headline
stringlengths
2
1.42k
category
stringclasses
6 values
date
stringlengths
9
35
views
stringlengths
1
7
article
stringlengths
63
36.2k
link
stringlengths
28
740
word_len
int64
16
6.74k
label
class label
6 classes
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማት ሊያሸንፉ እንደሚችሉ ተጠቆመ
ሀገር አቀፍ ዜና
October 9, 2019
Unknown
በመጪው አርብ በኖርዌይ መዲና ኦስሎ በሚዘጋጀው የ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማት ያሸንፋሉ ተብለው ከሚጠበቁ ሰዎች አንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ሊሆኑ እንደሚችሉ ታይም መፅሄት አስነብቧል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ከሁለት አስርት አመታት ፍጥጫ እልባት በመስጠት፤ ሰላም በማምጣት፣ የፖለቲካ እስረኞችን በመፍታትና ሌሎች ባመጧቸውም መሻሻሎች ሽልማቱን ሊያሸንፉ እንደሚችሉ በእንግሊዝ የተለያዩ ፖለቲካዊ ትንበያዎችን በመስጠት የሚወራረደው ላድብሮክ አሳውቋል። ድርጅቱ 80% (4/1) ሊያሸንፉ እንደሚችሉ ግምቱን አስቀምጧል።ዓመታዊው ሽልማት በአለም ውስጥ ለሰላም አስተዋፅኦ ያደረጉ ግለሰቦችን ወይም ድርጅቶችን እውቅና ይሰጣል።በባለፈው ዓመት የኮንጎ ዜግነት ያለው ዶክተር ዴኒስ ሙክዌጋና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቿ ናዲያ ሙራድ ወሲባዊ ጥቃትን ለጦርነት መሳሪያነት መጠቀሚያነት ለማቆም በሰሩት ስራ አሸናፊ ሆነዋል።በዚህ ዓመቱ ሽልማት 301 ዕጩዎች ያሉ ሲሆን፤ 223 ግለሰቦች እንዲሁም 78 ድርጅቶች መሆናቸውንም የኖቤል ተቋም አስታውቋል። ምንም እንኳን እነማን ዕጩዎች እንደሆኑ ባይታወቁም የተለያዩ ግለሰቦችና ድርጅቶች ግምቶቻቸውን እያስቀመጡ ነው።ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በተጨማሪ የአየር ንብረት ለውጥ ተሟጋቿ ግሬታ ተንበርግና የኒውዚላንዷ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርደርን ግምት ተሰጥቷቸዋል። (ምንጭ፡-ቢቢሲ)
https://waltainfo.com/am/32786/
141
0ሀገር አቀፍ ዜና
ከአዕምሮ ጤና ችግር አምራች የሆነውን የህብረተሰብ ክፍል ለመጠበቅ መስራት እንደሚያስፈልግ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
October 9, 2019
Unknown
የአዕምሮ ጤና ችግር በከፍተኛ ሁኔታ እያጠቃው የሚገኘውን አምራች የሆነውን የህብረተሰብ ክፍል ከችግሩ ለመጠበቅ መስራት እንደሚያስፈልግ ተገለጸ።የዓለም የአዕምሮ ጤና ቀን ዘንድሮ “ትኩረት ራስን ማጥፋትን ለመከላከል” በሚል መሪ ሃሳብ እየተከበረ ነው።የአዕምሮ ጤና የሚያስከትሉ ችግሮች እንዳሉ ሆነው በሕሙማኑ ላይ የሚደረገው ማግለል እና መድሎ ችግሩን አሁንም ከባድ አድርጎታል ተብሏል።አለማችን በተለያዩ ክስተቶች ከምታስተናግዳቸው ሞት በአዕምሮ ህመም ምክኒያት ራሳቸውን የሚያጠፉት 78 በመቶውን እንደሚይዝና ከዚህ ውስጥ 50 በመቶዎቹ ደግሞ እድሜያቸው 15 እስከ 44 ክልል ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውን ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ተላላፊ በሽታ ያልሆነው የአዕምሮ ህመም፤ በኢትዮጵያ ራስን በማጥፋት ረገድ ከሳሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ ሀገራት ሶስተኛ ደረጃ ላይ እንደትቀመጥ አድርጓታል ነው የተባለው፡፡የአዕምሮ ህመም በአማካይ እድሜን በ30 አመት እንደሚቀንስ ጥናቶች የሚያመለክቱ ሲሆን፣ እንደ ኢትዮጵያም 27 ሚሊዮን ዜጎች ከአዕምሮ ጋር በተያያዘ የባለሞያ እገዛ እንደሚያስፈልጋቸው መረጃዎች ያሳያሉ፡፡የአለም ጤና ድርጅት በአውሮፓዊያኑ 2030 ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን መቀነስ ላይ ትኩረቱን አድረጎ እየሰራ ሲሆን፣ ራስን ማጥፋት አንደኛው ነው፡፡በቅዱስ አማኑኤል የአዕምሮ ህክምና ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል  የአዕምሮ ህክምና ሳይካትሪስት የሆኑት ዶ/ር መሀመድ ንጉሴ ራስን ለማጥፋት መንስኤ የሆነውን የአዕምሮ ህመም አስመልክቶ አበረታች እርምጃዎች እየተወሰዱ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡በአለምዓቀፍ ደረጃ አስሩ የአዕምሮ ህሙማን መካከል አንዱ ብቻ ተገቢውን የህክምና አገልግሎት እንደሚያገኝ ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡
https://waltainfo.com/am/32787/
168
0ሀገር አቀፍ ዜና
አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከደቡብ ሱዳን አቻቸው አወት ዴንግ አኩይል ጋር ተወያዩ
ፖለቲካ
October 9, 2019
Unknown
የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አወት ዴንግ አኩይልን ዛሬ በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።ሚኒስትሮቹ በነበራቸው ውይይት የደቡብ ሱዳን የሰላም ሂደት ያለበትን ደረጃና ወደ ፊት ማስቀጠል በሚቻልበት ዙሪያ መክረዋል።በደቡብ ሱዳን በኢጋድ አደራዳሪነት በተደረሰው ስምምነት መሰረት በአገሪቱ ያለው ሰላም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መሄዱን አድንቀዋል።በስምምነት በተደረሰው የጊዜ ሰሌዳ መሰረትም ቀሪ ጉዳዮችን ወደ ተግባር ለማስገባት በትኩረት መስራት እንደሚያስፈልግ ሁለቱ ሚኒስትሮች ከመግባባት መድረሳቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
https://waltainfo.com/am/31385/
70
5ፖለቲካ
አሜሪካ ቱርክ ሶሪያ ላይ ጥቃት እንድትፈፅም ይኹንታዋን እንዳልሰጠች ገለፀች
ፖለቲካ
October 10, 2019
Unknown
አሜሪካ ለቱርክ ሰሜናዊ ሶሪያ ላይ ጥቃት እንድትፈፅም 'ይኹንታዋን' እንዳልሰጠች የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሯ ማይክ ፖምፒዮ ገለፁ።ፖምፒዮ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቱርክ የድንበር አካባቢ ጦራቸው እንዲወጣ ማድረጋቸውንም ደግፈዋል።ይህ እርምጃ ግን በአሜሪካ ባሉ ፓለቲከኞችም ሆነ በሌሎች ወገኖች ዘንድ ድጋፍ አላገኘም።ቱርክ የአሜሪካ ጦር መውጣቱን ተከትሎ በድንበር አካባቢ በሚገኙና በኩርዶች የሚመራ ጦር ላይ ጥቃት ከፍታለች።የቱርክ ፕሬዝዳንት ጣይብ ኤርዶጋን እንዳሉት፤ ጥቃቱ "ድንበር አካባቢ የሚፈጠር የሽብር ተግባርን መከላከል" ነው።የቱርክ ጦር ድንበር አካባቢ በከፈተው ጦርነት ኢላማ ያደረገው የኩርድ ወታደሮችን አስወግዶ "ደህንነቱ የተጠበቀ ዞን" መፍጠር ሲሆን ስፍራው ላይ የሶሪያ ስደተኞችም ይኖሩበታል።የአውሮፓ ሕብረት ግን ይህ ቱርክ ያቀረበችውን ደህንነቱ የተጠበቀ አካባቢ መፍጠር የሚል ሀሳብ መሳካቱ ላይ ጥርጣሬ እንዳለው ተናግሯል።አክሎም ስደተኞች ሊኖሩበት የሚችሉትና የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ መስፈርት ያሟላ ይሆናል የሚለውም ላይ ስጋት እንዳለው አስታውቋል።ዩ ኬ፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ቤልጂየምና ፖላንድ ከተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ጋር በቀጣይ ስለሚወሰዱ ርምጃዎች ለመነጋገር ጥያቄ አቅርበዋል።የአረብ ሊግም አስቸኳይ ስብሰባ የጠራ ሲሆን፣ ስብሰባው ቅዳሜ ዕለት በካይሮ ይካሄዳል ተብሏል።በኩርዶች የሚመራው ጦር የቱርክ ጦርን ለመመከት ቃል የገባ ሲሆን፣ ለሚፈፀምበትም ጥቃት ምላሽ መስጠት ጀምሯል።ኩርዶች አሜሪካ አይ ኤስን ለማሸነፍ ባደረገችው ጦርነት ውስጥ ዋነኛ አጋር የነበሩ ሲሆን በርካታ የአይ ኤስ ተዋጊዎችና ቤተሰቦቻቸውን በእስር ቤትና በመጠለያ ካምፖች በማቆየት እየጠበቁ ይገኛሉ።ጦርነቱ ከቀጠለ ይህንን ተግባራቸውን ስለመቀጠል አለመቀጠላቸው የታወቀ ነገር የለም።የአሜሪካ ጦር በሰሜን ሶሪያ የነበሩ ሁለት ከ30 በላይ ምዕራባውያን ገድለዋል በሚል ክስ የቀረበባቸውን የብሪቴይን ዜጎች እንደወሰደ ተናግሯል።ሁለቱ ሰዎች ኤል ሻፌ ኤልሻኪህ እና አሌክሳንዳ ኮቴይ የሚባሉ ሲሆን 'ዘ ቢትልስ' በሚል ቅፅል ስምም ይታወቁ ነበር።የቱርክ ጦር ከትናንት ጀምሮ በበርካታ መንደሮች ላይ የአየር ጥቃት ፈፅሟል። በዚህም የተነሳ በርካታ ሰዎች ከመኖሪያ ሠፈራቸውን ጥለው መሸሽ ጀምረዋል።የኩርድ ጦር ቢያንስ አምስት ንፁኃን ዜጎች በጥቃቱ መሞታቸውን ተናግሮ 25 ሰዎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል ብሏል።የቱርክ መከላከያ ሚኒስትርም ጦሩ ወደ ድንበር ከተሞቹ መግባቱን ገልጿል።የቱርክ መከላከያ ኃይል በትዊተር ገፁ ላይ 181 "አሸባሪዎች" ላይ ያነጣጠረ ጥቃት መፈፀሙን ተናግሯል። (ምንጭ፡-ቢቢሲ)
https://waltainfo.com/am/34012/
268
5ፖለቲካ
የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላህ አምዶክ አዲስ አበባ ገቡ
ፖለቲካ
October 10, 2019
Unknown
የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላህ አምዶክ ዛሬ ረፋዱ ላይ አዲስ አበባ ገቡ።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም ዓቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲፈደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላህ በቆይታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ እና ከሌሎች የስራ ሃላፊዎች ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ እንዲሁም የአንድነት ፓርክ ምረቃ ስነስርዓት ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡(ምንጭ፡-የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)
https://waltainfo.com/am/31387/
59
5ፖለቲካ
የአንበጣ ወረርሽኝን ለመከላከል ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል ርብርብ እንዲያደርግ የግብርና ሚኒስቴር አሳሰበ
ቢዝነስ
October 9, 2019
Unknown
የዓለም የምግብ እና እርሻ ድርጅት የአንበጣ መረጃ ክፍል፣ አንበጣ መቼ ሊከሰት እንደሚችል ሀገራትን ያስጠነቀቀ ሲሆን፣ ወደ ኢትዮጵያም ከ2011 ግንቦት ጀምሮ ሊገባ እንደሚችል በነበረው ትንበያ መሠረት የነፋስን አቅጣጫ ተከትሎ ከሳውዲ አረቢያ ቀይ ባሕርን አቋርጦ በየመን በኩል ሰኔ መጨረሻ በአፋር ክልል ተላላክ ወረዳ ተከስቷል።የግብርና ሚኒስቴር እንዳለው ይህ የአንበጣ መንጋ ከድንጋይ በስተቀር ሁሉንም ሰብሎች እና የዕፅዋት ዓይነቶች በሙሉ የሚበላ፣ የሀገራት ድንበር የማይገታው ድንበር ዘለል (ተዛማች) የአንበጣ መንጋ በቀን ከ150 እስከ 300 ኪ.ሜ የሚጓዝ፣ እጅግ አደገኛ ነፍሳት ስለሆነ የሀገሪቱን የምግብ ዋስትና ሊፈታተን ይችላል።እስካሁን በሰብል ላይ ያደረሰው ጉዳት ባይኖርም፣ በእንስሳት ግጦሽ፣ ደን እና ቁጥቋጦ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያስከተለ ይገኛል። ይህም ለእንስሳት ድርቅ በማምጣት፣ ምርት እና ምርታማነት በመቀነስ በሀገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት ላይ ጠባሳ ሊፈጥር ይችላል።ግብርና ሚኒስቴር አንበጣ ወደ ሀገራችን እንደሚገባ መረጃው ስለነበረው በተከሰተበት ወቅት በአውሮፕላን ለማጥፋት ጥረት የተደረገ ቢሆንም፣ ኅብረተሰቡ ፀረ ተባይ ላይ ስጋት ስለነበረው ፈቃደኛ ባለመሆኑ አወያይቶ ለማሳመን ጊዜ በመውሰዱ አንበጣው ሊራባ ችሏል።በብሔራዊ ሚቲዮሮሎጂ መረጃ መሠረት ዓመቱን ሙሉ በአብዛኛው አካባቢ ምቹ የዝናብ ስርጭት ስለሚኖር ይህ ደግሞ ለአንበጣ መራቢያ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል።በመሆኑም ይህ የአንበጣ ወረርሽኝ ወደ ሌሎች ክልሎች ተዛምቶ በሰብሎች እና ሌሎች ዕፅዋት ላይ የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ ለማድረግ የሚያስችሉ የማጥፋት ሥራዎች ላይ አርብቶ እና አርሶ አደሩ፣መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ የልማት አጋር አካላት፣ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል ተዋናይ እንዲሆን የግብርና ሚኒስቴር ትናንት ባወጣው መግለጫ ጥሪ አቅርቧል።
https://waltainfo.com/am/24000/
199
3ቢዝነስ
ፌዴራል ፖሊስ በቅርቡ የተከበሩት በዓላት በሰላም እንዲጠናቀቁ ላበረከቱት አስተዋፆ ህዝቡንና የፀጥታ አካላትን አመሰገነ
ፖለቲካ
October 8, 2019
Unknown
በ2011 አ/ም መጨረሻ እና በአዲሱ አመት መጀመሪያ ላይ የተከበሩ በአላት በሰላም ለመጠናቀቃቸው መላው የፀጥታ ሀይልና ህብረተሰቡ ላደረጉት አሰተዋፅኦ ፌዴራል ፖሊስ አመሰገነ፡፡ፌዴራል ፖሊስ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ለእሬቻ በአል ስኬትም የአዲስ አበባ ህዝብና የበአሉ ተሳታፊዎች ላደረጉት አሰተዋፅኦ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡መግለጫዉን የሰጡት በፌዴራልፖሊስ የወንጀል ዘርፍ ሃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ ህዝቡ እንደሃገር የሚከበሩ በአላትና አህጉራዊና አለምአቀፋዊ ስብሰባዎች በሚኖሩበት ጊዜ ለዝግጅቶቹ ስኬቶችና በሰላም መጠናቀቅ የሚያደርገዉን አስተዋፅኦ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል፡፡ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አሳሳቢ እየሆነ የመጣዉ ህገ-ወጥ የጦር መሳርያ ዝዉዉር ችግርን ለመፍታት የሚከናወነዉ ስራ ዉጤታማ ቢሆንም የችግሩን አሳሳቢነት የሚረዳዉ ፖሊስ ህብረተሰቡ አሁንም ከጎኑ እንዲቆም ጥሪ አቅረቧል፡፡በአንዳንድ የአገሪቱ አካባቢዎች እየተነሱ ባሉ ግጭቶች ሰላማዊ ሰዎችና ህግ አስከባሪዎች በስፋት ለጉዳት እየተዳረጉ መሆናቸዉንም ፖሊስ ገልጿል፡፡ህዝብና ህዝብ መቼም ቢሆን ተጋጭቶ አያዉቅም ያለዉ ፖሊስ ለራሳቸዉ ሲሉ ችግሮችን የሚፈጥሩ አካላት ከድርጊታቸዉ እንዲታቀቡ ፖሊስ ጠይቋል፡፡በያዝነዉ አመት ከሚከናወኑ ስራዎች የፌዴራል ፖሊስን ማዘመን እንደሚገኝበት የተናገሩት ሃላፊዉ በምድርና በአየር ጭምር ደረጃዉን በጠበቀ መልኩ ሰራዉን ማከናወን የሚያስችል አደረጃጀት ዕዉን ይደረጋል ብለዋል፡፡  
https://waltainfo.com/am/31384/
143
5ፖለቲካ
ግብፅ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ዙሪያ ያቀረበችው የመነሻ ሃሳብ ውድቅ መደረጉ ተገለፀ
ፖለቲካ
October 8, 2019
Unknown
ግብፅ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ዙሪያ ያቀረበችው የመነሻ ሃሳብ(ፕሮፖዛል) ውድቅ መደረጉን በውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር የድንበርና ድንበር ተሻጋሪ ወንዞች አማካሪ አቶ ተፈራ በየነ ገልፀዋል፡፡አማካሪው እንዳሉት ግብፅ ሀምሌ 25፣ 2011 ዓ.ም ለኢትዮጵያና ሱዳን የግድቡ የውሃ ሙሌትና አለቃቀቅን እንዲሁም ቀጣይ ቅንጅታዊ አሰራርን በተመለከተ አዲስ የመነሻ ሃሳብ(ፕሮፖዛል) ልካ በኢትዮጵያ በኩል ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል፡፡ፕሮፖዛሉ ውድቅ የተደረገው ኢትዮጵያን ጨምሮ የላይኛው ተፋሰስ ሀገራትን ጥቅም የማያሥጠብቅ በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡የግብፅ ወገን ላለመስማማት ተስማምቶ የመጣ ነው የሚመስለው ያሉት አማካሪው፤ ግብፅ ያቀረበችው ፕሮፖዛል የሶስትዮሽ ምክክር አሰራሩን የጣሰ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ግብፅ የአባይ ተፈጥሯዊ ፍሰት ሳይዛባ እንዲቀጥል ጠይቃለች ፣ ይህ ደግሞ የላይኛው ተፋሰስ ሀገራት የልማት ተጠቃሚ እንዳይሆኑ ያደርጋል ነው ያሉት፡፡የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ ብሄራዊ አሰተባባሪ ም/ቤት ፅ/ቤት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፍቅርተ ታምር ለግድቡ ግንባታ ድጋፍ በ2011 ዓ.ም 970 ሚሊየን ብር መገኘቱን ገልፀዋል፡፡እስካለፈው ሰኔ መጨረሻ ድረስ በአጠቃላይ ከህብረተሰቡ ለግንባታው 12 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ድጋፍ መደረጉንም ነው ያስታወቁት፡፡የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ የፕሮጀክቱን አሁናዊ ሁኔታ በተመለከተ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው ውይይት ላይ ለተገኙ ተሳታፊዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡በዚህም የኮርቻ ግድብ(ሳድል ዳም) 96 በመቶ፣የሃይል ማመንጫዎች 69 በመቶ፣ የኤሌክትሮ መካኒካል ስራው 25 በመቶ፣ የሲቪል ስራው 84 በመቶ መጠናቀቃቸውን ገልፀዋል፡፡በአጠቃላይ የፕሮጀክት አፈፃፀም ደግሞ 68 ነጥብ 5 በመቶ መድረሱን አብራርተዋል፡፡እስካሁን ለግድኑ ግንባታ 99 ቢሊየን ብር ወጪ ሲደረግ፣ ፕሮጀክቱን ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅም ተጨማሪ 40 ቢሊየን ብር እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡በ2013 ዓ.ም ግድቡ የመጀመሪያው ምዕራፍ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጨት እንደሚጀምርም ነው የገለፁት፡፡
https://waltainfo.com/am/31383/
213
5ፖለቲካ
የፌዴሬሽን ምክር ቤት የክልሎች የድጎማ በጀት የማከፋፈያ ቀመርን ለሁለት ዓመት አራዘመ
ቢዝነስ
October 8, 2019
Unknown
የፌደሬሽን ምክር ቤት 5ኛ የፓርላማ ዘመን 5ኛ ዓመት አንደኛ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ አካሂዷል፡፡በዚህ ወቅት ምክር ቤቱ የፌዴራል መንግስት ለክልሎች የሚያደረገው የድጎማ በጀት የማከፋፈያ ቀመርን ለሁለት ዓመት አራዝሟል።በስብሰባውም የ5ኛው የፓርላማ ዘመን 4ኛ ዓመት ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤውን አጽድቋል፡፡ቀደም ሲል የበጀት ድጎማና የጋራ ገቢዎች ደልድል ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ በ2010 በጀት ዓመት ይካሄዳል ተብሎ የተጠበቀው የህዝብና ቤት ቆጠራ በወቅቱ ስላልተካሄደ አሁን ያለውን የድጎማ ማከፋፈያ ቀመር ለሶስት ዓመታት ብቻ እንዲያገለግል ተደርጎ ነበር፡፡አሁን ላይ ግን በተለየዩ ምክንያቶች ቀመሩ ተግባር ላይ የሚውልበት ጊዜ እስከ 2014 በጀት ዓመት እንዲራዘም የውሳኔ ሃሳብ አቅርቧል፡፡የምክር ቤቱ አባላትም በጉዳዩ ላይ የተለያዩ ጥያቄዎችን ያነሱ ሲሆን፤ የሚመለከታቸው የቋሚ ኮሚቴው አባላትም ምላሽ ሰጥተዋል፡፡የበጀት ድጎማና የጋራ ገቢዎች ደልድል ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ለምክር ቤቱ ያቀረበው የውሳኔ ሐሳብ የድጎማ ማከፋፈያ ቀመር በአንድ ዓመት ፤ ይራዘም የሚለው በ28 ድምጽ በሁለት ዓመት ይራዘም የሚለው ደግሞ በ48 ድምፅ በማግኘት እስከ 2014 ድረስ እንዲራዘም ተወስኗል፡፡የማንነት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የህገ መንግስት ትርጉም ያስፈልጋቸዋል ያላቸውን ስድስት ጉዳዮች እና የህገ መንግስት ትርጉም አያስፈልጋቸውም ያላቸው ሁለት ጉዳዮችን በተመለከተ አባላቱ ተወያይተው ውሳኔ አሳልፈዋል፡፡  
https://waltainfo.com/am/23998/
158
3ቢዝነስ
በአዲስ አበባ የታክሲ አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎችን በአዲስ በመተካቱ ሂደት ላይ ድጋፍ እንዲደረግ ተጠየቀ
ቢዝነስ
October 9, 2019
Unknown
በአዲስ አበባ የታክሲ አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎችን በአዲስ በመተካቱ ሂደት ላይ ድጋፍ እንዲደረግ ተጠየቀ፡፡የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የታክሲ አገልግሎት (ኤታስ) ከሚሰጡ 13 ተቋማት ጋር ተወያይተዋል፡፡በዚህም የከተማ አስተዳደሩ በቅርቡ የኤታስ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንዲከተሉት ባወጣው መመሪያ ዙሪያ እና የትራንስፖርት ሴክተሩን በዘላቂነት ዘመናዊ ለማድረግ በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ከኤታስ እና ሶፍትዌር ማበልፀጊያ ተቋማት ጋር ምክክር ተካሂዷል፡፡የኤታስ አገልግሎት ሰጪ ተቋማቱ በከተማ አስተዳደሩ ረቆ በቅርቡ ይፋ የሆነው መመሪያ ቴክኖሎጂው ላይ ምንም ተፅዕኖ እንደሌለው በመግለፅ፤ ህጉን እንደማይቃወሙ እና ለተፈፃሚነቱ ከከተማ አስተዳደሩ ጎን በመቆም እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡ኢንጅነር ታከለ ኡማ በበኩላቸው የከተማ አስተዳደሩ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የትራንስፖርት አሰጣጥ በከተማዋ ውስጥ እንዲስፋፋ ፍላጎቱ እንዳለው ተናግረዋል፡፡በከተማዋ ውስጥ ያለውን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ የሚረዱ ሌሎች ተጨማሪ ቴክኖሎጂዎችን ለሚያመጡ በራቸው ክፍት መሆኑንም ምክትል ከንቲባው ጠቁመዋል፡፡በቀጣይነትም የከተማ አስተዳደሩ የተቀላጠፈ እና ህዝቡን የሚጠቅም መመሪያ ቀርጾ በከተማዋ ውስጥ ያለውን የትራንስፖርት እጥረት ለመቅረፍ እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡የኤታስ ተቋሞቹም በከተማዋ ውስጥ የታክሲ አገልግሎት በመስጠት ላይ ያሉ ተሽከርካሪዎች ያረጁ በመሆናቸው የከተማ አስተዳደሩ ተሽከርካሪዎቹን በአዲስ በመተካቱ ሂደት ከጎናቸው እንዲቆም ጥሪ አቅርቧል፡፡ (ምንጭ፡-የከንቲባ ፅህፈት ቤት)
https://waltainfo.com/am/23999/
156
3ቢዝነስ
መንግስት ሰልፈኞች ሁከትና ብጥብጥ እንዲያባብሱ እንደማይፈቅድ የግብጹ ጠቅላይ ሚኒስትር  አስጠነቀቁ
ፖለቲካ
October 9, 2019
Unknown
መንግስት ሰልፈኞች ሁከትና ብጥብጥ እንዲያባብሱ እንደማይፈቅድ የግብጹ ጠቅላይ ሚኒስትር ሙስጠፋ ማድቡሊ አስጠንቅቀዋል፡፡መናሻውን ሰሜን አፍሪካዊቷን  ቱኒዚያ ያደረገው የአረቡ አለም የፀደይ አቢዮት ከስምንት አመታ በፊት ነበር ግብፅን የመታው፡፡ህዝባዊ አመፁ ወታደራዊ ስርዓትን ገርስሶ በፈርኦኖች ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሲቪል አስተዳዳር ተክሎም ነበር፡፡ ምንም እንኳን እድሜ ባይኖረውም ቅሉ፡፡ ይህ አቢዮት ግዜ ጠብቆ  ያገረሸ ይመስላል፡፡ባለፈው ወር በግብጹ በፕሬዚዳንት አብድል ፋታህ አል ሲሲ ላይ የተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞም አሁንም ድረስ እንደቀጠለ ነው፡፡ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ እ.አ.አ በ2016 ይፋ ያደረጉት የግብጽ የኢኮኖሚ ሪፎርም ተግባራዊ ባለመሆኑና የሀገሬው ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው የኢኮኖሚ ጫና መበርታቱን ተከትሎ ህዝባዊ ተቃውሞዎቹ ተበራክተዋል፡፡ ተቃውሞዎቹም ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ከስልጣን እንዲወርዱ የሚጠይቁ ናቸው፡፡የግብጹ ጠቅላይ ሚኒስትር ሙስጠፋ ማድቡሊ መንግስታቸው ሰልፈኞች ብጥብጥ እንዲያሰራጩ አይፈቅድም ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተቃውሞው በሀገሪቱ ግራ መጋባትን ለመፍጠር የተነደፈ የውጭ ሀይሎች እጅ ያለበትና ጭካኔ የተሞላው የጦርነት አካል ነው ሲሉ አውግዘውታል፡፡ወደፊት ሊከሰቱ የሚችሉ መጠነ ሰፊ ተቃውሞዎች አደጋቸው የበዛ ነው ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስጠንቅቀዋል፡፡እ.አ.አ በ2011 አምባገነኑን መሪ ሆስኒ ሙባረክን ከስልጣን ለማውረድ በሀገሪቱ ተከስቶ የነበረውን ህዝባዊ አመጽ በማስታወስ የግብጽ ህዝብ መሰል ብጥብጥና ሁከት ዳግም እንዲደገም አይፈቅድም ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡በግብጽ በተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ እስካሁን አክቲቪስቶችን ጨምሮ 3000 ሰዎች መታሰራቸውን መረጃዎች አመላክተዋል፡፡   ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግን እስካሁን የተወሰዱ እርምጃዎች ህግን መሰረት ያደረጉ ናቸው ብለዋል፡፡ቀውሱን ተከትከሎ ምንም አይነት የከፋ ችግር አላስተናገድንም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዚህም የሀገሪቱን የፖሊስ አባላት አመስግነዋል፡፡ኢኮኖሚያዊ ጫናው በግብጻውያን ላይ እያሳደረ ያለውን አሉታዊ ተጽዕኖ ያመኑት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀገር መገንባት ከፍተኛ በጀት የሚጠይቅ ሂደት ነው ማለታቸውን ሜይል ኦንላይን ዘግቧል፡፡ 
https://waltainfo.com/am/33344/
224
5ፖለቲካ
ምርጫን ፍትሃዊና ተዓማኒ ማድረግ ወደ ዴሞክራሲ የሚደረገውን ጉዞ የማቃናት ሚናው ከፍተኛ ነው-ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ
ፖለቲካ
October 8, 2019
Unknown
በተያዘው ዓመት ሊካሄድ በታቀደው ሀገራዊ ምርጫ ዙሪያ ያተኮረ አለምአቀፍ ምክክር እየተካሄደ ነው፡፡ኮንፈረንሱ ቀጣዩ ምርጫን እንዴት ነጻ፣ ፍትሃዊና ተዓማኒ ማድረግ ይቻላል፣ በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ አባል ማሻሻያና የምርጫ ዝግጅት እና በሌሎችም ነጥቦች ላይ በመምከር ላይ ይገኛል፡፡በመድረኩ የተገኙት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ምርጫን ፍትሃዊ እና ተዓማኒ ማድረግ ሀገሪቱ የጀመረችውን ለውጥ ለማሳካትና ወደ ዴሞክራሲ የሚደረገውን ጉዞ የማቃናት ሚናው ከፍተኛ ነው ብለዋል ፡፡እስከ ነገ በሚቆየው በዚህ መድረክ በአዲሱ የምርጫ ማዕቀፍ ውስጥ ያሉ የመንግሥት ግዴታና የፖለቲካ ፖርቲዎች መብት የሚሉ ጭብጦችን ጨምሮ በመጭው ምርጫ ወቅት ሠላምና ደኅንነትን ለማረጋገጥ መወሰድ ያለባቸዉ ሁኔታዎች ላይ ምክክር ይደረጋል፡፡በዚህ የምክክር መድረክ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የብዙሃን መገናኛ ተቋማትና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሌሎች አካላት እየተሳተፉ ይገኛል፡፡  
https://waltainfo.com/am/31382/
101
5ፖለቲካ
የእነብርጋዲዬር ጀኔራል ተፈራ ማሞ ጉዳይ ለጥቅምት 12 ቀን ተቀጠረ
ሀገር አቀፍ ዜና
October 8, 2019
Unknown
የእነብርጋዲዬር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የምርመራ ጉዳይ ላይ የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግና የፖሊስ ምርመራ ቡድን የጠየቁት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ይግባኝ ውድቅ ተደርጓል፡፡ጉዳዩን ሲመለከት የቆየው የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ዛሬ ረፋድ ባስቻለው ችሎት የመርማሪ ቡድኑ የጠየቀውን የተጨማሪ ቀጠሮ ይግባኝ ውድቅ አድርጓል፡፡እስከ ጥቅምት 12 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስም ክስ እንዲመሠርት ትዕዛዝ በመስጠት መዝገቡን ዘግቷል፡፡መርማሪ ቡድኑ ይግባኝ ከጠየቀበት ጊዜ ጀምሮ ተጠርጣሪዎቹ ለ64 ቀናት በማረፊያ ቤት የቆዩ በመሆናቸውና መርማሪ ቡድኑ በእነዚህ ጊዜያት ውስጥ መረጃ እያጣራ ያለ መሆኑን፣ ቀሪ ምስክሮችም ጥቂት መሆናቸውን ግምት ውስጥ በማስገባት ጥቅምት 12 ቀን 2012ዓ.ም ክስ እንዲመሠረት ትዕዛዝ በመስጠት መዝገቡን ዘግቷል፡፡ (ምንጭ፡-አብመድ)
