headline
stringlengths
2
1.42k
category
stringclasses
6 values
date
stringlengths
9
35
views
stringlengths
1
7
article
stringlengths
63
36.2k
link
stringlengths
28
740
word_len
int64
16
6.74k
label
class label
6 classes
‹‹መልካም ነገርን ማበርከት እንጂ መጥፎ ተግባራት ላይ መተባበርና መተጋገዝ ተገቢ አይደለም›› ኡስታዝ መሐመድ ፈረጂ
ሀገር አቀፍ ዜና
July 31, 2020
11
አዲስ አበባ፡- የሰው ልጆች መተባበርና መረዳዳት ያለባቸው አገርና ወገን በሚጠቅሙ መልካም ተግባራት እንጂ በመጥፎ ድርጊቶች መሆን እንደማይገባና በፈጣሪም ዘንድ የተከለከለ መሆኑን ኡስታዝ መሐመድ ፈረጂ ገለጹ። ኡስታዝ መሐመድ እንደተናገሩት፤ መልካምና ጥሩ በሆኑ ነገሮች ላይ ሁሉ እርስ በርስ ልትተጋገዙ፣ልትተባበሩ፣ልትረዳዱ ይገባል፤ ነገር ግን በወንጀል ላይ፣በክፋት ላይ፣ድንበር በማለፍ ላይ፣ የሰውን መብትና ስብዕና በመንካት ላይ በፍጹም መተጋገዝና መረዳዳት በፈጣሪም የተከለከሉ የሕይወት መመሪያዎች እንደሆኑ ገልጸዋል። ኡስታዝ መሐመድ እንዳሉት፤ መተጋገዝ እንደሚገባ መረጋጋት እንደሚገባ ከፈጣሪ የወረደ መለኮታዊ ትዕዛዝ ነው። ለሰውኛ ምልከታና ለሰውኛ እይታ የተተወ ጉዳይ አይደለም። የሰው ልጅ ጥሮግሮ፣ለፍቶ ደክሞ መተጋገዝ ያስፈልገኛል። መረዳዳት ይኖርብኛል ብሎ እስኪያምን ድረስ የተተወለት ጉዳይ አይደለም። ቀድሞውኑ የሰውን ልጅ የፈጠረው አላህ ይህን ጉዳይ የሚያውቅ በመሆኑ ከጅምሩ ተባበሩና ተጋገዙ የሚል መመሪያን ያስቀመጠበት ጉዳይ ነው።በዚያው ልክ በጥፋት በተንኮልና በመጥፎ ጉዳዮች ላይም የሰው ልጆች መተባበርና መተጋገዝ እንደሌለባቸው በፈጣሪ ስለመከልከሉም ገልጸዋል።እነዚህ ትዕዛዞች ከፈጣሪ ለሰው ዘር በሙሉ የተላለፉ መሆናቸውን የተናገሩት ኡስታዝ መሐመድ፤ እነዚህን ሰምቶ በፈጸመና እውን ባደረገ ጊዜ ይችን ዓለም በማሳመር የምድራዊ ሕይወት ውብ እንዲሆን ከማድረጉም በላይ በወዲያኛውም ዓለም በጀነት (በገነት)ም ያማረ ሕይወት መኖር እንደሚያስችል አስረድተዋል። ኡስታዝ መሐመድ እንዳሉት፤ ‹‹ማገዝ›› ማለት በራሱ ፈጣሪ ካሉት ስሞች መካከል አንዱ ነው። ፈጣሪ ፍጡራኖቹን የሚረዳና የሚያግዝ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ የሰው ልጆች በዚህ መንገድ እንዲተዳደሩና እንዲኖሩ የተሰጠ መመሪያም ነው። አላህ በቁርዓን ውስጥ በመልካም ነገሮች ተጋገዙ ብሎ ሲያዝ፣ አንዳንድ ሰዎች መዝረፍን፣ መስረቅን፣ ማቃጠልን፣ መግደልን፣ ዝሙት መሥራትን መልካም ነገሮች ናቸው ብለው ሊያስቡ የሚችሉ ከሆነ በፍጹም ሊሆኑ አይችሉም። ምክንያቱም መጥፎ ድርጊቶችን፣ ክፉ ተግባራትን፣ እና የሰው ልጆችን በሚያስከፉ፣በሚያስቀይሙና ደስታቸውን በሚያሳጡ ተግባሮች ላይ በፍጹም መተባበር እንደሌለበት በፈጣሪው ተከልክሏል።ፈጣሪ የሰው ልጆችን እንዲረዳዱና እንዲተባበሩ ሲያዝ በሚችሉት፣ ባላቸው እና በተሰጣቸው ነገር ላይ ነው። በማይችሏቸውና በሌላቸው ነገሮች ላይ ይሄን እንዲያደርጉ አላዘዘም። ነፍሳቸውንም ከችሎታዋ በላይ እንድታደርግ አላስገደደም። ስለዚህ የሰው ልጆች በሚችሉትና ባላቸው ነገር መተባበር አለባቸው። እውቀት ያለው በእውቀቱ፣ ሙያ ያለው በሙያው፣ ገንዘብ ያለው በገንዘቡ፣ ጉልበት ያለው በጉልበቱ እና ማንኛውም ሰው ባለው ነገር መተባበርና መተጋገዝ ይኖርበታል። አንዳንድ ሰዎች በወገኖቻቸው ላይ የሚፈጽሟቸው ግፎች መነሻቸውም መድረሻቸውም በፈጣሪ የተወገዙና የተከለከሉ ናቸው። በፍጹም ወንድም በወንድሙ ላይ ወገን በወገኑ ላይ መጥፎ እንዲሠራ ፣ቢላዋ እንዲያነሳ፣እሳት እንዲለኩስ አልተፈቀደለትም። ነብዩ መሐመድ (ሱ.ዐ.ወ) በእያንዳንዱ ተግባራቸው፣ ስነምግባራቸው እና ስብዕናቸው ለሰው ልጆች ሞዴልና አርዓያ ናቸው። አማኝና ከሃዲ ሳይሉ፤ ሀብታምና ደሃ ሳይሉ፣ብሔርና ጎሳ ሳይለዩ፣ ቀለምና ዜግነትን ጭምር ሳይመርጡ ለተቸገረ፣ ለተጎዳ፣ ለተበደለ፣ ለተሰቃየ፣ ለተጎሳቆለ በሙሉ አላህ በሰጣቸው አቅም እጃቸውን ዘርግተዋል። ሩህሩህና አዛኝነታቸውን አሳይተዋል። የታረዘን አልብሰዋል። የተራበን አብልተዋል። በደል የደረባቸው ፍትሕ እንዲያገኙ አድርገዋል። የሰው ልጆችም በእንዲህ ዓይነት መልካም ስብዕና ሊገነቡ እንጂ እንደመንጋ ተመርተውና መጥፎ ተግባር ፈጽመው ሕይወታቸውንም ኑሯቸውንም ሊያጎድፉ አይገባቸውም ሲሉ ኡስታዝ መሐመድ ፈረጂ መክረዋል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 24/2012 ሙሐመድ ሁሴን
https://www.press.et/Ama/?p=36359
381
0ሀገር አቀፍ ዜና
ዳኛ በአምላክ ተሰማ ከ20 ዓመት በታች ዓለም አቀፍ ውድድር ያመራል
ስፖርት
May 12, 2019
25
በፖላንድ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የ20 19 የፊፋ ከ20 ዓመት በታች ውድድር ኢት ዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዳኛ በአምላክ ተሰማ ተመርጧል። በፖላንድ አስተናግጅነት ከግንቦት 15 እስከ ሰኔ 8 በሚካሄደው በዚህ ውድድር ላይ የዓለም አቀፉ እግር ኳስ የበላይ አስተዳዳሪ ፊፋ ከመላው ዓለም 27 ዋና ዳኞች፣ 42 ረዳት ዳኞች እንዲሁም 21 የቪዲዮ (ቫር) ረዳት ዳኞች መርጧል። ከነዚህም ውስጥ ኢትዮጵያዊ ኢንተርናሽናል ዳኛ በአምላክ ተሰማ ወይሶ በቪዲዮ ረዳት ዳኝነት ተመድቧል። ኢንተርናሽናል ዳኛ በአምላክ ከቀናት በፊት በሞሮኮ ተካሂዶ በተጠናቀቀውና የአፍሪካ ዋንጫ ለመምራት ከታጩ ዳኞች ጋር ሥልጠና ሲወስድ መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን፣ በፖላንዱ ውድድር ላይ በአምላክን ጨምሮ ሌሎች የተመረጡ ልምድ ያላቸው በቫር ዳኝነት እንደሚሳተፉ ታውቋል። ከአፍሪካም ተመሳሳይ ታላላቅ ጨዋታዎችን በመሐል ዳኝነት የማጫወት ልምድ ያላቸው ግብፃዊው ገሂድ ጊርሻ እና ጋምቢያዊው ባካሪ ጋሳማ ከበአምላክ ጋር ተመሳሳይ ሚና ተሰጥቷቸዋል። አፍሪካ በዋና ዳኝነት ሦስት፣ በረዳት ደግሞ ሰባት ዳኞችን ለውድድሩ አስመርጣለች። ይህ ውድድር ከተጠናቀቀ ከስድስት ቀናት በኋላ የአፍሪካ ዋንጫ በግብፅ አስተናጋጅነት መካሄድ የሚጀምር ሲሆን በአምላክ ተሰማም ጨዋታዎችን ከሚመሩ ዳኞች አንዱ እንደሚሆን ይጠበቃል።አዲስ ዘመን ግንቦት 4/2011አብርሃም ተወልደ
https://www.press.et/Ama/?p=10668
150
2ስፖርት
ኤርትራ የሴካፋ ከ15 ዓመት በታች ዋንጫ ልታዘጋጅ ነው
ስፖርት
May 12, 2019
24
የኬንያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት እና የወቅቱ የሴካፋ ፕሬዚዳንት ኒክ ምዌንድዋ ኤርትራ ሴካፋ ከ15 ዓመት በታች ዋንጫ እንደምታዘጋጅ ተናገሩ። ባለፈው ወር የሠላም እና ወዳጅነት ዋንጫን የማዘጋጀት ውጥኗ በአንዳንድ ጉዳዮች ያልተሳካላት ኤርትራ የመጀመሪያው የሴካፋ ከ15 ዓመት በታች ዋንጫን እንደምታዘጋጅ ከወደ ኬንያ ተሰምቷል። የኬንያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከግብፁ ክለብ ዋዲ ዴግላ ጋር አብሮ ለመስራት በተስማማበት መድረክ ላይ ተገኝተው ሃሳባቸውን የገለፁት የወቅቱ የሴካፋ ፕሬዚዳንት ኒክ ምዌንድዋ የቀጣናው የወጣቶችን እግር ኳስ ለማሳደግ በቀጣዩ ነሐሴ የመጀመሪያው ከአስራ አምስት ዓመት በታች የሴካፋ ዋንጫ በኤርትራ ለማዘጋጀት እንደወሰኑ ገልፀዋል። ፕሬዚዳንቱ ውድድሩ መዘጋጀቱ ለቀጣናው እግር ኳስ እድገት ወሳኝ እንደሆነ አውስተዋል። «ይህን ውድድር ለማዘጋጀት ያሰብነው በቀጣናው ለታዳጊዎች እግር ኳስ የሚሰጠውን ትኩረት ከፍ ለማድረግ ነው» ብለዋል። በአሰልጣኝ ዓለምሰገድ ኤፍሬም እየተመሩ ከሃያ ዓመት በላይ ዕድሜ ያላቸውን ተጫዋቾች ይዘው ላለፉት አራት ወራት የሠላም ዋንጫን በመጠባበቅ የነበሩት «የቀይ ባህር ግመሎች» በቀጣይ ቀናት የተጫዋቾች ምርጫ በማድረግ ዝግጅት ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል።አዲስ ዘመን ግንቦት 4/2011አብርሃም ተወልደ
https://www.press.et/Ama/?p=10674
139
2ስፖርት
ደደቢት ፈርሷል፣ ቀጣዩስ ?
ስፖርት
May 12, 2019
40
ደደቢት እግር ኳስ ክለብ መፍረሱ አዲስ ዜና አይደለም፡፡ አዲስ ነገር ቢኖር ክለቡ ራሱ በቃኝ ብሎ በይፋ ሊጉን የሚሰናበትበት ቀን ነበር፡፡ ያም ቀን ደርሶ ክለቡ ከዚህ በኋላ እንኳን በቀጣይ ዓመታት ይቅርና ያገባደደውን የዘንድሮ የውድድር ዓመት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጥቂት ጨዋታዎች መቀጠል እንደማይችል አሳውቋል፡፡ ክለቡ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ባስገባው ደብዳቤ መሠረት ከዚህ ቀደም በተለያዩ አካላት ቃል የተገቡለትን ገቢዎች ማግኘት ስላልቻለ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ በውድድር ለመቆየት ጥረት አድርጓል፡፡ አሁን ግን ከአቅሙ በላይ ስለሆነበትና ዕዳ ውስጥ ስለገባ ከ24ኛው ሳምንት ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ጀምሮ በውድድር መቆየት እንደማይችል ነው፡፡ በሊጉ ላይ ዋንጫ ማሳካት ከቻሉ ጥቂት ክለቦች መካከል አንዱ የሆነው ደደቢት ከፍተኛ በሆነ የፋይናንስ ቀውስ ውስጥ መሆኑን ካሳወቀ ሰንብቷል፡ ፡ የ2005 ዓ.ም የፕሪሚየር ሊጉ ቻምፒዮን ደደቢት በመፍረስ ዋዜማ ላይ እያለ ስፖንሰሩ ከነበረው ሜቴክ ያገኝ የነበረው የስፖንሰርሽፕ ገቢ በመቅረቱ የገንዘብ አቅሙ እየተመናመነ ሄዶ ለተጫዋቾች ደመወዝ ለመክፈልና ከሜዳው ውጪ ጨዋታዎችን ለማድረግ ለትራንስፖርት የሚሆን እንኳን እጅ ሲያጥረው ሰንብቷል፡፡ ስለዚህ አሁን በቃኝ ቢል የሚያስገርም አይሆንም፡፡ ከዚህ ይልቅ ግን አንዳች ገቢ በሌለው ሊግ በርካታ ሚሊዮኖችን እያፈሰሱ የሚገኙት ሌሎች የአገራችን ክለቦች ተመሳሳይ ዕጣ ፈንታ መች እንደሚደርሳቸው ሲታሰብ ጊዜው ቅርብ መሆኑን መረዳት አስደንጋጭ ይሆናል፡፡ ትናንት እንደ ቀላል በመቶ ሺዎች ለተጫዋቾች ደመወዝ ከፋይ የነበሩና ለገበያው ጣሪያ መንካት ዋና ተዋናይ የሆኑት ክለቦች ዛሬ ላይ ካዝናቸው ተራቁቷል። ለወሳኝ ተጫዋቾቻቸው በጊዜው የሚከፍሉት አጥተው ከዋክብቶቻቸው የተሻለ አቅም ወዳለው ክለብ ሲኮበልሉ እጃቸውን አጣጥፈው መመልከት ዕጣ ፈንታቸው ሆኗል። ለዚህ ደግሞ ከዓመትና ሁለት ዓመት በፊት ከፍተኛውን የተጫዋቾች ደመወዝ ከፋይ ከነበረው ከደደቢት የበለጠ ማሳያ የለም። ደደቢት በዚህ ማዕበል ክፉኛ ከተመታ ወዲህ መቀመጫውን ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ ቀይሯል። ከፍተኛውን የተጫዋቾች የደመወዝ ጣሪያም ሃያ አምስት ሺ ብር ለማድረግ ተገዷል። በዚህም ሳይበቃ የተሻለ ውጤታማ የሆነው የሴቶች ቡድኑን ለማፍረስ ሲወስን ሁለት ጊዜ አላሰበበትም። በአገራችን እግር ኳስ እንኳን በፋይናንስ ቀውስ ውስጥ የገባ ክለብ ቀርቶ ጠንካራ የፋይናንስ አቅምና ታሪክ ያላቸው ክለቦች ከሊጉ ለመፍረስ ቅርብ ሆነዋል። ለዚህም ኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ሙገር ሁነኛ ማሳያ መሆናቸው የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው። የክለቦች ቅጥ ያጣ የገንዘብ አወጣጥ የኋላ ኋላ ራሳቸውን ጠልፎ እንደሚጥላቸው ማሳያ ደደቢት ብቻ አይደለም። የአምናው ቻምፒዮን ጅማ አባ ጅፋር የዚሁ ችግር ተመሳሳይ ሰለባ ሆኗል። ዋንጫውን ባነሳ ማግስት አሁን እየገጠመው የሚገኘውን የፋይናንስ ቀውስ መመልከት ይቻላል። ጅማ አባ ጅፋር አምና በጉብዝናው ወራት የውጭ ተጫዋቾችን ጭምር ረብጣ ገንዘብ አውጥቶ በመግዛት በሊጉ ማማ ላይ ተቀምጦ እንደነበር አይዘነጋም። ይህም የአንድ ተጫዋች የወር ደመወዝ እንኳን መሸፈን የማይችል የመቶ ሃምሳ ሺ ብር ሽልማት አስገኘለት። ዘንድሮ ግን በአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግና ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ሙሉ ቡድኑን እንኳን ይዞ ባህር መሻገር ተሳነው። ለአሰልጣኝና ተጫዋቾች ከሁለት ወር በላይ ደመወዝ መክፈል አቅቶትም ውዝግብ ውስጥ እንደሰነበተ ይታወሳል። ሌሎቹም ክለቦች ከዚህ የተለዩ አይደሉም። የወጪ ዕድገት ጣሪያው እንዳደጉት አገራት ሊጎች ክለቦቻችን በነዳጅ ገንዘብ ኪሳቸው ባበጠ የአረብ ባለሀብቶች ካልተደገፈ በስተቀር ቀና ብለው የሚያዩትና ውሉን የሚጨብጡት ዓይነት አይደለም። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያጠናክሩትም በኢትዮጵያ እግር ኳስ ክለቦች በተለይም የፕሪሚየር ሊጉ ተሳታፊዎች የሚያወጡት ገንዘብ ቅጥ ያጣ ስለመሆኑ አያጠራጥርም። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች የተጫዋቾች ደመወዝ ዓመታዊ ወጪ መጠን በሚያስደነግጥ መልኩ ከፍተኛ ዕድገት ማሳየቱ ለማንም የተደበቀ አይደለም። የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ የ2010 የሂሳብ ሪፖርት አንድ ተጨባጭ ማስረጃ ነው። ኢትዮጵያ ቡና ለተጫዋቾች የሚያወጣው የገንዘብ መጠን በአራት ዓመት ልዩነት ውስጥ ከብር 3 ነጥብ 1 ሚሊዮን ወደ 30 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር ንሯል። ይህን ተከትሎም ኢትዮጵያ ቡና ዓመታዊ በጀቱን መሙላት ዳገት እየሆነበት መምጣቱን በይፋ ማሳወቅ ከጀመረም ሰንብቷል። የገንዘብ ጉዳይ አሳስቦት የማያውቀው ቅዱስ ጊዮርጊስም ቢሆን ገቢና ወጪው እኩል መራመድ እየተሳነው ኪሱ እየሳሳ ስለመምጣቱ የአደባባይ ወሬ ከሆነ ቆይቷል። የገቢ መንገዶች እየቀነሱ ወጪያቸውም ከዚህ በኋላ ይበልጥ እየተመነደገ እንደሚሄድ ከሁኔታዎች ተነስቶ ቢተነበይ ደግሞ ችግሩ ይበልጥ ጥርስ ያወጣ ይመስላል። የፕሪሚየር ሊጉ ከከተማ ከተማ ተዟዙሮ የመጫወት መርሐግብር የሊጉ ተሳታፊ ክለቦች መልክዓምድራዊ አቀማመጥ የተራራቁ መሆን ሌላው ችግር ነው፡፡ ከሁለት ዓመት በፊት አንድ የአዲስ አበባ ክለብ ለሊጉ ውድድር አንድም ጊዜ ወደ ትግራይ ክልል አይጓዝም ነበር። ዘንድሮ ግን አራት ጊዜ መጓዝ ግድ ይለዋል። ባለፉት ሦስት የውድድር ዘመናት በየዓመቱ አንዳንድ የአዲስ አበባ ክለቦች ከሊጉ መውጣታቸውን ተከትሎ (አዲስ አበባ ከተማ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክና ደደቢት) ከአምና እና ከካቻምና ይልቅ የአዲስ አበባ ክለቦች ለበለጠ ጊዜያት ወደ ክልሎች እየተጓዙ ለመጫወት ተገድደዋል። ክለቦቹ ብዙ በተጓዙ ቁጥር ወጪያቸው እየጨመረ መሄዱን ማስተዋል ይቻላል። በቀጣይ ዓመታትም ፕሪሚየር ሊጉን የሚቀላቀሉ ሦስት አዳዲስ ክለቦች ከየትኛውም ክልልና ከተማ ሊሆኑ እንደሚችሉ ከግምት ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል። ይህ ደግሞ ለብዙሃኑ የክልል ክለቦች ችግሩ ይበልጥ ብርቱ እንዲሆን ያደርገዋል። እነዚህ ክለቦች የሕዝብ ሀብት የሚፈስባቸው እንደመሆናቸው «ሚሊዮኖችን ዘርተው ምን አጨዱ?» ብለን ብንጠይቅ መልሱ በቀላሉ ምንም ይሆናል። አሳዛኙ ነገር በእግር ኳሱ ይህን ያህል ገንዘብ እየተረጨ ከፋይናንስ ዕድገቱ ጋር ኳሱ አብሮ መራመድ ይቅርና በግማሽ መንገድ እንኳን ሊከተለው አቅሙ አለመፍቀዱ ነው። ከአስር ጨዋታ ዘጠኙ አንድ ለዜሮ በሆነ ውጤት በሚጠናቀቅበት አሰልቺ ሊግ ሆኗል። የስፖርት ቤተሰቡ ለመዝናናት ካምቦሎጆ ገብቶ ፀያፍ ስድብ ሰምቶ ከመመለስ የዘለለ ያገኘው ነገር የለም። ይህ ሁሉ የገንዘብ ክምር ብሔራዊ ቡድኑ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳታፊ አገራት ከአስራ ስድስት ወደ ሃያ አራት አድጎ እንኳን ተወዳጁ መድረክ ጋር ሊያደርሰው የሚችል አቅም አልፈጠረለትም።አዲስ ዘመን ግንቦት 4/2011ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=10665
732
2ስፖርት
ኤሌክትሪክ ጌዴኦ ዲላ ላይ ግማሽ ደርዘን ጎል በማስቆጠር ከግርጌው ተላቋል
ስፖርት
May 12, 2019
55
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን 20ኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሐ ግብር በኤሌክትሪክ እና ጌዴኦ ዲላ መካከል ተከናውኖ ኤሌክትሪክ 6ለ0 አሸንፎ ላለመውረድ የሚያደርገውን ትግል ቀጥሏል። ጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ ተመጣጣኝ ፉክክር ቢስተዋልበትም ያገኟቸውን ዕድሎች በአግባቡ በመጠቀም ረገድ ስኬታማ የሆኑት ግን ኤሌክትሪኮች ነበሩ። በመሐል ሜዳ ተገድቦ የቆየው እንቅስቃሴ የመጀመሪያውን ሙከራ ለማስመልከት 18 ደቂቃዎች አስጠብቋል። በግምት ከ20 ሜትር ርቀት ፀባኦት መሐመድ በቀጥታ መትታ ግብ ጠባቂዋ ገነት አንተነህ ወደ ውጪ ስታወጣው ከሦስት ደቂቃዎች በኋላ ከመሐል ሜዳ የተላከውን ኳስ ረድኤት አሳሳኸኝ በጥሩ ሁኔታ ተከላካዮችን አምልጣ በመውጣት ግብ ጠባቂዋን ብታልፋትም ኳሱን ወደ ግብ መምታት ሳትችል ያመከነችው ኳስ ጌዴኦ ዲላዎችን መሪ ሊያደርጉ የተቃረቡ ሙከራዎች ነበሩ። ከሁለቱ ሙከራዎች በኋላ የተሻለ ብልጫ የወሰዱት ኤሌክትሪኮች አጋጣሚዎችን በመፍጠር ጎሎችን ማስቆጠር ችለዋል። በ27ኛው ደቂቃ መሳይ ተመስገን ለመሐል ሜዳ ከቀረበ ቦታ በቀጥታ ወደ ግብ የላከችውን ቅጣት ምት ግብ ጠባቂዋ ምህረት ተሰማ ስትተፋው አጠገቧ የነበረችው ቅድስት ዓባይነህ ወደ ጎልነት ቀይራ ኤሌክትሪክን ቀዳሚ አድርጋለች። በቀጣዮቹ ደቂቃዎች የጨዋታው እንቅስቃሴ ከቅብብል የዘለለ የጎል ሙከራዎችን ሳያሳይ የዘለቀ ሲሆን የአጋማሹ የመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ኤሌክትሪኮች የተለየ ሆነው ታይተዋል። በዚህም 44ኛው ደቂቃ ላይ ከራሳቸው የግብ ክልል በረጅሙ የተጣለውን ኳስ ወርቅነሽ ሜልሜላ በአግባቡ ተጠቅማ ፍጥነቷን በመጨመር ከቀኝ የሳጥኑ ክፍል መታ ሁለተኛውን ጎል አስቆጥራለች። ብዙም ሳይቆይ በጭማሪው ደቂቃ ላይ ደግሞ ከትበይን መስፍን ከመስመር የተሻገረውን ኳስ መሳይ ተመስገን ከግብ ጠባቂዋ ቀድማ በግንባሯ በመግጨት ሦስተኛውን አክላ የመጀመሪያው አጋማሽ በኤሌክትሪክ 3ለ0 መሪነት ተጠናቋል። በሁለተኛው አጋማሽ ጌዴኦ ዲላዎች ይበልጥ ተዳክመው ሲቀርቡ ኤሌክትሪኮች ደግሞ የዲላ ተከላካዮች ከጀርባቸው ትተውት የሚወጡትን ክፍተት በመጠቀም ተጨማሪ ሦስት ጎሎችን አስቆጥረዋል። በ57ኛው ደቂቃ ወርቅነሽ በፍጥነት ከቀኝ መስመር ገብታ ያመቻቸችውን ጥሩ ዕድል መሳይ ተመስገን መትታ ወደ ላይ ሲወጣባት በ61ኛው ደቂቃ ዓለምነሽ ገረመው ከርቀት አክርራ የመታችው ኳስ በግብ ጠባቂዋ ተጨርፎ ለጥቂት ወደ ውጪ ወጥቷል። የተገኘው የማዕዘን ምት ተሻምቶ ሲመለስም ወርቅነሽ ሜልሜላ ከሳጥኑ የቀኝ ጠርዝ አቅራቢያ በቀጥታ መትታ አራተኛውን ጎል አስቆጥራለች። በቀላሉ የጎል ዕድል መፍጠራቸውን የቀጠሉት ኤሌክትሪኮች ከተመሳሳይ ቦታ ተመሳሳይ ሁለት ጎሎችን አከታትለው አስቆጥረዋል። በ65ኛው ደቂቃ ዓለምነሽ ደካማ የነበረው የጌዴኦ የመከላከል አደረጃጀትን አምልጣ በመውጣት ከቀኝ መስመር በቀጥታ ወደ ጎል የላከችው ኳስ አምስተኛ ሆኖ ሲቆጠር በ72ኛው ደቂቃ የዕለቱ ኮከብ ወርቅነሽ ሜልሜላ የግብ ጠባቂዋን መውጣት አይታ በጥሩ ሁኔታ የማሳረጊያውን፤ ለግሏ ደግሞ ሐትሪክ የሰራችበትን ግሩም ጎል አስቆጥራ ጨዋታው በኤሌክትሪክ 6ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል። ኤሌክትሪክ በድሉ ተጠቅሞ ከግርጌው በዝቅተኛ የጎል ዕዳ አንድ ደረጃ ከፍ ቢልም ከመውረድ ለመትረፍ ቀሪዎቹን ሁለት ጨዋታዎች አሸንፎ በአራት ነጥብ ከፍ ብለው የሚገኙትን ቡድኖች ውጤት ለመጠባበቅ እንደሚገደድ ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል ።አዲስ ዘመን ግንቦት 4/2011አብርሃም ተወልደ
https://www.press.et/Ama/?p=10671
364
2ስፖርት
«የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ክለብ ቀጣይነት በጥያቄ ምልክት ውስጥ ይገኛል» – ዋና ሱፐር ኢንቴንዳንት ሁሴን ሸቦ
ስፖርት
May 13, 2019
65
 ፡- እኔም አመሰግናለሁ። – ትልልቅ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት የተጀመረ እና ታዋቂ አትሌቶችም የተሳተፉበት ውድድር እንደመሆኑ በጥሩ ጎኑ እመለከተዋለሁ። ከአትሌቶች ብዛት አኳያም የተሻለ ነገር መኖሩን ታዝቤያለሁ። የሜዳ ተግባራትን ጨምሮ በተለያዩ ውድድሮች ላይ በፊት ጥቂት አትሌቶች ብቻ ተሳታፊ የነበሩባቸው ውድድሮች አሁን በበርካቶች ተፎካካሪነት ተካሂዷል። ይህ እንደ ቀላል ሊታይ ይችል ይሆናል፤ ለእኔ ግን አጃኢብ ነው፤ ምክንያቱም 10ሺ ሜትርን አራትና አምስት አትሌቶች ብቻ ሲሮጡ አስታውሳለሁ። አሁን ግን 50 እና 60 አትሌት ሮጦ የተሻለ ሰዓት ማስመዝገብ መቻል ትልቅ ነገር ነው። አሰልጣኝ የሆንኩት ባልተለመደ መልኩ፤ በ25ዓመቴ ነው። በኢት ዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያው ወጣት አሰልጣኝም ነኝ። ላለፉት 27ዓመታት በነበረኝ የአሰልጣኝነት ቆይታም፤ ዛሬ ለሀገራቸው በኦሊምፒክ፣ ዓለም ሻምፒዮና፣ መላ አፍሪካ ጨዋታዎችና በሌሎች ውድድሮች በ70 ሀገራት ተካፋይ ሆኛለሁ። ረዳት በመሆን በጀመርኩት ስልጠናም ከበርካታ ውጤታማ አትሌቶች ጋር ሰርቻለሁ። ዛሬ አመራር፣ አሰልጣኝ እና ሌሎች ሥራዎች ላይ ያሉ አትሌቶችን የማሰልጠን ዕድሉ ገጥሞኛል። ከቀድሞዎቹ እነ ብርሃኔ አደሬ፣ ጌጤ ዋሚ፣ ደራርቱ ቱሉ፣ ፋጡማ ሮባ፣ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ ዱቤ ጂሎ፣…ን መጥቀስ ይቻላል። መሃል ላይ ካሉት ጀግኖችም፤ ጥሩነሽ ዲባባ፣ ስለሺ ስህን፣ መሠረት ደፋር፣ ቀነኒሳ በቀለ፣ እጅጋየሁ ዲባባ፣ ገንዘቤ ዲባባን አሰልጥኛለሁ። ከአዳዲሶቹ አትሌቶች ደግሞ ሰለሞን ባረጋ፣ አንዱአምላክ በልሁ፣ ደራ ዲዳ፣ ሰምበሬ ተፈሪ፣ …ን በማሰልጠን ላይ እገኛለሁ። በርካታ ልዩነት አለ፤ በዚያን ጊዜ እንደ ባህል ተይዞ ይሰራ የነበረው የብሔራዊ ቡድን አትሌቶችን በማዕከል ይዞ ማሰልጠን ነው። አሁን ግን ስልጠናው በተበታተነ መልኩ፤ በክለብ፣ በግል እና በማናጀር ነው የሚሰጠው። በዚህ ወቅት አትሌቶች ካላቸው ብዛት አኳያ በተቀናጀ መልኩ ቢሰራ ውጤታማ መሆን ይቻል ነበር። ካጠቃላይ ዝግጅት እስከ ውድድር መባቻ ድረስ አንድ አትሌት ከአሰልጣኝ ጋር ሊለማመድ ካልቻለ በመካከ ላቸው መግባባት ሊኖር አይችልም። አሁን እንደሚደረገው በሳምንታት አሊያም በአንድና ሁለት ወራት ቆይታም የአንድነት ስሜቱን ማምጣት አይቻልም። እንደ ድሮ በብሔራዊ ቡድን ይሰባሰቡ ለማለትም አዳጋች ነው። ድሮ አዲስ አበባ ውስጥ የነበሩት ክለቦች ከስድስት አይበልጡም። አሁን የእነዚህ ክለቦች በተለይ በረጅም ርቀት ላይ ያላቸው ብቃት ወርዷል፤ በአንጻሩ ያሉት ደግሞ መቀመጫቸው በክልሎች ነው። ታዲያ እነዚህን አትሌቶች በብሔራዊ ቡድን አሰባስቦ ወደ ማዕከል እንዴት ማምጣት ይቻላል? ምክንያቱም የቤት ኪራይን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ወጪዎችን ይጠይቃል። ስለዚህም አትሌቶቹ ባሉበት ቦታ ነው ድጋፍና ክትትል ማድረግ የሚያስፈልገው። ውድድሮች ሲቃረቡም ወደ ማዕከል በማምጣት ማዘጋጀቱ የተሻለ ነው። ወጥ ያልሆነ ስልጠና የሚሰጥ ከሆነ ውጤቱ መዋዠቁ አይቀርም። የስልጠና ፕሪንሲፕሎችን ተከትለን መስራት ካልቻልን ውጤታማ መሆን አንችልም፤ ከአጠቃላይ ዝግጅት ጀምሮ እስከ ውድድር ወቅት ያለው ስልጠና ሳይንሳዊና ወጥ መሆን አለበት። ካልሆነ ግን ዛሬ ውጤታማ የነበረውን አትሌት ነገ በዚያ አቋሙ ልናገኘው አንችልም። እነ ኃይሌ በአንድ ሥርዓት በማለፋቸው ለ20ዓመታት መሮጥ ችለዋል። አሁን ግን አንድ አትሌት ከአንድ እና ሁለት ኦሊምፒክና ዓለም ሻምፒዮና በላይ አይታይም። አሁንም ወጥነት ያለው ስልጠና ከሌለ ብቅ ጥልቅ ማለቱ የሚቀጥል ነው የሚሆነው። ክለባችን ከባርሴሎና እስከ ሪዮ በኦሊምፒክ ወርቅ በማምጣት አንደኛ ደረጃ ላይ ነው የሚገኘው። ቀድመውት ከተመሰረቱት ክለቦችም የተሻለ ታሪክ አለው፤ አሁን ግን ያንን እያሳየ አይደለም። ከዚህ ቀደም ከሠራዊቱ በሚገኘው መዋጮ የተሰራ ሆቴል ነበር፤ ነገር ግን ባልታወቀ መንገድ በጳውሎስ ሆስፒታል ተወስዶብን አትሌቶቻችንን የምንደጉምበት አጥተን ሞራላችን በከፍተኛ ደረጃ ተነክቷል። ይህንኑ ለመንግሥት አቤት ብንልም እልባት አላገኘንም፤ በዚህም የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ክለብ ቀጣይነት በጥያቄ ምልክት ውስጥ ይገኛል። በዚህ ወቅት ምንም ዓይነት የገቢ ምንጭ የለንም፤ ከሠራዊቱ የወር ደመወዝ የሚገኝ አንድ ብር ላይ ተመስርተን ነው ያለነው። በመንግሥት በኩልም እገዛ ሊደረግለት የሚችልበት መንገድ አለ፤ እኛም እንደ ክለብ ተቆርቋሪነታችን እልባት የሚገኝበትን መንገድ መፈለግ የግድ ነው። የፌዴራል ማረሚያ ቤት ክለብ ወደቀ ማለት ደግሞ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ግማሽ ክፍል ወደቀ እንደማለት ነው። የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ፣ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እንዲሁም ሌሎች የስፖርት ማህበራትን (ቦክስ፣ እጅ ኳስ፣ ቮሊቦል) ይመለከታል። ነገር ግን አሁን ምንም እየተደረገልን አይደለም፤ እነ ደራርቱ ቱሉን፣ ፋጡማ ሮባን፣ ስለሺ ስህንን፣ ጥሩነሽ ዲባባን፣ ሰንበሬን ተፈሪን፣ ዱቤ ጂሎን፣ ቁጥሬ ዱለቻን፣ ገለቴ ቡርቃን፣ ንጉሴ ጌቻሞን፣ … ያፈራ ክለብ ዛሬ ሊቆም ነው። እነ አበበ ቢቂላን፣ ማሞ ወልዴ፣ ምሩጽ ይፍጠር፣ አዲስ አበበ፣ ቲኪ ገላና፣ ጸጋዬ ከበደ፣ ኢማና መርጋ፣ ሙክታር እድሪስ፣…ን ያፈራው መከላከያ አሁን ብዙም እየታየ አይደለም። እነ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በላይነህ ዴንሳሞ፣ ፊጣ ባዪሳ፣ ወርቁ ቢቂላ፣ ብርሃኔ አደሬ፣ ጌጤ ዋሚ፣ ከበደ ባልቻ፣ ሂርፓሳ ለሚ፣…ን ያፈራው ኦሜድላም ደብዛው ጠፍቷል። እንደ አንድ ባለሙያ በጣም ይቆጨኛል፤ መንግሥትም ለምን ዝም እንዳለ አልገባኝም። አሁን ስፖርትና ስፖርተኛ የተገናኘበት ወቅት ነው። ፌዴሬሽኑ በባለሙያዎች ተደራጅቷል፤ ጠንክረው የሚሰሩ ከሆነም ትልቅ አጋጣሚ ነው የሚሆንላቸው። ፕሬዚዳንቷን ኮሎኔል ደራርቱ ቱሉን ጨምሮ እነ ገብረእግዚአብሔር ገብረማርያም፣ ዶ/ር በዛብህ ወልዴ፣ አቶ አድማሱ ሳጂ፣ ስለሺ ስህን እና መሠረት ደፋር በሥራ አስፈጻሚው ውስጥ መኖር ጥሩ አጋጣሚ ነው። ይህንንም መጠቀም ይገባል፤ በማንም ማሳበብ የማንችልበት ወቅት ላይ ነን። ደራርቱ በዴንማርኩ ውድድር ወቅት የአመራርና የማቀናጀት ሥራዋ አስደናቂ ነበር። ሁላችንም ተባብረን የምንሰራ ከሆነም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ትንሳኤ አሁን ነው። ለአትሌቶች በርካታ የውድድር ዕድል እንዲያገኙ የሚያመቻችላቸው መሆኑን በበጎ ጎኑ እመለከተዋለሁ። ከ25 ዓመታት በፊት የነበረውን ብናስታውስ ደግሞ ቤትና መኪና ያላቸው አትሌቶች ሁለት ብቻ ነበሩ፤ አሁን ተቆጥረው አያልቁም። ከራሳቸውና ከቤተሰቦቻቸው አልፈው ተቋማ ትን በመክፈትም ለሌሎች ዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠር ላይ ነው የሚገኙት። ይህንን ያመጣው ደግሞ ከአትሌቶችና አሰልጣኞች ጥረት ባሻገር የማናጀሮች ዕድሉን ማመቻቸት ነው። ይሁን እንጂ የሀገር ፍቅር እና የአንድነት ስሜት ቀንሷል። የአሁኖቹ አትሌቶች ሀገራቸውን አይወዱም ማለት ሳይሆን በተግባር የሚታይ ነገር ተቀዛቅዟል። በፊት እነ ኃይሌ፣ ቀነኒሳና ጥሩነሽ ካሉ ወርቅ አለ በሚል ነበር የሚጠበቀው። አሁን ግን እንደዛ ዓይን ውስጥ ሊገባ የሚችል አትሌት ስለመኖሩ የማንተማመንበት ደረጃ ላይ በመድረሳችን ይህንን መጠበቅ ይከብዳል። ቀድሞ የዓለም ክብረወሰኖች እና ፈጣን ሰዓቶች ይመዘገቡ የነበሩት በኢትዮጵያውያን በመሆኑ መተማመን ይቻል ነበር። አሁን ማረጋገጫ የለም፤ ውድድሮችም የሉም። አትሌቶችም ቢሆኑ 5ሺ እና 10ሺ ሜትርን ሳይሮጡ ወደ ማራቶን ይገባሉ፤ በያዙት ርቀትም ብዙ አይቆዩም። ለዓለም ሻምፒዮና የቀረን አራት ወር ብቻ ነው፤ አትሌቶች አሁኑኑ ካምፕ ገብተው ካልተዘጋጁ ተዓምር ካልተፈጠረ ድረስ ለመገመት አስቸጋሪ ነው። የአሰልጣኞችን መብት ከማስከበር ባሻገር በስልጠና፣ በውድድር እንዲሁም በምልመላ ላይ እገዛ እናደርጋለን። አሰልጣኞች በዘመናዊ ትምህርትም ራሳቸውን እንዲያበቁ ከክልሉ ፌዴሬሽን ጋር በመሆን አጫጭር ኮርሶች እንዲሰጥ እያደረግን ነው። በኢትዮጵያ ታሪክ ከአትሌቲክስ የሚወዳደር ስፖርት የለም። መላው የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት አትሌቲክሳችንን በእንክብካቤ መያዝ ይገባናል። ውድድር ሲደርስና ውጤት ሲጠፋ ብቻ መጮህ የለብንም። አትሌቶች የት ነው ያሉት፣ ክለቦችና አሰልጣኞችስ ምን እየሰሩ ነው በማለት ክትትል ማድረግ ተገቢ ነው። በመጨረሻም ለዓለም ሻምፒዮናው እና ቶኪዮ ኦሊምፒክ ጥሩ ዕድል እንዲገጥመን ከወዲሁ እመኛለሁ።አዲስ ዘመን ግንቦት 5/2011 ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=10708
886
2ስፖርት
የሊጉ የዋንጫ ትንቅንቅ ምዕራፍ ተገልጧል
ስፖርት
May 14, 2019
49
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2011 ዓ.ም ዋንጫ መቋጫውን ሊያገኝ በጣት የሚቆጠሩ ጨዋታዎች ቀርተዋል። ይሁንና እንደወትሮው ሻምፒዮን የሚሆነው ክለብ ከወዲሁ ለመጠቆም አልተቻለውም። ተፋላሚ ክለቦችም የሊጉ ሻምፒየን ለመሆን ብርቱ ትንቅንቅ እያደረጉ ይገኛሉ። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 24ኛ ሳምንት መርሐ ግብርም ካሳለፈነው አርብ ጀምሮ በሳምንቱ የእረፍት ቀናት በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች ተካሂዷል፤ በዚህም ከአንድ እስከ ሶስት የተቀመጡት ክለቦች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2011 ዓ.ም የሊግ ዋንጫ ዋነኛ ተፋላሚ ስለመሆናቸው አስመስክረዋል። የዚህ ሳምንት መርሃግብር ባሳልፈነው አርብ ሲጀመርም፤ ወደ ትግራይ በማቅናት ስሁል ሽረን የገጠመው ኢትዮጵያ ቡና ያልተጠበቀ ሽንፈት ገጥሞታል። ቡናዎች ባለፉት አምስት ጨዋታዎች በወላይታ ድቻ፣ በአዳማ ከተማና በስሁል ሽሬ ሲሸነፉ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ነጥብ ተጋርተው፤ አዲስ አበባ ላይ ባህር ዳር ከተማን አስተናግደው አምስት ግቦችን በማስቆጠር ማሸነፋቸው ይታወሳል። ሊጉ ወጥ የሆነ አቋም ማሳየት ያልሆነለት የ2003ቱ የሊጉ ሻምፒዮን ኢትዮጵያ ቡና ምንም እንኳን በሁለተኛው ዙር አሰልጣኝ በመቀየር ለሊጉ ሻምፒዮንነት ብርቱ ትንቅንቅን ቢያደርግም፤ ባለፉት አምስት ጨዋታዎች የጣላቸው ነጥቦች የዋንጫ ጉዞውን አጨናግፍውበታል። አሁን ላይ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ በ33 ነጥብ ስምንተኛ ላይ የተቀመጠው ኢትዮጰያ ቡና፣ ከመሪው መቀሌ ያለው የነጥብ ልዩነት 15 መሆኑም የሻምፒዮንነት ጉዞው የተጨናገፈ ሰለመሆኑ ምስክርን ሰጥቷል። በሊጉ ሁለተኛ ምዕራፍ ተሽለው የታዩትና በተለይ በ20ኛው ሳምንት አዳማ ከተማ 2ለ1 እንዲሁም በ22ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ሀዋሳ ከተማን ሳይጠበቅ አራት ለዜሮ ያሸነፉት ስሁል ሽሮች፤ በዚህ ሳምንት ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡናን አንድ ለዜሮ ማሸነፋቸውን ተከትሎ በተለይ በሊጉ ሰንጠረዥ ከግርጌ ለመውጣት በሚያደርጉት ትንቅንቅ ከፍተኛ መነቃቃትን አግኝተዋል። ደረጃቸውን በማሻሻል በሊጉ ለመቆየት አንድ እርምጃን የሚያራምዳቸው ሆኗል። መርሃ ግብሩ ባሳለፈነው ቅዳሜ ሲቀጥል ወላይታ ዲቻን ከደደቢት ለማገናኛት ቀጠሮ ቢይዝም፤ በእንግዳው አለመገኘት ጨዋታው ሳይካሄድ ቀርቷል። በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ግርጌ ላይ የሚገኘው ደደቢት ከፋይናንስ ችግር ጋር በተገናኘ ከ24ኛ ሳምንት የሊጉ መርሃ ግብር አንስቶ በሊጉ እንደማይቀጥል ለኢትዮጰያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ደብዳቤን ማስግባቱን ተከትሎ ወላይታ ዲቻዎች ጨዋታውን አሸንፈው፤ ከሶስት ነጥብ ተቀዳጅተዋል። ከዚህ ባሻገር ከጨዋታው ውጤት 3 ንጹህ ጎል ማግኘታቸው ያልታሰበ ሲሳይ ሆኖላቸዋል። ነጥባቸውን 27 ከፍ በማድረግ በደረጃ ሰንጠረዡ 12 ላይ ተቀምጠዋል። የ24ኛው ሳምንት መርሃ ግብር ተጠባቂ ፍልሚያ አዋሳ ላይ የሲዳማ ቡና ከመቀሌ 70 እንደርታ አፋልሟል። ሁለቱ ክለቦች እርስ በእርስ ከመገናኘታቸው ቀድሞ በሃያኛው ሳምንት ከጣና ሞገዶቹ ሽንፈት በኋላ አዳማ ከተማን 2 ለ 1 በመርታት ወደ አሸናፊነት የተመለሱት መቀሌዎች፤ በ22ኛ ሳምንት በፈረሰኞቹ የአንድ ለዜሮ ሽንፈት ሲያስትናግዱ፤ ባሳልፈነው ሳምንት መርሃ ግብርደግሞ በትግራይ ደርቢ ስሁልን በመፋለም የጨዋታው አሸናፊ መሆናቸው ይታወሳል። ሲዳማዎች በአንፃሩ፤ በዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር አስደናቂ ብቃትና ውጤት በማስመዝገብ የሊጉ መሪ እስከመሆን በቅተው የነበሩት ሲዳማ ቡናዎች ምንም እንኳን በሁለተኛ ዙር ላይ መዳከም ቢያሳዩም፤ አሁን ላይ ይህን ድክመታቸውን እያረሙ የመጡ መስለዋል። በተለይ በሃያኛ ሳምንት በቅዱስ ጊዮርጊስ ለደረሰበት ሁለት ለዜሮ ሽንፈት መቀሌዎችን በቅርብ ርቀት የሚከተልበትን እድል ቢያመክንባቸውም፤ በ21ኛ ሳምንት ስሑል ሽረን 3ለ2 በማሸነፉ ወደ ሊጉ ፉክክር ተመልሰዋል። ይሁንና በቀጣዩ መርሃ ግብር በአምናው የሊጉ ሻምፒዮን ሽንፈት ማስተናግድ ግድ ብሏቸዋል። ሆኖም ግን ባሳልፈነው ሳምንት መርሃ ግብር ሃዋሳን ያስተናገዱት ሲዳማዎች ድል ከእነርሱ ጋር ሆናለች። ጨዋታውንም አንድ ለዜሮ ማሸነፍ የቻሉ ሲሆን፣ ይህም ነጥባቸው 40 በማድረስ ደረጃቸውንም ወደ ሶስተኛ ከፍ እንዲያደርጉ አስችሏቸዋል። የዚህ ሳምንት የሊጉ መርሃግብር እነዚህ ሁለት ክለቦች ሲያገናኝም፤ ሁለቱ ከለቦች በአንደኛና በሶስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጣቸውም ጨዋታውን ይበልጥ ተጠባቂ አድርጎታል። በሊጉ የሻምፒዮና ጉዞ ላይ የሞት ሸረት ትግል እያደረጉ የሚገኙት ሁለቱ ክለቦች መካከል የተካሄደው ፍልሚያም ባለሜዳዎቹ ሲዳማዎች 2ለ1 አሸናፊነት ተጠናቋል። ግቡን ሃብታሙ ገዛህኝና አዲስ ግደይ ለሲዳማ፤ አማኑኤል ገብረሚካኤል ደግሞ ለመቀሌ አስቆጥረዋል። ከሜዳው ወጪ ያደረጋቸውን ጨዋታዎች ለማሸነፍ የሚቸግረው መቀሌ ከሃያኛው ሳምንት ጨዋታዎች በኋላ ያለውን ስንመለከት እንኳን በባህር ዳር፣ በቅዱስ ጊዮርጊስና በሲዳማ ቡና ተሸንፏል። በተለይ ከወልዋሎ ጋር በሜዳው ነጥብ መጣሉ ከተከታዮቹ ጋር የነበረውን የነጥብ ልዩነት አስጠብቆ እንዳይጓዝ አድርጎቷል። ከተከታዩ ፋሲል ከነማ የነበረው የአምስት ነጥብ ልዩነትም አሁን ላይ ወደ ሁለት ዝቅ ሲል፤ ሲዳማዎችም በአምስት ነጥብ ዝቅ ብለው ይከተሉታል። የዚህ ሳምንት መርሃ ግብር በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ሁለተኛ የሚገኘው ፋሲል ከነማ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ አገናኝቷል። በሃያኛው ሳምንት የሊጉ መርሃ ግብር በዐፄ ፋሲለደስ ስታዲየም ከደቡብ ፖሊስ ጋር ነጥብ በመጋራት የሊጉን መሪ በቅርብ ርቀት የመከታላቸውን ሩጫ ያቀዘቀዙት ፋሲሎች፤ በቀጣዩ አዲስ አበባ ላይ መከላከያ አራት ለዜሮ፤ በ22ኛው ሳምንት በሜዳቸው ድሬዳዋ ከተማን አስተናግደው 2 ለ 0 ማሸነፍ ችለዋል። ባሳለፍነው ሳምንት የሊጉ ፍልሚያም ደደቢትን አስተናግደው በሰፊ የግብ ልዩነት ባለድል መሆናቸው ይታወሳል። ቢጫ ሰርጓጆቹ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች በአንፃሩ፤ በአዲሱ አስልጣኝ እየተመሩ በሊጉ ሁለተኛ ዙር ድንቅ አቋም ውጤት በማሳየት ላይ ይገኛሉ። ያለፉት አራት ጨዋታዎቻቸውን ስንመለከትም፤ በሃያኛው ሳምንት አዲስ አበባ ላይ መከላከያን አንድ ለዜሮ አሸንፈዋል። በ21ኛው ሳምንት በድሬዳዋ ሁለት ለአንድ ሲሸነፉ፤ በቀጣዩ መርሃ ግብር ደደቢትን ሁለት ለዜሮ ድል አድርገዋል። ባሳልፈነው ሳምንት ጨዋታም ከአምናው ሻምፒዮን ጅማ አባጅፋር ጋር ተፋልመው ነጥብ ተጋርተዋል። የዚህ ሳምንት መርሃ ግብር ሁለቱ ክለቦች ሲያገናኝም፤ በሊጉ የሻምፒዮና ጉዞ ላይ የሞት ሸረት ትግል እያደረጉ የሚገኙት አፄዎቹ ባለድል ሆነዋል። በበዛብህ መለዩ ግብ ባለድል የሆኑት አፄዎቹ፣ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ከመሪው መቀሌ በሁለት ነጥብ ዝቅ ብለው በ46 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። በዚህ ሳምንት መርሃ ግብር የመቀሌዎች መሸነፍ፣ ፋሲልና ሲዳማ ደግሞ ማሸነፍ በሶስቱ ክለቦች መካከል የሊጉን የዋንጫ ትንቅንቅ ምዕራፍ በይፋ ከፍቶታል።ሌላኛው የዚህ ሳምንት መርሃ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስን ከደቡብ ፖሊስ አገናኝቷል። ባሳልፈነው የሊጉ መርሃ ግብርም በሸገር ደርቢ ኢትዮጵያ ቡናን አስተናግደው ነጥብ የተጋሩት ፈረሰኞቹ በዚህ ሳምንቱ ጨዋታም ነጥብ መጋራታቸውን ተከትሎ በሊጉ የሻምፒዮንነት ትንቅንቅ ጉዟቸው ላይ ቀዝቃዛ ውሃን ቸልሶባቸዋል። ፈረሰኞቹ በጨዋታው ያሳዩት ደካማ አቋም በበርካቶች ዘንድ አስተችቷቸዋል። ባሳልፈነው ሳምንትም አዳማን በሜዳውና በደጋፊያቸው ፊት ሁለት ለዜሮ በማሸነፍ ወደ አሸናፊነታችው የተመለሱት ደቡብ ፖሊሲች ከሊጉ የምንጊዜም ሻምፒዮን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ ነጥብ ተጋርተው መውጣታቸው ከሊጉ ግርጌ ለመውጣት የሚያደርጉትን ጥረት አሳምሮላቸዋል። ፈረሰኞቹ በሊጉ ሰንጠረዥ በ39 ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጡ ደቡብ ለፖሊሶች በ24 ነጥብ አስራ አራተኛ ደረጃን ይዘዋል። የዓምናው የሊጉ ሻምፒዮን ጅማ አባጅፋርን ከሀዋሳ ከተማ ያገናኘውም ሌላኛው የዚህ ሳምንት ተጠባቂ ጨዋታ ነበር። የዓምናው የሊጉ ሻምፒዮን ጅማ አባጅፋሮች በሊጉ የሁለተኛ ዙር ድንቅ አቋም በማሳየት ላይ ይገኛሉ። ከሃዋሳው ጨዋታ ቀድሞ ካለፉት አራት ጨዋታዎች ሶስቱን ሲያሸንፍ፤ በአንዱ ነጥብ ተጋርቷል። በሃያኛው የሊጉ መርሃ ግብር ላለመውረድ የሚታገለው ስሁል ሽሬ ሁለት ለዜሮ እንዲሁም በ21ኛ ሳምንት ደደቢትን እንዲሁም በ22ኛ ሳምንት ሲዳማን በማሸነፍ ወደ ሻምፒዮናው ፉክክር መጠጋት ችለዋል። ይሁንና ባሳለፍነው ሳምንት ወልዋሎን አስተናግደው ነጥብ መጋራታቸው በዋንጫው ፍልሚያ ሩጫቸው ላይ መቀዛቀዝን ፈጥሮባቸዋል። ጅማዎች በዚህ ጨዋታ ከሊጉ የዋንጫው ትንቅንቅ ላለመራቅ የሚያስቸላቸውን ውጤት ማስመዝገብ እንደሚችሉ ቢገመትም፤ አሽንፈው ሶስት ነጥብ ማግኘት አልሆነላቸውም። ጨዋታውም አንድ አቻ ተጠናቋል። ግቦቹን ለባለሜዳዎቹ ኦኪኪ አፎላቢ ለሃዋሳዎች ደግሞ ዳንኤል ደርቤ አስቆጥረዋል። የአምናው የሊጉ ሻምፒዮን በሜዳው ያገኘው ውጤትም ነጥቡን ከፍ በማድረግ ወደ መሪዎቹ ክለቦች የሚጠጋበትን እድል አሳጥቶታል። ሌላኛው መርሃ ግብር ባህርዳር ከተማ ከድሬዳዋ አገናኘቷል። በሁለተኛው የሊጉ መርሃ ግብር የጣና ሞገዶቹ አቋም ተዳክሞ እየታየ ይገኛል፤ በተለይ በኢትዮጰያ ቡና የደረሰባቸው የ5 ለ0 አስደንጋጭ ሽንፈትና በሜዳና በደጋፊያቸው ፊት ከደቡብ ፖሊስ ጋር ሶስት አቻ የተለያዩበት ጨዋታ በርካታ ደጋፊዎቻቸውን አስከፍቷል። በተለይ የተከላካይ ክፍሉ ደካማ ሆኖ መታየት ክለቡን ዋጋ እያስከፈለው መሆኑ ተስተውሏል። ክለቡ ባሳልፈነው ሳምንት ከወራጅ ቀጣና ለመራቅ በሚታገለው መከላከያ መሸነፉም ደግሞ፤ በሊጉ የዋንጫ ፍልሚያ ላይ ያደርግ የነበረውን ግስጋሴ ይበልጡን አደናቅፎበታል። ክለቡ በተለይ ያለፉት ሶስትና አራት ጨዋታዎች ያስመዘገበው ውጤት ተከትሎም በሊጉ የሻምፒዮንነት ትንቅንቅ ከመሪዎቸ ተርታ እየራቀ እንዲሄድ አስገድዶታል። በሃያኛው መርሃ ግብር ደደቢትን ሶስት ለሁለት በማሸነፍ በቀጣዩ መርሃ ግብር ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 2ለ1 በመርታት ተከታታይ ድል ማስመዝገብ የቻሉት ድሬዳዋዎች፤ ምንም እንኳን በ22ኛው ሳምንት በአፄዎቹ የሁለት ለባዶ ሽንፈት ቢቀምሱም፤ ባሳልፈነው ሳምንት ወላይታ ድቻን አስተናግደው ሁለት ለዜሮ በማሸነፍ ወደ ድል መመለሳቸው ይታወሳል። የጣና ሞገዶች በውጤት ቀውስ ውስጥ ሆነው የድል ጉዞን በማድረግ ላይ የሚገኘውን ድሬዳዋን የገጠሙ ሲሆን፣ ጨዋታውም በባለሜዳዎቹ የሁለት ለአንድ አሸናፊነት ተጠናቋል። የጣና ሞገዶቹ ከሽንፈታቸው አገግመው ወደ አሸናፊነታቸው የሚመልሳቸውን ውጤት ሲያስመዘግቡም ወሰኑ አሊና ዳግማዊ ሙሉጌታ የግቦቹ ባለቤት ሆነዋል። ድሬዳዋን ከመሸነፍ ያላዳነችውን ግብ ኤርምያስ ሃይሉ አስቆጥሯል። ሌላኛው የዚህ ሳምንት መርሃ ግብር አዳማን ከመከላከያ አገናኝቷል። በሊጉ የዋንጫ ፍልሚያ ወጥ የሆነ አቋም ማሳየት ከሚሳናቸው ቡድኖች አንዱ የሆነው አዳማ ከመቐለ 70 እንደርታ ከደረሰበት የ2 ለ 1 ሽንፈት በኋላ፤ በ22ኛ ሳምንት የሊጉ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ቡናን በማስተናገድ አንድ ለዜሮ ማሸነፍ ቢችሉም፤ በቀጣዩ ጨዋታ ሽንፈትን ማስተናገዳቸው ይታወሳል። መከላከያ በአንፃሩ በሁለተኛው የሊጉ ምዕራፍ ወጥ አቋም ማሳየት ተስኖት አሰልጣኙን እስከማሰናበት ተሻግሯል። በሃያኛው ሳምንት ወደ መቐለ ተጉዞ በወልዋሎ እንዲሁም በ21ኛው ሳምንት በፋሲል ተሸንፏል። ክለቡ ወቅታዊ አቋም እያደር መዋዠቅና በውጤት ቀውስ ላይ መሆኑን ተከትሎም የመውረድ አደጋ እንደተጋረጠበት ሲነገር ቆይቷል። ይሁንና ክለቡ ያለፉት ሁለት ጨዋታዎች ላይ ያሳየው አቋምና ድል ግን ምናልባትም ስጋቶቹን ሁሉ ከንቱ ሊሆኑ እንደሚችል አስመስክሯል። በውጤት ቀውስ ወደ ሊጉ ግርጌ የሚንደረደረው አዳማ ከሊጉ ግርጌ ለመውጣት ከሚጣጣረው መከላከያ ጋር ያገናኘው የዚህ ሳምንት ጨዋታም በአቻ ውጤት ተጠናቋል። በዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የደረጃ ሰንጠረዥ መቐሌ ሰባ እንደርታ አርባ ስምንት ነጥቦች በመሰብሰብ በቀዳሚነት ይመራል። ፋሲል ከነማ በአርባ ስድስት በሁለተኛነት ሲከተል፤ ሲዳማ ቡና በአርባ አምስት ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። የሊጉን ወራጅ ቀጣና ስንመለከት፤ ደቡብ ፖሊስ በ24 ነጥብ አስራ አራተኛ፣ ስሁል ሸረ በ22 ነጥብ አስራ አምስተኛ እንዲሁም ደደቢት በ10 ነጥብ የመጨረሻውን ደረጃ ይዘዋል። የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን ፉክክር የመቐሌው አማኑኤል ገብረሚካኤል በአስራ አምስት ግቦች፣ የሲዳማ ቡናው አዲስ ግደይ በአስራ ሶስት እንዲሁም የመከላከያው ምን ይሉህ ወንድሙ በአስራ አንድ ግቦች ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ ይዘዋል።አዲስ ዘመን ግንቦት 6/2011 በ
https://www.press.et/Ama/?p=10772
1,306
2ስፖርት
የክለቦች ሕጋዊነት ፍቃድ በመጪው ዓመት ይሰጣል
ስፖርት
May 13, 2019
21
ኢትዮጵያ በክለብ ፈቃድ አሰጣጥ ጠንክራ መስራት እንደሚገባት የካፍ ክለብ ፈቃድ አሰጣጥ ማናጀር አስታወቁ። በቀጣዩ የውድድር ዓመት ሁሉም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ ክለቦች የሕጋዊነት ፈቃድ የምስክር ወረቀት ለመጀመር ዝግጅት መጠናቀቁን ፌዴሬሽኑ ገልጿል። ኢትዮጵያ በክለብ ፈቃድ ጠንክራ መስራት እንደሚገባት በተደጋጋሚ ቢገለጽም፤ አሁንም ብዙ መስራት እንደሚጠበቅ የካፍ ክለብ ፈቃድ አሰጣጥ ማናጀር አህመድ ሃራዝ ማሳሰባቸውን ፌዴሬሽኑ በድረ ገጹ አስነብቧል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንም በ2012 ዓ.ም የውድድር ዓመት በፕሪሚየር ሊጉ ተሳታፊ የሚሆኑት 16ቱም ክለቦች ለሀገር ውስጥ መወዳደሪያ የሚያገለግል የሕጋዊነት ፍቃድ ማግኘት እንዳለባቸው አስታውቋል። ለዚህም ዝግጅቱ በመጠናቀቅ ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ እስከ ግንቦት 30/2011ዓ.ም ክለቦች ፊት ለፊት ግምገማ ለማድረግ መታቀዱን በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የክለብ ፈቃድ አሰጣጥ ማናጀር አቶ ተድላ ዳኛቸው ጠቁመዋል። ፍቃዱን ለማግኘት ክለቦች አምስት መስፈርቶችን ማሟላት እንደሚጠበቅባቸው ድረገጹ አስነብቧል። መስፈርቶቹም፤ የመወዳ ደሪያ ቦታ መያዝ፣ የወጣቶች ልማት፣ የሰው ሀብት አስተዳደራዊ መዋቅር፣ የፋይናንስ ሥርዓት (የገቢ እና ወጪ ሥርዓት) እንዲሁም ሕጋዊነት መስፈርት ናቸው። ነገር ግን ሁሉንም መስፈርት በአንዴ ማሟላት ክለቦችን እስከማፍረስ የሚያደርስ በመሆኑ፤ አንዳንድ ነገሮችን በስትራቴጂክ እቅድ በመያዝ ተግባራዊ መድረግ አስፈላጊ እንደሆነም ነው ፌዴሬሽኑ ያረጋገጠው። በተጠናቀቀው ወር በኡጋንዳ ካምፓላ በካፍ ባለሙያዎች ከየሀገራቱ ለተውጣጡ ተወካዮች ሥልጠና ተሰጥቷል። በዚህ ሥልጠና ላይም ሀገራቱ ለሁለት ተከፍለው ከካፍ ክለብ ፈቃድ ኢንስትራክተሮች ጋር ውይይት ተደርጓል። ኢትዮጵያ በተደለደለችበት ምድብ ሁለትም ከናይጄሪያ እና ጋና ኢንስትራክተሮች ጋር ግምገማ እና ውይይቱ ተካሂዷል። በወቅቱም ፌዴሬሽኑ ዕቅዱን ያቀረበ ሲሆን፤ በአህጉር አቀፍ ውድድር ተካፋይ ክለቦች ፍቃድ መሰጠቱም ተጠቁሟል። ይሁን እንጂ በሀገራዊ ፍቃድ ላይ የጥሪ ሂደት ቢተላለፍም ፍቃድ አልተሰጠም። በተጨማሪም የመጀመሪያ ውሳኔ ሰጪ አካል መቋቋሙን፤ በተለይም የሕግ እና የሂሳብ ባለሙያ ያሉት እንደሆነ ተጠቅሷል። የይግባኝ ሰሚ አካሉም ከዚህ በፊት የተቋቋመ ቢሆንም በዚህ ወቅት አባላቱ የሌሉ መሆኑን ተከትሎ በተደራቢነት እንዲሰራ ሃሳብ መኖሩ ተነስቷል። በተሰጠው አስተያየት ላይም ሀገሪቷ ከክለቦች ፈቃድ አሰጣጥ ባሻገር የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴው በድጋሚ መደራጀት እንዳለበት ተጠቁሟል። በስትራቴጂክ ፕላን በመጠቀምም ከፕሪሚየር ሊጉ በመቀጠል በከፍተኛ ሊግ እና በተዋረድ ባሉ ሊጎች ላይ መስራት እንደሚገባ ማናጀሩ ገልጸዋል። እስከ ሰኔ 23/2011 ዓ.ም ድረስም የሚታይ ሥራ መከናወን እንዳለበት አሳስበዋል።አዲስ ዘመን ግንቦት 5/2011 ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=10711
296
2ስፖርት
ሻምፒዮናው በአዳዲስ ክብረ ወሰኖች 
ስፖርት
May 14, 2019
27
የ48ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሳምንቱ መጨረሻ ፍፃሜውን አግኝቷል። በሻምፒዮናው ፍፃሜም የተለያዩ ክብረ ወሰኖች ተመዝግበዋል። በመዝጊያው ቀን በተካሄደው የወንዶች የ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ጌትነት ዋለ ከኢትዮጵያ ወጣቶችና ስፖርት አካዳሚ ቀዳሚ በመሆን አጠናቋል፡፡ አትሌቱ ውድድሩን ለማጠናቀቅ የወሰደበት ሰዓትም 8:29.09 ሆኖ ተመዝግቧል። ታከለ ንጋቴ ከአማራ ማረሚያ 8:31.32 በሆነ ሰዓት ሁለተኛ ሲሆን፤ ተስፋዬ ድሪባ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሶስተኛ ሆኖ አጠናቋል። አትሌት ተስፋዬ የገባባት ሰዓትም 8:32.20 ሆኖ ተመዝግቧል። በወንዶች መካከል በተካሄደው 4 በ400 ሜትር ዱላ ቅብብል፣ ኦሮሚያ ክልል 3:08.03 በሆነ ሰዓት አንደኛ በመሆን የወርቅ ሜዳሊያ ሲያገኝ፤ የኢትዮጵያ ወጣቶችና ስፖርት አካዳሚ 3:13.60 በሆነ ሰዓት የብር እንዲሁም ዘቢዳር ቢራ ፋብሪካም 3:13.93 በሆነ ሰዓት የነሃስ ሜዳሊያ አግኝተዋል። በእለቱ ከታዩት ውድድሮች ከፍተኛ ግምት ያገኘውና እስክ መጨረሻው ዙር ብርቱ ፉክክር ያስተናገደው በሁለቱም ፆታዎች መካከል የተካሄደው የአምስት ሺህ ሜትር ውድድር ነው። በተለይ በወንዶች መካከል የተካሄደው ውድድር እስከመጨረሻው ድረስ እልህ አስጨራሽ ፉክክር የታየበት ሲሆን፤ የሃዋሳ ከተማው አትሌት ጥላሁን ሃይሌ በበላይነት አጠናቆታል። አትሌቱ የገባባት ሰዓትም 13:36.21 ሆኖ ተመዝግቧል። የአማራ ማረሚያው አትሌት አቤ ጋሻው 13:40.02 በሆነ ሰዓት ሁለተኛ ሆኗል። አትሌት ገመቹ ዳዲ ከኦሮሚያ ክልል ሶስተኛ ሆኖ ያጠናቀቀ ሲሆን፤ ውድድሩን ለማጠናቀቅ የፈጀበት ሰዓትም 13:46.42 ሆኖ ተመዝግቧል። የ10ሺህ ሜትር እርምጃ በወንዶችና በሴቶች ፌዴራል ማረሚያ ቤት የበላይ ሆኗል። በሴቶች መካከል የተካሄደውን ውድድር የፌዴራል ማረሚያ ቤት አትሌቷ የኋልዬ በለጠው፣ ሪከርድ በመሰበር ቀዳሚ ሆናለች። ማሬ ቢተው፣ አማራ ክልል፣ ሁለተኛ ስትሆን፤አይናለም እሸቱ፣ ከፌዴራል ማረሚያ ሶስትኛ ሆና አጠናቃለች። በወንዶች መካከል የተካሄደውን ውድድር፤ የፌዴራል ማረሚያ ዮሐንስ አልጋው፣ ክብረ ወሰን በሆነ ሰዓት ቀዳሚ ሲሆን፤ የአማራ ክልሏ ታድሎ ጌጡ፣ ሁለተኛ፤ የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲው ቢራራ አለም፣ ሶስትኛ ሆኗል። 1ሺህ 500 ሜትር ሴቶች ለምለም ኃይሉ ከሃዋሳ ከተማ አንደኛ ሆናለች። የገባችበት ሰዓት 4:18.31 ሆኗል። የሱሉልታ ከተማዋ አትሌት አዳነች አንበሳ፣ 4:19.32 በሆነ ሰዓት ሁለተኛ ስትሆን፤ መልካም አለማዬሁ፣ ከመከላከያ፣ 4:19.66 በሆነ ሰዓት ሶስትኛ ደረጃን ይዛለች። በወንዶች ጦር ውርወራ ኡቶ ኦኬሎ ከሲዳማ ቡና 69 ነጥብ 30 ሜትር በመወርወር አንደኛ ሆኗል። ኡባንግ ኡባንግ ከመከላከያ 68 ነጥብ 14 ሜትር በመወርወር ሁለተኛ ሲሆን ከረዩ ቡላላ ከ ኦሮሞያ ክልል፣ 66.71 ሜትር በመወርወር ሶስተኛ ሆኗል። የ48ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኦሮሚያ በወንዶች አጠቃላይ ሻምፒዮና ሲሆን መከላከያና ሲዳማ ቡና ሁለተኛና ሶስተኛ ሆነዋል። መከላከያ በሴቶችና የውድድሩ አጠቃላይ አሸናፊ ሲሆን፤ ኦሮሚያና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተከታዩን ደረጃ አግኝተዋል። በዚህ ዓመት ሻምፒዮና ዘጠኝ አትሌቶች ክብረ ወሰን ማሻሻላቸው ታውቋል። አዲር ጉር በስሉዝ ዝላይ፤ ዙርጋ ኡስማን በአሎሎ ውርወራ፤ ለተሰንበት ግደይ በ10 ሺህ ሜትር፤ ገበያነሽ ገደቻ በአራት መቶ ሜትር መሰናክል፤ አርያት ዲቦ በከፍታ ዝላይ፤ የኋልዬ በለጠው በ10 ሺህ ሜትር እርምጃ፤ ዩሃንስ አልጋው በ10 ሺህ ሜትር እርምጃ፤ ኡቶ አክሎ በጦር ውርውራ፤ዶኘ ሊም ክፍታ ዝላይ ክብረ ወሰን ያሻሻሉ አትሌቶች ሆነዋል። አምስት አትሌቶች ሁለት ወርቅ አግኝተዋል። ናታን አበበ በ100 እና 200 ሜትር፤ ገበያነሽ ጉዴቻ፤ በ100 እና በ400 ሜትር መሰናክል፤ አብዱረህማን አብዶ በ400 ሜትርና በ4 በ 400 መቶ ሜትር ሪሌ፤ ሰዓዳ ሲራጅ በ200 ሜትር፤ ሜትርና በ4 በ100 ሜትር ሪሌ፤ ኢብራሂም ጀማል፤ በ 110 ሜትር መሰናክልና እና 4 በ 100 ሜትር ሪሊ የድርብ ድል ባለቤት የሆኑ አትሌቶች ናቸው። በእለቱ ሪከርድ ያሻሻሉና ሁለት ወርቅ ያገኙ አትሌቶችን ጨምሮ አጠቃላይ አሸናፊዎች ከክብር እንግዶች የዋንጫና የብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የ48ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተካፋይ የሆኑና ሪከርድ ላሻሻሉ አትሌቶች ለእያንዳዳቸው የ10ሺህ ብር ሽልማት አበርክቷል፡፡አዲስ ዘመን ግንቦት 6/2011
https://www.press.et/Ama/?p=10775
475
2ስፖርት
አዲስ የብስክሌት ቱር ውድድር በኢትዮጵያ ይፋ ሆነ
ስፖርት
May 15, 2019
37
አዲስ አበባ፤- ከበርካታ ዓመታት በኋላ በሪዮ 2016 ኦሊምፒክ ኢትዮጵያን ወክሎ በብስክሌት ስፖርት መሳተፍ የቻለው ብስክሌተኛ ፅጋቡ ግርማይ በስፖርቱ አዲስ ነገር ይዞ ብቅ ብሏል፡፡ ፅጋቡ ከሌሎች ብስክሌተኞች ጋር በመሆን በአገራችን አዲስ የተባለውን የብስክሌት ቱር ውድድር በኢትዮጵያ የሚያዘጋጅ ካምፓኒ ማቋቋሙን አሳውቋል፡፡ “ኢትዮ ሳይክሊንግ ሆሊዴይስ” የተባለው ይህ ውድድር አዘጋጅ ካምፓኒ መቀመጫውን በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ ያደረገ ሲሆን፤ ዓለም አቀፍ የጎዳና ላይ የብስክሌት ውድድር እንደሚያዘጋጅ ታውቋል፡፡ ይህም የአገራችንን ብስክሌተኞች ጨምሮ ለመላው ዓለም የብስክሌት ስፖርት አፍቃሪዎች ሌላ አማራጭ እንደሚሆን ካምፓኒው ለዝግጅት ክፍላችን በላከው መረጃ አሳውቋል፡፡ “ይሄንን የብስክሌት ውድድር አዘጋጅ ካምፓኒ ማቋቋም የረጅም ጊዜ ህልሜ ነበር” ያለው ብስክሌተኛ ፅጋቡ ባለፉት ሁለት ዓመታት ይህንን ካምፓኒ እውን ለማድረግ አስፈላጊ ነገሮችን ከማሟላት ባሻገር የውጪ አገር ጎብኚዎች ትግራይ አካባቢ በሚደረጉ የብስክሌት ውድድሮች ግንዛቤ እንዲጨብጡ ማድረጉን ተናግሯል፡፡ በርካታ የብስክሌት ስፖርት አፍቃሪዎች አዲስ ውድድር ከመፈለጋቸው አኳያም ይህን ካምፓኒ በተገቢው ጊዜ አቋቁሞ ይፋ ማድረግ እንደተቻለ አብራርቷል፡፡ ካምፓኒው ወጣት ኢትዮጵያውያን ብስክሌተ ኞችን የማገዝ እቅድ እንዳለው የገለፀው ፅጋቡ፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ብስክሌተኛ እንዲሆን በርካቶች ድጋፍ እንዳደረጉለት አስታውሷል፡፡ አሁን ተራው የእሱ ሆኖም በር  ካታ ወጣት ኢትዮጵያውያን ብስክሌተኞችን ልምድ ከማጋራት ባለፈ የተለያዩ እድሎች እንዲፈጠሩላቸው እንደሚሰራ ተናግ ሯል፡፡ የካምፓኒው ትርፍ ግማሽ በግማሽም ወጣት ኢትዮጵያውያን ብስክሌተኞችን ለመደገፍ እንደ ሚውል አስታውቋል፡፡ ፅጋቡ ይህን ካምፓኒ እውን ሲያደርግ ብቻውን ሳይሆን ከሌሎች የቀድሞ ኦሊምፒያንና ብስክሌተኞች ጋር በጋራ በመሆን ነው፡፡ አንደኛው የቀድሞው የእንግሊዝ የኦሊምፒክ የረጅም ርቀት አትሌት ሪቻርድ ኔሩርካር ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ለረጅም ዓመታት መቆየቱ ተነግ ሯል፡፡ በተለይም ባለፉት ሁለት ዓመታት ይህ የቀድሞ ኦሊምፒያን ይህን ካምፓኒ እውን ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት ማድረጉ ተገልጿል፡፡ የቀድሞው የኢትዮጵያዊ ኦሊምፒክ ብስክሌተኛ አለማየሁ ስጦታው ካምፓኒውን ከመሰረቱት መካከል እንደሚገኝበትም ታውቋል፡፡ አለማየሁ ከሰላሳ ዓመታት በፊት ከስፖርቱ ራሱን ካገለለ ወዲህ በኢትዮጵያ ብስክሌት ስፖርት ውስጥ ሲሰራ ቆይቷል፡፡ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያ አዳዲስ መንገዶች በተራሮች ላይ ጭምር መገንባታቸውን ተከትሎ በአገሪቱ የጎዳና ላይ ብስክሌት ውድድሮች እየተበራከቱ መምጣታቸውን የገለፀው ካም ፓኒው ውድድር ለማካሄድ አመቺ ሁኔታ እንዳለ አብራርቷል፡፡ ፅጋቡ በበኩሉ የዓለማችን ዝነኛው የብስክሌት ውድድር በሆነው ቱር ደ ፍራንስን ጨምሮ በበርካታ የአውሮፓ ውድድሮች ለመሳተፍ ልምምዱን የሚሰራባቸው የትግራይ ዳገታማ መንገዶች ፈታኝ ቢሆኑም ጥሩ ውድድር ማስተናገድ የሚችሉ መሆናቸውን ተናግሯል፡፡ በ31ኛው ኦሊምፒያድ በብስክሌት ስፖርት ኢትዮጵያን ለመወከል የበቃው ፕሮፌሽናል ብስክሌተኛ ፅጋቡ ግርማይ በ103ኛ ቱር ደ ፍራንስ በመሳተፍ የመጀመርያው ኢትዮጵያዊ መሆኑ ይታወሳል፡፡ ፅጋቡ ግርማይ፤ የጣሊያኑን ላምፕሬ ሜሪዳን ክለብ በመወከል በቱር ደ ፍራንስ ከሚጋልቡ 9 ብስክሌቶች አንዱ ነበር። በፕሮፌሽናል ደረጃ በላምፓሬ ሜሪዳ ክለብ ስኬታማ ሆኖ ያሳለፈው ፅጋቡ፤ በተለይ በጂሮ ዲ ኢታሊያ እና በቩሌ ታ ዲ ኤስፓኛ የጎዳና ላይ የብስክሌት ውድድሮች ተሳትፎ ስኬታማ መሆኑ በቱር ደ ፍራንስ ለመሳተፍ አብቅቶታል፡፡ ፅጋቡ ግርማይ ትውልዱ በመቐለ ሲሆን ፕሮፌሽናል ብስክሌተኛ ለመሆን ከበቃ ወዲህም ባለፉት አምስት ዓመታት፤ በስፖርቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የፉክክር ደረጃ ያሳደገ እና የቀየረ የመጀመሪያው ብስክሌተኛ ሆኖ ይጠቀ ሳል፡፡ የትራንስ ኢትዮጵያ ክለብ ተወዳዳሪ ሆኖ የስፖርቱን ጉዞ የጀመረው ፅጋቡ ግርማይ በኢትዮጵያ የብስክሌት ቻምፒዮና ለሁለት ጊዜያት ካሸነፈ በኋላ የፕሮፌሽናልነት ዕድል አግኝቶ የመጀመርያ ዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን ክለብ ለመቀላቀል ወደ ደቡብ አፍሪካ ለማቅናት የበቃ ነበር፡፡ ወደዚያ ከመሄዱ በፊት 2011 እና 2012 እኤአ በትምህርት እና በውድድር በደቡብ አፍሪካ ፔተርሽሩም እንዲሁም በስዊዘርላንድ ዎርልድ ሳይክሊንግ ማዕከል በአማተር ብስክሌተኛነት ተሳታፊ ነበር፡፡ በፕሮፌሽናል ብስክሌተኛነት ከ2012 እኤአ ጀምሮ ለሶስት ዓመታት በደቡብ አፍሪካው ኤም ቲ ኤን ኩቤካ ስር ሲወዳደር ቆይቶ ላምፕሬ ሜሪዳ ለተባለ ክለብ ኮንትራት የፈረመው ከሁለት ዓመት በፊት ነበር፡፡አዲስ ዘመን ግንቦት 7/2011 
https://www.press.et/Ama/?p=10819
484
2ስፖርት
ደደቢት የቅጣት ውሳኔ ተላለፈበት
ስፖርት
May 15, 2019
23
አዲስ አበባ፡- የደደቢት እና ፋሲል ከተማ እግር ኳስ ቡድን በ23ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መርሃ ግብር፤ በመቀሌ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ላይ በታየው የስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል፤ የዲሲፕሊን ኮሚቴው ውሳኔ አስተላለፈ። አቤቱታው የቀረበው በተጋጣሚው የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዲሲፕሊን ኮሚቴ በጨዋታ አመራሮችና በክለቡ የቀረበውን ሪፖርትና አቤቱታ ከመረመረ በኋላ ቅጣት አስተላልፏል። በዚህም መሰረት አስተናጋጁ የደደቢት እግር ኳስ ክለብ 150 ሺህ ብር እንዲቀጣ፤ በራሱ ሜዳ ላይ የሚያደርጋቸውን ቀጣይ ሁለት ጨዋታዎች በዝግ ስታዲየም ያለ ተመልካች እንዲያካሂድ፤ እንዲሁም በ30 ቀናት ውስጥ ደጋፊዎቹን ስፖርታዊ ጨዋነት ላይ እንዲያስተምር ተወስኖ በታል። ቅሬታው የቀረበው የደደቢት እግር ኳስ ቡድን እና ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ቡድን በ26/08/2011 ዓ.ም በመቀሌ ስታዲየም ተደርጎ፤ ፋሲል ከነማ 5 ለ1 ባሸነፈበት ጨዋታ ነው። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በይፋዊ ድረ-ገጹ እንዳስነበበው ከሆነም፤ ጨዋታ ከመጀመሩ በፊት የፋሲል ከነማ ክለብ ተጫዋቾች በማሟሟቅ ላይ እያሉ የመቀሌ ሰባ እንደርታን መለያ የለበሱ ደጋፊዎች አጸያፊ ስድብ ሲያደርሱባቸው ነበር። በ64ኛው ደቂቃ ላይም እንግዳው ፋሲል ከነማ ግብ ማስቆጠሩን ተከትሎ ጨዋታው ሊጀመር በሂደት ላይ እያለ፤ የመቀሌ ሰባ እንደርታ እግር ኳስ ቡድን ማሊያ የለበሱ ደጋፊዎች በፋሲል ከተማ እግር ኳስ ቡድን ተጠባባቂ ተጫዋቾችና አሰልጣኞች ላይ ድንጋይ ወርውረዋል። ተጫዋቾችና አሰልጣኞቹም የድንጋይ ውር ወራውን በመሸሽ ወደ ሜዳ መግባታቸውን ተከትሎም ጨዋታው ለአንድ ሰዓት ከ30 ደቂቃ ያህል ተቋርጧል። ወደ መልበሻ ክፍል በመሄድ ካሉ ተጫዋቾች መካከልም ሶስቱ በድንጋይ ተፈንክተዋል። ጨዋታውም በዝግ ስታዲየም የተደረገ ሲሆን፤ በቅድመ ውድድር ስብሰባ ወቅት የሁለቱም ተጋጣሚ ቡድኖች ደጋፊ እንደሌላቸው አሳውቀው እንደነበረ የጨዋታ  አመራሮቹ በሪፖርታቸው አስታውቀዋል። የፋሲል ከነማ ክለብም በመቀሌ ሰባ እንደርታ ደጋፊዎች ያደረሰበትን በደል በደብዳቤ በመግለጽ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አቤቱታውን አቅርቧል። የዲሲፕሊን ኮሚቴው በጨዋታ አመራሮችና በክለቡ የቀረበውን ሪፖርትና አቤቱታም መርም ሯል። በዚህም በጨዋታው አመራሮች እንዲሁም ቅሬታ አቅራቢው ክለብ፤ “ፋሲል ከተማ ክለብ ላይ ችግር የፈጠሩት የመቀሌ ሰባ እንደርታ ክለብ ደጋፊዎች ናቸው” በሚል ያቀረበው ቅሬታ ውድቅ ሆኗል። ምክንያቱ ደግሞ መቀሌዎች በዕለቱ በሜዳቸው ጨዋታ ያልነበራቸው መሆኑን ተከትሎ የክለቡን መለያ የለበሱ ስለመሆናቸው እንጂ የክለቡ ደጋፊዎች መሆናቸውን፤ እንዲሁም የመቀሌ ሰባ እንደርታ ክለብን ፍላጎት ለማራመድ ስታዲየም ስለመግባታቸው ማረጋገጫ ባለመገኘቱ ነው። በቅድመ ውድድር ስብሰባ ወቅትም፤ የፋሲልም ሆነ የደደቢት ክለብ ደጋፊ እንደ ሌላቸው አሳውቀው ከነበረ ወደ ሜዳ ለሚገባው ተመልካች ባለሜዳው ክለብ ደደቢት ኃላፊነት ለመውሰድ ዝግጁ አልነበረም። ኃላፊነት የማይወስድ ከሆነ ደግሞ ሜዳውን ለተመልካች ክፍት ማድረግ አይገባም ነበር። በመሆኑም የባለ ሜዳው ክለብ ደጋፊ የለንም ቢልም በውድድሩ ሜዳ ውስጥ ለሚፈጠረው የጸጥታ ችግር ኃላፊነት ያለበት፤ ወይም ተመልካች ችግር ሲፈጥር ኃላፊነት ያለበት፤ ወይም ተመልካች ችግር ሲፈጥር መቆጣጠርና ችግር እንዳይፈጠር ማድረግ የነበረበት ደደቢት የስፖርት ክለብ እንጂ ሌላ ሊሆን አይችልም። በመሆኑም፤ የጨዋታው አመራሮች ባቀረቡት ሪፖርት እንደተረጋገጠው፤ ባለሜዳው የደደቢት ስፖርት ክለብ የስፖርታዊ ጨዋነት ጥሰቱ በተፈጠረበት ወቅት ችግሩን ለማስቆም ያደረገው ጥረት አነስተኛ ነው። ይህንን ተከትሎም የደደቢት እግር ኳስ ክለብ በዲሲፕሊን ኮሚቴው የ150 ሺህ ብር ቅጣት ተጥሎበታል። ክለቡ በራሱ ሜዳ ላይ የሚያደርጋቸውን ቀጣይ ሁለት ጨዋታዎች በዝግ ስታዲየም እንዲያካሂድ፤ ውድድሩ የሚካሄድበት ሁኔታና ቀኑንም የሊግ ኮሚቴው እንዲያሳውቅ ተወስኗል። ክለቡ ደጋፊዎቹን ለ30 ቀናት በስፖርታዊ ጨዋነት ላይ ግንዛቤ በማስጨበጥ ለፌዴሬሽኑ ሪፖርት እንዲያደርግም ተወስኖበታል።አዲስ ዘመን ግንቦት 7/2011 
https://www.press.et/Ama/?p=10822
441
2ስፖርት
በሱማሌ ክልል በአንድ ጀምበር ከ1 ሚሊዮን 100 ሺህ በላይ ችግኞች ተተከሉ
ሀገር አቀፍ ዜና
July 31, 2020
11
አዲስ አበባ፡- በሱማሌ ክልል በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎችና ዞኖች ሐምሌ 22 ቀን 2012 ዓ.ም በአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በአንድ ጀምበር ከ1 ሚሊዮን 100 ሺህ በላይ ችግኞችን ተተከሉ። የክልሉ የአካባቢ፣ የደንና የአየር ንብረት ለውጥ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሐሰን ፈራህ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ በአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በአንድ ጀንበር 1 ሚሊዮን 147 ሺህ 695 ችግኞች መተከላቸውን አስታውቀዋል። በዘንድሮ ዓመት የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በክልሉ ሊተከሉ ከታቀዱት 3 ሚሊዮን 800 ሺህ ችግኞች ውስጥ እስከአሁን በተለያዩ መርሐ ግብሮች 1 ሚሊዮን 210 ሺህ 405 ችግኞች በአጠቃላይ 2 ሚሊዮን 358 ሺ,100 ሚሊዮን ችግኞች መተከላቸውን አመልክተዋል። በችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ ላይ የሱማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ከሙሀመድ ጨምሮ የተለያዩ ሥራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን የጠቁሙት ኃላፊው ፤ የችግኝ ተከላ ፕሮግራሙ በሁሉም የክልሉ ዞኖች፣ ወረዳዎችና ከተሞች የተካሄደ መሆኑን አስታውቀዋል።የችግኝ ተከላ ሥራ በአግባቡ ለመከናወን የሚያስችሉ ተለያዩ ኮሚቴዎች በማቋቋም የዝግጅት ሥራ የተሠራ መሆኑን ጠቁመው፤ የችግኞች ዝግጅት ሥራው ችግኞች መትከያ ጉድጓድ መቆፈሩን በአግባብ የተከናወነ መሆኑን አስታውቀው። ለዚህም ስምንት መቶ ሄክታር መሬት መዘጋጀቱን አመልክተዋል።በክልሉ በገጠርና በከተማ ከሚገኙ ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ችግኝ መትከል ባህል እንዲሆን ለማድረግ የሚያስችል ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራን መሥራቱን ጠቁመው፤ ህብረተሰቡ ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እራሱን በመጠበቅ ርቀቱን ጠብቀው የችግኝ ተከላው ማካሄዱንም አመልክተዋል። ዓምና ከተተከሉት ችግኞች ውስጥ 86 በመቶ መጽደቃቸውን የገለጹት ኃላፊው ፤ የተቀሩት ችግኞች ያልጸደቁበት ምክንያት የክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች የዝናብ እጥረት በመከሰቱ እንደ ነበር አስታውሰው፤ የዘንድሮ ከአምና የተሻለ እንዲጸድቅ እየተሠራ መሆኑን አስታውቀዋል። ባለፈው ዓመት የነበሩ ችግሮችን በመቅረፍ ሰፊ የዝግጅት ሥራ መሠራቱን የሚገልጹት ኃላፊው ፤ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር እስአአሁን የችግኝ ተከላ ፕሮግራሙ በሁሉም የክልሉ ዞኖች፣ ወረዳዎችና ከተሞች የተለያዩ ሁነቶች በመሞርኮዝ እየተካሄደ መሆኑን አመልክተዋል።በቀጣይ የተጀመረውን የችግኝ ተከላ ሥራ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ የሚናገሩት ኃላፊው፤ ለዚህ የህብረተሰቡን ርብርብ እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል። ከዓምና ጀምሮ የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብና ለመጽደቃቸው የሁሉምን ጥረት የሚጠይቅ በመሆን ሁሉም ሰው የተከላቸውን ችግኞች መንከባከብ አለበትም ብለዋል፡፡አዲስ ዘመን ሐምሌ 24/2012ወርቅነሽ ደምሰው
https://www.press.et/Ama/?p=36361
285
0ሀገር አቀፍ ዜና
ዋልያዎቹ በዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ከሌሴቶ ጋር ተደልድለዋል
ስፖርት
July 31, 2019
40
በካታር አስተናጋጅነት በ2022 ለሚከናወነው የዓለም ዋንጫ የአፍሪካ ዞን ማጣርያ ድልድል ከትናንት በስቲያ በግብፅ መዲና ካይሮ ይፋ ተደርጓል። የአፍሪካ ዞን የማጣርያ ድልድሉ በዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ማህበር ፊፋ መመሪያ መሰረት ድልደላው መደረጉ ተነግሯል። የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ወርሐዊ የፊፋ ደረጃን መሰረት ያደረገው የማጣርያ አካሄድ የቅድመ ማጣርያ፣ የምድብ ማጣርያ እና የመለያ ሒደቶች የተከተለ ሲሆን በሀገራት ደረጃ ከዝቅተኞቹ የሚመደቡ ሃገራት የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታዎች የሚጠብቃቸው እንደሆነ የፊፋ መመሪያ ያስረዳል።በዚሁ መመሪያ መሰረት በአፍሪካ የሚገኙት ሃገራት በወቅታዊ ደረጃቸው ዝቅተኛ የሆኑትና የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታቸውን የሚያደርጉት 28 ሃገራት በቋት አንድ ተደልድለዋል። በቋት አንድ ከተደለደሉት ሃገራት ውስጥ ኢትዮጵያ፣ ዚምባብዌ፣ ሞዛምቢክ፣ ሴራሊዮን፣ ናሚቢያ፣ ጊኒ ቢሳዋ፣ ማላዊ፣ ቶጎ፣ ሱዳን፣ ሩዋንዳ፣ ታንዛኒያ፣ ኢኳቶርያል ጊኒ፣ ኢስዋቲኒ እና ሌሶቶ ናቸው። ሃገራቱ እርስ በእርስ ተጫውተው አሸናፊ የሆኑት 14 ሃገራት ወደ ምድብ ማጣርያው የሚገቡ ይሆናል። በቅድመ ማጣሪያ ጨዋታው ማን ከማን እንደሚጫወት ለመለየት ከትናንት በስቲያ በግብዕ የዕጣ ማውጣት ሥነ ስርዓት ተከናውኗል።በዚህ ቋት ውስጥ የምትገኘው በወቅታዊ ደረጃዋ 150ኛ ላይ የተቀመጠችው ኢትዮጵያ በቅድመ ማጣርያ ጨዋታዋን ከሌሴቶ ጋር ትጫወታለች። ኢትዮጵያም የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታዋን ነሐሴ 26 በሜዳዋ የምታደርግ ይሆናል። ኢትዮጵያ እና ሌሴቶ ለ2017 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ በአንድ ምድብ እንደነበሩ የሚታወስ ሲሆን ባህር ዳር ላይ በተደረገው ጨዋታ ኢትዮጵያ በጋቶች ፓኖም እና ሳላዲን ሰዒድ ጎሎች 2 ለ 1 ስታሸንፍ በተመሳሳይ ሌሶቶ ላይም በጌታነህ ከበደ ሁለት ጎሎች ኢትዮጵያ 2 ለ 1 ማሸነፏ የሚታወስ ነው። በተመሳሳይ እንደ ኢትዮጵያ ሁሉ በቋት አንድ የሚገኙትና ዝቅተኛ ወርሐዊ ደረጃን የያዙት ሃገራት የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታቸው የተለየ ሲሆን ፤ሶማሊያ ከዚምባብዌ፣ ኤርትራ ከናሚቢያ፣ ቡሩንዲ ከታንዛኒያ፣ ጅቡቲ ከኢስዋቲኒ፣ ቦትስዋና ከማላዊ፣ጋምቢያ ከአንጎላ፣ላይቤርያ ከሴራሊዮን፣ ሞሪሸስ ከሞዛምቢክ፣ ሳኦቶሜ ከጊኒ ቢሳው፣ደቡብ ሱዳን ከኢኳቶርያል ጊኒ፣ኮሞሮስ ከቶጎ፣ቻድ ከሱዳን እና ሲሸልስ ከሩዋንዳ ናቸው።አዲስ ዘመን ረቡዕ ሐምሌ 24/2011 
https://www.press.et/Ama/?p=15158
246
2ስፖርት
አገር አቀፍ የሠራተኞች ስፖርት የተቋጨባቸው ውድድሮች
ስፖርት
August 1, 2019
32
