Datasets:
headline
stringlengths 2
1.42k
| category
stringclasses 6
values | date
stringlengths 9
35
| views
stringlengths 1
7
| article
stringlengths 63
36.2k
| link
stringlengths 28
740
| word_len
int64 16
6.74k
| label
class label 6
classes |
---|---|---|---|---|---|---|---|
የኦሊምፒክ ማጣሪያ ተሳታፊዎች የሚለዩበት ቻምፒዮና እየተካሄደ ይገኛል | ስፖርት | January 14, 2021 | 2 | ብርሃን ፈይሳየኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን በየዓመቱ የሚያዘጋጀው የክለቦች ቻምፒዮና በአዲስ አበባ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል። የተሻለ ብቃት ያሳዩ ቦክሰኞች ለቶኪዮ ኦሊምፒክ ማጣሪያ ተሳታፊ እንደሚሆኑም ታውቋል።በቦክስ ስፖርት ከሚካሄዱት ዓመታዊ ቻምፒዮናዎች መካከል አንዱ በክለቦች መካከል የሚካሄደው ነው፤ የዚህ ውድድር የመጀመሪያው ዙር በአዲስ አበባ ከተማ ተጀምሯል። የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን ከአዲስ አበባ ቦክስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር በተዘጋጀው በዚህ ቻምፒዮና፤ ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከሰት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደ ውድድርም ነው። በውድድሩም ላይ አምስት ክለቦች ከአዲስ አበባ (ፌዴራልፖሊስ፣ ፌዴራል ማረሚያ ቤቶች፣ አዲስ አበባ ፖሊስ፣ የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ እና ኦሞቲክ ቦክስ)፣ ሁለት ክለቦች ከአማራ ክልል (ጎንደር ከነማ እና ደሴ ከነማ) እንዲሁም ድሬዳዋ ከነማ በድምሩ ስምንት ክለቦች ተሳታፊ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያሳያል። በአጠቃላይ ክለቦቻቸውን ወክለውም 12 ሴትና 76 ወንድ ቦክሰኞች በጥቅሉ 88 ተወዳዳሪዎች ተሳታፊ ይሆናሉ። ውድድሩ የሚካሄደው በራስ ኃይሉ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል ሲሆን፤ በ10 ክብደቶች በ49፣ 52፣ 57፣ 60፣ 63፣ 69፣ 70፣ 81፣ 89 እና 91 ኪሎ ግራሞች እየተካሄደም ይገኛል። የቦክስ ስፖርት ከንክኪ ስፖርቶች መካከል አንዱ እንደመሆኑ ጨዋታው በሚካሄድበት ወቅት ቦክሰኞቹ አካላዊ ቅርርብ ሊያደርጉ እና ሊነካኩ ይችላሉ። በመሆኑም በዚህ ረገድ ውድድሩ ሙሉ ለሙሉ የኮቪድ 19 ጥንቃቄን በተላበሰ መልኩ እየተካሄደ መሆኑን ነው ፌዴሬሽኑ ያረጋገጠው። ይኸውም ተወዳዳሪዎችና አሰልጣኞች የኮቪድ ምርመራ እንዲያደርጉና ከሌሎች ሰዎች ጋር እንዳይገናኙ በካምፕ እንዲቆዩ በማድረግ ነው። ከዚህ ባሻገር ውድድር የሚደረግበት ሪንግ ቶሎ ቶሎ በኬሚካል እንዲጸዱ እንዲሁም ተመልካቾች ውድድሩ ላይ እንዳይገኙም ተደርጓል። ኮቪድ 19 ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ እንደመሆኑ በመላው ዓለም ስፖርታዊ ውድድሮች ተቋርጠው መቆየታቸው የሚታወስ ነው። ከእነዚህ ውድድሮች መካከል ለቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ የቦክስ ስፖርት ማጣሪያ የሚካሄደው ውድድር ይጠቀሳል። ውድድሮች ወደ እንቅስቃሴ መግባታቸውን ተከትሎም ማጣሪያው የሚቀጥል ይሆናል። ኢትዮጵያም በዚህ ቻምፒዮና (በመጀመሪያው ዙር) የተሻለ ብቃት ያሳዩ ቦክሰኞችን በማጣሪያው የምታሳትፍ መሆኑ ታውቋል። ቻምፒዮናው አራት ዙሮች ያሉት ሲሆን፤ ሁለተኛው ዙር ከአማራ ክልል ቦክስ ፌዴሬሽን ጋር በመሆን ጎንደር ላይ፣ ሶስተኛውን ከደቡብ ክልል ቦክስ ፌዴሬሽን ጋር በመሆን ወላይታ እንዲሁም የመጨረሻውና የማጠቃለያው ውድድር አዲስ አበባ ላይ የሚካሄድም ይሆናል። ቻምፒዮናው ጥር 4/2013 ዓም የተጀመረ ሲሆን እስከ ጥር 7/2013 ዓም ድረስም ይቆያል። | https://www.press.et/Ama/?p=39481 | 298 | 2ስፖርት
|
አዲስ ዘመን ድሮ | መዝናኛ | December 28, 2020 | 4 | የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ቀደምት ዘገባዎች በእጅጉ ተነባቢ ዛሬም ላገኛቸው በእጅጉ ተነባቢ ናቸው።እኛም ከእነዚህ ዘገባዎች ጋዜጣው በ1950ቹ ያስነበባቸውን ወጣ ያሉ ዘገባዎች ለዛሬ ይዘንላችሁ ቀርበናል። በዛሬው የአዲስ ዘመን ዱሮ አምዳችን አዲስ ዘመን ጋዜጣ በ1950ዎቹ ይዟቸው ከወጣ ዘገባዎች በአዘጋገባቸውና በይዘታቸው ተነባቢ ናቸው ያልናቸውን እና ሌሎች አስደናቂ ዘገባዎችን ይዘን ቀርበናል። ማገጃ ምልክት ይሰጠውማንኛውም የሥራ ድርጅት በብዙ ድካም ከተቋቋመ በኋላ አስፈላጊው ጥንቃቄ ካልተደረገለት የተሠራው እንዳልተሠራ የነበረው እንዳልነበር መሆኑ የማይጠረጠር ነው።በሲዳሞ ጠ/ግዛት ዋና ከተማ ይርጋዓለም የቴሌኮሙኒኬሽን ቦርድ ያቋቋመው ከፍተኛ መሥሪያ ቤት ይገኛል። የተቋቋመውም በትልቁ መኪና መንገድ አጠገብ ስለሆነ ፤ተሽከርካሪዎች የሚመላለሱበት ቦታ ነው።አንዳንድ ጊዜም ከባድ ጭነት የያዙ መኪናዎች ለምሳሌ አውቶቡስን የመሳሰሉት በሁለተኛው መንገድ እንዲያልፉ የሚታዘዙበት ቀን ስለሚያጋጥም በተጠቀሰው መሥሪያ ቤት አደባባይ የሚገኙትን ሽቦዎች ሳይመለከቱ ለማለፍ ሲሞክሩ በብዙ መጯጯህ ስልኩ ሽቦ ከመጣስ የዳነበትና መኪናውንም ለመመለስ የቻለበትን ጊዜ ለማታወስ የማይችል የለም፤ ታናናሽ መኪናዎችን ለማሳለፍ የቦታው ስፋት ይፈቅዳል።ስለ ታላላቅ መኪናዎች ግን የክፍሉ ባለሥልጣን የማገጃ ምልክት ቢያደርግበት የሚሻል መሆኑን አስታውሳለሁ። አቧራ አዋዜ አይደለም። በዚሁ ከተማ ትልቁን
መንገድ በመከተል አልፎ
አልፎ በሚገኙት ሰፈሮች
ብዙዎች የልኳንዳ ሥጋ
የተሰቀለባቸውና ፉርኖ ይህንንም የመሳሰሉት ምግቦች የተደረደረባቸው ቤቶች ይገኛሉ። ሥጋው የሚገኝበት ብዙ ቦታ በረንዳ ስለሆነ ማናቸውም ተንቀሳቃሽና ይልቁንም በማይቋረጠው የመኪና ኃይል ከመንገዱ ላይ የሚነሳው አቧራ በሥጋውና በማናቸውም ምግብ ላይ ሲሰፍርበት ይታያል።ለማስረጃ ያህል በመንገዱ ዳር የሚገኘውን የቡና የሌላውንም ቅጠል የተመለከትን እንደሆነ በአንዱ ቅጠል ላይ ብቻ አንድ ጥርኝ የሚሞላ አቧራ ስለምናገኝ በየቀኑ በያንዳንዱ ብልት ሥጋ ላይ ተደባልቆ ወደ ሆድ የገባውን አቧራ ለመገመት እንችላለን። ስለዚህ ሥጋና ፉርኖ ይህንንም የመሳሰለ ምግብ የሚያሰናዱ ነጋዴዎች ለዚሁ አገልግሎት በዘመናዊ ዕቅድ በተሰናዳው መስታወት ውስጥ ማኖር ይገባቸዋል።ይህም ባይቻል አቧራ ወደሌለበት ሁለተኛው መንገድ እንዲዛወሩ ማድረግ ስለሚገባ ፤ሥራው የሚመለከተው ባለሥልጣን ያስብበት ዘንድ ሳስታውስ በትሕትና ነው። መመሳሰል ይገባዋልበዚሁ ከተማ የሚገኘው የጠቅላይ ግዛቱ በጅሮንድ ጽ/ቤት በሦስት ቦታ ተከፋፍሎ የሚገኝ ከመሆኑም በላይ ቤቱም በጠላት ጊዜ የተሠራ አሁን መፍረስ የጀመረ ነው።ስለ የውስጥ ዕቃውም አጠባበቅ ከቤቱ ይልቅ ዘበኞቹንና ካዝናውን ማመን ግድ ሳይሆን አይቀርም። ይኸውም ሆኖ ለሥራው የተመጠነ ስፋት ያለው አይደለም። በአካባቢው የሚገኙት ቢሮዎች በአማረና በጥሩ ሕንፃ የተሠሩ ሲሆኑ፤ የተጠቀሰው መሥሪያ ቤት እርጅና የእነሱን ውበት ግርማ አሳንሶታል።ስለዚህ ጓደኞቹን እንዲመስል የክፍሉ ባለሥልጣን ይተጋበት ዘንድ ማሳሰብ የጋዜጣው ፋንታ ነው። የሲዳሞ ጠ/ግዛት አዣንስ ኃይለ መስቀል ወልደየስ (የካቲት 20 ቀን 1951 የወጣው አዲስ ዘመን) ሁለት ወንዶች ልጆችእናት በአስር ቀን ልዩነት ሁለት ወንዶች ልጆች ወለደች። በወቅቱ ዜናው ጋዜጣችን ላይ ሲወጣ ርዕሰ ዜናው ከላይ እንደተጠቀሰው ሁለት ወንዶች ልጆች ብቻ ነበር የሚለው በሚከተለው መልኩ ተዘግቦ ስለነበር እንድታነቡት እንጋብዛለን። በደብረ ታቦር ከተማ ዙሪያ ቃናት ማርያም ከተባለው አገር የአቶ መኰንን ካሳ ባለቤት ያልጋነሽ አድማሱ የተባለችው ፤ጥር 22 ቀን 51ዓ.ም ከሌሌቱ 8 ሰዐት ሲሆን አንድ ወንድ ልጅ ከወለደች በኋላ 10 ቀን ቆይታ የካቲት 2 ቀን 1951 ዓ.ም ከጥዋቱ 1 ሰዐት ሲሆን አንድ ወንድ ልጅ ደግማ መውለዷንና ሁለቱም ልጆች እስካሁን በሕይወታቸው መኖራቸውን የነዚሁ ልጆች አባት አቶ መኰንን ካሳ አስታውቀውናል። የደብረ ታቦር ከተማው ዙሪያ ምክትል ገዥ ባላምባራስ ኃይሌ ታምራት በቁጥር100/1951የካቲት 10 ቀን በተጻፈ ደብዳቤ አረጋግጠውልናል።እኒህ የምክትል ወረዳ ገዥ እንደዚህ ያለው ሁኔታ በጋዜጣ እንዲገለጥ በቶሎ ለአውራጃው ግዛት አዣንስ ጽ/ቤት በማስተላለፋቸው እናመሰግናለን። ሌላዎችም ምክትል ገዥዎች የርሳቸውን አርአያ ተከትለው ይህን የመሰለ ጉዳይ ሲያጋጥማቸው በፍጥነት የሚያስታውቁን ቢሆን ከፍ ያለ ምስጋና የሚያገኙበት መሆኑን እንገልጻለን።የደብረ ታቦር አውራጃ አዣንስ አሰፋ ረታ (የካቲት 17 ቀን 1951 የወጣው አዲስ ዘመን) | https://www.press.et/Ama/?p=38334 | 475 | 1መዝናኛ
|
የአረንጓዴ ጎርፍ በጎ አድራጎት አምባሳደሮች ተሰየሙ | ስፖርት | January 6, 2021 | 6 | ቦጋለ አበበየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን ከኢትዮጵያ አረንጓዴ ጎርፍ የአትሌቲክስ የበጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተባበር‹‹የገና በዓልን ከአንጋፋ አትሌቶች ጋር እናሳልፍ›› በሚል ትናንት በኢትዮጵያ ሆቴል በተዘጋጀው የእውቅናና የሽልማት መድረክ የበጎ አድራጎት ድርጅቱ ሁለት አምባሳደሮች ተሰይመዋል፡፡ በዚህም ከሴት ፈር ቀዳጇ የአንድ ሺ አምስት መቶ ሜትር የቀድሞ ኮከብ አትሌት ኮማንደር ቁጥሬ ዱለቻ የተሰየመች ሲሆን በወንድ ፋና ወጊው የኦሊምፒክ የሦስት ሺ ሜትር መሰናክል የነሐሴ ሜዳሊያ ባለቤትና የርቀቱ አሰልጣኝ ሻምበል እሸቱ ቱራ የዕውቅና አምባሳደርነት የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።አምባሳደሮቹ በተሰየሙበት መርሃግብር በህይወት ዘመናቸው ለኢትዮጵያ ስፖርት የላቀ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ግለሰቦች የዕውቅናና የምስጋና ካባ እንዲሁም የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል፡፡ አንጋፋው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሐኪም ዶክተር አያሌው ጥላሁን እንዲሁም አንጋፋው የስፖርት ጋዜጠኛ ሰለሞን ገብረእግዚያብሔር የዕውቅናና የምስክር ወረቀት ከተቀበሉ በኋላ በሞሀ ለስላሳ መጠጦች እንዱስትሪ አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጌታቸው ቢርቦ የክብር ካባ ተጠልቆላቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ አረንጓዴ ጎርፍ አትሌቲክስ የበጎ አድራጎት ድርጅት መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ አትሌት መልካም ተገኝ፣ ‹‹መረዳዳት በህይወት›› በሚል ሀሳብ ለአገራቸው የሰሩ፣ የለፉ ፣ የደከሙና ለአገር ክብር የተጉ አትሌቶችንና ቀጣይ ተተኪዎችን በማንኛውም ማህበራዊ ህይወታቸው ለመታደግ በጎ አድራጎት ድርጅቱ መመስረቱን ጠቅሰው ለዚህ የተቀደሰ አላማ ሁሉም አካላት ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽነር በላይ ደጀን በበኩላቸው ‹‹መረዳዳት በህይወት›› የሚለው መሪ ቃል በጎ አድራጎት ድርጅቱን እንደሚወክል በመግለፅ፣ ለአገራቸው ክብር ፣ ህዝብና ባንዲራ የለፉ አንጋፋ አትሌቶችና ጋዜጠኞች እንዲሁም ሌሎች ባለሙያዎች በዚህ ደረጃ ዕውቅና ማግኘታቸው ተገቢ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ በቀጣይ በጎ አድራጎት ድርጅቱ የበለጠ ውጤታማ እንዲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን በጋራ እንደሚሰሩም ቃል ገብተዋል፡፡ በክብር እንግድነት የተገኙት የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዱቤ ጅሎ በበኩላቸው ይህን በጎ አላማ እውን ላደረጉና መርሃግብሩን ላዘጋጁና ለዚህ ያበቁ የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን አመራሮችን አመስግነዋል። በርካታ አንጋፋ አትሌቶች በመርሃግብሩ ታድመውም የእውቅናና የምስክር ወረቀት ተቀብለዋል፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 28/2013 | https://www.press.et/Ama/?p=39010 | 265 | 2ስፖርት
|
የሊጉ በቢዝነስ ሞዴል መመራት አበረታች ጅምር መሆኑ ተገለጸ | ስፖርት | January 6, 2021 | 5 | ብርሃን ፈይሳአዲስ አበባ፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በሼር ካምፓኒ እንዲተዳደር መደረጉና የቴሌቪዥን ሽፋን ማግኘቱ ለሌሎች ስፖርቶችም አበረታች ጅምር መሆኑ ተገለጸ። በብሄራዊ ስፖርት ምክር ቤት የ2013ዓም የስፖርት ዘርፍ አፈጻጸም ሰነድ ላይ እንደተመለከተው፤የሃገሪቷ ስፖርት በቢዝነስ ሞዴል እንዲመራ በማድረግ ረገድ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሪሚየር ሊጉን (ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ) በሼር ካምፓኒ እንዲመራ ማድረጉ መልካም ጅማሬ ነው። በአጭር ጊዜ ውስጥ የተደራጀው ካምፓኒው ውድድሩን የቴሌቪዥን መብት እንዲያገኝ እና የውድድር ስያሜውንም መሸጥ መቻሉ በስፖርት ላይ ትልቅ ተስፋን እና መነቃቃት ፈጥሯል። የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽነር ኤሊያስ ሽኩር፤ ሃገር አቀፍ የስፖርት ማህበራት ስፖርቱን በቢዝነስ ሞዴል ከመምራት አንጻር ሰፊ ስራ መሰራቱን ጠቅሰው፣ ለእዚህም በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሊግ ካምፓኒው መቋቋም ተጠቃሽ መሆኑን አመላክተዋል። የውድድሩ መሸጥ በተለይ ክለቦች በገቢ ራሳቸውን እንዲችሉ የሚያደርግ፣ ለተጫዋቾችም መልካም ዕድል የፈጠረና የሃገርን ገጽታ ለመገንባት ትልቅ አስተዋጽኦ ያደረገ ነው ነው ያሉት ኮሚሽነሩ፣በተመሳሳይ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብም ወደ አክሲዮን የተለወጠበት ሁኔታ ሌሎች ክለቦች ልምድ የሚወስዱበት ነው ብለዋል። ይህም በቢዝነስ ሞዴል ከመመራት አንጻር የተጀመሩ ስራዎች እንዳሉ ማሳያ መሆኑንም ጠቅሰዋል።የኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው በበኩላቸው፤ በዓመቱ
(2012ዓም) የሊግ ኮሚቴ በመፍጠር እግር ኳስ የስፖርታዊ ጨዋነትና የስፖርት መርህን የሚያከብር ዘርፍ እንዲሆን መደረጉ መልካም መሆኑን ጠቁመዋል። የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ራሱን መቻልም ለሌሎች እንዴት ራስን በገቢ መቻል ይቻላል የሚለውን ያሳየ መሆኑን ተናግረው፣ ጥሩ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ጠቋሚ ነው ብለዋል። ይህንንም አጠናክሮና ተባብሮ ማስኬድ ከተቻለ በስፖርቱ የሚነሱ ጥያቄዎችና ችግሮች ይቀረፋሉ ሲሉም ተስፋቸውን አንጸባርቀዋል። ብሔራዊው የስፖርት ሪፎርም ክለቦችና የስፖርት ማህበራት በገቢ ራሳቸውን ችለው ከመንግስት ድጎማ እንዲላቀቁ እንዲሁም ሃብት እንዲያፈሩ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ያመላክታል። እንደ ኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን የአፈጻጸም ሪፖርት፤ መንግስት እስካሁን ከክልል እስከ ፌዴራል ባለው ደረጃ 163 ሚሊዮን 177ሺ 165 ብር ድጋፍ አድርጓል። ይህንን ለመቅረፍም ሃገር አቀፍ የስፖርት ማህበራት ያሉበት ሁኔታና ቁመና ለማወቅ ቅኝት በማድረግ ያሉበትን ደረጃ ለመለየት ጥረት ተደርጓል። የስፖርት ማህበራት ስፖርቱን በቢዝነስ ሞዴል በመምራት ከድጎማ የሚላቀቁበትና የራሳቸውን አቅም በማጎልበት የ10 ዓመቱን የስፖርት ልማት እቅድ ግቦች የሚያሳኩበትን ቁመና መፍጠርም በተያዘው ዓመት የኮሚሽኑ እቅድ መሆኑም ተጠቁሟል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 28/2013 | https://www.press.et/Ama/?p=39011 | 296 | 2ስፖርት
|
የኦሊምፒክ ሥራ አስፈፃሚው እስከ ቶኪዮ ኦሊምፒክ ማግስት ይቀጥላል | ስፖርት | January 6, 2021 | 12 | ቦጋለ አበበ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አርባ አምስተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ባለፈው እሁድ በሐዋሳ ከተማ ሲያካሂድ የተለያዩ ውሳኔዎች ተላልፈዋል፡፡ ባለፉት አራት ዓመታት ሲያገለግል ቆይቶ ዘንድሮ ይጠናቀቅ የነበረው የኮሚቴው የስራ አስፈፃሚና የፕሬዚዳንት የስልጣን ዘመን በመጪው ክረምት እስከሚካሄደው የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ማግስት ድረስ እንዲቀጥል ጉባዔው ወስኗል፡፡ የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ባለፈው ዓመት ሊካሄድ የነበረ ቢሆንም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ለአስራ ስድስት ወራት ተራዝሞ በመጪው ክረምት ሊካሄድ ቀን ተቆርጦለታል፡፡ ኮሚቴውን ሲመራ የነበረው ሥራ አስፈፃሚ በኦሊምፒኩ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የተለያዩ ዝግጅቶችን ሲያደርግ የቆየ ሲሆን ዘንድሮ የስራ ዘመኑን አጠናቆ በጠቅላላ ጉባዔ ምርጫ ይካሄድ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ኦሊምፒኩ በመራዘሙ ሲዘጋጅ የቆየው ስራ አስፈፃሚ የልፋቱን ውጤት እንዲመለከት እስከ ኦሊምፒኩ ማግስት እንዲቀጥል ጠቅላላ ጉባዔው ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ ጉባዔውን በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ፣ ኢትዮጵያ የአኖካን ጉባኤ ባስተናገደችበት ማግስት አስረኛ ክልል ሆኖ እንደ አዲስ በተዋቀረው የሲዳማ ክልል ጉባዔው መካሄዱ ልዩ እንደሚያደርገው ገልፀዋል፡፡ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ግዜ የአፍሪካ ወጣቶች ኦሊምፒክን በ2022 ለማስተናገድ እድል ባገኘችበት ማግስት በሲዳማ ክልል ዘንድሮ የኢትዮጵያ ወጣቶች ኦሊምፒክ ጨዋታ እንደሚካሄድም ጠቁመዋል፡፡ ኮሚቴው በቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ የአበበ ቢቂላን የ1964 የቶኪዮ ኦሊምፒክ ገድል ለመድገም በምትዘጋጅበት ወቅት ጉባዔውን ማካሄዱና በኮቪድ-19 ስጋት ውስጥ ሆኖ መከናወኑ ጉባዔውን የተለየ እንደሚያደርገውም ተናግረዋል፡፡ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው፣ ስፖርት የማህበራዊና ተፈጥሯዊ ሳይንስ ዘውግ መሆኑን ጠቅሰው ማህበራዊ ትስስርን በእጅጉ የሚፈጥር በመሆኑ ህብረተሰቡ ስፖርትን ባህሉ እንዲያደርግ የተጀመሩ እንቅስቃሴዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል። እስካሁን ድረስ በስፖርት ዘርፍ የተፈጠረው ተወዳዳሪነት ዝቅተኛ መሆኑን በመጥቀስም በአትሌትክስ ስፖርት ኢትዮጵያ ያስመዘገበችው ውጤት በሌሎችም እንዲደገም መሠራት እንዳለበት አብራርተዋል። ሚኒስትሯ የህብረተሰብ ስፖርትንም ለማስፋፋት በትምህርት ቤትና በስራ ቦታ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መሠራት እንዳለበት ገልፀዋል። የኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሸነር ኤሊያስ ሽኩር በበኩላቸው፣ 45ኛው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የተካሄደው በስፖርት ህብረተሰቡ ዘንድ መነቃቃት በተፈጠረበት ወቅትና በብሔራዊ የስፖርት ምክር ቤት መደበኛ አንደኛ ስብሰባ ትላልቅ ውሳኔዎች በተላለፈበት ወቅት መሆኑን አስታውሰዋል፡፡ የአኖካ ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ የተካሄደ መሆኑን ጠቅሰውም ሠላማዊና አስተማማኝ ሁኔታ በኢትዮጵያ መኖሩን አኖካ በማረጋገጡ ቀጣይ ስብሰባዎችን በራሱ ሙሉ ወጪ በኢትዮጵያ ለማካሄድ መነሳሳት እንዳሳየ አብራርተዋል። ለቶኪዮ 2020 የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ዝግጅት ማድረግ በተጀመረበት ወቅት ላይ ጉባዔው በስፖርት ምክር ቤት በተቀመጡ ወሳኔዎችና አቅጣጫዎች መሠረት በጥልቀት መምከር እንዳለበት አስረድተዋል፡፡ ስፖርት ለሠላም፣ ለወዳጅነት፣ ለአንድነት፣ለወንድማማችነትና ለብልፅግና መሆኑን በመገንዘብ ጠቃሚ ውይይት እንዲደረግ አሳስበዋል፡፡ የሲዳማ