https://waltainfo.com/am/32784/
94
0ሀገር አቀፍ ዜና
ሙዚቀኛ ኤሊያስ መልካ ተሸኘ
ሀገር አቀፍ ዜና
October 7, 2019
Unknown
የሙዚቀኛ ኤሊያስ መልካ የስንብት መርሃ ግብር በዛሬው እለት በብሄራዊ ቴአትር ተካሂዷል።   በመርሃ ግብሩ ላይ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ፣ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዩን ጨምሮ ቤተሰቦቹ፣ የሙያ አጋሮቹ እና አድናቂዎቹ በተገኙበት ተካሂዷል።ኤልያስ የሙዚቃ አቀናባሪ፣ የዜማና ግጥም ደራሲ፣ ጊታርና ፒያኖ ተጫዋች ሲሆን፥ አዳዲስ ሙዚቀኞችን ለኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ አስተዋውቋል።  ከያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ቼሎ የሙዚቃ መሳሪያን ተምሮ ከጨረሰ በኋላ ከመምህሩ አክሊሉ ዘውዴ፣ ከእዝራ አባተ ከያሬድ ተፈራና ከሌሎችም ጋር በመሆን በመዲና ባንድ ውስጥ ሰርቷል።በተጨማሪም ከመሃሙድ አህመድ፣ ከፍቅርአዲስ ነቃጥበብ፣ ከአለማየሁ እሸቴ፣ ቴዲ አፍሮ፣ እዮብ መኮንን፣ ሚካኤል በላይነህ፣ ዘሪቱ ከበደ፣ ልኡል ሀይሉ፣ ሀይሌ ሩትስ፣ ሚካያ በሃይሉ፣ ትግስት በቀለ፣ ቤሪ እና ዳን አድማሱ ጋር አብሮ በመስራት በሙያው አሻራውን አኑሯል፡፡ከዜማ ላስታስና ከአፍሮ ሳውንድስ ባንዶች ጋርም የሰራበት ጊዜ ነበር። ኤልያስ ከ40 በላይ ሙሉ አልበሞችን አቀናብሯል። ሙዚቀኛ ኤልያስ መልካ የስኳር እና ኩላሊት ህመም ገጥሞት ህክምናውን የቆየ ቢሆንም ሕመሙ ተባብሶበት ባሳለፍነው ቅዳሜ መስከረም 24/2012 ዓ.ም በሆስፒታል ህይወቱ እንዳለፈ ታውቋል፡፡ዋልታ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ኮርፖሬት በሙዚቀኛ ኤልያስ መልካ ከዚህ ዓለም በሞት መለየት የተሰማውን ትልቅ ሀዘን እየገለፀ፥ ለቤተሰቦቹ፣ ለሙያ ጓደኞቹ እና ለአድናቂዎቹ መጽናናትን ይመኛል።       
https://waltainfo.com/am/32783/
168
0ሀገር አቀፍ ዜና
በህገ-ወጥ ደላሎች ላይ እርምጃ ይወሰዳል ተባለ
ቢዝነስ
October 8, 2019
Unknown
በህገወጥ ደላሎች ላይ የተጀመረው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚአብሄር ተናገሩ ፡፡በሀገራችን በሚገኙ ትልልቅ ከተሞች በአገልግሎትና በመሠረታዊ የፍጆታ ሸቀጦች ላይ የተከሰተው ከፍተኛ የዋጋ ንረት በአቅርቦት ችግር ሳይሆን የህገወጥ ደላሎች ጣላቃ ግብነት መሆኑን የተናገሩት ሚኒስትሯ፤ የዋጋ ንረቱ በተለይም በደሃው ማህበረሰብ የእለት ተዕለት እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ጫና ከማሳደሩም ባሻገር ጥቂቶች አላስፈላጊ ንዋይ በመሰብሰብ ኢ-ፍትሃዊ የሆነ የሃብት ክፍፍል እንዲፈጠር አድርጓልም ብለዋል ፡፡በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በህገ- ወጥ ደላሎች አማካኝነት አየር በአየር በመኪና ላይ ህገወጥ ግብይት ሲያካሂዱ የተገኙ 59 መኪኖች አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም 52 መኪኖች ጤፍና ሌሎች እህሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የተናገሩት ወ/ሮ ፈትለወርቅ፤ ይህም የቁጥጥርና እርምጃ የመውሰድ ስራ በሁሉም የሀገሪቷ ክልሎች ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡ከሚኒስቴሩ ያገኘው መረጃ እንዳሚያመለክተው ደላሎችን ከሰንሰለት ውጪ በማድረግና የግብይት ሰንሰለቱን በማሳጠር አምራቾችና ተጠቃሚዎች በቀጥታ የሚገናኙበትን አግባብ ለመፍጠር ሚኒስቴር መ/ቤቱ የረጅም ጊዜ እቅድ አቅዶ እየሰራ መሆኑንም ሚኒስትሯ ገልጸዋል፡፡
https://waltainfo.com/am/23996/
131
3ቢዝነስ
ለዜጎች ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ለመስጠት የግሉ ዘርፍ መጠናከር እንደሚገባው ተገለፀ
ሀገር አቀፍ ዜና
October 8, 2019
Unknown
አራተኛው የአፍሪካ የጤና ክብካቤ ፌዴሬሽን ጉባኤ  በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።በጉባኤው መክፈቻ ላይ ሚኒስትር ዴኤታዋ ዶክተር ሊያ ታደሰ እንዳሉት የዜጎችን የጤና አገልግሎት ለማሻሻልና ተደራሽነቱን ለማሳደግ  በዘርፉ የተሰማሩ ባለድርሻ አካላቶች  ቅንጅት ወሳኝ ነው።በብሄራዊ ደረጃ የተያዘውን የጤናው ዘርፍ ዕቅድ ለማሳካት ከመንግስት የጤና ተቋማት ባለፈ በዘርፉ የተሰማሩ የግል ተቋማት ተሳትፎ እንደሚያስፈልግም ገልፀዋል።አገሪቱ ከሚያስፈልጋት አጠቃላይ የመድሃኒትና የህክምና መገልገያ መሳሪያ ውስጥ 85 በመቶ የሚሆነው ከውጭ እንደሚገባ የጠቆሙት ሚኒስትር ዲኤታዋ ይህንን በአገር ውስጥ ለመተካት በዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎችና ባለሃብቶች  ያስፈልጋሉ ብለዋል።በተለይ በውጭ አገር ድጋፍ በመንግስት ጤና ተቋማት ብቻ በነጻ የሚሰጡ አገልግሎቶችም በግል ዘርፉ እንዲሰጥ መንግስት ፍላጎት ያለው መሆኑን ዶክተር ሊያ አመልክተዋል።በአገሪቱ እየተበራከተ በመጣው ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች መከላከልና ማከም ላይ የግሉ ዘርፍ በስፋት እንዲሳተፍ መንግስት ምቹ ሁኔታን እየፈጠረ ነውም ብለዋል።ጉባኤው በዘርፉ የተሰማሩ የአገር ውስጥና የውጭ ባለሃብቶች በስፋት በዘርፉ እንዲሰማሩና በአገሪቱ ያለውን መልካም አጋጣሚ እንዲያዩ ያግዛቸዋል ብለዋል።በኢትዮጵያ የጤና ክብካቤ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ዶክተር ማርቆስ ዘለቀ እንዳሉት ጉባኤው በዘርፉ የተሰማሩ የአፍሪካ አገራት ልምድ የሚለዋወጡበት ነው።በተለይ በመንግስታት በቂ ድጋፍ ያልተሰጠውን የግሉ ዘርፍ ድጋፍ እንዲያገኝ በጋራ የሚመክሩበት መሆኑንም ጠቁመዋል።በኢትዮጵያ በዘርፉ ለሚሰማሩ አካላት የሚደረገው ድጋፍ የተሻለ ቢሆንም አሁንም በመሬት አቅርቦት መንግስት በሚሰጠው ማበረታቻና በሌሎችም ከፍተት እንዳለ ጠቁመዋል።የአፍሪካ የጤና ክብካቤ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ዶክተር አሚር ታከር በበኩላቸው በአፍሪካ በጤናው ዘርፍ የግልና የመንግስት ቅንጅት የሚፈለገው ደረጃ አልደረሰም።ይህ ደግሞ በጤናው ዘርፍ የሚሰጠውን አገልግሎት በሚፈለገው ደረጃ ማድረስ አልተቻለም።በጉባኤ የሚካሄደው የልምድና የእውቀት ልውውጥ ፖሊሲ አውጪዎች ለግሉ ዘርፍ ትኩረት እንዲሰጡ የሚያደርግ ነው ብለዋል።እንደ ኢዜአ ዘገባ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ያስተናገደችው አራተኛው የአፍሪካ የጤና ክብካቤ ፌዴሬሽን ጉባኤ ከመስከረም 26 እስከ 28፣ 2011 ዓ.ም ይቆያል።በጉባኤው ከ50 ከተለያዩ የዓለም አገራት የተውጣጡ ከ350 በላይ ሰዎችና ከ9 አገራት የተወከሉ የጤና ሚኒስትሮች እየተካፈሉ ነው።
https://waltainfo.com/am/32785/
245
0ሀገር አቀፍ ዜና
በሃገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያዉ ላይ ከክልል የካቢኔ አባላት ጋር ዉይይት ተደረገ
ቢዝነስ
October 8, 2019
Unknown
የገንዘብ ሚኒስቴር በሃገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያዉ ላይ ከ9ኙ ክልሎችና ከሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች ከተዉጣጡ የካቢኔ አባላት ጋር ዉይይት አደረገ፡፡ዉይይቱ በአገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያዉ ላይ ያተኮረ ሲሆን አላማዉም ኢትዮጵያ ባለፉት አመታት ያስመዘገበችዉ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት አሁን ላይ የገጠሙትን ተግዳሮቶች በመለየት መዋቅራዊ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ማምጣትና የኢኮኖሚ እድገትን ማስቀጠል ነዉ፡፡በዉይይቱ ላይ የተገኙት የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ባደረጉት ንግግር የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ እድገት ለማስቀጠል አመራሩ በርካታ ስራዎች እንደሚጠበቁበትና የተረጋጋ ማክሮኢኮኖሚ ለመፍጠር ከግብርናና ኢንዱስትሪ በተጨማሪ ሌሎች ዘርፎችም ላይ በትኩረት መሰራት አለበት ብለዋል፡፡አገሪቱ ያላትን የሰዉና ተፈጥሮ ሃብት በጥናት ላይ ተመርኩዞ በጥቅም ላይ ማዋልና በኢኮኖሚዉ ላይም የጎላ አስተዋፅኦ እንዲኖራቸዉ ማድረግ እንደሚያስፈልግም ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ ዶ/ር እዮብ ተካልኝ በበኩላቸዉ በጉዳዩ ዙሪያ በሰጡት ገለፃ ኢኮኖሚዉ ከገጠሙት ተግዳሮቶች መካከል ምርታማነትን ማሳደግ አለመቻል፣ የወጭና ገቢ ንግድ አለመመጣጠንና አገር በቀል ሃብቶች ላይ ትኩረት አድርጎ አለመስራትን በዋናነት አንስተዋል፡፡በቀጣይም በተለይ በቱሪዝም፣ በኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ፣ በማዕድን፣ በግብርናና ሌሎች በኢኮኖሚዉ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖራቸዋል በተባሉ ሴክተሮች ላይ በሪፎርሙ ትኩረት አድርጎ አለመስራትን በዋናነት አንስተዋል፡፡   በሪፎርሙ በቀጣይ 10 አመታት የነፍስወከፍ ገቢን በ3 ዕጥፍ ማሳደግና ድህነትን በግማሽ ለመቀነስ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራም በዉይይት መድረኩ ተወስቷል፡፡ 
https://waltainfo.com/am/23997/
166
3ቢዝነስ
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዙር 5ኛ አመት የሥራ ዘመን ዛሬ በይፋ ይከፈታል
ፖለቲካ
October 7, 2019
Unknown
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዙር 5ኛ አመት የሥራ ዘመን ዛሬ በይፋ ይከፈታል፡፡በመክፈቻው ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ተገኝተው ለሁለቱም ምክር ቤቶች የመክፈቻ ንግግር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።በሌላ በኩል የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶች፣ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች፣ የሀይማኖት አባቶች እና ታዋቂ ግለሰቦች በሂደቱ ላይ እንደሚገኙ ይጠበቃል።ዋልታ ቴሌቪዥንም የምክር ቤቱን ውሎ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በቀጥታ እንደሚያስተላልፍ ከወዲሁ ይገልጻል፡፡
https://waltainfo.com/am/31379/
60
5ፖለቲካ
በአሜሪካዊቷ ፖሊስ አምበር ጉይገር የፍርድ ሂደት ምስክርነት የሰጠው የዐይን እማኝ ተገደለ
ፖለቲካ
October 7, 2019
Unknown
አሜሪካዊቷ ፖሊስ አምበር ጉይገር በዳላስ ቴክሳስ ውስጥ ነዋሪ ስትሆን፤ ቦታም ጂን የተባለ ግለሰብን አፓርትመንቱ ውስጥ በጥይት ተኩሳ በመግደል ከሰሞኑም ተፈርዶባታል።በግድያው ላይ የዐይን እማኝ ሆኖ ቀርቦ ምስክርነት የሰጠውም ጆሹዋ ብራውን በተተኮሰበት ጥይት ሞቷል።ፖሊሷ የራሷ አፓርትመንት መስሏት ስትገባ ጂን ሶፋ ላይ ተቀምጦ የነበረ ሲሆን ቤቷን ሰብሮ የገባ መስሏት ያለምንም ጥያቄ ሁለት ጊዜ በጥይት ተኩሳ ገድለዋለች።ግለሰቡ ከካሪቢያን ደሴቶች አንዷ ከሆነችው ሴንት ሉሺያ የመጣ ሲሆን በሒሳብ ሠራተኝነት ይሠራ ነበር ተብሏል።የዐይን እማኙ ጆሹዋ ብራውን ከሟቹ ጋር በአንድ ህንፃ፤ በአራተኛ ፎቅ ላይ ይኖሩ የነበረ ሲሆን ምስክርነቱንም በሰጠበት ወቅት ከእንባ ጋር በተቀላቀለ ሁኔታ ነበር። እንባውንም በቲሸርቱ ሲጠርግ ታይቷል።ከሟቹ አፓርትመንትም ውስጥ የጥይት ተኩስ መስማቱን አስረድቶ ሁለት ሰዎች በድንገት ሲገናኙ የሚሰማ ድምፅ ከተሰማ በኋላ ተኩሶች ተከትለዋል ብሏል።አምበር ጉይገር ባለፈው ሳምንት ረቡዕ የአስር አመት ፍርድ ተፈርዶባታል።አርብ እለት ከሚያልፍ ተሽከርካሪ በተተኮሰበት ጥይትም ምስክርነቱን ከሰጠ ከቀናት በኋላ ሕይወቱ አልፏል።በመኪና ማቆሚያ ቦታ ላይ ሰውነቱ በብዙ ጥይት ተበሳስቶ ወድቆ የተገኘ ሲሆን ሆስፒታል ቢወሰድም ሕይወቱን ለማትረፍ አለመቻሉን ነው ቢቢሲ በዘገባው ያመለከተው።ፖሊስ ጉዳዩ ላይ ምርመራየን አልጨረስኩም ያለ ሲሆን፤ እስካሁን ባለው ግን ከፖሊሷ የፍርድ ሂደት ጋር መገናኘቱን የሚያሳይ ፍንጭ የለም ተብሏል።በፖሊሷ የተገደለው የቦታም ጂን ቤተሰቦች ጠበቃ ሊ ሜሪት በበኩላቸው የአሜሪካ የፍትህ ሥርዓት ሕይወታቸውን የተቀጠፉትን ጥቁር አሜሪካውያን ሊፋረዳቸው ይገባል ብለዋል።"ለጂን ቤተሰቦች ፍትህን ለማምጣት ያላሰለሰ ጥረት ከማድረጉ አንፃር እሱም በተመሳሳዩ ፍትህ ይሻል" በማለት ሊ ሜሪት በመግለጫቸው አትተዋል።የ28 አመቱ ጆሹዋ ብራውን የቀድሞ አትሌትና የሥራ ፈጣሪም በሚል ሁኔታ በአሜሪካ ሚዲያዎች ዘንድ ሲገለፅ ቆይቷል።
https://waltainfo.com/am/34011/
212
5ፖለቲካ
አምባሳደሮች የትግራይ ክልልን የኢንቨስትመንት አማራጮች እንዲያስተዋውቁ ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ጥሪ አቀረቡ
ቢዝነስ
October 7, 2019
Unknown
ተቀማጭነታቸውን በኢትዮጵያ ያደረጉ የተለያዩ ሃገራት አምባሳደሮች በትግራይ ክልል ያለውን የቱሪዝምና የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማስተዋወቅ እንዲሳተፉ የክልሉ ምክትል ርዕሰ-መስተዳደር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ጥሪ አቀረቡ።አምባሳደሮቹ ላለፉት ሁለት ቀናት በክልሉ ሲያካሔዱት በቆዩት ጉብኝት ማጠቃለያ ውይይት ላይ ምክትል ርዕሰ-መስተዳደሩ እንደገለጹት፥ የትግራይ ክልል ከመካ ቀጥሎ በእስልምና ተከታዮች ዘንድ ታሪካዊና ጥንታዊ የሆነውን አልነጃሺ መስጊድን ጨምሮ የተለያዩ የቱሪዝም መስህብ ስፍራዎች ባለቤት ነው።“በተጨማሪም የተለያዩ ድንቅና ጥንታውያን አብያተ ክርስትያናት፣ የተለያዩ አስተሳሰቦችና እምነቶች ያሏቸው ህዝቦች አንድ ላይ የሚገኝበት ክልል ነው” ብለዋል ዶክተር ደብረጽዮን።“አምባሳደሮቹ ለባለሃብቶቻቸው በማስተዋወቅና ሃብታቸውን እንዲያፈሱ በማነሳሳት ሊያግዙ ይገባል” ያሉት ዶክተር ደብረጽዮን “የእኛ ፍላጎት ከልማት አጋር ወድሞቻችን ጋር በመሆን አብረን ሰርተን አብረን የማደግ ነው” ብለዋል።የትግራይ ክልል የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ኢንጅነር አበበ ግርማይ በበኩላቸው፥ በክልሉ ላሉ ሰፋፊ የኢንቨስትመንት አማራጮች ምቹ ሁኔታዎች መዘጋጀታቸውን አስረድተዋል።ክልሉ ለተለያዩ የመውጫና መግቢያ ወደቦች ቅርብ በመሆኑና የተለያዩ የትራንስፖርት አማራጮችም ስላሉት ለኢንቨስትመንት ተመራጭ እንደሚያደርገው ገልጸዋል።የትግራይ ክልል ወርቅና ሳፋሪን ጨምሮ በርካታ ውድ ማእድናት፣ የእንስሳት ሃብት፣ ሁለት ትላልቅ የኢንዱስትሪ ፓርኮችና የኢንቨስትመንት ማበረታቻዎችም ያሉበት መሆኑን ተናግረዋል።ክልሉን ከጎበኙ የስድስት የተለያዩ ሃገራት አምባሳደሮች መካከል በኢትዮጵያ የካዛኪስታን አምባሳደር ሚስተር ቢ.ሳዲኮቭ በጉብኝታቸው መደነቃቸውንና ክልሉ የበርካታ የተፈጥሮ ሃብት ባለቤት መሆኑን መረዳታቸውን ገልጸዋል።በተለይ ጥንታዊና ታሪካዊው አልነጃሽ መስጊድን መጎብኘታቸው ልዩ ስሜት እንደፈጠረባቸው የተናገሩት አምባሳደሩ፥ ባለሃብቶቻቸው ወደ ክልሉ መጥተው መዋእለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ የድርሻቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል።“በአዲስ አበባና በአዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ አምስት ትላልቅ የሀገሬ ኩባንያዎች በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች ተሰማርተው ይገኛሉ” ያሉት ደግሞ በኢትዮጵያ የኢንዶዠያ አምባሳደር አል ቡስራ ባስኑርን/Al Busyra Basnurn/ ናቸው።በቀጣይ ሌሎች የሃገራቸው ባለሃብቶችም ትግራይ ክልል ውስጥ ሃብታቸውን እንዲያፈሱ ጥረት እንደሚያደርጉ ገልጸው የየሃገሮቻቸው ባለሃብቶች ከኢትዮጵያ ብሎም ከክልሉ ጋር በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት መፍጠር ለላቀ ብልጽግና አስፈላጊ እንደሆነም አስረድተዋል። (ምንጭ፡-ኢዜአ)
https://waltainfo.com/am/23995/
239
3ቢዝነስ
በሩዋንዳ ታዋቂ የጎብኚዎች መናኸሪያ በተፈፀመ ጥቃት 14 ሰዎች ሞቱ
ፖለቲካ
October 7, 2019
Unknown
በሩዋንዳ ታዋቂ የጎብኚዎች መናኸሪያ በተፈፀመ ጥቃት 14 ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል፡፡ጥቃቱ መፈጸሙን ተከትሎ የሩዋንዳ ፖሊስ በወሰደው አፀፋዊ ምላሽ ከጥቃት አድራሾቹ መካከል 19ኙ መገደላቸውንና ሌሎች ማምለጣቸውን አስታውቋል፡፡የሩዋንዳ ፖሊስ ቃል አቀባል ጆን ቦስኮ በኮንጎ ጠረፍ አካባቢ በሚገኘው የመዝናኛ ስፍራ ባለፈው አርብ የተፈፀመውን ጥቃት ተከትሎ ሌሎች 5 ግለሰቦች ታስረው ምርመራ እየተካሄደባቸው እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡የእሳተ ገሞራ ብሄራዊ ፓርክ የሚገኝበት ይህ አካባቢ በበርካታ ቱሪስቶች የሚጎበኝ ስፍራ ነው፡፡በተለይም በሩዋንዳ ብቻ የሚገኙትን ጎሬላዎች ለመመልከት በርካታ ጎብኚዎች ወደስፍራው እንደሚያቀኑ የሲጂቲኤን ዘገባ አመልክቷል፡፡እስካሁን በቱሪስቶች ላይ ስለደረሰው ዝርዝር ጉዳት ዘገባው ባያመለክትም በጥቃቱ 18 ሩዋንዳውያን መቁሰላቸው ተነግሯል፡፡ባለፉት ጊዜያት በማዕድን ሃብት በበለፀገችው ምስራቃዊ ኮንጎ እና በሩዋንዳ አዋሳኝ ቀጠና በርካታ ታጣቂ ቡድኖች ጥቃቶችን በመሰንዘር ላይ ይገኛሉ፡፡የሩዋንዳ ቱሪዝም እንቅስቃሴዎችን የሚደግፈው የሩዋንዳ ልማት ቦርድ በሰጠው መግለጫ ችግሩ በአሁኑ ወቅት በቁጥጥር ስር መዋሉን ነው የገለፀው፡፡
https://waltainfo.com/am/33343/
117
5ፖለቲካ
ለሶስት ክልሎችና አንድ የከተማ አስተዳደር የምርጫ ክልል ኃላፊነት በቂ አመልካቾች አለመቅረባቸው ተገለጸ
ፖለቲካ
October 7, 2019
Unknown
ለሐረሪ ክልል፣ ለድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር፣ ለጋምቤላ ክልል እና ለአማራ ክልል የምርጫ ክልል ኃላፊነት በቂ አመልካቾች አለመቅረባቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገልጿል፡፡ቦርዱ ለዘጠኙ ክልሎችና ለሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የምርጫ ክልል ኃላፊነት ባለሙያዎችን አወዳድሮ ለመመደብ የስራ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡መስፈርት የሚያሟሉ እና በሶስቱ ክልሎች እና በድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር መስራት ለሚፈልጉ ባለሙያዎች የማመልከቻ ጊዜው መራዘሙን ቦርዱ ገልጿል፡፡የማመልከቻ ጊዜው በአንድ ሳምንት በመራዘሙ አመልካቾች ከዛሬ መስከረም 26 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ ቀናት ማመልከቻቸውን ማስገባት እንደሚችሉ አሳውቋል፡፡
https://waltainfo.com/am/31380/
72
5ፖለቲካ
የምክር ቤቶቹ የጋራ ስብሰባ በይፋ ተከፈተ
ፖለቲካ
October 7, 2019
Unknown
የህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 5ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን በይፋ ተከፍቷል። የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በሁለቱ ምክር ቤቶች መክፈቻ ላይ ንግግር ያቀረቡ ሲሆን፣ 2012 ዓ.ም የለውጡን ጉዞ የተሻለ መሠረት የምናስይዝበት ይሆናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡በሀገሪቱ የተጀመረው የለውጥ ጉዞ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አነሳሽነት በመተግበር ላይ የሚገኘውን የመደመርን እሳቤ መሠረት አድርጎ እንደሚጓዝና በሦስት ዋነኛ ሀገራዊ ዓላማዎች ላይ የተመሠረተ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በሀገሪቱ የነበሩ መልካም የሆኑ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ድሎችን ጠብቆ ማስፋት፣ ባለፉት ዘመናት የተሠሩ ስህተቶችን ማረምና የመጭውን ትውልድ ፍላጎትና ጥቅም ማሳካት ናቸው ብለዋል ፕሬዝዳንቷ፡፡ያለፈው ዓመት በሀገሪቱ የተጀመረው የለውጥ እንቅስቃሴ ዘርፈ ብዙና ሁሉን አቀፍ በሆነ መልኩ እንዲተገበር ጥረት የተደረገበት ወቅት እንደነበርም አንስተዋል፡፡በፖለቲካ፣ በዴሞክራሲ፣ በሰብአዊ መብት አያያዝ፣ በፍትሐዊ ተጠቃሚነት፣ በፍትሕ ሥርዓት እና በኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የነበረብንን ሀገራዊ ጉድለት ማስተካከል የተጀመረበት መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ ይሁንና ጉድለቱን በተሟላ ያቃናንበት ደረጃ ላይ ገና አልደረስንም ያሉት ፕሬዝዳንቷ፣ አንዳንዶቹም በባሕሪያቸው መዋቅራዊ በመሆናቸው ከአንድ ዓመት አለፍ የሚል ምክንያታዊ ጊዜን የሚጠይቁም ናቸው ብለዋል፡፡የደኅንነትና የጸጥታ ተቋማትን እንዲሁም የመከላከያ ሠራዊትን የሕጋዊ ማዕቀፎችና አቅሞችን በማዳበርና በቴክኖሎጂ እንዲታገዝ በማድረግ በሀገሪቱ ያለውን አንጻራዊ ሠላም ወደ አስተማማኝ ሠላም ለማሳደግ በትኩረት ይሠራል ሲሉ ተናገረዋል፡፡  በቀጣይ ሀገሪቱ የምታስተናግዳቸውን ሀገራዊ ምርጫ እና ሌሎች ክስተቶች ሠላማዊ በሆነ መልኩ ለመፈጸም የሚያስችል አቅም ይፈጠራልም ነው ያሉት ፕሬዝዳንቷ።ኢትዮጵያ ከጎረቤት አገራት የተሰደዱትን ማስተናገዷን የቀጠለችውን ያህል በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች በገዛ ሀገራቸው ተፈናቃይ የሆኑበትን አሳዛኝ የታሪክ ገጽ አልፈናል ያሉት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ፣ የፌዴራልና የክልል መንግሥታት ባለፈው አንድ ዓመት በጋራ ባደረጉት ርብርብ ከሁለት ሚሊዮን በላይ የነበረው የውስጥ ተፈናቃዮች ቁጥር በአሁኑ ወቅት ከመቶ ሺ የማይዘል እንደሆነ ገልጸዋል።“ያለፍንባቸው የታሪክ ምዕራፎቻችን መልካም ጸጋዎች እንዳሉት ሁሉ በርካታ ስህተቶችም እንዳሉት የጠቆሙት ፕሬዝዳንቷ፣ እኩልነትን፣ ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን፣ የብሔር ብሔረሰቦች መብትን፣ አካታችነትን፣ የሰብአዊ መብት አያያዝን፣ የፍትሕ ሥርዓት መዛነፍን በተመለከተ የተፈጸሙ ስህተቶች እንዳሉ ተናግረዋል።“በቅርቡ ታሪካችን እንኳን ልዩነቶቻችን ላይ የሠራነውን ያህል አንድነታችን ላይ አልሠራንም፣ የኢኮኖሚ እድገቱ ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን በሚገባው ልክ አላረጋገጠንም፣ በሰብአዊ መብት አያያዛችንና በፖለቲካዊ መብቶቻችን ላይ ሰፊ ጉድለቶች ተመዝግበዋል። እነዚህ የተወዘፉ ዕዳዎቻችን ናቸው። ውዝፍ ስህተቶቻችንን ያለ ምሕረት ማረም ይኖርብናል” ሲሉም አንስተዋል፡፡ 
https://waltainfo.com/am/31381/
291
5ፖለቲካ
የኢሬቻ በዓል በሆራ ፊንፊኔ ተከበረ
ሀገር አቀፍ ዜና
October 5, 2019
Unknown
የኦሮሞ ገዳ ሥርዓት አካል የሆነው የኢሬቻ በዓል በሆራ ፊንፊኔ በገዳ ሥርዓት መሰረት በአባ ገዳዎች ምርቃት ተጀምሮ በድምቀት ተከብሯል፡፡  ከአዲስ አበባ እና ዙሪያዋ እንዲሁም ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ለበዓሉ በባህል አልባሳት ደምቀው ሆራ ፊንፊኔ ላይ የተገኙት የኦሮሞ እና የሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ተወላጆች ኢሬቻውን በአንድነት መንፈስ በጋራ አክብረውታል፡፡በኢሬቻ በዓል የኦሮሞ ሕዝቦች ላገኙት ፀጋና በረከት፣ ሰላምና ደስታ፣ ጤናና ዕድሜ፣ ፍቅርና ክብር፣ ብርሃንና ተሥፋ፣ ከአንድ ወቅት ወደ ሌላ ወቅት በአጠቃላይ ከዘመን ወደ ዘመን በሰላም ላሸጋገራቸው አንድ አምላካቸው – ለዋቃ – ከመዲናዋ እና ከተለያዩ የሀገሪቱ አቅጣጫዎች የተሰባሰቡ ዜጎች በተለያዩ የኦሮሞ ባህላዊ ልብሶች ደምቀው በሆራ ፊንፊኔ ለፈጣሪያቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡በርካታ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችም ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን በዓሉ በሰላም እንዲከበር ጉልህ አስተዋፅዖ ማበርከታቸው ታውቋል፡፡  የገዳ ስርዓት በውስጡ ካቀፋቸው ክንዋኔዎች መካከል አንዱ የሆነው የኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ ከ150 ዓመት በኋላ ዘንድሮ ሲከበር የመጀመሪያው ነው።በዓሉ በተለያዩ ቦታዎች የሚከበር ሲሆን፥ የኦሮሞ ህዝብ የማንነቱ መገለጫ የሆነውን በዓል በአንድ ላይ ተሰብስቦ በየዓመቱ የመስቀል/ጉባ/ በዓልን ተከትሎ ባለው የመጀመሪያ እሁድ ቢሾፍቱ በሚገኘው ሆረ አርሰዲ ያከብራል።ኢሬቻ በዓመት ሁለት ጊዜ ይከበራል፤ በበጋ ወቅት በከፍታ ቦታ ላይ የሚከበር ወይም ኢሬቻ ቱሉ እንዲሁም በጸዳይ ወቅት መግቢያ ላይ በወንዝ ዳር የሚከበረው ወይም ኢሬቻ መልካ በመባል የሚታወቅ ነው።   
https://waltainfo.com/am/32780/
177
0ሀገር አቀፍ ዜና
ሰሜን ኮሪያና አሜሪካ እንደገና ድርድር ሊጀምሩ ነው
ፖለቲካ
October 6, 2019
Unknown
የአሜሪካና የሰሜን ኮሪያ ባለስልጣናት በሁለቱ አገራት የተቋረጠውን የኒዩክሌር ጦር መሳሪያ ንግግር መልሶ ለማስጀመር ያስችላል ተብሎ ተስፋ የተጣለበትን ድርድር መልሶ ለማስጀመር ሲዊዲን ገቡ።በፕሬዝዳንት ትራምፕና በሰሜን ኮሪያው መሪ መካከል በመጨረሻ የተደረገው ውይይት ያለስምምነት ነበር የተጠናቀቀው።ከዚያ በኋላ ሁለቱም አገራት ድርድሩን ለመቀጠል ፍላጎት እንዳላቸው ቢገልጹም ብዙም የጎላ እርምጃ ሳያሳይ ቆይቷል።የአሁኑ የንግግር ፈቃደኝነት የመጣው ሰሜን ኮሪያ ቀደም ካሉት ሙከራዎቹ ከፍ ባለ ሁኔታ አዲስ ሚሳኤል ለሙከራ ከተኮሰች ከቀናት በኋላ ነው።ይህ ሚሳኤል ባሕር ላይ ከሚገኝ ማስወንጨፊያ ላይ የተተኮሰ ሲሆን፣ ከባሕር ሰርጓጅ መርከብ ሊተኮስም ይችላል፤ ይህም ማለት ሰሜን ኮሪያ ከግዛቷ ውጪ ሚሳኤሎችን የማስወንጨፍ ብቃት እንዳላት ያመለክታል።ሰሜን ኮሪያ ተወንጫፊ ሚሳኤሎችን እንዳትጠቀም በተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት እገዳ የተጣለባት ሲሆን፤ እያካሄደችው ባለው የኒዩክሌር ግንባታ ፕሮግራም ምክንያት ደግሞ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና በአሜሪካ ማዕቀብ ተጥሎባታል።ከሲዊዲኗ ዋና ከተማ ስቶክሆልም ሰሜን ምሥራቅ በምትገኘው ሊዲንጎ በተባለችው ደሴት ላይ በሚካሄደ የሁለቱ አገራት ድርድር ላይ የአሜሪካ የሰሜን ኮሪያ ልዩ ተወካይ ስቴፈን ቢገን እንዲሁም የሰሜን ኮሪያው ኪም ጊል ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። (ምንጭ፡-ቢቢሲ)
https://waltainfo.com/am/34009/
144
5ፖለቲካ
​​​​​​​ከ2 ሺህ በላይ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
ፖለቲካ
October 6, 2019
Unknown
