headline
stringlengths 2
1.42k
| category
stringclasses 6
values | date
stringlengths 9
35
| views
stringlengths 1
7
| article
stringlengths 63
36.2k
| link
stringlengths 28
740
| word_len
int64 16
6.74k
| label
class label 6
classes |
---|---|---|---|---|---|---|---|
አራት የኢንዱስትሪ ፓርኮች በታኅሣሥ መጨረሻ ለባለሀብቶች ይተላለፋሉ | ቢዝነስ | September 24, 2019 | Unknown | አራት ክልሎች በመገንባት ላይ የሚገኙ የግብርና ምርት ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች በታኅሣሥ መጨረሻ ለባለሀብቶች እንደሚተላለፉ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ።«ክልሎች ባልተጠና መልኩ ሕገወጥ የኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ መጀመራቸውም አስግቶኛል››ብሏል።በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተቀናጀ የግብርና ምርት ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርክ ልማት ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ አያልነህ አባዋ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት፤ ግብርናውን ከኢንዱስትሪ ጋር በማስተሳሰር ከጥምረቱ ፍሬ ተጠቃሚ ለመሆን በ2009 ዓ.ም የአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ ተጀምሯል።ለዚህም 17 ቀጣናዎች የተለዩ ሲሆን፤ በፓይለት ፕሮጀክት ደረጃ የጥሬ ዕቃዎች ምርት መገኛ መሆናቸውን መሠረት በማድረግ የመጀመሪያዎቹ ፓርኮች ግንባታ በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በትግራይና በደቡብ ክልል ተግባራዊ ተደርጓል።ባለፉት ዓመታትም ፓርኮቹን ገንብቶ ሥራ ለማስጀመር የተለያዩ ተግባራት ሲከናወኑ መቆየታቸውን የገለፁት አቶ አያልነህ፤ በአሁኑ ወቅት ፓርኮቹን ወደ ሥራ ለማስገባት የሚያስችሉ መሠረታዊ ግንባታዎች መጠናቀቃቸውንና በመጪው ታኅሣሥ መጨረሻ ለባለሀብቶች እንደሚተላለፉም ጠቁመዋል።አቶ አያልነህ በፓርኮቹ ውስጥ የሚሰማሩ ብቃት ያላቸው ባለሀብቶችን በመመልመል ረገድ ጥናትና የሌሎች አገራት ተሞክሮ የመቃኘት ተግባር በጥንቃቄና በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም አመላክተዋል።በአሁኑ ወቅትም ወደ ፓርኮቹ ለመግባት በርካታ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ባለሀብቶች ተመዝግበው እየተጠባበቁ እንደሚገኙ የጠቆሙት አቶ አያልነህ፤ ቀደም ብለው ወደ ሥራ በመግባት ማምረትና ግንባታ የጀመሩ ስለመኖራቸውም አስታውቀዋል።የፓርኮቹ ግንባታ የተጀመረው በተመሳሳይ ጊዜ መሆኑን ጠቅሰው፤ በበጀት እጥረት የትግራይ ክልል ወደ ኋላ መቅረቱንና አንዳንድ ግንባታዎች አለመጀመራቸውንም አብራርተዋል።‹‹የኢንዱስትሪ ፓርኮቹ ዋነኛ ፈተና የኤሌክትሪክ ኃይል እጦት ነው›› ያሉት አቶ አያልነህ፣ በአሁኑ ወቅት በፓርኮቹ ሥራ የጀመሩ ባለሀብቶችም ቢሆኑ በእራሳቸው አቅም ለችግሩ መፍትሄ ለመስጠት ወስነው የገቡበት መሆናቸውን ጠቁመዋል።ከችግሩ አሳሳቢነት አንፃር ድርድር ተካሂዶ አቅርቦቱን ለማፋጠን እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው፣ ጉዳዩ ግን ልዩ ትኩረት እንደሚሻው አስገንዝበዋል።‹‹ከኃይል አቅርቦቱ በተጓዳኝ በአሁኑ ወቅት ከፌዴራል መንግሥት እውቅና ውጪ አንዳንድ ክልሎች የፓርኮች ግንባታ እያከናወኑ መሆናቸው በጣም ያሳስበናል›› ያሉት አቶ አያልነህ፣ አንዳንዶቹ ክልሎችም ተጨማሪ ፓርክ ለመገንባት ቦታ ከመምረጥ ባለፈ በልማቱ ለሚነሱ አርሶ አደሮች ካሳ ከፍለው መጨረሳቸውን አስታውቀዋል። | https://waltainfo.com/am/23981/ | 251 | 3ቢዝነስ
|
በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች የተካሄዱት ሰላማዊ ሰልፎች ያለምንም የፀጥታ ችግር መጠናቀቃቸው ተገለጸ | ሀገር አቀፍ ዜና | September 22, 2019 | Unknown | በአማራ ክልል ባሕርዳርን ጨምሮ በአስር ዞኖች፣ በ47 ወረዳዎች የተካሄዱት ሰላማዊ ሰልፎች ያለምንም የፀጥታ ችግር መጠናቀቃቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
የኮሚሽኑ የሚዲያ አስተባባሪ ምክትል ኮማንደር መሰረት ላቀ ለዋልታ እንደገለፁት ፖሊስ ሰልፎቹ እንደሚካሄዱ አስቀድሞ መረጃ ስለነበረውና ዝግጅት በማድረጉ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቁ ረድቷል ።
ወጣቶች፣ የሃይማኖት አባቶች እና አጠቃላይ ህብረተሰቡ ከፖሊስ ጎን ሆነው በመስራታቸው ሰልፎቹ ያለምንም የፀጥታ ችግር ተጠናቀዋል ብለዋል።
የወንጀል መከላከል ስራ ውጤታማ የሚሆነው በህብረተሰቡ ተሳትፎ ሲታገዝ በመሆኑ ስለተደረገው ትብብር ምክትል ኮማንደሩ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናንና ካሕናት በምዕመናን እና በቤተ ክርስቲያኗ ላይ የሚፈፀመውን ግፍ እንዲቆም የሚጠይቅ ሠላማዊ ሰልፎች በባሕር ዳር፣ ቢቸና፣ ቡሬ፣ እንጅባራ፣ መርዓዊ፣ ወልድያ፣ ፍኖተ ሠላም፣ ደባርቅ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ደብረ ብርሃን፣ ቆቦ፣ ማጀቴ፣ ጫጫ፣ ዋድላ፣ ዳንግላ፣ ሞጣ፣ ዳባት፣ መሐል ሜዳ፣ ውጫሌ፣ ሮቢትና፣ ላልይበላ ከተሞች አካሂደዋል፡፡ | https://waltainfo.com/am/32753/ | 119 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
በአየር ንብረት ተጎጂ ለሆኑት ታዳጊ ሀገራት ቃል የተገባው የገንዘብ ድጋፍ በአፋጣኝ ሊደርስ ይገባል-ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ | ሀገር አቀፍ ዜና | September 23, 2019 | Unknown | በአለም አቀፍ ደረጃ ወደ ታዳሽ ሃይል የሚደረገው ሽግግር ፈጣንና የተሳካ እንዲሆን በአየር ንብረት ይበልጥ ተጎጂ ለሆኑት ታዳጊ ሀገራት ቃል የተገባው የገንዘብ ድጋፍ በአፋጣኝ ማድረስ እንደሚገባ ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ጥሪ አቀረቡ፡፡ኢትዮጵያ ወደ ታዳሽ የሃይል ምንጮች አጠቃቀም ለመሸጋገር የምታደርገውን ጥረትም ለማሳካት የዘረጋችው የብሄራዊ ኤሌክትሪፊኬሽን መርሃግብር መልካም ውጤት በማሳየቱ በአለም ባንክ አማካኝነት በሌሎች ታዳጊ አገራትም እየተተገበረ ነው ብለዋል፡፡ፕሬዘዳንት ሳህለውርቅ ዘውዴ በኒውዮርክ የመጀመሪያ ቀን ውሏቸው በታዳሽ የሃይል አጠቃቀም ሽግግር ላይ አተኩሮ በመክረው ስብሰባ ማጠናቀቂያ ላይ ንግግር አድረገዋል፡፡ኢትዮጵያ በገጠር እና በከተማ አሁን ያለውን 44 በመቶ የኤሌክትሪክ ሽፋን በአውሮፓውያኑ 2025 መቶ በመቶ ለማድረስ ብሄራዊ የኤልክትሪፊኬሽን መርኃግበር ቀርፃ እየሰራች መሆኑን ፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገለፀዋል፡፡መርሃግብሩ በኢትዮጵያ ባመጣው መልካም ውጤት የተነሳም የአለም ባንክ በሌሎች ታዳጊ ሀገራት እንዲተገበር እያደረገ መሆኑንም አውስተዋል፡፡በአለም አቀፍ ደረጃ ወደ ታዳሽ ሃይል የሚደረገው ሽግግር የተሳካ እንዲሆን በአየር ንብረት ለውጥ ይበልጥ ተጎጂ ለሆኑት ታዳጊ ሀገራት ቃል የተገባው የገንዘብ ድጋፍ በወቅቱና በበቂ ሁኔታ ማድረስ ይገባልም ነው ያሉት፡፡የመንግስታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ የአለም መሪዎችን በአንድ ላይ የሚያሰባስብ ትልቁ መድረክ ሲሆን ለዓለማችን አንግብጋቢ የሆኑ ርእሰ ጉዳዮች የሚመከሩበት ነው፡፡የኒውክሌር ቅነሳ ፤ቀጣይነት ያለው ልማት እንዲሁም የአለም የጤና ጉዳይ ከዘንድሮው 74ተኛው የድርጅቱ ጠቅላላ ጉባኤው ዋነኛ አጀንዳዎች መካካል ናቸው፡፡እንደ ኢቲቢ ዘገባ የአየር ንብረት ለውጥም በዘንድሮው ጉባኤ በትኩረት ውይይት የሚደረግበት ሌላው ርዕሰ ጉዳይ መሆኑ ተገልጿል፡፡ | https://waltainfo.com/am/32754/ | 190 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
550 ኮንቴነር መድኃኒቶችና የሕክምና ግብዓቶች መግባታቸውን የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ ድርጅት አስታወቀ | ሀገር አቀፍ ዜና | September 23, 2019 | Unknown | የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ ድርጅት ባለፋት 2 ወራት ከ550 ኮንቴነር በላይ መድኃኒቶችንና የሕክምና መገልገያ ግብዓቶችን ከሞጆ ደረቅ ወደብ ማንሣቱን አስታወቀ፡፡ከ25 ዓይነት በላይ መድኃኒቶችን ከሞጆ ደረቅ ወደብ ባጠረ ጊዜ ውስጥ ለማንሳት መቻሉን የኤጀንሲው የመድኃኒት ኮንትራት አስተዳደር ባለሙያ ወ/ሮ አጋር ተስፋዬ ገልጸዋል፡፡መድኃኒቶቹ ለኤች.አይ.ቪ፣ ለሆድ ሕመም፣ ለኢንፌክሽን፣ ለስነተዋልዶ እና ለሌሎች አገልግሎት የሚውሉ መድኃኒቶች፣ የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎችና ሪኤጀንቶች እንደሆኑ ወ/ሮ አጋር አብራርተዋል፡፡መድሀኒቶቹን በቀጥታ በተለያዩ ቅርንጫፎችና በዋናው መ/ቤት የመድኃኒት ማከማቻ መጋዘን እንደገቡ አስረድተዋል፡፡ወደ ቅርንጫፍ ቀጥታ መሄዱም ጊዜንና ወጪን በመቆጠብ ለማህበረሠቡ በቶሎ መድኃኒቶችን ተደራሽ ለማድረግ ወሣኝ ሚና አለው ሲሉ ባለሙያዋ አክለዋል፡፡እክሎች እንዳይከሠቱ በባንኩ፣ በሞጆ ደረቅ ወደብ፣ በኢትዮጵያ የምግብና የመድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን እና በኤጀንሲው መካከል ውል ለመፈራረም በዝግጅት ላይ መሆናቸውንም ባለሙያዋ ገልፀዋል፡፡(ምንጭ፡- የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ ድርጅት) | https://waltainfo.com/am/32756/ | 108 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