ክልል
ርዕሰ
መስተዳድር
ፕሬዚዳንት
አቶ
ደስታ
ሌዳሞ
ጉባኤውን
በንግግር
የከፈቱ
ሲሆን፣በዕለቱ በስፖርት ላይ በመስራት እውቅና ለተሰጣቸው ፈርጦች ምስጋና አቅርበዋል። በጉባኤው በስፖርት አመራርነት በፌደራልና በክልል ደረጃ አገልግሎት ሲሰጡ ቆይተው በአሁኑ ጊዜ በተለያዩ አመራር ቦታዎች ላይ ለሚገኙ አካላት የእውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።ከነዚህም መካከል የቀድሞ
የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር
የነበሩትና በአሁኑ ወቅት
የደቡብ ብሔራዊ ክልላዊ
መንግስት ምክትል ፕሬዚዳንት
አቶ ርስቱ ይርዳው፣
የቀድሞ ወጣቶችና ስፖርት
ሚኒስትር ዴዔታ ወይዘሮ
ሃቢባ ሲራጅ፣ የቀድሞ
ወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር ዴዔታ የነበሩትና አሁን የደቡብ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዚዳንት በመሆን እያገለገሉ የሚገኙት አቶ ተስፋየ ይገዙ፣ የቀድሞ የኢፌዴሪ ምክትል ስፖርት ኮሚሽነርና አሁን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ጌታቸው ባልቻ የእውቅና ሽልማት ከተበረከተላቸው መካከል ዋነኞቹ ናቸው። ጠቅላላ ጉባዔው የ44ኛው መደበኛ ጉባኤ ቃለ ጉባኤ ፣ የ2012 ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና የውጪ ኦዲተር ሪፖርት መርምሮ ያፀደቀ ሲሆን የ2013 ዓ.ም ዕቅድና የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ቀጣይ 46ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔን በተመለከተ መክሮ ውሳኔ አስተላልፏል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 28/2013 | https://www.press.et/Ama/?p=39012 | 476 | 2ስፖርት
|
‹‹ሃገራዊ ችግሮችን ለማረምና አብሮነትን ለማጠናከር ስፖርት ወሳኝ ነው››- አቶ ደመቀ መኮንን የብሄራዊ ስፖርት ምክር ቤት ሰብሳቢ | ስፖርት | December 30, 2020 | 10 | ብርሃን ፈይሳ አዲስ አበባ፡- እንደ ሃገር እየታዩ ያሉትን ስብራቶችና ችግሮች ለማረምና የአብሮነትን ጉዞ ለማጠናከር ስፖርት ወሳኝ ሚና አለው ሲሉ የብሄራዊ ስፖርት ምክር ቤት ሰብሳቢ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን አስታወቁ። ለስፖርቱ ዘርፍ ተገቢው ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ተጠቆመ። የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የውጪ ጉዳይ ሚኒስትርና የብሄራዊ ስፖርት ምክር ቤት ሰብሳቢ ደመቀ መኮንን ትናንት የብሄራዊ ስፖርት ምክር ቤት የመጀመሪያ መደበኛ ጉባኤ በተካሄደበት ወቅት እንዳስታወቁት፤ ስፖርት የሰላምና የአብሮነት መሰረት፤ ሰላም ደግሞ ለስፖርት ሁነኛ ነባራዊ ሁኔታ ነው። በመሆኑም እንደ ሃገር ያሉትን ስብራቶችና በተለያየ መልክ የሚታዩ ችግሮችን ለማረምና የአብሮነት ጉዞን ለማጠናከር ስፖርት ወሳኝ ነው። አሁን ባለው ሃገራዊ ሁኔታ በጣም ብዙ ስብራቶች መኖራቸውን የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ጠቅሰው፣ እነዚህን ከመጠገንና አብሮነትን ከማጠናከር አኳያ ስፖርት ሁነኛ መስተጋብር መሆኑን አመልክተዋል። የስፖርቱ መርሆዎች በአንድም ሆነ በሌላ መልክ በአስር ዓመት ሃገራዊ ዕቅድ መሪ ሃሳብ ውስጥ የተንጸባረቁ መሆናቸውን ተናግረው፣ ከየትኛውም ተቋም በላይ ሃገሪቷ በመጪዎቹ ዓመታት በሚሰራው ስራ አፍሪካዊ የብልጽግና ተምሳሌት ትሆናለች የሚል መሪ ሃሳብ ተይዟል ብለዋል። በዚህ
ጭብጥ ውስጥም ዋና ዋና
የስፖርት መርሆዎች ይገኛሉ ያሉት
የምክር ቤት ሰብሳቢው፣ ‹‹የስፖርት
መርሆዎች ከብልጽግና እንዲሁም የስፖርት
መርሆዎች ከአብሮነት አኳያ፣ የስፖርት
መርሆዎች በወንድማማችነት፣ በወዳጅነት፣ ጤናማ ማህበረሰብን በመፍጠር
አብሮነትን የሚያስተሳስሩ እሴቶችን የተላበሱ ናቸው።
በመሆኑም ለእዚህ ኢንዱስትሪ ትኩረት
መስጠትና ማጠናከር ለራሳችንና ለሃገራችን
ስንል ትውልዱ የሚታወቅባቸውን ስፖርቶች
ለማስቀጠል ኃላፊነትና አደራም አለብን። የበለጠ ሆኖ ለመገኘት
ስንልም በጣም መሰረታዊውንና ስፖርትን
ከዚህ አኳያ ትርጉሙን ከፍ
አድርጎ መመልከት ያሻል›› ሲሉም አብራርተዋል። ስፖርት ተገቢው ትኩረት ሊሰጠው ይገባል የሚለው በምክር ቤቱ የተለመደ አባባል መሆኑን ጠቅሰው፣ ወደ ተግባር ተሟልቶ እስካልተገባ ድረስ አጉልቶ መያዝ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። ‹‹ታላላቅና የኩራታችን ምንጭ የሆኑ ስፖርተኞች በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና እያስገኙ በመጡበት ሂደት አሁን ላይ ሆነን ሌጋሲውን እንዴት ማስቀጠል እንችላለን፤ ስፖርትስ እንዴት በሃገሪቷ ብልጽግና ጉዞ ውስጥ ሁነኛ ቦታ ይዞ ይሄዳል በሚለው ላይ ኃላፊነት አለብን›› ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፣ ስፖርት በተወሰኑ አካላት ብቻ የሚታጠር መሆን እንደሌለበትም አስገንዝበዋል። ከታዳጊ ህጻናት እስከ ብሄራዊ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ድረስ ተሳትፎ ማድረግ እንደሚገባም ሰብሳቢው አመላክተዋል።በብዙ ትውልዶችና በጀግኖች ጥረት ስፖርቱ ዓለም አቀፋዊ ሆኗል፤ እነዚህ ጀግኖችም ሃገራቸውንም አስተዋውቀዋል፤ አሁንም በብዙ መልኩ ስፖርቱ ዓለም አቀፋዊ መሆን ይኖርበታል፤ ለዚህ ደግሞ ምቹ ሁኔታ ያስፈልጋል፤ በተለይ በታዳጊ ህጻናት ላይ ከተሰራ መጪው ዘመን በስፖርት ያለውን አቅም ወደ ውጤት መመንዘር ያስችላል ብለዋል።አዲስ ዘመን ታኅሳስ 21/2013 | https://www.press.et/Ama/?p=38512 | 336 | 2ስፖርት
|
በውድድር ወቅት በወረርሽኙ መከላከያ መመሪያዎች አተገባበር ላይ ስጋት እንዳለው ሚኒስቴሩ ጠቆመ | ስፖርት | December 30, 2020 | 3 | ብርሃን ፈይሳ አዲስ አበባ፡- ስፖርታዊ እንቅስቃሴና ውድድሮች በሚከናወኑበት ወቅት የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል የተቀመጡ መመሪያዎች አተገባበር ላይ ስጋት እንዳለው የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ትናንት በተካሄደው በብሄራዊ የስፖርት ምክር ቤት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን በጤና ሚኒስትር እንዲሁም በባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር የወጡ የኮቪድ 19 መከላከያ መመሪያዎችን ታሳቢ አድርጎ ውድድሮችንና እንቅስቃሴዎችን ለማከናወን ጥረት እየተደረገ መሆኑ መገለጹን አስታውቀው፣ የጤና ሚኒስቴር ግን በአተገባበሩ ላይ ስጋት እንዳለው ጠቁመዋል። በዚህ ወቅት የቫይረሱ ስርጭት ያለበት ምጣኔ ከ9-10 በመቶ ነው ያሉት ሚኒስትሯ፣ ከዚህ አኳያ ኢትዮጵያ የዓለም ጤና ድርጅት ከፍተኛ ስጋት አለባቸው በሚል ካስቀመጣቸው ሃገሮች ውስጥ ትመደባለች ብለዋል። መመሪያዎቹም ይህንን ተከትለው የወጡ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ አተገባበራቸው ላይ ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ አሳስበዋል። እንደ ዶክተር ሊያ ገለጻ፤ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ከተከሰተ ጀምሮ በስፖርት ዘርፍ ወረርሽኙን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተወሰዱ እርምጃዎች በርካታና የሚያስመሰግኑ ናቸው። በማህበረሰቡ ዘንድ የሚታየው በሽታውን የማቃለል ሁኔታ የሚስተዋል ሲሆን፣ ይህም በሁሉም ዘርፍ እየታየ ይገኛል፤ ይህን ችግር ለመፍታት አመራሮች ትኩረት ሊሰጡ ይገባል። መመሪያውን መከተልና ውድድሮችን ያለተመልካች ማካሄድ ያስፈልጋል ሲሉም አስገንዝበዋል። ሚኒስቴሩ በዚህ በኩል ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው፣ ለእዚህም ከታላቁ ሩጫ አዘጋጆች ጋር እየተሰራ ያለውን በአብነት ጠቅሰዋል። ታላቁ ሩጫን ለማካሄድ በሚደረገው ዝግጅት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከአዘጋጆቹ ጋር እየሰራ መሆኑንም ጠቅሰው፣ በውድድሩ የታቀደው ብዙ ቁጥር ያላቸው ተሳታፊዎችን ለማካተት መሆኑን አመልክተዋል። ይህን አሀዝ ለመቀነስ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል። ውድድሩን ከዚህ ቀደም ከነበረው ለየት ባለ ሁኔታ ለማድረግም ፈቃደኝነት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል። በአዲስ አበባ ያለው የወረርሽኝ መጠን በጣም ከፍተኛ የሚባል መሆኑን አመልክተው፣ መመሪያዎቹን ብቻ ማዘጋጀት ሳይሆን ለተግባራዊነቱም መስራት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።አዲስ ዘመን ታኅሳስ 21/2013 | https://www.press.et/Ama/?p=38515 | 233 | 2ስፖርት
|
ስፖርትን ከፖለቲካ የመለየት ፈተናዎች | ስፖርት | December 31, 2020 | 11 | ቦጋለ አበበ‹‹ስፖርትና ፖለቲካ አንድ ናቸው ወይም ጠንካራ ግንኙነት አላቸው›› ብለው የሚያምኑ በርካቶች የመሆናቸውን ያህል ‹‹ስፖርት ከፖለቲካ ነፃና ገለልተኛ ነው ወይም መሆን አለበት›› ብለው በምክንያት የሚሞግቱ ጥቂት አይደሉም።ከዚህ በተለየ መልኩ በዘመናዊው ዓለም ስፖርት የፖለቲካ መጠቀሚያ ዋነኛ መሳሪያ እየሆነ በመምጣቱ ነፃ ሊወጣ እንደሚገባ የሚሞግቱ አልጠፉም።እነዚህ ሞጋቾች ግን ስፖርትን ከፖለቲካ ሙሉ በሙሉ ነፃ ለማውጣት ወይም የመሰንጠቅ ፈተናዎች እንዳሉባቸው በርካታ ማሳያዎችን በመደርደር የሚከራከሩ የየዘርፎቹ ተንታኞች በዓለም ዙሪያ ድምፃቸውን ሲያሰሙ መገንዘብ ይቻላል።ባለፈው ዓመት በሞንቴ ካርሎ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የሰላምና የስፖርት ኮንፍረንስ ላይ ስፖርትን ከፖለቲካ የመነጠል ጉዳይ ብዙ ክርክር አስነስቷል። ‹ስፖርትና ሰላም› በሚል እኤአ 2007 ላይ በፈረንሳዊው የቀድሞ አትሌትና የዓለም ኦሊምፒያኖች ማህበር ፕሬዝዳንት ጆኤል ቦዞ የተመሰረተው ተቋም በሞንቴ ካርሎ የተካሄደው የስፖርትና ሰላም ኮንፍረንስ አዘጋጅ ነበር።ይህ ተቋም ‹‹ቻምፒዮኖች ለሰላም›› በሚል መርህ የስፖርቱ ዓለም ከዋክብቶችን በአምባሳደርነት በመያዝ ተፅዕኖው ከዓመት ዓመት እየጨመረ ይገኛል። ኮትዲቯራዊው የእግር ኳስ ኮከብ ዲዲየር ድሮግባ፣ ሰርቢያዊው የሜዳ ቴኒስ ኮከብ ኖቫክ ጆኮቪችና እንግሊዛዊቷ ስመ ጥር አትሌት ፓውላ ራድክሊፍ ከዚህ ተቋም አምባሳደሮች መካከል ይገኙበታል።ተቋሙ በሚያዘጋጃቸው ኮንፍረንሶች የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች፣ የፆታ እኩልነት፣ ስፖርትና ቴክኖሎጂ እንዲሁም ስደተኞችና የበጎ አድራጎት ስራዎች አጀንዳ ሆነው ይነሳሉ።ከዓለም ዙሪያ በርካታ ባለሙያዎች፣ የዓለም አቀፍ ስፖርት ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንቶችና ተወካዮቻቸው እንዲሁም መንግስታዊ ያልሆኑ ዓለም አቀፍ ተቋማት ኮንፍረንሱ ላይ ተገኝተውም በአጀንዳዎቹ ላይ ይወያያሉ።ስፖርትን ከየትኛውም አይነት የፖለቲካ ተፅዕኖ ነፃ ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በሚደረጉ ሰፊ ውይይቶች ቀልብ ከመሳባቸው ባሻገር መደምደሚያ ያልተበጀላቸው አጀንዳዎች ስፍር ቁጥር የላቸውም።የስፖርትና ሰላም ተቋም መስራቹ ቦዞ ስፖርትን ከፖለቲካ ተፅዕኖ መነጠል በሚቻልበት አከራካሪ ሁኔታ ላይ በሰጠው አስተያየት ‹‹ሁል ጊዜም ቢሆን የስፖርትን ገለልተኝነት እናከብራለን፣ ስፖርት ከሰላም ጋር እንዲቆራኝም ምክኒያታዊ ሆነን እንሰራለን›› በማለት ይናገራል።ቦዞ ስፖርት ከተለመደው ፖለቲካ ነፃ እንደሆነ በማመን ተቋሙ ስፖርትን ከፖለቲካ ጋር በማይገናኝበት በማንኛውም ሁኔታ ከተለያዩ አካላት ጋር ለመስራት ጥረት እንደሚያደርግም ያስረዳል።ይህም በየትኛውም የዓለም ክፍል ከሚገኝ አገር ጋር በመስራት የስፖርትን ዓለም አቀፋዊነት እስከ ማረጋገጥ እንደሚደርስ እምነቱ ነው።የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ስራ አስፈፃሚዎች በቅርቡ በሉዛን ባደረጉት ስብሰባ አትሌቶች የኦሊምፒክ መድረክ ላይ በፍፁም የፖለቲካ ተቃውሞ፣ የሐይማኖትና የዘረኝነት መልዕክት ማስተላለፍ እንደሌለባቸው ውሳኔ ላይ መድረሳቸው ይታወሳል። የኮሚቴው ፕሬዝዳንት ቶማስ ባኽ በቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ አትሌቶች የትኛውንም አይነት የፖለቲካ፣ የሐይማኖት፣ የዘርና መሰል ተቃውሞና መልዕክት እንዳያስተላልፉ ማሳሰቢያ መስጠታቸውን ተከትሎም ስፖርት ከፖለቲካ ነፃ መሆን አለበት የለበትም? የሚሉ ሙግቶች ፍጥጫ ፈጥረዋል። በኦሊምፒኩ ወቅት በየትኛውም ስፍራ አትሌቶች ለተፎካካሪዎቻቸው ክብር ማሳየት እንዳለባቸውም ፕሬዝዳንቱ ደጋግመው ሲናገሩ ይደመጣል። ቶማስ ባኽ ስፖርትን የፖለቲካ መጠቀሚያ የማድረግ አዝማሚያ እየሰፋ በመጣበት በዚህ ወቅት በኦሊምፒክ መድረክ አላስፈላጊ መልዕክቶችን ማስተላለፍ ምንም ጥቅም እንደሌለውና የዓለምን ሕዝቦች ከመነጣጠል የዘለለ ፋይዳ እንደማይኖረው ያምናሉ። ‹‹የኦሊምፒክ መድረክ ዓለም አቀፋዊ ይዘት ያለው አትሌቶች ስፖርታዊ ብቃታቸውን የሚያሳዩበት እንጂ የፖለቲካ ወይም ሌላ ፕሮፓጋንዳ የሚያስተላልፉበት አይደለም›› የሚሉት ቶማስ ባኽ፣ ስፖርትን የፖለቲካ መጠቀሚያ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት ለመታገል በመድረኩ እንደዚህ አይነት ማሳሰቢያዎችን ቀድሞ ማሳወቅ እንደሚገባ ይናገራሉ።የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የአትሌቶች ኮሚሽን ሊቀመንበር ኪርስቴይ ኮቬንትሪ ከዓመት በፊት በርካታ አትሌቶች ኦሊምፒክ መድረክ ላይ የፖለቲካ ተቃውሞ ለማድረግ ተገቢው ቦታ መሆኑን እንደሚያምኑ በመናገር የአትሌቶቹን ሃሳብ መደገፋቸው በዓለም አቀፉ ኮሚቴ ውስጥ የተከፋፈለ ሃሳብ እንዳለ አሳይተዋል። ይህንንም ተከትሎ አትሌቶች በኦሊምፒክ መድረክ የፖለቲካ ተቃውሞ ማድረግ፣ የሐይማኖትና የዘረኝነት መልዕክት ማስተላለፍ አለባቸው የለባቸውም የሚለው ሃሳብ አከራካሪ ሆኖ ቆይቷል፡፡የዓለም መንግስታት ስፖርትን ለፖለቲካ መጠቀሚያ የሚያደርጉበት አጋጣሚ እንዳለ ሁሉ ከፖለቲካው ትርፍ ጎን ለጎን በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ከሰላም ጋር ተያይዞ ለአገርና ለሕዝብ የሚጠቅሙ ክስተቶች ሲፈጠሩ ይታያል።ለአብነት ያህል የቦስኒያና ሄርዝጎቪኒያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከዓመት በፊት በሳራጄቮና ምስራቅ ሳራጄቮ ከተሞች የአውሮፓን ወጣቶች ኦሊምፒክ በጥምረት በማዘጋጀት ተሸላሚ ሆነዋል። ይህም እኤአ ከ1992 እስከ 1995 በቦስኒያ ተካሂዶ ከነበረው ደም አፋሳሽ ጦርነት ወዲህ ሁለቱ የተከፋፈሉ አገራት የዲፕሎማሲ ግንኙነት እንዲሻሻል አድርጓል።በሌላ መልኩ የወርልድ ቴኳንዶና ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ፌዴሬሽኖች በግልፅ የሚታወቅ የተቀናቃኝነት ታሪክ ቢኖራቸውም ጥቂት ልዩነቶቻቸውን ወደ ጎን ትተው ውድድሮችን አንድ ላይ ያካሄዱበት አጋጣሚ ከስፖርትም የዘለለ ትርጉም ነበረው።ወርልድ ቴኳንዶ መሰረቱን በደቡብ ኮሪያ ሲዎል ከተማ ያደረገ ሲሆን ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ መሰረቱ የሰሜን ኮሪያ ነው። ሁለቱ አካላት መቀመጫቸው በአውስትራሊያ ቬና ቢሆንም ሰሜን ኮሪያና ደቡብ ኮሪያን የመሰንጠቅ አቅም እንደነበራቸው ይታወቃል። በተመሳሳይ እንደ ጠላት የሚተያዩት ሰሜን ኮሪያና ደቡብ ኮሪያ ጉዳይ እስካሁን መቋጫ ያላገኘ ቢሆንም በ2018 የፒዮንግያንግ የበጋ ኦሊምፒክ የሁለቱ አገራት የሴቶች የሆኪ ስፖርት ቡድኖች አንድ ሆነው በመድረኩ መሳተፋቸው በሁለቱ አገራት መካከል የነበረውን የፖለቲካ ውጥረት ወደ ተሻለ የዲፕሎማሲ ደረጃ ያሸጋገረ ነበር። ከዚህ ኩነት አኳያ ፖለቲካና ስፖርትን ሙሉ በሙሉ እንዴት መነጠል እንደሚቻል ግልፅ እንዳልሆነ ብዙዎች ይስማማሉ።ስፖርትን ለሰላም መጠቀም ማንም የሚቃወመው ጉዳይ እንዳልሆነ ሁሉ በስፖርት ሽፋን የማይሆን የፖለቲካ ትርፍ ማጋበሻ የማዋል አዝማሚያም በተለያዩ አገራት ይስተዋላል።ዓለም አቀፋዊ ውድድሮችን ማዘጋጀት የሁሉም አገራት መንግስታት ፍላጎት የሚሆነው በዋናነት የአገርን ገፅታ ለመገንባት በማሰብ ነው። አምባገነን መንግስታት ይህን በመጠቀም የአገራቸውን የፖለቲካ ገፅታ ለመቀየር ሲሞክሩ ግን ይታያል።ለዚህ በርካታ ምሳሌዎችን መጥቀስም ይቻላል።በቅርቡ እንግሊዛዊው ቦክሰኛ አንቶኒ ጆሹአ ከሜክሲኳዊው ቦክሰኛ አንዲ ሩይዝ ጋር በሳውዲ አረቢያ ያደረገው የክፍለ ዘመኑ ምርጥ የተባለለት ግጥሚያ መነጋገሪያ ነበር።ሳውዲ አረቢያ በሰብዓዊ መብት አያያዝ ተወቃሽ አገር ከመሆኗ ባሻገር ከዓመት በፊት ቱርክ ኢስታንቡል በሚገኘው ኤምባሲዋ የተገደለው ጋዜጠኛ ጀማል ካሾጊ ጉዳይ አሁንም ድረስ መነጋገሪያ ነው።ያም ሆኖ ቦክሰኛው ጆሹአ በሳውዲ አረቢያው የቡጢ ፍልሚያ ወቅት የጀማል ካሾጊን ግድያ አዘዋል በሚል ሲ አይ ኤ ከፈረጃቸው የሳውዲው ልዑል ሞሐመድ ቢን ሳልማን ጋር ፎቶ በመነሳት በማህበራዊ መገናኛዎች መልቀቁ ውድድሩ በሳውዲ ከመካሄዱ በበለጠ ብዙ ቁጣን የቀሰቀሰ ነበር።ከዓመት በፊት ሁለተኛው የአውሮፓ ጨዋታዎች በቤላሩስ መዲና ሚኒስክ መካሄዱ ይታወሳል።ከአራት ዓመት በፊትም ይህ ውድድር በአዘርባጃን መዲና ባኩ ተካሂዶ ነበር።በሩሲያ የ2018 የዓለም ዋንጫን ጨምሮ በርካታ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ተካሂደዋል።በነዚህ አገራት የተጋነነ ባይሆንም ከሰብዓዊ መብት አያያዝ ጋር በተገናኘ ጥያቄዎች የሚነሱ በመሆናቸው አገራቱ ስፖርትን ለፖለቲካ ገፅታ መገንቢያነት ተጠቅመውታል የሚል ወቀሳ ይነሳል።ወደፊትም ቤጂንግ 2022 የበጋ ኦሊምፒክን የምታዘጋጅ ከተማ እንደመሆኗ በቻይና ሰሜን ምዕራብ ክፍል በዢንጃንግ የሚኖሩ የሙስሊም ማህበረሰቦች ላይ ከሚደርሰው የሰብዓዊ መብት ረገጣ ጋር ተያይዞ አወዛጋቢ ነገሮች መፈጠራቸው እንደማይቀር ተንታኞች ከወዲሁ ስጋታቸውን ይገልፃሉ። በተመሳሳይ ዓመት ከዚሁ ከሰብዓዊ መብት አያያዝ ጋር የምትታማው ኳታር የዓለም ዋንጫን ታስተናግዳለች። ሚድል ኢስተርን ኒውስ የተባለ ተቋም ያወጣው ሪፖርት እንደሚያመለክተው 1400 ስደተኞች ኳታር በምታስገነባቸው ስቴድየሞች ስራ ላይ እያሉ በችልተኝነት ሕይወታቸው አልፏል። ኳታር ምናልባት የተሳካ የዓለም ዋንጫ ካስተናገደች ግን ይህ ሁሉ ሊረሳ ይችላል።ኳታር ከሰብዓዊ መብት አያያዝ ጋር በተገናኘ በዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ዘንድ የጎደፈ ስሟንና ገፅታዋን ለመገንባት ታላላቅ ስፖርታዊ ውድድሮች በስፋት እያዘጋጀች የምትገኝ ሲሆን፣ የአገሪቱ ባለሃብቶችና መንግስት በአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች ክለቦችን ከፍተኛ ገንዘብ በማውጣት ሲገዙ ማየት እየተለመደ መጥቷል።