በነዳጅ ማመላለሻ ቦቴ ተጭኖ የነበረ ከ2 ሺህ 200 በላይ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች እና አሽከርካሪው ጎንደር ከተማ ላይ ትላንት ማምሻውን በቁጥጥር ስር ውለዋል።አሽከርካሪው የጦር መሳሪያዎቹን በመጫን መነሻውን ከሱዳን አድርጎ ወደ ጎንደር ሲገባ እንደተያዘ ከስፍራው የተገኘው መረጃ ያመላክታል። ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በተደረገ ቆጠራ 2 ሺህ 221 ቱርክ ሰራሽ ሽጉጥ፣ 34 ባለ ሁለት እግር ታጣፊ ክላሸንኮቭ፣ አንድ ባለ አንድ እግር ታጣፊ ክላሸንኮቭ፣ 35 ባለሰደፍ ክላሸንኮቭ እና አንድ ጄ ኤም-3 እንደተያዘ ታውቋል።የጦር መሳሪያዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ሰራተኞች እና በአማራ ክልል የሰላምና ደኅንነት ግንባታ ቢሮ በጥምረት እንደሆነ ተገልጿል።ህብረተሰቡ አካባቢውን ነቅቶ እንዲጠብቅ፣ ለፀጥታ አስጊ እና አጠራጣሪ ሁኔታዎችን ሲመለከትም ለፀጥታ ኃይሉ እንዲያሳውቅ የክልሉ የሰላምና ደኅንነት ግንባታ ቢሮ ጥሪ አቅርቧል። (መንጭ፡-አብመድ)
https://waltainfo.com/am/31378/
109
5ፖለቲካ
የተባበሩት መንግሥታት ብዙዎችን እየቀጠፈ ያለውን የኢራቅ ተቃውሞ እንዲቆም ጠየቀ
ፖለቲካ
October 6, 2019
Unknown
የተባበሩት መንግሥታት ብዙዎችን እየቀጠፈ ያለውን የኢራቅ ተቃውሞ እንዲቆም ጠየቀ፡፡የተባበሩት መንግሥታት "ትርጉም አልባ ሞት" ባለው የኢራቅ ተቃውሞ የሟቾች ቁጥር መቶ ደርሷል።ተቃዋሚዎቹ ሥራ አጥነት፣ ያልተሟሉ የሕዝብ አገልግሎቶችና በአገሪቱ ውስጥ የተንሰራፋውን ሙስናን ለመቃወም የወጡ መሆናቸው ተነግሯል።በኢራቅ የተባበሩት መንግሥታት እርዳታ ተልዕኮ ዋና ኃላፊ ጂኒ ሄኒስ ፕላስቻርት "አምስት ቀናት ሙሉ ሞትና ጉዳት ተከስቷል፤ ይህ ሊቆም ይገባል" ብለዋል።ኃላፊዋ አክለውም ከፍተኛ ቁጥር ላላቸው ሰዎች ሕይወት መቀጠፍ ምክንያት የሆኑ ግለሰቦች ችሎት ፊት ሊቆሙ እንደሚገባ ተናግረዋል።ቅዳሜ መስከረም 24፣ 2012 የፀጥታ ኃይሎች ከፍተኛ ቁጥር የነበረውን የተቃውሞ ሰልፍ በምስራቃዊ ባግዳድ በትነዋል።ይህንንም ተከትሎ በመዲናዋ ባግዳድ አምስት ሰዎች የሞቱ ሲሆን፤ የፀጥታ ኃይሎች የጎማ ጥይቶችን እንዲሁም አስለቃሽ ጋዞችን ተጠቅመዋል ተብሏል።የኢራቅ የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ ምክር ቤት እንዳሳወቀው፤ ቢያንስ 99 ሰዎች እንደሞቱና አራት ሺህ የሚሆኑ ግለሰቦች ደግሞ ተቃውሞ ከጀመረበት ማክሰኞ እለት ጀምሮ እንደቆሰሉ ነው። ተቃውሞው ከመዲናዋ ወደ ደቡባዊ ኢራቅም ተዛምቷል።የብዙዎችን ሕይወት የቀጠፈ የተባለው ይህ አለመረጋጋት ከሁለት ዓመት በፊት አይኤስ ተሸንፏል መባሉ ከታወጀ በኋላ ካጋጠመው የከፋ ነው ተብሏል።እየተፍረከረከ ያለውን የጠቅላይ ሚኒስትር አደል አብደል ማሃዲን መንግሥትንም የፈተነ ተብሏል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ሥልጣን ከመጡ ዓመት ሆኗቸዋል።የአገሪቱ ባለሥልጣናት የሰዓት እላፊ በማወጅ እንዲሁም ኢንተርኔትን ሙሉ በሙሉ በመዝጋት ተቃውሞውን ለመቆጣጠር እየሞከሩ ነው ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡።
https://waltainfo.com/am/34010/
173
5ፖለቲካ
ግብጽ ሶስተኛ ወገን በጉዳዩ ጣልቃ እንዲገባ እያቀረበች ያለው ሃሳብ ኢትዮጵያ እንደማትቀበለው ገለፀች
ቢዝነስ
October 6, 2019
Unknown
የግብጽ መንግስት ሶስተኛ ወገን በጉዳዩ ጣልቃ እንዲገባ እያቀረበ ያለው ሃሳብ በሶስቱ አገራት የትብብር መድረክ የታየውን አበረታች ሂደት የሚያጣጥል በመሆኑ ኢትዮጵያ እንደማትቀበለው ገለፀች ።የግብጽ፣ ኢትዮጵያ እና ሱዳን የውሀ ጉዳይ ሚኒስትሮች መስከረም 5 እና 6 ቀን 2012 ዓ.ም በካይሮ ባካሄዱት ስብሰባ ባስቀመጡት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት በካርቱም የሶስትዮሽ ስብሰባቸውን አካሂደዋል፡፡ከሚኒስትሮቹ ስብሰባ አስቀድሞ የአገራቱ ገለልተኛ የሳይንሳዊ ጥናት ቡድን ከመስከረም 19 እስከ 22 ቀን 2012 ዓ.ም በካርቱም አምስተኛ ዙር ስብሰባውን አካሂዶ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሙሌት እና የውሃ አለቃቅ ቴክኒካዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክሯል፡፡የኢትዮጵያ መንግስት በአገራቱ መካከል የሚደረገው ቴክኒካዊ ምክክር ብቸኛው የመፍትሄ አማራጭ በመሆኑ መቀጠል እንደሚኖርበት ያምናል፡፡የሳይንሳዊ ቡድኑ አራት ስብሰባዎችን አድርጎ አበረታች ውጤት እያሳየ ባለበት ወቅት ግብጽ በተናጠል ያቀረበችው የውሃ ሙሌት እና አለቃቀቅን የሚመለከተው ሰነድ ከትብብር ማዕቀፉ ውጪ የሆነ እና ሂደቱን ያናጠበ ሆኗል፡፡ሆኖም የውሃ ሚኒስትሮች የኢትዮጵያ የውሃ ሙሌት እና አለቃቀቅ እቅድ፣ የግብጽ መንግስት የሚያቀርበው ሰነድ እንዲሁም ሱዳን በጉዳዩ ላይ የምታቀርበው ሰነድ ለሳይንሳዊ ቡድኑ ቀርቦ ዝርዝር ትንታኔ እንዲደረግበት እና ምክረ ሃሳብ እንዲቀርብለት በመስከረም ወር 2012 ዓ.ም በካይሮ በተደረገው ስብሰባ ወስነዋል፡፡በካርቱም አራት ቀናትን ወስዶ በተካሄደው ስብሰባ የሳይንሳዊ ቡድኑ በመስከረም ወሩ የካይሮ ስብሰባ በተሰጠው አቅጣጫ መሠረት የኢትዮጵያን የግድብ ሙሌት እና የውሃ አለቃቅ ዕቅድ፣ እንዲሁም ሱዳን እና ግብጽ ያቀረቡትን የሙሌት እና የውሃ አለቃቅ ቴክኒካዊ ጉዳዮችን የሚዳስሰውን ሃሳብ አዳምጦ ውይይቶችን አካሂዷል፡፡ውይይቱ ሶስቱም ቡድኖች በተስማሙበት የርዕሰ ጉዳይ መዘርዝር ላይ የተመሰረተ ሲሆን በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ከመስማማት ተደርሶ በሌሎቹ ላይ የሃሳብ መለያየቶች ተመዝግበዋል፡፡እነዚህ የሃሳብ ልዩነቶች በሳይንሳዊ እና ጥናት ቡድኑ ውይይት እና ትንተና መግባባት ሊደረስባቸው የሚችሉ ናቸው፡፡ኢትዮጵያ ግድቡን እሰከ ሰባት አመት ድረስ በሚወስድ ሂደት ለመሙላት ያቀረበችው እቅድ የታችኛውን ተፋሰስ አገራት ጥቅም ለመጠበቅ ያላትን አቋም ያሳያል፡፡ይህም በተጨማሪም ኢትዮጵያ እና ሱዳን ማናቸውም ቴክኒካዊ ጉዳዮች ለሳይንሳዊ ጥናት ቡድኑ ቀርበው ትንተና እንዲደረግባቸው ገንቢ እና አካታች የውይይት አካሄድ ቢከተሉም የግብጽ ወገን ያቀረብኳቸው ሃሳቦች በሙሉ ተቀባይነት ካላገኙ ውይይቱ ሊቀጥል አይችልም በሚለው የማያሰራ አቋሙ በመቀጠሉ የሳይንሳዊ ጥናት ቡድኑ ስራውን በተሟላ አኳኋን ማከናወን ሳይችል ቀርቷል፡፡ይህ የግብጽ አቋም የሳይንሳዊ ጥናት ቡድኑ ስብሰባ እንዲሁም የሚኒስትሮች ስብሰባው ስምምነት በተደረሰባቸው ጉዳዮች ላይ ጭምር ሪፖርት እንዳያዘጋጁ አድርጓል፡፡ይህ የግብጽ አካሄድ አዲስ ሳይሆን ከዚህ ቀደምም በግድቡ ላይ ሶስቱ አገራት ሊያከናውኑት የነበረውን የውሃ፣ የአካባቢያዊ እና ማህበራዊ ተጽእኖ ጥናት በግብጽ ወገን እንዲስተጓጎል በተደረገ ጊዜ የታየ የሳይንስ እና የምክክር የመፍትሄ አማራጭን የማፋለስ ዘዴ ነው፡፡ኢትዮጵያ አለመግባባት መፍቻ ዘዴን የሚደነግገውን የመርህ መግለጫ ስምምነቱን አንቀጽ 10 ጠቅሶ መፍትሄ ለመፈለግ ጊዜው እንዳልሆነ እና ቴክኒካዊ ምክክሩ ሊቀጥል እንደሚገባ ታምናለች፡፡የውሃ ሚኒስትሮቹ በሁለት ቀናት ስብሰባቸው የሳይንሳዊ ጥናት ቡድኑ የደረሰበትን ተመልክተው አቅጣጫ ለማስቀመጥ ከፍተኛ ጥረት ቢያደርጉም የግብጽ ወገን ቀድሞውኑ የምክክር ሂደቱ እንዲፋረስ አቋም ይዞ የመጣ በመሆኑ ጉባኤው የሳይንሳዊ ጥናት ቡድኑ በቀጣይነት ማከናወን ስላለበት ተግባር መመሪያ ሳያስተላልፍ ቀርቷል፡፡የግብጽ መንግስት ሶስተኛ ወገን በጉዳዩ ጣልቃ እንዲገባ እያቀረበ ያለው ሃሳብ በሶስቱ አገራት የትብብር መድረክ የታየውን አበረታች ሂደት የሚያጣጥል እና ሶስቱም አገራት በመጋቢት 2007 ዓ.ም. የፈረሙትን የመርሆዎች መግለጫ ስምምነት የሚጥስ ተግባር ነው፡፡የሶስተኛ ወገን ጣልቃ-ገብነት ኢትዮጵያ እና ሱዳን የማይቀበሉት እና ተገቢ ያልሆነ፤ በአገራቱ መካከል ያለውን ዘላቂ ትብብር የሚጎዳ፤ ለውይይት ያለውን በቂ እድል ወደጎን የሚያደርግ እና ገንቢ የሆነውን የውይይት መንፈስ የሚያደፈርስ ነው፡፡ቴክኒካዊ ምክክር የሚጠይቀው የግድብ ሙሌት እና ውሃ አለቃቀቅ ጉዳይ ለፖለቲካ ምክክር እንዲቀርብ የሚጠይቀው ሃሳብም የጉዳዩን ጠባይ ያላገናዘበ፣ የሶስቱ አገራት መሪዎች የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጉዳዩን ለመፍታት የሰጡትን መመሪያ የጣሰ እንዲሁም ተገቢ መፍትሄ ለመስጠት የማያስችልም ነው፡፡የኢትዮጵያ መንግስት ልዩነቶችን ለመፍታት እድል የሚፈጥረውን የምክክር ሂደት ለማጠናከር እንደሚሰራ እየገለጸ በጉዳዩ ላይ የሚሰራጨው የመገናኛ ብዙሃን እንዲሁም ሌላ አሉታዊ ዘመቻ የሶስቱን አገራት መተማመን ከመሸርሸር ያለፈ ውጤት እንደማይኖረው ይገልጻል፡፡የኢትዮጵያ መንግስት በተደጋጋሚ እንደገለጸው የአባይን ውሃ የኢትዮጵያ ህዝቦችን የአሁን እና የወደፊት ፍላጎት ለማሟላት እና ብሄራዊ ጥቅምን ለማረጋገጥ ማልማቱን በመቀጠል ርትዕን የጠበቀ እና በማናቸውም የተፋሰሱ አገራት ላይ ጉልህ ጉዳት የማያደርስ አጠቃቀም እንዲኖር ይሰራል፡፡በተጨማሪ የኢትዮጵያ መንግስት በሕዳሴ ግድብ ላይ በሚደረገው ውይይት የሚከተለው አቅጣጫ የናይል ውሃን አስመልክቶ ለተደረጉት እና በኢትዮጵያ ላይ ምንም አይነት ተፈጻሚነት የሌላቸውን ስምምነቶች እውቅና የማይሰጥ እንዲሁም የላይኛውን የናይል ተፋሰስ አገራት መብት የማይጥስ እንዲሆን ነው፡፡ (ምንጭ:-የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር)
https://waltainfo.com/am/23994/
570
3ቢዝነስ
የኢሬቻ በዓል በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዴ በድምቀት ተከበረ
ሀገር አቀፍ ዜና
October 6, 2019
Unknown
የኢሬቻ በዓል ከንጋት 11 ሰዓት ጀምሮ በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዴ በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል፡፡በዓሉ በሆራ አርሰዴ በአባገዳዎች ምርቃትና የምስጋና ስነስርዓት ነው የተጀመረው፡፡ከኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በመምጣት በስፍራው የተገኙ አባቶች፣ እናቶች፣ ወጣቶችና ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች የምስጋና ስነስርአት አድርሰዋል።የሲዳማ እና ሃላባ ወጣቶችም ታድመው በስፍራው በመገኘት የየባህላቸውን መገለጫዎች አሳይተዋል።ከንጋቱ 11 ሰዓት በተጀመረው ፕሮግራም በተለያዩ መርሃ ግብሮች አባ ገዳዎችና ከተለያዩ አካባቢዎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡ኢሬቻ በዓመት ሁለት ጊዜ የሚከበር ሲሆን፣ በበጋ ወቅት በከፍታ ቦታ ላይ የሚከበር ወይም ኢሬቻ ቱሉ እንዲሁም በጸዳይ ወቅት መግቢያ ላይ በወንዝ ዳር የሚከበረው ወይም ኢሬቻ መልካ በመባል የሚታወቅ ነው፡፡በዛሬው ዕለት በቢሾፍቱ የተከበረው ኢሬቻ መልካ የኦሮሞ ህዝብ የክረምት ወቅት ማለፉንና የጸደይ ወቅት መምጣቱን አስመልክቶ ለታና አደይ አበባን በመያዝ ለፈጣሪ ምስጋና የሚቀርብበት በዓል ነው፡፡ትላንትና በአዲስ አበባ በዓሉ በተመሳሳይ ሁኔታ በድምቀት ተከብሮ ማለፉ ይታወቃል።
https://waltainfo.com/am/32782/
119
0ሀገር አቀፍ ዜና
በቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት የተገነባው የቁስቋም ብርሃን የህፃናት ማሳደጊያ ማዕከል ተመረቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
October 3, 2019
Unknown
በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት በ12 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የቁስቋም ብርሃን የህፃናት ማሳደጊያ ማዕከል ዛሬ ተመረቀ፡፡ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው በምረቃ ሥነስርዓቱ ላይ የቁስቋም ብርሃን የህፃናት ማሳደጊያ ማዕከል ግንባታ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ በአጭር ጊዜ በመጠናቀቁ መደሰታቸውን ገልፀዋል፡፡መሰል የበጎ አድራጎት ስራዎችን መስራት ለሚፈልጉ አካላት ጽህፈት ቤታቸው ክፍት መሆኑን በመግለፅ  ጽህፈት ቤቱ የጀመራቸውን ስራዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል፡፡ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የካቲት 29 ቀን በቁስቋም የህፃናት ማሳደጊያ ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ማስቀመጣቸው ይታወሳል፤ ከስድስት ወራት በኋላ የቁስቋም ብርሃን የህፃናት ማሳደጊያ ማዕከልን ለዘውዲቱ መሸሻ የህጻናት ማሳደጊያ አስረክበዋል፡፡ከ1984 ዓ.ም ጀምሮ ለ250 ህጻናት እናት ሆነው ሲያሳድጉ የነበሩት የዘውዲቱ መሸሻ የህፃናት ማሳደጊያ መስራች ወ/ሮ ዘውዲቱ መሸሻ በበኩላቸው ለተደረገላቸው መልካም ስራ አመስግነዋል፡፡በምርቃት ስነ ስርአቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በበኩላቸው የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት በከተማዋ ውስጥ ለሚሰራቸው ስራዎች ሁሉ የከተማ አስተዳደሩ ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡የቁስቋም ብርሃን የህፃናት ማሳደጊያ ማዕከል ከ90 በላይ ህጻናትንም ማስተናገድ እንደሚችል ተገልጿል፡፡በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት እስከአሁን 20 ትምህርት ቤቶች በመገንባት ላይ ይገኛሉ፡፡ 
https://waltainfo.com/am/32779/
151
0ሀገር አቀፍ ዜና
የአዲስ አበባ ፖሊስ የደንብ ልብስ ተቀየረ
ፖለቲካ
October 3, 2019
Unknown
የአዲስ አበባ ፖሊስ ለበርካታ ጊዜ ሲጠቀምበት የነበረውን የደንብ ልብስ በአዲስ ዘመናዊ የደንብ ልብስ ተቀይሯል፡፡የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ አዲሱን የአዲስ አበባ የፖሊስ አባላት የደንብ ልብስ መርቀዋል፡፡በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የከተማዋን ሰላም እና ደህንነት ለመጠበቅ ጠንካራ ስራ እየሰራ ያለውን የአዲስ አበባ ፖሊስ የማዘመን ስራ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡በዘላቂነትም የከተማ አስተዳደሩ አዲስ አበባን የሚመጥን ዘመናዊ እና የተደራጀ የፖሊስ ሰራዊት ግንባታ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ምክትል ከንቲባ ተናግረዋል፡፡የተመረቀው የአዲስ አበባ ፖሊስ የደንብ ልብስ የኮሚሽኑ አርማ ያለበት ሲሆን በሂደት ለሁሉም አባላት እንደሚሰራጭ ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
https://waltainfo.com/am/31376/
84
5ፖለቲካ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ልዩ መልእክተኛን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ
ፖለቲካ
October 4, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራምፓሳ ልዩ መልእክተኛ የሆኑትን ጄፍ ራዴብ እና ዶ/ር ኩሁሉ ባታን ጠዋት በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ::ልዩ መልእክተኞቹ የፕሬዝዳንት ሲሪል ራምፖሳን የሁለቱን ሀገራት ታሪካዊ ግንኙነት ያነሳውን መልእክት ሲያስተላልፉ ግንኙነቱን ወደ ስትራቴጃዊ ደረጃ ከፍ ለማድረግም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በደቡብ አፍሪካ ኦፊሴላዊ ጉብኝት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል::በቅርቡ በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ የውጭ ሀገር ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት እና ዝርፊያ በበቂ ለመከላከል መንግሥታቸው እየሰራ መሆኑን የገለፁት መልእክተኞቹ እዛ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እየተጫወቱት ያለውን በጎ ሚናም አድንቀዋል::በተጨማሪም መልእክተኞቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እስረኞችን በመፍታትና ከኤርትራ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር ላሳዩት የአመራር ብቃት ያላቸውን አድናቆት ገልፀዋል::ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በበኩላቸው፤ በኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካ መካከል ያለውን መልካም ግንኙነት ማሳያዎች ጠቅሰዋል:: ደቡብ አፍሪካ የአፍሪካ የኢኮኖሚ እድገትና ዴሞክራሲ እድገት ማሳያ መሆኗንም አድንቀዋል::በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ አትዮጵያውያን በሚኖሩበትም ሆነ በሀገራቸው ኢትዮጵያ እየተጫወቱ ያለውን ሚና በማንሳትም የደቡብ አፍሪካ መንግስት ይህንኑ ትጋታቸውን እንዲደግፍ ጥሪ አቅርበዋል:: (ምንጭ፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት)
https://waltainfo.com/am/31377/
142
5ፖለቲካ
የገዳ ሥርዓትን የሚያሳይ ሐውልት ተመረቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
October 3, 2019
Unknown
የገዳ ሥርዓትን የሚያሳይ ሐውልት በሰበታ ከተማ ዛሬ ተመርቋል፡፡በሐውልቱ የምረቃ ሥነሥርዓት ላይ የተገኙት በኦዴፓ ማዕከላዊ ጽሕፈት ቤት የከተማ አደረጃጀትና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ካሣሁን ጎፌ የኦሮሞ ሕዝብ ለዘመናት ሲተዳደርበት የነበረው የገዳ ሥርዓት የሁሉም ኢትዮጵያዊ መገለጫ ነው ብለዋል፡፡የሐውልቱ መመረቅ ዘንድሮ በአዲስ አበባ ከሚከበረው የኢሬቻ በዓል ጋር ሲገናኝ ትርጉሙ የጎላ እንደሆነ አቶ ካሣሁን አክለው ገልጸዋል፡፡የገዳ ሥርዓት ለዘመናት ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲሸጋገር የመጣ የኦሮሞ ሕዝብ እሴት ቢሆንም፣ የሐውልቱ መቆም ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የአንድነት መገለጫ እንደሆነም ተገልጿል፡፡የሰበታ ከተማ ከንቲባ አቶ ብርሃኑ በቀለ በበኩላቸው የሐውልቱን የግንባታ 8 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ወጪ የሰበታ ከተማ አስተዳድር መሸፈኑንና ሐውልቱ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የሠላም ምልክት ነው ብለዋል፡፡ለሐውልቱ ተጨማሪ እንክብካቤዎችና የማስዋብ ሥራዎች እንደሚከናወኑለትም ከንቲባው አክለው ገልጸዋል፡፡ሐውልቱ ከአዲስ አበባ ቅርብ በሆነ ከተማ መቆሙ ለከተማዋም ሆነ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ኩራትና የመተሳሰብ ማሳያ ነው ሲሉ የኦሮሞ አባ ገዳዎች ተወካዮች ተናግረዋል፡፡ ወጣቱ ትውልድ ለዘመናት የቀጠለውን የአባ ገዳዎች ሥርዓት በመጠበቅ ለኢትዮጵያዊያን በጋራና በሠላም መኖር ማሳያነቱን ማስጠበቅ አለበት ብለዋል፡፡       
https://waltainfo.com/am/32778/
139
0ሀገር አቀፍ ዜና
ኤልያስ መልካ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
ሀገር አቀፍ ዜና
October 5, 2019
Unknown
የሙዚቃው ሰው ኤልያስ መልካ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።ኤልያስ የሙዚቃ አቀናባሪ፣ የዜማና ግጥም ደራሲ፣ ጊታርና ፒያኖ ተጫዋች ሲሆን፥ አዳዲስ ሙዚቀኞችን ለኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ አስተዋውቋል።  ከያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ቼሎ የሙዚቃ መሳሪያን ተምሮ ከጨረሰ በኋላ ከመምህሩ አክሊሉ ዘውዴ፣ ከእዝራ አባተ ከያሬድ ተፈራና ከሌሎችም ጋር በመሆን በመዲና ባንድ ውስጥ ሰርቷል።በተጨማሪም ከመሃሙድ አህመድ፣ ከፍቅርአዲስ ነቃጥበብ፣ ከአለማየሁ እሸቴ፣ ቴዲ አፍሮ፣ እዮብ መኮንን፣ ሚካኤል በላይነህ፣ ዘሪቱ ከበደ፣ ልኡል ሀይሉ፣ ሀይሌ ሩትስ፣ ሚካያ በሃይሉ፣ ትግስት በቀለ፣ ቤሪ እና ዳን አድማሱ ጋር አብሮ በመስራት በሙያው አሻራውን አኑሯል፡፡ከዜማ ላስታስና ከአፍሮ ሳውንድስ ባንዶች ጋርም የሰራበት ጊዜ ነበር። ኤልያስ ከ40 በላይ ሙሉ አልበሞችን አቀናብሯል። ሙዚቀኛ ኤልያስ መልካ የስኳር እና ኩላሊት ህመም ገጥሞት ህክምናውን የቆየ ቢሆንም ሕመሙ ተባብሶበት በሆስፒታል ህይወቱ እንዳለፈ ታውቋል፡፡     
https://waltainfo.com/am/32781/
110
0ሀገር አቀፍ ዜና
ኢሬቻ የኦሮሞ ህዝብ በሃይማኖትና በፖለቲካ አመለካከት ሳይለያይ አንድነቱን የሚያሳይበት በዓል ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ
ሀገር አቀፍ ዜና
October 3, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው ኢሬቻ የኦሮሞ ህዝብ በሃይማኖትና በፖለቲካ አመለካከት ሳይለያይ አንድነቱን የሚያሳይበት በዓል ነው ብለዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለበዓሉ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ለኦሮሞ ህዝብ ምስጋና ለሚቀርብበትና፣ የፍቅር፣ አንድነት፣ ይቅርታና የእርቅ መገለጫ ለሆነው የኢሬቻ በዓል እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል፡፡በዓሉ የኦሮሞ ህዝብ ሰማይና ምድር፣ ወንዞችና ሐይቆች፣ ክረምትና በጋ፣ ሌሊትና ቀን፣ ሕይወትና ሞትን ለፈጠረው ፈጣሪ ምስጋና የሚያቀርብበት ቀን ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ የኢሬቻ በዓል የፈጣሪና ፍጥረታት ግንኙነት የሚንጸባረቅበት በዓል ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት፡፡ኢሬቻ በመንግስታቱ ድርጅት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ተመዝግቦ ያለው የገዳ ስርዓት አካል ሲሆን፣ ገዳ ስርዓት ከስርዓትነትም አልፎ ዘመናዊ የአመራር ስልትን ለዓለም ያበረከተ ነው ብለዋል፡፡የገዳ ስርዓት ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር የሚደረግበት ሲሆን፣ የስልጣን ዘመን በአግባብ ከተመራ በኋላ የስልጣን ሽግግሩ ዴሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ በመግባባትና በመረዳዳት የሚከናወን መሆኑን ዶ/ር ዐቢይ ገልጸዋል፡፡“ዛሬም ለችግራችን መፍትሔ የሚሆነው ወደ ቀደመው ባህላችን ተመልሰን ከዘመናዊ ስርዓት ጋር በማስተሳሰር የገዳ ስርዓትም መጠቀም ነው” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡
https://waltainfo.com/am/32777/
145
0ሀገር አቀፍ ዜና
የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ፖሊሲ እየተዘጋጀ መሆኑ ተገለፀ
ሀገር አቀፍ ዜና
October 3, 2019
Unknown
የ2011 ዓ.ም የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃግብር የማጠቃለያ ፕሮግራም ላይ አገልግሎቱን ለማጠናከር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ፖሊሲ እየተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል፡፡በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ በጎ ፈቃድ ማለት ከያገባኛል ስሜት የሚመነጭ የሰብአዊነት መርህ ተግባራዊ የሚደረግበት አገልግሎት ነዉ ብለዋል፡፡መንግስት የወጣቶችን ችግር ለመፍታት የበኩሉን እየተወጣ መሆኑን አፈጉባኤው ጠቁመዉ፣ ለዚህም የበጎ ፈቃድ ሚናን ለማጎልበት ለዘርፉ አስፈላጊዉ ፖሊሲ እየተዘጋጀ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ወጣቶች የአገር አንድነትን ለማስቀጠል በስነ ምግባር የታነፁ፣ ራዕይ ያላቸዉና ጠንካራ የስራ ባህልንም ሊያዳብሩ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡በፕሮግራሙ ላይ በበጀት አመቱ ዉጤታማ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላከናወኑ ወጣቶችና ባለድርሻ አካላት የሽልማትና ዕዉቅና መስጠት ስነ ስርአት ተከናዉኗል፡፡በ2011 ዓ.ም የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ ግብር የ1ሺህ 441 አቅመ ደካሞች ቤቶች ታድሰዋል፡፡       ከ2002 እስከ 2011 ዓ.ም ከ92 ሚሊየን በላይ ወጣቶች በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሳትፈዋል፡፡ 
https://waltainfo.com/am/32776/
116
0ሀገር አቀፍ ዜና
በኮንጎ የ’ሕገወጥ’ የማዕድን ፈላጊዎች ላይ ጉድጓድ ተደርምሶ በርካቶች ሞቱ
ሀገር አቀፍ ዜና
October 3, 2019
Unknown
በዲሞክራቲክ ኮንጎ ወርቅ በሕገወጥ መንገድ ሲያወጡ የነበሩ ሰዎች ላይ ጉድጓድ ተደርምሶ ቢያንስ 14 ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ።የመንግሥት አስተዳደር ሚኒስትር የሆኑት ስቲቭ ምቢካዪ እንዳሉት፤ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሶስት ሰዎች ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል። ጉድጓዱ ውስጥ አፈር ተደርምሶባቸው የቀሩ ካሉ በሚል ፍለጋው እንደቀጠለ ነው።በዲሞክራቲክ ኮንጎ ሕገ ወጥ ማዕድን ፈላጊዎች ላይ እንዲህ አይነት አደጋ የተለመደ ሲሆን፣ የደህንነት መጠበቂያዎችም እጅጉን ኋላ ቀር ናቸው ተብሏል።ምቢካዪ በትዊተራቸው ላይ እንዳሉት ከሆነ የሟቾቹ ቁጥር ከዚህም ሊጨምር ይችላል።የዜጎች መብት ተሟጋች የሆነው ጀስቲን ኪያንጋ አሱማኒ፣ አደጋው ረቡዕ ረፋዱ ላይ መድረሱን ገልጾ፣ ማዕድን አውጪዎቹ እየቆፈሩ የነበረው ማኔይማ በተሰኘቸው ግዛት እንደነበር ተናግሯል።አደጋው በደረሰበት ወቅት "እድሜያቸው 18 ያልሞላ ታዳጊዎችና ነፍሰጡር ሴቶች በስፍራው ማዕድን ፍለጋ ላይ ተሰማርተው ነበር" ሲል አክሏል።በሰኔ ወር ላይ በኮንጎዋ ሉአላባ ግዛት፣ ኮፐርና ኮባልት ማዕድን እየፈለጉ የነበሩ በርካቶች ጉድጓድ ተደርምሶባቸው መሞታቸው ይታወሳል።ዲሞክራቲክ ኮንጎን ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት በተሻለ የመዳብ፣ ኮባልት፣ ዳይመንድ፣ እና ወርቅ ክምችት ያላት ብትሆንም ሕዝቦቿ ግን ዛሬም በከፋ ድህነት ስር ይኖራሉ።በማዕድን በበለፀጉ አካባቢዎች በሕገወጥ መልኩ የሚደረጉ የማዕድን ፍለጋዎች የተስፋፉ ሲሆን፣ ይህንን ለማስቆም በፀጥታ ኃይሉ የሚወሰዱ እርምጃዎች በሙሉ ፍሬ አልባ ሆነው ቀርተዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
https://waltainfo.com/am/33481/
162
0ሀገር አቀፍ ዜና
በአዲስ አበባ እና በቢሾፍቱ የሚከበረውን የኢሬቻ በዓልን ለማክበር ዝግጅት መጠናቀቁን የኦሮሚያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
October 2, 2019
Unknown
መስከረም 24 እና 25 ቀን 2012 ዓ.ም. በአዲስ አበባ እና በቢሾፍቱ የሚከበረው የሆራ-ፊንፊኔ እና ሆራ ሃር-ሳዲ የኢሬቻ ክብረ በዓልን ከዋዜማው ጀምሮ በደማቅ ስነስርዓት ለማክበር ዝግጅት መጠናቀቁን የኦሮሚያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ፡፡ባህላዊ ፌስቲቫሉን በአንድ በኩል የህዝቦች ትስስር ተምሳሌት በሌላ በኩል ደግሞ በቀጣይ የኢሬቻ ፌስቲቫል የሰላምና የአንድነት በዓል አድርጎ በማክበር ለሃገሪቱ ከፍተኛ የቱሪስት ፍሰትን እንዲጨምር ታስቦ እየተሰራበት መሆኑም ተገልፃል፡፡የልምላሜ ምልክት፣ የመልካም ምኞት መገለጫም ተደርጎ በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ በፍስሃ እና ፍቅር ተመስሎ ይከበራል፡፡ በዚህ ስፍራ ስለህብረት እና አንድነት አብዝቶ ማዜም፣ ማወደስ በጉልህ ይስተዋላል፡፡ፖለቲካን ከባህል፤ የህዝብ አስተዳደርንም ከፈርሃ ፈጣሪ አጣምሮ የያዘው የገዳ ስርዓት አንዱና ዋነኛ መገለጫ የሆነው የኢሬቻ በዓል በህዝቡ ዘንድ ያለምንም ሃይማኖታዊ ብሎም ፖለቲካዊ አመለካከት ደምቆ እየተከበረ፤ ከትውልድ ትውልድም ሲወርድ ሲዋረድ እንደመጣ ይነገራል፡፡በዓሉን በባለቤትነት የሚመራው የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮም ዘንድሮ የሚከበረው የኢሬቻ በዓል ከድፍን ምዕተ አመትም ለዘለለው ጊዜ ተቋርጦ የቆየውን የሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ ፊስቲቫልን ዳግም የሚያስጀምር በመሆኑ ሰፋፊ ዝግጅቶች መደረጋቸውን በሰጠው መግለጫ አብራርቷል፡፡በዓሉ ሲከበርም እንዲሁ ህዝብ ተሰባስቦ የሚበተንበት ሳይሆን የእሬቻን እሴት ወደ ላቀ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትና የህዝቦች ትስስር ማጠናከሪያ ገመድ እንዲሆንም መወጠኑ ነው የተጠቆመው፡፡የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊው አቶ ግርማ ኃይሉ ለመገናኛ ብዙሃኑ በሰጡት መግለጫቸው ከወትሮ ከፍ ባለ ዝግጅት ሊደረግ በመሰናዶ ላይ ያለው የዘንድሮ ኢሬቻ ክብረ በዓል ኢኮኖሚውን በማነቃቃት ሚና ውስጥ ጠብታ ውሃን የሚጥል ለመሆኑ በባህላዊ ልብሶች ዘርፍ የተፈጠረውን የባህል ልብስ ገበያን እንደአመላካች ነጥብ ተጠቅሷል፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ ወደ መዲናይቱ ሲመጣም የሚፈጠረው የገበያ እድል ብቻ ሳይሆን የበዓሉን አኩሪ እሴት ለህዝቦች ለማስተዋወቅ ሰፊ ዕድል እንደሚፈጥር ታምኖበት ነው፡፡የኢሬቻ ፌስቲቫል አንዱ አካል የሆነው በበዓሉ እሴት ላይ ያጠነጠነ፣ የመንግስት የስራ ሃለፊዎችና ምሁራን አንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላትን የሚያሳትፈው ኮንፌረንስ ሃሙስ መስከረም 22 ይካሄዳል፡፡ ፎረሙም በሃገሪቱ እና በመላው ዓለም ያለው የኦሮሞ ህዝብ ባለበት ሁሉ የገዳ ስርዓትና እሬቻን ማክበር ባለበት አግባብ ላይ ይመክራል፣ ወደፊት ለሚከበረው የኢሬቻ በዓለም አቅጣጫን ይጠቁማል፡፡ መስከረም 23 በእለተ ዋዜማም ከቀኑ 8 ሰዓት አስከ 12 ሰዓት በመስቀል አደባባይ የተሰናዳውን ዝግጅት ጨምሮ የተለያዩ ባህላዊ ትርዕቶች እና የኦሮሞን ባህል ማስተዋወቅና የአንድነትንም ጥሪ ያስተላልፋል የተባለለት ኮንሰርት ይደረጋል፡፡መስከረም 24 በበዓሉ እለትም እሬቻ ሰላማዊ እና የፍቅር በዓል መሆኑን ለዓለም ሁሉ ለማሳት ይረዳ ዘንድ፤ መልዕክት የሰፈረበት 5 ሚሊየን ነጭ ባነዲራ ተዘጋጅቷል፡፡ በአዘጋጅነቱ የመሪነት ሚናን እየተወጣ ያለው የአአ ከተማ አስተዳደርም የእሬቻ እንግዶቹን ለመቀበል ዝግጅት ማጠናቀቁም በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡ ከሃገር ውጭ በበዓሉ ለመሳተፍ ጥያቄ ያቀረቡ አሉ፡፡ በሃገር ቤት ከኦሮሚያ ክልል ውጭ የበዓሉ ተሳታፊ የሚሆኑ ከተለያዩ ክልሎች ወደ አአ የሚመጡ እንግዶችንም ለመቀበል በአራቱም አቅጣጫ ዝግጅት ተደርጓል፡፡   
https://waltainfo.com/am/32774/
359
0ሀገር አቀፍ ዜና
ዩኒቨርስቲዎች የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና የልህቀት ማዕከላት ለመሆን ቆርጠው መስራት ይገባቸዋል- ፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማርያም
ሀገር አቀፍ ዜና
October 3, 2019
Unknown
ዩኒቨርስቲዎች የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና የልህቀት ማዕከላት ለመሆን ቆርጠው መስራት እንደሚገባቸው ፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማርያም አሳሰቡ፡፡የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማርያም በትናንትናው ዕለት የአክሱም ዩኒቨርስቲን ጎብኝተዋል፡፡ሚኒስቴሩ ላለፉት ሁለት ቀናት በአክሱም ዩኒቨርስቲ ሲያደርገው የነበረውን ግምገማ ሲያጠናቅቅም የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትሯ ፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማርያም በዩኒቨርስቲው በመገኘት ጉብኝትና ከስራ አመራር አካላት ጋር ውይይት አካሂደዋል፡፡በውይይቱ ወቅት ፕሮፌሰር ሂሩት እንዳሉት ዩኒቨርስቲዎች የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና የልህቀት ማዕከላት ለመሆን ቆርጠው መስራት ይገባቸዋል ብለዋል፡፡አያይዘውም አክሱም ዩኒቨርስቲ ቀጣዩን ዓመት ሰላማዊ ለማድረግ ከአከባቢው ማህበረሰብና በዙሪያው ካሉ አጋሮች እንዲሁም ከከተማው የፀጥታ መዋቅሮች ጋር ተቀናጅቶ መስራት መጀመሩን ተናግረዋል፡፡በተለይ የተባረሩ ተማሪዎችም ሆኑ ሌሎች ወደ ዩኒቨርስቲው ሾልከው እንዳይገቡ በዩኒቨርስቲው መግቢያ በር ላይ የጣት አሻራ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ቁጥጥር ማድረግ መጀመሩንም አድንቀዋል፡፡በውይይቱ ወቅት የተለያዩ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን ከነዚህም መካከል የውሃና መብራት እንዲሁም የኢንተርኔት መቆራረጥ ችግሮች ይገኙበታል፡፡ፕሮፌሰር ሂሩት ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽ በሰጡበት ወቅት እንደተናገሩት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የችግሮችንም መፍትሔ ሊያመነጩ ይገባል ብለዋል፡፡ለምሳሌ ያህልም የአካባቢውን የውሃ ችግር የሚቀርፉ ጥናትና ምርምሮችን በማድረግ ችግሩን ለመቅረፍ የሚያስችሉ መንገዶችን ማመላከት እንደሚጠበቅባቸው ጠቁመዋል፡፡የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጸሐዬ አስመላሽም ሰላማዊ መማር ማስተማር ለማስፈን የተለያዩ ስራዎች ሲከናወኑ መቆየታውን ገልጸው የውሃ አቅርቦት፣ የኢንተርኔትና የመብራት መቆራረጥ እንዳይኖር ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ዩኒቨርስቲው በአሁኑ ጊዜ ነባር ተማሪዎችን እየተቀበለ እንደሆነ የገለፁት ፕሬዝዳንቱ 2012 የትምህርት ዘመንን ፍፁም ሰላማዊ ለማድርግ ከከተማው ነዋሪዎች እና ከሚመለከታው የጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር በመስራት ላይ እንገኛለን ብለዋል፡፡ (ምንጭ፡-የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር)
https://waltainfo.com/am/32775/
202
0ሀገር አቀፍ ዜና
ኬንያ ገንዘብ ከመቀየሯ ጋር ተያይዞ ከሰባት ቢሊዮን ሺልንግ በላይ ጥቅም አልባ ሆነ
ቢዝነስ
October 3, 2019
Unknown
የኬንያ ማዕከላዊ ባንክ እንዳሳወቀው ኬንያ የመገበያያ ገንዘብ ከመቀየሯ ጋር ተያይዞ ከ95% በላይ የሚሆነው የአንድ ሺ ሺልንግ ተመልሶ በአዲሱ ተተክቷል።በዚህ መካከል ግን መሃል ላይ ተንሳፎ የቀረ ገንዘብ እንዳለም ተገልጿል።"ይህ ማለት 7.3 ቢሊዮን ሺልንግ ጥቅም አልባ ሆኗል፤ እንደ ወረቀት ነው የሚቆጠረው" በማለት የባንኩ አስተዳዳሪ ፓትሪክ እንጆሮጌ ለጋዜጠኞች አስረድተዋል።ባንኩ እንዳሳወቀው አዲስ የመገበያያ ገንዘብ የታወጀው ሰኔ አንድ ቀን ሲሆን፣ ከዚያ ዕለትም ጀምሮ ሲዘዋወር የነበረ 217 ሚሊዮን ሽልንግም ተገኝቷል።ከመስከረም ሃያ ጀምሮ አሮጌው የመገበያያ ገንዘብ ከጥቅም ውጭ ሆኗል።በዚህ ወቅትም ከሶስት ሺ የሚበልጡ አጠራጣሪ ልውውጦች ሪፖርት የተደረጉ ሲሆን፣ በሚመለከተው የመንግሥት አካልም ምርመራ እንደሚደረግም ኢንጆሮጌ አክለው ገልፀዋል።የገንዘብ ቅየራው በሃገሪቷ ውስጥ የተንሰራፋውን ሙስና ለማስቀረትና ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርንም ለመቆጣጠር እንዲያስችል ነው።አፍሪካ ታክስ ጀስቲስ ኔትወርክ የተባለ ድርጅት እንዳሳወቀው በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ምክንያት ኬንያ በየአመቱ 400 ሚሊዮን ዶላር እንደምታጣ አስታውቋል።ባንኩ እንዳስታወቀውም የገንዘብ ቅይይሩ መሳካቱንና ከዚህ በኋላ ስርአት ባለው መንገድ የገንዘብ ዝውውር እንደሚከናወን ነው። (ምንጭ፡-ቢቢሲ)
https://waltainfo.com/am/32907/
132
3ቢዝነስ
አሜሪካ ከ30 ዓመት በኋላ በሶማሊያ ኤምባሲዋን ከፈተች
ፖለቲካ
October 3, 2019
Unknown
አሜሪካ ከሶማሊያ የርስ በርስ ጦርነት ጋር በተያያዘ ዘግታው የነበረውን ኤምባሲዋን ከ30 ዓመት በኋላ ከፈተች።ሶማሊያን ለረዥም ጊዜ አስተዳድረዋት የነበሩት ዚያድ ባሬ በጎርጎሳውያኑ 1991 ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ የተለያዩ የጎሳ መሪዎች እርስ በእርሳቸው ሲዋጉ ቆይተዋል።ሶማሊያ ከዚህ በኋላ በጎሳ የጎበዝ አለቆች እና በእስላማዊ ቡድን ወታደሮች በሚደረጉ ውጊያዎች ስትታመስ ቆይታለች።ረቡዕ ዕለት ከአሜሪካ ኤምባሲ የወጣ መግለጫ እንደሚያስረዳው አሜሪካ ኢምባሲዋን በሞቃዲሾ ለመክፈት የቻለችው ባለፈው አመት ቋሚ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በሞቃዲሾ እንዲኖራት ማድረጓን ተከትሎ መሆኑ ተገልጿል።አክሎም "ይህ መደበኛ የሆነውን የአሜሪካና የሶማሊያ ግንኙነትን ዳግም ማስቀጠል፣ የአሜሪካና ሶማሊያ ግንኙነት መጠናከሩንን ማሳያ፣ እንዲሁም የመረጋጋቷ፣ የዕድገቷ፣ እንዲሁም የሶማሊያና የአካባቢው ሰላም መሻሻሉን ማሳያ ነው" ይላል።በሶማሊያ የአሜሪካ አምባሳደር ዶናልድ ያማማቶ የኤምባሲውን መከፈት "ወሳኝና ታሪካዊ" ያሉ ሲሆን፣ ዓላማውም "በሶማሊያ በ2013 ለተቋቋመው የፌደራል መንግሥት እውቅና በመስጠት አሜሪካ በሞቃዲሾ ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ተሳትፎ መደበኛ ማድረግ" መሆኑን ገልፀዋል።እንደ ሮይተርስ ዘገባ ከሆነ አሜሪካ የሶማሊያ ዋነኛ አጋር ስትሆን ባለፈው ዓመት ብቻ 730 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አድርጋለች። (ምንጭ፡-ቢቢሲ)
https://waltainfo.com/am/33342/
135
5ፖለቲካ
ተጨማሪ የፌዴራል መንግስት የስራ ቋንቋዎች እንዲኖሩ ለማድረግ እየተሰራ ነው- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ
ፖለቲካ
October 2, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ተጨማሪ የፌዴራል መንግስት የስራ ቋንቋዎች እንዲኖሩ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገለጹ፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ (ኦቢኤን) ጋር ባደረጉት ቆይታ ተጨማሪ የፌዴራል መንግስት የስራ ቋንቋዎች እንዲኖሩ ለማድረግ ጥናት መደረጉን ተናግረዋል፡፡ይህ ተግባራዊ መሆን ያለበት ጥናትና እውቀትን መሰረት አድርጎ መሆን እንዳለበት የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ አፋን ኦሮሞን ጨምሮ ሌሎች ቋንቋዎችን የፌዴራል መንግስት የስራ ቋንቋዎች ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
https://waltainfo.com/am/31375/
58
5ፖለቲካ
ያልተመዘገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎችን በተመለከተ ሊደረግ የነበረው ውይይት ተራዘመ
ፖለቲካ
October 1, 2019
Unknown
ከውጭ ሀገራት የመጡና ሀገር ውስጥ ያሉ ያልተመዘገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎችን በተመለከተ ሊደረግ የነበረው ውይይት ያለስምምነት ተራዘመ፡፡ቀደም ሲል በፈረሙት የቃል ኪዳን ስምምነት መሠረት ለውይይት የተገናኙት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድና የፖለቲካ ፓርቲዎች ውይይቱ ይካሄድ-አይካሄድ በሚለው ውሳኔ ላይ የተከራከሩ ሲሆን፣ በመጨረሻም ውይይቱ እንዲራዘም ወስነዋል፡፡ዋልታ ያነጋገራቸው የኦብኮ፣ መኢአድ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ኮንግረስ ፓርቲ አመራሮች በቦርዱ ላይ የነበራቸው እምነት መሸርሸሩን ገልጸው፣ በተለይም በህጉ ላይ ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች 10 ሺህ መስራች አባላት እንዲሁም ለክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች 4 ሺህ መስራች አባላት እንዲኖራቸው ማስገደዱ በፓርቲዎቹ ቅሬታ አስነስቷል፡፡በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፀደቀው የምርጫ ህግ 32 አንቀጾች እንዲሰረዙ እና 50 አንቀጾች ላይ ማሻሻያ እንዲደረግ በውይይቱ ወቅት ተስማምተው እንደነበረ የገለጹት የፓርቲዎቹ አመራሮች፣ ስምምነቱ ሳይፈጸም መጽደቁን አንስተዋል፡፡የፓርቲዎቹን ቅሬታ በማስመልከት ጥያቄ የቀረበበት የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምላሽ ለመስጠት ፍቃደኛ መሆን አልቻለም፡፡የህግ አማካሪና ጠበቃ የሆኑት አቶ አምሃ መኮንን ለዋልታ በሰጡት አስተያየት የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ ህጉ ላይ መስተካከል አለበት የሚሉት ጉዳይ ካለ እንዲስተካከል በየደረጃው ግፊት ማድረግ እንደአማራጭነት የሚቀርብ ሃሳብ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
https://waltainfo.com/am/31371/
146
5ፖለቲካ
የኦሮሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ለመስራት ተስማሙ
ፖለቲካ
October 2, 2019
Unknown
የኦሮሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከ5 ወራት በላይ ከተደራደሩ በኋላ አብረው በጋራ ለመስራት ተፈራርመዋል፡፡እነዚህ ፓርቲዎች በህዝብ ጉዳይ ላይ በከፍተኛ ትብብር አብረው ለመስራት ነው ከስምምነት የደረሱት፡፡ፓርቲዎቹ በጋራ ባወጡት የአቋም መግለጫ፣ መጪው ምርጫ ፍትሓዊና ነፃ እንዲሆን ለማድረግ አብረን እንሰራን፣ ከ150 ዓመታት በኋላ የሚከበረው የሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል የኦሮሞ ትግል ውጤት በመሆኑ ህዝባችን በዓሉን በሰላም፣ በፍቅርና በአንድነት እንዲያከብር እንመኛለን ብለዋል፡፡የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ODP) ሊቀመንበር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በስምምነቱ ወቅት "ኦሮሞ በጋራ ተሰባስቦ በሀሳብ መሸናነፍ፣ እርስ በርስ መመካከርና መስማማት አዲስ አይደለም፣ ባህላችን ነው፣ መወያየት፣ እርስ በርስ መማማር በጣም ወሳኝ ነው" ብለዋል፡፡መጪው ምርጫ ነፃና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን እንሰራለን፣ ይህ ስምምነታችን ወደ ሰሜንና ወደ ደቡብ ተሻግሮ ከሌሎች ጋር በእኩልነትና በነፃነት አብረን መኖር የምንችልበት ሁኔታ ላይ ማተኮር አለብን ብለዋል ዶ/ር ዐቢይ፡፡በስምምነቱ ላይ የODP ም/ሊቀመንበር አቶ ለማ መገርሳ፣ የኦሮሚያ ክልል ም/ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፣ አቶ ዳውድ ኢብሳ፣ ብ/ጄኔራል ከማል ገልቹ፣ አቶ ሌንጮ ለታና የሌሎች የኦሮሞ ፓርቲ አመራሮች መገኘታቸውን ከOBN ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
https://waltainfo.com/am/31372/
144
5ፖለቲካ
የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ቅስቀሳ ከጥቅምት 18 እስከ 22 ድረስ እንደሚካሄድ ቦርዱ ገለፀ
ፖለቲካ
October 2, 2019
Unknown
የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ቅስቀሳ ከጥቅምት 18 እስከ 22 ድረስ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ::የሲዳማ ክልልነት ህዝበ ውሳኔ አፈጻጸም መርሃ-ግብር መሰረት የቅስቀሳ ጊዜ ከመስከረም 23- 28 ቀን 2012 ዓ.ም በሚል ታቅዶ እንደነበረ ይታወሳል፡፡ነገር ግን የህዝበ ውሳኔ ቅስቀሳው የመራጮች ምዝገባ ከሚደረግበት ጊዜ ጋር የተቀራረበ ቢሆን ይሻላል በሚል ስለታመነበት የቅስቀሳ መርሃ ግብሩ ከጥቅምት 18- 22 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት እንዲሆን ተብሎ ተሻሽሏል፡፡ቦርዱ በአፈጻጸም ጉዳዮች የተነሳ የሚኖሩ የቀናት ለውጥና መሸጋሸጎችን ለወደፊትም ይፋ የሚያደርግ መሆኑን ገልጿል፡፡
https://waltainfo.com/am/31373/
74
5ፖለቲካ
የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አባላት ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው
ፖለቲካ
October 2, 2019
Unknown
የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አባላት ጥቅምት ወር ላይ ኢትዮጵያን ሊጎበኙ እንደሆነ ተገለፀ፡፡የምክር ቤቱ አባላት በአፍሪካ በሚያደርጉት ጉብኝት ከአዲስ አበባ ባሻገር የደቡብ ሱዳንን ጁባ ከተማ እንደሚጎበኙ ተነግሯል፡፡የመንግስታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በጥቅምት 12 እና 13 በአዲስ አበባ በሚያደርገው ቆይታውም ከአፍሪካ ህብረት የሰላምና የፀጥታ ምክር ቤት እና ከአጋር አካላት ጋር ዓመታዊ ምክክር እንደሚያደርግ ተመልክቷል፡፡በማግስቱም ምክር ቤቱ በመንግስታቱ ድርጅት የአሜሪካ አምባሳደር ኬሊ ክራፍት ጋር በመሆን በጁባ ጉብኝት እንደሚያደርግ ይጠበቃል ተብሏል፡፡በዚህም በአገሪቱ ጉዳዮች ላይ በተቀመጡ የውይይት አጀንዳዎች ላይ ምክክር እንደሚደረግ ነው የተነገረው፡፡ምክር ቤቱ አፍሪካ የሚያደርገውን ጉብኝት ካጠናቀቀ በኋላም በኒውዮርክ በሚያደርገው ስብሰባ በመካከለኛው ምስራቅና በአፍሪካ የሰላምና የፀጥታ ሁኔታ እንዲሁም በኮሶቮ ጉዳይ ላይ ውይይት እንደሚያደርግ ተጠቁሟል፡፡ (ምንጭ፡-ሽንዋ)
https://waltainfo.com/am/31374/
102
5ፖለቲካ
የጀርመን ተራድኦ ድርጅት በሰራተኞች ላይ የሚደርሰውን አደጋ መቀነስ የሚያስችሉ የመቆጣጠሪያ መሳሪዎች ለገሰ
ሀገር አቀፍ ዜና
October 2, 2019
Unknown
የጀርመን ተራድኦ ድርጅት በሰራተኞች ላይ የሚደርሰውን አደጋ መቀነስ የሚያስችሉ የመቆጣጠሪያ መሳሪዎች ለሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አበረከተ፡፡መሳሪዎች ዘጠኝ የተለያዩ አይነት ያላቸው ሲሆን፣ በሰራተኞች ላይ የሚደርሰውን አደጋ መቆጣጠር የሚያስችሉ በመሆናቸው የኢንዱስትሪ ስፋት ላላቸዉ ለ5 ክልሎችና ለፌዴራል መስሪያ ቤት ተሰጥተዋል፡፡መሳሪያዎቹም የጨረር፣ የሙቀት፣ የብርሃን፣ የብናኝ እና ትነት መጠንን መለካት የሚያስችሉ እንደሆኑ ታውቋል፡፡በርክክብ ስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የሰራተኛና ማህበራዊ ሚኒስትሯ ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ለተደረገላቸው ድጋፍ አመስግነው፣ ከዚህ በፊት የነበረው የነበረው የቁጥጥርና የክትትል ስርዓት ምልከታ ላይ ብቻ ያተኮረ እንደነበርና በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡ድጋፉ ጥሩ መነሻ እንደሚሆንና ይህን ወደ ፊት ለማሳደግ እንደሚሰሩም ገልጸዋል፡፡ከክልሎች የመጡና ድጋፎችን የተረከቡት የስራ ኃላፊዎች መሳሪዎቹ ዘመናዊ በመሆናቸው በሰራተኞች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት በመለካትና በማወቅ ጉዳቱን ለመከላከል እንደሚረዳ ገልጸዋል፡፡የተደረገዉን ድጋፍ የሰራተኛዉን ጤንነት ከማስጠበቅ ባለፈ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለዉ በመሆኑ ተደራሽነቱን በማስፋት ቀጣይነት ሊኖረዉ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡መሳሪዎቹ ለአማራ፣ ትግራይ፣ ደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች፣ ኦሮሚያ ክልሎች፣ ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እንዲሁም ለፌዴራል መስሪያ ቤት ተበርክተዋል፡፡  
https://waltainfo.com/am/32773/
136
0ሀገር አቀፍ ዜና
የይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ በከፊል ስራ መጀመሩ ተገለፀ
ቢዝነስ
October 1, 2019
Unknown
የይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ 11 ሼዶች የተጠናቀቁ ሲሆን ከነዚህ መካከል 4ቱ ስራ ጀምረዋል፡፡ፓርኩ 152 ሼዶች ይገነቡበታል ተብሎ የታቀደ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት 11 ሼዶች ተጠናቀው 4ቱ ነው ወደ ስራ የገቡት ተብሏል፡፡የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው የይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክን በጎበኙት ጊዜ  እንደተናገሩት ፓርኩ ለሀገር ኢኮኖሚ ካለው ፋይዳ በዘለለ ለአካባቢው አርሶ አደሮች ምርትና ምርታማነት፣ ዕድገትና ተጠቃሚነት ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል፡፡ወደ ስራ የገባው የአቡካዶ ዘይት ማምረቻ ፋብሪካ አንድ ማሳያ መሆኑንም ነው ምክትል ርዕሰ መስዳደድሩ የገለፁት፡፡በቴክኖሎጂ ሽግግር ረገድ የአርሶ አደሩን አቅም የማጎልበት ሥራ እየተሰራ እንደሆነም አቶ ርስቱ ተናግረዋል፡፡ ተቋሙ ያሉበትን ችግሮች ቀርፎ በፍጥነት ወደ ሥራ እንዲገባ የክልሉ መንግስት ተገቢውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል፡፡የፓርኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ብሩ ወልዴ በበኩላቸው ፓርኩ የምግብ ማቀነባበሪያ በመሆኑ ጥንቃቄ ማድረግ ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡የቀሪ ሼዶች ግንባታ የፋብሪካዎቹ አይነት ወይም ፍላጎት ሲታወቅ የሚገነባ ሲሆን፣ ተቋሙ የውጪ ምንዛሪ እጥረት እንዳለበት ሥራ አስፈፃሚው አክለው ጠቁመዋል፡፡ 
https://waltainfo.com/am/23993/
136
3ቢዝነስ
የብሄር ብሄረሰቦች ቀን አንድነትን በሚያጠናክር መልኩ እንዲከበር ዝግጅት እየተደረገ ነው- የፌዴሬሽን ምክር ቤት
ፖለቲካ
October 1, 2019
Unknown
የዘንድሮው የብሄር ብሄረሰቦች በዓል አከባበር ኢትዮጵያዊ አንድነትን በሚያጠናክር መልኩ እንዲሆን የተለያዩ ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አስታወቀ።ለ14ኛ ጊዜ የሚከበረውን የብሔር ብሔረሰብ በዓል የዝግጅት አስመልክቶ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤና የበዓሉ አዘጋጅ የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤ በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ኬሬያ ኢብራሂም እንደተናገሩት ላለፉት 13 ዓመታት የተከበረው የብሔር ብሔረሰቦች በዓል ጠንካራም ደካማም ጎኖች ነበሩት።በምክር ቤቱ ዕውቅና የተሰጣቸው 76 ብሔሮችና ብሔረሰቦች ማንነታቸውን፣ ቋንቋቸውንና ባህላቸውን ማስተዋወቅ የቻሉበት አጋጣሚ በጥሩ ጎኑ ይጠቀሳል።ኢትዮጵያ ሲባል የተለያዩ ማንነቶች፣ ባህልና እሴቶች ውህድ መሆኗን በአደባባይ ማሳየት የተቻለበት ጥሩ አጋጣሚም ነበር ብለዋል።በዓሉን ተሰባስቦ የተለያዩ ማንነቶች፣ ባህልና እሴቶችን ከማስተዋወቅ ባለፈ፤ ልዩነቶቻችን ለአንድነታችን ውበት ሆነው እንዲጎሉ በማድረግ ላይ ግን ክፍተት ነበር ብለዋል ወይዘሮ ኬሪያ።የዘንድሮው በዓል አከባበር ግን ባለፉት ጊዜያት የነበሩትን ክፍተቶች በመሙላት ጠንካራ ጎኑን በማስቀጠል የሚከወን መሆኑን ገልጸዋል።አከባበሩ ኢትዮጵያዊ አንድነትን በሚያጠናክር መልኩ እንዲሆን የተለያዩ ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑንም አፈጉባዔዋ ተናግረዋል። (ምንጭ፡-ኢዜአ)
https://waltainfo.com/am/31370/
133
5ፖለቲካ
ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ በቱሪዝም ዘርፍ ላደረጉት አስተዋፅኦ የአለም ቱሪዝም ድርጅት የ2019 ተሸላሚ ሆኑ
ሀገር አቀፍ ዜና
October 1, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በቱሪዝም ዘርፍ ላደረጉት አስተዋጽኦ የ2019 የአለም ቱሪዝም ድርጅት የ2019 ተሸላሚ ሆኑ፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሽልማቱን ከወርልድ ቱሪዝም ፎረም ፕሬዚዳንት ቡሉት ባጊቺ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለዋል፡፡በተጨማሪም ኢትዮጵያ በቱሪዝም ዘርፍ ላስመዘገበችው እመርታ ማሳያ እንዲሆንም የ2012 የአለም የቱሪዝም ጉባኤን እንድታስተናግድ የተደረሰው ስምምነት ሰነድም ቀርቧል::የልኡካን ቡድኑ የብሄራዊ ሙዚየም እድሳት ሥራን የጎበኙ ሲሆን ለኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ድጋፍ እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል::
https://waltainfo.com/am/32772/
55
0ሀገር አቀፍ ዜና
ቻይና ኮሚዩኒስት ፓርቲ የተመሰረተበትን 70ኛ አመት እያከበረች ነው
ፖለቲካ
October 1, 2019
Unknown
ቻይና- የቻይና ህዝቦች ሪፐብሊክ (ፒአርሲ) ተብሎ የሚጠራውን የኮሚዩኒስት ፓርቲ የተመሰረተበትን ሰባኛ አመት በደመቀ ሁኔታ እያከበረች ነው።በጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር 1949 ማኦ ዜዱንግ ወይም ሊቀመንበር ማኦ የኮሚዩኒስት ጥምር ኃይሎች ደም አፋሳሹን የእርስ በርስ ጦርነት ማሸነፋቸውን ተከትሎ ፒአርሲ መመስረቱን አወጁ።ዘመናዊት ቻይና በሚያስገርም ፍጥነት እያደገች ቢሆንም በብዙዎች ዘንድ ነፃነትን በመግታትም የሰላ ትችት ይቀርብባታል።ፕሬዚዳንት ዢ ሺንፒንግ በቲናንማን አደባባይ የተደረገውን ከፍተኛ ወታደራዊ ትዕይንትን ተከትሎ እንደተናገሩት የትኛውም ኃይል ቻይናን እንደማያነቃንቃት ነው።"የትኛውም ኃይል ቢሆን ቻይናንም ሆነ ህዝቦቿን ወደፊት ከመሄድ አያግዳቸውም" በማለት ለተሰበሰበው ህዝብ ንግግር አድርገዋል።ፕሬዝዳንቱ ማኦ የቻይና ህዝቦች ሪፐብሊክን መመስረት ባወጁበት ተመሳሳይ ቦታ ከመቆም በተጨማሪ ማኦ በጊዜው ለብሰውት የነበረውን ተመሳሳይ ልብስም ለብሰው ታይተዋል ነው የተባለው።ፕሬዚንዳት ዢ አብዮታዊውንና መስራቹን አባትም ራዕይም ሆነ ትዝታ ከማጋራትም አልተቆጠቡም፡፡ ነገር ግን በዛሬው ዕለት የሚደረገውን አከባባበር በሆንግ ኮንግ የሚደረገው ተቃውሞ እንዳያጠለሸው ተሰግቷል።በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች ቤጂንግ በሆንግ ኮንግ ማህበረሰብና ፖለቲካ ላይ የምታደርገውን ቅጥ አልባ ቁጥጥር በመቃወም ተቃውሟቸውን ማሰማት ከጀመሩ ዋል አደር ያሉ ሲሆን፤ በዛሬውም ዕለት ተቃውሟቸውን ይቀጥላሉ ተብሎ ይጠበቃል።የመከላከያ ሚኒስትር እንዳሳወቀው፤ 15ሺ ወታደሮች፣ 580 ወታደራዊ ቁሶች እንዲሁም 160 የጦር አውሮፕላኖች በዚህ ወታደራዊ ትዕይንት ተሳታፊ ሆነዋል።የሀገሪቷ አዲስ ወታደራዊ የቴክኖሎጂ ግኝቶች በትእይንቱ ላይ የቀረቡ ሲሆን፤ ታንኮች፣ ሄሊኮፕተሮች፣ ዲኤፍ 41 የሚል መጠሪያ የተሰጠው የባሊስቲክ ሚሳይልም ይገኙበታል።ከወታደራዊ ትዕይንቱ በተጨማሪ ከተለያየ የማህበረሰቡ ክፍል የተውጣጡ ከመቶ ሺ በላይ ግለሰቦች የሚሳተፉበት ደመቅ ያለ ዝግጅትም የተደረገ ሲሆን፤ በዚህም አርሶ አደሮች፣ መምህራን፣ ዶክተሮችና ተማሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል።ዝግጀቱ ለመንግሥት የስራ ኃላፊዎች፣ ለተጋበዙ ግለሰቦችና ለውጭ ሀገር ዲፕሎማቶች ክፍት ሲሆን፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ግለሰቦች በያሉበት ሆነው የሚከታተሉት ይሆናል።የፀጥታው ቁጥጥር በማዕከላዊ ቤጂንግ ለሳምንታት ያህል በጣም የጠበቀ ሲሆን፣ በተለይም በትዕይንቱ አካባቢ ድሮን (ሰው አልባ አውሮፕላንን) ጨምሮ ለውድድር የሚሆኑ እርግቦችም ተከልክሏል።ሚዲያን ሳንሱር በማድረግ በምትተቸው ቻይና ወታደራዊ ትዕይንቱን ተከትሎ በከፍተኛ ሁኔታ ቁጥጥር የጠበቀ ሲሆን፣ የተለያዩ ፕሮግራሞችን የሚያስተላልፉ ሚዲያዎች የፕሮግራሞች ዝርዝር የተሰጣቸው ሲሆን በኦንላይንም ላይ የኮሚዩኒስት ፖርቲንም ሆነ መሪዎቹን መተቸት ክልክል ነው። (ምንጭ፡-ቢቢሲ)
https://waltainfo.com/am/34008/
268
5ፖለቲካ
የናይጀሪያ ፖሊስ በሌጎስ ‘የሕፃናት ማምረቻ’ ናቸው ያላቸውን ቤቶች በቁጥጥር ሥር አዋለ
ሀገር አቀፍ ዜና
October 1, 2019
Unknown
የናይጀሪያ ፖሊስ ሌጎስ ውስጥ ‘የሕፃናት ማምረቻ’ በሚል በገለፃቸው ቤቶች ላይ በከፈተው ዘመቻ 19 ነፍሰ ጡር ሴቶችን ነፃ ማውጣቱ ታውቋል።አብዛኞቹ ሴቶች “አርግዘው እንዲወልዱ ለማድረግ እና ልጆቻቸውን ለመሸጥ ዓላማ” በጠለፋ የተያዙ መሆናቸውን ፖሊስ አስታውቋል።ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በቦታው ላይ እንደ ነርስ የሚያገለግሉ ሁለት ሴቶች በቁጥጥር ሥር የዋሉ ቢሆንም ዋነኛው ተጠርጣሪ እንዳልተያዘ ታውቋል።በፖሊስ መረጃ መሠረት ወንድ ሕፃናት 1400 ዶላር ሲሸጡ፣ ሴት ሕፃናት ደግሞ በ830 ዶላር ለገበያ ይቀርባሉ።ሕፃናቱ ወደ ሌላ ሥፍራ የሚጓጓዙ መሆኑ ቢታወቅም ዋነኞቹ ገዥዎች እነማን እንደሆኑ ግን አልታወቀም ብሏል መረጃው።‘የሕፃናት ማምረቻ’ የሚለው ጉዳይ ናይጀሪያ ውስጥ የተለመደ ሲሆን፣ ይህን ድርጊት ለማስቆም ከተካሄዱ በርካታ ዘመቻዎች መካከል ባለፈው ዓመት 160 ሕፃናት ነፃ የወጡበት ይገኝበታል።በአሁኑ ዘመቻ አራት ሕፃናት ነፃ መውጣታቸው ተገልጿል።በአገሪቱ ዋና ከተማ ሌጎስ ውስጥ የተገኙት ዕድሜያቸው ከ15 እስከ 28 የሆኑት ልጃገረዶች እና ሴቶች ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ሥራ ትቀጠራላችሁ ተብለው የመጡ እና በአንድ ግቢ ውስጥ እንዲቀመጡ ተደርገው የተደፈሩ መሆናቸው ታውቋል።በአሁኑ ወቅት ነፃ የወጡት ሴቶች እና ሕፃናት ወደ ሌላ ሥፍራ ተዛውረው እያገገሙ መሆኑን ፖሊስ ተናግሯል። (ምንጭ፡-ቢቢሲ)
https://waltainfo.com/am/33480/
148
0ሀገር አቀፍ ዜና
የአዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻ አረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት በይፋ ተጀመረ
ቢዝነስ
October 1, 2019
Unknown
በቻይና መንግሥት ድጋፍ የሚገነባው የአዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻ አረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት ዛሬ በይፋ ተጀምሯል።አጠቃላይ 56 ኪ.ሜ ከሚሆነው የወንዝ ዳርቻ አረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት ውስጥ በቻይና መንግሥት የሚደገፈው 12 ኪ.ሜ ፕሮጀክት ነው።የ12 ኪ.ሜ ፕሮጀክቱ በሁለት ዙር የሚሠራ ሲሆን አሁን የተጀመረው የመጀመሪያው ዙር ፕሮጀክት በዚህ ዓመት መጨረሻ ላይ ይጠናቀቃል ተብሏል። ሁለተኛው ዙር ደግሞ በሚቀጥለው ዓመት እንደሚጠናቀቅ ነው የተነገረው።ፕሮጀክቱ አዲስ አበባን ጽዱ፣ ውብ እና ማራኪ በማድረግ ለመዝናናት እና ለቱሪዝም ምቹ የሆነ አካባቢን ለመፍጠር ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው እና ለአፍሪካም አርአያነት ያለው ሥራ እንደሚሠራ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ተናግረዋል።የቻይና መንግሥት የሚያስገነባው ፕሮጀክት የትምህርት፣ የኮንሰርት ማቅረቢያ፣ አረንጓዴ ቦታዎች እና ሰው ሠራሽ ሐይቆች ያሉት እና ዘመናዊ የመዝናኛ ስፍራ መሆኑን ስለዚሁ ፕሮጀክት በቪዲዮ የቀረበው ናሙና ያመለክታል። 
https://waltainfo.com/am/23992/
112
3ቢዝነስ
የትምህርት ተቋማት የአካዳሚ ቴክኒክ ረዳቶችን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች የሚቀርፍ መመሪያ እየተዘጋጀ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
September 30, 2019
Unknown
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚያገለግሉ የአካዳሚ ቴክኒክ ረዳቶችን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች መቅረፍ የሚያስችል ደንብና መመሪያ እየተዘጋጀ መሆኑ ተገለጸ።በተዘጋጀው ረቂቅ ደንብና መመሪያ ዙሪያ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አዘጋጅነት በአዲስ አበባ ከተማ ውይይት ተካሂዷል፡፡በውይይት መድረክም ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን፣ ደንብና መመሪያው የሰራተኞችን መብትና ግዴታ እንዲሁም የተለያዩ ጥቅማጥቅሞችን ለማስከበር የሚያስችል እንደሆነ ተገልጿል።ይህም የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የሚደረገውን እንቅስቃሴ ለመደገፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ነው የተባለው።ረቂቅ ደንብና መመሪያው በቀጣይነት በሚደረጉ ተጨማሪ ውይይቶች ከዳበረ በኋላ የሚጸድቅ መሆኑም ተመላክቷል።  
https://waltainfo.com/am/32771/
72
0ሀገር አቀፍ ዜና
የሳዑዲው ልዑል ኢራን ለዓለም ነዳጅ ምርት ስጋት ናት አሉ
ቢዝነስ
September 30, 2019
Unknown
የሳዑዲ አረቢያው ልዑል መሃመድ ቢን ሳልማን ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ኢራን ከድርጊቷ እንድትታቀብ ማድረግ ካልቻለ የነዳጅ ዋጋ በማይታመን ሁኔታ ይጨምራል ሲሉ አስጠነቀቁ።በሳዑዲ አረቢያና በኢራን መካከል የሚደረግ ጦርነት ዓለም አቀፉን የኢኮኖሚ ሥርዓትን ሊያቃውስ ይችላል ብለዋል።ለዚህም መነሻ የሆናቸው ከሁለት ሳምንት በፊት በሳዑዲ ሁለት የነዳጅ ማምረቻ ተቋማት ላይ ቴህራን ጥቃት አድርሳለች ብላ ከመወንጀሏ ጋር ተያይዞ ነው።ልዑሉ ከሲቢኤስ የዜና ወኪል ጋር በነበራቸው ቆይታ በጋዜጠኛው ጀማል ካሾጊ ግድያም ላይም የተወሰነ ኃላፊነት እንደሚወስዱ ቢናገሩም ለግድያው ትዕዛዝ አልሰጠሁም ሲሉ ክደዋል።የሳዑዲ አረቢያ መሪ ተደርገው የሚታዩት ልዑሉ በሰላ ትችቱ የሚታወቀውን የሳዑዲ ጋዜጠኛ ጀማል ካሾጊ ግድያ በቀጥታ ተሳትፈዋል ተብለውም ይጠረጠራሉ።ካሾጊ የተገደለው በቱርክ በሚገኘው የሳዑዲ ቆንስላ ውስጥ ባለፈው አመት ነው።የመካካለኛው ምሥራቅ ቀጠና በዓለም ላይ ያለውን 30 በመቶ ነዳጅ አቅራቢ ሲሆን፣ 20 በመቶ የሚሆነው የዓለም አቀፉ ንግድ መተላለፊያ እንዲሁም 4 በመቶ የዓለም ሃገራት አጠቃላይ ምርት ድምርን የሚያበረክት ነው ብለዋል።"እስቲ እነዚህ ሦስቱ ነገሮች ቀጥ ቢሉ ብላችሁ አስቡ፤ ዓለም አቀፉ ኢኮኖሚ ሙሉ በሙሉ ይወድቃል፤ የሚጎዱት ሳዑዲ አረቢያ ወይም የመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች ብቻ አይሆኑም" ብለዋል።ሳዑዲ አረቢያ እንደምትለው በ18 ሰው አልባ አውሮፕላኖችና በሰባት ሚሳይሎች አማካኝነት ከሁለት ሳምንታት በፊት በሁለት የነዳጅ ተቋማቷ ላይ ጥቃት እንደደረሰባት ነው።በኢራን የሚደገፈው የሁቲ አማፅያን ቡድን ከጥቃቱ ጀርባ መኖራቸውን ቢያሳውቁም ሳዑዲ አረቢያ ግን የዓለም 5 በመቶ ነዳጅ የሚያቀርበውን ስፍራ በማጥቃትና የዓለምን የነዳጅ ዋጋ በማዛባት ኢራንን በመወንጀል ፀንታለች።የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው፤ ለዚህ ምላሽ የሚሆን ብዙ አማራጭ እንዳላቸውና "የሚያስገድድ አማራጭ" ሊጠቀሙ እንደሚችሉም አስጠንቅቀዋል። (ምንጭ፡-ቢቢሲ)
https://waltainfo.com/am/33562/
209
3ቢዝነስ
የባህል መድሃኒት ጥናትና ምርምር ፍኖተ ካርታ ይፋ ሆነ
ሀገር አቀፍ ዜና
September 30, 2019
Unknown
አገር በቀል የመድሃኒት ህክምና እውቀትን በመሰነድ፣ በመጠበቅ እና የተጠናከረ ጥናትና ምርምርን በማከናወን የባህል ህክምናን ለማሳደግ ይረዳል የተባለው የኢትዮጵያ የባህል መድሃኒት ጥናትና ምርምር ፍኖተ ካርታ ዛሬ ይፋ ተደረገ፡፡   በባህል መድሃኒት ጥናትና ምርምር ፍኖተ ካርታ ዙሪያ የተለያዩ ባለድርሻ ተቋማት እና ከአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተወጣጡ የባህል ሐኪሞች በተገኙበት በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለሶስት ቀናት የሚቆይ ምክክር እየተካሄደ ነው።የጤና ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን ፍኖተ ካርታውን ይፋ ባደረጉበት ወቅት እንደተናገሩት፣ ፍኖተ ካርታው የባህል ህክምናውን በሳይንሳዊ ምርምሮች በመደገፍ፣ ጠቀሜታውን በማጎልበት፣ የጎንዮሽ ጉዳቶችን በመቀነስ እና ከዘመናዊ ህክምና ጋር ለማቀናጀት ያለመ ነው።የባህል ሕክምና ኢትዮጵያ ካሏት እምቅ ሐብቶች አንዱ ቢሆንም እስካሁን ብዙ እንዳልተሰራበት ሚኒስትሩ ገልጸው፣ ህክምናውን ከመደበኛ ትምህርት ጋር በማቀናጀትና ለባህል ሕክምና የሚሆኑ እንስሳትንና እፅዋትን በማሰባሰብ በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ሥራ ለማከናወን የሚያስችል እንደሆነም ተናግረዋል፡፡ከመድሐኒት አምራቾችና የባህል ሕክምና አዋቂዎች ጋር በመስራት የባህል ሕክምና ጥራትና ደረጃን በማጎልበት ፈዋሽነታቸው ላይ ትኩረት ይደረጋል ተብሏል፡፡  የባህል ህክምና አዋቂዎች በበኩላቸው ለረጅም ዓመታት ተሳቀው ይሰሩ እንደነበር ገልጸው፣ ፍኖተ ካርታው መዘጋጀቱ በቀጣይ የተሻለ ስራ ለመስራት የሚያስችል እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡ ፍኖተ ካርው መዘጋጀቱ ለሀገር በቀል ህክምና የሚሰጠውን ትኩረት እንደሚያሳድገውና ለህክምና ይወጣ የነበረውን የውጭ ምንዛሬም እንደሚቀንስ ገልጸዋል፡፡ፍኖተ ካርታው ይፋ በተደረገበት ጊዜ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እና የባህል አዋቂዎች ማህበር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡በኢትዮጵያ ካለው የባህል ሕክምና አገልግሎት 80 በመቶ የሚሆነው ለሰዎች አገለግሎት እንደሚውልና 90 በመቶ የሚሆነው ደግሞ ለእንስሳት ህክምና እንደሚውል በመድረኩ ተገለጿል፡፡
https://waltainfo.com/am/32770/
201
0ሀገር አቀፍ ዜና
ኢትዮጵያ በ40ኛው አለም አቀፍ የሲቪል አቪዬሽን ጉባኤ ላይ እየተሳተፈች ነው
ቢዝነስ
September 30, 2019
Unknown
በካናዳ ሞንትሪያል እየተካሄደ በሚገኘው 40ኛው አለም አቀፍ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት (ICAO) ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያም በትራንስፖርት ሚንስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስን በመወከል እየተሳተፈች ነው፡፡አለም አቀፍ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት (ICAO) ዘንደሮ 75ኛ አመቱን አስቆጥሯል፡፡በዘንደሮው ጉባኤ ከመስራቾቹ መካከል አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ በትራንስፖርት ሚንስትሯ ወ/ሮ ዳግማዊ ሞገስ የተወከለች ሲሆን፣ ኢትዮጵያ በአቪዬሽን ኢንዱስትሪው ዘርፍ እያበረከተች ላለው አስተዋጽኦ በጉባኤው ተወስቷል፡፡በጉባኤው ኢትዮጵያ በኢንተርናሽናል ሬቨኑ ፓሴንጀር ሬት (IRP) 90 በመቶ አስተዋጽኦ ከሚያደርጉ 36 የአለም ሃገራት ውስጥ አንዷና መሆኗም ተገልጿል፡፡በአፍሪካም በቀዳሚነት ደረጃ የምትገኝ መሆኗ በጉባኤው ከተነሱ ጉዳዮች መካከል አንዱ መሆኑን ወ/ሮ ዳግማዊት በማህበራዊ ድረገፅ ላይ አስታውቀዋል፡፡በሌላ በኩል ሚኒስትሯ ከጉባኤው ጎን ለጎን ከኳታር ትራንስፖርትና ኮሙዩኒኬሽን ሚኒስትር ጃሲም ቢን ሳይፍ አል ሱልታኒ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።በዚህም ሀገራቱ በትራንስፖርትና በሲቪል አቪዬሽን ዘርፋ ያላቸውን ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።
https://waltainfo.com/am/23990/
118
3ቢዝነስ
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ 5ኛው ብሔራዊ የገለልተኛ የሳይንሳዊ ጥናት ቡድን ስብሰባ ተጀመረ
ቢዝነስ
September 30, 2019
Unknown
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ 5ኛው ብሔራዊ የገለልተኛ የሳይንሳዊ ጥናት ቡድን ስብሰባ በካርቱም ሱዳን መካሄድ ተጀመረ።የጥናት ቡድኑ ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽን ያሳተፈ ሲሆን በግድቡ የውሃ ሙሌትና አለቃቀቅ ዙሪያ የሚመክር ገለልተኛ አካል ነው ተብሏል፡፡የጥናት ቡድኑ እ.አ.አ ከመስከረም 15 እስከ16/2019 በካይሮ በተደረገው ስብሰባ ወቅት በሦስቱ አገራት የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች በተለዩ አጀንዳዎች ላይ በመወያየት እ.አ.አ ከጥቅምት 4 እስከ 5 2019 በካርቱም በሚካሄደው የሦስቱ አገራት ውሃ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ሪፖርት እንደሚያቀርብ ይጠበቃል።(ምንጭ፦የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር)
https://waltainfo.com/am/23991/
69
3ቢዝነስ
የቱሪዝም ኃብት በኢኮኖሚ ልማት ጉልህ ድርሻ እንዲኖረው እየተሰራ መሆኑን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ገለጸ
ቢዝነስ
September 30, 2019
Unknown
በኢትዮጵያ የቱሪዝም ኃብትን ለስራ እድል ፈጠራና የኢኮኖሚ ልማት ጉልህ ሚና እንዲኖረው ለማድርግ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ገለጸ።የቱሪዝም ቀን በዓለም ለ40ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ32ኛ ጊዜ በድሬዳዋ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች በመከበር ላይ ይገኛል።የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶክተር ሂሩት ካሳው በስፍራው ተገኝተው ባደረጉት ንግግር የቱሪዝም ዘርፍ ለአገር ልማት ወሳኝ በመሆኑ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራበት ነው።የቱሪዝም መዳረሻዎች መሰረተ ልማታቸው ምቹ እንዲሆንና የአገልግሎት አሰጣቱ አስደሳችና ቀልጣፋ እንዲሆን መንግስት የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።ኢትዮጵያ በሰው ሠራሽና የተፈጥሮ ሀብቷ ብቻ ሳይሆን በእንግዳ ተቀባይ ሕዝቧ በታሪኳ፣ ባህላዊና ሃይማኖታዊ እሴቷ ለቱሪስት መስህብነት ከቀዳሚ አገሮች ተርታ ያሰልፏታል።ሆኖም ይህንን እምቅ ሃብቷን እስካሁን በአግባቡ እየተጠቀመችበት አለመሆኑ ይነገራል።በቀጣይ ከዘርፉ የሚመነጨው ሃብት ለአገር ልማትና ለስራ እድል ፈጠራ  አይነተኛ ሚና እንዲኖረው ለማስቻል በትብብር መስራት እንደሚገባ ሚኒስትሯ ተናግረዋል።ለዚህም ህዝቡ ከመንግስት ጎን በመሆን ለዘርፉ ስኬታማነት ሰላሟ ተጠብቆ ለጎብኝዎች ምቹና ተመራጭ አገር ለመፍጠር ርብርብ እንዲያደረግ ጠይቀዋል።የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙራድ በደዊ እንዳሉትም ቱሪዝም ትልቅ የገቢ ምንጭና የበርካቶች ስራ እድል ማግኛ ዘርፍ እንዲሆን ስትራቴጂክ እቅድ ወጥቶ እየተሰራ ነው።ድሬዳዋ ያሏት እምቅ ታሪካዊና ባህላዊ ቅርሶች ተጠብቀው ለትውልድ እንዲተላለፉ እንዲሁም የከተማዋ አይነተኛ የገቢ ምንጭ እንዲሆን የተለያዩ ተግበራት እየተከናወኑ መሆኑም ታውቋል።በዚሁ ዙሪያ በጥናት ላይ በመመስረት ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውንም አቶ ሙራድ ተናግረዋል።ቱሪዝም ከሰላምና ደህንነት ጋር ቀጥታ ቁርኝት ያለው በመሆኑ ከማህበረሰቡ፣ የኃይማኖት አባቶች፣ የፀጥታ መዋቅርና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።የኢትዮጵያ የቱሪዝም ቀን “ለስራ እድል ፈጠራና ለተሻለ ህይወት በሚል መሪ ሃሳብ” በድሬዳዋ ከተማ በመከበር ላይ ይገኛል።እለቱን ታሪካዊና ባህላዊ ቅርሶችን ከመጎብኘት በተጨማሪ በስፖርታዊ ውድድሮች ለማክበር መርሃ ግብር ተይዞለታል።የዓለም የቱሪዝም ቀን በየዓመቱ መስከረም 17 ቀን የሚከበር ሲሆን ኢትዮጵያም 157 አባል አገሮችን ያቀፈው የዓለም ቱሪዝም ድርጅት አባል መሆኗ ይታወቃል። (ምንጭ፡-ኢዜአ)
https://waltainfo.com/am/23989/
249
3ቢዝነስ
በህንድ ከ120 በላይ ሰዎች በጎርፍ መሞታቸው ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
September 30, 2019
Unknown
በህንድ ኡታር ፕራዴሽ እና ቢሃር በሚባሉ ግዛቶች በጣለ ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት ባጋጠመ ጎርፍ ከ120 በላይ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ተገለጸ።በሁለቱም ግዛቶች የባቡር አገልግሎት፣ ተሽከርካሪዎች፣ ሆስፒታሎች፣ ትምህርት ቤቶችና የሃይል አቅርቦት ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጪ መሆናቸውም ታውቋል።የኡታር ፕራዴሽ ግዛት አስተዳደር እንዳስታወቀው፤ 93 ሰዎች በጎርፉ ምክንያት ህይወታቸውን አጥተዋል።በቢሃር ግዛት ደግሞ የሟቾች ቁጥር 29 የደረሰ ሲሆን፣ በግዛቷ ዋና ከተማ ፓትና ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባት የአደጋ መከላከል ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ገልጿል።የየግዛቶቹ ነዋሪዎችም እንደ ጀልባ ባሉ ውሃ ላይ መንሳፈፍ የሚያስችሉ መገልገያዎችን በመጠቀም በተለያዩ ጎዳናዎች ሲንቀሳቀሱ ተስተውለዋል። አንዳንዶቹም በውሃ የተዋጡ መኪናዎችንና ንብረቶችን ሲሰበስቡ ታይተዋል።ከባለፈው አርብ ጀምሮ ከፍተኛ ዝናብ ሲጥልባቸው በነበሩት ግዛቶች የሚገኙ ብዙ የመኖሪያ መንደሮች ሙሉ በሙሉ በውሃ የተዋጡ ሲሆን፣ ህጻናትና እድሜያቸው የገፉ ዜጎችም ተጋላጭ ሆነዋል።ግዛቶቹም የጎርፉ መጠን ከአቅማቸው በላይ ስለሆነባቸው የህንድ አየር ሃይል ሄሊኮፍተሮችና አንዳንድ ማሽኖች በመታገዝ ውሃውን የማፋሰስ ስራ እንዲጀምር ጥያቄ አቅርበዋል። (ምንጭ፡-ቢቢሲ)
https://waltainfo.com/am/34139/
127
0ሀገር አቀፍ ዜና
የሳኡዲ አረቢያው ንጉሥ ጠባቂ በጥይት ተገደለ
ፖለቲካ
September 29, 2019
Unknown
የሳኡዲው ንጉሥ ሳልማን ቢን አብዱላዚዝ የግል ጠባቂ የነበረው ግለሰብ ከጓደኞቹ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ተተኩሶበት መገደሉን ባለስልጣናት አስታወቁ።ጀነራል አብደል አዚዝ አል ፋጋም ቅዳሜ ምሽት ላይ ነበር ጓደኛውን ለመጠየቅ በሄደበት ከሞሃመድ ቢን ሚሻል ሰል አሊ ጋር ግጭት ተፈጥሮ ለሞት የበቃው።የፖሊስ መግለጫ እንደሚያመለክተው ሁለቱ ግለሰቦች ከተጋጩ በኋላ አሊ የተባለው ተጠርጣሪ ጅዳ ሁለቱ ከነበሩበት ቦታ ወጥቶ በመሄድ ሽጉጥ ይዞ በመመለስ ተኩስ ከፍቷል። ተኳሹም ለፖሊስ እጁን እንዲሰጥ ቢጠየቅም እምቢ በማለት ተተኩሶበት መሞቱ ተገልጿል። ጀነራል ፋጋም በደረሰበት ከፍተኛ ጉዳት ምከንያት ሆስፒታል ውስጥ ህይወቱ አልፋለች።በተጨማሪም ሌሎች ሰባት ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱም ታውቋል። ጉዳት ከደረሰባቸው መካከል ሁለቱ የሟች ጀነራል ፋጋም ጓደኞች ሲሆኑ ቀሪዎቹ ግን የደህንነት አባላት ናቸው ተብሏል።ጀነራል ፋጋም በብዙ የሳኡዲ ዜጎች ዘንድ የሚታወቅ ሲሆን ከንጉሥ ሳልማን ጋርም የቅርብ ግንኙነት ነበረው። ለብዙ ዓመታትም የንጉሡ ግል ጠባቂ ሆኖ አገልግሏል።ብዙዎችም በማህበራዊ ሚዲያዎች 'ጀግና' ነበር እያሉ አሞካሽተውታል።
https://waltainfo.com/am/34007/
126
5ፖለቲካ
የወላይታ ብሔር ዘመን መለወጫ ጊፋታ በዓል እየተከበረ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
September 29, 2019
Unknown
ከመስከረም 15 ጀምሮ እየተከበረ ያለው የወላይታ ብሔር ዘመን መለወጫ ጊፋታ በዓል በዛሬው እለት መስከረም 18 ቀጥሎ በደማቅ ስነ-ስርአት እንደሚከበር ተገለፀ።የወላይታ ብሔር ዘመን መለወጫ የጊፋታ በዓል በዛሬው እለት ተጋባዥ እንግዶች በሚገኙበት በተለያዩ ደማቅ ስነስርዓቶች እንደሚከበር የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኩምቤ ገልፀዋል።ጊፋታ አዲስ ዓመትን አሀዱ ብሎ የሚጀምርበት የአዲስ ዓመት መግቢያ ብቻም ሳይሆን የብርሃን ጊዜ ማብሰሪያ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡በዓሉ በየዓመቱ በሚከበርበት ወቅት ወጣቶች፣ ሴቶች እና ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች በዓሉን በተለያዩ ስነ ስርዓቶች ያከብሩታል፡፡የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኩምቤ እና የዞኑ በህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ሃላፊ አቶ ፀጋው ስምኦን በዓሉን በማስመልከ ለጋዜጠኞች በስጡት መግለጫ የዘንድሮ የጊፋታ በዓል ከሌላው ጊዜ በተለየ መልኩ እየተከበረ መሆኑን ተናግረዋል።የወላይታ ብሔር ዘመን መለወጫ ጊፋታ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለጊፋታ እሮጣለሁ በሚል የተዘገጀ የ3ኪሎ ሚትር የሩጫ ውድድር መካሄዱ ይታወሳል፡፡
https://waltainfo.com/am/32769/
117
0ሀገር አቀፍ ዜና
የቢሾፍቱ -ጨፌ ዶንሳ-ሰንዳፋ የአስፋልት ኮንክሪት የመንገድ ግንባታ በይፋ ተጀመረ
ቢዝነስ
September 29, 2019
Unknown
የቢሾፍቱ -ጨፌ ዶንሳ-ሰንዳፋ የአስፋልት ኮንክሪት የመንገድ ግንባታ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሺመልስ አብዲሳ በተገኙበት በይፋ ተጀምሯል ።ይህ መንገድ 55 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍን ሲሆን ከኢትዮጵያ መንግስት በተመደበ 914 ሚሊየን ብር ግንባታዉ የሚከናወን ይሆናል ።የመንገዱን ግንባታ ራማ የተባለ ሀገር በቀል የስራ ተቋራጭ እንደሚያከናውን ተገልጿል ።የግንባታ ስራዉ በሶስት አመታት ጊዜ እንደሚጠናቀቅ ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡በይፋዊ የመንገድ ግንባታ ማስጀመሪያ ስነስርዓት ላይ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ሃብታሙ ተገኝን ጨምሮ የፌዴራል እና የክልል የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል ።ግንባታው በተያዘለት የግዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ የባለስልጣኑ መ/ቤት አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ እንደሚያደርግ የተገለፀ ሲሆን በመስመሩ ያሉ የህበረተሰብ ክፍለ እና መስተደድር አካላት ለግንባታው አስፈላጊውን ትብብርና ድጋፍ እንዲሰጡ ተጠይቋል።
https://waltainfo.com/am/23988/
105
3ቢዝነስ
በግሪክ ሞሪያ የስደተኞች ካምፕ በተነሳው እሳት የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
September 30, 2019
Unknown
በግሪኳ ደሴት ሌስቦስ በከፍተኛ ሁኔታ በተጨናነቀው የሞሪያ ስደተኞች ካምፕ በተነሳው እሳት ቢያንስ የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉን የአገሪቱ ባለሥልጣናት አስታወቁ።ባለሥልጣናቱ እንዳሉት የሟቿ ሴት አስክሬን በሞሪያ ካምፕ ውስጥ የተገኘ ሲሆን፣ ማረጋገጥ ባይቻልም ሌላ አንድ ሕፃንም ሳይሞት እንዳልቀረ ተነግሯል።አደጋው ሲከሰት የእሳት አደጋ ሠራተኞች በጣም ዘግይተው ነው የደረሱት በማለት ተቃውሟቸውን ባሰሙት ስደተኞች ላይ ፖሊስ አስለቃሽ ጭስ ተኩሷል።የስደተኞች ካምፑ መያዝ የሚችለው 3 ሺህ የሚሆኑ ስደተኞችን ቢሆንም፤ 12 ሺህ የሚሆኑ ስደተኞች በድንኳንና በእቃ ማጓጓዣ ኮንቴይነር ውስጥ ይኖሩበታል። ይህም መጨናነቅንና መተፋፈግን ፈጥሯል።ባሳለፍነው ዓመት የቢቢሲዋ ቪክቶሪያ ደርብይሻየር ፕሮግራም በካምፑ ውስጥ ያለውን ሁኔታ ካጋለጠ በኋላ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኤጀንሲ ግሪክ ጥገኝነት ፈላጊ ስደተኞችን ከሌስቦስ እንዲያስወጣ አሳስቦ እንደነበር ይታወሳል።የግሪኳ ደሴት ሌስቦስ የስደተኞች ቀውስ የምታስተናግድ ከተማ ናት። ግሪክ ባለፉት ሳምንታት በቱርክ አድርገው ወደ አገሪቷ የሚገቡ ስደተኞች መልሶ ለማቋቋም እየሰራች ትገኛለች።በጎርጎሳውያኑ 2015 በሶሪያ የተከሰተውን ጦርነት ተከትሎ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ስደተኞች በጎረቤት አገር ቱርክ አድርገው ወደ ግሪኳ ደሴት መግባታቸው ተገልጿል። (ምንጭ፡-ቢቢሲ)
https://waltainfo.com/am/34138/
138
0ሀገር አቀፍ ዜና
የደመራ በዓል ተከበረ
ሀገር አቀፍ ዜና
September 30, 2019
Unknown
የደመራ በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አማንያን ዘንድ ተከበረ፡፡ይህ በዓል የሚከበረው በ326 ዓመተ ምህረት መስከረም 17 የንጉሥ ቆስጠንጢኖስ እናት ንግሥት ዕሌኒ ክርስቶስ የተሰቀለበትን መስቀል ፍለጋ የጀመረችበት ዕለት መሆኑ ይነገራል፡፡በተለይ የደመራ በዓል በመስቀል አደባባይ በመከበር ላይ ሲሆን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳን ጨምሮ ፣ በርካታ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አማኞች፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ዲፕሎማቶች፣ ቱሪስቶች እንዲሁም በርካታ የአዲስ አበባ እና አካባቢዋ ነዋሪዎችም በተገኙበት ተከብሯል፡፡በዚህ ወቅት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የኢትዮጵያዊያን የጋራ ሀብት የሆነውን ሰላም እና አንድነት መጠበቅ ይገባል ብለዋል፡፡በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ላይ የሚደርሰው ግፍና በደል ሊቆም እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ከመዘላለፍ በመተባበር ከመጠላላፍ በመደጋገፍ ላይ ትኩረት በማድረግ የሀገር አንድነትን ፣ ሰላምን እና ፍቅርን እንዲያስቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል፡፡በዓሉን የሚመለከቱ ወረብ እና ዝማሬዎች በጽርኃ አርአያም ቅዱስ ሩፋኤል ሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች የቀረበ ሲሆን፤ በዓሉን የሚወክሉ ትዕይንቶችም ቀርበዋል፡፡ የማህበረ ቅዱሳን አባላት እና መስማት የተሳናቸው የሰንበት ት/ቤት አባላትም እየዘመሩ በታዳሚያኑ ፊት አልፈዋል፡፡ለበዓሉ የተዘጋጀው ደመራ ከከተለኮሰ በኋላም የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል፡፡በተመሳሳይ የደመራ በዓል በክልል ከተሞችም ተከብሯል፡፡በዓሉ በአማራ ክልል በባሕር ዳር፣ ደብረ ብርሃን፣ ወልድያና፣ ደብረ ማርቆስ በትግራይ ክልል መቐለ፣ አዲግራትና፣ ዓጋመ በኦሮሚያ ክልል በጅማ፣ አሰላና በሌሎችም ከተሞች ተከብሯል፡፡   በተጨማሪም በቤኒሻንጉል ክልል አሶሳ ከተማን ጨምሮ በበርካታ አካባቢዎች በዓሉ ተከብሯል፡፡የደመራ በዓል በተባበሩት መንግስታት የትምህርት ሳይንስ እና ባህል ድርጅት /ዩኒስኮ/ በማይዳሰሱ ቅርሶች መዝገብ መመዝገቡ ይታወሳል፡፡ 