ባለፉት ሁለት ሳምንታት በሠራተኛው መካከል ሲካሄድ የሰነበተው አገር አቀፍ የሠራተኞች ስፖርት ተጠናቋል። በተለያዩ ስፖርቶች የፍፃሜ ውድድሮች የተካሄዱ ሲሆን ቻምፒዮኖቹ ተለይተው ታውቀዋል። በዚህም መሰረት በሁለተኛ ዲቪዚዮን እግር ኳስ ውድድር ከመጀመሪያ አንስቶ ማራኪ ጨዋታ በመጫወት የተመልካቹን ቀልብ መግዛት የቻሉት የበበቃ ቡና ልማት፣ መተሃራ ስኳር ፋብሪካን በፍፃሜው ጨዋታ ሦስት ለአንድ በመርታት የዋንጫው ባለቤት መሆን ችለዋል። በደረጃው ጨዋታ ኦሞ ኩራዝ ብርሸለቆ እርሻ ልማትን ሁለት ለዜሮ በመርታት ሦስተኛ ሆኖ ጨርሷል። በአንደኛ ዲቪዚዮን እግር ኳስ ውድድር ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ወንጂ ስኳር ፋብሪካን አምስት ለአንድ በሆነ ሰፊ ውጤት በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት ሲሆን ኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት ኢትዮ ፐርፕልና ወረቀት ፋብሪካን ሁለት ለአንድ አሸንፎ ሁለተኛ ሆኖ ማጠናቀቅ ችሏል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ አንበሳ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅትን ሦስት ለአንድ በመርታት ሦስተኛ ደረጃን ይዟል። በሴቶች ቮሊቦል አንደኛ ዲቪዚዮን ውድድር አንበሳ ከተማ አውቶቡስ ብሄራዊ አልኮል እና አረቄ ፋሪካን ሦስት ለአንድ አሸንፎ የዋንጫ ባለቤት ሲሆን መከላከያ ኮንስትራክሽን ድርጅት ሦስተኛ ደረጃ ይዞ ማጠናቀቁን የኢሠማኮ የስፖርት ክፍል ኃላፊ አቶ ዮሴፍ ካሳ ያደረሱን መረጃ ያመለክታል። በሁለተኛ ዲቪዚዮን የወንዶች ቮሊቦል ጨዋታ የፋፋ ምግብ አክሲዮን ማህበርና ፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት ጨዋታ በተጫዋች ተገቢነት ጥያቄ መጨረሻ ላይ ውዝግብ ያስነሳ ሲሆን ፋፋ ምግብ ሦስት ለዜሮ በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት ሆኗል። በዋንጫ አሰጣጥ ስነስርዓቱ ላይ የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት ተጫዋቾች ተጋጣሚያቸው ተገቢ ያልሆነ ተጫዋች አሰልፏል በሚል ያነሱት ጥያቄ የውዝግቡ መነሻ ሲሆን አንዳንድ ተጫዋቾች ጥያቄውን ለማቅረብ የሄዱበት መንገድ ከስፖርታዊ ጨዋነት ያፈነገጠና ‹‹ስፖርት ለወዳጅነትና ለምርታማነት›› በሚል መርህ ከሚካሄደው የሠራተኛው ስፖርት የማይጠበቅ ነበር። ይህ ጉዳይ በኢሰማኮ የስፖርት ኮሚቴ እየታየ እንደሚገኝና በቅርቡ ጥፋተኛ ሆኖ በተገኘው አካል ላይ ቅጣት ሊያስከትል እንደሚችል አቶ ዮሴፍ አብራርተዋል። ያም ሆኖ ፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት በውድድሩ ሁለተኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ አዲስ መድሀኒት ፋብሪካ በሦስተኛነት አጠናቋል። በወንዶቹ አንደኛ ዲቪዚዮን የቮሊቦል ጨዋታ ሙገር ስሚንቶ ብሄራዊ አልኮል እና አረቄ ፋብሪካን 3ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፎ ዋንጫውን ወስዷል። በሴቶች ጠረጴዛ ቴኒስ ውድድር አንበሳ ከተማ አውቶቡስ ኢትዮ ቴሌኮምን 3ለ1 በመርታት ቻምፒዮን ሲሆን ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ደርጅት ሦስተኛ ሆኖ አጠናቋል። በተመሳሳይ በአንደኛ ዲቪዚዮን የወንዶች ጠረጴዛ ቴኒስ ውድድር ብርሃንና ሠላም ማተሚያ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 3ለ2 አሸንፎ ዋንጫውን አንስቷል። ሃረር ቢራ ፋብሪካ ውድድሩን በሦስተኛነት ጨርሷል። ኢትዮ ኤሌክትሪክ በሁለተኛ ዲቪዚዮን የጠረጴዛ ቴኒስ ውድድርም ለፍፃሜ ደርሶ በአዲስ አበባ ኢንተርናሽናል ሂልተን ሆቴል 3ለ2 ተረቷል። ብራና ማተሚያ ቤት ሦስተኛ ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀ የውድድሩ ተሳታፊ ነው። በወንዶች አትሌቲክስ ወንጂ ስኳር ፋብሪካ አጠቃላይ አሸናፊ ሲሆን በሴቶች ነፋስ ስልክ ሞሀ ለስላሳ መጠጦች ፋሪካ አሸናፊ ነው። የአገር አቀፍ ውድድሩ አጠቃላይ አሸናፊ አንበሳ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት መሆኑን አቶ ዮሴፍ ተናግረዋል። በሠራተኛው መካከል በሚደረገው ውድድር ከሁሉም ክልል የተውጣጡ የሠራተኛ ስፖርት ማህበራት ተሳታፊ መሆናቸውን የተናገሩት አቶ ዮሴፍ፣ ውድድሩ ሠራተኛው በስፖርቱ ጤንነቱ የተጠበቀ አምራች ዜጋ እንዲሆን ከማስቻል ባሻገር በአሁኑ ወቅት አንገብጋቢ ከሆነው የሰላም ጉዳይ ጋር በተያያዘ ‹‹ስፖርት ለሰላም፣ ለአንድነት፣ ለጤንነትና ለምርታማነት›› በሚል መርህ እየተካሄደ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በስፋት የተለያዩ ማህበራትን እያሳተፈ የሚገኘው ይህ ውድድር የመገናኛ ብዙሃን ትኩረትን እየሳበ ይገኛል። ይህም አዳዲስ ተሳታፊ ማህበራትን ወደ ውድድር ከመሳብ በዘለለ ቀድሞ ዝነኛ ተፎካካሪ የነበሩና ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከውድደሩ የራቁ ማህበራትን ወደ ውድድር እየመለሰ ይገኛል። ያም ሆኖ ለረጅም ዓመታ ጠንካራ ተፎካካሪ በመሆን በርካታ ሠራተኞችን እያሳተፉ የነበሩ እንደ ንግድ ባንክ ዓይነት ማህበራት ዘንድሮ ከውድድሩ መራቃቸውን ኃላፊው አስረድተዋል። ኢሠማኮ የሚካሄደው ዓመታዊ የስፖርት ውድድር ሦስት ዓይነት ገፅታን የተላበሰ ከፉክክርም በላይ በርካታ ዓላማዎችን የሰነቀ የስፖርት መድረክ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ዮሴፍ፣ ረጅም ወራትን ሠራተኛው በስፖርት አማካኝነት አብሮነቱን የሚያጠናክርበትና ልምድ የሚለዋወጥበት የበጋ ወራት የስፖርት ውድድር የበርካታ ድርጅትና ተቋማት ሠራተኞችን ማዕከል ያደረገ የውድድር መድረክ ሲሆን፤ የሠራተኛውን ዓመታዊ በዓል ታኮ የሚካሄደው የሜይ ዴይ ውድድር ሌላኛው አካል ነው። ክረምት ወራት ላይ በውቡ የወንጂ ሁለገብ ስቴድየም የሚካሄደው አገር አቀፍ የሠራተኞች ውድድርም በድምቀቱና አገር አቀፍ ሠራተኞችን በአንድ ላይ ለሁለት ሳምንታት በትንሿ ከተማ ይዞ የሚከርም መሆኑን አስረድተዋል። ሦስቱም የውድድር ገፅታዎች ሠራተኛውን ከማቀራረብና ልምዱን እንዲለዋወጥ ዕድል ከመፍጠር ባሻገር በሠራተኛው መካከል ቤተሰባዊ ስሜት እንዲጎለብት ሚናቸው ቀላል እንዳልሆነም ተናግረዋል። ሠራተኛው በስፖርት ጤንነቱ የተጠበቀ ምርታማ ዜጋ እንዲሆን ከማስቻል በተጨማሪ ሦስቱ የስፖርት መድረኮች ሠራተኛው «የእኔ ነው» የሚለው የመዝናኛ አማራጩ ጭምር መሆናቸውንም ኃላፊው አስረድተዋል። በውድድሩ የሚካፈሉ በርካታ ድርጅትና ተቋማት በተለያዩ የስፖርት ዓይነቶች ሠራተኞቻቸው ያላቸውን ክህሎት አውጥተው በመጠቀም ለአገር ስፖርት ዕድገት የበኩላቸውን ድርሻ ከመወጣት አልፈው ምርትና አገልግሎታቸውን ለማስተዋወቅ መልካም አጋጣሚ እንዳገኙም ባለፉት ዓመታት ውድድሮች ለመታዘብ እንደተቻለ አክለዋል።አዲስ ዘመን  ሐምሌ 25/2011 
https://www.press.et/Ama/?p=15221
622
2ስፖርት
በኦሮሚያ ክልል በአንድ ጀንበር 327 ሚሊዮን 399 ሺ 570 ችግኞች ተተከሉ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 1, 2020
11
አዲስ አበባ፦ በኦሮሚያ ክልል በአንድ ጀንበር ማለትም ከጠዋቱ 12 እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት ድረስ 327 ሚሊዮን 399 ሺህ 570 ችግኞች ተተክሏል።በአንድ ጀንበር በመጀመሪያ በክልሉ 304 ሚሊዮን ለመትከል ታቅዶ የነበረ ሲሆን፣ አፈፃፀሙ ከእቅዱ ከ20 ሚሊዮን በላይ ብልጫ አለው።አቶ ሽመልስ አብዲሳ በችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ ወቅት፣ ሀገሪቱ ካለችበት የድህነት አረንቋ ለመውጣት መንግሥት ህብረተሰቡን በማሳተፍ ወደ ብልጽግና የሚሸጋገርበትን ስትራቴጂ በመንደፍ እየሠራ ነው ብለዋል።የዚህ እቅድ አካል የሆነው አረንጓዴ አሻራ የማኖር መርሐ ግብር የነገው ትውልድ ያለምንም ችግር ውሃ በማግኘት በመስኖ ማልማት እንዲችል እና በኢኮኖሚ አስተማማኝ ደረጃ ላይ እንዲደርስ በማለም የሚከናወን ተግባር መሆኑን ተናግረዋል።በዘንድሮው ዓመት በመላው ሀገሪቱ ለመትከል ከታቀደው 5 ቢሊዮን ችግኞች መካከል 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኞች በክልሉ እንደተዘጋጀ የኦሮሚያ ክልል እርሻ እና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳባ ደበሌ ገልጸዋል።በክልሉ ሁሉም ዞኖችና ከተሞች በችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ላይ ለተሳተፉ ምስጋና አቅርበዋል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 25 ቀን 2012 ዓ.ም በጋዜጣው ሪፖርተር
https://www.press.et/Ama/?p=36414
135
0ሀገር አቀፍ ዜና
የታጁራ ወደብ የድንጋይ ከሰልና የብረት ምርቶች እጥረት ለመቀነስ እንደሚያስችል ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 1, 2020
12
አዲስ አበባ፡- ኢትዮጵያ የታጁራ ወደብን መጠቀም መጀመሯ የድንጋይ ከሰል እና የብረት ምርቶች እጥረትን በመቀነስ የልማት ፕሮጀክቶችን ሥራ ለማፋጠን ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ገለጸ።የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አሸብር ኖታ እንደገለጹት፤ ጅቡቲ ካሏት ወደቦች ውስጥ አንዱ የሆነው የታጁራ ወደብ ኢትዮጵያ መጠቀም ጀምራለች። ወደቡ የከሰል ድንጋይ እና ብረት ምርቶች ወደኢትዮጵያ ለማስገባት ታልሞ የተገነባ ነው። በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ ወደቡን መጠቀም መጀመሯ የድንጋይ ከሰል እና የብረት ምርቶችን የሚፈልጉ የልማት ሥራዎችን ለማፋጠን ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ይታመናል። እንደ አቶ አሸብር ገለጻ፤ የድንጋይ ከሰል ምርት በተለይ ለሲሚንቶ ፋብሪካዎች እና ለተለያዩ አምራች ፋብሪካዎች የኃይል አቅርቦት በመስጠት ምርትን ለማሳደግ ይረዳል። የብረት ምርቶችም ለህዳሴ ግድብ እና ሌሎች ትላልቅ ፕሮጀክቶች እንዲሁም ለኮንስትራክሽን ሥራዎች ዋነኛው አስፈላጊ ግብዓት ነው። በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ የታጁራ ወደብን ተጠቅማ በዋነኛነት ምርቶቹን ማስገባት መጀመሯ በግብዓት እጥረት ይፈጠር የነበረውን የልማት ሥራዎች መጓተት ለመቀነስ የበኩሉን አስተዋጽኦ ያደርጋል። ኢትዮጵያ ለረጅም ዓመታት እየተጠቀመችበት ከሚገኘው ከዋናው የጅቡቲ ወደብ ጋር ሲነጻጸር የታጁራ ወደብ የ13 ኪሎ ሜትር ርቀትን እንደሚቀንስ የገለጹት አቶ አሸብር፤ ወደቡ ለኢትዮጵያ ያለው ቅርበት የተሽከርካሪዎችን ምልልስ በመቀነስ ምርቶች በፍጥነት ለማስገባት እንደሚያስችል ተናግረዋል። ወደወደቡ የሚወስደው እና ከወደቡ ወደኢትዮጵያ የሚያስገባው መንገድም ደረጃን በጠበቀ መልኩ የተገነባ በመሆኑ ለእቃ ጫኝ ተሽከርካሪዎችም አመቺ መሆኑን አስረድተዋል። በወደቡ ያለው የአገልግሎት አሰጣጥ እና የማሽነሪ አቅርቦት ዘመናዊ በመሆኑ ከመርከብ ላይ አንድ ቀን 5ሺ 670 ቶን እቃ ማራገፍ የሚያስችል አቅም መኖሩን ተናግረዋል። ይህም በፍጥነት ምርቶቹን ወደኢትዮጵያ ለማስገባት እና ለሚፈለገው አገልግሎት ለማዋል ዓይነተኛ ሚና እንዳለው አቶ አሸብር ገልጸዋል። እንደ አቶ አሸብር ገለፃ፤ ቀደም ባለው ጊዜ የታጁራ ወደብ ግንባታ የተጀመረው የኢትዮጵያን የፖታሽ ምርት ወደውጭ ሀገራት ለመላክ ነበር። ይሁንና በጅቡቲ ወደብ ላይ የድንጋይ ከሰል ምርት ከሌሎች ምርቶች ጋር አብሮ በሚራገፍበት ወቅት በተለይ የምግብ እና የፋርማሲውቲካል ምርቶች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ መፍጠሩን ለማወቅ ተችሏል። በወደቡ የድንጋይ ከሰል በሚራገፍበት ወቅትም በዙሪያው የሚገኙ ሌሎች ምርቶች ላይ ጥቁር ብናኝ እየተራገፈ በመሆኑ መንግሥት ምርቱን ለብቻው ማስገባት እንደሚገባ ወስኗል። በመሆኑም የድንጋይ ከሰሉ ሲገባ ተጽእኖ የማያደርስበት ምርት የብረት ምርት በመሆኑ በዋናነት ሁለቱ ምርቶች በታጁራ ወደብ እንዲገቡ እየተደረገ ይገኛል። የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት መረጃ እንደሚያመለክተው፤ ቀደም ብሎ በ90 ሚሊዮን ዶላር ተገንብቶ ያለሥራ የተቀመጠውን የጅቡቲ ወደብ ኢትዮጵያ መጠቀም ከመጀመሯ ጋር ተያይዞ በርካታ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ተገቢውን የኮሮና ቫይረስ ጥንቃቄ እያደረጉ ምርቶችን ወደ ኢትዮጵያ በማስገባት ላይ ናቸው።አዲስ ዘመን ሐምሌ 25 ቀን 2012 ዓ.ም በጌትነት ተስፋማርያም
https://www.press.et/Ama/?p=36417
350
0ሀገር አቀፍ ዜና
እንስትነቷን የተካደችው ሴት
ስፖርት
May 8, 2019
57
እኤአ በ1991 ትውልዷ በደቡብ አፍሪካ ሊምፖፖ ግዛት ውስጥ በምትገኝ አነስተኛ መንደር ውስጥ ነው። በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ በሚገኙት ቤተሰቦቿ ውስጥ አራተኛ ልጅ በመሆን ይህቺን አለም ተቀላቀለች። በገጠራማው የትውልድ ቀዬዋ አብዛኛውን የልጅነት ጊዜዋን ከተፈጥሮ ጋር ብቻዋን በማውጋት የማሳለፍ ልምድ ነበራት። ካስተር ሰሜንያ፤ ብዙዎች ከማያውቁት ከትንሿ መንደር የተገኘችው ይህቺ እንስት ዛሬ ሯሷን ብቻም ሳይሆን ያፈራትን አካባቢም ጭምር ማስተዋወቅ ችላለች። በ800 ሜትር ሩጫ በወጣትነቷ የሰራችው ታሪክ ከዓለም ህዝብ መወድስ እንዲቀርብላት ያስገደደም ነበር። እንስቷ በተለይ ደግሞ በሁለት ኦሎምፒኮች ላይ በርቀቱ አሸንፋ ባለድል መሆኗ ከፍ ያለ ቦታና አክብሮትን ለማግኘት ያስቻላት እንደሆነ ይነገራል። የዓለማችን ትልቁ መድረክ በሚባለው በኦሎምፒክ ከባለድልነቷ ገድል ባሻገር በዓለም ሻምፒዮና ላይ ለሶስት ጊዜያት በርቀቱ ማሸነፏ ስሟን በጀግኖች ሰገነት ላይ ከፍ ብሎ እንዲጻፍ ያደረገ ነበር። ደቡብ አፍሪካዊቷ ካስተር ሰሜንያ በተመሳሳይ በሌሎች የውድድር መድረኮች ላይ የምታስመዘግበው ድል ከፍተኛ አድናቆትና ተወዳጅነት ለመጎናጸፍ አስችሏታል። ከትንሿ መንደር መገኘቷ ከትልቁ ዓለም የዝና ማማ ላይ ከመውጣት እንዳላገዳት የምትናገረው አትሌቷ፤ ወደ አትሌቲክሱ እንዴት እንደገባች ስትናገር አጋጣሚው ለብዙዎች ግርምትን ይፈጥራል። ሴሜንያ እንደምትለው፤ ወደ ስፖርት ህይወት የገባሁት በትምህርት ቤት ውስጥ ነው። በዚያ አዘወትር የነበረው ግን አትሌቲክስ አልነበረም። እግር ኳስን እንጂ፤ እጫወት የነበረው ደግሞ ከወንዶች ጋር ነበር። በእግር ኳስ የነበረኝ እንቅስቃሴ ደግሞ ዛሬ ባለ ድል ያደረገኝን የአትሌቲክስ ስፖርት አቅሜን እንዳውቅ አስችሎኛል። ካስተር ሴሜኒያ ትቀጥላለች፤ ከጓደኞቼ ጋር ኳስ በምንጫወትበት ወቅት ፈጣን ሩጫ አሳይ ነበር። አሯሯጤ በእጅጉ አስደናቂ ስለነበር አቅጣጫዬን እንድቀይር በዙሪያዬ በሚገኙ ጓደኞቼ አስተያየት ተሰጠኝ። እኔም ሃሳቡን በመቀበል ወደ ሩጫው አዘነበልኩ። አጋጣሚውም እጣ ፈንታዬን እንዲወለድና እንዳውቀው አደረገኝ። በሃገር አቀፍ ውድድሮች የመሳተፍ እድሉም ተከተለ። ድልም አብሮ መጣ፤ ወደ አለም ዓቀፍ መድረኮች ተሳትፎ ተሻገረ። ስትልም ትናንትን ታስታውሳለች። ካስተር ሰሜንያ ባለድል ለመሆኗ ምስጢሩ ያለመታከት ያደረገችው ጥረት መሆኗን ትናገራለች። የሚወዷትና የሚያደንቋት “ኮብራ” በሚል ቅጽል ስም ይጠሯታል። ለተወዳዳሪዎቿ በእጅጉ አደገኛና ፈታኝ መሆኗ ይሄንኑ ስያሜ እንዲሰጣት አድርጓል። ምክንያቱም የትም ይሁን የት ከሮጠች ማሸነፏ አይቀርምና፤ የካስተር ሴሜኒያ የርቀቱ ንግስትነት አነጋጋሪ ሆና ከመቅረቧ በላይ ጾታዋን መሰረት ያደረጉ ጥያቄዎች በተደጋጋሚ ይነሳሉ። የተፈጥሮ ልግስና ሆነና ተባእታዊ የሰውነት አቋም ያላት አትሌቷ እንደ ሴት መቆጠር እንደሌለባት ሙገት ሲገጥማት ለመታዘብ ተችሏል። አንዳንዶች የእርሷን ድል የለም “የወንድ ሆርሞን” ከፍ ባለ ሁኔታ እንዳላት በመግለጽ ድሏን ሲያራክሱ ይደመጣሉ። በእንስቷ ላይ የሚነሳው ይህ አይነቱ አስተያየት በመገናኛ ብዙሃን ዘንድ አትሌቷን እንድትብጠለጠል ያደረገም ነበር። የጉዳዩ ትኩረት ከፍ ማለትም በዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን በኩልም ቅቡልነት ያገኘ መሆኑ ነበር። ፌደሬሽኑ ‘ቴስቶስትሮን’ ለሴት ሯጮች ከፍተኛ ጉልበት ስለሚሆን ይህ ሆርሞን በከፍተኛ መጠን ያላቸው እንደ ሰሜንያ ያሉ ሴት ሯጮች በውድድር ፍትሃዊ ያልሆነ ብልጫ ያሳያሉ። በመሆኑም በሴት ሯጮች የቴስቶስትሮን መጠን በመድኃኒት መገደብ አለበት በማለት የተፈጥሮን ህግ ለመሻር ሙግት ገጥሟል። የመገናኛ ብዙሃንንም ሆነ የዓለም አቀፉን አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አካሄድ በእጅጉ አምርራ የተቸችው አትሌቷ እስከ ፍርድ ቤት በመጓዝ ሙግት አድርጋለች። ህጉን ተገቢነት እንደሌለው ተከራክራለች። ሰሜንያም “ይህ ህግ እንደ ተፈጥሮዬ እንዳልሆን የሚያደርግ ነው” በማለት ነበር ጉዳዩን ወደ ዓለም አቀፉ የስፖርት የግልግል ዳኝነት ተቋም የወሰደችው፤ ቀደም ሲልም መሮጥ የምትፈልገው ምንም ምንም ሳይባል ተፈጥሮ እንደሰጣት፤ እንደማንነቷ እንደተፈጥሮዋ እንደሆነ ተናግራ ነበር። የግልግል ዳኝነቱ ተቋም ግን ከሰሞኑ ሙግቷን ከጥቅም ውጪ የሚያደርገውን ውሳኔ አስተላልፏል። ፍርድ ቤቱ ክሱን ውድቅ ስላደረገው እንደ ሰሜንያ ያሉና ከ400 ሜትር ጀምሮ እስከ ማይል የሚሮጡ ሴቶች በህጉ መሠረት በመድኃኒት የወንድ ሆርሞን ማለትም ‘ቴስቶስትሮን’ መጠናቸውን ለመቀነስ ወይም የሚሮጡበትን መጠን ለመቀየር የሚያስገድድ ነው። በአትሌቲክሱ ብዙ ርቀት የመጓዝ አቅም ያላት የ28 ዓመቷ ሴሜኒያ “ለአስር ዓመታት ያህል ዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌደሬሽን ፍጥነቴን ሊገታ ሞክሯል። ይህ ግን እንዲያውም ጠንካራ አደረገኝ” በማለት የአሁኑ የፍርድ ውሳኔም ወደ ኋላ እንደማያስቀራት ትናግራለች። ዳግም ከዚህ ፍርድ በላይ ከፍ ብላ የደቡብ አፍሪካ እንዲሁም ለዓለም ወጣት ሴቶችና ሯጮች ምሳሌ እንደምትሆንም አስታውቃለች። የስፖርት ግልግል ዳኝነት ፍርድ ቤቱ የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ውሳኔ አድሏዊነት ያለው ነው ቢባልም ተቋሙ ውሳኔውን ግን አስፈላጊ፤ ምክንያታዊና ሚዛናዊ ሲል ገልጾታል። ለሌሎች ሴት ሯጮች ውድድሮች ፍትሃዊ እንዲሆኑ ከማድረግ አንፃርም ውሳኔው አስፈላጊ እንደሆነም አስረግጧል። በፍርድ ቤቱ የተሰጠው ውሳኔ ለእርሷና ለአድናቂዎቿ በእጅጉ ያሳዘነና የተፈጥሮን ልግስና በእጅጉ የካደ መሆኑን በስፋት እንዲነገር ያደረገ ውሳኔ ሆኖ አልፏል።አዲስ ዘመን ሚያዚያ 30/2011
https://www.press.et/Ama/?p=10417
578
2ስፖርት
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና እየተካሄደ ነው
ስፖርት
May 8, 2019
55
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በበላይነት ከሚመራቸው መርሐ ግብሮች መካከል በየዓመቱ የሚከናወነው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተጠቃሽ ነው፡፡ አንጋፋውና ያለምንም መቆራረጥ በየዓመቱ ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዘንድሮ ለ48ኛ ጊዜ እየተካሄደ ይገኛል። ክለቦችና ክልሎች ከፍተኛ ፉክክር እንደሚያሳዩበት የሚጠበቀው ሻምፒዮናው በኦሊምፒክ ባህል መሰረት የውድድሩ የመክፈቻ ዝግጅት ትናንት አመሻሽ ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በይፋ ተጀምሯል። በዕለቱ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ አንጋ ታዋቂና ስመ ጥር አትሌቶች፤ እንዲሁም የአትሌቲክሱ ባለድርሻ አካላት፤ የተቋማት ከፍተኛ አመራሮች ታድመዋል። በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚካሄደው ሻምፒዮና በተሳካ ሁኔታ ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ ዝግጅት መደረጉም ተገልጿል። ለውድድር የሚሆኑ ቁሳቁሶችና ግብዓቶች ከማሟላታቸውም በላይ ውድድሩን የሚመሩ አደረጃጀቶችም ተፈጥረዋል። ለዚህም ከሁለት ነጥብ አንድ ሚሊዮን ብር በላይ በጀት በመመደብ ዓመታዊ ውድድሩን ከምንጊዜውም በተሻለ ሁኔታ ስኬታማ ለማድረግ ጥረት ማድረጉን ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ አስታውቋል። በፌዴሬሽኑ አዘጋጅነት የሚካሄደው ሻምፒዮናው ለአትሌቶች የሃገር ውስጥ የውድድር ዕድሎችን ከመፍጠሩ ባሻገር በክልሎች፤ በከተማ አስተዳደሮችና በክለቦች መካከል ፉክክር መፍጠርን፤ እንዲሁም ለብሄራዊ ቡድን የሚሆኑ አትሌቶችን የመምረጥ ዓላማ አንግቧል። በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሃገርን የሚወክሉና ሚኒማ ያሟሉትን አትሌቶች የሚመለመሉበት ትልቅ መድረክ ነው። ሻምፒዮናው በተጓዘባቸው ዓመታት ከያዘው ዓላማ አኳያ ስኬታማ እንደነበርና በኢትዮጵያ የአትሌቲክስ የስኬት ጉዞ ውስጥ ትልቅ ስም ያለው መሆኑ በመክፈቻው ዕለት ተነግሯል። ባለፉት ዓመታት ከዚህ ሻምፒዮና ውድድር በርካታ ብርቅዬ አትሌቶች ተገኝተዋል። ይሁን እንጂ፤ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ መቀዛቀዝ እየተስተዋለበት ነው። በተለይ በውጭ ሃገራት ውድድሮች ላይ ተሳታፊ የሆኑ ታዋቂ አትሌቶች በሃገር ውስጥ ውድድሮች አለመታየታቸው በብዙዎች ዘንድ ወቀሳ እንዲሰነዘርበት ያደርጋል። በመሆኑም በዚህ ዓመት በርካታ ታዋቂ አትሌቶች የተሳተፉ ሲሆን፤ አማን ወጤ፣ ጫላ በዮ፣ ዲኖ ስፍር፣ አንዷምላክ በልሁ፣ አባዲ ሃዲስ፣ የኔው አላምረው፣ ሰለሞን ባረጋ፣ አዲር ጉር፣… በወንዶች በኩል ተሳታፊ አትሌቶች ናቸው። በሴቶች በኩልም፤ ደራ ዲዳ፣ ነፃነት ጉደታ፣ በላይነሽ ጉደታ፣ ሱሌ ኡቱራ፣ ብርቱኳን ፈንቴ፣ ህይወት አያሌው፣ ፎቴን ተስፋይ፣ ሰንበሬ ተፈሪ፣ አራያት ዲቦ፣… ከተካፋዮቹ ጥቂቶቹ ይገኙበታል። ዘንድሮም እንደዚህ ቀደሙ ሃገራቸውን በዓለም አቀፍ ደረጃ ማስጠራት የሚችሉ አትሌቶች ተብሎ ይጠበቃል። ከውድድሩ አንጋፋነት አንጻር ብዙ የተነገረለት ሻምፒዮና ዘጠኝ ክልሎችና ሁለት ከተማ አስተዳደሮች፤ እንዲሁም 36 ክለቦችን ተሳታፊ አድርጓል። በዚህም በአጠቃላይ አንድ ሺህ 376 አትሌቶች ተሳታፊ ይሆናሉ። ከ47ኛው የኢትዮጵያ ሻምፒዮና የዘንድሮው በ122 ተሳታፊ አትሌቶች ብልጫ ያሳየም ሆኗል። ሻምፒዮናው ከዓመት ዓመት የፉክክር መንፈሱ እያየለ በመምጣቱ ዘንድሮም ጠንካራ አትሌቶችን በጥራትና በብዛት ለማግኘት የሚረዳ መሆኑ ተጠቁሟል። በአዲስ አበባ ስታዲየም በድምቀት እየተከናወነ የሚገኘውን በሻምፒዮናው የመጀመሪያ ቀን ውሎ የተለያዩ ውድድሮች የተካሄዱ ሲሆን፤ በእለቱ በተካሄዱት ውድድሮች በወንዶች የስሉስ ዝላይ ፍፃሜ ውድድር ፤አዲር ጉር ከመከላከያ 15 ነጥብ 88 ሜትር 1ኛ (ሪከርድ በመስበር) የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆኗል ። የኢትዮጵያ ንግድ ባንኩ ቢኒኒ አንበሴ 15 ነጥብ 57 ሜትር በመዝለል 2ኛ በመሆን የብር ሜዳሊያ አጥልቋል። የሲዳማ ቡናው ጆሴፍ ኦባንግ 15 ነጥብ 35 ሜትር በመዝለል 3ኛ ደረጃን በመያዝ የነሃስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆኗል። ሌላው ፍጻሜ ያገኘው ውድድር የሴቶች አሎሎ ውርወራ ሲሆን፤ በዚህም፣ 1ኛ ዙርጋ ኡስማን ከሲዳማ ቡና 13 ነጥብ 55 ሜትር (ሪከርድ በማስመዝገብ) ባለድል ሆናለች። ሌላዋ ተወዳዳሪ አመለ ይበልጣል ከመከላከያ 12 ነጥብ 63 ሜትር በመወርወር 2ኛ ስትሆን፤ ሰላማዊት ማሬ ከደቡብ ፖሊስ 12 ነጥብ 15 ሜትር በመወርወር 3ኛ በመሆን አጠናቅቃለች። ውድድሩ ዛሬን ጨምሮ ለቀጣዮቹ አምስት ቀናት በድምቀት እንደሚቀጥል ይጠበቃል። ውድድሩ ዛሬን ጨምሮ ለቀጣዩቹ አምስት ቀናት በ80 የአትሌቲክስ ዳኞች፣በ45 የፌዴሬሽኑ አመራሮችና ባለሙያዎች፣ በ3 የህክምና ባለሙያዎችና አንድ አምቡላንስ ፣በ32 በጎፍቃድ አገልጋዮች እንዲሁም ሌሎች ሥራዎችን በሚያከናውኑ ሙያተኞች እየተመራበድምቀት እንደሚቀጥል ይጠበቃል። በ42ቱ ውድድሮች አሸናፊ ለሚሆኑ አትሌቶችም የ2,000.00 (ሁለት ሺህ)፣ 1,400.00 (አንድ ሺህ አራት መቶ) እና 1,000.00 (አንድ ሺህ) ብር ሽልማት እንደየደረጃቸው የሚያስገኝ ይሆናል። ክብረወሰን ለሚያሻሽሉ እና ከሦስት ወርቅ በላይ ለሚያስመዘግቡ አትሌቶችም 6,000.00 (ስድስት ሺህ) ብር ተጨማሪ ሽልማት የሚያገኙ ሲሆን፤ ሁለት ወርቅ ለሚያጠልቁ አትሌቶች ደግሞ 5,000.00 (አምስት ሺህ) ብር ይሰጣቸዋል። በአጠቃላይ በቡድን አሸናፊ ለሚሆኑት አትሌቶችም 20,000.00 (ሃያ ሺህ)፣ 16,000.00 እንዲሁም 10,000.00 ብር እንደሚበረከት ታውቋል። ዘንድሮ ለ48ኛ ጊዜ የሚካሄደው ውድድር በከፍተኛ ድምቀት በትናንትናው ዕለት የተጀመረ ሲሆን ለቀጣዮቹ ስድስት ቀናትም ይቆያል። በዓመት አንድ ጊዜ በሚካሄደው ይህ ውድድር በተመሳሳይ አምና ለ47ኛ ጊዜ ሲካሄድ ከፍተኛ ፋክክር የታየበት ነበር። በሻምፒዮናው በሴቶች አጠቃላይ አሸናፊዎች፣ 1ኛ. መከላከያ ስፖርት ክለብ በ158 ነጥብ ዋንጫ ተሸላሚ፣ 2ኛ. ኦሮሚያ ክልል በ148 ነጥብ፣ 3ኛ. ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ107 ነጥብ የደረጃ ሰንጠረዥ ውስጥ መካተት ችለዋል። በወንዶች አጠቃላይ አሸናፊዎች፣ 1ኛ. መከላከያ ስፖርት ክለብ በ180 ነጥብ ዋንጫ ተሸላሚ ሲሆን፣ 2ኛ. ኦሮሚያ ክልል በ177 ነጥብ፣ 3ኛ. ሲዳማ ቡና በ106 ነጥብ ባለድል ነበሩ። ከፍተኛ ፉክክር በታየበት ሻምፒዮና በሁለቱም ጾታ አጠቃላይ አሸናፊዎች መከላከያ ስፖርት ክለብ በ338 ነጥብ አንደኛ ሆኖ የዋንጫ ተሸላሚ ነበር። የኦሮሚያ ክልል ደግሞ በ325 ነጥብ በሁለተኛ ደረጃ ሲያጠናቅቅ፤ ሲዳማ ቡና በ202 ነጥብ በሦስተኛ ደረጃ ነበር ያጠናቀቁት፡ ፡ ትናንት የተጀመረውና እስከ መጪው ግንቦት 04 ቀን 2011 ዓ.ም ለስድስት ተከታታይ ቀናት በሚካሄደው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የአትሌቲክስ ስፖርት ወዳዱ ህብረተሰብ በአዲስ አበባ ስታዲየም ተገኝቶ ይደግፋል ተብሎ ይጠበቃል።አዲስ ዘመን ሚያዚያ 30/2011በዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=10414
680
2ስፖርት
የመጀመሪያው ታዳጊ አትሌቶች ስልጠና ማኑዋል
ስፖርት
May 9, 2019
19
የአትሌቲክስ ስፖርት እና ኢትዮጵያ ሊነጣጠሉ የማይችሉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች መሆናቸው ይታወቃል። ነገር ግን ስፖርቱ ለዘመናት ይከወን የነበረው በልምድ መሆኑ ውጤታማነቱ ከጊዜው ጋር እየተራመደ አለመሆኑ በባለሙያዎች ይጠቆማል። በስፖርቱ ተተኪዎችን ለማፍራት እንዲሁም ውጤታማነትን ለማረጋግጥ ሲባልም ትኩረቱን በታዳጊዎች ላይ ያደረገ ሳይንሳዊ ስልጠና መስጠት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል። ማሰልጠኛ ማዕከላት ከተበራከቱ እና ታዳጊዎች ላይም ትኩረት ከተደረገ በኋላም ግን የሚፈለገውን ውጤት ለማስመዝገብ አልተቻለም። በእኩል ደረጃ በሚገኙት ማዕከላት እንዲሁም ፕሮጀክቶች የሚታየው አፈጻጸምም የተለያየ መሆኑ ተረጋግጧል። ለዚህም እንደ ምክንያት የሚነሳው ስልጠናው ወጥ ባልሆነና በተዘበራረቀ መልኩ የሚሰጥ በመሆኑ ነው። ለዚህም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን፤ የታዳጊ አትሌቶች አትሌቲክስ ስፖርት ስልጠና ማኑዋል አዘጋጅቷል። ይህ የስልጠና ማኑዋልም በሃገሪቷ የመጀመሪያ ሲሆን፤ ዕድሜያቸው ከ14-17 ለሆናቸው ታዳጊዎች የተዘጋጀ ነው። ይህም ማለት በፕሮጀክቶች፣ ማሰልጠኛ ማዕከላት እንዲሁም አካዳሚዎች ውስጥ ለሚሠለጥኑ ታዳጊዎች የሚያገለግል ነው። ሰነዱን መሰረት አድርጎ መሥራትም በትክክለኛ ዕድሜ ላይ የተመሰረተ፣ ወጥነትና ተመጋጋቢነት ያለውን ስልጠና ለመስጠት የሚረዳ ይሆናል። በዕድሜ እርከን ከማሰልጠን ባሻገርም ያለ ዕድሜ የሚመጣን ጉዳት ለመከላከል የሚያግዝ ይሆናል። የበርካታ ሃገራት ተሞክሮ የተጠናቀረበት ማኑዋሉ፤ ምልመላን፣ የዕድሜ ልየታን፣ የስልጠና መስክ መረጣን፣ ስልጠናን፣ ምዘናን እንዲሁም ሽግግርን ያካተተ ነው። በፌዴሬሽኑ የፕሮጀክት፣ ማዕከላት፣ የአካዳሚ፣ ክለቦች እንዲሁም ብሄራዊ ቡድንና ማናጀሮች ስልጠና ዋና አስተባባሪ ዶክተር ይልማ በርታ ሰብሳቢነት በተዘጋጀው በዚህ ማኑዋል ላይም አሰልጣኞች እና ከፌዴሬሽኑ የተወጣጡ ባለሙያዎች ተሳትፎ አድርገውበታል። በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በተደራጀ መልኩ በተዘጋጀው የማኑዋል ማስተዋወቂያ መርሐ ግብር ላይም፤ ወጥ ስልጠና በመስጠት ውጤታማ መሆን እንደሚቻል በአዘጋጆቹ ተጠቁሟል። ባለድርሻ አካላት በተገኙበትም በመጽሐፍ መልክ ስለተዘጋጀው ማኑዋል ገለጻ ተደርጓል። የአሰላ ከተማ የታዳጊ ፕሮጀክት ጣቢያ አሰልጣኝ ሳሙኤል ዳኜ፤ የማኑዋሉ መዘጋጀት በታዳጊዎች ስልጠና ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ይገልጻል። ከዚህ ቀደም እንደሚታወቀው አሰልጣኞች ስልጠናውን ለአትሌቶች ይሰጡ የነበረው በራሳቸው ዘይቤ ነው። የማኑዋሉ ዝግጅት ግን ስልጠናውን ለይቶ በታዳጊዎቹ ዕድሜ ልክ በመስጠት ለማብቃት የሚያስችል ይሆናል። ታዳጊዎን ማሰልጠን ፈታኝ ሲሆን፤ ከምልመላው ጀምሮ የሚሳተፉበትን የስፖርት ዓይነት በመለየት አሠልጥኖ ለሌሎች ማቀበልን የሚጠይቅ ሥራም ነው። በመሆኑም የማኑዋሉ ዝግጅት ስልጠናውን ከመደገፉም ባሻገር በዕድሜ ጉዳይም አነጋጋሪ የሆነውን ችግር ሊፈታ የሚችል እነደሆነ እምነቱን ያንጸባርቃል። በደቡብ ክልል የሚገኘው የሃገረ ሰላም አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል አሰልጣኝ መሰለ አበረ፤ ማኑዋሉ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ይጠቁማል። ማኑዋሉ ከዚህ ቀደም ተዘጋጅቶ ቢሆን እስከአሁንም አሰልጣኞች ሥራቸውን በአግባቡ ያከናውኑ ነበር። ከዚህ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብም ይቻል ነበር፤ ይህ ባለመኖሩ ግን አሰልጣኞች ያላቸውን ነገር በትክክል ማሳየት እንዳልቻሉ ያስረዳል። ስልጠና የሚጀምረው ከታች ሆኖ ሳለ እንደ ሃገር የዕድሜን ጨምሮ በርካታ ችግሮች በስልጠናው ላይ ይስተዋላሉ። በመሆኑም የማኑዋሉ ዝግጅት ከችግሮቹ መካከል ጥቂቱን የሚያቃልል ይሆናል። ሰልጣኞች በዕድሜያቸው የሚገቡ ከሆነም ተገቢውን ስልጠና በመውሰድ ውጤታማ መሆን ይችላሉምም ወደ ተለያዩ ክልሎች እና ትምህርት ቤቶች ወርዶ መሥራት የሚቻል ከሆነ ደግሞ የተሻለ ነገር ለማስመዝገብ ይቻላል። ማኑዋሉ ለመዘጋጀት ምክንያት የሆነው አሰልጣኞች ካላቸው ክህሎት በተጓዳኝ እገዛ እንዲያደርግላቸው እንዲሁም ከተለመደው ባሻገር በስፖርታዊ ስልጠና ታዳጊዎቻቸውን እንዲያዘጋጁ ለማድረግ በሚል መሆኑን፤ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስልጠና ጥናትና ምርምር የሥራ ሂደት መሪ አቶ ሳሙኤል ብርሃኑ ይገልጻሉ። ከዚህ ቀደም ፌዴሬሽኑ በተለያዩ ፕሮጀክቶች ላይ ባደረገው ቅኝት አብዛኛዎቹ ስኬታማ እንዳልሆኑ ለመታዘብ ተችሏል። ችግሩም ትክክለኛ እና ወጥ የሆነ የማሰልጠኛ ማኑዋል የሌላቸው በመሆኑ ነው። አብዛኛዎቹ ተመልማዮች በሚገባቸው ስልጠና ላይ አለመሆናቸውንም ይጠቁማሉ። በስፖርቱ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እንደሚረዳ የታመነበት ማኑዋሉ፤ ከውጭ ሃገራት ልምድ ከመውሰድ ባለፈ በሃገሪቷ በተደረገው ዳሰሳ ላይ መሰረት ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑንም ያስረዳሉ። በመሆኑም በአቋራጭ አትሌቶችን በተለያዩ ውድድሮች ላይ በማሳተፍ ውጤት ለማግኘት የሚደረገውን አካሄድም ይቀርፋል። ይህም በፕሮጀክት የሚሠለጥኑ ታዳጊዎች ላይ ትኩረት በማድረግ አትሌቶች እንደየመስካቸው እንዲሠለጥኑ በማድረግ ነው። ማኑዋሉ ውጤታማ እንደሚያደርግ የታመነበት ቢሆንም ጊዜ እንደሚያስፈልግ የሥራ ሂደት መሪው አያይዘው ይጠቅሳሉ። ከአትሌቶችም ባሻገር አሠልጣኞች ማኑዋሉን ተረድተው ስልጠናውን መስጠት እንዲችሉ እየተሠራ ይገኛል። ከውጭ ሃገራት ከሚመጡ ዓለም አቀፍ አሰልጣኞች ባሻገርም ኢትዮጵያዊያን ሙያተኞች በየደረጃው የሃገር ውስጥ የአሰልጣኞች የሙያ ማሻሻያ ስልጠና እንዲያገኙ ይደረጋል። በየጊዜው ለሚቀየሩና ለሚከለሱ ነገሮችም ራሳቸውን እንዲያበቁ በማገዝ ከሌላው ዓለም እኩል እንዲራመዱ እንደሚደረግም ያስረዳሉ።አዲስ ዘመን  ግንቦት 1/2011በብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=10468
541
2ስፖርት
ሶስተኛ ቀኑን የያዘው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና
ስፖርት
May 9, 2019
24
በመክፈቻው ዕለት በመም እና በሜዳ ላይ ተግባራት ሀገር አቀፍ ክብረወሰን በመስበር የተጀመረው፤ 48ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ሶስተኛ ቀኑን ይዟል። ከሰዓት በኋላ በሚኖረው መርሃ ግብርም ስድስት የፍጻሜ ውድድሮች ይካሄዳሉ። ከትናንት በስቲያ በተጀመረው በዚህ ሻምፒዮና ላይ ጠዋት እና አመሻሽ ላይ የተለያዩ የማጣሪያ እና የፍጻሜ ውድድሮች ተካሂደዋል። ጠዋት በተካሄደው የወንዶች ሱሉስ ዝላይ የፍጻሜ ውድድር የመከላከያው አትሌት አዲር ጉር፤ 15 ነጥብ 88 ሜ በመዝለል በራሱ ተይዞ የቆየውን ክብረወሰን አሻሽሏል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንኩ ቡኒኒ አንበሴ እና የሲዳማ ቡናው ጆሴፍ ኦባንግ ደግሞ እርሱን ተከትለው የሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃን የያዙ አትሌቶች ሆነዋል። በዕለቱ የተካሄደው ሌላኛው የፍጻሜ ውድድር ደግሞ የሴቶች አሎሎ ውርወራ ነው። በዚህ ውድድር ላይም ዙርጋ ኡስማን ከሲዳማ ቡና፣ አመለ ይበልጣል ከመከላከያ እንዲሁም ሰላማዊት ማሬ ደቡብ ፖሊስ ቀዳሚውን ደረጃ በመያዝ አጠናቀዋል። አመሻሽ ላይም በወንዶች እና ሴቶች የ10ሺ ሜትር ውድድሮች ተካሂደዋል። አስቀድሞ በተደረገው የወንዶች ውድድር ላይም በ87 አትሌቶች መካከል ከፍተኛ ፉክክር የተካሄደ ሲሆን፤ ወጣቱ አትሌት ሰለሞን ባረጋ አሸናፊ ሆኗል። አንዱዓለም በልሁ እና አባዲ ሀዲስ ደግሞ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ የብር እና ነሃስ ሜዳሊያ ተሸላሚዎች ሆነዋል። ሌላኛው ከፍተኛ ፉክክር የተካሄደበትና ሀገር አቀፍ ክብረወሰንም የተሻሻለበት ውድድር በሴቶች መካከል የተካሄደው ነው። ታዋቂ አትሌቶችን ጨምሮ ከ54 በላይ አትሌቶች የተሳተፉበትን ውድድርም የትራንስ ክለብ አትሌት የሆነችው ለተሰንበት ግደይ 32 ደቂቃ ከ10 ሰከንድ ከ13 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት ሸፍናለች። አትሌት ፀሐይ ገመቹ እና ነፃነት ጉደታ ደግሞ በማይክሮ ሰከንዶች (32:17.20 እና 32:17.82 በሆነ) ተቀዳድመው ውድድራቸውን አጠናቀዋል። ትናንት በሁለተኛው ቀንም የተለያዩ ውድድሮች ፍጻሜያቸውን አግኝተዋል። በሱሉስ ዝላይ የሴቶች ፍፃሜ ውድድርም፤ የመከላከያዋ አጁዳ ኡመድ፣ የንግድ ባንኮቹ አራያት ዲቦ እና አማር ኡባንግ አሸናፊዎች ሆነዋል። በወንዶች 400 ሜትር ደግሞ አብዱራህማን አብዱ ኦሮሚያ ክልል፣ ኤፍሬም መኮንን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ፣ ሙስጠፋ ኢደኦ ከኦሮሚያ ክልል ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ ይዘዋል። በ100 ሜትር የወንድ እና የሴት ውድድሮችም በትናንትናው ዕለት የተፈጸሙ ሲሆን፤ የትኛው አትሌት እንደቀደመ መለየት እስኪያዳግት ድረስ እጅግ ከፍተኛ ፉክክር የታየበትም ነበር። በሴቶች በተካሄደው ውድድርም ወርቄ ኩማሎ ከንግድ ባንክ፣ ሰዓዳ ሲራጅ ከመከላከያ እንዲሁም አቤቤ ከበደ ከኦሮሚያ ክልል በማይክሮ ሰከንዶች ልዩነት ገብተዋል። በወንዶች በተካሄደው ውድድር ደግሞ የኤሌክትሪኩ ናታን አበበ፣ የሲዳማ ቡናው ቴዎድሮስ አጥናፉ እንዲሁም የኦሮሚያ ክልሉ አብዱልሰታር ከማል አሸናፊዎች ሆነዋል። ዛሬ 9 ሰዓት ላይ በሚጀምረው የሶስተኛ ቀን መርሃ ግብር ላይም የወንዶች ዲስከስ ውርወራ፣ የሴቶች የርዝመት ዝላይ፣ የሴትና ወንድ 400 ሜትር መሰናክል እንዲሁም በሁለቱም ጾታ የ800 ሜትር ውድድር የሚካሄድ ይሆናል።አዲስ ዘመን  ግንቦት 1/2011በብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=10470
348
2ስፖርት
ስፖርት አካዳሚው በዘርፉ ችግር ፈች ጥናትና ምርምር ማድረግ አለበት ተባለ
ስፖርት
May 8, 2019
41
ኢትዮጵያ የወጣቶች ስፖርት አካዳሚ በስፖርት ባለሙያዎች አቅም ግንባታና በዘርፉ ችግር ፈች ጥናትና ምርምር በማድረግ የመፍትሄ አቅጣጫ ማስቀመጥ እንዳለበት ተገለፀ። አካዳሚው የ9 ወር የእቅድ አፈጻጸም እንዲሁም በሚሻሻሉ የአካዳሚ ፖሊሲዎች ህጎችና መመሪያዎች ላይ ያተኮረ ለሁለት ቀን የሚቆይ ውይይት በአዳማ ጀምሯል። የስፖርት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ጌታቸው ባልቻ በዚሁ ወቅት እንደገለፁት የወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ብሄራዊ ጀግና አትሌቶችንና እነሱን የሚያፈሩ ብቁ ባለሙያዎችን እንዲያፈራ ታልሞ የተመሰረተ ነው።ከዚህም ባሻገር በዘርፉ የጥናትና ምርምር ስራዎችን የመስራት ተልእኮ የተሰጠው የስፖርት ተቋም ነውም ብለዋል።የስፖርት ልማት ከሳይንሳዊ ጥናትና ምርምር ውጭ ሊሳካ እንደማይችል የገለፁት ምክትል ኮሚሽነሩ ፤ በዚህም እየተተገበረ ያለው ስራ በሚፈለገው ደረጃ ተግባራዊ ለማድረግና መፍትሄ ለመስጠት የዘርፉ ባለሙያዎች ርብርብ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ጠቁመዋል። የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሃብታሙ ሲሳይ በበኩላቸው አካዳሚው የተቋቋመበትን አላማ እንዲያሳካ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።በስፖርቱ ልማት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት አካዳሚው መሬት ላይ ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉና ችግር ፈች ጥናትና ምርምር ላይም ጠንክሮ መስራት እንዳለበት አሳስበዋል። የኢትዮጵያ ወጣቶችና ስፖርት አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር አቶ አንበሳው እንየው እንዳሉት አካዳሚው ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ኢትዮጵያን በአህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የውድድር መድረኮች ስሟን ያስጠሩና ተተኪ ስፖርተኞችን በማፍራት ስኬታማ ተግባራትን አከናውኗል።ያም ቢሆን የስፖርት ባለሙያዎች አቅም በመገንባትና ችግር ፈች ጥናትና ምርምር ከማካሄድ አንፃር አካዳሚው የሚጠበቅበትን ስራ እንዳልሰራ ጠቅሰው ያሉትን ችግሮች ለመፍታት ትኩረት ሰጥቶ መስራት አለበት ማለታቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው። አካዳሚው የ9 ወር የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርቦ ውይይት እየተካሄደበት ነው።አካዳሚው በ2003 ዓ.ም የተቋቋመ ሲሆን በ10 የስፖርት አይነቶች በአዲስ አበባና በአሰላ እያሰለጠነ ይገኛል።አዲስ ዘመን ሚያዚያ 30/2011
https://www.press.et/Ama/?p=10420
218
2ስፖርት
የሁለቱ ክለቦች ደብዳቤና የብሄራዊ ፌዴሬሽኑ ዝምታ
ስፖርት
May 9, 2019
61
በእግር ኳስ ጨዋታ ታሪክ ውስጥ በተለያዩ አገሮች ሊግ ላይ የሚስተዋል የአልሸነፍ ባይነት ስሜት እንደየዘመኑ የራሱን ታሪክ አስፍሮ አል ፏል፡፡ የሁሉም አገሮች ሊግ መልካም፣ መጥፎ፣ አስደንጋጭ፣ አከራካሪ፣ አሳዛኝና አስቆጪ የሆኑ ክንውኖች ነበሩት፡፡ በሁለት ክለብ ደጋፊዎች መካከል በሚፈጠር የአልሸነፍ ባይነት ስሜትና ፀብ አጫሪነት በስታዲየሞች የሚገኙትን ተመልካቾች ወደ ማያስፈልግ ሁከት ውስጥ ሲከት ይስተዋላል፡፡ በሌሎች አገሮች መካከል የሚፈጠረው የባላንጣነት ስሜት እግር ኳስና እግር ኳስን መሠረት ያደረገው ሚዛኑ ይደፋል፡፡ በኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ በተለይ በክልል ስታዲየሞች በርካታ ሁከቶች ተከስተው በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡ የተመልካቾች አካል መጉደል፣ የስታዲየም መሠረተ ልማቶች መጥፋትና ለቀጣይ ውድድር ቂም ቋጥሮ፣ አንድ ክለብ ወደ ሌላ ክልል ስታዲየም ሄዶ ጨዋታ ሲያደርግ እስከመበቀል ደረጃ ተደርሷል፡፡ ሒደቱ በክልል ከተማ ሳይወሰን በአዲስ አበባም መስተዋሉ በብዙዎች ዘንድ አግራሞትን የጫረ ነገር ያደርገዋል፡፡ የጉዳዩን ስፋትና ጥልቀት እንዲሁም አሳሳቢነትን በመረዳት በብሄራዊ ፌዴሬሽኑ ሆነ ባለድርሻ አካላት መፍትሄ፣ መፍትሄ……ያላሉበት ወቅት አልነበረም። የስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል ከጊዜ ወደ ጊዜ እያየለ ቢሆንም፤ ውጤት ያመጣሉ ተብለው የታመነባቸው የውይይት መድረኮች፣ ጥናቶች፣ አስተያየቶች ከሰሞኑም ሳይቀር ሲካሄዱ ነበር። ወደ ፊትም ይቀጥላሉ፤ ነገር ግን ውጤት መቼ ያመጣሉ ? የሚለውን ለመመለስ ትግስት ያስፈልጋል የሚሉ የስላቅ ምላሾች እንዲበረክቱ አድርጓል። የስፖርታዊ ጨዋነት ችግር በተመለከተ በስፋት ከመነገሩ የመነጨ ይመስል ችግሩ እስከ መለመድ ተደርሷል። ይሄው የተለመደው ችግር ከሰሞኑ ደግሞ ከወደ መቐለና ጎንደር አካባቢ ሌላ ውዝግብ ፈጥሯል። የፋሲል ከነማና ደደቢት እግር ኳስ ክለቦችን ደብዳቤ አማዟል። ጉዳዩ እንዲህ ነበር። በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 23ኛ ሳምንት ከተደረጉት ጨዋታዎች መካከል ቅዳሜ ዕለት ደደቢት እና ፋሲል ከነማ ተፋጠዋል። መቐለ በሚገኘው በትግራይ አለም ዓቀፍ ስታዲየም ረፋድ ላይ ጨዋታው ተጀምሯል። በጥሩ ፍጥነት ሲጀምር ግብ ለማስተናገድም ብዙ ደቂቃ አልፈጀበትም። በአራተኛው ደቂቃ በሳጥኑ ቀኝ በኩል የተሰራውን ጥፋት ተከትሎ የተገኘውን ቅጣት ምት አምሳሉ ጥላሁን በግሩም ሁኔታ አስቆጠረ ። ዐፄዎቹ ቀዳሚ መሆን ቻሉ ፤ ደደቢቶች ተመሩ። የግቡ መቆጠርን ተከትሎ በፋሲል ተቀያሪ ተጫዋቾች ላይ በተወረወሩ ቁሳቁስ ምክንያት ጨዋታው ለጥቂት ደቂቃዎች ተቋረጠ። ሳይቆይ እንዲቀጥል ተደረገ። ፈጣን የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ ያሳዩት አጼዎቹ በተደጋጋሚ የደደቢቶችን መረብ ይደፍሩ ጀመር። በዚህ መልክ እስከ 65 ኛው ደቂቃ 4 ግቦችን ማስቆጠር ቻሉ። አራት ግቦችን ያስተናገደው የደደቢቶች መረብን ተከትሎ በ65ኛው ደቂቃ ከተመልካቾች ድንጋይ እና ቁሶች ተጀመረ። በዚህም ምክንያት ጨዋታው ለአንድ ሰዓት ያህል ለሁለተኛ ጊዜ ለመቋረጥ በቃ። በተመልካቾቹ የተወረወረው ቁሳቁስ በርካታ የፋሲል ከነማን ተጫዋቾች ለጉዳት የዳረገ ሲሆን ፤ በወቅቱ ጨዋታውን በዝግ ስታድየም ላድረግ ግድ ያለ ሲሆን ጨዋታው ቀጥሎ በፋሲል 5 ለ 1 ተጠናቋል። ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላም ፋሲል ከነማ ለብሄራዊ ፌዴሬሽኑ ቅሬታውን አሰማ። ፋሲል ከነማ ከጨዋታው በፊት እና በጨዋታው ዕለት የስፖርታዊ ጨዋነት ጥሰት እንደተፈፀመበት በመጥቀስ በመቐለ 70 እንደርታ እና የትግራይ እግርኳስ ፌዴሬሽን ላይ እርምጃ መወሰድ ይገባል ሲል ተደምጧል። ክሱንም ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ማቅረቡን በፌስ ቡክ ገፁ አስታውቋል። ክለቡ ሁለት ገጽ ደብዳቤ በመላክ ጉዳዩን እንዲያጤን ለፌዴሬሽኑ እንደላከና ምላሽ እየተጠባበቀ መሆኑን አስታውቋል። ፋሲል ከነማ ለብሄራዊ ፌዴሬሽኑ የላከውን ደብዳቤ ምላሽ እየተጠባበቀ ባለበት ወቅት፤ ከወደ መቐለ ሌላ ደብዳቤ ዜና መሰማቱ ጉዳዩን ትኩረት ሳቢ እንዲሆን አድርጎታል። ደደቢት ፋሲል ከነማን ባስተናገደበት ጨዋታ ስለተፈጠረው ስርዓት አልበኝነት ያለውን አቋም በደብዳቤ ለፌደሬሽን ማሳወቁን በተመሳሳይ ወጥቷል። ሶከር ስፖርት የክለቡ ፕሬዝዳንት አቶ ሚካኤል ዓምደ መስቀል በማነጋገር ባወጣው ዘገባ፤ በወቅቱ በተፈጠረው ስርአት አልበኝነት ላይ ክለቡ ሙሉ ኃላፊነት የሚወስድ ይሆናል እንዳሉ ጽፏል። «ጨዋታው ካለቀ በኃላ ጉዳዩ በጣም እንደሚያሳዝን እና መደገም የሌለበት መሆኑ አቋም ተይዟል ። ኃላፊነቱም ደደቢት ሙሉ ለሙሉ ለመውሰድ ከስምምነት ተደርሷል። ክለቡ ይሄንኑም ለጨዋታው ኮሚሽነር ገልጸናል» ሲሉ መናገራቸውን ዘግቧል። ፕሬዝዳንቱ ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ለፌዴሬሽኑ ደብዳቤ መላኩን ተከትሎ የቀረበ ሃሳብ ስለመሆኑ እንደተናገሩት፤ «አሁን ጉዳዩ ከሶስተኛ ወገን ጋር ሲያያዝ እሱን ተከትለን የሰጠነው ኃሳብ አይደለም። ልክ ጨዋታው እንዳለቀ ለጨዋታው ኮምሽነር አቋማችን አስረግጠን ተናግረናል»። ደደቢት ለተፈጸመው ድርጊት ክለቡ ኃላፊነት ከመውሰድ ባለፈ የሚመጣውን ቅጣት ለመቀበል ዝግጁ መሆኑን ያስታወቅ እንጂ፤ በሌላ ወገን የያዘው አቋም ከፋሲል ከነማ ክስ ጋር የሚጋጭ መሆኑ ተሰምቷል። ፋሲል ከነማ ለፌዴሬሽኑ በላከው ደብዳቤ እንዳሰፈረው፤ ከጨዋታው በፊት እና በጨዋታው ዕለት የስፖርታዊ ጨዋነት ጥሰት እንደተፈፀመበት በመጥቀስ በመቐለ 70 እንደርታ እና የትግራይ እግርኳስ ፌዴሬሽን ላይ እርምጃ መወሰድ እንደሚገባ ያመላክታል። የደደቢት እግር ኳስ ክለብ በሌላ ወገን ድርጊቱን የፈጸሙት የእኔ ደጋፊዎች ናቸው ሲል ችግሩ ወደ ሶስተኛ ወገን መገፋት እንደሌለበት ለሶከር ኢትዮጵያ በሰጡት ቃለ ምልልስ፤ «በሜዳችን እየተጫወትን እንዴት ነው ደጋፊ የለንም ማለት የምንችለው። ባለፉት ጨዋታዎችም እኮ ደጋፊዎች ነበሩን። በርካታ የመቐለ ማልያ የለበሱ ደጋፊዎች ነበሩ ለተባለውም እኛ ለደጋፊያችን ማልያ ለማቅረብ አቅም ስሌለለን ደጋፊው የመቐለም የሌላም ክለብ ማልያ አድርጎ ነው የሚገባው» ሲሉ የፋሲል ከነማ ክስ አቅጣጫውን የሳተ መሆኑን አመላክተዋል ። በዚህ ጉዳይ ላይም የመቐለ እግር ኳስ ክለብ ምላሽ የሰጠ ሲሆን፤ «በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 23ኛ ሳምንት ቅዳሜ ዕለት በተካሄደው የደደቢት እና ፋሲል ከነማ ጨዋታ ላይ የተከሰተውን ስርዓት አልበኝነት በተመለከተ ፋሲል ለፌዴሬሽን በላከው ደብዳቤ መቐለ 70 እንደርታ እና የትግራይ እግርኳስ ፌዴሬሽን ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ክስ ማቅረቡ ይታወሳል። ክለቡ ያቀረበው ክስ ተገቢ ያልሆነና የመቐለ ክለብ ደጋፊዎችን ባልዋሉበት የወነጀለ መሆኑን ለብሄራዊ ፌዴሬሽኑ ደብዳቤ ልኳል። ፋሲል ከነማ ለፌዴሬሽኑ የላከው የክስ ደብዳቤ ምላሽ ያልተሰጠው ሲሆን፤ በደደቢት በኩል ለችግሩ ኃላፊነት እንወስዳለን በሚል ስለ ተጻፈው ደብዳቤ በብሄራዊ ፌዴሬሽኑ በኩል እስካሁን ከዝምታ ውጪ ምላሽ አልተሰማም። የሁለቱ ክለቦች ደብዳቤና የብሄራዊ ፌዴሬሽኑ ዝምታን በምን መልኩ መቋጫ ያገኛል የሚለው በስፖርት ቤተሰቡ ዘንድ አነጋጋሪ ሆኗል። ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ ስፖርታዊ ጨዋነትን በእግር ኳሱ ፈር ለማስያዝ በቁርጠኝነት እየሠራ መሆኑን በተደጋጋሚ በሚናገርበት ወቅት ለሁለቱ ክለቦች ደብዳቤ የሚሰጠውን ምላሽ በጉጉት እንዲጠበቅ ያደረገው ሆኗል።አዲስ ዘመን  ግንቦት 1/2011በዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=10472
773
2ስፖርት
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 24ኛ ሳምንት ጨዋታዎች
ስፖርት
May 10, 2019
28
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ24ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በመዲናዋና በክልል ከተሞች ዛሬ፣ ነገና እሁድ ስምንት ጨዋታዎች የሚካሄዱ ሲሆን፤ የሊጉ የሳምንቱ ትልቁ ጨዋታ ሲዳማ ቡና ከመቐለ 70 እንደርታ የሚያደርጉት ፍልሚያ እሁድ ግንቦት 4/2011 ዓ.ም በሀዋሳ ስታዲየም ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ላይ ይካሄዳል። ከዚህ ባለፈ ዛሬ በሊጉ አንድ ጨዋታ ሲካሄድ፤ ስሑል ሽረ በሜዳው ኢትዮጵያ ቡናን ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ያስተናግዳል። እንዲሁም ቅዳሜ ዕለት አንድ የሊጉ ጨዋታ ሲካሄድ፤ ላለ መውረድ እየታገለ ያለው ወላይታ ድቻ በሜዳው ወራጅ ቀጣና ውስጥ የሚገኘውን ሰማያዊዎቹን ደደቢትን ያስተናግዳል። ሊጉ እሁድ ዕለት ስድስት ጨዋታዎች የሚያካሂድ ሲሆን፤ የጣና ሞገዶቹ ባህርዳር ከተማ በሜዳቸው ከድሬዳዋ ከተማ፣ ጅማ አባ ጅፋር ከሀዋሳ ከተማ፣ አዳማ ከተማ ላለመውረድ ከሚታገለው ከመከላከያ እንዲሁም አፄዎቹ ፋሲል ከነማ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በፋሲል ስታዲየም የሚያደርጉት ፍልሚያ በተመሳሳይ ሰዓት ከቀኑ 9፡00 ሰዓት የሚፋለሙ ይሆናል። በአንጻሩ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወራጅ ቀጣና ውስጥ የሚገኘውን ደቡብ ፖሊስን በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚያስተናግድበትጨዋታ በዚሁ ዕለት ምሽት 10፡00 ሰዓት ይካሄዳል። ፕሪሚየር ሊጉን መቐለ 70 እንደርታ በ48 ነጥብ ሲመራ፣ ፋሲል ከነማ በ43 ነጥብ በሁለተኛ ደረጃ ተቀምጧል። ሲዳማ ቡና ደግሞ በ40 ነጥብ ሦስተኛ ደረጃን ይዞ ይከተላል። ደቡብ ፖሊስ፣ ስሑል ሽረ እና ደደቢት ደግሞ ከ14ኛ እስከ 16ኛ ያሉትን የመጨረሻዎቹን ሦስት ደረጃዎች ይዘው ወራጅ ቀጣና ውስጥ ይገኛሉ፡ የፕሪሚየር ሊጉን ኮከብ ጎል አግቢነት የመቐለ 70 እንደርታው አማኑኤል ገብረሚካኤል በ14 ጎሎች፣ የሲዳማ ቡናው አዲስ ግደይ በ13 ጎሎች እንዲሁም የመከላከያው ምንይሉ ወንድሙ በ11ጎሎች ከአንድ እሰከ ሦስት ያሉትን ደረጃዎች ይዘው ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነቱን እየመሩ ይገኛሉአዲስ ዘመን ግንቦት 2/2011
https://www.press.et/Ama/?p=10525
216
2ስፖርት
ስፖርቱን ‹‹በተሰጥኦ ሥፍራዎች››
ስፖርት
May 10, 2019
33
በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የፈለቁ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለበርካታ ዓመታት በታላላቅ የዓለማችን የአትሌቲክስ ውድድሮች ላይ ለኢትዮጵያ የላቁ ውጤቶችን እያስመዘገቡ ቆይተዋል፡፡ በረጅም ርቀት 10ሺ እና 5ሺ ሜትር፤ እንዲሁም በመካከለኛ ርቀት የአትሌቲክስ ውድድሮች ዓለምን ተቆጣጥረዋል፡፡ በማራቶንና በጎዳና ላይ ሩጫዎች በሚያስመዘግቧቸው ውጤቶችም የገነኑ ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ የሰንደቅ ዓላማዋ ምልክትና መታወቂያዋ የሆነው የአትሌቲክስ ስፖርት ከእጅ ሳያመልጥ፤ እንዲሁም በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በፍፁም የበላይነት በሜዳሊያ እያሸበረቅን ውጤት ባስመዘገብንባቸው የአት ሌቲክስ ውድድሮችን ጠብቆ ለማስጓዝም ሆነ ተጨማሪ ድሎችን ለማስመዝገብ አዳዲስ የአሠራር ስልቶችን መከተል እንደሚገባ ምሁራን ይናገራሉ፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስሟ በገነነው የሯጮች ምድር ኢትዮጵያ በተንጣለሉ መስኮች እና ጋራዎች ልምምድ እና ስልጠና ማካሄድ የተለመዱ ትእይንቶች ቢሆኑም፤ የትኛው አካባቢ ለየትኛው የስፖርት ዓይነት ልምምድ ይሆናል የሚል ሳይንሳዊ እሳቤን ተከትሎ በመስራት ረገድ ከፍተት መኖሩንና፤ ለአትሌቲክሱ ስፖርት የተሰጥኦ አካባቢዎችን ለይቶ አትሌቶችን ማፍለቅ ትኩረት የሚሻው ጉዳይ ስለመሆኑ የሚናገሩት የዘርፉ ምሁራን ይህን መሰል ሳይንሳዊ ጥናትና ዘመናዊ የልምምድ መዋቅር በአግባቡ ተዘርግቶ ሊሰራበት እንደሚገባም ያሳስባሉ፡፡ በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ሳይንስ መምህር ረዳት ፕሮፌሰር አረፋይኔ መስፍን እንደሚሉት፤ የተሰጥኦ ስፍራ የሚባለው በዋናነት በኢትዮጵያ የተለመደውን የረጅም ርቀት ሩጫ መነሻ ያደረገ ነው፡፡ ሳይንሱም የሚደግፈው ይህንኑ ነው፡፡ ረጅም ርቀትን በሚመለከት ከዚህ ቀደም የተጀመሩ ሥራዎች አሉ፡፡ ለምሳሌ ደብረ ብርሃንና አሰላ በቆጂ አካባቢዎች ለረጅም ርቀት ተስማሚ ስፍራዎች ናቸው ተብለው ይታሰባሉ፡ ፡ በደቡባዊ የትግራይ ክፍል ማይጨውና ራያ አካባቢ ለረጅም ርቀት ሩጫ ተስማሚ ከሚባሉት ስፍራች መካከል ናቸው፡፡ በአማራ ክልል ጎጃም ጢስ አባይ አካባቢም ተከላ የሚባለው ስፍራ እንዲሁ አመቺ ቦታ ነው፡፡ ደቡብ ጎንደር ወረታን ተከትሎ ባሉት ደጋማ አካባቢዎች እስካሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ከተሰጥኦ ስፍራዎች ውስጥ ተመድበው እየተሰራባቸውና የተሻለ የአትሌቲክስ ስፖርተኞች እየፈለቁባቸው ይገኛል፡፡ በዋናነት አሁን ያሉት የረጅም ርቀት ቦታዎች ለመካከለኛ ርቀት ሩጫዎችም ያገለግላሉ፡፡ ‹‹ለአጭር ርቀትና የሜዳ ተግባራት የስፖርት ዓይነቶች በአብዛኛው በአገሪቱ ያሉ ቆላማ አካባቢዎች ተመራጮች ናቸው፡፡ ነገር ግን በዚህ መስክ ያን ያህል በዓለም መድረክ አንታወቅበትም፡፡ ለዚህ የስፖርት ዓይነት የተሰጥኦ ቦታዎችን ለይቶ መስራት ከተቻለ ግን ውጤት ይገኝበታል፡፡ በእርግጥ ጅማሬዎች አሉ፡፡ ለምሳሌ ቆቦ አካባቢ ይህንን በተከተለ መንገድ የተጀመሩ ሥራዎች አሉ፡፡ በምሥራቅ የአገሪቱ አካባቢዎች ሱማሌና አፋር አካባቢ ተስማሚ ቦታዎች አሉ፡፡ የሜዳ ተግባራት በተለይ ውርወራ በደቡብ ኦሞ አካባቢ ያሉት ስፍራዎች ልምምድ ቢደረግባቸው ምቹ መሆናቸው ይመከራል፡፡ በጋምቤላና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ አካባቢዎችም በፕሮጀክትም ሆነ በክለብ ደረጃ ያሉ አትሌቶች ኢትዮጵያን በመወከል ትልቅ ውጤት እያመጡ በመሆናቸው ስፍራው ትኩረት እንዲደረግበት ያነሳሳል›› ሲሉ ረዳት ፕሮፌሰር አረፋይኔ የትኛው ሥፍራ ለየትኛው የስፖርት ዓይነት መለማመጃ እንደሆነ ያብራራሉ፡፡ የተሰጥኦ ስፍራ የሚባሉ ቦታዎችን ለመለየት የረጅም ርቀት ከፍታን መሠረት ያደረጉ የአየር ጣባዮች፣ ለአጭር ርቀትና ለሜዳ ተግባር ስፖርቶች በባህሪያቸው ኃይልን ስለሚፈልጉ፤ የጡንቻና ሌሎች አካላት ውህደትን በመጠቀም ስለሚሰራ፤ ለአተነፋፈስ ሥርዓቱ ምቹ የሆኑ የአየር ጠባያትን በመለየት አካባቢዎችን ማወቅ እንደሚቻል ነው ረዳት ፕሮፌሰር አረፋይኔ የሚናገሩት፡፡ እንደ እርሳቸው ማብራሪያ፤ በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ የተሰጥኦ አካባቢዎችን በመለየት ልምምድ የማድረግ ሁኔታው በከፊል ያለ ቢሆንም ከውጤት አኳያ ሲመዘን ግን በዚህ ሂደት የመጓዝ ልምዱ ተጨማሪ ሥራዎችን የሚጠይቅ ሆኗል፡፡ ለዚህም ጥናት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ የተጀማመሩ ነገሮች ቢኖሩም ሙሉ ለሙሉ አጥጋቢ ናቸው ለማለት ግን አያስደፍርም፡፡ ለስፖርቱ የተለዩ የተሰጥኦ ስፍራችን መጠቀም ማለት 50 በመቶውን የስፖርቱን ሥራ እንደማቃለል ነው የሚሉት ረዳት ፕሮፌሰሩ፤ በተፈጥሮ ላይ ተመስርቶ መስራቱ በዋናነት የበለጠ ውጤታማ እንደሚያደርግ፤ በመሆኑም የአትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከላትን የተሰጥኦ ስፍራዎች ባሉባቸው አካባቢዎች በመገንባት የላቀ ሥራ መስራት እንደሚያስፈልግ ይመክራሉ፡፡ በተለይ ለአጭር ርቀት ተስማሚ የሆኑ ቆላማ አካባቢዎችን ለይቶ ማዕከላትን ማስፋፋት ከተቻለ በዚህ ዘርፍ ውጤታማ መሆን እንደሚቻልም ይጠቁማሉ፡፡ በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ሳይንስ መምህር የሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር አማረ ጥጋቡ በበኩላቸው፤ ስፖርትን በሚመለከት የተሰጥኦ ሥፍራ የሚባለው ለስፖርቱ በቂ አቅም መስጠት የሚችል አካባቢ ነው ይላሉ፡፡ አክለውም በኢትዮጵያ በተለምዶ ደጋማው አካባቢ ብቻ የተሰጥኦ ስፍራ የሚመስላቸው መኖራውንና ነገር ግን ምቹ የአትሌቲክስ ቦታዎች ደጋማ አካባቢዎች ብቻ አለመሆናቸውን፤ ስፍራዎቹም የሚወሰኑት በስፖርቱ ዓይነት መሆኑን ይናገራሉ፡፡ ረዳት ፕሮፌሰር አማረ እንደሚሉት፤ በኢትዮጵያ ያሉ አትሌቶች በረጅምም ይሁን በአጭር ርቀት ላይ የሚሳተፉት አንዱን አካባቢ ብቻ መርጠው ነው፡፡ ይህም በተደጋጋሚ ስለሚተገበር አካባቢው ላይ ያለውና ስፖርቱን የሚያዘወትረው የማህበረሰብ ክፍል አዕምሮ ውስጥ በመያዙ፤ ሙያተኛውም ቢሆን ለአትሌት የተመረጡት እነዚህ ስፍራዎች ብቻ ናቸው ብሎ በመፈረጁ አማራጭ የተሰጥኦ ስፍራዎችን ለይቶ መተግበር አልተቻለም፡፡ ጥናትንና ሳይንስን መሠረት ባደረጉ በተለይም ከአየር ንብረቱ ጋር ተያይዞ የትኛው ስፖርት በየትኛው አካባቢ መሰራት እንዳለበት ግንዛቤ መያዝ ሲገባ ከዚህ አንጻር ብዙ ያልተሰሩ ጉዳዮች መኖራቸው ተስተውሏል፡፡ ‹‹በተለይ በምሥራቅ አፍሪካ አካባቢ ያሉ አትሌቶች ልምምዳቸውን በዘልማድ ስለሚያደርጉ እነዚህን አትሌቶች ምሳሌ በማድረግ ገና ከጀማሪነታቸው ተለምዷዊ የሆነውን የስልጠና ሥፍራ ለመምረጥ ይገደዳሉ፡፡ ታዋቂ አትሌቶችን ምሳሌ የማድረጉ አዝማሚያ ከቦታ መረጣ ብቻ ሳይሆን የሩጫውንም ርዝመት መነሻ ያደረገ ነው፡፡ ለምሳሌ በአንድ ቦታ በብዛት የረጅም ርቀት አትሌቶች ካሉ አዳዲሶቹም መሮጥ የሚፈልጉት ረጅም ርቀቱን ነው፡፡ ይህ እንደ ባህል የቀድሞ አትሌቶችን እግር ተከትሎ የመጣ ነው›› ይላሉ ረዳት ፕሮፌሰር አማረ ጥጋቡ፡፡ ረዳት ፕሮፈሰር አማረ፤ የአጭር ርቀት ሩጫዎች የበለጠ ሳይንሳዊ እውቀትን ስለሚጠይቁና እንደ አገርም ለዚህ የሚያበቃ አቅም ባለመኖሩ ባልተጠኑና ለዚህ የሩጫ ዘርፍ ተብለው ባልተመረጡ ስፍራዎች ላይ የመሮጥ ችግርም በተደጋጋሚ እንደሚስተዋል፤ አብዛኛውንም ልምምዱን የሚያደርጉት በራሳቸው ጥረት እንደ ሆነና ሙያዊ እገዛ ላይ ክፍተቶች እንዳሉም ጠቅ ሰዋል፡፡ ‹‹በኢትዮጵያ ያሉ አትሌቶች እንደየስፖርቱ ተፈጥሯዊ ሁኔታ በተመረጡ የተሰጥኦ ስፍራዎች ላይ ልምምድ ቢሰሩ አሁን በተለመደው የ5ሺ እና የ10ሺ ርቀቶች ላይ ብቻ ተንጠልጥለው አይቀሩም ነበር፡፡ በሁሉም የስፖርት ዓይነቶች ተጠቃሚ መሆን ይቻል ነበር፡፡ ለምሳሌ በኦሊምፒክ ውድድር በብዙ የስፖርት ዓይነት ባለመሳተፍ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ እንገኛለን፡፡ በመሆኑም በአገሪቱ የሚገኙትን ተፈጥሯዊ ሁኔታን እንደ ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም የስፖርት ዓይነት ተሳትፎን ማብዛት ያስፈልጋል፡፡ በእያንዳንዱ የስፖርት ዓይነት በርካታ ቁጥር ያላቸው ስፖርተኞችን ማፍለቅ ከተቻለ አገሪቷ ስሟ ከሚወሳው የአምስትና አስር ሺ ሩጫ በተጨማሪ በአጭር ርቀትና የሜዳ ተግባራት የውድድር ዓይነቶች የመሳተፍ እድሏ ከፍ ይላል፡፡ ይህን ተግባራዊ ለማድረግ ደግሞ እያንዳንዱን ስፖርት ለይቶ ስልጠና መስጠትና በርካታ ፕሮጀክቶችን ማስፋፋትን ያካትታል›› ሲሉም ረዳት ፕሮፌሰሩ አማረ ምክረ ሀሳባቸውን ያስቀምጣሉ፡፡አዲስ ዘመን ግንቦት 2/2011
https://www.press.et/Ama/?p=10522
810
2ስፖርት
የሊጉን ዋንጫ ማንቸስተር ሲቲ ወይንስ ሊቨርፑል
ስፖርት
May 10, 2019
56
የዓለማችን ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በያዝነው ዓመትም የሊጉን ዋንጫ ማን ያነሳ ይሆን የሚለውን ግምት ለመገመት አዳጋች እንደሆነና አጓጊነቱን እንደያዘ እስከ ውድድር ዓመቱ የመጨረሻ ጨዋታዎች ድረስ የዘለቀ ሲሆን፤ ሁሉም የሊጉ 38ኛው ሳምንት የመጨረሻ አስር ጨዋታዎች እሁድ በተመሳሳይ ሰዓት ምሽት 11:00 ሰዓት የሚደረጉ ይሆናል። ከነዚህ ፍልሚያዎች መካከል የሊጉን ዋንጫ ማን ያነሳ ይሆን የሚለውን ጥያቄ መልስ ከሚሰጡት ጨዋታዎች አንዱ «ብራይተን ሆቨ አልቢዮን በሜዳው ውሃ ሰማያዊዎቹን ማንቸስተር ሲቲን» የሚያስተናግድበት ነው። በዚህ ጨዋታ ላይ የሊጉ መሪ ሲቲ አቻ የሚወጣ ወይም የሽንፈትን ጽዋ የሚጎነጭ ከሆነና ምትሀተኛው የመርሲ ሳይዱ ሊቨርፑል ያለበትን ጨዋታ የሚያሸንፍ ከሆነ ዋንጫውን ሊቨርፑል የሚያነሳ ይሆናል። ነገርግን በዓለማችን ቁጥር አንድ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዎላ የሚመሩት ሲቲዎች በ11ኛው ሰዓት በጃቸው የጨበጡትን ድል አሳልፈው ይሰጣሉ ተብሎ ባይጠበቅም፤ ኳስ ነውና 90 ደቂቃው አልቋል የመሀል ዳኛው የጨዋታውን ማጠናቀቂያ ፊሽካ ድምጽ እስኪያሰሙ ድረስ የሚፈጠረውን ውጤት ማወቅ ስለማይቻል፤ ብራይተኖች በሲቲዎች የዓመት ልፋት ላይ ውሃ ይቸልሱባቸው ይሆናል የሚል ግምት ከወዲሁ የስፖርት ቤተሰቡ እየሰነዘረ ይገኛል። በሌላ በኩል የሊጉን ዋንጫ ማን ያነሳ ይሆን የሚለውን ጥያቄ ምላሽ የሚሰጠው ጨዋታ «ቀያዮቹ ሊቨርፑል በአንፊልድ ወልቨርሃምፕተን ወንድረርስን» የሚያስተናግድበት ጨዋታ ነው። የመርሲ ሳይዱ ሊቨርፑል የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ እንደገና ከተቋቋመ ከ22 ዓመት ወዲህ የሊጉን ዋንጫ ለማንሳት የተሳነው ሲሆን፤ በነውጠኛው ጀርመናዊው አሰልጣኝ ጀርገን ክሎፕ እየተመራ የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ለማንሳት ከዋንጫ ዋነኛ ተቀናቃኙ ማንቸስተር ሲቲ በአንድ ነጥብ ዝቅብሎ ተቀምጧል። በመሆኑም ቀያዮቹ በአውሮፓ ሻምፒዮን ሊግ ከባርሴሎና ጋር ባደረጉት የግማሽ ፍጻሜ ፍልሚያ ዓለም በታሪኩ የማይዘነጋውን ገድል ባስመዘገቡ ማገስት የሚያደርጉት ጨዋታ በመሆኑ፤ በቀላሉ ጨዋታውን በሰፊ የጎል ልዩነት በማሸነፍ ሲቲዎች ሊፈጽሙት የሚችሉትን ስህተት በአግባቡ በመጠቀም የ22 ዓመት የዋንጫ ጥማቸውን ሊያረኩ ይችላሉ የሚል መላምት በስፖርት ቤተሰቡ እየተነገረ ይገኛል። በአጠቃላይ እ.አ.አ. የ2018/19 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የዋንጫ ባለቤት ማነው የሚለውን ጥያቄ በነዚህ ሁለት ፍልሚያዎች የሚመለስ ሲሆን፤ ከነዚህ ጨዋታዎች በተጨማሪ ቶተነሃም ሆትስፐርስ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ከአንድ እስከ አራት በመያዝ በሚቀጥለው ዓመት በሻምፒዮንስ ሊጉ ተፋላሚ ለመሆን የሚያስችለውን ደረጃ ይዞ ለማጠናቀቅ ከኤቨርተን ጋር በሜዳው ይፋለማል። በአንጻሩ አርሴናል ቶተነሃሞች ሊፈጥሩት የሚችሉትን ስህተት በመጠቀም በሚቀጥለው ዓመት በሻምፒዮንስ ሊጉ ተሳታፊ ለመሆን ከበርንሌይ ጋር ይፋለማሉ። በተጨማሪም ከምንም ነገር ነፃ የሆኑት ሌስተር ሲቲ እና ቼልሲ ለክብር የሚያደርጉት ፍልሚያም ተጠባቂ ነው። ፕሪሚየር ሊጉን ውሃ ሰማያዊዎቹ ማንቸስተር ሲቲ በ95 ነጥብ ሲመራ፤ የመርሲሳይዱ ሊቨርፑል በ94 ነጥብ ይከተላል። ሰማያዊዎቹ ቼልሲ በ71 ነጥብ ሦስተኛ ደረጃን ሲይዝ፤ ስፐርሶቹ ቶተነሃም ሆትስፐርስ በ70 ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዞ ይከተላል። በአንጻሩ ካርዲፍ ሲቲ፣ ፉልሃም እና ሀደርስፊልድ ታውን ደግሞ ከ18ኛ እስከ 20ኛ ያሉትን የመጨረሻዎቹን ሦስት ደረጃዎችን ይዘው ከወዲሁ ወደታችኛው ዲቪዚዮን መውረዳቸውን አረጋግጠዋል፡፡ እንዲሁም የፕሪሚየር ሊጉን ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነት የሊቨርፑሉ ሙሀመድ ሳላህ በ22ጎሎች ሲመራ፤ የማንቸስተር ሲቲው ኩን አጉኤሮ፣ የአርሴናሉ ፔር ኢሜሪክ ኦባሚያንግ እና የሊቨርፑሉ ሴኔጋላዊው ኮከብ ሳዲዮ ማኔ በእኩል 20ጎሎች በሁለተኛ ደረጃ ተቀምጠዋል። የሌስተር ሲቲው እንግሊዛዊው ምትሀተኛ አጥቂ ጀሚ ቫርዲ በ18 ጎሎች ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን እየተከተለ ይገኛል።አዲስ ዘመን ግንቦት 2/2011
https://www.press.et/Ama/?p=10529
410
2ስፖርት
በድርጅቱ የኮሮና ቫይረስ መከሰት ምስጢር መደረጉ ለአደጋ እንዳጋለጣቸው ሠራተኞች አመለከቱ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 1, 2020
32
አዲስ አበባ፡- በድርጅታችን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት እየተስፋፋ በመሆኑ ደህንነታችን ለአደጋ እየተጋለጠ ነው ሲሉ የራይዘን ኮንስትራክሽንና ፀሜክስ ግሎባል ኢንተርራይዝ ሠራተኞች አመለከቱ። ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉና በተለያዩ የሙያ መስኮች ላይ ተሰማርተው የሚገኙ የድርጅቱ ሠራተኞች በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ በአሁኑ ጊዜ በመስሪያቤታቸው በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ ሠራተኞች ቁጥር በመጨመር ላይ ይገኛል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመስሪያቤቱ ጥቂት የማይባሉ ሠራተኞች የታመሙ ሲሆን፤ ሥራአስኪያጁን ጨምሮ አስራአንድ ያህሉ በሦስት ለይቶ ማቆያ ማዕከላት ህክምና በመከታተል ላይ ናቸው። በድርጅቱ እስከአሁን የተለየ ጥንቃቄና ግንዛቤ ካለመኖሩ ጋር የሠራተኞቹ መታመም በምስጢር ተይዞ ቆይቷል ያሉት እኒሁ ሠራተኞች፤ በዚህ የተነ ሳም አብዛኞቹ ሠራተኞች ለቫይረሱ እንዲጋለጡና ብሎም ተገቢውን ምርመራ እንዳያደርጉ ሆነዋል ሲሉ ተናግረዋል። በለይቶ ማቆያ ውስጥ ከሚገኙ ሠራተኞች መካከል አንደኛው በሰጠው አስተያየት በቫይረሱ መያዙን ያወቀው የሌሎች መታመምን ሰምቶና ተጠራጥሮ ባደረገው ምርመራ ሲሆን፤ ይህን እስኪያረጋግጥ ግን ከድርጅቱ ያገኘው ምንም መረጃ ያለመኖሩን ተናግሯል። ድርጅቱ ሠራተኞቹ በማቆያው ከገቡ በኋላም የት ደረሳችሁ አለማለቱ እንዳሳዘነው የጠቀሰው አስተያየት ሰጪው፣ አሁንም የበርካቶች ጤንነት በስጋት ላይ መሆኑንና ድርጅቱ ለምርመራው ካልፈጠነ የሁሉም ሠራተኞች ህይወት አደጋ ላይ መውደቁ ሊታወቅ ይገባል ብሏል። ለቫይረሱ መስፋፋትና ለሠራተኞቹ መታመም ተጠያቂው ድርጅቱ ነው የሚሉት ሠራተኞቹ ፣ መስሪያ ቤቱ ከጤና ይልቅ ሥራን ብቻ የሚያስቀድም በመሆኑ ከጉዳዩ መታወቅ በኋላም ሠራተኞች በሥራ ላይ እንዲገኙ በማስገደድ ላይ ነው ብለዋል። በቅርብ ቀን በአካባቢያቸው በኮሮና ቫይረስ ተጠርጥረው በቤታቸው እንዲቆዩ የተደረጉ ሠራተኞች ጭምር ወደሥራ እንዲገቡ ተደርገዋል የሚሉት አስተያየት ሰጪዎቹ፣ ድርጅቱ በቅንነት እያገለገሉት ያሉ ሠራተኞቹን ያለምንም ዕረፍት እንዲሠሩና ጤንነታቸው ስጋት ላይ እንዲወድቅ በማድረጉ ሊጠየቅ ይገባል ሲሉ ጠቁመዋል። በድርጅቱ ለበርካታ ዓመታት አገልግያለሁ የሚ ሉት ሌላው አስተያየት ሰጪ በበኩላቸው ድርጅቱ በአሁኑ ወቅት በሙሉ ጊዜ ሠራተኞችን እያሠራ ስለመሆኑ ይናገራሉ። ድርጅቱ ችግሩ ከታወቀ ወዲህ የተወሰኑ ሠራተኞች በንክኪ ምክንያት ቤት እንደቀሩ ከመስማታቸው ውጪ በግልጽ የተወሰደ ዕርምጃና የተሰጠ ማስጠንቀቂያ አለመኖሩ የሁሉም ተቀጣሪ ስጋት እንዲጨምር ምክንያት ሆኗል ይላሉ። እንደ አስተያየት ሰጪው ገለጻ በተለያዩ ክፍሎች የሚገኙ ሠራተኞች የሥራ ባህርይና የእርስ በርሰ ግንኙነት ለቫይረሱ መስፋፋት ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ይገልጸሉ። ድርጅቱ በየጊዜው የሚደርሰውን ችግር እያወቀ ዝምታን መምረጡም ብዙዎች በመሳቀቅ እንዲኖሩና ለቤተሰቦቻቸው ጤንነት ጭምር ስጋት እንዲሆኑ ምክንያት ሆኗል። ሠራተኞች ለሚያነሱት የኮሮና ቫይረስ ተጠቂነትና ሥጋት ተጠያቂ ነው የተባለው የራይዘን ኮንስትራክሽንና ጸሜክስ ግሎባል ኢንተርፕራይዝ አስተዳደር ኃላፊ አቶ አውሎአለም ወልዱ በበኩላቸው፣ ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ ድርጅቱ እንደማንኛውም ተቋም አስፈላጊውን ጥንቃቄ እያደረገ ስለመሆኑ ይናገራሉ። በአሁኑ ጊዜ በድርጅቱ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሠራተኞች እየተመረመሩ ራሳቸውን ስለማወቃቸው መረጃው እንዳላቸው የሚናገሩት የአስተዳደር ኃላፊው፣ ድርጅታቸው ለሠራተኞቹ ምን ያህል እገዛ እያደረገ ነው ለሚለው ጥያቄ ግን ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት አልፈቀዱም። ከሠራተኞች የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው፣ በአሁኑ ጊዜ ዋና ሥራ አስኪያጁን ሳይጨምር በቫይረሱ የተጠቁ አስር የድርጅቱ ሠራተኞች በሚሊኒየም አዳራሽ፣ በእንዶዴና በተስፋ ኮከብ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በተከፈቱ የለይቶ ማቆያ ማዕከላት ህክምናቸውን በመከታተል ላይ ይገኛሉ።አዲስ ዘመን ሐምሌ 25 ቀን 2012 ዓ.ም በመልካምስራ አፈወርቅ
https://www.press.et/Ama/?p=36423
398
0ሀገር አቀፍ ዜና
«ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ሜዳዎች አንዳቸውም የካፍን መመዘኛ አያሟሉም ተብለናል» አቶ ኢሳያስ ጂራ
ስፖርት
August 7, 2019
39
 ካፍ በቅርቡ ባደረገው ግምገማ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ሜዳዎች ዓለም አቀፍ ውድድሮችን የማስተናገድ አቅም የሌላቸውና የቀጣይ የአፍሪካ መድረክ ጨዋታዎችን በሜዳ የማጫወት ጉዳይም ጥያቄ ምልክት ውስጥ ገብቷል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በመላ ሀገሪቱ ግዙፍ የሚባሉ ስታዲየሞች በመገንባት ላይ ቢሆኑም አንዳቸውም ሙሉ ለሙሉ ካለመጠናቀቃቸውም በላይ ለተመልካች መቀመጫ፣ ለውጫዊ ገጽታ፣ ለመጫወቻ ሜዳ ጥራትና አስፈላጊ ለሆኑ ውስጣዊ ግንባታዎች የተሰጠው ትኩረት አናሳነት ዋጋ እያስከፈለ መጥቷል። በ 2020 የቻን ውድድር ለማስተናገድ በካፍ ተመርጣ የነበረችው ኢትዮጵያ ለሁለት ጊዜያት ሀዋሳ፣ መቐለ፣ ባህርዳር እና አዲስ አበባ የሚገኙ ስታዲየሞቿን አስገምግማ ያሉበት ወቅታዊ ሁኔታ ውድድሩን ለማስተናገድ ብቁ አይደሉም በሚል የማዘጋጀት እድሏ ለካሜሩን ተላልፎ መሰጠቱም የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። በሀገሪቱ የተለያዩ ክልል ከተሞች የተገነቡና በመገንባት ላይ የሚገኙ አለም ዓቀፍ ስታዲየሞች በአግባቡ ማጠናቀቅ አለመቻላቸው ሀገሪቱን አጣብቂኝ ውስጥ እያስገቡ መሆኑም በተለያዩ አካላት እየተነገረ ይገኛል። የስታዲየም ጉዳይ የኢትዮጵያ አህጉር አቀፍና ዓለም አቀፍ የስፖርት መድረኮችን የማዘጋጀት እድሏን ብቻ ሳይሆን፤ ኢንተርናሽናል ውድድሮችን በሜዳዋ የማድረግ አጋጣሚዋን ጥያቄ ውስጥ ያስገባ መሆኑን ሶከር ኢትዮጵያ ያወጣው መረጃ አመላክቷል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጂራ ለሶከር ኢትዮጵያ እንደተናገሩት ፤ አገር ውስጥ የሚገኙ ሜዳዎች አንዳቸውም የካፍን መመዘኛ አያሟሉም ከመባሉም በላይ የአዲስ አበባ ስታዲየምን ከአሁን በኃላ መጠቀም አትችሉም የሚል ደብዳቤ ተጽፎልናል ብለዋል። ሆኖም የመቐለን ስታዲየም ለማስመዝገብ መላኩን በመግለጽ ቀደም ብሎ የተመዘገበው የባህር ዳርን ስታዲየም ብቻ እድል ሊኖረው እንደሚችል ጠቁመዋል ። አቶ ኢሳያስ የሃዋሳ ስታዲየም ሳር በመበላሸቱ በአዲስ ሳር ለመተካት እድሳት ላይ የሚገኝ ሲሆን የአዲስ አበባ ስታዲየም በተለይ የመልበሻና መጸዳጃ ቤቱ እጅጉን የማይመጥን በመሆኑ ዓለም አቀፍ ውድድሮችን እንዳያስተናግድ መታገዱን አብራርተዋል። በዚህም መሰረት ብሄራዊ ፌዴሬሽኑና ካፍ ለስፖርት ኮሚሽን ተደጋጋሚ ደብዳቤ ቢጽፉም ምላሹ ፈጣን አለመሆኑን አብራርተዋል። «ይህ የሀገር ጉዳይ ነው። መንግሥትም እንዲያውቀው አድርገናል። የፊፋ አባል ሀገር ሆነን ሜዳ የላችሁም መባልም በራሱ ውርደት ነው። እኔም ለስራ አስፈጻሚዎቹ እንድታውቁት ብዬ በደብዳቤ አሳውቄያለሁ። በኛ ሀገር ሜዳዎች መሰራታቸው መልካም ቢሆንም በተለይ የመጫወቻ ሜዳዎቹ እጅጉን ደካሞች ናቸው» ብለዋል። በድሬዳዋ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከጅቡቲ በነበረው ጨዋታ ተመልካች ስታዲየም እንዳይገባ መደረጉን አቶ ኢሳያስ አስታውሰው ይህ የሆነው ስታዲየሙ ገና ያልተጠናቀቀ በመሆኑ ነው። በቀጣይ ጊዜያት በዓለም ዋንጫ፣ ቻን፣ በአፍሪካ ዋንጫ እንዲሁም የወጣቶች እና ሴቶች ውድድሮች በርካታ የማጣሪያ ጨዋታዎች ያሉ ቢሆንም ያሉን ሜዳዎች ብቁ ባለመሆናቸው ሁኔታው አስቸጋሪ ሆኗል፡፡ ይህንን አስቸጋሪ ሁኔታ የተረዳው ካፍም በቅርቡ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በጻፈው ደብዳቤ ከአሁን በኃላ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረጉ ጨዋታዎችን ወደ ጎረቤት ሀገር እንደሚወስድ አስታውቋል በመሆኑም ከወዲሁ መስተካከል ያለበትን ማስተካከል ካልቻልን ኢንተርናሽናል ጨዋታን በሃገራችን አናስተናግድም ሲሉ ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል ።አዲስ ዘመን ነሃሴ 1/2011ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=15661