አገሪቱ እኤአ የ2027 መላው ኤሽያ ጨዋታዎችን ለማዘጋጀት ከሌሎች የአካባቢው አገራት ጋር ጨረታ ውስጥ የገባች ሲሆን ይህንኑ ውድድር ከሦስት ዓመታት በኋላ በ2030 ለማዘጋጀት ፅኑ ፍላጎት እንዳላት መግለጿ ይታወቃል።ይህንንም የዲፕሎማሲ ቀውስ ውስጥ ከገባችው ጎረቤቷ ሳውዲ አረቢያ ጋር ጡንቻ ለመለካካት ያደረገችው እንደሆነ ተቺዎቿ ደጋግመው ያነሱታል፡፡ሳውዲ አረቢያና ኳታር የ2030 የመላው ኤሽያ ጨዋታዎችን ለማዘጋጀት ጨረታ ውስጥ ከገቡ በኋላ የዓለም አቀፉ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ለኤሽያ ኦሊምፒክ ምክር ቤት አገራቱ በሰብዓዊ መብት ላይ ያላቸውን መጥፎ ስም በተግባር አሻሽለው እስካልተገኙ ክልከላ እንዲያደርግ መጠየቁ ይታወቃል፡፡ከወር በፊት ኳታር ይህን ውድድር ማስተናገድ የአገሪቱ ቀዳሚ ትኩረት መሆኑን የገለፀች ሲሆን ዋነኛ ተቀናቃኟ የሆነው የሪያድ መንግስትም ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ትኩረት ሰጥተው ሲዘግቡ ቆይተዋል። በነዳጅ ሃብት የበለፀጉት ሁለቱ የመካከለኛው ምስራቅ አገራት የዲፕሎማሲ ቀውስ ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ ድንበሮቻቸውን የዘጉ ቢሆንም ከአስር ዓመታት በኋላ የሚካሄድ የስፖርት ውድድርን ጡንቻ መለካኪያ ማድረጋቸው ትዝብት ላይ ጥሏቸዋል፡፡የኤሽያ ኦሊምፒክ ምክር ቤት ከሳምንት በፊት በሙስካት ባደረገው ጠቅላላ ጉባዔ የሁለቱን አገራት ውድድር የማዘጋጀት ፉክክር ምላሽ ለመስጠት መፍትሄ ያለውን ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል። በዚህም ዶሃ የ2030ን መላ ኤሽያ ጨዋታ እንድታዘጋጅ የወሰነ ሲሆን ከአራት ዓመት በኋላ በ2034 የሚካሄደውን ተመሳሳይ ውድድር ሪያድ እንድታዘጋጅ መርጧል። እዚህ ውሳኔ ላይ ለመድረስ የኤሽያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዘዳንት ሼክ አሕመድ አል ፋሃድ አል ሳባህ፣ ሁለቱንም አገራት ሊያስማማ ይችላል ብለው ባሰቡት መንገድ መሰረት በጠቅላላ ጉባዔው ብዙ ድምፅ ያገኘ አገር ቀድሞ ውድድሩን እንዲያዘጋጅ ማድረጋቸው ታውቋል። ውሳኔው ሁለቱን አገራት ያስማማል ተብሎ ቢታመንበትም በምርጫ ወቅት በተፈጠረ የቴክኒክ እክል ድራማ ሳይሰራ እንዳልቀረ መረጃዎች መጠቆማቸው ይታወቃል፡፡ዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የዓለም መንግስታት በስፖርት ውስጥ እጃቸውን እንዳያስገቡ ፍላጎቱን ከመግለፁ ባሻገር አገራት በበጎም ይሁን በመጥፎ ጎኑ ስፖርትን እንዴት የፖለቲካ መጠቀሚያ ከማድረግ እንደሚቆጠቡ ያስቀመጠው ግልፅ አቅጣጫ የለም። ወይም መንግስታት ለፖለቲካ ፍጆታ እጃቸውን ከስፖርት በምን መልኩ መሰብሰብ እንዳለባቸው የመቆጣጠሪያ ቁልፉን ያገኘ አይመስልም። በዓለም አቀፍ መድረኮች በሚሊየን የሚቆጠሩ አትሌቶችም ቢሆኑ እንደየአመለካከታቸው የፖለቲካ፣ የሐይማኖትና የዘረኝነት መልዕክትን ከማስተላለፍ የሚቆጠቡበትን መንገድ ለመቆጣጠር እንደሚከብደው የበርካቶች እምነት ነው። | https://www.press.et/Ama/?p=38578 | 1,179 | 2ስፖርት
|
የዓለም አትሌቲክስና 2020 የውድድር ዓመት | ስፖርት | January 1, 2021 | 10 | ቦጋለ አበበ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት የዓለም ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ገፅታ ዝብርቅርቁ በወጣበት የፈረንጆች 2020 ዓመት የዓለም ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችም ቀላል የማይባል አሉታዊ ተፅዕኖ አርፎባቸዋል። ኦሊምፒክን ጨምሮ ታላላቅ ዓለም አቀፋዊና የአገር ውስጥ ስፖርታዊ ውድድሮች በተሰረዙበትና በተራዘሙበት የውድድር ዓመት የአትሌቲክስ ስፖርት በርካታ ፈተናዎችን ማሳለፉ ይታወቃል። በዓለም ሕዝብ ዘንድ ጥሩ ትውስታን ጥሎ ያላለፈው
2020 ተሸኝቶ ዛሬ በ2021 የውድድር ዓመት አንድ ብሎ የሚጀምርበት ቀን ነው። በአብዛኛው መጥፎ ትዝታውን ጥሎ ባለፈው ዓመት የአትሌቲክሱ ዓለም በርካታ አሉታዊ ተጽእኖዎች አርፈውበታል፤ በርካታ አዎንታዊ ክስተቶችንም አስተናግዷል። ከእነዚህ መካከልም አበይት ክስተት የሆኑት እንደሚከተለው ተዳሰዋል። ጥር የ2020 የውድድር ዓመት በጀመረበት ታህሳስ መጨረሻና ጥር ወር ላይ የአትሌቲክሱ ዓለም በርካታ የዓለም ክብረወሰኖችን አስተናግዷል።
ኬንያዊው አትሌት ሮኔክስ ኪፕሩቶ የአስር ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ የዓለም ክብረወሰንን
ቫሌንሲያ ላይ 26፡24 በሆነ ሰዓት ያስመዘገበው በዚህ ወር ሲሆን፣ ሌላኛዋ ኬንያዊት
ሼላ ቺፕኪሩይ በተመሳሳይ
ውድድር የሴቶቹን የዓለም ከገጽ 46 የዞረክብረወሰን 29፡46 በሆነ ሰዓት በማሻሻል የውድድር ዓመቱን በስኬት ጀምራለች። በዚሁ ወር የማራቶን ቁጥር አንድና ቁጥር ሁለት የሆኑት ኢትዮጵያዊና ኬንያዊ አትሌቶች ቀነኒሳ በቀለና ኢሉድ ኪፕቾጌ በለንደን ማራቶን እንደሚፋለሙ ይፋ መደረጉም የውድድር ዓመቱ ትልቅ ክስተት ነበር። ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በየዓመቱ የሚደምቁበት የዱባይ ማራቶን በውድድሩ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፈው ኦሊካ አዱኛ አሸናፊ ሲሆን፣ በሴቶች ወርቅነሽ ደገፋ የኢትዮጵያውያንን የተለመደ ድል ማስቀጠል ችላለች። በቻይና ናጂንግ ባለፈው መጋቢት ወር ሊካሄድ ቀጠሮ የተያዘለት የዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ቻምፒዮና መራዘሙ የተሰማው በዚሁ ወር ነበር፤ ይህ ወድድር በኮቪድ-19 ስጋት የተራዘመ የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ ውድድርም ሆኗል። የካቲት ያለፈው የካቲት ወርም በዓለም አትሌቲከስ የተለያዩ የዓለም ክብረወሰኖች የተሻሻሉበት ሆኖ ይታወሳል። በተለይም ስዊድናዊው ምርኩዝ ዘላይ ሞንዶ ዱፕሌንቲስ 2014 ላይ በፈረንሳዊው ሪናውድ ላቪሌኒ ተይዞ የቆየውን የዓለም ክብረሰወን 6 ነጥብ 17 ሜትር በመዝለል በአንድ ሴንቲሜትር ያሻሻለበት አጋጣሚ ትልቁ ክስተት ነበር። ላቪሌኒ በተመሳሳይ ወር ግላስጎ ላይ 6 ነጥብ 18 ሜትር በመዝለልም ተጨማሪ የዓለም ክብረወሰን በአንድ ወር ውስጥ ያሻሻለበት አጋጣሚ የሚዘነጋ አይደለም። የውድድር ዓመቱን በበርካታ የዓለም ክብረወሰኖች ታጅቦ ያጠናቀቀው ዩጋንዳዊው አትሌት ጆሽዋ ቺፕቴጌ የዓመቱን የስኬት ጉዞ ሞናኮ ላይ የአምስት ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ የዓለም ክብረወሰንን 12፡51 በሆነ ሰዓት በማሻሻል የጀመረው በዚሁ የካቲት ወር ነበር። ኢትዮጵያዊቷ አትሌት አባብል የሻነህ የግማሽ ማራቶን የዓለም ክብረወሰንን በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ራስ አል ካይማህ 64፡31 በሆነ ሰዓት ያሻሻለችበትም አጋጣሚ በጉልህ የሚጠቀስ ነው። ቬንዙዌላዊቷ ስሉስ ዘላይ ዩሊማር ሮጃስ በማድሪድ በተካሄደው የቤት ውስጥ ውድድር ለአስራ ስድስት ዓመታት በታትያና ሌቢዴቫ ተይዞ የቆየውን የዓለም ክብረወሰን 15 ነጥብ 43 ሜትር በመዝለል ያሻሻለችበት አጋጣሚም ይታወሳል። መጋቢት የውድድር ዓመቱ ሦስተኛ ወር በሆነው መጋቢት ሕዝብ ባልተሳተፈበት የቶኪዮ ማራቶን ብርሃኑ ለገሰ ባለድል የሆነበት አጋጣሚ ሳይጠቀስ አይታለፍም። ቀነኒሳ በቀለም በለንደን ግማሽ ማራቶን አስደናቂ ብቃት አሳይቶያሸነፈበት ውድድርም አይዘነጋም። በዚህ ወር የኮቪድ-19 ስርጭት እየተስፋፋ መሄዱን ተከትሎ የዓለም ግማሽ ማራቶን ቻምፒዮናም የመራዘም ዕድል ገጥሞታል። በተመሳሳይ ታላላቅ የሚባሉት የለንደንና የቦስተን ማራቶን ውድድሮችም በዚሁ የካቲት ወር እንደተራዘሙ ታውቋል። እንዲካሄድ በርካታ ጥረቶች ሲደረጉ ከቆዩ በኋላ የውድድር ዓመቱ ታላቅ የስፖርት መድረክ ቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ የተራዘመውም በዚሁ ወር ነበር። ሚያዝያ-ግንቦትበአሜሪካ ኦሪገን በሰኔ ወር ሊካሄድ የነበረው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ቻምፒዮና በ2022 እንዲካሄድ ውሳኔ ላይ የተደረሰው በሚያዝያ ወር ነበር። የሚያዝያ ወር ምናልባትም በአትሌቲክሱ ዓለም ውድድሮችና ክብረወሰኖች የተመዘገቡበት ሳይሆን በርካታ ተጠባቂ ውድድሮች የተራዘሙበትና የተሰረዙበት መጥፎ ትዝታ ጥሎ ያለፈ ነው ማለት ይቻላል። ከቤት ውስጥ ቻምፒዮናው በተጨማሪ በፓሪስ ሊካሄድ የነበረው የአውሮፓ አትሌቲክስ ቻምፒዮና በዚህ ወቅት ለመሰረዝ በቅቷል። ጥቁር አሜሪካዊው ጂዮርጅ ፍሎይድ ሜይዌዘር በፖሊስ በአሰቃቂ ሁኔታ መገደሉን ተከትሎ የዓለም አትሌቲክስ ‹‹የጥቁር ሕይወት ዋጋ አለው›› በሚል በዓለም አቀፍ ደረጃ የተጀመረውን እንቅስቃሴ የተቀላቀለበት ወቅት ነው። የዓለም አትሌቲክስ አዲስ የኦሊምፒክ ተሳትፎ ማረጋገጫ ሂደትን ይፋ ያደረገውም በዚህ ወቅት ነበር። የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስፖርቱን እያዳከመው በመምጣቱም የዓለም አትሌቲክስ ስፖርቱን ለመደገፍ አዲስ ስትራቴጅክ ፕላን ይፋ አድርጓል። ተጠባቂው የኒውዮርክ ማራቶንም መሰረዙ የተሰማው በዚሁ ወቅት ነው። ሰኔ-ሐምሌ ውድድሮች ለወራት በዓለም ላይ አለመካሄዳቸውን ተከትሎ የስፖርቱ ዓለም በዘርፉ ፖለቲካ ተጠምዶ የቆየበት ጊዜ ነበር። በዚህም ከውድድርና ውጤቶች ይልቅ የተለያዩ ጉዳዮች የስፖርቱ ቤተሰብ መነጋገሪያ ሆነው ሰንብተዋል። በሰኔ ወር ትልቅ መነጋገሪያ ከሆኑ የአትሌቲክስ ጉዳዮች የቀድሞው የማራቶን ባለክብረወሰን ኬንያዊው ዊልሰን ኪፕሳንግ አበረታች ንጥረነገር ተጠቅሞ በመገኘቱ ለአራት ዓመታት ከስፖርቱ መታገዱ ትልቅ ትኩረት ስቦ ነበር። ተቋርጠው የቆዩ የዳይመንድ ሊግ ውድድሮች በወሩ መጨረሻ እየተመለሱ መምጣታቸው ግን በወረርሽኙ ሳቢያ ድብርት ውስጥ ለነበረው የስፖርቱ ቤተሰብ ተስፋ ሆነው ነበር። በዚህም በዙሪክ የተካሄደው የዳይመንድ ሊግ ውድድር ተጠቃሽ ነው። ያም ሆኖ እንደ ቺካጎ ያሉ ታላላቅ የማራቶን ውድድሮች በዚህ ወር ከመሰረዝ አልዳኑም። ወሩ ከመጠናቀቁ አስቀድሞም የዓለም አትሌቲክስ በመሮጫ ጫማዎች ላይ አዲስ ሕግ ይፋ ማድረጉ ይታወቃል። ውድድሮች ከወራት በኋላ በሂደት መመለሳቸውን ተከትሎ ለረጅም ዓመታት ያልተደፈሩ የዓለም ክብረወሰኖች ጭምር ሐምሌ ወር ላይ ተሰብረዋል። በተለይም ዩጋንዳዊው አትሌት ጆሽዋ ቺፕቴጌ ሞናኮ ላይ በቀነኒሳ በቀለ ለአስራ አምስት ዓመታት ተይዞ የቆየውን የዓለም ክብረወሰን በ12፡35፡36 ማሻሻሉ ያልተጠበቀ የዓመቱ አበይት ክስተት ነበር። ነሐሴ ሐምሌ ወር ላይ የታየው ትልልቅ የዓለም ክብረወሰን የማሻሻል ሂደት በነሐሴም ተደግሟል። በተለይም በኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች ኃይሌ ገብረስላሴና ድሬ ቱኔ ለረጅም ዓመታት ተይዘው የቆዩት የአንድ ሰዓት ውድድር የዓለም ክብረወሰኖች መሰበራቸው ያልተጠበቀ ነበር። ትውልደ ሶማሊያዊው የእንግሊዝ አትሌት ሞ ፋራህ የወንዶቹን ክብረወሰን ሲያሻሽል ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ የኔዘርላንድስ አትሌት ሲፈን ሃሰን የሴቶቹን ክብረወሰን መጨበጥ ችላለች። ኬንያዊቷ አትሌት ፒርስ ጂፕቺርቺር በፓራጓይ ግማሽ ማራቶን የርቀቱን የሴቶች ብቻ የዓለም ክብረወሰን ያሻሻለችበት አጋጣሚም አይዘነጋም። የቀድሞው የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ፕሬዚዳንት ሴኔጋላዊው ላሚን ዲያክ በሙስና ቅሌት በፓሪስ ለዓመታት በቁም እስር ቆይተው ፍርድ የተበየነባቸውም በዚሁ ወር ነው። የውድድር ዓመቱን በክብረወሰኖች ታጅቦ ያሳለፈው ስዊድናዊው ምርኩዝ ዘላይ ሞንዶ ዱፕሌንቲስ ከቤት ውጪ ባሉ ውድድሮች በዩክሬናዊው ታሪካዊ አትሌት ሰርጌ ቡካ ተይዞ የቆየውን የዓለም ክብረወሰን በ6 ነጥብ 15 ሜትር ያሻሻለበት አጋጣሚም ትልቅ ነው። የዓለም የማራቶን ክብረወሰን ባለቤት የሆነችው ኬንያዊት አትሌት ብሪጊድ ኮስጌ የለንደን ማራቶንን ለሁለተኛ ጊዜ አሸንፋለች። በዚህ ውድድር ለወራት ሊፋለሙ ቀጠሮ ይዘው ትልቅ ትኩረት የተሰጣቸው ቀነኒሳ በቀለና ኢሉድ ኪፕቾጌ ፍልሚያ አንድ ቀን ሲቀረው ቀነኒሳ በጉዳት ከውድድር ውጪ መሆኑ አሳዛኝ ነበር። ያም ሆኖ የርቀቱ የክብረወሰን ባለቤትና ባለፉት ዓመታት ሽንፈት ያልገጠመው ኪፕቾጌ ባልተጠበቀው ኢትዮጵያዊ አትሌት ሹራ ቂጣታ ከመሸነፉ ባሻገር ሰባተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ አስገራሚ ነበር።ዩጋዳዊው ቺፕቴግ ቀነኒሳ ለአስራ ስድስት ዓመታት ይዞት የቆየውን የአስር ሺ ሜትር የዓለም ክብረወሰን ቫሌንሲያ ላይ ሲያሻሽል ኢትዮጵያዊቷ ለተሰንበት ግደይ በጥሩነሽ ዲባባ ለአስራ ሁለት ዓመታት የተያዘውን የአምስት ሺ ሜትር የዓለም ክብረወሰን ማሻሻሏ የውድድር ዓመቱ ግንባር ቀደም አበይት ክስተት ሆኖ አልፏል። ኬንያዊቷ ፒርስ ጂፕቺርቺር በፖላንድ ጊዲኒያ የዓለም ግማሽ ማራቶን ቻምፒዮና የርቀቱን የሴቶች ብቻ የዓለም ክብረወሰን መስበሯም ወሩን አስደናቂ አድርጎት አልፏል። መስከረም -ታህሳስ የ2023 የአውሮፓ አትሌቲከስ ቻምፒዮናን ቱርክ ኢስታንቡል ላይ እንድታዘጋጅ ዕድል ባገኘችበት መስከረም ወር በአየርላንድ ደብሊን ሊካሄድ የነበረው የ2020 የአውሮፓ አገር አቋራጭ ቻምፒዮና ከመሰረዙ በቀር በአትሌቲክሱ ዓለም ብዙም አነጋጋሪ ጉዳዮች ሳይፈጠሩ አልፈዋል። ከዚያ በኋላ ባሉት ሦስት ወራት ግን የዓለማችን ፈጣኑ አትሌት ጃማይካዊው ዩዜን ቦልት እንዲሁም የረጅም ርቀት ንግስቷ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ በእውቁ የእንግሊዝ የአትሌቲክስ መፅሔት የምን ጊዜም ምርጥ አትሌት ተብለው መሰየማቸው አብይ ጉዳይ ነበር። ቬንዙዌላዊቷ አትሌት ዩሊማር ሮጃስ እንዲሁም ስዊድናዊው ሞንዶ ዱፕሌንቲስ የዓመቱ ምርጥ አትሌቶች ተብለው ተሸልመዋል። ኬንያዊው ኪቢዎት ካንዲም በዓለም ግማሽ ማራቶን ቻምፒዮና ሲያሸንፍአዲስ
ዘመን ታህሳስ 23/2013 | https://www.press.et/Ama/?p=38650 | 1,005 | 2ስፖርት
|
ለራስ ሲባል ሌላውን … | መዝናኛ | April 27, 2020 | 24 | ኧሯ! እንዴት ሆኖ እንዴት ሆኖ እኛንማ አይደፍርም! ብለን ነበር ደፈረን። በሩቅ ሆኖ የሰማነው ዜና ገስግሶ መጥቶ አጠገባችን ከደረሰ የወራት እድሜን አስቆጠረ። በሰው ሀገር ሲነገር፤ ሲወራ እኛ ዘንድ የማይደርስ መስሎን ተዘናግተንማል። እኛ ሀገር አይገባም ፤ ጥቁሮችን አይነካም በማለት እራሳችንን በማይሆን ተስፋ እያታለልን ቆይተናል። ቁርጡ ቀን ደርሶ በሀገራችን የቫይረሱን መገኘት እውነታ ሲነገር ሰምተን ላለማመን ያመነታነው ስንቶቻችን እንሆን? ታዲያ አስፈሪ ዝናውን አስቀድሞ በርካቶቻችንን ኮርኩሮ ሃሳብ በማሰንዘር ፤ ከሃሳባችን መደምደሚያ ሳንደርስ ከች ብሎ ጉድ ያደረገን እሱም አይደል ወይ ኮሮና። ስለ ቫይረሱ ያለን እውቀት እንደ ግንዛቤ የሚለያይ ነው። አንዳንዱ ህይወቱ ግድ ሰጥቶ ለራሱ ኖሮ ሌላውን ለማትረፍ የሚጥረው ነው። ሌላው ደግሞ ለራሱም ሆነ ለሌላው ግድ የሌለው ቢነገረው ቢዘከር ሰምቶ እንዳልሰማ አይቶ እንዳላየ የሚሆን ነው። ራሱን በመኖርና ባለመኖር መካከል ከቶ በደመነፍስ እንደሚኖር ሰው ቫይረሱ ምንም እንደሚያመጣ የሚናገርም ዛሬ ድረስ አልጠፋም። ሰውን ለማዳን ራሱን ያልሰሰተውን ተመልክተን እሰየው በርታልን ጓድ እንዳላልን ሁላ ፤ በግዴለሽነት የሚኖረውን ደግሞ በትዝብት እያየን ከማለፍ ለመምከር የሞከርን እንኖራለን። የሚጠነቀቀውም ሆነ ግዴለሹ፤ የአንዱ ጤንነት የሌላው መኖር ዋስትና ነው ። የሰው ልጅ በምድር ላይ የሚኖረው ለራሱ ብቻ አይደለም፤ ለሌሎችም ነው። አንዱ ከሌለ የሌላው መኖር ትርጉም አልባ ነውና ። ህይወት ጣዕም የሚኖራት በመኖር ነው። መኖር ትርጉሟ ሙሉ የሚሆነው አንዳችን ለአንዳችን በሚኖረን አብሮነት ፤ መረዳዳትና መደጋገፍ ነው። ለዚህ ዋንኛው ደግም የኔ ጤንነት ሲጠበቅ የጎረቤት፤ የአካባቢዬ ፤ የሀገር፤ የሁሉም ጤና መሆን ግድ ይላል ። ታዲያ አለመታዘዛችን ከምን የመነጨ ይሆን? ለመኖር ራሳችን ከመጠበቅ ሌላው አማራጭ ይኖር ይሆን። ታላላቆቻችን፤ አባቶቻችን ማድመጥ፤ መደማመጣችንን እሴቶቻችንን ማን ነጠቀን? ለምን ረሳነው? በራሳችን ፈርደን በሌሎችም የመጨከን አባዜን ከየት አመጣነው? የሰውን ልጅ ሳይመርጥ ከምድረ ገጽ እያጠፋ ያለው ይህ ጨካኝ ቫይረስን እንዴት ልባችንን ሊያደነድን ቻለ። ሰው የሚችለውን ነውና የሚታዘዘው እራሳችንን እንመርምር ለመለወጥ መትጋት አለብን። የማንችለውን ትተን የምንችለውን መምረጥ ፤ ዛሬን መኖር ለነገ ተስፋ ነው። የእኛ ጥንቃቄ ለወገን መሆኑ ማመን አለብን። ነጭ፤ ጥቁር፤ ዘመድ፤ ባዕድ እያልን ራሳችንን ሳንከፋፈል ከስጋት ራስን ጠብቆ በማስመለጥ አብሮ ማምለጥ ይቻላልና ነው። ካለበለዚያ ግን “ከኑግ ጋር ያለህ ሰሊጥ አብረህ ተወቀጥ” ከሆነ ጉዳይ የታሪክ ተወቃሽ መሆናችን አይቀርም። መቼም ቫይረስ በሀገራችን ከተከሰተ ማግስት ጀምሮ ብዙ ለውጦችን፣ አዳዲስ ነገሮችን ታዝበናል። ለመከላከል የሚረዱን እጅን በሳሙና ቶሎ ቶሎ በደንብ መታጠብን ፤ ፊት በእጅ አለመንካት፤ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ በዋናነት ከህክምና ባለሙያዎች የሚሰጡትን ምክሮች ተግባራዊ ለማድረግ ተሞክሯል። ለራሱ ያለ ራሱ ተጠንቅቆ ሌላውን ለማዳን እየጣረ እየተጋ ታይቷል። ይገርማችኋል! ለዛሬ ትዝብቴ መነሻ የሆኑት ይህንን የሰሙ የማይመስሉ የሰፈሬ ወጣቶች ናቸው። በከተማችን የሚገኙ በርካታ ወጣቶች በጎ ተግባራት ላይ በመሳተፍ ከወገናቸው ጎን የቆሙበትን አይተናል፤ ሰምተናልም። የነገ የሀገሪቱ ተስፋዎች መሆናቸውንም አስመስክረዋል። የኔ ሰፈር ወጣቶች ግን ቫይረስ መኖሩን አልሰሙም!! በአንድ ላይ በጋራ በመሆን መጠጥ ይጠጣሉ ፤ ጫት ይቅማሉ፤ መንገድ ዳር ተዛዝለው በሚባል ሁኔታ ሆነው ያወጋሉ። የቫይረሱ የተከሰተ ሰሞን አልነበሩም፤ ጠፍተው ነበር ። እሰየው አልኩኝ፤ ራሳቸውን ለመከላከል ወስነው ቤት ለመቀመጥ የከተሙ መስሎኝ። አልሰሜን ግባ በለው አሉ። ለካ የቦታ ለውጥ በማድረግ ከሰው አይን ዞር ብለው ነበር። ታዲያ እኔም የግዴታዬን ለመወጣት ወደእነሱ አመራሁ። በእግዜር ስላምታ ተቀላቀልኳቸው። ስለቫይረሱ አስከፊነት የነሱ መጠንቀቅ ለሚወዷቸው ሁሉ ፤ ለወላጆቻቸው፤ ለሰፈራችን ሁሉም እንደሆነ አስረዳኋቸው። ለማዳመጥ ፈቃደኛ ባልሆነ ጆሮ ሰሙኝ ። መልስ አልሰጡኝም። አንደኛው እሺ አለኝ ቀልድ በተሞላበት ፌዝ ። በእውነት አመመኝ። ለምን አትተሳሰቡም እርስ በርሳችሁ እንኳን አትዋደዱም አልኳቸው። እሺ ሌላው ቢቀርስ ለምን አትታዘዙም አልኩት? አቀርቀረው ስልካቸውን መጎርጎር ተያያዙት ። ትቻቸው ስሄድ መታዘዝ ከመሰዋዕትነት ይበልጣል አልኩ ሰምተውኛል፤ ግን ዝምታን መርጠዋል። ለብቻዬ እንዳስብበት የቤት ስራ የሰጡኝ ወጣቶች ዞር ብዬ በማየት ጉዞዬን በሃሳብ ቀጠልኩ። “ለምን ይሆን የተከለከለ ነገር የሚያምረን?” አልኩኝ ለራሴ ። ወደ አፈጣጣራችን ተመለስኩ ለካ አዳምን ከገነት ያስባረረው አታድርግ የተባለው በማድረጉ ነው። እኛም ዛሬ ለመቅጽበት ለሚያልፍ ቀን ብለን አታደርጉ የተባልነውን በማድረግ በጎ ተግባር እንደፈጸመ ጀግና በየአደባባዩ እንታያለን። ማንንም መስማት አንፈልገም፤ እራሳችንን ብቻ ካልሆነ በስተቀር ፤ ራሳችንን በቅጡ አውቀን ብናዳምጥ ጥሩ ነው። በዓለም ያሉ ሀገራት እንደኛ አይነት ተው ተብለው የማይሰሙ ዜጎች በመያዛቸው ነው። ዛሬ ለመስማት የሚቀፍ ዜና እየሰማን የምንገኘው። እነሱ ቢጸጸቱም ወደ ኋላ ሊመልሱት የማይችሉት ነገር ሆኖባቸዋል። ለኛ ትምህርት መሆን አለባቸው። እኛ ላይ በቅድሚያ ያልተፈጸመብን መሆኑን እያመሰገን ከሰማነው፣ ካየነው ቀድሞ መገኘት የግድ ይለናል። ጊዜው ፈጣን ነው ፤ ዛሬ ላይ እንኳን ቆመን ነገን ለማየት በተሰጠን መልካም እድል መጠቀም አለብን። ያለመታዘዛችን ዋጋ እንዳያስከፍል መበርታት ያስፈልገናል። ለዚህም ቀኑ ዛሬ እንጂ ነገ አይደለም። የቤት ስራን ከወዲሁ በመፈጸም ለወገን አለኝታነታችን በመግለጽ እራስን ሆኖ መገኘት፤ ታዝዞ መታዘብ ማስተማር ፤ቀዳሚ ሆኖ ለሌሎች አርአያ በመሆን መስመሩን በመጥረግ ከመስመሩ ያፈነገጡትን መመለስ ይገባል። የዛሬ ሁላችንም አብሮነትና ትብብርን አንዱ ለአንዱ መኖር ግድ ይሆናል። ታላላቆቻችንን በማስቀደም እነሱን አድምጠን ከዚህ አስከፊ አደጋ ማምለጥ ይኖርብናል። አብረን ስንሆን፣ ስንተባበር፣ ስንደማምጥ፤ ስንረዳዳ ያምርብናል። ባህሩን አቋርጠን መሻገር እንችላለን። የሰው ልጆችን እየጠረገ ያለውን አስከፊ ወረርሽን ለመከላከል ወኔ አቅም ጉልበት ይኖረናልና ። መጪው ጊዜ መልካም ዜና የምንሰማበት ጊዜ ይሁንልን ። አዲስ ዘመን ሚያዝያ 19/2012 ወርቅነሽ ደምሰው | https://www.press.et/Ama/?p=31198 | 695 | 1መዝናኛ
|
የ2023 አፍሪካ ዋንጫ ዝግጅት ቀጥሏል | ስፖርት | December 22, 2020 | 8 | ቦጋለ አበበ ምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር ኮትዲቯር የ2023 አፍሪካ ዋንጫን ለማስተናገድ የምታደርገው ዝግጅት በሚፈለገው ደረጃ ቀጥሏል።የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ባለፈው ዓመት ከተከሰተ ወዲህ በርካታ የዓለማችን አገራት ስፖርታዊ ውድድሮችን ከማቆም ባለፈ ዓለም አቀፍና አህጉር አቀፍ ውድድሮችን ለማስተናገድ የሚያደርጉት ዝግጅት ተስተጓጉሏል።የ2023 አፍሪካ ዋንጫን ለማስተናገድ ዕድሉ የተሰጣት ኮትዲቯር ግን ወረርሽኙ ሳያግዳት ዝግጅቷን በተገቢው መንገድ እንደቀጠለች ኢንሳይድ ዘጌምስ አስነብቧል። የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የግምገማ ቡድን ከሳምንት በፊት ወደ ኮትዲቯር አቅንቶ አገሪቱ እያደረገች የሚገኘውን ዝግጅት የተመለከተ ሲሆን ምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር ለአፍሪካ ዋንጫው ተገቢውን ዝግጅት በማድረግ ሂደት ላይ እንደምትገኝ አሳውቋል።በዝግጅት ግምገማ ቡድኑ ውስጥ የካፍ ምክትል ዋና ፀሐፊ አንቶኒ ባፎይ፣ የውድድር ዳይሬክተሩ ሳምሶን አዳሙ፣ የብሔራዊ ቡድን ውድድሮች ማኔጀሩ ኢስማሊ ዋሊ እንዲሁም የአገልግሎትና የጉዞ ዋና ሃላፊው ራንዳ ሚትዋሊ ተካተው ወደ ስፍራው አቅንተዋል። የግምገማ ቡድኑ ከኮትዲቯር ከተመለሰ በኋላ ለኢንሳይድ ዘጌምስ አስተያየታቸውን የሰጡት ምክትል ዋና ፀሐፊው ባፎይ ምንም እንኳን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የዓለም ሕዝብ የጤና ቀውስ በመሆን ቢቀጥልም ያሳደረውን ጫና ተቋቁማ ኮትዲቯር በጥሩ ሁኔታ ዝግጅቷን እንደቀጠለች ማረጋገጫ ሰጥተዋል። ‹‹ጉብኝቱ በደንብ የታሰበበት ነው፣ በጉዟችንና የውድድሩ አዘጋጆች እየሠሩ በሚገኙት ሥራ ረክተናል›› ያሉት ባፎይ አብዛኛው ለውድድሩ የሚገነቡት ስቴድየሞች በ2021 አጋማሽ እንደሚጠናቀቁ ጠቁመዋል።ይህም አዘጋጆቹ እስከ ውድድሩ ድረስ በቂ ጊዜ እንዳላቸው የሚያሳይ ሲሆን ለሙከራ የተለያዩ ጨዋታዎችን የማካሄድ ዕድልም እንደሚኖራቸው ባፎይ አብራርተዋል። የውድድሩ አዘጋጆች በዕቅዳቸው መሰረት እየተመሩ ትክክለኛ ሰዎችን በትክክለኛው ቦታ በማሰራት ተጨባጭ ነገር እንዳሳዩ የጠቆሙት ባፎይ‹‹ ሁሌም የምናገረው ነገር አንድ ነው፣ ትክክለኛውን ሰው በትክክለኛው ቦታ ማስቀመጥ›› በማለት አዘጋጆቹን አድንቀዋል።ኮትዲቯር እ.ኤ.አ 2014 ላይ የ2021 አፍሪካ ዋንጫን እንድታዘጋጅ ዕድሉን ያገኘች አገር መሆኗ ይታወሳል።ይሁን እንጂ የ2019 አፍሪካ ዋንጫን ለማዘጋጀት ዕድሉ የተሰጣት ሌላኛዋ ምዕራብ አፍሪካዊት አገር ካሜሩን 2018 ላይ ውድድሩን ለማዘጋጀት የምትገነባቸው ስቴድየሞች በመጓተታቸውና በወቅቱ በአገሪቱ የነበረው የፖለቲካ አለመረጋጋት ከደህንነነት አኳያ ስጋት ስለፈጠረ የአዘጋጅነት ዕድሉ ለግብጽ ተሰጥቷል።ካሜሩንም በምትኩ የ2021 አፍሪካ ዋንጫን እንድታዘጋጅና ኮትዲቯር የ2023 አፍሪካ ዋንጫን እንድታሰናዳ ሽግሽግ ተደርጓል። በዚህም መሰረት ኮትዲቯር የአፍሪካን ትልቁ የስፖርት መድረክ በተሳካ ሁኔታ ለማዘጋጀት በቂ ጊዜና ዕድል ማግኘት ችላለች።ውድድሮቹንም ከ2023 ሰኔ ወር መጨረሻ አንስቶ በመዲናዋ አቢጃን፣ ቦኬ፣ ኮርሆጎ፣ ሳን ፔድሮ እና ያሙሱክሮ ከተሞች እንደ ምታከናውን ይጠበቃል። | https://www.press.et/Ama/?p=37905 | 299 | 2ስፖርት
|
የባለሀብቶች ተሳትፎ ያልታከለበት የማዘውተሪያ ስፍራዎች ግንባታ | ስፖርት | December 24, 2020 | 7 | ብርሃን ፈይሳወቅቱ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ግንባታ በዓለም አቀፍ ደረጃ እጅግ የሰፋበት መሆኑን ጥናቶች ያመላክታሉ። የማዘውተሪያዎች ዘመናዊነትና ጥራት የሰለጠኑ ከተሞች አንዱ መለያ እየሆነ ከመምጣቱም ባሻገር ኦሊምፒክ፣ ዓለም ዋንጫ እና የተለያዩ ስፖርት ቻምፒዮናዎችን ለማሰናዳት ዋነኛው መስፈርትም ነው። ሀገሮች ዜጎቻቸው በአእምሮና በአካል የተዋጣላቸውና ብቁ እንዲሆኑም በማዘውተሪያ ስፍራዎች አስፈላጊነትም እምነት ጥለዋል። በመሆኑም የከተሞቻቸውን ዲዛይን ሲያዘጋጁም ሆነ ግንባታውን ሲያከናውኑ ነዋሪዎቻቸው በቂ የጊዜ ማሳለፊያና ስፖርታዊ እንቅስቃሴ የሚከውኑባቸው ስፍራዎች ስለመኖራቸው ያረጋግጣሉ። የአፍሪካ መዲናዋ አዲስ አበባም በዓለም ላይ ካሉና ታላላቅ ጉባኤዎችን ለማስተናገድ ከሚመረጡ እንዲሁም የአህጉር አቀፍ ተቋማት መቀመጫ እንድትሆን ተመራጭ ከሆኑት መካከል ትገኛለች። ይህም ስፖርታዊ ውድድሮችን ለማስተናገድ ምቹ ሁኔታን ቢፈጥርላትም እስካሁን ግን ጉባኤዎችን ብቻ በማካሄድ ተወስናለች። ምክንያቱ ደግሞ ደረጃውን የጠበቀ የማዘውተሪያ ስፍራ የሌላት በመሆኑ ነው። አዲስ አበባ ከተማም ደረጃቸውን የጠበቁ የማዘውተሪያ ስፍራዎች ብቻም ሳይሆኑ በየአካባቢው ለነዋሪዎቿ የሚበቃ የማዘውተሪያ ስፍራ ማግኘትም ፈተና ሆኖባታል። በመሆኑም የየከተማ አስተዳደሩ ስፖርት ኮሚሽን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ትኩረቱን በማዘውተሪያ ስፍራዎች ግንባታ ላይ አድርጓል። ከሰሞኑ ጉባኤውን ያከናወነው የከተማዋ ስፖርት ምክር ቤትም አትኩሮቱን በተለይ በስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ላይ አድርጎ ነበር። ምክር ቤቱ በጉባኤው ላይ ባቀረበው የ2012 በጀት ዓመት የአፈጻጸም ሪፖርት የአዳዲስና ነባር የማዘውተሪያ ስፍራዎች ያሉበትን ደረጃ በዝርዝር አመልክቷል። በዚህም በበጀት ዓመቱ ብቻ 95 የሚሆኑ 3በ1 እንዲሁም የጥርጊያ ሜዳዎች እንዲገነቡና እንዲታደሱ ተደርጓል። እነዚህም በክፍለ ከተሞች እንዲሁም በ14 የጋራ መኖሪያ ስፍራዎች ላይ የተገነቡና የታደሱ ናቸው። ከፍተኛ ወጪ ተደርጎባቸው የሚገነቡ ደረጃቸውን የጠበቁ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን በተመለከተም በዚህ ዓመት ተጠናቀው ወደ አገልግሎት የሚገቡና አዳዲስ የሚጀመሩ መሆኑም ተጠቁሟል። በዚህም የራስ ኃይሉ የመዋኛ ገንዳ እና የአበበ ቢቂላ ስታዲየም የግንባታ ምዕራፍ 99 ከመቶ የተጠናቀቀ ሲሆን፤ በተያዘው በጀት ዓመት ወደ ሥራ ይገባሉ በሚል ይጠበቃል። በሁለቱም የማዘውተሪያ ስፍራዎች የውሃ እጥረት በመኖሩ ምክንያት የከርሰ ምድር ውሃ ለማውጣት እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል። የአቃቂ ስታዲየም ግንባታም 70 ከመቶ ደርሷል፤ የአራት ኪሎ እና የጃንሜዳ ማዘውተሪያ ስፍራዎች ግንባታ በቴክኒክ ችግር ተቋርጦ ቆይቷል። በዚህ ዓመት ዕቅድም
በዋናነት የማዘውተሪያ ስፍራ
ቁጥርን ማሳደግና ሕጋዊነታቸውን
ማረጋገጥ ላይ ትኩረት
መሰጠቱ በመድረኩ ላይ
ተጠቁሟል። በዚህም መሠረት
የአቃቂና የአበበ ቢቂላ
ስታዲየሞች እንዲሁም የራስ
ኃይሉ የመዋኛ ገንዳዎች ግንባታን በዚህ ዓመት ሙሉ ለሙሉ በማጠናቀቅ አገልግሎት ለማስጀመር ታቅዷል። ግንባታው 67 ከመቶ ደርሶ የተቋረጠው የጃንሜዳ ጂምናዚየም እና ወደ ግንባታ ያልገባው የአራት ኪሎ ትምህርትና ስልጠና ማዕከል ሕንፃም በዓመቱ ወደ ግንባታ የሚገቡ ይሆናል። በተለያዩ ክፍለ ከተማዎች አንድ የአትሌቲክስ መንደር እና ሦስት ዞናል ስታዲየሞችን አስገንብቶ ለኅብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግም የበጀት ዓመቱ ዕቅድ መሆኑም ተጠቁሟል። የቀረበውን ሪፖርትና ዕቅድ ተከትሎም የምክር ቤቱ አባላት የተለያዩ ሃሳቦችን አንጸባርቀዋል። አጸንኦት የተሰጠው ሃሳብ ግን ከስፖርት ኢንቨስትመንት አንጻር በከተማዋ ባለሀብቱን የማሳተፍ ሂደት የሌለ መሆኑ ነው። የግል ባለሀብቱ በተለይ እጥረት ባለበት የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ግንባታ ላይ የማሳተፍ አስፈላጊነት ተጠቁሟል። በዚህም ባለሀብቱን ከመጥቀም አልፎ ነዋሪውንም ተጠቃሚ ማድረግ ይቻላል።በከተማዋ የሚስተዋለው የግሉ ተሳትፎ ጂምናዚየሞች ላይ የተወሰነ ነው። በመሆኑም የኦሊምፒክ ስፖርት በሆኑ ሌሎች የቤት ውስጥ ስፖርቶች ላይም ተሳታፊ ለመሆን የሚፈልጉ ባለሀብቶችን በማበረታታት ስፖርቱን መደገፍ ይገባል። ለግል ባለሀብቶች ለስፖርቱ
በዋናነት ግብዓት የሚሆኑ
ቁሳቁስ ከቀረጥ ነፃ
እንዲገቡ ማድረግ አስፈላጊ
መሆኑንም በመድረኩ ተጠቁሟል።
ከባለሀብቱ ባሻገር የስፖርት
ክለቦችም በማዘውተሪያ ስፍራ
ልማት ቢሰማሩ ለመንግሥት
ላይ ብቻ የተተወውን
ዘርፍ ሊደግፉ እንደሚችሉም
ተነስቷል። ጉባኤተኞቹ የሚገነቡ ማዘውተሪያዎች ሁሉንም ስፖርቶች ያማከሉ መሆን እንደሚገባቸውም አመልክተዋል። በከተማዋ ከ30 በላይ የሚሆኑ የአትሌቲክስ ቡድኖች እያሉ ለስፖርቱ የሚሆን ማዘውተሪያ ያለው በአዲስ አበባ ስታዲየም ብቻ መገኘቱ ሌላው አሳሳቢ ችግር መሆኑ ተጠቁሟል። ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ የሰጡት የከተማ አስተዳደሩ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር በላይ ደጀን፤ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች መንግሥታዊ በሆኑና ባልሆኑ አካላት በየአካባቢው ሊጠናከሩ እንደሚገባ ነው ያመለከቱት። እንደ ኮሚሽነሩ ገለጻ፤ የታዳጊ ፕሮጀክት ስልጠናን ለማስፋፋትም ሆነ ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት የሚቻለው ማዘውተሪያዎችን ማስፋትና ማልማት ሲቻል ነው። የመዘውተሪያ ስፍራዎች ጉዳይ የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ርብርብ የሚጠይቅ ቁልፍ ሥራ በመሆኑ በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል። ከሚሽነሩ ትምህርት ቤቶች በአካልም በአእምሮ የበለጸገ ዜጋ ለማፍራት የሚያስችል ስፍራ እንደመሆናቸው 300 የሚሆኑ የሰውነት ማጎልመሻ መምህራን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ስልጠና እንዲያገኙ መደረጉን ጠቅሰው፣ ይህንን ተከትሎ የመጣው ጥያቄ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን የሚመለከት መሆኑን ይጠቅሳሉ። ስለዚህም ማዘውተሪያዎቹን በትምህርት ቤቶች ውስጥ ማልማት እንዲሁም ተማሪዎች ከሚጠቀሙበት ሰዓት በኋላ በሚኖረው ጊዜ የአካባቢው ወጣቶችና ታዳጊዎች የሚጠቀሙበትን ሁኔታ ማመቻቸት እንደሚያስፈልግ ያብራራሉ። ከዚህ ባሻገር በከተማዋ የሚገኙ ነባር ማዘውተሪያዎችን በማደስና አዳዲሶችንም በጥራትና በፍጥነት ለማስገንባት ቢሮው በእንቅስቃሴ ላይ መሆኑንም ኮሚሽነሩ ጠቁመዋል። ለዓመታት ጥያቄ ሲነሳባቸው የቆዩ የማዘውተሪያ ስፍራዎች ግንባታን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተሞከረ ነው። ከባድ የሆነው ግን ከዚህ ቀደም የተጀመሩና በግንባታ ላይ የቆዩ ነባር ማዘውተሪያዎችን የጥራት ጉድለት እያለባቸው ወደ ሥራ ማስገባት ነው ሲሉ ያመለክታሉ። ለአብነት ያህል የአበበ ቢቂላ ስታዲየም ሜዳውን ለእግር ኳስ መሙን ደግሞ ለአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች መስጠት ይቻላል ነገር ግን አሁን የጥራት ጉድለት አለ ይላሉ። በሌሎችም እንዲሁ የዲዛይን ችግር፣ የግንባታ ክፍተት፣ የክትትልና ቁጥጥር ድጋፍ የሚጎድላቸው እንዲሁም በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ ያልተጠናቀቁም እንዳሉም ይናገራሉ። በእነዚህ ላይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶበት የሚሰራ ይሆናል ብለዋል።የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የስፖርት ምክር ቤቱ ሰብሳቢ አዳነች አቤቤም፤ በከተማዋ ታዳጊዎች የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች በማጣታቸው ባልተገባ ስፍራ እንደሚውሉ ጠቅሰዋል። ይህንን በመረዳትም በየአካባቢው የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ግንባታ እየተካሄደ መሆኑን ያመለክታሉ። ምክትል ከንቲባዋ ይህ ግን በቂ እንዳልሆነ ተናግረው፣ ከዚህም በላይ መስራት እንደሚገባም ይጠቁማሉ። የጠቅላላ ጉባኤው አባላት በተናጠልም ሆነ በጋራ ኃላፊነትን በመወጣት የተጀመሩትን ውጤታማ ማድረግና በሁሉም አካባቢ ማዳረስ እንደሚገባም አሳስበዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 15/2013 | https://www.press.et/Ama/?p=38041 | 743 | 2ስፖርት
|
ቡናን ያለዛፍ ጥላ – በቀርጫንሼ ደበቃ | ሀገር አቀፍ ዜና | January 18, 2021 | 32 | አስቴር ኤልያስስፍራው ሞቃታማ ቢሆንም ቅጥር ጊቢው ግን በቡና ችግኞችና በተለያዩ የፍራፍሬ ዛፎች በመሙላቱ ለአይን አርንጓዴነቱ ደምቆ፤ ለአፍንጫ ደግሞ መልካም መዓዛው ዘልቆ ስለሚመጣ ለጎብኚው ማየትም መማግም ግዴታ ሳይሆን በውዴታ የሚያጣጥመው ነገር ነው። ወዲህ ለቡና ተክሉ የተስተካከለ ውሃ ይደርሰው ዘንድ አዲስ የሆነና የውሃው ልክ በኮምፒውተር የሚታዘዝበት ቴክኖሎጂ ያለበት አንድ ክፍል ይታያል፤ ወዲያ ደግሞ ወደ 750 ሜትር ኪዩብ ውሃ የሚይዝ የውሃው ሪዘርቫይር ይስተዋላል ፤ ቦታው በምዕራብ ጉጂ ዞን አባያ ወረዳ ልዩ ስሙ ደበቃ እርሻ ልማት ነው። የቀርጫንሼ እርሻዎች አስተባባሪ ስራ አስኪያጅ አቶ ደጀኔ ዳባ እንደሚሉት፤ በቀርንጫንሼ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ቀደም ሲል ጥራቱን የጠበቀ ቡና ወደ ውጭ አገር በመላክ ለአገሪቱ የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት ረገድ በግንባር ቀደምትነት እየሰራ ነው። ከንግዱ በተጨማሪ ከቅርብ ጊዜ ወደዚህ ጎን ለጎን በቡና እርሻ ልማት ተሰማርቷል። ድርጅቱ፣ በዓለማችን ላይ ዘመናዊ የሆነ በቡና ማምረት ቴክኖሎጂ ጫፍ ከደረሱ እንደብራዚል ካሉት አገራት ባልተናነሰ ዘመናዊ ቴክሎጂን ወይም ዲሪፕ እሪጌሽንን በመጠቀም ወደቡና ልማት እርሻ የገባ ነው። የቡና እርሻው የሚገኘው በምዕራብ ጉጂ ዞን አባያ ወረዳ ልዩ ስሙ ደበቃ እርሻ ልማት ሲሆን፣ያረፈው ደግሞ በ72 ሄክታር መሬት ላይ ነው። በዚህም ላይ 110 ሺህ የቡና ችግኞችን በመተክል ወደ ስራ መግባታቸውን ጠቅሰው፤ በቀጣይም በአንድ ሄክታር ላይ ዘመናዊ የቡና ማፍያ የችግኝ ጣቢያ ወይም ዲጂታል ስፕሪንግ ክለር እሪጌሽ በመጠቀም 600 ሺህ ችግኞችን በማፍላት ለአካባቢው ህብረተሰብም ጭምር ለማደል ወደ ስራ መግባታቸውን ይናገራሉ። ቀደም ሲል በአገራችን ያለው አስተሳሰብ ቡናን ያለጥላ ዛፍ ማልማት አይቻልም የሚል ኋላ ቀር አስተሳሰብ ሲሆን፣ ይህን አስተሳሰብ በአዲስ አስተሳሰብ ለመቀየር እየሰራን ነው ሲሉ ያስረዳሉ። በድርጅቱ አግሮኖሚስት ሆነው የሚሰሩት የሆርቲካልቸር ባለሙያው አቶ ጉተማ ጎቤ በበኩላቸው፤ በድሪፕ እሪጌሽን (ጠብታ መስኖ) በአንድ አይነት መልኩ ውሃ ለቡናው እንዴት ሆኖ ይሰራጫል የሚለውን እንደሚከታተሉ ይናገራሉ። ውሃው ለችግኙ ሲደርሰው ለእያዳንዱ ቡና እኩል የሆነ የውሃ መጠን ነው በሜትር ኪዩብ የተለቀቀው ውሃ ወደ ቡናው ሲሄድ የሚደርሰው በሚሊ ሊትር ተቀይሮ መሆኑን ይጠቅሳሉ። ይህ ቴክኖሎጂ የነበረውን ተልምዷዊ አሰራር ያለዛፍ ቡና መብቀል አይችልም የሚል አስተሳሰብን የሰበረ ነው። ቀደም ሲል ዛፍ ያስፈልግ የነበረው ብዙ ውሃ ስለማይጠጣ የዛፍ ጥላው ያለውን ውሃ እርጥበቱን ጠብቆ እንዲሄድ ስለሚያርገው ነው ይላሉ። አጠቃላይ የቀርጫንሼ ካምፓኒ ስራ አስፈጻሚ አቶ እስራኤል ደገፋ፣ ካምፓኒው የሚሰራው አጠቃላይ የአገራችን ኢኮኖሚ በሚፈልግበት በግብርናና ማኑፋክቸሪንግ ላይ መሆኑን ይገልጻሉ። በግብርናው ላይ ወደ 26 ሺህ የስራ እድሎችን በመፍጠር እንዲሁም ከ56 ሺህ አርሶ አደሮች ጋር የገበያ ትስስር በመፍጠር የሚሰራ ድርጅት እንደሆነም ያመለክታሉ። አቶ እስራኤል እንደሚሉት፤ ላለፉት አራት አምስት ዓመታት ትልቁን የአገሪቱን የቡና ኤክስፖርት ከሁለት አኃዝ በላይ ድርሻ በመውሰድ የሚልከው ይኸው የቀርጫንሼ ኩባንያ ነው። በየትኛውም የኢትዮጵያ ቡና አብቃይ ክልሎችም ሆነ ወረዳዎች ይገኛል። አጠቃላይ ወደ 57 ኢንዱስትሪዎች እንዲሁም ደግሞ ወደ አምስት እርሻዎችን በቡናው ሴክተር ላይ ማኔጅ ያደርጋል። ጉብኝት የተደረገበት የደበቃ እርሻ ጣቢያ፣ ኩባንያው ካሉት እርሻዎች ሁሉ አነስተኛው ነው ያሉት አቶ እስራኤል፣ ነገር ግን እንዴት አድርገን ግብርናን
ከተለምዶ አሰራራችን መቀየር አለብን ሲሉ በማሰብ በቡናው ፋርም ትልቅ ደረጃ ላይ የደረሱ አገሮችን
ተሞክሮ ከእነእስራኤልና ብራዚል መውሰድ ላይ መሆናቸውን ያመለክታሉ።
የወሰዱትም ቴክኖሎጂ ድሪፕ ኢሪጌሽን ሲሆን፣ በአሁኑ ሰዓት በዓለም ላይ የመጨረሻው የሚባለው
በግብርናው ዘርፍ የተገኘና
ውጤታማ የሆነ የመስኖ ሲስተም ነው ይላሉ። ከዚህ አንጻር በደበቃ ያለው የተሻለው
ቴክኖሎጂ እንደሚያሰኘው ያስረዳሉ።