https://waltainfo.com/am/32765/
218
0ሀገር አቀፍ ዜና
በአሰላ ተከስቶ የነበረው ግጭት በባህላዊ የእርቅ ሥነ-ሥርዓት ተፈታ
ሀገር አቀፍ ዜና
September 29, 2019
Unknown
በአርሲ አሰላ ከተማ አስተዳደር ተከስቶ የነበረው ግጭት በባህላዊ የእርቅ ሥነ-ሥርዓት ተፈትቷል፡፡ከዚህ ቀደም አጋጥሞ የነበረውን ግጭት አባ ገዳዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በጋራ በመሆን የእርቅ ውይይት ሲካሄድ ቆይቶ አሁን ላይ ከኅብረተሰቡ ጋር የእርቁ የማጠቃለያ ሥነ-ሥርዓት ተከናውኗል።በተሳሳተ መረጃ የተፈጠረውን አለመግባባት የሃይማኖት ግጭት ለማስመሰል ተሞክሮ እንደነበረም ተገልጿል።በተከሰተው ግጭት የአንድ ሰው ሕይወት ሲጠፋ የአካል ጉዳት እና የንብረት ውድመትም ደርሷል።በዚህ ግጭት መነሻነት የኅብረተሰቡ የእርስ በርስ ግንኙነት ተቀዛቅሶ እንደነበረ እና አሁን ላይ የተደረገው እርቀ-ሰላም ግንኙነቱን ወደነበረበት እንደሚመልሰው መገለፁን ኢቢሲ ዘግቧል።
https://waltainfo.com/am/32768/
76
0ሀገር አቀፍ ዜና
ሩዋንዳ ከሊቢያ የመጀመሪያዎቹን 66 ስደተኞች ተቀበለች
ሀገር አቀፍ ዜና
September 27, 2019
Unknown
በሩዋንዳ መንግሥት፣ በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን እና በአፍሪካ ህብረት መካከል የተደረሰውን ስምምነት ተከትሎ ነው የመጀመሪያው የስደተኞች ቡድን ሩዋንዳ የገባው፡፡ሩዋንዳ አውሮፓ ለመድረስ ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ እና በሊቢያ በአደገኛ ሁኔታ ላይ የሚገኙ ከ500 በላይ ስደተኞችን ለመቀበል ተስማምታለች፡፡ከእነዚህ ውስጥ ታዲያ 66ቱ ስደተኞች ሩዋንዳ መድረሳቸው ተገልጿል፡፡በዚህም የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን ለሩዋንዳ ህዝብና መንግስት ልዩ ምስጋና ማቅረቡን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ሩዋንዳ ከደረሱት ስደተኞች ከፊሉ የምስራቅ አፍሪካ ዜጎች ሲሆኑ ከመካከላቸው አንዲት የሁለት ወር ጨቅላ እንዲሁም ብቸኛ ሕፃናት እና ሴቶች ይገኙባቸዋል፡፡ 
https://waltainfo.com/am/33479/
75
0ሀገር አቀፍ ዜና
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ የመስቀል በዓልን በማስመልከት መልእክት አስተላለፉ
ሀገር አቀፍ ዜና
September 28, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የመስቀል በዓልን በማስመልከት መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ ማን ያውቃል? የመስቀል ወፍ እና የአደይ አበባ ቀጠሮ እንዳላቸው መስከረም ሲጠባ፡፡ ማን ያውቃል?እንዲል ኢትዮጵያዊው ባለቅኔ – እኛ እና መስከረም፤ እኛ እና መስቀልም ዓመት ጠብቀን የምንገናኝ ተነፋፋቂ ባለ ቀጠሮ ነን፡፡ እናም ናፍቆታችንን እንወጣጣ- ፍቅራችንንም እንቀባበል ዘንድ ዓመት ጠብቀን አደባባይ እንወጣለን – ያኔ ደመራ ነው፡፡ የመስቀል በዓል በዐደባባይ ከሚከበሩ የኢትዮጵያውያን በዓላት መካከል አንዱ ነው፡፡ ቀደምት አባቶቻችንና እናቶቻችን ይህንን ታላቅ በዓል በዐደባባይ እንድናከብረው ሥርዓት ሲሠሩ ያለ ምክንያት አልነበረም፡፡ ከበዓሉ ጋር የተያያዙ ሦስት ታላላቅ ሐሳቦችን ሁላችንም እንድንመራባቸው ፈልገው ሳይሆን አይቀርም፡፡ እውነትን ቀብሮ መኖር እንደማይቻል፤ ታሪክ የሚለወጠው በቆራጥነትና በአንድነት መሆኑን፣ አንድ ታላቅ ሐሳብ ኢትዮጵያውያንን እንዲጠቅም ከፈለግን ሐሳቡን ኢትዮጵያዊ ማድረግ እንዳለብን በዓሉ በደመራው ብርሃን ወገግ አድርጎ ያሳየናል፡፡ የክርስቶስን መስቀል የቀበሩት ሰዎች እውነትን ለዘለዓለም ቀብረው ማስቀረት የሚችሉ መስሏቸው ነበር፡፡ ለጊዜው መስቀሉ ከአፈር ሥር ሲቀበር ዓላማቸው የተሳካላቸው መስሏቸው ነበር፡፡ በመስቀሉ ላይ የቆሻሻ ክምር እንዲከመር ሲያደርጉ መስቀሉን ከታሪክ ገጽ ያጠፉት መስሏቸው ነበር፡፡ ይህ ግን የመሰላቸውን መስሎ መቆየት የቻለው እና የዋሆችም መስቀሉ ተቀብሮ፣ ተረስቶ፣ ትቢያ ሆኖ ጠፍቷል ብለው እንዲረሱት ያስቻላቸው ዕሌኒ የምትባል ብርቱ እንስት ከተለየ ብርታት፣ ጽናት እና የይቻላል መንፈስ ጋር እስክትከሠት ድረስ ብቻ ነበር፡፡በየዘመናቱ እውነትን ለመቅበር የሞከሩ ነበሩ፡፡ በተንኮል፣ በሤራ፣ በግጭት፣ በክፍፍል፣ በጦርነት፣ በጉልበትና በኃይል እውነትን ለመቅበር ብዙዎች ሞክረዋል፡፡ እውነተኞችን በማጥፋትና በመግደል፣ በማሠርና በማስፈራራት እውነት የምትጠፋ መስሏቸው ብዙ ደክመዋል፡፡ መጻሕፍትን አቃጥለዋል፤ የዕውቀት ቦታዎችን አውድመዋል፡፡ እውነት ግን ብትቀጥንም አትበጠስም፡፡ እውነተኞችን በመግደል እና በመቅበር በፍጹም እውነትን ማጥፋት አይቻልም፡፡ እውነትና ተስፋ አብረው የሚሄዱ ናቸው፡፡ እውነተኞች ተስፈኞች ናቸው፡፡ ውሸተኞች ጨለምተኞች ናቸው፡፡ ከእውነት ጋር ያልቆመ ሰው ተስፋ ሊኖረው አይችልም፡፡ ተስፋ እውነተኛ ሰው ብቻ የሚያደርገው መነጽር ነውና፡፡ ተስፋ ባለበት ሁሉ እውነት ትኖራለች – እውነት ባለችበትም እንዲሁ ተስፋ አለ፡፡መስቀሉን የቀበሩት ሰዎች ሐሰተኞች ስለነበሩ ወደፊት የሚወጣ አልመሰላቸውም፡፡ የመስቀሉ ወዳጆች ግን እውነተኞች ስለነበሩ አንድ ቀን እንደሚገለጥ ያምኑ ነበር፡፡ ለዚህ ነው መስቀሉ የት እንደተቀበረ ከልጅ ልጅ በሚተላለፍ የቃል ትውፊት መረጃውን ለዘመናት አቆይተው ለመስቀሉ አስተርእዮት ዘላለማዊ ገድል የፈጸሙት፡፡ ኢትዮጵያን ታላቅ፣ የበለጸገችና ለሁላችንም እንድትሆን ለማስቻል የያዝነው ዓላማ መሳካቱ የማይቀር እውነት ነው፡፡ ይህን እውነት የሚገዳደሩ ኃያላን ይኖራሉ፡፡ ለጊዜው ዝናራቸውን እስኪጨርሱ፣ ጉልበታቸውንም እስኪያፈሱ ድረስ ያሸነፉ ይመስላሉ፡፡ ድምፃቸው እንደ ነጎድጓድ፣ ጩኸታቸውም እንደ ብዙ ፏፏቴዎች የወል ጩኸት ጎልቶ ይሰማ ይሆናል፡፡ እውነታችንን የቀበሩት መስሏቸው ለጊዜው ይደሰታሉ፡፡ በዙሪያችን ያሉትም እውነታችን የተቀበረ መስሏቸው ተስፋ ይቆርጣሉ፡፡ ይህ ግን የእውነትን ባሕሪይ ካለመረዳት የሚመጣ ነው፡ ፡እውነትን መገዳደር እንጂ ማሸነፍ፣ መቃወም እንጂ ማጥፋት ፈጽሞ አይቻልም፡፡ የብዙዎች ጩኸት- የሰነፎች ተረት እና የአላዋቂዎች ትምክህት እውነትን ሊያጠፋት እንደማይችል በጽኑ እናምናለን፡፡ እውነት የተቀበረችበትን ዐመድ እንደ ፍግ እሳት አሙቃ እንደ ገሞራ ትፈነዳለች፤ የተሸፈነችበትን አቧራ እና የክፋት ቁልል ቅርፊቱን እንደሚሰብር ጫጩት ፈንቅላ ትነሣለች፡፡ ነገ ከእውነተኞች ጋር ናት፡፡ እውነተኞች ዛሬ ጥቂቶች ቢመስሉም ነገ እየበዙ ይሄዳሉ፤ ሐሳውያን ዛሬ ብዙዎች ቢመስሉም ነገ እንደ ስንቅ እያነሡ ይሄዳሉ፡ ፡ ለዚህ ነው ከኢትዮጵያ እውነት ጋር እንቆም ዘንድ እስከ የትኛውም ጥግ ተጉዘን፤ የትኛውንም እንቅፋት በጀግንነት እንሻገር ዘንድ የምንታገሰው፡፡ ማንም በማያስብበት፣ ነገሩ ሁሉ የተረሳ በሚመስልበት፣ ኃያላን ሁሉ ዝም ባሉበት በዚያ ጊዜ ዕሌኒ የምትባል ቆራጥ እናት ተነሣች፤ ማንም የማይደፍረውን ደፈረች፣ ከእውነት ጋር ለመቆምም ቆረጠች፤ ያልተሞከረውን ለመሞከር፣ የማይታሰበውን ለማሰብ ወሰነች፡፡ ታሪክ በሥራ እንጂ በወሬ አይለወጥም፤ የሚያወሩ ሰዎች በታሪክ ውስጥ ያልፋሉ፤ ታሪክ ግን አይሠሩም፡፡ ማኅበረሰቡ የሚያውቀውን፣ የለመደውን፣ ደጋግሞ የሞከረውን ነገር በማድረግ ታሪክ አይለወጥም፡፡ ሌሎች ባዘገሙበት መንገድ ብቻ ደጋግሞ በመጓዝ ካሰቡት ለመድረስ አይቻልም፡፡አዲስ ታሪክ ለመጻፍ አዲስ መንገድ መከተል፣ አዲስ ልማድም መትከል – አዲስ ሥራም መሥራት ይጠይቃል፡፡ ጫካ የሚያቃጥል እሳት ከአንዲት ክብሪት ይነሳል፤ ሀገር የምትለውጥ ውብ ሐሣብም ከአንዲት ቦታ ትመነጫለች፡፡ ተገዳድለን፣ ተጨፋጭፈን፣ ተናቁረን ሞክረነዋል፤ ማሳደድና ማሠር የታሪካችን አካላት ሆነዋል፤ ሤራና ሸር፣ ይውደምና ይመታ መዛግብተ ቃላትን ሞልተውታል፡፡ ለዚህ ነው በአዲስ መንገድ እንሂድ ብለን የተነሣነው፡፡ ዕሌኒ እንደብዙዎቹ የዓለማችን ባለ ቅን ልብ ቅን ሰዎች ዓይነተኛ የመደመር ተምሳሌት ናት፡፡ የእርሷ ቆራጥነት፣ የሕዝቡ ጸሎት፣ የወታደሮቹ ብርታት፣ በኢየሩሳሌም የነበሩት ሰዎች ትጋት፣ መረጃውን የሰጧት ሰዎች ቀናነት፡፡እነዚህን ሁሉ አስተባብራ ሐሳቧን ተግባር – ተግባሯን ታሪክ ለማድረግ ቻለች፡፡ ‹ተቀበረ› የሚለውን ታሪክ ‹ወጣ› በሚለው ቀየረችው፡፡ ‹ጠፋ›ን በ‹ተገኘ›- ‹ተሰወረ›ን በ‹ተገለጠ› አጸደለችው፡፡ እውነት እና ተስፋ ነበሯትና የሚቻል የማይመስለውን ቻለች፤ ተራራውን ናደች፡፡ የውሸትን ክምር አፍርሳ የእውነትን ሐውልት አቆመች፡፡ አይሆንም የተባለው ሆነ፤ አይቻልም የተባለው ተቻለ፤ ቀባሪዎቹ አልፈው የተቀበረው ህያው ሆነ፡፡ የቀባሪዎቹ ታሪክ ተዘግቶ የተቀበረው ታሪክ ተከፈተ፡፡ ለዚህ ነው ቀደምት አባቶቻችንና እናቶቻችን የመስቀልን በዓል ከየቦታው በሚሰበሰብ እንጨት፣ ከእንጨቶችም በሚሠራ ደመራ እንድናከብረው ያደረጉን፡፡ እውነትን ለማጽናት ከመደመር የተሻለ ነገር የለም ሲሉን ነው፡፡መሟላት እንጂ መባላት እንደማይበጀን፤ ትግግዝ እንጂ ውግግዝ እንደማይረባን፤ ትቅቅፍ እንጂ ንቅቅፍ ዋጋ እንደሌለው፤ ዕሌኒ አሳይታናለች፡፡ በዚያ የመስቀል ፍለጋ ጉዞዋ፣ ክርስቲያኖችንም፣ አይሁድንም፣ ሌላ እምነት ያምኑ የነበሩትንም አስተባብራለች፡፡ መንገዷ የጥበብ እንጂ የመጥበብ አልነበረም፡፡ ጉዞዋ ሁሉንም ለእውነት ለማንበርከክ እንጂ አንዱን ለሌላው ለማንበርከክ አልነበረም፡፡ ዛሬ ሁሉም የታሪኩ ባለቤት ሆነዋል፡፡ ከዕሌኒ የምንማረው መንገዳችን ጠላት የመቀነስ፣ ወዳጅ የማብዛት መሆን እንዳለበት ነው፡፡መስቀሉ የለም፤ ተቀብሮ ጠፍቷል፤ ከእንግዲህ አይገኝም፤ አለቀለት አበቃለት – ሲሉ ለነበሩ ሰዎች ከልኬቷ ወርዳ በመነታረክ፤ ሥራ ፈትታ በመወራወር ዕሌኒ ጊዜ አላጠፋችም፡፡ ታሪክ ልኬት ከወረዱ ጋር በመውረድ፣ ካነሱ ጋር በማነስ ታሪክ እንደማይቀየር ዐውቃለች፡፡ በጮኹት ውሾች ላይ መልሳ በመጮህ ጉልበት አላባከነችም፡፡ እነርሱ ወደ ዝቅታ ሲሄዱ እርሷ ወደ ከፍታ በማምራት ላይ ነበረች፡፡ በየመንገዱ የነበሩ ተስፋ አስቆራጭ ጩኸቶችንና ልብ አፍሳሽ ዕንቅፋቶችን አልፋ፣ የማይሞከረውን ሞክራ፣ አይቻልም የተባለውን ችላ፣ ታሪክን በሠገነት ላይ አስቀመጠችው፡፡ አፈኞች ከማያወርዱበት፣ ወሬኞች ከማይደርሱበት፣ ተንኮለኞች ከማያገኙት ከፍታ ላይ ሰቀለችው፡፡ የእኛም ጉዞ እንደዚያ ይሁን፤ ለሥራ ካልደረሱ፣ ለመብል ካላነሱ ሰዎች ጋር ጊዜያችንን አናጥፋው፡፡ ጉልበታችንን አናባክነው፡፡ ጠላቶቻችን በዘረጉልን የአሽክላ መንገድ ሳይሆን ወደ ልዕልና በሚያደርሰን የራሳችን ጎዳና ላይ እንጓዝ፡፡ ወገባችን አሥረን፣ ዐቅማችንን ቋጥረን፣ ድምፃችንን አጥፍተን ታሪክ የቀየርን ለታ – የውሸት ክምር ይናዳል፤ የወሬ ኩይሳ ይፈርሳል፡፡ መስቀሉ የተገኘው፣ የመጀመሪያው ደመራም የተደመረው፣ የመጀመሪያው በዓልም የተከበረው ኢትዮጵያ ውስጥ አይደለም፡፡ አባቶቻችንና እናቶቻችን ግን ይህን ታላቅ ነገር ወደ ሀገራችን አምጥተው ኢትዮጵያዊ አድርገውታል፡፡ ከእኛው መልክአ ምድር፣ ከእኛው የዘመን አቆጣጠር፣ ከእኛው ባህል ጋር አስማምተው ኢትዮጵያዊ መልክ ሰጥተውታል፡፡ በብዙ ማኅበረሰቦች ዘንድ፣ በየአንዳንዱ ገጠር፣ ዘመናትን እየተሻገረ እንዲሄድ አስችለውታል፡፡የእኛው የመስቀል አከባበር ዓይነተኛ ቅርሳችን ሆኖ በዩኔስኮ የተመዘገበውም ለዚህ ነው፡፡ ኢትዮጵያዊ ስለሆነ፡፡ ሁሉን ነገር መቅዳት፣ ቀድተን እንዳለ በሀገራችን ምድር ላይ መድፋት፤ ውጤት አላመጣም፡፡ ሐሳቦችን፣ ልምዶችን፣ መርሖችን፣ ዕውቀቶችን ከሚገኙበት ወስደን ኢትዮጵያዊ መልክ ልንሰጣቸው ይገባል፡፡ ከኛው ባህል፣ እምነት፣ ልማድ፣ አስተሳሰብ፣ አኗኗርና ፍላጎት ጋር ማጣጣም አለብን፡፡ መደመር እንዲህ ነው፡፡ ከምዕራብም ከምሥራቅም አየን፤ በጎ በጎው ወሰድን፤ የራሳችንን ሐሳብ አዋለድን፤ ከኢትዮጵያ ባህልና ታሪክ፣ ፍላጎትና ዐቅም ጋር አዋሐድን – ኢትዮጵያዊ የሆነ የመደመር መንገድንም ጀመርን፡፡ ቀደምቶቻችን የመስቀል በዓል በየመንደሩ እስኪደርስ ድረስ እንደደከሙት ሁሉ መደመርም በየኪሳችን እስኪገባ ድረስ መድከም አለብን፡ ፡ አንዴ ከምዕራብ፣ ሌላ ጊዜ ከምሥራቅ አምጥተን፣ ምሥራቁንና ምዕራቡን ለመሆን ጥረን ነበር፡፡ እየቀዳን የምናመጣው ዘር ግን በኢትዮጵያ ምድር ሊያፈራ አልቻለም፡፡ ለዚህ ነው ግራ ቀኙን አይተን የኛኑ ችግር በኛው መፍትሔ ለመሞከር የተነሣነው፡፡ በመደመር፡፡ መደመር እንደ ደመራው ሁሉ በየመንደሩ – በየጥጋቱ ሁሉ ማብራት አለበት፡፡ ዛሬ የደመራ በዓላችንን ለማየት ዓለም ሁሉ ወደ እኛ እንደሚመጣው ሁሉ፣ ነገ መደመር ያስገኘልንን ለውጥና ብልጽግና – የተለምነውንም የፍቅር ጎዳና ለማየት፣ አይተውም ለመደመር ብዙዎች ይመጣሉ፡፡ እውነተኞች ተስፋ አላቸው፡፡ ደመራን በየዓመቱ የሚያይ ሕዝብ መደመር የሚኖረውን ኃይል ይገነዘባል፡፡ መደመርም እንደ ደመራው ሁሉ ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ ለኢትዮጵያ የሚበጅ ኢትዮጵያዊ – የኢትዮጵያ መንገድ፡፡ እንደ ዕሌኒ ታሪክ ለመለወጥ ቆርጠን፣ በዙሪያችን ያሉትን ሁሉ በእውነትና በፍቅር አስተባብረን፤ እንደ ደመራው ተደምረን – ኢትዮጵያን ማንም ከማያወርድበት ሠገነት ላይ ለማውጣት እንነሣ፡፡መልካም የመስቀል በዓል ይሁን!ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራ፣ ተከብራና በልጽጋ ለዘላለም ትኑር! ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ! መስከረም 15 ቀን 2012 ዓ.ም
https://waltainfo.com/am/32763/
1,059
0ሀገር አቀፍ ዜና
የተለያዩ እምነት ተከታዮች ከኢ/ር ታከለ ጋር መስቀል አደባባይን አፀዱ
ሀገር አቀፍ ዜና
September 28, 2019
Unknown
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ከተለያዩ እምነት ተከታዮች ጋር መስቀል አደባባይን አፅድተዋል፡፡ዛሬ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች የሚከበረውን የደመራ በዓልን አስመልክቶ የከተማ ነዋሪዎች በዓሉ የሚከበርበትን ስፍራ እንዲያፀዱ ምክትል ከንቲባው ጥሪ ማቅረባቸው ተከትሎ ነው ፅዳቱ የተካሄደው፡፡ዛሬ ከማለዳ ጀምሮ በተካሄደው የፅዳት ዘመቻ ላይ የእስልምና እምነት ተከታዮችን ጨምሮ በርካታ የከተማው ነዋሪዎች መሳተፋቸውን ከከንቲባ ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡የደመራ በዓል የሀይማኖት መሪዎች፣ በርካታ የእምነቱ ተከታዮችና የውጭ ሀገራ ጎብኚዎች በተገኙበት በመስቀል አደባባይ ዛሬ በታላቅ ስነ-,ስርዓት ይከበራል፡፡
https://waltainfo.com/am/32764/
73
0ሀገር አቀፍ ዜና
የደመራ በዓል በሰላም መከበሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
September 28, 2019
Unknown
በርካታ የኃይማኖቱ ተከታዮች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ተቀማጭነታቸውን ኢትዮጵያ ውስጥ ያደረጉ የውጪ ሀገራት ዲፕሎማቶች እና የተለያዩ ሀገራት ቱሪስቶች በስፋት የታደሙበት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የተከረው የደመራ በዓል በሰላም መከበሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡በተያዘው ዓመት በርካታ ህዝብ የታደመባቸው ሃይማኖታዊ እና ስፖርታዊ ዝግጅቶች በሰላም መከበራቸውን ኮሚሽኑ አስታወሶ፣ የዘንድሮ የደመራ በዓል በሰላም እንዲከበር ህብረተሰቡ በዋናነት ደግሞ የአዲስ አበባ ወጣቶች እያበረከቱት ላለው ቀና ትብብር እንዲሁም በፀጥታው ስራ ላይ ሃላፊነታቸውን በብቃት ለተወጡ መላው የፀጥታ አካላት ኮሚሽኑ ላቅ ያለ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡ዛሬ መስከረም 17 ቀን 2012 ዓ.ም የሚከበረው የመስቀል በዓልም በሰላም እንዲከበር ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በድጋሚ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡በኢትዮጵያ በርከታ ህዝብ ወደ አደባባይ በመውጣት ከሚያከብራቸው ሃይማኖታዊ በዓላት መካከል የመስቀል ደመራ በዓል ተጠቃሽ ነው፡፡ (ምንጭ፡- የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን )
https://waltainfo.com/am/32766/
117
0ሀገር አቀፍ ዜና
በኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራበት ነው- ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ
ሀገር አቀፍ ዜና
September 27, 2019
Unknown
ኢትዮጵያ የምግብ እና ስርዐተ ምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው የልማት ተግባራት አንዱ በማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራበት መሆኑን ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ፡፡በኢትዮጵያ በህጻናት ላይ የሚታየውን የመቀንጨር ችግር ለመፍታት የተቀረጸው የሰቆጣ የውሳኔ ሃሳብ ላይ የሚመክረው ጉባኤ በኒውዮርክ ተካሂዷል፡፡በዚህ መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉት ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ እንዳሉት ኢትዮጵያ ባለፉት 16 አመታት የህጻናት መቀንጨርን በ20 በመቶ መቀነስ ችላለች፡፡ከአንድ አመት በፊት የጸደቀው የምግብና የስርዐተ ምግብ ፖሊሲ መቀንጨርን ለመከላከል የተቀረጸውን የሰቆጣን የውሳኔ ሀሳብ ተግባራዊ ለማድረግ ቁልፍ እርምጃ ነው ብለዋል፡፡ችግሩን ለመቅረፍም ከሁሉም አጋሮች ጋር ተባብሮ ለመስራት ኢትዮጵያ ያላትን ቁርጠኝነት የገለጹት ፕሬዝደንት ሣህለወርቅ፣ አጋር አካላትም ድጋፋቸውን የበለጠ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡በስብሰባው ላይ የተሳተፉት አጋሮች በበኩላቸው፣ እስካሁን የተገኘው ውጤት አበረታች መሆኑን ነው ያመለከቱት፡፡ በቀጣይም በሰቆጣ የውሳኔ ሀሳብ ላይ የተቀመጡት ግቦች እንዲሳኩ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በቅርበት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል፡፡ጥናቶች እንደሚጠቁሙት በኢትዮጵያ 38 በመቶ የሚሆኑት ህጻናት የመቀንጨር ችግር እንደሚያጋጥማቸው ከፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
https://waltainfo.com/am/32762/
133
0ሀገር አቀፍ ዜና
“አንድነታችንንና ሰላማችንን የጋራ ሃብታችን አድርገን እንጠብቅ” – ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ
ሀገር አቀፍ ዜና
September 28, 2019
Unknown
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ ፓትሪያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በደመራ በዓል ላይ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡‹‹የጎደለውን ፍቅር እና ሠላም፣ አንድነት እና እኩልነት፣ ፍትሕ እና ወንድማማችነት በመስቀሉ ውስጥ ተትረፍርፎ እናገኘዋለን›› ያሉት አቡነ ማቲያስ ይቅርታና መተባበር፣ መከባበር እና መተባበር በመስቀሉ ሥር ስለሚገኙ ለእነዚህ ፍላጎቶች የመስቀሉን ጥያቄዎች መመለስ ግድ እንደሚል አሳስበዋል፡፡‹‹የቤተ ክርስቲያን ጥያቄዎች ካልተመለሱ ምኞቶች ሁሉ ቅዥት ከመሆን በቀር ሊሳኩ አይችሉም›› ብለዋል፡፡ በአንድነትንና ሠላምን የጋራ ሀብት አድርጎ ለሁሉም የምትበጅ ሀገር እንድትኖር መሥራት እንደሚያስፈልግም አሳስበዋል፡፡ ብፁዕነታቸው በመልዕክታቸው የኢትዮጵያውያን የጋራ ሀብት የሆነውን ሰላም እና አንድነት መጠበቅ ይገባል ብለዋል፤ የቤተ ክርስቲያን ግብረ አድኅኖ ፍጹም እንደሆነና ቅዱስ መስቀልም የሰው ልጆች የድኅነት ምልክት መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡  ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ በሀገሪቱ ውስጥ በቤተ ክርስቲያን ላይ እየተፈፀሙ ያሉ በደሎችን በፅኑ አውግዘዋል፡፡ ‹‹የመስቀሉ ነገረ ድኅነት በአንድ ጊዜ ተሠርቶ የተጠናቀቀ አይደለም፤ የተጣሉትን ያስታረቀ በአንድ መዓድ የሚያስቀምጥ፣ ሠላምና ፍቅርን የሚያድል አምላካዊ ምስጢር ነው›› ብለዋል፡፡አቡነ ማቲያስ እንደገለጹት ቀደምት ኢትዮጵያውያን ነገረ መስቀሉን በትክክል ተግብረው በዓለም ብቸኛ የሆነ ነፃነት እና አንድነትን ለትውልድ አስረክበዋል፡፡ ‹‹ይህንን እውነት ትቶ ቤተ ክርስቲያንን እያቃጠሉ ልማትን ማምጣት አይቻልም፡፡ መስል ድርጊቶች በአስቸኳይ እስከ መጨረሻው መቆም አለባቸው›› ሲሉም አሳስበዋል፡፡ሊቀ ጳጳሱ “በዚህ ዙሪያ የተፈጠረ ነገር ሁሉ መግባባት አያደርስም፤ መስቀልን ይሳለሙታል እንጂ አያቃጥሉትም፤ ኢትዮጵያውያን አበው መስቀልን አክብረው ይሰግዱለታል እንጂ አይረግጡትም፤ አያዋርዱትም” ብለዋል፡፡ በመስቀሉ እና በቃሉ ክብራቸውን እና ደኅንነታቸውን እንዳገኙበትም ተናግረዋል፡፡ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ ‹ትመኛላችሁ ለእናንተም አይሆንም፤ ትገድላላችሁ በብርቱም ትፈልጋላችሁ ልታገኙት አትችሉም፤ ትጣላላችሁ፣ ትዋጋላችሁ ነገር ግን አትለምኑምና ለእናንተ አይሆንም› ሲል ያስቀምጣል’ ምኞት ሁሉ ሊሳካ ያልቻለው ከመስቀሉ እየተራቀ በመሄዱ ነው›› ብለዋል፡፡ሊቀ ጳጳሱ የነብዩ ኢሳያስ አስተምህሮንም አበይት ርዕስ አድርገው አቅርበዋል፡፡ ‹‹እናንተም ዳር ዳር ትሄዳላችሁ፤ እኔም ዳርዳሩን እሄዳለሁ›› የተባለው በኢትዮጵያ ላይ እየተፈጸመ እንደሆነም በመልዕክታቸው አንስተዋል፡፡  
https://waltainfo.com/am/32767/
257
0ሀገር አቀፍ ዜና
በሳዑዲ ነዳጅ ማጣሪያ ላይ ለተፈጸመው ጥቃት ኢራንን ብቻ ተጠያቂ ማድረግ ተገቢ አለመሆኑን ፕሬዚዳንት ኤርዶጋን ገለጹ
ፖለቲካ
September 26, 2019
Unknown
በቅርቡ በሳዑዲ ዓረቢያ ሁለት የነዳጅ ማጣሪያ ተቋማት ላይ ለተፈጸመው ጥቃት ኢራንን ብቻ ተጠያቂ ማድረግ ተገቢ አለመሆኑን የቱርክ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ገለጹ።ፕሬዝዳንቱ በመካከለኛው ምስራቅ የተፈጠረውን ውጥረት አስመልክተው ከፎክስ ኒውስ ጋር በነበራቸው ቆይታ በቅርቡ በሳዑዲ ዓረቢያ የነዳጅ ማጣሪያ ተቋማት ላይ የተፈጸመው ጥቃት በኢራን የተወሰደ እርምጃ መሆኑን የሚያሳይ ተጨባጭ መረጃ አለመቅረቡን አንስተዋል።በመሆኑም ተጨባጭና ተዓማኒ መረጃ ባልቀረበበት ሁኔታ ኢራንን ብቻ ለጥቃቱ ተጠያቂ ማድረግ ውጤቱ የከፋ ቀውስ ሊያስከትል እንደሚችል ጠቁመዋል።በአንፃሩ ጥቃቱ የተፈጸመው ከተለያዩ የየመን አካባቢዎች በመጡ የሁቲ አማጽያን አማካኝነት መሆኑን የሚያሳዩ መረጃዎች መኖራቸውን ተናግረው፤ ቡድኑ ለጥቃቱ ሃላፊነት የወሰደ መሆኑ መረጃውን ይበልጥ ተዓማኒ ያደርገዋል ብለዋል ፕሬዚዳንቱ፡፡ሳዑዲ ዓረቢያ፣ አሜሪካና የአውሮፓ ሀገራት ያለምንም ተጨባጭ መረጃ በድርጊቱ ኢራንን የሚወነጅሉበት ሁኔታ ተቀባይነት የሌለውና የቀጠናውን ሰላም ይበልጥ የሚያባብስ መሆኑንም ገልጸዋል።በተያዘው ወር መጀመሪያ አካባቢ በሳዑዲ ሁለት የነዳጅ ማጣሪያ ተቋማት ላይ በድሮን የታገዘ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ ሳዑዲ ዓረቢያ፣ አሜሪካና የአውሮፓ ሀገራት ለጥቃቱ ኢራንን ተጠያቂ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡በሌላ በኩል በየመን በስፋት የሚንቀሳቀሱትና በኢራን መንግስት የሚደገፉት የሁቲ አማጽያን ለጥቃቱ ሃላፊነት ወስደዋል።ኢራን በበኩሏ በጥቃቱ እጇ የሌለበት መሆኑን በመግለፅ ጉዳዩን አስመልክቶ ሊፈጸምባት የሚችልን ማንኛውም ጥቃት ለመመከት ዝግጁ መሆኗን ማስታወቋ የኒታወስ ነው ሲል ሬውተርስ ዘግቧል፡፡
https://waltainfo.com/am/34006/
167
5ፖለቲካ
የውጪ ጎብኚዎች የቆይታ ጊዜን ለማራዘም እየተሰራ ነው
ቢዝነስ
September 26, 2019
Unknown
ቱሪዝም ኢትዮጵያ ባዘጋጀው የ10 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር ተካሂዷል፡፡አሁን ላይ ለስትራቴጂክ እቅዱ ጠቃሚ የሆኑ የተለያዩ ግብዓቶችን  በመሰብሰብ ለማፀደቅ እየተሰራ እንደሚገኝም የቱሪዝም ኢትዮጵያ  ማኔጀር ስለሺ ግርማ ተናግረዋል፡፡በመድረኩ በቱሪዝም ኢትዮጵያና በዓለም ባንክ ትብብር እውን የሆነ ጥናት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ጥናቱ በዋናነት የኮንፈረንስ  እና የማረፊያ /ስቶፕ ኦቨር ቱሪዝምን ለማጠናከር ያለመ ነው፡፡የማረፊያ ቱሪዝም ቱሪስቶች ከ24 ሰዓት ለበለጠ ጊዜ በእንድ ስፍራ እንዲቆዩ የሚያደርግ ዘዴ ነው፡፡ጥናቱ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ቱሪስቶች እንዴት የቆይታ ጊዜያቸውን ማራዘም ይችላሉ? የሚለውን በሚመልስ መልኩ ጥናቱ መዘጋጀቱም ተገልጿል፡፡ኢትዮጵያን በ2030 ከአፍሪካ በኮንፈረንስ ቱሪዝም ቀዳሚ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል፡፡ ,
https://waltainfo.com/am/23987/
87
3ቢዝነስ
የቀድሞ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ዣክ ሺራክ በ86 ዓመታቸው አረፉ
ሀገር አቀፍ ዜና
September 26, 2019
Unknown
የቀድሞ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ዣክ ሺራክ በ86 ዓመታቸው አርፈዋል ።በአውሮፓ በፖለቲካ ለረዥም ዓመታት የዘለቁት ዣክ ሺራክ ፈረንሳይን በፕሬዚዳንትነትና በጠቅላይ ሚኒስትርነት አገልግለዋታል፡፡ዣክ ሺራክ በሁለት ተከታታይ የምርጫ ዘመን በፕረዚዳንትነት እንዲሁም በጠቅላይ ሚኒስትርነት በማሸነፍ መምራት የቻሉ ሲሆን ለ18 ዓመታትም የፓሪስ ከንቲባ በመሆን አገልግለዋል፡፡ ዣክ ሺራክ የአሜሪካ መንግስት በኢራቅ የነበረው አገዛዝ ለማስወገድ ያካሄደው ጦርነት በመቃወምም ይታወቃሉ፡፡የቀድሞዉ ፕሬዚዳንትና ጠቅላይ ሚኒስትር ጡረታ ከወጣ ከሁለት ዓመት ብሃላ ከሙስና ጋር ተያይዞ በቀረበባቸው ክስ የሁለት ዓመት እስራት ተበይኖባቸው ነበር፡፡ፓሪስ የሚገኘው የሺራክ ፋውንዴሽን የቀድሞ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ዣክ ሺራክ በ86 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ይፋ አድርጓል፡፡ (ሲጂቲኤን አፍሪካ)
https://waltainfo.com/am/34136/
87
0ሀገር አቀፍ ዜና
የራስ መኮንን ፓርክ ተመረቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
September 26, 2019
Unknown
በአዲስ መልክ ለህብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሠጥ የተደራጀውን የራስ መኮን ፓርክ የአዲስ አበባ ም/ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ መርቀው ስራ አስጀምረውታል፡፡ከ4 ሺህ 300 ካ.ሜ በላይ ስፋት ያለው የራስ መኮንን ፓርክ የአረንጓዴ ቦታን ጨምሮ የህፃናት መጫወቻ ስፍራ እና ለአከባቢው ወጣቶች የስፖርት ማዘውተሪያ ማዕከልን ያካተተ ነው፡፡ከራስ መኮንን ፓርክ በተጨማሪ ጦር ኃይሎች አከባቢ የሚገኘው ሆላንድ ፓርክ (65 ሺህ ካ.ሜ) እና የአቃቂ ፓርክ (62 ሺ ካ.ሜ) በተመሳሳይ መልኩ ለህብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሠጡ ተመርቀው ወደ ስራ ገብተዋል፡፡በዛሬው ዕለት የተመረቁት 3 ፓርኮች በአጠቃላይ 13.9 ሔክታር በላይ ስፋት ያላቸው ናቸው፡፡በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ኢ/ር ታከለ ኡማ ራስ መኮንን ፓርክ ውስጥ ያለውን የስፖርት ማዘውተሪያ ማዕከል በማህበር ለተደራጁ የአከባቢው ወጣቶች አስረክበዋል፡፡የከተማ አስተዳደሩ ጤናማ እና አረንጓዴ አዲስ አበባን ለመገንባት ትላልቅ ፕሮጀክቶችን ነድፎ እየሰራ እንደሆነ ተገልጿል፡፡(ምንጭ፦ ከንቲባ ፅ/ቤት)
https://waltainfo.com/am/32761/
112
0ሀገር አቀፍ ዜና
አሜሪካ ወደ ሀገሯ የሚገቡ ስደተኞችን ቁጥር በግማሽ ልትቀንስ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
September 27, 2019
Unknown
የአሜሪካ መንግሥት ወደ ሀገሪቱ የሚገቡ የስደተኞችን ቁጥር በግማሽ እንደሚቀንስ አስታወቀ።በቀጣዮቹ 12 ወራት 18 ሺህ ስደተኞችን ብቻ በሀገሪቱ የስደተኞች መርሀግብር መሰረት እንደሚቀበል የተናገረ ሲሆን፣ ይህም በታሪክ ታይቶም ተሰምቶም በማይታወቅ ሁኔታ ትንሹ ተብሏል።የአሜሪካ ጦርን ለረዱ ኢራቃውያን የተወሰነ ቦታ መያዙ የተገለፀ ሲሆን፣ በሀገራቸው በእምነታቸው ምክንያት ለተገፉና ለተሰደዱ ሰዎችም የተወሰነ ኮታ መያዙ ተሰምቷል።ይህንን የአሜሪካ እርምጃ የሰብኣዊ መብት ተሟጋቾች ተችተውታል።ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ግዛቶችና የአካባቢ አስተዳዳሪዎች በማህበረሰባቸው ውስጥ እነዚህን ስደተኞች ከሰፈራቸው እንዲያስወጧቸው የሚያስችላቸውን ትዕዛዝ ያረፈበት መመሪያ ፈርመዋል።መመሪያው "ስደተኞቹ ሊረዷቸው፣ ሊደግፏቸውና በቀላሉ ከአሜሪካውያን ጋር እንዲቀራረቡ ከሚረዷቸው ማህበረሰብ አካባቢ ይሰፍራሉ" ይላል።ፕሬዝዳንት ትራምፕ የስደተኞችን ቁጥር መቀነስ የአስተዳደራቸው ቀዳሚ ዓላማ መሆኑን ይናገራሉ።እኤአ በ2017 አሜሪካ የምትቀበላቸውን የስደተኞች ቁጥር ወደ 50ሺህ ለመቀነስ የወሰኑ ሲሆን፣ በቀጣዩ ዓመት ደግሞ 40ሺህ፣ ከዚያም 30 ሺህ እንደሚሆን ወስነው ነበር።በመግለጫቸው ላይም በደቡባዊ የሜክሲኮ ድንበር በኩል ወደ ሀገሪቱ እየገቡ ጥገኝነት የሚጠይቁ ሰዎች "ከአቅም በላይ የሆነ ጫና " መፍጠራቸውን ባለስልጣናት መናገራቸውን ገልፀዋል።"በአሁኑ ሰዓት ያለው የአሜሪካ የስደተኞች ስርዓት ጫና ሌላ ነው፤ በርካታ ስደተኛ ከመቀበላችን በፊት መሻሻል አለበት" ብሏል ይህን ጉዳይ በኃላፊነት የሚመራው ቢሮ በመግለጫው።አሜሪካውያንን ለረዱ ኢራቃውን 5ሺህ፣ ከጓቲማላ፣ ሆንዱራስ፣ ኤል ሳልቫዶር በሐይማኖታቸው ምክንያት መድረሻ አጥተው ለተሰደዱ 1ሺህ 500 ቦታ ተይዞላቸዋል።የሰብዓዊ ርዳታ አቅራቢዎች ይህንን ርምጃ ለመተቸት የቀደማቸው አልነበረም።"ይህ ለአሜሪካ ጥቁር ቀን ነው" ያሉት የዓለም አቀፉ ሬስኪዩ ኮሚቴ የበላይ ኃላፊ ዴቪድ ሚሊባንድ ናቸው።ሌሎች የዓለም አቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅቶችም አሜሪካ በዓለም ላይ ተጋላጭ የሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ለመከላከልና ከለላ ለመስጠት ፍላጎት አለማሳየቷ የወደፊት ጥቅሟን ይጎዳዋል ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
https://waltainfo.com/am/34137/
216
0ሀገር አቀፍ ዜና
በዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ የተመራ ልዑክ የህዳሴ ግድብን ጎበኘ
ቢዝነስ
September 25, 2019
Unknown
የውሃ፣ መስኖና ኢኔርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ የተመራ ልዑካን ቡድን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ዛሬ ጎብኝቷል፡፡   ልዑኩ የግድቡ ግንባታ ያለበትን ደረጃ ተዘዋውሮ የጎበኘ ሲሆን፣ የግንባታው በተሻለ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው ወቅት አጠቃላይ የግድቡ ግንባታ በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ገልጸው፣ ሁለት የታችኛው የውሃ ማስወጫ መስመሮች ከዚህ ቀደም የነበራቸው ችግሮች ተቀርፈው ተርባይኖቹ እየተገጠሙ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡የግድቡ ግንባታ 68 ነጥብ 3 በመቶ መድረሱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በትላንትናው ዕለት በሰጠው መግለጫ መግለጹ ይታወሳል።    
https://waltainfo.com/am/23986/
70
3ቢዝነስ
ያለፈቃድ መንገድ ያጸዳው ናይጄሪያዊ ስደተኛ ቅጣቱ ተነሳለት
ሀገር አቀፍ ዜና
September 26, 2019
Unknown
በሰሜናዊ ጣልያን በምትገኝ ከተማ ፈቃድ ሳያገኝ መንገድ አጽድቷል በሚል ቅጣት ተጥሎበት የነበረው ናይጄሪያያዊ ስደተኛ በነዋሪዎች ጥያቄ ቅጣቱ እንዲነሳለት ተደረገ።የ29 ዓመቱ ስደተኛ ስራ አጥ ሲሆን፣ አላፊ አግዳሚውን ቁጭ ብሎ ገንዘብ ከመጠየቅ ሌላው ቢቀር መንገዱን አጽድቼላቸው ገንዘብ ቢሰጡኝ ብዬ ነው ተግባሩን የፈጸምኩት ብሏል።ያለፈቃድ መንገዱን በማጽዳቱም 383 ዶላር (11ሺ ብር አካባቢ) እንዲቀጣ ተወስኖበት ነበር። ነገር ግን የከተማዋ ነዋሪዎች ውሳኔውን በመቃወማቸው የከተማዋ ምክር ቤት ቅጣቱን አንስቻለሁ ብሏል።ጉዳዩን የሰሙ ጣልያናውያንም በማህበራዊ ሚዲያ ሰዎችን በማስተባበር የቅጣቱን ገንዘብ ለማሰባሰብ ጥረት አድርገዋል።ናይጄሪያዊው መንገድ ሲያጸዳ የነበረው '' ምንም አይነት ልመና ውስጥ ሳልገባ በታማኝነት ከማህበረሰባችሁ ጋር መቀላቀል እፈልጋለሁ፤ መንገዶቻችሁን ንጹህና ማራኪ አደርግላችኋለሁ፤ እናንተ ደግሞ ለስራዬ ትንሽ ትከፍሉኛላችሁ'' የሚል መልእክት በወረቀት ላይ ጽፎ ነበር።መጀመሪያ ላይ ጉዳዩን በማህበራዊ ሚዲያ ይዞት የወጣው ማቴዎ ዲ አንጀሎ የተባለ ጣልያናዊ በፌስቡክ ገጹ ላይ ባሰፈረው መልእክት '' ቅጠሎች፣ የሲጋራ ቁራጭ እና ሌሎች የምንጥላቸው ቆሻሻዎች የውሃ መፍሰሻውን እየደፈኑት ነበር፤ ይህ ግለሰብ ይህንን ችግር ነው ያቃለለልን'' ብሏል።ናይጄሪያዊው ግለሰብ የፖሊስ አይን ውስጥ የገባው በአካባቢው የነበሩ አንዳንድ ነዋሪዎች ቅሬታ በማሰማታቸው ነበር።ነገር ግን ሌሎች የከተማዋ ነዋሪዎች ወደ ከተማዋ ምክር ቤት ስልክ በመደወል ግለሰቡ ምንም ያጠፋው ነገር እንደሌለ በመግለጻቸው ምክንያት ቅጣቱ እንዲነሳ መደረጉ ታውቋል።ምክር ቤቱም ቅጣቱን ያስተላለፉት ለስራው አዲስና ልምድ የሌላቸው የፖሊስ አባላት መሆናቸውን አስታውቋል። (ምንጭ፡-ቢቢሲ)
https://waltainfo.com/am/33478/
183
0ሀገር አቀፍ ዜና
የከተማ አስተዳደሩ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነባር አብያተ ክርስቲያን የይዞታ ማረጋገጫ አዘጋጅቶ ለቤተክርስቲያኗ አስረከበ
ሀገር አቀፍ ዜና
September 26, 2019
Unknown
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለረዥም ጊዜያት ጥያቄ ስታቀርብባቸው ለነበሩ 15 ነባር የቤተ ክርስቲያኗ ይዞታዎች የተዘጋጁ ካርታዎችን በዛሬው ዕለት ቅዱስ ፓትሪያርኩ በተገኙበት አስረክበዋል፡፡የከተማ አስተዳደሩ ለቤተክርስቲያኗ ተገቢና ትክክለኛ ጥያቄዎች በቀጣይነት ምላሽ እንደሚሰጥ ኢ/ር ታከለ ኡማ በርክክቡ ወቅት ተናግረዋል፡፡ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ በበኩላቸው የከተማ አስተዳደሩ ለቤተ ክርስቲያኗ የዘመናት የይዞታ ጥያቄዎች በጎ ምላሽ በመስጠቱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ቤተ ክርስቲያኗ በቀጣይም ከከተማ አስተዳደሩ ጋር እየተመካከረች እንደምትሰራ እና አስተዳደሩ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ነዋሪዎችን ለመደገፍ የሚሰራውን ስራ በዘላቂነት እንደምትደግፍ ቅዱስ ፓትሪያርኩ ተናግረዋል፡፡በመጨረሻም ኢ/ር ታከለ ኡማ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የዘመናት ጥያቄዎች ምላሽ ማግኘት ላበረከቱት ጉልህ አስተዋፅኦ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡(ምንጭ፡- የከንቲባ ጽ/ቤት)
https://waltainfo.com/am/32760/
103
0ሀገር አቀፍ ዜና
ኔቶ የአፍሪካ ቀንድ ሰላምን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ጋር በጋራ እንደሚሰራ አስታወቀ
ፖለቲካ
September 26, 2019
Unknown
የኢፌዲሪ ሰላም ሚኒስቴር ሚኒስቴር ዲኤታ ወ/ሮ አልማዝ መኮንን የሰሜን አትላንቲክ የቃል ኪዳን ሀገሮች ድርጅት (ኔቶ) ንዑስ-ኮሚቴ ሊቀመንበር የሆኑትን ሚሮ ኮቫችን እና ከልዩ ልዩ ሀገራት የተውጣጡ የድርጅቱን የፓርላማ አባላት በሚኒስትር ጽህፈት ቤት ተቀብለው አነጋገሩ፡፡ በውይይታቸውም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሀገሪቱን ሰላም ከማስጠበቅ አፃር በርካታ ስራዎች እየተሰራ እንደሆነ እና ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ጋር ሰላማዊ የሆነ ግንኙነትን በዘላቂነት ይዛ ለመጓዝ እንድትችል በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ እንዳሉ አስረድተዋል፡፡ ሊቀመንበሩ ሚሮ ኮቫች በበኩላቸው በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሀገሪቱን ሰላም ከማስጠበቅ አንፃር እየተሰራ ያለውን ስራ አድንቀው በቀጣናው ሰላምን ለማስፈን ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱና ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በትብብር ለመስራት ፍላጎቱ እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡የኢትዮጵያ  መንግሥት በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላምን እንዲኖርና ዜጎች ዋስትናቸው የተጠበቀ እንዲሆን ልዩ ልዩ ሥራዎችን እያከናወነ በአፍሪካ ቀንድ ሀገራትም እንዲሁ ይህንን ለመተግበር መትጋቱ ለሉላዊ ሰላም የሚያበረክተው አስተዋጾ የላቀ መሆኑን የልዑካን ቡድኑ አስምሮበታል፡፡ ሁለቱ ተቋማት ከጎረቤት አገራት ጋር ያለውን ሰላም በዘላቂነት ለማስፈን የሚያስችሉ የትብብር አቅጣጫዎች ላይ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የማህበራዊ መገናኛ ገፅ ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል፡፡
https://waltainfo.com/am/31368/
144
5ፖለቲካ
የኢጋድ አባል ሃገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ተወያዩ
ፖለቲካ
September 26, 2019
Unknown
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በኒውዮርክ እየተካሄደ ከሚገኘው 74ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ጎን ለጎን በኢጋድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሊቀመንበርነታቸው የአባል ሃገራት ሚንስትሮች ስብሰባ በመጥራት በጋራ መክረዋል።በውይይቱ የአባል ሃገራት ሚኒስትሮች የኢጋድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባል ሆነው የተቀላቀሉትን የደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር እንዲሁም የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በተዘጋጀ የእራት ፕሮግራም ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።የደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አውት ዴንግ አኩይ በሃገራቸው የሠላም ሂደት የደረሰበትን ዝርዝር ሂደት አስረድተው፥ አባል ሃገራት ድጋፋቸውን እንዲሠጡ ጠይቀዋል።አዲሱን የሱዳን ካቢኔ የተቀላቀሉት የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስማ አብደላ በበኩላቸው፥ የአካባቢው ሃገራትና ኢጋድ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንዲሠጣቸው ጠይቀዋል።የአባል ሃገራት ሚኒስትሮች አፍሪካዊ መፍትሄ ለአፍሪካዊ ችግሮች በሚለው መሠረት ሁለንተናዊ ድጋፋቸውን ለመስጠት ቃል ገብተዋል።በዝግጅቱ የጂቡቲ፣ የሱዳን፣ የደቡብ ሱዳን፣ የሶማሊያና የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እንዲሁም፥ የኬንያና ኡጋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታዎች መገኘታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት አስታውቋል።
https://waltainfo.com/am/31367/
131
5ፖለቲካ
በሲዳማ የህዝብ ውሳኔ ጥቅም ላይ በሚውሉ ምልክቶች ዙሪያ ውይይት እየተደረገ ነው
ፖለቲካ
September 26, 2019
Unknown
የሲዳማ ዞን ክልል ሆኖ ለመደራጀት በሚካሄደው የህዝብ ውሳኔ ጥቅም ላይ በሚውሉ ምልክቶች ውይይት እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል፡፡በምልክቶቹ የመጀመሪያው ረቂቅ ላይ ለመወሰን የደቡብ ክልል ምክር ቤት ውይይት እየተደረገ መሆኑን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ኮምዩኒኬሽንስ አማካሪ ወ/ት ሶሊያና ሽመልስ ተናግረዋል፡፡በህዝበ ውሳኔው የሚቀርቡ ምልክቶቹ ምን አይነት ይሁኑ በሚለው እና ምልክቶቹ በተቀመጠው መስፈርት መሰረት ገለልተኛ፣ የማህበረሰቡን ምስል የሚያሳዩ እንዲሁም ጥያቄዎቹ ግልጽ እንዲሆኑ እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡በውይይቱ ላይ ስምምነት የተደረሰባቸው ምልክቶች ለህዝብ ይፋ እንደሚደረጉ ተጠቁሟል፡፡የህዝበ ውሳኔው አፈጻጸሞች በክልሉ ጥያቄ ለተወሰኑ ቀናቶች ከተራዘሙት ውጪ አብዛኞቹ በተያዘላቸው መርሀ ግብር እየተከናወኑ እንደሆነም ተነግሯል፡፡የህግ አስፈጻሚ እና የጸጥታ አካላት እንዲሁም የቦርዱ የስራ አመራር አባላት የህዝበ ውሳኔውን አፈጻጸም ሰላማዊነት ለማረጋገጥ ውይይት ማካሄዳቸው ታውቋል፡፡የድምፅ ሰጪዎች ምዝገባ፣ እንዲሁም የድምፅ መስጫ እና ድህረ ምርጫ ሂደቱን ሰላማዊነት ለማረጋገጥ እንዲሁም የምርጫ አስፈጻሚዎችን ደህንነት ለማስጠበቅ የህግ አስፈጻሚ አካላት ትብብር እንደሚያስፈልግ ቦርዱ ለተሳታፊዎቹ ማስገንዘቡ ተገልጿል፡፡ለህዝበ ውሳኔ ምርጫ አስፈፃሚዎች ስልጠና በአዲስ አበባ ከተማ ከመስከረም 24 እስከ 30 ከተሰጠ በኋላ እንደሚሰማሩም የኢቢሲ ዘገባ አመልክቷል፡፡በቀጣይ የሚካሄዱ ተግባራትም በመርሃ ግብሩ መሰረት ለማከናወን ዝግጅቶች እየተካሄዱ እንዳለ ለማወቅ ተችሏል፡፡በተያያዘ ዜና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመጪው ህዳር 3 ቀን 2012 ዓ.ም የሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄን ህዝበ ውሳኔ አማራጭ ሃሳቦችና የሚወከሉበት ምልክቶችን ይፋ አድርጓልበዚህም መሰረት “ሲዳማ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ውስጥ እንዲቆይ እፈልጋለሁ” ለሚለው አማራጭ የጎጆ ቤት ምልክት፣  “ሲዳማ ራሱን ችሎ በክልልነት እንዲደራጅ እፈልጋለሁ” ለሚለው አማራጭ የሻፌታ ምልክት ሆኖ ለህዝበ ውሳኔው ድምጽ መስጫነት እንዲያገለግል ተወስኗል ።
https://waltainfo.com/am/31369/
213
5ፖለቲካ
አዴፓ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነትን በመፍጠር የክልሉን ህዝብ ጥያቄ ለመመለስ እንደሚሰራ አስታወቀ
ፖለቲካ
September 25, 2019
Unknown
በአዲሱ ዓመት በመላ አመራሩና አባላቱ ዘንድ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት በመፍጠር የአማራ ክልልን ህዝብ የዘመናት መሰረታዊና መዋቅራዊ ጥያቄዎች ለመፍታት በትኩረት እንደሚሰራ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ/አዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።የአማራ ክልል የ2012 የድርጅትና የመንግስት የልማት እቅድ የንቅናቄ መድረክ በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።የጽህፈት ቤቱ የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ተተካ በቀለ እንዳስታወቁት በዚህ ዓመት በመላ አመራሩ፣ አባላቱና በህዝቡ ዘንድ አዲስ የትግልና የስራ መንፈስ ለመፍጠር በቅንጅት እየተሰራ ይገኛል።በክልሉ ባለፉት ዓመታት በተፈጠሩ የመልካም አስተዳደርና የአገልጋይነት መንፈስ መጓደልና የህዝቡን ተጠቀሚነት የሚያረጋግጡ የልማት ስራዎችን በተሟላ መንግድ አለመከናወን ህዝቡን ወደ ቅሬታ እንዲገባ አድርጎት ቆይቷል።በዚህ የተነሳም በየወቅቱ በሚፈጠሩ አለመረጋጋቶችና የፀጥታ ችግሮች አመራሩ እሳት የማጥፋት ስራ ላይ ተጠምዶ ዘላቂ የልማት ስራዎች እንዲጓተቱ ምክንያት መሆኑንም ተናግረዋል።“የችግሮችን መንስኤ በጥልቀት በመገምገም በስትራቴጂ እንዲፈቱ ለማድረግ የአስተሳሰብ ፣ የአመለካከትና የተግባር አንድነት በመፍጠር በዘላቂነት እንዲፈቱ አዴፓ ጠንካራ የመሪነት ሚናውን በላቀ ደረጃ ለመወጣት ተዘጋጅቷል” ብለዋል።“በመሆኑም በህዝብ ዘንድ በተደጋጋሚ የሚነሱ የልማት፣ የዴሞክራሲ፣ የመልካም አስተዳደር፣ የፍትሃዊ ተጠቃሚነትና መሰል ጥያቄዎች የአመራሩን ብስለትና ቁመና በማዳበር በሂደት እንዲመለሱ ይደረጋል”ብለዋል።“ህዝብን ማገልገልና ሀገርን በመለወጥ ጎዳና መምራት የአመራሩ ቁልፍ ሚና ነው” ያሉት ኃላፊው ይህን በመረዳትም አመራሩ የራሱን አሻራ እንዲያሳርፍ መሰረት የሚጣልበት ዓመት እንደሆነም አብራርተዋል።“አዴፓ እንደ ድርጅት ውስጣዊ አንድነቱን በማጠንከር ልማትና ሰላም ፈላጊውን ህዝብ አደራጀቶ በመምራት ክልሉ የእድገት ማማ ላይ እንዲወጣ የሚያግዙ ተጨባጭ ተግባራት ይከናወናሉ” ብለዋል።የህዝቡ ዘላቂ ፍላጎትና ጥቅም እንዲከበርም አዴፓ ከሚያደርገው ጠንክራ ትግል ጎን ለጎን ባለሃብቱና ምሁራን ህዝባቸውን ለማገልገል እያሳዩት ያለው ቁርጠኛነት በመደጋገፍ ላይ ተመስርቶ ወደ ላቀ ውጤት እንዲመዘገብ ይደረጋል ብለዋል።ስቪል ሰርቫንቱም ህዝቡን የሚያማርሩ የአገልግሎት መጓደልን ችግሮችን በመፍታት ምስጉንና ደረጃውን የጠበቀ ፈጣን አገልግሎት በመስጠት ለለውጡ ዋና አጋዥ እንዲሆንም ተለይቶ ይሰራል ብለዋል።በዚህ ዓመት የሚከናወነውን ሃገራዊ ምርጫ ጨምሮ ሌሎች ታላላቅ ስራዎችን በስኬታማነት ለማከናወንም አመራሩን የማደራጀት ስራ መጀመሩንም አስታውቀዋል።አሁን በከፌዴራል እስከ ወረዳ ባለው አመራር የተጀመረው የፖለቲካ ፣ የድርጅትና የመንግስት አቅድ ትውውቅም በቀጣይ እስከ ቀበሌ ባለው መዋቅር ውይይት በማድረግ ጠንካራ አንድነትን ለመፍጠር የሚቀጥል መሆኑን አስታውቀዋል።የእቅድ ትውውቁ ትናንት በቡድን ተከፋፍሎ ሲካሄድ የዋለ ሲሆን በዛሬው እለት ደግሞ በሃይል መድረክ በተነሱ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር እየተደረገ ይገኛል። (ምንጭ፡-ኢዜአ)
https://waltainfo.com/am/31366/
295
5ፖለቲካ
በክልሎች በተፈጠሩ ግጭቶች ላይ ተሳትፈዋል በተባሉ 1 ሺህ 323 ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ተመሰረተ
ፖለቲካ
September 24, 2019
Unknown
በተለያዩ ክልሎች በተፈጠሩ ግጭቶች ላይ ተሳትፈዋል በተባሉ 1 ሺህ 323 ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ተመሰረተ።በ2011 በጀት ዓመት በተለያዩ ክልሎች በተፈጠሩ ግጭቶች ተሳትፈዋል በተባሉ 1 ሺህ 323 ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ መመስረቱን የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታወቀ፡፡በተፈጠረው ሁከትና ብጥብጥ 1 ሺህ 229 ሰዎች ህይዎት ያለፈ ሲሆን በ1 ሺህ 393 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ሲደርስ በ19 ሰዎች ላይ የግድያ ሙከራ መደረጉን በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የተደራጁ ድንበር ተሸጋሪ ወንጀሎች ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ፍቃዱ ፀጋ ገልፀዋል፡፡በግጭቶቹ ከ2.2 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት የዜጎች ንብረት የወደመ ሲሆን፤ 1.2 ሚሊዮን ዜጎች ከመኖሪያ ቤታቸውና ከአካባቢያቸው ተፈናቅለዋል፡፡ከተከሳሾቹ መካከል 645 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየታየ ሲሆን 667 የሚሆኑ ተጠርጣሪዎች ደግሞ በቁጥጥር ስር አልዋሉም፡፡የ10 ተጠርጣሪዎች ክስም በምህረት መነሳቱን ዳይሬክተሩ አክለዋል፡፡በመጨረሻም አቶ ፍቃዱ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል በሚደረግ እንቅስቃሴ ዙሪያ የሚስተዋለው ክፍተት አስመልክቶ መፍትሔ ያሉትን ሀሳብ ሲጠቁሙ ይህንን ችግር ለመቅረፍ ህብረተሰቡና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ከፍትህ አካላት ጎን በመቆምና ተጠርጣሪዎችን አሳልፎ በመስጠት በኩል በጉዳዩ ላይ በባለቤትነት ስሜት ሊሰሩ እንደሚገባ አጽእኖት ሰጥተው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡በሌላ በኩል በአማራ ክልል በጃዊ ወረዳና በመተክል ዞን፤ በጎንደርና አካባቢው በተፈጠረ ሁከትና ብጥብጥ፤ በሰሜን ሸዋ አስተዳደር እንዲሁም በቤንሻጉል ጉምዝ ክልል ከማሻ ዞን ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎችና ቀበሌዎችና የዚሁ ዞን አጎራባች በሆነው በኦሮሚያ ክልል ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ ዞን በተለያዩ ቀበሌዎች ላይ በተፈፀመ ብጥብጥና ሁከት በአሶሳ ዞን አራት ወረዳዎች ውስጥ በኦሮሚያና በበርታ ብሄረሰብ መካከል በተፈጠረ ግጭት ተሳታፊ የነበሩ በአጠቃላይ 1647 ተጠርጣሪዎች ተለይተውና አስፈላጊው የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች ተሰባስበው እስካሁን ድረስ 185 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር የማዋሉ ስራ የተከናወነ መሆኑን የጠቀሱት ሀላፊዉ ቀሪዎችን 1462 ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ የማፈላለግ ስራም እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ምንጭ:-ጠቅላይ አቃቢ ህግ
https://waltainfo.com/am/31365/
239
5ፖለቲካ
ፕሬዝዳንት ትራምፕን ከስልጣናቸው ለማስወገድ በአሜሪካ ምክር ቤት ድምጽ እንዲሰጥባቸው ሊደረግ ነው
ፖለቲካ
September 25, 2019
Unknown
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከስልጣናቸው እንዲወገዱ የአገሪቱ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት /ኮንግረስ/ ድምጽ እንዲሰጥባቸው የዲሞክራቲክ ፓርቲ ከወዲሁ ጥያቄ አቅርቧል፡፡ምክር ቤቱ ድምጹን የሚሰጠው በአውሮፓዊያኑ 2016 በተደረገው የፕሬዝዳንት ምርጫ ዶናልድ ትራምፕ የወቅቱን ተቀናቃኛቸውን ለማሸነፍ በሚል በዮክሬን ላይ ተገቢ ያልሆነ ጫና አድርገዋል የሚል ክስ ስለቀረበባቸው መሆኑን ተነግሯል፡፡ዶናልድ ትራምፕ ምርጫውን ካሸነፉ በሃላ የፖለቲካ ተፎካካሪያቸውን ጆን ባይደንና ልጃቸውን ዩክሬን በሙስና እንድትከሳቸው፣ አለበለዚያ ግን አሜሪካ የምትሰጠውን ወታደራዊ ድጋፍ እንደምታቆም ጫና አድርገዋል በሚል ነው ዴሞክራቶች ክሱን ያቀረቡት፡፡ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጉዳዮ ትክክል እንዳልሆነና የፈጠራ ወሬ እንደሆነ አድርገው ክሱን አጣጥለውታል ተብሏል፡፡በአሜሪካ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አብላጫውን ድምጽ የያዙት ዲሞክራቶች በመሆናቸው ክሱን ገፍተው ከሄዱበት ፕሬዝዳንቱን ከስልጣናቸው ለማንሳት የሚሰጠው ድምጽ በአመዛኙ ይሁንታ ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ይሁን እንጂ በአገሪቱ ሴኔት አብላጫ ወንበር የያዙት ፕሬዝዳንቱን የሚደግፉት የሪፐብሊካን ፓርቲ በመሆናቸው የዴሞክራቶች ውሳኔ በሴኔቱ ውድቅ የመደረግ እድሉ ሰፊ መሆኑ ተመልክቷል፡፡ (ምንጭ፡-ቢቢሲ)
https://waltainfo.com/am/34005/
125
5ፖለቲካ
የይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ፓርክ ግንባታ በመፋጠን ላይ መሆኑ ተገለጸ
ቢዝነስ
September 25, 2019
Unknown
በደቡብ ክልል የሚገኘው የይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ፓርክ ግንባታ በመፋጠን ላይ መሆኑ ተገለጸ፡፡የደቡብ ክልል ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ብሩ ወልዴ ለዋልታ እንደተናገሩት የፓርኩ ግንባታን በማፋጠን የአስተዳደር ህንፃዎችን ጨምሮ በዚህ ዓመት ሊገነቡ ከታቀዱት 11 የፋብሪካ ሼዶች አስካሁን አራቱ ሙሉ በሙሉ ተጠናቀዋል፡፡በፓርኩ ለመሳተፍ ከተመዘገቡ ባለሀብቶች ማካከል ከፓርኩ ውጭ በጊዜያዊነት በተዘጋጀላቸው ቦታዎች የማር በማምረት ላይ የሚገኙ ኩባንያዎች መኖራቸውን የጠቀሱት አቶ ብሩ፣ ሳንቫዶ የተባለ የሆላንድ ኩባንያ በፓርኩ ቅጥር ግቢ የተገነባለትን አንድ ሼድ ተጠቅሞ አቮካዶ እና ዘይቱን ማቀነባበር ጀምሯል፡፡ አንድ የጣሊያን ኩባንያም ቡናን ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ በማቀነባበር ስራ ላይ ለመሳተፍ ዝግጅቱን አጠናቋል ብለዋል፡፡ጥሬ ዕቃዎችን ለፋብሪካው የሚያቀርቡት አርሶአደሮች የክህሎት ስልጠናዎች የሚያገኙበትና የምርት ማስረከቢያ ቦታ ሆኖ የሚያገለግሉ ማዕከላት በበንሳ ደላ እና የይርጋጨፌ ከተሞች በእያንዳንዳቸው 10 ሄክታር መሬት ላይ እየተገነቡ ነው፡፡ በፓርኩ ውስጥ ለውስጥና ፓርኩን ከዋና መንገዶች ላይ ለማገናኘትም የ13 ኪሎሜትር የአስፋልት መንገድ በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡  በቡና፣ ፍራፍሬና ወተት ማቀነባር ዘርፎች አተኩሮ ይሰራል የተባለው የይርጋለም የተቀናጀ አግሮ ፕሮሰሲንግ ፓርክ በቀጥታና በተዘዋዋሪ ከ 400 ባለይ ለሚሆኑ አርሶአደሮች የሥራ እድል ፈጥሯል፡፡በ2010 ግንባታው የተጀመረው ፓርኩ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ 152 የማምረቻ ፋብሪካዎች የሚገነቡለት ሼዶች ይኖረዋል፡፡ 300 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው የይርጋለም የተቀናጀ አግሮ ፕሮሰሲንግ ፓርክ ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ 6 ቢሊየን ብር ገደማ ይፈጃል ተብሏል፡፡በደቡብ ክልል ሲዳማ ዞን ይርጋለም ከተማ እየተገነባ ያለው የይርጋለም የተቀናጀ አግሮፕሮሰሲንግ ፓርክ በሀገር አቀፍ ደረጃ በትግራይ በከር፣ በኦሮሚያ ቡልቡላና በአማራ ክልል ቡሬ እየተገነቡ ካሉት የተቀናጁ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ፓርኮች አንዱ ነው፡፡ 
https://waltainfo.com/am/23985/
218
3ቢዝነስ
የአብዱላዚዝ ቡተፍሊካ ወንድም  የ15 ዓመት እስር ተበየነባቸው
ፖለቲካ
September 25, 2019
Unknown
የአልጀሪያ ወታደራዊ ፍርድ ቤት የቀድሞ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት አብዱላዚዝ ቡተፍሊካ ወንድም ላይ የ15 ዓመት እስር አስተላልፏል።በመንግስት ላይ ሴራ በመጎንጎን እና የሀገሪቱን ጦር ሚና ዝቅ አድርገዋል በሚል የቀድሞ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት አብዱላዚዝ ቡተፍሊካ ወንድም ሰይድ ቡተፍሊካ  እስሩ ተላልፎባቸዋል፡፡በተባባሪነት የተጠረጠሩ ሌሎች ሶስት ግለሰቦችም ተማሳሳይ እስር ተበይኖባቸዋል፡፡ለእስር የተዳረጉት ሁለት የሀገሪቱ የቀድሞ የደህንነት መስሪያ ቤት አለቃዎች እና እንድ የፓለቲካ ፓርቲ መሪ ናቸው፡፡ሰይድ ቡተፍሊካ የሀገሪቱ የቀድሞ ፕሬዚዳንት አብዱላዚዝ ቡተፍሊክ በስትሮክ ህመም ከተጠቁበት ጊዜ ጀምሮ ከጀርባ በመሆን የፕሬዚዳንትነቱን ስልጣን በመያዝ ሀገሪቱን ሲመሩ መቆየታው ይታወሳል፡፡ለእስር የተዳረጉትም በሀገሪቱ ላይ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማወጅና የሀገሪቱን ጦር አለቃ አህመድ ጋይድ ሳላህን ከስልጣን ለማንሳት አሲረዋል በሚል ነበር።ምንጭ፦አልጀዚራ
https://waltainfo.com/am/33341/
94
5ፖለቲካ
ዋና ሳጅን ሲራጅ አብደላ ከፌዴራል ፖሊስ ስማርት ስልክ እና የምስክር ወረቀት ተበረከተለት
ሀገር አቀፍ ዜና
September 25, 2019
Unknown
በአፋር ህገ ወጥ መሳሪያን በገንዘብ ተደልሎ አላሳልፍም ያለው ዋና ሳጅን ሲራጅ አብደላ ስራው አርአያነት ያለው ነው በሚል የፈደራል ፖሊስ ኮሚሽን በዛሬው ዕለት እውቀና ሰጥቶታል።ዋና ሳጅን ሲራጅ አብደላ ከፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ጄኔራል መላኩ ፋንታ እጅ የስማርት ስልክ እና የእውቅና ምስክር ወረቀት ተቀብሏል።ምክትል ኮሚሽነሩ ፖሊሱ በሰራው አኩሪ የህግ ማስከበር ስራ አርዓያ በመሆኑ በኮሚሽኑ ስም ምስጋና አቅርበውለታል።ዋና ሳጅን ሲራጅ አርዓያነት ላለው ተግባሩ ከአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባና ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድም እውቅና መሰጠቱ ይታወሳል።
https://waltainfo.com/am/32759/
75
0ሀገር አቀፍ ዜና
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ 68 ነጥብ 3 በመቶ መድረሱ ተገለፀ
ቢዝነስ
September 24, 2019
Unknown
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ 68 ነጥብ 3 በመቶ መድረሱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል አስታውቋል።በግራ ሃይል ማመንጫ ቤት የሚገኙት ሁለት የሃይል ማመንጫ ዩኒቶች ማለትም ዩኒት ዘጠኝ እና 10 የብረታ ብረት ገጠማ ስራ 50 በመቶ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ኢንጂነር አብርሃም በላይ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል ፡፡ሁለቱ ተርባይኖችም በቅርብ ማመንጨት እንዲችሉ ሆኖ ስራቸው በፍጥነት እየተሰራ መሆኑንም አስታውቀዋል።በሳሊኒ ኮንስትራክሽን ተቋራጭ እየተሰራ ያለው የሲቪል ስራ በመገባደድ ላይ ያለ መሆኑና በተቋራጩ እየተገነባ ያለው አጠቃላይ የሲቪል ስራ በፍጥነት እየተሰራ መሆኑን የገለጹ ሲሆን፤ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሲጠናቀቅ በዓመት በአማካይ 15 ሺህ 670 ጊጋ ዋት በሰዓት ሀይል እንደሚያመነጭ ተናግረዋል።ከግድቡ በታች ለሚለቀቀው ውሃ የሚያገለግለው ከዋናው ግድብ በስተግራ በኩል መዝጊያ ያለው የጎርፍ ማስተንፈሻ (ጌትድ ስፒልዌይ) ደግሞ 96 በመቶ ተጠናቋል ተብሏል።ግድቡ የታቀደለትን ውሃ መያዝ እንዲችል እና የውሃውን ፍሰት ወደ ዋናው ግድብ እንዲሆን የሚያደርገው የግድቡ ክፍል የኮርቻ ቅርጽ ያለውና የኮቻ ግድብ በሚል የሚጠሩት (ሳድል ዳም) 96 በመቶ መጠናቀቁን የገለጹት ዋና ስራ አስፈጻሚው ዶ/ር ኢንጂነር አብርሃም፤ የኮርቻ ግድቡ በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ውስጥ ሙሉ በሙሉ የ ሚጠናቀቅ መሆኑን አስረድተዋል።ሰሞኑን ከግብጽ ጋር ተያይዞ የተነሳው አለግባባት የውሃ አሞላል ላይ ግድቡን በረዥምጊዜ እንዲሞላ የሚጠይቅ በመሆኑ፣ ኢትዮጵያ ያደረገቻቸው ኢንቨስትመንት ታሳቢ ያላደረገ በመሆኑና የኢትዮጵያን ህልውና የሚጋፋ በመሆኑ ብቻ ኢትዮጵያ የግብጽን ምክረ ሃሳብ ኢትዮጵያ ውድቅ ያደረገችው መሆኑን ተናግረዋል።የግብጽ የተለየ አቋም በግድቡ ግንባታ ሂደት ላይ ምንም ዓይነት ተጽእኖ እንደማያስከትል ዶ/ር ኢንጂነር አብርሃም ተናግረዋል። 
https://waltainfo.com/am/23984/
203
3ቢዝነስ
ኢራን የአውሮፓ አገራትን ውንጀላ አጣጣለች
ፖለቲካ
September 24, 2019
Unknown
ፈረንሳይ፣ ጀርመን እና ዩናይትድ ኪንግደም በጥምረት፤ በሳዑዲ ነዳጅ ማቀነባበሪያ ላይ ከደረሰው ጥቃት ጀርባ ያለችው ኢራን ናት ቢሉም፤ ኢራን ውንጀላቸውን አጣጥላዋለች።የኢራን የውጪ ጉዳይ ሚንስትር የሦስቱን አገራት ክስ "የአሜሪካን ከንቱ ክስ ያስተጋባ" ሲሉ ውድቅ አድርገዋል።የአውሮፓ አገራት መሪዎች እንዳሉት፤ ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ ከኢራን ውጪ ማንም ላይ ጣት መቀሰር አይቻልም። ኢራን የምትደግፈው የየመኑ የሁቲ አማጽያን ቡድን ጥቃቱን የሰነዘርኩት እኔ ነኝ ሲል ኃላፊነቱን ቢወስድም፤ አሁንም ተጠያቂ የተደረገችው ኢራን ናት።ስምንት ሰው አልባ አውሮፕላኖች እና ሰባት ሚሳኤሎች የሳዑዲን የነዳጅ ማቀነባበሪያ ከመቱ በኋላ፤ ሳዑዲ እንዲሁም አሜሪካ ኢራንን ወንጅለዋል። ኢራን በበኩሏ በጥቃቱ እጄ የለበትም ማለቷ ይታወሳል።የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን፣ የፈረንሳዩ ፕሬዘዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እና የጀርመኗ መራሔተ መንግስት አንግላ መርኬል በጋራ በሰጡት መግለጫ፤ ኢራን ለጥቃቱ ተጠያቂ ናት ብለዋል። እየተካሄደ ያለውን ምርመራ እንደሚደግፉም አሳውቀዋል።"ኢራን በኒውክሌር ፕሮግራሟ ላይ ለድርድር ዝግጁ መሆን የሚጠበቅባት ጊዜ ላይ ነን" ሲሉም መሪዎቹ ተናግረዋል።እንደ ጎርጎሮሳውያኑ 2015 ላይ የተደረሰውን የኒውክሌር ስምምነት (ጆይንት ኮምፕሪሄንሲቭ ፕላን ፎር አክሽን) በማክበር እንደሚቀጥሉም ገልጸዋል።የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከስምምነቱ አገራቸውን አውጥተው ኢራን ላይ ማዕቀብ ከጣሉ በኋላ ሁለቱ አገራት ተፋጠዋል።ፕሬዘዳንት ትራምፕ "የቀድሞው ስምምነት ብዙ ችግሮች አሉት። አዲስ እና ከቀደመው የተሻለ ስምምነት ለመፈራረም ዝግጁ ነኝ" ካሉ በኋላ ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን ሀሳቡን እንደሚደግፉ ተናግረዋል።ቦሪስ ከኢራኑ ፕሬዘዳንት ጋር እንደሚገናኙም ተነግሯል።የኢራን የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ሞሀመድ ዣቪድ ዛሪፍ፤ አዲስ የኒውክሌር ስምምነት እንደማይረቀቅ ገልጸዋል። አሜሪካ ከስምምነቱ በመውጣቷ ሦስቱ የአውሮፓ አገራትም ከስምምነቱ የሚጠበቅባቸውን እየተወጡ አለመሆኑንም አክለዋል።"አሁን ያለው ስምምነት ሳይከበር አዲስ ስምምነት አይረቀቅም" ብለዋል።አሜሪካ እና አጋር አገራት፤ የሳዑዲ ነዳጅ ማቀነባበሪያ ላይ ለደረሰው ጥቃት ወታደራዊ ምላሽ ለመስጠት ከቃጡ፤ ኢራን አጸፋውን እንደምትመልስም ተናግራለች። (ምንጭ፡-ቢቢሲ)
https://waltainfo.com/am/34004/
230
5ፖለቲካ
አንቶኒዮ ጉተሬዝ በኢትዮጵያ እየተካሄደ የሚገኘውን ለውጥ አደነቁ
ፖለቲካ
September 24, 2019
Unknown
ፕሬዝዳንት ሣሕለወርቅ ዘውዴ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር ኒውዮርክ ተገናኝተው መክረዋል፡፡ዋና ፀሃፊው በኢትዮጵያ እየተካሄደ የሚገኘውን ለውጥ በእድናቆት እንደሚመለከቱት በዚህን ወቅት አንስተዋል፡፡ የተመድ ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ኢትዮጵያ በሱዳን ድርድር ላይ ያሳደረችውን ተፅእኖ በማድነቅ በደቡብ ሱዳንም ተመሳሳይ ስራ እንድትሰራ ጠይቀዋል፡፡ከኒዉዮርኩ ጉባኤ ጎን ለጎን የኘሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘዉዴ የጀርመኗ ቻንስለር አንጌላ ሜርክል በመሩትና በአፍሪካ የሰላምና፣የደህንነትና የልማት ጉዳይ ላይ በተነጋገረዉ የምክክር መድረክ ላይ ተሳትፈዋል ።ውይይቱ በዋናነት በሰላም፣ ደህንነትና የልማት ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንደነበር ከፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
https://waltainfo.com/am/31364/
79
5ፖለቲካ
ኢትዮጵያና እስራኤል በቴክኖሎጂ የተደገፈ የስራ ዕድል መፍጠር በሚቻልባቸዉ መስኮች ዙሪያ ምክክር እያደረጉ ነዉ
ቢዝነስ
September 24, 2019
Unknown
ኢትዮጵያ ከእስራኤል የካበተ የቴክኖሎጂ አቅምና ልምድ አስፈላጊዉን ክህሎት በመቅሰም የበለጠ የስራ ዕድል መፍጠር በምትችልበት ሁኔታ ላይ የሚመክር ጉባኤ ዛሬ በአዲስ አበባ ተጀምሯል፡፡በጉባዉ ላይ ተገኝተዉ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ አቶ ጀማል በከር ኢትዮጵያ ከእስራኤል ሰፊ የቴክኖሎጂ ተሞክሮ ብዙ መማርና መጠቀም እንደምትችል አመልክተዋል፡፡ከአገሪቱ አጠቃላይ ህዝብ 73 በመቶ የሚሆነዉ ወጣት መሆኑንና ይህን ሃይል በመጠቀምና በቴክኖሌጂ የታገዘ የስራ ዕድል በመፍጠር አገሪቱን ይበልጥ ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚቻልም ተወስቷል፡፡በምክክር መድረኩ ላይ የተገኙት በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ራፋኤል ሞራቭ በበኩላቸዉ እስራኤል በቴክኖሎጂ ዘርፍ ያላትን ልምድ ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ጋር በሚጣጣም መልኩ በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላት ገልፀዋል፡፡ለሁለት ቀናት በሚቆየዉ የምክክር መድረክ በዘርፉ በኢትዮጵያ ያሉ ተግዳሮቶች፣ ምቹ ሁኔታዎች እንዲሁም የእስራኤል ልምድ ከዘርፉ ባለሙያዎች ምክክር እንደሚደረግበት ታዉቋል፡፡ 
https://waltainfo.com/am/23982/
109
3ቢዝነስ
ቦይንግ በአውሮፕላን አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ሰዎች ቤተሰቦች ካሳ ሊከፍል ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
September 24, 2019
Unknown
በቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን አደጋ የሞቱ ሰዎች ቤተሰቦች ከቦይንግ ኩባንያ ለእያንድንዱ ሟች 144 ሺህ 500 ዶላር ሊከፈላቸው ነው።በኢንዶኔዢያው ላየን ኤርና በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላኖች ላይ በደረሰው አደጋ ለሞቱት 346 ሰዎች ከቦይንግ የገንዘብ ድጋፍ ፈንድ ወጪ ተደርጎ ለአደጋዎቹ ሰለባ ቤተሰቦች እንዲከፈል 50 ሚሊዮን ዶላር ተመድቧል።በሐምሌ ወር ቦይንግ ይፋ ያደረገው ቀሪ የ100 ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ ደግሞ ለትምህርትና ለልማት ፕሮግራሞች ይውላል ተብሏል።ገንዘቡን የሚከፍለው አካል የይገባናል ጥያቄዎችን መቀበል የጀመረ ሲሆን፣ ጥያቄዎች ከፈረንጆቹ 2020 በፊት መቅረብ አለባቸው ተብሏል።ኩባንያው ባወጣው መግለጫ ላይ የቦይንግ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዴኒስ ሙሊንበርግ፤ ገንዘብ ለመስጠት የተወጠነው ሃሳብ መጀመሩ በቦይንግ 737 ማክስ 8 አደጋዎች ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቤተሰቦችን ለመርዳት ኩባንያው ለሚያደርገው ጥረት "ጠቃሚ እርምጃ" ነው ሲሉ ጠቅሰዋል።አደጋው ከደረሰባቸው አውሮፕላኖች ጋር ተመሳሳይ የሆኑ 737 ማክስ አውሮፕላኖች በሙሉ ከባለፈው ዓመት መጋቢት ወር ጀምሮ በመርማሪዎች የአውሮፕላኖቹ ደህንነት አስተማማኝነት እስኪረጋገጥ ድረስ ከበረራ ውጪ እንዲሆኑ ተደርጓል።ቦይንግ ሐምሌ ወር ላይ በአደጋው ለሞቱት ሰዎች ቤተሰቦች ገንዘብ ለመስጠት እንዳሰበ ባሳወቀበት ጊዜ የአንዳንድ ቤተሰቦች ጠበቆች ከቦይንግ የቀረበው ገንዘብ በቂ እንዳልሆነ በመጥቀስ ውድቅ አድርገውት ነበር። በርካቶችም ኩባንያው ላይ በፍርድ ቤት ክስ ከፍተውበታል።ቦይንግ ለአደጋዎቹ ሰለባ ቤተሰቦች ሊሰጥ ያዘጋጀውን ገንዘብ የሚከታተሉት የሕግ ባለሙያ ኬኔት ፋይንበርግ እንደተናገሩት፤ ቤተሰቦች ገንዘቡን ሲወስዱ በሙሉ ፈቃዳቸው ሲሆን፣ በኩባንያው ላይ የተናጠል ክስ ለመመስረት ያላቸውን መብት እንዲተዉ የማያስገድድ መሆኑን አመልክተዋል።የሕግ ባለሙያው ለአደጋው ሰለባዎች የተዘጋጀን ገንዘብ የማከፋፈል ሥራን በመወጣት በኩል ልምድ እንዳላቸው ተነግሯል።ዴኒስ ፋይንበርግ ከዚህ ቀደም ካከናወኗቸው ተመሳሳይ ተግባራት መካከል ለአሜሪካ የመስከረም አንዱ የሽብር ጥቃት ሰለባዎችና ዲፕዋተር ሆራይዘን ለተሰኘ የነዳጅ ዘይት ፍሳሽ የቀረቡ የገንዘብ ድጋፎችን በአግባቡ ፈጽመዋል ተብሏል። (ምንጭ፡-ቢቢሲ)
https://waltainfo.com/am/34135/
228
0ሀገር አቀፍ ዜና
ኢትዮጵያ ከሆቴል ኢንቨስትመንት ዘርፍ ተጠቃሚ እንድትሆን በትኩረት ይሰራል ተባለ
ቢዝነስ
September 24, 2019
Unknown
በሆቴል ኢንቨስትመንት ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን መቅረፍ የሚያስችል ሀገር አቀፍ የሆቴልና ቱሪዝም ኮንፍረነስ በነሀሴ ወር መደረጉ ይታወሳል፡፡የዚሁ ጅምር አካል የሆነው የአፍሪካ ሆቴል ኢንቨስትመንት አለምአቀፍ ጉባኤ እየተካሄደ  ይገኛል፡፡ጉባኤው በዋናነት በአፍሪካ የሆቴል ኢንቨስትመንት ዘርፍ ያሉ መልካም ዕድሎችና ተግዳሮቶች እንዲሁም መፍትሄዎች ላይ በማተኮር ነው በመካሄድ ላይ የሚገኘው፡፡በመክፈቻ ስነስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው አፍሪካ ያላትን ዘርፈ ብዙ የቱሪዝምና ተያያዥ ሃብቶች በሚገባ እንዳልተጠቀመችበት አንስተው ይህን ሀብት በአግባቡ ለመጠቀም በመንግስት በኩል በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡ኢትዮጵያ የበርካታ ብሄር ብሄረሰቦች፣ የተለያዩ ባህላዊ፣ ሃይማኖታዊ፣ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ ሃብቶች መያዟን ተከትሎ የቱሪዝም መናኸሪያ ብትሆንም በአግባቡ እየተጠቀመችበት አለመሆኑን አንስተዋል።በቅርቡ በተደረገ ጥናት መሰረት አንድ ቱሪስት ወደ ሀገር ውስጥ ሲገባ በአማካይ እስከ 10 ለሚደርሱ ዜጎች የስራ እድል ይፈጥራል፡፡ከዝቅተኛው ስፍራ ዳሎል እስከ ራስ ዳሽን ባለው አስር አይነት የተለያየ ስነ ምህዳር እንዳላት የሚነገረው ኢትዮጵያ 11 ቅርሶቿን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፤ የሳይንስና ባህል ተቋም አስመዝግባለች፡፡ዘርፉ ለኢኮኖሚ ያለውን አበርክቶ ለማጎልበት የሰለጠነ የሰው ሀይል በበቂ ሁኔታ አለመኖር፤ ወጥነት ያለው አስራራ አለመዘርጋትና በቴክኖሎጂ የተደገፈ አለመሆኑ ተግዳሮት እንደሆነም ይጠቀሳል፡፡እስከ ነገ መስከረም 14፣ 2012 ዓ.ም በሚቆየው ጉባኤ ከ52 ሀገራት የተወጣጡ የዘርፉ ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት እየተካፈሉ ይገኛል፡፡  
https://waltainfo.com/am/23983/
168
3ቢዝነስ
የደቡብ ክልል ምክር ቤት በሁለት አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ
ፖለቲካ
September 23, 2019
Unknown
የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት በ202ኛ መደበኛ ስብሰባው በሁለት አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ።ምክር ቤቱ የሲዳማ ዞንን በክልል የመደራጀት ህዝበ ውሳኔ ለማካሄድ የማስፈፀሚያ ፕሮጀክት ማቋቋሚያ ደንብ ላይ ተወያይቷል።ጥያቄው ለክልሉ ምክር ቤት ቀርቦ ጉዳዩን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መርምሮ ህዝበ ውሳኔ እንዲደራጅ ቀን በቆረጠው መሰረት፥ ውሳኔውን የሚመራ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት የሚቋቋምበት ደንብን በዝርዝር ተመልክቶታል።በዚህም በቅድመ ህዝበ ውሳኔ፣ በህዝበ ውሳኔና በድህረ ህዝበ ውሳኔ ሊከናወኑ በሚገባቸው ተግባራት ላይ እና በፕሮጀክት ጽህፈት ቤቱ አደረጃጀት ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡የፕሮጀክት ጽህፈት ቤቱ ተጠሪነቱ ለክልሉ ምክር ቤት ሆኖ በእውቀት፣ በክህሎት እና በመልካም ስነ ምግባር የታነፁ አመራሮች እና ባለሙያዎችን በመመደብ ተግባሩን ሀላፊነት በተሞላበት ሁኔታ እንዲመሩትም ውሳኔ አሳልፏል።ከዚህ ባለፈም ምክር ቤቱ በሁለተኛ አጀንዳው የወላይታ ዞን የወጣቶች መልካም ስብዕና ማዕከልን ለማቋቋም የቀረበውን ፕሮጀክት በዝርዝር ገምግሟል።ማዕከሉ የወጣቶችን ስነ ምግባር ለመገንባት እና በሀገር የልማት እና የዴሞክራሲ ግንባታ ሂደት ላይ የበኩሉን አስተዋጽኦ የሚያደርግ በመሆኑም የተጠየቀው የግንባታ ቦታ ተግባራዊ እንዲሆንም ወስኗል። መረጃው የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤት ነው።
https://waltainfo.com/am/31363/
154
5ፖለቲካ
በኦሮሚያ ክልል የትምህርት ጥራትን የማረጋገጥ ስራዎች በልዩ ትኩረት እንደሚሰሩ የክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
September 23, 2019
Unknown
በኦሮሚያ ክልል የትምህርት ጥራትን የማረጋገጥ ስራዎች በልዩ ትኩረት እንደሚሰሩ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ጉባኤ ‘‘የትምህርት ጥራት ለሁለንተናዊ የሀገር ዕድገት’’ በሚል መሪ ቃል ከዞኖች እና ከተማ መስተዳድሮች ከተውጣጡ የትምህርት ባለድርሻ አካላት ጋር እየተካሄደ ነው፡፡በጉባኤው የ2011 ትምህርት ዘመን ዕቅድ አፈፃፀም ቀርቦ ውይይት እየተደረገ የሚገኝ ሲሆን፣ በአጠቃላይ በክልሉ የትምህርት ጥራት ጉድለት መኖሩ ተገልጿል፡፡በዘንድሮ የትምህርቴ ዘመን በክልሉ የትምህርት ጥራትን የማረጋገጥ ስራዎች በልዩ ትኩረት እንደሚሰሩ የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ቶላ በሪሶ ገልጸዋል፡፡በክልሉ የጎልማሶች እና ልዩ ፍላጎት ትምህርትን ለማሳደግ እንደሚሰራም ተናግረዋል፡፡ባለፈው የትምህርት ዘመን የመምህራን እጥረት ለትምሀርት ጥራት ጉድለት ምክንያት በመሆኑ በዚህ አመት 5 ሺህ መምህራን መቀጠራቸውንም አስታውቀዋል፡፡በተጨማሪም የትምህርት ቤቶችን ጥራት የማሻሻል ስራ በትኩረት እንደተሰራም ተገልጿል፡፡በፌዴራል ደረጃ የ12ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱት 314ሺህ 853 ተፈታኞች 142 ሺህ 821 ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲ መግባታቸውን የጠቆሙት ኃላፊው፣ ከኦሮሚያ ክልል 37 ሺህ 285 ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲ መግባታቸውን ገልጸዋል፡፡ይህም ከክልሉ ተፈታኞች 48 ነጥብ 9 በመቶ ማለፉን ያመለክታል ብለዋል፡፡በጉባኤው ማጠቃለያ በ2011 የትምህርት ዘመን በክልሉ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎችና የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ ተቋማት የማበረታቻ ሽልማት እንደሚበረከትም ተገልጿል፡፡
https://waltainfo.com/am/32757/
155
0ሀገር አቀፍ ዜና
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ክህሎት ለማሳደግ የሚረዳ የ2 ሚሊየን ዶላር ፕሮጀክት ስምምነት ተፈረመ
ሀገር አቀፍ ዜና
September 23, 2019
Unknown
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ክህሎት ለማሳደግ የሚረዳ የ2 ሚሊየን ዶላር ፕሮጀክት ስምምነት ተፈራረመ።ፕሮጀክቱ በባህርዳር፣ ሀዋሳ፣ ጅግጅጋ፣ ጅማ፣ መቐለ እና ሠመራ ዩኒቨርሲቲዎች ይተገበራል ተብሏል።ስምምነቱ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከህፃናት አድን ድርጅት ሴቭ ዘ ቺልድረን እና ከአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅት ዩ ኤስ አይ ዲ ጋር ተፈርሟል፡፡የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማርያም ከድርጅቶቹ ተወካዮች ጋር ተፈራርመውታል።ፕሮጀክቱ ተቋማዊ የአቅም ግንባታ ድጋፍ በኢትዮጵያ ለሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሚል ለ1 አመት የሚተገበር ነው፡፡ሚኒስትሯ በዚህ ወቅት የፕሮጀክቱን ሃሳብ አድንቀው ተመራቂ ተማሪዎችን የስራ ገበያው የሚፈልገው አይነት ክህሎት ይዘው እንዲወጡ ድጋፍ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።አያይዘውም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለትምህርት ጥራት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።በስምምነቱ ዩኒቨርሲቲዎቹ ከቴክኒክና ሙያ ተቋማት ጋር ትስስር በመፍጠር በትምህርት በሚገኙ ክህሎቶችና የስራው ዓለም በሚፈልጋቸው ችሎታዎች መካከል የሚኖርን ያለመጣጣም ችግር ለመቅረፍ ይሰራሉ ተብሏል። (ምንጭ፡-የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር)
https://waltainfo.com/am/32758/
126
0ሀገር አቀፍ ዜና
አልሲሲን ለመቃወም አደባባይ የወጡ ግብፃውያን መታሰራቸው ተገለጸ
ፖለቲካ
September 24, 2019
Unknown
በመንግሥት የሚፈፀምን ሙስና ተቃውመው አደባባይ ከወጡ ግብፃውያን መካከል 500 ያህሉ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ተናገሩ።የተቃውሞ ሠልፎቹ በካይሮ፣ አሌክሳንድሪያ እና ሌሎች ከተሞች አርብ ማታ የተካሄዱ ሲሆን፤ በወደብ ከተማዋ ስዊዝ ደግሞ ቅዳሜ ምሽት ተከናውኗል።የመንግሥት ባለስልጣናት የታሳሪዎቹን ቁጥር እስካሁን ድረስ አልገለፁም።የፕሬዝዳንት አብደል ፈታህ አልሲሲ አገዛዝ ተቃውመውት አልያም ተችተውት ድምፃቸውን በሚያሰሙ፣ ሠልፍ በሚያደርጉ ላይ እርምጃ በመውሰድ ይታወቃል።እኤአ ከ2013 ጀምሮ አልሲሲ በሕዝብ የተመረጡት ሙርሲን በወታደራዊ ኃይል ከስልጣን ካወረዱ በኋላ፤ በሕዝብ መሰብሰቢያ ስፍራዎች ከ10 ሰው በላይ ሆኖ መገኘት የተከለከለ ሆኖ ቆይቷል።የመብት ተሟጋቾች እንደሚሉት፤ ባለፉት ስድስት አመታት ከ60 ሺህ ግብፃውያን በላይ የሙርሲ ደጋፊ ናችሁ፣ አልያም በሕግ የታገደው የሙስሊም ወንድማማቾች አባል ናችሁ በሚል በእስር ቤት የሚገኙ ሲሆን፤ የተወሰኑት በፍርድ ቤት ሞት ተፈርዶባቸዋል። የደረሱበት የማይታወቅ ግለሰቦችም አሉ ብለዋል።አርብ ምሽት በመቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች በዋና ከተማዋ ካይሮ ታሕሪር አደባባይ አቅራቢያ፣ አሌክሳንድሪያ፣ ዳሚታ እና ማሀላ አልኩብራ በሚባሉ ስፍራዎች ሠልፍ ማድረጋቸውን የአይን ምስክሮች እና ማኅበራዊ መገናኛ ብዙኀን ዘግበዋል።ተቃዋሚ ሠልፈኞቹን ፖሊስ ከመበተኑ በፊት ድምፃቸውን ከፍ አድርገው "አልሲሲ ይውረድ" እንዲሁም "ሕዝቡ ሥርዓቱ እንዲፈርስ ይፈልጋል" እያሉ ሲጮሁ እንደነበር ተዘግቧል።አንድ የሕግ ባለሙያ ለቢቢሲ 500 ያህል ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረው፤ በሚቀጥሉት ቀናትም ይህ ቁጥር እያሻቀበ እንደሚሄድ ያላቸውን እምነት አስረድተዋል።መንግስታዊ ያልሆነው የግብፅ ምጣኔ ኃብትና ማኅበራዊ መብት ማዕከልም የታሳሪዎች ቁጥር 516 እንደሆነ ተናግሯል።በቁጥጥር ስር የዋሉት በሕግ በታገደ ድርጅት ውስጥ በመሳተፍ፣ በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኀን ሐሰተኛ መረጃ በማሰራጨት፣ ያልተፈቀደ ሰልፍ ላይ በመሳተፍና በሌሎች ወንጀሎች ተጠያቂ ይሆናሉ ተብሏል።ከታሰሩት መካከል እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆነም ይገኝበታል ነው የተባለው፡፡በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል ታዋቂ የሰብዓዊ መብት ጠበቃዋ ማሄኑር አል ማስሪ ትገኝበታለች። እንደ ፈረንሳዩ የዜና ወኪል ከሆነ ጠበቃዋ በቁጥጥር ስር የዋለችው ቅዳሜ እለት ካይሮ ወደሚገኘው አቃቤ ሕግ ቢሮ የታሰሩ ሰዎችን በመወከል ከሄደች በኋላ ነው።በመንግሥት ቁጥጥር ስር ያሉ መገናኛ ብዙኀን፤ በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኀን ሠልፍ ተደረገ ተብለው የሚሰራጩ ምስሎች በ2011 የተካሄደው ሠልፍ ምስሎች መሆናቸውን በመጥቀስ ሕዝቡን ለማወናበድ ሆን ተብለው የተደረጉ ሲል ገልጿቸዋል።በመላው ዓለም ኢንተርኔትን የሚከታተለው ኔት ብሎክስ የተባለው ድርጅት በበኩሉ፤ ቅዳሜ ግብፅ ውስጥ የፌስቡክ መልዕክት መቀበያና መላኪያ፣ ቢቢሲ እና ሌሎች የማኅበራዊ መገናኛ ብዙኀን ሰርቨሮች እቀባ ተጥሎባቸው ነበር ብሏል።በግብፅ ተቃዋሚ ሠልፈኞች አደባባይ የወጡት በስፔን በስደት ላይ የሚገኘው ባለሀብት በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኀን ላይ ፕሬዝዳንት አልሲሲንና ወታደራዊ ባለስልጣናትን በሙስና የሚከስ ተንቀሳቃሽ ምስል ከለቀቀ በኋላ ነው።ይህ ግለሰብ ግብፃውያን ፕሬዝዳንት አልሲሲ ከስልጣን እንዲወርዱ ለመጠየቅ አርብ ዕለት ሕዝባዊ ሰልፍ እንዲወጡ ጠርቶ ነበር።ፕሬዝዳንት አል ሲሲ የግለሰቡን ክስ "ሐሰተኛና ስም ማጥፋት ነው"ሲሉ አጣጥለውታል። (ምንጭ፡-ቢቢሲ)
https://waltainfo.com/am/33340/
352
5ፖለቲካ
አቶ ገዱ ከፊንላንድና ኢንዶኔዢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ተወያዩ
ቢዝነስ
September 24, 2019
Unknown
የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በኒውዮርክ እየተካሄደ ካለው የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ጎን ለጎን ከፊንላንድና ኢንዶኔዢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ተወያይተዋል።አቶ ገዱ ከፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ፔካ ሃቪስቶ ጋር ባደረጉት ምክክር ሁለቱ ሀገራት ግንኙነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር መስራት እንዳለባቸው መግባባት ላይ ደርሰዋል።ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ሠላም ለማስፈን እያደረገች ያለውን ጥረት የፊንላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በዚሁ ወቅት አድንቀዋል፡፡በተለይም በቅርቡ በሱዳን ስምምነት ለማምጣት ኢትዮጵያና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለተጫወቱት ዲፕሎማሲያዊ ሚና አድናቆታቸውን መግለፃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በበኩላቸው ፥ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ ለሠላም አበክራ እንደምትሰራና በአፍሪካ ቀንድ የሚፈጠር ሠላምም ቀጣናውን የልማትና የብልፅግና አካባቢ ለማድረግ ለሚሠሩ ስራዎች ከፍተኛ ሚና እንዳለው አንስተዋል።ኢትዮጵያና ፊንላንድ ቀጣናዊ ሠላም ለማምጣት በጋራ ከመስራት ባሻገር በሁለትዮሽ ግንኘነታቸው ፊንላንድ በኢትዮጵያ የግሉን ዘርፍ ለማጠናከር እንደምትሰራ መግባባት ላይ መድረሳቸውም ተመላክቷል።በተመሳሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ ከኢንዶኔዢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬትኖ ማርሱዲ ጋር ባደረጉት ውይይት ሀገራቱ የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት እና ሰርቪስ ፓስፖርት ለያዙ ዜጎቻቸው ያለ ቪዛ መንቀሳቀስ የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል።በዚህ ወቅትም ኢትዮጵያና ኢንዶኔዢያ ያላቸውን ታሪካዊ ግንኙነት የሚመጥን የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት እንዲኖራቸው መስራት እንደሚያስፈልግ አቶ ገዱ ተናግረዋል።
https://waltainfo.com/am/23980/
166
3ቢዝነስ