362
2ስፖርት
የቤት ሰራተኞች በአሰሪና ሰራተኛ አዋጁ ባለመካተታቸው ለጥቃቶች ተጋልጠዋል
ሀገር አቀፍ ዜና
August 4, 2020
11
አዲስ አበባ፡- በኢትዮጵያ በቤት ሰራተኝነት ተቀጥረው የሚሰሩ ዜጎች በአሰሪና ሰራተኛ አዋጁ ድንጋጌ አለመገዛታቸው ለአካላዊ፣ ስነልቦናዊና ማህበራዊ ጥቃቶች እየተዳረጉ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር አስታወቀ።የኢትዮጵያ ህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር አባልና ነፃ የህግ ማማከር አገልግሎት ባለሙያ ወይዘሪት ቅድስት አባይነህ በተለይም ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ በኢትዮጵያ ውስጥ በቤት ሰራተኝነት ተቀጥረው የሚሰሩ ዜጎችን የአሰሪና ሰራተኛ አዋጁ ያገለላቸው በመሆኑ ለተለያዩ ጥቃቶች እየተጋለጡ ናቸው።እንደ ህግ ባለሙያዋ ገለፃ፣ የቤት ሰራተኞች መብታቸውንና ግዴታቸውን አውቀው እንዲሰሩ የሚያደርግ የህግ ማዕቀፍ የወጣ ባለመሆኑ ድብደባ፣ ማዋከብ፣ ከፍተኛ የስራ ጫና፣ የአስገድዶ መድፈርና መሰል ጥቃቶች ይፈፀምባቸዋል። የአሰሪና ሰራተኛ አዋጁ በቤት ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች ያገለለ በመሆኑ መብታቸውንና ግዴታቸውን አውቀው እንዳይሰሩ ከማድረጉም ባሻገር ለጉልበት ብዝበዛ አለፍ ሲልም ለፆታዊ ጥቃት ዳርጓቸዋል። መብቶቻቸው እስከምን ድረስ መሆኑን ስለማያውቁ በአሰሪዎቻቸው የሚባሉትን ሁሉ ለመፈፀም ይገደዳሉ ያሉት የህግ ባለሙያዋ፤ ይህ ደግሞ ከአቅማቸው በላይ ከመስራት ጀምሮ ለተለያዩ አካላዊ፣ ስነ ልቦናዊ ጉዳት እንዲዳረጉ ምክንያት ሆኗል ብለዋል። የአሰሪና ሰራተኛ አዋጁ የዘነጋችው የቤት ሰራተኞች መብት የላቸውም ተብሎ እንዲገመትና ሁልጊዜ ተመሳሳይ የሆነ ወንጀል እንዲፈፀምባቸውና ሆነዋል የሚሉት የህግ ባለሙያዋ ረጅም ሰዓት ያለ እረፍት ከሰኞ እስከ እሁድ ድረስ መስራት፣ የትምህርት እድል አለማግኘት እና እራሳቸውን የሚያሳድጉበትን መንገድ እንዲጠብ አድርጓቸዋል። በተለይ በፍትሀ ብሔሩ እንደማንኛውም ሰራተኛ የሚዳኝ ሕግ አለመኖሩ ከፍተኛ ጉዳት እያስከተለባቸው ይገኛል ብለዋል። የህግ ባለሙያዋ አክለው እንደገለፁት፤ የቤት ሰራተኞችን መብት የሚያስከብር የህግ ማዕቀፍ የሚመለከተው አካል ሊያወጣ ይገባል። ይህ ሲሆን ፍትሀዊ የሆነ የሰራተኞች ተጠቃሚነት መፈጠር ይቻላል። በደመወዝ በተለያዩ ሁኔታዎች የሚደርስባቸው ችግሮች ታይተው ድጋፍ ሊደረግላቸው እና ሰብአዊ መብታቸውም መከበር መቻል አለበት። ሰራተኞች በመሆናቸውም እንደሌላው ሰራተኛ ሁሉ መብታቸውን የሚያስከብሩበት ህግ ሊኖር እንደሚገባ ጠቁመው የሚመለከተው የመንግስት አካልም ሕግ በማውጣትና በማስፈፀም በኩል ትኩረት አድርጎ መስራት እንዳለበት አሳስበዋል። በአሁኑ ጊዜ የኮቪድ 19 በሽታን ለመግታት ሲባል በቤት ይቆዩ በሚል ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል በቤት ውስጥ እንዲቆይ በመደረጉ በቤት ውስጥ ሰራተኞች ላይ የሚደርሰው የስራ ጫና እየተባባሰ መምጣቱን ተናግረዋል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 28/2012  ሞገስ ተስፋ
https://www.press.et/Ama/?p=36559
274
0ሀገር አቀፍ ዜና
‹‹ስፖርቶችን እኩል ያለማየት ችግር አለ›› ማስተር አዲስ ዑርጌሳ
ስፖርት
May 11, 2019
73
በአፍሪካ ካሉ ስመጥር የወርልድ ቴኳንዶ አሰልጣኞች ትልቁ ነው::በዓለም አቀፉ ወርልድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ደግሞ ብቸኛው ኢትዮጵያዊ የአሰልጣኞች እና የዳኞች አሰልጣኝ ነው። የአፍሪካ ወርልድ ቴኳንዶ አሰልጣኞች ሊቀመንበር በመሆንም በቅርቡ ተመርጧል::ማስተር አዲስ ዑርጌሳ::እአአ በ2010/11 የውድድር ዓመት በተሳተፈባቸው ዓለምአቀፍ እና አህጉራዊ ውድድሮች ላይ ባልተመቻቸ ሁኔታ በጥቂት ስፖርተኞች ተሳትፎ 5 ወርቅ፣ 2 ብር እና 3 የነሀስ ሜዳሊያዎች ለኢትዮጵያ አስገኝቷል፡፡ባለፈው ሪዮ ኦሊምፒክ የማጣሪያ ውድድሮች በሁለቱም ፆታ ያሰለጠናቸው ተወዳዳሪዎች ወደ ታላቁ መድረክ ለማለፍ ከጫፍ ደርሰው ሳይሳካላቸው ቀርቷል::በቀጣዩ 2020 ቶኪዮ ኦሊምፒክም ኢትዮጵያ በወርልድ ቴኳንዶ ስፖርት ለመጀመሪያ ጊዜ ለመሳተፍ የሚያስችላትን እድል ከወዲሁ ለመፍጠር ጠንክሮ እየሰራ ይገኛል::ኢትዮጵያዊ ሰለሞን ቱፋ ባለፈው የአፍሪካ ወርልድ ቴኳንዶ ቻምፒዮና ኮከብ ተጫዋች ሆኖ ሲመረጥ አሰልጣኙ ማስተር አዲስ ነበር:: በ2ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ኦሊምፒክ እንዲሁም በተለያዩ የግል ውድድሮች በርካታ የወርቅ ሜዳሊያዎችን ባሰለጠናቸው ተወዳዳሪዎች አማካኝነት ለአገሩ በማስመዝገብም ትልቅ ተስፋ ተጥሎበታል::ማስተር አዲስ በአገራችን ወርልድ ቴኳንዶ ስፖርት ተስፋና ስጋት እንዲሁም ሌሎች በርካታ ጉዳዮችን ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ እንደሚከተለው ይናገራል::ከሪዮ ኦሊምፒክ በኋላ በኦሊምፒኩ ማለፍ ባለመቻላችን ብዙ ውጣ ውረድ ነበር፣ከዚያ በኋላ ፌዴሬሽኑን የሚመሩ አዲስ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴዎች መጡና ያለፈው ውጤታችንን ገመገሙ፣ ችግሩ ምን ነበር? ለምን ማጣሪያውን ማለፍ አልቻልንም? ብለን ገመገምን::ትልቁ የነበረው ችግር ልጆቹን በልምምድ ብቻ ነበር የያዝናቸው፣ እያወጣን ውድድሮች ላይ እያጫወትን፣ልምድ እንዲያገኙና ነጥብ እንዲሰበስቡ እያደረግን አልነበረም::በዚህ ምክንያት ከሌሎች አገራት ጋር ስንጫወት የእነሱና የእኛ ልጆች ልምድ በጣም ልዩነት ነበረው::ይሄን ለመቅረፍ መደረግ የነበረበት ቀደም ብሎ ወደ ውጭ ለመሄድ ስናስብ ነበር ልጆችን ስንይዝ የነበረው፣ ከዚህ ስንሄድ ሰብስበን እንይዛለን ስንመለስ ይበተናሉ፣ ይሄ ስራ አስፈፃሚ ሲመጣ ግን ብሔራዊ ቡድኑ ዓመቱን ሙሉ ሳይበተን ልጆቹ ተይዘው እንዲሰሩ አደረግንና ትልቅ ለውጥ መጣ::ልጆቹን እያሰራን በተገኘው አጋጣሚ ወደ ውድድር ይዘን መውጣት ጀመርን፣ ከዚያ በኋላ ጥሩ ነበር፣ በተለይም ባለፉት አንድ ዓመታት በላይ ወደ ውጤት መምጣት ጀመርን፣ ሞሮኮ ላይ በአፍሪካ ቴኳንዶ ቻምፒዮና ወርቅ አመጣን፣ እዚያው ሞሮኮ ላይ ፕሬዝደንሺያል ካፕ ከሚባል ውድድር ወርቅ አመጣን፣ ከዚያ ተመልሰን በወጣቶች ኦሊምፒክ አልጄሪያ ላይ ለመጀመሪያ ተሳትፎ የሄዱ ልጆች አንድ ወርቅ፣ሁለት ብርና አንድ የነሐስ ሜዳሊያ ማምጣት ቻልን::እነዚህ ልጆች ጀማሪና ከአገር ወጥተው የማያውቁ ናቸው::ከዚህ መልስ ደግሞ በፓራሊምፒክ አንድ ተጫዋች ወስደን እሱም ወርቅ አመጣ፣ ፖላንድ ሄደን በአንድ ልጅ የነሐስ ሜዳሊያ አምጥተናል፣ቱርክ ሄደንም በዚሁ ልጅ ወርቅ አመጣን፣ ይሄንኑ ልጅ መልሰን የመወዳደሪያ ኪሎውን ጨምረን ለኦሊምፒክ ዝግጅት እንዲያደርግ በማሰብ የነሐስ ሜዳሊያ አመጣን::ውድድሩን ስናየው በጣም ጥሩና አበረታች ነበር::ብዙ ውጣ ውረድና ብዙ መሰራት ያለበት ነገር ግን አሁንም አለ::አፍሪካ ላይ ካሉ ነባር አሰልጣኞች አንዱ እኔ ነኝ፣ በስፖርቱ በአፍሪካ ደረጃ ብዙ ቆይቻለሁ፣አሁን እንደውም በአፍሪካ የአሰልጣኞች ሊቀመንበር እኔ ነኝ፣ ያለኝ ልምድና ልጆቹ ላይ በየጊዜው የምንሰራው ልምምድ ውጤት አለው ጥሩ ነው፣ በአፍሪካ ግን ምርጥ ቡድን ነን ማለት አንችልም፣ የኛ ተሳትፎ በጣም ውስን ነው፣ ሌሎቹ አገራት በትልቁ ነው ስፖርቱ ላይ ኢንቨስት የሚያደርጉት፣ ስምንት ወንድና ስምንት ሴት በተለያየ ኪሎ ግራም ነው ይዘው ወደ ውድድር የሚመጡት::እኛ ደግሞ አንድ፣ሁለት ወይም ሦስት ልጆችን ይዘን ነው የምንሄደው፣ ስፖርቱ ገንዘብ ይፈልጋል፣ ለጉዞ የምናወጣው ወጪ ከባድ ነው፣ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ለአራት ልጆች ከኪሱ እያወጣ ደመወዝ ይከፍላል፣ ቤት ኪራይ ይከፍላል፣ የትምህርት ቤት ይከፍላል፣ ይሄን በማድረጉ ልጆቹን አበረታትቶ ይዞ ነው እንጂ በመንግስት በሚደረገው ድጎማ መንቀሳቀስ በጣም ከባድ ነው፣ እዚህ ደረጃ እንደርሳለን ብሎ መናገርም የማይሆን ነገር ነው፣ውድድርም ሲደረግ ፕሬዘዳንቱ ራሱ ተሯሩጦ ስፖንሰር እየፈለገ ነው እዚህ መድረስ የቻልነው፣ በአንድ ሰው ፍላጎት ላይ ብቻ የተንጠለጠለ ነው እንጂ እንደ አገር የተደገፈ አይደለም፣ ይሄ ሰው ቢያቆም ይቆማል::ውጤታችን ግን የሁላችንም ድምር ነው::የመጨረሻ ግቤ ለኦሊምፒክ ማለፍ ነው፣ የምፈልገውም በየሄድኩበት ወርቅ ማምጣት ሳይሆን ኦሊምፒክ ላይ መሳተፍ ነው፣ የልጆቹን ውጤት ከፍ ለማድረግ ግን ትልቅ ውጤት ማምጣት አለብኝ::አሁን ልጆቹንም ለማብቃት እየሄድኩኝ ያለሁትም ለኦሊምፒክ ማለፍ የምንችልበትን መንገድ እየጠረግኩ ነው የምሄደው፣ ለምሳሌ ኪሎ ጨምሬ ሳጫውተው ወርቅ ላመጣ እችል ይሆናል፣ ለኔ ጠቃሚው ነገር ግን ነገ ራሳችንን እየለካን ወደ ኦሊምፒክ የምንሄድበት ነው፣ በዚህ በጣም እየሰራሁ ነው፣ ነገር ግን በትንሽ ተጫዋች ላይ ተንጠልጥለህ መሄድ ከባድ ነው፣ ልጆቹ ቢጎዱ ያበቃል፣ በዛ አድርገህ ይዘህ ከዚያ ውስጥ እየመረጥክ እያጫወትክ ቢሆን ጥሩ ነው፣ እየሞከርንም ነው፡፡አዎን ይቻላል፣ ግን ድጋፍ በደንብ ይፈልጋል::ትኩረት በደንብ ተሰጥቶት ልጆቹ ሚመገቡበት፣የሚተኙበት፣ትምህርታቸውና ጤናቸው ላይ በደንብ ድጋፍ ከተደረገ፣ ብዙ ውድድሮች እንዲያገኙ ከተደረጉ ልጆቹ ብዙ ነገሮችን እያወቁ ስለሚሄዱ ይቻላል::ልጆቹ ለልምምድ ያላቸው አስተሳሰብ ጥሩ ነው፣ለምሳሌ አንድ ልጅ ውጪ አገር ሄዶ ተጫውቶ የመጣና ከአገር ያልወጣ ልጅ እኩል የስልጠና አስተሳሰብ የላቸውም፣ ወጥቶ የመጣው ምን መደረግ እንዳለበት ያውቃል፣ ከማን ጋር ሄዶ እንደሚወዳደር ስለሚያውቅ እንዴት መዘጋጀት እንዳለበት ጠንቅቆ ያውቃል::ይህም የስልጠና አስተሳሰባቸውን በደንብ ይቀይረዋል::በዚህ መንገድ ከሄድን የ2020 ቶኪዮ ኦሊምፒክን ተሳትፎ እናሳካለን ብየ አስባለሁ::አዲስ ዘመን፡- የቴኳንዶ ስፖርት በግለሰቦች ጥረት ላይ የተመረኮዘ ቢሆንም ትልቅ እድገት እያሳየ መጥቷል::ምናልባትም በቶኪዮ ኦሊምፒክ ከአትሌቲክስ በተጨማሪ እንሳተፋለን ብለን ተስፋ የምናደርግበት ስፖርት እስከመሆን ደርሷል::ያም ሆኖ ከትጥቅ ጀምሮ በርካታ ችግሮች እንዳሉባችሁ ይታወቃል::ኦሊምፒክ ኮሚቴና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት እነዚህን ችግሮች ተመልክተው ሊረዷችሁ አልሞከሩም?ይሄንን ጥያቄ እነሱ ቢመልሱት ይሻላል::ኦሊምፒክ ኮሚቴ በቅርቡ አንድ ውድድር ላይ ስንሄድ የገንዘብ ድጋፍ አድርጎልናል፣ እንደ አንድ ስፖርት የሚያስፈልገውን ሁሉ አሟልቶ እየሄድን ነው ማለት ግን አይቻልም::እቅድ አስገብተናል::ከዚህ በኋላ የሚያደርጉልን ይመስለኛል፣ አሁን ባለው ሁኔታ ግን ምንም እየተደረገ ያለ ነገር የለም::የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ለኛ ጥሩ አመለካከት አላቸው፣ እነዚህ ልጆችን ለኦሊምፒክ ለማብቃት በአግባቡ መደገፍ ቢጀመር ውጤት የሚመጣ ይመስለኛል:: ይሄን እናንተም የምታውቁት ነው፣ ለምሳሌ አንድ ልጅ ውጭ አገር ሄዶ በዓለም አቀፍ ውድድሮች ወርቅ ይዞ ሲመጣ በመገናኛ ብዙሃን አይዘገብም፣ ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ወይም ኦሊምፒክ ኮሚቴ አይሸልምም፣ አትሌቲክስ ላይ አሸንፈው መጡ ሲባል በነጋታው አራትና አምስት መቶ ሺ ብር ወጥቶ ሲሸለሙ እናያለን::ፍትሃዊ አይደለም፣ ሁሉም ወርቅ ያመጣው ለአገሩ ነው፣ ሌሎች አገራት ላይ መስፈርት አለ፣ አንድ ስፖርተኛ ለአገሩ ወርቅ ካመጣ ይሄን ያህል ሽልማት ያገኛል ተብሎ በግልፅ ለሁሉም እኩል ነው ሽልማት የሚሰጠው፣ እኛ የምናመጣውን ሜዳሊያ ዞር ብሎ የሚያየውም የለም::በጣም ብዙ ተስፋ የሚያስቆርጡ ነገሮች ነው ያሉት፣ ልክ ነው እኛ ከአትሌቲክስ መወዳደር አንችልም፣ አትሌቲክስ ትልቅ ውጤት የምናመጣበት ትልቅ ስፖርት ነው፣ ግን እሱን ብቻ ይዞ ከመሄድ ይሄንንም የአገራችንን ውጤት እንዲደግፍ ማድረግ፣ እኛ በሄድንበት ውድድር ሜዳሊያ ይዘን ሳንመጣ አልቀረንም፣ ሌሎችም ስፖርቶች እኩል ቢታዩ::ለምሳሌ ለንደን ኦሊምፒክ ላይ ለአገሪቱ ባንዲራ ይዛ የገባችው የቴኳንዶ የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊዋ ናት፣ ይሄ የሆነው እነሱ ጋር ሁሉም ስፖርቶች እኩል ስለሚታዩ ነው፣ እኛ ጋር ግን ትልቅ የማበላለጥ ስራ አለ፣ በድካምና ላብ በማፍሰስ አንደኛ የሚሆን ስፖርት አለ ብየ አላስብም፣ ምክንያቱም የንኪኪ ስፖርት ነው፣ደምህን ነው የምታፈሰው፣አጥንትህን ሰብረህ ነው የምትወዳደረው፣በአንድ ቀን ስድስት ሰባት ውድድር ልታደርግ ትችላለህ::በአንድ ቀን ስድስትና ሰባት አገሮችን ልታሸንፍ ትችላለህ፣ ያን ሁሉ መስዋእትነት ከፍለህ ስትመጣ ሽልማትም የለም፣ ትኩረትም የለም፣ ምን እንደሰራህም የሚያውቅልህ የለምና በጣም ነው ውስጥህን የሚሰማህ፣ ምናልባት ግን ይሄ ታሪክ ይቀየራል ብየ አስቤ ነው የምሰራው፣ አንድ ቀን ምናልባት ኦሊምፒክ ብናልፍ ይሄን ወጥተን ለህዝብ እንናገራለን::እንዴት አድርገን እዚህ እንደደረስን ህዝቡ እንዲረዳው እናደርጋለን፣ የዛኔ ታሪክ ሊቀየር ይችላል::አሁን ያለው ሁኔታ ግን በጣም ነው የሚያሳዝነው፣ ሁሉንም ስፖርቶች እኩል የማየት ምንም አይነት ሃሳብ ያለ አይመስለኝም::በቅርቡም ይሄን ነገር ምክትል የስፖርት ኮሚሽነሩ በተገኙበት ፊት ለፊት ተናግሬያለሁ::እሳቸውም ይሄ ነገር ወደ ፊት ታርሞ እንደሚሰራ ነግረውናል፤ የምናየው ይሆናል::ከቢሮና ከሙያተኞች ጀምሮ ያሉትን ነገሮች መንግስት ማስተካከል አለበት፣ በጀት መስተካከል አለበት፣ እንደ ስራውና እንደ ስፖርቱ ፀባይ መደገፍ አለበት፣ ስፖርቶች እኩል መታየት አለባቸው፣ የሚመጡ አመራሮች ለስፖርቱ እድገት ረጅም ስትራቴጂ ቀርፀው ከሁለት ኦሊምፒክ በኋላ እዚህ እንደርሳለን ብለን የምንሰራበት ትልቅ የሆነ ነገር ይዘው የሚመጡ መሆን አለባቸው::አንዳድ ጊዜ ጥሩ ሰዎች ታገኛለህ አንዳንዴ ደግሞ የማይሆን ሰው ልታገኝ ትችላለህ፣ ጥሩ ሰዎች ከተገኙ ጥሩ ነገር ይመጣል ካሆነ ግን ስፖርቱ አሁንም የመውደቅ ፀባይ አለው፣ በእኛ አገር አስፈላጊ ነው ብየ ከምገምተው አንዱ ልክ እንደ እግር ኳስና ሌሎች ስፖርቶች በወርልድ ቴኳንዶ ክለቦች መቋቋም አለባቸው የሚለውን ነው፣ ልጆቹ በክለቦች ተይዘው ደመወዝ እያገኙ የገቢ ምንጭ ሆኖ ቢሰራበት፣ በጣም ብዙ የማሰልጠኛ ማዕከላት በየቦታው አሉ፣በኛ በኩል ከአምስት መቶ በላይ የማሰልጠኛ ማዕከላት አሉ፣ እነዚህ ማዕከላት በርካታ ታዳጊዎችን ያወጣሉ፣ ነገ ወደ ክለቦች ገብተው እንደሌላው ስፖርት ገቢ ካላገኙ በጣም ትልቅ ስጋት አለኝ፣ የኛን የብሔራዊ ቡድን ተወዳዳሪ ብንወስድ ውጭ ሊወዳደደር ሲሄድ ለምን አትጠፋም እዚህ መጥተህ ምን ታገኛለህ ይሉታል፣ እውነት ነው የሚያገኘው ነገር የለም፣ትኩረትና ሽልማት የለም፣ ሌሎቹስ ምን አይተው ነው የሚሰሩት፣ ይሄ ልጅ አሁን ይሄን ሁሉ ነገር አድርጎ ተመልሶ ነገ ምንም የሌለው ተራ ልጅ ሆኖ ነው እዚህ የምታገኘው::ክለብ ቢኖር ግን ይሄ ልጅ ነገ ተጫውቶ በክለብ ተሸልሞና የክለብ አሰልጣኝ ሆኖ እንዲሄድ ያስፈልጋል::ክለቦችን በሚቀጥለው ዓመት ማቋቋም ካልቻልን ስፖርታችን በጣም በጣም አዘቅት ውስጥ ነው የሚገባው::በዚህ ዓመት ስራ አስፈፃሚዎች ተወያይተውበት ለሚቀጥለው ዓመት ክለቦችን ለማቋቋም መስራት ያለባቸው ይመስለኛል::እኔም አመሰግናለሁ፡፡አዲስ ዘመን ቅዳሜ ግንቦት 3/2011በቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=10606
1,192
2ስፖርት
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ህልውና በመንታ መንገድ ላይ
ስፖርት
August 7, 2019
40
የ2011 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከወትሮው በተለየ አጨቃጫቂ ሁኔታ፣ በተደጋጋሚ መቆራረጥ እንዲሁም በአሰልቺ የውድድር መርሐ ግብር ተጠናቋል፡፡ የዘንድሮው የፕሪሚየር ሊግ ከዚህ ቀደም ይታዩ ከነበሩ ስፖርታዊ ባላንጣነት ይልቅ ‹‹ብሔር ተኮር›› መጠቃቃቶችና ግጭቶችን አስተናግዶ አልፏል፡፡ በሊጉ በተፈጠሩ አለመግባባቶች ምክንያት በተለይ የአዲስ አበባ ክለቦች የተለየ አቋም እንዲይዙ አድርጓል፡፡ አንጋፋው ቅዱስ ጊዮርጊስ የሊጉን የመጨረሻ ሦስት ጨዋታዎች ሳያከናውን የውድድር ዓመቱ መርሐ ግብር ተጠናቋል ቢባልም፣ የክለቡ ቀጣይ ዕጣ ፋንታ እንዴት ሊሆን ነው? የሚለውና ሌሎች ከስፖርት መርህና ባህል ባፈነገጠ መልኩ ሲሰጡ የነበሩ ውሳኔዎች፣ ፌዴሬሽኑ ከፊት ለፊቱ የተደቀኑበት ጥያቄዎችን ሳይፈታና የሊጉን ቀጣይ አካሄድ እንዴት እንደሚሆን ሳይወስን የ2012 ዓ.ም. የውድድር ዘመን በወርሃ ጥቅምት አልያም ህዳር ለመጀመር ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ ሽር ጉድ እያለ መሆኑን እየተሰማ ይገኛል።ከአዲስ አበባ ክለቦች በኩል የተያዘው አቋም ገፍቶ መሄድ የፕሪሚየር ሊጉ ህልውና ጥያቄ ውስጥ መሆኑን ምልክት እያሳየም ይገኛል። ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ የሊጉን አደረጃጀት እንዲቀየር አጥብቀው ሲጠይቁና ሲሞግቱ የሰነበቱት ክለቦቹ ይህንን መንገድ በመተው በራሳቸው በመጓዝ ውጤታማ ለመሆን ከጫፍ ደርሰዋል። ከብሄራዊ እግር ኳስ ፌዴሬሽኑ በኩል ቅቡልነት ያጣው የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጥያቄም ጥናትን መሰረት በማድረግ ተቀብሎ ተግባራዊ ሊያደርገው መሆኑ ታውቋል። የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በኢትዮጵያ እግር ኳስ የሚታየውን የሊግ ውድድር የአደረጃጀት ችግሮች በመለየትና የመፍትሔ ሀሳቦች በማስቀመጥ ላይ ያተኮረ የአውደ ጥናት መድረክ ከትናንት በስቲያ በሸራተን ሆቴል አዘጋጅቷል።በመድረኩ ላይ ዋነኛ ትኩረት የነበረው የሊግ አደረጃጀት ጉዳይ ሲሆን፤ «በኢትዮጵያ አሁን ያለው የሊግ አደረጃጀት በፋይናንስ ረገድ ክለቦች ላይ ያለው ተጽእኖ ምንድ ነው? » በሚል ጥናታዊ ጽሁፍ ቀርቦ ነበር። የጥናቱ አቅራቢ የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ሥራ አስኪያጅ አቶ ገዛኸኝ ወልዴ እንዳሉት በኢትዮጵያ የሊግ ውድድር ፕሪሚየር ሊግ፣ ከፍተኛ ሊግና አንደኛ ሊግ ናቸው፤ በእነዚህ ውድድሮች ላይ በየዓመቱ ሁለት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር ወጪ ይደረጋል። አብዛኞቹ ክለቦች የከተማ ቡድኖች በመሆናቸው ከዚህ ውስጥ 95 በመቶ ከመንግስት ካዝና ወጪ የሚሸፈን ነው። ገንዘቡም ለተጫዋቾች ወርሃዊ ደሞዝ፣ ለምግብ፣ ለመኝታ፣ ተዟዙሮ ለመጫወትና ለትራንስፖርት እንደሚውል ተናግረዋል።የወጪውን ከፍተኝነት ከትራንስፖርት ጋር ተያይዞ ያለውን ሁኔታ አቶ ገዛኽኝ ሲገልጹ ፤ « በዋናነት ተዟዙሮ መጫወት በሁሉም እርከኖች ለትራንስፖርት ብቻ ግማሽ ቢሊዮን (490 ሚሊዮን 800 ሺህ) ብር በየዓመቱ ወጪ ይሆናል። ይህ ሁሉ ወጪ ወጥቶ አንድ በፕሪሚየር ሊግ ውድድር የሚሳተፍ ቡድን ሲያሸንፍ 150 ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት ያገኛል። ከዚህ አኳያ ወጪና ገቢው የማይመጣጠን የገንዘብ ቀውስ ያለበት የሊግ አደረጃጀት እንደሚገኝ ማሳያ ነው» ሲሉ ተናግረዋል። የጥናቱ አቅራቢ እንዳሉት የፊፋ የክለቦች ፈቃድ የሚለው በምንም መንገድ የአንድ ክለብ ወጪና ገቢ መበላለጥ የለበትም ነው፤ ሆኖም በኢትዮጵያ ያለው ነባራዊ ሁኔታ ይሄንን የሚያሳይ አለመሆኑን ገልጸዋል።ሌላው የሊግ አደረጃጀቱ ከጸጥታና ደህንነት፣ ከፋይናንስ አኳያ ያለበት ሁኔታ ምን እንደሚመስል ያቀረቡ ሲሆን ችግሮች መኖራቸውን አስረድተዋል። የሊጉ አደረጃጀት ስፖርታዊ ጨዋነት እንዲጓደል በር ከፋች መሆኑን አመላክተዋል። አሁን ያለው የሊግ አደረጃጀት ከክልሎችና ከከተማ አስተዳደሮች ተሳትፎ አንጻር ሲመዘን ሁሉንም ውድድር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጠቅልሎ የያዘ መሆኑ አቅም ያላቸው ተጫዋቾች እድል እንዳይኖራቸው አድርጓል። የክልሎችን የውስጥ ውድድር አዳከሟል ሲሉ አደረጃጀቱ በሌላ ማዕዘን ያለበትን ክፍተት በጥናቱ አስረድተዋል። በአጠቃላይ የኢትዮጵያ እግር ኳስ የሊግ አደረጃጀት ከፋይናንስ አንጻር ሲታይ ከፍተኛ ችግር ያለበት፣ የመንግስትን ገንዘብ ጥቅም በሌለው መንገድ የሚያስወጣ፣ ስፖርታዊ ጨዋነትን በአጉል መንገድ እንዲጓዝ ያደረገም በመሆኑ ያሉትን ክፍተቶች መስመር በማስያዝና የወደቀውን እግር ኳስ ለማዳን አዲስ የሊግ አደረጃጀት ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ እንደሚሆን አሳስበዋል።በአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የቀረበውን ጥናትና የሊጉ አደረጃጀት እጣ ፈንታ መሰረት በማድረግ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማኅበር ቦርድ ሊቀመንበር አቶ አብነት ገብረመስቀል እንዳሉት የአዲስ አበባ ክለቦች እስከ ዛሬ ድረስ በየክልሉ ስንሄድ ያልደረሰበን ዛቻና ድብደባ የለም። የእኛ አንድ አለመሆንና ምስቅልቅሉ የወጣ ስራ አስፈጻሚ መምረጣችን ነው ዋጋ እየከፈልን ያለው በመሆኑም ከዚህ በኋላ የአዲስ አበባ እግር ካስ ፌዴሬሽን ከጎናችን ቆሞ አንድ መሆንና ያለው የውድድር አደረጃጀት (ፎርማት) መቀየር አለብን ብለዋል ። “እንደ አዲስ አበባ አንድ ሆነን በራሳችን ውድድር እናካሂድ። በዚህ ምክንያት ጉሮሯቸው የሚዘጋ ጥቅማቸው የሚቀር ግለሰቦች የተለያየ ስም ሊሰጡን ይችላሉ። እኛ የፖለቲካ እና የብሄር ቡድኖች አይደለንም። ለሃገራችን ሰላም የሚጠቅመውን እያሰብን ነው ያለነው” ብለዋል።የኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ መሥራችና የቦርድ ሰብሳቢ መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ በበኩላቸው፤ ባለፉት ጊዜያት የተለያዩ ውይይቶችን ስናደርግ ቆይተን አሁን ወሳኝ ጊዜ ላይ ደርሰናል። እስከ ዛሬ የሊግ አደረጃጀት ( ፎርማት) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ ከፍተኛ ሃብት ያካበቱ ግለሰቦች ምን አይነት ሀብት እንዳፈሩ ከነመረጃው በጥናት የምናቀርብ ይሆናል ብለዋል። መቶ አለቃ ፈቃደ አክለው፤ እነዚህ ግለሰቦች የራሳችንን ውድድር ስናካሂድ ከፍተኛ ጥቅም ስለሚቀርባቸው ቡናና ጊዮርጊስ የራሳቸውን ውድድር ብቻቸውን ያድርጉ እያሉ ይሳለቃሉ። አሁን ጉዳዩ የቡናና የቅዱስ ጊዮርጊስ ብቻ አይደለም። የኢትዮጵያን እግር ኳስ ከውድቀት፣ ከሞት የማዳን ነው። ከዚህ በኋላ ለአንድ ቀን ማደር አንችልም። ይህን የመግባቢያ ሰነድ መፈረም አለብን ሲሉ በተደጋጋሚ ጥያቄን ሲያቀርቡበት የነበረውን የሊግ አደረጃጀት እንዲሻር ተማጽኖን አቀረቡ። በመድረኩ ላይ ተሳትፎ ያደረጉ 22 የአዲስ አበባ ክለቦችም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ህልውና በአዲስ የሚቀይረውን የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተቀበሉ። ከፌደራል ፖሊስ ክለብ በቀር በስብሰባው ላይ የተገኙ ለእግር ኳሱ እድገት ሆነ አላግባብ የሚወጡ የመንግስት የገንዘብ ወጪን ለማስቀረት በሚል ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስር በመሆን ለመወዳደር በጋራ ተስማምተው ተፈራርመዋል። ስምምነታቸውም የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለሚመለከተው አካላት በሙሉ እንዲያደርስ ወስነው ጉባኤው ተጠናቋል።የዚህ አይነቱ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ህልውና መንታ መንገድ ላይ እንዲቆም ያደረገው ሆኗል። በጉዳዩ ላይ ከብሄራዊ እግር ኳስ ፌዴሬሽኑ በኩል ምንም አይነት ምላሽም ሆነ አስተያየት ያልቀረበ ሲሆን፤ የአዲስ አበባ ክለቦችን ውሳኔ ተከትሎ ሌሎች ክልሎችም ተመሳሳይ አቅጣጫን እንደሚከተሉ ይጠበቃል።አዲስ ዘመን ነሃሴ 1/2011ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=15658
764
2ስፖርት
ኢትዮጵያዊያኑ በበርሊን ማራቶን የአሸናፊነት ግምት አግኝተዋል
ስፖርት
August 12, 2019
17
በየዓመቱ መስከረም ወር የመጨረሻው እሁድ በሚካሄደው የበርሊን ማራቶን አራት ስመጥር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ተሳታፊ እንደሚሆኑ ታውቋል። በአለም አቀፉ የአትሌቲ ክስ ፌዴሬሽ ኖች ማህበር የወርቅ ደረጃ የተሰጠው ይህ ውድድር፤ ቀዳሚ ከሆኑት ውድድሮች መካከል አንዱ ሲሆን በማራቶን የዓለም ክብረወሰን የሆነ ሰዓት የተመዘገበበትም ነው። በዘንድሮው ውድድር ላይም ኢትዮጵያዊያኑ ጉዬ አዶላ፣ ልዑል ገብረስላሴ፣ ሲሳይ ለማ እና ብርሃኑ ለገሰ አሸናፊ ይሆናሉ በሚል ባለሙያዎች ቅድመ ግምታቸውን አስቀምጠዋል። ምክንያታቸው ደግሞ የሁሉም አትሌቶች የግል ፈጣን ሰዓት ከ2 ሰዓት ከ04 ደቂቃ በታች በመሆኑ ነው። የዚህ ውድድር ዳይሬክተር የሆኑት ማርክ ሚልዴ «በወንዶቹ በኩል የተሻለ ብቃት እንደሚመዘገብ ተስፋ እናደርጋለን። በዚህ ውድድር ላይ የዓለም ክብረወሰን ይሰበራል ብለን ባንጠብቅም ፈጣን ሰዓት እንደሚመዘገብ እንጠብቃለን» ብለዋል። የጀርመኑ ታላቅ የአትሌቲክስ ውድድር ለአስር ዓመታት ያህል በኢትዮጵያዊያን ክብር የደመቀ ነበር። አንጋፋው አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ እአአ ከ2006-2009 ለተከታታይ ዓመታት አሸናፊ ሲሆን፤ ሁለት የዓለም ክብረወሰኖችንም መስበር ችሏል። ከሁለት ዓመታት በፊት የቦታው አሸናፊ የነበረው ቀነኒሳ በቀለም ሁለተኛውን ፈጣን ሰዓት የግሉ ያደረገበት ስፍራ ነው። በዚህ ውድድር ላይ ከሁለት ዓመታት በፊት ተሳትፎ ሁለተኛ ደረጃ ያስመዘገበው ጉዬ አዶላ የአሸናፊነት ተራውን ከኬንያዊያን የሚነጥቅበት ጊዜ አሁን መሆኑን ማህበሩ በድረገጹ ያስነብባል። በወቅቱ ጉዬ የገባበት ሰዓትም 2:03:46 የግሉ ፈጣን ሰኣት በመሆን ተመዝግቦለታል። ጠንካራ አትሌት መሆኑ ሲጠቀስ፤ በዚህ ውድድር የዓለምን ክብረወሰን ያስመዘገበው ኬንያዊው ኢሉድ ኪፕቾጌን የሚያሰጋ ጭምር መሆኑም ነው ድረገጹ ያስነበበው። እአአ የ2014 የዓለም ግማሽ ማራቶን ሻምፒዮኑ ጉዬ ለረጅም ጊዜ በጉዳት ላይ ቢቆይም አገግሞ ወደ ውድድር ተመልሷል። በመሆኑም ጥንካሬውንና በቦታው ያለውን ልምድ ተጠቅሞ አሸናፊ እንደሚሆን አዘጋጆቹ ተስፋ አድርገዋል። በውድድሩ ከፍተኛ የአሸናፊነት ቅድመ ግምት ያገኘው ልኡል ገብረስላሴ፤ 2:04:02 ከአንድ ዓመት በፊት በአረብ ኤሜሬትስ ያስመዘገበው ሰዓት ነው። የ25 ዓመቱ ወጣት አትሌት በቫሌንሺያ ማራቶንም 2:04:31 የሆነ ሰዓት በማስመዝገብ የቦታው የክብረወሰን ባለቤት ነው። ሲሳይ ለማ የውድድሩ ብርቱ ተፎካካሪ እንደሚሆን የሚጠበቀው ሌላኛው አትሌት ነው። በዱባይ ማራቶን ተሳትፎው አምስተኛ ደረጃን ያስመዝግብ እንጂ፤ ውድድሩን ያጠናቀቀበት 2:04:08 የሆነ ሰዓት ግን የግሉ ምርጥ ነው። በቬና እና ፍራንክፈርት ማራቶኖች አሸናፊ የሆነው የ28 ዓመቱ ሲሳይ፤ በበርሊን ማራቶን ተሳትፎ 2:06:56 ሰዓት በማስመዝገብ አራተኛ ሆኖ ነበር የጨረሰው። በመሆኑም አትሌቱ ልምዱን ተጠቅሞ ለአሸናፊነት ይበቃል የሚል ግምት አግኝቷል። በዚህ ዓመት በተካሄደው አቦት ማራቶን አሸናፊ የሆነው የ24 ዓመቱ ብርሃኑ ለገሰ፤ የቶኪዮ ማራቶንን የገባበት 2:04:48 የሆነ ሰዓት የግሉ ፈጣን ነው። በዱባይ ማራቶን ተሳትፎውም ፈጣን ሰዓቱን በማሻሻል 2:04:15 ገብቷል። አትሌቱ በቺካጎ ማራቶን የተካፈለ ሲሆን፤ እአአ በ2015 በበርሊን የግማሽ ማራቶን አሸናፊ ነበር። ይህም አትሌቱ የሌሎች ውድድሮችንና በቦታው ያለውን ልምድ ተጠቅሞ ጥሩ ውጤት ያስመዘግባል በሚል እንዲጠበቅ አድርጎታል።አዲስ ዘመን ነሃሴ 6/2011
https://www.press.et/Ama/?p=15948
360
2ስፖርት
ተስፋ የተጣለበት የባየር ሙኒክ አካዳሚ በኢትዮጵያ
ስፖርት
May 3, 2019
31
የጀርመኑ አንጋፋ ክለብ ባየር ሙኒክ በኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ባሉ ታዳጊ ስፖርተኞች ላይ በመስራት በአገሪቱ ውጤታማ የእግር ኳስ ስፖርተኞችን ለማፍራት የሚያስችለውን የእግር ኳስ አካዳሚ ለመክፈት ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በያዝነው ወር የስምምነት ፊርማ ተካሂዷል፡፡ ክለቡ በአፍሪካ የመጀመሪያውን የእግር ኳስ አካዳሚ በኢትዮጵያ መክፈቱን ተከትሎ ለኢትዮጵያ ምን ፋይዳ እንደሚኖረው እና ፌዴሬሽኑ ከክለቡ ጋር ያደረገው ስምምነት ምን እንደሚመስል ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ከአቶ ባህሩ ጥላሁን ጋር እንደሚከተለው ቆይታ አድርገናል።ስምምነቱ ከ17 ዓመት በታች የሆኑ ልዩ የእግር ኳስ ችሎታና ተሰጥኦ ያላቸውን ታዳጊ ተጫዋቾችን በመላ አገሪቱ በሳይንሳዊ መንገድና ከፍተኛ ብቃትና ችሎታ ባላቸው ባለሙያዎች በመታገዝ በመመልመል ባየር ሙኒክ አዲስ አበባ በተሰኝው የእግር ኳስ አካዳሚ ታቅፈው ኢንተርናሽናል ስልጠና እንዲከታተሉ ስለሚያደርግ ነው። ፊርማው ከታዳጊዎች ስልጠና በተጨማሪ በአገሪቱ ውስጥ ያሉ የእግር ኳስ አሰልጣኞች ከባየር ሙኒክ በሚመጡ አሰልጣኞች ወይም ጀርመን አገር ድረስ በመሄድ የተሻለ ስልጠና እንዲያገኙ እድል ይሰጣል። የክለቡ ዋና አላማ የኢትዮጵያ እግር ኳስን በቴክኒክና በክህሎት የተሻለ ለማድረግ ነው። የክለቡ ባለሙያዎች ባደረጉት ጥናት የኢትዮጵያ ልጆች የተሻለ ስልጠና ካገኙ በእግር ኳሱ ውጤታማ መሆን ይችላሉ የሚል እሳቤ በመቅረቡ ነው። እንዲሁም ጀርመን ከመቶ ዓመት በላይ ከኢትዮጵያ ጋር በእግር ኳሱም ሆነ በሌሎች ማህበራዊ ጉዳዮች መልካም ግንኙነት ያላት በመሆኑ፤ ክለቡ ከታች ከታዳጊዎች ጀምሮ በመስራት ታዳጊ ስፖርተኞን በስፖርታዊ ጨዋነት ተቀርፀው በክህሎትና በቴክኒክ ዳብረው እንዲወጡ በማድረግ ለወደፊት አገሪቱ ጠንካራ ብሔራዊ ቡድን መገንባት እንድትችል እና የእግር ኳስ ደረጃዋ ከፍ እንዲል የሚያስችል ነው። ሌሎች የአፍሪካ አገራት ከሌሎች የአውሮፓ አገራት ጋር ባላቸው ግንኙነት ታዳጊ ተጫዋቾቻቸውን እንደ ፈረንሳይና እንግሊዝ መሰል በእግር ኳሱ ወደ አደጉ አገሮች በመላክ በተለያዩ የእግር ኳስ አካዳሚዎች እንዲታቀፉ ያደርጋሉ። ታዳጊዎቹም የተሻለ ስልጠና በማግኝ ታቸው ህልም ያላቸው ተጫዋቾችን ማፍራት የቻሉ አገራቶች አሉ። ስለዚህ ክለቡ አካዳሚውን በአገሪቱ መክፈቱ ታዳጊ ተጫዋቾች በአገራቸው ከቤተሰቦቻቸው እርቀው ሳይሄዱ ደረጃውን የጠበቀ ሳይንሳዊ የሆነ ስልጠና የሚያገኙበትን እድል የሚፈጥር ነው። በዚህም አገሪቱ ነገ ከነገ ወዲያ የተሻለ ክህሎትና ብቃት ያላቸውን ተጫዋቾች እንድታገኝ ያስችላታል። በሌላ በኩል ክለቡ በኤዥያ ሲንጋፖር ካለው አካዳሚ ቀጥሎ በአፍሪካ የመጀመሪያውን አካዳሚ በኢትዮጵያ ውስጥ መክፈቱ ስፖርቱ በአገሪቱ እንዲያድግ መነሳሳትን የሚፈጥር ነው። የቀድሞ የክለቡ ተጫዋች ብራዚላዊው ጆቫኒ ኤልበር በመክፈቻ ስነስርዓቱ ስምንት የታዳጊ እግር ኳስ ቡድኖች በአዲስ አበባ እስቴዲየም እርስ በእርስ ያደረጉትን ጨዋታዎች እንዲመለከት ተደርጎ ነበር። በስምምነቱ ስነስርዓት ላይ በነበረው የፕሬስ ኮንፈረንስ ላይ ተጋባዥ እንግዳ የነበረው ይኸው ብራዚላዊ ተጫዋች በፕሬስ ኮንፈረንሱ ላይ ሲናገር <<በኢትዮጵያ ያየሁት በብራዚልና በጀርመን ከማያቸው ታዳጊ ተጫዋቾች ተመሳሳይ ታለንት ያላቸው ተጫዋቾችን ነው። በታለንትና በክህሎት ተመሳሳይነት ቢኖራቸውም ነገር ግን በቴክኒክና በታክቲክ የሚቀራቸውና ማስተካከል የሚገባቸው ነገር አለ>> በማለት ተናግሯል። ስለዚህ ክለቡ አካዳሚውን ኢትዮጵያ ውስጥ መክፈቱ በስፖርቱ ያሉ ችግሮችን በመለየት ለችግሮቹ አይነተኛ መፍትሄ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል። ለታዳጊዎችም የተሻለ ደረጃውን የጠበቀ ስልጠና በመስጠት ብሔራዊ ቡድኑንና የክለቦችን አቅም ከፍ የሚያደረጉ ብቃት ያላቸው ተጫዋቾች እንዲፈሩ አይነተኛ ሚና የሚጫወት ይሆናል ተብሎ ይታሰባል። አገር በቀል አካዳሚዎች ያሉ ታዳጊዎች ከአገር ውጭ በሚደረጉ በተለያዩ ውድድሮች ላይ ለመሳተፍ ከፍተኛ ወጭ ስለሚጠይቅ ከአገር ውጭ ተጉዘው ውድድሮችን ለማድረግ ይቸገራሉ። በዚህም ታዳጊዎች የተለያዩ ኢንተርናሽናል ውድድሮች ላይ የመሳተፍ እድ ላቸው ዝቅተኛ በመሆኑ በአለም ገበያ ተወዳዳሪ የሆኑ ስፖርተኞችን ለማፍራት አልቻሉም። ነገር ግን ባየር ሙኒክ በአለም ከፍተኛ ስምና ዝና ያለው ውጤታማ ክለብ እንደ መሆኑ መጠን አካዳሚውን በአገራችን መክፈቱ፤ የአገራችን ታዳጊ እግር ኳስ ተጫዋቾች ነገ ከነገወዲያ አልጋ ባልጋ ሆኖላቸው ወደ አውሮፓና ሌሎች የዓለም አገራት ተጉዘው የመጫወት እድሉን በቀላሉ ማግኝት ያስችላቸዋል። እንዲሁም ታዳጊ እግር ኳስ ተጫዋቾችን ሳይንሳዊ የሆነ ስልጠና በመስጠት ከአለም አቀፍ ስፖርተኞች ጋር በቴክኒኩም በታክቲኩም ብቁና ተወዳዳሪ ስፖርተኞችን በማፍራት ለአለም አቀፍ ገበያ አገሪቱ ተጫዋቾችን ማፍራት የምትችልበትን እድል የሚፈጥር ነው። በአገራችን በአይነቱ ልዩ የሆነ በአፍሪካ የመጀመሪያው አካዳሚ መከፈቱ የተሻለ አቅምና ተሰጥኦ ያላቸው ተጫዋቾች ሳይንሳዊና ሙያዊ በሆነ መንገድ ተመልምለው በየደረጃቸው ማግኝት የሚገባቸውን ስልጠና እንዲያገኙ ያስች ላቸዋል። ተተኪ ስፖርኞች ከታች ጀምረው ደረጃውን የጠበቀ ስልጠና አግኝተው ወደፊት የተሻለ ብሔራዊ ቡድን የምንምለከትበት እድል የሚፈጥር ነው። በአፍሪካ ጠንካራ የሆነ ብሔራዊ ቡድን ካሏቸው አገራት ተርታ ለመሰለፍ የሚያስችልም ነው። በተጨማሪም ይህ አካዳሚ በአገሪቱ መከፈቱ ሌሎች ትልልቅ የሚባሉ በአውሮፓና በሌሎች የአለም አገራት የሚገኙ ክለቦች የባየር ሙኒክን ተሞክሮ በማየት አካዳሚያቸውን በአገሪቱ እንዲከፍቱ የሚያነሳሳና እኛም እንደ ፌዴሬሽን አካዳሚያቸውን በአገሪቱ እንዲከፍቱ በራቸውን እንድናንኳኳ እድል የሚሰጥ ነው። በአጠቃላይ ስልጠናው ከክለቡ በሚመጡ አሰልጣኞች በበላይነት የሚሰጥ ቢሆንም የአገር ውስጥ አሰልጣኞችም በማሰልጠኑ ተሳታፊ የሚሆኑበት እድል በመኖሩ፤ የአገር ውስጥ አሰልጣኞች እውቀት የሚቀስሙበትና የእውቀት ሽግግር የሚፈጠርበት ሁኔታ ይኖራል። ስምምነቱ የተፈረመው በኢትዮጵያ መንግሥትና በጀርመን መንግሥት መካከል ብቻ ስለሆነና አካዳሚው የተቋቋመው የኢትዮጵያን እግር ኳስ የማሳደግ ዓላማን ያነገበ በመሆኑ፤ የሌሎች አገር ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው አካዳሚውን መቀላቀል የሚችሉበት አግባብ አይኖርም። ስለዚህ በይበልጥ አካዳሚው ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራው የኢትዮጵያዊያን ተጫዋቾች የእግር ኳስ ክህሎት ከፍ እንዲል ታሳቢ ያደረገ ነው። አካዳሚው አዲስ አበባ ላይ ይከፈት እንጂ ስልጠናውን የሚሰጠው በመላ አገሪቱ በእግር ኳሱ ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው ተጫዋቾች ተመልምለው አካዳሚውን የሚቀላቀሉ ይሆናል። የምልምላ ሂደቱ በምን መንገድ እንደሚካሄድ አሁን ላይ ይፋ ባያደርጉም፤ እድሉ በአራቱም ማእዘን ላሉ የአገሪቱ ታዳጊዎች ታለንታቸውን እንዲያወጡ ትልቅ እድል የሚፈጥር ይሆናል። ስለዚህ ልዩ ችሎታ ያላቸው ተጫዋቾች ያለምንም ክፍያ አካዳሚውን የሚቀላቀሉ ይሆናል። በመ ሆኑም አካዳሚው ስራውን ሲጀምር በምን መንገድ ተጫዋቾች ይመረጣሉ የሚሉ ነገሮችን ፌዴሬሽኑ ከአካዳሚው ጋር በመሆን በቅርበት የሚሰራ ይሆ ናል።ስፖርት ወዳጅነትንና አንድነትን የሚያጠናክር በመሆኑ፤ መጤ ባህልን የሚያስፋፋ የአሰልጣኞችን የስራ እድል የሚነፍግ አይሆንም። በአንጻሩ ግን አሰልጣኞች ተወዳዳሪ የሆነ ስራ እንዲሰሩ የራሱን የቤት ስራ የሚሰጥ ነው። የተለያዩ አካዳሚዎችና አሰልጣኞች ከዚህ አካዳሚ የተሻለ ወይም ያነሰ ስልጠናና ትምህርት የሚሰጡ ሊኖሩ ይችላሉ። ስለዚህ እያንዳንዱ አሰልጣኝና አካዳሚ የትኛው ደረጃ ላይ ነኝ የሚለውን በደንብ እራሳቸውን እንዲፈትሹ ያደርጋቸዋል የሚል እምነት አለኝ። በተጨማሪም አካዳሚው እንደኢትዮጵያዊያን ባህል እና እምነት መጫወት የሚችሉ ኢትዮጵያዊያን ተጫዋቾችን ማፍራት የሚል አላማን አንግቦ የሚሰራ በመሆኑ፤ ከክለቡ ከፍተኛ ባለ ስልጣናት ጋር ስምምነቱን ስንፈጽም ከኢትዮጵያ ባህል ጋር የሚጣረስ ነገር እንደማይኖር ተገልጿል። እንዲሁም ለአሰልጣኞቻችን ተጨማሪ አቅምና የፉክክር መንፈስን የሚፈጥር እንጂ የስራ እድል የሚነፍግ አለመሆኑንም አስገንዝበዋል። ክለቡ ባየር ሙኒክ አካዳሚውን ለመክፈት ስምምነቱን ከመፈራረም ባሻገር የተለያዩ አጫጭር ስልጠናዎችን በመስጠት የመጀመሪያ ምዕራፉን የጀመረ ሲሆን፤ የክለቡ ትልልቅ ባለስልጣኖች ከፌዴሬሽኑ አመራሮች ጋር በመሆን አካዳሚው በትክክል ወደ ስራ እንዲገባ የሚያስችለውን የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ገምግመው ለክለቡ የቦርድ አባላት ሪፖርት አቅርበዋል። ቦርዱ አካዳሚው ስራ እንዲጀምር ውሳኔውን ያስተላለፈ ሲሆን፤ የአካዳሚውን ስራ መጀመር በጉጉት በመጠባበቅ ላይ ነን። እኔም አመሰግናለሁ::አዲስ ዘመን ሚያዝያ 25/2011በሶሎሞን በየነ
https://www.press.et/Ama/?p=10061
890
2ስፖርት
ተጠባቂው የማንቸስተር ሲቲ እና የሌስተር ሲቲ ፍልሚያ
ስፖርት
May 3, 2019
34
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 37ኛው ሳም ንት ጨዋታዎች ዛሬ፣ ነገ፣ እሁድ እና ሰኞ የሚካሄዱ ሲሆን፤ የሊጉ የሳምንቱ ትልቁ ጨዋታ “ውሃ ሰማያዊዎቹ” ማንቸስተር ሲቲንና “ሰማያ ዊዎቹ”ሌስተር ሲቲን የሚያገናኘው ግጥሚያ ሰኞ በኢትሃድ ስታዲየም ምሽት አራት ስዓት ላይ ይካሄዳል። የአለማችን ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በያዝነው ዓመትም የሊጉን ዋንጫ ማን ያነሳ ይሆን የሚለውን ለመገመት አዳጋች እንደሆነና አጓጊነቱን እንደያዘ የቀጠለ ሲሆን፤ ሊጉ ሊጠናቀቅ ሁለት ጨዋታዎች የቀሩት ቢሆንም የሊጉን ዋንጫ ማን ያነሳ ይሆን? የሚለው የአለምን ቀልብ የገዛ ጉዳይ ነው። በመሆኑም ጨዋታውን ተጠባቂ ያደርገው የሁለቱ ክለቦች ፍልሚያ ዋንጫውን ማንቸስተር ሲቲ ወይስ ሊቨርፑል ያነሳ ይሆን የሚለውን ፍንጭ የሚሰጥ ሲሆን፤ ሌስተር ሲቲ የቀድሞው የሊቨር ፑል አሰልጣኝ የነበሩትን አዲሱ አሰልጣኛቸውን ብሮንዳር ሮጀርስን ከሴልቲክ አስኮብልለው ከቀጠሩ ማግስት ጀምሮ ተከታታይ ድል እያስመዘገበ ይገኛል። በመሆኑም ባለፈው ሳምንት በ36ኛው ሳምንት የሊጉ የጨዋታ መርሃግብር ሌስተር ሲቲ አርሴናልን በሜዳው አስተናግዶ ሶስት ለባዶ በመርታት አርሴናሎች በሚቀጥለው ዓመት በሻምፒወንስ ሊጉ ለመሳተፍ የነበራቸውን ተስፋ ውሃ ቸልሰውበታል። ስለዚህ ሌስተር ሲቲዎች ከጫና ነጻ ሆነው ከውሃ ሰማያዊዎቹ ጋር ለክብር የሚፋለሙ መሆኑ፤ ውሃ ሰማያዊዎቹን ውጤት በማስጣል የዋንጫ ተስፋቸውን ሊያደበዝዙ ይችላሉ የሚል ግምት በስፖርት ቤተሰቡ እየተነሳ በመሆኑ ጨዋታውን አጓጊ አድርጎታል። ከዚህ ባለፈ ጨዋታውን ተጠባቂ ያደረገው ለውሃ ሰማያዊዎቹ ማንቸስተር ሲቲ የሞት የሽረት ጨዋታ በመሆኑ ነው። ምክንያቱም በመርሲሳይዱ ሊቨርፑልና በውሃ ሰማያዊዎቹ ማንቸስተር ሲቲ መካከል ያለው የነጥብ ልዩነት አንድ ነጥብ ብቻ ነው። በዚህ ጨዋታ ሲቲ ነጥብ የሚጥል ከሆነና ቀያዮቹ ሊቨርፑሎች ያለባቸውን ጨዋታ የሚያሸንፉ ከሆነ በአስራ አንደኛው ስዓት ሲቲዎች ከዋንጫ ፉክክሩ ውጭ የሚሆኑ በመሆኑ የሁለቱ ክለቦች ግጥሚያ ከመቼውም ጊዜ በላይ የስፖርት ቤተሰቡ በጉጉት እንዲጠብቀው ሆኖል። ከዚህ ባለፈ ዛሬ በሊጉ አንድ ጨዋታ ሲካሄድ ኢቨርተን በሜዳው በርንሌይን ምሽት አራት ስዓት ላይ ያስተናግዳል። እንዲሁም ነገ በፕሪሚየር ሊጉ አምስት ጨዋታዎች ሲካሄዱ፤ ከነዚህ መካከል ቦርንማውዝ በሜዳው ስፐርሶቹን ቶተነሃም ሆትስፐርስን የሚያስተናግድበትና ኒውካስትል ዩናየትድ ሊቨርፑልን በሜዳው የሚፈትንበት ፍልሚያ ይጠቀሳሉ። እንዲሁም እሁድ ዕለት ሊጉ ቀጥሎ ሲውል ሶስት ጨዋታዎች የሚካሄዱ ሲሆን፤ ቼልሲ ከዋትፎርድ፣ ሀደርስፊልድ ታውን ከማንቸሰተር ዩናይትድ እና ብራይተን ሆቨ አልቢዮን ከአርሴናል የሚያደርጉት ጨዋታዎች ማን በሊጉ አራተኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ ለሚቀጥለው ዓመት በሻምፒዮንስ ሊጉ ተሳሳፊ ይሄናል የሚለውን ፍንጭ የሚሰጥ ነው። ፕሪሚየር ሊጉን ውሃ ሰማያዊዎቹ ማንቸስተር ሲቲ በ92 ነጥብ ሲመራ፤ የመርሲሳይዱ ሊቨርፑል በ91 ነጥብ ይከተላል። ስፐርሶቹ ቶተነሃም ሆትስፐርስ በ70 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ሲይዝ፤ ሰማያዊዎቹ ቼልሲ በ68 ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዞ ይከተላል። በአንጻሩ ካርዲፍ ሲቲ፣ ፉልሃም እና ሀደርስፊልድ ታውን ደግሞ ከ18ኛ እስከ 20ኛ ያሉትን የመጨረሻዎቹን ሦስት ደረጃዎች ይዘው ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛሉ፡፡ እንዲሁም የፕሪሚየር ሊጉን ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነት የሊቨርፑሉ ሙሀመድ ሳላህ በ21ጎሎች ሲመራ፤ የማንቸስተር ሲቲው ኩን አጉኤሮና የሊቨርፑሉ ሴኔጋላዊው ኮከብ ሳዲዮ ማኔ በ20 ጎሎች በሁለተኛ ደረጃ ተቀምጠዋል። የአርሴናሉ ፔር ኢሜሪክ ኦባሚያንግ በ19 ጎሎች ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን እየተከተለ ይገኛል።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 25/2011በሶሎሞን በየነ
https://www.press.et/Ama/?p=10065
392
2ስፖርት
አበራ ኩማ በኦታዋ ማራቶን ለክብረ ወሰን ይሮጣል
ስፖርት
May 5, 2019
28
ኢትዮጵያዊው አትሌት አበራ ኩማ በዘንድሮው የኦታዋ ማራቶን የቦታውን ክብረወሰን ለማሻሻል እንደሚሮጥ አሳውቋል። ውድድሩ በመጪው ወር አጋማሽ ሲካሄድ አበራ የቦታውን ክብረወሰን እንደሚያሻሽል አዘጋጆቹ ተስፋ ማድረጋቸውን አይ.ኤኤ.ኤፍ በድረ-ገጹ አስነብቧል። በዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር የወርቅ ደረጃ በተሰጠው በዚህ ውድድር ከሚሳተፉ አትሌቶች አበራ ኩማ የአሸናፊነት ግምት የተሰጠው ቀዳሚው አትሌት ሆኗል። የሃያ ስምንት ዓመቱ አበራ ከዚህ ቀደም ባደረጋቸው የማራቶን ውድድሮች አርባ ሁለት ኪሎ ሜትሩን ሁለት ጊዜ ከ2፡06 በታች ማጠናቀቅ የቻለ ጠንካራ አትሌት ነው። ባለፈው ዓመት የሮተርዳም ማራቶን ሁለተኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ የራሱ ምርጥ የሆነውን 2፡05፡50 ሰዓት ያስመዘገበ ሲሆን በ2014 የበርሊን ማራቶን ሦስተኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ 2፡05፡56 የሆነ ሰዓት ማስመዝገቡ ይታወሳል። በዚህ ውድድር ኬንያዊው ዴኒስኪ ሜቶ 2:02:57 የሆነውን የዓለም ክብረ ወሰን ማስመዝገቡ አይዘነጋም። አበራ በእነዚህ ሁለት ውድድሮች ፈጣን ሰዓቶችን ካስመዘገበ ወዲህ በማራቶን ጠንካራ ከሚባሉ አትሌቶች ተርታ ተሰልፏል። አሁን ደግሞ ትኩረቱን በካናዳዋ መዲና ኦታዋ በሚካሄደው ትልቅ ውድድር የቦታውን ክብረ ወሰን መስበር እንደሆነ ተናግሯል። ‹‹ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ ይህን ውድድር ማሸነፍ እፈልጋለሁ›› ያለው አበራ የኦታዋ የአየር ፀባይ ክብረ ወሰን ለማስመዝገብ እንደሚያመቸው አብራርቷል። አበራ ካለው የራሱ ምርጥ ሰዓት አኳያ የቦታውን ክብረ ወሰን ለማሻሻል እንደሚችል ይታመናል። የዚህ ውድድር ክብረ ወሰን በኢትዮጵያዊው አትሌት የማነ ፀጋዬ 2014 ላይ የተመዘገበ ሲሆን ሰዓቱም 2፡06፡54 ነው። አበራ ሮተርዳም ላይ ከመሮጡና ፈጣን ሰዓት ከማስመዝገቡ ሰላሳ አምስት ቀናት አስቀድሞ በጃፓን ሌክቢዋ ማራቶን 2፡09፡31 ሰዓት ያስመዘገበበት አጋጣሚ ጥሩ ከማይባሉ ሰዓቶቹ መካከል ይጠቀሳል። ይሁን እንጂ ይህን ሰዓትያስመዘገበው ለሮተርዳም ማራቶን ዝግጅት ይረዳኛል ብሎ ባደረገው ውድድር ነው። አበራ ይህን ውድድር ሲያስታውስ ‹‹በሌክቢዋ ማራቶን ምቾት አልተሰማኝም ነበር፣ በ95 የሙቀት መጠን የምሮጥ ያህል ነበር የተሰማኝ፣ ከዚያ ውድድር ወዲህ ጥሩ ስሜትና ጥንካሬ ይሰማኛል፣ ውድድሩን ከጨረስኩኝ በኋላ ብናደድም አሁን የተሻለ ሰዓት በማስመዝገብ ለማካካስ እሮጣለሁ›› በማለት ለአይ.ኤኤ.ኤፍ ተናግሯል። አበራ ከፍተኛ የራስ መተማመን ያለው አትሌት እንደሆነ ይነገርለታል። ወደ ማራቶን ሲመጣም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንደምናያቸው አትሌቶች በአንድ ጊዜ አይደለም። ውጤታማ የሆኑ የቀድሞ በርካታ አትሌቶች ረጅም ዓመታትን በመም ውድድሮች አሳልፈው ወደ ማራቶን እንደሚመጡት ሁሉ አበራም በመም ውድድሮች ረጅም ልምድ አካብቷል። ሁለት ጊዜ በዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ኢትዮጵያን ወክሎ መወዳደር የቻለው አበራ እ.ኤ.አ 2011 ዴጉ ላይ በተካሄደው ቻምፒዮና በአምስት ሺህ ሜትር አምስተኛ ሆኖ አጠናቋል። በ2013 ሞስኮ ላይ በተካሄደው ቻምፒዮና ደግሞ በ10ሺህ ሜትር አገሩን ወክሎ አምስተኛ ሆኖ ፈፅሟል። አበራ በአምስት ሺህ ሜትር 13፡00፡ 15 የሆነ የራሱ ምርጥ ሰዓት ያለው ሲሆን በ10ሺህ ሜትርም 26፡52፡85 የሆነ ምርጥ ሰዓት አለው። ይህም ከአብዛኞቹ የማራቶን አትሌቶች በተሻለ መሰረታዊ የሆነ የፍጥነት ክህሎት እንዲኖረው ማድረጉን ባለሙያዎች ይመሰክሩለታል። ‹‹በመም ውድድሮች ላይ ያለኝ ቆይታ አጭር ቢሆንም ሁልጊዜ ወደ ጎዳና ላይ ውድድሮች መጥቼ ፈጣን ሰዓት ለመሮጥ አስብ ነበር፣ የመም ውድድሮች ቆይታ ወደጎዳና ላይ ውድድሮች ስመጣ ጠንካራ አትሌት እንድሆን ረድቶኛል›› የሚለው አበራ ከማራቶንና የጎዳና ላይ ውድድሮች አኳያ አስፈላጊ የሆኑ የአካል ብቃት ልምምዶችን መስራት እንደሚያዘወትር ያስረዳል። ሩጫን እንደመዝናኛነት እንደሚመለከተው የሚናገረው አበራ ስራውም ጭምር መሆኑን ይናገራል። በተለይም ወደ ማራቶን ከሚያስገኘው ጥቅም ጋር በተያያዘ ወሳኝ መሆኑን አይደብቅም። በእርግጥም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የመም ውድድሮች ቁጥር እየቀነሰ መሄዱና የጎዳና ላይ ውድድሮች እየበረከቱ የሚያስገኙትም ጥቅም ከፍ እያለ መሄዱ አበራን ብቻ ሳይሆን አብዛኞቹን የምስራቅ አፍሪካ አትሌቶች በለጋ እድሜያቸው ወደ ማራቶን ወስዷቸዋል። አበራ በቀድሞው አትሌት ተሰማ አብሽሮ ስር ከሚሰለጥኑ በርካታ አትሌቶች ጋር ነው ልምምዱን የሚያደርገው። ለወጣት አትሌቶችም የመም ውድድሮች እጥረት አሳሳቢ ቢሆንም ወደ ማራቶን ከመምጣታቸው በፊት ቢሞክሩት የሚል ምክር አለው። በሙምባይ ማራቶን ጥሩ የማይባል ሰዓት ካስመዘገበ ወዲህ የተሻለ ዝግጅትና ልምምድ እያደረገ እንደሚገኝ የገለፀው አበራ በኦታዋ ማራቶን ሌሎች ጠንካራ አትሌቶች ሊፈትኑት እንደሚችሉ ገምቷል። ይሁን እንጂ ጠንካራ ፉክክር ያሰበውን የቦታውን ክብረ ወሰን ለማሻሻል እንደሚረዳው አምኖበታል። በኦታዋ ማራቶን ቀዳሚ ሆኖ የሚያጠናቅቅ አትሌት ሰላሳ ሺህ የካናዳ ዶላር ተሸላሚ ይሆናል። ከዚህ በተጨማሪ የቦታውን ክብረ ወሰን ካሻሻለም አስር ሺህ የካናዳ ዶላር ጉርሻ ይኖረዋል። አዲስ ዘመን ሚያዚያ 27 ቀን 2011 ዓ.ምቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=10228
542
2ስፖርት
ሁለት ክብር በሁለት ዓይነት መጫሚያ
ስፖርት
May 5, 2019
38
ድልን ለማብሰር ከማራቶን እስከ አቴንስ የሮጠው ግሪካዊው መልዕክተኛ ፊሊፒደስ፣ በባዶ እግሩ 42 ኪሎ ሜትር በመሸፈን ለጥቁሮች ኩራት ለዓለም ህዝብ ትንግርት የሆነው አበበ ቢቂላ፣ ለጥቁሮች መብት ትግል ከኦሊምፒክ ስኬት ይልቅ ሰብዓዊነትን ያስቀደመው ቦክሰኛው መሃመድ አሊ፣ በቴሌቪዥን የቀጥታ ስርጭት በእንብርክክ ተማጽኖው የአምስት ዓመታትን የእርስ በእርስ ግጭት ማብቂያ ያበጀለት የእግር ኳስ ፈርጥ ዲድየር ድሮግባ፣… ዓለም ካከበራቸው ታሪክም ከጀግኖች መዛግብት ካሰፈራቸው ስፖርተኞች ጥቂቶች ናቸው። ከ18ኛው ክፍለ ዘመን ወዲህ ስፖርት በሰው ልጅ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ውስጥ ሰፊውን ድርሻ መያዙ ገሃድ ነው። በዚህ ተወዳጅ ክንዋኔ ላይም በጦርነት አውድ ከሚዋደቁት ባላነሰ በርካታ ጀግኖች ተፈጥረው አልፈዋል፤ በዚህ ዘመንም እየተፈጠሩ ይገኛሉ። ስፖርተኞች ደረታቸውን ለጥይት ነፍሳቸውንም ለአገራቸው መገበር ባይጠበቅባቸውም፤ በእልህ አስጨራሽ ትግል ነጭ ላባቸውን አፍስሰው በሚያገኙት ድል ግን አገራቸውን ያስጠራሉ፣ ባንዲራቸውንም በማውለብለብ ህዝባቸውን ያኮራሉ። ታሪክም ከራሳቸው ይልቅ ህዝባቸውን ያስቀደሙ፤ ራሳቸውን ለአደጋ አጋልጠውም አገራቸውን ያስጠሩትን እነዚህን ጀግኖች እያነሳ ሲዘክራቸው ይኖራል። ለዛሬም ከጀግና ስፖርተኞች መካከል አንዱን 100 ዓመታትን ወደኋላ ተመልሰን እናስታውስ። በአገረ አሜሪካ ከታዩ ስፖርተኞች መካከል በቀዳሚነት ይጠቀሳል፤ ጂም ትሮፔ። በኦሊምፒክ ተሳትፎው ያሳየው ቁርጠኝነት አገር ወዳድነቱን የመሰከረ ሲሆን፤ ተግባሩም ለብዙዎችም ትምህርት ሆኗል። እርግጡን የሚያወሳ የልደት የምስክር ወረቀት ባይገኝም አሁን ኦክለሃማ ከተሰኘው የአሜሪካ ግዛት እ.አ.አ በ1887 እንደተወለደ በህይወት ታሪኩ ተጠቅሷል። ትሮፔ በልጅነቱ ከባድ እና ውስብስብ የሆነ ቤተሰባዊ ህይወት የነበረው ሲሆን፤ የመንትያ ወንድሙ እናቱ እንዲሁም የአባቱ ሞት ደግሞ የልጅነት ህይወቱን ይበልጥ ፈታኝ ሊያደርግበት ችሏል። ትምህርቱን ለበርካታ ጊዜ እያቋረጠ እና እየቀጠለ ቢቆይም፤ ፔንሲልቫኒያ በሚገኝ የኢንዱስትሪ ትምህርት ቤት ተማሪ በነበረበት ወቅት ስፖርታዊ ተሳትፎውን ጀምሯል። እንደ እድል ሆኖም በወቅቱ በአሜሪካ ስመጥር በሆኑት የእግር ኳስ አሰልጣኝ ግሌን ስኮቤይ የመሰልጠን አጋጣሚ ተፈጥሮለት ነበር። ነገር ግን በዚያው ዓመት አሰልጣኙ ከዚህ ዓለም በማለፋቸው ከስፖርት ሊርቅ የግድ ሆነበት፤ ከዓመታት በኋላ ኮሌጅ እስኪገባ ድረስም በድጋሚ ወደ ስፖርት አልተመለሰም ነበር። ወደ ስፖርት ከተመለሰ በኋላም በእግር ኳስ እና ቤዝቦል ስፖርቶች ባሻገር በተለያዩ የስፖርት ዓይነቶች መሳተፍ ብቃቱ ተደናቂ አድርጎት ቆይቷል። ከኮሌጅ ቡድን እስከ ክለቦች ድረስም በተለያዩ ውድድሮች ላይ ተሳትፎ ሻምፒዮን ለመሆን ችሏል። በእግር ኳስ ስፖርት የነበረው ብቃት በተለይ የሚደነቅ ይሆን እንጂ በአትሌቲክስ ስፖርቶች ላይ የሚያሳየው ችሎታ ግን የሚያስገርም ነበር። ይህንን ተከትሎም እ.አ.አ በ1912 የስዊድኗ ስቶኮልም አዘጋጅ ለሆነችበት ኦሊምፒክ የአሜሪካ ብሔራዊ ቡድንን ከሚወክሉት መካከል አንዱ በመሆን ተመረጠ። ወቅቱ የፔንታቶሎን እና ዴክታቶሎን የውድድር ዓይነቶች በኦሊምፒክ የተካተቱበት እንደመሆኑም ቶርፔ የታጨው ለእነዚህ የውድድር ዓይነቶች ነበር። የውድድሩ ዕለት ደርሶም ቶርፔ አስደማሚ ብቃቱን ለዓለም ሊያሳይ ሰዓታት ብቻ ቀሩት። ነገር ግን የእዚያን ዕለት ጠዋት ከእንቅልፉ ሲነቃ ጫማውን ካስቀመጠበት ሊያገኝ አልቻለም፤ ከፍለጋ በኋላም እንደተሰረቀ አወቀ። በታላቁ የኦሊምፒክ መድረክ መሳተፍ በግሉ ከሚያስገኝለት ክብር በላይ አገሩን መወከል የዜግነት ግዴታው በመሆኑ ተስፋ መቁረጥ የማይታሰብ ነው። በመሆኑም በአጋጣሚው ከመቆጨት ይልቅ አማራጭ ፍለጋውን ተያያዘው። ከቆሻሻ ማጠራቀሚያ ቅርጫት ውስጥም አገልግሎት የማይሰጡ ሁለት የተለያዩ ጫማዎችን አገኘ። የውድድር ሰዓቱ እየደረሰ በመሆኑም ጫማዎቹን ሳያቅማማ ለካቸው። አንዱ ጫማ ለእርሱ የማይሆን ሰፊ መሆኑ ሌላ ችግር ነበር። ምን ማድረግ እንዳለበትም አሰበ፤ ያገኘው መላም ሰፊውን ጫማ በሁለት ካልሲዎች ደራርቦ ማድረግ ነበር፤ እናም አደረገው። የእርሱ ባልሆኑት ሁለት ዓይነት ጫማዎችን በነጭ እና ጥቁር ካልሲዎች ተጫምቶም ወደ ውድድር ስፍራው አመራ። በተሳተፈባቸው ሁለት ውድድሮችም ብቃቱን አስመሰከረ። ሁለት የወርቅ ሜዳሊያዎችን ለማጥለቅ በቃ። በፔንታቶሎን (ርዝመት ዝላይ፣ ዲስከስ ውርወራ፣ አጭር ርቀት ሩጫ እንዲሁም ትግል) ካደረጋቸው አምስት ውድድሮች መካከል አንዱን ብቻ ተሸንፎ (በጦር ውርወራ) በሰበሰባቸው ነጥቦች ብልጫ አሸናፊ ሊሆን ችሏል። በተሳተፈባቸው የፔንታቶሎን እና ዴክታቶሎን 15 ውድድሮች በድምሩ ስምንቱን በማሸነፍም የቁጥር አንድነትን ማዕረግ ለመጎናጸፍ ችሏል። ቶርፔ በወቅቱ በውድድር አሸናፊነቱ ካጠለቃቸው ሁለት የወርቅ ሜዳሊያዎች ባሻገር ሌሎች ሁለት ሽልማቶችንም ተቀዳጅቷል። የመጀመሪያው ገጸ- በረከት በውድድር አዘጋጇ አገር ስዊድን ንጉስ ጉስታቭ አምስተኛ እጅ የተበረከተለት ሲሆን፤ «የዓለም ምርጡ አትሌት ነህ» በማለትም አበረታተውታል። የሩሲያው ኒኮላስ ሁለተኛም ለትሮፔ ሁለተኛውን የማበረታቻ ሽልማት ሰጥተውታል። ነገር ግን ይህ ታሪክ በጋዜጦች ታትሞ ለንባብ የበቃው ትሮፔ ገድሉን ከፈጸመ ከ36 ዓመታት በኃላ እ.አ.አ በ1948 ነበር። መጽሐፍትም በስሙ ተጽፈው ገበያ ላይ የዋሉት እ.አ.አ በ1952 ነው። አትሌቱ ከዓመታት በኋላ በዓለም ላይ ታዋቂ መሆኑ በአሜሪካ ዜጎች ልብ ሰፊ ቦታ አላሳጣውም፤ አሁንም ድረስ ብዙዎች «ጀግናችን» ሲሉ ያወድሱታል። በፔንሲልቫኒያ ግዛትም በስሙ «ጂም ቶሮፔ» በሚል የተሰየመ ከተማ አለው።አዲስ ዘመን ሚያዚያ 27 ቀን 2011 ዓ.ም ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=10234
591
2ስፖርት
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ23ኛ ሳምንት ጨዋታዎች
ስፖርት
May 3, 2019
19
 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ23ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በመዲናዋና በክልል ከተሞች ነገ፣ እሁድና ሰኞ ስምንቱም ጨዋታዎች የሚካሄዱ ሲሆን፤ የሊጉ የሳምንቱ ትልቁ ጨዋታ በሸገር ደርቢ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ቡና የሚያ ደርጉት ፍልሚያ እሁድ ሚያዝያ 27 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየ ምሽት አስር ስዓት ላይ ይካሄዳል። ከዚህ ባለፈ ቅዳሜ እለት ሶስት የሊጉ ጨዋታዎች ሲካሄዱ፤ ደቡብ ፖሊስ ከአዳማ ከተማ እና ሰማያዊዎቹ ደደቢት ከአፄዎቹ ፋሲል ከነማ በተመሳሳይ ስዓት ከቀኑ ዘጠኝ ስዓት ግጥ ሚያቸውን ያካሂዳሉ። በአንጻሩ መከላከያ ከጣና ሞገዶቹ ባህር ዳር ከተማ ምሽት አስር ስዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም ጨዋታቸውን የሚያካሂዱ ይሆናል። ሊጉ እሁድ ዕለት ቀጥሎ ሲውል አራት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ፡፡ በትግራይ ስታዲየም መቐለ 70 እንደርታ ከስሑል ሽረ፣ ሀዋሳ ከተማ ከሲዳማ ቡና እና ድሬዳዋ ከተማ ከወላይታ ድቻ በተመሳሳይ ስዓት ከቀኑ ዘጠኝ ስዓት የሚፋለሙ ይሆናል። እንዲሁም ሰኞ ዕለት በሊጉ አንድ ጨዋታ ሲካሄድ፤ በትግራይ ስታዲየም ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከጅማ አባ ጁፋር ከቀኑ ዘጠኝ ስዓት የሚፋለሙ ይሆናል። ፕሪሚየር ሊጉን መቐለ 70 እንደርታ በ45 ነጥብ ሲመራ፣ ፋሲል ከነማ በ40 ነጥብ በሁለተኛ ደረጃ ተቀምጧል። ቅዱስ ጊዮርጊስ በ37 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ይከተላል። በአንፃሩ ደቡብ ፖሊስ፣ ስሑል ሽረ እና ደደቢት ደግሞ ከ14ኛ እስከ 16ኛ ያሉትን የመጨረሻዎቹን ሦስት ደረጃዎች ይዘው ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛሉ። የፕሪሚየር ሊጉን ኮከብ ጎል አግቢነት የመቐለ 70 እንደርታው አማኑኤል ገብረሚካኤል በ13 ጎሎች፣ የሲዳማ ቡናው አዲስ ግደይ በ12 ጎሎች እንዲሁም የመከላከያው ምንይሉ ወንድሙ በ11ጎሎች ከአንድ እስከ ሶስት ያሉትን ደረጃዎች ይዘው ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነቱን እየመሩ ይገኛሉ።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 25/2011በሶሎሞን በየነ
https://www.press.et/Ama/?p=10068
218
2ስፖርት
በገንዳ እጦት የባከነው የውሃ ዋና ስፖርት እልባት ሊያገኝ ነው
ስፖርት
May 6, 2019
43
ኢትዮጵያ ካልተጠቀመችባቸው ነገር ግን እምቅ አቅም እንዳላት በባለሙያዎች ከሚጠቆሙ ስፖርቶች መካከል አንዱ የውሃ ዋና ነው። የ«ውሃ ማማ» በሚል የምትጠራው ኢትዮጵያ የዋናተኞች እንዲሁም የውሃ ችግር ሳይኖርባት ለዘመናት በስፖርቱ እንዳትጠራ ሸብቦ ወደኋላ ያስቀራት ችግርም የውሃ ዋና ገንዳ አለመኖር ነው። ለአንድ ስፖርት የማዘውተሪያ ሥፍራዎች መኖር ዓይነተኛ ሚና እንዳለው የሚታወቅ ሲሆን፤ የውሃ ስፖርቶች ፌዴሬሽንም ይህ ሲፈትነው ቆይቷል። አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች ባሉ ሆቴሎች በርካታ የውሃ ዋና ገንዳዎች ይኑሩ እንጂ፤ በአገሪቷ ውስጥ የውድድር ደረጃን የሚያሟሉት የውሃ ዋና ገንዳዎች በግዮን ሆቴል፣ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፣ ሌሎች ተቋማት እንዲሁም በጊዜያዊነት ለአንድ ውድድር በሚል በየክልሉ የሚገነቡት ብቻ ናቸው። ከዚህ ባሻገር በወጣቶች ስፖርት አካዳሚ የሚገኘው የውሃ ዋና ገንዳ አገልግሎት የማይሰጥ ሲሆን፤ በሌሎች ስፍራዎች የሚገነቡትም በተለያዩ እንከኖች ከተያዘላቸው ጊዜ በእጥፍ የዘገዩ ናቸው። ነገር ግን በዚህ ፌዴሬሽን ተሳታፊ የነበሩ ባለሙያዎች እና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ፌዴሬሽኑ ለገንዳ መገንቢያ የሚሆን ቦታ እንደተሰጠው ያወሳሉ። ፌዴሬሽኑ የራሱ ገንዳ ሊኖረው ይገባል በሚል እንቅስቃሴ የተጀመረው ከ15ዓመታት በፊት እንደ ነበር በ1990ዎቹ ፌዴሬሽኑን በፕሬዚዳንትነት የመሩት አቶ ግርማ ዳምጤ በአንድ ወቅት ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ መግለጻቸውን ማስታወስ ይቻላል። ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የኦሊምፒክ ደረጃውን የሚጠብቅ ገንዳ የምትገነባ ከሆነም ዓለም አቀፉ ፌዴሬሽን የተለያዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ እንደሚያደርግ ቃል ገብቶ እንደነበርም ያስታውሳሉ። ከዚያ በኋላም ፌዴሬሽኑ መሬት አግኝቷል። አዲስ ዘመን ጋዜጣም ጉዳዩን በመያዝ በሰራቸው ተከታታይ ዘገባዎች ላይ ቦታው ያለ ግንባታ ተዘንግቶ ባዶውን ለዓመታት መቆየቱን ታዝቧል። ግንባታ ያልተጀመረበት መሆኑን ተከትሎም ቦታው በከተማ አስተዳደሩ በኩል ለሌሎች አካላት ሊሰጥ ይችላል የሚል ስጋትም ከባለሙያዎች ዘንድ ሲሰነዘር ቆይቷል። አሁን ግን ይህ ቦታ መኖሩ ተረጋግጦ በድጋሚ በኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን የባለቤትነት ማረጋገጫ ማግኘቱ ተሰምቷል። ቦታው ለኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን በ1998 ዓ.ም፤ ለውሃ ስፖርቶች ፌዴሬሽን እንዲሁም ሜዳ ቴኒስ ፌዴሬሽን በጋራ የማዘውተሪያ ስፍራ እንዲገነቡበት በሚል የተሰጠም ነው። ይህ ቦታ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ሃያት ሪሊስቴት አካባቢ የሚገኝ ሲሆን፤ ለውሃ ስፖርቶች 16ሺ ካሬ ሜትር እንዲሁም ለሜዳ ቴኒስ 15ሺ ካሬ ሜትር የተከፈለ ነው። ኮሚሽኑ የቦታውን ካርታ በ2000ዓ.ም ቢያገኝም፤ ምንም ሳይሰራበት ከ10ዓመት በላይ መቆየቱን በኢትዮጵያ ውሃ ስፖርቶች ፌዴሬሽን የጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ቀልቤሳ ኤባ ይገልጻሉ። አሁን ፌዴሬሽኑ ባቀረበው ጥያቄ መሰረትም ከኮሚሽኑ የስፖርት ፋሲሊቲ ጋር በመሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቦታውን ለሌላ መስጠት አለመስጠቱን የማጣራት ሥራ ተሰርቷል። ባለሙያዎችም በቦታው ተገኝተው ከተመለከቱ በኋላ መታጠር ስላለበት የግንባታ ፍቃድ ለማውጣት ተችሏል። በዚህም የሁለቱ ፌዴሬሽኖች የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ከኮሚሽኑ ኃላፊዎች ጋር መክረዋል። በምክክሩም ፌዴሬሽኖች የመገንባት አቅም የሌላቸው በመሆኑ በኮሚሽኑ በኩል በ2012ዓ.ም በጀት ተይዞለት የአጥር ግንባታው እንዲጀመር ወደ ፊትም ምን መሆን ይገባል የሚለው በንግግር አቅጣጫ እንዲይዝ ከውሳኔ ላይ ተደርሷል። ኮሚሽኑ በዚህ ወቅት በብሄራዊ ደረጃ ዓለም አቀፍና ዘመናዊ ስታዲየም በመገንባት ላይ የሚገኝ በመሆኑም ገንዳውን ለመገንባት እንደማይቻል እንደ ምክንያት ተነስቷል። ሁኔታዎች ቢመቻቹና ገንዳው ቢገነባ ፌዴሬሽኑ የማዘውተሪያ ስፍራ የሚያገኝ በመሆኑ፤ ለብሄራዊ ቡድን ስልጠና፣ ለአገር አቀፍ ሻምፒዮናዎች እንዲሁም ሌሎች ዞን አቀፍ ውድድሮችን ወደ አገር ለማምጣት እንደሚረዳ ኃላፊው ይጠቁማሉ። ከዚህ ባሻገር ለፌዴሬሽኑ የገቢ ምንጭ የሚያገኝበት አንድ መንገድ ይሆናል። ዓለም አቀፉ የውሃ ስፖርቶች ፌዴሬሽንም እገዛ እንዲያደርግ ፌዴሬሽኑ ጥያቄ እንደሚያነሳም አስታውቀዋል። ከዚህ ቀደም ለስፖርቱ ልማት እንዲውል የገንዘብ ድጋፍ መደረጉንም ያስታውሳሉ። ቦታው ከግንባታ ውጪ ለዓመታት ሊቀመጥ የቻለው በተለያዩ ፕሮጀክቶች ግንባታ መደራረብ መሆኑን በኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን የስፖርት ፋሲሊቲ ዳይሬክተር ኢንጂነር አዝመራው ግዛው ይገልጻሉ። ካርታው የተሰጠው በ2000ዓ.ም ሲሆን፤ በወቅቱ ደግሞ መንግሥት የኢትዮጵያ ወጣቶችና ስፖርት አካዳሚ፣ የጥሩነሽ ዲባባ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል፣ የብሄራዊ ስታዲየም ዲዛይን እንዲሁም ግንባታ በእነዚህ ዓመታት ሲከናወኑ ቆይተዋል። እነዚህ ትልልቅ ፕሮጀክቶች ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቁ በመሆናቸው ቅድሚያ በመስጠት የውሃ ዋናው እንዲሁም የሜዳ ቴኒስ ሜዳው ግንባታ መዘግየቱን ያነሳሉ። ሁሉንም በአንድ ጊዜ ለመገንባት በበጀት እጥረት ምክንያት አልተቻለም። እንዲያም ሆኖ ሲገነቡ የቆዩት ፕሮጀክቶች ለእነዚህ ስፖርቶች የሚሆኑ ማዘውተሪያዎችን ያካተቱ ነበሩ። ለአብነት ያህል የወጣቶች ስፖርት አካዳሚ የውሃ ዋና ገንዳ እንዲያካትት መደረጉን እንዲሁም የሜዳ ቴኒስም በአንዳንድ አካባቢዎች መኖራቸውንም ዳይሬክተሩ ይጠቅሳሉ። በከፍተኛ ደረጃ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እጥረት አለ፤ በመሆኑም በአግባቡ ማልማትና ሥራ ላይ ማዋል ተገቢ ነው። መንግሥት ስፖርቱን ለማሳደግ በሚያደርገው ጥረት ለስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ መገንቢያ ቦታውን ቢሰጡም፤ ለዓመታት የቆየው ያለ ሥራ ነበር። በወቅቱ ቦታውን ከልሎ ማስቀመጥ ይገባ እንደነበረም አልሸሸጉም፤ እስካሁንም ወደ መሬት ባንክ ሳይገባ እንዲሁ ቆይቷል። አሁን ግን ካርታውን የማደስ ሥራ የተከናወነ ሲሆን፤ ከዚህ በኋላም አጥር የመከለል እና በአግባቡ እንዲጠበቅ የማድረግ ሥራ እንደሚከናወን ዳይሬክተሩ ይጠቁማሉ። ከማጠሩ ሥራ በተጓዳኝ ስፍራውን በችግኝ የማልማት እንዲሁም መጠነኛ ግንባታ ይከናወናል። ከዚህ ቀደም የተሰሩ ዲዛይኖች በመኖሩ ይህንን የመገምገም አሊያም አዲስ መስራት የሚገባ ከሆነም እርሱን የማወዳደር ሥራዎችም በቀጣይ በጀት ዓመት የሚከናወን ይሆናል። አሁን በግንባታ ላይ የሚገኘው የብሄራዊ ስታዲየም ከፍተኛ ገቢ የሚጠይቅ በመሆኑ ርብርብ የሚደረገው ይህንን ለማጠናቀቅ ነው። የቦታው ፕሮጀክትም በቀጣይ የሚከናወን ይሆናል። ከዚህ በተጨማሪም ዘርፉ የማዘውተሪያ ስፍራዎች ላይ የተለያዩ ሥራዎችን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ዳይሬክተሩ ይጠቁማሉ። የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን በተመለከተ በ2004ዓ.ም በወጣው አዋጅ ላይ በአንድ ወረዳ ቢያንስ አንድ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ መኖር እንዳለበት ይጠቁማል። በመሆኑም በየትኞቹ አካባቢዎች የማዘውተሪያ ስፍራዎቹ ይገኛሉ በሚል መረጃ ለማጠናቀር በግብረ ኃይል እየተሰራ ይገኛል። ይህ ሲጠናቀቅም የትኞቹ የማዘውተሪያ ስፍራዎች የይዞታ ባለቤትነት ማረጋገጫ አላቸው? በየትኞቹ አካባቢዎችስ ማዘውተሪያ ስፍራዎቹ ይገኛሉ? የሚለውን መረጃ ማግኘት ይቻላል። ከዚህ በኋላም ያሉት የማዘውተሪያ ስፍራዎች ጥበቃ እንዲያገኙና እንዲለሙ የማድረግ ሥራ ይከናወናል። የይዞታ ማረጋገጫ የሌላቸው ስፍራ ዎችም እንዲያገኙ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የሚሰራ መሆኑን ዳይሬክተሩ አብራርተዋል።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 28/2011ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=10283
747
2ስፖርት
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ማክሰኞ ይጀመራል
ስፖርት
May 5, 2019
32
በኢትዮጵያ አትሌቲክስ አንጋፋውና ያለምንም መቆራረጥ በየዓመቱ ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ማክሰኞ ይጀምራል። ዘንድሮ ለ48ኛ ጊዜ የሚካሄደው ይህ ውድድር ሁሉንም የአትሌቲክስ እና የሜዳ ላይ ተግባራትን አካቶ የሚከናወን ሲሆን፤ ለዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሚኒማ ማሟላት የሚችሉ አትሌቶችም የሚታጩበት መድረክ ነው። ባለፉት ዓመታት ከዚህ ውድድር በርካታ ብርቅዬ አትሌቶች የፈሩ ይሁን እንጂ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን መቀዛዝ እየተስተዋለበት ይገኛል። በተለይ በውጪ ሃገራት ውድድሮች ላይ ተሳታፊ የሆኑ ታዋቂ አትሌቶች በሃገር ውስጥ ውድድሮች አለመታየታቸው በብዙዎች ዘንድ ወቀሳ እንዲሰነዘርበት ያደርጋል። በመሆኑም በዚህ ዓመት በርካታ ታዋቂ አትሌቶች የተሳተፉ ሲሆን፤ አማን ወጤ፣ ጫላ በዮ፣ ዲኖ ስፍር፣ አንዷምላክ በልሁ፣ አባዲ ሃዲስ፣ የኔው አላምረው፣ ሰለሞን ባረጋ፣ አዲር ጉር፣ … በወንዶች በኩል ተሳታፊ የሚሆኑ አትሌቶች ናቸው። በሴቶች በኩልም፤ ደራ ዲዳ፣ ነጻነት ጉደታ፣ በላይነሽ ጉደታ፣ ሱሌ ኡቱራ፣ ብርትኳን ፈንቴ፣ ህይወት አያሌው፣ ፎቴን ተስፋይ፣ ሰንበሬ ተፈሪ፣ አራያት ዲቦ፣… ከተካፋዮቹ ጥቂቶቹ ናቸው። የዚህ ውድድር ዓላማ፤ ለአትሌቶች የሃገር ውስጥ የውድድር ዕድሎችን ከመፍጠርም ባሻገር በክልሎች፣ ከተማ አስተዳደሮችና ክለቦች መካከል ፉክክር ለመፍጠር እንዲሁም ለብሄራዊ ቡድን የሚሆኑ አትሌቶችን ለመምረጥ ነው። ውድድሩን ለማካሄድ ዝግጅቱ የተጠናቀቀ ሲሆን፤ 2ነጥብ1 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት ተመድቦለታል። ለውድድር የሚሆኑት ቁሳቁሶችና ግብዓቶች ከመሟላታቸውም በላይ ውድድሩን የሚመሩ አደረጃጀቶች መፈጠራቸውንም በፌዴሬሽኑ ጋዜጣዊ መግለጫ በተሰጠበት ወቅት ተጠቅሷል። ማክሰኞ በሚጀመረው ሻምፒዮና ላይም ከዘጠኝ ክልሎችና ሁለት ከተማ አስተዳደሮች  እንዲሁም ከ36 ክለቦች የተወጣጡ አንድ ሺ376 አትሌቶች ተሳታፊ ይሆኑበታል። ይህም ካለፈው ዓመት ሻምፒዮና ጋር ሲነጻጸር በ122 አትሌቶች ብልጫ የታየበት ነው። ውድድሩ የሚመራውም፤ በ80የአትሌቲክስ ዳኞች፣ 45 የፌዴሬሽኑ አመራሮችና ባለሙያዎች፣ 3 የህክምና ባለሙያዎችና አንድ አምቡላንስ፣ 32 በጎ ፍቃድ አገልጋዮች እንዲሁም ሌሎች ስራዎችን የሚያከናውኑ ሙያተኞች እንደሆነም ታውቋል። የመክፈቻ መርሃ ግብሩ በቴሌቪዥን የቀጥታ ስርጭት ሽፋን የሚሰጠው ሲሆን፤ የማጣሪያ እና የፍጻሜ ውድድሮችም ይካሄዳሉ። ጠዋት ከሚካሄዱ ውድድሮች መካከል የሴቶች አሎሎ ውርወራ እና የወንዶች ሱሉስ ዝላይ ፍጻሜያቸውን ያገኛሉ። በ800፣ 400እና 100 ሜትር የወንድ እና ሴት የማጣሪያ ውድድሮችም ይካሄዳሉ። በኦሊምፒክ ባህል መሰረት የውድድሩ የመክፈቻ ዝግጅት አመሻሹ ላይ የሚካሄድ ሲሆን፤ ውድድሮችም ይኖራሉ። በዚህም መሰረት የሴትና ወንድ የ10ሺ ሜትር የፍጻሜ እንዲሁም የ100ሜትር እና 400 ሜትር የግማሽ ፍጻሜ ውድድሮች በሁለቱም ጾታ ይከናወናሉ። በ42ቱ ውድድሮች አሸናፊ ለሚሆኑ አትሌቶችም የ2ሺ፣ 1ሺ400 እና 1ሺ ብር ሽልማት እንደየደረጃቸው የሚያስገኝ ይሆናል። ክብረወሰን ለሚያሻሽሉ እና ከሶስት ወርቅ በላይ ለሚያስመዘግቡ አትሌቶችም 6ሺ ብር ተጨማሪ ሽልማት የሚያገኙ ሲሆን፤ ሁለት ወርቅ ለሚያጠልቁ አትሌቶች ደግሞ 5ሺ ብር ይሰጣቸዋል። በአጠቃላይ አሸናፊ ለሚሆኑት አተሌቶችም 20ሺ፣ 16ሺ እንዲሁም 10ሺ ብር ይበረከትላቸዋል። ውድድሩ እስከ መጪው ግንቦት 04 ቀን /2011ዓም ለስድስት ተከታታይ ቀናት የሚካሄድ ሲሆን፤ የአትሌቲክስ ስፖርት ወዳዱ ህብረተሰብ በአዲስ አበባ ስታዲየም ተገኝቶ ስፖርቱን እንዲደግፍም በፌዴሬሽኑ ጥሪ ቀርቧል።አዲስ ዘመን ሚያዚያ 27 ቀን 2011 ዓ.ምብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=10232
376
2ስፖርት
ኢትዮጵያ ያጣችው ጋላቢ ነው ፈረስ?