በኬንያ በአንድ ትምህርት ቤት በደረሰ የመደርመስ አደጋ የሰባት ህፃናት ህይወት አለፈ | ሀገር አቀፍ ዜና | September 23, 2019 | Unknown | በኬንያ በአንድ ትምህርት ቤት በደረሰ የመደርመስ አደጋ የሰባት ህፃናት ህይወት አልፏል፡፡በኬንያ ርዕሰ መዲና ናይሮቢ በሚገኝ አንድ ትምህርት ቤት የሚገኝ በእንጨት የተሰራ የመማሪያ ክፍል በመደርመሱ አደጋው መከሰቱን ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡ትምህርት ከተጀመረ ከደቂቃዎች በኋላ አደጋው በመከሰቱ ውጤቱ የከፋ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ከአደጋው በኋላም የትምህርት ቤቱ መግቢያ በሰው በመጨናነቁ የነፍስ አድን ስራው ላይ እንቅፋት መፍጠሩ ተገልጿል፡፡ፕሪሽየስ ታለንት ቶፕ የተሰኘው የዚህ ትምህርት ቤት ዳይሬክተር ሞስስ ኒራንጉ በአቅራቢያው እየተከናወና ያለው የፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦ ቀበራ ስራ አደጋው እንዲከሰት አድርጓል ሲሉ ውንጀላ አቅርበዋል፡፡ህይወታቸው ካለፈ ህጻናት በተጨማሪ በርካታ ህጻናት በእንጨት ክምሩ ውስጥ እንደሚገኙ ተነግሯል፡፡የኬንያ ቀይ መስቀል ድርጅት ከአደጋው በህይወት የወጡ ህፃናትን ወደ ኬንያታ ሆስፒታል ማጓጓዙን የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል፡፡ | https://waltainfo.com/am/33477/ | 97 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
አለምዓቀፍ የሰላም ቀን በኢትዮጵያ እየተከበረ ነው | ሀገር አቀፍ ዜና | September 23, 2019 | Unknown | ከአውሮፓዊያኑ 1982 ጀምሮ በአለምዓቀፍ ደረጃ የሚከበረው የሰላም ቀን በአዲስ አበባ የተባበሩት መንግስታት የስብሰባ ማዕከል እየተከበረ ነው፡፡በበዓሉ የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፌሪያት ካሚል በተወካዮቻቸው በኩል ባስተላለፉት መልዕክት፤ ኢትዮጵያ ከልማት አጋሮቿ ጋር በመሆን የአካባቢን ጥበቃ በማጎልበትና የአየር ንብረት ለውጥን በመከላከል ሰላሟንና ልማቷን አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል፡፡የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት አጋሮች ከኢትዮጵያ ጎን በመቆም የኢትዮጵያን ልማትና ሰላም በመደገፍ እያበረከቱት ላለው አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡በመድረኩ ላይ የአየር ንብረት ለውጥ ችግሮች፤ የሰዎችን መፈናቀል ብሎም የልማት ተሳትፏቸውን እንደሚቀንስ ተገልጿል፡፡ ይህም የዜጎች የሰላም እጦት መነሻ እንደሚሆን ተጠቁሟል፡፡ስለዚህም የአየር ንብረትን መጠበቅና አካባቢን ማልማት ለሰላም መጠበቅ ዋስትና ስለሚሆን ሁሉም ዜጋ የበኩሉን እንዲወጣ ተጠይቋል፡፡የዘንድሮ አለምአቀፍ የሰላም ቀን ‘‘የአየር ንብረት ጥበቃ ለሰላም’’ በሚል መሪ ቃል ነው እየተከበረ የሚገኘው፡፡ | https://waltainfo.com/am/32755/ | 104 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ሚኒስቴሩ ግጭቶችን አስቀድሞ ለመለየት እና መቆጣጠር የሚያስችል ስርዓት ይፋ አደረገ | ፖለቲካ | September 23, 2019 | Unknown | የሰላም ሚኒስቴር ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን ያዘጋጀውን ብሔራዊ የግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂያ እና ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የዘረጋውን ስርዓት በዛሬው ዕለት ይፋ አደረገ።ይህ ስርዓት በአጭር የፅሑፍ ምልዕክትና መልእክትና በኢንተርኔት ዳታ ስስተም የሚሰራ ሲሆን መረጃዎችን በመለዋወጥ እና በማጣራት ግጭት በሚኖርባቸው አካባቢዎች አስቀድሞ ለማስቀረት የሚያስችል ነው ተብሏል።ግጭቶቹ ቢፈጠሩ እንኳን በተለያዩ የመገናኛ አውታሮች በመጠቀም አፋጣኝ የሆነ ምላሽ መስጠት ያስችላልም ነው የተባለው።ለዚህ የስርዓት ዝርጋታ አለም አቀፍ ተቋማት ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን፣ በየቦታው የሚከሰቱ ግጭቶችን ከማስቀረት እና ህይወትን ከማዳን አንፃር ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ተጠቁሟል፡፡ስርዓቱ በጋምቤላ ክልል፣ በደቡብ ብሔሮች ብሔርሰቦችና ህዝቦች ክልል እና በኦሮሚያ ክልል የሚተገበር እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፣ በቀጣይ የስርዓቱ ውጤታማነት ታይቶ በሌሎች ክልሎችም ተግባራዊ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡ስርዓቱ ከቀበሌዎችና ወረዳዎች ጀምሮ እስከ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያለውን ተዋረድ በመጠቀም ግጭቶችን ከምንጩ ለማስቀረት ይሰራል ተብሏል።በቀጣይ ለስርዓቱ ተግባራዊነት ነፃ የስልክ መስመሮችና አጭር የፅሑፍ መልዕክት መላኪያ መስመሮች ይፋ ይደረጋልም ነው የተባለው፡፡ይህ የማስጀመሪያ ስርዓት ይፋ የተደረገው የሰላም ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ አለማየሁ እጅጉ፣ የዩ ኤስ ኤድ፣ የአውሮፓ ህብረት እና የተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማት በተገኙበት ነው። | https://waltainfo.com/am/31362/ | 151 | 5ፖለቲካ
|
ጠ/ሚ ዐቢይ ከሆሳዕና ከተማ ነዋሪዎች ጋር ተወያዩ | ፖለቲካ | September 22, 2019 | Unknown | ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ከሆሳዕና ከተማ ነዋሪዎች ጋር ተወያዩ፡፡በውይይቱ ወቅት የሆሳዕና ከተማ ነዋሪዎች ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድን ስለጉብኝታቸው አመስግነው፣ ዋና ዋና የልማት ጥያቄዎች አንስተዋል:: ለሥራ ፈጠራ በመሰረተ ልማት፣ በጤናና በአግሮፕሮሰሲንግ ኢንቨስትመንት ዙሪያ ጥያቄዎችን የነሱት ነዋሪዎቹ፣ የሀድያ ህዝቦችን የቆየ ልምድ በማጠናከር ጥያቄዎቻቸውን በሰላማዊ መንገድ ማቅረብ እንደሚቀጥሉ አንስተዋል::ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቅሬታዎች በሚዛናዊና የጋራ እሴትና መርሆችን በማያጠፋ መልኩ መቅረብ አለባቸው ብለዋል:: የሆሳዕና ነዋሪዎች እውቀትና በክልሉ በአንድነት ለመቆየት ያነሱትን ሀሳብ አድንቀዋል:: በተጨማሪም በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ የሆሳዕና ተወላጅ ኢትዮጵያውያን ያላቸውን ነዋይ በማሰባሰብ በአካባቢው ልማት ኢንቨስትመንት ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል::ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለመሰረተ ልማት ጥያቄዎች ሲመልሱም የጉብኝቱ አካል ለሆኑት ለጤናና ለግብርና ሚንስትሮችና ለመንገዶች ባለስልጣን ኃላፊዎች ጥናት እንዲያካሂዱና ለየዘርፎቹ ቁልፍ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲሰጡ አቅጣጫ አስቀምጠዋል ሲል የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል። | https://waltainfo.com/am/31361/ | 116 | 5ፖለቲካ
|
የሽብር ጥቃት ለመፈጸም በዝግጅት ላይ የነበሩ የአልሸባብና የአይ ኤስ የሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ | ፖለቲካ | September 21, 2019 | Unknown | በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሽብር ጥቃት ለመፈጸም ዝግጅት የነበራቸው የአልሸባብና የአይ ኤስ የሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ።ጉዳዩን አስመልክቶ የብሄራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት የሰጠው መግለጫ ሙሉ ቃል ይህን ይመስላል።በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሽብር ጥቃት ለመፈጸም ዝግጅት የነበራቸውየአልሸባብ እና የአይ ኤስ የሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር ውለዋል።አልሸባብ እና አይ ኤስ የሽብር ቡድኖቻቸውን ወደ አዲስ አበባ እና የተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በመላክ በኢትዮጵያ የሽብር ጥቃት በመፈፀም በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳይ ለማድረስ እንዲሁም የሀገራችንን በጎ ገፅታ ለማበላሸት በዝግጅት ላይ እንዳሉ የብሄራዊ የመረጃ ደህንነት አገልግሎት ባደረገው ጥብቅና የተቀናጀ ክትትል ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን በቁጥጥር ስር ውለዋል።ይህንን የጥፋት ተግባር ለመፈፀም ሀገር ውስጥ የገባው አንድኛው የአልሸባብ የሽብር ቡድን በሙሐመድ አብዱላሂ ዱለት በሀሰተኛ ስሙ ያህያ አሊ ሃሰን የሚመራ ሲሆን፤ የሽብር ጥቃት ተልዕኮ ይዞ በጅቡቲ በኩል ወደ አዲስ አበባ ከተማ በመግባት ህዝብ የሚባዛባቸውን ቦታዎች እንዲሁም የሀይማኖት ክብረ በዓል የሚካሄድባቸውንና የተለያዩ ሆቴሎችን የመለየትና የፎቶግራፍ መረጃዎችን የመሰብሰብ ጥናት በማድረግ ወደ ሽብር ተግባር ለመግባት በዝግጅት ላይ እንዳለ በብሄራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት ከጅቡቲ ወደ ሀገራችን ሲገባ ጀምሮ ክትትል ሲደረግበት ስለነበር በአዲስ አበባ ቦሌ አካባቢ በቁጥጥር ስር ውሏል።