label
class label
4 classes
headline
stringlengths
17
80
text
stringlengths
1
16.8k
headline_text
stringlengths
28
16.8k
url
stringlengths
36
49
0business
ኮሮናቫይረስ፡ ሳኡዲ ለዜጎቿ የምትሰጠውን ድጎማ በማቋረጥ ተጨማሪ ዕሴት ታክስን በሦስት እጥፍ ጨመረች
የሳኡዲ አረቢያ በኮሮናቫይረስ ምክንያት የደቀቀውን ኢኮኖሚዋን ለመደገፍ በተጨማሪ እሴት ታክስ ላይ ሦስት አጥፍ ጭማሪ ልታደርግ መሆኑን አስታወቀች። የአገሪቱ መንግሥት ከዚህ በተጨማሪም ለዜጎቹ ይሰጠው የነበረውን የኑሮ መደጎሚያ ገንዘብ እንደሚያቋርጥም አስታውቋል። የኮሮናቫይረስ ባስከተለው ዓለም አቀፍ ቀውስ ምክንያት የነዳጅ ዋጋ በመቀነሱ በነዳጅ ሀብት የበለጸገችው ሳኡዲ አረቢያ የገቢ መጠኗ በእጅጉ አሽቆልቁሏል። ሳኡዲ አረቢያ ከሁለት ዓመታት በፊት ነበር ኢኮኖሚው በነዳጅ ላይ ብቻ እንዳይንጠለጠል በሚል ተጨማሪ እሴት ታክስን ያስተዋወቀችው። የሳኡዲ አረቢያ ዜና ተቋም እንደዘገበው ተጨማሪ እሴት ታክሱ ከፈረንጆቹ ሰኔ ወር ጀምሮ ከ5% ወደ 15% ከፍ ይላል። "እነዚህ እርምጃዎች በጣም ከባድ ነገር ግን አሁና ካለው ሁኔታ አንጻር እጅግ አስፈላጊ ናቸው። የአገሪቱን የገንዘብና ኢኮኖሚያዊ ደኅንነትን ለማረጋገጥ ነው እርምጃዎቹ የተወሰዱት" ብለዋል የገንዘብ ሚኒስትሩ ሞሐመድ አል ጃዳን። ይህ ውሳኔ የተላለፈው አገሪቱ የምታወጣው ወጪ ከምታስገባው ገቢ በማነሱ ምክንያት መንግሥት ባለፉት ሦስት ወራት ብቻ የ9 ቢሊዮን ዶላር የበጀት ጉድለት ማጋጠሙን ተከትሎ ነው። ይህም ሊሆን የቻለው በተጠቀሰው የጊዜ ሰሌዳ ውስጥ ከነዳጅ የሚገኝ ትርፍ 22 በመቶ በመቀነሱ አገሪቱ ማግኘት የቻለችው 34 ቢሊዮን ዶላር ብቻ በመሆኑ ነው። በነዚሁ ሦስት ወራትም የሳኡዲ አረቢያ ማዕከላዊ ባንክ እንዳስታወቀው የውጭ ምንዛሪ መጠባበቂያ ገንዘብ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ዝቅ ብሏል። ልዑል ሞሐመድ ቢን ሳልማን የሳኡዲ አረቢያ ኢኮኖሚን ለማነቃቃትና አጠቃላይ የአገሪቱን ገጽታ ለመቀየር እየወሰዱት የነበረውን እርምጃ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ፈተና እንደሚሆንበት ይጠበቃል።
ኮሮናቫይረስ፡ ሳኡዲ ለዜጎቿ የምትሰጠውን ድጎማ በማቋረጥ ተጨማሪ ዕሴት ታክስን በሦስት እጥፍ ጨመረች የሳኡዲ አረቢያ በኮሮናቫይረስ ምክንያት የደቀቀውን ኢኮኖሚዋን ለመደገፍ በተጨማሪ እሴት ታክስ ላይ ሦስት አጥፍ ጭማሪ ልታደርግ መሆኑን አስታወቀች። የአገሪቱ መንግሥት ከዚህ በተጨማሪም ለዜጎቹ ይሰጠው የነበረውን የኑሮ መደጎሚያ ገንዘብ እንደሚያቋርጥም አስታውቋል። የኮሮናቫይረስ ባስከተለው ዓለም አቀፍ ቀውስ ምክንያት የነዳጅ ዋጋ በመቀነሱ በነዳጅ ሀብት የበለጸገችው ሳኡዲ አረቢያ የገቢ መጠኗ በእጅጉ አሽቆልቁሏል። ሳኡዲ አረቢያ ከሁለት ዓመታት በፊት ነበር ኢኮኖሚው በነዳጅ ላይ ብቻ እንዳይንጠለጠል በሚል ተጨማሪ እሴት ታክስን ያስተዋወቀችው። የሳኡዲ አረቢያ ዜና ተቋም እንደዘገበው ተጨማሪ እሴት ታክሱ ከፈረንጆቹ ሰኔ ወር ጀምሮ ከ5% ወደ 15% ከፍ ይላል። "እነዚህ እርምጃዎች በጣም ከባድ ነገር ግን አሁና ካለው ሁኔታ አንጻር እጅግ አስፈላጊ ናቸው። የአገሪቱን የገንዘብና ኢኮኖሚያዊ ደኅንነትን ለማረጋገጥ ነው እርምጃዎቹ የተወሰዱት" ብለዋል የገንዘብ ሚኒስትሩ ሞሐመድ አል ጃዳን። ይህ ውሳኔ የተላለፈው አገሪቱ የምታወጣው ወጪ ከምታስገባው ገቢ በማነሱ ምክንያት መንግሥት ባለፉት ሦስት ወራት ብቻ የ9 ቢሊዮን ዶላር የበጀት ጉድለት ማጋጠሙን ተከትሎ ነው። ይህም ሊሆን የቻለው በተጠቀሰው የጊዜ ሰሌዳ ውስጥ ከነዳጅ የሚገኝ ትርፍ 22 በመቶ በመቀነሱ አገሪቱ ማግኘት የቻለችው 34 ቢሊዮን ዶላር ብቻ በመሆኑ ነው። በነዚሁ ሦስት ወራትም የሳኡዲ አረቢያ ማዕከላዊ ባንክ እንዳስታወቀው የውጭ ምንዛሪ መጠባበቂያ ገንዘብ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ዝቅ ብሏል። ልዑል ሞሐመድ ቢን ሳልማን የሳኡዲ አረቢያ ኢኮኖሚን ለማነቃቃትና አጠቃላይ የአገሪቱን ገጽታ ለመቀየር እየወሰዱት የነበረውን እርምጃ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ፈተና እንደሚሆንበት ይጠበቃል።
https://www.bbc.com/amharic/news-52613715
0business
የኮሮናቫይረስ መከሰትን ተከትሎ የዓለም ምጣኔ ሃብት ወደቀ ወይስ ደቀቀ?
የኮሮናቫይረስ ጥምር ኪሳራ እያስከተለ ነው። በመላው ዓለም በሚባል ደረጃ በሰዎች ጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ቫይረሱን ለመከላከል ሲባል የሚዘጉ ምርት፣ የንግድና የመዝናኛ ተቋማት ምንም ዓይነት የግብይት እንቅስቃሴ እንዳይኖር በማድረግ ምጣኔ ሃብቱ ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ደቅኗል።
የኮሮናቫይረስ መከሰትን ተከትሎ የዓለም ምጣኔ ሃብት ወደቀ ወይስ ደቀቀ? የኮሮናቫይረስ ጥምር ኪሳራ እያስከተለ ነው። በመላው ዓለም በሚባል ደረጃ በሰዎች ጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ቫይረሱን ለመከላከል ሲባል የሚዘጉ ምርት፣ የንግድና የመዝናኛ ተቋማት ምንም ዓይነት የግብይት እንቅስቃሴ እንዳይኖር በማድረግ ምጣኔ ሃብቱ ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ደቅኗል።
https://www.bbc.com/amharic/news-51978777
5sports
የቀነኒሳ በቀለ ክብረ ወሰን በኡጋንዳዊው ወጣት ተሰበረ
ኡጋንዳዲው ጆሹዋ ቼፕቴጌ በፈረንሳይ ሞናኮ በተካሄደው የዳይመንድ ሊግ ውድድር ለ16 ዓመታት በቀነኒሳ በቀለ ተይዞ የነበረውን የ5000 ሜትር ሩጫ ክብረ ወሰን በሁለት ሰከንድ ማሻሻል ችሏል። የ23 ዓመቱ ወጣት ባላፈው ዓመት በዶሃ የዓለም ሻምፒዮና ላይ የ10 ሺህ ሜትር አሸናፊ በሆነበት ወቅት የ5 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰንን ለማሻሻል እቅድ እንዳለው ገልጾ የነበረ ሲሆን በቅርብ ዓመታት ያሳካዋል ተብሎ ግን አልተገመተም ነበር። ነገር ግን በትላንቱ የሞናኮው ውድድር ላይ 5 ሺህ ሜትሩን 12 ደቂቃ 35.36 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በመጨረስ ቀነኒሳን ክብረ ወሰን መስበር ችሏል። ቀነኒሳ በቀለ የዛሬ 16 ዓመት ክብረ ወሰኑን ሲያስመዘግብ ውድድሩን የጨረሰው በ12 ደቂቃ 37 ሰከንድ ከ35 ማይክሮ ሰከንድ ነበር። በሚያስገርም ሁኔታ ቼፕቴጌ በዚህ ዓመት ክብረ ወሰን ሲሰብር ይሄ ሁለተኛው ነው። ባለፈው የካቲት ወር ላይ ደግሞ በተካሄደ የ5 ኪሎ ሜትር ሩጫ ሰዓት ማሻሻል እንደቻለ ተነግሯል። ''ሞናኮ በጣም ልዩ ቦታ ናት፤ የዓለም ክብረ ወሰኖችን ልሰብርባት የምችልባት ከተማ ናት'' ሲል በደስታ ተውጦ ቼፕቴጌ ተናግሯል። ''በዚህ ዓመት በእውነቱ ሞራልን ሰብሰብ አድርጎ ለመስራት ትንሽ ይከብዳል፤ ምክንያቱም በወረርሽኙ ምክንያት ሰዎች ከቤታቸው አይወጡም፤ ብዙ ነገሮችም በፊት እንደነበሩት አይደሉም፤ ተቀይረዋል። ነገር ግን በዚህ ሁኔታ ውስጥ በማሸነፌ በጣም ደስተኛ ነኝ።'' በሌሎች ውድድሮች የዓለም ሻምፒዮኑ ኖዋህ ሊይስ የ200 ሜትር ውድድሩን በ19 ሰከንድ ከ72 ማይክሮሰከንድ በሆነ ሰዓት በማሸነፍ አይበገሬነቱን አሳይቷል። ታናሽ ወንድሙ ጆሴፈስ ደግሞ በመጀመሪያው የዳይመንድ ሊግ ተሳትፎው እሱን ተከትሎ ሁለተኛ ሆኖ መጨረስ ችሏል። ኖርዌያዊው ዓለም ሻምፒዮን ካርስተን ዋርሆልም ደግሞ በ400 ሜትር መሰናክል ውድድር በአውሮፓውያኑ 1992 በኬቨን ያንግ ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን መስበር ችሏል። ለብቻው ለማለት በሚያስደፍር መልኩ ሲሮጥ የነበረው ካርስተን ውድድሩን በ47 ሰከንድ ከ10 ማይክሮ ሰከንድ ጨርሷል። ኬንያዊቷ ሄለን ኦቢሪ ደግሞ የሴቶች 5 ሺህ ሜትር ውድድሩን በበላይነት ስታጠናቅቅ ሲፋን ሀሰን ደግሞ ጥቂት ዙሮች ሲቀሩት ውድድሩን አቋርጣ ወጥታለች። 5 ሺህ ብቻ ሰዎች እንዲመለከቱት በተፈቀደው የሞናኮው የዳይመንድ ሊግ ውድድር ላይ ተመልካቾች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ ግዴታቸው ሲሆን አካላዊ ርቀትም መጠበቅ ነበረባቸው።
የቀነኒሳ በቀለ ክብረ ወሰን በኡጋንዳዊው ወጣት ተሰበረ ኡጋንዳዲው ጆሹዋ ቼፕቴጌ በፈረንሳይ ሞናኮ በተካሄደው የዳይመንድ ሊግ ውድድር ለ16 ዓመታት በቀነኒሳ በቀለ ተይዞ የነበረውን የ5000 ሜትር ሩጫ ክብረ ወሰን በሁለት ሰከንድ ማሻሻል ችሏል። የ23 ዓመቱ ወጣት ባላፈው ዓመት በዶሃ የዓለም ሻምፒዮና ላይ የ10 ሺህ ሜትር አሸናፊ በሆነበት ወቅት የ5 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰንን ለማሻሻል እቅድ እንዳለው ገልጾ የነበረ ሲሆን በቅርብ ዓመታት ያሳካዋል ተብሎ ግን አልተገመተም ነበር። ነገር ግን በትላንቱ የሞናኮው ውድድር ላይ 5 ሺህ ሜትሩን 12 ደቂቃ 35.36 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በመጨረስ ቀነኒሳን ክብረ ወሰን መስበር ችሏል። ቀነኒሳ በቀለ የዛሬ 16 ዓመት ክብረ ወሰኑን ሲያስመዘግብ ውድድሩን የጨረሰው በ12 ደቂቃ 37 ሰከንድ ከ35 ማይክሮ ሰከንድ ነበር። በሚያስገርም ሁኔታ ቼፕቴጌ በዚህ ዓመት ክብረ ወሰን ሲሰብር ይሄ ሁለተኛው ነው። ባለፈው የካቲት ወር ላይ ደግሞ በተካሄደ የ5 ኪሎ ሜትር ሩጫ ሰዓት ማሻሻል እንደቻለ ተነግሯል። ''ሞናኮ በጣም ልዩ ቦታ ናት፤ የዓለም ክብረ ወሰኖችን ልሰብርባት የምችልባት ከተማ ናት'' ሲል በደስታ ተውጦ ቼፕቴጌ ተናግሯል። ''በዚህ ዓመት በእውነቱ ሞራልን ሰብሰብ አድርጎ ለመስራት ትንሽ ይከብዳል፤ ምክንያቱም በወረርሽኙ ምክንያት ሰዎች ከቤታቸው አይወጡም፤ ብዙ ነገሮችም በፊት እንደነበሩት አይደሉም፤ ተቀይረዋል። ነገር ግን በዚህ ሁኔታ ውስጥ በማሸነፌ በጣም ደስተኛ ነኝ።'' በሌሎች ውድድሮች የዓለም ሻምፒዮኑ ኖዋህ ሊይስ የ200 ሜትር ውድድሩን በ19 ሰከንድ ከ72 ማይክሮሰከንድ በሆነ ሰዓት በማሸነፍ አይበገሬነቱን አሳይቷል። ታናሽ ወንድሙ ጆሴፈስ ደግሞ በመጀመሪያው የዳይመንድ ሊግ ተሳትፎው እሱን ተከትሎ ሁለተኛ ሆኖ መጨረስ ችሏል። ኖርዌያዊው ዓለም ሻምፒዮን ካርስተን ዋርሆልም ደግሞ በ400 ሜትር መሰናክል ውድድር በአውሮፓውያኑ 1992 በኬቨን ያንግ ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን መስበር ችሏል። ለብቻው ለማለት በሚያስደፍር መልኩ ሲሮጥ የነበረው ካርስተን ውድድሩን በ47 ሰከንድ ከ10 ማይክሮ ሰከንድ ጨርሷል። ኬንያዊቷ ሄለን ኦቢሪ ደግሞ የሴቶች 5 ሺህ ሜትር ውድድሩን በበላይነት ስታጠናቅቅ ሲፋን ሀሰን ደግሞ ጥቂት ዙሮች ሲቀሩት ውድድሩን አቋርጣ ወጥታለች። 5 ሺህ ብቻ ሰዎች እንዲመለከቱት በተፈቀደው የሞናኮው የዳይመንድ ሊግ ውድድር ላይ ተመልካቾች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ ግዴታቸው ሲሆን አካላዊ ርቀትም መጠበቅ ነበረባቸው።
https://www.bbc.com/amharic/news-53789764
5sports
ወደፊት እግር ኳስ ተጫዋቾች 'ቴስታ' መምታት ይከለከሉ ይሆን?
ቴስታ ወይም የጭንቅላት ኳስ ወደፊት ከእግር ኳሱ ዓለም ሊወገድ ይሆን? የሚለው ጥያቄ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መነጋገሪያ ሆኗል። ለዚህ ደግሞ ዋነኛው ምክንያት ጤና ነው። ተመራማሪዎች ኳሰን በጭንቅላት መግጨት ጣጣ አለው እያሉ ነው። እንግሊዝ ይህን በማስመልከት ሕፃናት እግር ኳስ ሲጫወቱ ቴስታ እንዳይመቱ የሚከለክል ሕግ እያወጣች ነው። አንድ ጥናት እንደሚያመለክተው የቀድሞ ተጫዎቾች ከሌሎች በተለየ በጭንቅላት ሕመም የመሞት ዕድላቸው በሦስት እጥፍ የጨመረ ነው። በዚህ ሃሳብ እግር ኳስ ተጫዎቾችም ይስማማሉ። የቀድሞው የቶተንሃምና የሃል ሲቲ ተጫዋች ራያን ሜሰን ቴስታ በሚቀጥሉት ከ10 አስከ 15 ዓመታት ባለው ጊዜ ሊቀር ይችላል ይላል። ሜሰን በ2017 ጭንቅላቱ ላይ በደረሰበት ጉዳት ምክንያት በጊዜ ከእግር ኳስ ሕይወት ራሱን አሰናብቷል። የ29 ዓመቱ ሜሰን "በሚቀጥሉት ዓመታት ቴስታ ከእግር ኳስ ዓለም መወገድ አለበት ቢባል አልደነቀም" ሲል ለቢቢሲ ይናገራል። ሜሰን እንደሚለው ቴስታን በተመለከተ የሚሠሩ ጥናቶች ከዚህም በላይ በጣም አስደንጋጭ ውጤቶች ይዘው ሊመጡ ይችላሉ። "እኔ እግር ኳስ ተጫዋቾች ቴስታ የሚያመጣውን ተፅዕኖ በቅጡ ያወቁት አይመስለኝም። ለዚህ ነው ተጨማሪ ጥናቶች ያስፈልጋሉ የምለው።" "በጣም አስጨናቂ ጉዳይ ነው" ይላል ሜሰን ስለጭንቅላት ኳስ ሲያወራ። "ችግሩ የቴስታን ጉዳት አሁን አናየውም። ጉዳቱ የሚመጣው ከዓመታት በኋላ ነው።" ቴስታ በእግር ኳስ ተጫዋቾች ላይ የሚያመጣው ጉዳት ምንድነው የሚለውን ያጠኑት ዶ/ር ዊሊ ስቴዋርት ቴስታ የጭንቅላት ሕመምና የመርሳት በሽታ ሊያስከትል ይችላል ይላሉ። በፈረንጆቹ 1966 ከእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ጋር የዓለም ዋንጫ ያነሳው ኖቢ ስታይልስ ባለፈው ጥቅምት ከመሞቱ በፊት በተደጋጋሚ ኳስን በጭንቅላቱ በመምታቱ ለመርሳት በሽታ እንደተጋለጠ ተናግሮ ነበር። ከቴስታ ጋር ተያይዞ የሚነሳው ሌላው ጉዳይ የአየር ላይ ኳስ በጭንቅላት ለመግጨት በሚደረግ ፍልሚያ የሚከሰተው አደጋ ነው። ከጥቂት ሳምንታት በፊት አርሰናልና ዎልቭስ በነበራቸው ጨዋታ የአርሴናሉ ዴቪድ ሉዊዝና የዎልቭሱ ራዉል ሂሜኔዝ ለጭንቅላት ኳስ ሲሻሙ ተጋጭተው ሂሜኔዝ ክፉኛ ተጎድቶ ነበር። በወቅቱ ሂሜኔዝ በቃሬዝ ነበር ከጨዋታው የወጣው። ሉዊዝ ደግሞ ጭንቅላቱን በፋሻ አስሮ ጨዋታውን ቀጥሎ ነበር። እንግሊዛዊው የቀድሞ የፕሪሚዬር ሊግ ኮከብ አለን ሺረር አርሴናል ሉዊዝን ከሜዳ ማስወጣት ነበረበት ብሎ ትችት መሰንዘሩ አይዘነጋም። የቀድሞው የቶተንሃም ተጫዋች ያን ቬርቶንገን ከሁለት የውድድር ዘመን በፊት በቻይምፒየንስ ሊግ ጨዋታ የጭንቃላት አደጋ አጋጥሞት ነበር። ተጫዋቾ የዚህ አደጋ ሕመም ለዘጠኝ ወራት ያህል ይሰማው እንደነበር ከጥቂት ሳምንታት በፊት ተናግሮ ነበር። ሜሰን ከቼልሲው ተከላካይ ጋሪ ካሂል ጋር ተጋጭቶ ባጋጠመው አደጋ ነው ጉዳት የደረሰበት። "በሕይወቴ መቆየቴ በራሱ ዕድለኛነት ነው" ይላል። ከሚቀጥለው ጥር ወር ጀምሮ ክለቦች የጭንቅላት አደጋ ሲያጋጥም ከመደበኛው ቅያሪ በተጨማሪ ሁሉት ተጫዋቾችን መቀየር እንዲችሉ ይፈቀድላቸዋል። አሁን የቶተንሃም አካዳሚ አሠልጣኝ ሆኖ የሚያገለግለው ሜሰን ግን ይህ ከሚሆን የጭንቅላት ኳስ ሕግ ሙሉ በሙሉ መቀየር አለበት ብሎ ያምናል። ቴስታ ወደፊት ከእግር ኳስ ዓለም ይወገድ ይሆን? የሚለው ጥያቄ ግን አከራካሪነቱ እንደቀጠለ ነው።
ወደፊት እግር ኳስ ተጫዋቾች 'ቴስታ' መምታት ይከለከሉ ይሆን? ቴስታ ወይም የጭንቅላት ኳስ ወደፊት ከእግር ኳሱ ዓለም ሊወገድ ይሆን? የሚለው ጥያቄ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መነጋገሪያ ሆኗል። ለዚህ ደግሞ ዋነኛው ምክንያት ጤና ነው። ተመራማሪዎች ኳሰን በጭንቅላት መግጨት ጣጣ አለው እያሉ ነው። እንግሊዝ ይህን በማስመልከት ሕፃናት እግር ኳስ ሲጫወቱ ቴስታ እንዳይመቱ የሚከለክል ሕግ እያወጣች ነው። አንድ ጥናት እንደሚያመለክተው የቀድሞ ተጫዎቾች ከሌሎች በተለየ በጭንቅላት ሕመም የመሞት ዕድላቸው በሦስት እጥፍ የጨመረ ነው። በዚህ ሃሳብ እግር ኳስ ተጫዎቾችም ይስማማሉ። የቀድሞው የቶተንሃምና የሃል ሲቲ ተጫዋች ራያን ሜሰን ቴስታ በሚቀጥሉት ከ10 አስከ 15 ዓመታት ባለው ጊዜ ሊቀር ይችላል ይላል። ሜሰን በ2017 ጭንቅላቱ ላይ በደረሰበት ጉዳት ምክንያት በጊዜ ከእግር ኳስ ሕይወት ራሱን አሰናብቷል። የ29 ዓመቱ ሜሰን "በሚቀጥሉት ዓመታት ቴስታ ከእግር ኳስ ዓለም መወገድ አለበት ቢባል አልደነቀም" ሲል ለቢቢሲ ይናገራል። ሜሰን እንደሚለው ቴስታን በተመለከተ የሚሠሩ ጥናቶች ከዚህም በላይ በጣም አስደንጋጭ ውጤቶች ይዘው ሊመጡ ይችላሉ። "እኔ እግር ኳስ ተጫዋቾች ቴስታ የሚያመጣውን ተፅዕኖ በቅጡ ያወቁት አይመስለኝም። ለዚህ ነው ተጨማሪ ጥናቶች ያስፈልጋሉ የምለው።" "በጣም አስጨናቂ ጉዳይ ነው" ይላል ሜሰን ስለጭንቅላት ኳስ ሲያወራ። "ችግሩ የቴስታን ጉዳት አሁን አናየውም። ጉዳቱ የሚመጣው ከዓመታት በኋላ ነው።" ቴስታ በእግር ኳስ ተጫዋቾች ላይ የሚያመጣው ጉዳት ምንድነው የሚለውን ያጠኑት ዶ/ር ዊሊ ስቴዋርት ቴስታ የጭንቅላት ሕመምና የመርሳት በሽታ ሊያስከትል ይችላል ይላሉ። በፈረንጆቹ 1966 ከእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ጋር የዓለም ዋንጫ ያነሳው ኖቢ ስታይልስ ባለፈው ጥቅምት ከመሞቱ በፊት በተደጋጋሚ ኳስን በጭንቅላቱ በመምታቱ ለመርሳት በሽታ እንደተጋለጠ ተናግሮ ነበር። ከቴስታ ጋር ተያይዞ የሚነሳው ሌላው ጉዳይ የአየር ላይ ኳስ በጭንቅላት ለመግጨት በሚደረግ ፍልሚያ የሚከሰተው አደጋ ነው። ከጥቂት ሳምንታት በፊት አርሰናልና ዎልቭስ በነበራቸው ጨዋታ የአርሴናሉ ዴቪድ ሉዊዝና የዎልቭሱ ራዉል ሂሜኔዝ ለጭንቅላት ኳስ ሲሻሙ ተጋጭተው ሂሜኔዝ ክፉኛ ተጎድቶ ነበር። በወቅቱ ሂሜኔዝ በቃሬዝ ነበር ከጨዋታው የወጣው። ሉዊዝ ደግሞ ጭንቅላቱን በፋሻ አስሮ ጨዋታውን ቀጥሎ ነበር። እንግሊዛዊው የቀድሞ የፕሪሚዬር ሊግ ኮከብ አለን ሺረር አርሴናል ሉዊዝን ከሜዳ ማስወጣት ነበረበት ብሎ ትችት መሰንዘሩ አይዘነጋም። የቀድሞው የቶተንሃም ተጫዋች ያን ቬርቶንገን ከሁለት የውድድር ዘመን በፊት በቻይምፒየንስ ሊግ ጨዋታ የጭንቃላት አደጋ አጋጥሞት ነበር። ተጫዋቾ የዚህ አደጋ ሕመም ለዘጠኝ ወራት ያህል ይሰማው እንደነበር ከጥቂት ሳምንታት በፊት ተናግሮ ነበር። ሜሰን ከቼልሲው ተከላካይ ጋሪ ካሂል ጋር ተጋጭቶ ባጋጠመው አደጋ ነው ጉዳት የደረሰበት። "በሕይወቴ መቆየቴ በራሱ ዕድለኛነት ነው" ይላል። ከሚቀጥለው ጥር ወር ጀምሮ ክለቦች የጭንቅላት አደጋ ሲያጋጥም ከመደበኛው ቅያሪ በተጨማሪ ሁሉት ተጫዋቾችን መቀየር እንዲችሉ ይፈቀድላቸዋል። አሁን የቶተንሃም አካዳሚ አሠልጣኝ ሆኖ የሚያገለግለው ሜሰን ግን ይህ ከሚሆን የጭንቅላት ኳስ ሕግ ሙሉ በሙሉ መቀየር አለበት ብሎ ያምናል። ቴስታ ወደፊት ከእግር ኳስ ዓለም ይወገድ ይሆን? የሚለው ጥያቄ ግን አከራካሪነቱ እንደቀጠለ ነው።
https://www.bbc.com/amharic/news-55445728
0business
ኢኮኖሚ፡ የብር የምንዛሪ ዋጋ በገበያ መወሰኑ ምን ይዞ ይመጣል?
ብሔራዊ ባንክ የብር የውጭ ምንዛሪ ፍላጎትን መሠረት በማድረግ የብር ዋጋ በገበያ ተመን እንዲወሰን ማድረግ ተገቢ በመሆኑ፤ ኢትዮጵያ በሦስት ዓመታት ውስጥ ብርን ወደ ፍሎቲንግ ካረንሲሥርዓት (የገንዘብን ተመን በገበያ ዋጋ ላይ መመስረት) እንደምትሸጋገር ተገልጿል። ለመሆኑ ፍሎቲንግ ካረንሲ ምንድነው? ኢትዮጵያ ፊቷን ወደዚህ ሥርዓት ማዞሯ ምን ያስከትላል? በንግድ ላይ የተሰማሩ ሰዎች ላይ የሚያሳድረሰው ተጽዕኖ ምንድነው? በተራው ዜጋ ህይወት ላይስ ምን አንድምታ አለው? ለእኒዚህ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲሰጡን የምጣኔ ሃብት ባለሙያ የሆኑቱን እዮብ ተስፋዬ (ዶ/ር)፣ አለማየሁ ገዳ (ዶ/ር) እና አቶ ዋሲሁን በላይን ጠይቀናል። የውጪ ምንዛሬ ሥርዓቶች የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎቹ የተለያዩ አይነት የውጪ ምንዛሬ ሥርዓቶች እንዳሉ ይጠቅሳሉ። የገንዘብን ዋጋ በገበያ መሠረት መተመን (Floating Exchange Rate)፣ የገንዘብ ዋጋ መጠን በማዕካለዊ ባንክ የሚወሰንበት (Fixed Exchange Rate) እና ማዕከላዊ ብንኩ እንደ አስፈላጊነቱ ጣልቃ የሚገባበት (Managed Floating Exchange Rate) ይጠቀሳሉ። የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎቹ ሁሉም አይነት የውጪ ምንዛሪ ሥርዓቶች የራሳቸው የሆነ አውንታዊና አሉታዊ ውጤቶች እንዳላቸው ይስማማሉ። የምጣኔ ሃብት ባለሙያው አቶ ዋሲሁን በላይ፤ አገራት የተወሰነ የውጪ ምንዛሪ ሥርዓትን ስለመረጡ ብቻ ውጤታማ ይሆናሉ ማለት አይደለም ይላሉ። እንደምሳሌም ሳዑዲ አረቢያ ምንዛሪው በማእከላዊ ባንክ የሚወሰን የተመን ሥርዓትን እየተከተለች ውጤታማ መሆኗን በማስታወስ፤ "ዋናው ቁምነገሩ የውጪ ምንዛሬ ሥርዓቱን በነጻ ገበያ ወይም በመንግሥት የሚወሰን አይደለም። የአገር ውስጥ ምርታማነትን በማሳደግ ለዓለም አቀፍ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶችን ማሳደግ ነው" ይላሉ። በገበያ ከሚወሰነው ምንዛሪ ኢትዮጵያ ምን ታተርፋለች? ብር በአሁኑ ወቅት ከሚገባው በላይ ዋጋ እንዳለው የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች የሚስማሙበት ጉዳይ ነው። ስለዚህም የብር ዋጋ በገበያ ወደሚተመንበት ሥርዓት ሲሸጋገር ዋጋው አሁን ካለው እንደሚቀንስ ወይም በብር እና በዶላር መካከል ያለው ልዩነት እንደሚሰፋ ይታመናል። አቶ ዋሲሁን የብር የመግዛት አቅም ሲቀንስ ኢትዮጵያ የምታመርታው ምርት ዋጋ በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ ርካሽ ይሆናል ይህም የአገር ውስጥ አምራቾችን ተወዳዳሪ ያደርጋቸዋል ይላሉ። "ለምሳሌ 1 የአሜሪካ ዶላር 25 ብር ነው ብለን እናስብ። አንድ አሜሪካዊ 1 ዶላር ይዞ ቢመጣ፤ 25 ብር ዋጋ ያለውን እቃ በ1 ዶላር ይገዛናል። የብር የመግዛት አቅምን በቀነስን ቁጥር ከውጪ የሚመጣ ሰው በርካሽ ዋጋ እንዲገዛን እያደረግን ነው። የዚህ እሳቤ ምንድነው ብዙ ምርት ለገበያ ባቀረብን ቁጥር ብዙ ዶላር እናገኛለን ማለት ነው።" አቶ ዋሲሁን በሌላ በኩል ደግሞ የዚህን ተገላቢጦሽ እንመልከት ይላሉ። "የ1 ዶላር ወደ 33 ከፍ ተደረገ ብለን እናስብ። አሁን የ1 ዶላር እቃ ለመግዛት 33 ብር መያዝ ያስፈልገናል። በፊት ግን 25 ብር ነበር የሚያስፈልገው" ብለዋል። በዚህም ይህ የሚያሳየን ብር ከዶላር ጋር ያለውን ልዩነት በሰፋ ቁጥር ኢትዮጵያዊ እቃ ከውጪ ለመግዛት ይወደድበታል። የአገር ውስጥ ምርትን ግን ውጪ ለመሸጥ ተወዳዳሪ ይሆናል። ይህ ማለት የአገራችን የውጪ ምንዛሪ ክምችት ያድጋል፤ ምርትና ምርታማነት ይጨምርልናል ሲሉ ሊኖረው የሚችለውን ውጤት ይናገራሉ። ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ግሽበት ሊያስከትል ይችላል በአሁኑ ጊዜ ብር ከሚገባው በላይ ዋጋ እንደተሰጠው የሚናገሩት እዮብ (ዶ/ር)፤ የብር የዋጋ በገበያው መሠረት ሲተመን ከውጪ አገራት ገንዘብ ጋር የሚኖረው ልዩነት እንደሚሰፋ ይገልጻሉ። ለምሳሌ አንድ የአሜሪካ ዶላር ዛሬ ላይ በባንኮች 35 ብር የሚመነዘር ከሆነ፤ በትክክለኛው የገበያ ዋጋ ይተመን ቢባል አንድ ዶላር እስከ 45 ብር ድረስ ሊመነዘር ይችላል። "በዚህም ወደ በገበያ ዋጋ በሚወሰን የምንዛሪ ተመን ስንሸጋገር የብር ዋጋ በከፍተኛ ዋጋ ሊያሽቆለቁል ይችላል፤ ይህም የዋጋ ግሽበትን ይከሰታል። ሌሎች እክሎችም ሊከሰቱ ይችላሉ" ይላሉ እዮብ (ዶ/ር)። የምጣኔ ሃብት ባለሙያው አለማየሁ ገዳ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ወደዚህ የውጪ ምንዛሬ ሥርዓት ሽግግር ሲደረግ ከሚያጋጥሙ አሉታዊ ተጽዕኖዎች መካከል ዋነኛው የዋጋ ግሽበት ሊሆን ይችላል ይላሉ። "ለምሳሌ ከሰሞኑ መንግሥት የ1 ዶላር ምንዛሬን ከ32 ወደ 35 ብር ከፍ ብሏል። ይህ ከ5 እና 6 ወራት በኋላ እስከ 24 በመቶ ድረስ በእቃዎች ላይ ጭማሪ ያመጣል" ሲሉ ይናገራሉ። አለማየሁ (ዶ/ር) በሱዳን የተከሰተውን እንደምሳሌ ያነሳሉ። 1 የአሜሪካ ዶላር 29 የሱዳን ፓወንድ ሳለ ሱዳን የውጪ ምንዛሬ ሥርዓቷን በገበያ ወደ ሚወሰነው አሰራር መቀየሯን ያስታወሳሉ። "በዚህም ሱዳን ውስጥ የ1 ዶላር ምንዛሪ 48 የሱዳን ፓወንድ ገባ። በሕገ-ወጡ ገበያ ደግሞ 1 ዶላር 58 የሱዳን ፓወንድ ደረሰ። በዚህን ጊዜ ሰዎች በሱዳን ፓወንድ ላይ እምነት አጡ" በዚህም ሁሉም ሰው ወደ ኤቲኤም በመሄድ ገንዘብ ማውጣት ላይ ተረባረበ፤ ባንኮች ደግሞ የሚከፍሉት ማጣታቸውን አለማየሁ (ዶ/ር) ይናገራሉ። "ከዚያም ችግሩ ተባብሶ ሄዶ እንደ ዳቦ ባሉ መሠረታዊ ፍጆታዎች ላይ ጭማሪ ታየ። ተቃውሞ ተቀስቅሶ አሁን ለመጣው የመንግሥት ለውጥ ምክንያቶች መካከል አንዱ ሆነ " ይላሉ። የውጪ ምንዛሬ ስርዓት ከ3 ዓመት በኋላ ይቀየራል መባሉ 'ግራ አጋቢ ነው' ብሔራዊ ባንክ የብር ዋጋ በገበያው የሚተመነው በሦስት ዓመት ውስጥ ነው ማለቱ ይታወሳል። ለመሆኑ ኢትዮጵያ የውጪ ምንዛሬ ሥርዓቷን በዚህ ጊዜ ውስጥ መቀየር ይቻላታል? እዮብ (ዶ/ር) በበለጸጉ አገራት ዘንድ የውጪ ምንዛሬ ሥርዓታቸውን በሦስት ዓመት ውስጥ የመቀየር ልምድ እንዳለ አውስተው፤ በብሔራዊ ባንክ በኩል ግን ቅድሞ ሊታሰብባቸው የሚገቡ ጉዳዮች እያሉ "ከሦስት ዓመት በኋላ የተባለው ከምን ተነስቶ እንደሆነ 'ግራ አጋቢ' ነው" ይላሉ። በኮቪድ-19 ምክንያት የዓለምና የኢትዮጵያ ምጣኔ ሃብት እድገት እየተጓተት መሆኑን ያስታወሱት እዮብ (ዶ/ር)፤ በወረርሽኙ ሳቢያ የተወሰነው የአገሪቱ ኢኮኖሚ ክፍል ክፉኛ መጎዳቱን ይናገራሉ። "ከእነዚህ ጫናዎች ሳንላቀቅና የኮቪድ-19ን ሙሉ ጫና ሳንረዳ ከአሁኑ ሦስት ዓመት ብሎ መወሰን ለእኔ ግራ አጋቢ ነው። በበኩሌ የምቀበለው ነገር አይደለም" ሲሉ ይሞግታሉ። እዮብ (ዶ/ር) እንደሚሉት ወደዚህ አይነት የውጪ ምንዛሬ አስተዳደር ለማምረት የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶች እንደሚያስፈልጉ በማውሳት፤ ኢትዮጵያ ወደዚህ ከመሸጋገሯ በፊት "የማክሮ ኢኮኖሚውን ማረጋጋት ያስፈልጋል፣ የዋጋ ግሽበትን መቆጣጠር ያስፈልጋል፣ በቂ የውጪ ምንዛሬ ክምችት መኖር ይኖርበታል እንዲሁም የንግድ ሚዛን ጉድለት መጥበብ ይኖርበታል" ሲሉ ይመክራሉ። እንደ እዮብ (ዶ/ር) አመለካከት በገበያ ወደሚወሰን የምንዛሪ ሥርዓት ከመሸጋገራችን በፊት የዋጋ ግሽበት መጠንን ወደ አንድ አሃዝ ማምጣት "እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው።" "በገበያው ላይ በቂ የሆነ የውጪ ምንዛሪ መኖር ይኖርበታል። ይህ እንዲሆን ደግሞ በቂ የውጪ ምንዛሪ ክምችት ያስፈልጋል። ኢትዮጵያም የውጪ ምንዛሪ የምታገኘባቸውን መንገዶች መጨምር ይኖርባታል። ከውጪ የሚላክ ገንዘብ እንዲጨምር ማበረታቻ ማድረግ፣ ቱሪዝምና ኤክስፖርት ማደግ ይኖርባቸዋል" ይላሉ። ይህን የውጪ ምንዛሬ ሥርዓት ለመተግበር የተማረ ሰው ኃይልና ተቋማዊ ለውጥ የግድ እንደሚልም እዮብ ተስፋዬ (ዶ/ር) ያሳስባሉ። አይኤምኤፍ እና የዓለም ባንክ ግፊት ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅትና የዓለም ባንክ ኢትዮጵያ ገንዘቧ በገበያ ዋጋ እንዲተመን ግፊት እንደሚያሳድሩ ይነገራል። እዮብ (ዶ/ር) ለዚህ አንዱን ምክንያት ሲያስረዱ፤ አይኤምኤፍ ከተመሰረተባቸው ምክንያቶች አንዱ የዓለም አገራት የመገበያያ ገንዘብ ዋጋ እንዲረጋጋ ለማድረግ በመሆኑ ነው። "በእነሱ ፍልስፍና የምንዛሪ ተመን የተረጋጋ የሚሆነው ከመንግሥት ጣልቃ ገብነት ነጻ ሲሆን ነው። ምክንያቱም ምንዛሪ እንደማንኛውም ሸቀጥ ዋጋ አለው። እንደ ሌሎች ሸቀጦች ሁሉ ይህ ዋጋ በገበያ ኃይል መወሰን አለበት ብለው ያምናሉ" ሲሉ ያስረዳሉ። አለማየሁ ገዳ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ወደ ውጪ ከምትልከው ምርት በላይ ከውጪ የምታስገበው በብዙ እጥፍ የሚበልጥ በመሆኑ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ይህንን ልዩነት ለማጥበብ የብር ዋጋ በገበያ ቢወሰን በተሻለ መልኩ የውጪ ምንዛሪ እንዲገኝ ይረዳል የሚል እሳቤ ስላለ አገሪቱ ወደዚህ ሥርዓት እንድትገባ ጫና እንደሚደረግ ይናገራሉ። ይሁን እንጂ አለማየሁ (ዶ/ር) እንደሚሉት በኢትዮጵያዊያን ላኪዎች እንደችግር ከሚቀርቡት መካከል የውጪ ምንዛሬ አቅርቦት እጥረት ትልቁ ራስ ምታት አይደለም ባይ ናቸው። "እኔ ከመቶ በላይ ላኪዎችን አነጋግሬ የደረስኩበት ነገር፤ ለእኛ አገር ላኪዎች መሠረታዊ ችግር የሆነው የጥሬ እቃ አቅርቦት እጥረት፣ የመሬትና የፋይናንስን አቅርቦት ችግር፣ ሙስናና ጉምሩክ ላይ ያለው ውጣ ውረድ ነው እንጂ የዶላር እጥረት የላኪዎች ትልቁ ችግር አይደለም" ይላሉ። "ዋናው ጉዳይ መሆን ያለበት በትይዩ ገበያ [ጥቁር ገበያ] እና በባንክ መካከል ያለው ልዩነት እንዲሁም ወደ አገር በሚገባውና ወደ ውጪ በሚላከው መካከል ያለውን ልዩነት ማጥበብ ነው።" በእነዚህ መካከል ልዩነቱ የሰፋበት ዋነኛ ምክንያት ወደ ውጪ የሚላከው ምርት ስላላደገ እንደሆነ የሚናገሩት አለማየሁ (ዶ/ር) "በእኔ ስሌት ወደ አገር በሚገባውና ከውቺ በሚመጣው መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብ ወደ ውጪ የምንልካቸው ምርቶች በአማካይ በዓመት 20 በመቶ ለስምንት ተከታታይ ዓመት ማደግ ይኖርበታል" ይላሉ። ስለዚህም የመንግሥት ትኩረት መሆን ያለበት "ወደ ውጪ የሚላኩ ምርቶች የሚጨምሩበትን መንገድና ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን በአገር ውስጥ ለማምረት አምራቾችን ማበረታት ላይ ነው" ይላሉ አለማየሁ (ዶ/ር)። አዋጭ ነው? የባለሙያዎቹ ጠቅላላ ግምገማ ኢትዮጵያ ከሦስት ዓመታት በኋላ የብር የዋጋ ተመን በገበያ እንዲወሰን ብታደርግ ያዋጣታል? የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎቹ ማጠቃለያ ሃሳብ የሚከተለው ነው። እዮብ (ዶ/ር) - የምንዛሪ ሥርዓት መቀየርና በገበያ ዋጋ መወሰን እንዳለበት አምናለሁ። አካሄዱ ግን ቀስ በቀስ በሂደት መሆን አለበት። ብሔራዊ ባንክ በመጪዎቹ ሦስት ዓመታት ውስጥ መከናወን ያለባቸው ነገሮችን መሰራት ይኖርበታል፤ ለዚህ ደግሞ የዘርፉ ባለሙያና ተቋም ያስፈልጋል። አለማየሁ (ዶ/ር) - ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል። የውጪ ምንዛሪ ሥርዓታችንን ከመቀየራችን በፊት ቀድሞ መከናወን ያለባቸው የቤት ሥራዎች አሉ። አቶ ዋሲሁን - በጠቅላላው አዋጭ ነው ብዬ አስባለሁ። ሥርዓቱ በራሱ ጊዜ ወደ ዚያው እየወሰደን ይገኛል። በመጪው ሦስት ዓመታት ውስጥ የሚጠበቅብንን የቤት ሥራዎች ማከናወን የምንችል ከሆነ የሚየቀሩ ነገሮች ቢኖሩም ከሦስት ዓመታት በኋላ የብር ዋጋ በገበያ እንዲተመን ማድረጉ ትክክለኛ አካሄድ ነው።
ኢኮኖሚ፡ የብር የምንዛሪ ዋጋ በገበያ መወሰኑ ምን ይዞ ይመጣል? ብሔራዊ ባንክ የብር የውጭ ምንዛሪ ፍላጎትን መሠረት በማድረግ የብር ዋጋ በገበያ ተመን እንዲወሰን ማድረግ ተገቢ በመሆኑ፤ ኢትዮጵያ በሦስት ዓመታት ውስጥ ብርን ወደ ፍሎቲንግ ካረንሲሥርዓት (የገንዘብን ተመን በገበያ ዋጋ ላይ መመስረት) እንደምትሸጋገር ተገልጿል። ለመሆኑ ፍሎቲንግ ካረንሲ ምንድነው? ኢትዮጵያ ፊቷን ወደዚህ ሥርዓት ማዞሯ ምን ያስከትላል? በንግድ ላይ የተሰማሩ ሰዎች ላይ የሚያሳድረሰው ተጽዕኖ ምንድነው? በተራው ዜጋ ህይወት ላይስ ምን አንድምታ አለው? ለእኒዚህ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲሰጡን የምጣኔ ሃብት ባለሙያ የሆኑቱን እዮብ ተስፋዬ (ዶ/ር)፣ አለማየሁ ገዳ (ዶ/ር) እና አቶ ዋሲሁን በላይን ጠይቀናል። የውጪ ምንዛሬ ሥርዓቶች የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎቹ የተለያዩ አይነት የውጪ ምንዛሬ ሥርዓቶች እንዳሉ ይጠቅሳሉ። የገንዘብን ዋጋ በገበያ መሠረት መተመን (Floating Exchange Rate)፣ የገንዘብ ዋጋ መጠን በማዕካለዊ ባንክ የሚወሰንበት (Fixed Exchange Rate) እና ማዕከላዊ ብንኩ እንደ አስፈላጊነቱ ጣልቃ የሚገባበት (Managed Floating Exchange Rate) ይጠቀሳሉ። የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎቹ ሁሉም አይነት የውጪ ምንዛሪ ሥርዓቶች የራሳቸው የሆነ አውንታዊና አሉታዊ ውጤቶች እንዳላቸው ይስማማሉ። የምጣኔ ሃብት ባለሙያው አቶ ዋሲሁን በላይ፤ አገራት የተወሰነ የውጪ ምንዛሪ ሥርዓትን ስለመረጡ ብቻ ውጤታማ ይሆናሉ ማለት አይደለም ይላሉ። እንደምሳሌም ሳዑዲ አረቢያ ምንዛሪው በማእከላዊ ባንክ የሚወሰን የተመን ሥርዓትን እየተከተለች ውጤታማ መሆኗን በማስታወስ፤ "ዋናው ቁምነገሩ የውጪ ምንዛሬ ሥርዓቱን በነጻ ገበያ ወይም በመንግሥት የሚወሰን አይደለም። የአገር ውስጥ ምርታማነትን በማሳደግ ለዓለም አቀፍ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶችን ማሳደግ ነው" ይላሉ። በገበያ ከሚወሰነው ምንዛሪ ኢትዮጵያ ምን ታተርፋለች? ብር በአሁኑ ወቅት ከሚገባው በላይ ዋጋ እንዳለው የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች የሚስማሙበት ጉዳይ ነው። ስለዚህም የብር ዋጋ በገበያ ወደሚተመንበት ሥርዓት ሲሸጋገር ዋጋው አሁን ካለው እንደሚቀንስ ወይም በብር እና በዶላር መካከል ያለው ልዩነት እንደሚሰፋ ይታመናል። አቶ ዋሲሁን የብር የመግዛት አቅም ሲቀንስ ኢትዮጵያ የምታመርታው ምርት ዋጋ በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ ርካሽ ይሆናል ይህም የአገር ውስጥ አምራቾችን ተወዳዳሪ ያደርጋቸዋል ይላሉ። "ለምሳሌ 1 የአሜሪካ ዶላር 25 ብር ነው ብለን እናስብ። አንድ አሜሪካዊ 1 ዶላር ይዞ ቢመጣ፤ 25 ብር ዋጋ ያለውን እቃ በ1 ዶላር ይገዛናል። የብር የመግዛት አቅምን በቀነስን ቁጥር ከውጪ የሚመጣ ሰው በርካሽ ዋጋ እንዲገዛን እያደረግን ነው። የዚህ እሳቤ ምንድነው ብዙ ምርት ለገበያ ባቀረብን ቁጥር ብዙ ዶላር እናገኛለን ማለት ነው።" አቶ ዋሲሁን በሌላ በኩል ደግሞ የዚህን ተገላቢጦሽ እንመልከት ይላሉ። "የ1 ዶላር ወደ 33 ከፍ ተደረገ ብለን እናስብ። አሁን የ1 ዶላር እቃ ለመግዛት 33 ብር መያዝ ያስፈልገናል። በፊት ግን 25 ብር ነበር የሚያስፈልገው" ብለዋል። በዚህም ይህ የሚያሳየን ብር ከዶላር ጋር ያለውን ልዩነት በሰፋ ቁጥር ኢትዮጵያዊ እቃ ከውጪ ለመግዛት ይወደድበታል። የአገር ውስጥ ምርትን ግን ውጪ ለመሸጥ ተወዳዳሪ ይሆናል። ይህ ማለት የአገራችን የውጪ ምንዛሪ ክምችት ያድጋል፤ ምርትና ምርታማነት ይጨምርልናል ሲሉ ሊኖረው የሚችለውን ውጤት ይናገራሉ። ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ግሽበት ሊያስከትል ይችላል በአሁኑ ጊዜ ብር ከሚገባው በላይ ዋጋ እንደተሰጠው የሚናገሩት እዮብ (ዶ/ር)፤ የብር የዋጋ በገበያው መሠረት ሲተመን ከውጪ አገራት ገንዘብ ጋር የሚኖረው ልዩነት እንደሚሰፋ ይገልጻሉ። ለምሳሌ አንድ የአሜሪካ ዶላር ዛሬ ላይ በባንኮች 35 ብር የሚመነዘር ከሆነ፤ በትክክለኛው የገበያ ዋጋ ይተመን ቢባል አንድ ዶላር እስከ 45 ብር ድረስ ሊመነዘር ይችላል። "በዚህም ወደ በገበያ ዋጋ በሚወሰን የምንዛሪ ተመን ስንሸጋገር የብር ዋጋ በከፍተኛ ዋጋ ሊያሽቆለቁል ይችላል፤ ይህም የዋጋ ግሽበትን ይከሰታል። ሌሎች እክሎችም ሊከሰቱ ይችላሉ" ይላሉ እዮብ (ዶ/ር)። የምጣኔ ሃብት ባለሙያው አለማየሁ ገዳ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ወደዚህ የውጪ ምንዛሬ ሥርዓት ሽግግር ሲደረግ ከሚያጋጥሙ አሉታዊ ተጽዕኖዎች መካከል ዋነኛው የዋጋ ግሽበት ሊሆን ይችላል ይላሉ። "ለምሳሌ ከሰሞኑ መንግሥት የ1 ዶላር ምንዛሬን ከ32 ወደ 35 ብር ከፍ ብሏል። ይህ ከ5 እና 6 ወራት በኋላ እስከ 24 በመቶ ድረስ በእቃዎች ላይ ጭማሪ ያመጣል" ሲሉ ይናገራሉ። አለማየሁ (ዶ/ር) በሱዳን የተከሰተውን እንደምሳሌ ያነሳሉ። 1 የአሜሪካ ዶላር 29 የሱዳን ፓወንድ ሳለ ሱዳን የውጪ ምንዛሬ ሥርዓቷን በገበያ ወደ ሚወሰነው አሰራር መቀየሯን ያስታወሳሉ። "በዚህም ሱዳን ውስጥ የ1 ዶላር ምንዛሪ 48 የሱዳን ፓወንድ ገባ። በሕገ-ወጡ ገበያ ደግሞ 1 ዶላር 58 የሱዳን ፓወንድ ደረሰ። በዚህን ጊዜ ሰዎች በሱዳን ፓወንድ ላይ እምነት አጡ" በዚህም ሁሉም ሰው ወደ ኤቲኤም በመሄድ ገንዘብ ማውጣት ላይ ተረባረበ፤ ባንኮች ደግሞ የሚከፍሉት ማጣታቸውን አለማየሁ (ዶ/ር) ይናገራሉ። "ከዚያም ችግሩ ተባብሶ ሄዶ እንደ ዳቦ ባሉ መሠረታዊ ፍጆታዎች ላይ ጭማሪ ታየ። ተቃውሞ ተቀስቅሶ አሁን ለመጣው የመንግሥት ለውጥ ምክንያቶች መካከል አንዱ ሆነ " ይላሉ። የውጪ ምንዛሬ ስርዓት ከ3 ዓመት በኋላ ይቀየራል መባሉ 'ግራ አጋቢ ነው' ብሔራዊ ባንክ የብር ዋጋ በገበያው የሚተመነው በሦስት ዓመት ውስጥ ነው ማለቱ ይታወሳል። ለመሆኑ ኢትዮጵያ የውጪ ምንዛሬ ሥርዓቷን በዚህ ጊዜ ውስጥ መቀየር ይቻላታል? እዮብ (ዶ/ር) በበለጸጉ አገራት ዘንድ የውጪ ምንዛሬ ሥርዓታቸውን በሦስት ዓመት ውስጥ የመቀየር ልምድ እንዳለ አውስተው፤ በብሔራዊ ባንክ በኩል ግን ቅድሞ ሊታሰብባቸው የሚገቡ ጉዳዮች እያሉ "ከሦስት ዓመት በኋላ የተባለው ከምን ተነስቶ እንደሆነ 'ግራ አጋቢ' ነው" ይላሉ። በኮቪድ-19 ምክንያት የዓለምና የኢትዮጵያ ምጣኔ ሃብት እድገት እየተጓተት መሆኑን ያስታወሱት እዮብ (ዶ/ር)፤ በወረርሽኙ ሳቢያ የተወሰነው የአገሪቱ ኢኮኖሚ ክፍል ክፉኛ መጎዳቱን ይናገራሉ። "ከእነዚህ ጫናዎች ሳንላቀቅና የኮቪድ-19ን ሙሉ ጫና ሳንረዳ ከአሁኑ ሦስት ዓመት ብሎ መወሰን ለእኔ ግራ አጋቢ ነው። በበኩሌ የምቀበለው ነገር አይደለም" ሲሉ ይሞግታሉ። እዮብ (ዶ/ር) እንደሚሉት ወደዚህ አይነት የውጪ ምንዛሬ አስተዳደር ለማምረት የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶች እንደሚያስፈልጉ በማውሳት፤ ኢትዮጵያ ወደዚህ ከመሸጋገሯ በፊት "የማክሮ ኢኮኖሚውን ማረጋጋት ያስፈልጋል፣ የዋጋ ግሽበትን መቆጣጠር ያስፈልጋል፣ በቂ የውጪ ምንዛሬ ክምችት መኖር ይኖርበታል እንዲሁም የንግድ ሚዛን ጉድለት መጥበብ ይኖርበታል" ሲሉ ይመክራሉ። እንደ እዮብ (ዶ/ር) አመለካከት በገበያ ወደሚወሰን የምንዛሪ ሥርዓት ከመሸጋገራችን በፊት የዋጋ ግሽበት መጠንን ወደ አንድ አሃዝ ማምጣት "እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው።" "በገበያው ላይ በቂ የሆነ የውጪ ምንዛሪ መኖር ይኖርበታል። ይህ እንዲሆን ደግሞ በቂ የውጪ ምንዛሪ ክምችት ያስፈልጋል። ኢትዮጵያም የውጪ ምንዛሪ የምታገኘባቸውን መንገዶች መጨምር ይኖርባታል። ከውጪ የሚላክ ገንዘብ እንዲጨምር ማበረታቻ ማድረግ፣ ቱሪዝምና ኤክስፖርት ማደግ ይኖርባቸዋል" ይላሉ። ይህን የውጪ ምንዛሬ ሥርዓት ለመተግበር የተማረ ሰው ኃይልና ተቋማዊ ለውጥ የግድ እንደሚልም እዮብ ተስፋዬ (ዶ/ር) ያሳስባሉ። አይኤምኤፍ እና የዓለም ባንክ ግፊት ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅትና የዓለም ባንክ ኢትዮጵያ ገንዘቧ በገበያ ዋጋ እንዲተመን ግፊት እንደሚያሳድሩ ይነገራል። እዮብ (ዶ/ር) ለዚህ አንዱን ምክንያት ሲያስረዱ፤ አይኤምኤፍ ከተመሰረተባቸው ምክንያቶች አንዱ የዓለም አገራት የመገበያያ ገንዘብ ዋጋ እንዲረጋጋ ለማድረግ በመሆኑ ነው። "በእነሱ ፍልስፍና የምንዛሪ ተመን የተረጋጋ የሚሆነው ከመንግሥት ጣልቃ ገብነት ነጻ ሲሆን ነው። ምክንያቱም ምንዛሪ እንደማንኛውም ሸቀጥ ዋጋ አለው። እንደ ሌሎች ሸቀጦች ሁሉ ይህ ዋጋ በገበያ ኃይል መወሰን አለበት ብለው ያምናሉ" ሲሉ ያስረዳሉ። አለማየሁ ገዳ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ወደ ውጪ ከምትልከው ምርት በላይ ከውጪ የምታስገበው በብዙ እጥፍ የሚበልጥ በመሆኑ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ይህንን ልዩነት ለማጥበብ የብር ዋጋ በገበያ ቢወሰን በተሻለ መልኩ የውጪ ምንዛሪ እንዲገኝ ይረዳል የሚል እሳቤ ስላለ አገሪቱ ወደዚህ ሥርዓት እንድትገባ ጫና እንደሚደረግ ይናገራሉ። ይሁን እንጂ አለማየሁ (ዶ/ር) እንደሚሉት በኢትዮጵያዊያን ላኪዎች እንደችግር ከሚቀርቡት መካከል የውጪ ምንዛሬ አቅርቦት እጥረት ትልቁ ራስ ምታት አይደለም ባይ ናቸው። "እኔ ከመቶ በላይ ላኪዎችን አነጋግሬ የደረስኩበት ነገር፤ ለእኛ አገር ላኪዎች መሠረታዊ ችግር የሆነው የጥሬ እቃ አቅርቦት እጥረት፣ የመሬትና የፋይናንስን አቅርቦት ችግር፣ ሙስናና ጉምሩክ ላይ ያለው ውጣ ውረድ ነው እንጂ የዶላር እጥረት የላኪዎች ትልቁ ችግር አይደለም" ይላሉ። "ዋናው ጉዳይ መሆን ያለበት በትይዩ ገበያ [ጥቁር ገበያ] እና በባንክ መካከል ያለው ልዩነት እንዲሁም ወደ አገር በሚገባውና ወደ ውጪ በሚላከው መካከል ያለውን ልዩነት ማጥበብ ነው።" በእነዚህ መካከል ልዩነቱ የሰፋበት ዋነኛ ምክንያት ወደ ውጪ የሚላከው ምርት ስላላደገ እንደሆነ የሚናገሩት አለማየሁ (ዶ/ር) "በእኔ ስሌት ወደ አገር በሚገባውና ከውቺ በሚመጣው መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብ ወደ ውጪ የምንልካቸው ምርቶች በአማካይ በዓመት 20 በመቶ ለስምንት ተከታታይ ዓመት ማደግ ይኖርበታል" ይላሉ። ስለዚህም የመንግሥት ትኩረት መሆን ያለበት "ወደ ውጪ የሚላኩ ምርቶች የሚጨምሩበትን መንገድና ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን በአገር ውስጥ ለማምረት አምራቾችን ማበረታት ላይ ነው" ይላሉ አለማየሁ (ዶ/ር)። አዋጭ ነው? የባለሙያዎቹ ጠቅላላ ግምገማ ኢትዮጵያ ከሦስት ዓመታት በኋላ የብር የዋጋ ተመን በገበያ እንዲወሰን ብታደርግ ያዋጣታል? የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎቹ ማጠቃለያ ሃሳብ የሚከተለው ነው። እዮብ (ዶ/ር) - የምንዛሪ ሥርዓት መቀየርና በገበያ ዋጋ መወሰን እንዳለበት አምናለሁ። አካሄዱ ግን ቀስ በቀስ በሂደት መሆን አለበት። ብሔራዊ ባንክ በመጪዎቹ ሦስት ዓመታት ውስጥ መከናወን ያለባቸው ነገሮችን መሰራት ይኖርበታል፤ ለዚህ ደግሞ የዘርፉ ባለሙያና ተቋም ያስፈልጋል። አለማየሁ (ዶ/ር) - ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል። የውጪ ምንዛሪ ሥርዓታችንን ከመቀየራችን በፊት ቀድሞ መከናወን ያለባቸው የቤት ሥራዎች አሉ። አቶ ዋሲሁን - በጠቅላላው አዋጭ ነው ብዬ አስባለሁ። ሥርዓቱ በራሱ ጊዜ ወደ ዚያው እየወሰደን ይገኛል። በመጪው ሦስት ዓመታት ውስጥ የሚጠበቅብንን የቤት ሥራዎች ማከናወን የምንችል ከሆነ የሚየቀሩ ነገሮች ቢኖሩም ከሦስት ዓመታት በኋላ የብር ዋጋ በገበያ እንዲተመን ማድረጉ ትክክለኛ አካሄድ ነው።
https://www.bbc.com/amharic/news-53634447
3politics
የዶናልድ ትራምፕ መኖሪያ ቤት በኤፍቢአይ የተበረበረበት ምክንያት ይፋ ሊደረግ ነው
የኤፍቢአይ ወኪሎች የቀድሞውን የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን ቤት የበረበሩበት የፍተሻ ማዘዣ ይፋ እንዲደረግ የአገሪቱ ፍትህ ቢሮ የፍሎሪዳውን ፍርድ ቤት ጠየቀ። ያልተለመደ ነው የተባለለት ጥያቄ ፈቃድ ካገኘ የትራምፕ መኖሪያ ቤት እንዲፈተሽ የተደረገበት ምክንያት ለሕዝብ ይፋ ይሆናሉ ተብሏል። ዶናልድ ትራምፕ በተመሳሳይ የብርበራ ፍቃዱ ሰነድ ለሕዝብ ይፋ እንዲሆን ፍላጎታቸው እንደሆነ ገልጸዋል። የፍትህ ቢሮ ፍተሻው ለምን እንደተካሄደ እስካሁን ይፋ አላደረገም። የአሁኑ ጥያቄ ግን ለዚህ ምላሽ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል። ሰኞ ዕለት በኤፍቢአይወኪሎች የተደረገው ብርበራ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ጥብቅ እና ሚስጢራዊ ሰነዶች አያያዝ ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል ተብሎ ነበር። ስማቸው ያልተገለጸ አንድ ምንጭን ጠቅሶ ዋሽንግተን ፖስት እንዳስነበበው የኤፍቢአይ ወኪሎች ከኒውክለር መሣሪያዎች ጋር የተያያዙ ሰነዶችን ጭምር በትራምፕ መኖሪያ ቤት ስፈልጉ ነበር። ወኪሎቹ የቀድሞዋ ቀዳማዊት እመቤት ሜላኒያ ትራምፕን ቁም ሳጥን እና የግል ቁሳቁሶቻቸውን መበርበራቸውን ትራምፕ ገልጸዋል። ቀደም ሲል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ሜሪክ ጋርላንድ በትራምፕ መኖሪያ ቤት ላይ ፍተሻው እንዲካሄድ መፍቀዳቸውን ገልጸዋል። ከፍርድ ቤት ፍተሻ ማዘዣ ጋር የተገናኙ ሰነዶች ለሕዝብ ጥቅም ሲባሉ ይፋ እንዲሆኑ እየጠየቁ መሆኑን ጋርላንድ ተናግረዋል። የፍትህ ቢሮ ሁሌም መደበኛ ምርመራ በሚደረግበት ጊዜ እንደሚያደርገው ዝምታ የመምረጥ ልምዱን እየተከተለ ነው። የፍትህ ቢሮ ጠበቆች ሐሙስ ዕለት በፌዴራል ፍርድ ቤት ባቀረቡት አቤቱታ ላይ "በዚህ ሁኔታ የተከሰተውን ነገር ለመረዳት የሕዝቡ ግልጽ እና ከፍተኛ ፍላጎት ስላለው ይፋ መሆኑ ይጠቅማል” ብለዋል። የቀድሞ ፕሬዝዳንት መኖሪያ ቤት ከወንጀል ምርመራ ጋር በተያያዘ ሲፈተሽ የሰኞው በአሜሪካ ታሪክ የመጀመሪያው ነው። ትራምፕ እና ሌሎች ሪፐብሊካኖች እርምጃውን ፖለቲካዊ ይዘት ያለው ሲሉ አውግዘዋል። ሐሙስ ዕለት በጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት ጋርላንድ የኤፍቢአይ ወኪሎችን እና የፍትህ ክፍል ኃላፊዎችን ተከላክለዋል። ጠቅላይ ዓቃቤ ህጉ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ “ታማኝነታቸው ኢ-ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ሲጠቃ በዝምታ አላይም” ብለዋል። የፍተሻ ማዘዣውን ለማስፈጸም መወሰኑም ቀላል እንዳልነበር ተናግረዋል። የትራምፕ ጠበቃ የሆኑት ሊንሴይ ሃሊጋን ፍርድ ቤት ውሳኔ ከማስተላለፉ በፊት የህግ ቡድናቸው ማዘዣውን በመልቀቅ ጉዳይ ላይ እየተወያ ነው። የብርበራውን ፎቶ እና ቪዲዮ ይፋ ለማድረግም እያሰቡ ነው። የኤፍቢአይ ወኪሎች የማር-አ-ላጎ የሲሲቲቪ ካሜራዎች እንዲጠፉ ጠይቀው ነበር። የትራምፕ ሠራተኞች ግን ይህንን ለመቀበል ፈቃደኛ አልሆኑም ተብሏል።
የዶናልድ ትራምፕ መኖሪያ ቤት በኤፍቢአይ የተበረበረበት ምክንያት ይፋ ሊደረግ ነው የኤፍቢአይ ወኪሎች የቀድሞውን የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን ቤት የበረበሩበት የፍተሻ ማዘዣ ይፋ እንዲደረግ የአገሪቱ ፍትህ ቢሮ የፍሎሪዳውን ፍርድ ቤት ጠየቀ። ያልተለመደ ነው የተባለለት ጥያቄ ፈቃድ ካገኘ የትራምፕ መኖሪያ ቤት እንዲፈተሽ የተደረገበት ምክንያት ለሕዝብ ይፋ ይሆናሉ ተብሏል። ዶናልድ ትራምፕ በተመሳሳይ የብርበራ ፍቃዱ ሰነድ ለሕዝብ ይፋ እንዲሆን ፍላጎታቸው እንደሆነ ገልጸዋል። የፍትህ ቢሮ ፍተሻው ለምን እንደተካሄደ እስካሁን ይፋ አላደረገም። የአሁኑ ጥያቄ ግን ለዚህ ምላሽ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል። ሰኞ ዕለት በኤፍቢአይወኪሎች የተደረገው ብርበራ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ጥብቅ እና ሚስጢራዊ ሰነዶች አያያዝ ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል ተብሎ ነበር። ስማቸው ያልተገለጸ አንድ ምንጭን ጠቅሶ ዋሽንግተን ፖስት እንዳስነበበው የኤፍቢአይ ወኪሎች ከኒውክለር መሣሪያዎች ጋር የተያያዙ ሰነዶችን ጭምር በትራምፕ መኖሪያ ቤት ስፈልጉ ነበር። ወኪሎቹ የቀድሞዋ ቀዳማዊት እመቤት ሜላኒያ ትራምፕን ቁም ሳጥን እና የግል ቁሳቁሶቻቸውን መበርበራቸውን ትራምፕ ገልጸዋል። ቀደም ሲል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ሜሪክ ጋርላንድ በትራምፕ መኖሪያ ቤት ላይ ፍተሻው እንዲካሄድ መፍቀዳቸውን ገልጸዋል። ከፍርድ ቤት ፍተሻ ማዘዣ ጋር የተገናኙ ሰነዶች ለሕዝብ ጥቅም ሲባሉ ይፋ እንዲሆኑ እየጠየቁ መሆኑን ጋርላንድ ተናግረዋል። የፍትህ ቢሮ ሁሌም መደበኛ ምርመራ በሚደረግበት ጊዜ እንደሚያደርገው ዝምታ የመምረጥ ልምዱን እየተከተለ ነው። የፍትህ ቢሮ ጠበቆች ሐሙስ ዕለት በፌዴራል ፍርድ ቤት ባቀረቡት አቤቱታ ላይ "በዚህ ሁኔታ የተከሰተውን ነገር ለመረዳት የሕዝቡ ግልጽ እና ከፍተኛ ፍላጎት ስላለው ይፋ መሆኑ ይጠቅማል” ብለዋል። የቀድሞ ፕሬዝዳንት መኖሪያ ቤት ከወንጀል ምርመራ ጋር በተያያዘ ሲፈተሽ የሰኞው በአሜሪካ ታሪክ የመጀመሪያው ነው። ትራምፕ እና ሌሎች ሪፐብሊካኖች እርምጃውን ፖለቲካዊ ይዘት ያለው ሲሉ አውግዘዋል። ሐሙስ ዕለት በጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት ጋርላንድ የኤፍቢአይ ወኪሎችን እና የፍትህ ክፍል ኃላፊዎችን ተከላክለዋል። ጠቅላይ ዓቃቤ ህጉ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ “ታማኝነታቸው ኢ-ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ሲጠቃ በዝምታ አላይም” ብለዋል። የፍተሻ ማዘዣውን ለማስፈጸም መወሰኑም ቀላል እንዳልነበር ተናግረዋል። የትራምፕ ጠበቃ የሆኑት ሊንሴይ ሃሊጋን ፍርድ ቤት ውሳኔ ከማስተላለፉ በፊት የህግ ቡድናቸው ማዘዣውን በመልቀቅ ጉዳይ ላይ እየተወያ ነው። የብርበራውን ፎቶ እና ቪዲዮ ይፋ ለማድረግም እያሰቡ ነው። የኤፍቢአይ ወኪሎች የማር-አ-ላጎ የሲሲቲቪ ካሜራዎች እንዲጠፉ ጠይቀው ነበር። የትራምፕ ሠራተኞች ግን ይህንን ለመቀበል ፈቃደኛ አልሆኑም ተብሏል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c80qyv0xrwqo
0business
ኮሮናቫይረስ፡' 'ጨለምተኛው' ፕሮፌሰር "ዓለም ለ10 ዓመታት ትማቅቃለች" አሉ
ኖሪኤል ሮቢኒ ስመ ጥር የምጣኔ ሃብት ፕሮፌሰር ናቸው። መጪውን ዘመን በመተንበይ ይታወቃሉ። ሆኖም ሰውየው በጎ በጎው ስለማይታያቸው 'ጨለምተኛው ኢኮኖሚስት' የሚል ቅጽል ተበጅቶላቸዋል። ትንቢታቸው ጠብ አይልም የሚባሉት ፕሮፌሰር ሮቢኒ ከዚህ በፊት ባንኮችና የቁጠባ ቤት ገዢዎች በፈጠሩት ሀሳዊ የቢዝነስ ሽርክና የዓለም ኢኮኖሚ ይናጋል ብለው ከማንም በፊት ተንብየው ነበር፤ እንዳሉትም ሰመረላቸው። ይህ የሆነው በፈረንጆች 2008 የዛሬ 12 ዓመት ነበር። ዓለም አቀፉ የምጣኔ ሃብት ቀውስ ሊከሰት እንደሚችል ቀድመው ያዩት እኚህ ሰው ታዲያ ከሰሞኑ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ኮቪድ-19 የፈጠረው ምስቅልቅል ቢያንስ ለሚቀጥሉት 10 ዓመታት ዓለምን ያናጋታል፤ የዓለም ምጣኔ ሃብትም ለ10 ዓመታት ይማቅቃል ብለዋል። ሰውየው እንደሚሉት ይህ ወረርሽኝ በቁጥጥር ስር ውሎ በዓመት ውስጥ ምጣኔ ሃብቱ ማንሰራራት ቢጀምርም ነቀርሳው ግን ለሚቀጥሉት 10 ዓመታት ይቆያል። እንዲያውም አንዳንድ የሥራ ዘርፎች ጨርሶውኑ ላያንሰራሩ እንደሚችሉም ተንብየዋል። ወረርሽኙን ከ2008ቱ የምጣኔ ሃብት ቀውስ ጋር ሲወዳደርም ሆነ በ1930ዎቹ ከተከሰተው የዓለም ክፉው የምጣኔ ሃብት ድቀት ጋር ሲተያይ የአሁኑ የከፋ እንደሆነ ሮቢኒ ያብራራሉ። ያን ጊዜ ምርት በዓለም ላይ እንዲቀንስ ወይም የቀውሱን ምልክቶች በተግባር ለማየት ከችግሩ በኋላ ዓመታትን ወስዶ ነበር። ኮሮናቫይረስ ግን ከእነዚህ ሁለቱ ቀውሶችም በላይ ነው። በባህሪው ይለያል። ያስከተለውን የምርት ማሽቆልቆልን በግላጭ ለማየት ዓመታት ወይም ወራት አልወሰደበትም። በሳምንታት ውስጥ በመላው ዓለም ምርት ተንኮታክቷል። ይህ የሚነግረን መጪው ዘመን ፍጹም ጭጋጋማ መሆኑን ነው ይላሉ ፕሮፌሰሩ። "በዚያ ዘመን 3 ዓመት የወሰደው የምርት መንኮታኮት በዚህ ዘመን 3 ሳምንት ነው የወሰደበት።" ፕሮፌሰሩ ከምጣኔ ሃብት ቀውስ በኋላ የማገገሙን ሂደት ሲያስረዱ በሁለት የእንግሊዝኛ ሆሄያት ይመረኮዛሉ። ዩ እና ኤል ["U" እና "L"]። ዩ በእኛ ሀሌታው 'ሀ' ብለን ልንተረጉመው እንችላለን። የሀሌታው ሀ የማገገም ሂደት የሚያሳየው አንድ ምጣኔ ሀብት በአንዳች መጥፎ አጋጣሚ ሲንኮታኮት ቀስ በቀስ መሬት ይነካል። ከዚያ ወደነበረበት ለመመለስ የሀሌታው ሀ ቅርጽን ይዞ ሲንፏቀቅ ቆይቶ፣ በብዙ አዝጋሚ ሂደት ምጣኔ ሃብቱ ይመለሳል። ይህ ሂደት ዓመታትን የሚወስድ ነው። ከዚህ የተሻለው ደግሞ በቪ "V" ይወከላል። ቶሎ ወድቆ ቶሎ የሚያንሳራራ ምጣኔ ሃብት። አሁን የገጠመን ይላሉ ፕሮፌሰሩ፤ ኮቪድ-19 ያስከተለው የምጣኔ ሃብት ድቀት የሀሌታው ሀ ቅርጽን ሳይሆን የእንግሊዝኛው ሆሄ "L"ን ወይም በእኛ የ"ረ" ቅርጽ የያዘ ነው። ይህም ማለት በአንድ ጊዜ ዘጭ ያለው ምጣኔ ሃብት ጨርሱኑ አያንሰራራም ወይም ለማንሰራራት አሥር ዓመት ይወስድበታል። 'ጨለምተኛው' ፕሮፌሰር እንዲያውም የኮቪድ-19 ተጽእኖ የመጪውን ዘመን ምጣኔ ሃብት በአይ ሆሄ "I" የሚወከል እንዳይሆን ይሰጋሉ። እንደወደቀ የሚቀር ኢኮኖሚ። በፕሮፌሰሩ ትንቢት መሠረት በዚህ ወረርሽኝ ሥራ ያጡ ዜጎች ወደ ሥራቸው የመመለስ ዕድላቸው አነስተኛ ነው። ከተመለሱም በጊዝያዊ ሠራተኝነት እንጂ ቋሚ ሥራ የሚያገኙት በጣም ጥቂቶች ናቸው። ከደመወዝ ውጭ ያሉ ጥቅማጥቅሞች ከዚህ በኋላ የሚታሰቡ አይሆኑም። በዝቅተኛና መካከለኛ የቅጥር ሥራ ላይ ያሉ ሰዎችም ቢሆን የሥራ ዋስትና አይኖራቸውም። ይህ በብዙ የምርት ዘርፎች ላይ ይታያል ይላሉ ፕሮፌሰሩ። ከዚህ በኋላ ምርት አይጨምርም፤ የአገራትም ሆነ የኩባንያዎች እድገት ባለበት እርገጥ ይሆናል፣ ሰዎች ገቢያቸው ይደቃል፤ ገበያ ይተናል፣ ፍላጎት ይከስማል። "ሰዎች ስለ ቢዝነስ መልሶ መከፈት ያወራሉ፤ ቢከፍቱስ ማን ይገዛቸዋል? ጀርመን ሱቆችን ከፈተች፤ ገዢ ግን የለም። ቻይና ትልልቅ የንግድ መደብሮቿ ክፍት ናቸው፤ ማን ይገዛቸዋል? ከፍተው ነው የሚዘጉት፤ በረራዎች ተስተጓጉለዋል…ይህ ሁኔታ ለዓመታት የሚቀጥል ነው የሚሆነው" ይላሉ ፕሮፌሰሩ። ፕሮፌሰር ሮቤኒን ከበለጸጉ አገራት ይልቅ ታዳጊ የእሲያ ምጣኔ ሃብት በሁለት እግሩ ለመቆም የተሻለ እድል እንዳለውም ተናግረዋል። ፕሮፌሰር ኖሪኤል ሮቢኒ ሌላው ትንቢታቸው ዓለም ልክ እንደ ቀዝቃዛው ጦርነት ዘመን በሁለት ግዙፍ እድሮች እንደሚሰባሰብ ነው። የእድሮቹ አባቶች የሚሆኑትም ቻይናና አሜሪካ ይሆናሉ ይላሉ። ሁለቱ አገራት ግንኙነታቸው እየሻከረ እንደሚሄድና የራሳቸውን የምጣኔ ሃብት አጋሮች ማሰባሰብ እንደሚጀምሩ አስምረውበታል። አብዛኛዎቹ የእሲያና ታዳጊ አገራት ከእነዚህ ሁለት አገሮች ወደ አንዱ እድር እንዲገቡ የሚገደዱበት ሁኔታ እንደሚፈጠርም ፕሮፌሰሩ ተንብየዋል። "ሁለቱ የእድር አባቶች ወይ ከእኔ ጋር ነህ፣ ከእኔ ካልሆንክ ደግሞ ከጠላቴ ጋር ነህ ማለት ይጀምራሉ። ይህ ማለት ወይ የእኔን 5ጂ ትጠቀማለህ፣ አልያም የጠላቴን፤ ወይ የእኔን አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ትጠቀማለህ ወይም የጠላቴን…እየተባለ ሁለት ዓለም ይፈጠራል። ታዳጊ አገራትም በሁለት ቢላ መብላት አይፈቀድላቸውም" ይላሉ ፕሮፌሰሩ። ከኒውዮርክ ቤታቸው ሆነው ቢቢሲ ጋር ቆይታ ያደረጉት ፕሮፌሰር ሮቢኒ ጨለምተኛው ፕሮፌሰር ስለመባላቸው አስተያየት ሲጠየቁ "ከዚያ ይልቅ እቅጩን ነጋሪው ፕሮፌሰር የሚለው ስም ይመጥነኛል" ብለዋል።
ኮሮናቫይረስ፡' 'ጨለምተኛው' ፕሮፌሰር "ዓለም ለ10 ዓመታት ትማቅቃለች" አሉ ኖሪኤል ሮቢኒ ስመ ጥር የምጣኔ ሃብት ፕሮፌሰር ናቸው። መጪውን ዘመን በመተንበይ ይታወቃሉ። ሆኖም ሰውየው በጎ በጎው ስለማይታያቸው 'ጨለምተኛው ኢኮኖሚስት' የሚል ቅጽል ተበጅቶላቸዋል። ትንቢታቸው ጠብ አይልም የሚባሉት ፕሮፌሰር ሮቢኒ ከዚህ በፊት ባንኮችና የቁጠባ ቤት ገዢዎች በፈጠሩት ሀሳዊ የቢዝነስ ሽርክና የዓለም ኢኮኖሚ ይናጋል ብለው ከማንም በፊት ተንብየው ነበር፤ እንዳሉትም ሰመረላቸው። ይህ የሆነው በፈረንጆች 2008 የዛሬ 12 ዓመት ነበር። ዓለም አቀፉ የምጣኔ ሃብት ቀውስ ሊከሰት እንደሚችል ቀድመው ያዩት እኚህ ሰው ታዲያ ከሰሞኑ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ኮቪድ-19 የፈጠረው ምስቅልቅል ቢያንስ ለሚቀጥሉት 10 ዓመታት ዓለምን ያናጋታል፤ የዓለም ምጣኔ ሃብትም ለ10 ዓመታት ይማቅቃል ብለዋል። ሰውየው እንደሚሉት ይህ ወረርሽኝ በቁጥጥር ስር ውሎ በዓመት ውስጥ ምጣኔ ሃብቱ ማንሰራራት ቢጀምርም ነቀርሳው ግን ለሚቀጥሉት 10 ዓመታት ይቆያል። እንዲያውም አንዳንድ የሥራ ዘርፎች ጨርሶውኑ ላያንሰራሩ እንደሚችሉም ተንብየዋል። ወረርሽኙን ከ2008ቱ የምጣኔ ሃብት ቀውስ ጋር ሲወዳደርም ሆነ በ1930ዎቹ ከተከሰተው የዓለም ክፉው የምጣኔ ሃብት ድቀት ጋር ሲተያይ የአሁኑ የከፋ እንደሆነ ሮቢኒ ያብራራሉ። ያን ጊዜ ምርት በዓለም ላይ እንዲቀንስ ወይም የቀውሱን ምልክቶች በተግባር ለማየት ከችግሩ በኋላ ዓመታትን ወስዶ ነበር። ኮሮናቫይረስ ግን ከእነዚህ ሁለቱ ቀውሶችም በላይ ነው። በባህሪው ይለያል። ያስከተለውን የምርት ማሽቆልቆልን በግላጭ ለማየት ዓመታት ወይም ወራት አልወሰደበትም። በሳምንታት ውስጥ በመላው ዓለም ምርት ተንኮታክቷል። ይህ የሚነግረን መጪው ዘመን ፍጹም ጭጋጋማ መሆኑን ነው ይላሉ ፕሮፌሰሩ። "በዚያ ዘመን 3 ዓመት የወሰደው የምርት መንኮታኮት በዚህ ዘመን 3 ሳምንት ነው የወሰደበት።" ፕሮፌሰሩ ከምጣኔ ሃብት ቀውስ በኋላ የማገገሙን ሂደት ሲያስረዱ በሁለት የእንግሊዝኛ ሆሄያት ይመረኮዛሉ። ዩ እና ኤል ["U" እና "L"]። ዩ በእኛ ሀሌታው 'ሀ' ብለን ልንተረጉመው እንችላለን። የሀሌታው ሀ የማገገም ሂደት የሚያሳየው አንድ ምጣኔ ሀብት በአንዳች መጥፎ አጋጣሚ ሲንኮታኮት ቀስ በቀስ መሬት ይነካል። ከዚያ ወደነበረበት ለመመለስ የሀሌታው ሀ ቅርጽን ይዞ ሲንፏቀቅ ቆይቶ፣ በብዙ አዝጋሚ ሂደት ምጣኔ ሃብቱ ይመለሳል። ይህ ሂደት ዓመታትን የሚወስድ ነው። ከዚህ የተሻለው ደግሞ በቪ "V" ይወከላል። ቶሎ ወድቆ ቶሎ የሚያንሳራራ ምጣኔ ሃብት። አሁን የገጠመን ይላሉ ፕሮፌሰሩ፤ ኮቪድ-19 ያስከተለው የምጣኔ ሃብት ድቀት የሀሌታው ሀ ቅርጽን ሳይሆን የእንግሊዝኛው ሆሄ "L"ን ወይም በእኛ የ"ረ" ቅርጽ የያዘ ነው። ይህም ማለት በአንድ ጊዜ ዘጭ ያለው ምጣኔ ሃብት ጨርሱኑ አያንሰራራም ወይም ለማንሰራራት አሥር ዓመት ይወስድበታል። 'ጨለምተኛው' ፕሮፌሰር እንዲያውም የኮቪድ-19 ተጽእኖ የመጪውን ዘመን ምጣኔ ሃብት በአይ ሆሄ "I" የሚወከል እንዳይሆን ይሰጋሉ። እንደወደቀ የሚቀር ኢኮኖሚ። በፕሮፌሰሩ ትንቢት መሠረት በዚህ ወረርሽኝ ሥራ ያጡ ዜጎች ወደ ሥራቸው የመመለስ ዕድላቸው አነስተኛ ነው። ከተመለሱም በጊዝያዊ ሠራተኝነት እንጂ ቋሚ ሥራ የሚያገኙት በጣም ጥቂቶች ናቸው። ከደመወዝ ውጭ ያሉ ጥቅማጥቅሞች ከዚህ በኋላ የሚታሰቡ አይሆኑም። በዝቅተኛና መካከለኛ የቅጥር ሥራ ላይ ያሉ ሰዎችም ቢሆን የሥራ ዋስትና አይኖራቸውም። ይህ በብዙ የምርት ዘርፎች ላይ ይታያል ይላሉ ፕሮፌሰሩ። ከዚህ በኋላ ምርት አይጨምርም፤ የአገራትም ሆነ የኩባንያዎች እድገት ባለበት እርገጥ ይሆናል፣ ሰዎች ገቢያቸው ይደቃል፤ ገበያ ይተናል፣ ፍላጎት ይከስማል። "ሰዎች ስለ ቢዝነስ መልሶ መከፈት ያወራሉ፤ ቢከፍቱስ ማን ይገዛቸዋል? ጀርመን ሱቆችን ከፈተች፤ ገዢ ግን የለም። ቻይና ትልልቅ የንግድ መደብሮቿ ክፍት ናቸው፤ ማን ይገዛቸዋል? ከፍተው ነው የሚዘጉት፤ በረራዎች ተስተጓጉለዋል…ይህ ሁኔታ ለዓመታት የሚቀጥል ነው የሚሆነው" ይላሉ ፕሮፌሰሩ። ፕሮፌሰር ሮቤኒን ከበለጸጉ አገራት ይልቅ ታዳጊ የእሲያ ምጣኔ ሃብት በሁለት እግሩ ለመቆም የተሻለ እድል እንዳለውም ተናግረዋል። ፕሮፌሰር ኖሪኤል ሮቢኒ ሌላው ትንቢታቸው ዓለም ልክ እንደ ቀዝቃዛው ጦርነት ዘመን በሁለት ግዙፍ እድሮች እንደሚሰባሰብ ነው። የእድሮቹ አባቶች የሚሆኑትም ቻይናና አሜሪካ ይሆናሉ ይላሉ። ሁለቱ አገራት ግንኙነታቸው እየሻከረ እንደሚሄድና የራሳቸውን የምጣኔ ሃብት አጋሮች ማሰባሰብ እንደሚጀምሩ አስምረውበታል። አብዛኛዎቹ የእሲያና ታዳጊ አገራት ከእነዚህ ሁለት አገሮች ወደ አንዱ እድር እንዲገቡ የሚገደዱበት ሁኔታ እንደሚፈጠርም ፕሮፌሰሩ ተንብየዋል። "ሁለቱ የእድር አባቶች ወይ ከእኔ ጋር ነህ፣ ከእኔ ካልሆንክ ደግሞ ከጠላቴ ጋር ነህ ማለት ይጀምራሉ። ይህ ማለት ወይ የእኔን 5ጂ ትጠቀማለህ፣ አልያም የጠላቴን፤ ወይ የእኔን አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ትጠቀማለህ ወይም የጠላቴን…እየተባለ ሁለት ዓለም ይፈጠራል። ታዳጊ አገራትም በሁለት ቢላ መብላት አይፈቀድላቸውም" ይላሉ ፕሮፌሰሩ። ከኒውዮርክ ቤታቸው ሆነው ቢቢሲ ጋር ቆይታ ያደረጉት ፕሮፌሰር ሮቢኒ ጨለምተኛው ፕሮፌሰር ስለመባላቸው አስተያየት ሲጠየቁ "ከዚያ ይልቅ እቅጩን ነጋሪው ፕሮፌሰር የሚለው ስም ይመጥነኛል" ብለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-52796482
5sports
"እንዴት ለሴት ልጅ የወንዶች ክለብ ይሰጣል?' ተብሎ ነበር" ኢንስትራክተር መሠረት ማኒ
ውልደቷ ድሬዳዋ ነው፤ ልዩ ስሙ አንደኛ መንገድ ከሚባል ሥፍራ፤ ደቻቱ ግድም ማለት ነው። ይህ ሠፈር ደግሞ ለአሸዋው ቅርብ ነው። ኳስ እያንቀረቀቡ ለማደግ የሰጠ ነው። አንደኛ ደረጃ ትምህርቷን በለገሃሬ፤ ሁለተኛውን ደግሞ በድሬዳዋ አጠቃላይ ትምህርት ቤት ተስተምራለች። ፊፋ በ1983 የዓለም የሴቶች እግር ኳስ ዋንጫን በይፋ ከማካሄዱ በፊት ሴቶቹ በይፋ እግር ኳስ እንዲጫወቱ አይፈቀድም [አይፈለግምም] ነበር። ነገር ግን ይህ ኳስ ከመጫወት አላገዳትም [በፕሮፌሽናል ደረጃ ባይሆንም]። ማንም ከተጫዋችነት ወደ አሠልጣኝነት ወደ መምጣት የከለከላት አልነበረም፤ በኢትዮጵያ [በአፍሪካም] ታሪክ የመጀመሪያዋ ሴት የወንዶች እግር ኳስ ቡድን አሠልጣኝ ከመሆን ሊመልሳት የቻለም አልተገኘም. . . እርሷም ማንም ወደኋላ እንዲጎትታት አልፈቀደችም. . . መሠረት ማኒ። • «የኔ ትውልድ ታሪክ እንደሚሠራ እምነት አለኝ» ሎዛ አበራ «አሠልጣኝነትን የጀመርኩት ገና በልጅነቴ ነው ። ልጅ እያለሁ ራሱ 'የሊደርሺፕ' ተሰጥዖ ነበረኝ። ከዚያ ጓደኞቼን ሰብስቤ 'ድል በትግል' የሚባል ቡድን መሠረትኩ። ከዚያ የሕንፃ ቡድን፤ ቀጥሎ የመድህን ድርጅት የተወሰነ ድጋፍ እያደረገልኝ ማሠልጠን ጀምርኩ። ከዚያ የ'ሴቭ ዘ ቺልድረን' የሴቶች እና ወንዶች ቡድንን መሥርቼ ማሠልጠን ያዝኩ።» መሠረት የምታሠለጥነው የእግር ኳስ ቡድኖችን ብቻ አልነበረም። የቴኒስ እና መረብ ኳስ ቡድኖችንም ታሠለጥን ነበር። 'ማቴሪያል' ስለነበር ፍላጎቱ ያላቸው የድሬዳዋ ልጆች እንዲሠለጥኑ አደርግ ነበር። 1970 ዎቹ ላይ እነ ማክዳ፣ ታጠቅ፣ አየር ኃይል እና መሰል የሴት እግር ኳስ ቡድኖች፤ የሴቶች እግር ኳስ ሲቋረጥ በዚያ ከሰሙ። ከዚያ 1986 ላይ የመጀመሪያውን የሴቶች እግር ኳስ ቡድን በማቋቋም በታሪክ መዝገብ ስሟን አሰፈረች። 2004 ላይ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚዬር ሊግ ሲጀመር መሠረት የከተማዋን ሴቶች ቡድን ይዛ ተቀላቀለች። 2007 ላይ ድሬዳዋ ከነማ የፕሪሚዬር ሊጉ ታናሽ በሆነው የሊግ ውድድር ላይ ተሳታፊ ነበር። ይሄኔ ነው መሠረት ማኒ የወንዶቹን ቡድን ተረክባ ለፕሪሚዬር ሊግ ለማሰለፍ ቃል በመግባት ሥራ የጀመረችው። «እርግጥ በጣም 'ቻሌንጂንግ' ነበር። ቢሆንም ለእኔ ብዙ ያልከበደኝ፤ ከልጅነቴም ጀምሮ ወንዶችን እያሠለጠንኩ ማደጌ ነው። ትላልቆቹም ሳሰለጥናቸው የሚሠጡኝ አክብሮትና ፍቅር እንዲሁም ኃላፊነታቸውን የሚወጡበት መንገድ አቅም ሆኖኝ ነበር። በፆታ መለካቴ ግን አልቀረም። 'እንዴት ለሴት ልጅ የወንዶች ክለብ ይሰጣል? ቀልድ ነው እንዴ የያዙት?' ያሉ አልጠፉም ነበር። አንዳንዶቹም እንደውም ይሄ ለፖለቲካ 'ኮንሳምፕሽን' ነው ብለው ከንቲባው [የድሬዳዋ] ድረስ ይሄዱ ነበር። ነገር ግን ለኔ የበለጠ አቅም ነበር የሆነኝ። ምክንያቱም ይህንን መቀየር አለብኝ አልኩኝ፤ በምን? በውጤት።» ከውጭ ብዙ ፈተና የገጠማት መሠረት ከውስጥም መንገዱ አልጋ 'ባልጋ አልሆነላትም። በዚያ ላይ የመጀመሪያው ዙር ለመሠረት ቀላል የሚባል አልነበረም፤ ሦስት ነጥብ ማግኘት። «ተጨዋቾቼን ማሳመን አንዱ ፈተና ነበር። በሴት ሠልጥነው አያውቁም፤ ትልልቅ ተጨዋቾች ናቸው። 'እንዴት ነው አሁን እሷ እኛን የምትመራን?' የሚል ጥያቄ ነበራቸው። አንዳንዶቹ የመሥራት ፍላጎታቸው ውርድ ያለም ነበር። ነገር ግን ልጆቼን በሥራ ማሳመን ቻልኩኝ። በተለይ ሁለተኛው ዙር ላይ በውጤት በጣም አሪፍ ነበርን። እንደውም ከ12 ጨዋታ 11 አሸንፈን በአንዱ ብቻ ነው አቻ የተለያየነው።» ጉዞ ወደፕሪሚዬር ሊግ ድሬዳዋ ከነማ በአሠልጣኝ መሠረት ማኒ እየተመራ ፕሪሚዬር ሊግ ገባ። ሁሉም 'ሴት የወንዶች አሠልጣኝ?' ሲል መጠየቅ ጀመረ። አድኖቆት ጎረፈላት። ተጫዋቾች፣ ኢትዮጵያውያን፣ በተለይ ደግሞ ድሬዎች ቆመው አጨበጨቡላት። ፕሪሚዬር ሊግ ከብሔራዊ ሊግ ሲነፃፀር ከበድ [በጥራት] ያለ ቢሆንም መሠረትን የሚያቆም ግን አልተገኘም። ክለቧ ትልቁ ዓላማው የነበረው ከፕሪሚዬር ሊጉ ተመልሶ አለመውረድ ነበር። መሠረት ግን አለመውረድ አላስጨነቃትም፤ ውጤቱ የበለጠ እንዲያምር ጣረች። «ስንጀምረው አራት ጨዋታ ማሸነፍ አልቻልንም ነበር። ከአምስተኛው ጨዋታ በኋላ ግን ሁሉንም እያስተካከልን መጣን። እንደውም በአንደኛው ዙር አምስተኛ ሆነን ጨረስን፤ ይሄ ደግሞ ትልቅ ድል ነው። በተለይ ከብሔራዊ ሊግ ለመጣ ቡድን ሊያውም በሴት አሠልጣኝ ለሚሠለጥን።» ቢሆንም ሁለተኛው ዙር የድሬዳዋ ውጤት ዕለት ተ'ለት ያሽቆለቁል ያዘ። በመጀመሪያዎቹ አምስት ጨዋታዎች ጥሩ ውጤታ ማምጣት የቻለው ድሬዳዋ ከነማ ሦስት ነጥብ ብርቁ ሆነ። ምን ተፈጠረ? «እኔ እስከዛሬም ድረስ ሳስበው ግራ ይገባኛል። ምንድን ነው ነገሩ ብዬ ልጆቼን ጠየቅኩ፤ ግን አጥጋቢ ምላሽ አላገኘሁም። አንድ የማላውቀው እና ውጤታችንን እንዲያሽቆለቁል ያደረገ ነገር እንዳለ አሁንም ድረስ ይሰማኛል። አሁን ራሱ አንዳድንድ ተጨዋቾችን ሳገኝ እጠይቃለሁ፤ ግን ብዙም አይነግሩኝም። የሆነ ነገር እንዳለ ግን ይሰማኛል፤ ከውጭም ከውስጥም። ወደፊትም መጠየቄን አላቆምም።» • ሴት እግር ኳሰኞች ስንት ይከፈላቸው ይሆን? ከዚያ «በዚህ መንገድ መቀጠል አልቻልኩም ትላለች» መሠረት። «ገንዘብ ፈልጌ አይደለም የመጣሁት እኔ። እኔ መሥራት ነው የምፈልገው። በዚህ መንገድ መቀጠል ደግሞ አልፈልግም። ጫናዎች በዝተዋል። እግር ኳስ ደግሞ ነፃነት ይፈልጋል። እኔ በቃኝ 'ቴንኪው' ብዬ፤ ልጆቼን እና 'ስታፉን' ተሰናብቼ ቡደኑን ለቅቄ ወጣሁ።» ይህ የሆነው እንግዲህ 2008 ላይ ነው። መሠረት 2002 ላይ ሉሲዎችን ተረክባ ታሪክ ፅፋለች፤ ታሪኩ ምንድን ነው? ብሎ ለሚጠይቅ 'ቡድኑ ለመጀመሪያ ጊዜ በሴት አሠልጣኝ የተመራበት ወቅት በመሆኑ [የተሰጣት ኮንትራት የ3 ወራት ብቻ ቢሆንም]' መልሷ ነው። መሠረት ከዚያ በኋላ በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን ስፖርት ፌዴሬሽን በቀረበላት ግብዣ ወደ አሜሪካ አቀናች። ለሁለተኛ ጊዜ ደግሞ ከአሜሪካ ኤምባሲ በቀረባለት ግብዣ አሜሪካ ደርሳ ተመልሳለች። ወደ አሜሪካ ከማቅናቷ በፊት ሉሲዎችን እንደገና ተረክባ ነበር [2009]። ስትመለስ ግን የአሠልጣኝነት ቦታው በሌላ ሰው ተይዞ ጠበቃት። እንደገና ሉሲዎችን ተረክባ ወደ ኡጋንዳ አቀናች፤ በሴካፋ ዋንጫ ላይ ለመሳተፍ። ኳስ ይዞ በማጥቃት የአጨዋወት ስልት የምትታወቀው መሠረት ውድድሩን ሦስተኛ ሆና በማጠናቀቅ የነሃስ ሜዳሊያ ይዛ ተመለሰች [የራሳችን ድክመት ነው እንጂ ዋንጫ ማምጣት ይገባን ነበር ትላለች]። ቢሆንም ኮንትራቷ ከመጠናቀቁ በፊት ሉሲዎች ሌላ አሠልጣኝ ተሾመላቸው። መሠረት አዲሱን መፅሐፏን ለማስመረቅ ጉድ ጉድ በማለት ላይ ትገኛለች። 'የስኬት ተምሳሌት' የተሰኘ ርዕስ ሰጥታዋለች። ያለፈችበትን ውጣ ውረድ የሚያትት 198 ገፆች ያሉት መፅሐፍ ነው። «ይሄኔ ነው ጀምሬው የነበረውን መፅሐፍ ልጨርስ ብዬ ትኩረቴን ወደዚያ ያደርግኩት» ብላናለች። መሠረት ድሬዳዋ ከነማ እያለሽ ምን ያህል ነበር የሚከፈልሽ? እንደው ፈቃደኛ ከሆንሽ ብትነግሪን? «ኧረ በደንብ ነው ምነግርህ [ፈገግታ]. . . እንግዲህ እኔ ፕሪሚዬር ሊግ እያለሁ 14 ክለቦች ነበሩ። በወቅቱ ዝቅተኛው የአሠልጣኝ ክፍያ የኔ ነበር። ተቆራርጦ እጄ ላይ 'ሚደርሰኝ 13ሺህ 500 ብር ነበር። ያኔ የወረዱት ዳሸንና የሆሳዕና ቡድን አሠልጣኞች ከኔ የተሻለ ክፍያ ያገኙ እንደነበር አውቃለሁ። ምክንያቱም እኔ ብዙ ጊዜ በፆታዬ ነው 'ምለካው። እንጂ ባለኝ አቅም አልነበረም። ይሄን ሳስብ ያመኛል ግን በቃ ፍቅር ነው፤ ኳሱን እወደዋለሁ፤ እሠራዋለሁ። አሠልጣኞች እና ተጨዋቾች በድህረ-ጨዋታ መጨባበጥና ማልያ መቀያየር የተለመደ ነው። እርግጥ አሁን አሁን በሰላም ጨዋታን መጨረስ በራሱ ትልቅ ድል እየሆነ ቢመጣም። እንደው በመሠረት እንዴት እንሸነፋለን ያሉ አሠልጣኞች እና ተጫዋቾች እጅ ነስተዋት ያውቁ ይሆን? «የነፈጉኝን እንኳ ብዙም አላስታውስም፤ ግን እኔ አንድ ጊዜ በደስታ ውስጥ ሆኜ ሳልጨባበጥ በመቅረቴ ተከስሻለሁ። እዚሁ ድሬዳዋ ላይ ነው። ከሙገር ሲሚንቶ ጋር እየተጫወትን ነበር። ደርቢ በመሆናችን ጨዋታው ደመቅ ያለ ነበር። 0-0 ነበርንና ባለቀ ሰዓት አገባንና አሸነፍን። በቃ በጣም ደስተኛ ስለነበርኩ የሙገር አሠልጣኝን ሳልጨብጠው ቀረሁ። ከዚያ እስከ ክስ ደረጃ ደርሶ ነበር።» ሰዎች አሠልጣኝ መሠረትን ሲያስቡ ቀድሞ ትዝ የሚለቸው ከድሬዳዋ ከነማ ጋር የተጎናፀፈችው ስኬት ነው። እርሷም ከማትረሳቸው ድሎች መካከል አንዱ እርሱ ነው። ግን ከዚያም በላይ የማልረሳው ትላለች መሠረት. . . «የማልረሳቸው ሁለት ቀናት አሉ። አንደኛው ከአዲስ አበባ ከነማ ጋር አራት ውስጥ ለመግባት የተጫወትነው ነው። 1 ለ 0 እየመራን ነበር፤ ከዚያ አቻ ሆንን። አንድ ጨምረን መምራት ያዝን፤ ግን መልሶ ተቆጠረብን። በስመዓብ አሁን በቃ 2 ለ 2 ሆነን ወደ ፍፁም ቅጣት ምት ልንሄድ ነው። ከምክትሌ ጋር ተነጋገርኩና 'ቤንቹ' በረኛ 'ፔናሊቲ' ጎበዝ ስለሆነ ብለን አስገባነው። በረኛችን ሦስት ጎል አዳነልንና አሸነፍን።» «ሁለተኛው ቅዱስ ጊዮርጊስን የረታንበትን ነው። እንግዲህ ጊዮርጊስ በጣም ትልቅ ቡድን ነው። እኔ ደግሞ ፕሪሚዬር ሊጉ አዲሴ ነው። እና በሜዳዬ ሊያውም በጨዋታ ብልጫ ማሸነፌ ፍፁም አልረሳውም። በጣም ልዩ ነበር። መሠረት አሁን ላይ የአዲስ አበባ ሴቶች እግር ኳስ ቡድንን በማሠልጠን ላይ ትገኛለች። አንደኛ ዲቪዚዮን ላይ እየተጫወተ የሚገኘው አ.አ. ስድስተኛ ደረጃን ይዞ የውድድር ዘመኑን አጠናቋል። መሠረት ስለወደፊቱ ዕቅዷ እጅጉን እያሰበችበት እንደሆነ አልደበቀችንም። «ብዙ ዕቅዶች አሉኝ። የሕፃናት አካዳሚም አለኝ [120 ሕፃናት ያሉት]። እሱን ከፍ ማድረግም ሕልሜ ነው። የአሠልጣኝነት ጥያቄዎችም ይመጣሉ። እውነት ለመናገር ብዙ 'ፍራስትሬት' የሚያደርጉ አጋጣሚዎች ገጥመውኛል። ሙያውን ለመተው ሁላ አስቤ አውቃለሁ፤ ግን ደግሞ ብዙ ሰዎች ይህን ውሳኔዬን ሲቃወሙ አያለሁ። በተለይ ያሠለጠንኳቸው ልጆች 'ኖ መቀጠል አለብሽ' የሚል አስተያየት ይሰጡኛል። ስለዚህ ቁጭ ብዬ ማሰብ አለብኝ ብያለሁ።» በኢትዮጵያም ሆነ በአህጉረ አፍሪካ ከመሠረት ሌላ ሴት የወንዶች እግር ኳስ ክለብ አሠልጣኝ እንዳለች አልሰማንም፤ አላየንም። ይህንን ክብር መጎናፀፍ ምን ዓይነት ስሜት ይሰጥ ይሆን? «በጣም ነው ደስ የሚለኝ። ሌላ ሴት አለመኖሯ ሳይሆን፤ ስኬታማ መሆን መቻሌ ደስ ያሰኘኛል። ሴት ልጅ ይህንን ማድረግ እንደምትችል ደግሞ ማሳየት መቻሌ እጅግ ያኮራኛል። እንጂ ብቸኛ ስለሆንኩኝ አይደለም፤ በቃ ይቻላል የሚለውን መንፈስ ማንገስ መቻሌ ነው። ሁሌም የምለው ሴቶች በፆታቸው ሳይሆን በአቅማቸው ቢለኩ ነው።» «አንዲት ሴት አናጢም መሆን ትፈልግ፣ ኢንጅነር ወይም ኤሌክትሪሺያን ለዚያ ሙያ የሚሆን ዕውቀት ያስፈልጋታል። ይህ ደግሞ እንዲሁ አይገኝም፤ ልፋት ይጠይቃል፤ ጥረት ያስፈልጋል፤ ድካም ያስፈልጋል፤ በቀላሉ የሚገኝ ነገር የለም። እኔ ሴት ስለሆንኩ እንደው እንደ ገፀ-በረከት እንዲሰጠኝ አልፈልግም። በራሴ ልክ፤ ባለኝ አቅም እንጂ። የማይቻል ምንም ነገር የለም። ሕልም ይኑረን።» እኛም ምክር ያፅና ብለናል፤ ለመሠረትም መልካም ዕድል! • "የናንዬ ሕይወት" የአይዳ ዕደማርያም ምስል ከሳች መፀሐፍ
"እንዴት ለሴት ልጅ የወንዶች ክለብ ይሰጣል?' ተብሎ ነበር" ኢንስትራክተር መሠረት ማኒ ውልደቷ ድሬዳዋ ነው፤ ልዩ ስሙ አንደኛ መንገድ ከሚባል ሥፍራ፤ ደቻቱ ግድም ማለት ነው። ይህ ሠፈር ደግሞ ለአሸዋው ቅርብ ነው። ኳስ እያንቀረቀቡ ለማደግ የሰጠ ነው። አንደኛ ደረጃ ትምህርቷን በለገሃሬ፤ ሁለተኛውን ደግሞ በድሬዳዋ አጠቃላይ ትምህርት ቤት ተስተምራለች። ፊፋ በ1983 የዓለም የሴቶች እግር ኳስ ዋንጫን በይፋ ከማካሄዱ በፊት ሴቶቹ በይፋ እግር ኳስ እንዲጫወቱ አይፈቀድም [አይፈለግምም] ነበር። ነገር ግን ይህ ኳስ ከመጫወት አላገዳትም [በፕሮፌሽናል ደረጃ ባይሆንም]። ማንም ከተጫዋችነት ወደ አሠልጣኝነት ወደ መምጣት የከለከላት አልነበረም፤ በኢትዮጵያ [በአፍሪካም] ታሪክ የመጀመሪያዋ ሴት የወንዶች እግር ኳስ ቡድን አሠልጣኝ ከመሆን ሊመልሳት የቻለም አልተገኘም. . . እርሷም ማንም ወደኋላ እንዲጎትታት አልፈቀደችም. . . መሠረት ማኒ። • «የኔ ትውልድ ታሪክ እንደሚሠራ እምነት አለኝ» ሎዛ አበራ «አሠልጣኝነትን የጀመርኩት ገና በልጅነቴ ነው ። ልጅ እያለሁ ራሱ 'የሊደርሺፕ' ተሰጥዖ ነበረኝ። ከዚያ ጓደኞቼን ሰብስቤ 'ድል በትግል' የሚባል ቡድን መሠረትኩ። ከዚያ የሕንፃ ቡድን፤ ቀጥሎ የመድህን ድርጅት የተወሰነ ድጋፍ እያደረገልኝ ማሠልጠን ጀምርኩ። ከዚያ የ'ሴቭ ዘ ቺልድረን' የሴቶች እና ወንዶች ቡድንን መሥርቼ ማሠልጠን ያዝኩ።» መሠረት የምታሠለጥነው የእግር ኳስ ቡድኖችን ብቻ አልነበረም። የቴኒስ እና መረብ ኳስ ቡድኖችንም ታሠለጥን ነበር። 'ማቴሪያል' ስለነበር ፍላጎቱ ያላቸው የድሬዳዋ ልጆች እንዲሠለጥኑ አደርግ ነበር። 1970 ዎቹ ላይ እነ ማክዳ፣ ታጠቅ፣ አየር ኃይል እና መሰል የሴት እግር ኳስ ቡድኖች፤ የሴቶች እግር ኳስ ሲቋረጥ በዚያ ከሰሙ። ከዚያ 1986 ላይ የመጀመሪያውን የሴቶች እግር ኳስ ቡድን በማቋቋም በታሪክ መዝገብ ስሟን አሰፈረች። 2004 ላይ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚዬር ሊግ ሲጀመር መሠረት የከተማዋን ሴቶች ቡድን ይዛ ተቀላቀለች። 2007 ላይ ድሬዳዋ ከነማ የፕሪሚዬር ሊጉ ታናሽ በሆነው የሊግ ውድድር ላይ ተሳታፊ ነበር። ይሄኔ ነው መሠረት ማኒ የወንዶቹን ቡድን ተረክባ ለፕሪሚዬር ሊግ ለማሰለፍ ቃል በመግባት ሥራ የጀመረችው። «እርግጥ በጣም 'ቻሌንጂንግ' ነበር። ቢሆንም ለእኔ ብዙ ያልከበደኝ፤ ከልጅነቴም ጀምሮ ወንዶችን እያሠለጠንኩ ማደጌ ነው። ትላልቆቹም ሳሰለጥናቸው የሚሠጡኝ አክብሮትና ፍቅር እንዲሁም ኃላፊነታቸውን የሚወጡበት መንገድ አቅም ሆኖኝ ነበር። በፆታ መለካቴ ግን አልቀረም። 'እንዴት ለሴት ልጅ የወንዶች ክለብ ይሰጣል? ቀልድ ነው እንዴ የያዙት?' ያሉ አልጠፉም ነበር። አንዳንዶቹም እንደውም ይሄ ለፖለቲካ 'ኮንሳምፕሽን' ነው ብለው ከንቲባው [የድሬዳዋ] ድረስ ይሄዱ ነበር። ነገር ግን ለኔ የበለጠ አቅም ነበር የሆነኝ። ምክንያቱም ይህንን መቀየር አለብኝ አልኩኝ፤ በምን? በውጤት።» ከውጭ ብዙ ፈተና የገጠማት መሠረት ከውስጥም መንገዱ አልጋ 'ባልጋ አልሆነላትም። በዚያ ላይ የመጀመሪያው ዙር ለመሠረት ቀላል የሚባል አልነበረም፤ ሦስት ነጥብ ማግኘት። «ተጨዋቾቼን ማሳመን አንዱ ፈተና ነበር። በሴት ሠልጥነው አያውቁም፤ ትልልቅ ተጨዋቾች ናቸው። 'እንዴት ነው አሁን እሷ እኛን የምትመራን?' የሚል ጥያቄ ነበራቸው። አንዳንዶቹ የመሥራት ፍላጎታቸው ውርድ ያለም ነበር። ነገር ግን ልጆቼን በሥራ ማሳመን ቻልኩኝ። በተለይ ሁለተኛው ዙር ላይ በውጤት በጣም አሪፍ ነበርን። እንደውም ከ12 ጨዋታ 11 አሸንፈን በአንዱ ብቻ ነው አቻ የተለያየነው።» ጉዞ ወደፕሪሚዬር ሊግ ድሬዳዋ ከነማ በአሠልጣኝ መሠረት ማኒ እየተመራ ፕሪሚዬር ሊግ ገባ። ሁሉም 'ሴት የወንዶች አሠልጣኝ?' ሲል መጠየቅ ጀመረ። አድኖቆት ጎረፈላት። ተጫዋቾች፣ ኢትዮጵያውያን፣ በተለይ ደግሞ ድሬዎች ቆመው አጨበጨቡላት። ፕሪሚዬር ሊግ ከብሔራዊ ሊግ ሲነፃፀር ከበድ [በጥራት] ያለ ቢሆንም መሠረትን የሚያቆም ግን አልተገኘም። ክለቧ ትልቁ ዓላማው የነበረው ከፕሪሚዬር ሊጉ ተመልሶ አለመውረድ ነበር። መሠረት ግን አለመውረድ አላስጨነቃትም፤ ውጤቱ የበለጠ እንዲያምር ጣረች። «ስንጀምረው አራት ጨዋታ ማሸነፍ አልቻልንም ነበር። ከአምስተኛው ጨዋታ በኋላ ግን ሁሉንም እያስተካከልን መጣን። እንደውም በአንደኛው ዙር አምስተኛ ሆነን ጨረስን፤ ይሄ ደግሞ ትልቅ ድል ነው። በተለይ ከብሔራዊ ሊግ ለመጣ ቡድን ሊያውም በሴት አሠልጣኝ ለሚሠለጥን።» ቢሆንም ሁለተኛው ዙር የድሬዳዋ ውጤት ዕለት ተ'ለት ያሽቆለቁል ያዘ። በመጀመሪያዎቹ አምስት ጨዋታዎች ጥሩ ውጤታ ማምጣት የቻለው ድሬዳዋ ከነማ ሦስት ነጥብ ብርቁ ሆነ። ምን ተፈጠረ? «እኔ እስከዛሬም ድረስ ሳስበው ግራ ይገባኛል። ምንድን ነው ነገሩ ብዬ ልጆቼን ጠየቅኩ፤ ግን አጥጋቢ ምላሽ አላገኘሁም። አንድ የማላውቀው እና ውጤታችንን እንዲያሽቆለቁል ያደረገ ነገር እንዳለ አሁንም ድረስ ይሰማኛል። አሁን ራሱ አንዳድንድ ተጨዋቾችን ሳገኝ እጠይቃለሁ፤ ግን ብዙም አይነግሩኝም። የሆነ ነገር እንዳለ ግን ይሰማኛል፤ ከውጭም ከውስጥም። ወደፊትም መጠየቄን አላቆምም።» • ሴት እግር ኳሰኞች ስንት ይከፈላቸው ይሆን? ከዚያ «በዚህ መንገድ መቀጠል አልቻልኩም ትላለች» መሠረት። «ገንዘብ ፈልጌ አይደለም የመጣሁት እኔ። እኔ መሥራት ነው የምፈልገው። በዚህ መንገድ መቀጠል ደግሞ አልፈልግም። ጫናዎች በዝተዋል። እግር ኳስ ደግሞ ነፃነት ይፈልጋል። እኔ በቃኝ 'ቴንኪው' ብዬ፤ ልጆቼን እና 'ስታፉን' ተሰናብቼ ቡደኑን ለቅቄ ወጣሁ።» ይህ የሆነው እንግዲህ 2008 ላይ ነው። መሠረት 2002 ላይ ሉሲዎችን ተረክባ ታሪክ ፅፋለች፤ ታሪኩ ምንድን ነው? ብሎ ለሚጠይቅ 'ቡድኑ ለመጀመሪያ ጊዜ በሴት አሠልጣኝ የተመራበት ወቅት በመሆኑ [የተሰጣት ኮንትራት የ3 ወራት ብቻ ቢሆንም]' መልሷ ነው። መሠረት ከዚያ በኋላ በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን ስፖርት ፌዴሬሽን በቀረበላት ግብዣ ወደ አሜሪካ አቀናች። ለሁለተኛ ጊዜ ደግሞ ከአሜሪካ ኤምባሲ በቀረባለት ግብዣ አሜሪካ ደርሳ ተመልሳለች። ወደ አሜሪካ ከማቅናቷ በፊት ሉሲዎችን እንደገና ተረክባ ነበር [2009]። ስትመለስ ግን የአሠልጣኝነት ቦታው በሌላ ሰው ተይዞ ጠበቃት። እንደገና ሉሲዎችን ተረክባ ወደ ኡጋንዳ አቀናች፤ በሴካፋ ዋንጫ ላይ ለመሳተፍ። ኳስ ይዞ በማጥቃት የአጨዋወት ስልት የምትታወቀው መሠረት ውድድሩን ሦስተኛ ሆና በማጠናቀቅ የነሃስ ሜዳሊያ ይዛ ተመለሰች [የራሳችን ድክመት ነው እንጂ ዋንጫ ማምጣት ይገባን ነበር ትላለች]። ቢሆንም ኮንትራቷ ከመጠናቀቁ በፊት ሉሲዎች ሌላ አሠልጣኝ ተሾመላቸው። መሠረት አዲሱን መፅሐፏን ለማስመረቅ ጉድ ጉድ በማለት ላይ ትገኛለች። 'የስኬት ተምሳሌት' የተሰኘ ርዕስ ሰጥታዋለች። ያለፈችበትን ውጣ ውረድ የሚያትት 198 ገፆች ያሉት መፅሐፍ ነው። «ይሄኔ ነው ጀምሬው የነበረውን መፅሐፍ ልጨርስ ብዬ ትኩረቴን ወደዚያ ያደርግኩት» ብላናለች። መሠረት ድሬዳዋ ከነማ እያለሽ ምን ያህል ነበር የሚከፈልሽ? እንደው ፈቃደኛ ከሆንሽ ብትነግሪን? «ኧረ በደንብ ነው ምነግርህ [ፈገግታ]. . . እንግዲህ እኔ ፕሪሚዬር ሊግ እያለሁ 14 ክለቦች ነበሩ። በወቅቱ ዝቅተኛው የአሠልጣኝ ክፍያ የኔ ነበር። ተቆራርጦ እጄ ላይ 'ሚደርሰኝ 13ሺህ 500 ብር ነበር። ያኔ የወረዱት ዳሸንና የሆሳዕና ቡድን አሠልጣኞች ከኔ የተሻለ ክፍያ ያገኙ እንደነበር አውቃለሁ። ምክንያቱም እኔ ብዙ ጊዜ በፆታዬ ነው 'ምለካው። እንጂ ባለኝ አቅም አልነበረም። ይሄን ሳስብ ያመኛል ግን በቃ ፍቅር ነው፤ ኳሱን እወደዋለሁ፤ እሠራዋለሁ። አሠልጣኞች እና ተጨዋቾች በድህረ-ጨዋታ መጨባበጥና ማልያ መቀያየር የተለመደ ነው። እርግጥ አሁን አሁን በሰላም ጨዋታን መጨረስ በራሱ ትልቅ ድል እየሆነ ቢመጣም። እንደው በመሠረት እንዴት እንሸነፋለን ያሉ አሠልጣኞች እና ተጫዋቾች እጅ ነስተዋት ያውቁ ይሆን? «የነፈጉኝን እንኳ ብዙም አላስታውስም፤ ግን እኔ አንድ ጊዜ በደስታ ውስጥ ሆኜ ሳልጨባበጥ በመቅረቴ ተከስሻለሁ። እዚሁ ድሬዳዋ ላይ ነው። ከሙገር ሲሚንቶ ጋር እየተጫወትን ነበር። ደርቢ በመሆናችን ጨዋታው ደመቅ ያለ ነበር። 0-0 ነበርንና ባለቀ ሰዓት አገባንና አሸነፍን። በቃ በጣም ደስተኛ ስለነበርኩ የሙገር አሠልጣኝን ሳልጨብጠው ቀረሁ። ከዚያ እስከ ክስ ደረጃ ደርሶ ነበር።» ሰዎች አሠልጣኝ መሠረትን ሲያስቡ ቀድሞ ትዝ የሚለቸው ከድሬዳዋ ከነማ ጋር የተጎናፀፈችው ስኬት ነው። እርሷም ከማትረሳቸው ድሎች መካከል አንዱ እርሱ ነው። ግን ከዚያም በላይ የማልረሳው ትላለች መሠረት. . . «የማልረሳቸው ሁለት ቀናት አሉ። አንደኛው ከአዲስ አበባ ከነማ ጋር አራት ውስጥ ለመግባት የተጫወትነው ነው። 1 ለ 0 እየመራን ነበር፤ ከዚያ አቻ ሆንን። አንድ ጨምረን መምራት ያዝን፤ ግን መልሶ ተቆጠረብን። በስመዓብ አሁን በቃ 2 ለ 2 ሆነን ወደ ፍፁም ቅጣት ምት ልንሄድ ነው። ከምክትሌ ጋር ተነጋገርኩና 'ቤንቹ' በረኛ 'ፔናሊቲ' ጎበዝ ስለሆነ ብለን አስገባነው። በረኛችን ሦስት ጎል አዳነልንና አሸነፍን።» «ሁለተኛው ቅዱስ ጊዮርጊስን የረታንበትን ነው። እንግዲህ ጊዮርጊስ በጣም ትልቅ ቡድን ነው። እኔ ደግሞ ፕሪሚዬር ሊጉ አዲሴ ነው። እና በሜዳዬ ሊያውም በጨዋታ ብልጫ ማሸነፌ ፍፁም አልረሳውም። በጣም ልዩ ነበር። መሠረት አሁን ላይ የአዲስ አበባ ሴቶች እግር ኳስ ቡድንን በማሠልጠን ላይ ትገኛለች። አንደኛ ዲቪዚዮን ላይ እየተጫወተ የሚገኘው አ.አ. ስድስተኛ ደረጃን ይዞ የውድድር ዘመኑን አጠናቋል። መሠረት ስለወደፊቱ ዕቅዷ እጅጉን እያሰበችበት እንደሆነ አልደበቀችንም። «ብዙ ዕቅዶች አሉኝ። የሕፃናት አካዳሚም አለኝ [120 ሕፃናት ያሉት]። እሱን ከፍ ማድረግም ሕልሜ ነው። የአሠልጣኝነት ጥያቄዎችም ይመጣሉ። እውነት ለመናገር ብዙ 'ፍራስትሬት' የሚያደርጉ አጋጣሚዎች ገጥመውኛል። ሙያውን ለመተው ሁላ አስቤ አውቃለሁ፤ ግን ደግሞ ብዙ ሰዎች ይህን ውሳኔዬን ሲቃወሙ አያለሁ። በተለይ ያሠለጠንኳቸው ልጆች 'ኖ መቀጠል አለብሽ' የሚል አስተያየት ይሰጡኛል። ስለዚህ ቁጭ ብዬ ማሰብ አለብኝ ብያለሁ።» በኢትዮጵያም ሆነ በአህጉረ አፍሪካ ከመሠረት ሌላ ሴት የወንዶች እግር ኳስ ክለብ አሠልጣኝ እንዳለች አልሰማንም፤ አላየንም። ይህንን ክብር መጎናፀፍ ምን ዓይነት ስሜት ይሰጥ ይሆን? «በጣም ነው ደስ የሚለኝ። ሌላ ሴት አለመኖሯ ሳይሆን፤ ስኬታማ መሆን መቻሌ ደስ ያሰኘኛል። ሴት ልጅ ይህንን ማድረግ እንደምትችል ደግሞ ማሳየት መቻሌ እጅግ ያኮራኛል። እንጂ ብቸኛ ስለሆንኩኝ አይደለም፤ በቃ ይቻላል የሚለውን መንፈስ ማንገስ መቻሌ ነው። ሁሌም የምለው ሴቶች በፆታቸው ሳይሆን በአቅማቸው ቢለኩ ነው።» «አንዲት ሴት አናጢም መሆን ትፈልግ፣ ኢንጅነር ወይም ኤሌክትሪሺያን ለዚያ ሙያ የሚሆን ዕውቀት ያስፈልጋታል። ይህ ደግሞ እንዲሁ አይገኝም፤ ልፋት ይጠይቃል፤ ጥረት ያስፈልጋል፤ ድካም ያስፈልጋል፤ በቀላሉ የሚገኝ ነገር የለም። እኔ ሴት ስለሆንኩ እንደው እንደ ገፀ-በረከት እንዲሰጠኝ አልፈልግም። በራሴ ልክ፤ ባለኝ አቅም እንጂ። የማይቻል ምንም ነገር የለም። ሕልም ይኑረን።» እኛም ምክር ያፅና ብለናል፤ ለመሠረትም መልካም ዕድል! • "የናንዬ ሕይወት" የአይዳ ዕደማርያም ምስል ከሳች መፀሐፍ
https://www.bbc.com/amharic/news-48715607
2health
ሕንዳውያን የስኳር ምርት ስለተትረፈረፈ አብዝተው እንዲጠቀሙ ተነግሯቸዋል
ሕንድ በጣም የበዛ ስኳር በማምረቷ ሕዝቧ ስኳር አብዝቶ እንዲጠቀም እየመከረች ነው። የሕንድ ስኳር ምርት ማሕበር ስኳር ጤና ላይ ጉዳት ያመጣል የሚባለውን ችላ ብለው ሰዎች አብዝተው እንዲጠቀሙ መክሯል። ሕንዳውያን በአማካይ በዓመት 19 ኪሎ ግራም ስኳር ይጠቀማሉ። ይህ ደግሞ ከተቀረው ዓለም ሲነፃፀር አነስተኛ ነው። ቢሆንም ሕንድ ካላት ሕዝብ አንፃር ከፍተኛ ስኳር ተጠቃሚዋ ሃገር ናት። . ሕንዳውያን ከልጅና የልጅ ልጆቻቸው ጋር የሚኖሩት ለምንድን ነው? . ትራምፕ ስለ ሕንድ የአየር ብክለት የተናገሩት በርካቶችን አስቆጣ . የቶልስቶይ መፅሐፍ ህንዳውያን 'አክቲቪስቶች' ላይ መዘዝ አምጥቷል የሕንድ የስኳር ምርት መጠን በዚህ ዓመት በ13 በመቶ አድጎ 31 ሚሊዮን ቶን ምርት እንደሚመረት ይጠበቃል። ነገር ግን መንግሥት እንደ ሌላ ጊዜው በገፍ ለውጭ ገበያ ማቅረቡን ትቶ ለሕዝብ ሊያከፋፍል ይችላል ተብሏል። የስኳር ምርት ማሕበሩ ድረ-ገፁ ላይ ስኳር መጠቀም እንደማይጎዳ የሚጠቁም ማስታወቂያ ለቋል። ማሕበሩ ሰዎች ለሚሰሯቸው ምግቦች ሌላ ዓይነት ማጣፈጫ ከሚጠቀሙ ስኳር ቢጠቀሙ የተሻለ እንደሆነ የሚጠቁሙ ማስታወቂያዎች እየለቀቀ ነው። የሕንድ የምግብ ሚኒስቴር ሱዳንሹ ፓንዴይ የሕንድ ማሕበረሰብ ለስኳር ያለው አስተሳሰብ የተዛባ ነው ሲሉ ተደምጠዋል። እርግጥ ነው በሌሎች ሃገራት ሰዎች የስኳር አጠቃቀማቸውን እንዲያስተካክሉና ቀነስ እንዲያደርጉት ነው የሚመከሩት። ስኳር ከመጠን ላለፈ ክብደትና በተለምዶ ስኳር በሽታ ተብሎ ለሚታወቀው ዳያቢቲስ ሊያጋልጥ ይችላል ይላሉ ባለሙያዎች። የዓለም ጤና ድርጅት የተለያዩ ምግቦች ውስጥ፤ በተለይ ደግሞ ማርና የፍራፍሬ ጭማቂ ላይ የሚታከል ስኳር ለጤና አሳሳቢ ነው ይላል። ሕንድ ውስጥ 50 ሚሊዮን ገደማ ገበሬዎች ሸንኮራ አገዳ ያመርታሉ። ሚሊዮኖች ደግሞ ስኳር በሚያመርቱ ፋብሪካዎች ውስጥ ተቀጥረው ይሠራሉ። ሕንድ የተረፈ የስኳር ምርቷን ወደ ውጭ ለመላክ ማቀዷ በሌሎች ስኳር አምራች ሃገራት ዘንድ ቅራኔ ፈጥሯል። ሌላኛው የተረፈ የስኳር ምርትን ማስወገጃ መንገድ ወደ ኢታኖል ቀይሮ መጠቀም ነው። የሕንድ ስኳር ምርት ማሕበር የኢታኖል ምርት አሁን ካለው 1.9 ቢሊዮን ሊትር ምርት በሚቀጥለው ዓመት ወደ 3 ቢሊዮን ሊያድግ እንደሚችል ገምቷል።
ሕንዳውያን የስኳር ምርት ስለተትረፈረፈ አብዝተው እንዲጠቀሙ ተነግሯቸዋል ሕንድ በጣም የበዛ ስኳር በማምረቷ ሕዝቧ ስኳር አብዝቶ እንዲጠቀም እየመከረች ነው። የሕንድ ስኳር ምርት ማሕበር ስኳር ጤና ላይ ጉዳት ያመጣል የሚባለውን ችላ ብለው ሰዎች አብዝተው እንዲጠቀሙ መክሯል። ሕንዳውያን በአማካይ በዓመት 19 ኪሎ ግራም ስኳር ይጠቀማሉ። ይህ ደግሞ ከተቀረው ዓለም ሲነፃፀር አነስተኛ ነው። ቢሆንም ሕንድ ካላት ሕዝብ አንፃር ከፍተኛ ስኳር ተጠቃሚዋ ሃገር ናት። . ሕንዳውያን ከልጅና የልጅ ልጆቻቸው ጋር የሚኖሩት ለምንድን ነው? . ትራምፕ ስለ ሕንድ የአየር ብክለት የተናገሩት በርካቶችን አስቆጣ . የቶልስቶይ መፅሐፍ ህንዳውያን 'አክቲቪስቶች' ላይ መዘዝ አምጥቷል የሕንድ የስኳር ምርት መጠን በዚህ ዓመት በ13 በመቶ አድጎ 31 ሚሊዮን ቶን ምርት እንደሚመረት ይጠበቃል። ነገር ግን መንግሥት እንደ ሌላ ጊዜው በገፍ ለውጭ ገበያ ማቅረቡን ትቶ ለሕዝብ ሊያከፋፍል ይችላል ተብሏል። የስኳር ምርት ማሕበሩ ድረ-ገፁ ላይ ስኳር መጠቀም እንደማይጎዳ የሚጠቁም ማስታወቂያ ለቋል። ማሕበሩ ሰዎች ለሚሰሯቸው ምግቦች ሌላ ዓይነት ማጣፈጫ ከሚጠቀሙ ስኳር ቢጠቀሙ የተሻለ እንደሆነ የሚጠቁሙ ማስታወቂያዎች እየለቀቀ ነው። የሕንድ የምግብ ሚኒስቴር ሱዳንሹ ፓንዴይ የሕንድ ማሕበረሰብ ለስኳር ያለው አስተሳሰብ የተዛባ ነው ሲሉ ተደምጠዋል። እርግጥ ነው በሌሎች ሃገራት ሰዎች የስኳር አጠቃቀማቸውን እንዲያስተካክሉና ቀነስ እንዲያደርጉት ነው የሚመከሩት። ስኳር ከመጠን ላለፈ ክብደትና በተለምዶ ስኳር በሽታ ተብሎ ለሚታወቀው ዳያቢቲስ ሊያጋልጥ ይችላል ይላሉ ባለሙያዎች። የዓለም ጤና ድርጅት የተለያዩ ምግቦች ውስጥ፤ በተለይ ደግሞ ማርና የፍራፍሬ ጭማቂ ላይ የሚታከል ስኳር ለጤና አሳሳቢ ነው ይላል። ሕንድ ውስጥ 50 ሚሊዮን ገደማ ገበሬዎች ሸንኮራ አገዳ ያመርታሉ። ሚሊዮኖች ደግሞ ስኳር በሚያመርቱ ፋብሪካዎች ውስጥ ተቀጥረው ይሠራሉ። ሕንድ የተረፈ የስኳር ምርቷን ወደ ውጭ ለመላክ ማቀዷ በሌሎች ስኳር አምራች ሃገራት ዘንድ ቅራኔ ፈጥሯል። ሌላኛው የተረፈ የስኳር ምርትን ማስወገጃ መንገድ ወደ ኢታኖል ቀይሮ መጠቀም ነው። የሕንድ ስኳር ምርት ማሕበር የኢታኖል ምርት አሁን ካለው 1.9 ቢሊዮን ሊትር ምርት በሚቀጥለው ዓመት ወደ 3 ቢሊዮን ሊያድግ እንደሚችል ገምቷል።
https://www.bbc.com/amharic/news-54791680
3politics
ሩሲያ በነዳጅ ማከማቻዋ ላይ ዩክሬን ጥቃት መፈጸሟን አስታወቀች
ከዩክሬን በስተሰሜን በምትገኘው የሩሲያ ከተማ የሚገኝ የነዳጅ ማከማቻ ላይ ጥቃት መፈጸሙን የከተማዋ አስተዳዳሪሪ አስታወቁ። ጥቃቱ የተፈጸመው በዩክሬን ሁለት የጦር አውሮፕላኖችም ነው ተብሏል። ዩክሬንና ሩሲያ በሚዋሰኑበት ድንበር 40 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ቤልጎሮድ ከተማ ውስጥ በጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ ቃጠሎ መነሳቱንም በትዊተር የተጋራ ቪዲዮ ያሳያል። እንዲሁም አንዳንድ ቪዲዮች የነዳጅ ዲፖው በሮኬቶች ሲመታም አሳይተዋል። ይሁን እንጂ የዩክሬን አውሮፕላኖች ቀደም ሲል በሩሲያ ኢላማዎችን መምታት አልቻሉም ነበር። የከተማዋ አስተዳዳሪ ቪያቼስላቭ ግላድኮቭ ጥቃት ደርሷል ቢሉም የዩክሬን ባለስልጣናት ምላሽ አልሰጡም። የፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ቃለ አቀባይም ለቃጠሎው ተጠያቂው ዩክሬን መሆኗን ተናግረው ይህ ክስተት ከዩክሬን ጋር ያለውን "ውይይት ለመቀጠል ምቹ ሁኔታዎችን ይፈጥራል ተብሎ ሊታሰብ አይችልም" ብለዋል። እስካሁን እየተደረጉ ያሉ የሰላም ድርድሮች እምብዛም መሻሻል አላሳዩም። የሩሲያ ባለስልጣናት የነዳጅ አቅርቦት ሰንሰለቱን እንደገና ለማስቀጠል እንዲሁም በቤልጎሮድ የኃይል አቅርቦት እንዳያስተጓጉል የተቻላቸውን እያደረጉ መሆናቸውን ቃለ አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ተናግረዋል ። በሩሲያ ጦር ከፍተኛ ውድመትና በአሁኑም ወቅት ተከባ ከምትገኘው ከዩክሬን ሁለተኛዋ ትልቅ ከተማ ካርኪቭ በስተሜን የምትገኘው ይህች የሩሲያ ከተማ ከ370 ሺህ በላይ ነዋሪ አላት። የከተማዋ አስተዳዳሪ ግላድኮቭ በቴሌግራም ባስተላለፉት መልእክት "በዝቅተኛ ከፍታ ላይ ወደ ሩሲያ ግዛት የገቡት ሁለት የዩክሬን ጦር ሄሊኮፕተሮች ባደረጉት የአየር ድብደባ ምክንያት በነዳጅ ማከማቻው ላይ የእሳት ቃጠሎ ተነስቷል" ብለዋል። በዚህ ጥቃትም የተገደለ ሰው የለም ብለዋል። የድንገተኛ አደጋ ሰራተኞች እሳቱን በተቻለ ፍጥነት ለመቆጣጠር እየሞከሩ እንደሆነ እና በነዋሪዎች ላይ ምንም አይነት ስጋት እንደሌለም ተናግረዋል። የድንገተኛ አደጋ ሚኒስቴር የእሳቱን ቪዲዮ በቴሌግራም ገጹ አስፍሯል። የሩሲያው ኢንተርፋክስ የዜና ወኪል እንደዘገበው በአቅራቢያው ያሉ ነዋሪዎችን ማስወጣት እንደተቻለና በዲፓው ላይ የነበሩ ሁለት ሰዎችም መቁሰላቸውን አስነብቧል። ስምንት የነዳጅ ታንኮች በእሳት መያያዛቸውን እና ወደ 200 የሚጠጉ የእሳት አደጋ ተከላካዮች በቦታው ላይ እየተረባረቡ እንደሆነም ዘገባው አክሎ ገልጿል። ዲፖው የሚተዳደረው በሩሲያ መንግሥት የነዳጅ ኩባንያ ሮስኔፍት ነው። ቃጠሎውን ተከትሎ የመኪና ወረፋዎች በአካካቢው የነዳጅ ማደያዎች ላይ የታየ ቢሆንም ነገር ግን አስተዳዳሪው በከተማዋ የነዳጅ አቅርቦት እጥረት የለም ብለዋል። የሩሲያው አርአይኤ ኖቮስቲ የዜና ወኪል እንደገለጸው በዲፖው በሚገኘው ሶስት የነዳጅ ታንኮች ላይ የተነሳው የእሳት ቃጠሎ ሙሉ በሙሉ ቢጠፋም አሁንም እሳቱ የመስፋፋቱ ስጋት አልተቀረፈም ብሏል። ከሁለት ቀናት በፊት በቤልጎሮድ ዲፖት አቅራቢያ በሚገኝ የጥይት መጋዘን ላይ በርካታ ፍንዳታዎች ተዘግበዋል።
ሩሲያ በነዳጅ ማከማቻዋ ላይ ዩክሬን ጥቃት መፈጸሟን አስታወቀች ከዩክሬን በስተሰሜን በምትገኘው የሩሲያ ከተማ የሚገኝ የነዳጅ ማከማቻ ላይ ጥቃት መፈጸሙን የከተማዋ አስተዳዳሪሪ አስታወቁ። ጥቃቱ የተፈጸመው በዩክሬን ሁለት የጦር አውሮፕላኖችም ነው ተብሏል። ዩክሬንና ሩሲያ በሚዋሰኑበት ድንበር 40 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ቤልጎሮድ ከተማ ውስጥ በጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ ቃጠሎ መነሳቱንም በትዊተር የተጋራ ቪዲዮ ያሳያል። እንዲሁም አንዳንድ ቪዲዮች የነዳጅ ዲፖው በሮኬቶች ሲመታም አሳይተዋል። ይሁን እንጂ የዩክሬን አውሮፕላኖች ቀደም ሲል በሩሲያ ኢላማዎችን መምታት አልቻሉም ነበር። የከተማዋ አስተዳዳሪ ቪያቼስላቭ ግላድኮቭ ጥቃት ደርሷል ቢሉም የዩክሬን ባለስልጣናት ምላሽ አልሰጡም። የፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ቃለ አቀባይም ለቃጠሎው ተጠያቂው ዩክሬን መሆኗን ተናግረው ይህ ክስተት ከዩክሬን ጋር ያለውን "ውይይት ለመቀጠል ምቹ ሁኔታዎችን ይፈጥራል ተብሎ ሊታሰብ አይችልም" ብለዋል። እስካሁን እየተደረጉ ያሉ የሰላም ድርድሮች እምብዛም መሻሻል አላሳዩም። የሩሲያ ባለስልጣናት የነዳጅ አቅርቦት ሰንሰለቱን እንደገና ለማስቀጠል እንዲሁም በቤልጎሮድ የኃይል አቅርቦት እንዳያስተጓጉል የተቻላቸውን እያደረጉ መሆናቸውን ቃለ አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ተናግረዋል ። በሩሲያ ጦር ከፍተኛ ውድመትና በአሁኑም ወቅት ተከባ ከምትገኘው ከዩክሬን ሁለተኛዋ ትልቅ ከተማ ካርኪቭ በስተሜን የምትገኘው ይህች የሩሲያ ከተማ ከ370 ሺህ በላይ ነዋሪ አላት። የከተማዋ አስተዳዳሪ ግላድኮቭ በቴሌግራም ባስተላለፉት መልእክት "በዝቅተኛ ከፍታ ላይ ወደ ሩሲያ ግዛት የገቡት ሁለት የዩክሬን ጦር ሄሊኮፕተሮች ባደረጉት የአየር ድብደባ ምክንያት በነዳጅ ማከማቻው ላይ የእሳት ቃጠሎ ተነስቷል" ብለዋል። በዚህ ጥቃትም የተገደለ ሰው የለም ብለዋል። የድንገተኛ አደጋ ሰራተኞች እሳቱን በተቻለ ፍጥነት ለመቆጣጠር እየሞከሩ እንደሆነ እና በነዋሪዎች ላይ ምንም አይነት ስጋት እንደሌለም ተናግረዋል። የድንገተኛ አደጋ ሚኒስቴር የእሳቱን ቪዲዮ በቴሌግራም ገጹ አስፍሯል። የሩሲያው ኢንተርፋክስ የዜና ወኪል እንደዘገበው በአቅራቢያው ያሉ ነዋሪዎችን ማስወጣት እንደተቻለና በዲፓው ላይ የነበሩ ሁለት ሰዎችም መቁሰላቸውን አስነብቧል። ስምንት የነዳጅ ታንኮች በእሳት መያያዛቸውን እና ወደ 200 የሚጠጉ የእሳት አደጋ ተከላካዮች በቦታው ላይ እየተረባረቡ እንደሆነም ዘገባው አክሎ ገልጿል። ዲፖው የሚተዳደረው በሩሲያ መንግሥት የነዳጅ ኩባንያ ሮስኔፍት ነው። ቃጠሎውን ተከትሎ የመኪና ወረፋዎች በአካካቢው የነዳጅ ማደያዎች ላይ የታየ ቢሆንም ነገር ግን አስተዳዳሪው በከተማዋ የነዳጅ አቅርቦት እጥረት የለም ብለዋል። የሩሲያው አርአይኤ ኖቮስቲ የዜና ወኪል እንደገለጸው በዲፖው በሚገኘው ሶስት የነዳጅ ታንኮች ላይ የተነሳው የእሳት ቃጠሎ ሙሉ በሙሉ ቢጠፋም አሁንም እሳቱ የመስፋፋቱ ስጋት አልተቀረፈም ብሏል። ከሁለት ቀናት በፊት በቤልጎሮድ ዲፖት አቅራቢያ በሚገኝ የጥይት መጋዘን ላይ በርካታ ፍንዳታዎች ተዘግበዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-60956542
0business
ባለ 14 ካራት ትንሽዬ አልማዝ በ26 ሚሊዮን ዶላር ተሸጠች
ለማግኘት በጣም ከባድና ውድ የተባለ አንድ ሐምራዊ አልማዝ ክብረ ወሰን በሚባል ዋጋ ተሸጠ። ይህ አልማዝ የተሸጠው በጨረታ ሲሆን ጨረታው ስዊዘርላንድ አገር ነው የተካሄደው። 14.8 ካራት የሚመዝነው ይህ አልማዝ "ዘ ስፕሪት ኦፍ ሮዝ" የሚል ስም ተሰጥቶታል። እስከዛሬም ለጨረታ ከቀረቡ አልማዞች ትልቁ ነው። 99 ከመቶ የሚሆኑ የሐምራዊ ሮዛማ ቅይጥ ቀለም ያላቸው አልማዞች የካራት መጠን ከ10 በታች እንጂ 14 ካራት አይደርሱም። ይህን አልማዝ ልዩ የሚያደርገውም መጠኑና የቀለም ስብጥሩ ነው ተብሏል። ይህን ውድ አልማዝ በጨረታ አሸንፎ የገዛው ግለሰብ ማንነት ይፋ አልተደረገም። ሐምራዊውን አልማዝ ለጨረታ ያቀረበው ግን የሩሲያ የማዕድን ኩባንያ አልሮሳ ነው። "ዘ ስፕሪት ኦፍ ዘ ሮዝ" የተሰኘው ይህ ሐምራዊው አልማዝ ከድፍድፍ የአልማዝ ድንጋይ ነጥሮ የወጣው በሩሲያ በጎሮጎሳውያኑ 2017 ድፍድፍ አልማዙ ያን ጊዜ ሲወጣ ኒጂንስኪ የሚል የክብር ስም ተሰጥቶት ነበር። አልማዙ በዚህ ስም የተሰየመው የሩሲያ ፖሊሽ የባሌት ዳንስ ጥበበኛ ክብር ለመስጠት ነው። ቮስላቭ ኒጂንስኪ በ20ኛው ክፍለ ዘመን ወደር ያልተገኘለት የባሌት ዳንሰኛ ነበር። በዓለም ላይ እስከዛሬ ለፒንክ (ሮዝ) አልማዝ የተከፈለው ትልቁ ሽያጭ 71 ሚሊዮን ዶላር ነው። ይህም በ2017 በሆንግ ኮንግ በተደረገ ጨረታ የተሸጠው 59 ካራት አልማዝ ነው። አልማዞች ብዙውን ጊዜ 150 ኪሎ ሜትር ጥልቀት ውስጥ የኖሩና ወደላይኛው የምድር ክፍል በእሳተ ጎመራ አማካኝነት የወጡ ውድ የከበሩ ደንጋዮች ሲሆኑ እነዚህን ውድ የከበሩ ድንጋዮች ፈልጎ አግኝቶና አጽድቶ ለገበያ ለማቅረብ በአማካይ እስከ 20 ዓመት ሊወስድ ይችላል። የተፈጥሮ አልማዝ እስከ 3 ቢሊዮን ዓመት ያህል እድሜ ያለው በብዙ የእሳት ጎመራና የመልከዓ ምድር ለውውጦች የተቀየጠ እንደሆነ ይታመናል። ከከበሩ ድነጋዮች ውስጥ እንደ አልመዝ ጠንካራ ማዕድን የለም።
ባለ 14 ካራት ትንሽዬ አልማዝ በ26 ሚሊዮን ዶላር ተሸጠች ለማግኘት በጣም ከባድና ውድ የተባለ አንድ ሐምራዊ አልማዝ ክብረ ወሰን በሚባል ዋጋ ተሸጠ። ይህ አልማዝ የተሸጠው በጨረታ ሲሆን ጨረታው ስዊዘርላንድ አገር ነው የተካሄደው። 14.8 ካራት የሚመዝነው ይህ አልማዝ "ዘ ስፕሪት ኦፍ ሮዝ" የሚል ስም ተሰጥቶታል። እስከዛሬም ለጨረታ ከቀረቡ አልማዞች ትልቁ ነው። 99 ከመቶ የሚሆኑ የሐምራዊ ሮዛማ ቅይጥ ቀለም ያላቸው አልማዞች የካራት መጠን ከ10 በታች እንጂ 14 ካራት አይደርሱም። ይህን አልማዝ ልዩ የሚያደርገውም መጠኑና የቀለም ስብጥሩ ነው ተብሏል። ይህን ውድ አልማዝ በጨረታ አሸንፎ የገዛው ግለሰብ ማንነት ይፋ አልተደረገም። ሐምራዊውን አልማዝ ለጨረታ ያቀረበው ግን የሩሲያ የማዕድን ኩባንያ አልሮሳ ነው። "ዘ ስፕሪት ኦፍ ዘ ሮዝ" የተሰኘው ይህ ሐምራዊው አልማዝ ከድፍድፍ የአልማዝ ድንጋይ ነጥሮ የወጣው በሩሲያ በጎሮጎሳውያኑ 2017 ድፍድፍ አልማዙ ያን ጊዜ ሲወጣ ኒጂንስኪ የሚል የክብር ስም ተሰጥቶት ነበር። አልማዙ በዚህ ስም የተሰየመው የሩሲያ ፖሊሽ የባሌት ዳንስ ጥበበኛ ክብር ለመስጠት ነው። ቮስላቭ ኒጂንስኪ በ20ኛው ክፍለ ዘመን ወደር ያልተገኘለት የባሌት ዳንሰኛ ነበር። በዓለም ላይ እስከዛሬ ለፒንክ (ሮዝ) አልማዝ የተከፈለው ትልቁ ሽያጭ 71 ሚሊዮን ዶላር ነው። ይህም በ2017 በሆንግ ኮንግ በተደረገ ጨረታ የተሸጠው 59 ካራት አልማዝ ነው። አልማዞች ብዙውን ጊዜ 150 ኪሎ ሜትር ጥልቀት ውስጥ የኖሩና ወደላይኛው የምድር ክፍል በእሳተ ጎመራ አማካኝነት የወጡ ውድ የከበሩ ደንጋዮች ሲሆኑ እነዚህን ውድ የከበሩ ድንጋዮች ፈልጎ አግኝቶና አጽድቶ ለገበያ ለማቅረብ በአማካይ እስከ 20 ዓመት ሊወስድ ይችላል። የተፈጥሮ አልማዝ እስከ 3 ቢሊዮን ዓመት ያህል እድሜ ያለው በብዙ የእሳት ጎመራና የመልከዓ ምድር ለውውጦች የተቀየጠ እንደሆነ ይታመናል። ከከበሩ ድነጋዮች ውስጥ እንደ አልመዝ ጠንካራ ማዕድን የለም።
https://www.bbc.com/amharic/news-54913705
2health
ኮሮናቫይረስ፡ ኮቪድ-19 ምን እንደሆነ አናውቅም የሚሉት 10 አገራት