ስፖርት
May 4, 2019
76
የፈረስ ስፖርት በዓለም ላይ ተወዳጅ ከሆኑ የኦሊምፒክ ስፖርቶች አንዱ ነው። ኢትዮጵያም ከዚህ ስፖርት ጋር ለበርካታ ዘመናት ትተዋወቃለች። በዓለም አቀፉ ውድድሮችም ውጤታማ የሆኑ የስፖርቱ ጀግኖች ነበሯት። ለዚህም ከመቶ በላይ ሜዳሊያዎችና ዋንጫዎችን በዓለም አቀፍ መድረኮች ማሸነፍ የቻሉት እንደ ጋሽ በቀለ መርጊያ አይነት ባለታሪኮችን መጥቀስ በቂ ነው። ኢትዮጵያ በጋማ ከብቶች ሀብት ከዓለም ትልቅ ደረጃ የያዘች አገር ከመሆኗ ባሻገር በፈረስ ሀብቷም ከዓለም አስረኛ ከአፍሪካ ደግሞ ቀዳሚውን ደረጃ ትይዛለች። ፈረስ ከቀደምት ነገስታት ጀምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ቦታ ምን ያህል ትልቅ እንደሆነ ይታወቃል። አሁንም ቢሆን ፈረስ በተለይም ከገጠራማው የማህበረሰብ ክፍል የእለት ከእለት ኑሮ ጋር ያለው ጥብቅ ቁርኝት በቀላሉ የሚታይ አይደለም። ይሁን እንጂ ቀድሞ የነበረን የፈረስ ስፖርት ታሪክ አሁን ላይ በምን ደረጃ ላይ እንኳን እንደሚገኝ ለብዙዎች ግልፅ አይደለም። በርካቶችም ካለን እምቅ ሀብት አኳያ ኢትዮጵያ ያጣችው ፈረሱን ነው ጋላቢውን? ብለው መጠየቃቸው አይቀርም። አዲስ ዘመንም የኢትዮጵያ ፈረስ ስፖርት በምን ደረጃ እንደሚገኝና በስፖርቱ ዙሪያ ስላሉ ሌሎች ጉዳዮች ከኢትዮጵያ ፈረስ ስፖርት አሶሴሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዘሪሁን ቢያድግልኝ ጋር ያደረገው ቃለ መጠይቅ እንደሚከተለው ቀርቧል። አዲስ ዘመን፡- የኢትዮጵያ ፈረስ ስፖርት አሁን በምን ደረጃ ላይ ይገኛል?አቶ ዘሪሁን፡- የኢትዮጵያ ፈረስ ስፖርት አሶሴሽን አሁን በምን ደረጃ ላይ ነው የሚገኘው? የሚለውን ለማየት ወደ ኋላ ሄዶ ዘመናዊው የፈረስ ስፖርትን ማየት አስፈላጊ ይመስለኛል። በኢትዮጵያ የዘመናዊ ስፖርት ታሪክ ውስጥ የፈረስ ስፖርት ቀዳሚ ነው ማለት ይቻላል፣ በአገራችን ዘመናዊ የፈረስ ስፖርት መዘውተር የጀመረው በዳግማዊ ሚኒሊክ ዘመነ መንግሥት ነው፣ ያን ጊዜ ለጋሲዮን አሁን ደግሞ ኤምባሲ በሚባሉት የጣሊያን፣ የፈረንሳይ፣ እንግሊዝና አሜሪካን ኤምባሲ ሰራተኞች አማካኝነት ነው የተጀመረው። የተለያዩ ሰራተኞች በየኤምባሲዎቻቸው የፈረስ ስፖርትን ያዘወትሩ ነበር፣ በኋላም ውድድሮችን ጃን ሜዳ ላይ ያደርጉ ነበር። ዘመናዊ የፈረስ ስፖርት በዚህ አይነት መልኩ ከተጀመረ በኋላ እንቅስቃሴው እየጠነከረ በተለይም በወታደራዊው ክፍልና የቤተ መንግሥት አስተዳደር አይነት አንዳንድ የሲቪል መስሪያ ቤቶችም እየተዘወተረ ሲሄድ የፈረስ ስፖርትን በበላይነት የሚመራ አካል ማቋቋም አስፈለገና 1950 ዓ.ም በቻርተር የኢምፔሪያል ሬሲንግ ክለብ ወይንም የኢትዮጵያ ፈረስ እሽቅድምድም ክለብ በሚል በአዋጅ ተቋቋመ። ከ1950 ዓ.ም ጀምሮ የፈረስ ስፖርት እንቅስቃሴ በጣም ተወዳጅ ውድድሮችም ከአገር አልፎ ውጪ አገር ድረስ እየሄዱ የኛ ተወዳዳሪዎች የሚሳተፉበት የውጪዎቹም እኛ አገር በመምጣት የሚወዳደሩበት ሁኔታ ነበር። በዚህ አይነት ከቀጠለ በኋላ በደርግ ዘመን የስፖርቱ አደረጃጀት ሲቀየር የኢትዮጵያ ፈረስ ስፖርት ፌዴሬሽን ተብሎ 1979 ዓ.ም አካባቢ ተቋቋመ። ከዚያ በኋላ በ1992 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፈረስ ስፖርት አሶሴሽን ተባለ። ወደ አሶሴሽን የተለወጠበት ምክንያት በስፖርቱ አደረጃጀት ህግ መሰረት አንድ ፌዴሬሽን እንደ ፌዴሬሽን ለመቋቋም ቢያንስ በአምስት ክልሎች ስፖርቱን የሚመሩ አካላት መደራጀት አለባቸው ስለሚልና ከስፖርቱ ባህሪ አንፃር ይህንን ማሟላት ስላልቻለ የኢትዮጵያ ፈረስ ስፖርት አሶሴሽን ሆኖ ተደራጀ። ከቀድሞው ሁኔታ ጋር ስናመዛዝነው አሁን የሚገኝበት ደረጃ በጣም በተቀዛቀዘ ሁኔታ ላይ ነው የሚገኘው። ካለፈው አንድ ወይም ሁለት ዓመት ወዲህ ግን አዲስ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ተቋቁሞ የተለያዩ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል። አንዱ ትልቁ ስራ የጽህፈት ቤቱን አደረጃጀት ማቅናትና በሰው ኃይልና በተለያየ መንገድ ማጠናከር ነው፣ ሁለተኛው ስራ የአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶችን ማጠናከር ነው። እስከተወሰነ ዓመት ድረስ የኢትዮጵያ ፈረስ ስፖርት አሶሴሽን የዓለም አቀፍ ፈረስ ስፖርት ፌዴሬሽንና በአህጉር ደረጃ የቡድን ዘጠኝ አባል አገራት አሶሴሽን አባል ይሁን እንጂ ያለው ግንኙነት የላላ ነበር። ስለዚህ አንዱ የአሶሴሽኑ ስራ ይህ ሊሆን ችሏል። በዚህም አሁን ላይ ከዓለም አቀፍ ፌዴሬሽኑም ከቡድን ዘጠኝ አባል አገራት አሶሴሽንም ጋር ጠንካራ ግንኙነት ሊፈጠር ችሏል። በዚህም መሰረት ባለፈው ዓመት ለዓለም አቀፍ ፌዴሬሽኑ ጥያቄ አቅርበን በአገር ውስጥ ስልጠና እንዲሰጠን ከሦስት ወራት በፊት ለፈረስ ተንከባካቢዎችና ለፈረስ አሰልጣኞች የመጀመሪያ ደረጃ ስልጠና ተሰጥቶልናል። ይሄ የግንኙነቱ ውጤት ነው ማለት ይቻላል። ከዚህ ቀጥሎም የኢትዮጵያ ፈረስ ስፖርት አሶሴሽን አሁን ያለበትን ደረጃ እንቅስቃሴው ምን ይመስላል፣ የሰው ኃይሉና ግንኙነቱ እንዴት ነው፣ ምን ጥሩ ነገር አለው፣ ምንስ ይጎድለዋል የሚለውን ገምግሞ የማሻሻያ አስተያየት የሚሰጥ ባለሙያ ከወር በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ይመጣል። በሚቀጥለው ዓመትም የፈረስ ተንከባካቢዎች ዓለም አቀፍ ስልጠና በአገራችን ይሰጣል። ከፌዴራል ስፖርት ኮሚሽንና ከኦሊምፒክ ኮሚቴ ጋር የነበረውን ግንኙነት በማጠናከር፣ የፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን ዓመታዊ በጀት ድጎማ ከመስጠት ባሻገር አሶሴሽኑ በሚያከናውናቸው የተለያዩ እንቅስቃሴዎች የተለያዩ ድጋፎች ያደርጋል። ኦሊምፒክ ኮሚቴም ለስልጠናዎች የሚሆን የበጀት ድጋፍ ያደርጋል። አዲስ ዘመን፡- ስፖርቱን ለማሳደግ ክለቦች ወሳኝ ሚና አላቸው። የፈረስ ስፖርት ክለቦች በአገራችን አሉ?አቶ ዘሪሁን፡- በአሁኑ ጊዜ ስምንት ክለቦች አሉ፣ እነዚህን አባል ክለቦች የማጠናከር ስራና ህጋዊ አቋም እንዲኖራቸው ማድረግ ትልቁ ስራ ነው። በዚህም መሰረት እስካሁን በተደረገው እንቅስቃሴ ሁለት ክለቦች የህጋዊነት የምስክር ወረቀት ወስደዋል፣ ሌሎቹም በሂደት ላይ ናቸው። ከውድድር ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ፈረስ ስፖርት አሶሴሽን ከሌሎች ፌዴሬሽኖች የተለየ ባህሪ አለው፣ በዓመት ውስጥ ስድስትና ሰባት የሚደርሱ ውድድሮችን ያካሂዳል፣ ውድድሮችን ሲያካሂድ ግን ራሱ የሚያዘጋጃቸው አሉ። ከክለቦች ጋር በጋራ ሆኖ የሚያዘጋጃቸው ውድድሮች አሉ፣ የዓመቱ የመርሃግብር መክፈቻ በአሶሴሽኑ አማካኝነት ሲካሄድ ሌሎቹ ከክለቦች ጋር በጋራ በመሆን ነው። አዲስ ዘመን፡- እነዚህ ሁሉ ውድድሮች ሲካሄዱ ግን ሚዲያውም ሌላውም ሰው አያውቃቸውም ለምንድነው?አቶ ዘሪሁን፡- በእኛም በኩሉ ችግር አለ፣ የተጠናከረ የግንኙነት ስራዎችን እየሰራን አይደለም። በሌላ በኩል ደግሞ ሚዲያው ሁል ጊዜ እስኪጠራ መጠበቅ የለበትም፣ አሁን እናንተን ጠርተናችሁ አይደለም የመጣችሁት፣ ሚዲያው የቆመው ለአገር ስፖርት እስከሆነ ድረስ ወደ ፍለጋ መሄድ አለበት። የሁለትዮሽ ግንኙነት መፈጠር አለበት። ዋናው ባለቤቶች በእርግጥ እኛ ነን፣ ማሳወቅና መቀስቀስ አለብን።አዲስ ዘመን፡- ኢትዮጵያ ከፈረስ ጋር ልዩ ቁርኝት ያላት አገር ናት፣ የኢትዮጵያ ፈረስ ስፖርት ግን አላደገም፣ ምክንያቱ ምንድነው?አቶ ዘሪሁን፡- እኛ ኢትዮጵያውያን በፈረስ ሀብት ዙሪያ በጣም የታደልን ነን፣ በፈረስ ሀብት ብዛት ከዓለም 10ኛ ከአፍሪካ ደግሞ 1ኛ ነን፣ በአፍሪካ ውስጥ ከሚገኘው የፈረስ ሀብት ብዛት 42 ከመቶ ያህሉ በኢትዮጵያ ነው የሚገኘው፣ የባህላዊውን ፈረስ እንቅስቃሴ ስንመለከት በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች በፌስቲቫል፣ በባህል ማድመቂያ በርካታ የሸርጥና የጉግስ ውድድሮች ይካሄዳሉ፣ የኛም አንዱ ትኩረት የባህላዊው ስፖርት እንደተጠበቀ ሆኖ ጎን ለጎን የኢትዮጵያን የፈረስ ሀብት በዘመናዊው መልክ የማስኬዱን ስራ ትኩረት ሰጥተን መስራት እንዳለብን ተረድተናል። ለዚህም ግንኙነት ጀምረናል፣ ለምሳሌ በአማራ ክልል አዊ ዞን የአድዋን ድል ምክንያት በማድረግ ትልቅ በዓል አለ። ከእነሱ ጋር ስራ ጀምረናል፣ አጋጣሚው ጥሩ ሆነና ከሳምንት በፊት የእነሱ ማህበር ፕሬዚዳንት መጥቶ ተነጋግረናል፣ ጥያቄያቸው ምንድነው የባህላዊውን እኛ እንመራዋለን ዘመናዊውን ለማዘውተር እንድንችል አግዙን አሉ፣ እኛ ደግሞ ልናግዝ የምንችለው ስልጠና ላይ ነው፣ የኢትዮጵያን ፈረስ ስፖርት እንቅስቃሴ ስንመለከት ፈረስ አለ፣ ሰው አለ፣ ሜዳው አለ፣ እነዚህ መሰረታዊ ነገሮች አሉ፣ የሚጎድለው ነገር አንደኛው ስልጠና ሁለተኛው ያለውን የፈረስ ማዘውተሪያ ቁሳቁስ ዘመናዊ የማድረግ ነው፣ እነዚህን ለማድረግ ደግሞ እኛ ማገዝ እንችላለን። ከስልጠናው ጎን ለጎን የማደራጀትም ስራ መሰራት እንዳለበት እናምናለን። ለምሳሌ ከኦሮሚያ ስፖርት ኮሚሽን፣ ከአማራ ክልል ስፖርት ኮሚሽንና ከሌሎች ጋርም ግንኙነት ጀምረናል። በየክልሉ ይስፋፋ ስንል በየክልሉ ስፖርቱን የሚመራ አካል መፈጠር አለበት ለማለት ነው። ጅምሩ አለ፤ ግን ተጠናክሮ መሄድ እንዳለበት እናምናለን። አዲስ ዘመን፡- ከአንድ ወይም ከሁለት ዓመት በፊት ከውጪ አገር ምርጥ ፈረሶች በማምጣት ለማዳቀል ተሞክሮ ነበር፣ አገር ውስጥ ፈረስ ጠፍቶ ነው? ከመጣስ ወዲህ ምን ፈየደ?አቶ ዘሪሁን፡- ይሄንን ትልቅ ስራ የሰራው በቤተ መንግሥት አስተዳደር የባልደራስ ፈረስ ስፖርት ክለብ ነው፣ እንዲያውም ከዝርያው በተጨማሪ ባለሙያዎችን ወደ ጀርመን አገር ልኮ እዚያ ያለው እንቅስቃሴ ምን ይመስላል የሚለውን ትልቅ ልምድ ወስዶ ነው የመጣው፣ የውጪ አገር ፈረስ ዝርያዎችን በማምጣት አዳቅሎ ያለውን የፈረስ አቅም የመገንባት ስራ ሰርተዋል። የፈረስ ስፖርት ሲባል የራሱ ባህሪ አለው፣ ለምሳሌ የዝላይ ፈረሶች በጣም ግዙፍ መሆን አይገባቸውም፣ የራሳቸው አቋም ሊኖራቸው ይገባል፣ የሸርጥ ፈረሶች ደግሞ የራሳቸው ነገር አላቸው፣ ለእያንዳንዱ የፈረስ ስፖርት ደግሞ የሚፈለገው የፈረስ አቋም እንደየ ስፖርቱ ባህሪ የተለየ ነው። የእኛ ፈረሶች የራሳቸው የሆነ ልዩ አቅም አላቸው፣ በሽታና ችግርን የመቋቋም ትልቅ አቅም አላቸው፣ በሌላ በኩል ልክ እንደ አትሌቲክሱና አትሌቶቻችን ብርታትና የአካል ብቃት አላቸው፣ ስለዚህ በፈረሶቻችን አቅም ማግኘት የሚገባን ነገር አለ፣ የውጪውንም ስናመጣ ደግሞ ሙሉ በሙሉ ወደ ውጪ እንቀይረው ሳይሆን ከእኛ ፈረሶች ጋር በማዳቀል ልናሻሽል የሚገባው ነገር አለ፣ ዋናውና ትልቁ የኛ አገር ፈረሶች የሚጎድላቸው ነገር የጤንነትና የተለያየ እንክብካቤዎች ነገር ነው።አዲስ ዘመን፡-ከአቅም ጋር ይወሰናል ለማለት ነው?አቶ ዘሪሁን፡- የአቅም ብቻም አይደለም፣ የግንዛቤና የእውቀት ማነስም ይታያል፣ የፈረሶቻችን አያያዝ እንዴት ነው ካልን አመጋገባቸው በአብዛኛው ሳር ነው፣ መኖ ካልን የእህል ዝርያ ነው፣ ይሄንን አሻሽለን አመጋገባቸው ስርዓትን በጠበቀ፣ ወቅቱን በጠበቀ በእለት ፕሮግራም ውስጥ አካተን ብንመግባቸው በሽታን ሊከላከሉ የሚችሉበትን ክትባትም ሆነ መድሃኒት ብንሰጣቸው ሌላ ምን ይፈልጋሉ?፣ ይህንን የማሻሻል ነገር የፈረሶቻችንን አቅም ሊገነባው ይችላል።አዲስ ዘመን፡-ኢትዮጵያ ያጣችው ፈረሱን ነው ወይስ ጋላቢውን የቱ ጋር ነው ችግሩ?አቶ ዘሪሁን፡- እኔ የሚመስለኝ ችግሩ ያለው ስፖርቱን የሚመሩ አካላት ጋር ነው እንጂ ፈረሱም ጋላቢውም አለ፣ የተፈጥሮ ሀብት አለን፣ ስለዚህ ስፖርቱን እንምራ ካልን ሁሉም ባለ ድርሻ አካል ለዚህ ስፖርት ትኩረት መስጠት አለበት፣ እኛ የምንመራው የዘመናዊ ስፖርት አለ፣ የባህሉን ዘርፍ ደግሞ የሚመራው የኢትዮጵያ ባህል ስፖርት ፌዴሬሽን ነው፣ ሁለቱ ተቀናጅተው መስራት አለባቸው፣ ስራው የጎደለው እዚህ ጋር ይመስለኛል፣ በኛ በኩል ጅምሩ አለ፣ ከባህል ስፖርት ጋር አንድ ላይ በመሆን ብንሰራ ውጤት ልናመጣ እንችላለን፣ እዚህ ላይ መንግሥትም ሊያግዝ ይገባል፣ ይህን ስፖርት እናዳብር፣ እናሻሽልና ወደ ዓለም አቀፍ ደረጃ እንውሰደው ካልን ትልቁ ጥያቄ የሚመጣው የመሬት ጉዳይ ላይ ነው፣ ለምሳሌ አንድ ባለሀብት የፈረስ ስፖርት ክለብ ማቋቋም እፈልጋለሁ፣ የራሴ ፈረሶች እንዲኖሩኝ እፈልጋለሁ ይሄንን ላደርግ የምችለው ግን መሬት ሲኖረኝ ነው፣ መሬት ካገኘሁ የፈረሶች መኖሪያ ጋጣ እገነባለሁ፣ የፈረስ ስፖርት ማዘውተሪያ እገነባለሁ ሲል ጥያቄው ወደ መንግሥት ይሄዳል፣ ስለዚህ የመንግሥት እገዛ ያስፈልጋል ማለት ነው።አዲስ ዘመን፡-መንግሥት በእንደዚህ አይነት ጉዳዮች መሬት ሲሰጥ ለተለየ አላማ የሚውልበት አጋጣሚ አለ፣ መሬት አዲስ አበባ ላይ ውድ ከመሆኑ አኳያ ባለሀብቶች ከአዲስ አበባ ወጥተው ሌሎች ክልሎች ላይ እንዲሰሩ ማድረግ አይሻልም። አሶሴሽኑም ውድድሮችን ከአዲስ አበባ ወጥቶ ክልሎች ላይ በማድረግ የማስተዋወቅ ስራ ለምን አይሰራም?አቶ ዘሪሁን፡- ቅድም እንደገለፅኩት አሶሴሽኑ ከተለያዩ ክለቦች ጋር ነው ውድድሮችን የሚያካሂደው፣ ውድድሮችም ጃን ሜዳ ብቻ አይደለም የሚካሄዱት፣ ለምሳሌ ከመከላከያ ጋር ውድድር ስናዘጋጅ ሆለታ ላይ ነው የሚካሄደው፣ ቤካ ፈርዳ ክለብ ውድድር ሲያዘጋጅ ሱሉልታ ነው የሚያካሂደው፣ ባልደራስ የሚያዘጋጀው ውድድርም ወደ ሲኤም ሲ ሃያት አካባቢ ነው የሚካሄደው፣ በቅርቡ አምቦ ላይ ስልጠና ከሰጠን በኋላ የኤግዚቢሽን ውድድር እዚያው እናደርጋለን፣ አዊ ዞን ላይም የማደራጀትና እንቅስቃሴውን እዚያ የመፍጠር ስራ እንሰራለን፣ እንዲህ እያደረግን ነው እያሰፋን የምንሄደው፣ አዲስ አበባ ላይ የመሬት ችግር እንዳለ እናውቃለን ይሰጠን ብንልስ ከየት ይመጣል፣ ወጣ ስንል ወደ ክልል የተሻለ እድል እንዳለ እንገነዘባለን፣ የክልል መስተዳደሮችም ያግዙናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን፣ እቅዳችንም ሰፊ ነው። አሁን ግን ገና ጅምር ላይ ነን።አዲስ ዘመን፡-የፈረስ ስፖርት በዓለም ላይ ሀብታም ከሚባሉ የስፖርት አይነቶች አንዱ ነው፣ የእኛ አገር ሀብታሞች ይህን ስፖርት ደፍረው ለመግባት ለምን ተቸገሩ፣ እናንተስ ደፍረው እንዲገቡ ምን አደረጋችሁ?አቶ ዘሪሁን፡- መልሼ የማነሳው ነገር አበረታች ጅምሮች እንዳሉ ነው፣ ለምሳሌ የቤካ ፈርዳ ክለብ የአንድ ግለሰብ ነው፣ ግለሰቡ የፈረስ ፍቅር ስላለው ነው ክለቡን የመሰረተው፣ ሲያቋቁም ግን መጀመሪያ የት ነበር አሁን ምን ላይ ደርሷል የሚለውን ማየት ያስፈልጋል፣ መጀመሪያ አንድ ሁለት ፈረሶች ገዛና ጃን ሜዳ ላይ ነበር የሚገለገለው። ከዚያ በኋላ በኦሮሚያ ክልል ከሱሉልታ ከተማ አስተዳደር ጋር ተነጋገሩና መሬት ተሰጠው፣ በአሁኑ ጊዜም ወደ ሃያ የሚጠጉ ፈረሶችን ይዞ የራሱን ማዕከል ገንብቶ የፈረስ ስፖርትን ብቻ ሳይሆን ጎን ለጎን ሌሎችንም የመዝናኛ ፕሮግራሞች እያከናወነ ይገኛል። የፈረስ ስፖርት ቀላል አይደለም። ከፈረስ ግዢ ጀምሮ እንክብካቤው ራሱ ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ ነው፣ የፈረሱን ምግብ ማዘጋጀት አለብህ፣ ህክምናና እንክብካቤ ማደረግ አለብህ፣ አሰልጣኝ ቀጥረህ፣ ተንከባካቢ ቀጥረህ፣ ጋጣ ሰርተህ ሌሎች ጉዳዮችንም አሟልተህ መሄድ አለብህ። ገንዘብ ስላለው ብቻ ሳይሆን አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች ከተሟሉ ነው አንድ ባለሀብት ወደ ስፖርቱ እንዲመጣ የሚበረታታው፣ ጃን ሜዳ ላይ አሁን አርባ ሦስት ፈረሶች አሉ፣ እነዚህ ፈረሶች ሁሉም የግለሰብ ናቸው፣ አንዳንዱ አምስት አንዳንዱ ደግሞ ሦስት አለው፣ አስራ ስድስት ባለሀብቶች ናቸው እነዚህን ፈረሶች ገዝተው ጃን ሜዳ ውስጥ እያኖሩ እየተንከባከቡ የሚገኙት፣ በውድድር እየተሳተፉም ያሉት። ይሄ ቀላል ስራ አይደለም፣ ግን የበለጠ መበረታታት አለበት። ስናበረታታ ግን በምን መልኩ ነው የሚለውን ማየት ያስፈልጋል፣ የስፖርቱ ፍቅር ያላቸው ነገር ግን ፈረስ የሌላቸው ወጣቶችና አዋቂዎች ብዙ ናቸው፣ እኛ ጋር ግን የአቅም ውስንነት አለ፣ የራሳችን የሆኑ ፈረሶች የሉንም፣ የግለሰቦችን ፈረስ ደግሞ እንደፈለጋችሁ ተጠቀሙ ማለት አንችልም፣ ነገር ግን ማቀናጀት ይቻላል። ለምሳሌ አሁን በቅርብ እንጀምራለን ብለን ያሰብነው ስልጠናዎችን በየፈረስ ስፖርት ክለቦች እንዲሰጡ ማድረግ፣ ይህን ለማድረግ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የስልጠና በጀት ሰጥቶናል፣ እቅዱና ተጠቀሙበት አንድ ነገር አሳዩን ብለዋል፣ ስልጠናውን እንስጥ ስንል በየክለቡ የተለያዩ ቦታዎች ላይ ነው፣ ይህም ወጣቶችን ወደ ስፖርቱ እንዲሳቡና ተሳታፊውም እንዲጨምር ያደርጋል ማለት ነው። አዲስ ዘመን፡- ለሰጡን ጊዜ እናመሰግናለን።አቶ ዘሪሁን፡- እኔም አመሰግናለሁ።አዲስ ዘመን ቅዳሜ ሚያዝያ 26/2011በቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=10178
1,704
2ስፖርት
የሊጉ መርሐግብር በክለቦች ብርቱ ፉክክር ቀጥሏል
ስፖርት
May 7, 2019
29
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2011 ዓ.ም ዋንጫ እስከአሁን የትኛው ቡድን ሻምፒየን እንደሚሆን ፍንጭ አልሰጠም የ23ኛ ሳምንት መርሐ ግብር በሳምንቱ የዕረፍት ቀናትና በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች ሲካሄድም ክለቦች ብርቱ ትንቅንቅ አሳይተዋል። የሳምንቱ ተጠባቂ ፍልሚያ በአዲስ አበባ ስታዲየም ቅዱስ ጊዮርጊስን ከኢትዮጵያ ቡና አፋልሟል። ፈረሰኞቹ ከቡናው ጨዋታ ቀድመው ያከናወኗቸው ሁለት ጨዋታዎች ከሃዋሳ ጋር ነጥብ ተጋርተው መሪው መቀሌ ሰባ አንድርታን አንድ ለባዶ መርታት ችለዋል። ውጤቱን ተክተሎም ደረጃቸውን ወደ ሦስተኝነት ማስቀመጥና ከሊጉ መሪ ጋር የነበራቸውን የነጥብ ልዩነትም ወደ ስምንት ዝቅ ማድረግ መቻላቸው ይታወሳል። በሊጉ ወጥ የሆነ አቋም ማሳየት ያልሆነለት የ2003ቱ የሊጉ ሻምፒዮን ኢትዮጵያ ቡና በአንፃሩ ፤በሃያኛው ሳምንት በወላይታ ድቻ ከደረሰባቸው የሁለት ለባዶ ሽንፈት በኋላ በቀጣዩ መርሐ ግብር አዲስ አበባ ላይ ባህር ዳር ከተማን አስተናግዶ አምስት ግቦችን ማስቆጠሩ ይታወሳል። ቡናማዎቹ በማራኪ ጨዋታ የጣና ሞገዶቹን የተከላካይ መስመር ያፍረከረኩበት አቋም በቀጣይ ከአዳማ ከተማ ጋር የነበራቸውን ግንኙነት በመድገም የደጋፊዋቻቸውን ደስታ ያስቀጥላሉ ተብለው ቢጠበቁም፤ ይህ ሳይሆን ቀርቶ አንድ ለባዶ መሸነፋቸው ይታወሳል። በ23ኛው ሳምንት መርሐ ግብር የተካሄደው የሁለቱ ክለቦች ፍልሚያ በተለይ ከመሪዎቹ ተርታ ላለመራቅ የሚያደርጉት እንደመሆኑ በርካቶች በጉጉት እንዲጠብቁት አስግደዷል።ይሁንና በአስደማሚ የደጋፊ ድባብ የታጀበው ጨዋታ ያለምንም ግብ ተጠናቋል። ከሽሬ ጨዋታ ጀምሮ ምንም ግብ ያልተቆጠረባቸው ፈረሰኞቹ፤በዚህ ጨዋታም የግብ ክልላቸውን ሳያስደፍሩ መውጣት የቻሉ ቢሆንም ከመሪው ጋር ያላቸውን የነጥብ ልዩነት ግን በነበረበት ማስቀጠል አልሆነላቸውም። ይልቅስ ልዩነቱ ወደ አስር ከፍ ብሎባቸዋል። በመርሐ ግብሩ የተካሄደው የሁለቱ ክለቦች ፍልሚያ በአዲስ አበባ ስታዲየም ደጋፊዎችም ውብና ማራኪ ሆኖ አጊጦና ደምቆ ታይቷል። የሁለቱ ክለብ ደጋፊዎችም እንደ ሁል ጊዜውም የካንቦሎጆው እውነተኛ መልክና ውበት የድምቀቱ ምስጢር መሆናቸውን አሳይተዋል። መቀለ ሰባ እንደርታን ከስሁል ሽረ ያገናኘው የትግራይ ደርቢም ሌላኛው የዚህ ሳምንት ተጠባቂ መርሐ ግብር ነበር። ስሁል ሽረን ከወራጅ ቀጠና ያወጣል ወይስ መቀሌ ሰባ እንደርታ ወደ ዋንጫው የሚያደርገውን ጉዞ ያስቀጥላል በሚል የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በበርካታ እግር ኳስ አፍቃሪያን ዘንድ በጉጉት ተጠብቋል። በጨዋታው መቀሌዎች ለዋንጫው ከሚያደርጉት ትንቅንቅ የበለጠ ሽሬዎች ከወራጅ ቀጠና ለመውጣት የበለጠ መፋለማቸው ተስትውሏል። ከጣና ሞገዶቹ ሽንፈት በኋላ አዳማ ከተማን 2 ለ 1 በመርታት ወደ አሸናፊነት የተመለሱት መቀሌዎች፤ በ22ኛ ሳምንት የሊጉ መርሐ ግብር በፈረሰኞቹ የአንድ ለባዶ ሽንፈት እንደደረሰባቸው ይታወሳል። በ20ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አዳማ አበበ ቢቂላ ስታድየም ላይ አዳማ ከተማ 2ለ1 በማሸነፍ በቀጣዩ መርሐ ግብር ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የተለያዩት ስሁል ሽረዎች በአንፃሩ፤ በ22ኛ ሳምንት መርሐ ግብርም ሃዋሳ ከተማን ሳይጠበቅ አራት ለባዶ ማሸነፋቸውም ይታወሳል። በተለይ በሊጉ ሰንጠረዥ ወራጅ ቀጠና ከግርጌው ደደቢት ከፍ ብለው የተቀመጡትን ደረጃቸው በማሻሻል በሊጉ ለመቆየት ጨዋታውን ማሸነፍ ግድ ይላቸው ነበር። በሊጉ የሻምፒዮናነት ትንቅንቅ ላይ ወሳኝ ውጤትን በሚሰጠው በሁለቱ ክለቦች መካከል የተካሄደውን ጨዋታ ታዲያ፤በመቀለ ሰባ እንደርታ ሦስት ለአንድ አሸናፊነት ተጠናቋል። ውጤቱን ተከትሎ መቀሌዎች፤ ከተከታያቸው ፋሲል ከነማ ጋር የነበራቸውን የአምስት ነጥብ ልዩነት ማስጠበቅ ችልዋል። ይህም የሊጉን ዋንጫ ወደ ትግራይ ለመውስድ የሚያደርጉትን ሩጫ እንዲያፋጥኑ አግዟቸዋል። ተሸናፊዎቹ ስሁሎችን በአንፃሩ በሊጉ የደረጃ ግርጌ መዳከራቸውን ለመቀጠል ተገደዋል። ደደቢት እና ፋሲል ያደረገት ጨዋታም ተጠባቂ ነበር። በሃያኛው ሳምንት የሊጉ መርሐ ግብር በዐፄ ፋሲለደስ ስታዲየም ከደቡብ ፖሊስ ጋር የተፋለሙትና ጨዋታውን አንድ አቻ በማጠናቀቅ የሊጉን መሪ በቅርብ ርቀት የመከታላቸውን ሩጫ ያቀዘቀዙት ፋሲሎች፤ በቀጣዩ መርሐ ግብር፤አዲስ አበባ ላይ መከላከያን አራት ለባዶ በመርታት ወደ አሸናፊነታቸው መመለሳቸው ይታወሳል። በ22ተኛው መርሐ ግብርም በዐፄ ፋሲለደስ ስታዲየም ድሬዳዋ ከተማን አስተናግደው 2 ለ0 በማሸነፍ ከመሪው ጋር የነበራቸውን የነጥብ ልዩነት ወደ አምስት ማጥበብ ችለዋል። ደደቢቶች በአንፃሩ በዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች እጅጉን እስከፊ የሚባል አቋምና ተደጋጋሚ የሽንፈት ውጤት ቢያስመዘግቡም በሁለተኛው ዙር ተሽለው ጨዋታዎችን አሸንፈው ታይተዋል። ያለፉት ሁለት ጨዋታዎች በድሬዳዋዎች ሦስት ለሁለት፤በጅማ አባጅፋር አንድ ለባዶ መሸነፋቸው ይታወሳል። ደደቢቶች ቀጣዩን ዓመት በሊጉ ለመቆየት እያንዳንዱን ፍልሚያ እንደ ዋንጫ ጨዋታ መመልከት ግድ ይላቸው ነበር። የዚህ ሳምንት የሊጉ መርሐግብር እነዚህን ሁለት ክለቦች ሲያገናኝም፤በሊጉ የሻምፒዮና ጉዞ ላይ የሞት ሸረት ትግል እያደረጉ የሚገኙት አፄዎቹ ባለድል ሆነውበታል። ጨዋታውን አምስት ለአንድ ማሸነፍ የቻሉት ፋሲለደሶች ውጤቱ ለአንድ ቀንም ቢሆን ከመሪው ጋር የነበራቸውን ልዩነት ወደ ሁለት ነጥብ ዝቅ እንዲል ማድረግም አስችሏቸዋል። ይሁንና በቀጣዩ ቀን መሪው በመቐለ ሰባ እንደርታ ስሁል ሸረን ማሸነፉን ተከትሎ በአፄዎቹና በመሪው መካከል የነበረው የአምስት ነጥብ ልዩነት ባለበት እንዲቀጥል ሆኗል። በ23ኛ ሳምንት ትላንት የተካሄደው መርሐ ግብርም ወልዋሎን ከጅማ አባጅፋር አገናኝቷል። ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች በአዲሱ አስልጣኝ እየተመሩ በሊጉ ሁለተኛ ዙር ድንቅ አቋም ውጤት በማሳያት ላይ የሚገኙ ሲሆን በሃያኛው ሳምንትም አዲስ አበባ ላይ መከላከያን በሜዳውና በደጋፊው ፊት አንድ ለባዶ ማሸነፍ ቢችሉም በቀጣዩ መርሐ ግብር በድሬዳዋ ሁለት ለአንድ መሸነፋቸው ይታወሳል።ይሁንና በቀጣዩ መርሐ ግብር ደደቢትን በመግጠም በሁለት ለባዶ ድል ወደ አሸናፊነት መመለሱም ይታወሳል። የዓምናው የሊጉ ሻምፒዮን ጅማ አባጅፋሮች በሃያኛው የሊጉ መርሐ ግብር ላለመውረድ የሚታገለው ሽሬ እንደስላሴን አስተናግዶ በሜዳውና በደጋፊው ፊት ሁለት ለባዶ እንዲሁም በ21ኛ ሳምንት ደደቢትን እንዲሁም በሃያ ሁለተኛ ሳምንት ሃዋሳን በማሸነፍ ወደ ሻምፒዮናው ፉክክር መጠጋታቸው ይታወሳል። በሜዳቸው በዚህ ሳምንት ወልዋሎን ያስተናገዱት ጅማዎች ጨዋታውን 1 አቻ አጠናቅቀዋል፡፡ ውጤቱም በሊጉ የዋንጫው ትንቅንቅ ላለመራቅ የሚያደርጉትን ጉዞ አቀዝቅዞባቸዋል፡፡ 4ኛ የሚሆኑበትን ዕድል ሳይጠቀሙበት ቀርተዋል፡፡ ወልዋሎዎች በአንፃሩ ውጤታማነታቸውን በማስቀጠል ነጥባቸውን ከፍ ማድረግ ችለዋል፡፡ ሃዋሳ ከተማ ከሲዳማ ያገናኘውም ሌላኛው የዚህ ሳምንት መርሐ ግብር ነው። በዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር አስደናቂ ብቃትና ውጤት በማስምዝገብ የሊጉ መሪ እስከመሆን በቅተው የነበሩት ሲዳማ ቡናዎች በሁለተኛ ዙር ላይ መዳካም በማሳየት ወሳኝ ነጥቦችን አጥተዋል። በተለይ ለቻምፒዮንነት እየተፎካከረ የሚገኘው ሲዳማ በሃያኛ ሳምንት በቅዱስ ጊዮርጊስ የደረሰበትን ሁለት ለባዶ ሽነፈት መቀሌዎችን በቅርብ ርቀት የሚከተልበትን ዕድል አምክኖበታል።ይሁንና በ21ኛ ሳምንት ላለመውረድ እየታገለ ያለው ስሑል ሽረን 3 ለ 2 በማሸነፋቸው ወደ ሊጉ ፉክክር መመለሳቸው ይታወሳል። በቀጣዩ ጨዋታ የሊጉን ሻምፒዮናነት ጉዞ አሳልፈው ላለመስጠት፤ ብርቱ ጥረት ቢያድርጉም በአምናው የሊጉ ሻምፒዮን ሽንፈት ደርሶባቸዋል። ይሁንና በዚህ ሳምንት መርሐ ግብር ሃዋሳን ያስተናገዱት ሲዳማዎች ድል ከእነርሱ ጋር ሆናለች። ጨዋታውንም አንድ ለባዶ ማሸነፍ የቻሉ ሲሆን፤ይህም ነጥባቸውን 40 በማድረስ ደረጃቸውንም ወደ ሦስተኛ ከፍ እንዲያደርጉ አስችሏቸዋል። ሌላኛው መርሐ ግብር ደቡብ ፖሊስን ከአዳማ አገናኝቷል። አዳማዎች ከመቐለ ሰባ እንደርታ ከደረሰባቸው የ2 ለ1 ሽንፈት በኋላ፤ በ22ተኛ ሳምንት የሊጉ መርሐ ግብር በሜዳቸው ባህር ዳር ላይ አምስት ግቦችን ያዘነበውን ኢትዮጵያ ቡናን በማስተናገድ አንድ ለባዶ ማሸነፋቸው ይታወሳል። ከሃያኛው ሳምንት ከአፄዎቹ ጋር ነጥብ መጋራት የጀመሩት ደቡብ ፖሊሲች በቀጣዩ መርሐ ግብር ከዲቻ እንዲሁም ባሳልፈነው ሳምንት ከባህር ዳር ጋር ነጥብ ተጋርተው መመለሳቸው ይታወሳል። የደቡብ ፖሊሲችን የመከላከያ መሸነፍ ከወራጅ ቀጠና ስጋት ቢያላቅቃቸውም የጦሩ ዳግም ማሸነፍ ግን ከአደጋ ቀጠናው ሙሉ በሙሉ እንዳይርቁ አድርጓቸው ታይቷል። ይሁንና ባሳልፈነው ቅዳሜ አዳማን በሜዳና በደጋፊያቸው ፊት ሁለት ለባዶ ማሸነፍ ችለዋል። ውጤቱም ከሊጉ ግርጌ ለመውጣት የሚያደርጉትን ጥረት የማሳመር አቅሙ ግዙፍ መሆኑ ታምኖበታል። በሊጉ የዋንጫ ፍልሚያ ወጥ የሆነ አቋም ማሳየት ከሚሳናቸው ቡድኖች አንዱ መሆኑ የሚነገርለት ተሸናፊው አዳማ ከተማ በበኩሉ፤ የአቋም ለውጥ እንደሚያስፈልገው እያስመሰከረ ይገኛል። መርሐ ግብሩ መከላከያን ከባህርዳር አገናኝቷል። የጣና ሞገዶቹ፤በኢትዮጰያ ቡና የ5 ለ 0 አስዳንጋጭ ሽንፈት በኋላ በሜዳና በደጋፊያቸው ፊት ደቡብ ፖሊስን አስተናግደው ሦስት አቻ መለያየታቸው ይታወሳል። በጨዋታ 2 ለ0 ሲመሩ የነበሩት የጣና ሞገዶቹና በስምንት ደቂቃ ልዩነት ሦስት ግቦች እንደተቆጠረባቸው ይታወሳል። በሁለተኛው የሊጉ ምዕራፍ ወጥ አቋም ማሳየት ተስኖት አሰልጣኙን እስከ ማሰናበት የደረሰው መከላከያ፤ በሃያኛው ሳምንት ወደ መቐለ ተጉዞ በወልዋሎ እንዲሁም በ21ኛው ሳምንት በፋሲል በሜዳውና በደጋፊው ፊት አራት ለባዶ መሸነፉ ይታወሳል። ክለቡ ወቅታዊ አቋሙ እያደር መዋዠቁና በውጤት ቀውስ ላይ መሆኑን ተከትሎም የመውረድ አደጋ ተጋረጠቦታል፡፡ በሚቀጠለው ዓመት ወደ ብሄራዊ ሊግ ከመውረዱ አስቀድሞ አቋሙን በጊዜ በማስተካከል ወደ አሸናፊነት መመለስ የግድ እንደሚለው ሲወተወት የቆየው መከላከያ ጨዋታውን አንድ ለባዶ ማሸነፍ ችሏል። ክለቡ ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ያሳየው አቋም ምናልባትም ስጋቶቹን ሁሉ ከንቱ የማድረግ አቅማቸው ከፍተኛ መሆኑም ታምኖበታል። የጨዋታው ተሸናፊ የጣና ሞገደች በአንፃሩ፤ ከሽንፈታቸው አገግመው ወደ አሸናፊነታቸው የሚመልሳቸውን ውጤት ማስመዝገብ ተስኖቸዋል። ክለቡ በተለይ ያለፉት ሦስትና አራት ጨዋታዎች ያስመዘገበውን ውጤት ትከተሎም በሊጉ የሻምፒዮንነት ትንቅንቅ ከመሪዎች ተርታ እየራቀ እንዲሄድ አስገድዶታል። ሌላኛው የዚህ ሳምንት መርሐ ግብር ድሬዳዋ ከወላይታ ያገናኘው ነው። በሃያኛው መርሐ ግብር ደደቢትን ሦስት ለሁለት በማሸነፍ በቀጣዩ መርሐ ግብር ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 2 ለ 1 በመርታት ተከታታይ ድል ማስመዝገብ የቻሉት ድሬዳዋዎች፤ ውጤቱን ተከትሎ ካንዣበበባቸው ወራጅ ቀጠና በፍጥነት መራቅ ችለዋል። ይሁንና በ22ተኛው ሳምንት በአፄዎቹ የሁለት ለባዶ ሽንፈት ደርሶባቸዋል። ዲቻዎች በአንፃሩ ኢትዮጵያ ቡናን አስተናግደው በፀጋዬ አበራ ሁለት የጭንቅላት ኳሶች ባለድል በመሆን ከሊጉ የወራጅ ቀጠና በመፋታት ነጥባቸውንም ከፍ ማድረግ የቻሉ ሲሆን፤ በቀጣዩ ጨዋታ ከመከላከያ ጋር ተፋልመው በሜዳና በደጋፊያቸው ፊት የሦስት ለሁለት ሽንፈት ደርሶባቸዋል። በዚህ ሳምንት ምርሐ ግብር የሁለቱ ከለቦች ጨዋታ ድሬዳዋ ላይ ሲከናወንም ጨዋታው በብርቱካናማዎቹ ሁለት ለአንድ አሸናፊነት ተጠናቋል። የአሸናፊነት ጉዟቸውን በማስቀጠልና ሠላሳ አንድ ንጥቦችን በመሰብሰብ ደረጃቸውን ወደ ሊጉ ሰንጠረዥ አጋማሽ ማስቀመጥ አስችሏቸዋል። ተሸናፊው ወላይታ በአንፃሩ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ በ24 ነጥብ፤ወደ ወራጅ ቀጠናው የሚያንድርድረውን ውጤት እያስመዘገበ ይገኛል። በዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የደረጃ ሰንጠረዥ መቀሌ ሰባ እንደርታ አርባ ስምንት ነጥቦች በመሰብሰብ በቀዳሚነት ይመራል። ፋሲል ከነማ በአርባ ሦስት ነጥብ በሁለተኛነት ሲከተል፤ሲዳማ ቡና በአርባ ነጥብ ሦስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። የሊጉን ወራጅ ቀጠና ስንመለከት፤ ደቡብ ፖሊስ በሃያ ሦስት ነጥቦች አስራ አራተኛ፤ ስሁል ሸሬ በአስራ ዘጠኝ ነጥቦች አስራ አምስተኛ እንዲሁም ደደቢት በአስር ነጥብ የመጨረሻውን ደረጃ ይዘዋል። የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን ፉክክር የመቀሌው አማኑኤል ገብረሚካኤል በአስራ አራት ግቦች፤ የሲዳማ ቡናው አዲስ ግደይ በአስራ ሦስት እንዲሁም የመከላከያው ምን ይሉህ ወንድሙ በአስራ አንድ ግቦች ከአንድ እስከ ሦስት ያለውን ደረጃ ይዘዋል።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 29/2011
https://www.press.et/Ama/?p=10361
1,296
2ስፖርት
ህዝቡ የኦሊምፒክ ቤተሰብና ደጋፊ እንዲሆን ተጠየቀ
ስፖርት
May 7, 2019
15
በዓለም አቀፍ ደረጃ ዘመናዊ ኦሊምፒክ ጨዋታ የተመሰረተበትን ቀን ለማሰብ በየዓመቱ የኦሊምፒክ ሳምንት በወርሃ ሰኔ ይከበራል። በዓሉም በኢትዮጵያ በሁሉም ክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች በተለያዩ ስፖርታዊ ኩነቶች ይከበራል፡፡ የ2011 ዓ.ም የኦሊምፒክ ሳምንትም «ኦሊምፒዝም ለሰው ልጆች ክብር፣ ለሰላምና አንድነት” በሚል መሪ ቃል በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አስተናጋጅነት ከሰኔ 16 ቀን ጀምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚከበር ይሆናል። በተለያዩ ኩነቶች የሚከበረውን የኦሊምፒክ ሳምንትም በሀገሪቱ ኦሊምፒዝምን ከማስፋፋት፣ የኦሊምፒክ ሙቭመንት (Movement) ከማሳደግና ለሕዝቦች ሰላም፣ አንድነት፣ ፍቅር እና መተሳሰብን ከማጐልበት አንፃር ያለው ፋይዳ ከፍተኛ እንደሚሆንም ታምኖበታል።፡ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከበዓሉ ዝግጅት ጋር በተገናኘ፤ ህብረተሰቡ በኦሊምፒክ እንቅስቃሴ ተሳታፊ የሚሆንበትና እንደወትሮው በሃሳቡ፣ በገንዘቡና በዕውቀቱ የሚረዳበትን የኦሊምፒክ ስፖርትን በቀጥታ የሚደግፍበትን ስርዓት ለመፍጠር በድረ ገጹ / ዌብ ሳይት/ ላይ አዲስ ሊንክ ከፍቷል። ህብረተሰቡም በዚህ ሊንክ በመጠቀም የኦሊምፒክ ቤተሰብ አባልና ደጋፊ ለመሆን በድረ ገጹ www.ethiopianolym­pic.org በመግባት Register የሚለውን ሊንክ በመጫን ወይም ቀጥታ http://on­lineregister.ethiopianolympic. org/ መመዝገብ እንደሚችል ታውቋል። ለአባልነቱም በዓመት 100.00/አንድ መቶ/ ብር እንደሚካፍል ለማወቅ ተችሏል። ህብረተሰቡ ከላይ የተገለጹትን የመመዝገቢያ አድራሻዎች በመጠቀም አባል ለመሆን ምዝገባውን ማካሄድ እንደሚችል የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በድረ ገፁ አስታውቋል።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 29/2011
https://www.press.et/Ama/?p=10366
164
2ስፖርት
ለመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ቡድኖቹ ዝግጅት እያደረጉ ነው
ስፖርት
August 12, 2019
26
በሞሮኮ ራባት የሚካሄደው 12ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ሊጀመር የአንድ ሳምንት ዕድሜ ብቻ ይቀረዋል። በዚህ ውድድር ላይ ኢትዮጵያ በ13 የስፖርት ዓይነቶች የምትሳተፍ ሲሆን፤ ብሄራዊ ቡድኖቹም ዝግጅታቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል። ጠንካራ ዝግጅት በማድረግ ላይ ከሚገኙት መካከልም የሜዳ ቴኒስ እና ጂምናስቲክስ ይጠቀሳሉ። በሜዳ ቴኒስ ስፖርት ኢትዮጵያ በሶስት ሴት እና አራት ወንድ ስፖርተኞች ትወከላለች። ቡድኑ ውጤታማ ለመሆን ከሚያደርገው ልምምድ በተጓዳኝ በስፖርቱ ባለሙያዎች ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ተሞክሮ እንዲያገኙ መደረጉንም የኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን በድረገጹ አስነብቧል። በምስራቅ አፍሪካ በተካሄዱ ውድድሮች ጥሩ ውጤት ያለው ቡድኑ፤ ውጤታማነቱን በመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ለመድገምም ዝግጅት እያደረጉ ይገኛሉ። ብሄራዊ ቡድኑን የሚመሩት አሰልጣኝ ህሩይ አምሳሉም ለቡድኑ አባላት እየተደረገላቸው ያለው ድጋፍ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል። የኢትዮጵያ ቴኒስ ፌዴሬሽ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ይልማ ከፈለኝ፤ በዚህ ስፖርት የሚወክሉ ስፖርተኞች ፍትሐዊ በሆነ መልኩ መመልመላቸውን እና ለስልጠናው የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን በማሟላት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ይገልጻሉ። ፌዴሬሽኑ የሚስተዋልበትን የውድድር ቁጥር ማነስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ክፍተቱን በመለየት፤ በሀገርና ዓለም አቀፍ ውድድሮች እንዲሁም ስልጠናዎች ላይ በስፋት ለመሳተፍ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራም ጠቁመዋል። የጂምናስቲክስ ብሄራዊ ቡድንም በውድድሩ ለመሳተፍ በቂ ዝግጅት ማድረጉን አስታውቋል። በአርቲስቲክ ጅምናስቲክስ የምትሳተፈው ኢትዮጵያ በአምስት ሴት እና አምስት ወንድ ስፖርተኞች ትወከላለች። ፍሎር ኤክሰርሳይስ፣ ቮልቲግ ቴብል እና ቢም ባላንስ ሴቶች የሚወዳደሩባቸው የውድድር ዓይነቶች ናቸው። ወንዶች በበኩላቸው በፓራራል ባር፣ ፍሎር ኤክሰርሳይስ እና ቮልቲግ ቴብል ይሳተፋሉ። የብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሠልጣኝ ቢንያም ዓለሙ ዝግጅቱን አስመልክተው፤ ቀደም ብለው እንደጀመሩ ጠቁመዋል። በዚህ ወቅትም በሳምንት ለስድት ቀናት ለሁለት ጊዜያት ልምምድ እያደረጉ መሆኑን ገልጸዋል። ሠልጣኞችም የሚሰጣቸውን ስልጠና የመቀበል አቅማቸው ከፍተኛ በመሆኑ በውድድሩ ብርቱ ፉክክር በማድረግ ውጤት ለማስመዝገብ በቂ ዝግጅት ማድረጋቸውን ጠቁመዋል። ከዚህ ባሻገር የልምምድ መሳሪያዎች ጊዜ ያለፈባቸውና ያረጁ በመሆናቸው በቀጣይ ዘመናዊ መሳሪያ ወደ ሀገር የሚገባበት ሁኔታ እንዲመቻች አሰልጣኙ ጠይቀዋል። የኢትዮጵያ ጅምናስቲክስ ፌዴሬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ስንታየሁ ፍቅረዮሐንስ በበኩላቸው፤ ለውድድሩ እየተደረገ ያለው ዝግጅት እና ከመንግስት እየተደረገ ያለው ድጋፍ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል። ጅምናስቲክስ ስፖርት የዘመናዊ ስፖርት መሠረት ቢሆንም ለስፖርቱ አገልግሎት የሚውሉ መሳሪያዎች በጣም ኋላቀር በመሆናቸው ተጠግነው አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ። መሳሪያዎቹን ገዝቶ ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባትም በፌዴሬሽኑ አቅም የሚቻል ባለመሆኑ ጥያቄው ለመንግስት ቀርቦ በጎ ምላሽ ማግኘቱን ኃላፊዋ ገልጸዋል። በሁለቱም ስፖርቶች ሃገራቸውን ለመወከል ዝግጅት በማድረግ ላይ የሚገኙት የብሄራዊ ቡድን አባላትም በሚካፈሉበት ውድድር የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እየተዘጋጁ መሆኑን ገልፀዋል።አዲስ ዘመን ነሃሴ 6/2011
https://www.press.et/Ama/?p=15951
329
2ስፖርት
አጼው የመጀመሪያውን የአፍሪካ መድረክ ተሳትፎውን በድል አወራረደ
ስፖርት
August 13, 2019
41
በ2011ዱ የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ዋንጫ ጨዋታ ሐዋሳ ከተማን በማሸነፍ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ መድረክን የተቀላቀለው ፋሲል ከነማ ውድድሩን በድል ጀመረ። በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ በሜዳው በባህር ዳር አለም አቀፍ ስታዲየም መቶ ሺ በሚገመት ደጋፊው ፊት የታንዛኒያውን አዛም እግር ካስ ክለብ ያስተናገደው ፋሲል፣ ጨዋታውን አንድ ለባዶ በሆነ ውጤት ነው ማሸነፍ የቻለው። በህብረ ቀለማት በደመቁ ደጋፊዎች፤ ከአራቱም ማዕዘን ጎልተው በሚሰሙ የድጋፍ ድምጾችና ማራኪ ጭፈራዎች በሚያስደንቅ መልኩ ታጅቦ በተካሄደው ጨዋታ የፋሲል ከነማን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ በመጀመሪያው 45 ደቂቃ ማጠናቀቂያ ላይ ያስቆጠረው በዛብህ መለዮ ነው። በዛብህ አጼዎቹን ከመቀላቀሉ ከአመት በፊት በወላይታ ዲቻ ቆይታው በተመሳሳይ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ መድረክ ላይ ክለቡ በሃዋሳ አለም አቀፍ ስታዲም የግብፁን ዛማሊክ 2ለ1 ሲያሸንፍ ግብ ማስቆጠሩ አይዘነጋም። ውጤቱን ተከትሎም ፋሲል ከነማ በሜዳው 3 ነጥብ በመያዝ በቀጣይ ከ 12 ዓመታት በፊት የተመሰረተው እና በ2018/19 የውድድር ዓመት 3ኛ ደረጃ ይዞ ካጠናቀቀው ከአዛም የእግር ኳስ ክለብ ጋር የመልስ ጨዋታ የሚደርግ ይሆናል። የሁለቱ ከለቦች የመልስ ጨዋታም ከ15 ቀናት በኋላ በታንዛኒያ ዳሬ ሰላም ከተማ እንደሚካሄድ ይጠበቃል። አጼው የመጀመሪያ የአፍሪካ መድረክ ተሳትፎውን በድል የጀመረበት ጨዋታም ከአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ጋር የተለያየበት ሆኗል። የመጨረሻ ጨዋታቸውን በድል በመወጣት ከክለቡ ጋር የተለያዩት አስልጣኝ ውበቱ፣ ከጨዋታው በኋላ በሰጡት አስተያየት፣ በውጤቱ መደሰታቸውን ተናግረዋል። ፍላጎታቸው ባይሆንን በግል ጉዳይ ከክለቡ ጋር በይፋ መለያየታቸውን ጠቅሰው፣በቀጣይ ከለቡን የሚረከብ አሰልጣኝ የክለቡን ውጤት እንዲያስቀጥል ጥሪ አቅርበዋል። በጨዋታው የኢትዮጵያ እግር ካስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጂራ፣የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጥኝ ኢንስተራክተር አብረሃም መብራቱ፣ የባህር ዳርና ጎንደር ከተማ ከንቲባዎችን ጨምሮ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎች ታድመውበታል። ከተማዋና ታላቁ ስታዲየም ዳግም የሐገር ኩራት መሆናቸውን አስመስክረውበታል። ይሁንና በመስተንግዶ ረገድ በዕለቱ በነበረው ያልተቀናጀ የቲኬት አቆራረጥ ችግር ከገባው ደጋፊ አንፃር የተገኘው ገቢ አነስተኛ መሆኑ እንደሚያስቆጭም ተጠቁሟል። በተመሳሳይ በአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎ ወደ ኢኳቶሪያል ጊኒ ያቀናው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮኑ መቐለ 70 እንደርታ በካኖ ስፖርት 2 ለ 1 በሆነ ጠባብ ውጤት ተሸንፏል። በአፍሪካ የውድድር መድረክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፉት መቐለ 70 እንደርታዎች እስከ 80ኛው ደቂቃ 2 ለ 0 ተመርተው ከቆዩ በኋላ አማኑኤል ገብረሚካኤል ወሳኟን 1 ግብ በጨዋታው ማጠናቀቂያ ላይ አስቆጥሯል። መቐለ 70 እንደርታዎች ከሜዳቸው ውጪ አንድ ግብ ማስቆራቸው ወደ ቀጣይ ዙር የማለፉ እድላቸው ከፍ ያደርገዋል። በዚህ መሰረት መቐለ 70 እንደርታዎች ከ15 ቀናት በኋላ በሜዳቸው የሚያደርጉትን ጨዋታ ግብ ሳይቆጠርባቸው 1 ለ 0 ማሸነፍ ከቻሉ ወደ ቀጣይ ዙር ማለፍ ይችላሉ።አዲስ ዘመን ነሀሴ 7/2011 ታምራት ተስፋዬ
https://www.press.et/Ama/?p=15997
345
2ስፖርት
የእምነት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች ጥቃት የደረሰባቸውን ሰዎች አጽናኑ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 5, 2020
10
 አጋርፋ:- የእምነት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣የሰላም ኮሚቴዎችና የማህበራት ህብረት በጋራ የአርቲስት ሐጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ ጥቃት ደርሶባቸው በማሰልጠኛና በእምነት ተቋማት ተጠልለው የሚገኙ ሰዎችን በተጠለሉበት ስፍራ በመገኘት አጽናኑ። የልኡካን ቡድኑ በሃረር፣ በሻሸመኔና ከአርሲ እስከ ባሌ የተንቀሳቀሰ ቡድን ሲሆን፤ ጥቃት የደረሰባቸው ሰዎች ያሉበትን ሁኔታ መመልከት፣ ማጽናናትና የተጠቃለለ ሪፖርት በመያዝ የክልል፣ የፌዴራል መንግስታትና የሚመለከታቸው አካላት አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ በማስተባበር መልሶ ለማቋቋም ጥረት የሚያደርግ ነው። የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማህበራት ህብረት ዋና ዳይሬክተርና ማህበረ ካህናትና ማህበረ ምእመናን የኮሚቴ አባል በመሆን ሰሞኑን እስከ ባሌ የተጓዘውን ቡድን የመሩት ንጉሱ ለገስ (ዶክተር) ጉዳት ከደረሰበት ህብረተሰብ ችግሩን ማዳመጡ መጠኑን ለመገንዘብ እንደሚረዳ፣ ለሚመለከታቸው ሁሉ ለማስረዳት እንደሚያስችልና አደጋው የደረሰው በእምነት ተለይቶ በመሆኑ ህብረተሰቡን ለማጽናናት ጭምር እንደሚጠቅም አክለዋል። ጥቃት አድራሾች ከክርስትና ውጭ ያሉ በሙሉ እንዳልሆኑና ጥቂቶች መሆናቸውን በማስገንዘብ አልፈውም ይቅርታ እንዲያደርጉላቸው ለማረጋጋትና ለማጽናናት መሆኑንም ነው ያከሉት። ችግሩ የጥቃት ሰለባዎቹ ብቻ ሳይሆን፤ የመንግስት፣ የህዝብ፣ የመላው ኢትዮጵያውያን መሆኑንና በጋራ ለመወጣት ጥረት እንደሚደረግ ጭምር ለማስገንዘብ መሆኑንም ነው ዶክተር ንጉሱ ያመለከቱት። የደቡብ ኦሞ ጂንካ ሐገረ ስብከትና የቅዱስ ስላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ የበላይ ሃላፊ ሊቀጳጳስ ብጹዕ አቡነ ፊሊጶስ፤ የተፈጸመው ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ሰው ሊፈጽመው የማይገባ የወንጀል ድርጊት መሆኑን አንስተዋል። ሞት፣ የንብረት መጥፋት፣ መፈናቀልና እንግልት መድረሱን መታዘባቸውን ጠቁመዋል። እንደ አገር ለመቀጠል፣ ህዝብ በሰላም ወጥቶ እንዲገባ መንግስት የጀመረውን ህግ የማስከበርና የወንጀል ተሳታፊዎችን ተጠያቂ የማድረጉ ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል። መንግስት ከታችኛው የመንግስት መዋቅር እስከ ላይ ድረስ የተዘረጋውን የተንኮል ስራ የሚሰሩ፣ ለሰዎች ሞት ምክንያት የሆኑና ህዝብ ያፈናቅሉ አካላትን ማጥራት አለበት ብለዋል። መንግስት ትክክለኛ ጥናት በማድረግ ንብረታቸው ለወደመባቸው የሚተካበት ስራ መሰራት አለበት ብለዋል። የጥፋት መልእክተኞች ዳግም ወደጥፋት እንዳይገቡ ጥብቅ ስነ ምግባር በተሞላበት መንገድ መሰራት አለበትም ብለዋል። ክስተቱ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መቆም እንዳለበት አሳስበዋል። ጉዳቱ የደረሰባቸው ሰዎች ዘንድ በመቅረብ ‹‹ጉዳታችሁ ጉዳታችን ነው፣ ቁስላችሁ ቁስላችን ነው፣ ችግራችሁ ችግራችን ነው›› በማለት እንዳጽናኗቸውም ጠቁመዋል። ቤተ ዕምነቶች ስለአብሮ መኖርና አንድነት ሊያስተምሩ እንደሚገባ የጠቆሙት የጉራጌ ሐገረ ስብከት ብጹዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ በበኩላቸው፤ ተከታዮቻቸው የፍቅርና የሰላም መልእክተኞች እንዲሆኑ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል። የሌላውን እምነት መንካት፣ ማንቋሸሽና የድፍረት ስራ መስራት የማይቻል በመሆኑም ቤተ እምነቶች ይህንን ትምህርት ለተከታዮቻቸው ማስተማር ይጠበቅባቸዋል ነው ያሉት። ሰላም ፍቅር፣ አንድነት፣የቀደመው ኢትዮጵያዊነት ጨዋነትና ስነ ምግባር እንዲቀጥል ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተስተዋለ ያለው ሃይማኖታዊ መልክ የተላበሰው ጥቃት እንዲቆምም መክረዋል። የአጋርፋ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ ሃላፊ አቶ ሽመልስ ቶሎሳ፤ ሰኔ 22 እና 23 ቀን በአካባቢው የደረሰው አደጋ ከባድና አሳዛኝ እንደነበረ ተናግረዋል። የተፈናቀሉትን ለማቋቋም፣ ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። በወንጀል ድርጊቱ ተሳታፊዎችን በቁጥጥር ስር የማዋል፣ በህግ እንዲጠየቁ ማድረግና የማረጋጋት ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል። በአካባቢው የሰባት ሰው ሕይወት መጥፋቱን፣ 59 ቤቶች ሙሉ ለሙሉ መቃጠላቸውን፣ የቀንድ ከብቶችም መዘረፋቸውንና 38 የመንግስት ተቋማት መውደማቸውንም ተናግረዋል። ዳግም ተመሳሳይ ጥቃት እንዳይከሰት የጸጥታ ሃይል የመመደብ ስራ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።የሃይማኖት መቻቻልና የህግ የበላይነት እንዲከበር በትኩረት ይተገበራል ብለዋል። በብሄርና በፖለቲካ ሽፋን የራሳቸውን የፖለቲካ ዓላማ ለማሳካት የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች ሴራ እንዲከሽፍ እንደሚሰራም ጠቁመዋል። በአካባቢው ብቻ የተፈጠረ ሳይሆን ከሌሎች አካባቢዎች ጋር ትስስር ያለው መሆኑንም ነው የጠቆሙት።አዲስ ዘመን ሐምሌ 29/2012 ዘላለም ግዛው
https://www.press.et/Ama/?p=36634
438
0ሀገር አቀፍ ዜና
ታሪካዊ እጆች
ስፖርት
August 19, 2019
22
በእግር ኳስ ታሪክ ውስጥ ግዙፍ ስፍራን ከያዙ አጋጣሚዎች መካከል ዛሬ አንዱን መርጠን ለመመልከት ወደናል። ታዲያ ይህ በብራና የተከተበ ዶሴ በአንድ እለት እና አጋጣሚ የተፈጠረ ሳይሆን እራሱን በአስደናቂ ሁኔታ እየደጋገመ የስፖርቱ አፍቃሪዎችን በትውስታና አቁማዳ ውስጥ እየደጋገመ ሲከት የቆየ ነው።ነገም ራሱን ስላለመድገሙ ምንም ማስተማመኛ አልተገኘለትም። ታዲያ በዚህ ምልሰት ውስጥ የምንመለከተው ታሪካዊ እጆች እግር ኳሱ ላይ ያሳረፉት የማይለቅ አሻራን ነው። ብራዚል ከ ቺኮዝላቫኪያ ጊዜው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ሰኔ 17 /1962 ነው። የዓለም ዋንጫ ፍፃሜ የሚደረግበት። ለፍልሚያው የደረሱት ደግሞ ብራዚል እና ቺኮዝላቪያ። ይህ ጨዋታ ብዙ የእግር ኳስ አፍቃሪዎች ዘንድ በድራማ እንደተጠናቀቀ ተዘንግቷል። የድራማው ዋና ተዋናይ ደግሞ ብራዚላዊው ጃሌማ ሳንቶስ ነው ∷በግማሽ ጎኑ ፖርቹጋላዊ የሆነው ሳንቶስ በዚህ ጨዋታ የማይረሳ አሻራ ጥሎ አልፏል። ሳንቶስ ታሪክ የማይዘነጋውን ድርጊት የከወነው በእግሩ ሳይሆን በእጆቹ ነበር። ጨዋታው እየተካሄደ ነው። ብራዚል ቺኮዝላቪያን 2ለ1 በሆነ ውጤት እየመራች ነበር። ቺኮዝላቪያ ደግሞ ዋንጫው እንዳያመልጣት ጠንክራ እያጠቃች ወደ ብራዚል የግብ ክልል በተደጋጋሚ ትደርሳለች። ጨዋታው ሊጠናቀቅ 20 ደቂቃዎች ሲቀሩት አስገራሚ ጉዳይ ተከሰተ። በብራዚል የግብ ክልል ላይ ቺኮዝላቪያዎች እያጠቁ ነው። ሆኖም ግን ወደ ግብ መቀየር የምትችል ኳስ ሳንቶስ ሆን ብሎ በእጁ አስቀራት። አስገራሚው ነገር ደግሞ ዳኛው ፍፁም ቅጣት ምት መስጠት ሲገባው በቸልታ አለፈው። ብራዚሎች ሲፈነጥዙ። ቺኮዝላቪያዎች ግን ክፉኛ አዘኑ። ብራዚል አንድ ተጨማሪ ጎል አስቆጥራ ጨዋታው 3ለ1 በሆነ ውጤት ተጠናቀቀ። አርጀንቲና ከፖላንድ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1978 የተካሄደውን የዓለም ዋንጫ አርጀንቲና እያስተናገደችው ነው። ቡድኗ ደግሞ በምድብ «ለ» ውስጥ ተደልድሏል። ጨዋታውን ከፖላንድ ጋር እያከናወነ ነበር። አርጀንቲናዊው ማሪዮ ኬምፔ በሁለተኛው አጋማሽ አገሩን መሪ የሚያደርግ ጎል አስቆጠረ። ጨዋታው ቀጥሏል። አርጀንቲና እየመራች ነው። ፖላንዶች እያጠቁ ነው። በክንፍ በኩል አንድ ኳስ ተሻገረ። ወደ ጎል እንደሚቀየር ምንም ጥርጥር አልነበረውም። ሆኖም ግን አገሩን መሪ ያደረገው አጥቂው ማሪዮ ልክ እንደግብ ጠባቂ ኳሷን በእጁ አጉኗት ግብ እንዳትሆን አደረጋት። ሁኔታው አስገራሚ ነበር። ዳኛው በዚህ ጊዜ የፍፁም ቅጣት ምት ሰጠ። ሆኖም ፖላንዶች ማሪዮ በእጁ ስላዳናት ግብ የምትሆን ኳስ ሲያስቡ ፍፁም ቅጣት ምቱን ሳቱት። አስገራሚው ደግሞ ኬምፔ በድጋሚ ለአገሩ ግብ አስቆጥሮ ሁለት ለዜሮ እንዲጠናቀቅ እና ከምድቧ እንድታልፍ አደረጋት። ኧረ እንዲያውም ዋንጫውንም ያነሳችው እርሷው ናት። አርጀንቲና ከ እንግሊዝ (የእግዜር እጅ) ያለ ምንም ጥርጥር በእጅ ተነክተው ወደ ግብነት ከተቆጠሩ ኳሶች ውስጥ ታዋቂዋ እና ዓለምን ያነጋገረች ነች። ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና በእንግሊዝ ላይ በምትሀት ያስቆጠራት ጎል። ዳኛው ተሸውዷል። ማራዶና አጭበርብሯል። ሁለተኛው አጋማሸ ላይ የእግር ኳስ ባላንጣዎቹ 0ለ0 በሆነ ውጤት ጨዋታቸውን እያከናወኑ ነበር። ኳስ በአየር ላይ ሆና ማራዶናን እና የእንግሊዙን በረኛ ፒተር ሺልተንን አፋጣለች። በዚያ ቅፅበት ቆቁ ማራዶና ቅልጥፍናውን ተጠቅሞ ኳሷን በውጪኛው እጆ ወደ መረቡ ሰደዳት። በተደጋጋሚ በምስል ካልታየ በስተቀር በእጅ የተቆጠረ አይመስልም ነበር። ዳኛው ተጭበረበረ። እሱም እንግሊዞችን በጠራራ ፀሀይ አንድ ጎል ሰረቃቸው። በዚህ ጨዋታ ላይ ማራዶና ይሄን ብቻ ግን አልነበረም የሰራው። ቢያንስ ከግማሽ በላይ የሚሆኑ የእንግሊዝ ተጫዋቾችን ከመሀል ሜዳ ጀምሮ በመረፍረፍ «የክፍለ ዘመኑ ምርጥ ጎል» ተብሎ የሚጠራውን ታሪከኛ ግብ አስቆጠረ። ማራዶና በሁሉም የሰውነቱ ክፍል ግብ እንደሚያስቆጥር አስመስክሮ እንግሊዝን እጅ ወደላይ አስባለ። ከማራዶና ታሪካዊ የእጅ ጎሎች አልወጣንም። ይሄ ሰው ተአምረኛ ነው። ከቻለ በእግሩ ካቃተው አጭበርብሮ በእጁ አገሩን ቀዳሚ ማድረግ ይፈልጋል። ጊዜው የ19 86 የዓለም ዋንጫ ነው። አቆጣጠሩ እንደ አውሮፓውያን። የቀድሞዋ ዩ ኤስ ኤስ አር የአሁና የዓለም ዋንጫ አዘጋጅ ሩሲያ ከማራዶና አገር ጋር ተፋጣለች። ጨዋታው ቀጥሏል። እስካሁን ባዶ ለባዶ በሆነ ውጤት ላይ ናቸው። ሩሲያ በማጥቃት ላይ ትገኛለቸ። የአርጀንቲና የግብ ክልል ላይ ደርሰዋል። ኳስ ወደ ግብ ክልል ተመታ። አንድ ተጫዋች ግን ግጥም አድርጎ በእጁ መለሳት። ግብ ጠባቂው አይደለም። ይህ ተጫዋች ማራዶና ነው። ዩ ኤስ ኤስ አር መሪ መሆን የምትችልበት አጋጣሚ በዚህ ከሸፈ። በተቃራኒው አርጀንቲና ሁለት ግቦችን አስቆጥራ ጨዋታው ተጠናቀቀ። ራሺያ ከምድቧም ገና በጠዋቱ ተሰናበተች። ይሄ ክስተት ቅስም ሰባሪ ነበር። የወቅቱን ጨዋታ የዳኘው ኢንስትራክተር ሲውዲናዊው ኤሪክ ፍሬድሪክሰን ነበር። የእውነትም ይህን ጨዋታ ሲያስቡ የእጅ ኳሷን ችላ ያላትን ሲውዲናዊውን ዳኛ ራሺያዎች ሲረግሙ ይኖራሉ። ፈረንሳይ ከ አየርላንድ ይሄ ጨዋታ አንድ ትዝታ ውስጥ ይከተናል። የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጥሎ ማለፍ ውድድር ነው። ጊዜው ደግሞ እአአ በ2009። ፈረንሳይ ከአየርላንድ 1ለ1 ናቸው። ውጤቱ እስከ ዘጠነኛው ደቂቃ ድረስ ምንም ልዩነት አላመጣም። ሁሉም ነገር ሚዛኑን ጠብቆ እየተጓዘ ነው። አራተኛ ዳኛው ተጨማሪ ሰዓት አሳየ። ሆኖም በባከነ ሰዓት በቅጣት ምት ከዊሊያም ጋላስ የተሻገረለትን ኳስ የአርሰናሉ ንጉስ ቴሪ ዳንኤል ሆነሪ በእጁ ወደ ግብ ቀየራት። አየርላንድ 2ለ1 በሆነ እጅግ አሳዛኝ ውጤት ተሸንፋ ወጣች። ይሄ ጨዋታ እንዲደገም ለፊፋ በተደጋጋሚ ክስ ቢቀርብም ጥያቄው ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል። ጋና ከ ኡራጋይ ጊዜው እ.አ.አ 2010 ነው። ኡራጋይ ከጋና አራት ውስጥ ለመግባት የሚያደርጉት ፍልሚያ ነበር። ሁለቱ ቡድኖች አንላቀቅም ብለው በባከነው ሰአት እንዲሁም በተጨማሪው 30 ደቂቃ ድረስ ያለምንም ግብ በአቻ ውጤት ቆይተዋል። ሆኖም ባለቀ ሰዓት ኦሳማ ጊያን ወደ ኡራጋይ የግብ ክልል የላካት ኳስ መስመሩን አለፈች ተብሎ አፍሪካውያን ለፈንጠዝያ ሲዘጋጁ ያልታሰቡት የአጥቂው ሊውስ ሱዋሬዝ እጆች ኳሷን ግብ ከመሆን በተአምር አዳናት። ለስፖርት አፍቃሪው በተለይ ደግሞ በታሪክ አራት ውስጥ ገብታ ለማታውቀው ጋና እጅጉን አብሻቂ እና ለግጭት የሚዳርግ ድርጊት ነበር። ዳኛው ፍፁም ቅጣት ምት ሰጠ። ይሄም ሌላ ተስፋ ቢሆንም በሚያስቆጭ ሁኔታ ኦሳማ ጊያን እድሉን አመከነው። ከማስቆጨት በዘለለ ቃል የጠፋለት አጋጣሚ ታሪክ በማይዘነጋው መልኩ ተመዘገበ። ሁለቱ ቡድኖች ወደ መለያ ምት ሄዱ። ኡራጋይ የበላይነቱን በመያዝ ወደ አራት ውስጥ ገባች። እጅግ አስገራሚ አጋጣሚ ነበር። ጋና ድል በሯ ላይ ደርሶ የተመለሰበት ጊዜ። ኮሎምቢያ ከጃፓን «2018 ሩሲያ የዓለም ዋንጫ» ታሪክ እራሱን እያደሰ እና አዳዲስ ክስተቶችን በዓለም ዋንጫው ላይ እየታየ ፤ የሩሲያው ዓለም ዋንጫ ደረሰ። ሁሌም አዲስ ነገር የማያጣው አዝናኙ የዓለማችን እግር ኳስ በጃፓን እና በኮሎምቢያ ጨዋታ ላይ የማራዶናን ያህል ባይሳካም ለአገር ክብር ሲባል ኳስን በእጅ አፈፍ አድርጎ የመመለስ ሙከራን አሳየን። ጃፓን ኳሱን ይዛ ጫና በኮሎምቢያ ግብ ክልል እየፈጠረች ነው። በድንገት ወደ ግብ ክልል ኳስ ተመታ። ኮሎምቢያዊው ካርሎስ ሳንቼዘ አሻፈረኝ ብሎ ኳሷን ከግብ ለማዳን በእጁ ተከላከለ። ውጤቱ ግን ያማረ አልነበረም። እርሱ በቀይ ካርድ ከሜዳ ሲወጣ ኮሎምቢያ በፍፁም ቅጣት ምት ግብ ተቆጠረባት። ሺንጂ ካጋዋ ጃፓንን ቀዳሚ አደረጋት። የቀይ ካርድ ሰለባ የሆኑት ኮሎምቢያዎች በዩሃን ፈርናንዶ ከርቀት በተመታች ኳስ አንድ አቻ መሆን ቻሉ። ሆኖም ግን በቁጥር ብልጫ የነበራቸው ጃፓኖች በዩአያ ኦሳኮ የ73ተኛ ደቂቃ ግብ ኮሎምቢያን በመርታት የመጀመሪያቸውን 3 ነጥብ በሩሲያ ዓለም ዋንጫ ማሳካት ቻሉ። ከላይ የጠቀስናቸው በእጅ ተነክተው ግብ የሆኑ እንዲሁም ጎል ከመሆን የዳኑ ታሪካዊ የእግር ኳስ ክስተቶች ናቸው። በጊዜው ለተሸናፊው ትልቅ ቁጭት ለአሸናፊው ደግሞ ያልተጠበቀ ድልን አምጥተዋል። ፈንጠዝያን ቁጭትን የፈጠሩት እነዚህ ጊዜያቶች ካለፉ በኋላ የእግር ኳስ አፍቃሪው በቂም እና በድል አድራጊነት መንፈስ ሳይሆን በታሪክነታቸው ብቻ ሲያስታውሳቸው ይኖራሉ።አዲስ ዘመን ነሃሴ 12/2011ዳግም ከበደ
https://www.press.et/Ama/?p=16360
930
2ስፖርት
አፍሪካዊያን ተጫዋቾች በዘንድሮው ፕሪምየር ሊግ
ስፖርት
August 12, 2019
37
ከአውሮፓ እና ከደቡብ አሜሪካ አህጉራት ቀጥሎ የተሻለ የእግር ኳስ ክህሎት ያላቸው ተጫዋቾች እንዳሏት ይነገራል፤ አፍሪካ። በአህጉሪቷ ከተንሰራፋው ድህነት ለማምለጥ በሚደረገው ጥረትም ታዳጊዎች እግር ኳስን እንደ አማራጭ ይይዙታል። የተሻለ ብቃት ያላቸው በርካታ ተጫዋቾችም ባህር አቋርጠው ከዘመነው ዓለም ክለቦች ተቀላቅለዋል። ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ በአዲስ የውድድር ዓመት በተመለሰው ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግም በርካታ አፍሪካዊያን ተጫዋቾች ይገኛሉ። ፉታ የተሰኘ አንድ ድረገጽ እንደሚያስነብበው ከሆነም ባለፈው የፕሪምየር ሊግ ዓመት (እአአ 2018/19) ከ12 ሃገራት የተወጣጡ 42 አፍሪካዊያን በፕሪምየር ሊጉ ክለቦች ተጫውተዋል። ከአፍሪካዊያኑ ሃገራት መካከልም ሴኔጋል ስድስት፣ ናይጄሪያና ኮትዲቯር አምስት አምስት ተጫዋቾችን በመያዝ ቀዳሚውን ስፍራ ይቆናጠጣሉ። የእንግሊዝን ጨምሮ በተለያዩ ሃገራት ሊጎች ውስጥም ምርጥ ብቃት በማሳየት ችሎታቸውን አስመስክረዋል። ባለፈው የፕሪምየር ሊግ ዓመትም አፍሪካዊያን ተጫዋቾች የተሻሉ እንደነበሩ፤ ለወርቃማ ጫማ ክብር የታጩትን ሶስት ተጫዋቾችን (ፔሪ ኤምሪክ ኡባሚያንግ፣ ሳዲዮ ማኔ እና ሞሃመድ ሳላህ) በማሳያነት ማንሳት ይቻላል። ከዚሁ በተጓዳኝ የሻምፒዮንስ ሊጉ ባለቤት የሆነው ሊቨርፑልም የሁለቱ አፍሪካዊያን ተጫዋቾቹ ጥምረት ከስኬት እንዳበቃው ይታወቃል። ግብጻዊው ሞሃመድ ሳላህ እና ሴኔጋላዊው ሳዲዮ ማኔ አሁን ያሉበት ሁኔታም ከአስር ዓመታት በላይ የቆየውን የአንጋፋዎቹን ዲዲየር ድሮግባ እና ሳሙኤል ኤቶን ዘመን የሚያስታውስ ሆኗል። ሁለቱ አንጋፋ ተጨዋቾች የአፍሪካ መለያ ቀለም እስከ መሆን ከመድረሳቸውም ባሻገር ለአህጉሪቷ የእግር ኳስ ከዋኝ ታዳጊዎች ተምሳሌትም ሆነው ቆይተዋል። በዚህ ወቅት ደግሞ የሊቨርፑሎቹ ተጫዋቾች ጥምረት የሚጠቀስ ይሁን እንጂ «እንደ ድሮግባ እና ኤቶ በወጥ ብቃት ዓመታትን ይዘልቁ ይሆን?» የሚለው አጠያያቂና አጠራጣሪም ነው። ምክንያቱ ደግሞ እነዚህን ተጫዋቾች በብርቱ ሊፈትኑ የሚችሉና በእነርሱ ምትክ መድመቅ የሚችሉ አፍሪካዊያን ተጫዋቾች በሊጉ መኖራቸው መሆኑን አፍሪካን ፉትቦል ዶት ኮም ያትታል በዘገባው። ድረ-ገጹ የሁለቱ ተጫዋቾች ተቀናቃኝ ይሆናሉ ያላቸውን ተጫዋቾችም እንደሚከተለው ጠቁሟል።የተሻለ የውድድር ዓመት በማሳለፍ የሁለቱን ተጫዋቾች ክብር ይገዳደራል በሚል የተጠቀሰው የመጀመሪያው ተጫዋች የሰማያዊዎቹ ሪያድ ማህሬዝ ነው። አልጄሪያዊው ማህሬዝ የተጠናቀቀውን የውድድር ዓመት ከክለቡ ማንቺስተር ሲቲ ጋር የሊጉን ዋንጫ በማንሳት ስኬት ያስመዘገበ ሲሆን፤ በቅርቡ በተካሄደው የአፍሪካ ዋንጫም ሃገሩን ለድል ማብቃቱ የሚታወስ ነው። ተጫዋቹ እአአ በ2015/2016 የውድድር ዓመት ሳይጠበቅ ዋንጫውን ባነሳው ሌስተር ሲቲ ያሳየው ብቃት አይዘነጋም። በወቅቱ በርካታ ክብሮችን የግሉ እንዳደረገም የሚታወቅ ነው። በዚህ ዓመት ከክለቡ እና ከብሄራዊ ቡድኑ ጋር ያነሳቸው ሁለት ዋንጫዎችም በውድድር ዓመቱ በተሻለ ብቃት እንዲገኝ የሚያግዘው እንዲሁም ወደ ቀድሞ ብቃቱ የሚመለስበት እንደሚሆን ተስፋ ተጥሎበታል። ሌላኛው ተጫዋች ደግሞ የመድፈኞቹ ፔሪ ኤምሪክ ኡባሚያንግ ነው። ትውልደ ፈረንሳዊውና የጋቦን ብሄራዊ ቡድን አባል በቡንደስሊጋ የነበረውን ጎል አምራችነት በሊጉ ክለብ አርሰናልም እንደሚደግመው ይጠበቃል። በመጀመሪያው ዓመት የክለብ ቆይታው በሊጉ 22 ግቦችን፤ በዩሮፓ ሊግ ደግሞ ስምንት ግቦችን አስቆጥሯል። የፕሪምየር ሊጉ የወርቃማ ጫማ አሸናፊው የ30 ዓመቱ ተጫዋች በዚህ የውድድር ዓመትም ወደ ግብ አዝናቢነቱ እንደሚመለስ ድረገጹ ቅድመ ግምቱን አስቀምጧል። የመድፈኞቹ ሌላኛው ተጫዋች ኒኮላስ ፔፔም በሊጉ የተሻለ ብቃት ያሳያሉ በሚል ከሚጠበቁት አፍሪካዊያን ተጫዋቾች መካከል ተገኝቷል። በውድድር ዓመቱ የፈረንሳዩን ክለብ ሊልን ለቆ አርሰናልን የተቀላቀለው ወጣቱ ተጫዋች በመጀመሪያው ዓመት የፕሪምየር ሊግ ቆይታው ጥሩ ብቃት እንደሚያሳይ ይጠበቃል። ኮትዲቯራዊው ፔፔ የእንግሊዙን ክለብ የተቀላቀለው የክለቡ ክብረወሰን በሆነ ዋጋ ሲሆን፤ በኡባሚያንግ የተያዘውን 62 ሚሊዮን ዩሮ ወደ 72 ሚሊዮን ዩሮ አሳድጎታል። ያለፈውን የውድድር ዓመት በሊግ ዋን ምርጥ አፍሪካዊ ተጫዋች ቢሰኝም፤ በግብጹ የዓለም ዋንጫ ግን ብሄራዊ ቡድኑ እንደተጠበቀው ውጤት ማስመዝገብ አልቻልም። ይሁን እንጂ ጥሩ ተስፋ ያለው ወጣት በመሆኑ በውድድር ዓመቱ ስመ ጥር አፍሪካዊ የፕሪምየር ሊግ ተጫዋች እንደሚሆን ይጠበቃል። የክሪስታል ፓላሶቹ ዌልፍሬድ ዛሃ እና ጆርዳን አየውም በተያዘው የሊግ ዓመት ጥሩ አቋም እንደሚያሳዩ ዕምነት የተጣለባቸው ተጫዋቾች ሆነዋል። ቀድሞ ለእንግሊዝ ይጫወት የነበረው ዛሃ ዝሆኖቹን መቀላቀሉን ተከትሎ ከስመ ጥር አፍሪካዊያን የፕሪምየር ሊግ ተጫዋቾች ተርታ ተገኝቷል። ጋናዊው አየውም በተመሳሳይ በሊጉ ጎልተው ሊጠቀሱ ከሚችሉ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ይሆናል በሚል ድረገጹ ቅድመ ግምት ሰጥቶታል።አዲስ ዘመን ነሃሴ 6/2011
https://www.press.et/Ama/?p=15954
512
2ስፖርት
‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ የቴኳንዶ ስፖርትን ያዳከሙት አሠልጣኞች ናቸው››
ስፖርት
April 26, 2019
98
ማስተር ኢዮብ ኃይሉ የሚክስድ ማርሻል አርት ስፖርት እና የስነ ልቦና አሰልጣኝ ነው። ከግል ትምህርት ቤቶች እስከ መንግሥት ትምህርት ቤቶች የቴኳንዶ ስፖርትን ከስነ ልቡና አንጻር በመቃኘት ሥልጠናዎችን በመስጠት ላይ ይገኛል። ለዛሬው የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል የስፖርት አምድ እንግዳ አድርገነዋል።አዲስ ዘመን፡- በማርሻል አርት ስፖርት ላይ አሁን ያለው እንቅስቃሴ ምን ይመስላል? ማስተር ኢዮብ፡- ማርሻል አርት ማወቅ እና የማርሻል አርት ሳይንስ ማወቅ የተለያዩ ናቸው። አንድ ሰው በስፖርቱ በተግባር የተዋጣለት ስለሆነ ብቻ አሰልጣኝ መሆን አይችልም። ማለትም አሁን በአገራችን ላይ እየታየ ያለው ማንም ሰው ጥቁር ቀበቶ አሊያም ዳን ካለው ወደ አሠልጣኝነት እየተሸጋገረ ነው። በትክክለኛው ሙያዊ እይታ ግን አሰልጣኝ ለመባል በትምህርት የበሠለ፣ ዕድሜው ከ25 ዓመት በላይ የሆነ፣ በማኅበራዊ ሕይወቱ መልካም መስተጋብር ያለውና ለማኅበረሰቡ ጥሩ እይታ ያለው መሆን አለበት። በአገር አቀፍ ደረጃ ወደ ሁለት ሚሊዮን የሚሆኑ የቴኳንዶ ተማሪዎች አሉ። ለእነዚህ ተማሪዎች እያንዳንዱ አሰልጣኝ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ አለ። በዚህ ላይ ግን የመንግሥት ድጋፍ አናሳ ነው። ልጆች ከፍተኛ የሆነ የስፖርት ፍቅር ካላቸው የስፖርቱን መርህ ባልጣሰ መንገድ በሥነ ምግባር፣ በማህበራዊ ህይወታቸውና በትምህርታቸው ላይ ለውጥ እንዲያመጡ ማድረግ ይቻላል። ይህ የሚሆነው ግን አሰልጣኙ በስፖርቱ ብቻ ሳይሆን በሥነ ልቦናም የዳበረ ሲሆን ነው። በአገሪቷ ብዙ ሥራ አጥ ወጣት አለ። ከዚህ ጋር ተያይዞ በርካታ ወጣቶች መጥፎ ድርጊቶች ውስጥ ሲገቡ ታይተዋል። በተለይ እንዲህ ዓይነት ወጣቶች ወደ ስፖርቱ ሲመጡ ስፖርቱን በጎ ላልሆነ ዓላማ እንዳያውሉት መደረግ አለባቸው። ከስፖርቱ በላይ የባህሪ ለውጥ እንዲያመጡ ማስቻል ይገባል። ከሥራ አጥነት መንፈስ ተላቅቀው እንዴት ሥራ መፍጠር እንዳለባቸው ሥልጠናዎችን ጎን ለጎን መስጠት ያስፈልጋል። እኔ እንደ አሰልጣኝነቴ በማሰልጠኛ ማዕከሌ ውስጥ በዚህ ጉዳይ ላይ በትኩረት ነው የምሠራው።አዲስ ዘመን፡- የቴኳንዶ ስፖርትን የማስተማር ዓላማ ስፖርቱን ማስፋፋት ወይስ ግብረ ገብነትን ማስተማር ነው?ማስተር ኢዮብ፡- እዚህ ላይ የአሰልጣኙ ብቃት ይወስነዋል። ለምሳሌ እኔ በቀን ለሁለት ሰዓታት አሰለጥናለሁ። ከዚህ ውስጥ አንዱን ሰዓት ለስነ ምግባርና ተያያዥ ጉዳዮች ጋር የተገናኙ ሥልጠናዎችን እሰጣለሁ። ስፖርቱንም ሥነ ምግባሩንም አስተባብሮ ማስኬድ ይቻላል። ሰልጣኞቹ ቢጫ ቀበቶ ለማግኘት እዚህ ላይ የሚያስደርሳቸውን ብቃት ብቻ መያዝ ትርጉም የለውም። በዚህ ረገድ እኔ እየተከተልኩ ያለሁት ፍልስፍና የቢጫ ቀበቶ ደረጃ ላይ ለመድረስ ከስፖርታዊ ብቃቱ በዘለለ የሥነ ምግባር ሁኔታ ይታያል። ለምሳሌ በሱስ ውስጥ ያለው ሰው በአንድ ቀን መተው አይችልም፤ ሲለምደውም ቀስ እያለ ስለለመደ በጊዜ ሂደት እንዲተወው ማድረግ ይቻላል። የተማሪዎችን ባህሪ ቀስ በቀስ መለወጥ እንደሚገባ በመገንዘብ ነው ስፖርቱን የማስተምረው። በመሆኑም ልጆች ስፖርቱን በሚሠሩበት ወቅት ምን ያህል ለውጥ አመጡ የሚለው አብሮ መታየት አለበት። ቀበቶ ለመስጠትም እንደ አንድ መመዘኛ መወሰድ ይኖርበታል።አዲስ ዘመን፡- ስፖርትን ለጤንነት መጠበቂያ ብለው የሚሠሩና ከዚህ የዘለለ የወደፊት ራእይ ያላቸው ስፖርተኞችን ምኞታቸው እንዳይከስም በምን መልኩ ታግዛላችሁ? ማስተር እዮብ፡- ሕፃናት ጥሩ የዶክተር ፊልም ካዩ፣ አሊያም ዶክተር እናት ወይም አባት ቢኖራቸው በአብዛኛው ዶክተር የመሆን ዓላማ ይኖራቸዋል። የእነርሱ እውነተኛ ዓለማ ስለመሆኑ ግን እርግጠኛ መሆን አይቻልም። ከውስጣቸው እምቅ ችሎታ ጋር የተገናኘ አይደለም። ወደ ስፖርት ቤት ሲመጡ ለምን ዶክተር፣ ኢንጂነር፣ ጋዜጠኛ ሌላም ሙያ ባለቤት መሆን እንደፈለጉ እንጠይቃቸዋለን። ከስፖርቱ ጋር ተያይዞ የሚሄድ የስነ ልቡና ሥልጠና ከወሰዱ በኋላ ፍላጎታቸውን ከራሳቸው የውስጥ እምቅ አቅም ጋር በማገናኘት ትክክለኛውን ዓላማ ይከተላሉ። የእነርሱን የውስጥ ተሰጥኦ ከተረዳን በኋላ ከወላጆቻቸው ጋር በመወያየት በራሳቸው ዓላማ ውስጥ እንዲያልፉ ይደረጋል። ከዚህ በኋላ ኢንጂነር መሆን የሚፈልጉ ልጆች በስፖርት ቤቱ ውስጥ ኢንጂነር እገሌ፣ ዶክተር መሆን የሚፈልጉም እንዲሁ ዶክተር እገሌ ተብለው እንዲጠሩ ይደረጋል። ዓላማቸውንም ከልጅነታቸው ጀምሮ እያዳበሩ እንዲሄዱ የሚያደርጉ ስፖርታዊ ተግባራት አሉ። በሌላ በኩል ማንኛውም ልጅ ቤት ውስጥገንዘብ ሲፈልግ ወላጅ ብር ይሰጣል። ይህ ግን ልጆችን ለስንፍና ስለሚዳርግ ከዚህም አልፎ ወደ ፊት ለሙሰኝነት እንዲጋለጡ ያደርጋል። ገንዘብ ለማግኘት በትንሹ ቤት ውስጥ ሥራ መሥራት እንዳለባቸውና ሠርቶ ገንዘብ ማግኘት እንደሚቻል የሚማሩበትን ስልት በስፖርቱ ዓውድ ውስጥ በመሆን ከወላጆቻቸው ጋር ምክክር እናደርጋለን። በዚህ ያደጉ ልጆች በዕድል አያምኑም፣ ከጠባቂነት ይልቅ ሠርቶ ማግኘትን ይለምዳሉ።አዲስ ዘመን፡- ስፖርቱ ጤናማ የሆነ ማኅበረሰብን ከመገንባት ባሻገር በሥነ ምግባር የበለጸገ ማኀበረሰብን የመገንባት ቁመና ላይ ነው ማለት እንችላለን? ማስተር ኢዮብ፡- በአገሪቷ ላይ የተማሩ በርካታ ዜጎች አሉ። የተማሩ ሆነው ስፖርተኛ ቢሆኑ ደግሞ ተመራጭ ነው። ለእያንዳንዱ ሥራ ስፖርት ወሳኝ ነው። የአገር መሪ እንኳን ሰውነቱ በስፖርት መበልጸግ አለበት። ስፖርቱ በሥራ ላይ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ስላለ ነው። በተለይ እንደ ማርሻል አርት ያሉ ስፖርቶች ግብረ ገብነትን በሰፊው ስለሚያስተምሩ ማዘውተሩ ክፋት የለውም። ዕውቀትና ስፖርት ተደጋግፈው እንዲሄዱ የሚያግዝ መርህ አለ።አዲስ ዘመን፡- የማርሻል ዓርት ስፖርት ለኢትዮጵያውያን ያስፈለገው የስፖርት አማራጭን ለማስፋት ነው ወይስ የተለየ ጥቅም ይሰጣል? ማስተር ኢዮብ፡- ሁሉም ስፖርት የራሱ የሆነ ጥቅምና ጉዳት አለው። አንዱ ስፖርት ከሌላው አይበልጥም፤ አያንስም። ሊለያይ የሚችለው ፍላጎት ነው። ቴኳንዶ የሚሠሩ ሰዎች ከቴኳንዶ ውጪ ሌላ ስፖርት ለእነርሱ እንደ ስፖርት ላይታይ ይችላል። ነገር ግን የስፖርቱን ጥቅምና ፍልስፍና መረዳት ያስፈልጋል። ለምሳሌ ‹‹ታች ችዋን›› የሚባለው የውሹ ዓይነት የቻይናውያን ስፖርት ከማርሻል አርት ስልጠና ማዕከል አልፎ ሆስፒታል ውስጥም ይሰጣል። ምክንያቱም ነርቭን የማነቃቃት አቅም ስላለው ነው። የጀርባ ህመምን ለመከለካልም የማርሻል አርት ስፖርቶች ጠቀሜታቸው የጎላ ነው። በሌላ በኩል በማርሻል አርት ውስጥ እስከ 3ሺ የሚጠጋ ሥልታዊ እንቅስቃሴ ስላለ ልጆች እነዚህን መያዝ ለመዱ ማለት የቀለም ትምህርታቸውንም በቀላል ለመያዝ ይረዳቸዋል።አዲስ ዘመን፡- ስፖርቱን በተጓዳኝ ከሚሰጠው ጠቀሜታ በተጨማሪ እንደ ስፖርትነቱ አገርን በሚጠቅም ቁመና ላይ ነው? ማስተር ኢዮብ፡- ቴኳንዶ ሌላ አገር ላይ በሥርዓተ ትምህርት ውስጥ ገብቶ ለማስተማሪያነት ይገለገሉበታል።ይህ የሆነውም የማርሻል አርት ሙያተኞቹ ከፍተኛ ተጽዕኖ ስለፈጠሩ ነው። የስፖርቱን ፍልስፍና መንግሥት እንዲገነዘበውና የተለየ ድጋፍ እንዲሰጠው ማድረግ ችለዋል። ስፖርቱም ተስፋፍቶ እንደ ኮርያ ያሉት አገራት በዓለም መድረክ ተዋውቀውበታል። ኢትዮጵያ ውስጥ የቴኳንዶ ስፖርትን ያዳከሙትአሰልጣኞች ናቸው። ሁሉም ሳይሆኑ አብዛኞቹ አሰልጣኞች ‹‹ቢዝነስ ተኮር አዕምሮ ነው ያላቸው›› የስፖርት ፍልስፍናው በትክክል ገብቶን ካልሠራን ደግሞ ስፖርቱ ከአሁኑ በላይ እየቀጨጨ ይሄዳል። አትሌቲክስ ካደገ ቴኳንዶ የማያድግበት ምክንያት የለም። ችግሩ ግን ስፖርቱን ከገንዘብ ጋር በማገናኘት ወደ ፊት ማራመድ አለመቻሉ ነው። ስለዚህ አሰልጣኞች በስፖርቱ ሳይንስም በስነ ልቦናም የበቁ መሆን አለባቸው። እንዲህ ሲሆኑ ተጽዕኖ ይፈጥራሉ። ቴኳንዶ ሰው እንደሚያስበው የእርግጫ ስፖርት አይደለም።አዲስ ዘመን፡- አንዳንዶች የቴኳንዶ ስፖርት ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል በማለት በስፖርቱ አማካኝነት ዝርፊያ እየተፈጸመ ነው የሚል ማሳያ የካራቴ ፊልሞችን ማጣቀሻ አድርገው ያቀርባሉ፤ እዚህ ላይ የአንተ አስተያየት ምንድነው? ማስተር ኢዮብ፡- ይህንን ለመፈረጅ ያለህበት አገር ይወስነዋል። በውጭ አገር ስፖርተኞች ቴኳንዶ ቤት ሄደው ባይሰለጥኑም በየጫካውና በየቤቱ ምስሎችን እያዩ ለብቻቸው የሚሠሩ አሉ። በየፊልሞቻቸውም ሌባና ፖሊስ ሆነው ነው ሲተውኑ የሚታዩት። ይህንን እያየ ያደገ ሰውም ስፖርቱን ላልተገባ ዓላማ ሊጠቀምበት ይችላል። በዝርፊያ የተሳካለት ካራቲስት ካለ ለዚህ ብቻ ብሎ የሚሠራ ይኖራል። ዋናው ነገር ግን የፊልም ነጥብ መሆን ያለበት በዘራፊውና በተዘራፊው መካከል የሚደረገው ጭብጥ መታሰብ አለበት። ለምሳሌ በፊልሙ ውስጥ ሌባው ገጸ ባህሪ በዝርፊያ ላይ የተሰጠው ሽፋን ረጅም ሆኖ መጨረሻ ላይ የሚገጥመው እክል ትንሽ ከሆነ መልካም ነገር ላያስተምር ይችላል። ነገር ግን ዘራፊ በያንዳንዱ እንቅስቃሴ ውስጥ እክል ሲገጥመው በማሳየት ዓላማውን ማስቀየር ይቻላል። ሌባው በካራቴ አሸንፎ ሲሳካለት ለህዝብ ማሳየት ሌላው ትውልድም በዚህ መስመር ውስጥ ላለማለፉ ማረጋገጫ አይኖርም። ስለዚህ በካራቴ ፊልሞች ላይ እኩይ ገጸ ባህሪያት ለሆኑት ከውድቀት ይልቅ ለስኬት ብዙ ሽፋን መስጠት አይገባም። በኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ የቴኳንዶ ተማሪዎች በዝርፊያ ላይ ይሰማራሉ የሚባለው ችግሩ ከአሰልጣኙ ስለሚጀምር ነው። ይህ ማለት አሰልጣኙ ስፖርተኞችን የቀረጸበት መንገድ ነው መታየት ያለበት። አብዛኞቹ ኢትዮጵያዊያን አሰልጣኞች በትምህርት ዝግጅታቸው ደካማ በመሆናቸውና ራሳቸውን በየጊዜው ስለማያሻሽሉት ለእንዲህ ዓይነት ችግር ይዳረጋሉ። ራስን በየጊዜው ካላሻሻሉ ሥልጠና መስጠት አስቸጋሪ ነው። የቴኳንዶ ስፖርተኞች ከወላጆቻቸው በላይ አሰልጣኞቻቸውን ይሰማሉ። ጥሩም መጥፎም ሆነው የማደግ ዕድላቸው በአስተማሪዎቻቸው እጅ ላይ ነው። አዲስ ዘመን፡- አመሰግናለሁ። ማስተር ኢዮብ፡- እኔም አመሰግናለሁ።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 18/2011አዲሱ ገረመው
https://www.press.et/Ama/?p=9624
1,033
2ስፖርት
አንጋፋው ሰው ስለ አንጋፋው ስፖርት ይናገራሉ
ስፖርት
April 27, 2019
51
በኢትዮጵያ አንጋፋ ከሆኑ የስፖርት መድረኮች ቀዳሚ እንደሆነ የሚነገርለት የሠራተኛ ስፖርት ነው:: ይህ የስፖርት መድረክ በሠራተኛው መካከል በሚካሄዱ ውድድሮች አገራቸውን በዓለም አቀፍ መድረኮች ወክለው ማስጠራት የቻሉ ስመ ጥርና የስፖርቱ ባለውለታ የሆኑ ስፖርተኞችን ማበርከቱም በውስጡ ያለፉ አንጋፋ ሰዎች ይመሰክሩለታል:: ይሁን እንጂ ይህ የስፖርት መድረክ እንደቀድሞ ዝናውን ይዞ መዝለቅ አልቻለም:: ለአገር እንደዋለውና እንዳበረከተው አስተዋፅኦም ሲነገርለት አይስተዋልም:: ይህ የስፖርት መድረክ ቀድሞ የነበረውን ዝና የሚመሰክር በወቅቱ የነበረ ሰው በቀላሉ ማግኘትም ከባድ ነው:: የሠራተኛው ስፖርት ወርቃማ ዘመን ላይ ከነበሩት አንጋፋ ግለሰቦች አንዱ አቶ ብርሃኑ አበራ ናቸው:: አቶ ብርሃኑ በኢትዮጵያ ሠራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) የስፖርት ክፍል ኃላፊ ሆነው ለበርካታ ዓመታት አገልግለዋል:: በ1990 ዓ.ም ከኃላፊነታቸው ከለቁቁ በኋላ የሠራተኛው ስፖርት በሚካሄድባቸው ስፍራዎች አይጠፉም:: የፊታችን ረቡዕ ዓለም አቀፉ የሠራተኞች ቀን ሲከበር ጅማ ከተማ ላይ በተለያዩ ስፖርታዊ ውድድሮች አብሮ ይከበራል:: ይህንንም አስመልክቶ የሠራተኛው ስፖርት ድሮና ዘንድሮ ምን አይነት ገፅታ እንዳለው አቶ ብርሃኑ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደሚከተለው ያወጋሉ::የሠራተኛው ስፖርት አጀማመር የስፖርት እንቅስቃሴ በሠራተኛው መካከል ሲጀመር አብረው የጀመሩት አቶ ብርሃኑ አንጋፋው የስፖርት መድረክ ኢሠማኮ ከመመስረቱ በፊት የኢትዮጵያ ሠራተኞች የስፖርት ማህበር በሚል ይንቀሳቀስ እንደነበር ያስታውሳሉ:: እዚያ ውስጥም የተወሰነ ሠራተኛ በራሱ ተሰባስቦ በስፖርቱ ይንቀሳቀስ እንደነበር:: ኢሠማኮ በዘጠኙ ኢንዱስትሪዎች ተከፋፍሎ ሲመሰረት አቶ ብርሃኑ በፋብሪካ ኢንዱስትሪ ማህበር ውስጥ ነበሩ:: መጀመሪያ የተደራጀውም ይህ እንደነበር ይናገራሉ:: ዘጠኙ ኢንዱስትሪ ማህበራት ከተቋቋሙ በኋላ የስፖርት ማህበር ስለማቋቋም ሲነሳም ለአመራርነት ኮሚቴ ሰዎች ተወክለው ነበር:: ታዲያ ያኔ እንደ አጋጣሚ አቶ ብርሃኑ የመመረጥ እድሉ ገጠማቸው:: የሠራተኛው ስፖርት በዓል ተብሎ 1970 ዓ.ም ላይ ተከብሮ እንደነበር የሚናገሩት አንጋፋው የሠራተኛ ስፖርት መሪ፣ የላብአደሩ የስፖርት እንቅስቃሴ ከዚያ ጊዜ አንስቶ እየተጠናከረ መምጣቱን ያወሳሉ:: ‹‹1975 ዓ.ም ላይ የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ሲቋቋም (የታወቁ የስፖርት ድርጅቶች ነበር ያኔ የሚባለው) አንዱ የሠራተኛው የስፖርት ማህበር ነበር ይላሉ›› በወቅቱም እሱን ጨምሮ ሃምሳ አንድ ክለቦች ተቋቋሙ፣ አሁን የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ሥራ አስኪያጅ የሆነው ሰለሞን በቀለ ነበር አዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን የነበረው:: አሁን ላይ በአገራችን ትልልቅ ስም ያላቸው እነ ቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ቡና ያሉ ክለቦችም በዚያን ወቅት ተወዳድረው እንደወጡ ያስታውሳሉ:: ከነዚህም በተጨማሪ ወደ አስራ አምስት ክለቦች በወቅቱ የወጡት ከሠራተኛው ነበር:: ይህም ከዚያ በፊት ፈርሶ ለነበረው የአገሪቱ ስፖርት የሠራተኛው ስፖርት መቋቋም ዳግም የአገሪቱን ስፖርት እንዲያንሰራራ ማድረጉንም ይመሰክራሉ::የዚያን ጊዜ ከነበሩ ክለቦች የፈረሱ ቢኖሩም አሁንም ድረስ በአገር አቀፍ ደረጃ ትልቅ ስም ያላቸው ሆነው እንደዘለቁም በማስታወስ የሠራተኛው ስፖርት የነበረውን አስተዋፅኦ ያብራራሉ::የሠራተኛው ስፖርት ድሮና ዘንድሮ የሠራተኛው ስፖርት በወርቃማ ዘመኑ በበርካታ የስፖርት አይነቶች ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ መድረክ የወከሉ ባለውለታዎችን ማፍራት ችሏል:: በተለይም በሦስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ ቻምፒዮን ስትሆን የሠራተኛው ስፖርት ትልቅ አቅም ነበረው:: አቶ ብርሃኑ ያን ዘመን ሲያስታውሱ ‹‹ሁሉም ነገር እንደጊዜው ነው›› ይላሉ:: ባለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት የነበረው አመራር በስፖርቱ ላይ የሚያረካ ባለመሆኑ የሠራተኛውን ስፖርት ስምና ዝና ይዞ መቀጠል እንዳልቻለም ያብራራሉ:: ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህም ቢሆን የተወሰነ መነቃቃት ቢኖርም ሠራተኛው በስፖርቱ ላይ አልነበረም የሚል እምነት አላቸው:: እንዲያውም አሁን ያሉት አመራሮች እነ ፍሰሃፂዮን ቢያድግልኝ (የኢሠማኮ ስፖርት ኮሚቴ ሰብሳቢ) የተወሰነ እያነቃነቁት መጡ እንጂ ስፖርቱ አልነበረም ማለት እንደሚቻል ይናገራሉ:: አቶ ብርሃኑ በእርሳቸው ዘመን የነበረውን ሰፊ የሠራተኛ ስፖርት እንቅስቃሴ መለስ ብለው ሲያወጉም ‹‹በእኛ ዘመን ስፖርት ለጤንነት፣ ለሰላምና ለምርታማነት በሚል ከዳር እስከ ዳር ይንቀሳቀስ ነበር›› ይላሉ:: ይህ ነገር አሁንም አስፈላጊ መሆኑንም ይጠቁማሉ:: ዛሬ ላይ በኢትዮጵያ እግር ኳስ አሉ ከሚባሉት አሰልጣኞች መካከል እነ አስራት ኃይሌ፣ ነብሱን ይማርና እነ ስዩም አባተ በእግር ኳስ ላይ ስልጠና እንዲወስዱና ውጭ ድረስ እንዲማሩ ያደረገው ይሄው ቤት መሆኑን የሚናገሩት አቶ ብርሃኑ እነዚህ የቀድሞ ተጫዋቾችና የአሁን አሰልጣኞች እንዳሁኑ ዘመን የገንዘብ ፍቅር እንዳልነበራቸው ይመሰክራሉ:: እነ ትግል ፌሬ፣ ርምጃችንና ሌሎችትላልቅ ክለቦች የወቅቱ የስፖርቱ ወርቃማ ዘመን መገለጫዎች ነበሩ:: እነዚህ ክለቦች ሲመሰረቱ በዚህ መምሪያ ስር እንደነበሩ የሚናገሩት አቶ ብርሃኑ፤ ኋላ ላይ ወደ ኢንዱስትሪያቸው ይመለሱ ተብለው ከተመለሱ በኋላም በጥንካሬያቸው መቀጠላቸውን ያስታውሳሉ:: ‹‹አሁን ላይ እኔ የሚመስለኝ አመራሩ ለሠራተኛው የሰጠው ግምትና አመለካከት ዝቅተኛ ነው:: የሠራተኛው ስፖርት አሁን ላይ እንዲቀዘቅዝ ያደረገውም ይህ ነው፣ ይሄ ቤት ቢጠነክር ከዲሲፕሊን ጋር በተያያዘም ይሁን ከሥራ አጥነት ጋር በተያያዘ ወጣቱ በስፖርቱ የሚያበረክተው አስተዋፅኦ ትልቅ ነበረ›› በማለት የአሁኑን ዘመን የሠራተኛ ስፖርት ይገልፁታል:: የሠራተኛው ስፖርት ቀደም ሲል እንደነበረውአስመራ፣ ሐረር፣ ድሬዳዋ፣ ባህርዳር፣ ጎንደርና ሌሎች አካባቢዎች እንቅስቃሴው ቢጠናከር ወጣቱ ወደ ስፖርቱ እንደሚገባ ጠንካራ እምነት አላቸው:: ወጣቱ ሥራውን እየሠራ ስፖርቱ ተጨማሪ የገቢ ምንጭ ይሆንለታል ብለው ያምናሉ:: በቀድሞው ዘመን እንዳሁኑ ምቾት እንዳልነበረ የሚያስታውሱት አቶ ብርሃኑ ‹‹ወጣቱ የሠራተኛ ክፍል ለስፖርቱና ለማለያው የነበረው ፍቅር ቀላል አልነበረም›› ይላሉ:: ይህም ለብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ሲመረጥ ከጦሩና ከሠራዊቱ ሁለት ወይም ሦስት ተጫዋች ካልሆነ በስተቀር አብዛኛው ከሠራተኛው ቡድን እንዲገኝ ማድረጉን ያስታውሳሉ::የሠራተኛው ስፖርትና ዓለም አቀፉ የሠራተኛ ቀን አቶ ብርሃኑ ሜይ ዴይን አስመልክቶ በቀድሞው ዘመን ሁሉም ቡድኖች አስቀድመው በየኢንዱስትሪያቸው ጨዋታዎችን እንደሚያደርጉ አይዘነጉትም:: በእርግጥ እንዲህ በዓል ጠብቆ ሳይሆን በየቀኑ ውድድሮች እንደነበሩም ይናገራሉ:: ዘጠኙም ኢንዱስትሪዎች የራሳቸውን ውድድር ካደረጉ በኋላ አሸናፊዎቹ ተለይተው ሜይ ዴይ ላይ ለዋንጫ ጨዋታ ይቀርባሉ:: ከዚህ ውድድር በላይ ግን ብዙ ጊዜ ሜይ ዴይ ይከበር የነበረው ወንጂ ስቴድየም ላይ እንደመሆኑ ድምቀቱ የተለየና የማይረሳ መሆኑን ያስታውሳሉ:: ከስፖርተኛው ጋር አብሮ የሚመጣው ሠራተኛ ቁጥርም የበዓሉ ሌላ ድምቀት እንደነበር አይረሱትም:: ክረምት ላይም ሠራተኛው ውድድር ያዘጋጅ እንደነበር የሚናገሩት አቶ ብርሃኑ፣ በተለይም ድሬዳዋ በሚዘጋጁት ውድድሮች ከአሥመራ ድረስ እየመጡ የተለያዩ ቡድኖች እንደሚሳተፉ ያስታውሳሉ:: እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሚያዘጋጀው የኢትዮጵያ ዋንጫ የሚባል ነበር:: ከዚያ ውድድር ሁለትና ሦስት ሳምንት ቀደም ብለው የተለያዩ ቡድኖች ወደ ሠራተኛው ውድድር ለመምጣት የማያደርጉት ጥረት አልነበረም፣ ከጎንደር፣ ከጅማ ድረስ ይመጣሉ:: ይህም አዳዲስ ተጫዋቾችን እያዩ ክለቦች ራሳቸውን የሚያጠናክሩበት አጋጣሚ ይፈጥርላቸው እንደነበር አንጋፋው ሰው ይናገራሉ::የሠራተኛው ስፖርና ስፖርታዊ ጨዋነት የሠራተኛው ስፖርት ከቀድሞ ዝናው ይዞት የቀጠለው ነገር ቢኖር ስፖርታዊ ጨዋነት ነው:: አሁን የሚመሰገንበት ስፖርታዊ ጨዋነትም መሰረቱ ያኔ የወርቃማው ዘመን እንደሆነ አቶ ብርሃኑ እንዲህ በማለት ያስታውሱታል ‹‹በሠራተኛው ስፖርት ወርቃማ ዘመን ሥራና ስፖርት እንጂ ፖለቲካና ሌሎች ነገሮች ውስጥ ጊዜ አይባክንም ነበር። አሁንም የሠራተኛው ስፖርት በስፖርታዊ ጨዋነት አይታማም›› አቶ ብርሃኑ ከሠራተኛው ስፖርት ወጣ ብለው በአገራችን እግር ኳስ ስለሚስተዋለው የስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል ካካበቱት ልምድ በመነሳት ሃሳባቸውን ይሰነዝራሉ:: በአንድ ወቅት ለአምስት ዓመት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስኪያጅ ሆነው በሠሩበት ጊዜ የነበረውን ሁኔታ ሲያስታውሱ እንዲህ ይላሉ ‹‹ ያኔ እንዳሁኑ ጠብ ሳይሆን ትልቅ ፍቅር ነበር፣ ሜዳ ላይ ማንም ተጫወተ ማንም የኔ ነው ብሎ የሚደግፈው ስፖርቱ ላይ ብቻ ትኩረት አድርጎ ነው፣ ያኔ አይደለም ተጫዋች ስፖርት የሚወዱ ትላልቅ ባለስልጣናት ከስፖርታዊ ጨዋነት ውጭ አንድም ነገር ቢያደርጉ ስቴድየም እንዳይገቡ ይቀጡ ነበር››::ይህን ሀሳብ ለማጠናከርም በአንድ ወቅት የገጠማቸውን ያወሳሉ::‹ ጄነራል አበራ አያኔ የሚባሉ ኳስ አፍቃሪ ነበሩ፣ እኚህ ጄነራል አንድ ቀን ስቴድየም ውስጥ ከስፖርታዊ ጨዋነት ውጭ የሆነ ነገር ተናገሩ፣ በዚህም ስቴድየም እንዳይገቡ ታገዱ:: አሁን ይሄ ይደረጋል? እኚህ ጄነራል ቅጣቱን ተቀብለው ስፖርቱን ከመውደዳቸው የተነሳ ካታንጋና ሚስማር ተራ ተደብቀው በመግባት ጨዋታ ይመለከቱ ነበር። ይህን የሚያደርጉት ከስፖርቱ ፍቅር የተነሳ እንጂ ለሌላ ነገር አይደለም በሚል እገዳውን በኋላ ላይ አነሳንላቸው» የአገራችን የስፖርታዊ ጨዋነት ችግር አንዱም የስፖርት ጋዜጠኞች እውነት አለመናገራቸው ሲሆን አመራር ላይ ያሉትም ሰዎች ችግር አለባቸው የሚል እምነት አላቸው:: «አንዱ ክለብ ወደ አንዱ ሄዶ መጫወት መፍራት የለበትም» የሚሉት አቶ ብርሃኑ፤ ክለቦች በሜዳቸው እንዳይጫወቱ ማድረግ ነገሩን ማባባስ ነው ይላሉ:: ‹‹በእኛ ጊዜ የስፖርት ምክር ቤት ነበር፣ እንዲህ አይነት ችግር ሲኖር ክለቦች ተሰብስበው ይመክሩ ነበር። አሁን እንደዚያ አይነት ነገር ያለ አይመስለኝም። እውነተኛ የስፖርት እንቅስቃሴም አይታየኝም። የውሳኔ ችግር አለ። ተገቢና ተመጣጣኝ ቅጣት ቢኖር ይሄ ሁሉ አይፈጠርም›› በማትም ሃሳባቸውን ያጠናክራሉ:: ወገንተኝነታችን ለስፖርቱ እንጂ ለሌላ ነገር መሆን የለበትም። የስፖርቱን ሕግ ማወቅ በስፖርቱ ሕግ መቅጣት ትኩረት ሊደረግበት እንደሚገባም ምክረ ሃሳባቸውን ይለግሳሉ::የሠራተኛው ስፖርት ዕጣ ፋንታ ኢትዮጵያ ከግብርና መር ወደ ኢንዱስትሪ መር በምታደርገው ሽግግር ውስጥ በርካታ ኢንዱስትሪዎች የመቋቋም ዕድል አላቸው ተብሎ ይታመናል:: በዚህ አጋጣሚም ወጣቶች በብዛት የሥራ ዕድል እንዲያገኙ ሊያደርጋቸው ይችላል:: ያም ማለት አብዛኛው የሠራተኛ ክፍል ወጣት ሲሆን ከስፖርቱ ጋር ለማቆራኘት መልካም አጋጣሚ ይፈጥራል:: ይሄን አጣጥሞ መሄድ ትልቁ የቤት ሥራ ነው:: አቶ ብርሃኑ ከያኔው ይልቅ አሁን ኢንዱስትሪዎች ተበራክተዋል ሰፊ እንቅስቃሴም እንዳለ የታዘቡትን ይናገራሉ:: በዚህ ውስጥ ሠራተኛና አሰሪውን አንድ ማድረግና መያዝ የሚቻለውም በስፖርቱ አማካኝነት መሆን እንደሚገባው ያብራራሉ::‹‹ይህን ስናደርግ ስራውም ጥሩ ይሠራል፣ አሰሪውም ከሠራተኛው ጋር በስፖርቱ ምክንያት ይቀራረባል። ቤተሰባዊ ስሜት መፍጠር ይቻላል›› ይላሉ። በዚህ አጋጣሚ ወደ ስፖርት ማህበሩ ያልገባ ድርጅት ካለ ቆም ብሎ ማሰብ እንዳለበት አፅኖት ሰጥተው ይናገራሉ:: ሠራተኛውን በስፖርት ማደራጀት ለጤንነት፣ ለአንድነትና ለስነ ምግባር ቁልፍ ፋይዳ አለው ‹‹ሠራተኛው ዝም ብሏል፣ ይህ ዝምታ ደግሞ ጥሩ አይደለም፣ አንዳንዴ ሠራተኛው በስፖርት ሲደራጅ ቅር የሚለው ይኖራል። የሚያስፈልገው ግን ሠራተኛውን በስፖርቱ በቀላሉ ማደራጀት ›› መፍትሄ መሆኑን ያስቀምጣሉ:: የሠራተኛው ስፖርት አሁንም ጠንካራ ስራ ከታከለበት እንደቀድሞው በእግር ኳስ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ስፖርቶች ለብሔራዊ ቡድን ሊመረጡ የሚችሉ ሠራተኞችን የማፍራት ዕድል አለው:: ኢሰማኮ የጀመረውን የማነቃቃት ሥራ አጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል:: አሁን በአብዛኛው የሠራተኛው ክፍል ወጣት ነው፤ የበለጠ መቅረብና ማጠናከር ያስፈልጋል፤ ይቺ አገር በሌላት የውጭ ምንዛሬ ተጠባባቂ ወንበር የሚያሞቅ ተጫዋች ከውጭ ክለቦቻችን ማምጣት የለባቸውም የሚል አቋም አላቸው። ክለቦች ታዳጊዎችን ማየት ቢከብዳቸው ከሠራተኛው ስፖርት ዞር ብለው መመልከት እንዲችሉ ማድረግ እንደሚገባ በመግለፅም ሃሳባቸውን ይቋጫሉ::አዲስ ዘመን ሚያዝያ 19/2011ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=9715