ከእርሱ ጋር በመሆን የተለያዩ ጥናቶችን ሲያካሄዱ የነበሩና ጁቡቲ የሚገኙ አብደክ መሃመድ ሁሴንና ሬድዋን መሃመድ ሁሴን የተባሉት ግብረ አበሮቹም ጅቡቲ ከሚገኘውና ሁኔታውን ሲያመቻችላቸው ከነበረው ሌላ የአልሸባብ አባል በቅፅል ስሙ ስመተር መሀመድ ኢማን ዩሱፍ የተባለውን ጨምሮ ከሀገሪቱ የመረጃ ተቋም ጋር በመቀናጀት በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል።አልሸባብ የሽብር ጥቃት እንዲፈፅሙ ካሰማራቸው ሌሎች ቡድኖች ውስጥም ከደቡባዊ ሶማሊያ ተነስተው ሱማሊላንድ ሐርጌሳ ከተማ ከገቡ በኋላ ወደ ሀገር ውስጥ ለመግባት ዝግጅት ሲያደርጉ ከነበሩ ሌሎች የሽብር ቡድኑ አባላት መካከልም ይሳቅ አሊ አደንና አደን ሙሃሙድ መሃመድ በቅፅል ስሙ አደን ቦራይ የተባሉት የፈንጅና የአጥፍቶ መጥፋት ስልጠና የወሰዱና የቡድኑ ቁልፍ አባላት ከመነሻቸው ጀምሮ በተደረገባቸው ክትትል ከሱማሊላንድ የመረጃ ተቋም ጋር በመቀናጀት በቁጥጥር ስር ውለዋል።ሶማሊላንድ በቁጥጥር ስር ከዋሉት ሌሎች የአልሸባብ ሽብር ቡድን አባላት መካከል ኢሳቅ አሊ አደን የተባለው የሽብር እቅዱን ለመፈፀም እንዲያመቸው ከሶማሊያ ክልል ቦህ ወረዳ ጨርቃን ቀበሌ ኢብራሂም ዓሊ አደን በሚል ሃሰተኛ የነዋሪነት መታወቂያ በእጁ ይዞ የተገኘ ሲሆን አደን ማሕሙድ መሐመድ ወይም አደን ቦራይ የተባለው በበኩሉ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁለት የሂሳብ አካውንት በመክፈት ለሽበር ተልዕኮ መፈፀሚያ ሊጠቀሙበት የነበረ ከ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ በተደረገው ጥብቅ ክትትል መገኘቱን ለማረጋገጥ ተችሏል።ከእነዚህ በተጨማሪም ተመሳሳይ ተልእኮ ይዞው ወደ ሃገር ውስጥ ከገቡት መካከል ዒድ መሃመድ ዓሊ የተባለው በሶማሊ ክልል ጨርጨር ዞን አራርሶ ወረዳ፣ በሽር ዑስማን አብዲ በዚሁ ክልል ፊቅ አከባቢ እንዲሁም ዑስማን አሊ ሁሴን የተባለው በኦሮሚያ ክልል በሞያሌ ከተማ በቁጥጥር ስር ውሏል።በተያያዘ በኢትዮጵያ ላይ በተደጋጋሚ የሽብር ጥቃት እንደሚፈጽም ሲዝት የነበረው ሁለተኛው የአይ ኤስ የሽብር ቡድን ደግሞ ከቦሳሶ በሶማሌላንድ ሃርጌሳ በኩል ወደ አዲስ አበባ በመግባት የሽብር ጥቃት ለመፈፀም ሲንቀሳቀስ በብሄራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት በተደረገበት ጥብቅ ክትትል ፋዕድ አብሽር የሱፍ የተባለው የቡድኑ አባል አዲስ አበባ ቦሌ አካባቢ በቁጥጥር ስር እንዲውል የተደረገ ሲሆን ፤ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የዚሁ ቡድን አባላት መካከልም ሙህመድ ጉሀድ ቡዲል የተባለው በሱማሌ ክልል በአፍዴር ዞን ምዕራብ ኢሚ ወረዳ በቁጥጥር ስር ዉሏል።
ሌላ በሀገር ውስጥ የአይ ኤስ የሽብር ቡድን አባል የሆነ ሰይድ ዑመር ሸበሺ የተባለው በፀጥታ አካላት በአዋሽ አካባቢ በቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጓል።እነዚህ አሸባሪዎች የጥፋት ተለዕኮቸውን ለማስፈፀም የሚጠቀሙባቸው የግንኙነት መሳሪያዎችና ሌሎች ቁሳቁሶች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል።የሸብር ቡድኖችን በመከታተል በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ለማድረግ በተካሄደው ሰፊ የኦፕሬሽን ስራም የተለያዩ የፌዴራልና የክልል የፀጥታ አካላት እንዲሁም የተለያዩ ሃገራት አጋር የመረጃ ተቋማት ድጋፍ አድርገዋል፡፡ በተለይም ደግሞ የጁቡቲ፣ የሶማሊላንድ፣ የፑንትላንድ የአሜሪካ፤ የጣሊያን፣ የፈረንሳይና የስፔን የመረጃ ተቋማት እገዛ ማድረጋቸውን ብሄራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት በመግለጫው አሳውቋል።ይህ በእንዲህ እንዳለ ብሄራዊ የመረጃና ደህንነት አግልግሎት በከፍተኛ ክትትል ያገኛቸውን መረጃዎች ለአሜሪካ፣ ለአውሮፓ፤ ለመካከለኛው ምስራቅ እንዲሁም ለአፍሪካና ለኤዢያ በአጠቃላይ 16 ለሚሆኑ ሀገራት ከተያዙት የሽብር ቡድኖች ጋር ግንኙነት እንዳላቸው የተደረሰባቸውን የሽብር ቡድኑ ህዋስ አባላት በሀገራቱ እንደሚገኙ የሚያረጋግጥ የመረጃ ልውውጥ በማድረግ የበኩሉን ድርሻ ተወጥቷል።አሸባሪዎቹ በሀገራችን ህዝብ በሚበዛባቸው ቦታዎች፤ ሆቴሎች፤ በመንግስትና በግል ተቋማት እንዲሁም የሃይማኖት ክብረ ባዓላት በሚከበርባቸው ስፍራዎች በፈንጂ ፍንዳታና በተኩስ የታጀበ የሸብር ጥቃታ በመፈፀም በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ውድመት ለማድረስ ተዘጋጅተውበት የነበረው የሽብር ጥቃትም የከሸፈው በህብረተሰቡ ከፍተኛ ተሳትፎ መሆኑን ብሄራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት አስታውቋል።በቀጣይም የሽበር ቡድኑ በሀገራችን ጥቃት ለመፈፀም ካለው ዝግጅት አንጻር ህዝባችን ይሄን ተገንዝቦ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደረግና የተለየ ነገር ሲመለከትም በአካባቢው ላለ የፀጥታ አካል መረጃ በመስጠት የተለመደ ትብብሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል በመግለፅ፤ ብሄራዊ የመረጃና ደህንነት አግልግሎት በሀገራችንና በህዝባችን ብሄራዊ ጥቅምና ደህንነት ላይ የሚቃጡ ማናቸውንም የሽብር ጥቃቶች አስቀድሞ በማወቅ አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ ከምንግዜውም በላይ ዝግጁ መሆኑን ገልፆ፤ የህዝቡ ድጋፍ እንዳይለየው ጥሪ አቅርቧል። | https://waltainfo.com/am/31359/ | 663 | 5ፖለቲካ
|
ጠ/ሚ ዐቢይ ሆሳዕና ከተማ ገቡ | ፖለቲካ | September 22, 2019 | Unknown | ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ሀድያ ዞን ሆሳዕና ከተማ ገብተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በከተማዋ በሚኖራቸው ቆይታ ከዞኑ ከተውጣጡ ነዋሪዎች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡ በከተማዋ ስታዲየም ለተሰበሰበው ህዝብም ንግግር እንደሚያደርጉ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ጠቁሟል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ባለፈው ሳምንት ከካፋ ዞን ነዋሪዎች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡ | https://waltainfo.com/am/31360/ | 51 | 5ፖለቲካ
|
ኢሬቻ የሰላም ሩጫ በአዲስ አበባ ተካሄደ | ሀገር አቀፍ ዜና | September 22, 2019 | Unknown | ‘‘ኢሬቻ ለሰላም’’ በሚል ስያሜ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡በአባቶች ምርቃት በተጀመረው ሩጫ ላይ ከ50 ሺህ በላይ ሰዎች ተሳትፈውበታል፡፡መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ባደረገው የሩጫ ውድድር ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ ከ15 በላይ አትሌቶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡በውድድሩ ከወንዶች አትሌት በሪሁ አረጋዊ እና ከሴቶች ደግሞ አትሌት ኦብሴ አብደታ የ‘‘ኢሬቻ ለሰላም’’ የጎዳና ላይ ሩጫ አሸናፊዎች ሆነዋል፡፡ለአሸናፊዎቹ የዋንጫ፣ የምስክር ወረቀት እና የ50 ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡በውድድሩ በወንዶች ኃይለማሪያም ኪሮስ 2ኛ ሲወጣ ደጀኔ ደበላ 3ኛ በመሆን አጠናቀዋል፡፡በሴቶች ደግሞ መስታወት ፍቅሬ 2ኛ አንቻለም ሀይማኖት ደግሞ 3ኛ በመውጣት አሸናፊ ሆነዋል፡፡በውድድሩ በሁለቱም ፆታዎች 2ኛ እና 3ኛ ለወጡ ተወዳዳሪዎች የ30 ሺህ እና የ20 ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮሎኔል ደራርቱ ቱሉ እና የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ሽልማቱን ለአሸናፊዎቹ አበርክተውላቸዋል፡፡የኢሬቻ የሰላም ሩጫ በዘንድሮው ዓመት በአዲስ አበባ የሚከበረውን የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ ነው የተካሄደው፡፡ | https://waltainfo.com/am/32752/ | 130 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖት ተከታዮች ሰልፍ እያካሄዱ ነው | ሀገር አቀፍ ዜና | September 22, 2019 | Unknown | የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናንና ካሕናት በባሕር ዳር፣ ቢቸና፣ ቡሬ፣ እንጅባራ፣ መርዓዊ፣ ወልድያ፣ ፍኖተ ሠላም፣ ደባርቅ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ደብረ ብርሃን፣ ቆቦ፣ ማጀቴ፣ ጫጫ፣ ዋድላ፣ ዳንግላ፣ ሞጣ፣ ዳባት፣ መሐል ሜዳ፣ ውጫሌ፣ ሮቢትና፣ ላልይበላ ሰልፎች እያካሄዱ ነው፡፡ በተጠቀሱት ከተሞች በምዕመናን እና በቤተ ክርስቲያኗ ላይ የሚፈፀመውን ግፍ እንዲቆም የሚጠይቅ ሠላማዊ ሠልፍ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡በሰልፉ ላይ “በቤተ ክርስቲያንና በምዕመኖቿ ላይ የሚፈጸመው ግፍና መከራ ይቁም! በቤተ ክርስቲያንና ምዕመኖቿ ላይ ግፍ የፈጸሙት በሕግ ይጠየቁ!” የሚሉ መልዕክቶች እየተላለፉ ነው፡፡ | https://waltainfo.com/am/32751/ | 73 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የህዳሴ ግድብ ግንባታ ያለእረፍት በቀንና በሌሊት እየተከናወነ መሆኑ ተገለጸ | ቢዝነስ | September 22, 2019 | Unknown | የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከምንግዜም በላይ በቀንና በሌሊት ያለምንም እረፍት እየተከናወነ መሆኑ ተገለጸ።
የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ቆሟል በሚል የሚሰራጨው ፕሮፖጋንዳ ከእውነት የራቀ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር አብርሃም በላይ ገለፁ።በየጊዜው ግድቡ ቆሟል በሚል በግብፅና በተለያዩ አፍራሽ ኃይሎች የሚሰራጨውን የሀሰት ፕሮፓጋንዳ በመያዝ አሉታዊ መልዕክት የሚያስተላልፉ አካላትን ውሸትና ሴራ የምናጋልጠው ግንባታውን በተግባር በማፋጠን ብቻ መሆኑን በመግለጽ፤ አሁን ላይ የግድቡ ግንባታ ከምንግዜም በላይ በቀንና ሌሊት ያለምንም እረፍት እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ከግንባታው ጋር ተያይዞ የሚናፈሰው ወሬም ምንም እውነት የሌለውና ግብፅ መቼውንም ቢሆን ለኢትዮጵያ አስባ የምታቀርበው ሃሳብ እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል በማለት ተናግረዋል።ይልቁንም የግድቡን ግንባታ ማስቆም እንደማትችል የተረዳችው ግብፅ አሁን ላይ አካሄዷን በመቀየር ግድቡ በረጅም ጊዜ እንዲሞላና ግንባታው ተጠናቅቆ ወደ ስራ ሲገባ ኦፕሬሽኑ እንዴት ይካሄድ የሚሉ፤ ፍላጎቶቿን ያሳኩልኛል ያለቻቸው ጉዳዮች ላይ ማተኮሯን ዶ/ር አብርሃም ጠቁመዋል፡፡ከሰሞኑ በተደረገው የሶስትዮሽ ውይይት ላይም የህዳሴ ግድብ የውሃ አሞላልና ፍሰት፤ የአስዋን ግድብ በሚኖረው የውሃ መጠን ላይ እንዲመሰረት ግብፅ ያቀረበችው ምክረ ሃሳብ የኢትዮጵያን የመልማት ጥያቄና ሉዓላዊ መብት የሚጋፋ በመሆኑ ተቀባይነት እንደሌለው ገልፀዋል፡፡ግድቡ የምንገነባው ተገንብቷል ለማለት ሳይሆን ሀገሪቱ የምትፈልገውን ኃይል ለማሟላት በዓመት በአማካይ 15670 ጊጋ ዋት ሰዓት ኃይል በማመንጨት ለሀገራችን ኢኮኖሚያዊ ሽግግር ጉልህ ሚና እንዲኖረው ለማድረግ በመሆኑ ይህን መብታችንን ለድርደር አይቀርብም ብለዋል::ከኃይል ማመንጨት አቅም ጋር ተያይዞም ከግብፅ ጋር በመደራደር የግድቡ የማመንጨት አቅም እንዲቀንስ ተደርጓል በሚል የተናፈሰው ዘገባም ከእውነት የራቀ እና አሉባልታ መሆኑን ዋና ስራ አስፈፃሚው የተናገሩት ዋና ስራ አስፈጻሚው፤ አሁን ባለው ሁኔታ ግድቡ መያዝ የሚችለው ውሃንም ሆነ የማመንጨት አቅም መቀየር የሚቻልበት እድል እንደሌለ ገልጸዋል።የአንድ ግድብ የማመንጨት አቅም በመሰረቱ የሚወሰነው ግድቡ በሚይዘው የውሃ መጠን እና ውሃው ከተርባይን ማእከል በሚኖረው ከፍታ ልዩነት እንጂ በሚተከሉት ተርባይኖች ብዛትና መጠን ብቻ አለመሆኑንም ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል።ከግብፅ በመደራደር የጀነሬተር ወይም ተርባይን ቁጥሩ ተቀንሷል የሚባል አሉባልታ የሚያናፍሱ አካላት የውሃ ኃይል ማመንጫ እንዴት እንደሚሰራ ግንዛቤ የሌላቸው አልያም ሆን ብለው ሰዎችን ለማደናገር የሚሞክሩ ናቸው ብለዋል፡፡(ምንጭ:- የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል) | https://waltainfo.com/am/23979/ | 279 | 3ቢዝነስ
|
ሁሉንም ኢትዮጵያውያን ያሳተፈ፣ የፌዴራሊዝም ሥርዓትን የሚያጠናክር ሕገ መንግሥታዊ ማሻሻያ እንዲደረግ ተጠየቀ | ፖለቲካ | September 21, 2019 | Unknown | የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤ ስብሰባ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል።ለሁለት ቀናት በባሕር ዳር ከተማ ሲካሄድ የቆየው የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ መክሯል፡፡የመማክርት ጉባኤው በዋናነት የአማራ ሕዝብ በሚያነሳቸው ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ በስፋት ሲመክር ቆይቷል፡፡ ዛሬ ጉባኤው ሲጠናቀቅም ባለዘጠኝ ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥቷል።በዚህ የአቋም መግለጫ ከተካተቱ ሀሳቦች መካከልም ሁሉንም ኢትዮጵያውያን ያሳተፈ፣ የፌዴራሊዝም ሥርዓትን የሚያጠናክር ሕገ መንግሥታዊ ማሻሻያ እንዲደረግ የሚጠይቀው ይገኝበታል።የሕዝቦችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ፣ ሁሉም ቋንቋዎችና ባሕሎች እንዲበለፅጉ በሚያግዝ መልኩም ማሻሻያው እንዲከናወንም ነው የመማክርት ጉባኤው የጠየቀው፡፡ዲሞክራሲ፣ ፍትህ እኩልነትና ነፃነት እንዲሁም ብልፅግና የሰፈነባት ኢትዮጵያን እውን ለማድረግም ከሌሎች ወንድምና እህት ኢትዮጵያውያን ጋር ይበልጥ ተባብሮ ለመስራት መወሰኑንም በመግለጫው አንስቷል፡፡የህዝቡ ፈታኝ ችግር የሆኑትን የስራ አጥነትና የኑሮ ውድነትን ለመቀነስም የክልሉንና የመላ ኢትዮጵያውያንን እምቅ አቅምና ክህሎት በመጠቀም ይሰራል ነው ያለው፡፡የክልሉን ተፈጥሯዊ፣ ባህላዊ፣ ቁሳዊ፣ መንፈሳዊ ፀጋዎችንና ሀገር በቀል እውቀቶችን በመጠቀምና በቴክኖሎጂ በማገዝ ለህዝብ ጥቅም ለማዋል በትኩረት እንደሚሰራ አንስቷል፡፡ቀደምት አባቶች በሀገር መንግስት ግንባታ ሂደት የነበራቸውን ጉልህ ሚናና ውለታ በፅንፈኛ ትርክት ያልተገባ ትርጉም መስጠት አማራ ጠልነት እንዲስፋፋ በሴራና በተደራጀ ሁኔታ ሲሰራበት ቆይቷል ያለው መግለጫው፤ ይህ ለሀገራዊ ህብረት አደጋ በመሆኑ እንዲቆምና እንዳይቀጥል ይሰራል ብሏል፡፡ሰሜኑን ከደቡብ ምስራቁን ከምዕራብ ያገናኘው፣ የኢትዮጵያ እውቀትና ጥበብ ከዘመን ዘመን የተሻገረበትና ትውልድ የተጋመደበትን የአማርኛ ቋንቋ በማጥላላት እየተደረገ ያለውን ዘመቻ አውግዟል የአቋም መግለጫው፡፡አብሮነት የሚዳብረውና ብልፅግና የሚረጋገጠው ሁሉም ኢትዮጵያዊ በነጻነት በፈለገው ስፍራ የመኖርና የመስራት መብቱ ሲጠበቅለትና ሀብት የማፍራት መብቱ ሲረጋገጥለት እና ዴሞክራሲያዊ ጥያቄዎቹ ሲመለሱለት መሆኑን አንስቷል፡፡የአማራ ህዝብ የእኩልነት፣ የፍትህ፣ የዴሞክራሲና የነፃነት ትግል ግብ እንዲመታ በየትኛውም ስፍራ የሚገኝ የአማራ ህዝብ የፖለቲካ፣ የሃይማኖትና ሌሎች የአመለካከት ልዩነቶች ሳይበግሩት በአንድነት እንዲቆምም ነው ጥሪ ያቀረበው፡፡ | https://waltainfo.com/am/31358/ | 233 | 5ፖለቲካ
|
የምዕራብ ምድብ አየር ኃይል የተሟላ የመሥሪያ ሕንጻውን አስመረቀ | ፖለቲካ | September 21, 2019 | Unknown | የኢፌዴሪ የምዕራብ ምድብ አየር ኃይል የተሟላ የመሥሪያ ሕንጻውን ዛሬ አስመርቋል፡፡የኢፌዴሪ አየር ኃይል ምዕራብ አየር ምድብ ኃላፊ ኮሎኔል ቸርነት መንገሻ "24 ሰዓት የአየር ክልሉንና ሕዋውን ጥበቃ ለማድረግ በቴክኖሎጂና በዕውቀት እየተሻሻለ ነው" ብለዋል።ኮሎኔል ቸርነት የምድቡ ማስፋፊያ ግንባታ ስር ነቀል ተቋማዊ ለውጥ በማድረግ ላይ ላለው መከላከያ ተጨማሪ ጉልበት እንደሚሆንም ተናግረዋል።በሚግ 23 ቅርፅ የተሠራው አዲሱ የማስፋፍያ ሕንጻ በርካታ ወታደራዊ አገልግሎቶችን ያቀፈ እንደሆነም ተነግሯል።የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተመስገን ጥሩነህ በክልሉ አንፃራዊ ሠላም እንዲሰፍን መከላከያ ከፍተኛ እገዛ ማድረጉን አንስተው አመሥግነዋል።አቶ ተመስገን መከላከያው በፖለቲካ ልምሻ ምክንያት ከተፈጠረው የመንደር ስምሪት ወጥቶ ትልልቅ ጉዳዮች ላይ እንዲያተኩር ጠይቀዋል።ሠራዊቱን መከታ በማድረግ ፍላጎታቸውን ማስፈፀም ለሚፈልጉ ሕልመኞች ሠራዊቱ መጠቀሚያ መሆን እንደሌለበትም ነው ያሳሰቡት።"የፖለቲከኞች በሐሳብ በተለያዩ ቁጥር መሳሪያ አስነግቶ በሕዝብ ላይ ጥይት ማስተኮስ ነውረኛ ተግባር በመሆኑ ሠራዊቱ የሌላ ፖለቲካ ተሸካሚ ከመሆን ራሱን ሊጠብቅ ይገባል" ብለዋል።የኢፌዴሪ አየር ኃይል ምዕራብ አየር ምድብ የዕውቀትና የቴክኖሎጂ ልህቀት ማዕከል ሆኖ የሀገሪቷን ሕዋና የአየር ክልል ከማንኛውም ጥቃት በአስተማማኝነት መጠበቅ ራዕይ ያደረገ ነው።ማዕከሉ ከአየር ክልልና ሕዋ ጥበቃ በተጨማሪ የኤሌክትሮኒክስ ደኅንነትን እና የሳይበር ተጋላጭነትን ለመከላከልና ለመመከት የሚሠራ ነው።የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ይልማ መርጋሳ እና የኢፌድሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዥር ሹም አደም መሀመድ በምረቃው መገኘተታቸወውነን አብመድ ዘግቧል። | https://waltainfo.com/am/31357/ | 177 | 5ፖለቲካ
|
ድርጅቱ 705 ሚሊዮን ቶን የእቃ ጭነት አገልግሎት ለመስጠት እየሰራ ነው | ቢዝነስ | September 21, 2019 | Unknown | የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት በ2012 ዓ.ም 705 ሚሊዮን ቶን የእቃ ጭነት አገልግሎት ለመስጠት ማቀዱን የድርጀቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሮባ መርገሳ በሰጡት መግለጫ አስታወቁ፡፡ኢትዮጵያ አሁን ላይ 2 ነዳጅ ጫኝ እና 9 ሁለገብ አገልግሎት የሚሰጡ መርከቦች እንዳሏት የገለፁት ዋና ስራ አስፈፃሚዉ ፤ ባለፈዉ አመት የሀገሪቱን የወጪ ንግድ ተወዳዳሪነትን ለማረጋገጥ የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱንም ጠቅሰዋል፡፡ድርጅቱ ባለፉት አመታት የገጠሙትን ዉስንነቶች ለመቅረፍም እንደሚሰራ ገልፆ ፤ ለመንግስት የልማት ድርጅቶች የዱቤ አገልግሎት ዉስጥ ሜቴክ 2 ቢሊየን ብር ውዝፍ እዳ እንዳለበትና በቀጣይ የሚመለስበት ወይም የሚሰረዝበት መንገድ ካለም የሚሰራ ይሆናል ብሏል፡፡የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሳደግ የአይ ሲ ቲ አጠቃቀምና የካይዘን ስራ አመራር ላይ በትኩረት እንደሚሰራ ገልፆ፤ የቀጣይ ድርጅቱ ዋና ዋና እቅዶችንም አሳዉቋል፡፡ቀደም ሲል የነበረዉ አሰራር አገልግሎት አሰጣጥ ላይ እንቅፋት ሆኖ የቆየዉን የባህር ወደብ አጠቃቀም አሰራርን ለማስተካልም ይሰራል ብለዋል ዋና ስራ አስፈፃሚዉ፡፡የኢትዮጵያ ባሕር ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት በ2011 በጀት ዓመት የ1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን አስታውቋል፡፡ | https://waltainfo.com/am/23977/ | 137 | 3ቢዝነስ