ኮቪድ ዓለምን አምሷል፡፡ እኛ ግን አናውቀውም የሚሉ 10 አገሮች አሉ ብንላችሁስ፡፡ ለመሆኑ እነዚህ አገሮች እነማን ናቸው? የማያውቁት ኮቪድ እንዴት እያደረጋቸው ይሆን? 1.ፕላው (Palau) ይቺ አገር የት ያለች ትመስልዎታለች? ሩቅ ምዕራብ ፓስፊክ ነው የምትገኘው፡፡ ማይክሮኒዢያ ሪጂን በሚባለው አካባቢ ከነ ፊሊፒንስ እና ኢንዶኒዢያ ነጠል ብላ በባትሪ ተፈልጋ የምትገኝ ጢኒጥ ደሴት ናት፡፡ እዚያ ፕላው የሚባል ሆቴል አለ፡፡ ድሮ በ1982 ነበር የተከፈተው፡፡ ያኔ የአገሩን ስም የያዘው ይኸው እስከዛሬ አለ፡፡ በአገሩ ሌላ ሆቴል የሌለ ይመስል፡፡ በፓስፊክ ውቅያኖስ ሰማያዊ ቀለም ውሀ ውስጥ ጠብ ያለች ነጥብ የምትመስለው ይቺ አገር የቱሪስት አገር ናት፡፡ ያለፈውን ዓመት ብቻ አሐዝ ብንወስድ፣ ወደ ፕላው ደሴት 90ሺህ ቱሪስት ገብቷል፡፡ ይህ አሐዝ ከፕላው ጠቅላላ ሕዝብ አምስት እጥፍ ይበልጣል ብንላችሁስ? 40 ከመቶ የአገሪቱ ጥቅል አገራዊ ምርት ገቢ በቱሪዝም የሚታለብ ነው፡፡ ይህ ግን ከኮቪድ በፊት ያለ ታሪክ ነው፡፡ ኮቪድ ድንበሯን ሲያዘጋት ፕላው ደሴት ጉሮሮዋ ተዘጋ፡፡ እንኳን ሌላው መዝናኛ ይቅርና የአገሪቱን ስም የያዘው ሆቴል ሳይቀር ተዘጋ፡፡ ‹‹ለውድ ደንበኞቻችን፡- ኮቪድ የሚባል በሽታ በተቀረው ዓለም ስለተከሰተ ፕላው ሆቴል ለጊዜው ዝግ መሆናችንን ለውድ እንገልጻለን›› ብለው በር ላይ ሳይለጥፉ አልቀሩም፡፡ ፕላው አገር አንድም ዜጋ በቫይረሱ ባይያዝባትም ቫይረሱ ግን ቱሪዝማዊ ኢኮኖሚዋን ደም እያስተፋው ነው፡፡ 2. የማርሻል ደሴቶች 4ሺህ ኪሎ ሜትር ርቀው በማዕከላዊ ፓስፊክ ውቅያኖስ መሀል፣ ከምድር ወገብ ሰሜን፣ ብጥስጥስ ብለው ከሚገኙት የእሳተ ገሞራ ደሴቶች ውስጥ የማርሻል ደሴቶች ይገኙበታል፡፡ በሀዋይ እና በፊሊፒንስ መሀል ነው የሚገኙት፡፡ በውስጣቸው 1200 ጥቃቅን ደሴቶችና የጎመራ ፍንጥቅጣቂ የሆኑ የሰመጡ ደቂቀ ደሴቶች (ኮራል አቶልስ) ይገኛሉ፡፡ ሁለተኛውን የዓለም ጦርነት ተከትሎ የአሜሪካ የሩቅ ግዛት ሆነው የቆዩ ቢሆንም ከ1986 ወዲህ ራሳቸውን ችለዋል። ደህንነቱና መከላከያን እንዲሁም ጠቀም ያለ ድጎማን ግን አሁንም ከአሜሪካ ነው የሚያገኙት። የሕዝብ ብዛት 55ሺህ ሲሆን ዋና ከተማቸው ማጁራ ትባላለች፡፡ እነዚህ ደቂቀ ደሴቶችና የቱሪስት መዳረሻ የሆኑ ስብስቦች ማርሻል ደሴቶች ተብለው ይጠራሉ፡፡ ኮቪድ ምን እንደሆነ ባያውቁም ምጣኔ ሀብታዊ ቁንጥጫው ግን ፓሲፊክን አቋርጦ ተሰምቷቸዋል። ታዲያ አንድ ፕላው በቱሪዝም በኩል አይደለም ቁንጥጫው፡፡ በዓሣ ማጥመድና መላክ ጥሩ ገንዘብ ያገኙ ነበር፡፡ ኮቪድ ይህንን አስተጓጎለባቸው፡፡ በኮቪድ ምክንያት 700 ሰዎች ሥራ አጥተዋል፡፡ ይህ ትንሽ ሕዝብ ላላት ማርሻል አይላንድስ ብዙ ቁጥር ነው፡፡ የሕዝብ ብዛቷ 300ሺህ ቢሆን ነው፡፡ ዋና ከተማዋ ፖርትቪላ ይባላል፡፡ በ1ሺህ 300 ኪሎ ሜትር ላይ የተሰፉ የሚመስሉ 80 ደሴቶች የፈጠሯት አገር ናት፡፡ ከፈረንሳይና እንግሊዝ ቅኝ ነጻ የወጣችው ገና በ1980 ነበር፡፡ አብዛኛው ሕዝቧ ገጠር የሚኖር ገበሬ ነው፡፡ የብዙ አገር ህዝቦች ድንበር ክፈቱልን ሥራ እንስራበት እያሉ ነው የሚያስቸግሩት፡፡ ቫኑዋቱ ብትሄዱ ግን በተቃራኒው ነው የምትሰሙት፡፡ ዶ/ር ሌን ታሪቮንዳ የኅብረተሰብ ጤና ዳይሬክተር ናቸው፣ የቫኑዋቱ ደሴት፡፡ ዶ/ር ሌን የመጡባት ደሴት አምባኡ ደሴት ትባላለች፡፡ 10ሺ ሰዎች ይኖሩባታል፡፡ ‹‹እኔ የመጣሁበት ደሴት ሄዳችሁ ድንበሩ ይከፈት ወይ ብትሏቸው አረ እንዳታስጨርሱን ነው የሚሏችሁ›› ይላሉ ለቢቢሲ፡፡ መታመም አንፈልግም ነው የሚሉት፡፡ 80 ከመቶ የታሪቮንዳ አገር ሕዝብ ገጠር ነው የሚኖር፡፡ የኮቪድ ሕመም ብዙም አልተሰማቸውም፡፡ እርሻ እንጂ ቱሪዝም ላይ ስላልተንጠላጠሉ ሊሆን ይችላል፡፡ ዶር ሌን ድንበር ለመክፈት አስበው ነበር፡፡ ነገር ግን ጎረቤት ፓፓዎ ጊኒ ለወራት ከቫይረሱ ነጻ ሆና ቆይታ ሐምሌ ላይ እንዴት ጉድ እንደሆነች ሰምተዋል፡፡ ስለዚህ ድንበር መክፈቱ ይቆየን ብለዋል፡፡ 4. ቶንጋ ቶንጋን የፈጠሩት ደግሞ 170 ደቂቀ ደሴቶች ናቸው፡፡ እዚያው ደቡባዊ ፓስፊክ ነው የሚገኙት፡፡ ቶንጋ ደሴቶቿን ብትሰበስብ በስፋት ከጃፓን አታንስም፡፡ ለ165 አመታት ንጉሣዊ የፊውዳል አስተዳደር ነበራት፡፡ ከዚህ ፊውዳላዊ ሥርዓት የወጣችው በ2010 ዓ. ም ነበር፡፡ ጥብቅ ክርስቲያን አማኞች ያሏት ቶንጋ ከእንግሊዝ ነጻ የሆነችው በ1970 ዓ.ም ነበር፡፡ ቶንጋ ምን አይነት ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ የሌላት አገር ተደርጋ ትታያለች፡፡ ማዕድን አልባም ናት ይባላል፡፡ ይህ ነው የሚባል የተፈጥሮ ማዕድን ሀብት ባይኖራትም በዓሣ ሀብት ራሷን ትደጉማለች፡፡ ሌላው የገቢ ምንጭ እርሻ ነው፡፡ ሌላው ደግሞ ቶንጋዊያውን ከውጭ አገር የሚልኩት ገንዘብ ነው፡፡ ብዙዎቹ ቶንጋዊያን ያሉት በኒዊዚላንድ ነው፡፡ በአገሪቱ የሥራ አጥ ቁጥር ከፍ ያለ ነው፡፡ ያም ሆኖ የውጭ ምንዛሬዋን የምታገኝበት አንዱ ቀዳዳ ቱሪዝም ስለነበር ኮቪድ ባይደርስባትም ምጣኔ ሀብታዊ ጉዳት አድርሶባታል፡፡ 5. ሰሙዋ በፓስፊክ ውቅያኖስ የምትገኘው ሰሙዋ እስከ 1961 ዓ. ም ድረስ በኒውዚላንድ ሥር ነበር የምትተዳደረው፡፡ 9 የእሳተ ገሞራ ደሴቶች ነው የፈጠሯት ይቺን አገር፡፡ ሆኖም 99 ከመቶ ሕዝቧ የሚኖረው በኡፖሉና ሳቫይ ደሴቶች ነው፡፡ ዋና ከተማዋ አፒያ ይባላል፡፡ ምጣኔ ሀብቷ በእርሻና በዓሣ ሀብት የተንጠለጠለ ነው፡፡ ሆኖም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቱሪዝም ሞቅ ደመቅ ብሎላት ነበር፡፡ በተለይ ያማሩ የባሕር ዳርቻዎቿ ተወዳጅ ሆነውላታል፡፡ ከቱሪዝም ጋር የባሕር ማዶ ዓለም አቀፍ ኦፍሾር የባንክ አገልግሎት በማሳለጧ ሀብታሞች ሸሸግ ማድረግ የፈለጉትን ገንዘብ ይዘው እዚያ ይሄዳሉ፡፡ አንድም ለመዝናናት፣ አንድም ለባንክ አገልግሎት፡፡ 200ሺህ የማይሞላው ሕዝቧ የወግ አጥባቂ ባህልና የጥብቅ ክርስትና ተከታይ ነው፡፡ አሁንም ቢሆን ዜጎቿ ወደ ኒውዚላንድና ሌሎች አገሮች እየተሰደዱ ገንዘብ ወደ ቤተሰብ ይልካሉ፡፡ ኮሮና በሌሎች አገሮች ያደረሰው ጉዳት ሕመሙ ተሰምቷል፣ ሩቅ በምትገኘው በሰሙዋ ደሴት፡፡ 6.ቱቫሉ ቱቫሉን የፈጠሩት 9 ደሴቶች ናቸው፡፡ ከነዚህ ውስጥ 5ቱ እሳተ ገሞራ ወልዶ፣ አሳብጦ፣ በድጋሚ አስምጦ ዳግም የወለዳቸው (ኮራል አቶልስ) ናቸው፡፡ የተቀሩት አራቱ ደግሞ ሕዝብ በደንብ ይኖርባቸዋል፡፡ ቱቫሉ በማዕከላዊ ፓስፊክ ውቅያኖስ ነው የምትገኘው፡፡ ፉናፉቲ ይባላል ዋና ከተማዋ፡፡ በቱቫሉ ተራራ አይታሰብም፡፡ ከባሕር ጠለል በላይ ከ4.5 ሜትር ከፍ ያለ ቦታ የለም፡፡ የአየር ንብረት በቱቫሉ ትልቁ ጉዳይ ቢሆን የማይገርመውም ለዚሁ ነው፡፡ የባሕር ጠለል ከፍታ ከምድረ ገጽ ከሚያጠፋቸው አገሮች አንዷ ቱቫሉ ነው የምትሆነው፡፡ በቱቫሉ ወንዝም ምንጭም ስለሌለ ኑሮ የዝናብ ጥገኛ ነው፡፡ የኮኮናት ተክል የአገሪቱ ገቢ ምንጭ ነው፡፡ ይህ ገቢ እንዲታወክ ምክንያት በመሆኑ ኮቪድ ቱቫሉ ባይገባም ገብቷል፡፡ 7. ናውሩ በዓለም ትንሽዋ አገር ናውሩ ናት፡፡ ይቺ ደሴት ስሟ በቅርብ ጊዜ ይነሳ የነበረው አውስትራሊያ አገሪቱን እንደ ጓሮ እየተጠቀመቻት ነው በሚል ነው፡፡ ናውሩ ስደተኞች ማጎርያ አለ፤ ንብረትነቱ የአውስትራሊያ የሆነ፡፡ ይሄ ማጎርያ ታዲያ ለናውሩ አንድ የገቢ ምንጭ መሆኑ ይገርማል፡፡ ናውሩዎች አንዱ ሥራ ቀጣሪ ኢንደስትሪያችሁ ምንድነው ቢባሉ የአውስታራሊያ የስደተኛ ካምፕ ብለው ሊመልሱ ይችላሉ፡፡ ከ2013 ጀምሮ አውስትራሊያ በጀልባ ወደ አገሯ ሊገቡ የሚሞክሩ ስደተኞችን በሙሉ ወደ ናውሩ ነው የምትወስዳቸው፡፡ ካልሆነም ፓፓው ኒው ጊኒ፡፡ ከአውስትራሊያ 3ሺህ ኪሎ ሜትር ርቃ በሰሜን ምሥራቅ ፓስፊክ አቅጣጫ የምትገኘው ናውሩ የዜጎቿ ብዛት 10 ሺህ ቢሆን ነው፡፡ ናውሩን የሚያኖራት እርዳታ ነው፡፡ ሌላው ብቸኛ ሀብቷ ፎስፌት ማዕድን ነው፡፡ በናውሩ የውጭ ጋዜጠኛ ሄዶ መዘገብ አይችልም፡፡ ምክንያቱም በካምፖቹ ውስጥ ያለውን ኢሰብአዊ ድርጊት ያጋልጣል፡፡ ይህ ደግሞ ናውሩ የገቢ ምንጬን ሊጎዳብኝ ይችላል ትላለች፡፡ ናውሩን በዓመት የሚጎበኛት ሰው ከ200 አይበልጥም ይባላል፡፡ ቴሌግራፍ በአንድ ዘገባው በናውሩ እስከዛሬ የገባው ቱሪስት ቢደመር ከ15ሺህ አይበልጥም ሲል ጽፏል፡፡ በስፋት ቫቲካን ሲቲና ሞናኮ ብቻ ናቸው የሚበልጧት፤ ለዚህም ነው የዓለም ትንሽዋ ሪፐብሊክ ደሴት የምትባለው፡፡ ቱሪስት የአገሪቱ ገቢ ምንጭ አለመሆኑ በኮቪድ-19 አልተጎዳችም ማለት ግን አይደለም፡፡ ለጊዜው ከ10ሺህ ዜጎቼ አንድም ሰው ኮቪድ-19 አልያዘውም ብትልም ሕመሙ ግን ናውሩም ደርሷል፡፡ 8. ኪሪባቲ ኪሪባቲ የብጥስጣሽ ደሴቶች አገር በመሆኗ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ 4ሺህ ኪሎ ሜትር፣ ከሰሜን ደቡብ ደግሞ 2ሺህ ኪሎ ሜትር ታስኬዳች፡፡ ይህ ማለት ግን ይህ ሁሉ ርቀት ሰው የሚኖርበት ደረቅ መሬት ነው ማለት አይደለም፡፡ ነጻነቷን ያገኘችው ከእንግሊዝ በ1979 ዓ.ም ነው፡፡ በ1960ዎቹ ይቺ አገር አንዳንድ ደሴቶቿ ለእንግሊዝ የኑክሌር መሞከሪያ ሆነው አገልግለዋል፡፡ እንደ ብዙዎቹ የፓስፊክ ደቂቀ ደሴቶች ሁሉ ኪሪባቲም የዓለም ሙቀት መጨመር ከምድረ ገጽ ሊያጠፋት እንደሚችል ይገመታል፡፡ ኪሪባቲ ከፊጂ ደሴት መሬት ተከራይታ ምግብ ታመርታለች፡፡ ኢኮኖሚዋ ደካማ ሲሆን ኮኮናትና ኮፕራ በመላክ ነው የምትታወቀው፡፡ የዓሣ ማጥመድ ፍቃድ ለውጭ ኩባንያዎች እየቸበቸበች ኢኮኖሚዋን በከፊል ትደጉማለች፡፡ 9ኛ የሰለሞን ደሴቶች፤ 10ኛ ማይክሮኒዢያ በዝርዝሩ 9ኛ እና 10ኛ ላይ ያሉት የሰለሞን ደሴቶች እና ማይክሮኒዢያ ናቸው፡፡ ሁለቱም አገራት በዓሣ ምርትና በቱሪዝም ይታወቃሉ፡፡ ሁሉም በኮቪድ-19 የተጠቃ ዜጋ የለባቸውም፡፡ ይህ ዝርዝር ታዲያ ሰሜን ኮሪያና ቱርከሜኒስታን አላካተተም፡፡ ሆኖም እነዚህ ሁለት አገራት በይፋ ከኮቪድ-19 የያዘው ዜጋ አለም የለምም ብለው አያውቁም፡፡ ወይም አይታመኑ ይሆናል፡፡
ኮሮናቫይረስ፡ ኮቪድ-19 ምን እንደሆነ አናውቅም የሚሉት 10 አገራት ኮቪድ ዓለምን አምሷል፡፡ እኛ ግን አናውቀውም የሚሉ 10 አገሮች አሉ ብንላችሁስ፡፡ ለመሆኑ እነዚህ አገሮች እነማን ናቸው? የማያውቁት ኮቪድ እንዴት እያደረጋቸው ይሆን? 1.ፕላው (Palau) ይቺ አገር የት ያለች ትመስልዎታለች? ሩቅ ምዕራብ ፓስፊክ ነው የምትገኘው፡፡ ማይክሮኒዢያ ሪጂን በሚባለው አካባቢ ከነ ፊሊፒንስ እና ኢንዶኒዢያ ነጠል ብላ በባትሪ ተፈልጋ የምትገኝ ጢኒጥ ደሴት ናት፡፡ እዚያ ፕላው የሚባል ሆቴል አለ፡፡ ድሮ በ1982 ነበር የተከፈተው፡፡ ያኔ የአገሩን ስም የያዘው ይኸው እስከዛሬ አለ፡፡ በአገሩ ሌላ ሆቴል የሌለ ይመስል፡፡ በፓስፊክ ውቅያኖስ ሰማያዊ ቀለም ውሀ ውስጥ ጠብ ያለች ነጥብ የምትመስለው ይቺ አገር የቱሪስት አገር ናት፡፡ ያለፈውን ዓመት ብቻ አሐዝ ብንወስድ፣ ወደ ፕላው ደሴት 90ሺህ ቱሪስት ገብቷል፡፡ ይህ አሐዝ ከፕላው ጠቅላላ ሕዝብ አምስት እጥፍ ይበልጣል ብንላችሁስ? 40 ከመቶ የአገሪቱ ጥቅል አገራዊ ምርት ገቢ በቱሪዝም የሚታለብ ነው፡፡ ይህ ግን ከኮቪድ በፊት ያለ ታሪክ ነው፡፡ ኮቪድ ድንበሯን ሲያዘጋት ፕላው ደሴት ጉሮሮዋ ተዘጋ፡፡ እንኳን ሌላው መዝናኛ ይቅርና የአገሪቱን ስም የያዘው ሆቴል ሳይቀር ተዘጋ፡፡ ‹‹ለውድ ደንበኞቻችን፡- ኮቪድ የሚባል በሽታ በተቀረው ዓለም ስለተከሰተ ፕላው ሆቴል ለጊዜው ዝግ መሆናችንን ለውድ እንገልጻለን›› ብለው በር ላይ ሳይለጥፉ አልቀሩም፡፡ ፕላው አገር አንድም ዜጋ በቫይረሱ ባይያዝባትም ቫይረሱ ግን ቱሪዝማዊ ኢኮኖሚዋን ደም እያስተፋው ነው፡፡ 2. የማርሻል ደሴቶች 4ሺህ ኪሎ ሜትር ርቀው በማዕከላዊ ፓስፊክ ውቅያኖስ መሀል፣ ከምድር ወገብ ሰሜን፣ ብጥስጥስ ብለው ከሚገኙት የእሳተ ገሞራ ደሴቶች ውስጥ የማርሻል ደሴቶች ይገኙበታል፡፡ በሀዋይ እና በፊሊፒንስ መሀል ነው የሚገኙት፡፡ በውስጣቸው 1200 ጥቃቅን ደሴቶችና የጎመራ ፍንጥቅጣቂ የሆኑ የሰመጡ ደቂቀ ደሴቶች (ኮራል አቶልስ) ይገኛሉ፡፡ ሁለተኛውን የዓለም ጦርነት ተከትሎ የአሜሪካ የሩቅ ግዛት ሆነው የቆዩ ቢሆንም ከ1986 ወዲህ ራሳቸውን ችለዋል። ደህንነቱና መከላከያን እንዲሁም ጠቀም ያለ ድጎማን ግን አሁንም ከአሜሪካ ነው የሚያገኙት። የሕዝብ ብዛት 55ሺህ ሲሆን ዋና ከተማቸው ማጁራ ትባላለች፡፡ እነዚህ ደቂቀ ደሴቶችና የቱሪስት መዳረሻ የሆኑ ስብስቦች ማርሻል ደሴቶች ተብለው ይጠራሉ፡፡ ኮቪድ ምን እንደሆነ ባያውቁም ምጣኔ ሀብታዊ ቁንጥጫው ግን ፓሲፊክን አቋርጦ ተሰምቷቸዋል። ታዲያ አንድ ፕላው በቱሪዝም በኩል አይደለም ቁንጥጫው፡፡ በዓሣ ማጥመድና መላክ ጥሩ ገንዘብ ያገኙ ነበር፡፡ ኮቪድ ይህንን አስተጓጎለባቸው፡፡ በኮቪድ ምክንያት 700 ሰዎች ሥራ አጥተዋል፡፡ ይህ ትንሽ ሕዝብ ላላት ማርሻል አይላንድስ ብዙ ቁጥር ነው፡፡ የሕዝብ ብዛቷ 300ሺህ ቢሆን ነው፡፡ ዋና ከተማዋ ፖርትቪላ ይባላል፡፡ በ1ሺህ 300 ኪሎ ሜትር ላይ የተሰፉ የሚመስሉ 80 ደሴቶች የፈጠሯት አገር ናት፡፡ ከፈረንሳይና እንግሊዝ ቅኝ ነጻ የወጣችው ገና በ1980 ነበር፡፡ አብዛኛው ሕዝቧ ገጠር የሚኖር ገበሬ ነው፡፡ የብዙ አገር ህዝቦች ድንበር ክፈቱልን ሥራ እንስራበት እያሉ ነው የሚያስቸግሩት፡፡ ቫኑዋቱ ብትሄዱ ግን በተቃራኒው ነው የምትሰሙት፡፡ ዶ/ር ሌን ታሪቮንዳ የኅብረተሰብ ጤና ዳይሬክተር ናቸው፣ የቫኑዋቱ ደሴት፡፡ ዶ/ር ሌን የመጡባት ደሴት አምባኡ ደሴት ትባላለች፡፡ 10ሺ ሰዎች ይኖሩባታል፡፡ ‹‹እኔ የመጣሁበት ደሴት ሄዳችሁ ድንበሩ ይከፈት ወይ ብትሏቸው አረ እንዳታስጨርሱን ነው የሚሏችሁ›› ይላሉ ለቢቢሲ፡፡ መታመም አንፈልግም ነው የሚሉት፡፡ 80 ከመቶ የታሪቮንዳ አገር ሕዝብ ገጠር ነው የሚኖር፡፡ የኮቪድ ሕመም ብዙም አልተሰማቸውም፡፡ እርሻ እንጂ ቱሪዝም ላይ ስላልተንጠላጠሉ ሊሆን ይችላል፡፡ ዶር ሌን ድንበር ለመክፈት አስበው ነበር፡፡ ነገር ግን ጎረቤት ፓፓዎ ጊኒ ለወራት ከቫይረሱ ነጻ ሆና ቆይታ ሐምሌ ላይ እንዴት ጉድ እንደሆነች ሰምተዋል፡፡ ስለዚህ ድንበር መክፈቱ ይቆየን ብለዋል፡፡ 4. ቶንጋ ቶንጋን የፈጠሩት ደግሞ 170 ደቂቀ ደሴቶች ናቸው፡፡ እዚያው ደቡባዊ ፓስፊክ ነው የሚገኙት፡፡ ቶንጋ ደሴቶቿን ብትሰበስብ በስፋት ከጃፓን አታንስም፡፡ ለ165 አመታት ንጉሣዊ የፊውዳል አስተዳደር ነበራት፡፡ ከዚህ ፊውዳላዊ ሥርዓት የወጣችው በ2010 ዓ. ም ነበር፡፡ ጥብቅ ክርስቲያን አማኞች ያሏት ቶንጋ ከእንግሊዝ ነጻ የሆነችው በ1970 ዓ.ም ነበር፡፡ ቶንጋ ምን አይነት ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ የሌላት አገር ተደርጋ ትታያለች፡፡ ማዕድን አልባም ናት ይባላል፡፡ ይህ ነው የሚባል የተፈጥሮ ማዕድን ሀብት ባይኖራትም በዓሣ ሀብት ራሷን ትደጉማለች፡፡ ሌላው የገቢ ምንጭ እርሻ ነው፡፡ ሌላው ደግሞ ቶንጋዊያውን ከውጭ አገር የሚልኩት ገንዘብ ነው፡፡ ብዙዎቹ ቶንጋዊያን ያሉት በኒዊዚላንድ ነው፡፡ በአገሪቱ የሥራ አጥ ቁጥር ከፍ ያለ ነው፡፡ ያም ሆኖ የውጭ ምንዛሬዋን የምታገኝበት አንዱ ቀዳዳ ቱሪዝም ስለነበር ኮቪድ ባይደርስባትም ምጣኔ ሀብታዊ ጉዳት አድርሶባታል፡፡ 5. ሰሙዋ በፓስፊክ ውቅያኖስ የምትገኘው ሰሙዋ እስከ 1961 ዓ. ም ድረስ በኒውዚላንድ ሥር ነበር የምትተዳደረው፡፡ 9 የእሳተ ገሞራ ደሴቶች ነው የፈጠሯት ይቺን አገር፡፡ ሆኖም 99 ከመቶ ሕዝቧ የሚኖረው በኡፖሉና ሳቫይ ደሴቶች ነው፡፡ ዋና ከተማዋ አፒያ ይባላል፡፡ ምጣኔ ሀብቷ በእርሻና በዓሣ ሀብት የተንጠለጠለ ነው፡፡ ሆኖም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቱሪዝም ሞቅ ደመቅ ብሎላት ነበር፡፡ በተለይ ያማሩ የባሕር ዳርቻዎቿ ተወዳጅ ሆነውላታል፡፡ ከቱሪዝም ጋር የባሕር ማዶ ዓለም አቀፍ ኦፍሾር የባንክ አገልግሎት በማሳለጧ ሀብታሞች ሸሸግ ማድረግ የፈለጉትን ገንዘብ ይዘው እዚያ ይሄዳሉ፡፡ አንድም ለመዝናናት፣ አንድም ለባንክ አገልግሎት፡፡ 200ሺህ የማይሞላው ሕዝቧ የወግ አጥባቂ ባህልና የጥብቅ ክርስትና ተከታይ ነው፡፡ አሁንም ቢሆን ዜጎቿ ወደ ኒውዚላንድና ሌሎች አገሮች እየተሰደዱ ገንዘብ ወደ ቤተሰብ ይልካሉ፡፡ ኮሮና በሌሎች አገሮች ያደረሰው ጉዳት ሕመሙ ተሰምቷል፣ ሩቅ በምትገኘው በሰሙዋ ደሴት፡፡ 6.ቱቫሉ ቱቫሉን የፈጠሩት 9 ደሴቶች ናቸው፡፡ ከነዚህ ውስጥ 5ቱ እሳተ ገሞራ ወልዶ፣ አሳብጦ፣ በድጋሚ አስምጦ ዳግም የወለዳቸው (ኮራል አቶልስ) ናቸው፡፡ የተቀሩት አራቱ ደግሞ ሕዝብ በደንብ ይኖርባቸዋል፡፡ ቱቫሉ በማዕከላዊ ፓስፊክ ውቅያኖስ ነው የምትገኘው፡፡ ፉናፉቲ ይባላል ዋና ከተማዋ፡፡ በቱቫሉ ተራራ አይታሰብም፡፡ ከባሕር ጠለል በላይ ከ4.5 ሜትር ከፍ ያለ ቦታ የለም፡፡ የአየር ንብረት በቱቫሉ ትልቁ ጉዳይ ቢሆን የማይገርመውም ለዚሁ ነው፡፡ የባሕር ጠለል ከፍታ ከምድረ ገጽ ከሚያጠፋቸው አገሮች አንዷ ቱቫሉ ነው የምትሆነው፡፡ በቱቫሉ ወንዝም ምንጭም ስለሌለ ኑሮ የዝናብ ጥገኛ ነው፡፡ የኮኮናት ተክል የአገሪቱ ገቢ ምንጭ ነው፡፡ ይህ ገቢ እንዲታወክ ምክንያት በመሆኑ ኮቪድ ቱቫሉ ባይገባም ገብቷል፡፡ 7. ናውሩ በዓለም ትንሽዋ አገር ናውሩ ናት፡፡ ይቺ ደሴት ስሟ በቅርብ ጊዜ ይነሳ የነበረው አውስትራሊያ አገሪቱን እንደ ጓሮ እየተጠቀመቻት ነው በሚል ነው፡፡ ናውሩ ስደተኞች ማጎርያ አለ፤ ንብረትነቱ የአውስትራሊያ የሆነ፡፡ ይሄ ማጎርያ ታዲያ ለናውሩ አንድ የገቢ ምንጭ መሆኑ ይገርማል፡፡ ናውሩዎች አንዱ ሥራ ቀጣሪ ኢንደስትሪያችሁ ምንድነው ቢባሉ የአውስታራሊያ የስደተኛ ካምፕ ብለው ሊመልሱ ይችላሉ፡፡ ከ2013 ጀምሮ አውስትራሊያ በጀልባ ወደ አገሯ ሊገቡ የሚሞክሩ ስደተኞችን በሙሉ ወደ ናውሩ ነው የምትወስዳቸው፡፡ ካልሆነም ፓፓው ኒው ጊኒ፡፡ ከአውስትራሊያ 3ሺህ ኪሎ ሜትር ርቃ በሰሜን ምሥራቅ ፓስፊክ አቅጣጫ የምትገኘው ናውሩ የዜጎቿ ብዛት 10 ሺህ ቢሆን ነው፡፡ ናውሩን የሚያኖራት እርዳታ ነው፡፡ ሌላው ብቸኛ ሀብቷ ፎስፌት ማዕድን ነው፡፡ በናውሩ የውጭ ጋዜጠኛ ሄዶ መዘገብ አይችልም፡፡ ምክንያቱም በካምፖቹ ውስጥ ያለውን ኢሰብአዊ ድርጊት ያጋልጣል፡፡ ይህ ደግሞ ናውሩ የገቢ ምንጬን ሊጎዳብኝ ይችላል ትላለች፡፡ ናውሩን በዓመት የሚጎበኛት ሰው ከ200 አይበልጥም ይባላል፡፡ ቴሌግራፍ በአንድ ዘገባው በናውሩ እስከዛሬ የገባው ቱሪስት ቢደመር ከ15ሺህ አይበልጥም ሲል ጽፏል፡፡ በስፋት ቫቲካን ሲቲና ሞናኮ ብቻ ናቸው የሚበልጧት፤ ለዚህም ነው የዓለም ትንሽዋ ሪፐብሊክ ደሴት የምትባለው፡፡ ቱሪስት የአገሪቱ ገቢ ምንጭ አለመሆኑ በኮቪድ-19 አልተጎዳችም ማለት ግን አይደለም፡፡ ለጊዜው ከ10ሺህ ዜጎቼ አንድም ሰው ኮቪድ-19 አልያዘውም ብትልም ሕመሙ ግን ናውሩም ደርሷል፡፡ 8. ኪሪባቲ ኪሪባቲ የብጥስጣሽ ደሴቶች አገር በመሆኗ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ 4ሺህ ኪሎ ሜትር፣ ከሰሜን ደቡብ ደግሞ 2ሺህ ኪሎ ሜትር ታስኬዳች፡፡ ይህ ማለት ግን ይህ ሁሉ ርቀት ሰው የሚኖርበት ደረቅ መሬት ነው ማለት አይደለም፡፡ ነጻነቷን ያገኘችው ከእንግሊዝ በ1979 ዓ.ም ነው፡፡ በ1960ዎቹ ይቺ አገር አንዳንድ ደሴቶቿ ለእንግሊዝ የኑክሌር መሞከሪያ ሆነው አገልግለዋል፡፡ እንደ ብዙዎቹ የፓስፊክ ደቂቀ ደሴቶች ሁሉ ኪሪባቲም የዓለም ሙቀት መጨመር ከምድረ ገጽ ሊያጠፋት እንደሚችል ይገመታል፡፡ ኪሪባቲ ከፊጂ ደሴት መሬት ተከራይታ ምግብ ታመርታለች፡፡ ኢኮኖሚዋ ደካማ ሲሆን ኮኮናትና ኮፕራ በመላክ ነው የምትታወቀው፡፡ የዓሣ ማጥመድ ፍቃድ ለውጭ ኩባንያዎች እየቸበቸበች ኢኮኖሚዋን በከፊል ትደጉማለች፡፡ 9ኛ የሰለሞን ደሴቶች፤ 10ኛ ማይክሮኒዢያ በዝርዝሩ 9ኛ እና 10ኛ ላይ ያሉት የሰለሞን ደሴቶች እና ማይክሮኒዢያ ናቸው፡፡ ሁለቱም አገራት በዓሣ ምርትና በቱሪዝም ይታወቃሉ፡፡ ሁሉም በኮቪድ-19 የተጠቃ ዜጋ የለባቸውም፡፡ ይህ ዝርዝር ታዲያ ሰሜን ኮሪያና ቱርከሜኒስታን አላካተተም፡፡ ሆኖም እነዚህ ሁለት አገራት በይፋ ከኮቪድ-19 የያዘው ዜጋ አለም የለምም ብለው አያውቁም፡፡ ወይም አይታመኑ ይሆናል፡፡
https://www.bbc.com/amharic/news-53864759
5sports
የ105 ዓመቷ እማማ ራምባይ በሩጫ ክብረ ወሰን ሰበሩ
ወ/ሮ ራምባይ 105 ዓመታቸው ነው። 100 ሜትርን በ45.40 ሰከንድ በመጨረስ በአዛውንቶች የተያዘውን የሕንድን ክብረ ወሰን ሰብረዋል። ይህንን ውድድር የሚያዘጋጀው አካል እስካሁን ትልቁ የውድድር ተሳታፊ የ85 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋ ነው።
የ105 ዓመቷ እማማ ራምባይ በሩጫ ክብረ ወሰን ሰበሩ ወ/ሮ ራምባይ 105 ዓመታቸው ነው። 100 ሜትርን በ45.40 ሰከንድ በመጨረስ በአዛውንቶች የተያዘውን የሕንድን ክብረ ወሰን ሰብረዋል። ይህንን ውድድር የሚያዘጋጀው አካል እስካሁን ትልቁ የውድድር ተሳታፊ የ85 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋ ነው።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cglrkjmrvngo
0business
ሕዳሴ የግድብ 3ኛ ዙር የውሃ ሙሌት መጠናቀቁ ተገለጸ
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውሃ ሙሌት ተጠናቆ በግድቡ አናት ላይ ውሃ መፍሰስ መጀመሩ ተገለጸ። የ3ኛው ዙር የግደቡ የውሃ ሙሌት መጠናቀቁን ተከትሎ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ እና ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት በስፍራው ተገኝተዋል። ባለፉት ሁለት የክረምት ወቅቶች የመጀመሪያው እና ሁለተኛው የግድቡ የውሃ ሙሌት መካሄዱ ይታወሳል። የ3ኛው ዙር የግደቡ የውሃ ሙሌት መጠናቀቁ የተገለጸው ትናንት ነሐሴ 5/2014 ዓ.ም. የሁለተኛው የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ተርባይን ሥራ መጀመሩ ከተገለጸ በኋላ ነው። ትናንት ኃይል ማመንጨት የጀመረው የግድቡ 2ኛው ተርባይን ዩኒት ዘጠኝ የተባለው ሲሆን 270 ሜጋ ዋት የአሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም አለው ተብሏል። የካቲት 2014 ዓ.ም. ወደ ሥራ የገባው ዩኒት 10 ተርባይን በተመሳሳይ 270 ሜጋ ዋት ሃይል የማመንጨት አቅም እንዳለው ተገልጿል። በዚህም መሠረት ሁለቱ ኃይሎች በድምሩ 540 ሜጋ ዋት የአሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳላቸው ተመልክቷል። የግድቡ ግንባታ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ የግድቡ የሲቪል ሥራዎች ግንባታ 95 በመቶው መጠናቀቁን የገለጹ ሲሆን፤ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎች ግንባታና እና ተከላ ወደ 61 በመቶ ከፍ ማለቱንና የውሃ ማስተላለፊያ የብረታ ብረት ሥራዎችን ደግሞ 73 በመቶ መድረሱን ገልጸዋል። ዋና ሥራ አስኪያጁ የግድቡ ሁለተኛው የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ተርባይን ኃይል የማመንጨት ሥራን ለማስጀመር በተካሄደ ሥነ ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር የግድቡ አጠቃላይ የግንባታ ሥራ 83.3 በመቶ ደርሷል ብለዋል። ግንባታው ሲጠናቀቅ በአፍሪካ ግዙፉ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድብ እንደሚሆን የሚጠበቀው የሕዳሴ ግድብ ከፍታው 145 ሜትር ሲሆን፤ ርዝመቱ ደግሞ 1 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር ነው። ከአምስት ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ ፈሶበት ከአምስት ሺህ በላይ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫል የተባለው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ከኢትዮጵያ አልፎ ለአካባቢው አገራት የኤሌክትሪክ ኃይል ያቀርባል ተብሎ ይጠበቃል። የግንባታው መሠረተ ድንጋይ መጋቢት 24/2003 ዓ.ም የተጣለው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያ በስተምዕራብ ከሱዳን ጋር በምትዋሰንበት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ በጉባ ወረዳ እየተገነባ ይገኛል።
ሕዳሴ የግድብ 3ኛ ዙር የውሃ ሙሌት መጠናቀቁ ተገለጸ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውሃ ሙሌት ተጠናቆ በግድቡ አናት ላይ ውሃ መፍሰስ መጀመሩ ተገለጸ። የ3ኛው ዙር የግደቡ የውሃ ሙሌት መጠናቀቁን ተከትሎ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ እና ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት በስፍራው ተገኝተዋል። ባለፉት ሁለት የክረምት ወቅቶች የመጀመሪያው እና ሁለተኛው የግድቡ የውሃ ሙሌት መካሄዱ ይታወሳል። የ3ኛው ዙር የግደቡ የውሃ ሙሌት መጠናቀቁ የተገለጸው ትናንት ነሐሴ 5/2014 ዓ.ም. የሁለተኛው የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ተርባይን ሥራ መጀመሩ ከተገለጸ በኋላ ነው። ትናንት ኃይል ማመንጨት የጀመረው የግድቡ 2ኛው ተርባይን ዩኒት ዘጠኝ የተባለው ሲሆን 270 ሜጋ ዋት የአሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም አለው ተብሏል። የካቲት 2014 ዓ.ም. ወደ ሥራ የገባው ዩኒት 10 ተርባይን በተመሳሳይ 270 ሜጋ ዋት ሃይል የማመንጨት አቅም እንዳለው ተገልጿል። በዚህም መሠረት ሁለቱ ኃይሎች በድምሩ 540 ሜጋ ዋት የአሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳላቸው ተመልክቷል። የግድቡ ግንባታ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ የግድቡ የሲቪል ሥራዎች ግንባታ 95 በመቶው መጠናቀቁን የገለጹ ሲሆን፤ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎች ግንባታና እና ተከላ ወደ 61 በመቶ ከፍ ማለቱንና የውሃ ማስተላለፊያ የብረታ ብረት ሥራዎችን ደግሞ 73 በመቶ መድረሱን ገልጸዋል። ዋና ሥራ አስኪያጁ የግድቡ ሁለተኛው የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ተርባይን ኃይል የማመንጨት ሥራን ለማስጀመር በተካሄደ ሥነ ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር የግድቡ አጠቃላይ የግንባታ ሥራ 83.3 በመቶ ደርሷል ብለዋል። ግንባታው ሲጠናቀቅ በአፍሪካ ግዙፉ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድብ እንደሚሆን የሚጠበቀው የሕዳሴ ግድብ ከፍታው 145 ሜትር ሲሆን፤ ርዝመቱ ደግሞ 1 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር ነው። ከአምስት ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ ፈሶበት ከአምስት ሺህ በላይ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫል የተባለው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ከኢትዮጵያ አልፎ ለአካባቢው አገራት የኤሌክትሪክ ኃይል ያቀርባል ተብሎ ይጠበቃል። የግንባታው መሠረተ ድንጋይ መጋቢት 24/2003 ዓ.ም የተጣለው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያ በስተምዕራብ ከሱዳን ጋር በምትዋሰንበት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ በጉባ ወረዳ እየተገነባ ይገኛል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cqqdgz7ydg0o
0business
የኑሮ ውድነት፡ በኢትዮጵያ የዋጋ ጭማሪ እንጂ ቅናሽ የማይታየው ለምን ይሆን?
በአዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑት እና በኑሮ ውድነቱ የተማረሩት የቤተሰብ አስተዳዳሪ ሁሌም ለሸቀጦች ዋጋ መጨመር ነጋዴው ምክንያት የሚሰጣቸው የነዳጅ ዋጋ መጨመር እና የዶላር ምንዛሬ ዋጋ መናርን እንደሆነ ለቢቢሲ ይናገራሉ። "ፈሳሹ ዘይት ተፈልጎ አይገኘም" የሚሉት እኚህ የአዲስ አበባ ነዋሪ፣ ከዚህ ቀደም አንድ እንጀራ በ10 ብር ይገዙ እንደነበር አስታውሰው 12 ብር መግባቱን በምሬት ይናገራሉ። የኑሮ ውድነቱ ግን አዲስ አበባን መኖሪያቸው ያደረጉትን ብቻ አይደለም የተጫነው፣ በሐረር ከተማ የሚኖሩት ወ/ሮ ሽርካ አሕመድ ዘንድሮ የገጠማቸው የዕቃዎች ዋጋ መጨመር ከዚህም በፊት ከነበረው ሁሉ የተለየ መሆኑን ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ኑሮ እጅግ ተወዶብናል። ለምሳሌ አንድ ኪሎ ቲማቲም 12 ብር የነበረው በአሁኑ ሰዓት 25 ብር ገብቷል። ከጥቂት ቀናት በፊት በ265 ብር ይገዛ የነበረው ዘይት 430 ገብቷል። ከሶስት ወራት ወዲህ ያልጨመረ አንድም ነገር የለም። ከአቅማችን በላይ ሆኗል" ሲሉ ተስፋ በመቁረጥ ይናገራሉ።። ወ/ሮ ሽርካ በሁሉም እቃዎች ላይ የሚታየው የዋጋ ጭማሪ 'ዶላር ስለጨመረ ነው' ሲባል ከመስማት ውጪ ምክንያቱ ይህ ነው ብሎ ያስረዳቸው የለም።። በችርቻሮ ንግድ ላይ የተሰማሩት የአጋሮ ከተማ ነዋሪ ወ/ሮ እመቤት ከድር በበኩላቸው፣ በገበያ የሚታየው የዋጋ ንረት "ጠዋትና እና ከሰዓት በኋላ የዋጋ ልዩነት ማሳየት ጀምሯል" ይላሉ። "እኔ የችርቻሮ ነጋዴ ነኝ፤ ከኅብረተሰቡ ጋር በቀጥታ እገናኛለሁ፤ እኛ ደግሞ ከጅምላ አከፋፋዮች እንገዛለን። እኛ እነርሱን ስንጠይቅ፣ የጨመረው ከላይ ነው ይሉናል፤ ግልጽ የሆነ ምክንያት የለም። እኔ አሁን ይህንን የሕዝብ ምሬት መስማት አቅቶኝ ሥራዬን እያቆምኩ ነው" ይላሉ ወ/ሮ እመቤት። አክለውም "አንድም ዋጋው አልጨመረም የምንለው ነገር የለም። አንተ ጠዋት አንድ እቃ ከሸጥክ፣ ከሰዓት በኋላ ዋጋው ጨምሯል። እቃው ግን ያው ጠዋት የነበረው ነው። ተገቢ ቁጥጥር መደረግ አለበት" ሲሉ ለመፍትሄው የመንግሥትን እጅ ይማፀናሉ። በዚህ ወር ውስጥ ዋጋቸው ከጨመረ ነገሮች መካከል የነዳጅ ዘይት አንዱ ነው። በዚህም ምከንያት የትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ማስተካከያ ተደርጓል። ኢትዮጵያ ከውጪ የምታስገባው የነዳጅ ዘይት በሁለት አቅጣጫዎች፣ በሱዳን እና ጅቡቲ በኩል የነበረ ሲሆን፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በሱዳን በኩል የሚገባው መቋረጡን የቢሮው ኃላፊዎች ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ አለማየሁ ፀጋዬ በሱዳን በኩል የሚገባው ነዳጅ ቢቋረጥም፣ አገሪቷ ከውጪ በምታስመጣው ነዳጅ ላይ ግን የታየ ለውጥ የለም ይላሉ። "በነዳጅ አቅርቦት ላይ ከዚህ በፊት በነበረው ላይ ልዩነት የለም። በሱዳን በኩል ይገባ የነበረው ቤንዚን ብቻ ነው። እንደውም በጥገና ምክንያት ይገባ ከነበረው የቀነሰ እና ለተወሰኑት ከተሞች ብቻ ሲቀርብ የነበረ ነው። በኮሮናቫይረስ ምክንያት ደግሞ ይገባ የነበረው ራሱ ተቋርጦ ነው የቆየው" መሆኑን ገልፀዋል። በሱዳን በኩል ይቀርብ የነበረው ነዳጅ፣ ቀድሞ የተቋረጠ እና በሁለቱ አገራት መካከል ካለው የድንበር ውዝግብ ጋር የማይገናኝ መሆኑንም ጨምረው አስረድተዋል። ኢትዮጵያ ነዳጅን ከመካከለኛው ምስራቅ፣ በጅቡቲ በኩል እያስገባች መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው የሚናገሩት የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያው፣ በሱዳን በኩል የነበረው አቅርቦት ከተቋረጠ ወዲህም የአቅርቦት እጥረት አልተፈጠረም ብለዋል። በኢትዮጵያ ከሰላሳ በላይ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅቶች ከውጪ የሚገባውን ይህንን ነዳጅ ለተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ያቀርባሉ። በነዳጅ ላይ የተደረገው የዋጋ ጭማሪም ከዓለም ገበያ ዋጋ ጋር የተያያዘ እንጂ በአቅርቦት መቀነስ ምክንያት እንዳልሆነ ኀብረተሰቡ ሊረዳ ይገባል ሲሉ አቶ አለማየሁ ፀጋዬ ያስረዳሉ። የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋን የሚወስነው የንግድ ሚኒስቴር በመሆኑ፣ በአሁኑ ወቅት የነዳጅ ምርቶች ዋጋ የጨመረበትን ምክንያት ለማጣራት የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱን ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። የምጣኔ ኃብት ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር ጉቱ ቴሶ አሁን በኢትዮጵያ ለገጠመው የኑሮ ውድነት ምክንያቶቹ በርካታ መሆናቸውን ያስረዳሉ። ቀዳሚዎቹ ግን ከዓመት ዓመት መጨመር እንጂ መቀነስ የማያሳየው ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት አንዱ መሆኑን ይጠቅሳሉ። ይህ በየዓመቱ መጨመር ብቻ የሚያሳየው የዋጋ ግሽበት መንስዔው መሠረታዊ የሆኑ የምጣኔ ኃብት መዋቅሮች አለመስተካከል ጋር ተያይዞ መሆኑን ገልፀዋል። ቀሪዎቹ ደግሞ ወቅታዊ የሆኑ እና የአገሪቱን ምጣኔ ኃብት ፈተና ውስጥ የሚጥሉ ክስተቶች መሆናቸውን ተናግረዋል፥። ዶ/ር ጉቱ የምርት አቅርቦት እየቀነሰ መምጣት፤ የሰላም መታጣት፣ በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ መፈናቀሎች ለገበያው ዋጋ መናር ምክንያቶች መሆናቸውንም ይጠቅሳሉ። በአገሪቱ ውስጥ የተካሄዱ ሕዝባዊ አመጾች፣ የተደረጉ ተከታታይ የገበያ እቀባዎች፣ የንግድ ሰንሰለቱን በተጋጋሚ መሰበራቸውን፣ በተለይ ደግሞ ትርፍ አምራች በሆኑ አካባቢዎች በሰላም እጦት ምክንያት ተደራራቢ ጫና መፍጠሩን ያስረዳሉ። ገበሬው በሰላም እጦት ምክንያት ቢያርስ እንኳ አልጎለጎለም የሚሉት ባለሙያው፣ የጎለጎለው መዝራት ሳይችል ሲቀር፣ የዘራ ደግሞ መሰብሰብ አለመቻሉ የእርሻ ምርቶች አቅርቦት እየቀነሰ እንዲመጣ ማድረጉን ይገልጻሉ። የምጣኔ ኃብት ባለሙያው አክለውም በርካታ ኢንደስትሪዎችም ከውጪ አገር ግብዓት ስላላገኙ ወይንም በሰላም እጦት ፍራቻ ምክንያት ምርት መቀነሳቸው ወይንም ማቆማቸው ሌላው ለኑሮ ውድነቱ አስተዋጽኦ ካደረጉ ነገሮች መካከል አንዱ ነው። እነዚህ ማምረት የሚያቆሙ ኩባንያዎች በበዙ ቁጥር ለኑሮ ውድነቱ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ የሚገልጹት ዶ/ር ጉቱ፣ የውጪ ምንዛሬ እጥረት እና የገንዘብ የመግዛት አቅም መዳከም ተደራርበው የኑሮ ውድነትን ማክበዳቸውን ይገልጻሉ። "ከ2017 እስከ 2021 (እኤአ) የኢትዮጵያ ብር የመግዛት አቅም በ54 በመቶ ወርዷል፤ በአጠቃላይ ሲታይ በአስር ዓመታት ውስጥ የኢትዮጰያ ብር የመግዛት አቅም በመቶ እጅ ወድቋል" የሚሉት ዶ/ር ጉቱ፣ የምግብ አቅርቦትና ሌሎች የዕለት ፍጆታ የሆኑ ምርቶች የብር የመግዛት አቅም በወደቀበት በዚህ ጊዜ ከውጪ ሲገቡ የኑሮ ውድነትን እንደሚያባብሱ ይናገራሉ። በኢትዮጵያ ውስጥ ምርት የሚያመርቱ አብዛኞቹ ኢንደስትሪዎች ከውጪ በሚገባው ግብዓት ላይ የተንጠለጠሉ በመሆናቸው ይህንን ችግር ለመፍታት ያላቸውን ሚና ማሳነሱንም ይገልጻሉ። በኢትዮጵያ እየታየ ያለው የኑሮ ውድነት ዘላቂ መፍትሄ ሳያገኝ ከቀጠለ አገሪቷን ውስብስብ ወደ ሆነ ችግር ሊመራት እንደሚችል ባለሙያው ይመለክታሉ። "ሰው በኢኮኖሚ ሲዳከም ከአንድ ቦታ ወደ አንድ ቦታ ይሰደዳል። እንደዚህ ዓይነት ስደት ደግሞ በከተሞች ላይ ማህበራዊ ቀውስን ያስከትላል። የሚበላው ያጣ ሕብረተሰብ ደግሞ ወደ ተቃውሞ እና ሽብር ይሄዳል። ይህ ደግሞ አሁንም ምልክቱ እየታየ ነው" ብለዋል። የሥራ ማጣት፣ የኑሮ ውድነት እና ሌሎች ምክንያቶች ችግሮች፣ መጀመሪያውኑ አሁን ካለንበት አዙሪት ውስጥ እንዳንወጣ ያደርጉናል የሚል ስጋት እንዳላቸው ጨምረው ይናገራሉ። የኑሮ ውድነትን ጨምሮ ለበርካታ የአገሪቱ ችግሮች መነሻ የሆነው ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት የመጀመሪያው ምርጫ መሆን እንዳለበት ዶ/ር ጉቱ ያመለክታሉ። "ሰላም ከሌለ ኢንቨስትመንት የለም፣ ወደ ውጪ መላክ የለም፣ ምርትን አጓጉዞ ማከፋፈል የለም። ሰላም ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ መኖር ያለበት ጉዳይ ነው። ለዚህ ደግሞ መንግሥትና ሌሎች ድርጅቶች አብረው ሆነው መወያየት አለባቸው። ግጭት ከሁሉም ወገን መቆም አለበት" ሲሉ ይመክራሉ። የውጪ ምንዛሬ ላይ በፍጥነት ማስተካከያ መደረግ አለበት የሚሉት የምጣኔ ኃብት ባለሙያው፣ በዚህ ሁኔታ አገሪቱ ከቀጠለች አስቸጋሪ የምጣኔ ኃብት ቅርቃር ውስጥ ልትገባ እንደምትችል ገልፀዋል። ብር የመግዛት አቅሙ ከቀን ወደ ቀን መቀነሱ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ መቆም እንዳለበትም ይመክራሉ። አሁን ያለው የውጪ ምንዛሬ ከዚህም ባነሰ በ30 እጅ ወደ ኋላ መመለስ አለበት ይላሉ። አሁን የብርን ዋጋ እንዲወርድ ማድረግ በኢንቨስትመንትም ሆነ በውጪ ንግድ አንጻር ለኢትዮጵያ የሚያመጣው ፋይዳ የለውም ብለዋል። የአገሪቷን ኢኮኖሚ እንዲያገግም ለማድረግ፣ የባህልና ማህበረሰባዊ እንቅስቃሴ ማካሄድ አለበትም የሚሉት ዶ/ር ጉቱ፣ የህዝቦች የሥራ ባህልም ላይ መሻሻል መደረግ አለበት በማለት ሃሳባቸውን ያጠናቅቃሉ።
የኑሮ ውድነት፡ በኢትዮጵያ የዋጋ ጭማሪ እንጂ ቅናሽ የማይታየው ለምን ይሆን? በአዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑት እና በኑሮ ውድነቱ የተማረሩት የቤተሰብ አስተዳዳሪ ሁሌም ለሸቀጦች ዋጋ መጨመር ነጋዴው ምክንያት የሚሰጣቸው የነዳጅ ዋጋ መጨመር እና የዶላር ምንዛሬ ዋጋ መናርን እንደሆነ ለቢቢሲ ይናገራሉ። "ፈሳሹ ዘይት ተፈልጎ አይገኘም" የሚሉት እኚህ የአዲስ አበባ ነዋሪ፣ ከዚህ ቀደም አንድ እንጀራ በ10 ብር ይገዙ እንደነበር አስታውሰው 12 ብር መግባቱን በምሬት ይናገራሉ። የኑሮ ውድነቱ ግን አዲስ አበባን መኖሪያቸው ያደረጉትን ብቻ አይደለም የተጫነው፣ በሐረር ከተማ የሚኖሩት ወ/ሮ ሽርካ አሕመድ ዘንድሮ የገጠማቸው የዕቃዎች ዋጋ መጨመር ከዚህም በፊት ከነበረው ሁሉ የተለየ መሆኑን ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ኑሮ እጅግ ተወዶብናል። ለምሳሌ አንድ ኪሎ ቲማቲም 12 ብር የነበረው በአሁኑ ሰዓት 25 ብር ገብቷል። ከጥቂት ቀናት በፊት በ265 ብር ይገዛ የነበረው ዘይት 430 ገብቷል። ከሶስት ወራት ወዲህ ያልጨመረ አንድም ነገር የለም። ከአቅማችን በላይ ሆኗል" ሲሉ ተስፋ በመቁረጥ ይናገራሉ።። ወ/ሮ ሽርካ በሁሉም እቃዎች ላይ የሚታየው የዋጋ ጭማሪ 'ዶላር ስለጨመረ ነው' ሲባል ከመስማት ውጪ ምክንያቱ ይህ ነው ብሎ ያስረዳቸው የለም።። በችርቻሮ ንግድ ላይ የተሰማሩት የአጋሮ ከተማ ነዋሪ ወ/ሮ እመቤት ከድር በበኩላቸው፣ በገበያ የሚታየው የዋጋ ንረት "ጠዋትና እና ከሰዓት በኋላ የዋጋ ልዩነት ማሳየት ጀምሯል" ይላሉ። "እኔ የችርቻሮ ነጋዴ ነኝ፤ ከኅብረተሰቡ ጋር በቀጥታ እገናኛለሁ፤ እኛ ደግሞ ከጅምላ አከፋፋዮች እንገዛለን። እኛ እነርሱን ስንጠይቅ፣ የጨመረው ከላይ ነው ይሉናል፤ ግልጽ የሆነ ምክንያት የለም። እኔ አሁን ይህንን የሕዝብ ምሬት መስማት አቅቶኝ ሥራዬን እያቆምኩ ነው" ይላሉ ወ/ሮ እመቤት። አክለውም "አንድም ዋጋው አልጨመረም የምንለው ነገር የለም። አንተ ጠዋት አንድ እቃ ከሸጥክ፣ ከሰዓት በኋላ ዋጋው ጨምሯል። እቃው ግን ያው ጠዋት የነበረው ነው። ተገቢ ቁጥጥር መደረግ አለበት" ሲሉ ለመፍትሄው የመንግሥትን እጅ ይማፀናሉ። በዚህ ወር ውስጥ ዋጋቸው ከጨመረ ነገሮች መካከል የነዳጅ ዘይት አንዱ ነው። በዚህም ምከንያት የትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ማስተካከያ ተደርጓል። ኢትዮጵያ ከውጪ የምታስገባው የነዳጅ ዘይት በሁለት አቅጣጫዎች፣ በሱዳን እና ጅቡቲ በኩል የነበረ ሲሆን፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በሱዳን በኩል የሚገባው መቋረጡን የቢሮው ኃላፊዎች ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ አለማየሁ ፀጋዬ በሱዳን በኩል የሚገባው ነዳጅ ቢቋረጥም፣ አገሪቷ ከውጪ በምታስመጣው ነዳጅ ላይ ግን የታየ ለውጥ የለም ይላሉ። "በነዳጅ አቅርቦት ላይ ከዚህ በፊት በነበረው ላይ ልዩነት የለም። በሱዳን በኩል ይገባ የነበረው ቤንዚን ብቻ ነው። እንደውም በጥገና ምክንያት ይገባ ከነበረው የቀነሰ እና ለተወሰኑት ከተሞች ብቻ ሲቀርብ የነበረ ነው። በኮሮናቫይረስ ምክንያት ደግሞ ይገባ የነበረው ራሱ ተቋርጦ ነው የቆየው" መሆኑን ገልፀዋል። በሱዳን በኩል ይቀርብ የነበረው ነዳጅ፣ ቀድሞ የተቋረጠ እና በሁለቱ አገራት መካከል ካለው የድንበር ውዝግብ ጋር የማይገናኝ መሆኑንም ጨምረው አስረድተዋል። ኢትዮጵያ ነዳጅን ከመካከለኛው ምስራቅ፣ በጅቡቲ በኩል እያስገባች መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው የሚናገሩት የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያው፣ በሱዳን በኩል የነበረው አቅርቦት ከተቋረጠ ወዲህም የአቅርቦት እጥረት አልተፈጠረም ብለዋል። በኢትዮጵያ ከሰላሳ በላይ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅቶች ከውጪ የሚገባውን ይህንን ነዳጅ ለተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ያቀርባሉ። በነዳጅ ላይ የተደረገው የዋጋ ጭማሪም ከዓለም ገበያ ዋጋ ጋር የተያያዘ እንጂ በአቅርቦት መቀነስ ምክንያት እንዳልሆነ ኀብረተሰቡ ሊረዳ ይገባል ሲሉ አቶ አለማየሁ ፀጋዬ ያስረዳሉ። የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋን የሚወስነው የንግድ ሚኒስቴር በመሆኑ፣ በአሁኑ ወቅት የነዳጅ ምርቶች ዋጋ የጨመረበትን ምክንያት ለማጣራት የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱን ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። የምጣኔ ኃብት ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር ጉቱ ቴሶ አሁን በኢትዮጵያ ለገጠመው የኑሮ ውድነት ምክንያቶቹ በርካታ መሆናቸውን ያስረዳሉ። ቀዳሚዎቹ ግን ከዓመት ዓመት መጨመር እንጂ መቀነስ የማያሳየው ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት አንዱ መሆኑን ይጠቅሳሉ። ይህ በየዓመቱ መጨመር ብቻ የሚያሳየው የዋጋ ግሽበት መንስዔው መሠረታዊ የሆኑ የምጣኔ ኃብት መዋቅሮች አለመስተካከል ጋር ተያይዞ መሆኑን ገልፀዋል። ቀሪዎቹ ደግሞ ወቅታዊ የሆኑ እና የአገሪቱን ምጣኔ ኃብት ፈተና ውስጥ የሚጥሉ ክስተቶች መሆናቸውን ተናግረዋል፥። ዶ/ር ጉቱ የምርት አቅርቦት እየቀነሰ መምጣት፤ የሰላም መታጣት፣ በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ መፈናቀሎች ለገበያው ዋጋ መናር ምክንያቶች መሆናቸውንም ይጠቅሳሉ። በአገሪቱ ውስጥ የተካሄዱ ሕዝባዊ አመጾች፣ የተደረጉ ተከታታይ የገበያ እቀባዎች፣ የንግድ ሰንሰለቱን በተጋጋሚ መሰበራቸውን፣ በተለይ ደግሞ ትርፍ አምራች በሆኑ አካባቢዎች በሰላም እጦት ምክንያት ተደራራቢ ጫና መፍጠሩን ያስረዳሉ። ገበሬው በሰላም እጦት ምክንያት ቢያርስ እንኳ አልጎለጎለም የሚሉት ባለሙያው፣ የጎለጎለው መዝራት ሳይችል ሲቀር፣ የዘራ ደግሞ መሰብሰብ አለመቻሉ የእርሻ ምርቶች አቅርቦት እየቀነሰ እንዲመጣ ማድረጉን ይገልጻሉ። የምጣኔ ኃብት ባለሙያው አክለውም በርካታ ኢንደስትሪዎችም ከውጪ አገር ግብዓት ስላላገኙ ወይንም በሰላም እጦት ፍራቻ ምክንያት ምርት መቀነሳቸው ወይንም ማቆማቸው ሌላው ለኑሮ ውድነቱ አስተዋጽኦ ካደረጉ ነገሮች መካከል አንዱ ነው። እነዚህ ማምረት የሚያቆሙ ኩባንያዎች በበዙ ቁጥር ለኑሮ ውድነቱ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ የሚገልጹት ዶ/ር ጉቱ፣ የውጪ ምንዛሬ እጥረት እና የገንዘብ የመግዛት አቅም መዳከም ተደራርበው የኑሮ ውድነትን ማክበዳቸውን ይገልጻሉ። "ከ2017 እስከ 2021 (እኤአ) የኢትዮጵያ ብር የመግዛት አቅም በ54 በመቶ ወርዷል፤ በአጠቃላይ ሲታይ በአስር ዓመታት ውስጥ የኢትዮጰያ ብር የመግዛት አቅም በመቶ እጅ ወድቋል" የሚሉት ዶ/ር ጉቱ፣ የምግብ አቅርቦትና ሌሎች የዕለት ፍጆታ የሆኑ ምርቶች የብር የመግዛት አቅም በወደቀበት በዚህ ጊዜ ከውጪ ሲገቡ የኑሮ ውድነትን እንደሚያባብሱ ይናገራሉ። በኢትዮጵያ ውስጥ ምርት የሚያመርቱ አብዛኞቹ ኢንደስትሪዎች ከውጪ በሚገባው ግብዓት ላይ የተንጠለጠሉ በመሆናቸው ይህንን ችግር ለመፍታት ያላቸውን ሚና ማሳነሱንም ይገልጻሉ። በኢትዮጵያ እየታየ ያለው የኑሮ ውድነት ዘላቂ መፍትሄ ሳያገኝ ከቀጠለ አገሪቷን ውስብስብ ወደ ሆነ ችግር ሊመራት እንደሚችል ባለሙያው ይመለክታሉ። "ሰው በኢኮኖሚ ሲዳከም ከአንድ ቦታ ወደ አንድ ቦታ ይሰደዳል። እንደዚህ ዓይነት ስደት ደግሞ በከተሞች ላይ ማህበራዊ ቀውስን ያስከትላል። የሚበላው ያጣ ሕብረተሰብ ደግሞ ወደ ተቃውሞ እና ሽብር ይሄዳል። ይህ ደግሞ አሁንም ምልክቱ እየታየ ነው" ብለዋል። የሥራ ማጣት፣ የኑሮ ውድነት እና ሌሎች ምክንያቶች ችግሮች፣ መጀመሪያውኑ አሁን ካለንበት አዙሪት ውስጥ እንዳንወጣ ያደርጉናል የሚል ስጋት እንዳላቸው ጨምረው ይናገራሉ። የኑሮ ውድነትን ጨምሮ ለበርካታ የአገሪቱ ችግሮች መነሻ የሆነው ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት የመጀመሪያው ምርጫ መሆን እንዳለበት ዶ/ር ጉቱ ያመለክታሉ። "ሰላም ከሌለ ኢንቨስትመንት የለም፣ ወደ ውጪ መላክ የለም፣ ምርትን አጓጉዞ ማከፋፈል የለም። ሰላም ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ መኖር ያለበት ጉዳይ ነው። ለዚህ ደግሞ መንግሥትና ሌሎች ድርጅቶች አብረው ሆነው መወያየት አለባቸው። ግጭት ከሁሉም ወገን መቆም አለበት" ሲሉ ይመክራሉ። የውጪ ምንዛሬ ላይ በፍጥነት ማስተካከያ መደረግ አለበት የሚሉት የምጣኔ ኃብት ባለሙያው፣ በዚህ ሁኔታ አገሪቱ ከቀጠለች አስቸጋሪ የምጣኔ ኃብት ቅርቃር ውስጥ ልትገባ እንደምትችል ገልፀዋል። ብር የመግዛት አቅሙ ከቀን ወደ ቀን መቀነሱ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ መቆም እንዳለበትም ይመክራሉ። አሁን ያለው የውጪ ምንዛሬ ከዚህም ባነሰ በ30 እጅ ወደ ኋላ መመለስ አለበት ይላሉ። አሁን የብርን ዋጋ እንዲወርድ ማድረግ በኢንቨስትመንትም ሆነ በውጪ ንግድ አንጻር ለኢትዮጵያ የሚያመጣው ፋይዳ የለውም ብለዋል። የአገሪቷን ኢኮኖሚ እንዲያገግም ለማድረግ፣ የባህልና ማህበረሰባዊ እንቅስቃሴ ማካሄድ አለበትም የሚሉት ዶ/ር ጉቱ፣ የህዝቦች የሥራ ባህልም ላይ መሻሻል መደረግ አለበት በማለት ሃሳባቸውን ያጠናቅቃሉ።
https://www.bbc.com/amharic/news-56136264
5sports
ማኔ፣ ኬሲ. . . የአምስቱ ቀዳሚ አፍሪካውያን ተጫዋቾች ዝውውር
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች የዝውውር መስኮቱ ከመዘጋቱ በፊት ወደ ሁለት ቢሊዮን ፓውንድ የሚጠጋ ገንዘብ አውጥተዋል። እንደዚህም ሆኖ ሊጉ ከኮከቦቹ አንዱ የሆነውን ሳዲዮ ማኔን አጥቷል። የዝውውር እንቅስቃሴው ከኮቪድ በፊት ወደ ነበረበት ተመልሷል። ስም ካላቸው ዝውውሮች በተጨማሪ ብዙ ክለቦች የክፍያ ክብረ ወሰናቸውን ሰባብረዋል። በዝውውር መስኮተቱ የመጨረሻ ቀን ፒየር-ኤሜሪክ ኦባሚያንግ ወደ ለንደን መመለሱን አረጋግጧል። በባርሴሎና ከነበረው የስድስት ወራት ቆይታ በኋላ ቼልሲን ተቀላቅሏል። የዝውውር መስኮቱ ተጠናቋል። ተጫዋቾች ለአዳዲስ ቡድኖቻቸው መፋለም ጀምረዋል። ዛሬ አምስቱን የአፍሪካ ትልልቅ ተጨዋቾችን ዝውውር እንመልከት። የማኔ ከሊቨርፑል ወደ ባየር መዛወሩ በሴኔጋላዊው የፊት መስመር ተጫዋች ላይ ጫና ፈጥሮ ነበር። አሁን ለለባሎንዶር ዕጩ ለሆነው ተጫዋች ነገሮች ፈር እየያዙ ይመስላል። ጀርመናዊው ጋዜጠኛ ራፋኤል ሆኒግስቴይን ለቢቢሲ እንደተናገረው ባየርን “ጥሩ ዝውውር ለማከናወን ከፍተኛ ጫና ገጥሞት ነበር።” የ30 ዓመቱ ተጫዋች ወደ ቡንደስ ሊጋው ማቅናቱ ደረጃውን ዝቅ አያደርገውም ይላል። በየካቲት ወር የአፍሪካ ዋንጫን ያነሳው ማኔ በመጀመሪያዎቹ ሰባት ጨዋታዎች አምስት ግቦችን በማስቆጠር ምላሽ ሰጧል። በመጀመሪያዎቹ 4 የቡንደስሊጋ ጨዋታዎች ተጨማሪ ጎሎችን ቢያስቆጥርም ተሰርዘውበታል። ሮበርት ሌዋንዶውስኪን እንዲተካ ስለሚጠበቅ ከፍተኛ ጫና ውስጥ ይቆያል። ፖላንዳዊው በ374 የባየር ሙኒክ ጨዋታዎች 344 ጎሎችን አስመዝግቧል። የሴኔጋል አምበል ካሊዱ ኩሊባሊ ከብዙዎቹ የአውሮፓ ታላላቅ ክለቦች ጋር ስሙ ሲያያዝ ቆይቷል። በማንቸስተር ዩናይትድ በጥብቅ ሲፈለግ የነበረው ተከላካዩ በመጨረሻም ማረፊያው ቼልሲ ሆኗል። በለንደኑ ክለብ የአራት ዓመት ውል ፈርሟል። ቼልሲ ከቶተንሃም ጋር 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ሲለያይ የ31 ዓመቱ ተጫዋች በሜዳቸው ባደረገው የመጀመሪያ ጨዋታ ጎል አስቆጥሯል። ከናፖሊ የመጣው ተጫዋች በሊድስ 3 ለ 0 ሲሸነፉ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል። አንጋፋው ቲያጎ ሲልቫ፣ አዲስ ፈራሚዎቹ ዌስሊ ፎፋና እና ማርክ ኩኩሬላ ጋር እንዴት ተጣጥሞ ውጤታማ እንደሚሆን በጉጉት ይጠበቃል። ከሁለት ዓመት በፊት ባሲ በሌስተር ሲቲ ተጠባባቂ ቡድን ውስጥ ነበር። አሁን አያክስን ከተቀላቀለ በኋላ በቻምፒየንስ ሊግ የመጀመሪያ ጨዋታው ለማከናወን እየተዘጋጀ ነው። የ22 ዓመቱ ናይጄሪያዊ ያለፈው የውድድር ዓመት የዩሮፓ ሊግ ጉዞ ድንቅ ነበር። ከሬንጀርስ ጋር አስከ ፍጻሜው መጓዝ ችሏል። ዋንጫውን በኢንትራክት ፍራንክፈረት መነጠቃቸው ይታወሳል። ተከላካዩ የኔዘርላንድን ሕይወቱን በአሳዛኝ መልኩ ጀምሯል። በሱፐር ካፕ በፒኤስቪ አይንድሆቨን 5 ለ 2 ተሸንፈው ዋንጫውን አጥተዋል። ቡድኑ ከዚያን በኋላ ያደረጋቸውን ሦስት የኤርዲቪዜ ጨዋታዎች በሙሉ አሸንፏል። ያለፈው የውድድር ዘመን ባሲ ምን ማድረግ እንደሚችል ያሳየ ነው። አያክስ ትልልቅ ክለቦች የሚመኟቸውን ተጫዋቾች ለማብቃት እና ለማሻሻል ጥሩ ቦታ ነው። ኬሴ ከኤሲ ሚላን ወደ ባርሴሎና በነጻ ነው የተዘዋወረው። ይህም በአይቮሪ ኮስታዊው ተጫዋች በሜዳም ሆነ ከሜዳ ውጪ ፈተና ፈጥሮበታል። ምክንያት ከተባለ ደግሞ የስፔኑ ኃያላን ቡድኖች የገንዘብ ችግር ነው። የ25 ዓመቱን ተጫዋች ቡድኑ ማስፈረሙን ለማረጋገጥ የውድድር ዘመኑ ማስጀመሪያ ዋዜማን መጠበቅ ከነበረባቸው የባርሳ ፈራሚዎች አንዱ ነበር። የመጫወት ፈቃድ ያገኘበትን ወረቀት ያገኘው ከራዮ ቫልካኖ ጨዋታ ትንሽ ቀደም ብሎ ነው። በተቀያሪ ወንበር ላይ የጀመረው አማካዩ ከጋቪ፣ ፔድሪ ወይም ሰርጂዮ ቡስኬትስ አንዱን ለማስቀመጥ ይፎካከራል። ባለፉት አራት ጨዋታዎችም ተቀያሪ ወንበር ላይ ለመቀመጥ ተገዷል። የመሐል አማካዩ የጨዋታ ዘመኑን በአታላንታ ጀመረ። እአአ በ2019 ሳን ሲሮ ያቆየውን ቋሚ ዝውውር ከማጠናቀቁ በፊት በሚላን ሁለት የውሰት ዓመታትን አሳልፏል። ከሮሶነሪዎች ጋር ባለፈው የውድድር ዓመት የሴሪአውን ዋንጫ እንዲያነሳ አስችሎታል። የቼልሲ በዝውውር መስኮቱ የመጨረሻ ቀን ፊቱን ወደ ፒየር-ኤምሪክ ኦባሚያንግ ማዞሩ ለሁሉም አካላት ጥሩ ይመስላል። ግን ጋቦናዊው አጥቂ በቦርሺያ ዶርትሙንድ ለቶማስ ቱሄል የተሳካለትን ያህል ተፅዕኖ ሊኖረው ይችላል? ቱሄል የዶርትሙንድ አሰልጣኝ እያሉ ነበር የፊት አጥቂውን ወደ መሐል አጥቂነት የቀየሩት። ውጤቱ እአአ በ2018 ኦባሚያንግ በ56 ሚሊየን ፓውንድ ወደ መድፈኞቹ እንዲዛወር እገዛ አድርጓል። የ33 ዓመቱ ተጫዋች በነበረው አለመግባባት በጥር ወር ከሰሜን ለንደኑ ቡድን ለቅቆ ወደ ካታላኑ ክለብ አመራ። ለባርሴሎና በ24 ጨዋታዎች 13 ጎሎችን አስቆጠረ። በኋላም በ10.3 ሚሊየን ፓውንድ ወደ ቼልሲ ተዛወረ። የኦባሚያንግ የፕሪሚየር ሊግ ልምድ ስላለው የተከፈለው ዋጋ ጥሩ ነው። ዋናው ጥያቄ ግን ሮሜሉ ሉካኩ እና ቲሞ ወርነር የወደቁበትን ስፍራ እሱ ይሳካት ይሆን የሚለው ነው።
ማኔ፣ ኬሲ. . . የአምስቱ ቀዳሚ አፍሪካውያን ተጫዋቾች ዝውውር የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች የዝውውር መስኮቱ ከመዘጋቱ በፊት ወደ ሁለት ቢሊዮን ፓውንድ የሚጠጋ ገንዘብ አውጥተዋል። እንደዚህም ሆኖ ሊጉ ከኮከቦቹ አንዱ የሆነውን ሳዲዮ ማኔን አጥቷል። የዝውውር እንቅስቃሴው ከኮቪድ በፊት ወደ ነበረበት ተመልሷል። ስም ካላቸው ዝውውሮች በተጨማሪ ብዙ ክለቦች የክፍያ ክብረ ወሰናቸውን ሰባብረዋል። በዝውውር መስኮተቱ የመጨረሻ ቀን ፒየር-ኤሜሪክ ኦባሚያንግ ወደ ለንደን መመለሱን አረጋግጧል። በባርሴሎና ከነበረው የስድስት ወራት ቆይታ በኋላ ቼልሲን ተቀላቅሏል። የዝውውር መስኮቱ ተጠናቋል። ተጫዋቾች ለአዳዲስ ቡድኖቻቸው መፋለም ጀምረዋል። ዛሬ አምስቱን የአፍሪካ ትልልቅ ተጨዋቾችን ዝውውር እንመልከት። የማኔ ከሊቨርፑል ወደ ባየር መዛወሩ በሴኔጋላዊው የፊት መስመር ተጫዋች ላይ ጫና ፈጥሮ ነበር። አሁን ለለባሎንዶር ዕጩ ለሆነው ተጫዋች ነገሮች ፈር እየያዙ ይመስላል። ጀርመናዊው ጋዜጠኛ ራፋኤል ሆኒግስቴይን ለቢቢሲ እንደተናገረው ባየርን “ጥሩ ዝውውር ለማከናወን ከፍተኛ ጫና ገጥሞት ነበር።” የ30 ዓመቱ ተጫዋች ወደ ቡንደስ ሊጋው ማቅናቱ ደረጃውን ዝቅ አያደርገውም ይላል። በየካቲት ወር የአፍሪካ ዋንጫን ያነሳው ማኔ በመጀመሪያዎቹ ሰባት ጨዋታዎች አምስት ግቦችን በማስቆጠር ምላሽ ሰጧል። በመጀመሪያዎቹ 4 የቡንደስሊጋ ጨዋታዎች ተጨማሪ ጎሎችን ቢያስቆጥርም ተሰርዘውበታል። ሮበርት ሌዋንዶውስኪን እንዲተካ ስለሚጠበቅ ከፍተኛ ጫና ውስጥ ይቆያል። ፖላንዳዊው በ374 የባየር ሙኒክ ጨዋታዎች 344 ጎሎችን አስመዝግቧል። የሴኔጋል አምበል ካሊዱ ኩሊባሊ ከብዙዎቹ የአውሮፓ ታላላቅ ክለቦች ጋር ስሙ ሲያያዝ ቆይቷል። በማንቸስተር ዩናይትድ በጥብቅ ሲፈለግ የነበረው ተከላካዩ በመጨረሻም ማረፊያው ቼልሲ ሆኗል። በለንደኑ ክለብ የአራት ዓመት ውል ፈርሟል። ቼልሲ ከቶተንሃም ጋር 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ሲለያይ የ31 ዓመቱ ተጫዋች በሜዳቸው ባደረገው የመጀመሪያ ጨዋታ ጎል አስቆጥሯል። ከናፖሊ የመጣው ተጫዋች በሊድስ 3 ለ 0 ሲሸነፉ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል። አንጋፋው ቲያጎ ሲልቫ፣ አዲስ ፈራሚዎቹ ዌስሊ ፎፋና እና ማርክ ኩኩሬላ ጋር እንዴት ተጣጥሞ ውጤታማ እንደሚሆን በጉጉት ይጠበቃል። ከሁለት ዓመት በፊት ባሲ በሌስተር ሲቲ ተጠባባቂ ቡድን ውስጥ ነበር። አሁን አያክስን ከተቀላቀለ በኋላ በቻምፒየንስ ሊግ የመጀመሪያ ጨዋታው ለማከናወን እየተዘጋጀ ነው። የ22 ዓመቱ ናይጄሪያዊ ያለፈው የውድድር ዓመት የዩሮፓ ሊግ ጉዞ ድንቅ ነበር። ከሬንጀርስ ጋር አስከ ፍጻሜው መጓዝ ችሏል። ዋንጫውን በኢንትራክት ፍራንክፈረት መነጠቃቸው ይታወሳል። ተከላካዩ የኔዘርላንድን ሕይወቱን በአሳዛኝ መልኩ ጀምሯል። በሱፐር ካፕ በፒኤስቪ አይንድሆቨን 5 ለ 2 ተሸንፈው ዋንጫውን አጥተዋል። ቡድኑ ከዚያን በኋላ ያደረጋቸውን ሦስት የኤርዲቪዜ ጨዋታዎች በሙሉ አሸንፏል። ያለፈው የውድድር ዘመን ባሲ ምን ማድረግ እንደሚችል ያሳየ ነው። አያክስ ትልልቅ ክለቦች የሚመኟቸውን ተጫዋቾች ለማብቃት እና ለማሻሻል ጥሩ ቦታ ነው። ኬሴ ከኤሲ ሚላን ወደ ባርሴሎና በነጻ ነው የተዘዋወረው። ይህም በአይቮሪ ኮስታዊው ተጫዋች በሜዳም ሆነ ከሜዳ ውጪ ፈተና ፈጥሮበታል። ምክንያት ከተባለ ደግሞ የስፔኑ ኃያላን ቡድኖች የገንዘብ ችግር ነው። የ25 ዓመቱን ተጫዋች ቡድኑ ማስፈረሙን ለማረጋገጥ የውድድር ዘመኑ ማስጀመሪያ ዋዜማን መጠበቅ ከነበረባቸው የባርሳ ፈራሚዎች አንዱ ነበር። የመጫወት ፈቃድ ያገኘበትን ወረቀት ያገኘው ከራዮ ቫልካኖ ጨዋታ ትንሽ ቀደም ብሎ ነው። በተቀያሪ ወንበር ላይ የጀመረው አማካዩ ከጋቪ፣ ፔድሪ ወይም ሰርጂዮ ቡስኬትስ አንዱን ለማስቀመጥ ይፎካከራል። ባለፉት አራት ጨዋታዎችም ተቀያሪ ወንበር ላይ ለመቀመጥ ተገዷል። የመሐል አማካዩ የጨዋታ ዘመኑን በአታላንታ ጀመረ። እአአ በ2019 ሳን ሲሮ ያቆየውን ቋሚ ዝውውር ከማጠናቀቁ በፊት በሚላን ሁለት የውሰት ዓመታትን አሳልፏል። ከሮሶነሪዎች ጋር ባለፈው የውድድር ዓመት የሴሪአውን ዋንጫ እንዲያነሳ አስችሎታል። የቼልሲ በዝውውር መስኮቱ የመጨረሻ ቀን ፊቱን ወደ ፒየር-ኤምሪክ ኦባሚያንግ ማዞሩ ለሁሉም አካላት ጥሩ ይመስላል። ግን ጋቦናዊው አጥቂ በቦርሺያ ዶርትሙንድ ለቶማስ ቱሄል የተሳካለትን ያህል ተፅዕኖ ሊኖረው ይችላል? ቱሄል የዶርትሙንድ አሰልጣኝ እያሉ ነበር የፊት አጥቂውን ወደ መሐል አጥቂነት የቀየሩት። ውጤቱ እአአ በ2018 ኦባሚያንግ በ56 ሚሊየን ፓውንድ ወደ መድፈኞቹ እንዲዛወር እገዛ አድርጓል። የ33 ዓመቱ ተጫዋች በነበረው አለመግባባት በጥር ወር ከሰሜን ለንደኑ ቡድን ለቅቆ ወደ ካታላኑ ክለብ አመራ። ለባርሴሎና በ24 ጨዋታዎች 13 ጎሎችን አስቆጠረ። በኋላም በ10.3 ሚሊየን ፓውንድ ወደ ቼልሲ ተዛወረ። የኦባሚያንግ የፕሪሚየር ሊግ ልምድ ስላለው የተከፈለው ዋጋ ጥሩ ነው። ዋናው ጥያቄ ግን ሮሜሉ ሉካኩ እና ቲሞ ወርነር የወደቁበትን ስፍራ እሱ ይሳካት ይሆን የሚለው ነው።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cg3187dvd0wo
5sports
እውቁ የአውሮፓን እግር ኳስ የሚዘውረው ቱጃር 'ደላላ' በሞት ተለየ
"ሚኖ" በሚለው በመጀመሪያ ስሙ የሚጠራው እውቁ የእግር ኳስ ተጫዋቾች ወኪል ሚኖ ራዮላ በ54 ዓመቱ ሕይወቱ አልፏል። የሆላንድ እና ጣሊንያን ጥምር ዜግነት ያለው ሚኖ፤ እንደ የዶርትመንዱ የፊት መስመር ተጫዋች ሃላንድ፣ የማንችስተር ዩናይትዱ ፖል ፖግባ፣ ዝላታን ኢብራሂሞቪች፣ ሄንሪክ ሚኪታሪያንና ዴ ሊት የመሳሰሉ ተጨዋቾች ወኪል ነበር። ከዚህ በተጨማሪም ሚኖ እውቅ የተጫዋቾች ወኪሎችን የሚወክለው 'ፉትቦል ፎረም' ፕሬዝደንት ነበር። ሕልፈተ ሕይወቱን ተከትሎ፤ 'ሚኖ ሁሌም ይናፈቃል' ሲሉ የሚኖ ቤተሰብ መግለጫ አውጥተዋል። ሚኖ ማን ነበር? ጣልያን ተወልዶ በኔዘርላንድስ ሃርለም ከተማ እንዳደገ የሚነገርለት ራዮላ ሁሉም የሚስማሙለት 'ምርጥ ደላላ' ነው። በልጅነቱ አባቱ በከፈቱት ሬስቶራንት ውስጥ ደፋ ቀና ብሎ አስተናግዷል። በጎንዮሽ ደግሞ ዩኒቨርሲቲ በመግባት በሕግ ተመርቋል። ጣልያንኛ፣ ጀርመንኛ፣ ስፓኒሽ፣ ፈረንሳይኛ፣ ፓርቹጊዝ፣ ደች እና እንግሊዝኛ ቋንቋዎችን አቀላጥፎ የሚናገረው ራዮላ ገና የ18 ዓመት ለጋ ሳለ ነበር ኔዝርላንድስ ውስጥ የሚገኝ አንድ የታዳጊዎች እግር ኳስ ኃላፊ ሆኖ ራሱን ያገኘው። ከዚያም የነብስ ጥሪው ወደሆነው የወኪልነት ሥራ ገባ፤ ለአንድ ወኪል ድርጅት ተቀጥሮ ይሠራም ጀመር። የመጀመሪያው ሥራ የሆነው ደግሞ ተስፋ የሚጣልባቸውን ታዳጊ ደች ተጫዋቾችን ለጣልያኑ ሴሪ ኤ ማሻሻጥ። በታዳጊነታቸው በራዮላ ደላይነት ወደ ጣልያን ብሎም ወደ እንግሊዝ ገብተው ስማቸውን በጉልህ መፃፍ ከቻሉ ተጫዋቾች መካከል ዴኒስ ቤርግካምፕ የሚጠቀስ ነው። ምንም ቢሆን የራሥ የራሥ ነው ያለው ራዮላ ተቀጥሮ ይሠራበት የነበረበትን ድርጅት ለቆ የራሱን የውክልና ድርጅት ሊያቋቁም ቻለ። አሁን ላይ አውሮፓ ውስጥ ከሚጫወቱ እግር ኳሰኞች ስም ያላቸው በርካታ ተጨዋቾች ውክልናቸውን ለሚኖ ሰጥተው ነበር። እንደ አውሮፓዊያኑ 2016 ላይ ራዮላ 'ታሪክ ሠራ'። ያኔ የዓለም ሬከርድ በነበረ ዋጋ ፖል ፖግባን ከዩቬንቱስ ወደ ማንችስተር ዩናይትድ እንዲዛወር አደረገ፤ ዋጋው ደግሞ 105 ሚሊዮን ዩሮ። ጉደኛው ራዮላ ከዚህ ዝውውር 25 ሚሊዮን ዩሮ ገደማ ወደ ኪሱ እንዳስገባ ይነገራል። ከዚያ በኋላ ወደ አሜሪካዋ የባህር ዳርቻ ግዛት ማያሚ አቅንቶ 9 ሚሊዮን ዩሮ ማፍሰስ ቤተ-መንግሥት የሚያስንቅ መኖሪያ 'መንደር' ሸመተ። ሚኖ ከፈጸማቸው ውድ የተጫዋቾች ዝውውሮች መካከል ፎርብስ እአአ 2018 ላይ ባወጣው ዘገባ ሚኖ 69 ሚሊዮን ዶላር የተጣራ ገቢ ያለው ሲሆን በእርሱ ውክልና ሥራ ያሉ 70 ተጫዋቾች 629 ሚሊዮን ዶላር ሊያወጡ ይችላሉ ሲል አትቷል። ሰውየው ያሻውን ከመናገር ወደኋላ የሚልም አይደለም። በአትንኩኝ ባይነቱ የሚታወቀው ራዮላ በእርሱ ውክልና ሥር ያሉ ተጨዋቾችን የሚተቹ የቀድሞ እግር ኳሰኞችም ሆነ ተንታኞችን በመወረፍ ይታወቃል።
እውቁ የአውሮፓን እግር ኳስ የሚዘውረው ቱጃር 'ደላላ' በሞት ተለየ "ሚኖ" በሚለው በመጀመሪያ ስሙ የሚጠራው እውቁ የእግር ኳስ ተጫዋቾች ወኪል ሚኖ ራዮላ በ54 ዓመቱ ሕይወቱ አልፏል። የሆላንድ እና ጣሊንያን ጥምር ዜግነት ያለው ሚኖ፤ እንደ የዶርትመንዱ የፊት መስመር ተጫዋች ሃላንድ፣ የማንችስተር ዩናይትዱ ፖል ፖግባ፣ ዝላታን ኢብራሂሞቪች፣ ሄንሪክ ሚኪታሪያንና ዴ ሊት የመሳሰሉ ተጨዋቾች ወኪል ነበር። ከዚህ በተጨማሪም ሚኖ እውቅ የተጫዋቾች ወኪሎችን የሚወክለው 'ፉትቦል ፎረም' ፕሬዝደንት ነበር። ሕልፈተ ሕይወቱን ተከትሎ፤ 'ሚኖ ሁሌም ይናፈቃል' ሲሉ የሚኖ ቤተሰብ መግለጫ አውጥተዋል። ሚኖ ማን ነበር? ጣልያን ተወልዶ በኔዘርላንድስ ሃርለም ከተማ እንዳደገ የሚነገርለት ራዮላ ሁሉም የሚስማሙለት 'ምርጥ ደላላ' ነው። በልጅነቱ አባቱ በከፈቱት ሬስቶራንት ውስጥ ደፋ ቀና ብሎ አስተናግዷል። በጎንዮሽ ደግሞ ዩኒቨርሲቲ በመግባት በሕግ ተመርቋል። ጣልያንኛ፣ ጀርመንኛ፣ ስፓኒሽ፣ ፈረንሳይኛ፣ ፓርቹጊዝ፣ ደች እና እንግሊዝኛ ቋንቋዎችን አቀላጥፎ የሚናገረው ራዮላ ገና የ18 ዓመት ለጋ ሳለ ነበር ኔዝርላንድስ ውስጥ የሚገኝ አንድ የታዳጊዎች እግር ኳስ ኃላፊ ሆኖ ራሱን ያገኘው። ከዚያም የነብስ ጥሪው ወደሆነው የወኪልነት ሥራ ገባ፤ ለአንድ ወኪል ድርጅት ተቀጥሮ ይሠራም ጀመር። የመጀመሪያው ሥራ የሆነው ደግሞ ተስፋ የሚጣልባቸውን ታዳጊ ደች ተጫዋቾችን ለጣልያኑ ሴሪ ኤ ማሻሻጥ። በታዳጊነታቸው በራዮላ ደላይነት ወደ ጣልያን ብሎም ወደ እንግሊዝ ገብተው ስማቸውን በጉልህ መፃፍ ከቻሉ ተጫዋቾች መካከል ዴኒስ ቤርግካምፕ የሚጠቀስ ነው። ምንም ቢሆን የራሥ የራሥ ነው ያለው ራዮላ ተቀጥሮ ይሠራበት የነበረበትን ድርጅት ለቆ የራሱን የውክልና ድርጅት ሊያቋቁም ቻለ። አሁን ላይ አውሮፓ ውስጥ ከሚጫወቱ እግር ኳሰኞች ስም ያላቸው በርካታ ተጨዋቾች ውክልናቸውን ለሚኖ ሰጥተው ነበር። እንደ አውሮፓዊያኑ 2016 ላይ ራዮላ 'ታሪክ ሠራ'። ያኔ የዓለም ሬከርድ በነበረ ዋጋ ፖል ፖግባን ከዩቬንቱስ ወደ ማንችስተር ዩናይትድ እንዲዛወር አደረገ፤ ዋጋው ደግሞ 105 ሚሊዮን ዩሮ። ጉደኛው ራዮላ ከዚህ ዝውውር 25 ሚሊዮን ዩሮ ገደማ ወደ ኪሱ እንዳስገባ ይነገራል። ከዚያ በኋላ ወደ አሜሪካዋ የባህር ዳርቻ ግዛት ማያሚ አቅንቶ 9 ሚሊዮን ዩሮ ማፍሰስ ቤተ-መንግሥት የሚያስንቅ መኖሪያ 'መንደር' ሸመተ። ሚኖ ከፈጸማቸው ውድ የተጫዋቾች ዝውውሮች መካከል ፎርብስ እአአ 2018 ላይ ባወጣው ዘገባ ሚኖ 69 ሚሊዮን ዶላር የተጣራ ገቢ ያለው ሲሆን በእርሱ ውክልና ሥራ ያሉ 70 ተጫዋቾች 629 ሚሊዮን ዶላር ሊያወጡ ይችላሉ ሲል አትቷል። ሰውየው ያሻውን ከመናገር ወደኋላ የሚልም አይደለም። በአትንኩኝ ባይነቱ የሚታወቀው ራዮላ በእርሱ ውክልና ሥር ያሉ ተጨዋቾችን የሚተቹ የቀድሞ እግር ኳሰኞችም ሆነ ተንታኞችን በመወረፍ ይታወቃል።
https://www.bbc.com/amharic/news-61283418
3politics
የኡጋንዳ ምርጫ 2021፡በኡጋንዳ ምርጫ ፕሬዚዳንት ሙሴቪኒ እየመሩ ነው ተባለ
ምሥራቅ አፍሪካዊቷ አገር ኡጋንዳ ሐሙስ ጥር 6/2013 ዓ.ም ብሔራዊ ምርጫ አካሂዳለች። በዚህ ምርጫ አገሪቷን ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ የመሯት ፕሬዚዳንት ሙሴቬኒና ሙዚቀኛና ፖለቲከኛው ቦቢ ዋይን ዋነኛ ተፎካካሪ ሆነዋል። በምርጫ ቅስቀሳውም ወቅት ከፍተኛ ሁከትን ባስተናገደችው ኡጋንዳ ከ50 ሰዎች በላይ ህይወታቸውን አጥተዋል። በምርጫው ሰሞንም ማህበራዊ ሚዲያዎችን ያገደች ሲሆን ከዋዜማውም ጀምሮ ኢንተርኔት ተቋርጧል። የምርጫ ውጤቱ በነገው ዕለት፣ ቅዳሜ የሚገለፅ ይሆናል። በትናንትናው ዕለት በኡጋንዳ በተደረገው ምርጫ ዩዌሪ ሙሴቪኒ የመሪነት ቦታውን ጨብጠዋል ተባለ። በዛሬው ዕለት የምርጫ ኮሚሽኑ የመጀመሪያ ደረጃ ውጤቱ ይፋ ባደረገበትም ዕለት እስካሁን ባለው ቆጠራ የመጪውን ፕሬዚዳንትነት ቦታ ሙሴቪኒ እየመሩ መሆኑን አሳውቋል። ፕሬዚዳንት ሙሴቪኒ 1 ሚሊዮን 536 ሺህ 205 ድምፅ (65.02 በመቶ) በማግኘት እየመሩ ሲሆን፣ ዋነኛ ተቃናቃኙ ሮበርት ክያጉላንያ በመድረክ ስሙ ቦቢ ዋይን በበኩሉ 647 ሺህ 146 ድምፅ (27.39) በማግኘት እየተከተለ መሆኑንም የምርጫ ኮሚሽኑ መረጃ ያሳያል። ውጤቱ የተሰበሰበው ከ8 ሺህ 310 የምርጫ ጣቢያዎች ነው። በአጠቃላይ በአገሪቱ 34 ሺህ 684 የምርጫ ጣቢያዎች አሉ። ቦቢ ዋይን በበኩሉ ትናንትና በተደረገው ምርጫ ከፍተኛ ማጭበርበርና በግጭቶች የተሞላ ነው ቢልም ውንጀላውን አስመልክቶ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል። የኡጋንዳ መንግሥት በበኩሉ ምርጫው ሰላማዊ ነበር ብሏል። በትናንትናው ዕለት ብሔራዊ ምርጫዋን ባካሄደችው ኡጋንዳ ኢንተርኔት ሙሉ በሙሉ ቢዘጋም የምርጫ ውጤቶቹ ወደ ዋናው ማዕከል እየተላኩ እንደሆነ የአገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን አስታውቋል። የኮሚሽኑ ኃላፊ ሲሞን ብያባካማ የምርጫውን ውጤትም ለማስተላለፍ ሌሎች ውስጣዊ መንገዶችን እየተጠቀሙ እንደሆነ ቢናገሩም ዝርዝር ከመስጠት ተቆጥበዋል፥ "የምርጫውን ውጤት ለመላክ ኢንተርኔት እየተጠቀምን አይደለም። የራሳችንን ስርአት እየተጠቀም ነው። አትጨነቁ፣ ኢንተርኔቱ ቢቋረጥም ውጤቱ መድረሱ አይቀርም፤ ይፋም ይሆናል" በማለት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። ዛሬ ጥዋትም ኮሚሽኑ ከ330 የምርጫ ጣቢያዎች ድምፅ ሰበሰብኩት ባለው መረጃ መስረት የመጀመሪያ ደረጃ ውጤት ያሳወቀ ሲሆን በዚህም መሰረት አገሪቷን ከሶስት አስርት አመታት በላይ የመሯት ዩዌሪ ሙሴቪኒ እየመሩ ነው ማለቱንም ደይሊ ሞኒተር ጋዜጣ አስነብቧል። አገሪቷ በአጠቃላይ 34 ሺህ 684 የምርጫ ጣቢያዎች አሏት። በኡጋንዳ ህግ መስረት ምርጫው በተካሄደ በ48 ሰዓታት ውስጥ የምርጫው ኮሚሽን ከሁሉም ግዛቶች ድምፆችን ሰብስቦ ውጤቱን ማሳወቅ አለበት። የፓርላማ መቀመጫ ያሸነፉ አባላት በተለያዩ ግዛቶች በሚገኙ ማዕከላት ዝርዝራቸው የሚገለፅ ሲሆን በሌላ በኩል የፕሬዚዳንትነቱ አሸናፊ በመዲናዋ ካምፓላ በሚገኘው ማዕከል ይፋ ይሆናል። ሮበርት ክያጉላንይ ወይም በመድረክ ስሙ ቦቢ ዋይን ተብሎ የሚታወቀው ሙዚቀኛና ፖለቲከኛ የፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ዋነኛ ተቀናቃኝም ሆኖ ወጥቷል። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ባለስልጣናቱ የትኛውንም ማህበራዊ ሚዲያዎች እንዲሁም ቪፒኤኖችም እንዲዘጉ ትዕዛዝ ሰጥተዋል።
የኡጋንዳ ምርጫ 2021፡በኡጋንዳ ምርጫ ፕሬዚዳንት ሙሴቪኒ እየመሩ ነው ተባለ ምሥራቅ አፍሪካዊቷ አገር ኡጋንዳ ሐሙስ ጥር 6/2013 ዓ.ም ብሔራዊ ምርጫ አካሂዳለች። በዚህ ምርጫ አገሪቷን ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ የመሯት ፕሬዚዳንት ሙሴቬኒና ሙዚቀኛና ፖለቲከኛው ቦቢ ዋይን ዋነኛ ተፎካካሪ ሆነዋል። በምርጫ ቅስቀሳውም ወቅት ከፍተኛ ሁከትን ባስተናገደችው ኡጋንዳ ከ50 ሰዎች በላይ ህይወታቸውን አጥተዋል። በምርጫው ሰሞንም ማህበራዊ ሚዲያዎችን ያገደች ሲሆን ከዋዜማውም ጀምሮ ኢንተርኔት ተቋርጧል። የምርጫ ውጤቱ በነገው ዕለት፣ ቅዳሜ የሚገለፅ ይሆናል። በትናንትናው ዕለት በኡጋንዳ በተደረገው ምርጫ ዩዌሪ ሙሴቪኒ የመሪነት ቦታውን ጨብጠዋል ተባለ። በዛሬው ዕለት የምርጫ ኮሚሽኑ የመጀመሪያ ደረጃ ውጤቱ ይፋ ባደረገበትም ዕለት እስካሁን ባለው ቆጠራ የመጪውን ፕሬዚዳንትነት ቦታ ሙሴቪኒ እየመሩ መሆኑን አሳውቋል። ፕሬዚዳንት ሙሴቪኒ 1 ሚሊዮን 536 ሺህ 205 ድምፅ (65.02 በመቶ) በማግኘት እየመሩ ሲሆን፣ ዋነኛ ተቃናቃኙ ሮበርት ክያጉላንያ በመድረክ ስሙ ቦቢ ዋይን በበኩሉ 647 ሺህ 146 ድምፅ (27.39) በማግኘት እየተከተለ መሆኑንም የምርጫ ኮሚሽኑ መረጃ ያሳያል። ውጤቱ የተሰበሰበው ከ8 ሺህ 310 የምርጫ ጣቢያዎች ነው። በአጠቃላይ በአገሪቱ 34 ሺህ 684 የምርጫ ጣቢያዎች አሉ። ቦቢ ዋይን በበኩሉ ትናንትና በተደረገው ምርጫ ከፍተኛ ማጭበርበርና በግጭቶች የተሞላ ነው ቢልም ውንጀላውን አስመልክቶ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል። የኡጋንዳ መንግሥት በበኩሉ ምርጫው ሰላማዊ ነበር ብሏል። በትናንትናው ዕለት ብሔራዊ ምርጫዋን ባካሄደችው ኡጋንዳ ኢንተርኔት ሙሉ በሙሉ ቢዘጋም የምርጫ ውጤቶቹ ወደ ዋናው ማዕከል እየተላኩ እንደሆነ የአገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን አስታውቋል። የኮሚሽኑ ኃላፊ ሲሞን ብያባካማ የምርጫውን ውጤትም ለማስተላለፍ ሌሎች ውስጣዊ መንገዶችን እየተጠቀሙ እንደሆነ ቢናገሩም ዝርዝር ከመስጠት ተቆጥበዋል፥ "የምርጫውን ውጤት ለመላክ ኢንተርኔት እየተጠቀምን አይደለም። የራሳችንን ስርአት እየተጠቀም ነው። አትጨነቁ፣ ኢንተርኔቱ ቢቋረጥም ውጤቱ መድረሱ አይቀርም፤ ይፋም ይሆናል" በማለት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። ዛሬ ጥዋትም ኮሚሽኑ ከ330 የምርጫ ጣቢያዎች ድምፅ ሰበሰብኩት ባለው መረጃ መስረት የመጀመሪያ ደረጃ ውጤት ያሳወቀ ሲሆን በዚህም መሰረት አገሪቷን ከሶስት አስርት አመታት በላይ የመሯት ዩዌሪ ሙሴቪኒ እየመሩ ነው ማለቱንም ደይሊ ሞኒተር ጋዜጣ አስነብቧል። አገሪቷ በአጠቃላይ 34 ሺህ 684 የምርጫ ጣቢያዎች አሏት። በኡጋንዳ ህግ መስረት ምርጫው በተካሄደ በ48 ሰዓታት ውስጥ የምርጫው ኮሚሽን ከሁሉም ግዛቶች ድምፆችን ሰብስቦ ውጤቱን ማሳወቅ አለበት። የፓርላማ መቀመጫ ያሸነፉ አባላት በተለያዩ ግዛቶች በሚገኙ ማዕከላት ዝርዝራቸው የሚገለፅ ሲሆን በሌላ በኩል የፕሬዚዳንትነቱ አሸናፊ በመዲናዋ ካምፓላ በሚገኘው ማዕከል ይፋ ይሆናል። ሮበርት ክያጉላንይ ወይም በመድረክ ስሙ ቦቢ ዋይን ተብሎ የሚታወቀው ሙዚቀኛና ፖለቲከኛ የፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ዋነኛ ተቀናቃኝም ሆኖ ወጥቷል። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ባለስልጣናቱ የትኛውንም ማህበራዊ ሚዲያዎች እንዲሁም ቪፒኤኖችም እንዲዘጉ ትዕዛዝ ሰጥተዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-55672696
2health
የአፍሪካ አገራት ግዜው ያለፈበት የኮቪድ ክትባትን እንዳያስወግዱ ተጠየቁ
የዓለም ጤና ድርጅት የመጠቀሚያ ግዜያቸው ያለፈ የኮሮናቫይረስ ክትባት በእጃቸው የሚገኝ የአፍሪካ አገራት ክትባቱን ከማስወገድ እንዲቆጠቡ አሳሰበ። አገራቱ ቀጣይ መመሪያዎች እስኪሰጡ ድረስ የመጠቀሚያ ግዜያቸው ያለፈባቸውን ክትባቶችን ይዘው እንዲያቆዩ ተጠይቀዋል። ማላዊ እና ደቡብ ሱዳን በሚያዚያ ወር አጋመሽ ላይ 70 ሺህ የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው ክትባቶችን ለማስወገድ ማሰባቸውን ይፋ ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው የዓለም የጤና ድርጅት ይህን ማሳሰቢያ የሰጠው። ማላዊ 16 ሺህ የአስትራ ዜኔካ ብልቃጦችን፤ ደቡብ ሱዳን ደግሞ 59 ሺህ ተመሳሳይ ብልቃጦችን ለማስወገድ አስበዋል። የአፍሪካ የበሽታዎች መቆጣጠሪያ (ሲዲሲ) ግን ምንም እንኳን ክትባቶቹን ለመጠቀም የተቀመጠው ግዜ ቢያልፍም ክትባቶቹ ጥቅም ላይ መዋል እንደሚችሉ ገልጾ ነበር። በዓለማችን ያሉ ሌሎች ክትባቶች ከተመረቱ ጀምሮ እስከ 36 ወር ድረስ ጥቅም ላይ የሚውሉ ሲሆን የኮቪድ ክትባት ግን አዲስ መሆኑን ተከትሎ ነው ለምን ያህል ግዜ ውጤታማ ሆኖ መቆየት እንደሚችል ገና ያልተለየው። እነዚህ ግዜያቸው ያለፈባቸውን ክትባቶች ጥቅም ላይ የማዋል ውሳኔ የሚሰጠው በብሔራዊ የመድሃኒት ተቆጣጣሪዎች እንደሆነ የቢቢሲ የጤና ጉዳዮች ዘጋቢ ርሆዳ ኦዲያምቦ ታብራራለች። የአፍሪካ የበሽታዎች መቆጣጠሪያ ዋና ዳይሬክተር ማክሰኞ ዕለት በሰጡት መግለጫቸው ላይ፤ "ለአባል አገራት የማቀርበው ጥሪ ቢኖር፤ እኛ ክትባቱን አስተባብረን ለማቅረብ የራሳችንን ድርሻ እየተወጣን ነው፤ እናንተም ክትባቶቹን በመጠቀም የድርሻችሁን ተወጡ" ሲሉ ተማጽነዋል። የኮሮናቫይረስ ክትባትን በአፍሪካ በሚፈለገው ፍጥነት እስካሁን ማድረስ ያልተቻለ ሲሆን፤ ለዚህም የአቅርቦት እጥረት እንዲሁም ስለ ክትባቱ ጥርጣሬዎች መኖራቸው እንደ ምክንያት ይነሳሉ።
የአፍሪካ አገራት ግዜው ያለፈበት የኮቪድ ክትባትን እንዳያስወግዱ ተጠየቁ የዓለም ጤና ድርጅት የመጠቀሚያ ግዜያቸው ያለፈ የኮሮናቫይረስ ክትባት በእጃቸው የሚገኝ የአፍሪካ አገራት ክትባቱን ከማስወገድ እንዲቆጠቡ አሳሰበ። አገራቱ ቀጣይ መመሪያዎች እስኪሰጡ ድረስ የመጠቀሚያ ግዜያቸው ያለፈባቸውን ክትባቶችን ይዘው እንዲያቆዩ ተጠይቀዋል። ማላዊ እና ደቡብ ሱዳን በሚያዚያ ወር አጋመሽ ላይ 70 ሺህ የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው ክትባቶችን ለማስወገድ ማሰባቸውን ይፋ ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው የዓለም የጤና ድርጅት ይህን ማሳሰቢያ የሰጠው። ማላዊ 16 ሺህ የአስትራ ዜኔካ ብልቃጦችን፤ ደቡብ ሱዳን ደግሞ 59 ሺህ ተመሳሳይ ብልቃጦችን ለማስወገድ አስበዋል። የአፍሪካ የበሽታዎች መቆጣጠሪያ (ሲዲሲ) ግን ምንም እንኳን ክትባቶቹን ለመጠቀም የተቀመጠው ግዜ ቢያልፍም ክትባቶቹ ጥቅም ላይ መዋል እንደሚችሉ ገልጾ ነበር። በዓለማችን ያሉ ሌሎች ክትባቶች ከተመረቱ ጀምሮ እስከ 36 ወር ድረስ ጥቅም ላይ የሚውሉ ሲሆን የኮቪድ ክትባት ግን አዲስ መሆኑን ተከትሎ ነው ለምን ያህል ግዜ ውጤታማ ሆኖ መቆየት እንደሚችል ገና ያልተለየው። እነዚህ ግዜያቸው ያለፈባቸውን ክትባቶች ጥቅም ላይ የማዋል ውሳኔ የሚሰጠው በብሔራዊ የመድሃኒት ተቆጣጣሪዎች እንደሆነ የቢቢሲ የጤና ጉዳዮች ዘጋቢ ርሆዳ ኦዲያምቦ ታብራራለች። የአፍሪካ የበሽታዎች መቆጣጠሪያ ዋና ዳይሬክተር ማክሰኞ ዕለት በሰጡት መግለጫቸው ላይ፤ "ለአባል አገራት የማቀርበው ጥሪ ቢኖር፤ እኛ ክትባቱን አስተባብረን ለማቅረብ የራሳችንን ድርሻ እየተወጣን ነው፤ እናንተም ክትባቶቹን በመጠቀም የድርሻችሁን ተወጡ" ሲሉ ተማጽነዋል። የኮሮናቫይረስ ክትባትን በአፍሪካ በሚፈለገው ፍጥነት እስካሁን ማድረስ ያልተቻለ ሲሆን፤ ለዚህም የአቅርቦት እጥረት እንዲሁም ስለ ክትባቱ ጥርጣሬዎች መኖራቸው እንደ ምክንያት ይነሳሉ።
https://www.bbc.com/amharic/56855661
2health
በአውስትራሊያ አረጋውያን እንክብካቤ ማዕከላት በየሳምንቱ 50 ወሲባዊ ጥቃቶች ይደርሳሉ ተባለ
በአውስትራሊያ የሚገኙ የአረጋውያን እንክብካቤ ማዕከላት ውስጥ በየሳምንቱ አምሳ ያህል ወሲባዊ ጥቃቶች እንደሚደርሱ ከሰሞኑ ብሔራዊ አጣሪ ኮሚቴ ይፋ አድርጓል። ለሁለት አመታት ያህልም በአረጋውያን እንክብካቤ ማዕከላት የሚደርሱ የተለያዩ ጥቃቶችንና መንገላቶችን ይፋ ባደረገበት መረጃ ነው ሮያል ኮሚሽን ይህንንም ያካተተው። መርማሪዎቹ እንዳሉት በጎሮጎሳውያኑ 2018-2019 ጊዜ 2 ሺህ 520 አረጋውያን ወሲባዊ ጥቃት ደርሶባቸዋል። "ይህ ሁኔታ ብሔራዊ እፍረት ነው" ብለውታል የምክር ቤት አባሉ ፒተር ሮዝን ኪው ሲ ለአጣሪው ኮሚቴ "ቁጥሮቹ የሚረብሹትን ያህል እነዚህን መረጃዎች ያገኘው የመንግሥት አካል ክትትትልና ቁጥጥር አለማድረጉ የበለጠ የከፋ ነው" ብለዋል። በአረጋውያኑ የእንክብካቤ ማዕከል ላይ የሚታየው ቸልተኝነት ከፍተኛ ውዝግብና ጥያቄ ያስነሳ ሲሆን ከዚህ ቀደምም በአውስትራሊያ በኮሮናቫይረስ ከሞቱት አብዛኛዎቹ በአረጋውያን ማዕከል የሚገኙ ናቸው። አውስትራሊያ በኮሮናቫይረስ ሞተዋል ብላ ከመዘገበችው 903 ሰዎች መካከል 75 በመቶ በነዚህ ማዕከላት የሚገኙ ናቸው። በእነዚህ ማዕከላት ላይ የሚደርሱ ወሲባዊ ጥቃቶች የቀደመ ስጋት ሆነው የቆዩ መሆናቸውን ያመኑት ፒተር ሮዝን ቁጥሩም በአገሪቱ ያሉትን 13-18 በመቶ ጥቃት እንደደረሰባቸው ያሳያል። በርካቶች በዕድሜያቸው የበለፀጉ ወይም ተጋላጭ የሆኑ ቤተሰቦቻቸውን በአረጋውያኑ ማዕከል የሚያስገቡት ደህንነታቸው ይጠበቃል በሚል ዕምነትም እንደሆነም የምክር ቤት አባሉ አስረድተዋል። "በአረጋውያን ማዕከላት የሚገኙ ሰዎች ከማህበረሰቡ በበለጠ ለወሲባዊ ጥቃት ተጋላጭ መሆናቸው ተቀባይነት የለውም" ብለዋል ፒተር ሮዝን በአጠቃላይ መርማሪዎች እንደሚገምቱት 32 ሺህ ያህል ወሲባዊ፣ አካላዊና የስነልቦናዊ ጥቃቶች መድረሳቸውን ነው። ይህም ቁጥር በአንድ አመት ያህል እንደደረሰ መረጃው ጠቁሟል። ወሲባዊ ጥቃቱ እንክብካቤ በሚሰጡ ግለሰቦች እንዲሁም እዛው ባሉ ነዋሪዎች እንደሚፈፀምም መረጃው ይፋ አድርጓል።
በአውስትራሊያ አረጋውያን እንክብካቤ ማዕከላት በየሳምንቱ 50 ወሲባዊ ጥቃቶች ይደርሳሉ ተባለ በአውስትራሊያ የሚገኙ የአረጋውያን እንክብካቤ ማዕከላት ውስጥ በየሳምንቱ አምሳ ያህል ወሲባዊ ጥቃቶች እንደሚደርሱ ከሰሞኑ ብሔራዊ አጣሪ ኮሚቴ ይፋ አድርጓል። ለሁለት አመታት ያህልም በአረጋውያን እንክብካቤ ማዕከላት የሚደርሱ የተለያዩ ጥቃቶችንና መንገላቶችን ይፋ ባደረገበት መረጃ ነው ሮያል ኮሚሽን ይህንንም ያካተተው። መርማሪዎቹ እንዳሉት በጎሮጎሳውያኑ 2018-2019 ጊዜ 2 ሺህ 520 አረጋውያን ወሲባዊ ጥቃት ደርሶባቸዋል። "ይህ ሁኔታ ብሔራዊ እፍረት ነው" ብለውታል የምክር ቤት አባሉ ፒተር ሮዝን ኪው ሲ ለአጣሪው ኮሚቴ "ቁጥሮቹ የሚረብሹትን ያህል እነዚህን መረጃዎች ያገኘው የመንግሥት አካል ክትትትልና ቁጥጥር አለማድረጉ የበለጠ የከፋ ነው" ብለዋል። በአረጋውያኑ የእንክብካቤ ማዕከል ላይ የሚታየው ቸልተኝነት ከፍተኛ ውዝግብና ጥያቄ ያስነሳ ሲሆን ከዚህ ቀደምም በአውስትራሊያ በኮሮናቫይረስ ከሞቱት አብዛኛዎቹ በአረጋውያን ማዕከል የሚገኙ ናቸው። አውስትራሊያ በኮሮናቫይረስ ሞተዋል ብላ ከመዘገበችው 903 ሰዎች መካከል 75 በመቶ በነዚህ ማዕከላት የሚገኙ ናቸው። በእነዚህ ማዕከላት ላይ የሚደርሱ ወሲባዊ ጥቃቶች የቀደመ ስጋት ሆነው የቆዩ መሆናቸውን ያመኑት ፒተር ሮዝን ቁጥሩም በአገሪቱ ያሉትን 13-18 በመቶ ጥቃት እንደደረሰባቸው ያሳያል። በርካቶች በዕድሜያቸው የበለፀጉ ወይም ተጋላጭ የሆኑ ቤተሰቦቻቸውን በአረጋውያኑ ማዕከል የሚያስገቡት ደህንነታቸው ይጠበቃል በሚል ዕምነትም እንደሆነም የምክር ቤት አባሉ አስረድተዋል። "በአረጋውያን ማዕከላት የሚገኙ ሰዎች ከማህበረሰቡ በበለጠ ለወሲባዊ ጥቃት ተጋላጭ መሆናቸው ተቀባይነት የለውም" ብለዋል ፒተር ሮዝን በአጠቃላይ መርማሪዎች እንደሚገምቱት 32 ሺህ ያህል ወሲባዊ፣ አካላዊና የስነልቦናዊ ጥቃቶች መድረሳቸውን ነው። ይህም ቁጥር በአንድ አመት ያህል እንደደረሰ መረጃው ጠቁሟል። ወሲባዊ ጥቃቱ እንክብካቤ በሚሰጡ ግለሰቦች እንዲሁም እዛው ባሉ ነዋሪዎች እንደሚፈፀምም መረጃው ይፋ አድርጓል።
https://www.bbc.com/amharic/news-54637492
3politics
ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ 44 የአማፂያን ታጣቂዎችን መግደሏን አሳወቀች
የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ የጦር መኮንኖች መዲናዋ ባንጉይን ከበው ነበር ያላቸውን 44 የአማፂያን ታጣቂዎችን መግደላቸውን አሳውቀዋል። አማፂያኑ በቅርቡ የተመረጡትን ፕሬዚዳንት ፎስ አርቸንግ ቱዋዴራ በኃይል ለመገልበጥ በሚል ከተማዋን እንደከበቡ ተነግሯል። የመንግሥት ቃለ አቀባይ ለፈረንሳዩ ዜና ወኪል እንደተናገሩት ወታደሮቹ ከሩሲያ ልዩ ኃይል ጋር በመተባበር ቦዳ የተባለችውን ከተማ መቆጣጠር እንደቻሉ ነው። ከመንግሥት በኩል የሞተ ሰው ባይኖርም ከአማፂያኑ በኩል ግን ከቻድ፣ ሱዳንና ፉላኒ ብሔር የተውጣጡ ቅጥር ወታደሮች እንደተገደሉ መንግሥት በፌስቡክ ላይ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ከመንግሥት የወጣውን መረጃ የሚያጣራ ነፃ አካል አልተገኝም። አማፂው ቡድን ሶስት አራተኛውን የአገሪቱን ክፍል በቁጥጥር ስሩ ያለ ሲሆን በቅርቡም ቡድኑን ለመታገል በሚል የአገሪቱ መንግሥት ለአስራ አምስት ቀናት የሚሆን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አስተላልፏል። በአገሪቱ ያሉ ስድስት ከፍተኛ ታጣቂ ቡድኖች በታህሳስ ወር ኃይላቸውን በማጣመር 'ኮኦሊሽን ኦፍ ፓትሪየትስ ፎር ቸንጅ' የሚባል አንድ ቡድን መስርተዋል። ነገር ግን መዲናዋ ከ12 ሺህ በሚበልጡ ከተባበሩት መንግሥታት ሰላም አስከባሪ የተውጣጡ ወታደሮች፣ የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ወታደሮችና የሩሲያና ሩዋንዳ ልዩ ኃይሎች በመተባበር በከባድ ጦር መሳሪያ እየጠበቋት ይገኛሉ። የተባበሩት መንግሥታት አማፂ ቡድኖቹ ዋና መዲናዋን ለመቆጣጠር በሚል ከከተማዋ ጋር የሚያገናኙ ሶስት ዋና መንገዶችን ዘግተዋል በማለት አስጠንቅቋል። አገሪቱ ባለፈው ወር ባደረገችው ምርጫ ለሁለተኛ ጊዜ ያሸነፉት ፕሬዚዳንት ፎስ አርቸንግ ቱዋዴራ ማሸነፋቸውን አማፂው ቡድን አይቀበለውም። ከዚህም ጋር ተያይዞ በግጭት እየተናጠች ባለችው የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቿም ወደ ጎረቤት አገር ተሰደዋል።
ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ 44 የአማፂያን ታጣቂዎችን መግደሏን አሳወቀች የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ የጦር መኮንኖች መዲናዋ ባንጉይን ከበው ነበር ያላቸውን 44 የአማፂያን ታጣቂዎችን መግደላቸውን አሳውቀዋል። አማፂያኑ በቅርቡ የተመረጡትን ፕሬዚዳንት ፎስ አርቸንግ ቱዋዴራ በኃይል ለመገልበጥ በሚል ከተማዋን እንደከበቡ ተነግሯል። የመንግሥት ቃለ አቀባይ ለፈረንሳዩ ዜና ወኪል እንደተናገሩት ወታደሮቹ ከሩሲያ ልዩ ኃይል ጋር በመተባበር ቦዳ የተባለችውን ከተማ መቆጣጠር እንደቻሉ ነው። ከመንግሥት በኩል የሞተ ሰው ባይኖርም ከአማፂያኑ በኩል ግን ከቻድ፣ ሱዳንና ፉላኒ ብሔር የተውጣጡ ቅጥር ወታደሮች እንደተገደሉ መንግሥት በፌስቡክ ላይ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ከመንግሥት የወጣውን መረጃ የሚያጣራ ነፃ አካል አልተገኝም። አማፂው ቡድን ሶስት አራተኛውን የአገሪቱን ክፍል በቁጥጥር ስሩ ያለ ሲሆን በቅርቡም ቡድኑን ለመታገል በሚል የአገሪቱ መንግሥት ለአስራ አምስት ቀናት የሚሆን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አስተላልፏል። በአገሪቱ ያሉ ስድስት ከፍተኛ ታጣቂ ቡድኖች በታህሳስ ወር ኃይላቸውን በማጣመር 'ኮኦሊሽን ኦፍ ፓትሪየትስ ፎር ቸንጅ' የሚባል አንድ ቡድን መስርተዋል። ነገር ግን መዲናዋ ከ12 ሺህ በሚበልጡ ከተባበሩት መንግሥታት ሰላም አስከባሪ የተውጣጡ ወታደሮች፣ የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ወታደሮችና የሩሲያና ሩዋንዳ ልዩ ኃይሎች በመተባበር በከባድ ጦር መሳሪያ እየጠበቋት ይገኛሉ። የተባበሩት መንግሥታት አማፂ ቡድኖቹ ዋና መዲናዋን ለመቆጣጠር በሚል ከከተማዋ ጋር የሚያገናኙ ሶስት ዋና መንገዶችን ዘግተዋል በማለት አስጠንቅቋል። አገሪቱ ባለፈው ወር ባደረገችው ምርጫ ለሁለተኛ ጊዜ ያሸነፉት ፕሬዚዳንት ፎስ አርቸንግ ቱዋዴራ ማሸነፋቸውን አማፂው ቡድን አይቀበለውም። ከዚህም ጋር ተያይዞ በግጭት እየተናጠች ባለችው የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቿም ወደ ጎረቤት አገር ተሰደዋል።
https://www.bbc.com/amharic/55807194
0business
ሶማሊያ በዓለም አቀፍ አበዳሪዎች ከፍተኛ የብድር ስረዛ ተደረገላት
የዓለም ባንክና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ሶማሊያ ብድር እንዲቃለልላት የሚያስችሉ እርምጃዎችን መውሰዷን ማስታወቃቸውን ተከትሎ የአበዳሪዎችን ድጋፍ አግኝታለች። እንደ መግለጫው ከሆነ ሶማሊያ አጠቃላይ ብድሯ ከ5.2 ቢሊዮን ዶላር በከፍተኛ ደረጃ ዝቅ ይደረግላታል። ይህም የሚሆነው በሦስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ነው። በሶማሊያ የዓለም ባንክ ተወካይ ሁግ ራይደል ለቢቢሲ እንደገለጹት የሶማሊያን የብድር መጠን ለማቃለል ከሚወሰደው የተቀናጀና ሰፊ ሂደት መካከል ይህ የመጀመሪያው እርምጃ ነው ብለዋል። ሶማሊያ ከ30 ዓመት በፊት ከነበረው የእርስ በርስ ጦርነት ጀምሮ ብድሯን ከፍላ አታውቅም፤ በዚህ ምክንያትም ሶማሊያ ከተለያዩ አበዳሪ ተቋማት እንደገና ብድር ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት ከባድ አድርጎባታል። አሁን ግን ይህ የብድር ስረዛ ስለተደረገላት መንግሥት በመላ አገሪቱ ለሚያከናውናቸው አገልግሎቶች ብድር ለመጠየቅ ያስችለዋል። የሶማሊያው ጠቅላይ ሚንስትር ሃሰን አሊ ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት አስተያየት "ይህ ከነጻነት በኋላ ያገኘነው ሁለተኛው ነጻነት ነው" ብለዋል፤ ከቅኝ ግዛት ነጻ የወጡበትን ሁኔታ በማጣቀስ። "አሁን ያለንበት ጊዜ በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ በመሆኑ በአበዳሪ ተቋማቱ በተወሰደው እርምጃ መሰረት ልናገኘው የምንችለው የበጀት ድጋፍ በመላ አገራችን ለሕዝቡ አገልግሎት ለመስጠት ትልቅ እገዛ ያደርጋል። ከሁሉም በላይ ደግሞ ሁላችንንም እያሸበረን ያለውን ኮሮናቫይረስን ለመዋጋት ይረዳናል" ብለዋል ጠቅላይ ሚንስትሩ። እንደ ሶማሊያ ባለ በሽብርተኞች በተደጋጋሚ ጥቃት ለሚደርስበት አገርም ሽብርተኝነትን ማሸነፍ የሚቻለው ምጣኔ ሃብትን በማሳደግ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ ወጣቶችንና ሴቶችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል። አክለውም ፍትሃዊና ግልጽ የሃብት ክፍፍል በመፍጠር ሽብርተኝነትን ማሸነፍ ስለሚቻል የብድር ቅነሳ ውሳኔው ለሶማሊያ ዘርፈ ብዙ ጥቅም የሚያመጣ መሆኑን ጠቅላይ ሚንስትር ሃሰን ተናግረዋል።
ሶማሊያ በዓለም አቀፍ አበዳሪዎች ከፍተኛ የብድር ስረዛ ተደረገላት የዓለም ባንክና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ሶማሊያ ብድር እንዲቃለልላት የሚያስችሉ እርምጃዎችን መውሰዷን ማስታወቃቸውን ተከትሎ የአበዳሪዎችን ድጋፍ አግኝታለች። እንደ መግለጫው ከሆነ ሶማሊያ አጠቃላይ ብድሯ ከ5.2 ቢሊዮን ዶላር በከፍተኛ ደረጃ ዝቅ ይደረግላታል። ይህም የሚሆነው በሦስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ነው። በሶማሊያ የዓለም ባንክ ተወካይ ሁግ ራይደል ለቢቢሲ እንደገለጹት የሶማሊያን የብድር መጠን ለማቃለል ከሚወሰደው የተቀናጀና ሰፊ ሂደት መካከል ይህ የመጀመሪያው እርምጃ ነው ብለዋል። ሶማሊያ ከ30 ዓመት በፊት ከነበረው የእርስ በርስ ጦርነት ጀምሮ ብድሯን ከፍላ አታውቅም፤ በዚህ ምክንያትም ሶማሊያ ከተለያዩ አበዳሪ ተቋማት እንደገና ብድር ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት ከባድ አድርጎባታል። አሁን ግን ይህ የብድር ስረዛ ስለተደረገላት መንግሥት በመላ አገሪቱ ለሚያከናውናቸው አገልግሎቶች ብድር ለመጠየቅ ያስችለዋል። የሶማሊያው ጠቅላይ ሚንስትር ሃሰን አሊ ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት አስተያየት "ይህ ከነጻነት በኋላ ያገኘነው ሁለተኛው ነጻነት ነው" ብለዋል፤ ከቅኝ ግዛት ነጻ የወጡበትን ሁኔታ በማጣቀስ። "አሁን ያለንበት ጊዜ በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ በመሆኑ በአበዳሪ ተቋማቱ በተወሰደው እርምጃ መሰረት ልናገኘው የምንችለው የበጀት ድጋፍ በመላ አገራችን ለሕዝቡ አገልግሎት ለመስጠት ትልቅ እገዛ ያደርጋል። ከሁሉም በላይ ደግሞ ሁላችንንም እያሸበረን ያለውን ኮሮናቫይረስን ለመዋጋት ይረዳናል" ብለዋል ጠቅላይ ሚንስትሩ። እንደ ሶማሊያ ባለ በሽብርተኞች በተደጋጋሚ ጥቃት ለሚደርስበት አገርም ሽብርተኝነትን ማሸነፍ የሚቻለው ምጣኔ ሃብትን በማሳደግ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ ወጣቶችንና ሴቶችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል። አክለውም ፍትሃዊና ግልጽ የሃብት ክፍፍል በመፍጠር ሽብርተኝነትን ማሸነፍ ስለሚቻል የብድር ቅነሳ ውሳኔው ለሶማሊያ ዘርፈ ብዙ ጥቅም የሚያመጣ መሆኑን ጠቅላይ ሚንስትር ሃሰን ተናግረዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-52046300
0business
አዲሱ የኬንያ ፕሬዝደንት መሠረታዊ ድጎማዎችን አነሱ
በምርጫ ቅስቀሳቸው የመደበኛ ኬንያዊያንን ህይወት አሻሽላለሁ፣ የስራ ዕድል ፈጥራለሁ እና የኑሮ ውድነትን እቀንሳለሁ በማለት ቃል የቡት ዊልያም ሩቶ፣ የነዳጅ ድጎማን ማንሳታቸው በርካታ ኬንያውያንን እያነጋገረ ነው። በመላው ዓለም በተለያዩ ምክንያቶች እየናረ የመጣውን የኑሮ ውድነት ዜጎች እንዲቋቋሙ በማሰብ መንግሥታት ድጎማዎችን እያስተዋወቁ ባሉበት በዚህ ወቅት አዲሱ የኬንያ መሪ ግን ቀዳሚ ባደረጉት የፖሊሲ ማስተካከያ የነዳጅ ድጎማን አንስተዋል። በዚህ ኬንያውያንን ባስገረመ ውሳኔ የነዳጅ ዋጋ በአገሪቱ ታሪክ ከፍተኛው የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ እንዲደርስ የሚያደርግ ነው። በርካቶች በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ ቅሬታቸውን እየገለጹ ሲሆን የኢኮኖሚ ተንታኞች በበኩላቸው ምርጫውን እጅግ ጠባብ በሆነ ልዩነት ያሸነፉት ዊልያም ሩቶ ገና በስልጣን ዘመናቸው መጀመሪያ ላይ ድጋፍ ሊያሳጣቸው የሚችል ውሳኔ ነው ያሳለፉት ሲሉ አስጠንቅቀዋል። የናይሮቢ ነዋሪ የሆኑት ጆን ማና "ከወራት በፊት ወደ ስራ ለመሄድ መኪና መንዳት አቁሜያለሁ። አሁን ደግሞ ማታቱዎች (የሕዝብ ታክሲዎች እና አውቶብሶች) የታሪፍ ጭማሪ አድርገው ይህንንም ጉዞ የበለጠ ውድ ይሆንብኛል ብዬ እየሰጋሁ እገኛለሁ’’ ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ፕሬዚደንት ሩቶ በምርጫ ቅስቀሳቸው የመደበኛ ኬንያውያንን ህይወት አሻሽላለሁ፣ የስራ ዕድል ፈጥራለሁ እና የኑሮ ውድነትን እቀንሳለሁ በሚል ቃል የገቡ ሲሆን ለዚህም ራሳቸው ከዝቅተኛ ኑሮ ተነስተው አሁን ያሉበት ደረጃ መድረሳቸውን በማጉላት አስተጋብተዋል። በምርጫ ዘመቻው ከገቡት ቃል ውስጥ አንዱ የነዳጅ ዋጋን ለመቀነስ፣ በነዳጅ ላይ የሚጣለውን ግብር ማንሳት እና ይህንንም ተከትሎ የመሰረታዊ ሸቀጦችን ዋጋ ዝቅ ማድረግ ነበር። ነገር ግን ፕሬዝዳንቱ በበዓለ ሲመታቸው ላይ ባደረጉት ንግግር የድጎማ ፕሮግራሙ ማብቃቱን አስታውቀው ድጎማው ቢቀጥል እስከ መጪው ሰኔ ወር ድረስ ኬንያ 2.3 ቢሊየን ዶላር ታወጣ እንደነበር ተናግረዋል። "ይህ ከጠቅላላው የአገሪቱ የመንግሥት የልማት በጀት ጋር ሲነጻጸር እኩል ነው" ያሉት ፕሬዘዳንቱ ድጎማው የኑሮ ውድነቱን ለመቀነስ የታለመለትን ዓላማ ማሳካት አልቻለም ብለዋል። የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ድጎማ ለኬንያ ዘላቂነት የሌለው መፍትሄ ብሎም ለአጭበርባሪዎች ዕድል ከመስጠት ባሻገር ለመደበኛው ዜጋ ያን ያህል ፋይዳ እንደሌለው ይናገራሉ። ነገር ግን የነዳጅ ዋጋ በ13 በመቶ ጨምሮ 1.49 ዶላር ወይም 78 ብር መግባቱ ጫና መፍጠሩ አይቀሬ ነው ሲሉ ይስማማሉ። "ተፅዕኖው በእርግጠኝነት መሰማቱ አይቀርም። ምክንያቱም የሁሉም ነገር ዋጋ ከነዳጅ ዋጋ መናር ጋር ተያይዞ መጨመሩ ስለማይቀር’’ ሲሉ ተንታኙ ኸርማን ማንዮራ ለቢቢሲ ተናግረዋል። እንዲህ ያለ ትልቅ ውሳኔ ገና አዲስ መንግሥት ሳይቋቋም በፊት መደረጉ አላስፈላጊ ብሎም “ከታሰበበት የመንግሥት ውሳኔ ይልቅ የአንድ ሰው ውሳኔ እንዲመስል አድርጓል’’ ሲሉም ተናግረዋል። ፕሬዝዳንት ሩቶ የካቢኔ አባላቶቻቸውን አዋቅረው ብሎም የፓርላማውን ይሁንታ የሚሹ የካቢኔ ሚኒስትሮቻቸውን አላሾሙም። ተንታኙ ጃቫስ ቢጋምቦ በበኩላቸው ፕሬዘዳንቱ ጉዳዩን በቅድሚያ ለኬንያውያን ማስረዳት ብሎም የድጎማውን ገንዘብ በምን ላይ ሊያውሉት እንዳሰቡ ለማስረዳት ተጨማሪ ጊዜ ወስደው እርምጃውን ህዝባዊ ድጋፍ እንዲያገኝ ማድረግ ነበረባቸው ብለዋል። ፕሬዘዳንት ሩቶ የኬንያውያን የዕለት ተዕለት ተቀዳሚ ምግቦችን ለማዘጋጀት ጥቅም ላይ የሚውለውን  የበቆሎ ዱቄትዋጋ በግማሽ የቀነሰውን ድጎማ ግዜው ማብቃቱን ተከትሎ ለተጨማሪ ግዜ አላራዝምም ብለዋል። ኬንያ በከፍተኛ እዳ ውስጥ የምትገኝ አገር ስትሆን ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ጋር ባላት የብድር ውል መሠረት ድጎማውን ማንሳቷ አስፈላጊ ተብሎ የተቀመጠ ነበር። "እነዚህ ድጎማዎች ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው ቤተሰቦች ይልቅ ከፍተኛ ገቢ ላላቸው ቤተሰቦች የበለጠ የማገዝ አዝማሚያ አላቸው" ሲሉ የአይኤምኤፍ የአፍሪካ ዳይሬክተር አበበ ሥላሴ ተናግረዋል። ፕሬዚደንት ሩቶ በናፍጣ እና ኬሮሲን ላይ አነስተኛ ድጎማ አድርገዋል። ናፍጣ በአብዛኛው የሕብ ትራስፖርት አግልግሎት ሰጪዎች እና ፋብሪካዎች ጥቅም ላይ ይውላል። እንዲሄም ኬሮሲን በተለይም የገጠር ቤተሰቦች ምግብ ለማብሰል እና በምሽት ብርሃን ለማግኘት የሚጠቀሙበት ነው። በነዳጅ እና በቆሎ ዱቄት ላይ የሚደረገው ድጎማ ተቀንሶ በምትኩ የማዳበሪያ ወጪን ለመቀነስ መታሰቡም ይፋ ሆኗል። በኬንያ የማዳበሪያ ዋጋ፣ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ጦርነት ከከፈተች በኋላ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል። ኬንያ ራሷን ለመመገብ የሚያስችል በቂ በቆሎ ስለማታመርት በአገር ውስጥ ምርት ፍላጎትን ማሟለት ካስፈለጋት አገራዊ ምርትን ማሳደግ ይጠበቅባታል። በኬንያ አርሶ አደር ማህበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ ድጋፍ ያላቸው አዲሱ ፕሬዘዳንት ሩቶ "የኑሮ ውድነት ዝቅ የማድረግ ስትራቴጂያችን አምራቾችን በማብቃት ላይ የተመሰረተ ነው" ብለዋል። በመሆኑም አዲሱ አስተዳደር ከመጪው ሰኞ ጀምሮ 1.4 ሚሊዮን ባለ 50 ኪሎ ግራም ማዳበሪያ የያዙ ከረጢቶችን አሁን ከሚሸጥበት 54 ዶላር ወደ 29 ዶላር ዝቅ ለማድረግ ማሰባቸውን ፕሬዝደንቱ ይፋ አድርገዋል። ፕሬዝደንቱ የወሰዷቸው እነዚህ ውሳኔዎች በሚቀጥሉት ወራት የኑሮ ውድነቱን ጋብ ካላደረጉት የሩቶ ተቀባይነት ላይ ትልቅ ጫና ሊያመጣ እንደሚችል ተንታኙ ቢጋምቦ አስጠንቅቀዋል። "በሚቀጥሉት ስድስት እና ስምንት ወራት ውስጥ የሚደረጉት ውሳኔዎች የኑሮ ውድነቱን ካልቀነሱት የዜጎች ደስታ ብዙም አይቆይም" ሲሉ ተናግረዋል።
አዲሱ የኬንያ ፕሬዝደንት መሠረታዊ ድጎማዎችን አነሱ በምርጫ ቅስቀሳቸው የመደበኛ ኬንያዊያንን ህይወት አሻሽላለሁ፣ የስራ ዕድል ፈጥራለሁ እና የኑሮ ውድነትን እቀንሳለሁ በማለት ቃል የቡት ዊልያም ሩቶ፣ የነዳጅ ድጎማን ማንሳታቸው በርካታ ኬንያውያንን እያነጋገረ ነው። በመላው ዓለም በተለያዩ ምክንያቶች እየናረ የመጣውን የኑሮ ውድነት ዜጎች እንዲቋቋሙ በማሰብ መንግሥታት ድጎማዎችን እያስተዋወቁ ባሉበት በዚህ ወቅት አዲሱ የኬንያ መሪ ግን ቀዳሚ ባደረጉት የፖሊሲ ማስተካከያ የነዳጅ ድጎማን አንስተዋል። በዚህ ኬንያውያንን ባስገረመ ውሳኔ የነዳጅ ዋጋ በአገሪቱ ታሪክ ከፍተኛው የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ እንዲደርስ የሚያደርግ ነው። በርካቶች በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ ቅሬታቸውን እየገለጹ ሲሆን የኢኮኖሚ ተንታኞች በበኩላቸው ምርጫውን እጅግ ጠባብ በሆነ ልዩነት ያሸነፉት ዊልያም ሩቶ ገና በስልጣን ዘመናቸው መጀመሪያ ላይ ድጋፍ ሊያሳጣቸው የሚችል ውሳኔ ነው ያሳለፉት ሲሉ አስጠንቅቀዋል። የናይሮቢ ነዋሪ የሆኑት ጆን ማና "ከወራት በፊት ወደ ስራ ለመሄድ መኪና መንዳት አቁሜያለሁ። አሁን ደግሞ ማታቱዎች (የሕዝብ ታክሲዎች እና አውቶብሶች) የታሪፍ ጭማሪ አድርገው ይህንንም ጉዞ የበለጠ ውድ ይሆንብኛል ብዬ እየሰጋሁ እገኛለሁ’’ ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ፕሬዚደንት ሩቶ በምርጫ ቅስቀሳቸው የመደበኛ ኬንያውያንን ህይወት አሻሽላለሁ፣ የስራ ዕድል ፈጥራለሁ እና የኑሮ ውድነትን እቀንሳለሁ በሚል ቃል የገቡ ሲሆን ለዚህም ራሳቸው ከዝቅተኛ ኑሮ ተነስተው አሁን ያሉበት ደረጃ መድረሳቸውን በማጉላት አስተጋብተዋል። በምርጫ ዘመቻው ከገቡት ቃል ውስጥ አንዱ የነዳጅ ዋጋን ለመቀነስ፣ በነዳጅ ላይ የሚጣለውን ግብር ማንሳት እና ይህንንም ተከትሎ የመሰረታዊ ሸቀጦችን ዋጋ ዝቅ ማድረግ ነበር። ነገር ግን ፕሬዝዳንቱ በበዓለ ሲመታቸው ላይ ባደረጉት ንግግር የድጎማ ፕሮግራሙ ማብቃቱን አስታውቀው ድጎማው ቢቀጥል እስከ መጪው ሰኔ ወር ድረስ ኬንያ 2.3 ቢሊየን ዶላር ታወጣ እንደነበር ተናግረዋል። "ይህ ከጠቅላላው የአገሪቱ የመንግሥት የልማት በጀት ጋር ሲነጻጸር እኩል ነው" ያሉት ፕሬዘዳንቱ ድጎማው የኑሮ ውድነቱን ለመቀነስ የታለመለትን ዓላማ ማሳካት አልቻለም ብለዋል። የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ድጎማ ለኬንያ ዘላቂነት የሌለው መፍትሄ ብሎም ለአጭበርባሪዎች ዕድል ከመስጠት ባሻገር ለመደበኛው ዜጋ ያን ያህል ፋይዳ እንደሌለው ይናገራሉ። ነገር ግን የነዳጅ ዋጋ በ13 በመቶ ጨምሮ 1.49 ዶላር ወይም 78 ብር መግባቱ ጫና መፍጠሩ አይቀሬ ነው ሲሉ ይስማማሉ። "ተፅዕኖው በእርግጠኝነት መሰማቱ አይቀርም። ምክንያቱም የሁሉም ነገር ዋጋ ከነዳጅ ዋጋ መናር ጋር ተያይዞ መጨመሩ ስለማይቀር’’ ሲሉ ተንታኙ ኸርማን ማንዮራ ለቢቢሲ ተናግረዋል። እንዲህ ያለ ትልቅ ውሳኔ ገና አዲስ መንግሥት ሳይቋቋም በፊት መደረጉ አላስፈላጊ ብሎም “ከታሰበበት የመንግሥት ውሳኔ ይልቅ የአንድ ሰው ውሳኔ እንዲመስል አድርጓል’’ ሲሉም ተናግረዋል። ፕሬዝዳንት ሩቶ የካቢኔ አባላቶቻቸውን አዋቅረው ብሎም የፓርላማውን ይሁንታ የሚሹ የካቢኔ ሚኒስትሮቻቸውን አላሾሙም። ተንታኙ ጃቫስ ቢጋምቦ በበኩላቸው ፕሬዘዳንቱ ጉዳዩን በቅድሚያ ለኬንያውያን ማስረዳት ብሎም የድጎማውን ገንዘብ በምን ላይ ሊያውሉት እንዳሰቡ ለማስረዳት ተጨማሪ ጊዜ ወስደው እርምጃውን ህዝባዊ ድጋፍ እንዲያገኝ ማድረግ ነበረባቸው ብለዋል። ፕሬዘዳንት ሩቶ የኬንያውያን የዕለት ተዕለት ተቀዳሚ ምግቦችን ለማዘጋጀት ጥቅም ላይ የሚውለውን  የበቆሎ ዱቄትዋጋ በግማሽ የቀነሰውን ድጎማ ግዜው ማብቃቱን ተከትሎ ለተጨማሪ ግዜ አላራዝምም ብለዋል። ኬንያ በከፍተኛ እዳ ውስጥ የምትገኝ አገር ስትሆን ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ጋር ባላት የብድር ውል መሠረት ድጎማውን ማንሳቷ አስፈላጊ ተብሎ የተቀመጠ ነበር። "እነዚህ ድጎማዎች ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው ቤተሰቦች ይልቅ ከፍተኛ ገቢ ላላቸው ቤተሰቦች የበለጠ የማገዝ አዝማሚያ አላቸው" ሲሉ የአይኤምኤፍ የአፍሪካ ዳይሬክተር አበበ ሥላሴ ተናግረዋል። ፕሬዚደንት ሩቶ በናፍጣ እና ኬሮሲን ላይ አነስተኛ ድጎማ አድርገዋል። ናፍጣ በአብዛኛው የሕብ ትራስፖርት አግልግሎት ሰጪዎች እና ፋብሪካዎች ጥቅም ላይ ይውላል። እንዲሄም ኬሮሲን በተለይም የገጠር ቤተሰቦች ምግብ ለማብሰል እና በምሽት ብርሃን ለማግኘት የሚጠቀሙበት ነው። በነዳጅ እና በቆሎ ዱቄት ላይ የሚደረገው ድጎማ ተቀንሶ በምትኩ የማዳበሪያ ወጪን ለመቀነስ መታሰቡም ይፋ ሆኗል። በኬንያ የማዳበሪያ ዋጋ፣ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ጦርነት ከከፈተች በኋላ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል። ኬንያ ራሷን ለመመገብ የሚያስችል በቂ በቆሎ ስለማታመርት በአገር ውስጥ ምርት ፍላጎትን ማሟለት ካስፈለጋት አገራዊ ምርትን ማሳደግ ይጠበቅባታል። በኬንያ አርሶ አደር ማህበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ ድጋፍ ያላቸው አዲሱ ፕሬዘዳንት ሩቶ "የኑሮ ውድነት ዝቅ የማድረግ ስትራቴጂያችን አምራቾችን በማብቃት ላይ የተመሰረተ ነው" ብለዋል። በመሆኑም አዲሱ አስተዳደር ከመጪው ሰኞ ጀምሮ 1.4 ሚሊዮን ባለ 50 ኪሎ ግራም ማዳበሪያ የያዙ ከረጢቶችን አሁን ከሚሸጥበት 54 ዶላር ወደ 29 ዶላር ዝቅ ለማድረግ ማሰባቸውን ፕሬዝደንቱ ይፋ አድርገዋል። ፕሬዝደንቱ የወሰዷቸው እነዚህ ውሳኔዎች በሚቀጥሉት ወራት የኑሮ ውድነቱን ጋብ ካላደረጉት የሩቶ ተቀባይነት ላይ ትልቅ ጫና ሊያመጣ እንደሚችል ተንታኙ ቢጋምቦ አስጠንቅቀዋል። "በሚቀጥሉት ስድስት እና ስምንት ወራት ውስጥ የሚደረጉት ውሳኔዎች የኑሮ ውድነቱን ካልቀነሱት የዜጎች ደስታ ብዙም አይቆይም" ሲሉ ተናግረዋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c2j41x59zpko
5sports
የሳዑዲ አረቢያ ድል በአርጀንቲና ላይ፣ የዓለም ዋንጫው ቀዳሚ ያልተጠበቀ ውጤት