1,273
2ስፖርት
የኢትዮጵያ እግር ኳስ – በሳምንቱ
ስፖርት
August 19, 2019
37
በተጠናቀቀው ሳምንት በእግር ኳስ ስፖርት በርካታ የአገር ውስጥ ዜና ዎችን ተመልክተናል። እነዚህ ወሬዎች ከተጫዋቾች ዝውውር አንስቶ ውዝግብ እስካስተናገደው የተጫዋቾች ደመወዝ በቀጥታ ተያያዥነት ያላቸው ነበሩ። በተለይ የተጫዋቾች ደመወዝን አስመልክቶ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከሰሞኑ ያሰማው ዜና እና ያወጣው መመሪያ ብዙሃኑን በሁለት ጎራ ከፍሎ እያጨቃ ጨቀ ይገኛል። የአዲስ ዘመን የእሁድ ገፅ የስፖርት ዝግጅት ክፍላችን ለዛሬ በዚህ ሳምንት የተከሰቱ የእግር ኳስ ዜናዎችን ሊያስታውሳችሁ ወዷል። ለዜናዎቹ ዋቢም የሶከር ኢትዮጵያ ድረ ገፅን በዋናነት ተጠቅሟል። በቀዳሚነትም የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ቀዳሚ ተሰላፊ የሆነችውን የሎዛ አበራን ጉዳይ እ ነሆ ይላል። ሎዛ አበራ በሳምንቱ ከተሰሙ ጆሮ ገብ ዜናዎች መካከል በዋናነት ጉዳይ ሆኖ የሰነበተው የሎዛ አበራ ለማልታው ክለብ ‹‹ቢርኪርካራ›› ፊርማዋን ለማኖር ትናንት እረፋዱ ላይ መብረሯን የሚገልፀው ዜና ነበር። ሶከር ኢትዮጵያ እንደዘገበው ባለፈው የውድድር ዓመት አጋማሽ ከሲዊድኑ ከንግስባካ ክለብ ጋር ረዘም ያለ የሙከራ ጊዜ አሳልፋ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሰችው ሎዛ አበራ ፊርማዋን ለአዳማ ከተማ በማስፈር በውድድር ላይ ቆይታለች። ዳግም ከኢትዮጵያ ውጭ የመጫወት እድል ያገኘችው ተጫዋቿ ነገ ምሳ ሰዓት ወደ ማልታ በማቅናት ለቢርኪርካራ የሁለት ዓመት ኮንትራት እንደምትፈርም ወኪሏ ሳምሶን ናስሮ ለድረገፁ መግለፁን አስነብቧል። ተጫዋቿ ወደ ማልታ ስታመራ ያለምንም የሙከራ ጊዜ እንደሆነም ተዘግቧል። ብቃቷን እንድትጠብቅ ለተከታታይ ቀናት በትንሿ የአዲስ አበባ ስታዲየም ከባለሙያ ጋር ልምምድ ስትሠራ እንደቆየች ታውቋል። የተጫዋቿ የጉዞ እና ሆቴል ወጪ በክለቡ እንደሚሸፈንም ተገልጿል። በ1999 ዓ.ም የተመሰረተው ቢርኪርካራ የአገሪቱን የሴቶች ሊግ ላለፉት ተከታታይ ሦስት ዓመታት ማንሳቱ ይታወቃል። የደመወዝ ጣርያውን ተቃውሞ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በሳምንቱ ውስጥ የማንኛውም የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ተጫዋች ደመወዝ ከ50 ሺ ብር መብለጥ የለበትም ብሎ ያሳለፈው ውሳኔ ከወዲሁ ውዝግብ እያስነሳ ነው። በዚህም የኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋቾች ማህበር ውሳኔውን በቀዳሚነት ተቃውሟል። የተለያዩ መገናኛ ብዙሃንም ይህን ጉዳይ በስፋት ዘግበውታል። አሶሴሽኑ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በፃፈው እና ለባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ ለወጣቶች እና ስፖርት ኮሚሽን፣ ለበጎ አድራጎት እና ማህበራት ኤጀንሲ ፣ ለሠራተኛ እና አሰሪ ኤጀንሲ እንዲሁም ለመገናኛ ብዙሃን ግልባጭ ባደረገው ደብዳቤ የደመወዝ ጣሪያ ውሳኔውን ተቃውሟል። በቅርቡ ህጋዊነቱን በማረጋገጥ የተቋቋመባቸውን ዓላማዎች ወደ ማስፈፀም ሥራ የገባው የኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋቾች ማህበር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የተጨዋቾችን ደመወዝ ጣሪያ ሃምሳ ሺ ብር እንዲሆን ያሳለፈውን ውሳኔ በፕሬዚዳንቱ ዮሃንስ ሳህሌ ፊርማ በወጣ ደብዳቤ በመቃውም እንደማህበር የመጀመሪያ ፈተናውን ጀምሯል። ደብዳቤው የፌዴሬሽኑን የመጨረሻ ውሳኔ ከመቃወም ባለፈ ለውሳኔው የተጠራው ስብሰባ የነበረበትን የአካሄድ ግድፈትም አንቀፆችን በመጥቀስ ተቃውሟል። በዚህም ደብዳቤው እግር ኳስ ፌዴሬሽኑ እየተጠቀመበት ባለው ደንብ መሰረት አሶሴሽኑ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ሙያተኞች ማህበር አባል መሆኑን በመጥቀስ በውሳኔው ወቅት ፌዴሬሽኑ ስላቀረበው ጥናት እንደ ሙያተኞች አባል ስለጉዳዩ ቅድመ ዝግጅት እንዳያደርግ ምንም አይነት ማስረጃ እንዳልተሰጠው ያትታል። በተጨማሪም ማህበሩ በሥሩ ያሉትን ሙያተኞች ወክሎ ስምምነቶችን ለማድረግ ምንም አይነት አማራጭ ያልተሰጠው መሆኑን በመግለፅ የቢሾፍቱው ስብስባ ላይ በተሳተፉ እና ውሳኔው በደረሷቸው ክለቦች አግባብነት ላይም ጥያቄ ያነሳል። በመጨረሻው የደብዳቤው ክፍልም ፌዴሬሽኑ የሄደበት መንገድ የፊፋን የስፖርት ችሎት ደንብ የጣሰ በመሆኑ ማህበሩ ህጋዊ መስመሮችን በመከተል በጉዳዩ እንደሚገፋበት አስታውቋል። ወላይታ ድቻ አሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራን የቀጠረው ወላይታ ድቻ ሁለት የአማካይ ስፍራ ተጫዋቾችን ወደ ክለቡ ማቀላቀሉን በድጋሚ የሶከር ኢትዮጵያ ድረ ገፅ አስነብቧል። አስቀድሞ አማካዩን ዘላለም ኢሳያስን የመጀመሪያ ፈራሚ ያደረጉ ሲሆን አሁን ደግሞ ሰለሞን ወዴሳ እና ነጋሽ ታደሰን በሁለት ዓመት ስምምነት ወደ ክለቡ አምጥቷል። የተከላካይ አማካዩ ሰለሞን ወዴሳ በሀዋሳ ከተማ ወጣት ቡድን ከ17 እና 20 ዓመት ቡድን የተገኘ ተጫዋች ሲሆን በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ሀዋሳን ከለቀቀ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ መድን አምርቶ በክለቡ ጥሩ የውድድር ጊዜን አሳልፏል። ሌላው የክለቡ አዲስ ፈራሚ ነጋሽ ታደሰ እንደ ሰለሞን ሁሉ በሀዋሳ ወጣት ቡድን የእግር ኳስ ህይወቱን ጅማሮ ያደረገ ሲሆን በሀዋሳ ዋናው ቡድን ውስጥም በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ካደገ በኃላ ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴን ያደረገ ተጫዋች ነው። እስከ አሁን ሦስት አዳዲስ ተጫዋችን ያስፈረሙት የጦና ንቦቹ የነባር ተጫዋቾችን ውል ለማራዘምም በእንቅስቃሴ ላይ የሚገኙ ሲሆን በአዳማ እየተደረገ ያለውን ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ እየተመለከቱ የሚገኙት አሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ በርከት ያሉ ወጣቶችን ለማሳደግ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ከሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል። ሴካፋ ከ15 ዓመት በታች በሳምንቱ ተነግረው ጆሮ ገብ ከሆኑ ዜናዎች መካከል አንዱ የሆነው ከ15 ዓመት በታች የሴካፋ ውድድር ነው። በዚህም በኤርትራ አዘጋጅነት በሚካሄደው ውድድር ላይ ተሳታፊ የሚሆነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን አስመልክቶ መግለጫ ተሰጥቶ ነበር። የፌደሬሽኑ የቴክኒክ እና ልማት ክፍል ኃላፊ አቶ መኮንን ኩሩ ስለ ውድድሩ ገለፃ ባደረጉበት ወቅት እንደተናገሩት፤ ከዚህ ቀደም ከ11 ዓመት በታች ቡድን ወደ ቻይና ተልኮ ጥሩ እንቅስቃሴ አሳይቷል። አሁን ደግሞ በአገሪቷ ለመጀመሪያ ጊዜ ተብሎ በሚታሰበው የእድሜ እርከን ቡድን ተዋቅሮ ወደ ኤርትራ ተልኳል። ብሔራዊ ቡድኑ በመጀመሪያ ከሴካፋ ጥሪ የደረሰው በሰኔ ወር መጨረሻ አካባቢ ነው። ይህም የተጣበበ ጊዜ እንዲፈጠር የሆነው ደግሞ የውድድሩ አዘጋጅ ኤርትራ ውድድሩን ለማከናወን ቶሎ ፈቅዳ ምላሽ ስላልሰጠች ነበር። ቢሆንም ግን ቡድኑ ዝግጅቱን ቀደም ብሎ በሐምሌ ወር መጀመሪያ ማድረግ ጀምሯል። እንደ አቶ መኮንን ገለፃ፤ በኢትዮጵያ በዚህ የእድሜ እርከን የሚወዳደር ሊግ የለም። እንደ አማራጭ የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌደሬሽን ሲያወዳድር ቢቆይም ሙሉ ለሙሉ ከዛ ውድድር ብቻ የተውጣጣ ብሔራዊ ቡድን መገንባት አስፈላጊ ሆኖ አልተገኘም። በዚህ ምክንያት ሁለት አማራጮች መመልከት አስፈላጊ ሆኗል። የመጀመሪያው የነበረው የኮፓ ኮካኮላ ውድድር ነበር። ‹‹በዚህ ውድድር ጥሩ ነገር እናገኛለን ብለን አስበን ነበረ›› ያሉት አቶ መኮንን ነገር ግን ሰዎችን አሰማርተው በየውድድር ስፍራው የተመለከቱት ነገር አጥጋቢ እንዳልነበር ገልፀዋል። ምክንያቱ ደግሞ በየውድድሮቹ የነበረው የክልሎች የእድሜ ጉዳይ ችግር ስለነበረበት ነው። እንደ ሁለተኛ አማራጭም በየክልሉ ያሉ ተጨዋቾችን በመሰብሰብ ምልመላ ለማድረግ ተሞክሯል። በዚህም ከ400 በላይ ተጨዋቾችን ከየክልሎቹ ተሰብስበው በምልመላው ውስጥ ተሳታፊ ሆነዋል። በዚህም 92 ተጫዋቾችን ወደ አዲስ አበባ ተጠርተው ወደ ሁለተኛ ዙር መረጣ ተገብቷል። ምልመላውም በወጣቶችና ስፖርት አካዳሚ ለሦስት ቀናት ተደርጎ 20 ተጨዋቾች ተለይተዋል።አዲስ ዘመን ነሃሴ 12/2011 ዳግም ከበደ
https://www.press.et/Ama/?p=16357
801
2ስፖርት
የመጀመሪያው የግማሽ ፍጻሜ ፍልሚያ
ስፖርት
April 29, 2019
22
እአአ 2005 የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ የእንግሊዙ ሊቨርፑል ከጣሊያኑ ኤ ሲ ሚላን ተገናኙ። እስከ መጀመሪያው የጨዋታ አጋማሽ የጣሊያኑ ክለብ 3 ለምንም በሆነ ጨዋታ ሲመራ ቆየ። ከሁለተኛው አጋማሽ በኋላ ግን ቀያዮቹ በጄራርድ የመጀመሪያ ጎል አስቆጣሪነትና አነቃቂነት አከታትለው ባስቆጠሯቸው ግቦች በእኩል ውጤት መደበኛው የጨዋታ ሰዓት ተጠናቀቀ። በሰጠው የመለያ ምትም የእንግሊዙ ክለብ በሻምፒዮንስ ሊግ መድረክ አምስተኛ ዋንጫውን አነሳ። ይህ ውጤት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ በአዲስ መልክ ከተቋቋመ ጀምሮ የሊቨርፑልን ዋንጫ ያለማንሳት ቁጭቱን ባይሽረውም፤ ከሊጉ ክለቦች ግን በቀዳሚ ስፍራ እንዲገኝ ያስችለዋል። እአአ 2007 እና 2018 ክለቡ ከፍጻሜው የደረሰ ይሁን እንጂ ዳግም ዋንጫውን ለማንሳት ግን አልታደለም። እእአ በ2015 በበርሊን በተካሄደው የሻምፒዮንስ ሊጉ የፍጻሜ ጨዋታ የስፔኑ ባርሴሎና አሸናፊ በመሆን ዋንጫውን አነሳ። በግማሽ ፍጻሜው የስፔኑን ሪያል ማድሪድን በመርታት ለፍጻሜው ጨዋታ የበቁት አሮጊቷ 3ለ1 በሆነ ውጤት በመረታት ነበር ወደ ጣሊያን የተመለሱት። በዚህ ጨዋታ የአምስተኛ ዋንጫ ባለቤት የሆነው ባርሴሎና የእንግሊዙ ሊቨርፑል ለዓመታት የያዘውን ደረጃ እንዲጋራ ምክንያት ሆኗል። ሁለቱ ክለቦች በሻምፒዮንስ ሊግ ሰንጠረዥ፤ ለአምስት ጊዜያት ዋንጫውን በማንሳት እንዲሁም በእኩል ለሶስት ጊዜያት ለፍጻሜ በመድረስ ተመሳሳይ ታሪክ ይጋራሉ። በእርግጥ ዋንጫውን በማንሳት ቅድሚያ ታሪክ የጻፈው የእንግሊዙ ክለብ ነው፤ የስፔኑ ክለብ የመጀመሪያውን ዋንጫ ከማንሳቱ በፊትም አራት የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫዎችን የግሉ ማድረግ ችሏል። እአአ 2005 እና 2006 ደግሞ ሁለቱ ክለቦች ተከታትለው የመድረኩን ክብር መጎናጸፍ ችለዋል። የዘንድሮው የአውሮፓ ሻምፒዮንስ፤ በሩብ ፍጻሜው የደርሶ መልስ ውጤት ፖርቶን 6ለ1 የረቱት ቀያዮቹ፣ በድምር ውጤት ማንቺስተር ዩናይትድን 4ለ0 ካሸነፉት ካታላኖቹ ጋር በግማሽ ፍጻሜው አገናኝቷል። ክለቦቹን በድጋሚ ባገናኘው በዚህ ፍልሚያ ከሁለት አንዳቸው ግማሽ ፍጻሜውን አልፈው በዋንጫ ጨዋታው ድል የሚያስመዘግቡ ከሆነም በሰንጠረዡ የደረጃ መሸጋሸግ የሚፈጠርም ይሆናል። ነገ በካምፕ ኑ ከነገ በስቲያ በሚካሄደው ጨዋታ ላይም አንድ እግራቸውን ወደ ፍጻሜው ጨዋታ ለማሳለፍ የሚገናኙ ይሆናል። ያለፈው ዓመት ለፍጻሜ ደርሰው በሪያል ማድሪድ ሽንፈት የደረሰባቸው የየርገን ክሎፕ ልጆች የዘንድሮ ግስጋሴያቸው የፕሪምየር ሊጉን ብቻም ሳይሆን የሻምፒዮንስ ሊጉንም ዋንጫ ለማንሳት በመሆኑ ብርቱ ፉክክር እንደሚያደርጉ እርግጥ ነው። ቁልፍ ተጫዋቾቹ፤ መሃመድ ሳላህ፣ ሳዲዮ ማኔ፣ ሮቤርቶ ፈርሚኖ እንዲሁም ቨርጅል ቫን ዳይክ ደግሞ በጥምረት ክለባቸውን ለስኬት እንደሚያበቁ ተስፋ ተጥሎባቸዋል። የክለቡ ፊትአውራሪ የሆኑት የርገን ክሎፕ ለተከታታይ ዓመት ግማሽ ፍጻሜውን በመቀላቀላቸው ያላቸውን ደስታ በመግለጽ ተጋጣሚያቸውን ለማቆም እንደሚጫወቱ ነው የገለጹት። የስፔን ላሊጋን በደረጃ ሰንጠረዥ የመሪነት ስፍራ ላይ የሚገኘው ባርሴሎናም የሻምፒዮንስ ሊጉን ዋንጫ ለስድስተኛ ጊዜ ለማንሳት ወጥኗል። በሜዳቸው በሚያደርጉት በዚህ ጨዋታ የበላይነት በመያዝ በመልሱ ጨዋታ ውጤታቸውን የሚያስጠብቁ ከሆነም ፍጻሜውን ለመቀላቀል ቀላሉ መንገድ ይሆንላቸዋል። 65 ዓመታትን ባስቆጠረው የአውሮፓሻምፒዮንስ ሊግ ውድድር የሁለቱ ክለቦች ለበርካታ ጊዜያት ተገናኝተዋል። የመጀመሪያው ግንኙነታቸውም ከ40 ዓመታት በፊት ቀያዮቹ የመጀመሪያውን ዋንጫ ባነሱበት ዓመት ዋዜማ ነው። እአአ 1976 ሊቨርፑል በሜዳው ባደረገው ጨዋታ ላይም ሁለቱ ክለቦች የተለያዩት አንድ እኩል በሆነ ውጤት ነበር። በባርሴሎና ሜዳ በተካሄደው የመልስ ጨዋታም ሁለቱ ክለቦች አንድ እኩል በሆነ ውጤት መለያየታቸውን ተከትሎ ሊቨርፑል በድምር ውጤት ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ ችሏል። እአአ በ2001 የምድብ ጨዋታ ቀያዮቹ በተጋጣሚያቸው ላይ ግብ በማስቆጠሩ ቀዳሚ ቢሆኑም፤ ጨዋታው የተጠናቀቀው ግን በስፔኑ ኃያል ክለብ የበላይነት ነበር። በአንፊልድ በተካሄደው ጨዋታ በመጀመሪያው ግማሽ አንድ እኩል ሆነው ቢቆዩም ባርሴሎናዎች በሁለተኛው ግማሽ አከታትለው ባስቆጠሯቸው ሁለት ግቦች 3ለ1 በሆነ ውጤት ነበር የተለያዩት። በቀጣዩ ዓመት በድጋሚ ኑ ካምፕ ላይ የተገናኙት ሁለቱ ክለቦች ያለምንም ግብ ነበር ጨዋታቸውን ያጠናቀቁት። ባርሴሎናዎች ዋንጫውን ባገኙበት ቀጣዩ ዓመት እአአ በ2007፤ ሁለቱ ክለቦች ተገናኝተው ነበር። ካምፕ ኑ ላይ በተካሄደው ጨዋታ የማሸነፍ ተራው የእንግሊዙ ክለብ በመሆኑ፤ 2ለ1 በሆነ ጠባብ ውጤት ባለሜዳውን ክለብ ከውድድር ውጪ በማድረግ እስከ ፍጻሜ ደርሰዋል።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 21/2011ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=9822
495
2ስፖርት
የእግር ኳስ ተጫዋቾችና የአካል ብቃት
ስፖርት
April 29, 2019
27
ዘመናዊው ዓለም ስፖርትን ከአካል እንቅስቃሴ፣ ውድድር እና መዝናኛነቱ ባለፈ፤ ከትምህርት፣ ከጥናትና ምርምር፣ ከማህበራዊ ህይወት፣ ከኢኮኖሚ፣ ከቴክኖሎጂ፣… ጋር ያያይዘዋል። በተለይ ልምምድና ስልጠናን ዘመናዊ በማድረግ ተፎካካሪና ውጤታማ ለመሆን አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም እየተለመደ ነው። እነዚህ የቴክኖሎጂ ውጤቶችም ስፖርተኛው ስላለበት ወቅታዊ አቋም ለማሳወቅ፣ በልምምድና በውድድር ወቅት ያሳየውን ብቃት ለማነጻጸር፣ መስፈርት ለማስቀመጥ፣ ጉዳትን ለመቀነስ እንዲሁም የአሰልጣኞችን ስራ ለማቅለል ዓይነተኛ ሚና ይጫወታሉ። በተወዳጁ የእግር ኳስ ስፖርት በዚህ ወቅት በስፋት ጥቅም ላይ እየዋሉ ከሚገኙት መሳሪያዎች መካከል አንዱ የተጫዋቾችን አቅም የሚለካው «ጂፒኤስ» ነው። ይህ መሳሪያ በእጅ ሊያዝ የሚችል አነስተኛ መጠን ያለው ሲሆን፤ ለመያዣ በተዘጋጀለት መልበሻ ተጫዋቾች ለብሰውት ልምምዳቸውን ያደርጋሉ። አሰልጣኙም ከመሳሪያው ጋር በሚገናኝ ኮምፒውተር አማካኝነት ተጫዋቹ በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ እየለካ ግብረመልስ ይሰጣል። ኢትዮጵያ ውጤታማ ባልሆነችበት በዚህ ስፖርት በባለሙያዎች እንደ ድክመት ከሚነሱት መካከል አንዱ የተጫዋቾች የአካል ብቃት ደረጃ ማነስ ነው። በአንድ ወቅት ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ቆይታ ያደረጉት የስፖርት ሳይንስ ባለሙያ ዶክተር ኤሊያስ አቢሻክራ፤ ለስልጠና መሰረታዊ ነገር የአካል ብቃት ሆኖ ሳለ በኢትዮጵያ ያለው ግን ከዚህ በተቃራኒ እንደሆነ በማንሳት ሃሳቡን ያጠናክራሉ። እርሳቸው በዘመናዊ መሳሪያ ታግዘው በአምስት ክለቦች ባደረጉት ልኬት ችግር መኖሩን ተገንዝበዋል። ከ17ዓመት በታች ቡድን የተመለከቱትም፤ ጥቂት የሚሆኑት በዓለም አቀፍ ደረጃ በእድሜያቸው የሚጠበቀውን ፍጥነት የሚያሟሉ መሆኑን ነው። ግማሾቹ የተሻለ ሰዓት ሲኖራቸው በተቀሩት ደግሞ ቢሰራባቸው ፈጣን መሆን ይችላሉ። በአውሮፓ አካዳሚ ባለው ተሞክሮም፤ አንድ የ14ዓመት ታዳጊ፤ በሰዓት 17ኪሎ ሜትሮችን ይሸፍናል። በኢትዮጵያ አዋቂ የሚባሉት ተጫዋቾች ግን በሰዓት 13 ኪሎ ሜትር ብቻ ይሮጣሉ። ይህ ደግሞ ተጫዋቾችን ለ70ደቂቃ ብቻ ነው ለመጫወት የሚያስችላቸው። ከዚህ በመነሳትም አውሮፓውያኑ እድሜያቸው እየጨመረ ሲሄድ ቅልጥፍናቸው ሲጨምር፤ በአንጻሩ ኢትዮጵያውያን እየተዳከሙ እንደሚሄዱ ነው መረጃው የሚያሳው። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ሳይንስ መምህር የሆኑት ዶክተር ዘሩ በቀለ በመሳሪያው የተጫዋቾችን ብቃት በመለካት ላይ የሚገኙ ባለሙያ ናቸው። የኢትዮጵያውያን ተጫዋቾች የአካል ብቃት በምን ዓይነት ሁኔታ ላይ ይገኛል የሚለውን በተደራጀ መልኩ ማግኘት እንደማይቻል ይገልጻሉ። ሊኖር የሚችለው ምናልባትም በዚህ ዙሪያ ጥናት ባደረጉ ግለሰቦች እጅ አሊያም አሰልጣኞች ጋር ነው። ከዚህ ባሻገር ከ17 ዓመት በታች እንደ ስታንዳርድ የተቀመጠውን ብቻ ነው ማግኘት የሚቻለው። ከዚህ ባለፈ የተቀመጠ ልኬት ባይኖርም ለወደፊት ብሄራዊ ቡድኖች ደረጃ ይቀመጥላቸው ይሆናል የሚል ሃሳብ አላቸው። ይህንን ችግር ለመፍታት በቀጥታም ባይሆን በተዘዋዋሪ መንገድ የ«ጂፒኤስ» ቴክኖሎጂን መጠቀም ይመከራል። በሌላው ዓለም ይህንን መሰል መሳሪያ በፕሮፌሽናሎች ብቻም ሳይሆን በተራ ስፖርተኞችም ደረጃ እየተጠቀሙት እንደሚገኙ ዶክተር ዘሩ ይጠቁማሉ። በብዛት ገበያ ላይ የሚገኘው መሳሪያው የተጫዋቾችን ውሳጣዊና ውጫዊ የልምምድ ጫና እስከመለካትም የሚደርስ ነው። መሳሪያው የተጫዋቾችን ሁኔታ በመመዝገብና በመተንተን ግብዓት የሚሰጥ በመሆኑ በአሰልጣኝ ላይ የሚኖረውን ጫና የሚቀንስ ነው። የአሰልጣኙ ስራ የሚሆነውም የተጫዋቾችን ብቃት መጨመር ነው። አሁን ባለው ሁኔታ አሰልጣኞች የ11ተጫዋቾችን ሁኔታ በትክክል መገምገም አይችሉም፤ መሳሪያው ግን እያንዳንዱ ተጫዋች በእያንዳንዱ ደቂቃ የነበረውን ሁኔታ የሚያሳይ ነው። ተጫዋቾች ከውድድር ውድድር ያላቸውን አቅምም ያነጻጽራል።በአሰልጣኞችና ተጫዋቾች መካከል የሚነሳውን ጭቅጭቅ የሚያስወግድ ሲሆን፤ ተጫዋቾች ከልምምድ ብዛት ወደ ጉዳት እንዳይገቡ ይታደጋል። ቡድኖች በመሳሪያው ልኬት መሰረት የራሳቸውን ምርጥ ማውጣት አሊያም ከፕሮፌሽናል ተጫዋቾች አኳያ ማነጻጸር ይቻላል። ከዚህ ባሻገር ከውድድር አስቀድሞ አሊያም ውድድሮች በመጠናቀቅ ላይ እያሉ ተደጋጋሚ ልኬቶችን መውሰድ መስፈርቶችን ለማስቀመጥ እንደሚችልም ዶክተር ዘሩ ያስረዳሉ። ለዚህም የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን 50 የመለኪያ መሳሪያዎችን ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መለገሱ የሚታወቅ ነው። 60ግራም የሚመዝነው ይህ መሳሪያ፤ «ካታፑልት ጂፒኤስ» ይሰኛል። እጅግ ዘመናዊ በመሆኑም የሰውነት ብቁነትን ሲለካ፣ ለታክቲካዊ ትንተናዎች የሚረዱ ግብዓቶችንም ይሰጣል። አንድ ተጫዋች የሚሸፍነው ርቀት፣ ያስመዘገበውን ፍጥነት፣ ጉልበት እና መሰል መረጃዎችን በማጠናቀርም፤ በአንድ ሰከንድ ውስጥ 1ሺ የሚጠጉ መረጃዎችን የመመዝገብ አቅም አለው። ከመሳሪያው የሚሰበሰበው ይህ መረጃም በቀጣይ የሚኖሩ የልምምድ መርሃ ግብሮችን ለመቅረጽ እንዲሁም የተጫዋቾችን ጤንነት በመጠበቅ ከጉዳት ለመከላከል እንደሚውልም ፌዴሬሽኑ ተስፋ አድርጓል። መሳሪያው ለመጀመሪያ ጊዜ በኦሊምፒክ ማጣሪያ ጨዋታ ላይ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ተጫዋቾች ልምምድ ላይ መተግበሩ የሚታወስ ነው። በእርግጥ መረጃውን ለመስጠት ተደጋጋሚ ልኬቶችን ማድረግ አስፈላጊ ቢሆንም፤ በትግበራው ምን ታይቷል የሚለውን ግን መጥቀስ ይቻላል። ቡድኑ ወደ ውድድር ከመግባቱ አስቀድሞ በተደረጉት የተወሰኑ ልኬቶች፤ ተጫዋቾቹ በአንድ ደቂቃ ምን ያህል ርቀት መሸፈን ይችላሉ የሚለው መታየቱን ዶክተርዘሩ ይጠቅሳሉ። በዚህም መሰረት ለማረጋገጥ የተቻለው አብዛኛዎቹ ተጫዋቾች ከአማካይ በላይ የሚሸፈኑ መሆኑን ነው። በጨዋታ ወቅት ለማየት እንደተቻለው ከሆነም ተጫዋቾቹ በሜዳ ላይ ጥሩ እንቅስቃሴ እንዳላቸው ነው። ጥቂት ነገር የሚቀራቸው ተጫዋቾችም ተለይተውበታል፤ ከዚህ ባሻገር ግን ተጫዋቾቹ በወቅታዊ አቋማቸው ከተቀመጡት መስፈርቶች አብዛኛውን የሚያሟሉ ነበሩ። የቡድኑ ዋና አሰልጣኝም ይህንን ልኬት እንደ ግብዓት በመጠቀም አሰላለፏ ላይ ተግባራዊ ማድረጓንም ዶክተር ዘሩ ያስታውሳሉ። ከብሄራዊ ቡድኖች ባሻገር ክለቦችም መሳሪያው ቢኖራቸው ደግሞ ተጫዋቾቻቸውን ለብሄራዊ ቡድን ለማስመረጥ የሚጠቀሙበት ይሆናል። የብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝም ተጫዋቹ በጨዋታዎች ላይ የሚያሳየውን አቋም በመሳሪያው አማካኝነት በመገምገም ግብረመልስ ሊሰጥና ከክለቡ ጋርም ሊወያይ ይችላል። ይህም የብሄራዊ ቡድን አሰልጣኞች በየጨዋታው ተገኝተው ተጫዋቾችን ለመምረጥ የሚያደርጉትን ጥረት በመቀነስ፤ መረጃዎች ላይ ተመስርተው ስራቸውን ለማከናወን የሚጠቅማቸው ይሆናል። ጠንካራ እና ደካማ ጎኖችን በመለየት ከአጨዋወቱ ጋር የሚሄደውን ተጫዋች እያዘጋጁ መሄድም ያስችላል። በርካታ ጥቅሞች ያሉት ይህ መሳሪያ በቀጣይ በምን መልኩ ተግባር ላይ ይውላል ለሚለውም፤ በዚህ ጉዳይ ከብሄራዊ ቡድን አሰልጣኞች ጋር ውይይት እንደሚደረግ ዶክተር ዘሩ ይጠቁማሉ። ክለቦችም ራሳቸውን ችለው በዚህ መሳሪያ ተጠቃሚ መሆን እንዲችሉ ስልጠና የመስጠት እቅድ አለ። ክለቦች መሳሪያውን ለመግዛት ብዙም የሚቸግራቸው አይሆንም፤ ስለዚህም በአጭር ጊዜ ስልጠና ወደ ተግባር የሚገቡበትን ሁኔታ ማመቻቸት ይቻላል። ክለቦች ይህንን ነገር መጠቀም ከቻሉም እንደ ሃገር ስታንዳርዶችን ለማውጣት የሚረዳ ይሆናል። የትኞቹ ጠንካራ የትኞቹ ደግሞ ደካማ ተጫዋቾች ናቸው የሚለውንም በዚህ መለየት እንደሚያስችልም ነው ተስፋ የተጣለበት።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 21/2011ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=9820
755
2ስፖርት
የትምህርት ቤቶች ውድድር መቀዛቀዝ ተተኪ ስፖርተኞች እንዳናፈራ አድርጓል
ስፖርት
April 29, 2019
21
20 ዓመት ወዲህ ያለው የትምህርት ቤቶች ውድድር መቀዛቀዙ የሀገሪቱን ዕምቅ የስፖርት አቅም እንዳንጠቀም እንቅፋት የፈጠረ መሆኑን አንድ ጥናት አመለከተ። የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ከሰላም ሚኒስቴር፣ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴርና ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በመሆን “የስፖርታዊ ጨዋነት ምንጮች” በሚል ፅንሰ ሃሳብ ለሁለት ቀናት በተካሄደው ውይይት ላይ የቀረበው ጥናት እንዳመለከተው በኢትዮጵያ ከሃምሳ አመት በፊት የነበሩ የትምህርት ቤት ውድድሮች ጠንካራ ስፖርተኞችን ከማፍራት አንጻር የተሻለ ውጤታማ ነበሩ:: ጥናታዊ ጽሁፉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ሳይንስ መምህር ዶክተር ዘሩ በቀለ የቀረበ ሲሆን፤ ከ20 ዓመት ወዲህ ያለው የትምህርት ቤቶች ውድድር ባለመጠናከሩ የሀገሪቱ ዕምቅ የስፖርት አቅም ቀንሷል። የትምህርት ቤቶችና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ስፖርት ውድድሮችን አስመልክቶም ግልፅ ችግሮች ቀርበዋል። ዶክተር ዘሩ እንደገለፁት የችግሩ ዋነኛ ምክንያት የትምህርት አደረጃጀቱ የስፖርት ስነ-ምግባርን የዘነጋ መሆኑ ነው:: በዚህም «ያልሰራነውን ነገር እየጠበቅን ነው የምንገኘው፤ ትምህርት ቤቶችን ገድለናቸዋል» ሲሉ ገልጸዋል። ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ በስብሰባዎች የትምህርት ፖሊሲው ይስተካከል ሲባል በፌዝ መልኩ እንደሚታይ የጠቀሱት ዶክተር ዘሩ፤ አሁን እየተፈጠረ ያለው ትውልድ በስፖርት ስነ-ምግባር ያልታነፀ እንዲሆን አድርጎታል ብለዋል:: በአሁኑ ወቅት በሃገሪቱ የሚታዩ የስፖርታዊ ጨዋነት ችግሮችም በዚህ ማዕቀፍ ውስጥ ማለፍ ባለመቻሉ የተፈጠሩ መሆናቸውን ነው በጥናታቸው ያመለከቱት:: ስለዚህም ውጤታማ ወደ ነበረውና ትምህርት ቤቶች ለስፖርት ትምህርት በቂ ጊዜ እንዲሰጡ ማድረግ ይገባል ያሉት ዶክተር ዘሩ የውስጥ (የክፍል) ውድድሮችን እያደረጉ ወደ ወረዳ፣ ክፍለ ከተማ እንዲሁም ሀገር አቀፍ ውድድሮች ማደግ አለባቸው ብለዋል። ይህም በግለሰቦች ይሁንታ ሳይሆን በህገ በደንብ መቀመጥ እንዳለበት ጥናት አቅራቢው አስግነዝበዋል። በመድረኩ ላይም በስፖርታዊ ጨዋነት ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን፤ የብሄር ጽንፈኝነት፣ የፌዴሬሽንና የክለቦች አደረጃጀት ችግር፣ የውድድር ፎርማት፣ ሙስና፣ የህግ የበላይነትን አለማክበር፣ የተሳሳተና ኃላፊነት የጎደለው የመረጃ ስርጭት፣… አሁን ላይ ለስፖርታዊ ጨዋነት መደፍረስ እንደ ሁነኛ ምክንያቶች ተነስተዋል። በመሆኑም እነዚህን ችግሮች ሁሉ ሊፈታ የሚችል ራሱን የቻለ የስፖርት ህግ ማዕቀፍ ሊኖር እንደሚገባ ተገልጿል።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 21/2011ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=9824
259
2ስፖርት
የእግር ኳስ ተጫዋቾችና የአካል ብቃት
ስፖርት
April 29, 2019
16
ዘመናዊው ዓለም ስፖርትን ከአካል እንቅስቃሴ፣ ውድድር እና መዝናኛነቱ ባለፈ፤ ከትምህርት፣ ከጥናትና ምርምር፣ ከማህበራዊ ህይወት፣ ከኢኮኖሚ፣ ከቴክኖሎጂ፣… ጋር ያያይዘዋል። በተለይ ልምምድና ስልጠናን ዘመናዊ በማድረግ ተፎካካሪና ውጤታማ ለመሆን አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም እየተለመደ ነው። እነዚህ የቴክኖሎጂ ውጤቶችም ስፖርተኛው ስላለበት ወቅታዊ አቋም ለማሳወቅ፣ በልምምድና በውድድር ወቅት ያሳየውን ብቃት ለማነጻጸር፣ መስፈርት ለማስቀመጥ፣ ጉዳትን ለመቀነስ እንዲሁም የአሰልጣኞችን ስራ ለማቅለል ዓይነተኛ ሚና ይጫወታሉ። በተወዳጁ የእግር ኳስ ስፖርት በዚህ ወቅት በስፋት ጥቅም ላይ እየዋሉ ከሚገኙት መሳሪያዎች መካከል አንዱ የተጫዋቾችን አቅም የሚለካው «ጂፒኤስ» ነው። ይህ መሳሪያ በእጅ ሊያዝ የሚችል አነስተኛ መጠን ያለው ሲሆን፤ ለመያዣ በተዘጋጀለት መልበሻ ተጫዋቾች ለብሰውት ልምምዳቸውን ያደርጋሉ። አሰልጣኙም ከመሳሪያው ጋር በሚገናኝ ኮምፒውተር አማካኝነት ተጫዋቹ በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ እየለካ ግብረመልስ ይሰጣል። ኢትዮጵያ ውጤታማ ባልሆነችበት በዚህ ስፖርት በባለሙያዎች እንደ ድክመት ከሚነሱት መካከል አንዱ የተጫዋቾች የአካል ብቃት ደረጃ ማነስ ነው። በአንድ ወቅት ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ቆይታ ያደረጉት የስፖርት ሳይንስ ባለሙያ ዶክተር ኤሊያስ አቢሻክራ፤ ለስልጠና መሰረታዊ ነገር የአካል ብቃት ሆኖ ሳለ በኢትዮጵያ ያለው ግን ከዚህ በተቃራኒ እንደሆነ በማንሳት ሃሳቡን ያጠናክራሉ። እርሳቸው በዘመናዊ መሳሪያ ታግዘው በአምስት ክለቦች ባደረጉት ልኬት ችግር መኖሩን ተገንዝበዋል። ከ17ዓመት በታች ቡድን የተመለከቱትም፤ ጥቂት የሚሆኑት በዓለም አቀፍ ደረጃ በእድሜያቸው የሚጠበቀውን ፍጥነት የሚያሟሉ መሆኑን ነው። ግማሾቹ የተሻለ ሰዓት ሲኖራቸው በተቀሩት ደግሞ ቢሰራባቸው ፈጣን መሆን ይችላሉ። በአውሮፓ አካዳሚ ባለው ተሞክሮም፤ አንድ የ14ዓመት ታዳጊ፤ በሰዓት 17ኪሎ ሜትሮችን ይሸፍናል። በኢትዮጵያ አዋቂ የሚባሉት ተጫዋቾች ግን በሰዓት 13 ኪሎ ሜትር ብቻ ይሮጣሉ። ይህ ደግሞ ተጫዋቾችን ለ70ደቂቃ ብቻ ነው ለመጫወት የሚያስችላቸው። ከዚህ በመነሳትም አውሮፓውያኑ እድሜያቸው እየጨመረ ሲሄድ ቅልጥፍናቸው ሲጨምር፤ በአንጻሩ ኢትዮጵያውያን እየተዳከሙ እንደሚሄዱ ነው መረጃው የሚያሳው። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ሳይንስ መምህር የሆኑት ዶክተር ዘሩ በቀለ በመሳሪያው የተጫዋቾችን ብቃት በመለካት ላይ የሚገኙ ባለሙያ ናቸው። የኢትዮጵያውያን ተጫዋቾች የአካል ብቃት በምን ዓይነት ሁኔታ ላይ ይገኛል የሚለውን በተደራጀ መልኩ ማግኘት እንደማይቻል ይገልጻሉ። ሊኖር የሚችለው ምናልባትም በዚህ ዙሪያ ጥናት ባደረጉ ግለሰቦች እጅ አሊያም አሰልጣኞች ጋር ነው። ከዚህ ባሻገር ከ17 ዓመት በታች እንደ ስታንዳርድ የተቀመጠውን ብቻ ነው ማግኘት የሚቻለው። ከዚህ ባለፈ የተቀመጠ ልኬት ባይኖርም ለወደፊት ብሄራዊ ቡድኖች ደረጃ ይቀመጥላቸው ይሆናል የሚል ሃሳብ አላቸው። ይህንን ችግር ለመፍታት በቀጥታም ባይሆን በተዘዋዋሪ መንገድ የ«ጂፒኤስ» ቴክኖሎጂን መጠቀም ይመከራል። በሌላው ዓለም ይህንን መሰል መሳሪያ በፕሮፌሽናሎች ብቻም ሳይሆን በተራ ስፖርተኞችም ደረጃ እየተጠቀሙት እንደሚገኙ ዶክተር ዘሩ ይጠቁማሉ። በብዛት ገበያ ላይ የሚገኘው መሳሪያው የተጫዋቾችን ውሳጣዊና ውጫዊ የልምምድ ጫና እስከመለካትም የሚደርስ ነው። መሳሪያው የተጫዋቾችን ሁኔታ በመመዝገብና በመተንተን ግብዓት የሚሰጥ በመሆኑ በአሰልጣኝ ላይ የሚኖረውን ጫና የሚቀንስ ነው። የአሰልጣኙ ስራ የሚሆነውም የተጫዋቾችን ብቃት መጨመር ነው። አሁን ባለው ሁኔታ አሰልጣኞች የ11ተጫዋቾችን ሁኔታ በትክክል መገምገም አይችሉም፤ መሳሪያው ግን እያንዳንዱ ተጫዋች በእያንዳንዱ ደቂቃ የነበረውን ሁኔታ የሚያሳይ ነው። ተጫዋቾች ከውድድር ውድድር ያላቸውን አቅምም ያነጻጽራል።በአሰልጣኞችና ተጫዋቾች መካከል የሚነሳውን ጭቅጭቅ የሚያስወግድ ሲሆን፤ ተጫዋቾች ከልምምድ ብዛት ወደ ጉዳት እንዳይገቡ ይታደጋል። ቡድኖች በመሳሪያው ልኬት መሰረት የራሳቸውን ምርጥ ማውጣት አሊያም ከፕሮፌሽናል ተጫዋቾች አኳያ ማነጻጸር ይቻላል። ከዚህ ባሻገር ከውድድር አስቀድሞ አሊያም ውድድሮች በመጠናቀቅ ላይ እያሉ ተደጋጋሚ ልኬቶችን መውሰድ መስፈርቶችን ለማስቀመጥ እንደሚችልም ዶክተር ዘሩ ያስረዳሉ። ለዚህም የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን 50 የመለኪያ መሳሪያዎችን ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መለገሱ የሚታወቅ ነው። 60ግራም የሚመዝነው ይህ መሳሪያ፤ «ካታፑልት ጂፒኤስ» ይሰኛል። እጅግ ዘመናዊ በመሆኑም የሰውነት ብቁነትን ሲለካ፣ ለታክቲካዊ ትንተናዎች የሚረዱ ግብዓቶችንም ይሰጣል። አንድ ተጫዋች የሚሸፍነው ርቀት፣ ያስመዘገበውን ፍጥነት፣ ጉልበት እና መሰል መረጃዎችን በማጠናቀርም፤ በአንድ ሰከንድ ውስጥ 1ሺ የሚጠጉ መረጃዎችን የመመዝገብ አቅም አለው። ከመሳሪያው የሚሰበሰበው ይህ መረጃም በቀጣይ የሚኖሩ የልምምድ መርሃ ግብሮችን ለመቅረጽ እንዲሁም የተጫዋቾችን ጤንነት በመጠበቅ ከጉዳት ለመከላከል እንደሚውልም ፌዴሬሽኑ ተስፋ አድርጓል። መሳሪያው ለመጀመሪያ ጊዜ በኦሊምፒክ ማጣሪያ ጨዋታ ላይ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ተጫዋቾች ልምምድ ላይ መተግበሩ የሚታወስ ነው። በእርግጥ መረጃውን ለመስጠት ተደጋጋሚ ልኬቶችን ማድረግ አስፈላጊ ቢሆንም፤ በትግበራው ምን ታይቷል የሚለውን ግን መጥቀስ ይቻላል። ቡድኑ ወደ ውድድር ከመግባቱ አስቀድሞ በተደረጉት የተወሰኑ ልኬቶች፤ ተጫዋቾቹ በአንድ ደቂቃ ምን ያህል ርቀት መሸፈን ይችላሉ የሚለው መታየቱን ዶክተርዘሩ ይጠቅሳሉ። በዚህም መሰረት ለማረጋገጥ የተቻለው አብዛኛዎቹ ተጫዋቾች ከአማካይ በላይ የሚሸፈኑ መሆኑን ነው። በጨዋታ ወቅት ለማየት እንደተቻለው ከሆነም ተጫዋቾቹ በሜዳ ላይ ጥሩ እንቅስቃሴ እንዳላቸው ነው። ጥቂት ነገር የሚቀራቸው ተጫዋቾችም ተለይተውበታል፤ ከዚህ ባሻገር ግን ተጫዋቾቹ በወቅታዊ አቋማቸው ከተቀመጡት መስፈርቶች አብዛኛውን የሚያሟሉ ነበሩ። የቡድኑ ዋና አሰልጣኝም ይህንን ልኬት እንደ ግብዓት በመጠቀም አሰላለፏ ላይ ተግባራዊ ማድረጓንም ዶክተር ዘሩ ያስታውሳሉ። ከብሄራዊ ቡድኖች ባሻገር ክለቦችም መሳሪያው ቢኖራቸው ደግሞ ተጫዋቾቻቸውን ለብሄራዊ ቡድን ለማስመረጥ የሚጠቀሙበት ይሆናል። የብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝም ተጫዋቹ በጨዋታዎች ላይ የሚያሳየውን አቋም በመሳሪያው አማካኝነት በመገምገም ግብረመልስ ሊሰጥና ከክለቡ ጋርም ሊወያይ ይችላል። ይህም የብሄራዊ ቡድን አሰልጣኞች በየጨዋታው ተገኝተው ተጫዋቾችን ለመምረጥ የሚያደርጉትን ጥረት በመቀነስ፤ መረጃዎች ላይ ተመስርተው ስራቸውን ለማከናወን የሚጠቅማቸው ይሆናል። ጠንካራ እና ደካማ ጎኖችን በመለየት ከአጨዋወቱ ጋር የሚሄደውን ተጫዋች እያዘጋጁ መሄድም ያስችላል። በርካታ ጥቅሞች ያሉት ይህ መሳሪያ በቀጣይ በምን መልኩ ተግባር ላይ ይውላል ለሚለውም፤ በዚህ ጉዳይ ከብሄራዊ ቡድን አሰልጣኞች ጋር ውይይት እንደሚደረግ ዶክተር ዘሩ ይጠቁማሉ። ክለቦችም ራሳቸውን ችለው በዚህ መሳሪያ ተጠቃሚ መሆን እንዲችሉ ስልጠና የመስጠት እቅድ አለ። ክለቦች መሳሪያውን ለመግዛት ብዙም የሚቸግራቸው አይሆንም፤ ስለዚህም በአጭር ጊዜ ስልጠና ወደ ተግባር የሚገቡበትን ሁኔታ ማመቻቸት ይቻላል። ክለቦች ይህንን ነገር መጠቀም ከቻሉም እንደ ሃገር ስታንዳርዶችን ለማውጣት የሚረዳ ይሆናል። የትኞቹ ጠንካራ የትኞቹ ደግሞ ደካማ ተጫዋቾች ናቸው የሚለውንም በዚህ መለየት እንደሚያስችልም ነው ተስፋ የተጣለበት።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 21/2011ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=9826
755
2ስፖርት
አጓጊው ፍልሚያ በዛሬው ቀጠሮ
ስፖርት
April 30, 2019
32
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ22ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ በተለያዩ ከተሞች ይከሄዳሉ። በሳምንቱ ተጠባቂ ፍልሚያ በአዲስ አበባ ስታዲየም በቅዱስ ጊዮርጊስና በመቐለ ሰባ እንደርታ መካከል ይካሄዳል። መቐለ ሰባ እንደርታዎች ሃያኛው ሳምንት ወደ በባህር ዳር ዓለም ዓቀፍ ስታዲየም በማቅናት በጣና ሞገዶቹ ከደረሰባቸው የአንድ ለባዶ ሽንፈት አገግመው በቀጣዩ መርሃ ግብር በሜዳቸው አዳማ ከተማን 2 ለ 1 በመርታት ወደ አሸናፊነት መመለሳቸው ይታወሳል። ፈረሰኞቹ በአንፃሩ በሃያኛው ሳምንት መርሃግብር በአዲስ አበባ ስታዲየም የተካሄደውና በአስደማሚ የደጋፊ ድባብ የታጀበው ጨዋታ ሲዳማ ቡናን ሁለት ለባዶ እንዲሁም በቀጣዩ መርሃ ግብር ከሃዋሳን ጋር አቻ ተለያይተዋል። በሊጉ የሻምፒዮናነት ትንቅንቅ ላይ ወሳኝ ውጤት በሚያስገኘው የሁለቱ ከለቦች ፍልሚያ በአብዛኛው ስፖርት አፍቃሪ በጉጉት ይጠበቃል። መቐሌዎች ከፈረሰኞቹ ጋር በሚያደርጉት የዛሬ ጨዋታ ማሸነፍ ከቻሉ ከተከታዮቻቸው ፋሲል ከነማና ሲዳማ ቡና ጋር ያላቸውን የስምንት ነጥብ ልዩነት ማስጠበቅ ይቻላቸዋል። ይህን ጨዋታ በድል ማጠናነቅ ከቻሉም በታሪካቸው የመጀመሪያውን ዋንጫ ወደ ትግራይ ለመውሰድ የሚያደርጉትን ሩጫ ያፋጥንላቸዋል። ፈረሰኞቹ ማሸነፍ ከቻሉ ደግሞ ከመሪው ጋር ያላቸውን የአስራ ሁለት ነጥብ ልዩነት ይቀንሳሉ። ይህም ይበልጥ ወደ ዋንጫው ለመቅረብና ባሳልፈነው ዓመት በጅማ አባጅፋር የተነጠቁትን የሊጉን ዋንጫ ዳግም ለማስመለስ አንድ እርምጃ ያሻግራቸዋል። መቐሌዎች በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ አርባ አምስት ነጥቦችን በመሰብሰብ በቀዳሚነት ይመራሉ። ቅዱስ ጊዮርጊሶች በአንፃሩ በሰላሳ አራት ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ 11:00 ሰዓት ላይ ቀጠሮ ተይዞለታል። ሌላኛው መርሃ ግብር ጎንደር ላይ ፋሲል ከነማን ከድሬዳዋ ከተማ ያገናኛል። በሃያኛው ሳምንት የሊጉ መርሃ ግብር በዐፄ ፋሲለደስ ስታዲየም ከደቡብ ፖሊስ ጋር የተፋለሙትና ጨዋታውን አንድ አቻ በማጠናቀቅ የሊጉን መሪ በቅርብ ርቀት የመከታተላቸውን ሩጫ ያቀዘቀዙት ፋሲሎች፤ በቀጣዩ መርሃ ግብር አዲስ አበባ ላይ መከላከያን አራት ለባዶ በመርታት ወደ አሸናፊነታቸው መመለሳቸው ይታወሳል። ውጤቱም ሲዳማ ቡናን በግብ ልዩነት በመብለጥ ወደ ሁለተኛነት ከፍ እንዲሉ አድርጓቸዋል። በሃያኛው መርሃ ግብር ደደቢትን ሶስት ለሁለት በማሸነፍ በቀጣዩ መርሃ ግብር ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 2ለ በመርታት ተከታታይ ድል ማስመዝገብ የቻሉት ድሬደዋዎች፤ ውጤቱን ተከትሎ ካንዣበባቸው ወራጅ ቀጠና በፍጥነት መራቅ ችለዋል። የዛሬው ጨዋታ በሊጉ የሻምፒዮና ጉዞ ላይ የሞት ሽረት ትግል እያደረጉ የሚገኙት አፄዎቹ እጅጉን ወሳኝ ነው። ከዋንጫው ትንቅንቅ እንዳይረቁ አሸናፊ መሆናቸው የግድ ነው። አሁን በፋሲል ከነማና በመቐለ ሰባ እንደርታ መካከል የስምንት ነጥብ ልዩነት ይታያል። ፋሲሎች ጨዋታውን ማሸነፍ ከቻሉና መሪው የሚሸነፍ ከሆነም ውጤቱ ወደ አምስት ዝቅ ይላል። ብርቱካናማዎቹ በአንፃሩ የአሸናፊነት ጓዟቸውን በማስቀጠል ደረጃቸውን ወደ ሊጉ ሰንጠረዥ አጋማሽ ለማሸጋገር እጅጉን ወሳኝ ይሆናላቸዋል። በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ፋሲል በ37 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ድሬዳዋ በ28 ነጥብ አስረኛ ደረጃን ይዟል። የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ 09:00 ሰዓት ላይ የሚካሄድ ይሆናል። በ22ተኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ የሚካሄደው ሌላው ጨዋታ ጅማ አባ ጅፋርንና ሲዳማ ቡናን የሚያፋልመው ነው። ጅማ አባጅፋሮች በሃያኛው የሊጉ መርሃ ግብር ላለመውረድ የሚታገለውን ሽሬ እንደስላሴን አስተናግደው በሜዳውና በደጋፊው ፊት ሁለት ለባዶ እንዲሁም በ21ኛው ሳምንት መቐለ ላይ ደደቢትን በመግጠም በኦኪኪ ኦፎላቢ ብቸኛ ግብ በማሸነፍ ወደ ሻምፒዮናው ፉክክር መጠጋታቸው ይታወሳል። በዘንድሮው የኢትዮጵያ ፐሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር አስደናቂ ብቃትና ውጤት በማስመዝገብ የሊጉ መሪ እስከመሆን ደርሰው የነበሩት ሲዳማ ቡናዎች በሁለተኛው ዙር ላይ በመዳካም ወሳኝ ነጥቦችን አጥተዋል። በተለይ ለሻምፒዮንነት እየተፎካከረ የሚገኘው ሲዳማ በሃያኛው ሳምንት በቅዱስ ጊዮርጊስ ለደረሰበት የሁለት ለባዶ ሽነፈት መቐሌዎችን በቅርብ ርቀት የሚከተልበትን እድል አምክኖበታል። ይሁንና በ21ኛው ሳምንት ላለመውረድ እየታገለ ያለው ስሑል ሽረን 3-2 በማሸነፉ ወደ ሊጉ ፉክክር መመለሳቸው ይታወሳል። በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ጅማ አባጅፋር በ 34 ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ሲይዝ ተጋጣሚው ሲዳማ ቡና በአንፃሩ በ37 ነጥብ ሶስተኛ ላይ ተቀምጧል። የሁለቱ ክለቦች የዛሬው ጨዋታም ሌላኛው በእግር ኳስ አፍቃሪው ዘንድ በጉጉት የሚጠበቅ ነው። በጨዋታውም ሲዳማዎች የሊጉን ሻምፒዮናነት ጉዞ አሳልፈው ላለመስጠት፤ የዓምናው የሊጉ ሻምፒዮን ጅማዎች ደግሞ ከዋንጫው ትንቅንቅ ላለመራቅ ይፋለሙበታል። ጅማዎች በሜዳቸው እንደ መጫወታቸው ለሲዳማዎች ከባድ የቤት ስራ ሊሆኑ እንደሚችሉም ከወዲሁ ተገምቷል። ጨዋታው ዘጠኝ ሰዓት ላይ ይጀመራል። አዳማ ከተማን ከኢትዮጵያ ቡና የሚያገናኘው ፍልሚያም የ22ተኛ ሳምንት የሊጉ መርሃ ግብር አካል ነው። በሊጉ የዋንጫ ፍልሚያ ወጥ የሆነ አቋም ማሳየት ከሚሳናቸው ቡድኖች አንዱ መሆኑ የሚነገርለት አዳማ ከተማ በሁለተኛ የሊጉ ምዕራፍ ይበልጡን ተዳክሞ ታይቷል። ከሲዳማ ቡና ሽንፈት በኋላ በ20ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በሜዳውና በደጋፊው ፊት ሀዋሳ ከተማን አስተናግዶ ሁለት ለ አንድ ተሸንፏል። በቀጣዩ መርሃ ግብርም ወደ መቐሌ አምርቶ ከመሪው መቐለ ሰባ እንደርታ ጋር ባደረገው ጨዋታ 2 ለ 1 መሸነፉ ይታወሳል። በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ በ26ነጥብ አስራ አንደኛ ላይ የተቀመጠው አዳማ፤ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር የሚያደርገው ጨዋታ ከውጤት ቀውስ ለመውጣት እጅግ ወሳኝ ይሆንለታል። ይህን ማድረግ የሚሳነው ከሆነም አራተኛ ተከታታይ ሽንፈቱን መቀበል ግድ ይለዋል። በሊጉ ወጥ የሆነ አቋም ማሳየት ያልሆነለት የ 2003ቱ የሊጉ ሻምፒዮን ኢትዮጵያ ቡና፤ በሃያኛው ሳምንት በወላይታ ድቻ ከደረሰበት የሁለት ለባዶ ሽንፈት በኋላ በቀጣዩ መርሃ ግብር አዲስ አበባ ላይ ባህር ዳር ከተማን አስተናግዶ አምስት ግቦችን ማስቆጠሩ ይታወቃል። በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ በ 32 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡት ቡናማዎቹ በማራኪ ጨዋታ የጣና ሞገዶቹን የተከላካይ መስመር ተጫዋቾች ያፍረከረኩበት አቋም በአብዛኛው ስፖርት አፍቃሪ ዘንድ ያስጨበጨበላቸው ሲሆን፤ በዛሬ ጨዋታም ይህን ያሳያሉ ተብለው ይጠበቃሉ። በተለይ ከመሪዎቹ ተርታ ላለመራቅ የሚያደርጉትን ሩጫ ለማስቀጠል ይህ ጨዋታ ለቡናማዎቹ እጅጉን ወሳኝ መሆኑ ታምኖበታል። የሊጉ መርሀ ግብር ባህርዳር ከተማን ከደቡብ ፖሊስ ያገናኛል። በሃያኛው ሳምንት በአስደማሚ ደጋፊያቸው ታጅበው በሳላምላክ ተገኝ ብቸኛ ግብ መሪው መቐሌን ያሸነፉት የጣና ሞገዶቹ፤ በቀጣዩ መርሃ ግብር በኢትዮጰያ ቡና የ5ለ0 አስዳንጋጭ ሽንፈት እንደደረሰባቸው ይታወሳል። በሊጉ ተሳትፏቸው በጨዋታ ከሁለት ግቦች በላይ ተቆጥሮባቸው የማያውቁትና ከአንድ ግብ ልዩነት በላይ ያልተሸነፉት የጣና ሞገዶች፤ በሜዳና በደጋፊያቸው ፊት ከደቡብ ፖሊስ ጋር በሚያደርጉት በዚህ ጨዋታ ከሽንፈታቸው አገግመው ወደ አሸናፊነታቸው የሚመልሳቸ ውን ውጤት ማስመዝገብ ግድ ይላቸዋል። በሃያኛው ሳምንት ከአፄዎቹ ጋር ነጥብ መጋራት የቻሉት ደቡብ ፖሊሲች በቀጣዩ መርሃ ግብር ከዲቻ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ በአቻ ውጤት ማጠናቀቃቸው ይታወሳል። ምንም እንኳን የመከላከያ ውጤት ማጣት የደቡብ ፖሊሶችን ከወራጅ ቀጠና የመውጣት ጉዞ እያሳመረው ቢሆንም፤ አሁንም ከአደጋ ቀጠናው ሙሉ በሙሉ መራቃቸውን ማረጋጋጥ አልሆነላቸውም። በደረጃ ሰንጠረዡ በ32 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡት የጣናው ሞገዶች፤ በዚህ ጨዋታ ተጋጣሚያቸውን በሊጉ የሻምፒዮንነት ትንቅንቅ አለመራ ቃቸውን ለማስመስከር ከዚህ ጨዋታ ድል ማስመዝገብ ይኖርባቸዋል። በ18 ነጥብ 13ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡት ደቡብ ፖሊሶች በአንፃሩ በሊጉ የመቆየት ዋስትናቸውን ለማስቀጠል ከዚህ ጨዋታ ውጤት ማግኘት ግድ ይላቸዋል። ጨዋታው በባህር ዳር ዓለም ዓቀፍ ስታዲየም ዘጠኝ ሰዓት ላይ ቀጠሮ ተይዞለታል። ወላይታ ድቻና መከላከያም በዚሁ የሊጉ መርሃ ግብር ይገናኛሉ። ከአስራ ዘጠነኛው ሳምንት የመቐሌው ሽንፈት በስተቀር በሊጉ ሁለተኛ ምዕራፍ ተከታታይ ድሎችን በማስመዝገብ ላይ የሚገኙት ወላይታ ድቻዎች በሃያኛው ሳምንት መርሃ ግብር በሜዳቸውና በደጋፊያቸው ፊት ኢትዮጵያ ቡናን አስተናግደው በፀጋዬ አበራ ሁለት የጭንቅላት ኳስ ግቦች ባለድል መሆናቸው ይታወሳል። በቀጣይም ከደቡብ ፖሊስ ጋር ነጥብ ተጋርተው ከሊጉ የወራጅ ቀጠና በመፋታት ነጥባቸውንም ከፍ ማድረግ የቻሉ ሲሆን፤ ከመከላከያ ጋር የሚያደረጉትን ጨዋታም ማሸነፍ ከቻሉ የወራጅነት ስጋታቸውን በእጅጉ ይቀንሳሉ። በአሁኑ ወቅትም በ24ነጥብ አስራ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። ተጋጣሚያቸው መከላከያ በአንፃሩ የዘንድሮው የውድድር ዓመት መጀመሪያ ላይ አስደናቂ አቋምና ውጤት ቢያስመዘግብም እያደር ወጥ የሆነ አቋም ማሳየት ተስኖታል። በተለይ በሁለተኛው የሊጉ ምዕራፍ በውጤት ቀውስ ውስጥ እየናወዘ ይገኛል። በሃያኛው ሳምንት ወደ መቐለ ተጉዞ በወልዋሎ እንዲሁም በ21ኛው ሳምንት በፋሲል በሜዳውና በደጋፊው ፊት አራት ለባዶ መሸነፉ ይታወሳል። የመውረድ አደጋ የተጋረጠበት ክለቡ በአሁኑ ወቅትም በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ በ18 ነጥብ አስራ አራተኛ ላይ ተቀምጧል። በሚቀጥለው ዓመት ወደ ብሄራዊ ሊግ ከመውረዱ በፊት አቋሙን በጊዜ በማስተካከል ወደ አሸናፊነት መመለስ የግድ ይለዋል። ይህን ማድረግ ካልቻለም እጣ ፈንታው አስከፊ ይሆናል። ይህ ደግሞ በሊጉ የሚሳተፉ የአዲስ አበባን ከለቦች ወደ ሁለት ያወርዳቸዋል። የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ22ኛ ሳምንት ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን ከደደቢት ያጫውታል። ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች በአዲሱ አስልጣኝ እየተመሩ በሊጉ ሁለተኛ ዙር ድንቅ አቋም ውጤት በማሳያት ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ በሃያኛው ሳምንትም አዲስ አበባ ላይ መከላከያን በሜዳውና በደጋፊው ፊት አንድ ለባዶ ማሸነፍ ቢችሉም በቀጣዩ መርሃ ግብር በድሬዳዋ ሁለት ለአንድ መሸነፋቸው ይታወሳል። ደደቢቶች በአንፃሩ በዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች እጅጉን አስከፊ የሚባል አቋምና ተደጋጋሚ ሽንፈት ቢደርስባቸውም በሁለተኛው ዙር ተሽለው አሸንፈው ታይተዋል። ያለፉት ሁለት ጨዋታዎች በድሬዳዋዎች ሶስት ለሁለት፤ በጅማ አባጅፋሩ አንድ ለባዶ መሸነፋቸው ይታወሳል። ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከደደቢት በሚያደርገው ጨዋታም ካሸነፈ ውጤታማነቱን ለማስቀጠል ነጥቡን ከፍ በማድረግ ወደ መሪዎቹ አራት ከለቦች ማስጠጋት ይሆንለታል። ደደቢቶች በአንፃሩ ከዚህ ጨዋታ በተጓዳኝ ቀጣዩን ዓመት በሊጉ ለመቆየት እያንዳንዱን ፍልሚያ እንደ ዋንጫ ጨዋታ መመልከት ግድ ይላቸዋል። ወልዋሎ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ በ30 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ሲሆን፣ ተጋጣሚው ደደቢት በ10 ነጥብ የደረጃው ግርጌ ላይ ይገኛል። የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ዘጠኝ ሰዓት ላይ ይካሄዳል። ስሁል ሽረ ከ ሀዋሳ ከተማ የሚያገናኘው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ22ኛ ሳምንት መርሃ ግብርም ሌላው ተጠባቂ ጨዋታ ነው። በተለይ በሊጉ ሰንጠረዥ ወራጅ ቀጠና ከግርጌ ከተቀመጡት ደደቢቶች ከፍ ብለው የሚገኙት ስሁል ሽረዎች ደረጃቸውን በማሻሻል በሊጉ ለመቆየት ጨዋታውን ማሸነፍ ግድ ይላቸዋል።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 22/2011
https://www.press.et/Ama/?p=9893
1,221
2ስፖርት
የሻንጋይ ዳይመንድ ሊግ የሚጠብቃቸው ጠንካራ ፉክክሮች
ስፖርት
May 2, 2019
27
የ2019 የዳይመንድ ሊግ ውድድሮች በይፋ ሊጀመሩ ከሁለት ሳምንት ያነሰ ጊዜ ይቀራቸዋል። ፉክክሮቹ ከመጀመራቸው ቀደም ብሎ የተለያዩ መርሃግብሮች እየወጡ ሲሆን የውድድር ዓመቱ ሁለተኛዋ መዳረሻ ከተማ የሆነችው የቻይናዋ ሻንጋይ የምታስተናግደውን የውድድር አይነትና ብዛት አሳውቃለች። በዚህም መሰረት በርካታ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በመካከለኛና ረጅም ርቀት ውድድሮች እንደሚሳተፉ ታውቋል። ሻንጋይ በአጠቃላይ አስራ ስድስት ዓለም አቀፍ ፉክክሮችን ስታሰናዳ በዘጠኙ ፉክክሮች(100፣ 200፣ 400፣ 5000 ሜትሮች፣ 110 ሜትር የዱላ ቅብብል፣400 ሜትር የዱላ ቅብብል፣ከፍታ ዝላይ፣ርዝመት ዝላይና ጦር ውርወራ )ውድድሮች ወንዶች ተሳታፊ ይሆናሉ። ሴቶች በሰባት ውድድሮች ሲፎካከሩ (100፣400፣1500፣3ሺመሰናክል፣ምርኩዝ ዝላይ፣መዶሻ ውርወራና ጦር ውርወራ) ፉክክሩ የሚካሄድባቸው ይሆናሉ። በነዚህ ውድድሮች የ3ሺመሰናክል የዓለም ክብረወሰን ባለቤቷ ኬንያዊት ቢትሪስ ኪፕኮይች፣ የአውሮፓ 5ሺ ሜትር ቻምፒዮን ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ የኔዘርላንድስ አትሌት ሲፈን ሃሰን፣ የአንድ ማይል የቤት ውስጥ የዓለም ክብረወሰን ባለቤቱ ዮሚፍ ቀጄልቻ ተሳታፊ እንደሚሆኑ አይ.ኤኤ.ኤፍ በድረ ገፁ አሳውቋል።እኤአ ከ2020 ጀምሮ ከዳይመንድ ሊግ ፉክክር የሚሰረዘው የ5ሺ ሜትር ውድድር ዘንድሮ ሻንጋይ ላይ በኢትዮጵያውያኑ የቤት ውስጥና ከቤት ውጪ ቻምፒዮኖች እንደሚደምቅ ይጠበቃል። ዮሚፍ ቀጄልቻ በዚህ ውድድር ትልቅ ትኩረት የተሰጠው አትሌት ሲሆን የ2018 የውድድር ዓመትን የአንድ ማይል የቤት ውስጥ የዓለም ክብረወሰን ከሃያ ሦስት ዓመታት በኋላ ማሻሻሉ አይዘነጋም። የውድድር ዓመቱን በ5ሺ ሜትር የዓለማችን ቁጥር ሁለት አትሌት በመሆን ያጠናቀቀው ዮሚፍ ስድስተኛ ሆኖ ካጠናቀቀው የአገሩ ልጅ ሙክታር ኢድሪስ ጋር በሻንጋይ ዳይመንድ ሊግ ብርቱ ፉክክር ያደርጋል። ሙክታር ካቻምና የለንደን የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ላይ የእንግሊዛዊው አትሌት ሞ ፋራህን የ5ሺ ሜትር የበላይነት አስቀርቶ ቻምፒዮን ከሆነ በኋላ በተለያዩ ውድድሮች ውጤታማ መሆን አልቻለም። ዘንድሮ የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ኳታር ዶሃ ላይ የሚካሄድ በመሆኑ የተለያዩ የዓለማችን አትሌቶች በዚህ ታላቅ መድረክ አገራቸውን ለመወከል ከፍተኛ ጥረት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። ዮሚፍና ሙክታርም በዓለም ቻምፒዮናው ኢትዮጵያን ለመወከል የሚያበቃቸውን ሰዓት ለማስመዝገብ ከወዲሁ ጠንካራ ፉክክር እንደሚያደርጉ መገመት ይቻላል። አሜሪካዊው የዓለም ቻምፒዮናና የኦሊምፒክ የሜዳሊያ ባለቤት ፖል ቼሊሞ የውድድር ዓመቱን አምስተኛ ደረጃ ይዞ የፈፀመ አትሌት ከመሆኑ አኳያ በሻንጋይ ዳይመንድ ሊግ ቀላል ግምት የሚሰጠው አትሌት አይሆንም። ከዚህ ባሻገር የ2012 የዓለም የቤት ውስጥ የ1500 ሜትር ቻምፒዮን ሞሮኳዊው አብደላቲ ኢጊደር በዚህ ውድድር ጠንካራ ተፎካካሪ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። እነዚህ አትሌቶች በሻንጋይ ዳይመንድ ሊግ እንደሚሳተፉ ይገለፅ እንጂ በቀጣይ ቀናት ሌሎች የርቀቱ ኮከብ አትሌቶችም እንደሚካተቱ ይጠበቃል። በሴቶች መካከል በሚካሄደው የ1500 ሜትር ውድድር ዓመቱን በ5ሺ ሜትር ቁጥር አንድ ሆና ያጠናቀቀችው ሲፈን ሃሰን ከፍተኛ የአሸናፊነት ግምት አግኝታለች። ሲፈን 2014 ላይ በዚሁ የሻንጋይ ዳይመንድ ሊግ በርቀቱ የመጀመሪያ ውድድሯን ካደረገች ወዲህ ኮከብ ከሆኑ አትሌቶች ተርታ መሰለፍ ችላለች። በርቀቱ አራት የአውሮፓ ቻምፒዮናዎችን ጨምሮ የዓለም የቤት ውስጥ ቻምፒዮናን ከማሸነፏ ባሻገር ከቤት ውጪም በዓለም ቻምፒዮና ሁለት ጊዜ የነሐስ ሜዳሊያ ማጥለቅ ችላለች። በዚህ ውድድር የ2016 የዓለም የቤት ውስጥ ቻምፒዮና የነሐስ ሜዳሊያ አሸናፊዋ ኢትዮጵያዊት ጉዳፍ ፀጋየ ለአሸናፊነት ከታጩ አትሌቶች መካከል ተካታለች። የውድድር ዓመቱን በርቀቱ ሁለተኛ ሆና ያጠናቀቀችው ጉዳፍን ጨምሮ ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት ዳዊት ስዩም ለሲፈን ፈተና እንደሚሆኑባት ተገምቷል። ዳዊት ስዩም 2016 የዓለም የቤት ውስጥ ቻምፒዮና የብር ሜዳሊያ ካጠለቀች ወዲህ በርቀቱ ጠንካራ ከሚባ አትሌቶች መካከል አንዷ ሆናለች። የአፍሪካ ቻምፒዮኗ ኬንያዊት ዊኒ ቺቤት ሌላኛዋ ጠንካራ ተፎካካሪ ትሆናለች። ሻንጋይ ላይ ትኩረት ከሳቡ ውድድሮች አንዱ የሆነው የሴቶች ሦስት ሺ ሜትር መሰናክል ይገኝበታል። በዚህ ውድድር ዓመቱን በርቀቱ ቁጥር አንድ ሆና የፈፀመችው ኬንያዊት ቺፕኮይች ያለፈውን ዓመት አስደናቂ ብቃት እንደምትደግም ይጠበቃል። ኮይች ባለፈው የውድድር ዓመት የ2015 የዓለም ቻምፒዮኗን ሄቪን ኪንግን በድንቅ ብቃት ማሸነፍ ችላለች። በዚህ ውድድር ባለፈው ዓመት ሁለተኛ፣አራተኛና አምስተኛ ሆነው ማጠናቀቅ የቻሉ ኬንያውያን የሚያደርጉት ፉክክርም ተጠባቂ ነው።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 24/2011
https://www.press.et/Ama/?p=9991
484
2ስፖርት
በድል የታጀበው የቀያዮቹ አስጨናቂ ምሽት
ስፖርት
May 2, 2019
44
እኤአ ሜይ 25 ቀን 2005 ነው። ኢስታ ምቡል፣ ቱርክ። በካማል አታቱርክ ስታዲየም። በዚያች ምሽት፣ ታሪክ ብዕርና ወረቀት ይዞ ልብወለድ የሚመስል እውነት መፃፉን ቀጠለ። ያ ምሽት ለማንም የማይታመን ነው። ፈፅሞ የማይታመን! ለሊቨርፑል ደጋፊ በህልም ዓለም ውስጥ ያለ ያህል፣ አሁኑኑ ከእንቅልፉ ባንኖ ሁሉ ነገር ውሸት የሚሆን ይመስል ነበር። ለኤሲ ሚላን አናብስትም ያላመጡትን የድል ሙዳ ሳይውጡ ከመንጋጋቸው መነጠቃቸው ያስቆጫል። ሁኔታዎች በፍጥነት ተቀያይረው ከ3-0 መምራት፣ ወደ 3-3 መሻገራቸው እንቆቅልሽ ነበር። ቢሆንም አሸናፊው አልተለየም። ጭማሪው ሰዓት ተፋላሚዎቹን አልገላገለም። በአምስት አምስቱ የመለያ ምት ባለክብሩ ሊለይ የጨዋታው ህግ አስገደደ። ያን ጊዜ የኃላፊነቱ ሸክም በተለይ በአንድ ሰው ላይ ከብዶ ተጫነ። በሊቨርፑሉ ግብ ጠባቂ ጀርዚ ዱዴክ ላይ።ሁለት ተጫዋቾች ወደ ፖላንዳዊው በረኛ ቀረቡ።‹‹ጀርዚ ድንቅ ስራ ሰርተሃል። አሁን ደግሞ በመለያ ፍፁም ቅጣት ምቶቹ ላይ አተኩር። አሁን ጨዋታው ያንተ ነው። ልታሸንፍልን የምትችለው አንተ ነህ›› አሉት። ተከላካዩ ጄሚ ካራገር በተራው ወደ ዱዴክ መጣ። በማበረታታትና በማነሳሳት መልክ እየገፈተረው ፊቱን ወደ ዱዴክ ፊት አቅርቦ መከረው። ‹‹ጀርዚ አይዞህ! አይዞህ!›› ይለዋል። የ120 ደቂቃዎች ፍልሚያ አዝሏቸዋል። ድካም፣ መገረምና ውጥረት ተጭነዋቸዋል።ጄሚ ቀጠለ። ‹‹አንድ ነገር አድርግ። ግራ አጋባቸው። ብሩስ ግሮብላርን ታስታውሰዋለህ? እንደ እርሱ እግርህን ፈርከክ አድርገህ ቁም፣ በግቡ መስመር ላይ ወዲያ ወዲህ በል።›› በዚያች ሰዓት ጀርዚ የሚፈልገው ካራገርን አልነበረም። ‹‹እሺ! እሺ!›› እያለ አሳለፈው። አሁን የሚያስፈልገው ሌላ ሰው ነው። የበረኞቹ አሰልጣኝ ሆዜ ኦቾቴሪና። በ1988ቱ የአውሮፓ የክለቦች ዋንጫ ፍፃሜ ስመጥሩ የፋይኖርድ ግብ ጠባቂ ሃንስ ቫን ብሮክለን የቤንፊካ ተጫዋቾች የፍፁም ቅጣት ምት ዓመታት ልማድን የተመለከተ ማስታወሻ ነበረው። ዱዴክ ከደቹ በረኛ ተምሯል። በፌይኖርድ ሳለም ተመሳሳይ መረጃዎች ያሉት ማስታወሻ ደብተር ነበረው። ተጫዋቾች አንድ ዓይነት የፍፁም ቅጣት ምት ስልት አይከተሉም። ይለያያሉ። በዚያች ፈታኝ ምሽት የኤሲ ሚላን ተጫዋቾችን ባህሪያት አንድ በአንድ ለይቶ ማወቅ አስፈላጊ ነበር። ኦቾቶሪና ደግሞ የቤት ስራቸውን በጥሞና ሰርተዋል። አሁን ጨዋታው ወደ መለያ ምት መጥቷል። የካራ ማበረታታት የሚጠላ ባይሆንም፣ ለዱዴክ የሚያስፈልገው የኦቾቶሪና ተጨባጭ መነሻ ያለው መመሪያ ነበር። ዱዴክ በግራ ይውደቅ፣ በቀኝ የሚወሰነው እንደ መቺው ሁኔታ ነው። የዚህ ቁልፍ ያለው ደግሞ የግብ ጠባቂዎቹ አሰልጣኝ ዘንድ ነበር። ለጥቃቅን ዝርዝሮች ልዩ ትኩረት የሚሰጡት ራፋ ቤኒቴዝ ከኦቾቶሪና ጋር ተዘጋጅተዋል። ከጨዋታው በፊት መላው የሚላን ተጫዋቾች ፍፁም ቅጣት ምቶችና ቅጣት ምቶችን እንዴት እንደሚመቱ የሚገልፅ ዝርዝር መረጃ በመልበሻ ቤት ሰሌዳ ላይ ፅፈው ነበር። ዱዴክ በሁለቱም ምቶች ላይ የሚላን ተጫዋቾችን ስልቶች የሚገልፁ የቪዲዮ ክሊፖችንም እንዲመለከት ተሰጥቶታል። በዚያ ሲዝን ራፋ ግብ ጠባቂውን ፍፁም ቅጣት ምቶችን እንዴት ማዳን እንዳለበት ለማሰልጠን ብዙ ደክመዋል። ዱዴክ በዓይነ ህሊናው የግቡን ክፍሎች በስድስት ካሬዎች ከፍሎ እንዲመለከት አለማምደውታል። ላይኛው ቀኝ፣ በላይኛው መሃል፣ በላይኛው ግራ፣… በታችኛው ቀኝ፣ በታችኛው መሐል፣ በታችኛው ግራ። ምቶቹ ወደ እነዚህ ካሬዎች ካልተመቱ ኳሷ መረቡን አታገኘውም። ስለዚህ ዱዴክ መከላከል ያለበት እነዚህን ካሬዎች ብቻ ነው። ሚላኖቹ ደግሞ የየራሳቸው ልማድ አላቸው። ሁሉም ተጠንቷል። ማን ወደየትኛው ካሬ የመምታት ልምድ እንዳለው የሊቨርፑል አሰልጣኞች በማስታወሻቸው ላይ አኑረውታል። ሁሉን አውቀውታል። ከኢስታምቡል ጨረቃ በታች ምንም አዲስ ነገር አልነበረም። ቢሆንም ዱዴክ የሁሉንም የመምቻ አቅጣ ጫ በቃሉ ማስታወስ አይችልም። በየምቱ ላይ አቅጣጫ ጠቋሚ ያስፈልገዋል። ቢችል ኦቾቶሪና ከግቡ በስተጀርባ ሆኖ ‹‹በግራ ውደቅ፣ በቀኝ›› እያለ ቢመራው ጥሩ ነበር። አርቢትሩ አይፈቅዱለትም እንጂ። የቤኒቴዝን ስነ አእምሯዊ ስልጠና ለመልመድ ዱዴክ አራት ወራት ፈጅተውበታል። ከብዙ ልፋት በኋላ ዋና ዋና ተጫዋቾችን የተመለከቱ የቤኒቴዝን ጥያቄዎች መመለስ ችሏል። ‹‹ላምፓርድ የሚመታው ወደየት ነው?›› ሲሉት ‹‹ወደ ካሬ ስድስት›› ሲል ይመልስላቸዋል። በታችኛው ቀኝ ካሬ በኩል ማለት ነው። ከዱዴክና ከራፋ በስተቀር እነዚህን ኮዶች የሚያውቁ ጥቂቶች ብቻ ነበሩ። የሊቨርፑል ደጋፊዎች በጥፍራቸው ቆመው የምሽቱን ድራማ ይከታተላሉ። የዱዴክ ኃላፊነት ክብድ ነው። የሁሉም ስሜት ከእርሱ ውሳኔ ጋር ተያይዟል። የመምቻው ሰዓት ሲደርስ ኦቾቶሪና ማስታወሻቸውን አወጡ። በእያንዳንዱ የሚላን ተጫዋች ስም ፊት ኮዱ ተፅፏል። ጀርዚ ከእያንዳንዱ ምት በፊት ወደ አሰልጣኞቹ አቅጣጫ ማየት አለበት። ኮዱ ይነገረዋል። ያን ጊዜ ወደየትኛው ምናባዊ ካሬ እንደሚወድቅ ይወስናል። ኮዱን በእጅ ምልክት ለዱዴክ የሚነግር ሰው ተመረጠ። ሁለተኛው ግብ ጠባቂ ስኮት ካርሰን። ካርሰንም ከኦቾ በሚነገረው መሰረት ምልክቱን ይሰጣል። ዱዴክም የሚወድቅበትን አቅጣጫ ይወስናል። አንዳንድ ተጫዋቾች የተለመደ ዓመታታቸውን ቀይረው ስለሚመጡ የበረኛውና የኦቾቶሪና ውሳኔም እንደ አዳዲሶቹ ሁኔታዎች መቀየር ሊኖርባቸው ይችላል። አንዳንድ ጊዜ ፍፁም ቅጣት ምቶች አይተነበዩምና። የቁርጡ ሰዓት ደረሰ። እንደ ኤርፖርት ትራፊክ ወደ ግራ ወደ ቀኝ በሚሰጠው የእጅ ምልክት ዱዴክ አቅጣጫውን እየቀየረ የሊቨርፑላዊያንን ስሜት ይዞ በረረ። 69600 ተመልካች በስታዲየሙ ተሳፍሯል። መላው ዓለም በቴሌቪዥን ፊት አፍጥጧል። ሜርሲሳይድ በቆዳዋ ላይ ያለ ፀጉሯ ሁሉ ቆሟል። 18 ዲግሪ በሚሞቀው ከማል አታቱርክ ስታዲየም የስሜት ባሮሜትር ይወጣል፣ ይወርዳል። በሚላን በኩል ሰርጂንሆ፣ ፒርሎ አከታትለው ሳቱ። ሃማንና ሲሴ ለቀዮቹ አስቆጠሩ። ቶማሰን ለሚላን አገባ፣ ሪሰ ለሊቨርፑል ሳተ። ካካ አስቆጠረ፣ ስሚሰር አገባ። ሊቨርፑል 3፣ ሚላን 2። ጨዋታው ገና አላለቀም። አንድሪያስ ሼቭቼንኮ ተነሳ። በግብ ፊት ሼቫ ቀላል ሰው አይደለም። ኳስ ከመረብ የማሳሳም ሱሰኛ ነው። በረኞችን የሚያርድ የአጥቂነት ግርማ አለው። ዱዴክ የዩክሬናዊውን ‹‹ሚሳኤል›› ካመከነ ሜርሲሳይድ በፍንጠዛ እንደ ሰም ትቀልጣለች። ዱዴክ ተጋፈጠው። ተጋፍጦም አሸነፈው። ወደ ቀኙ ቢወድቅም በመሐል አቅጣጫ የመጣችውን ኳስ በእግሩ አዳናት። የአታቱርክ ኦሊምፒክ ስታዲየም በቀዮቹ ደጋፊዎች የማያቋርጥ ደስታ ነዘረ። ከዕረፍት በፊት የሞተው ሊቨርፑል አፈር ልሶ ተነስቶ በመለያ ምት የአውሮፓ ዘውዱን ጫነ። ዘንድሮስ ቀያዮቹ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ ይህን ታሪክ ለመድገም ይችላሉ?። የባርሴሎናን ግንብ ንደው ወደ ፍፃሜ ያመራሉ? ጊዜ ይመልሰዋል።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 24/2011
https://www.press.et/Ama/?p=9994
731
2ስፖርት
መድኅን የሚሻው፤በ«ዘረኝነት» ያበደው እግር ኳሳችን
ስፖርት
May 1, 2019
35
ስፖርት ብሄራዊ ስሜትን በማጠናከር አሊያም በማደብዘዝ ረገድ ሚናው ግዙፍ የሆነ ትልቅ ማህበራዊ ክንውን ነው። በብሄራዊ ስሜት ግንባታ ውስጥ የስፖርቱን የተለያዩ ሚናዎችን ያሳዩ በርካታ አጋጣሚዎች ይጠቀሳሉ። ስፖርት ብሄራዊ ስሜትን የመገንባት አቅምን ለመፍጠር የሚያ ስችል ስለመሆኑ እ.ኤ.አ የ2013ቱ የደቡብ አፍሪካ ዋንጫ ትልቁ ማሣያ ይሆናል። የዋልያዎቹ ከ31 ዓመታት በኋላ በአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ላይ መሳተፍ በእግር ኳሱ ውስጥ የብሄራዊ ስሜት ማነሳሳትን ሲፈጥር ታዝበናል። ኢትዮጵያዊነትን ከገባበት የተቀዛቀዘ ስሜት ውስጥ አውጥቶ ከዳር እስከ ዳር በሞቀ የአንድነት መንፈስ ሲያስፈነጥዝም ተመልክተናል። የልዩነት ነጋሪት ጉሰማውን ድምጽ የዋጠና የአንድነቱን ድምፀት ያጎላም ጭምር እንደነበር አይተናል። ይህ አጋጣሚ ስፖርት የወንድማማችነት፣ የወዳጅነትና የአንድነት ማጠናከሪያ አብነት ነው እየተባለ ሲነገር የነበረውን በተጨባጭ አሳይቷል። ከሰሞኑ አዲስ አበባ ውስጥ አንጋፋው የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ የተንፀባረቀው ሁኔታም ይህንኑ የሚያጠናክር ነው። «የስፖርት ጨዋነት ምንጮች» በሚል መሪ ቃል በሸራተን ሆቴል ለሁለት ቀናት በተካሄደው የምክክር ጉባዔ ላይ በርካታ ቁምነገሮች ተነስተዋል። በዚሁ ወቅት የሠላም ሚኒስትር ዴኤታ አልማዝ መኮንን እንዳሉት ስፖርት ለሠላም ዘብ የመሆኑን ጉዳይ በተገቢው መጠቀም ካልተቻለ በተቃራኒው ሲውል የሠላም ፀር መሆኑ አይቀሬ ይሆናል። «ስፖርት ትልቅ የሠላም ምንጭ ነው። ስፖርት በአንድ አገር ሠላም ሲደፈርስና መረጋጋት ሲታጣ ወደ ቀደመው ሁኔታ ለመመለስ ትልቅ አቅም አለው። ስፖርት የታመመን ፖለቲካ የማከም ከፍ ያለ ስጦታም አለው» ብለዋል። ሚኒስትር ዴኤታዋ የዓለም ነባራዊ ሁኔታን መሠረት በማድረግ ይህንን ይበሉ እንጂ፤ በኢትዮጵያ እየተስተዋለ ያለው አሁናዊ ሁኔታ ከዚህ ፍጹም ተቃራኒ ሲሆን እየተስተዋለ ነው። በተለይ በእግር ኳሱ ስፖርት ለሠላምና ለጤንነት የሚለው መርህ ተገልብጦ ለሁከትና ብጥብጥ ምንጭ ከሆነ ሰንበትበት ብሏል። ይህንኑ መነሻ በማድረግ ሚኒስትር ዴኤታዋ ለችግሩ ዘላቂ የሆነ መፍትሄ በመስጠት ሂደቱን መስመር ማስያዝ እንደሚገባ አሳስበዋል። የአገሪቱ እግር ኳስ ክፉኛ በሆነ መልኩ «ዘረኝነት» በሚባል ወቅት አመጣሽ በሽታ ሽምድምድ ብሎ ከስታዲየም ውጪ ተኝቷል። በተለይ ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ክፉኛ ታሟል። ይህ ሁኔታ በዚህ ደረጃ ከቀጠለ እስከ ሞት ሊያደርሰው እንደሚችል በመድረኩ ላይ የታደሙ የዘርፉ ባለሙያዎች ምክረ ሃሳባቸውን ለግሰዋል። ኢንተርናሽናል ዳኛ ሊዲያ ታፈሰ በአገሪቱ እግር ኳስ ውስጥ ከዳኝነት ጋር ተያይዞ ዘርፈ ብዙ ችግሮች ይስተዋሉበታል። እነዚህም ለስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል መንስዔ ይሆናሉ ሲሉ ገልፀዋል። ፖለቲካ እና እግር ኳሱ መለያየት እንዳለበት አፅንኦት የሰጡት ኢንተርናሽናል ዳኛዋ ዘረኞችን፣ ጎሰኞችን፣ ፖለቲከኞችን ከስፖርቱ ለይቶ መዳኘት አቅቶናል ሲሉ ችግሩ የቱን ያህል ውስብስብ ደረጃ ላይ መገኘቱን ጠቁመዋል። የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር የቦርድ ሊቀመንበር አቶ አብነት ገብረመስቀል የሥነ ምግባር መጓደልና ሥርዓት አልበኝነት እግር ኳሱን ከመጉዳት አልፎ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በጎሣ፣ በዘር፣ በሃይማኖትና በፖለቲካ አመለካከት ላይ ያተኮሩ ልዩነቶችና መቆራቆዞች እዚህም እዚያም እየተበራከቱ መጥተዋል፤ ስፖርት ከፍ ያለ የሞራል ልዕልናን የመጠየቁን ያህል በአግባቡ ካልተመራ በተቃራኒው ነውጠኝነትና ሥርዓት አልበኝነት ሊነግስበት ይችላል ብለዋል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሣይያስ ጂራ በሰጡት አስተያየት እግር ኳሱ የሌላ አጀንዳ መናኸሪያ እየሆነ መጥቷል። ከስፖርታዊ መርህ ውጪ «የእከሌ ዘር ተሸነፈ፣ ይኸኛው ብሔር አሸነፈ» በሚል ጤናማ ያልሆነ አስተሳሰብ ላይ ደርሰናል ሲሉ የችግሩን አሳሳቢነት ገልፀዋል። አሰልጣኝ መሠረት ማኔ በበኩላቸው በስፖርቱ አደረጃጀት ላይ ትልቅ ክፍተት መኖሩን በመጥቀስ፤ ስፖርቱ በሙያተኞች አለመመራቱ ሌላው መሠረታዊ ችግር እንደሆነ ጠቁመዋል። የባህል ቱሪዝምና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሐብታሙ ሲሳይ «የመንግሥት የስፖርት ተቋማት ግንኙነት እስከምን ድረስ» በሚል ርዕስ ባቀረቡት ጽሁፍ ክለቦች በፖሊስ፣ በመከላከያ፣ በከተማ አስተዳደር፣ በማህበር እና መሰል አደረጃጀቶች እየተመሩ መገኘታቸው ለስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል ተፅዕኖ ፈጥሯል ብለዋል። አንድ ክለብ ምን ምን መስፈርቶችን ማሟላት እንዳለበት በግልፅ ተለይቶ መቀመጥ ይገባዋል። ወጥ የሆነ ሕግም ያስፈልገዋል፤ ይህም አለመኖሩ ክፍተት መፍጠሩን አስረድተዋል። የዘረኝነትና ብሄርተኝነት በሽታ ውስጥ የሚገኘው የኢትዮጵያ እግር ኳስን ለመታደግ በስፖርታዊ እንቅስቃሴ ውስጥ የዘር ልዩነት እንዲጠፋ፣ የኦሊምፒክና የዓለም አቀፍ የስፖርት ማኅበራት ደንብና መመሪያዎች እንዲከበሩ፣ ብሔርን መሠረት አድርገው የሚቋቋሙ ክለቦች ስማቸውን እንዲቀይሩ፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴን ጨምሮ ሌሎችም ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች መሪዎቻቸውን በችሎታና ብቃት ላይ ተመሥርተው እንዲመርጡ፣ ስፖርት በትምህርት ቤቶችና ዩኒቨር ሲቲዎች እንዲስፋፋ የመድረኩ ተሳታ ፊዎች ጠይቀዋል።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 23/2011 በዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=9947
545
2ስፖርት
“የትግራይ ህዝብ ጁንታውን ከዛሬ ሶስት ዓመት በፊት ነው አንቅሮ የተፋው” – አቶ ጊደና መድህን የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ዋና ጸሃፊ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 5, 2020
35
 እፀገነት አክሊሉአዲስ አበባ፦ የትግራይ ህዝብ የህወሓት ወንጀለኛ ጁንታ በስሙ እየነገደበት እንደሆነ ገብቶት አንቅሮ የተፋው የዛሬ ሶስት ዓመት በፊት መሆኑን የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አስታወቀ፡፡ የፓርቲው ዋና ጸሃፊ አቶ ጊደና መድህን በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደገለጹት፣ የትግራይ ህዝብ በተለይ ከለውጡ ሶስትና አራት ዓመት በፊት ጀምሮ የጁንታውን አመራሮች አንቅሮ ተፍቷቸዋል፡፡ በስሙ እየተከናወኑ ስላሉ ነገሮችም ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ይህንን ሁኔታ ግን የሚዘግብ የመገናኛ ብዙሃን በክልሉ አለመኖሩ ሁኔታው እንዳይታወቅ አድርጎታል፡፡ባለፉት 20 ዓመታት እንኳን በባስኔቲ፣ አብያዲ፣ እግረአሪባ፣ ዋጀራት፣ ራያና ሽሬ አካባቢ ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ ነበር፡፡ ባስኔቲ ላይ ህብረተሰቡ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተመረጡ ሰዎችን አይወክሉንም በማለት አልተቀበለም ያሉት አቶ ጊደና፣ ይህንን የህዝቡን ተቃውሞ የሚዘግብ መገናኛ ብዙሃን ባለመኖሩ አደባባይ መውጣጥ አልቻለም ብለዋል። በተመሳሳይ እግረሀሪባ (በመቀሌ አየር ማረፊያ አካባቢ) በጉልበት መሬታቸው የተቀማባቸው ነዋሪዎች ፖሊስን አባረው የራሳቸውን አስተዳደር እስከ መመስረት ደርሰው ነበር፤ በዚህ ሂደትም ብዙዎች መታሰራቸውንና መገረፋቸውን አመልክተዋል። ባለፉት ሁለት ዓመታት በተለይም ወንጀለኛው ጁንታ ከአዲስ አበባ ተገፍትሮ መቀሌ ከመሸገ በኋላ ግን ህዝቡን አማራ እንዲሁም ሻዕቢያ መጣብህ፤ የፌዴራል መንግስቱ ጨፍላቂ ነው ፤በማለት ከፍተኛ የሆነ ፕሮፖጋንዳ ስራ ሰርቷል ያሉት አቶ ጊደና፣ ይህ ደግሞ ህብረተሰቡ በፌዴራል መንግስቱ ላይ እምነት እንዲያጣ እንዳደረገውም አመልክተዋል፡፡ በቀጣይም የፌዴራል መንግስት ይህንን የሚያጠራ ስራን መስራት እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡ ነጻ በወጡት ነገር ግን የማንነት ጥያቄ ባለባቸው አካባቢዎች ላይ መንግስት ከሚያስበው ጋር የማይሄዱ ስራዎች እየተሰሩ በመሆኑ ይህ ጁንታውን እስከ መጨረሻው ለመቅበር በምናደርገው ትግል ላይ አሉታዊ ሚና ስለሚኖረው በከፍተኛ ትኩረትና ጥንቃቄ ሊሰራ የሚገባው ነው፡፡ ከጁንታው እኩይ ተግባር አንጻር የኢትዮጵያ ህዝብ እጅግ ሊመሰገን ይገባል፡፡ ምክንያቱም በአሰቃቂ ሁኔታ መከላከያውን ሲጨፈጭፉ ማይካድራ ላይ እንደዛ ዜጎችን ሲያርዱና በጅምላ መቃብር ሲቀብሩ የነበረው አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በሌላው ክልል የሚኖር የትግራይ ተወላጅ ላይ ሌላው ኢትዮጵያዊ እንዲነሳ ለማድረግ ነበር፤ ህዝቡ ግን ሩህሩህና ቀና ልብ ያለው በመሆኑ እነሱ ባሰቡት መንገድ አልሄደላቸውም ብለዋል። በኢትዮጵያ ከድህነት ወለል በታች ከሚኖሩ ዜጎች 27 ከመቶውን በመያዝ የትግራይ ህዝብ በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል ያሉት አቶ ጊዲና፤ የጁንታው ልጆች ግን በጣም ውድ በሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩበት፤ እና ራሳቸውም እጅግ የተቀናጣ ኑሮ የሚኖሩ መሆናቸውን አስታውቀዋል። እንደ አቶ ጊዲና ገለጻ፤ የኢፈርት ድርጅቶች ትልልቅ ኩባንያዎች ናቸው፤ ሲቋቋሙም በጦርነቱ ለተጎዱ የሰማዕታት ቤተሰቦችና የጦርነቱ አካል ጉዳተኞች እንዲሁም በጦርነት የወደመን የትግራይ ክልል መልሶ ለማቋቋም በሚል ቅዱስ ሃሳብ ቢሆንም ፤ በሂደት ግን እነዚህ የጁንታ አባላት ኩባንያዎቹን በስማቸው ማዞራቸውን ፤ ከዛም አለፍ ሲል ከ20 ዓመት በላይ ለሚሆን ጊዜ የውጭ ኦዲተር ወደነዚህ ኩባንያዎች ድርሽ እንዳይል መደረጉን አስታውቀዋል ። ስለ ኢፈርት ትልልቅ ኩባንያዎች የሚታወቅ ነገር የለም፤ ራሳቸው ያቦኩታል፣ ይጋግሩታል፣ ይበሉታል ያሉት ዋና ጸሀፊው ፣ ከነዚህ ኩባንያዎች የትግራይ ህዝብ ምንም ያገኘው ነገር እንደሌለ ገልጸዋል። በጣም የሚያስገርመው ነገር የመሶቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ አቅራቢያ ያሉ ነዋሪዎች አዋራው ለመተንፈሻ አካላት ህመም አጋለጠን እባካችሁ መፍትሔ ስጡን ብለው ቢጠይቁ እንኳን ምላሽ አለማግኘታቸውን አመልክተዋል ። መንግስት ለትግራይ ህዝብ ወገንተኛና ጠቃሚ መሆኑን፤ እንዲሁም ወጣቱ ላይ የተዘራውን አላስፈላጊ አረም በአጭር ጊዜ መንቀልና ወደ መስመር ማምጣት ከቻለ በእርግጠኝነት ህዝቡ ሙሉ በሙሉ ይህንን መንግስት ይደግፋል ብለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምክር ቤቱ ገለጻቸው በክልሉ ህጋዊ ሆነው የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ትግራይን በጋራ እንዲያስተዳድሩ ግልጽ የሆነ መልዕክት አስተላልፈዋል ያሉት አቶ ጊደና ፤ በመሆኑም አሁን እየተመሰረተ ያለው አስተዳደር በተቻለ መጠን አካታች ሊሆን እንደሚገባውም ጠቁመዋል። የትግራይ ጊዜያዊ ስራ አስፈጻሚ ሽሬ ከተማ ተገኝተው ህዝቡን አወያይተው አዲስ አስተዳደር እንዲመረጥ ማድረጋቸው በጣም ጥሩ አካሄድ መሆኑን የገለጹት አቶ ጊደና፣ ከዚህ በኋላም ቢሆን በተቻለ መጠን ከጁንታው ጋር ወግነው ህዝቡን ያልበደሉ፣ ቅን ልቦና ያላቸውና ህዝብን ለማስተዳደር የሚፈልጉ ሰዎች ወደ ስልጣን እንዲመጡ ማድረግ እንደሚያስፈልግም አመልክተዋል፡፡ “የትግራይ ህዝብ ሊያውቅ የሚገባው የጁንታው እድሜ ማለቁን ነው፤ ስለዚህ ነጻ እየወጣ መሆኑን ተገንዝቦ እራሱን ወደማስተዳደር፣ ወደ ልማትና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ሊገባ ይገባል “ ብለዋል፡፡አዲስ ዘመን ህዳር 26 ቀን 2013 ዓ.ም
https://www.press.et/Ama/?p=36737
533
0ሀገር አቀፍ ዜና
ጠሪ ያላከበሩት እንግዶች
ስፖርት
August 20, 2019
26
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ክለቦች ፈርጣማ የገንዘብ ጡንቻቸውን ለማሳየት በማይጠቅም እልህ፣ባልተገባ የእርስ በርስ ሽኩቻ እንዲሁም አሸናፊና ተሸናፊ በሌለበት ብስለት የጎደለው የዝውውር ፉክክር እርስ በርስ በመጠላለፍ ህልውናቸውን ለአደጋ ካጋለጡ ይተዋል። ይህን ፍልሚያ ያስተዋሉ ተጫዋቾችም ተደራ ጅተው የመደራደሪያ ገንዘባቸውን እየወሰኑና እየተ መካከሩ ዋጋቸውን ከፍ በማድረግ ክለቦችን እነርሱ በሚፈልጉት የዝውውር ቀለበት ውስጥ ከተዋቸዋል። ተጫዋቾች በጋራ ድምፅ ከአንድ ወይም ከሁለት አመት ኮንትራት ውጪ አንፈርምም እያሉ ከክለብ ወደ ክለብ ይዘዋወራሉ። በዚህም ረብጣ የደሞዝ ክፍያ ይቋደሳሉ። በተለይ የክልል ክለቦች እጅግ የተጋነነ ክፍያ ለተጫዋቾች በመክፈል ወደር አልተገኘላቸውም። ከህዝብ፣ ከግብርና ታክስ በተሰበሰበ ገንዘብ፣ ከክልል መስተዳድሮች በሚሰጥ በጀት እየተመደበ ያለተጠያቂና ውጤት ተኮር ዓላማ ለተጫዋቾች የሚወጣው በሚሊየኖች የሚቆጠር ገንዘብ እጅጉን ያስደነግጣል። በዚህም ምክንያት በሊጉ የተጫዋቾች ደመወዝ ባልተጠና መንገድ ተመንድጓል። ክለቦችም ገደብ የለሽ ከፍተኛ ገንዘብ ለተጫዋቾ እየከፈሉ ቡድን ለመስራት መሯሯጡን ቀጥለውበታል። ይህም የፋይናንስ አቅማቸውን ክፉኛ ፈትኖታል። የፋይናንስ ቀውስ ማሳያ ከሆኑ ከለቦች አንዱ የሆነው ጅማ አባ ጅፋር ለተጫዋቾቹ ደመወዝ መክፈል ተቸግሮ ከመቆየቱ ባለፈ ለካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ከቡድን አባላቱ መካከል ግማሽ ያህሉን ተጫዋቾች ብቻ ይዞ ወደ ሞሮኮ እንዲጓዝ አስገድዶታል። ክለቡ ሃገርን በወከለበት ውድድር ላይ ተጫዋቾቹን በዚህ አይነት መልኩ ይዞ ለመጓዝ የተገደደው ቢብስበት እንጂ ተገቢ እንዳልሆነ ይታወቃል። ከለቡ ከዚህ ደረጃ በላይ በውድድሩ አለመዝለቁ እንጂ በውጤት ወደፊት ቢራመድ ቀጣይ ወጪውን ሸፍኖ በውድድሩ እንደማይዘልቅ ያስታውቅ ነበር። ከፍተኛ የተጫዋቾች ዝውውር ክፍያን ከኢት ዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጋር ያስተዋወቀው ደደቢትም ሌላኛው ቅጥ ያጣ ገንዘብ አወጣጥ ላይ የቆየ ክለብ ነበር። ክለቡ በዚህ የተነሳም ነው ለቀውስ የተዳረገው። ክለቡ ባሳለፍነው አመት ‹‹በስህተቴ ወድቄአለሁ፣ በተጫዋቾች የዋጋ ንረት ከስሬለሁ፣ ህልውናዬ አደጋ ላይ ነው፣ እናም መንገድን ቀይሬአለሁ፣ ከእኔ ተማሩ›› በሚል መቀመጫውን ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ ማዛወሩም ይታወሳል። በ2011 ከኢትዮጲያ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር አመትም ለተጫዋች ደሞዝ ለመክፈል ተቸግሮ ሲንገዳገድ ተስተውላል። በሊጉም የደረጃ ሰንጠረዥ መጨረሻ ሲዳክር ከርሞም በጣር ውድድሩን በማጠናቀቅ ወደ ታችኛው ሊግ መውረዱም ይታ ወሳል። በወቅቱ ይህ አስደንጋጭ የደደቢት እግር ኳስ ክለብ ውድቀት ለተቀሩት የፕርሚሪየር ሊግ ክለቦች ቀይ መስመር ያመላከተ ቢሆንም፣ አብዛኞቹ የኢትዮጵያ ክለቦች ግን እርስ በእርስ ባልተገባ ፉክክር እየተጠላለፉ ከዚህ መማር የፈለጉ አይመስሉም፤መማር ያቃታቸውም ይመስላል። በዚህ ውጤት አልባ ጉዞም ተጨዋቾችን ከአንዱ ክለብ ወደ አንድ ክለብ ክብረ ወሰን በሆነ ገንዘብ ማዘዋወራቸውን ቀጥለዋል። ዘግይቶም ቢሆን ታዲያ በቅርቡ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የክለብ ተጫዋቾች የደመወዝ ጣሪያ በወር ከ50 ሺህ ብር እንዳይበልጥ ውሳኔ ተላልፏል። ዓርብ ነሐሴ 3 ቀን 2011 ዓ.ም የኢፊዲሪ ስፖርት ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ የክልል ስፖርት ቢሮ ኃላፊዎችና የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች አመራሮች በተገኙበት ቢሾፍቱ በተደረገው ጉባዔ ላይ ነው ውሳኔው የተላለፈው። ይህን የተጫዋቾች የደመወዝ ጣሪያ ውሳኔ ተከትሎም ሁለት አይነት አስተያየቶች ተሰምተዋል። በርካቶች ውሳኔው ቅጥ ያጣውን የከለቦች ከፍተኛ የደሞዝ ክፍያ መጠን ፈር ለማስያዝ ወሳኝ ሰለመሆኑ ተስማምተውበታል። አንዳንዶች በአንፃሩ ውሳኔው ‹‹በቂ ጥናቶች አልተደረገበትም፣እንዲህ በግርድፉ አገሪቱ ከሌሎች የአፍሪካ አገራት በላይ ልትከፍል አይገባም በሚል የተወሰነ ነው። ማንኛውም አይነት ውሳኔ ወደ ተግባር ከመተላለፉ በፊት የጊዜ ገደብ ያስፈልገዋል፤ የተጫዋቾች የደመወዝ ጣሪያ ውሳኔው ይህን ከግምት አላስገባም›› የሚሉ ትችቶችን ሰንዝረውበታል። ከሁሉም በላይ ግን በተጫዋቾች የደመወዝ ጣሪያ ውሳኔው ‹‹የሚመለከታቸው ዋነኛ ባለድርሻዎች ተጫዋቾች ሆነው ሳለ በመድረኩ አልተወከሉም፣ በጉዳዩ ላይም በቂ ውይይት አልተደረገም፣ ጉዳዩ በአግባቡ አልተብራራም፣ ግንዛቤም አልተ ፈጠረበትም፣ የሁሉም ባለድርሻዎች አካላት አስተያየት አልተደመጠም›› የሚሉ ቅሬታዎችም ቀርበውበታል። ይህን ቅሬታ ያደመጠው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንም ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በከፍተኛ እና አንደኛ ሊግ ላይ የሚገኙ ተጫዋቾችን “የደሞዝ ጣሪያ” በተመለከተ የምክክር መድረክ አዘግጅቶ ነበር። ዓለም ገና በሚገኘው ‹‹ኢንኮር››ሆቴል፣ በተጠራው የውይይት መድረክ ላይም ለ36 የከፍተኛ እንዲሁም ለ55 የአንደኛ ሊግ (በቀድሞ መጠሪያው ብሄራዊ ሊግ) ክለቦች ጥሪ ተደርጎላቸዋል። መድረኩ ከማካሄዱ አስቀድሞም ምልአተ ጉባኤው ሙሉ በሙሉ መሟላት አሊያም ከሶስት አራተኛው በላይ ስለመገኘታቸው ቆጠራ የተካሄደ ሲሆን፣ ግኝቱም ምልአተ ጉባኤው ሙሉ ሆኖ አለመቅረቡን ተረጋግጧል። ከ36 የከፍተኛ ሊግ ተወካዮች መካከል 19 እንዲሁም ከ55 የአንደኛ ሊግ ከለቦች መካከል 14 ብቻ በአጠቃላይ ከ91 ተወካዮች 33ቱ ብቻ መገኘታቸው ታውቋል። ውይይቱን ለማካሄድ የታዳሚውን ፈቃድ ማግኘት ግድ ብሏል። ታዳሚውም ሁለት አይነት አስተያየቶችን ሰንዝሯል። አንዳንድ የስብሰባው ተሳታፊዎች ‹‹ደንብ፣ስርአት፣ መመሪያና ሰአት፣ አክብረን በቦታው ስለተገኘን ውይይቱ ሊካሄድ ይገባል፣ይህ ካልሆነ ቀሪዎቹ ሲመጡ፣ ዛሬ የተገኙት ቀርተዋል እየተባለ ‹ተጨማሪ ጊዜ ስለሚወስድ ውይይቱ መካሄድ አለበት›› ሲሉም ጠይቀዋል። በጣም ርቀት ካላቸው ክልሎች የመጡ የጉባኤው ታዳሚዎች በበኩላቸው ‹‹ምልአተ ጉባኤው ባይማሏም ውይይቱ ዛሬ መካሄድ አለበት፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንም ለድካማችን እውቅና ሊሰጠን ይገባል›› ሲሉ በብርቱ ተከራክረዋል። አንዳንዶች በአንፃሩ ይህን ታሳቢ በማድረግ ውይይቱ ቢካሄድ እንኳ በመድረኩ ያልተገኙት ባለድርሻዎች ቅሬታ ማቅረባቸው አይቀሬ ነው፣ነገ ‹‹እኔ አልወሰንኩም›› የሚል አቋም ይንፀባረቃል፤ እናም እነርሱ ባልተገኙበት ውይይቱን ማካሄድ ትርፉ ድካም ነው፤ ያላወቁት እንዲያውቁ፣ የዘነጉትም እንዲያስታውሱ በማድረግ ዳግም ብንገኛኝ ይሻላል›› የሚል አስተያየት ሰጥተዋል። ከሁሉም በላይ ግን አንዳንድ ክለቦች በዝውውር መስኮቱ ተጫዋቾችን ማስፈረም ቢጀምሩም ደሞዝ ክፍያውን አስመልክቶ ይህ ነው የሚባል ደንብ፣ ስርአትና መመሪያ አለማግኘታቸውን በመጥቀስ ይህም በስራቸው ላይ እንቅፋት መፍጠሩን አስገንዝበዋል። ‹‹ይህ በመሆኑም ውይይቱ ተካሂዶ ችግሮች በቶሎ መፍትሄ መያዝ ይኖርባቸዋል›› ብለዋል። በዚህ መልኩ የየቅል አስተያየትን ያስተናገደውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በሳምንቱ መጨረሻ ሊያካሂድ ያቀደው ይህ የውይይትና የግንዛቤ ፈጠራ መድረክም ጠሪአቸውን አክብረው ባልተገኙ ባለ ድርሻዎች ምክንያት ሳይካሄድ ቀርቷል። ባለድርሻዎቹ በውይይቱ ላይ ላለመገኘታቸውም ከእለቱ ዝናባማ መሆን በላይ ፌዴሬሽኑ ጥሪ ሲያደርግ በመድረኩ ለመታደም የሚመጡ ግለሰቦች ወጪአቸውን በራሳቸው እንዲችሉ ማሳወቁ እንደ አንድ ምክንያት በጉባኤተኛው የተገለፀ ሲሆን፣ ‹‹ፌዴሬሽኑ የውሎ አበል እከፍላለሁ›› የሚል ቢያካትት አዳራሹ ሙሉ ይሆን ነበር›› ተብሏል። ከቀጣዩ አመት በፊት ተጫዋቾችን በማስፈረም ቶሎ ወደ ዝግጅት ምእራፍ ስለመግባትና በደሞዝ ጣሪያው ውሳኔ ላይ በፍጥነት ስለመግባባትና ወደ ስራ ስለ መግባት ከመጠየቅ ይልቅ የውሎ አበል ወጪ ጥያቄ ተደጋግሞ በተነሳበት በዚህ መድረክም፣ በቀጣይም ፌዴሬሽኑ የተሳታፊዎችን ወጪ ሸፍኖ በመድረኩ የሚገኙበትን መንገድ ቢያመቻች፣ጥሪውም በድጋሚ ተደርጎ በአጭር ጊዜ ውስጥ መድረኩ እንዲካሄድ ይደረግ የሚል አስተያየት ቀርቧል። ‹‹ጥያቄው ከእናንተው ተነስቶ እናንተው ከመድረኩ መቅረታችሁ ግር የሚያሰኝ›› ነው ያሉት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጂራ፣ባለድርሻዎች በዚህ መድረክ እንዲገኙለትም ከአምስት ቀናት በፊት ጥሪ ማቅረቡን ተናግረዋል። ‹‹አንድ ሊታወቅ የሚገባው ነገር ቢኖርም፣ ፌዴሬሽኑ የደሞዝ ጣሪያው ውሳኔ አካል አይደለም፣ ወሳኙ እናንተው ናችሁ›› ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ ‹‹እኛ ምንም የምንሰጠው አጀንዳ ወይም ሰነድ የለም፤ የእናንተው ጉዳይ ነው፤ እኔም ተቋሜም በዚህ ጉዳይ ወሳኝ አይደለንም አመቻቺዎች ነን» ብለዋል። ፕሬዚዳንቱ በቀጣይም በፌዴሬሽኑ ግፊት የሚሆን ነገር እንደማይኖር አስገንዝበው፣ጥሪ ያላከበሩት እንግዶች ሌላ ጥሪ ቀርቦላቸው የውይይቱም ቀን ከሁለት ሳምንት በኋላ ለነሀሴ 25 እንዲሆን ውሳኔ ተላልፏል። አዲስ ዘመን ነሀሴ 14/2011ታምራት ተስፋዬ