|
ባለስልጣኑ በህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ላይ ያለውን የኪሎ ሜትር ገደብ ለአጭር ጊዜ ብቻ አነሳ | ቢዝነስ | September 21, 2019 | Unknown | የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን በተማሪዎች የዩኒቨርስቲ መግቢያ ወቅት ተማሪዎችን የትራንስፖርት እጥረት ችግር እንዳያጋጥማቸው በህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ላይ ያለውን የኪሎ ሜትር ገደብ ለአጭር ጊዜ ብቻ አንስቷል፡፡በሀገሪቱ በትምህርት መስኩ መጠነ ሰፊ የማስፋፋት ስራ እየተሠራ በመሆኑ የበርካታ ዩኒቨርሲቲዎች መከፈትና የተማሪ ቅበላ መጠን እየጨመረ መምጣቱ እንዲሁም ዩኒቨርሲቲዎች ጥሪ የሚያደርጉበት ወቅት የተለያዩ ህዝባዊ እና ሃይማኖታዊ በዓላት የሚደራረቡበት ወቅት በመሆኑ የትራንስፖርት አቅርቦት እጥረት ማጋጠሙን ባለስልጣኑ ጠቅሷል፡፡ስለሆነም አቅርቦቱን ለማሻሻልና የተማሪዎችን እንግልት ለመቀነስ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሠጡ ተሽከርካሪዎች የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ለማጓጓዝ ብቻ ከመስከረም 10 ቀን 2012 ጀምሮ እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ብቻ በኪሎ ሜትር ሳይገደቡ አገልግሎት መስጠት ይችላሉ ብሏል፡፡በዚሁ መሰረት የክልልና ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ተቋማት በመናኸሪያዎች ሠራተኞችን በመመደብ ተማሪዎች ሳያቆራርጡ በቀጥታ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚደርሱበትን ትራንስፖርት በማቀናጀት ሁኔታዎችን እንዲያመቻቹና የሚመለከተው ተቆጣጣሪ አካልም ጉዳዩን አውቆ ትብብር እንዲያደርግ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡በተሽከርካሪዎች ላይ የነበረው የኪሎ ሜትር ገደብ ለአነስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪዎች እስከ 150 ኪሎ ሜትር፣ ለመለስተኛ ከ150 እስከ 250 ኪሎ ሜትርና ለአገር አቋራጭ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ከ250 ኪሎ ሜትር በላይ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ | https://waltainfo.com/am/23978/ | 154 | 3ቢዝነስ
|
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከአባ ገዳዎችና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር ተወያዩ | ሀገር አቀፍ ዜና | September 21, 2019 | Unknown | ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በእሬቻ በዓል አከባበር ዙሪያ ከአባ ገዳዎችና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር ተወያይተዋል።በውይይታቸውም የእሬቻ በዓል የኦሮሞ ባህል እሴትና መርህ በሆኑት የአንድነት፣ የፍቅርና የይቅርታ መሠረቶች ላይ በመመርኮዝ በሰላማዊ መንገድ መከበር እንዳለበት ተወስቷል።አባ ገዳዎችና የሀገር ሽማግሌዎች ክብረ በዓሉ በሰላማዊ መንገድና ሁሉም ኢትዮጵያውያን በአንድነት የሚያከብሩት የደስታ በዓል እንዲሆን ባለድርሻ አካላት እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርበዋል።ከዚህ ባለፈም ከመላ ኢትዮጵያውያን ጋር በመናበብ እሴትን፣ ቋንቋንና የኦሮሞ ህዝብ ባህልን የበለጠ ለማሳደግ እንደሚሰራ ተመላክቷል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የእሬቻ በዓል ዝግጅትና አከባበር ሰላማዊና አንድነታችንን ባንጸባረቀ መልኩ እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ እና ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ የክልሉን ነዋሪዎች የሚመለከቱ የልማት፣ የሰላምና ለውጡን የማስቀጠል ስራዎች ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።በዚህም ከአባ ገዳዎችና ሀገር ሽማግሌዎች ጋር ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ከጠቅለይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። | https://waltainfo.com/am/32749/ | 128 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
አስተዳደሩ የ100 የኩላሊት ህሙማንን የአንድ ዓመት የኩላሊት እጥበት ወጪ ሸፈነ | ሀገር አቀፍ ዜና | September 21, 2019 | Unknown | የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በገንዘብ እጦት ምክንያት የኩላሊት እጥበት ማድረግ ላልቻሉ 100 ህመምተኞች ለአንድ ዓመት የኩላሊት እጥበት ማድረግ የሚያስችላቸውን የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡በዚህም መሠረት ህመምተኞቹ በሃኪም የታዘዘላቸውን የኩላሊት እጥበት መርሃ ግብር ሳይቆራረጥ በሳምንት ሶስት ቀን ለአንድ ዓመት የሚያደርጉ ይሆናል፡፡የኩላሊት ህመምተኞቹ ላለፉት በርካታ ጊዜያት በሳምንት የታዘዘላቸውን የሶስት ቀን የኩላሊት እጥበት መርሃ ግብር በገንዘብ እጥረት ምክንያት ማድረግ ሳይችሉ ቆይተዋል፡፡በዛሬው ዕለት ኢ/ር ታከለ ኡማ እና ሌሎች የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በጳውሎስ ሆስፒታል የኩላሊት ህክምና ክፍሎች በመዘዋወር ታካሚዎችን አነጋግረዋል፡፡የከተማ አስተዳደሩ የኩላሊት እጥበት ለሚያከናውኑ ህመምተኞች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ዘላቂ መፍትሄ እንደሚያፈላልግ ኢ/ር ታከለ ኡማ በጉብኝታቸው ወቅት ተናግረዋል፡፡ድጋፉ በጳውሎስ ፣ ዘውዲቱ እና ሚኒሊክ ሆስፒታል ተኝተው ህክምናቸውን በመከታተል ላይ ለሚገኙ 100 የኩላሊት ህመምተኞች የተደረገ ሲሆን፤ በገንዘብ ሲተመን ከ9 ሚሊየን ብር በላይ መሆኑን ከከንቲባ ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። | https://waltainfo.com/am/32750/ | 121 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ግብፃውያን ፕሬዝዳንት አል-ሲሲን በመቃወም ሰልፍ ወጡ | ፖለቲካ | September 21, 2019 | Unknown | ግብፃውያን ፕሬዝዳንት አል-ሲሲን በመቃወም ሰልፍ መውጣታቸው ተዘገበ፡፡ሰልፉ፤ ፕሬዘዳንት አብዱል ፈታህ አል-ሲሲ ወደ ሥልጣን ከመጡ ወዲህ በግብፅ በተካሄደው የመጀመሪያ የተቃውሞ ሰልፍ ሲሆን፣ ፖሊስ ሰልፈኞችን ለመበተን አስለቃሽ ጭስ መጠቀሙ ተገልጿል።በመቶዎች የሚቆጠሩ ግብፃውያን በታህሪር አደባባይ ሰልፍ ወጥተው፤ ፕሬዝዳንት አል-ሲሲ ሥልጣን እንዲለቁ ጠይቀዋል። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ2011ዱ ተቃውሞ ማዕከል ከነበረው ታህሪር አደባባይ በተጨማሪ በሌሎች አካባቢዎችም ሰላማዊ ሰልፍ ተደርጓል ነው የተባው።በተለያዩ አካባቢዎች ሰላማዊ ሰልፍ የተካሄደው የአል-ሲሲ ሙስና መወንጀላቸውን ተከትሎ ነበር።ግብፃዊው ተዋናይና የቢዝነስ ሰው ሞሀመድ አሊ፤ አል-ሲሲ በቅንጡ ቤቶችና ሆቴሎች ላይ በርካታ ገንዘብ እያባከኑ እንደሚገኙ በመግለጽ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ቪድዮዎች አሰራጭቷል።በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ግብፃውያን በድህነት እየማቀቁ ሳለ ፕሬዝዳንቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ እያባከኑ መሆኑንም ተናግሯል።አል-ሲሲ የተባለው ነገር "ውሸት እና የስም ማጥፋት ዘመቻ ነው" ሲሉ ውንጀላውን አጣጥለዋል።ትላንት በትዊተር ላይ በስፋት ሲሰራጩ የነበሩ መልዕክቶች ሕዝቡ አል-ሲሲ ከሥልጣን እንዲነሱ እንደሚፈልግ የሚጠቁሙ ነበሩ።አል ጀዚራ እንደዘገበው፤ በአሌክሳንድርያ እና ሱዌዝ ከተሞችም ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል።ስፔን ውስጥ በስደት የሚኖረው ግብፃዊው ተዋናይና የቢዝነስ ሰው ሞሀመድ አሊ፤ የመጀመሪያ ቪድዮውን የለቀቀው መስከረም ሁለት ነበር። ፕሬዝዳንቱ ከሥልጣን የሚወርዱበት ቀነ ገደብ አስቀምጦ፤ አል-ሲሲ በተባለው እለት ከሥልጣን ካልወረዱ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚካሄድ ገልጾም ነበር።ሞሀመድ ባስቀመጠው ቀነ ገደብ መሰረት፤ አል-ሲሲ ከሥልጣናቸው አለመነሳታቸውን ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ ግብፃውያን ሰልፍ ወጥተዋል።ግብፅ ነጻነቷን ከተቀዳጀች በኋላ የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት የሆኑት ሞሀመድ ሙርሲን በማስወገድ አል-ሲሲ ስልጣን የጨበጡት 2013 ላይ እንደነበር ይታወሳል።የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፤ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች መታሰራቸውን በማጣቀስ፤ የአል-ሲሲን አስተዳደር በጽኑ ይተቻሉ።2018 ላይ በተካሄደው ምርጫ አል-ሲሲ ጠንካራ ተቀናቃኝ ሳይኖር 97 በመቶ ድምፅ በማግኘት አሸንፈዋል። አል-ሲሲ እስከ 2030 ስልጣን ላይ እንዲቆዩ ሕገ መንግሥታዊ ማሻሻያ የማድረግ ሀሳብ አብላጫ ድምፅ ማግኘቱም ይታወሳል። (ምንጭ፡-ቢቢሲ) | https://waltainfo.com/am/33339/ | 230 | 5ፖለቲካ