አርሶአደሩ በተለምዶ በሄክታር ቡና የሚያገኘው ከስድስት ኩንታል የዘለለ አይደለም የሚሉት አቶ እስራኤል፣ እኛ በዚህ ቴክኖሎጂ ተጠቅመን ግን በሄክታር እስከ 35 ኩንታል ማሳካት ችለናል ብለዋል። ይህ ሙከራ ደግሞ የመጀመሪያው ሲሆን፣ የሚጠበቀው በሄክታር እስከ 65 ኩንታል ድረስ ነው ብለን እየሰራን ነው ሲሉ ተናግረዋል። ያንን ማሳካት ከቻልን የአገራችንን የውጭ ምንዛሬ ማሳደግ እንዲሁም የአርሶ አደሮችን ገቢ ከፍ ማድረግ ይቻላል ብለዋል። የእኛ ትልቁ እቅዳችን የራሳችን ማሳ ላይ ትልቁን ምርት ማምረት ላይ ብቻ አይደለም። በአቅራቢያው የሚገኙ የአርሶ አደሮችንም ማሳዎች ወደእኛ ቴክኖሎጂ በመቀየር እነርሱም ተጠቃሚ የሚሆኑበትን መሰረት ማደላደልና በፋይናንስም ለመደጎም ሲሆን፣ ይህን ተግባራዊ ለማድረግ ዲዛይን አድርገን ጨርሰናል ይላሉ። በዕለቱ ቀርጫንሼ ትሬዲግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ኤክስፖርት ስታንዳርድ የቡና ላቦራቶሪን የመረቁት የግብርና ግብአትና ግብይት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ አይናለም ንጉሴ እና የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አዱኛ ደበላ ሲሆኑ፣ ሚኒስትር ዴኤታዋ በዕለቱ እንደተናገሩት፤ የድርጅቱን የቡና ማዘጋጃ መጋዘንና የቡና መቅመሻ ላቦራቶሪ እንዲሁም እርሻዎቹን ጎብኝተናል። ከዚህ ደርጅት ባለቤት ጋር አርሶ አደሮችም አብረው ነው ያሉት። ለምርት መሻሻል ደግሞ ዋናው አርሶ አደሮቻችን ከባህላዊ የቡና አመራረት ዘዴ በመጠኑም ቢሆን በመቀየር የቡናን ምርታማነት ሊቀየሩ የሚችሉ አሰራሮችን ተግባራ እያደረጉ ነው ያሉት። ቡሌ ሆራ ላይ እንደማየውና ሞዴል አርሶአደሮችም እንዳረጋገጡልን በምርትም፣በአቅርቦትም ሆነ በገበያ ትስሰርም የተሻለ እድል ያለበት አካባቢ መሆኑን ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ፣ እዚህ የሚሰሩ ባለሀብቶች የአርሶአደሩንም ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ስለመሆናቸው ማስተዋል መቻላቸውን ይናገራሉ። እርሳቸው እንደሚናገሩት፤ እንደግብርና ሚኒስቴር የበለጠ ምርትና ምርታማነትን ሊያሳድግ የሚችል ስራ ይሰራሉ። ቡና ወደውጭ በመላክ ረገድ በተለይ ቀርጫንሼ ላለፉት ሁለትና ሶስት ዓመታት የቀዳሚነት ድርሻውን እየተወጣ ነው። በመጋዘን ውስጥ የተመለከትነውም ደረጃውን የማያስለቅቅ ለአገርም ኢኮኖሚ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሊያደርግ የሚችል ክምችት የያዘ ቡና መኖሩን ነው፤ ለዚህም በጣም ደስተኞች ነን። አርሶአደሮቹ ጥሩ የቴክኖሎጂ ስራ ካላቸው ከግል ሴአልሚዎች ጋር በመቀናጀት ምርታቸውን እንዲያሳድጉ ለማድረግ የሚያስችል የአሰራር ማዕቀፍ መዘርጋት ነው። የተሻለ ገበያ እንዲያገኝ ከማድረግ አኳያ የተዘረጉ አሰራሮች አሉ፤ ትልቁ ነገር አርሶ አደሩ ያመረተውን ምርት ቀጥታ ወደ ገበያ ለማድረስ የሚያስችለው አቅም ገበያ የማፈላለግ ችሎታ የማዳበር ስራ መሰራት ይኖርበታል። እንዲህ ከሆነ በለፋው ልክ ጥቅም እንዲያገኝ ያችለዋልና በዚህ ደረጃ እንቅስቃሴዎች ተጀምረዋል ብለዋል። ዶክተር አዱኛ በበኩላቸው እንደተናገሩት፤ ባለስልጣኑ ቡና ከማብቀል ጀምሮ ውጭ አገር እስከ መላክ ድረስ ያለውን ሂደት በማገዝ እንዲሁም ገበያ በማፈላለግ ረገድ በመስራት ላይ ይገኛል። አርሶ አደሮቻችን እስከ ውጭ አገር በራሳቸው እንዲልኩ ይሰራል። 500 ያህል አርሶ አደሮች ወደውጭ አገር መላክ የሚያስችላቸውን ሰነድ አውጥተዋል። በዚህም እየሄዱበት ነው። ቀርጫንሼ የሰራው ስራ በአርአያነት መጠቀስ የሚያስችል ስራ ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፣ በቦታው ተገኝተን ያስተዋልነው ነገር ቢኖር ይህን ነው ብለዋል። ይህም ወደሌሎቹም መስፋፋት ያለበት ቴክኖሎጂ መሆኑን ጠቅሰው፤ በዚህ ስራው ደግሞ እንደ መንግስት ድጋፍ እናደርግለታለን ብለዋል።አዲስ ዘመን ጥር 10/2013 ዓ.ም | https://www.press.et/Ama/?p=39687 | 838 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ኮቭድ-19- ዳግም የቶኪዮ ኦሊምፒክ ሥጋት | ስፖርት | December 25, 2020 | 7 | ቦጋለ አበበ ጃፓን ከሰባት ዓመታት በላይ ብዙ የለፋችበት የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ዝግጅት ካለፈው ዓመት ጀምሮ የዓለም ሕዝብ የጤና ጠንቅ በሆነው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ለአስራ ስድስት ወራት ተራዝሞ ዘንድሮ ሊካሄድ ቀጠሮ ተይዞለታል። ኦሊምፒኩ በተራዘመው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እንደሚካሄድም እርግጠኛ ሆነው የውድድሩ አዘጋጆች መናገር ከጀመሩ ሰነባብተዋል። የተለያዩ አገራትም በአዘጋጆቹ ተማምነው የስፖርት ልዑካን ቡድኖቻቸውን እያዘጋጁ ይገኛሉ።የዓለም አቀፉን ኦሊምፒክ ኮሚቴ ጨምሮ የውድድሩ አዘጋጆች አሁንም ድረስ ውድድሩ እንደሚካሄድ እርግጠኛ የሆኑት ወረርሽኙ ኦሊምፒኩ እስኪቃረብ አንድ መፍትሄ ያገኛል በሚልና በሙከራ ላይ የሚገኙትን የተለያዩ ክትባቶች ተማምነው ነው። ያም ሆኖ ሰሞኑን እየወጡ የሚገኙ መረጃዎች ወረርሽኙ እየቀነሰ ከመሄድ ይልቅ በፍጥነት እየተስፋፋ እንደሚገኝ ያመላክታሉ። ጃፓን ውድድሩን በምታካሂድበት ወቅት ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ ከአገሪቱ ዜጎች በበለጠ ብዙ ቁጥር ያላቸው እንግዶች ስጋት ሊሆኑ እንደሚችሉ የገመተች ቢሆንም፣ በተቃራኒው ራሷ ጃፓን የእንግዶቿ ስጋት ልትሆን እንደምትችል በቅርብ የወጡ መረጃዎች እየጠቆሙ ነው።ወረርሽኙ ለዓለም ስጋት ከሆነ ወዲህ ኦሊምፒኩን በዋናነት የምታስተናግደው ከተማ ቶኪዮ ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድ ወር ውስጥ ብቻ በቫይረሱ የተጠቁ አስር ሺህ ሰዎች የተገኙባት ሆናለች። ይህም በቀጣዩ ክረምት በሚካሄዱት የኦሊምፒክና የፓራሊምፒክ ውድድሮች ላይ ዳግም ተመሳሳይ ስጋት እንዲፈጠር ያደረገ ሲሆን በብዙዎች ዘንድ ጥያቄ እየተነሳበት ይገኛል።ኦሊምፒኩ ሊካሄድ ስድስት ወራት በቀሩበት በዚህ ወቅት ባለፈው ሐሙስ ብቻ ቶኪዮ በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ ስምንት መቶ ሃያ ሁለት ሰዎች በቫይረሱ የተያዙባት ከተማ ሆናለች። ይህም ወረርሽኙ በሀገሪቱ ከተከሰተበት ወቅት ወዲህ የታየ ከፍተኛው ቁጥር ሆኖ ተመዝግቧል። የቶኪዮ ከተማ አስተዳዳሪ ዩሪኮ ኮኢኬ ከጃፓን ታይምስ ጋር በነበራቸው ቃለ ምልልስም የቶኪዮ የጤና ተቋማት ከአቅማቸው በላይ ሕመምተኞችን እያስተናገዱ እንደሚገኙ ተናግረዋል። ‹‹ሆስፒታሎች ተዘግተዋል፣ በዚህ ወሳኝ ወቅት በቅርቡ መሰረታዊ አገልግሎት መስጠት ሊያቆሙም ይችላሉ›› በማለትም በከተማዋ ያለውን ሁኔታ ገልፀዋል።ቶኪዮ ወረርሽኙ ከተከሰተ ወዲህ እስካለፈው ሳምንት መጨረሻ ብቻ ሃምሳ ሁለት ሺህ ሰዎች በቫይረሱ የተጠቁባት ከተማ ስትሆን አምስት መቶ ያህል ሰዎችም ሕይወታቸው አልፏል። በአጠቃላይ በጃፓን ደግሞ እስካፈው ሰኞ ድረስ በአማካይ ከሁለት ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ እየተጠቁ እንደሚገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ፤ እስካሁን ከሁለት ሺህ ዘጠኝ መቶ በላይ ሰዎች በቫይረሱ መሞታቸው ታውቋል።የቶኪዮ ተላላፊ በሽታዎች መቆጣጠሪያ ማዕከል ዳይሬክተር ኖሮዪ ኦማጋሪ በበኩላቸው ‹‹የቫይረሱ ሥርጭት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል፣ ከዚህ የበለጠ ብዙ ሰዎች በቫይረሱ እንዳይጠቁ ጠንካራ እርምጃዎች መወሰድ አለባቸው›› በማለት ለአገሪቱ ጋዜጣ ተናግረዋል።ጥቂት ቀናት በቀሩት የፈረንጆቹ አዲስ ዓመትና የገና በዓል አከባበር ወቅት በርካታ የአውሮፓ አገራት የወረርሽኙን ሥርጭት ለመቀነስ ጠንካራ መመሪያዎችን ከማውጣት ባሻገር በአገር አቀፍ ደረጃ እንቅስቃሴዎችን እስከ መግታት ደርሰዋል። ይህን በመመልከትም ጃፓን በአንፃራዊነት የተሻለ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ የሚናገሩ አሉ። ከቀናት በፊት የእንግሊዝ መንግሥት የጤና ቢሮ ሃላፊ ክሪስ ዊቲይ በአይነቱ ልዩ የሆነና በፍጥነት የመዛመት ባህሪ ያለው የኮቪድ-19 ቫይረስ በአገሪቱ እንደተገኘ ለዓለም ጤና ድርጅት ጭምር በማሳወቅ ጥንቃቄ እንዲደረግ ማሳሰቡ ይታወቃል። በአገሪቱ የቫይረሱ ሥርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ በመምጣቱም ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን በአዲስ ዓመትና በገና በዓል ዋዜማዎች ወቅት በሚደረጉ መዝናኛዎች ላይ ጠንካራ እግድ አስቀምጠዋል። መዲናዋ ለንደንን ጨምሮ ቫይረሱ በስፋት በተሰራጨባቸው የደቡብ እንግሊዝ ከተሞችም ጠንካራ የተባሉ ገደቦች ተጥለዋል።አስቀድሞ በቫይረሱ ከፉኛ የተጠቃችው ጣሊያንን ጨምሮ ኔዘርላንድስና ጀርመን እስከ አዲሱ ዓመት ድረስ ማንም ከቤቱ እንዳይወጣ እግድ አስቀምጠዋል። አውስትራሊያም ከገና በዓል በኋላ ተመሳሳይ እርምጃ እንደምትወስድ መረጃዎች ጠቁመዋል። በቅርቡ በቤልጂየም ብራሰልስ የተካሄደውን የአውሮፓ ሕብረት ስብሰባ ከተካፈሉ በኋላ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑዔል ማክሮንና የስሎቫኪያው ጠቅላይ ሚኒስትር ኢጎር ማቶቪች እንዲሁም ሌሎች የአገር መሪዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ይታወቃል። ባለፈው ዓመት በቫይረሱ ሥርጭት ስጋት የገባቸው የኦሊምፒክ አዘጋጆች ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ታላቁን የስፖርት መድረክ ለማራዘም መገደዳቸው ይታወቃል። በዚህም የተነሳ አዘጋጅ ኮሚቴው ሁለት ነጥብ ስምንት ቢሊየን ዶላር ኪሳራ እንደደረሰበት ከወር በፊት አሳውቋል። ወረርሽኙ ዳግም በከፍተኛ ሁኔታ ማገርሸቱን ተከትሎም የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ላይ ጥያቄ ተነስቷል። የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ቶማስ ባኽን ጨምሮ የተለያዩ ሃላፊዎች ግን አሁንም ውድድሩን በጥንቃቄ ለማካሄድ ሃሳብ አለወጡም።ቶኪዮ በኦሊምፒኩ ወቅት ወረርሽኙን ለመቆጣጠር በምትወስደው እርምጃ ከዘጠኝ መቶ ስልሳ ሚሊየን ዶላር በላይ ወጪ እንደምታደርግ የተዘገበ ሲሆን፣ የውድድሩ አዘጋጆች ቫይረሱን ለመዋጋት ከአገሪቱ መንግሥት ጋር በየጊዜው ውይይት እያደረጉ ይገኛሉ። በኦሊምፒኩ የሚሳተፉ አትሌቶችና የስፖርት ልዑካን ቡድኖች የፊት ጭምብል ማጥለቅና ርቀትን መጠበቅ እንደሚገባቸው አዘጋጆቹ በቅርቡ ጠቁመዋል፤ ከውድድሩ በኋላ በጃፓን የሚቆዩበት ጊዜ አጭር እንደሚሆንም አሳውቀዋል።እንግሊዝ፣ አሜሪካ፣ ቻይናና ሩሲያን የመሳሰሉ የተለያዩ አገራት ለወረርሽኙ መፍትሄ ይሆን ዘንድ የተለያዩ ክትባቶችን በማምረት የተሳካ ሙከራ እንዳደረጉ መናገር ከጀመሩ ሰንብተዋል። ክትባቱ በምን አይነት ፍጥነት ለዓለም ሕዝብ ተዳርሶ የቶኪዮ ኦሊምፒክ ከስጋት ነፃ በሆነ መልኩ ይካሄዳል የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ነው። በኦሊምፒኩ ለመሳተፍ ወደ ቶኪዮ የሚያቀኑ ከቫይረሱ ነፃ የሆኑ አትሌቶች ክትባቱን ለማግኘት ቅድሚያ ይሰጣቸዋል አይሰጣቸውም የሚሉ ጥያቄዎችም ከወዲሁ እየተነሱ ይገኛሉ።የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ቶማስ ባኽ ባለፈው ወር በጃፓን ባደረጉት ጉብኝት ወቅት የተሳካ የኮቪድ-19 ክትባት ተገኘ መባሉን ተከትሎ እንኳን ስፖርተኞች የስፖርቱ አፍቃሪዎች ስቴድየም ገብተው የኦሊምፒክ ውድድሩን ካለ ስጋት እንደሚመለከቱ እርግጠኛ ሆነው ሲናገሩ ተደምጠዋል።የጃፓን መንግሥትና የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አትሌቶች የወረርሽኙን ክትባት እንዲያገኙ የተለያዩ ጥረቶችን እያደረጉ ይገኛሉ። ከዚህ ባሻገር በኦሊምፒኩ የሚሳተፉ አትሌቶችና የስፖርት ቤተሰቦች ወረርሽኙን ለመከላከል የተለያዩ ጥብቅ መመሪያዎችን ማክበር እንደሚገባቸው ቀደም ሲል አዘጋጆቹ አሳውቀዋል።ባለፈው ዓመት ወረርሽኙ በኦሊምፒኩ አዘጋጅ ጃፓንም ይሁን በሌሎች አገራት እንዲህ እንዳሁኑ ባልጠነከረበት ወቅት ለመራዘም የተገደደውን ይህን ውድድር፣ ዘንድሮ ወረርሽኙ ‹‹ክትባት ተገኝቶለታል›› እየተባለም መልኩን እየቀያየረ የብዙዎች ስጋት በሆነበት ጊዜ እንዲካሄድ መወሰን ለብዙዎች አልተዋጠም። ዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴውም ይሁን የጃፓን መንግሥት ውድድሩን ለማካሄድ እርግጠኛ ሆነው እየተንቀሳቀሱ የሚገኙትም ኦሊምፒኩ ካልተካሄደ የሚደርስባቸውን ትልቅ ኪሳራ በማስላት ሊሆን እንደሚችል ትችቶች ይሰነዘራሉ።ኦሊምፒኩ ባለፈው ዓመት መካሄድ ሲገባው ወደ ዘንድሮ በመራዘሙ ብቻ ሁለት ነጥብ ስምንት ቢሊየን ዶላር ኪሳራ እንዳደረሰ የቅርብ ጊዜ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ይህን ኪሳራ ለመሸፈን የቶኪዮ ከተማ አንድ ነጥብ አንድ ቢሊየን ዶላር ወጪ እንዳደረገ ተዘግቧል፤ የውድድር አዘጋጅ ኮሚቴው አንድ ቢሊየን ዶላር ወጪ አድርጓል። ቀሪውን ሰባት መቶ ሚሊየን ዶላር ደግሞ የጃፓን መንግሥት እንደሚሸፍን ታውቋል። ኦሊምፒኩ ከመራዘሙ አስቀድሞ አስራ ሦስት ቢሊየን ዶላር ወጪ እንደሚጠይቅ ተገልጿል።በዘንድሮው ዓመት ሳይካሄድ ከተራዘመ ወይም ከተሰረዘ ቀድሞ ከተያዘለት በጀት እስከ አራት እጥፍ ኪሳራ ሊያደርስ እንደሚችል መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 16/2013 | https://www.press.et/Ama/?p=38136 | 827 | 2ስፖርት
|
ምክር ቤቱ አቅጣጫና ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል | ስፖርት | December 28, 2020 | 9 | ብርሃን ፈይሳ አዲስ አበባ፡- ብሄራዊ የስፖርት ምክር ቤት ነገ የመጀመሪያ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን እንደሚያከናውን ተገለጸ። በጉባኤው ላይም አቅጣጫዎችን እንደሚሰጥና ውሳኔዎችንም እንደሚያስተላልፍ ይጠበቃል። የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ብሄራዊ የስፖርት ምክር ቤቱ ባለፈው ዓመት ህዳር 4 ቀን 2012 ዓ.ም መስራች ጉባኤውን ማካሄዱ ይታወሳል፤ ይሁን እንጂ ኮቪድ 19 በኢትዮጵያ መከሰትን ተከትሎ የመጀመሪያ ጠቅላላ ጉባኤውን በተያዘለት ወቅት ማካሄድ አልተቻለም። በመሆኑም ነገ የመጀመሪያ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ያከናውናል። በጉባኤው ላይም የጉባኤው አባላት የሆኑት፤ የክልልና ከተማ አስተዳደር ርዕሳነ መስተዳድሮች ከንቲባዎች፣ ከዘጠኝ ሚኒስትር መስሪያ ቤቶች የተወጣጡ ሚኒስትሮች፣ የስፖርት ኮሚሽነሮች፣ የሃገር አቀፍ ስፖርት ማህበራት አመራሮች፣ የስፖርት ተቋማት እንዲሁም ለስፖርት ጉልህ ሚና ያላቸው የክብር እንግዶች ይገኛሉ። የጉባኤው አጀንዳዎችም የመስራች ጉባኤውን አጀንዳ ማጽደቅ፣ በወቅቱ የተሰጡ አቅጣጫዎችን አፈጻጸም መገምገም፣ በቀጣይ በትኩረት የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፣ የ10 ዓመቱ መሪ እቅድና የ2013 በጀት ዓመት እቅድ እንዲሁም ልዩ ልዩ መመሪያዎችን አቅርቦ ማጸደቅ የሚሉት መሆናቸው ተጠቁሟል። አጀንዳዎቹን ተከትሎ አቅጣጫ እንደሚሰጥና ውሳኔዎችም እንደሚያስተላለፉ ይጠበቃል።የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽነር ኤሊያስ ሽኩር ጉባኤው ትኩረት የሚሰጥበት አጀንዳም ምክር ቤቱ በመስራች ጉባኤ ወቅት ያስቀመጣቸው ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች አፈጻጸምን በዝርዝር ተመልክቶ መገምገምን የተመለከተ መሆኑን አስታውቀዋል። የሃገሪቷ ስፖርት መሰረታዊ ችግሮችና መፍትሄ የሚል ጥናት በማካሄድ በተዘጋጀው የሪፎርም ሰነድ ምክር ቤቱ ተወያይቶ በዝርዝር እንዲከናወኑ አቅጣጫ የሰጣቸው ጉዳዮች ላይ ግምገማ የሚያካሂድም መሆኑን ተናግረዋል። እንደ ኮሚሽነሩ ገለጻ፤ከአቅጣጫዎቹ መካከል አንዱ ባለድርሻ አካላትን በማወያየት ሰነዱ እንዲዳብር ነበር፤ ይህም እስከ ታችኛው እርከን በመውረድ የማዳበር ስራው ተከናውኗል። ሰነዱ ሲዘጋጅ የተቀመጡት ምክረ ሃሳቦች በእቅድ እንዲካተቱ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በ10 ዓመቱ ስትራቴጂክ እና የዓመቱ እቅድ ላይ እንዲካተት ተደርጓል። አሰራሮችን ከመፈተሽና አዳዲስ የአሰራር ማኑዋሎችን ከመፍጠር ረገድም የስፖርት ፖሊሲውን የማሻሻል ስራ ተጀምሯል፣ ሃገሪቷ የሌላት የስፖርት ህግም እየተረቀቀ ነው፣ ሃገር አቀፍ የስፖርት ማህበራት የሚመዘኑበት ስታንዳርድ የማዘጋጀት፣ የማዘውተሪያ ስፍራዎች ስታንዳርድና የስፖርት ፈንድ ሰነድ ማዘጋጀት እንዲሁም የስፖርት መመሪያ በማሻሻል ረገድ ያሉትን ፈትሾ በማስተካከልና የሌሉትን አዳዲስ በማዘጋጀት የተሳካ ስራ ማከናወን ተችሏል። ተጠናቀው ወደ ስራ የገቡ መኖራቸውንና ሌሎች ደግሞ እርከኑን ጠብቆ በሌሎች አካላት መጽደቅ ያለባቸውም በሂደት ላይ ይገኛሉ።የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን፣ የስልጠና ማዕከላትና የስፖርት ቁሳቁስን በሚመለከትም ትልልቅ ግንባታዎች በተያዘላቸው ጊዜና በጥራት እንዲጠናቀቁ እየተሰራም መሆኑም በመግለጫው ተጠቁሟል። ከጥርጊያ ሜዳ ጀምሮ በየአካባቢው ያሉ ማዘውተሪያዎችም የባለቤትነት ማረጋገጫ እንዲኖራቸውና እጥረት ባለባቸውም ተጨማሪ እንዲያገኙም እየተደረገ ነው። ያሉት የስልጠና ማዕከላትም በሙሉ አቅማቸው እንዲሰሩ የማድረግ ስራ እየተሰራ ከሚሽነሩ ጠቅሰው፣ በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች ከማስፋፋት አኳያ ያለው ተነሳሽነትም መልካም የሚባል መሆኑን ኮሚሽነሩ ይጠቁማሉ። የህዝብ ተሳትፎን በሚመለከትም ኮቪድን እንደ ምክንያት በመጠቀም በህብረተሰቡ ዘንድ መነሳሳትን በመፍጠር ረገድ የተሻለ ጅማሮ ታይቷል ብለዋል። በጉባኤው ላይ በህብረተሰቡ የስፖርት ተሳትፎ ፍትሃዊነትና ተደራሽነት ላይም ውይይት ይደረጋል ተብሏል። በስፖርት አደረጃጀት ላይ ሕዝባዊ አካሉ በምን መልክ ሊደራጅ ይገባዋል የሚለውም ሌላው ውይይት የሚደረግበት መሆኑ ተጠቁሟል። በመግለጫው ላይ እንደተመለከተው፤ በ2011 ዓም አሳሳቢ የነበረው የስፖርታዊ ጨዋነት መጓደልም በወረርሽኙ መከሰት ውድድሮች እስከተቋረጡ ድረስ ውጤታማ ስራዎችን ማከናወን ተችሏል። ኮቪድ 19 በኢትዮጵያ ከተከሰተ ወዲህም በስፖርቱ ላይ ያስከተላቸው ጉዳቶችን እና ቫይረሱ እያለ እንዴት ወደ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ መገባቱን ተከትሎ ክትትል ለሚያደርገው ኮሚቴ አቅጣጫ የሚሰጥም ይሆናል። በቀጣይ የሚካሄዱ ሃገር እና ዓለም አቀፍ ውድድሮችን በሚመለከትና ለሚቀጥለው የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ በምን መልክ ውጤት ማስመዝገብ ይቻላል በሚለው ላይም ምክር ቤቱ ይመክራል። | https://www.press.et/Ama/?p=38365 | 448 | 2ስፖርት
|
የከተማ አቀፍ አካል ብቃት እንቅስቃሴ ተመልሷል | ስፖርት | December 29, 2020 | 7 | ቦጋለ አበበ ከተማ አቀፍ የአካል ብቃት ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በአዲስ አበባ አዲሱ ለሚ ኮራ ክፍለ ከተማ በደማቅ ሁኔታ በይፋ ተጀምሯል። የአካል ብቃት እንቅስቃሴው ‹‹ለሀገሬ ሰላም ዘብ እቆማለሁ፤ ለመከላከያ ሰራዊት ቅድሚያ እሰጣለሁ›› በሚል መሪ ቃል በየካ አባዶ የጋራ መኖሪያ ቤቶች አደባባይ ከትናንት በስቲያ የተካሄደ ሲሆን በርካታ ቁጥር ያላቸው የአካባቢው ነዋሪዎችም ተሳታፊ ሆነዋል ። በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ፣ ‹‹በስፖርት የተገነባ ኃይል የትኛውንም ጠላት መመከት ይችላል፤ በመሆኑም በየትኛውም አካባቢ በተገኘው ቦታ ሁሉ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በማድረግ እራሳችንን ከበሽታ ልንከላከል ይገባል›› ብለዋል። ለዚህም ከተማ አስተዳደሩ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል። ‹‹መከላከያችን
ባደረገው የሰላም ማስከበር ተልዕኮ
በአጭር ጊዜ ውስጥ ድል
የተቀዳጀው በስፖርት የተገነባ ስለሆነ
ነው፣ መከላከያችንን እያሰብን ሁሌም ስፖርትን
ባህላችን ልናደርግ ይገባል›› በማለትም
አቶ ጃንጥራር ተናግረዋል::የኢፌዴሪ
ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ
ኤሊያስ ሽኩር በበኩላቸው፣ የማህበረሰብ
አቀፍ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በሁሉም
የማህበረሰብ ክፍሎች በፍታሐዊነት ተደራሽ
እና ባህል እስኪሆን ድረስ
ከሚመለከታቸው አካላት በጋራ እንደሚሰሩ
ገልጸዋል::በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ለረጅም ወራት ተቋርጦ ከትናንት በስቲያ የተጀመረው ከተማ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መርሃ ግብር በየሳምንቱ በአስራ አንዱም የአዲስ አበባ ክፍለ ከተሞች በወጣው መርሃ ግብር መሠረት ለአንድ ወር የሚቀጥል ሲሆን በሚቀጥለው ሳምንት በየካ ክፍለ ከተማ እንደሚካሄድ ታውቋል።በአካል ብቃት ስፖርታዊ እንቅስቃሴው ላይ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር በላይ ደጀን፣ የለሚ ኩራ፣ የቦሌና የየካ ክፍለ ከተሞች ዋና ስራ አስፈፃሚዎች እንዲሁም በርካታ ቁጥር ያላቸው የየካ አባዶ የጋራ መኖሪያ ቤት ነዋሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል።የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን የከተማዋን ሁለንተናዊ የስፖርት ልማት፣ የስፖርት ንቅናቄ ፣ የስፖርት ተሳታፊነትና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እየሰራ እንደሚገኝ የተገለጸ ሲሆን ስፖርት ለሰላም፣ ለአንድነት፣ ለፍቅር፣ ለጤንነት፣ ለመቻቻል፣ ለአብሮነት፣ ለልማትና ለትብብር ያለው ፋይድ ታላቅ መሆኑን ስፖርት በተግባር እያሳየ እንደሚገኝም ተጠቁሟል፡፡አዲስ ዘመን ታኅሣሥ 20/2013 | https://www.press.et/Ama/?p=38442 | 264 | 2ስፖርት