https://www.press.et/Ama/?p=16415
889
2ስፖርት
ማብራሪያው ጁንታው በጠቅላይ ሚኒስትሩና በአገሪቱ ላይ የነበረውን አሉታዊ ጫና ያሳየ እንደሆነ ተጠቆመ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 5, 2020
17
አንተነህ ቸሬአዲስ አበባ፡- ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ኅዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ማብራሪያና ምላሽ የህ.ወ.ሓ.ት ጁንታ በጠቅላይ ሚኒስትሩም ሆነ በአገሪቱ ላይ ሲያደርስ የነበረውን አሉታዊ ጫና ያሳየ እንደነበር የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለጹ። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጣሂር መሐመድ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የሰጡት ማብራሪያ ለውጥ መጣ ከተባለበት ጊዜ ጀምሮ የነበረውን አገራዊ ሁኔታ የሚያስረዳ በጎ ገለፃ ነው። ማብራሪያው አሸባሪው የትሕነግ ቡድን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስራቸውን በነፃነት እንዳይሰሩና በአጠቃላይ የአገሪቱ ቁመና ላይ ሲያደርስ የነበረውን ጫና አመላካች ነው። እንደርሳቸው ገለፃ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለፃ የአገር መከላከያ ሰራዊት የደረሰበት አሳዛኝ ጥቃት እንዲሁም ሰራዊቱ የአገሪቱን ሕልውና ለማስጠበቅ የከፈለው መስዋዕትነት የተብራራበት ነው። ከዚህ በተጨማሪም በመከላከያውና በደህንነት መስሪያ ቤቱ ውስጥ ስለነበረው የብሔር የበላይነት እንዲሁም እርሳቸው ስለነበረባቸው ጫና ማብራሪያ መስጠታቸው በጉዳዩ ላይ ብዥታ ለነበረባቸው አካላት የጠራ መረጃ ለመስጠት አስተዋፅኦ ነበረው። ‹‹ብዙዎቻችን የኃይል አሰላለፍና የሁኔታ ትንተና ላይ ትኩረት አድርገን እንሰራለን። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለማብራራት እንደሞከሩት በትሕነግ ላይ ቀደም ብሎ እርምጃ መውሰድ ይቻል ነበር ወይንስ አይቻልም የሚለው ጉዳይ በእኛም በኩል አነጋጋሪ ሆኖ ቆይቷል›› ያሉት አቶ ጣሒር፣ ቡድኑ አሁን የደረሰበት ውርደት አገራዊ እፎይታ ሊሰጥ የሚችል እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው እንዳመለከቱ ተናግረዋል። ስለመጪው የአገሪቱ ሁኔታ ተስፋ የታየበት ገለፃ እንደነበርም አስረድተዋል።የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ትሕነግ በአሸባሪነት እንዲፈረጅ ጥያቄ ማቅረባቸውን አድንቀው፤ ጥያቄው ተጠናክሮ ቀጥሎ ቡድኑ በአሸባሪነት መፈረጅ እንዳለበትም አሳስበዋል። ሕገ መንግሥቱን ጨምሮ ትህነግ የመሰረታቸውን ተቋማዊ የጭቆና መዋቅሮችንና ሰነዶችን እንዲሁም በመንግስት መዋቅር ውስጥ ያሉ አሰራሮችን በማስተካከልና ትርክቱን በመቀየር ቀጣዩን ጊዜ የተሻለ ማድረግ እንደሚቻልም አቶ ጣሂር ተናግረዋል።የኦሮሞ ነፃነት ንቅናቄ ሊቀመንበር እና የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት ሊቀ መንበር አቶ ደረጀ በቀለ በበኩላቸው፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ብዙ ፈተናዎችን እንዳለፉ የሚያሳይ እንደሆነ ገልጸዋል። ማብራሪያው ህ.ወ.ሓ.ት የማፍያ ቡድን እንጂ አገር የሚያስተዳድር አካል እንዳልሆነም ያሳየ እንደነበር ጠቁመዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ የህ.ወ.ሓ.ት ጁንታ በአገሪቱ ላይም ሆነ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ያደርሰው የነበረው ጫና ከፍተኛ እንደነበር ለማየት ያስቻለ ፣ ቡድኑ አገሪቱ ለሱ ብቻ እንደተሰጠች አድርጎ የሚያስብ እንደሆነ ያሳየ ነው ብለዋል። ‹‹ንግግራቸው የወደፊቷ ኢትዮጵያ የሁላችንም መሆኗን፣ ሕዝብንና አገርን የሚስጨንቅ ቡድን ቦታ እንደማይኖረውና ስልጣን ሕዝብን ማገልገያ ሊሆን እንደሚገባ ያመላከተ ቁም ነገር አዘል ንግግር ነው›› ብለዋል።አዲስ ዘመን ህዳር 26 ቀን 2013 ዓ.ም
https://www.press.et/Ama/?p=36738
334
0ሀገር አቀፍ ዜና
«ጨዋታው አልቋል ብዬ አላስብም»- ሰላም ዘርዓይየኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ
ስፖርት
August 28, 2019
36
ኦሊምፒክ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ለቶኪዮ ኦሊምፒክ ለማለፍ ከካሜሮን ሴት ብሄራዊ ቡድን ጋር ያደረገውን የቅድመ ማጣሪያ የሁለተኛ ዙር ጨዋታ በአቻ ውጤት ነበር ያጠናቀቀው። በባህርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ነሃሴ 20 ቀን 2011 ዓ.ም የተካሄደው ጨዋታው 1 ለ1 በሆነ ውጤት መጠናቀቁ የቡድኑን ቀጣይ እጣ ፈንታ የሚወስን አለመሆኑን የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሰላም ዘርዓይ ገልጻለች።በአቻ ውጤት የተጠናቀቀውንና በዚህ ሳምንት መጨረሻ ላይ የሚከናወነውን የመልስ ጨዋታ በማስመልከት አስልጣኟ በሰጠችው አስተያየት፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በመጀሪያው የጨዋታ አጋማሽ በኳስ ቁጥጥርና የግብ እድሎችን በመፍጠር ከተጋጣሚው የተሻለ ነበር። በሁለተኛው አጋማሽ ደግሞ የካሜሮን ብሔራዊ ቡድን የተሻለ እንቅስቃሴ ማሳየት ችሏል። ‹‹ከካሜሮን ሴት ብሄራዊ ቡድን ጋር የነበረን ጨዋታ ምንም እንኳን በሜዳችን የነበረ ቢሆንም ከባድና አስቸጋሪ ነበር›› ብላለች። እንደ አሰልጣኟ ገለጻ፣ በመጀመሪያው አጋማሽ ቡድኑን አክብዶ ከማየት አንጻር በእንቅስቃሴ ውስጥ በራስ መተማመን ሲያጡ ተስተውለዋል። ሁለተኛው አጋማሽ ላይ በካሜሮኖች በኩል ፈጣን የማጥቃት እንቅስቃሴ መኖርን ተከትሎ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ቅርፁን የማጣት ሁኔታዎች ተስተውለውበት ነበር። የቡድኑ መረጋጋት ማጣት ግብ እንዲቆጠር ምክንያት የሆነም ነበር። ‹‹በቡድናችን ላይ በተለይ የአካል ብቃት ችግር ጎልቶ ይታይ ነበር። ለጨዋታው ያደረግነው ዝግጅት ወደ 17 ቀናት አካባቢ ሲሆን፤የዝግጅቱ ሁኔታ በቂ ነው ለማለት አዳጋች ነው። ተጫዋቾቹ ከሁለት ወራት በላይ እረፍት ላይ ስለነበሩ ተጽዕኖ ፈጥሯል›› ብላለች።በጨዋታው የካሜሮን ብሄራዊ ቡድንን ማሸነፍ ባይቻልም እንኳ ውጤቱ ጥሩ የሚባል እንደሆነ የገለጸችው አሰልጣኟ፤ የካሜሮን ቡድን የሚናቅ እንዳልሆነና ቡድኑ አሁን በሚያሳየው እንቅስቃሴ ብቻ ሳይሆን ትልቅ እና የሚከበር ቡድን መሆኑንም ተናግራለች። በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በኩል የልምድ ማነስና በራስ የመተማመን ችግር ባይስተዋል ማሸነፍ ይቻል እንደነበርም ጠቁማለች።«ጨዋታው አልቋል ብዬ አላስብም። በባህር ዳር የነበረው ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ እንጂ ጨዋታው ሙሉ ለሙሉ አልቋል ብለን አናምንም። የጨዋታው 90 ደቂቃ አልቋል፤ቀሪውና ወሳኙ 90 ደቂቃ ይቀራል» በማለት ተናግራለች።የባህር ዳሩ ጨዋታ በዚህ መልኩ ቢጠናቀቅም ለመልሱ ጨዋታ ጊዜ ሳያጠፉ ወደ ዝግጅት እንደሚገቡ የገለጸችው አሰልጣኝ ሰላም፤ ነሐሴ 26 ቀን 2011 ዓ.ም በካሜሮን ዋና ከተማ ያውንዴ ለሚጠብቃቸው የመልስ ጨዋታ በቀሩት ጊዜያት ተዘጋጅተው ድክመታቸው አሻሽለው ውጤት ለማስመዝገብ እንደሚሞክሩ ገልፃለች።በባህር ዳር ዓለም ዓቀፍ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ለስፔኑ ክለብ ሪያል ቤቲስ የሴት ቡድን የምትጫወተው የአጥቂ መስመር ተጫዋቿ ሚካኤላ አባም በ50ኛው ደቂቃ ባስቆጠረችው ግብ ካሜሮንን ቀዳሚ ማድረግ ችላ ነበር። ከእረፍት መልስ ተቀይራ የገባቸው የአዳማ ከተማዋ ተጫዋች ሰናይት ቦጋለ፣ የካሜሮን የተከላካይ ክፍል የሰራውን ስህተት ተጠቅማ በ82ኛው ደቂቃ ያስቆጠረችው ግብ ሉሲዎችን አቻ ማድረግ ችሏል። በጨዋታው ኬንያዊቷ ኢንተርናሽናል ዳኛ ናፓኞር አኜታ የካሜሮኗን የተካላካይ መስመር ተጫዋች ሌዩኮ ዩቬኔ በቀይ ካርድ ያሰናበተች ሲሆን ለሁለት የካሜሮን ተጫዋቾችም የቢጫ ካርድ አሳይታለች።የሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች የመልስ ጨዋታ ነሐሴ 26 ቀን 2011 ዓ.ም በካሜሮን ዋና ከተማ ያውንዴ ይሄዳል። የኢትዮጵያ ሴቶች ኦሊምፒክ ብሔራዊ ቡድን በደርሶ መልስ ውጤት ካሸነፈ በሶስተኛ ዙር ማጣሪያ በመስከረም 2012 ዓ.ም ከዴሞክራቲክ ኮንጎ እና ከኢኳቶሪያል ጊኒ አሸናፊ ጋር የሚጫወት ይሆናል። ብሔራዊ ቡድኑ በመጋቢት 2011 ዓ.ም የመጀመሪያ ዙር የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታዎን ከዩጋንዳ ጋር አድርጎ በድምር ውጤት 4 ለ 2 ማሸነፉ ይታወሳል።እ.አ.አ በ2020 በጃፓን ቶኪዮ በሚካሄደው 32ኛው የኦሊምፒክ ውድድር የአፍሪካ ዞን የእግር ኳስ የማጣሪያ ውድድር ከመጋቢት 2011 ዓ.ም ጀምሮ በመካሄድ ላይ ይገኛል።አዲስ ዘመን  ረቡዕ ነሀሴ 22/2011ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=16884
443
2ስፖርት
ሉሲዎቹ ዛሬ የኦሊምፒክ ማጣሪያ ጨዋታ ያደርጋሉ
ስፖርት
August 26, 2019
21
የኢትዮጰያ ሴት ብሄራዊ ቡድን (ሉሲዎቹ) ዛሬ የኦሊምፒክ ማጣሪያ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። እአአ 2020 በጃፓን ቶኪዮ በሚካሄደው ኦሊምፒክ ተሳታፊ ለመሆን በሚደረገው ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ሉሲዎቹ ሁለተኛ ዙር ጨዋታቸውን ከካሜሩን ብሄራዊ ቡድን ጋር በባህር ዳር ስታዲየም ያከናውናሉ። ብሄራዊ ቡድኑ የመጀመሪያ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታውን ከኡጋንዳ አቻው ጋር ያደረገ ሲሆን፤ በሜዳው ሶስት ለሁለት ከሜዳው ውጪ ደግሞ አንድ ለባዶ በሆነ ውጤት ነበር ያጠናቀቀው። አራት ለሁለት በሆነው የደርሶ መልስ ውጤት ማሸነፉም ለሁለተኛ ማጣሪያው እንዲበቃ አድርጎታል። ሁለተኛውን ጨዋታም ከምዕራብ አፍሪካዊቷ ሃገር ካሜሩን ጋር ዛሬ በሜዳው ያደርጋል። የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ሰላም ዘርዓይ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ በማቅረብ አስቀድማ ወደ ዝግጅት የገባች ሲሆን፤ የቡድኑን ወቅታዊ አቋም መፈተሽ ይችል ዘንድ ባለፈው ሳምንት ከኬንያ አቻው ጋር የወዳጅነት ጨዋታ አድርጓል። በጨዋታው ሦስት ለሁለት በሆነ ጠባብ ውጤት ተሸንፎ ቢመለስም፤ ቡድኑ ጥንካሬና ክፍተቶቹን የለየበት እንዲሁም ትምህርት ያገኘበት መሆኑን አሰልጣኟ ጠቁማለች። የሴቶች ብሔራዊ የኦሊምፒክ ቡድኑ ከኬንያው የወዳጅነት ጨዋታ መልስ በቀጥታ ወደ ባህር ዳር ያመራ ሲሆን፤ ለአንድ ሳምንት ያህልም ዝግጅቱን ሲያደርግ ነው የቆየው። ሉሲዎቹን የሚገጥሙት የካሜሩን ብሄራዊ ቡድን አባላትም በተመሳሳይ የዛሬ ሳምንት ባህር ዳር በመግባት ልምምዳቸውን ሲያካሂዱ መቆየታቸው ታውቋል። የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሰላም ዘርዓይ፤ ካሜሩኖች ጠንካራ ቢሆኑም፤ ሉሲዎቹ ድክመቶቻቸውን መቅረፍ ከቻሉ ጥሩ ተፎካካሪ መሆን እንደሚችሉ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ በሰጠችው አስተያየት ገልጻለች። የዛሬውን ጨዋታ አስመልክቶም «የወዳጅነት ጨዋታው የኬንያዊያንን ጥንካሬ ለመለካት ሳይሆን የቡድናችንን ጥንካሬ ለመፈተሽ ነው ያደረግነው። በመሆኑም ቡድናችን በጥንካሬ ላይ ተመስርቶ ነው የተሰራው። እስካሁንም ድክመቶቻችን ላይ ስንሰራ ቆይተናል፤ ስለዚህም ለማንኛውም ቡድን ብቁ የማንሆንበት ምክንያት የለም» ብላለች። የቡድኑ አባላት የ2011 ዓ.ም የጨዋታ ዓመት ከተጠናቀቀ በኋላ እረፍት ላይ በመቆየታቸው፤ ከ13 ቀናት በፊት በአዳማ ከተማ በመሰባሰብ የመጀመሪያ ዙር ዝግጅቱን መጀመሩንም ታስታውሳለች። ከዚያም የዝግጅቱ አካል ወደ ሆነው የወዳጅነት ጨዋታ በማምራት አቅማቸውን ፈትሸዋል። በዚህም ቡድኑ ጥሩ ነገር አግኝቶ ሁለተኛ ዙር ውድድሩን በባህርዳር ሲያደርግ ቆይቷል። ከተማው ለቡድኑ ጥሩ አቀባበል ያደረገ ሲሆን፤ቡድኑ ውጤት እንዲያመጣም ሁሉም የበኩሉን አድርጓል። በርካታ አህጉር አቀፍ ውድድሮችን ያስተናገደው ባህር ዳር፤ ለጨዋታው ምቹ የሚባል ሜዳ እንዳለውም አሰልጣኟ ጠቁማለች። የምትመራው ቡድን በወጣቶች የተዋቀረ መሆኑን የምታነሳው አሰልጣኟ፤ ከዘጠና በመቶ በላይ የሚሆኑት ተጫዋቾች ባለፉት ሁለት ዓመታት በብሄራዊ ቡድኑ ውስጥ እንደቆዩ ገልጻለች። ይህ የቡድኑ ጥንካሬ ሲሆን፤ ያላቸውን ጠንካራ የሃገር ስሜትና ፍላጎት በመጠቀም መሻሻል እንደሚያሳይ ተስፋ ተጥሎበታል። የካሜሩንን ጥንካሬና ድክመት በመተው ቡድናቸው ላይ አተኩረው መስራታቸውን ጠቅሳ፤ ጨዋታውም ጠንካራ እንደመሆኑ ቡድኑ ያለበትን ደረጃ የሚያሳይ መሆኑንም አመላክታለች። ቡድኑ ጥቂት ጉዳቶችን ያስተናገደ ሲሆን፤ በአጠቃላይ ሶስት ተጫዋቾች በጨዋታው አይካተቱም። አጥቂዋ ሎዛ አበራ በአውሮፓ ክለብ ሙከራ ላይ ስትገኝ፤ የ2011 ዓ.ም ኮከብ ግብ አስቆጣሪ በመሆን የውድድር ዓመቱን ያጠናቀቀችው ሲናፍ ዋቁማ መጠነኛ ጉዳት አስተናግዳለች። የተከላካይ መስመሯ ቅድስት ዘለቀ የትርፍ አንጀት ቀዶ ጥገና በማድረጓ ምክንያት በጨዋታው ላይ አትሳተፍም። ከእነዚህ ውጪ ያሉት የቡድኑ አባላት ግን በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ። ብሄራዊ ቡድኑ ባህር ዳር ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ ባሻገር የክልሉን ስፖርት ለማነቃቃት የሚጠቅም መሆኑንም አሰልጣኟ አንስታለች። በክልሉ ከዚህ ቀደም የነበረው አንድ ክለብ አሁን በመፍረሱ፤ ምንም ዓይነት የሴት ቡድን የለም። ይህም እንደ ማነሳሻ በመሆን ለውጥ ሊያመጣ እንደሚችል ተስፋ ማድረጓንም አያይዛ ጠቁማለች። ካሜሮን በሴቶች እግር ኳስ ከአህጉር አቀፍ ተሳትፎ ባሻገር የዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይም አፍሪካን በመወከል ከቀዳሚዎቹ መካከል ይጠቀሳል። በአራት የአፍሪካ ዋንጫ ውድድሮች ላይ የተሳተፈው ቡድኑ፤ የዘንድሮውን ጨምሮ በሁለት ዓለም ዋንጫዎች ላይም ተካፋይ መሆን የቻለ ነው። የእንግሊዟ ለንደን ባስተናገደችው ኦሊምፒክ ላይም በመሳተፍ የተሻለ ታሪክ ማስመዝገብ ችሏል። ቡድኑ ባለፈው ወር በወጣው የፊፋ የሃገራት የእግር ኳስ ደረጃ 41ኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝም መረጃዎች ያመላክታሉ። ጨዋታው በካፍ የሁለት ወር የጊዜ ገደብ ከሰጣቸው ስታዲየሞች መካከል አንዱ በሆነው የባህርዳር ስታዲየም ዛሬ ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ የሚካሄድ ሲሆን፤ በቴሌቪዥን ቀጥታ ስርጭት እንደሚተላለፍ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። ፌዴሬሽኑ ከኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ ጨዋታውን ለእይታ እንደሚያበቃም ነው በድረገጹ ያስነበበው። የመልሱ ጨዋታም ከስምንት ቀናት በኋላ በመጪው ማክሰኞ በካሜሩን ይካሄዳል። የማጣሪያ ጨዋታው በአጠቃላይ አምስት ዙሮች ያሉት ሲሆን፤ ኢትዮጵያ በደርሶ መልስ ጨዋታው ጠንካራዋን ካሜሩንን ማሸነፍ ከቻለች ሶስተኛ ጨዋታዋን ከዴሞክራቲክ ኮንጎ እና ኢኳቶሪያል ጊኒ አሸናፊ ጋር የምታደርግ ነው የሚሆነው። ኢትዮጵያ በተያዘው የነሃሴ ወር በሁለቱም ጾታ ለምትወከልባቸው አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ውድድሮች በሜዳዋ ሶስት ወሳኝ ጨዋታዎችን እንደምታከናውን የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ያወጣው መርሃ ግብር ያሳያል። እንደ ሴቶቹ ሁሉ ወሳኝ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ የሚጠብቀው የወንድ ብሄራዊ ቡድንም ለ2022 የኳታር ዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ እንዲሁም በ2020 ካሜሮን ለምታስተናግደው ቻን ዝግጅት የተጨዋቾች ጥሪ መደረጉን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል። ቡድኑ ነሃሴ 28/2011 ዓ.ም በባህር ዳር ስታድየም የሌሴቶ አቻውን የሚያስተናግድ ሲሆን፤ የቻን ማጣሪያውን ደግሞ መስከረም 11/2012 ዓ.ም በትግራይ ስታዲየም ከሩዋንዳ ጋር ያካሂዳል። አዲስ ዘመን ነሀሴ 20/2011ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=16777
650
2ስፖርት
ታላቁ ሩጫ ለታላቅ ሽልማት ታጨ
ስፖርት
September 5, 2019
13
 በጀግናው አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ መስራችነት የተቋቋመው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ባለፉት አስራ ስምንት ዓመታት አስር ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር በአዲስ አበባ በማካሄድ ተወዳጅነትን ማትረፉ ይታወቃል፡፡ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የተሳታፊዎቹን ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሳደገም በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ እውቅናን አትርፏል፡ ፡ አሁን ደግሞ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለታላቅ ሽልማት ለመብቃት እጩ መሆን እንደቻለ ኢትዮ ስፖርት በድረ ገፁ አስነብቧል፡፡ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በዓለም ላይ ከሚካሄዱ ሃያ ምርጥ የጎዳና ላይ ውድድሮች አንዱ በመሆን ‹‹ሌትስ ዱ ዚስ›› በተባለ ድረ ገፅ እጩ ተደርጓል፡፡ ሽልማቱን የሚያዘጋጀው ድረ ገፅ በዓለም ላይ ትልቅ እውቅና ያለው ሲሆን ከአስራ ስምንት ሺህ በላይ የጎዳና ላይ ውድድሮችን በዝርዝሩ የያዘ ነው፡፡ በአንድ ወር ውስጥም ከአንድ ሚሊየን በላይ ተመልካቾች አሉት፡፡ ሽልማቱ የሚካሄደው ብስክሌትን ጨምሮ በተለያዩ ስፖርቶች በአስራ ሦስት የሽልማት ዘርፎች ተከፍሎ ሲሆን ታላቁ ሩጫ የታጨበት የሽልማት ዘርፍ ዓለም አቀፍ የጎዳና ላይ ውድድር መሆኑ ታውቋል፡፡ ሽልማቱ በመጪው ጥቅምት ለንደን ከተማ ላይ ሲከናወን የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ የተከላካይ አማካይ ተጫዋችና በአሁኑ ወቅት የቴሌቪዥን ተንታኝ ሪዮ ፈርዲናንድ እንዲሁም ሌሎች ዝነኛ የስፖርቱ ዓለም ሰዎች እንደሚታደሙ ዘገባው ያመለክታል፡፡ ታላቁ ሩጫ እጩ በሆነበት የሽልማት ዘርፍ ዝነኞቹ የማራቶን ውድድሮች ኒውዮርክ ማራቶንና ቦስተን ማራቶን ተካተዋል፡፡ የሽልማቱ አሸናፊዎች በየዘርፉ የሚወሰኑት ውድድሮቹ ላይ የተሳተፉ የሕብረተሰብ አካላት በድረ ገፅ አማካኝነት በሚሰጡት ድምፅ ቁጥር መሰረት ይሆናል፡፡ ታላቁ ሩጫ ባለፉት 18 ዓመታት እንደስሙ ታላላቅ ስኬቶችን ማስመዝገብ የቻለ ውድድር መሆኑን በርካቶች ይመሰክራሉ፡፡ በተለይ ተተኪ አትሌቶችን በማፍራት በኩል ረጅም ርቀት መጓዙን የሚገልጸው የውድድሩ ድረ ገጽ የበጎ አድራጎት ሥራዎችን በማከናወንም ስኬታማ መሆኑ ተገልጿል። ከበጎ አድራጎትና ተተኪ አትሌቶችን ከማፍራቱ በተጨማሪ ታላቁ ሩጫ ኢትዮጵያን በሌላ መንገድ በማስተዋወቅ ስኬታማ ጉዞ ማድረጉ ይታወቃል።አዲስ ዘመን  ነሐሴ 30/2011 ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=17340
244
2ስፖርት
ስለ ዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ቁጥሮች ምን ይላሉ
ስፖርት
August 31, 2019
24
በዘንድሮው ዓመት ዓለማችን ከምትጠብቀው ታላቅ የስፖርት መድረክ አንዱና ዋነኛው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና መሆኑ ጥርጥር የለውም። ይህን ታላቅ ድግስ ለማሰናዳት የመካከለኛው ምስራቅ ከበርቴ አገር ኳታር በመዲናዋ ዶሃ ከሊፋ ዓለም አቀፍ ስቴድየም ሽርጉዷን ጨርሳ እንግዶቿን እየተጠባበቀች ነው። ቻምፒዮናው ሊጀመር ዛሬ ሃያ አምስት ቀናት ብቻ ይቀሩታል። አዲስ ዘመን ቅዳሜ እንዳለፉት ሳምንታት ሁሉ በዓለም ቻምፒዮናው ዙሪያ ልዩ ዘገባዎችን እያደረሰ ሲሆን ለዛሬ በዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ቁጥሮች የሚናገሩትን የተለያየ ስታስቲካዊ መረጃ እንደሚከተለው ቃኝቶታል።የዓለም ቻምፒዮና ከየት ወደ የት?የዓለማችን ትልቁ የአትሌቲክስ መድረክ ከአርባ አምስት ዓመታት በላይ ታሪክ አለው። የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና እኤአ በ1983 ፊንላንድ ሄልሲንኪ ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ መካሄድ ጀመረ። እኤአ በ1987ና 1991 በአራት ዓመት ልዩነት የጣሊያኗ መዲና ሮምና የጃፓኗ ቶኪዮ ይህን ታላቅ ውድድር ያዘጋጁ አገሮች ናቸው። ከቶኪዮ ወዲህ ግን ውድድሩ በሁለት ዓመት ልዩነት ነው እየተካሄደ የሚገኘው። የጀርመኗ ስቱትጋርት፤ የስዊድኗ ጉተንበርግ፤ የግሪኳ አቴንስ፤ የስፔኗ ሴቪሊ፤ የካናዳዋ ኤድመንተን፤ የፈረንሳይ መዲና ፓሪስ፤ የፊንላንዷ ሄልሂንኪ(ለሁለተኛ ጊዜ) የጃፓኗ ኦሳካ፤ የጀርመኗ በርሊን፤ የደቡብ ኮሪያዋ ዴጉ፤ የሩሲያዋ ሞስኮ፣ የቻይናዋ ቤጂንግና የእንግሊዟ ለንደን ቻምፒዮናውን በሁለት ዓመት ልዩነት በቅደም ተከተል አዘጋጅተውታል። የዘንድሮው ዓመት ተረኛዋ የመካከለኛው ምስራቅ ቁንጮ የሆነችው የኳታሯ መዲና ዶሃ ስትሆን፤ የአሜሪካዋ ዩጂን፣ የሃንጋሪዋ ቡዳፔስት ቀጣዮቹን ሁለት ቻምፒዮናዎች ለማዘጋጀት ወረፋ ይዘዋል። ኢትዮጵያም ቻምፒዮናው ከተጀመረ አንስቶ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ላይ ትገኛለች።የዓለም ቻምፒዮና ድሮና ዘንድሮየዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና አሁን ያለውን መልክ ይዞ መካሄድ ከመጀመሩ በፊት እኤአ በ1913 የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ማህበር ኦሊምፒክ እንደ ዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ያገለግላል ብሎ አምኖበት ነበር። ይህም ለሃምሳ ዓመታት ያህል አገልግሎት 1960ዎቹ ውስጥ በርካቶቹ የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ማህበር አባል አገሮች «የራሳችን የሆነ ውድድር ይኑረን» ብለው ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት እኤአ በ1976 ፑርቶሪኮ ላይ በተደረገ ዓመታዊ የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ማህበር ስብሰባ ላይ የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ከኦሊምፒክ ተለይቶ ራሱን የቻለ ውድድር እንዲያካሂድ ተወሰነ። በእዚህ ወቅት የመጀመሪያውን ውድድር ለማስተናደግ የምዕራብ ጀርመኗ ስቱትጋርትና የፊንላንዷ ሄልሲንኪ ጥያቄ አቀረቡ። እኤአ በ1952 ኦሊምፒክን ያስተናገደችው ሄልሲንኪ እድሉን አገኘች።የተሳታፊ አገራት ክብረወሰንየዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና በውድድር አይነትና በተሳታፊዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ በርካታ ለውጦችን አስተናግዷል። እኤአ በ1983 ከመቶ ሃምሳ አራት አገራት የተውጣጡ አንድ ሺ ሦስት መቶ አትሌቶች ተሳታፊ ነበሩ። ይህ ቁጥር እኤአ 2003 ፓሪስ ላይ ተካሂዶ በነበረው ቻምፒዮና ከሁለት መቶ ሦስት አገሮች የተውጣጡ አንድ ሺ ዘጠኝ መቶ ሰባት አትሌቶች አሻቅቧል።የውድድሮች ብዛትና አይነትበዓለም ቻምፒዮና የተሳታፊዎች ቁጥር ብቻ ሳይሆን በተለያዩ የውድድር አይነቶችም በርካታ ለውጦች ታይተዋል። በተለይም ወንዶች በሚወዳደሩባቸው የውድድር አይነቶች ሴቶችም ተካፋይ እንዲሆኑ መደረጉ የቻምፒዮናው ትልቅ ለውጥ ነው። በዚህ መነሻም አሁን ላይ በዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ወንዶች የሚወዳደሩበት ለሴቶች ያልተፈቀደ የሃምሳ ኪሎ ሜትር የርምጃ ውድድር ብቻ ነው።እኤአ በ1987 የሴቶች አስር ሺ ሜትር ሩጫና አስር ኪሎ ሜትር ርምጃ ውድድር የዓለም ቻምፒዮናን የተቀላቀለ አዲስ የውድድር አይነት ነው። ከስድስት ዓመት በኋላም የሴቶች ስሉስ ዝላይ የውድድሩ አካል ሆኗል። እኤአ በ1995 የሴቶች አምስት ሺ ሜትር ሩጫ የሦስት ሺ ሜትርን ወክሎ የውድድር አካል ሆነ። እኤአ በ1999 ደግሞ የሴቶች ምርኩዝ ዝላይና መዶሻ ውርወራ የውድድር አካል ከመሆናቸው በተጨማሪ የሴቶች አስር ኪሎ ሜትር ርምጃ ውድድር በሃያ ኪሎ ሜትር ርምጃ ውድድር ተተካ። እኤአ በ2005 የሴቶች ሦስት ሺ ሜትር መሰናክል ውድድርም ተጨመረ። የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ሲጀመር በአርባ አንድ የውድድር ምድቦች ብቻ የተወሰነ ቢሆንም አሁን ላይ ወደ አርባ ዘጠኝ ከፍ ተደርጓል። ዘንድሮም ዶሃ ይ 4 በ 400 ዱላ ቅብብል ተጨማሪ ምድብ ሆኖ ቻምፒዮናውን ይቀላቀላል። የአገራት የሜዳሊያ ፉክክርባለፉት 17 የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮናዎች 101 አገራት የሜዳልያ ሰንጠረዥ ውስጥ የገቡ ሲሆን 2198 ሜዳልያዎች (730 የወርቅ ፤ 738 የብርና 730 የነሐስ) ሜዳሊያዎች ለአሸናፊዎች ተበርክተዋል። ከ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና በፊት የምንግዜም የሜዳልያ ስብስብ ደረጃን በድምሩ 352 ሜዳልያዎች (156 የወርቅ፤ 105 የብርና 91 የነሐስ) በመሰብሰብ አሜሪካ አንደኛነቷን አስጠብቃ ትገኛለች ። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ራሽያ አትሌቶቿን በመንግስት ድጋፍ ጭምር (state sponsored) የአበረታች ንጥረነገር ተጠቃሚነት እንዲሆኑ ታደርጋለች በሚል ከታላላቅ ውድድሮች መታገዷን ተከትሎ በዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ታሪክ በርካታ ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ አሜሪካን በቅርብ ርቀት የምትከተልበት ጉዞ ተገኝቷል። የሁለተኛነቷን ደረጃ ለምስራቅ አፍሪካዊቷ አገር ኬንያ ለማስረከብም ተገዳለች። በዚህም ኬንያ 55 የወርቅ፣48 የብር፣37 የነሐስ በአጠቃላይ 140 ሜዳሊያዎች ይህን ቁንጮ ደረጃ ይዛለች። ራሽያ ቀደም ሲል በ172 ሜዳልያዎች (55 የወርቅ ፤ 60 የብርና 57 የነሐስ)፤ሁለተኛ የነበረችበት ታሪክ ከዚሁ ከአበረታች ንጥረ ነገር ተጠቃሚነት ጋር ተያይዞ በርካታ ሜዳሊያዎችን መነጠቋ ከውድድር ከመታገዷ ጋር ተደምሮ ክፉኛ ተጎድታለች። ያም ሆኖ በ43 ወርቅ፣52 ብር፣48 ነሐስ በአጠቃላይ በ143 ሜዳሊያዎች ሦስተኛ ደረጃን ጨብጣለች። ጀርመን በ115 ሜዳልያዎች (36 የወርቅ፤ 35 የብርና 44 የነሐስ)፤ ጃማይካ 115 ሜዳልያዎች (32 የወርቅ፤ 44 የብርና 39 የነሐስ)፤ ታላቋ ብሪታኒያ በ99 ሜዳልያዎች (28 የወርቅ፤ 33 የብርና 38 የነሐስ) ሜዳሊያዎች ሰብስበው እስከ ስድስት ባለው ደረጃ ውስጥ ተቀምጠዋል። ኢትዮጵያ 27 የወርቅ፤25 የብር እንዲሁም 25 የነሃስ በድምሩ 77 ሜዳልያዎችን በመሰብሰብ ሜዳልያ ዝርዝር ውስጥ ከገቡት 101 የዓለማችን አገራት መካከል 7ኛ ደረጃን የያዘች የምንጊዜም ውጤታማ አገር ነች። የሜዳሊያ ክብረወሰንጃማይካዊው የአጭር ርቀት ንጉስ ዩሴን ቦልትን ያክል በዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና በርካታ ሜዳሊያዎችን የሰበሰበ አትሌት የለም። ቦልት አስራ አንድ የወርቅና ሁለት የብር በማጥለቅ ቀዳሚ ነው። አሜሪካዊው ካርል ሌዊስ ስምንት የወርቅ፤ አንድ የብርና አንድ የነሐስ ሜዳሊያዎች በማጥለቅ ተከታይ ነው። በተመሳሳይ አሜሪካዊው ሚካኤል ጆንሰን ስምንት የወርቅ ሜዳሊያ በማጥለቅ ሦስተኛ ነው። ሌላኛው አሜሪካዊ ላሻውን ሜሪት ስድስት የወርቅና ሁለት የብር ሜዳሊያ በመውሰድ አራተኛ ነው። የረጅም ርቀት ነጉሱ ኃይሌ ገብረስላሴ አራት የወርቅ ሁለት የብርና አንድ የነሐስ ሜዳሊያ በማጥለቅ አምስተኛ ደረጃ ላይ ይቀመጣል። የቀድሞ የምርኩዝ ዝላይ ባለ ክብረወሰኑ ዩክሬናዊው ሰርጌ ቡካ ስድስት የወርቅ ሜዳሊያዎችን በዓለም ቻምፒዮና መድረክ በማጥለቅ ኃይሌን ይከተላል። አሜሪካዊው ጃርሚ ዋሪነር አምስት የወርቅና አንድ የብር ሜዳሊያ ይዞ ሰባተኛ ነው። የአስርና አምስት ሺ ሜትር ባለ ክበረወሰኑ ቀነኒሳ በቀለ በአምስት የወርቅና አንድ የነሐስ ሜዳሊያ ይከተላል።በሴቶች የረጅም ርቀት ንግስቷና የአምስትና አስር ሺ ሜትር የዓለም ክበረወሰን ባለቤቷ ጥሩነሽ ዲባባ በዓለም ቻምፒዮና መድረክ አምስት የወርቅ ሜዳሊያ ያጠለቀች አትሌት ብትሆንም ከአንድ እስከ አስር ባለው ደረጃ ውስጥ አትካተትም። ጃማይካዊቷ ማርሌን ኦቴይ ሦስት የወርቅ፤ አራት የብርና ሰባት የነሐስ ሜዳሊያ በመሰብሰብ በአስራ አራት ሜዳሊያዎች ቀዳሚ ነች። አሜሪካዊቷ አሊሰን ፌሊክስ ስምንት የወርቅ፤ አንድ የብርና አንድ የነሐስ በማጥለቅ በአስር ሜዳሊያዎች ሁለተኛ ነች። ሌላኛዋ አሜሪካዊት ጄርል ሚልስ ክላርክ በአራት ወርቅ፤ ሦስት ብርና ሁለት ነሐስ ትከተላለች። ጃማይካዊቷ ቬሮኒካ ካምቤም ብሮውን ቀጣዩ ደረጃ ላይ ትገኛለች።የአትሌቶች የተሳትፎ ክብረወሰንበዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ታሪክ በበርካታ ቻምፒዮናዎች ላይ በመካፈል ፖርቹጋላዊቷ የአስርና የሃያ ኪሎ ሜትር ርምጃ ተወዳዳሪ ሰሳን ፌተር እኤአ ከ1991 እስከ 2011 ድረስ በአስራ አንድ ቻምፒዮናዎች በመሳተፍ ትልቅ ታሪክ አላት። ስፔናዊው የሃምሳ ኪሎ ሜትር ርምጃ ተወዳዳሪ ጂሰስ ኤንጅል ጋርሺያም እኤአ ከ1993 እስከ 2013 ድረስ በአስራ አንድ ቻምፒዮናዎች በመካፈል ተመሳሳይ ታሪክ አለው። አዲስ ዘመን ቅዳሜ ነሐሴ 25/ 2011  ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=17012
937
2ስፖርት
ኢትዮጵያውያን ለድል የታጩባቸው የሳምንቱ ውድድሮች
ስፖርት
April 20, 2019
31
 እየተጋመሰ የሚገኘው የሚያዝያ ወር በዓለም ላይ በርካታ የጎዳናና የማራቶን ውድድሮች የሚስተናገዱበት ነው። ኢትዮጵያውያን አትሌቶችም የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር የወርቅ ደረጃ በሰጣቸው የተለያዩ ውድድሮች ከፍተኛ ድል በማስመዝገብ ገፍተውበታል። ባሳለፍነው ሳምንት እንኳን ፓሪስና ቦስተን ማራቶኖች ላይ አስደናቂ ድሎችን በማስመዝገብ የረጅም ርቀት ኮከብነታቸውን ለዓለም ማሳየት ችለዋል። ዛሬና ነገ በሚካሄዱ የማራቶንና የግማሽ ማራቶን ዓለም አቀፍ ውድድሮችም ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከወዲሁ ለድል ታጭተዋል። የወርቅ ደረጃ የተሰጠው ዶንግዪንግ ዓለም አቀፍ ማራቶን ዛሬ ሲካሄድ በሁለቱም ፆታ የቦታው ክብረወሰን ይሻሻላል ተብሎ ይጠበቃል። በውድድሩ በተለይም በሴቶች ከዚህ ቀደም አሸናፊ የነበረችው ዋጋነሽ መካሻ ዳግም ለአሸናፊነት መታጨቷን አዘጋጆቹን ጠቅሶ አይ.ኤኤ.ኤፍ በድረ ገፁ አስነብቧል።ባለፈው ጥር ወር በዱባይ ማራቶን አራተኛ ደረጃን ይዛ ስታጠናቅቅ 2:22:45 የሆነ የግል ምርጥ ሰዓቷን በማራቶን ያስመዘገበችው ዋጋነሽ በርቀቱ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተስፋ ከሚጣልባቸው ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አንዷ ነች። የመጀመሪያ የማራቶን ውድድሯን እአአ 2014 ሲንጋፖር ላይ ካደረገች ወዲህ ከፍተኛ መሻሻል እያሳየች የምትገኘው የ27 ዓመቷ አትሌት፣ ባለፈው ዓመት በቻይና ሄንግሹ ያሸነፈችበትን ውድድር ጨምሮ በአራት ውድድሮች የተሻለ ሰዓት እያስመዘገበች መምጣቷ በዛሬው ውድድር ከአሸናፊነት ባለፈ ክብረወሰን ለማሻሻል አቅም እንዳላት እምነት ተጥሎባታል። ባለፈው ዓመት በለተብርሃን ሃይላይ የተመዘገበው 2:24:45የውድድሩ ክብረወሰን ሲሆን ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ከኬንያውያን ተፎካካሪዎቿ ጋር ልታሻሽለው ትችላለች ተብሎ ይጠበቃል።ለዚህም በውድድሩ የመጀመሪያውን ፈጣን ሰዓት የያዘችው ኬንያዊት ካሮሊን ቼፕታኑይ ያላት ጥንካሬ ፈጣን ሰዓት ሊመዘገብ እንደሚችል ማሳያ ተደርጓል። ይህች አትሌት 2:22:34 የሆነ ግል ፈጣን ሰዓት በርቀቱ ማስመዝገብ የቻለች ሲሆን፣ እአአ 2013 በፍራንክፈርት ማራቶን ባሸነፈችበት ውድድር ነበር ሰዓቱን ያስመዘገበችው። የ38 ዓመቷ ኬንያዊት እአአ 2016 የዴጉ ማራቶንን 2:27:39 በሆነ ሰዓት ካሸነፈች ወዲህ ባደረገቻቸው ውድድሮች ርቀቱን ከ2፡30 በታች ማጠናቀቅ አልቻለችም። ባለፈው ዓመትም በዚሁ ዶንግዪንግ ማራቶን አምስተኛ ሆና ስትፈፅም ማስመዝገብ የቻለችው ሰዓት 2፡34፡39 ነው።ይህም የአሸናፊነቱ ግምት ወደ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት እንዲያደላ አድርጓል። ከዚህ ውድድር ክብረወሰን የተሻለ የራሷ ፈጣን ሰዓት ያላት ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አፈራ ጎደፋይ ለአሸናፊነት ከታጩ አትሌቶች መካከል ተካታለች። የ27 ዓመቷ አትሌት ባለፈው ዓመት በሻንጋይ ማራቶን አራተኛ ሆና ስታጠናቅቅ ቀድሞ በርቀቱ የነበራትን ፈጣን ሰዓት ከአምስት ደቂቃ ባላነሰ በማሻሻል 2:23:54 ማስመዝገቧ ይታወሳል። በዚሁ ውድድር በወንዶች መካከል የሚኖረው ፉክክር በኢትዮጵያዊው ግርማይ ብርሃኑ አሸናፊነት እንደሚደመደም ይጠበቃል። እአአ 2014 ዱባይ ማራቶን ላይ ሦስተኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ 2፡05፡49 የሆነ የራሱ ምርጥ ሰዓት ያስመዘገበው የ32 ዓመቱ ግርማይ የዴጉ ማራቶንን ባሸነፈበት ውድድር ተቀራራቢ የሆነ 2፡07፡26 ሰዓት አስመዝግቧል። የቀድሞው የራባት ማራቶን ሻምፒዮን ፍቃዱ ከበደም ባለፈው የዱባይ ማራቶን የራሱን ምርጥ ሰዓት በሰባ ሰከንድ አሻሽሎ 2:08:27 ማጠናቀቁን ተከትሎ ለአሸናፊነት ይጠበቃል።በዚሁ በቻይና የወርቅ ደረጃ ተሰጥቶት ነገ በሚካሄደው ያንግዞ ዓለም አቀፍ ማራቶን የቀድሞ የውድድሩ ሻምፒዮን የሆነች ኢትዮጵያዊቷ ሱቱሜ አሰፋ የአሸናፊነት ግምት አግኝታለች። 2017 ላይ የዚህ ውድድር አሸናፊ የነበረችው የ24 ዓመቷ ሱቱሜ ከሁለት ዓመት በፊት ለድል ስትበቃ 1፡10፡30 በሆነ ሰዓት አጠናቃለች። ባለፈው የሚላን ግማሽ ማራቶን ውድድር የራሷን ምርጥ ሰዓት ወደ 1፡07፡54 ማሻሻሏ ይታወሳል። በዚህ ውድድር ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት ደጊቱ አዝመራው ቀላል ግምት የሚሰጣት አትሌት አይደለችም። የ20 ዓመቷ ደጊቱ በዚህ ዓመት ገና በመጀመሪያዋ የግማሽ ማራቶን ውድድር 1:06:47 ሰዓት በማስመዝገብ ጥንካሬዋን ማሳየት ችላለች። ከሁለት ወራት በፊትም በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች የራክ ግማሽ ማራቶን ውድድር አራተኛ ሆና ስታጠናቅቅ ሰዓቷን ወደ1:06:07 አሻሽላለች። የዚህ ውድድር የአራት ጊዜ አሸናፊው ኢትዮጵያዊ አትሌት ሞስነት ገረመው በሌለበት የዘንድሮው ውድድር ትውልደ ኬንያዊው የባህሬን አትሌት አብረሃም ቺሮበን የአሸናፊነት ግምት ወስዷል። ቺሮበን በነገው ውድድር እአአ 2015 በሞስነት ገረመው 59፡52 ሰዓት ተይዞ የቆየውን የቦታውን ክብረወሰን ያሻሽላል ተብሎ ይጠበቃል። ቺሮበን ባለፈው ዓመት በውድድሩ ሁለተኛ ሆኖ ማጠናቀቁም አይዘነጋም።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 12/2011 
https://www.press.et/Ama/?p=9263
487
2ስፖርት
«ጨዋታዎች በቀጥታ ስርጭት የተላለፉት ፍቃድ አግኝተው ነው»የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን
ስፖርት
April 20, 2019
30
 ከሁለት ሳምንታት በፊት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያለ ፍቃድ ውድድሮችን በሬዲዮም ሆነ በቴሌቪዥን በቀጥታ ስርጭት የሚያስተላልፉ ክለቦች ላይ ቅጣት እንደሚጥል በጥብቅ ማሳሰቡ ይታወቃል። ፌዴሬሽኑ የቀጥታ ስርጭት የሚያስተላልፉ ክለቦች ፍቃድ በመውሰድ እንዲያስተላልፉ በደብዳቤ የጠየቀ ሲሆን ይህን ተግባራዊ ሳያደርጉ ሲያስተላልፉ በተገኙ ክለቦች ላይ ጠበቅ ያለ ቅጣት እንደሚያስተላልፍ አሳውቋል። ከዚህ ቀደም ፌዴሬሽኑ በተመሳሳይ መልኩ የቀጥታ ስርጭት እንዳይተላለፍ እግድ አውጥቶ የነበረ ቢሆንም በኋላ ላይ የቀጥታ ስርጭት ከሚያስተላለፉ ተቋማት ጋር ፌዴሬሽኑ ባዘጋጀው የውል ስምምነት ለመፈፀም በመስማማት በቴሌቪዥንም ሆነ በሬዲዮ እያስተላለፉ መቆየታቸው ይታወቃል።ፌዴሬሽኑ ይህን ማሳሰቢያ በቅርቡ ካወጣ ወዲህ በተለያዩ ክልሎች የተካሄዱ የወንዶች ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች በተለያዩ የክልል ቴሌቪዥን ጣቢያዎች በቀጥታ ሲተላለፉ ነበር። ይህም በስፖርት ቤተሰቡ ዘንድ ጨዋታዎችን በቀጥታ ያስተላለፉ አካላት የፌዴሬሽኑን ማሳሰቢያ ወደ ኋላ ትተው በራሳቸው ፍቃድ ነው ወይስ ከፌዴሬሽኑ ፍቃድ አግኝተው ነው? የሚል ጥያቄ አስነስቷል። አዲስ ዘመን ጋዜጣ በጉዳዩ ዙሪያ የፌዴሬሽኑን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ባህሩ ጥላሁንን በስልክ አነጋግሯል። አቶ ባህሩ በቅድሚያ ፌዴሬሽኑ ማሳሰቢያ የሰጠው ክለቦች ጨዋታዎችን እንዳያስተላልፉ ሳይሆን ፍቃድ እንዲጠይቁና በህግ አግባብ እንዲጓዙ መሆኑን ተናግረዋል። ማሳሰቢያው ከወጣ ወዲህ ድሬዳዋ ላይ አንድ ጨዋታ በሬዲዮ እንዲሁም ባለፈው ሳምንት መቐለ 70 እንደርታ ከባህርዳር ከተማ ጋር ያደረጉት ጨዋታ በቴሌቪዥን የቀጥታ ስርጭት መተላለፋቸው ይታወሳል። እነዚህም ውድድሮች የተላለፉት ከፌዴሬሽኑ ፍቃድ ተሰጥቷቸውና አስፈላጊውን ክፍያ ፈፅመው በስምምነት መሆኑን አስረድተዋል። ቀደም ሲል ፌዴሬሽኑ ጨዋታዎችን ክለቦች ፍቃድ ሳይጠይቁ ማስተላለፍ እንደሌለባቸው ማሳሰቡ ህጋዊ መሰረት እንደሌለው በተለያዩ አካላት ሲገለፅ ነበር። ይሁን እንጂ ክለቦች ፕሪሚየር ሊጉን የማስተዳደር ስልጣን አምነውና ፈቅደው ለፌዴሬሽኑ እስከሰጡ ድረስ የጨዋታዎችን የቀጥታ ስርጭት የመቆጣጠር መብት እንዳለው ገልፀዋል። ይህም በፌዴሬሽኑ የመተዳደሪያ ደንብ አንቀፅ 51 ላይ ተቀምጧል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን በቀጥታ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ስርጭት ሲያስተላልፉ የምናያቸው የክለቦቹ ጣቢያዎች ሳይሆኑ የክልል መገናኛ ብዙሃን ናቸው። ክለቦቹ በሌሎች አገራት እንደምናያቸው ትልልቅ ክለቦች የራሳቸው ጣቢያ ቢኖራቸው እንኳን ጨዋታዎችን የፌዴሬሽኑን ይሁንታ ሳይጠብቁ የማስተላለፍ መብት እንደሌላቸው በማስታወስ፤ ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችም ከዚህ የተለዩ እንዳልሆኑ ገልፀዋል። በዓለማችን ትልቅ ደረጃ ላይ የደረሱ ሊጎች ከቴሌቪዥን መብት ጋር በተያያዘ ገቢ የሚሰበስቡት ክለቦች አይደሉም። ይሁን እንጂ ሊጉን የሚመራው አካል ከቴሌቪዥን መብት ጋር በተያያዘ የሚሰበስበውን ትልቅ ገቢ ለክለቦች ያከፋፍላል። ለምሳሌ ያህል የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች አወዳዳሪው አካል ከቴሌቪዥን መብት ከሰበሰበው ገንዘብ ሃምሳ በመቶውን ለሁሉም ክለቦች እኩል ያካፍላል፣ ሃያ አምስት በመቶው ደግሞ ክለቦች በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ በሚያጠናቅቁበት መሰረት ሲሆን ቀሪው ሃያ አምስት በመቶ በርካታ ጨዋታዎቻቸው ተመርጠው በቴሌቪዥን የተላለፉላቸው ክለቦች በአማካኝ ተሰልቶ ይደርሳቸዋል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሁን ይህን መንገድ ለመክፈት እየሞከረ ቢሆንም ገና ጅማሬ ላይ ያለ በመሆኑ ከቴሌቪዥን መብት የሚያገኘው ገቢ ለሽልማትና ሌሎች ነገሮች ሊውል ይችላል እንጂ ክለቦች የሚካፈሉበት ደረጃ አልደረሰም። ያም ሆኖ ፌዴሬሽኑ እንዳደጉት አገራት ክለቦችን ከቴሌቪዥን መብት ተጠቃሚ ለማድረግ ይህን ልምድ አሁን ማስጀመር እንዳለበት አቶ ባህሩ ይናገራሉ። ‹‹በቀጣይም የቴሌቪዥን መብትን እንዴት ማስኬድ አለብን፣ በምን መንገድ ክለቦች ተጠቃሚ መሆን አለባቸው የሚሉ ጉዳዮችን እያመቻቹ መሄድ ያስፈልጋል›› ያሉት አቶ ባህሩ ፌዴሬሽኑ ይህን ጉዳይ ገና ጀማሪ በመሆኑ ማሻሻል የሚገባውን እያሻሻለ እንደሚሄድ አብራርተዋል።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 12/2011 
https://www.press.et/Ama/?p=9258
424
2ስፖርት
“ የትኩረት ችግራችንን በመልስ ጨዋታ ሙሉ ለሙሉ ቀርፈነዋል” አሰልጣኝ ሠላም ዘርዓይ
ስፖርት
April 21, 2019
42
 ኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በቶኪዮ ኦሊምፒክ ማጣሪያ ዩጋንዳን በድምር ውጤት 4-2 በማሸነፍ ወደ ተከታዩ የማጣሪያ ዙር ማለፉ ይታወሳል። በደርሶ መልስ ጨዋታዎች ላይ የሚነሱ ጉዳዮችን አስመልክቶ ማክሰኞ በአዲስ አበባ ስታድየም አሰልጣኝ ሠላም ዘርዓይ እና በመልሱ ጨዋታ ብቸኛዋን የማሸነፍያ ጎል ያስቆጠረችው ሎዛ አበራ ተገኝተው ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል። የተሰጡት ዋና ዋና ሀሳቦችን እንደሚከተለው አሰናድተነዋል። እዛ ከደረስን በኋላ ሁለት ልምምዶች ነው የሰራነው። የመጀመሪያው ቀን ቀላል፤ በሁለተኛው ቀን ከባድ ልምምድ ሰርተናል። ጨዋታውን ስናየው በጣም ከባድ ነበር። እዚህ አዲስ አበባ ከገጠመን ቡድን በጣም ተቃራኒ ነበሩ። ውጤቱን ለማግኘት የገባ ደጋፊ አለ። የተወሰነ የዳኝነት ተፅዕኖ ከመኖሩ በተጨማሪ የአየር ንብረቱ በጣም ሞቃታማ ነበር። በዚህ ሁሉ ውስጥ ሆነን ነው ውጤቱን ማምጣት የቻልነው። በሰናይት እና በህይወት መካከል የሚና እና የልምድ ልዩነት አለ። በመጀመሪያው ጨዋታ ማጥቃት እንደመፈለጋችን መጠን ሰናይትን ተጠቅመናል። ሰናይት እና ብርቱካን ተመሳሳይ የጨዋታ ባህሪ ያላቸው ናቸው። በጨዋታው ላይ ሰናይት እና ብርቱካን ወደፊት በሚጠጉበት ወቅት በመሀል ክፍሉ እመቤት ብቻዋን በመጋለጧ እኛ ተደጋጋሚ የግብ እድል ሲፈጠርብን ስለታየ በማጥቃቱ እና መከላከሉ ላይ ሚዛናዊ ለማድረግ ህይወት ገብታለች። ከህይወት መግባት በኋላ ቡድኑ ሚዛኑን መጠበቅ ችሏል። ሁለት ተጨማሪ ግቦችም ማግባት ችለናል። ስለዚህ ይህንን ዩንጋዳ ላይ በተደረገው ጨዋታ ላይ ተግብሬዋለሁ። ህይወትን ለመከላከል እንዲሁም ሰናይትን ለማጥቃት የሚል አስተሳሰብ አለ፤ ይህ ሊታረም ይገባዋል። ሁለቱም የራሳቸው የሆነ የኳስ ችሎታ አላቸው። ሙቀቱን ለመቋቋም ተመሳሳይ አየር ንብረት ወዳለው አካባቢ ተጓዞ ልምምድ ማከናወን ይጠቅማል። እኛ የመጀመሪያው ጨዋታ አዲስ አበባ ላይ በመሆኑ እዚሁ ነው የተዘጋጀነው። የመልስ ጨዋታ ለማድረግ ደግሞ ወዲያውኑ ነው የሄድነው። እዛ የነበረው ሙቀት እስከ 37°c ይደርሳል። የትም ብትሄድ ተመሳሳይ የአየር ንብረት አታገኝም። ነገር ግን ተመሳሳይ ወደ ሆነው እየተጓዙ ልምምድ ማድረግ ይቻላል። ቡድኔ 90 ደቂቃ ጠንካራ ሆኖ መቆየት ይችላል። ይህንንም በዩንጋዳው ጨዋታ ላይ አሳይቷል። ነገር ግን ቡድኖች የጨዋታ  መጠነቃቂያ ላይ ትኩረት ያጣሉ። ይህ የብዙ ትልልቅ ቡድኖች ችግርም ነው። ወደ እኛ ቡድን ስትመጡ አዲስ አበባ ላይ ሶስት ጎሎችን ከማስቆጠራችን በተጨማሪ የጨዋታ እንቅስቃሴ ብልጫ መውሰዳችን በተጫዋቾቼ ላይ የራስ መተማመን መፍጠሩን እና ውጤቱ ያሳልፋል የሚል እምነት ማሳደሩን ነው ያየሁት። ይህም በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ትኩረት እንድናጣ አድርጎናል። ይህን ችግራችንን በመልስ ጨዋታ ሙሉ ለሙሉ ቀርፈናዋል። አንድ ቡድን 90 ደቂቃ ለመጨረስ የሚያስፈልገው አካል ብቃት አይደለም፤ ትኩረት እንጂ። በዚሁ አጋጣሚ በዩንጋዳ ተጫዋቾቼ ያሳዩትን ተጋድሎ ሳላደንቅ አላልፍም። ላመስግናቸውም እፈልጋለሁ። በሷ ላይ የተነሱ ሀሳቦች ቢኖሩም ሎዛ ትልቅ ተጫዋች መሆኗን አሳይታለች። የቅጥሩ ሁኔታ ለ6 ወር የሚቆይ ነው። በቀጣይ ላለብን ጨዋታ ከ5 ወር በላይ ጊዜ አለን። በነዚህ ጊዚያት ውስጥ በየቡድኖቹ ውስጥ ተኝተው የሚመጡ ከሆነ ለውጥ አይመጣም። ነገር ግን ብሔራዊ ቡድኑ በየወሩ የወዳጅነት ጨዋታ እንዲሁም ለሁለት ወይም ለሶስት ቀን ሆቴል ቆይታ እንዲኖራቸው እንዲሁም በነዚህ አምስት ወራት 5 ያህል ወዳጅነት ጨዋታ ታስቧል። ሁለቱ ኢንተርናሽናል እንዲሁም በቃል ደረጃ ከፌዴሬሽኑ ኃላፊዋች ጋር አውርተናል። ቡድኑ ተደጋጋሚ የሆነ የወዳጅነት ጨዋታ እንዲያደርግ ጥረት እናደርጋለን። ፌዴሬሽኑም ሆነ የኦሊምፒክ ኮሚቴ በቂ ትጥቅ አቅርቦ ነበር። ነገር ግን ችግሩ የተፈጠረው ብሔራዊ ቡድኑ የተሰጠው መለያ ቢጫ ነበር፤ እኔ ጋርም ያሉት ልብሶች ቢጫ ቀለም ያላቸው በመሆኑ ቀይ ማድረግ አለብሽ ተባልኩኝ። በአጋጣሚ ሻንጣዬ ውስጥ ያገኘሁትን ቲሸርት ለበስኩት። በሰዓቱ በልብሱ ላይ ስለተፃፈው ፅሁፍ አትኩሮት ሳልሰጥ ቡድኔን ለመምራት ማሰቤን ቀጠልኩኝ። ቢጫ ጃኬት ከላይ ደርቤ ነበር፤ ነገር ግን አራተኛ ዳኛዋ አስወልቃኛለች። ከጨዋታው በኋላ ጋዜጣዊ መግለጫ በቢጫው ልብስ ሰጥቼ ወጥቻለሁ። በዚሁ አጋጣሚ ሙሉ ለሙሉ የኔ ስህተት ነው፤ ይቅርታ እጠይቃለሁ። በትክክል መስመር ላይ ችግር ነበር። አዲስ አበባ ላይ በተደረገው ጨዋታ ሁለቱም ከ17 ዓመት በታች ካለው ብሔራዊ ቡድን የተመረጡ ናቸው። የኢንተርናሽናል ጨዋታ ልምድ አለመኖሩ ጫና ውስጥ ከቶን ነበር። በተለይም አንደኛዋ የመስመር ተጫዋች በፕሪምየር ሊጉ የአጥቂነት ሚና ያላት ነበረች። መልስ ጨዋታ በቦታው ላይ ለውጥ ለማድረግ ሞክረናል። አረጋሽ ከአካዳሚ የተገኘች ድንቅ ልጅ ነች። በኢትዮጵያ እግር ኳስ ተስፋ የሚታይባት እምቅ ችሎታ ያላት ተጫዋች ነች። በይበልጥ ልምዱን እና እድሉን ስታገኝ የበለጠ የምታኮራን ተጫዋቾች ነች። የካሜሩንን ጨዋታ ስናከናውን ቡድኖች መርሐ ግብራቸውን የሚጨርሱበት በመሆኑ በቂ የመዘጋጃ ጊዜ ስላለን ይበልጥ ጠንክረን የምንሰራበት ጊዜ ይሆናል። ካሉት አሰልጣኞች ጋር በይበልጥ ተቀራርበን የምንሰራ ይሆናል። ከዚህ ቀደምም ስንሰራ ቆይተናል። ተጋጣሚያችን ካሜሩን ጠንካራ ነው። ይህ ማለት እኛ እጆቻችን አጣምረን እንቀመጣለን ሳይሆን ባለቡን ድክመቶችን ጠንክረን ሰርተን የተሻለ ቡድን ይዘን እንገባለን። በስተመጨረሻ የቡድኑ ስብስብ እንደ አስፈላጊነቱ የሚጨምር የሚቀንስ ይሆናል። ብሔራዊ ቡድኑ የሰላም ወይም የሎዛ አይደለም። የኢትዮጵያን ህዝብ ነው። ማንም አቅም ያለው ተጫዋች የሚጫወትበት ነው። አሁን ባለው ነገር ሁሉንም በየቡድኑ ያላቸውን እንቅስቃሴ በመከታተል እንደ አስፈላጊነቱ ባለብን ክፍት ወይም ደካማ ቦታዎች ላይ ተጫዋቾችን የምንጨምር ይሁንልን። የዩንጋዳው ጨዋታ ደስ ይል ነበር። ሙቀት ባለበት ቦታ ላይ እንደመጫወታችን ብዙ ፈትኖናል፤ ሜዳውም አርቴፍሻል እንደመሆኑ መጠን ይህን ውጤት በማሳካታችን በጣም ደስተኛ ነን። ከመልሱ ጨዋታ በፊት የቡድኑ መንፈስ በጥሩ መነሳሳት ላይ ነበር። ሀገራችንን አንድ ደረጃ ከፍ ማድረግ መቻል አለብን ብለን አስበን ስለነበር ይህን ማሳካት በመቻላችን ሁላችንም ደስተኛ ነን። ከጨዋታው በፊት ጫናዎች ነበሩ። ነገር ግን ይህ ነገር በየትኛውም ተጫዋች ላይ የሚፈጠር ነው። እኔ በግሌ በመልካም ጎኑ ነው የተቀበልኩት። ይህም ደሞ ይበልጥ እንድሰራ እና ራሴን በይበልጥ እንዳሳይ አነሳስቶኛል። የተባለውን ነገር ተቋቁሞ ማለፍ እንዳለብኝ ትምህርት ሰጥቶኝ አልፏል። ጫና ግን አለው። እኔ ራሴን አውቀዋለሁ። ብሔራዊ ቡድን እንደመጫወቴ መጠን ሀገሬን እንደመወከሌ መጠን ሜዳ ውስጥ ያለኝን ሁሉ ለመስጠት ዝግጁ ነኝ። ይህንን ለማድረግ ሞክሬያለሁ። በኢንተርናሽናል ጨዋታም 23 ግቦች አሉኝ። በአዲስ አበባው ጨዋታ የጎል እድሎችን አምክኛለሁ። ከጨዋታው በኋላ ቪዲዮ ቁጭ ብዬ ስመለከተው ሁለት ንፁህ ጎል የሚሆኑ አጋጣሚዎችን አልተጠቀምኩም። ይህ ደግሞ በእግር ኳስ ያጋጥማል። ማንም ትልቅ ተጫዋች ይህ ያጋጥመዋል። ማድረግ የነበረብኝ የሳትኩትን ኳስ ረስቼ ጎል ማግባት እንደምችል ለራሴ ነገሬዋለሁ። ሌላ ጎል ማግባት እንድምችል ነበር ለራሴ እየነገርኩት ወደ ሜዳ የገባሁት። ይህንንም ማሳካት ችያለሁ።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 13/2011 
https://www.press.et/Ama/?p=9348
799
2ስፖርት
በአቢጃን የደመቀው የልዑካን ቡድን አቀባበል ተደረገለት
ስፖርት
April 23, 2019
25
በኮትዲቯር አቢጃን ከተማ በተካሄደው ከ18 እና ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተካፍሎ በድል የተመለሰው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሄራዊ ቡድን ትናንት በኢትዮጵያ ሆቴል አቀባባል ተደረገለት። 32 የአፍሪካ ሀገራት በተሳተፉበት በዚህ ውድድር ቀደም ሲል ኢትዮጵያ ብዙ ውጤታማ ባልነበረችባቸው የሜዳ ላይ ተግባራትም አቢጃ ላይ ደምቃለች። ኢትዮጵያ በውድድሩ በአጭር ፣መካከለኛ፣ ረጅም ርቀትና በሜዳ ላይ የአትሌቲክስ ስፖርት ተግባራት በሆኑት በውርወራና ዝላይ የተካፈለች ሲሆን፣ በአጠቃላይም 6 የወርቅ፣ 10 የብርና 14 የነሐስ በድምሩ 30 ሜዳሊያዎችን ማግኘት ችላለች። በኢትዮጵያ ሆቴል በተካሄደው የአቀባባል ስነስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዚዳንት አትሌት ገብረእግዚአብሄር ገብረማርያም፤ «በአትሌቲክስ ከመሳተፍ አልፈን ማሸነፍ፥ ከማሸነፍም ወርቅ የምንጠብቅበት ዘርፍ ነው፤ ይህ እንደመሆኑም በሻምፒዮናው ኢትዮጵያን የወከሉ አትሌቶች የአገራቸውን ስምና ሰንደቅ አላማ ከፍ አድርገው ማስጠራት ችለዋል» ብለዋል። ኢትዮጵያ ቀደም ሲል ብዙም ውጤታማ ባልነበረችባቸው የሜዳ ላይ ተግባራት የተመዘገቡ ውጤቶችን መስራት ከተቻለ የሚፈለገውን ለውጥ ማምጣት እንደሚችል ምስክር ስለመሆናቸው አስገንዝበዋል። ሻምፒዮናውም በተለይ የኢትዮጵያ ተፎካካዎች የአየር ንብረትን መሰረት ያደረጉ ልምምዶች ላይ ምን ያህል እየተዘጋጁ እንደሆነ ለቀጣዩ ዓለም ሻምፒዮና ጥሩ አመላካች መሆኑንም ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ፣ ‹‹በሻምፒዮና የተካፈሉ አትሌቶች ከሌሎች አገራት በተለየ ሁኔታ እድሜ ካጭበርበሩ ውስጥ ሳይሳተፍ ያስመዘገበው ውጤት እጅግ የሚደነቅ ነው፡፡›› ብለዋል። አምስትና አስር ሺ ሜትር ርቀቶች ከውድድር እየራቁ መምጣታቸውን ያስታወሱት ዶክተር አሸብር፤ በዚህ ረገድ ዘንድሮ ኢትዮጵያ ቀደም ሲል የናይጄሪያና የምዕራብ አፍሪካ ውድድር ናቸው ተብለው የተለዩ አጭር ርቀቶችን ጨምሮ ብዙም ውጤታማ ባልነበረችባቸው የሜዳ ላይ ተግባራት ውጤታማ መሆኗ የሚበረታታ መሆኑን አብራርተዋል። በአትሌቲክስ ሻምፒዮናው የተሳተፉ አትሌቶችም በአቢጃው ውድድር ምንም እንኳን የአየር ንብረቱ በእጅጉ ቢፈትናቸውም ሙቀታማነቱን ተቋቁመው ውጤት በማምጣት የአገራቸውን ስም በማስጠራታቸው ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ተናግረዋል። በቀጣይ ሻምፒዮናዎችም ከዚህ የተሻለ ውጤት ለማስመዘገብ ከወዲሁ ጠንካራ ልምምዳቸውን እንደሚያከናውኑም አስገንዝበዋል። በአቀባባል ስነስርዓቱ ላይ ለልዑካን ቡድኑ አባላት ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንና ከኦሎምፒክ ኮሚቴ የማበረታቻ ገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። ፌዴሬሽኑ ለሽልማት ብቻ ብር 875 ሺ፤ ከፌዴሬሽኑ ጋር በመተባበር የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴም ለቡድኑ አባላት በጥቅል ብር 450 ሺ መመደባቸውም ታውቋል። የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የኢትዮጵያ ሆቴል ባለቤትና በተለያዩ የኢንቨስትመንት ስራ የተሰማሩት አቶ በላይነህ ክንዴም ውጤታማ ለሆኑ አትሌቶች በግላቸው ከብር መቶ ሃምሳ ሺ በላይ የገንዘብ ሽልማት አበርክተዋል። አዲስ ዘመን ሚያዝያ 15/2011
https://www.press.et/Ama/?p=9453
311
2ስፖርት
የባየርሙኒክ ክለብ አካዳሚ ኢትዮጵያን የመምረጥ እንድምታ
ስፖርት
April 23, 2019
58
ከአውሮፓ ሃያል ክለቦች መካከል ስሙ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሰው የጀርመኑ አንጋፋና ሃያል የእግር ኳስ ክለብ ባየርሙኒክ 28 የቡንደስሊጋ፤አምስት የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ እንዲሁም ሌሎችም ክብሮችን ተቀዳጅቷል።ለዚህ ስኬታማነቱም እኤአ 1990 እድሜአቸው ከ15 እስክ 18 የሚሆኑ ታዳጊዎችን በመያዝ በሙኒክ ከተማ የተቋቋመ የክለቡ አካዳሚም ዋነኛው መሰረት ስለመሆኑ ይታመናል። የባቫሪያው ክለብ አካዳሚ ‹‹የ21ኛው ክፍለ ዘመን ምርጡ ተከላካይ›› ሲሉ የሚያሞካሹት ፍሊፕ ለሃምን ጨምሮ ዴቪድ አላባ፤ባስቲያን ሾዋን እስታይገር፤ቶኒ ክሩዝ፤ ኦውን ሃርግሬቭስ፤ ቶማስ ሙለርና ሳሚ ኮፎርን የመሳሰሉ የእግር ኳስ ጠቢባን አፍርቷል። ክለቡ በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ በአሜሪካ፣ ቻይና፣ታይላንድ፣ ጃፓን እና ሲንጋፖር የታዳጊ እግር ኳስ ማሰልጠኛ ተቋማት ያሉት ሲሆን፤የተቋማቱን ቁጥር ከፍ የማድረግ ፍላጎቱን እውን ለማድረግም በኢትዮጵያ የእግር ኳስ ስፖርት ላይ አሻራውን ለማሳረፍ ከሰሞኑ አዲስ አበባ ተገኝቷል። ቡድኑ በአዲስ አበባ በነበረው ቆይታም የወጣቶች አካዳሚ ለመክፈት ከኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጋር ቅድመ ስምምነቶችን ፈፅሟል።የስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ርስቱ ይርዳው፣ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጂራ እና የባየር ሙኒክ ተወካዮችም በዚህ ስነ-ስርዓት ላይ ተገኝተዋል።በስምምነቱም የጀርመኑ ሃያል ክለብ በስሙ የሚጠራውና በአፍሪካ የመጀመሪያው የሆነውን የእግር ኳስ ማሰልጠኛ አዲስ አበባ ላይ እውን እንደሚያደርግና ከ17 ዓመት በታች ታዳጊ የሆኑ ውጤታማ የእግር ኳስ ስፖርተኞችን እንደሚያሰለጥንም ታውቋል።በስምምነቱ መሰረት የስፖርት አካዳሚው የሶስት ዓመት ፕሮጀክት ሲሆን፣ በየዓመቱ ሊታደስ እንደሚችል ተጠቁሟል። እኤአ ከ1997 እስከ 2003 በየባየር ሙኒክ የተጫወተውና የጀርመን ቡንድስሊጋንና የሻምፒየንስ ሊግ ክብሮችን ማሳካት የቻለው ብራዚላዊው የክለቡ አምባሳደር ጆቫኒ ኤልቨር፤‹‹ኢትዮጵያውያን ለእግር ኳስ ልዩ ፍቅር ብቻም ሳይሆን ስፖርቱንም በብቃት መጫወት እንደሚችሉ መረዳት ችለናል፤እኛም የአገሪቱን ታዳጊዎች የኳስ ክህሎት ለማብቃት፣ለማጎልበትና ለማዳበር እንስራን።›› ሲል ተደምጧል። አዲስ ዘመንም ለመሆኑ ወቅታዊ የኢትዮጵያ ታዳጊ ፕሮጀክቶች ቁመና ምን ገፅታ አለው? ባየርሙኒክ ኢትዮጵያን የመምረጡ እንድምታ ምን ይሆን? ለአገሪቱ እግር ኳስ ልማት ምን አስተዋፆኦ ይኖረዋል? ከዚህ ተጠቃሚ ለመሆንስ ምን ተግባራት መከናወን አባቸው? የሚለውን ጥያቄ በማንሳት የስፖርት ሳይንስ ባለሙያዎችን አነጋግሯል። ከአስተያየት ሰጪዎቻችን አንዱ የሆኑት የኮተቤ ሜትሮፖሊታንት ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ሳይንስ መምህር አቶ ሲያምረኝ በርሄ፣ የእግር ኳስ ማሰልጠኛ ተቋማት፣ አካዳሚዎች እንዲሁም የታዳጊና ወጣት ፕሮጀክቶች የአንድን አገር ስፖርት ለማስፋትና ለማሳደግ ዋነኛ መሰረቶች ስለመሆናቸው ይገልፃሉ። እንደ እርሳቸው ገለፃ፤የታዳጊዎች እግር ኳስ ስልጠና እንደ መደበኛ ትምህርት ግዙፍ ሳይንስና ጥናት የሚጠይቅ ነው። በየደረጃው ቅደም ተከተሉን የጠበቀ የስርዓተ ስልጠና በጥንቃቄ ሊዘጋጅለትና በየጊዜውም በቂ ክትትል ሊደረግለት ይገባል። ይህ ሳይሆን ፍሬያማነቱን መጠየቅም አግባብነት የለውም። ‹‹በዚህ ረገድ ሲቃኝ በኢትዮጵያ ታዳጊዎችን በእግር ኳስ ለማብቃት የሚሰሩ ተግባራት፤ ታቅደውና አስፈላጊው ሁሉ ተሟልቶ በተደራጀ መልኩ የሚጀመሩ አለመሆናቸውን በቀላሉ መረዳት ይቻላል›› የሚሉት አቶ ሲያምረኝ፤ ‹‹አጀማመራቸው የይስሙላ በመሆኑም የሚፈለገው ውጤት እንዳይመጣ ዋነኛ ማነቆ ስለመሆኑ ጥርጥር የላቸውም።››ሲሉ ገልፀዋል። ‹‹በዓለምም ሆነ በአውሮፓ እግር ኳስ ሃያል ከሚባሉት ግንባር ቀደም ተጠቃሽ የሆኑት ጀርመኖችና ቀዳሚው ክለባቸው ባየርሙኒክ ወደ አገራችን መጥተው አካዳሚ ለመክፈት ሲወስኑ እኛ ያልተረዳነው እምቅ አቅምና ተስፋ አለ ማለት ነው» የሚሉት አቶ ሲያምረኝ፤ይህን እምቅ አቅም ሳያጠኑ በደመነፍስ መሰል ግዙፍ ውሳኔ ይወስናሉ ብሎ ማሰብ እንደማያስፈልግም ምክንያታዊ ስለመሆናቸው መረዳት እንደሚገባም አስምረውበታል።ታላላቅ የዓለም እግር ኳስ ተፅዕኖ ፈጣሪ አገራት መሰል አካዳሚዎች ለመክፈት መወሰናቸው የታዳጊዎች ፕሮጀክት ምን ያህል ትኩረት እንደሚያሻው አጉልቶ የሚያሳይ መሆኑንም አፅዕኖት ሰጥተውታል። የአካዳሚው እውን መሆንም ለአገሪቱ ታዳጊዎች መጪ ተስፋ ብሩህ ከማደረግ ባሻገር በውሳኔ ሰጪነቱ ወንበር ላይ የሚገኙ ግለሰቦች ለታዳጊዎች ስልጠና ተገቢውን ትኩረት እንዲሰጡ እንደሚያስገድዳቸው አቶ ሲያምረኝ ያስረዳሉ። ባለሙያዎችም ከአካዳሚው ጋር በሚኖራቸው ቅርበት ታዳጊውን በምን አይነት ሳይንሳዊ ስልጠና እንደሚያበቁ ተጨባጭ በሆነ መልኩ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸውና አንድ ማሰልጠኛ ሲቋቋም ምን ምን ሊኖሩት ይገባል የሚለውንም ለማሳየት የሚያግዝ እንደሆነ ይናገራሉ። ከለቦችም በየጊዜው ራሳችውን እንዲያጠናክሩና የሚያፈሯቸውን ተጨዋቾች ለዝውውር ገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንዲሁም በከፍተኛ ወጪ የውጭ ተጫዋቾችን ከማምጣት ለአገር ውስጥ ተጫዋቾች ትኩረታቸውን እንዲመለሱ የሚያግዝ መሆኑን ነው ያብራሩት። «አጠቃላይ ባየርሙኒክ ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱ በእግር ኳሳችን እድገት ላይ መልካም እድል የሚፈጥር ነው፤ዛሬ ጀርመኖች መጥተዋል፤ ነገ ደግሞ ማን እንደሚመጣ አይታወቅም» ያሉት አቶ ሲያምረኝ፣ አሁን ላይ የተገኘውን ይህን እድል በአግባቡ ተጠቅሞ የአገሪቱን ስፖርት አንድ እርምጃ ለማራመድ የሚመለከታቸው ባለድርሻዎች ተገቢውን ትኩረት ሊሰጡት እንደሚገባ ነው ያሰመሩበት። በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በስፖርት አካዳሚ በማስተማርና በምርምር የሚሳተፉት ረዳት ፕሮፌሰር ደምሴ ጋሹ፣ በአሁን ወቅት በተለያዩ ቦታዎች አካዳሚዎች መኖራቸውና ስልጠና መሰጠቱ መልካም መሆኑን ይጠቅሳሉ፤ ነገር ግን ዓለም ከደረሰበት ደረጃ አንፃር ሲቃኝ በኢትዮጵያ ያለው የታዳጊዎች ስልጠና ዘመናዊም ባህላዊም ለማለት የሚያስችግርና ክትትሉም ሆነ ቁጥጥሩ የለም ለማለት የሚያስደፍር እንደሆነ ያመለክታሉ። ይህ በሆነበት ዝነኛው የጀርመን ሃያል ክለብ ባየር ሙኒክ ኢትዮጵያን ምርጫው በማድረግ የእግር ኳስ አካዳሚውን በአዲስ አበባ ለመገንባት የስምምነት ፊርማ ማኖሩ፤ ‹‹አጠቃላይ የአገሪቱ ስፖርት አውድ የሚቀየር ነው» የሚሉት ረዳት ፐሮፌሰሩ፤ ፋይዳውም ዘርፈ ብዙ ስለመሆኑ ይገልፃሉ። መሰል የውጭ ክለቦች አካዳሚያቸውን በአንድ አገር ለመክፈት ሲወስኑ በርካታ መረጃዎችን በጥልቀት በመዳሰስ መሆኑንና ያስገነዘቡት ረዳት ፕሮፌሰሩ፤ባየርሙኒክም ከዚህ ውሳኔ ከመደረሱ ቀድሞ ኢትዮጵያውያን ታዳጊዎች በሳይንሳዊ ስልጠና ቢታገዙ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስመጥር መሆን የሚችሉ ልጆች ስለመሆናቸው በቂ ዳሰሳ በማድረግና መረጃ መያዙ ሊታወቅ እንደሚገባም አፅጽእኖት ሰጥተውታል። ለረዳት ፕሮፌሰር ደምሴ፤ የእግር ኳስ ማሰልጠኛው እውን መሆን ትሩፋቶቹ በርካታ ናቸው። ኢትዮጵያውያን ታዳጊዎች ፕሮፌሽናል ተጫዋች የመሆን እድላቸው ክፍት ያደርገዋል።ስፖርት አካዳሚዎች በታዳጊዎቸ አዕምሮ ላይ የሚሰሩ ተግባራትን ጠንካራ በመሆናቸው የአስተሳሰብ ለውጥ እንዲያምጡ ያስችላል። ኢትዮጵያውያን ታዳጊዎች እግር ኳስ በእግር ሳይሆን በዓዕምሮአቸው እንዲጫወቱም ያስችላል።በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ስመጥር እንደ ሆኑት ኮከቦች ሊዮኔል አድሬስ ሜሲ ኳስንና መሰሎቹ በእውቀት የመጫወት፣ የመረዳትና የማንባብ ብቃት እንዲያብሩ ያግዛል።ስፖርቱ ባይሳካላቸው እንኳን በቀለም ትምህርትም ሆነ በስነ ባህሪያቸው መልካም ዜጋ የሚሆኑበት እድል የላቀ ያርገዋል። ስፖርት አካዳሚዎች፣ ፕሮጀክትና ክለቦች እንዲሁም ፌዴሬሽኖች ልምድ በመቅስም አሰራርና አደረጃጀታቸውን ከውጪዎቹ ጋር ተቀራራቢ ለማድረግ እንዲጥሩ ምክንያት ይሆናቸዋል። የአገሪቱ አሰልጣኞችም ለስልጠና ያላቸው የተዛባ አመለካካት በአጠቃላይ ይቀየራል። ከጊዜው ጋር መጓዝ ለእውቀት ትኩረት በመስጠት ራሳቸውን ማብቃት ካልቻሉ ወደ አካዳሚዎች የመግባት እድላቸው ዜሮ በመሆኑ ራሳቸውን ለማበቃት እንዲደክሙና ልምድና ሳይንሳዊ እውቀትን አጣምረው እንዲጓዙ ያስግድዳቸዋል።ጋዜጠኞችም ተጨባጭ የሆነ ማስረጃ በማግኘት ማነፃፀሪያና ማመሳከሪያ በመጠቀም አሰራሮችን ለመተቸትም ሆነ ለማወደስ አቅማቸውን ያዳብርላቸዋል። እነዚህን ትሩፋቶች ብቻውን ታሳቢ ከማድረግ በተጓዳኝ ቀጣይ ስጋቶችን ማጤን እንደሚገባ የሚያሳስቡት ረዳት ፐሮፌሰሩ፤መሰል ታላላቅ የእግር ኳስ ማሰልጠኛዎች እውን ሲሆኑ ብቃትን መሰረት የሚያደረጉና የአገሪቱን ስፖርት አውድ የሚቀይሩ እንደመሆናቸው አንዳንድ ክለቦችና ፌዴሬሽኖች አካባቢ ያሉ ሰዎችን ምቾት ሊነሳ ስለሚችል በስልጠና ትግበራው ላይ ደንቃራ ሊሆኑ እንደሚችሉ ስጋት እንዳላቸው ያመለክታሉ። በመሆኑም ዓለም የሚሄድበት የሳይንስ መስመር፤ የመቀበል፣ የማመንና የመከተል ሂደቶችን የሚጎተቱ መሰናከሎችን በማስወገድ ረገድም የስፖርት ኮሚሽን ትልቅ ስራ እንደሚጠብቀውም አስገንዝበዋል። አስፈላጊው ሁሉ ተደርጎ አሁን ላይ የተገኘውን መልካም እድል መጠቀም ካልተቻለና ዓለም አቀፍ ታዋቂ ከለቦችና አካዳሚዎች የሚከተሉትን መንገድ መጓዝ የማይቻል ከሆነ ከላይ የተጠቀሱት ትሩፋቶች በሙሉ ፋይዳ ቢስ መሆናቸው ሊታወቅ እንደሚገባ አጽእኖት ሳይሰጡት አላለፉም። በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የስፖርት አካዳሚ ምክትል ዲንና መምህር ረዳት ፕሮፌሰር ወንድማገኝ ሸዋንግዛው፤ጀርመኖች እግር ኳሳቸውን ውጤታማ ለማድረግ ለስምንት ዓመታት በራቸውን ዘግተው በሃላም ስኬታማ ቡድን ይዘው መምጣታቸውን ይናገራሉ፤ ባየርሙኒክ በታዳጊ ፕሮጀክቶች ክፍተኛ ልምድ ያለውና ምርጥ ምርጥ ተጫዋቾችን በዓለም እግር ኳስ ማፍራት የቻለም እንደሆነ ይጠቅሳሉ። በዚህ መጠን ራሳቸውን ለማበልፀግ የሚጥሩት ጀርመኖችና ዋነኛው ክለባቸው ባየርሙኒክ ኢትዮጵያን ምርጫው በማድረግ የእግር ኳስ አካዳሚውን በአዲስ አበባ ለመገንባት የስምምነት ፊርማ ማኖሩም፤ ለኢትዮጵያ ትልቅ እድል፤ ለእግር ኳሱም ትልቅ ትንሳኤ መሆኑን ይስማሙበታል። አካዳሚው ለአገሪቱ እግር ኳስ ትንሳኤ በመሆን የስፖርት አስተዳደር ስርዓት በዓለም ዓቀፍ ሂደት ከማስጓዝ ፈይዳው የላቀ መሆኑን የገለፁት ረዳት ፐሮፌሰሩ፤ ለአገሪቱ አካዳሚዎች የሚሰጠው ትሩፋትም በርካታ ስለመሆኑ ነው ያስረዱት። ‹‹ከአካዳሚው ትሩፋቶች ለመቋደስም አሁን ላይ የተገኘውን እድል በጥንቃቄ መጠቀም የግድ ይላል›› የሚሉት ረዳት ፕሮፌሰሩ፤ፕሮፌሽናልን መሰረት ያደረገ የግለሰቦች ምልምላ እንዲሁም ማዳረስን ታሳቢ ያደረገ ሳይሆን ሙያና ብቃትን ያማከለ መረጣና ክትትል ማድረግ የግድ እንደሚልም ነው አፅእኖት የሰጡት።ለዚህ ተገቢውን ትኩረት መስጠት ከተቻለም ከአምስትና ስድስት ዓመታተ በኋላ የሚፈለገውን ውጤትም ማምጣት እንደሚቻል ነው ያብራሩት።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 15/2011
https://www.press.et/Ama/?p=9446
1,049
2ስፖርት
የእግር ኳስ ክለቦችና የፖለቲካ ፓርቲዎች ተመሳስሎ
ስፖርት
April 24, 2019
70
በእግር ኳሱ ዓለም በደጋፊዎች መካከል ግጭትና ሁከት ሲፈጠር ማየት የተለመደ ነው። የኢትዮጵያ እግር ኳስም በደጋፊዎች መካከል ለሚፈጠር ግጭት እና እሱን ተከትሎ ለሚፈጠር የስቴድየም ሁከት ባይተዋር አይደለም። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን በአገራችን ስቴድየሞች የሚከሰቱ ግጭቶችና ሁከቶች ስፖርታዊ ብቻ እየመሰሉ አይደለም። በተለይም ባለፉት ሁለትና ሦስት ዓመታት በተለያዩ የአገራችን ስቴድየሞች እየተስተዋሉ የመጡት የስቴድየም ሥርዓት አልበኝነት ጉዳዮች ከስፖርታዊ አንድምታ ይልቅ ወቅታዊ አገራዊ የፖለቲካ ጥላ ያንዣበበባቸው ስለመሆኑ ማሳያዎችን ማስቀመጥ ይቻላል። በተለያዩ የእግር ኳስ ደጋፊዎች በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ስፖርትና ፖለቲካን ደበላልቀውት በየስታዲየም ውስጥ ተጽፈው የሚታዩት ባነሮች፣ ወረቀቶች ተጽፈው የሚታዩት አዎንታዊና አሉታዊ መፈክሮች የዚህን ድብልቅልቆሽ ፍንትው አድርገው የሚያሳዩ ናቸው። ስፖርትና ፖለቲካ ምንና ምን ናቸው? የሚለውን ጥያቄ ዛሬም ድረስ ምላሽ አለማግኘቱን እዚህ ጋር ገታ እናድርግ። የሀገራችን የፖለቲካ ፓርቲዎች ወቅታዊ ሁኔታና የእግር ኳስ ክለቦቻችን ወቅታዊ ቁመና በእጅጉ ተመሳስሏል። የሁለቱ ዘውጎች ተመሳስሎን ከአደረጃጀት፣ ከስያሜ፣ በተተኪ ካለማመን አኳያ ያለውን እውነታ አፍታተን እንመልከት።የሀገራችን እግር ኳስ ክለቦችና ፖለቲካ ፓርቲዎች የአደረጃጀት ሁናቴ ተመሳስሎ ከሚታይባቸው አንኳር ጉዳይ ይጠቀሳል። ይህንኑ እግር ኳሱ መነሻ አድርገን እንመልከት። የእግር ኳስ ክለቦች የተደራጁበት ሁኔታ መሠረት ያደረጉት አካባቢን፣ ማንነትን፣ ከተማን፣ ክልልን … ያደረጉ ናቸው። በስያሜያቸው ያዘሉት ማንነት «ስፖርት ለወዳጅነትን የሚለውን ገልብጦ ለጦርነት» እንዲውል ምክንያት እስከመሆን ደርሷል። ለዚህ አመክንዮ የስፖርት ሳይንስ ምሁሩ ፒተር አልጊ/Peter እኤአ 2009 ያሳተመው ጆርናል እንደ ማሳያ እንጥቀስ። ፒተር በተለያዩ የስፖርት ዓይነቶች ብሔርተኛ ክለቦች መበራከት ብሔራዊ ስሜትን ወደ ፈተና የሚከቱ መሆናቸውን የሚያትት ሲሆን፤ ስፖርት የአንድነት ስሜት እንዲያደበዝዝ በተለየ መልኩ በቅኝ ገዥዎች ተግባራዊ ሲደረግ ነበር።የፒተር ሃተታ፤ ብሔርተኛ ክለቦች በአንድ ብሔር፣ ብሔረሰብ፣ጎሳ እና ዘር ተለይቶ እንዲታወቅ ብሎም እንዲደገፍ ተደርጎ የሚመሰረት የእግር ኳስ ክለብ ሲሆን በዘመነ ቅኝ ግዛት በተለይም በአፍሪካ ተስፋፍቶ የነበረ የክለብ አደረጃጀት ነው። ቅኝ ገዥዎች ስፖርትን በተለይም ደግሞ እግር ኳስን በመጠቀም የዘር እና የባህል ልዩነቶችን በአፍሪካውያን ላይ እንዲሰርጽ ለማስቻል በነገድ ላይ የሚያጠነጥኑ ቡድኖች በሥራ ቦታዎች (በፋብሪካ፣በማዕድን ቁፋሮ) ላይ ያቋቁሙ ነበር። በዚህ መልኩ ክለቦችን በመመስረት የአንድ አገር ሕዝቦችን በልዩነትና በብሔርተኝነት፣ በጎሰኝነት፣ በጎጠኝነት…አስተሳሰብ እንዲወጠሩ በማድረግ ብሔራዊ ስሜታቸውን በመሸርሸር የሀብት ብዝበዛውን ያለ ጥያቄ ሲያከናውኑ ቆይተዋል። ልዩነቱን ለመፍጠር በነገድ ላይ የሚያጠነጥኑ ቡድኖች እንዲስፋፉ በማድረግ ስፖርትን የአንድነት ፀር ለማድረግ ተጠቅመውበታል።በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በተለይ የእግር ኳስ ክለቦች በአብዛኛው ማለት ይቻላል ህልውናቸው ከተማን መሠረት ያደረጉ ቢሆንም የስፖርት ሜዳውን የጦርነት አውድማ ሲያደርጉት ታዝበናል። የእግር ኳስ ክለቦች አደረጃጀት መሠረቱን የልዩነትን ሚዛንን የማጉላቱ ሀቅ፤ በፖለቲካው ላይ ትልቅ ተመሳስሎ የሚስተዋልበት ነው።በሀገራችን ያሉ 107 ፓርቲዎች በፖለቲካ ሜዳው በቡድንነት ራሳቸውን ከማስመዝገብ ባሻገር፤ ከመንግሥት የሚደረገውን ድጎማ ለመቀራመት ከመሻት በዘለለ፤ የቡድናቸውን ስያሜ የተጠቀሙለትን አካል ፖለቲካዊ ባለ ድል ከማድረግ አኳያ ምንያህል ውጤታማ ያደርገን ይሆን? በሚል እሳቤ የተቃኘ አይመስልም። እውነታውን መካድ «ግመል ሰርቆ አጎንብሶ መሄድ አይቻልም» እና ሕዝብም እውነታ በገሃድ የሚናገረው ነው።የክለቦች መጠናከርና መብዛት ግቡ ጠንካራ ብሔራዊ ቡድን መፍጠር ሲሆን፤ በፖለቲካ ፓርቲዎች በኩል ደግሞ ዴሞክራሲያዊ ሀገርን መገንባትና ሕዝብን የሥልጣን ባለቤት ማድረግ ነው። የእግር ኳሱ ክለቦች የአደረጃጀት መሠረታቸውን ያልተቃና መሆኑ ጠንካራ ብሔራዊ ቡድን ለመፍጠር ዋልታና ማገር የመሆን ሚናቸውን አጥተውታል።መሰንበት ደጉ መቼም ብዙ ያሳየናል። «ምን አየን ደግሞ» መባሉ አይቀርምና ወደ ማብራሪያዬ ልግባ። የእግር ኳስ ክለቦች ሆኑ ፓርቲዎች አደረጃጀት መሠረቱ ልዩነት እንጂ አንድነትን የሚጋብዝ መሆኑ ለመጥቀስ ተሞክሯል። በሁለቱም ማዕዘን በኩል ያለው ስያሜ አካባቢን፣ ከተማን…መሠረት ባደረገ መልኩ እንደሆነ ተገልጿል። «ታዲያ ክፋቱ ምንድነው?» የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀርም። ክፋቱማ በግልጽ እየታየ ይገኛል፤ከእግር ኳስ ክለቦች በኩል ካለውን እውነታ ስንነሳ፤የብሔራዊ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከወራት በፊት «በስፖርታዊ ጨዋነት፣ የተመልካቾች ረብሻ፣ ሁከትና ብጥብጥ በኢትዮጵያ እግር ኳስ» በሚል ያስጠናውን ጥናት በመነሻነት እንጥቀስ። ፌዴሬሽኑ ጥናቱ በማሳያነት እንዳቀረበው፤ ቁጥራቸው ትንሽ የማይባል ስያሜ ቅጽል ስያሜ፣ አርማ፣ ዜማ ከተፈጥሯዊ አሰፋፈር ጋር ተዳብሎ በአንድም ይሁን በሌላ ምክንያት ከብሔር/ፖለቲካ ጋር ተያያዥነት ኖሮት እንዲቀርብ መደረጉ ጠቅሷል።በስፖርት ውስጥ ልዩነት ለመፍጠር መንገድ የሆነውን እንዲህ ዓይነቱን አደረጃጀትን ተመልክቶ መፍትሄ መስጠት የሚገባ መሆኑን በጥናቱ ውጤት በመፍትሄነት ቀርቧል። ከክለቦቻችን ስያሜ ጀርባ ለምንዛሬው ወደ ማንነት የቀረቡ መሆናቸው በስፖርት ተፈጥሯዊ ሕግ ውስጥ «ማሸነፍና መሸነፍ» መሆኑን እንዲረሳ ሲያደርግ ለመታዘብ ተችሏል። የሀገራችንን ነባራዊ ሀቅ ወደ ጎን ትተን እስቲ ወደ ስፔን እናቅና። በስፔን ፕሪሚየር ሊግ የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ጨዋታ ወቅት የሚፈጠረው ድባብ የስፖርት ሳይሆን የጦርነት ነው። ምክንያቱም ጨዋታው በተገንጣዩ የካታላን ግዛት ወኪል ባርሴሎና እና በማዕከላውያን ወኪል ማድሪድ መካከል የሚደረግ ስለሆነ። የባርሴሎናው ተከላካይ ጀራርድ ፒኬ በአንድ ወቅት ከአሁን በኋላ ካታላን ለሚባል ሀገር እንጂ ስፔን ለሚባል ሀገር አልጫወትም ብሎ በአደባባይ ማወጁ ጨዋታው የሚካሄድበትን ድባቡ መለወጡ ይገልጻል። በዚህ ስሜት ውስጥ ሆነን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን እንመልከት።በፕሪሚየር ሊጉ አሁናዊ ሁኔታ የጨዋታው ድልና ሽንፈት ከስፖርት አውድ አርቆ ወደማንነት ድል በማድረግ ወደ ጸብና ወደ ዱላ ማሻገር እየተለመደ መጥቷል። የስፖርቱን መልክም በግልጽ ፖለቲካዊ መልክ ብቻም ሳይሆን የብሔር አንድምታን በመስጠት ሌላ የጦርነት አውድ ሊሆን ሲከጅለው መታዘብ «መሰንበት ደጉ ብዙ ያሳየናል» ከሚለው አባባል ላይ ይጥለናል። ክለቦች የተደራጁበት ሁኔታ የመጣመም ክፋትን እንደተመለከትነው ሁሉ የፓርቲዎቹን እንመልከት።የእግር ኳስ ክለቦች ስያሜ በፖለቲካ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ ላይም ያለውን ተጽእኖ ተመሳሳይ ነው። የብሔር፣ የአካባቢ፣ ጥቂት ቡድንና ቤተሰብ መሠረት ያደረጉ ፓርቲዎች መፈልፈል፤ «ስያሜህ እኔን አይመስልምና አካባቢዬ ድርሽ ትልና….» የሚሉ ቅድመ ማስጠንቀቂያዎች እስከ መስጠት ሲደረስ ለመታዘብ ተችሏል። የቤተሰቡን ህልውና ለማስከበር የተቋቋመው ፓርቲ እኔ ለእኔ ቤተሰብ ብቸኛው ወኪል ነኝና «ዋ ቤቴ ትመጣና» እስከ መባባል ተደርሷል። የፓርቲዎቹ ደጋፊዎችም ቢሆኑ ብደግፈው ይበጀኝ፣ ይጠቅመኝ ይሆን በሚል ሚዛን ሰርቶ ሳይሆን «ብሔሬን፣ሰፈሬን…»ተሸክሟልና ልደግፈው የሚል ጭፍን ጉዞ ውስጥ እንዲጓዙ ሲያደርጋቸው ለመታዘብ ተቸሏል። ሃሳብ ትቶ ማንነት ላይ ያተኮረ የድጋፍ ስልት ለመኖሩ ደግሞ ትልቁ ምክንያት ከፓርቲዎች ስያሜው ጀርባ ያለው መዘዝ እንጂ ሌላ አይደለም። በፖለቲካው አካባቢ ያለውን መዘዝ በስፖርቱም ሲመዘዝ ምን እንደሚፈጠር አሳይቶ ማለፍ ይገባል።አሰልጣኝ ዘማሪያም ወልደጊዮርጊስ ከቀናት በፊት በጄቲቪኢትዮጵያ በነበረው ቃለ ምልልስ «በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውስጥ እኮ ከውጪ የመጡ ተጫዋቾች ያለምንም ስጋት እየተጫወቱ የኛ ተጫዋቾች ግን ዘራቸው እየተነሳ የመጡበት አካባቢ እየተጠቀሰ እንዲሳቀቁ መደረጉ ያሳፍራል…»ሲል የተናገረውን ማስታወስ ተገቢ ይሆናል። አሰልጣኙ የገለጸው እንዳለ ሆኖ የሁኔታው አደገኝነት ከዚህ ከፍ ሲል ደግሞ ክለቦች የሚቀጥሯቸው ተጫዋቾች፣ በተለይ አሰልጣኞች ከአካባቢውና ነዋሪ ተመሳስሎ መኖርን እንደ ቅድሚያ መስፈርትነት እስከ መመልከት የደረሰ መሆኑ ነው። ደጋፊዎች ክለቦችን የሚደግፉት የራሳቸውን አካባቢና አካባቢ ብቻ ሆኗል። በመሠረታዊነት ደግሞ እግር ኳሱን ሳይሆን ማንነቴን ያንጸባርቅልኛል የሚል መስፈርት መኖሩ ችግሩን ያገዝፈዋል። በተጨማሪም ለብሔራዊ ቡድን የሚመረጡ ተጫዋቾች ለመመልመል እዚሁ ስሌት ውስጥ እስከ መግባት የተደረሰ መሆኑ ይህቺ ሀገር ወዴት እየሄደች ይሆን የሚለውን የግርምት ጥያቄን ለመሰንዘር ያስገድዳል። እግር ኳሱም ሆነ ፖለቲካው በዚህ ደረጃ የመውረዱና እንዘጭ የማለቱ ሀቅ ሁለቱም የተደራጁበት መንገድ የተጣመመ ከመሆኑ ጋር እንደሚያያዝ ጥሬ ሀቅ ነው።የፖለቲካውና እግር ኳስ የጨዋታ ተስፋ ቢስ ካደረጉ ምክንያቶች አንዱና ዋነኛ ተደርጎ ቢነሳ ድፍረት አይሆንም፤ የተተኪ ችግር። ከተተኪ ጋር ተያይዞ ያለውን ችግርንና ተመሳስሎ ከእግር ኳሱ በመነሳት እንመልከት። ክለቦች ተጫዋቾችን ከታች ኮትኩተው በማሳደግ ወደ ዋናው ቡድን የማስገባት ዝንባሌን ብዙም አይታይባቸውም። ከዚህ ይልቅ ተጫዋቾችን ከሌላ ክለብ በማዘዋወር (በከፍተኛ የዝውውር ገንዘብ) ራሳቸውን መገንባት የተለመደ ነው። በተለይ አንጋፋ የሚባሉ ተጫዋቾች በአንድ ክለብ ለረጅም ዓመት ከተጫወቱ በኋላ ጫማ ከመስቀል ይልቅ እታች ወዳለ ክለብ በመዘዋወር የጡረታ ዕድሜያቸውን ሲያጣጥሙ መታዘብ አዲስ አይደለም። በክለቦች በኩል ልምድ የሆነው ተተኪዎችን ያገለለ የተጫዋቾች ዝውውር፤ አሁን አሁን ደግሞ ቅኝቱን ቀይሯል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ብቻም ሳይሆን በብሔራዊ ሊጉ ሳይቀር የውጭ ሀገራትን ተጫዋቾች የማስፈረሙ ልምድ ቦታውን ይዟል። የተጫዋቾች ዝውውር ሂደቱ በዚህ መልኩ መሆኑ ታዳጊዎችን በእግር ኳሱ ለማየት መታደል እንዳይቻል ሳንካ ሲፈጥር ለመታዘብ ተችሏል። በእግር ኳሱ እንደሚታየው የተተኪ ድርቅ ሁሉ በፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ በተመሳሳይ ይስተዋላል።በሀገራችን ከ107 በላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች ይገኛሉ። ከፓርቲዎቹ ዘጠና በመቶ በሚባል መልኩ በ60 ዎቹ ትውልዶች ተመስርተው በራሳቸው የሚመሩ ናቸው። የፓርቲዎቹ ርዕዮት ይሄኛውን ትውልድ ገሸሽ የሚያደርግ ሲሆን፤ ፖለቲካውንም እንዲዘውሩ ለሚያስችል የአመራርነት ዕድልን ያልጋበዘ መሆኑ፤ በፓርቲዎቹ ውስጥ የሚንጸባረቀውን በተተኪ ያለማመን ዝንባሌ ፍንትው አድርጎ ያሳያል። በዚህ እሳቤ ውስጥ የመዳከሩ ጉዳይ ደግሞ የፖለቲካውን ሜዳ ደጋፊ አልባ በማድረግ፤ የፓርቲዎች ቁጥር ብቻ ሆኖ እንዲጓዝ አድርጎታል። የሀገራችን ፖለቲካና እግር ኳስ የሜዳ ላይ ቆይታን በእጅጉ አሰልቺና ውጤት አልባ በመሆን ለመጓዙ ምክንያት ሆኗል።በአጠቃላይ የሀገራችን አሁናዊ የፖለቲካውና የስፖርቱ ጭብጫቦና ድጋፍ የሜዳ ላይ እንቅስቃሴንና የጨዋታ አሰላለፍን መሠረት ያደረገ ሳይሆን ማንነትን በመመዘን የሚደረግ መሆኑ ስፖርቱን ከስታዲየም፤ ዴሞክራሲውንም ከሀገር እንዲወጣ ሲታገለው ለመታዘብ ችለናል። ሃሳብና ችሎታ ከሚዛን ርቀው፤ የክለቡንና ፓርቲውን ስያሜ ብቻ ዋነኛ መስፈርት በሆነበት ሜዳ ላይ መቼም ቢሆን፤ ፖለቲካው ሆነ የስፖርቱ እርካብ ከስኬት መንበር ለመድረስ አይቻለውም። በመሆኑም ኢትዮጵያ እንደ አገር ልትቀጥልና ሕዝቧም በልዩነት በሰላም መኖር የሚችለው የታጠቀውም ያልታጠቀውም በጎሳና በዘር የተደራጁት ድርጅቶች በአዋጅ ሲታገዱ፤ ብሎም የፖለቲካ ፓርቲዎች ማቋቋሚያ አዋጅ ማሻሻያ ማድረግን እንደ ዋነኛ መፍትሄ መመልከት ይገባል። በስፖርቱም በተመሳሳይ በእግር ኳሱ በተመሳሳይ ክለቦች የተደራጁበት መንገድ ብሔርን፣ አካባቢን፣ ቡድንን መሠረት ያደረጉ እንደመሆናቸው ይሄንኑ ዓይነት ስያሜን በማስተካከል ስፖርቱ ከገባበት ህመም ማዳን ይገባል።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 16/2011