በዓለም እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ ይህ ነው የሚባል የጎላ ስም የሌላት ሳዑዲ አረቢያ በኳታሩ የዓለም ዋንጫ ለፍጻሜው ከሚጠበቁ ቡድኖች መካከል አንዱ የሆነውን የአርጀንቲናን ቡድን ድል አድርጋለች። እሁድ ዕለት በተጀመረው በዚህ የዓለም ዋንጫ ከማይጠበቁ ክስተቶች ሁሉ ቀዳሚ በሆነ ውጤት፣ የሳዑዲ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ከመመራት ተነስተው የሁለት ጊዜ የዓለም ዋንጫ ባለቤት የሆነችውንና ሜሲን ጨምሮ በባለ ዝናዎች የተዋቀረውን የአርጀንቲናን ቡድን አሸንፈዋል። ሳዑዲዎች በሉሳይል ስታዲየም ባደረጉት የመጀመሪያ ጨዋታቸው አንድ ለባዶ ከመመራት በመነሳት ሁለት ግቦችን አስቆጥረው የምድብ ሐ መሪነት ቦታን ተቆናጠዋል። በዓለም የእግር ኳስ ደረጃ ላይ 51ኛ የሆነችው ሳኡዲ አረቢያ በመጀመሪያው አጋማሽ ላይ የተሰጠባትን የፍጹም ቅጣት ምት ሊዮኔል ሜሲ አስቆጥሮ ነው ጨዋታውን እየተመራች የጀመረችው። በአርጀንቲና በኩል በርካታ ግቦችን ለማስቆጠር ተደጋጋሚ ጥረቶች ተደርገው ተጨማሪ ሦስት ግቦችን ማስቆጠር ቢችሉም ዕድለኛ ሳይሆኑ ቀርተው ከጨዋታ ውጪ በመሆናቸው ሳይመዘገቡላቸው ቀርተዋል። የጨዋታው ግማሽ ድረስ አርጀንቲና በአንድ ለባዶ ውጤት መሪ ሆና እረፍት ከተደረገ በኋላ፣ ሁለተኛው አጋማሽ ተጀምሮ በ10 ደቂቃ ውስጥ ሳዑዲ ውጤት ቀያሪውን ግብ አስቆጠረች። የመጀመሪያው ግብ በሳሌህ አል-ሼህሪ ሲመዘገብ፣ ተከትሎ ደግሞ ሳሌም አል ዳወሳሪ ያስቆጠራት ግብ ለአርጀንቲና ድንጋጤን ለሳዑዲዎች ደግሞ ፈንጠዝያን አጎናጸፈች። አርጀንቲናዎች በመጀመሪያው ጨዋታቸው ተጨማሪ ግቦችን በማስቆጠር ድልን በእጃቸው አሊያም አቻ ለመውጣት ቢጥሩም ሳይሳካላቸው ቀርቷል። በዓለም ዋንጫ ጨዋታ ላይ በአሸናፊነት የተመዘገበላት አራተኛ ጨዋታ ብቻ ያላት ሳዑዲ አረቢያ፤ አርጀንቲናን በመርታት ሜክሲኮ እና ፖላንድ ያሉበትን ምድብ አጓጊ አድርጋዋለች። የሊዮኔል ሜሲው የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን በዚህ ውድድር ለዋንጫ ከሚጠበቁጥ መካከል ሲሆን፣ ቡድኑ ከዓለም ዋንጫ ቀደም ብሎ ባደረጋቸው 36 ጨዋታዎች ምንም ሽንፈት ካለማስተናገዱ በተጨማሪ፣ ባለፈው ዓመት የአህጉራዊው ኮፓ አሜሪካ ባለድል ነው። አርጀንቲና ከአውሮፓውያኑ 1986 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ዋንጫ ለማንሳት ያላት ተስፋ አሁንም የጨለመ ባይሆንም ከባድ ፈተና ይጠብቃታል። ይህ የዓለም ዋንጫ ለታዋቂው ሊዮኔል ሜሲ የመጨረሻው ሊሆን ይችላል እየተባለ ሲሆን፣ ቡድኑ በሳዑዲ የገጠመውን የሽንፈት ጥላ በመግፈፍ ወደ ቀጣይ ዙሮች አልፎ እንደተጠበቀው ዋንጫ ካነሳ ለሜሴ የክብር ስንብት ይሆንለታል እየተባለ ነው። አሁን ግን ሳዑዲ አረቢያ በምድብ ሐ ከተመደቡት ቡድኖች ሙሉ ሦስት ነጥብ ከአንድ ንጹህ ጎል ጋር በመያዝ መሪ ሆናለች። አርጀንቲና ደግሞ ካለ ነጥብ በአንድ የግብ ዕዳ ለጊዜው ከምድቡ ግርጌ ተቀምጣለች። ቅዳሜ ኅዳር 17/2015 ዓ.ም ሳዑዲ አረቢያ ከፖላንድ፣ አርጀንቲና ደግሞ ከሜክሲኮ ቀጣይ ጨዋታ ያደርጋሉ።
የሳዑዲ አረቢያ ድል በአርጀንቲና ላይ፣ የዓለም ዋንጫው ቀዳሚ ያልተጠበቀ ውጤት በዓለም እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ ይህ ነው የሚባል የጎላ ስም የሌላት ሳዑዲ አረቢያ በኳታሩ የዓለም ዋንጫ ለፍጻሜው ከሚጠበቁ ቡድኖች መካከል አንዱ የሆነውን የአርጀንቲናን ቡድን ድል አድርጋለች። እሁድ ዕለት በተጀመረው በዚህ የዓለም ዋንጫ ከማይጠበቁ ክስተቶች ሁሉ ቀዳሚ በሆነ ውጤት፣ የሳዑዲ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ከመመራት ተነስተው የሁለት ጊዜ የዓለም ዋንጫ ባለቤት የሆነችውንና ሜሲን ጨምሮ በባለ ዝናዎች የተዋቀረውን የአርጀንቲናን ቡድን አሸንፈዋል። ሳዑዲዎች በሉሳይል ስታዲየም ባደረጉት የመጀመሪያ ጨዋታቸው አንድ ለባዶ ከመመራት በመነሳት ሁለት ግቦችን አስቆጥረው የምድብ ሐ መሪነት ቦታን ተቆናጠዋል። በዓለም የእግር ኳስ ደረጃ ላይ 51ኛ የሆነችው ሳኡዲ አረቢያ በመጀመሪያው አጋማሽ ላይ የተሰጠባትን የፍጹም ቅጣት ምት ሊዮኔል ሜሲ አስቆጥሮ ነው ጨዋታውን እየተመራች የጀመረችው። በአርጀንቲና በኩል በርካታ ግቦችን ለማስቆጠር ተደጋጋሚ ጥረቶች ተደርገው ተጨማሪ ሦስት ግቦችን ማስቆጠር ቢችሉም ዕድለኛ ሳይሆኑ ቀርተው ከጨዋታ ውጪ በመሆናቸው ሳይመዘገቡላቸው ቀርተዋል። የጨዋታው ግማሽ ድረስ አርጀንቲና በአንድ ለባዶ ውጤት መሪ ሆና እረፍት ከተደረገ በኋላ፣ ሁለተኛው አጋማሽ ተጀምሮ በ10 ደቂቃ ውስጥ ሳዑዲ ውጤት ቀያሪውን ግብ አስቆጠረች። የመጀመሪያው ግብ በሳሌህ አል-ሼህሪ ሲመዘገብ፣ ተከትሎ ደግሞ ሳሌም አል ዳወሳሪ ያስቆጠራት ግብ ለአርጀንቲና ድንጋጤን ለሳዑዲዎች ደግሞ ፈንጠዝያን አጎናጸፈች። አርጀንቲናዎች በመጀመሪያው ጨዋታቸው ተጨማሪ ግቦችን በማስቆጠር ድልን በእጃቸው አሊያም አቻ ለመውጣት ቢጥሩም ሳይሳካላቸው ቀርቷል። በዓለም ዋንጫ ጨዋታ ላይ በአሸናፊነት የተመዘገበላት አራተኛ ጨዋታ ብቻ ያላት ሳዑዲ አረቢያ፤ አርጀንቲናን በመርታት ሜክሲኮ እና ፖላንድ ያሉበትን ምድብ አጓጊ አድርጋዋለች። የሊዮኔል ሜሲው የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን በዚህ ውድድር ለዋንጫ ከሚጠበቁጥ መካከል ሲሆን፣ ቡድኑ ከዓለም ዋንጫ ቀደም ብሎ ባደረጋቸው 36 ጨዋታዎች ምንም ሽንፈት ካለማስተናገዱ በተጨማሪ፣ ባለፈው ዓመት የአህጉራዊው ኮፓ አሜሪካ ባለድል ነው። አርጀንቲና ከአውሮፓውያኑ 1986 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ዋንጫ ለማንሳት ያላት ተስፋ አሁንም የጨለመ ባይሆንም ከባድ ፈተና ይጠብቃታል። ይህ የዓለም ዋንጫ ለታዋቂው ሊዮኔል ሜሲ የመጨረሻው ሊሆን ይችላል እየተባለ ሲሆን፣ ቡድኑ በሳዑዲ የገጠመውን የሽንፈት ጥላ በመግፈፍ ወደ ቀጣይ ዙሮች አልፎ እንደተጠበቀው ዋንጫ ካነሳ ለሜሴ የክብር ስንብት ይሆንለታል እየተባለ ነው። አሁን ግን ሳዑዲ አረቢያ በምድብ ሐ ከተመደቡት ቡድኖች ሙሉ ሦስት ነጥብ ከአንድ ንጹህ ጎል ጋር በመያዝ መሪ ሆናለች። አርጀንቲና ደግሞ ካለ ነጥብ በአንድ የግብ ዕዳ ለጊዜው ከምድቡ ግርጌ ተቀምጣለች። ቅዳሜ ኅዳር 17/2015 ዓ.ም ሳዑዲ አረቢያ ከፖላንድ፣ አርጀንቲና ደግሞ ከሜክሲኮ ቀጣይ ጨዋታ ያደርጋሉ።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c2vqle7png2o
3politics
የኢሕዲሪ ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩት ሌ/ኮሎኔል ፍሰሐ ደስታ አረፉ
ከሰላሳ ዓመታት በፊት በነበረው የኢትዮጵያ መንግሥት ውስጥ የአገሪቱ ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩት ሌ/ኮሎኔል ፍሰሐ ደስታ በ81 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። የቀድሞው መሪ ኮሎኔል መንግሥቱ ኃ/ማሪያም ምክትል በመሆን የኢሕዲሪ ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩት ሌ/ኮሎኔል ፍሰሐ ደስታ፣ ኢሕአዴግ አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ ለ20 ዓመታት ያህል በእስር ቆይተዋል። ቢቢሲ ከቤተሰባቸው ለመረዳት እንደቻለው ሌ/ኮሎኔል ፍሰሐ የልብ ሕመም የነበረባቸው ሲሆን ለዚህም በአገር ውስጥና በውጪ ክትትል ሲያደርጉ ቆይተዋል። ባለትዳርና የአንድ ልጅ አባት የነበሩት ፍሰሐ ሕይወታቸው ያለፈው አርብ ሚያዚያ 28/2014 ዓ. ም. እኩለ ሌሊት አካባቢ ሲሆን የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው እሁድ ሚያዚያ 30/2014 ዓ. ም. በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንደሚፈጸም ተገልጿል። ከእስር ከወጡ በኋላ በሥልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት ስላለፉባቸው ሁኔታዎች የሚተርክ "አብዮቱና ትዝታዬ" የሚል መጽሐፍ ያበረከቱ ሲሆን፣ በዚህም "ደርግ በወሰዳቸው በጎ ዕርምጃዎች እንደምደሰት ሁሉ በማወቅ፣ በድፍረት፣ ባለማወቅና በስህተት ለተፈጸሙት ደግሞ ሙሉ ኃላፊነት በመውሰድ በበኩሌ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እጠይቃለሁ" ብለው ነበር። ሌ/ኮሎኔል ፍሰሐ ከመጀመሪያው መጽሐፋቸው በተጨማሪ ሁለተኛ መጽሐፍ በማዘጋጀት ላይ እንደነበሩ ቤተሰቦቻቸው ለቢቢሲ ገልጸዋል። ትግራይ አድዋ ውስጥ የተወለዱት ሌፍተናንት ኮሎኔል ፍሰሐ፣ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በአደዋ ንግሥተ ሳባ እንዲሁም ሁለተኛ ደረጃን አዲግራት ውስጥ በሚገኘው አግአዚ ትምህርት ቤት ተከታትለዋል። በተጨማሪም አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው ኮተቤ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማሩ ሲሆን፣ ከዚያም በኋላ ወደ ሐረር ጦር ትምህርት ቤት ገብተው ከሰለጠኑ በኋላ በክብር ዘበኛ ውስጥ ገብተው በንጉሡ ቤተ መንግሥት ውስጥ ተመድበው አገልግለዋል። ሌ/ኮሎኔል ፍሰሐ ወደ አሜሪካ በመሄድ ከፍተኛ ወታደራዊ ሥልጠና ወስደዋል። ከዚህ በሻገርም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሕግ ትምህርት ተከታትለዋል። ንጉሡን ከሥልጣን ያስወገደው ሕዝባዊ አብዮት ሲፈነዳና በደርግ አማካይነት ጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ሲመሠረት ከጦር ኃይሉ ተወጣጥተው የአመራርነት ቦታውን ከያዙት የወቅቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት መካከል አንዱ ነበሩ። ከዓመታት ቆይታ በኋላ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲ (ኢሠፓ) እንዲሁም የኢትዮጵያ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኢሕዲሪ) ሲመሠረት የቀድሞው ፕሬዝዳንት መንግሥቱ ኃይለማሪም ምክትል በመሆን የአገሪቱ ሁለተኛ ሰው ለመሆን በቅተው ነበር። ከአማጺያኑ ጋር ለ17 ዓመታት የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ የቆየው አስተዳደራቸው እየተዳከመ መጥቶ ፕሬዝዳንቱ አገር ለቀው ከተሰደዱ በሳምንታት ውስጥ የአማጺያኑ ስብስብ ኢሕአዴግ አዲስ አበባን ሲቆጣጠር የኢሕዲሪ መንግሥት ፍጻሜ ሆነ። ሌ/ኮሎኔል ፍሰሐን ጨምሮ በአገር ውስጥ የተገኙት የቀድሞው መንግሥት ባለሥልጣናት በአገሪቱ ውስጥ በተፈጸሙ ጭፍጨፋዎችና በሰብአዊነት ላይ በተፈጸሙ ወንጀሎች ተከሰው ለዓመታት በተካሄደ የፍርድ ሂደት እስር ተፈርዶባቸዋል። ሌ/ኮሎኔል ፍሰሐ ደስታም ለ20 ዓመታት በእስር ካሳለፉ በኋላ ከ10 ዓመት በፊት በይቅርታ መለቀቃቸው ይታወሳል።
የኢሕዲሪ ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩት ሌ/ኮሎኔል ፍሰሐ ደስታ አረፉ ከሰላሳ ዓመታት በፊት በነበረው የኢትዮጵያ መንግሥት ውስጥ የአገሪቱ ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩት ሌ/ኮሎኔል ፍሰሐ ደስታ በ81 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። የቀድሞው መሪ ኮሎኔል መንግሥቱ ኃ/ማሪያም ምክትል በመሆን የኢሕዲሪ ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩት ሌ/ኮሎኔል ፍሰሐ ደስታ፣ ኢሕአዴግ አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ ለ20 ዓመታት ያህል በእስር ቆይተዋል። ቢቢሲ ከቤተሰባቸው ለመረዳት እንደቻለው ሌ/ኮሎኔል ፍሰሐ የልብ ሕመም የነበረባቸው ሲሆን ለዚህም በአገር ውስጥና በውጪ ክትትል ሲያደርጉ ቆይተዋል። ባለትዳርና የአንድ ልጅ አባት የነበሩት ፍሰሐ ሕይወታቸው ያለፈው አርብ ሚያዚያ 28/2014 ዓ. ም. እኩለ ሌሊት አካባቢ ሲሆን የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው እሁድ ሚያዚያ 30/2014 ዓ. ም. በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንደሚፈጸም ተገልጿል። ከእስር ከወጡ በኋላ በሥልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት ስላለፉባቸው ሁኔታዎች የሚተርክ "አብዮቱና ትዝታዬ" የሚል መጽሐፍ ያበረከቱ ሲሆን፣ በዚህም "ደርግ በወሰዳቸው በጎ ዕርምጃዎች እንደምደሰት ሁሉ በማወቅ፣ በድፍረት፣ ባለማወቅና በስህተት ለተፈጸሙት ደግሞ ሙሉ ኃላፊነት በመውሰድ በበኩሌ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እጠይቃለሁ" ብለው ነበር። ሌ/ኮሎኔል ፍሰሐ ከመጀመሪያው መጽሐፋቸው በተጨማሪ ሁለተኛ መጽሐፍ በማዘጋጀት ላይ እንደነበሩ ቤተሰቦቻቸው ለቢቢሲ ገልጸዋል። ትግራይ አድዋ ውስጥ የተወለዱት ሌፍተናንት ኮሎኔል ፍሰሐ፣ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በአደዋ ንግሥተ ሳባ እንዲሁም ሁለተኛ ደረጃን አዲግራት ውስጥ በሚገኘው አግአዚ ትምህርት ቤት ተከታትለዋል። በተጨማሪም አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው ኮተቤ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማሩ ሲሆን፣ ከዚያም በኋላ ወደ ሐረር ጦር ትምህርት ቤት ገብተው ከሰለጠኑ በኋላ በክብር ዘበኛ ውስጥ ገብተው በንጉሡ ቤተ መንግሥት ውስጥ ተመድበው አገልግለዋል። ሌ/ኮሎኔል ፍሰሐ ወደ አሜሪካ በመሄድ ከፍተኛ ወታደራዊ ሥልጠና ወስደዋል። ከዚህ በሻገርም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሕግ ትምህርት ተከታትለዋል። ንጉሡን ከሥልጣን ያስወገደው ሕዝባዊ አብዮት ሲፈነዳና በደርግ አማካይነት ጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ሲመሠረት ከጦር ኃይሉ ተወጣጥተው የአመራርነት ቦታውን ከያዙት የወቅቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት መካከል አንዱ ነበሩ። ከዓመታት ቆይታ በኋላ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲ (ኢሠፓ) እንዲሁም የኢትዮጵያ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኢሕዲሪ) ሲመሠረት የቀድሞው ፕሬዝዳንት መንግሥቱ ኃይለማሪም ምክትል በመሆን የአገሪቱ ሁለተኛ ሰው ለመሆን በቅተው ነበር። ከአማጺያኑ ጋር ለ17 ዓመታት የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ የቆየው አስተዳደራቸው እየተዳከመ መጥቶ ፕሬዝዳንቱ አገር ለቀው ከተሰደዱ በሳምንታት ውስጥ የአማጺያኑ ስብስብ ኢሕአዴግ አዲስ አበባን ሲቆጣጠር የኢሕዲሪ መንግሥት ፍጻሜ ሆነ። ሌ/ኮሎኔል ፍሰሐን ጨምሮ በአገር ውስጥ የተገኙት የቀድሞው መንግሥት ባለሥልጣናት በአገሪቱ ውስጥ በተፈጸሙ ጭፍጨፋዎችና በሰብአዊነት ላይ በተፈጸሙ ወንጀሎች ተከሰው ለዓመታት በተካሄደ የፍርድ ሂደት እስር ተፈርዶባቸዋል። ሌ/ኮሎኔል ፍሰሐ ደስታም ለ20 ዓመታት በእስር ካሳለፉ በኋላ ከ10 ዓመት በፊት በይቅርታ መለቀቃቸው ይታወሳል።
https://www.bbc.com/amharic/news-61361343
0business
ኢትዮጵያን ጨምሮ ባፈለው ዓመት ኢንተርኔት በመዝጋት የከሰሩ ሃገራት
ባፈለው የፈረንጆቹ ዓመት ኢንተርኔት በመዝጋት የከሰሩ ሃገራትን ዝርዝር ይፋ ያደረገ አንድ ጥናት "ዓለም በዚህ ምክንያት 8 ቢሊዮን ዶላር ከስራለች" ብሏል። ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት ኢንተርኔትን በአንድም ሆነ በሌላ ምክንያት የዘጉ ሃገራት ቁጥር ከምን ጊዜውም የላቀ ነው ሲል ኔትብሎክ የተባለው አጥኚ ድርጅት ይፋ አድርጓል። ጥናቱ ላይ እንደተጠቀሰው በተለያዩ ሃገራት 122 ጊዜ ኢንተርኔት የተቋረጠ ሲሆን በጠቅላላ 22 ሺህ ሰዓታትን እነዚህ ሃገራት ያለ ኢንተርኔት አሳልፈዋል ብሏል። ባለፉት 12 ዓመታት ጥናቱ ውስጥ የተካቱት መንግሥታት በሃገር ደረጃ ወይም በክልል ደረጃ ኢንተርኔትን ሆን ብለው አጥፍተዋል፤ ዋነኛው ዓለማው ደግሞ ተጠቃሚውን ፌስቡክ ከመሳሰሉ ከማህበራዊ ድር አምባዎች ለማገድ ነው። ድርጅቱ የኢንተርኔት አዘጋግ ሂደቱን በሁለት ይከፍለዋል። አንደኛው ሙሉ በሙሉ የኢንተርኔቱን ባልቦላ መቁረጥ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ማሕበራዊ ድር-አምባዎችን ከጥቅም ውጭ ማድረግ ነው። ፌስቡክ፣ ዋትስአፕ፣ ትዊተር፣ ዩቲዩብ እና መሰል ድር አምባዎች ቢታገዱም ተጠቃሚዎች 'ቪፒኤን' በመጠቀም ሊያገኟቸው ይችላሉ። ጥናቱ ይፋ ባደረገው መሠረት አብዛኛዎች የኢንተርኔት መቋረጦች ከተቃውሞ እና አለመረጋጋት እንዲሁም ምርጫ ጋር የተያያዙ ናቸው። የባልቦላው መዘጋት በተለይ 'በደሃ' ሃገራት በልማዳዊው ገበያ ላይ ያለው ተፅዕኖ ከፍተኛ መሆኑን ጥናቱ ደርሶበታል። ይህ ማለት ጥፋቱ ጥናቱ ላይ ከተቀመጠው በላይ ሊሆንም ይችላል ማለት ነው። የኢንተርኔት መዘጋቱ የሰው ልጅ የመናገር ነፃነትን የሚገፍ ነው የሚለው ድርጅቱ ኢንተርኔት መዝጋቱ ለበለጠ አመፅ እንደጋበዘ ታዝቤያለሁ ይላል። በዚህ ረገድ መካከለኛው ምስራቅና ሰሜን አፍሪቃ ኢንተርኔት በመዝጋት የሚስተካከላቸው አልተገኝም። ከሰሃራ በታች ያሉ ሃገራት ደግሞ ተከታዩን ደረጃ ይእዛሉ። እስያ በሶስተኛ ደረጃ የምትገኝ ሲሆን የደቡብ አሜሪካ ሃገራት በአራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። ድርጅቱ ኢንተርኔት የዘጉ ሃገራትን ዝርዝር፤ ያጡትን ገንዘብ [በዶላር] እንዲሁም የኢንተርኔት ተጠቃሚዎችን ቁጥር ከዚህ እንደሚከተለው አስቀምጧል። ዚምባብዌ፣ ሞሪታኒያ፣ ፓኪስታን፣ ግብፅ፣ ካዛኪስታን፣ ቤኒን፣ ጋቦን፣ ኤርትራ እና ላይቤሪያ ሌሎች በዝርዝሩ ውስጥ የተካተቱ ሃገራት ናቸው። ከማሕበራዊ ድር-አምባ አንፃር ሲታይ ደግሞ ዋትስአፕ የተሰኘው መልዕክት መላላከያ ብዙ ሃገራት የዘጉት ሆኖ ተመዝግቧል። ፌስቡክ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ፤ ኢንስታግራም ትዊተር እና ዩቲዩብ ተከታትለው ይመጣሉ። ኢራቅ፣ ሱዳን፣ ሕንድ እና ቬንዝዌላ ኢንተርኔት በመዝጋታቸው ምክንያት 1 ቢሊዮንና ከዚያ በላይ ያጡ ሃገራት ሆነው ተመዝግበዋል። ይህም ምጣኔ ሃብታቸው ላይ ከፍተኛ ድቀት እንዳደረሰ የድርጀቱ መረጀ ያመለክታል። አራቱም ሃገራት ሕዝባዊ ተቃውሞን ለማብረድ ሲሉ ነው የኢንተርኔታቸውን ባልቦላ የቆረጡት። ኢትዮጵያ ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት ኢንተርኔቷን ለ274 ሰዓታት ዘግታለች። በተለይ ወርሃ ሰኔ ላይ [አማራ ክልል እና አዲስ አበባ ላይ ከተከሰተው የባለሥልጣናት ግድያ ጋር በተያያዘ] ኢንተርኔት በሃገሪቱ ለተወሰኑ ቀናት ሙሉ በሙሉ ተቋርጦ ነበር። ከዚያ ባለፈ ሃገር አቀፍ የተማሪዎች ፈተና በሚኖርበት ወቅት ኢንተርኔት በበርካታ የሃገሪቱ ክፍሎች ተቋርጧል። ነገር ግን ኢንተርኔቱን የሚያስተዳድረው ኢትዮ ቴሌኮምም ሆነ መንገሥት ይፋዊ መግለጫ አልሰጡም። ከሃገር አቀፍ የኢንተርኔት መቋረጦች ባለፈ በተመረጡ አካባቢዎችም ተጠቃሚዎች ለቀናት ከኢንተርኔት ጋር ተቆራርጠው ቆይተዋል። ይህም ኢትዮጵያን ባላፈው ዓመት ብቻ 2 ቢሊዮን ብር ገደማ አሳጥቷታል።
ኢትዮጵያን ጨምሮ ባፈለው ዓመት ኢንተርኔት በመዝጋት የከሰሩ ሃገራት ባፈለው የፈረንጆቹ ዓመት ኢንተርኔት በመዝጋት የከሰሩ ሃገራትን ዝርዝር ይፋ ያደረገ አንድ ጥናት "ዓለም በዚህ ምክንያት 8 ቢሊዮን ዶላር ከስራለች" ብሏል። ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት ኢንተርኔትን በአንድም ሆነ በሌላ ምክንያት የዘጉ ሃገራት ቁጥር ከምን ጊዜውም የላቀ ነው ሲል ኔትብሎክ የተባለው አጥኚ ድርጅት ይፋ አድርጓል። ጥናቱ ላይ እንደተጠቀሰው በተለያዩ ሃገራት 122 ጊዜ ኢንተርኔት የተቋረጠ ሲሆን በጠቅላላ 22 ሺህ ሰዓታትን እነዚህ ሃገራት ያለ ኢንተርኔት አሳልፈዋል ብሏል። ባለፉት 12 ዓመታት ጥናቱ ውስጥ የተካቱት መንግሥታት በሃገር ደረጃ ወይም በክልል ደረጃ ኢንተርኔትን ሆን ብለው አጥፍተዋል፤ ዋነኛው ዓለማው ደግሞ ተጠቃሚውን ፌስቡክ ከመሳሰሉ ከማህበራዊ ድር አምባዎች ለማገድ ነው። ድርጅቱ የኢንተርኔት አዘጋግ ሂደቱን በሁለት ይከፍለዋል። አንደኛው ሙሉ በሙሉ የኢንተርኔቱን ባልቦላ መቁረጥ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ማሕበራዊ ድር-አምባዎችን ከጥቅም ውጭ ማድረግ ነው። ፌስቡክ፣ ዋትስአፕ፣ ትዊተር፣ ዩቲዩብ እና መሰል ድር አምባዎች ቢታገዱም ተጠቃሚዎች 'ቪፒኤን' በመጠቀም ሊያገኟቸው ይችላሉ። ጥናቱ ይፋ ባደረገው መሠረት አብዛኛዎች የኢንተርኔት መቋረጦች ከተቃውሞ እና አለመረጋጋት እንዲሁም ምርጫ ጋር የተያያዙ ናቸው። የባልቦላው መዘጋት በተለይ 'በደሃ' ሃገራት በልማዳዊው ገበያ ላይ ያለው ተፅዕኖ ከፍተኛ መሆኑን ጥናቱ ደርሶበታል። ይህ ማለት ጥፋቱ ጥናቱ ላይ ከተቀመጠው በላይ ሊሆንም ይችላል ማለት ነው። የኢንተርኔት መዘጋቱ የሰው ልጅ የመናገር ነፃነትን የሚገፍ ነው የሚለው ድርጅቱ ኢንተርኔት መዝጋቱ ለበለጠ አመፅ እንደጋበዘ ታዝቤያለሁ ይላል። በዚህ ረገድ መካከለኛው ምስራቅና ሰሜን አፍሪቃ ኢንተርኔት በመዝጋት የሚስተካከላቸው አልተገኝም። ከሰሃራ በታች ያሉ ሃገራት ደግሞ ተከታዩን ደረጃ ይእዛሉ። እስያ በሶስተኛ ደረጃ የምትገኝ ሲሆን የደቡብ አሜሪካ ሃገራት በአራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። ድርጅቱ ኢንተርኔት የዘጉ ሃገራትን ዝርዝር፤ ያጡትን ገንዘብ [በዶላር] እንዲሁም የኢንተርኔት ተጠቃሚዎችን ቁጥር ከዚህ እንደሚከተለው አስቀምጧል። ዚምባብዌ፣ ሞሪታኒያ፣ ፓኪስታን፣ ግብፅ፣ ካዛኪስታን፣ ቤኒን፣ ጋቦን፣ ኤርትራ እና ላይቤሪያ ሌሎች በዝርዝሩ ውስጥ የተካተቱ ሃገራት ናቸው። ከማሕበራዊ ድር-አምባ አንፃር ሲታይ ደግሞ ዋትስአፕ የተሰኘው መልዕክት መላላከያ ብዙ ሃገራት የዘጉት ሆኖ ተመዝግቧል። ፌስቡክ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ፤ ኢንስታግራም ትዊተር እና ዩቲዩብ ተከታትለው ይመጣሉ። ኢራቅ፣ ሱዳን፣ ሕንድ እና ቬንዝዌላ ኢንተርኔት በመዝጋታቸው ምክንያት 1 ቢሊዮንና ከዚያ በላይ ያጡ ሃገራት ሆነው ተመዝግበዋል። ይህም ምጣኔ ሃብታቸው ላይ ከፍተኛ ድቀት እንዳደረሰ የድርጀቱ መረጀ ያመለክታል። አራቱም ሃገራት ሕዝባዊ ተቃውሞን ለማብረድ ሲሉ ነው የኢንተርኔታቸውን ባልቦላ የቆረጡት። ኢትዮጵያ ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት ኢንተርኔቷን ለ274 ሰዓታት ዘግታለች። በተለይ ወርሃ ሰኔ ላይ [አማራ ክልል እና አዲስ አበባ ላይ ከተከሰተው የባለሥልጣናት ግድያ ጋር በተያያዘ] ኢንተርኔት በሃገሪቱ ለተወሰኑ ቀናት ሙሉ በሙሉ ተቋርጦ ነበር። ከዚያ ባለፈ ሃገር አቀፍ የተማሪዎች ፈተና በሚኖርበት ወቅት ኢንተርኔት በበርካታ የሃገሪቱ ክፍሎች ተቋርጧል። ነገር ግን ኢንተርኔቱን የሚያስተዳድረው ኢትዮ ቴሌኮምም ሆነ መንገሥት ይፋዊ መግለጫ አልሰጡም። ከሃገር አቀፍ የኢንተርኔት መቋረጦች ባለፈ በተመረጡ አካባቢዎችም ተጠቃሚዎች ለቀናት ከኢንተርኔት ጋር ተቆራርጠው ቆይተዋል። ይህም ኢትዮጵያን ባላፈው ዓመት ብቻ 2 ቢሊዮን ብር ገደማ አሳጥቷታል።
https://www.bbc.com/amharic/51166093
2health
ኮሮናቫይረስ፡ በኢትዮጵያ ለኮቪድ-19 ጽኑ ህሙማን የኦክስጂንና የቬንትሌተር እጥረት ማጋጠሙ ተነገረ
በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የሚያዙና የጽኑ ህሙማን ህክምናና ክትትል የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ የሰው ሰራሽ መተንፈሻ መሳሪያና የኦክስጂን እጥረት እያጋጠመ መሆኑ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ገለጸ። ተቋሙ በአሁኑ ጊዜ በአገሪቱ ውስጥ በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከዕለት ዕለት በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ በመምጣቱ የባለሙያ ድጋፍና እንክብካቤ የሚሹ ሰዎች ቁጥር "የህክምና ማዕከላት ማስተናገድ ከሚችሉት አቅም በላይ" እየሆነ መምጣቱን ጨምሮ ገልጿል። በዚህም ሳቢያ በኮሮናቫይረስ በጽኑ ታምመው በህክምና ተቋማት ድጋፍ ለማግኘት ለሚመጡ ህሙማን አገልግሎት የሚውሉ "የሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መሳሪያ (ቬንትሌተር) እና የኦክስጅን እጥረት እያጋጠመ ነው" ሲል ገልጿል። በኢትዮጵያ እስከ ትናንት እሁድ ድረስ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 175,467 ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ፣ 2,550 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው አልፏል። የኮሮናቫይረስ የመተንፈሻ አካላትን በተለይም ሳንባን የሚያጠቃ ሲሆን በበሽታው ክፉኛ ለተጠቁ ጽኑ ህሙማን ሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መርጃ (ቬንትሌተር) እና ኦክስጂን ህይወታቸውን ለመታደግ ለሚደረገው ጥረት በእጅጉ አስፈላጊ ናቸው። በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ በጽኑ የታመሙ ሰዎችን ህይወት ለመታደግ በአሁኑ ወቅት በአገልግሎት ላይ የሚገኙት የሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መርጃ ቬንትሌተሮች ቁጥር ከ500 ብዙም የበለጠ አይደለም። ስለዚህም በበሽታው የሚያዙት ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩ የህክምና ድጋፍ የሚፈልጉ ሰዎችን መጠን በመጨመር በህክምና ተቋማቱ ላይና በባለሙያዎች ላይ ጫናን በመፍጠር ከአቅም በላይ ሊሆን እንደሚችል ተሰግቷል። በተለይም በወረርሽኙ በጽኑ ታምመው የቬንትሌተርና የኦክስጂን ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ህሙማን ቁጥር እየጨመረ በመሆኑ የነፍስ አድን አገልግሎቱን መስጠት ከማይቻልበት ደረጃ ላይ ከደረሰ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ሊያሻቅብ ይችላል። በአሁኑ ወቅት በመላው አገሪቱ በየዕለቱ የሚመዘገበው በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን የገለጸው ኢንስቲትዩቱ፤ ከዚሁ ጋር ተያይዞም በወረርሽኙ ሳቢያ የጽኑ ህሙማን የህክምና አገልግሎት የሚፈልጉ ህሙማንና ህይወታቸውን የሚያጡ ሰዎች ቁጥር "አስደንጋጭ በሆነ ሁኔታ እየጨመረ ይገኛል" ይገኛል ብሏል። የኮሮናቫይረስ በኢትዮጵያ ውስጥ መገኘቱ ይፋ ከተደረገ ባለፈው ቅዳሜ አንድ ዓመት የሞላው ሲሆን፣ በዚህ ጊዜ እስካሁን ድረስ በወረርሽኙ ሳቢያ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 2550 ደርሷል። በኮቪድ-19 ለሞት ከተዳረጉት ሰዎች መካከል 74 በመቶ የሚሆኑት በህክምና ማዕከላት ውስጥ ሲሆን 24 በመቶዎቹ ደግሞ በአስክሬን ላይ ከተወሰደ ናሙና ላይ በተደረገ ምርመራ የተገኘ መሆኑ ተገልጿል። ኢንስቲቲዩቱ እንደሚለው ባለፉት ጥቂት ቀናት እየተመዘገበ ያለው የሟቾች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ነው። እስካሁን ድረስ በየዕለቱ ከተመዘገቡት ሞቶች ሁሉ ከፍተኛው በእነዚህ ቀናት ውስጥ ተመዝግቧል። በወረርሽኙ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር በተለያዩ የአገሪቱ ከፍሎች የተመዘገቡ ሲሆን በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ውስጥ የተመዘገበው የሟቾች ቁጥር ከሌሎቹ ቦታዎች አንጻር በእጅጉ ከፍተኛ ነው። በዚህም መሠረት በአዲስ አበባ 1,852 ሰዎች በኮቪድ-19 ሳቢያ ለህልፈት ሲዳረጉ ይህም ከአጠቃላዩ የሟቾች ቁጥር 73 በመቶውን ይይዛል። በተከታይነት በኦሮሚያ ክልል 256 ሰዎች (10 በመቶ)፣ በአማራ ክልል 105 ሰዎች (4 በመቶ)፣ በሲዳማ ክልል 75 ሰዎች (3 በመቶ) የሚሆኑት በበሸውታው ህይወታቸው አልፏል። በየዕለቱ በሚደረገው ምርመራ ቫይረሱ የሚገኝባቸው ሰዎች ቁጥርም በፍጥነት እየጨመረ መሆኑ ተገልጿል። ቬንትሌተር ምንድን ነው? ቬንትሌተር የሰውነታችንን የአተነፋፈስ ሥርዓት ተክቶ የሚሠራ ማሽን ነው። የህሙማን ሳምባ እክል ሲገጥመው ቬንትሌተር የመተንፈስ ተግባር ስለሚያከናውን ህይወትን ይታደጋል። በኮቪድ-19 በጽኑ ከታመሙ ስድስት ህሙማን መካከል ቢያንስ አንዱ የመተንፈስ ችግር ይገጥመዋል። ይህም የሚሆነው ቫይረሱ ሳምባን ስለሚያውክ ነው። በዚህ ወቅት ቬንትሌተር ከሌለ ግለሰቡን ማዳን አዳጋች ነው። ሁለት ዓይነት የመተንፈሻ መርጃ መሣሪያዎች (ቬንትሌተር) አሉ። አንዱ መካኒካል ቬንትሌተር ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ቱቦ-አልባ ቬንትሌተር ይባላል። መካኒካል ቬንትሌተር የአየር ቱቦ በአፍ በኩል እንዲገባ ተደርጎ ታማሚው ካርቦንዳይኦክሳይድ እንዲያስወጣና ኦክስጂን እንዲያስገባ የሚያደርግ ነው። ቱቦ-አልባው ቬንትሌተር ወይም በእንግሊዝኛው ግን ወደ ሳምባ የሚወርድ ቧንቧ ሳይኖረው አፍና አፍንጫ ላይ በሚደረግ ጭምብል ብቻ የሚሰራ ነው። ቬንትሌተሮቹ ሂሙዲፋየር [እርጥበት የሚፈጥር] ክፍል አላቸው። ይህም ማለት ወደ ሰውነት የሚገባን ሙቀትና እርጥበት የሚቆጣጠርና ህመምተኛው የሚተነፍሰው አየር ለሰውነት ሙቀት ተስማሚ በሆነ መጠን እንዲሆን የሚያደርግ ነው። በዚህ ወቅት በሽተኞች የመተንፈሻ አካል ጡንቻዎች ዘና እንዲሉላቸው የሚያስችል መድኃኒት ይሰጣቸዋል። መጠነኛ የኮሮናቫይረስ ምልክቶችን የሚያሳዩ በሽተኞች ግን የፊት ጭምብል ቬንትሌተር ብቻ ሊሰጣቸው ይችላል። ይህም በአፍና አፍንጫ በኩል በግፊት አየር ወደ ሳምባ እንዲገባ የማድረግ ዘዴ ነው።
ኮሮናቫይረስ፡ በኢትዮጵያ ለኮቪድ-19 ጽኑ ህሙማን የኦክስጂንና የቬንትሌተር እጥረት ማጋጠሙ ተነገረ በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የሚያዙና የጽኑ ህሙማን ህክምናና ክትትል የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ የሰው ሰራሽ መተንፈሻ መሳሪያና የኦክስጂን እጥረት እያጋጠመ መሆኑ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ገለጸ። ተቋሙ በአሁኑ ጊዜ በአገሪቱ ውስጥ በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከዕለት ዕለት በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ በመምጣቱ የባለሙያ ድጋፍና እንክብካቤ የሚሹ ሰዎች ቁጥር "የህክምና ማዕከላት ማስተናገድ ከሚችሉት አቅም በላይ" እየሆነ መምጣቱን ጨምሮ ገልጿል። በዚህም ሳቢያ በኮሮናቫይረስ በጽኑ ታምመው በህክምና ተቋማት ድጋፍ ለማግኘት ለሚመጡ ህሙማን አገልግሎት የሚውሉ "የሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መሳሪያ (ቬንትሌተር) እና የኦክስጅን እጥረት እያጋጠመ ነው" ሲል ገልጿል። በኢትዮጵያ እስከ ትናንት እሁድ ድረስ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 175,467 ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ፣ 2,550 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው አልፏል። የኮሮናቫይረስ የመተንፈሻ አካላትን በተለይም ሳንባን የሚያጠቃ ሲሆን በበሽታው ክፉኛ ለተጠቁ ጽኑ ህሙማን ሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መርጃ (ቬንትሌተር) እና ኦክስጂን ህይወታቸውን ለመታደግ ለሚደረገው ጥረት በእጅጉ አስፈላጊ ናቸው። በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ በጽኑ የታመሙ ሰዎችን ህይወት ለመታደግ በአሁኑ ወቅት በአገልግሎት ላይ የሚገኙት የሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መርጃ ቬንትሌተሮች ቁጥር ከ500 ብዙም የበለጠ አይደለም። ስለዚህም በበሽታው የሚያዙት ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩ የህክምና ድጋፍ የሚፈልጉ ሰዎችን መጠን በመጨመር በህክምና ተቋማቱ ላይና በባለሙያዎች ላይ ጫናን በመፍጠር ከአቅም በላይ ሊሆን እንደሚችል ተሰግቷል። በተለይም በወረርሽኙ በጽኑ ታምመው የቬንትሌተርና የኦክስጂን ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ህሙማን ቁጥር እየጨመረ በመሆኑ የነፍስ አድን አገልግሎቱን መስጠት ከማይቻልበት ደረጃ ላይ ከደረሰ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ሊያሻቅብ ይችላል። በአሁኑ ወቅት በመላው አገሪቱ በየዕለቱ የሚመዘገበው በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን የገለጸው ኢንስቲትዩቱ፤ ከዚሁ ጋር ተያይዞም በወረርሽኙ ሳቢያ የጽኑ ህሙማን የህክምና አገልግሎት የሚፈልጉ ህሙማንና ህይወታቸውን የሚያጡ ሰዎች ቁጥር "አስደንጋጭ በሆነ ሁኔታ እየጨመረ ይገኛል" ይገኛል ብሏል። የኮሮናቫይረስ በኢትዮጵያ ውስጥ መገኘቱ ይፋ ከተደረገ ባለፈው ቅዳሜ አንድ ዓመት የሞላው ሲሆን፣ በዚህ ጊዜ እስካሁን ድረስ በወረርሽኙ ሳቢያ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 2550 ደርሷል። በኮቪድ-19 ለሞት ከተዳረጉት ሰዎች መካከል 74 በመቶ የሚሆኑት በህክምና ማዕከላት ውስጥ ሲሆን 24 በመቶዎቹ ደግሞ በአስክሬን ላይ ከተወሰደ ናሙና ላይ በተደረገ ምርመራ የተገኘ መሆኑ ተገልጿል። ኢንስቲቲዩቱ እንደሚለው ባለፉት ጥቂት ቀናት እየተመዘገበ ያለው የሟቾች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ነው። እስካሁን ድረስ በየዕለቱ ከተመዘገቡት ሞቶች ሁሉ ከፍተኛው በእነዚህ ቀናት ውስጥ ተመዝግቧል። በወረርሽኙ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር በተለያዩ የአገሪቱ ከፍሎች የተመዘገቡ ሲሆን በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ውስጥ የተመዘገበው የሟቾች ቁጥር ከሌሎቹ ቦታዎች አንጻር በእጅጉ ከፍተኛ ነው። በዚህም መሠረት በአዲስ አበባ 1,852 ሰዎች በኮቪድ-19 ሳቢያ ለህልፈት ሲዳረጉ ይህም ከአጠቃላዩ የሟቾች ቁጥር 73 በመቶውን ይይዛል። በተከታይነት በኦሮሚያ ክልል 256 ሰዎች (10 በመቶ)፣ በአማራ ክልል 105 ሰዎች (4 በመቶ)፣ በሲዳማ ክልል 75 ሰዎች (3 በመቶ) የሚሆኑት በበሸውታው ህይወታቸው አልፏል። በየዕለቱ በሚደረገው ምርመራ ቫይረሱ የሚገኝባቸው ሰዎች ቁጥርም በፍጥነት እየጨመረ መሆኑ ተገልጿል። ቬንትሌተር ምንድን ነው? ቬንትሌተር የሰውነታችንን የአተነፋፈስ ሥርዓት ተክቶ የሚሠራ ማሽን ነው። የህሙማን ሳምባ እክል ሲገጥመው ቬንትሌተር የመተንፈስ ተግባር ስለሚያከናውን ህይወትን ይታደጋል። በኮቪድ-19 በጽኑ ከታመሙ ስድስት ህሙማን መካከል ቢያንስ አንዱ የመተንፈስ ችግር ይገጥመዋል። ይህም የሚሆነው ቫይረሱ ሳምባን ስለሚያውክ ነው። በዚህ ወቅት ቬንትሌተር ከሌለ ግለሰቡን ማዳን አዳጋች ነው። ሁለት ዓይነት የመተንፈሻ መርጃ መሣሪያዎች (ቬንትሌተር) አሉ። አንዱ መካኒካል ቬንትሌተር ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ቱቦ-አልባ ቬንትሌተር ይባላል። መካኒካል ቬንትሌተር የአየር ቱቦ በአፍ በኩል እንዲገባ ተደርጎ ታማሚው ካርቦንዳይኦክሳይድ እንዲያስወጣና ኦክስጂን እንዲያስገባ የሚያደርግ ነው። ቱቦ-አልባው ቬንትሌተር ወይም በእንግሊዝኛው ግን ወደ ሳምባ የሚወርድ ቧንቧ ሳይኖረው አፍና አፍንጫ ላይ በሚደረግ ጭምብል ብቻ የሚሰራ ነው። ቬንትሌተሮቹ ሂሙዲፋየር [እርጥበት የሚፈጥር] ክፍል አላቸው። ይህም ማለት ወደ ሰውነት የሚገባን ሙቀትና እርጥበት የሚቆጣጠርና ህመምተኛው የሚተነፍሰው አየር ለሰውነት ሙቀት ተስማሚ በሆነ መጠን እንዲሆን የሚያደርግ ነው። በዚህ ወቅት በሽተኞች የመተንፈሻ አካል ጡንቻዎች ዘና እንዲሉላቸው የሚያስችል መድኃኒት ይሰጣቸዋል። መጠነኛ የኮሮናቫይረስ ምልክቶችን የሚያሳዩ በሽተኞች ግን የፊት ጭምብል ቬንትሌተር ብቻ ሊሰጣቸው ይችላል። ይህም በአፍና አፍንጫ በኩል በግፊት አየር ወደ ሳምባ እንዲገባ የማድረግ ዘዴ ነው።
https://www.bbc.com/amharic/news-56359828
5sports
ብሔራዊ ቡድኑን ወደ የአፍሪካ መድረክ ለመመለስ የሚመኘው ሽመልስ በቀለ
ትውልድ እና እድገቱ አዋሳ ከተማ ኮረም ሰፈር ነው። እንደ አብዛኛው የኢትዮጵያ ልጆች ኳስ እና ሽመልስ በቀለን ያስተዋዋቃቸው ትምህርት ቤት ነው። በእረፍት ጊዜ ባለችው ትንሽ ክፍተት ኳስን መጫወት የጀመረው ሽመልስ ወደ ሰፈሩ ሲመለስም ከሰፈር ጓደኞቹ ጋር ከማታ ጥናት በፊት ያለችውን የ አንድ ሰዓት ክፍተት ኳስ በመጫወት ያሳልፋ ነበር። ዛሬ ላይ በግብጽ ፕሪሚየር ሊግ ተወዳዳሪ ለሆነው ሚሰረ ሌል ማካሳ እየተጫወተ ይገኛል። ዛሬ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ለማለፍ ከማደጋስካር አቻዋ ለምታደርገው ጨዋታ ቁልፍ ሚና ከሚኖራቸው መካከል አንዱ የሆነው እግር ኳሰኛው ሽመልስ በቀለ ስለ 'ፕሮፌሽናል' የእግር ኳስ ሕይወቱ ለቢቢሲ የሚከተለውን አጋርቷል። በግብፅ ሊግ የመጫወት እድል ግብፅ ሄጄ የመጫወት እድል የተፈጠረልኝ፤ በቅድሚያ ሊቢያ እና ሱዳን ሄጄ የነበረኝ አጭር ቆይታ ብሎም በኢትዮጵያ ውስጥ የነበሩኝ እንቅስቃሴዎች ናቸው። በሱዳን ለስድስት ወር ያክል ተጫውቼ ነበር። ብሔራዊ ቡድን ውስጥ ለ ሁለት ወር ያክል ዝግጅት ላይ እያለሁ አሁን ያለው ወኪሌ ቪዲዮዎችን እንድልክለት ይጠይቀኝ ነበር። እኔም በውጪ የነበረኝን እና በአገር ውስጥ የነበሩኝን ቆይታ የሚያሳዩ ምስሎች ላኩለት። በተጨማሪም አጭር ግዜ ቢሆንም ወጥቼ የመጫወት ሪከርድ ስላለኝ አሱ ያገዘኝ ይመስለኛል። ፔትሮጅክት የሚባል ክለብ ቪዲዮዎቹን ተመልክቶ ነበር። አሰልጣኞቹ ደስተኛ ነበሩ። በተለይ ምክትል አሰልጣኙ የበለጠ በእኔ ደስተኛ ነበር። ከቪዲዮ በተሸለ በአካል መጥተው ለማየት ተነጋገሩ እኔም ደስተኛ ነበርኩ። አዲስ አበባ ላይ ከአልጄሪያ ጋር በነበረን ጨዋታ መጥተው ተመለከቱኝ፤ ምንም እንኳን ሁለት ለአንድ ብንሸነፍም በእንቅስቃሴዬ ደስተኛ ስለነበሩ ለክለቡ ለመፈረም እድሉን አገኘሁ ማለት ነው። በፕሮፌሽናል የኳስ ህይወትህ ወርቃማ የምትለው ጊዜ የቱ ነው? በፕሮፌሽናል የእግር ኳስ ህይወቴ ወርቃማ ብዬ የማስበው ከሁለት አመታት በፊት ፔትሮጄት የነበርኩበት ነው። ይህም በእግር ኳስ ህይወቴ አምበል ሆኜ ቡድን መርቼ አላውቅም ነበር። በወቅቱ አምበል ሁኜ ነበር። ይህ ከአገር ወጥቼ ለመጀመሪያ ክለቤ ፔትሮጄት መሪ መሆኔ ለእኔ ትልቅ ነገር ነው። የብሔራዊ ቡድኑን አቋም እንዴት አገኘኸው? የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አቋም ከዓመት ዓመት ልዩነት አለው። እኔ በሄድኩበት ግዜ በተለይ በመጨረሻው ዓመት በፕሪሚየር ሊጉ 18 ጠንካራ ክለቦች ነበሩ። በዚህ ዓመት እንደሚታወቀው 13 ክለቦች ነው ያሉት። ይሄ በራሱ በብሔራዊ ቡድኑ አቋም ላይ የራሱ ጫና አለው። ነገር ግን አሁን ላይ ሊጋችን በቀጥታ ለዓለም መታየቱ [በዲኤስቲቪ አማካኝነት] ደግሞ የራሱ የሆነ በጎ ነገር ያመጣል ብዬ አስባለሁ። እግር ኳስና የኮሮናቫይረስ እንዴት እየሄዱ ነው? ኮሮናቫይረስ ከመጣ በኋላ ፊፋ ባወጣው ሕግ መሰረት ሁል ጊዜ ጨዋታ ሲኖረን ከሁለት ቀን በፊት ምርመራ እናደርጋለን። ኮሮናቫይረስ ያለበት ሰው አይጫወትም። ይሄ በኢትዮጵያም ተመሳሳይ ነው። ለአፍሪካ ዋንጫ እየተዘጋጃችሁ ነው። ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ዋንጫ ካለፈች ዘጠኝ ዓመት አለፈ። አሁን ያለው ቡድን የሚያልፍ ይመስልሃል? አዎ ለአፍሪካ ዋንጫ እናልፋለን ብዬ አምናለሁ። ባፈው ሳምንት ከማላዊ ጋር ያካሄድነው የወዳጅነት ጨዋታ በብቃት ነው የተወጣነው። ጎበዝ ተጫዋቾች ከተለያዩ ክለቦች ወደ ብሔራዊ ቡድኑ ተጠርተዋል። ሁሉም ተጫዋች ጥሩ አቋም ላይ ነው ያለው። ያለፈውን ሳምንት ጨዋታ በብቃት እንደጨረስነው ሁሉ ከማዳጋስካር ጋር የምናደርገውን ጨዋታም በድል እንወጣዋለን። ለዚህም ምክንያቱ አሪፍ ተጫዋቾች እና አሪፍ አሰልጣኞች ስላሉን ነው። ስለዚህ እነዚህን በድል ከቋጨን ወደ አፍሪካ ዋንጫ የማናልፍበት ምን ምክንያት አለ? ያኔ አንተ የነበርክበት ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ሲያልፍ በአገሪቱ የነበረው ስሜት እንዴት ታስታውሰዋለህ? ባለፉት ዘጠኝ ዓመታት ምንም የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ተሳትፎ አላደረግንም። ይሄ በጣም ረጅም ጊዜ ነው። አሁን ግን ወደ 10ኛ ዓመት ከመግባታችን በፊት እኛ ቡድኑን አሳልፈን ያኔ እኛ የነበረንን ስሜት ድጋሚ ለሁለተኛ እንዲሰማን እፈልጋለሁ። የዚያን ጊዜ ለአፍሪካ ዋንጫ ካለፈው ቡድን ውስጥ አሁን ያለነው ሦስት ተጫዋቾች ብቻ ነን። እኛ ያለፍንበትን ስሜት አሁን ያሉት አዳዲስ ልጆች እንዲሰማቸው እንፈልጋለን። እሱ ጊዜ ሲነሳ በብሔራዊ ቡድኑ ውስጥ ተፈጥሮ ያለፈው ከፍተኛ መነቃቃት እና ደስታ ይታወሰኛል። ያ ስሜት እንዲደገም እፈልጋለሁ። ሕዝቡ ጋር የነበረው ስሜት ከባድ ነበር። ብዙ ነገሩን ትቶ ያኔ ኳስ ለመመለከት እና ለአገሩም የነበረው ትልቅ ስሜት ያንጸባርቅ ነበር። ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፋችን የፈጠረው ደስታ በጣም ትልቅ ነበር። አገራችን አሁን ካለችበት ሁኔታ አንጻር ያ ስሜት እንደገና እንዲመጣ እንፈልጋለን። ከእግዚአብሔር ጋር ለአፍሪካ ዋንጫ የምናልፍ ከሆነ ሁሉንም ነገር የምናስረሳበት ጊዜ ይመጣል ብዬ አስባለሁ። በፖለቲካ ምክንያት ሁሉም ቦታ ጭንቀት ነው የሚሰማው፤ ምንም ሰላም የለም። ሕዝቡ ሰላሙን እንዲያገኝ እና ያኔ የነበረው የደስታ ስሜት እንዲመጣ እፈልጋለሁ። በብሔራዊ ቡድኑ ውስጥ አዲስ እየመጡ ካሉ ጎበዝ ተጫዋቾች ውስጥ አንዱ አቡበከር ናስር ተደጋግሞ ስሙ ይነሳል። ከእሱ ጋር ተጣምሮ መጫወትን እንዴት አገኘኸው? አቡበከር ናስር እና እኔ አሁን በብሔራዊ ቡድን ውስጥ አብረን የመጫወት እድል አግኝተናል። በእኔ አይን ባጭሩ ምርጡ ተጫዋች ነው። ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም። ጎበዝ ተጫዋች ነው። ልጁ ገና 21 ዓመቱ ነው፤ ትልቅ ደረጃ መድረስ የሚችል ነው። ከዚህ በኋላ ራሱን አጠንክሮ እና ታግሶ የሚሰራ ከሆነ የሚያሳየው ብቃት ተስፋ ያሳድራል። ራሱን ወደ ላይ ሳያደርግ የሚጫወት ልጅ ነው። እያደርም እኔ ካለሁበት ደረጃ የበለጠ ትልቅ ቦታ ላይ መድረስ የሚችል ልጅ ነው። የኳስ ተንታኞች የኢትዮጵያ ተጫዋቾች እድል አጥተው እንጂ የቴክኒክ ብቃት አላቸው ይላሉ። አንተ ከአገር ወጥተህ ስትጫወት ምን ታዘብክ? አዎ በቴክኒክ በኩል ጥሩ ተጫዋቾች አሉን ከኳስ ጋር የተያያዙ ብዙ እድሎች ግን የሉም። ኢትዮጵያ ውስጥ በጣም ብዙ ተሰጥኦ ያላቸው አግር ኳስ የሚችሉ ምርጥ ልጆች አሉ። ያሰልጣኝ ችግር፣ የቁሳቁስ ችግር እና የመሳሰሉት ነው ጎልተው እንዳይወጡ ያደረጋቸው። እነዚህ እድል ቢሰጣቸው የኢትዮጵያ ተጫዋቾች በጣም ስኬታማ መሆን እና ወደ ፕሮፌሽናል እግር ኳስ መምጣት ይችላሉ። ሰባት ዓመት በግብጽ ስትኖር ሕዝቡን እንዴት አገኘኸው? ብዙ ግብጻዊያን ጓደኞች አሉኝ። ከክለብ አጋሮቼ ባሻገርም በምኖርበትም አከባቢ ግብጻዊያን ጓደኞች አሉኝ። በደንብ እንነጋገራለን ጥሩ ጓደኝነት አለን። በኳስ ህይወቴ ላይም ምንም ያደረሰብኝ ጫናም የለም። ፖለቲካዊ ጉዳዮችን አንስተን ብዙም ተነጋግረን አናውቅም፤ ያው ግን ሁሉም ለአገሩ አይደለ፤ በተረፈ ግን አሪፍ ባህሪ አላቸው። በታዳጊነት እድሜህ ላይ ብትሆን እና አሁን ባለው እውቀትህ ላይ ሆነህ የእግር ኳስ አካዳሚ ብትገባ የትኛው ክህሎትህን ታሻሽል ነበር? ያለኝን የኳስ ክህሎት ላይ በደንብ ብሰራ ደስ ይለኛል። ነገር ግን ዋናው የአካል ብቃት ጥንካሬ ላይ በጣም አተኩሬ የምሰራ ይመስለኛል። ምክኒያቱም አንድ ሰው ምንም ያህል የቴክኒክ ብቃት ቢኖረው ጥንካሬው ዝቅተኛ ከሆነ መቋቋም ይከብዳል። ምን አልባት ተመልሼ በልጅነት አካዳሚ ብገባ የአካል ጥንካሬዬ ላይ በጣም የምሰራ ይመስለኛል። ብዙ ግዜ የኢትዮጵያ ተጫዋቾች ከአገር ሲወጡ ሳይሳካላቸው በቶሎ ይመለሳሉ። ምክንያቱ ምድነው? የሥነ ልቦና ጉዳይ በእግር ኳስ ህይወት ላይ ከባድ ችግር ነው። ሌላው ከአገር ቤት ይዘን የምንሄደው ብቃትን እዚያ ሄደን ከፍ ማድረግ ያስፈለጋል። እንደዛ ካልሆነ ብቃት ይወርዳል፤ ያኔ ተፈላጊነት ይቀንሳል። ብዙ ትንንሽ የሚመስሉ ከፍተኛ ጫና የሚፈጥሩ ፈተናዎች አሉ። ለምሳሌ ተጫዋች ቤቱ ነው መመገብ ያለበት። እኔ ደግሞ ማብሰል አልችልም ነበር። ከፍተኛ ፈተና ሆኖብኝ ነበር። አገርም ይናፍቃል። እና እመለሳለሁ እያለ የሚጫወት ሰው ደግሞ ወዲያው ተመልሷል። ለሥራ እስከወጣን ድረስ ዋናው የሥነ ልቦና መጠንከር እና ትዕግስተኛ መሆን ለስኬት ቁልፍ ነው። በጣም ብዙ ችግሮች አሉ እነዚያን መቋቋም እና ዲሲፕሊንም ይጠይቃል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በቴሌቪዝን መታየቱ የሚጨምረው ፋይዳ አለ? አሁን ያለው ፕሪሚያር ሊግ በቀጥታ በቴሊቪዥን መቅረቡ ከፍተኛ የመታየት እድል መፍጠሩ አይቀርም። ቅድም እንዳልኩት ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ የኳስ ተሰጥኦ ያላቸው ተጫዋቾች አሉ። ክለቦች ተጫዋቾቻው ወጥተው እንዲጫወቱ ማበረታታት አለባችው። ክለብ ብቻ ሳይሆን ፌዴሬሽኑ የራሱ ኃላፊነት አለበት። ፌዴሬሽኑ ከመንግሥት ጋር ተባብሮ ትልቅ ነገር መስራት ይጠበቅበታል። ለምሳሌ ሌሎች አገራት ለተጫዋቾቻቸው ነፃ ቪዛ ስለሚያመቻቹ ሄደው ይሞክራሉ። ብዙ ግንኙነት ማድረግ እና ከሌሎች የአፍሪካ አገራት ጋር መነጋገር አለበት። ባለሞያዎች እንደሚሉት አንድ ቡድን ከተገነባ ከ 4 እስከ 10 ዓመት ዋና ቡድን ውስጥ ያሉ ሰዎች ሳይቀያየሩ በተመሳሳይ ብቃት መቀጠል ይችላል ይላሉ። ያኔ ለአፍሪካ ዋንጫ ያለፈው ቡድን ወዲያውኑ ለምን ደከመ? ወይስ ያኔ ለአፍሪካ ዋንጫ ያለፋችሁት በአጋጣሚ ነበር? ጠንካራ ክለብ ያለመኖሩ ነው ብሔራዊ ቡድኑን ያደከመው። ቡና እና ጊዮርጊስን ጨምሮ ብዙ ጠንካራ የክልል ክለቦች ነበሩ። አሪፍ ብሔራዊ ቡድን የተሰራው በዕድል ሳይሆን በጥንካሬ ነው። ተጫዋቾችም በትንሽ ነገር እንሸወዳለን። ትንሽ ድል ያታልለናል። በዚያ ውስጥ እንጠፋለን። ተጫዋቾች ትንሽ ድል ስናገኝ ብዙ ነገር የሰራን ይመስለናል። የዓለም ዋንጫን ደጋግመው የወሰዱት እንደ ጀርመን እና ብራዚል እንኳን በዚያው ነው ጠንክረው የሚቀጥሉት።
ብሔራዊ ቡድኑን ወደ የአፍሪካ መድረክ ለመመለስ የሚመኘው ሽመልስ በቀለ ትውልድ እና እድገቱ አዋሳ ከተማ ኮረም ሰፈር ነው። እንደ አብዛኛው የኢትዮጵያ ልጆች ኳስ እና ሽመልስ በቀለን ያስተዋዋቃቸው ትምህርት ቤት ነው። በእረፍት ጊዜ ባለችው ትንሽ ክፍተት ኳስን መጫወት የጀመረው ሽመልስ ወደ ሰፈሩ ሲመለስም ከሰፈር ጓደኞቹ ጋር ከማታ ጥናት በፊት ያለችውን የ አንድ ሰዓት ክፍተት ኳስ በመጫወት ያሳልፋ ነበር። ዛሬ ላይ በግብጽ ፕሪሚየር ሊግ ተወዳዳሪ ለሆነው ሚሰረ ሌል ማካሳ እየተጫወተ ይገኛል። ዛሬ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ለማለፍ ከማደጋስካር አቻዋ ለምታደርገው ጨዋታ ቁልፍ ሚና ከሚኖራቸው መካከል አንዱ የሆነው እግር ኳሰኛው ሽመልስ በቀለ ስለ 'ፕሮፌሽናል' የእግር ኳስ ሕይወቱ ለቢቢሲ የሚከተለውን አጋርቷል። በግብፅ ሊግ የመጫወት እድል ግብፅ ሄጄ የመጫወት እድል የተፈጠረልኝ፤ በቅድሚያ ሊቢያ እና ሱዳን ሄጄ የነበረኝ አጭር ቆይታ ብሎም በኢትዮጵያ ውስጥ የነበሩኝ እንቅስቃሴዎች ናቸው። በሱዳን ለስድስት ወር ያክል ተጫውቼ ነበር። ብሔራዊ ቡድን ውስጥ ለ ሁለት ወር ያክል ዝግጅት ላይ እያለሁ አሁን ያለው ወኪሌ ቪዲዮዎችን እንድልክለት ይጠይቀኝ ነበር። እኔም በውጪ የነበረኝን እና በአገር ውስጥ የነበሩኝን ቆይታ የሚያሳዩ ምስሎች ላኩለት። በተጨማሪም አጭር ግዜ ቢሆንም ወጥቼ የመጫወት ሪከርድ ስላለኝ አሱ ያገዘኝ ይመስለኛል። ፔትሮጅክት የሚባል ክለብ ቪዲዮዎቹን ተመልክቶ ነበር። አሰልጣኞቹ ደስተኛ ነበሩ። በተለይ ምክትል አሰልጣኙ የበለጠ በእኔ ደስተኛ ነበር። ከቪዲዮ በተሸለ በአካል መጥተው ለማየት ተነጋገሩ እኔም ደስተኛ ነበርኩ። አዲስ አበባ ላይ ከአልጄሪያ ጋር በነበረን ጨዋታ መጥተው ተመለከቱኝ፤ ምንም እንኳን ሁለት ለአንድ ብንሸነፍም በእንቅስቃሴዬ ደስተኛ ስለነበሩ ለክለቡ ለመፈረም እድሉን አገኘሁ ማለት ነው። በፕሮፌሽናል የኳስ ህይወትህ ወርቃማ የምትለው ጊዜ የቱ ነው? በፕሮፌሽናል የእግር ኳስ ህይወቴ ወርቃማ ብዬ የማስበው ከሁለት አመታት በፊት ፔትሮጄት የነበርኩበት ነው። ይህም በእግር ኳስ ህይወቴ አምበል ሆኜ ቡድን መርቼ አላውቅም ነበር። በወቅቱ አምበል ሁኜ ነበር። ይህ ከአገር ወጥቼ ለመጀመሪያ ክለቤ ፔትሮጄት መሪ መሆኔ ለእኔ ትልቅ ነገር ነው። የብሔራዊ ቡድኑን አቋም እንዴት አገኘኸው? የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አቋም ከዓመት ዓመት ልዩነት አለው። እኔ በሄድኩበት ግዜ በተለይ በመጨረሻው ዓመት በፕሪሚየር ሊጉ 18 ጠንካራ ክለቦች ነበሩ። በዚህ ዓመት እንደሚታወቀው 13 ክለቦች ነው ያሉት። ይሄ በራሱ በብሔራዊ ቡድኑ አቋም ላይ የራሱ ጫና አለው። ነገር ግን አሁን ላይ ሊጋችን በቀጥታ ለዓለም መታየቱ [በዲኤስቲቪ አማካኝነት] ደግሞ የራሱ የሆነ በጎ ነገር ያመጣል ብዬ አስባለሁ። እግር ኳስና የኮሮናቫይረስ እንዴት እየሄዱ ነው? ኮሮናቫይረስ ከመጣ በኋላ ፊፋ ባወጣው ሕግ መሰረት ሁል ጊዜ ጨዋታ ሲኖረን ከሁለት ቀን በፊት ምርመራ እናደርጋለን። ኮሮናቫይረስ ያለበት ሰው አይጫወትም። ይሄ በኢትዮጵያም ተመሳሳይ ነው። ለአፍሪካ ዋንጫ እየተዘጋጃችሁ ነው። ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ዋንጫ ካለፈች ዘጠኝ ዓመት አለፈ። አሁን ያለው ቡድን የሚያልፍ ይመስልሃል? አዎ ለአፍሪካ ዋንጫ እናልፋለን ብዬ አምናለሁ። ባፈው ሳምንት ከማላዊ ጋር ያካሄድነው የወዳጅነት ጨዋታ በብቃት ነው የተወጣነው። ጎበዝ ተጫዋቾች ከተለያዩ ክለቦች ወደ ብሔራዊ ቡድኑ ተጠርተዋል። ሁሉም ተጫዋች ጥሩ አቋም ላይ ነው ያለው። ያለፈውን ሳምንት ጨዋታ በብቃት እንደጨረስነው ሁሉ ከማዳጋስካር ጋር የምናደርገውን ጨዋታም በድል እንወጣዋለን። ለዚህም ምክንያቱ አሪፍ ተጫዋቾች እና አሪፍ አሰልጣኞች ስላሉን ነው። ስለዚህ እነዚህን በድል ከቋጨን ወደ አፍሪካ ዋንጫ የማናልፍበት ምን ምክንያት አለ? ያኔ አንተ የነበርክበት ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ሲያልፍ በአገሪቱ የነበረው ስሜት እንዴት ታስታውሰዋለህ? ባለፉት ዘጠኝ ዓመታት ምንም የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ተሳትፎ አላደረግንም። ይሄ በጣም ረጅም ጊዜ ነው። አሁን ግን ወደ 10ኛ ዓመት ከመግባታችን በፊት እኛ ቡድኑን አሳልፈን ያኔ እኛ የነበረንን ስሜት ድጋሚ ለሁለተኛ እንዲሰማን እፈልጋለሁ። የዚያን ጊዜ ለአፍሪካ ዋንጫ ካለፈው ቡድን ውስጥ አሁን ያለነው ሦስት ተጫዋቾች ብቻ ነን። እኛ ያለፍንበትን ስሜት አሁን ያሉት አዳዲስ ልጆች እንዲሰማቸው እንፈልጋለን። እሱ ጊዜ ሲነሳ በብሔራዊ ቡድኑ ውስጥ ተፈጥሮ ያለፈው ከፍተኛ መነቃቃት እና ደስታ ይታወሰኛል። ያ ስሜት እንዲደገም እፈልጋለሁ። ሕዝቡ ጋር የነበረው ስሜት ከባድ ነበር። ብዙ ነገሩን ትቶ ያኔ ኳስ ለመመለከት እና ለአገሩም የነበረው ትልቅ ስሜት ያንጸባርቅ ነበር። ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፋችን የፈጠረው ደስታ በጣም ትልቅ ነበር። አገራችን አሁን ካለችበት ሁኔታ አንጻር ያ ስሜት እንደገና እንዲመጣ እንፈልጋለን። ከእግዚአብሔር ጋር ለአፍሪካ ዋንጫ የምናልፍ ከሆነ ሁሉንም ነገር የምናስረሳበት ጊዜ ይመጣል ብዬ አስባለሁ። በፖለቲካ ምክንያት ሁሉም ቦታ ጭንቀት ነው የሚሰማው፤ ምንም ሰላም የለም። ሕዝቡ ሰላሙን እንዲያገኝ እና ያኔ የነበረው የደስታ ስሜት እንዲመጣ እፈልጋለሁ። በብሔራዊ ቡድኑ ውስጥ አዲስ እየመጡ ካሉ ጎበዝ ተጫዋቾች ውስጥ አንዱ አቡበከር ናስር ተደጋግሞ ስሙ ይነሳል። ከእሱ ጋር ተጣምሮ መጫወትን እንዴት አገኘኸው? አቡበከር ናስር እና እኔ አሁን በብሔራዊ ቡድን ውስጥ አብረን የመጫወት እድል አግኝተናል። በእኔ አይን ባጭሩ ምርጡ ተጫዋች ነው። ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም። ጎበዝ ተጫዋች ነው። ልጁ ገና 21 ዓመቱ ነው፤ ትልቅ ደረጃ መድረስ የሚችል ነው። ከዚህ በኋላ ራሱን አጠንክሮ እና ታግሶ የሚሰራ ከሆነ የሚያሳየው ብቃት ተስፋ ያሳድራል። ራሱን ወደ ላይ ሳያደርግ የሚጫወት ልጅ ነው። እያደርም እኔ ካለሁበት ደረጃ የበለጠ ትልቅ ቦታ ላይ መድረስ የሚችል ልጅ ነው። የኳስ ተንታኞች የኢትዮጵያ ተጫዋቾች እድል አጥተው እንጂ የቴክኒክ ብቃት አላቸው ይላሉ። አንተ ከአገር ወጥተህ ስትጫወት ምን ታዘብክ? አዎ በቴክኒክ በኩል ጥሩ ተጫዋቾች አሉን ከኳስ ጋር የተያያዙ ብዙ እድሎች ግን የሉም። ኢትዮጵያ ውስጥ በጣም ብዙ ተሰጥኦ ያላቸው አግር ኳስ የሚችሉ ምርጥ ልጆች አሉ። ያሰልጣኝ ችግር፣ የቁሳቁስ ችግር እና የመሳሰሉት ነው ጎልተው እንዳይወጡ ያደረጋቸው። እነዚህ እድል ቢሰጣቸው የኢትዮጵያ ተጫዋቾች በጣም ስኬታማ መሆን እና ወደ ፕሮፌሽናል እግር ኳስ መምጣት ይችላሉ። ሰባት ዓመት በግብጽ ስትኖር ሕዝቡን እንዴት አገኘኸው? ብዙ ግብጻዊያን ጓደኞች አሉኝ። ከክለብ አጋሮቼ ባሻገርም በምኖርበትም አከባቢ ግብጻዊያን ጓደኞች አሉኝ። በደንብ እንነጋገራለን ጥሩ ጓደኝነት አለን። በኳስ ህይወቴ ላይም ምንም ያደረሰብኝ ጫናም የለም። ፖለቲካዊ ጉዳዮችን አንስተን ብዙም ተነጋግረን አናውቅም፤ ያው ግን ሁሉም ለአገሩ አይደለ፤ በተረፈ ግን አሪፍ ባህሪ አላቸው። በታዳጊነት እድሜህ ላይ ብትሆን እና አሁን ባለው እውቀትህ ላይ ሆነህ የእግር ኳስ አካዳሚ ብትገባ የትኛው ክህሎትህን ታሻሽል ነበር? ያለኝን የኳስ ክህሎት ላይ በደንብ ብሰራ ደስ ይለኛል። ነገር ግን ዋናው የአካል ብቃት ጥንካሬ ላይ በጣም አተኩሬ የምሰራ ይመስለኛል። ምክኒያቱም አንድ ሰው ምንም ያህል የቴክኒክ ብቃት ቢኖረው ጥንካሬው ዝቅተኛ ከሆነ መቋቋም ይከብዳል። ምን አልባት ተመልሼ በልጅነት አካዳሚ ብገባ የአካል ጥንካሬዬ ላይ በጣም የምሰራ ይመስለኛል። ብዙ ግዜ የኢትዮጵያ ተጫዋቾች ከአገር ሲወጡ ሳይሳካላቸው በቶሎ ይመለሳሉ። ምክንያቱ ምድነው? የሥነ ልቦና ጉዳይ በእግር ኳስ ህይወት ላይ ከባድ ችግር ነው። ሌላው ከአገር ቤት ይዘን የምንሄደው ብቃትን እዚያ ሄደን ከፍ ማድረግ ያስፈለጋል። እንደዛ ካልሆነ ብቃት ይወርዳል፤ ያኔ ተፈላጊነት ይቀንሳል። ብዙ ትንንሽ የሚመስሉ ከፍተኛ ጫና የሚፈጥሩ ፈተናዎች አሉ። ለምሳሌ ተጫዋች ቤቱ ነው መመገብ ያለበት። እኔ ደግሞ ማብሰል አልችልም ነበር። ከፍተኛ ፈተና ሆኖብኝ ነበር። አገርም ይናፍቃል። እና እመለሳለሁ እያለ የሚጫወት ሰው ደግሞ ወዲያው ተመልሷል። ለሥራ እስከወጣን ድረስ ዋናው የሥነ ልቦና መጠንከር እና ትዕግስተኛ መሆን ለስኬት ቁልፍ ነው። በጣም ብዙ ችግሮች አሉ እነዚያን መቋቋም እና ዲሲፕሊንም ይጠይቃል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በቴሌቪዝን መታየቱ የሚጨምረው ፋይዳ አለ? አሁን ያለው ፕሪሚያር ሊግ በቀጥታ በቴሊቪዥን መቅረቡ ከፍተኛ የመታየት እድል መፍጠሩ አይቀርም። ቅድም እንዳልኩት ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ የኳስ ተሰጥኦ ያላቸው ተጫዋቾች አሉ። ክለቦች ተጫዋቾቻው ወጥተው እንዲጫወቱ ማበረታታት አለባችው። ክለብ ብቻ ሳይሆን ፌዴሬሽኑ የራሱ ኃላፊነት አለበት። ፌዴሬሽኑ ከመንግሥት ጋር ተባብሮ ትልቅ ነገር መስራት ይጠበቅበታል። ለምሳሌ ሌሎች አገራት ለተጫዋቾቻቸው ነፃ ቪዛ ስለሚያመቻቹ ሄደው ይሞክራሉ። ብዙ ግንኙነት ማድረግ እና ከሌሎች የአፍሪካ አገራት ጋር መነጋገር አለበት። ባለሞያዎች እንደሚሉት አንድ ቡድን ከተገነባ ከ 4 እስከ 10 ዓመት ዋና ቡድን ውስጥ ያሉ ሰዎች ሳይቀያየሩ በተመሳሳይ ብቃት መቀጠል ይችላል ይላሉ። ያኔ ለአፍሪካ ዋንጫ ያለፈው ቡድን ወዲያውኑ ለምን ደከመ? ወይስ ያኔ ለአፍሪካ ዋንጫ ያለፋችሁት በአጋጣሚ ነበር? ጠንካራ ክለብ ያለመኖሩ ነው ብሔራዊ ቡድኑን ያደከመው። ቡና እና ጊዮርጊስን ጨምሮ ብዙ ጠንካራ የክልል ክለቦች ነበሩ። አሪፍ ብሔራዊ ቡድን የተሰራው በዕድል ሳይሆን በጥንካሬ ነው። ተጫዋቾችም በትንሽ ነገር እንሸወዳለን። ትንሽ ድል ያታልለናል። በዚያ ውስጥ እንጠፋለን። ተጫዋቾች ትንሽ ድል ስናገኝ ብዙ ነገር የሰራን ይመስለናል። የዓለም ዋንጫን ደጋግመው የወሰዱት እንደ ጀርመን እና ብራዚል እንኳን በዚያው ነው ጠንክረው የሚቀጥሉት።
https://www.bbc.com/amharic/news-56471330
2health
በዓለም የመጀመሪያ የሆነው ሰው ሰራሽ ደም በሰዎች ላይ መሞከር ተጀመረ
በቤተ ሙከራ ውስጥ የዳበረ ሰው ሰራሽ ደም ለመጀመሪያ ጊዜ በሚደረግ ክሊኒካዊ ሙከራ ለሰዎች መሰጠቱን የዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) ተመራማሪዎች አስታወቁ። አሁን ለሙከራ ለሰዎች የተሰጠው ሰው ሰራሽ ደም መጠኑ ትንሽ ሲሆን፣ የተወሰነ የሻይ ማንኪያ መጠን እንደሆነ ተገልጿል። በዚህም ደሙ በሰው አካል ውስጥ ገብቶ ምን ውጤት እንደሚኖረው ለማወቅ ሙከራ ይደረጋል። አስካሁን በዓለም ዙሪያ ደም ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ከሌሎች በልገሳ የተገኘ ደምን በመስጠት ጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛል። ይህ በቤተ ሙከራ የተሰራው ደም ስኬታማ ከሆነ፣ በተለይ ለማግኘት አስቸጋሪ የሆኑ የተለዩ የደም አይነቶችን በማምረት ላይ ትኩረት ይደረጋል። በተለይ የደም ካንሰር እና ሲክል ሴል አኒሚያ ላለባቸው እንዲሁም መደበኛ የደም ለውጥ ለሚያስፈልጋቸው ህሙማን ይህ አዲሱ ሰው ሰራሽ ደም ስኬታማ ከሆነ ችግራቸውን ያቀላል ተብሏል። በደም ልገሳ ወቅት ተቀባዩ ግለሰብ በትክክል ተመሳሳይ የደም አይነት የማያገኝ ከሆነ ሰውነቱ ሊቆጣና ህክምናው ሊሰናከል ይችላል። ይህም የደም አይነት ተመሳሳይነት በስፋት ከሚታወቁት የደም አይነት ከሆኑት ኤ፣ ቢ፣ ኤቢ እና ኦ ባሻገር ዝርዝር ልዩነቶችን መለየትን የሚጠይቅ ነው። አንዳንድ የደም አይነቶች ከተጠቀሱት በተለየ “በጣም፣ በጣም የተለዩ ከመሆናቸው ባሻገር፤ በአንድ አገር ውስጥ የዚያ አይነት ደም ያላቸው ሰዎች 10 ሰዎች ብቻ ሊሆኑ ይችላሉ” ይላሉ የብሪስቶል ዩኒቨርስቲው ፕሮፌሰር አሽሊ ቶዬ። ሰው ሰራሹን ደም ለማዳበር የብሪስቶል፣ የኬምብሪጅ፣ የለንደን እና የዩኬ ብሔራዊ የጤና አግልግሎት የምርምር አባላት እየተሳተፉ ነው። የፕሮጀክቱ ትኩረት ከሳንባ ወደ ቀሪው የሰውነት ክፍል ኦክስጂን በሚወስደው ቀይ የደም ህዋስ ላይ ነው። ሰው ሰራሽ ደሙን ለመሞከር ቢያንስ 10 ጤናማ በጎ ፈቃደኞች የሚያስፍልጉ ሲሆን፣ አሁን የመጀመሪያዎቹ ሁለት ሰዎች በሙከራው ላይ እየተሳተፉ ነው። በዚህም ሙከራው የሚደረግባቸው ሰዎች በአራት ወራት ልዩነት ውስጥ ከ5 አስከ 10 ሚሊ ሊትር የሚሆን ደም በመጀመሪያ ትክክለኛ ደም፣ ቀጥሎ ደግሞ በቤተ ሙከራ የዳበረ ደም ይሰጣቸዋል ተብሏል። ይህ በቤተሙከራ የዳበረው ደም ስኬታማ ከሆነ በወጪ ረገድ አሳሳቢ እንደሚሆን ባለሙያዎቹ የተናገሩ ሲሆን፣ ከለጋሾች ተፈጥሯዊ ደምን ለማግኘት የሚወጣው ወጪ፣ ሰው ሰራሽ ደሙን ለማምረት ከሚያስፈልገው ያነሰ ነው። በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ብሔራዊው የጤና አገልግሎት እንደሚለው ተፈጥሯዊው የደም ልገሳ በአማካይ 130 ፓወንድ ያክል ያስወጣል። ምርምሩን የሚያካሂደው ቡድን ባይገልጸውም በቤተ ሙከራ ውስጥ ሰው ሰራሽ ደም ማዳበር ከፍተኛ ወጪን ይጠይቃል ተብሏል። በተጨማሪም በቤተሙከራ ውስጥ የስቴም ህዋሳትን ለማዳበር በሚከናወነው ሂደት ውስጥ ሌሎች ተግዳሮቶች ስለሚኖሩ በምርቱ ወቅት የተለያዩ ችግሮች መግጠማቸው እንደማይቀር ተገልጿል። ነገር ግን ይህ በቤተ ሙከራ የሚዳብረው ደም መደበኛ የደም ዝውውር ለሚፈልጉ እና እጅግ ለየት ያለ የደም አይነት ላላቸው ሰዎች የሚሆን ደም በማምረት በኩል ትልቅ መፍትሔ እንደሚሆን ባለሙያዎች ይናገራሉ።
በዓለም የመጀመሪያ የሆነው ሰው ሰራሽ ደም በሰዎች ላይ መሞከር ተጀመረ በቤተ ሙከራ ውስጥ የዳበረ ሰው ሰራሽ ደም ለመጀመሪያ ጊዜ በሚደረግ ክሊኒካዊ ሙከራ ለሰዎች መሰጠቱን የዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) ተመራማሪዎች አስታወቁ። አሁን ለሙከራ ለሰዎች የተሰጠው ሰው ሰራሽ ደም መጠኑ ትንሽ ሲሆን፣ የተወሰነ የሻይ ማንኪያ መጠን እንደሆነ ተገልጿል። በዚህም ደሙ በሰው አካል ውስጥ ገብቶ ምን ውጤት እንደሚኖረው ለማወቅ ሙከራ ይደረጋል። አስካሁን በዓለም ዙሪያ ደም ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ከሌሎች በልገሳ የተገኘ ደምን በመስጠት ጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛል። ይህ በቤተ ሙከራ የተሰራው ደም ስኬታማ ከሆነ፣ በተለይ ለማግኘት አስቸጋሪ የሆኑ የተለዩ የደም አይነቶችን በማምረት ላይ ትኩረት ይደረጋል። በተለይ የደም ካንሰር እና ሲክል ሴል አኒሚያ ላለባቸው እንዲሁም መደበኛ የደም ለውጥ ለሚያስፈልጋቸው ህሙማን ይህ አዲሱ ሰው ሰራሽ ደም ስኬታማ ከሆነ ችግራቸውን ያቀላል ተብሏል። በደም ልገሳ ወቅት ተቀባዩ ግለሰብ በትክክል ተመሳሳይ የደም አይነት የማያገኝ ከሆነ ሰውነቱ ሊቆጣና ህክምናው ሊሰናከል ይችላል። ይህም የደም አይነት ተመሳሳይነት በስፋት ከሚታወቁት የደም አይነት ከሆኑት ኤ፣ ቢ፣ ኤቢ እና ኦ ባሻገር ዝርዝር ልዩነቶችን መለየትን የሚጠይቅ ነው። አንዳንድ የደም አይነቶች ከተጠቀሱት በተለየ “በጣም፣ በጣም የተለዩ ከመሆናቸው ባሻገር፤ በአንድ አገር ውስጥ የዚያ አይነት ደም ያላቸው ሰዎች 10 ሰዎች ብቻ ሊሆኑ ይችላሉ” ይላሉ የብሪስቶል ዩኒቨርስቲው ፕሮፌሰር አሽሊ ቶዬ። ሰው ሰራሹን ደም ለማዳበር የብሪስቶል፣ የኬምብሪጅ፣ የለንደን እና የዩኬ ብሔራዊ የጤና አግልግሎት የምርምር አባላት እየተሳተፉ ነው። የፕሮጀክቱ ትኩረት ከሳንባ ወደ ቀሪው የሰውነት ክፍል ኦክስጂን በሚወስደው ቀይ የደም ህዋስ ላይ ነው። ሰው ሰራሽ ደሙን ለመሞከር ቢያንስ 10 ጤናማ በጎ ፈቃደኞች የሚያስፍልጉ ሲሆን፣ አሁን የመጀመሪያዎቹ ሁለት ሰዎች በሙከራው ላይ እየተሳተፉ ነው። በዚህም ሙከራው የሚደረግባቸው ሰዎች በአራት ወራት ልዩነት ውስጥ ከ5 አስከ 10 ሚሊ ሊትር የሚሆን ደም በመጀመሪያ ትክክለኛ ደም፣ ቀጥሎ ደግሞ በቤተ ሙከራ የዳበረ ደም ይሰጣቸዋል ተብሏል። ይህ በቤተሙከራ የዳበረው ደም ስኬታማ ከሆነ በወጪ ረገድ አሳሳቢ እንደሚሆን ባለሙያዎቹ የተናገሩ ሲሆን፣ ከለጋሾች ተፈጥሯዊ ደምን ለማግኘት የሚወጣው ወጪ፣ ሰው ሰራሽ ደሙን ለማምረት ከሚያስፈልገው ያነሰ ነው። በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ብሔራዊው የጤና አገልግሎት እንደሚለው ተፈጥሯዊው የደም ልገሳ በአማካይ 130 ፓወንድ ያክል ያስወጣል። ምርምሩን የሚያካሂደው ቡድን ባይገልጸውም በቤተ ሙከራ ውስጥ ሰው ሰራሽ ደም ማዳበር ከፍተኛ ወጪን ይጠይቃል ተብሏል። በተጨማሪም በቤተሙከራ ውስጥ የስቴም ህዋሳትን ለማዳበር በሚከናወነው ሂደት ውስጥ ሌሎች ተግዳሮቶች ስለሚኖሩ በምርቱ ወቅት የተለያዩ ችግሮች መግጠማቸው እንደማይቀር ተገልጿል። ነገር ግን ይህ በቤተ ሙከራ የሚዳብረው ደም መደበኛ የደም ዝውውር ለሚፈልጉ እና እጅግ ለየት ያለ የደም አይነት ላላቸው ሰዎች የሚሆን ደም በማምረት በኩል ትልቅ መፍትሔ እንደሚሆን ባለሙያዎች ይናገራሉ።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c06xl7dg58go
0business
አሁን ባለው የዋጋ ግሽበት ገንዘብ መቆጠብ ያዋጣል?
በአጠቃላይ ገንዘብ ቆጠብን ስንል ወደ ወጪ ያልተቀየረ ገንዘብ አለን ወይንም ወጪያችንን በመቀነስ የምናስቀምጠው ገንዘብ ማለታችን ነው። በምጣኔ ኃብት ቋንቋ ደግሞ ገቢያችን የወጪያችን እና የቁጠባችን ድምር ነው። የምጣኔ ኃብት ባለሙያው ተሾመ ተፈራ (ዶ/ር) በመርህ ደረጃ ከወጪ የሚተርፍ ገንዘብ መቆጠብ አለበት። ይሁን እንጂ ቁጠባ ከሰዎች ባህሪ ጋር የሚገናኝ ጉዳይ ነው ይላሉ። “አንዳንድ ሰዎች ከወጪያቸው ቆጥበው ለወደፊት ኑሯቸው፣ ለጡረታ ዘመናቸው ወይንም ለልጆቻቸው ይቆጥባሉ። ሌሎች ደግሞ ከወጪያቸው እንደፈለጉ አውጥተው የሚተርፋቸውን ያስቀምጣሉ፤ ሌሎች ዛሬን ብቻ መኖር የሚፈልጉ አይቆጥቡም። ስለዚህ ቁጠባ ሌሎች ነገሮች ላይ ከምናሳየው ከባህሪያችን ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለው” ይላሉ። የምጣኔ ኃብት ባለሙያው እንደሚሉት በግለሰብ ደረጃ የምናደርገው የሀብት አጠቃቀም ውሳኔ አንድ ሰው ደስታ ያመጣልኛል ብሎ በሚያምነው ነገር ላይ የተመሰረተ ነው። “ለምሳሌ አንድ ሰው ዛሬ ደስ የሚለውን ልብስ መግዛት ያስደስተኛል ካለ፣ ሊቆጥብ የሚገባውን ገንዘብ እዚያ ላይ ያወጣዋል። ሌላው ሰው ደግሞ ለወደፊት መግዛት ለሚፈልገው ደስታ አሁን ብሩን ይቆጥባል ማለት ነው” ተሾመ (ዶ/ር) እንደሚሉት ገንዘብ የሚቆጥበውም ሆነ አባካኝ የሆነው፣ ሌላ ሰው ከውጪ ስም ይሰጣል እንጂ ሁለቱም በገንዘባቸው ደስታን የመግዛት ስራ እየሰሩ ነው ያሉት። በምንኖርባት አገር ውስጥ የምንቆጥበው ገንዘብ ጥቅም ሊያስገኝልን የሚችለው የገበያው የዋጋ ንረት እኛ በመቆጠብ ከምናገኘው ጥቅም በታች ከሆነ ብቻ ነው ይላሉ የምጣኔ ሀብት ባለሙያው። ይህንንም በምሳሌ ሲያስረዱ “አንድ ሰው ያለፈው ዓመት አንድ መቶ ብር ባንክ ቢያስቀምጥ ከአመት በኋላ ቢበዛ ስድስት በመቶ ብቻ ነው ሊወልድለት የሚችለው። አሁን ባለው የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ የዋጋ ግሽበቱ ከ34 በመቶ በላይ ሆኗል።” የምጣኔ ኃብት ምሁሩ እንደሚሉት አምና የቆጠብነው አንድ መቶ ብር ዘንድሮ የመግዛት አቅሙ በ34 በመቶ ይወርዳል። “ስለዚህ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ግሽበት ባለበት አገር ገንዘብ ዝም ብሎ ማስቀመጥ አዋጭ አይደለም። ከዚህ የዋጋ ግሽበት የቆጠቡትን ገንዘብ ለማስመለጥ ሰዎች መሬት እና የመሳሰሉ ሀብቶችን በመግዛት ገንዘባቸውን የተሻለ ነገር ላይ ቢያውሉት ተመራጭ ነው” ይላሉ። አክለውም “ግን በአጠቃላይ ቁጠባ ጥቅም ሊያስገኝ የሚችለው የአንድ አገር የዋጋ ንረት ከባንክ ወለድ በታች ከሆነ ብቻ ነው። በዚህ ሁኔታ ገንዘብ መቆጠብን እንደ መነሻ ተጠቅመን ገንዘባችንን ኢንቨስት ማድረግ የተሻለ አማራጭ ነው። ገንዘብ ኢንቨስት ማድረግ ማለት፣ ገንዘብ ማስቀመጥ ሳይሆን እንዲያድግ ማድረግ ነው፝ ይህንንም በምሳሌ ሲያስረዱ፣ የባንክ ሼር በመግዛት እና በተለያዩ ሌሎች አማራጮች ተግባር ላይ ማዋል እንደሚቻል በመጥቀስ ይመክራሉ። ለምሳሌ ይላሉ ዶ/ር ተሾመ፣ “ የኢትዮጵያ ባንኮች ለአንድ አክስዮን ከ20 በመቶ በላይ ትርፍ ይከፍላሉ። ስለዚህ ከምንቆጥበው ገንዘብ በላይ እንጠቀማለን ማለት ነው።” እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገራት ኢንቨስትመንት ስላልተስፋፋ ከኢንቨስትመንት ላይ የምናገኘው ጥቅም ትልቅ ሊሆን ይችላል። እንደ ጃፓን ያሉ አገራት ውስጥ ግን ያለው የዋጋ መውረድ (ዲፊሌሽን) በመሆኑ ገንዘብ መያዝ ኢንቨስት ከማድረግ የተሻለ አማራጭ የሚሆንብት አጋጣሚ መኖሩን አቶ ተሾመ ያስረዳሉ። የተረጋጋ ምጣኔ ሀብት ባለበት አገር ገንዘባቸንን ስራዬ ብለን ብንቆጥብ ሀብት ማካበት እንችላለን የሚል ጥያቄ ለምጣኔ ኃብት ምሁሩ አቅርበን ነበር። ባለሙያውም የአንዳንድ አገራትን ልምድ በማንሳት ይህንን ጉዳይ ያብራራሉ። እንደ ቤልጂየም ያሉ አገራት ቁጠባን አያበረታቱም። ስለዚህ የቁጠባ የባንክ አካውንት ለሚከፍቱ ሰዎች ዓመታዊ ክፍያ ያስከፍላሉ። ይህንንም የሚያደርጉት ብሩ እንዳይቀመጥ እና ስራ ላይ እንዲውል ስለሚፈልጉ ነው። በአገራችን ግን ባንኮች እነርሱ ጋር አንድንቆጥብ በዘመቻ የሚያበረታቱን ከተጠቃሚው የሚሰበስቡትን ገንዘብ ለኢንቬስተር አበድረው ጥቅም ማግኝት ስላለባቸው ነው ይላሉ። ስለዚህ እንደ ምሁሩ ገለጻ፣ ገንዘብ መቆጠብ እድል የሚከፍት ቢሆን እንጂ ብቻውን ወደ ሀብት ማካበት አያደርሰንም። ለምሳሌ አንድ ተቀጥሮ የሚሰራ ሰራተኛ ገንዘቡን ቢቆጥብ በግሽበት እየተበላበት ነው የሚሄደው። በተለይ ደግሞ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ እና የሰራተኞች ማህበራት ጠንካራ ባልሆኑበት አገር፣ የዋጋ ግሽበት በመጣ ቁጥር የሰራተኛው ደመወዝ ስለማይስተካከል መቆጠብ የማይችሉበት ደረጃ ላይ ይደርሳሉ። ነገር ግን አንድ ሱቅ ያለ ሰው ከተቀጣሪ ራሱን በተሻለ ሁኔታ ማስተዳደር ይችላል። ምክንያቱም የሽያጭ እና ግዢ ሁኔታው ከዋጋ ግሽበቱ ጋር ማስተካከል ስለሚችል ነው። እንዲሁ በአጠቃላይ የተረጋጋ ኢኮኖሚ ባለበት አገር ገንዘብ መቆጠብ ኢንቨስት ለማድረግ መንገድ ሊከፍት እና ሊያሳድግ ይችላል። ነገር ግን በራሱ መቆጠብ ወደ ሀብት ማካበት አያደርስም። የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች እንደሚያስረዱት የቁጠባ እና የኢንቨስትመንት ዋና ልዩነት ገንዘብን ለአጭር እና ለረዥመ ጊዜ ማስቀመጥ ነው። በተጨማሪም ሌሎች እነዚህ ሁለቱ ሀሳቦች የሚለያዩበት ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው።
አሁን ባለው የዋጋ ግሽበት ገንዘብ መቆጠብ ያዋጣል? በአጠቃላይ ገንዘብ ቆጠብን ስንል ወደ ወጪ ያልተቀየረ ገንዘብ አለን ወይንም ወጪያችንን በመቀነስ የምናስቀምጠው ገንዘብ ማለታችን ነው። በምጣኔ ኃብት ቋንቋ ደግሞ ገቢያችን የወጪያችን እና የቁጠባችን ድምር ነው። የምጣኔ ኃብት ባለሙያው ተሾመ ተፈራ (ዶ/ር) በመርህ ደረጃ ከወጪ የሚተርፍ ገንዘብ መቆጠብ አለበት። ይሁን እንጂ ቁጠባ ከሰዎች ባህሪ ጋር የሚገናኝ ጉዳይ ነው ይላሉ። “አንዳንድ ሰዎች ከወጪያቸው ቆጥበው ለወደፊት ኑሯቸው፣ ለጡረታ ዘመናቸው ወይንም ለልጆቻቸው ይቆጥባሉ። ሌሎች ደግሞ ከወጪያቸው እንደፈለጉ አውጥተው የሚተርፋቸውን ያስቀምጣሉ፤ ሌሎች ዛሬን ብቻ መኖር የሚፈልጉ አይቆጥቡም። ስለዚህ ቁጠባ ሌሎች ነገሮች ላይ ከምናሳየው ከባህሪያችን ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለው” ይላሉ። የምጣኔ ኃብት ባለሙያው እንደሚሉት በግለሰብ ደረጃ የምናደርገው የሀብት አጠቃቀም ውሳኔ አንድ ሰው ደስታ ያመጣልኛል ብሎ በሚያምነው ነገር ላይ የተመሰረተ ነው። “ለምሳሌ አንድ ሰው ዛሬ ደስ የሚለውን ልብስ መግዛት ያስደስተኛል ካለ፣ ሊቆጥብ የሚገባውን ገንዘብ እዚያ ላይ ያወጣዋል። ሌላው ሰው ደግሞ ለወደፊት መግዛት ለሚፈልገው ደስታ አሁን ብሩን ይቆጥባል ማለት ነው” ተሾመ (ዶ/ር) እንደሚሉት ገንዘብ የሚቆጥበውም ሆነ አባካኝ የሆነው፣ ሌላ ሰው ከውጪ ስም ይሰጣል እንጂ ሁለቱም በገንዘባቸው ደስታን የመግዛት ስራ እየሰሩ ነው ያሉት። በምንኖርባት አገር ውስጥ የምንቆጥበው ገንዘብ ጥቅም ሊያስገኝልን የሚችለው የገበያው የዋጋ ንረት እኛ በመቆጠብ ከምናገኘው ጥቅም በታች ከሆነ ብቻ ነው ይላሉ የምጣኔ ሀብት ባለሙያው። ይህንንም በምሳሌ ሲያስረዱ “አንድ ሰው ያለፈው ዓመት አንድ መቶ ብር ባንክ ቢያስቀምጥ ከአመት በኋላ ቢበዛ ስድስት በመቶ ብቻ ነው ሊወልድለት የሚችለው። አሁን ባለው የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ የዋጋ ግሽበቱ ከ34 በመቶ በላይ ሆኗል።” የምጣኔ ኃብት ምሁሩ እንደሚሉት አምና የቆጠብነው አንድ መቶ ብር ዘንድሮ የመግዛት አቅሙ በ34 በመቶ ይወርዳል። “ስለዚህ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ግሽበት ባለበት አገር ገንዘብ ዝም ብሎ ማስቀመጥ አዋጭ አይደለም። ከዚህ የዋጋ ግሽበት የቆጠቡትን ገንዘብ ለማስመለጥ ሰዎች መሬት እና የመሳሰሉ ሀብቶችን በመግዛት ገንዘባቸውን የተሻለ ነገር ላይ ቢያውሉት ተመራጭ ነው” ይላሉ። አክለውም “ግን በአጠቃላይ ቁጠባ ጥቅም ሊያስገኝ የሚችለው የአንድ አገር የዋጋ ንረት ከባንክ ወለድ በታች ከሆነ ብቻ ነው። በዚህ ሁኔታ ገንዘብ መቆጠብን እንደ መነሻ ተጠቅመን ገንዘባችንን ኢንቨስት ማድረግ የተሻለ አማራጭ ነው። ገንዘብ ኢንቨስት ማድረግ ማለት፣ ገንዘብ ማስቀመጥ ሳይሆን እንዲያድግ ማድረግ ነው፝ ይህንንም በምሳሌ ሲያስረዱ፣ የባንክ ሼር በመግዛት እና በተለያዩ ሌሎች አማራጮች ተግባር ላይ ማዋል እንደሚቻል በመጥቀስ ይመክራሉ። ለምሳሌ ይላሉ ዶ/ር ተሾመ፣ “ የኢትዮጵያ ባንኮች ለአንድ አክስዮን ከ20 በመቶ በላይ ትርፍ ይከፍላሉ። ስለዚህ ከምንቆጥበው ገንዘብ በላይ እንጠቀማለን ማለት ነው።” እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገራት ኢንቨስትመንት ስላልተስፋፋ ከኢንቨስትመንት ላይ የምናገኘው ጥቅም ትልቅ ሊሆን ይችላል። እንደ ጃፓን ያሉ አገራት ውስጥ ግን ያለው የዋጋ መውረድ (ዲፊሌሽን) በመሆኑ ገንዘብ መያዝ ኢንቨስት ከማድረግ የተሻለ አማራጭ የሚሆንብት አጋጣሚ መኖሩን አቶ ተሾመ ያስረዳሉ። የተረጋጋ ምጣኔ ሀብት ባለበት አገር ገንዘባቸንን ስራዬ ብለን ብንቆጥብ ሀብት ማካበት እንችላለን የሚል ጥያቄ ለምጣኔ ኃብት ምሁሩ አቅርበን ነበር። ባለሙያውም የአንዳንድ አገራትን ልምድ በማንሳት ይህንን ጉዳይ ያብራራሉ። እንደ ቤልጂየም ያሉ አገራት ቁጠባን አያበረታቱም። ስለዚህ የቁጠባ የባንክ አካውንት ለሚከፍቱ ሰዎች ዓመታዊ ክፍያ ያስከፍላሉ። ይህንንም የሚያደርጉት ብሩ እንዳይቀመጥ እና ስራ ላይ እንዲውል ስለሚፈልጉ ነው። በአገራችን ግን ባንኮች እነርሱ ጋር አንድንቆጥብ በዘመቻ የሚያበረታቱን ከተጠቃሚው የሚሰበስቡትን ገንዘብ ለኢንቬስተር አበድረው ጥቅም ማግኝት ስላለባቸው ነው ይላሉ። ስለዚህ እንደ ምሁሩ ገለጻ፣ ገንዘብ መቆጠብ እድል የሚከፍት ቢሆን እንጂ ብቻውን ወደ ሀብት ማካበት አያደርሰንም። ለምሳሌ አንድ ተቀጥሮ የሚሰራ ሰራተኛ ገንዘቡን ቢቆጥብ በግሽበት እየተበላበት ነው የሚሄደው። በተለይ ደግሞ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ እና የሰራተኞች ማህበራት ጠንካራ ባልሆኑበት አገር፣ የዋጋ ግሽበት በመጣ ቁጥር የሰራተኛው ደመወዝ ስለማይስተካከል መቆጠብ የማይችሉበት ደረጃ ላይ ይደርሳሉ። ነገር ግን አንድ ሱቅ ያለ ሰው ከተቀጣሪ ራሱን በተሻለ ሁኔታ ማስተዳደር ይችላል። ምክንያቱም የሽያጭ እና ግዢ ሁኔታው ከዋጋ ግሽበቱ ጋር ማስተካከል ስለሚችል ነው። እንዲሁ በአጠቃላይ የተረጋጋ ኢኮኖሚ ባለበት አገር ገንዘብ መቆጠብ ኢንቨስት ለማድረግ መንገድ ሊከፍት እና ሊያሳድግ ይችላል። ነገር ግን በራሱ መቆጠብ ወደ ሀብት ማካበት አያደርስም። የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች እንደሚያስረዱት የቁጠባ እና የኢንቨስትመንት ዋና ልዩነት ገንዘብን ለአጭር እና ለረዥመ ጊዜ ማስቀመጥ ነው። በተጨማሪም ሌሎች እነዚህ ሁለቱ ሀሳቦች የሚለያዩበት ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cd1v20381w3o
3politics
የባይቶና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አቶ ክብሮም በርኸ መታሰራቸው ተነገረ
የብሔራዊ ባይቶ አባይ ትግራይ ወይም ባይቶና የሚባለው የፖለቲካ ፓርቲ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ የሆኑት አቶ ክብሮም በርኸ አዲስ አበባ ውስጥ በፀጥታ ኃይሎች መታሰራቸው ተነገረ። በትግራይ ከሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል አንዱ የሆነው የባይቶና ከፍተኛ አመራር አንዱ የሆኑት አቶ ክብሮም በቅርቡ “ምጽአት” የሚል ርዕስ ያለው በትግራዩ ጦርነት ላይ የሚያጠነጥን መጽሐፍ ለንባብ አቅርበዋል። አቶ ክብሮም እሑድ ምሽት አዲስ አበባ ውስጥ በፀጥታ ኃይሎች መያዛቸውን ለቢቢሲ የተናገሩት የፓርቲው የቁጥጥር ኮሚሽን ኃላፊ የሆኑት አቶ ዮሴፍ ኃይለሥላሴ ናቸው። ምሽት ከአንድ ሰዓት እስከ ሁለት ሰዓት ባለው ጊዜ ሲቪል የለበሱ ሰዎች በቅድሚያ የአቶ ክብሮም ባለቤትን መያዛቸውን የተናገሩት አቶ ዮሴፍ “ባለቤትሽን አምጪ ብለው ጠይቀዋት፣ ከዚያ በኋላ እርሱ ሲሄድ በቁጥጥር ስር አዋሉት” ብለዋል። ጦርነቱ በተስፋፋበትና የትግራይ ኃይሎች ወደ አፋርና አማራ ክልሎች በገቡበት ወቅት የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ፣ የባይቶና ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ክብሮም ተይዘው በአፋር ክልል ውስጥ ለወራት በእስር ላይ ቆይተው እንደነበር ተነግሯል። አቶ ክብሮም በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከመዋላቸው በፊት ስልክ በመወደል ባለቤታቸው መያዛቸውንና እሳቸውም በፖሊስ እንደሚፈለጉ እንደተነገሯቸው የጠቀሱት አቶ ዮሴፍ፣ አቶ ክብሮም በአሁኑ ጊዜ በቃሊቲ ክፍለ ከተማ በሚገኝ እስር ቤት እንዳሉም ጨምረው ገልጸዋል። የአቶ ክብሮም ባለቤት እሳቸው በቁጥጥር ሥር ሲውሉ መለቀቃቸውን የተናገሩት አቶ ዮሴፍ፣ የባይቶና የውጭ ጉዳይ ኃላፊው አቶ ክብሮም በርኸ ለምን እንደታሰሩ የሚያውቁት ነገር እንደሌለና ፍርድ ቤትም አለመቅረባቸውን አመልክተዋል። የአቶ ክብሮም እስርን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ቢቢሲ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ስልክ በመደወል ያደረገው ተደጋጋሚ ሙከራ ለጊዜው አልተሳካለትም። ከቅርብ ወራት ወዲህ መንግሥት ሕግ ማስከበር ባለው ዘመቻ በአዲስ አበባ፣ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች ውስጥ ጋዜጠኞችን ጨምሮ በርካታ ሰዎች በፀጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወሳል።
የባይቶና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አቶ ክብሮም በርኸ መታሰራቸው ተነገረ የብሔራዊ ባይቶ አባይ ትግራይ ወይም ባይቶና የሚባለው የፖለቲካ ፓርቲ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ የሆኑት አቶ ክብሮም በርኸ አዲስ አበባ ውስጥ በፀጥታ ኃይሎች መታሰራቸው ተነገረ። በትግራይ ከሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል አንዱ የሆነው የባይቶና ከፍተኛ አመራር አንዱ የሆኑት አቶ ክብሮም በቅርቡ “ምጽአት” የሚል ርዕስ ያለው በትግራዩ ጦርነት ላይ የሚያጠነጥን መጽሐፍ ለንባብ አቅርበዋል። አቶ ክብሮም እሑድ ምሽት አዲስ አበባ ውስጥ በፀጥታ ኃይሎች መያዛቸውን ለቢቢሲ የተናገሩት የፓርቲው የቁጥጥር ኮሚሽን ኃላፊ የሆኑት አቶ ዮሴፍ ኃይለሥላሴ ናቸው። ምሽት ከአንድ ሰዓት እስከ ሁለት ሰዓት ባለው ጊዜ ሲቪል የለበሱ ሰዎች በቅድሚያ የአቶ ክብሮም ባለቤትን መያዛቸውን የተናገሩት አቶ ዮሴፍ “ባለቤትሽን አምጪ ብለው ጠይቀዋት፣ ከዚያ በኋላ እርሱ ሲሄድ በቁጥጥር ስር አዋሉት” ብለዋል። ጦርነቱ በተስፋፋበትና የትግራይ ኃይሎች ወደ አፋርና አማራ ክልሎች በገቡበት ወቅት የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ፣ የባይቶና ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ክብሮም ተይዘው በአፋር ክልል ውስጥ ለወራት በእስር ላይ ቆይተው እንደነበር ተነግሯል። አቶ ክብሮም በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከመዋላቸው በፊት ስልክ በመወደል ባለቤታቸው መያዛቸውንና እሳቸውም በፖሊስ እንደሚፈለጉ እንደተነገሯቸው የጠቀሱት አቶ ዮሴፍ፣ አቶ ክብሮም በአሁኑ ጊዜ በቃሊቲ ክፍለ ከተማ በሚገኝ እስር ቤት እንዳሉም ጨምረው ገልጸዋል። የአቶ ክብሮም ባለቤት እሳቸው በቁጥጥር ሥር ሲውሉ መለቀቃቸውን የተናገሩት አቶ ዮሴፍ፣ የባይቶና የውጭ ጉዳይ ኃላፊው አቶ ክብሮም በርኸ ለምን እንደታሰሩ የሚያውቁት ነገር እንደሌለና ፍርድ ቤትም አለመቅረባቸውን አመልክተዋል። የአቶ ክብሮም እስርን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ቢቢሲ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ስልክ በመደወል ያደረገው ተደጋጋሚ ሙከራ ለጊዜው አልተሳካለትም። ከቅርብ ወራት ወዲህ መንግሥት ሕግ ማስከበር ባለው ዘመቻ በአዲስ አበባ፣ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች ውስጥ ጋዜጠኞችን ጨምሮ በርካታ ሰዎች በፀጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወሳል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c97pw1q3gqno
5sports
ኦሌ ጉና ሶልሻየር፡ አራተኛ ሆኖ መጨረስ በቂ አይደለም
ኦሌ ጉና ሶልሻየር ማንችሰተር ዩናይትድ በቀጣዩ የውድድር ዘመን ''አራተኛ ሆኖ ከመጨረስ በላይ ነው የሚያልመው'' ሲሉ ለቢቢሲ ቃላቸውን ሰጡ። የ46 ዓመቱ አስልጣኝ ማንችስተር ዩናይትድን ከጆሴ ሞሪኒሆ መቀበላቸው ይታወሳል። ሶልሻየር የቀያይ ሴጣኖቹ ቋሚ አሰልጣኝ ሆነው ከመሾማቸው በፊት ካደረጉት 19 ጨዋታዎች 14ቱን ማሸነፍ ችለው ነበር። ኦሌ ቋሚ አሰልጣኝ ሆነው ከተሾሙ በኋላ ግን ካደረጓቸው 10 ጨዋታዎች ሙሉ ነጥብ መሰብሰብ የቻሉት ከሁለት ጨዋታዎች ብቻ ነው። ዩናይትዶች አዲሱ የውድድር ዘመን ከመጀመሩ በፊት የሚከናወኑ ጨዋታዎችን ለማድረግ አውስትራሊያ የሚገኙ ሲሆን፤ ኦሌ ጉና ሶልሻየር ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ስለ የቀጣዩ የውድድር ዘመን እቅዳቸውን ጨምሮ ስለ አሌክሲስ ሳንቼዝ እና ፖል ፖግባ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። • "እንዴት ለሴት ልጅ የወንዶች ክለብ ይሰጣል?' ተብሎ ነበር" መሠረት ማኒ ኦሌ ጉና ስለቀጣዩ የውድድር ዓመት ሲናገሩ፤ በሊጉ ሰንጠረዥ የመጀመሪያዎቹ አራት ውስጥ ለመጨረስ ከሚደረገው ጥረት በላይ ማድረግ ይኖርብናል ብለዋል። "ተሰጥኦ ያላቸው ተጫዋቾች አሉን በተጨማሪም ለቡድኑ በትክክል የሚመጥኑ ተጨዋቾችን በማስፈረም ከምንፈልገው ቦታ ላይ መድረስ እንችላለን። የሚጠበቅብን ወጥ የሆነ አቋም ላይ መገኘት መቻል ነው። በየቀኑ ጠንክረን እየሰራን ከእቅዳችን ዘንበል ማለት የለብንም።" የዩናይትዶቹ አሰልጣኝ ኦሌ ጉና ሶልሻየር ለቡድኑ ስኬት የፖል ፖግባ አሰተዋጽኦ ከፍተኛ እንደሆነ ይናገራሉ። ኦሌ ''ፖል ድንቅ ተጫዋች እና የሚደንቅ ሰው። በሞልዴ ክለብ እያለሁ፤ 'ፖል በቡድን ውስጥ ካለ፤ በእሱ ላይ በመመስረት ቡደን መመስረት ይቻላል' እል ነበር። አሁንም ተመሳሳይ እምነት ነው ያለኝ። የዩናትድ ደጋፊዎች የቡድናቸውን አጨዋወት ያውቃሉ። ፖልን የሚተቹ ብዙ ቢሆንም በበርካቶች ግን ይወደዳል። • «የኔ ትውልድ ታሪክ እንደሚሠራ እምነት አለኝ» ሎዛ አበራ ከአርሰናል ወደ ማንችስተር የተዘዋወረው አሌክሲስ ሳንቼዝ በክለቡ ውስጥ ትልቅ ስም እና ክፍያ ካላቸው ቀዳሚ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነው። ይሁን እንጂ ሳንቼዝ ወደ ማንችስትር ከተዘዋወረ በኋላ በክለቡ ወጥ አቋም ማሳየት አልቻለም። ''የአሌክሲስን አቅም ሳስብ ትልቅ እረፍት ይሰጠኛል። ማድረግ የሚችለውን እናውቃለን። ምን ማድረግ እንዳለብን ነው መለየት ያለብን። ምክንያቱም አሌክሲስ በቀላሉ 20 ጎሎችን ሊሰጠን የሚችል ተጫዋች ነው። በኮፓ አሜሪካ ላይ ይህን አይተናል። ወጥ አቋም ማየት አልቻለንም በተጨማሪም ጎዳቶች ሲያጋጥሙት ነበር። ወደ ድንቅ አቋሙ ይመለሳል ብለን እናስባለን'' በማንችሰተር ዩናይትድ ቤት ውስጥ የተጫዋቾች ዝውውር ስትራቴጂን በሚመለከት ''እዚህ የማልፈልጋቸው ተጫዋቾች የሉም። አሁንም አንድ ወይም ሁለት ተጫዋቾችን ለማስፈረም እየሞከርን ነው። ክለቡን የሚለቁ ተጫዋቾች ካሉ እነሱን ለመተካት ሌሎች ተጫዋቾችን የማስፈረሙ ስራ ይኖራል'' ሲሉ መልሰዋል። ኦሌ ጉና ስለ ወጣቱ ሜይሰን ግሪንውድ አስተያየታቸውን ሲሰጡ ''ተፈጥሯዊ የእግር ኳስ ክህሎት ያለው ተጫዋች ነው። በቀኝ እግሩም ሆነ በግራ እግሩ ጎል ያስቆጥራል። ሁለቱንም እግሮቹን በሚገርም ብቃት ይጠቀማል። ቀኝ ወይም ግራኝ ስለመሆኑ እርሱ እራሱ የሚያውቀው አይመስለኝም። መቶ በመቶ እርግጠኛ የምሆነው በዚህ የውድድር ዘመን ጎሎችን ያስቆጥራል'' ከቀድሞ የክለቡ አልጣኝ ሰር አሌክ ፈርጉሰን ጋር ስላላቸው ግነኙነት የተጠየቁት ኦሌ ''ለ14 ዓመት ከፈርጉሰን ጋር አብሬ ሰርቻለሁ። አብዛኛው የእግር ኳስ ህይወቴ ከእርሱ ጋር ነው ያሳለፍኩት። ከፈርጉሰን ብዙ ትመሬያለሁ ይህ እውነት ነው። ከጨዋታ በኋላ አልፎ አልፎ እንነጋገራለን፣ የጽሁፍ መልዕክት እንላላካለን ከዚህ ውጪ ሌሎች ብዙ የሚባሉት ነገሮች ግን ስህተት ናቸው። • ያለእድሜ ጋብቻን በእግር ኳስ የምትታገለው ታዳጊ ኦሌ ጉና በስተመጨረሻም ቡድን እንደ አዲስ ማዋቀር ጊዜ የሚወስድ መሆኑን በመጠቀስ የዩናይትድ ደጋፊዎች ትዕግስት እንዲኖራቸው ጠይቀዋል።
ኦሌ ጉና ሶልሻየር፡ አራተኛ ሆኖ መጨረስ በቂ አይደለም ኦሌ ጉና ሶልሻየር ማንችሰተር ዩናይትድ በቀጣዩ የውድድር ዘመን ''አራተኛ ሆኖ ከመጨረስ በላይ ነው የሚያልመው'' ሲሉ ለቢቢሲ ቃላቸውን ሰጡ። የ46 ዓመቱ አስልጣኝ ማንችስተር ዩናይትድን ከጆሴ ሞሪኒሆ መቀበላቸው ይታወሳል። ሶልሻየር የቀያይ ሴጣኖቹ ቋሚ አሰልጣኝ ሆነው ከመሾማቸው በፊት ካደረጉት 19 ጨዋታዎች 14ቱን ማሸነፍ ችለው ነበር። ኦሌ ቋሚ አሰልጣኝ ሆነው ከተሾሙ በኋላ ግን ካደረጓቸው 10 ጨዋታዎች ሙሉ ነጥብ መሰብሰብ የቻሉት ከሁለት ጨዋታዎች ብቻ ነው። ዩናይትዶች አዲሱ የውድድር ዘመን ከመጀመሩ በፊት የሚከናወኑ ጨዋታዎችን ለማድረግ አውስትራሊያ የሚገኙ ሲሆን፤ ኦሌ ጉና ሶልሻየር ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ስለ የቀጣዩ የውድድር ዘመን እቅዳቸውን ጨምሮ ስለ አሌክሲስ ሳንቼዝ እና ፖል ፖግባ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። • "እንዴት ለሴት ልጅ የወንዶች ክለብ ይሰጣል?' ተብሎ ነበር" መሠረት ማኒ ኦሌ ጉና ስለቀጣዩ የውድድር ዓመት ሲናገሩ፤ በሊጉ ሰንጠረዥ የመጀመሪያዎቹ አራት ውስጥ ለመጨረስ ከሚደረገው ጥረት በላይ ማድረግ ይኖርብናል ብለዋል። "ተሰጥኦ ያላቸው ተጫዋቾች አሉን በተጨማሪም ለቡድኑ በትክክል የሚመጥኑ ተጨዋቾችን በማስፈረም ከምንፈልገው ቦታ ላይ መድረስ እንችላለን። የሚጠበቅብን ወጥ የሆነ አቋም ላይ መገኘት መቻል ነው። በየቀኑ ጠንክረን እየሰራን ከእቅዳችን ዘንበል ማለት የለብንም።" የዩናይትዶቹ አሰልጣኝ ኦሌ ጉና ሶልሻየር ለቡድኑ ስኬት የፖል ፖግባ አሰተዋጽኦ ከፍተኛ እንደሆነ ይናገራሉ። ኦሌ ''ፖል ድንቅ ተጫዋች እና የሚደንቅ ሰው። በሞልዴ ክለብ እያለሁ፤ 'ፖል በቡድን ውስጥ ካለ፤ በእሱ ላይ በመመስረት ቡደን መመስረት ይቻላል' እል ነበር። አሁንም ተመሳሳይ እምነት ነው ያለኝ። የዩናትድ ደጋፊዎች የቡድናቸውን አጨዋወት ያውቃሉ። ፖልን የሚተቹ ብዙ ቢሆንም በበርካቶች ግን ይወደዳል። • «የኔ ትውልድ ታሪክ እንደሚሠራ እምነት አለኝ» ሎዛ አበራ ከአርሰናል ወደ ማንችስተር የተዘዋወረው አሌክሲስ ሳንቼዝ በክለቡ ውስጥ ትልቅ ስም እና ክፍያ ካላቸው ቀዳሚ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነው። ይሁን እንጂ ሳንቼዝ ወደ ማንችስትር ከተዘዋወረ በኋላ በክለቡ ወጥ አቋም ማሳየት አልቻለም። ''የአሌክሲስን አቅም ሳስብ ትልቅ እረፍት ይሰጠኛል። ማድረግ የሚችለውን እናውቃለን። ምን ማድረግ እንዳለብን ነው መለየት ያለብን። ምክንያቱም አሌክሲስ በቀላሉ 20 ጎሎችን ሊሰጠን የሚችል ተጫዋች ነው። በኮፓ አሜሪካ ላይ ይህን አይተናል። ወጥ አቋም ማየት አልቻለንም በተጨማሪም ጎዳቶች ሲያጋጥሙት ነበር። ወደ ድንቅ አቋሙ ይመለሳል ብለን እናስባለን'' በማንችሰተር ዩናይትድ ቤት ውስጥ የተጫዋቾች ዝውውር ስትራቴጂን በሚመለከት ''እዚህ የማልፈልጋቸው ተጫዋቾች የሉም። አሁንም አንድ ወይም ሁለት ተጫዋቾችን ለማስፈረም እየሞከርን ነው። ክለቡን የሚለቁ ተጫዋቾች ካሉ እነሱን ለመተካት ሌሎች ተጫዋቾችን የማስፈረሙ ስራ ይኖራል'' ሲሉ መልሰዋል። ኦሌ ጉና ስለ ወጣቱ ሜይሰን ግሪንውድ አስተያየታቸውን ሲሰጡ ''ተፈጥሯዊ የእግር ኳስ ክህሎት ያለው ተጫዋች ነው። በቀኝ እግሩም ሆነ በግራ እግሩ ጎል ያስቆጥራል። ሁለቱንም እግሮቹን በሚገርም ብቃት ይጠቀማል። ቀኝ ወይም ግራኝ ስለመሆኑ እርሱ እራሱ የሚያውቀው አይመስለኝም። መቶ በመቶ እርግጠኛ የምሆነው በዚህ የውድድር ዘመን ጎሎችን ያስቆጥራል'' ከቀድሞ የክለቡ አልጣኝ ሰር አሌክ ፈርጉሰን ጋር ስላላቸው ግነኙነት የተጠየቁት ኦሌ ''ለ14 ዓመት ከፈርጉሰን ጋር አብሬ ሰርቻለሁ። አብዛኛው የእግር ኳስ ህይወቴ ከእርሱ ጋር ነው ያሳለፍኩት። ከፈርጉሰን ብዙ ትመሬያለሁ ይህ እውነት ነው። ከጨዋታ በኋላ አልፎ አልፎ እንነጋገራለን፣ የጽሁፍ መልዕክት እንላላካለን ከዚህ ውጪ ሌሎች ብዙ የሚባሉት ነገሮች ግን ስህተት ናቸው። • ያለእድሜ ጋብቻን በእግር ኳስ የምትታገለው ታዳጊ ኦሌ ጉና በስተመጨረሻም ቡድን እንደ አዲስ ማዋቀር ጊዜ የሚወስድ መሆኑን በመጠቀስ የዩናይትድ ደጋፊዎች ትዕግስት እንዲኖራቸው ጠይቀዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-49013411
3politics
በኢትዮጵያ መንግሥትና በትግራይ አመራሮች መካከል ንግግር መቀጠሉን ተመድ አስታወቀ
በኢትዮጵያ መንግሥት እና በትግራይ አመራሮች መካከል ያለው ውይይት መቀጠሉን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና መሐመድ አዲስ አበባ ውስጥ ዛሬ ረቡዕ የካቲት 02/2014 ዓ.ም ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ ነው ይህንን የተናገሩት። ምክትል ዋና ፀሐፊዋ በጦርነቱ የተጎዱትን የትግራይ፣ የአማራና የአፋር ክልሎችን ከጎበኙ በኋላ ለሰላም ተስፋ እንዳለ የገለጹ ሲሆን "በእርግጥከጥቂት ወራት በፊት ከነበረው አንፃር አነስተኛ ግጭቶች ናቸው የሚታዩት" ብለዋል። ምክትል ዋና ፀሐፊዋ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ "በአሁኑ ወቅት በእርግጠኛነት የተሻለ ቦታ ላይ ነን። ተጨማሪ ውይይቶችም አሉ" በማለት አስረድተዋል። ከትግራይ አመራሮች፣ ከአማራ እንዲሁም ከፌደራል መንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ውይይት ያደረጉት አሚና መሐመድ ግጭቱ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል። ለአስራ አምስት ወራት የዘለቀውን የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ተፋላሚ ወገኖች በቅርቡ ለሰላም ያሳዩትን እርምጃ በበጎ እንደሚያዩት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ከቀናት በፊትም መግለጻቸው ይታወሳል። ሰላም ለማስፈን ግጭቱን እንዲሁም ተኩስ ማቆም ወሳኝ እርምጃ እንደሆነ የተናገሩት አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ተፋላሚ ወገኖች ይህንን እርምጃ እንዲወስዱ ጠይቀዋል። አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ከዚህ ቀደምም ጦርነቱን ለማብቃትና ሰላም ለማውረድ የሚያስችል የሚታይ ጥረት እየተደረገ መሆኑ እንዳስደሰታቸው መግለጻቸው ይታወሳል። ዋና ፀሐፊው የአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ ከሆኑት ከኦሉሴጎን ኦባሳንጆ ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት፣ በሰሜን ኢትዮጵያ የሚካሄደውን ጦርነት ለማስቆም የኢትዮጵያ መንግሥትና ህወሓት እያደረጉት ስላላው ጥረት ከሕብረቱ ተወካይ መረዳታቸውን በወቅቱ አስታውቀው ነበር። በአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ዋና ፀሐፊውን በመወከል የመንግሥታቱ ድርጅት ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና መሐመድ የተገኙ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ቆይታቸው በጦርነቱ የተጎዱ የአማራና የትግራይ ክልል ከተሞችን ጎብኝተዋል። እንዲሁም ከክልል አመራሮችም ጋር ተገናኝተዋል። ምክትል ዋና ፀሐፊዋ በክልሎቹ ከሴቶችና ተማሪዎች ጋር ባደረጉት ቆይታ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ወሲባዊ እንዲሁም ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን እንደማይታገስ አፅንኦት በመስጠት ተናግረዋል። ወሲባዊ ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች አጋርነታቸውን የገለጹት አሚና፣ በጦርነቱ ሳቢያ በሴቶች ላይ የደረሰውን ግፍና በደል እንዲሁም አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ጉዳት ለማቃለል ድርጅታቸው መፍትሄ በማፈላለግ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል። ሴቶች ካለባቸው ህመም እንዲፈወሱ በተሃድሶ እና በመልሶ ማቋቋም ሥራዎች ውስጥ እንዲካተቱም አመራሮቹን አሳስበዋል። በተጨማሪም ተመድ በኢትዮጵያ የሚደረገውን የሰላም ጥረትም ይደግፋል ብለዋል። ከአሚና በተጨማሪ በአፍሪካ ቀንድ የአፍሪካ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ ኦሉሴጎን ኦባሳንጆ ሰኞ ዕለት በአማራ ክልል የኮምቦልቻ ከተማን እንዲሁም ወደ ትግራይ እና አፋር ክልሎችም በመሄድ ጉብኝት አድርገዋል። ባለፈው ዓመት ጥቅምት መጨረሻ ላይ ትግራይ ውስጥ ተከስቶ ወደ አማራና አፋር ክልሎች የተዛመተው ደም አፋሳሽ ጦርነት ሺዎችን በመቅጠፍና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን በማፈናቀል መጠነ ሰፊ ሰብዓዊ ቀውስ አድርሷል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከቀናት በፊት ባወጣው ሪፖርት እንዳመለከተው በትግራይ ክልል ውስጥ 40 በመቶ የሚጠጉ ሰዎች በአስከፊ የምግብ እጥረት እየተሰቃዩ መሆናቸውን ገልጿል። ከአስራ አምስት ወራት በላይ ያስቆጠረው ይህ ጦርነት እንዲቋጭ አሜሪካን ጨምሮ ኬንያና ሌሎች አገሮች ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ። በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ዴቪድ ሳተርፊልድ በቅርቡ ወደ አዲስ አበባ የተጓዙ ሲሆን የአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴንጎ ኦባሳንጆም የትግራይ መሪዎችን አነጋግረዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥታቸው ከትግራይ ኃይሎች ጋር ለመነጋገር ዝግጁ መሆኑን መናገራቸውን አሶሺየትድ ፕሬስ የዜና ወኪል (ኤፒ) ዘግቦ ነበር። የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) መሪ ደብረጽዮን ገብረሚካኤል በህወሓትና በኢትዮጵያ መንግሥት መካከል ቀጥተኛ ያልሆነ ንግግር እየተደረገ መሆኑን ለቢቢሲ ከሳምንት በፊት ተናግረዋል። ደብረጽዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) ይህ እየተደረገ ያለው ቀጥተኛ ያልሆነ ውይይት የተወሰነ ውጤት እያሳየ መሆኑንና የመሻሻል ምልክቶች እንዳሉ አመልክተው ነበር። እየተካሄደ ነው ስለተባለው ቀጥተኛ ያልሆነ ውይይትን በተመለከተ ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል አስካሁን የተባለ ነገር የለም።
በኢትዮጵያ መንግሥትና በትግራይ አመራሮች መካከል ንግግር መቀጠሉን ተመድ አስታወቀ በኢትዮጵያ መንግሥት እና በትግራይ አመራሮች መካከል ያለው ውይይት መቀጠሉን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና መሐመድ አዲስ አበባ ውስጥ ዛሬ ረቡዕ የካቲት 02/2014 ዓ.ም ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ ነው ይህንን የተናገሩት። ምክትል ዋና ፀሐፊዋ በጦርነቱ የተጎዱትን የትግራይ፣ የአማራና የአፋር ክልሎችን ከጎበኙ በኋላ ለሰላም ተስፋ እንዳለ የገለጹ ሲሆን "በእርግጥከጥቂት ወራት በፊት ከነበረው አንፃር አነስተኛ ግጭቶች ናቸው የሚታዩት" ብለዋል። ምክትል ዋና ፀሐፊዋ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ "በአሁኑ ወቅት በእርግጠኛነት የተሻለ ቦታ ላይ ነን። ተጨማሪ ውይይቶችም አሉ" በማለት አስረድተዋል። ከትግራይ አመራሮች፣ ከአማራ እንዲሁም ከፌደራል መንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ውይይት ያደረጉት አሚና መሐመድ ግጭቱ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል። ለአስራ አምስት ወራት የዘለቀውን የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ተፋላሚ ወገኖች በቅርቡ ለሰላም ያሳዩትን እርምጃ በበጎ እንደሚያዩት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ከቀናት በፊትም መግለጻቸው ይታወሳል። ሰላም ለማስፈን ግጭቱን እንዲሁም ተኩስ ማቆም ወሳኝ እርምጃ እንደሆነ የተናገሩት አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ተፋላሚ ወገኖች ይህንን እርምጃ እንዲወስዱ ጠይቀዋል። አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ከዚህ ቀደምም ጦርነቱን ለማብቃትና ሰላም ለማውረድ የሚያስችል የሚታይ ጥረት እየተደረገ መሆኑ እንዳስደሰታቸው መግለጻቸው ይታወሳል። ዋና ፀሐፊው የአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ ከሆኑት ከኦሉሴጎን ኦባሳንጆ ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት፣ በሰሜን ኢትዮጵያ የሚካሄደውን ጦርነት ለማስቆም የኢትዮጵያ መንግሥትና ህወሓት እያደረጉት ስላላው ጥረት ከሕብረቱ ተወካይ መረዳታቸውን በወቅቱ አስታውቀው ነበር። በአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ዋና ፀሐፊውን በመወከል የመንግሥታቱ ድርጅት ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና መሐመድ የተገኙ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ቆይታቸው በጦርነቱ የተጎዱ የአማራና የትግራይ ክልል ከተሞችን ጎብኝተዋል። እንዲሁም ከክልል አመራሮችም ጋር ተገናኝተዋል። ምክትል ዋና ፀሐፊዋ በክልሎቹ ከሴቶችና ተማሪዎች ጋር ባደረጉት ቆይታ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ወሲባዊ እንዲሁም ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን እንደማይታገስ አፅንኦት በመስጠት ተናግረዋል። ወሲባዊ ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች አጋርነታቸውን የገለጹት አሚና፣ በጦርነቱ ሳቢያ በሴቶች ላይ የደረሰውን ግፍና በደል እንዲሁም አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ጉዳት ለማቃለል ድርጅታቸው መፍትሄ በማፈላለግ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል። ሴቶች ካለባቸው ህመም እንዲፈወሱ በተሃድሶ እና በመልሶ ማቋቋም ሥራዎች ውስጥ እንዲካተቱም አመራሮቹን አሳስበዋል። በተጨማሪም ተመድ በኢትዮጵያ የሚደረገውን የሰላም ጥረትም ይደግፋል ብለዋል። ከአሚና በተጨማሪ በአፍሪካ ቀንድ የአፍሪካ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ ኦሉሴጎን ኦባሳንጆ ሰኞ ዕለት በአማራ ክልል የኮምቦልቻ ከተማን እንዲሁም ወደ ትግራይ እና አፋር ክልሎችም በመሄድ ጉብኝት አድርገዋል። ባለፈው ዓመት ጥቅምት መጨረሻ ላይ ትግራይ ውስጥ ተከስቶ ወደ አማራና አፋር ክልሎች የተዛመተው ደም አፋሳሽ ጦርነት ሺዎችን በመቅጠፍና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን በማፈናቀል መጠነ ሰፊ ሰብዓዊ ቀውስ አድርሷል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከቀናት በፊት ባወጣው ሪፖርት እንዳመለከተው በትግራይ ክልል ውስጥ 40 በመቶ የሚጠጉ ሰዎች በአስከፊ የምግብ እጥረት እየተሰቃዩ መሆናቸውን ገልጿል። ከአስራ አምስት ወራት በላይ ያስቆጠረው ይህ ጦርነት እንዲቋጭ አሜሪካን ጨምሮ ኬንያና ሌሎች አገሮች ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ። በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ዴቪድ ሳተርፊልድ በቅርቡ ወደ አዲስ አበባ የተጓዙ ሲሆን የአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴንጎ ኦባሳንጆም የትግራይ መሪዎችን አነጋግረዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥታቸው ከትግራይ ኃይሎች ጋር ለመነጋገር ዝግጁ መሆኑን መናገራቸውን አሶሺየትድ ፕሬስ የዜና ወኪል (ኤፒ) ዘግቦ ነበር። የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) መሪ ደብረጽዮን ገብረሚካኤል በህወሓትና በኢትዮጵያ መንግሥት መካከል ቀጥተኛ ያልሆነ ንግግር እየተደረገ መሆኑን ለቢቢሲ ከሳምንት በፊት ተናግረዋል። ደብረጽዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) ይህ እየተደረገ ያለው ቀጥተኛ ያልሆነ ውይይት የተወሰነ ውጤት እያሳየ መሆኑንና የመሻሻል ምልክቶች እንዳሉ አመልክተው ነበር። እየተካሄደ ነው ስለተባለው ቀጥተኛ ያልሆነ ውይይትን በተመለከተ ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል አስካሁን የተባለ ነገር የለም።
https://www.bbc.com/amharic/news-60319702
3politics
ለሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ሰላማዊ መፍትሄ ለማግኘት ያሉ እድሎችና ተግዳሮቶች
በትግራይ አማፂያን ላይ ድል መቀዳጀቱ የሚገልጸው የኢትዮጵያ መንግሥት፣ ወደ ትግራይ ሰፊ ወታደራዊ ዘመቻ ለማካሄድ ዕቅድ እንደሌለውና በያዛቸው ቦታዎች ተወስኖ እንዲሚቆይ ካሳወቀ ሰነባብቷል። የትግራይ ኃይሎች በበኩላቸው፣ ከአንድ ዓመት በላይ ያስቆጠረውና ከፍተኛ ማኅበራዊ ቀውስ ላስከተለው የእርስ በርስ ጦርነት የሰላም ዕድል ለመስጠት በሚል ከአፋርና ከአማራ ክልሎች ጠቅልለው መውጣታቸውን ይናገራሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ የአፋር ክልላዊ መንግሥት የህወሓት አማፂያን በሰላማዊ የክልሉ ነዋሪዎች ላይ ጥቃት መክፈታቸውን እና የተወሰኑ አካባቢዎችን መቆጣጠራቸውን አሳውቋል። ይህንንም ተከትሎ የፌደራል መንግሥቱ የህወሓት አማፂያን የሚያደርጉትን ትንኮሳ ለመከላከል የመከላከያ እና የክልል ፀጥታ ኃይሎች እርምጃ እንዲወስዱ ትዕዛዝ ሰጥቷል። በትግራይና በተለያዩ አዋሳኝ አካባቢዎች ውጊያዎች መኖራቸው የሚገጸው የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት በበኩሉ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ አሳሳቢ እና ሊተነበይ የማይችል እንደሆነ ባወጣው ሪፖርት አመልክቷል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የፖለቲካ ተንታኞች አንዱ ወገን የሌላውን የማድረግ አቅም ለማደከም ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን ጠቅሰው ነገር ግን በሁለቱም በኩል በጦርነት የመቀጠል ፍላጎታቸው መቀነሱን ያስረዳሉ። ያገረሹ ግጭቶች የትግራይ ኃይሎች ከሁለቱም ክልሎች መውጣታቸው የኢትዮጵያ መንግሥትም፣ ወደ ትግራይ ክልል አልዘልቅም ማለቱ በተወሰነ ደረጃ ጦርነቱ ረገብ እንዲል አድርጎታል። በአንዳንድ ድንበር አካባቢዎች ያለው አለመረጋጋት ግን ተጨማሪ ስጋት እያስከተለ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታትም ሆነ የፖለቲካ ተንታኞች ያነሱታል። "የሰላም ምልክት ያለ ቢመስልም አሳሳች ድምዳሜ ላይ መድረስ ግን አይገባም። ምክንያቱም ጦርነቱ ረገብ ቢልም፣ በአንዳንድ የትግራይ አዋሳኝ አካባቢዎች ውጊያ የቀጠለበት ሁኔታ አለ። በአላማጣ፣ በማይ ጸብሪና በዓዲ ዓርቃይ አካባቢዎች ከባድ ውጊያ መካሄዱን ሰምተናል" ይላሉ የክራይስ ግሩፕ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ዊልያም ዴቪሰን። ከዊሊያም ዴቪሰን ሃሳብ ጋር የሚስማሙት የፖለቲካ ተንታኙ አደም ካሴ (ዶ/ር)፤ በበኩላቸው በአንዳንድ የድንበር አካባቢዎች የሚስተዋለው ግጭት እየታየ ያለውን የሰላም ተስፋ የሚያጨልም እንዳይሆን ስጋት እንደሆነ ይናገራሉ። "ግጭቱን ማነው ያስነሳው የሚለው ለማወቅ ከባድ ነገር ቢሆንም፣ በትግራይ ኃይሎች በኩል ግን ወደ ሰላም ድርድር መግባታችን ስለማይቀር በምንችለው መጠን አቅሙን እናዳክመው የሚል እሳቤ ሊኖር ይችላል" ሲሉም ያክላሉ። "ያም ሆነ ይህ በሁለቱም በኩል በጦርነት ዓላማቸውን ለማሳካት ያለው ፍላጎት የቀነሰ ይመስላል። ሁለተኛው ነገር ስምምነት ላይ እስኪደረስ በቻሉት መጠን አንደኛው የሌላኛውን አቅም የማዳከም ጥረት እያደረጉ ሊሆን ይችላል ብዬ አስባለሁ።'" እስከ አሁን ድረስ ከፌደራል መንግሥቱ በኩል የተሰማ ነገር ባይኖርም የሰላም ዕድል መኖሩን ግን ዶክተር አደም ይገልጻሉ። "ድምዳሜ ለመስጠት ልንቸኩል አይገባም። ምክንያቱም በትግራይ በኩል አንድ ድርጅት ነው ያለው፤ በፌዴራል በኩል ግን ብዙ ተሳታፊዎች አሉ፣ ብዙ ፍላጎቶች አሉ። በፓርቲቹ በኩል የአስተሳሰብም የአካሄድም ልዩነትም አለ" በማለት አደም (ዶ/ር) ሁኔታውን ያስረዳሉ። የሰላምጭላንጭል ዊልያም ዴቪሰን ሁኔታው በሁለቱም ወገኖች መካከል የሰላም ፍላጎት እንዳለ የሚያመለክት ሁኔታ መኖሩን ያምናሉ። ከማሳያዎቹም "የትግራይ ኃይሎች ከአፋርና ከአማራ ክልሎች መውጣታቸው አንዱን የፌዴራል መንግሥት ፍላጎት አሟልቷል ማለት ይቻላል።" የፖለቲካ ተንታኙ አደም ካሴ (ዶ/ር) በበኩላቸው ሁለቱም ተፋላሚ ኃይሎች አላማቸውን በጦርነት ለማሳካት ያላቸውን ፍላጎት እየተዉ መምጣታቸውን ያስረዳሉ። "የፌዴራል መንግሥቱ ወደ ትግራይ ክልል ዘልቆ አለመግባት፣ የትግራይ ኃይሎች ደግሞ ተገድደውም ይሁን ፈቅደው ወደ ኋላ መመለሳቸው፤ ሁለቱም 'የምንፈልገውን ዓላማ በጦርነት ብቻ እናሳካለን የሚለውን ነገር ያቆሙ ይመስለኛል" ይላሉ። ዊሊያም አክለውም የትግራይ አማፂያን ከአማራ እና ከአፋር ክልል መውጣታቸውን ተከትሎ ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ለተባበሩት መንግሥታት በጻፉት ደብዳቤ፤ የአማራ እና የኤርትራ ኃይሎች ከምዕራብ ትግራይ እንዲወጡና እርምጃ እንዲወሰድ መጠየቃቸው፣ በትግራይ አመራር በኩል የአስተሳሰብ ለውጥ መኖሩ የሚያመላክት ነው ይላሉ። እንዲሁም፣ በፌዴራል መንግሥት በኩል የተቃውሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራር እና አባል የሆኑ እሰረኞቹን መፍታቱ በአገሪቱ ያለው ቀውስ በሰላማዊ ድርድር እንዲያልቅ ፍላጎት እንዳለ የሚሳይ መሆኑን ይናገራሉ። አደም ካሴ (ዶ/ር) በበኩላቸው "በሥርዓትና ይፋዊ በሆነ መልኩ የተኩስ ማቆም ስምምነት እስካልታወጀ ድረስ ያለው ሁኔታ አስተማማኝ አይደለም" በማለት ያለውን የታየውን ለውጥ ይገልጹታል። "በእኔ እምነት ያንን ግምት ውስጥ በማስገባት ይመስላል የፌዴራል መንግሥቱ የአየር ላይ ጥቃት እያካሄደ ያለው፤ ከመደራደራችን በፊት በተቻለ መጠን የትግራይ ኃይሎች የመደራደር አቅም ማዳከም አለብን የሚል እሳቤ ያለ ይመስለኛል" ሲሉም ግምታቸውን ያስቀምጣሉ። ስጋቶችና እንቅፋቶች በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ካለው ጦርነት ጋር በተያያዘ አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር ወደ 9.4 ሚሊዮን እንደደደረሰ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ካለፈው ዓመት ሰኔ ወር አጋማሽ ጀምሮ ከትግራይ ለቅቆ ቢወጣም ክልሉ "ይፋዊ ባልሆነ የሰብዓዊ እርዳታ እቀባ" ውስጥ በመሆኑ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው የማቅረቡ ሥራ አስቸጋሪ መሆኑንም ጨምሮ ገልጿል። ምንም እንኳ የኢትዮጵያ መንግሥት በወቅቱ የሰብዓዊ እርዳታ እንዳይደርስ ምንም አይነት እቀባ አለማድረጉን ቢገልፅም፣ በክልሉ የሚገኙ አስቸኳይ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች በከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደሚገኙ በተደጋጋሚ ሲገለጽ ቆይቷል። የሕክምና አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትም ቢሆኑም ከመድኃኒት እና አስፈላጊ ቁሳቁሶች ውጪ መሆናቸውን በመጥቀስ በቀላል ሕክምና የሚድኑ ሕሙማን ህይወታቸውን እያጡ መሆኑን ይናገራሉ። በቅርቡም በአፋር ክልል በአባላ እየተካሄደ ባለው ጦርነት የተነሳ ምንም ዓይነት የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ መኪኖች ማለፍ አለመቻላቸውን የኢትዮጵያ መንግሥት እንዲሁም ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ድርጅቶች ገልጸዋል። ዊልያም ዴቪሰን በአጭር ጊዜ የሰላም ድርድር ካልተጀመረ የትግራይ ኃይሎች ይህንን 'የሰብዓዊ እርዳታ ዕቀባ' ለማስከፈት እና የትግራይ ክልልን ከጦርነቱ በፊት ወደ ነበረበት ለመመለስ፣ በተለይ በምዕራብ ትግራይ ጦርነት መክፈታቸው አይቀርም ይላሉ። "የትግራይ ኃይሎች ወደ ኋላ ሲመለሱ ብዙ ጉዳት ደርሶባቸው ሊሆን ይችላል" የሚል ግምት ያላቸው ዳቪሰን፣ አሁንም ድረስ ግን ከፍተኛ የጦር ኃይል እንዳለቸው ያምናሉ። "የትግራይ ኃይሎች በማናቸውም መመዘኛ አሁንም ከፍተኛ ጦር ነው ያላቸው። እነርሱ ሕዝባቸው ላይ ተከፍቶበታል ከሚሉት 'የዘር ማጥፋት' ዘመቻ ለመከላከል የህልውና ትግል እያደረጉ እንደሆነ በጽኑ ያምናሉ።" በተጨማሪም "አዲስ አበባ እና አሥመራ ያሉት መንግሥታት ደግሞ የትግራይ ኃይሎች ለራሳቸውና ለሕዝባቸው ዋነኛ ስጋት አድርገው ነው የሚመለከቷቸው" ይላሉ ዴቪሰን። ይህ በሁለቱም ወገን ያለው አመለካከት ደግሞ ለሚታሰበው የሰላም ሂደት "ከባዱ እንቅፋቱ" ሊሆን እንደሚችልና "በመካከላቸው ካለው አለመተማመንና መጠራጠር አንጻር የትግራይ ኃይሎች ሠራዊታቸውን ለመበተን የሚስማሙ አይመስለኝም" ይላሉ። አደም (ዶ/ር) በበኩሉ፣ በተለይ በአፋርና በአማራ ክልል በኩል ጦርነቱ በሰላም የማያልቅ ከሆነ መልሶ ጥቃት እንዳይደርስባቸው ተጨባጭ ስጋት እንዳለ ይገምታሉ። በትግራይ በኩልም፣ የፌዴራል መንግሥቱ ወደ ትግራይ ክልል ገፍቼ 'አልሄድም' ቢልም ጥርጣሬዎች እንደሚፈጠሩ ያስገነዝባል። ለዚህ ደግሞ "በትግራይ፣ በአፋርና በአማራ ክልል አንዳቸው ወደሌላኛው በኩል ዘልቆ የመግባት ዕቅድ እንደሌላቸው ሁሉም ማሳየት አለባቸው።" የእስረኞች መፈታት በቅርቡ አቶ ጃዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለን ገርባ እንዲሁም አቶ እስክንደር ነጋን ጨምሮ ከፍተኛ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ከእስር ተፈትተዋል። ዊልያም ዴቪሰን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የወሰዱት እሰረኞችን የመፍታት እርምጃ፣ በተለይ ሊካሄድ ለታቀደው አገራዊ ውይይት አሳታፊ እንዲሆን ለማድረግ ጉልህ ሚና እንዳለው ያምናሉ። አቶ ስብሐት ነጋን ጨምሮ ስድስት ነባር የህወሓት አመራሮች መፈታታቸውን በተመለከተ ግን "እምብዛም ፖለቲካዊ ትርጉም የለውም" ይላሉ ዴቪሰን። "እነዚህ የህወሓት የፖሊት ቢሮ አባላት ያልሆኑትን መፍታት እንደ ትልቅ ጉዳይ አድርጌ አላየውም፤ ሰላማዊ ድርድር እንዳይደርግ እንቅፋት የሆኑት ጉዳዮችን ከመቀነስ አንጻር፤ እምብዛም ለውጥ የሚያመጣ እርምጃ መስሎም አይታየኝም።" ይህ ብቻ ሳይሆን ህወሓትና ኦነግ-ሸኔ በሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት በአሸባሪነት መዝገብ መስፈራቸው ለሚደረጉ የሰላም ንግግሮች እና ድርድሮች እንቅፋት ሊሆን እንደሚችል ሁለቱም ተንታኞች ይስማማሉ። ድርጅቶቹ ከዚህ ፍረጃ ካልወጡ በስተቀር፣ የሰላም ድርድር እንዳይደርግ እንቅፋት ሊሆን ይችላል የሚል ስጋትም እዚህም እዚያም ይደመጣል። ይህንን በተመለከተ ዊሊያም ዴቪሰን፣ ድርጅቶቹ ከዚህ ፍረጃ ወጥተው፣ የተኩስ አቁም ስምምነት ተደርጎ፣ የአገር አቀፍ መድረኩ ውስጥ እንዲሳተፉ ካልተደረገ፣ አገራዊ ውይይቱ ውጤት አያመጣም የሚል እምነት እንዳላቸው ያስረዳሉ። ማምለጥ የሌለበት ዕድል የዓለም አቀፍ እና አህጉራዊ ተቋማት እንዲሁም አገራት ትግራይ ውስጥ ተጀምሮ ወደ አጎራባች ክልሎች ተዛምቶ ከፍተኛ ቀውስ ያስከተለው ጦርነት በሰላማዊ መገድ እንዲፈታ ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል። ከጦርነቱ ጋር ተያይዞ ሻክሮ የነበረው የኢትዮጵያና የአሜሪካ መንግሥታት ግንኙነት መሻሻል ሰላም ለማውረድ አዎንታዊ ሚና ሊኖረው እንደሚችል ይታመናል። ዊልያም ዴቪሰን የሰላም ሂደቱ ውጤት እንዲያመጣና ጦርነቱ እንዲቆም ግን በተለይ በትግራይ ያለውን 'የሰብዓዊ እርዳታ እቀባ' በአስቸኳይ መፈታት አለበት ይላሉ። "ሁለቱም ወገኖች የሰላም ዕድሉ ሊያመልጣቸው አይገባም" የሚሉት ዳቪሰን፤ ስልክ፣ መብራትና ባንክን የመሳሰሉ መሠረታዊ አገልግሎቶች መከፈት እንዳለባቸው እንደ መፍትሄ ሃሳብ ያቀርባሉ። አደም ካሴ (ዶ/ር) በበኩላቸው የምዕራብ ትግራይን ጉዳይ በማንሳት በሁለቱም የፖለቲካ ተፋላሚ ወገኖች በኩል "አስቸጋሪ የፖለቲካ ጭቅጭቅ" ሊሆን እንደሚችል ይናገራሉ። "ሁለቱም ወገኖች ቢያንስ የሕግ ሥርዓቱን መከተል አለባቸው" ነገር ግን ችግሩ የመጨረሳውን ዕልባት የሚያገኘው በፖለቲካዊ መንገድ በመሆኑ ይህም ወደተሻለ መተማመን እንደሚያደርስ በመግለጽ ሃሳባቸውን ያጠናቅቃሉ።
ለሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ሰላማዊ መፍትሄ ለማግኘት ያሉ እድሎችና ተግዳሮቶች በትግራይ አማፂያን ላይ ድል መቀዳጀቱ የሚገልጸው የኢትዮጵያ መንግሥት፣ ወደ ትግራይ ሰፊ ወታደራዊ ዘመቻ ለማካሄድ ዕቅድ እንደሌለውና በያዛቸው ቦታዎች ተወስኖ እንዲሚቆይ ካሳወቀ ሰነባብቷል። የትግራይ ኃይሎች በበኩላቸው፣ ከአንድ ዓመት በላይ ያስቆጠረውና ከፍተኛ ማኅበራዊ ቀውስ ላስከተለው የእርስ በርስ ጦርነት የሰላም ዕድል ለመስጠት በሚል ከአፋርና ከአማራ ክልሎች ጠቅልለው መውጣታቸውን ይናገራሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ የአፋር ክልላዊ መንግሥት የህወሓት አማፂያን በሰላማዊ የክልሉ ነዋሪዎች ላይ ጥቃት መክፈታቸውን እና የተወሰኑ አካባቢዎችን መቆጣጠራቸውን አሳውቋል። ይህንንም ተከትሎ የፌደራል መንግሥቱ የህወሓት አማፂያን የሚያደርጉትን ትንኮሳ ለመከላከል የመከላከያ እና የክልል ፀጥታ ኃይሎች እርምጃ እንዲወስዱ ትዕዛዝ ሰጥቷል። በትግራይና በተለያዩ አዋሳኝ አካባቢዎች ውጊያዎች መኖራቸው የሚገጸው የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት በበኩሉ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ አሳሳቢ እና ሊተነበይ የማይችል እንደሆነ ባወጣው ሪፖርት አመልክቷል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የፖለቲካ ተንታኞች አንዱ ወገን የሌላውን የማድረግ አቅም ለማደከም ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን ጠቅሰው ነገር ግን በሁለቱም በኩል በጦርነት የመቀጠል ፍላጎታቸው መቀነሱን ያስረዳሉ። ያገረሹ ግጭቶች የትግራይ ኃይሎች ከሁለቱም ክልሎች መውጣታቸው የኢትዮጵያ መንግሥትም፣ ወደ ትግራይ ክልል አልዘልቅም ማለቱ በተወሰነ ደረጃ ጦርነቱ ረገብ እንዲል አድርጎታል። በአንዳንድ ድንበር አካባቢዎች ያለው አለመረጋጋት ግን ተጨማሪ ስጋት እያስከተለ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታትም ሆነ የፖለቲካ ተንታኞች ያነሱታል። "የሰላም ምልክት ያለ ቢመስልም አሳሳች ድምዳሜ ላይ መድረስ ግን አይገባም። ምክንያቱም ጦርነቱ ረገብ ቢልም፣ በአንዳንድ የትግራይ አዋሳኝ አካባቢዎች ውጊያ የቀጠለበት ሁኔታ አለ። በአላማጣ፣ በማይ ጸብሪና በዓዲ ዓርቃይ አካባቢዎች ከባድ ውጊያ መካሄዱን ሰምተናል" ይላሉ የክራይስ ግሩፕ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ዊልያም ዴቪሰን። ከዊሊያም ዴቪሰን ሃሳብ ጋር የሚስማሙት የፖለቲካ ተንታኙ አደም ካሴ (ዶ/ር)፤ በበኩላቸው በአንዳንድ የድንበር አካባቢዎች የሚስተዋለው ግጭት እየታየ ያለውን የሰላም ተስፋ የሚያጨልም እንዳይሆን ስጋት እንደሆነ ይናገራሉ። "ግጭቱን ማነው ያስነሳው የሚለው ለማወቅ ከባድ ነገር ቢሆንም፣ በትግራይ ኃይሎች በኩል ግን ወደ ሰላም ድርድር መግባታችን ስለማይቀር በምንችለው መጠን አቅሙን እናዳክመው የሚል እሳቤ ሊኖር ይችላል" ሲሉም ያክላሉ። "ያም ሆነ ይህ በሁለቱም በኩል በጦርነት ዓላማቸውን ለማሳካት ያለው ፍላጎት የቀነሰ ይመስላል። ሁለተኛው ነገር ስምምነት ላይ እስኪደረስ በቻሉት መጠን አንደኛው የሌላኛውን አቅም የማዳከም ጥረት እያደረጉ ሊሆን ይችላል ብዬ አስባለሁ።'" እስከ አሁን ድረስ ከፌደራል መንግሥቱ በኩል የተሰማ ነገር ባይኖርም የሰላም ዕድል መኖሩን ግን ዶክተር አደም ይገልጻሉ። "ድምዳሜ ለመስጠት ልንቸኩል አይገባም። ምክንያቱም በትግራይ በኩል አንድ ድርጅት ነው ያለው፤ በፌዴራል በኩል ግን ብዙ ተሳታፊዎች አሉ፣ ብዙ ፍላጎቶች አሉ። በፓርቲቹ በኩል የአስተሳሰብም የአካሄድም ልዩነትም አለ" በማለት አደም (ዶ/ር) ሁኔታውን ያስረዳሉ። የሰላምጭላንጭል ዊልያም ዴቪሰን ሁኔታው በሁለቱም ወገኖች መካከል የሰላም ፍላጎት እንዳለ የሚያመለክት ሁኔታ መኖሩን ያምናሉ። ከማሳያዎቹም "የትግራይ ኃይሎች ከአፋርና ከአማራ ክልሎች መውጣታቸው አንዱን የፌዴራል መንግሥት ፍላጎት አሟልቷል ማለት ይቻላል።" የፖለቲካ ተንታኙ አደም ካሴ (ዶ/ር) በበኩላቸው ሁለቱም ተፋላሚ ኃይሎች አላማቸውን በጦርነት ለማሳካት ያላቸውን ፍላጎት እየተዉ መምጣታቸውን ያስረዳሉ። "የፌዴራል መንግሥቱ ወደ ትግራይ ክልል ዘልቆ አለመግባት፣ የትግራይ ኃይሎች ደግሞ ተገድደውም ይሁን ፈቅደው ወደ ኋላ መመለሳቸው፤ ሁለቱም 'የምንፈልገውን ዓላማ በጦርነት ብቻ እናሳካለን የሚለውን ነገር ያቆሙ ይመስለኛል" ይላሉ። ዊሊያም አክለውም የትግራይ አማፂያን ከአማራ እና ከአፋር ክልል መውጣታቸውን ተከትሎ ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ለተባበሩት መንግሥታት በጻፉት ደብዳቤ፤ የአማራ እና የኤርትራ ኃይሎች ከምዕራብ ትግራይ እንዲወጡና እርምጃ እንዲወሰድ መጠየቃቸው፣ በትግራይ አመራር በኩል የአስተሳሰብ ለውጥ መኖሩ የሚያመላክት ነው ይላሉ። እንዲሁም፣ በፌዴራል መንግሥት በኩል የተቃውሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራር እና አባል የሆኑ እሰረኞቹን መፍታቱ በአገሪቱ ያለው ቀውስ በሰላማዊ ድርድር እንዲያልቅ ፍላጎት እንዳለ የሚሳይ መሆኑን ይናገራሉ። አደም ካሴ (ዶ/ር) በበኩላቸው "በሥርዓትና ይፋዊ በሆነ መልኩ የተኩስ ማቆም ስምምነት እስካልታወጀ ድረስ ያለው ሁኔታ አስተማማኝ አይደለም" በማለት ያለውን የታየውን ለውጥ ይገልጹታል። "በእኔ እምነት ያንን ግምት ውስጥ በማስገባት ይመስላል የፌዴራል መንግሥቱ የአየር ላይ ጥቃት እያካሄደ ያለው፤ ከመደራደራችን በፊት በተቻለ መጠን የትግራይ ኃይሎች የመደራደር አቅም ማዳከም አለብን የሚል እሳቤ ያለ ይመስለኛል" ሲሉም ግምታቸውን ያስቀምጣሉ። ስጋቶችና እንቅፋቶች በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ካለው ጦርነት ጋር በተያያዘ አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር ወደ 9.4 ሚሊዮን እንደደደረሰ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ካለፈው ዓመት ሰኔ ወር አጋማሽ ጀምሮ ከትግራይ ለቅቆ ቢወጣም ክልሉ "ይፋዊ ባልሆነ የሰብዓዊ እርዳታ እቀባ" ውስጥ በመሆኑ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው የማቅረቡ ሥራ አስቸጋሪ መሆኑንም ጨምሮ ገልጿል። ምንም እንኳ የኢትዮጵያ መንግሥት በወቅቱ የሰብዓዊ እርዳታ እንዳይደርስ ምንም አይነት እቀባ አለማድረጉን ቢገልፅም፣ በክልሉ የሚገኙ አስቸኳይ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች በከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደሚገኙ በተደጋጋሚ ሲገለጽ ቆይቷል። የሕክምና አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትም ቢሆኑም ከመድኃኒት እና አስፈላጊ ቁሳቁሶች ውጪ መሆናቸውን በመጥቀስ በቀላል ሕክምና የሚድኑ ሕሙማን ህይወታቸውን እያጡ መሆኑን ይናገራሉ። በቅርቡም በአፋር ክልል በአባላ እየተካሄደ ባለው ጦርነት የተነሳ ምንም ዓይነት የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ መኪኖች ማለፍ አለመቻላቸውን የኢትዮጵያ መንግሥት እንዲሁም ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ድርጅቶች ገልጸዋል። ዊልያም ዴቪሰን በአጭር ጊዜ የሰላም ድርድር ካልተጀመረ የትግራይ ኃይሎች ይህንን 'የሰብዓዊ እርዳታ ዕቀባ' ለማስከፈት እና የትግራይ ክልልን ከጦርነቱ በፊት ወደ ነበረበት ለመመለስ፣ በተለይ በምዕራብ ትግራይ ጦርነት መክፈታቸው አይቀርም ይላሉ። "የትግራይ ኃይሎች ወደ ኋላ ሲመለሱ ብዙ ጉዳት ደርሶባቸው ሊሆን ይችላል" የሚል ግምት ያላቸው ዳቪሰን፣ አሁንም ድረስ ግን ከፍተኛ የጦር ኃይል እንዳለቸው ያምናሉ። "የትግራይ ኃይሎች በማናቸውም መመዘኛ አሁንም ከፍተኛ ጦር ነው ያላቸው። እነርሱ ሕዝባቸው ላይ ተከፍቶበታል ከሚሉት 'የዘር ማጥፋት' ዘመቻ ለመከላከል የህልውና ትግል እያደረጉ እንደሆነ በጽኑ ያምናሉ።" በተጨማሪም "አዲስ አበባ እና አሥመራ ያሉት መንግሥታት ደግሞ የትግራይ ኃይሎች ለራሳቸውና ለሕዝባቸው ዋነኛ ስጋት አድርገው ነው የሚመለከቷቸው" ይላሉ ዴቪሰን። ይህ በሁለቱም ወገን ያለው አመለካከት ደግሞ ለሚታሰበው የሰላም ሂደት "ከባዱ እንቅፋቱ" ሊሆን እንደሚችልና "በመካከላቸው ካለው አለመተማመንና መጠራጠር አንጻር የትግራይ ኃይሎች ሠራዊታቸውን ለመበተን የሚስማሙ አይመስለኝም" ይላሉ። አደም (ዶ/ር) በበኩሉ፣ በተለይ በአፋርና በአማራ ክልል በኩል ጦርነቱ በሰላም የማያልቅ ከሆነ መልሶ ጥቃት እንዳይደርስባቸው ተጨባጭ ስጋት እንዳለ ይገምታሉ። በትግራይ በኩልም፣ የፌዴራል መንግሥቱ ወደ ትግራይ ክልል ገፍቼ 'አልሄድም' ቢልም ጥርጣሬዎች እንደሚፈጠሩ ያስገነዝባል። ለዚህ ደግሞ "በትግራይ፣ በአፋርና በአማራ ክልል አንዳቸው ወደሌላኛው በኩል ዘልቆ የመግባት ዕቅድ እንደሌላቸው ሁሉም ማሳየት አለባቸው።" የእስረኞች መፈታት በቅርቡ አቶ ጃዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለን ገርባ እንዲሁም አቶ እስክንደር ነጋን ጨምሮ ከፍተኛ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ከእስር ተፈትተዋል። ዊልያም ዴቪሰን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የወሰዱት እሰረኞችን የመፍታት እርምጃ፣ በተለይ ሊካሄድ ለታቀደው አገራዊ ውይይት አሳታፊ እንዲሆን ለማድረግ ጉልህ ሚና እንዳለው ያምናሉ። አቶ ስብሐት ነጋን ጨምሮ ስድስት ነባር የህወሓት አመራሮች መፈታታቸውን በተመለከተ ግን "እምብዛም ፖለቲካዊ ትርጉም የለውም" ይላሉ ዴቪሰን። "እነዚህ የህወሓት የፖሊት ቢሮ አባላት ያልሆኑትን መፍታት እንደ ትልቅ ጉዳይ አድርጌ አላየውም፤ ሰላማዊ ድርድር እንዳይደርግ እንቅፋት የሆኑት ጉዳዮችን ከመቀነስ አንጻር፤ እምብዛም ለውጥ የሚያመጣ እርምጃ መስሎም አይታየኝም።" ይህ ብቻ ሳይሆን ህወሓትና ኦነግ-ሸኔ በሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት በአሸባሪነት መዝገብ መስፈራቸው ለሚደረጉ የሰላም ንግግሮች እና ድርድሮች እንቅፋት ሊሆን እንደሚችል ሁለቱም ተንታኞች ይስማማሉ። ድርጅቶቹ ከዚህ ፍረጃ ካልወጡ በስተቀር፣ የሰላም ድርድር እንዳይደርግ እንቅፋት ሊሆን ይችላል የሚል ስጋትም እዚህም እዚያም ይደመጣል። ይህንን በተመለከተ ዊሊያም ዴቪሰን፣ ድርጅቶቹ ከዚህ ፍረጃ ወጥተው፣ የተኩስ አቁም ስምምነት ተደርጎ፣ የአገር አቀፍ መድረኩ ውስጥ እንዲሳተፉ ካልተደረገ፣ አገራዊ ውይይቱ ውጤት አያመጣም የሚል እምነት እንዳላቸው ያስረዳሉ። ማምለጥ የሌለበት ዕድል የዓለም አቀፍ እና አህጉራዊ ተቋማት እንዲሁም አገራት ትግራይ ውስጥ ተጀምሮ ወደ አጎራባች ክልሎች ተዛምቶ ከፍተኛ ቀውስ ያስከተለው ጦርነት በሰላማዊ መገድ እንዲፈታ ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል። ከጦርነቱ ጋር ተያይዞ ሻክሮ የነበረው የኢትዮጵያና የአሜሪካ መንግሥታት ግንኙነት መሻሻል ሰላም ለማውረድ አዎንታዊ ሚና ሊኖረው እንደሚችል ይታመናል። ዊልያም ዴቪሰን የሰላም ሂደቱ ውጤት እንዲያመጣና ጦርነቱ እንዲቆም ግን በተለይ በትግራይ ያለውን 'የሰብዓዊ እርዳታ እቀባ' በአስቸኳይ መፈታት አለበት ይላሉ። "ሁለቱም ወገኖች የሰላም ዕድሉ ሊያመልጣቸው አይገባም" የሚሉት ዳቪሰን፤ ስልክ፣ መብራትና ባንክን የመሳሰሉ መሠረታዊ አገልግሎቶች መከፈት እንዳለባቸው እንደ መፍትሄ ሃሳብ ያቀርባሉ። አደም ካሴ (ዶ/ር) በበኩላቸው የምዕራብ ትግራይን ጉዳይ በማንሳት በሁለቱም የፖለቲካ ተፋላሚ ወገኖች በኩል "አስቸጋሪ የፖለቲካ ጭቅጭቅ" ሊሆን እንደሚችል ይናገራሉ። "ሁለቱም ወገኖች ቢያንስ የሕግ ሥርዓቱን መከተል አለባቸው" ነገር ግን ችግሩ የመጨረሳውን ዕልባት የሚያገኘው በፖለቲካዊ መንገድ በመሆኑ ይህም ወደተሻለ መተማመን እንደሚያደርስ በመግለጽ ሃሳባቸውን ያጠናቅቃሉ።
https://www.bbc.com/amharic/news-60182998
2health
ኮሮናቫይረስ፡ ማህበራዊ ርቀትን መጠበቅ እና ጭምብል ማድረግ ለዓመታት ሊዘልቅ እንደሚችል ተጠቆመ
በእግሊዝ የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎችን ማድረግ ብሎም ማህበራዊ ርቀትን መጠበቅ ለዓመታት ሊቀጥል እንደሚችል የአገሪቱን የክትባት ዘርፍ የሚመሩ ባለሙያ ገለፁ። በእንግሊዝ የጤና ሚኒስቴር ውስጥ የክትባት ዘርፍ ሃላፊ የሆኑት ዶክተር ሜሪ ራምሴ ሌሎች አገራት የክትባት ዘመቻቸውን በስኬት እስከሚያጠናቅቁ እና ይህንንም ተከትሎ ወደ መደበኛ ህይወት ለመመለስ እነዚህ ገደቦች ሊቀጥሉ እንደሚችሉ ተናግረዋል። በተጨማሪም ብዙ ሰው የሚታደማቸው ዝግጅቶች ጥንቃቄ የተሞላበት የደህነንት መመሪያዎች ትግበራ እና ክትትል እንደሚያስፈልጋቸውም ተናግረዋል። ዶክተር ራምሴ እንዳሉት በተለይም ጭምብሎችን እንደማድረግ ያሉ ገደቦች በማህበረሰቡ ውስጥ ተቀባይነትን እያገኙ የመጡ ሲሆን ይህም በተለይ ኢኮኖሚው እንዲንቀሳቀስ እድል ከፍቷል ብለዋል። ‹‹ሰዎች ከእንዲህ ያሉ ገደቦች ጋር እየተለማመዱ አብረዋቸው መኖር ይችላሉ። ኢኮኖሚውም ከባድ ካልሆኑ ክልከላዎችን ጋር መንቀሳቀስ ይችላል›› ብለዋል። ‹‹የኮሮናቫይረስ ቁጥር በሌላው ዓለም እስከሚቀንስ እና ክትባት በበቂ ሁኔታ እስከሚዳረስ ድረስ እነዚህ ገደቦች በእርግጠኝነት ለተወሰኑ ዓመታት የሚቀጥሉ ሲሆን ቀስ በቀስ ወደ መደበኛ ህይወት እንመለሳለን›› ሲሉም ጨምረው ገልፀዋል። ዶክተር ራምሴ ጨምረው ቫይረስ በቀላሉ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎችን ሊያጠቃ ስለሚችል ‹‹በችኮላ ወደ መዘናጋት መግባት የለብንም›› ሲሉም አሳስበዋል። የእንግሊዝ መንግሥት ዋና የጤና አማካሪ ፕሮፌሰር ክሪስ ዊቲ በያዝነው ወር መጀመሪየ ላይ ለተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሰጡት ማብራሪያ እጅ መታጠብ፣ ጭምብል ማጥለቅ፣ ምርመራ በማድረግ መለየት እና ከሁሉም በላይ ደግሞ ክትባት መጀመር ቫይረሱን ከበጋው ወራት በፊት ለመቆጣጠር ያግዛል የሚል ተስፋ ተጥሎ ነበር ብለዋል። መንግሥትን የሚያማክሩ የሳይንትስቶች ቡድንም የቫይረሱን ስርጭት ሊቀንሱ የሚችሉ መሰረታዊ የሆኑ ፖሊሲዎችን መተግበር ለተወሰነ ግዜ አስፈላጊ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመው ነበር። እነዚሁ ባለሙያዎች በምርመራ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን መለየት፣ ራስን በለይቶ ማቆያ ውስጥ ማቆየት፣ በፈቃደኘነት የሚደረጉ እና በሽታውን አደጋዎች ለመቀነስ የሚያበረታቱ ሕዝባዊ መልዕክቶች ሊቀጥሉ እንደሚችሉም ተናግረው ነበር። የእንግሊዝ መንግሥት የእንቅስቃሴ ገደቦችን ቀስ በቀስ ለማንሳት ያዘጋጀው ፍኖተ ካርታ እንደሚለው ማህበራዊ መራራቅን የሚያስገድዱ ሕጋዊ ግዴታዎች ከሰኔ 14 በፊት እንደማይነሱ ያስረዳሉ።
ኮሮናቫይረስ፡ ማህበራዊ ርቀትን መጠበቅ እና ጭምብል ማድረግ ለዓመታት ሊዘልቅ እንደሚችል ተጠቆመ በእግሊዝ የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎችን ማድረግ ብሎም ማህበራዊ ርቀትን መጠበቅ ለዓመታት ሊቀጥል እንደሚችል የአገሪቱን የክትባት ዘርፍ የሚመሩ ባለሙያ ገለፁ። በእንግሊዝ የጤና ሚኒስቴር ውስጥ የክትባት ዘርፍ ሃላፊ የሆኑት ዶክተር ሜሪ ራምሴ ሌሎች አገራት የክትባት ዘመቻቸውን በስኬት እስከሚያጠናቅቁ እና ይህንንም ተከትሎ ወደ መደበኛ ህይወት ለመመለስ እነዚህ ገደቦች ሊቀጥሉ እንደሚችሉ ተናግረዋል። በተጨማሪም ብዙ ሰው የሚታደማቸው ዝግጅቶች ጥንቃቄ የተሞላበት የደህነንት መመሪያዎች ትግበራ እና ክትትል እንደሚያስፈልጋቸውም ተናግረዋል። ዶክተር ራምሴ እንዳሉት በተለይም ጭምብሎችን እንደማድረግ ያሉ ገደቦች በማህበረሰቡ ውስጥ ተቀባይነትን እያገኙ የመጡ ሲሆን ይህም በተለይ ኢኮኖሚው እንዲንቀሳቀስ እድል ከፍቷል ብለዋል። ‹‹ሰዎች ከእንዲህ ያሉ ገደቦች ጋር እየተለማመዱ አብረዋቸው መኖር ይችላሉ። ኢኮኖሚውም ከባድ ካልሆኑ ክልከላዎችን ጋር መንቀሳቀስ ይችላል›› ብለዋል። ‹‹የኮሮናቫይረስ ቁጥር በሌላው ዓለም እስከሚቀንስ እና ክትባት በበቂ ሁኔታ እስከሚዳረስ ድረስ እነዚህ ገደቦች በእርግጠኝነት ለተወሰኑ ዓመታት የሚቀጥሉ ሲሆን ቀስ በቀስ ወደ መደበኛ ህይወት እንመለሳለን›› ሲሉም ጨምረው ገልፀዋል። ዶክተር ራምሴ ጨምረው ቫይረስ በቀላሉ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎችን ሊያጠቃ ስለሚችል ‹‹በችኮላ ወደ መዘናጋት መግባት የለብንም›› ሲሉም አሳስበዋል። የእንግሊዝ መንግሥት ዋና የጤና አማካሪ ፕሮፌሰር ክሪስ ዊቲ በያዝነው ወር መጀመሪየ ላይ ለተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሰጡት ማብራሪያ እጅ መታጠብ፣ ጭምብል ማጥለቅ፣ ምርመራ በማድረግ መለየት እና ከሁሉም በላይ ደግሞ ክትባት መጀመር ቫይረሱን ከበጋው ወራት በፊት ለመቆጣጠር ያግዛል የሚል ተስፋ ተጥሎ ነበር ብለዋል። መንግሥትን የሚያማክሩ የሳይንትስቶች ቡድንም የቫይረሱን ስርጭት ሊቀንሱ የሚችሉ መሰረታዊ የሆኑ ፖሊሲዎችን መተግበር ለተወሰነ ግዜ አስፈላጊ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመው ነበር። እነዚሁ ባለሙያዎች በምርመራ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን መለየት፣ ራስን በለይቶ ማቆያ ውስጥ ማቆየት፣ በፈቃደኘነት የሚደረጉ እና በሽታውን አደጋዎች ለመቀነስ የሚያበረታቱ ሕዝባዊ መልዕክቶች ሊቀጥሉ እንደሚችሉም ተናግረው ነበር። የእንግሊዝ መንግሥት የእንቅስቃሴ ገደቦችን ቀስ በቀስ ለማንሳት ያዘጋጀው ፍኖተ ካርታ እንደሚለው ማህበራዊ መራራቅን የሚያስገድዱ ሕጋዊ ግዴታዎች ከሰኔ 14 በፊት እንደማይነሱ ያስረዳሉ።
https://www.bbc.com/amharic/56484252
3politics
ሙሴቪኒ ከአሜሪካዋ ዲፕሎማት ጉብኝት አስቀድመው ‘ማንም ትዕዛዝ አይሰጠንም’ አሉ
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአሜሪካ አምባሳደር የኡጋንዳ ጉብኝትን ተከትሎ ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ማንም ትዕዛዝ አይሰጠንም ሲሉ ለቢቢሲ ተናገሩ። አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ-ግሪንፊልድ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝታቸው ዛሬ ሐሙስ ሐምሌ 28/2014 ዓ.ም. ከኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ ጋር ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። አምባሳደሯ ከዋሽንግተን ዲሲ መመሪያዎችን ይዘው ይመጡ እንደሆነ የተጠየቁት ሙሴቬኒ፤ “ማንም ትዕዛዝ አይሰጠንም” ሲሉ መልሰዋል። ሙሴቬኒ አገራቸው ኡጋንዳ ከምዕራባውያን የሚላከውን እርዳታ በመልካም ጎኑ እንደምትመለከተው ጠቅሰው፤ አገራቸው ያለ እርዳታ መኖር እንደምትችልም ተናግረዋል። ፕሬዝዳንቱ ኡጋንዳ በሩሲያ እና በዩክሬን ጦርነት ዙሪያ የያዘችውን አቋም ለማስቀየር የተደረገ ጥረት እንደሌለ ገልጸዋል። የተባበሩት መንግሥታት ሩሲያ በዩክሬን ላይ የከፈተችውን ወረራ እንድታቆም ያወጣውን ምክር ሃሳብ በድምጸ ታዕቅቦ ካለፉት 16 የአፍሪካ አገራት መካከል ኡጋንዳ አንዷ መሆኗ ይታወቃል። አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ-ግሪን ፊልድ ወደ ካምፓል የሚያመሩት የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኡጋንዳ ጉብኝት ካደረጉ ከቀናት በኋላ ነው። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ በቅርቡ ኡጋንዳ እና ኢትዮጵያን ጨምሮ በአራት የአፍሪካ አገራት ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል። ሙሴቬኒ፤ “ጥሩ ጓደኛ” ሲሉ የገለጿቸው አምባሳደር ቶማስ-ግሪንፊልድን ሁሌም ወደ ኡጋንዳ እንዲመጡ በራችን ከፍት ነው ካሉ በኋላ፤ አስተዳደራቸው ለምዕራባውያን ጫና እንደማይበረከክ ተናግረዋል። ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ በሩሲያ እና በዩክሬን ጦርነት ዙሪያ አቋማቸው ምን እንደሆነ ሲጠየቁ፤ ጦርነቱን ከ1962ቱ የኩባ ሚሳኤል ቀውስ ጋር አነጻጸረውታል። ሙሴቪኒ ዛሬ ላይ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) በሩሲያ ዙሪያ መገኘትን ሶቪየት ሕብረት አሜሪካ አፍንጫ ስር ኩባ ውስጥ ሚሳኤል ከመትከሏ ጋር አነጻጽረውታል። የኩባ ሚሳኤል ቀውስ ተብሎ የሚታወቀው ክስተት የወቅቱ የዓለማችን ኃያላንን ወደ ኒውክሌር ጦርነት እንዲገቡ ከጫፍ አድርሶ ነበር። በወቅቱ ሶቪየት ሕብርት የኩባን ደኅንነት ከአሜሪካ ጥቃት ለመጠበቅ በሚል፣ ኩባ ውስጥ የአሜሪካ ከተሞችን መምታት በሚያሰችሉ ስፍራዎች ላይ የኒውክሌር አረሮችን ማስወንጨፍ የሚችሉ ሚሳኤሎችን ተክላ ነበር። ሙሴቬኒ ይህ ክስተት የአሜሪካንን የደኅንነት ስጋት ውስጥ ከትቶ እንደነበረ ተናግረው፤ በወቅቱ አገራቸው ለአሜሪካ ድጋፏን መሽጠቷን አስታውሰዋል። ሙሴቬኒ ዛሬም ተመሳሳይ መርኅ ማረመድ አለብን ብለዋል። ሙሴቬኒ ኔቶ በሩሲያ ዙሪያ መክተሙ፤ የሩሲያን እርምጃ እንዲገነዘቡ ያደርግዎታል ወይ ተብለው ሲጠይቁ፤ “በትክክል” ሲሉ መልሰዋል። “ታሪክ የምትሉትን፤ እኔ ወቅታዊ ጉዳይ እለዋለሁ” ብለዋል ሙሴቬኒ።
ሙሴቪኒ ከአሜሪካዋ ዲፕሎማት ጉብኝት አስቀድመው ‘ማንም ትዕዛዝ አይሰጠንም’ አሉ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአሜሪካ አምባሳደር የኡጋንዳ ጉብኝትን ተከትሎ ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ማንም ትዕዛዝ አይሰጠንም ሲሉ ለቢቢሲ ተናገሩ። አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ-ግሪንፊልድ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝታቸው ዛሬ ሐሙስ ሐምሌ 28/2014 ዓ.ም. ከኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ ጋር ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። አምባሳደሯ ከዋሽንግተን ዲሲ መመሪያዎችን ይዘው ይመጡ እንደሆነ የተጠየቁት ሙሴቬኒ፤ “ማንም ትዕዛዝ አይሰጠንም” ሲሉ መልሰዋል። ሙሴቬኒ አገራቸው ኡጋንዳ ከምዕራባውያን የሚላከውን እርዳታ በመልካም ጎኑ እንደምትመለከተው ጠቅሰው፤ አገራቸው ያለ እርዳታ መኖር እንደምትችልም ተናግረዋል። ፕሬዝዳንቱ ኡጋንዳ በሩሲያ እና በዩክሬን ጦርነት ዙሪያ የያዘችውን አቋም ለማስቀየር የተደረገ ጥረት እንደሌለ ገልጸዋል። የተባበሩት መንግሥታት ሩሲያ በዩክሬን ላይ የከፈተችውን ወረራ እንድታቆም ያወጣውን ምክር ሃሳብ በድምጸ ታዕቅቦ ካለፉት 16 የአፍሪካ አገራት መካከል ኡጋንዳ አንዷ መሆኗ ይታወቃል። አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ-ግሪን ፊልድ ወደ ካምፓል የሚያመሩት የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኡጋንዳ ጉብኝት ካደረጉ ከቀናት በኋላ ነው። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ በቅርቡ ኡጋንዳ እና ኢትዮጵያን ጨምሮ በአራት የአፍሪካ አገራት ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል። ሙሴቬኒ፤ “ጥሩ ጓደኛ” ሲሉ የገለጿቸው አምባሳደር ቶማስ-ግሪንፊልድን ሁሌም ወደ ኡጋንዳ እንዲመጡ በራችን ከፍት ነው ካሉ በኋላ፤ አስተዳደራቸው ለምዕራባውያን ጫና እንደማይበረከክ ተናግረዋል። ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ በሩሲያ እና በዩክሬን ጦርነት ዙሪያ አቋማቸው ምን እንደሆነ ሲጠየቁ፤ ጦርነቱን ከ1962ቱ የኩባ ሚሳኤል ቀውስ ጋር አነጻጸረውታል። ሙሴቪኒ ዛሬ ላይ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) በሩሲያ ዙሪያ መገኘትን ሶቪየት ሕብረት አሜሪካ አፍንጫ ስር ኩባ ውስጥ ሚሳኤል ከመትከሏ ጋር አነጻጽረውታል። የኩባ ሚሳኤል ቀውስ ተብሎ የሚታወቀው ክስተት የወቅቱ የዓለማችን ኃያላንን ወደ ኒውክሌር ጦርነት እንዲገቡ ከጫፍ አድርሶ ነበር። በወቅቱ ሶቪየት ሕብርት የኩባን ደኅንነት ከአሜሪካ ጥቃት ለመጠበቅ በሚል፣ ኩባ ውስጥ የአሜሪካ ከተሞችን መምታት በሚያሰችሉ ስፍራዎች ላይ የኒውክሌር አረሮችን ማስወንጨፍ የሚችሉ ሚሳኤሎችን ተክላ ነበር። ሙሴቬኒ ይህ ክስተት የአሜሪካንን የደኅንነት ስጋት ውስጥ ከትቶ እንደነበረ ተናግረው፤ በወቅቱ አገራቸው ለአሜሪካ ድጋፏን መሽጠቷን አስታውሰዋል። ሙሴቬኒ ዛሬም ተመሳሳይ መርኅ ማረመድ አለብን ብለዋል። ሙሴቬኒ ኔቶ በሩሲያ ዙሪያ መክተሙ፤ የሩሲያን እርምጃ እንዲገነዘቡ ያደርግዎታል ወይ ተብለው ሲጠይቁ፤ “በትክክል” ሲሉ መልሰዋል። “ታሪክ የምትሉትን፤ እኔ ወቅታዊ ጉዳይ እለዋለሁ” ብለዋል ሙሴቬኒ።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cl57jk5n4jeo
3politics
ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ወደ ሥልጣናቸው ተመለሱ
ጥቅምት ወር ላይ በመፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣናቸው የተወገዱት የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ወደ ሥልጣናቸው መመለሳቸው ተገለጸ። በቤታቸው ውስጥ በቁም አስር ላይ የሰነበቱት ሐምዶክ ከመፈንቅለ መንግሥቱ መሪ ጄነራል አብደል ፋታህ አል ቡርሐን ጋር አዲስ የሥልጣን መጋራት ስምምነት ለመፈራረም ዛሬ እሁድ በአገሪቱ ቴሌቪዥን ቀርበው ታይተዋል። ከሁለት ዓመት በፊት አብደላ ሐምዶክን ለጠቅላይ ሚኒስትርነት የሾመው የሲቪል ፖለቲከኞች ስብስብ ግን ከወታደሮች ጋር የሚደረግን ማንኛውንም አይነት አዲስ ስምምነት እንደማይቀበለው አሳውቋል። "የሱዳን የወደፊት ዕጣ የሚወሰነው በአገሪቱ ውስጥ ባሉ ወጣቶች ነው" ሲል የነጻነትና የለውጥ ኃይሎች የተባለው ጥምረት ቃል አቀባይ የሆነው ሲዲቅ አቡ ፋዋዝ ለቢቢሲ ተናግሯል። ከመፈንቅለ መንግሥቱ መካሄድ በኋላ የተቀሰቀሰውና ለበርካታ ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው። በዋና ከተማዋ ካርቱም ጦር ሠራዊቱ ከአገሪቱ ፖለቲካ ሙሉ ለሙሉ እንዲወጣ የሚጠይቁ ሰልፈኞች ወደ ፕሬዝዳንታዊው ቤተመንግሥት በሚያመሩበት ጊዜ የፀጥታ ኃይሎች አስለቃሽ ጋዝ እንደተኮሱባቸው ተዘግቧል። በጥቅምት ወር አጋማሽ ላይ ሠራዊቱ መፈንቅለ መንግሥት አካሂዶ የሲቪል አስተዳደሩን አመራሮች ከበተነና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከደነገገ በኋላ መፈንቅለ መንግሥቱን ተቃውመው አደባባይ ከወጡ ሰዎች መካከል ቢያንስ 40 የሚሆኑ ሰዎች ተገድለዋል። ሮይተርስ የዜና ወኪል እንደዘገበው አብደላ ሐምዶክ "የሱዳናውያን ደም ውድ ነው፣ ደም መፋሰሱን እስቁመን ወጣቱን ኃይል ወደ ግንባታና ልማት እንምራው" በማለት ግጭቶች እንዲቆሙ ከስምምነት መድረሳቸውን ተናግረዋል። ወደ ሥልጣን የተመለሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ሐምዶክና ሲቪል ሚኒስትሮቻቸው ምን ያህል ሥልጣን እንደሚኖራቸው ግን ግልጽ አይደለም። ከሥልጣናቸው የተወገዱት ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ መንበራቸው እንዲመለሱ የተደረገው የሱዳን ጦር፣ ሲቪል መሪዎች እንዲሁም የቀድሞ አማጺያን ስምምነት ላይ ከደረሱ በኋላ ነው ሲሉ አሸማጋዮች አስታውቀዋል። ይህ ስምምነት ቅዳሜ ምሽት የተደረሰ ሲሆን እሁድ ከሰዓት በኋላ ነው ተግባራዊ የተደረገው። ምሁራን፣ ጋዜጠኞች እንዲሁም ፖለቲከኞች የተካተቱበት አሸማጋይ ቡድን የስምምነቱን ይዘት ለሕዝብ ይፋ አድርጓል። ይዘቱ እንደሚያትተው በቁጥጥር ሥር የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክና የካቢኔ አባሎቻቸው ይለቀቃሉ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደግሞ ወደ ሥልጣናቸው ይመለሳሉ። አክሎም ሱዳን ወደ ዲሞክራሲ የምታደርገው ሽግግር እንደሚቀጥል ይዘቱ ያትታል። የሱዳን ሲቨል መሪዎችና የአገሪቱ ጦር ላለፉት ሁለት ዓመታት በሥልጣን ክፍፍል ሳቢያ እሰጥ-አገባ ውስጥ ነበሩ። የሱዳን ጦር ወደ ሥልጣን የመጣው ለረዥም ዓመታት ሱዳንን የመሩት ፕሬዝደንት ኦማር አል-ባሽር ከመንበራቸው ከተወገዱ በኋላ ነው። አገሪቱን በጋራ ለመምራት ሥልጣን የተረከቡት ወታደራዊው ኃይልና የሲቪሉ መንግሥት በበርካታ ጉዳዮች ሊስማሙ አልቻሉም ነበር። ባለፈው ወር የጦር ኃይል ጄኔራል የሆኑት አብደል ፋታህ አል ቡርሐን ሲቪሉን መንግሥት መበተናቸውንና ባለሥልጣናቱን በቁጥጥር ሥር ማዋላቸው ይታወሳል። ጄኔራሉ ክስተቱ "መፈንቅለ መንግሥት አይደለም የእርስ በርስ ጦርነትን ለማስቀረት እንጂ" ካሉ በኋላ አዲስ ምክር ቤት አቋቁመው ራሳቸውን የበላይ አድርገው ሾመው ነበር። ከዚህ የፖለቲካ ውጥንቅጥ በኋላ ዋና ከተማዋ ካርቱምን ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ሕዝባዊ አመጽ የተቀጣጠለ ሲሆን ይህንንም ለመመከት የተሰማራው የአገሪቱ ጦር ሰልፈኞች ላይ ተኩሷል ተብሎም ተወቅሷል። ሱዳናዊያን ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እሑድ ቀነ ቀጠሮ ይዘው ሰልፍ ከመውጣታቸው በፊት ነው ስምምነቱ ይፋ የሆነው። ወታደራዊው መንግሥት ከመፈንቅለ መንግሥቱ በኋላ አገሪቱን ወደ ዲሞክራሲያዊ ሽግግር እንዲመልሳት ከባድ ጫና ሲደረግብት የቆየ ሲሆን፤ የአፍሪካ ሕብረት አገሪቱን ከአባልንት ሲያግድ የዓለም ባንክ ደግሞ ለሱዳን ሊሰጥ ያቀደውን ድጋፍ አግዷል። ኦማር ሐሰን አል ባሽር ከሥልጣን ተወግደው የሽግግር አስተዳዳር ከተመሰረተ በኋላ በሠራዊቱ መሪዎችና በሲቪል ባለሥልጣንት መካከል አለመግባባት የቆየ ሲሆን፤ በዚህ ወር አል ቡርሐን ሥልጣናቸውን ለሲቪል መሪ ያስርክባሉ ተብሎ ሲጠበቅ ነው መፈንቅለ መንግሥት ያካሄዱት።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ወደ ሥልጣናቸው ተመለሱ ጥቅምት ወር ላይ በመፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣናቸው የተወገዱት የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ወደ ሥልጣናቸው መመለሳቸው ተገለጸ። በቤታቸው ውስጥ በቁም አስር ላይ የሰነበቱት ሐምዶክ ከመፈንቅለ መንግሥቱ መሪ ጄነራል አብደል ፋታህ አል ቡርሐን ጋር አዲስ የሥልጣን መጋራት ስምምነት ለመፈራረም ዛሬ እሁድ በአገሪቱ ቴሌቪዥን ቀርበው ታይተዋል። ከሁለት ዓመት በፊት አብደላ ሐምዶክን ለጠቅላይ ሚኒስትርነት የሾመው የሲቪል ፖለቲከኞች ስብስብ ግን ከወታደሮች ጋር የሚደረግን ማንኛውንም አይነት አዲስ ስምምነት እንደማይቀበለው አሳውቋል። "የሱዳን የወደፊት ዕጣ የሚወሰነው በአገሪቱ ውስጥ ባሉ ወጣቶች ነው" ሲል የነጻነትና የለውጥ ኃይሎች የተባለው ጥምረት ቃል አቀባይ የሆነው ሲዲቅ አቡ ፋዋዝ ለቢቢሲ ተናግሯል። ከመፈንቅለ መንግሥቱ መካሄድ በኋላ የተቀሰቀሰውና ለበርካታ ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው። በዋና ከተማዋ ካርቱም ጦር ሠራዊቱ ከአገሪቱ ፖለቲካ ሙሉ ለሙሉ እንዲወጣ የሚጠይቁ ሰልፈኞች ወደ ፕሬዝዳንታዊው ቤተመንግሥት በሚያመሩበት ጊዜ የፀጥታ ኃይሎች አስለቃሽ ጋዝ እንደተኮሱባቸው ተዘግቧል። በጥቅምት ወር አጋማሽ ላይ ሠራዊቱ መፈንቅለ መንግሥት አካሂዶ የሲቪል አስተዳደሩን አመራሮች ከበተነና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከደነገገ በኋላ መፈንቅለ መንግሥቱን ተቃውመው አደባባይ ከወጡ ሰዎች መካከል ቢያንስ 40 የሚሆኑ ሰዎች ተገድለዋል። ሮይተርስ የዜና ወኪል እንደዘገበው አብደላ ሐምዶክ "የሱዳናውያን ደም ውድ ነው፣ ደም መፋሰሱን እስቁመን ወጣቱን ኃይል ወደ ግንባታና ልማት እንምራው" በማለት ግጭቶች እንዲቆሙ ከስምምነት መድረሳቸውን ተናግረዋል። ወደ ሥልጣን የተመለሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ሐምዶክና ሲቪል ሚኒስትሮቻቸው ምን ያህል ሥልጣን እንደሚኖራቸው ግን ግልጽ አይደለም። ከሥልጣናቸው የተወገዱት ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ መንበራቸው እንዲመለሱ የተደረገው የሱዳን ጦር፣ ሲቪል መሪዎች እንዲሁም የቀድሞ አማጺያን ስምምነት ላይ ከደረሱ በኋላ ነው ሲሉ አሸማጋዮች አስታውቀዋል። ይህ ስምምነት ቅዳሜ ምሽት የተደረሰ ሲሆን እሁድ ከሰዓት በኋላ ነው ተግባራዊ የተደረገው። ምሁራን፣ ጋዜጠኞች እንዲሁም ፖለቲከኞች የተካተቱበት አሸማጋይ ቡድን የስምምነቱን ይዘት ለሕዝብ ይፋ አድርጓል። ይዘቱ እንደሚያትተው በቁጥጥር ሥር የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክና የካቢኔ አባሎቻቸው ይለቀቃሉ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደግሞ ወደ ሥልጣናቸው ይመለሳሉ። አክሎም ሱዳን ወደ ዲሞክራሲ የምታደርገው ሽግግር እንደሚቀጥል ይዘቱ ያትታል። የሱዳን ሲቨል መሪዎችና የአገሪቱ ጦር ላለፉት ሁለት ዓመታት በሥልጣን ክፍፍል ሳቢያ እሰጥ-አገባ ውስጥ ነበሩ። የሱዳን ጦር ወደ ሥልጣን የመጣው ለረዥም ዓመታት ሱዳንን የመሩት ፕሬዝደንት ኦማር አል-ባሽር ከመንበራቸው ከተወገዱ በኋላ ነው። አገሪቱን በጋራ ለመምራት ሥልጣን የተረከቡት ወታደራዊው ኃይልና የሲቪሉ መንግሥት በበርካታ ጉዳዮች ሊስማሙ አልቻሉም ነበር። ባለፈው ወር የጦር ኃይል ጄኔራል የሆኑት አብደል ፋታህ አል ቡርሐን ሲቪሉን መንግሥት መበተናቸውንና ባለሥልጣናቱን በቁጥጥር ሥር ማዋላቸው ይታወሳል። ጄኔራሉ ክስተቱ "መፈንቅለ መንግሥት አይደለም የእርስ በርስ ጦርነትን ለማስቀረት እንጂ" ካሉ በኋላ አዲስ ምክር ቤት አቋቁመው ራሳቸውን የበላይ አድርገው ሾመው ነበር። ከዚህ የፖለቲካ ውጥንቅጥ በኋላ ዋና ከተማዋ ካርቱምን ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ሕዝባዊ አመጽ የተቀጣጠለ ሲሆን ይህንንም ለመመከት የተሰማራው የአገሪቱ ጦር ሰልፈኞች ላይ ተኩሷል ተብሎም ተወቅሷል። ሱዳናዊያን ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እሑድ ቀነ ቀጠሮ ይዘው ሰልፍ ከመውጣታቸው በፊት ነው ስምምነቱ ይፋ የሆነው። ወታደራዊው መንግሥት ከመፈንቅለ መንግሥቱ በኋላ አገሪቱን ወደ ዲሞክራሲያዊ ሽግግር እንዲመልሳት ከባድ ጫና ሲደረግብት የቆየ ሲሆን፤ የአፍሪካ ሕብረት አገሪቱን ከአባልንት ሲያግድ የዓለም ባንክ ደግሞ ለሱዳን ሊሰጥ ያቀደውን ድጋፍ አግዷል። ኦማር ሐሰን አል ባሽር ከሥልጣን ተወግደው የሽግግር አስተዳዳር ከተመሰረተ በኋላ በሠራዊቱ መሪዎችና በሲቪል ባለሥልጣንት መካከል አለመግባባት የቆየ ሲሆን፤ በዚህ ወር አል ቡርሐን ሥልጣናቸውን ለሲቪል መሪ ያስርክባሉ ተብሎ ሲጠበቅ ነው መፈንቅለ መንግሥት ያካሄዱት።
https://www.bbc.com/amharic/news-59365382
5sports
ዋልያዎቹ በቀጣዩ የአፍሪካ ዋንጫ ለመሳተፍ ወሳኝ 90 ደቂቃዎች ቀራቸው
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ማደጋስካርን በሰፊ የግብ ልዩነት ካሸነፈ በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ውድድር ለመግባት አንድ ቀጣይ ጨዋታ ብቻ ቀረው። ብሔራዊ ቡድኑ በአሁኑ ጊዜ የምድቡን መሪነት የያዘ ሲሆን በቀጣይ ከኮትዲቯር ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ ማሸነፍ ከቻለ ከዓመታት በኋላ በአፍሪካ ዋንጫ ውድድር የመሳተፍ እድል ይኖረዋል። ዋልያዎቹ ረቡዕ መጋቢት 15/2013 ዓ.ም ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በባሕር ዳር ላከተማ ባደረገው ጨዋታ የማደጋስካር አቻቸውን ማሸነፋቸውን ተከትሎ በቀጣዩ የአፍሪካ ዋንጫ የመሳተፍ እድላቸው ከፍ ብሏል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ትናንት ከሰዓት በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታድየም በተካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ጨዋታ ማዳጋስካርን 4 ለ 0 በማሸነፍ የደረጃ ሰንጠረዡን መምራት ጀምሯል። ግቦቹን አማኑኤል ገብረሚካኤል ፣ጌታነህ ከበደ፣ አቡበከር ናስር እና ሽመልስ በቀለ አስቆጥረዋል። በዋሊያዎቹ ምድብ ውስጥ የሚገኙት ኮትዲቯር እና ኒጀር ነገ የሚጫወቱ ሲሆን፤ የጨዋታው ውጤት እስከሚታወቅ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የደረጃ ሰንጠረዡን በ9 ነጥብ መምራቱን ይቀጥላል። በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከኮትዲቯር፣ ማደጋስካር እና ኒጀር ጋር የተመደበችው ኢትዮጵያ፤ በመጀመሪያው ጨዋታ በማደጋስካር አንድ ለባዶ ተሸንፋ የነበረ ሲሆን በቀጣይ በባሕር ዳር በተደረገ ጨዋታ ኮትዲቯርን ሁለት ለአንድ በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችላለች። በመቀጠል ዋልያዎቹ ወደ ኒጀር ተጉዘው፤ አንድ ለባዶ ቢሸንፉም በመልሱ ጨዋታ ሦስት ለባዶ ማሸነፍ ችለዋል። በወዳጅነት ጨዋታ በቀላሉ ማላዊን በሰፊ የጎል ልዩነት ያሸነፉት ዋልያዎቹ ከማደጋስካር ጋር በነበራቸው የምድብ ጨዋታ ደግሞ አራት ለባዶ በማሸነፍ ነው ምድቡን በዘጠኝ ነጥብ መምራት የቻሉት። በምድቡ ወሳኝ ጨዋታ ነገ አርብ ኮትዲቯር ከኒጀር የሚያደርጉት ሲሆን ጨዋታው በኮትዲቯር አሸናፊነት የሚጠናቀቅ ከሆነ ኢትዮጵያ በምድቡ ወደ ሁለተኛ ደረጃ ዝቅ ትላለች። ጨዋታው በኒጀር አሸናፊነት አልያም አቻ የሚጠናቀቅ ከሆነ ደግሞ ዋልያዎቹ መሪነታቸውን አስጠብቀው ወደ መጨረሻው የምድብ ጨዋታ ይጓዛሉ ማለት ነው። ዋልያዎቹ በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታቸውን መጋቢት 21/2013 ዓ.ም ወደ ኮትዲቯር ተጉዘው የሚያደርጉ ሲሆን ማደጋስካር ከኒጀር የሚያደርጉትም ጨዋታ በጉጉት የሚጠበቅ ነው። ኢትዮጵያ ኮትዲቯርን የምታሸንፍ ከሆነ በካሜሩን አዘጋጅነት በሚካሄደው ጨዋታ ተሳታፊነቷን የምታረጋግጥ ሲሆን፤ ማደጋስካር ከኒጀር የሚያደርጉት ጨዋታ በኒጀር አሸናፊነት የሚጠናቀቅ ከሆነ ደግሞ ሰፊ የማለፍ እድል ይኖራታል። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በአንድ ዓመት በተራዘመው 33ኛው የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ከወዲሁ አምስት አገራት ማለፋቸውን አረጋግጠዋል። እነዚህም አገራት አዘጋጇ ካሜሩን፣ ሴኔጋል፣ ቱኒዚያ፣ ማሊ እና አልጄሪያ ናቸው።
ዋልያዎቹ በቀጣዩ የአፍሪካ ዋንጫ ለመሳተፍ ወሳኝ 90 ደቂቃዎች ቀራቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ማደጋስካርን በሰፊ የግብ ልዩነት ካሸነፈ በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ውድድር ለመግባት አንድ ቀጣይ ጨዋታ ብቻ ቀረው። ብሔራዊ ቡድኑ በአሁኑ ጊዜ የምድቡን መሪነት የያዘ ሲሆን በቀጣይ ከኮትዲቯር ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ ማሸነፍ ከቻለ ከዓመታት በኋላ በአፍሪካ ዋንጫ ውድድር የመሳተፍ እድል ይኖረዋል። ዋልያዎቹ ረቡዕ መጋቢት 15/2013 ዓ.ም ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በባሕር ዳር ላከተማ ባደረገው ጨዋታ የማደጋስካር አቻቸውን ማሸነፋቸውን ተከትሎ በቀጣዩ የአፍሪካ ዋንጫ የመሳተፍ እድላቸው ከፍ ብሏል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ትናንት ከሰዓት በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታድየም በተካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ጨዋታ ማዳጋስካርን 4 ለ 0 በማሸነፍ የደረጃ ሰንጠረዡን መምራት ጀምሯል። ግቦቹን አማኑኤል ገብረሚካኤል ፣ጌታነህ ከበደ፣ አቡበከር ናስር እና ሽመልስ በቀለ አስቆጥረዋል። በዋሊያዎቹ ምድብ ውስጥ የሚገኙት ኮትዲቯር እና ኒጀር ነገ የሚጫወቱ ሲሆን፤ የጨዋታው ውጤት እስከሚታወቅ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የደረጃ ሰንጠረዡን በ9 ነጥብ መምራቱን ይቀጥላል። በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከኮትዲቯር፣ ማደጋስካር እና ኒጀር ጋር የተመደበችው ኢትዮጵያ፤ በመጀመሪያው ጨዋታ በማደጋስካር አንድ ለባዶ ተሸንፋ የነበረ ሲሆን በቀጣይ በባሕር ዳር በተደረገ ጨዋታ ኮትዲቯርን ሁለት ለአንድ በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችላለች። በመቀጠል ዋልያዎቹ ወደ ኒጀር ተጉዘው፤ አንድ ለባዶ ቢሸንፉም በመልሱ ጨዋታ ሦስት ለባዶ ማሸነፍ ችለዋል። በወዳጅነት ጨዋታ በቀላሉ ማላዊን በሰፊ የጎል ልዩነት ያሸነፉት ዋልያዎቹ ከማደጋስካር ጋር በነበራቸው የምድብ ጨዋታ ደግሞ አራት ለባዶ በማሸነፍ ነው ምድቡን በዘጠኝ ነጥብ መምራት የቻሉት። በምድቡ ወሳኝ ጨዋታ ነገ አርብ ኮትዲቯር ከኒጀር የሚያደርጉት ሲሆን ጨዋታው በኮትዲቯር አሸናፊነት የሚጠናቀቅ ከሆነ ኢትዮጵያ በምድቡ ወደ ሁለተኛ ደረጃ ዝቅ ትላለች። ጨዋታው በኒጀር አሸናፊነት አልያም አቻ የሚጠናቀቅ ከሆነ ደግሞ ዋልያዎቹ መሪነታቸውን አስጠብቀው ወደ መጨረሻው የምድብ ጨዋታ ይጓዛሉ ማለት ነው። ዋልያዎቹ በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታቸውን መጋቢት 21/2013 ዓ.ም ወደ ኮትዲቯር ተጉዘው የሚያደርጉ ሲሆን ማደጋስካር ከኒጀር የሚያደርጉትም ጨዋታ በጉጉት የሚጠበቅ ነው። ኢትዮጵያ ኮትዲቯርን የምታሸንፍ ከሆነ በካሜሩን አዘጋጅነት በሚካሄደው ጨዋታ ተሳታፊነቷን የምታረጋግጥ ሲሆን፤ ማደጋስካር ከኒጀር የሚያደርጉት ጨዋታ በኒጀር አሸናፊነት የሚጠናቀቅ ከሆነ ደግሞ ሰፊ የማለፍ እድል ይኖራታል። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በአንድ ዓመት በተራዘመው 33ኛው የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ከወዲሁ አምስት አገራት ማለፋቸውን አረጋግጠዋል። እነዚህም አገራት አዘጋጇ ካሜሩን፣ ሴኔጋል፣ ቱኒዚያ፣ ማሊ እና አልጄሪያ ናቸው።
https://www.bbc.com/amharic/56520048
3politics
ቶማስ ሳንካራ፡ 'የአፍሪካውን ቼ ጉቬራ' ማን ገደለው?
ከሠላሳ አራት ዓመት ገደማ በፊት የወቅቱ የቡርኪናፋሶ ፕሬዝዳንት ቶማስ ሳንካራ አስደንጋጭ ግድያ የተፈጸመበት። እነሆ አሁን ከ34 ዓመት በኋላ "የአፍሪካው ቼ ጉቬራ" በመባል በሚታወቀው ሰው ግድያ ተባባሪ በመሆን 14 ሰዎች ክስ ተመስርቶባቸው ፍርድ ቤት ቀርቡ። የባለግርማ ሞገሱ የፓን አፍሪካኒዝም አቀንቃኝ እአአ ጥቅምት 15/1987 በተካሄደ መፈንቅለ መንግሥት በወታደሮቹ ነበር በጥይት ተገደለው። ይህን ተከትሎ የቅርብ ጓደኛው ብሌዝ ኮምፓዎሬ ወደ ሥልጣን መጣ። ከግድያው ከአራት ዓመት ቀድም ብሎ ሳንካራና ካምፓዎሬ ሳንካራን ፕሬዝዳንትነት ያበቃውን መፈንቅለ መንግሥት መርተዋል። ኮምፓዎሬም ከ14ቱ ተከሳሾች መካከል ነበር። በጎረቤት አይቮሪ ኮስት በግዞት የሚገኘው ኮምፓዎሬ እአአ በ2014 በተካሄደው ሕዝባዊ ተቃውሞ ሥልጣኑን ለቆ ነው የተሰደደው። ነገር ግን በሳንካራ ግድያ ውስጥ እጁ እንደሌለበት በተደጋጋሚ አስተባብሏል። በፍርድ ሂደቱ እንደማይገኝም አስታውቋል። ምንም እንኳን ጊዜው ቢቆይም ሳንካራ በመላው አፍሪካ እንደ ተምሳሌት ሆኖ ይታያል። በምዕራብ አፍሪካ ታክሲዎችን በምስሉ ያስጌጣሉ። የደቡብ አፍሪካው የተቃዋሚ መሪ ጁሊየስ ማሌማ ከምሳሌዎቹ አንዱ አድርጎ ሳንከራን ይጠቅሳል። ሳንካራ ለምን እንደ ጀግና ይታያል? የቶማስ ሳንካራ የመታሰቢያ ኮሚቴ ዋና ጸሐፊ ሉክ ዳሚባ "ለእኛ ሳንካራ ጀግናችን ነበር። ሕዝቡን ይወዳል። አገሩን ይወዳል። አፍሪካን ይወዳል። ሕይወቱን ለእኛ ሰጥቷል" ብለዋል። አገሪቱ በእሱ የስልጣን ዘመን ነበር ከአፐር ቮልታ ወደ ቡርኪና ፋሶ ስያሜዋን የቀየረችው። ትርጉሙ "የቀና ሰዎች ምድር" ማለት ነው። ሳንካራ ቅንጡ የሚባል የአኗኗር ዘይቤ አልነበረውም። የራሱን እና የመንግሥት ሠራተኞችን ደመወዝ ሁሉ ቀንሷል። የመንግሥት ሹፌሮችን እና አንደኛ ደረጃ የአየር መንገድ ትኬቶች እንዳይጠቀሙም አግዷል። ለትምህርት ቅድሚያ ይሰጥ ነበር። ሥልጣን ላይ በነበረበት ጊዜ በአገሪቱ ማንበብ እና መጻፍ የሚችሉ ሰዎች በ1983 ከነበረበት 13 በመቶ በ1987 ወደ 73 በመቶ አድጓል። እንዲሁም ግዙፍ ብሔራዊ የክትባት ዘመቻን በበላይነት መርቷል። ከፊውዳል ባለንብረቶችም መሬት በቀጥታ ለድሃ ገበሬዎች አከፋፍሏል። ይህም የስንዴ ምርት በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምር አድርጓል። ተባበረችው አፍሪካ የ"ኒዮ-ቅኝ አገዛዝ" ተቋማት ብሎ ከጠራቸው እንደ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) እና የዓለም ባንክ ተቃራኒ እንድትቆም ጥሪ ያቀርብ ነበር። አንድ ጊዜ "የሚያበላህ ይቆጣጠርሃል" ሲል መናገሩ ይጠቀሳል። አፍሪካ ውስጥ እንደ ቡርኪና ፋሶ ባሉ በርካታ ቅኝ ግዛቶቿ ከፍተኛ ተጽዕኖ የነበራትን የፈረንሳይን የበላይነት የሚገዳደር የፀረ-ኢምፔሪያሊስት የውጭ ፖሊሲን ይፋ አደረገ። ፈረንሳይን እሱን ለመግደል ፊታውራሪ ነበረች ስትል ባለቤቱ ማሪያም ትከሳለች። በኡጋዱጉ የሚገኘው የቶማስ ሳንካራ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ለቢቢሲ እንደተናገረው "እሱ ፕሬዝዳንቴ ሆኖ ይኖራል። ለሕዝቡ ያደረገው ነገር እኛ ወጣቶች እሱ ያደረገውን እንድናደርግ ያበረታታናል" ብሏል። በዋና ከተማዋ ኡጋዱጉ በሚገኘው ቶማስ ሳንካራ የመታሰቢያ ፓርክ ውስጥ ስድስት ሜትር ርዝማኔ ያለው የነሐስ ሐውልት እ.ኤ.አ. በ2019 ይፋ ተደርጓል። የመጀመሪያው ሐውልት ላይ ቅሬታዎች በመነሳታቸው ባለፈው ዓመት በድጋሚ ተሠርቷል። ዳሚባ እንዳሉት ፓርኩን ለማስፋፋት ዕቅድ ተይዟል። ኦዋጋዱጉን ወደታች የሚመለከት 87 ሜትር ከፍታ ያለው ማማ ደግሞ አንዱ ነው። ለሳንካራ መቃብር ቤት፣ የሲኒማ አዳራሽ እና በስሙ የተሰየመ የሚዲያ ቤተ መጽሐፍትም ይኖራል። እነዚህ ማስታወሻዎች የሳንካራን አብዮታዊ ሃሳቦች ለትውልድ ያስተላልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ተቺዎቹስ? የሳንካራ አክራሪ የግራ ክንፍ ፖሊሲዎች በሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ተተችቷል። እአአ በ 1986 አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው ዘገባ የፖለቲካ ተቃዋሚዎች ናቸው የተባሉ ሰዎች ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ታስረው ከፍተኛ ስቃይ ደርሶባቸዋል። በሳንካራ መንግሥት ውስጥ የመረጃ ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉት ሰርጌ ቴኦፊል ባልማ "የብዝሃነት ዴሞክራሲ ሃሳብን ለመቀበል በጣም የዘገየ ይመስለኛል። ተቃዋሚዎቹን ለማናገርና እና ሊያዳምጣቸው አልቻለም" ብለዋል። ፕሮፌሰር ባሊማ አክለውም "ለሕዝብ ሥልጣን መስጠት ስለፈለገ የሕዝቡን ግላዊና ሕዝባዊ የህይወት ዘይቤ በተገቢው መንገድ ለመምራት ለተመለመሉት የአብዮቱ መከላከያ ኮሚቴዎችን [ሲዲአር] ለሚመሩት ሠርቶ አደሮች ሥልጣን ሰጠ። በእውነቱ እነሱም የእሱን ሥልጣን ያጠለሹ ጥቃቶችን ሲፈጽሙ ተገኝተዋል።" እአአ በ 2020 ከአፍሪካ ሪፖርት ድርገጽ ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት እና በሳንካራ ከስልጣን የተባረሩት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዣን-ባፕቲስት ኦውድራጎ "በግል ፍላጎት እና የፖለቲካ ማኪያቬሊያኒዝም" በባህሪው ውስጥ ቦታ እንዳላቸው ገልጸዋል። የፍርድ ሂደቱ ለምን ረዥም ጊዜ ፈጀ? ወንድሙ ፖል ሳንካራ "የ27 ዓመታቱ የብሌዝ ኮምፓዎሬ አገዛዝ ተጨምሮበት ረዥም ጊዜን ጠብቀናል። በእሱ አገዛዝ ዘመን ፍርድ አለ ብለን እንኳን ማለም አልቻልንም" ብሏል። ሚስቱ ስለባለቤቷ ግድያ እአአ በ1997 የወንጀል ቅሬታ ብታቀርብም ምርመራው ሊቀጥል ይችላል የሚለውን ለመወሰን ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ 15 ዓመት ፈጅቶበታል። ሆኖም ኮምፓዎሬ እአአ በ2014 ከስልጣን እስኪወርዱ ድረስ ብዙም ፈቀቅ አላለም ነበር። በቀጣዩ ዓመት የእሱ ነው የተባለ አስከሬን ተቆፍሮ ቢወጣም በዘረመል (ዲኤንኤ) ምርመራ የእሱ መሆኑን ማረጋገጥ አልተቻለም። እአአ በ2016 የቡርኪናፋሶ ባለሥልጣናት የፈረንሳይ መንግሥት ስለ ሳንካራ ግድያ ያለውን ወታደራዊ ሰነዶችን እንዲለቅን በይፋ ጠይቀዋል። እነዚያ ሰነዶች በሦስት ደረጃ ወደ ቡርኪና ፋሶ ተዛውረዋል። የመጨረሻው ኦጋዱጉ የደረሰው እአአ ሚያዝያ 2021 ነው። በፍርድ ሂደቱ ላይ ሌላ ማን ይቀርባል? የኮምፓዎሬ የቀድሞው አዛዥ ጄኔራል ጊልበርት ዲንዴሬ እና ሌሎች 11 ሰዎች በወታደራዊው ፍርድ ቤት እንደሚገኙ ይጠበቃል። "የመንግሥትን ደኅንነት በማጥቃት"፣ "በግድያ ተባባሪነት" እና "አስከሬን በመደበቅ" ክስ ይቀርብባቸዋል። እአአ በ2015 ባልተሳካው መፈንቅለ መንግሥት ሚና ነበረው በሚል ዲንዴሬ 20 ዓመት ተፈርዶበት በእስር ላይ ይገኛል። ከተከሳሾቹ መካከል የሞት የምስክር ወረቀቱን የፈረመው ዶክተር ዲቤሬ ዣን ክሪስቶፍ ይገኝበታል። ሐኪሙ የቀድሞው ፕሬዚዳንት በተፈጥሯዊ ምክንያቶች ሞተዋል ሲል ፈርሟል። ሐኪሙ የሕዝብ ሰነድ በማጭበርበር ክስ ቀርቦበታል። በሌለበት የሚከሰሰው የኮምፓዎሬ የቀድሞ የደኅንነት ኃላፊ ሂያሲን ካፋንዶ ነው። ዓለም አቀፉ የእስራት ማዘዣ ወጥቶበታል። ሳንካራን እና ሌሎች 12 ሰዎችን የገደለውን ቡድን በመምራት ክስ ተመስርቶበታል። የፍርድ ሂደቱ ምን ተጽዕኖ ይኖረዋል? ከአልቃይዳ እና ከእስላማዊ መንግሥት ቡድን ጋር የተቆራኙ የጂሃዲስት ቡድኖች የሚያደርሱባትን ተደጋጋሚ ጥቃቶች እየታገለች ያለችው ቡርኪና ፋሶ የፍርድ ሂደቱ የበለጠ እንዳትረጋጋ ሊያደርጋት ይችላል የሚል ሥጋት አለ። ኮምፓዎሬ አሁንም በአገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያለው ሲሆን የእሱ ታማኝ የሆኑ የወታደር ክፍሎች ችግር ሊቀሰቅሱ እንደሚችሉ አንዳንድ ተንታኞች አስጠንቅቀዋል። ይህ ስለመሆኑ ግን ትንሽ ምልክት ነው ያለው። በተቃራኒው ፕሬዝዳንት ሮች ማርክ ካቦሬ የፍርድ ሂደቱ ውጥረትን አቃሎ ብሔራዊ ዕርቅን ያጠናክራል ብለው ተስፋ ያደርጋሉ። በኢንተርናሽናል ክራይወሲስ ግሩፕ የሳህል ተንታኝ የሆነው ማቲው ፔሌሪን "እንዲህ ዓይነቱ ፍርድ አለመረጋጋትን ሊያዳብር ይችላል ብዬ አላምንም" ሲል እአአ በ2020 ለፈረንሳዩ መጽሔት ጁን አፍሪክ ተናግሯል። አክሎም "ያለ ፍትህ ዕርቅ እምብዛም አይገኝም" ብሏል።
ቶማስ ሳንካራ፡ 'የአፍሪካውን ቼ ጉቬራ' ማን ገደለው? ከሠላሳ አራት ዓመት ገደማ በፊት የወቅቱ የቡርኪናፋሶ ፕሬዝዳንት ቶማስ ሳንካራ አስደንጋጭ ግድያ የተፈጸመበት። እነሆ አሁን ከ34 ዓመት በኋላ "የአፍሪካው ቼ ጉቬራ" በመባል በሚታወቀው ሰው ግድያ ተባባሪ በመሆን 14 ሰዎች ክስ ተመስርቶባቸው ፍርድ ቤት ቀርቡ። የባለግርማ ሞገሱ የፓን አፍሪካኒዝም አቀንቃኝ እአአ ጥቅምት 15/1987 በተካሄደ መፈንቅለ መንግሥት በወታደሮቹ ነበር በጥይት ተገደለው። ይህን ተከትሎ የቅርብ ጓደኛው ብሌዝ ኮምፓዎሬ ወደ ሥልጣን መጣ። ከግድያው ከአራት ዓመት ቀድም ብሎ ሳንካራና ካምፓዎሬ ሳንካራን ፕሬዝዳንትነት ያበቃውን መፈንቅለ መንግሥት መርተዋል። ኮምፓዎሬም ከ14ቱ ተከሳሾች መካከል ነበር። በጎረቤት አይቮሪ ኮስት በግዞት የሚገኘው ኮምፓዎሬ እአአ በ2014 በተካሄደው ሕዝባዊ ተቃውሞ ሥልጣኑን ለቆ ነው የተሰደደው። ነገር ግን በሳንካራ ግድያ ውስጥ እጁ እንደሌለበት በተደጋጋሚ አስተባብሏል። በፍርድ ሂደቱ እንደማይገኝም አስታውቋል። ምንም እንኳን ጊዜው ቢቆይም ሳንካራ በመላው አፍሪካ እንደ ተምሳሌት ሆኖ ይታያል። በምዕራብ አፍሪካ ታክሲዎችን በምስሉ ያስጌጣሉ። የደቡብ አፍሪካው የተቃዋሚ መሪ ጁሊየስ ማሌማ ከምሳሌዎቹ አንዱ አድርጎ ሳንከራን ይጠቅሳል። ሳንካራ ለምን እንደ ጀግና ይታያል? የቶማስ ሳንካራ የመታሰቢያ ኮሚቴ ዋና ጸሐፊ ሉክ ዳሚባ "ለእኛ ሳንካራ ጀግናችን ነበር። ሕዝቡን ይወዳል። አገሩን ይወዳል። አፍሪካን ይወዳል። ሕይወቱን ለእኛ ሰጥቷል" ብለዋል። አገሪቱ በእሱ የስልጣን ዘመን ነበር ከአፐር ቮልታ ወደ ቡርኪና ፋሶ ስያሜዋን የቀየረችው። ትርጉሙ "የቀና ሰዎች ምድር" ማለት ነው። ሳንካራ ቅንጡ የሚባል የአኗኗር ዘይቤ አልነበረውም። የራሱን እና የመንግሥት ሠራተኞችን ደመወዝ ሁሉ ቀንሷል። የመንግሥት ሹፌሮችን እና አንደኛ ደረጃ የአየር መንገድ ትኬቶች እንዳይጠቀሙም አግዷል። ለትምህርት ቅድሚያ ይሰጥ ነበር። ሥልጣን ላይ በነበረበት ጊዜ በአገሪቱ ማንበብ እና መጻፍ የሚችሉ ሰዎች በ1983 ከነበረበት 13 በመቶ በ1987 ወደ 73 በመቶ አድጓል። እንዲሁም ግዙፍ ብሔራዊ የክትባት ዘመቻን በበላይነት መርቷል። ከፊውዳል ባለንብረቶችም መሬት በቀጥታ ለድሃ ገበሬዎች አከፋፍሏል። ይህም የስንዴ ምርት በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምር አድርጓል። ተባበረችው አፍሪካ የ"ኒዮ-ቅኝ አገዛዝ" ተቋማት ብሎ ከጠራቸው እንደ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) እና የዓለም ባንክ ተቃራኒ እንድትቆም ጥሪ ያቀርብ ነበር። አንድ ጊዜ "የሚያበላህ ይቆጣጠርሃል" ሲል መናገሩ ይጠቀሳል። አፍሪካ ውስጥ እንደ ቡርኪና ፋሶ ባሉ በርካታ ቅኝ ግዛቶቿ ከፍተኛ ተጽዕኖ የነበራትን የፈረንሳይን የበላይነት የሚገዳደር የፀረ-ኢምፔሪያሊስት የውጭ ፖሊሲን ይፋ አደረገ። ፈረንሳይን እሱን ለመግደል ፊታውራሪ ነበረች ስትል ባለቤቱ ማሪያም ትከሳለች። በኡጋዱጉ የሚገኘው የቶማስ ሳንካራ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ለቢቢሲ እንደተናገረው "እሱ ፕሬዝዳንቴ ሆኖ ይኖራል። ለሕዝቡ ያደረገው ነገር እኛ ወጣቶች እሱ ያደረገውን እንድናደርግ ያበረታታናል" ብሏል። በዋና ከተማዋ ኡጋዱጉ በሚገኘው ቶማስ ሳንካራ የመታሰቢያ ፓርክ ውስጥ ስድስት ሜትር ርዝማኔ ያለው የነሐስ ሐውልት እ.ኤ.አ. በ2019 ይፋ ተደርጓል። የመጀመሪያው ሐውልት ላይ ቅሬታዎች በመነሳታቸው ባለፈው ዓመት በድጋሚ ተሠርቷል። ዳሚባ እንዳሉት ፓርኩን ለማስፋፋት ዕቅድ ተይዟል። ኦዋጋዱጉን ወደታች የሚመለከት 87 ሜትር ከፍታ ያለው ማማ ደግሞ አንዱ ነው። ለሳንካራ መቃብር ቤት፣ የሲኒማ አዳራሽ እና በስሙ የተሰየመ የሚዲያ ቤተ መጽሐፍትም ይኖራል። እነዚህ ማስታወሻዎች የሳንካራን አብዮታዊ ሃሳቦች ለትውልድ ያስተላልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ተቺዎቹስ? የሳንካራ አክራሪ የግራ ክንፍ ፖሊሲዎች በሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ተተችቷል። እአአ በ 1986 አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው ዘገባ የፖለቲካ ተቃዋሚዎች ናቸው የተባሉ ሰዎች ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ታስረው ከፍተኛ ስቃይ ደርሶባቸዋል። በሳንካራ መንግሥት ውስጥ የመረጃ ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉት ሰርጌ ቴኦፊል ባልማ "የብዝሃነት ዴሞክራሲ ሃሳብን ለመቀበል በጣም የዘገየ ይመስለኛል። ተቃዋሚዎቹን ለማናገርና እና ሊያዳምጣቸው አልቻለም" ብለዋል። ፕሮፌሰር ባሊማ አክለውም "ለሕዝብ ሥልጣን መስጠት ስለፈለገ የሕዝቡን ግላዊና ሕዝባዊ የህይወት ዘይቤ በተገቢው መንገድ ለመምራት ለተመለመሉት የአብዮቱ መከላከያ ኮሚቴዎችን [ሲዲአር] ለሚመሩት ሠርቶ አደሮች ሥልጣን ሰጠ። በእውነቱ እነሱም የእሱን ሥልጣን ያጠለሹ ጥቃቶችን ሲፈጽሙ ተገኝተዋል።" እአአ በ 2020 ከአፍሪካ ሪፖርት ድርገጽ ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት እና በሳንካራ ከስልጣን የተባረሩት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዣን-ባፕቲስት ኦውድራጎ "በግል ፍላጎት እና የፖለቲካ ማኪያቬሊያኒዝም" በባህሪው ውስጥ ቦታ እንዳላቸው ገልጸዋል። የፍርድ ሂደቱ ለምን ረዥም ጊዜ ፈጀ? ወንድሙ ፖል ሳንካራ "የ27 ዓመታቱ የብሌዝ ኮምፓዎሬ አገዛዝ ተጨምሮበት ረዥም ጊዜን ጠብቀናል። በእሱ አገዛዝ ዘመን ፍርድ አለ ብለን እንኳን ማለም አልቻልንም" ብሏል። ሚስቱ ስለባለቤቷ ግድያ እአአ በ1997 የወንጀል ቅሬታ ብታቀርብም ምርመራው ሊቀጥል ይችላል የሚለውን ለመወሰን ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ 15 ዓመት ፈጅቶበታል። ሆኖም ኮምፓዎሬ እአአ በ2014 ከስልጣን እስኪወርዱ ድረስ ብዙም ፈቀቅ አላለም ነበር። በቀጣዩ ዓመት የእሱ ነው የተባለ አስከሬን ተቆፍሮ ቢወጣም በዘረመል (ዲኤንኤ) ምርመራ የእሱ መሆኑን ማረጋገጥ አልተቻለም። እአአ በ2016 የቡርኪናፋሶ ባለሥልጣናት የፈረንሳይ መንግሥት ስለ ሳንካራ ግድያ ያለውን ወታደራዊ ሰነዶችን እንዲለቅን በይፋ ጠይቀዋል። እነዚያ ሰነዶች በሦስት ደረጃ ወደ ቡርኪና ፋሶ ተዛውረዋል። የመጨረሻው ኦጋዱጉ የደረሰው እአአ ሚያዝያ 2021 ነው። በፍርድ ሂደቱ ላይ ሌላ ማን ይቀርባል? የኮምፓዎሬ የቀድሞው አዛዥ ጄኔራል ጊልበርት ዲንዴሬ እና ሌሎች 11 ሰዎች በወታደራዊው ፍርድ ቤት እንደሚገኙ ይጠበቃል። "የመንግሥትን ደኅንነት በማጥቃት"፣ "በግድያ ተባባሪነት" እና "አስከሬን በመደበቅ" ክስ ይቀርብባቸዋል። እአአ በ2015 ባልተሳካው መፈንቅለ መንግሥት ሚና ነበረው በሚል ዲንዴሬ 20 ዓመት ተፈርዶበት በእስር ላይ ይገኛል። ከተከሳሾቹ መካከል የሞት የምስክር ወረቀቱን የፈረመው ዶክተር ዲቤሬ ዣን ክሪስቶፍ ይገኝበታል። ሐኪሙ የቀድሞው ፕሬዚዳንት በተፈጥሯዊ ምክንያቶች ሞተዋል ሲል ፈርሟል። ሐኪሙ የሕዝብ ሰነድ በማጭበርበር ክስ ቀርቦበታል። በሌለበት የሚከሰሰው የኮምፓዎሬ የቀድሞ የደኅንነት ኃላፊ ሂያሲን ካፋንዶ ነው። ዓለም አቀፉ የእስራት ማዘዣ ወጥቶበታል። ሳንካራን እና ሌሎች 12 ሰዎችን የገደለውን ቡድን በመምራት ክስ ተመስርቶበታል። የፍርድ ሂደቱ ምን ተጽዕኖ ይኖረዋል? ከአልቃይዳ እና ከእስላማዊ መንግሥት ቡድን ጋር የተቆራኙ የጂሃዲስት ቡድኖች የሚያደርሱባትን ተደጋጋሚ ጥቃቶች እየታገለች ያለችው ቡርኪና ፋሶ የፍርድ ሂደቱ የበለጠ እንዳትረጋጋ ሊያደርጋት ይችላል የሚል ሥጋት አለ። ኮምፓዎሬ አሁንም በአገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያለው ሲሆን የእሱ ታማኝ የሆኑ የወታደር ክፍሎች ችግር ሊቀሰቅሱ እንደሚችሉ አንዳንድ ተንታኞች አስጠንቅቀዋል። ይህ ስለመሆኑ ግን ትንሽ ምልክት ነው ያለው። በተቃራኒው ፕሬዝዳንት ሮች ማርክ ካቦሬ የፍርድ ሂደቱ ውጥረትን አቃሎ ብሔራዊ ዕርቅን ያጠናክራል ብለው ተስፋ ያደርጋሉ። በኢንተርናሽናል ክራይወሲስ ግሩፕ የሳህል ተንታኝ የሆነው ማቲው ፔሌሪን "እንዲህ ዓይነቱ ፍርድ አለመረጋጋትን ሊያዳብር ይችላል ብዬ አላምንም" ሲል እአአ በ2020 ለፈረንሳዩ መጽሔት ጁን አፍሪክ ተናግሯል። አክሎም "ያለ ፍትህ ዕርቅ እምብዛም አይገኝም" ብሏል።
https://www.bbc.com/amharic/news-58867138
5sports
ላሚን ዲያክ፡ የቀድሞው የዓለም አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕሬዚደንት በሙስና ወንጀል የ4 ዓመት እስር ተፈረደባቸው
የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር (አይኤኤኤፍ) የቀድሞ ፕሬዚደንት ላሚን ዲያክ፤ በሙስና ወንጀል ጥፋተኛ ተብለው አራት ዓመት በእስር እንዲያሳልፉ ውሳኔ ተላለፈባቸው። ሌሎች ሁለት ግለሰቦች ደግሞ ከሥራ መታገዳቸው ተገልጿል። የ87 ዓመቱ ሴኔጋላዊ ከአበረታች መድሃኒት ጋር ተያይዞ በሙስናና በገንዘብ ዝውውር ነው ክስ የቀረበባቸው። ዲያክ አበረታች መድሃኒት ይጠቀማሉ ተብለው ከተጠረጠሩ አትሌቶች የምርመራ ውጤታቸውን ለመደበቅ እና የ2012ቱ የለንደን ኦሎምፒክን ጨምሮ ውድድር ላይ እንዲሳተፉ ለማድረግ ጉቦ በመቀበል ጥፋተኛ ተብለዋል። የቀድሞ ፕሬዚደንቱ የ500 ሺህ ዩሮ ቅጣትም ተጥሎባቸዋል። ዲያክ የአትሌቶቹን ጉዳይ ለመሸፋፈን ከ3 ሚሊየን ዩሮ በላይ ገንዘብ ተቀብለዋል የሚል ክስ ከቀረበባቸው በኋላ የፈረንሳይ ባለሥልጣናት ለ አራት ዓመታት ምርመራ ሲያካሂዱ ቆይተዋል። ውሳኔውን ያስተላለፉት ዳኛም የቀድሞ ፕሬዚደንቱን ድርጊት "የአትሌቲክስን እሴትና አበረታች መድሃኒት ላይ የሚደረገውን ትግል የጣሰ " ብለውታል። ዲያክ ከህዳር 2015 ጀምሮ በፓሪስ በቁም እስር ላይ ነበሩ። የቀድሞ ፕሬዚደንቱ በዓለም ስፖርት የዓለማችን ተፅዕኖ ፈጣሪ ከሆኑ ግለሰቦች አንዱ የነበሩ ሲሆን በዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌደሬሽኖች ማህበር በአሁኑ የዓለም አትሌቲክስ ለ16 ዓመታት አገልግለዋል። በእንግሊዛዊው ሎርድ ሴባስቲያን ኮ የተተኩትም ከአምስት ዓመታት በፊት ነበር።
ላሚን ዲያክ፡ የቀድሞው የዓለም አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕሬዚደንት በሙስና ወንጀል የ4 ዓመት እስር ተፈረደባቸው የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር (አይኤኤኤፍ) የቀድሞ ፕሬዚደንት ላሚን ዲያክ፤ በሙስና ወንጀል ጥፋተኛ ተብለው አራት ዓመት በእስር እንዲያሳልፉ ውሳኔ ተላለፈባቸው። ሌሎች ሁለት ግለሰቦች ደግሞ ከሥራ መታገዳቸው ተገልጿል። የ87 ዓመቱ ሴኔጋላዊ ከአበረታች መድሃኒት ጋር ተያይዞ በሙስናና በገንዘብ ዝውውር ነው ክስ የቀረበባቸው። ዲያክ አበረታች መድሃኒት ይጠቀማሉ ተብለው ከተጠረጠሩ አትሌቶች የምርመራ ውጤታቸውን ለመደበቅ እና የ2012ቱ የለንደን ኦሎምፒክን ጨምሮ ውድድር ላይ እንዲሳተፉ ለማድረግ ጉቦ በመቀበል ጥፋተኛ ተብለዋል። የቀድሞ ፕሬዚደንቱ የ500 ሺህ ዩሮ ቅጣትም ተጥሎባቸዋል። ዲያክ የአትሌቶቹን ጉዳይ ለመሸፋፈን ከ3 ሚሊየን ዩሮ በላይ ገንዘብ ተቀብለዋል የሚል ክስ ከቀረበባቸው በኋላ የፈረንሳይ ባለሥልጣናት ለ አራት ዓመታት ምርመራ ሲያካሂዱ ቆይተዋል። ውሳኔውን ያስተላለፉት ዳኛም የቀድሞ ፕሬዚደንቱን ድርጊት "የአትሌቲክስን እሴትና አበረታች መድሃኒት ላይ የሚደረገውን ትግል የጣሰ " ብለውታል። ዲያክ ከህዳር 2015 ጀምሮ በፓሪስ በቁም እስር ላይ ነበሩ። የቀድሞ ፕሬዚደንቱ በዓለም ስፖርት የዓለማችን ተፅዕኖ ፈጣሪ ከሆኑ ግለሰቦች አንዱ የነበሩ ሲሆን በዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌደሬሽኖች ማህበር በአሁኑ የዓለም አትሌቲክስ ለ16 ዓመታት አገልግለዋል። በእንግሊዛዊው ሎርድ ሴባስቲያን ኮ የተተኩትም ከአምስት ዓመታት በፊት ነበር።
https://www.bbc.com/amharic/news-54181586
0business
ማኅበራዊ ሚዲያ፡ ኡጋንዳውያን ለሚጠቀሙት የኢንተርኔት አገልግሎት ታክስ መክፈል ጀመሩ
ኡጋንዳውያን የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ከዛሬ ሐሙስ ዕለት ጀምሮ የሞባይል ዳታ 12 በመቶ ኤክሳይዝ ታክስ መክፈል ጀመሩ። ይህ ታክስ እአአ በ2018 የተዋወቀውና በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የተጣለውን የማኅበራዊ ሚዲያ አገልግሎት ዕለታዊ ታክስ [ኦቲቲ] ን ተክቷል። አዲስ የተጣለው ኤክሳይዝ ታክስ ተግባራዊ መሆን የጀመረው አዲስ የበጀት ዓመት መጀመሩን ተከትሎ ነው። ኤክሳይዝ ታክስ በተመረጡ እቃዎች ወይም አገልግሎቶች፤ በተለይም የቅንጦት ተብለው በሚታሰቡት ላይ የሚጣል ቀጥተኛ ያልሆነ የታክስ ዓይነት ነው። ይህ ታክስ የተዋወቀው በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ በአገሪቱ ምክር ቤት ማሻሻያ ከተደረገበት በኋላ ነው። ለሕክምና እና ለትምህርት አገልግሎት ለሚገዛ የሞባይል ዳታ ላይ ታክሱ አይጣልም ተብሏል። ይሁን እንጅ ይህንን አገልግሎት ከሌላው እንዴት መለየት እንደሚቻል ግልፅ ያለ ነገር የለም። እአአ ሐምሌ 2018 የማኅበራዊ ሚዲያ ታክስ ተቃውሞን ቀስቅሶ ነበር። ተቃውሞው በተቃዋሚው ፖለቲከኛውና ሙዚቀኛ ሮበርት ክያጉላኒ ወይም ቦቢ ዋይን የተመራ ነበር። በወቅቱ ተቃውሞው የጸጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ ተበትኗል። አብዛኞቹ ኡጋንዳውያን ቪፒኤን የተባለውንና እገዳውን ለማለፍ የሚያስችሉ መተግበሪያዎችን ኢንተርኔትን ለመጠቀም አማራጭ አድርገዋል። በዚህም ምክንያት የሚጠበቀውን ያህል ግብር መሰብሰብ ሳይቻል ቀርቷል። የአገሪቷ የገቢዎች ባለሥልጣን በ2018 - 2019 የበጀት ዓመት ለመሰብሰብ አቅዶ ከነበረው 80 ሚሊየን ዶላር፤ መሰብሰብ የቻለው 14 ሚሊየን ዶላር መሆኑን በዚያው ዓመት አስታውቆ ነበር። ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ላይ ታክስ መጣል በኡጋንዳ፤ በተለይም አነስተኛ ንግዶችን ለመጀመር በብዛት ኢንተርኔትን የሚጠቀሙ ወጣቶችን አስቆጥቷል።
ማኅበራዊ ሚዲያ፡ ኡጋንዳውያን ለሚጠቀሙት የኢንተርኔት አገልግሎት ታክስ መክፈል ጀመሩ ኡጋንዳውያን የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ከዛሬ ሐሙስ ዕለት ጀምሮ የሞባይል ዳታ 12 በመቶ ኤክሳይዝ ታክስ መክፈል ጀመሩ። ይህ ታክስ እአአ በ2018 የተዋወቀውና በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የተጣለውን የማኅበራዊ ሚዲያ አገልግሎት ዕለታዊ ታክስ [ኦቲቲ] ን ተክቷል። አዲስ የተጣለው ኤክሳይዝ ታክስ ተግባራዊ መሆን የጀመረው አዲስ የበጀት ዓመት መጀመሩን ተከትሎ ነው። ኤክሳይዝ ታክስ በተመረጡ እቃዎች ወይም አገልግሎቶች፤ በተለይም የቅንጦት ተብለው በሚታሰቡት ላይ የሚጣል ቀጥተኛ ያልሆነ የታክስ ዓይነት ነው። ይህ ታክስ የተዋወቀው በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ በአገሪቱ ምክር ቤት ማሻሻያ ከተደረገበት በኋላ ነው። ለሕክምና እና ለትምህርት አገልግሎት ለሚገዛ የሞባይል ዳታ ላይ ታክሱ አይጣልም ተብሏል። ይሁን እንጅ ይህንን አገልግሎት ከሌላው እንዴት መለየት እንደሚቻል ግልፅ ያለ ነገር የለም። እአአ ሐምሌ 2018 የማኅበራዊ ሚዲያ ታክስ ተቃውሞን ቀስቅሶ ነበር። ተቃውሞው በተቃዋሚው ፖለቲከኛውና ሙዚቀኛ ሮበርት ክያጉላኒ ወይም ቦቢ ዋይን የተመራ ነበር። በወቅቱ ተቃውሞው የጸጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ ተበትኗል። አብዛኞቹ ኡጋንዳውያን ቪፒኤን የተባለውንና እገዳውን ለማለፍ የሚያስችሉ መተግበሪያዎችን ኢንተርኔትን ለመጠቀም አማራጭ አድርገዋል። በዚህም ምክንያት የሚጠበቀውን ያህል ግብር መሰብሰብ ሳይቻል ቀርቷል። የአገሪቷ የገቢዎች ባለሥልጣን በ2018 - 2019 የበጀት ዓመት ለመሰብሰብ አቅዶ ከነበረው 80 ሚሊየን ዶላር፤ መሰብሰብ የቻለው 14 ሚሊየን ዶላር መሆኑን በዚያው ዓመት አስታውቆ ነበር። ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ላይ ታክስ መጣል በኡጋንዳ፤ በተለይም አነስተኛ ንግዶችን ለመጀመር በብዛት ኢንተርኔትን የሚጠቀሙ ወጣቶችን አስቆጥቷል።
https://www.bbc.com/amharic/news-57682386
3politics
በአሜሪካ ምክር ቤት መሪዎች መኖሪያ ቤት ላይ ጥቃት መፈጸሙ ተነገረ
በአሜሪካ ምክር ቤት አፈጉባኤ ናንሲ ፔሎሲና የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት የብዙሃን መሪው ሚች ማኮኔል መኖሪያ ቤት ላይ ጥቃት መፈጸሙ ተነገረ። ካሊፎርኒያ ውስጥ ከሚገኘው የናንሲ ፔሎሲ ቤት ውጪ አንገቱ የተቆረጠ አሳማና ደም የሚመስል ቀለም የተገኘ ሲሆን ግድግዳውም በተለያየ ጽሁፍ ተበላሽቶ ተገኝቷል። ኬንተኪ ውስጥ በሚገኘው የሪፐብሊካኑ ማኮኔል ቤት ግድግዳ ላይ ደግሞ "ገንዘቤ የታለ" የሚል ጽሁፍና የስድብ ቃላት ተጽፈው ተገኝተዋል። ይህ በባለስልጣናቱ መኖሪያ ላይ የተፈጸመው ጥቃት የተከሰተው በኮሮናቫይረስ ምክንያት ያጋጠመውን ችግር ለመቅረፍ በቀረበው የድጋፍ ዕቅድ ላይ በምክር ቤት ከባድ ፖለቲካዊ ውዝግብ መካሄዱን ተከትሎ ነው። ባለፈው ማክሰኞ በዲሞክራቶች በሚመራው የአሜሪካ ምክር ቤት የ40 ሪፐብሊካን አባላት ድጋፍን በማግኘት በኮሮናቫይረስ ምክንያት ገቢያቸው ለተጎዳ ዜጎች እንዲሰጥ ሐሳብ ቀርቦበት የነበረውን የ600 ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ወደ 2000 ዶላር ከፍ እንዲል ተወስኖ ነበር። ምንም ችንኳን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቀረበውን ረቂው የምክር ቤት አባላቱ እንዲያጸድቁ ቢጠይቁም በሪፐብሊካኖች የሚመራው የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ከፍተኛ የገንዘብ ወጪን የሚጠይቀውን በጀት ሳይቀበለው ቀርቷል። ረቡዕ ዕለት ሚች ማኮኔል እንደተናገሩት በሚደረግ ማንኛውም ጫና "በብድር የሚገኘውን ገንዘብ ድጋፉ ለማያስፈልጋቸው ለዲሞክራት ሐብታም ወዳጆች በጥድፊያ እንዲሰጥ አናደርግም" ሲሉ ተደምጠው ነበር። ሚች ማኮኔል ቅዳሜ በቤታቸው ላይ ጥቃት ከተፈጸመ በኋላ ባወጡት መግለጫ ላይ "ቢስማሙም ባይስማሙም" በምክር ቤቱ የሥራ ሂደት ወቅት የተሳተፉትን በሙሉ አመስግነዋል። ጨምረውም "ይህ የተለየ ጉዳይ ነው" በማለት የተፈጸመውን ጥቃት በመቃወም "ንብረት ማውደምና ጉዳት ማድረስ እንዲሁም ፍርሃት ለመፍጠር የሚደረገው ፖለቲካም በማኅበረሰባችን ውስጥ ቦታ የለውም" ብለዋል። የሳንፍራንሲስኮ ፖሊስ በአፈጉባኤዋ ቤት ላይ በተፈጸመው ጥቃት ዙሪያ ምርመራ እያደረጉ ሲሆን ፔሎሲ ግን እስካሁን ምንም አስተያየት አልሰጡም። ባለፈው አርብ የአሜሪካ ምክር ቤት በፕሬዝዳንት ትራምፕ የስልጣን ዘመን አጋጥሞ በማያውቅ ሁኔታ የፕሬዝዳንቱን ውሳኔ ውድቅ ማድረጉ ይታወሳል። በቅርቡ በተደረገው ምርጫ ለአሜሪካ ምክር ቤት አባልነት የተመረጡ የኮንግረስ አባላት ዛሬ እሁድ ቃለ መሐላ ይፈጽማሉ።
በአሜሪካ ምክር ቤት መሪዎች መኖሪያ ቤት ላይ ጥቃት መፈጸሙ ተነገረ በአሜሪካ ምክር ቤት አፈጉባኤ ናንሲ ፔሎሲና የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት የብዙሃን መሪው ሚች ማኮኔል መኖሪያ ቤት ላይ ጥቃት መፈጸሙ ተነገረ። ካሊፎርኒያ ውስጥ ከሚገኘው የናንሲ ፔሎሲ ቤት ውጪ አንገቱ የተቆረጠ አሳማና ደም የሚመስል ቀለም የተገኘ ሲሆን ግድግዳውም በተለያየ ጽሁፍ ተበላሽቶ ተገኝቷል። ኬንተኪ ውስጥ በሚገኘው የሪፐብሊካኑ ማኮኔል ቤት ግድግዳ ላይ ደግሞ "ገንዘቤ የታለ" የሚል ጽሁፍና የስድብ ቃላት ተጽፈው ተገኝተዋል። ይህ በባለስልጣናቱ መኖሪያ ላይ የተፈጸመው ጥቃት የተከሰተው በኮሮናቫይረስ ምክንያት ያጋጠመውን ችግር ለመቅረፍ በቀረበው የድጋፍ ዕቅድ ላይ በምክር ቤት ከባድ ፖለቲካዊ ውዝግብ መካሄዱን ተከትሎ ነው። ባለፈው ማክሰኞ በዲሞክራቶች በሚመራው የአሜሪካ ምክር ቤት የ40 ሪፐብሊካን አባላት ድጋፍን በማግኘት በኮሮናቫይረስ ምክንያት ገቢያቸው ለተጎዳ ዜጎች እንዲሰጥ ሐሳብ ቀርቦበት የነበረውን የ600 ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ወደ 2000 ዶላር ከፍ እንዲል ተወስኖ ነበር። ምንም ችንኳን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቀረበውን ረቂው የምክር ቤት አባላቱ እንዲያጸድቁ ቢጠይቁም በሪፐብሊካኖች የሚመራው የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ከፍተኛ የገንዘብ ወጪን የሚጠይቀውን በጀት ሳይቀበለው ቀርቷል። ረቡዕ ዕለት ሚች ማኮኔል እንደተናገሩት በሚደረግ ማንኛውም ጫና "በብድር የሚገኘውን ገንዘብ ድጋፉ ለማያስፈልጋቸው ለዲሞክራት ሐብታም ወዳጆች በጥድፊያ እንዲሰጥ አናደርግም" ሲሉ ተደምጠው ነበር። ሚች ማኮኔል ቅዳሜ በቤታቸው ላይ ጥቃት ከተፈጸመ በኋላ ባወጡት መግለጫ ላይ "ቢስማሙም ባይስማሙም" በምክር ቤቱ የሥራ ሂደት ወቅት የተሳተፉትን በሙሉ አመስግነዋል። ጨምረውም "ይህ የተለየ ጉዳይ ነው" በማለት የተፈጸመውን ጥቃት በመቃወም "ንብረት ማውደምና ጉዳት ማድረስ እንዲሁም ፍርሃት ለመፍጠር የሚደረገው ፖለቲካም በማኅበረሰባችን ውስጥ ቦታ የለውም" ብለዋል። የሳንፍራንሲስኮ ፖሊስ በአፈጉባኤዋ ቤት ላይ በተፈጸመው ጥቃት ዙሪያ ምርመራ እያደረጉ ሲሆን ፔሎሲ ግን እስካሁን ምንም አስተያየት አልሰጡም። ባለፈው አርብ የአሜሪካ ምክር ቤት በፕሬዝዳንት ትራምፕ የስልጣን ዘመን አጋጥሞ በማያውቅ ሁኔታ የፕሬዝዳንቱን ውሳኔ ውድቅ ማድረጉ ይታወሳል። በቅርቡ በተደረገው ምርጫ ለአሜሪካ ምክር ቤት አባልነት የተመረጡ የኮንግረስ አባላት ዛሬ እሁድ ቃለ መሐላ ይፈጽማሉ።
https://www.bbc.com/amharic/news-55516801
3politics
ጦርነት እንዲቆም የሰላም ጥሪ ለማቅረብ የተጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ ታገደ
በአገሪቱ ባሉ በርካታ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የሰሜን ኢትዮጵያው የእርስ በእርስ ጦርነት እንዲቆም የሰላም ጥሪ ለማስተላለፍ የተጠራ ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳይካሄድ በፀጥታ ኃይሎች መታገዱ ተገለጸ። ጋዜጣዊ መግለጫውን ከጠሩት 35 የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች መካከል አንዱ የሆነው የመብቶች እና የዴሞክራሲ እድገት ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አቶ በፍቃዱ ኃይሉ፤ መግለጫ ሊሰጥበት በነበረው ሆቴል ሲቪል የለበሱ የመንግሥት የፀጥታ ኃይል አባላት ነን ያሉ ግለሰቦች መግለጫውን መስጠት አይቻልም በማለት ከልክለዋል ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። “የትኛው የመንግሥት አካል ክልከላውን እንደፈጸመ አልተነገረንም። እንዲሁ በጥቅሉ ይህን መግለጫ መሰጠት የለባችሁም የሚል መልዕክት ብቻ ነው የተላለፈልን” ብለዋል አቶ በፈቃዱ። ቢቢሲ ስለጉዳዩ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ምላሽ ጠይቆ ኮሚሽኑ ስለክልከላው የሚያውቀው ነገር እንደሌለ የገለጸ ሲሆን፣ የፌደራል ፖሊስ ምላሽን ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ ግን አልተሳካም። የመንግሥት የፀጥታ ሰዎች ነን ያሉት ግለሰቦች ጋዜጣዊ መግለጫውን ለመዘገብ በሆቴሉ ተገኝተው የነበሩ ጋዜጠኞችም መግለጫው እንደማይካሄድ በመግለጽ እንዲያሰናብቱ ለሆቴሉ ሠራተኞች ተናግረዋል ሲሉ አቶ በፍቃዱ ተናግረዋል። “ለማካሄድ አቅደን የነበረው የአደባባይ ስብሰባ ስላልነበረ ቀድመን ማሳወቅ አይጠበቅብንም ነበር” ያሉት አቶ በፍቃዱ፤ ወደፊት ማን ለምን እንደከለከለን ለማጣራት እንሞከራለን ብለዋል። 35ቱ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ሊሰጡት የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ መከልከሉን ተከትሎ “ይህ ዓይነቱ አሠራር የሕግ የበላይነትን የሚፃረር ከመሆኑ ባሻገር የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ለሰላም ሊጫወቱ የሚገባቸውን ድርሻ ይነፍጋል” በማለት ደርጊት እንዲታረም ጠይቀዋል። 35ቱ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በአንድ ስፍራ ተገኝተው ሊያስተላልፉት የነበረውን መልዕክት በጋዜጣዊ መግለጫ አሰራጭተዋል። በዚህም በትግራይ ክልል ተቀስቅሶ ወደ አማራ እና አፋር ክልል የተዛመተው ጦርነት አገሪቷን እና ሕዝቧን ለሰብዓዊ እና ቁሳዊ ከፍተኛ ኪሳራ ዳርጓል ብለዋል ሲቪል ማኅብራቱ። አክለውም ተፋላሚ ወገኖች ለሰብዓዊነት ሲባል የተኩስ አቁም ማድረጋቸው እና ለሰላም ድርድር ፍላጎት ማሳየታቸው ትልቅ ተስፋ እንዲሰንቁ አድርጓቸው እንደነበር አመልክተው፣ ይሁንና ጦርነቱ ዳግም ማገርሸቱ በእጅግ እንዳሳዘናቸው ግልጸዋል። ከሰሜኑ ጦርነት ባሻገር በምዕራብ እና ደቡብ ኦሮሚያ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና በአንዳንድ የደቡብ ክልል አካባቢዎች ግጭቶች እየተካሄዱ ነው ያሉት ማኅበራቱ፤ ግጭቶቹ በሕይወት የመኖር መብትን ጨምሮ መሠረታዊ የዜጎችን መብቶችን ከመንፈጋቸው ባሻገር የአገርን ኅልውናን የሚፈታተኑበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል ብለዋል። ስለሆነም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ያለው ጦርነት እና በሌሎችም አካባቢዎች ያሉ ግጭቶች በአስቸኳይ ቆመው፤ “ሐቀኛ፣ ሰላማዊና የግጭቶቹ ተሳታፊ አካላትን በሙሉ ያካተቱ የእርቅ ንግግሮች እንዲጀመሩ” ጠይቀዋል። በትግራይ እና ጦርነት ባለባቸው አካባቢዎች የተቋረጡ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ አገልግሎቶች በአፋጣኝ እንዲጀመሩ እና ሰብዓዊ ዕርዳታ ያለ እንቅፋት እንዲደርስ የጠየቁ ሲሆን፤ በጦርነት ወቅት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ያደረሱ አካላት ላይ ምርመራ ተደርጎ የተጠያቂነት እርምጃ ይወሰድ ሲሉ ጠይቀዋል። ሁለት ዓመት ሊሞላው የተቃረበው የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ለአምስት ወራት ያህል ጋብ ብሎ ከቆየ በኋላ ከሁለት ሳምንት በፊት ዳግም ተቀስቅሷል። ቀደም ባለው ጦርነት ከፍተኛ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ውድመትን ያስከተለው ግጭት፣ ዳግም ወደ ደም መፋሰስ እንዳያመራ መንግሥትና የትግራይ ኃይሎች በአስቸኳይ ድርድር እንዲጀምሩ ጥሪ እያደረጉ ነው።
ጦርነት እንዲቆም የሰላም ጥሪ ለማቅረብ የተጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ ታገደ በአገሪቱ ባሉ በርካታ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የሰሜን ኢትዮጵያው የእርስ በእርስ ጦርነት እንዲቆም የሰላም ጥሪ ለማስተላለፍ የተጠራ ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳይካሄድ በፀጥታ ኃይሎች መታገዱ ተገለጸ። ጋዜጣዊ መግለጫውን ከጠሩት 35 የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች መካከል አንዱ የሆነው የመብቶች እና የዴሞክራሲ እድገት ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አቶ በፍቃዱ ኃይሉ፤ መግለጫ ሊሰጥበት በነበረው ሆቴል ሲቪል የለበሱ የመንግሥት የፀጥታ ኃይል አባላት ነን ያሉ ግለሰቦች መግለጫውን መስጠት አይቻልም በማለት ከልክለዋል ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። “የትኛው የመንግሥት አካል ክልከላውን እንደፈጸመ አልተነገረንም። እንዲሁ በጥቅሉ ይህን መግለጫ መሰጠት የለባችሁም የሚል መልዕክት ብቻ ነው የተላለፈልን” ብለዋል አቶ በፈቃዱ። ቢቢሲ ስለጉዳዩ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ምላሽ ጠይቆ ኮሚሽኑ ስለክልከላው የሚያውቀው ነገር እንደሌለ የገለጸ ሲሆን፣ የፌደራል ፖሊስ ምላሽን ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ ግን አልተሳካም። የመንግሥት የፀጥታ ሰዎች ነን ያሉት ግለሰቦች ጋዜጣዊ መግለጫውን ለመዘገብ በሆቴሉ ተገኝተው የነበሩ ጋዜጠኞችም መግለጫው እንደማይካሄድ በመግለጽ እንዲያሰናብቱ ለሆቴሉ ሠራተኞች ተናግረዋል ሲሉ አቶ በፍቃዱ ተናግረዋል። “ለማካሄድ አቅደን የነበረው የአደባባይ ስብሰባ ስላልነበረ ቀድመን ማሳወቅ አይጠበቅብንም ነበር” ያሉት አቶ በፍቃዱ፤ ወደፊት ማን ለምን እንደከለከለን ለማጣራት እንሞከራለን ብለዋል። 35ቱ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ሊሰጡት የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ መከልከሉን ተከትሎ “ይህ ዓይነቱ አሠራር የሕግ የበላይነትን የሚፃረር ከመሆኑ ባሻገር የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ለሰላም ሊጫወቱ የሚገባቸውን ድርሻ ይነፍጋል” በማለት ደርጊት እንዲታረም ጠይቀዋል። 35ቱ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በአንድ ስፍራ ተገኝተው ሊያስተላልፉት የነበረውን መልዕክት በጋዜጣዊ መግለጫ አሰራጭተዋል። በዚህም በትግራይ ክልል ተቀስቅሶ ወደ አማራ እና አፋር ክልል የተዛመተው ጦርነት አገሪቷን እና ሕዝቧን ለሰብዓዊ እና ቁሳዊ ከፍተኛ ኪሳራ ዳርጓል ብለዋል ሲቪል ማኅብራቱ። አክለውም ተፋላሚ ወገኖች ለሰብዓዊነት ሲባል የተኩስ አቁም ማድረጋቸው እና ለሰላም ድርድር ፍላጎት ማሳየታቸው ትልቅ ተስፋ እንዲሰንቁ አድርጓቸው እንደነበር አመልክተው፣ ይሁንና ጦርነቱ ዳግም ማገርሸቱ በእጅግ እንዳሳዘናቸው ግልጸዋል። ከሰሜኑ ጦርነት ባሻገር በምዕራብ እና ደቡብ ኦሮሚያ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና በአንዳንድ የደቡብ ክልል አካባቢዎች ግጭቶች እየተካሄዱ ነው ያሉት ማኅበራቱ፤ ግጭቶቹ በሕይወት የመኖር መብትን ጨምሮ መሠረታዊ የዜጎችን መብቶችን ከመንፈጋቸው ባሻገር የአገርን ኅልውናን የሚፈታተኑበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል ብለዋል። ስለሆነም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ያለው ጦርነት እና በሌሎችም አካባቢዎች ያሉ ግጭቶች በአስቸኳይ ቆመው፤ “ሐቀኛ፣ ሰላማዊና የግጭቶቹ ተሳታፊ አካላትን በሙሉ ያካተቱ የእርቅ ንግግሮች እንዲጀመሩ” ጠይቀዋል። በትግራይ እና ጦርነት ባለባቸው አካባቢዎች የተቋረጡ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ አገልግሎቶች በአፋጣኝ እንዲጀመሩ እና ሰብዓዊ ዕርዳታ ያለ እንቅፋት እንዲደርስ የጠየቁ ሲሆን፤ በጦርነት ወቅት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ያደረሱ አካላት ላይ ምርመራ ተደርጎ የተጠያቂነት እርምጃ ይወሰድ ሲሉ ጠይቀዋል። ሁለት ዓመት ሊሞላው የተቃረበው የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ለአምስት ወራት ያህል ጋብ ብሎ ከቆየ በኋላ ከሁለት ሳምንት በፊት ዳግም ተቀስቅሷል። ቀደም ባለው ጦርነት ከፍተኛ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ውድመትን ያስከተለው ግጭት፣ ዳግም ወደ ደም መፋሰስ እንዳያመራ መንግሥትና የትግራይ ኃይሎች በአስቸኳይ ድርድር እንዲጀምሩ ጥሪ እያደረጉ ነው።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cjqvwwxyljjo
0business
ዛፍ መትከል የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ይረዳል?
ዛፍ መትከል የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ይረዳል?