|
አዳዲስ የአትሌቲክስ ማዘውተሪያዎች ግንባታ ይከናወናል | ስፖርት | December 24, 2020 | 10 | ብርሃን ፈይሳአዲስ አበባ፡- ለአትሌቲክስ ስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ የሚሆኑ ቦታዎች ምልከታ ተደረገ። ማዘውተሪያዎቹ በአዲስ አበባ አቅራቢያ በሚገኙ አራት ከተሞች ላይ የሚገኙ መሆኑም ታውቋል። በቅርቡ በለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር የተመረቀውን የአትሌቲክስ ስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ ተከትሎ ሌሎች ግንባታዎችም እንደሚከናወኑ ተጠቁሞ ነበር። በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ፤ ከለገዳዲ ለገጣፎ ባሻገር በተለያዩ ከተሞች በአጭር ጊዜ ቦታ በማዘጋጀት ተጨማሪ ማዘውተሪያ ስፍራዎች እንደሚገነቡ ጠቁመው ነበር። የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን በድረገጹ እንዳስታወቀው፤ለማዘውተሪያ ስፍራዎቹ ግንባታ በሚሆኑ ስፍራዎች ላይ ሰሞኑን ምልከታ ተከናውኗል። በመልክታው መሰረት ማዘውተሪያዎቹ የሚገነቡት በአዲስ አበባ አቅራቢያ በሚገኙት አራት ከተሞችም ቡራዩ ፣ ሰበታ ፣ ዱከም እና ሱልልታ ይሆናል። ለግንባታውም በቡራዩ 50 ሄክታር፣ በሰበታ 8 ነጥብ 5 ሄክታር፣ በዱከም 23 ሄክታር እንዲሁም በሱልልታ 20 ሄክታር መሬት ተዘጋጅቷል። በምልከታው ላይም የኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው፣ ሚኒስትር ዲኤታው ሃብታሙ ሲሳይ፣ የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽነር ኤሊያስ ሽኩር፣ ምክትል ኮሚሽነር ዱቤ ጂሎ፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ደራርቱ ቱሉ እና ምክትል ፕሬዚዳንቱ ገዛኸኝ አበራ እንዲሁም የኦሮሚያ ስፖርት ኮሚሽን አመራሮች ተገኝተዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 15/2013 | https://www.press.et/Ama/?p=38042 | 164 | 2ስፖርት
|
የአገር አቋራጭ ሩጫና የፆታ እኩልነት ሙግቶች | ስፖርት | December 26, 2020 | 9 | በታሪክ አጋጣሚ ቀደም ባሉት ዓመታት በተለያዩ የአትሌቲክስ ውድድሮች ወንድና ሴት አትሌቶች በተለያዩ ርቀቶች በተመሳሳይ ውድድር ላይ ሲሮጡ መመልከት የተለመደ ነው። ‹‹ወንዶች የሚሮጡትን ርቀት ሴቶች መሮጥ አይችሉም›› የሚል አስተሳሰብ በነበረበት ዘመን በተመሳሳይ ውድድር ላይ ሴቶች ከወንዶች ያነሰ ርቀት ለመሮጥ ይገደዱ ነበር። እንዲያውም በአንዳንድ ዓለም አቀፍ የውድድር መድረኮች ላይ ወንዶች በሚሮጡበት ርቀት ሴቶች እንደማይወዳደሩ ከታሪክ መረዳት ይቻላል። ለምሳሌ ያህል በታላቁ የዓለማችን የስፖርት መድረክ ኦሊምፒክ ማራቶን አንጋፋና ምናልባትም ከመጀመሪያ አንስቶ የሚካሄድ የውድድር አይነት ቢሆንም ሴቶች በርቀቱ መወዳደር የጀመሩት ዘግይተው ነው።በኦሊምፒክ መድረክ ብቸኛው የጎዳና ላይ ውድድር በሆነው ማራቶን ወንዶች መሳተፍ የጀመሩት እኤአ 1896 ላይ ነው። የሴቶች ማራቶን የኦሊምፒክ ውድድር ውስጥ የተካተተው ግን ዘጠና ዓመታትን ዘግይቶ በ1984 ኦሊምፒክ ነበር። ከማራቶን በተጨማሪም በርካታ በተለይም ረጅም ርቀት ውድድሮች በኦሊምፒክም ይሁን በዓለም ቻምፒዮና ሴቶችን ማካተት የጀመሩት ዘግይተው ነው። ይሁን እንጂ በዘመናዊው የአትሌቲክስ ዓለም ሴቶች ወንዶች በሚወዳደሩበት ርቀት ሙሉ በሙሉ ለማለት በሚያስችል ደረጃ ተወዳዳሪ ናቸው።ከአታካቹ ማራቶን አንስቶ እስከ ተለያዩ የጎዳና ላይ ውድድሮች ሴቶች ወንዶች የሚሮጡትን ርቀት በመሮጥ ብቃታቸውን አስመስክረዋል። ርቀቶቹን ሮጠው ለማጠናቀቅ የሚፈጅባቸው ሰዓት ከተፈጥሮ ጋር በተያያዘ ከወንዶች የዘገየ ቢሆንም የትኛውንም ርቀት ሴቶች አይሮጡም ብሎ የሚያምን ሰው ፈልጎ ማግኘትም ከባድ የሚመስልበት ዘመን ላይ ተደርሷል። ይሁንና ሴቶች በአገር አቋራጭ ውድድሮች ላይ ከወንዶች ያነሰ ርቀት እንዲሮጡ መደረጉ በአትሌቲክሱ ቤተሰቦች መከራከሪያ አጀንዳ ከሆነ ዓመታት ተቆጥረዋል።እንግሊዛዊቷ የቀድሞ የአገር አቋራጭ ቻምፒዮና የሜዳሊያ ባለቤት አትሌት ጆ ፓቬይ «በአገር አቋራጭ ውድድሮች ሴቶች ከወንዶች ባነሰ ርቀት መወዳደራቸው የፆታ እኩልነትን አያሳይም» የሚል አስተያየት ከሁለት ዓመት በፊት ለስካይ ኒውስ መስጠቷን ተከትሎም የአገር አቋራጭ ውድድር አዘጋጆች ከአትሌቲክስ ቤተሰቡ ጋር ሙግት ገጥመው እንደነበር ይታወሳል። በርካታ የስፖርቱ ባለሙያዎችና የውድድር አዘጋጆችም በጉዳዩ ላይ ሲሟገቱ ይስተዋላል። አገር አቋራጭ ውድድሮች በየዓመቱ በተለያዩ ከተሞች በተለይም በአውሮፓ ይካሄዳሉ። የዓለም አትሌቲክስም በየሁለት ዓመቱ የዓለም አገር አቋራጭ ቻምፒዮና ያዘጋጃል። በእነዚህ ውድድሮች ሴትና ወንድ አትሌቶች በእኩል ርቀት ሲወዳደሩ አይታይም። እኤአ ከ2017 በፊት በዓለም አገር አቋራጭ ቻምፒዮና የሚካሄደው ፉክክር በአራት አይነት መንገድ ተከፍሎ ነው። የመጀመሪያው አዋቂ ወንዶች የሚወዳደሩበት የአስራ ሁለት ኪሎ ሜትር ውድድር ሲሆን አዋቂ ሴቶች ስምንት ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ርቀት ላይ ብቻ ተፎካካሪ ነበሩ። በወጣት ወንዶች መካከል የሚካሄደው ውድድር ደግሞ ስምንት ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን ወጣት ሴቶች ስድስት ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ፉክክር ያደርጋሉ። እነዚህ ርቀቶች በዓለም ቻምፒዮናም ይሁን በግል አገር አቋራጭ ውድድሮች በብዛት የተለመዱ ናቸው። አልፎ አልፎ ግን በዓለም ቻምፒዮናም ይሁን በግል ውድድሮች እንደየሁኔታው ወንዶች ከሴቶች እኩል ርቀቶችን የሚሮጡበት አጋጣሚ ሲፈጠር ይታያል። ለአብነት ያህልም በ2017 በዩጋንዳ ካምፓላ ተካሂዶ የነበረው የዓለም አገር አቋራጭ ቻምፒዮናን ማንሳት ይቻላል። በዚህ ቻምፒዮና ለመጀመሪያ ጊዜ አዋቂ ሴቶችና ወንዶች እኩል አስር ኪሎ ሜትር የሸፈነ ውድድር ማድረጋቸው ይታወሳል። «ታዲያ ሴቶች በዚህ ውድድር ከወንዶች እኩል መሮጥ እየቻሉ አነስተኛ ርቀት እንዲሮጡ መደረጋቸው ለመጪው ትውልድ ምን አይነት መልዕክት ያስተላልፋል?» የሚል ከጾታ እኩልነት አኳያ ጥያቄ የሚያነሱ ቁጥራቸው ብዙ ነው።በምስራቅ ለንደን የአትሌቶች ማህበር አባል የሆነችው ማዑድ ሆድሰን በዚህ ውድድር የጾታ እኩልነት መረጋገጥ ካለበት ሴትም ወንድም እኩል ርቀት መሮጥ አለባቸው የሚል አቋም ይዛ ባለፉት ዓመታት ስትከራከር ቆይታለች። ይህን ሃሳቧንም በርካቶች ደግፈውታል። ሆድሰን በጉዳዩ ላይ ለራነርስ ዌብ ከዓመታት በፊት እንደገለፀችው፣ በአገር አቋራጭ ውድድሮች ሴትና ወንድ እኩል ርቀት እስካልሮጡ ድረስ መጪው የአትሌቲክስ ትውልድ በሩጫው ዓለም ሴትም ወንድም እኩል መሆናቸውን ሊረዳ አይችልም። ወንዶች ከፍ ያለውን ርቀት መሮጣቸው በአገር አቋራጭ ውድድሮች የሴቶቹ ፉክክር ከወንዶቹ ያነሰ የሚመስል ትርጉም ይሰጠዋልም ትላለች። ሆድሰን በዚህም ሳታበቃ በጉዳዩ ላይ አንድ መፍትሄ ለማምጣት በኤሌክትሮኒክስ መንገድ ፊርማ አሰባስባ በቀናት ውስጥ ከአንድ ሺ በላይ ተከታዮችን አግኝታለች። ይህ ሃሳብ በፌስ ቡክ ገፅም«አይ ወዝ ኦር አም ራነር» በሚል በተፈጠረ የቡድን ገፅም በርካታ ወንዶች የደገፉት ሲሆን ብዙ ተከታዮች አግኝቶ መነጋገሪያነቱ እየጨመረ መጥቷል።አዳጋች በሆነው የአገር አቋራጭ ውድድር አትሌቶች በጭቃ፤ በዳገትና ቁልቁለት አልፎ አልፎም በበረዶ ይፈተናሉ። ይህን ከግምት የሚያስገቡ በርካታ ሰዎች ሴቶች በውድድሩ እንደ ወንዶች ረጅም ኪሎ ሜትር መሮጥ አይችሉም የሚል አስተሳሰብ እንዲይዙ ያደርጋቸዋል። አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያመላክቱት ግን ሴቶች በሌሎች ፈታኝ በሚባሉ ማራቶንና ግማሽ ማራቶን ውድድሮች ላይ ከወንዶች እኩል ርቀት ሮጠው ከሚያስመዘግቡት የሰዓት ልዩነት የተጋነነ አያስመዘግቡም። በቢኬት ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ሳይንስና ባዮሜካኒክስ መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ብሬን ሃንሌይ ጥናታዊ ፅሁፍ ግን በአገር አቋራጭ ውድድር ሴቶች ከወንዶቹ ባልተናነሰ ተመሳሳይ ርቀት መወዳደር እንደሚችሉ ይጠቁማል። ጥናቱ ልክ እንደ ወንዶቹ የሴቶቹም ውድድር መጀመሪያ ላይ ቀዝቃዛ ፉክክር የሚታይበት ቢሆንም መጨረሻው በፉክክር የታጀበ እንደሚሆን አረጋግጧል። አብዛኞቹ የውድድር አዘጋጆች ግን ሴቶች በዚህ ውድድር ከወንዶች እኩል ርቀት ቢሮጡ መጨረሻው በፉክክር እንደማይታጀብና አሰልቺ እንደሚሆን ስለሚያምኑ ሴቶች አነስተኛ ርቀት እንዲወዳደሩ ያደርጋሉ የሚል ክርክር ይነሳል። ይህ ግን ዞሮ ዞሮ ከፆታ እኩልነት ጋር ባይያያዝ እንኳን በርካታ ወጣት አትሌቶችን ወደ ውድድሩ እንዳይመጡ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል መላ ምቶች ይቀመጣሉ። ይህም ርቀቱ በረዘመ ቁጥር በርካታ አትሌቶች እንደ ጎዳና ላይ ረጅም ርቀት ውድድሮች ሁሉ የመወዳደራቸው አጋጣሚ ሰፊ ይሆናል የሚል ነው።የአርባ ስድስት ዓመቷ ጆ ፓቬይ አትሌቲክስን ካቆመች በርካታ ዓመታት ቢቆጠሩም ሴቶች በአትሌቲክሱ ዓለም አስደናቂ ታሪኮችን ከወንዶች እኩል መስራታቸውን በማስታወስ በአገር አቋራጭ ውድድሮችም ከወንዶች እኩል ርቀት መሮጥ እንዳለባቸው ከስካይ ኒውስ ጋር በነበራት ቆይታ ገልፃለች። «ለበርካታ ዓመታት በአስቸጋሪው የማራቶን ውድድር ሴቶች ከወንዶች እኩል ርቀት ሲወዳደሩ ቆይተዋል፤ በአገር አቋራጭ ውድድሮች እኩል ርቀት ያለመሮጣቸው ሴቶች ከወንዶች እኩል አቅም የላቸውም የሚል አመለካከትን ይፈጥራል» በማለትም ፓቬይ አቋም ይዛለች።የማራቶን ባለክብረወሰኗና የቀድሞ የዓለም አገር አቋራጭ ቻምፒዮኗ አትሌት ፓውላ ራድክሊፍ ሰሞኑን በጉዳዩ ላይ በማህበራዊ ሚዲያው የሚደረገውን ክርክር ተቀላቅላ ‹‹ርቀቶች መመሪያ ናቸው፣ የአገር አቋራጭ መወዳደሪያ ቦታዎች ጥሩ ከሆኑ በሁለቱም ፆታ ተመሳሳይ ርቀት ቢሮጥ ችግር የለውም፣ የውድድሩ ተፈጥሯዊ ባህሪ ሆኖ አንዳዶች አጭር ርቀት መሮጥ ሲፈልጉ ሌሎች ረጅም መሮጥ ሊፈልጉ ይችላሉ፣ ወንድም ሴትም ተመሳሳይ ርቀት መሮጥ እንደሚችሉ ግን አምናለሁ›› በማለት ፅፋለች። የአገር አቋራጭ ውድድር አዘጋጆች ይህ ልዩነት ለምን እንደተፈጠረ አሳማኝ ምክንያት ማቅረብ ባይችሉም በተለምዶ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ በመሆኑ ብቻ አሁን ላይ እየተገበሩት እንደሚገኙ ይታመናል። ይህ ግን በአንዳንድ የስፖርት ቤተሰቦች የፆታ ልዩነት እንዳለ ለማሳየት ሆን ተብሎ የተደረገ ሳይሆን የሴቶቹን ፉክክር ረዘም ላለ ሰዓት መመልከት ስለማይፈለግ ነው የሚል ትችት ይቀርባል። የእንግሊዝ አገር አቋራጭ ውድድር ማህበርም ይህ ልዩነት በተለምዶ አሰራር የመጣ መሆኑን በማመን በአገር አቀፍ ውድድር ላይ ሴቶች ከወንዶች እኩል ርቀት መሮጥ እንዳለባቸው ሲከራከርና ተፅዕኖ ሲያሳድር ቆይቷል። በዚህም የእንግሊዝ አትሌቲክስ ማህበርን ድጋፍ ማግኘት ችሏል። የእንግሊዝ አትሌቲክስ ማህበርም ጥያቄውን ወደ ፊት በማምጣት የተለያዩ ሙግቶችን ሲያደርግ ቆይቷል። ለረጅም ጊዜ ጉዳዩ የተዘነጋና ተድበስብሶ ያለፈ ቢመስልም የእንግሊዝ አትሌቲክስ ማህበር ከቀናት በፊት ዳግም ጉዳዩን በማንሳት በጥናት ጭምር አስደግፎ እየተሟገተ ይገኛል። አትሌቲክስ ማህበሩ በፈጠረው ተፅዕኖ በአገሪቱ በሚደረጉ የአገር አቋራጭ ውድድሮች ላይ ለውጦች ማምጣት ቢችልም በዓለም አቀፍ ደረጃ የተለያዩ የውድድር አዘጋጆችን ለማሳመን ተጨማሪ ስራዎች ይቀሩታል። ለዚህም የአውሮፓ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ላይ የሰራውን ጥናት ሰሞኑን ይፋ አድርጓል። 2016 ላይ ከሃምሳ አንድ የአውሮፓ አገራት አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ሰላሳ ሰባቱ ለጥናቱ ምላሽ የሰጡ ሲሆን ከሰላሳ ሰባቱ ሃያ አንዱ ሴቶችና ወንዶች በአገር አቋራጭ ውድድሮች እኩል ርቀት መሮጥ አለባቸው የሚል እምነት እንዳላቸው ጠቁሟል። አገር አቋራጭ ውድድር እንደ ረጅም ርቀት ውድድሮች ሁሉ በስፋት የሚታወቁት ምስራቅ አፍሪካውያኑ ኢትዮጵያና ኬንያ ቢሆኑም በጉዳዩ ላይ የተነሳው ሙግት ከወደ ምዕራባውያኑ መሆኑ አስገራሚ ነው። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ ዳይሬክተር የነበሩትና አሁን የፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር የሆኑት አቶ ዱቤ ጂሎ በአንድ ወቅት ከአዲስ ዘመን ጋር በነበራቸው ቃለ ምልልስ በዚህ ጉዳይ ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያለውን አቋም አሳውቀው ነበር። አቶ ዱቤ ይህ በሴቶችና በወንዶች አገር አቋራጭ ውድድሮች ላይ ያለው የመወዳደሪያ ርቀት በተለምዶ ሲሰራበት ስለመጣ እንጂ ሴቶች ወንዶች የሚሮጡትን ርቀት መሮጥ ስለማይችሉ የተፈጠረ እንዳልሆነ ያብራራሉ። የርቀቱ ልዩነት የመጣው ቀደም ሲል በውድድሩ ደንብ ላይ የተቀመጠ በመሆኑ እንጂ ከጤናም አኳያ ይሁን ከሌሎች ነገሮች ሴቶች በአገር አቋራጭ ውድድር ከወንዶች ያነሰ ርቀት እንዲሮጡ የሚያደርጋቸው ምንም አይነት አሳማኝ ምክንያት እንደሌለ ገልፀው ነበር። «ሴቶች ከወንዶች እኩል በአገር አቋራጭ ውድድር መሮጥ አለባቸው፤ ማራቶንም ይሁን ግማሽ ማራቶን እኩል እስከ ሮጡ ድረስ በአገር አቋራጭም እኩል ርቀት መሮጥ አለባቸው፤ ይህ ካልሆነ ማራቶንም እኩል ኪሎ ሜትር መሮጥ የለባቸውም» በማለትም አቶ ዱቤ ሃሳባቸውን ሰንዝረው ነበር። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በየዓመቱ ጃን ሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ውድድሮችን በክልሎችና በክለቦች መካከል እንደሚያካሂድ ይታወቃል። በነዚህ ውድድሮች ወንዶቹም ሴቶቹም እኩል ርቀት የሚሸፍን ውድድር እንዲያካሂዱ ማድረግ ይቻላል ያሉት አቶ ዱቤ፣ ይህን ጥያቄ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለዓለምአቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ሊያቀርብ እንደሚችልም ጠቁመዋል። ከዚያም ዓለምአቀፍ ማህበሩ አሁን ያለውን ህግ አሻሽሎ በተመሳሳይ ርቀት እንዲወዳደሩ ከፈቀደ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንም በእኩል ርቀት ውድድሮቹን ለማካሄድ የሚያግደው ነገር እንደሌለ አብራርተዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 17/2013 ዓ.ም | https://www.press.et/Ama/?p=38194 | 1,192 | 2ስፖርት
|
የዓለም አትሌቲክስ በዶፒንግ ጉዳይ ጥርስ አውጥቷል | ስፖርት | December 28, 2020 | 10 | ቦጋለ አበበ ኢትዮጵያ አበረታች ንጥረ ነገሮችን በመጠቀም በስፖርቱ ዓለም በተለይም በአትሌቲክስ ትልቅ ስጋት ካንዣበበባቸው የዓለማችን አምስት አገራት አንዷ እንደሆነች ጉዳዩ የሚመለከታቸው ዓለም አቀፍ ተቋማት ሲያሳስቡ ቆይተዋል። በተቃራኒው ኢትዮጵያ ይህን ስጋት ለመቀነስ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በብሔራዊ ደረጃ የፀረ አበረታች ንጥረ ነገሮች ፅሕፈት ቤት አቋቁማ አበረታች ለውጥ ማምጣቷንም የዓለም አቀፉ ፀረ አበረታች ንጥረ ነገሮች ኤጀንሲ መስክሮላታል። ይሁን እንጂ ስጋት አለባቸው ከተባሉት አምስት አገራት ተርታ ለመውጣት ብዙ ስራ እንደሚጠብቃት ይታወቃል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፀረ አበረታች ንጥረ ነገሮች ጽሕፈት ቤት አትሌቶች አውቀውም ይሁን ሳያውቁ የችግሩ ሰለባ እንዳይሆኑ የተለያዩ ግንዛቤዎችን ከማስጨበጥ ባሻገር የችግሩ ሰለባ ሆነው የተገኙ በርካታ አትሌቶች ላይ የቅጣት ውሳኔዎችን ሲያስተላልፍ ቆይቷል። ባለፈው ሳምንት አጋማሽ እንኳን አትሌት ወንድወሰን ከተማ ማሞና አትሌት እዮብ ኃብተስላሴ ጎሳ የስፖርት አበረታች ቅመሞች (ዶፒንግ) የሕግ ጥሰቶችን በመፈፀም ተጠርጥረው ላለፉት ጊዜያት ጊዜያዊ እገዳ ላይ ሆነው ጉዳያቸውን ሲያጣራ መቆየቱን ገልጿል። በዚህም መሰረት በተካሄደው ተጨማሪ ምርመራ አትሌት እዮብ ኃብተስላሴ ጎሳ እ.ኤ.አ የካቲት 02/2020 ዓ.ም ታይላንድ በተካሄደ ውድድር ላይ
(Cathinone) የተባለውን የተከለከለ የስፖርት አበረታች ቅመም መጠቀሙ ተረጋግጧል። በዚህም አትሌቱ እ.ኤ.አ ከሚያዝያ 03/2020 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ አራት ዓመታት በማንኛውም ውድድር ላይ እንዳይሳተፍ ቅጣት ተጥሎበታል። በውድድሩ የተገኘው ውጤትና ውጤቱን ተከትሎ የሚሰጥ የእውቅና ሽልማትም እንዲሰረዝ ተወስኗል። በተመሳሳይ መልኩ አትሌት ወንድወሰን ከተማ ማሞ ቀደም ሲል
(Cathinone) የተባለውን የተከለከለ የስፖርት አበረታች ቅመም መጠቀሙ በመረጋገጡ እ.ኤ.አ እስከ የካቲት 01/2024 ድረስ በማንኛውም ውድድር ላይ እንዳይሳተፍ እገዳ የተጣለበት መሆኑ ይታወቃል። ይሁን እንጅ አትሌቱ የተሳሳቱ የሰነድ ማስረጃዎችን በማቅረብ የህግ ጥሰት የማጣራት ሂደቱን በተለያየ መልኩ በማስተጓጎልና በድጋሚ ለማጭበርበር በመሞከር ተደራራቢ የህግ ጥሰት በመፈፀም ተጠርጥሮ ጉዳዩ ሲጣራ ቆይቷል። በመሆኑም አትሌት ወንድወሰን ያቀረባቸው ሰነዶች የሐሰት መሆናቸው በመረጋገጡና በፀረ- ዶፒንግ ህጉ አንቀፅ 2ነጥብ5 ላይ የተደነገገውን የፀረ-ዶፒንግ እንቅስቃሴውን የማስተጓጎልና አቅጣጫ የማሳት የህግ ጥሰት መፈፀሙ በመረጋገጡ ቀደም ሲል ከተጣለበት የአራት ዓመት የእገዳ ቅጣት በተጨማሪ የመጀመሪያው ቅጣት ከሚያበቃበት የካቲት 01/2024 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ስምንት ዓመታት እስከ የካቲት
01/2032 ዓ.ም በማንኛውም ስፖርታዊ ውድድር ላይ
እንዳይሳተፍ የእገዳ ቅጣት
ተላልፎበታል።የኢትዮጵያ
ብሔራዊ የፀረ-አበረታች
ቅመሞች ጽሕፈት ቤት
በቀጣይም የምርመራና ቁጥጥር
ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል
አስታውቋል። የዓለም
አትሌቲክስም ከዶፒንግ ጋር
በተያያዘ በስፖርቱ ትልቅ
ክብርና ዝና ያተረፉ
አትሌቶች ላይ ሳይቀር
ጥርስ እንዳወጣ የሚጠቁም
አቋም በሳምንቱ መጨረሻ
ይፋ አድርጓል። ኢትዮጵያን
ጨምሮ የዓለምን አትሌቲክስ
በበላይነት የሚመራው ተቋምና
ሌሎች አገራት ባለፉት
ዓመታት ከዶፒንግ ጋር
በተያያዘ በስፖርቱ ትልቅ
ክብርና ዝና ካላቸው
አትሌቶች ይልቅ እምብዛም
በማይታወቁና በአንፃራዊነት በትንንሽ
ውድድሮች በሚካፈሉ አትሌቶች
ላይ ትኩረት እንዳደረጉ
ወቀሳ ሲቀርብባቸው መቆየቱ
ይታወቃል።ማህበሩ
በተለይም የዓለም አትሌቲክስ
የስፖርቱ ስም እንዳይጠለሽና
የተለያዩ አጋሮቹን ላለማጣት
ሲል በስፖርቱ ትልቅ
ስምና ዝና ላላቸው
አትሌቶች ሽፋን እንደሚሰጥ
ምክንያታዊ ሙግቶችን የሚያቀርቡ
በርካታ ናቸው። ለዚህም
በስፖርቱ ትልቅ ስም
ያላቸው የኦሊምፒክና የዓለም
ሻምፒዮን የሆኑ በርካታ
የዓለማችን አትሌቶች እምብዛም
የችግሩ ሰለባ ሆነው
ቅጣት ሲተላለፍባቸው እንደማይስተዋል
ያስቀምጣሉ። የዓለም
አትሌቲክስ ፕሬዚዳንት ሴባስቲያን
ኮ ሰሞኑን በዶፒንግ
ጉዳይ አትሌቶች ትልቅ
ስምና ዝናቸው ከጥፋተኝነት
እንደማያስጥላቸው አስገንዝበዋል። ለዚህም
ባለፉት ዓመታት አሜሪካዊው
የመቶ ሜትር የዓለም
ሻምፒዮን ክርስቲያን ኮሊማንን
ጨምሮ በስፖርቱ ትልቅ
ዝናና ስኬት ያላቸው
አትሌቶች እንደተቀጡ አስታውሰዋል።
እንደ
ኮ ገለፃ፣ በአበረታች
ንጥረ ነገሮች ላይ
የሚደረገው ምርመራ እየተሻሻለ
በሄደ ቁጥር ዶፒንግ
ተጠቅመው ለሚወዳደሩ አትሌቶች
ነገሮች ከባድ እየሆኑ