|
በግንባታ ጥራትና አፈጻጸም ላይ ለውጥ ማምጣት የሚያስችል ቴክኖሎጂ ሊተገበር ነው | ቢዝነስ | September 21, 2019 | Unknown | የግንባታዎች ጥራትና አፈጻጸም ላይ ጉልህ ለውጥ ማምጣት የሚያስችል ቴክኖሎጂ ለመተግበር በዝግጅት ላይ መሆኑን የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት አስታወቀ።ቴክኖሎጂውን በመጠቀም ሁለት የግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ በተካሄደ ሙከራ ጥራትን በማሻሻል፣ የባለ ድርሻ አካላትን ቅንጅት በማጠናከርና በሌሎችም ለውጦች ተገኝተዋል ተብሏል።ኢንስቲትዩቱ ‘አውቶ ዴስክ’ ከተሰኘ የአሜሪካ ሶፍትዌር አምራች ድርጅት ጋር በመተባበር የሶፍትዌር ቴክኖሎጂዎች ላይ ያተኮረ ውይይት ሲያካሂድ የኢንስቲትዩቱ ዳይሬክተር አቶ አስመሮም ታደሰ እንደተናገሩት፤ ግንባታዎችን በጥራት፣ በጊዜና ወጪን በቆጠበ መልኩ ማከናወን የሚያስችል የህንጻ መረጃ ሞዴል ሶፍትዌር ተግባራዊ ለማድረግ እየተሰራ ነው።የቴክኖሎጂው ሶፍትዌርና አስፈላጊ መሳሪያዎች ግዢ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ መፈጸሙን ተናግረዋል።የፕሮጀክት አስተዳደር ብቃት አነስተኛ መሆን፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በስፋት ያለመጠቀም፣ የጥራት መጓደልና ሌሎችም ከኮንስትራክሽን ዘርፉ ዋነኛ ችግሮች መካከል ጠቅሰዋል።የግንባታ ወጪዎች ከተመደበው በጀት ጋር ያላቸው ልዩነት ከፍተኛ መሆን፣ የባለ ድርሻ አካላት ቅንጅት ማነስ፣ በግንባታ ወቅት ሊፈጠሩ የሚችሉ ችግሮችን አስቀድሞ አለመለየትና መፍትሄዎችን ያለማዘጋጀት፣ የስራ ተቋራጮችና አማካሪዎች ብቃት ማነስንም እንዲሁ።በመሆኑም ከፕሮጀክቶች ዲዛይንና እቅድ አወጣጥ እስከ አፈጻጸም ባሉት ደረጃዎች ላይ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎችን ስራ ላይ ማዋል ያስፈልጋል ብለዋል።የህንጻ መረጃ ሞዴል ሶፍትዌር ቴክኖሎጂው በኮንስትራክሽን ዘርፉ ያሉ በርካታ ችግሮችን ለመፍታት እንደሚያስችልም ነው የተናገሩት።እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ ቴክኖሎጂውን በመጠቀም ሁለት የግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ ሙከራ የተደረገ ሲሆን በተያዘው ዓመት ሶስተኛ ፕሮጀክት ላይ ይተገበራል።በሙከራ ፕሮጀክቶቹም በግንባታ ወቅት ሊፈጠሩ የሚችሉ ችግሮችን በመቀነስ፣ ጥራት በማሻሻል፣ የባለ ድርሻ አካላትን ቅንጅት በማጠናከሩ በኩል ለውጦች መገኘታቸውን ገልጸዋል።ስለ ቴክኖሎጂው አጠቃቀም ለ18 ባለሙያዎች ስልጠና መሰጠቱን፣ በቀጣይም ከሶፍትዌር ፈጣሪው ድርጅት ጋር በመሆን ስልጠና እንደሚሰጥ ተናግረዋል።ቴክኖሎጂው በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ዘርፍ ሙሉ ለሙሉ በቅንጅት እንዲተገበር ፍኖተ ካርታ መዘጋጀቱንና በቅርቡ ይጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል። | https://waltainfo.com/am/23975/ | 233 | 3ቢዝነስ
|
የገናሌ ዳዋ 3 የኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድብ በጥቅምት መጀመሪያ የሙከራ ኃይል ያመነጫል | ቢዝነስ | September 21, 2019 | Unknown | 254 ሜጋ ዋት የሚያመነጨው የገናሌ ዳዋ ኤሌክትሪክ ኃይል ግድብ ኤሌክትሪክ ለማመንጨት የሚያስችለው ውሃ በግድቡ በመሙላቱ በጥቅምት መጀመሪያ የሙከራ ኃይል ማመንጨት እንደሚጀምር የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፤ በገናሌ እና ዳዋ ተፋሰሶች በጉጂ እና ባሌ ዞኖች መካከል እየተገነባ የሚገኘው የኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድቡ ሙሉ ለሙሉ ስራ ሲጀምር 254 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም አለው።በአሁኑ ወቅት በግድቡ ለተተከሉት ሶስት ተርባይኖች ማንቀሳቀሻ የሚሆነው እና ከግድቡ የታችኛው ወለል አንስቶ 70 ሜትር ከፍታ የሚደርሰው ውሃ በመሙላቱ በጥቅምት ወር መጀመሪያ የሙከራ ኃይል ማመንጨት ይጀመራል።እንደ አቶ ሞገስ ገለጻ፤ በግድቡ እንዲገባ የተደረገው ውሃ በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንኛዎች ታሪክ ረጅሙ በሆነው እና 12 ነጥብ 4 ኪሎሜትር በሚረዝመው የኮንክሪት ዋሻ ውስጥ አልፎ ነው ተርባይኖቹን የሚያንቀሳቅሰው።በአሁኑ ወቅትም ዋሻው በውሃ ተሞክቶ የፍተሻ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛል። እስከአሁን ድረስ ያለውሃ እና በእርጥበት አማካኝነት በተደረጉ የተርባይን ፍተሻዎች የተሳካ ውጤት ተገኝቷል።ሶስቱ ተርባይኖችም በሙሉ አቅም ሲሰሩ እያንዳንዳቸው 84 ነጥብ 7 ሜጋ ዋት ማመንጨት ይችላሉ፡፡ግድቡ ጥቅምት ላይ የሙከራ ኃይል ማመንጨት ሲጀመርም የሚመረተው ኤሌክትሪክ በይርጋለምና ወላይታ ሶዶ ከተሞች አድርጎ አዲስ አበባ የሚገኘው ብሔራዊ የኤሌክትሪክ ቋት እንዲገባና ወደሚያስፈልጉ አካባቢዎች እንዲሰራጭ እንደሚደረግ አስረድተዋል።ከአዲስ አበባ 630 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው የገናሌ ዳዋ 3 የኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድብ ግንባታው የተጀመረው መጋቢት 2003 ዓ.ም ላይ ነው።ከየካቲት ወር 2011 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ ለግድቡ የሚሆን ውሃ ሙሌት ሲካሄድ ቆይቷል። ቀሪ ስራዎች የሚቀሩት ግድቡ 451 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ያለው ሲሆን፤ ግንባታው በቻይናው ሲጂጂሲ ድርጅት እየተከናወነ ይገኛል።ለግድቡ ወጪ የኢትዮጵያ መንግስት 40 ከመቶ ሲሸፍን የቻይናው ኤግዚም ባንክ ደግሞ 60 በመቶ የሚሆነውን ፋይንናንስ አቅርቧል። | https://waltainfo.com/am/23976/ | 230 | 3ቢዝነስ
|
ትናንት ምሽት በአንበሳ አውቶብስ ላይ በደረሰው የመገልበጥ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አረጋገጠ | ሀገር አቀፍ ዜና | September 21, 2019 | Unknown | በትናትናው ምሽት በአንበሳ አውቶብስ ላይ በደረሰው የመገልበጥ አደጋ የ2ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፤ 17 ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ፖሊስ አረጋገጠ።በትናትናው እለት ከፈረንሳይ ለጋሲዮን ተነስቶ ወደ ለገሃር በማምራት ላይ የነበረ 55 ቁጥር አንበሳ አውቶብስ ድልድይ ውስጥ በመግባቱ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉና በ17 ሰዎች ላይም ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አረጋገጠ፡፡የታርጋ ቁጥሩ ኮድ 3 አ.አ 38377 የሆነው አውቶብሱ ከፈረንሳይ ለጋሲዮን ተነስቶ ወደ ለገሃር በማቅናት ላይ ሳለ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን አከባቢ በሚገኝ ድልድይ ወስጥ ነው የገባው፡፡በአደጋው ከሞቱት 2 ሰዎች በተጨማሪ 17 ሰዎች ከባድ ጉዳት፣ 28 ሰዎች ደገሞ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡በሌሎች ሁለት ተሸከርካሪዎችም ላይ ጉዳት መድረሱ ታውቋል፡፡
በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ የሆኑት ምክትል ኢንስፔክተር ተዘራ አብሽር ለዋልታ እንደገለጹት የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ ነው፡፡ተጎጂዎቹ በተለያዩ ሆስፒታሎች እርዳታ እየተደረገላቸው ሲሆን፤ ህክምና ተደርጎላቸው ወደ ቤታቸው የሄዱ እንዳሉም ምክትል ኢንስፔክተር ተዘራ አብሽር ተናግረዋል፡፡ | https://waltainfo.com/am/32748/ | 130 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የኢሬቻ በዓል ሩጫ በሰላም እንዲፈፀም ዝግጅት ማጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ | ሀገር አቀፍ ዜና | September 21, 2019 | Unknown | የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የሚካሄደው ሩጫ በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን አስታወቋል፡፡መስከረም 11 ቀን 2012 ዓ/ም መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ የሚያደርገዉና ከ50 ሺህ ሰው በላይ ይሳተፍበታል ተብሎ የሚጠበቀው “ኢሬቻ ለሰላም” በሚል መሪሃሳብ የሚካሄደው የጎዳና ላይ ሩጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ ዝግጅት ጨርሶ ወደ ሰራ መገባቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ ገልፀዋል፡፡ ኮማንደር ፋሲካ ህብረተሰቡ ከዚህ በፊት የተደረጉ ልዩ ልዩ የአደባባይ ኩነቶች በሰላም እንዲጠናቀቁ በትዕግስት፣ በኢትዮጵያዊ ጨዋነትና በመደጋገፍ ላሳየው ቀና ትብብር የአዲስ አበባ ኮሚሽን ምስጋናውን ያቀርባል ብለዋ፡፡ ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ የ“ኢሬቻ ለሰላም” የጎዳና ላይ ሩጫ ከመስቀል አደባባይ በመነሳት በለገሃር ፣ ቡናና ሻይ ፣ ገነት መብራት፣ ቡልጋሪያ ማዞሪያ ፣ ቄራ ጎተራ ፣ አጎና ሲኒማ ፣ ግሎባል ሆቴል እና በመሿለኪያ አድርጎ ስለሚካሄድ ከዋዜማው ጀምሮ እስከ ሩጫው ፍፃሜ ድረስ በእነዚህ መስመሮች ላይ ለረዥምም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ በፍፁም የተከለከለ በመሆኑ ህብረተሰቡ የትራፊክ ፖሊስ አባላት እና የፀጥታ አካላት የሚሰጡትን ትዕዛዝ በማክበር የተለመደ ትብብር እንዲያርግ ኮሚሽኑ ይጠይቃል ብለዋል፡፡ውድድሩ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ፡- | https://waltainfo.com/am/32747/ | 162 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
14ኛው የብሄረሰቦች ቀን አንድነትን በሚያጠናክር መልኩ በድምቀት ይከበራል ተባለ | ፖለቲካ | September 21, 2019 | Unknown | 14ኛውን የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓል ለውጡን ተከትሎ ያጋጠሙ ሃገራዊ ችግሮችን ለመቅረፍ በሚያስችል መልኩ ለማክበር ዝግጅት በመደረግ ላይ መሆኑ ተገለፀ።በዓሉ አንድነትን በሚያጠናክር መልኩ በድምቀት ይከበራል ያለው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ቅድመ ዝግጀቱን በማስመልከት ከ9ኙ ክልልና ከ2ቱ ከተማ መስተዳድር ምክር ቤት አፈ ጉባኤዎች እና የፌዴራል ተቋማት ተወካዮች ጋር በመምከር ላይ ነው።በዓሉ ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ እየተከበረ እንደሚገኝ ያስታወቁት የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ዘንድሮም ለ14ኛ ጊዜ በኦሮሚያ ክልል አዘጋጅነት በአዲስ አበባ እንደሚከበር መናገራቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።ህገ መንግሥቱ በፀደቀ በ25ኛ ዓመት የሚከበር መሆኑ በዓሉን ልዩ ያደርገዋል ያሉት ወ/ሮ ኬሪያ የብሄር ጥላቻንና መካረርን በማስቀረት ህገ መንግሥቱን ባከበረ መልኩ እንዲከበር ጥሪ አቅርበዋል።አፈ ጉባዔዋ አያይዘውም በአመለካከት ልዩነቶች ሳቢያ በሚፈጠሩ ችግሮች ህዝብ ሰለባ እየሆነ ነው ያሉ ሲሆን በዓሉ ይህንንና መሰል ችግሮችን ለማስቀረት በሚያስችል መልኩ እንደሚከበር ነው ያስታወቁት። | https://waltainfo.com/am/31356/ | 122 | 5ፖለቲካ
|
አሜሪካ ጦሯን ወደ ሳዑዲ ልትልክ መሆኑን አስታወቀች | ፖለቲካ | September 21, 2019 | Unknown | አሜሪካ በሳዑዲ ነዳጅ ማቀነባበሪያ ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ወታደሮቿን ልትልክ መሆኑን አስታወቀች።የመከላከያ ሚኒስቴር ፀሐፊ የሆኑት ማርክ ኤስፐር፤ በሳዑዲ የሚሰማራው ጦር "መከላከል ላይ ያተኮረ" ተልዕኮ ሊሰጠው እንደሚችል ለጋዜጠኞች ጠቁመዋል። ምን ያህል ወታደር እንደሚሰማራ ግን ያሉት ነገር የለም።በኢራን የሚደገፉት የየመን ሁቱ አማፂያን ባለፈው ሳምንት በሳዑዲ ሁለት የነዳጅ ማቀነባበሪያ ላይ ለደረሰው ጥቃት ኃላፊነቱን እንወስዳለን ብለዋል። ሆኖም አሜሪካም ሆነች ሳዑዲ አረቢያ ለጥቃቱ ተጠያቂ ያደረጉት ኢራንን ነው።አርብ ዕለት ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከኢራን ጋር ወታደራዊ እሰጥ አገባ ውስጥ ላለመግባት በሚል "ከፍተኛ የሆነ" ማዕቀብ ሊጣል እንደሚችል ተናግረው እንደነበር የሚታወስ ነው።አዲሱ ማዕቀብ የሚያነጣጥረው የኢራን ማዕከላዊ ባንክንና ሉዓላዊ የሀብት ፈንድን መሆኑን ትራምፕ ተናግረዋል።ሚስተር ኤስፐር መግለጫ የሰጡት የጥምር ጦሩ የበላይ ኃላፊ ከሆኑት ጄነራል ጆሴፍ ደንፎርድ ጁኒየር ጋር ነው።ሳዑዲ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስን ድጋፍ ጠይቀዋል ብለዋል ሚስተር ኤስፐር። የሚላከው ኃይል የአየርና የሚሳኤል መከላከል አቅምን ከፍ ያደርጋል ተብሎ የታቀደ ሲሆን፤ አሜሪካ ደግሞ ለሁለቱ አገራት "ወታደራዊ ቁሳቁስን ማቅረቡን ታፋጥናለች" ብለዋል።ጄነራል ደንፎርድ የወታደራዊ ስምሪቱን "የተለሳለሰ" ያሉ ሲሆን፤ በሺዎች የሚቆጠር እንዳልሆነም አስታውቀዋል። ከዚህ ውጪ ግን ምን ዓይነት ጦር እንደሚሰማራ ፍንጭ አልሰጡም።እንደ ኒውዮርክ ታይምስ ከሆነ፤ ጋዜጠኞች ሚስተር ኤስፐርን ኢራን ላይ የአየር ድብደባ ለማካሄድ ታቅዶ እንደሆነ ሲጠየቁ "በአሁኑ ሰዓት እዚያ ውሳኔ ላይ አልደረስንም" ማለታቸውን ዘግቧል።የሳዑዲ መከላከያ ሚኒስትር፤ በአገሪቱ የነዳጅ ማቀነባበሪያ ተቋማት ላይ ከደረሰው ጥቃት የተሰበሰቡ ናቸው ያላቸውን የድሮን እና የሚሳዔል ስብርባሪዎች በማሳየት "ጥቃቱን ያደረሰችው ኢራን ነች" ሲል ከስሷል።"18 ድሮኖች እና ሰባት ሚሳዔሎች ወደ ሳዑዲ ተተኩሰዋል" ያለው የሳዑዲ መከላከያ፤ የጥቃቶቹ መነሻ የመን አይደለችም ሲል አስረግጦ ይናገራል። (ምንጭ፡-ቢቢሲ) | https://waltainfo.com/am/34003/ | 217 | 5ፖለቲካ
|
ድህነትን ለመቀነስ የሚሰራው የቻይና ግብረሰናይ ድርጅት በኢትዮጵያ ተከፈተ | ሀገር አቀፍ ዜና | September 20, 2019 | Unknown | ‘ቻይና ፋውንዴሽን ፎር ፖቨርቲ አሊቬሽን’ በመባል የሚታወቀው ዓለም አቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅት የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ቢሮ መክፈቱን የተመለከተ መርሃግብር ተካሂዷል።በመርሃግብሩ ላይ በኢትዮጵያ የቻይና መንግሥት ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ታን ጂያን ኢትዮጵያ ድህነትን ለመቀነስና ኢኮኖሚዋን ለማሻሻል ይፋ ያደረገችውን አገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው እውን እንዲሆን የቻይና መንግሥትና ሕዝብ እንደሚደግፉት አስታውቀዋል፡፡ ኢትዮጵያ የዘላቂ ልማት ግብን ለማሳካት የምታደርገውን ጥረትና በቅርቡ ይፋ ያደረገችውን የአገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ ግብር የቻይና መንግሥትና ሕዝብ ለማገዝ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።በፋውንዴሽኑ የኢትዮጵያ ምክትል ፕሬዝዳንት ዋንግ ሺንዙይ በበኩላቸው ፋውንዴሽኑ ባለፉት አራት ዓመታት በኢትዮጵያ ከሚሠሩ አገር በቀልና ዓለም አቀፍ ግብረሰናይ ድርጅቶች ጋር በመተባባር በትምህርት ቤት ምገባ፣ በንጹህ ውሃ አቅርቦትና በሴቶች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ላይ በ74 ሚሊዮን ብር ወጪ 27 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን ተጠቃሚ ማድረጉን ተናግረዋል።‘ቻይና ፋውንዴሽን ፎር ፖቨርቲ አሊቬሽን’ በቀጣይ የዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት ኢትዮጵያ በትምህርት፣ በንጹህ መጠጥ ውሃና ሃይጅን፣ በኢኮኖሚ ዕድገት ያስቀመጠችውን ግብ ዕውን እንዲሆኑ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሠሩ ምክትል ፕሬዝዳንቱ አስረድተዋል።ፋውንዴሽኑ ቢሮውን በኢትዮጵያ መከፈቱን ይፋ ባደረገበት ወቅት ‘ፓንዳ ፓክ’ ብሎ በሰየመው ግብረ ሰናይ መርሐ ግብር 43 ሺህ የደብተር ቦርሳዎች ከትምህርት ቁሳቁሶቹ ጋር ለተለያዩ አገር በቀል ግብረሰናይ ድርጅቶች አስረክቧል።ፋውንዴሽኑ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ በሚያንማር፣ ኔፓል፣ ሱዳን ኡጋንዳ እና ካምቦዲያ ዘላቂ ፕሮጄክቶችን ከፍቶ እየሰራ ነው፡፡ኢትዮጵያና ቻይና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩበትን 50ኛ ዓመት በተያዘው ዓመት ለማክበር በዝግጅት ላይ እንደሚገኙ አምባሳደሩ ጠቁመዋል። የቻይና መንግሥት ባለፉት 50 ዓመታት ከመሠረተ ልማት ግንባታና ከኢንቨስትመንት ትብብር በተጨማሪ በርካታ የሰብዓዊ ልማት ድጋፎችን ለኢትዮጵያ ማድረጉን አስረድተዋል። | https://waltainfo.com/am/32745/ | 209 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
በ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ወደ 11ኛ ክፍል መግቢያ ነጥብ ይፋ ሆነ | ቢዝነስ | September 20, 2019 | Unknown | በ2011ዓ.ም የአጠቃላይ ትምህርት (10ኛ ክፍል) ማጠቃለያ ሀገር አቀፍ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ወደ 11ኛ ክፍል መግቢያ ነጥብ ዛሬ ይፋ መሆኑን የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡በዚህም መሰረት፡-የመደበኛ፣ የማታና የግል ተፈታኝ ተማሪዎች ለወንድ 2.00 እና በላይ ለሴት 1.86 እና በላይ ሆኖ የማታና የግል ተፈታኝ ተማሪዎች በማታው ፕሮግራም ይቀጥላሉ፡፡ለአካል ጉዳተኞች መስማት የተሳናቸው ለወንድ 1.86 እና በላይ ለሴት 1.71 እና በላይ እንዲሁም ለዓይነ ስውራን ለወንድ 1.71 ለሴት 1.61 እንዲሆን ተወስኗል፡፡ልዩ ድጋፍ የሚሹ ክልሎች፣አርብቶ አደር አካባቢዎች እና የፀጥታ ችግር የታየባቸው አካባቢዎች ደግሞ ለወንድ 1.86 ለሴት 1.71 እንዲሆን መወሰኑን ኤጀንሲው ማስታወቁን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡ከዚህ በተጨማሪሁሉም ወደ 11ኛ ክፍል የሚገቡ ተማሪዎች የሚመርጡት የትምህርት መስክ በትምህርትና ሥልጠና ፍኖተ-ካርታው በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት በምርጫ ተፈጥሮ ሳይንስና ማህበራዊ ሳይንስ ብቻ ይሆናል፡፡ከዚህ በፊት የአጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት 10ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና 2.00 ነጥብ እና ከዚያ በላይ ያመጡ በማታው ፕሮግራም የ11ኛ ክፍል ትምህርታቸውን መቀጠል የሚችሉ መሆኑን ኤጀንሲው አስታውቋል፡፡የ2012 የትምህርት ዘመን ትምህርት የሚጀመረው የፊታችን ሰኞ መስከረም 12 ስለሆነ የተማሪ ወላጆች ልጆቻችሁን ወደ ትምህርት ቤት በመላክ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ለማድረግ የድርሻችሁን እንድትወጡ ሲል ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል፡፡ | https://waltainfo.com/am/23973/ | 161 | 3ቢዝነስ
|
በ1.4 ቢሊዮን ብር ወጪ የሚገነባው የአባይ ወንዝ ተለዋጭ ድልድይ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ | ቢዝነስ | September 20, 2019 | Unknown | በባህር ዳር ከተማ የአባይ ወንዝ ላይ ተለዋጭ ድልድይ 1 ቢለዮን 400 ሚሊዮን ብር በሆነ ወጪ ለመገንባት ዛሬ የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል።ድልድዩ 380 ሜትር ርዝመት እና 43 ሜትር ስፋት እንደሚኖረውና ወጪውም በመንግስት የሚሸፈን መሆኑን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ወንድሙ ተናግረዋል።የድልድዩ ግንባታ 3 ዓመታት እንደሚፈጅ እና ስራው የሚከናወነው በቻይናው ሲሲሲሲ ተቋራጭ ድርጅት መሆኑም ተገልጿል።አንድ ቢሊዮን 400 ሚሊዮን ብር ወጪ የሚጠይቀው የድልድዩ ግንባታ ዛሬ ይጀመራል።የባህር ዳር ጭስ አባይ የ22 ኪሎ ሜትር መንገድ ግንባታ ትናንት መጀመሩ በወቅቱ ተገልጿል።(ምንጭ፡-ኢዜአ) | https://waltainfo.com/am/23974/ | 76 | 3ቢዝነስ
|
የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ቅበላ ጊዜ ይፋ ተደረገ | ሀገር አቀፍ ዜና | September 20, 2019 | Unknown | የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ቅበላ ጊዜን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ይፋ አደረገ፡፡ሚኒስቴሩ በ2012 የትምህርት ዘመን በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሠላማዊ የመማር ማስተማር እንዲኖር የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶችን እንዳደረገ መግለጫ ሰጥቷል፡፡በተከለሰው አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት መሠረትም የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች የመጀመሪያ ሴሚስቴር በአራት ቅበላ ዓይነቶች እንደሚሆን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትሯ ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማሪያም በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል፡፡በተፈጥሮ ሳይንስ፣ በተፈጥሮ ሳይንስ በመምህርነት፣ በማህበራዊ ሳይንስና በማህበራዊ ሳይንስ በመምህርነት የቅበላ ክፍል በመምህርነት የተከፈለ ነው ብለዋል፡፡በሁለተኛው ወሰነ ትምህርት ደግሞ የመጀመሪያውን ወሰነ ትምህርት ውጤት መሠረት በማድረግ በአምስት የሙያ መስኮች ማለትም በሕግ፣ ሕክምናና የጥርስ ሕክምና፣ ፋርማሲ፣ የእንስሳት ሕክምና እና ምሕንድስና ናቸው፡፡ሌሎቹ የትምህርት መስኮች ምደባ የሚደረገው ከአንድ ዓመት የትምህርት ቆይታ በኋላ ነው፡፡ በ‹ቪዲዮ ኮንፈረንስ› ዝግጅት ግምገማ በማድረግ የመምህራን ቅጥር እንደሚካሄድም ተጠቅሷል፡፡አዳዲስ ፟ዩኒቨርሲቲዎችም ለተማሪ ቅበላ ዝግጁ እንደሆኑ ተጠቁሟል፡፡ የቅበላው ጊዜም ለነባር ተማሪዎች ከመስከረም 5 እስከ 25 እየተካሄደ ይገኛል፡፡ አዲስ ለሚገቡ ተማሪዎች ከመስከረም 25 እስከ 29 ቅበላው ይካሄዳል ተብሏል፡፡ ጥቅምት 03 ቀን 2012 ዓ.ም ደግሞ ሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርት የሚያስጀምሩ ይሆናል ነው የተባለው፡፡አዲስ ተማሪዎች በክልሉ ወይም በየወረዳው ስለመብቶቻቸውና ግዴታዎቻቸው ስልጠና ይሰጣቸዋል፡፡ ወላጆችና ተማሪዎች በሚፈርሙት ውል መሠረት ወደ ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ፡፡142 ሺህ 943 ተማሪዎችን የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ተቀብለው እንደሚያስተምሩና የሴት ተማሪዎች ብዛት 43 ከመቶ እንደምይዝ ተገልጿል፡፡የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ዝውውር የሚጠይቁት በጤና እክል ምክንያት ብቻ እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡ከተፈጥሮ ሳይንስ ወደ ማኅበራዊ ሳይንስና ከማኅበራዊ ሳይንስ ወደ ተፈጥሮ ሳይንስ ዝውውር ማድረግ ይቻላል፤ ዝውውር ማድረግ የሚቻለው ግን የየመስኮቹን የማለፊያ ውጤት ሲያሟሉ እንደሆነ ሚኒስትሯ ፕሮፌሰር ሂሩት ተናግረዋል፡፡ | https://waltainfo.com/am/32746/ | 215 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
በህዳሴ ግድቡ ዙሪያ ከግብጽ ጋር የተፈጠረው አለመግባባት በግንባታው ሂደት ላይ ተፅዕኖ እንደማይፈጥር ተገለጸ | ቢዝነስ | September 20, 2019 | Unknown | ከሰሞኑ በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ከግብፅ ጋር የተፈተረዉ አለመግባባት በግድቡ ግንባታ ሂደት ላይ ምንም ዓይነት ተፅዕኖ እንደማይፈጥር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ከሰሞኑ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ከግብጽ ጋር የተፈጠረው አለመግባባት በግደቡ ግንባታ ላይ ምንም ዓይነት ተፅዕኖ እንደማይፈጥር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነቢያት ጌታቸው ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል ፡፡ከኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ የተዉጣጣዉ 15 ሳይንቲስቶችን ያካተተዉ ብሔራዊ ገለልተኛ ሳይንሳዊ ቡድን ያቀረበዉን ሃሳብ የሚፃረር አካሄድን ግብፅ እየተከተለች መሆኑ ዛሬ በተሰጠው መግለጫ ተመልክቷል።ግብጽ የያዘችው አቋም የኢትዮጵያን ህልዉና አደጋ ላይ የሚጥል ሆኖ በመገኘቱ አለመግባባት መፈጠሩን አስታውሰው፤ይሁን እንጂ የተፈጠረው አለመግባባት በግድቡ ግንባታ ላይ ምንም ዓይነት ተጽዕኖ የማይፈጥር መሆኑን ገልጸዋል፡፡ኢትዮጵያ የሳይንቲሰቶቹ ቡድን የሚያቀርበዉን ሀሳብ ተቀባይነት እንዲኖረውና ባለፉት 7 ዓመታት በተፋሰሱ ሀገራት መካከል የነበረዉ የትብብርና የጋራ ተጠቃሚነት መንፈስ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ትሻለች ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነብያት ጌታቸው፤ ከግድቡ ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያን ህልውና የሚፈታተኑ የተፋሰሱ ሀገራት አካሄዶች ተቀባይነት አይኖራቸዉም ብለዋል፡፡ኢትዮጵያ የጋራ ተጠቃሚነትን ባማከለና ጥቅሞቿን በጠበቀ መልኩ በአባይ ወንዝ መጠቀሟን ትቀጥላለችም ብለዋል፡፡ቃል አቀባዩ አክለዉም ባሳለፍነዉ ማክሰኞ በተጀመረዉ 74ኛዉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ኢትዮጵያ ንቁ ተሳትፎ እንደምታደርግና ይህም ጥቅሞቿን ባስከበረ መልኩ እንደሚሆን ጠቁመዋል፡፡በተለይም ኢትዮጵያ በዘንድሮዉ ጉባኤ በምክትል ፕሬዝደንትነት መመረጧ ለኢትዮጵያ መልካም አጋጣሚን የሚፈጥር መሆኑን ያነሱት አቶ ነቢያ፤ ጉባኤዉ የኢትዮጵያን ጥቅሞች ያስጠበቀ እንዲሆን ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን አንስተዋል፡፡ | https://waltainfo.com/am/23972/ | 189 | 3ቢዝነስ
|
የቀድሞው የቱኒዚያ ፕሬዚዳንት አብዲን ቢን አሊ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ | ሀገር አቀፍ ዜና | September 20, 2019 | Unknown | የቀድሞው የቱኒዚያ ፕሬዚዳንት ዚን ኢል አብዲን ቢን አሊ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡የቀድሞው ፕሬዚዳንት በ83 ዓመታቸው በስደት እየኖሩ ባሉበት ሳዑዲ አረቢያ ነው ህይወታቸው ያለፈው፡፡ቱኒዚያን ለ23 ዓመታት የመሩት ቢን አሊ ሀገሪቱ እንድትረጋጋ እና እንድትበለጽግ አድርገዋል ተብለው በብዙዎች ይነገርላቸዋል፡፡በአውሮፓውያኑ 2011 በሀገሪቱ የተነሳው ህዝባዊ አመፅ በአረብ ሀገራት ሁሉ ተቀጣጥሎ ለእርሳቸውና ለሌሎች የአረብ ሀገራት ባለስልጣናት የስልጣን ማክተሚያ ምክንያት እንደነበር ቢቢሲ ዘግቧል፡፡የቢን አሊ የቀብር ስነስርዓት በሳዑዲ አረቢያ እንደሚፈፀም ጠበቃቸው ለሮይተርስ የዜና ወኪል ተናግሯል፡፡ | https://waltainfo.com/am/33476/ | 67 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የባሕር ዳር – ዘማ ወንዝ – ፈለገ ብርሃን የአስፓልት ኮንክሪት መንገድ ተመረቀ | ቢዝነስ | September 19, 2019 | Unknown | የባሕር ዳር – ዘማ ወንዝ – ፈለገ ብርሃን የአስፓልት ኮንክሪት መንገድ ተመረቀ።የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ያስገነባው የባሕር ዳር- ዘማ ወንዝ- ፈለገ ብርሃን የአስፓልት ኮንክሪት መንገድ ዛሬ ተመርቋል፡፡የባሕር ