዊ አይደለም ሲል ወቅሷል። ናሳ ቅድሚያ አቅዶ የነበረው ሥራውን ለሁለት ድርጅቶች ለመስጠት ነበር። ነገር ግን ባለፈው ሚያዚያ ጨረታውን ካወጣ በኋላ በበጀት እጥረት ምክንያት ለአንድ ድርጅት መስጠቱን ተናግሮ ነበር። ምንም እንኳ ናሳ እስካሁን በክሱ ዙሪያ አስተያየት ባይሰጥም አንድ ብሔራዊ ተቋም ይደግፈዋል እየተባለ ነው። ባለፈው አርብ ክሱን የመሠረተው ብሉ ኦሪጂን ሁለት ተቋማት ቴክኖሎጂውን ለመገንባት ያስፈልጋሉ የሚል እምነት እንደነበረው በክስ መዝገቡ ላይ አስፍሯል። ናሳ ሊያሠራ ያሰበው ቴክኖሎጂ የጠፈር ተመራማሪዎችን ይዞ ወደ ጨረቃ የሚያቀና መንኩራኩርን ለማሳረፍ የሚውል ነው። የአሜሪካ ሕዋ ምርምር ተቋም ናሳ ይህን ቴክኖሎጂ በፈረንጆቹ 2024 ለመሞከር አቅዷል። ነገር ግን ብሉ ኦሪጂን በጨረታው ሂደት ናሳ "ሕጋዊ ያልሆነ ግምገማ አድርጎብናል" ሲል ከሷል። ናሳ ጨረታውን ማን እንዳሸነፈ ይፋ ባደረገበት ወቅት የተቋሙ 'ሂዩማን ኤክስፕሎሬሽን' አለቃ የሆኑት ካቲ ሉደርስ ናሳ ሁለት ኩባንያዎችን ከመቅጠር የተቆጠበው በበጀት እጥረት ምክንያት ነው ብለው ነበር። ናሳ ለፕሮጀክቱ ማስኬጃ 3.3 ቢሊዮን ዶላር ከመንግሥት ቢጠይቅም ኮንግረሱ 850 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ነው የፈቀደው። ስፔስኤክስ የተባለው የኢላን መስክ ተቋም የተሳኩ የኦርቢት [ምህዋር] ሚሽኖች ማካሄዱ እንዲመረጥ እንዳደረገው ናሳ ተናግሮ ነበር። ነገር ግን ስፔስኤክስ ከሌሎች ተቋማት ጋር ሲነፃፀር እጅግ አነስ ያለ ገንዘብ ማቅረቡ ጨረታውን እንዲያሸንፍ እንዳገዘው እየተነገረ ነው። ባለፈው ወር ጄፍ ቤዞስ ናሳ ያጠረውን 2 ቢሊዮን ዶላር ከፍሎ በፕሮጀክቱ መካተት እንደሚፈልግ ቢናገርም ሐሳቡ ተቀባይነት አላገኘም። የመንግሥት ተጠያቂነት ቢሮ የተሰኘው የአሜሪካ ፌዴራላዊ ተቋም ግን የብሉ ኦሪጂንና ዳይኔቲክ የተሰኘውን ሌላ የሕዋ ተቋም ክስ አጣጥሎታል። ናሳ እስከ ጥቅም 2/2015 ባለው ጊዜ ውስጥ ምላሽ መስጠት አለበት። የኢላን መስክ ስፔስኤክስ እካሁን ምንም አስተያየት አልሰጠም። ናሳ በአዲሱ ቴክኖሎጂ ታግዞ ከፈረንጆቹ 1972 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ጨረቃ ለመመለስ አቅዷል።
የዓለማችን ዋነኛ ቱጃር ጄፍ ቤዞስ ናሳን ሊከስ ነው የጄፍ ቤዞስ የሕዋ ምርምር ተቋም ብሉ ኦሪጂን፤ ናሳ የተሰኘው የአሜሪካው የሕዋ ተቋምን ሊከስ እንደሆነ ተሰምቷል። ናሳ ሉናር ላንደር የተሰኘ ቴክኖሎጂ እንዲሠራለት ጨረታ አውጥቶ ለኢላን መስክ ድርጅት የ2.9 ቢሊዮን ብር ኮንትራት መስጠቱን ተከትሎ ነው ብሉ ኦሪጂን ክስ ሊመሠርት የተሰናዳው። የቤዞስ ብሉ ኦሪጂን በሁለቱ ድርጅቶች መካከል የተገባው ስምምነት "ችግሮች አሉበት"፤ አልፎም ፍትሃዊ አይደለም ሲል ወቅሷል። ናሳ ቅድሚያ አቅዶ የነበረው ሥራውን ለሁለት ድርጅቶች ለመስጠት ነበር። ነገር ግን ባለፈው ሚያዚያ ጨረታውን ካወጣ በኋላ በበጀት እጥረት ምክንያት ለአንድ ድርጅት መስጠቱን ተናግሮ ነበር። ምንም እንኳ ናሳ እስካሁን በክሱ ዙሪያ አስተያየት ባይሰጥም አንድ ብሔራዊ ተቋም ይደግፈዋል እየተባለ ነው። ባለፈው አርብ ክሱን የመሠረተው ብሉ ኦሪጂን ሁለት ተቋማት ቴክኖሎጂውን ለመገንባት ያስፈልጋሉ የሚል እምነት እንደነበረው በክስ መዝገቡ ላይ አስፍሯል። ናሳ ሊያሠራ ያሰበው ቴክኖሎጂ የጠፈር ተመራማሪዎችን ይዞ ወደ ጨረቃ የሚያቀና መንኩራኩርን ለማሳረፍ የሚውል ነው። የአሜሪካ ሕዋ ምርምር ተቋም ናሳ ይህን ቴክኖሎጂ በፈረንጆቹ 2024 ለመሞከር አቅዷል። ነገር ግን ብሉ ኦሪጂን በጨረታው ሂደት ናሳ "ሕጋዊ ያልሆነ ግምገማ አድርጎብናል" ሲል ከሷል። ናሳ ጨረታውን ማን እንዳሸነፈ ይፋ ባደረገበት ወቅት የተቋሙ 'ሂዩማን ኤክስፕሎሬሽን' አለቃ የሆኑት ካቲ ሉደርስ ናሳ ሁለት ኩባንያዎችን ከመቅጠር የተቆጠበው በበጀት እጥረት ምክንያት ነው ብለው ነበር። ናሳ ለፕሮጀክቱ ማስኬጃ 3.3 ቢሊዮን ዶላር ከመንግሥት ቢጠይቅም ኮንግረሱ 850 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ነው የፈቀደው። ስፔስኤክስ የተባለው የኢላን መስክ ተቋም የተሳኩ የኦርቢት [ምህዋር] ሚሽኖች ማካሄዱ እንዲመረጥ እንዳደረገው ናሳ ተናግሮ ነበር። ነገር ግን ስፔስኤክስ ከሌሎች ተቋማት ጋር ሲነፃፀር እጅግ አነስ ያለ ገንዘብ ማቅረቡ ጨረታውን እንዲያሸንፍ እንዳገዘው እየተነገረ ነው። ባለፈው ወር ጄፍ ቤዞስ ናሳ ያጠረውን 2 ቢሊዮን ዶላር ከፍሎ በፕሮጀክቱ መካተት እንደሚፈልግ ቢናገርም ሐሳቡ ተቀባይነት አላገኘም። የመንግሥት ተጠያቂነት ቢሮ የተሰኘው የአሜሪካ ፌዴራላዊ ተቋም ግን የብሉ ኦሪጂንና ዳይኔቲክ የተሰኘውን ሌላ የሕዋ ተቋም ክስ አጣጥሎታል። ናሳ እስከ ጥቅም 2/2015 ባለው ጊዜ ውስጥ ምላሽ መስጠት አለበት። የኢላን መስክ ስፔስኤክስ እካሁን ምንም አስተያየት አልሰጠም። ናሳ በአዲሱ ቴክኖሎጂ ታግዞ ከፈረንጆቹ 1972 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ጨረቃ ለመመለስ አቅዷል።
https://www.bbc.com/amharic/news-58240626
2health
ኮሮረናቫይረስ፡ በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ጽኑ ህሙማን ቁጥር በከፍተኛ ፍጥነት አሻቀበ
የኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ውስጥ መገኘቱ ከታወቀ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የጽኑ ታማሚዎች ቁጥር ከአንድ ሺህ ማለፉን ተገለጸ። የጤና ሚኒስቴርና የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ሐሙስ ሚያዝያ 07/2013 ዓ.ም ባወጣው ዕለታዊ የወረርሽኙ መግለጫ ላይ እንዳመለከተው በበሽታው በጽኑ የታመሙ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 031 መድረሱን አመልክቷል። ኮቪድ-19 በኢትዮጵያ ውስጥ መገኘቱ ከታወቀ ከአንድ ዓመት በኋላ ባሉት ሦስት ወራት፤ ማለትም ባለፉት ጥር፣ የካቲትና መጋቢት ውስጥ በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ቀስ በቀስ እያሻቀበ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እየደረሰ መሆኑን የኢትዮጵያ የጤና ባለሥልጣናት በተደጋጋሚ ሲገልጹ ነበር። የወረርሽኙ በማኅበረሰብ ደረጃ መስፋፋቱ አሳሳቢ ከመሆኑ በተጨማሪ በወረርሽኙ ሳቢያ በጽኑ የሚታመሙና ለሞት የሚዳረጉ ሰዎችም ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል። ከወራት በፊት ምርመራ ከሚያደርጉ ሰዎች መካከል ቫይረሱ ይገኝባቸው የነበሩት ከአምስት መቶ ብዙም ሳይርቅ በመቶዎቹ የሚቆተሩ የነበረ ሲሆን አሁን ግን በየቀኑ ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች በበሽታው ተይዘው ይገኛሉ። ከዚህ በተጨማሪም በበሽታው ክፉኛ ታመው የጽኑ ህሙማን ክትትልና ድጋፍን የሚሹ ሰዎች ቁጥር ከአምስት መቶ በታች ሆኖ ለረጅም ጊዜ የቆየ ሲሆን፤ ባለፉት ሁለት ወራት ግን አሃዙ ከአምስት መቶ አልፎ አሁን ከአንድ ሺህ በላይ ደርሷል። በተመሳሳይ በየቀኑ በበሽታው ሳቢያ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በአስራዎቹ የሚቆጠር ሆኖ ለረጅም ጊዜ ቆይቶ አሁን ግን ከሃያዎቹ አስከ ሰላሳዎቹ የሚደርሱ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ እየተመዘገበ ነው። በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የሚያዙና የጽኑ ህሙማን ህክምናና ክትትል የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ የሰው ሰራሽ መተንፈሻ መሳሪያና የኦክስጂን እጥረት እያጋጠመ መሆኑ ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ገልጾ የነበረ ሲሆን ቁጥሩ በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩ ችግሩን የበለጠ ያባብሰዋል። ተቋሙ በአሁኑ ጊዜ በአገሪቱ ውስጥ በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከዕለት ዕለት በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ በመምጣቱ የባለሙያ ድጋፍና እንክብካቤ የሚሹ ሰዎች ቁጥር "የህክምና ማዕከላት ማስተናገድ ከሚችሉት አቅም በላይ" እየሆነ መምጣቱን ጨምሮ ገልጿል። በዚህም ሳቢያ በኮሮናቫይረስ በጽኑ ታምመው በህክምና ተቋማት ድጋፍ ለማግኘት ለሚመጡ ህሙማን አገልግሎት የሚውሉ "የሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መሳሪያ (ቬንትሌተር) እና የኦክስጅን እጥረት እያጋጠመ ነው" ሲል ገልጿል። የኮሮናቫይረስ የመተንፈሻ አካላትን በተለይም ሳንባን የሚያጠቃ ሲሆን በበሽታው ክፉኛ ለተጠቁ ጽኑ ህሙማን ሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መርጃ (ቬንትሌተር) እና ኦክስጂን ህይወታቸውን ለመታደግ ለሚደረገው ጥረት በእጅጉ አስፈላጊ ናቸው። በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ በጽኑ የታመሙ ሰዎችን ህይወት ለመታደግ በአሁኑ ወቅት በአገልግሎት ላይ የሚገኙት የሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መርጃ ቬንትሌተሮች ቁጥር ከ500 ብዙም የበለጡ እንዳልሆኑ ሲገለጽ ቆይቷል። በየዕለቱ በበወረርሽኙ በጽኑ ታመው ድጋፍ የሚሹት ህሙማን ቁጥር በመቶዎች ከመቆጠር አልፎ በአሁኑ ጊዜ ከአንድ ሺህ በላይ መድረሱ የጤና ተቋማት ለህሙማኑ እንክብካቤና ድጋፍ ለመስጠት ችግር እየገጠማቸው መሆኑ ቀደም ሲል መገለጹ ይታወሳል። በተለይም በወረርሽኙ በጽኑ ታመው የቬንትሌተርና የኦክስጂን ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ህሙማን ቁጥር እየጨመረ በመሆኑ የነፍስ አድን አገልግሎቱን መስጠት ከማይቻልበት ደረጃ ላይ ከደረሰ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ሊያሻቅብ ይችላል። በአሁኑ ወቅት በመላው አገሪቱ በየዕለቱ የሚመዘገበው በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን የገለጸው ኢንስቲትዩቱ፤ ከዚሁ ጋር ተያይዞም በወረርሽኙ ሳቢያ የጽኑ ህሙማን የህክምና አገልግሎት የሚፈልጉ ህሙማንና ህይወታቸውን የሚያጡ ሰዎች ቁጥር "አስደንጋጭ በሆነ ሁኔታ እየጨመረ ይገኛል" ይገኛል ብሏል። ሐሙስ ዕለት በወጣው የበሽታው ዕለታዊ ሪፖርት መሠረትም 33 ሰዎች በኮቪድ-19 በሽታ ምክንያት መሞታቸው ተገልጿል። በዕለቱ 8 ሺህ 878 ሰዎች ምርመራ ተደርጎላቸው 2 ሺህ 149ኙ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን፤ ቀደም ሲል በበሽታው ተይዘው ከነበሩት መካከል ደግሞ 1 ሺህ 288 አገግመዋል። አስካሁን በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ውስጥ 236 ሺህ 554 ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 3 ሺህ 285 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ 175 ሺህ 879 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።
ኮሮረናቫይረስ፡ በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ጽኑ ህሙማን ቁጥር በከፍተኛ ፍጥነት አሻቀበ የኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ውስጥ መገኘቱ ከታወቀ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የጽኑ ታማሚዎች ቁጥር ከአንድ ሺህ ማለፉን ተገለጸ። የጤና ሚኒስቴርና የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ሐሙስ ሚያዝያ 07/2013 ዓ.ም ባወጣው ዕለታዊ የወረርሽኙ መግለጫ ላይ እንዳመለከተው በበሽታው በጽኑ የታመሙ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 031 መድረሱን አመልክቷል። ኮቪድ-19 በኢትዮጵያ ውስጥ መገኘቱ ከታወቀ ከአንድ ዓመት በኋላ ባሉት ሦስት ወራት፤ ማለትም ባለፉት ጥር፣ የካቲትና መጋቢት ውስጥ በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ቀስ በቀስ እያሻቀበ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እየደረሰ መሆኑን የኢትዮጵያ የጤና ባለሥልጣናት በተደጋጋሚ ሲገልጹ ነበር። የወረርሽኙ በማኅበረሰብ ደረጃ መስፋፋቱ አሳሳቢ ከመሆኑ በተጨማሪ በወረርሽኙ ሳቢያ በጽኑ የሚታመሙና ለሞት የሚዳረጉ ሰዎችም ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል። ከወራት በፊት ምርመራ ከሚያደርጉ ሰዎች መካከል ቫይረሱ ይገኝባቸው የነበሩት ከአምስት መቶ ብዙም ሳይርቅ በመቶዎቹ የሚቆተሩ የነበረ ሲሆን አሁን ግን በየቀኑ ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች በበሽታው ተይዘው ይገኛሉ። ከዚህ በተጨማሪም በበሽታው ክፉኛ ታመው የጽኑ ህሙማን ክትትልና ድጋፍን የሚሹ ሰዎች ቁጥር ከአምስት መቶ በታች ሆኖ ለረጅም ጊዜ የቆየ ሲሆን፤ ባለፉት ሁለት ወራት ግን አሃዙ ከአምስት መቶ አልፎ አሁን ከአንድ ሺህ በላይ ደርሷል። በተመሳሳይ በየቀኑ በበሽታው ሳቢያ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በአስራዎቹ የሚቆጠር ሆኖ ለረጅም ጊዜ ቆይቶ አሁን ግን ከሃያዎቹ አስከ ሰላሳዎቹ የሚደርሱ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ እየተመዘገበ ነው። በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የሚያዙና የጽኑ ህሙማን ህክምናና ክትትል የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ የሰው ሰራሽ መተንፈሻ መሳሪያና የኦክስጂን እጥረት እያጋጠመ መሆኑ ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ገልጾ የነበረ ሲሆን ቁጥሩ በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩ ችግሩን የበለጠ ያባብሰዋል። ተቋሙ በአሁኑ ጊዜ በአገሪቱ ውስጥ በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከዕለት ዕለት በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ በመምጣቱ የባለሙያ ድጋፍና እንክብካቤ የሚሹ ሰዎች ቁጥር "የህክምና ማዕከላት ማስተናገድ ከሚችሉት አቅም በላይ" እየሆነ መምጣቱን ጨምሮ ገልጿል። በዚህም ሳቢያ በኮሮናቫይረስ በጽኑ ታምመው በህክምና ተቋማት ድጋፍ ለማግኘት ለሚመጡ ህሙማን አገልግሎት የሚውሉ "የሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መሳሪያ (ቬንትሌተር) እና የኦክስጅን እጥረት እያጋጠመ ነው" ሲል ገልጿል። የኮሮናቫይረስ የመተንፈሻ አካላትን በተለይም ሳንባን የሚያጠቃ ሲሆን በበሽታው ክፉኛ ለተጠቁ ጽኑ ህሙማን ሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መርጃ (ቬንትሌተር) እና ኦክስጂን ህይወታቸውን ለመታደግ ለሚደረገው ጥረት በእጅጉ አስፈላጊ ናቸው። በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ በጽኑ የታመሙ ሰዎችን ህይወት ለመታደግ በአሁኑ ወቅት በአገልግሎት ላይ የሚገኙት የሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መርጃ ቬንትሌተሮች ቁጥር ከ500 ብዙም የበለጡ እንዳልሆኑ ሲገለጽ ቆይቷል። በየዕለቱ በበወረርሽኙ በጽኑ ታመው ድጋፍ የሚሹት ህሙማን ቁጥር በመቶዎች ከመቆጠር አልፎ በአሁኑ ጊዜ ከአንድ ሺህ በላይ መድረሱ የጤና ተቋማት ለህሙማኑ እንክብካቤና ድጋፍ ለመስጠት ችግር እየገጠማቸው መሆኑ ቀደም ሲል መገለጹ ይታወሳል። በተለይም በወረርሽኙ በጽኑ ታመው የቬንትሌተርና የኦክስጂን ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ህሙማን ቁጥር እየጨመረ በመሆኑ የነፍስ አድን አገልግሎቱን መስጠት ከማይቻልበት ደረጃ ላይ ከደረሰ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ሊያሻቅብ ይችላል። በአሁኑ ወቅት በመላው አገሪቱ በየዕለቱ የሚመዘገበው በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን የገለጸው ኢንስቲትዩቱ፤ ከዚሁ ጋር ተያይዞም በወረርሽኙ ሳቢያ የጽኑ ህሙማን የህክምና አገልግሎት የሚፈልጉ ህሙማንና ህይወታቸውን የሚያጡ ሰዎች ቁጥር "አስደንጋጭ በሆነ ሁኔታ እየጨመረ ይገኛል" ይገኛል ብሏል። ሐሙስ ዕለት በወጣው የበሽታው ዕለታዊ ሪፖርት መሠረትም 33 ሰዎች በኮቪድ-19 በሽታ ምክንያት መሞታቸው ተገልጿል። በዕለቱ 8 ሺህ 878 ሰዎች ምርመራ ተደርጎላቸው 2 ሺህ 149ኙ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን፤ ቀደም ሲል በበሽታው ተይዘው ከነበሩት መካከል ደግሞ 1 ሺህ 288 አገግመዋል። አስካሁን በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ውስጥ 236 ሺህ 554 ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 3 ሺህ 285 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ 175 ሺህ 879 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-56755324
3politics
የአሜሪካ የፌደራል ወንጀል ምርመራ ከትራምፕ መኖሪያ ቤት ጥብቅ ምስጢራዊ ሰነዶችን ወሰደ