ቢሄዱም የችግሩ ሰለባ
ላለመሆን እንዲጠነቀቁ ያደርጋቸዋል።
በተለይም በመጪው የቶኪዮ
2020 ኦሊምፒክ ቁጥጥሩ ከምን
ጊዜውም በላይ የጠበቀ
እንደሚሆን ጠቁመዋል። የኮሊማ
ቅጣት አትሌቶች የቱንም
ያህል በስፖርቱ ስምና
ዝና ቢገነቡ አበረታች
ንጥረ ነገር ተጠቅመው
ከተገኙ ከቅጣት እንደማያመልጡ
ማሳያና የዓለም አትሌቲክስ
የሚፈራው ነገር እንደሌለ
ማረጋገጫ መሆኑንም የእንግሊዝ
የቀድሞ የአንድ ሺ
አምስት መቶ ሜትር
የሁለት ኦሊምፒኮች አሸናፊው
ኮ ለአገራቸው መገናኛ
ብዙሃን ገልፀዋል። የዓለም አትሌቲክስ እንደ አበረታች ንጥረ ነገሮች ያሉ ጉዳዮችን የሚያጣራ ገለልተኛ ቡድን አቋቁሞ ባለፉት ዓመታት ተጨባጭ ለውጥ እያስመዘገበ እንደሚገኝ የገለፁት ኮ፣ ዓለም አቀፍ ተቋሙ በራስ መተማመኑን በመገንባት ካለአንዳች ፍርሃት አበረታች ንጥረ ነገር የተጠቀሙ የትኞቹንም የዓለማችን አትሌቶች ለማጋለጥ ከልቡ እየሰራ መሆኑን አክለዋል። | https://www.press.et/Ama/?p=38366 | 547 | 2ስፖርት
|
በቻን ውድድር ስቴዲየሞች በከፊል ለተመልካች ክፍት ይሆናሉ | ስፖርት | December 29, 2020 | 10 | ቦጋለ አበበ በአገር ውስጥ ሊጎች ብቻ የሚሳተፉ ተጫዋቾች የሚሳተፉበት የአፍሪካ ሁለተኛው ትልቁ የእግር ኳስ ውድድር(ቻን) ላይ ደጋፊዎች ስቴድየም ገብተው ጨዋታዎችን እንደሚመለከቱ ተገለፀ። ከመጪው ጥር አጋማሽ ጀምሮ በካሜሩን በሚካሄደው ውድድር የኮቪድ- 19
ወረርሽኝ ቅድመ ጥንቃቄ እርምጃዎችን ተግባራዊ በማድረግ ተመልካቾች ስቴድየም እንዲገቡ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን(ካፍ) ማሳወቁን ኢንሳይድ ዘ ጌምስ ዘግቧል። ባለፈው ሚያዝያ ወር ሊካሄድ የነበረው የቻን ውድድር በኮቪድ- 19 ስጋት ወደ ዘንድሮው ዓመት መራዘሙ ይታወሳል። የውድድሩን ዝግጅት ለመገምገም ወደ ካሜሩን አማዶ አሂጆ ስቴድየም ያቀኑት የካፍ የግምገማ ቡድን አባላት ለአገሪቱ ስፖርት ሚኒስትር ናርሲስ ሞውሌ ኮምቢ እንደገለፁት ከወር በኋላ በሚካሄደው የቻን ውድድር ወረርሽኙ የሚፈልገውን ጥንቃቄ በማድረግ ተመልካች ስቴድየም እንዲገባ ካፍ ውሳኔ ላይ ደርሷል። እንደ ስፖርት ሚኒስትሩ ገለፃ፣ በውድድሮች ወቅት ጨዋታዎችን የሚያስተናግዱ ስቴድየሞች ከመያዝ አቅማቸው ሃያ አምስት በመቶውን ብቻ ተመልካች እንዲያስተናግዱ ይደረጋል። ካሜሩን በውድድሩ ወቅት በፊፋና በጤና ባለስልጣናት የተቀመጡ መስፈርቶችን ተግባራዊ በማድረግ ተመልካች ስቴድየም እንዲገባ ባደረገችው ጥረት ከካፍ ፍቃድ ማግኘቱንም ጠቁመዋል። ውድድሩ በሚካሄድባቸው የተለያዩ ስቴድየሞች በምድብ ጨዋታዎች ወቅት ስቴድየሞች ተመልካች ከመያዝ አቅማቸው ሃያ አምስት በመቶውን ብቻ እንደሚጠቀሙ የገለፁት ሚኒስትሩ፣ ከምድብ ጨዋታዎች በኋላ በጥሎ ማለፍ ውድድሮች ስቴድየሞች ተመልካች የመያዝ አቅማቸው ወደ ሃምሳ በመቶ ከፍ ሊል እንደሚችል አስረድተዋል። በዱዋላ ከተማ የሚገኘው ስቴድየም በተጎበኘበት የካሜሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆሴፍ ኢኦን ንጉቴ ‹‹ውድድሩ ካለፈው ዓመት ተራዝሞ ዘንድሮ በሚካሄድበት ወቅት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጉዳይ በአፍሪካ እንደሚሻሻል እርግጠኛ ነኝ›› በማለት መናገራቸው ይታወቃል። የቅርብ ቀናት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በካሜሩን ከሃያ ስድስት ሺ በላይ ሰዎች በኮቪድ-19 የተያዙ ሲሆን አራት መቶ ሃምሳ ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል። የካሜሩን ከተሞች መዲናዋ ያውንዴን ጨምሮ ዱአላና ሊምቤ ውድድሩን የሚያስተናግዱ ይሆናል። በዋናው የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ በሌሎች አገራት ትልልቅ ሊጎች በሚጫወቱ ተጫዋቾች ተሸፍነው የመታየት እድል ያላገኙ በአገር ውስጥ ሊጎች ብቻ የሚጫወቱ ተጫዋቾች እንዲሳተፉ ለማድረግ ካፍ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ተግባራዊ ያደረገው የቻን ውድድር በኮቪድ-19 ምክንያት ካለፈው ዓመት ወደ ዘንድሮው ዓመት ከተሸጋገሩት አንዱ ነው። ካሜሩን በመጪው ሰኔ አጋማሽ ዋናውን የ2021 አፍሪካ ዋንጫ ጨዋታን የምታስተናግድ አገር መሆኗም ይታወቃል። የ2019 አፍሪካ ዋንጫን ለማዘጋጀት 2014 ላይ እድሉ የተሰጣት ምዕራብ አፍሪካዊት አገር ካሜሩን 2018 ላይ ውድድሩን ለማዘጋጀት የምትገነባቸው ስቴድየሞች በመጓተታቸውና በወቅቱ በአገሪቱ የነበረው የፖለቲካ አለመረጋጋት ከደህንነነት አኳያ ስጋት ስለፈጠረ የአዘጋጅነት እድሉ ለግብፅ ተሰጥቷል። ካሜሩንም በምትኩ የ2021 አፍሪካ ዋንጫን እንድታዘጋጅና ኮትዲቯር የ2023 አፍሪካ ዋንጫን እንድታሰናዳ ሽግሽግ መደረጉ ይታወቃል።አዲስ ዘመን ታኅሣሥ 20/2013 | https://www.press.et/Ama/?p=38441 | 331 | 2ስፖርት
|
ከተራ – የጎንደር ልዩ ውበት | ሀገር አቀፍ ዜና | January 19, 2021 | 7 | ክፍለዮሐንስ አንበርብርጎንደር አሸብርቃለች:: ተፈጥሮም
ሰውም አጅቧታል:: ከተራ ለጎንደር፤ ጎንደርም
ለከተራ ውበት ናቸው::
ቆነጃጅት ሽሩባቸውን በባህላዊ
አሠራር አስውበው፣ በሐበሻ አለባበስ አምረውና
ደምቀው ወደ ማደሪያው
የሚሸኙትን ታቦታት ይከተላሉ::
ወጣት ወንዶች በሀገርኛ
አለባበስ አምረውና ደምቀው፣
ሽመል ይዘው በሆታ እያደመቁ፤ በእግራቸው
መሬት ረግጠው እየነቀነቁ አቧራው ወደ ላይ ቡን! ቡን! ብሎ በሰዎች መሐል ወደ ላይ ቦለል ሲል እንደ ሰኔ ደመና እየተቆራረጥ
ወደ ላይ ሲወጣ አንዳች የተለየ ውበት አለው::ጎንደር ከተማን በዙሪያ የከበበው ተራራ ታቦታቱን ያጅብ ይመስል ደረቱን ነፍቶ የቁልቁሊት እየተመለከተ የተለየ ውበት አላብሷል ለአካባቢው::የጎንደር ታቦታት በሰዎች ብቻ ሳይሆን ተራራ የሚታዘዝላቸው፤ ተራራ የሚከተላቸው ይመስላል::አንዳንዶቹ ደግሞ ፈረስ ላይ ሆነው ጎፈሬ አበጥረው እና በጃኖ ተሞሽረው እየተገማሸሩ፤ ጎንደር እሽሩሩ በሚለው ሙዚቃ ታጅበው ከፈረሶቹ ወገብ ላይ ሆነው እዩኝ እዩን በሚል ሁኔታ በታቦታቱ በቅርብ እርቀት ይጓዛሉ::የሰንበት ተማሪዎች በመለከት፣ በገና እና ከበሮ በታጀበ ህብረ ዝማሬ እያሰሙ ከታቦታቱ ኋላ ኋላ እየተከተሉ ወደ ማደሪያው ሥፍራ ሲሸኙ የጎንደር ከተራ በዓልን ውበት በእጁጉ ያጎላዋል::ካሜራቸውን ደቅነው ወዲህ ወዲያ ዝርው ዝርው የሚሉት ቱሪስቶች የታሪክ አካል ለመሆን የሚያደርጉት ሽሚያ በራሱ ዕይታን ይስባል::ቀሳውስቱ ግራ ቀኝ እያዘመሙ፣ ጽናጽል እየጸነጸሉ ታቦታቱን አጅበው ወደማደሪያው ሥፍራ ሲሸኙ ውበቱን በቃላት ለመግለፅ መሞከር አዳጋች ያደርገዋል::በአራቱም ነፋሳት የሚታጠነው ዕጣን አካባቢውን እንደ ናርዶስ ሽታ እያወደው ጥሩ መዓዛ አላብሶታል::ከተራ በጎንደር አንዳች የማይገለፅ መግነጢሳዊ ኃይል አለው::የአማራ ልዩ ኃይል በየአቅጣጫው ሆነው ከበጎ ፈቃድ ወጣቶች ጋር በመቀናጀት የአካባቢውንና የከተማዋ ሠላምና ፀጥታ ለማስከበር የሚያደርጉት መውተርተር ምንኛ የሀገር ፍቅርና የበዓል ክብር እንዳላቸው ያሳብቃል::እንደ ንሥር አሞራ ዓይናቸውን በርቀት በቅርበት እየላኩ አካባቢውን ይቃኛሉ::የከተራ ውበት በጎንደር፤ የጎንደር ከተማም ውበትም በከተራ ይገለፁ ዘንድ ተዋህደው የተሠሩ ይመስል አንዳቸው ካለአንዳኛው ምሉዕ አይመስሉም::ከተማዋ በዓል በዓል በሚሸቱ ሙዚቃ እና ዝማሬ ተንጣለች::በየህንፃዎቹ አናት ላይ የተሰቀሉት ሰንደቅ ዓላማዎች የከተማውን ድባብ በጠላት ጦር ላይ ድል በተቀዳጀ ማግስት የተገኘ ልዩ ድል አስመስለውታል::ጎንደር በሽለላ እና ቀረርቶም ለምን ይቅርብኝ ያለች ይመስላል::በርካታ ወጣቶች በአፄ ቴዎድሮስ አደባባይ እያቅራሩና እየፎከሩ በሐውልቱ ዙሪያ እየተሽከረከሩ ኢትዮጵያዊ ወኔ የሚቀሰቅሱና ለበዓሉ ድምቀት የሆኑ አያሌ ትዕይንተ ህዝብ ያሳያሉ::ሁሉንም እንቅስቃሴ በአንክሮ ለተመለከተው አንዳች ንዝረታዊ ኃይል አለው::በቃ ጎንደር ድምቅ! ብላለች::ወጣት ይድነቃቸው ታደሰ ከተራ ለእኔ ልዩ ስሜት ይሰጠኛል:: በዓሉ ነብስና ሥጋዬ ተዋህደው ደስታዬ እጥፍ ድርብ የሚሆንበት ነው::በተለይም ደግሞ በጎ አድራጎትን በመከወን ስለማሳልፍ ነብሴ በሐሴት ትረሰርሳለች ይላል::እርሱ ከከተራ እና ጥምቀት መቅረት አይሆንለትም::ጎንደር አፍ አውጥታ ትጠይቀው፤ በአሽሙር ወጋ ታደርገው ይመስል በዓሉን ሌላ ሥፍራ ማሳለፍ አይፈልግም::ወጣት ተረፈ መልካሙ ባለፈው ዓመት የምዕምናን መቀመጫ ደረጃ ተደርምሶ ጉዳት በማድረሱ በከተራውም ሆነ በጥምቀት በዓል ላይ ጥቁር ጥላ አጥልቶ ያላፈ በመሆኑ፤ መሰል ችግሮች እንዳይደገሙ ከከተማው ወጣቶች ጋር በመቀናጀት በጎ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል::በበዓሉ ወቅት ባህረ ጥምቀት ሄዶ መጠመቅና ከተራ በዓል ላይ መታደም ለእርሱ የፍሰሐ ጥግ ነው:: ከተራና ጥምቀትን በጎንደር ማሳለፍና መታደም የሁልጊዜ ዕቅዱ ነው::ከተራ ብሎም ጥምቀት በዓል የነፍስ የሥጋም በዓል እንደሆነ የሚናገሩት የማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሊቀህሩያን አባ ዮሴፍ ደስታ ናቸው:: በዚህ በዓል በርካታ የአገር ውስጥና የአገር ውጭ ታዳሚዎች ወደ ጎንደር የሚመጡ ሲሆን ይህም ለጎንደርና ለአካባቢው ነዋሪዎች ፀጋ ይዞ የሚመጣ እንደሆነ ያብራራሉ::ማህበራዊ እሴቶችን በማጠናከር፣ መንፈሳዊ ሕይወትን በማደስና ነብስን በማረስረስ የሚሰጠው ስሜት ልዩ ስለመሆኑም ያስገነዝባሉ::ሊቀህሩያን አባ ዮሴፍ ደስታ እንደሚሉት፤ የጎንደር ከተራ እና ጥምቀት በዓል ሁሌም አዲስ ሰርክ ልዩ እየሆኑ ዘመናትን አስቆጥረዋል::በቀጣይም የበዓሉ ድምቀት በዚሁ ድባብ እንደሚቀጥል ተስፋ አላቸው::ለዚህም የወጣቶች፣ የምዕምናን ትግስትና ፅናት፣ የሀገር ታሪክ ወዳድነት፣ ለቤተክርስቲያንና የባህል እሴቶች ያላቸው ክብር ህያው ምስክር ስለመሆናቸውም ይገልፃሉ::በዚህ ዓመት የሚከበረው የከተራ እና ጥምቀት በዓል ከመቼውም በላይ ደስታየው የተለየ ስለመሆኑም ይናገራሉ::አገሪቱ ሠላም ሰፍኖባት የኤርትራ ወንድምና እህቶች በበዓሉ ታዳሚ የሚሆኑበት መሆኑም ታላቅ ፍስሐ እንደሆነም ይጠቁማሉ::የከተራ በዓል ሠላማዊና ፍሰሐ እንዲሆንም የመንግሥት አካላት ከአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ከሃይማኖት አባቶች፣ ከወጣቶችና ከሌሎች የሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመናበብ ስለሚሠሩ ሁሉም ነገሩ ሸጋ ነው ይላሉ:: ከተራ እና ጥምቀት በጎንደር ልዩ ስሜትና እንደሚሰጥ በመጠቆም፤ የተቻላቸው ኢትዮጵውያን እንዲታደሙት ይመክራሉ::አዲስ ዘመን ጥር 11 ቀን 2013 ዓ.ም | https://www.press.et/Ama/?p=39749 | 541 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
” የሱዳን ሃይል በተጠናከረ ሁኔታ ወደ ውስጥ እየተስፋፋ መሄዱ የግድቡን ግንባታ ለማስተጓጎል ነው‘ – ብርጋዴል ጀነራል ዋሲሁን ንጋቱ | ሀገር አቀፍ ዜና | January 17, 2021 | 48 | ዘላለም ግዛው አዲስ አበባ:- የሱዳን ሃይል በተጠናከረ ሁኔታ ወደ ውስጥ እየተስፋፋ መሄዱ የግድቡን ግንባታ ለማስተጓጎል የተደረገ መሆኑን ብርጋዴል ጀነራል ዋሲሁን ንጋቱ አስታወቁ። ትዕግስቱ ከበቂ በላይ በመሆኑ የሃይል አጸፋ እንደሚያስፈልግ አመለከቱ። የቀድሞ መከላከያ ሰራዊት ባልደረባ ብርጋዴል ጀነራል ዋሲሁን በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቁት ፤ የሱዳን አሁናዊ የመሬት ወረራ ዋናው ግብ በማጠናቀቂያ ምዕራፍ ላይ የሚገኘውን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ለማስቆም፣ ወደ ሃይል ማመንጨት ሂደቱ ከመሸጋገሩ አስቀድሞ ለማስተጓጎል የተወጠነ ሴራ መሆኑን ነው። ኢትዮጵያ የግድቡን ግንባታ
ለማጠናቀቅ ተርባይኖቹንም
ተክሎ
ሃይል እንዲያመነጩ ስራ
ለማስጀመር እያደረገች ያለው
ሂደት በምንም ሁኔታ
የማይቆም ነው ያሉት
ብርጋዴል ጀነራሉ፤ ከሱዳን
ድርጊት ጀርባ የግብጽ
እና የሱዳን ተባባሪ
የሆኑ አንዳንድ የአረብ
አገራት እጅ ሊኖርበት
እንደሚችል ጥርጣሬያቸውን ገልጸዋል።
በመንግስት በኩል እየታየ
ያለው ትእግስት ከበቂ
በላይ መሆኑን አመልክተዋል።
ሱዳን በኃይለስላሴ አገዛዝና በደርግ ሥርዓትም የመስፋፋት አዝማሚያ ታሳይ እንደነበር ያስታወሱት ብርጋዴል ጀነራል፣ በአሁኑ ወቅት ድንበር ጥሶ የገባውን ሃይሏን በሰላም የሚወጣ ከሆነ መልካም፣ ካልሆነ ግን የሃይል አማራጭን መጠቀም እንደሚያስፈልግ አስታውቀዋል። ለሰላም አማራጩ ተገዢ ካልሆኑ ወታደራዊ አቅምን በመጠቀም ማባረር እንደሚገባም ጠቁመዋል። እንደርሳቸው ማብራሪያ፤ ኢትዮጵያ መሬቷ ተወርሮ አሁንም ችግሩን በዲፕሎማሲ ለመፍታት እያደረገች ያለው ጥረት የሚደነቅ ነው። ለጎረቤት አገራት ያላትን ፍቅር፣ የሰላም ፍላጎቷንና ለቀጠናው ሰላም መጠበቅ ያላትን ቁርጠኝነት ያሳያል። ትዕግስቱ፣ ስምምነት ላይ ለመድረስ መሞከሩና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ድርጊቱን ለማስቆም እና ለማስመለስ መንቀሳቀሱ ተገቢ ነው። መንግስት በከፍተኛ ጥንቃቄ ጉዳዩን ለመያዝ ያለውን ፍላጎት የሚያመለክት እንደሆነም አመልክተዋል። የሱዳን ሉአላዊ ምክር ቤት ሰብሳቢ ሌተናል ጀነራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን እና የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ጉብኝት እና ውይይት ማድረጋቸውን፤ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶክተር) እንዲሁም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ወደ ሱዳን ተጉዘው ተመሳሳይ ጥረት እያደረጉ ባለበት ሁኔታ ፣ ወረራ ማካሄድ ተገቢ አይደለም ብለዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ትዕግስት ማድረጉ ከዚህ በላይ አያስኬድም ትዕግስትም ወሰን አለው ያሉት ብርጋዴል ጀነራል ዋሲሁን ፣ፍቅርና የሰላም ፍላጎት ያልገዛውን ሃይል እንደሚገዛ አስታውቀዋል። | https://www.press.et/Ama/?p=39619 | 274 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የአትሌቶችን ጥያቄ የሚመልስ ማዘውተሪያ | ስፖርት | December 13, 2020 | 12 | ብርሃን ፈይሳበኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በኦሮሚያ ክልል ለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ የተገነባው የአትሌቲክስ ማዘውተሪያ የአሸዋ ትራክ ተመረቀ። በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎችም ተመሳሳይ ማዘውተሪያዎች እንደሚገነቡ ታውቋል።በኦሮሚያ ክልል ለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ የተገነባው የአትሌቲክስ ማዘውተሪያ ስፍራ ትናንት ተመርቆ ለአገልግሎት በቅቷል። ግንባታው ለረጅም ርቀትና አጭር ርቀት አትሌቲክስ ስፖርት መለማመጃ የሚውለው የአሸዋ ትራክ እንዲሁም የአትሌቶች ልብስ መቀየሪያ፣ የማረፊያና የንጽህና መጠበቂያ ስፍራን ያጠቃልላል። ከለገዳዲ ለገጣፎ ባሻገር በክልሉ ባሉ የተለያዩ ከተሞችም ተመሳሳይ ማዘውተሪያዎች የሚገነቡ መሆኑም ተጠቁሟል። በምረቃ ስነስርአቱ ላይ የፌዴሬሽኑ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ ከአትሌቶች ወቅታዊና አንገብጋቢ ጥያቄዎች አንጻር ለአትሌቲክስ ስፖርት ምቹ ከሆኑት አካባቢዎች መካከል አንዱን በመምረጥ ለምረቃ የበቃውን የለገጣፎ ለገዳዲ የአሸዋ ትራክ ለማስገንባት እንደተቻለ ገልጻለች። ፌዴሬሽኑ ለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር ጋር በተደረሰው ስምምነት መሰረት የዲዛይን ስራ በማሰራትና ለግንባታውም ፌዴሬሽኑ 18 ሚሊየን ብር ወጪ በማድረግ ግንባታው ተካሂዶ ለምረቃ በቅቷል። ትራኩ 1ነጥብ 6 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን፤ ወደ 2ኪሎ ሜትር እንዲያድግ ለቀረበው ጥያቄም የክልሉ መንግስት ፈቃደኝነቱን በመስጠቱ ምክትል ፕሬዚዳንቷ ምስጋና አቅርባለች። ግንባታው ፌዴሬሽኑን ብቻም ሳይሆን ከተማ አስተዳደሩን፣ ክልሉንና ኢትዮጵያንም ጭምር በማበልጸግና የስፖርት ቱሪዝምን በመሳብ ከሃገር ገጽታ በተጨማሪ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታም እንደሚኖረው ጠቅሳ፣ ከፌዴራል መንግስት ጀምሮ ሁሉም አካላት የማዘውተሪያ ስፍራ ችግርን ለመቅረፍ በትኩረትና በርብርብ የሃገር በጎ ገጽታ መገንባት እንደሚኖርባቸው አስገንዝባለች። ማዘውተሪያውን የመረቁት የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ ፌዴሬሽኑ ማዘውተሪያውን በመገንባት በጎ ተግባር መስራቱን አስታውቀዋል። በፌዴሬሽኑ የቀረበውን 1ነጥብ6 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ትራክ ወደ 2 ኪሎ ሜትር ለማሳደግ የክልሉ መንግስት እንደሚሰራም አረጋግጠዋል። ከለገዳዲ ለገጣፎ ባሻገር በሱሉልታ፣ በቡራዩ፣ ሰበታ እና ገላን ቦታዎችን በአጭር ጊዜ በማዘጋጀት፤ የማዘውተሪያ ስፍራዎች በፌዴሬሽኑ እና በክልሉ መንግስት ድጋፍ እንደሚገነቡም ጠቁመዋል። ይህም አትሌቶችን ከመኪና አደጋ እና ከመሳሰሉት ጉዳቶች ተጠብቀው ልምምዳቸውን እንዲያደርጉ እና ለሃገራቸው ክብር እንዲቆሙ እንደሚያስችሉ አስታውቀዋል።ለእዚህም የክልሉ መንግስት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል። የለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ ሃቢባ ሲራጅ፤ በርካታ አትሌቶች ከከተማው የአትሌቲክስ ክለብ በመውጣት በዓለም አቀፍ ደረጃ ውጤት ማስመዝገባቸውን እንዲሁም ለቶኪዮ ኦሊምፒክ ስድስት አትሌቶችንና ሁለት አሰልጣኞች ለብሄራዊ ቡድን መመረጣቸውን ጠቅሰዋል። ይህ ውጤት ሊገኝ የቻለውም በመንግስት በተደረገለት ድጋፍ መሆኑን ተናግረው፤ ፖሊሲው ስፖርት በህዝባዊ አካል እየተመራ በመንግስት እንዲታገዝ ቢሆንም፤ በርካታ የማዘውተሪያ ስፍራዎች የተገነቡት በመንግስት ነው ብለዋል። በዚህም አትሌቶች የመለማመጃ ስፍራ አንድ ለእናቱ ከነበረው የአዲስ አበባ ስታዲየም ወደ አጎራባች ከተሞች በመውሰድ አትሌቶች አማራጭ መሮጫዎችን እንዲያገኙ ተደርጓል ያሉት ከንቲባዋ፤ እንደ ከተማም በስፖርቱ ምክንያት ወደ ማዘውተሪያው የሚጓዙ የሃገር ውስጥና የውጪ ሃገራት አትሌቶች ሰላማቸው ተጠብቆ ማዘውተሪያው ለታለመለት ዓላማ እንዲውል እንደሚሰራ አረጋግጠዋል። መዋዕለ ነዋያቸውን በስፖርት ላይ ለማፍሰስ ለሚፈልጉ ባለሃብቶችም ከምንጊዜውም በላይ ድጋፍ እንደሚሰጥም ገልጸዋል። በእለቱ ከተካሄደው ምረቃ
ስነስርአት ጎን ለጎን
ፌዴሬሽኑ ለሚያስገነባው ባለ
12 ወለል ህንጻም የመሰረተ
ድንጋይ በእለቱ ተቀምጧል።
ይህም ጂምናዚየም፣ የህክምና
እና የማገገሚያ ማዕከል፣
ከአትሌቲክስ ጋር የተያያዙ
አገልግሎቶችን የሚሰጥ እንዲሁም
ገቢ የሚያስገኝ እንደሚሆንም
ታውቋል።አዲስ ዘመን
ታህሳስ 4/2013 | https://www.press.et/Ama/?p=37292 | 397 | 2ስፖርት
|
ከቅጣት ያመለጠው ታሪካዊ ጥፋት | ስፖርት | December 13, 2020 | 13 | ቦጋለ አበበእግር ኳስን በመሳሰሉ ተወዳጅና ንክኪ በሚበዛባቸው ስፖርቶች ተጫዋቾች በእንቅስቃሴ ውስጥ እያሉ አውቀውም ይሁን ሳያውቁ በተቃራኒ ቡድን ተጫዋቾች ላይ ጥፋት(ፋውል) ይሰራሉ። እነዚህ ጥፋቶች ከቀላል እስከ ከባድ የአካል ጉዳት ሊያስከትሉ የሚችሉና ያስከተሉበት አጋጣሚም በርካታ እንደነበር መመልከት ይቻላል። በስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ወቅት ስፖርተኞች መሰል ጥፋት ሲሰሩ ውድድሩን በሚመሩ ዳኞች ከቢጫ የማስጠንቀቂያ ካርድ አስከ በርካታ ጨዋታዎች መታገድ ሊያደርሱ የሚችሉ ቅጣቶች ይከተሏቸዋል። ዳኞች አውቀውም ይሁን ሳያውቁ ከትንሽ እስከ ትልቅ ጥፋቶች በዝምታ ሲያልፉ የሚታይበት አጋጣሚም ጥቂት አይደለም። በዛሬው የስፖርት ማህደር አምዳችንም እኤአ በ1982 የዓለም ዋንጫ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ወቅት የተከሰተውን ከባድና ታሪካዊ ጥፋት ከቅጣት የዳነበትን አጋጣሚ እንደሚከተለው እንዳስሳለን።ታሪካዊው ፈረንሳዊ ተጫዋች ሚሼል ፕላቲኒ ያሻገራት ኳስ ፓትሪክ ባቲስቶን ከጀርመኑ ግብ ጠባቂ ጋር አገናኘችው። በአጠገቡ ተከላካዮች የሉም፣ ከጨዋታ ውጭ አይደለም። የተከላካይን መስመር ሰንጥቆ ያለፈ ለጎል የተመቻቸ ያለቀለት ዕድል ነበር። ሄራርድ ሹማኸር ኳሷን ማዳን አለበት። አለበለዚያ ጀርመን ለዓለም ዋንጫው ፍፃሜ ላትደርስ ትችላለች። ከባቲስቶ ጋር ፊት ለፊት ተጋፈጠ። በረኛው እየተንደረደረ ኳሷን ተከትሎ ወደ ፈረንሳዊው መጣ። ሁለቱም ወደ አንድ አቅጣጫ ፈጠኑ። ሁለቱም የሀገሮቻቸው ጀግና ለመሆን በየፊናቸው እየሮጡ ነው…።የ1982ቱ የዓለም ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ነበር፣ ፈረንሳይ ከምዕራብ ጀርመን። ውጤቱ 1-1 እያለ ባቲስቶ ተቀይሮ ገባ። ከመግባቱ በፊት በተጠባባቂዎች ወንበር ላይ የምዕራብ ጀርመኑ በረኛ ባህሪይ አልተመቸውም ነበር። ከፈረንሳይ ተጫዋቾች ጋር ሲናቆር ታዝቦታል። የበዛ ግልፍተኛነት ይታይበታል። ከደቂቃዎች በኋላ አሰልጣኙ ወደ ጨዋታው አስገቡት። ከሰባት ደቂቃ በኋላም ከሹማኸር ጋር ተፋጠጠ። ፈረንሳዊያን ጎል ሲጠብቁ ሹማኸር ባለ በሌለ ጉልበቱ እንደ ፊጋ በሬ ተንደርድሮ በትከሻውና ዳሌው ተላተመው። ባቲስቶ ከሹማኸር ጉልበት ጋር አልተመጣጠነም። ከወገቡ በላይ ወደኋላው ተገፍትሮ አካሉን ሊቆጣጠር በማይችልበት ኃይል በጀርባው ከመሬት ተደባለቀ። በክርኑ መሬቱን የተደገፈው የቀኝ እጁ፣ ጣቶቹ እንደታጠፉ ቀና ብሎ ቀስ እያለ መሬቱ ላይ አረፈ። ከዚያም ተጫዋቹ በወደቀበት ሳይነቃነቅ በድን ሆነ። ግጭቱ እጅግ ከባድ ስለነበር ባቲስቶ ራሱን ሳተ። ሁለት ጥርሶቹ ወለቁ፣ ሶስት የጎድን አጥንቶቹ ተሰበሩ። በሜዳ ላይ የህክምና እርዳታ ሲደረግለት በተጫዋቹ ዙሪያ ሆነው አሰቃቂውን ጉዳት በቅርበት የሚከታተሉ የፈረንሳይ ተጫዋቾች ፊታቸውን ወደ ሹማኸር መለስ ቀለስ እያደረጉ ቁጣቸውን ይገልፃሉ። በረኛው ግን ከቁብም አልቆጠራቸው። በመጀመሪያ ወገቡን በእጆቹ ይዞ ባለበት ቆሞ ቆየ። ከዚያም ከሌላ የቡድን ጓደኛው ጋር ኳስ እየተቀባበለ ሰውነቱ እንዳይቀዘቅዝ ማድረጉን ቀጠለ። በኦክስጅን ጭምብል ከሜዳ እንዲወጣ ያስገደደ ከባድ ጥፋት ቢፈጽምም አርቢትር ቻርልስ ኮርበር ለሹማኸር ቀይ ካርድ ቀርቶ የማስጠንቀቂያ ካርድ እንኳን አልመዘዙበትም። ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ በረኛው በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የባቲስቶ ጥርሶች መውለቃቸውን ሲነግሩት ‹‹እኔ ወጪውን እሸፍናለሁ›› በሚል ስላቅ እብሪተኛነቱን ጨምሮ አሳየ። በወቅቱ አንድ ቡድን መቀየር የሚችለው ሁለት ተጫዋቾችን ብቻ በመሆኑ ሁለተኛው ተቀያሪ በጉዳት ከሜዳ የወጣበት የፈረንሳይ ቡድን አጋጣሚው ለፍፃሜ የመድረስ አቅሙን ክፉኛ አዳከመበት። በጭማሪ ሰዓት ፈረንሳይ አከታትላ ባስቆጠረቻቸው ሁለት ጎሎች 3-1 መምራት ብትችልም፣ አልሞት ባዮቹ ጀርመናዊያን ሁለት ጎሎች አግኝተው በ3-3 የመጨረሻ ውጤት ወደ መለያ ምት ሄዱ። ከዚያም የሹማኸር ምዕራብ ጀርመን ለፍፃሜው በቃች። አጋጣሚው በፈረንሳይ ህዝብ ዘንድ ፀረ-ጀርመን ጥላቻን ፈጠረ። ሹማኸር የፈረንሳይ ቁጥር አንድ ጠላት ሆነ። አንድ የሀገሪቱ ጋዜጣ በሰበሰበው የህዝብ መጠይቅ ሹማኸር ከናዚው አዶልፍ ሂትለር በላይ በዚያች ሀገር እንደተጠላ ተረጋገጠ። የጀርመኑ መራሔ መንግስት ሄልሙት ሽሚድት ቁጣውን ለማቀዝቀዝ ለፈረንሳዩ አቻቸው ፍራንሷ ሚቴሯ የቴሌግራም መልዕክት ላኩ። የጋራ መግለጫ ሊያወጡም ተገደዱ። ተጫዋቾቹም እንዲገናኙ ለማድረግ ሞከሩ። በሰዎች ግፊትም ይሁን ዘግይቶ በመጸጸቱ፣ ሹማኸር ተጎጂው ባለበት ሄዶ ይቅርታ ሊጠይቀው ቢሞክርም በጋዜጠኞች መገኘት ምክንያት ያሰበውን ያህል ሳይሳካለት ቀረ። አሁን ባቲስቶ ከስልሳ ዓመት ያለፈው ጎልማሳ ሆኗል። ጉዳቱ በጀርባ አጥንቱ ላይ የፈጠረው አደጋ እስካሁንም የህመም ስሜት እንዳለው ይናገራል። ራስ ምታት ልማዱ ነው። በቃሬዛ ከወጣ በኋላ የተከናወነውን ቀሪ የጨዋታ ፊልም ላለማየት ወስኖ ቢቆይም በመጨረሻ ከሰላሳ ዓመታት በኋላ ተመልክቶታል። ወደ እርጅናው የተጠጋው ሹማኸርም አሁን ደርሶ በአጋጣሚው መጸጸቱን ይናገራል። ከጨዋታው ሁለት ዓመት
በኋላ፣ በ1984፣
ፈረንሳይና ምዕራብ ጀርመን
በወዳጅነት መርሃ ግብር
ተገናኙ። ከጉዳቱ በኋላ
ወደ ጨዋታ የተመለሰው
ባቲስቶ በድጋሚ በብሔራዊው
ማሊያ ከሹማኸር ጋር
በተቃራኒ ቆመ። በመጨረሻ
ሁለቱ ሰዎች ማሊያ
ተቀያየሩ። ቅይይሩ ግን
በህዝብና በሚድያው ፊት
ሳይሆን በተጫዋቾች መልበሻ
ቤት ውስጥ፣ ብቻቸውን
ያደርጉት ነበር።አዲስ ዘመን
ታህሳስ 4/2013 | https://www.press.et/Ama/?p=37293 | 561 | 2ስፖርት
|
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተሰበሩ ከሚገኙ የዓለም ክብረወሰኖች ጀርባ | ስፖርት | December 14, 2020 | 7 | ቦጋለ አበበበኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስጋት ለበርካታ ወራት ተቋርጠው የቆዩ ዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድሮች ካለፈው ሐምሌ መጨረሻ ጀምሮ በሂደት ወደ መደበኛ መርሃግብራቸው እየተመለሱ ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ውድድሮች በተመለሱበት ጥቂት ወራትም በተለይም የረጅም ርቀት የዓለም ክብረወሰኖች ለማመን በሚቸግር መልኩ ሲሰበሩ እየተስተዋለ ይገኛል፡፡ ይህም የስፖርቱን አፍቃሪዎች ከማነጋገሩ ባሻገር ተንታኞች ጭምር ግራ እንዲጋቡ ያደረገ ክስተት ሆኗል፡፡ በተለይም የዓለም ግማሽ ማራቶን ክብረወሰን ከወረርሽኙ በፊትም ቢሆን ከሌሎች ርቀቶች በተለየ በሁለቱም ፆታ በተደጋጋሚ ሲሰበር መስተዋሉ አነጋጋሪ አድርጎታል፡፡ የዓለም ግማሽ ማራቶን ክብረወሰን በዓለም አትሌቲክስ እኤአ ከ2004 አንስቶ እውቅና እየተሰጠው ከመጣ ወዲህ በወንዶች አምስትና በሴቶች ስድስት የዓለም ክብረወሰኖች ተመዝግበዋል፡፡ ከዚህ ዓመት በፊት በርቀቱ የተመዘገቡ ሰዓቶች በዓለም አትሌቲክስ ‹‹የዓለም ፈጣን ሰዓት›› በሚል ይታወቅ ነበር፡፡ የወንዶች ግማሽ ማራቶን የዓለም ክብረወሰን ባለፈው እሁድ በቫሌንሲያ የተመዘገበ ሲሆን ኬንያዊው አትሌት ኪቢዎት ኬንዲ 57፡32 በሆነ ሰዓት የክብረወሰኑ ባለቤት ሆኗል::የሴቶቹ ደግሞ ባለፈው የካቲት በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች የራስ አል ኪማህ ግማሽ ማራቶን ውድድር ላይ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት አባብል የሻነህ በ1፡04፡31 በሆነ ሰዓት ያስመዘገበችው ነው፡፡ ይህም በጥቅምት 2017 ኬንያዊቷ ጆይስሊን ጂፕኮስጌ በቫሌንሲያ ግማሽ ማራቶን ካስመዘገበችው የቀድሞው የዓለም ክብረወሰን በሃያ ሰከንድ የተሻለ ነበር፡፡ በመስከረም 2019 ሌላኛዋ ኬንያዊት
ብሪጊድ ኮስጌ በኒውካስትል ታላቁ
ሩጫ 64፡28 በሆነ ሰዓት
ከቀድሞው ክብረወሰን በሃያ ሦስት
ሰከንድ የተሻለ ፈጣን ሰዓት
ብታስመዘግብም የዓለም አትሌቲክስ ለክብረወሰኑ
እውቅና አልሰጠውም። እኤአ ከ2011 ጀምሮ
የዓለም አትሌቲክስ የሴቶች ግማሽ
ማራቶን ክብረወሰኖችን በሴትና በወንድ አሯሯጭ
የተመዘገቡ ብሎ በሁለት ከፍሏቸዋል። በሴት
አሯሯጮች የተመዘገበው የርቀቱ ክብረወሰንም በኬንያዊቷ
አትሌት ፔርስ ጂፕቺርቺር 1፡05፡16 በሆነ ሰዓት
ከወር በፊት በፖላንድ ጊዲኒያ
የዓለም ግማሽ ማራቶን ቻምፒዮና
የተመዘገበ ነው። ባለፈው ሐምሌ መጨረሻ ለአስራ ስድስት ዓመታት ያልተደፈረው የቀነኒሳ በቀለ የአምስት ሺ ሜትር ክብረወሰን በዩጋንዳዊው አትሌት ጆሽዋ ቺፕቴጌ ሞናኮ ላይ ከተሰበረ ወዲህ የዓለም ክብረወሰኖች በተለይም በረጅም ርቀት ውድድሮች እንደልብ የሚሰበሩ ሆነዋል። ከዩጋዳዊው ያልተጠበቀ ክብረወሰን በኋላ አንድ ወር ባልሞላ ልዩነት ትውልደ ሶማሊያዊው የእንግሊዝ አትሌት ሞ ፋራህ እኤአ 2007 ላይ በጀግናው አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ተይዞ የቆየው ‹የአንድ ሰዓት ውድድር› የዓለም ክብረወሰን ብራሰልስ ዳይመንድ ሊግ ላይ ከ21፡330 ወደ 21፡285 ተሻሽሏል። በተመሳሳይ ርቀት እንዲሁም በተመሳሳይ ቀንና ውድድር በኢትዮጵያዊቷ አትሌት ድሬ ቱኔ 18፡930 ተይዞ የቆየው የዓለም ክብረወሰን በትውልደ ኢትዮጵያዊቷ የኔዘርላንድስ አትሌት ሲፈን ሃሰን 18፡517 በሆነ ሰዓት ተሻሽሏል። የሁለቱ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የአንድ ሰዓት ውድድር የዓለም ክብረወሰኖች በተሰበሩ በአንድ ወር ልዩነት ዩጋንዳዊው አትሌት ጆሽዋ ቺፕቴጌ ለአስራ አምስት ዓመታት ያልተደፈረውን የቀነኒሳ በቀለ የአስር ሺ ሜትር ክብረወሰን በ6፡53 ሰከንድ መስበር ችሏል። በተመሳሳይ ቀን ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ለተሰንበት ግደይ በሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌትና የረጅም ርቀት ንግስት ጥሩነሽ ዲባባ ለአስራ ሁለት ዓመታት ተይዞ ሳይሰበር የቆየውን የአምስት ሺ ሜትር ክብረወሰን 14፡06 በሆነ ሰዓት ሰብራዋለች። ኬንያውያን አትሌቶችም ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኋላ ባንሰራራው የአትሌቲክስ ውድድር የክብረወሰን ተቋዳሽ ናቸው። ለዚህም በዓለም ግማሽ ማራቶን በአርባ ሁለት ቀናት ልዩነት ሁለት የዓለም ክብረወሰኖችን የጨበጠችው ኬንያዊቷ ፔስር ጂፕቺርቺር ትክክለኛ ማሳይ ናት። መስከረም ላይ በፓራጓይ ግማሽ ማራቶን የሴቶችን ብቻ የርቀቱን የዓለም ክብረወሰን በ1፡05፡24 ሰዓት ያሻሻለችው ኬንያዊት አትሌት ከአርባ ሁለት ቀናት በኋላ በፖላንድ ጊዲኒያ የዓለም ግማሽ ማራቶን ቻምፒዮና የራሷን ክብረወሰን በአስራ ስምንት ሰከንድ ማሻሻል ችላለች። እነዚህ ሁሉ ክብረወሰኖች ሲሰባበሩና አትሌቶች በተለየ መልኩ አስደናቂ ብቃት ሲያሳዩ አብዛኛው የስፖርት ቤተሰብ ሁለት ነገሮችን ጠርጥሯል። ይህም በወረርሽኙ ምክንያት አትሌቶች ለረጅም ጊዜ ከውድድር በመራቃቸው ሰፊ የዝግጅት ጊዜ በማግኘት ወደ ውድድር ሲመለሱ ምርጥ ብቃት ሊኖራቸው እንደቻለና በነዚያ የረፍት ጊዜያት በጉዳት ላይ የነበሩ አትሌቶች በበቂ ሁኔታ ማገገም በመቻላቸው እንደሆነ ይታሰባል። ስፖርቱን በጥልቀት የሚመለከቱ በርካታ ተንታኞች ግን ከዚህም የበለጡ ገፊ ምክንያቶች ከክብረወሰኖቹ መሰባበር ጀርባ እንዳሉ ያምናሉ። የልምምድ ስነልቦናና ሂደት በወረርሽኙ ምክንያት እየተለወጠ መምጣቱ ለክብረወሰኖቹ መሻሻል አንድ ምክንያት ተደርጎ ይወሰዳል። ይህም የወረርሽኙ ስጋት ቀደም ብሎ አትሌቶች በርከት ብለው በአንድ አሰልጣኝና በአንድ ካምፕ ውስጥ ሆነው የሚያደርጉትን የተለመደ ዝግጅት ወደ ጎን ትተው በተናጠል በሚመቻቸው ስፍራና በቤታቸው ሆነው እንዲዘጋጁ እድል መስጠቱ ነው። ይህ አጋጣሚ አትሌቶች አንዱ አንዱን ሳይጠብቅ በራሳቸው መርሃግብር መሰረት ወጥ በሆነ መልኩ እስከ አቅማቸው ጥግ ድረስ እንዲዘጋጁ ያስቻላቸው ሲሆን በስነልቦናውም ረገድ ጠንካራ እንዲሆኑ አድርጓል። ለዚህም ከወረርሽኙ በኋላ ክብረወሰኖችን ያሻሻሉ አትሌቶች ቀደም ሲል ይከተሉት የነበረው የልምምድ መልክ በወረርሽኙ ሳቢያ መቀየሩ ለክብረወሰኖች መሻሻል ቁልፍ ሚና እንዳለው የሚያስቀምጡ ባለሙያዎች በርካታ ናቸው። በሌላ መልኩ አትሌቶች በወረርሽኝ ምክንያት ውድድሮች ቢቆሙም የሆነ ጊዜ ላይ እንደሚቀጥሉ አውቀው ዝግጅታቸውን ሳያቋርጡ ተግተው መስራታቸው የክብረወሰን ባለቤት እንዳደረጋቸው ይታመናል። አትሌቶች ወረርሽኙ የጤና ስጋት ቢሆንም መጥፎን አጋጣሚ ወደ ጥሩ ለውጠው ተጠቅመዋል። አቋማቸው እንዳይወርድ በመጠንቀቅ መዘጋጀታቸው ኋላ ላይ ለስኬት አብቅቷቸዋል። በተለይም እቤት የመቀመጥ አስገዳጅ ሁኔታው ቀደም ሲል የነበረባቸውን የተጣበበ የልምምድና የውድድር ጫና በማስቀረቱ በበቂ ሁኔታ እንዲዘጋጁ በር ስለከፈተላቸው በደህናው ጊዜ ማሳካት ያልቻሉትን ክብረወሰን እንዲያሳኩ አድርጓቸዋል። ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ የተፈጠሩ መልካም አጋጣሚዎች እንዳሉ ሆነው የስፖርት ቴክኖሎጂ እየዘመነ መምጣት ለተመዘገቡት ክብረወሰኖች የአንበሳውን ድርሻ እንደሚይዝም ዓለም አቀፍ የስፖርቱ ምሁራን የሚስማሙበት ጉዳይ ነው። ባለፉት ጥቂት ወራት ሲመዘገቡ ያየናቸው በርካታ ክብረወሰኖች አትሌቶች የሚያስመዘግቧቸው ሰዓቶች ላይ ሰፊ ልዩነት በሚፈጥሩ ዘመናዊ የመሮጫ ጫማ እንዲሁም አሯሯጮች በተለይም በመም ውድድሮች ከሰው ይልቅ ቴክኖሎጂ ሆኖ አትሌቶችን እስከ መጨረሻ ድረስ በሚፈለገው ደረጃ በማገዝ የተመዘገቡ ናቸው። ግዙፉ የስፖርት ትጥቅ አምራች ኩባንያ ናይኪ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሚያቀርባቸው የመሮጫ ጫማዎች ቀደም ሲል የዓለም ክብረወሰን ሲመዘገብባቸው ከቆዩ የመሮጫ ጫማዎች አንፃር በአትሌቶች ፍጥነት ላይ የጎላ ተፅዕኖ እንዳላቸው አትሌቶችም ይሁን የስፖርት ቤተሰቡ ይስማማሉ። ከዚህ በላይ የጥሩነሽ ዲባባ የአምስት ሺ ሜትር ክብረወሰን በሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ለተሰንበት ግደይ እና የቀነኒሳ በቀለ የአምስትና አስር ሺ ሜትር ክብረወሰኖች በዩጋዳዊው አትሌት ጆሽዋ ቺፕቴጌ ሲሰበሩ አትሌቶቹን በአሯሯጭነት ያገዛቸው በመሮጫው መም ዙሪያ የተገጠመው መብራት(Wave-lights) እንደነበር ይታወቃል። ይህ ቴክኖሎጂ አትሌቶቹ በምን ያህል ፍጥነት እያንዳንዱን ዙር ሮጠው ክብረወሰን እንደሚጨብጡ አስልቶ በማሯሯጥ እስከ መጨረሻ ድረስ ደግፏቸዋል። አሯሯጭ በአትሌቲክሱ ዓለም ክብረወሰኖችን ለማስመዝገብ ወሳኙ ነገር እንደሆነ ይታወቃል። አንዳንድ ጊዜ ሴት አትሌቶች በወንድ አሯሯጮች ታግዘውም አሯሯጮች በሚፈለገው ፍጥነት መጓዝ ካልቻሉ ክብረወሰን የማይሰበርበት አጋጣሚ ጥቂት እንዳልሆነ ይታወቃል። አሯሯጩ ቴክኖሎጂ ሆኖ እስከ መጨረሻ ድረስ ወጥ በሆነ ስሌት አትሌቶችን ሲያግዝ ግን የተለየ እንደሚሆን የቅርቦቹ ክብረወሰኖች ምስክር ናቸው።አዲስ ዘመን ታኅሣሥ 5/2013 | https://www.press.et/Ama/?p=37367 | 844 | 2ስፖርት
|
Amharic News Category Classification
This amharic text dataset can be used to train/finetune models for the following tasks
- classification : using the categories
- summarization : using the headlines
Finetuning
Here is a github repo that contains three notebooks that use this dataset to finetune the following models.
- xlm-roberta-base : a multilingual transformer model with 280M parameters
- bert-small-amharic : a new amharic version of the bert-small transformer model with 25.7M parameters, pretrained from scratch using unlabelled amharic text data
- bert-mini-amharic : a new amharic version of the bert-mini transformer model with 9.67M parameters, pretrained from scratch using unlabelled amharic text data
https://github.com/rasyosef/amharic-news-category-classification
The finetuned model classifies a given Amharic news article into one of the following 6 categories.
- ሀገር አቀፍ ዜና (Local News)
- መዝናኛ (Entertainment)
- ስፖርት (Sports)
- ቢዝነስ (Business)
- ዓለም አቀፍ ዜና (International News)
- ፖለቲካ (Politics)
Fine-tuned Model Performance
Since this is a multi-class classification task, the reported precision, recall, and f1 metrics are macro averages.
Model | Size (# params) | Accuracy | Precision | Recall | F1 |
---|---|---|---|---|---|
xlm-roberta-base | 279M | 0.9 | 0.88 | 0.88 | 0.88 |
bert-small-amharic | 25.7M | 0.89 | 0.86 | 0.87 | 0.86 |
bert-mini-amharic | 9.67M | 0.87 | 0.83 | 0.83 | 0.83 |
Original CSV and Paper
The original csv file can be found in this git repository https://github.com/IsraelAbebe/An-Amharic-News-Text-classification-Dataset
While there is a version of this dataset that's already available on huggingface hub (israel/Amharic-News-Text-classification-Dataset), that version had been preprocessed to remove punctuation from the articles, while this version contains the entire text along with punctuations. As a result, this version is more preferable for finetuning transformer models.
In NLP, text classification is one of the primary problems we try to solve and its uses in language analyses are indisputable. The lack of labeled training data made it harder to do these tasks in low resource languages like Amharic. The task of collecting, labeling, annotating, and making valuable this kind of data will encourage junior researchers, schools, and machine learning practitioners to implement existing classification models in their language. In this short paper, we aim to introduce the Amharic text classification dataset that consists of more than 50k news articles that were categorized into 6 classes. This dataset is made available with easy baseline performances to encourage studies and better performance experiments.
@misc{https://doi.org/10.48550/arxiv.2103.05639,
doi = {10.48550/ARXIV.2103.05639},
url = {https://arxiv.org/abs/2103.05639},
author = {Azime, Israel Abebe and Mohammed, Nebil},
keywords = {Computation and Language (cs.CL), Artificial Intelligence (cs.AI), FOS: Computer and information sciences, FOS: Computer and information sciences},
title = {An Amharic News Text classification Dataset},
publisher = {arXiv},
year = {2021},
copyright = {arXiv.org perpetual, non-exclusive license}
}
- Downloads last month
- 48