ዛፍ መትከል የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ይረዳል? ዛፍ መትከል የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ይረዳል?
https://www.bbc.com/amharic/news-49165027
2health
ኮቪድ-19: በእስራኤል ለመጀመሪያ ጊዜ ለተከታታይ 10 ወራት ሞት አልተመዘገበም
ፈጣን የክትባት ዘመቻ እያካሄደች ያለችው እስራኤል ለ10 ተከታታይ ወራት በኮቪድ-19 ምክንያት ሞት አለመመዝገቧን አስታወቀች። በአገሪቱ በኮሮናቫይረስ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች አሃዝ 6ሺህ 346 ሆኖ ሳይቀየር ለወራት መዝለቁን የእስራኤል ጤና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። በእስራኤል በጥር ወር ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሶ የነበረው የወረርሽኙ ስርጭት አሁን ላይ ቅናሽ አሳይቷል። የኮቪድ-19 ክትባት በሰፊው መሰጠቱን ተከትሎ የእስራኤል መንግሥት የእንቅስቃሴ ገደቦችን እያላላ ይገኛል። በርካታ ዜጎቻቸውን ከከተቡ አገራት መካከል እስራኤል ተጠቃሽ ናት። እስከ ሐሙስ ብቻ አምስት ሚሊዮን የኮቪድ -19 ክትባቶችን ሰጥታለች። ዘጠኝ ሚሊዮን ገደማ ከሚሆነው የሃገሪቱ ህዝብ ቁጥር ከ53 በመቶ በላይ የሚሆኑት ሁለት ዙር ክትባቶችን እንደወሰዱ የጤና ሚኒስትሩ ገልፀዋል። ሚኒስትሩ ጁሊ ኤደልስቴይን አርብ ዕለት በትዊተር ገጻቸው "ይህ ለጤናው ስርዓት እና ለእስራኤል ዜጎች ትልቅ ስኬት ነው። በጋራ የኮሮናቫይረስን እናጠፋለን" ብለዋል። በእስራኤል ትልቅ በሆነው የሼባ ሕክምና ማዕከል ዳይሬክተር የሆኑት ኤያል ሌሸም እንዳሉት አገሪቱ ወደ "ሄርድ ኢሙኒቲ" ልትደርስ ተቃርባለች ብለዋል። ከፍተኛ መጠን ያለው ሕዝብ በሽታውን የመከላከል አቅም ሲያዳብሩ የቫይረሱ ስርጭት ይገታል፤ ይህም 'ሄርድ ኢሙኒቲ' ይባላል። የዓለም ጤና ድርጅት ባለሙያዎች 'ሄርድ ኢሙኒቲ' ደረጃ ላይ ለመድረስ አገራት ከ65-70 በመቶ የሚሆነው ሕዝባቸውን መከተብ ይኖርባቸዋል ይላሉ። ተጨማሪ ገደቦች መነሳታቸውን ተከትሎ በእስራኤል የቫይረሱ ስርጭት መቀነስ ብቸኛው ምክንያት 'ሄርድ ኢሙኒቲ' ነው ብለዋል ሌሸም። እስራኤል ፋይዘር እና ባዮንቴክ የተሠራውን እና ሁለት ጊዜ የሚሰጠውን ክትባት እየሰጠች ነው። የእስራኤል ጤና ሚኒስቴር በየካቲት ወር እንደገለጸው ሁለቱንም ዙር የፋይዘር ክትባት በወሰዱ ሰዎች ላይ የቫይረሱ ህመም በ95.8 በመቶ ቀንሷል።
ኮቪድ-19: በእስራኤል ለመጀመሪያ ጊዜ ለተከታታይ 10 ወራት ሞት አልተመዘገበም ፈጣን የክትባት ዘመቻ እያካሄደች ያለችው እስራኤል ለ10 ተከታታይ ወራት በኮቪድ-19 ምክንያት ሞት አለመመዝገቧን አስታወቀች። በአገሪቱ በኮሮናቫይረስ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች አሃዝ 6ሺህ 346 ሆኖ ሳይቀየር ለወራት መዝለቁን የእስራኤል ጤና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። በእስራኤል በጥር ወር ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሶ የነበረው የወረርሽኙ ስርጭት አሁን ላይ ቅናሽ አሳይቷል። የኮቪድ-19 ክትባት በሰፊው መሰጠቱን ተከትሎ የእስራኤል መንግሥት የእንቅስቃሴ ገደቦችን እያላላ ይገኛል። በርካታ ዜጎቻቸውን ከከተቡ አገራት መካከል እስራኤል ተጠቃሽ ናት። እስከ ሐሙስ ብቻ አምስት ሚሊዮን የኮቪድ -19 ክትባቶችን ሰጥታለች። ዘጠኝ ሚሊዮን ገደማ ከሚሆነው የሃገሪቱ ህዝብ ቁጥር ከ53 በመቶ በላይ የሚሆኑት ሁለት ዙር ክትባቶችን እንደወሰዱ የጤና ሚኒስትሩ ገልፀዋል። ሚኒስትሩ ጁሊ ኤደልስቴይን አርብ ዕለት በትዊተር ገጻቸው "ይህ ለጤናው ስርዓት እና ለእስራኤል ዜጎች ትልቅ ስኬት ነው። በጋራ የኮሮናቫይረስን እናጠፋለን" ብለዋል። በእስራኤል ትልቅ በሆነው የሼባ ሕክምና ማዕከል ዳይሬክተር የሆኑት ኤያል ሌሸም እንዳሉት አገሪቱ ወደ "ሄርድ ኢሙኒቲ" ልትደርስ ተቃርባለች ብለዋል። ከፍተኛ መጠን ያለው ሕዝብ በሽታውን የመከላከል አቅም ሲያዳብሩ የቫይረሱ ስርጭት ይገታል፤ ይህም 'ሄርድ ኢሙኒቲ' ይባላል። የዓለም ጤና ድርጅት ባለሙያዎች 'ሄርድ ኢሙኒቲ' ደረጃ ላይ ለመድረስ አገራት ከ65-70 በመቶ የሚሆነው ሕዝባቸውን መከተብ ይኖርባቸዋል ይላሉ። ተጨማሪ ገደቦች መነሳታቸውን ተከትሎ በእስራኤል የቫይረሱ ስርጭት መቀነስ ብቸኛው ምክንያት 'ሄርድ ኢሙኒቲ' ነው ብለዋል ሌሸም። እስራኤል ፋይዘር እና ባዮንቴክ የተሠራውን እና ሁለት ጊዜ የሚሰጠውን ክትባት እየሰጠች ነው። የእስራኤል ጤና ሚኒስቴር በየካቲት ወር እንደገለጸው ሁለቱንም ዙር የፋይዘር ክትባት በወሰዱ ሰዎች ላይ የቫይረሱ ህመም በ95.8 በመቶ ቀንሷል።
https://www.bbc.com/amharic/56870712
3politics
ቦሪስ ጆንሰን የካቢኔ አባሎቻቸው ሥራ መልቀቃቸውን ተከትሎ ጫና በረታባቸው
የዩናይትድ ኪንግድም (ዩኬ) ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ከፍተኛ ባለሥልጣኖቻቸው አስተዳደራቸውን ተችተው ሥራ መልቀቃቸውን ተከትሎ ከፍተኛ ጫና ውስጥ ገብተዋል። የገንዘብ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ እና የጤና ሚኒስትር የነበሩት ሳጂድ ጃቪድ በ10 ደቂቃ ልዩነት ሥራቸውን በገዛ ፍቃዳቸው መልቀቃቸውን አስታውቀዋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ተቺዎች የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖለቲካ ሕይወት “አብቅቶለታል” ያሉ ሲሆን ሌበር ፓርቲ ደግሞ የቦሪስ ጆንሰን አስተዳደር በብልሹ አሰራር የተሞላ ነው ብሏል። በብዙ ውጣ ውረዶች ውስጥ እያለፉ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ዛሬ ረቡዕ ሰኔ 29/2014 ዓ.ም. ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት በፓርላማ ይገኛሉ። ከጥቂት ሳምንታት በፊት የመተማመኛ ድምጽ የተሰጠባቸው ቦሪስ ጆንሰን፤ ምንም እንኳ ተቃውሞ ቢበዛባቸውም በሥልጣናቸው እንደሚቆዩ ገልጸዋል። ሥልጣናቸውን በገዛ ፍቃዳቸው በለቀቁት ሁለቱ የካቢኔ አባላት ምትክም ሌሎች ፖለቲከኞችን ሾመዋል። የጤና ሚኒስትር የነበሩት ሳጂድ ጃቪድ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አስተዳደር ብሔራዊ ጥቅምን ባማከል ሁኔታ አገር እየመራ አይደለም ሲሉ፤ የገንዘብ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ ሕዝቡ መንግሥት አገሪቱን በአግባቡ እንዲያገለግል ይጠብቃል ብለዋል። የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች የቦሪስ ጆንሰን ካቢኔ አባላት ሁለቱን ግለሰቦች በመከተል ከሥልጣናቸው እንዲወርዱ እየጠየቁ ይገኛሉ። ወግ አጥባቂው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አንድር ሚሼል የቦሪስ ጆንሰን ጉዳይ “አብቅቶለታል” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ምንም እንኳ የምክር ቤት አባሉ ይህን ይበሉ እንጂ፣ አሁንም በርካታ ተጽእኖ ፈጣሪ የሆኑ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የካቢኔ አባላት ድጋፋቸውን ለቦሪስ ጆንሰን እንደሰጡ ናቸው። ከእነዚህም መካከል ቦሪስ ጆንሰንን በመተካታ የወግ አጥባቂ ፓርቲ መሪ የመሆን ዕድል አላቸው የሚባሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትሯ ሊዝ ትረስ ይገኙበታል። ሚንስትሯ፤ 100 ፐርሰንት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ድጋፌን እስጣለሁ ብለዋል። ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በተጨማሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶሞኒክ ራብ እና መከላከያ ሚኒስትሩ ቤን ዋላስ በሥራቸው እንደሚቀጥሉ ከገለጹት መካከል ይገኙበታል።
ቦሪስ ጆንሰን የካቢኔ አባሎቻቸው ሥራ መልቀቃቸውን ተከትሎ ጫና በረታባቸው የዩናይትድ ኪንግድም (ዩኬ) ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ከፍተኛ ባለሥልጣኖቻቸው አስተዳደራቸውን ተችተው ሥራ መልቀቃቸውን ተከትሎ ከፍተኛ ጫና ውስጥ ገብተዋል። የገንዘብ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ እና የጤና ሚኒስትር የነበሩት ሳጂድ ጃቪድ በ10 ደቂቃ ልዩነት ሥራቸውን በገዛ ፍቃዳቸው መልቀቃቸውን አስታውቀዋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ተቺዎች የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖለቲካ ሕይወት “አብቅቶለታል” ያሉ ሲሆን ሌበር ፓርቲ ደግሞ የቦሪስ ጆንሰን አስተዳደር በብልሹ አሰራር የተሞላ ነው ብሏል። በብዙ ውጣ ውረዶች ውስጥ እያለፉ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ዛሬ ረቡዕ ሰኔ 29/2014 ዓ.ም. ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት በፓርላማ ይገኛሉ። ከጥቂት ሳምንታት በፊት የመተማመኛ ድምጽ የተሰጠባቸው ቦሪስ ጆንሰን፤ ምንም እንኳ ተቃውሞ ቢበዛባቸውም በሥልጣናቸው እንደሚቆዩ ገልጸዋል። ሥልጣናቸውን በገዛ ፍቃዳቸው በለቀቁት ሁለቱ የካቢኔ አባላት ምትክም ሌሎች ፖለቲከኞችን ሾመዋል። የጤና ሚኒስትር የነበሩት ሳጂድ ጃቪድ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አስተዳደር ብሔራዊ ጥቅምን ባማከል ሁኔታ አገር እየመራ አይደለም ሲሉ፤ የገንዘብ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ ሕዝቡ መንግሥት አገሪቱን በአግባቡ እንዲያገለግል ይጠብቃል ብለዋል። የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች የቦሪስ ጆንሰን ካቢኔ አባላት ሁለቱን ግለሰቦች በመከተል ከሥልጣናቸው እንዲወርዱ እየጠየቁ ይገኛሉ። ወግ አጥባቂው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አንድር ሚሼል የቦሪስ ጆንሰን ጉዳይ “አብቅቶለታል” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ምንም እንኳ የምክር ቤት አባሉ ይህን ይበሉ እንጂ፣ አሁንም በርካታ ተጽእኖ ፈጣሪ የሆኑ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የካቢኔ አባላት ድጋፋቸውን ለቦሪስ ጆንሰን እንደሰጡ ናቸው። ከእነዚህም መካከል ቦሪስ ጆንሰንን በመተካታ የወግ አጥባቂ ፓርቲ መሪ የመሆን ዕድል አላቸው የሚባሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትሯ ሊዝ ትረስ ይገኙበታል። ሚንስትሯ፤ 100 ፐርሰንት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ድጋፌን እስጣለሁ ብለዋል። ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በተጨማሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶሞኒክ ራብ እና መከላከያ ሚኒስትሩ ቤን ዋላስ በሥራቸው እንደሚቀጥሉ ከገለጹት መካከል ይገኙበታል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c6pw4q7p371o
5sports
ክርስቲያኖ ሮናልዶ በከፍተኛ ደረጃ 800 ግቦችን ያስቆጠረ ብቸኛው ተጫዋች ሆነ
የፖርቹጋል እና የማንስችተር ዩናይትድ አጥቂው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በከፍተኛ ደረጃ በታሪክ 800 ጎሎችን ያስቆጠረ ተጫዋች ሆነ። ክርስቲያኖ ሮናልዶ ትላንት ማንቸስተር ዩናይትድ አርሰናልን 3 ለ 2 ባሸነፈበት ጨዋታ ሁለቱን ግቦች በማግባቱ 800 ግቦች ያስቆጠረ በታሪክ የመጀመሪያው ተጫዋች ሆኗል። ሮናልዶ ለአገሩ እና ለተጫወተባቸው ክለቦች 1097 ጊዜ ተሰልፎ 801 ግቦች ያስቆጠረ ተጫዎች መሆን ችሏል። ሮናልዶ ለዩናይትድን በሁለት የተጫዋችነት ዘመናት 130 ግቦችን ሲያስቆጥር ለስፖርቲንግ ሊዝበን 5፣ ለሪያል ማድሪድ 450፣ ለጁቬንቱስ 101 እና ለፖርቹጋል 115 ግቦችን በስሙ አስመዝግቧል። ይህም ተጫዎቹን በወንዶች አለም አቀፍ እግር ኳስ፣ በሻምፒዮንስ ሊግ እና በሪያል ማድሪድ የምንግዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ እንዲሆን አድርጎታል። የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የምንግዜም ከፍተኛ ግብ አግቢ አላን ለሮናልዶ ያለውን አድናቆት ለሺረር ለአማዞን ፕራይም ተናግሯል። "ይህ የእርሱ ቁርጠኝነት ነው። ከፍተኛ ደረጃ መድረስ በጣም ከባድ ነው። እንደገና ከፍ ብሎ መቆየትም አለ። በጠዋት ተነስተህ እንደገና መጎዝ አለብህ። ዓለም ሁሉ በየሳምንቱ ስትጫወት ማየት ይፈልግል። ይህን አስደናቂ ነገር ነው ያደረገው።" የሮናልዶ ዩናይትድ እና ፖርቱጋል የቡድን አጋር ብሩኖ ፈርናንዴዝ ደግሞ "አስደናቂ ነው። ሁላችንም ከዓመት ዓመት ከጨዋታ ጫዋታ እያሻሻለ እንደሆነ እናውቃለን። ምርጥ ሆኖ መቀጠል ይፈልጋል፤ ያደረገውም ያንን ነው" ብሏል። የብራዚል ስመ ገናና ተጫዋቾች ፔሌ እና ሮማሪዮ በየግላቸው ከ1ሺህ በላይ ጎሎችን አስቆጥረዋል ይላል። ይሁን እንጂ ይፋዊ ባልሆኑ እና በዋዳጅነት ጨዋታዎች ላይ ያስቆጠሯቸው ጎሎች ቢቀናነሱ ያስቆጠሩት የጎል መጠን ወደ 700ዎች ይወርዳል። ሊዮኔል ሜሲ 756 ጎሎችን ለአርጀንቲና፣ ባርሴሎች እና ፓሪስ አስቆጥሯል።
ክርስቲያኖ ሮናልዶ በከፍተኛ ደረጃ 800 ግቦችን ያስቆጠረ ብቸኛው ተጫዋች ሆነ የፖርቹጋል እና የማንስችተር ዩናይትድ አጥቂው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በከፍተኛ ደረጃ በታሪክ 800 ጎሎችን ያስቆጠረ ተጫዋች ሆነ። ክርስቲያኖ ሮናልዶ ትላንት ማንቸስተር ዩናይትድ አርሰናልን 3 ለ 2 ባሸነፈበት ጨዋታ ሁለቱን ግቦች በማግባቱ 800 ግቦች ያስቆጠረ በታሪክ የመጀመሪያው ተጫዋች ሆኗል። ሮናልዶ ለአገሩ እና ለተጫወተባቸው ክለቦች 1097 ጊዜ ተሰልፎ 801 ግቦች ያስቆጠረ ተጫዎች መሆን ችሏል። ሮናልዶ ለዩናይትድን በሁለት የተጫዋችነት ዘመናት 130 ግቦችን ሲያስቆጥር ለስፖርቲንግ ሊዝበን 5፣ ለሪያል ማድሪድ 450፣ ለጁቬንቱስ 101 እና ለፖርቹጋል 115 ግቦችን በስሙ አስመዝግቧል። ይህም ተጫዎቹን በወንዶች አለም አቀፍ እግር ኳስ፣ በሻምፒዮንስ ሊግ እና በሪያል ማድሪድ የምንግዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ እንዲሆን አድርጎታል። የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የምንግዜም ከፍተኛ ግብ አግቢ አላን ለሮናልዶ ያለውን አድናቆት ለሺረር ለአማዞን ፕራይም ተናግሯል። "ይህ የእርሱ ቁርጠኝነት ነው። ከፍተኛ ደረጃ መድረስ በጣም ከባድ ነው። እንደገና ከፍ ብሎ መቆየትም አለ። በጠዋት ተነስተህ እንደገና መጎዝ አለብህ። ዓለም ሁሉ በየሳምንቱ ስትጫወት ማየት ይፈልግል። ይህን አስደናቂ ነገር ነው ያደረገው።" የሮናልዶ ዩናይትድ እና ፖርቱጋል የቡድን አጋር ብሩኖ ፈርናንዴዝ ደግሞ "አስደናቂ ነው። ሁላችንም ከዓመት ዓመት ከጨዋታ ጫዋታ እያሻሻለ እንደሆነ እናውቃለን። ምርጥ ሆኖ መቀጠል ይፈልጋል፤ ያደረገውም ያንን ነው" ብሏል። የብራዚል ስመ ገናና ተጫዋቾች ፔሌ እና ሮማሪዮ በየግላቸው ከ1ሺህ በላይ ጎሎችን አስቆጥረዋል ይላል። ይሁን እንጂ ይፋዊ ባልሆኑ እና በዋዳጅነት ጨዋታዎች ላይ ያስቆጠሯቸው ጎሎች ቢቀናነሱ ያስቆጠሩት የጎል መጠን ወደ 700ዎች ይወርዳል። ሊዮኔል ሜሲ 756 ጎሎችን ለአርጀንቲና፣ ባርሴሎች እና ፓሪስ አስቆጥሯል።
https://www.bbc.com/amharic/59515621
0business
ኬንያ በአንድ ቢሊዮን ዶላር ብድር የሰራችውን የባቡር መንገድ ልትመርቅ ነው
ኬንያ የባቡር መንገዷ ግንባታ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን የኬንያ ባቡር መንገድ በፌስቡክ ገፁ አስታውቋል። አዲሱ የኬንያ የባቡር መስመር ከመዲናዋ ናይሮቢ ወደ ናይቫሻ ሲሆን በዛሬው ዕለትም ለአገልግሎት ክፍት ይሆናል። መስመሩ ለጊዜው አገልግሎት የሚሰጠው ለሰዎች ሲሆን የጭነት ማጓጓዝ አገልግሎት ደረቁ ወደብ እስኪገነባ ድረስ ይጠበቃል ተብሏል። •የሆሊውዱ ሃኪም ገብረወልድን ያውቁታል? •"ሰልፍ የዜጎች መሰረታዊ መብት ነው" መስፍን ነጋሽ ግንባታውም ረዘም ያለ ጊዜ እንደሚወስድም ተገምቷል። ለዚህም በአካባቢው የሚኖሩ የማሳይ ማህበረሰብ ግንባታውን በመቃወም ጉዳዩን ወደ ፍርድ በመውሰዳቸው እንደሆነ ተገልጿል። በቻይና ኮሚዩኒኬሽንና ግንባታ ኩባንያ የተገነባው ይህ መስመር 120 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ ያለው ሲሆን 1.4 ቢሊዮን ዶላር ፈጅቷል። የተጓዦች አገልግሎት ከአስራ ሁለቱ ጣቢያዎች በአራቱ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀመር ዘ ቢስነስ ደይሊ ኒውስፔፐር የኬንያ የባቡር አገልግሎት ኃላፊ የሆኑት ፊሊፕ ማይንጋን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። የመጀመሪያው የባቡር መንገድ ከመዲናዋ ናይሮቢ ወደ ሞምባሳ ከሁለት አመት በፊት በተመረቀበት ወቅት ከፍተኛ ደስታና ፈንጠዝያ የነበረ ሲሆን ይህ መስመር ግን እንደ መጀመሪያው አልሆነም ተብሏል። በወቅቱም ኬንያ ለምርጫ ስትዘጋጅ ነበር። •በኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ የሞቱ ሰዎች አጽም ለቤተሰቦቻቸው እየተሰጠ ነው • በተሻሻለው የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ህግ ረቂቅ ጥፋተኛና አቃቤ ህግ ይደራደራሉ የአዲሱ የባቡር መንገድ ዋጋ ከአለም አቀፉ ስታንዳርድ አንፃር ጋር ሲታይ ሶስት እጥፍ እንዲሁም መጀመሪያ ያወጣል ተብሎ ከተገመተው አራት እጥፍ ነው ተብሏል። መንግሥት ዋጋው እንዲህ ለምን ናረ ለሚለው የሰጠው ምክንያት የመልክአ ምድሩ አስቸጋሪነት ድልድዮችንና ቱቦችን በመገንባት ላልታሰበ ወጪ እንደተዳረጉ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ለመሬት ካሳ ተከፍሏል ተብሏል። ከዚህ ወጪ ውስጥ 80% የተገኘው ከቻይና በተገኘ ብድር ነው። የባቡር መስመሩ የመጀመሪያ እቅድ ከሞምባሳ- ኪሱሙን በመሻገር ኡጋንዳ ይደርሳል ተብሎ ነበር። አገሪቷ ይህንን የባቡር መስመር ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ 3.3 ቢሊዮን ዶላር ብድር ያስፈልጋታል ተብሏል።
ኬንያ በአንድ ቢሊዮን ዶላር ብድር የሰራችውን የባቡር መንገድ ልትመርቅ ነው ኬንያ የባቡር መንገዷ ግንባታ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን የኬንያ ባቡር መንገድ በፌስቡክ ገፁ አስታውቋል። አዲሱ የኬንያ የባቡር መስመር ከመዲናዋ ናይሮቢ ወደ ናይቫሻ ሲሆን በዛሬው ዕለትም ለአገልግሎት ክፍት ይሆናል። መስመሩ ለጊዜው አገልግሎት የሚሰጠው ለሰዎች ሲሆን የጭነት ማጓጓዝ አገልግሎት ደረቁ ወደብ እስኪገነባ ድረስ ይጠበቃል ተብሏል። •የሆሊውዱ ሃኪም ገብረወልድን ያውቁታል? •"ሰልፍ የዜጎች መሰረታዊ መብት ነው" መስፍን ነጋሽ ግንባታውም ረዘም ያለ ጊዜ እንደሚወስድም ተገምቷል። ለዚህም በአካባቢው የሚኖሩ የማሳይ ማህበረሰብ ግንባታውን በመቃወም ጉዳዩን ወደ ፍርድ በመውሰዳቸው እንደሆነ ተገልጿል። በቻይና ኮሚዩኒኬሽንና ግንባታ ኩባንያ የተገነባው ይህ መስመር 120 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ ያለው ሲሆን 1.4 ቢሊዮን ዶላር ፈጅቷል። የተጓዦች አገልግሎት ከአስራ ሁለቱ ጣቢያዎች በአራቱ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀመር ዘ ቢስነስ ደይሊ ኒውስፔፐር የኬንያ የባቡር አገልግሎት ኃላፊ የሆኑት ፊሊፕ ማይንጋን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። የመጀመሪያው የባቡር መንገድ ከመዲናዋ ናይሮቢ ወደ ሞምባሳ ከሁለት አመት በፊት በተመረቀበት ወቅት ከፍተኛ ደስታና ፈንጠዝያ የነበረ ሲሆን ይህ መስመር ግን እንደ መጀመሪያው አልሆነም ተብሏል። በወቅቱም ኬንያ ለምርጫ ስትዘጋጅ ነበር። •በኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ የሞቱ ሰዎች አጽም ለቤተሰቦቻቸው እየተሰጠ ነው • በተሻሻለው የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ህግ ረቂቅ ጥፋተኛና አቃቤ ህግ ይደራደራሉ የአዲሱ የባቡር መንገድ ዋጋ ከአለም አቀፉ ስታንዳርድ አንፃር ጋር ሲታይ ሶስት እጥፍ እንዲሁም መጀመሪያ ያወጣል ተብሎ ከተገመተው አራት እጥፍ ነው ተብሏል። መንግሥት ዋጋው እንዲህ ለምን ናረ ለሚለው የሰጠው ምክንያት የመልክአ ምድሩ አስቸጋሪነት ድልድዮችንና ቱቦችን በመገንባት ላልታሰበ ወጪ እንደተዳረጉ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ለመሬት ካሳ ተከፍሏል ተብሏል። ከዚህ ወጪ ውስጥ 80% የተገኘው ከቻይና በተገኘ ብድር ነው። የባቡር መስመሩ የመጀመሪያ እቅድ ከሞምባሳ- ኪሱሙን በመሻገር ኡጋንዳ ይደርሳል ተብሎ ነበር። አገሪቷ ይህንን የባቡር መስመር ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ 3.3 ቢሊዮን ዶላር ብድር ያስፈልጋታል ተብሏል።
https://www.bbc.com/amharic/news-50065673
2health
ሐሰተኛ መድኃኒት በግብፅ ሕጻናትን ገደለ
በግብፅ ሐሰተኛ አንቲባዮቲክስ የተሰጣቸው በርካታ ልጆች መሞታቸው ተገለጸ። አንድ የሁለት ዓመት ሕጻን ከፍተኛ ሙቀት ገጥሞት ወደ ሆስፒታል ከተወሰደ በኋላ ሐኪሞች መርፌ ወግተውት ሕይወቱ አልፏል። ልጁ የተወጋው መድኃኒት ሐሰተኛ ሆኖ ተገኝቷል። የግብጽ መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት፣ ባለፈው ወር ብቻ 160 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ ሐሰተኛ መድኃኒቶች ተይዘዋል። የሐሰተኛ መድኃኒት ስርጭት በተለያዩ አገራት እየተስፋፋ ይገኛል። የአሜሪካው ‘ጆርናል ኦፍ ትሮፒካል ሜድስን ኤንድ ሀይጅን’ በቅርቡ ባወጣው ሪፖርት መሠረት በሐሰተኛ መድኃኒቶች በዓመት 300 ሺል ሕጻናት ይሞታሉ። የግብፅ መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት ከሆነ ሴፍትሪአግዞን የተባለው አንቲባዮቲክስ ጥቅም ላይ እንዳይውል እያሳሰቡ ነው። ካፍር ዚያት በተባለው ከተማ ፈቃድ የሌላቸው ፋብሪካዎች ላይ ፍተሻ ተደርጓል። ሐሰተኛ መድኃኒት ከሚበዛባቸው የመድኃኒት ዓይነቶች መካከል አንቲባዮቲክስ ይጠቀሳል። ጥቅምት ላይ በጋምቢያ ወደ 70 የሚጠጉ ሕጻናት የሕንድ ምርት የሆነ የሳል መድኃኒት ወስደው ሕይወታቸው ማለፉ ይታወሳል። ይህንን ተከትሎ፣ የሕንድ የጤና ባለሥልጣናት የሕጻናቱ ሕይወት እንዲያልፍ ምክንያት ሆኗል የተባለውን የሳል መድኃኒት የሚያመርተው ተቋም ምርቱን እንዲያቆም ማገዷ ይታወሳል። ከዚያ በኋላ ግን መድኃኒቶቹ ምንም ብክለት እንደሌላቸው ሕንድ ገልጻለች። የዓለም ጤና ድርጅት ግን አራት መድኃኒቶች ላይ ተቀባይነት የሌለው የተበከለ ኬሚካል እንደተገኘ አሳውቋል።
ሐሰተኛ መድኃኒት በግብፅ ሕጻናትን ገደለ በግብፅ ሐሰተኛ አንቲባዮቲክስ የተሰጣቸው በርካታ ልጆች መሞታቸው ተገለጸ። አንድ የሁለት ዓመት ሕጻን ከፍተኛ ሙቀት ገጥሞት ወደ ሆስፒታል ከተወሰደ በኋላ ሐኪሞች መርፌ ወግተውት ሕይወቱ አልፏል። ልጁ የተወጋው መድኃኒት ሐሰተኛ ሆኖ ተገኝቷል። የግብጽ መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት፣ ባለፈው ወር ብቻ 160 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ ሐሰተኛ መድኃኒቶች ተይዘዋል። የሐሰተኛ መድኃኒት ስርጭት በተለያዩ አገራት እየተስፋፋ ይገኛል። የአሜሪካው ‘ጆርናል ኦፍ ትሮፒካል ሜድስን ኤንድ ሀይጅን’ በቅርቡ ባወጣው ሪፖርት መሠረት በሐሰተኛ መድኃኒቶች በዓመት 300 ሺል ሕጻናት ይሞታሉ። የግብፅ መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት ከሆነ ሴፍትሪአግዞን የተባለው አንቲባዮቲክስ ጥቅም ላይ እንዳይውል እያሳሰቡ ነው። ካፍር ዚያት በተባለው ከተማ ፈቃድ የሌላቸው ፋብሪካዎች ላይ ፍተሻ ተደርጓል። ሐሰተኛ መድኃኒት ከሚበዛባቸው የመድኃኒት ዓይነቶች መካከል አንቲባዮቲክስ ይጠቀሳል። ጥቅምት ላይ በጋምቢያ ወደ 70 የሚጠጉ ሕጻናት የሕንድ ምርት የሆነ የሳል መድኃኒት ወስደው ሕይወታቸው ማለፉ ይታወሳል። ይህንን ተከትሎ፣ የሕንድ የጤና ባለሥልጣናት የሕጻናቱ ሕይወት እንዲያልፍ ምክንያት ሆኗል የተባለውን የሳል መድኃኒት የሚያመርተው ተቋም ምርቱን እንዲያቆም ማገዷ ይታወሳል። ከዚያ በኋላ ግን መድኃኒቶቹ ምንም ብክለት እንደሌላቸው ሕንድ ገልጻለች። የዓለም ጤና ድርጅት ግን አራት መድኃኒቶች ላይ ተቀባይነት የሌለው የተበከለ ኬሚካል እንደተገኘ አሳውቋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/czdy794z1nvo
3politics
የአማራ እና አፋር ክልላዊ መንግሥታት ሕዝቡ የህወሓት አማፂያንን 'እንዲመክት' ጥሪ አቀረቡ
የአፋር ክልላዊ መንግሥት ነዋሪዎች ታጥቀው የትግራይ አማፂያንን እንዲመክቱ ጥሪ አቅርቧል ሲል ኤኤፍፒ የዜና ወኪል ዘገበ። "እያንዳንዱ አፋር መሬቱን በተቻለው መንገድ ሊጠብቅ ይገባል። በጥይትም ይሁን፣ በዱላ አሊያም በድንጋይ" ሲሉ የክልሉ ፕሬዝደንት አዎል አርባ ተናግረዋል ሲል ኤኤፍፒ አስነብቧል። "የትኛውም መሣሪያ ዝቅ እንድንል ሊያደርገን አይችልም። ይህንን ጦርነት በጠንካራ ኃይላችን እንረታዋለን።" የአማራ ክልል ብሔራዊ መንግሥት የህወሓት አማጺያንን ለመውጋት የክተት አዋጅ ጥሪ ማስተላለፉ ይታወሳል። የህወሓት አማፂያን ትግራይ እና አፋር ድንበር አቅራቢያ ጥቃት ስለመክፈታቸው በስፋት ተዘግቧል። የአፋር ክልል አደጋ መከላከል ኃላፊ ባለፈው ሳምንት ከ70 ሺህ በላይ ሰዎች በግጭቱ ተፈናቅለዋል ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። ኤኤፍፒ ደግሞ አንድ የመንግሥት ባለሥልጣን ከ20 በላይ ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል ብለዋል ሲል ዘግቧል። የአማፂያኑ ቃል አቀባይ ግታቸው ረዳ በአፋር ክልል ያለውን ኦፕሬሽን ለመንግሥት ወግነው አፋር ክልል ውስጥ በሚዋጉ የኦሮሚያ ልዩ ኃይሎች ላይ የተሰነዘረ "በጣም የተገደበ" ጥቃት ነው ብለው ነበር። ነገር ግን የአፋር ክልል ፕሬዝደንት ይህ ሃሰት ነው ሲሉ አስተባብለዋል። "አንዳንድ ሰዎች አማፂያኑ የወረሩን የኦሮሚያ ልዩ ኃይልን ስላስጠለልን ነው ብለው ያስባሉ። ነገር ግን ይህ ከእውነት የራቀ ነው። እነሱ ከኢትዮጵያ በኃይል ሊገነጥሉን ይፈልጋሉ" ብለዋል። በተያያዘ ዜና የአማራ ክልል ፕሬዝደንት ሕዝቡ መሣሪያውን በመታጠቅ የሕወሓት ኃይሎችን "እንዲመክት" ጥሪ አቅርበዋል። ፕሬዝደንቱ በክልሉ ቴሌቪዥን ቀርበው ባወጁት ክተት "በመንግሥትም ሆነ በግላቸው መሣሪያ የታጠቁ ሰዎች ዘመቻውን እንዲቀላቀሉ" ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ፕሬዝደንት አገኘሁ ተሻገር "ከተሠለፈብን ጠላት አኳያ ብዙ ኃይል የምናሰልፍበትና ሎጅስቲክስ የሚያስፈልግ ነው" ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል። በተያያዘ ዜና በ6ኛው አገራዊ ምርጫ የፖርላማ መቀመጫ ካሸነፉ ጥቂት ተፎካካሪ ፓርቲዎች መካከል አንዱ የሆነው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ በአማራ ክልል መንግሥት የታወጀውን የክተት አዋጅ ጥሪን ተቀብያለሁ ብሏል። ፓርቲው ". . . በጠላትነት የተፈረጀውን ህዝባችን ለመታደግ የአወጀውን የክተት ጥሪ በሙሉ ልብ የምንቀበለውና ለተግባራዊነቱም የበኩላችን ከፍተኛ ጥረት የምናደርግ መሆኑን እየገለፅን የክልሉ መንግስትም አልፎ አልፎ የሚታዩ አስተዳደራዊ ችግሮችን በመፍታት የመሪነት ሚናውን በተገቢው መንገድ እንዲወጣ እንጠይቃለን" ብሏል ትናንት ባወጣው መግለጫ ላይ። የድጋፍ ሰልፎች ትናንት እና ከትናንት በስቲያ በበርካታ የአገሪቱ ከተሞች ሰልፎች ተካሂደዋል። የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በጎንደር ዙሪያ ወረዳ፣ በዳንሻ ከተማ፣ በጎንደር እና እንጅባራ ለአገር መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፉ እና ህወሓትን የሚቃወሙ ሰልፎች መካሄዳቸውን ዘግቧል። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ለአገር መከላከያ ሠራዊት አጋርነትን ለማሳየት ያለመ ህዝባዊ ሰልፍ በአፋር ክልል ሰመራ-ሎግያ፣ አይሳኢታና አበአላ ከተሞች መካሄዱን ዘግቧል። በሠመራ-ሎግያ ከተማ በተካሄው ሰልፍ ላይ በከተማው የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ተሳትፈውበታል ሲል ኢዜአ ጨምሮ ዘግቧል። ከቀናት በፊት በተመሳሳይ በአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ የተካፈለበት የአገር መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፍ እና ህወሓትን የሚቃወም ሰልፍ መካሄዱ ይታወሳል። ስምንት ወራት የዘለቀው በሕወሓትና በመንግሥት መካከል እየተደረገ ያለው ጦርነት ከትግራይ አልፎ ወደ ሌሎች ክልሎች እየተስፋፋ ነው። የተባበሩት መንግሥታት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በዚህ ግጭት ሞተዋል፤ በመቶ ሺዎች የሚሆኑ ደግሞ ለረሃብ አደጋ ተጋልጠዋል ይላል። የፌደራሉ መንግሥት የተናጠል የተኩስ አቁም አዋጅ አውጆ ከትግራይ አካባቢዎች ለቅቆ መውጣቱን ተከትሎ የህወሓት አማጺያን የክልሉን በርካታ ስፍራዎች መልሶ መያዝ ችሏል።
የአማራ እና አፋር ክልላዊ መንግሥታት ሕዝቡ የህወሓት አማፂያንን 'እንዲመክት' ጥሪ አቀረቡ የአፋር ክልላዊ መንግሥት ነዋሪዎች ታጥቀው የትግራይ አማፂያንን እንዲመክቱ ጥሪ አቅርቧል ሲል ኤኤፍፒ የዜና ወኪል ዘገበ። "እያንዳንዱ አፋር መሬቱን በተቻለው መንገድ ሊጠብቅ ይገባል። በጥይትም ይሁን፣ በዱላ አሊያም በድንጋይ" ሲሉ የክልሉ ፕሬዝደንት አዎል አርባ ተናግረዋል ሲል ኤኤፍፒ አስነብቧል። "የትኛውም መሣሪያ ዝቅ እንድንል ሊያደርገን አይችልም። ይህንን ጦርነት በጠንካራ ኃይላችን እንረታዋለን።" የአማራ ክልል ብሔራዊ መንግሥት የህወሓት አማጺያንን ለመውጋት የክተት አዋጅ ጥሪ ማስተላለፉ ይታወሳል። የህወሓት አማፂያን ትግራይ እና አፋር ድንበር አቅራቢያ ጥቃት ስለመክፈታቸው በስፋት ተዘግቧል። የአፋር ክልል አደጋ መከላከል ኃላፊ ባለፈው ሳምንት ከ70 ሺህ በላይ ሰዎች በግጭቱ ተፈናቅለዋል ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። ኤኤፍፒ ደግሞ አንድ የመንግሥት ባለሥልጣን ከ20 በላይ ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል ብለዋል ሲል ዘግቧል። የአማፂያኑ ቃል አቀባይ ግታቸው ረዳ በአፋር ክልል ያለውን ኦፕሬሽን ለመንግሥት ወግነው አፋር ክልል ውስጥ በሚዋጉ የኦሮሚያ ልዩ ኃይሎች ላይ የተሰነዘረ "በጣም የተገደበ" ጥቃት ነው ብለው ነበር። ነገር ግን የአፋር ክልል ፕሬዝደንት ይህ ሃሰት ነው ሲሉ አስተባብለዋል። "አንዳንድ ሰዎች አማፂያኑ የወረሩን የኦሮሚያ ልዩ ኃይልን ስላስጠለልን ነው ብለው ያስባሉ። ነገር ግን ይህ ከእውነት የራቀ ነው። እነሱ ከኢትዮጵያ በኃይል ሊገነጥሉን ይፈልጋሉ" ብለዋል። በተያያዘ ዜና የአማራ ክልል ፕሬዝደንት ሕዝቡ መሣሪያውን በመታጠቅ የሕወሓት ኃይሎችን "እንዲመክት" ጥሪ አቅርበዋል። ፕሬዝደንቱ በክልሉ ቴሌቪዥን ቀርበው ባወጁት ክተት "በመንግሥትም ሆነ በግላቸው መሣሪያ የታጠቁ ሰዎች ዘመቻውን እንዲቀላቀሉ" ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ፕሬዝደንት አገኘሁ ተሻገር "ከተሠለፈብን ጠላት አኳያ ብዙ ኃይል የምናሰልፍበትና ሎጅስቲክስ የሚያስፈልግ ነው" ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል። በተያያዘ ዜና በ6ኛው አገራዊ ምርጫ የፖርላማ መቀመጫ ካሸነፉ ጥቂት ተፎካካሪ ፓርቲዎች መካከል አንዱ የሆነው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ በአማራ ክልል መንግሥት የታወጀውን የክተት አዋጅ ጥሪን ተቀብያለሁ ብሏል። ፓርቲው ". . . በጠላትነት የተፈረጀውን ህዝባችን ለመታደግ የአወጀውን የክተት ጥሪ በሙሉ ልብ የምንቀበለውና ለተግባራዊነቱም የበኩላችን ከፍተኛ ጥረት የምናደርግ መሆኑን እየገለፅን የክልሉ መንግስትም አልፎ አልፎ የሚታዩ አስተዳደራዊ ችግሮችን በመፍታት የመሪነት ሚናውን በተገቢው መንገድ እንዲወጣ እንጠይቃለን" ብሏል ትናንት ባወጣው መግለጫ ላይ። የድጋፍ ሰልፎች ትናንት እና ከትናንት በስቲያ በበርካታ የአገሪቱ ከተሞች ሰልፎች ተካሂደዋል። የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በጎንደር ዙሪያ ወረዳ፣ በዳንሻ ከተማ፣ በጎንደር እና እንጅባራ ለአገር መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፉ እና ህወሓትን የሚቃወሙ ሰልፎች መካሄዳቸውን ዘግቧል። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ለአገር መከላከያ ሠራዊት አጋርነትን ለማሳየት ያለመ ህዝባዊ ሰልፍ በአፋር ክልል ሰመራ-ሎግያ፣ አይሳኢታና አበአላ ከተሞች መካሄዱን ዘግቧል። በሠመራ-ሎግያ ከተማ በተካሄው ሰልፍ ላይ በከተማው የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ተሳትፈውበታል ሲል ኢዜአ ጨምሮ ዘግቧል። ከቀናት በፊት በተመሳሳይ በአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ የተካፈለበት የአገር መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፍ እና ህወሓትን የሚቃወም ሰልፍ መካሄዱ ይታወሳል። ስምንት ወራት የዘለቀው በሕወሓትና በመንግሥት መካከል እየተደረገ ያለው ጦርነት ከትግራይ አልፎ ወደ ሌሎች ክልሎች እየተስፋፋ ነው። የተባበሩት መንግሥታት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በዚህ ግጭት ሞተዋል፤ በመቶ ሺዎች የሚሆኑ ደግሞ ለረሃብ አደጋ ተጋልጠዋል ይላል። የፌደራሉ መንግሥት የተናጠል የተኩስ አቁም አዋጅ አውጆ ከትግራይ አካባቢዎች ለቅቆ መውጣቱን ተከትሎ የህወሓት አማጺያን የክልሉን በርካታ ስፍራዎች መልሶ መያዝ ችሏል።
https://www.bbc.com/amharic/news-57966979
3politics
ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የመረጧቸው ተተኪ ባለማሸነፋቸው እንዳዘኑ ገለጹ
የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ሥልጣናቸውን ለቀጣዩ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በደስታ እንደሚያስረክቡ ቢናገሩም የመረጧቸው ተተኪ ራይላ ኦዲንጋ አገሪቱን ለመምራት የተሻሉ ነበሩ ብለዋል። “ሥልጣኔን ፈገግ ብዬ አስረክባለሁ ምክንያቱም ሕገ መንግሥታዊ ግዴታዬ ነው፤ ነገር ግን መሪዬ ባባ ናቸው።" ሲሉ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ራይላ ኦዲንጋን በቅፅል ስማቸው በመጥራት አሞካሽተዋቸዋል። አክለውም “ አገሪቱን ወደ አንድነት ለማምጣት የነበረውን ዕድል ነው የተከላከላችሁት እንጂ ራይላን አይደለም የከለከላችሁት” በማለት በምርጫው ውጤት የተሰማቸውን ኃዘን ገልጸዋል። ራይላ ኦዲንጋ ምርጫው ተጭበርብሯል በማለት ያቀረቡት ተቃውሞ በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውድቅ ተደርጓል። በመሆኑም ቀጣዩ ፕሬዚዳንት መሆናቸውን ያረጋገጡት ዊሊያም ሩቶ በመጪው ማክሰኞ ቃለ መሃላ ይፈጽማሉ። ፕሬዝዳንት ኡሁሩ እስካሁን ለምክትላቸው የእንኳን ደስ ያለዎት መልዕክት ባያስተላልፉም የሥልጣን ሽግግሩን በተመለከተ በትናንትናው ዕለት ውይይት አድርገዋል። ሁለቱ መሪዎች ሐሙስ ፓርላማው ከመከፈቱ  በፊት ከየፓርቲዎቻቸው ጋር ተገናኝተዋል። ፕሬዚዳንት ኡሁሩ፣ ራይላ ኦዲንጋን እጩ ፕሬዚዳንት አድርጎ የነበረው የአዚሚዮ ጥምረት ሊቀመንበር ናቸው። ሁለቱም ወገኖች የሁለቱን ምክር ቤቶች አፈ ጉባኤነት እንዴት ማሸነፍ እንደሚችሉ ስትራቴጂ እየነደፉ ነው። ሁለቱም ፓርቲዎች በፓርላማ ውስጥ አብላጫ ድምፅ አላገኙም። ተመራጩ ፕሬዚደንት ዊሊያም ሩቶ ወሳኝ የሆኑ ፖሊሲዎችን ለማሳለፍ፣ የካቢኔ እጩዎችን፣ ዋና ጸሐፊዎችን፣ አምባሳደሮችን እና ከፍተኛ ኮሚሽነሮችን ለመሾም አብላጫ ድምጽ ማግኘት ይጠበቅባቸዋል።
ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የመረጧቸው ተተኪ ባለማሸነፋቸው እንዳዘኑ ገለጹ የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ሥልጣናቸውን ለቀጣዩ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በደስታ እንደሚያስረክቡ ቢናገሩም የመረጧቸው ተተኪ ራይላ ኦዲንጋ አገሪቱን ለመምራት የተሻሉ ነበሩ ብለዋል። “ሥልጣኔን ፈገግ ብዬ አስረክባለሁ ምክንያቱም ሕገ መንግሥታዊ ግዴታዬ ነው፤ ነገር ግን መሪዬ ባባ ናቸው።" ሲሉ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ራይላ ኦዲንጋን በቅፅል ስማቸው በመጥራት አሞካሽተዋቸዋል። አክለውም “ አገሪቱን ወደ አንድነት ለማምጣት የነበረውን ዕድል ነው የተከላከላችሁት እንጂ ራይላን አይደለም የከለከላችሁት” በማለት በምርጫው ውጤት የተሰማቸውን ኃዘን ገልጸዋል። ራይላ ኦዲንጋ ምርጫው ተጭበርብሯል በማለት ያቀረቡት ተቃውሞ በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውድቅ ተደርጓል። በመሆኑም ቀጣዩ ፕሬዚዳንት መሆናቸውን ያረጋገጡት ዊሊያም ሩቶ በመጪው ማክሰኞ ቃለ መሃላ ይፈጽማሉ። ፕሬዝዳንት ኡሁሩ እስካሁን ለምክትላቸው የእንኳን ደስ ያለዎት መልዕክት ባያስተላልፉም የሥልጣን ሽግግሩን በተመለከተ በትናንትናው ዕለት ውይይት አድርገዋል። ሁለቱ መሪዎች ሐሙስ ፓርላማው ከመከፈቱ  በፊት ከየፓርቲዎቻቸው ጋር ተገናኝተዋል። ፕሬዚዳንት ኡሁሩ፣ ራይላ ኦዲንጋን እጩ ፕሬዚዳንት አድርጎ የነበረው የአዚሚዮ ጥምረት ሊቀመንበር ናቸው። ሁለቱም ወገኖች የሁለቱን ምክር ቤቶች አፈ ጉባኤነት እንዴት ማሸነፍ እንደሚችሉ ስትራቴጂ እየነደፉ ነው። ሁለቱም ፓርቲዎች በፓርላማ ውስጥ አብላጫ ድምፅ አላገኙም። ተመራጩ ፕሬዚደንት ዊሊያም ሩቶ ወሳኝ የሆኑ ፖሊሲዎችን ለማሳለፍ፣ የካቢኔ እጩዎችን፣ ዋና ጸሐፊዎችን፣ አምባሳደሮችን እና ከፍተኛ ኮሚሽነሮችን ለመሾም አብላጫ ድምጽ ማግኘት ይጠበቅባቸዋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c251x3vr8jzo
0business
አየር መንገዶች "ከምድራችን ይልቅ ጥቅማቸውን ያስቀድማሉ" የሚል ክስ ቀረበባቸው
በብሪቲሽ አየር መንደገድ ውስጥ የሚሰራ አንድ የዘርፉ ባለሙያ እንዳጋለጠው፤ በአየር መንገድ ኢንዱስትሪ ውስጥ ሆነ ተብሎ አውሮፕላኖች ብዙ ነዳጀ ጭነው እንዲጓዙ ይደረጋል። ይህም አውሮፕላኑ በሚይዘው ክብደት ልክ ብዙ ነዳጅ ተቃጥሎ አየር እንዲበከል እየተደረገ ነው ተብሏል። አየር መንገዶች አውሮፕላኖቻቸው ከመነሻቸው ብዙ ነዳጅ ጭነው የሚነሱት በመዳረሻ አየር መንገዶች ለነዳጅ የሚጠየቁትን ብዙ የነዳጅ ገንዘብ ለማስቀረት ነው። ብሪቲሽ አየር መንገድ "ለደህንነት እና ከዋጋ ጋር በተያያዙ ምክንያቶች" ተጨማሪ ነዳጅ ይዞ መብረር የተለመደ ነው ብሏል። ቢቢሲ ፓኖራማ የተሰኘው የቢቢሲ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ባለፈው ዓመት የብሪቲሽ አየር መንገድ አውሮፕላኖች ተጨማሪ ነዳጅ ይዘው በመብረራቸው ተጨማሪ 18ሺህ ቶን ካርበን ዳይኦክሳይድ አመንጭተዋል ሲል መዘገቡ ይታወሳል። አንድ ጥናት እንዳረጋገጠው ደግሞ አውሮፓ ውስጥ ከሚደረጉ ከአምስት በረራዎች ቢያንስ በአንዱ አውሮፕላኑ ተጨማሪ ነዳጅ ይዞ ወደ መዳረሻው ይበራል። ተቺዎች እንደሚሉት ይህ ተግባር አየር መንገዶች የአየር ብክለትን ለመቀነስ እንሰራለን የሚሉትን ቃል ጥያቄ ውስጥ የሚከት ነው። ከተቺዎቹ መካከል አንዱ የሆኑት ጆህን ሳኡቨን አየር መንገዶች "ከምድራችን ይልቅ ጥቅማቸወን ያስቀድማሉ" ለምንለው ይህ ትክክለኛ ማሳያ ነው ሲሉ ተደምጠዋል።
አየር መንገዶች "ከምድራችን ይልቅ ጥቅማቸውን ያስቀድማሉ" የሚል ክስ ቀረበባቸው በብሪቲሽ አየር መንደገድ ውስጥ የሚሰራ አንድ የዘርፉ ባለሙያ እንዳጋለጠው፤ በአየር መንገድ ኢንዱስትሪ ውስጥ ሆነ ተብሎ አውሮፕላኖች ብዙ ነዳጀ ጭነው እንዲጓዙ ይደረጋል። ይህም አውሮፕላኑ በሚይዘው ክብደት ልክ ብዙ ነዳጅ ተቃጥሎ አየር እንዲበከል እየተደረገ ነው ተብሏል። አየር መንገዶች አውሮፕላኖቻቸው ከመነሻቸው ብዙ ነዳጅ ጭነው የሚነሱት በመዳረሻ አየር መንገዶች ለነዳጅ የሚጠየቁትን ብዙ የነዳጅ ገንዘብ ለማስቀረት ነው። ብሪቲሽ አየር መንገድ "ለደህንነት እና ከዋጋ ጋር በተያያዙ ምክንያቶች" ተጨማሪ ነዳጅ ይዞ መብረር የተለመደ ነው ብሏል። ቢቢሲ ፓኖራማ የተሰኘው የቢቢሲ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ባለፈው ዓመት የብሪቲሽ አየር መንገድ አውሮፕላኖች ተጨማሪ ነዳጅ ይዘው በመብረራቸው ተጨማሪ 18ሺህ ቶን ካርበን ዳይኦክሳይድ አመንጭተዋል ሲል መዘገቡ ይታወሳል። አንድ ጥናት እንዳረጋገጠው ደግሞ አውሮፓ ውስጥ ከሚደረጉ ከአምስት በረራዎች ቢያንስ በአንዱ አውሮፕላኑ ተጨማሪ ነዳጅ ይዞ ወደ መዳረሻው ይበራል። ተቺዎች እንደሚሉት ይህ ተግባር አየር መንገዶች የአየር ብክለትን ለመቀነስ እንሰራለን የሚሉትን ቃል ጥያቄ ውስጥ የሚከት ነው። ከተቺዎቹ መካከል አንዱ የሆኑት ጆህን ሳኡቨን አየር መንገዶች "ከምድራችን ይልቅ ጥቅማቸወን ያስቀድማሉ" ለምንለው ይህ ትክክለኛ ማሳያ ነው ሲሉ ተደምጠዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-50371705
3politics
ተጭበርብሯል ተብሎ በተተቸው የሩስያ ምርጫ የፑቲን ፓርቲ አሸነፈ
የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ፓርቲ በምክር ቤት አብላጫ ድምጽ በማግኘት ምርጫውን አሸነፈ። ምንም እንኳን ምርጫው ተጭበርብሯል ተብሎ ቢተችም በፑቲን የሚመራው ዩናይትድ ራሽያ ፓርቲ ወደ 50% ድምጽ አግኝቷል። የፑቲን ቀንደኛ ተቺዎች በምርጫው እንዳይሳተፉ ከመታገዳቸው ባሻገር መራጮች ድምጽ እንዲሰጡ እንደተገደዱና የምርጫ ኮሮጆ ውስጥ የተጭበረበሩ ድምጾች እንደተገኙ ተገልጿል። የሩስያ ምርጫ ኮሚሽን በበኩሉ ምርጫው ተጭበርብሯል በማሉን አስተባብሏል። ከፑቲን ፓርቲ ጋር በዋነኛነት የተፎካከረው ኮምኒስት ፓርቲ 19% ድምጽ አግኝቷል። ስለዚህም የፑቲን ፓርቲ ከምክር ቤቱ 450 መቀመጫዎች መካከል ከሁለት ሦስተኛው በላይ የሚሆኑትን ይቆጣጠራል። እአአ በ2016 በተካሄደው ምርጫ ፓርቲው 54% ድምጽ ነበር ያገኘው። ዘንድሮ ያገኘው ድምጽ በመጠኑም ቢሆን ቀንሷል። ምክር ቤት ውስጥ የፑቲንን ፓርቲ ሐሳብ ከሞላ ጎደል የሚደግፈው ኮምኒስት ፓርቲ ባለፈው ምርጫ 6% ድምጽ አግኝቶ ነበር። ዘንድሮ ግን የመረጡት ሰዎች ቁጥር ከፍ ብሏል። አሶሽየትድ ፕረስ እንደዘገበው፤ የኮምኒስት ፓርቲ መሪ ጌንዳይ ዚጋኖቭ ምርጫው በተለያዩ አይነት የማጭበርበሪያ መንገዶች የተሞላ ነበር ሲሉ ተችተዋል። የምርጫ ኮሚሽን ኃላፊ ኤላ ፓምፊቮላ የፊታችን አርብ አጠቃላይ ውጤት ይፋ ይደረጋል ብለዋል። ሩስያ ውስጥ ያለው ፈታኝ የኑሮ ሁኔታ እንዲሁም አስተዳደሩ በሙስና ተዘፍቋል የሚሉ ክሶች የፑቲን ደጋፊዎች ቁጥር እንዲቀንስ ማድረጋቸውን ተንታኞች ይናገራሉ። በተለይም እስር ላይ የሚገኘው የፑቲን ተቺ አሌክሲ ናቫልኒ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድሯል። በሌላ በኩል ፑቲን ለምዕራባውያን ጫና የማይንበረከኩ እንዲሁም ብሔራዊ ጥቅምን የሚያስቀድሙ ናቸው የሚለው አመለካከት ብዙ ሩስያውያን ፕሬዝዳንቱን እንዲደግፉ አድርጓቸዋል። ትላንት በቴሌቭዥን የቀረቡት ፑቲን መራጩን ሕዝብ አመስግነዋል። ፓርቲያቸው ምርጫውን ያሸነፈው በነጻና ፍትሐዊ የምርጫ ሂደት እንደሆነ ያምናሉ። የናቫንሊ ደጋፊዎች ደግሞ ምርጫውን እንደማይቀበሉት ገልጸው ተቃውሞ ጠርተዋል። የናቫንሊ ደጋፊዎችን ጨምሮ ፑቲን ላይ የሰላ ሂስ ያሰሙ የነበሩ ተቃዋሚዎች በምርጫው እንዲሳተፉ አልተፈቀደላቸውም። በምርጫ ሂደቱ መራጮች ላይ ጫና እንደተደረገ፣ የምርጫ ታዛቢዎች ማስፈራሪያ እንደደረሳቸው እና የምርጫ ኮሮጆ ውስጥ የተጭበረበሩ ድምጾች እንደተገኙ ተገልጿል። መራጮች ከአንድ በላይ የድምጽ መስጫ ወረቀት ኮሮጆ ውስጥ ሲከቱ የሚያሳዩ ተንቀሳቃሽ ምስሎችም ሾልከው ወጥተዋል። እንደ መዲናዋ ሞስኮ ባሉ ከተሞች የድምጽ መስጫ ሰዓት ሲቃረብ ድምጽ የሚሰጠው በኤሌክትሮኒክስ መሣሪያ ነው በማሉም ጥያቄ አስነስቷል። ሚካሂል ሎባኖቭ የተባለ የኮምኒስት ፓርቲ አባል የፑቲን ፓርቲ "እንዲህ ያለው ውጤት ሊያገኝ እንደማይችል አውቃለሁ" ሲል ትዊት አድርጓል። ሰኪውሪቲ ኤንድ ኮኦፕሬሽን ኢን ዩሮፕ የተባለው ተቋም ምርጫውን እንዳይታዘብ በሩስያ መንግሥት እገዳ ተጥሎበታል። ተቋሙ ከ1993 ወዲህ የሩስያን ምርጫ ሳይታዘብ ሲቀር የዘንድሮው የመጀመሪያው ነው። የአውሮፓ ሕብረት ቃል አቀባይ ምርጫው በተገቢው ሁኔታ ቁጥጥር አልተደረገበትም ብለው ተችተዋል። የዩናይድት ኪንግደም፣ የጀርመን እና የአሜሪካ መንግሥታትም ምርጫው ነጻና ፍትሐዊ አልነበረም ብለዋል። ገለልተኛው እና ጎሎስ የተባለው ምርጫ ታዛቢ ቢያንስ 5,000 የተጭበረበሩ ድምጾች እንዳሉ ሪፖርት ደርሶኛል ቢልም የሩስያ መንግሥት ድርጅቱን "የውጪ ኃይሎች ተላላኪ" ሲል አጣጥሎታል። የናቫልኒ ቃል አቀባይ ኪራ ያራምሽ "2011 ላይ እንዳደረጉት ሁሉ አሁንም ምርጫውን አጭበረበሩ" ስትል ቃሏን ሰጥታለች። አንድ የጸጉር ቤት ሠራተኛ "ድምጽ የመስጠት ጥቅሙ አይታየኝም። እነሱ እንደሆነ ምርጫውን እንደሚያሸንፉ ቀድመው ያውቃሉ" ስትል አስተያየቷን ሰጥታለች።
ተጭበርብሯል ተብሎ በተተቸው የሩስያ ምርጫ የፑቲን ፓርቲ አሸነፈ የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ፓርቲ በምክር ቤት አብላጫ ድምጽ በማግኘት ምርጫውን አሸነፈ። ምንም እንኳን ምርጫው ተጭበርብሯል ተብሎ ቢተችም በፑቲን የሚመራው ዩናይትድ ራሽያ ፓርቲ ወደ 50% ድምጽ አግኝቷል። የፑቲን ቀንደኛ ተቺዎች በምርጫው እንዳይሳተፉ ከመታገዳቸው ባሻገር መራጮች ድምጽ እንዲሰጡ እንደተገደዱና የምርጫ ኮሮጆ ውስጥ የተጭበረበሩ ድምጾች እንደተገኙ ተገልጿል። የሩስያ ምርጫ ኮሚሽን በበኩሉ ምርጫው ተጭበርብሯል በማሉን አስተባብሏል። ከፑቲን ፓርቲ ጋር በዋነኛነት የተፎካከረው ኮምኒስት ፓርቲ 19% ድምጽ አግኝቷል። ስለዚህም የፑቲን ፓርቲ ከምክር ቤቱ 450 መቀመጫዎች መካከል ከሁለት ሦስተኛው በላይ የሚሆኑትን ይቆጣጠራል። እአአ በ2016 በተካሄደው ምርጫ ፓርቲው 54% ድምጽ ነበር ያገኘው። ዘንድሮ ያገኘው ድምጽ በመጠኑም ቢሆን ቀንሷል። ምክር ቤት ውስጥ የፑቲንን ፓርቲ ሐሳብ ከሞላ ጎደል የሚደግፈው ኮምኒስት ፓርቲ ባለፈው ምርጫ 6% ድምጽ አግኝቶ ነበር። ዘንድሮ ግን የመረጡት ሰዎች ቁጥር ከፍ ብሏል። አሶሽየትድ ፕረስ እንደዘገበው፤ የኮምኒስት ፓርቲ መሪ ጌንዳይ ዚጋኖቭ ምርጫው በተለያዩ አይነት የማጭበርበሪያ መንገዶች የተሞላ ነበር ሲሉ ተችተዋል። የምርጫ ኮሚሽን ኃላፊ ኤላ ፓምፊቮላ የፊታችን አርብ አጠቃላይ ውጤት ይፋ ይደረጋል ብለዋል። ሩስያ ውስጥ ያለው ፈታኝ የኑሮ ሁኔታ እንዲሁም አስተዳደሩ በሙስና ተዘፍቋል የሚሉ ክሶች የፑቲን ደጋፊዎች ቁጥር እንዲቀንስ ማድረጋቸውን ተንታኞች ይናገራሉ። በተለይም እስር ላይ የሚገኘው የፑቲን ተቺ አሌክሲ ናቫልኒ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድሯል። በሌላ በኩል ፑቲን ለምዕራባውያን ጫና የማይንበረከኩ እንዲሁም ብሔራዊ ጥቅምን የሚያስቀድሙ ናቸው የሚለው አመለካከት ብዙ ሩስያውያን ፕሬዝዳንቱን እንዲደግፉ አድርጓቸዋል። ትላንት በቴሌቭዥን የቀረቡት ፑቲን መራጩን ሕዝብ አመስግነዋል። ፓርቲያቸው ምርጫውን ያሸነፈው በነጻና ፍትሐዊ የምርጫ ሂደት እንደሆነ ያምናሉ። የናቫንሊ ደጋፊዎች ደግሞ ምርጫውን እንደማይቀበሉት ገልጸው ተቃውሞ ጠርተዋል። የናቫንሊ ደጋፊዎችን ጨምሮ ፑቲን ላይ የሰላ ሂስ ያሰሙ የነበሩ ተቃዋሚዎች በምርጫው እንዲሳተፉ አልተፈቀደላቸውም። በምርጫ ሂደቱ መራጮች ላይ ጫና እንደተደረገ፣ የምርጫ ታዛቢዎች ማስፈራሪያ እንደደረሳቸው እና የምርጫ ኮሮጆ ውስጥ የተጭበረበሩ ድምጾች እንደተገኙ ተገልጿል። መራጮች ከአንድ በላይ የድምጽ መስጫ ወረቀት ኮሮጆ ውስጥ ሲከቱ የሚያሳዩ ተንቀሳቃሽ ምስሎችም ሾልከው ወጥተዋል። እንደ መዲናዋ ሞስኮ ባሉ ከተሞች የድምጽ መስጫ ሰዓት ሲቃረብ ድምጽ የሚሰጠው በኤሌክትሮኒክስ መሣሪያ ነው በማሉም ጥያቄ አስነስቷል። ሚካሂል ሎባኖቭ የተባለ የኮምኒስት ፓርቲ አባል የፑቲን ፓርቲ "እንዲህ ያለው ውጤት ሊያገኝ እንደማይችል አውቃለሁ" ሲል ትዊት አድርጓል። ሰኪውሪቲ ኤንድ ኮኦፕሬሽን ኢን ዩሮፕ የተባለው ተቋም ምርጫውን እንዳይታዘብ በሩስያ መንግሥት እገዳ ተጥሎበታል። ተቋሙ ከ1993 ወዲህ የሩስያን ምርጫ ሳይታዘብ ሲቀር የዘንድሮው የመጀመሪያው ነው። የአውሮፓ ሕብረት ቃል አቀባይ ምርጫው በተገቢው ሁኔታ ቁጥጥር አልተደረገበትም ብለው ተችተዋል። የዩናይድት ኪንግደም፣ የጀርመን እና የአሜሪካ መንግሥታትም ምርጫው ነጻና ፍትሐዊ አልነበረም ብለዋል። ገለልተኛው እና ጎሎስ የተባለው ምርጫ ታዛቢ ቢያንስ 5,000 የተጭበረበሩ ድምጾች እንዳሉ ሪፖርት ደርሶኛል ቢልም የሩስያ መንግሥት ድርጅቱን "የውጪ ኃይሎች ተላላኪ" ሲል አጣጥሎታል። የናቫልኒ ቃል አቀባይ ኪራ ያራምሽ "2011 ላይ እንዳደረጉት ሁሉ አሁንም ምርጫውን አጭበረበሩ" ስትል ቃሏን ሰጥታለች። አንድ የጸጉር ቤት ሠራተኛ "ድምጽ የመስጠት ጥቅሙ አይታየኝም። እነሱ እንደሆነ ምርጫውን እንደሚያሸንፉ ቀድመው ያውቃሉ" ስትል አስተያየቷን ሰጥታለች።
https://www.bbc.com/amharic/58634883
5sports
ኮቢ ብራያንት ሕይወቱን ያጣበት ሄሊኮፕተር አደጋ የምርመራ ውጤት ይፋ ሆነ
ታዋቂው አሜሪካዊ የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ኮቢ ብራያንትና ታዳጊ ሴት ልጁን ጨምሮ 9 ሰዎች አሳፍሮ የተከሰከሰው ሄሊኮፕተር አደጋ ሪፖርት ይፋ ሆኗል። ሪፖርቱ ዘጠኙም ተሳፋሪዎች ለሞት የበቁት ሰውነታቸው ላይ በደረሰ ከባድ ግጭት ሳቢያ ነው ብሏል። 180 ገፆች ያሉት ይህ ሪፖርት የሄሊኮፕተሯ አብራሪ የ50 ዓመቱ አራ ዞባያን አደንዛዥ ዕፅም ሆነ የአልኮም መጠጥ አልወሰደም ሲል ደምድሟል። ባለፈው ጥር በአሜሪካዋ የካሊፎርኒያ ግዛት የተከሰተው የሄሊኮፕተር አደጋ መንስዔ ምን እንደሆነ አሁንም እየተጣራ ነው። አነስተኛዋ ሄሊኮፕተር ስትከሰከስ የአየር ሁኔታው ደመና እንደነበር ይታወሳል። ታዋቂው የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ብራያንትና የ13 ዓመት ልጁ ጂያና ከዘጠኙ ተሳፋሪዎች መካከል ነበሩ። ከእነሱ በተጨማሪ ሁለት የጂያና እኩያ ሴት ቅርጫት ኳስ ተጫዋቾች፣ ቤተሰቦቻቸውና አሠልጣኛቸው ሄሊኮፕተሯ ውስጥ ነበሩ። ተሳፋሪዎቹ ለታዳጊ ሴቶች የቅርጫት ኳስ ፍልሚያ ነበር ታውዘንድ ኦክስ ወደ ተሰኘው ሥፍራ ሲያቀኑ የነበረው። ዘጠኙንም ሰዎች ያሳፈረችው ሄሊኮፕተር በሰሜናዊ ሎስ አንጀለስ የሚገኝ ተራራ ላይ የተከሰከሰችው። ሪፖርቱ የሁሉም ሟቾች የሞት ምክንያት አደጋ ነው ሲል ደምድሟል። የድህረ-አደጋ ምርመራው በከተማዋ ጤና ጉዳዮች ድረ-ገፅ ላይ በይፋ ተሰቅሏል። አምስት ጊዜ የአሜሪማካ ቅርጫት ኳስ ሻምፒዮን መሆን የቻለው ኮቢ ብራያንት ዕድሜውን ሙሉ ኤልኤ ሌከርስ ለተበላው ቡድን ነው የተጫወተው። በአሜሪካ ቅርጫት ኳስ ማሕበር [ኤንቢኤ] ታሪክ ከታላላቅ ተጫዋቾች መካከል የሚመደብ ነው። ለ20 ዓመታት ቅርጫት ኳስ የተጫወተው ኮቢ በፈረንጆቹ ሚያዝያ 2016 ነበር ቅርጫቱን የሰቀለው። የኮቢ ብራያንት ባለቤት ቫኔሳ ብራያንት ጠበቆች የሄሊኮፕተር አብራሪውን ድርጅት ከሰዋል። ክሱ፤ አብራሪው ለበረራ ከመነሳቱ በፊት የአየር ሁኔታውን አላጣራም ይላል። የሎስ አንጀለስ ከተማ ፖሊስ መርማሪዎች በአደጋው ሥፍራ ተገኝተው እጅግ አሰቃቂ ፎቶዎች ማንሳታቸውን አምነው ነበር። ከዚያ በኋላ ግን ፎቶዎቹን ከማሕህሮቻቸው እንዲያጠፉ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸዋል።
ኮቢ ብራያንት ሕይወቱን ያጣበት ሄሊኮፕተር አደጋ የምርመራ ውጤት ይፋ ሆነ ታዋቂው አሜሪካዊ የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ኮቢ ብራያንትና ታዳጊ ሴት ልጁን ጨምሮ 9 ሰዎች አሳፍሮ የተከሰከሰው ሄሊኮፕተር አደጋ ሪፖርት ይፋ ሆኗል። ሪፖርቱ ዘጠኙም ተሳፋሪዎች ለሞት የበቁት ሰውነታቸው ላይ በደረሰ ከባድ ግጭት ሳቢያ ነው ብሏል። 180 ገፆች ያሉት ይህ ሪፖርት የሄሊኮፕተሯ አብራሪ የ50 ዓመቱ አራ ዞባያን አደንዛዥ ዕፅም ሆነ የአልኮም መጠጥ አልወሰደም ሲል ደምድሟል። ባለፈው ጥር በአሜሪካዋ የካሊፎርኒያ ግዛት የተከሰተው የሄሊኮፕተር አደጋ መንስዔ ምን እንደሆነ አሁንም እየተጣራ ነው። አነስተኛዋ ሄሊኮፕተር ስትከሰከስ የአየር ሁኔታው ደመና እንደነበር ይታወሳል። ታዋቂው የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ብራያንትና የ13 ዓመት ልጁ ጂያና ከዘጠኙ ተሳፋሪዎች መካከል ነበሩ። ከእነሱ በተጨማሪ ሁለት የጂያና እኩያ ሴት ቅርጫት ኳስ ተጫዋቾች፣ ቤተሰቦቻቸውና አሠልጣኛቸው ሄሊኮፕተሯ ውስጥ ነበሩ። ተሳፋሪዎቹ ለታዳጊ ሴቶች የቅርጫት ኳስ ፍልሚያ ነበር ታውዘንድ ኦክስ ወደ ተሰኘው ሥፍራ ሲያቀኑ የነበረው። ዘጠኙንም ሰዎች ያሳፈረችው ሄሊኮፕተር በሰሜናዊ ሎስ አንጀለስ የሚገኝ ተራራ ላይ የተከሰከሰችው። ሪፖርቱ የሁሉም ሟቾች የሞት ምክንያት አደጋ ነው ሲል ደምድሟል። የድህረ-አደጋ ምርመራው በከተማዋ ጤና ጉዳዮች ድረ-ገፅ ላይ በይፋ ተሰቅሏል። አምስት ጊዜ የአሜሪማካ ቅርጫት ኳስ ሻምፒዮን መሆን የቻለው ኮቢ ብራያንት ዕድሜውን ሙሉ ኤልኤ ሌከርስ ለተበላው ቡድን ነው የተጫወተው። በአሜሪካ ቅርጫት ኳስ ማሕበር [ኤንቢኤ] ታሪክ ከታላላቅ ተጫዋቾች መካከል የሚመደብ ነው። ለ20 ዓመታት ቅርጫት ኳስ የተጫወተው ኮቢ በፈረንጆቹ ሚያዝያ 2016 ነበር ቅርጫቱን የሰቀለው። የኮቢ ብራያንት ባለቤት ቫኔሳ ብራያንት ጠበቆች የሄሊኮፕተር አብራሪውን ድርጅት ከሰዋል። ክሱ፤ አብራሪው ለበረራ ከመነሳቱ በፊት የአየር ሁኔታውን አላጣራም ይላል። የሎስ አንጀለስ ከተማ ፖሊስ መርማሪዎች በአደጋው ሥፍራ ተገኝተው እጅግ አሰቃቂ ፎቶዎች ማንሳታቸውን አምነው ነበር። ከዚያ በኋላ ግን ፎቶዎቹን ከማሕህሮቻቸው እንዲያጠፉ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-52689130
3politics
የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ስለታይዋን ምንም ነገር ሳይሉ ጉብኝታቸውን ጀመሩ
የአሜሪካ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የሆኑት ናንሲ ፔሎሲ የቻይናን ማስጠንቀቂያ ተከትሎ ታይዋን የጉብኝታቸው አካል ትሁን አትሁን ምንም ነገር ሳይገለጽ ወደ እስያ ተጓዙ። ፔሎሲ በጉዟቸው ሴንጋፖርን፣ ማሌዢያን፣ ደቡብ ኮሪያን እና ጃፓንን እንደሚጎበኙ ጽህፈት ቤታቸው የገለጸ ሲሆን፣ ቻይና የግዛቴ አካል ናት የምትላትን ታይዋንን ግን ሳይጠቅስ አልፏታል። አፈ ጉባኤዋ ጉብኝት እንደሚያደርጉ በተገለጸበት ጊዜ ወደ እራስ ገዟ ታይዋን ሊጓዙ እንደሚችሉ በስፋት ሲወራ ነበር። ይህንንም ተከትሎ ታይዋን የግዛቴ አካል ናት የምትለው ቻይና፣ ፔሎሲ ታይዋንን የሚጎበኙ ከሆነ “ከባድ መዘዝ” እንደሚከተል አስጠንቅቃለች። ባለፉት 25 ዓመታት አንድም ከፍተኛ ሥልጣን ያለው በሕዝብ የተመረጠ የአሜሪካ ባለሥልጣን ታይዋንን ጎብኝቶ አያውቅም። የዲሞክራቲክ ፓርቲ ተመራጯ ናንሲ ፔሎሲ ጉብኝታቸውን በተመለከተ በትዊተር ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት፣ የአገሪቱ ምክር ቤት ልዑካን ቡድን ስድስት አባላት “በአካባቢው ላሉ ወዳጆቻችንና አጋሮቻችን አሜሪካ ያላትን የማይወላውል አቋም የምናጸናበት ነው” ብለዋል። የአፈ ጉባኤዋ ጽህፈት ቤት ጉዞውን በተመለከተ እንዳለው፣ ጉብኝቱ “ሴንጋፖር፣ ማሌዢያ፣ ደቡብ ኮሪያ እና ጃፓንን ጨምሮ የኢንዶ-ፓሲፊክ አካባቢን” የሚመለከት ነው ብሏል። ቻይና ታይዋን ወደ እናት አገሯ መመለስ ያለባት አፈንጋጭ ግዛቷ እንደሆነች ትመለከታታለች። ይህንንም ለማሳካት ወደፊት ቤይጂንግ ኃይል መጠቀምን እንደ አንድ አማራጭ ታየዋለች። የቻይና ባለሥልጣናት አሜሪካ ከታይዋን ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እያደረገች ነው በሚል ቁጣቸውን ሲገልጹ ቆይተዋል። ባለፈው ሚያዚያ ወርም ስድስት የአሜሪካ ምክር ቤት አባላት በታይዋን ድንገተኛ ጉብኝት አድርገው ነበር። አሜሪካ ከቻይና ጋር እንጂ ከታይዋን ጋር መደበኛ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙት የላትም። ናንሲ ፔሎሲ በቻይና የሰብአዊ መብት አያያዝ የተነሳ የአገሪቱን መሪዎች ለረጅም ጊዜ ሲተቹ ቆይተዋል። በተጨማሪም ከዲሞክራሲ ደጋፊ ቻይናውያን ጋር የተገናኙ ሲሆን፣ የታይናሚን አደባባይ ጭፍጨፋ ሰለባዎችን ለማስታወስ አደባባዩን ጎብኝተዋል። አፈ ጉባኤዋ ታይዋንን ለመጎብኘት አቅደው የነበረው ባለፈው ሚያዚያ ወር ላይ የነበረ ቢሆንም፣ በኮቪድ በመያዛቸው ጉዟቸውን አዘግይተውት ቆይተዋል። ከጥቂት ሳምንታት በፊት “ለታይዋን ያለንን ድጋፍ ማሳየት ለእኛ አስፈላጊ ነገር ነው” ብለው ተናግረውም ነበር። ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የአሜሪካ ጦር ኃይል ፔሎሲ ወደ ታይዋን ሊያደርጉ ያሰቡት ጉብኝት “በአሁኑ ወቅት ጥሩ ሃሳብ አይደለም” ብሎ እንደሚያምን ተናግረዋል። ከአፈ ጉባኤዋ ጽህፈት ቤት ዛሬ እሁድ የወጣው መግለጫ ጉዞው “በኢንዶ-ፓሲፊክ አካባቢ ስላላው የጋራ የደኅንነት፣ ምጣኔ ሀብታዊ አጋርነት እና ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ላይ የሚያተኩር ይሆናል” ብሏል። በውይይቱ ላይ ንግድ፣ የአየር ፀባይ ለውጥ እና የሰብአዊ መብት ጉዳዮችም እንደሚነሱ ተነግሯል። ከፔሎሲ ጋር በጉዞው የሚሳተፉት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋነኛ አባላት የሆኑት ግሪጎሪ ሚክስ፣ ማርክ ታካኖ፣ ሱዛን ዴልቤኔ፣ ራጃ ክሪሽናሙርቲ እና ኤንዲ ኪም ናቸው። ታይዋንን የጎበኙ የመጨረሻው የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሪፐብሊካኑ ኒውት ጊንግሪች ሲሆኑ፣ እሱም በአውሮፓውያኑ 1997 ነበረ።
የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ስለታይዋን ምንም ነገር ሳይሉ ጉብኝታቸውን ጀመሩ የአሜሪካ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የሆኑት ናንሲ ፔሎሲ የቻይናን ማስጠንቀቂያ ተከትሎ ታይዋን የጉብኝታቸው አካል ትሁን አትሁን ምንም ነገር ሳይገለጽ ወደ እስያ ተጓዙ። ፔሎሲ በጉዟቸው ሴንጋፖርን፣ ማሌዢያን፣ ደቡብ ኮሪያን እና ጃፓንን እንደሚጎበኙ ጽህፈት ቤታቸው የገለጸ ሲሆን፣ ቻይና የግዛቴ አካል ናት የምትላትን ታይዋንን ግን ሳይጠቅስ አልፏታል። አፈ ጉባኤዋ ጉብኝት እንደሚያደርጉ በተገለጸበት ጊዜ ወደ እራስ ገዟ ታይዋን ሊጓዙ እንደሚችሉ በስፋት ሲወራ ነበር። ይህንንም ተከትሎ ታይዋን የግዛቴ አካል ናት የምትለው ቻይና፣ ፔሎሲ ታይዋንን የሚጎበኙ ከሆነ “ከባድ መዘዝ” እንደሚከተል አስጠንቅቃለች። ባለፉት 25 ዓመታት አንድም ከፍተኛ ሥልጣን ያለው በሕዝብ የተመረጠ የአሜሪካ ባለሥልጣን ታይዋንን ጎብኝቶ አያውቅም። የዲሞክራቲክ ፓርቲ ተመራጯ ናንሲ ፔሎሲ ጉብኝታቸውን በተመለከተ በትዊተር ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት፣ የአገሪቱ ምክር ቤት ልዑካን ቡድን ስድስት አባላት “በአካባቢው ላሉ ወዳጆቻችንና አጋሮቻችን አሜሪካ ያላትን የማይወላውል አቋም የምናጸናበት ነው” ብለዋል። የአፈ ጉባኤዋ ጽህፈት ቤት ጉዞውን በተመለከተ እንዳለው፣ ጉብኝቱ “ሴንጋፖር፣ ማሌዢያ፣ ደቡብ ኮሪያ እና ጃፓንን ጨምሮ የኢንዶ-ፓሲፊክ አካባቢን” የሚመለከት ነው ብሏል። ቻይና ታይዋን ወደ እናት አገሯ መመለስ ያለባት አፈንጋጭ ግዛቷ እንደሆነች ትመለከታታለች። ይህንንም ለማሳካት ወደፊት ቤይጂንግ ኃይል መጠቀምን እንደ አንድ አማራጭ ታየዋለች። የቻይና ባለሥልጣናት አሜሪካ ከታይዋን ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እያደረገች ነው በሚል ቁጣቸውን ሲገልጹ ቆይተዋል። ባለፈው ሚያዚያ ወርም ስድስት የአሜሪካ ምክር ቤት አባላት በታይዋን ድንገተኛ ጉብኝት አድርገው ነበር። አሜሪካ ከቻይና ጋር እንጂ ከታይዋን ጋር መደበኛ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙት የላትም። ናንሲ ፔሎሲ በቻይና የሰብአዊ መብት አያያዝ የተነሳ የአገሪቱን መሪዎች ለረጅም ጊዜ ሲተቹ ቆይተዋል። በተጨማሪም ከዲሞክራሲ ደጋፊ ቻይናውያን ጋር የተገናኙ ሲሆን፣ የታይናሚን አደባባይ ጭፍጨፋ ሰለባዎችን ለማስታወስ አደባባዩን ጎብኝተዋል። አፈ ጉባኤዋ ታይዋንን ለመጎብኘት አቅደው የነበረው ባለፈው ሚያዚያ ወር ላይ የነበረ ቢሆንም፣ በኮቪድ በመያዛቸው ጉዟቸውን አዘግይተውት ቆይተዋል። ከጥቂት ሳምንታት በፊት “ለታይዋን ያለንን ድጋፍ ማሳየት ለእኛ አስፈላጊ ነገር ነው” ብለው ተናግረውም ነበር። ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የአሜሪካ ጦር ኃይል ፔሎሲ ወደ ታይዋን ሊያደርጉ ያሰቡት ጉብኝት “በአሁኑ ወቅት ጥሩ ሃሳብ አይደለም” ብሎ እንደሚያምን ተናግረዋል። ከአፈ ጉባኤዋ ጽህፈት ቤት ዛሬ እሁድ የወጣው መግለጫ ጉዞው “በኢንዶ-ፓሲፊክ አካባቢ ስላላው የጋራ የደኅንነት፣ ምጣኔ ሀብታዊ አጋርነት እና ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ላይ የሚያተኩር ይሆናል” ብሏል። በውይይቱ ላይ ንግድ፣ የአየር ፀባይ ለውጥ እና የሰብአዊ መብት ጉዳዮችም እንደሚነሱ ተነግሯል። ከፔሎሲ ጋር በጉዞው የሚሳተፉት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋነኛ አባላት የሆኑት ግሪጎሪ ሚክስ፣ ማርክ ታካኖ፣ ሱዛን ዴልቤኔ፣ ራጃ ክሪሽናሙርቲ እና ኤንዲ ኪም ናቸው። ታይዋንን የጎበኙ የመጨረሻው የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሪፐብሊካኑ ኒውት ጊንግሪች ሲሆኑ፣ እሱም በአውሮፓውያኑ 1997 ነበረ።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cd1jlkx1lzro
0business
በኢትዮጵያ ከባንኮች በሚወጣ የገንዘብ መጠን ላይ ገደብ ተጣለ
ኢትዮጵያ ከባንኮችና ከማክሮ ፋይናንስ ተቋማት በሚወጣ የጥሬ ገንዘብ ላይ ገደብ መጣሏን አስታወቀች። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ዛሬ ይፋ ባደረገውና ተግባራዊ በሚሆነው መመሪያው መሰረት ተቋማትና ግለሰቦች ከባንኮች በቀንና በወር ውስጥ ከባንኮች በሚያወጡት የጥሬ ገንዘብ መጠን ላይ ገደብ ተጥሏል። በዚህም መሰረት አንድ ግለሰብ በቀን እስከ 200 ሺህ ብር እንዲሁም በወር እስከ 1 ሚሊየን ብር በጥሬ ገንዘብ ከባንኮች ማውጣት የሚችል ሲሆን፤ ተቋማት ደግሞ በቀን እስከ 300 ሺህ ብር እና በወር እስከ 2.5 ሚሊየን ብር በጥሬ ገንዘብ ማንቀሳቀስ እንደሚችሉ ተገልጿል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶክተር ይናገር ደሴ ይህንን እርምጃ በተመለከተ እንደተናገሩት "የገንዘብ ዝውውርን ሥርዓት በማስያዝ ወንጀልንና የግብር ስወራን ለመከላከል ይረዳል" ማለታቸውን የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በጥሬ ገንዘብ ዝውውር ላይ የተጣለውን የመጠን ገደብ በተመለከተ የወጣው መመሪያ እንዳመለከተው ግን ከተቀመጠው መጠን በላይ ለማንቀሳቀስ ለሚፈልጉ በገንዘብ ተቋማቱ ከፍተኛ ኃላፊዎች በኩል የሚያቀርቡት ምክንያት ተመርምሮ እንደሚፈቀድላቸው ተገልጿል። በተጨማሪም የመጠን ገደብ ከተጣለበት በላይ ጥሬ ገንዘብ ለሚያንቀሳቅሱ ግለሰቦችና ተቋማት ከአንድ ሒሳብ ወደ ሒሳብ፣ በቼክ፣ወይም በሲፒኦ ተጨማሪ ገንዘብ ማዘዋወር እንደሚችሉም ተመልክቷል። ከዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 11/2012 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን የተነገረው መመሪያን ተግባራዊነትን በተመለከተ ብሔራዊ ባንክ ጥብቅ ክትትል እንደሚያደርግ የተገለጸ ሲሆን፤ ባንኮችም በየሳምንቱ የጥሬ ገንዘብ እንቅስቃሴያቸውን ለማዕከላዊው ባንክ ሪፖርት እንዲያደርጉ ይጠበቅባቸዋል። ይህ መመሪያም በአገሪቱ ያሉትን ሁሉንም ባንኮችና አነስተኛና ጥቃቅን የገንዘብ ተቋማትንም የሚመለከት መሆኑ ተገልጿል። ይህንን የብሔራዊ ባንኩን መመሪያ ተላልፈው የተገኙ የገንዘብ ተቋማት ላይ ከፍተኛ መጠን ያለው የገንዘብ ቅጣት እንደሚጣልባቸውም ተመልክቷል።
በኢትዮጵያ ከባንኮች በሚወጣ የገንዘብ መጠን ላይ ገደብ ተጣለ ኢትዮጵያ ከባንኮችና ከማክሮ ፋይናንስ ተቋማት በሚወጣ የጥሬ ገንዘብ ላይ ገደብ መጣሏን አስታወቀች። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ዛሬ ይፋ ባደረገውና ተግባራዊ በሚሆነው መመሪያው መሰረት ተቋማትና ግለሰቦች ከባንኮች በቀንና በወር ውስጥ ከባንኮች በሚያወጡት የጥሬ ገንዘብ መጠን ላይ ገደብ ተጥሏል። በዚህም መሰረት አንድ ግለሰብ በቀን እስከ 200 ሺህ ብር እንዲሁም በወር እስከ 1 ሚሊየን ብር በጥሬ ገንዘብ ከባንኮች ማውጣት የሚችል ሲሆን፤ ተቋማት ደግሞ በቀን እስከ 300 ሺህ ብር እና በወር እስከ 2.5 ሚሊየን ብር በጥሬ ገንዘብ ማንቀሳቀስ እንደሚችሉ ተገልጿል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶክተር ይናገር ደሴ ይህንን እርምጃ በተመለከተ እንደተናገሩት "የገንዘብ ዝውውርን ሥርዓት በማስያዝ ወንጀልንና የግብር ስወራን ለመከላከል ይረዳል" ማለታቸውን የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በጥሬ ገንዘብ ዝውውር ላይ የተጣለውን የመጠን ገደብ በተመለከተ የወጣው መመሪያ እንዳመለከተው ግን ከተቀመጠው መጠን በላይ ለማንቀሳቀስ ለሚፈልጉ በገንዘብ ተቋማቱ ከፍተኛ ኃላፊዎች በኩል የሚያቀርቡት ምክንያት ተመርምሮ እንደሚፈቀድላቸው ተገልጿል። በተጨማሪም የመጠን ገደብ ከተጣለበት በላይ ጥሬ ገንዘብ ለሚያንቀሳቅሱ ግለሰቦችና ተቋማት ከአንድ ሒሳብ ወደ ሒሳብ፣ በቼክ፣ወይም በሲፒኦ ተጨማሪ ገንዘብ ማዘዋወር እንደሚችሉም ተመልክቷል። ከዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 11/2012 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን የተነገረው መመሪያን ተግባራዊነትን በተመለከተ ብሔራዊ ባንክ ጥብቅ ክትትል እንደሚያደርግ የተገለጸ ሲሆን፤ ባንኮችም በየሳምንቱ የጥሬ ገንዘብ እንቅስቃሴያቸውን ለማዕከላዊው ባንክ ሪፖርት እንዲያደርጉ ይጠበቅባቸዋል። ይህ መመሪያም በአገሪቱ ያሉትን ሁሉንም ባንኮችና አነስተኛና ጥቃቅን የገንዘብ ተቋማትንም የሚመለከት መሆኑ ተገልጿል። ይህንን የብሔራዊ ባንኩን መመሪያ ተላልፈው የተገኙ የገንዘብ ተቋማት ላይ ከፍተኛ መጠን ያለው የገንዘብ ቅጣት እንደሚጣልባቸውም ተመልክቷል።
https://www.bbc.com/amharic/news-52703739
3politics
በአርባ ምንጭ በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩት የባልደራስ አመራሮች ተፈቱ
በትላንትናው ዕለት ሚያዝያ 12፣ 2014 ዓ.ም ማምሻውን በአርባ ምንጭ ከተማ ካረፉበት ሆቴል ተወስደው በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩት አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ አራት የባልደራስ አመራሮች በዛሬው ዕለት መፈታታቸውን የፓርቲው ጽህፈት ቤት ምክትል ሃላፊ ወ/ሮ ቀለብ ስዩም ለቢቢሲ ገልጸዋል። ሃላፊዋ ባልደራስ አሁን ክልል አቀፍ ፓርቲ መሆኑን ገልጸው ወደ ሀገር አቀፍ ፓርቲነት ለማደግ የሚያስችለውን የደጋፊዎች ፊርማ ለማሰባሰብ እና ህዝባዊ ስብሰባ ለማድረግ የመጀመሪያ ጉዞውን ወደ አርባ ምንጭ ማድረጉን ተናግረዋል። "ምርጫ ቦርድ ሀገሪቱ ውስጥ ባሉ ክልሎች ተዘዋውረን ህዝባዊ ስብሰባ እንድናደግ፣ ፊርማ እንድናሰባስብ፣ ቢሮም እንድንከፍት የሚያግዙ የትብብር ደብዳቤዎችን" ጽፎልናል የሚሉት ወ/ሮ ቀለብ በአርባ ምንጭ ከተማ ስብሰባ ለማድረግ ፓርቲው ከከተማ አስተዳደሩ ቀደም ብሎ ፍቃድ ተሰጥቶት እንደነበርም ተናግረዋል። "ስለዚህ ዋናው ዓላማው የህዝብ ስብሰባ ለማድረግ እና እዛው ቢሮ ለመክፈት ታስቦ ነው ጉዞ የተደረገው" ሲሉም አክለዋል። በዚህ መሰረት የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ እስክንድር ነጋን እና ሌሎች ሶስት አመራሮች ትላንት ጠዋት ወደ አርባ ምንጭ መጓዛቸውን ጠቅሰዋል። ሆኖም ፓርቲው ቀደም ብሎ ከተሰጠው ፍቃድ በተቃራኒ ማድረግ እንዳይችል መከልከሉን ሃላፊዋ ገልጸዋል። "እንዴት ልትከለክሉን ቻላችሁ? ብለው ሲጠይቁ 'ከላይ በመጣ ትእዛዝ ነው' የሚል መልስ ነው የሰጧቸው" ብለዋል። ወ/ሮ ቀለብ ስብሰባው ከተከለከለ በኋላ ግን አመራሮች ሀገር አቀፍ ፓርቲ ለመመስረት የሚያስችለውን ፊርማ በከተማው የተለያዩ አከባቢዎች እየተዘዋወሩ እየሰባሰቡ መዋላቸውን እና ማምሻውን ወደ ሆቴል ከሄዱ በኋላ በፖሊስ መያዛቸውን ገልጸዋል። "አቶ እስክንድር ስልኬ ላይ ደውለው በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደዋሉ ነገሩኝ" ብለዋል። አመራሮቹ ለሊቱን 'በማይመች ሁኔታ' ፖሊስ ጣቢያ ማደራቸውን የገለጹት ሃላፊዋ የነበሩበት ፖሊስ ጣቢያ ቃላቸውን ሊሰጡ የነበረ ቢሆንም ወደ ጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ መወሰዳቸውን ጠቁመዋል። ሆኖም በዛሬው እለት መፈታታቸውንና ወደ አውሮፕላን ማረፊያ ማቅናታቸውን ቢቢሲ መረዳት ችሏል። የባልደራስ አመራሮችን በቁጥጥር ስር ለምን ዋሉ የሚለውን በተመለከተ ምላሽ ለማግኘት የጋሞ ዞን ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት በተደጋጋሚ ስልክ ብንደውልም ስልክ ባለማንሳታቸው ምላሻቸውን ማካተት አልቻልንም።
በአርባ ምንጭ በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩት የባልደራስ አመራሮች ተፈቱ በትላንትናው ዕለት ሚያዝያ 12፣ 2014 ዓ.ም ማምሻውን በአርባ ምንጭ ከተማ ካረፉበት ሆቴል ተወስደው በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩት አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ አራት የባልደራስ አመራሮች በዛሬው ዕለት መፈታታቸውን የፓርቲው ጽህፈት ቤት ምክትል ሃላፊ ወ/ሮ ቀለብ ስዩም ለቢቢሲ ገልጸዋል። ሃላፊዋ ባልደራስ አሁን ክልል አቀፍ ፓርቲ መሆኑን ገልጸው ወደ ሀገር አቀፍ ፓርቲነት ለማደግ የሚያስችለውን የደጋፊዎች ፊርማ ለማሰባሰብ እና ህዝባዊ ስብሰባ ለማድረግ የመጀመሪያ ጉዞውን ወደ አርባ ምንጭ ማድረጉን ተናግረዋል። "ምርጫ ቦርድ ሀገሪቱ ውስጥ ባሉ ክልሎች ተዘዋውረን ህዝባዊ ስብሰባ እንድናደግ፣ ፊርማ እንድናሰባስብ፣ ቢሮም እንድንከፍት የሚያግዙ የትብብር ደብዳቤዎችን" ጽፎልናል የሚሉት ወ/ሮ ቀለብ በአርባ ምንጭ ከተማ ስብሰባ ለማድረግ ፓርቲው ከከተማ አስተዳደሩ ቀደም ብሎ ፍቃድ ተሰጥቶት እንደነበርም ተናግረዋል። "ስለዚህ ዋናው ዓላማው የህዝብ ስብሰባ ለማድረግ እና እዛው ቢሮ ለመክፈት ታስቦ ነው ጉዞ የተደረገው" ሲሉም አክለዋል። በዚህ መሰረት የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ እስክንድር ነጋን እና ሌሎች ሶስት አመራሮች ትላንት ጠዋት ወደ አርባ ምንጭ መጓዛቸውን ጠቅሰዋል። ሆኖም ፓርቲው ቀደም ብሎ ከተሰጠው ፍቃድ በተቃራኒ ማድረግ እንዳይችል መከልከሉን ሃላፊዋ ገልጸዋል። "እንዴት ልትከለክሉን ቻላችሁ? ብለው ሲጠይቁ 'ከላይ በመጣ ትእዛዝ ነው' የሚል መልስ ነው የሰጧቸው" ብለዋል። ወ/ሮ ቀለብ ስብሰባው ከተከለከለ በኋላ ግን አመራሮች ሀገር አቀፍ ፓርቲ ለመመስረት የሚያስችለውን ፊርማ በከተማው የተለያዩ አከባቢዎች እየተዘዋወሩ እየሰባሰቡ መዋላቸውን እና ማምሻውን ወደ ሆቴል ከሄዱ በኋላ በፖሊስ መያዛቸውን ገልጸዋል። "አቶ እስክንድር ስልኬ ላይ ደውለው በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደዋሉ ነገሩኝ" ብለዋል። አመራሮቹ ለሊቱን 'በማይመች ሁኔታ' ፖሊስ ጣቢያ ማደራቸውን የገለጹት ሃላፊዋ የነበሩበት ፖሊስ ጣቢያ ቃላቸውን ሊሰጡ የነበረ ቢሆንም ወደ ጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ መወሰዳቸውን ጠቁመዋል። ሆኖም በዛሬው እለት መፈታታቸውንና ወደ አውሮፕላን ማረፊያ ማቅናታቸውን ቢቢሲ መረዳት ችሏል። የባልደራስ አመራሮችን በቁጥጥር ስር ለምን ዋሉ የሚለውን በተመለከተ ምላሽ ለማግኘት የጋሞ ዞን ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት በተደጋጋሚ ስልክ ብንደውልም ስልክ ባለማንሳታቸው ምላሻቸውን ማካተት አልቻልንም።
https://www.bbc.com/amharic/news-61172477
2health
ኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ክትባትን በመጪው ሚያዚያ ወር እንደምታስገባ ገለጸች
ኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ክትባትን በመጪው ሚያዚያ ወር ወደ አገር ውስት እንደምታስገባ ገለጸች። የሚገባው የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባት ቢያንስ 20 ከመቶ ለሚሆኑ ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚዳረስ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ይህንን የክትባት ሥራ የሚያስተባብር ግብረሃይል በብሄራዊ ደረጃ መቋቋሙም ተገልጿል። በጤና ሚኒስቴር የክትባትና ተያያዥ ጉዳዮች የሚኒስትሯ ከፍተኛ አማካሪ ዶክተር ሙሉቀን ዮሃንስ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በሰጡት መረጃ መሰረት፣ ከጤና ሚኒስቴር፣ ከጠቅላይ ሚኒስቴር እና ከፕሬዚዳንት ፅ/ት ቤቶች ጋር በመቀናጀት የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባትን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ዝግጅቶች እየተደረጉ ነው፡፡ ክትባቱን ለመውሰድ ቅድሚያ የሚያገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የዓለም ጤና ድርጅት ባወጣው መስፈርት መሰረት የጤና ባለሙያዎች፣ እድሜያቸው የገፉ፣ ተደራራቢ የጤና ችግር ያለባቸው ሰዎችና መጪውን ምርጫ ተከትሎ ተደራራቢ ስራና ሃላፊነት ያለባቸው የጥበቃ ኃይሎች መሆናቸውን ተገልጿል። የክትባቱ ብዛት እየታየም ለአውቶብስና የባቡር አሽከርካሪዎች እንዲሁም በመንግስት ትምህርት ቤቶች ለሚሰሩ መምህራን እንዲዳርስ የሚደረግ መሆኑን ተመልክቷል። ኢትዮጵያ ክትባቱን ወደ ሃገር ውስጥ የምታስገባው ‹‹ኮቫክስ›› በተሰኘው ዓለም አቀፍ የክትባት ሸማች ማህበር መሆኑንም ዶክተር ሙሉቀን ተናግረዋል። የመጀመሪያው ዙር ክትባት እስከ መጪው ሚያዝያ ወር ወደ ሀገር ውስጥ እንደሚገባና በፈረንጆቹ አቆጣጠር እስከ 2021 መጨረሻ ድረስ ደግሞ ክትባቱ ሙሉ በሙሉ ወደ ሃገር ውስጥ እንደሚገባም አማካሪው ጠቁመዋል። ኮቫክስ (COVAX) ምጣኔ ኀብታቸው ደካማና መካከለኛ ለሆኑ አገራት ክትባቱን ለማቅረብ ያለመ፣ በዓለም ጤና ድርጅት እና በሌሎች ዓለም አቀፍ የጤና ተቋማት የተመሰረተ ኢኒሼቲቭ ነው። ሁሉም የአፍሪካ አገራት ይህንን ኢኒሼቲቭ ተቀብለውታል። ይህም ማለት አፍሪካ በዚህ ኢኒሼቲቭ በኩል ክትባቱ ፍቃድ ካገኘና ከፀደቀ በኋላ፣ 220 ሚሊዮን ክትባቶችን ታገኛለች። እኤአ በ2021 መጨረሻ ላይ ኮቫክስ 2 ቢሊዮን የኮቪድ-19 ክትባቶችን ለመግዛት እቅድ ይዟል።አፍሪካ ለአህጉሩ የሚሰራጭ ለጊዜው 270 ሚሊዮን 'ዶዝ' (መጠን) የኮቪድ-19 ክትባት በአፍሪካ ሕብረት በኩል ማግኘቷ ተገለፀ። አጠቃላይ የተገኘው ክትባት በዚህ ዓመት ጥቅም ላይ እንደሚውል የሕብረቱ መሪ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚደንት ሲሪል ራማፎሳ ቃል ገብተዋል። ይህ ክትባት ከዚህ ቀደም ቃል ከተገባው 600 ሚሊየን 'ዶዝ 'ተጨማሪ ቢሆንም አሁንም ግን ሙሉ አህጉሩን ለመከተብ በቂ አይደለም። በዚህም የዓለማችን ድሃ አገራት ከሃብታም አገራት ይልቅ ክትባቱን ለመከተብ ረዥም ጊዜ ሊጠብቁ ይችላሉ የሚል ስጋት አለ። ምንም እንኳን በአፍሪካ በቫይረሱ የተያዙ እና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በንፅፅር ዝቅተኛ ቢሆንም በአንዳንድ አገራት በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በድጋሜ እየጨመረ ነው። አፍሪካ ለአህጉሩ የሚሰራጭ ለጊዜው 270 ሚሊዮን 'ዶዝ' (መጠን) የኮቪድ-19 ክትባት በአፍሪካ ሕብረት በኩል ማግኘቷ መገለፁ ይታወሳል። አጠቃላይ የተገኘው ክትባት በዚህ ዓመት ጥቅም ላይ እንደሚውል የሕብረቱ መሪ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚደንት ሲሪል ራማፎሳ ቃል ገብተዋል። ይህ ክትባት ከዚህ ቀደም ቃል ከተገባው 600 ሚሊየን 'ዶዝ 'ተጨማሪ ቢሆንም አሁንም ግን ሙሉ አህጉሩን ለመከተብ በቂ አይደለም። በዚህም የዓለማችን ድሃ አገራት ከሃብታም አገራት ይልቅ ክትባቱን ለመከተብ ረዥም ጊዜ ሊጠብቁ ይችላሉ የሚል ስጋት አለ። ምንም እንኳን በአፍሪካ በቫይረሱ የተያዙ እና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በንፅፅር ዝቅተኛ ቢሆንም በአንዳንድ አገራት በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በድጋሜ እየጨመረ ነው።
ኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ክትባትን በመጪው ሚያዚያ ወር እንደምታስገባ ገለጸች ኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ክትባትን በመጪው ሚያዚያ ወር ወደ አገር ውስት እንደምታስገባ ገለጸች። የሚገባው የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባት ቢያንስ 20 ከመቶ ለሚሆኑ ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚዳረስ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ይህንን የክትባት ሥራ የሚያስተባብር ግብረሃይል በብሄራዊ ደረጃ መቋቋሙም ተገልጿል። በጤና ሚኒስቴር የክትባትና ተያያዥ ጉዳዮች የሚኒስትሯ ከፍተኛ አማካሪ ዶክተር ሙሉቀን ዮሃንስ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በሰጡት መረጃ መሰረት፣ ከጤና ሚኒስቴር፣ ከጠቅላይ ሚኒስቴር እና ከፕሬዚዳንት ፅ/ት ቤቶች ጋር በመቀናጀት የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባትን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ዝግጅቶች እየተደረጉ ነው፡፡ ክትባቱን ለመውሰድ ቅድሚያ የሚያገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የዓለም ጤና ድርጅት ባወጣው መስፈርት መሰረት የጤና ባለሙያዎች፣ እድሜያቸው የገፉ፣ ተደራራቢ የጤና ችግር ያለባቸው ሰዎችና መጪውን ምርጫ ተከትሎ ተደራራቢ ስራና ሃላፊነት ያለባቸው የጥበቃ ኃይሎች መሆናቸውን ተገልጿል። የክትባቱ ብዛት እየታየም ለአውቶብስና የባቡር አሽከርካሪዎች እንዲሁም በመንግስት ትምህርት ቤቶች ለሚሰሩ መምህራን እንዲዳርስ የሚደረግ መሆኑን ተመልክቷል። ኢትዮጵያ ክትባቱን ወደ ሃገር ውስጥ የምታስገባው ‹‹ኮቫክስ›› በተሰኘው ዓለም አቀፍ የክትባት ሸማች ማህበር መሆኑንም ዶክተር ሙሉቀን ተናግረዋል። የመጀመሪያው ዙር ክትባት እስከ መጪው ሚያዝያ ወር ወደ ሀገር ውስጥ እንደሚገባና በፈረንጆቹ አቆጣጠር እስከ 2021 መጨረሻ ድረስ ደግሞ ክትባቱ ሙሉ በሙሉ ወደ ሃገር ውስጥ እንደሚገባም አማካሪው ጠቁመዋል። ኮቫክስ (COVAX) ምጣኔ ኀብታቸው ደካማና መካከለኛ ለሆኑ አገራት ክትባቱን ለማቅረብ ያለመ፣ በዓለም ጤና ድርጅት እና በሌሎች ዓለም አቀፍ የጤና ተቋማት የተመሰረተ ኢኒሼቲቭ ነው። ሁሉም የአፍሪካ አገራት ይህንን ኢኒሼቲቭ ተቀብለውታል። ይህም ማለት አፍሪካ በዚህ ኢኒሼቲቭ በኩል ክትባቱ ፍቃድ ካገኘና ከፀደቀ በኋላ፣ 220 ሚሊዮን ክትባቶችን ታገኛለች። እኤአ በ2021 መጨረሻ ላይ ኮቫክስ 2 ቢሊዮን የኮቪድ-19 ክትባቶችን ለመግዛት እቅድ ይዟል።አፍሪካ ለአህጉሩ የሚሰራጭ ለጊዜው 270 ሚሊዮን 'ዶዝ' (መጠን) የኮቪድ-19 ክትባት በአፍሪካ ሕብረት በኩል ማግኘቷ ተገለፀ። አጠቃላይ የተገኘው ክትባት በዚህ ዓመት ጥቅም ላይ እንደሚውል የሕብረቱ መሪ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚደንት ሲሪል ራማፎሳ ቃል ገብተዋል። ይህ ክትባት ከዚህ ቀደም ቃል ከተገባው 600 ሚሊየን 'ዶዝ 'ተጨማሪ ቢሆንም አሁንም ግን ሙሉ አህጉሩን ለመከተብ በቂ አይደለም። በዚህም የዓለማችን ድሃ አገራት ከሃብታም አገራት ይልቅ ክትባቱን ለመከተብ ረዥም ጊዜ ሊጠብቁ ይችላሉ የሚል ስጋት አለ። ምንም እንኳን በአፍሪካ በቫይረሱ የተያዙ እና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በንፅፅር ዝቅተኛ ቢሆንም በአንዳንድ አገራት በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በድጋሜ እየጨመረ ነው። አፍሪካ ለአህጉሩ የሚሰራጭ ለጊዜው 270 ሚሊዮን 'ዶዝ' (መጠን) የኮቪድ-19 ክትባት በአፍሪካ ሕብረት በኩል ማግኘቷ መገለፁ ይታወሳል። አጠቃላይ የተገኘው ክትባት በዚህ ዓመት ጥቅም ላይ እንደሚውል የሕብረቱ መሪ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚደንት ሲሪል ራማፎሳ ቃል ገብተዋል። ይህ ክትባት ከዚህ ቀደም ቃል ከተገባው 600 ሚሊየን 'ዶዝ 'ተጨማሪ ቢሆንም አሁንም ግን ሙሉ አህጉሩን ለመከተብ በቂ አይደለም። በዚህም የዓለማችን ድሃ አገራት ከሃብታም አገራት ይልቅ ክትባቱን ለመከተብ ረዥም ጊዜ ሊጠብቁ ይችላሉ የሚል ስጋት አለ። ምንም እንኳን በአፍሪካ በቫይረሱ የተያዙ እና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በንፅፅር ዝቅተኛ ቢሆንም በአንዳንድ አገራት በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በድጋሜ እየጨመረ ነው።
https://www.bbc.com/amharic/news-55883638
0business
የዓለማችን ውዱ የመኪና ማቆሚያ ቦታ በ1.3 ሚሊየን ዶላር ተሸጠ
ሆንግ ኮንግ ውስጥ አንድ የመኪና ማቆሚያ አገልግሎት የሚሰጥ ቦታ በዓለማችን ውድ በሆነ 1.3 ሚሊየን ዶላር ዋጋ መሸጡ ተሰምቷል። የሆንግ ኮንግ መገናኛ ብዙሀን እንደዘገቡት በከተማዋ በጣም ምርጥ በሚባለው መኖሪያ አካባቢ የሚገኘው የመኪና ማቆሚያ እጅግ ቅንጡ ከሚባሉት መካከል ነው። 'ማውንት ኒኮልሰን' የተባለው የግንባታና የቤቶች ሽያጭ ድርጅት እሲያ ውስጥ በጣም ውድ የሆኑ መኖሪያ ቤቶችን የሚያስተዳድር ሲሆን፤ በሆንግ ኮንግም 'ቪችቶሪያ ሃርበር' የተባለውን ውድ አካባቢም ያስተዳድራል። ይሄው ድርጅት ነው ታዲያ በዓለማችን ውድ የተባለውን የመኪና ማቆሚያ ቦታ የሚያስተዳድረው። ሆንግ ኮንግ በጣም የተጨናነቀች ከተማ መሆኗን ተከትሎ በ1.3 ሚሊየን ዶላር ዋጋ የተሸጠው ቦታ ለመኖሪያም ሆነ ለመኪና ማቆሚያ አገልግሎት ቢውል የበርካታ ሰዎችን ቀልብ መሳብ እንደሚችል ከወዲሁ ተገምቷል። በዓለማችን ከፍተኛ የገንዘብ ዝውውር ከሚካሄድባቸው ከተሞች አንዷ የሆነችው ሆንግ ኮንግ በጣም ውድ የሚባሉ መኖሪያ ቤቶች እንደሚገኙባት ይገመታል። ከተማዋ ለኑሮ ምቹ ብትሆንም የኑሮ ዋጋ ግን በጣም ከፍተኛ እንደሆነ ይነገራል። ከዚህ በፊት ለመኪና ማቆሚያ ቦታ ከፍተኛው ዋጋ የተከፈለው በዛው ሆንግ ኮንግ ውስጥ ሲሆን፤ በወቅቱ በአውሮፓውያኑ 2019፤ 980 ሺህ ዶላር ነበር ወጪ የተደረገበት። ለማውንት ኒኮልሰን የሽያጭ ሥራውን የሚያከናውንለት 'ዊሎክ ፕሮፐርቲስ' በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጥ ከቢቢሲ የተጠየቀ ቢሆንም እስካሁን ምላሽ አልሰጠም። በቅርብ ወራት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስርጫት በመጠኑም ቢሆን መቀነሱን ተከትሎ በሆንግ ኮንግ የንግድ እንቅስቃሴዎች እየደሩ ነው። ገዢዎችም ቢሆኑ በርካታ ሚሊየኖችን እያወጡ ቅንጡ ቤቶችና ሌሎች ቦታዎችን እየገዙ ነው። ባለፈው ወር በከተማዋ የሚገኝ አንድ ቅንጡ መኖሪያ ቤት የዓለም ሪከርድ በሆነ 210 ሺህ ዶላር በወር ተከራይቷል።
የዓለማችን ውዱ የመኪና ማቆሚያ ቦታ በ1.3 ሚሊየን ዶላር ተሸጠ ሆንግ ኮንግ ውስጥ አንድ የመኪና ማቆሚያ አገልግሎት የሚሰጥ ቦታ በዓለማችን ውድ በሆነ 1.3 ሚሊየን ዶላር ዋጋ መሸጡ ተሰምቷል። የሆንግ ኮንግ መገናኛ ብዙሀን እንደዘገቡት በከተማዋ በጣም ምርጥ በሚባለው መኖሪያ አካባቢ የሚገኘው የመኪና ማቆሚያ እጅግ ቅንጡ ከሚባሉት መካከል ነው። 'ማውንት ኒኮልሰን' የተባለው የግንባታና የቤቶች ሽያጭ ድርጅት እሲያ ውስጥ በጣም ውድ የሆኑ መኖሪያ ቤቶችን የሚያስተዳድር ሲሆን፤ በሆንግ ኮንግም 'ቪችቶሪያ ሃርበር' የተባለውን ውድ አካባቢም ያስተዳድራል። ይሄው ድርጅት ነው ታዲያ በዓለማችን ውድ የተባለውን የመኪና ማቆሚያ ቦታ የሚያስተዳድረው። ሆንግ ኮንግ በጣም የተጨናነቀች ከተማ መሆኗን ተከትሎ በ1.3 ሚሊየን ዶላር ዋጋ የተሸጠው ቦታ ለመኖሪያም ሆነ ለመኪና ማቆሚያ አገልግሎት ቢውል የበርካታ ሰዎችን ቀልብ መሳብ እንደሚችል ከወዲሁ ተገምቷል። በዓለማችን ከፍተኛ የገንዘብ ዝውውር ከሚካሄድባቸው ከተሞች አንዷ የሆነችው ሆንግ ኮንግ በጣም ውድ የሚባሉ መኖሪያ ቤቶች እንደሚገኙባት ይገመታል። ከተማዋ ለኑሮ ምቹ ብትሆንም የኑሮ ዋጋ ግን በጣም ከፍተኛ እንደሆነ ይነገራል። ከዚህ በፊት ለመኪና ማቆሚያ ቦታ ከፍተኛው ዋጋ የተከፈለው በዛው ሆንግ ኮንግ ውስጥ ሲሆን፤ በወቅቱ በአውሮፓውያኑ 2019፤ 980 ሺህ ዶላር ነበር ወጪ የተደረገበት። ለማውንት ኒኮልሰን የሽያጭ ሥራውን የሚያከናውንለት 'ዊሎክ ፕሮፐርቲስ' በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጥ ከቢቢሲ የተጠየቀ ቢሆንም እስካሁን ምላሽ አልሰጠም። በቅርብ ወራት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስርጫት በመጠኑም ቢሆን መቀነሱን ተከትሎ በሆንግ ኮንግ የንግድ እንቅስቃሴዎች እየደሩ ነው። ገዢዎችም ቢሆኑ በርካታ ሚሊየኖችን እያወጡ ቅንጡ ቤቶችና ሌሎች ቦታዎችን እየገዙ ነው። ባለፈው ወር በከተማዋ የሚገኝ አንድ ቅንጡ መኖሪያ ቤት የዓለም ሪከርድ በሆነ 210 ሺህ ዶላር በወር ተከራይቷል።
https://www.bbc.com/amharic/57354351
3politics
ዩክሬን ፡ ዩኬ በዩክሬን ያለውን ውጥረት ተከትሎ በርካታ ወታደሮችን ለማሰማራት እያሰበች ነው
ዩናይትድ ኪንግደም በምሥራቅ አውሮፓ የምታሰማራውን ወታደሮቿን በእጥፍ ለማሳደግ እያሰበች መሆኑ ተገለጸ። ይህ የተሰማው ሚኒስትሮች በዩክሬን ላይ ከፍተኛ ውጥረት በነገሰበት ወቅት ሩሲያ ላይ ጫና ለማሳደር አማራጮችን እያሰላሰሉ ባሉበት ወቅት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ወታደሮችን ለማሰማራት መታሰቡ "ለክሬምሊን ግልጽ መልእክት ያስተላልፋል" ብለዋል። በሌላ በኩል የመከላከያ እና የውጭ ጉዳይ ኃላፊዎች ውጥረቱን ለማርገብ በሞስኮ ከሚገኙ አቻዎቻቸው ጋር ለመገናኘት በዝግጅት ላይ ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስም በቀጣይ ቀናት ከሩሲያው ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በስልክ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል። በዚህ ሳምንት ምሥራቅ አውሮፓን የሚጎበኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ዩኬ "የሩሲያን የጥፋት እንቅስቃሴ እንደማትታገስ" እና ሁል ጊዜም ከሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ድርጅት [ኔቶ] አጋሮቻቸው ጋር እንደሚቆሙ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጨምረውም ፕሬዚደንት ፑቲን የደም መፋሰስ እና የጥፋት መንገድን ከመረጡ ለአውሮፓ አሳዛኝ ነው የሚሆነው። ዩክሬን የራሷን መጻኢ እድል ለመምረጥ ነጻ መሆን አለባት " ብለዋል። " የኔቶ አጋሮቻችንን በየብስ፣ በባህር እና በአየር ለመደገፍ ወታደሮቻችን በሚቀጥለው ሳምንት በአውሮፓ ለመሰማራት እንዲዘጋጁ ትዕዛዝ ሰጥቻለሁ" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ። ሩሲያ በዩክሬን ድንበር አቅራቢያ 100 ሺህ ወታደሮችን፣ ታንኮችን፣ ከባድ መሳሪያዎችን እና ሚሳይሎችን አስፍራለች። ይሁን እንጂ ከአውሮፓ እና ከሩሲያ ጋር የምትዋሰነውን የቀድሞዋን ሶቭየት ሪፐብሊክ ለመውረር አቅዳለች መባሉን አስተባብላለች። ዩናይትድ ኪንግደም በኢስቶኒያ የሰፈሩ ከ900 በላይ የጦር መኮንኖች ያሏት ሲሆን ከ100 በላይ የሚሆኑት ለሥልጠና ተልዕኮ ዩክሬን ይገኛሉ። 150 የሚጠጉ የጦር ፈረሰኞች ቡድን ደግሞ ወደ ፖላንድ ተሰማርቷል። የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ሰኞ ዕለት በሩሲያ ስትራቴጂያዊ እና የፋይናንስ ፍላጎቶች ላይ ጠንካራ ማዕቀብ ላይ ፓርላማው ያሳለፈውን ውሳኔ ያሳውቃል ተብሎ ይጠበቃል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የዩናይትድ ኪንግደም ባለሥልጣናት አገሪቷ ያቀረበችው ሃሳብ በዝርዝር ተነጋግሮ ለመቋጨት ወደ ብራስልስ ያቀናሉ ተብሏል።
ዩክሬን ፡ ዩኬ በዩክሬን ያለውን ውጥረት ተከትሎ በርካታ ወታደሮችን ለማሰማራት እያሰበች ነው ዩናይትድ ኪንግደም በምሥራቅ አውሮፓ የምታሰማራውን ወታደሮቿን በእጥፍ ለማሳደግ እያሰበች መሆኑ ተገለጸ። ይህ የተሰማው ሚኒስትሮች በዩክሬን ላይ ከፍተኛ ውጥረት በነገሰበት ወቅት ሩሲያ ላይ ጫና ለማሳደር አማራጮችን እያሰላሰሉ ባሉበት ወቅት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ወታደሮችን ለማሰማራት መታሰቡ "ለክሬምሊን ግልጽ መልእክት ያስተላልፋል" ብለዋል። በሌላ በኩል የመከላከያ እና የውጭ ጉዳይ ኃላፊዎች ውጥረቱን ለማርገብ በሞስኮ ከሚገኙ አቻዎቻቸው ጋር ለመገናኘት በዝግጅት ላይ ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስም በቀጣይ ቀናት ከሩሲያው ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በስልክ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል። በዚህ ሳምንት ምሥራቅ አውሮፓን የሚጎበኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ዩኬ "የሩሲያን የጥፋት እንቅስቃሴ እንደማትታገስ" እና ሁል ጊዜም ከሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ድርጅት [ኔቶ] አጋሮቻቸው ጋር እንደሚቆሙ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጨምረውም ፕሬዚደንት ፑቲን የደም መፋሰስ እና የጥፋት መንገድን ከመረጡ ለአውሮፓ አሳዛኝ ነው የሚሆነው። ዩክሬን የራሷን መጻኢ እድል ለመምረጥ ነጻ መሆን አለባት " ብለዋል። " የኔቶ አጋሮቻችንን በየብስ፣ በባህር እና በአየር ለመደገፍ ወታደሮቻችን በሚቀጥለው ሳምንት በአውሮፓ ለመሰማራት እንዲዘጋጁ ትዕዛዝ ሰጥቻለሁ" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ። ሩሲያ በዩክሬን ድንበር አቅራቢያ 100 ሺህ ወታደሮችን፣ ታንኮችን፣ ከባድ መሳሪያዎችን እና ሚሳይሎችን አስፍራለች። ይሁን እንጂ ከአውሮፓ እና ከሩሲያ ጋር የምትዋሰነውን የቀድሞዋን ሶቭየት ሪፐብሊክ ለመውረር አቅዳለች መባሉን አስተባብላለች። ዩናይትድ ኪንግደም በኢስቶኒያ የሰፈሩ ከ900 በላይ የጦር መኮንኖች ያሏት ሲሆን ከ100 በላይ የሚሆኑት ለሥልጠና ተልዕኮ ዩክሬን ይገኛሉ። 150 የሚጠጉ የጦር ፈረሰኞች ቡድን ደግሞ ወደ ፖላንድ ተሰማርቷል። የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ሰኞ ዕለት በሩሲያ ስትራቴጂያዊ እና የፋይናንስ ፍላጎቶች ላይ ጠንካራ ማዕቀብ ላይ ፓርላማው ያሳለፈውን ውሳኔ ያሳውቃል ተብሎ ይጠበቃል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የዩናይትድ ኪንግደም ባለሥልጣናት አገሪቷ ያቀረበችው ሃሳብ በዝርዝር ተነጋግሮ ለመቋጨት ወደ ብራስልስ ያቀናሉ ተብሏል።
https://www.bbc.com/amharic/news-60187251
3politics
እነ አቶ ጃዋር መሐመድ ከሦስት ሳምንት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት በአካል ቀረቡ
በረሃብ አድማ ላይ እንደሚገኙ የሚነገረው እነ አቶ ጃዋር መሐመድ ዛሬ ረፋድ ላይ ፍርድ ቤት ለነበራቸው ቀጠሮ ሲቀርቡ አካላቸው ደክሞ እና ከስተው ታዩ። የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ የክስ መዝገብ የተከሰሱ የ24 ሰዎችን የእምነት ክህደት ቃል ለመቀበል ዛሬ ጠዋት ላይ ቀጠሮ ይዞ ነበር። ከእነዚህ መካከል እነ አቶ ጃዋር መሐመድ እና በቀለ ገርባን ጨምሮ 21 ሰዎች በፍርድ ቤት ተገኝተው ነበር። ይኹን እንጂ ጠበቆች ደንበኞቻቸው እነ አቶ ጃዋር መሐመድ፣ በቀለ ገርባ፣ ሐምዛ አዳነ እና ደጀኔ ጣፋ የረሃብ አድማ ከጀመሩ 33 ቀናት እንዳለፋቸው ለፍርድ ቤት ተናግረው፤ ደንበኞቻቸው አሁን ባሉበት ሁኔታ የእምነት ክህደት ቃላቸውን መስጠት አይችሉም በማለት ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። ዐቃቤ ሕግም ተለዋጭ ቀጠሮ ቢሰጥ እንደማይቃወም ለፍርድ ቤቱ ተናግሯል። በዚህም መሠረት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የፀረ ሽብርና ሕገ-መንግሥታዊ ጉዳዮች አንደኛ ችሎት የተከሳሾችን የእምነት ክህደት ቃል ለመቀበል ለመጋቢት 6/2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። ከድምጻዊ ሃጫሉ ግድያ በኋላ በቁጥጥር ስር የዋሉት እና ክስ ተመስርቶባቸው በእስር የሚገኙት እነ አቶ ጃዋር መሐመድ፣ በቀለ ገርባ፣ ሸምሰዲን ጠሃ እና ሃምዛ አዳነ በፖለቲከኞች እና በቤተሰብ አባላቶቻቸው ላይ የሚደርሰውን እስር እና ወከባ በመቃወም የረሃብ አድማ ማድረግ ከጀመሩ ከ33 ቀናት በላይ እንዳስቆጠሩ ጠበቆቻቸው ይናገራሉ። የተከሳሽ ጠበቆች ምን አሉ? የተከሳሽ ጠበቆች "መንግሥት እና ሕግ ባለበት አገር ደብዳቤ ስናመላልስ ደንበኞቻችን ሕይወታቸው ሊያልፍብን ነው" በማለት የደንበኞቻቸው በሕይወት የመኖር መብት አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኝ ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል። ከደንበኞቻቸው መካከል አቶ ጀዋር መሐመድ እና አቶ ሐምዛ አዳነን ጨምሮ አራት ተከሳሾች በጠና ታምመው እንደሚገኙ በዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ ጠበቆች ለችሎቱ አስረድተዋል። ተከሳሾች የሚገኙበት ሁኔታ የቢቢሲ ሪፖርተር እንደተመለከተው ዛሬ ጋዜጠኞች ወደ ፍርድ ቤቱ ሲገቡ፤ አቶ በቀለ ገርባ ጭንቅላታቸውን በተከሳሽ አረፋት አቡበከር ላይ እንዲሁም እግራቸውን ደግሞ በአቶ ጃዋር መሐመድ ላይ አድርገው በአግዳሚ ወንበር ላይ በጀርባቸው ተኝተው ነበር። አቶ ጃዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ እና አቶ ሐምዛ አዳነ ሰውነታቸው እጅጉን ከስቶ እና ጸጉራቸውን ተላጭተው ታይተዋል። አቶ ሐምዛ አዳነ በሰዎች ድጋፍ ወደ ችሎቱ ሲገቡ የቢቢሲ ሪፖርተር ተመልክቷል። ችሎቱ ሲጀመር አቶ በቀለ ገርባ በሰዎች ድጋፍ በጀርባቸው ተኝተው ከነበሩበት አግዳሚ ወንበር ተነስተው ተቀምጠዋል። የተከሳሽ ቤተሰብ አባላት መካከል አንዳንዶቹ በችሎት ውስጥ ሲያለቅሱ ሪፖርተራችን ተመልክቷል። እነ አቶ ጃዋር ለመጨረሻ ጊዜ ጋዜጠኞች እና ታዳሚዎች በተገኙበት በፍርድ ቤት ቀርበው የታዩት ጥር 27/2013 ዓ.ም ነበር። በዕለቱ የችሎት ውሎውን ለመዘገብ እና ለመከታተል በስፍራው የተገኙ ጋዜጠኞች እና የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ተቋም ሠራተኞች ተፈትሸው ወደ ችሎቱ ከገቡ በኋላ በጸጥታ አስከባሪዎች ከችሎቱ እንዲወጡ ተደርገው ነበር። 'የደረሰብን ክፍት ከፍተኛ ነው' በዛሬው የችሎት ውሎ ከተከሳሾች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ በቀለ ገርባ ከተቀመጡበት ሳይነሱ እንዲናገሩ ተፈቅዶላቸዋል። አቶ በቀለ ለፍርድ ቤቱ ክብር እንዳላቸው ተናግረው፤ ለሕክምና ወደ ላንድማርክ ሆስፒታል እየተወሰዱ ሳለ፤ መንገድ ተዘግቶባቸው በኃይል ወደ ጦር ኃይሎች ሆስፒታል መወሰዳቸውን ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል። "ይህ ቡድን የፍርድ ቤት ትዕዛዝን የማያከብር ነው" ያሉት አቶ በቀለ ገርባ፤ "ጨካኝ የሆነውን ሥርዓትን መታገል እንፈልጋለን። እኛ ላይ የደረሰው ክፋት ከፍተኛ ነው" ብለዋል። አሁን ባሉበት ሁኔታ ወደፊት በችሎት መቅረብ እንደማይገባቸው የተናገሩት አቶ በቀለ፤ ወደፊት ጤናቸው የሚመለስ ከሆነ ለጤና መቃውስ ዳርገውናል ያሉትን አካል ካሳ እንደሚጠይቁ ተናግረዋል። አቶ በቀለ ደብዳቤ በመጻፍ ላንድማርክ በተሰኘው የግል ሕክምና ተቋም እንዳይታከሙ የከለከሉት ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ መሆናቸውን ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል። እነ አቶ ጃዋር መሐመድ የረሃብ አድማውን እያደረጉ ያሉት በፖለቲከኞች ላይ የሚደርሰውን እንግልት እና እስር፣ እነሱን ለመጠየቅና የችሎት ሂደታቸውን ለመከታተል ወደ ፍርድ ቤት በሚመጡ ሰዎች ላይ የሚፈጸም እስር እና ወከባ እንዲቆም ለመጠየቅ እንደሆነም ቢቢሲ ከጠበቆቻቸው ለመረዳት ችሏል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) የረሃብ አድማው ተከሳሾችን የከፋ አደጋ ላይ እንዳይጥል የቅርብ ክትትል ማድረግ እንደሚያስፈልግ መግለጻቸውን ኮሚሽኑ ባሳለፍነው አርብ ባወጣው መግለጫ አስነብቧል። "ለታሳሪዎች ምክንያታዊ የሆኑ ጥያቄዎች ተገቢውን አፋጣኝ ምላሽ መስጠትና የእስረኞች ጠያቂዎችን በማረሚያ ቤቱም ሆነ በፍርድ ቤቶች በአግባቡ ማስተናገድ ይገባል" ስለማለታቸው በመግለጫው ሰፍሯል። የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በቁጥጥር ሥር የዋሉት እነ አቶ ጃዋር ከቀረቡባቸው ተደራራቢ አስር ክሶች ስድስቱ እንዲቋረጡ ፍርድ መወሰኑ ይታወሳል። የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ፤ የቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀል አዋጅ፤ የጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ የመተላለፍ ክሶች ከተመሰረቱባቸው ክሶች መካከል ሲሆኑ፤ እንዲቋረጡ የተደረጉት ክሶች የጦር መሳሪያ አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅ 1177/2021 ጋር የተያያዙ ናቸው።
እነ አቶ ጃዋር መሐመድ ከሦስት ሳምንት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት በአካል ቀረቡ በረሃብ አድማ ላይ እንደሚገኙ የሚነገረው እነ አቶ ጃዋር መሐመድ ዛሬ ረፋድ ላይ ፍርድ ቤት ለነበራቸው ቀጠሮ ሲቀርቡ አካላቸው ደክሞ እና ከስተው ታዩ። የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ የክስ መዝገብ የተከሰሱ የ24 ሰዎችን የእምነት ክህደት ቃል ለመቀበል ዛሬ ጠዋት ላይ ቀጠሮ ይዞ ነበር። ከእነዚህ መካከል እነ አቶ ጃዋር መሐመድ እና በቀለ ገርባን ጨምሮ 21 ሰዎች በፍርድ ቤት ተገኝተው ነበር። ይኹን እንጂ ጠበቆች ደንበኞቻቸው እነ አቶ ጃዋር መሐመድ፣ በቀለ ገርባ፣ ሐምዛ አዳነ እና ደጀኔ ጣፋ የረሃብ አድማ ከጀመሩ 33 ቀናት እንዳለፋቸው ለፍርድ ቤት ተናግረው፤ ደንበኞቻቸው አሁን ባሉበት ሁኔታ የእምነት ክህደት ቃላቸውን መስጠት አይችሉም በማለት ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። ዐቃቤ ሕግም ተለዋጭ ቀጠሮ ቢሰጥ እንደማይቃወም ለፍርድ ቤቱ ተናግሯል። በዚህም መሠረት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የፀረ ሽብርና ሕገ-መንግሥታዊ ጉዳዮች አንደኛ ችሎት የተከሳሾችን የእምነት ክህደት ቃል ለመቀበል ለመጋቢት 6/2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። ከድምጻዊ ሃጫሉ ግድያ በኋላ በቁጥጥር ስር የዋሉት እና ክስ ተመስርቶባቸው በእስር የሚገኙት እነ አቶ ጃዋር መሐመድ፣ በቀለ ገርባ፣ ሸምሰዲን ጠሃ እና ሃምዛ አዳነ በፖለቲከኞች እና በቤተሰብ አባላቶቻቸው ላይ የሚደርሰውን እስር እና ወከባ በመቃወም የረሃብ አድማ ማድረግ ከጀመሩ ከ33 ቀናት በላይ እንዳስቆጠሩ ጠበቆቻቸው ይናገራሉ። የተከሳሽ ጠበቆች ምን አሉ? የተከሳሽ ጠበቆች "መንግሥት እና ሕግ ባለበት አገር ደብዳቤ ስናመላልስ ደንበኞቻችን ሕይወታቸው ሊያልፍብን ነው" በማለት የደንበኞቻቸው በሕይወት የመኖር መብት አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኝ ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል። ከደንበኞቻቸው መካከል አቶ ጀዋር መሐመድ እና አቶ ሐምዛ አዳነን ጨምሮ አራት ተከሳሾች በጠና ታምመው እንደሚገኙ በዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ ጠበቆች ለችሎቱ አስረድተዋል። ተከሳሾች የሚገኙበት ሁኔታ የቢቢሲ ሪፖርተር እንደተመለከተው ዛሬ ጋዜጠኞች ወደ ፍርድ ቤቱ ሲገቡ፤ አቶ በቀለ ገርባ ጭንቅላታቸውን በተከሳሽ አረፋት አቡበከር ላይ እንዲሁም እግራቸውን ደግሞ በአቶ ጃዋር መሐመድ ላይ አድርገው በአግዳሚ ወንበር ላይ በጀርባቸው ተኝተው ነበር። አቶ ጃዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ እና አቶ ሐምዛ አዳነ ሰውነታቸው እጅጉን ከስቶ እና ጸጉራቸውን ተላጭተው ታይተዋል። አቶ ሐምዛ አዳነ በሰዎች ድጋፍ ወደ ችሎቱ ሲገቡ የቢቢሲ ሪፖርተር ተመልክቷል። ችሎቱ ሲጀመር አቶ በቀለ ገርባ በሰዎች ድጋፍ በጀርባቸው ተኝተው ከነበሩበት አግዳሚ ወንበር ተነስተው ተቀምጠዋል። የተከሳሽ ቤተሰብ አባላት መካከል አንዳንዶቹ በችሎት ውስጥ ሲያለቅሱ ሪፖርተራችን ተመልክቷል። እነ አቶ ጃዋር ለመጨረሻ ጊዜ ጋዜጠኞች እና ታዳሚዎች በተገኙበት በፍርድ ቤት ቀርበው የታዩት ጥር 27/2013 ዓ.ም ነበር። በዕለቱ የችሎት ውሎውን ለመዘገብ እና ለመከታተል በስፍራው የተገኙ ጋዜጠኞች እና የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ተቋም ሠራተኞች ተፈትሸው ወደ ችሎቱ ከገቡ በኋላ በጸጥታ አስከባሪዎች ከችሎቱ እንዲወጡ ተደርገው ነበር። 'የደረሰብን ክፍት ከፍተኛ ነው' በዛሬው የችሎት ውሎ ከተከሳሾች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ በቀለ ገርባ ከተቀመጡበት ሳይነሱ እንዲናገሩ ተፈቅዶላቸዋል። አቶ በቀለ ለፍርድ ቤቱ ክብር እንዳላቸው ተናግረው፤ ለሕክምና ወደ ላንድማርክ ሆስፒታል እየተወሰዱ ሳለ፤ መንገድ ተዘግቶባቸው በኃይል ወደ ጦር ኃይሎች ሆስፒታል መወሰዳቸውን ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል። "ይህ ቡድን የፍርድ ቤት ትዕዛዝን የማያከብር ነው" ያሉት አቶ በቀለ ገርባ፤ "ጨካኝ የሆነውን ሥርዓትን መታገል እንፈልጋለን። እኛ ላይ የደረሰው ክፋት ከፍተኛ ነው" ብለዋል። አሁን ባሉበት ሁኔታ ወደፊት በችሎት መቅረብ እንደማይገባቸው የተናገሩት አቶ በቀለ፤ ወደፊት ጤናቸው የሚመለስ ከሆነ ለጤና መቃውስ ዳርገውናል ያሉትን አካል ካሳ እንደሚጠይቁ ተናግረዋል። አቶ በቀለ ደብዳቤ በመጻፍ ላንድማርክ በተሰኘው የግል ሕክምና ተቋም እንዳይታከሙ የከለከሉት ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ መሆናቸውን ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል። እነ አቶ ጃዋር መሐመድ የረሃብ አድማውን እያደረጉ ያሉት በፖለቲከኞች ላይ የሚደርሰውን እንግልት እና እስር፣ እነሱን ለመጠየቅና የችሎት ሂደታቸውን ለመከታተል ወደ ፍርድ ቤት በሚመጡ ሰዎች ላይ የሚፈጸም እስር እና ወከባ እንዲቆም ለመጠየቅ እንደሆነም ቢቢሲ ከጠበቆቻቸው ለመረዳት ችሏል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) የረሃብ አድማው ተከሳሾችን የከፋ አደጋ ላይ እንዳይጥል የቅርብ ክትትል ማድረግ እንደሚያስፈልግ መግለጻቸውን ኮሚሽኑ ባሳለፍነው አርብ ባወጣው መግለጫ አስነብቧል። "ለታሳሪዎች ምክንያታዊ የሆኑ ጥያቄዎች ተገቢውን አፋጣኝ ምላሽ መስጠትና የእስረኞች ጠያቂዎችን በማረሚያ ቤቱም ሆነ በፍርድ ቤቶች በአግባቡ ማስተናገድ ይገባል" ስለማለታቸው በመግለጫው ሰፍሯል። የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በቁጥጥር ሥር የዋሉት እነ አቶ ጃዋር ከቀረቡባቸው ተደራራቢ አስር ክሶች ስድስቱ እንዲቋረጡ ፍርድ መወሰኑ ይታወሳል። የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ፤ የቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀል አዋጅ፤ የጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ የመተላለፍ ክሶች ከተመሰረቱባቸው ክሶች መካከል ሲሆኑ፤ እንዲቋረጡ የተደረጉት ክሶች የጦር መሳሪያ አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅ 1177/2021 ጋር የተያያዙ ናቸው።
https://www.bbc.com/amharic/news-56240090
3politics
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ከሴት ልጃቸው ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ በአደባባይ ታዩ
ለረዥም ጊዜ ሴት ልጅ እንዳላቸው ሲወራ የቆዩት የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ለመጀመሪያ ጊዜ አብረዋት በአደባባይ ታዩ። ስለ ኪም ሴት ልጅ እስካሁን በዝርዝር የሚታወቅ ምንም ነገር የሌለ ሲሆን፣ ስሟም ኪም ቹ-ኢ እንደሆነ ይታመናል። ሴት ልጃቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ከአባቷ ጋር የታየችው ኪም ጆንግ ኡን ለዓመታት ከምዕራባውያን ጋር በሚወዛገቡበት የጦር መሣሪያ ፕሮግራም ሙከራ ወቅት ነው። የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ትናንት አርብ የአገሪቱ ትልቁ ነው የተባለው አህጉር አቋራጭ ባለስቲክ ሚሳኤል ሙከራ በተደረገበት ሥነ ሥርዓት ላይ ነው ከሴት ልጃቸው ጋር የተገኙት። አሜሪካ ባወገዘችው የሚሳኤል ሙከራ ላይ አባት እና ሴት ልጃቸው እጅ ለእጅ ተያይዘው ታድመው ነበር። በዓለም ላይ እጅግ ከፍተኛ ቁጥጥር የሚደረግባትን አገር ስለሚመሩት ኪም ጆንግ ኡን የግል ሕይወት የሚታወቀው ነገር እጅግ በጣም ጥቂት ነው። ከሴት ልጃቸው ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ በይፋ የታዩትን የአባት እና ልጅን የተለያዩ ፎቶዎችን የሰሜን ኮሪያው የዜና አገልግሎት ኬሲኤንኤ አሰራጭቷል። የኪም ጆንግ ኡን ሴት ልጅ የሆነችው ቹ-ኤ ለሕዝብ በይፋ መታየቷ ትልቅ ነገር ነው፣ ሲሉ በዋሽንግተን በሚገኘው የስቲምሰን ማዕከል የሰሜን ኮሪያ ተንታኝ የሆኑት ማይክል ማደን ይናገራሉ። ሰሜን ኮሪያን በመምራት ከቤተሰባቸው ሦስተኛው ትውልድ የሆኑት ኪም፣ አሁንም በአገራቸው የመሪነት ሥልጣን ላይ ጠንካራ ቁጥጥር እንዳላቸው እያሳዩ መሆናቸውን ተንታኙ ያምናሉ። ማደን እንደሚሉት ኪም ከሴት ልጃቸው ጋር መታየታቸው “አገሪቱን የሚመራው አራተኛው ትውልድ ከእሳቸው የቤተሰብ ግንድ እንደሚመጣ ለማሳየትም ሊሆን ይችላል” ብለዋል ለቢቢሲ። መሪው ከልጃቸው ጋር የታዩት “በኪም እና በአመራሩ ከፍተኛ ሰዎች መካከል ባለፈው ዓመት ግጭት መኖሩን የሚያመለክት ሪፖርት መውጣቱን ተከትሎ ነው” ይላሉ። በዚህም ኪም ለተቀናቃኞቻቸው ማስተላለፍ የፈለጉት መልዕክት “የምትገዳደሩኝ ከሆነ፣ ቦታችሁን ትለቃላችሁ” የሚል ነው። ማደን እንደሚያምኑት የኪም ሴት ልጅ በአሁኑ ወቅት ዕድሜዋ በ12 እና በ13 መካከል ነው፣ በዚህም ከአራት እና ከአምስት ዓመታት በኋላ ወደ ዩኒቨርስቲ ወይም ወደ ወታደራዊ አገልግሎት ለመግባት ትዘጋጃለች። ቹ-ኤ በይፋ ስትታይ የአሁኑ የመጀመሪያዋ አይደለም የሚሉት በርካታ የሰሜን ኮሪያ ጉዳይን የሚከታተሉ ባለሙያዎች፣ ቹ ባለፈው መስከረም ላይ በተከበረው የአገሪቱ ብሔራዊ ቀን ክብረ በዓል ላይ በተቀረጹ ቪዲዮዎች ላይ ታይታለች። ነገር ግን ይህ ከግምት ባለፈ ማረጋገጫ አልተገኘለትም። የሰሜን ኮሪያ ባለሥልጣናትም በቪዲዮው ላይ የታየችው የመሪው ሴት ልጅ ስለመሆኗ ምንም ዓይነት ማረጋገጫ አልሰጡም። ኪም ጆንግ ኡን ሴት ልጅ እንዳላቸው ለመጀመሪያ ጊዜ የተገለጸው ከዘጠኝ ዓመት በፊት የቀድሞው የአሜሪካ ቅርጫት ኳስ ኮከብ ዴኒስ ሮድማን አወዛጋቢ ጉዞ ወደ ሰሜን ኮሪያ ባደረገበት ጊዜ ነው። ሮድማን በወቅቱ ከኪም ቤተሰብ ጋር ጊዜ ማሳለፉን በመጥቅስ፣ በባሕር ዳርቻ ላይ ዘና ማለቱንና የመሪውን ሕጻን ልጅ ቹ-ኤን ማየቱን በገለጸበት ወቅት ነበር። የሰሜን ኮሪያን ጉዳይ በቅርበት የሚከታተሉ ባለሙያዎች እንደሚያምኑት ኪም ሦስት ልጆች ያሏቸው ሲሆን፣ ሁለቱ ሴቶች አንዱ ወንድ ናቸው፤ ቹ-ኤ ደግሞ የመጀመሪያ ልጅ ናት ይላሉ። ኪም ጆንግ ኡን ቤተሰባቸውን በሚመለከት ሁሉንም ነገር በጥብቅ ምስጢርነት የያዙ መሪ ናቸው። ባለቤታቸው ሪ ሶል-ጁን ካገቡ በኋላ እንኳን እስከተወሰነ ጊዜ ድረስ ጋብቻቸውን በምስጢር ይዘውት ቆይተዋል።
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ከሴት ልጃቸው ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ በአደባባይ ታዩ ለረዥም ጊዜ ሴት ልጅ እንዳላቸው ሲወራ የቆዩት የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ለመጀመሪያ ጊዜ አብረዋት በአደባባይ ታዩ። ስለ ኪም ሴት ልጅ እስካሁን በዝርዝር የሚታወቅ ምንም ነገር የሌለ ሲሆን፣ ስሟም ኪም ቹ-ኢ እንደሆነ ይታመናል። ሴት ልጃቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ከአባቷ ጋር የታየችው ኪም ጆንግ ኡን ለዓመታት ከምዕራባውያን ጋር በሚወዛገቡበት የጦር መሣሪያ ፕሮግራም ሙከራ ወቅት ነው። የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ትናንት አርብ የአገሪቱ ትልቁ ነው የተባለው አህጉር አቋራጭ ባለስቲክ ሚሳኤል ሙከራ በተደረገበት ሥነ ሥርዓት ላይ ነው ከሴት ልጃቸው ጋር የተገኙት። አሜሪካ ባወገዘችው የሚሳኤል ሙከራ ላይ አባት እና ሴት ልጃቸው እጅ ለእጅ ተያይዘው ታድመው ነበር። በዓለም ላይ እጅግ ከፍተኛ ቁጥጥር የሚደረግባትን አገር ስለሚመሩት ኪም ጆንግ ኡን የግል ሕይወት የሚታወቀው ነገር እጅግ በጣም ጥቂት ነው። ከሴት ልጃቸው ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ በይፋ የታዩትን የአባት እና ልጅን የተለያዩ ፎቶዎችን የሰሜን ኮሪያው የዜና አገልግሎት ኬሲኤንኤ አሰራጭቷል። የኪም ጆንግ ኡን ሴት ልጅ የሆነችው ቹ-ኤ ለሕዝብ በይፋ መታየቷ ትልቅ ነገር ነው፣ ሲሉ በዋሽንግተን በሚገኘው የስቲምሰን ማዕከል የሰሜን ኮሪያ ተንታኝ የሆኑት ማይክል ማደን ይናገራሉ። ሰሜን ኮሪያን በመምራት ከቤተሰባቸው ሦስተኛው ትውልድ የሆኑት ኪም፣ አሁንም በአገራቸው የመሪነት ሥልጣን ላይ ጠንካራ ቁጥጥር እንዳላቸው እያሳዩ መሆናቸውን ተንታኙ ያምናሉ። ማደን እንደሚሉት ኪም ከሴት ልጃቸው ጋር መታየታቸው “አገሪቱን የሚመራው አራተኛው ትውልድ ከእሳቸው የቤተሰብ ግንድ እንደሚመጣ ለማሳየትም ሊሆን ይችላል” ብለዋል ለቢቢሲ። መሪው ከልጃቸው ጋር የታዩት “በኪም እና በአመራሩ ከፍተኛ ሰዎች መካከል ባለፈው ዓመት ግጭት መኖሩን የሚያመለክት ሪፖርት መውጣቱን ተከትሎ ነው” ይላሉ። በዚህም ኪም ለተቀናቃኞቻቸው ማስተላለፍ የፈለጉት መልዕክት “የምትገዳደሩኝ ከሆነ፣ ቦታችሁን ትለቃላችሁ” የሚል ነው። ማደን እንደሚያምኑት የኪም ሴት ልጅ በአሁኑ ወቅት ዕድሜዋ በ12 እና በ13 መካከል ነው፣ በዚህም ከአራት እና ከአምስት ዓመታት በኋላ ወደ ዩኒቨርስቲ ወይም ወደ ወታደራዊ አገልግሎት ለመግባት ትዘጋጃለች። ቹ-ኤ በይፋ ስትታይ የአሁኑ የመጀመሪያዋ አይደለም የሚሉት በርካታ የሰሜን ኮሪያ ጉዳይን የሚከታተሉ ባለሙያዎች፣ ቹ ባለፈው መስከረም ላይ በተከበረው የአገሪቱ ብሔራዊ ቀን ክብረ በዓል ላይ በተቀረጹ ቪዲዮዎች ላይ ታይታለች። ነገር ግን ይህ ከግምት ባለፈ ማረጋገጫ አልተገኘለትም። የሰሜን ኮሪያ ባለሥልጣናትም በቪዲዮው ላይ የታየችው የመሪው ሴት ልጅ ስለመሆኗ ምንም ዓይነት ማረጋገጫ አልሰጡም። ኪም ጆንግ ኡን ሴት ልጅ እንዳላቸው ለመጀመሪያ ጊዜ የተገለጸው ከዘጠኝ ዓመት በፊት የቀድሞው የአሜሪካ ቅርጫት ኳስ ኮከብ ዴኒስ ሮድማን አወዛጋቢ ጉዞ ወደ ሰሜን ኮሪያ ባደረገበት ጊዜ ነው። ሮድማን በወቅቱ ከኪም ቤተሰብ ጋር ጊዜ ማሳለፉን በመጥቅስ፣ በባሕር ዳርቻ ላይ ዘና ማለቱንና የመሪውን ሕጻን ልጅ ቹ-ኤን ማየቱን በገለጸበት ወቅት ነበር። የሰሜን ኮሪያን ጉዳይ በቅርበት የሚከታተሉ ባለሙያዎች እንደሚያምኑት ኪም ሦስት ልጆች ያሏቸው ሲሆን፣ ሁለቱ ሴቶች አንዱ ወንድ ናቸው፤ ቹ-ኤ ደግሞ የመጀመሪያ ልጅ ናት ይላሉ። ኪም ጆንግ ኡን ቤተሰባቸውን በሚመለከት ሁሉንም ነገር በጥብቅ ምስጢርነት የያዙ መሪ ናቸው። ባለቤታቸው ሪ ሶል-ጁን ካገቡ በኋላ እንኳን እስከተወሰነ ጊዜ ድረስ ጋብቻቸውን በምስጢር ይዘውት ቆይተዋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cv27nlz2225o
3politics
ማግዳሊና አንደርሰን፡ የስዊድን የመጀመሪያዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ ሥልጣናቸው ተመለሱ
ባለፈው ሳምንት በፖለቲካ ውዥንብር በተሾሙ በሰዓታት ውስጥ ሥልጣናቸውን የለቀቁት የስዊድን የመጀመሪያዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ ሥልጣናቸው ተመለሱ። የፓርላማ አባላት ሰኞ ዕለት በሰጡት አዲስ ድምጽ የሶሻል ዲሞክራቲክ መሪ ማግዳሊና አንደርሰንን በጠባብ ልዩነት ደግፈዋል። በዚህም መሠረት ማግዳሊና በሚቀጥለው ዓመት መስከረም ወር እስከሚካሄደው ምርጫ ድረስ የአንድ ፓርቲ መንግሥት ይመራሉ ተብሏል። ማግዳሊና ባለፈው ረቡዕ ዕለት ከርሳቸው ፓርቲ ጋር ጥምረት የፈጠረው የፖለቲካ ድርጅት ከጥምረቱ በመልቀቁና የሳቸው ፓርቲ ሶሻል ዲሞክራት ያቀረበው የበጀት ጥያቄ በምክር ቤቱ ሊያልፍ ባለመቻሉ ነበር ከተሰጣቸው የጠቅላይ ሚኒስትርነት ሹመት የለቀቁት። ማግዳሊና ሥልጣን ከመልቀቃቸው ከሰዓታት በፊት ነበር የስዊድን የመጀመሪያዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በፓርላማው የተመረጡት። ነገር ግን የ54 ዓመቷ ዓመቷ የምጣኔ ሐብት ምሁር ከግሪን ፓርቲ ጋር አዲስ ጥምር መንግሥት ለመመስረት ይዘውት የነበረው እቅድ የበጀት ረቂቃቸው ባለመጽደቁ ሳይሳካላቸው ቀርቷል። ይልቁኑ ፓርላማው የቀኝ አክራሪዎቹን የስዊድን ዲሞክራቶችን ጨምሮ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ቡድን ያዘጋጁትን በጀት ተቀብሏል። ግሪን ፓርቲ በቀኝ አክራሪዎቹ የረቀቀውን በጀት እንደማይቀበል ገልጿል። ማግዳሊና በዚህ ሁኔታ ለመቀጠል እንደማይፈልጉና የገዛ ፓርቲያቸው አብላጫ ድምጽ አግኝቶ መንግሥት ሲመሰርት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው መመረጥ እንደሚፈልጉ ተናግረው ነበር። ሰኞ ዕለት በተካሄደው የስዊድን ፓርላማ ድምጽ አሰጣጥ ግን ሪክስዳግ የተባለው የስዊድን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ካሉት 349 አባላቱ 101 የድጋፍ ፣ 75 ድምጸ ታቅቦ፣ 173 ደግሞ የተቃውሞ ደምጽ ሰጥተዋል። በስዊድን የፖለቲካ ሥርዓት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኖ ለመሾም አንድ እጩ አብላጫ የተቃውሞ ደምጽን ማግኘት የለበትም። ከድምጽ አጣጡ ሥርዓት በኋላ ማግሊንዳ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በደህንነት ፣ በአየር ንብረት ለውጥ እና በወንጀል ላይ ያተኮረ ፕሮግራም በመዘርጋት ስዊድንን ወደ ፊት ለማራመድ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረው ነበር። ነገር ግን አሁንም የሌሎች ፓርቲዎችን ድጋፍ ካላገኙ ሴንተር ሌፍት ሶሻል ዲሞክራቶች ከ349፣ 100 መቀመጫ ባላቸው ፓርላማ ሕግ ለማጽደቅ ይቸገራሉ ተብሏል። ማግዳሊና በዩኒቨርስቲ ሲቲ ኡፕሳላ የአዳጊዎች የውሃ ዋና ሻምፒዮን የነበሩ ሲሆን ፖለቲካ ውስጥ የገቡት በ1996 የጠቅላይ ሚኒስትር ጎራን ፐርሰን አማካሪ በመሆን ነበር፡፡ ላለፉት ሰባት ዓመታትም በገንዘብ ሚኒስትርነት አገልግለዋል፡፡ ማግደሊና አንደርሰን በሕዝብ እንደራሴዎች ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆኑ ድምጽ ከማግኘታቸው በፊት ስዊድን ከኖርዲክ አገሮች ሁሉ ብቸኛዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ኖሯት የማያውቅ አገር ሆና ቆይታለች፡፡ ስዊድን የጾታ እኩልነት ከፍ ባለ ደረጃ የምታከብር አገር ናት፡፡
ማግዳሊና አንደርሰን፡ የስዊድን የመጀመሪያዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ ሥልጣናቸው ተመለሱ ባለፈው ሳምንት በፖለቲካ ውዥንብር በተሾሙ በሰዓታት ውስጥ ሥልጣናቸውን የለቀቁት የስዊድን የመጀመሪያዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ ሥልጣናቸው ተመለሱ። የፓርላማ አባላት ሰኞ ዕለት በሰጡት አዲስ ድምጽ የሶሻል ዲሞክራቲክ መሪ ማግዳሊና አንደርሰንን በጠባብ ልዩነት ደግፈዋል። በዚህም መሠረት ማግዳሊና በሚቀጥለው ዓመት መስከረም ወር እስከሚካሄደው ምርጫ ድረስ የአንድ ፓርቲ መንግሥት ይመራሉ ተብሏል። ማግዳሊና ባለፈው ረቡዕ ዕለት ከርሳቸው ፓርቲ ጋር ጥምረት የፈጠረው የፖለቲካ ድርጅት ከጥምረቱ በመልቀቁና የሳቸው ፓርቲ ሶሻል ዲሞክራት ያቀረበው የበጀት ጥያቄ በምክር ቤቱ ሊያልፍ ባለመቻሉ ነበር ከተሰጣቸው የጠቅላይ ሚኒስትርነት ሹመት የለቀቁት። ማግዳሊና ሥልጣን ከመልቀቃቸው ከሰዓታት በፊት ነበር የስዊድን የመጀመሪያዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በፓርላማው የተመረጡት። ነገር ግን የ54 ዓመቷ ዓመቷ የምጣኔ ሐብት ምሁር ከግሪን ፓርቲ ጋር አዲስ ጥምር መንግሥት ለመመስረት ይዘውት የነበረው እቅድ የበጀት ረቂቃቸው ባለመጽደቁ ሳይሳካላቸው ቀርቷል። ይልቁኑ ፓርላማው የቀኝ አክራሪዎቹን የስዊድን ዲሞክራቶችን ጨምሮ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ቡድን ያዘጋጁትን በጀት ተቀብሏል። ግሪን ፓርቲ በቀኝ አክራሪዎቹ የረቀቀውን በጀት እንደማይቀበል ገልጿል። ማግዳሊና በዚህ ሁኔታ ለመቀጠል እንደማይፈልጉና የገዛ ፓርቲያቸው አብላጫ ድምጽ አግኝቶ መንግሥት ሲመሰርት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው መመረጥ እንደሚፈልጉ ተናግረው ነበር። ሰኞ ዕለት በተካሄደው የስዊድን ፓርላማ ድምጽ አሰጣጥ ግን ሪክስዳግ የተባለው የስዊድን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ካሉት 349 አባላቱ 101 የድጋፍ ፣ 75 ድምጸ ታቅቦ፣ 173 ደግሞ የተቃውሞ ደምጽ ሰጥተዋል። በስዊድን የፖለቲካ ሥርዓት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኖ ለመሾም አንድ እጩ አብላጫ የተቃውሞ ደምጽን ማግኘት የለበትም። ከድምጽ አጣጡ ሥርዓት በኋላ ማግሊንዳ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በደህንነት ፣ በአየር ንብረት ለውጥ እና በወንጀል ላይ ያተኮረ ፕሮግራም በመዘርጋት ስዊድንን ወደ ፊት ለማራመድ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረው ነበር። ነገር ግን አሁንም የሌሎች ፓርቲዎችን ድጋፍ ካላገኙ ሴንተር ሌፍት ሶሻል ዲሞክራቶች ከ349፣ 100 መቀመጫ ባላቸው ፓርላማ ሕግ ለማጽደቅ ይቸገራሉ ተብሏል። ማግዳሊና በዩኒቨርስቲ ሲቲ ኡፕሳላ የአዳጊዎች የውሃ ዋና ሻምፒዮን የነበሩ ሲሆን ፖለቲካ ውስጥ የገቡት በ1996 የጠቅላይ ሚኒስትር ጎራን ፐርሰን አማካሪ በመሆን ነበር፡፡ ላለፉት ሰባት ዓመታትም በገንዘብ ሚኒስትርነት አገልግለዋል፡፡ ማግደሊና አንደርሰን በሕዝብ እንደራሴዎች ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆኑ ድምጽ ከማግኘታቸው በፊት ስዊድን ከኖርዲክ አገሮች ሁሉ ብቸኛዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ኖሯት የማያውቅ አገር ሆና ቆይታለች፡፡ ስዊድን የጾታ እኩልነት ከፍ ባለ ደረጃ የምታከብር አገር ናት፡፡
https://www.bbc.com/amharic/news-59472445
5sports
ወደ አገሬ አልመለስም ያለቸው የቤላሩስ አትሌት ወደ ቪዬና አቀናች
ወደ አገሯ እንድትመለስ የተሰጣትን ትዕዛዝ አልቀበልም ያላችው የቤላሩስ አትሌት ከቶኪዮ ወደ ኦስትሪያ፣ ቪዬና አቀናች። የ24 ዓመቷ ክሪስቲሲና ትሲማኑስካያ ረቡዕ ጠዋት ወደ ፖላንድ ትሄዳለች ተብሎ የነበረ ቢሆንም ቪየና በሚያቀና አውሮፕላን ተሳፍራለች ተብሏል። ፖላንድ ቪዛ ስለሰጠቻት በቀጥታ ወደ ፖላንድ መዲና ዋርሶ ትጓዛለች ተብሎ ቢጠበቅም በመጨረሻው ሰዓት መዳረሻዋ ተቀይሯል ሲሉ አንድ የአየር ማረፊያው ባለሥልጣን ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። አትሌቷ ወደ አገሬ አልመለስም ያለቸው በፖለቲካዊ ምክንያት እንዳልሆነ ለቢቢሲ ተናገረች። "አገሬን እወዳለሁ፤ አገሬን አልከዳሁም" ብላለች። አትሌቷ ለውሳኔዋ ምክንያቱ "በኦሎምፒክ ባለሥልጣኖቻችን የተፈጠሩ ስህተቶች ናቸው" ብላለች። አትሌቷ ባለፈው ሳምንት አሰልጣኞቿን በመተቸቷ ዕቃዎቿን ጠቅልላ ወደ ቶኪዮ ሃኔዳ አውሮፕላን ማረፊያ ብትወሰድም ለደኅንነቴ እሰጋለሁ በሚል ወደ ቤላሩስ አልጓዝም ብላ ነበር። በቶኪዮ ወደሚገኘው የፖላንድ ኤምባሲ ከመዛወሯ በፊት የፖሊስ ጥበቃ የተደረገላት ሲሆን ረቡዕ ወደ አውሮፕላን ማረፊያ እስክትጓዝ ድረስ በኤምባሲው ቆይታለች። የቤላሩስ አትሌቲክስ ቡድን አትሌቷ ከአዕምሮ ዝግጁነት ጋር በተያያዘ ከብሔራዊ ቡድኑ እንደተቀነሰች አስታውቋል። ማክሰኞ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ ያደረገችው ክሪስቲሲና ትሲማኑስካያ ግን ምንም ዓይነት የአዕምሮ ጤና ችግር እንዳልነበራት እና በኦሎምፒክ መንደሩ ከሐኪሞች ጋር ምንም ውይይት እንዳላደረገች ተናግራለች። "የፖለቲካ ነገር ስላልተናገረች" ከውድድሩ እንደምትወጣ ሲነግሯት በጣም እንደተገረመች ተናግራለች። ደኅንነቷ የተጠበቀ መሆኑን ስታውቅ ወደ ቤላሩስ መመለስ እንደምትፈልግ ገልጻለች። ምናልባት ከአምስት ወይም ከ10 ዓመታት በኋላ መመለስ ይቻላል ብላለች። ቤላሩስ ክሪስቲሲና ትሲማኑስካያን ወደ አገሯ እንድትመለስ ለማስገደድ ሞክራለች በሚለው ክስ ላይ የዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ (አይኦሲ) ምርመራ ጀመሯል። የአይኦሲው ቃል አቀባይ ማርክ አዳምስ "ሙሉ እውነታውን ማግኘት አለብን። ያ ጊዜ ሊወስድ ይችላል። እስከዚያ ድረስ የእኛ የመጀመሪያ ጉዳይ አትሌቷ ናት" ብለዋል። የቤላሩስ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሪፖርቱን እስከ ማክሰኞ ድረስ እንዲያቀርብ አይኦሲ ጠይቋል።
ወደ አገሬ አልመለስም ያለቸው የቤላሩስ አትሌት ወደ ቪዬና አቀናች ወደ አገሯ እንድትመለስ የተሰጣትን ትዕዛዝ አልቀበልም ያላችው የቤላሩስ አትሌት ከቶኪዮ ወደ ኦስትሪያ፣ ቪዬና አቀናች። የ24 ዓመቷ ክሪስቲሲና ትሲማኑስካያ ረቡዕ ጠዋት ወደ ፖላንድ ትሄዳለች ተብሎ የነበረ ቢሆንም ቪየና በሚያቀና አውሮፕላን ተሳፍራለች ተብሏል። ፖላንድ ቪዛ ስለሰጠቻት በቀጥታ ወደ ፖላንድ መዲና ዋርሶ ትጓዛለች ተብሎ ቢጠበቅም በመጨረሻው ሰዓት መዳረሻዋ ተቀይሯል ሲሉ አንድ የአየር ማረፊያው ባለሥልጣን ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። አትሌቷ ወደ አገሬ አልመለስም ያለቸው በፖለቲካዊ ምክንያት እንዳልሆነ ለቢቢሲ ተናገረች። "አገሬን እወዳለሁ፤ አገሬን አልከዳሁም" ብላለች። አትሌቷ ለውሳኔዋ ምክንያቱ "በኦሎምፒክ ባለሥልጣኖቻችን የተፈጠሩ ስህተቶች ናቸው" ብላለች። አትሌቷ ባለፈው ሳምንት አሰልጣኞቿን በመተቸቷ ዕቃዎቿን ጠቅልላ ወደ ቶኪዮ ሃኔዳ አውሮፕላን ማረፊያ ብትወሰድም ለደኅንነቴ እሰጋለሁ በሚል ወደ ቤላሩስ አልጓዝም ብላ ነበር። በቶኪዮ ወደሚገኘው የፖላንድ ኤምባሲ ከመዛወሯ በፊት የፖሊስ ጥበቃ የተደረገላት ሲሆን ረቡዕ ወደ አውሮፕላን ማረፊያ እስክትጓዝ ድረስ በኤምባሲው ቆይታለች። የቤላሩስ አትሌቲክስ ቡድን አትሌቷ ከአዕምሮ ዝግጁነት ጋር በተያያዘ ከብሔራዊ ቡድኑ እንደተቀነሰች አስታውቋል። ማክሰኞ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ ያደረገችው ክሪስቲሲና ትሲማኑስካያ ግን ምንም ዓይነት የአዕምሮ ጤና ችግር እንዳልነበራት እና በኦሎምፒክ መንደሩ ከሐኪሞች ጋር ምንም ውይይት እንዳላደረገች ተናግራለች። "የፖለቲካ ነገር ስላልተናገረች" ከውድድሩ እንደምትወጣ ሲነግሯት በጣም እንደተገረመች ተናግራለች። ደኅንነቷ የተጠበቀ መሆኑን ስታውቅ ወደ ቤላሩስ መመለስ እንደምትፈልግ ገልጻለች። ምናልባት ከአምስት ወይም ከ10 ዓመታት በኋላ መመለስ ይቻላል ብላለች። ቤላሩስ ክሪስቲሲና ትሲማኑስካያን ወደ አገሯ እንድትመለስ ለማስገደድ ሞክራለች በሚለው ክስ ላይ የዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ (አይኦሲ) ምርመራ ጀመሯል። የአይኦሲው ቃል አቀባይ ማርክ አዳምስ "ሙሉ እውነታውን ማግኘት አለብን። ያ ጊዜ ሊወስድ ይችላል። እስከዚያ ድረስ የእኛ የመጀመሪያ ጉዳይ አትሌቷ ናት" ብለዋል። የቤላሩስ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሪፖርቱን እስከ ማክሰኞ ድረስ እንዲያቀርብ አይኦሲ ጠይቋል።
https://www.bbc.com/amharic/58079204
0business
ኢትዮጵያ ከኮሮናቫይረስ ምጣኔ ሐብታዊ ጫና ትተርፋለች?