የአሜሪካ የፌደራል ወንጀል ምርመራ (ኤፍ.ቢ.አይ) በፍሎሪዳ  በሚገኘው የቀድሞው የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ መኖሪያ ቤት በተካሄደ ብርበራ ጥብቅ ምስጢራዊ ሰነዶች መውሰዳቸውን የፍተሻ ማዘዣው አመለከተ። በዚህም የኤፍቢአይ ወኪሎች በአገሪቱ ብሔራዊ ደኅንነት ላይ አደገኛ ጉዳት ሊያደርስ የሚችል ቲ.ኤስ/ ኤስ.ሲ.አይ በሚል ስያሜ የተለዩ እና ምልክት የተደረገባቸው አስራ አንድ ሰነዶችን መያዝ ችለዋል። በአሜሪካ ታሪክ በወንጀል ምርመራ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ቤት ብርበራ ሲካሄድ ይህ የትራምፕ ቤት የመጀመሪያው ነው። የሰነዶቹ ዝርዝር አርብ ለሕዝብ ይፋ የሆነው ዳኛው፣ ማር አ ላጎ የሚገኘውን የትራምፕ መኖሪያ ቤት ለመፈተሽ የሚያስችል የማዘዣ ዝርዝር ያካተተ ባለ ሰባት ገጽ ሰነድ ይፋ ካደረጉ በኋላ ነው። ሰነዱ እንደሚለው የፎቶግራፍ አልበም፣ በእጅ የተጻፈ ማስታወሻ፣ ያልተገለጸ፤ ነገር ግን ስለ "የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት" መረጃ እና የረጅም ጊዜ የትራምፕ አጋር የሆነውን ሮጀር ስቶንን ወክለው የተጻፈ የምህረት ደብዳቤን ጨምሮ ከ20 ሳጥን በላይ ሰኞ ዕለት በወንጀል መርማሪዎቹ ተወስደዋል። ከዚህ በተጨማሪም ከፍተኛ ምስጢራዊ ሰነዶችን የያዙ አራት ፋይሎች የተገኙ ሲሆን፣ በፋይሎቹ ውስጥ ሦስት ምስጢራዊ ሰነዶች እና ምስጢራቸው የተጠበቀ ቁሳቁሶች ተገኝተዋል። ማዘዣው እንዳመለከተው የኤፍቢአይ ወኪሎች፣ አደገኛ ሊሆኑ የሚችሉ የብሔራዊ ደኅንነት መረጃዎችን መያዝ ወይም ማስተላለፍ ሕገ ወጥ የሚያደርገውን የሕግ ጥሰትን እየተመለከቱ ነው። በምስጢራዊነታቸው ተለይተው የተቀመጡ ሰነዶች እና ቁሳቁሶችን መውሰድ በሕግ የተከለከለ ነው። ትራምፕ በሥልጣን ላይ በነበሩበት ጊዜም በዚህ ወንጀል የሚያስቀጣውን ቅጣት ጨምረውታል። ድርጊቱ አሁን ላይ እስከ አምስት ዓመት በሚደርስ እስር ሊያስቀጣ ይችላል። የማዘዣው ማስታወሻ እንደሚለው ማር አ ላጎ የተካሄደው ፍተሻ በትራምፕ መኖሪያ ቤት ብቻ የተገደበ አልነበረም። ‘45 ኦፊስ’ እና የሰነዶች ማከማቻ ክፍሎችን ያካተተ ሲሆን፤ ነገር ግን ትራምፕ እና ባልደረቦቻቸው ይጠቀሙበት የነበረውን የግል የእንግዳ ክፍሎችን አይጨምርም። የአሜሪካ ፍትሕ መሥሪያ ቤት  ጉዳዩ ሐሙስ ዕለት ለሕዝብ ይፋ እንዲደረግ ፍርድ ቤቱን ጠይቋል። ጉዳዩ በምርመራ ላይ ባለበት ወቅት ይፋ እንዲደርግ መጠየቁም ያልተለመደ ነው ተብሏል። የትራምፕ ጽህፈት ቤት በበኩሉ አርብ ምሽት ላይ ባወጣው መግለጫ፣ የቀድሞው ፕሬዝዳንት በሥልጣን ዘመናቸው፣ ሥልጣናቸውን ተጠቅመው ምስጢራዊ የነበሩ ሰነዶችን ምስጢራዊነታቸው እንዲያበቃ (Declassify) አድርገዋል ብሏል። “ሰነዶቹን ከቢሯቸው ወደ መኖሪያ ቤታቸው መወሰዳቸው ለዚህ ማሳያ ነው” ሲልም መግለጫው አክሏል። "ሰነዶቹን የመለየትና የመከፋፈል ሥልጣኑም የፕሬዝዳንቱ ብቻ ነው” ብሏል መግለጫው። የሕግ ባለሙያዎች ለአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን እነዚህ ክርክሮች በፍርድ ቤት ይቀጥሉ አይቀጥሉ ግልጽ አይደለም ብለዋል። ቀደም ብሎ በፍትሕ መሥሪያ ቤት ሲያገለግሉ የነበሩት የሕግ ባለሙያ ቶም ዱፕሪ፣ “ፕሬዝዳንቶች ሰነዶችን መለየት ይችላሉ፤ ነገር ግን የአሠራር ሂደቶችን መከተል አለባቸው” ይላሉ። “ፎርሞችን መሙላት አለባቸው። ፈቃድ መስጠት አለባቸው። ዝም ብሎ እነዚህ ሰነዶች ተለይተዋል ማለት አይቻልም። ምክንያቱም ሂደቶችን መከተል አለባቸው። ትራምፕ ይህን ስለመከተላቸው ግልጽ አይደለም” ብለዋል። የትራምፕ ቃል አቀባይ ታይለር ቡዶዊች፣ የጆ ባይደንን አስተዳደር በዋና የፖለቲካ ተቀናቃኞቻቸው ላይ ሐሰተኛ መረጃዎችን በማውጣት ይከሳሉ። የትራምፕ አጋሮችም ትራምፕ በ2024 ምርጫ ለመወዳደር እያሰቡ በመሆናቸው በቤታቸው ላይ የተፈጸመው ፍተሻ ፖለቲካዊ ነው ሲሉ አውግዘውታል። የሕግ አስፈጻሚ ወኪሎችም የኤፍቢአይ ብርበራን ተከትሎ በመንግሥት ባለሥልጣናት ላይ በኦንላይን የሚደርሰውን ማስፈራሪያ እየተከታተሉ መሆኑ ተገልጿል። ማዘዣውን በግል ያጸደቀው የአሜሪካ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሜሪክ ጋርላንድ፣ ሐሙስ ዕለት “ቁርጠኛ እና አገር ወዳድ የሕዝብ አገልጋዮች” ሲሉ የፌደራል የወንጀል ምርመራ ወኪሎችን ተከላክለዋል። “ታማኝነታቸው ፍትሐዊ ባልሆነ መንገድ ሲጠቃ ዝም ብዬም አልመለከትም” ሲሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
የአሜሪካ የፌደራል ወንጀል ምርመራ ከትራምፕ መኖሪያ ቤት ጥብቅ ምስጢራዊ ሰነዶችን ወሰደ የአሜሪካ የፌደራል ወንጀል ምርመራ (ኤፍ.ቢ.አይ) በፍሎሪዳ  በሚገኘው የቀድሞው የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ መኖሪያ ቤት በተካሄደ ብርበራ ጥብቅ ምስጢራዊ ሰነዶች መውሰዳቸውን የፍተሻ ማዘዣው አመለከተ። በዚህም የኤፍቢአይ ወኪሎች በአገሪቱ ብሔራዊ ደኅንነት ላይ አደገኛ ጉዳት ሊያደርስ የሚችል ቲ.ኤስ/ ኤስ.ሲ.አይ በሚል ስያሜ የተለዩ እና ምልክት የተደረገባቸው አስራ አንድ ሰነዶችን መያዝ ችለዋል። በአሜሪካ ታሪክ በወንጀል ምርመራ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ቤት ብርበራ ሲካሄድ ይህ የትራምፕ ቤት የመጀመሪያው ነው። የሰነዶቹ ዝርዝር አርብ ለሕዝብ ይፋ የሆነው ዳኛው፣ ማር አ ላጎ የሚገኘውን የትራምፕ መኖሪያ ቤት ለመፈተሽ የሚያስችል የማዘዣ ዝርዝር ያካተተ ባለ ሰባት ገጽ ሰነድ ይፋ ካደረጉ በኋላ ነው። ሰነዱ እንደሚለው የፎቶግራፍ አልበም፣ በእጅ የተጻፈ ማስታወሻ፣ ያልተገለጸ፤ ነገር ግን ስለ "የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት" መረጃ እና የረጅም ጊዜ የትራምፕ አጋር የሆነውን ሮጀር ስቶንን ወክለው የተጻፈ የምህረት ደብዳቤን ጨምሮ ከ20 ሳጥን በላይ ሰኞ ዕለት በወንጀል መርማሪዎቹ ተወስደዋል። ከዚህ በተጨማሪም ከፍተኛ ምስጢራዊ ሰነዶችን የያዙ አራት ፋይሎች የተገኙ ሲሆን፣ በፋይሎቹ ውስጥ ሦስት ምስጢራዊ ሰነዶች እና ምስጢራቸው የተጠበቀ ቁሳቁሶች ተገኝተዋል። ማዘዣው እንዳመለከተው የኤፍቢአይ ወኪሎች፣ አደገኛ ሊሆኑ የሚችሉ የብሔራዊ ደኅንነት መረጃዎችን መያዝ ወይም ማስተላለፍ ሕገ ወጥ የሚያደርገውን የሕግ ጥሰትን እየተመለከቱ ነው። በምስጢራዊነታቸው ተለይተው የተቀመጡ ሰነዶች እና ቁሳቁሶችን መውሰድ በሕግ የተከለከለ ነው። ትራምፕ በሥልጣን ላይ በነበሩበት ጊዜም በዚህ ወንጀል የሚያስቀጣውን ቅጣት ጨምረውታል። ድርጊቱ አሁን ላይ እስከ አምስት ዓመት በሚደርስ እስር ሊያስቀጣ ይችላል። የማዘዣው ማስታወሻ እንደሚለው ማር አ ላጎ የተካሄደው ፍተሻ በትራምፕ መኖሪያ ቤት ብቻ የተገደበ አልነበረም። ‘45 ኦፊስ’ እና የሰነዶች ማከማቻ ክፍሎችን ያካተተ ሲሆን፤ ነገር ግን ትራምፕ እና ባልደረቦቻቸው ይጠቀሙበት የነበረውን የግል የእንግዳ ክፍሎችን አይጨምርም። የአሜሪካ ፍትሕ መሥሪያ ቤት  ጉዳዩ ሐሙስ ዕለት ለሕዝብ ይፋ እንዲደረግ ፍርድ ቤቱን ጠይቋል። ጉዳዩ በምርመራ ላይ ባለበት ወቅት ይፋ እንዲደርግ መጠየቁም ያልተለመደ ነው ተብሏል። የትራምፕ ጽህፈት ቤት በበኩሉ አርብ ምሽት ላይ ባወጣው መግለጫ፣ የቀድሞው ፕሬዝዳንት በሥልጣን ዘመናቸው፣ ሥልጣናቸውን ተጠቅመው ምስጢራዊ የነበሩ ሰነዶችን ምስጢራዊነታቸው እንዲያበቃ (Declassify) አድርገዋል ብሏል። “ሰነዶቹን ከቢሯቸው ወደ መኖሪያ ቤታቸው መወሰዳቸው ለዚህ ማሳያ ነው” ሲልም መግለጫው አክሏል። "ሰነዶቹን የመለየትና የመከፋፈል ሥልጣኑም የፕሬዝዳንቱ ብቻ ነው” ብሏል መግለጫው። የሕግ ባለሙያዎች ለአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን እነዚህ ክርክሮች በፍርድ ቤት ይቀጥሉ አይቀጥሉ ግልጽ አይደለም ብለዋል። ቀደም ብሎ በፍትሕ መሥሪያ ቤት ሲያገለግሉ የነበሩት የሕግ ባለሙያ ቶም ዱፕሪ፣ “ፕሬዝዳንቶች ሰነዶችን መለየት ይችላሉ፤ ነገር ግን የአሠራር ሂደቶችን መከተል አለባቸው” ይላሉ። “ፎርሞችን መሙላት አለባቸው። ፈቃድ መስጠት አለባቸው። ዝም ብሎ እነዚህ ሰነዶች ተለይተዋል ማለት አይቻልም። ምክንያቱም ሂደቶችን መከተል አለባቸው። ትራምፕ ይህን ስለመከተላቸው ግልጽ አይደለም” ብለዋል። የትራምፕ ቃል አቀባይ ታይለር ቡዶዊች፣ የጆ ባይደንን አስተዳደር በዋና የፖለቲካ ተቀናቃኞቻቸው ላይ ሐሰተኛ መረጃዎችን በማውጣት ይከሳሉ። የትራምፕ አጋሮችም ትራምፕ በ2024 ምርጫ ለመወዳደር እያሰቡ በመሆናቸው በቤታቸው ላይ የተፈጸመው ፍተሻ ፖለቲካዊ ነው ሲሉ አውግዘውታል። የሕግ አስፈጻሚ ወኪሎችም የኤፍቢአይ ብርበራን ተከትሎ በመንግሥት ባለሥልጣናት ላይ በኦንላይን የሚደርሰውን ማስፈራሪያ እየተከታተሉ መሆኑ ተገልጿል። ማዘዣውን በግል ያጸደቀው የአሜሪካ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሜሪክ ጋርላንድ፣ ሐሙስ ዕለት “ቁርጠኛ እና አገር ወዳድ የሕዝብ አገልጋዮች” ሲሉ የፌደራል የወንጀል ምርመራ ወኪሎችን ተከላክለዋል። “ታማኝነታቸው ፍትሐዊ ባልሆነ መንገድ ሲጠቃ ዝም ብዬም አልመለከትም” ሲሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c04k0e03905o
3politics
በኦሮሚያ ክልል አደአ በርጋ ወረዳ በርካታ ሰዎች በኦሮሚያ ልዩ ኃይል አባላት መገደላቸው ተነገረ
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን አደአ በርጋ ወረዳ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ፖሊስ አባላት በርካታ ንጹሃን ሰዎችን መግደላቸውን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናገሩ። ዛሬ ከሰዓት ቢቢሲ ያነጋገራቸው የኦሮሚያ ክልል ፀጥታ ጉዳዮች ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ በበኩላቸው፣ "ይህ ውሸት ነው" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። እንደ ነዋሪዎች ከሆነ የኦሮሚያ ልዩ ፖሊስ አባላት ትናንት አርብ ሚያዚያ 21/2014 ዓ.ም. በነዋሪዎች ላይ ግድያ የፈጸሙት ከአንድ ቀን በፊት ታጣቂዎች የኦሮሚያ ልዩ ኃይል አባላትን ከገደሉ በኋላ ነው። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ሁለት የአካባቢው ነዋሪዎች ትናንት አርብ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ቢያንስ 21 ይሆናሉ ሲሉ ሌላኛው ነዋሪ ደግሞ የሟቾች ቁጥር ወደ 40 ይጠጋል ብለዋል። በአካባቢው በስፋት የሚንቀሳቀሰው እና ከመንግሥት ኃይሎች ጋር ጦርነት ውስጥ የሚገኘው እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ብሎ የሚጠራው ቡድን ትናንት በመንግሥት ኃይሎች የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 46 መሆኑን ጠቅሶ ከተገደሉት መካከል የ15 ሰዎችን ስም ዝርዝር አውጥቷል። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) በበኩሉ ዛሬ ባወጣው መግለጫ በአደአ በርጋ ወረዳ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች 15 ንጹሃን ዜጎችን ገድለዋል ብሏል። ከተገደሉት ንጹሃን ዜጎች መካከል የ70 ዓመት አዛውንት እንደሚገኙበት መግለጫው ጠቁሞ "የታጠቁት ኃይሎች ገንዘብ፣ ጌጣጌጥ እና ሌላም ቁሳቁስ እየዘረፉ እንዲሁም የሰዎችን መኖሪያ እያቃጠሉም ነው" ሲል አክሏል። የአካባቢው ነዋሪዎች በአሁን ወቅት ሕይወታቸውን ለማዳን ወደ ጫካ እየሸሹ እንደሆነም የኦነግ መግለጫ ያመለክታል። ሐሙስ እና አርብ ያጋጠመው ምንድን ነው? ሐሙስ ሚያዚያ 20/2014 ዓ.ም. የኦሮሚያ ልዩ ኃይል አባላት በወረዳው በሚገኝ ገጠራማ ስፍራ በፒክ አፕ መኪና ተጭነው ሲጓዙ ድንገተኛ ጥቃት በታጣቂዎች ተፈጽሞባቸዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች በዚህ ጥቃት ከ10 የማያንሱ የልዩ ኃይል ፖሊስ አባላት መገደላቸውን እና ቢያንስ 3 ሰዎች ደግሞ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተናግረዋል። በልዩ ኃይል አባላቱ ላይ የተሰነዘረውን ጥቃት ተከትሎ በቀጣይ ቀን ማለትም አርብ ሚያዚያ 21/2014 ዓ.ም. በወረዳው በሚገኙ ኢንጪኒ፣ ሙገር፣ ሬጂ እና ጂማታ ተብለው በሚጠሩ አካባቢዎች ከፍተኛ ውጥረት ነግሶ ነበር ይላሉ ነዋሪዎች። "በጂማታ ቤት ለቤት እየዞሩ ፍተሻ እያደረጉ ሰዎችን መግደል ጀመሩ" ሲሉ አንድ ነዋሪ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ሬሳ በቤት ውስጥ፣ በየጓሮ፣ ከዋናው መንገድ ዳር ሁሉ ይታይ ነበር" ሲሉ በጂማታ ከተማ የነበሩ እና አሁን በሆለታ ከተማ የሚገኙ ነዋሪ ነግረውናል። የፖሊስ አባላቱ በነዋሪዎች ቤት ላይ ብርበራ ሲፈጽሙ እና ሲገድሉ፤ 'ሸኔን የምትደብቁት እናንተ ናችሁ' ሲሉ እንደነበረ በቦታው ካለ ነዋሪ እንደሰሙ ቢቢሲ ያነጋገራቸው ነዋሪ ይናገራሉ። የኢንጪኒ ከተማ ነዋሪ ደግሞ ከሰዎች መኖሪያ ቤት የወጡ ታጣቂዎች በልዩ ኃይል አባላቱ ላይ ጥቃት ካደረሱ በኋላ የፖሊስ አባላቱ በቀጣይ ቀን በነዋሪዎች ላይ ግድያ መፈጸማቸውን ተናግረዋል። ነዋሪው ትናንት አርብ ምሽት በከተማዋ በሚገኝ ሆስፒታል "ብዙ ግርግር ነበር" ብለዋል። "ሁሉም ስለሚፈራ ወደዛ ሄደን ምን እየተካሄደ እንደሆነ አልጠየቅንም" ሲሉ ተናግረዋል። ከግድያው በተጨማሪ በጂማታ በርካታ መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸውን ከነዋሪዎች መረዳት ተችሏል። የኦሮሚያ ክልል ፀጥታ ጉዳዮች ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ፣ "ይህ ውሸት ነው። እንደዚህ ዓይነት ሪፖርት አልደረሰንም" ሲሉ ለቢቢሲ ምላሽ ሰጥተዋል። ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ሌሎች ጥያቄዎች ብናቀርብም "ሐሰት ነው" ከሚለው በዘለለ የገለጹልን ነገር የለም። ስለ ጉዳዮ ማብራሪያ ለማግኘት ወደ መንግሥት ኮምንኬሸን አገልግሎት ዶ/ር ለገሰ ቱሉ እንዲሁም ሰላማዊት ካሳ ብንደውልም ስልክ ስላልተነሳ ምላሽ ማካተት አልቻልንም። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ስለተፈጠረው ነገር መረጃ እንዳለው ለመጠየቅ ወደ ሕዝብ ግንኙት ባልደረባዎች ብንደውልም አልተሳካም። ከሰሞኑ መንግሥት 'ሸኔ' ብሎ የሚጠራውን ታጣቂ ቡድን "የማጽዳት ዘመቻ" ጀምሬያለሁ ካለ በኋላ በሁለቱ አካላት መካከል የሚደረገው ውጊያ ተጠናክሮ ቀጥሏል። እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ብሎ የሚጠራው እና የፌደራሉ መንግሥት አሸባሪ ሲል የፈረጀውን 'ሸኔ' ቡድን ለማጥፋት ለአንድ ወር የሚዘልቅ የተጠናከረ ወታደራዊ ዘመቻ መጀመሩን የክልሉ መንግሥት ከጥቂት ሳምንታት በፊት አስታውቆ ነበር። ይህን ተከትሎ ባለፉት ሳምንታት በተለይ በምዕራብ ሸዋ ዞን የፌደራሉ መንግሥት በሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) የታዘገ ጥቃት ሲያካሂድ መቆየቱ ተዘግቧል። ክልሉ ከቀናት በፊት "ሸኔን የማጽዳት" ዘመቻው ተጠናክሮ መቀጠሉን እና ይህ ወታደራዊ ዘመቻ የተፈለገለትን ዒላማ እያሳካ እንደሆነ በመግለጫ አውጥቶ ነበር። ይሁን እንጂ የታጣቂ ቡድኑ ቃል አቀባይ ኦዳ ተርቢ፤ "ወታደሮቻችን እየተዋጉ ነው። ድል እንጂ ሽንፈት አልገጠመንም። . . . ከ400 በላይ ወታደር ማርከናል። የተለያዩ ጦር መሣሪያዎችን ማርከናል" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
በኦሮሚያ ክልል አደአ በርጋ ወረዳ በርካታ ሰዎች በኦሮሚያ ልዩ ኃይል አባላት መገደላቸው ተነገረ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን አደአ በርጋ ወረዳ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ፖሊስ አባላት በርካታ ንጹሃን ሰዎችን መግደላቸውን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናገሩ። ዛሬ ከሰዓት ቢቢሲ ያነጋገራቸው የኦሮሚያ ክልል ፀጥታ ጉዳዮች ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ በበኩላቸው፣ "ይህ ውሸት ነው" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። እንደ ነዋሪዎች ከሆነ የኦሮሚያ ልዩ ፖሊስ አባላት ትናንት አርብ ሚያዚያ 21/2014 ዓ.ም. በነዋሪዎች ላይ ግድያ የፈጸሙት ከአንድ ቀን በፊት ታጣቂዎች የኦሮሚያ ልዩ ኃይል አባላትን ከገደሉ በኋላ ነው። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ሁለት የአካባቢው ነዋሪዎች ትናንት አርብ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ቢያንስ 21 ይሆናሉ ሲሉ ሌላኛው ነዋሪ ደግሞ የሟቾች ቁጥር ወደ 40 ይጠጋል ብለዋል። በአካባቢው በስፋት የሚንቀሳቀሰው እና ከመንግሥት ኃይሎች ጋር ጦርነት ውስጥ የሚገኘው እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ብሎ የሚጠራው ቡድን ትናንት በመንግሥት ኃይሎች የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 46 መሆኑን ጠቅሶ ከተገደሉት መካከል የ15 ሰዎችን ስም ዝርዝር አውጥቷል። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) በበኩሉ ዛሬ ባወጣው መግለጫ በአደአ በርጋ ወረዳ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች 15 ንጹሃን ዜጎችን ገድለዋል ብሏል። ከተገደሉት ንጹሃን ዜጎች መካከል የ70 ዓመት አዛውንት እንደሚገኙበት መግለጫው ጠቁሞ "የታጠቁት ኃይሎች ገንዘብ፣ ጌጣጌጥ እና ሌላም ቁሳቁስ እየዘረፉ እንዲሁም የሰዎችን መኖሪያ እያቃጠሉም ነው" ሲል አክሏል። የአካባቢው ነዋሪዎች በአሁን ወቅት ሕይወታቸውን ለማዳን ወደ ጫካ እየሸሹ እንደሆነም የኦነግ መግለጫ ያመለክታል። ሐሙስ እና አርብ ያጋጠመው ምንድን ነው? ሐሙስ ሚያዚያ 20/2014 ዓ.ም. የኦሮሚያ ልዩ ኃይል አባላት በወረዳው በሚገኝ ገጠራማ ስፍራ በፒክ አፕ መኪና ተጭነው ሲጓዙ ድንገተኛ ጥቃት በታጣቂዎች ተፈጽሞባቸዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች በዚህ ጥቃት ከ10 የማያንሱ የልዩ ኃይል ፖሊስ አባላት መገደላቸውን እና ቢያንስ 3 ሰዎች ደግሞ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተናግረዋል። በልዩ ኃይል አባላቱ ላይ የተሰነዘረውን ጥቃት ተከትሎ በቀጣይ ቀን ማለትም አርብ ሚያዚያ 21/2014 ዓ.ም. በወረዳው በሚገኙ ኢንጪኒ፣ ሙገር፣ ሬጂ እና ጂማታ ተብለው በሚጠሩ አካባቢዎች ከፍተኛ ውጥረት ነግሶ ነበር ይላሉ ነዋሪዎች። "በጂማታ ቤት ለቤት እየዞሩ ፍተሻ እያደረጉ ሰዎችን መግደል ጀመሩ" ሲሉ አንድ ነዋሪ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ሬሳ በቤት ውስጥ፣ በየጓሮ፣ ከዋናው መንገድ ዳር ሁሉ ይታይ ነበር" ሲሉ በጂማታ ከተማ የነበሩ እና አሁን በሆለታ ከተማ የሚገኙ ነዋሪ ነግረውናል። የፖሊስ አባላቱ በነዋሪዎች ቤት ላይ ብርበራ ሲፈጽሙ እና ሲገድሉ፤ 'ሸኔን የምትደብቁት እናንተ ናችሁ' ሲሉ እንደነበረ በቦታው ካለ ነዋሪ እንደሰሙ ቢቢሲ ያነጋገራቸው ነዋሪ ይናገራሉ። የኢንጪኒ ከተማ ነዋሪ ደግሞ ከሰዎች መኖሪያ ቤት የወጡ ታጣቂዎች በልዩ ኃይል አባላቱ ላይ ጥቃት ካደረሱ በኋላ የፖሊስ አባላቱ በቀጣይ ቀን በነዋሪዎች ላይ ግድያ መፈጸማቸውን ተናግረዋል። ነዋሪው ትናንት አርብ ምሽት በከተማዋ በሚገኝ ሆስፒታል "ብዙ ግርግር ነበር" ብለዋል። "ሁሉም ስለሚፈራ ወደዛ ሄደን ምን እየተካሄደ እንደሆነ አልጠየቅንም" ሲሉ ተናግረዋል። ከግድያው በተጨማሪ በጂማታ በርካታ መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸውን ከነዋሪዎች መረዳት ተችሏል። የኦሮሚያ ክልል ፀጥታ ጉዳዮች ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ፣ "ይህ ውሸት ነው። እንደዚህ ዓይነት ሪፖርት አልደረሰንም" ሲሉ ለቢቢሲ ምላሽ ሰጥተዋል። ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ሌሎች ጥያቄዎች ብናቀርብም "ሐሰት ነው" ከሚለው በዘለለ የገለጹልን ነገር የለም። ስለ ጉዳዮ ማብራሪያ ለማግኘት ወደ መንግሥት ኮምንኬሸን አገልግሎት ዶ/ር ለገሰ ቱሉ እንዲሁም ሰላማዊት ካሳ ብንደውልም ስልክ ስላልተነሳ ምላሽ ማካተት አልቻልንም። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ስለተፈጠረው ነገር መረጃ እንዳለው ለመጠየቅ ወደ ሕዝብ ግንኙት ባልደረባዎች ብንደውልም አልተሳካም። ከሰሞኑ መንግሥት 'ሸኔ' ብሎ የሚጠራውን ታጣቂ ቡድን "የማጽዳት ዘመቻ" ጀምሬያለሁ ካለ በኋላ በሁለቱ አካላት መካከል የሚደረገው ውጊያ ተጠናክሮ ቀጥሏል። እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ብሎ የሚጠራው እና የፌደራሉ መንግሥት አሸባሪ ሲል የፈረጀውን 'ሸኔ' ቡድን ለማጥፋት ለአንድ ወር የሚዘልቅ የተጠናከረ ወታደራዊ ዘመቻ መጀመሩን የክልሉ መንግሥት ከጥቂት ሳምንታት በፊት አስታውቆ ነበር። ይህን ተከትሎ ባለፉት ሳምንታት በተለይ በምዕራብ ሸዋ ዞን የፌደራሉ መንግሥት በሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) የታዘገ ጥቃት ሲያካሂድ መቆየቱ ተዘግቧል። ክልሉ ከቀናት በፊት "ሸኔን የማጽዳት" ዘመቻው ተጠናክሮ መቀጠሉን እና ይህ ወታደራዊ ዘመቻ የተፈለገለትን ዒላማ እያሳካ እንደሆነ በመግለጫ አውጥቶ ነበር። ይሁን እንጂ የታጣቂ ቡድኑ ቃል አቀባይ ኦዳ ተርቢ፤ "ወታደሮቻችን እየተዋጉ ነው። ድል እንጂ ሽንፈት አልገጠመንም። . . . ከ400 በላይ ወታደር ማርከናል። የተለያዩ ጦር መሣሪያዎችን ማርከናል" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