https://www.press.et/Ama/?p=9502
1,211
2ስፖርት
ጂኦቫኒ ኤልበር ባየርን በኢትዮጵያ ሊከፈት ስለታሰበው አካዳሚ ይናገራል
ስፖርት
April 21, 2019
20
የባየርን ሙኒክ አምባሳደር የሆነው ብራዚላዊው የቀድሞ አጥቂ ጂኦቫኒ ኤልበር በኢትዮጵያ ሊገነባ ከታሰበው አካዳሚ ጋር በተያያዘ እና ታዳጊዎችን ለመመልከት ከሌሎች ኃላፊዎች ጋር በመሆን እሁድ አዲስ አበባ መግባቱ ሶከር ኢትዮጵያ አስነብቧል። የባየርሙኒክ የረጅም ዓመት ስፖንሰር የሆነው የስፖርት ትጥቆች አምራች አዲዳስ በአዲስ አበባ የሚገኘው የምርት አከፋፋይ ድርጅት በአካል በመገኘት ጉብኝት አድርጓል። በጉብኝቱ ወቅት የቡንዲስ ሊጋው ዋንጫ ለተመልካች ክፍት የሆነ ሲሆን የፎቶ መነሳት መርሐ ግብርም ተካሂዷል። በመጨረሻም ጂኦቫኒ ኤልበር ከጋዜጠኞች ለቀረቡለት ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥቷል። ስለ ኢትዮጵያውያን ተጫዋቾች የነበረኝ እውቀት ውስን ነበር። ኢትዮጵያ ከመጣሁ ጀምሮ ግን ያየሁት ነገር ከጠበኩት በላይ ነው። በስታዲየም በመገኘት ብዙ ተመልካች እንደሚከታተል፣ ህብረተሰቡ ለእግር ኳስ ትልቅ ፍቅር እንዳለው አስተውያለሁ። በየመንገዱ ብዙ ሰው ኳስ ሲጫወትም ተመልክቻለሁ። ስለ ባየር ሙኒክም አብዛኛው ሰው እንደሚያውቅ መረዳት ይቻላል። አዎ። የመጣነውም ያንን ለመከታተል እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ለመነጋገር ነው። የኢትዮጵያ እግር ኳስን በጣም ማገዝ እንፈልጋለን። እዚህ አካዳሚ ውስጥ ታዳጊዎችን በማካተት ስለ እግር ኳስ ታክቲክ አጠቃላይ እውቀት እንዲኖራቸው ማድረግ እንፈልጋለን። የመጣነው ሀሳቦችን ሰጥተን ለመመለስ ብቻ አይደለም። ከባየርሙኒክ የሚመጡ የአካዳሚ አሰልጣኞች ስልጠና ይሰጣሉ፣ ታዳጊዎቹም ወደ ጀርመን እየሄዱ የሚማሩበትን እድል ማመቻቸት እንፈልጋለን። ከስፖርት ሚኒስቴሩ ጋር ጥሩ ግንኙነት አለን። አሁን ላይ ሆነን መቼ ይቋቋማል? ምን ያህል ታዳጊ በውስጡ አቅፎ ይይዛል? መቼ ይጀምራል? የሚለውን አሁን መመለስ አንችልም። ግን እየተነጋገርን ነው። በተቻለ መጠን በፍጥነት ለመጀመር እንሞክራለን። አሁን ትኩረት የምናደርገው ታዳጊዎችን በእግር ኳስ ክህሎት ማብቃት፣ ማጎልበት፣ ማዳበር ላይ እና እዚሁ በሀገራቸው የሚጫወቱበትን መንገድ ማመቻቸት ነው። በቀጣይ በባየር ሙኒክ ብቻ ሳይሆን በአውሮፓ የሚጫወቱበትን ዕድል ማመቻቸት እንፈልጋለን። (እየሳቀ) ይሆናል ብዬ ተስፋ አደር ጋለሁ፤ የማይሆንበት ምክንያት የለም። የባየር ሙኒክ ተጫዋቾችም እዚህ መምጣት ለኢትዮጵያውያን ተመልካች በጣም አስፈላጊ ነው። ባየር ሙኒክ አካዳሚ የሚጫወት በአባቱ ኢትዮጵያዊ የሆነ የ14 ዓመት ታዳጊ ተጫዋች አለ። በጣም ተስፋ ያለው ታዳጊ ነው። ማን ያውቃል ይህ ልጅ ትልቅ ሆኖ ለባየርሙኒክ ዋናው ቡድን ሲጫወት የቡድኑ አባላትን ይዞ ሊመጣ ይችላል።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 13/2011
https://www.press.et/Ama/?p=9351
275
2ስፖርት
ለንደን ማራቶን-የከዋክብቶች ፍልሚያ
ስፖርት
April 25, 2019
28
የዓለማችን ታላላቅ ከተሞች በየዓመቱ ከሚያ ስተናግዷቸው በርካታ የማራቶን ውድድሮች በሚያፎካክራቸው አትሌቶች ደረጃና ጥራት ቀዳሚ ሆኖ የሚገኘው የለንደን ማራቶን ነው። ይህ ውድድር የፊታችን እሁድ ሲካሄድ እንደተለመደው በርቀቱ ስመ ጥር የሆኑ በርካታ አትሌቶችን በሁለቱም ፆታ ለማፎካከር ተዘጋጅቷል። ባለፉት ሦስት ዓመታት በኬንያዊው የርቀቱ ፈርጥና የዓለም ክብረወሰን ባለቤት ኢሉድ ኪፕቾጌ የበላይነት ተይዞ የቆየው የለንደን ማራቶን ዘንድሮ በአገሩና በደጋፊው ፊት በሚሮጠው ሞሐመድ ፋራህ ይደምቃል ተብሎ ይጠበቃል። የዘንድሮው ውድድር በሦስት ጊዜ ባለ ድሉ ኪፕቾጌና በፋራህ መካከል የሚደረገው ፉክክር ከወዲሁ ትኩረት ቢያገኝም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በርቀቱ አስደናቂ ብቃት እያሳዩ በሚገኙት ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች ሹራ ቂጣታ፣ ሞስነት ገረመውና ልዑል ገብረሥላሴ የበለጠ እንደሚደምቅ ይጠበቃል። በሁለት ኦሊምፒኮችና በሦስት የዓለም ቻምፒዮናዎች የአምስትና አስር ሺ ሜትር ንጉሥ ሆኖ መዝለቅ የቻለው ሞ ፋራህ ካለፈው ዓመት ወዲህ ፊቱን ወደ ማራቶን መመለሱ ይታወቃል። ባለፈው የለንደን ማራቶን ሦስተኛ ሆኖ ያጠናቀቀው ፋራህ ጥቅምት ወር ላይ በቺካጎ ማራቶን በ2:05:11 የአውሮፓን ክብረወሰን አስመዝግቦ የመጀመሪያ ድሉን ካጣጣመ ወዲህ የዓለማችን የወቅቱ ኮከብ የማራቶን አትሌቶችን ጎራ ተቀላቅሏል። ድንቅ የማራቶን አትሌት መሆኑን ለማወጅም የእንግሊዝ መገናኛ ብዙኃን የእሁዱን የለንደን ማራቶን ድል አሰፍስፈው እየጠበቁ ይገኛሉ። ጥያቄው ግን ሌላው ይቅርና ፋራህ ኪፕቾጌን ማቆም እንዴት ይቻለዋል ነው? አንዳንድ የአገሬው መገናኛ ብዙኃን ኪፕቾጌ ምንም ያህል የርቀቱ ኮከብና ባለ ክብረወሰን ቢሆን ከእድሜው መግፋት ጋር ተያይዞ አንድ ቀን እጅ እንደሚሰጥ እርግጠኛ ሆነዋል። ያም ቀን የፊታችን እሁድ ሊሆን እንደሚችል ግምታቸውን እያስቀመጡ ነው። ያም ሆኖ ኪፕቾጌ አሁን ያለው አቋም ካለፈው ዓመት አኳያ የተሻለ እንጂ የባሰ እንደማይሆን ከልምምዶቹ መረዳት ይቻላል። ኪፕቾጌ ባለፈው ዓመት ወደ ተመሳሳይ ውድድር ከመምጣቱ በፊት በተለያዩ ውድድሮች ማራቶንን ከ2፡00 በታች ለማጠናቀቅ ብዙ ጥረት አድርጎ ነበር። ይህም ከአቅሙ በላይ ጉልበቱን እንዲያሟጥጥ አድርጎታል በሚል የለንደን ማራቶንን እንደማያሸንፍ ተጠርጥሮ ነበር። ይሁን እንጂ ይህ ድንቅ ኬንያዊ ለሦስተኛ ጊዜ ለንደን ላይ ነግሷል። ከዚያም ባለፈ ባለፈው የበርሊን ማራቶን 2:01:39 የሆነውን የዓለም ክብረወሰን በአስደናቂ ብቃት የግሉ ማድረግ ችሏል። ኪፕቾጌ በርሊን ላይ ያስመዘገበው ክብረሰወን የብቃቱ ጥግ ነው። ይህን ብቃቱን ዘንድሮ ላይደግመው ቢችል እንኳን ባለፉት ሦስት የለንደን ማራቶኖች ሲያሸንፍ ያስመዘገባቸው ሰዓቶች በአማካኝ ሲሰሉ 2:04:01 ነው። ታዲያ ፋራህም ይሁን ሌሎቹ ጠንካራ ተፎካካሪዎች ይህን እንዴት መመከት ይቻላቸዋል የሚሉ የስፖርቱ ቤተሰቦች በርካታ ናቸው። ኪፕቾጌ የዓለም ክብረወሰን የሆነውን ሰዓት ማስመዝገብ የቻለው በሂደት እየበሰለ መጥቶ በአስራ አንደኛው የማራቶን ውድድሩ ነው። እድሜው ሰላሳ አራት ሲሆን ሞ ፋራህን በሁለት ዓመት ብቻ ይበልጠዋል። ፋራህ እንደ ቀደምቶቹ ኮከብ አትሌቶች ወደ ማራቶን የመጣው በርካታ ዓመታትን በመም ውድድሮች አልፎ መሆኑ በማራቶን ጥሩ አትሌት እንደሚሆን ጥርጥር የለውም። ባለፈው ዓመት በመጀመሪያ የማራቶን ውድድሩም ሦስተኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ የነበረው በራስ መተማመንና በልምድ የሚበልጡትን የስነ ልቦና ጫና መቋቋም መቻሉ ዘንድሮ የተሻለ ነገር እንዲያሳይ ይረዳዋል የሚል መደምደሚያ ላይ አድርሷል። ሁለቱ ታላላቅ አትሌቶች ቀድመው ከገነቡት ስም አኳያ በዘንድሮው የለንደን ማራቶን በፉክክሩ ግንባር ቀደም ሆነው ይጠቀሱ እንጂ ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች ያልተገመተ ነገር ሊፈጥሩ እንደሚችሉ መጠበቅ ያስፈልጋል። በተለይም ባለፈው ዓመት በዚሁ ውድድር ኪፕቾጌን ተከትሎ ሁለተኛ በመሆን ያጠናቀቀው ሹራ ቂጣታ ፋራህን በ1፡ 32 ሰከንድ ልዩነት ቀድሞ መግባቱ ሊሰመርበት ይገባል። በሌላ በኩል ባለፈው የዱባይ ማራቶን የቦታውን ክብረወሰን በማሻሻል ያሸነፋው ሞስነት ገረመው ፋራህ በቺካጎ ማራቶን ሲያሸንፍ በአስራ ሦስት ሰከንዶች ዘግይቶ ሁለተኛ ማጠናቀቁ በቀላሉ የሚታይ አይደለም። ሌላኛው ትኩረት የሚሰጠው ኢትዮጵያዊ ልዑል ገብረሥላሴ ባለፈው ዓመት ማራቶንን ከ2፡05 በታች ማጠናቀቅ ከቻሉ ሦስት አትሌቶች አንዱ እንደመሆኑ ቀላል ተፎካካሪ አይሆንም። ይህ አትሌት በዱባይ ማራቶን 2፡ 04፡02 ያስመዘገበ ሲሆን ቫሌንሲያ ላይ 2፡04፡ 31 በሆነ ሰዓት የቦታውን ክብረወሰን ማሻሻል ችሏል። ስለዚህ በዘንድሮው የለንደን ማራቶን ከፋራህ ይልቅ ለኪፕቾጌ አስፈሪ ሊሆኑ የሚችሉት ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች ናቸው። እንደ ዘንድሮው የለንደን ማራቶን የትኛውም የማራቶን ውድድር በሴቶች ድንቅ የሆነ ፉክክር እንደማይታይ ከወዲሁ እየተነገረ ነው። በሴቶች መካከል ተፎካካሪ የሚሆኑት አትሌቶች ባለፈው ጥር ይፋ ሲደረጉ ከ2018 የወርልድ ማራቶን ሜጀርስ (WMM) ስድስት አሸናፊዎች አምስቱ መካተታቸው ጉድ ተብሎለት ነበር። ከነዚህ በተጨማሪ የ2018 የዱባይ ማራቶን ቻምፒዮንና በታሪክ በርቀቱ ፈጣን ከሆኑት አምስት አትሌቶች አራቱ መካተታቸው የዘንድሮውን የለንደን ማራቶን ከየትኛውም ጊዜ በላይ ተጠባቂ አድርጎታል። ከዚያን ጊዜ ወዲህ ግን የተቀየሩ ነገሮች መኖራቸው አልቀረም። የረጅም ርቀት ንግስቷ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ሁለተኛ ልጇን እንደ ፀነሰች መረጃዎች መውጣታቸውን ተከትሎ የዘንድሮው የለንደን ማራቶን የሴቶች ፉክክር ላይ ቀድሞ የነበረው አሰላለፍ እንደሚቀየር ይጠበቃል። ቀደም ሲል የዓለማችን ሁለተኛ፣ ሦስተኛ፣ አራተኛና አምስተኛ ፈጣን ሰዓት ባለቤት የሆኑ አትሌቶች እንደሚፎካከሩበት የተነገረው ውድድር አሁን ሁለተኛ፣ ስድስተኛ፣ ሰባተኛና ዘጠነኛ ፈጣን ሰዓት ያላቸው አትሌቶች የሚፎካከሩበት ሆኗል። የሦስት ጊዜ የለንደን ማራቶንና የአራት ጊዜ የኒውዮርክ ማራቶን አሸናፊዋ ኬንያዊት ማሪ ኪታኒ የዘመኗ ምርጥ አትሌት ነች። ይህም በዘንድሮው የለንደን ማራቶን ቀዳሚ የትኩረት ማረፊያ አድርጓታል። የኦሊምፒክ 5ሺ ሜትር ቻምፒዮኗ ቪቪያን ቼሪዮት ያለፈው ለንደን ማራቶን አሸናፊና የኒውዮርክ ማራቶንን ሁለተኛ ሆና ያጠናቀቀች አትሌት መሆኗ በሁለተኛነት ትኩረት አሰጥቷታል። 2:18:11 በሆነ ሰዓት የበርሊን ማራቶንን ክብረወሰን የጨበጠችው ግላዲ ቺሮኖ ትልቅ ትኩረት ያገኘች ሌላኛዋ ኬንያዊት ነች። እነዚህ ግዙፍ ስም ያላቸው ኬንያውያን ከእነሱ እኩል አቅም ያላቸውን የዘወትር ተፎካካሪ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚፎካከሩበት ውድድር አጓጊ ባይሆን ይገርማል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በማራቶን ጎልቶ የሚጠራ የኢትዮጵያውያን ስም መካከል ሮዛ ደረጄ አንዷ ናት። 2:19:17 በሆነ ሰዓት ባለፈው ዓመት የዱባይ ማራቶን ክብረወሰንን ሰብራለች። ባለፈው የካቲት ደግሞ በባርሴሎና ግማሽ ማራቶን 66፡01 በሆነ ሰዓት ማሸነፍ ችላለች። ሮዛ በዘንድሮው የለንደን ማራቶን ለኬንያውያን ፈተና እንደምትሆን ይጠበቃል። ባለፈው ቶኪዮ ማራቶን 2:19:51በሆነ ሰዓት ስታሸንፍ የቦታውን ክብረወሰን በአራት ሰከንዶች ከማሻሻል የቀረችው ብርሃኔ ዲባባ በእሁዱ ውድድር ጠንካራ ተፎካካሪ እንደምትሆን ትጠበቃለች።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 17/2011 
https://www.press.et/Ama/?p=9545
759
2ስፖርት
የእግር ኳስ ውድድርን እስከ ማቆም የሚደርስ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚችል ተገለጸ
ስፖርት
April 24, 2019
36
በእግር ኳሱ የሚስተዋለው ችግር ካልታረመ ውድድርን እስከ ማቆም የደረሰ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚችል ሚኒስቴሩ አስጠነቀቀ። በቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማኅበር አዘጋጅነት ለሁለት ቀናት «የስፖርት ጨዋነት ምንጮች» በሚል መሪ ቃል ከሚያዚያ 14 እስከ 15 ቀን 2011 ዓ.ም የምክክር ጉባዔ በሸራተን ሆቴል ተካሂዷል። የባህል ቱሪዝምና ስፖርት ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው እንደተናገሩት፤ በሀገራችን በስፖርታዊ ሁነቶች ላይ ስፖርታዊ ጨዋነት ሲጓደልና በርካታ ያልተገቡ ድርጊቶች ሲፈጸሙ እየተስተዋለ ይገኛል። በተለይ በእግር ኳሱ ከደጋፊዎች ጋር ተያይዞ የሚስተዋለው መስመር የለቀቀ ባህርይ እየተስተዋለ ነው፡፡ ችግሩ ካልታረመ ውድድርን እስከ ማቆም የደረሰ እርምጃ ሊወሰድ ይችላል። እንደ ዶክተር ሂሩት ገለጻ ፤ ስፖርት ለሰላም መሆኑ ቀርቶ ውድድሮች ዘርንና ማንነት መሰረት ባደረገ መልኩ የግጭት ምንጭ እየሆኑ ይገኛሉ። ስፖርት አለ በተባለ ቁጥር ሰው መረበሽ የለበትም። ህዝቡ ተረጋግቶ መኖር መቻል አለበት። ህብረተሰቡ ጨዋታ አለ በተባለ ቁጥር ለከፋ ስነ ልቦና ረብሻ መዳረግ የለበትም፤ አይገባውምም። ስለዚህ በእግር ኳሱ የሚታየው ስፖርታዊ ጨዋነት ችግር እስከሚስተካከል ውድድሩን እስከማቆም የሚደርስ እርምጃ ሊወሰድ የሚችል ይሆናል። ስፖርት ለወንድማማችነት የሚለው ብሂል ተረስቶ፤ በስፖርት ሁነቶች ላይ አጀንዳዎች እየተፈጠሩ እርስ በእርስ ወደ መጠቃቃት የመግባት ሁኔታዎች በስፋት እንደሚስተዋሉ አመልክተዋል። በስፖርት ማህበረሰቡ መካከል መጠራጠርና ጥላቻን ከመዝራት ባሻገር ኢትዮጵያዊ ባህልን፣ እኛነታችንን የሚያዋርድና የስፖርቱን እድገት የሚያቀጭጭ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህ ረገድ ክለቦችና ደጋፊ ማህበራት ሰፊ ስራ መስራት አለባቸው። በተለይ ክለቦችና የደጋፊ ማህበራትን የሚመሩ አካላት ለሚመሩት ወገን አርዐያ ሆነው መገኘት እንደሚኖርባቸው አስገንዝበዋል።«ጨዋ ተጫዋች ከጨዋ አሰልጣኝ ይፈጠራል፤ ጨዋ ደጋፊ ከጨዋ የደጋፊ ማህበራት፣ ክለብና የክለብ አመራር ይፈጠራሉ። ወጣቱ የሚማረው በዙሪያ ከሚታዩት ነባራዊ ሁኔታዎች በመሆኑ አመራር ላይ የምትገኙ አባላትና አካላት ተነባቢ መጽሀፍት መሆናችሁን አውቃችሁ መልካም አርዐያ በመሆን ቆርጣችሁ ልትነሱ ይገባል። ባለድርሻ አካላትም በመመካከርና በመወያየት ችግሩን መፍታትና እልባት ለመስጠት መስራት ይገባል» ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። የብሄራዊ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳይያስ ጂራ በበኩላቸው፤ ‹‹እግር ኳሱ የሌላ ነገር አጀንዳ መናኸርያ ከማድረጋችን ባሻገር ቂም እያወረስን እንገኛለን። እከሌ ሲያሸንፍ ከስፖርት መርህ ውጭ እከሌ ዘር ተሸነፈ፣ አሸነፈ በሚል ጤናማ ያልሆነ አስተሳሰብ ላይ ደርሰናል። ከስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል የተነሳ ሙሉ ጤና ይዞ መጥቶ ጤናውን አጉድሎ የሚመለስበት ጊዜ ላይ ደርሰናል›› ብለዋል። እንደ አቶ ኢሳያስ ገለጻ ፤ ችግሮችን ለመቅረፍ ጥረት እየተደረገ ቢሆንም ይህ በቂ አይደለም። እግር ኳሱን ከዚህ ስፖርታዊ ካልሆነ ተግባር ለመታደግ እንዲህ አይነት ውይይቶች ሊጎለብቱ ይገባል ። የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ፕሬዝዳንት አቶ አብነት ገብረመስቀል ፤ ‹‹በሀገራችን እግር ኳስ ውስጥ ሥርዓት አልበኝነት እግር ኳሱን እየጎዳው በመሆኑ በርካታ የስፖርት ቤተሰቦችን ከስፖርት ማዘውተሪያ እያራቀ ይገኛል። በጊዜ መስራት የሚገባውን የቤት ስራ ባለመስራታችን ችግሩ እየተባባሰ መጥቶ በዘር ፣ በጎሳ፣ በሃይማኖት እና በፖለቲካ አመለካከት ያተኮሩ ልዩነቶች እዚም እዛም እየታዩ ይገኛሉ። ስለሆነም ይህ እየተባባሰ የመጣውን ችግር ለመቅረፍ የውይይት መድረኩ የራሱ ድርሻ አለው የሚል እምነት አለኝ» ብለዋል።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 16/2011በ
https://www.press.et/Ama/?p=9498
386
2ስፖርት
ኢትዮጵያ በ12ኛው መላ አፍሪካ ጨዋታ ያስመዘገበችው ውጤት አመርቂና የሚበረታታ መሆኑ ተገለፀ
ስፖርት
September 6, 2019
38
 አዲስ አበባ ፦ ኢትዮጵያ በ12ኛው መላ አፍሪካ ጨዋታ ያስመዘገበችው ውጤት አመርቂና የሚበረታታ መሆኑን የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት እና የልዑካን ቡድኑ መሪ ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ገለጹ። በሞሮኮ አዘጋጅነት በተካሄደው በ12ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ላይ ከዝግጅትና ከተሳትፎ አንጻር በነበረው አፈጻጸም ዙሪያ ኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ መሰብሰቢያ አዳራሽ በትናንትናው እለት ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጥ፤ የኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ እንደተናገሩት ፤ ኢትዮጵያ በ12ኛው መላ አፍሪካ ጨዋታ ያስመዘገበችው ውጤት አመርቂና የሚበረታታ ነው። ዶክተር አሸብር በውድድሩ ላይ በ13 የስፖርት አይነቶች በመሳተፍ በስድስት ወርቅ፣ አምስት ብር እና 12 ነሐስ ሜዳሊያዎች 23 ሜዳሌያዎች በመሰብሰብ ዘጠነኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ አስታውሰዋል። በውድድሩ ወቅት የነበሩትን ፈታኝ ችግሮችን በመቋቋም አትሌቶቻችን ያስመዘገቡት ውጤት እጅግ የሚያኮራና የተገኘው ድል ጥሩና የሚያበረታታ ነው። ለዚህም ድል ላበቁን አትሌቶቻችን እና አሰልጣኞቻችን ክብር ይገባቸዋል ብለዋል። በውድድር መድረኩ ላይ ከዚህ የበለጠ ውጤት ማስመዝገብ የሚቻልባቸው አጋጣሚዎች እንደነበሩም ገልጸዋል። በአትሌቶቻችን ላይ የአለም አቀፍ መድረኮች ልምድ አለመኖሩ ቀድሞ ተሸንፎ ወደ ውድድር የመግባት አዝማሚያዎች መስተዋላቸውን ገልጸዋል። «በሃገር ውስጥ የሚገኙት የማዘውተሪያ ቦታዎችና በውድድሩ ላይ ከነበሩት ጋር ልዩነት መኖሩ በአትሌቶቹ ላይ ተጽእኖ መፍጠሩን ነው። በተለይ የቅርጫት ኳስ ሜዳው በእኛ ሀገር ያለውና በሞሮኮ የነበረው በእጅጉ ልዩነት ነበረው። በጅምላስቲክ ላይም የነበረው ሁኔታ ተመሳሳይ ሲሆን የመወዳደሪያ ቁሳቁሶቹ ለአትሌቶቹ አዲስ ስለነበሩ የውድድር ሂደቱ ላይ ተጎጂ አድርጓቸዋል » በማለት በውድድሩ የነበሩት እንቅፋቶች ነበሩ በማለት አስረድተዋል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ ዳይሬክተር አቶ ዱቤ ጂሎ በበኩላቸው፤ በውድድር መድረኩ ከዳኝነት ጋር ተያይዞ የነበረው ችግሮች ሌላውና ትልቁ ነበር። በሁሉም የውድድር አይነቶች ላይ ግልጽና በሚታይ መልኩ በዳኞቹ በኩል ክፍተቶች እንደነበር አንስተዋል። በዚህም ምክንያት በተለይ የእኛ ተወዳዳሪዎች በበርካታ የስፖርት አይነቶች ተጎጂ በማድረግ ችግሮች በውጤቱ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ እንዳሳደረ አብራርተዋል። «በቦክስ በሴትም በወንድም ክፍተት መታየቱት ጠቅሰው፤ የእኛ ተጫዋቾች የተሻለ መጫወት ቢችሉም የጨዋታው ውጤት ሲገለጽ ግን አሸናፊው ሌላ የሆነበት አጋጣሚ መኖሩን አስታውሰዋል። በካራቴና በወርልድ ቴክዋንዶ ተመሳሳይ የዳኝነት ችግር ነበር። በሴቶች እርምጃ ውድድር ሌላው ከዳኝነት ጋር ተያይዞ የወርቅ ሜዳሊያን ያሳጣ መሆኑን ገልጸው፤ የዳኝነት ሸፍጡ ዋጋ አስከፍሎናል »ብለዋል። በውድድር መድረኩ በተለይ ከዳኝነት ጋር ተያይዞ የነበረውን ችግር ወደ ሚመለከተው አካል ክስ መቅረቡን የገለጹት ደግሞ የስፖርት ኮሚሽን የስፖርት ተሳትፎና ውድድር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ በቀለ ሲሆኑ፤ ውሳኔ እየተጠበቀ መሆኑን ተናግረዋል። አቶ ተስፋዬ አክለው፤ «አጠቃላይ በውድድሩ የመጣው ውጤት አመርቂ የሚባል ሲሆን ይሄውም ከዝግጅት አንስቶ እስከ ተሳትፎ ላለው ሂደት ከፍተኛ ትኩረት ከመሰጠቱ የመነጨ ነው» ብለዋል። በመድረኩም ላይ የተመዘገበው ውጤት አኩሪ የሚባል ሲሆን፤ አረንጓዴው ጎርፍ ከረጅም ጊዜ በኋላ ተመልሶ የታየበት መሆኑን አመልክተዋል። የውጤቱ ባለቤት የሆኑት አብዛኛዎቹ ወጣት አትሌቶች መሆናቸው የድሉን ደረጃ ከፍ በማድረግና በቀጣይ ትላልቅ አለም አቀፍ ውድድሮች ላይ ኢትዮጵያን የሚያኮሩ የተስፋ ባለቤት የሆኑ አትሌቶች እንዳሏት የሚያሳይ መሆኑን አብራርተዋል። በ12ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች 54 ሀገሮች በ26 የስፖርት አይነት 6ሺ አትሌቶች ተሳትፈውበታል።አዲስ ዘመን ጳጉሜ 1/2011 ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=17386
400
2ስፖርት
ከባህር ዳር ሰማይ ስር በዋልያዎቹ የተመሰለው ብሄራዊ ኩራት
ስፖርት
September 6, 2019
207
ስፖርታዊ ክንዋኔዎች ከመዝናኛነት ባሻገር ጥልቅ የሃገር ፍቅር መውጫ የጦር አውድ መሆኑን በርካቶች ሲናገሩ ይደመጣሉ። «የአትሌቶች ሀገር» ሲል አለም የመሰከረላት ኢትዮጵያችን ለዚህ ንግርት ማረጋገጫ በመሆን ትጠቀሳለች። በአትሌቶቿ በአለም አቀፍ መድረኮች ዘመን ተሻጋሪ የድል ታሪክ በማስመዝገብ አለም የአትሌቶች ሃገር የሚል ተቀጽላን አክሎ እንዲጠራት አድርጓል። ኢትዮጵያን በጀግንነት ለማስጠራት እነዚህ ጀግና አትሌቶች አድካሚና ፈታኝ መንገድ መጓዝ ግድ ይላቸዋል። ፈተናዎቹንም በአሸናፊነት በጣጥሶ ማለፍ ይጠይቃል። ከአትሌቶቹ ጽናት በተሞላው የድል መዳረሻ ጀርባ «የሃገር ክብር»የሚባል ጥልቅ የሃገር ፍቅር ብርታትና ጉልበት ሲሆናቸው ታዝበናል። በአትሌቶቹ ድል በአለም ፊት አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ቀይ ሰንደቅ አላማ ከፍ ብሎ ተውለብልቧል። የድሉ ባለቤት የሆኑት አትሌቶቻችን የሃገር ፍቅር፣ ክብርና ነጻነት ትርጓሜን ያዘለው ሰንደቅ ከፍታ፤ጥልቁን የሃገር ፍቅር ለመግለጽ እንባቸውን መገደብ በተሳነው ሁናቴ ሲገልጹ ተመልክተናል። የኢትዮጵያ ክብርና አርማ በሆነው ኃይሌ ገብረስላሴ፣ በእንስቷ ንግስታችን ደራርቱ ቱሉ የ2001 የሲድኒ ኦሎምፒክ የዘላለም ምስክር ናቸው። በተለያየ የእድሜ ክልል የሚገኘው ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ የአትሌቶቹ በጥልቅ የሃገር ፍቅር ተሞልቶ ድልን የመሻት እሩጫን በማበረታታትና በማገዝ ረገድ ሚናውን ይወጣል። በድሉ ግኝት በሃገር ፍቅር ስሜትና አብሮነት ደስታውን ያጣጥማል። በአንድነት ብሮ ወሸባዬን ይጨፍራል። በኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ቀለም ሰንደቅ አላማውን በክብር ከፍ አድርጎ በአንድነት ይሰቅላል። በስፖርቱ ድል የሃገር አሸናፊነትን ስሜቱን ይወጣል። በአትሌቲክሱ ድል የሚቀዳው ሃገራዊ ስሜት በእግር ኳሱም ቢሆን በተለያዩ አጋጣሚዎች ሲንጸባረቅ ታዝበናል። እኤአ በ2013 የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በደቡብ አፍሪካ ዋንጫ ማለፏን ተከትሎ በህዝቡ ልብ ውስጥ የነበረው ደስታ ከጥልቅ የሃገር ስሜት እንጂ ሌላ ምክንያት አልነበረውም። ዋልያዎቹ ከ31 ዓመት በኋላ በአፍሪካ ዋንጫ መሳተፍ የህዝቡ ብሄራዊ ስሜት እንዲገነፍል አድርጎት ታይታል። የኢትዮጵያዊነትን ስሜት ከገባበት ሰመመን በመቀስቀስ ህዝቡን ከዳር እስከ ዳር በአንድነት አስተሳስሯል፣ አስፈንጥዟልም። የልዩነት ነጋሪት ጉሰማውን ድምጽ በመዋጥ፤ የአንድነቱን ድምጸት አጉልቷል። ይህም በአትሌቲክስ ስፖርት የተገነባው ብሄራዊ ስሜትን ዳግም እንዲያንሰራራ ያደረገ ትልቅ አጋጣሚ ከመሆን በተጓዳኝ ብሄራዊ መግባባት የፈጠረ ልዩ አጋጣሚ እንደነበርም ይታወሳል። ከትናንት በስቲያም ዋሊያው በቀጣዩ አመት ኳታር ለምታዘጋጀው የአለም ዋንጫ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታውን ከሌሴቶ ጋር ሲያከናውን ከባህር ዳር ሰማይ ስር የሆነውም ይህን የታሪክ አጋጣሚ ዳግም ያስመለከተ ነበር። ብሄራዊ ቡድኑን ለመደገፍ ከባህርዳርና አካባቢዋ የሚገኝ የሃገር ስሜት የኮረኮረው ደጋፊ ወደ ስታዲየም ማልዶ ነበር መትመም የጀመረው። ብሄራዊ ኩራቱን የተሸከሙለትን ዋልያዎቹን ለማበረታታት ከረፋዱ 5 ሰዓት ጀምሮ በህብረ ቀለማት ደምቆና ታጅቦ የተለያዩ ትዕይንቶች ያሳየበት ሁኔታም እጅጉን ደማቅ ነበር። አረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀዩ ሰንደቅ በባህር ዳር ጎዳናዎች በድምቀትና በክብር ሲውለበለብ የነበረበት ሁናቴ ታሪክ ራሱን የደገመበት ነበር። ሁለቱ ብሄራዊ ቡድኖች ከሁለት አመት በፊት ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በባህር ዳር ስታዲየም ጨዋታቸውን ማካሄዳቸውና በዋልያዎቹ 2 ለ 1 አሸናፊነት መቋጨቱ የሚታወስ ሲሆን በወቅቱ በስታዲየም ከአፍ እስከ ገደፍ ሞልቶ በተጋጣሚው ቡድን ትልቅ የስነ ልቦና ችግር መፈጠር የቻለው ደጋፊ፣ ለዋልያዎቹ ተጨማሪ አቅምና ጉልበት ሆኖም ነበር። የትናንት በስቲያም ፍልሚያ ምንም እንኳን በውጤት ሲቃኝ ታሪክ ራሱን ደግሞ ባይታይበትም፤ ደጋፊው ግን በጥልቅ የሃገር ፍቅር ብሄራዊ ኩራቱ የሆነውን ብሄራዊ ቡድን ከማበረታታት አኳያ ታሪክን ደግሞ ሰርቶታል። ከማለዳ ጀምሮ በባህር ዳር ጎዳኖዎች የነበረው ከአገር ወዳድነት የሚፈለቀቀው ጥልቅ ስሜትም፤ ጨዋታው ከተጀመረ በኋላ ይበልጥ ተጋግሎና ከፍ ብሎ ተሰምቷል። ሙሉ ዘጠና ደቂቃ በተለያዩ ህብረ ዝማሬዎች በማጀብ ብሄራዊ ኩራት ለሆኑት ዋልያዎቹ ብርታት ሲሆኑ ታዝበናል።”…ዋልያ… ዋልያ…” “… ድሌ ማታ ነው ድሌ…” የደስታ ማጣጣሚያ ሆነው ሲሰሙ የነበሩ የባህር ዳር ስታዲየም ድምጾች ነበሩ። በእለቱ ከአፍ እስከ ገደፍ በሞላው ስታዲየም የነበረው ትዕይንት በእርግጥም፤ ከባህር ዳር ሰማይ ስር በዋልያዎቹ ተመስሎ ብሄራዊ ኩራት በከፍታ ላይ ሲውለበለብ ለመታዘብ ተችሏል። ምንም እንኳን በብሄራዊ ስሜት ብሄራዊ ቡድኑን ለማበረታታት የተሄደበት ርቀት ታሪክ ራሱን ቢደግምም በውጤት ደረጃ ግን ራሱን መድገም የቻለ አልሆነም። በጨዋታ እንቅስቃሴ ብልጫ ማሳየት የቻሉት ዋልያዎቹ የሌሴቶን መረብ ለመድፈር ሳይችሉ ሙሉ ዘጠና ደቂቃ ተጠናቋል። መከላከልን መሰረት ያደረጉት ሌሴቶዎች ግባቸው ሳይደፈር ነጥብ እንዲጋሩ አድርጓቸዋል። ከጨዋታው በኋላ የዋልያዎቹ አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ «ከምንግዜውም በተሻለ ጥሩ ተጫውተናል፤ በርካታ የግብ እድሎችንም መፍጠር ችለናል፤ ነገር ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎላ የመጣው የአጥቂ መስመር ክፍተት ጎል ሳናስቆጥር እንድንወጣ አድርጎናል። በቀጣይ ጊዜ ግብ የማስቆጠር ችግራችን ለመቅረፍ በርትተን እንሰራለንም» ብለዋል። «90 ደቂቃ ያለእረፍት ከጎናችን በመሆን ያበረታንን ደጋፊ ከልብ ማመስገን እፈልጋለሁ።» ሲሉም በከፍተኛ ድጋፍ ለታጀቡት ዋልያዎቹ በተጋጣሚውን ቡድን ላይ የጨዋታ የበላይነት እንዲያሳይ ሞራል እንደሆናቸው አስምረውበታል። የሁለቱ ብሄራዊ ቡድኖች የመልሱ ጨዋታም የፊታችን ጳጉሜን 3 ቀን ቀጠሮ ተይዞለታል።አዲስ ዘመን ጳጉሜ 1/2011 ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=17389
600
2ስፖርት
ዘረኝነት በእግር ኳስ ማጥላቱን ቀጥሏል
ስፖርት
September 5, 2019
32
በተወዳጅና አዝናኝነቱ ከዓለም ህዝብ ዘንድ መንገስ የቻለ ስፖርት ነው፤ እግር ኳስ። ድምበር አልባነቱም ህዝቦች ያለ ልዩነት እንዲቀራረቡና በአንድ ቋንቋ እንዲግባቡም አድርጓል። በርካታ ሃገራት መልካም ገጽታቸውን የገነቡበት አንደኛው መሳሪያ እንዲሁም ከፍተኛ ገንዘብ የሚያንቀሳቅስ የንግድ አካልም ሆኗል። ባለሃብቶችን በቀላሉ መሳብ የቻለው ስፖርቱ በርካታ ተጫወቾችንም ባህር አቋርጠው እንዲጫወቱ አስችሏቸዋል። ነገር ግን ስፖርቱ ሰለጠነ በተባለ ዘመንና ሃገራት ሳይቀር ጥላሸት ከሚቀባው ዘረኝነት እስከ አሁንም መላቀቅ አልቻለም። እንዲያውም በዚህ ወቅት በተለይ ይስተዋልባቸው ከነበሩ ሃገራትና ሊጎችም አልፎ በርካቶች ዘንድ እየተተገበረ መሆኑ ይነገራል። በቃላት፣ በምልክት፣ በድምጽ እንዲሁም በሌሎች መንገዶች የሚከናወነው ድርጊቱ በተጫዋቾች ላይ በሚያደርሰው የስነልቦና ጫና ምክንያት ከሚወዱት እግር ኳስ ሊያርቃቸው እንደሚችልም የስፖርቱ ከዋኞች በመጠቆም ላይ ይገኛሉ። የቅርቡን ለማስታወስ ያህልም፤ ባለፈው እሁድ በቅርቡ ኢንተርሚላንን የተቀላቀለው ሮሜሉ ሉካኩ የቅጣት ምት ማግኘቱን ተከትሎ ተመልካቾች የጦጣ ድምጽ ያሰሙ ነበር። ፓውል ፖግባ፣ ታሚ አብርሃም እና ኩርት ዙማም ይህ ዓይነቱ ጥቃት በቅርቡ የደረሰባቸው ተጫዋቾች ናቸው። የእንግሊዝና የቦርሲያ ዶርትመንድ የክንፍ ተጫዋቹ ጃደን ሳንቾም በአውሮፓ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ላይ ተመሳሳይ ጥቃትን አስተናግዷል። ይህንን ተከትሎም ተጫዋቹ በሰጠው አስተያየት «ይህ ነገር መቆም አለበት፤ ምክንያቱም የትኛውም ተጫዋች ጥቃት እየደረሰበት እግር ኳስን መጫወት ስለማይፈልግ። የተጫዋቾችን በራስ መተማመን የሚያወርድ ከመሆኑም ባሻገር ለስፖርቱ ያላቸውንም  ፍቅር ያሳጣል» ማለቱን ጎል ዶፐት ኮም አስነብቧል። ተጫዋቹ በዚህም ሳያበቃ «ሁላችንም ደስተኛ መሆን አለብን ማድረግ ያለብንንም ለማድረግ የዘረኝነት ጥቃቱ ሊቆም ይገባል። ደጋፊዎች የሚናገሯቸውን ነገሮች መለየት ይገባቸዋል ምክንያቱም እኛም ሰው ነን። ሰዎች ታዋቂ በመሆናችን ይህ ዓይነቱ ነገር ሲከሰት በዝምታ እንደምናልፍ ያስባሉ። ነገር ግን ለምንድነው እግር ኳስ የምንጫወተው ብለን እንዳስብ ያደርገናል» ሲልም ስሜቱን አንጸባርቋል። የቀድሞ የማንቺስተር ሲቲ እና የአሁኑ የጣሊያን ብሔራዊ ቡን አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማንቺኒ በበኩላቸው፤ «እንዲህ ያለው የዘረኝነት ጥቃት ያበቃ መስሎን ነበር፤ ነገር ግን አሁንም እንደ እንግሊዝ ሁሉ በጣሊያንም ይስተዋላል። ይህንን ስህተት የሚፈጽሙ ሰዎችም ማጥፋታቸውን በጊዜ ሂደት ይረዳሉ። እንደሚመስለኝ ከሆነም ተግባሩን የሚፈጽሙት ተመሳሳይ ሰዎች ይመስሉኛል» ሲሉ ገልጸዋል። የኢንተር ሚላን ደጋፊዎች በበኩላቸው ጣሊያናዊያን ደጋፊዎች ዘረኞች አለመሆናቸውን ገልጸዋል። «በካግላሪ ደጋፊዎች ለተንጸባረቀው ዘረኝነት ማዘናችንን እንገልጻለን» ሲሉም ከአዲሱ ተጫዋቻቸው ጎን መቆማቸውን አሳይተዋል። በደጋፊዎቹ ይፋዊ የፌስ ቡክ ገጽ በሰፈረው ጽሑፍ ላይም ተጫዋቹን «መረዳት ያለብህ ጣሊያን እንደ ሰሜን አውሮፓ ሃገራት የተጋነነ የዘረኝነት ችግር የሌለ መሆኑን ነው። ተጫዋቾቻንን ለማበረታታት እንዲሁም ተቃራኒውን ቡድን ለማሸበርም የተለያዩ ድምጾችን እናሰማለን። በመሆኑም የእኛን እንደ ድጋፍ እንጂ እንደ ተቃውሞ አትረዳው» ማለታቸውንም ቢቢሲ በድረ ገጹ አስነብቧል። የሰሞነኛው መነጋገሪያ የሆነው ካግላሪ ክለብም ክስተቱን «አሳፋሪ» በማለት የገለጸው ሲሆን፤ በአሳፋሪው ድርጊት የተሳተፉትን በመለየት እስከ እገዳ የሚደርስ ቅጣት እንደሚያስተላልፍባቸው አስታውቋል።አዲስ ዘመን  ነሐሴ 30/2011ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=17343
358
2ስፖርት
ሜዳ ሳር ብቻ ሳይሆን ሰው ያበቅላል
ስፖርት
September 8, 2019
63
ከሳምንት በፊት ነው። ከጓደኛዬ ጋር ከስራ በኋላ በእግራችን እየተጓዝን ነበር። የእግር ጉዞ ለጤናም ለጨዋታም ይጠቅማል አይደል የሚባለው። በአጋጣሚ ለብዙ ጊዜ እየተመለከትኩት ያላስተዋልኩትን አንድ የእግር ኳስ ሜዳ ጋር ስደርስ ድንገት ቀልቤን የሳበው ነገር አጋጠመኝ እና ቆም አልኩ። ቢያንስ ከ30 የሚበልጡ ሰዎች ሙሉ የእግር ኳስ ትጥቅ ለብሰው ልምምድ ያደርጋሉ። ታዲያ ይሄ ምን ይገርማል? ትሉ ይሆናል። እኔን የገረመኝ ሰዎቹ ያላቸው ተክለ ሰውነት አንድ እግር ኳስ ተጫዋች ሊኖረው የሚገባ አቋም ባለመሆኑ ነበር። ቢሆንስ ታዲያ ለጤናቸው እየሰሩ ነዋ! ትሉ ይሆናል። እውነት ነው ለጤናቸው ነው የሚሰሩት። ግን ስነምግባራቸው እና ያላቸው ሞራል ከማስገረምም አልፎ ቀልብን ይስብ ነበር። ልምምዳቸውን ከመመልከት ባለፈ የቡድን መሪያቸውን ጠጋ ብዬ አናገርኩት። የእግር ኳስ ጤና ማህበር እንደሆነ አጫወተኝ። ሜዳው ቀበና አካባቢ የሚገኘው «የቤሌር እግር ኳስ ሜዳ ነው» ። «ይህ ስፍራ አንተ ከምታስበው በላይ ታዋቂና አንጋፋ እግር ኳስ ተጫዋቾችን አፍርቷል። ነገር ግን ለበርካታ ጊዜያት ተረስቶ የቆሻሻ መጣያ ሆኖ ነበር። ታዳጊዎችም ማዘውተሪያ ስፍራ አልነበራቸውም» ብሎኝ ላለፉት አራት ዓመታት ሜዳው የነበረውን የቀድሞ ስም ለመመለስ፣ ማህበራቸውም ጤናን መሰረት አድርጎ ስፖርትን ከማበረታታት ባለፈ ለታዳጊ ወጣቶች ተስፋ የሚፈነጥቁ ስራዎች ለመስራት እየለፋ መሆኑን ነገረኝ። በሰፊው ለመጨዋወት ተቀጣጥረን በሳምንቱ ተገናኘን። ዳዊት ግርማ ይባላል። በቀበና 15 ሜዳና አካባቢ እየተባለ በሚጠራው ሰፈር ነዋሪ ነው። ከልጅነቱ ጀምሮ በአካባቢው «ቤሌር» እየተባለ በሚታወቀው ሜዳ ከጓደኞቹ ጋር ኳስን እያንከባለለ ነው ያደገው። በግል ስራ ላይ ተሰማርቶ የሚገኘው ጎልማሳ ከስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ እግር ኳስን በተለየ ሁኔታ ይወዳል። በአሁኑ ወቅት ከአብሮ አደጎቹ ጋር በጋራ በመሆን «የአስራ አምስት ሜዳና አካባቢው የጤና እግር ኳስ ማህበር» መስርተዋል። እርሱም የማህበሩ ሰብሳቢ በመሆን ያገለግላል። «የእግር ኳስ ማህበሩ ከተመሰረተ አራት ዓመታትን አስቆጠሯል» በማለት በዋናነት ምስረታው በርካታ አላማዎችን አንግቦ እንደሆነ የሚናገረው ዳዊት፤ የቤሌር ሜዳ ከዚህ ቀደም ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ያበረከተው አስተዋጽዖ ከፍተኛ እንደሆነ ይናገራል። ሆኖም ለብዙ ዓመታት «የቆሻሻ መጣያ እና መፀዳጃ» ሆኖ የአካባቢውን ሰው ለጤና ችግር ሲያጋልጠው ቆይቷል። የአካባቢው አብሮ አደጎችም ይህንን በመገንዘብ የቀድሞውን ዝና ለመመለስ፣ ህብረተሰቡንም ለጤና ችግር የሚያጋልጡ ቆሻሻዎችን ለማስወገድ እና ሌሎች በጎ አላማዎችን ለመስራት በአንድ ጥላ ስር ተሰባስበዋል። በሳምንት ሶስት ጊዜ ልምምድ እንዲሁም በየጊዜው የተለያዩ ውድድሮችን በማድረግ ጤናቸውን ይጠብቃሉ። «አሁን በራሳችን ጥረት እና በአንዳንድ በጎ ፍቃደኛ ባለሀብቶች የሜዳውን ፅዳት መጠበቅ እና ከዚህ ቀደም ከነበረው የተሻለ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ ለማድረግ ጥረት አድርገናል» የሚለው የማህበሩ ሰብሳቢ አሁንም ድረስ በስፍራው ላይ መሰራት ያለባቸው ቀሪ ተግባራት መኖራቸውን ይናገራል። የአዲስ አበባ ጤና ስፖርት ማህበር የሚመራቸው በከተማዋ የሚገኙ ከ30 በላይ ማህበራት አሉ። ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ጤናን መጠበቅ እና ማህበራዊ ግንኙነትን ማጠናከርን ታሳቢ አድርገው የተመሰረቱ ናቸው። የአስራ አምስት ሜዳና አካባቢው የጤና እግር ኳስ ማህበርም ከነዚህ መካከል የሚመደብ ነው። ከሌሎች ማህበራት ልዩ የሚያደርገው ግን በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ጉልህ ስፍራ ያላቸው ተጫዋቾችን ማፍራት የቻለው «የቤሌር ሜዳ» ቀድሞ የነበረውን ስም እና ዝና በመመለስ አሁንም ብቃት ያላቸው ተጫዋቾች እንዲያፈራ ለማስቻል በሚያደርገው ብርቱ ጥረት ነው። የማህበሩ አባላት ከልጅነታቸው ጀምሮ በዚህ ሜዳ ላይ እየተፎካከሩ አንዳንዴም እየተጣሉ በአንዳንድ ምክንያት ሲለያዩ ደግሞ እየተነፋፈቁ ለረጅም ዓመታት አሳልፈዋል። ከሁሉም ከሁሉም ይህን ማህበር በቁርጠኝነት መስርተው የሜዳውን የቀድሞ ዝና ከዚያም አልፎ የአብሮ አደግነታቸውን ፍቅር ለመመለስ ያነሳሳቸው የአንድ ጓደኛቸው ሞት ነበር። የዚህ ሰው ሞት ከምንም ነገር በላይ ያስቆጫቸው ደግሞ በህክምና መዳን በሚችል ህመም ደጋፊ በማጣቱ ብቻ በመሞቱ ነበር። ክስተቱ የእነርሱ አለመሰባሰብ በአንድነት አለመረዳዳት ምን ያክል ጉዳት እንዳለው በይበልጥ አስረድቷቸዋል። አባላቱ «እግር ኳስ» ሁላችንንም በአንድነት የማሰባሰብ እና እንድንደጋገፍ የማድረግ ሀይል አለው የሚል እሳቤ አላቸው። ተዳፍኖ የቆየውን የቤሌር ሜዳ በድጋሚ እንዲያንሰራራ ከማድረግ እና ተስፋ ያላቸው እግር ኳስ ተጫዋቾችን ለአገሪቷ ከማበርከትም በላይ በአካባቢው የተቸገሩ ነዋሪዎችን መርዳት እንድንችል ስፖርቱ ትልቅ ሀይል ይሆነናል ይላሉ። አራት ዓመታትን ያስቆጠረው የጤና ስፖርት ማህበራቸው ሲጀመር ትንሽ ሆኖ ጊዜያት በረዘሙ ቁጥር ደግሞ አቅሙን እያጠናከረ የአባላት ቁጥሩን እየጨመረ መጥቷል። አሁን ከ90 በላይ አባላቶችን ይዞ ይንቀሳቀሳል። ለረጅም ዘመናት የአካባቢው ተወላጆችን ጨምሮ በሜዳው ፍቅር ተይዘው ኳስን ለማንከባለል ከአጎራባች ሰፈሮች የሚመጡ ልጆችን ያለ ልዩነት ሲቀበል የነበረውን ሜዳ ባላቸው አቅም ለማስተካከል ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ። የማህበሩ ሰብሳቢ ዳዊት ከዝግጅት ክፍላችን ጋር ባደረገው ቆይታ( እጁን ወደ ሜዳው እየጠቆመ) «ይህቺ ሜዳ ለብዙ ሰዎች ባለውለታ ነች» በማለት የቤሌር ሜዳን ታሪካዊ ባለውለታነት ይናገራል። በንግግሩ ለመረዳት የሞከረ ሰው «ታዲያ ውለታ ለሰራችልን ሜዳ ብንሰባሰብላት እና የቀድሞውን ስም እና ዝና ለመመለስ ብንሞክር ምን ይገርማል፤ ሜዳዋ እኮ ሳር ብቻ ሳይሆን ሰውም አብቅላለች» የሚል ድምፀት የተደበቀ ይመስላል። ለመሆኑ ይህቺ ሜዳ እነማንን አፍርታ ይሆን? መልሱ ዳዊት እና ጓደኞቹ ጋር አለ። አሰልጣኝ ንጉሴ ገብሬ አስረኛው የአፍሪካ ዋንጫና በ1974 በሊቢያ በተዘጋጀው 13ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ኢትዮጵያ እንድትሳተፍ ያስቻሉ ተጠቃሽ ተጫዋቾችን አገራችን አፍርታለች። ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ውለታ ከሰሩት ተጫዋቾች መካከልም መንግስቱ ወርቁ፣ ይድነቃቸው ተሰማ ߹ ንጉሴ ገብሬ በቀዳሚነት የሚጠሩ ናቸው። በእነዚህ ሁለት የመጨረሻዎቹ የኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ ከፍተኛ ሚና ከነበራቸው ውስጥ አንዱ የሆነው የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋችና በአሁን ሰዓት በፕሮጀክት አሰልጣኝነት እየሠራ የሚገኘው ንጉሴ ገብሬ በታሪካዊቷ «የቤሌር ሜዳ ላይ ኳስን ካንከባለሉት» ውስጥ የሚጠቀስ ነው። በ1948 ዓ.ም የተወለደው ንጉሴ ገብሬ በአዲስ አበባ ቀበና አካባቢ ተወልዶ አድጓል። ለንጉሴ ስኬት የቤሌር ሜዳ ትልቅ ትርጉም ነበራት። እርሱም «በልጅነቴ እንደ ማንኛውም ታዳጊ ሰፈር ውስጥ እግር ኳስ እጫወት ነበር፡፡ በትምህርት ቤት ቆይታዬም ኳስ ተጫውቻለሁ» በማለት ይናገራል። ታዲያ የልጅነት የእግር ኳስ ጨዋታው የሚጀምረው በዚችሁ ሜዳ ላይ ነበር። ንጉሴ ለዋናው ብሔራዊ ቡድን ከ1967 እስከ 1983 ዓ.ም ለ16 ዓመታት ያህል ተጫውቷል። ባዩ ሙሉ ሌላኛው በቤሌር ሜዳ ተጫወተው ለሰኬት ከበቁ ታዋቂ እግር ኳስ ተጫዋቾች ውስጥ ባዩ ሙሉ ተጠቃሽ ነው። በኢትዮጵያ እግር ኳስ አፍቃሪ ልብ ውስጥ ያለው ባዩ «የቤሌር ሜዳ» እድል ቀንቶት በታዋቂው የቅዱስ ጊዮርጊስ ታዳጊ ቡድን ለመጫወት በር ተከፍቶለታል። ባዩ የመጀመሪያውን የምሥራቅ አፍሪካ የታዳጊዎች ሻምፒዮና ለኢትዮጵያ ይዘው ከመጡ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ሲሆን የእርሱ ድርሻ ጉልህም ነበር። ከዚህም ሌላ ኬንያ ባዘጋጀችው «የሴካፋ ሻምፒዮና» ላይ ኮከብ ተጨዋች ሆኖ ለመመረጥም በቅቷል። የምሥራቅ አፍሪካ ውድድር ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአገር ውጪ በሩዋንዳ ዋንጫ ስታነሳ በፍፃሜው ጨዋታ ላይ የማሸነፊያዎቹን ሁለት ግቦች አስቆጥሯል። ባዩ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ሁለት ዓመት በዋናው ክለብ ተሰልፎ ተጫውቷል። የእግር ኳስ ህይወቱ ከማብቃቱም በፊት በቤልጂየም አገር ለረጅም ጊዜ ተጫውቷል። የቀበናዋ ቤሌር ሜዳም ካበቀለቻቸው የአገር ባለውለታዎች ተርታ አሰልፋዋለች። የቀድሞው ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ እና በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በአሁኑ ሰዓት ተሳትፎ የሚያደርገውን መቀሌ ከተማ በማሰልጠን ላይ የሚገኘው ዮሐንስ ሳህሌ በዚህች ታሪካዊ ሜዳ ላይ እግራቸውን አሟሽተዋል። ጌቱ ተሾመ «ድክሬ»፣ ጳውሎስ ማንጎ የመሳሰሉት በትንሿ ሜዳ ላይ ኳስን ሲያንሸራሽሩ ነበር። የወደፊት እንጀራቸውንም የወሰነችው ይህችው ሜዳ ነበረች። በቅርብ ጊዜም ይህቺ ታሪካዊ ሜዳ እንደ ቀድሞው ባይሆን እንኳን ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እና ለቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ የሚጫወተውን ናትናኤል ዘለቀን አፍርታለች። የቀድሞውን ታሪክ ለማስቀጠል የአስራ አምስት ሜዳና አካባቢው የጤና እግር ኳስ ማህበር የአካባቢያቸውን የቀድሞውን ስም ለማስቀጠል፤ ለአገሪቷ እግር ኳስ እድገት ጉልህ ሚና የሚኖራቸው ታዳጊዎችን ለማፍራት ቆርጠን ተነስተናል ይላሉ። ሜዳውን ደረጃውን በጠበቀ መንገድ አዘጋጅተው ከዚህ በኋላ ለሚተኩ ህፃናቶች ለማበርከት ፍላጎት አላቸው። የአካባቢያቸው ወረዳ ስፖርት ፅህፈት ቤትም በጉዳዩ ላይ ፈቃደኛ ሆኖ ሜዳውን እንዲጠቀሙበት አድርጓል። ነገር ግን የአራዳ ክፍለ ከተማ ትብብር አነስተኛ እንደሆነ ነው የማህበሩ አባላት የሚናገሩት። አንዴ «በስፖንሰር አድራጊ ድርጅቶች ሊሰራ ነው» ሌላ ጊዜ ደግሞ «መንግስት ራሱ በጀት ይዞ ደረጃውን በጠበቀ መንገድ ሊገነባው ነው» የሚሉ ምክንያቶች ማህበሩ አቅዶ ሊያከናውነው ያሰበውን ሰፊ ስራ እንዳያከናውን እንቅፋት እንደሆነባቸው ይናገራሉ። አቶ ሽመልስ ተስፋዬ በቀበና መድኃኒአለም አካባቢ ነው ተወልዶ ያደገው። እግር ኳስን እንደ ሙያ አድርጎ ባይዘውም ለረጅም ጊዜያት ተጫውቷል። ኳስን ያስተዋወቀው ይህ ሜዳ ነው። ከጊዜያት በኋላ ግን ሜዳው የቆሻሻ መጣያ መሆን ጀመረ። በሀላፊነት የሚያስተዳድረው አካል ባለመኖሩም ለዓመታት በዚያ ስፍራ ኳስን ማንከባለል ከሚሰጠው ጥቅም ይልቅ ይዞት የሚመጣው የጤና መዘዝ ከባድ ሆነ። እሁድ እሁድ ጤናውን ለመጠበቅ እግር ኳስን የሚያዘወትረው አቶ ሽመልስም ከአካባቢው ርቆ በካዛንቺስ «መብርቅ» በሚባል የጤና ቡድኑ ውስጥ ተካቶ መጫወት ጀመረ። ሆኖም ግን ሁሌም አንድ የሚቆጨው ነገር ነበር። እርሱ በሚኖርበት ሰፈር ለብዙሀን የእግር ኳስ ህይወት በር የከፈተው ሜዳ እያለ ካዛንቺስ ድረስ እየሄደ መጫወቱ ያሳዝነው ነበር። ሽመልስ ላይ ቁጭት የተፈጠረበት በሜዳው ላይ አለመጫወቱ ብቻ ሳይሆን አሁን ላይ ያሉት ወጣቶች የቀድሞዎቹን አንጋፋ ተጫዋቾች ፈለግ ተከትለው ውጤታማ የእግር ኳስ ህይወት እንዳይመሩ እና ለአገሪቷ የኳስ እድገት አበርክቶ እንዳይኖራቸው እንቅፋት ስለሆነ ብቻ ነው። ለአንድ ዓመት ያክል በካዛንችስ የመብረቅ የጤና እግር ኳስ ቡድን ውስጥ የተጫወተው ሽመልስ በተፈጠረበት ቁጭት ምክንያት ከቡድኑ መልቀቂያውን ወስዶ በአካባቢው ተመሳሳይ ቡድን ለመመስረት አሰበ። ከአብሮ አደጎቹ ጋር ተመካክሮም አሁን ያለውን ማህበር እውን አደረጉት። ከምንም ነገር በላይ ለእነ ሽመልስ እግር ኳስ እየተጫወቱ የራሳቸውን ጤና መጠበቅ ብቻ ሳይሆን አላማቸው ቀድሞ «የቤሌር ሜዳ» ወጣት ተጫዋቾችን በማፍራት የሚታወቅበትን ስም በድጋሚ መመለስም ጭምር መሆኑን ይናገራል። «የዚህ ሜዳ በአካባቢያችን መኖር ጠቀሜታው ከፍተኛ ነው» የሚለው ሽመልስ በዋናነት ሜዳው ለጤና ማህበሩ ከሚሰጠው ጠቀሜታ ይልቅ ታዳጊዎች በማፍራት እና በአገሪቷ እግር ኳስ ላይ ለውጥ ማምጣት ይችላል በማለት ይናገራል። በመሆኑን ማዘውተሪያ ስፍራውን ሁሉም የአካባቢው ህብረተሰብ እና መንግስት ትኩረት ሰጥቶት ሊጠብቀው ይገባል የሚል መልእክት አለው። ሚኪያስ አምባቸው ሌላኛው የስፖርት ማህበሩ አባል እና ምክትል ሊቀመንበር ነው። በቤሌር ሜዳ ላይ ከልጅነቱ ጀምሮ ከአብሮ አደጎቹ ጋር ይጫወት ነበር። እርሱ እግር ኳስ ከጨዋታም በላይ ነው ይላል። በአካባቢው ላይ የሚኖሩት ወጣቶች ብሎም ጎልማሳዎችን በአንድ ጥላ ስር በማሰባሰብ ማህበራዊ ህይወታቸው እንዲጠናከር የሚጫወተው ሚና ይህነው ተብሎ የሚገለፅ አይደለም ። «ማህበሩ ከተመሰረተ አንስቶ ባለን አቅም የተቸገረን እና የታመመን እንጠይቃለን» የሚለው ሚኪያስ ይህን ማድረግ የቻልነው ይህ ታሪካዊ ሜዳ እስካሁንም ድረስ በዚህ ስፍራ በመኖሩ ነው ይላል። ታዋቂ ተጫዋቾችን ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ከማበርከት ባለፈ ሜዳው ማህበራዊ ህይወትን በማጠናከር ያለው ፋይዳ ሊታወቅ ይገባል የሚል መልእክት አለው። በዚህ የተነሳ ማዘውተሪያ ስፍራውን የመጠበቅ እና ወደ ተሻለ ደረጃ የማሳደግ ሀላፊነቱ የሁሉም መሆን አለበት። የአስራ አምስት ሜዳና አካባቢው የጤና እግር ኳስ ማህበር በየወሩ አስፈላጊ ለሆኑ ጉዳዮች እንዲውል መዋጮ ያደርጋሉ። ድጋፍ አድራጊ አካላትን በማስተባበር ሜዳውን ለማሻሻል ይጥራሉ። በሳምንት ሶስት ቀን የልምምድ መርሀ ግብር ሲኖራቸው እሁድ እሁድ ደግሞ ከሌሎች ቡድኖች ጋር የአቋም መለኪያ ውድድር ያደርጋሉ። በቤሌር ሜዳ የማህበሩ አባላት ብቻ አይደለም ጨዋታ የሚያደርጉት። በፕሮጀክት ታቅፈው የሚሰሩ ታዳጊ ህፃናትም አሉ። ትርፍ ጊዜያቸውን ኳስ በመጫወት ማሳለፍ የሚፈልጉ የአካባቢው ነዋሪዎችም በዚሁ ሜዳ ላይ እንደየፈርጃቸው ይሳተፋሉ። ጨዋታውን ማየት የሚፈልጉ ሰዎችም በሜዳዋ ዙሪያ መመልከት አሁን አሁን እየተለመደ ነው። ለዘመናት ሳትሰስት እራሷን የሰጠችው ሜዳም ጥቁር ከነጭ፣ ትንሽ ከትልቅ ሳትል ሁሉንም ተቀብላ ታስተናግዳለች። እርሷ የባረከችው ደግሞ እንደ ንጉሴ ገብሬ እና ሌሎች አንጋፋ ተጫዋቾች ተባርኮ የህይወት መስመሩን ይዟል። አሰልጣኙ ምን ይላል ኤሊያስ ኢብራሂም ይባላል። በደደቢት እግር ኳስ ቡድን ውስጥ ምክትል አሰልጣኝ ነው። የአስራ አምስት ሜዳና አካባቢው የጤና እግር ኳስ ማህበር በበጎ ፍቃድ ያሰለጥናል። ለሶስት ዓመታት ያህል በቤሌር ሜዳ ቡድኑን ሲያሰለጥን ቆይቷል። በእድሜ ከእነርሱ ትንሹ ቢሆንም ባለው የማሰልጠን ክህሎት ሁሉም አባላቱን አስፈላጊውን ሳይንሳዊ የእግር ኳስ መርህ ያሰራቸዋል። እነርሱም ቢሆኑ በመልካም ስነ ምግባር ከኤሊያስ ጋር ልምምዳቸውን ያደርጋሉ። እንደ አሰልጣኙ አመለካከት «አካባቢው ላይ ተዳክሞ የነበረውን እግር ኳስ ለማንሳት» የዚህ ማህበር መመስረት ትልቅ ፋይዳ ነበረው። ጎልማሶች ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በዚህ ሜዳ ላይ ማድረጋቸው በቀዳሚነት የራሳቸውን ጤና እንዲጠብቁ እረድቷቸዋል የሚል አመለካከትም አለው። ከዚህ አንፃር ማህበራቸው ግቡን እያሳካ ነው። በሌላ መልኩ በመሰረታዊ ሁኔታ ታዳጊዎች ሞራል ሰንቀው በተሻለ ተስፋ እና ምቹ በሆነ ሜዳ እንዲጫወቱ ስብስቡ የበኩሉን አስተዋጽኦ አድርጓል። ኤሊያስ ለቡድኑ አባላት በሳምንት ሶስት ጊዜ ስልጠና ይሰጣል። በኮሚቴዎቹም ላይ በመሳተፍ ያለውን ሙያ ሳይሰስት ያካፍላል። ምክንያቱም ተጫውቶ ያደገባት ሜዳ ትወቅሰዋለችና። ከዚህም ሌላ ታሪካዊው ስም ወደ ቀድሞው ስፍራ ተመልሶ አሁንም ታዋቂ እና አንጋፋ ተጫዋቾች ከአካባቢው እንዲወጡ ይፈልጋል። ለዚህ ደግሞ ሙያዊ እገዛ ማድረጉ የውዴታ ግዴታው ይሆናል። ኤሊያስ የእግር ኳስን ክህሎት ያዳበረው እና ፍቅሩን ያገኘው አሁን በአሰልጣኝነት ከሚመራው የጤና ቡድን አባላቶች ነው። በሰፈር ውስጥ እነሱን እየተመለከተ ነው ያደገው። ከዚያ ባለፈ ግን አሁን ስብስቡን በመልካም ስነምግባር የታነፀ እግር ኳስን ለጤናና ለማህበራዊ ሀላፊነት ለመወጣት የሚጫወት አድርጎ የማሰልጠን ሀላፊነቱን ተቀብሏል። የእግር ኳስ እና የአሰልጣኝነት ክህሎቱ ደግሞ የጤና ማህበር ቁንጮ አሰልጣኝ ሆኖ እንዲመረጥ አድርጎታል። አሰልጣኙ ቡድኑ ከጤና አኳያ ምን አይነት ሳይንሳዊ የእግር ኳስ ልምምድ ማድረግ እንዳለበት ይወስናል። እነርሱም ይህንን ተከትለው ልምምዳቸውን ያደርጋሉ። በዚህ ረገድ አሰልጣኝ ኤሊያስ ስኬታማ እንደሆነ ይናገራል። «በሁለት ቡድን የተከፈሉት የማህበሩ አባላት እንዲያውም ክለቦች ከሚሰሩት ልምምድ በላይ ነው የሚሰሩት» በማለት ያላቸውን ተነሳሽነት ይመሰክራል። እርሱም አካላዊ ጤንነታቸው የተስተካከለ እንዲሆን ከማድረጉም ባለፈ የቡድን እና የአጋርነት መንፈስ እንዲኖራቸው እገዛ አድርጎላቸዋል። ኤሊያስ አብዛኛውን የልጅነት ጊዜውን በቤሌር ሜዳ እግር ኳስን በመጫወት እንዳሳለፈ ይናገራል። ወደኋላ መለስ ብሎ የልጅነት ጊዜውን ሲያስታውስ የማዘውተሪያ ስፍራው ለአካባቢው ወጣቶች በቃላት የማይገለፅ ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ነው በቅድሚያ በአዕምሮው ላይ የሚከሰትለት። ከዚያም በዘለለ «አሁን ላለሁበት ደረጃ ሜዳው የህይወቴ መሰረት ነው» በማለት እርሱ እና እግር ኳስ ሜዳው ያላቸውን ቁርኝት ይገልፃል። ለኤሊያስ ቤሌር ከእግር ኳስ ሜዳም ባለፈ እራሱ እግር ኳስ ምን እንደሆነ ያስተዋወቀው ነው። ስለዚህ ሁሌም ለዚህ ስፍራ የተለየ ክብር አለው። «ከመሰረታዊ የእግር ኳስ የታዳጊዎች ፕሮጀክት አንስቶ ክለብ እንድመሰረት የዚህ ታሪካዊ የማዘውተሪያ ስፍራ መኖር ጠቅሞኛል» በማለት ይገልፃል። የጤና ስፖርት ማህበሩ እና እርሱ በግል የጀመረው የታዳጊዎች ፕሮጀክት ቤሌርሜዳ እንዲሁ የቆሻሻ መጣያ ሜዳ ሆኖ እንዳይቀር ትልቅ ትግል አድርገዋል። ታሪካዊነቱን ጠብቆ እንዲቆይ ከማድረግም በዘለለ ታዳጊዎች በዚህ ስፍራ ውጤታማ ስፖርት ተጫዋች ሆነው እንዲያድጉ ይህን ማዘውተሪያ ስፍራ ወደ ተሻለ ደረጃ ማሳደጉ ተገቢ በመሆኑም ጭምር ነው።ኤሊያስ በእርሱ እድሜ በዚህ ስፍራ ከልጅነታቸው ጀምሮ እግር ኳስን በመጫወት ትልቅ ስፍራ ደርሰዋል∷ ለአገራቸውም ስፖርት አበርክቷቸው ሰፊ ነው∷ ያላቸውን እነ ጌቱ ተሾመ፣ ባዩ ሙሉ፣ ደብሮም ሀጎስ፣ መስፍን ደምሴ «ድክሬ» እና ቻይና አድማሱ የመሳሰሉ ሰዎች በድጋሚ በዚህኛው ትውልድ፤ በዚህች ታሪካዊ ሜዳ ላይ ማፍራት ይኖርብል ይላል። ለዚያም ነው በርካታ ታዳጊዎችን በፕሮጀክት አቅፈው በማሰልጠን ላይ የሚገኘው። ለልጆቹ መልካም ስነምግባር መቀረፅ ደግሞ «የጤና ቡድኑን» ራእይ እንዲከተሉ መንገዱን በመክፈት ላይ የሚገኘው። ኤሊያስ «ራእይ ታዳጊዎች የእግር ኳስ ፕሮጀክትን» ከ1996 ዓ.ም ጀምሮ አቋቁሞ በዚሁ ቤሌር ሜዳ ላይ እያሰለጠነ ቆይቷል። ሶስት ቡድኖችንም በተለያየ ዓመት በማሰልጠን ለተለያዩ የእግር ኳስ ክለቦች እንዲመለመሉ አስችሏል። ይህ ሜዳ ባይኖር አሁንም እነዚህን ወጣቶች ማብቃት አይቻልም ነበር የሚል አመለካከት አለው። የረጅም ዓመት እቅዶችን በማውጣትም እየሰራም ነው። ኤሊያስ የሚመራው የታዳጊዎች ፕሮጀክት እና «የአስራ አምስት ሜዳና አካባቢው የጤና እግር ኳስ ማህበር» በርካታ እንቅፋቶችን እንደሚያጋጥማቸው ያነሳሉ። ሆኖም የተነሱበትን አላማ ለማሳካት ካላቸው ፍላጎት እና ጉጉት አንፃር ለረጅም ዓመታት መፍትሄ ሲፈልጉላቸው እና ጎንበስ ብለው ሲያልፏቸው ነበር። ነገር ግን ይህን ችግር ይፈቱልናል ያሏቸው አካላት ድጋፍ ቢያደርጉላቸው መንገዳቸው ቀና ስለሚሆን ተባበሩን የሚል ጥሪ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ያስተላልፋሉ። በዚህም ታሪካዊውን ሜዳ ዘመናዊ ለማድረግ ብሎም የእግር ኳስ ማህበሩን እና ፕሮጀክቱን በገንዘብ አቅም ለመደገፍ የሚፈልጉ ባለሀብቶች እንዲሁም የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ግዴታቸውን መወጣት አለባቸው ይላሉ። ምክንያቱም «ሜዳው ሳር ብቻ ሳይሆን ሰውም ያበቅላልና»∷ አዲስ ዘመን ጳጉሜ 3/2011ዳግም ከበደ
https://www.press.et/Ama/?p=17501
2,055
2ስፖርት
የወላይታ ድቻ እና የደቡብ ፖሊስ ጨዋታ በዝግ ይካሄዳል
ስፖርት
April 25, 2019
26
አዲስ አበባ፡- በ21ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በደጋፊዎች መካከል በነበረው ግጭት ምክንያት ያልተካሄደው የወላይታ ድቻ እና የደቡብ ፖሊስ ጨዋታ በዝግ ሜዳ በአዲስ አበባ ስታዲየም ዛሬ ይካሄዳል። ክለቦቹ ሚያዝያ 12 ቀን 2011 ዓ.ም በሐዋሳ ስታዲየም ወላይታ ድቻና ደቡብ ፖሊስ በ21ኛ ሳምንት ጨዋታቸውን ማድረግ እንደነበረባቸው ተገልጾ፤ ከጨዋታው በፊት በሁለቱ ደጋፊዎች መካከል በተፈጠረው ግጭት ምክንያት ጨዋታው በማግስቱ 3፡00 ሰዓት እንዲካሄድ ተወስኖ እንደነበር አስታውሷል። የተፈጠረው ችግር ጨዋታውን ማካሄድ የሚያስችል ባለመሆኑ ጨዋታው ለሌላ ጊዜ ለማራዘም ምክንያት ሆኗል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሊግ ኮሚቴ ባሳለፈው ውሳኔ መሠረት በስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል ምክንያት ያልተካሄደው የወላይታ ድቻ እና የደቡብ ፖሊስ ጨዋታ በዛሬው ዕለት ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ይካሄዳል። ጨዋታው ያለምንም ደጋፊ በዝግ ስታዲየም የሚደረግ ይሆናል።በስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል እየተናጠ በሚገኘው በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በሃዋሳ ስታዲየም የሚደረገው የቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሐዋሳ ከተማ ሚያዝያ 22 ቀን 2011ዓ.ም በአሰላ ስታዲየም ለማካሄድ የፌዴሬሽኑ ሊግ ኮሚቴ ውሳኔ አስተላልፏል። የሃዋሳ ከነማ ጨዋታውን አዳማ ላይ ጨዋታውን ለማድረግ ጥያቄውን ቢያቀርብም ኮሚቴው የሀዋሳን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ በአሰላ ስታዲየም በደጋፊዎች ታጅቦ እንዲካሄድ መወሰኑን ይፋ አድርጓል:: የሀዋሳና ጊዮርጊስ ጨዋታ የዲሲፕሊን ስህተት የለበትም ስለዚህ በዝግ ይካሄድ ብለን መወሰን አንችልም ሀዋሳዎች የተፈጠረባቸው ፍርሐት ይገባናል የአሰላ ከተማ የጸጥታ ኃይል ሙሉ ዝግጅት በማድረግ ኃላፊነቱን በመውሰዱ ጨዋታው ለተመልካች ክፍት እንዲሆን ውሳኔ ማሳለፉን ኮሚቴው አስታውቋል:: በተመሳሳይ እንደ ቅዱስ ጊዮርጊስና ሃዋሳ ሁሉ በዚህ ሳምንት ሊካሄዱ የነበሩት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 22ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ወደ ቀጣይ ሳምንት ተላልፈዋል። በዚህ መሠረት በጅማ ስታዲየም ጅማ አባ ጅፋር ከሲዳማ ቡና፣ በሽረ ስታዲየም ስሑል ሽረ ከሐዋሳ ከተማ፣ በአዳማ አበበ በቂላ ስታዲየም አዳማ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና፣ በባህርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ባህርዳር ከተማ ከደቡብ ፖሊስ፣ በሶዶ ስታዲየም ወላይታ ድቻ ከመከላከያ፣ በአፄ ፋሲለደስ ስታዲየም ፋሲል ከነማ ከድሬዳዋ ከተማ እንዲሁም በመቐለ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከደደቢት ጋር ይጫወታሉ። ሁሉም የክልል ጨዋታዎች የሚካሄዱት በተመሳሳይ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት መሆኑም ታውቋል። የፕሪሚየር ሊጉን የደረጃ ሰንጠረዥ መቐለ ሰብዓ እንደርታ በ45 ነጥብ ሲመራ፣ ፋሲል ከነማ እና ሲዳማ ቡና በተመሳሳይ 37 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠው በቅደም ተከተል ሁለተኛና ሦስተኛ ደረጃን ይዘዋል። መከላከያ፣ ስሑል ሽረ እና ደደቢት ከ14ኛ እስከ 16ኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ ወራጅ ቀጣና ውስጥ ይገኛሉ። የፕሪሚየር ሊጉን ኮከብ ግብ አግቢነት የመቐለ ሰብዓ እንደርታው አማኑኤል ገብረሚካኤል በ13 ግቦች ሲመራ፣ የሲዳማ ቡናው አዲስ ግደይ በ12 የመከላከያው ምንይሉ ወንድሙ በ11 ግቦች ይከተላሉ።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 17/2011በዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=9548
341
2ስፖርት
አራተኛው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በአዲስ አበባ
ስፖርት
September 9, 2019
30
 የዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት ጥናት እንደሚያሳየው ከሆነ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማከናወን የሚያስከትለው የጤና ጉዳት በገዳይነታቸው ቅድሚያ የተሰጣቸውን በሽታዎች ተከትሎ በአራተኛ ደረጃ ላይ ይቀመጣል። በዓለም ላይ ለሚከሰተው ሞትም ስድስት ከመቶ ሚና ያለው ነው። ይህም አካላዊ እንቅስቃሴዎችን ብቻ በማድረግ ጤናን መጠበቅ እንዲሁም እድሜንም ማራዘም እንደሚቻል ያመላክታል። በዚህ ወቅት ከዘመናዊ አኗኗር እና ከከተሞች መስፋፋት ጋር በተያያዘ ሰዎች በተለይ ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች እንዲሁም ከመጠን በላይ ለሆነ ውፍረት ይጋለጣሉ። የዚህ መንስኤ እንቅስቃሴ አለማድረግ ሲሆን፤ መፍትሄው ደግሞ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ መሆኑን ባለሙያዎች ይናገራሉ። ባደጉት አገራትም ይህ ዓይነቱ ችግር ከመስፋፋቱ ጋር በተያያዘ መንግሥታት ዜጎቻቸው የተለያዩ አካላዊ እንቅስቃሴዎችን እንዲያደርጉ ያበረታታሉ። ኢትዮጵያም እንቅስቃሴውን በቅርቡ የጀመረች አገር ብትሆንም በፍጥነት እያደገና በርካቶችን እያሳተፈ ይገኛል። ወርሃዊ መርሐ ግብሮችን በማዘጋጀትም በአገርና ከተማ አቀፍ ደረጃ መንገዶችን ከትራፊክ እንቅስቃሴ ነጻ በማድረግ ህብረተሰቡ አካላዊ እንቅስቃሴ እንዲያደርግ እየተሰራ ነው። በ1990ዓ.ም የተቀረጸው የኢትዮጵያ ስፖርት ፖሊሲ ህብረተሰቡ አካላዊ ጤንነቱን ለመጠበቅ በሚኖርበት፣ በሚሰራበት እና በሚማርበት አካባቢ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን የማድረግ መብት እንዳለው ይጠቅሳል። ይህንን ለማጠናከርና የአካል እና የአእምሮ ጤናው የተጠበቀ ዜጋ ለማፍራትና ህብረተሰቡን ተሳታፊና ተጠቃሚ ለማድረግ እንቅስቃሴዎች በመከናወን ላይ እንደሚገኝም ማስተዋል ይቻላል። አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ህብረተሰብ አቀፍ ስፖርታዊ እንቅስቃሴውን አጠንክረው ከያዙት ከተሞች መካከል ቀዳሚው ነው። የከተማዋ ነዋሪዎች በስፖርታዊ ክንዋኔዎች በመሳተፍ ጤናቸውን እንዲጠብቁ፣ ታዳጊ ወጣቶች ከዚህ እንቅስቃሴ በመነሳት ለስፖርቱ ፍላጎት እንዲኖራቸውና ተተኪ ስፖርተኞች መሆን እንዲችሉ እንዲሁም የተለያዩ መልዕክቶችን ማስተላለፍ ደግሞ የዚህ እንቅስቃሴ ዋነኛ ዓላማ ነው። በአዲስ አበባም የተጀመረው ወርሃዊ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ከተጀመሩ እነሆ አራት ወራት ተቆጥረዋል። በመጀመሪያው ዙር ህብረተሰብ አቀፍ እንቅስቃሴ ላይም 21ሺ ሰው የተሳተፈ ሲሆን፤ በሁለተኛው 35ሺ እንዲሁም በሶስተኛው ዙር 55ሺ ነዋሪዎች ተካፍለዋል። ትናንት በተካሄደው አራተኛው መርሐ ግብር ላይም እንቅስቃሴው ከብሄራዊ የኩራት ቀን ጋር ተያይዞ ተከናውኗል። በመስቀል አደባባይ ከንጋቱ 12ሰዓት ጀምሮ በተካሄደው እንቅስቃሴ ላይም ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች መሳተፋቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን አስታውቋል። በመርሐ ግብሩ ላይም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ፣ የአስተዳደሩ ስፖርት ኮሚሽነር አቶ ዮናስ አረጋይ፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ፣ የፌዴራልና የከተማዋ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የአገር መከላከያ፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት፣ በተለያዩ ስፖርት ማህበራት የሚንቀሳቀሱ ስፖርተኞች እንዲሁም የከተማዋ ክለብ ደጋፊዎች ተገኝተዋል። «የአካል ብቃት እንቅስቃሴያችን ለሁለንተናዊ ጤናችን» በሚል መሪ ቃል በተካሄደው እንቅስቃሴ ላይም የአካል ብቃት እንቅስቃሴው እንዴት መከወን እንዳለበት በባለሙያዎች እገዛ ተደርጓል። ይህ የስፖርት ፖሊሲውን የሚደግፍ ተግባርም ቀጣይነት ያለው መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውቋል። በቀጣዩ አዲስ ዓመትም ከወርሐዊው ከተማ አቀፍ መርሐ ግብር ባሻገር፤ በየሳምንቱ በየክፍለ ከተማውና ወረዳዎች እንዲከወን የማድረግ ዕቅድ ይዟል።  አዲስ ዘመን ጳጉሜ 4/2011 ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=17535
371
2ስፖርት
የአበበ ቢቂላ ስታዲየም እድሳት በቅርቡ ይጠናቀቃል
ስፖርት
September 16, 2019
74
በእግር ኳስ ሶስት የአፍሪካ ዋንጫዎችን፣ አራት ሴካፋ፣ የአፍሪካ ከ21 ዓመት በታች ሻምፒዮና፣ በርካታ ኢንተርናሽናል የማጣሪያ እንዲሁም የክለብ ጨዋታዎችን አስተናግደዋል። አህጉር አቀፉን እንዲሁም የታዳጊዎች የአትሌቲክስ ሻምፒዮናም በዚሁ ስታዲየም ተከናውነዋል። ይህ በርካታ አህጉር አቀፍ ውድድሮችን እንዲሁም ሃገር አቀፍ ሁነቶችን ሲያስተናግድ የኖረው አንጋፋው የአዲስ አበባ ስታዲየም አሁን ግን ዘመኑን ከማይመጥንበት ደረጃ ደርሷል። እንደሚታወቀው ከተማዋ ዓለም ዓቀፍ ሁነቶችን ለማስተናገድ ተመራጭ ናት። ከእነዚህ ሁነቶች መካከል አንዱ ስፖርት እንደመሆኑ፤ አህጉርና ዓለም ዓቀፍ ውድድሮች በተለይም ለእግር ኳስና አትሌቲክስ ውድድሮች ከአዲስ አበባ ስታዲየም ውጪ አማራጭ ሳያገኙ ቆይተዋል። በዚህ ወቅት ግን የኢትዮጵያ ዋና ከተማ እና የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ የሆነችው አዲስ አበባ ከተማ ስሟን የሚመጥን ስታዲየም የላትም በሚል ትታማለች። የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽንም (ካፍ) «ከደረጃ በታች» ሲል መፈረጁም በዚሁ ምክንያት ነው። ከአዲስ አበባ ስታዲየም በተጓዳኝ በከተማዋ በሚካሄዱ ስፖርታዊ ሁነቶች አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው የአበበ ቢቂላ ስታዲየምም ለሁለት ዓመታት እገዛውን አቋርጦ ቆይቷል። በታላቁ ኢትዮጵያዊ አትሌት አበበ ቢቂላ የተሰየመው ስታዲየሙ በ1995 ዓ.ም ነበር ተገንብቶ ወደ ስራ የገባው። ይሁን እንጂ ስታዲየሙ ደረጃውን ያልጠበቀ በመሆኑ ምክንያት እንደሚጠበቀው ዘርፈ ብዙ አገልግሎት መስጠት አልቻለም። ስታዲየሙ 30ሺ ሰው ይይዛል ቢባልለትም፤ ከትሪቡኑ ውጪ ያለው ስፍራ ከኮንክሪት የተሰራ ከመሆኑ በዘለለ ወንበር አልነበረውም። በትሪቡኑ የሚገኘው ጣራና ወንበርም ቢሆን ከአገልግሎት ብዛት ምቹ የሚባል አልነበረም። የእግር ኳስ መጫወቻ ሜዳው ከፊፋ በተገኘ ድጋፍ ሰው ሰራሽ ሳር የለበሰ ቢሆንም በዙሪያው የሚገኘው ኮሮኮንች በመሆኑ፤ በአጋጣሚ ከሜዳ ወጥቶ የወደቀ ተጫዋች ላይ ጉዳት ያስከትል ነበር። በተለይ የስታዲየሙ መም አልባነት በከተማ አስተዳደሩ ለሚገኙ የአትሌቲክስ ክለቦች መለማመጃም ሆነ በፌዴሬሽኑ አዘጋጅነት ለሚካሄዱ ውድድሮች ፈተና በመሆኑ፤ በአዲስ አበባ ስታዲየም ለመስራት ይገደዱ ነበር። ከተማ አስተዳደሩ ለስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች በሰጠው ትኩረት መሰረትም ስታዲየሙ ሙሉ እድሳት ሊደረግለት ችሏል። በእድሳቱ ምክንያት ያለፉትን ሁለት ዓመታት የቆየው ስታዲየሙ አሁን አብዛኛው ስራው በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል። በተያዘው አዲስ ዓመት የውድድር ዘመን እስከሚጀመርበት ጊዜም ሙሉ ለሙሉ ስራው ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆንም ይጠበቃል። በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በዚህ ወቅት ደረጃውን የጠበቀ የመሮጫ መም እንዲሁም የተመልካቾች መቀመጫ ሙሉ ለሙሉ ተገንብቶ ተጠናቋል። ዋናውና የስራውን ከፍተኛ ድርሻ የሚይዘው የዙሪያ ጣራ ማልበስ ስራውም አብዛኛው ተጠናቆ ጥቂት ቋሚዎች ብቻ ናቸው የሚቀሩት። ከዚህ በኋላም ጣራውን የሚሸከሙትን ቋሚዎች ተመልካቾች እንዳይወጡባቸው የመሸፈን ስራ ብቻ ይቀራል። ከዚህ በኋላም ዙሪያውን ያሉት ሱቆች ጥቂት የማጥራት ስራ ብቻ ሲቀራቸው፤ የውሃ ታንከር ማቆሚያ፣ የኤሌክትሪክ ስራዎች፣ የስክሪን ገጠማ እንዲሁም የማጽዳት ስራዎች ብቻ የሚሰሩ መሆኑን የአበበ ቢቂላ ትምህርት እና ስልጠና ማዕከል ስራ አስኪያጅ አቶ ብርሃኑ ባዩ ይጠቁማሉ። እነዚህ ቀሪ ስራዎችም በቅርቡ የሚጠናቀቁ ሲሆን፤ በሶስት ወራት ጊዜ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ መደበኛ አገልግሎቱን እንደሚሰጥ በከተማው ስፖርት ኮሚሽን ታቅዷል። ፕሮጀክቱ በአጠቃላይ የግንባታ ሂደቱ 105ሚሊዮን ብር የፈጀ ሲሆን፤ በውለታው መሰረት ለተቋራጩ የሚከፈለው 60 በመቶ በብር እንዲሁም 40 በዶላር ነው። ነገር ግን እስካሁን ክፍያው ተጠቃሎ ለተቋራጩ አልተሰጠም፤ ለዚህም ምክንያት የሆነው እንደ ሃገር ያለው የምንዛሬ እጥረት ነው። ይህንንም ለሚመለከተው አካል በማሳወቅ ምላሽ በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኙ ስራአስኪያጁ ጠቁመዋል። የስታዲየሙ እድሳት ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ ለከተማዋ ተጨማሪ ብስራት እንደሚሆን ይጠበቃል። ከዚህ ባሻገር በከተማ ደረጃ ያለውን የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እጥረት እንደሚቀርፍ ይታመናል። የከተማዋ የፕሪምየር ሊግ ክለቦችስ ጨዋታዎችን ያስተናግዱባቸው ይሆን በሚል ለተነሳው ጥያቄ ስራ አስኪያጁ፤ ማዕከሉ የትምህርትና ስልጠና ማዕከል እንደመሆኑ ታዳጊ ወጣቶችን ለማፍራት የሚውል መሆኑን በምላሻቸው ጠቁመዋል። እንደሚታወቀው በሃገር አቀፍ ደረጃ በሚካሄዱ የአትሌቲክስ ውድድሮች ላይ ከተማ አስተዳደሩ የሚያስመዘግበው ውጤት እየቀነሰ መምጣቱ ይታወቃል። በተለይ በአትሌቲስ ስፖርት በርካታ ክለቦች በከተማዋ ቢገኙም አትሌቶች ሲቸገሩና ለአደጋም ሲጋለጡ ቆይተዋል። ይህ የሆነበት ምክንያትም በከተማዋ ለስልጠና የሚሆን ስፍራ ባለመኖሩ ነው። በመሆኑም የስታዲየሙ መታደስ ፍላጎቱና ችሎታው ያላቸውን ታዳጊዎች ለማፍራት እንደሚያስችልም ያክላሉ ስራ አስኪያጁ። በተመሳሳይ የእግር ኳስ ሜዳው እንዲሁም የሶስት በአንድ(እጅ ኳስ፣ መረብ ኳስ እና ቮሊቦል) ሜዳውም ታዳጊዎች በኳስ ስፖርቶች ተተኪ ለመሆን የሚያስችላቸውን ስልጠና የሚያገኙበት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። በቀጣይም የእግር ኳስ ሜዳውን እንዲሁም ስታዲየሙ በሃገሪቷ አሰራር መሰረት ደረጃው እንዲለይም ለሚመለከተው አካል እንደሚያሳውቁም ስራ አስኪያጁ ያመላክታሉ። ከዚህ ባሻገር የአካባቢውን ህብረተሰብ በማሳተፍና ተጠቃሚ በማድረግ የራሱን ገቢ ማመንጨት እንዲችልም ይደረጋል። በዚህም በዓመት ከ20ሚሊዮን ብር በላይ ለምክር ቤቱ ለማስገባት ታቅዷል፤ ይህ ብርም በየአካባቢው ላሉ ታዳጊዎች ድጋፍ የሚውልም ይሆናል። በእድሳት ስራው ላይ በስታዲየሙ የሱቅ ተከራዮች በቶሎ አለመልቀቅ፣ የውጪ ምንዛሬ እጥረት እንዲሁም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባለሙያዎች የተሳተፉበት የጣራ ናሙና መረጣ ላይ ጥቂት መዘግየቶች ገጥመዋል። ሌላው የስታዲየሙ እድሳት ለከተማዋ ነዋሪዎች የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ዘርፈ ብዙ መሆኑ ባያጠያይቅም የአካባቢው ለተጠቃሚዎች ምቹ መሆን አጠራጣሪ ነው። በተለይ ወደ ስታዲየሙ የሚወስዱት መንገዶች በእጅጉ መጎዳት እንዲሁም ለመኪና ማቆሚያ የሚሆን ምቹ ቦታ አለመኖር በችግርነት ተጠቃሽ ነው። ይህንን ጉዳይም ኮሚሽኑ ከዓመታት በፊት ለአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ቢያሳውቅም እስካሁን ለውጥ አለመኖሩን የማዕከሉ ስራ አስኪያጅ ያመለክታሉ። ከዋና መንገዱ ጋር የሚገናኘው እንዲሁም ሌሎች ወደ ስታዲየሙ የሚያደርሱ መጋቢ መንገዶች ጥናትና ይደረግባቸው በሚልና በሌሎች ምክንያቶች መዘግየቶች ቢኖሩም ኮሚሽኑ ጥያቄውን አላቋረጠም። በመጨረሻም በስታዲየሙ እድሳት ወቅት የአካባቢው ነዋሪ ላደረገው ከፍተኛ ድጋፍ ስራ አስኪያጁ ምስጋና አቅርበዋል።አዲስ ዘመን መስከረም 5/2012ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=18114
690
2ስፖርት
እግር ኳስ ላይ ተፅዕኖ ያሳረፈ ፍልስፍናዎች
ስፖርት
April 16, 2019
59
የዘመናዊው እግር ኳስ ፍልሙያ በጠለቀ የታክቲክ እውቀትና የበላይነት ላይ ይመሰረታል።ማሰልጠን የራሱ ፍልስፍና አለው:: አዲስ አጨዋወት እና ታክቲክ ፈጥሮ፣ቡድንን አስተባብሮ ለውጤት ማብቃት ግዴታ አለበት። የአሰልጣኞች የሜዳ ላይ አጨዋወት ቀመር የሽንፈትም የአሸናፊነትም መሰረት ነው። አሰልጣኞች በአንድ ክለብ በሚኖራቸው ቆይታም ውጤታማ ለመሆን ያስችለናል የሚሉት የአጨዋወት ፍልስፍና፣ስልትና ቀመር አላቸው።በዘመናዊ እግር ኳስ የዓመታት ቆይታም በርካታ የአጨዋወት ፍልስፍናዎች ተዋውቀዋል።ከእነዚህ መካከልም ሶስቱ የስፖርቱን አቅጣጫ ስለመለወጣቸው ይታመናል። በዓለም እግር ኳስ ላይ ተፅዕኖ ካሳረፉት ፍልስፍናዎች አንደኛው ካቴናቺዮ ነው። ካቴናቺዮ በጥብቅ የመከላከል ስርዓት የተዋቀረ፤በዋነኝነትም መከላከልን መሰረቱን ያደረገ ፍልስፍና ነው።የመከላከል ክፍሉን ጥብቅ ማድረግና የተጋጣሚ ቡድን ተጫዋችን መፈናፈኛ ማሳጣት ቀዳሚ ምርጫው ነው።ተቃራኒ ቡድን ግብ ማስቆጠር ካልቻለ ጨዋታውን ማሸነፍ አይችልም የሚል አቋም አለው።በጣም የተጣበበ የመከላከልና ተቃራኒ ተጫዋቾችን በጥብቅ መቆጣጠርን ምርጫው ያደርጋል። በዚህ ፍልስፍና የተቃራኒ ቡድንን የማጥቃት እንቅስቃሴ ማጨናገፍ ዋነኛ የሜዳ ላይ ክዋኔ ነው።የታክቲክ ፍልስፍናው መከላከል ላይ ሰፊ ጉልበቱን የሚያባክን ቢሆንም፤ግብ ማስቆጠርን የዘነጋም አይደለም። በተለይ በመልሶ ማጥቃት እንቅስቃሴ እጅግ አደገኛ ነው። ካቴናቺዮን ለመጀመሪያ ጊዜ የተገበረው ኦስትሪያ ዊው አሰልጣኝ ካርል ራፓን ነው።እ.ኤ.አ በ1930ዎቹ የተዋወቀው ይህ ፍልስፍና በአርጀንቲናዊው አሰልጣኝ ሄሌንዮ ሄሬራ ይበልጥ ጎልብቷል።በተለይ 1960ዎቹ ኢንተር ሚላን ለበርካታ ድሎች የበቃው በእኚሁ አሰልጣኝ ፍልስፍና ታግዞ ነው።ይህ የኢንተር ሚላን ስኬት ለበርካታ የጣልያን ክለቦችም ሆነ ለብሄራዊ ቡድኑ ምሳሌ መሆን ችሏል።በተለይ በ1960ዎቹ የጣሊያን ብሄራዊ ቡድን መገለጫ ሆኖ ታይቷል።እ.ኤ.አ በ1980ዎቹ ቶታል ፉትቦልን የመሳሰሉ አዳዲስና ለየት ያሉ የማጥቃት ፍልስፍናዎች ብቅ ማለታቸውን ተከትሎ የካቴናቺዎ ፍልስፍና ተግባሪ ወደ ማጣት ተሸጋግሯል። ሌላኛው ቶታል ፉትቦል ነው።በቶታል ፉትቦል የአጨዋወት ፍልስፍና ተጫዋቾች በአንድ የሜዳ ክፍል ውስጥ እንዲንቀሳቀስና የተወሰነ ተግባር ብቻ እንዲከውን አይፈቀድለትም።እየተተካ ከአንድ በላይ በሆነ የጨዋታ ምልልሳዊ ሂደት ውስጥ ተሳትፎ ማድረጉ የግድ ነው። ለአንድ ተጫዋች የተሰጠ ቦታ አይኖርም።ተጫዋቹ አንድ ቦታ ላይ ብቻ በቋሚነት አይጫወትም። በማጥቃት፤ በመሃል ሜዳ መጫወት አለያም የተከላካይ ክፍሎን ማገዝ ግድ ይለዋል። በዚህ ፍልስፍና ከተወሰነለት ቦታ ውጪ ተንቀሳቅሶ መጫወት የሚችለው ግብ ጠባቂው ብቻ ነው።ፈጣንና ሁለገብ ተጫዋች የሚቀመርና በፍጥነት ቦታ መቀየርና መተካካትን የሚጠይቅ ነው።ተጫዋቹ ቦታውን ለቆ ሲንቀሳቀስ በፍጥነት በሌላ ተጫዋች ይተካል። የፍልስፍና ግኝቱ እ.ኤ.አ 1950ዎቹ ነው።በ1970ዎቹ በሆላንዱ አያክስ አምስተርዳም ክለብ ይበልጡኑ ዝነኛ ለመሆን የቻለ ሲሆን፤ክለቡ በዚህ ፍልስፍና ያሳየው የነበረው የኳስ ጥበብ እስካሁን ድረስ የውብ ጨዋታ መለያ መስፈርት እንደሆነ ዘልቋል። ከተጫዋችነቱ በተጨማሪ በአሰልጣኝነቱ ትልልቅ ውጤቶችን ማስመዝገብ የቻለው ሁዋን ክራይፍ፣ ለዓለም እግር ኳስ ያበረከተው ‹‹ቶታል ፉትቦል ›› የሚሰኘው ይህ የአጨዋወት ፍልስፍና አሁንም ድረስ ከፍተኛ ተቀባይነት ያለውና በሆላንድ ፣ በአያክስ አምስተርዳም ፣ በባርሴሎናና በሌሎች በርካታ ታላላቅ የአውሮፓ ክለቦች የሚተገበር ነው ፡፡ በአሁኑ ወቅትም በርካቶች የፍልስፍናው አቀንቃኝ ሆነዋል። በቶታል ፉትቦል የአጨዋወት ፍልስፍና ተፅዕኖ ስር ከወደቁ ዝነኛ አሰልጣኞችና ተጫዋቾች መካከል ፍራንክ ራይካርድ፣ ፔፕ ጋርድዮላ፣ ሚሼል ላውድሩፕ፣ አርሴን ቬንገር፣ ኤሪክ ካንቶናና መጥቀስ ይቻላል። ቲኪታካ በዓለም እግር ኳስ ላይ ተፅዕኖ ካሳደሩ ፍልስፍናዎች በዋነኝነት የሚጠቀስ ነው።በርካቶች ፍልስፍናውን የእግር ኳስ ውበት መለኪያ ምሳሌ ስለመሆኑ ያምናሉ።በስፖርቱ ከጉልበትና ፍጥነት ባሻገር ሌሎች የላቁ ቴክኒኮች መኖራቸውን አስተዋውቋል። በአጭርና፤ተጠጋግቶ በመቀባበል የተቀመረ የአጨዋወት ፍልስፍና ነው። ፍልስፍናውም ኳስን በተለያዩ የሜዳ ክልሎች መቆጣጠርን በመሃል ሜዳው ላይ የሚጫወቱ ተጫዋቾችን በማበርከት ይተገብራል።ግብ ጠባቂን የጨዋታው አካል ማድረግ፣ተቀራርቦ በመጫወት የተጋጣሚ ተጫዋችን እየቀነሱ መሔድ፣ከባላጋራ ተጫዋች የሚኖር ትግልን መቀነስ ምርጫው ነው። ፍልስፍናው ከዓለም የተዋወቀው በዋነኝነት እ.ኤ.አ በ1980ዎቹ መጨረሻና በ1990ዎቹ መጀመሪያ ነው።በወቅቱ ባርሴሎናን በአሰልጣኝነት ይመራ የነበረው ሆላንዳዊው ሁዋን ክራይፍ ፈጣሪው ስለመሆኑ ይታመናል። ፍልስፍናው በአሰልጣኝ ሊዊስ ቫንሃልና፤ፍራንክ ሪያካርድ ዘመን ኑካምፕ ላይ የተተገበረ ቢሆንም በተለይ እ.ኤ.አ ከ2008 እስከ 2012 በቀድሞው የባርሴሎና በወቅቱ የማንቸስተር ሲቱ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ይበልጡን ደምቆ ታይቶበታል። ፔድሮ፤ ሻቪ፤ አንድሬስ ኢኒይስታ ሴስክ ፋብሪጋስ እንዲሆን ሊዮኔል እንድሬስ ሜሲ የታክቲኮ ልህቀታቸው ጎልቶ ከታየባቸው ተጫዋቾች ቀዳሚዎቹ ናቸው።ክለቡ እ.ኤ.አ 2009 በቲኪ ታካ ጨዋታን ከላቀ ድል ጋር ማጣጣም የቻለ ሲሆን በአንድ ዓመት ውስጥ ላሊጋ፤ኮፓ ዴል ሬይ፤ሻምፒዮንስ ሊግ ስፓኒሽ ሱፐር ካፕ፤ሱፐር ካፕ እና የዓለም የክለቦች ዋንጫን ማንሳት ችሏል። ቪሴንቴ ዴልቮስኬም ፍልስፍናው ወደ ስፔን ብሄራዊ ቡድን በመውሰድ በተለይ እ.ኤ.አ 2010ደቡብ አፍሪካ ባስተናገደችው 19ኛው ዓለም ዋንጫ ኳስን ተቆጣጥሮ አጫጭር ቅብብሎች የሚተገበረው ቲኪ ታካ አጨዋወት ውጤታማ ሆነውበታል። ከዚህ የዓለም ዋንጫ ድል በፊት እና በኋላ የስፔን ቲኪ ታካ ለ6 ዓመታት የዓለምን እግር ኳስ ተቆጣጥሮ ቆይቷል፡፡በ20ኛው ዓለም ዋንጫው የሻምፒዮናነት ክብርን በሁለት ተከታታይ የዓለም ዋንጫዎች የማለፍ ክብረወሰን ለማስመዝገብ የቀረበችው ስፔን በቲኪ ታካው አጨዋወት አልሆነላትም፡፡በአሁኑ ወቅት ፈጣን የመልሶ ማጥቃት አጨዋወት ተመራጭ መሆን የቲኪታካን ተፅዕኖ አዳክሞታል።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 8/2011በ
https://www.press.et/Ama/?p=9006
604
2ስፖርት
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በቦስተን ማራቶን ድል ቀናቸው
ስፖርት
April 17, 2019
24
የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር (አይኤኤፍ)፣ በወርቅ ደረጃ ከሚመድባቸው ታላላቅ የማራቶን ውድድሮች አንዱ በሆነውና በትናንትናው እለት ለ123ኛ ጊዜ በተካሄደው የቦስተን ማራቶን አራት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል፡፡ በሴቶች የተሳተፈችው አትሌት ወርቅነሽ ደገፋ ሁለት ሰዓት ከ23 ደቂቃ ከ31 ሰከንድ በመግባት ውድድሩን ማሸነፍ ችላለች። አትሌት ወርቅነሽ ውድድሩ ከተጀመረ ከአምስት ኪሎ ሜትር በኋላ ሌሎቹን ተወዳዳሪዎች ቀድማ በመውጣት ብቻዋን እየመራች ማሸነፏም ተነግሯል። ኬንያዊቷ አትሌት ኤድና ኪፕላጋት ደግሞ ሁለት ሰዓት ከ24 ደቂቃ ከ13 ሰከንድ በመግባት ሁለተኛ ደረጃን ይዛ ስታጠናቅቅ፤ አሜሪካዊቷ ጆርዳን ሀሳይ ሁለት ሰዓት ከ25 ደቂቃ ከ20 ሰከንድ በመግባት ሦስተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቅቃለች። በውድድሩ ላይ የተሳተፈችው ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት መስከረም አሰፋ በበኩሏ ሁለት ሰዓት ከ25 ደቂቃ ከ40 ሰከንድ በመግባት አራተኛ ደረጃን አግኝታለች። በወንዶቹ ምድብ ደግሞ ኬንያዊው ላውሬንስ ቼሮን የቦስተን ማራቶንን ሁለት ጊዜ ያሸነፈውን ባለድሉን ሌሊሳ ዴሲሳን በመቅደም አሸናፊ ሆኗል። ላውረንስ ቼሮኖ አሸናፊ ሆኖ የገባበት ሰዓት ሁለት ሰዓት ከሰባት ደቂቃ ከ57 ሰከንድ ነው። ኢትዮጵያዊው አትሌት ሌሊሳ ዴሲሳ በሁለት ሰከንዶች ብቻ ዘግይቶ፣ ሁለት ሰዓት ከሰባት ደቂቃ ከ59 ሰከንድ በመግባት ሁለተኛ ደረጃን ሲይዝ፤ ሌላኛው ኬንያዊው አትሌት ካኔት ኪፔሞይ ሁለት ሰዓት ከስምንት ደቂቃ ከሰባት ሰከንድ በመግባት 3ኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቅ ችሏል። አትሌት ሌሊሳ ከውድድሩ ቀደም ብሎ የማሸነፍ ግምትን ቢያገኝም የላውሬንስ ቼሮን ብርቱ እግሮችን ቀድሞ ባለድል መሆን ሳይችል ቀርቷል። ሌሊሳ እ.አ.አ በ2013 እና በ2015 የውድድሩ አሸናፊ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ሌሊሳ በ2013 የተሸለመውን ሜዳሊያ በዕለቱ ለተፈፀመው የቦምብ ጥቃት ሰለባዎች መስጠቱም የሚታወስ ነው። በሁለቱም ፆታዎች የውድድሩ አሸናፊዎች ዋንጫና 150 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ሽልማት ወስደዋል። ሁለተኛና ሦስተኛ የወጡት ደግሞ የብርና የነሀስ ሜዳልያ እና የ75 ሺህ እና የ40 ሺህ ዶላር (እንደቅደም ተከተላቸው) ተሸልመዋል። የቦስተን ማራቶን ወድድር መካሄድ የጀመረው እ.ኤ.አ በ1897 ነው፡፡ እስካሁን ድረስ በተካሄዱት ውድድሮች ኢትዮጵያዊቷ ብዙነሽ ዳባ በ2014 ውድድሩን በሁለት ሰዓት ከ19 ደቂቃ ከ59 ሰከንድ በማጠናቀቅ የቦታውን ክብረወሰን ማስመዝገብ የቻለች ሲሆን በወንዶች ደግሞ ኬንያዊው ጂኦ ሙቲ እ.አ.አ በ2011 የገባበት የሁለት ሰዓት ከሦስት ደቂቃ ከሁለት ሰከንድ የውድድሩ ክብረ ወሰን ሆኖ ተመዝግቧል።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 9/2011በ
https://www.press.et/Ama/?p=9065
288
2ስፖርት
ከኢትዮጵያ እጅ ያመለጠው ቻን በካሜሩን ቤት
ስፖርት
April 17, 2019
26
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በአገር ውስጥ ሊጎች የሚጫወቱ ተጫዋቾች ብቻ የሚሳተፉበትን የአፍሪካ አገራት ሻምፒዮን ሺፕ / ቻን/ እኤአ በ2020 ለማስተናገድ ከካፍ ኃላፊነቱን ከተረከበ ዓመታት ተቆጥረዋል። ለዚህም ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ በርካታ ስታዲየሞች በሀገሪቱ መገንባታቸው ተቀባይነትን ለማግኘት ዋና ምክንያት ሆኖ ተመዝግቧል። የካፍ ፕሬዚዳንት ማዳጋስካራዊው አህመድ አህመድ ወደ ተመረጡባት ኢትዮጵያ ብቅ ባሉበት ወቅት፤ አገሪቱ በስፖርት መሰረተ ልማት በተለይም ለእግር ኳሱ ዕድገት ከፍተኛ ወጪ መድባ የምታከናውናቸውን የተለያዩ ተግባራት አድንቀዋል። ኢትዮጵያ አህጉራዊ ውድድሮችን የማዘጋጀት ፍላጎቷንም በስኬት የማድመቅ ተስፋ እንዳላት ጭምር ምስክርነት ሰጥተዋል። ኢትዮጵያ፤ ለቻን አዘጋጅነት ከመታጨቷም በላይ እያደረገች ያለውን ዝግጅት አስመልክቶ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጪ መገናኛ ብዙሀን ሰፊ ዘገባዎች ሲሰራጩ ቆይተዋል። የኋላ ኋላ ግን እየተሰሩ ያሉት ስራዎች ውድድሩን ኢትዮጵያ በብቃት ስለማስተናገዷ ጥያቄን አስነስቷል። በተለይም ሀገሪቱ ለመስተንግዶ የምታደርገው ዝግጅት ሲፈተሽ በሚፈለገው ፍጥነት መጓዝ እንዳልቻለ ታይቷል። ውድድሩን ያስተናግዳሉ ተብለው የተለዩት ስታዲየሞችም አጠቃላይ ለውድድሩ የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች መሟላት አለመሟላታቸው ከካፍ በተላኩ ባለሙያዎች ባሳለፍነው ወር መጀመሪያ ተጎብኝቷል። በጉብኝቱም የተገኘው ውጤት ኢትዮጵያ ውድድሩን ለማዘጋጀት ያደረገችው ጥረት እንዳልተሳካና መከናወን ያለባቸው በርካታ ስራዎች በአግባቡ እንዳልተከናወኑና አጥጋቢ ስራዎችም እንዳልተሰሩ በሪፖርት ቀርቧል። ኢትዮጵያ ያገኘችው የአስተናጋጅነት ዕድል ጥያቄ ውስጥ የወደቀ ቢሆንም በብሄራዊ ፌዴሬሽኑ በኩልም ሆነ ከመንግስት ምንም ዓይነት ማረጋገጫ ሳይገኝ ቆይቷል። ይሁን እንጂ ከሰሞኑ ግን ድብብቆሹ ማክተም እንዳለበት በማመን እውነታው ለህዝብ ይፋ ተደርጓል። በመሆኑም የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የስፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ፤ መንግስት ለውድድሩ ዝግጅት አስፈላጊውን ወጪ ለመሸፈን ዝግጁ አለመሆኑን በምክንያትነት ጠቅሰው ኢትዮጵያ በ2020 እንድታሰናዳ በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን የተሰጣትን የአፍሪካ አገሮች ዋንጫ (ቻን) እንደማትቀበል አስታውቀዋል። የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽን (ካፍ) ፕሬዚዳንት አህመድ አህመድ የኢትዮጵያ መንግስትን የዘገየ ውሳኔን መሰረት በማድረግ የ2020 የቻን ዋንጫን በአጭር ዝግጅትና ፍጥነት በተሟላበት ሁናቴ ማስተናገድ ለሚችል አገር ለማስተላለፍ በካይሮ መምከር ግድ ብሏቸዋል። በመሆኑም የአዘጋጅነት ዕድሉን ለምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ካሜሩን ተላልፏል። ካሜሩን ውድድሩን በተሻለ ሁኔታ ማስተናገድ እንደምትችል እምነታቸውን ገልፀዋል። በ2022 ለማዘጋጀት እድል የነበራት ካሜሩን አሁን ያገኘችውን እድል ተጠቅማ ለውድድሩ ዝግጅቷን አጠናክራ በመቀጠል የተሳካ መድረክ ትፈጥራለች ተብሎ እንደሚጠበቅም አስታውቀዋል። የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ባሳለፈው ውሳኔ መሠረት የአስተናጋጅነት ዕድሉን ከኢትዮጵያ የተቀበለችው ምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ካሜሩን በደስታ መረከቧን ቢቢሲ ጽፏል። ከኢትዮጵያ እጅ ያመለጠው የቻን አዘጋጅነት በካሜሩን ቤት እንደ መልካም አጋጣሚ የታየም መሆኑን አስፍሯል። ከኢትዮጵያ መዳፍ ውስጥ ፈለቅቃ ከወሰደችው ከካሜሩን ቤት የ2019 የአፍሪካ ዋንጫን የማስተናገድ ዕድሉን አግኝታ የነበረ ቢሆንም፤ በተቀመጠው ጊዜ ዝግጅቷን የማጠናቀቅ አቅሟ ጥያቄ ውስጥ መግባቱን ተከትሎ ለግብፅ መሰጠቱ አስታውሶ፤ በከፍተኛ ደስታ አጋጣሚውን ለመጠቀም የምትሰራ መሆኑን የሚያሳይ አስተያየት መሰጠቱንም አስነብቧል። የአፍሪካ አገሮች ዋንጫ (ቻን) በአገር ውስጥ ሊግ ብቻ የሚጫወቱ ተጫዋቾችን ብቻ የሚያሳትፍ የውድድር መድረክ ሲሆን፤ በሁለት ዓመት አንዴ ይደረጋል። እኤአ 2009 የተጀመረው ቻን የመጀመሪያዋ ዋንጫ ኮትዲቯር ስታዘጋጅ፤ 2ኛውና በ2011 የተካሄደውን ደግሞ ሱዳን አዘጋጅታለች። በ2014 ደቡብ አፍሪካ ሶስተኛውን ስታስተናግድ፤ በ2016 ሩዋንዳ 4ኛውን አዘጋጅታለች። በ2018 በሞሮኮ አዘጋጅነት ለ5ኛ ጊዜ የተካሄደ ሲሆን፤ 6ኛውና በ2020 የሚካሄደው የቻን ዋንጫ ደግሞ ወደ ምዕራብ አፍሪካ በመጓዝ ካሜሩን ቤት መግባቱ ተረጋግጧል።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 9/2011