እስከ ሚያዝያ አንድ ድረስ ኢትዮጵያ ውስጥ ስድሳ አምስት ሰዎችን አጥቅቶ፣ ሦስቱን ለሞት ያበቃው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ፤ እንደሌሎች የዓለም ክፍሎች ሁሉ ተያያዥ የሥነ ጤና፣ ማኅበራዊ እና ምጣኔ ኃብታዊ ጠንቆችን እንደሚያስከትል ይጠበቃል። ወረርሽኙ ከዚህ ቀደም ባልተለመደ አኳኋን በፍጥነት መዛመት፤ ይዟቸው የሚመጣቸውን ጣጣዎችም በዚያው ልክ የገዘፉ እንዲሁም በዓለም ዙርያ የተሰራጩ አድርጓቸዋል። በዚያውም ልክ መጭውን ለመተነብይም አዳጋች ሆኗል። ይሁንና በልዩ ልዩ ዘርፎች የተሰማሩ ባለሞያዎች የጉዳቱን መጠን ለመስፈር፤ የድኅረ-ወረርሽኝ አቅጣጫዎችንም ለመቀየስ መሞከራቸው አልቀረም። ወረርሽኙ በሰዎች የሥራ እና የገቢ ሁኔታ ላይ የሚያሳርፈውን ጡጫ በተመለከተ ጥናት ያደረገው ዓለም አቀፉ የሥራ ድርጅት (አይ.ኤል.ኦ) እ.ኤ.አ መጋቢት 18 ቀን 2020 ባሳተመው ግምገማው ምንም እንኳ የኮሮናቫይረስ በዕድሜ የገፉትን እና ቀደም ሲል በሽታ የነበረባቸውን ግለሰቦችን የማጥቃት ከፍ ያለ ዕድል ቢኖረውም፤ ከወረርሽኙ በኋላ የሚከሰት የሥራ አጥነት ቀውስ ወትሮውኑም ሥራ ማጣት የሚያበረታባቸው ወጣቶች ላይ ሊጠነክር ይችላል ይላል። በአገልግሎት ዘርፍ በብዛት ተሰማርተው የሚገኙት ሴቶች፣ ዋስትና አልባ ሥራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች (ለምሳሌ የራሳቸውን ሥራ የሚሰሩ እና በጊዜያዊነት የተቀጠሩ) አንዲሁም ስደተኛ ሠራተኞች አንዲሁ ክፉኛ በሥራ አልባነት ማዕበል ክፉኛ ሊደቆሱ ይችላሉ ይላል የአይ.ኤል.ኦ ግምገማ። በምጣኔ ኃብት ያልጠነከሩ አገራት ኢትዮጵያም ወረርሽኙ የሚያስከትለውን የጤና ቀውስ ለመቋቋም ከምታደርጋቸው ጥረቶች ባሻገር ይዞት የሚመጣው የምጣኔ ኃብት ጡጫ ያሳሰባት ይመስላል። ከሳምንታት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የበለፀጉ አገራት ኢትዮጵያን ለመሳሰሉ የአፍሪካ አገራት የዕዳ ቅነሳ እና የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ እንዲያደርጉ መጠየቃቸው ይታወሳል። ባገባደድነው ሳምንት አዲስ አበባ ላይ በተደረገ የድረ ገፅ ላይ ውይይት የሥራ ፈጠራ ኮሚሽነሩ ኤፍሬም ተክሌ ሌማንጎ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ሥራዎቻቸውን ሊያጡ እንደሚችሉ መናገራቸው ተዘግቧል። የሥራ ዕጦቱ በአገሪቱ ትልቁ ኩባንያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጀመረ ይመስላል። የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ድርጅታቸው ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ 550 ሚሊዮን ዶላር ማጣቱን በገለፁበት መገለጫቸው ላይ ቋሚ ያልሆኑ ሠራተኞችን ለጊዜው ሥራ እንዲያቆሙ መደረጋቸውን ገልፀዋል። የኢትዮጵያ የምጣኔ ኃብት ማኅበር ያሳተመው የአራት ባለሞያዎች ምልከታ ከወረርሽኑም በፊት ለብዙዎቹ ኢትዮጵያውያን መሠረታዊ ግልጋሎቶችን ማግኘት አዳጋች ነበር፤ ይህም ወረርሽኙን ለመከላከል መደረግ ያለባቸውን እርምጃዎች ቀላል እንዳይሆኑ ያደርጋቸዋል ይላል። እንደአብነትም ከጠቅላላው ሕዝብ መካከል ስድስት በመቶ የሚሆነው ያህል በመኖርያው አቅራቢያ የመታጠቢያ ውሃ አለው ይላል። • “ገደቦችን በአጭር ጊዜ ማንሳት ወረርሽኙ በአስከፊ ሁኔታ እንዲሰራጭ ያደርጋል” ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም • ኮሮናቫይረስ ካለበት ሰው ጋር ንክኪ ላደረጉ ሰዎች ጥቆማ የሚሰጥ መሣሪያ እየተሠራ ነው ባለሞያዎቹ ብሔራዊው የስታትስቲክስ ድርጅት በማጠቀስ ከአራት ዓመት በፊት በተጠናቀረ መረጃ መሠረት አገሪቱ ውስጥ ካሉ ቤቶች ሰማንያ አምስት በመቶው ባለአንድ ወይንም ባለሁለት ክፍል መሆናቸውን አስታውሰው በኮቪድ 19 በሽታ ጥርጣሬ ቤት ውስጥ ተነጥሎ መቀመጥ አዋጭ አማራጭ ያለመሆኑን ይናገራሉ። ወረርሽኑ የሚፈጥረው የምጣኔ ኃብት ንዝረት የአገልግሎት ዘርፉን፣ ቱሪዝምን እና የመስተንገዶ ኢንዱስትሪውን፣ የውጭ ንግድን እና የመጓጓዣ ዘርፍን ሊጎዳ እንደሚችል የሚገምተው የባለሞያዎቹ ምልከታ ግብርናም ቢሆን ከዚህ የሚተርፍ አይደለም ይላል- በተለይ በቀላሉ የሚበላሹ ምርቶች አብቃዮች እና አከፋፋዮች ለጉዳት ተጋላጭ መሆናቸው አይቀርም። ወረርሽኙ የአቅርቦት ሰንሰለትን ያውካል። የሥራ መቀዛቀዝ በሚፈጥረው የገቢ እጥረት እንዲሁም የሚመጣው አይታወቅም በሚል ስጋት ምክንያት ሰዎች ገንዘብ ከማውጣት ስለሚቆጠቡ የፍላጎት እጥረትን ያስከትላል፤ አንዲሁም የንግድ ተቋማት የመንቀሳቀሻ ገንዘብ እጥረት እንዲያጋጥማቸው፣ ዕዳ መክፈል እንዲሳናቸውም ሊያደርግ ይችላል የባለሞያዎቹ ግምገማ እንደሚያመላክተው። እነዚህ ችግሮች እርስ በእርስ እየተመጋገቡ የምጣኔ ኃብት እንቅስቃሴው በአዝጋሚነት ዘለግ ላለ ጊዝ የሚዘልቅ ከሆነ ምጣኔ ኃብታዊ መኮማተር (ሪሰሽን) ሊከተልም ይችላል። ከኢትዮጵያ ጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት (ጂ.ዲ.ፒ.) ሰላሳ ዘጠኝ በመቶውን ድርሻ የሚይዘው የአገልገሎት ዘርፍ በወረርሽኙ ከሌሎች ዘርፎች በበለጠ ሊጎሳቆል ይችላል። ሰላሳ ሦሰት በመቶውን ድርሻ የሚይዘው ግብርና ግን ቢያንስ በአጭር ጊዜ ውስጥ በአንፃራዊነት ያነሰ ጉዳት ሊደርስበት ይችላል። በባለሞያዎቹ ግምት መሠረት ወረርሽኙ አነስ ባለ የጉዳት ለሦስት ወራት ያህል ቢቆይ እንኳ ምጣኔ ኃብቱ እስከ 44 ቢሊዮን ብር የሚደርስ እጦትን ሊያስተናግድ ይችላል። ወረርሽኙ ለስድስት ወራት ቢቆይና የከፋ ጉዳት የሚያደርስ ቢሆን የእጦቱ መጠን ከሁለት መቶ ቢሊዮን ብር ይሻገራል። ኮሮናቫይረስ ሠራተኞች ላይ ስለሚኖረው ተፅዕኖ የተሠራ አንድ ጥናት 3 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ሥራ-አጥ ሊሆኑ ይችላሉ ይላል። የኢትዮጵያ ኢኮኖሚስቶች ማኅበር ያሳተመው ጥናት ቫይረሱ ለረዥም ጊዜ የሚቆይ ከሆነ በርካቶች ሥራ-አጥ ሊሆኑ ይችላሉ ባይ ነው። በቅርቡ የኢትዮጵያ ሥራ ፈጠራ ኮሚሽን በሠራው ጥናት እንደሚጠቁመው ቫይረሱ ለስድስት ወራት የሚቆይ ከሆነ በማኒዩፈክቸሪንግ ዘርፍ የተሰማሩ 60 በመቶ ሰዎች ሥራቸውን ሊያጡ ይችላሉ።በተመሳሳይም በአገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ 74 በመቶ ሰዎች ሥራ-አጥ ይሆናሉ። ጥናቱ አክሎም ከ9 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ተሰማርተውበታል በሚባለው የአገልግሎት ዘርፍ ብቻ 3 ሚሊዮን ሰዎች ሥራቸውን ሊያጡ ይችላሉ ይላል። ቫይረሱ በኅብረተሰቡ ውስጥ ከተንሰራፋ አደጋው የከፋ ሊሆን እንደሚችል ጥናቱ ያስጠነቅቃል።ጥናቱ የተሠራው የቫይረሱን ቆይታ በሁለት በመከፋፈል ነው። የመጀመሪያው ለሦስት ወራት ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ስድስት ወራት ነው። የቫይረሱ ተፅዕኖ የከፋ ከሆነ ከ50 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን ችግር ላይ ሊወድቁ ይችላሉ ይላል።
ኢትዮጵያ ከኮሮናቫይረስ ምጣኔ ሐብታዊ ጫና ትተርፋለች? እስከ ሚያዝያ አንድ ድረስ ኢትዮጵያ ውስጥ ስድሳ አምስት ሰዎችን አጥቅቶ፣ ሦስቱን ለሞት ያበቃው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ፤ እንደሌሎች የዓለም ክፍሎች ሁሉ ተያያዥ የሥነ ጤና፣ ማኅበራዊ እና ምጣኔ ኃብታዊ ጠንቆችን እንደሚያስከትል ይጠበቃል። ወረርሽኙ ከዚህ ቀደም ባልተለመደ አኳኋን በፍጥነት መዛመት፤ ይዟቸው የሚመጣቸውን ጣጣዎችም በዚያው ልክ የገዘፉ እንዲሁም በዓለም ዙርያ የተሰራጩ አድርጓቸዋል። በዚያውም ልክ መጭውን ለመተነብይም አዳጋች ሆኗል። ይሁንና በልዩ ልዩ ዘርፎች የተሰማሩ ባለሞያዎች የጉዳቱን መጠን ለመስፈር፤ የድኅረ-ወረርሽኝ አቅጣጫዎችንም ለመቀየስ መሞከራቸው አልቀረም። ወረርሽኙ በሰዎች የሥራ እና የገቢ ሁኔታ ላይ የሚያሳርፈውን ጡጫ በተመለከተ ጥናት ያደረገው ዓለም አቀፉ የሥራ ድርጅት (አይ.ኤል.ኦ) እ.ኤ.አ መጋቢት 18 ቀን 2020 ባሳተመው ግምገማው ምንም እንኳ የኮሮናቫይረስ በዕድሜ የገፉትን እና ቀደም ሲል በሽታ የነበረባቸውን ግለሰቦችን የማጥቃት ከፍ ያለ ዕድል ቢኖረውም፤ ከወረርሽኙ በኋላ የሚከሰት የሥራ አጥነት ቀውስ ወትሮውኑም ሥራ ማጣት የሚያበረታባቸው ወጣቶች ላይ ሊጠነክር ይችላል ይላል። በአገልግሎት ዘርፍ በብዛት ተሰማርተው የሚገኙት ሴቶች፣ ዋስትና አልባ ሥራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች (ለምሳሌ የራሳቸውን ሥራ የሚሰሩ እና በጊዜያዊነት የተቀጠሩ) አንዲሁም ስደተኛ ሠራተኞች አንዲሁ ክፉኛ በሥራ አልባነት ማዕበል ክፉኛ ሊደቆሱ ይችላሉ ይላል የአይ.ኤል.ኦ ግምገማ። በምጣኔ ኃብት ያልጠነከሩ አገራት ኢትዮጵያም ወረርሽኙ የሚያስከትለውን የጤና ቀውስ ለመቋቋም ከምታደርጋቸው ጥረቶች ባሻገር ይዞት የሚመጣው የምጣኔ ኃብት ጡጫ ያሳሰባት ይመስላል። ከሳምንታት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የበለፀጉ አገራት ኢትዮጵያን ለመሳሰሉ የአፍሪካ አገራት የዕዳ ቅነሳ እና የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ እንዲያደርጉ መጠየቃቸው ይታወሳል። ባገባደድነው ሳምንት አዲስ አበባ ላይ በተደረገ የድረ ገፅ ላይ ውይይት የሥራ ፈጠራ ኮሚሽነሩ ኤፍሬም ተክሌ ሌማንጎ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ሥራዎቻቸውን ሊያጡ እንደሚችሉ መናገራቸው ተዘግቧል። የሥራ ዕጦቱ በአገሪቱ ትልቁ ኩባንያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጀመረ ይመስላል። የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ድርጅታቸው ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ 550 ሚሊዮን ዶላር ማጣቱን በገለፁበት መገለጫቸው ላይ ቋሚ ያልሆኑ ሠራተኞችን ለጊዜው ሥራ እንዲያቆሙ መደረጋቸውን ገልፀዋል። የኢትዮጵያ የምጣኔ ኃብት ማኅበር ያሳተመው የአራት ባለሞያዎች ምልከታ ከወረርሽኑም በፊት ለብዙዎቹ ኢትዮጵያውያን መሠረታዊ ግልጋሎቶችን ማግኘት አዳጋች ነበር፤ ይህም ወረርሽኙን ለመከላከል መደረግ ያለባቸውን እርምጃዎች ቀላል እንዳይሆኑ ያደርጋቸዋል ይላል። እንደአብነትም ከጠቅላላው ሕዝብ መካከል ስድስት በመቶ የሚሆነው ያህል በመኖርያው አቅራቢያ የመታጠቢያ ውሃ አለው ይላል። • “ገደቦችን በአጭር ጊዜ ማንሳት ወረርሽኙ በአስከፊ ሁኔታ እንዲሰራጭ ያደርጋል” ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም • ኮሮናቫይረስ ካለበት ሰው ጋር ንክኪ ላደረጉ ሰዎች ጥቆማ የሚሰጥ መሣሪያ እየተሠራ ነው ባለሞያዎቹ ብሔራዊው የስታትስቲክስ ድርጅት በማጠቀስ ከአራት ዓመት በፊት በተጠናቀረ መረጃ መሠረት አገሪቱ ውስጥ ካሉ ቤቶች ሰማንያ አምስት በመቶው ባለአንድ ወይንም ባለሁለት ክፍል መሆናቸውን አስታውሰው በኮቪድ 19 በሽታ ጥርጣሬ ቤት ውስጥ ተነጥሎ መቀመጥ አዋጭ አማራጭ ያለመሆኑን ይናገራሉ። ወረርሽኑ የሚፈጥረው የምጣኔ ኃብት ንዝረት የአገልግሎት ዘርፉን፣ ቱሪዝምን እና የመስተንገዶ ኢንዱስትሪውን፣ የውጭ ንግድን እና የመጓጓዣ ዘርፍን ሊጎዳ እንደሚችል የሚገምተው የባለሞያዎቹ ምልከታ ግብርናም ቢሆን ከዚህ የሚተርፍ አይደለም ይላል- በተለይ በቀላሉ የሚበላሹ ምርቶች አብቃዮች እና አከፋፋዮች ለጉዳት ተጋላጭ መሆናቸው አይቀርም። ወረርሽኙ የአቅርቦት ሰንሰለትን ያውካል። የሥራ መቀዛቀዝ በሚፈጥረው የገቢ እጥረት እንዲሁም የሚመጣው አይታወቅም በሚል ስጋት ምክንያት ሰዎች ገንዘብ ከማውጣት ስለሚቆጠቡ የፍላጎት እጥረትን ያስከትላል፤ አንዲሁም የንግድ ተቋማት የመንቀሳቀሻ ገንዘብ እጥረት እንዲያጋጥማቸው፣ ዕዳ መክፈል እንዲሳናቸውም ሊያደርግ ይችላል የባለሞያዎቹ ግምገማ እንደሚያመላክተው። እነዚህ ችግሮች እርስ በእርስ እየተመጋገቡ የምጣኔ ኃብት እንቅስቃሴው በአዝጋሚነት ዘለግ ላለ ጊዝ የሚዘልቅ ከሆነ ምጣኔ ኃብታዊ መኮማተር (ሪሰሽን) ሊከተልም ይችላል። ከኢትዮጵያ ጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት (ጂ.ዲ.ፒ.) ሰላሳ ዘጠኝ በመቶውን ድርሻ የሚይዘው የአገልገሎት ዘርፍ በወረርሽኙ ከሌሎች ዘርፎች በበለጠ ሊጎሳቆል ይችላል። ሰላሳ ሦሰት በመቶውን ድርሻ የሚይዘው ግብርና ግን ቢያንስ በአጭር ጊዜ ውስጥ በአንፃራዊነት ያነሰ ጉዳት ሊደርስበት ይችላል። በባለሞያዎቹ ግምት መሠረት ወረርሽኙ አነስ ባለ የጉዳት ለሦስት ወራት ያህል ቢቆይ እንኳ ምጣኔ ኃብቱ እስከ 44 ቢሊዮን ብር የሚደርስ እጦትን ሊያስተናግድ ይችላል። ወረርሽኙ ለስድስት ወራት ቢቆይና የከፋ ጉዳት የሚያደርስ ቢሆን የእጦቱ መጠን ከሁለት መቶ ቢሊዮን ብር ይሻገራል። ኮሮናቫይረስ ሠራተኞች ላይ ስለሚኖረው ተፅዕኖ የተሠራ አንድ ጥናት 3 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ሥራ-አጥ ሊሆኑ ይችላሉ ይላል። የኢትዮጵያ ኢኮኖሚስቶች ማኅበር ያሳተመው ጥናት ቫይረሱ ለረዥም ጊዜ የሚቆይ ከሆነ በርካቶች ሥራ-አጥ ሊሆኑ ይችላሉ ባይ ነው። በቅርቡ የኢትዮጵያ ሥራ ፈጠራ ኮሚሽን በሠራው ጥናት እንደሚጠቁመው ቫይረሱ ለስድስት ወራት የሚቆይ ከሆነ በማኒዩፈክቸሪንግ ዘርፍ የተሰማሩ 60 በመቶ ሰዎች ሥራቸውን ሊያጡ ይችላሉ።በተመሳሳይም በአገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ 74 በመቶ ሰዎች ሥራ-አጥ ይሆናሉ። ጥናቱ አክሎም ከ9 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ተሰማርተውበታል በሚባለው የአገልግሎት ዘርፍ ብቻ 3 ሚሊዮን ሰዎች ሥራቸውን ሊያጡ ይችላሉ ይላል። ቫይረሱ በኅብረተሰቡ ውስጥ ከተንሰራፋ አደጋው የከፋ ሊሆን እንደሚችል ጥናቱ ያስጠነቅቃል።ጥናቱ የተሠራው የቫይረሱን ቆይታ በሁለት በመከፋፈል ነው። የመጀመሪያው ለሦስት ወራት ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ስድስት ወራት ነው። የቫይረሱ ተፅዕኖ የከፋ ከሆነ ከ50 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን ችግር ላይ ሊወድቁ ይችላሉ ይላል።
https://www.bbc.com/amharic/52254173
2health
ህንድ፡በሬሳ ማቀዝቀዣ ውስጥ በህይወት የተገኙት ህንዳዊ ከቀናት በኋላ ሞቱ
በስህተት ሞተዋል ተብለው 'ሬሳቸው' ማቀዝቀዣ ውስጥ እንዲገባ የተደረጉት ህንዳዊ ከቀናት በኋላ ህይወታቸው አልፏል። ባላስቡራማንያም የተባሉት የ74 አመቱ ህንዳዊ ታሚል ግዛት ውስጥ በሚገኝ የግል ክሊኒክ ውስጥ ሞተዋል ተብለውም የሬሳ ማቀዝቀዣ ውስጥ አስገብተዋቸዋል። በነገታውም የቀብር ስነ ስርአታቸውን ለመፈፀም ማቀዝቀዣውን ከፍተው በሚያዩበት ወቅት ሰውነታቸው እየተንቀጠቀጠና በህይወት መኖራቸውም ታወቀ። ሆስፒታል እንደገና ቢወሰዱም ከአምስት ቀናት በኋላ ህይወታቸው እለፏል። ተመልሰው የተወሰዱበት የመንግሥት ሆስፒታል ኃላፊ ዶክተር ባላጂናታን እንደተናገሩት ህመምተኛው በከፍተኛ ሁኔታ ደክመው እንደነበርና ከሳንባ ጋር በተገናኘ እክልም ህይወታቸው ማለፉን ለቢቢሲ ታሚል ተናግረዋል። በሬሳ ማቀዝቀዣው ውስጥም ምን ያህል ሰዓታትን እንዳሳለፉ የተገለፀ ነገር የለም። ሰኞ እለት ሞተዋል ብሎ ዶክተሩ ከተናገረ በኋላ ቤተሰቡ አስከሬኑን ይዘው ወደቤታቸው ከወሰዱ በኋላም በአካባቢው የሚገኝ የጤና ባለሙያም ማቀዝቀዣ እንዲልክላቸው ጠየቁ። ለወዳጅ፣ ዘመድ አዝማዱም በነገታው የቀብር ስነ ስርአታቸውም እንደሚፈፀም ተነግሮም ነበር። የቀብር ስነ ስርአት አስፈፃሚ ድርጅቱም የባላስቡራማንያም ወንድም በጤና ባለሙያ የተፈረመ የሞት ሰርቲፊኬት እንዳላቸውም መነገራቸውን አስረድተዋል። ሆኖም የፖሊስ ኃላፊው ሴንቲል ኩማር እንዳሉት ከሆነ ቤተሰቡ የሞት ሰርቲፊኬቱን ማምጣት አልቻሉም። ፖሊስም ቤተሰቡ በመጣደፍና ችላ በማለት የሰውን ህይወት አደጋ ላይ ጥለዋል በማለትም ወንጅሏቸዋል። ግለሰቡ በነርቭ ህመም ችግርም ይሰቃዩ እንደነበር ቤተሰቡ ለፖሊስ ማሳወቃቸውን ኃላፊው አክለው ተናግረዋል። ባላስቡራማንያም ከባለቤታቸው፣ ሁለት ልጆቻቸውና ወንድማቸው ጋር ይኖሩ ነበር። በአስከሬን ማቀዝቀዣው ውስጥ ለሰዓታት ያህል በዚያ ቅዝቃዜ ውስጥ በህይወት እንዴት ቆዩ የሚለው ሚስጥራዊ ሆኗል። ከዚህም በተጨማሪ መጀመሪያ ግለሰቡን ሞቷል ያለው የግል ሆስፒታል እንዲሁም ዶክተር ምርመራ ተከፍቶባቸዋል።
ህንድ፡በሬሳ ማቀዝቀዣ ውስጥ በህይወት የተገኙት ህንዳዊ ከቀናት በኋላ ሞቱ በስህተት ሞተዋል ተብለው 'ሬሳቸው' ማቀዝቀዣ ውስጥ እንዲገባ የተደረጉት ህንዳዊ ከቀናት በኋላ ህይወታቸው አልፏል። ባላስቡራማንያም የተባሉት የ74 አመቱ ህንዳዊ ታሚል ግዛት ውስጥ በሚገኝ የግል ክሊኒክ ውስጥ ሞተዋል ተብለውም የሬሳ ማቀዝቀዣ ውስጥ አስገብተዋቸዋል። በነገታውም የቀብር ስነ ስርአታቸውን ለመፈፀም ማቀዝቀዣውን ከፍተው በሚያዩበት ወቅት ሰውነታቸው እየተንቀጠቀጠና በህይወት መኖራቸውም ታወቀ። ሆስፒታል እንደገና ቢወሰዱም ከአምስት ቀናት በኋላ ህይወታቸው እለፏል። ተመልሰው የተወሰዱበት የመንግሥት ሆስፒታል ኃላፊ ዶክተር ባላጂናታን እንደተናገሩት ህመምተኛው በከፍተኛ ሁኔታ ደክመው እንደነበርና ከሳንባ ጋር በተገናኘ እክልም ህይወታቸው ማለፉን ለቢቢሲ ታሚል ተናግረዋል። በሬሳ ማቀዝቀዣው ውስጥም ምን ያህል ሰዓታትን እንዳሳለፉ የተገለፀ ነገር የለም። ሰኞ እለት ሞተዋል ብሎ ዶክተሩ ከተናገረ በኋላ ቤተሰቡ አስከሬኑን ይዘው ወደቤታቸው ከወሰዱ በኋላም በአካባቢው የሚገኝ የጤና ባለሙያም ማቀዝቀዣ እንዲልክላቸው ጠየቁ። ለወዳጅ፣ ዘመድ አዝማዱም በነገታው የቀብር ስነ ስርአታቸውም እንደሚፈፀም ተነግሮም ነበር። የቀብር ስነ ስርአት አስፈፃሚ ድርጅቱም የባላስቡራማንያም ወንድም በጤና ባለሙያ የተፈረመ የሞት ሰርቲፊኬት እንዳላቸውም መነገራቸውን አስረድተዋል። ሆኖም የፖሊስ ኃላፊው ሴንቲል ኩማር እንዳሉት ከሆነ ቤተሰቡ የሞት ሰርቲፊኬቱን ማምጣት አልቻሉም። ፖሊስም ቤተሰቡ በመጣደፍና ችላ በማለት የሰውን ህይወት አደጋ ላይ ጥለዋል በማለትም ወንጅሏቸዋል። ግለሰቡ በነርቭ ህመም ችግርም ይሰቃዩ እንደነበር ቤተሰቡ ለፖሊስ ማሳወቃቸውን ኃላፊው አክለው ተናግረዋል። ባላስቡራማንያም ከባለቤታቸው፣ ሁለት ልጆቻቸውና ወንድማቸው ጋር ይኖሩ ነበር። በአስከሬን ማቀዝቀዣው ውስጥ ለሰዓታት ያህል በዚያ ቅዝቃዜ ውስጥ በህይወት እንዴት ቆዩ የሚለው ሚስጥራዊ ሆኗል። ከዚህም በተጨማሪ መጀመሪያ ግለሰቡን ሞቷል ያለው የግል ሆስፒታል እንዲሁም ዶክተር ምርመራ ተከፍቶባቸዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-54554015
5sports
የፕሪሚየር ሊግ ተጫዋቾች የኮቪድ ክትባት እንዲወስዱ በመንግሥትና በሊጉ ተጠየቁ
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ እና የዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) መንግሥት የእግር ኳስ ተጫዋቾች የኮቪድ-19 ክትባትን እንዲወስዱ አሳሰቡ። በሳምንቱ መጨረሻ ሊደረጉ የነበሩት የከፍተኛ ሊግ ጨዋታዎች ግማሾቹ ክለቦች ላይ እንደ አዲስ በተቀሰቀሰው ወረርሽኝ ምክንያት ለሌላ ጊዜ ተላልፏል። 25 በመቶ የሚሆኑ ተጫዋቾች ክትባት የማግኘት ፍላጎት እንደሌላቸው በመግለጻቸው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ቅዳሜ ሊደረጉ የታቀዱ 19 ጨዋታዎች ተሰርዘዋል። የዩኬ የስፖርት ሚኒስትር ኒጄል ሃድልስተን "ክትባት መውሰድ ማኅበራዊ ኃላፊነት ያለበት ተግባር ነው" ብለዋል። "እግር ኳስ ተጫዋቾችን ጨምሮ ማንኛውም ሰው እራሱን፣ ባልደረቦቹን እና የሚወዳቸውን ሰዎች ከቫይረሱ ለመጠበቅ ማድረግ የሚችለው እና በጣም ወሳኙ ነገር ክትባት መውሰድ እና ማጠናከሪያ ክትባት ማግኘት ነው" ብለዋል ሚኒስትሯ። "አንዳንድ ተጫዋቾች ለምን ክትባት ለመውሰድ እንደሚያመነቱ ለመረዳት የእግር ኳስ አመራሮች ከተጫዋቾች ጋር እየሰሩ መሆናቸውን አውቃለሁ" ሲሉም አክለዋል። የሊቨርፑሉ አስልጣኝ የርገን ክሎፕ ክትባቱን መውሰድ ግዴታ መሆን አለበት ብለው የሚያምኑ ሲሆን "ከሥነ ምግባር አንጻር" 99 በመቶ የሚሆኑት የቡድናቸው አባላት ሁለቱንም ዙር ክትባት ወስደዋል። ዋናው "የማሳመን ጉዳይ ነው" ነው የሚሉት አሰልጣኙ "በዙሪያዬ ያሉትን ሰዎች የሚረዳ አንድ ነገር ካደረግኩ እንደ ግዴታዬ እወስደዋለሁ። አንዳንድ ሰዎች ግን ይህንን በተለየ መንገድ እንደሚያዩት ግልጽ ነው" ሲሉ ተናግረዋል። "እኔ 54 ዓመቴ ነው እናም ሰዎችን ስለ ትክክለኛ ነገሮች ማሳመን እንደምችል በትልቁ አምናለሁ። ነገር ግን በዚህ ልዩ ጉዳይ ላይ ሰዎችን ማሳመን እንደምችል እርግጠኛ አይደለሁም" ሲሉም አክለዋል። በጥቅምት ወር የታተመ አንድ የፕሪሚየር ሊግ መረጃ 81 በመቶ የሚሆኑት የሊጉ ተጫዋቾች ቢያንስ አንድ ጊዜ የተከተቡ ሲሆን 68 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ሁለት ዙር ክትባት አግኝተዋል። በመላው ዩናይትድ ኪንግደም 89 በመቶ የሚሆኑት ከ12 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች የመጀመሪያውን ክትባት ወስደዋል፣ 82 በመቶዎቹ ደግሞ ሁለተኛውን ዙር የወሰዱ ሲሆን 44 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ የማጠናከሪያ ክትባት አግኝተዋል። በዩኬ ያልተከተቡ ሰዎች በኮሮናቫይረስ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ግንኙነት ካላቸው ለ10 ቀናት ራሳቸውን ማግለል እንዳለባቸው መንግሥት ያወጣው ሕጋዊ መመሪያ ያዛል። የፕሪሚየር ሊጉ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሪቻርድ ማስተርስ ሁሉም የሊጉ ክለቦች ተጫዋቾቻቸውን እንዲከተቡ "አበክረው እንዲያበረታቱ" በደብዳቤ ጠይቀዋል። "የክትባትን አስፈላጊነት በጋራ አስምረንበታል እናም ከዚህ የበለጠ አስፈላጊ የሆነ ነገር የለም" ሲሉ አስፍረዋል። ጨምረውም ኃላፊው "እባካችሁ ሙሉ በሙሉ ያልተከተቡት ክትባቱን እንዲወስዱ አጥብቃችሁ አበረታቷቸው። የኦሚክሮን ዝርያን ብቸኛው የመከላከያ ሽፋን የሆነውን ማጠናከሪያ እንዲያገኙም አበረታቷቸው" ሲሉ ጠይቀዋል። አንዳንዳንዶች በክትባቱ ውጤታማነት ላይ እምነት በማጣት፣ ሌሎች ደግሞ የጎንዮሽ ጉዳቶችን ወይም መርፌን መፍራትን ጨምሮ በርካታ ምክንያቶችን በመጥቀስ አለመከተብን ይመርጣሉ። በቁጥር አነስ ያሉ ሌሎች ደግሞ ከኢንተርኔት በተለይም በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በሚያገኟቸው የተሳሳቱ መረጃዎች እና የሴራ ትንታኔዎች ምክንያት ክትባት አይወስዱም።
የፕሪሚየር ሊግ ተጫዋቾች የኮቪድ ክትባት እንዲወስዱ በመንግሥትና በሊጉ ተጠየቁ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ እና የዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) መንግሥት የእግር ኳስ ተጫዋቾች የኮቪድ-19 ክትባትን እንዲወስዱ አሳሰቡ። በሳምንቱ መጨረሻ ሊደረጉ የነበሩት የከፍተኛ ሊግ ጨዋታዎች ግማሾቹ ክለቦች ላይ እንደ አዲስ በተቀሰቀሰው ወረርሽኝ ምክንያት ለሌላ ጊዜ ተላልፏል። 25 በመቶ የሚሆኑ ተጫዋቾች ክትባት የማግኘት ፍላጎት እንደሌላቸው በመግለጻቸው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ቅዳሜ ሊደረጉ የታቀዱ 19 ጨዋታዎች ተሰርዘዋል። የዩኬ የስፖርት ሚኒስትር ኒጄል ሃድልስተን "ክትባት መውሰድ ማኅበራዊ ኃላፊነት ያለበት ተግባር ነው" ብለዋል። "እግር ኳስ ተጫዋቾችን ጨምሮ ማንኛውም ሰው እራሱን፣ ባልደረቦቹን እና የሚወዳቸውን ሰዎች ከቫይረሱ ለመጠበቅ ማድረግ የሚችለው እና በጣም ወሳኙ ነገር ክትባት መውሰድ እና ማጠናከሪያ ክትባት ማግኘት ነው" ብለዋል ሚኒስትሯ። "አንዳንድ ተጫዋቾች ለምን ክትባት ለመውሰድ እንደሚያመነቱ ለመረዳት የእግር ኳስ አመራሮች ከተጫዋቾች ጋር እየሰሩ መሆናቸውን አውቃለሁ" ሲሉም አክለዋል። የሊቨርፑሉ አስልጣኝ የርገን ክሎፕ ክትባቱን መውሰድ ግዴታ መሆን አለበት ብለው የሚያምኑ ሲሆን "ከሥነ ምግባር አንጻር" 99 በመቶ የሚሆኑት የቡድናቸው አባላት ሁለቱንም ዙር ክትባት ወስደዋል። ዋናው "የማሳመን ጉዳይ ነው" ነው የሚሉት አሰልጣኙ "በዙሪያዬ ያሉትን ሰዎች የሚረዳ አንድ ነገር ካደረግኩ እንደ ግዴታዬ እወስደዋለሁ። አንዳንድ ሰዎች ግን ይህንን በተለየ መንገድ እንደሚያዩት ግልጽ ነው" ሲሉ ተናግረዋል። "እኔ 54 ዓመቴ ነው እናም ሰዎችን ስለ ትክክለኛ ነገሮች ማሳመን እንደምችል በትልቁ አምናለሁ። ነገር ግን በዚህ ልዩ ጉዳይ ላይ ሰዎችን ማሳመን እንደምችል እርግጠኛ አይደለሁም" ሲሉም አክለዋል። በጥቅምት ወር የታተመ አንድ የፕሪሚየር ሊግ መረጃ 81 በመቶ የሚሆኑት የሊጉ ተጫዋቾች ቢያንስ አንድ ጊዜ የተከተቡ ሲሆን 68 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ሁለት ዙር ክትባት አግኝተዋል። በመላው ዩናይትድ ኪንግደም 89 በመቶ የሚሆኑት ከ12 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች የመጀመሪያውን ክትባት ወስደዋል፣ 82 በመቶዎቹ ደግሞ ሁለተኛውን ዙር የወሰዱ ሲሆን 44 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ የማጠናከሪያ ክትባት አግኝተዋል። በዩኬ ያልተከተቡ ሰዎች በኮሮናቫይረስ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ግንኙነት ካላቸው ለ10 ቀናት ራሳቸውን ማግለል እንዳለባቸው መንግሥት ያወጣው ሕጋዊ መመሪያ ያዛል። የፕሪሚየር ሊጉ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሪቻርድ ማስተርስ ሁሉም የሊጉ ክለቦች ተጫዋቾቻቸውን እንዲከተቡ "አበክረው እንዲያበረታቱ" በደብዳቤ ጠይቀዋል። "የክትባትን አስፈላጊነት በጋራ አስምረንበታል እናም ከዚህ የበለጠ አስፈላጊ የሆነ ነገር የለም" ሲሉ አስፍረዋል። ጨምረውም ኃላፊው "እባካችሁ ሙሉ በሙሉ ያልተከተቡት ክትባቱን እንዲወስዱ አጥብቃችሁ አበረታቷቸው። የኦሚክሮን ዝርያን ብቸኛው የመከላከያ ሽፋን የሆነውን ማጠናከሪያ እንዲያገኙም አበረታቷቸው" ሲሉ ጠይቀዋል። አንዳንዳንዶች በክትባቱ ውጤታማነት ላይ እምነት በማጣት፣ ሌሎች ደግሞ የጎንዮሽ ጉዳቶችን ወይም መርፌን መፍራትን ጨምሮ በርካታ ምክንያቶችን በመጥቀስ አለመከተብን ይመርጣሉ። በቁጥር አነስ ያሉ ሌሎች ደግሞ ከኢንተርኔት በተለይም በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በሚያገኟቸው የተሳሳቱ መረጃዎች እና የሴራ ትንታኔዎች ምክንያት ክትባት አይወስዱም።
https://www.bbc.com/amharic/news-59708916
3politics
ኦፌኮ በብሔራዊ ውይይቱ የታጠቁ ቡድኖች እንዲካተቱ እና ጦርነት እንዲቆም ጠየቀ
በኢትዮጵያ ሊደረግ የታቀደው ብሔራዊ ውይይት የታጠቁ ተቃዋሚ ቡድኖችን ማሳተፍ ጨምሮ ሌሎች አራት ቅድመ ሁኔታዎች ሊያሟሉ እንደሚገባ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) አስታወቀ። እውነተኛ፣ ሐቀኛ እና ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ ውይይቶች ማካሄድ አገሪቱ የገባችበትን ፖለቲካዊ ቀውስ መፍታት እንደሚያስችልም ፓርቲው ጥቅምት 15/2013 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ኦፌኮ እንደ ቅድመ ሁኔታዎች ካስቀመጣቸው መካከል በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ጦርነት የአገሪቱን ሁለንተናዊ ህልውና አደጋ ላይ በመጣሉ ሊቆም እንደሚገባና ተፋላሚ ወገኖችም ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ ውይይት ማድረግ አለባቸው ብሏል። "በጦርነቱ አሸናፊና ተሸናፊ የለም" በማለትም የኦፌኮ ምክትል ሊቀ መንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ጦርነትን በማወጅ የምናመጣው ነገር የለም። ጠመንጃን የሚያነሱና በዚህ የሚያመልኩ ሰዎች ይህንን ጉዳይ ትተው ወደ ጠረጴዛ እንዲመጡ ነው። ዕልባት ሊሆን የሚችለው በጠረጴዛ ዙሪያ አንድ ላይ ሆነን ችግሮቻችን አንድ ላይ ስንማከር ነው። ወደ ውይይት መምጣት ታላቅነት ነው፣ ጀግንነት ነው። መዋጋቱና መገዳደሉ ዋና መፍትሔ አይሆንም"" ብለዋል አቶ ሙላቱ። ብሔራዊ ውይይቱ የአገሪቱን አንገብጋቢ ጥያቄ ሰላምን ትርጉም ባለው መልኩ ለመፍታትም ተቃዋሚ ታጣቂ ቡድኖችን ጨምሮ ሁሉንም የፖለቲካ አካላት ባሳተፈ መልኩ ሊሆን እንደሚገባው ፓርቲው አሳስቧል። መግለጫው ተቃዋሚ ታጣቂ ያላቸውን ቡድኖች በስም ባይጠቅስም ነገር ግን የሁሉንም ቡድኖች ውክልና ለማስጠበቅ የሕግ እና የደኅንነት እንቅፋቶች ሊወገዱም እንደሚገባም በቅድመ ሁኔታው አስቀምጧል። እነዚህን ታጣቂ ኃይሎች ማንነት በተመለከተ ቢቢሲ ለአቶ ሙላቱ ጥያቄ ያቀረበላቸው ሲሆን የኦሮሞ ነፃነት ጦርን ጨምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ጦርነት የሚያካሂዱና ስማቸው የማይነሳ አካላት እንዳሉም ይናገራሉ። ከእነዚህም መካከል "በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ ያለው የጉሙዝ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ታጣቂ ኃይል፣ በሰሜን በኩል ባለው ጦርነት የሚሳተፉ አካላት፣ በአፋርና በሶማሌ በኩል እየተካሄደ ባለው ጦርነት ያሉ ታጣቂዎችና፣ በአማራ ክልል ውስጥ መንግሥትን የሚገዳደሩና ለመብት የሚታገሉ ታጣቂ ኃይሎች" እንዳሉና በርካታም እንደሆኑ ያስረዳሉ። "እኛ ከጥይት የሚመጣ ምንም ነገር የለም። ከጠመንጃ አፈሙዝ ለጊዜው ሰላም ቢያመጣም ቋሚ አይደለም። ጊዜያዊ ነው" የሚሉት አቶ ሙላቱ አገሪቱ በጦርነት አዙሪት ውስጥ ለዘመናት መቆየቷ ወደ ኋላ እንደጎተታትና ብዙም መስዋዕነትም አስከፍሏል ይላሉ። ህወሓትን ጨምሮ መንግሥት ኦነግ ሸኔ የሚለው የኦሮሞ ነፃነት ጦር ሽብርተኛ ተብለው በኢትዮጵያ መንግሥት ከመፈረጃቸው አንፃር በምን መንገድ ድርድሩ ሊካሄድ ይችላል? ተብሎም ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄ አቶ ሙላቱ ሲመልሱ፡ "ሁሉንም በሆደ ሰፊነት ችሎ ለሰላም መንበርከክ መቻል አለብን። ሁሉም ወገኖች ኢትዮጵያውያን ናቸው። ማንም ሰው ለዚህ አገር ለብቻው ሰርቲፊኬት የያዘ የለም። ሰርቲፊኬት ሰጪና ነሽ የለም። የአንዱ ቃል ለአንዱ የሚጎረብጠው ቢሆን ቁጭ ብለን መነጋገሩ ነው ዋናው እንጂ አንዱ ኢትዮጵያዊ ሌላውን ኢትዮጵያዊ መግደሉ ጀግንነት አይደለም" ብለዋል። "በጠላት ተፈራርጆ እንዴት ነው አገር የሚፈርሰው? ወደየት እየሄድን ነው ተብሎ አይታሰብም? "በማለትም አቶ ሙላቱ ጨምረው ይጠይቃሉ። አንዳንዶች የሰላምና የድርድር ሃሳብ ሲያነሱ በህወሓት ወገንተኝነት የሚፈርጇቸው እንዳሉ አቶ ሙላቱ ጠቅሰው "ከማን ጋር ነው የምንደራደረው?" ብለው ጥያቄ ለሚያቀርቡ ሰዎችም አቶ ሙላቱ ምላሽ አላቸው። "የፈለገ ጠላትም ቢሆን በኢትዮጵያዊነቱ ቁጭ ብለን መደራደር አለብን። ለሰላም ስንል ወንበራችንንም ለቀን መሬት ቁጭ ብለን ተደራድረን አገራችንን ሰላም ማድረጉ አዋቂነት እንዲሁም ጀግንነት ነው" ይላሉ። አክለውም "የምናካሂደው የእርስ በርስ ጦርነት ነው። ትውልድ የሚገደልበት፣ የሚያልቅበት፣ በጠቅላላው ሲታይ ወጣት አሰልጥነን፣ ድሮን ከውጭ አምጥተን፣ በሌለን የውጭ ምንዛሬ ጥይት ገዝተን ሄደን አንደኛውን መግደል እብድነት ነው" በማለትም ያስረዳሉ። አቶ ሙላቱ ከጦርነቱ በተጨማሪ የተፈጥሮ ሁኔታና ረሃብም አገሪቱን እያቆረቆዛት ይገኛል በማለትም በትግራይና በአማራ ክልሎች ጦርነቱን ተከትሎ ከተከሰቱ ረሃቦች በተጨማሪ በጉጂና አካባቢው፣ ቦረናና ደቡብ በኩል ከፍተኛ ድርቅ መኖሩንና በየአቅጣጫው በተፈጠረው ችግር አገሪቱ እየተጎዳች መሆኑ አሳሳቢ መሆኑንም ያስረዳሉ። ሆኖም መፍትሄውና የአገሪቱ የመዳን እጣ ፈንታ በኢትዮጵያውያን ላይ መሆኑንም ጠቅሰው "ሁሉም ኢትዮጵያዊ አገሪቱ የገባችበትን እልቂት፣ ረሃብና አዘቅት በማት ልንታደጋት ይገባል። ሕዝቡም ቢሆን ይህ እልቂት የሚፈጠረው ለምንድን ነው ብሎ ሊጠይቅ ይገባል" በማለትም መፍትሄውም ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ ውይይት እንደሆነም አስምረዋል። የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ፣ ብልፅግና ያቀረበው ብሔራዊ ውይይት አንዳንዶች ዘግይቷል ሲሉ ማጣጣላቸውን የጠቀሰው መግለጫው ኦፌኮ በበኩሉ ዘግይቶም ቢሆን መካሄዱም እንደ ጥሩ እመርታ እንደሚያየው አስታውቆ ሆኖም እውነተኛና በሃቀኛ መንገድ ሊካሄድ እንደሚገባውም አመልከቷል። ብሔራዊ ውይይቱ በሁሉም ወገኖች ዘንድ ተቀባይነት ባለው እንዲሁም በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እውቅና እና ድጋፍ ባለው ገለልተኛ አካል ሊካሄድም እንሚገባም ፓርቲው እንደ ቅድመ ሁኔታ አስቀምጧል። "አገሪቱ ካለችበት የፖለቲካ ሁኔታ አንፃር ሲታይ በአገር ውስጥ ገለልተኛ እና በሁሉም ዘንድ ተቀባይነት ያለው ታማኝ አካል ማግኘትም አስቸጋሪ መሆኑ ልብ ሊባል ይገባል" በማለትም አትቷል። ከዚህም በተጨማሪ የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱና በዚህም ሂደት ተሳታፊ እንዲሆኑም ኦፌኮ በመግለጫው ጠይቋል። በቅርቡ በመስቀል አደባባይ የአዲስ መንግሥት ምስረታና በዓለ ሲመት ወቅት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ባደረጉት ንግግር፤ በአገሪቱ የፖለቲካ ኃይሎች መካከል መግባባትን ለመፍጠር ሁሉን አካታች ውይይት እንደሚካሄድ አመልክተው ነበር። የኢትዮጵያ ፖለቲካ አሸናፊ ብቻውን የሚገንበት ሳይሆን የመግባባትና በጋራ የመሥራት እንደሚሆን በንግግራቸው ጠቁመዋል። እንዲሁም የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ሁሉን አካታች የሆነ ብሔራዊ ውይይት እንደሚካሄድ በመንግሥት ምስረታው ወቅት መናገራቸው የሚታወስ ነው። ሆኖም ከአገሪቱ መሪዎች ከተናገሩት ውጪ ብሔራዊ ውይይቱ እንዴት እንደሚካሄድ፣ ማንን እንደሚያሳትፍ እንዲሁም ሌሎች ዝርዝር ሁኔታዎችን በተመለከተ መረጃ እንዳልደረሳቸው አቶ ሙላቱ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ባለፉት ሦስት ዓመታት እና ከዚያም በፊት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) የኢትዮጵያን ስር የሰደደ እና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣውን የፖለቲካ ቀውስ ለመፍታት የሚያግዝ ትርጉም ያለው አገራዊ ውይይት እንዲደረግ በተደጋጋሚ መጠያቁን አቶ ሙላቱ ያስታውሳሉ። ከዚያን ጊዜም ጀምሮ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ የኦፌኮ አመራሮች በስብሰባዎችም በአካልም ሆነ በመገናኛ ብዙኃን "ደካማውን ሽግግር" ለመታደግ እና አገሪቱን ወደከፋ ትርምስ ውስጥ እንዳትገባ የውይይት እና የድርድር ጥሪ ሲያቀርብ መቆየቱንም መግለጫው ጠቅሷል። ለአብነትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ወደ ስልጣን ሲመጡ ኦፌኮ የአገሪቱን አንገብጋቢ የፖለቲካዊ ጉዳዮች የሚወያይበት የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ሽግግር የሚረጋገጥበት የጋራ ፍኖተ ካርታ የሚቀረጽበት አገር አቀፍ የውይይት መድረክ እንዲዘጋጅ ተማፅኗል በማለትም ጠቅሶ ሆኖም እስካሁን ባለው ሁኔታ ሰሚ እንዳላገኙም አትቷል። በኦፌኮ ግምምገማ መሰረት በአገሪቱ በልሂቃን መካከል ያለው አለመተማመን ለወቅታዊው ቀውስ ትልቅ አስተዋፅኦ ካደረጉት መካከል አንዱ ነው በማለት "በብሔራዊ ውይይት ስም ሁሉን አቀፍ ያልሆነ ስብሰባ ማድረግ መተማመንን የበለጠ እንደሚሽርና ግጭቶች በሚፈጠሩበት ወቅት በውይይት መፍታት እንኳን የማይቻል ያደርገዋል" በማለት አስፍሯል። ስለዚህ ኦፌኮ ከዚህ ቀደምም እውነተኛ ብሔራዊ ውይይት እንዲደረግ በመጥራት ግንባር ቀደም የነበረ ቢሆንም የመጪው ብሔራዊ ውይይት ኦፌኮ ያስቀመጣቸውን ቅድመ ሁኔታዎች እስካላሟላ ድረስ "በግማሽ ልብ የሚደረግ ተሳትፎ ትርጉም የለሽ እና አጠቃላይ ሁኔታው ከንቱ ነው" በማለትም አስቀምጧል። መንግሥት በተለያዩ ጊዜያት ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ ውይይት በዚህ ዓመት እንደሚካሄድ የገለጸ ሲሆን ይህ ውይይት ማንን እንደሚያካትና መቼ እንደሚካሄድ አስካሁን በይፋ የተገለጸ ነገር ለም።
ኦፌኮ በብሔራዊ ውይይቱ የታጠቁ ቡድኖች እንዲካተቱ እና ጦርነት እንዲቆም ጠየቀ በኢትዮጵያ ሊደረግ የታቀደው ብሔራዊ ውይይት የታጠቁ ተቃዋሚ ቡድኖችን ማሳተፍ ጨምሮ ሌሎች አራት ቅድመ ሁኔታዎች ሊያሟሉ እንደሚገባ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) አስታወቀ። እውነተኛ፣ ሐቀኛ እና ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ ውይይቶች ማካሄድ አገሪቱ የገባችበትን ፖለቲካዊ ቀውስ መፍታት እንደሚያስችልም ፓርቲው ጥቅምት 15/2013 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ኦፌኮ እንደ ቅድመ ሁኔታዎች ካስቀመጣቸው መካከል በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ጦርነት የአገሪቱን ሁለንተናዊ ህልውና አደጋ ላይ በመጣሉ ሊቆም እንደሚገባና ተፋላሚ ወገኖችም ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ ውይይት ማድረግ አለባቸው ብሏል። "በጦርነቱ አሸናፊና ተሸናፊ የለም" በማለትም የኦፌኮ ምክትል ሊቀ መንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ጦርነትን በማወጅ የምናመጣው ነገር የለም። ጠመንጃን የሚያነሱና በዚህ የሚያመልኩ ሰዎች ይህንን ጉዳይ ትተው ወደ ጠረጴዛ እንዲመጡ ነው። ዕልባት ሊሆን የሚችለው በጠረጴዛ ዙሪያ አንድ ላይ ሆነን ችግሮቻችን አንድ ላይ ስንማከር ነው። ወደ ውይይት መምጣት ታላቅነት ነው፣ ጀግንነት ነው። መዋጋቱና መገዳደሉ ዋና መፍትሔ አይሆንም"" ብለዋል አቶ ሙላቱ። ብሔራዊ ውይይቱ የአገሪቱን አንገብጋቢ ጥያቄ ሰላምን ትርጉም ባለው መልኩ ለመፍታትም ተቃዋሚ ታጣቂ ቡድኖችን ጨምሮ ሁሉንም የፖለቲካ አካላት ባሳተፈ መልኩ ሊሆን እንደሚገባው ፓርቲው አሳስቧል። መግለጫው ተቃዋሚ ታጣቂ ያላቸውን ቡድኖች በስም ባይጠቅስም ነገር ግን የሁሉንም ቡድኖች ውክልና ለማስጠበቅ የሕግ እና የደኅንነት እንቅፋቶች ሊወገዱም እንደሚገባም በቅድመ ሁኔታው አስቀምጧል። እነዚህን ታጣቂ ኃይሎች ማንነት በተመለከተ ቢቢሲ ለአቶ ሙላቱ ጥያቄ ያቀረበላቸው ሲሆን የኦሮሞ ነፃነት ጦርን ጨምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ጦርነት የሚያካሂዱና ስማቸው የማይነሳ አካላት እንዳሉም ይናገራሉ። ከእነዚህም መካከል "በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ ያለው የጉሙዝ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ታጣቂ ኃይል፣ በሰሜን በኩል ባለው ጦርነት የሚሳተፉ አካላት፣ በአፋርና በሶማሌ በኩል እየተካሄደ ባለው ጦርነት ያሉ ታጣቂዎችና፣ በአማራ ክልል ውስጥ መንግሥትን የሚገዳደሩና ለመብት የሚታገሉ ታጣቂ ኃይሎች" እንዳሉና በርካታም እንደሆኑ ያስረዳሉ። "እኛ ከጥይት የሚመጣ ምንም ነገር የለም። ከጠመንጃ አፈሙዝ ለጊዜው ሰላም ቢያመጣም ቋሚ አይደለም። ጊዜያዊ ነው" የሚሉት አቶ ሙላቱ አገሪቱ በጦርነት አዙሪት ውስጥ ለዘመናት መቆየቷ ወደ ኋላ እንደጎተታትና ብዙም መስዋዕነትም አስከፍሏል ይላሉ። ህወሓትን ጨምሮ መንግሥት ኦነግ ሸኔ የሚለው የኦሮሞ ነፃነት ጦር ሽብርተኛ ተብለው በኢትዮጵያ መንግሥት ከመፈረጃቸው አንፃር በምን መንገድ ድርድሩ ሊካሄድ ይችላል? ተብሎም ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄ አቶ ሙላቱ ሲመልሱ፡ "ሁሉንም በሆደ ሰፊነት ችሎ ለሰላም መንበርከክ መቻል አለብን። ሁሉም ወገኖች ኢትዮጵያውያን ናቸው። ማንም ሰው ለዚህ አገር ለብቻው ሰርቲፊኬት የያዘ የለም። ሰርቲፊኬት ሰጪና ነሽ የለም። የአንዱ ቃል ለአንዱ የሚጎረብጠው ቢሆን ቁጭ ብለን መነጋገሩ ነው ዋናው እንጂ አንዱ ኢትዮጵያዊ ሌላውን ኢትዮጵያዊ መግደሉ ጀግንነት አይደለም" ብለዋል። "በጠላት ተፈራርጆ እንዴት ነው አገር የሚፈርሰው? ወደየት እየሄድን ነው ተብሎ አይታሰብም? "በማለትም አቶ ሙላቱ ጨምረው ይጠይቃሉ። አንዳንዶች የሰላምና የድርድር ሃሳብ ሲያነሱ በህወሓት ወገንተኝነት የሚፈርጇቸው እንዳሉ አቶ ሙላቱ ጠቅሰው "ከማን ጋር ነው የምንደራደረው?" ብለው ጥያቄ ለሚያቀርቡ ሰዎችም አቶ ሙላቱ ምላሽ አላቸው። "የፈለገ ጠላትም ቢሆን በኢትዮጵያዊነቱ ቁጭ ብለን መደራደር አለብን። ለሰላም ስንል ወንበራችንንም ለቀን መሬት ቁጭ ብለን ተደራድረን አገራችንን ሰላም ማድረጉ አዋቂነት እንዲሁም ጀግንነት ነው" ይላሉ። አክለውም "የምናካሂደው የእርስ በርስ ጦርነት ነው። ትውልድ የሚገደልበት፣ የሚያልቅበት፣ በጠቅላላው ሲታይ ወጣት አሰልጥነን፣ ድሮን ከውጭ አምጥተን፣ በሌለን የውጭ ምንዛሬ ጥይት ገዝተን ሄደን አንደኛውን መግደል እብድነት ነው" በማለትም ያስረዳሉ። አቶ ሙላቱ ከጦርነቱ በተጨማሪ የተፈጥሮ ሁኔታና ረሃብም አገሪቱን እያቆረቆዛት ይገኛል በማለትም በትግራይና በአማራ ክልሎች ጦርነቱን ተከትሎ ከተከሰቱ ረሃቦች በተጨማሪ በጉጂና አካባቢው፣ ቦረናና ደቡብ በኩል ከፍተኛ ድርቅ መኖሩንና በየአቅጣጫው በተፈጠረው ችግር አገሪቱ እየተጎዳች መሆኑ አሳሳቢ መሆኑንም ያስረዳሉ። ሆኖም መፍትሄውና የአገሪቱ የመዳን እጣ ፈንታ በኢትዮጵያውያን ላይ መሆኑንም ጠቅሰው "ሁሉም ኢትዮጵያዊ አገሪቱ የገባችበትን እልቂት፣ ረሃብና አዘቅት በማት ልንታደጋት ይገባል። ሕዝቡም ቢሆን ይህ እልቂት የሚፈጠረው ለምንድን ነው ብሎ ሊጠይቅ ይገባል" በማለትም መፍትሄውም ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ ውይይት እንደሆነም አስምረዋል። የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ፣ ብልፅግና ያቀረበው ብሔራዊ ውይይት አንዳንዶች ዘግይቷል ሲሉ ማጣጣላቸውን የጠቀሰው መግለጫው ኦፌኮ በበኩሉ ዘግይቶም ቢሆን መካሄዱም እንደ ጥሩ እመርታ እንደሚያየው አስታውቆ ሆኖም እውነተኛና በሃቀኛ መንገድ ሊካሄድ እንደሚገባውም አመልከቷል። ብሔራዊ ውይይቱ በሁሉም ወገኖች ዘንድ ተቀባይነት ባለው እንዲሁም በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እውቅና እና ድጋፍ ባለው ገለልተኛ አካል ሊካሄድም እንሚገባም ፓርቲው እንደ ቅድመ ሁኔታ አስቀምጧል። "አገሪቱ ካለችበት የፖለቲካ ሁኔታ አንፃር ሲታይ በአገር ውስጥ ገለልተኛ እና በሁሉም ዘንድ ተቀባይነት ያለው ታማኝ አካል ማግኘትም አስቸጋሪ መሆኑ ልብ ሊባል ይገባል" በማለትም አትቷል። ከዚህም በተጨማሪ የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱና በዚህም ሂደት ተሳታፊ እንዲሆኑም ኦፌኮ በመግለጫው ጠይቋል። በቅርቡ በመስቀል አደባባይ የአዲስ መንግሥት ምስረታና በዓለ ሲመት ወቅት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ባደረጉት ንግግር፤ በአገሪቱ የፖለቲካ ኃይሎች መካከል መግባባትን ለመፍጠር ሁሉን አካታች ውይይት እንደሚካሄድ አመልክተው ነበር። የኢትዮጵያ ፖለቲካ አሸናፊ ብቻውን የሚገንበት ሳይሆን የመግባባትና በጋራ የመሥራት እንደሚሆን በንግግራቸው ጠቁመዋል። እንዲሁም የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ሁሉን አካታች የሆነ ብሔራዊ ውይይት እንደሚካሄድ በመንግሥት ምስረታው ወቅት መናገራቸው የሚታወስ ነው። ሆኖም ከአገሪቱ መሪዎች ከተናገሩት ውጪ ብሔራዊ ውይይቱ እንዴት እንደሚካሄድ፣ ማንን እንደሚያሳትፍ እንዲሁም ሌሎች ዝርዝር ሁኔታዎችን በተመለከተ መረጃ እንዳልደረሳቸው አቶ ሙላቱ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ባለፉት ሦስት ዓመታት እና ከዚያም በፊት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) የኢትዮጵያን ስር የሰደደ እና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣውን የፖለቲካ ቀውስ ለመፍታት የሚያግዝ ትርጉም ያለው አገራዊ ውይይት እንዲደረግ በተደጋጋሚ መጠያቁን አቶ ሙላቱ ያስታውሳሉ። ከዚያን ጊዜም ጀምሮ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ የኦፌኮ አመራሮች በስብሰባዎችም በአካልም ሆነ በመገናኛ ብዙኃን "ደካማውን ሽግግር" ለመታደግ እና አገሪቱን ወደከፋ ትርምስ ውስጥ እንዳትገባ የውይይት እና የድርድር ጥሪ ሲያቀርብ መቆየቱንም መግለጫው ጠቅሷል። ለአብነትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ወደ ስልጣን ሲመጡ ኦፌኮ የአገሪቱን አንገብጋቢ የፖለቲካዊ ጉዳዮች የሚወያይበት የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ሽግግር የሚረጋገጥበት የጋራ ፍኖተ ካርታ የሚቀረጽበት አገር አቀፍ የውይይት መድረክ እንዲዘጋጅ ተማፅኗል በማለትም ጠቅሶ ሆኖም እስካሁን ባለው ሁኔታ ሰሚ እንዳላገኙም አትቷል። በኦፌኮ ግምምገማ መሰረት በአገሪቱ በልሂቃን መካከል ያለው አለመተማመን ለወቅታዊው ቀውስ ትልቅ አስተዋፅኦ ካደረጉት መካከል አንዱ ነው በማለት "በብሔራዊ ውይይት ስም ሁሉን አቀፍ ያልሆነ ስብሰባ ማድረግ መተማመንን የበለጠ እንደሚሽርና ግጭቶች በሚፈጠሩበት ወቅት በውይይት መፍታት እንኳን የማይቻል ያደርገዋል" በማለት አስፍሯል። ስለዚህ ኦፌኮ ከዚህ ቀደምም እውነተኛ ብሔራዊ ውይይት እንዲደረግ በመጥራት ግንባር ቀደም የነበረ ቢሆንም የመጪው ብሔራዊ ውይይት ኦፌኮ ያስቀመጣቸውን ቅድመ ሁኔታዎች እስካላሟላ ድረስ "በግማሽ ልብ የሚደረግ ተሳትፎ ትርጉም የለሽ እና አጠቃላይ ሁኔታው ከንቱ ነው" በማለትም አስቀምጧል። መንግሥት በተለያዩ ጊዜያት ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ ውይይት በዚህ ዓመት እንደሚካሄድ የገለጸ ሲሆን ይህ ውይይት ማንን እንደሚያካትና መቼ እንደሚካሄድ አስካሁን በይፋ የተገለጸ ነገር ለም።
https://www.bbc.com/amharic/news-59046893
3politics
የህወሓትና በትግራይ ያሉ ተቃዋሚዎች ውዝግብ
በቅርቡ በትግራይ የሚንቀሳቀሱ ሦስት ተቃዋሚ ፓርቲዎች በትግራይ ክልል ስለተካሄደው ጦርነት እና ስለ ክልሉ አስተዳደር ላይ በጋራ መግለጫ ያወጡ ሲሆን፣ በክልሉ ሁሉን አቀፍ የሽግግር አስተዳደር እንዲቋቋምም ጠይቀዋል። በክልሉ ሥልጣን ላይ ህወሐት ለዘመናት የበላይ ሆኖ መቆየቱን የሚቃወሙት ሦስቱ ፓርቲዎች ሳልሳይ ወያነ ትግራይ (ሳወት)፣ የትግራይ ነፃነት ፓርቲ (ውናት) እንዲሁም ባይቶ ዓባይ ትግራይ (ባይቶና) ናቸው። እነዚህ ፓርቲዎች ሁለት ዓመት ሊሞላው የተቃረበውን ጦርነት ለማብቃት ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ይካሄዳል በተባለው ድርድር ላይ ህወሓት ትግራይን ወክሎ የመደራደርም ሆነ ክልሉን በብቸኝነት የማስተዳደር ህጋዊምና ሞራላዊ መብት የለውም ይላሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን መምጣታቸውን ተከትሎ ከማዕከላዊው መንግሥት ፖለቲካ የተገፋው ህወሓት፣ በፌደራል መንግሥቱ ተቀባይነት ያላገኘ ክልላዊ ምርጫዎች በማካሄድ ‘የሕዝብ ተቀባይነት’ አግኝቻለሁ በማለት ሥልጣኑን ለማጠናከር የሚያስችለው ሁኔታ ፈጥሮ ነበር። ነገር ግን በጥቅምት ወር 2013 ዓ.ም. የተቀሰቀሰን ጦርነት ተከትሎ ህወሓት ከክልላዊ ሥልጣኑ ተወግዶ በሕዝቡ ዘንድ ብዙም ተቀባይነት ያላገኘ በገዢው ብልጽግና ፓርቲ መሪነት በትግራይ ለአጭር ጊዜ የቆየ ጊዜያዊ አስተዳደር ተመስርቶ ነበር። ጦርነቱን ተከትሎ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የጅምላ ግድያ፣ ዘረፋ፣ ጾታዊ ጥቃት እና የመሠረተ ልማቶች ውድመት ደርሷል። የተባበሩት መንግሥታት እና ሌሎችም የመብት ተቋማት ለተፈጸሙት ጥፋቶች ህወሓትን ጨምሮ ሁሉንም ተጻራሪ ኃይሎች ተጠያቂ ያደርጋል። የሳልሳይ ወያነ ትግራይ የውጭ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ኃይሉ ከበደ “በልጆቹና ባለቤቱ፣ በእናቱ እና በእህቶቹ ላይ ግፍና በደል የተፈጸመበት የትግራይ ሕዝብ የታገለው ለሉአላዊነቱ እና ለደኅንነቱ እንጂ ለህወሓት አልነበረም” ይላሉ። “ህወሓት በሕግ ይሁን በሞራል ከሥልጣን በኃይል ተወግዷል። በዚህ መካከልም ሌላ አስተዳደር ተመስርቶ ነበር። ትግላችን የትግራይን መንግሥትነት መመለስ ነበር” ሲሉ ያስረዳሉ። የባይቶና ፓርቲ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ክብሮም በርኸ ከመታሰራቸው ከቀናት በፊት ለቢቢሲ እንደተናገሩት “ህወሓት ከፕሮፓጋንዳ በዘለለ ተገቢውን ወታደራዊ ዝግጅት ባለማድረጉ የትግራይ ሕዝብን ለአደጋ እንዲጋለጥ ስላደረገ ከሕዝቡ ጋር የነበረው ውል ፈርሷል” ይላሉ። በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱት ተቃዋሚ ፓርቲዎች በክልሉ ውስጥ ለተፈጸተው ክፈተት ተጠያቂ የሚያደርጉት ህወሓትን ነው። በአዲስ መልክ የተደራጁት የትግራይ ኃይሎች ሰኔ 21/2013  ዓ.ም. ላይ መቀለን ከተቆጣጠሩ በኋላ የህወሓት ሊቀመንበር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) የቀድሞ የክልሉ አስተዳደር ወደ ቦታው መመለሱን አስታውቀዋል። ነገር ግን በትግራይ ሁሉን አሳታፊ አስተዳደር መመስረትን በተመለከተ ጥያቄ ሲያቀርቡ የነበሩት የትግራይ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በአዲሱ መንግሥት ውስጥ ምንም ቦታና እውቅና አልተሰጣቸውም። የሦስቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሊቀመንበሮችን ጨምሮ በርካታ አባሎቻቸው በትጥቅ ትግሉ የተሳተፉ ቢሆንም ህወሓት ግን ከበረሃ ተመልሶ ሥልጣኑን ብቻውን መቆጣጠር ነው የመረጠው ይላሉ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አንዳንዶች የሽግግር መንግሥት እንዲቋቋም ሲጠይቁ ሌሎች ደግሞ ጥምር ክልላዊ ምክር ቤት እንዲቋቋም ጠይቀዋል። ሆኖም ከህወሓት ምንም አይነት አዎንታዊ ምላሽ አላገኙም። ለአቶ ኃይሉ ከበደ በትግራይ ሁሉን አሳታፊ መንግሥት መመስረት ማለት በሕዝባዊ ተቋማቱ በኩል አዲስና አሳታፊ ሕዝባዊ አስተዳደርን ማወቀር ማለት ነው። “ሕዝባዊ ትግል ነው ያካሄድነው፤ ስለሆነም ሕዝባዊ መንግሥት መመስረት አለበት የሚል እምነት ነበረን” ይላሉ። አያይዘውም “እኛ የምንታገለው የትግራይ መንግሥትነት እንዲመለስ እንጂ ህወሓት እንዲመለስና ብቻውን ያለፉትን 30 ዓመታት እንዲደግም አይደለም” በማለት ያስረዳሉ። የትግራይ ነፃነት አገርነት አላማው አድርጎ የሚንቀሳቀሰው የትግራይ ነፃነት ፓርቲ (ውናት) ከፍተኛ አመራር የሆኑት ዶ/ር ደጀን መዝገበ በቅርቡ በሰጡት መግለጫ “ጥምር መንግሥት መሥርተን በጋራ ለመሥራት ተስፋ አድርገን ነበር” ብለዋል። ህወሓትን “ህገወጥ” የሚሉት የትግራይ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የጋራ አቋም በመያዝ ባወጡት የጋራ መግለጫ ህወሓትን ያካተተ ሕዝባዊ የሽግግር መንግሥት በክልሉ እንዲመሰረት ጠይቀዋል። ነገር ግን በአሜሪካ የህወሓት ተወካይ የሆኑት አቶ ዮሐንስ አብረሃ “ከዚህ ቀደም ሕጋዊ ክልላዊ መንግሥት ወደ ቦታው ይመለስ ብለው ሲጠይቁ ቆይተው፣ ዛሬ ደግሞ ተመልሰው የሽግግር መንግሥት ጥያቄ ማቅረባቸው ልክ አይደለም” ብለዋል። አክለውም “የትግራይ መንግሥትን ሕገወጥ ነው” በማለት መክሰሳቸው፣ ፓርቲዎቹን እሳቸው ‘የጠላት ኃይሎች’ ሲሉ ከሚገልጿቸው አካላት ነጥለው ለማየት እንደሚቸገሩ ገልፀዋል። የህወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ ተቃዋሚዎችን “ቀበጦች” ሲሉ በማኅበራዊ ሚድያ ላይ የወረፏቸው ሲሆን ለዚህ አባባላቸውም ከብዙዎች ዘንድ ጠንካራ ትችት ቀርቦባቸዋል። በውጭ አገራት የሚኖሩ ሌሎች የህወሓት ‘ቀንደኛ’ ደጋፊዎች በበኩላቸው ተቃዋሚዎቹን ‘የዐቢይ ተላላኪዎች’ በማለት እርምጃ እንዲወሰድባቸው ጠይቀዋል። ‘የሥልጣን ጥመኞች’ ሲሉም የሚከሷቸው አሉ። ክብሮም በርኸ “ሥልጣን ፈላጊዎች ይሉናል። ሥልጣን ብንፈልግም ሃጢአት አይደለም። እኛ ፖለቲከኞች ነን፤ ምንም የሚያሳፍር ነገር የለውም። ሊያፍሩ የሚገባቸው እነዚያ በመጠቃቀምና በስብስብ ሥልጣን የተቆጣጠሩ ሰዎች ናቸው” ብሏል። ጦርነቱ በሰላማዊ መንገድ እንዲያበቃ በተለይም በአሜሪካ፣ በኬንያ እና በአፍሪካ ኅብረት የሚመሩ የድርድር ጥረቶች እየተሞከሩ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድም በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የሚመራ ተደራዳሪ ኮሚቴ መሰየሙን አስታውቀዋል። የህወሓት መሪዎችም በኬንያ መንግሥት ለሚመራ ውይይት ዝግጁ መሆናቸውን የገለጹ ሲሆን፣ ተደራዳሪዎቻቸውን ግን እስካሁን ይፋ አላደረጉም። ከባድ ሰብዓዊና ቁሳዊ ቀውስ ያስከተለው ጦርነት ብዙዎች በሰላማዊ መንገድ ይፈታ ይሆን በሚል ተስፋ ቢያደርጉም ሌሎች ደግሞ “ጊዜ መግዣ ነው” የሚል ጥርጣሪ አላቸው። በሰሜን አሜሪካ የህወሓት ተወካይ አቶ ዮሐንስ አብረሃ “በእኛ በኩል በውይይት መፍትሄ ሊመጣ ይችላል ብለን እናምናለን” በማለት ከሌላኛው ወገን በኩል ግን ጥርጣሬ እንዳላቸው ለቢቢሲ ገልፀዋል። አቶ ኃይሉ ከበደ ግን “የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት አንዴ ፈርሷል። ለቀጣይ አቅጣጫም መነሻ ሊሆን አይችልም። የትግራይን ሕዝብ ጥቅም ሊያስከብር አይችልም። በእሱ ተደራድረን የምናሳካው ጥቅምም የለም” ይላሉ። ተቃዋሚ ፓርቲዎቹም ከዚህ በመነሳት ነው ህወሓት የመደራደር ውክልና የለውም በማለት “የትግራይን ሕዝብ ለዚህ ውርደት አጋልጦ ትንሽ መፀፀት ያስፈልግ ነበር። እነዚህ ግን በድርቅና አድራጊ ፈጣሪ እኛ ነን እያሉ ነው” በማለት አቶ ኃይሉ ህወሓትን ይወቅሳሉ። ዶ/ር ደጀን በበኩላቸው ይህንን ተቃዋሚዎች አለ የሚሉትን የሕግ ክፍተት በመጥቀስ “ህወሓት ብቻውን ለመደራደርም ሆነ ትግራይን ለመምራት ምንም አይነት የሕግ መሰረት የለውም” ሲሉ ይቃወማሉ። ይህን ያሉበት ምክንያት ሲያስረዱም “በየትኛው ሕግ ነው ሠራዊት ሊገነባ እና ዲፕሎማሲን ማስቀጠል የሚችለው?” በማለት በሕገ መንግሥቱ መሰረት እነዚህ የፌደራል መንግሥት ተግባራት መሆናቸውን ያስታውሳሉ። አክለውም “ከሕገ መንግሥቱ ውጪ የሆነ ኃላፊነት የያዘ መንግሥት አለ። ይህን መስራት የሚችል ኃላፊነት ያለው ፓርቲ የለም።። የወደፊት የትግራይ ዕጣ ለዘላለም ብቻውን እንዲወስን የተመረጠ ፓርቲ የለም። የህወሓት ስርወ መንግሥትንም ለመመስረት የመረጠ ሕዝብም የለም” ይላሉ። “ህወሓት ለረጅም ጊዜ በሥልጣን ላይ ቆይቷል ለማለት ከሆነ ይገባኛል” በማለት የሚናገሩት አቶ ዮሐንስ ነገር ግን ፓርቲው በሕግ አግባብ መመረጡን ይጠቅሳሉ። ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ በመላ ትግራይ ተንቀሳቅሰው የህዝቡን ቀልብ መሳብ የሚችሉበትን ሁኔታ ፈጥረው፣ ሕዝቡ ህወሓትን በቃህ የሚለው ከሆነ የሕዝቡን ፍላጎት እንደሚያከብሩ አቶ ዮሐንስ ያስዳሉ። ነገር ግን ፓርቲዎቹ ሕዝባዊ ስብሰባ እንኳን እንዳያካሂዱ መከልከላቸውን እና እንቅስቃሴያቸውም መገደቡን በማስመልከት ስለሚያርቡት አቤቱታ ከቢቢሲ የተጠየቁት አቶ ዮሐንስ በጉዳዩ ላይ መረጃ እንደሌላችው በመግለጽ “እንደዚያ የተደረገ ግን አይመስለኝም” ብለዋል። የትግራይ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከህወሓት ጋር በጋራ ለመሥራት ‘የፓርቲዎች የጋራ መድረክ’ ተቋቁሞ በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ በጋራ መወያየት ጀምረው እንደነበረ ያስታውሳሉ። “የፓርቲዎች ፎረምን የልጆች መጫወቻ አድርገውታል” የሚሉት አቶ ኃይሉ ከበደ፣ ህወሓት ሲፈልግ ብቻ እንደሚሰበሰቡና ወታደራዊ ድሎች ሲገኙ ግን እንደሚረሱ ጠቅሰዋል። አቶ ጌታቸው ረዳ ግን የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮች ከስምንት ጊዜ በላይ ከዶ/ር ደብረፂዮን ጋር  መወያየታቸውን በማኅበራዊ ሚድያ ጽሁፋቸው ላይ አስፍረው ነበር። አቶ ኃይሉ ከበደ ግን “ከኅዳር ወር በኋላ ‘መከበብና መዘጋት’ ወደ ሚለው ግልፅ ወዳልሆነ ፖለቲካ ገባን። የትግራይ ሕዝብ እየጠፋና እየረገፈ ነው። በህወሓት ምክንያት ዲፕሎማሲያዊ ሥራ መሥራት አልተቻለም። የትግራይ ሕዝብ ትግል ዲፕሎማሲያዊ አጋር አላገኘም” ይላል። ተቃዋሚዎቹ ትግራይ ውስጥ በተካሄደው ጦርነት ምክያት ሕገ መንግሥቱ በአገር አቀፍ እና በክልል ደረጃ ፈርሷል ብለው እንደሚያምኑ ይናገራሉ። የህወሓት ተወካይ አቶ ዮሐንስ ግን “ሕገ መንግሥቱ ፈርሷል ካልን እነሱስ በየትኛው አሰራር ነው ሕጋዊ ተቃዋሚ የሆኑት?” ሲሉ ይጠይቃሉ። “ሕገ መንግሥታዊ ቀውስ ነው ያጋጠመው” የሚለው ፖለቲከኛ ክብሮም በርኸ በበኩሉ አዲስ ውል ማሰር እንደሚያስፈልግ ያምናል። "ለዓላማችን ስንል ሠራዊት ልንገነባና ዲፕሎማሲ መሥራት ስላለብን የሕግ ክፍተቱን ለመሙላት ፓርቲዎችና ሌሎች ግለሰቦች የሚሳተፉበት የጋራ መድረክ ሊኖር ይገባል” ይላሉ ዶክተር ደጀን በበኩላቸው። በአሜሪካ የህወሓት ተወካይ የሆኑት አቶ ዮሐንስ አብርሃ “ሕገ መንግሥቱ ተሸራርፏል እንጂ ፈርሷል” ብለው እንደማያምኑ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ሕገ መንግሥቱ ፈርሷል ካልን ያለሱ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ለመንቀሳቀስ ይከብደናል” ሲሉም ይሞግታሉ። “አሁን የሽግግር መንግሥት ቢቋቋም ተቃዋሚ ኃይሎቹ ከድርጊታቸው ይቆጠቡ ነበር?” የሚል ጥያቄ በማንሳትም የቀረበው ሐሳብ መፍትሔ እንደማያመጣ ይናገራሉ። የምዕራብ ትግራይ ጉዳይ እና ሌሎች የትግራይን ሕዝብ ዕጣ ፈንታን ሊወስኑ የሚችሉ ሁኔታዎች ሕገ መንግሥቱን መሰረት በማድረግ ሊፈቱ እንደሚችሉ ነው የሚያምኑት። እሳቸው ይህን ቢሉም፣ ተቃዋሚዎቹ ግን በአንድ ድምፅ “ህወሓት በኢትዮጵያ ውስጥ መኖርን ነው የሚመርጠው። ከሕዝባችን የነፃነት ምኞት ጋር አልተስማማም” በማለት ይከሱታል። ‘ሕዝበ ውሳኔ’ የሚለው ቃልም ማደናገሪያና በተደጋጋሚ የትግራይን ህዝብ ጥቅም አሳልፎ የሰጠ መሆኑን ይገልፃሉ።። ይህንን ክስ የማይቀበሉት አቶ ዮሐንስ በበኩላቸው “የእኛ ምርጫ የሕዝባችን ውሳኔ ነው የሚሆነው። ሕዝባችን ምን እንደሚፈልግ ለመወቅም ለድርድር የማይቀርብ መድረክ እናዘጋጃለን” ብለዋል። የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት ዙሪያ በአሁኑ ወቅት የህወሓት አቋሙ ምን እንደሆነ የተጠየቁት አቶ ዮሐንስ፣ ፓርቲው በቅርቡ ጠቅላላ ጉባኤ ካካሄደ በኋላ ግልጽ እንደሚሆን ተናግረዋል።
የህወሓትና በትግራይ ያሉ ተቃዋሚዎች ውዝግብ በቅርቡ በትግራይ የሚንቀሳቀሱ ሦስት ተቃዋሚ ፓርቲዎች በትግራይ ክልል ስለተካሄደው ጦርነት እና ስለ ክልሉ አስተዳደር ላይ በጋራ መግለጫ ያወጡ ሲሆን፣ በክልሉ ሁሉን አቀፍ የሽግግር አስተዳደር እንዲቋቋምም ጠይቀዋል። በክልሉ ሥልጣን ላይ ህወሐት ለዘመናት የበላይ ሆኖ መቆየቱን የሚቃወሙት ሦስቱ ፓርቲዎች ሳልሳይ ወያነ ትግራይ (ሳወት)፣ የትግራይ ነፃነት ፓርቲ (ውናት) እንዲሁም ባይቶ ዓባይ ትግራይ (ባይቶና) ናቸው። እነዚህ ፓርቲዎች ሁለት ዓመት ሊሞላው የተቃረበውን ጦርነት ለማብቃት ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ይካሄዳል በተባለው ድርድር ላይ ህወሓት ትግራይን ወክሎ የመደራደርም ሆነ ክልሉን በብቸኝነት የማስተዳደር ህጋዊምና ሞራላዊ መብት የለውም ይላሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን መምጣታቸውን ተከትሎ ከማዕከላዊው መንግሥት ፖለቲካ የተገፋው ህወሓት፣ በፌደራል መንግሥቱ ተቀባይነት ያላገኘ ክልላዊ ምርጫዎች በማካሄድ ‘የሕዝብ ተቀባይነት’ አግኝቻለሁ በማለት ሥልጣኑን ለማጠናከር የሚያስችለው ሁኔታ ፈጥሮ ነበር። ነገር ግን በጥቅምት ወር 2013 ዓ.ም. የተቀሰቀሰን ጦርነት ተከትሎ ህወሓት ከክልላዊ ሥልጣኑ ተወግዶ በሕዝቡ ዘንድ ብዙም ተቀባይነት ያላገኘ በገዢው ብልጽግና ፓርቲ መሪነት በትግራይ ለአጭር ጊዜ የቆየ ጊዜያዊ አስተዳደር ተመስርቶ ነበር። ጦርነቱን ተከትሎ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የጅምላ ግድያ፣ ዘረፋ፣ ጾታዊ ጥቃት እና የመሠረተ ልማቶች ውድመት ደርሷል። የተባበሩት መንግሥታት እና ሌሎችም የመብት ተቋማት ለተፈጸሙት ጥፋቶች ህወሓትን ጨምሮ ሁሉንም ተጻራሪ ኃይሎች ተጠያቂ ያደርጋል። የሳልሳይ ወያነ ትግራይ የውጭ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ኃይሉ ከበደ “በልጆቹና ባለቤቱ፣ በእናቱ እና በእህቶቹ ላይ ግፍና በደል የተፈጸመበት የትግራይ ሕዝብ የታገለው ለሉአላዊነቱ እና ለደኅንነቱ እንጂ ለህወሓት አልነበረም” ይላሉ። “ህወሓት በሕግ ይሁን በሞራል ከሥልጣን በኃይል ተወግዷል። በዚህ መካከልም ሌላ አስተዳደር ተመስርቶ ነበር። ትግላችን የትግራይን መንግሥትነት መመለስ ነበር” ሲሉ ያስረዳሉ። የባይቶና ፓርቲ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ክብሮም በርኸ ከመታሰራቸው ከቀናት በፊት ለቢቢሲ እንደተናገሩት “ህወሓት ከፕሮፓጋንዳ በዘለለ ተገቢውን ወታደራዊ ዝግጅት ባለማድረጉ የትግራይ ሕዝብን ለአደጋ እንዲጋለጥ ስላደረገ ከሕዝቡ ጋር የነበረው ውል ፈርሷል” ይላሉ። በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱት ተቃዋሚ ፓርቲዎች በክልሉ ውስጥ ለተፈጸተው ክፈተት ተጠያቂ የሚያደርጉት ህወሓትን ነው። በአዲስ መልክ የተደራጁት የትግራይ ኃይሎች ሰኔ 21/2013  ዓ.ም. ላይ መቀለን ከተቆጣጠሩ በኋላ የህወሓት ሊቀመንበር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) የቀድሞ የክልሉ አስተዳደር ወደ ቦታው መመለሱን አስታውቀዋል። ነገር ግን በትግራይ ሁሉን አሳታፊ አስተዳደር መመስረትን በተመለከተ ጥያቄ ሲያቀርቡ የነበሩት የትግራይ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በአዲሱ መንግሥት ውስጥ ምንም ቦታና እውቅና አልተሰጣቸውም። የሦስቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሊቀመንበሮችን ጨምሮ በርካታ አባሎቻቸው በትጥቅ ትግሉ የተሳተፉ ቢሆንም ህወሓት ግን ከበረሃ ተመልሶ ሥልጣኑን ብቻውን መቆጣጠር ነው የመረጠው ይላሉ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አንዳንዶች የሽግግር መንግሥት እንዲቋቋም ሲጠይቁ ሌሎች ደግሞ ጥምር ክልላዊ ምክር ቤት እንዲቋቋም ጠይቀዋል። ሆኖም ከህወሓት ምንም አይነት አዎንታዊ ምላሽ አላገኙም። ለአቶ ኃይሉ ከበደ በትግራይ ሁሉን አሳታፊ መንግሥት መመስረት ማለት በሕዝባዊ ተቋማቱ በኩል አዲስና አሳታፊ ሕዝባዊ አስተዳደርን ማወቀር ማለት ነው። “ሕዝባዊ ትግል ነው ያካሄድነው፤ ስለሆነም ሕዝባዊ መንግሥት መመስረት አለበት የሚል እምነት ነበረን” ይላሉ። አያይዘውም “እኛ የምንታገለው የትግራይ መንግሥትነት እንዲመለስ እንጂ ህወሓት እንዲመለስና ብቻውን ያለፉትን 30 ዓመታት እንዲደግም አይደለም” በማለት ያስረዳሉ። የትግራይ ነፃነት አገርነት አላማው አድርጎ የሚንቀሳቀሰው የትግራይ ነፃነት ፓርቲ (ውናት) ከፍተኛ አመራር የሆኑት ዶ/ር ደጀን መዝገበ በቅርቡ በሰጡት መግለጫ “ጥምር መንግሥት መሥርተን በጋራ ለመሥራት ተስፋ አድርገን ነበር” ብለዋል። ህወሓትን “ህገወጥ” የሚሉት የትግራይ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የጋራ አቋም በመያዝ ባወጡት የጋራ መግለጫ ህወሓትን ያካተተ ሕዝባዊ የሽግግር መንግሥት በክልሉ እንዲመሰረት ጠይቀዋል። ነገር ግን በአሜሪካ የህወሓት ተወካይ የሆኑት አቶ ዮሐንስ አብረሃ “ከዚህ ቀደም ሕጋዊ ክልላዊ መንግሥት ወደ ቦታው ይመለስ ብለው ሲጠይቁ ቆይተው፣ ዛሬ ደግሞ ተመልሰው የሽግግር መንግሥት ጥያቄ ማቅረባቸው ልክ አይደለም” ብለዋል። አክለውም “የትግራይ መንግሥትን ሕገወጥ ነው” በማለት መክሰሳቸው፣ ፓርቲዎቹን እሳቸው ‘የጠላት ኃይሎች’ ሲሉ ከሚገልጿቸው አካላት ነጥለው ለማየት እንደሚቸገሩ ገልፀዋል። የህወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ ተቃዋሚዎችን “ቀበጦች” ሲሉ በማኅበራዊ ሚድያ ላይ የወረፏቸው ሲሆን ለዚህ አባባላቸውም ከብዙዎች ዘንድ ጠንካራ ትችት ቀርቦባቸዋል። በውጭ አገራት የሚኖሩ ሌሎች የህወሓት ‘ቀንደኛ’ ደጋፊዎች በበኩላቸው ተቃዋሚዎቹን ‘የዐቢይ ተላላኪዎች’ በማለት እርምጃ እንዲወሰድባቸው ጠይቀዋል። ‘የሥልጣን ጥመኞች’ ሲሉም የሚከሷቸው አሉ። ክብሮም በርኸ “ሥልጣን ፈላጊዎች ይሉናል። ሥልጣን ብንፈልግም ሃጢአት አይደለም። እኛ ፖለቲከኞች ነን፤ ምንም የሚያሳፍር ነገር የለውም። ሊያፍሩ የሚገባቸው እነዚያ በመጠቃቀምና በስብስብ ሥልጣን የተቆጣጠሩ ሰዎች ናቸው” ብሏል። ጦርነቱ በሰላማዊ መንገድ እንዲያበቃ በተለይም በአሜሪካ፣ በኬንያ እና በአፍሪካ ኅብረት የሚመሩ የድርድር ጥረቶች እየተሞከሩ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድም በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የሚመራ ተደራዳሪ ኮሚቴ መሰየሙን አስታውቀዋል። የህወሓት መሪዎችም በኬንያ መንግሥት ለሚመራ ውይይት ዝግጁ መሆናቸውን የገለጹ ሲሆን፣ ተደራዳሪዎቻቸውን ግን እስካሁን ይፋ አላደረጉም። ከባድ ሰብዓዊና ቁሳዊ ቀውስ ያስከተለው ጦርነት ብዙዎች በሰላማዊ መንገድ ይፈታ ይሆን በሚል ተስፋ ቢያደርጉም ሌሎች ደግሞ “ጊዜ መግዣ ነው” የሚል ጥርጣሪ አላቸው። በሰሜን አሜሪካ የህወሓት ተወካይ አቶ ዮሐንስ አብረሃ “በእኛ በኩል በውይይት መፍትሄ ሊመጣ ይችላል ብለን እናምናለን” በማለት ከሌላኛው ወገን በኩል ግን ጥርጣሬ እንዳላቸው ለቢቢሲ ገልፀዋል። አቶ ኃይሉ ከበደ ግን “የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት አንዴ ፈርሷል። ለቀጣይ አቅጣጫም መነሻ ሊሆን አይችልም። የትግራይን ሕዝብ ጥቅም ሊያስከብር አይችልም። በእሱ ተደራድረን የምናሳካው ጥቅምም የለም” ይላሉ። ተቃዋሚ ፓርቲዎቹም ከዚህ በመነሳት ነው ህወሓት የመደራደር ውክልና የለውም በማለት “የትግራይን ሕዝብ ለዚህ ውርደት አጋልጦ ትንሽ መፀፀት ያስፈልግ ነበር። እነዚህ ግን በድርቅና አድራጊ ፈጣሪ እኛ ነን እያሉ ነው” በማለት አቶ ኃይሉ ህወሓትን ይወቅሳሉ። ዶ/ር ደጀን በበኩላቸው ይህንን ተቃዋሚዎች አለ የሚሉትን የሕግ ክፍተት በመጥቀስ “ህወሓት ብቻውን ለመደራደርም ሆነ ትግራይን ለመምራት ምንም አይነት የሕግ መሰረት የለውም” ሲሉ ይቃወማሉ። ይህን ያሉበት ምክንያት ሲያስረዱም “በየትኛው ሕግ ነው ሠራዊት ሊገነባ እና ዲፕሎማሲን ማስቀጠል የሚችለው?” በማለት በሕገ መንግሥቱ መሰረት እነዚህ የፌደራል መንግሥት ተግባራት መሆናቸውን ያስታውሳሉ። አክለውም “ከሕገ መንግሥቱ ውጪ የሆነ ኃላፊነት የያዘ መንግሥት አለ። ይህን መስራት የሚችል ኃላፊነት ያለው ፓርቲ የለም።። የወደፊት የትግራይ ዕጣ ለዘላለም ብቻውን እንዲወስን የተመረጠ ፓርቲ የለም። የህወሓት ስርወ መንግሥትንም ለመመስረት የመረጠ ሕዝብም የለም” ይላሉ። “ህወሓት ለረጅም ጊዜ በሥልጣን ላይ ቆይቷል ለማለት ከሆነ ይገባኛል” በማለት የሚናገሩት አቶ ዮሐንስ ነገር ግን ፓርቲው በሕግ አግባብ መመረጡን ይጠቅሳሉ። ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ በመላ ትግራይ ተንቀሳቅሰው የህዝቡን ቀልብ መሳብ የሚችሉበትን ሁኔታ ፈጥረው፣ ሕዝቡ ህወሓትን በቃህ የሚለው ከሆነ የሕዝቡን ፍላጎት እንደሚያከብሩ አቶ ዮሐንስ ያስዳሉ። ነገር ግን ፓርቲዎቹ ሕዝባዊ ስብሰባ እንኳን እንዳያካሂዱ መከልከላቸውን እና እንቅስቃሴያቸውም መገደቡን በማስመልከት ስለሚያርቡት አቤቱታ ከቢቢሲ የተጠየቁት አቶ ዮሐንስ በጉዳዩ ላይ መረጃ እንደሌላችው በመግለጽ “እንደዚያ የተደረገ ግን አይመስለኝም” ብለዋል። የትግራይ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከህወሓት ጋር በጋራ ለመሥራት ‘የፓርቲዎች የጋራ መድረክ’ ተቋቁሞ በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ በጋራ መወያየት ጀምረው እንደነበረ ያስታውሳሉ። “የፓርቲዎች ፎረምን የልጆች መጫወቻ አድርገውታል” የሚሉት አቶ ኃይሉ ከበደ፣ ህወሓት ሲፈልግ ብቻ እንደሚሰበሰቡና ወታደራዊ ድሎች ሲገኙ ግን እንደሚረሱ ጠቅሰዋል። አቶ ጌታቸው ረዳ ግን የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮች ከስምንት ጊዜ በላይ ከዶ/ር ደብረፂዮን ጋር  መወያየታቸውን በማኅበራዊ ሚድያ ጽሁፋቸው ላይ አስፍረው ነበር። አቶ ኃይሉ ከበደ ግን “ከኅዳር ወር በኋላ ‘መከበብና መዘጋት’ ወደ ሚለው ግልፅ ወዳልሆነ ፖለቲካ ገባን። የትግራይ ሕዝብ እየጠፋና እየረገፈ ነው። በህወሓት ምክንያት ዲፕሎማሲያዊ ሥራ መሥራት አልተቻለም። የትግራይ ሕዝብ ትግል ዲፕሎማሲያዊ አጋር አላገኘም” ይላል። ተቃዋሚዎቹ ትግራይ ውስጥ በተካሄደው ጦርነት ምክያት ሕገ መንግሥቱ በአገር አቀፍ እና በክልል ደረጃ ፈርሷል ብለው እንደሚያምኑ ይናገራሉ። የህወሓት ተወካይ አቶ ዮሐንስ ግን “ሕገ መንግሥቱ ፈርሷል ካልን እነሱስ በየትኛው አሰራር ነው ሕጋዊ ተቃዋሚ የሆኑት?” ሲሉ ይጠይቃሉ። “ሕገ መንግሥታዊ ቀውስ ነው ያጋጠመው” የሚለው ፖለቲከኛ ክብሮም በርኸ በበኩሉ አዲስ ውል ማሰር እንደሚያስፈልግ ያምናል። "ለዓላማችን ስንል ሠራዊት ልንገነባና ዲፕሎማሲ መሥራት ስላለብን የሕግ ክፍተቱን ለመሙላት ፓርቲዎችና ሌሎች ግለሰቦች የሚሳተፉበት የጋራ መድረክ ሊኖር ይገባል” ይላሉ ዶክተር ደጀን በበኩላቸው። በአሜሪካ የህወሓት ተወካይ የሆኑት አቶ ዮሐንስ አብርሃ “ሕገ መንግሥቱ ተሸራርፏል እንጂ ፈርሷል” ብለው እንደማያምኑ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ሕገ መንግሥቱ ፈርሷል ካልን ያለሱ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ለመንቀሳቀስ ይከብደናል” ሲሉም ይሞግታሉ። “አሁን የሽግግር መንግሥት ቢቋቋም ተቃዋሚ ኃይሎቹ ከድርጊታቸው ይቆጠቡ ነበር?” የሚል ጥያቄ በማንሳትም የቀረበው ሐሳብ መፍትሔ እንደማያመጣ ይናገራሉ። የምዕራብ ትግራይ ጉዳይ እና ሌሎች የትግራይን ሕዝብ ዕጣ ፈንታን ሊወስኑ የሚችሉ ሁኔታዎች ሕገ መንግሥቱን መሰረት በማድረግ ሊፈቱ እንደሚችሉ ነው የሚያምኑት። እሳቸው ይህን ቢሉም፣ ተቃዋሚዎቹ ግን በአንድ ድምፅ “ህወሓት በኢትዮጵያ ውስጥ መኖርን ነው የሚመርጠው። ከሕዝባችን የነፃነት ምኞት ጋር አልተስማማም” በማለት ይከሱታል። ‘ሕዝበ ውሳኔ’ የሚለው ቃልም ማደናገሪያና በተደጋጋሚ የትግራይን ህዝብ ጥቅም አሳልፎ የሰጠ መሆኑን ይገልፃሉ።። ይህንን ክስ የማይቀበሉት አቶ ዮሐንስ በበኩላቸው “የእኛ ምርጫ የሕዝባችን ውሳኔ ነው የሚሆነው። ሕዝባችን ምን እንደሚፈልግ ለመወቅም ለድርድር የማይቀርብ መድረክ እናዘጋጃለን” ብለዋል። የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት ዙሪያ በአሁኑ ወቅት የህወሓት አቋሙ ምን እንደሆነ የተጠየቁት አቶ ዮሐንስ፣ ፓርቲው በቅርቡ ጠቅላላ ጉባኤ ካካሄደ በኋላ ግልጽ እንደሚሆን ተናግረዋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c8vqvgr8gjlo
0business
የነዳጅ ዋጋ እንዲንር ወይም እንዲቀንስ የሚያደርገው ምንድን ነው? የሚወስነውስ ማን ነው?
ባለፈው ዓመት ሚያዝያ ወር ማብቂያ ላይ የዓለማችን ቀዳሚ ነዳጅ ላኪ አገራት ስብሰባ አድርገው ነበር። አጀንዳቸው የነበረውም የድፍድፍ ነዳጅን ዋጋ ለመቀነስ ያለመ ነበር። በአሁኑ ወቅት የነዳጅ ዋጋ ካለፉት ስምንት ዓመታት የበለጠ ሆኗል። ነዳጅ ከውጭ አስመጥተው የሚጠቀሙ አገራት፣ ነዳጅ አምርተው የሚልኩ አገራት ስብስብ የኦፔክ ፕላስ (Opec+) የነዳጅ ምርትን እንዲጨምሩ ተማጽነዋል። ዋነኞቹ ነዳጅ ላኪ አገራት እምብዛም ተማጽኖውን የሰሙ አይመስልም። ይልቁንም በቀን የሚመረተውን ነዳጅ በሁለት ሚሊዮን በርሜል ለመቀነስ ተስማምተዋል። ሩሲያን ጨምሮ የኦፔክ ፕላስ አባል አገራት የነዳጅ ዋጋን ለመጨመር እርምጃ እየወሰዱ ነው። የነዳጅ ዋጋ ባለፈው ዓመት የመቀነስ አዝማሚያ አሳይቶ የነበረ ቢሆንም፤ ሩሲያ ዩክሬንን መውረሯን ተከትሎ ዋጋው ንሯል። ዋነኞቹ የዓለማችን የነዳጅ ዘይት አምራች አገራት የምርታቸውን መጠንና ዋጋን ለመቆጣጠር ኦፔክ ፕላስ በተባለ ማኅበር ተሰባስበዋል። አባላቱም 23 አገራት ናቸው። በዓለም ገበያ ድፍድፍ ነዳጅ በስንት ይሸጥ የሚለውን ለመወሰን ውይይት ያካሂዳሉ። በዚህ ስብስብ ውስጥ ካሉት አገራት መካከል 13ቱ ከመካከለኛው ምሥራቅ እና ከአፍሪካ ናቸው። ከኦፔክ ፕላስ በፊት በ1960ዎቹ ኦፔክ ሲመሠረት አላማው የዓለምን የነዳጅ ዘይት ገበያ ፈር ማስያዝ ነበር። ዛሬ ላይ የዓለም 30 በመቶ ነዳጅ የሚመረተው በኦፔክ አገራት ነው። ሳዑዲ አረቢያ በቀን ከ10 ሚሊዮን በርሜል በላይ ነዳጅ በማምረት የአንበሳውን ድርሻ ትይዛለች። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ2016 የነዳጅ ዋጋ እጅግ አሽቆልቁሎ ነበር። ኦፔክ ከሌሎች 10 ነዳጅ አምራቾች ጋር ተዋህዶ ኦፔክ ፕላስ የተፈጠረውም የዚያን ጊዜ ነበር። ኦፔክ ፕላስ የዓለምን 40 በመቶ ድፍድፍ ነዳጅ ያመርታል። በኢነርጂ ኢንስቲትዩት የምትሠራው ኬት ዶውሪን “ኦፔክ ፕላስ ገበያውን ለማረጋጋት አቅርቦት እና ፍላጎትን ያመጣጥናል” ትላለች። “የነዳጅ ፍላጎት ሲቀንስ፣ የነዳጅ አቅርቦትን ዝቅ በማድረግ ዋጋውን ይጨምራሉ” ስትልም ታስረዳለች። በርከት ያለ ነዳጅ ገበያው ላይ በማቅረብ ዋጋ እንዲቀንስ ማድረግም ይችላሉ። የኦፔክ ፕላስ አባል አገራት ከሁለት ዓመት በፊት ኦስትሪያ፣ ቪየና ውስጥ ከተገናኙ በኋላ፣ ካለፈው ነሐሴ ወር ጀምሮ በቀን የሚመረተውን ነዳጅ በሁለት ሚሊዮን በርሜል በመቀነስ ምርታቸውን ከ42 ሚሊዮን በርሜል በታች ለማድረግ ወስነዋል። ይህ ውሳኔም ካለንበት ጥቅምት ወር ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል። በዚህም የሚደረገው ቅነሳ ከዓለም አጠቃላይ የነዳጅ ምርት ሁለት በመቶውን ሲይዝ፣ ከሚጠበቀውም በላይ ነው። ከአውሮፓውያኑ 2020 ወዲህ የኦፔክ ፕላስ አባላት ነዳጅ ምርት ላይ ያደረጉት ከፍተኛው ቅነሳ እንደሆነም ተገልጿል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በተከሰተበት ጊዜ የነዳጅ ምርትን በቀን ከዘጠኝ ሚሊዮን በርሜል በላይ ለመቀነስ ወስነው ነበር። ውሳኔው የተላለፈው የነዳጅ ዋጋን ለመጨመር ነው። በወቅቱ የነዳጅ ዋጋ ከነበረበት 122 ዶላር ወደ 90 ዶላር ዝቅ ብሎ ነበር። የነዳጅ ምርትን ለመቀነስ ውሳኔ ሲተላለፍ የነዳጅ ዋጋ ጨምሯል። የነዳጅ ዋጋ መጨመር በመላው ዓለም የዋጋ ንረትን አስከትሏል። አሜሪካ ኦፔክ ፕላስ የነዳጅ ምርትን እንዳይቀንስ ጠይቃለች። የነዳጅ ዋጋ አነስተኛ ከሆነ ሩሲያ የምታገኘው ገቢም ያንሳል ማለት ነው። ዋይት ሐውስ የኦፔክ ፕላስን ውሳኔ “የረጅም ጊዜ ሁኔታን ያላጋዘበ” ሲል ተችቷል። ያለፈው ሐምሌ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ሳዑዲ አረቢያ ተጉዘው አልጋ ወራሽ ልዑል ሞሐመድ ቢን ሳልማን የነዳጅ ምርትን እንዲጨምሩ ጠይቀው ነበር። ነገር ግን ጥያቄውን አልተቀበሉትም። የቀድሞው የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰንም በተመሳሳይ ሳዑዲ አረቢያ እና ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ የነዳጅ ምርት እንዲጨምሩ ቢጠይቁም አልተሳካላቸውም። ከሁለት ዓመት በፊት ኮሮናቫይረስ ሲነሳ፣ አገራትም በራቸውን ሲዘጉ፣ ድፍድፍ ነዳጅ ገዢ አጥቶ ዋጋው አሽቆልቁሎ ነበር። “ነዳጅ አምራቾች ምርታቸውን ለመሸጥ ለገዢዎች ገንዘብ እየከፈሉ ነበር። አምራቾቹ ነዳጁን የሚያከማቹበት ቦታ አጥተውም ነበር” ስትል በኢነርጂ ኢንስቲትዩት የምትሠራው ኬት ዶውሪን ታስረዳለች። የኦፔክ ፕላስ አባላት የነዳጅ ምርትን በቀን በአስር ሚሊዮን በርሜል ለመቀነስ የወሰኑት የነዳጅ ዋጋ እንዲያንሰራራ ነበር። ከዚያ ወዲህ ኦፔክ ፕላስ የነዳጅ ፍላጎት እየጨመረ በመምጣቱ ቀስ በቀስ ምርቱን እያሳደገ መጥቷል። ሩሲያ ዩክሬንን ስትወር ግን የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በበርሜል ከ100 ዶላር በላይ ሆነ። በሩሲያ ላይ የተጣሉ ዓለም አቀፍ ማዕቀቦች የሩሲያ ነዳጅ ምርት ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉ ተብሎ ተሰግቷል። እየቀነሰ ያለው የነዳጅ ዋጋ እንዲያንሰራራ ኦፔክ ፕላስ አምራች አገራት ምርታቸውን ለመቀነስ መወሰናቸው ተጠቁሟል። ሩሲያ ዩክሬንን ከወረረች በኋላ በርካታ አገራት ከሩሲያ የሚገዙትን የነዳጅ መጠን ቀንሰዋል። የሩሲያ ነዳጅ ዋጋ እየቀነሰም መጥቷል። የሩሲያ ድፍድፍ ነዳጅ በበርሜል ከ30 ዶላር በላይ የተሸጠበት ጊዜም ነበር። መስከረም መጨረሻ ላይ ወደ 20 ዶላር ወርዷል። ሩሲያ ላይ ማዕቀብ ከጣሉት ምዕራባውያን አገራት ጋር ያልተባበሩት ሕንድ እና ቻይና፣ አሁን ላይ ከአገሪቱ ምርት ከግማሽ በላዩን ይረከባሉ። በዚህም ሩሲያ የቻይና ትልቋ ነዳጅ አቅራቢ ሆናለች። ከዚህ ቀደም ወደ ቻይና ነዳጅ በዋናነት የምትልከው ሳዑዲ አረቢያ ነበረች። መጋቢት ላይ ቻይና እና ሕንድ ከሩሲያ የገዙት ነዳጅ ከ27ቱ የአውሮፓ ኅብረት አባላት ይበልጣል። በዚህ በጥቅምት ወርም የአውሮፓ ኅብረት በሩሲያ የድፍድፍ ነዳጅ ምርት ላይ ማዕቀብ ለመጣል አቅዷል።
የነዳጅ ዋጋ እንዲንር ወይም እንዲቀንስ የሚያደርገው ምንድን ነው? የሚወስነውስ ማን ነው? ባለፈው ዓመት ሚያዝያ ወር ማብቂያ ላይ የዓለማችን ቀዳሚ ነዳጅ ላኪ አገራት ስብሰባ አድርገው ነበር። አጀንዳቸው የነበረውም የድፍድፍ ነዳጅን ዋጋ ለመቀነስ ያለመ ነበር። በአሁኑ ወቅት የነዳጅ ዋጋ ካለፉት ስምንት ዓመታት የበለጠ ሆኗል። ነዳጅ ከውጭ አስመጥተው የሚጠቀሙ አገራት፣ ነዳጅ አምርተው የሚልኩ አገራት ስብስብ የኦፔክ ፕላስ (Opec+) የነዳጅ ምርትን እንዲጨምሩ ተማጽነዋል። ዋነኞቹ ነዳጅ ላኪ አገራት እምብዛም ተማጽኖውን የሰሙ አይመስልም። ይልቁንም በቀን የሚመረተውን ነዳጅ በሁለት ሚሊዮን በርሜል ለመቀነስ ተስማምተዋል። ሩሲያን ጨምሮ የኦፔክ ፕላስ አባል አገራት የነዳጅ ዋጋን ለመጨመር እርምጃ እየወሰዱ ነው። የነዳጅ ዋጋ ባለፈው ዓመት የመቀነስ አዝማሚያ አሳይቶ የነበረ ቢሆንም፤ ሩሲያ ዩክሬንን መውረሯን ተከትሎ ዋጋው ንሯል። ዋነኞቹ የዓለማችን የነዳጅ ዘይት አምራች አገራት የምርታቸውን መጠንና ዋጋን ለመቆጣጠር ኦፔክ ፕላስ በተባለ ማኅበር ተሰባስበዋል። አባላቱም 23 አገራት ናቸው። በዓለም ገበያ ድፍድፍ ነዳጅ በስንት ይሸጥ የሚለውን ለመወሰን ውይይት ያካሂዳሉ። በዚህ ስብስብ ውስጥ ካሉት አገራት መካከል 13ቱ ከመካከለኛው ምሥራቅ እና ከአፍሪካ ናቸው። ከኦፔክ ፕላስ በፊት በ1960ዎቹ ኦፔክ ሲመሠረት አላማው የዓለምን የነዳጅ ዘይት ገበያ ፈር ማስያዝ ነበር። ዛሬ ላይ የዓለም 30 በመቶ ነዳጅ የሚመረተው በኦፔክ አገራት ነው። ሳዑዲ አረቢያ በቀን ከ10 ሚሊዮን በርሜል በላይ ነዳጅ በማምረት የአንበሳውን ድርሻ ትይዛለች። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ2016 የነዳጅ ዋጋ እጅግ አሽቆልቁሎ ነበር። ኦፔክ ከሌሎች 10 ነዳጅ አምራቾች ጋር ተዋህዶ ኦፔክ ፕላስ የተፈጠረውም የዚያን ጊዜ ነበር። ኦፔክ ፕላስ የዓለምን 40 በመቶ ድፍድፍ ነዳጅ ያመርታል። በኢነርጂ ኢንስቲትዩት የምትሠራው ኬት ዶውሪን “ኦፔክ ፕላስ ገበያውን ለማረጋጋት አቅርቦት እና ፍላጎትን ያመጣጥናል” ትላለች። “የነዳጅ ፍላጎት ሲቀንስ፣ የነዳጅ አቅርቦትን ዝቅ በማድረግ ዋጋውን ይጨምራሉ” ስትልም ታስረዳለች። በርከት ያለ ነዳጅ ገበያው ላይ በማቅረብ ዋጋ እንዲቀንስ ማድረግም ይችላሉ። የኦፔክ ፕላስ አባል አገራት ከሁለት ዓመት በፊት ኦስትሪያ፣ ቪየና ውስጥ ከተገናኙ በኋላ፣ ካለፈው ነሐሴ ወር ጀምሮ በቀን የሚመረተውን ነዳጅ በሁለት ሚሊዮን በርሜል በመቀነስ ምርታቸውን ከ42 ሚሊዮን በርሜል በታች ለማድረግ ወስነዋል። ይህ ውሳኔም ካለንበት ጥቅምት ወር ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል። በዚህም የሚደረገው ቅነሳ ከዓለም አጠቃላይ የነዳጅ ምርት ሁለት በመቶውን ሲይዝ፣ ከሚጠበቀውም በላይ ነው። ከአውሮፓውያኑ 2020 ወዲህ የኦፔክ ፕላስ አባላት ነዳጅ ምርት ላይ ያደረጉት ከፍተኛው ቅነሳ እንደሆነም ተገልጿል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በተከሰተበት ጊዜ የነዳጅ ምርትን በቀን ከዘጠኝ ሚሊዮን በርሜል በላይ ለመቀነስ ወስነው ነበር። ውሳኔው የተላለፈው የነዳጅ ዋጋን ለመጨመር ነው። በወቅቱ የነዳጅ ዋጋ ከነበረበት 122 ዶላር ወደ 90 ዶላር ዝቅ ብሎ ነበር። የነዳጅ ምርትን ለመቀነስ ውሳኔ ሲተላለፍ የነዳጅ ዋጋ ጨምሯል። የነዳጅ ዋጋ መጨመር በመላው ዓለም የዋጋ ንረትን አስከትሏል። አሜሪካ ኦፔክ ፕላስ የነዳጅ ምርትን እንዳይቀንስ ጠይቃለች። የነዳጅ ዋጋ አነስተኛ ከሆነ ሩሲያ የምታገኘው ገቢም ያንሳል ማለት ነው። ዋይት ሐውስ የኦፔክ ፕላስን ውሳኔ “የረጅም ጊዜ ሁኔታን ያላጋዘበ” ሲል ተችቷል። ያለፈው ሐምሌ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ሳዑዲ አረቢያ ተጉዘው አልጋ ወራሽ ልዑል ሞሐመድ ቢን ሳልማን የነዳጅ ምርትን እንዲጨምሩ ጠይቀው ነበር። ነገር ግን ጥያቄውን አልተቀበሉትም። የቀድሞው የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰንም በተመሳሳይ ሳዑዲ አረቢያ እና ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ የነዳጅ ምርት እንዲጨምሩ ቢጠይቁም አልተሳካላቸውም። ከሁለት ዓመት በፊት ኮሮናቫይረስ ሲነሳ፣ አገራትም በራቸውን ሲዘጉ፣ ድፍድፍ ነዳጅ ገዢ አጥቶ ዋጋው አሽቆልቁሎ ነበር። “ነዳጅ አምራቾች ምርታቸውን ለመሸጥ ለገዢዎች ገንዘብ እየከፈሉ ነበር። አምራቾቹ ነዳጁን የሚያከማቹበት ቦታ አጥተውም ነበር” ስትል በኢነርጂ ኢንስቲትዩት የምትሠራው ኬት ዶውሪን ታስረዳለች። የኦፔክ ፕላስ አባላት የነዳጅ ምርትን በቀን በአስር ሚሊዮን በርሜል ለመቀነስ የወሰኑት የነዳጅ ዋጋ እንዲያንሰራራ ነበር። ከዚያ ወዲህ ኦፔክ ፕላስ የነዳጅ ፍላጎት እየጨመረ በመምጣቱ ቀስ በቀስ ምርቱን እያሳደገ መጥቷል። ሩሲያ ዩክሬንን ስትወር ግን የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በበርሜል ከ100 ዶላር በላይ ሆነ። በሩሲያ ላይ የተጣሉ ዓለም አቀፍ ማዕቀቦች የሩሲያ ነዳጅ ምርት ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉ ተብሎ ተሰግቷል። እየቀነሰ ያለው የነዳጅ ዋጋ እንዲያንሰራራ ኦፔክ ፕላስ አምራች አገራት ምርታቸውን ለመቀነስ መወሰናቸው ተጠቁሟል። ሩሲያ ዩክሬንን ከወረረች በኋላ በርካታ አገራት ከሩሲያ የሚገዙትን የነዳጅ መጠን ቀንሰዋል። የሩሲያ ነዳጅ ዋጋ እየቀነሰም መጥቷል። የሩሲያ ድፍድፍ ነዳጅ በበርሜል ከ30 ዶላር በላይ የተሸጠበት ጊዜም ነበር። መስከረም መጨረሻ ላይ ወደ 20 ዶላር ወርዷል። ሩሲያ ላይ ማዕቀብ ከጣሉት ምዕራባውያን አገራት ጋር ያልተባበሩት ሕንድ እና ቻይና፣ አሁን ላይ ከአገሪቱ ምርት ከግማሽ በላዩን ይረከባሉ። በዚህም ሩሲያ የቻይና ትልቋ ነዳጅ አቅራቢ ሆናለች። ከዚህ ቀደም ወደ ቻይና ነዳጅ በዋናነት የምትልከው ሳዑዲ አረቢያ ነበረች። መጋቢት ላይ ቻይና እና ሕንድ ከሩሲያ የገዙት ነዳጅ ከ27ቱ የአውሮፓ ኅብረት አባላት ይበልጣል። በዚህ በጥቅምት ወርም የአውሮፓ ኅብረት በሩሲያ የድፍድፍ ነዳጅ ምርት ላይ ማዕቀብ ለመጣል አቅዷል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cd1v5xnn3e2o
0business
ከጎጃም እናቶች አንገት ላይ ስለማይታጣው ማርትሬዛ ምን ያክል ያውቃሉ?
በኢትዮጵያ በተለይ ደግሞ የጎጃም እናቶች አንገታቸው ላይ ለመዋቢያነት የሚያደርጉት 'ማርትሬዛ' ወይም 'ጠገራ' ተብሎ የሚጠራው ሳንቲም ምንጩ ከወዴት እንደሆነ ጠይቀው ያውቃሉ? ከየት መጣ? እንዴት መጣ? እንዴትስ ለመዋቢያነት ጥቅም ላይ ዋለ? ጠገራውን ለመዋቢያነት ከአንገቷ ላይ አኑራ በባህር ዳር ከተማ ገብያ መሃል ያገኘናት ወ/ሮ እሙዬ ጓዴ "በባህላችን ሴት ልጅ ስትዳር ይሄ ይሰጣታል። ለእርሷ የሚቀርባት ሰው ነው የሚሰጣት። ይሄ የቀድሞ ጠገራ ነው፤ የትም አይገኝም" ትላለች። • ከፕላስቲክ የጫማ ቀለም የሚያመርቱት የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች • እሷ ማናት? የበለስ ማርማላታ ወደ ውጪ የምትልከው ኢትዮጵያዊት ወ/ሮ እሙዬ ጠገራው ከየት እንደመጣ እርግጠኛ ባይሆኑም፤ ከቀደመ ትውልድ እንደወረሱት ይናገራሉ። "ጠገራው የአያቴ ነበር። አያቴ ለእናቴ ሰጠቻት። እናቴ ደግሞ ለእኔ ሰጠችኝ። አሁን አንገቴ ላይ ካኖርኩት ከ40 ዓመት በላይ ይሆነዋለ" ብላለች። "የሃገር ባህል ነው። ሴቶች ሲዳሩ እንደ ጥሎሽ ነበር የሚሰጣቸው። ጠገራው ከብር ስለሚሰራ ብዙ ገንዘብ ያወጣል። ስለሚያምር ለመዋቢያነት ይውላል" የሚሉት ደግሞ እዚያው ገብያ መሃል ያገኘናቸው አቶ አማረ ናቸው። ሙሉ መጠሪያው ማሪያ ቴሬሳ ቴለር ሲሆን ለመገበያያነት ጥቅም ላይ ይውል የነበረ ሳንቲም ነው። መጠሪያውን ያገኘው ከኦስትሪያ-ሃነጋሪ ንግስት ስም ማሪያ ቴሬዛ ታለር ነው። ይህ ለመገበያያነት ይውል የነበረው ሳንቲም በአውሮፓዊቷ ሃገረ ኦስትሪያ ከ1730ዎቹ እስከ 1770ዎቹ ድረስ ባሉት የማሪያ ቴሬዛ ታለር ንግስና ዓመታት ታትሟል። ማሪያ ቴሬሳ ቴለር በዓለም ላይ በስፋት ከሚታወቁት መገበያያ ሳንቲሞች መካከል አንዱ የነበረ ሲሆን፤ የአረብ ሃገራት ነጋዴዎች ከአውሮፓ ሃገራት ጋር ለሚያደርጉት ግብይት የሚቀበሉት ማሪያ ቴሬሳ ቴለርን ብቻ ስለመሆኑ የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ። በአማራ ክልል ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ የታሪክ ጥናት ባለሙያ የሆኑት አቶ ዳምጤ ደምሴ፤ ''ማርትሬዛ በተለያዩ የታሪክ አጋጣሚዎች ወደ ኢትዮጵያ ገብቷል" ይላሉ። አቶ ዳምጤ "የጎንደሩ ዳግማዊ አጼ እያሱ የንግስና ዘመን ማብቂያ አካባቢ ሳንቲሙ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ ነበር። ነጋዴዎች፣ አውሮፓውያን አሳሾች እና ተጓዦች ወደ ሃገራችን ይዘውት መጥተዋል" ብለውናል። • ከብራና ወደ ኮምፒውተር . . . ክርስቲያን ጎቲች የተባሉ ክሮሺያዊ የታሪክ ተመራማሪ ''ዘ ቴለር ኦፍ ማሪያ ቴሬዛ'' በተሰኘው ጽሁፋቸው፤ በአውሮፓ በተለይ ደግሞ በቪዬና ከተማ ከተቀረጹ 245 ሚሊዮን ከሚሆኑት ማሪያ ቴሬሳ ቴለር ሳንቲሞች መካከል 20 በመቶ ያክሉ ወደ ኢትዮጵያ ስለመወሰዳቸው አትተዋል። ይህ ሳንቲም ደግሞ በስፋት ወደ ኢትዮጵያ የገባው፤ በአጼ ቴዎድሮስ II ወቅት ወራሪው የእግሊዝ ጦር በፊልድ ማርሻል ሮቤርት ናፒየር እየተመራ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ፤ ለጉልበት ሥራ ለሚያሰማራቸው ሰዎች በክፍያ መልክ ይህን የጠገራ ሳንቲም ለመክፈል በብዛት ይዞ በመምጣቱ እንደሆነ ሪቻርድ ፓንክረስት ''ዘ ማሪያ ቴሬሳ ዶላር ኢን ፕሪ-ዋር ኢትዮጵያ'' በተሰኘው ጥናታዊ ጽሁፋቸው ላይ ጠቅሰዋል። ከኢትዮጵያ በተጨማሪ በአውሮፓ እና መካከለኛው ምስራቅ ሃገራት ውስጥ ይህ ሳንቲም በስፋት እንደሚገኝ ይነገራል። ከብር የተቀረጹት እኚህ ሳንቲሞች በኢንተርኔት ገበያዎች ላይ በመጠን እና በተቀረጹበት ዓመት ልዩነት መሰረት ከ15 እስከ 500 የአሜሪካ ዶላር ይሸጣሉ። በኢትዮጵያም ከብር የተሰሩ ጠገራዎች እስከ 1500 ብር ይጠየቅባቸዋል።
ከጎጃም እናቶች አንገት ላይ ስለማይታጣው ማርትሬዛ ምን ያክል ያውቃሉ? በኢትዮጵያ በተለይ ደግሞ የጎጃም እናቶች አንገታቸው ላይ ለመዋቢያነት የሚያደርጉት 'ማርትሬዛ' ወይም 'ጠገራ' ተብሎ የሚጠራው ሳንቲም ምንጩ ከወዴት እንደሆነ ጠይቀው ያውቃሉ? ከየት መጣ? እንዴት መጣ? እንዴትስ ለመዋቢያነት ጥቅም ላይ ዋለ? ጠገራውን ለመዋቢያነት ከአንገቷ ላይ አኑራ በባህር ዳር ከተማ ገብያ መሃል ያገኘናት ወ/ሮ እሙዬ ጓዴ "በባህላችን ሴት ልጅ ስትዳር ይሄ ይሰጣታል። ለእርሷ የሚቀርባት ሰው ነው የሚሰጣት። ይሄ የቀድሞ ጠገራ ነው፤ የትም አይገኝም" ትላለች። • ከፕላስቲክ የጫማ ቀለም የሚያመርቱት የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች • እሷ ማናት? የበለስ ማርማላታ ወደ ውጪ የምትልከው ኢትዮጵያዊት ወ/ሮ እሙዬ ጠገራው ከየት እንደመጣ እርግጠኛ ባይሆኑም፤ ከቀደመ ትውልድ እንደወረሱት ይናገራሉ። "ጠገራው የአያቴ ነበር። አያቴ ለእናቴ ሰጠቻት። እናቴ ደግሞ ለእኔ ሰጠችኝ። አሁን አንገቴ ላይ ካኖርኩት ከ40 ዓመት በላይ ይሆነዋለ" ብላለች። "የሃገር ባህል ነው። ሴቶች ሲዳሩ እንደ ጥሎሽ ነበር የሚሰጣቸው። ጠገራው ከብር ስለሚሰራ ብዙ ገንዘብ ያወጣል። ስለሚያምር ለመዋቢያነት ይውላል" የሚሉት ደግሞ እዚያው ገብያ መሃል ያገኘናቸው አቶ አማረ ናቸው። ሙሉ መጠሪያው ማሪያ ቴሬሳ ቴለር ሲሆን ለመገበያያነት ጥቅም ላይ ይውል የነበረ ሳንቲም ነው። መጠሪያውን ያገኘው ከኦስትሪያ-ሃነጋሪ ንግስት ስም ማሪያ ቴሬዛ ታለር ነው። ይህ ለመገበያያነት ይውል የነበረው ሳንቲም በአውሮፓዊቷ ሃገረ ኦስትሪያ ከ1730ዎቹ እስከ 1770ዎቹ ድረስ ባሉት የማሪያ ቴሬዛ ታለር ንግስና ዓመታት ታትሟል። ማሪያ ቴሬሳ ቴለር በዓለም ላይ በስፋት ከሚታወቁት መገበያያ ሳንቲሞች መካከል አንዱ የነበረ ሲሆን፤ የአረብ ሃገራት ነጋዴዎች ከአውሮፓ ሃገራት ጋር ለሚያደርጉት ግብይት የሚቀበሉት ማሪያ ቴሬሳ ቴለርን ብቻ ስለመሆኑ የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ። በአማራ ክልል ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ የታሪክ ጥናት ባለሙያ የሆኑት አቶ ዳምጤ ደምሴ፤ ''ማርትሬዛ በተለያዩ የታሪክ አጋጣሚዎች ወደ ኢትዮጵያ ገብቷል" ይላሉ። አቶ ዳምጤ "የጎንደሩ ዳግማዊ አጼ እያሱ የንግስና ዘመን ማብቂያ አካባቢ ሳንቲሙ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ ነበር። ነጋዴዎች፣ አውሮፓውያን አሳሾች እና ተጓዦች ወደ ሃገራችን ይዘውት መጥተዋል" ብለውናል። • ከብራና ወደ ኮምፒውተር . . . ክርስቲያን ጎቲች የተባሉ ክሮሺያዊ የታሪክ ተመራማሪ ''ዘ ቴለር ኦፍ ማሪያ ቴሬዛ'' በተሰኘው ጽሁፋቸው፤ በአውሮፓ በተለይ ደግሞ በቪዬና ከተማ ከተቀረጹ 245 ሚሊዮን ከሚሆኑት ማሪያ ቴሬሳ ቴለር ሳንቲሞች መካከል 20 በመቶ ያክሉ ወደ ኢትዮጵያ ስለመወሰዳቸው አትተዋል። ይህ ሳንቲም ደግሞ በስፋት ወደ ኢትዮጵያ የገባው፤ በአጼ ቴዎድሮስ II ወቅት ወራሪው የእግሊዝ ጦር በፊልድ ማርሻል ሮቤርት ናፒየር እየተመራ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ፤ ለጉልበት ሥራ ለሚያሰማራቸው ሰዎች በክፍያ መልክ ይህን የጠገራ ሳንቲም ለመክፈል በብዛት ይዞ በመምጣቱ እንደሆነ ሪቻርድ ፓንክረስት ''ዘ ማሪያ ቴሬሳ ዶላር ኢን ፕሪ-ዋር ኢትዮጵያ'' በተሰኘው ጥናታዊ ጽሁፋቸው ላይ ጠቅሰዋል። ከኢትዮጵያ በተጨማሪ በአውሮፓ እና መካከለኛው ምስራቅ ሃገራት ውስጥ ይህ ሳንቲም በስፋት እንደሚገኝ ይነገራል። ከብር የተቀረጹት እኚህ ሳንቲሞች በኢንተርኔት ገበያዎች ላይ በመጠን እና በተቀረጹበት ዓመት ልዩነት መሰረት ከ15 እስከ 500 የአሜሪካ ዶላር ይሸጣሉ። በኢትዮጵያም ከብር የተሰሩ ጠገራዎች እስከ 1500 ብር ይጠየቅባቸዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-50781921
0business
በአሜሪካ ከጭነት መኪና ላይ ቲማቲም ተደፍቶ ለትራፊክ አደጋ ምክንያት ሆነ
በአሜሪካዋ የካሊፎርኒያ ግዛት ከፍተኛ የትራፊክ ፍሰት ባለበት መንገድ ላይ አንድ የጭነት መኪና 150 ሺህ ቲማቲም አስፓልት ላይ ከደፋ በኋላ የትራፊክ አደጋ አጋጠመ። ቲማቲም ጭኖ የነበረው የደረቅ ጭንት ተሽከርካሪ አደጋ ካጋጠመው በኋላ ነው ግዛቶችን በሚያገናኘው አውራ ጎዳና ላይ ቲማቲሙ የተደፋው። መንገዱ ላይ የተደፋው ቲማቲም አራት መኪኖች እንዲጋጩ እና የተለያዩ ግዛቶችን የሚያገናኘው አውራ ጎዳና አብዛኛው የመንገዱ ክፍል እንዲዘጋ ምክንያት ሆኗል። ባጋጠመው የመኪና አደጋ ሦስት ሰዎች ቀላል ጉዳት ያጋጠማቸው ሲሆን፣ አንድ ሰው ደግሞ የእግር መሰበር አደጋ ደርሶበት በሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት መሆኑን የካሊፎርኒያ የመንገድ ተቆጣጣሪ ፖሊስ አስታውቋል። የቲማቲም ምርት ከተሰበሰበ በኋላ አሸከርካሪዎች ምርቱን ወደ ሌሎች ግዛቶች ለማጓጓዝ ይህን አውራ ጎዳና ይጠቀማሉ። ቲማቲም ጭኖ የነረበው የደረቅ ጭነት ተሸከርካሪ ተንሸራቶ ከመንገድ ሲወጣ የደፋው ቲማቲም 200 ጫማ የመንገዱን ክፍል ሸፍኖታል። መጠናቸው ከፍ ያሉ 150 ሺህ ቲማቲሞች ተጨፈላልቀው እስከ 60 ሳንቲ ሜትር ከፍታ ያለው “ቀይ ስልስ” ፈጥረው ነበር ሲሉ የመንገድ ተቆጣጣሪ ፖሊስ አባሉ ጄሰን ታይረስት ተናግረዋል። መኪኖች የተጨፈላለቁ ቲማቲሞች ላይ ሲሄዱ እየተንሸራተቱ አደጋ ማጋጠሙም የፖሊስ አባሉ ተናግረዋል። “የቲማቲም ልጣጭ አስፓልት ከደረሰ በረዶ ላይ እንደመራመድ ነው” ሲሉ ጄሰን ታይረስት ለኒዮርክ ታይምስ ተናግረዋል። አደጋው ካጋጠመ ከበርካታ ሰዓታት በኋላ ዳግም የተሽከርካሪ አደጋ እንዳያጋጥም መንገዱ እንዲጸዳ ተደርጎ ዳግም ለትራፊክ ክፍት ሆኗል።
በአሜሪካ ከጭነት መኪና ላይ ቲማቲም ተደፍቶ ለትራፊክ አደጋ ምክንያት ሆነ በአሜሪካዋ የካሊፎርኒያ ግዛት ከፍተኛ የትራፊክ ፍሰት ባለበት መንገድ ላይ አንድ የጭነት መኪና 150 ሺህ ቲማቲም አስፓልት ላይ ከደፋ በኋላ የትራፊክ አደጋ አጋጠመ። ቲማቲም ጭኖ የነበረው የደረቅ ጭንት ተሽከርካሪ አደጋ ካጋጠመው በኋላ ነው ግዛቶችን በሚያገናኘው አውራ ጎዳና ላይ ቲማቲሙ የተደፋው። መንገዱ ላይ የተደፋው ቲማቲም አራት መኪኖች እንዲጋጩ እና የተለያዩ ግዛቶችን የሚያገናኘው አውራ ጎዳና አብዛኛው የመንገዱ ክፍል እንዲዘጋ ምክንያት ሆኗል። ባጋጠመው የመኪና አደጋ ሦስት ሰዎች ቀላል ጉዳት ያጋጠማቸው ሲሆን፣ አንድ ሰው ደግሞ የእግር መሰበር አደጋ ደርሶበት በሆስፒታል ሕክምና እየተደረገለት መሆኑን የካሊፎርኒያ የመንገድ ተቆጣጣሪ ፖሊስ አስታውቋል። የቲማቲም ምርት ከተሰበሰበ በኋላ አሸከርካሪዎች ምርቱን ወደ ሌሎች ግዛቶች ለማጓጓዝ ይህን አውራ ጎዳና ይጠቀማሉ። ቲማቲም ጭኖ የነረበው የደረቅ ጭነት ተሸከርካሪ ተንሸራቶ ከመንገድ ሲወጣ የደፋው ቲማቲም 200 ጫማ የመንገዱን ክፍል ሸፍኖታል። መጠናቸው ከፍ ያሉ 150 ሺህ ቲማቲሞች ተጨፈላልቀው እስከ 60 ሳንቲ ሜትር ከፍታ ያለው “ቀይ ስልስ” ፈጥረው ነበር ሲሉ የመንገድ ተቆጣጣሪ ፖሊስ አባሉ ጄሰን ታይረስት ተናግረዋል። መኪኖች የተጨፈላለቁ ቲማቲሞች ላይ ሲሄዱ እየተንሸራተቱ አደጋ ማጋጠሙም የፖሊስ አባሉ ተናግረዋል። “የቲማቲም ልጣጭ አስፓልት ከደረሰ በረዶ ላይ እንደመራመድ ነው” ሲሉ ጄሰን ታይረስት ለኒዮርክ ታይምስ ተናግረዋል። አደጋው ካጋጠመ ከበርካታ ሰዓታት በኋላ ዳግም የተሽከርካሪ አደጋ እንዳያጋጥም መንገዱ እንዲጸዳ ተደርጎ ዳግም ለትራፊክ ክፍት ሆኗል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cyrxd87m5rdo
2health
ሁለቴ የተከተቡ ሰዎች ኮሮናቫይረስ ሊያስተላልፉ ይችላሉ ተባለ
ሁለት ጊዜ የኮቪድ-19 ክትባትን የወሰዱ ሰዎች በቫይረሱ እየተያዙ እንደሆነ እና አብረዋቸው የሚኖሩ ሰዎችንም እያስያስያዙ እንደሚገኙ ባለሙያዎች ተናገሩ። ይህንን ያሳወቁት በዩናይትድ ኪንግደም የሚገኙ ቤተሰቦች ላይ ጥናት ያካሄዱ ባለሙያዎች ናቸው። እንደ ባለሙያዎቹ ከሆነ፤ ክትባቱን ሁለት ጊዜ የወሰዱ ሰዎች ክትባቱን ካልወሰዱ ሰዎች ባልተለየ መልኩ ቫይረሱን ወደ ሌሎች ሰዎች ያስተላልፋሉ። በቫይረሱ ከተያዙ በኋላ ምልክቶችን ቢያሳዩም ባያሳዩም፤ ቫይረሱን ክትባቱን ወዳልወሰዱ ሰዎች የማስተላለፍ እድላቸው ከፍተኛ እንደሆነ ተገልጿል። ይህም ከአምስት ሰዎች ሁለቱ እንደማለት ነው ይላሉ ባለሙያዎቹ። በሌላ አገላለጽ ደግሞ ቫይረሱን የማስተላለፍ ዕድላቸው 38 በመቶ ነው። ነገር ግን ሁሉም የቤተሰብ አባላት ክትባቱን ወስደው ከሆነ ቁጥሩ የሚቀንስ ሲሆን፤ ከአራት ሰዎች አንድ ሰው ቫይረሱን ያስተላልፋል። በመቶዎች ሲሰላ ደግሞ ሁለቱንም ዙር ክትባት ከወሰዱ ሰዎች መካከል 25 በመቶ የሚሆኑት ሰዎች ቫይረሱን ያስተላልፋሉ ማለት ነው። የላንሴት ተላላፊ በሽታዎች ምርምር ማዕከል እንደሚለው፤ ሁሉንም ሰው እንዲከተብ ማድረግ ከሰዎች ወደ ሰዎች የመተላለፍ እድሉን ስለሚቀንሰው አሁንም ክትባቱ ላይ ማተኮር ጠቃሚ ነው። ክትባቱን ያልወሰዱ ሰዎች በቫይረሱ ያለመያዝ እድላቸውን ከፍ ለማድረግ በዙሪያቸው ያሉ ሰዎች መከተባቸውን ማረጋገጥ ብቻ ሳይሆን እራሳቸውም ክትባቱን ቢወስዱ ይመረጣል ሲሉ ተመራማሪዎቹ ያስጠነቅቃሉ። ክትባቶች በኮቪድ-19 ምክንያት የሚከሰት ከፍተኛ ህመምን እና ሞትን ለማስቀረት ትልቅ ሚና እንደሚጫወቱ ምንም ጥርጥር የለውም። ነገር ግን የቫይረሱን ስርጭት መቀነስ ላይ አሁንም ብዙ የሚቀሩት ነገሮች አሉ። በተጨማሪ ደግሞ እንደ ዴልታ ያሉ አዳዲስ ዝርያዎች መምጣት ክትባቶቹ የታሰበላቸውን ያክል ውጤታማ እንዳይሆኑ አድርጓቸዋል። በጊዜ ብዛት ደግሞ የክትባቶቹ የመከላከል አቅም እየቀነስ ስለሚመጣ ተጨማሪ ድጋፍ የሚሰጡ ክትባቶችን (ቡስተር) መውሰድ ግድ እያለ ነው። በአሁኑ ሰዓት በተለይ በአውሮፓ አገራት ከፍተኛው የቫይረሱ ስርጭት እየተከሰተ ያለው በመኖሪያ ቤቶች አካባቢ መሆኑን ተከትሎ በተቻለ መጠን ክትባቱን መውሰድ የሚችል የቤተሰብ አባል በሙሉ ቢከተብ ይመረጣል ይላሉ ባለሙያዎቹ። እንግሊዝ ውስጥ በተሠራ አንድ ጥናት መሠረት ሁለት ጊዜ ክትባቱን የወሰዱ ሰዎች ካልተከተቡት ጋር ሲነጻጸር በአዲሱ የዴልታ ቫይረስ የመያዝ ዕድላቸው በከፍተኛ ሁኔታ የቀነሰ እንደሆነ ተመልክቷል። ሆኖም በቫይረሱ የተያዘ ሰው በሰውነቱ ውስጥ ያለው የቫይረሱ ስርጭት ከፍተኛ በሚሆንበት ወቅት የቫይረስ ክምችት እና የተከተበ ሰው የሚኖረው የቫይረስ ክምችት ተመሳሳይ ነው። ለዚህም ነው ምንም እንኳን የተከተቡት ሰዎች ምንም አይነት ምልክት ባያሳዩም ወደ ሌሎች ሰዎች ግን የሚያስተላልፉት።
ሁለቴ የተከተቡ ሰዎች ኮሮናቫይረስ ሊያስተላልፉ ይችላሉ ተባለ ሁለት ጊዜ የኮቪድ-19 ክትባትን የወሰዱ ሰዎች በቫይረሱ እየተያዙ እንደሆነ እና አብረዋቸው የሚኖሩ ሰዎችንም እያስያስያዙ እንደሚገኙ ባለሙያዎች ተናገሩ። ይህንን ያሳወቁት በዩናይትድ ኪንግደም የሚገኙ ቤተሰቦች ላይ ጥናት ያካሄዱ ባለሙያዎች ናቸው። እንደ ባለሙያዎቹ ከሆነ፤ ክትባቱን ሁለት ጊዜ የወሰዱ ሰዎች ክትባቱን ካልወሰዱ ሰዎች ባልተለየ መልኩ ቫይረሱን ወደ ሌሎች ሰዎች ያስተላልፋሉ። በቫይረሱ ከተያዙ በኋላ ምልክቶችን ቢያሳዩም ባያሳዩም፤ ቫይረሱን ክትባቱን ወዳልወሰዱ ሰዎች የማስተላለፍ እድላቸው ከፍተኛ እንደሆነ ተገልጿል። ይህም ከአምስት ሰዎች ሁለቱ እንደማለት ነው ይላሉ ባለሙያዎቹ። በሌላ አገላለጽ ደግሞ ቫይረሱን የማስተላለፍ ዕድላቸው 38 በመቶ ነው። ነገር ግን ሁሉም የቤተሰብ አባላት ክትባቱን ወስደው ከሆነ ቁጥሩ የሚቀንስ ሲሆን፤ ከአራት ሰዎች አንድ ሰው ቫይረሱን ያስተላልፋል። በመቶዎች ሲሰላ ደግሞ ሁለቱንም ዙር ክትባት ከወሰዱ ሰዎች መካከል 25 በመቶ የሚሆኑት ሰዎች ቫይረሱን ያስተላልፋሉ ማለት ነው። የላንሴት ተላላፊ በሽታዎች ምርምር ማዕከል እንደሚለው፤ ሁሉንም ሰው እንዲከተብ ማድረግ ከሰዎች ወደ ሰዎች የመተላለፍ እድሉን ስለሚቀንሰው አሁንም ክትባቱ ላይ ማተኮር ጠቃሚ ነው። ክትባቱን ያልወሰዱ ሰዎች በቫይረሱ ያለመያዝ እድላቸውን ከፍ ለማድረግ በዙሪያቸው ያሉ ሰዎች መከተባቸውን ማረጋገጥ ብቻ ሳይሆን እራሳቸውም ክትባቱን ቢወስዱ ይመረጣል ሲሉ ተመራማሪዎቹ ያስጠነቅቃሉ። ክትባቶች በኮቪድ-19 ምክንያት የሚከሰት ከፍተኛ ህመምን እና ሞትን ለማስቀረት ትልቅ ሚና እንደሚጫወቱ ምንም ጥርጥር የለውም። ነገር ግን የቫይረሱን ስርጭት መቀነስ ላይ አሁንም ብዙ የሚቀሩት ነገሮች አሉ። በተጨማሪ ደግሞ እንደ ዴልታ ያሉ አዳዲስ ዝርያዎች መምጣት ክትባቶቹ የታሰበላቸውን ያክል ውጤታማ እንዳይሆኑ አድርጓቸዋል። በጊዜ ብዛት ደግሞ የክትባቶቹ የመከላከል አቅም እየቀነስ ስለሚመጣ ተጨማሪ ድጋፍ የሚሰጡ ክትባቶችን (ቡስተር) መውሰድ ግድ እያለ ነው። በአሁኑ ሰዓት በተለይ በአውሮፓ አገራት ከፍተኛው የቫይረሱ ስርጭት እየተከሰተ ያለው በመኖሪያ ቤቶች አካባቢ መሆኑን ተከትሎ በተቻለ መጠን ክትባቱን መውሰድ የሚችል የቤተሰብ አባል በሙሉ ቢከተብ ይመረጣል ይላሉ ባለሙያዎቹ። እንግሊዝ ውስጥ በተሠራ አንድ ጥናት መሠረት ሁለት ጊዜ ክትባቱን የወሰዱ ሰዎች ካልተከተቡት ጋር ሲነጻጸር በአዲሱ የዴልታ ቫይረስ የመያዝ ዕድላቸው በከፍተኛ ሁኔታ የቀነሰ እንደሆነ ተመልክቷል። ሆኖም በቫይረሱ የተያዘ ሰው በሰውነቱ ውስጥ ያለው የቫይረሱ ስርጭት ከፍተኛ በሚሆንበት ወቅት የቫይረስ ክምችት እና የተከተበ ሰው የሚኖረው የቫይረስ ክምችት ተመሳሳይ ነው። ለዚህም ነው ምንም እንኳን የተከተቡት ሰዎች ምንም አይነት ምልክት ባያሳዩም ወደ ሌሎች ሰዎች ግን የሚያስተላልፉት።
https://www.bbc.com/amharic/59086852
2health
ኮሮናቫይረስ፡ የፕሬዝዳንት ትራምፕ ልጅ ኮቪድ-19 ተገኘበት
የዶናልድ ትራምፕ ልጅ ዶናልድ ትራምፕ ጁንየር ኮሮናቫይተስ እንደተገኘበት ቃል አቀባዩ ተናገረ። የ42 ዓመቱ ትራምፕ ጁንየር በሳምንቱ መባቻ ላይ ነው በቫይረሱ መያዙ የታወቀው። አሁን ራሱን ለይቶ ይገኛል። እስካሁን የበሽታውን ምልክቶች እንዳላሳየና በህክምና ባለሙያዎች የሚሰጠውን መርህ እየተከተለ መሆኑ ተገልጿል። ሌላው የትራምፕ ልጅ የ14 ዓመቱ ባሮን ትራምፕ ባለፈው ወር በወረርሽኙ ተይዞ በፍጥነት ማገገሙ ይታወሳል። ትራምፕ ጁንየር በአባቱ የምርጫ ቅስቀሳ ጉልህ ሚና ተጫውቷል። የፖለቲካ ዝንባሌ እንዳለውና ምርጫ መወዳደር እንደሚፈልግም ይነገራል። የትዳር አጋሩ ኪምበርሊ ጉይልፎይ ሐምሌ ላይ በቫይረሱ ተይዛ አገግማለች። በትራምፕ ዙሪያ ካሉ ሰዎች ሌላው ቫይረሱ የተገኘበት አንድሪው ጁሊያኒ የተባለው አማካሪያቸው ነው። አንድሪው የትራምፕ የግል ጠበቃ ሩዲ ጁሊያኒ ልጅ ነው። ሲቢኤስ እንደሚለው ቢያንስ አራት የዋይት ሐውስ ሠራተኞች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል። ትራምፕ ቫይረሱ ሲይዛቸው ሦስት ቀን ሆስፒታል ቆይተው መውጣታቸው አይዘነጋም። ልጃቸው ትራምፕ ጁንየር አንድ ቃለ ምልልስ ላይ መገናኛ ብዙኃን የሞቱ ሰዎችን ቁጥር አጋነው እንደሚገልጹና ያገገሙ ሰዎች ቁጥር እንደሚበልጥ ተናግረው አሜሪካ ቫይረሱን እየተቆጣጠረችው እንደሆነ ገልጸዋል። እስካሁን 11.8 ሚሊዮን አሜሪካውያን በቫይረሱ ተይዘው 253,000 ሞተዋል።
ኮሮናቫይረስ፡ የፕሬዝዳንት ትራምፕ ልጅ ኮቪድ-19 ተገኘበት የዶናልድ ትራምፕ ልጅ ዶናልድ ትራምፕ ጁንየር ኮሮናቫይተስ እንደተገኘበት ቃል አቀባዩ ተናገረ። የ42 ዓመቱ ትራምፕ ጁንየር በሳምንቱ መባቻ ላይ ነው በቫይረሱ መያዙ የታወቀው። አሁን ራሱን ለይቶ ይገኛል። እስካሁን የበሽታውን ምልክቶች እንዳላሳየና በህክምና ባለሙያዎች የሚሰጠውን መርህ እየተከተለ መሆኑ ተገልጿል። ሌላው የትራምፕ ልጅ የ14 ዓመቱ ባሮን ትራምፕ ባለፈው ወር በወረርሽኙ ተይዞ በፍጥነት ማገገሙ ይታወሳል። ትራምፕ ጁንየር በአባቱ የምርጫ ቅስቀሳ ጉልህ ሚና ተጫውቷል። የፖለቲካ ዝንባሌ እንዳለውና ምርጫ መወዳደር እንደሚፈልግም ይነገራል። የትዳር አጋሩ ኪምበርሊ ጉይልፎይ ሐምሌ ላይ በቫይረሱ ተይዛ አገግማለች። በትራምፕ ዙሪያ ካሉ ሰዎች ሌላው ቫይረሱ የተገኘበት አንድሪው ጁሊያኒ የተባለው አማካሪያቸው ነው። አንድሪው የትራምፕ የግል ጠበቃ ሩዲ ጁሊያኒ ልጅ ነው። ሲቢኤስ እንደሚለው ቢያንስ አራት የዋይት ሐውስ ሠራተኞች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል። ትራምፕ ቫይረሱ ሲይዛቸው ሦስት ቀን ሆስፒታል ቆይተው መውጣታቸው አይዘነጋም። ልጃቸው ትራምፕ ጁንየር አንድ ቃለ ምልልስ ላይ መገናኛ ብዙኃን የሞቱ ሰዎችን ቁጥር አጋነው እንደሚገልጹና ያገገሙ ሰዎች ቁጥር እንደሚበልጥ ተናግረው አሜሪካ ቫይረሱን እየተቆጣጠረችው እንደሆነ ገልጸዋል። እስካሁን 11.8 ሚሊዮን አሜሪካውያን በቫይረሱ ተይዘው 253,000 ሞተዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-55026686
0business
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተጓዦች ቁጥር ከኮቪድ ወረርሽኝ በኋላ መጨመሩ ተገለጸ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ መንገደኞች ቁጥር ከዓለም አቀፉ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በኋላ ጭማሪ ማሳየቱን የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተናገሩ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ለሮይተርስ የዜና ወኪል እንደተናገሩት ኩባንያው የበጀት ዓመቱ ሰኔ 2015 ዓ.ም. ማብቂያ ላይ የተጓዦች ቁጥር ወረርሽኙ ከመከስቱ በፊት ወደነበረበት ይመለሳል ብለዋል። ሮይተርስ አቶ መስፍን ጣሰውን ጠቅሶ እንደዘገበው አየር መንገዱ በበጀት ዓመቱ መጨረሻ 12.7 ሚሊዮን መንገደኞችን አጓጉዛለሁ ብሎ ይጠብቃል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለፈው ዓመት 8.6 ሚሊዮን ሰዎችን ያጓጓዘ ሲሆን፣ የኮሮናቫይረስ ከመቀስቀሱ በፊት ደግሞ ያጓጓዛቸው የደንበኞቹ ቁጥር 12.1 ሚሊዮን ነበር። ዓለም አቀፍ ስጋት የነበረው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከፍተኛ የሆነ ምጣኔ ሃብታዊ ቀውስን አስከትሎ የነበረ ሲሆን በተለይ ደግሞ በአቪዬሽን ኢንዱስትሪው ላይ ከፍተኛ ጉዳትን አስከትሏል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግን በወረርሸኙ ስርጭት ወቅትም የመንገደኞች አውሮፕላኖችን ወደ ዕቃ ጫኝ አውሮፕላኖች በመቀየር በመንገደኞች መቀነስ ያጣውን ገቢ ማካካስ ችሏል። ሮይተርስ በዘገባው ከወረርሽኙ በኋላ አየር መንገዱ የተጓዦቹን ቁጥር ከፍ ማድረግ አስችለውታል ያላቸውን ምክንያቶች የኩባንያውን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጠቅሶ ዘግቧል። አየር መንገዱ አዳዲስ አውሮፕላኖች መግዛቱ፣ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎቹን መጨመሩ እና የሰሜን ኢትዮጵያ የእርስ በርስ ጦርነት ለማብቃት የሰላም ስምምነት መፈረሙ ለስኬቱ እንደምክንያት ተጠቅሰዋል። ከአየር መንገዱ የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ኩባንያው በአሁኑ ወቅት 141 አውሮፕላኖች አሉት። ከእነዚህ መካከል እጅግ ዘመናዊ እና ግዙፍ የሆኑት 19 ኤርባስ ኤ350-900 እና 19 ቦይንግ ቢ787-8 እና 8 ቦይንግ ቢ787-9 የመንገደኞች አውሮፕላኖች ይገኙበታል። ዘመናዊዎቹን 4 ኤርባስ ኤ350-1000 አውሮፕላኖችን ጨምሮ 21 ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላኖች ደግሞ አንዲቀርቡለት ትዕዛዝ ሰጥቷል። አየር መንገዱ ተጨማሪ አውሮፕላኖችን ለመግዛት ከአሜሪካው ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ ኦፍ ዘ ዩናይትድ ስቴትስ የጠየቀው ብድር ዋስትና በዚህ ሳምንት ሊፈቅድለት እንደሚችል የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዋና ሥራ አስኪያጁን ጠቅሶ ዘግቦ ነበር። አየር መንገዱ ባንኩን የጠየቀው የብድር ዋስትና በሰሜን ኢትዮጵያ ሲካሄድ በነበረው የርስ በርስ ጦርነት እና በፖለቲከኞች ጫና ምክንያት መዘግየቱን መስፍን ጣሰው ተናግረዋል። ይሁን እንጂ የብድር ሂደቱን የማጽደቅ ሂደት መጀመሩን እና በተያዘው ሳምንት ፍቃዱ ሊገኝ እንደሚችል ተዘግቧል። አየር መንገዱ ለስኬቱ እንደ ምክንያት የተጠቀሰው ዓለም አቀፍ መዳረሻዎችን መጨመሩ ነው። ኩባንያው በአውሮፓውያኑ 2035 የአውሮፕላን ቁጥሮችን እና መዳረሻዎችን ከፍ በማድረግ ዓመታዊ ገቢውን በ400 ፐርሰንት እንዲሁም የተጓዦቹን ቁጥር ደግሞ በ440 ፐርሰንት የመጨመር ዕቅድ እንዳለው ተጠቅሷል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቅርብ ከጀመራቸው ወይም ከሚጀምራቸው አዳዲስ መዳረሻዎች መካከል የስዊትዘርላንዷ ዙሪክ፣ ሕንዷ ቺናይ፣ ጆርዳን አማን እና የዚምባብዌዋ ቡላዋዮ ተጠቃሽ ናቸው። ከወራት በኋላ ደግሞ ወደ ሲንጋፖር የሚያደርገውን የቀጥታ በረራ ዳግም ይጀምራል። “በተመሳሳይ ጊዜ የመንገደኞች ቁጥር እና የዕቃ ጫኝ በረራዎችን እየጨመርን ነው” ሲሉ ለዜና ወኪሉ የተናገሩት መስፍን፤ የኮቪድ ወረርሽኝን ተከትሎ አገራት ጥለው የነበሩትን የጉዞ ገደቦችን እያላሉ እና እያነሱ በሄዱ ቁጥር የመንደኖች ቁጥር እንዲጨምር ይፈቅዳል ሲሉ ተናግረዋል። የ2022 የስካይትራክስ የዓለም አየር መንገዶች ውድድር ላይ በርካታ ሽልማትን የተቀበውለው አየር መንገድ ሥራ አስኪያጅ፤ ኩባንያው ካላደገ በቅር ተልዕኮውን ማሳካት አይችልም ያሉ ሲሆን ይህን ለማድረግም የአየር መንገዱን ኦፕሬሽን ማስፋፋት እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል። ይሁን እንጂ መንገደኞችምን ይሁን የዕቃ ማጓጓዝ ሥራ ላይ ቁልፍ መዳረሻ በሆነችው ቻይና የአገሪቱ መንግሥት የኮቪድ ስርጭትን ለመቆጣጠር ሲባል እየተገበራቸው ያሉት ጥብቅ ቁጥጥሮች ለአየር መንገዱ ፈተና ሊሆን እንደሚችል ተመላክቷል። ከሦስት ወራት በፊት በተካሄደው የስካይትራክስ የሽልማት ሥነ ሥርዓት ላይ አየር መንደጉ ለተከታታይ አምስት ዓመታት የአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ፣ የአፍሪካ ምርጥ ቢዝነስ ክላስ፣ የአፍሪካ ምርጥ የኢኮኖሚ ክለስ ተብሎ ተመርጧል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተጓዦች ቁጥር ከኮቪድ ወረርሽኝ በኋላ መጨመሩ ተገለጸ የኢትዮጵያ አየር መንገድ መንገደኞች ቁጥር ከዓለም አቀፉ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በኋላ ጭማሪ ማሳየቱን የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተናገሩ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ለሮይተርስ የዜና ወኪል እንደተናገሩት ኩባንያው የበጀት ዓመቱ ሰኔ 2015 ዓ.ም. ማብቂያ ላይ የተጓዦች ቁጥር ወረርሽኙ ከመከስቱ በፊት ወደነበረበት ይመለሳል ብለዋል። ሮይተርስ አቶ መስፍን ጣሰውን ጠቅሶ እንደዘገበው አየር መንገዱ በበጀት ዓመቱ መጨረሻ 12.7 ሚሊዮን መንገደኞችን አጓጉዛለሁ ብሎ ይጠብቃል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለፈው ዓመት 8.6 ሚሊዮን ሰዎችን ያጓጓዘ ሲሆን፣ የኮሮናቫይረስ ከመቀስቀሱ በፊት ደግሞ ያጓጓዛቸው የደንበኞቹ ቁጥር 12.1 ሚሊዮን ነበር። ዓለም አቀፍ ስጋት የነበረው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከፍተኛ የሆነ ምጣኔ ሃብታዊ ቀውስን አስከትሎ የነበረ ሲሆን በተለይ ደግሞ በአቪዬሽን ኢንዱስትሪው ላይ ከፍተኛ ጉዳትን አስከትሏል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግን በወረርሸኙ ስርጭት ወቅትም የመንገደኞች አውሮፕላኖችን ወደ ዕቃ ጫኝ አውሮፕላኖች በመቀየር በመንገደኞች መቀነስ ያጣውን ገቢ ማካካስ ችሏል። ሮይተርስ በዘገባው ከወረርሽኙ በኋላ አየር መንገዱ የተጓዦቹን ቁጥር ከፍ ማድረግ አስችለውታል ያላቸውን ምክንያቶች የኩባንያውን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጠቅሶ ዘግቧል። አየር መንገዱ አዳዲስ አውሮፕላኖች መግዛቱ፣ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎቹን መጨመሩ እና የሰሜን ኢትዮጵያ የእርስ በርስ ጦርነት ለማብቃት የሰላም ስምምነት መፈረሙ ለስኬቱ እንደምክንያት ተጠቅሰዋል። ከአየር መንገዱ የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ኩባንያው በአሁኑ ወቅት 141 አውሮፕላኖች አሉት። ከእነዚህ መካከል እጅግ ዘመናዊ እና ግዙፍ የሆኑት 19 ኤርባስ ኤ350-900 እና 19 ቦይንግ ቢ787-8 እና 8 ቦይንግ ቢ787-9 የመንገደኞች አውሮፕላኖች ይገኙበታል። ዘመናዊዎቹን 4 ኤርባስ ኤ350-1000 አውሮፕላኖችን ጨምሮ 21 ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላኖች ደግሞ አንዲቀርቡለት ትዕዛዝ ሰጥቷል። አየር መንገዱ ተጨማሪ አውሮፕላኖችን ለመግዛት ከአሜሪካው ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ ኦፍ ዘ ዩናይትድ ስቴትስ የጠየቀው ብድር ዋስትና በዚህ ሳምንት ሊፈቅድለት እንደሚችል የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዋና ሥራ አስኪያጁን ጠቅሶ ዘግቦ ነበር። አየር መንገዱ ባንኩን የጠየቀው የብድር ዋስትና በሰሜን ኢትዮጵያ ሲካሄድ በነበረው የርስ በርስ ጦርነት እና በፖለቲከኞች ጫና ምክንያት መዘግየቱን መስፍን ጣሰው ተናግረዋል። ይሁን እንጂ የብድር ሂደቱን የማጽደቅ ሂደት መጀመሩን እና በተያዘው ሳምንት ፍቃዱ ሊገኝ እንደሚችል ተዘግቧል። አየር መንገዱ ለስኬቱ እንደ ምክንያት የተጠቀሰው ዓለም አቀፍ መዳረሻዎችን መጨመሩ ነው። ኩባንያው በአውሮፓውያኑ 2035 የአውሮፕላን ቁጥሮችን እና መዳረሻዎችን ከፍ በማድረግ ዓመታዊ ገቢውን በ400 ፐርሰንት እንዲሁም የተጓዦቹን ቁጥር ደግሞ በ440 ፐርሰንት የመጨመር ዕቅድ እንዳለው ተጠቅሷል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቅርብ ከጀመራቸው ወይም ከሚጀምራቸው አዳዲስ መዳረሻዎች መካከል የስዊትዘርላንዷ ዙሪክ፣ ሕንዷ ቺናይ፣ ጆርዳን አማን እና የዚምባብዌዋ ቡላዋዮ ተጠቃሽ ናቸው። ከወራት በኋላ ደግሞ ወደ ሲንጋፖር የሚያደርገውን የቀጥታ በረራ ዳግም ይጀምራል። “በተመሳሳይ ጊዜ የመንገደኞች ቁጥር እና የዕቃ ጫኝ በረራዎችን እየጨመርን ነው” ሲሉ ለዜና ወኪሉ የተናገሩት መስፍን፤ የኮቪድ ወረርሽኝን ተከትሎ አገራት ጥለው የነበሩትን የጉዞ ገደቦችን እያላሉ እና እያነሱ በሄዱ ቁጥር የመንደኖች ቁጥር እንዲጨምር ይፈቅዳል ሲሉ ተናግረዋል። የ2022 የስካይትራክስ የዓለም አየር መንገዶች ውድድር ላይ በርካታ ሽልማትን የተቀበውለው አየር መንገድ ሥራ አስኪያጅ፤ ኩባንያው ካላደገ በቅር ተልዕኮውን ማሳካት አይችልም ያሉ ሲሆን ይህን ለማድረግም የአየር መንገዱን ኦፕሬሽን ማስፋፋት እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል። ይሁን እንጂ መንገደኞችምን ይሁን የዕቃ ማጓጓዝ ሥራ ላይ ቁልፍ መዳረሻ በሆነችው ቻይና የአገሪቱ መንግሥት የኮቪድ ስርጭትን ለመቆጣጠር ሲባል እየተገበራቸው ያሉት ጥብቅ ቁጥጥሮች ለአየር መንገዱ ፈተና ሊሆን እንደሚችል ተመላክቷል። ከሦስት ወራት በፊት በተካሄደው የስካይትራክስ የሽልማት ሥነ ሥርዓት ላይ አየር መንደጉ ለተከታታይ አምስት ዓመታት የአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ፣ የአፍሪካ ምርጥ ቢዝነስ ክላስ፣ የአፍሪካ ምርጥ የኢኮኖሚ ክለስ ተብሎ ተመርጧል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cw0w008g05wo
0business
በኢትዮጵያ ሚሊዮኖች ሥራ ሊያጡ እና የአገር ውስጥ ምርት እድገት 11.2 በመቶ ሊቀንስ ይችላል
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በዓለም ምጣኔ ሃብት ላይ ያሳደረው ተፅዕኖ ከበድ ያለ ነው። ግዙፍ የምጣኔ ሃብት አላቸው የሚባሉት እንደ አሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንገድደም እና ሕንድ ባሉ አገራት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎቻቸው ቫይረሱ ባመጣው ሰበብ ሥራ ፈላጊ ሆነዋል። ወረርሽኙ በአገራችንም ምጣኔ ሃብት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንደሚኖረው ግልጽ ነው። ወረርሽኙ የኢትዮጵያ ምጣኔ ሃብት ላይ ሊያደርስ የሚችለው ተፅዕኖ ምን ይመስላል? ለሚለው ጥያቄ ምላሽ ለማግኘት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ክፍል መምህር የሆኑት ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ ጥናት ሠርተዋል። • "ጆርጅ ፍሎይድን አንቆ የገደለው ፖሊስ 'አስቦና አቅዶ' ነው" የፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ ጥናት እንዳሳየው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የአገሪቱን ምጣኔ ሃብት 5.6 በመቶ ሊጎዳው እንደሚችል ይጠቁማል። "ልክ አውሮፓ እና አሜሪካ እንደተስፋፋው፤ ቫይረሱን እኛም አገር ቢሰራጭ ኢኮኖሚያችን እሱን የሚሸከምበት አቅም የለውም። ከሚጠበቀው በላይ ነው የሚጎዳን። ምክንያቱም እነሱ [ምዕራባውያን አገራት] የተሻለ ኢኮኖሚ፣ የሰው ኃይል እና ቁጠባ አላቸው። እኔ ባሰላሁት መሠረት ኢኮኖሚያዊ ጉዳቱ እጅግ ትልቅ ነው" ይላሉ የኢኮኖሚክስ ፕሮፌሰሩ አለማየሁ ገዳ። የፕሮፌሰሩ ጥናት እንደጠቆመው ኢትዮጵያ በ2020 (በአውሮፓውያን አቆጣጠር) የበጀት ዓመት የአገር ውስጥ ምርት እድገት (ጂዲፒ) በአማካይ 11.2 በመቶ ሊላሽቅ ይችላል። ፕሮፌሰር አለማየሁ እንደሚሉት ከሆነ፤ ከሐምሌ 2012 እስከ ሰኔ 2013 በሚዘልቀው የበጀት ዓመት ላይ ቫይረሱ የሚያስከትለው ጉዳት በመጀመሪያው ሩብ ዓመት የሚገታ ከሆነ፤ የአገር ውስጥ ምርት እድገቱ ሊቀንስ የሚችለው በ5.6 በመቶ ነው። ቫይረሱ የሚስከትለው ጉዳት ግን እስከ ሶስተኛው ሩብ ዓመት የሚዘልቅ ከሆነ የአገር ውስጥ ምርት እድገቱ የሚቀንሰው በ16.7 በመቶ ይሆናል። • “ሚድያውን ደፍረን ማስተካከል ካልቻልን፤ ይህቺን አገር ነገ ላናገኛት እንችላለን” ዘነበ በየነ (ዶ/ር) ፕሮፌሰሩ የቫይረሱ ስርጭት የሚያስከትለውን ኢኮኖሚያዊ ድቀት ለመቀነስ "ያለ ኃይልን በማሰባሰብ ቫይረሱ ወደ ህብረተሰቡ ከመሰራጨቱ በፊት በቁጥጥር ሥር ማድረግ ነው" ሲሉ ይመክራሉ። ፕሮፌሰር አለማየሁ ዘመዶቻችን ከውጪ በባንክ በኩል የሚልኩት ገንዘብ አገሪቱ ምርት ወደ ውጪ ልካ ከምታገኘው ዶላር በላይ መሆኑን ይናገራሉ። "የመንግሥት አሃዞችን ብንመለከት እንኳ፣ አገሪቱ ወደ ውጪ አገራት ምርት ልካ የምታገኘው ገቢ 2.8 እስከ 3 ቢሊዮን ነው። እንደውም ወደ ውጪ የሚላከው ምርት እየቀነሰ ነው። ከውጪ የሚላከው ገንዘብ ግን ከ4.5 እስከ 6 ቢሊዮን ዶላር ነው" ይላሉ። "መንግሥት ወደ ውጪ እንደሚላኩ ምርቶች ሁሉ ከውጪ ወደ አገር በሚላክ ገንዘብ ላይ በቂ አትኩሮት አይሰጥም የሚሉት ፕሮፌሰሩ፣ "ምርት ወደ ውጪ ልከን የምንሸጠው 3 ቢሊዮን ነው። የምናስገባው ደግሞ 17-18 ቢሊዮን ዶላር ነው" በማለት ይሄን የንግድ ክፍተት ለመሸፈን 'ሬሚታንሱ' ከፍተኛውን ሚና እንደሚጫወት ይናገራሉ። • የደረሱበት ያልታወቀው ተማሪዎች ስድስት ወር ሆናቸው በኮቪድ-19 ምክንያት ወደ ኢትዮጵያ ገንዘብ ይልኩ የነበሩ ሰዎች እንደ ከዚህ ቀደም መላክ ባለመቻላቸው አገሪቱ ከ'ሬሚታንስ' ወይም ከውጪ ይላክ ከነበረ ዶላር ታገኝ ነበረውን ገንዘብ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲቀንስ አድርጓል ይላሉ። ዓለም አቀፍ ትንበያዎች ከሃብታም አገራት ወደ ትውልድ አገራት የሚላክ ገንዘብ መጠን በ26 በመቶ እንደሚቀንስ ማሳየታቸውን የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ይናገራሉ። ኮቪድ-19 ወረርሽኝ በአሜሪካ እና አውሮፓ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩትን ሥራ አጥ አድርጎ የመንግሥት ድጎማን እንዲጠብቁ አስገድዷል። ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳም፤ በአገራችንም ኮቪድ-19 ቢያንስ እስከ 2.5 ሚሊዮን ሰዎች ሥራ አጥ ሊያደርግ እንደሚችል በጥናታቸው አመላክተዋል። "1.8 ሚሊዮን ሰው የመንግሥት ሰራተኛ ነው። የመንግሥት ሰራተኛው በወረርሽኙ ሳብያ ከሥራው ይፈናቀላል ብለን አንጠብቅም" የሚሉት ፕሮፌሰሩ፤ "የግል ሴክተሩ ደግሞ 1.5 ሚሊዮን ሰዎችን ቀጥሯል። ከእነዚህም መካከል ግማሽ ያክሉ ሥራ አጥ ሊሆኑ ይችላሉ" ይላሉ። ከእነዚህ በተጨማሪ "ራሱን ቀጥሮ የሚያሳድር ደግሞ 3.1 ሚሊዮን አለ። እነዚህም ተጋላጭ ናቸው። ሥራቸውን በቀላሉ ሊያጡ ይችላሉ" ይላሉ። "የእርሻው ክፍለ ኢኮኖሚ ብዙ አይጎዳም። ብዙ የሚጎዱት የአገልግሎት እና ኢንደስትሪ ዘረፎች ናቸው። ስለዚህ ያለ የሌለ አቅማችንን በእርሻው ላይ ማድረግ አለብን። ግብርናው የሚወድቀውን ኢኮኖሚያችንን ሊታደግልን ይችላል" በማለት እንደመፍትሄ ካስቀመጧቸው የመጀመሪያውን ነጥብ ያነሳሉ። ለዚህም በሽታው ወደ ገጠር እንዳይገባ ጥንቃቄ መድረግ እንዳለበት ፕሮፌሰር አለማየሁ ያሳስባሉ። መንግሥት ከግል ሴክተሩ ጋር በመነጋገር ሊታገዙ የሚቻልበት ሁኔታ ላይ እቅድ ማውጣት ያስፈልጋል ሲሉም ያክላሉ። • በምዕራብ ወለጋ የአራት ልጆች እናት የሆኑትን ግለሰብ ማን ገደላቸው? ፕሮፌሰር አለማየሁ እንደሚሉት በቫይረሱ ስርጭት እጅጉን ከሚጎዱት መካከል ራሳቸውን ቀጥረው የሚገኙት 3.1 ሚሊዮን ዜጎች እና ቤተሰቦቻቸው ናቸው በማለት "ሥራ በሌለበት የሥራ ቦታ እና የመኖሪያ ቤት ኪራይ እየከፈሉ ነው። መንግሥት እያለ ያለው 'እባካችሁ ቤት ኪራይ ቀንሱላቸው' ነው። እንደዛ ብቻ መሆን የለበትም። መንግሥት የቤት ኪራይ የማይከፍሉበትን መንገድ ቢፈልግ እና ለአከራዮች ደግሞ እንደ ቼክ ወይም ቦንድ ባሉ ሰነዶች ማረጋገጫ ቢሰጥ ይረዳል ብዬ አስባለሁ" ብለዋል። የግል ዘርፉም ከመንግሥት ድጋፍ ማግኘት እንዳለበትም ሃሳባቸውን ኣቀርባሉ።
በኢትዮጵያ ሚሊዮኖች ሥራ ሊያጡ እና የአገር ውስጥ ምርት እድገት 11.2 በመቶ ሊቀንስ ይችላል የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በዓለም ምጣኔ ሃብት ላይ ያሳደረው ተፅዕኖ ከበድ ያለ ነው። ግዙፍ የምጣኔ ሃብት አላቸው የሚባሉት እንደ አሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንገድደም እና ሕንድ ባሉ አገራት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎቻቸው ቫይረሱ ባመጣው ሰበብ ሥራ ፈላጊ ሆነዋል። ወረርሽኙ በአገራችንም ምጣኔ ሃብት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንደሚኖረው ግልጽ ነው። ወረርሽኙ የኢትዮጵያ ምጣኔ ሃብት ላይ ሊያደርስ የሚችለው ተፅዕኖ ምን ይመስላል? ለሚለው ጥያቄ ምላሽ ለማግኘት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ክፍል መምህር የሆኑት ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ ጥናት ሠርተዋል። • "ጆርጅ ፍሎይድን አንቆ የገደለው ፖሊስ 'አስቦና አቅዶ' ነው" የፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ ጥናት እንዳሳየው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የአገሪቱን ምጣኔ ሃብት 5.6 በመቶ ሊጎዳው እንደሚችል ይጠቁማል። "ልክ አውሮፓ እና አሜሪካ እንደተስፋፋው፤ ቫይረሱን እኛም አገር ቢሰራጭ ኢኮኖሚያችን እሱን የሚሸከምበት አቅም የለውም። ከሚጠበቀው በላይ ነው የሚጎዳን። ምክንያቱም እነሱ [ምዕራባውያን አገራት] የተሻለ ኢኮኖሚ፣ የሰው ኃይል እና ቁጠባ አላቸው። እኔ ባሰላሁት መሠረት ኢኮኖሚያዊ ጉዳቱ እጅግ ትልቅ ነው" ይላሉ የኢኮኖሚክስ ፕሮፌሰሩ አለማየሁ ገዳ። የፕሮፌሰሩ ጥናት እንደጠቆመው ኢትዮጵያ በ2020 (በአውሮፓውያን አቆጣጠር) የበጀት ዓመት የአገር ውስጥ ምርት እድገት (ጂዲፒ) በአማካይ 11.2 በመቶ ሊላሽቅ ይችላል። ፕሮፌሰር አለማየሁ እንደሚሉት ከሆነ፤ ከሐምሌ 2012 እስከ ሰኔ 2013 በሚዘልቀው የበጀት ዓመት ላይ ቫይረሱ የሚያስከትለው ጉዳት በመጀመሪያው ሩብ ዓመት የሚገታ ከሆነ፤ የአገር ውስጥ ምርት እድገቱ ሊቀንስ የሚችለው በ5.6 በመቶ ነው። ቫይረሱ የሚስከትለው ጉዳት ግን እስከ ሶስተኛው ሩብ ዓመት የሚዘልቅ ከሆነ የአገር ውስጥ ምርት እድገቱ የሚቀንሰው በ16.7 በመቶ ይሆናል። • “ሚድያውን ደፍረን ማስተካከል ካልቻልን፤ ይህቺን አገር ነገ ላናገኛት እንችላለን” ዘነበ በየነ (ዶ/ር) ፕሮፌሰሩ የቫይረሱ ስርጭት የሚያስከትለውን ኢኮኖሚያዊ ድቀት ለመቀነስ "ያለ ኃይልን በማሰባሰብ ቫይረሱ ወደ ህብረተሰቡ ከመሰራጨቱ በፊት በቁጥጥር ሥር ማድረግ ነው" ሲሉ ይመክራሉ። ፕሮፌሰር አለማየሁ ዘመዶቻችን ከውጪ በባንክ በኩል የሚልኩት ገንዘብ አገሪቱ ምርት ወደ ውጪ ልካ ከምታገኘው ዶላር በላይ መሆኑን ይናገራሉ። "የመንግሥት አሃዞችን ብንመለከት እንኳ፣ አገሪቱ ወደ ውጪ አገራት ምርት ልካ የምታገኘው ገቢ 2.8 እስከ 3 ቢሊዮን ነው። እንደውም ወደ ውጪ የሚላከው ምርት እየቀነሰ ነው። ከውጪ የሚላከው ገንዘብ ግን ከ4.5 እስከ 6 ቢሊዮን ዶላር ነው" ይላሉ። "መንግሥት ወደ ውጪ እንደሚላኩ ምርቶች ሁሉ ከውጪ ወደ አገር በሚላክ ገንዘብ ላይ በቂ አትኩሮት አይሰጥም የሚሉት ፕሮፌሰሩ፣ "ምርት ወደ ውጪ ልከን የምንሸጠው 3 ቢሊዮን ነው። የምናስገባው ደግሞ 17-18 ቢሊዮን ዶላር ነው" በማለት ይሄን የንግድ ክፍተት ለመሸፈን 'ሬሚታንሱ' ከፍተኛውን ሚና እንደሚጫወት ይናገራሉ። • የደረሱበት ያልታወቀው ተማሪዎች ስድስት ወር ሆናቸው በኮቪድ-19 ምክንያት ወደ ኢትዮጵያ ገንዘብ ይልኩ የነበሩ ሰዎች እንደ ከዚህ ቀደም መላክ ባለመቻላቸው አገሪቱ ከ'ሬሚታንስ' ወይም ከውጪ ይላክ ከነበረ ዶላር ታገኝ ነበረውን ገንዘብ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲቀንስ አድርጓል ይላሉ። ዓለም አቀፍ ትንበያዎች ከሃብታም አገራት ወደ ትውልድ አገራት የሚላክ ገንዘብ መጠን በ26 በመቶ እንደሚቀንስ ማሳየታቸውን የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ይናገራሉ። ኮቪድ-19 ወረርሽኝ በአሜሪካ እና አውሮፓ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩትን ሥራ አጥ አድርጎ የመንግሥት ድጎማን እንዲጠብቁ አስገድዷል። ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳም፤ በአገራችንም ኮቪድ-19 ቢያንስ እስከ 2.5 ሚሊዮን ሰዎች ሥራ አጥ ሊያደርግ እንደሚችል በጥናታቸው አመላክተዋል። "1.8 ሚሊዮን ሰው የመንግሥት ሰራተኛ ነው። የመንግሥት ሰራተኛው በወረርሽኙ ሳብያ ከሥራው ይፈናቀላል ብለን አንጠብቅም" የሚሉት ፕሮፌሰሩ፤ "የግል ሴክተሩ ደግሞ 1.5 ሚሊዮን ሰዎችን ቀጥሯል። ከእነዚህም መካከል ግማሽ ያክሉ ሥራ አጥ ሊሆኑ ይችላሉ" ይላሉ። ከእነዚህ በተጨማሪ "ራሱን ቀጥሮ የሚያሳድር ደግሞ 3.1 ሚሊዮን አለ። እነዚህም ተጋላጭ ናቸው። ሥራቸውን በቀላሉ ሊያጡ ይችላሉ" ይላሉ። "የእርሻው ክፍለ ኢኮኖሚ ብዙ አይጎዳም። ብዙ የሚጎዱት የአገልግሎት እና ኢንደስትሪ ዘረፎች ናቸው። ስለዚህ ያለ የሌለ አቅማችንን በእርሻው ላይ ማድረግ አለብን። ግብርናው የሚወድቀውን ኢኮኖሚያችንን ሊታደግልን ይችላል" በማለት እንደመፍትሄ ካስቀመጧቸው የመጀመሪያውን ነጥብ ያነሳሉ። ለዚህም በሽታው ወደ ገጠር እንዳይገባ ጥንቃቄ መድረግ እንዳለበት ፕሮፌሰር አለማየሁ ያሳስባሉ። መንግሥት ከግል ሴክተሩ ጋር በመነጋገር ሊታገዙ የሚቻልበት ሁኔታ ላይ እቅድ ማውጣት ያስፈልጋል ሲሉም ያክላሉ። • በምዕራብ ወለጋ የአራት ልጆች እናት የሆኑትን ግለሰብ ማን ገደላቸው? ፕሮፌሰር አለማየሁ እንደሚሉት በቫይረሱ ስርጭት እጅጉን ከሚጎዱት መካከል ራሳቸውን ቀጥረው የሚገኙት 3.1 ሚሊዮን ዜጎች እና ቤተሰቦቻቸው ናቸው በማለት "ሥራ በሌለበት የሥራ ቦታ እና የመኖሪያ ቤት ኪራይ እየከፈሉ ነው። መንግሥት እያለ ያለው 'እባካችሁ ቤት ኪራይ ቀንሱላቸው' ነው። እንደዛ ብቻ መሆን የለበትም። መንግሥት የቤት ኪራይ የማይከፍሉበትን መንገድ ቢፈልግ እና ለአከራዮች ደግሞ እንደ ቼክ ወይም ቦንድ ባሉ ሰነዶች ማረጋገጫ ቢሰጥ ይረዳል ብዬ አስባለሁ" ብለዋል። የግል ዘርፉም ከመንግሥት ድጋፍ ማግኘት እንዳለበትም ሃሳባቸውን ኣቀርባሉ።
https://www.bbc.com/amharic/news-52831184
5sports
አርጀንቲናዊው የእግር ኳስ ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ ኮቪድ-19 ተገኘበት
ሊዮኔል ሜሲ ኮቪድ-19 ከተገኘባቸው አራት የፓሪስ ሴይንት-ዠርሜይን ተጫዋቾች አንዱ እንደሆነ ታወቀ። አርንቲናዊው አጥቂ እንዲሁም የቡድን አጋሮቹ የሆኑት ሁዋን በርናት፣ ናታን ቢቱማዛላ እንዲሁም ሰርጂዮ ሪኮ ናቸው ኮቪድ-19 እንደተገኘባቸው የተገለጸው። ተጫዋቾቹ ቡድናቸው ፒኤስጂ በፍሬንች ካፕ ፍልሚያ ከቫኔስ ጋር ሊጫወት ሲሰናዳ ነው ውጤታቸው የተነገራቸው። አራቱም ተጫዋቾች ራሳቸውን አግልለው የጤና ሁኔታቸውን እየተከታተሉ ነው። የፒሴስጂው አሠልጣኝ ሞሪሲዮ ፖቼቲኖ እንዳሉት ሜሲ ለበዓል እረፍት ወደ አገር ቤት ስለሄደ የኮቪድ-19 ምርመራ ውጤቱ ኔጋቲቭ እስኪሆን ድረስ እዚያው ይቆያል። ከጨዋታው በፊት እንደተለመደው ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት ፖቼቲኖ አክለው ሜሲ መቼ ሊመለስ ይችላል የሚለውን መገመት እንደሚያዳግታቸውም ተናግረዋል። ፒኤስጂ ከፍሬንች ካፕ ሲመለስ ከበዓል እረፍት በኋላ በሚቀጥለው እሑድ ሊዮንን ይገጥማል። ሌላኛው የክለቡ አጥቂ ብራዚላዊው ኔይማር ካጋጠመው ጉዳት ስላላገገመ በዚህ ጨዋታ የመሳተፉ ነገር አጠራጣሪ ሆኗል። ፒኤስጂ የ29 ዓመቱ ኔይማር በሚቀጥሉት ሦስት ሳምንታት ወደ ሜዳ ሊመለስ ይችላል ተብሏል። የፈረንሳይ ሊግን እየመራ የሚገኘው ፒኤስጂ በቻምፒዬንስ ሊግ ፍልሚያ በጥሎ ማለፍ ጨዋታ ከሪያል ማድሪድ ጋር ይፋለማል። አርጀንቲናዊው አጥቂ ሜሲ በፈረንሳይ ሊግ ብዙም እየተሳካለት አይደለም። ሜሲ እስካሁን በሊጉ ያስቆጠረው አንድ ጎል ነው። በቻምፒዬንስ ሊግ ደግሞ በምድብ ጨዋታ አምስት ጎሎችን በስሙ አስመዝግቧል።
አርጀንቲናዊው የእግር ኳስ ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ ኮቪድ-19 ተገኘበት ሊዮኔል ሜሲ ኮቪድ-19 ከተገኘባቸው አራት የፓሪስ ሴይንት-ዠርሜይን ተጫዋቾች አንዱ እንደሆነ ታወቀ። አርንቲናዊው አጥቂ እንዲሁም የቡድን አጋሮቹ የሆኑት ሁዋን በርናት፣ ናታን ቢቱማዛላ እንዲሁም ሰርጂዮ ሪኮ ናቸው ኮቪድ-19 እንደተገኘባቸው የተገለጸው። ተጫዋቾቹ ቡድናቸው ፒኤስጂ በፍሬንች ካፕ ፍልሚያ ከቫኔስ ጋር ሊጫወት ሲሰናዳ ነው ውጤታቸው የተነገራቸው። አራቱም ተጫዋቾች ራሳቸውን አግልለው የጤና ሁኔታቸውን እየተከታተሉ ነው። የፒሴስጂው አሠልጣኝ ሞሪሲዮ ፖቼቲኖ እንዳሉት ሜሲ ለበዓል እረፍት ወደ አገር ቤት ስለሄደ የኮቪድ-19 ምርመራ ውጤቱ ኔጋቲቭ እስኪሆን ድረስ እዚያው ይቆያል። ከጨዋታው በፊት እንደተለመደው ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት ፖቼቲኖ አክለው ሜሲ መቼ ሊመለስ ይችላል የሚለውን መገመት እንደሚያዳግታቸውም ተናግረዋል። ፒኤስጂ ከፍሬንች ካፕ ሲመለስ ከበዓል እረፍት በኋላ በሚቀጥለው እሑድ ሊዮንን ይገጥማል። ሌላኛው የክለቡ አጥቂ ብራዚላዊው ኔይማር ካጋጠመው ጉዳት ስላላገገመ በዚህ ጨዋታ የመሳተፉ ነገር አጠራጣሪ ሆኗል። ፒኤስጂ የ29 ዓመቱ ኔይማር በሚቀጥሉት ሦስት ሳምንታት ወደ ሜዳ ሊመለስ ይችላል ተብሏል። የፈረንሳይ ሊግን እየመራ የሚገኘው ፒኤስጂ በቻምፒዬንስ ሊግ ፍልሚያ በጥሎ ማለፍ ጨዋታ ከሪያል ማድሪድ ጋር ይፋለማል። አርጀንቲናዊው አጥቂ ሜሲ በፈረንሳይ ሊግ ብዙም እየተሳካለት አይደለም። ሜሲ እስካሁን በሊጉ ያስቆጠረው አንድ ጎል ነው። በቻምፒዬንስ ሊግ ደግሞ በምድብ ጨዋታ አምስት ጎሎችን በስሙ አስመዝግቧል።
https://www.bbc.com/amharic/news-59856473
2health
ኮሮናቫይረስ፡ ሳኡዲ አረቢያ የኡምራ ጉⶋን በመስከረም ወር መጨረሻ ልትጀምር ነው
በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ለሰባት ወራት ያህል ተቋርጦ የነበረው የኡምራ ሃይማኖታዊ ጉዞ በዚህ ወር እንደሚጀመር ሳዑዲ አረቢያ አስታወቀች። ከመስከረም 24፣ 2012 ዓ.ም ጀምሮም ስድስት ሺህ የሳዑዲ ዜጎች በየቀኑ የኡምራ ጉዞ እንዲያደርጉ ተፈቅዶላቸዋል። ከሌላ አገር የሚመጡ የኡምራ ፀሎተኞችም ከጥቅምት 22፣ 2013 ዓ.ም ጀምሮ መምጣት ይችላሉ ተብሏል። የየቀኑም ተጓዦች ቁጥር ወደ 20 ሺህ ያድጋል እንደሚያድገም ሳዑዲ አስታውቃለች። ከእስልምና እምነት መሰረቶች አንዱ የሆነው የኡምራ ጉዞ በየትኛውም ወቅት ማከናወን ቢቻልም የሃጂ ጉዞ ግን የእስልምና እምነት ተከታዮች በህይወት ዘመናቸው አንዱ ሊያደርጉት የሚገባ የተቀደሰ ተግባር ነው። በመላው ሙስሊም ማህበረሰብ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው የሃጅ ጉዞ በዘንድሮው እክል ገጥሞታል። ከዚህ ቀደም ከሁለት ሚሊዮን በላይ የእስልምና እምነት ተከታዮች ከየአገሩ ተሰባስበው ቢመጡም በዚህ አመት በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ሳዑዲ አረቢያ የፈቀደችው ጥቂት ሺዎች እንዲታደሙ ነው። ከሃጅ ጉዞ በተለየ መልኩ በየዓመቱ የትኛውም ጊዜ ላይ መደረግ ለሚችለው ለኡምራ ጉዞ ቢያንስ በዓመት ስምንት ሚሊዮን የሚሆኑ ወደ መካ ያቀኑ ነበር። በየቀኑ 20 ሺህ ተጓዦችን ለመቀበል ያቀደችው ሳዑዲ አረቢያ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ሙሉ በሙሉ ተቀርፏል የሚለው በይፋ እስኪነገር የምትቀበለው ተጓዦች ቁጥር ተወስኖ እንደሚቆይም የሳኡዲ ዜና ወኪል የአገር ውስጥ ሚኒስትሩን ዋቢ አድርገው ዘግበዋል። "ከሌላ አገራት የሚመጡ የኡምራ ፀሎተኞችና ተጓዦችን የምንቀበለው ቀስ በቀስ ሲሆን፤ ከወረርሽኙ ነፃ የሆኑ አገሮችንም ቅድሚያ እንሰጣለን" ማለታቸውም ተዘግቧል። ተጓዦች የኮሮናቫይረስ ወርርሽኝን ለመከላከል የወጡ መመሪያዎች እንደ የፊት ጭምብል፣ አካላዊ ርቀትን መጠበቅን ፅዳትን መጠበቅ እንደሚኖርባቸውም የዜና ወኪሉ አስነብቧል። በሳዑዲ አረቢያ ውስጥ እስካሁን ባለው 330 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 4 ሺህ 452 ሰዎችም ህይወታቸው አልፏል።
ኮሮናቫይረስ፡ ሳኡዲ አረቢያ የኡምራ ጉⶋን በመስከረም ወር መጨረሻ ልትጀምር ነው በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ለሰባት ወራት ያህል ተቋርጦ የነበረው የኡምራ ሃይማኖታዊ ጉዞ በዚህ ወር እንደሚጀመር ሳዑዲ አረቢያ አስታወቀች። ከመስከረም 24፣ 2012 ዓ.ም ጀምሮም ስድስት ሺህ የሳዑዲ ዜጎች በየቀኑ የኡምራ ጉዞ እንዲያደርጉ ተፈቅዶላቸዋል። ከሌላ አገር የሚመጡ የኡምራ ፀሎተኞችም ከጥቅምት 22፣ 2013 ዓ.ም ጀምሮ መምጣት ይችላሉ ተብሏል። የየቀኑም ተጓዦች ቁጥር ወደ 20 ሺህ ያድጋል እንደሚያድገም ሳዑዲ አስታውቃለች። ከእስልምና እምነት መሰረቶች አንዱ የሆነው የኡምራ ጉዞ በየትኛውም ወቅት ማከናወን ቢቻልም የሃጂ ጉዞ ግን የእስልምና እምነት ተከታዮች በህይወት ዘመናቸው አንዱ ሊያደርጉት የሚገባ የተቀደሰ ተግባር ነው። በመላው ሙስሊም ማህበረሰብ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው የሃጅ ጉዞ በዘንድሮው እክል ገጥሞታል። ከዚህ ቀደም ከሁለት ሚሊዮን በላይ የእስልምና እምነት ተከታዮች ከየአገሩ ተሰባስበው ቢመጡም በዚህ አመት በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ሳዑዲ አረቢያ የፈቀደችው ጥቂት ሺዎች እንዲታደሙ ነው። ከሃጅ ጉዞ በተለየ መልኩ በየዓመቱ የትኛውም ጊዜ ላይ መደረግ ለሚችለው ለኡምራ ጉዞ ቢያንስ በዓመት ስምንት ሚሊዮን የሚሆኑ ወደ መካ ያቀኑ ነበር። በየቀኑ 20 ሺህ ተጓዦችን ለመቀበል ያቀደችው ሳዑዲ አረቢያ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ሙሉ በሙሉ ተቀርፏል የሚለው በይፋ እስኪነገር የምትቀበለው ተጓዦች ቁጥር ተወስኖ እንደሚቆይም የሳኡዲ ዜና ወኪል የአገር ውስጥ ሚኒስትሩን ዋቢ አድርገው ዘግበዋል። "ከሌላ አገራት የሚመጡ የኡምራ ፀሎተኞችና ተጓዦችን የምንቀበለው ቀስ በቀስ ሲሆን፤ ከወረርሽኙ ነፃ የሆኑ አገሮችንም ቅድሚያ እንሰጣለን" ማለታቸውም ተዘግቧል። ተጓዦች የኮሮናቫይረስ ወርርሽኝን ለመከላከል የወጡ መመሪያዎች እንደ የፊት ጭምብል፣ አካላዊ ርቀትን መጠበቅን ፅዳትን መጠበቅ እንደሚኖርባቸውም የዜና ወኪሉ አስነብቧል። በሳዑዲ አረቢያ ውስጥ እስካሁን ባለው 330 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 4 ሺህ 452 ሰዎችም ህይወታቸው አልፏል።
https://www.bbc.com/amharic/news-54276747
5sports
ትምህርት፡ አራት ሜዳሊያ እና ዋንጫ የተሸለመችው ቆንጂት
ቆንጂት ሐብታሙ ትባለላች። ተወልዳ ያደገችው በሰሜን ሸዋ ጊዳ ሲሆን የከፍተኛ ትምህርቷን ያጠናቀቀችው ዘንድሮ ነው። ቆንጂት በመቱ ዩኒቨርስቲ ቆይታዋ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገቧ ሶስት ሜዳሊያ እና አንድ ዋንጫ ለመሸለም በቅታለች። ለስኬቷ ምክንያት የሆነውንና የወደፊት እቅዷን በማስመልከት ከቢቢሲ ጋር ቆይታ ባደረገች ወቅት " ፊደል ካልቆጠሩ የገጠር ቤተሰብ መገኘቴ ለስኬቴ እንቅፋት አልሆነብኝም" ብላለች። "ተወልጄ ያደግኩት ገጠር ነው። ቤተሰቦቼም ፊደል የቆጠሩ አይደሉም። እኔ እንድማር ግን አብረውኝ ለፍተዋል። ከተማረ ቤተሰብ ይልቅ ተምሬ ትልቅ ሰው እንድሆንላቸው ያስቡልኛል" በማለት ቤተሰቦቿ ያደረጉላትን ትገልጻለች። ቆንጂት ከመቱ ዩኒቨርስቲ በአፕላይድ ባዮሎጂ የትምህርት ዘርፍ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገቧ የተለያዩ ሽልማቶችን ለማግኘት በቅታለች። "ያስመዘገብኩት ውጤት 3.96 ነው" የምትለው ቆንጂት፣ በመቀጠልም "እንደ ኮሌጅ አንደኛ በመውጣቴ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸልሜያለሁ። እንዲሁም ከሴቶች አንደኛ በመሆን ሌላ ተጨማሪ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸለምኩ" በማለት ታስረዳለች። ሶስተኛ ወርቅ ያገኘችው ደግሞ ከአጠቃላይ መቱ ዩኒቨርስቲ ሴት ተማሪዎች አንደኛ በመውጣት መሆኑን ገልጻለች። ከዚህ በተጨማሪ ከአጠቃላይ ዩኒቨርስቲው በሶስተኛ ደረጃ በመገኘቷ የነሐስ ሜዳሊያ እና በአጠቃላይ በዩኒቨርስቲው ካሉ ተማሪዎች በመላቋ ደግሞ ዋንጫ አግኝታለች። በዩኒቨርስቲ ቆይታዋ ከፍተኛ ውጤት ለማስመዝገብ ያበቋትንም ነገሮች ስታስረዳ " ዩኒቨርስቲ እንደገባሁ እቅድ በማውጣት ጊዜዬን በአግባቡ ተጠቅሜ ነበር። ክፍልም በአግባቡ እከታተል ነበር። አጠቃላይ ትኩረቴ በትምህርቴ ላይ በማድረግ ነበር ስከታተል የነበረው" ትላለች። በመቀጠልም "የተማርነውን መከለስ ብቻም ሳይሆን ወደ ፊት ልንማራቸው የምንችላቸውን ቀድሜ በማንበብ እዘጋጅ ነበር።" በማለት ልምዷን መለስ በማለት ታስታውሳለች። የዩኒቨርሰቲ ቆይታ በራስ ሕይወት ላይ ትኩረት በማድረግ ከተሰራ የወደፊት ሕይወት መስመር የሚይዝበት ነው የምትለው ቆንጂት፣ ይህ ሳይሆን ቀርቶ የተወጣበት ዓላማ ከተዘነጋ ግን የወደፊት ሕይወት የሚጠፋበት ስፍራም መሆኑን ታስረዳለች። "እኔ ዩኒቨርስቲ እንደገባሁኝ ከኔ በፊት የነበሩትን ሰዎች ምክር አግኝቼ ነበር። ለምሳሌ በዩኒቨርስቲ ሕይወት ምን ማድረግ እንዳለብኝና እንደሌለብኝ አስመልክቶ ከኔ በፊት ከነበሩት ተማሪዎች ጥሩ ምክር አግኝቻለሁ" በማለት የቀድሞ ተማሪዎች የሰጧት ምክር ለዛሬ ውጤቷ ማማር ድርሻ እንዳለው ትናገራለች። ሕይወት በርካታ እንቅፋቶች አለው የምትለው ቆንጂት " ያጋጠሙኝን እንቅፋቶችና ፈተናዎች በትዕግሥትና በዓላማዬ ላይ ትኩረቴን በማድረጌ ስኬታማ ለመሆን በቅቻለሁ" ትላለች። " እኛ ሴቶች በዓላማችን ላይ ጠንክረን ከሰራን ላንደርስበት የምንችለው ስፍራ የለም። በሴትነት የሚደርሱብን ፈተናዎችን ደግሞ በትዕግሥት ማለፍ በጣም አስፈላጊ ነው በማለት ምክሯን ትለግሳለች። በዩኒቨርስቲ ሕይወት ሴት ተማሪዎች በተለያዩ ነገሮች ሊታለሉ ይችላሉ በማለትም፣ ይኹን እነጂ ለወጡለት ዓላማ ቅድሚያ መስጠት ለወደፊት ዓላማ መመቅናት ወሳኝ ነው በማለት ሃሳቧን ታካፍላለች። ተማሪዎእ ዩኒቨርስቲ መግባትን የዓለም መጨረሻ አድርጎ መውሰድ እንደሌለባቸውም ትናገራለች። "ሌሎች ሕይወቶች የወጣንበትን ዓላማ ካሳካን በኋላ የሚደረሱ ናቸው።" ቆንጂት ስለወደፊት ሕይወቷ ስትናገር የከፍተኛ ትምህርቷን በመቀጠል አቅም ሲኖራት ደግሞ ለሴቶች ድጋፍ የሚያደርግን ተቋም አቋቁማ ለመስራት እቅድ እንዳላት ገልጻለች።
ትምህርት፡ አራት ሜዳሊያ እና ዋንጫ የተሸለመችው ቆንጂት ቆንጂት ሐብታሙ ትባለላች። ተወልዳ ያደገችው በሰሜን ሸዋ ጊዳ ሲሆን የከፍተኛ ትምህርቷን ያጠናቀቀችው ዘንድሮ ነው። ቆንጂት በመቱ ዩኒቨርስቲ ቆይታዋ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገቧ ሶስት ሜዳሊያ እና አንድ ዋንጫ ለመሸለም በቅታለች። ለስኬቷ ምክንያት የሆነውንና የወደፊት እቅዷን በማስመልከት ከቢቢሲ ጋር ቆይታ ባደረገች ወቅት " ፊደል ካልቆጠሩ የገጠር ቤተሰብ መገኘቴ ለስኬቴ እንቅፋት አልሆነብኝም" ብላለች። "ተወልጄ ያደግኩት ገጠር ነው። ቤተሰቦቼም ፊደል የቆጠሩ አይደሉም። እኔ እንድማር ግን አብረውኝ ለፍተዋል። ከተማረ ቤተሰብ ይልቅ ተምሬ ትልቅ ሰው እንድሆንላቸው ያስቡልኛል" በማለት ቤተሰቦቿ ያደረጉላትን ትገልጻለች። ቆንጂት ከመቱ ዩኒቨርስቲ በአፕላይድ ባዮሎጂ የትምህርት ዘርፍ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገቧ የተለያዩ ሽልማቶችን ለማግኘት በቅታለች። "ያስመዘገብኩት ውጤት 3.96 ነው" የምትለው ቆንጂት፣ በመቀጠልም "እንደ ኮሌጅ አንደኛ በመውጣቴ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸልሜያለሁ። እንዲሁም ከሴቶች አንደኛ በመሆን ሌላ ተጨማሪ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸለምኩ" በማለት ታስረዳለች። ሶስተኛ ወርቅ ያገኘችው ደግሞ ከአጠቃላይ መቱ ዩኒቨርስቲ ሴት ተማሪዎች አንደኛ በመውጣት መሆኑን ገልጻለች። ከዚህ በተጨማሪ ከአጠቃላይ ዩኒቨርስቲው በሶስተኛ ደረጃ በመገኘቷ የነሐስ ሜዳሊያ እና በአጠቃላይ በዩኒቨርስቲው ካሉ ተማሪዎች በመላቋ ደግሞ ዋንጫ አግኝታለች። በዩኒቨርስቲ ቆይታዋ ከፍተኛ ውጤት ለማስመዝገብ ያበቋትንም ነገሮች ስታስረዳ " ዩኒቨርስቲ እንደገባሁ እቅድ በማውጣት ጊዜዬን በአግባቡ ተጠቅሜ ነበር። ክፍልም በአግባቡ እከታተል ነበር። አጠቃላይ ትኩረቴ በትምህርቴ ላይ በማድረግ ነበር ስከታተል የነበረው" ትላለች። በመቀጠልም "የተማርነውን መከለስ ብቻም ሳይሆን ወደ ፊት ልንማራቸው የምንችላቸውን ቀድሜ በማንበብ እዘጋጅ ነበር።" በማለት ልምዷን መለስ በማለት ታስታውሳለች። የዩኒቨርሰቲ ቆይታ በራስ ሕይወት ላይ ትኩረት በማድረግ ከተሰራ የወደፊት ሕይወት መስመር የሚይዝበት ነው የምትለው ቆንጂት፣ ይህ ሳይሆን ቀርቶ የተወጣበት ዓላማ ከተዘነጋ ግን የወደፊት ሕይወት የሚጠፋበት ስፍራም መሆኑን ታስረዳለች። "እኔ ዩኒቨርስቲ እንደገባሁኝ ከኔ በፊት የነበሩትን ሰዎች ምክር አግኝቼ ነበር። ለምሳሌ በዩኒቨርስቲ ሕይወት ምን ማድረግ እንዳለብኝና እንደሌለብኝ አስመልክቶ ከኔ በፊት ከነበሩት ተማሪዎች ጥሩ ምክር አግኝቻለሁ" በማለት የቀድሞ ተማሪዎች የሰጧት ምክር ለዛሬ ውጤቷ ማማር ድርሻ እንዳለው ትናገራለች። ሕይወት በርካታ እንቅፋቶች አለው የምትለው ቆንጂት " ያጋጠሙኝን እንቅፋቶችና ፈተናዎች በትዕግሥትና በዓላማዬ ላይ ትኩረቴን በማድረጌ ስኬታማ ለመሆን በቅቻለሁ" ትላለች። " እኛ ሴቶች በዓላማችን ላይ ጠንክረን ከሰራን ላንደርስበት የምንችለው ስፍራ የለም። በሴትነት የሚደርሱብን ፈተናዎችን ደግሞ በትዕግሥት ማለፍ በጣም አስፈላጊ ነው በማለት ምክሯን ትለግሳለች። በዩኒቨርስቲ ሕይወት ሴት ተማሪዎች በተለያዩ ነገሮች ሊታለሉ ይችላሉ በማለትም፣ ይኹን እነጂ ለወጡለት ዓላማ ቅድሚያ መስጠት ለወደፊት ዓላማ መመቅናት ወሳኝ ነው በማለት ሃሳቧን ታካፍላለች። ተማሪዎእ ዩኒቨርስቲ መግባትን የዓለም መጨረሻ አድርጎ መውሰድ እንደሌለባቸውም ትናገራለች። "ሌሎች ሕይወቶች የወጣንበትን ዓላማ ካሳካን በኋላ የሚደረሱ ናቸው።" ቆንጂት ስለወደፊት ሕይወቷ ስትናገር የከፍተኛ ትምህርቷን በመቀጠል አቅም ሲኖራት ደግሞ ለሴቶች ድጋፍ የሚያደርግን ተቋም አቋቁማ ለመስራት እቅድ እንዳላት ገልጻለች።
https://www.bbc.com/amharic/news-55883438
3politics
ሰሜን ኮሪያ አዲስ የፀረ-አውሮፕላን ሚሳኤል ሙከራ አደረገች
ሰሜን ኮሪያ ሐሙስ ዕለት አዲስ የፀረ-አውሮፕላን ሚሳኤል ሙከራ ማድረጓን የገለጸች ሲሆን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አራተኛ የጦር መሣሪያ ሙከራዋ ሆኖ ተመዝግቧል። ሰሜን ኮሪያ አዲሱን ሙከራዋን ያደረገችው የኒውክሌር አቅም እንዳለው የሚታመነውን አዲስ የሃይፐርሶኒክ ሚሳኤል ሙከራ ካደረገች ከጥቂት ቀናት በኋላ ነው። የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ሙከራዎቹ "አለመረጋጋትን እና አለመተማመንን የበለጠ ይፈጥራሉ" ብለዋል። ፒዮንግያንግ የጦር መሣሪያው ራስን ለመከላከል የሚያስፈልጉ መሆናቸውን በመግለጽ አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያን "ፍትሐዊ ያልሆነ አቋም ይዘዋል" በማለት ወንጅላለች። ሙከራዎቹ ምንም እንኳን ጥብቅ ማዕቀቦች ቢኖሩም ፒዮንግያንግ የጦር መሣሪያ መሥራቷን ለማዘግየት ፍላጎት እንደሌላት የሚያሳይ ግልፅ ምልክት ተደርገው ተወስደዋል። በመንግሥታዊው የዜና ማሰራጫ ኬሲኤንኤ መሠረት አዲሱ የፀረ-አውሮፕላን ሚሳኤል "አስደናቂ አፈፃፀም" ያሳየ ሲሆን "አዳዲስ ቁልፍ ቴክኖሎጂዎችን" አካቷል ሲል ዘግቧል። ሙከራው የተደረገው የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ-ኡን ከደቡብ ኮሪያ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ወደነበረበት መመለስ እንደሚፈልጉ መግለጻቸውን ተከትሎ ነው። ኪም የአሜሪካን ዲፕሎማሲያዊ ተሳትፎን ከሰዋል። " አሜሪካ ዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ በማታለል የጥላቻ ድርጊቱን ለመደበቅ ሞክራለች" ብለዋል። አንዳንድ ተንታኞች ፒዮንግያንግ ከደቡብ ኮሪያ ጋር ግንኙነቷን በማስቀጠል አሜሪካን በማስወጣት ዋሽንግተን እና ሴኡልን ለመለያየት እንደምትፈልግ አመላካች ነው ብለው ያምናሉ። ሆኖም ሰሜን ኮሪያ የማዕቀብ እፎይታን እና ሌሎች ድጋፎችን አሜሪካ እንድታደርግላት የደቡብ ኮሪያን ድጋፍ ትፈልጋለች። ሰሜን ኮሪያ ከዓለም ተቆራርጣ ከአንድ ዓመት በላይ አሳልፋለች። ወረርሽኙ በተከሰተበት ወቅት ከቅርብ አጋሯ ከቻይና ጋር አብዛኛውን ንግዶች አቋርጣለች። በዚህም ምክንያት ኢኮኖሚው በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ በመሆኑ የምግብ እጥረት አሳሳቢ ነው ተብሎ ይታሰባል። በመጋቢት ወር አገሪቱ ማዕቀቦችን ወደ ጎን በማለት የባልስቲክ ሚሳኤሎችን ሞክራለች። ይህም ከአሜሪካ፣ ከጃፓን እና ከደቡብ ኮሪያ ጠንካራ ወቀሳ አስነስቶባታል። ባለፈው ወር የተባበሩት መንግሥታት የአቶሚክ ኤጀንሲ ሰሜን ኮሪያ "በጣም አሳሳቢ" ያለውን ለኒዩክሌር መሣሪያዎች የሚረዳ ፕሉቶኒየም ማምረት የሚችል ማብላያዋን እንደገና እንደጀመረች ገልጿል።
ሰሜን ኮሪያ አዲስ የፀረ-አውሮፕላን ሚሳኤል ሙከራ አደረገች ሰሜን ኮሪያ ሐሙስ ዕለት አዲስ የፀረ-አውሮፕላን ሚሳኤል ሙከራ ማድረጓን የገለጸች ሲሆን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አራተኛ የጦር መሣሪያ ሙከራዋ ሆኖ ተመዝግቧል። ሰሜን ኮሪያ አዲሱን ሙከራዋን ያደረገችው የኒውክሌር አቅም እንዳለው የሚታመነውን አዲስ የሃይፐርሶኒክ ሚሳኤል ሙከራ ካደረገች ከጥቂት ቀናት በኋላ ነው። የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ሙከራዎቹ "አለመረጋጋትን እና አለመተማመንን የበለጠ ይፈጥራሉ" ብለዋል። ፒዮንግያንግ የጦር መሣሪያው ራስን ለመከላከል የሚያስፈልጉ መሆናቸውን በመግለጽ አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያን "ፍትሐዊ ያልሆነ አቋም ይዘዋል" በማለት ወንጅላለች። ሙከራዎቹ ምንም እንኳን ጥብቅ ማዕቀቦች ቢኖሩም ፒዮንግያንግ የጦር መሣሪያ መሥራቷን ለማዘግየት ፍላጎት እንደሌላት የሚያሳይ ግልፅ ምልክት ተደርገው ተወስደዋል። በመንግሥታዊው የዜና ማሰራጫ ኬሲኤንኤ መሠረት አዲሱ የፀረ-አውሮፕላን ሚሳኤል "አስደናቂ አፈፃፀም" ያሳየ ሲሆን "አዳዲስ ቁልፍ ቴክኖሎጂዎችን" አካቷል ሲል ዘግቧል። ሙከራው የተደረገው የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ-ኡን ከደቡብ ኮሪያ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ወደነበረበት መመለስ እንደሚፈልጉ መግለጻቸውን ተከትሎ ነው። ኪም የአሜሪካን ዲፕሎማሲያዊ ተሳትፎን ከሰዋል። " አሜሪካ ዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ በማታለል የጥላቻ ድርጊቱን ለመደበቅ ሞክራለች" ብለዋል። አንዳንድ ተንታኞች ፒዮንግያንግ ከደቡብ ኮሪያ ጋር ግንኙነቷን በማስቀጠል አሜሪካን በማስወጣት ዋሽንግተን እና ሴኡልን ለመለያየት እንደምትፈልግ አመላካች ነው ብለው ያምናሉ። ሆኖም ሰሜን ኮሪያ የማዕቀብ እፎይታን እና ሌሎች ድጋፎችን አሜሪካ እንድታደርግላት የደቡብ ኮሪያን ድጋፍ ትፈልጋለች። ሰሜን ኮሪያ ከዓለም ተቆራርጣ ከአንድ ዓመት በላይ አሳልፋለች። ወረርሽኙ በተከሰተበት ወቅት ከቅርብ አጋሯ ከቻይና ጋር አብዛኛውን ንግዶች አቋርጣለች። በዚህም ምክንያት ኢኮኖሚው በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ በመሆኑ የምግብ እጥረት አሳሳቢ ነው ተብሎ ይታሰባል። በመጋቢት ወር አገሪቱ ማዕቀቦችን ወደ ጎን በማለት የባልስቲክ ሚሳኤሎችን ሞክራለች። ይህም ከአሜሪካ፣ ከጃፓን እና ከደቡብ ኮሪያ ጠንካራ ወቀሳ አስነስቶባታል። ባለፈው ወር የተባበሩት መንግሥታት የአቶሚክ ኤጀንሲ ሰሜን ኮሪያ "በጣም አሳሳቢ" ያለውን ለኒዩክሌር መሣሪያዎች የሚረዳ ፕሉቶኒየም ማምረት የሚችል ማብላያዋን እንደገና እንደጀመረች ገልጿል።
https://www.bbc.com/amharic/news-58730483
3politics
ካዛኪስታን፡ የተባባሰውን አለመረጋጋት ተከትሎ የካዛኪስታን መንግሥት የሩስያን ድጋፍ ጠየቀ
ካዛኪስታን ውስጥ ፀረ-መንግሥት ሰልፎች በተጧጧፈበት በአሁኑ ወቅት አገሪቱን "ለማረጋጋት" በሩሲያ የሚመሩ ወታደሮች ሊሠማሩ ነው። ፕሬዝደንት ካሲም-ጆማርት ቶካዬቭ በአገር አቀፍ ደረጃ የተባባሰውን አለመረጋጋት ለመቆጣጠር ሴኩሪቲ ትሪቲ ኦርጋናይዜሽን (ሲኤስቲኦ) ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል። በነዳጅ ዋጋ መናር የተቀጣጠለው ተቃውሞው በሂደት የፖለቲካ ጥያቄዎችን በማካተት ተባብሷል። ፕሬዚደንት ቶካዬቭ ብጥብጡን በውጭ የሰለጠኑ "የአሸባሪ ቡድኖች" ተግባር ነው ብለውታል። በለንደን የሚገኘው ቻታም ሐውስ የመካከለኛው እስያ ኤክስፐርት የሆኑት ኬት ማሊንሰን በበኩላቸው የተቃውሞ ሰልፎቹ "የካዛኪስታን መንግሥት አገቱን ለማዘመን እና ለውጥ ማምጣት ባለመቻሉ ከፍተኛ ብስጭት እና ቁጣን ማሳያ ነው" ብለዋል። ፕሬዝዳንቱ የሌሊት ሰዓት እላፊ ገደብ እና መሰባሰቦችን ጨምሮ ሌሎች ክልከላዎችን የሚጥል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማውጣት ለተቃውሞ ሰልፎቹ ጠንከር ያለ ምላሽ እንደሚሰጡም ቃል ገብተዋል። ሐሙስ ማለዳ ላይ በቴሌቭዥን የተላለፈ ንግግራቸው ሲኤስቲኦ [ሩሲያ እና አምስት የቀድሞ የሶቪየት መንግሥታትን ያቀፈ ወታደራዊ ኅብረት ነው] አገሪቱን ለማረጋጋት እርዳታ እንዲያደርግላቸው መጠየቃቸውን ገልጸዋል። የሲኤስቲኦ ሊቀመንበር የሆነችው አርሜኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኒኮል ፓሺንያን ረቡዕ ዕለት በፌስቡክ በሰጡት መግለጫ ኅብረቱ የሠላም አስከባሪ ኃይሎችን "ለተወሰነ ጊዜ" እንደሚልክ አረጋግጠዋል። የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በካዛክስታን ያለውን ሁኔታ "በቅርበት እየተከታተለ" መሆኑን ጠቅሶ ቃል አቀባዩ ባለሥልጣናት እና ተቃዋሚዎች ካላስፈላጊ ድርጊት እንዲታቀቡ አሳስቧል። ፕሬዚደንት ቶካዬቭ ካዛኪስታንን እአአ በ1991 ነጻነቷን ካወጀች በኋላ አገሪቱን እየመሩ ያሉ ሁለተኛው ግለሰብ ናቸው። እአአ በ2019 ሲመረጡ ዴሞክራሲያዊ መስፈርቶች በዝቅተኛ ደረጃ የተከበሩበት ነበር ሲል በአውሮፓ የደኅንነት እና ትብብር ድርጅት (ኦኤስሲኢ) ሂደቱን አውግዟል። አደባባይ የወጡት ዜጎች አብዛኛው ቁጣቸው ያነጣጠረው ከሥልጣን ከወረዱ በኋላ በብሔራዊ ደኅንነት ቢሮ ቁልፍ ሚና በያዙት የቀድሞው መሪ ኑርሱልታን ናዛርባይቭ ላይ ይመስላል። እየጨመረ የመጣውን አለመረጋጋት ለማርገብ በማሰብ ረቡዕ ከሥራ እንዲሰናበቱ ተደርጓል። ተቃዋሚዎች የናዛርቤዬቭን ስም ሲጠሩ የነበረ ሲሆን የቀድሞውን መሪን ግዙፍ የነሐስ ሐውልት ለማፍረስ ሲሞክሩ የሚያሳይ ቪዲዮ በማኅበራዊ ድር አምባ ላይ ተሰራጭቷል። እንደ ቢቢሲ ሞኒተሪንግ ዘገባ ከሆነ አሁን የፈረሰው ሐውልት የናዛርባይቭ የትውልድ ክልል በሆነችው ታልዲኮርጋን የቆመ ይመስላል። የካዛክስታን ትልቁ አየር ማረፊያ ሠራተኞች የመንግሥት ህንጻዎችን ዒላማ ካደረጉት የፀረ-መንግሥት ተቃዋሚዎችን ሲሸሹ ታይተዋል። ተቃዋሚዎች በአልማቲ በሚገኘው የከንቲባ ጽህፈት ቤት ከተሰባሰቡ በኋላ ወረራ ፈጽመውበታል። በማኅበራዊ ድር አምባዎች ላይ የተለቀቁ ቪዲዮዎች ከህንጻው ከፍተኛ ጭስ ሲወጣ ያሳዩ ሲሆን የተኩስ ድምጽም ይሰማ ነበር። የከተማዋ ፖሊስ አዛዥ ካናት ታይመርዴኖቭ በበኩላቸው "ጽንፈኞች እና አክራሪዎች 500 ሠላማዊ ዜጎችን በማጥቃት በመቶዎች የሚቆጠሩ የንግድ ድርጅቶችን ዘርፈዋል" ብለዋል። በምዕራብ አክቶቤ ከተማ በተቃዋሚዎች ላይ የአድማ መበተኛ ውሃ ጥቅም ላይ ውሏል። በአንዳንድ ቦታዎች የጸጥታ ኃይሎች ከተቃዋሚዎች ጋር መወገናቸውን የሚገልጹ መረጃዎችም እየወጡ ነው። በመካከለኛው እስያ በምትገኘው ካዛኪስታን እየሆነ ስላለው ነገር ግልጽ የሆነ መረጃ ማግኘት አስቸጋሪ እየሆነ መጥቷል። የአገር ውስጥ ሚኒስቴር በጸጥታ ኃይሎች ላይ ጉዳት መድረሱን የሚገልጹ መረጃዎችን ይፋ ቢያደርግም በተቃዋሚዎች ስለደረሰው የአካል ጉዳት እና ሞት ምንም አልተባለም። "በአገር አቀፍ ደረጃ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ" መኖሩም ተገልጿል። እሑድ የጀመረውን ተቃውሞ ለማስቆም መንግሥት ብዙ ሰዎች ለመኪናቸው የሚጠቀሙበት የጋዝ ዋጋ ጭማሪ እንዲቀር አድርጓል። ከናዛርባይቭ ከኃላፊነት መነሳት በተጨማሪም ሁሉም የካቢኔ አባላት ከሥራ ለቀዋል።
ካዛኪስታን፡ የተባባሰውን አለመረጋጋት ተከትሎ የካዛኪስታን መንግሥት የሩስያን ድጋፍ ጠየቀ ካዛኪስታን ውስጥ ፀረ-መንግሥት ሰልፎች በተጧጧፈበት በአሁኑ ወቅት አገሪቱን "ለማረጋጋት" በሩሲያ የሚመሩ ወታደሮች ሊሠማሩ ነው። ፕሬዝደንት ካሲም-ጆማርት ቶካዬቭ በአገር አቀፍ ደረጃ የተባባሰውን አለመረጋጋት ለመቆጣጠር ሴኩሪቲ ትሪቲ ኦርጋናይዜሽን (ሲኤስቲኦ) ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል። በነዳጅ ዋጋ መናር የተቀጣጠለው ተቃውሞው በሂደት የፖለቲካ ጥያቄዎችን በማካተት ተባብሷል። ፕሬዚደንት ቶካዬቭ ብጥብጡን በውጭ የሰለጠኑ "የአሸባሪ ቡድኖች" ተግባር ነው ብለውታል። በለንደን የሚገኘው ቻታም ሐውስ የመካከለኛው እስያ ኤክስፐርት የሆኑት ኬት ማሊንሰን በበኩላቸው የተቃውሞ ሰልፎቹ "የካዛኪስታን መንግሥት አገቱን ለማዘመን እና ለውጥ ማምጣት ባለመቻሉ ከፍተኛ ብስጭት እና ቁጣን ማሳያ ነው" ብለዋል። ፕሬዝዳንቱ የሌሊት ሰዓት እላፊ ገደብ እና መሰባሰቦችን ጨምሮ ሌሎች ክልከላዎችን የሚጥል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማውጣት ለተቃውሞ ሰልፎቹ ጠንከር ያለ ምላሽ እንደሚሰጡም ቃል ገብተዋል። ሐሙስ ማለዳ ላይ በቴሌቭዥን የተላለፈ ንግግራቸው ሲኤስቲኦ [ሩሲያ እና አምስት የቀድሞ የሶቪየት መንግሥታትን ያቀፈ ወታደራዊ ኅብረት ነው] አገሪቱን ለማረጋጋት እርዳታ እንዲያደርግላቸው መጠየቃቸውን ገልጸዋል። የሲኤስቲኦ ሊቀመንበር የሆነችው አርሜኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኒኮል ፓሺንያን ረቡዕ ዕለት በፌስቡክ በሰጡት መግለጫ ኅብረቱ የሠላም አስከባሪ ኃይሎችን "ለተወሰነ ጊዜ" እንደሚልክ አረጋግጠዋል። የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በካዛክስታን ያለውን ሁኔታ "በቅርበት እየተከታተለ" መሆኑን ጠቅሶ ቃል አቀባዩ ባለሥልጣናት እና ተቃዋሚዎች ካላስፈላጊ ድርጊት እንዲታቀቡ አሳስቧል። ፕሬዚደንት ቶካዬቭ ካዛኪስታንን እአአ በ1991 ነጻነቷን ካወጀች በኋላ አገሪቱን እየመሩ ያሉ ሁለተኛው ግለሰብ ናቸው። እአአ በ2019 ሲመረጡ ዴሞክራሲያዊ መስፈርቶች በዝቅተኛ ደረጃ የተከበሩበት ነበር ሲል በአውሮፓ የደኅንነት እና ትብብር ድርጅት (ኦኤስሲኢ) ሂደቱን አውግዟል። አደባባይ የወጡት ዜጎች አብዛኛው ቁጣቸው ያነጣጠረው ከሥልጣን ከወረዱ በኋላ በብሔራዊ ደኅንነት ቢሮ ቁልፍ ሚና በያዙት የቀድሞው መሪ ኑርሱልታን ናዛርባይቭ ላይ ይመስላል። እየጨመረ የመጣውን አለመረጋጋት ለማርገብ በማሰብ ረቡዕ ከሥራ እንዲሰናበቱ ተደርጓል። ተቃዋሚዎች የናዛርቤዬቭን ስም ሲጠሩ የነበረ ሲሆን የቀድሞውን መሪን ግዙፍ የነሐስ ሐውልት ለማፍረስ ሲሞክሩ የሚያሳይ ቪዲዮ በማኅበራዊ ድር አምባ ላይ ተሰራጭቷል። እንደ ቢቢሲ ሞኒተሪንግ ዘገባ ከሆነ አሁን የፈረሰው ሐውልት የናዛርባይቭ የትውልድ ክልል በሆነችው ታልዲኮርጋን የቆመ ይመስላል። የካዛክስታን ትልቁ አየር ማረፊያ ሠራተኞች የመንግሥት ህንጻዎችን ዒላማ ካደረጉት የፀረ-መንግሥት ተቃዋሚዎችን ሲሸሹ ታይተዋል። ተቃዋሚዎች በአልማቲ በሚገኘው የከንቲባ ጽህፈት ቤት ከተሰባሰቡ በኋላ ወረራ ፈጽመውበታል። በማኅበራዊ ድር አምባዎች ላይ የተለቀቁ ቪዲዮዎች ከህንጻው ከፍተኛ ጭስ ሲወጣ ያሳዩ ሲሆን የተኩስ ድምጽም ይሰማ ነበር። የከተማዋ ፖሊስ አዛዥ ካናት ታይመርዴኖቭ በበኩላቸው "ጽንፈኞች እና አክራሪዎች 500 ሠላማዊ ዜጎችን በማጥቃት በመቶዎች የሚቆጠሩ የንግድ ድርጅቶችን ዘርፈዋል" ብለዋል። በምዕራብ አክቶቤ ከተማ በተቃዋሚዎች ላይ የአድማ መበተኛ ውሃ ጥቅም ላይ ውሏል። በአንዳንድ ቦታዎች የጸጥታ ኃይሎች ከተቃዋሚዎች ጋር መወገናቸውን የሚገልጹ መረጃዎችም እየወጡ ነው። በመካከለኛው እስያ በምትገኘው ካዛኪስታን እየሆነ ስላለው ነገር ግልጽ የሆነ መረጃ ማግኘት አስቸጋሪ እየሆነ መጥቷል። የአገር ውስጥ ሚኒስቴር በጸጥታ ኃይሎች ላይ ጉዳት መድረሱን የሚገልጹ መረጃዎችን ይፋ ቢያደርግም በተቃዋሚዎች ስለደረሰው የአካል ጉዳት እና ሞት ምንም አልተባለም። "በአገር አቀፍ ደረጃ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ" መኖሩም ተገልጿል። እሑድ የጀመረውን ተቃውሞ ለማስቆም መንግሥት ብዙ ሰዎች ለመኪናቸው የሚጠቀሙበት የጋዝ ዋጋ ጭማሪ እንዲቀር አድርጓል። ከናዛርባይቭ ከኃላፊነት መነሳት በተጨማሪም ሁሉም የካቢኔ አባላት ከሥራ ለቀዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-59891093
5sports
የበርሊን ማራቶን አሸናፊዋ ጎተይቶም ዕቅዴን አሳክቻለሁ አለች
በማራቶን ውድድር ለመጀረሚያ ጊዜ ተወዳድራ የ2021 የበርሊን ማራቶን ያሸነፈችው አትሌት ጎተይቶም ገብረ ስላሴ በውድድር መድረኩ ያሰብኩትን አሳክቻለሁ አለች። አትሌት ጎተይቶም ጀርመን በርሊን ላይ በተካሄደው የማራቶን ውድድር የጠበቀችውን ሰዓት ማሳካት መቻሏንም ተናግራለች። "የመጀመሪዬ ስለሆነም 2፡20 እሮጣለሁ ብዬ ነው የመጣሁት። ያሰብኩትን ነው የሮጥኩት" ብላለች። ጎተይቶም በውድድሩ በ2፡20፡09 በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው አሸናፊ በመሆን ያጠናቀቀችው። ትናንት በተካሄደው የበርሊን ማራቶን በተለይ በወንዶች የማራቶን ውድድር የዓለም ክብረ ወሰን ሳይሻሻል የቀረው በበርሊን የነበረው የአየር ሁኔታ ሞቃታማ መሆኑ በአትሌቶች እንደምክንያት ተነስቷል። አትሌት ጎተይቶም ግን ይህ የማራቶን ውድድሯ የመጀሪያዋ መሆኑን በማስታወስ፤ "የመጀመሪያዬ እንደመሆኑ ማራቶን ውስጡ ምን እንደሆነ እራሱ አላወኩም ነበረ። . . . ከ35ኛው ኪሎ ሜትር በኋላ ድካምም ስለነበር የዛኔ ነው ሙቀት እንደነበር የታወቀኝ" ብላለች። የበርሊን ማራቶን አሸናፊዋ ጎተይቶም ገብረ ስላሴ ከትናንት ውድድሯ የማራቶን ውድድር ልምድ ማግኘቷን በመጥቀስ ወደፊት ከ02፡20፡00 በታች ለመሮጥ እቅዷ እንደሆነ ተናግራለች።
የበርሊን ማራቶን አሸናፊዋ ጎተይቶም ዕቅዴን አሳክቻለሁ አለች በማራቶን ውድድር ለመጀረሚያ ጊዜ ተወዳድራ የ2021 የበርሊን ማራቶን ያሸነፈችው አትሌት ጎተይቶም ገብረ ስላሴ በውድድር መድረኩ ያሰብኩትን አሳክቻለሁ አለች። አትሌት ጎተይቶም ጀርመን በርሊን ላይ በተካሄደው የማራቶን ውድድር የጠበቀችውን ሰዓት ማሳካት መቻሏንም ተናግራለች። "የመጀመሪዬ ስለሆነም 2፡20 እሮጣለሁ ብዬ ነው የመጣሁት። ያሰብኩትን ነው የሮጥኩት" ብላለች። ጎተይቶም በውድድሩ በ2፡20፡09 በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው አሸናፊ በመሆን ያጠናቀቀችው። ትናንት በተካሄደው የበርሊን ማራቶን በተለይ በወንዶች የማራቶን ውድድር የዓለም ክብረ ወሰን ሳይሻሻል የቀረው በበርሊን የነበረው የአየር ሁኔታ ሞቃታማ መሆኑ በአትሌቶች እንደምክንያት ተነስቷል። አትሌት ጎተይቶም ግን ይህ የማራቶን ውድድሯ የመጀሪያዋ መሆኑን በማስታወስ፤ "የመጀመሪያዬ እንደመሆኑ ማራቶን ውስጡ ምን እንደሆነ እራሱ አላወኩም ነበረ። . . . ከ35ኛው ኪሎ ሜትር በኋላ ድካምም ስለነበር የዛኔ ነው ሙቀት እንደነበር የታወቀኝ" ብላለች። የበርሊን ማራቶን አሸናፊዋ ጎተይቶም ገብረ ስላሴ ከትናንት ውድድሯ የማራቶን ውድድር ልምድ ማግኘቷን በመጥቀስ ወደፊት ከ02፡20፡00 በታች ለመሮጥ እቅዷ እንደሆነ ተናግራለች።
https://www.bbc.com/amharic/news-58704716
3politics
'ሁላችንን ሊገድሉን አይችሉም'-የሱዳን መፈንቅለ መንግሥት ተቃዋሚዎች
በሱዳን ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ከተካሄደ ከሁለት ሳምንት በኋላ የዋና ከተማዋ ካርቱም ጎዳናዎች በየቦታው በተተከሉ ጊዜያዊ አጥሮች ተጨናንቀዋል። በአብዛኛዎቹ ቦታዎች ድንጋዮች እና የተቃጠሉ ጎማዎች መኪና እንዲተላለፍ ለማድረግ ተነስተዋል። ምክንያቱ ደግሞ ከመጋረጃ ጀርባ የሚደረገው የፖለቲካ ድርድር መፈንቅለ መንግሥቱን ሊፈታ ይችላል በሚል ነው። የመንገዱ መዘጋት፣ ተቃውሞዎች እና የሠራዊቱ አጸፋዊ ምላሽ በማንኛውም ጊዜ ሊባባስ ይችላል የሚል ሰፊ እምነት አለ። በሽግግር መንግሥቱ ውስጥ ሴቶችን እና ህጻናትን ከጥቃት የመጠበቅ ኃላፊነት የተሰጠው ክፍል መሪ የሆኑት ሱሌማ ኤልካሊፋ "ከንግግር እና ከድርድር ውጪ መውጫ መንገድ የለም" ይላሉ። "ሰዎች አሁን የበለጠ ቆራጥ ናቸው። የበለጠም ፖለቲካዊ ግንዛቤ አላቸው። ከ30 ዓመታት ወታደራዊ አምባገነንነት በኋላ ድጋሚ አንገዛም። ወጣቱ ከ50 በመቶ በላይ የሚሆነውን አገሪቱን ይወክላል። ስለዚህ ይህንን መንግሥት እንደማንፈልግ ግልጽ ነው። ሁላችንንም ሊገድሉን አይችሉም። ይህንን ህልምም መግደል አይችሉም" ብለዋል። "ወታደሮቹ እንደ እንስሳት ናቸው" በመፈንቅለ መንግሥቱ ወቅት በወታደሮች ተይዘው በቁም እስር ላይ የሚገኙት የሽግግር መንግሥቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ሰፊ ድጋፍ ያላቸው ይመስላል። "ሐምዶክ ቃሉን የሚጠብቅ ሰው መሆኑን አሳይቷል። [የኢኮኖሚ ችግር ቢኖርም] ለዚያም ነው ሰዎች በእሱ የሚተማመኑት። ግብፆች፣ ሳዑዲዎች እና ሌሎችም ሃሳባቸውን እንደሚቀይሩ ተስፋ እናደርጋለን" ሲሉ ኤልካሊፋ መፈንቅለ መንግሥቱን እንደሚደግፉ በሰፊው የሚታመኑባቸውን አገራት ጠቁመዋል። በካርቱም የሚገኘው እና የግል በሆነው የሮያል ኬር ሆስፒታል መፈንቅለ መንግሥቱን ተከትሎ በተፈጠረው የወታደራዊ ምላሽ ጉዳት ደርሶባቸው ህክምና የሚከታተሉትም ተመሳሳይ ቁርጠኝነት አላቸው። የ18 ዓመቱ ተማሪ ሙሃየድ ፋይሰል በቅርቡ በነበረው ተቃውሞ እግሩ ላይ ሁለት ጊዜ በጥይት ተመትቷል። "ከዘጠኝ ሰዎች ጋር በጥይት ተመታሁ። ምንም አይነት የማስጠንቀቂያ ተኩስ አልነበረም፣ በቃ በቀጥታ መተኮስ ጀመሩ። ወታደሮቹ… እንደ እንስሳት ናቸው። ምናልባት እንስሳት የተሻሉ ሊሆኑ ይችላሉ" ብሏል። በቀኝ እግሩ ላይ ሦስት ቀዶ ህክምና ተደርጎለታል። "ምክንያታችን አልተለወጠም። ወታደሩ አይገዛንም" ሲል ሐኪም እግሩን እየነካካ ሲያክመው ተናገሯል። በአቅራቢያው ባለ አልጋ ላይ ልብስ ሰፊውና የ54 ዓመቱ ያይር መሐመድ አሊ አብደላ በዘመዶችቹ ተከቧል። በመፈንቅለ መንግሥቱ ወቅት ተቃዋሚዎችን ለመቀላቀል ሱቁን ትቶ ወጣ። በካርቱም ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አካባቢ መኪና ላይ የተጫኑ ወታደሮች ሆን ብለው በመኪና እንደገጩት ተናግሯል። "ከዚያ በኋላ አምስት እና ስድስት ሰዎች ያለ ርህራሄ ጀርባዬ እና ደረቴ ላይ ደበደቡኝ። ወደ ሰልፉ የሄድኩት ነጻነትን፣ ሰላምንና ፍትህን ለመጠየቅ ነው። ሠራዊቱ ያንን ማድረግ ካልቻለ መወገድ አለበት። መለዮዋችሁን አስረክቡ የሚሉ መጥተው ኃላፊነቱን እንዲወስዱ ያድርጉ" ብሏል። እአአ በ2019 ሱዳንን ለረዥም ጊዜ የመሩትን ኦማር አልበሽርን በመቃወም ከስልጣን እንዲወርዱ ተደረገ። ከዚያ በኋላ ነበር የሽግግር መንግሥት የተቋቋመው። በጦር ኃይሉ እና በሽግግር መንግሥት ውስጥ በሚሳተፉ የተለያዩ አካላት እና ድርጅቶች መካከል ሊደረግ የሚችለው ስምምነት እና ዕጣ ፈንታ ላይ መላምት አለ። ነገር ግን በካርቱም የሚገኙ የዲፕሎማቲክ እና ሌሎች ምንጮች ድርድሩ በጠንካራ ዓለም አቀፍ ጫና እየተካሄደ በመሆኑ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚያሻው በመጥቀስ አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም። መፈንቅለ መንግሥቱን የመሩት አብደል ፋታህ አል-ቡርሐን እንዳሉት ወታደሮቹ የእርስ በርስ ጦርነትን ለማስወገድ ጣልቃ መግባታቸውን ጠቅሰው በ2023 ምርጫ እንደሚካሄድ ቃል ገብተዋል። ቢሊዮኖች ጠፍተዋል መፈንቅለ መንግሥቱን ተከትሎ በወታደሮች በፍጥነት የተዘጋው ተቋም በሽግግር መንግሥቱ የተቋቋመው አፍራሽ ኮሚቴ ነው። ኮሚቴው በአሮጌው ሥርዓት ኃያላን ሰዎች ተዘርፏል የተባለውን ንብረት ለመንጠቅ የተቋቋመ ድርጅት ነው። መፈንቅለ መንግሥቱ ከመደረጉ ከጥቂት ወራት በፊት ከኮሚቴው ከፍተኛ ባለሥልጣናት አንዱ የሆኑት ዋጅዲ ሳሌህ ለቢቢሲ ሥራውን አስጎብኝተዋል። ለወንጀለኝነት ማስረጃ ነው ያሉትንም ክምር አሳይተዋል። "እነዚህ በዓለማችን ትላልቁን ሕገወጥ የገንዘብ ማሸሽን ያደራጁ ሰዎች ነበሩ። የጠፉትን በቢሊዮኖች እያደነን ነው። የድሮው አገዛዝ [አብዮቱን ለማደናቀፍ] እየሞከሩ ቢሆንም በጭራሽ አይሳካላቸውም" ብለዋል። እሳቸው በመፈንቅለ መንግሥቱ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን በሽግግር መንግሥቱ ውስጥ ተፅዕኖ ካላቸው በርካታ ሰዎች ጋር በእስር ላይ ይገኛሉ። "በአፍራሽ ኮሚቴው በቅርቡ የተደረገው ምርመራ በወታደራዊው ከፍተኛ ባለሥልጣናት ዘንድ ጭንቀት መፍጠሩ በሰፊው ይታመናል። ኮሚቴው ከወርቅ ዝውውር እስከ ገንዘብ ሽያጭ እና ኮሚሽኖች ድረስ የተለያዩ ጉዳዮችን በማጣራት ላይ ሲሆን ይህም በከፍተኛ መኮንኖች መካከል ከፍተኛ የሆነ ሙስና መኖሩን ያሳያል" ሲል ከአብዮቱ ጀምሮ ለሱዳን መንግሥት ሲሠራ የነበረው የቀድሞ የቢቢሲ ጋዜጠኛ ሞሃናድ ሃሺም ገልጿል። ከመፈንቅለ መንግሥቱ በኋላ የቁልፉ ወደብ እገዳ ተነስቷል። ወታደሮቹ እገዳውን ያቀነባበሩት በሽግግር መንግሥቱ ላይ ኢኮኖሚያዊ ጫና ለመፍጠር ነው ተብሎ በሰፊው ይጠረጠራል። በዚህም በካርቱም ብዙ የምግብ አቅርቦቶች እንዲኖር እና አንዳንድ ዋጋዎች እንዲቀንሱ ረድቷል። የመፈንቅለ መንግሥቱ መሪዎች በወሰዱት ጥንቃቄ ለድርጊታቸው መሰረት ያዘጋጁ ቢመስሉም አብዮቱን ተከትሎ የመጣውን የኢኮኖሚ ችግር ተቋቁመው ለውጡን ለመደገፍ የቆረጡትን "ሰልፈኞች" በተሳሳተ መንገድ የተረዱ ይመስላል።
'ሁላችንን ሊገድሉን አይችሉም'-የሱዳን መፈንቅለ መንግሥት ተቃዋሚዎች በሱዳን ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ከተካሄደ ከሁለት ሳምንት በኋላ የዋና ከተማዋ ካርቱም ጎዳናዎች በየቦታው በተተከሉ ጊዜያዊ አጥሮች ተጨናንቀዋል። በአብዛኛዎቹ ቦታዎች ድንጋዮች እና የተቃጠሉ ጎማዎች መኪና እንዲተላለፍ ለማድረግ ተነስተዋል። ምክንያቱ ደግሞ ከመጋረጃ ጀርባ የሚደረገው የፖለቲካ ድርድር መፈንቅለ መንግሥቱን ሊፈታ ይችላል በሚል ነው። የመንገዱ መዘጋት፣ ተቃውሞዎች እና የሠራዊቱ አጸፋዊ ምላሽ በማንኛውም ጊዜ ሊባባስ ይችላል የሚል ሰፊ እምነት አለ። በሽግግር መንግሥቱ ውስጥ ሴቶችን እና ህጻናትን ከጥቃት የመጠበቅ ኃላፊነት የተሰጠው ክፍል መሪ የሆኑት ሱሌማ ኤልካሊፋ "ከንግግር እና ከድርድር ውጪ መውጫ መንገድ የለም" ይላሉ። "ሰዎች አሁን የበለጠ ቆራጥ ናቸው። የበለጠም ፖለቲካዊ ግንዛቤ አላቸው። ከ30 ዓመታት ወታደራዊ አምባገነንነት በኋላ ድጋሚ አንገዛም። ወጣቱ ከ50 በመቶ በላይ የሚሆነውን አገሪቱን ይወክላል። ስለዚህ ይህንን መንግሥት እንደማንፈልግ ግልጽ ነው። ሁላችንንም ሊገድሉን አይችሉም። ይህንን ህልምም መግደል አይችሉም" ብለዋል። "ወታደሮቹ እንደ እንስሳት ናቸው" በመፈንቅለ መንግሥቱ ወቅት በወታደሮች ተይዘው በቁም እስር ላይ የሚገኙት የሽግግር መንግሥቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ሰፊ ድጋፍ ያላቸው ይመስላል። "ሐምዶክ ቃሉን የሚጠብቅ ሰው መሆኑን አሳይቷል። [የኢኮኖሚ ችግር ቢኖርም] ለዚያም ነው ሰዎች በእሱ የሚተማመኑት። ግብፆች፣ ሳዑዲዎች እና ሌሎችም ሃሳባቸውን እንደሚቀይሩ ተስፋ እናደርጋለን" ሲሉ ኤልካሊፋ መፈንቅለ መንግሥቱን እንደሚደግፉ በሰፊው የሚታመኑባቸውን አገራት ጠቁመዋል። በካርቱም የሚገኘው እና የግል በሆነው የሮያል ኬር ሆስፒታል መፈንቅለ መንግሥቱን ተከትሎ በተፈጠረው የወታደራዊ ምላሽ ጉዳት ደርሶባቸው ህክምና የሚከታተሉትም ተመሳሳይ ቁርጠኝነት አላቸው። የ18 ዓመቱ ተማሪ ሙሃየድ ፋይሰል በቅርቡ በነበረው ተቃውሞ እግሩ ላይ ሁለት ጊዜ በጥይት ተመትቷል። "ከዘጠኝ ሰዎች ጋር በጥይት ተመታሁ። ምንም አይነት የማስጠንቀቂያ ተኩስ አልነበረም፣ በቃ በቀጥታ መተኮስ ጀመሩ። ወታደሮቹ… እንደ እንስሳት ናቸው። ምናልባት እንስሳት የተሻሉ ሊሆኑ ይችላሉ" ብሏል። በቀኝ እግሩ ላይ ሦስት ቀዶ ህክምና ተደርጎለታል። "ምክንያታችን አልተለወጠም። ወታደሩ አይገዛንም" ሲል ሐኪም እግሩን እየነካካ ሲያክመው ተናገሯል። በአቅራቢያው ባለ አልጋ ላይ ልብስ ሰፊውና የ54 ዓመቱ ያይር መሐመድ አሊ አብደላ በዘመዶችቹ ተከቧል። በመፈንቅለ መንግሥቱ ወቅት ተቃዋሚዎችን ለመቀላቀል ሱቁን ትቶ ወጣ። በካርቱም ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አካባቢ መኪና ላይ የተጫኑ ወታደሮች ሆን ብለው በመኪና እንደገጩት ተናግሯል። "ከዚያ በኋላ አምስት እና ስድስት ሰዎች ያለ ርህራሄ ጀርባዬ እና ደረቴ ላይ ደበደቡኝ። ወደ ሰልፉ የሄድኩት ነጻነትን፣ ሰላምንና ፍትህን ለመጠየቅ ነው። ሠራዊቱ ያንን ማድረግ ካልቻለ መወገድ አለበት። መለዮዋችሁን አስረክቡ የሚሉ መጥተው ኃላፊነቱን እንዲወስዱ ያድርጉ" ብሏል። እአአ በ2019 ሱዳንን ለረዥም ጊዜ የመሩትን ኦማር አልበሽርን በመቃወም ከስልጣን እንዲወርዱ ተደረገ። ከዚያ በኋላ ነበር የሽግግር መንግሥት የተቋቋመው። በጦር ኃይሉ እና በሽግግር መንግሥት ውስጥ በሚሳተፉ የተለያዩ አካላት እና ድርጅቶች መካከል ሊደረግ የሚችለው ስምምነት እና ዕጣ ፈንታ ላይ መላምት አለ። ነገር ግን በካርቱም የሚገኙ የዲፕሎማቲክ እና ሌሎች ምንጮች ድርድሩ በጠንካራ ዓለም አቀፍ ጫና እየተካሄደ በመሆኑ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚያሻው በመጥቀስ አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም። መፈንቅለ መንግሥቱን የመሩት አብደል ፋታህ አል-ቡርሐን እንዳሉት ወታደሮቹ የእርስ በርስ ጦርነትን ለማስወገድ ጣልቃ መግባታቸውን ጠቅሰው በ2023 ምርጫ እንደሚካሄድ ቃል ገብተዋል። ቢሊዮኖች ጠፍተዋል መፈንቅለ መንግሥቱን ተከትሎ በወታደሮች በፍጥነት የተዘጋው ተቋም በሽግግር መንግሥቱ የተቋቋመው አፍራሽ ኮሚቴ ነው። ኮሚቴው በአሮጌው ሥርዓት ኃያላን ሰዎች ተዘርፏል የተባለውን ንብረት ለመንጠቅ የተቋቋመ ድርጅት ነው። መፈንቅለ መንግሥቱ ከመደረጉ ከጥቂት ወራት በፊት ከኮሚቴው ከፍተኛ ባለሥልጣናት አንዱ የሆኑት ዋጅዲ ሳሌህ ለቢቢሲ ሥራውን አስጎብኝተዋል። ለወንጀለኝነት ማስረጃ ነው ያሉትንም ክምር አሳይተዋል። "እነዚህ በዓለማችን ትላልቁን ሕገወጥ የገንዘብ ማሸሽን ያደራጁ ሰዎች ነበሩ። የጠፉትን በቢሊዮኖች እያደነን ነው። የድሮው አገዛዝ [አብዮቱን ለማደናቀፍ] እየሞከሩ ቢሆንም በጭራሽ አይሳካላቸውም" ብለዋል። እሳቸው በመፈንቅለ መንግሥቱ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን በሽግግር መንግሥቱ ውስጥ ተፅዕኖ ካላቸው በርካታ ሰዎች ጋር በእስር ላይ ይገኛሉ። "በአፍራሽ ኮሚቴው በቅርቡ የተደረገው ምርመራ በወታደራዊው ከፍተኛ ባለሥልጣናት ዘንድ ጭንቀት መፍጠሩ በሰፊው ይታመናል። ኮሚቴው ከወርቅ ዝውውር እስከ ገንዘብ ሽያጭ እና ኮሚሽኖች ድረስ የተለያዩ ጉዳዮችን በማጣራት ላይ ሲሆን ይህም በከፍተኛ መኮንኖች መካከል ከፍተኛ የሆነ ሙስና መኖሩን ያሳያል" ሲል ከአብዮቱ ጀምሮ ለሱዳን መንግሥት ሲሠራ የነበረው የቀድሞ የቢቢሲ ጋዜጠኛ ሞሃናድ ሃሺም ገልጿል። ከመፈንቅለ መንግሥቱ በኋላ የቁልፉ ወደብ እገዳ ተነስቷል። ወታደሮቹ እገዳውን ያቀነባበሩት በሽግግር መንግሥቱ ላይ ኢኮኖሚያዊ ጫና ለመፍጠር ነው ተብሎ በሰፊው ይጠረጠራል። በዚህም በካርቱም ብዙ የምግብ አቅርቦቶች እንዲኖር እና አንዳንድ ዋጋዎች እንዲቀንሱ ረድቷል። የመፈንቅለ መንግሥቱ መሪዎች በወሰዱት ጥንቃቄ ለድርጊታቸው መሰረት ያዘጋጁ ቢመስሉም አብዮቱን ተከትሎ የመጣውን የኢኮኖሚ ችግር ተቋቁመው ለውጡን ለመደገፍ የቆረጡትን "ሰልፈኞች" በተሳሳተ መንገድ የተረዱ ይመስላል።
https://www.bbc.com/amharic/news-59196274
2health
ኦሚክሮን፡ በፍጥነት በሚዛመተው አዲሱ የኮቪድ ዝርያ የሚያዙ ሰዎች ምን ይሆናሉ?
እንሆ ሁለት ትላልቅ ጥያቄዎች፡ ኦሚክሮን በምን ያህል ፍጥነት ሊዛመት ይችላል? በኦሚክሮን ዝርያ የሚያዙ ሰዎች ምን ይሆናሉ? እኒህን ሁለት ጥያቄዎች መልስ አገኘንላቸው ማለት ኦሚክሮን የተሰኘው አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ምን ያህል አደገኛ ነው የሚለውን መለስን ማለት ነው። የምድራችን ሳይንቲስቶች እኒህን ጥያቄዎች ለመመለስ ደፋ ቀና እያሉ ነው። ትንሽ ፍንጭ የሚሰጥ ነገር ያገኙም ይመስላል። የመከላከል አቅም በጣም አስፈላጊ ነው። ኦሚክሮን ሁሉን ነገር ወደኋላ መልሶ እንደአዲስ እንድንድህ ሊያደርገን ነው ባይባልም አዲሱ የኮቪድ ዝርያ ምን ያህል አስጊ ነው የሚለውን መመልስ ጥቂት ሳምንታትን ሊጠይቅ ይችላል። ኦሚክሮን በምን ያህል ፍጥነት እየተዛመተ ይሆን? መልሱ "በፍጥነት" የሚል ነው። ይህ ዝርያ በክትባትም ይሁን በርካታ ሰዎች በመያዛቸው ምክንያት የተሻለ የመከላከል አቅም አዳብረዋል በሚባሉ ሥፍራዎችም በፍጥነት እየተስፋፋ ይገኛል። ለምሳሌ ደቡብ አፍሪካ ከአንድ ወር በፊት ዴልታ ከተሰኘው የኮቪድ ዝርያ ጋር ተላምዳ በቀን የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ወደ 300 ወርዶ ነበር። አሁን ግን አራተኛው የኮቪድ ማዕበል ከ10 ሺህ በላይ ሰዎችን አዳርሷል። ዩናይትድ ኪንግደምም ብትሆንም ኦሚክሮን እንደሰደድ እሣት እየተዛመተባት ይገኛል። ሳይንቲስቶች የኦሚክሮንን ዱካ እያገኙ ያሉት ዝርያው የኮቪድ ምርመራ በሚደረግበት ወቅት ትቶ በሚያልፋቸው አሻራዎች አማካይነት ነው። ይህ አሻራ ኤስ-ጂን ይሰኛል። ይህ ከኮቪድ ምርምራ ላይ የሚገኝ ቅንጣት ባለፈው ወር መጨረሻ ወደ 0.1 በመቶ ወርዶ ነበር። አሁን ግን ወደ 5 በመቶ አድጓል። ይህ በቁጥር ሲገለጥ በቀን 2500 ሰዎች በአዲሱ ዝርያ ይያዛሉ ማለት ነው። ይህ ስሌት ሙሉ በሙሉ ትክክል ነው ማለት ባይቻልም በአራተኛው የኮቪድ ማዕበል የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ማሻቀቡ የማይታበይ ሐቅ ነው። ለምሳሌ በዩናይትድ ኪንግደም የኦሚክሮን ቁጥር በየሦስት ቀኑ እጥፍ እየሆነ እንደሚሄድ መረጃዎች ጠቋሚ ናቸው። ኦሚክሮን የሚዛመትበት ፍጥነት ዴልታ ከተሰኘው ዝርያ በላይ ሲሆን ኮሮናቫይረስ ባለፈው ዓመት መባቻ ሲጀምር ሲስፋፋ የነበረውን ዓይነት ፍጥነት እንዳለው ተደርሶበታል። በዚህ ፍጥነቱ መዛመቱን ከቀጠለ በቀን 2500 የነበረው ቁጥር ከአንድ ወር በኋላ በቀን 100 ሺህ ይሆናል ማለት ነው። እኔን ይይዘኝ ይሆን? በሽታው ምን ያህል ከባድ ነው? ሳይንቲስቶች እስካሁን ድረስ ባደረጉት ጥናት ጭንቀት ውስጥ የከተተታቸው የኦሚክሮን ዝርያ የኮቨድ ክትባትን የመቋቋም አቅሙ ነው። ኦሚክሮን አሠራሩ ክትባቱ እንዲከላከል ከተሠራለት የመጀመሪያው የኮቪድ ዝርያ ለየት ያለ ነው። ጥናቶች እንደሚጠቁሙት የኮቪድ ክትባት ሁለት ጊዜ የወሰዱ ሰዎች አዲሱን ዝርያ የመከላከል አቅማቸው ከ20 እስከ 40 እጥፍ ሊቀንስ ይችላል። እርግጥ ነው እስካሁን በአዲሱ ዝርያ ዙሪያ አጠንጥነው የተሠሩ ጥናቶች ቁጥር ትንሽ ነው። ነገር ግን እኒህ ጥናቶች የአዲሱን ዝርያ የመዛመት ኃይል የሚያሳዩ ናቸው። ቢሆንም ስለ አዲሱ ዝርያ መልካም ዜናም አልጠፋም። ፋይዘር-ባዮንቴክ የሠራው ሙከራ እንደሚያመለክተው ማጠናከሪያ ክትባት [ሦስተኛ ክትባት] የወሰዱ ሰዎች ኦሚክሮንን የመከላከል አቅማቸው ከፍ ይላል። ለኦሚክሮን ሦስት ዙር መከተብ ማለት ለዋናውና የቀደመው ቫይረስ ሁለት ዙር እንደመከተብ ማለት ነው። የኤደንብራ ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር ኤሌኖር ራይሊ ይህን ሙከራ "አበረታች" ሲሉ ይገልፁትና "ማጠናከሪያው ክትባት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ የሚያሳይ ነው" ይላሉ። ኦሚክሮን ምን ያህል ከባድ የኮሮናቫይረስ ዝርያ እንደሆነ ግን እስካሁን የምናውቀው ጥቂት ነው። በዝርያው ተይዘው ሆስፒታል የገቡ ሰዎች ጥናት እስኪደርግባቸው ድረስ ስለበሽታው ኃያልነት ያለው እውቀት እፍኝ አይሞላም። እርስዎ ሁለት ጊዜ ክትባት ወሰዱ ማለት አሊያም ከዚህ በፊት ኮቪድ ይዞዎት ነበር ማለት ኦሚክሮንን የመከላከል አቅምዎ የተሻለ ነው ይላሉ ሳይንቲስቶች። እና ወደፊት ምን ሊሆን ይችላል? ኮሮናቫይረስን እንዲከላከሉ ተብለው የተዘጋጁት ክትባቶች ኦሚክሮንን ሊከላከሉ እንደሚችሉ ግምት አለ። ነገር ግን አብዛኛዎቻችን ጤና ብንሆን እንኳ ሁላችንም ደህና ላንሆን እንችላለን። አንዳንድ ሰዎች የመከላከል አቅማቸው እጅግ የደከመ ነው። አንዳንዶች ቢከተቡም ላይከላከሉ ይችላሉ። አንዳንዶች ክትባት መውሰድ አይችሉ ይሆናል። አንዳንዶች ደግሞ በውዴታ ክትባት አንወስድም እያሉ ነው። በዴልታ ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ሆስፒታል እስከመግባት ደርሰዋል። አዲሱ ዝርያ ብዙ ሰዎች በአንድ ጊዜ ወደ ሆስፒታል እንዲገቡ ካደረገ ችግር ሊፈጠር ይችላል። የዋርዊክ ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር ማይክል ቲልደስሊ "ማዕበል ትልቅ ከሆነ ባለፈው ጥር እንደተመለከትነው ዓይነት ሊሆን ይችላል። ሆስፒታሎችም ሊጨናነቁ ይችላሉ" ባይ ናቸው። ነገር ግን አሁን ያለን መረጃ ጥቂት ስለሆነ ይህ ነው ብሎ መናገር እንደሚከብድ ያስረዳሉ። የዓለም ሳይንቲስቶች የተስማሙበት ይህ ነው የሚባል ኦሚክሮን እየተዛመተበት ያለ ፍጥነት የለም። በሽታው ምን ያህል ከባድ ሊሆን እንደሚችልም በውል አይታወቅም። ክትባቱን ሊፈታተነው ይችላል ወይ የሚለውም ምላሽ አላገኘም። ማድረግ የሚቻለው ራስን ከበሽታው እየጠበቁ በቀጣይ ሳምንታት የሚሆነውን በቅርበት መከታተል ነው።
ኦሚክሮን፡ በፍጥነት በሚዛመተው አዲሱ የኮቪድ ዝርያ የሚያዙ ሰዎች ምን ይሆናሉ? እንሆ ሁለት ትላልቅ ጥያቄዎች፡ ኦሚክሮን በምን ያህል ፍጥነት ሊዛመት ይችላል? በኦሚክሮን ዝርያ የሚያዙ ሰዎች ምን ይሆናሉ? እኒህን ሁለት ጥያቄዎች መልስ አገኘንላቸው ማለት ኦሚክሮን የተሰኘው አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ምን ያህል አደገኛ ነው የሚለውን መለስን ማለት ነው። የምድራችን ሳይንቲስቶች እኒህን ጥያቄዎች ለመመለስ ደፋ ቀና እያሉ ነው። ትንሽ ፍንጭ የሚሰጥ ነገር ያገኙም ይመስላል። የመከላከል አቅም በጣም አስፈላጊ ነው። ኦሚክሮን ሁሉን ነገር ወደኋላ መልሶ እንደአዲስ እንድንድህ ሊያደርገን ነው ባይባልም አዲሱ የኮቪድ ዝርያ ምን ያህል አስጊ ነው የሚለውን መመልስ ጥቂት ሳምንታትን ሊጠይቅ ይችላል። ኦሚክሮን በምን ያህል ፍጥነት እየተዛመተ ይሆን? መልሱ "በፍጥነት" የሚል ነው። ይህ ዝርያ በክትባትም ይሁን በርካታ ሰዎች በመያዛቸው ምክንያት የተሻለ የመከላከል አቅም አዳብረዋል በሚባሉ ሥፍራዎችም በፍጥነት እየተስፋፋ ይገኛል። ለምሳሌ ደቡብ አፍሪካ ከአንድ ወር በፊት ዴልታ ከተሰኘው የኮቪድ ዝርያ ጋር ተላምዳ በቀን የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ወደ 300 ወርዶ ነበር። አሁን ግን አራተኛው የኮቪድ ማዕበል ከ10 ሺህ በላይ ሰዎችን አዳርሷል። ዩናይትድ ኪንግደምም ብትሆንም ኦሚክሮን እንደሰደድ እሣት እየተዛመተባት ይገኛል። ሳይንቲስቶች የኦሚክሮንን ዱካ እያገኙ ያሉት ዝርያው የኮቪድ ምርመራ በሚደረግበት ወቅት ትቶ በሚያልፋቸው አሻራዎች አማካይነት ነው። ይህ አሻራ ኤስ-ጂን ይሰኛል። ይህ ከኮቪድ ምርምራ ላይ የሚገኝ ቅንጣት ባለፈው ወር መጨረሻ ወደ 0.1 በመቶ ወርዶ ነበር። አሁን ግን ወደ 5 በመቶ አድጓል። ይህ በቁጥር ሲገለጥ በቀን 2500 ሰዎች በአዲሱ ዝርያ ይያዛሉ ማለት ነው። ይህ ስሌት ሙሉ በሙሉ ትክክል ነው ማለት ባይቻልም በአራተኛው የኮቪድ ማዕበል የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ማሻቀቡ የማይታበይ ሐቅ ነው። ለምሳሌ በዩናይትድ ኪንግደም የኦሚክሮን ቁጥር በየሦስት ቀኑ እጥፍ እየሆነ እንደሚሄድ መረጃዎች ጠቋሚ ናቸው። ኦሚክሮን የሚዛመትበት ፍጥነት ዴልታ ከተሰኘው ዝርያ በላይ ሲሆን ኮሮናቫይረስ ባለፈው ዓመት መባቻ ሲጀምር ሲስፋፋ የነበረውን ዓይነት ፍጥነት እንዳለው ተደርሶበታል። በዚህ ፍጥነቱ መዛመቱን ከቀጠለ በቀን 2500 የነበረው ቁጥር ከአንድ ወር በኋላ በቀን 100 ሺህ ይሆናል ማለት ነው። እኔን ይይዘኝ ይሆን? በሽታው ምን ያህል ከባድ ነው? ሳይንቲስቶች እስካሁን ድረስ ባደረጉት ጥናት ጭንቀት ውስጥ የከተተታቸው የኦሚክሮን ዝርያ የኮቨድ ክትባትን የመቋቋም አቅሙ ነው። ኦሚክሮን አሠራሩ ክትባቱ እንዲከላከል ከተሠራለት የመጀመሪያው የኮቪድ ዝርያ ለየት ያለ ነው። ጥናቶች እንደሚጠቁሙት የኮቪድ ክትባት ሁለት ጊዜ የወሰዱ ሰዎች አዲሱን ዝርያ የመከላከል አቅማቸው ከ20 እስከ 40 እጥፍ ሊቀንስ ይችላል። እርግጥ ነው እስካሁን በአዲሱ ዝርያ ዙሪያ አጠንጥነው የተሠሩ ጥናቶች ቁጥር ትንሽ ነው። ነገር ግን እኒህ ጥናቶች የአዲሱን ዝርያ የመዛመት ኃይል የሚያሳዩ ናቸው። ቢሆንም ስለ አዲሱ ዝርያ መልካም ዜናም አልጠፋም። ፋይዘር-ባዮንቴክ የሠራው ሙከራ እንደሚያመለክተው ማጠናከሪያ ክትባት [ሦስተኛ ክትባት] የወሰዱ ሰዎች ኦሚክሮንን የመከላከል አቅማቸው ከፍ ይላል። ለኦሚክሮን ሦስት ዙር መከተብ ማለት ለዋናውና የቀደመው ቫይረስ ሁለት ዙር እንደመከተብ ማለት ነው። የኤደንብራ ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር ኤሌኖር ራይሊ ይህን ሙከራ "አበረታች" ሲሉ ይገልፁትና "ማጠናከሪያው ክትባት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ የሚያሳይ ነው" ይላሉ። ኦሚክሮን ምን ያህል ከባድ የኮሮናቫይረስ ዝርያ እንደሆነ ግን እስካሁን የምናውቀው ጥቂት ነው። በዝርያው ተይዘው ሆስፒታል የገቡ ሰዎች ጥናት እስኪደርግባቸው ድረስ ስለበሽታው ኃያልነት ያለው እውቀት እፍኝ አይሞላም። እርስዎ ሁለት ጊዜ ክትባት ወሰዱ ማለት አሊያም ከዚህ በፊት ኮቪድ ይዞዎት ነበር ማለት ኦሚክሮንን የመከላከል አቅምዎ የተሻለ ነው ይላሉ ሳይንቲስቶች። እና ወደፊት ምን ሊሆን ይችላል? ኮሮናቫይረስን እንዲከላከሉ ተብለው የተዘጋጁት ክትባቶች ኦሚክሮንን ሊከላከሉ እንደሚችሉ ግምት አለ። ነገር ግን አብዛኛዎቻችን ጤና ብንሆን እንኳ ሁላችንም ደህና ላንሆን እንችላለን። አንዳንድ ሰዎች የመከላከል አቅማቸው እጅግ የደከመ ነው። አንዳንዶች ቢከተቡም ላይከላከሉ ይችላሉ። አንዳንዶች ክትባት መውሰድ አይችሉ ይሆናል። አንዳንዶች ደግሞ በውዴታ ክትባት አንወስድም እያሉ ነው። በዴልታ ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ሆስፒታል እስከመግባት ደርሰዋል። አዲሱ ዝርያ ብዙ ሰዎች በአንድ ጊዜ ወደ ሆስፒታል እንዲገቡ ካደረገ ችግር ሊፈጠር ይችላል። የዋርዊክ ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር ማይክል ቲልደስሊ "ማዕበል ትልቅ ከሆነ ባለፈው ጥር እንደተመለከትነው ዓይነት ሊሆን ይችላል። ሆስፒታሎችም ሊጨናነቁ ይችላሉ" ባይ ናቸው። ነገር ግን አሁን ያለን መረጃ ጥቂት ስለሆነ ይህ ነው ብሎ መናገር እንደሚከብድ ያስረዳሉ። የዓለም ሳይንቲስቶች የተስማሙበት ይህ ነው የሚባል ኦሚክሮን እየተዛመተበት ያለ ፍጥነት የለም። በሽታው ምን ያህል ከባድ ሊሆን እንደሚችልም በውል አይታወቅም። ክትባቱን ሊፈታተነው ይችላል ወይ የሚለውም ምላሽ አላገኘም። ማድረግ የሚቻለው ራስን ከበሽታው እየጠበቁ በቀጣይ ሳምንታት የሚሆነውን በቅርበት መከታተል ነው።
https://www.bbc.com/amharic/news-59596054
2health
ሕክምና ፡ ቁመት ለመጨመር ምን አይነት ቀዶ ሕክምና ነው የሚደረገው?