https://www.bbc.com/amharic/61283409
2health
በቀጣይ በዓለም ላይ የሚከሰቱ ወረርሸኞች ከኮቪድ በላይ ገዳይ ሊሆኑ ይችላሉ ተባለ
በዓለማችን ከዚህ በኋላ የሚከሰቱ ወረርሽኞች ከኮሮረናቫይረስ በላይ የከፉ ገዳይ ሊሆኑ እንደሚችሉ የኦክስፎርድ አስትራዜኔካ ክትባትን ከፈጠሩት ተመራማሪዎች መካከል አንዷ ባለሙያ ተናገሩ። ፕሮፌሰር ሳራህ ጊልበርት እንደሚሉት ወረርሽኞችን ለመቆጣጠር የሚደረገውን ዝግጁነት ለመደገፍ መንግሥታት በቂ ድጋፍ ማድረግ ያለባቸው ሲሆን አሁን የተገኙ ስኬቶችንም ማስቀጠል አስፈላጊ ነው። ፕሮፌሰሯ አክለውም ጥቅም ላይ እየዋሉ የሚገኙት ክትባቶች አዲሱን የቫይረስ አይነት ኦሚክሮን ለመከላከል ብዙም አቅም ላይኖራቸው እንደሚችልም ጠቁመዋል። ስለአዲሱ ቫይረስ በቂ መረጃ እስከሚገኝ ድረስ ሰዎች በጥንቃቄ እንዲንቀሳቀሱም መክረዋል። "ወረርሽኝ ሕይወታችንን እና አኗኗራችንን አደጋ ላይ ሲጥል ይህ የመጨረሻው የሚሆን አይመስለኝም። እውነታው ቀጣዩ ወረርሽኝ በጣም ከባድ ሊሆን እንደሚችል ነው። በፍጥነት የሚዛመት፣ በከፍተኛ ሁኔታ ገዳይ አልያም ሁለቱንም ያጣመረ ሊሆን ይችላል" ብለዋል። "በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ያለፍነውን ችግር መርሳት የለብንም። ወረርሽኙ በምጣኔ ሀብታችን ላይ ያሳደረው ጫና ወደፊት የሚከሰቱ ወረርሽኞችን እንዳንቆጣጠር ሊያደርገን አይገባም'' ሲሉ ያሳስባሉ። ፕሮፌሰር ሳራህ ጊልበርት ስለአዲሱ ኦሚክሮን ቫይረስ ሲናገሩ "አዲሱ ቫይረስ እራሱን አሻሽሎ ስለመጣ በክትባት መልክ ወይም በኮሮረናቫይረስ ስንያዝ የምናዳብረው በሽታ የመከላከል አቅም ብዙም ላይጠቅመን ይችላል" ብለዋል። አክለውም ስለአዲሱ ቫይረስ በቂ መረጃ እስከሚገኝና ምርምሮች እስከሚደረጉ ድረስ ሰዎች ስርጭቱን ለመቀነስ ጥንቃቄ እንዲያደርጉና የበኩላቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል። በኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት የተገኘው ትምህርትና ክትባቶችን በፍጥነት የማድረስ ልማድ ሊቀጥል እንደሚገባ ያሳሰቡት ፕሮፌሰሯ ከዚህ በኋላ መሰል እርምጃዎች የተለመዱ መሆን አለባቸው ብለዋል። የኦሚክሮን ስርጭትን ለመቆጣጠር እንዲቻል በማለት ቅዳሜ ዕለት ወደ ዩናይትድ ኪንግደም የሚጓዙ ሰዎች ከበረራቸው አስቀድመው የኮሮረናቫይረስ ምርምራ እንዲያደርጉ መንግሥት አሳስቧል። በዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) እስካሁን 246 ሰዎች በአዲሱ ኦሚክሮን መያዛቸው የተረጋተጠ ሲሆን ትናንት ዕሁድ ዕለት ብቻ 86 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን መንግሥት አስታውቋል። ነገር ግን የዩኬን መንግሥት የሚያማክሩ አንድ ተመራማሪ የጉዞ እገዳውና ሌሎች መመሪያዎች የዘገዩ መሆናቸውን ገልጸዋል። ፕሮፌሰር ማርክ ዉልሐውስ እንደሚሉት የመንግሥት ውሳኔ የዘገየ ሲሆን እዚህ ግባ የሚባል ለውጥ ያመጣል ብለው እንደማያምኑም ተናግረዋል።
በቀጣይ በዓለም ላይ የሚከሰቱ ወረርሸኞች ከኮቪድ በላይ ገዳይ ሊሆኑ ይችላሉ ተባለ በዓለማችን ከዚህ በኋላ የሚከሰቱ ወረርሽኞች ከኮሮረናቫይረስ በላይ የከፉ ገዳይ ሊሆኑ እንደሚችሉ የኦክስፎርድ አስትራዜኔካ ክትባትን ከፈጠሩት ተመራማሪዎች መካከል አንዷ ባለሙያ ተናገሩ። ፕሮፌሰር ሳራህ ጊልበርት እንደሚሉት ወረርሽኞችን ለመቆጣጠር የሚደረገውን ዝግጁነት ለመደገፍ መንግሥታት በቂ ድጋፍ ማድረግ ያለባቸው ሲሆን አሁን የተገኙ ስኬቶችንም ማስቀጠል አስፈላጊ ነው። ፕሮፌሰሯ አክለውም ጥቅም ላይ እየዋሉ የሚገኙት ክትባቶች አዲሱን የቫይረስ አይነት ኦሚክሮን ለመከላከል ብዙም አቅም ላይኖራቸው እንደሚችልም ጠቁመዋል። ስለአዲሱ ቫይረስ በቂ መረጃ እስከሚገኝ ድረስ ሰዎች በጥንቃቄ እንዲንቀሳቀሱም መክረዋል። "ወረርሽኝ ሕይወታችንን እና አኗኗራችንን አደጋ ላይ ሲጥል ይህ የመጨረሻው የሚሆን አይመስለኝም። እውነታው ቀጣዩ ወረርሽኝ በጣም ከባድ ሊሆን እንደሚችል ነው። በፍጥነት የሚዛመት፣ በከፍተኛ ሁኔታ ገዳይ አልያም ሁለቱንም ያጣመረ ሊሆን ይችላል" ብለዋል። "በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ያለፍነውን ችግር መርሳት የለብንም። ወረርሽኙ በምጣኔ ሀብታችን ላይ ያሳደረው ጫና ወደፊት የሚከሰቱ ወረርሽኞችን እንዳንቆጣጠር ሊያደርገን አይገባም'' ሲሉ ያሳስባሉ። ፕሮፌሰር ሳራህ ጊልበርት ስለአዲሱ ኦሚክሮን ቫይረስ ሲናገሩ "አዲሱ ቫይረስ እራሱን አሻሽሎ ስለመጣ በክትባት መልክ ወይም በኮሮረናቫይረስ ስንያዝ የምናዳብረው በሽታ የመከላከል አቅም ብዙም ላይጠቅመን ይችላል" ብለዋል። አክለውም ስለአዲሱ ቫይረስ በቂ መረጃ እስከሚገኝና ምርምሮች እስከሚደረጉ ድረስ ሰዎች ስርጭቱን ለመቀነስ ጥንቃቄ እንዲያደርጉና የበኩላቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል። በኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት የተገኘው ትምህርትና ክትባቶችን በፍጥነት የማድረስ ልማድ ሊቀጥል እንደሚገባ ያሳሰቡት ፕሮፌሰሯ ከዚህ በኋላ መሰል እርምጃዎች የተለመዱ መሆን አለባቸው ብለዋል። የኦሚክሮን ስርጭትን ለመቆጣጠር እንዲቻል በማለት ቅዳሜ ዕለት ወደ ዩናይትድ ኪንግደም የሚጓዙ ሰዎች ከበረራቸው አስቀድመው የኮሮረናቫይረስ ምርምራ እንዲያደርጉ መንግሥት አሳስቧል። በዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) እስካሁን 246 ሰዎች በአዲሱ ኦሚክሮን መያዛቸው የተረጋተጠ ሲሆን ትናንት ዕሁድ ዕለት ብቻ 86 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን መንግሥት አስታውቋል። ነገር ግን የዩኬን መንግሥት የሚያማክሩ አንድ ተመራማሪ የጉዞ እገዳውና ሌሎች መመሪያዎች የዘገዩ መሆናቸውን ገልጸዋል። ፕሮፌሰር ማርክ ዉልሐውስ እንደሚሉት የመንግሥት ውሳኔ የዘገየ ሲሆን እዚህ ግባ የሚባል ለውጥ ያመጣል ብለው እንደማያምኑም ተናግረዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-59545549
3politics
የአሜሪካ ሕዝብ እንደራሴዎች 'አክራሪዋን' የምክር ቤት አባል ለማስወገድ ድምፅ ሰጡ
የዩናይትድ ስቴትስ ሕዝብ እንደራሴዎች አክራሪዋን የሪፐብሊካን ፓርቲ አባል ከሁለት ኮሚቲዎች ለማስወገድ ድምፅ ሰጡ። ማርጆሪ ግሪን የተሰኙት የምክር ቤቱ አባል መሠረት የሌላቸው የሴራ ትንተናዎችን በማሰራጨት ይታወቃሉ። አልፎም እንደራሴዋ ዴሞክራቶች ላይ በሚሰንዝሯቸው ጠብ አጫሪ አስተያየቶቻቸውም ይታወቃሉ። ከምክር ቤቱ አባላት መካከል ሁሉም ዴሞክራቶች ሴትዬዋ ከኮሚቴ አባልነታቸው ይነሱ ብለው ድምፅ ሲሰጡ፣ 11 ሪፐብሊካኖችንም አብረዋል። በአጠቃላይ 230 ለ199 በሆነ ድምፅ የአሜሪካ ሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ሴትዬዋን ለመቅጣት ወስኗል። አሜሪካ ውስጥ ትምህርት ቤቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችና የ9/11 የሽብር ጥቃት የተቀነባበረ ነው ብለው የሚያምኑት እንደራሴዋ፣ ድምፅ ከመሰጠቱ በፊት ባደረጉት ንግግር ይህ ድርጊታቸው የሚያስወቅሳቸው እንደሆነ አልካዱም። በአሜሪካ ፖለቲካ መሰል ክስተቶች እምብዛም አይስተዋሉም። ብዙ ጊዜ አባላት አልባሌ ድርጊት ሲፈፅሙ ፓርቲው ነበር የሚቀጣቸው። እንደራሴዋ ድርጊታቸው የሚያስኮንናቸው እንደሆነ ይናገሩ እንጂ ይቅርታ ከመጠየቅ ተቆጥበዋል። እነዚህ ድርጊቶች የሕዝብ ተወካይ ከመሆኔ በፊት የፈፅምኳቸው ናቸው ሲሉም ተከራክረዋል። "እኒህ ያለፉ ድርጊቶች ናቸው። እነዚህ ነገሮች እኔን አይወክሉኝም" ብለዋል እንደራሴዋ በባልደረቦቻቸው ፊት ቀርበው ባደረጉት ንግግር። የ46 ዓመቷ የግዛተ ጆርጂያ ተወካይ የሴራ ትንተና ከሚያራምዱ እኩል መገናኛ ብዙሃንም ውሸትን በማራገብ ተጠያቂ ሊሆኑ ይገባል ብለዋል። ሴትዬዋ በበይነ መረብ ዓለም እጅግ ታዋቂ ናቸው። ማሕበራዊ ድር አምባዎች ላይ በንቃት ይሳተፋሉ። የዶናልድ ትራምፕ ቀንደኛ ደጋፊ ናቸው። አንድ ፌስቡከኛ የአሜሪካ ሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ "ጭንቅላታቸውን በጥይት ይመቱ" ብሎ የለጠፈውን መልክት በመውደዳቸው [ላይክ በማድረጋቸው] ምክንያት ብዙ ወቀሳ አስተናግደዋል። "ባራካ ኦባማ ይሰቀሉ" የሚል መልዕክት ሥር ገብተው ደግሞ "መድረኩ ተዘጋጅቷል" ሲሉ ኮምተው ነበር። ከአንድ ጅምላ ግድያ ያመለጠን ታዳጊ መንገድ ላይ አግኝተው 'አውሬ' ብለው ሲስደቡት የሚያሳይ ምስል ተለቆ አጃኢብ አሰኝቶ እንደነበር አይዘነጋም። በፈረንጆቹ 2018 ደግሞ በየሁለት ዓመቱ የሚደረገው የአሜሪካ የምክር ቤት ምርጫ "መንግሥታችን በሙስሊሞች እንዲወረር እያደረገ ነው" የሚል አስተያየት ሰንዝረው ነበር። ማርጆሪ በቅርቡ የተደረገውን የአሜሪካ ምርጫ ያሸነፉት ዶናልድ ትራምፕ ናቸው ብለው ያምናሉ። እንደራሴዋ ባደረጉት ንግግር ስለነዚህ ጉዳዮች አንዳችም ነገር አላሉም።
የአሜሪካ ሕዝብ እንደራሴዎች 'አክራሪዋን' የምክር ቤት አባል ለማስወገድ ድምፅ ሰጡ የዩናይትድ ስቴትስ ሕዝብ እንደራሴዎች አክራሪዋን የሪፐብሊካን ፓርቲ አባል ከሁለት ኮሚቲዎች ለማስወገድ ድምፅ ሰጡ። ማርጆሪ ግሪን የተሰኙት የምክር ቤቱ አባል መሠረት የሌላቸው የሴራ ትንተናዎችን በማሰራጨት ይታወቃሉ። አልፎም እንደራሴዋ ዴሞክራቶች ላይ በሚሰንዝሯቸው ጠብ አጫሪ አስተያየቶቻቸውም ይታወቃሉ። ከምክር ቤቱ አባላት መካከል ሁሉም ዴሞክራቶች ሴትዬዋ ከኮሚቴ አባልነታቸው ይነሱ ብለው ድምፅ ሲሰጡ፣ 11 ሪፐብሊካኖችንም አብረዋል። በአጠቃላይ 230 ለ199 በሆነ ድምፅ የአሜሪካ ሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ሴትዬዋን ለመቅጣት ወስኗል። አሜሪካ ውስጥ ትምህርት ቤቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችና የ9/11 የሽብር ጥቃት የተቀነባበረ ነው ብለው የሚያምኑት እንደራሴዋ፣ ድምፅ ከመሰጠቱ በፊት ባደረጉት ንግግር ይህ ድርጊታቸው የሚያስወቅሳቸው እንደሆነ አልካዱም። በአሜሪካ ፖለቲካ መሰል ክስተቶች እምብዛም አይስተዋሉም። ብዙ ጊዜ አባላት አልባሌ ድርጊት ሲፈፅሙ ፓርቲው ነበር የሚቀጣቸው። እንደራሴዋ ድርጊታቸው የሚያስኮንናቸው እንደሆነ ይናገሩ እንጂ ይቅርታ ከመጠየቅ ተቆጥበዋል። እነዚህ ድርጊቶች የሕዝብ ተወካይ ከመሆኔ በፊት የፈፅምኳቸው ናቸው ሲሉም ተከራክረዋል። "እኒህ ያለፉ ድርጊቶች ናቸው። እነዚህ ነገሮች እኔን አይወክሉኝም" ብለዋል እንደራሴዋ በባልደረቦቻቸው ፊት ቀርበው ባደረጉት ንግግር። የ46 ዓመቷ የግዛተ ጆርጂያ ተወካይ የሴራ ትንተና ከሚያራምዱ እኩል መገናኛ ብዙሃንም ውሸትን በማራገብ ተጠያቂ ሊሆኑ ይገባል ብለዋል። ሴትዬዋ በበይነ መረብ ዓለም እጅግ ታዋቂ ናቸው። ማሕበራዊ ድር አምባዎች ላይ በንቃት ይሳተፋሉ። የዶናልድ ትራምፕ ቀንደኛ ደጋፊ ናቸው። አንድ ፌስቡከኛ የአሜሪካ ሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ "ጭንቅላታቸውን በጥይት ይመቱ" ብሎ የለጠፈውን መልክት በመውደዳቸው [ላይክ በማድረጋቸው] ምክንያት ብዙ ወቀሳ አስተናግደዋል። "ባራካ ኦባማ ይሰቀሉ" የሚል መልዕክት ሥር ገብተው ደግሞ "መድረኩ ተዘጋጅቷል" ሲሉ ኮምተው ነበር። ከአንድ ጅምላ ግድያ ያመለጠን ታዳጊ መንገድ ላይ አግኝተው 'አውሬ' ብለው ሲስደቡት የሚያሳይ ምስል ተለቆ አጃኢብ አሰኝቶ እንደነበር አይዘነጋም። በፈረንጆቹ 2018 ደግሞ በየሁለት ዓመቱ የሚደረገው የአሜሪካ የምክር ቤት ምርጫ "መንግሥታችን በሙስሊሞች እንዲወረር እያደረገ ነው" የሚል አስተያየት ሰንዝረው ነበር። ማርጆሪ በቅርቡ የተደረገውን የአሜሪካ ምርጫ ያሸነፉት ዶናልድ ትራምፕ ናቸው ብለው ያምናሉ። እንደራሴዋ ባደረጉት ንግግር ስለነዚህ ጉዳዮች አንዳችም ነገር አላሉም።
https://www.bbc.com/amharic/55945222
5sports
ጉዳፍ ፀጋይ የ1500 ሜትር የቤት ውስጥ ሩጫ የዓለም ክብረ ወሰንን አሻሻለች
ጉዳፍ ፀጋይ ፈረንሳይ ሌቪን በተካሄደው የ1500 ሜትር የቤት ውስጥ ሩጫ የዓለም ክብረ ወሰንን በማሻሻል አሸነፈች። ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ የዓለም ክብረ ወሰን በ2 ሴኮንድ በማሻሻል 3፡53፡09 በሆነ ሰዓት ውድድሩን አጠናቃለች። ጉዳፍ ያሻሻለችው ክብረ ወሰን በሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት ገንዘቤ ዲባባ በ2014 (እአአ) ካርልስሩሄ ላይ የተያዘ ነበር። "የዓለምን የቤት ውስጥ ሩጫ ክብረ ወሰን በማሻሻሌ እጅግ ደስተኛ ነኝ" ያለችው አሸናፊዋ ጉዳፍ፤ "ጠንከራ ልምምድ ሰርቼ ስለነበር የዓለምን ክብረ ወሰን ለመስበር ራሴን አዘጋጅቼ ነበር" ብላለች። ትናንት ምሽት በወንዶች በተደረገ የ3 ሺህ ሜትር የቤት ውስጥ ሩጫም ኢትዮጵያውያን ተወዳዳሪዎቻቸውን በፍጹም የበላይነት አሸንፈዋል። ኢትዮጵያውያኑ ከአንድ እስከ አራት ያለውን ደረጃ ይዘው ሲያጠናቅቁ የዓለም ሁለኛው ፈጣን ሰዓትም በውድድሩ ተመዝግቧል። በመሰናክል ሩጫ ጌትነት ዋለ በ3 ሺህ ሜትር ሩጫ በአንደኝነት ሲያሸንፍ ሦስት ኢትዮጵያውያን አትሌቶችም ተከታትለው በመግባት ድሉን አድምቀውለታል። ሩጫውንም በ7፡24፡98 በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ የወርቅ ተሸላሚ ሆኗል። ጌትነት የገባበት ሰዓት የዓለም ሁለተኛው ፈጣን ሰዓትም ሆኖ ተመዝግቦለታል። የ20 ዓመቱ ጌትነት ለረጅም ጊዜ ክብረወሰኑን 7፡24፡90 በሆነ ሰዓት ለያዘው ዳንኤል ኮሜን ትልቅ ስጋት ፈጥሯል። የዓለም ሻምፒዮና የ5 ሺ ሜትር የብር ሜዳሊያ አሸናፊው ሰለሞን ባረጋ ደግሞ በእዚሁ ወድድር 7፡26.10 በሆነ ሰዓት ሁለተኛ ሆኖ አጠናቅቋል። ለሜቼ ግርማ በ7፡27፡98 ሦስተኛ ደረጃን ይዞ ሲያጠናቅቅ ሌላኛው ኢትዮጵያዊ በሪሁ አረጋዊ ደግሞ በ7፡29፡24 አራተኛ በመሆን ውድድሩን ጨርሷል። ከአሁን በፊት በ3 ሺህ ሜትር ሜትር የቤት ውስጥ ሩጫ ከ00፡07፡30 በታች መግባት የቻሉት 6 ሯጮች ብቻ ነበሩ። አሁን ግን እድሜያቸው ከ19 እስከ 21 የሆኑ አራት ሯጮች ከ00፡07፡30 በታች ይህንን ውድድር ማጠናቀቅ ችለዋል። ይህም ክብረወሰኑን በቅርቡ ለማሻሻል ተስፋ የታየበት ነው ተብሏል።
ጉዳፍ ፀጋይ የ1500 ሜትር የቤት ውስጥ ሩጫ የዓለም ክብረ ወሰንን አሻሻለች ጉዳፍ ፀጋይ ፈረንሳይ ሌቪን በተካሄደው የ1500 ሜትር የቤት ውስጥ ሩጫ የዓለም ክብረ ወሰንን በማሻሻል አሸነፈች። ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ የዓለም ክብረ ወሰን በ2 ሴኮንድ በማሻሻል 3፡53፡09 በሆነ ሰዓት ውድድሩን አጠናቃለች። ጉዳፍ ያሻሻለችው ክብረ ወሰን በሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት ገንዘቤ ዲባባ በ2014 (እአአ) ካርልስሩሄ ላይ የተያዘ ነበር። "የዓለምን የቤት ውስጥ ሩጫ ክብረ ወሰን በማሻሻሌ እጅግ ደስተኛ ነኝ" ያለችው አሸናፊዋ ጉዳፍ፤ "ጠንከራ ልምምድ ሰርቼ ስለነበር የዓለምን ክብረ ወሰን ለመስበር ራሴን አዘጋጅቼ ነበር" ብላለች። ትናንት ምሽት በወንዶች በተደረገ የ3 ሺህ ሜትር የቤት ውስጥ ሩጫም ኢትዮጵያውያን ተወዳዳሪዎቻቸውን በፍጹም የበላይነት አሸንፈዋል። ኢትዮጵያውያኑ ከአንድ እስከ አራት ያለውን ደረጃ ይዘው ሲያጠናቅቁ የዓለም ሁለኛው ፈጣን ሰዓትም በውድድሩ ተመዝግቧል። በመሰናክል ሩጫ ጌትነት ዋለ በ3 ሺህ ሜትር ሩጫ በአንደኝነት ሲያሸንፍ ሦስት ኢትዮጵያውያን አትሌቶችም ተከታትለው በመግባት ድሉን አድምቀውለታል። ሩጫውንም በ7፡24፡98 በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ የወርቅ ተሸላሚ ሆኗል። ጌትነት የገባበት ሰዓት የዓለም ሁለተኛው ፈጣን ሰዓትም ሆኖ ተመዝግቦለታል። የ20 ዓመቱ ጌትነት ለረጅም ጊዜ ክብረወሰኑን 7፡24፡90 በሆነ ሰዓት ለያዘው ዳንኤል ኮሜን ትልቅ ስጋት ፈጥሯል። የዓለም ሻምፒዮና የ5 ሺ ሜትር የብር ሜዳሊያ አሸናፊው ሰለሞን ባረጋ ደግሞ በእዚሁ ወድድር 7፡26.10 በሆነ ሰዓት ሁለተኛ ሆኖ አጠናቅቋል። ለሜቼ ግርማ በ7፡27፡98 ሦስተኛ ደረጃን ይዞ ሲያጠናቅቅ ሌላኛው ኢትዮጵያዊ በሪሁ አረጋዊ ደግሞ በ7፡29፡24 አራተኛ በመሆን ውድድሩን ጨርሷል። ከአሁን በፊት በ3 ሺህ ሜትር ሜትር የቤት ውስጥ ሩጫ ከ00፡07፡30 በታች መግባት የቻሉት 6 ሯጮች ብቻ ነበሩ። አሁን ግን እድሜያቸው ከ19 እስከ 21 የሆኑ አራት ሯጮች ከ00፡07፡30 በታች ይህንን ውድድር ማጠናቀቅ ችለዋል። ይህም ክብረወሰኑን በቅርቡ ለማሻሻል ተስፋ የታየበት ነው ተብሏል።
https://www.bbc.com/amharic/56006574
5sports
የጆርጅ ፍሎይድን ሞት የቀረጸችው ሴት ምን አለች?
ሰዎች ስለ ሟች ጆርጅ ፍሎይድ ያወራሉ። ሰዎች ስለ ጨካኙ ፖሊስ ዴሪክ ያወራሉ። ሰዎች ይህን ሁሉ ጉድ በስልኳ ቀርጻ ለዓለም ስላጋራችው አንዲት ትንሽ ልጅ ግን አያወሩም። የእርሷ የስልክ ቪዲዮ ባይኖር ዛሬ ስለ ጆርጅ ፍሎይድ የሚያወሩት ቤተሰቦቹ ብቻ በሆኑ ነበር። ማን ያውቃል? አንዳንድ ወንጀሎች ወንጀል የሚሆኑት ለአደባባይ ሲቀርቡ ነው። ስርቆት ሌብነት ሆኖ የሚያስከስሰው ሲደረስበት ብቻ ነው። በጆርጅ ፍሎይድ የደረሰው ሳይቀረጽ ቀርቶ ቢሆንስ? በዚህ ዘመን የማኅበራዊ ሚዲያ ጉልበት ኃያል ነው። ሰደድ እሳት ነው። ዓለምን ለማዳረስ ሰከንዶች ይበቁታል። አማዞን ጫካ ላይ የምትጫር ክብሪት…እንደማለት ነው። ዳርኔላ ፍሬዘር ገና 17 ዓመቷ ነው። ገና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መግባቷ ነው። የአክስቷን ልጅ ወደ ሰፈራቸው ምግብ ቤት ይዛት እየሄደች ነበር። የአክስቷ ልጅ ደግሞ ገና 9 ዓመቷ ነው፡። ልክ ምግብ ቤቱ አካባቢ ስትደርስ የሆነ ጥቁር ሰውዬ ፖሊሶች ሲያስጨንቁት አይታ ቆመች፤ ቆመችና እንደ ዋዛ ስልኳን ከኋላ ኪሷ መዘዝ አድርጋ አወጣች። 'ሪከርድ' የሚለውን ቀይ ምልክት ተጫነች። እርሷ መቅረጽ ስትጀምር ጆርጅ ፍሎይድ አየር አጥሮት ያቃስት ጀምሯል። "እባካችሁ! እባካችሁ" እያለ። የእርሱ እስትንፋስ እስከወዲያኛው ልትቋረጥ የመጨረሻ ቃሉ "I can't breathe," [መተንፍስ አልቻልኩም] ነበር። ይቺን "መተንፈስ አልቻልኩም" የምትለዋ ቃል ለመጨረሻ ጊዜ ከእስትንፋሱ ስትወጣ የዳርኔላ ስልክ ባትሪው አላለቀም። እርሷም መቅረጽ አላቆመችም። ከዚህ በኋላ ጆርጅ ፍሎይድ ምንም አላለም። እስከወዲያኛው አሸልቧል። የ44 ዓመቱ የፖሊስ መኮንን ዴሪክ ቾቪን ግን እጁን ኪሱ አድርጎ በጉልበቱ የፍሎይድን አንገት እንደተጫነው ነበር። ከዴሪክ ጋር ሦስት ፖሊሶችም ለዚህ ተግባሩ ተባባሪ ነበሩ። የ17 ዓመቷ ዳርኔላ ስልኳ መቅረጹን እንዲያቆም ያደረገችው ፖሊስ ዴሪክ በእግሩ ወደ ግራ፣ ጆርጅ ፍሎይድ በቃሬዛ ወደ ቀኝ ሲሄዱ ነበር። ዳርኔላ በድምሩ 10 ደቂቃ ከ9 ሰከንዶች ቀርጻለች። ድርጊቱን አጠናቃ ስልኳን ወደ ኪሷ ስትከት ግን በስልኳ ቋት ያኖረችው ተንቀሳቃሽ ምስል ዓለምን ሊንጥ እንደሚችል በፍጹም አልተከሰተላትም። በወቅቱ ምን እንዳደረገች፣ ምስሉ ከተሰራጨ በኋላ ምን እንደተሰማት ለቢቢሲ ለመናገር ፍቃደኛ አይደለችም። ለጊዜው ለቢቢሲም ሆነ ለሌላ ሚዲያ አስተያየት መስጠት ትታለች። ዕድሜዋም አንድ ምክንያት ይሆናል። የእርሷ ጠበቃ ሚስተር ኮቢን ግን ለምን ክስተቱን መቅረጽ እንደፈለገች ተጠይቀው ምላሽ ሰጥተዋል። "የዜግነት ግዴታዋን የመወጣት ስሜት ተሰምቷት ሊሆን ይችላል።" "ያም ሆነ ይህ በእርሷ ቪዲዮ የመብት ትግል እቅስቃሴ ድጋሚ ተወልዷል ብዬ አምናለሁ" ይላሉ ጠበቃዋ። የ2ኛ ደረጃ ተማሪዋ ዳርኔላ ከዚህ ክስተት በኋላ መጠነኛ የአእምሮ መታወክ ደርሶባት ሕክምና ጀምራለች። በሕይወቷ እንዲያ ያለ ሰቅጣጭ ነገር አይታ አታውቅም። ያን ቪዲዮ በፌስቡክ ሰሌዳዋ ላይ ከሰቀለችው በኋላ የነበረው ምላሽ በእርሷ ዕድሜ ለመቋቋም የሚቻል አልነበረም። በፖሊስ ድርጊት የተቆጡ እንዳሉ ሁሉ በእርሷ ድርጊት የተቆጡም ቁጥራቸው ትንሽ አልነበረም። ያመሰገኗት እንዳሉ ሁሉ "ጫካኝ፣ አውሬ" ሲሉ የሞለጯትም ጥቂት አይደሉም። የጆርጅ ፍሎይድ አሰቃቂ ሞት በግንቦት 25 ነበር፤ እርሷ ወደ ፌስቡክ ገጽ ያመራቸው ግን ከ2 ቀናት በኋላ በግንቦት 27 ነው። ወዲያውኑ እሳት ተቀጣጠለ። ነደደ፣ ጨሰ…። የእርሷ ቪዲዮ የእርሷ መሆኑ ቀረ። ሚሊዮኖች ቤት ገባ። መጀመርያ አካባቢ በፌስቡክ ሰሌዳዋ ስር ለተሰጧት አስተያየቶች ምላሽ ትሰጥ ነበር። አንዱ አስተያየት ሰጪ እርሷን ዝና ናፋቂ አድርጎ ይከሳታል። እንዲያ ባይሆን ኖሮ ሞባይልሽን አስቀምጠሸ የሚሞተውን ሰው ታድኚው ነበር ብሎ ይከሳታል። እርሷም ዝም አላለችም። የሚከተለውን መለሰችለት። "እኔ ያን ክስተት ባልቀርጽ ኖሮ፣ አራቱ ፖሊሶች ዛሬ በሥራ ላይ ነበሩ። ምናልባትም ሌላ ሰው እያነቁ…" ዳርኔላን 'ያን ያደረግሽው ዝና ፍለጋ ነው' የሚሏት ሰዎች ከምር ያበሳጯት። "ምን? ለዝና ነው ያደረግሽው ነው የምትሉኝ? ለገንዘብ ነው ያደረግሽ ነው የምትሉኝ? እናንተ ሰዎች ደደብና ደንቆሮዎች ሳትሆኑ አትቀሩም።" በዳርኔላ ላይ የደረሰው ትችት፤ አደጋ እየደረሰ ቪዲዮ መቅረጽ ጽድቅ ነው ኩነኔ የሚል ሌላ ዙር የክርክር ምዕራፍ ከፍቷል። ለመሆኑ እንዲህ ማድረግ ተገቢ ነው? በሞራል ሕግ እንዴት ይሰፈራል? ራስ ወደድነታችን ይሆን ሰው እየሞተ እኛ ቪዲዮ እንድንቀርጽ የሚያስችለን? በምንቀርጽበት ቅጽበት እየሞተ ላለው ሰው የምር ሐዘኔታ ይሰማናል? ነው ወይስ የሚያስጨንቀን በእኛ የሚቀረጸው የቪዲዮ ጥራትና ቀጥሎ የሚመጣው እውቅና? ዳርኔላ በእርሷ የተቀረጸው ተንቀሳቃሽ ምስል ዓለምን ከናጠ በኋላ ሽልማት አልጠበቃትም። እንዲያውም ነገሩ ሕይወቷን ረብሾታል። አሁን የአእምሮ ሐኪም እየተንከባከባት የሚገኘው ያለምክንያት አይደለም። ከዚህ ቀደም ቪዲዮ በመቅረጽ ወንጀል ያጋለጡም ቢሆኑ ሽልማት አልጠበቃቸውም። ሕይወታቸው በአንድም ይሁን በሌላ መንገድ ተረባብሿል። 1.ዴኒስ ፍሎረስ ይሄን ቪዲዮ እየቀረጹ የፖሊስን ጭካኔ ማጋለጥ የጀመረው ሰው ዴኒስ ፍሎረስ ሳይሆን አይቀርም። የኒው ዮርክ ሰው ነው። የኒው ዮርክ ከተማ ፖሊስን እንደሱ የቀረጸ የለም። ፖሊስ 70 ጊዜ አስሮታል። ከ90ዎቹ ጀምሮ እንደቀረጻቸው ነው ያለው። ዛሬ 'ፖሊስ አደብ ይግዛ፣ ዘረኝነቱን ይተው' የሚሉ እንቅስቃሴዎች እንዲጀመሩ ምክንያት የሆነው እርሱ ነው። ሞባይል ሳይጀመር እርሱ የፖሊስ ግፍ መቅረጽ ጀምሯል። ይህ ድርጊቱ ሕይወቱን እንዴት እንዳከበደው ወደኋላ ላይ ይነግረናል። ፍሎረስ የጀመረውን ተግባር ግን በብዙዎች ይተገበር ጀመር። 2.ቧንቧ ሠራተኛው ጆርጅ ሆሊዴይ ከፍሎረስ በኋላ በ1991 አካባቢ አንድ ጆርጅ ሆሊዴይ የሚባል የቧንቧ ሠራተኛ ከአፓርትመንቱ በርንዳ ላይ ሆኖ የቀረጸው ነገር ምናልባትም እንደ ወረርሽኝ የተዛመተ የመጀርመያ ቪዲዮ ሳይሆን አይቀርም። ያን ጊዜ እንደዛሬው ፌስቡክ የለ፣ ቅንጡ ሞባይል የለ! ምን የለ፣ ምን የለ! እርሱ ቀረጻ ያደረገውም በተለምዶ የልደት ካሜራ መቅረጫ በምንላት ትንሽ ሶኒ ቪዲዮ ካሜራ ነበር። ከበረንዳው ቀርጾ ያስቀረው ምስል ከባድ ውጤትን አስከተለ። በሎስ አንጀለስ ካሊፎርኒያ ሮድኒ ኪንግ የሚባልን አንድ ጥቁር ወጣት በርከት ያሉ ነጭ ፖሊሶች ከበውት እየተቀባበሉ ሲያዳፉት የሚያሳይ አሰቃቂ ቪዲዮ ነበር። ጆርጅ ሆሊዴይ ያን ጊዜ ይህን ክስተት ሲቀርጽ ሞባይል አልነበረም ብለናል። 5ጂ ኢንተርኔትም አልተፈጠረም፤ ፌስቡክ የለም። ታዲያ እንዴት ተዛመተ? ይህንን የቀረጸውን አሰቃቂ የቪዲዮ ቴፕ ወስዶ እዚያ ሰፈሩ ለሚገኝ ቴሌቪዥን ጣቢያ ሰጠ። ጣቢያው ተንቀሳቃሽ ምስሉን በዜና እወጃ ሰዓት ላይ አስተላለፈው፤ አገሪቱም በተቃውሞ ተናጠች። ከዓመት በኋላ ያንን ድርጊት የፈጸሙ ፖሊሶች ፍርድ ቤት ነጻ ናችሁ ሲላቸው ደግሞ ደም አፋሳሽ ተቃወሞ በመላው አሜሪካ ዳግም ተከሰተ። "ይሄ ሰው የቀረጸው ምስል ነው በአሜሪካ ምድር የፖሊስን ግፍ መቅረጽ እንዲለመድ ምክንያት የሆነው" ይላል በዚህ ተግባር ጥርሱን የነቀለው የኒው ዮርኩ ፍሎርስ፣ ለቢቢሲ። በአሜሪካ ሕገ መንግሥት ዜጎች በፖሊስ የሚፈጸምን ተግባር ቆመው የመቅረጽ መብት አላቸው። 3.ራምሴ ኦርታ ከዚህ ክስተት በኋላ የመጣው የኤሪክ ጋርነር ጉዳይ ነው። ሚስተር ጋርነር የ43 ዓመት ጥቁር አሜሪካዊ ነበር። በኒው ዮርክ ከተማ በ2014 ልክ እንደ ጆርጅ ፍሎይድ ሁሉ በነጭ ፖሊሶች አንገቱን ታንቆ ነበር የሞተው። ፖሊሶቹ አንገቱን አንቀው የያዙት የምትሸጣቸው ሲጃራዎች ሕጋዊ አይደሉም በሚል ምክንያት ነበር። ልክ እንደ ጆርጅ ፍሎይድ ሁሉ ሚስተር ጋርነርም ፖሊሶቹ አንገቱን ጠምልለው ሲያስጨንቁት፤ 'እባካችሁ መተንፈስ አቃተኝ፣ እባካችሁ!' እያለ ይጮኽ ነበር። "I can't breath" የሚለው ንግግርም የትግል መፈክር መሆን የጀመረው ከእርሱ በኋላ ነበር። በእርሱ የደረሰው የሞት አደጋ ፍርድ ቤት የነፍስ ማጥፋት ወንጀል ነው ቢልም ድርጊቱን የፈጸመው ፖሊስ ግን ነጻ ሆኗል። ያ ፖሊስ ስሙ ዳንኤል ፓንታሊዮ ይባል ነበር። ሟችና ገዳይን ለጊዜው ትተን ያን ድርጊት በቪዲዮ ስላስቀረው ሰው ትንሽ እናውራ። ራምሴ ኦርታ ይባላል። የእርሱ ጉዳይም እንደ ሌሎቹ ቀራጮች ሁሉ ሲያወዛግብ ነው የኖረው። "ይህን ክስተት ከቀረጽኩ በኋላ ፖሊሶች ሲከታተሉኝ ነው የኖርኩት" ብሏል ከዚህ በፊት በሰጠው አንድ ቃለ ምልልስ። በ2016 ራምሴ ኦርታ በአደገኛ እጽና በሕገ ወጥ መሳሪያ ዝውውር ክስ ተመሰረተበት። አራት ዓመትም ዘብጥያ ወረደ። እርግጥ ነው የተመሰረተበት ክስ የፖሊስን ድርጊት በቪዲዮ ከመቅረጽ ጋር የሚያገናኘው አንዳችም ነገር ባይኖርም ጓደኛው ሚስተር ፍሎረስ እንደሚያምነው ግን ፖሊስ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሲከታተለውና የሚታሰርበትን ሰበብ ሲፈልግለት፣ እንዲሁም ቀን ሲጠብቅለት ነበር። "ፖሊስን ማጋለጥ ለአደጋ መጋለጥ እንደሆነ ሊያስረዳ የሚችለው የራምሴ ኦርታ ጉዳይ ነው" ይላል ፍሎረስ። የሚገርመው ራምሴ ኦርታ ከእስሩ በኋላ ምነው ያን ጊዜ ፖሊስን ባልቀረጽኩ ኖሮ ሲል ተጸጽቷል። ያም ሆኖ ግፍ ሲፈጸም ዝም ብሎ ማለፍም ከባድ የሕሊና ጸጸት እንደሚተርፍ የፈይዲን ሳንታናን ታሪክ ማየት በቂ ነው። 4.ፈይዲን ሳንታና ፈይዲን ሳንታና በ2015 በሳውዝ ካሮላይና ግዛት፣ ቻርልስተን ከተማ ወደ ሥራ እየሄደ ነበር። አንድ ነጭ ፖሊስ ዋልተር ስኮት የሚባል አንድ ጥቁርን መኪናው ውስጥ ሳለ ሲያስቆመው ያያል። ነገሩ እንዲሁ ስላላማረው ወይም ልማድ ሆኖበት ይሆናል ስልኩን አውጥቶ መቅረጽ ይጀምራል። ፖሊሱ ትንሽ ዘወር ባለበት ቅጽበት ጥቁሩ ዋልተር ስኮት ድንገት ከመኪናው ወርዶ እግሬ አውጪኝ ይላል። ሳንታና ይህ ሁሉ ሲሆን በግማሽ ልብም ቢሆንም እየቀረጸው ነበር። በዚህ ቅጽበት ፖሊሱ ያደረገው ነገር ግን ፍጹም ያልጠበቀው ነበር። ፖሊሱ ሽጉጡን አውጥቶ እየሮጠ የነበረውን ጥቁሩን ዋልተር ስኮትን 8 ጥይቶችን ከጀርባ ለቀቀበት። አከታትሎ። ዋልተር ስኮት መሬት ላይ ወደቀ። ሳንታና እንደቀልድ የቀረጸው ነገር በኋላ ላይ ለከፍተኛ የአእምሮ መረበሽ ዳረገው። "ድንጋጤ ውስጥ የከተተኝ ምንም ያልታጠቀ አንድ ጥቁር ሰውዬ እንዲሁ ለማምለጥ ሲል ብቻ ስለሮጠ 8 ጥይት ከጀርባው ይዘንብበታል ብዬ አላሰብኩም ነበር" ብሏል ለቢቢሲ። ሳንታና ከዚህ ክስተት በኋላ ለሦሰት ቀናት ያህል ከቤት መውጣት አስጠላው። እርሱ ራሱ ስደተኛ ነው፣ በዚያ ላይ ከዶሚኒካን ሪፐብሊክ መጥቶ በፀጉር አስተካካይነት ነበር የሚተዳደረው። በስልኩ ያስቀረውን ነገር ለማንም አላሳየም። ለማንም አላጋራም። እንዲያ ቢያደርግ በኋላ ጣጣው ብዙ ነው ብሎ አሰበ። እንዲያውም ያስቀረውን ተንቀሳቃሽ ምስል እስከ ወዲያኛው ሊሰርዘውና ቻርለስተን ከተማን ጥሎ ለመሄድም አስቦ ነበር። በዚህ መወዛገብ ውስጥ ሳለ ታዲያ አንድ ቀን የፖሊስን ሪፖርት ተመለከተ። ያየውን ማመን አቅቶት ደርቆ ቀረ። በዚህ ሪፖርት 8 ጥይት በጥቁሩ ሰው ላይ ከጀርባው የለቀቀበት ራሱን ለማዳን ነው ይላል። "ፖሊስ ያን ያደረኩት ሰውየው መሳሪያ ይዞ ስለነበረ ሕይወቴ ላይ አደጋ እንዳያደርስ ፈርቼ ነው" የሚል ነገር ሳነብ ደነገጥኩ፤ "በዚህ ጊዜ ውሳኔዬን ቀለበስኩ" ይላል ሳንታና። "በዚያ ጊዜ ይህን ጭልጥ ያለ ውሸት ለማጋለጥ በምድር ላይ ያለሁት ብቸኛው ሰው እኔ እንደሆንኩ አውቃለሁ፤ ፍርሃቴን ለመጋፈጥ ወሰንኩ" ይላል ለቢቢሲ። ሳንታና ጨክኖ ያን ቪዲዮ ወስዶ ለሟች ቤተሰብ አስረከበ። ቪዲዮው ፖሊስ መዋሸቱን አጋለጠ። "እኔ የቀረጽኩት ቪዲዮ በቅጽበት እንደ ሰደድ እሳት ይዛመታል አላልኩም ነበር" ይላል ሳንታና። ከዚያ ቪዲዮ በኋላ የሳንታና ሕይወት እስከ ወዲያኛው ተቀየረ። "የእንገድልሀለን ዛቻ፣ ዘረኛ ስድቦች ሁሉ ይዘንቡብኝ ጀመር። ፍርሃቴን ለመጋፈጥ እኔም ነገሩን መጋፈጥ ፈለኩ…" ዕድሜ ለሳንታናና ለዚያ ቪዲዮ የፖሊስ መኮንንኑ ሚስተር ስላገር ክስ ተመሰረተበት። ፍርድም አገኘ። "አንዳንድ ጊዜ ዝም ማለት የወንጀል ተባባሪነት ነው። ላመንኩበት ነገር መታገል ጀመርኩ። ፍርሃቴንም እያሸነፍኩ መምጣት ጀመርኩ" ይላል ሳንታና፤ ለቢቢሲ በሰጠው አስተያየት። ሞባይል ስልክና ኢንተርኔት በሌለበት ዘመን የተወለደው የፖሊስን ግፍ የማጋለጥ ተግባር ዛሬ ቀላል ሆኗል። በርካታ ሰዎች ግፍ የመሰላቸውን ተግባር በስልካቸው እየቀረጹ በማኅበራዊ ድረ አምባው ያጋራሉ። ይህም ወንጀሎች ቸል እንዳይባሉ፣ ማኅበረሰቡ በአካባቢው ለሚፈጠሩ ነገሮች ዐይኑን እንዲገልጥ ምክንያት ሆነዋል። ወንጀል ፈጻሚዎችም ግፍ ሲፈጽሙ ዓለም እየተመለከታቸው እንደሆነ ማገናዘብ ጀምረዋል። ለሀቀኛ መርማሪዎችም ነገሩ ሥራ አቅልሎላቸዋል። ለምሳሌ የጆርጅ ፍሎይድን ክስተት ከወጣቷ ዳርኔላ ስልክ ወስደው አስቀምጠውታል። "ወደፊት ደግሞ ዳርኔላ ፍርድ ቤት ቀርባ እንድትመሰክር መደረጉ አይቀርም" ይላሉ ጠበቃዋ ሚስተር ኮቢን። ምንም እንኳ ገና የ2ኛ ደረጃ ጀማሪ ተማሪ ብትሆንም ድርጊቱን በመቅረጽዋ ለአሜሪካ የምርመራ ቢሮ ቃሏን ሰጥታለች። ቃሏን በምትሰጥበት ወቅት የነበራት ስሜት በዚህ ድርጊት ውስጥ መሳተፍ ተራ ተግባር እንዳልሆነ ማሳያ ነው። ጠበቃዋ ዳርኔላ ቃሏን ስትሰጥ የነበረውን ሁኔታ በዚህ መልኩ ገልጸውታል። "ያለማቋረጥ ታለቅስ ነበር። የደረሰባት ነገር ከባድ ነው። ለመርማሪዎች እንደገለጸቸው በማንኛው ሰዓት ዐይኗን ስትጨፍን የሚመጣባት ምስል ፖሊስ ጆርጅ ፍሎይድን አንቆ ሲገድለው ነው። የሚሰማት ድምጽ 'እርዱኝ መተንፈስ አልቻልኩም' የሚለው ነው። ጆርጅ ፍሎይድ እየሞተ ሳለ የነበረው ፊቱ ይመጣባታል። ዐይኗን ስትገልጥ ግን ምስሉ የለም። ዐይኗን ስትጨፍን ጆርጅ ፍሎይድ ነው የሚታያት።" ወጣቷ ዳርኔላ በዚህ ጉዳይ ፍርድ ቤት ቀርባ ባትመሰክር ምርጫዋ ነው። ይህን ቪዲዮ በፌስቡክ ሰሌዳዋ ላይ ባትሰቅለው ትመርጥ ነበር። ምንም የመታወቅ ፍላጎት አልነበራትም። በዚህ ረገድ ጠበቃዋ ሚስተር ኮቢን ለቢቢሲ ያቀረበው የታሪክ ምስስሎሽ መጠቀስ የሚገባው ነው። "ዳርኔላ ልክ እንደ ሮዛ ፓርክስ ነው የሆነችው፤ ሮዛ ፓርክስ በ1955 ዓ.ም በአላባማ ባቡር ተሳፍራ ሳለ ወንበር ለነጭ እንድትለቅ ስትጠየቅ እምቢ አለች፡፡… ይህ ድርጊቷ በጥቁር መብት ትግል ታሪክ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ነው፡፡ ነገር ግን እርሷ ያን ስታደርግ ወደፊት ማን እንደምትሆን አላሰበችውም። ማርቲን ሉተር ኪንግን ወይም ማልኮም ኤክስን ለመሆን አልነበረም እምቢ አልነሳም ያለችው። በቃ በዚያ ሰዓትና ሁኔታ ለነጭ ወንበሯን መልቀቅ ትክክል እንዳልሆነ ተሰማት አደረገችውም፡፡ የእኔ ደንበኛ ዳርኔላም እንዲያ ናት። መጥፎ ተግባር አየች፤ ስልኳን አውጥታ ቀረጸች።" ዳርኔላስ ልጅ ናት፤ አንድ አዋቂ ሰው እየሞተ ያለን ሰው መርዳት ሲገባው ካሜራውን አውጥቶ ቢቀርጽ ድርጊቱ ጽድቅ ነው ኩነኔ?
የጆርጅ ፍሎይድን ሞት የቀረጸችው ሴት ምን አለች? ሰዎች ስለ ሟች ጆርጅ ፍሎይድ ያወራሉ። ሰዎች ስለ ጨካኙ ፖሊስ ዴሪክ ያወራሉ። ሰዎች ይህን ሁሉ ጉድ በስልኳ ቀርጻ ለዓለም ስላጋራችው አንዲት ትንሽ ልጅ ግን አያወሩም። የእርሷ የስልክ ቪዲዮ ባይኖር ዛሬ ስለ ጆርጅ ፍሎይድ የሚያወሩት ቤተሰቦቹ ብቻ በሆኑ ነበር። ማን ያውቃል? አንዳንድ ወንጀሎች ወንጀል የሚሆኑት ለአደባባይ ሲቀርቡ ነው። ስርቆት ሌብነት ሆኖ የሚያስከስሰው ሲደረስበት ብቻ ነው። በጆርጅ ፍሎይድ የደረሰው ሳይቀረጽ ቀርቶ ቢሆንስ? በዚህ ዘመን የማኅበራዊ ሚዲያ ጉልበት ኃያል ነው። ሰደድ እሳት ነው። ዓለምን ለማዳረስ ሰከንዶች ይበቁታል። አማዞን ጫካ ላይ የምትጫር ክብሪት…እንደማለት ነው። ዳርኔላ ፍሬዘር ገና 17 ዓመቷ ነው። ገና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መግባቷ ነው። የአክስቷን ልጅ ወደ ሰፈራቸው ምግብ ቤት ይዛት እየሄደች ነበር። የአክስቷ ልጅ ደግሞ ገና 9 ዓመቷ ነው፡። ልክ ምግብ ቤቱ አካባቢ ስትደርስ የሆነ ጥቁር ሰውዬ ፖሊሶች ሲያስጨንቁት አይታ ቆመች፤ ቆመችና እንደ ዋዛ ስልኳን ከኋላ ኪሷ መዘዝ አድርጋ አወጣች። 'ሪከርድ' የሚለውን ቀይ ምልክት ተጫነች። እርሷ መቅረጽ ስትጀምር ጆርጅ ፍሎይድ አየር አጥሮት ያቃስት ጀምሯል። "እባካችሁ! እባካችሁ" እያለ። የእርሱ እስትንፋስ እስከወዲያኛው ልትቋረጥ የመጨረሻ ቃሉ "I can't breathe," [መተንፍስ አልቻልኩም] ነበር። ይቺን "መተንፈስ አልቻልኩም" የምትለዋ ቃል ለመጨረሻ ጊዜ ከእስትንፋሱ ስትወጣ የዳርኔላ ስልክ ባትሪው አላለቀም። እርሷም መቅረጽ አላቆመችም። ከዚህ በኋላ ጆርጅ ፍሎይድ ምንም አላለም። እስከወዲያኛው አሸልቧል። የ44 ዓመቱ የፖሊስ መኮንን ዴሪክ ቾቪን ግን እጁን ኪሱ አድርጎ በጉልበቱ የፍሎይድን አንገት እንደተጫነው ነበር። ከዴሪክ ጋር ሦስት ፖሊሶችም ለዚህ ተግባሩ ተባባሪ ነበሩ። የ17 ዓመቷ ዳርኔላ ስልኳ መቅረጹን እንዲያቆም ያደረገችው ፖሊስ ዴሪክ በእግሩ ወደ ግራ፣ ጆርጅ ፍሎይድ በቃሬዛ ወደ ቀኝ ሲሄዱ ነበር። ዳርኔላ በድምሩ 10 ደቂቃ ከ9 ሰከንዶች ቀርጻለች። ድርጊቱን አጠናቃ ስልኳን ወደ ኪሷ ስትከት ግን በስልኳ ቋት ያኖረችው ተንቀሳቃሽ ምስል ዓለምን ሊንጥ እንደሚችል በፍጹም አልተከሰተላትም። በወቅቱ ምን እንዳደረገች፣ ምስሉ ከተሰራጨ በኋላ ምን እንደተሰማት ለቢቢሲ ለመናገር ፍቃደኛ አይደለችም። ለጊዜው ለቢቢሲም ሆነ ለሌላ ሚዲያ አስተያየት መስጠት ትታለች። ዕድሜዋም አንድ ምክንያት ይሆናል። የእርሷ ጠበቃ ሚስተር ኮቢን ግን ለምን ክስተቱን መቅረጽ እንደፈለገች ተጠይቀው ምላሽ ሰጥተዋል። "የዜግነት ግዴታዋን የመወጣት ስሜት ተሰምቷት ሊሆን ይችላል።" "ያም ሆነ ይህ በእርሷ ቪዲዮ የመብት ትግል እቅስቃሴ ድጋሚ ተወልዷል ብዬ አምናለሁ" ይላሉ ጠበቃዋ። የ2ኛ ደረጃ ተማሪዋ ዳርኔላ ከዚህ ክስተት በኋላ መጠነኛ የአእምሮ መታወክ ደርሶባት ሕክምና ጀምራለች። በሕይወቷ እንዲያ ያለ ሰቅጣጭ ነገር አይታ አታውቅም። ያን ቪዲዮ በፌስቡክ ሰሌዳዋ ላይ ከሰቀለችው በኋላ የነበረው ምላሽ በእርሷ ዕድሜ ለመቋቋም የሚቻል አልነበረም። በፖሊስ ድርጊት የተቆጡ እንዳሉ ሁሉ በእርሷ ድርጊት የተቆጡም ቁጥራቸው ትንሽ አልነበረም። ያመሰገኗት እንዳሉ ሁሉ "ጫካኝ፣ አውሬ" ሲሉ የሞለጯትም ጥቂት አይደሉም። የጆርጅ ፍሎይድ አሰቃቂ ሞት በግንቦት 25 ነበር፤ እርሷ ወደ ፌስቡክ ገጽ ያመራቸው ግን ከ2 ቀናት በኋላ በግንቦት 27 ነው። ወዲያውኑ እሳት ተቀጣጠለ። ነደደ፣ ጨሰ…። የእርሷ ቪዲዮ የእርሷ መሆኑ ቀረ። ሚሊዮኖች ቤት ገባ። መጀመርያ አካባቢ በፌስቡክ ሰሌዳዋ ስር ለተሰጧት አስተያየቶች ምላሽ ትሰጥ ነበር። አንዱ አስተያየት ሰጪ እርሷን ዝና ናፋቂ አድርጎ ይከሳታል። እንዲያ ባይሆን ኖሮ ሞባይልሽን አስቀምጠሸ የሚሞተውን ሰው ታድኚው ነበር ብሎ ይከሳታል። እርሷም ዝም አላለችም። የሚከተለውን መለሰችለት። "እኔ ያን ክስተት ባልቀርጽ ኖሮ፣ አራቱ ፖሊሶች ዛሬ በሥራ ላይ ነበሩ። ምናልባትም ሌላ ሰው እያነቁ…" ዳርኔላን 'ያን ያደረግሽው ዝና ፍለጋ ነው' የሚሏት ሰዎች ከምር ያበሳጯት። "ምን? ለዝና ነው ያደረግሽው ነው የምትሉኝ? ለገንዘብ ነው ያደረግሽ ነው የምትሉኝ? እናንተ ሰዎች ደደብና ደንቆሮዎች ሳትሆኑ አትቀሩም።" በዳርኔላ ላይ የደረሰው ትችት፤ አደጋ እየደረሰ ቪዲዮ መቅረጽ ጽድቅ ነው ኩነኔ የሚል ሌላ ዙር የክርክር ምዕራፍ ከፍቷል። ለመሆኑ እንዲህ ማድረግ ተገቢ ነው? በሞራል ሕግ እንዴት ይሰፈራል? ራስ ወደድነታችን ይሆን ሰው እየሞተ እኛ ቪዲዮ እንድንቀርጽ የሚያስችለን? በምንቀርጽበት ቅጽበት እየሞተ ላለው ሰው የምር ሐዘኔታ ይሰማናል? ነው ወይስ የሚያስጨንቀን በእኛ የሚቀረጸው የቪዲዮ ጥራትና ቀጥሎ የሚመጣው እውቅና? ዳርኔላ በእርሷ የተቀረጸው ተንቀሳቃሽ ምስል ዓለምን ከናጠ በኋላ ሽልማት አልጠበቃትም። እንዲያውም ነገሩ ሕይወቷን ረብሾታል። አሁን የአእምሮ ሐኪም እየተንከባከባት የሚገኘው ያለምክንያት አይደለም። ከዚህ ቀደም ቪዲዮ በመቅረጽ ወንጀል ያጋለጡም ቢሆኑ ሽልማት አልጠበቃቸውም። ሕይወታቸው በአንድም ይሁን በሌላ መንገድ ተረባብሿል። 1.ዴኒስ ፍሎረስ ይሄን ቪዲዮ እየቀረጹ የፖሊስን ጭካኔ ማጋለጥ የጀመረው ሰው ዴኒስ ፍሎረስ ሳይሆን አይቀርም። የኒው ዮርክ ሰው ነው። የኒው ዮርክ ከተማ ፖሊስን እንደሱ የቀረጸ የለም። ፖሊስ 70 ጊዜ አስሮታል። ከ90ዎቹ ጀምሮ እንደቀረጻቸው ነው ያለው። ዛሬ 'ፖሊስ አደብ ይግዛ፣ ዘረኝነቱን ይተው' የሚሉ እንቅስቃሴዎች እንዲጀመሩ ምክንያት የሆነው እርሱ ነው። ሞባይል ሳይጀመር እርሱ የፖሊስ ግፍ መቅረጽ ጀምሯል። ይህ ድርጊቱ ሕይወቱን እንዴት እንዳከበደው ወደኋላ ላይ ይነግረናል። ፍሎረስ የጀመረውን ተግባር ግን በብዙዎች ይተገበር ጀመር። 2.ቧንቧ ሠራተኛው ጆርጅ ሆሊዴይ ከፍሎረስ በኋላ በ1991 አካባቢ አንድ ጆርጅ ሆሊዴይ የሚባል የቧንቧ ሠራተኛ ከአፓርትመንቱ በርንዳ ላይ ሆኖ የቀረጸው ነገር ምናልባትም እንደ ወረርሽኝ የተዛመተ የመጀርመያ ቪዲዮ ሳይሆን አይቀርም። ያን ጊዜ እንደዛሬው ፌስቡክ የለ፣ ቅንጡ ሞባይል የለ! ምን የለ፣ ምን የለ! እርሱ ቀረጻ ያደረገውም በተለምዶ የልደት ካሜራ መቅረጫ በምንላት ትንሽ ሶኒ ቪዲዮ ካሜራ ነበር። ከበረንዳው ቀርጾ ያስቀረው ምስል ከባድ ውጤትን አስከተለ። በሎስ አንጀለስ ካሊፎርኒያ ሮድኒ ኪንግ የሚባልን አንድ ጥቁር ወጣት በርከት ያሉ ነጭ ፖሊሶች ከበውት እየተቀባበሉ ሲያዳፉት የሚያሳይ አሰቃቂ ቪዲዮ ነበር። ጆርጅ ሆሊዴይ ያን ጊዜ ይህን ክስተት ሲቀርጽ ሞባይል አልነበረም ብለናል። 5ጂ ኢንተርኔትም አልተፈጠረም፤ ፌስቡክ የለም። ታዲያ እንዴት ተዛመተ? ይህንን የቀረጸውን አሰቃቂ የቪዲዮ ቴፕ ወስዶ እዚያ ሰፈሩ ለሚገኝ ቴሌቪዥን ጣቢያ ሰጠ። ጣቢያው ተንቀሳቃሽ ምስሉን በዜና እወጃ ሰዓት ላይ አስተላለፈው፤ አገሪቱም በተቃውሞ ተናጠች። ከዓመት በኋላ ያንን ድርጊት የፈጸሙ ፖሊሶች ፍርድ ቤት ነጻ ናችሁ ሲላቸው ደግሞ ደም አፋሳሽ ተቃወሞ በመላው አሜሪካ ዳግም ተከሰተ። "ይሄ ሰው የቀረጸው ምስል ነው በአሜሪካ ምድር የፖሊስን ግፍ መቅረጽ እንዲለመድ ምክንያት የሆነው" ይላል በዚህ ተግባር ጥርሱን የነቀለው የኒው ዮርኩ ፍሎርስ፣ ለቢቢሲ። በአሜሪካ ሕገ መንግሥት ዜጎች በፖሊስ የሚፈጸምን ተግባር ቆመው የመቅረጽ መብት አላቸው። 3.ራምሴ ኦርታ ከዚህ ክስተት በኋላ የመጣው የኤሪክ ጋርነር ጉዳይ ነው። ሚስተር ጋርነር የ43 ዓመት ጥቁር አሜሪካዊ ነበር። በኒው ዮርክ ከተማ በ2014 ልክ እንደ ጆርጅ ፍሎይድ ሁሉ በነጭ ፖሊሶች አንገቱን ታንቆ ነበር የሞተው። ፖሊሶቹ አንገቱን አንቀው የያዙት የምትሸጣቸው ሲጃራዎች ሕጋዊ አይደሉም በሚል ምክንያት ነበር። ልክ እንደ ጆርጅ ፍሎይድ ሁሉ ሚስተር ጋርነርም ፖሊሶቹ አንገቱን ጠምልለው ሲያስጨንቁት፤ 'እባካችሁ መተንፈስ አቃተኝ፣ እባካችሁ!' እያለ ይጮኽ ነበር። "I can't breath" የሚለው ንግግርም የትግል መፈክር መሆን የጀመረው ከእርሱ በኋላ ነበር። በእርሱ የደረሰው የሞት አደጋ ፍርድ ቤት የነፍስ ማጥፋት ወንጀል ነው ቢልም ድርጊቱን የፈጸመው ፖሊስ ግን ነጻ ሆኗል። ያ ፖሊስ ስሙ ዳንኤል ፓንታሊዮ ይባል ነበር። ሟችና ገዳይን ለጊዜው ትተን ያን ድርጊት በቪዲዮ ስላስቀረው ሰው ትንሽ እናውራ። ራምሴ ኦርታ ይባላል። የእርሱ ጉዳይም እንደ ሌሎቹ ቀራጮች ሁሉ ሲያወዛግብ ነው የኖረው። "ይህን ክስተት ከቀረጽኩ በኋላ ፖሊሶች ሲከታተሉኝ ነው የኖርኩት" ብሏል ከዚህ በፊት በሰጠው አንድ ቃለ ምልልስ። በ2016 ራምሴ ኦርታ በአደገኛ እጽና በሕገ ወጥ መሳሪያ ዝውውር ክስ ተመሰረተበት። አራት ዓመትም ዘብጥያ ወረደ። እርግጥ ነው የተመሰረተበት ክስ የፖሊስን ድርጊት በቪዲዮ ከመቅረጽ ጋር የሚያገናኘው አንዳችም ነገር ባይኖርም ጓደኛው ሚስተር ፍሎረስ እንደሚያምነው ግን ፖሊስ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሲከታተለውና የሚታሰርበትን ሰበብ ሲፈልግለት፣ እንዲሁም ቀን ሲጠብቅለት ነበር። "ፖሊስን ማጋለጥ ለአደጋ መጋለጥ እንደሆነ ሊያስረዳ የሚችለው የራምሴ ኦርታ ጉዳይ ነው" ይላል ፍሎረስ። የሚገርመው ራምሴ ኦርታ ከእስሩ በኋላ ምነው ያን ጊዜ ፖሊስን ባልቀረጽኩ ኖሮ ሲል ተጸጽቷል። ያም ሆኖ ግፍ ሲፈጸም ዝም ብሎ ማለፍም ከባድ የሕሊና ጸጸት እንደሚተርፍ የፈይዲን ሳንታናን ታሪክ ማየት በቂ ነው። 4.ፈይዲን ሳንታና ፈይዲን ሳንታና በ2015 በሳውዝ ካሮላይና ግዛት፣ ቻርልስተን ከተማ ወደ ሥራ እየሄደ ነበር። አንድ ነጭ ፖሊስ ዋልተር ስኮት የሚባል አንድ ጥቁርን መኪናው ውስጥ ሳለ ሲያስቆመው ያያል። ነገሩ እንዲሁ ስላላማረው ወይም ልማድ ሆኖበት ይሆናል ስልኩን አውጥቶ መቅረጽ ይጀምራል። ፖሊሱ ትንሽ ዘወር ባለበት ቅጽበት ጥቁሩ ዋልተር ስኮት ድንገት ከመኪናው ወርዶ እግሬ አውጪኝ ይላል። ሳንታና ይህ ሁሉ ሲሆን በግማሽ ልብም ቢሆንም እየቀረጸው ነበር። በዚህ ቅጽበት ፖሊሱ ያደረገው ነገር ግን ፍጹም ያልጠበቀው ነበር። ፖሊሱ ሽጉጡን አውጥቶ እየሮጠ የነበረውን ጥቁሩን ዋልተር ስኮትን 8 ጥይቶችን ከጀርባ ለቀቀበት። አከታትሎ። ዋልተር ስኮት መሬት ላይ ወደቀ። ሳንታና እንደቀልድ የቀረጸው ነገር በኋላ ላይ ለከፍተኛ የአእምሮ መረበሽ ዳረገው። "ድንጋጤ ውስጥ የከተተኝ ምንም ያልታጠቀ አንድ ጥቁር ሰውዬ እንዲሁ ለማምለጥ ሲል ብቻ ስለሮጠ 8 ጥይት ከጀርባው ይዘንብበታል ብዬ አላሰብኩም ነበር" ብሏል ለቢቢሲ። ሳንታና ከዚህ ክስተት በኋላ ለሦሰት ቀናት ያህል ከቤት መውጣት አስጠላው። እርሱ ራሱ ስደተኛ ነው፣ በዚያ ላይ ከዶሚኒካን ሪፐብሊክ መጥቶ በፀጉር አስተካካይነት ነበር የሚተዳደረው። በስልኩ ያስቀረውን ነገር ለማንም አላሳየም። ለማንም አላጋራም። እንዲያ ቢያደርግ በኋላ ጣጣው ብዙ ነው ብሎ አሰበ። እንዲያውም ያስቀረውን ተንቀሳቃሽ ምስል እስከ ወዲያኛው ሊሰርዘውና ቻርለስተን ከተማን ጥሎ ለመሄድም አስቦ ነበር። በዚህ መወዛገብ ውስጥ ሳለ ታዲያ አንድ ቀን የፖሊስን ሪፖርት ተመለከተ። ያየውን ማመን አቅቶት ደርቆ ቀረ። በዚህ ሪፖርት 8 ጥይት በጥቁሩ ሰው ላይ ከጀርባው የለቀቀበት ራሱን ለማዳን ነው ይላል። "ፖሊስ ያን ያደረኩት ሰውየው መሳሪያ ይዞ ስለነበረ ሕይወቴ ላይ አደጋ እንዳያደርስ ፈርቼ ነው" የሚል ነገር ሳነብ ደነገጥኩ፤ "በዚህ ጊዜ ውሳኔዬን ቀለበስኩ" ይላል ሳንታና። "በዚያ ጊዜ ይህን ጭልጥ ያለ ውሸት ለማጋለጥ በምድር ላይ ያለሁት ብቸኛው ሰው እኔ እንደሆንኩ አውቃለሁ፤ ፍርሃቴን ለመጋፈጥ ወሰንኩ" ይላል ለቢቢሲ። ሳንታና ጨክኖ ያን ቪዲዮ ወስዶ ለሟች ቤተሰብ አስረከበ። ቪዲዮው ፖሊስ መዋሸቱን አጋለጠ። "እኔ የቀረጽኩት ቪዲዮ በቅጽበት እንደ ሰደድ እሳት ይዛመታል አላልኩም ነበር" ይላል ሳንታና። ከዚያ ቪዲዮ በኋላ የሳንታና ሕይወት እስከ ወዲያኛው ተቀየረ። "የእንገድልሀለን ዛቻ፣ ዘረኛ ስድቦች ሁሉ ይዘንቡብኝ ጀመር። ፍርሃቴን ለመጋፈጥ እኔም ነገሩን መጋፈጥ ፈለኩ…" ዕድሜ ለሳንታናና ለዚያ ቪዲዮ የፖሊስ መኮንንኑ ሚስተር ስላገር ክስ ተመሰረተበት። ፍርድም አገኘ። "አንዳንድ ጊዜ ዝም ማለት የወንጀል ተባባሪነት ነው። ላመንኩበት ነገር መታገል ጀመርኩ። ፍርሃቴንም እያሸነፍኩ መምጣት ጀመርኩ" ይላል ሳንታና፤ ለቢቢሲ በሰጠው አስተያየት። ሞባይል ስልክና ኢንተርኔት በሌለበት ዘመን የተወለደው የፖሊስን ግፍ የማጋለጥ ተግባር ዛሬ ቀላል ሆኗል። በርካታ ሰዎች ግፍ የመሰላቸውን ተግባር በስልካቸው እየቀረጹ በማኅበራዊ ድረ አምባው ያጋራሉ። ይህም ወንጀሎች ቸል እንዳይባሉ፣ ማኅበረሰቡ በአካባቢው ለሚፈጠሩ ነገሮች ዐይኑን እንዲገልጥ ምክንያት ሆነዋል። ወንጀል ፈጻሚዎችም ግፍ ሲፈጽሙ ዓለም እየተመለከታቸው እንደሆነ ማገናዘብ ጀምረዋል። ለሀቀኛ መርማሪዎችም ነገሩ ሥራ አቅልሎላቸዋል። ለምሳሌ የጆርጅ ፍሎይድን ክስተት ከወጣቷ ዳርኔላ ስልክ ወስደው አስቀምጠውታል። "ወደፊት ደግሞ ዳርኔላ ፍርድ ቤት ቀርባ እንድትመሰክር መደረጉ አይቀርም" ይላሉ ጠበቃዋ ሚስተር ኮቢን። ምንም እንኳ ገና የ2ኛ ደረጃ ጀማሪ ተማሪ ብትሆንም ድርጊቱን በመቅረጽዋ ለአሜሪካ የምርመራ ቢሮ ቃሏን ሰጥታለች። ቃሏን በምትሰጥበት ወቅት የነበራት ስሜት በዚህ ድርጊት ውስጥ መሳተፍ ተራ ተግባር እንዳልሆነ ማሳያ ነው። ጠበቃዋ ዳርኔላ ቃሏን ስትሰጥ የነበረውን ሁኔታ በዚህ መልኩ ገልጸውታል። "ያለማቋረጥ ታለቅስ ነበር። የደረሰባት ነገር ከባድ ነው። ለመርማሪዎች እንደገለጸቸው በማንኛው ሰዓት ዐይኗን ስትጨፍን የሚመጣባት ምስል ፖሊስ ጆርጅ ፍሎይድን አንቆ ሲገድለው ነው። የሚሰማት ድምጽ 'እርዱኝ መተንፈስ አልቻልኩም' የሚለው ነው። ጆርጅ ፍሎይድ እየሞተ ሳለ የነበረው ፊቱ ይመጣባታል። ዐይኗን ስትገልጥ ግን ምስሉ የለም። ዐይኗን ስትጨፍን ጆርጅ ፍሎይድ ነው የሚታያት።" ወጣቷ ዳርኔላ በዚህ ጉዳይ ፍርድ ቤት ቀርባ ባትመሰክር ምርጫዋ ነው። ይህን ቪዲዮ በፌስቡክ ሰሌዳዋ ላይ ባትሰቅለው ትመርጥ ነበር። ምንም የመታወቅ ፍላጎት አልነበራትም። በዚህ ረገድ ጠበቃዋ ሚስተር ኮቢን ለቢቢሲ ያቀረበው የታሪክ ምስስሎሽ መጠቀስ የሚገባው ነው። "ዳርኔላ ልክ እንደ ሮዛ ፓርክስ ነው የሆነችው፤ ሮዛ ፓርክስ በ1955 ዓ.ም በአላባማ ባቡር ተሳፍራ ሳለ ወንበር ለነጭ እንድትለቅ ስትጠየቅ እምቢ አለች፡፡… ይህ ድርጊቷ በጥቁር መብት ትግል ታሪክ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ነው፡፡ ነገር ግን እርሷ ያን ስታደርግ ወደፊት ማን እንደምትሆን አላሰበችውም። ማርቲን ሉተር ኪንግን ወይም ማልኮም ኤክስን ለመሆን አልነበረም እምቢ አልነሳም ያለችው። በቃ በዚያ ሰዓትና ሁኔታ ለነጭ ወንበሯን መልቀቅ ትክክል እንዳልሆነ ተሰማት አደረገችውም፡፡ የእኔ ደንበኛ ዳርኔላም እንዲያ ናት። መጥፎ ተግባር አየች፤ ስልኳን አውጥታ ቀረጸች።" ዳርኔላስ ልጅ ናት፤ አንድ አዋቂ ሰው እየሞተ ያለን ሰው መርዳት ሲገባው ካሜራውን አውጥቶ ቢቀርጽ ድርጊቱ ጽድቅ ነው ኩነኔ?
https://www.bbc.com/amharic/news-53004401
3politics
የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር በጦር ኃይሉ ተሹመው የነበሩ አስተዳዳሪዎችን አሰናበቱ
የሱዳን ጦር መፈንቅለ መንግሥት አካሂዶ ሹመት ሰጥቷቸው የነበሩ የክልል አስተዳዳሪዎችና ሚኒስትሮች በጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሃምዶክ ከኃላፊነታቸው ተሰናበቱ። ከመፈንቅለ መንግሥቱ በኋላ በቁም እስር ላይ የነበሩት እና ዳግም ወደ ሥልጣን የተመለሱት ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ከክልል አስተዳዳሪዎች በተጨማሪ በጦሩ ተሹመው የነበሩ ሚኒስትሮችንም አንስተዋል። አብደላ ሐምዶክ ከሥልጣን ያነሷቸው ሚኒስትሮች ከቀድሞው የሱዳን የረዥም ጊዜ መሪ ኦማር አል በሽር መንግሥት ጋር ቁርኝት የነበራቸው ናቸው ተብሏል። ከጥቂት ወራት በፊት የሱዳን ጦር በጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ የሚመራውን የሲቪል መንግሥት ገልብጦ ሥልጣን ተቆጣጥሮ እንደነበረ ይታወሳል። አብደላ ሐምዶክ ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ ወደ ሥልጣናቸው የተመለሱት በጄነራል አብድል ፈታ አል ቡርሐን ከሚመራው መፈንቅለ መንግሥት አድራጊ ኃይል ጋር ባደረጉት ስምምነት ነው። ጄነራል አል-ቡርሐን ወደ ሥልጣናቸው እንዲመለሱ ከተደረጉት የሲቪል መንግሥቱ መሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ጋር አብሮ ለመሥራት እና ምርጫ እስኪከናወን ድረስ አብደላ ሐምዶክ ለሚመሰርቱት የሽግግር መንግሥት ድጋፍ እንደሚሰጡ ገልጸዋል። ሱዳናውያን ግን የወታደራዊ ሥርዓቱ አሁንም በአገሪቱ የፖለቲካ ምኅዳር ውስጥ ያለው ሚና መቀጠሉ እንዳስቆጣቸው በመግለጽ ተጨማሪ የአደባባይ ላይ ተቃውሞዎች ይቀጥላሉ ተብሎ ይጠበቃል። ድምጻቸውን በአደባባይ ለማሰማት የሚወጡ ሰዎች በሱዳን ጦር መሪዎች ላይ ያላቸው ተቃውሞ እና ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ያላቸውን ድጋፍ ሲገልጹ ቆይተዋል። በጥቅምት ወር አጋማሽ ላይ ሠራዊቱ መፈንቅለ መንግሥት አካሂዶ የሲቪል አስተዳደሩን አመራሮች ከበተነና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከደነገገ በኋላ መፈንቅለ መንግሥቱን ተቃውመው አደባባይ ከወጡ መካከል ቢያንስ 40 የሚሆኑ ሰዎች ተገድለዋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ ምዕራባውያን አገራት እና የአፍሪካ ሕብረትን ጨምሮ በርካቶች መፈንቅለ መንግሥቱን በመቃወም፤ የአገሪቱ ዜጎች ሱዳን ወደ ሰላማዊ የዲሞክራሲ ሽግግር እንድትመለስ ድጋፍ እንዲያደርጉ ሲጠይቁ ነበር።
የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር በጦር ኃይሉ ተሹመው የነበሩ አስተዳዳሪዎችን አሰናበቱ የሱዳን ጦር መፈንቅለ መንግሥት አካሂዶ ሹመት ሰጥቷቸው የነበሩ የክልል አስተዳዳሪዎችና ሚኒስትሮች በጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሃምዶክ ከኃላፊነታቸው ተሰናበቱ። ከመፈንቅለ መንግሥቱ በኋላ በቁም እስር ላይ የነበሩት እና ዳግም ወደ ሥልጣን የተመለሱት ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ከክልል አስተዳዳሪዎች በተጨማሪ በጦሩ ተሹመው የነበሩ ሚኒስትሮችንም አንስተዋል። አብደላ ሐምዶክ ከሥልጣን ያነሷቸው ሚኒስትሮች ከቀድሞው የሱዳን የረዥም ጊዜ መሪ ኦማር አል በሽር መንግሥት ጋር ቁርኝት የነበራቸው ናቸው ተብሏል። ከጥቂት ወራት በፊት የሱዳን ጦር በጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ የሚመራውን የሲቪል መንግሥት ገልብጦ ሥልጣን ተቆጣጥሮ እንደነበረ ይታወሳል። አብደላ ሐምዶክ ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ ወደ ሥልጣናቸው የተመለሱት በጄነራል አብድል ፈታ አል ቡርሐን ከሚመራው መፈንቅለ መንግሥት አድራጊ ኃይል ጋር ባደረጉት ስምምነት ነው። ጄነራል አል-ቡርሐን ወደ ሥልጣናቸው እንዲመለሱ ከተደረጉት የሲቪል መንግሥቱ መሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ጋር አብሮ ለመሥራት እና ምርጫ እስኪከናወን ድረስ አብደላ ሐምዶክ ለሚመሰርቱት የሽግግር መንግሥት ድጋፍ እንደሚሰጡ ገልጸዋል። ሱዳናውያን ግን የወታደራዊ ሥርዓቱ አሁንም በአገሪቱ የፖለቲካ ምኅዳር ውስጥ ያለው ሚና መቀጠሉ እንዳስቆጣቸው በመግለጽ ተጨማሪ የአደባባይ ላይ ተቃውሞዎች ይቀጥላሉ ተብሎ ይጠበቃል። ድምጻቸውን በአደባባይ ለማሰማት የሚወጡ ሰዎች በሱዳን ጦር መሪዎች ላይ ያላቸው ተቃውሞ እና ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ያላቸውን ድጋፍ ሲገልጹ ቆይተዋል። በጥቅምት ወር አጋማሽ ላይ ሠራዊቱ መፈንቅለ መንግሥት አካሂዶ የሲቪል አስተዳደሩን አመራሮች ከበተነና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከደነገገ በኋላ መፈንቅለ መንግሥቱን ተቃውመው አደባባይ ከወጡ መካከል ቢያንስ 40 የሚሆኑ ሰዎች ተገድለዋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ ምዕራባውያን አገራት እና የአፍሪካ ሕብረትን ጨምሮ በርካቶች መፈንቅለ መንግሥቱን በመቃወም፤ የአገሪቱ ዜጎች ሱዳን ወደ ሰላማዊ የዲሞክራሲ ሽግግር እንድትመለስ ድጋፍ እንዲያደርጉ ሲጠይቁ ነበር።
https://www.bbc.com/amharic/news-59633484
2health
የአየር ንብረት ለውጥ ተላላፊ በሽታዎች የበለጠ እንዲስፋፉ ምክንያት እየሆነ ነው
ሳይንቲስቶች እንደሚሉት 50 በመቶ የሚሆኑትን የምድራችንን ተላላፊ በሽታዎች የሚያባብሰው የአየር ንብረት ለውጥ ነው። የአየር ንብረት ሞቃታማ መሆኑን ተከትሎ እንስሳት እና ትንኞች ከቦታ ቦታ ስለሚዘዋወሩ በሽታዎች በከፍተኛ ሁኔታ ይስፋፋሉ። ይህ ቪዲዮ የአየር ንበረት ለውጥና የተላላፊ በሽታዎችን መስፋፋት በተመለከተ በአጭሩ ይዳስሳል።
የአየር ንብረት ለውጥ ተላላፊ በሽታዎች የበለጠ እንዲስፋፉ ምክንያት እየሆነ ነው ሳይንቲስቶች እንደሚሉት 50 በመቶ የሚሆኑትን የምድራችንን ተላላፊ በሽታዎች የሚያባብሰው የአየር ንብረት ለውጥ ነው። የአየር ንብረት ሞቃታማ መሆኑን ተከትሎ እንስሳት እና ትንኞች ከቦታ ቦታ ስለሚዘዋወሩ በሽታዎች በከፍተኛ ሁኔታ ይስፋፋሉ። ይህ ቪዲዮ የአየር ንበረት ለውጥና የተላላፊ በሽታዎችን መስፋፋት በተመለከተ በአጭሩ ይዳስሳል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/ceqyqzg71y4o
3politics
በሙስና ሲከሰሱ የነበሩት ሲሪል ራማፎሳ በኤኤንሲ መሪነታቸው እንዲቀጥሉ ተመረጡ
በሙስና ክስ ሲብጠለጠሉ የነበሩት እና በፓርቲያቸው መሪነት ላይ ጥያቄ የተነሳባቸው የደብብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ በአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ (ኤኤንሲን) መሪነታቸው እንዲቀጥሉ የመተማመኛ ድምጽ አገኙ። ራማፎሳ ተፎካካሪያቸው የሆኑትን የቀድሞ የጤና ሚኒስትራቸው የነበሩትን ዝዌሊ ምኺዜን ያሸነፉት 2,476 ለ 1,897 በሆነ ድምጽ ነው። ፕሬዝዳንት ራማፎሳ የፓርቲው መሪነትን ያሸነፉት ባለፉት ሳምንታት ስማቸው በሙስና ሲነሳ ከሰነበተ በኋላ ነው። ተቀናቃኛቸውም በተመሳሳይ በሙስና የሚከሰሱ ቢሆንም ለመሪነት ቦታው ሲወዳደሩ ቀላል ያማይባል ድጋፍን አግኝተዋል። ሁለቱም ፖለቲከኞች ግን የሚቀርብባቸውን ክስ አይቀበሉትም። ሲሪል ራማፎሳ በኤኤንሲ የመሪነት መንበር ላይ ለመቀጠል መመረጣቸው ከሁለት ዓመት በኋላ በሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ ለመወዳደር ቀዳሚ ቦታ ላይ ያስቀምጣቸዋል። ነገር ግን ራማፎሳ አሁንም ከቤታቸው ሶፋ ውስጥ በሌቦች ተዘርፏል ስለተባለው 580,000 ዶላር ምንጭ ጋር በተያያዘ በፖሊስ ምርመራ ይደረግባቸዋል እየተባለ ነው። በአገሪቱ ፓርላማ አፈጉባኤ የተቋቋመው የሕግ ባለሙያዎች ቡድን ራማፎሳ ሕገ መንግሥቱን እና የፀረ ሙስና ሕግን በመጣስ ከሥልጣን የሚያስነሳ ክስ እንዲመሰረትባቸው ሃሳብ አቅርቦ ነበር። ነገር ግን ኤኤንሲ በፓርላማው ያለውን የበላይነት በመጠቀም የሕግ ባለሙያዎች ያቀረቡትን የውሳኔ ሃሳብ ውድቅ በማድረጉ ነው ለፓርቲው መሪነት የተወዳደሩት። የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ የገዢው ፓርቲ መሪ ሆኖ ለመቀጠል ከዝዌሊ ምኺዜ ብርቱ ፉክክር ነው የገጠማቸው። ፕሬዝዳንቱ ለገዢው የአፍሪካ ናሽናል ኮንግረስ (ኤኤንሲ) ፓርቲ መሪነት ጠንካራ ፉክክር የገጠማቸው ከሙስና ጋር በታያያዘ ሥልጣን እንዲልቁ ካስገደዷቸው ከቀድሞው የጤና ሚኒስትራቸው ዝዌሊ ምኺዜ ነው። የቀድሞ የጤና ሚኒስትር በጆሃንስበግ በተካሄደው የፓርቲው ጉባኤ በመጨረሻዎቹ ሰዓታት ላይ ከፍተኛ ድጋፍ ለማግኘት ችለው ነበር ተብሏል። ሁለቱ ዕጩዎች የኤኤንሲ መሪ ለመሆን እንዲችሉ 4 ሺህ 426 ተሳታፊዎች ከታደሙበት የፓርቲው ጉባኤ ድጋፍ ለማግኝት ተፎካክረዋል። ራማፎሳ በግል የእርሻ ስፍራቸው ላይ ባለ ቤት ውስጥ የተሰረቀ የውጭ አገር ገንዘብ ሶፋ ስር ተገኝቷል መባሉን ለመሸፋፈን ሞክረዋል በሚል ክስ ከፓርቲው ጉባኤ በፊት ከሥልጣን እንዲለቁ ጫና እየተደረገባቸው ነበር። በአገሪቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ በኩል የቀረበው ገለልተኛ ሪፖርት ራማፎሳ ሕግ ተላልፈው ሊሆን እንደሚችል አመልክተዋል። ሆኖም ፕሬዝዳንቱ የፈጸምኩት ነገር የለም ብለዋል። ባለፈው ማክሰኞ የገዢው የኤኤንሲ ፓርቲ የፓርላማ አባላት ራማፎሳን ከሥልጣን ለማስነሳት የሚደረገውን ጥረት ለፕሬዝዳንቱ ድጋፍ በመስጠት እንዲያከሽፉ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸው ነበር። ባለፈው አርብ የተወሰኑ የጉባኤው ተሳታፊዎች ራማፎሳን ሲቃመው እና ገንዘብ የተሰረቀበትን ፓላፓላ የተባለውን የእርሻ ቦታ ስያሜ በጽሁፍ ይዘው ታይተዋል። የማካዚህ ደጋፊዎች “ለውጥ” የጠየቁ ሲሆን ራማፎሳ “ተመልሶ አይመጣም” ሲሉ ተደምጠዋል። የቀድሞ የጤና ሚኒስትር በኮቪድ ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ አንድ የኮሚኒኬሽን ኩባንያ ከቤተሰባቸው ጋር በጥቅም የተሳሰረ ውል ፈጽሟል ከተባለ በኋላ ነበር ከሥልጣን ለመውረድ የተገደዱት። እሳቸው ግን ይህንን የቀረበባቸውን የሙስና ክስ አይቀበሉትም።
በሙስና ሲከሰሱ የነበሩት ሲሪል ራማፎሳ በኤኤንሲ መሪነታቸው እንዲቀጥሉ ተመረጡ በሙስና ክስ ሲብጠለጠሉ የነበሩት እና በፓርቲያቸው መሪነት ላይ ጥያቄ የተነሳባቸው የደብብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ በአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ (ኤኤንሲን) መሪነታቸው እንዲቀጥሉ የመተማመኛ ድምጽ አገኙ። ራማፎሳ ተፎካካሪያቸው የሆኑትን የቀድሞ የጤና ሚኒስትራቸው የነበሩትን ዝዌሊ ምኺዜን ያሸነፉት 2,476 ለ 1,897 በሆነ ድምጽ ነው። ፕሬዝዳንት ራማፎሳ የፓርቲው መሪነትን ያሸነፉት ባለፉት ሳምንታት ስማቸው በሙስና ሲነሳ ከሰነበተ በኋላ ነው። ተቀናቃኛቸውም በተመሳሳይ በሙስና የሚከሰሱ ቢሆንም ለመሪነት ቦታው ሲወዳደሩ ቀላል ያማይባል ድጋፍን አግኝተዋል። ሁለቱም ፖለቲከኞች ግን የሚቀርብባቸውን ክስ አይቀበሉትም። ሲሪል ራማፎሳ በኤኤንሲ የመሪነት መንበር ላይ ለመቀጠል መመረጣቸው ከሁለት ዓመት በኋላ በሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ ለመወዳደር ቀዳሚ ቦታ ላይ ያስቀምጣቸዋል። ነገር ግን ራማፎሳ አሁንም ከቤታቸው ሶፋ ውስጥ በሌቦች ተዘርፏል ስለተባለው 580,000 ዶላር ምንጭ ጋር በተያያዘ በፖሊስ ምርመራ ይደረግባቸዋል እየተባለ ነው። በአገሪቱ ፓርላማ አፈጉባኤ የተቋቋመው የሕግ ባለሙያዎች ቡድን ራማፎሳ ሕገ መንግሥቱን እና የፀረ ሙስና ሕግን በመጣስ ከሥልጣን የሚያስነሳ ክስ እንዲመሰረትባቸው ሃሳብ አቅርቦ ነበር። ነገር ግን ኤኤንሲ በፓርላማው ያለውን የበላይነት በመጠቀም የሕግ ባለሙያዎች ያቀረቡትን የውሳኔ ሃሳብ ውድቅ በማድረጉ ነው ለፓርቲው መሪነት የተወዳደሩት። የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ የገዢው ፓርቲ መሪ ሆኖ ለመቀጠል ከዝዌሊ ምኺዜ ብርቱ ፉክክር ነው የገጠማቸው። ፕሬዝዳንቱ ለገዢው የአፍሪካ ናሽናል ኮንግረስ (ኤኤንሲ) ፓርቲ መሪነት ጠንካራ ፉክክር የገጠማቸው ከሙስና ጋር በታያያዘ ሥልጣን እንዲልቁ ካስገደዷቸው ከቀድሞው የጤና ሚኒስትራቸው ዝዌሊ ምኺዜ ነው። የቀድሞ የጤና ሚኒስትር በጆሃንስበግ በተካሄደው የፓርቲው ጉባኤ በመጨረሻዎቹ ሰዓታት ላይ ከፍተኛ ድጋፍ ለማግኘት ችለው ነበር ተብሏል። ሁለቱ ዕጩዎች የኤኤንሲ መሪ ለመሆን እንዲችሉ 4 ሺህ 426 ተሳታፊዎች ከታደሙበት የፓርቲው ጉባኤ ድጋፍ ለማግኝት ተፎካክረዋል። ራማፎሳ በግል የእርሻ ስፍራቸው ላይ ባለ ቤት ውስጥ የተሰረቀ የውጭ አገር ገንዘብ ሶፋ ስር ተገኝቷል መባሉን ለመሸፋፈን ሞክረዋል በሚል ክስ ከፓርቲው ጉባኤ በፊት ከሥልጣን እንዲለቁ ጫና እየተደረገባቸው ነበር። በአገሪቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ በኩል የቀረበው ገለልተኛ ሪፖርት ራማፎሳ ሕግ ተላልፈው ሊሆን እንደሚችል አመልክተዋል። ሆኖም ፕሬዝዳንቱ የፈጸምኩት ነገር የለም ብለዋል። ባለፈው ማክሰኞ የገዢው የኤኤንሲ ፓርቲ የፓርላማ አባላት ራማፎሳን ከሥልጣን ለማስነሳት የሚደረገውን ጥረት ለፕሬዝዳንቱ ድጋፍ በመስጠት እንዲያከሽፉ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸው ነበር። ባለፈው አርብ የተወሰኑ የጉባኤው ተሳታፊዎች ራማፎሳን ሲቃመው እና ገንዘብ የተሰረቀበትን ፓላፓላ የተባለውን የእርሻ ቦታ ስያሜ በጽሁፍ ይዘው ታይተዋል። የማካዚህ ደጋፊዎች “ለውጥ” የጠየቁ ሲሆን ራማፎሳ “ተመልሶ አይመጣም” ሲሉ ተደምጠዋል። የቀድሞ የጤና ሚኒስትር በኮቪድ ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ አንድ የኮሚኒኬሽን ኩባንያ ከቤተሰባቸው ጋር በጥቅም የተሳሰረ ውል ፈጽሟል ከተባለ በኋላ ነበር ከሥልጣን ለመውረድ የተገደዱት። እሳቸው ግን ይህንን የቀረበባቸውን የሙስና ክስ አይቀበሉትም።
https://www.bbc.com/amharic/articles/crgzypzj4jpo
3politics
የዩክሬን የአውሮፓ ህብረት አባል የመሆን ጥያቄ አስርት አመታትን ይወስዳል ተባለ
ዩክሬን የአውሮፓ ህብረት አባል ለመሆን ያቀረበችው ጥያቄ አስርት አመታትን እንደሚወስድ የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አስታወቁ። ፕሬዚደንቱ በስትራስቡርግ ለአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ባደረጉት ንግግር ዩክሬን ውሳኔውን እየጠበቀች በምትኩ ወደ ትይዩው የአውሮፓ ማህበረሰብ ልትቀላቀል እንደምትችል ጠቁመዋል። ይህም ሁኔታ የአውሮፓ ህብረት አባል ያልሆኑ አገራት የአውሮፓን የደህንነት መዋቅር በሌላ መንገድ እንዲቀላቀሉ ያስችላቸዋል ብለዋል ፕሬዚዳንት ማክሮን። የፕሬዚዳንቱ ንግግር የተደመጠው ሩሲያ ምስራቃዊ ዶንባስን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ፍልሚያ እያደረገችበት ባለችበት ወቅት ነው። አንድ ከፍተኛ የአሜሪካ መከላከያ ባለስልጣን የሩሲያን ግስጋሴ "አንድ አሃዝ ያለው የኪሎ ሜትር እርምጃ" ሲሉ ገልጸውታል። በሉሃንስክ ግዛት የሚገኙ የዩክሬን ባለስልጣን በበኩላቸው ከባድ ጦርነቶች እየተካሄዱ መሆናቸውን ተናግረዋል። ዩክሬን ለአውሮፓ ህብረት አባልነት ጥያቄ ያቀረበችው በዚህ አመት የካቲት ወር ላይ ከሩሲያ አራት ቀናት ወረራ በኋላ ነው። "ዩክሬን የአውሮፓ ህብረት አባል እንድትሆን የመፍቀድ ሂደት ብዙ አመታትን ምናልባትም በርካታ አስርት ዓመታትን እንደሚወስድ ሁላችንም በሚገባ እናውቃለን" ብለዋል ፕሬዚዳንቱ። አክለውም " የአባልነት መስፈርቶችን ዝቅ ለማድረግ ካልወሰንን በስተቀር እውነታው ይህ ነው። የአውሮፓ አንድነትን በሌላ መልኩ ልናስበው ይገባል" ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ዩክሬንን የአውሮፓ ህብረት አባል ለማድረግ የአውሮፓ ህብረት ጥብቅ የአባልነት መስፈርቶችን ከማስተካከል ይልቅ "ትይዩ የአውሮፓ ማህበረሰብ" ሊታሰብበት እንደሚገባ ገልጸዋል። ይህ ትይዩ የአውሮፓ ማህበረሰብ "በአውሮፓ ውስጥ ያሉና የእኛን እሴቶች የሚጋሩትን አንድ ላይ የማምጣት መንገድ ነው" ብለዋል። የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ፎን ደር ሌር፣ በሰኔ ወር በዩክሬን የአውሮፓ ህብረት አባልነት ጥያቄ ላይ የህብረቱ ስራ አስፈጸሚ የመጀመሪያ ምላሹን በጽሁፍ ይሰጣል ብለው ነበር። የዩክሬን ባለስልጣናት ሰኞ እለት እንዳረጋገጡት ዩክሬን የአውሮፓ ህብረት የአባልነት ማመልከቻ ሁለተኛውን ጥያቄ ለብራሰልስ ማቅረቧን አስረድተዋል።
የዩክሬን የአውሮፓ ህብረት አባል የመሆን ጥያቄ አስርት አመታትን ይወስዳል ተባለ ዩክሬን የአውሮፓ ህብረት አባል ለመሆን ያቀረበችው ጥያቄ አስርት አመታትን እንደሚወስድ የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አስታወቁ። ፕሬዚደንቱ በስትራስቡርግ ለአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ባደረጉት ንግግር ዩክሬን ውሳኔውን እየጠበቀች በምትኩ ወደ ትይዩው የአውሮፓ ማህበረሰብ ልትቀላቀል እንደምትችል ጠቁመዋል። ይህም ሁኔታ የአውሮፓ ህብረት አባል ያልሆኑ አገራት የአውሮፓን የደህንነት መዋቅር በሌላ መንገድ እንዲቀላቀሉ ያስችላቸዋል ብለዋል ፕሬዚዳንት ማክሮን። የፕሬዚዳንቱ ንግግር የተደመጠው ሩሲያ ምስራቃዊ ዶንባስን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ፍልሚያ እያደረገችበት ባለችበት ወቅት ነው። አንድ ከፍተኛ የአሜሪካ መከላከያ ባለስልጣን የሩሲያን ግስጋሴ "አንድ አሃዝ ያለው የኪሎ ሜትር እርምጃ" ሲሉ ገልጸውታል። በሉሃንስክ ግዛት የሚገኙ የዩክሬን ባለስልጣን በበኩላቸው ከባድ ጦርነቶች እየተካሄዱ መሆናቸውን ተናግረዋል። ዩክሬን ለአውሮፓ ህብረት አባልነት ጥያቄ ያቀረበችው በዚህ አመት የካቲት ወር ላይ ከሩሲያ አራት ቀናት ወረራ በኋላ ነው። "ዩክሬን የአውሮፓ ህብረት አባል እንድትሆን የመፍቀድ ሂደት ብዙ አመታትን ምናልባትም በርካታ አስርት ዓመታትን እንደሚወስድ ሁላችንም በሚገባ እናውቃለን" ብለዋል ፕሬዚዳንቱ። አክለውም " የአባልነት መስፈርቶችን ዝቅ ለማድረግ ካልወሰንን በስተቀር እውነታው ይህ ነው። የአውሮፓ አንድነትን በሌላ መልኩ ልናስበው ይገባል" ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ዩክሬንን የአውሮፓ ህብረት አባል ለማድረግ የአውሮፓ ህብረት ጥብቅ የአባልነት መስፈርቶችን ከማስተካከል ይልቅ "ትይዩ የአውሮፓ ማህበረሰብ" ሊታሰብበት እንደሚገባ ገልጸዋል። ይህ ትይዩ የአውሮፓ ማህበረሰብ "በአውሮፓ ውስጥ ያሉና የእኛን እሴቶች የሚጋሩትን አንድ ላይ የማምጣት መንገድ ነው" ብለዋል። የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ፎን ደር ሌር፣ በሰኔ ወር በዩክሬን የአውሮፓ ህብረት አባልነት ጥያቄ ላይ የህብረቱ ስራ አስፈጸሚ የመጀመሪያ ምላሹን በጽሁፍ ይሰጣል ብለው ነበር። የዩክሬን ባለስልጣናት ሰኞ እለት እንዳረጋገጡት ዩክሬን የአውሮፓ ህብረት የአባልነት ማመልከቻ ሁለተኛውን ጥያቄ ለብራሰልስ ማቅረቧን አስረድተዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-61369470
3politics
በቻይና የሚደገፈው የአፍሪካ ቀንድ የሰላምና የደኅንነት ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ
በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ደኅንነት ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን የሚያደርግና የአካባቢውን አገራት የሚያሳትፍ በቻይና የሚደገፍ ስብሰባ ከዛሬ ሰኞ ጀምሮ በአዲስ አበባ ይጀመራል። ይህ በዓይነቱ የመጀመሪያው የሆነ ስብሰባ የተሰናዳው በቻይና መንግሥት ድጋፍ እንደሆነ ተነግሯል። ስብሰባው በቻይና መንግሥት ድጋፍ መደረጉ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቻይና በአካባቢው ሁነኛ ተጽዕኖ እንዲኖራት መፈለጓ እንደ አንድ ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል። ቻይና የአካባቢው ድኅንነት ሁኔታ ያሳሰባትም በእነዚህ አገራት ከፍ ያለ መዋዕለ ነዋይ በማፍሰሷ ነው የሚሉ አልጠፉም። በዚህ የሁለት ቀናት ኮንፈረንስ ከምሥራቅ አፍሪካ አገራት የሚወከሉ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ይገኙበታል ተብሎ ይጠበቃል። እነዚህ ብዙዎቹ አገራት በአህጉሪቱ ከፍተኛ የሚባል የቻይናን የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኙ ናቸው። የኮንፈረንሱ አሰናጅ ኢትዮጵያም ከቻይና መንግሥት ከፍተኛ የሚባል የገንዘብ ድጋፍ እና መዋዕለ ነዋይ የምታገኝ አገር ናት። ይሁንና ባለፉት ዓመታት በአገሪቱ እየተባባሰ የመጣው አለመረጋጋትና የእርስ በእርስ ጦርነት ቻይናን ሊያሳስብ የሚችል እንደሚሆን ተገምቷል። በያዝነው የፈረንጆች ዓመት መባቻ በኬንያ ጉብኝት ላይ የነበሩት የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ለሰላም በሚደረገው ጥረት አገራቸው “ትልቅ ሚና” መጫወት እንደምትፈልግ ተናግረው ነበር። ይህን ካሉ በኋላ ብዙም ሳይሰነብት ቤይጂንግ ባልተለመደ ሁኔታ ለአካባቢው ልዩ መልዕክተኛ መሰየሟ አይዘነጋም። ምንም እንኳ ዛሬ የሚጀመረውን ኮንፈረንስ በቻይና ድጋፍ የሆነ ቢሆንም በኢትዮጵያ ተዋጊ ወገኖችን ለማደራደር ቻይና ያሳየችው ይፋዊ ፍላጎት የለም ። ኮንፈረንሱ ቻይና በአካባቢው ያላትን የኢንቨስትመንትና የውጭ ፖሊሲ ፍላጎቶች እየጨመረ ስለመምጣቱ እንደ አንድ ማሳያ የወሰዱት አልጠፉም። ቻይና ለአፍሪቃ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የሾመችው ባለፈው የካቲት ወር ነበር። አንጋፋ ዲፕሎማት ናቸው የሚባሉት ዡ ቢንግ ለዚህ ሹመት ከመታጨታቸው በፊት በፓፓዎ ኒው ጊኒ አምባሳደር ሆነው ማገልገላቸው ተጠቅሷል። ያም ብቻ ሳይሆን ግለሰቡ አገራቸውን ወክለው በአፍሪካ፣ በአሜሪካና በኦሽኒያ በተለያዩ ኃላፊነቶች ላይ የሠሩ ናቸው። ቤይጂንግ በምሥራቅ አፍሪካ ሰፊ የሆነ ወታደራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፍላጎቶች ያሏት ሲሆን በጂቡቲ ያቋቋመችው ግዙፍ የባሕር ኃይል ሰፈርም የሚጠቀስ ነው። ከዚህ በተጨማሪም ቻይና ኢትዮጵያን ጨምሮ በቀጠናው ለሚገኙ አገራት ከፍተኛ መጠን ያለው ብድር ከመስጠቷ በተጨማሪ በአገራቱ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ታከናውናለች። በኢትዮጵያ ያለው የእርስ በእርስ ጦርነት፣ የደቡብ ሱዳን እና ሶማሊያ አስተማማኝ መረጋጋት ሊሰፍን አለመቻሉ እንዲሁም አሁንም እልባት ያላገኘው የሱዳን ፖለቲካዊ ቀውስ ለቀጠናው ደኅንነት ፈተና የሆኑ ጉዳዮች ናቸው። ከቻይና በተጨማሪ አሜሪካ እና የአውሮፓ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ አገራት ጉዳይን በቅርበት የሚከታተሉ ልዩ መልዕክተኞች እንዳሏቸው ይታወቃል።
በቻይና የሚደገፈው የአፍሪካ ቀንድ የሰላምና የደኅንነት ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ደኅንነት ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን የሚያደርግና የአካባቢውን አገራት የሚያሳትፍ በቻይና የሚደገፍ ስብሰባ ከዛሬ ሰኞ ጀምሮ በአዲስ አበባ ይጀመራል። ይህ በዓይነቱ የመጀመሪያው የሆነ ስብሰባ የተሰናዳው በቻይና መንግሥት ድጋፍ እንደሆነ ተነግሯል። ስብሰባው በቻይና መንግሥት ድጋፍ መደረጉ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቻይና በአካባቢው ሁነኛ ተጽዕኖ እንዲኖራት መፈለጓ እንደ አንድ ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል። ቻይና የአካባቢው ድኅንነት ሁኔታ ያሳሰባትም በእነዚህ አገራት ከፍ ያለ መዋዕለ ነዋይ በማፍሰሷ ነው የሚሉ አልጠፉም። በዚህ የሁለት ቀናት ኮንፈረንስ ከምሥራቅ አፍሪካ አገራት የሚወከሉ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ይገኙበታል ተብሎ ይጠበቃል። እነዚህ ብዙዎቹ አገራት በአህጉሪቱ ከፍተኛ የሚባል የቻይናን የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኙ ናቸው። የኮንፈረንሱ አሰናጅ ኢትዮጵያም ከቻይና መንግሥት ከፍተኛ የሚባል የገንዘብ ድጋፍ እና መዋዕለ ነዋይ የምታገኝ አገር ናት። ይሁንና ባለፉት ዓመታት በአገሪቱ እየተባባሰ የመጣው አለመረጋጋትና የእርስ በእርስ ጦርነት ቻይናን ሊያሳስብ የሚችል እንደሚሆን ተገምቷል። በያዝነው የፈረንጆች ዓመት መባቻ በኬንያ ጉብኝት ላይ የነበሩት የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ለሰላም በሚደረገው ጥረት አገራቸው “ትልቅ ሚና” መጫወት እንደምትፈልግ ተናግረው ነበር። ይህን ካሉ በኋላ ብዙም ሳይሰነብት ቤይጂንግ ባልተለመደ ሁኔታ ለአካባቢው ልዩ መልዕክተኛ መሰየሟ አይዘነጋም። ምንም እንኳ ዛሬ የሚጀመረውን ኮንፈረንስ በቻይና ድጋፍ የሆነ ቢሆንም በኢትዮጵያ ተዋጊ ወገኖችን ለማደራደር ቻይና ያሳየችው ይፋዊ ፍላጎት የለም ። ኮንፈረንሱ ቻይና በአካባቢው ያላትን የኢንቨስትመንትና የውጭ ፖሊሲ ፍላጎቶች እየጨመረ ስለመምጣቱ እንደ አንድ ማሳያ የወሰዱት አልጠፉም። ቻይና ለአፍሪቃ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የሾመችው ባለፈው የካቲት ወር ነበር። አንጋፋ ዲፕሎማት ናቸው የሚባሉት ዡ ቢንግ ለዚህ ሹመት ከመታጨታቸው በፊት በፓፓዎ ኒው ጊኒ አምባሳደር ሆነው ማገልገላቸው ተጠቅሷል። ያም ብቻ ሳይሆን ግለሰቡ አገራቸውን ወክለው በአፍሪካ፣ በአሜሪካና በኦሽኒያ በተለያዩ ኃላፊነቶች ላይ የሠሩ ናቸው። ቤይጂንግ በምሥራቅ አፍሪካ ሰፊ የሆነ ወታደራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፍላጎቶች ያሏት ሲሆን በጂቡቲ ያቋቋመችው ግዙፍ የባሕር ኃይል ሰፈርም የሚጠቀስ ነው። ከዚህ በተጨማሪም ቻይና ኢትዮጵያን ጨምሮ በቀጠናው ለሚገኙ አገራት ከፍተኛ መጠን ያለው ብድር ከመስጠቷ በተጨማሪ በአገራቱ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ታከናውናለች። በኢትዮጵያ ያለው የእርስ በእርስ ጦርነት፣ የደቡብ ሱዳን እና ሶማሊያ አስተማማኝ መረጋጋት ሊሰፍን አለመቻሉ እንዲሁም አሁንም እልባት ያላገኘው የሱዳን ፖለቲካዊ ቀውስ ለቀጠናው ደኅንነት ፈተና የሆኑ ጉዳዮች ናቸው። ከቻይና በተጨማሪ አሜሪካ እና የአውሮፓ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ አገራት ጉዳይን በቅርበት የሚከታተሉ ልዩ መልዕክተኞች እንዳሏቸው ይታወቃል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cnexwjz3xx8o
0business
5 ጥያቄዎች ለስድስት ኢትዮጵያውያን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ባለሙያ ሴቶች
አዲሱን ዓመት 2015 ዓ.ም. ምክንያት አድርገን በተለያየ የሳይንስ ዘርፍ ያሉ ስድስት ኢትዮጵያውያን ሴቶችን አምስት ጥያቄዎች ጠይቀናል። ዶ/ር ሶስና ኃይሌ- በአሜሪካ፣ ኢሊኖይ ግዛት፣ በኖርዝዌስተርን ዩኒቨርስቲ የማቴሪያልስ ሳይንስ እና ኢንጂነሪንግ ፕሮፌሰር እንዲሁም ኬሚስት በ2014 ዓ. ም. ባንቺ ሙያ ከተፈጠሩ ወይም ከተሠሩ መካከል ያስደነቀሽ የቱ ነው? ለምን? ሥራዬ ከኢነርጂ ሳይንስ ጋር ይገናኛል። ዋናው ትኩረቴ ደግሞ ኤሌክትሮኬሚካል ኢነርጂ ትራንስፎርመሮች ናቸው። በሙያዬ እጅግ ያስገረመኝ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ነው። ይህም አሜሪካ የሰው ልጅን ጨረቃ ላይ ከላከችበት የስኬት ታሪክ ጋር ተመሳሳይ ነው። የሕዳሴ ግድቡን ጨረቃ ላይ ከመውጣት የሚለየው ዓለምን በሳይንስ ከማሳመን አልፎ የአየር ንብረት ቀውስን ሳያባብስ በአፍሪካ ቀንድ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ከኃይል ድህነት (Energy Poverty) መንጭቆ ማውጣቱ ነው። በ2014 ዓ. ም. ካደረግሻቸው መካከል ትልቁ ስኬቴ የምትይው የቱን ነው? ያለፈው ዓመት ትልቁ ስኬቴ ከአሜሪካ የኢነርጂ ክፍል በተመደበ ገንዘብ የጥናት ቡድን አሰባስቤ ‘ኢነርጂ ፍሮንቲርስ ሪሰርች ሴንተር’ የተባለ የጥናት ማዕከል መቋቋሙ ነው። ሥራችን፣ ሀይድሮጅን ከጠጣር አካሎች ጋር ስለሚያደርገው ግንኙነት የዓለምን መረዳት የሚያሳድግ ነው። ለአራት ዓመት 10 ሚሊዮን ዶላር አግኝተናል። ጥናታችን፣ በኤሌክትሪካል ኢነርጂ አማካይነት ውሃን በመክፈል ሃይድሮጅን ለማምረት መሠረት ይጥላል። ለ2015 ዓ. ም. ምን አቅደሻል? ኧረ ዕቅዶቼ ብዙ ናቸው! ያለው ጊዜም አጭር ነው! ዕቅዶችሽን ያለ ተጨባጭ ግብ በአደባባይ መናገር ደግሞ ወደ ውድቀት ሊያመራም ይችላል። እኔና የጥናት ቡድኔ፣ ኤሌክትሪሲቲ በመጠቀም ውሃን ለመክፈል የሚደረገውን ጥረት የሚያደናቅፉ መሰናክሎችን መፍታት ነው ዕቅዳችን። ልክ እንደ ሕዳሴ ግድቡ፣ የኤሌክትሪክ ኃይልን ከካርበን ነጻ ከሆኑ ምንጮች ማመንጨት ነው ሐሳቡ። ኤሌክትሪኩን ኋላ ላይ ለመጠቀም ሀይድሮጅን ማምረት ቁልፉ ነው። በ2014 ዓ. ም. አንብበሻቸው ከወደዳቸው መጻሕፍት መካከል ሰዎች ቢያነቧቸው የምትያቸው ሦስት መጻሕፍት የትኞቹ ናቸው? ሦሰት ቢታዩ የምትያቸው ፊልሞችስ? አይ ምንም የለኝም! የዳንኤል ካህንማን “Thinking, Fast and Slow” ማንበብ ፈልጌ ነበር ግን ገና ጊዜ አግኝቼ አልጀመርኩትም። ካጠቃላይ ሳይንሳዊ ፈጠራዎች ወይም ግኝቶች የቱ ያስገርምሻል? ለምን? የዌብ ስፔስ ቴሌስኮፕ ምሥሎች እጹብ ድንቅ ናቸው። አስትሮፊዚሲስቶች 13.7 ቢሊዮን ዓመታት ወደኋላ ተጉዘው ማየት ችለዋል። እንዴት ወደዚች ምድር እንደመጣን ለማወቅ መመራመራችን ከሌሎች የምድራችን ፍጡራን የተለየን ያደርገናል። እነዚህ ስለጋላክሲዎች አፈጣጠር የሚነግሩን ምሥሎች አንዳች መንፈሳዊ ኃይል አላቸው። ምድራችንን ጠብቀን ለልጅ ልጆቻችን እንደምናወርስ ተስፋ አደርጋለሁ። ቤተልሔም ደሴ- የአይኮግ ኤኒዋን ካን ኮድ ዋና ኃላፊትና ኮምፒውተር ሳይንቲስት በ2014 ዓ. ም. ባንቺ ሙያ ከተፈጠሩ ወይም ከተሠሩ መካከል ያስደነቀሽ የቱ ነው? ለምን? ቃላት፣ ሐረግና ዓረፍተ ነገር ተሰጥቶት ወደ ምሥል የሚቀይረው አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (ሰው ሠራሽ ልኅቀት) አስደናቂ ነው። ኤአይ የሥዕል ውድድርም አሸንፏል። ይህ እውን ሆኖ ስናይ፣ ሳናስበው ወዴት እየሄድን ነው? የሚል ጥያቄም ያጭራል። በ2014 ዓ. ም. ካደረግሻቸው መካከል ትልቁ ስኬቴ የምትይው የቱን ነው? የ2014 ዓ. ም. ከፍታዬ ‘Rebel Girls’ የተባለው መጽሐፍ ላይ መውጣቴ ነው። ከድሮም የልጆች መጽሐፍ ላይ መውጣት አልም ነበር። እኔ ባለሁበት መጽሐፍ እነ ቢሊ አይሊሽ፣ እነ ቴይለር ስዊፊት አሉበት። ስለዚህ ይገዙታል ማለት ነው። ሲገዙት ደግሞ እነሱ ጋር ደረስኩ ማለት ነው። መጽሐፉ እስካሁን 5 ሚሊዮን ኮፒ ተሸጧል። ትልቁ የሰው ልጅ ከፍታ ሌሎች ሰዎችን ማነሳሳት ነው። ለ2015 ዓ. ም. ምን አቅደሻል? የ2015 ዓ. ም. ዕቅዴ ከ13 ዓመቴ ጀምሮ ያለምኩትን ማሳካት ነው። ይህም ተንቀሳቃሽ የኮምፒውተር ማዕከል  ነው። ‘ዲጂ ትራክ ኢትዮጵያ’ ይባላል። ይህም 40 ጫማ ኮንቴነር ሲሆን በፀሐይ ይሠራል። በየከተማው እየዞረ ኮዲንግ እና ሮቦቲክስ ያስተምራል። በጣም በጣም በጉጉት የምጠብቀው እሱን ነው። በ2014 ዓ. ም. አንብበሻቸው ከወደዳቸው መጻሕፍት መካከል ሰዎች ቢያነቧቸው የምትያቸው ሦስት መጻሕፍት የትኞቹ ናቸው? ሦሰት ቢታዩ የምትያቸው ፊልሞችስ? ቢነበቡ የምላቸው መጻሕፍት፡ Shoe Dog [ፊል ናይት] 21 Lessons for the 21st Century [ዮቫል ኖሀ ሀሪሪ] The Thing Around Your Neck [ቺማማንዳ ንጎዚ አዲቺ] ቢታዩ የምላቸው ፊልሞች ደግሞ The Gentlemen፣ Rick and Morty እና Love, Death & Robots ካጠቃላይ ሳይንሳዊ ፈጠራዎች ወይም ግኝቶች የቱ ያስገርምሸል? ለምን? ኢንተርኔት! ምንም ጥያቄ የለውም። ኢንተርኔትን የመሰለ ፈጠራኮ የለም። ሕይወት ለውጧል። የዕውቀት ሽግግርን አስችሏል። ተደራሽነቱ በመስፋቱና በመላው ዓለም በመዳረሱ በተለይም በወጣቶች ላይ ትልቅ ተጽዕኖ አለው። ዶ/ር ሩት ድሪባ- የላስት ማይል ኸልዝ ቴክኒካል አማካሪና የሕክምና ባለሙያ በ2014 ዓ. ም. ባንቺ ሙያ ከተፈጠሩ ወይም ከተሠሩ መካከል ያስደነቀሽ የቱ ነው? ለምን? ከመቶ ዓመታት በላይ ለወባ በሽታ ክትባት ለማግኘት ሲሞከር ነበር። ክትባቱ ተገኝቶ በቅርቡ ይፋ ተደርጓል። እስከ 80 በመቶ የወባ በሽታን የመከላከል አቅም ስላለው በበሽታው ሕይወታቸውን የሚያጡ ሕጻናትን ሞት ለመቀነስ ተስፋ ሰጥቷል። በ2014 ዓ. ም. በጣም ያስገረመኝ እና ተስፋ የሰጠኝም ግኝት ነው። በ2014 ዓ. ም. ካደረግሻቸው መካከል ትልቁ ስኬቴ የምትይው የቱን ነው? ትልቁ ስኬቴ፣ በዓይነቱ ልዩ ሆኖ ለመጀመሪያ ጊዜ በጤና ጥበቃ እንዲሁም በላስት ማይል ኸልዝ የተተገበረው ለጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች በዲጂታል ቴክኖሎጂ ሥልጠና የሚሰጥበት (Blended Learning) ዲዛይን እና ትግበራ ላይ መሳተፌ ነው። ለ2015 ዓ. ም. ምን አቅደሻል? እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ፣ በ2015 ዓ. ም. የሕጻናትን ጤና የሚያሻሽል ሥራ ላይ የመሳተፍ፣ ማኅበረሰቡን እንዲሁም የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎችን ያማከለ ሥራም የመሥራት እቅድ አለኝ። በ2014 ዓ. ም. አንብበሻቸው ከወደዳቸው መጻሕፍት መካከል ሰዎች ቢያነቧቸው የምትያቸው ሦስት መጻሕፍት የትኞቹ ናቸው? ሦሰት ቢታዩ የምትያቸው ፊልሞችስ? ቢነበቡ የምላቸው መጻሕፍት፡ Winning with People [ጆን ማክስዌል] The Checklist Manifesto [በአቱል ጋውንዴ] Our Iceberg is Melting [ሆልገር ራታግበር እና ጆን ኮተር] ቢታዩ የምላቸው ፊልሞች ደግሞ Fractured፣ Unforgivable እና Sweet girl ካጠቃላይ ሳይንሳዊ ፈጠራዎች ወይም ግኝቶች የቱ ያስገርምሻል? ለምን? የሚደንቀኝ ፈጠራ ክትባት ነው። በሽታን፣ በበሽታ አምጭ ተሕዋስ ወይም ባለው ንጥረ ነገር ሰውነትን አለማምዶ በሽታን እንዲከላከል ቀድሞ ማዘጋጀት እና ስቃይን ብሎም ሞትን መቀነስ በጣም ትልቅ ፈጠራ ነው። ብርሃን ታዬ- የቴክኖሎጂ ፖሊሲ አጥኚ እና ተንታኝ በ2014 ዓ. ም. ባንቺ ሙያ ከተፈጠሩ ወይም ከተሠሩ መካከል ያስደነቀሽ የቱ ነው? ለምን? ያስገረመኝ ዶትፕሎት (DotPlot) መተግበሪያ ነው። ይሄ መተግበሪያ ስልክ ላይ ተጭኖ ሴቶች የጡት ካንሰርን ቀድመው ማወቅ እንዲችሉ ጡታቸው ላይ የሚታይ ለውጥን ይከታተሉበታል። ገና በሕክምና ፈቃድ ሰጪዎች ይሁንታ እስከሚሰጠው እየጠበቀ ቢሆንም፣ እንዲህ ያለ መተግበሪያ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ሴቶች የጡት ካንሰርን እንዲከላከሉ ይረዳል። በ2014 ዓ. ም. ካደረግሻቸው መካከል ትልቁ ስኬቴ የምትይው የቱን ነው? ትልቁ የ2014 ዓ. ም. ስኬቴ በቋሚነት የአካል ብቃት እየሠራሁ 10 ኪሎ ሜትር መሮጤ ነው። ለ2015 ዓ. ም. ምን አቅደሻል? ዕቅዴ ዋጋ ከምሰጣቸው ሰዎች ጋር ውብ ጊዜ ማሳለፍና በበይነ መረብ ላይ የማሳልፈውን ጊዜ ቀንሼ ከሰዎች ጋር የበለጠ መነጋገር ነው። በ2014 ዓ. ም. አንብበሻቸው ከወደዳቸው መጻሕፍት መካከል ሰዎች ቢያነቧቸው የምትያቸው ሦስት መጻሕፍት የትኞቹ ናቸው? ሦሰት ቢታዩ የምትያቸው ፊልሞችስ? ቢነበቡ የምላቸው መጻሕፍት፡ Do Not Disturb: The Story of a Political Murder and an African Regime Gone Bad [ሚሼላ ሮንግ] Seven and a half Lessons about the Brain [ሊሳ ፌልድማን] Race after Technology [ሩሀ ቤንጃሚን] ፊቸር ፊልም እንኳን ብዙ አላይም። ግን ተከታታይ ፊልሞች ልጠቁም። እነዚህም Paper Girls፣ Veep እና The office ናቸው። ካጠቃላይ ሳይንሳዊ ፈጠራዎች ወይም ግኝቶች የቱ ያስገርምሻል? ለምን? ኅትመትን የሚበልጥ ፈጠራ ያለ አይመስለኝም። ሕይወት የሰጠን ኅትመት ነው። ቤተልሔም ላቀው- የሊሄም ኒውትሪሽን መሥራች፣ የቤኑ ፉድስ አጋር መሥራችና ኃላፊት፣ የአክት ፎር ፉድ አክት ፎር ቼንጅ ንቅናቄ መሪ እንዲሁም ኒውትሪሽኒስት በ2014 ዓ. ም. ባንቺ ሙያ ከተፈጠሩ ወይም ከተሠሩ መካከል ያስደነቀሽ የቱ ነው? ለምን? ኢትዮጵያ ውስጥ ስብ መምጠጥ [Fat Removal] ተጀምሯል። ይሄ ሂደት እኛ አገር እንዲህ በቅርብ ጊዜ ይገባል ብዬ አልገመትኩም ነበር። በጣም ነው ያስደነቀኝ። በ2014 ዓ. ም. ካደረግሻቸው መካከል ትልቁ ስኬቴ የምትይው የቱን ነው? የዓለም አቀፉ ‘አክት ፎር ፉድ አክት ፎር ቼንጅ’ ንቅናቄ የኢትዮጵያ ወጣቶች ተወካይ ሆኜ የተለያዩ ሥራዎችን እሠራ ነበር። 2014 ዓ. ም. በጣም ስኬታማ የሆንበት ነው። ለ2015 ዓ. ም. ምን አቅደሻል? ሊሄም በትንሽ ደረጃ ነበር የሚሠራው። በ2014 ዓ. ም. ግን አድጎ፣ ቢሮ ተከራይተን መሥራት ጀምረናል። ቢዝነሱ ከተጀመረ እንኳን ቆይቷል። እና በ2015 ዓ. ም. ከአጋሮቻችን ጋር ተጣምረን ወደ ክሊኒክ የማሳደግ ዕቅድ ይዘናል። በ2014 ዓ. ም. አንብበሻቸው ከወደዳቸው መጻሕፍት መካከል ሰዎች ቢያነቧቸው የምትያቸው ሦስት መጻሕፍት የትኞቹ ናቸው? ሦሰት ቢታዩ የምትያቸው ፊልሞችስ? ቢነበቡ የምላቸው መጻሕፍት፡ ትንሿ ቤተክርስቲያን [ገብረእግዚአብሔር ኪዳን] Zero to One [ፒተር ታይል] ሕክምና በቤታችን [በቀለች ቶላ] ፊልም እንኳን አላይም። በምትኩ ቢጎበኙ ብዬ የማስባቸውን ሦስት ቦታዎች ልንገርሽ። ላሊበላ፣ አክሱም እና የሩዋንዳው ‘ኪጋሊ ጄኖሳይድ ሜሞሪያል’ ካጠቃላይ ሳይንሳዊ ፈጠራዎች ወይም ግኝቶች የቱ ያስገርምሻል? ለምን? የኢንዶስኮፒ ምርመራ መደረግ መቻሉ ያስገርመኛል። በእርግጥ ውስብስብ ሳይንስ አይደለም። አሁን ባለው መሣሪያ በቀላሉ የትኛውም ሆስፒታል ውስጥ ሊሠራ ይችላል። አንድን ግለሰብ ሳናፈርሰው ስላለበት ሂደት እንድናውቅ ያስችላል። የላብራቶሪ ምርመራና የደም ሕዋስ ማየት መቻል አሁን ላለንበት ዘመን ትልቅ ግኝት ነው። ሕሊና ኃይሉ ንጋቱ- በአሜሪካ ዩኒቨርስቲ ኦፍ ካሊፎርኒያ፣ በርክሌ የኮምፒውተር ሳይንስ የፒኤችዲ ሁለተኛ ዓመት ተማሪ በ2014 ዓ. ም. ባንቺ ሙያ ከተፈጠሩ ወይም ከተሠሩ መካከል ያስደነቀሽ የቱ ነው? ለምን? በ2014 ዓ. ም. ካስደመሙኝ ፈጠራዎች አንዱ በኤአይ ሞዴል የሚፈጠሩ ምሥሎች የጥራት ደረጃ ነው። እነዚህ ሞዴሎች በስፋት ጥቅም ላይ ይውላሉ። በአንድ በኩል እንደ ቤኖ ሳሙኤል ያሉ ባለሙያዎች በቴክኖሎጂ የታገዘ ሥነ ጥበብ ሲሠሩ ያስገርመኛል። በሌላ በኩል ደግሞ ተገቢው ቁጥጥር ያልተደረገበት ቴክኖሎጂ ጉዳቱ ያሰጋኛል። በ2014 ዓ. ም. ካደረግሻቸው መካከል ትልቁ ስኬቴ የምትይው የቱን ነው? ትልቁ ስኬቴ በአሶሴሽን ፎር ኮምፒውቲንግ ማሽነሪ ተቋም የኮምፒውቴሽናል እና ዳታ ሳይንስ ፌሎሺፕ ማሸነፌ ነው። ለ2015 ዓ. ም. ምን አቅደሻል? በ2015 ዓ. ም. በዩሲ በርክሌይ ዩኒቨርስቲ ሁለተኛ ዓመት ፒኤችዲ ትምህርቴን እከታተላለሁ። ዕቅዴም ከአፍሪካውያን አጋሮቼ ጋር ተጣምሬ ማኅበረሰባችንን የሚጠቅም ሥራ ማከናወን ነው። በ2014 ዓ. ም. አንብበሻቸው ከወደዳቸው መጻሕፍት መካከል ሰዎች ቢያነቧቸው የምትያቸው ሦስት መጻሕፍት የትኞቹ ናቸው? ሦሰት ቢታዩ የምትያቸው ፊልሞችስ? ቢነበቡ የምላቸው መጻሕፍት፡ All about Love [ቤል ሁክስ] Race After Technology [ሩሀ ቤንጃሚን] Shadow King [መዓዛ መንግሥቴ ] ቢታዩ የምላቸው ፊልሞች Queen of Katwe፣ Us እና እረኛዬ ካጠቃላይ ሳይንሳዊ ፈጠራዎች ወይም ግኝቶች የቱ ያስገርምሻል? ለምን? አንድ ፈጠራ መምረጥ ካለብኝ፣ የተለያዩ የሰውነት አካላትን በቀዶ ሕክምና መለወጥ (Organ Transplant) ይደንቀኛል። ለምን? የሚለው ግልጽ ነው። የሰዎችን ሕይወት ስለሚያተርፍ።
5 ጥያቄዎች ለስድስት ኢትዮጵያውያን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ባለሙያ ሴቶች አዲሱን ዓመት 2015 ዓ.ም. ምክንያት አድርገን በተለያየ የሳይንስ ዘርፍ ያሉ ስድስት ኢትዮጵያውያን ሴቶችን አምስት ጥያቄዎች ጠይቀናል። ዶ/ር ሶስና ኃይሌ- በአሜሪካ፣ ኢሊኖይ ግዛት፣ በኖርዝዌስተርን ዩኒቨርስቲ የማቴሪያልስ ሳይንስ እና ኢንጂነሪንግ ፕሮፌሰር እንዲሁም ኬሚስት በ2014 ዓ. ም. ባንቺ ሙያ ከተፈጠሩ ወይም ከተሠሩ መካከል ያስደነቀሽ የቱ ነው? ለምን? ሥራዬ ከኢነርጂ ሳይንስ ጋር ይገናኛል። ዋናው ትኩረቴ ደግሞ ኤሌክትሮኬሚካል ኢነርጂ ትራንስፎርመሮች ናቸው። በሙያዬ እጅግ ያስገረመኝ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ነው። ይህም አሜሪካ የሰው ልጅን ጨረቃ ላይ ከላከችበት የስኬት ታሪክ ጋር ተመሳሳይ ነው። የሕዳሴ ግድቡን ጨረቃ ላይ ከመውጣት የሚለየው ዓለምን በሳይንስ ከማሳመን አልፎ የአየር ንብረት ቀውስን ሳያባብስ በአፍሪካ ቀንድ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ከኃይል ድህነት (Energy Poverty) መንጭቆ ማውጣቱ ነው። በ2014 ዓ. ም. ካደረግሻቸው መካከል ትልቁ ስኬቴ የምትይው የቱን ነው? ያለፈው ዓመት ትልቁ ስኬቴ ከአሜሪካ የኢነርጂ ክፍል በተመደበ ገንዘብ የጥናት ቡድን አሰባስቤ ‘ኢነርጂ ፍሮንቲርስ ሪሰርች ሴንተር’ የተባለ የጥናት ማዕከል መቋቋሙ ነው። ሥራችን፣ ሀይድሮጅን ከጠጣር አካሎች ጋር ስለሚያደርገው ግንኙነት የዓለምን መረዳት የሚያሳድግ ነው። ለአራት ዓመት 10 ሚሊዮን ዶላር አግኝተናል። ጥናታችን፣ በኤሌክትሪካል ኢነርጂ አማካይነት ውሃን በመክፈል ሃይድሮጅን ለማምረት መሠረት ይጥላል። ለ2015 ዓ. ም. ምን አቅደሻል? ኧረ ዕቅዶቼ ብዙ ናቸው! ያለው ጊዜም አጭር ነው! ዕቅዶችሽን ያለ ተጨባጭ ግብ በአደባባይ መናገር ደግሞ ወደ ውድቀት ሊያመራም ይችላል። እኔና የጥናት ቡድኔ፣ ኤሌክትሪሲቲ በመጠቀም ውሃን ለመክፈል የሚደረገውን ጥረት የሚያደናቅፉ መሰናክሎችን መፍታት ነው ዕቅዳችን። ልክ እንደ ሕዳሴ ግድቡ፣ የኤሌክትሪክ ኃይልን ከካርበን ነጻ ከሆኑ ምንጮች ማመንጨት ነው ሐሳቡ። ኤሌክትሪኩን ኋላ ላይ ለመጠቀም ሀይድሮጅን ማምረት ቁልፉ ነው። በ2014 ዓ. ም. አንብበሻቸው ከወደዳቸው መጻሕፍት መካከል ሰዎች ቢያነቧቸው የምትያቸው ሦስት መጻሕፍት የትኞቹ ናቸው? ሦሰት ቢታዩ የምትያቸው ፊልሞችስ? አይ ምንም የለኝም! የዳንኤል ካህንማን “Thinking, Fast and Slow” ማንበብ ፈልጌ ነበር ግን ገና ጊዜ አግኝቼ አልጀመርኩትም። ካጠቃላይ ሳይንሳዊ ፈጠራዎች ወይም ግኝቶች የቱ ያስገርምሻል? ለምን? የዌብ ስፔስ ቴሌስኮፕ ምሥሎች እጹብ ድንቅ ናቸው። አስትሮፊዚሲስቶች 13.7 ቢሊዮን ዓመታት ወደኋላ ተጉዘው ማየት ችለዋል። እንዴት ወደዚች ምድር እንደመጣን ለማወቅ መመራመራችን ከሌሎች የምድራችን ፍጡራን የተለየን ያደርገናል። እነዚህ ስለጋላክሲዎች አፈጣጠር የሚነግሩን ምሥሎች አንዳች መንፈሳዊ ኃይል አላቸው። ምድራችንን ጠብቀን ለልጅ ልጆቻችን እንደምናወርስ ተስፋ አደርጋለሁ። ቤተልሔም ደሴ- የአይኮግ ኤኒዋን ካን ኮድ ዋና ኃላፊትና ኮምፒውተር ሳይንቲስት በ2014 ዓ. ም. ባንቺ ሙያ ከተፈጠሩ ወይም ከተሠሩ መካከል ያስደነቀሽ የቱ ነው? ለምን? ቃላት፣ ሐረግና ዓረፍተ ነገር ተሰጥቶት ወደ ምሥል የሚቀይረው አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (ሰው ሠራሽ ልኅቀት) አስደናቂ ነው። ኤአይ የሥዕል ውድድርም አሸንፏል። ይህ እውን ሆኖ ስናይ፣ ሳናስበው ወዴት እየሄድን ነው? የሚል ጥያቄም ያጭራል። በ2014 ዓ. ም. ካደረግሻቸው መካከል ትልቁ ስኬቴ የምትይው የቱን ነው? የ2014 ዓ. ም. ከፍታዬ ‘Rebel Girls’ የተባለው መጽሐፍ ላይ መውጣቴ ነው። ከድሮም የልጆች መጽሐፍ ላይ መውጣት አልም ነበር። እኔ ባለሁበት መጽሐፍ እነ ቢሊ አይሊሽ፣ እነ ቴይለር ስዊፊት አሉበት። ስለዚህ ይገዙታል ማለት ነው። ሲገዙት ደግሞ እነሱ ጋር ደረስኩ ማለት ነው። መጽሐፉ እስካሁን 5 ሚሊዮን ኮፒ ተሸጧል። ትልቁ የሰው ልጅ ከፍታ ሌሎች ሰዎችን ማነሳሳት ነው። ለ2015 ዓ. ም. ምን አቅደሻል? የ2015 ዓ. ም. ዕቅዴ ከ13 ዓመቴ ጀምሮ ያለምኩትን ማሳካት ነው። ይህም ተንቀሳቃሽ የኮምፒውተር ማዕከል  ነው። ‘ዲጂ ትራክ ኢትዮጵያ’ ይባላል። ይህም 40 ጫማ ኮንቴነር ሲሆን በፀሐይ ይሠራል። በየከተማው እየዞረ ኮዲንግ እና ሮቦቲክስ ያስተምራል። በጣም በጣም በጉጉት የምጠብቀው እሱን ነው። በ2014 ዓ. ም. አንብበሻቸው ከወደዳቸው መጻሕፍት መካከል ሰዎች ቢያነቧቸው የምትያቸው ሦስት መጻሕፍት የትኞቹ ናቸው? ሦሰት ቢታዩ የምትያቸው ፊልሞችስ? ቢነበቡ የምላቸው መጻሕፍት፡ Shoe Dog [ፊል ናይት] 21 Lessons for the 21st Century [ዮቫል ኖሀ ሀሪሪ] The Thing Around Your Neck [ቺማማንዳ ንጎዚ አዲቺ] ቢታዩ የምላቸው ፊልሞች ደግሞ The Gentlemen፣ Rick and Morty እና Love, Death & Robots ካጠቃላይ ሳይንሳዊ ፈጠራዎች ወይም ግኝቶች የቱ ያስገርምሸል? ለምን? ኢንተርኔት! ምንም ጥያቄ የለውም። ኢንተርኔትን የመሰለ ፈጠራኮ የለም። ሕይወት ለውጧል። የዕውቀት ሽግግርን አስችሏል። ተደራሽነቱ በመስፋቱና በመላው ዓለም በመዳረሱ በተለይም በወጣቶች ላይ ትልቅ ተጽዕኖ አለው። ዶ/ር ሩት ድሪባ- የላስት ማይል ኸልዝ ቴክኒካል አማካሪና የሕክምና ባለሙያ በ2014 ዓ. ም. ባንቺ ሙያ ከተፈጠሩ ወይም ከተሠሩ መካከል ያስደነቀሽ የቱ ነው? ለምን? ከመቶ ዓመታት በላይ ለወባ በሽታ ክትባት ለማግኘት ሲሞከር ነበር። ክትባቱ ተገኝቶ በቅርቡ ይፋ ተደርጓል። እስከ 80 በመቶ የወባ በሽታን የመከላከል አቅም ስላለው በበሽታው ሕይወታቸውን የሚያጡ ሕጻናትን ሞት ለመቀነስ ተስፋ ሰጥቷል። በ2014 ዓ. ም. በጣም ያስገረመኝ እና ተስፋ የሰጠኝም ግኝት ነው። በ2014 ዓ. ም. ካደረግሻቸው መካከል ትልቁ ስኬቴ የምትይው የቱን ነው? ትልቁ ስኬቴ፣ በዓይነቱ ልዩ ሆኖ ለመጀመሪያ ጊዜ በጤና ጥበቃ እንዲሁም በላስት ማይል ኸልዝ የተተገበረው ለጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች በዲጂታል ቴክኖሎጂ ሥልጠና የሚሰጥበት (Blended Learning) ዲዛይን እና ትግበራ ላይ መሳተፌ ነው። ለ2015 ዓ. ም. ምን አቅደሻል? እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ፣ በ2015 ዓ. ም. የሕጻናትን ጤና የሚያሻሽል ሥራ ላይ የመሳተፍ፣ ማኅበረሰቡን እንዲሁም የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎችን ያማከለ ሥራም የመሥራት እቅድ አለኝ። በ2014 ዓ. ም. አንብበሻቸው ከወደዳቸው መጻሕፍት መካከል ሰዎች ቢያነቧቸው የምትያቸው ሦስት መጻሕፍት የትኞቹ ናቸው? ሦሰት ቢታዩ የምትያቸው ፊልሞችስ? ቢነበቡ የምላቸው መጻሕፍት፡ Winning with People [ጆን ማክስዌል] The Checklist Manifesto [በአቱል ጋውንዴ] Our Iceberg is Melting [ሆልገር ራታግበር እና ጆን ኮተር] ቢታዩ የምላቸው ፊልሞች ደግሞ Fractured፣ Unforgivable እና Sweet girl ካጠቃላይ ሳይንሳዊ ፈጠራዎች ወይም ግኝቶች የቱ ያስገርምሻል? ለምን? የሚደንቀኝ ፈጠራ ክትባት ነው። በሽታን፣ በበሽታ አምጭ ተሕዋስ ወይም ባለው ንጥረ ነገር ሰውነትን አለማምዶ በሽታን እንዲከላከል ቀድሞ ማዘጋጀት እና ስቃይን ብሎም ሞትን መቀነስ በጣም ትልቅ ፈጠራ ነው። ብርሃን ታዬ- የቴክኖሎጂ ፖሊሲ አጥኚ እና ተንታኝ በ2014 ዓ. ም. ባንቺ ሙያ ከተፈጠሩ ወይም ከተሠሩ መካከል ያስደነቀሽ የቱ ነው? ለምን? ያስገረመኝ ዶትፕሎት (DotPlot) መተግበሪያ ነው። ይሄ መተግበሪያ ስልክ ላይ ተጭኖ ሴቶች የጡት ካንሰርን ቀድመው ማወቅ እንዲችሉ ጡታቸው ላይ የሚታይ ለውጥን ይከታተሉበታል። ገና በሕክምና ፈቃድ ሰጪዎች ይሁንታ እስከሚሰጠው እየጠበቀ ቢሆንም፣ እንዲህ ያለ መተግበሪያ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ሴቶች የጡት ካንሰርን እንዲከላከሉ ይረዳል። በ2014 ዓ. ም. ካደረግሻቸው መካከል ትልቁ ስኬቴ የምትይው የቱን ነው? ትልቁ የ2014 ዓ. ም. ስኬቴ በቋሚነት የአካል ብቃት እየሠራሁ 10 ኪሎ ሜትር መሮጤ ነው። ለ2015 ዓ. ም. ምን አቅደሻል? ዕቅዴ ዋጋ ከምሰጣቸው ሰዎች ጋር ውብ ጊዜ ማሳለፍና በበይነ መረብ ላይ የማሳልፈውን ጊዜ ቀንሼ ከሰዎች ጋር የበለጠ መነጋገር ነው። በ2014 ዓ. ም. አንብበሻቸው ከወደዳቸው መጻሕፍት መካከል ሰዎች ቢያነቧቸው የምትያቸው ሦስት መጻሕፍት የትኞቹ ናቸው? ሦሰት ቢታዩ የምትያቸው ፊልሞችስ? ቢነበቡ የምላቸው መጻሕፍት፡ Do Not Disturb: The Story of a Political Murder and an African Regime Gone Bad [ሚሼላ ሮንግ] Seven and a half Lessons about the Brain [ሊሳ ፌልድማን] Race after Technology [ሩሀ ቤንጃሚን] ፊቸር ፊልም እንኳን ብዙ አላይም። ግን ተከታታይ ፊልሞች ልጠቁም። እነዚህም Paper Girls፣ Veep እና The office ናቸው። ካጠቃላይ ሳይንሳዊ ፈጠራዎች ወይም ግኝቶች የቱ ያስገርምሻል? ለምን? ኅትመትን የሚበልጥ ፈጠራ ያለ አይመስለኝም። ሕይወት የሰጠን ኅትመት ነው። ቤተልሔም ላቀው- የሊሄም ኒውትሪሽን መሥራች፣ የቤኑ ፉድስ አጋር መሥራችና ኃላፊት፣ የአክት ፎር ፉድ አክት ፎር ቼንጅ ንቅናቄ መሪ እንዲሁም ኒውትሪሽኒስት በ2014 ዓ. ም. ባንቺ ሙያ ከተፈጠሩ ወይም ከተሠሩ መካከል ያስደነቀሽ የቱ ነው? ለምን? ኢትዮጵያ ውስጥ ስብ መምጠጥ [Fat Removal] ተጀምሯል። ይሄ ሂደት እኛ አገር እንዲህ በቅርብ ጊዜ ይገባል ብዬ አልገመትኩም ነበር። በጣም ነው ያስደነቀኝ። በ2014 ዓ. ም. ካደረግሻቸው መካከል ትልቁ ስኬቴ የምትይው የቱን ነው? የዓለም አቀፉ ‘አክት ፎር ፉድ አክት ፎር ቼንጅ’ ንቅናቄ የኢትዮጵያ ወጣቶች ተወካይ ሆኜ የተለያዩ ሥራዎችን እሠራ ነበር። 2014 ዓ. ም. በጣም ስኬታማ የሆንበት ነው። ለ2015 ዓ. ም. ምን አቅደሻል? ሊሄም በትንሽ ደረጃ ነበር የሚሠራው። በ2014 ዓ. ም. ግን አድጎ፣ ቢሮ ተከራይተን መሥራት ጀምረናል። ቢዝነሱ ከተጀመረ እንኳን ቆይቷል። እና በ2015 ዓ. ም. ከአጋሮቻችን ጋር ተጣምረን ወደ ክሊኒክ የማሳደግ ዕቅድ ይዘናል። በ2014 ዓ. ም. አንብበሻቸው ከወደዳቸው መጻሕፍት መካከል ሰዎች ቢያነቧቸው የምትያቸው ሦስት መጻሕፍት የትኞቹ ናቸው? ሦሰት ቢታዩ የምትያቸው ፊልሞችስ? ቢነበቡ የምላቸው መጻሕፍት፡ ትንሿ ቤተክርስቲያን [ገብረእግዚአብሔር ኪዳን] Zero to One [ፒተር ታይል] ሕክምና በቤታችን [በቀለች ቶላ] ፊልም እንኳን አላይም። በምትኩ ቢጎበኙ ብዬ የማስባቸውን ሦስት ቦታዎች ልንገርሽ። ላሊበላ፣ አክሱም እና የሩዋንዳው ‘ኪጋሊ ጄኖሳይድ ሜሞሪያል’ ካጠቃላይ ሳይንሳዊ ፈጠራዎች ወይም ግኝቶች የቱ ያስገርምሻል? ለምን? የኢንዶስኮፒ ምርመራ መደረግ መቻሉ ያስገርመኛል። በእርግጥ ውስብስብ ሳይንስ አይደለም። አሁን ባለው መሣሪያ በቀላሉ የትኛውም ሆስፒታል ውስጥ ሊሠራ ይችላል። አንድን ግለሰብ ሳናፈርሰው ስላለበት ሂደት እንድናውቅ ያስችላል። የላብራቶሪ ምርመራና የደም ሕዋስ ማየት መቻል አሁን ላለንበት ዘመን ትልቅ ግኝት ነው። ሕሊና ኃይሉ ንጋቱ- በአሜሪካ ዩኒቨርስቲ ኦፍ ካሊፎርኒያ፣ በርክሌ የኮምፒውተር ሳይንስ የፒኤችዲ ሁለተኛ ዓመት ተማሪ በ2014 ዓ. ም. ባንቺ ሙያ ከተፈጠሩ ወይም ከተሠሩ መካከል ያስደነቀሽ የቱ ነው? ለምን? በ2014 ዓ. ም. ካስደመሙኝ ፈጠራዎች አንዱ በኤአይ ሞዴል የሚፈጠሩ ምሥሎች የጥራት ደረጃ ነው። እነዚህ ሞዴሎች በስፋት ጥቅም ላይ ይውላሉ። በአንድ በኩል እንደ ቤኖ ሳሙኤል ያሉ ባለሙያዎች በቴክኖሎጂ የታገዘ ሥነ ጥበብ ሲሠሩ ያስገርመኛል። በሌላ በኩል ደግሞ ተገቢው ቁጥጥር ያልተደረገበት ቴክኖሎጂ ጉዳቱ ያሰጋኛል። በ2014 ዓ. ም. ካደረግሻቸው መካከል ትልቁ ስኬቴ የምትይው የቱን ነው? ትልቁ ስኬቴ በአሶሴሽን ፎር ኮምፒውቲንግ ማሽነሪ ተቋም የኮምፒውቴሽናል እና ዳታ ሳይንስ ፌሎሺፕ ማሸነፌ ነው። ለ2015 ዓ. ም. ምን አቅደሻል? በ2015 ዓ. ም. በዩሲ በርክሌይ ዩኒቨርስቲ ሁለተኛ ዓመት ፒኤችዲ ትምህርቴን እከታተላለሁ። ዕቅዴም ከአፍሪካውያን አጋሮቼ ጋር ተጣምሬ ማኅበረሰባችንን የሚጠቅም ሥራ ማከናወን ነው። በ2014 ዓ. ም. አንብበሻቸው ከወደዳቸው መጻሕፍት መካከል ሰዎች ቢያነቧቸው የምትያቸው ሦስት መጻሕፍት የትኞቹ ናቸው? ሦሰት ቢታዩ የምትያቸው ፊልሞችስ? ቢነበቡ የምላቸው መጻሕፍት፡ All about Love [ቤል ሁክስ] Race After Technology [ሩሀ ቤንጃሚን] Shadow King [መዓዛ መንግሥቴ ] ቢታዩ የምላቸው ፊልሞች Queen of Katwe፣ Us እና እረኛዬ ካጠቃላይ ሳይንሳዊ ፈጠራዎች ወይም ግኝቶች የቱ ያስገርምሻል? ለምን? አንድ ፈጠራ መምረጥ ካለብኝ፣ የተለያዩ የሰውነት አካላትን በቀዶ ሕክምና መለወጥ (Organ Transplant) ይደንቀኛል። ለምን? የሚለው ግልጽ ነው። የሰዎችን ሕይወት ስለሚያተርፍ።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c0wzew2yx90o