https://www.press.et/Ama/?p=9069
422
2ስፖርት
አሰልጣኝ ሥዩም ከበደና መከላከያ ተለያዩ
ስፖርት
April 17, 2019
21
ዓመቱን ወጥ ባልሆነ አቋም እየተጓዘ በወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኘው መከላከያ ከዋና አሰልጣኙ ጋር ከአንድ ዓመት ቆይታ በኋላ መለያየቱ ታውቋል። በከፍተኛ ሊግ እየተሳተፈ ከሚገኘው ሰበታ ከተማ ጋር በስምምነት ከተለያዩ በኋላ ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር ላይ ነበር አሰልጣኝ ሥዩም ከበደ መከላከያን ለማሰልጠን የተረከቡት። በክለቡ የኢትዮጵያ ዋንጫ እና የኢትዮጵያ አሸናፊዎች ዋንጫን በማንሳት ዓመቱን በስኬት የጀመሩት አሰልጣኙ በአዳማ ከተማ የ5-1 ያልተጠበቀ ሽንፈት በኋላ በቡድኑ ውስጥ መረጋጋት የጠፋ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በሃያ ጨዋታ አስራ ስምንት ነጥብ ይዞ 14ኛ ደረጃን በመያዝ በወራጅ ስጋት ውስጥ ይገኛል። በክለቡ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ሰፊ ግምገማ ያደረገው የቦርድ አመራሩ ከአሰልጣኝ ሥዩም ከበደ ጋር ለመለያየት ከውሳኔ የደረሰ ሲሆን እንደ ምክንያት የቀረበው በሁለተኛው ዙር ቡድኑ መሻሻል አለማሳየቱ ሆኗል። ቡድኑን በጊዜያዊነት እንዲያሰለጥኑ በቅርቡ የሴቶች ቡድን አሰልጣኝ ሆነው የተሾሙት የቀድሞው የቡድኑ አሰልጣኝ በለጠ ገብረኪዳን ሲሾሙ ምንያምር ፀጋዬ በረዳትነት እንዲቀጥሉ መወሰኑ ታውቋል። በ2011 ዓ.ም የውድድር ዓመት ብቻ በርካታ ክለቦች አሰልጣኞችን ያሰናበቱ ሲሆን፤ ከዚህ ውስጥ ደደቢት፣ አዲግራት ወልዋሎ ዩኒቨርሲቲ፣ ደቡብ ፖሊሰ፣ መከላከያ፣ ወላይታ ድቻ፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ ስሁል ሽረ ይጠቀሳሉ።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 9/2011
https://www.press.et/Ama/?p=9068
155
2ስፖርት
የአፍሪካ እግር ኳስ የነገ ተስፋዎች መድረክ
ስፖርት
April 17, 2019
37
የአፍሪካ ከ17 ዓመት በታች ዋንጫ ውድድር የአህጉሪቱን እግር ኳስ ለመረከብ ተስፋ የተጣለባቸው ታዳጊዎችን በአንድ መድረክ ያሰባስባል፡፡ በእግር ኳሱ መሰረትን የያዙ ተጫዋቾችን የሚፈሩበት ውድድሩ በታንዛኒያ አዘጋጅነት ለ13ኛ ጊዜ በመካሄድ ላይ ይገኛል። የውድድሩ አላማ በተለያዩ ደረጃዎች የሚገለጽ ሲሆን፤በአለም አቀፍ ደረጃ ተጽእኖ መፍጠር የቻሉ አፍሪካዊ ብሄራዊ ቡድኖችን ለማፍራት የሚለው ሚዛን የሚደፋ ሆኖ ይነገራል። በእግር ኳሱ ጠንካራና መሰረት ያለው ብሄራዊ ቡድን ለመገንባት ትልቅ ፋይዳን እንደያዘ ይነገርለታል። በአህጉሪቱ የእግር ኳስ ትንሳኤ ላይ ትልቅ ድርሻን የሚሰጠው ውድድሩ እ.ኤ.አ በ1995 ነበር የተጀመረው። ውድድሩ ‹‹የአፍሪካ ከ17 ዓመት በታች ቻምፒዮን ሺፕ›› በሚል ስያሜ መጀመሩን አበሰረ። በአፍሪካን የነገ እግር ኳስ ውጤት መሰረት የሆኑትን ታዳጊዎች የሚያሰባስበው ይህ ውድድር እ.ኤ.አ በማሊ አዘጋጅነት ለመካሄድ በቃ። በመጀመሪያው ውድድር ላይም አዘጋጇን ማሊን ጨምሮ ስምንት አገሮች በሻምፒዮናው ተሳታፊ ሆነውበታል። የጋና ከ17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን የውድድሩ አሸናፊ በመሆን ተጠናቀቀ። ከሁለት ዓመት በኋላ ደግሞ በቦትስዋና አዘጋጅነት ሻምፒዮናው የተዘጋጀ ሲሆን፤ከ17 ዓመት በታች የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሄራዊ ቡድን በውድድሩ ተሳታፊ ከነበሩት አገራት አንዱ ነበር። በውድድሩ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለመጀመሪያ ጊዜ ከመሳተፍ ባሻገር ጥሩ የሚባል ተፎካካሪ ሆኖ የታየበትም ጭምር ነው። በውድድሩ የግብጽ ብሄራዊ ቡድን የሁለተኛው የአፍሪካ ከ17 ዓመት በታች ውድድር ሻምፒዮን ሺፕ በመሆን ዋንጫውን ማንሳት ችሏል። በውድድሩ ጥሩ እንቅስቃሴ ካሳዩት አገራት አንዱ በመሆን ተጠቃሽ የነበረው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አራተኛ ደረጃን ይዞ ለማጠናቀቅ የቻለበትም ነው። ጊኒ እ.ኤ.አ በ1999 ሦስተኛውን ውድድር አስተናግዳለች። የመጀመሪያውን ውድድር አሸናፊ በመሆን ዋንጫ ያነሳችው ጋና ዳግም በተስፈኛ ልጆቿ ለሁለተኛ ጊዜ የውድድሩ ባለ ድል በመሆን ታሪክ የሰራችበት ነው። የጋና ብሄራዊ ቡድን የፍጻሜ ተጋጣሚውን ቡርኪና ፋሶን 3 ለ 1 በመርታት ነው አሸናፊ መሆን ችሏል። በመጀመሪያው የውድድሩ መድረክም ጋና ዋንጫ ያነሳችው ናይጀሪያን 3 ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፋ ነበር፡፡ እ.አ.ኤ በ2001 በሲሺየልስ አስተናጋጅነት የተካሄደው አራተኛው የአፍሪካ ከ17 ዓመት በታች ሻምፒዮን ሺፕ አሸናፊ ደግሞ ናይጀሪያ ነበረች፡፡ ቡድኑ የስድስተኛው ዙር ውድድር አሸናፊም ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የናይጀሪያ ቡድን ከሁለት ዓመት በኋላ በሲዋዚላንድ በተካሄደው ውድድር የአሸናፊነት ግምት ማግኘት ቢችልም የካሜሮን ብሄራዊ ቡድን የሻምፒዮናነት ክብር ሲያገኝ የናይጄሪያ ብሄራዊ ቡድን ለፍጻሜ እንኳ ሳይደርስ ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቋል። የናይጄሪያ ብሄራዊ ቡድን የከሸፈበትን ግምት ለማደስ አራት ዓመት በመጠበቅ እ.ኤ.አ በ2007 በቶጎ አዘጋጅነት በተካሄደው ሰባተኛው ውድድር ላይ አሸናፊ መሆን ችሏል። ከዚህ ውድድር ቀደም ብሎ በጋምቢያ አስተናጋጅነት የተካሄደውን ስድስተኛውን የአፍሪካ ከ17 ዓመት በታች ሻምፒዮን ሺፕ አስተናጋጇ ጋምቢያ አሸንፋለች። ጋምቢያ ውድድሩን አዘጋጅታ ዋንጫውን ያሸነፈች ቀዳሚ አገር መሆን የቻለች ሲሆን፤እ.አ.ኤ 2009 ለስምንተኛ ጊዜ በአልጄሪያ የተካሄደውን ውድድር በማሸነፍ ሌላ ታሪክ መፃፍም ችላለች። እ.አ.አ በ2011 እና በ2013 የተካሄዱትን ውድድሮች ሩዋንዳና ሞሮኮ (እንደ ቅደምተከተላቸው) አስተናግደው ቡርኪና ፋሶ እና አይቮሪኮስት (እንደ ቅደምተከተላቸው) አሸናፊ ሆነዋል። በአፍሪካ እግር ኳስ ውስጥ የተሻለ ነገን ለመፍጠር የሚያስችል መሰረት የመጣል ተስፋን የያዘው ውድድሩ፣ እ.ኤ.አ በ2015 የስያሜ ለውጥ በማድረግ ‹‹ከአፍሪካ ከ17 ዓመት በታች ቻምፒዮን›› ወደ ‹‹የአፍሪካ ከ17 ዓመት በታች ዋንጫ›› ተቀይሮ በናይጄሪያ አስተናጋጅነት ቀጠለ። የውድድሩ ድምቀትና ፉክክርም ከዓመት ወደ ዓመት እያየለ እንደመጣ ይነገርለታል፡፡ በናይጄሪያ አዘጋጅነት የተካሄደው 11ኛው ዙር ውድድርም ለዚሁ ምስክር ሆኖ ይቀርባል። ጠንካራ ፉክክርን ባሳየው በዚህ ውድድር የማሊ ብሄራዊ ቡድን አሸናፊ በመሆን ስያሜውን የቀየረውን ውድድር የመጀመሪያ ዋንጫ አንስቷል። የማሊ ቡድን ይህን ውድድር በበላይነት ማጠናቀቁ ማሊ የመጀመሪያው የአፍሪካ ከ17 ዓመት በታች ቻምፒዮን ሺፕ አዘጋጅ ከመሆኗ ጋር ሲደመር ልዩ የታሪክ አጋጣሚ ፈጥሮ አልፏል፡፡ የማሊ ብሄራዊ ቡድን በዚህ ብቻ ሳይወሰን ከሁለት ዓመት በፊት በጋቦን አስተናጋጅነት ለ12ኛ ጊዜ የተካሄደውን ውድድር ድል በማድረግ ሌላ ታሪክ መፃፍ ችሏል። የአፍሪካን ታዳጊዎች የሚያፋልመውን ውድድር ባለፉት 22 ዓመታት በነበረው ጉዞው ማሊ፣ ናይጄሪያ፣ ጋምቢያ እና ጋና እያንዳንዳቸው ሁለት ጊዜ ዋንጫውን ሲያነሱ፤ቡርኪና ፋሶ፣ አይቮሪኮስት፣ ግብጽ እና ካሜሮን እያንዳንዳቸው አንድ ጊዜ ማንሳት የቻሉ አገራት ሆነዋል። በአፍሪካ እግር ኳስ ውስጥ መጪውን ትውልድ ለማየት መስተዋት የሆነው ይህ ውድድር፣ ዘንድሮ (በ2019) በታንዛኒያ ለ13ኛ ጊዜ እየተካሄደ ይገኛል። አዘጋጇ አገር ታንዛኒያ ከ23 ዓመታት በፊት ጅማሮውን ያደረገውን የዚህን ውድድር ዝግጅት የተሳካና የተዋጣለት ለማድረግ ላይ ታች ብላ ወድድሩ ባሳለፍነው ሳምንት በይፋ ተጀምሯል። በውድድሩ ላይም አዘጋጇ አገርን ጨምሮ ስምንት ሀገራት እየተሳተፉ ሲሆን ውድድሩም በሁለት ምድቦች ተከፍሎ እየተደረገ ይገኛል። በዚህ መሰረትም በመጀመሪያው ምድብ ታንዛኒያ፣ ኡጋንዳ፣ ናይጄሪያ እና አንጎላ ተደልድለዋል። በሁለተኛው ምድብ ደግሞ ሴኔጋል፣ ካሜሮን፣ ጊኒ እና ሞሮኮ ተደልድለዋል። ባሳለፍነው እሁድ ውድድሩ ሲጀመር በመጀመሪያው ምድብ የሚገኙት አዘጋጇ ሀገር ታንዛኒያ ከናይጄሪያ ጋር ጨዋታቸውን አድርገው፣ ናይጄሪያ አዘጋጇን አገር 5ለ4 በመርታት የመጀመሪያውን ድል አስመዝግባለች። የውድድሩ ጨዋታዎች ዛሬና ነገ የሚቀጥሉ ሲሆን በዛሬው እለት ናይጄሪያ ከአንጎላ ፤ ኡጋንዳ ደግሞ ከአዘጋጇ ታንዛኒያ ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታቸውን ያሸነፉት ናይጄሪያና አንጎላ በዚህ ጨዋታ የሚያስመዘግቡት ውጤት መርታታቸው ወደ ቀጣዩ ዙር ለሚኖራቸው ጉዞ ወሳኝ ነው። በመጀመሪያው ጨዋታ ድል ያልቀናቸው ታንዛኒያና ኡጋንዳ ሽንፈትን ካስተናገዱ ቀጣይ ጉዟቸው የሚገታ ይሆናል። በሁለተኛው ምድብ የተደለደሉ አገራት ከነገ በስቲያ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ሲሆን ጨዋታ ሲሆን ካሜሮን ከሞሮኮ፤ሴኔጋል ከጊኒ የሚኖራቸው ጨዋታ የሚጠበቅ ሆኗል። በዘንድሮው ውድድር ከታዩ አስገራሚ ክስተቶች መካከል የእድሜ ተገቢነት ጉዳይ አንዱ ሆኗል። የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የእድሜ ተገቢነት ጉዳይ ‹‹ለድርድር የማይቀርብ›› ነው ብሏል፡፡ በዚህም ምክንያት ስድስት ተጫዋቾች ከእድሜ ተገቢነት ጋር ተያይዞ በተነሳባቸው ጥያቄ ከውድድሩ ታግደዋል። ካሜሮን ሶስት ተጫዋቾቿን በእድሜ ተገቢነት ስታጣ፤አዘጋጇ አገር ታንዛኒያ ደግሞ ሁለት ተጫዋቾች እንዲሁም የጊኒ ብሔራዊ ቡድን አንድ ተጫዋች ታግዶባቸዋል፡፡አዲስ ዘመን ሚጣዝያ 9/2011
https://www.press.et/Ama/?p=9073
737
2ስፖርት
በሜይ ዴይ የፍፃሜ ተፋላሚዎች ተለይተዋል
ስፖርት
April 18, 2019
36
በአገራችን ለአርባ አራተኛ በዓለም ደግሞ ለመቶ ሰላሳኛ ጊዜ የሚከበረውን የሰራተኞች ቀን (ሜይ ዴይን) አስመልክቶ በሰራተኛው መካከል በተለያዩ ስፖርቶች የሚካሄደው የጥሎ ማለፍ ውድድር ወደ ወሳኝ ምዕራፍ ተሸጋግሯል። ለአንድ ወር ያህል ሲካሄድ የቆየው የጥሎ ማለፍ ውድድር አዲስ አበባን ወክለው ለፍፃሜ የደረሱ ቡድኖችን ለይቷል። አዲስ አበባን ወክለው በተለያዩ የስፖርት አይነቶች ለፍፃሜ የደረሱ ቡድኖች የፍፃሜ ጨዋታቸውን የሰራተኞች ቀን በሚከበርበት እለት የፊታችን ሚያዝያ 23 ጅማ ላይ ከጅማና አካባቢዋ የጥሎ ማለፍ አሸናፊ ማህበራት ጋር እንደሚያደርጉ የኢሰማኮ የስፖርት ክፍል ኃላፊ አቶ ዮሴፍ ካሳ ለአዲስ ዘመን ተናግረዋል። አዲስ አበባን በሜይ ዴይ የፍፃሜ ጨዋታዎች ለመወከል በሳምንቱ መጨረሻ በርካታ ወሳኝ ጨዋታዎች በተለያዩ ማሕበራት መካከል ተካሂደዋል። በሰራተኛው ስፖርት ትልቅ ትኩረት በሚሰጠውና ጠንካራ ፉክክር በሚደረግበት እግር ኳስ በጎፋ ሜዳ የተገናኙት የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅትና ሙገር ሲሚንቶ ነበሩ። የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በመደበኛው ሰዓት ባለመጠናቀቁ ወደ መለያ ምት አምርተው ፖስታ ሦስት ለሁለት በሆነ ውጤት በመርታት የፍፃሜው ተፋላሚ መሆኑን አረጋግጧል። ሙገር ሲሚንቶ በሌላኛው ተጠባቂ ጨዋታ በወንዶች ቮሊ ቦል ስፖርትም በሜዳው ባደረገው ጨዋታ በብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ ሦስት ለዜሮ ተሸንፎ ወደ ፍፃሜ ሳያልፍ ቀርቷል። በጅማው የፍፃሜ ጨዋታ አዲስ አበባን ወክለው ከሚሳተፉ አስር ማህበራት መካከል ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ በሁለቱም ፆታ በቮሊ ቦል ተሳታፊ ይሆናል። አንበሳ የከተማ አውቶብስ፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ኢትዮ ኤሌክትሪክ፣ብርሃንና ሰላም ማተሚያና ሌሎች አንጋፋ ተቋማት በተለያዩ የስፖርት አይነቶች ተሳታፊ ናቸው። ውድድሩ ዓለም አቀፍ የሰራተኞች ቀንን አስመልክቶ የሚካሄድ እንደመሆኑ፤ ሰራተኛው የከፈለው መስዋዕትነት እየታወሰ ሰራተኛው በስፖርቱ ይበልጥ ተቀራርቦ መብትና ጥቅሙን በማስጠበቅ ያልተደራጀው ተደራጅቶ ኢንዱስት ሪውን ብሎም አገሩን የሚያሳድግበት መሆኑን የኢሰማኮ የስፖርት ክፍል ኃላፊው ተናግረዋል። ኢንዱስትሪ በአገሪቱ እየሰፋ ሲሄድ በስፖ ርቱም ታግዞ ሰራተኛው ጤንነቱን የጠበቀ አምራች መሆን እንዳለበት የጠቆሙት ኃላፊው ከዓለም አቀፍ ሰራተኛ ማህበር ጋር በመሆን ዓለማቀፍ ተሞክሮን ቀስሞ የሰራተኛውን መብት የማስጠበቅ ጥረቱ እንደሚቀጥልም አብራርተዋል። በአገራችን ስፖርት ታሪክ አንጋፋ ከሆኑት መድረኮች በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሰው በሠራተኛው መካከል የሚካሄደው ስፖርታዊ ውድድር ነው። የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) ሰራተኛውን እርስ በርስ በማቀራረብ አካላዊ ጤንነቱ ተጠብቆ ጠንካራ አምራች ዜጋ እንዲሆን አደረጃጀቱን በኮንፌዴሬሽኑ የማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ስር አንድ የስፖርት ክፍልን አዋቅሮ ላለፉት በርካታ ዓመታት በአገር አቀፍ ደረጃ የስፖርት ውድድሮችን ሲያከናውን ቆይቷል። ኢትዮጵያን ወክሎ በአንድ ወቅት የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ የእግር ኳስ ዋንጫ ካነሳው ቡድን ተጫዋቾች መካከል አብዛኞቹ ከሠራተኛው ስፖርት የተገኙ እንደሆኑ ይነገራል።ኢትዮጵያ ሦስተኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ስታነሳም የሰራተኛው ስፖርት ተጫዋቾችን በማበርከት ትልቅ አስተዋፅኦ እንደነበረው ከታሪክ ማህደር መረዳት ይቻላል። ይሁን እንጂ የሠራተኛው ስፖርት ወርቃማ ጊዜ በሂደት እየቀዘቀዘ መጥቶ ነበር። ኢሠማኮ እንደ አዲስ ከተደራጀ አንስቶ የሠራተኛውን ስፖርታዊ ተሳትፎ ወደ ነበረበት ደረጃ መልሶ ለማምጣት ጥረት እየተደረገ ይገኛል። በእዚህም ከፍተኛ ድምቀትን ተላብሰው የሚካሄዱ የስፖርት ውድድሮች ከዓመት ዓመት የተሳታፊ ማህበራት ቁጥር እየጨመረ፤ የመወዳደሪያ ስፖርቶች ቁጥርም እያደገ፤ የተመልካች ብዛት ለውጥ እየታየበት መጥቷል። ሴት ተሳታፊዎችም በተለያዩ የስፖርት አይነቶች ተካፋይ እየሆኑና ስፖርቱ በመገናኛ ብዙሃን የሚያገኘው ሽፋን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ ታዋቂነቱ በአገራችን ከሚካሄዱ ታላላቅ የውድድር መድረኮች አንዱ እየሆነ መጥቷል።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 10/2011በቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=9158
420
2ስፖርት
ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን የክለብ ባለቤት የማድረግ ጉዞ
ስፖርት
April 19, 2019
26
የኦሮሚያ ክልል ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ናስር ሁሴን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሥራቸው በአንድ በኩል የተማረውን የሰው ኃይል ማምረት ሲሆን፤ ማኅበራዊ አገልግሎትን መስጠትም አንዱ ተግባራቸው ነው።ይህ በመሆ ኑም በክልሉ ከማህበራዊ እንቅስቃሴ ጋር ተያይዞ በስፖርቱ ላይ የነበረውን ክፍተት ለመሙላትም ሰፊ ሥራዎችን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ይናገራሉ። በክልሉ ያሉ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከስፖርት ጋር ባላቸው እንቅስቃሴ የራሳቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ከማድረግ አኳያ የክልሉ ስፖርት ኮሚሽን ክፍተት እንደነበረበት፤ የስፖርት እንቅስቃሴውን ሳይንሳዊ መሠረት አስይዞ ለማስ ኬድና የራሳቸውን ክለብ አደራጅተው እንዲሰሩ ለማድረግ የተሰራው ሥራም አናሳ እንደሆነ ኮሚሽነሩ ያብራራሉ። እንደ ኮሚሽነሩ ማብራሪያ፤ በአሁኑ ወቅት አንዳንድ የኒቨርሲቲዎች የክለብ ባለቤት መሆን ጀምረዋል።እንደ ክልል ሥራውን በተጠናከረ መልኩ በመያዝ አዲስ 30 የአትሌቲክስ ክለብ ይቋቋማል።ከ30ዎቹ ውስጥ በክልሉ የሚገኙ የመንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እያንዳንዳቸው የአትሌቲክስ ክለብ እንዲያዋቅሩ ይደረጋል። ዩኒቨርሲቲዎቹ የስፖርት ደንቡንና ፕሮፖዛሉን ወስደዋል።በቀጣዩ ወር ውስጥ ክለቦቹ በሙሉ ተደራጅተው ወደ ሥራ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።በዚህ ሂደት አቅጣጫ ማስቀመጥ ብቻ ሳይሆን እንዴት እንደሚያዋቅሩ፣ የሚያስፈልገው በጀትና የመዋቅር አሰራር ተለይቶ ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ተሰጥቷል። የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ፕሬዚዳንቶች ከክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት ጋር ውይይት በማድረግ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።በመሆኑም የመደወላቡ ዩኒቨርሲቲ የአትሌቲክስ ክለብን በማቋቋም ሥራውን ጀምሯል።ሌሎች ዩኒቨርሲ ቲዎችም ይህንን ተሞክሮ ወስደው እንዲሰሩ ለማድረግ ክለብ በማቋቋም ላይ ናቸው። በአዲስ አበባ በጃንሜዳ በተካሄደው የከ ፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውድድር ላይ በክ ልሉ ያሉት ዩኒቨርሲቲዎች በዚሁ መንፈስ መወዳደር ችለዋል። በአጠቃላይ የከፍተኛ ትም ህርት ተቋማት በማኅበራዊ አገልግሎታቸው ግዴታቸውን እንዲወጡ ከስፖርት ጋር ተያይዞ የሚያስተምሩትን ሳይንስ በተግባር በማሳየት ለአገሪቷ ስፖርት እድገት አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ የማድረግ ሥራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል ኮሚሽነሩ።አክለውም ‹‹አሁን የተጀመረው በአት ሌቲክስ ስፖርት ዘርፍ ነው።ወደ ፊት በሁሉም የስፖርት አይነቶች የክለብ ባለቤት የሚሆኑበት ሁኔታ ይመቻቻል።አንድ ክለብ የሚያስፈልገውን የሰው ኃይልና ሌሎች ተያያዥ ነገሮችም አብረው ታሳቢ ይደረጋሉ።ይህም በባለሙያዎች ጥናት ተደርጎ ወደ ሥራ ተገብቷል›› ሲሉ በቀጣይ አሰራር ላይ ያላቸውን አስተያየት ሰጥተዋል። ኮሚሽነሩ፤ የስፖርት ፖሊሲው ሁሉም ሰው ጤንነቱን ለመጠበቅ የስፖርት እንቅስቃሴ እንዲያደርግ የሚያዝ ነው በማለት፤ ከዚህ ውስጥ ደግሞ ተሰጥኦ ያላቸው ስፖርተኞች ከዘርፉ ተጠቃሚ እንዲሆኑና ተሽለው ሲገኙም እስከ ከፍተኛ ውድድር እንዲደርሱ የሚያዝ መሆኑንና በዚህም መሰረት ከተለምዷዊ ስልጠና ለመላቀቅ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን የክለብ ባለቤት ማድረጉ አስፈላጊ መሆኑን ይጠቅሳሉ። ኮሚሽነሩ እንደሚሉት፤ በኢትዮጵያ አብዛኛው ስፖርተኛ እንቅስቃሴዎችን የሚሰራው በተለምዶ ነው።ችሎታ ያላቸውና በራሳቸው ተነሳሽነት ልምድ ያካበቱትን ስፖርተኞች ነው በአንድ ላይ በማጣመር እንዲወዳደሩ እየተደረገ ያለው።ይህ አካሄድ ደግሞ ተተኪ አትሌቶችን በማፍራት ረገድ ክፍተት እያመጣ ነው። ይህ ብቻ ሳይሆን በትራክ ላይ በሚካሄደው ውድድር ላይ ውጤት እየቀነሰ ነው። ይህ የሚያሳየውም የስፖርቱ ሳይንሳዊ መሠረቶች ላይ የተሰራው ሥራ አናሳ መሆኑን ነው። የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የክለብ ባለቤት መሆናቸው በአንድ በኩል ተሰጥኦ ያላቸውን ወጣቶች በሳይንስ የተደገፈ ሥልጠናን ለመስጠት ያስችላቸዋል።ከዚህም ባሻገር ስፖርተኞች በክለቦቹ ሲታቀፉ ማደሪያና ምግባቸውን ጭምሮ ሌሎች ግብአቶች እንዲሟሉላቸው ይደረጋል።ጎን ለጎን የራሳቸውን ሥራ እየሰሩ ስፖርቱን መስራት ይችላሉ።በአትሌቲክሱ ላይ ያለው ነባራዊ ሁኔታ ሲቃኝ በአገራዊ እድገቱ ውስጥ እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ አናሳ በመሆኑ፤ ይህ ተጠናክሮ ከቀጠለ ለአገሪቱ የኢኮኖሚ እድገትም አስተዋጽኦ ይኖረዋል።የአትሌቲክሱ ዘርፍ መጠንከር የውጭ ምዛሪንም ያነቃቃል።ይህንን ለማድረግ ኢትዮጵያ በዓለም አቅፍ ደረጃ ትልቅ አቅም አላት። ‹‹የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ክለብ በማ ደራጀታቸው ለአገሪቷ ስፖርት እድገትና ስፖርቱ በኢኮኖሚ ውስጥ ያለውን ጉልህ አስተዋጽኦ እንዲወጣ ያደርጋሉ።ጎን ለጎንም በዓለም አቀፍ ደረጃም ሆነ በአገር አቀፍ ደረጃ በውድድር በመድረኮች ላይ የራሳቸውን አርማ ይዘው ስለ ሚገቡ ራሳቸውን ማስተዋወቅ ይችላሉ። ክለቦቹ ስፖርተኞችን ካሰለጠኑና ካሳደጉ በኋላ አትሌቱ ወደ ቀጣዩ ደረጃ ከፍ ሲል ከሚያገኘው ገቢ ለክለቡ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ይኖራል›› ሲሉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የክለብ ባለቤት መሆናቸው የሚያስገኘውን ጥቅም አብራርተዋል።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 11/2011
https://www.press.et/Ama/?p=9211
489
2ስፖርት
የደደቢት ተጫዋቾች በደሞዝ ምክንያት ልምምድ መስራት አቆሙ
ስፖርት
April 18, 2019
31
በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሰንጠረዥ 16ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ደደቢት እግር ኳስ ክለብ ተጫዋቾች በደሞዝ ምክንያት ልምምድ መስራት ማቆማቸው ተገለጸ። ሁለተኛው ዙር ከተጀመረ ወዲህ መልካም የውጤት መሻሻል በማሳየት ላይ ያሉት የደደቢት ተጫዋቾች ያለፉት ወራት ደሞዛቸው ያልተከፈላቸው በመሆኑ ምክንያት ልምምድ ማቆማቸውን ለማወቅ ተችሏል። እንደጠበቁት ከአጋር ድርጅቶች ድጋፍ ማግኘት ያልቻሉት ሰማያዊዎቹ ከጥቂት ወራት በፊትም በተመሳሳይ ምክንያት ልምምድ አቋርጠው የነበረ ሲሆን በዚሁ የፋይናንስ ችግር ሳቢያም በተከታታይ ሁለት ዓመታት ከኢትዮጵያ ዋንጫ ራሳቸው ማግለላቸውም ይታወሳል። በጉዳዩ ዙሪያ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር አጭር ቆይታ ያደረጉት የቡድን መሪው አቶ ኤፍሬም አበራ እንዳሉት ከሆነ ክለቡ የተጫዋቾቹን ደሞዝ ለመክፈል ጥረት እያደረገ ሲሆን በአጭር ቀናት ውስጥም ክፍያው እንደሚጠናቅቁ ገልፀዋል። በሁለተኛው ዙር አሰልጣኝ ዳንኤል ፀሃዬን ቀጥረው በጥሩ መነቃቃት ላይ የሚገኙት ደደቢቶች በቀጣይ ሳምንት በትግራይ ስታድየም ጅማ አባ ጅፋርን የሚገጥሙ ይሆናል። በ2011 ዓ.ም መቀመጫውን ከአዲስ አበባ ወደ ትግራይ ክልል ያደረገው ክለቡ፤ የፋይናንስና የበጀት ጫና ከፍተኛ ተጽእኖ በክለቡ እያሳደረ በመሆኑ ክለቡ መቀመጫውን በትግራይ ክልል ማድረጉ ይታወሳል። ክለቡ ህልውናውን ለማስቀጠልና የረጅም ጊዜ ራዕዩን ለማሳካት ከ2011 ዓ.ም የውድድር ዓመት ጀምሮ አሁን ካለው የክፍያ ስርአትና ፉክክር በመውጣት አቅም ባገናዘበና በአነስተኛ ወጪ ለመወዳደር እስከመወሰን መጓዝ ችሏል። ክለቡ በወቅቱ የገጠመውን የበጀት ጫናውን ለመቀነስና ከነበረበት ችግር ለመውጣት ላለፉት ሶስት ዓመታት የተለያዩ እርምጃ መውሰዱን ቢያስታውቅም፤ አሁንም ከችግሩ አለመውጣቱን የሚያመላክት መሆኑን ከስፖርት ቤተሰቡ ዘንድ በስፋት እየተነገረ ይገኛል። በአሁኑ ወቅት የፋይናንስ አቅሙ ተዳክሞ ለተጫዋቾቹ በአግባቡ ደሞዝ መክፈል ባለመቻሉ ተጫዋቾች በደሞዝ ምክንያት ልምምድ መስራት ማቆማቸውን ከሶከር ኢትዮጵያ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል። ክለቡ ከገጠመው የፋይናንስ ቀውስ በተመሳሳይ የውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን፤ ክለቡ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ መሰረት 16ኛ ላይ የተቀመጠ ሲሆን የመውረድ አደጋም የተጋረጠበት መሆኑ ይታወቃል። የደደቢት እግር ኳስ ክለብ በአሁኑ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንትና የቀድሞ የክለቡ ፕሬዚዳንት ኮሎኔል አወል አብዱራሂም በ1989 ዓ.ም ከዘጠኝ ዓመት በታች የሆኑ ህጻናትን በመያዝ ተመስርቷል።በ2000 እና በ2001 ዓ.ም በብሔራዊ ሊግ ተወዳድሮ በ2002 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ያደገው የደደቢት እግር ኳስ ክለብ በ2005 ዓ.ም የፕሪሚየር ሊጉ አሸናፊ መሆኑ የሚታወስ ነው።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 10/2011በ
https://www.press.et/Ama/?p=9164
293
2ስፖርት
በአፍሪካ የወጣቶችና ታዳጊዎች አትሌቲክስ ሻምፒዮና የመጀመሪያ ቀን ውሎ ኢትዮጵያ አራት ሜዳሊያዎችን አገኘች
ስፖርት
April 18, 2019
177
፡- በኮትዲቯር አቢጃን የአፍሪካ የወጣቶችና ታዳጊዎች አትሌቲክስ ሻምፒዮና የመጀመሪያ ቀን ውሎ ኢትዮጵያ አራት ሜዳሊያዎችን ማግኘት ችላለች። ከአራቱ ሜዳሊያዎች ውስጥ አንዱ ወርቅ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ ሁለት የብርና አንድ የነሐስ ሜዳሊያዎች ናቸው። ለአምስት ቀናት በሚቆየው የአፍሪካ ከ20 ዓመትና ከ18 ዓመት በታች የአ ትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ 39 ሴትና 43 ወንድ፤ በድምሩ 82 አትሌቶችን በአጭር፣በመካከለኛ፣ በረጅም ርቀትና በሜዳ ላይ የአትሌቲክስ ስፖርት ተግባረት በሆኑት በውርወራና ዝላይ ስፖርቶች ትካፈላለች። ይህ ሻምፒዮና ከትናንት በስቲያ ሲጀመር ኢትዮጵያ በወንዶች በ10 ሺህ ሜትር፣ በ1ሺህ 500 ሜትር፣ በስሉስ ዝላይ እና በሴቶች ደግሞ በ3 ሺህ ሜትር ሩጫና በስሉስ ዝላይ ተካፍላለች። ከእነዚህ ውድድሮች በሴቶች ከ20 ዓመት በታች የወጣቶች ውድድር በ3 ሺህ ሜትር አትሌት አለሚቱ ታሪኩ አንደኛ በመውጣት ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ ማምጣት ችላለች። በዚሁ ርቀት አትሌት ፀሀይ ሀይሉ ደግሞ ሶስተኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቅ የነሐስ ሜዳሊያ አሸናፊ መሆን ችላለች። በሴቶች ከ18 ዓመት በታች የታዳጊዎች ውድድር ደግሞ አትሌት ሰንበቴ ሮቢ ለሀገሯ የብር ሜዳሊያ ማምጣት ችላለች። በወንዶች ከተደረጉት ውድድሮች መካከል ደግሞ በ1ሺህ 500 ሜትር ሩጫ ውድድር አትሌት ይሁን ፋንታሁን ሁለተኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ የብር ሜዳሊያ ለሀገሩ ማምጣት ችሏል። በ10 ሺህ ሜትር ውድድር ላይ የተካፈሉት አትሌት ደረጀ አዱኛና አትሌት ቢተው አደም አራተኛና አምስተኛ ደረጃን ይዘው በማጠናቀቃቸው ድል ሳይቀናቸው ቀርቷል።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 10/2011
https://www.press.et/Ama/?p=9161
185
2ስፖርት
በሳምንቱ መጨረሻ በተካሄዱ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን ባለድል ሆነዋል
ስፖርት
September 17, 2019
23
 በዓለም አቀፍ ደረጃ የሳምንቱ መጨረሻ በተለያዩ የርቀት አይነቶች በተካሄዱ አትሌቲክስ ውድድሮች ኢትዮጵያውኑ አትሌቶች ባለድል ሆነዋል፡፡ በዴንማርክ ኮፐን ሃገን በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች ምድብ አትሌት ብርሃኔ ዲባባ ቀዳሚ ሆና አጠናቃለች፡፡ አትሌቷ ውድድሩን ለማጠናቀቅ የወሰደባት ሰዓትም 1:05:57 ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በዚህ ውድድር መገርቱ አለሙ አራተኛ፣ በቀለች ጉደታ አምስተኛ ሆነዋል፡፡ የ2018ቶኪ ማራቶን አትሌት ብርሃኔ ዲባባ በሴቶች ማራቶን በተደረገ ውድድር 2፡19፡51 በመግባት በውድድሩ ታሪክ ሁለተኛውን ፈጣን ሰዓት ማስመዝገቧ ይታወሳል፡፡ በዴንማርክ ኮፐን ሃገን በወንዶች መካከል የተካሄደውን ውድድር ደግሞ ጂኦፍሬይ ካምዎሮር በበላይነት አጠናቋል፡፡ አትሌቱ ማሸነፍ ብቻም ሳይሆን የርቀቱን ክብረ ወሰን በግሉ ማድረግ ችሏል፡፡ ውድድሩን ለማጠናቀቅ የወሰደበት 58፡01 የሆነ ጊዜም ይህን ታሪክ እንዲሰራ አስችሎታል፡፡ ኢትዮጵያዊው አትሌት ብርሃኑ ወንድሙ 59:22 በሆነ ሰዓት ሶስተኛ ሆኖ ውድድሩን ማጠናቀቅ ችሏል፡፡ በደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን በተካሄደው የማራቶን ውድድርም በሴቶች ኢትዮጵያዊያኑ አትሌቶች ከሁለት እስከ አራተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል፡፡ ኑሪት ሽመልስ 2:27:40, በሆነ ሰዓት ሁለተኛ ስትሆን፣ ጌጤ ምንዳዬ 2:28:32, በሆነ ሰዓት ሶስተኛ በመሆን ወድድራቸውን አጠናቃለች፡፡ ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ኡርጌ ዲሮ አራተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን ስታጠናቅቅ፣ የገባችበት ሰዓትም 2:29:50, ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ አውስትራሊያ ሲድኒ ላይ በተካሄደ ሌላ የማራቶን ውድድርም በሴቶች ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ጠጂቱ ዳባ ሶስተኛ ሆናለች፡፡ አትሌቷ ውድድሩን ለማጠናቀቅ የወሰደባት ሰዓትም 2:28:22 ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በቱርክ በተካሄደው ራን ዘ አይላንድ ግማሽ ማራቶን በወንዶች ምድብ ኢትዮጵያዊው አትሌት የበላይ ሆኖባታል፡፡ አትሌት ጌታዬ ገላው ውድድሩን በቀዳሚነት ያጠናቀቀ ሲሆን፣ 1:07:51 ውድድሩን በበላይነት ያጠናቀቀበት ሰዓት ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በቤላሩስ፤ ሚንስክ በተካሄደው ግማሽ ማራቶንም በሴቶች አትሌት ሸጌ ማዕረጉ ሁለተኛ ሆናለች፡፡ አትሌቷ ውድድሩን ለማጠናቀቅ የወሰደባት ሰዓትም 1:12:18, ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ ሌላኛዋ ኢትዮጵዊት አትሌት ተስፋነሽ መርጋ 1:12:50 በሆነ ሰዓት ሶስተኛ ሆናለች፡፡አዲስ ዘመን መስከረም 6 / 2012  ታምራት ተስፋዬ
https://www.press.et/Ama/?p=18144
240
2ስፖርት
ደቡብ አፍሪካዊቷ አትሌት ወደ እግር ኳስ
ስፖርት
September 16, 2019
17
ውጤታማ ከሆኑበት አንድ ስፖርት ወደ ሌላ መሸጋገር አዲስ ነገር ባይሆንም በሁለተኛው የስፖርት ዓይነትም ስኬት ማስመዝገብ ግን አልተለመደም። ከሰሞኑ ሲራገብ የቆየው ዘገባ አወዛጋቢዋና በመካከለኛ ርቀት አትሌቲክስ ዝነኛዋ አትሌት እግር ኳስ ተጫዋች መሆኗን የሚያትት ነበር። እርግጥ ነው ደቡብ አፍሪካዊቷ ካስተር ሰመኒያ ለዚህ ጉዳይ አዲስ ባትሆንም፤ የአጭር ርቀት ንጉሱ ዩዚያን ቦልት ወደ እግር ኳስ እንዲሁም የቀድሞው የማንቺስተር ዩናይትድ አምበል ሪዮ ፈርዲናንድ ወደ ቦክስ ስፖርት መግባታቸው ውጤት አለማፍራቱን መመልከት ይቻላል። በወንድ መሳይ ተክለ ቁመናዋ እንዲሁም በውድድሮች ላይ በምትፈጥረው ከፍተኛ ልዩነት በፆታዋ ላይ ለበርካታ ጊዜያት ጥያቄ ተነስቶባታል፤ ሻምፒዮናዋ። በቅርቡም የዓለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ያወጣውን አዲስ ህግ ተከትሎ እስከ ላይኛው የፍትህ አካል በመክሰስ ቅሬታዋን ስታቀርብ ሰንብታለች። አሁን ደግሞ ስሟን ካስጠራችበት መም ወደ ሜዳ መሸጋገሯን አሳውቃለች። በአትሌቲክስ ዓለም ሻምፒዮና 800 እና 1 ሺ 500 ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚዋ ሰመኒያ፤ የእግር ኳስ ህይወቷን መቀመጫውን በዚያው በደቡብ አፍሪካ ካደረገው ጄቪ ደብሊው ከተባለ የእግር ኳስ ክለብ አድርጋለች። ይህም ለአትሌቷ ሌላኛውን ህልሟን ለማሳካት ለክለቡ ደግሞ መልካም ዝና እና ስም የሚገነባለት እንደሚሆን ተገምቷል። የ28 ዓመቷ የቀድሞ አትሌት በሩጫው ውጤታማ ትሁን እንጂ ትምህርት ቤት ሳለች ጀምሮ ለእግር ኳስ ስፖርት ልዩ ፍቅር ስለነበራት ትለማመድ እንደነበር ኦልአፍሪካ ተወካይዋን ዋቢ በማድረግ አስነብቧል። ይህም ፍላጎቷም ወደ እግር ኳሱ እንድትገባ እንዳደረጋትም ነው የተገለጸው። የቀድሞዋ አትሌት የአሁኗ እግር ኳስ ተጫዋች በክለቡ ድረገጽ ላይ ባሰፈረችው አስተያየትም «ይህንን እድል በማግኘቴ ደስተኛ ነኝ፤ ከፍተኛ ድጋፍ ላደረገልኝ ክለብም ምስጋናዬን አቀርባለሁ። በአዲሱ ጉዞዬም የቻልኩትን ያህል ለክለቤ ለማበርከት እጥራለሁ» ብላለች። ነገር ግን በዚህ የውድድር ዓመት በሊጉ የተመዘገበች ተጫዋች ባለመሆኗ እስከ አዲሱ የውድድር ዓመት 2020 ድረስ ከክለቡ ጋር ልምምድ ከማድረግ ውጪ ጨዋታዎች ላይ የማትሳተፍ ይሆናል። በጄቪ ደብሊው ክለብ ተጫዋችና የደቡብ አፍሪካ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን አምበል የሆነችው ጃኒን ቫን ዋይክ በበኩሏ፤ ክለቡ ሰመኒያን በማስፈረሙ የተሰማትን ደስታ ገልጻለች። «በዓለም ላይ ያሉ የሴት እግር ኳስ ክለብ ተጫዋቾች ሁሉ አትሌቷ ስፖርቱን በመቀላቀሏ ደስተኛ ናቸው። በቅድሚያ ለመጫወት የመረጠችው ክለብ ደግሞ በእግር ኳስ ስፖርት ምን ያህል ብቃት እንዳላት ማሳየት የሚችል ነው። ከአሰልጣኛችን ጋር በመሆን ስልጠናዋን በቅርበት እየተከታተልኩም ነው፤ እንደተመለከትኩት ከሆነም በ2020 ምርጥ ተጫዋች ትሆናለች» ስትልም ተስፋዋን ገልጻለች።አዲስ ዘመን መስከረም 5/2012ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=18116
309
2ስፖርት
የሁለቱ ኢትዮጵያዊያን ፉክክር በቶሮንቶ ማራቶን ይጠበቃል
ስፖርት
September 16, 2019
18
 በዓለም ላይ ታላላቅና ዝነኛ የጎዳና ላይ ውድድሮች በአብዛኛው በጥቅምት ወር ይካሄዳሉ። ከእነዚህ መካከል አንዱ የሆነውና በሰሜናዊው የአሜሪካ ክፍል በዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር የወርቅ ደረጃ ከተሰጣቸው አራት ማራቶኖች መካከል አንዱ የካናዳው ቶሮንቶ ማራቶን ነው። በተለያዩ ርቀቶች በሚካሄደው በዚህ የጎዳና ላይ ሩጫ ከ50 ሃገራት የተወጣጡ 26ሺ የሚሆኑ አትሌቶችና ጎብኚዎች እንደሚሳተፉበት ይጠበቃል። በዚህ ማራቶን ላይ በርካቶች ፈጣን እና ምርጥ ሰዓት የሚያስመዘግቡበት በመሆኑ እንዲሁም ለቦስተን ማራቶን እንደ መግቢያ ስለሚታይ በርካታ ታዋቂ አትሌቶች ይሳተፉበታል። በቀጣዩ ወር አጋማሽ በሚካሄደው 20ኛው ዙር ውድድር ላይም ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ተሳታፊ እንደሚሆኑ ታውቋል። በዚህ ውድድር ጠንካራ ተፎካካሪ ትሆናለች በሚል ስትጠበቅ የነበረችው አትሌት ትዕግስት ግርማ ከውድድሩ ራሷን ማግለሏን ቀድማ አስታውቃለች። የኦቶዋ ማራቶን አሸናፊዋ ትዕግስት በውድድሩ ራሷን ለማግለሏ እንደ ምክንያት የተነሳውም በጥሩ ብቃት ላይ አለመሆኗ ነው። በዚም ምክንያት ፉክክሩ በሁለቱ ኢትዮጵያዊያን መካከል እንደሚሆን ነው የሚጠበቀው። ብሩክታይት ደገፋ እና በላይነሽ ኦልጂራም በቶሮንቶው ማራቶን በሴቶች መካከል በሚካሄደው ውድድር ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶች ናቸው። እአአ የ2013 የዓለም ሻምፒዮና የ10ሺ ሜትር እንዲሁም በዚያው ዓመት በተካሄደው ሃገር አቋራጭ ሻምፒዮና የነሃስ ሜዳሊያ ባለቤቷ በላይነሽ ውድድሩን በበላይነት ታጠናቅቃለች የሚል ቅድመ ግምትም አግኝታለች። አትሌቷ እአአ በ2012 የለንደን ማራቶን ሃገሯን ወክላ በተካፈለችበት ማራቶን 2:21:53 የሆነ እና እስካሁንም የግሏ ፈጣን ሰዓት አስመዝግባለች። በዚህ ውድድር ሌላኛዋ ተፎካካሪ እና አሸናፊ የመሆን ዕድል እንዳላት ግምት የተሰጣት ብሩክታይት 2:23:28 የሆነ ፈጣን ሰዓት አላት። የአትሌቶቹ የግል ፈጣን ሰዓት በሁለት ደቂቃዎች የሚበላለጥ ይሁን እንጂ፤ በመካከላቸው ብርቱ ፉክክር እንደሚደረግ የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር በድረ ገጹ ጠቁሟል። ባለፈው ዓመት በተካሄደው የሂውስተን ማራቶን የተገናኙት ሁለቱ አትሌቶች በብሩክታይት ስድስት ሰከንዶች የበላይነት ነበር ፉክክራቸው የተጠናቀቀው። በአንድ ቡድን ውስጥ የታቀፉት አትሌቶቹ የጋራ ስልጠና ከሌላቸው በቀር አንድ ላይ እንደማይለማመዱም ነው በላይነሽ የገለጸችው። አትሌቷ ከድረገጹ ጋር በነበራት ቆይታ፤ «እኔ ቡድኑን የተቀላቀልኩት በቅርቡ ስለሆነ ጓደኛሞች አልሆንም። በሂውስተን ስንገናኝ ግን ተግባቢ ሰው መሆኗን ተረድቻለሁ፤ ስለዚህ ወደፊት ጓደኛሞች እንደምንሆን እገምታለሁ» ብላለች። አትሌቶቹ በአሰልጣኝ ገመዱ ደደፎ በሳምንት ለሁለት እና ሶስት ጊዜያት በሰንዳፋ የሚሰለጥኑ ቢሆንም፤ እንዲህ ዓይነቱ አለመግባባት ያልተለመደ እና ከፉክክር ስሜት የሚመነጭ እንደሆነም ነው በዘገባው የተጠቆመው። በዚህ ዓመት የሂውስተን ግማሽ ማራቶንን 1:02:09 በሆነ ሰዓት የገባችው ብሩክታይት በበኩሏ ውድድሩን በጥሩ ሰዓትና በአሸናፊነት ለማጠናቀቅ ማለሟን ነው የገለጸችው።አዲስ ዘመን መስከረም 5/2012ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=18122
319
2ስፖርት
የስፖርት ህገወጥነትን የመከላከል ህብረት
ስፖርት
September 23, 2019
13
 ከዓመታት በፊት የስፖርት አበረታች ቅመሞች (ዶፒንግ) ተጠቃሚነት ጉዳይ ጎልቶ የሚሰማ የዓለም ዜና ነበር። በርካታ አትሌቶችና ሃገራትም ስፖርት ላይ ጥቁር ነጥብ በጣለው በዚሁ ምክንያት ለዕገዳ እና ቅጣት ተዳርገዋል። ኢትዮጵያን የመሳሰሉ ሃገራትም ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጠንካራ ማስጠንቀቂያ እንደደረሳቸው ይታወሳል።በዚህ ረገድ በኢትዮጵያ ለዓመታት የተከናወነው ሥራ በርካታ መሻሻል ቢያሳይም፤ ሙሉ ለሙሉ ለመቆጣጠር ከፍተኛ ርብርብ እንደሚያስፈልግ ይታመናል፡፡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የጸረ-አበረታች ቅመሞች ጽህፈት ቤት ዋነኛው የጉዳዩ ተዋናይ ይሁን እንጂ፤ የስፖርት ህገ-ወጥነትን የመከላከልና የመቆጣጠር ጥረቱን ከሌሎች ተቋማት ጋር በህብረት እያከናወነ ይገኛል። ከቀናት በፊትም ሁለተኛውን የጸረ-አበረታች ቅመሞች የባለ ድርሻ አካላት ጉባኤ አካሂዷል። በመድረኩ ላይም ባለድርሻዎቹ በተጠናቀቀው ዓመት ያከናወኑትን እንዲሁም የአዲሱ ዓመት ዕቅዳቸውን አስታውቀዋል። ከአበረታች መድሃኒት ጋር በተያያዘ በተለይ የሚነሳው የአትሌቲክስ ስፖርት መሆኑ ይታወቃል። ኢትዮጵያም በዚህ ስፖርት በዓለም አቀፍ ደረጃ የተሻለ ተሳትፎና ውጤት ያላት እንደመሆኑ ትኩረት የሚደረገው በዚህ ስፖርት ላይ ነው። በመድረኩም ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተጠናቀቀው ዓመት ክንውኖቹን እንዲሁም የእዚህ ዓመት ዕቅዱን አቅርቧል። ፌዴሬሽኑ ከጽህፈት ቤቱ ጋር በቅርበት የሚሰራ ሲሆን፤ የመገኛ ቦታ አድራሻ፣ ቅድመ ውድድር የጤና ምርመራ እንዲሁም በምርመራ ላይ ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር ላይ በጋራ ሲሰሩ መቆየታቸው ተነስቷል። አበረታች ቅመሞች ተጠቃሚነትን ለመከላከል አትሌቶች እንዴት በተፈጥሯዊ መንገድ ብቃታቸውን ማሳደግ ይችላሉ? በሚልም ስልጠና ተሰጥቷል። በዚህም ኢትዮጵያዊ ይዘት ያላቸውና በሽታን ሊከላከሉ የሚችሉ የምግብ ዓይነቶች እንደየ ርቀቱ ተዘጋጅቶ እንዲያውቁት እየተደረገ ነው። የምክር አገልግሎት ለአትሌቶች፣ አሰልጣኞች እንዲሁም ሌሎች ባለሙያዎች በመስጠት ረገድ በዓመቱ 84 ባለሙያዎችን ተደራሽ ማድረግ ተችሏል። በዓለም አቀፉ ተቋም የሚከለከሉ ቅመሞች ዝርዝርንም ለሚመለከታቸው አካላት እንዲደርስ ተደርጓል። በዓመቱ በተካሄዱ ሃገር፣ አህጉር እና ዓለም አቀፍ ውድድሮች ለሚካፈሉ አትሌቶች እንዲሁም ድጋፍ ሰጪ አካላትም የግንዛቤ ማስጨበጫ በፌዴሬሽኑ ሲሰጥ መቆየቱም ተጠቁሟል። በተያዘው ዓመትም ፌዴሬሽኑ እአአ በ2020 ለሚካሄደው የጃፓን ኦሊምፒክ ከወዲሁ የተለያዩ ስራዎች እያከናወነ እንዳለ ተጠቅሷል። የአትሌቶችን አጠቃላይ መረጃ በአንድ ቋት ለመያዝ፣ የስፖርት ስነ- ምግብና ህክምና ስርዓትንም ለማጠናከር ታስቧል። የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችንም ማስፋት፣ በየጊዜው የሚቀየሩ ህጎችን ተከታትሎ ለተገቢው አካል ማሳወቅ እንዲሁም ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከርም ታቅዷል። በክብደት ማንሳት ስፖርት በ12ኛው የሞሮኮ ራባት የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ላይ የብሄራዊ ቡድኑ ገጠመኝም በመድረኩ ተንጸባርቋል። በዚህ ስፖርት ከዚህ ቀደም በተካሄደ ውድድር በርካታ የአበረታች ቅመም ተጠቃሚዎች መገኘታቸውን ተከትሎ ስፖርቱ በልዩ ሁኔታ የሚታይ ሆኗል። ፌዴሬሽኑ ግን ከዚህ በተቃራኒ በቀድሞው አካሄድ ነበር ቡድኑን ይዞ ወደ ውድድሩ ያቀናው። በዚህ ምክንያትም ከውድድር ውጪ ሊሆን ችሏል። በመሆኑም ፌዴሬሽኑ በዓለም አቀፉ ህግ መሰረት ለመንቀሳቀስ የተለያዩ ስራዎች በመተግበር ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል። የተሟላ ስፖርተኞችን መኖሪያና ስልጠና አድራሻ በመመዝገብ ለዓለም አቀፉ አካል በማሳወቅ ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ ሌሎች መሰል ህጎችን ወደ ተግባር ለመለወጥ እየተራመደ ይገኛል። ከዚህ ቀደም ከአበረታች ቅመም ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያ መድሃኒቶቹ በግልጽ የሚሸጥ መሆኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ መነጋገሪያ ነበር። ሁለት መድሃኒት መሸጫ መደብሮችም በዚሁ ምክንያት መታገዳቸው የሚታወስ ነው። በመሆኑም መድሃኒት መሸጫ መደብሮች ከጽህፈት ቤቱ ጋር በቅርበት የሚሰሩ ባለድርሻ አካል ሆነዋል።ይህንን ተከትሎም የኢትዮጵያ ፋርማሲዎች ማህበር ጉዳዩን እንዳስጠና በመድረኩ ላይ ተገልጿል። ዳሰሳዊ ጥናቱም በአምስት ክፍለ ከተሞች ላይ በሚገኙ ፋርማሲዎች በሚሰሩ 336 ባለሙያዎች ላይ ነው የተደረገው። በዚህም ስለ አበረታች መድሃኒት ምን ያህል ዕውቀት አላቸው የሚለውን ለማየት እንደተሞከረው ከፍተኛ የዕውቀት ክፈተት መኖሩ ተረጋግጧል። አትሌቶች በዓለም አቀፉ የጸረ አበረታች ቅመሞች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ(ዋዳ) የተከለከሉ መድሃኒቶችን ስለመፈለጋቸው በተደረገው መጠይቅም 33ነጥብ4 በመቶ የሚሆኑት «አዎ» የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። ከእነዚህ ውስጥ ስምንት የሚሆኑት ቢያንስ በሳምንት ለአንድ ጊዜ ሌሎቹ ደግሞ በወራት ውስጥ ይህ ዓይነት ጥያቄ ይቀርብላቸዋል። ከዚህ በመነሳትም ወደፊት የፋርማሲ እና የጤና ባለሙያዎች ላይ ከፍተኛ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ ሊከናወን እንደሚገባ በመድረኩ ተመላክቷል። በመደበኛ ትምህርት ካሪኩለም በውስጥ ቢካተትም፤ በፋርማሲ ትምህርት ካሪኩለም ውስጥ ግን አለመኖሩም ነው የተጠቆመው። በመሆኑም ባለሙያዎች ስለጉዳዩ እንዲረዱ ለማድረግ ጽህፈት ቤቱ በዚህ ላይ መስራት ይገባዋል። እንደ ሙያ ማህበርም የኢትዮጵያ ፋርማሲ ትምህርት ቤቶች ህብረት የሚሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል። ከህክምና ሙያ ማህበራት ጋር በመስራትም የህክምና ባለሙያዎች መድሃኒት ሲያዙ ይህንን ነገር ከግምት ማስገባት ይቻላል። ዓለም አቀፉ የጸረ አበረታች ቅመሞች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ የሚያወጣውን የተከለከለ መድሃኒት ዝርዝር በየመደብሩ እና ጤና ተቋማት መኖር እንዳለበትም ተነስቷል። በተጨማሪ በዓለም ላይ ከጦር መሳሪያ ቀጥሎ በህገወጥ መንገድ የሚዘዋወረው መድሃኒት ከመሆኑ ጋር በተያያዘ እንደ ሃገር ከፍተኛ ቁጥጥር ማድረግ አስፈላጊ እንደሆነም አጽንኦት ተሰጥቷል። በኢትዮጵያ ብሄራዊ የጸረ አበረታች ቅመሞች ጽህፈት ቤት ዳይሬክተር አቶ መኮንን ይደርሳል፤ በ2011ዓም በባለድርሻ የተከናወኑ ተግባራትን በግብዓትነት መያዝ በዚህ ዓመት የተጠናከረ ስራ ለመስራት እንደሚያግዝ ይገልጻሉ። በመሆኑም በየጊዜው በመገናኘትና የጋራ አቅጣጫ በማስቀመጥ መስራት ተገቢ ይሆናል። በቀጣይም ከሌሎች የሙያ ማህበራት ጋር ለመስራት ፎረሞችን የማቋቋም ዕቅድ ተይዟል። በዚህ የህብረት እንቅስቃሴም ፎረሞቹ የራሳቸውን ግብዓት በመስጠት እንዲሁም የድርሻቸውን በመወጣት አወንታዊ ስራ ማከናወን እንደሚቻል ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።አዲስ ዘመን መስከረም 12/2012 ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=18986
645
2ስፖርት
ተጠባቂው የ‹‹ውሃ ሰማያዊዎቹ›› እና የ‹‹የስፐርሶቹ›› ፍልሚያ
ስፖርት
April 19, 2019
36
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 35ኛው ሳምንት ጨዋታዎች ነገና እሁድ የሚካሄዱ ሲሆን፤ የሊጉ የሳምንቱ ትልቁ ጨዋታ «ውሃ ሰማያዊዎቹን» ማንቸስተር ሲቲንና «ስፐርሶችን» ቶተነሃም ሆትስፐርስን የሚያገናኘው ግጥሚያ ቅዳሜ በአንፊልድ ስታዲየም ከቀኑ ስምንት ሰዓት ተኩል ይካሄዳል። የዓለማችን ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በያዝነው ዓመትም የሊጉን ዋንጫ ማን ያነሳ ይሆን የሚለውን ግምት ለመስጠት አዳጋች እንደሆነና አጓጊነቱን እንደያዘ ቀጥሏል፡፡ ሊጉ ሊጠናቀቅ አራት ጨዋታዎች የቀሩት ቢሆንም የሊጉን ዋንጫ ማን ያነሳ ይሆን የሚለው የዓለምን ቀልብ የገዛ ጉዳይ ነው። በመሆኑም የሊጉን ዋንጫ ማን ያነሳ ይሆን የሚለውን ለመገመት ፍንጭ ሰጭና፤ ክለቦቹ ለሚቀጥለው ዓመት በሻምፒዮንስ ሊጉ ለመሳተፍ ተስፋ የሚሰንቁበትን ውጤት የሚያስመዘግቡበት ጨዋታ በመሆኑ ከመቼውም ጊዜ የሁለቱ ክለቦች ፍልሚያ ተጠባቂ እንዲሆን አድርጎታል። የአምናው የሊጉ ሻምፒዮና ማንቸስተር ሲቲ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እያለው ከሊጉ መሪ ሊቨርፑል በሁለት ነጥብ ዝቅብሎ የተቀመጠ ሲሆን፤ ከስፐርሶቹ ጋር በሚያደርጉት ፍልሚያ የሽንፈትን ጽዋ የሚጎነጭ ከሆነና፤ የመርሲሳይዱ ሊቨርፑል ያለበትን ጨዋታ የሚያሸንፍ ከሆነ፤ ከመርሲ ሳይዱ ሊቨርፑል ጋር ያለው የነጥብ ልዩነት ወደ አምስት ከፍ የሚል ይሆናል። ይህ ከሆነ ውሃ ሰማያዊዎቹ ማንቸስተር ሲቲ የዋንጫ ተስፋቸው አጣብቂኝ ውስጥ ስለሚገባ ከቶተነሃም ጋር የሚያደርጉትን ጨዋታ ተጠባቂ እንዲሆን አድርጎታል። በሌላ በኩል ስፐርሶቹ ቶተነሃም ሆትስፐርስ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ከአንድ እስከ አራት ያለውን ደረጃ ይዞ በማጠናቀቅና ለሚቀጥለው ዓመት በሻምፒዮንስ ሊጉ ተሳታፊ ለመሆን የሚያበቃውን ውጤት ለማስመዝገብ ይህን ግጥሚያ ማሸነፍ የግድ ይለዋል። ምክንያቱም በዚህ ጨዋታ ስፐርሶቹ ነጥብ የሚጥሉ ከሆነና አርሴናል፣ ማንቸስተር ዩናይትድና ቼልሲ ያለባቸውን ጨዋታ ካሸነፉ ሶስተኛ ደረጃነቱን ለ«መድፈኞቹ»፣ ለ«ሰማያዊዎቹ» ወይም ለ«ቀያይ ሰይጣኖቹ» በመልቀቅ ወደ ስድስተኛ ደረጃ የሚንሸራተት ይሆናል። እንዲሁም ከመድፈኞቹ አርሴናልና ከሰማያዊዎቹ ቼልሲ ጋር ያለው የነጥብ ልዩነት ወደ ሁለት ከፍ የሚል ይሆናል። ስለዚህ ስፐርሶቹ በሻምፒዮንስ ሊጉ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ሶስተኛ ደረጃን ላለመልቀቅና ከአርሴናል፣ ከማንቸስተር ዩናይትድ እና ከቼልሲ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ለማስፋት ከማንቸስተር ሲቲ ጋር የሚያደርጉት ትንቅንቅ ጨዋታውን ተጠባቂ እንዲሆን ያደረገ ሌላኛው ምክንያት ነው። ከዚህ ባለፈ ‹‹ጨዋታውን ማን ያሸንፋል›› የሚለውን ግምት ለመገመት በጣም አዳጋች ያደረገው፤ ሁለቱም ክለቦች ከቀናት በፊት ባደረጉት የሻምፒዮንስ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ የደርሶ መልስ ፍልሚያ ቶተነሃሞች በሜዳቸው አንድ ለባዶ እንዲሁም ከሜዳቸው ውጭ ተጉዘው በአንፊልድ ስታዲየም በማንቸስተር ሲቲ አራት ለሶስት ቢሸነፍም ከሜዳ ውጭ ብዙ ጎል ባገባ በሚለው ህግ ወደ ቀጣይ ዙር ማለፉን አረጋግጧል፡፡ ስለዚህ ሁለቱ ክለቦች በ11 ቀናት ውስጥ ለሦስተኛ ጊዜ የሚገናኙ ሲሆን፤ ስፐርሶቹ በሊጉ ጨዋታ ዳግም ውሃ ሰማያዊዎቹን አንገት ያስደፉ ይሆን የሚለው የስፖርት ቤተሰቡ ጨዋታውን በጉጉት እንዲጠብቀው አድርጎታል። ሲቲዎች ባለፈው ሳምንት በሴልሁረስት ፓርክ ከክሪስታል ፓላስ ጋር ባደረጉት የሊጉ ጨዋታ ክሪስታል ፓላስን በሜዳው ሶስት ለአንድ የረቱ ሲሆን፤ ስፐርሶቹ በአንጻሩ ሀደርስፊልድ ታውንን 62ሺ 62 ተመልካች በሚይዘው አዲሱ ስታዲየም የጎል ናዳ በመውረድ አራት ለባዶ ማሸነፉ ይታወሳል። ስለዚህ ሁለቱም ክለቦች በሊጉ እያሳዩት ባለው አስደናቂ ብቃትና ወቅታዊ አቋም ማን ያሸንፍ ይሆን የሚለው ጨዋታውን ተጠባቂ እንዲሆን ተጨማሪ ምክንያቶች ናቸው፡፡ በአጠቃላይ ነገ በፕሪሚየር ሊጉ ስድስት ጨዋታዎች ሲካሄዱ፤ ከነዚህ መካከል ዌስት ሃም ዩናይትድ 60ሺ ተመልካች በሚይዘው በለንደን ስታዲየም ሌስተር ሲቲን የሚያስተናግድበትና ኒውካስትል ዩናይትድ በሴንት ጀምስ ፓርክ ስታዲየም ከሳውዝ አምፕተም ጋር የሚያደርጉት ግጥሚያዎች ይጠቀሳሉ፡፡ እሁድ ዕለት ሊጉ ቀጥሎ ሲውል ሶስት ጨዋታዎች የሚካሄዱ ሲሆን፤ ኢቨርተን በጉዲሶን ፓርክ ስታዲየም ቀያይ ሰይጣኖቹን ሲያስተናግድ፤ መድፈኞቹ አርሴናል በኢሚሬትስ ስታዲየም ከክሪስታል ፓላስ ይፋለማሉ። እንዲሁም ወራጅ ቀጠና ላይ የሚገኘው ካርዲፍ ሲቲ በሜዳው በደረጃ ሰንጠረዡ አናት ላይ ከተቀመጠው ሊቨርፑል ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ይገኝበታል፡፡ ፕሪሚየር ሊጉን የመርሲሳይዱ ሊቨርፑል በ85 ነጥብ ሲመራ፤ ማንቸስተር ሲቲ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እያለው በ83 ነጥብ ይከተላል። ስፐርሶቹ ቶተነሃም ሆትስፐርስ በ67 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ሲይዝ፤ መድፈኞቹ አርሴናል በ66 ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዟ ይከተላል። በአንጻሩ ካርዲፍ ሲቲ፣ ፉልሃም እና ሀደርስፊልድ ታውን ደግሞ ከ18ኛ እስከ 20ኛ ያሉትን የመጨረሻዎቹን ሦስት ደረጃዎች ይዘው ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛሉ፡፡ የፕሪሚየር ሊጉን ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነት የሊቨርፑሉ ሙሀመድ ሳላህ እና የማንቸስተር ሲቲው ኩን አጉኤሮ በእኩል 19ጎሎች ሲመሩ፤ የአርሴናሉ ፔር ኢሜሪክ ኦባሚያንግና የሊቨርፑሉ ሴኔጋላዊው ኮከብ ሳዲዮ ማኔ በእኩል 18 ጎሎች በሁለተኛ ደረጃ ተቀምጠዋል። የቶተነሃሙ ሄሪ ኬንና የማንቸስተር ሲቲው ራሂም ስተርሊንግ በእኩል 17 ጎሎች ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን እየተከተሉ ይገኛሉ።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 11/2011 በ
https://www.press.et/Ama/?p=9214
566
2ስፖርት
«በመልሱ ጨዋታ ውጤት ለመቀልበስ የተቻለንን እናደርጋለን» -ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ
ስፖርት
September 24, 2019
18
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለ2020 የቻን አፍሪካ ዋንጫ የመጨረሻ የማጣሪያ ጨዋታ በሩዋንዳ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ሽንፈትን አስተናግዷል። በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ ሁለቱም ቡድኖች ለግብ የቀረበ ተደጋጋሚ ሙከራ ቢያደርጉም ኳስና መረብ ማገናኘት ሳይችሉ ለረፍት ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል። በተለይም ዋልያዎቹ ኳስን ተቆጣጥሮ በመጫወት ረገድ የተሻለ እንቅስቃሴ ቢያደርጉም ቡድኑ ከዚህ ቀደም እንደተለመደው የአጨራረስ ድክመቱን ማሻሻል ባለመቻሉ ግብ ሳይቆጠር ቀርቷል። በሁለተኛው አጋማሽ መከላከልን መሰረት ያደረጉት ሩዋንዳዎች በ60ኛው ደቂቃ ላይ በኤርነስት ሴጉራ አማካኝነት ባስቆጠሯት ድንቅ የአክሮባት ግብ የጨዋታው ድባብ ተቀይሯል። ዋልያዎቹ ግብ ከማስቆጠር ችግር ባሻገር ከዚህ ቀደም በነበሩት ጨዋታዎች ከቆመ ኳስ በቀላሉ የሚቆጠርባቸውን ግብ ማስቀረት እንዳልቻሉ ለመታዘብ ተችሏል። በተደጋጋሚ ወደ ተቃራኒ ግብ ክልል የመቅረብ አጋጣሚዎችን ወደ ፍሬ የሚቀይር ጨራሽ አጥቂ ማጣትም የቡድኑ ቁልፍ ችግር ሆኖ ተስተውሏል። ዋልያዎቹ ከጨዋታው በፊት በአጥቂው ክፍል የነበረባቸውን ከፍትት ማስተካከል ካልቻሉ ከፍተኛ ፈተና ሊገጥማቸው እንደሚችል ቢነገርም፤ ችግሩን ለመቅረፍ ሲቸገሩ ታይቷል። ዋልያዎቹ በዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ከሌሴቶ፣ በቻን ማጣሪያ ደግሞ ከጅቡቲ ጋር በነበራቸው ጨዋታ ጥሩ የሚባል እንቅስቃሴ ቢያሳዩም ኳስን ከመረብ የማዋሃድ ውስንነቶች በተደጋጋሚ ተስተውሎባቸዋል። በሜዳ ላይ እንቅስቃሴ የተሻሉ ነገሮች ቢታዩም ተጫዋቾቹ ያገኟቸው የጎል አጋጣሚዎች የመጠቀም ክህሎታቸው ደካማ መሆን ብሔራዊ ቡድኑን ዋጋ እያስከፈሉት እንደሚገኙ ለመታዘብ ተችሏል። በአንፃሩ መከላከልን መሰረት አደርገው የገቡት ሩዋንዳዎች ያገኙትን አጋጣሚ ወደ ግብ በመቀየር በመቻላቸው ከሜዳቸው ውጭ ሦስት ነጥብ ይዘው ለመውጣት ችለዋል። ከጨዋታው በኋላ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ በሰጡት አስተያየት ‹‹በጨዋታው ተጫዋቾቼ የሚችሉትን አድርገዋል›› በማለት ተጫዋቾቹን ለመከላከል ጥረት አድርገዋል። አሰልጣኙ በተለይም በመጀመሪያው አጋማሽ ሙሉ ለሙሉ ተጋጣሚያቸው በመከላከለ ላይ ያመዘነ ጨዋታ መከተሉን በማስታወስ፣ ዋልያዎቹ ይሄንን ሰብሮ በመግባት የተፈጠሯቸውን እድሎች መጠቀም ባለመቻላቸው በሥነ ልቦና ረገድ እንዲወርዱ ማድረጉን ተናግረዋል። በሁለተኛው አጋማሽ ግን ክፍተቶችን አርሞ ብልጫ ወስዶ ለመጫወት ብዙ ጥረት መደረጉን አሰልጣኙ ገልፀዋል። ያም ሆኖ አልተሳካም። በሁለተኛው አጋማሽ ተቀይረው የገቡ ተጫዋቾችም ልዩነት እንደፈጠሩ አሰልጣኙ አብራርተዋል። «በታክቲክ ያደረግነው ለውጥ ጥሩ እንቅስቃሴ ማምጣት እንድንችል አድርጎናል። በአጠቃላይ በጨዋታው ተጫዋቾቼ የሚችሉትን አድርገዋል። እንደተለመደው በግብ አካባቢ ስንደርስ መረጋጋት ባለመኖሩ ምክንያት የሳትናቸው ኳሶች ዋጋ አስከፍለውናል። እነርሱ ከቆመ ኳስ በተገኘ ዕድል ግብ ማስቆጠር ችለዋል።» በማትም አስተያየታቸውን በስፍራው ለነበሩ መገናኛብዙሃን ነግረዋል። አሰልጣኙ አክለውም ቡድናቸው በዚህ ጨዋታ እንኳን ድል ባይቀናውም በመልሱ ጨዋታ ውጤት ለመቀልበስ እንደሚሰሩ ተናግረዋል። «በሜዳችን በነበረን ጨዋታ ብዙም ብልጫ ሳይወሰድብን በጥቃቅን ስህተት ነው ግቡ የተቆጠረብን። ከዚህ ውጭ ግን አስፈሪ የሚባል ነገር አልገጠመንም ። በመሆኑም በመልሱ ጨዋታ ከዚህ በተሻለ ተንቀሳቅሰን ውጤት ይዘን ለመምጣት የተቻለንን እናደርጋለን።›› በማት አሰልጣኝ አብረሃም ቃል ገብተዋል። በቀጣይም ቡድኑ ከቆመ ኳስ በቀላሉ ግብ የሚቆጠርበትን ችግር ለማስተካከል ጠንክረው እንደሚሰሩ አብራርተዋል። የአጨራረስ ችግሮቻቸውንም በሚገባ በመገንዘብ ድክመቶችን አርሞ በመልሱ ጨዋታ የተሻለ ውጤት ለማምጣት ጥረት እንደሚያደርጉ ተናግረዋል። በተለይም ቡድኑ በሥነ ልቦና ላይ ያሉበትን ክፍተቶች በተለየ መልኩ አሻሽሎ የመልሱን ጨዋታ ውጤት ለመቀልበስ እንደሚዘጋጅ አብራርተዋል። የሩዋንዳ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ቪሴንት ሚሻሚ በጨዋታው ዙሪያ በሰጡት አስተያየት ‹‹ተጫዋቾቼ በጨዋታው ላሳዩት ጥሩ እንቅስቃሴ ማመስገን እፈልጋለሁ። ጥሩ ተከላክለናል ያገኘነውን እድልም ተጠቅመንበታል›› ብለዋል። የኢትዮጵያን ብሔራዊ ቡድን ማሸነፍ ቀላል ነገር እንዳልሆነ የተናገሩት አሰልጣኝ ሚሻሚ ለተጋጣሚያቸው ትልቅ ክብር እንዳላቸው ተናግራዋል። በጨዋታው ውጤት በጣም ደስተኛ መሆናቸውን ያስረዱት አሰልጣኙ ያስመዘገቡት ውጤት የሚገባቸውና አንድ ደረጃ ከፍ የሚያደርጋቸው መሆኑንም አስረድተዋል። አሰልጣኙ ቀሪ ጨዋታ እንዳለ በማስታወስ ከጥሩ ቡድን ጋር መጫወታቸውን አብራርተዋል። ለዚህም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በቴክኒክም፣ በታክቲክም የተቀናጀ ቡድን እንደነበር ጠቅሰዋል::: የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የዕድል ጉዳይ እንጂ ጥሩ ቡድን መሆኑንም አክለዋል። በመቖለ ስቴድየም ተገኝተው ጨዋታውን ለተከታተሉት ደጋፊዎችም አሰልጣኙ ምስጋናቸውን በማቅረብ የመልሱ ጨዋታ በሜዳቸው እንደመሆኑ የበለጠ ጠንካራ ሆነው እንደሚጠብቁ ጠቁመዋል። የመልሱ ጨዋታ ከ27 ቀናት በኋላ በሩዋንዳ ኪጋሊ የሚደረግ ሲሆን፤ በዚህ ጨዋታ በአጠቃላይ ውጤት አሸናፊ የሆነው ቡድን በ2019 ካሩን በምታስተናግደው የቻን ዋንጫ ተሳትፎውን የሚያረጋግጥ ይሆናል። አዲስ ዘመን  መስከረም 13/2012ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=19042
525
2ስፖርት
የብሔራዊ ስቴድየም ሁለተኛ ምዕራፍ ግንባታ በቅርቡ ይጀመራል
ስፖርት
September 24, 2019
22
የበርካታ ዓመታት የኢትዮጵያዊያን ስፖርት ወዳዶች ጥያቄ ነው፤ ዘመናዊ ስታዲየም። ይህንን ተከትሎም በርካታ ክልሎች ደረጃቸውን የጠበቁና ግዙፍ ስታዲየሞችን በማስገንባት ላይ ይገኛሉ። በአዲስ አበባ ከተማ የሚገነባው ብሔራዊ ስታዲየምም ለዚህ ጥያቄ መንግሥት የሰጠው ሌላኛው ምላሽ ነው። እ.ኤ.አ በ2016 የመጀመሪያው ወር የተጀመረው የስታዲየሙ ግንባታ፤ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ መሰረት ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት አጋማሽ የመጀመሪያው ምዕራፍ መጠናቀቅ ነበረበት። አዲስ ዘመን «ግንባታው የት ደርሷል?» ሲል ጠይቋል። በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ስፖርት ኮሚሽን የስፖርት ፋሲሊቲ ዳይሬክተር ኢንጂነር አዝመራው ግዛው፤ ከዚህ ቀደም ለህዝብ ይፋ የተደረገው የመጀመሪያ ዙር ግንባታው 95 በመቶ ላይ መድረሱን ሲሆን፤ አሁን ባለበት ደረጃ 98 ነጥብ 89 በመቶ ደርሶ ሥራው መቆሙን ይገልፃሉ። ይህም ሊሆን የቻለው ውስጣዊው የመም(ትራክ) አካል ሥራ ተጠናቆ ሴንቴቲኩ ከመነጠፉ በፊት ክረምቱ በመግባቱ ለመሥራት አመቺ ባለመሆኑ ነው። በተመሳሳይ የእግር ኳስ መጫወቻ ሜዳ ግንባታው ቢጀመርም ሣሩ እስካሁን አልተተከለም። ለዚህም ምክንያት የሆነው ሁለተኛው ዙር ግንባታ በቅርቡ የሚጀመር ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ከ900 ቀናት እስከ ሁለት ዓመት ከግማሽ ሊፈጅ ይችላል። በዚህ የግንባታ ሂደትም ሣሩ ሊበላሽ እንደሚችል ግምት ውስጥ በማስገባት እንዲዘገይ ተደርጓል። በቀጣይም ቀሪ ግንባታዎች ከተጠናቀቁ በኋላ በመጀመሪያ በተገባው ውል የሣር ተከላ ሥራው የሚቀጥል መሆኑን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል። በዚህ ወቅት የግንባታው ሁለተኛ ምዕራፍ ለማስጀመር ጨረታ ተከፍቶ ቴክኒካዊ ጉዳዮች በአማካሪው ድርጅት በመገምገም ላይ ይገኛሉ። በህጉ መሰረት የጨረታ ሂደቱ 15ቀናት ቢፈጅም፤ አማካሪው ከውጭ ድርጅት ጋር የሚሠራ በመሆኑ ዶክመንቶችን መላላክ የግድ ብሏል፡፡ የግምገማው ውጤት ከተጠናቀቀ በኋላ ያለው ቀሪ ሥራ ስለማያቆይ ሁለተኛው ዙር ግንባታው የሚጀመር ይሆናል። ሁለተኛው ዙር ግንባታም በስታዲየሙ፤ የአደይ አበባ ቅርጽ ያለውን ዙሪያ ጣራ ማልበስ፣ የደህንነትና የድምጽ ሲስተሞችን መዘርጋት፣ የወንበርና ስክሪኖች ገጠማ እንዲሁም የተለያዩ ክፍሎች፣ ቢሮዎችና የመገናኛ ብዙሃን መገልገያ ክፍሎች ሥራን ያጠቃልላል። ከስታዲየሞ ውጭም፤ ቢሮዎች፣ የዕቃ ማከማቻ ክፍሎች፣ የመኪና ማቆሚያና ሄሊኮፕተር ማረፊያ ስፍራዎች፣ ቲያትር ቤት፣ የባድሜንተን እና ሦስት በአንድ መጫወቻ ሜዳዎች፣ ሁለት የመለማመጃ ሜዳዎች እንዲሁም በስታዲየሙ አጠገብ የሚያልፈውን ወንዝ አልምቶ ለመዝናኛ ማዋልን የያዘ ሰፊ ሥራ ይከናወናል። ከመጀመሪያው ምዕራፍ በበለጠ እጅግ ከፍተኛ ሥራዎችን ላካተተው ለዚህ ሥራም በባለሙያዎች ግምታዊ ዋጋ ተተምኖ በጀት መዘጋጀቱን ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡ በዚህም መሰረት የጨረታ ሂደቱ ተጠናቆ አሸናፊው ሲታወቅ ምን ያህል ወጪ እንደሚጠይቅ ይፋ ይደረጋል። በተለያዩ ክልሎች የተገነቡ ስታዲየሞች የመጀመሪያ ዙር ግንባታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ሁለተኛውን ምዕራፍ ለመጀመር ሲቸገሩና ለዓመታትም ባሉበት ግንባታቸው ቆሞ ሲቀር ማየት የተለመደ ነው፡፡ የብሔራዊው ስታዲየም ግንባታ ግን ይህ ዕጣ እንዳይደርሰው መንግሥት በቂ በጀት መመደቡን እና በልዩ ሁኔታ የተያዘ ፕሮጀክት መሆኑን ኢንጂነር አዝመራው አብራርተዋል፡፡ ለዚህ ዓመት ሥራ የሚውለውና ለሁለትና ሦስት ክፍያዎች የሚሆነው በጀትም ፀድቋል። ከዚህ ባሻገር ፕሮጀክቶች ሊዘገዩ ከሚችሉባቸው ምክንያቶች መካከል አንዱ ቴክኒክ ነው፤ ለዚህም ከአማካሪው ጋር በመሆን ሥራውን እንደሚከታተሉ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል። የጨረታ ሂደቱ በቶሎ ተጠናቆ ወደ ሥራ ከተገባ በኋላም ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ካላጋጠመ ግንባታው አይቆምም። ከተያዘለት የጊዜ ገደብ በላይ የቆየው የመጀመሪያው ዙር ግንባታ፤ የውጭ ምንዛሬ እጥረት መግጠሙ ለመዘግየቱ እንደምክንያት የሚነሳ ነው። ተቋራጩ ውል ከገባ በኋላም በቦታው የነበሩ ህገወጥ ግንባታዎች እስኪነሱ ድረስ ጊዜ መውሰዱንም ዳይሬክተሩ ያስታውሳሉ። በዚህም ጊዜው ሁለቴ የተራዘመ ሲሆን አሁን የቀሩት ሥራዎች ግን በስምምነት የሚቆዩ ናቸው። ከዚህ በኋላ ለሚኖረው ሥራ ፈታኝ ሊሆኑ የሚችሉ ሁኔታዎች አሉ። ከእነዚህም መካከል አንዱ ከትራንስፖርት ጋር በተያያዘ መንግሥት ያወጣው ሕግ ነው። ግንባታው በ480ሺ ሜትር ስኩዌር ቦታ ላይ የሚያርፍ ሲሆን፤ በዚህም እስከ 1 ሚሊየን ሜትር ኪዩብ አፈር በቁፋሮ ሊወጣ ይችላል። ይህንን አፈር የሚያወጡት ከባድ ተሽከርካሪዎች ደግሞ በምሽት ብቻ እንዲሠሩ መደረጉ ጊዜውን ሊያራዝመው ይችላል። በመሆኑም በልዩ ሁኔታ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር በመነጋገር ማስፈቀድ አስፈላጊ ይሆናል። ሌላው አሁንም ድረስ ከግንባታው ስፍራ ያልተነሱ ቤቶች መኖራቸው ነው። ከሚመለከታቸው አካል ጋር በመሆን ቤቶቹ የማይነሱ ከሆነ አሁንም ከውል በኋላ በድጋሚ ችግር ሊገጥም ይችላል የሚል ሥጋት አለ። በመጨረሻም፤ የሁለተኛው ዙር ግንባታ ቅድመ ዝግጅት በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝና መንግሥትም በልዩ ሁኔታ ድጋፍ ማድረጉን ዳይሬክተሩ ይገልፃሉ። ፕሮጀክቱ የኢትዮጵያ ህዝብ በመሆኑ እንዲሁም ከተማዋን አዲስ ገጽታ ስለሚያላብስ መንግሥትና ደጋፊ ተቋማትም ድጋፋቸውን አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡ አዲስ ዘመን  መስከረም 13/2012ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=19046
554
2ስፖርት
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 20ኛ ሳምንት ጨዋታዎች
ስፖርት
April 12, 2019
29
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ20ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በመዲናዋና በክልል ከተሞች ነገና እሁድ ስምንት ጨዋታዎች የሚካሄዱ ሲሆን፤ የሊጉ የሳምንቱ ትልቁ ጨዋታ የጣና ሞገዶቹ ባህርዳር ከተማ ከመቐለ 70 እንደርታ የሚያገናኘው ግጥሚያ እሁድ ሚያዝያ 6 ቀን በባህርዳር ስታዲየም ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ይካሄዳል። ነገ አንድ ጨዋታ ክልል ላይ ሲካሄድ፤ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ በሜዳው መከላከያን ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ያስተናግዳል። ሊጉ እሁድ ዕለት ቀጥሎ ሲውል ሰባት ጨዋታዎች የሚካሄድ ሲሆን፤ ወራጅ ቀጣና ላይ የሚገኘው ደደቢት ከድሬዳዋ ከተማ፣ አፄዎቹ ፋሲል ከተማ ከደቡብ ፖሊስ፣ ጅማ ላይ ጅማ አባ ጅፋር ወራጅ ቀጣና ላይ ከሚገኘው ከስሑል ሽረ፣ አዳማ ላይ አዳማ ከተማ ከሃዋሳ ከተማ እንዲሁም ደቡብ ላይ ወላይታ ዲቻ ከኢትዮጵያ ቡና በተመሳሳይ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ሲሆን፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሲዳማ ቡና በዚሁ ዕለት በአዲስ አበባ ስታዲየም ከቀኑ አስር ሰዓት ላይ ፍልሚያቸውን የሚያካሂዱ ይሆናል። ፕሪሚየር ሊጉን መቐለ 70 እንደርታ በ42 ነጥብ፣ ሲዳማ ቡና በ34 ነጥብ እና ፋሲል ከነማ በ33 ነጥብ ከአንድ እስከ ሦስት ያሉትን ደረጃዎች ይዘው በደረጃ ሰንጠረዡ አናት ላይ ተቀምጠዋል። በአንፃሩ ደቡብ ፖሊስ፣ ስሑል ሽረ እና ደደቢት ደግሞ ከ14ኛ እስከ 16ኛ ያሉትን የመጨረሻዎቹን ሦስት ደረጃዎች ይዘው ወራጅ ቀጣና ውስጥ ይገኛሉ፡፡ የፕሪሚየር ሊጉን ኮከብ ጎል አግቢነት የመቐለ 70 እንደርታው አማኑኤል ገብረሚካኤል በ12 ጎሎች፣ የመከላከያው ምንይሉ ወንድሙ በ11ጎሎች እንዲሁም የሲዳማ ቡናው አዲስ ግደይ በ10 ጎሎች ከአንድ እስከ ሦስት ያሉትን ደረጃዎች ይዘው ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነቱን እየመሩ ይገኛሉ።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 4/2011በ
https://www.press.et/Ama/?p=8724
206
2ስፖርት
ሞሮኮና ኮትዲቯር በምድብ አራት ይገናኛሉ
ስፖርት
April 14, 2019
16
ግብፅ የምታዘጋጀው የ2019 የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ድልድል ዓርብ ምሽት በካይሮ ይፋ ሆኗል። በደማቅ ዝግጅቶች ታጅቦ የተከናወነውን የእጣ ማውጣት ሥነሥርዓት የተለያዩ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ሽፋን ሰጥተውታል። የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ድልድሉ በካ ይሮ ከተማ ሲካሄድ ከወዲሁ የበርካቶችን ትኩረት የሳቡ ተጠባቂ ጨዋታዎች የእግር ኳስ ማኅበረሰቡን እያነጋገሩ ይገኛሉ። በምሽቱ ያያ ቱሬ፣ ሬጎቤር ሶንግ፣ ሙስጣፋ ሃጂ፣ ሳሙኤል ኤቶ እና ሌሎች በርካታ የአፍሪካ እግር ኳስ ክዋክብት እጣ የማውጣት ሥነሥርዓቱ ላይ ተሳትፈዋል፡፡ ይህ ደማቅ እጣ የማውጣት ዝግጅት ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ጀምሮ ከትናንት በስቲያ በካይሮ ፒራሚድ አቅራቢያ በሚገኘው ጊዛ በተባለው ስፍራ ተከናውኗል። እጣው ከወጣ በኋላ በምድብ አንድ ግብፅ፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ኡጋንዳ እና ዚምባቡዬ፤ በምድብ ሁለት ናይጄሪያ፣ ጊኒ፣ ማዳጋስካር እና ብሩንዲ፤ በምድብ ሶስት ሴኔጋል፣ አልጄሪያ፣ ኬንያ እና ታንዛኒያ፤ በምድብ አራት ሞሮኮ፣ ኮትዲቯር ፣ ደቡብ አፍሪካና ናሚብያ፤ ቱኒዚያ፣ ማሊ፣ ሞሪታኒያ እና አንጎላ ሲገናኙ በምድብ ስድስት ደግሞ ካሜሮን፣ጋና፣ ቤኒን እና ጊኒ ቢሳኦ ተደልድለዋል፡፡ ሞሮኮ እና ኮትዲቯር ያሉበት ምድብ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል። ይህ ውድድር በኢትዮጵያ አቆጣጠር ሰኔ 14 የሚጀመር ሲሆን ውድድሩ በስድስት ስቴድየሞች ይከናወናል። ግብፅ በ16 ድምፅ የ2019 የአፍሪካ ዋንጫን እንድታዘጋጅ መመረጧ የሚታወስ ነው፡፡ በሰኔ ወር የሚካሄደው አፍሪካ ዋንጫ ለመጀመሪያ ጊዜ 24 ቡድኖች የሚሳተፉበት ውድድር ነው፡፡ ከጥር እና የካቲት ወሮች ውጭ በሰኔና ሀምሌ ወሮች የሚካሄድ የመጀመሪያው አፍሪካ ዋንጫ ያደርገዋል፡፡አዲስ ዘመን ሚያዝያ 6/2011በ
https://www.press.et/Ama/?p=8837
191
2ስፖርት
ተጠባቂው የ«የሊቨርፑል» እና የ«ቼልሲ» ፍልሚያ
ስፖርት
April 12, 2019
40
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 34ኛው ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ፣ ነገ፣ እሁድና ሰኞ የሚካሄዱ ሲሆን፤ የሊጉ የሳምንቱ ትልቁ ጨዋታ «ቀያዮቹን» ሊቨርፑልና «ሰማያዊዎቹን» ቼልሲን የሚያገናኘው ግጥሚያ እሁድ በአንፊልድ ስታዲየም ከምሽቱ አስራ ሁለት ሰዓት ተኩል ይካሄዳል። ጨዋታውን ተጠባቂ የሚያደርገው የመርሲ ሳይዱ ሊቨርፑል ሊጉ እንደአዲስ ከተዋቀረ ከ22 ዓመታት ወዲህ የሊጉን ዋንጫ ለማንሳት የተሳነው ሲሆን፤ በያዝነው የውድድር ዓመት ቀያዮቹ የሊጉን ዋንጫ ለማንሳት ከመቼውም ጊዜ የተሻለ የተጫዋች ስብስብና የተሻለ ወቅታዊ አቋም አለው። በመሆኑም ቀያዮቹ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ አናት ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ «ውሃ ሰማያዊዎቹ» ማንቸስተር ሲቲ ተስተካካይ አንድ ጨዋታ እያለው ከሊቨርፑል በሁለት ነጥብ ዝቅብሎ መቀመጡ ሊቨርፑል በቼልሲ የሚሸነፍ ከሆነ መሪነቱን ለውሃ ሰማያዊዎቹ የሚለቅና የዋንጫ ተስፋው አጣብቂኝ ውስጥ ስለሚገባ ከቼልሲ ጋር የሚያደርጉትን ጨዋታ ተጠባቂ እንዲሆን አድርጎታል። በሌላ በኩል ውሃ ሰማያዊዎቹ ቼልሲ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ከአንድ እስከ አራት ያለውን ደረጃ ይዞ ለማጠናቀቅ ይህን ግጥሚያ ማሸነፍ የግድ ይለዋል። ምክንያቱም በዚህ ጨዋታ ቼልሲዎች ነጥብ የሚጥሉ ከሆነና ቶተነሃም፣ አርሴናልና ማንቸስተር ዩናይትድ ያለባቸውን ጨዋታ የሚያሸንፉ ከሆነ ሦስተኛ ደረጃነቱን ለ«መድፈኞቹ» ወይም ለ«ስፐርሶቹ» አንድ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀራቸው ቼልሲዎች ለእነዚህ ክለቦች ደረጃውን የሚለቁ ሲሆን፤ «ቀያይ ሰይጣኖቹ» አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀራቸው ከቼልሲ ጋር ያላቸውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሁለት ነጥብ ዝቅ የሚያደርጉ ይሆናል። ስለዚህ ቼልሲዎች የሦስተኛ ደረጃን ላለመልቀቅና ከቶተነሃም፣ ከአርሴናልና ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ለማስፋት ከሊቨርፑል ጋር የሚያደርጉት ትንቅንቅ ጨዋታውን ተጠባቂ እንዲሆን ሌላኛው ምክንያት ሆኗል። ከዚህ ባለፈ «ጨዋታውን ማን ያሸንፋል?»የሚለውን ግምት በጣም አዳጋች ያደረገው፤ ሁለቱም ክለቦች ባለፈው ባደረጉት ሁለት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች «ቀያዮቹ» በአንፊልድ ቶተንሃም ሆትስፕርስን ሁለት ለአንድና ከሜዳቸው ውጪ ሳውዝ አምፕተምን ሦስት ለአንድ ያሸነፉ ሲሆን፤ ማክሰኞ ዕለት በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ በአንፊልድ ስታዲየም የፖርቹጋሉን ፖርቶን አስተናግዶ ሁለት ለባዶ ማሸነፍ ችለዋል። ሰማያዊዎቹ ቼልሲዎች በአንፃሩ በስታንፎርድ ብሪጅ ዌስት ሀም ዩናይትድን አስተናገደው ሁለት ለባዶ ያሸነፉ ሲሆን፤ ከሜዳቸው ውጪ ወራጅ ቀጣና ውስጥ ከሚገኘው ካርዲፍ ሲቲ ጋር ባደረጉት ግጥሚያም ሁለት ለአንድ አሸንፈዋል። ስለዚህ ሁለቱም ክለቦች እያሳዩት ባለው አስደናቂ ብቃትና ወቅታዊ አቋም ማን ያሸንፍ ይሆን የሚለው ጨዋታውን ተጠባቂ እንዲሆን ተጨማሪ ምክንያቶች ናቸው፡፡ በአጠቃላይ ዛሬ በፕሪሚየር ሊጉ አንድ ጨዋታ ሲካሄድ ሌስተር ሲቲ ከኒውካስትል ዩናይትድ ምሽት አራት ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን የሚያካሂዱ ይሆናል። እንዲሁም ነገ በፕሪሚየር ሊጉ ስድስት ጨዋታዎች ሲካሄዱ፤ ከነዚህ መካከል ቶተንሃም ሆትስፐርስ በአዲሱ ስታዲየም ሁለተኛ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታውን ወራጅ ቀጣና ውስጥ የሚገኘውን ሀደርስፊልድ ታውን የሚያስተናግድበትና በደረጃ ሰንጠረዡ ስድስተኛ ደረጃ የተቀመጠው ማንቸስተር ዩናይትድ በኦልትራፎርድ ከዌስት ሀም ዩናይትድ ጋር የሚያደርጉት ግጥሚያዎች ይጠቀሳሉ፡፡ እሁድ ዕለትም ሊጉ ቀጥሎ ሲውል ክሪስታል ፓላስ በሜዳው ውሃ ሰማያዊዎቹን ማንቸሰተር ሲቲን የሚያስተናግዱበት ጨዋታ ይገኝበታል፡፡ ሰኞ ዕለትም አንድ ቀሪ የሊጉ ጨዋታ የሚካሄድ ሲሆን፤ ዋትፎርድ ከመድፈኞቹ ምሽት አራት ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን የሚያካሂዱ ይሆናል። ፕሪሚየር ሊጉን የመርሲሳይዱ ሊቨርፑል በ82 ነጥብ ሲመራ፤ ማንቸስተር ሲቲ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እያለው በ80 ነጥብ ይከተላል። ሰማያዊዎቹ ቼልሲ በ66 ነጥብ ሦስተኛ ደረጃን ሲይዝ፤ ቶተንሃም ሆትስፕርስ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እያለው በ64 ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዟ ይከተላል። ካርዲፍ ሲቲ፣ ፉልሃም እና ሀደርስፊልድ ታውን ደግሞ ከ18ኛ እስከ 20ኛ ያሉትን የመጨረሻዎቹን ሦስት ደረጃዎች ይዘው ወራጅ ቀጣና ውስጥ ይገኛሉ፡፡ እንዲሁም የፕሪሚየር ሊጉን ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነት የሊቨርፑሉ ሙሀመድ ሳላህ በ18 ጎሎች ሲመራ፤ የአርሴናሉ ፔር ኢሜሪክ ኦባሚያንግ፣ የስፐርሶቹ ሄሪ ኬንና የሊቨርፑሉ ሴኔጋላዊው ኮከብ ሳዲዮ ማኔ በእኩል 17 ጎሎች ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን እየተከተሉ ይገኛሉ።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 4/2011በ
https://www.press.et/Ama/?p=8717
467
2ስፖርት
የኮከቡ የብሄራዊ ቡድን ቆይታና አስገራሚ ክስተቶች
ስፖርት
April 14, 2019
54
ሮናልዲንሆን ከሌሎች ብራዚላውያን ተጫዋቾች ልቆ ልዩ የሚያደርገው ነገር አለ። ይሄም በብሄራዊ ቡድን ውስጥ በሁሉም የእድሜ ክለል ላይ የሚደረጉ ለዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ መሳተፉ ነበር። በ1997 የፊፋ በግብፅ ባካሄደው ከ17 አመት በታች የዓለም ዋንጫ፣ በ1999 የደቡብ አሜሪካ ወጣቶች የእግር ኳስ ሻምፒዮና ከ20 ዓመት በታች እንዲሁም በዚያው ዓመት በተመሳሳይ ናይጄሪያ ውስጥ በተሰናዳው የዓለም ወጣቶች ዋንጫ ውድድሮች ላይ ተካፋይ ሆኗል። በዚህም የሚከተሉትን ስኬቶች አግኝቷል። ሮናልዲንሆ በብራዚል ብሄራዊ ቡድን በተለያዩ የእድሜ ደረጃዎች የጫወተ ሲሆን በ1999 ኮፓ አሜሪካን ውድድር ላይ ላቲቪያን 3ለ0 በሆነ ውጤት ብራዚል ስታሸንፍ የመጀመሪያውን ዋንጫ ማንሳት ችሏል። በዚያው አመት በተመሳሳይ ወር ላይ በተካሄደው የፊፋ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ላይ በተደረጉት እያንዳንዱ ጨዋታዎች ላይ ከዋንጫ ጨዋታው በስተቀር ለብሄራዊ ቡድኑ ግብ ማስቆጠር ችሏል። በዋንጫ ጨዋታው ላይ ብራዚል በሜክሲኮ የ4ለ3 ሽንፈት ደርሶባት ዋንጫውን ማግኘት ባትችልም ኮንፌዴሬሽን ካፕ ጎቾ የ«ጎልደን ግሎብ» የምርጥ ተጫዋችነት ሽልማት እና የወርቅ ጫማን በግሉ አሳክቷል። በ2000 ላይ ደግሞ ሲድኒ ላይ በተካሄደው ኦሎምፒክ ከብሄራዊ ቡድኑ ጋር በመጓዝ ተጫውቷል። በቅድመ ኦሎምፒክ ውድድሮች ላይም በሰባት ጨዋታዎች 9 ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል። ጎቾ በዓለም ዋንጫ ታሪኩ ከብራዚል ጋር የማይረሳ ትዝታን ያስተናገደው በኮሪያና ጃፓን አስተናጋጅነት በ2002 ዓ.ም ነው። በዚህ ውድድር ላይ በስሙ ሁለት ግቦች እና በርካታ ለግብ የሚሆኑ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር ችሏል። በተለይ በግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ላይ ከእንግሊዝ ጋር የተገናኘችውን ብራዚል ጨዋታውን በድል እንድትወጣ ያስቻላትን አስደናቂ ቅጣት ምት አስቆጥሯል። በተለይ ጎሏን ልዩ የሚያደርጋት ከ40 ሜትር ርቀት ላይ የተቆጠረች እና ዴቨድ ሴማንን በእጅጉ የፈተነች በመሆኗ ነበር። በ2005 ሮናልዲንሆ የብራዚል ብሄራዊ ቡድንን በአንበልነት እየመራ የፊፋ ኮንፌደሬሽን ካፕን አንስቷል። በተለይ በውድድሩ በሜክሲኳዊው ኩቲሞክ ብላንኮ የተያዘውን የ9 ጎል ክብረ ወሰን መጋራት ችሏል። በ1999 አሜሪካን ካፕ እንዲሁም በ1997 በፊፋ 17 ዓመት በታች የዓለም ሻምፒዮን ዋንጫን አንስቷል። በዋናው የብራዚል ብሄራዊ ቡድን በ97 ጨዋታዎች ተሰልፎ ያስመዘገባቸው 33 ጎሎች ናቸው። ከ1996 ጀምሮ በብራዚል ከ17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን በ6 ጨዋታዎች 2 ግብ አስቆጥሯል። ከ1999 ጀምሮ በብራዚል 20 ብሄራዊ ቡድን በ5 ጨዋታዎች 3 ጎሎችን፤ ከ1999 እስከ 2008 በብራዚል 23 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን በ27 ጨዋታዎች 18 ጎሎች፤ ከ1999 እስከ 2013 በብራዚል ብሄራዊ ቡድን በ97 ጨዋታዎች 33 ጎሎች አስመዝግቧል። 2006 ለጎቾ ጥሩ ጊዜ አልነበረም። ምክንያቱ ደግሞ አንድ ነው። የዓለም ዋንጫ። እርሱን፣ አድሪያኖን እና ካካን የያዘው ብሄራዊ ቡድን ዋንጫውን ያነሳል የሚል ከፍተኛ ግምት ተሰጥቶት ነበር። ነገር ግን በግልባጩ ያልታሰበ ነገር ተከሰተ። ስምንት ውስጥ ቢደርሱም በፈረንሳይ የ1ለ0 ሽንፈት ስለገጠማቸው ከውድድሩ ውጪ ለመሆን ተገደዱ። ጎቾ በዚህ ውድድር ላይ ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ አቋሙ ወርዶ ነበር። ዓለምን ያስደነቀው ምርጥ ተጫዋች በዚያን ዓመት ለአገሩ ሊደርስላት አልቻለም። በዚህ የተናደዱት ደጋፊዎችም 7 ነጥብ 5 ሜትር የሚደርሰውን ለክብሩ የተተከለለት ሀውልት ጥቃት አድርሰውበት ነበር።አዲስ ዘመን ሚያዝያ 6/2011
https://www.press.et/Ama/?p=8841
389
2ስፖርት