ሳም ቤከር የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪ ሳለ የክፍሉ ረዥም ልጅ ነበር። የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሆነው ጓደኞቹ ሁሉ ዘለግ ዘለግ ያሉ ሲሆኑ የእሱ ቁመት ግን አልጨመረም። "ኮሌጅ ስገባ ከሌሎች ወንዶችና ሴቶች ያጠርኩ መሆኔን አስተዋልኩ። ሴቶች ከእነሱ ከሚያጥር ሰው ጋር ፍቅር አይጀምሩም። እናም ሚስት አላገኝም ብዬ እሰጋ ነበር" ይላል። የ30 ዓመቱ የኒው ዮርክ ነዋሪ ሳም እረዝማለሁ ብሎ ቢጠብቅም ቁመቱ አልጨምር አለው። "ቁመትና ስኬትን አስተሳስሬ ነው የማየው" የሚለው ሳም ቁመት ለመጨመር አማራጮች ያስስ ጀመር። ከፍ ያለ ጫማ ማድረግ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ወዘተ. . . የሚሉት አማራጮች አላሳመኑትም። እግር ስለሚያረዝም ቀዶ ሕክምና ሲያነብ ግን ትኩረቱን ሳበው። "ጥቂት ኢንቾች ከጨመርኩ በኋላ መራመድና መሮጥ እችል ይሆን? ብዬ አሰብኩ" በየዓመቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቁመታቸውን ለመጨመር ቀዶ ሕክምና ያደርጋሉ። ቀዶ ሕክምናው ብዙ የጎንዮሽ ጉዳቶች እንደሚያስከትል ባለሙያዎች ይናገራሉ። ሳም ስለ ቀዶ ሕክምናው ከእናቱ ጋር ከተወያየ በኋላ የጎንዮሽ ጉዳት ቢኖርም እንኳን ለማካሄድ ወሰነ። ቀዶ ሕክምናውን ያደረገው ከዛሬ አምስት ዓመት በፊት ሲሆን፤ ይህም ከ162 ሴንቲ ሜትር ወደ 170 ሴንቲ ሜትር ከፍ እንዲል አስችሎታል። "ሐኪሙ መጀመሪያ ሲያገኘኝ ቀዶ ሕክምናው ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ነግሮኛል። ጥቂት ኢንቾች ከጨመርኩ በኋላ መራመድና መሮጥ እችል ይሆን? ብዬ አሰብኩ።" ከቀዶ ሕክምናው በኋላ ሆስፒታል ውስጥ የማገገሚያ ሕክምና ተደርጎለታል። ለስድስት ወራት፣ በሳምንት ለአራት ቀን ሕክምና ይሰጠው እንደነበር ያስታውሳል። "እንደ አዲስ መራመድ መማር ነበረብኝ" ይላል። ብዙ አገሮች እግር ለማርዘም ቀዶ ሕክምና ይሰጣሉ። እስከ አምስት ኢንች ወይም 13 ሴንቲ ሜትር ድረስ ቁመት መጨመርም ይቻላል። አሜሪካ፣ ጀርመን እና ደቡብ ኮርያ የሚገኙ ሆስፒታሎች በዓመት ከ100 እስከ 200 ቀዶ ሕክምናዎችን ያደርጋሉ። ስፔን፣ ሕንድ፣ ቱርክ እና ጣልያን ውስጥ በዓመት ከ20 እስከ 40 የሚደርሱ ቀዶ ሕክምናዎች ይካሄዳሉ። ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ደግሞ በዓመት 15 ጊዜ ቀዶ ሕክምናው ይደረጋል። ቀዶ ሕክምናውን የሚያደርጉ ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል። ቀዶ ሕክምናው እንዴት ይካሄዳል? ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ቀዶ ሕክምናው እስከ 50 ሺህ ፓውንድ ያስከፍላል። አሜሪካ ውስጥ ደግሞ ከ75 ሺህ እስከ 280 ሺህ ዶላር ያስወጣል። ቀዶ ሕክምናው ውድ ነው። ረዥም ሰዓታት ይወስዳል። ያማልም። በሕክምናው ፈር ቀዳጅ የሆኑት የሶቪየቱ ጋቪል ሊዝሮቭ ናቸው። ሕክምናውን የጀመሩት ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት የተረፉ ወታደሮችን ለማከም ነበር። ቀዶ ሕክምናው ባለፉት 70 ዓመታት ከፍተኛ መሻሻል አሳይቷል። ሕክምናው የሚካሄደው የእግር አጥንትን ቦርቡሮ ለሁለት ከከፈሉ በኋላ አነስተኛ ብረት በክፍተቱ በመክተት ነው። ግለሰቡ የሚፈለገው ርዝመት ላይ እስኪደርስ ብረቱ በየቀኑ አንድ ሚሊ ሜትር ከፍ እንዲል ይደረጋል። ታካሚው ከቀዶ ሕክምናው በኋላ ለወራት የማገገሚያ ሕክምና ይሰጠዋል። ቀዶ ሕክምናው ነርቭ ሊጎዳ፣ የደም ዝውውር ሊገታም ይችላል። የእግር አጥንትን መልሶ ለመግጠም የሚያስቸግርበትም ጊዜ አለ። "ቀዶ ሕክምናውን ያደረግኩት በ46 ዓመቴ ነበር" ባርኒ ቀዶ ሕክምናውን ያደረገው ከአምስት ዓመት በፊት ጣልያን ሲሆን፤ 3 ኢንች ጨምሯል። የእግር ቀዶ ሕክምና እንዲያደርግ የታዘዘው በሐኪሞች ምክር ነበር። "ቀዶ ሕክምናውን ያደረግኩት በ46 ዓመቴ ነበር። የእግሬ አጥንት መልሶ ሊገጥም አልቻለም። የሦስት ኢንች ክፍተት ተፈጥሮ ነበር" ይላል። ቀዶ ሕክምናው ምቾት ነስቶት እንደነበር ይናገራል። "እያንዳንዱ የእግሬ ነርቭ እንደተወጠረ ይሰማኝ ነበር። ህመሙ ቀላል አልነበረም።" የብሪትሽ የአጥንት ሕክምና [ኦርቶፒዲክ] ማኅበሩ ፕሮፌሰር ሀሚሽ ሲምሰን እንደሚሉት፤ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ሕክምናው እየተሻሻለ መጥቷል። "ሂደቱ አስተማማኝ እየሆነ ቢመጣም ከአጥንት በተጨማሪ ጡንቻ፣ ነርቭ፣ የደም መዘዋወሪያ እና ቆዳን ማሳደግም ስለሚያስፈልግ ሂደቱ ውስስብ ነው" ይላሉ። በዩናይትድ ኪንግደም የሚሠሩት ዶ/ር ዴቪድ ጎደር፤ አንዳንድ ሰዎች ገንዘብ ለማዳን ብለው ደኅንነቱ በማያስተማምን ቦታ ቀዶ ሕክምናውን እንደሚያገኙ ይናገራሉ። ባርኒ ቀዶ ሕክምናውን ካካሄደ ከአምስት ዓመታት በኋላ ነው የመጨረሻውን የሕክምና ደረጃ ያጠናቀቀው። በስተመጨረሻ እግሩ ውስጥ የቀረው ብረት እንዲወጣ ተደርጓል። "የአንዳንዶች ቀዶ ሕክምና በስኬት ይጠናቀቃል። እኔ ግን ለማገገም ገና ጊዜ ይወስድብኛል። ሆኖም ቀዶ ሕክምናውን ማድረጌ አይጸጽተኝም። አጭር ሰዎች ከሚገጥማቸው መድልዎ ነጻ ሆኜ ሕይወቴን እንድገፋ እድል ሰጥቶኛል" ይላል።
ሕክምና ፡ ቁመት ለመጨመር ምን አይነት ቀዶ ሕክምና ነው የሚደረገው? ሳም ቤከር የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪ ሳለ የክፍሉ ረዥም ልጅ ነበር። የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሆነው ጓደኞቹ ሁሉ ዘለግ ዘለግ ያሉ ሲሆኑ የእሱ ቁመት ግን አልጨመረም። "ኮሌጅ ስገባ ከሌሎች ወንዶችና ሴቶች ያጠርኩ መሆኔን አስተዋልኩ። ሴቶች ከእነሱ ከሚያጥር ሰው ጋር ፍቅር አይጀምሩም። እናም ሚስት አላገኝም ብዬ እሰጋ ነበር" ይላል። የ30 ዓመቱ የኒው ዮርክ ነዋሪ ሳም እረዝማለሁ ብሎ ቢጠብቅም ቁመቱ አልጨምር አለው። "ቁመትና ስኬትን አስተሳስሬ ነው የማየው" የሚለው ሳም ቁመት ለመጨመር አማራጮች ያስስ ጀመር። ከፍ ያለ ጫማ ማድረግ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ወዘተ. . . የሚሉት አማራጮች አላሳመኑትም። እግር ስለሚያረዝም ቀዶ ሕክምና ሲያነብ ግን ትኩረቱን ሳበው። "ጥቂት ኢንቾች ከጨመርኩ በኋላ መራመድና መሮጥ እችል ይሆን? ብዬ አሰብኩ" በየዓመቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቁመታቸውን ለመጨመር ቀዶ ሕክምና ያደርጋሉ። ቀዶ ሕክምናው ብዙ የጎንዮሽ ጉዳቶች እንደሚያስከትል ባለሙያዎች ይናገራሉ። ሳም ስለ ቀዶ ሕክምናው ከእናቱ ጋር ከተወያየ በኋላ የጎንዮሽ ጉዳት ቢኖርም እንኳን ለማካሄድ ወሰነ። ቀዶ ሕክምናውን ያደረገው ከዛሬ አምስት ዓመት በፊት ሲሆን፤ ይህም ከ162 ሴንቲ ሜትር ወደ 170 ሴንቲ ሜትር ከፍ እንዲል አስችሎታል። "ሐኪሙ መጀመሪያ ሲያገኘኝ ቀዶ ሕክምናው ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ነግሮኛል። ጥቂት ኢንቾች ከጨመርኩ በኋላ መራመድና መሮጥ እችል ይሆን? ብዬ አሰብኩ።" ከቀዶ ሕክምናው በኋላ ሆስፒታል ውስጥ የማገገሚያ ሕክምና ተደርጎለታል። ለስድስት ወራት፣ በሳምንት ለአራት ቀን ሕክምና ይሰጠው እንደነበር ያስታውሳል። "እንደ አዲስ መራመድ መማር ነበረብኝ" ይላል። ብዙ አገሮች እግር ለማርዘም ቀዶ ሕክምና ይሰጣሉ። እስከ አምስት ኢንች ወይም 13 ሴንቲ ሜትር ድረስ ቁመት መጨመርም ይቻላል። አሜሪካ፣ ጀርመን እና ደቡብ ኮርያ የሚገኙ ሆስፒታሎች በዓመት ከ100 እስከ 200 ቀዶ ሕክምናዎችን ያደርጋሉ። ስፔን፣ ሕንድ፣ ቱርክ እና ጣልያን ውስጥ በዓመት ከ20 እስከ 40 የሚደርሱ ቀዶ ሕክምናዎች ይካሄዳሉ። ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ደግሞ በዓመት 15 ጊዜ ቀዶ ሕክምናው ይደረጋል። ቀዶ ሕክምናውን የሚያደርጉ ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል። ቀዶ ሕክምናው እንዴት ይካሄዳል? ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ቀዶ ሕክምናው እስከ 50 ሺህ ፓውንድ ያስከፍላል። አሜሪካ ውስጥ ደግሞ ከ75 ሺህ እስከ 280 ሺህ ዶላር ያስወጣል። ቀዶ ሕክምናው ውድ ነው። ረዥም ሰዓታት ይወስዳል። ያማልም። በሕክምናው ፈር ቀዳጅ የሆኑት የሶቪየቱ ጋቪል ሊዝሮቭ ናቸው። ሕክምናውን የጀመሩት ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት የተረፉ ወታደሮችን ለማከም ነበር። ቀዶ ሕክምናው ባለፉት 70 ዓመታት ከፍተኛ መሻሻል አሳይቷል። ሕክምናው የሚካሄደው የእግር አጥንትን ቦርቡሮ ለሁለት ከከፈሉ በኋላ አነስተኛ ብረት በክፍተቱ በመክተት ነው። ግለሰቡ የሚፈለገው ርዝመት ላይ እስኪደርስ ብረቱ በየቀኑ አንድ ሚሊ ሜትር ከፍ እንዲል ይደረጋል። ታካሚው ከቀዶ ሕክምናው በኋላ ለወራት የማገገሚያ ሕክምና ይሰጠዋል። ቀዶ ሕክምናው ነርቭ ሊጎዳ፣ የደም ዝውውር ሊገታም ይችላል። የእግር አጥንትን መልሶ ለመግጠም የሚያስቸግርበትም ጊዜ አለ። "ቀዶ ሕክምናውን ያደረግኩት በ46 ዓመቴ ነበር" ባርኒ ቀዶ ሕክምናውን ያደረገው ከአምስት ዓመት በፊት ጣልያን ሲሆን፤ 3 ኢንች ጨምሯል። የእግር ቀዶ ሕክምና እንዲያደርግ የታዘዘው በሐኪሞች ምክር ነበር። "ቀዶ ሕክምናውን ያደረግኩት በ46 ዓመቴ ነበር። የእግሬ አጥንት መልሶ ሊገጥም አልቻለም። የሦስት ኢንች ክፍተት ተፈጥሮ ነበር" ይላል። ቀዶ ሕክምናው ምቾት ነስቶት እንደነበር ይናገራል። "እያንዳንዱ የእግሬ ነርቭ እንደተወጠረ ይሰማኝ ነበር። ህመሙ ቀላል አልነበረም።" የብሪትሽ የአጥንት ሕክምና [ኦርቶፒዲክ] ማኅበሩ ፕሮፌሰር ሀሚሽ ሲምሰን እንደሚሉት፤ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ሕክምናው እየተሻሻለ መጥቷል። "ሂደቱ አስተማማኝ እየሆነ ቢመጣም ከአጥንት በተጨማሪ ጡንቻ፣ ነርቭ፣ የደም መዘዋወሪያ እና ቆዳን ማሳደግም ስለሚያስፈልግ ሂደቱ ውስስብ ነው" ይላሉ። በዩናይትድ ኪንግደም የሚሠሩት ዶ/ር ዴቪድ ጎደር፤ አንዳንድ ሰዎች ገንዘብ ለማዳን ብለው ደኅንነቱ በማያስተማምን ቦታ ቀዶ ሕክምናውን እንደሚያገኙ ይናገራሉ። ባርኒ ቀዶ ሕክምናውን ካካሄደ ከአምስት ዓመታት በኋላ ነው የመጨረሻውን የሕክምና ደረጃ ያጠናቀቀው። በስተመጨረሻ እግሩ ውስጥ የቀረው ብረት እንዲወጣ ተደርጓል። "የአንዳንዶች ቀዶ ሕክምና በስኬት ይጠናቀቃል። እኔ ግን ለማገገም ገና ጊዜ ይወስድብኛል። ሆኖም ቀዶ ሕክምናውን ማድረጌ አይጸጽተኝም። አጭር ሰዎች ከሚገጥማቸው መድልዎ ነጻ ሆኜ ሕይወቴን እንድገፋ እድል ሰጥቶኛል" ይላል።
https://www.bbc.com/amharic/news-55198053
5sports
የቀድሞው የሊቨርፑል አጥቂ የጠፋ ውሻውን ላገኘለት ራፐር 30 ሺህ ዶላር እንዲከፍል ተፈረደበት
የቀድሞው የሊቨርፑል ተጫዋች ዳንኤል ሰተሬጅ ከሁለት ዓመታት በፊት ጠፍታ የነበረቸውን ሉሲ የተሰኘች ውሻውን ላገኘለት ግለሰብ 30 ሺህ ዶላር እንዲከፍል ፍርድ ቤት ወሰነበት። አሁን በአውስትራሊያ ላለ ክለብ የሚጫወተው ዳንኤል፤ ሉሲ የተሰኘች ውሻው በሎስ አንጀለስ ከሚገኘው ቤቱ መሰረቋን ተከትሎ ነበር ላገኛት ሰው ወረታውን ለመክፈል ቃል የገባው። ኪላ ፌም በሚለው የመድረክ ስሙ የሚታወቀው ፎስተር ዋሽንግተን የተሰኘው ራፐር ውሻውን አግኝቶ ለዳንኤል ቢሰጠውም ቃል የተገባው ክፍያ ግን እንዳልተፈጸመለት ተናግሯል። ይህንን ማመልከቻ ተከትሎም ችሎቱ ለዋሽንግተን ፈርዶለታል። ፒኤ በተሰኘው የዜና ወኪል እጅ የገቡት የችሎቱ ሰነዶች እንደሚያሳዩት ፍርዱ ዳንኤል ወደ ችሎት ቀርቦ ምላሽ ሳይሰጥበት በፊት ነው የተሰጠው። ዳኛው እግር ኳስ ተጫዋቹ ለራፕ ሙዚቃ አቀንቃኙ ከ30 ሺህ ዶላሩ ክፍያ በተጨማሪ ደረሰብኝ ያለው የመገፋት ስሜት ላደረሰበት ጉዳት የ85 ዶላር ካሳ እንዲከፍለውም አዟል። "ገንዘቡን እንደሚከፍል እና ወደ ይግባኝ እንደማይሄድ ተስፋ አደርጋለሁ። በጣም ደስ ብሎኛል። ለዚህ የፍርድ ቤት ጉዳይ ከአንድ ዓመት በላይ ስከራከር ቆይቻለሁ። ውሻውን ሳገኝ ሕይወቴ የተወሰነ ይሻሻላል ብዬ ተስፋ አድርጌ ነበር" ሲልም ዋሽንግተን ተናግሯል። በእግር ኳስ ተጫዋቹ የሆሊዉድ ቤት ውስጥ ተገጥመው በነበሩ የደኅንነት ካሜራ ቪዲዮዎች ኮፍያ ያለው ሹራብ ያደረጉ ሦስት ሰዎች ውሻዋ በጠፋችበት ጊዜ ላይ ታይተው ነበር። "ለውሻዋ ማንኛውንም ነገር እንከፍላለን" ሲል ዳንኤል ስተርጅ ተናግሮ ነበር። "ማንም ይሁን ማን ውሻዬን ካመጣልኝ ከ20 እስከ 30 ሺህ ዶላር እከፍላለሁ" ሲልም ገልጾ ነበር። ይህንን ካለ ከሁለት ቀን በኋላ ነበር ውሻውን ያገኘው። የቀድሞው የሊቨርፑል ቡድን ተጫዋቹ ወኪሎች በጉዳዩ ላይ አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።
የቀድሞው የሊቨርፑል አጥቂ የጠፋ ውሻውን ላገኘለት ራፐር 30 ሺህ ዶላር እንዲከፍል ተፈረደበት የቀድሞው የሊቨርፑል ተጫዋች ዳንኤል ሰተሬጅ ከሁለት ዓመታት በፊት ጠፍታ የነበረቸውን ሉሲ የተሰኘች ውሻውን ላገኘለት ግለሰብ 30 ሺህ ዶላር እንዲከፍል ፍርድ ቤት ወሰነበት። አሁን በአውስትራሊያ ላለ ክለብ የሚጫወተው ዳንኤል፤ ሉሲ የተሰኘች ውሻው በሎስ አንጀለስ ከሚገኘው ቤቱ መሰረቋን ተከትሎ ነበር ላገኛት ሰው ወረታውን ለመክፈል ቃል የገባው። ኪላ ፌም በሚለው የመድረክ ስሙ የሚታወቀው ፎስተር ዋሽንግተን የተሰኘው ራፐር ውሻውን አግኝቶ ለዳንኤል ቢሰጠውም ቃል የተገባው ክፍያ ግን እንዳልተፈጸመለት ተናግሯል። ይህንን ማመልከቻ ተከትሎም ችሎቱ ለዋሽንግተን ፈርዶለታል። ፒኤ በተሰኘው የዜና ወኪል እጅ የገቡት የችሎቱ ሰነዶች እንደሚያሳዩት ፍርዱ ዳንኤል ወደ ችሎት ቀርቦ ምላሽ ሳይሰጥበት በፊት ነው የተሰጠው። ዳኛው እግር ኳስ ተጫዋቹ ለራፕ ሙዚቃ አቀንቃኙ ከ30 ሺህ ዶላሩ ክፍያ በተጨማሪ ደረሰብኝ ያለው የመገፋት ስሜት ላደረሰበት ጉዳት የ85 ዶላር ካሳ እንዲከፍለውም አዟል። "ገንዘቡን እንደሚከፍል እና ወደ ይግባኝ እንደማይሄድ ተስፋ አደርጋለሁ። በጣም ደስ ብሎኛል። ለዚህ የፍርድ ቤት ጉዳይ ከአንድ ዓመት በላይ ስከራከር ቆይቻለሁ። ውሻውን ሳገኝ ሕይወቴ የተወሰነ ይሻሻላል ብዬ ተስፋ አድርጌ ነበር" ሲልም ዋሽንግተን ተናግሯል። በእግር ኳስ ተጫዋቹ የሆሊዉድ ቤት ውስጥ ተገጥመው በነበሩ የደኅንነት ካሜራ ቪዲዮዎች ኮፍያ ያለው ሹራብ ያደረጉ ሦስት ሰዎች ውሻዋ በጠፋችበት ጊዜ ላይ ታይተው ነበር። "ለውሻዋ ማንኛውንም ነገር እንከፍላለን" ሲል ዳንኤል ስተርጅ ተናግሮ ነበር። "ማንም ይሁን ማን ውሻዬን ካመጣልኝ ከ20 እስከ 30 ሺህ ዶላር እከፍላለሁ" ሲልም ገልጾ ነበር። ይህንን ካለ ከሁለት ቀን በኋላ ነበር ውሻውን ያገኘው። የቀድሞው የሊቨርፑል ቡድን ተጫዋቹ ወኪሎች በጉዳዩ ላይ አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-59788736
2health
''ኮሮናቫይረስ በሁለት ዓመታት ውስጥ ሊጠፋ ይችላል'' ደ/ር ቴድሮስ አድሃኖም
የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሊጠፋ እንደሚችል ገለጹ። ትላንት በሲዊዘርላንድ ጄኔቫ ባደረጉት ንግግር ዳይሬክተሩ ስፓኒሽ ፍሉ በጎርጎሮሳውያኑ 1918 በተከሰተበት ወቅት ለመጥፋት የወሰደበት ጊዜ ሁለት ዓመት ነበር ብለዋል። ዳይሬክተሩ አክለውም ዓለም አሁን ከደረሰችበት የቴክኖሎጂ መራቀቅና ከፍተኛ ምርምሮች አንጻር የኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ ከሁለት ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ሊጠፋ እንደሚችል ገልጸዋል። ''በሌላ በኩል ደግሞ አሁን ባለው ከፍተኛ የሰዎች ማህበራዊ ትስስር ምክንያት የቫይረሱ ስርጭት ከፍተኛ ሊሆንም ይችላል'' ብለዋል ዶ/ር ቴድሮስ። ''ነገር ግን የሰው ልጅ የደረሰበት የቴክኖሎጂ ርቀት ቫይረሱን ለማስቆም የሚረዳ እውቀት በቶሎ እንዲያዳብር ይረዳዋል'' ካሉ በኋላ አሁንም ቢሆንም ግን ብሄራዊ አንድነትና ዓለማቀፍ ትብብር ላይ ከፍተኛ አጽንኦት ሰጥተው አልፈዋል። የ1918ቱ ስፓኒሽ ፍሉ ቢያንስ 50 ሚሊየን ሰዎችን የገደለ ሲሆን ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎችን ቁጥር 800 ሺህ ነው። በአጠቃላይ ደግሞ 22.7 ሚሊየን ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ዶክተር ቴዎድሮስ በመግለጫቸው ላይ የግል መከላከያ መሳሪያዎች ወይም 'ፒፒኢ' ስርጭት በተመለከተ ሙስና እየተስተዋለ እንደሆነ ለቀረበላቸውም ጥያቄ መልስ ሲሰጡ ጉዳዩን ''ወንጀል'' ነው በማለት ገልጸውታል። ''ማንኛውም አይነት ሙስና ተቀባይነት የለውም'' ብለዋል። ''ነገር ግን ከፒፒኢ ጋር የተያያዘ ሙስና ለእኔ በግሌ እንደ ነብስ ማጥፋት ነው የምቆጥረው። ምክንያቱም የጤና ባለሙያዎች ፒፒኢ የማያገኙ ከሆነ ሕይወታቸውን አደጋ ላይ እየጣልን ነው። በተጨማሪም የሚያገለግሏቸው ሰዎችን ሕይወትም ነው ስጋት ውስጥ የምንከተው'' ብለዋል።
''ኮሮናቫይረስ በሁለት ዓመታት ውስጥ ሊጠፋ ይችላል'' ደ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሊጠፋ እንደሚችል ገለጹ። ትላንት በሲዊዘርላንድ ጄኔቫ ባደረጉት ንግግር ዳይሬክተሩ ስፓኒሽ ፍሉ በጎርጎሮሳውያኑ 1918 በተከሰተበት ወቅት ለመጥፋት የወሰደበት ጊዜ ሁለት ዓመት ነበር ብለዋል። ዳይሬክተሩ አክለውም ዓለም አሁን ከደረሰችበት የቴክኖሎጂ መራቀቅና ከፍተኛ ምርምሮች አንጻር የኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ ከሁለት ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ሊጠፋ እንደሚችል ገልጸዋል። ''በሌላ በኩል ደግሞ አሁን ባለው ከፍተኛ የሰዎች ማህበራዊ ትስስር ምክንያት የቫይረሱ ስርጭት ከፍተኛ ሊሆንም ይችላል'' ብለዋል ዶ/ር ቴድሮስ። ''ነገር ግን የሰው ልጅ የደረሰበት የቴክኖሎጂ ርቀት ቫይረሱን ለማስቆም የሚረዳ እውቀት በቶሎ እንዲያዳብር ይረዳዋል'' ካሉ በኋላ አሁንም ቢሆንም ግን ብሄራዊ አንድነትና ዓለማቀፍ ትብብር ላይ ከፍተኛ አጽንኦት ሰጥተው አልፈዋል። የ1918ቱ ስፓኒሽ ፍሉ ቢያንስ 50 ሚሊየን ሰዎችን የገደለ ሲሆን ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎችን ቁጥር 800 ሺህ ነው። በአጠቃላይ ደግሞ 22.7 ሚሊየን ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ዶክተር ቴዎድሮስ በመግለጫቸው ላይ የግል መከላከያ መሳሪያዎች ወይም 'ፒፒኢ' ስርጭት በተመለከተ ሙስና እየተስተዋለ እንደሆነ ለቀረበላቸውም ጥያቄ መልስ ሲሰጡ ጉዳዩን ''ወንጀል'' ነው በማለት ገልጸውታል። ''ማንኛውም አይነት ሙስና ተቀባይነት የለውም'' ብለዋል። ''ነገር ግን ከፒፒኢ ጋር የተያያዘ ሙስና ለእኔ በግሌ እንደ ነብስ ማጥፋት ነው የምቆጥረው። ምክንያቱም የጤና ባለሙያዎች ፒፒኢ የማያገኙ ከሆነ ሕይወታቸውን አደጋ ላይ እየጣልን ነው። በተጨማሪም የሚያገለግሏቸው ሰዎችን ሕይወትም ነው ስጋት ውስጥ የምንከተው'' ብለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-53872753
0business
ኮሮናቫይረስ ፡ ኮቪድ-19 ኒውዚላንድን ለዓመታት አጋጥሟት ለማያውቅ የኢኮኖሚ ውድቀት ዳርጓታል ተባለ
የኮቪድ- 19 ወረርሽኝ በተከሰተ በመጀመሪያዎቹ ወራት በርካቶችን እንደ ቅጠል ሲያረግፍ፤ ኒው ዚላንድ ግን በሌሎች የአውሮፓና አሜሪካ አገራት የሆነው አልገጠማትም። ይህ የሆነው የአገሪቷ መንግሥት ቀድሞ በወሰዳቸው ጥብቅ እርምጃዎች ምክንያት ነው። ኒው ዚላንድ ለወረርሽኙ ምላሽ በመስጠት ከተወደሱ አገራት መካከል አንዷ ናት። ጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርደርንም በዚህ ሥራቸው ተሞግሰዋል። ነገር ግን አገሪቷ ኮቪድ -19 ወረርሽኝን ለመቆጣጠር የጣለቻቸው ጥብቅ ገደቦች ባለፉት አስርት ዓመታት አጋጥሟት ወደማያውቅ የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ እንደከተታት ተገልጿል። በአገሪቷ የእንቅስቃሴ ገደቡ በተጣለባቸውና ድንበር በዘጋችበት ከሚያዚያ እስከ ሰኔ ባሉት ጊዜያት የኢኮኖሚ እድገቷ በ12̀.2 በመቶ ማሽቆልቆሉ ተገልጿል። ይህም ኒው ዚላንድ ዓለም አቀፉን የኢኮኖሚ ቀውስ ተከትሎ በጎርጎሮሳዊያኑ 1987 ከገጠማት የመጀመሪያው የኢኮኖሚ ድቀት ነው ተብሏል።. ይሁን እንጅ መንግሥት ለወረርሽኙ የሰጠው ምላሽ ኢኮኖሚው በፍጥነት ወደማንሰራራት እንደሚያመራው ተስፋ አድርጓል። 5 ሚሊየን የሚጠጋ የሕዝብ ብዛት ያላት ኒው ዚላንድ ከቫይረሱ ነፃ መሆኗን ያወጀች ቢሆንም አሁንም ግን በርካታ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ይገኛሉ። አገሪቷ በቫይረሱ ሳቢያ ያስተናገደችው ሞትም 25 ብቻ ነው። የኢኮኖሚው ጉዳይም ነሐሴ ወር ላይ ባልተጠበቀ መልኩ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በመጨመሩ የተራዘመውና በሚቀጥለው ወር በሚደረገው ምርጫ ላይም ዋነኛ ጉዳይ ሆኖ እንደሚነሳ ይጠበቃል። የኒው ዚላንድ ስታስቲክስ ኤጀንሲ ቃል አቀባይ ፖል ፓስኮ፤ ወረርሽኙን ተከትሎ ከመጋቢት ወደ ጀምሮ ተግባራዊ የተደረጉ ገደቦች በተወሰኑ የኢኮኖሚው ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እንደነበረው ተናግረዋል። "በኢንዱስትሪ ምርቶች ላይ፣ በሆቴሎችና ሬስቶራንቶች እንዲሁም በትራንስፖርት ዘርፉ ላይ ከፍተኛ የሆነ መዳከም ታይቷል። እነዚህ ዘርፎች በዓለም አቀፉ ጉዞ እገዳ እና በአገሪቷ ተጥሎ በነበረው ጥብቅ የእንቅስቃሴ ገደብ በቀጥታ ተጎጅ ሆነዋል" ብለዋል ቃል አቀባዩ ። የጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርደርን መንግሥትም ቫይረሱን በመቆጣጠር የተገኘው ውጤት ኢኮኖሚው እንዲያንሰራራ ያግዛል ብለዋል። የአገሪቷ የገንዘብ ሚኒስትር ግራንት ሮበርትሰን በበኩላቸው፤ የኢኮኖሚ እድገት [ጂዲፒ] አሃዝ ከተጠበቀው የተሻለ መሆኑን በመጥቀስ ወደ ፊት ኢኮኖሚው እንደሚሻሻል አስተያየታቸው ሰጥተዋል። አንዳንድ የምጣኔ ሐብት ባለሙያዎችም ኒው ዚላንድ ቫይረሱን ለመቆጣጠር ጠንካራ ምላሽ በመስጠቷ ኢኮኖሚዋ በፍጥነት እንደሚያገግም ተንብየዋል።
ኮሮናቫይረስ ፡ ኮቪድ-19 ኒውዚላንድን ለዓመታት አጋጥሟት ለማያውቅ የኢኮኖሚ ውድቀት ዳርጓታል ተባለ የኮቪድ- 19 ወረርሽኝ በተከሰተ በመጀመሪያዎቹ ወራት በርካቶችን እንደ ቅጠል ሲያረግፍ፤ ኒው ዚላንድ ግን በሌሎች የአውሮፓና አሜሪካ አገራት የሆነው አልገጠማትም። ይህ የሆነው የአገሪቷ መንግሥት ቀድሞ በወሰዳቸው ጥብቅ እርምጃዎች ምክንያት ነው። ኒው ዚላንድ ለወረርሽኙ ምላሽ በመስጠት ከተወደሱ አገራት መካከል አንዷ ናት። ጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርደርንም በዚህ ሥራቸው ተሞግሰዋል። ነገር ግን አገሪቷ ኮቪድ -19 ወረርሽኝን ለመቆጣጠር የጣለቻቸው ጥብቅ ገደቦች ባለፉት አስርት ዓመታት አጋጥሟት ወደማያውቅ የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ እንደከተታት ተገልጿል። በአገሪቷ የእንቅስቃሴ ገደቡ በተጣለባቸውና ድንበር በዘጋችበት ከሚያዚያ እስከ ሰኔ ባሉት ጊዜያት የኢኮኖሚ እድገቷ በ12̀.2 በመቶ ማሽቆልቆሉ ተገልጿል። ይህም ኒው ዚላንድ ዓለም አቀፉን የኢኮኖሚ ቀውስ ተከትሎ በጎርጎሮሳዊያኑ 1987 ከገጠማት የመጀመሪያው የኢኮኖሚ ድቀት ነው ተብሏል።. ይሁን እንጅ መንግሥት ለወረርሽኙ የሰጠው ምላሽ ኢኮኖሚው በፍጥነት ወደማንሰራራት እንደሚያመራው ተስፋ አድርጓል። 5 ሚሊየን የሚጠጋ የሕዝብ ብዛት ያላት ኒው ዚላንድ ከቫይረሱ ነፃ መሆኗን ያወጀች ቢሆንም አሁንም ግን በርካታ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ይገኛሉ። አገሪቷ በቫይረሱ ሳቢያ ያስተናገደችው ሞትም 25 ብቻ ነው። የኢኮኖሚው ጉዳይም ነሐሴ ወር ላይ ባልተጠበቀ መልኩ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በመጨመሩ የተራዘመውና በሚቀጥለው ወር በሚደረገው ምርጫ ላይም ዋነኛ ጉዳይ ሆኖ እንደሚነሳ ይጠበቃል። የኒው ዚላንድ ስታስቲክስ ኤጀንሲ ቃል አቀባይ ፖል ፓስኮ፤ ወረርሽኙን ተከትሎ ከመጋቢት ወደ ጀምሮ ተግባራዊ የተደረጉ ገደቦች በተወሰኑ የኢኮኖሚው ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እንደነበረው ተናግረዋል። "በኢንዱስትሪ ምርቶች ላይ፣ በሆቴሎችና ሬስቶራንቶች እንዲሁም በትራንስፖርት ዘርፉ ላይ ከፍተኛ የሆነ መዳከም ታይቷል። እነዚህ ዘርፎች በዓለም አቀፉ ጉዞ እገዳ እና በአገሪቷ ተጥሎ በነበረው ጥብቅ የእንቅስቃሴ ገደብ በቀጥታ ተጎጅ ሆነዋል" ብለዋል ቃል አቀባዩ ። የጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርደርን መንግሥትም ቫይረሱን በመቆጣጠር የተገኘው ውጤት ኢኮኖሚው እንዲያንሰራራ ያግዛል ብለዋል። የአገሪቷ የገንዘብ ሚኒስትር ግራንት ሮበርትሰን በበኩላቸው፤ የኢኮኖሚ እድገት [ጂዲፒ] አሃዝ ከተጠበቀው የተሻለ መሆኑን በመጥቀስ ወደ ፊት ኢኮኖሚው እንደሚሻሻል አስተያየታቸው ሰጥተዋል። አንዳንድ የምጣኔ ሐብት ባለሙያዎችም ኒው ዚላንድ ቫይረሱን ለመቆጣጠር ጠንካራ ምላሽ በመስጠቷ ኢኮኖሚዋ በፍጥነት እንደሚያገግም ተንብየዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-54193966
0business
ከኤሌክትሪክ መኪና አምራቹ ኩባንያ ሕንጻ ላይ የወደቀ መኪና ሁለት ሰዎችን ገደለ
ከቻይናው የኤሌክትሪክ መኪና አምራች ኩባንያ ኒዮ ዋና መሥሪያ ቤት ሕንጻ ላይ አንድ መኪና ወድቆ ሁለት ሰዎችን ገደለ። ሻንጋይ ከሚገኘው የኒዮ ዋና መሥሪያ ቤት ሦስተኛ ፎቅ ላይ መኪና መውደቁን ተከትሎ ነው ሰዎቹ ለህልፈት የተዳረጉት። ኒዮ የኤሌክትሪክ መኪና አምራች ሲሆን፣ ከሞቱት ሰዎች አንደኛው የድርጅቱ ተቀጣሪ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ የኒዮ አጋር ድርጅት ሠራተኛ ናቸው ተብሏል። ሟቾቹ መኪናው ሲወድቅ ውስጡ እንደነበሩ ተገልጿል። ከመንግሥት አመራሮች ጋር በመጣመር ክስተቱን እየመረመረ እንደሚገኝ የኤሌክትሪክ መኪና አምራቹ ኒዮ አስታውቋል። የዋና መሥሪያ ቤቱ ሦስተኛ ፎቅ መኪኖች ለዕይታ የሚቀርቡበት ሲሆን፣ መኪኖች ከመሸጣቸው በፊት የሚሞከሩትም በዚህ የሕንጻው ክፍል ነው። መኪና አምራቹ ባወጣው መግለጫ “ከአገር ውስጥ ደኅንነት ጋር ድርጅታችን ተጣምሮ ስለ አደጋው መንስኤ ምርመራ ጀምሯል። እስካሁን ባገኘነው መረጃ ክስተቱ ድንገተኛ ነው። የተፈጠረውም በመኪናው ምክንያት አይደለም” ብሏል። ለሟቾች ቤተሰቦች መጽናናትን የተመኘው ድርጅቱ፣ ቤተሰቦቻቸውን የሚደግፍ ቡድን እንዳቋቁመ አክሏል። ኒዮ ባወጣው መግለጫ፣ አደጋው ከመኪናው ጋር የተያያዘ አይደለም ማለቱ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ቁጣን ቀስቅሷል። “ይህ መግለጫ የካፒታሊዝምን አደገኛነትን ያሳብቃል” ሲል አንድ የቻይና ማኅበራዊ ሚዲያ ዌቦ ተጠቃሚ ተናግሯል። “ይህ አባባል ግድየለሽነታቸውን ነው የሚያሳየው። ሹፌሮች መኪኖችን እንዲሞክሩ እያደረጉ ክስተቱ ከመኪናው ጋር የማይገናኝ አደጋ ነው ይላሉ” ሲል ሌላ የዌቦ ተጠቃሚ ተችቷል። ሌላ አስተያየት ሰጪ ደግሞ “አደጋ ነበር ወይስ አልነበረም የሚለውን መወሰን ያለበት የአገር ውስጥ ደኅንነት ቢሮ ነው” ብሏል። መኪና አምራቹ መጀመሪያ ላይ የለጠፈውን መግለጫ አሻሽሎ ‘አደጋው የተከሰተው በመኪናው ምክንያት አይደለም’ የሚለውን አረፍተ ነገር በቅንፍ ውስጥ አስቀምጦታል። ከዚያ በኋላ የተሰጡት አስተያየቶች “ነፍስ ይማር” የሚሉ ናቸው። ኒዮ በኤሌክትሮኒክ ተሽከርካሪዎች ምርት ቻይና ውስጥ ግንባር ቀደም ከሚባሉት መካከል ይጠቀሳል። ኩባንያው መኪኖችን በተደጋጋሚ ቻርጅ ማድረግ ለጉዞ መሰናክል እንዳይሆን ተለዋጭ ባትሪ በማዘጋጀትም ይታወቃል። ሌላው የኤሌክትሪክ መኪና አምራች፣ የኤሎን መስክ ቴስላ ሻንጋይ ውስጥ ቅርንጫፍ አለው። ኒዮ የቴስላ ተቀናቃኝ እንደሆነም ይታመናል።
ከኤሌክትሪክ መኪና አምራቹ ኩባንያ ሕንጻ ላይ የወደቀ መኪና ሁለት ሰዎችን ገደለ ከቻይናው የኤሌክትሪክ መኪና አምራች ኩባንያ ኒዮ ዋና መሥሪያ ቤት ሕንጻ ላይ አንድ መኪና ወድቆ ሁለት ሰዎችን ገደለ። ሻንጋይ ከሚገኘው የኒዮ ዋና መሥሪያ ቤት ሦስተኛ ፎቅ ላይ መኪና መውደቁን ተከትሎ ነው ሰዎቹ ለህልፈት የተዳረጉት። ኒዮ የኤሌክትሪክ መኪና አምራች ሲሆን፣ ከሞቱት ሰዎች አንደኛው የድርጅቱ ተቀጣሪ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ የኒዮ አጋር ድርጅት ሠራተኛ ናቸው ተብሏል። ሟቾቹ መኪናው ሲወድቅ ውስጡ እንደነበሩ ተገልጿል። ከመንግሥት አመራሮች ጋር በመጣመር ክስተቱን እየመረመረ እንደሚገኝ የኤሌክትሪክ መኪና አምራቹ ኒዮ አስታውቋል። የዋና መሥሪያ ቤቱ ሦስተኛ ፎቅ መኪኖች ለዕይታ የሚቀርቡበት ሲሆን፣ መኪኖች ከመሸጣቸው በፊት የሚሞከሩትም በዚህ የሕንጻው ክፍል ነው። መኪና አምራቹ ባወጣው መግለጫ “ከአገር ውስጥ ደኅንነት ጋር ድርጅታችን ተጣምሮ ስለ አደጋው መንስኤ ምርመራ ጀምሯል። እስካሁን ባገኘነው መረጃ ክስተቱ ድንገተኛ ነው። የተፈጠረውም በመኪናው ምክንያት አይደለም” ብሏል። ለሟቾች ቤተሰቦች መጽናናትን የተመኘው ድርጅቱ፣ ቤተሰቦቻቸውን የሚደግፍ ቡድን እንዳቋቁመ አክሏል። ኒዮ ባወጣው መግለጫ፣ አደጋው ከመኪናው ጋር የተያያዘ አይደለም ማለቱ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ቁጣን ቀስቅሷል። “ይህ መግለጫ የካፒታሊዝምን አደገኛነትን ያሳብቃል” ሲል አንድ የቻይና ማኅበራዊ ሚዲያ ዌቦ ተጠቃሚ ተናግሯል። “ይህ አባባል ግድየለሽነታቸውን ነው የሚያሳየው። ሹፌሮች መኪኖችን እንዲሞክሩ እያደረጉ ክስተቱ ከመኪናው ጋር የማይገናኝ አደጋ ነው ይላሉ” ሲል ሌላ የዌቦ ተጠቃሚ ተችቷል። ሌላ አስተያየት ሰጪ ደግሞ “አደጋ ነበር ወይስ አልነበረም የሚለውን መወሰን ያለበት የአገር ውስጥ ደኅንነት ቢሮ ነው” ብሏል። መኪና አምራቹ መጀመሪያ ላይ የለጠፈውን መግለጫ አሻሽሎ ‘አደጋው የተከሰተው በመኪናው ምክንያት አይደለም’ የሚለውን አረፍተ ነገር በቅንፍ ውስጥ አስቀምጦታል። ከዚያ በኋላ የተሰጡት አስተያየቶች “ነፍስ ይማር” የሚሉ ናቸው። ኒዮ በኤሌክትሮኒክ ተሽከርካሪዎች ምርት ቻይና ውስጥ ግንባር ቀደም ከሚባሉት መካከል ይጠቀሳል። ኩባንያው መኪኖችን በተደጋጋሚ ቻርጅ ማድረግ ለጉዞ መሰናክል እንዳይሆን ተለዋጭ ባትሪ በማዘጋጀትም ይታወቃል። ሌላው የኤሌክትሪክ መኪና አምራች፣ የኤሎን መስክ ቴስላ ሻንጋይ ውስጥ ቅርንጫፍ አለው። ኒዮ የቴስላ ተቀናቃኝ እንደሆነም ይታመናል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cye9w6rl475o
5sports
የዓለም ዋንጫ፡ ብሔራዊ ቡድናቸው በመሸነፉ ደስታቸውን ሲገልጹ ከነበሩ ኢራናዊያን መካከል አንድ ሰው ተገደለ
ብሔራዊ ቡድናቸው ከዓለም ዋንጫ በጊዜ በመሰናበቱ ደስታቸውን ሲገልጹ ከነበሩ የኢራን መንግሥት ተቃዋሚዎች መካከል አንድ ሰው በጸጥታ አካላት መገደሉ ተገለጸ። ማከሰኞ ምሽት የህብረተሰብ አንቂ የሆነው ሜህራን ሳማክ በባንዳር አንዛሊ የመኪናውን ጥሩምባ ሲነፋ ግንባሩ ላይ በጥይት መመታቱ ተነግሯል። ከሌሎች ከተሞች የተገኙ ምስሎች እና ቪዲዮዎች እንደሚያሳዩት በርካታ ሰዎች መንገዶች ላይ ደስታቸውን ሲገልጹ ታይተዋል። ብሔራዊ ቡድኑ የኢስላሚክ ሪፐብሊክ ምልክት ነው በማለት ብዙ ኢራናዊያን ድጋፋቸውን ከመስጠት ተቆጥበዋል። የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን በሃገር ውስጥ እና በውጭ ያሉ ኃይሎች በአሜሪካ 1 ለ 0 በተሸነፈበት የመጨረሻው የምድብ ጨዋታ ወቅት ጫና እንዳሳደሩበት ገልጸዋል። በእንግሊዝ 6 ለ 1 በተሸነፉበት ጨዋታ ደግሞ ተጫዋቾችቹ ብሔራዊ መዝሙር አልዘመሩም። ይህም ለተቃዋሚዎች ያላቸውን ድጋፍ ያሳያል ተብሏል። ዌልስን 2 ለ 0 ባሸነፉበት እና ፖለቲካዊ ውጥረት በነበረው የአሜሪካ ጨዋታ ወቅት ግን ብሔራዊ መዝሙሩን ዘምረዋል። የቡድኑ አባላት በጸጥታ ሃይሎች ጫና ደርሶባቸው ነው ቢባልም አንዳንድ ተቃዋሚዎች ቡድኑ ብሔራዊ መዝሙሩን በመዘመሩ ከድቶናል የሚል ስሜት ፈጥሮባቸዋል። በኢራን አለመረጋጋት የጀመረው ከአስር ሳምንታት በፊት ነው። የ22 ዓመቷ ማህሳ አሚኒ የሂጃብ አለባበስ ደንብ ጥሳለች በሚል በስነ ምግባር ፖሊሶች እጅ ህይወቷ ማለፉ ቁጣውን ቀስቅሶታል። ባለስልጣናት “አመጹን” በውጭ ሃይላት የሚደገፍ ሲሉ ይገልጻሉ። መቀመጫውን ኖርዌይ ያደረገው የኢራን የሰብዓዊ መብት ቡድን 60 ህጻናትን ጨምሮ በትንሹ 448 ሰዎች መገደላቸውን ገልጿል። ከ18 ሺህ በላይ ሰዎች መታሰራቸውም ተነግሯል። ኢራን ብሔራዊ ቡድን ሽንፈትን በደስታ ለማክብር የመኪናውን ጥሩምባ ሲነፋ የነበረው የ27 ዓመቱ ሜህራን ሳማክ በጸጥታ ሃይሎች መገደሉን የኢራን ሰብዓዊ መብት ሪፖርት አድርጓል። ቢቢሲ ፐርዢያ ረቡዕ ጠዋት የተደረገለትን የቀብር ስነ ስርዓት ቪዲዮ ለመመልከት ችሏል። ሃዘንተኞች “ቆሻሻ ናችሁ፣ ሞራል የላችሁም፣ እኔ ነጻ ሴት ነኝ” የሚሉና በተቃዋሚዎች የሚዘወተሩ መፈክሮችን አሰምተዋል። የኢራን ጸጥታ ኃይሎች ሠላማዊ ተቃዋሚዎችን አልገደልንም ሲሉ ያስተባብላሉ። ሌሎች ቪዲዮዎች ደግሞ ቴህራንን ጨምሮ በተለይም በኩርዲስታን ከተሞች የብሔራዊ ቡድኑን ከዓለም ዋንጫ መሰናበት ደስታቸውን የገለጹ በርካታ ናቸው። በቅርቡ የጸጥታ ሃይሎች በወሰዷቸው እርምጃዎች በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋል። በማህሳ አሚኒ የትውልድ ከተማ ሳቄዝ ስካርፋቸውን በማውለብለብ ደስታቸውን ከመግልጽ ባለፈ ርችትም ሲተኩሱ ታይተዋል።
የዓለም ዋንጫ፡ ብሔራዊ ቡድናቸው በመሸነፉ ደስታቸውን ሲገልጹ ከነበሩ ኢራናዊያን መካከል አንድ ሰው ተገደለ ብሔራዊ ቡድናቸው ከዓለም ዋንጫ በጊዜ በመሰናበቱ ደስታቸውን ሲገልጹ ከነበሩ የኢራን መንግሥት ተቃዋሚዎች መካከል አንድ ሰው በጸጥታ አካላት መገደሉ ተገለጸ። ማከሰኞ ምሽት የህብረተሰብ አንቂ የሆነው ሜህራን ሳማክ በባንዳር አንዛሊ የመኪናውን ጥሩምባ ሲነፋ ግንባሩ ላይ በጥይት መመታቱ ተነግሯል። ከሌሎች ከተሞች የተገኙ ምስሎች እና ቪዲዮዎች እንደሚያሳዩት በርካታ ሰዎች መንገዶች ላይ ደስታቸውን ሲገልጹ ታይተዋል። ብሔራዊ ቡድኑ የኢስላሚክ ሪፐብሊክ ምልክት ነው በማለት ብዙ ኢራናዊያን ድጋፋቸውን ከመስጠት ተቆጥበዋል። የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን በሃገር ውስጥ እና በውጭ ያሉ ኃይሎች በአሜሪካ 1 ለ 0 በተሸነፈበት የመጨረሻው የምድብ ጨዋታ ወቅት ጫና እንዳሳደሩበት ገልጸዋል። በእንግሊዝ 6 ለ 1 በተሸነፉበት ጨዋታ ደግሞ ተጫዋቾችቹ ብሔራዊ መዝሙር አልዘመሩም። ይህም ለተቃዋሚዎች ያላቸውን ድጋፍ ያሳያል ተብሏል። ዌልስን 2 ለ 0 ባሸነፉበት እና ፖለቲካዊ ውጥረት በነበረው የአሜሪካ ጨዋታ ወቅት ግን ብሔራዊ መዝሙሩን ዘምረዋል። የቡድኑ አባላት በጸጥታ ሃይሎች ጫና ደርሶባቸው ነው ቢባልም አንዳንድ ተቃዋሚዎች ቡድኑ ብሔራዊ መዝሙሩን በመዘመሩ ከድቶናል የሚል ስሜት ፈጥሮባቸዋል። በኢራን አለመረጋጋት የጀመረው ከአስር ሳምንታት በፊት ነው። የ22 ዓመቷ ማህሳ አሚኒ የሂጃብ አለባበስ ደንብ ጥሳለች በሚል በስነ ምግባር ፖሊሶች እጅ ህይወቷ ማለፉ ቁጣውን ቀስቅሶታል። ባለስልጣናት “አመጹን” በውጭ ሃይላት የሚደገፍ ሲሉ ይገልጻሉ። መቀመጫውን ኖርዌይ ያደረገው የኢራን የሰብዓዊ መብት ቡድን 60 ህጻናትን ጨምሮ በትንሹ 448 ሰዎች መገደላቸውን ገልጿል። ከ18 ሺህ በላይ ሰዎች መታሰራቸውም ተነግሯል። ኢራን ብሔራዊ ቡድን ሽንፈትን በደስታ ለማክብር የመኪናውን ጥሩምባ ሲነፋ የነበረው የ27 ዓመቱ ሜህራን ሳማክ በጸጥታ ሃይሎች መገደሉን የኢራን ሰብዓዊ መብት ሪፖርት አድርጓል። ቢቢሲ ፐርዢያ ረቡዕ ጠዋት የተደረገለትን የቀብር ስነ ስርዓት ቪዲዮ ለመመልከት ችሏል። ሃዘንተኞች “ቆሻሻ ናችሁ፣ ሞራል የላችሁም፣ እኔ ነጻ ሴት ነኝ” የሚሉና በተቃዋሚዎች የሚዘወተሩ መፈክሮችን አሰምተዋል። የኢራን ጸጥታ ኃይሎች ሠላማዊ ተቃዋሚዎችን አልገደልንም ሲሉ ያስተባብላሉ። ሌሎች ቪዲዮዎች ደግሞ ቴህራንን ጨምሮ በተለይም በኩርዲስታን ከተሞች የብሔራዊ ቡድኑን ከዓለም ዋንጫ መሰናበት ደስታቸውን የገለጹ በርካታ ናቸው። በቅርቡ የጸጥታ ሃይሎች በወሰዷቸው እርምጃዎች በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋል። በማህሳ አሚኒ የትውልድ ከተማ ሳቄዝ ስካርፋቸውን በማውለብለብ ደስታቸውን ከመግልጽ ባለፈ ርችትም ሲተኩሱ ታይተዋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c979d3z0e2no
2health
አዲሱ ኮሮናቫይረስ ኦሚክሮን ምን ያህል አሳሳቢ ነው?
የዓለም ጤና ድርጅት ኦሚክሮን ብሎ የሰየመው አዲሱ የኮሮረናቫይረስ ዝርያ እንደ አዲስ ዓለምን ማስጨነቅ ከጀመረ ሰነባብቷል። በርካታ አገራትም ከወዲሁ ስርጭቱን በመስጋት በራቸውን እየዘጉ ይገኛሉ። ኦሚክሮን እራሱን የሚለውጥበትና የሚስፋፋበትን መንገድ የተመለከቱ ተመራማሪዎችም በጣም አስፈሪ እንደሆነ እየገለጹ ነው። ይህ የቫይረስ ዝርያ በብዙ የለውጥ ሂደት ውስጥ ያለፈ ሲሆን ማስረጃዎች ቀደም ሲል ተይዘው የነበሩ ሰዎች በቫይረሱ የመያዝ ምጥኔን እንደሚጨምር ይጠቁማሉ ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። አዲሱ ኦሚክሮን እስካሁን ከ30 በላይ አገራት ውስጥ የተገኘ ሲሆን ሰዎች በክትባትም ሆነ የኮሮረናቫይረስ ሲይዛቸው የሚያዳብሩትን በሽታ የመከላከል አቅም በቀላሉ ማለፍ የሚችል ነው። ነገር ግን ከዚህ በፊት ከነበሩት የኮሮረናቫይረስ አይነቶች አንጻር እስካሁን ቀላል የሚባሉ ምልክቶችን ብቻ ነው ያሳየው። በዚህም ምክንያት ስለ ቫይረሱ፣ ስለ ስርጭቱ እና ስለሚያደርሰው ጉዳት በርካታ መላ ምቶች እየተሰነዘሩ ነው። እስካሁን እኛ የምናውቀውን እናካፍላችሁ ኦሚክሮን እስከዛሬ ከታዩት የኮሮናቫይረስ አይነቶች በሙሉ በፍጥነት እራሱን ማሻሻሻልና መቀየር የቻለው የቫይረስ አይነት ነው። በበርካታ የዘረመል ለውጥ ውስጥ በማለፉ በአንድ ሳይንቲስት "አሰቃቂ" ተብሎ ሲገለጽ ሌላው ደግሞ እስካሁን ከታዩት "የከፋ" ዝርያ ነው ብለዋል። አዲሱ ዝርያ በምን ያህል በፍጥነት እንደሚሰራጭ እና ክትባቶችን በመቋቋም አቅሙ ዙሪያ ያልተመለሱ ጥያቄዎች አሉ። ይህ የዝርያ ለውጥ ቫይረሱን ማሸነፍ ካልቻለ አንድ ታካሚ የመጣ ሳይሆን አይቀርም ተብሏል። አሳሳቢው ነገር ይህ ቫይረስ በቻይና ዉሃን ከተፈጠረው የመጀመሪያው ቫይረስ በእጅጉ የተለየ ነው። ይህም ማለት የመጀመሪያውን ቫይረስ ከግምት በማስገባት የተመረቱት ክትባቶች ለዚህ አዲስ ዝርያ ያን ያህል ውጤታማ ላይሆኑ ይችላሉ። በደቡብ አሜሪካ የሚገኘው የተላላፊ በሽታዎች መካለከያና ምላሽ ሰጪ ማዕከል ዳይሬክተር የሆኑት ፕሮፌሰር ቱሊዮ ዴ ኦሊቬራ እንደሚሉት፣ ኦሚክሮን ከዚህ በፊት ከታዩት ቫይረሶች በሙሉ በተለየ መልኩ እራሱን መቀያያርና እንደ ሁኔታዎች መለዋወጥ የሚችል ነው። "ይህ ዝርያ አስገርሞናል። ለውጡ በከፍተኛ ሁኔታ የተካሄደ ሲሆን ከምንጠብቀው ብዙ ለውጥ አለው" ብለዋል። ፕሮፌሰር ዴ ኦሊቬራ አክለውም አዲሱ ቫይረስ በአጠቃላይ 50 የዘረ መል ለውጦች አሉት። የብዙዎቹ ክትባቶች ዒላማ ከሆነው ከስፔክ ፕሮቲን ከ30 በላይ ለውጥ ታይቷል። ይህም ቫይረሱ ወደ ሰውነታችን ህዋሳት መግቢያ በር ለመክፈት የሚጠቀምበት ቁልፍ ነው። ቫይረሱ ከሰውነታችን ህዋሳት ጋር የመጀመሪያ ግንኙነት ሲያደርግ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰው ዴልታ ዝርያ ሁለት ሲሆን አዲሱ ዝርያ ደግሞ 10 እጥፍ ለውጥ አለው። ባለሙያዎች እንደሚሉት ይህ የዝርያ ለውጥ ቫይረሱን ማሸነፍ ካልቻለ አንድ ታካሚ የመጣ ሳይሆን አይቀርም። አሳሳቢው ነገር ይህ ቫይረስ በቻይና ዉሃን ከተፈጠረው የመጀመሪያ ቫይረስ በእጅጉ የተለየ መሆኑ ነው። ይህም ማለት የመጀመሪያውን ቫይረስ ከግምት በማስገባት የተመረቱት ክትባቶች ለዚህ አዲስ ዝርያ ያን ያህል ውጤታማ ላይሆኑ ይችላሉ። አንዳንዶቹ ለውጦች በሌሎች ዝርያዎች ውስጥ ከዚህ ቀደም ታይተዋል። ይህም በዚህ ለውጥ ውስጥ ያለውን ሚና የተወሰነ ግንዛቤ ይሰጣል። ለምሳሌ ኤን501ዋይ የኮሮናቫይረስ መስፋፋትን ቀላል የሚያደርግ ይመስላል። የሰውነት የበሽታ መከላከያ ቫይረሱን እንዳያውቁ የሚያከብዱበት እና ክትባቶች ውጤታማ እንዳይሆኑ የሚያደርጉ ሌሎች ዝርያዎች አሉ። በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ተመራማሪዎች ቀደም ብለው እንደገለጹት ኦሚክሮን የሰውነታችንን በሽታ የመከላከል አቅም በቀላሉ ማለፍ ይችላል። በደቡብ አፍሪካ የኩዋዙሉ-ናታል ዩኒቨርሲቲ ባልደረባ የሆኑት ፕሮፌሰር ሪቻርድ ሌሰልስ "ይህ ቫይረስ የመተላለፍ ችሎታውን ከፍ አድርጎ ከሰው ወደ ሰው ከመተላለፍ ባለፈ የበሽታ ተከላካይ ክፍሎችን ማካለል ይችላል የሚል ስጋት አሳድሮብናል" ብለዋል። በወረቀት ላይ አስፈሪ የሚመስሉ ነገር ግን ጉዳት ያላደረሱ ብዙ የዝርያ ምሳሌዎች ነበሩ። በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት መጀመሪያ ላይ የቤታ ዝርያ የበሽታ መከላከል ሥርዓትን ሊያመልጥ ይችላል በሚል በሰዎች ዘንድ ስጋት ፈጥሮ ነበር። በደቡብ አፍሪካ ኦሚክሮን በእጅጉ እየተስፋፋ እንደሆነ እየተነገረ ነው። ባሳለፍነው ወር አጋማሽ አካባቢ በየቀኑ እስከ 250 የሚደርሱ አዳዲስ ሰዎች በቫይረሱ እየተያዙ ነበር። ሌሎች የኮሮረናቫይረስ አይነቶች እያስቸገሯት በምትገኘው ደቡብ አፍሪካ አሁን ላይ በኦሚክሮን የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በቀን እስከ 8 ሺህ ይደርሳል። አሁን ላይ ሰዎች ስለአዲሱ ቫይረሰ አይነት ያላቸው እውቀት ውስን ነው። በዚህም ምክንያት ተመራማሪዎችም ሆነ ሌሎች ሰዎች አዲሱን ቫይረስ በንቃት ሊከታተሉትና አካሄዱን በደንብ ሊያውቁት ይገባል። በተለይ የዘርፉ ተመራማሪዎች በዚህ ዙሪያ በርካታ ሥራዎች ይጠብቋቸዋል። ከኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ የተማርነው አንድ ነገር ቢኖር፤ ለጥያቄዎቻችን በሙሉ መልስ እስከምናገኝ ድረስ ዝም ብለን መቀመጥና መጠበቅ እንደሌለብን ነው።
አዲሱ ኮሮናቫይረስ ኦሚክሮን ምን ያህል አሳሳቢ ነው? የዓለም ጤና ድርጅት ኦሚክሮን ብሎ የሰየመው አዲሱ የኮሮረናቫይረስ ዝርያ እንደ አዲስ ዓለምን ማስጨነቅ ከጀመረ ሰነባብቷል። በርካታ አገራትም ከወዲሁ ስርጭቱን በመስጋት በራቸውን እየዘጉ ይገኛሉ። ኦሚክሮን እራሱን የሚለውጥበትና የሚስፋፋበትን መንገድ የተመለከቱ ተመራማሪዎችም በጣም አስፈሪ እንደሆነ እየገለጹ ነው። ይህ የቫይረስ ዝርያ በብዙ የለውጥ ሂደት ውስጥ ያለፈ ሲሆን ማስረጃዎች ቀደም ሲል ተይዘው የነበሩ ሰዎች በቫይረሱ የመያዝ ምጥኔን እንደሚጨምር ይጠቁማሉ ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። አዲሱ ኦሚክሮን እስካሁን ከ30 በላይ አገራት ውስጥ የተገኘ ሲሆን ሰዎች በክትባትም ሆነ የኮሮረናቫይረስ ሲይዛቸው የሚያዳብሩትን በሽታ የመከላከል አቅም በቀላሉ ማለፍ የሚችል ነው። ነገር ግን ከዚህ በፊት ከነበሩት የኮሮረናቫይረስ አይነቶች አንጻር እስካሁን ቀላል የሚባሉ ምልክቶችን ብቻ ነው ያሳየው። በዚህም ምክንያት ስለ ቫይረሱ፣ ስለ ስርጭቱ እና ስለሚያደርሰው ጉዳት በርካታ መላ ምቶች እየተሰነዘሩ ነው። እስካሁን እኛ የምናውቀውን እናካፍላችሁ ኦሚክሮን እስከዛሬ ከታዩት የኮሮናቫይረስ አይነቶች በሙሉ በፍጥነት እራሱን ማሻሻሻልና መቀየር የቻለው የቫይረስ አይነት ነው። በበርካታ የዘረመል ለውጥ ውስጥ በማለፉ በአንድ ሳይንቲስት "አሰቃቂ" ተብሎ ሲገለጽ ሌላው ደግሞ እስካሁን ከታዩት "የከፋ" ዝርያ ነው ብለዋል። አዲሱ ዝርያ በምን ያህል በፍጥነት እንደሚሰራጭ እና ክትባቶችን በመቋቋም አቅሙ ዙሪያ ያልተመለሱ ጥያቄዎች አሉ። ይህ የዝርያ ለውጥ ቫይረሱን ማሸነፍ ካልቻለ አንድ ታካሚ የመጣ ሳይሆን አይቀርም ተብሏል። አሳሳቢው ነገር ይህ ቫይረስ በቻይና ዉሃን ከተፈጠረው የመጀመሪያው ቫይረስ በእጅጉ የተለየ ነው። ይህም ማለት የመጀመሪያውን ቫይረስ ከግምት በማስገባት የተመረቱት ክትባቶች ለዚህ አዲስ ዝርያ ያን ያህል ውጤታማ ላይሆኑ ይችላሉ። በደቡብ አሜሪካ የሚገኘው የተላላፊ በሽታዎች መካለከያና ምላሽ ሰጪ ማዕከል ዳይሬክተር የሆኑት ፕሮፌሰር ቱሊዮ ዴ ኦሊቬራ እንደሚሉት፣ ኦሚክሮን ከዚህ በፊት ከታዩት ቫይረሶች በሙሉ በተለየ መልኩ እራሱን መቀያያርና እንደ ሁኔታዎች መለዋወጥ የሚችል ነው። "ይህ ዝርያ አስገርሞናል። ለውጡ በከፍተኛ ሁኔታ የተካሄደ ሲሆን ከምንጠብቀው ብዙ ለውጥ አለው" ብለዋል። ፕሮፌሰር ዴ ኦሊቬራ አክለውም አዲሱ ቫይረስ በአጠቃላይ 50 የዘረ መል ለውጦች አሉት። የብዙዎቹ ክትባቶች ዒላማ ከሆነው ከስፔክ ፕሮቲን ከ30 በላይ ለውጥ ታይቷል። ይህም ቫይረሱ ወደ ሰውነታችን ህዋሳት መግቢያ በር ለመክፈት የሚጠቀምበት ቁልፍ ነው። ቫይረሱ ከሰውነታችን ህዋሳት ጋር የመጀመሪያ ግንኙነት ሲያደርግ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰው ዴልታ ዝርያ ሁለት ሲሆን አዲሱ ዝርያ ደግሞ 10 እጥፍ ለውጥ አለው። ባለሙያዎች እንደሚሉት ይህ የዝርያ ለውጥ ቫይረሱን ማሸነፍ ካልቻለ አንድ ታካሚ የመጣ ሳይሆን አይቀርም። አሳሳቢው ነገር ይህ ቫይረስ በቻይና ዉሃን ከተፈጠረው የመጀመሪያ ቫይረስ በእጅጉ የተለየ መሆኑ ነው። ይህም ማለት የመጀመሪያውን ቫይረስ ከግምት በማስገባት የተመረቱት ክትባቶች ለዚህ አዲስ ዝርያ ያን ያህል ውጤታማ ላይሆኑ ይችላሉ። አንዳንዶቹ ለውጦች በሌሎች ዝርያዎች ውስጥ ከዚህ ቀደም ታይተዋል። ይህም በዚህ ለውጥ ውስጥ ያለውን ሚና የተወሰነ ግንዛቤ ይሰጣል። ለምሳሌ ኤን501ዋይ የኮሮናቫይረስ መስፋፋትን ቀላል የሚያደርግ ይመስላል። የሰውነት የበሽታ መከላከያ ቫይረሱን እንዳያውቁ የሚያከብዱበት እና ክትባቶች ውጤታማ እንዳይሆኑ የሚያደርጉ ሌሎች ዝርያዎች አሉ። በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ተመራማሪዎች ቀደም ብለው እንደገለጹት ኦሚክሮን የሰውነታችንን በሽታ የመከላከል አቅም በቀላሉ ማለፍ ይችላል። በደቡብ አፍሪካ የኩዋዙሉ-ናታል ዩኒቨርሲቲ ባልደረባ የሆኑት ፕሮፌሰር ሪቻርድ ሌሰልስ "ይህ ቫይረስ የመተላለፍ ችሎታውን ከፍ አድርጎ ከሰው ወደ ሰው ከመተላለፍ ባለፈ የበሽታ ተከላካይ ክፍሎችን ማካለል ይችላል የሚል ስጋት አሳድሮብናል" ብለዋል። በወረቀት ላይ አስፈሪ የሚመስሉ ነገር ግን ጉዳት ያላደረሱ ብዙ የዝርያ ምሳሌዎች ነበሩ። በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት መጀመሪያ ላይ የቤታ ዝርያ የበሽታ መከላከል ሥርዓትን ሊያመልጥ ይችላል በሚል በሰዎች ዘንድ ስጋት ፈጥሮ ነበር። በደቡብ አፍሪካ ኦሚክሮን በእጅጉ እየተስፋፋ እንደሆነ እየተነገረ ነው። ባሳለፍነው ወር አጋማሽ አካባቢ በየቀኑ እስከ 250 የሚደርሱ አዳዲስ ሰዎች በቫይረሱ እየተያዙ ነበር። ሌሎች የኮሮረናቫይረስ አይነቶች እያስቸገሯት በምትገኘው ደቡብ አፍሪካ አሁን ላይ በኦሚክሮን የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በቀን እስከ 8 ሺህ ይደርሳል። አሁን ላይ ሰዎች ስለአዲሱ ቫይረሰ አይነት ያላቸው እውቀት ውስን ነው። በዚህም ምክንያት ተመራማሪዎችም ሆነ ሌሎች ሰዎች አዲሱን ቫይረስ በንቃት ሊከታተሉትና አካሄዱን በደንብ ሊያውቁት ይገባል። በተለይ የዘርፉ ተመራማሪዎች በዚህ ዙሪያ በርካታ ሥራዎች ይጠብቋቸዋል። ከኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ የተማርነው አንድ ነገር ቢኖር፤ ለጥያቄዎቻችን በሙሉ መልስ እስከምናገኝ ድረስ ዝም ብለን መቀመጥና መጠበቅ እንደሌለብን ነው።
https://www.bbc.com/amharic/news-59594592
3politics
የኢትዮጵያ መንግሥት በሱዳን ያለውን ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለ እንደሆነ አስታወቀ
የኢትዮጵያ መንግሥት በሱዳን የተፈጠረውን ቀውስ በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታወቀ። የኢትዮጵያ መንግሥት በሱዳን የሽግግር መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት በወታደሮች ቁጥጥር ስር ውለው በአገሪቱ ተቃውሞ መቀስቀሱን ተከትሎ ጄነራል አል ቡርሐን አስቸኳይ ጊዜ ማወጃቸውን ተከትሎ ነው መግለጫውን ያወጣው። በሱዳን በተካሄደው መፈንቅለ መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክና ሚኒስትሮቻቸው በወታደሮች የተያዙ ሲሆን የአገሪቱ የሽግግር ምክር ቤት ተበትኗል። ሚኒስቴሩ በመግለጫው የኢትዮጵያ መንግሥት እንደ ከዚህ ቀደሙ ከሱዳን ሕዝብ ጎን እንደሚቆም ገልጿል። ይህም የሁለቱ አገራት ሕዝቦች ለዘመናት ካላቸው ጠንካራ ትስስር የመነጨ ነው ብሏል። በሱዳን ሲቪልና ወታደራዊ አባላትን ያካተተ የጥምር መንግሥት እንዲመሰረት እንዲሁም ለሽግግር ጊዜ የሚሆን ሕገ መንግሥታዊ ሰነድ በማዘጋጀት የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ሚና እንደነበረው መግለጫው አስታውሷል። በመሆኑም ሁሉም ወገኖች በመረጋጋት እና ሁኔታዎችን በማርገብ የተፈጠረው ቀውስ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ የተቻላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል። መግለጫው አክሎም የኢትዮጵያ መንግሥት ሱዳን ወደ ዲሞክራሲ የምታደርገውን ሽግግር እንደሚደግፍ እንዲሁም ለሽግግር ጊዜ ያለውን ሕገ መንግሥታዊ ሰነድ እንደሚያከብር ገልጿል። ኢትዮጵያ የሱዳን ሕዝብ የሚፈልገውን ሉዓላዊነት እንዲከበር ፍላጎት እንዳላት የገለፀች ሲሆን በሱዳን የውስጥ ጉዳይ የውጭ ኃይሎች ጣልቃ አለመግባታቸው አስፈላጊ እንደሆነ አፅንኦት ሰጥታለች። የኢትዮጵያ መንግሥት የሱዳን ሕዝብ የገጠመውን ተግዳሮት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት አቅሙ እንዳለው እምነት እንዳለውም ገልጿል። የሱዳን ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፍላጎት እንዲሟላ የኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ እንደ ከዚህ ቀደሙ ከጎናቸው እንደሚቆሙም መግለጫው አስታውቋል። በሱዳን በወታደሮችና በሲቪሎች የሚመራ የሽግግር መንግሥት እንዲቋቋም እና አገሪቱ እንድትረጋጋ ኢትዮጵያ በተለይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል። ባለፈው ዓመት ጥቅምት ወር ላይ የሱዳን ሠራዊት በኢትዮጵያውያን አርሶ አደሮች ተይዘው የነበሩትን የድንበር አካባቢዎች ወሮ ከያዘ በኋላ በሁለቱ አገራት መካከል ያለው ግንኙነት ሻክሮ ቆይቷል። በሕዳሴው ግድብ ግንባታ እና ውሃ ሙሌት ዙሪያ በቆየው አለመግባባትም ሁለቱ አገራት ሲወቃቀሱ መቆየታቸው ይታወሳል። ባለፈው መስከረም ወር በጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ላይ መፈንቅለ መንግሥት ተሞክሮ መክሸፉ የሚታወስ ሲሆን፣ ይህንንም ተከትሎ የሽግግር አስተዳደሩን በሚመራው ሉአላዊ ምክር ቤት አባላት መካከል ከፍተኛ ውጥረት ነግሶ ቆይቷል። ዛሬ ሰኞ ጠዋት የአገሪቱ ጦር ሠራዊት የሽግግር መንግሥቱን ጠቅላይ ሚኒስትርና ሲቪል አባላትን በቁጥጥር ስር በማድረግ አስተዳደሩን የበተነ ሲሆን የአስቸኳይ ጊዜ አውጇል። አገሪቱን ለረጅም ዓመታት በበላይነት የመሩት ኦማር ሐሰን አል ባሽር ከሥልጣን መወገዳቸውን ተከትሎ ከሁለት ዓመት በፊት በአገሪቱ ሠራዊት፣ በሲቪሎች እና ተቃውሞውን በመሩት ቡድኖች መካከል የሥልጣን ክፍፍል መደረጉ ይታወሳል።
የኢትዮጵያ መንግሥት በሱዳን ያለውን ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለ እንደሆነ አስታወቀ የኢትዮጵያ መንግሥት በሱዳን የተፈጠረውን ቀውስ በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታወቀ። የኢትዮጵያ መንግሥት በሱዳን የሽግግር መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት በወታደሮች ቁጥጥር ስር ውለው በአገሪቱ ተቃውሞ መቀስቀሱን ተከትሎ ጄነራል አል ቡርሐን አስቸኳይ ጊዜ ማወጃቸውን ተከትሎ ነው መግለጫውን ያወጣው። በሱዳን በተካሄደው መፈንቅለ መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክና ሚኒስትሮቻቸው በወታደሮች የተያዙ ሲሆን የአገሪቱ የሽግግር ምክር ቤት ተበትኗል። ሚኒስቴሩ በመግለጫው የኢትዮጵያ መንግሥት እንደ ከዚህ ቀደሙ ከሱዳን ሕዝብ ጎን እንደሚቆም ገልጿል። ይህም የሁለቱ አገራት ሕዝቦች ለዘመናት ካላቸው ጠንካራ ትስስር የመነጨ ነው ብሏል። በሱዳን ሲቪልና ወታደራዊ አባላትን ያካተተ የጥምር መንግሥት እንዲመሰረት እንዲሁም ለሽግግር ጊዜ የሚሆን ሕገ መንግሥታዊ ሰነድ በማዘጋጀት የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ሚና እንደነበረው መግለጫው አስታውሷል። በመሆኑም ሁሉም ወገኖች በመረጋጋት እና ሁኔታዎችን በማርገብ የተፈጠረው ቀውስ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ የተቻላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል። መግለጫው አክሎም የኢትዮጵያ መንግሥት ሱዳን ወደ ዲሞክራሲ የምታደርገውን ሽግግር እንደሚደግፍ እንዲሁም ለሽግግር ጊዜ ያለውን ሕገ መንግሥታዊ ሰነድ እንደሚያከብር ገልጿል። ኢትዮጵያ የሱዳን ሕዝብ የሚፈልገውን ሉዓላዊነት እንዲከበር ፍላጎት እንዳላት የገለፀች ሲሆን በሱዳን የውስጥ ጉዳይ የውጭ ኃይሎች ጣልቃ አለመግባታቸው አስፈላጊ እንደሆነ አፅንኦት ሰጥታለች። የኢትዮጵያ መንግሥት የሱዳን ሕዝብ የገጠመውን ተግዳሮት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት አቅሙ እንዳለው እምነት እንዳለውም ገልጿል። የሱዳን ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፍላጎት እንዲሟላ የኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ እንደ ከዚህ ቀደሙ ከጎናቸው እንደሚቆሙም መግለጫው አስታውቋል። በሱዳን በወታደሮችና በሲቪሎች የሚመራ የሽግግር መንግሥት እንዲቋቋም እና አገሪቱ እንድትረጋጋ ኢትዮጵያ በተለይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል። ባለፈው ዓመት ጥቅምት ወር ላይ የሱዳን ሠራዊት በኢትዮጵያውያን አርሶ አደሮች ተይዘው የነበሩትን የድንበር አካባቢዎች ወሮ ከያዘ በኋላ በሁለቱ አገራት መካከል ያለው ግንኙነት ሻክሮ ቆይቷል። በሕዳሴው ግድብ ግንባታ እና ውሃ ሙሌት ዙሪያ በቆየው አለመግባባትም ሁለቱ አገራት ሲወቃቀሱ መቆየታቸው ይታወሳል። ባለፈው መስከረም ወር በጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ላይ መፈንቅለ መንግሥት ተሞክሮ መክሸፉ የሚታወስ ሲሆን፣ ይህንንም ተከትሎ የሽግግር አስተዳደሩን በሚመራው ሉአላዊ ምክር ቤት አባላት መካከል ከፍተኛ ውጥረት ነግሶ ቆይቷል። ዛሬ ሰኞ ጠዋት የአገሪቱ ጦር ሠራዊት የሽግግር መንግሥቱን ጠቅላይ ሚኒስትርና ሲቪል አባላትን በቁጥጥር ስር በማድረግ አስተዳደሩን የበተነ ሲሆን የአስቸኳይ ጊዜ አውጇል። አገሪቱን ለረጅም ዓመታት በበላይነት የመሩት ኦማር ሐሰን አል ባሽር ከሥልጣን መወገዳቸውን ተከትሎ ከሁለት ዓመት በፊት በአገሪቱ ሠራዊት፣ በሲቪሎች እና ተቃውሞውን በመሩት ቡድኖች መካከል የሥልጣን ክፍፍል መደረጉ ይታወሳል።
https://www.bbc.com/amharic/news-59042599
3politics
በግብፅ የተገኙት የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወደ ኢትዮጵያ ሊጓዙ ነው
ከዩክሬን ጋር ጦርነት ውስጥ የምትገኘው የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ የአፍሪካ ጉብኝታቸውን በግብፅ ጀመሩ። ላቭሮቭ ከግብፅ ጉብኝት በኋላ ወደ ኮንጎ ብራዛቪል አቅርንተዋል። በማስከተልም ወደ ኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ እንደሚጓዙ ተገልጿል። ጉዟቸውን በካይሮ የጀመሩት ላቭሮቭ ከግብፁ አቻቸው ሳሚ ሹኩሪ ጋር ተገናኝተው የተነጋገሩ ሲሆን፤ ሩሲያ ለግብፅ የምታቀርበውን ስንዴ አጠናክራ እንደምትቀጥል ተናግረዋል። ሩሲያ በዩክሬን ላይ በከፈተችው ጦርነት የአረቡ ዓለም አገራት እና አፍሪካ በእህል አቅርቦት እጥረት ክፉኛ ተጎድተዋል። በግብፅ ለአረብ ሊግ አምባሳደሮች ንግግር ያደረጉት ላቭሮብ፣ በአገራቸው ላይ የተጣለው ማዕቀብ በዓለም የምግብ ዋስትና ላይ እያሳደረ ስላለው ተጽእኖ የምዕራባውያን አገራት እውነታውን እያጣመሙ ነው ብለዋል። "ምዕራባውያን አገራት የበላይነታቸውን በሌሎች ላይ ለመጫን እየሞከሩ ነው" ሲሉም ከሰዋል። እንዲሁም ሞስኮ የዓለምን የምግብ ቀውስ አስከትላለች የሚለውን ወቀሳ አጣጥለውታል። ምዕራባዊያኑ በሩሲያ ላይ እያደረሱ ያሉትን ዲፕሎማሲያዊ ጫናን ለመመከት ወደ አፍሪካ ጉዞ ማድረግ የጀመሩት ላቭሮቭ፤ ጨምረውም በአገራቸው ላይ የጣሏቸው ማዕቀቦች ዓላማቸው "ስለ ዩክሬን ሳይሆን ወደፊት ዓለምን ስለመቆጣጠር ነው" ሲሉ ተናግረዋል። \n\n"እያንዳንዱ ሰው ሕግን መሠረት ያደረገ የዓለም ሥርዓትን መደገፍ አለበት'' ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፤ ሕጎቹም የተፃፉት የምዕራባውያንን ፍላጎት በሚጠቅም መልኩ እና ልዩ ሁኔታዎች ላይ በመመስረት ነው ብለዋል። ዩክሬን እና ሩሲያ ከ40 በመቶ በላይ የሚሆነውን የአፍሪካን ስንዴ ፍላጎት እንደሚያቀርቡ የአፍሪካ ልማት ባንክ መረጃ ያሳያል።\n\nግብፅ ከፍተኛ የዩክሬን ስንዴ ተጠቃሚ ስትሆን እ.ኤ.አ. በ2019 ከማንኛውም አገር በበለጠ 3.62 ሚሊዮን ቶን ስንዴ ከዩክሬን ገዝታለች።
በግብፅ የተገኙት የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወደ ኢትዮጵያ ሊጓዙ ነው ከዩክሬን ጋር ጦርነት ውስጥ የምትገኘው የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ የአፍሪካ ጉብኝታቸውን በግብፅ ጀመሩ። ላቭሮቭ ከግብፅ ጉብኝት በኋላ ወደ ኮንጎ ብራዛቪል አቅርንተዋል። በማስከተልም ወደ ኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ እንደሚጓዙ ተገልጿል። ጉዟቸውን በካይሮ የጀመሩት ላቭሮቭ ከግብፁ አቻቸው ሳሚ ሹኩሪ ጋር ተገናኝተው የተነጋገሩ ሲሆን፤ ሩሲያ ለግብፅ የምታቀርበውን ስንዴ አጠናክራ እንደምትቀጥል ተናግረዋል። ሩሲያ በዩክሬን ላይ በከፈተችው ጦርነት የአረቡ ዓለም አገራት እና አፍሪካ በእህል አቅርቦት እጥረት ክፉኛ ተጎድተዋል። በግብፅ ለአረብ ሊግ አምባሳደሮች ንግግር ያደረጉት ላቭሮብ፣ በአገራቸው ላይ የተጣለው ማዕቀብ በዓለም የምግብ ዋስትና ላይ እያሳደረ ስላለው ተጽእኖ የምዕራባውያን አገራት እውነታውን እያጣመሙ ነው ብለዋል። "ምዕራባውያን አገራት የበላይነታቸውን በሌሎች ላይ ለመጫን እየሞከሩ ነው" ሲሉም ከሰዋል። እንዲሁም ሞስኮ የዓለምን የምግብ ቀውስ አስከትላለች የሚለውን ወቀሳ አጣጥለውታል። ምዕራባዊያኑ በሩሲያ ላይ እያደረሱ ያሉትን ዲፕሎማሲያዊ ጫናን ለመመከት ወደ አፍሪካ ጉዞ ማድረግ የጀመሩት ላቭሮቭ፤ ጨምረውም በአገራቸው ላይ የጣሏቸው ማዕቀቦች ዓላማቸው "ስለ ዩክሬን ሳይሆን ወደፊት ዓለምን ስለመቆጣጠር ነው" ሲሉ ተናግረዋል። \n\n"እያንዳንዱ ሰው ሕግን መሠረት ያደረገ የዓለም ሥርዓትን መደገፍ አለበት'' ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፤ ሕጎቹም የተፃፉት የምዕራባውያንን ፍላጎት በሚጠቅም መልኩ እና ልዩ ሁኔታዎች ላይ በመመስረት ነው ብለዋል። ዩክሬን እና ሩሲያ ከ40 በመቶ በላይ የሚሆነውን የአፍሪካን ስንዴ ፍላጎት እንደሚያቀርቡ የአፍሪካ ልማት ባንክ መረጃ ያሳያል።\n\nግብፅ ከፍተኛ የዩክሬን ስንዴ ተጠቃሚ ስትሆን እ.ኤ.አ. በ2019 ከማንኛውም አገር በበለጠ 3.62 ሚሊዮን ቶን ስንዴ ከዩክሬን ገዝታለች።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cyd43de07jzo
0business
ኢትዮጵያ ስንዴ ከውጭ ማስገባት ትታ ወደ ውጭ መላክ ትችላለች?
በምሥራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት አቶ መምሬ መሠረት፣ ከዚህ በፊት ስንዴ ያመርቱ የነበረው በክረምት ዝናብ ብቻ ተጠቅመው ነበር። ማሳቸው ውሃ የሚገባው በመሆኑ በበጋው ወራት ሽንኩርት እና ቲማቲም እያመረቱ ለገበያ ያቀርቡ እንደነበረም ለቢቢሲ ገልፀዋል። ከሦስት ዓመት በፊት ግን ‘ለምን አዲስ ነገር አልጀምርም’ በማለት በበጋ መስኖ ስንዴ ዘርተው ለማየት ወሰኑ። “ይህ ነገር መሆን አለበት ብዬ በራሴ ተነሳሽነት የበጋ ስንዴ ማምረት ጀመርኩ። በዚያን ወቅት አንድም ሰው በበጋ ስንዴ መዝራት የጀመረ የለም። ፈጣሪ ይመስገን ተሳክቶልኛል” ይላሉ አቶ መምሬ። ይህ የበጋ ስንዴ ምርት ከዓመት ወደ ዓመት እየጨመረ እና እየሰፋ እየመጣ መሆኑን አቶ መምሬ አክለው ተናግረዋል። ልክ እንደ አቶ መምሬ ሁሉ የሉሜ ወረዳው አርሶ አደር አቶ እንግዳ ብሩ፣ በበጋ መስኖ ተጠቅመው ጥሩ የስንዴ ምርት እንዳገኙ ይገልጻሉ። እኚህ አርሶ አደር በዚህ ዓመት ብቻ ከስድስት ሄክታር መሬት 320 ኩንታል ስንዴ ማግኘታቸውን ጠቅሰው፣ አዲስ ነገር ስለሆነ በፍርሃት እንደጀመሩት በመግለጽ አቶ እንግዳ “ያገኘነው ምርት ሸጋ ነው”  ብለዋል። ይህ የበጋ ስንዴ ከክረምቱ ወቅት ምርት በላይ ትርፋማ እንደሆነ የሚናገሩት አቶ እንግዳ ግሪሳ (የወፍ መንጋ)፣ የማዳበሪያ ወጪ እና ነዳጅ መፍትሔ ቢያገኝ ስንዴን በበጋ ማምረት “በጣም ትርፋማ” መሆኑን ገልፀዋል። በመጀመሪያ የምርት ዓመት በአንድ ሄክታር ላይ ብቻ ስንዴ ዘርተው የነበሩት አቶ መምሬ፣ መንግሥት ያቀረበላቸውን ድጋፍ በማየት በዚህ ዓመት ወደ 5 ተኩል ሔክታር አሳድገውታል። የበጋ ስንዴ በክረምት ወቅት ከሚመረተው በተሻለ ምርታማ እንደሆነ የሚናገሩት አርሶ አደሩ፣ ከአንድ ቀርጥ (የሄክታር አንድ አራተኛ) ከ16 ኩንታል በላይ ማግኘት እንደሚቻል ይናገራሉ። አቶ መምሬ እንደሚሉት ከአንድ ሄክታር እስከ 64 ኩንታል ይገኛል። ሽንኩርት እና ቲማቲም ማምረት አቁመው ወደ ስንዴ በመግባታቸው ያለውን ልዩነት ሲገልጹ “ይህ የበጋ ስንዴ ምርት ሥራው አድካሚ አይደለም። ትንሽ ማዳበርያ ብቻ ይፈልጋል እንጂ ሌሎች ብዙ ወጪዎች ስለሌሉበት ትርፋማ ነው” ብለዋል። አቶ መምሬ ካገኙት የበጋ ስንዴ ምርት 250 ኩንታል ያህሉን መንግሥት በጥሩ ዋጋ (በኩንታል 3680) እንደተረከባቸው ጨምረው አስረድተዋል። እንደ አሜሪካ ግብርና ቢሮ መረጃ ከሆነ በኢትዮጵያ የስንዴ ምርት ዘርፍ ትልቅ እመርታ እያሳየ እና ምርታማነቱ እየጨመረ ነው። የአሜሪካ የውጭ ግብርና ቢሮ ሪፖርት ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2022/2023 ዓመት ውስጥ 5.7 ሚሊዮን ቶን ስንዴ ታመርታለች ተብሎ እንደሚጠበቅ አመልክቷል። ይህም ካለፈው የምርት ዘመን በ3.26 በመቶ ከፍ ያለ ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት ባለፉት ሦስት ዓመታት የስንዴ ምርት እንዲጨመር በርካታ ድጋፎችን እያደረገ መሆኑን ያስታወሰው ይህ ሪፖርት፤ የኤክስቴንሽን ድጋፍ፣ የመስኖ ልማት፣ በዘመናዊ መሳሪያ የታገዘ የእርሻ ሥርዓት እንዲሁም ሌሎች ግብዓቶች እንደሚያቀርብም ዘርዝሯል። ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት 70 በመቶ ያህል የአገር ውስጥ ፍላጎቷን የምታመርት ሲሆን፣ 30 በመቶ ያህሉን ደግሞ ከውጭ እንደምታስገባ መረጃዎች ያመለክታሉ። ከውጭ ከምታስገባው የተወሰነውን ስንዴ የውጭ ምንዛሬ በማውጣት የምትገዛ ሲሆን፣ ቀሪውን ደግሞ ከአሜሪካ በእርዳታ እንደምታገኝ የአሜሪካ የውጭ ግብርና ምርት ቢሮ መረጃ ያሳያል። ኢትዮጵያ በ2023 (እኤአ) ያላትን የስንዴ ፍላጎት በአገር ውስጥ ምርት ለሟሟላት እና ከባሕር ማዶ የምታስገባውን ለማስቀረት አቅዳ እየሰራች መሆኑ በተደጋጋሚ ሲገለጽ ቆይቷል። ይህንንም ለማሳካት በመላ አገሪቱ ባለፉት ሦስት ዓመታት 1.3 ሚሊዮን አርሶ አደሮች በ30 ሺህ ክላስተር ተደራጅተዋል። እያንዳንዱ ክላስተርም የተሻሻለ ዘር እንዲሁም ለአካባቢው ተስማሚ የሆነ ማዳበርያ እንዲጠቀም ይደረጋል። እንዲሁም የኤክስቴንሽን ሠራተኞች ክትትል እና ድጋፍ በምርት ስብሰባ ወቅትም ብክነት ለመቀነስ የማሽን ድጋፍ ተደርጓል። በኦሮሚያ ግብርና ቢሮ የስንዴ ምርት ጉዳይን የሚከታተሉት ኃላፊ አቶ ጌቱ ገመቹ፣ ክልሉ በስንዴ ምርት ላይ ዕቅድ አውጥቶ እየሰራ መሆኑን ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቶ ጌቱ ገመቹ በበኩላቸው የስንዴ ምርትን ለመጨመር የተያዙትን አራት መሠረታዊ እቅዶች ሲያብራሩ “በምግብ ራስን መቻል፤ ከውጭ የሚገባውን ምርት በአገር ውስጥ ማምረት፣ በአገር ውስጥ የሚመረተውን ደግሞ ወደ ውጪ መላክ እና በእነዚህ ውስጥ የሥራ ዕድል መፍጠር” መሆናቸውን ገልፀዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ ካለፉት ሦስት ዓመታት ጀምሮ እየተሰራ መሆኑን የሚናገሩት ኃላፊው፣ በመጀመሪያው ዓመት ላይ ከምርምር ተቋማት ጋር በመሆን ውጤታማነቱን በምርምር ለማረጋገጥ ተችሏል ይላሉ። ግንቦት 2022 እኤአ የቡድን ሰባት አገራት ሚኒስትሮች በጀርመን ባካሄዱት ስብሰባ ላይ የተገኙት የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት፣ አክንዊሚ አዲሲና ኢትዮጵያ ከዚህ በኋላ ስንዴ ከውጪ እንደማታስገባ ተናግረዋል። የአፍሪካ ልማት ባንክ ለአፍሪካ በሚያቀርበው የግብርና ቴክኖሎጂ ፕሮግራም አማካኝነት የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋሙ የቴክኖሎጂ ድጋፍ ለኢትዮጵያ አድርጓል። በዚህም የተነሳ ኢትዮጵያ በዚህ ዓመት ምርት በመጨመሯ በዓመት 26 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ምርቷ ማደግ ችሏል ብለዋል። ካለፈው ዓመት ጀመሮ ኢትዮጵያ ከውጭ አለማስገባቷን የሚናገሩት ፕሬዝዳንቱ፣ ለሚቀጥለው ዓመት በ2 ሚሊዮን ሄክታር ላይ ለማምረት ዕቅድ ስላላት ይህንን ምርት በ2023 ለጎረቤት አገራት ጅቡቲ እና ኬንያ ለመሸጥ ማሰቧን ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሕዝብ ተወካዮች በበጋ ስንዴ ከፍተኛ ምርት መገኘቱን ገልፀው ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህ የስንዴ ምርት እንዴት እንደተገኘ ሲያብራሩ መስኖ እንዲሁም የክላስተር ግብርናን በአስረጂነት ጠቅሰዋል። ምንም እንኳ ኢትዮጵያ የምታመርተውን ስንዴ ብትጨምርም በአገሪቱ ውስጥ በተከሰቱ የተለያዩ ግጭቶች የተነሳ ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለው የዕለት እርዳታ የሚጠብቁ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ ነው። እንዲሁም ለ19 ወራት የቀጠለውን የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የምግብ እህል እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ቁጥርን ከፍተኛ አድርጎታል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን መረጃ እንደሚያሳየው በ2022/2023 ብቻ 10 ሚሊዮን ያህል ሰዎች የዕለት እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። በዚህም የተነሳ ኢትዮጵያ ከውጭ የምታስገባውን ስንዴ አቁማ ወደ ውጭ መላክ ለመጀመር የያዘችው ዕቅድ አጣብቂኝ ውስጥ ሊወድቅ ይችላል የሚል ስጋት አጭሯል። ኢትዮጵያ እኤአ በ2023 ከባሕር ማዶ የምታስገባውን ስንዴ ለማቆም ማቀዷን ያስታወሰው የአሜሪካ ግብርና ቢሮ ሪፖርት በበኩሉ ባለው ውስን ሀብት እና ቴክኖሎጂ አንዲሁም በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማሳካት ያለውን ተግዳሮት ሲገልጽ “ከተጨባጭ እውነታው የራቀ እና ሊሳካ የማይችል” ብሎታል።። ኢትዮጵያ በእርዳታ የምትቀበለውን ስንዴ ጨምሮ በየዓመቱ ከ15 እስከ 20 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ከውጭ ታስገባለች። ለዚህ የስንዴ ግዢም በየዓመቱ ከ600 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ እንደምታደርግ መረጃዎች ያሳያሉ። የኦሮሚያ ግብርና ቢሮ ኃላፊው አቶ ጌቱ እንደሚሉት በክልላቸው የስንዴ ምርት ከዚህ በፊት ከነበረው ከ42 እስከ 45 በመቶ ጨምሯል። ባለፈው የምርት ዓመት የተገኘው ውጤት በመነሳትም በዚህ ዓመት 607 ሺህ ሄክታር የሚሆነውን በሁለት ዙር ለማምረት እንዳቀዱ የሚናገሩት አቶ ጌቱ፣ በዚህም በክልሉ 17 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ እንደሚያገኙ ተስፋ አድርገዋል። የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ቃል ኪዳን ሽፈራው ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን፣ በዚህ ዓመት ከ40 ሺህ ሄክታር በላይ መሬትን በልዩ ትኩረት በማልማት በበጋ መስኖ ስንዴ እንዲሸፈን መደረጉን ገልፀዋል። አክለውም በ35 ሺህ ሄክታር ላይ የደረሰ ሰብል ተሰብስቦ 1 ነጥብ 4 ሚሊየን ኩንታል የሚሆን ስንዴ ምርት ተገኝቷል ብለዋል። “ከዚህ በመነሳት ስንዴን ስለወደድን ብቻ ሳይሆን ይህ ሰብል በተለያዩ የአገራችን የተለያዩ አየር ንብረቶች ሁሉ የሚመረት መሆኑን ስተለተረዳን በምግብ ራስን መቻል ብቻ ሳይሆን ወደ ውጭ ለመላክ አንደምንችል አረጋግጠናል” ይላሉ።
ኢትዮጵያ ስንዴ ከውጭ ማስገባት ትታ ወደ ውጭ መላክ ትችላለች? በምሥራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት አቶ መምሬ መሠረት፣ ከዚህ በፊት ስንዴ ያመርቱ የነበረው በክረምት ዝናብ ብቻ ተጠቅመው ነበር። ማሳቸው ውሃ የሚገባው በመሆኑ በበጋው ወራት ሽንኩርት እና ቲማቲም እያመረቱ ለገበያ ያቀርቡ እንደነበረም ለቢቢሲ ገልፀዋል። ከሦስት ዓመት በፊት ግን ‘ለምን አዲስ ነገር አልጀምርም’ በማለት በበጋ መስኖ ስንዴ ዘርተው ለማየት ወሰኑ። “ይህ ነገር መሆን አለበት ብዬ በራሴ ተነሳሽነት የበጋ ስንዴ ማምረት ጀመርኩ። በዚያን ወቅት አንድም ሰው በበጋ ስንዴ መዝራት የጀመረ የለም። ፈጣሪ ይመስገን ተሳክቶልኛል” ይላሉ አቶ መምሬ። ይህ የበጋ ስንዴ ምርት ከዓመት ወደ ዓመት እየጨመረ እና እየሰፋ እየመጣ መሆኑን አቶ መምሬ አክለው ተናግረዋል። ልክ እንደ አቶ መምሬ ሁሉ የሉሜ ወረዳው አርሶ አደር አቶ እንግዳ ብሩ፣ በበጋ መስኖ ተጠቅመው ጥሩ የስንዴ ምርት እንዳገኙ ይገልጻሉ። እኚህ አርሶ አደር በዚህ ዓመት ብቻ ከስድስት ሄክታር መሬት 320 ኩንታል ስንዴ ማግኘታቸውን ጠቅሰው፣ አዲስ ነገር ስለሆነ በፍርሃት እንደጀመሩት በመግለጽ አቶ እንግዳ “ያገኘነው ምርት ሸጋ ነው”  ብለዋል። ይህ የበጋ ስንዴ ከክረምቱ ወቅት ምርት በላይ ትርፋማ እንደሆነ የሚናገሩት አቶ እንግዳ ግሪሳ (የወፍ መንጋ)፣ የማዳበሪያ ወጪ እና ነዳጅ መፍትሔ ቢያገኝ ስንዴን በበጋ ማምረት “በጣም ትርፋማ” መሆኑን ገልፀዋል። በመጀመሪያ የምርት ዓመት በአንድ ሄክታር ላይ ብቻ ስንዴ ዘርተው የነበሩት አቶ መምሬ፣ መንግሥት ያቀረበላቸውን ድጋፍ በማየት በዚህ ዓመት ወደ 5 ተኩል ሔክታር አሳድገውታል። የበጋ ስንዴ በክረምት ወቅት ከሚመረተው በተሻለ ምርታማ እንደሆነ የሚናገሩት አርሶ አደሩ፣ ከአንድ ቀርጥ (የሄክታር አንድ አራተኛ) ከ16 ኩንታል በላይ ማግኘት እንደሚቻል ይናገራሉ። አቶ መምሬ እንደሚሉት ከአንድ ሄክታር እስከ 64 ኩንታል ይገኛል። ሽንኩርት እና ቲማቲም ማምረት አቁመው ወደ ስንዴ በመግባታቸው ያለውን ልዩነት ሲገልጹ “ይህ የበጋ ስንዴ ምርት ሥራው አድካሚ አይደለም። ትንሽ ማዳበርያ ብቻ ይፈልጋል እንጂ ሌሎች ብዙ ወጪዎች ስለሌሉበት ትርፋማ ነው” ብለዋል። አቶ መምሬ ካገኙት የበጋ ስንዴ ምርት 250 ኩንታል ያህሉን መንግሥት በጥሩ ዋጋ (በኩንታል 3680) እንደተረከባቸው ጨምረው አስረድተዋል። እንደ አሜሪካ ግብርና ቢሮ መረጃ ከሆነ በኢትዮጵያ የስንዴ ምርት ዘርፍ ትልቅ እመርታ እያሳየ እና ምርታማነቱ እየጨመረ ነው። የአሜሪካ የውጭ ግብርና ቢሮ ሪፖርት ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2022/2023 ዓመት ውስጥ 5.7 ሚሊዮን ቶን ስንዴ ታመርታለች ተብሎ እንደሚጠበቅ አመልክቷል። ይህም ካለፈው የምርት ዘመን በ3.26 በመቶ ከፍ ያለ ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት ባለፉት ሦስት ዓመታት የስንዴ ምርት እንዲጨመር በርካታ ድጋፎችን እያደረገ መሆኑን ያስታወሰው ይህ ሪፖርት፤ የኤክስቴንሽን ድጋፍ፣ የመስኖ ልማት፣ በዘመናዊ መሳሪያ የታገዘ የእርሻ ሥርዓት እንዲሁም ሌሎች ግብዓቶች እንደሚያቀርብም ዘርዝሯል። ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት 70 በመቶ ያህል የአገር ውስጥ ፍላጎቷን የምታመርት ሲሆን፣ 30 በመቶ ያህሉን ደግሞ ከውጭ እንደምታስገባ መረጃዎች ያመለክታሉ። ከውጭ ከምታስገባው የተወሰነውን ስንዴ የውጭ ምንዛሬ በማውጣት የምትገዛ ሲሆን፣ ቀሪውን ደግሞ ከአሜሪካ በእርዳታ እንደምታገኝ የአሜሪካ የውጭ ግብርና ምርት ቢሮ መረጃ ያሳያል። ኢትዮጵያ በ2023 (እኤአ) ያላትን የስንዴ ፍላጎት በአገር ውስጥ ምርት ለሟሟላት እና ከባሕር ማዶ የምታስገባውን ለማስቀረት አቅዳ እየሰራች መሆኑ በተደጋጋሚ ሲገለጽ ቆይቷል። ይህንንም ለማሳካት በመላ አገሪቱ ባለፉት ሦስት ዓመታት 1.3 ሚሊዮን አርሶ አደሮች በ30 ሺህ ክላስተር ተደራጅተዋል። እያንዳንዱ ክላስተርም የተሻሻለ ዘር እንዲሁም ለአካባቢው ተስማሚ የሆነ ማዳበርያ እንዲጠቀም ይደረጋል። እንዲሁም የኤክስቴንሽን ሠራተኞች ክትትል እና ድጋፍ በምርት ስብሰባ ወቅትም ብክነት ለመቀነስ የማሽን ድጋፍ ተደርጓል። በኦሮሚያ ግብርና ቢሮ የስንዴ ምርት ጉዳይን የሚከታተሉት ኃላፊ አቶ ጌቱ ገመቹ፣ ክልሉ በስንዴ ምርት ላይ ዕቅድ አውጥቶ እየሰራ መሆኑን ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቶ ጌቱ ገመቹ በበኩላቸው የስንዴ ምርትን ለመጨመር የተያዙትን አራት መሠረታዊ እቅዶች ሲያብራሩ “በምግብ ራስን መቻል፤ ከውጭ የሚገባውን ምርት በአገር ውስጥ ማምረት፣ በአገር ውስጥ የሚመረተውን ደግሞ ወደ ውጪ መላክ እና በእነዚህ ውስጥ የሥራ ዕድል መፍጠር” መሆናቸውን ገልፀዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ ካለፉት ሦስት ዓመታት ጀምሮ እየተሰራ መሆኑን የሚናገሩት ኃላፊው፣ በመጀመሪያው ዓመት ላይ ከምርምር ተቋማት ጋር በመሆን ውጤታማነቱን በምርምር ለማረጋገጥ ተችሏል ይላሉ። ግንቦት 2022 እኤአ የቡድን ሰባት አገራት ሚኒስትሮች በጀርመን ባካሄዱት ስብሰባ ላይ የተገኙት የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት፣ አክንዊሚ አዲሲና ኢትዮጵያ ከዚህ በኋላ ስንዴ ከውጪ እንደማታስገባ ተናግረዋል። የአፍሪካ ልማት ባንክ ለአፍሪካ በሚያቀርበው የግብርና ቴክኖሎጂ ፕሮግራም አማካኝነት የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋሙ የቴክኖሎጂ ድጋፍ ለኢትዮጵያ አድርጓል። በዚህም የተነሳ ኢትዮጵያ በዚህ ዓመት ምርት በመጨመሯ በዓመት 26 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ምርቷ ማደግ ችሏል ብለዋል። ካለፈው ዓመት ጀመሮ ኢትዮጵያ ከውጭ አለማስገባቷን የሚናገሩት ፕሬዝዳንቱ፣ ለሚቀጥለው ዓመት በ2 ሚሊዮን ሄክታር ላይ ለማምረት ዕቅድ ስላላት ይህንን ምርት በ2023 ለጎረቤት አገራት ጅቡቲ እና ኬንያ ለመሸጥ ማሰቧን ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሕዝብ ተወካዮች በበጋ ስንዴ ከፍተኛ ምርት መገኘቱን ገልፀው ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህ የስንዴ ምርት እንዴት እንደተገኘ ሲያብራሩ መስኖ እንዲሁም የክላስተር ግብርናን በአስረጂነት ጠቅሰዋል። ምንም እንኳ ኢትዮጵያ የምታመርተውን ስንዴ ብትጨምርም በአገሪቱ ውስጥ በተከሰቱ የተለያዩ ግጭቶች የተነሳ ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለው የዕለት እርዳታ የሚጠብቁ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ ነው። እንዲሁም ለ19 ወራት የቀጠለውን የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የምግብ እህል እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ቁጥርን ከፍተኛ አድርጎታል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን መረጃ እንደሚያሳየው በ2022/2023 ብቻ 10 ሚሊዮን ያህል ሰዎች የዕለት እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። በዚህም የተነሳ ኢትዮጵያ ከውጭ የምታስገባውን ስንዴ አቁማ ወደ ውጭ መላክ ለመጀመር የያዘችው ዕቅድ አጣብቂኝ ውስጥ ሊወድቅ ይችላል የሚል ስጋት አጭሯል። ኢትዮጵያ እኤአ በ2023 ከባሕር ማዶ የምታስገባውን ስንዴ ለማቆም ማቀዷን ያስታወሰው የአሜሪካ ግብርና ቢሮ ሪፖርት በበኩሉ ባለው ውስን ሀብት እና ቴክኖሎጂ አንዲሁም በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማሳካት ያለውን ተግዳሮት ሲገልጽ “ከተጨባጭ እውነታው የራቀ እና ሊሳካ የማይችል” ብሎታል።። ኢትዮጵያ በእርዳታ የምትቀበለውን ስንዴ ጨምሮ በየዓመቱ ከ15 እስከ 20 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ከውጭ ታስገባለች። ለዚህ የስንዴ ግዢም በየዓመቱ ከ600 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ እንደምታደርግ መረጃዎች ያሳያሉ። የኦሮሚያ ግብርና ቢሮ ኃላፊው አቶ ጌቱ እንደሚሉት በክልላቸው የስንዴ ምርት ከዚህ በፊት ከነበረው ከ42 እስከ 45 በመቶ ጨምሯል። ባለፈው የምርት ዓመት የተገኘው ውጤት በመነሳትም በዚህ ዓመት 607 ሺህ ሄክታር የሚሆነውን በሁለት ዙር ለማምረት እንዳቀዱ የሚናገሩት አቶ ጌቱ፣ በዚህም በክልሉ 17 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ እንደሚያገኙ ተስፋ አድርገዋል። የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ቃል ኪዳን ሽፈራው ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን፣ በዚህ ዓመት ከ40 ሺህ ሄክታር በላይ መሬትን በልዩ ትኩረት በማልማት በበጋ መስኖ ስንዴ እንዲሸፈን መደረጉን ገልፀዋል። አክለውም በ35 ሺህ ሄክታር ላይ የደረሰ ሰብል ተሰብስቦ 1 ነጥብ 4 ሚሊየን ኩንታል የሚሆን ስንዴ ምርት ተገኝቷል ብለዋል። “ከዚህ በመነሳት ስንዴን ስለወደድን ብቻ ሳይሆን ይህ ሰብል በተለያዩ የአገራችን የተለያዩ አየር ንብረቶች ሁሉ የሚመረት መሆኑን ስተለተረዳን በምግብ ራስን መቻል ብቻ ሳይሆን ወደ ውጭ ለመላክ አንደምንችል አረጋግጠናል” ይላሉ።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cn432yp5rlvo
5sports
ሮናሊዲኒሆ ሃሰተኛ ፓስፖርት በመያዝ ተጠርጥሮ በፓራጓይ በቁጥጥር ስር ዋለ
እውቁ የቀድሞ የብራዚል ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ሮናልዲንሆ ወደ ፓራጓይ ለመግባት ሃሰተኛ ፓስፖርት ተጠቅሟል በሚል ጥርጣሬ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰምቷል። በዚህም ምክንያት የፓራጓይ ፖሊስ ሮናልዲንሆ እና ወንድሙ በፓራጓይ መዲና ያረፉበትን ሆቴል በርብሯል። የፓራጓይ አገር ውስጥ ሚኒስትር ሮናልዲንሆና ወንድሙ እንዳልታሰሩ ነገር ግን ፖሊስ ምርመራ እያደረገባቸው እንዳለ ተናግረዋል። ሚኒስትሩ እንዳሉት ወንድማማቾቹ የተጠረጠሩበትን ወንጀል ክደዋል፤ በሚደረገው ምርመራ ላይ ግን አስፈላጊውን ትብብር እያደረጉ ነው። ሮናልዲንሆ ባለፈው የአውሮፓውያኑ ዓመት በታክስ ጉዳይ እንዲሁም በሕገወጥ ግንባታ የተጣለበትን ቅጣት ባለመክፈል የብራዚልና የስፔን ፓስፖርቱን ተነጥቆ ነበር። የፓራጓይ የአገር ውስጥ ሚኒስትሩ "በእግር ኳስ ችሎታው አደንቀዋለሁ ነገር ግን ማንም ሁን ማን ሕግ ደግሞ መከበር አለበት" ሲሉ ለአዣንስ ፈራንስ ፕሬስ ተናግረዋል። የ39 ዓመቱ ሮናልዲንሆ ወደ ፓራጓይ ያቀናው አንድ መፅሃፍን ለማስተዋወቅና ስለ ችግረኛ ህፃናት ዘመቻ ለማካሄድ እንደሆነ ተገልጿል። ሮናልዲንሆ እአአ በ2004 እና በ2005 የዓለም ምርጥ የዓመቱ እግር ኳስ ተጫዋች ሆኖ ተመርጦ ነበር። የሮናልዲንሆ አጠቃላይ ሃብት ከ80 እስከ 100 ሚሊዮን ፓውንድ ይገመታል።
ሮናሊዲኒሆ ሃሰተኛ ፓስፖርት በመያዝ ተጠርጥሮ በፓራጓይ በቁጥጥር ስር ዋለ እውቁ የቀድሞ የብራዚል ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ሮናልዲንሆ ወደ ፓራጓይ ለመግባት ሃሰተኛ ፓስፖርት ተጠቅሟል በሚል ጥርጣሬ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰምቷል። በዚህም ምክንያት የፓራጓይ ፖሊስ ሮናልዲንሆ እና ወንድሙ በፓራጓይ መዲና ያረፉበትን ሆቴል በርብሯል። የፓራጓይ አገር ውስጥ ሚኒስትር ሮናልዲንሆና ወንድሙ እንዳልታሰሩ ነገር ግን ፖሊስ ምርመራ እያደረገባቸው እንዳለ ተናግረዋል። ሚኒስትሩ እንዳሉት ወንድማማቾቹ የተጠረጠሩበትን ወንጀል ክደዋል፤ በሚደረገው ምርመራ ላይ ግን አስፈላጊውን ትብብር እያደረጉ ነው። ሮናልዲንሆ ባለፈው የአውሮፓውያኑ ዓመት በታክስ ጉዳይ እንዲሁም በሕገወጥ ግንባታ የተጣለበትን ቅጣት ባለመክፈል የብራዚልና የስፔን ፓስፖርቱን ተነጥቆ ነበር። የፓራጓይ የአገር ውስጥ ሚኒስትሩ "በእግር ኳስ ችሎታው አደንቀዋለሁ ነገር ግን ማንም ሁን ማን ሕግ ደግሞ መከበር አለበት" ሲሉ ለአዣንስ ፈራንስ ፕሬስ ተናግረዋል። የ39 ዓመቱ ሮናልዲንሆ ወደ ፓራጓይ ያቀናው አንድ መፅሃፍን ለማስተዋወቅና ስለ ችግረኛ ህፃናት ዘመቻ ለማካሄድ እንደሆነ ተገልጿል። ሮናልዲንሆ እአአ በ2004 እና በ2005 የዓለም ምርጥ የዓመቱ እግር ኳስ ተጫዋች ሆኖ ተመርጦ ነበር። የሮናልዲንሆ አጠቃላይ ሃብት ከ80 እስከ 100 ሚሊዮን ፓውንድ ይገመታል።
https://www.bbc.com/amharic/news-51764736
3politics
የአፍሪካ ሕብረት የሶማሊያው ፕሬዝደንት ሥልጣናቸውን ማራዘማቸውን ተቃወመ
የአፍሪካ ሕብረት የሶማሊያው ፕሬዝደንት ሞሐመድ አብዱላሂ ፎርማጆ የሥልጣን ዘመናቸውን ማራዘማቸውን ተቃወመ። ሕብረቱ ልዩ መልዕክተኛ ወደ ሞጋዲሾ በመላክ የፖለቲካ ውጥንቅጡን ለመፍትታ እንደሚሞክርም አስታውቋል። የአፍሪካ ሕብረት ሰላምና ፀጥታ ምክር ቤት ለሰዓታት ዝግ ስብሰባ ካካሄደ በኋላ ነው የሶማሊያን ፖለቲካዊ ችግር እፈታለሁ ያለው። ሐሙስ ዕለት ከተካሄደው ስብሰባ በኋላ የተለቀቀው መግለጫ ሁሉም በአገሪቱ ውስጥ ያሉ ፓርቲዎች በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲመክሩ አሳስቧል። ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት መስከረም የሶማሊያ ፌዴራል መንግሥትና ክልላዊ አስተዳደሮች እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎች መክረው ነበር። በዚህ ውይይት ወቅት በሶማሊያ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ እንዲደረግ ተስሰማምተው ነበር። ነገር ግን ባለፈው ሳምንት ፕሬዝደንት ፎርማጆ የሥልጣን ዘመናቸውን እንዲራዘም የሚያትት ረቂቅ አፅድቀዋል። የፕሬዝደንቱ አወዛጋቢ ውሳኔ ከብዙዎች ዘንድ ተቃውሞ እንዲገጥማቸው አድርጓል። ዩናይትድ ስቴትስ፣ ብሪታኒያ፣ የተባበሩት መንግሥታትና የአውሮፓ ሕብረት የፕሬዝደንቱን እርምጃ ከተቃወሙ መካከል ናቸው። "የመስከረም 2020 ስምምነት ለወደፊቱ ሶማሊያ አዋጭ የሆነ ዕቅድ ይዟል። ይህም ተዓማናኒ ነፃ ምርጫ ማድረግ ነው" ይላል ሕብረቱ የለቀቀው መግለጫ። የሰላምና ፀጥታ ምክር ቤት የሶማሊያ ፖለቲካዊ አመራሮች ነገሮች የበለጠ የሚያከሩ ድርጊቶች ከመፈፀም እንዲቆጠቡም አሳስቧል። ምክር ቤቱ ይህ ሆነ ማለት የሶማሊያ፣ የአፍሪካ ቀንድና የመላው አፍሪካ ሰላም ደፈረሰ ማለት ነው ሲል በመግለጫ አትቷል። የአፍሪካ ሕብረት የሰላምና ፀጥታ ምክር ቤት በዝግ ባካሄደው ስብሰባ በቻድ ስላለው ሁኔታም ቢመክርም ለጊዜው ምንም ዓይነት ውሳኔ ላይ አልደረሰም። የቻዱ ፕሬዝደንት ኢድሪስ ዴቢ ከታጣቂዎች ጋር በተደረገ ውጊያ ሕይወታቸው ማለፉን ይታወሳል። የአፍሪካ ሃገራት መሪዎች በዴቢ ቀብር ላይ ለመገኘት ወደ ቻድ እያመሩ ይገኛሉ።
የአፍሪካ ሕብረት የሶማሊያው ፕሬዝደንት ሥልጣናቸውን ማራዘማቸውን ተቃወመ የአፍሪካ ሕብረት የሶማሊያው ፕሬዝደንት ሞሐመድ አብዱላሂ ፎርማጆ የሥልጣን ዘመናቸውን ማራዘማቸውን ተቃወመ። ሕብረቱ ልዩ መልዕክተኛ ወደ ሞጋዲሾ በመላክ የፖለቲካ ውጥንቅጡን ለመፍትታ እንደሚሞክርም አስታውቋል። የአፍሪካ ሕብረት ሰላምና ፀጥታ ምክር ቤት ለሰዓታት ዝግ ስብሰባ ካካሄደ በኋላ ነው የሶማሊያን ፖለቲካዊ ችግር እፈታለሁ ያለው። ሐሙስ ዕለት ከተካሄደው ስብሰባ በኋላ የተለቀቀው መግለጫ ሁሉም በአገሪቱ ውስጥ ያሉ ፓርቲዎች በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲመክሩ አሳስቧል። ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት መስከረም የሶማሊያ ፌዴራል መንግሥትና ክልላዊ አስተዳደሮች እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎች መክረው ነበር። በዚህ ውይይት ወቅት በሶማሊያ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ እንዲደረግ ተስሰማምተው ነበር። ነገር ግን ባለፈው ሳምንት ፕሬዝደንት ፎርማጆ የሥልጣን ዘመናቸውን እንዲራዘም የሚያትት ረቂቅ አፅድቀዋል። የፕሬዝደንቱ አወዛጋቢ ውሳኔ ከብዙዎች ዘንድ ተቃውሞ እንዲገጥማቸው አድርጓል። ዩናይትድ ስቴትስ፣ ብሪታኒያ፣ የተባበሩት መንግሥታትና የአውሮፓ ሕብረት የፕሬዝደንቱን እርምጃ ከተቃወሙ መካከል ናቸው። "የመስከረም 2020 ስምምነት ለወደፊቱ ሶማሊያ አዋጭ የሆነ ዕቅድ ይዟል። ይህም ተዓማናኒ ነፃ ምርጫ ማድረግ ነው" ይላል ሕብረቱ የለቀቀው መግለጫ። የሰላምና ፀጥታ ምክር ቤት የሶማሊያ ፖለቲካዊ አመራሮች ነገሮች የበለጠ የሚያከሩ ድርጊቶች ከመፈፀም እንዲቆጠቡም አሳስቧል። ምክር ቤቱ ይህ ሆነ ማለት የሶማሊያ፣ የአፍሪካ ቀንድና የመላው አፍሪካ ሰላም ደፈረሰ ማለት ነው ሲል በመግለጫ አትቷል። የአፍሪካ ሕብረት የሰላምና ፀጥታ ምክር ቤት በዝግ ባካሄደው ስብሰባ በቻድ ስላለው ሁኔታም ቢመክርም ለጊዜው ምንም ዓይነት ውሳኔ ላይ አልደረሰም። የቻዱ ፕሬዝደንት ኢድሪስ ዴቢ ከታጣቂዎች ጋር በተደረገ ውጊያ ሕይወታቸው ማለፉን ይታወሳል። የአፍሪካ ሃገራት መሪዎች በዴቢ ቀብር ላይ ለመገኘት ወደ ቻድ እያመሩ ይገኛሉ።
https://www.bbc.com/amharic/news-56855691
3politics
ታሊባን ከምዕራባውያን አገራት ባለሥልጣናት ጋር በኦስሎ ንግግር ጀመረ
ታሊባን ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፓ ምድር ከምዕራባውያን አገራት ባለሥልጣናት ጋር ንግግር ጀመረ። ታሊባን እና ምዕራባውያኑ ባለሥልጣናት ለሦስት ቀናት በሚዘልቅ ውይይታቸው ስለ ሰብዓዊ መብት ጉዳዮች እና የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦትን በተመለከተ ይነጋገራሉ ተብሏል። የተባበሩት መንግሥታት 95 በመቶ የሚሆኑት አፍጋናውያን በቂ ምግብ የላቸውም ይላል። በአሁኑ ወቅት በአፍጋኒስታን የሥራ አጥ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል። የምግብ ዋጋ ንሯል፤ የአገሪቱ መገበያያ ገንዘብ ዋጋ እያጣ ነው። ባንኮችም ወጭ በሚደረግ የገንዘብ መጠን ላይ ገደብ ጥለዋል። የተባበሩት መንግሥታት 55 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ ለረሃብ ተጋላጭ ነው ሲል ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ ነበር። ዛሬ ሰኞ ጥር 16/2014 ታሊባን እና ምዕራባውያኑ ጥብቅ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ታሊባን በአሜሪካ ባንኮች ውስጥ እንዳይንቀሳቀስ የታገደው በቢሊዮን ዶላር የሚገመት ገንዘብ እንዲለቀቅለት ይጠይቃል ተብሏል። "ለአፍጋን ሕዝብ ገንዘብ እንዲለቁ እየጠየቅናቸው ነው። በፖለቲካ ልዩነት የአፍጋኒስታን ዜጎች ሊጎዱ አይገባም" ሲሉ የታሊባን ተወካዩ ሻፊኡላህ አዛም ለአሶሺዬትድ ፕሬስ ተናግረዋል። ተወካዩ በአፋጋኒስታን ተጋርጧል በተባለው ረሃብ እና በአገሪቱ ባለው ከባድ ቅዝቃዜ ምክንያት ዓለም አቀፉ ማሕብረሰብ አፍጋኒስታንን መርዳት እንጂ መቅጣት የለበትም በማለት ጨምረው ተናግረዋል። ታሊባን እና ምዕራባውያኑ በሚያደርጉት ውይይት ላይ የምዕራባውያኑ ተወካዮች ቡድኑ የበለጠ አካታች እንዲሆን እና የሰብዓዊ መብት ጥበቃዎች ላይም ትኩረት ያደርጋሉ። ታሊባን አፍጋኒስታንን መልሶ ከተቆጣጠረ ወዲህ ሴት ሠራተኞች በቤት እንዲቆዩ ማዘዙ ይታወሳል። ከዚህ በተጨማሪም ሁለተኛ ደረጃ ትምህር ቤቶች ለወንድ ተማሪዎች እና ለወንድ መምህራን ብቻ ከፍት ሆነዋል። ይህን የታሊባን ሥርዓት የተቃወሙ በርካታ ሴቶች በቡድኑ ዒላማ ተደርገዋል። አንዳንድ ሪፖርቶች እንደሚጠቁሙት ከሆነ አድራሻቸው የጠፉ ሴቶች አሉ። ታሊባን በበኩሉ ከሴቶቹ መጥፋት ጋር የሚያገናኘኝ የለም ይላል። ከመብት ተከራካሪ ሴቶች በተጨማሪ ጋዜጠኞችም በታሊባን ዒላማ ሲደረጉ ቆይተዋል። እስካሁን ድረስ የትኛውም አገር ለአዲሱ የታሊባን መንግሥት እውቅና አልሰጠም። የኖርዌይ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር አኒከን ሁኢትፌልደት ምዕራባውያን ከታሊባን ጋር የሚያደርጉት ውይይት ቡድኑ ለመሠረትው መንግሥት እውቅና መስጠት አይደለም ብለዋል። የታሊባን እና ምዕራባውያን አገራት ባለሥልጣናት ለውይይት መቀመጥ በአፍጋኒስታን የተከፋፈለ ስሜትን ፈጥሯል። አንዳንዶች ምዕራባውያኑ ከቡድኑ ተወካዮች ጋር መነጋገራቸው መልካም ነው ሱሉ ገሚሱ ደግሞ ታሊባን ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየፈጸመ በአውሮፓ ከተሞች ላይ ለውይይት መጋበዙ ትክክል አይደለም ይላሉ። የውይይቱን መካሄድ የሚቃወሙ ሰልፎች በአውሮፓ ከተሞች ተካሂደዋል።
ታሊባን ከምዕራባውያን አገራት ባለሥልጣናት ጋር በኦስሎ ንግግር ጀመረ ታሊባን ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፓ ምድር ከምዕራባውያን አገራት ባለሥልጣናት ጋር ንግግር ጀመረ። ታሊባን እና ምዕራባውያኑ ባለሥልጣናት ለሦስት ቀናት በሚዘልቅ ውይይታቸው ስለ ሰብዓዊ መብት ጉዳዮች እና የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦትን በተመለከተ ይነጋገራሉ ተብሏል። የተባበሩት መንግሥታት 95 በመቶ የሚሆኑት አፍጋናውያን በቂ ምግብ የላቸውም ይላል። በአሁኑ ወቅት በአፍጋኒስታን የሥራ አጥ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል። የምግብ ዋጋ ንሯል፤ የአገሪቱ መገበያያ ገንዘብ ዋጋ እያጣ ነው። ባንኮችም ወጭ በሚደረግ የገንዘብ መጠን ላይ ገደብ ጥለዋል። የተባበሩት መንግሥታት 55 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ ለረሃብ ተጋላጭ ነው ሲል ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ ነበር። ዛሬ ሰኞ ጥር 16/2014 ታሊባን እና ምዕራባውያኑ ጥብቅ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ታሊባን በአሜሪካ ባንኮች ውስጥ እንዳይንቀሳቀስ የታገደው በቢሊዮን ዶላር የሚገመት ገንዘብ እንዲለቀቅለት ይጠይቃል ተብሏል። "ለአፍጋን ሕዝብ ገንዘብ እንዲለቁ እየጠየቅናቸው ነው። በፖለቲካ ልዩነት የአፍጋኒስታን ዜጎች ሊጎዱ አይገባም" ሲሉ የታሊባን ተወካዩ ሻፊኡላህ አዛም ለአሶሺዬትድ ፕሬስ ተናግረዋል። ተወካዩ በአፋጋኒስታን ተጋርጧል በተባለው ረሃብ እና በአገሪቱ ባለው ከባድ ቅዝቃዜ ምክንያት ዓለም አቀፉ ማሕብረሰብ አፍጋኒስታንን መርዳት እንጂ መቅጣት የለበትም በማለት ጨምረው ተናግረዋል። ታሊባን እና ምዕራባውያኑ በሚያደርጉት ውይይት ላይ የምዕራባውያኑ ተወካዮች ቡድኑ የበለጠ አካታች እንዲሆን እና የሰብዓዊ መብት ጥበቃዎች ላይም ትኩረት ያደርጋሉ። ታሊባን አፍጋኒስታንን መልሶ ከተቆጣጠረ ወዲህ ሴት ሠራተኞች በቤት እንዲቆዩ ማዘዙ ይታወሳል። ከዚህ በተጨማሪም ሁለተኛ ደረጃ ትምህር ቤቶች ለወንድ ተማሪዎች እና ለወንድ መምህራን ብቻ ከፍት ሆነዋል። ይህን የታሊባን ሥርዓት የተቃወሙ በርካታ ሴቶች በቡድኑ ዒላማ ተደርገዋል። አንዳንድ ሪፖርቶች እንደሚጠቁሙት ከሆነ አድራሻቸው የጠፉ ሴቶች አሉ። ታሊባን በበኩሉ ከሴቶቹ መጥፋት ጋር የሚያገናኘኝ የለም ይላል። ከመብት ተከራካሪ ሴቶች በተጨማሪ ጋዜጠኞችም በታሊባን ዒላማ ሲደረጉ ቆይተዋል። እስካሁን ድረስ የትኛውም አገር ለአዲሱ የታሊባን መንግሥት እውቅና አልሰጠም። የኖርዌይ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር አኒከን ሁኢትፌልደት ምዕራባውያን ከታሊባን ጋር የሚያደርጉት ውይይት ቡድኑ ለመሠረትው መንግሥት እውቅና መስጠት አይደለም ብለዋል። የታሊባን እና ምዕራባውያን አገራት ባለሥልጣናት ለውይይት መቀመጥ በአፍጋኒስታን የተከፋፈለ ስሜትን ፈጥሯል። አንዳንዶች ምዕራባውያኑ ከቡድኑ ተወካዮች ጋር መነጋገራቸው መልካም ነው ሱሉ ገሚሱ ደግሞ ታሊባን ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየፈጸመ በአውሮፓ ከተሞች ላይ ለውይይት መጋበዙ ትክክል አይደለም ይላሉ። የውይይቱን መካሄድ የሚቃወሙ ሰልፎች በአውሮፓ ከተሞች ተካሂደዋል።
https://www.bbc.com/amharic/60107886
3politics
የደቡብ ሱዳን አመራሮች በሕገወጥ ገንዘብ ዝውውር ተዘፍቀዋል-ተመድ
በደቡብ ሱዳን ፖለቲካዊ፣ ወታደራዊ እና የንግዱን ዘርፍ እየመሩ ያሉ ግለሰቦች በሕገወጥ መንገድ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር በማዘዋወር በአገሪቱ ውስጥ ውስጥ ባለው አለመረጋጋት ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ነው በማለት የተባበሩት መንግሥታት የባለሙያዎች ቡድን ከሰሰ። የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን እንዳስታወቀው በደቡብ ሱዳን ከአውሮፓውያኑ 2018 ጀምሮ "የመንግሥት ባለስልጣናትና ከእነሱ ጋር ግንኙነት ያላቸው አካላት ቢያንስ በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር በሕገወጥ መንገድ አዘዋውረዋል እንዲሁም አጭበርብረዋል" ብሏል። ይህ ግን በአገሪቱ ውስጥ እየተፈፀመ ያለውን ሕገወጥ ገንዘብ ዝውውር ደረጃን አያሳይም ተብሏል። በአገሪቱ ውስጥ የተንሰራፋው ሙስና ያለውን የሰብዓዊ መብትና የፀጥታ ሁኔታን ያዳክማል ብሏል ሪፖርቱ። ከአውሮፓውያኑ 2018 ጀምሮ 73 ሚሊዮን ዶላር በሕገወጥ መንገድ ተዘዋውሯል። ኮሚሽኑ ይህ አሃዝ ከተዘረፈው አጠቃላይ የገንዘብ መጠን ባጣም ጥቂቱ ነው ብሏል። "የብዝበዛውንና ዘረፋውን ሁኔታ በምናይበት ወቅት ፖለቲከኞች፣ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ ዓለም አቀፍ ኮርፖሬሽኖች፣ ወታደራዊ አመራሮች እና ዓለም አቀፍ ባንኮች መሳተፋቸውን በግኝታችን ማረጋገጥ ችለናል" በማለት የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር ያሲሚን ሱካ ሪፖርቱን በሚያቀርቡበት ወቅት አስረድተዋል። ሪፖርቱ በተጨማሪም የደቡብ ሱዳን የነዳጅ ኢንዱስሪ "ተጠያቂነት በሌለው የነዳጅ ጥምረት ቡድን" በበላይነት የሚመራ ሲሆን በዚህም አካቢውን መበከል ጨምሮ ለማኅበረሰቡ ጤና ጠንቅ ሆኗል ብሏል። እንዲህ አይነት ብዝበዛዎችና ዘረፋዎች እየተፈፀሙባት ያለችው ደቡብ ሱዳን ሁለት ሦስተኛ ወይም 7.2 ሚሊዮን የሚሆነው ሕዝቧ ምግብ ለማግኘት በየቀኑ እየታገለ ይገኛል። የባለሙያዎቹን ሪፖርት በተመለከተ የደቡብ ሱዳን መንግሥት የሰጠው ምላሽ የለም።
የደቡብ ሱዳን አመራሮች በሕገወጥ ገንዘብ ዝውውር ተዘፍቀዋል-ተመድ በደቡብ ሱዳን ፖለቲካዊ፣ ወታደራዊ እና የንግዱን ዘርፍ እየመሩ ያሉ ግለሰቦች በሕገወጥ መንገድ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር በማዘዋወር በአገሪቱ ውስጥ ውስጥ ባለው አለመረጋጋት ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ነው በማለት የተባበሩት መንግሥታት የባለሙያዎች ቡድን ከሰሰ። የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን እንዳስታወቀው በደቡብ ሱዳን ከአውሮፓውያኑ 2018 ጀምሮ "የመንግሥት ባለስልጣናትና ከእነሱ ጋር ግንኙነት ያላቸው አካላት ቢያንስ በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር በሕገወጥ መንገድ አዘዋውረዋል እንዲሁም አጭበርብረዋል" ብሏል። ይህ ግን በአገሪቱ ውስጥ እየተፈፀመ ያለውን ሕገወጥ ገንዘብ ዝውውር ደረጃን አያሳይም ተብሏል። በአገሪቱ ውስጥ የተንሰራፋው ሙስና ያለውን የሰብዓዊ መብትና የፀጥታ ሁኔታን ያዳክማል ብሏል ሪፖርቱ። ከአውሮፓውያኑ 2018 ጀምሮ 73 ሚሊዮን ዶላር በሕገወጥ መንገድ ተዘዋውሯል። ኮሚሽኑ ይህ አሃዝ ከተዘረፈው አጠቃላይ የገንዘብ መጠን ባጣም ጥቂቱ ነው ብሏል። "የብዝበዛውንና ዘረፋውን ሁኔታ በምናይበት ወቅት ፖለቲከኞች፣ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ ዓለም አቀፍ ኮርፖሬሽኖች፣ ወታደራዊ አመራሮች እና ዓለም አቀፍ ባንኮች መሳተፋቸውን በግኝታችን ማረጋገጥ ችለናል" በማለት የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር ያሲሚን ሱካ ሪፖርቱን በሚያቀርቡበት ወቅት አስረድተዋል። ሪፖርቱ በተጨማሪም የደቡብ ሱዳን የነዳጅ ኢንዱስሪ "ተጠያቂነት በሌለው የነዳጅ ጥምረት ቡድን" በበላይነት የሚመራ ሲሆን በዚህም አካቢውን መበከል ጨምሮ ለማኅበረሰቡ ጤና ጠንቅ ሆኗል ብሏል። እንዲህ አይነት ብዝበዛዎችና ዘረፋዎች እየተፈፀሙባት ያለችው ደቡብ ሱዳን ሁለት ሦስተኛ ወይም 7.2 ሚሊዮን የሚሆነው ሕዝቧ ምግብ ለማግኘት በየቀኑ እየታገለ ይገኛል። የባለሙያዎቹን ሪፖርት በተመለከተ የደቡብ ሱዳን መንግሥት የሰጠው ምላሽ የለም።
https://www.bbc.com/amharic/news-58680865
3politics
በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ የሚደረግ ጫናን የሚቃወሙ ሰልፎች በበርካታ አገራት ተደረጉ
ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን በሰሜን አሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና እስራኤልን ጨምሮ በበርካታ ከተሞች የምዕራብ አገራትን ጫና በመቃወም ለኢትዮጵያ መንግሥት ያላቸውን ድጋፍ አደባባይ በመውጣት ገለጹ። ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን የኢትዮጵያ መንግሥት ከህወሓት አማጺያን ጋር በሚያደርገው ጦርነት ምዕራባውያን አገራት ለፌደራሉ መንግሥት ድጋፍ እንዲሰጡ ጠይቀዋል። መንግሥታዊው ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ በ27 ከተሞች የድጋፍ ሰልፉ መካሄዱን ዘግቧል። የድጋፍ ሰልፉ ከተደረገባቸው ከተሞች መካከል፤ ዋሽንግተን ዲሲ፣ ኒው ዮርክ፣ ሎስ አንጀለስ፣ ኦስቲን፣ ሂውስተን፣ ቶሮንቶ፣ ኦታዋ፣ ካልጋሪ፣ ዊኒፒግ እና ለንደን ተጠቃሽ ናቸው። የካናዳው ሲቢኤስ ኒውስ በካናዳዋ ማኒቶባ ግዛት ዊኒፒግ ከተማ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የኢትዮጵያ መንግሥት ከህወሓት ጋር በሚያደርገው ጦርነት የካናዳ መንግሥት ለኢትዮጵያ መንግሥት ድጋፍ እንዲያደርግ አደባባይ ወጥተው ጠይቀዋል ሲል ዘግቧል። በዊኒፒግ ከተማ የተዘጋጀውን የድጋፍ ሰልፍ ካስተባበሩት መካከል አንዱ የሆኑት ማርቆስ ተገኝ፤ "በኢትዮጵያ ውስጣዊ ጉዳይ በተለይ አሜሪካ ጣልቃ መግባት ማቆም አለባት፤ ኢትዮጵያውያን የራሳቸውን ችግር በራሳቸው እንዲፈቱ መፍቀድ አለባት" ሲሉ ሲቢኤስ ኒውስ ተናግረዋል። በሌላኛዋ የካናዳ ከተማ ካልጋሪ ተመሳሳይ የድጋፍ ሰልፍ መካሄዱን ሲቲቪ ኒውስ ካልጋሪ ዘግቧል። ለፌደራሉ መንግሥት ድጋፍ ለመስጠት በተጠራው ሰልፍ ላይ ሰዎች #NoMore (ከአሁን በኋላ ይብቃ) እንዲሁም #Handsoff (እጃችሁን አንሱ) የሚሉ መፈክሮችን ይዘው መውጣታቸው ሲቲቪ ኒውስ ካልጋሪ አሳይቷል። በተመሳሳይ በአሜሪካ ቴክሳስ ግዛት ኦስቲን ከተማ ተመሳሳይ ድጋፍ አድርገዋል። "እነዚህ በኢትዮጵያ ያሉ ጉዳዮች ናቸው፤ እራሳችን መፍታት እንችላለን። እዚህ የተገኘነው እባካችሁ አቁሙ፤ የራሳችንን ጉዳይ እራሳችን እንፈታዋለን ለማለት" በማለት የኦስቲን ሰልፍ ተሳታፊ የሆነው ቴድ ኃይሉ ለሲቢኤስ ኦስቲን ተናግሯል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ በተለያዩ ከተሞች የተካሄዱ ሰልፎችን የሚያሳዩ ፎቶግራፎችን በማጋራት "...ለእውነት ለቆሙ ኢትዮጵያውያን እና የአፍሪካ ቀንድ ዳያስፖራዎች አድናቆቴን እገልጻለሁ" ብለዋል። በየአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ፍጹም አረጋ በተለያዩ የአሜሪካ ከተሞች በኢትዮጵያውያን መንግሥትን በመደገፍ ሰልፍ የተደረገበትን የትናንቱን ቀን "በኢትዮጵያ የዲያስፖራ ታሪካዊ ቀን ነው" ሲሉ ትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል። በአውሮፓ እና አሜሪካ በሚገኙ ከተሞች ከተደረጉት የድጋፍ ሰልፎች በተጨማሪ፤ በትዊተር ላይ ሰዎች ደምጻቸውን ለማሰማት አደባባይ ይዘው የወጡት #Handsoff መፈክር ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ጊዜ ሪትዊት ተደርጓል። የውጭ ጣልቃ ገብነት የፌደራሉ መንግሥት ከህወሓት አማጺያን ጋር እያደረገ ያለው ጦርነት በድርድር እንዲፈታ ምዕራባውያን አገራት እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በተደጋጋሚ ድምጻቸውን ሲያሰሙ ቆይተዋል። የአሜሪካ መንግሥት አስተዳደር ጦርነቱ ይቁም ከማለት ባሻገር በጦርነቱ ተሳታፊ ናቸው አልያም ጦርነቱ እንዲራዘም ምክንያት ናቸው ባለቸው ግለሰቦች ላይ እቀባ መጣሉ ይታወሳል። ከዚህ በተጨማሪም አሜሪካ ከትግራይ ጦርነት ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያ ተፈጽመዋል ያለቻቸውን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ምክንያት በማድረግ ኢትዮጵያን ብዙ ከምትጠቀምበት ከአጎዋ የንግድ ስምምነት ለማገድ መወሰኗ ይታወሳል። የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ ወደ ትግራዩ ጦነርት ተገዶ መግባቱን በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቷል። ምዕራባውያን በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ጦርነት እንዲቆምና ሰብአዊ እርዳታ በችግር ላይ ላሉ ሰዎች ያለገደብ እንዲደርስ ጫና እያደረጉ መሆናቸውን ቢገልጹም፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ግን ለአማጺያን ድጋፍ በማድረግ የመንግሥት ለውጥ እንዲመጣ እየሞከሩ ነው ሲል ይከሳል።
በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ የሚደረግ ጫናን የሚቃወሙ ሰልፎች በበርካታ አገራት ተደረጉ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን በሰሜን አሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና እስራኤልን ጨምሮ በበርካታ ከተሞች የምዕራብ አገራትን ጫና በመቃወም ለኢትዮጵያ መንግሥት ያላቸውን ድጋፍ አደባባይ በመውጣት ገለጹ። ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን የኢትዮጵያ መንግሥት ከህወሓት አማጺያን ጋር በሚያደርገው ጦርነት ምዕራባውያን አገራት ለፌደራሉ መንግሥት ድጋፍ እንዲሰጡ ጠይቀዋል። መንግሥታዊው ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ በ27 ከተሞች የድጋፍ ሰልፉ መካሄዱን ዘግቧል። የድጋፍ ሰልፉ ከተደረገባቸው ከተሞች መካከል፤ ዋሽንግተን ዲሲ፣ ኒው ዮርክ፣ ሎስ አንጀለስ፣ ኦስቲን፣ ሂውስተን፣ ቶሮንቶ፣ ኦታዋ፣ ካልጋሪ፣ ዊኒፒግ እና ለንደን ተጠቃሽ ናቸው። የካናዳው ሲቢኤስ ኒውስ በካናዳዋ ማኒቶባ ግዛት ዊኒፒግ ከተማ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የኢትዮጵያ መንግሥት ከህወሓት ጋር በሚያደርገው ጦርነት የካናዳ መንግሥት ለኢትዮጵያ መንግሥት ድጋፍ እንዲያደርግ አደባባይ ወጥተው ጠይቀዋል ሲል ዘግቧል። በዊኒፒግ ከተማ የተዘጋጀውን የድጋፍ ሰልፍ ካስተባበሩት መካከል አንዱ የሆኑት ማርቆስ ተገኝ፤ "በኢትዮጵያ ውስጣዊ ጉዳይ በተለይ አሜሪካ ጣልቃ መግባት ማቆም አለባት፤ ኢትዮጵያውያን የራሳቸውን ችግር በራሳቸው እንዲፈቱ መፍቀድ አለባት" ሲሉ ሲቢኤስ ኒውስ ተናግረዋል። በሌላኛዋ የካናዳ ከተማ ካልጋሪ ተመሳሳይ የድጋፍ ሰልፍ መካሄዱን ሲቲቪ ኒውስ ካልጋሪ ዘግቧል። ለፌደራሉ መንግሥት ድጋፍ ለመስጠት በተጠራው ሰልፍ ላይ ሰዎች #NoMore (ከአሁን በኋላ ይብቃ) እንዲሁም #Handsoff (እጃችሁን አንሱ) የሚሉ መፈክሮችን ይዘው መውጣታቸው ሲቲቪ ኒውስ ካልጋሪ አሳይቷል። በተመሳሳይ በአሜሪካ ቴክሳስ ግዛት ኦስቲን ከተማ ተመሳሳይ ድጋፍ አድርገዋል። "እነዚህ በኢትዮጵያ ያሉ ጉዳዮች ናቸው፤ እራሳችን መፍታት እንችላለን። እዚህ የተገኘነው እባካችሁ አቁሙ፤ የራሳችንን ጉዳይ እራሳችን እንፈታዋለን ለማለት" በማለት የኦስቲን ሰልፍ ተሳታፊ የሆነው ቴድ ኃይሉ ለሲቢኤስ ኦስቲን ተናግሯል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ በተለያዩ ከተሞች የተካሄዱ ሰልፎችን የሚያሳዩ ፎቶግራፎችን በማጋራት "...ለእውነት ለቆሙ ኢትዮጵያውያን እና የአፍሪካ ቀንድ ዳያስፖራዎች አድናቆቴን እገልጻለሁ" ብለዋል። በየአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ፍጹም አረጋ በተለያዩ የአሜሪካ ከተሞች በኢትዮጵያውያን መንግሥትን በመደገፍ ሰልፍ የተደረገበትን የትናንቱን ቀን "በኢትዮጵያ የዲያስፖራ ታሪካዊ ቀን ነው" ሲሉ ትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል። በአውሮፓ እና አሜሪካ በሚገኙ ከተሞች ከተደረጉት የድጋፍ ሰልፎች በተጨማሪ፤ በትዊተር ላይ ሰዎች ደምጻቸውን ለማሰማት አደባባይ ይዘው የወጡት #Handsoff መፈክር ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ጊዜ ሪትዊት ተደርጓል። የውጭ ጣልቃ ገብነት የፌደራሉ መንግሥት ከህወሓት አማጺያን ጋር እያደረገ ያለው ጦርነት በድርድር እንዲፈታ ምዕራባውያን አገራት እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በተደጋጋሚ ድምጻቸውን ሲያሰሙ ቆይተዋል። የአሜሪካ መንግሥት አስተዳደር ጦርነቱ ይቁም ከማለት ባሻገር በጦርነቱ ተሳታፊ ናቸው አልያም ጦርነቱ እንዲራዘም ምክንያት ናቸው ባለቸው ግለሰቦች ላይ እቀባ መጣሉ ይታወሳል። ከዚህ በተጨማሪም አሜሪካ ከትግራይ ጦርነት ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያ ተፈጽመዋል ያለቻቸውን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ምክንያት በማድረግ ኢትዮጵያን ብዙ ከምትጠቀምበት ከአጎዋ የንግድ ስምምነት ለማገድ መወሰኗ ይታወሳል። የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ ወደ ትግራዩ ጦነርት ተገዶ መግባቱን በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቷል። ምዕራባውያን በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ጦርነት እንዲቆምና ሰብአዊ እርዳታ በችግር ላይ ላሉ ሰዎች ያለገደብ እንዲደርስ ጫና እያደረጉ መሆናቸውን ቢገልጹም፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ግን ለአማጺያን ድጋፍ በማድረግ የመንግሥት ለውጥ እንዲመጣ እየሞከሩ ነው ሲል ይከሳል።
https://www.bbc.com/amharic/news-59370730
2health
ኮሮናቫይረስ፡ የኦክስፎርድ-አስትራዜኔካ ክትባት በህጻናት ላይ ሊሞከር ነው
የኦክስፎርድ-አስትራዜኔካ ክትባት በህጻናት ላይ ምን ያህል ውጤታማ ይሆናል የሚለውን ለማጣራት አዲስ የክትባት ሙከራ መጀመሩ ተገልጿል። የመጀመሪያዎቹ ዙር የክትባት ሙከራዎች በያዝነው ወር መጨረሻ አካባቢ የሚጀመሩ ሲሆን በነዚህ ሙከራዎችም እስከ 300 የሚደርሱ በጎ ፈቃደኛ ህጻናት ይሳተፋሉ ተብሏል። ተመራማሪዎቹ እንደሚሉት ይህ ሙከራ እድሜያቸው ከ6 እስከ 17 የሆኑ ህጻናት የኦክስፎርድ-አስትራዜኔካ ክትባትን ከወሰዱ በኋላ ምን ያህል የመከላከል አቅማቸው ይጠነክራል የሚለውን ለማወቅ ወሳኝ ነው። ይህ ክትባት ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ በኮሮረናቫይረስ ምክንያት የሚከሰት ከፍተኛ ህመምን አልያም ሞትን ለመቀነስ ጥቅም ላይ እየዋለ ሲሆን የፋይዘር-ባዮንቴክ ክትባትም ቢሆን ለተመሳሳይ አገልግሎት ጥቅም ላይ እየዋለ ነው። በህጻናቱ ላይ በሚደረገው ሙከራ እስከ 240 የሚደርሱት ተሳታፉዎች የኦክስፎርድ-አስትራዜኔካ ክትባትን እንዲወስዱ የሚደረግ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ የማጅራት ገትር መድሀኒት በተመጠነ መልኩ እንዲወስዱ ይደረጋሉ ተብሏል። የክትባት ሙከራው በሚደረግባቸው አራት ማዕከላት፤ ዩኒርሲቲ ኦፈ ኦክስፎርድ፣ ሴንት ጆርጅ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል፣ ለንደን፣ ሳውዝሀም[ፕተን ዩኒቨርሲቲተ ሆስፒታል እና ብሪስቶል የህጻናት ሆስፒታል አቅራቢያ የሚኖሩ በጎ ፈቃደኞች በቶሎ እንዲመዘገቡ ተጠይቀዋል። ለመሳተፍ በጎ ፈቃደኛ የሆኑት ህጻናት ሙከራው ከመጀመሩ በፊት ግን ለይቶ ማቆያ መግባት ግዴታ እንደሆነ ተነግሯል። በዩናይትድ ኪንግደም እስካሁን የኦክስፎርድ-አስትራዜኔካ ክትባትን ለህጻናት ለመስጠት ምንም የታሰበ ነገር እንደሌለ የተገለጸ ሲሆን ለጊዜው ግን እድሜያቸው ከ28 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች ብቻ ናቸው ክትባቱን እየወሰዱ የሚገኙት። የፋይዘር-ባዮንቴክ ክትባት ደግሞ እድሜያቸው ከ16 ዓመት በላይ ለሆኑ ሰዎች ተፈቅዷል። በክትባቱ አሰጣጥ ስርአት መሰረት እድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎችና ህጻናት በጠና ቢታመሙ እንኳን ክትባቱ አይሰጣቸውም። የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ በበኩሉ እድሜያቸው ከ6 እስከ 17 ለሆኑ ህጻናት ክትባቱን መስጠት ምን አይነት አሉታዊና አዎንታዊ ተጽዕኖዎች እንደሚኖሩት ለማወቅ የሚደረገው ይህ ሙከራ የመጀመሪያው ይሁን እንጂ ከዚህ በኋላ በርካታ ሙከራዎች እንደሚደረጉ አስታውቋል።
ኮሮናቫይረስ፡ የኦክስፎርድ-አስትራዜኔካ ክትባት በህጻናት ላይ ሊሞከር ነው የኦክስፎርድ-አስትራዜኔካ ክትባት በህጻናት ላይ ምን ያህል ውጤታማ ይሆናል የሚለውን ለማጣራት አዲስ የክትባት ሙከራ መጀመሩ ተገልጿል። የመጀመሪያዎቹ ዙር የክትባት ሙከራዎች በያዝነው ወር መጨረሻ አካባቢ የሚጀመሩ ሲሆን በነዚህ ሙከራዎችም እስከ 300 የሚደርሱ በጎ ፈቃደኛ ህጻናት ይሳተፋሉ ተብሏል። ተመራማሪዎቹ እንደሚሉት ይህ ሙከራ እድሜያቸው ከ6 እስከ 17 የሆኑ ህጻናት የኦክስፎርድ-አስትራዜኔካ ክትባትን ከወሰዱ በኋላ ምን ያህል የመከላከል አቅማቸው ይጠነክራል የሚለውን ለማወቅ ወሳኝ ነው። ይህ ክትባት ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ በኮሮረናቫይረስ ምክንያት የሚከሰት ከፍተኛ ህመምን አልያም ሞትን ለመቀነስ ጥቅም ላይ እየዋለ ሲሆን የፋይዘር-ባዮንቴክ ክትባትም ቢሆን ለተመሳሳይ አገልግሎት ጥቅም ላይ እየዋለ ነው። በህጻናቱ ላይ በሚደረገው ሙከራ እስከ 240 የሚደርሱት ተሳታፉዎች የኦክስፎርድ-አስትራዜኔካ ክትባትን እንዲወስዱ የሚደረግ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ የማጅራት ገትር መድሀኒት በተመጠነ መልኩ እንዲወስዱ ይደረጋሉ ተብሏል። የክትባት ሙከራው በሚደረግባቸው አራት ማዕከላት፤ ዩኒርሲቲ ኦፈ ኦክስፎርድ፣ ሴንት ጆርጅ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል፣ ለንደን፣ ሳውዝሀም[ፕተን ዩኒቨርሲቲተ ሆስፒታል እና ብሪስቶል የህጻናት ሆስፒታል አቅራቢያ የሚኖሩ በጎ ፈቃደኞች በቶሎ እንዲመዘገቡ ተጠይቀዋል። ለመሳተፍ በጎ ፈቃደኛ የሆኑት ህጻናት ሙከራው ከመጀመሩ በፊት ግን ለይቶ ማቆያ መግባት ግዴታ እንደሆነ ተነግሯል። በዩናይትድ ኪንግደም እስካሁን የኦክስፎርድ-አስትራዜኔካ ክትባትን ለህጻናት ለመስጠት ምንም የታሰበ ነገር እንደሌለ የተገለጸ ሲሆን ለጊዜው ግን እድሜያቸው ከ28 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች ብቻ ናቸው ክትባቱን እየወሰዱ የሚገኙት። የፋይዘር-ባዮንቴክ ክትባት ደግሞ እድሜያቸው ከ16 ዓመት በላይ ለሆኑ ሰዎች ተፈቅዷል። በክትባቱ አሰጣጥ ስርአት መሰረት እድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎችና ህጻናት በጠና ቢታመሙ እንኳን ክትባቱ አይሰጣቸውም። የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ በበኩሉ እድሜያቸው ከ6 እስከ 17 ለሆኑ ህጻናት ክትባቱን መስጠት ምን አይነት አሉታዊና አዎንታዊ ተጽዕኖዎች እንደሚኖሩት ለማወቅ የሚደረገው ይህ ሙከራ የመጀመሪያው ይሁን እንጂ ከዚህ በኋላ በርካታ ሙከራዎች እንደሚደረጉ አስታውቋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-56059659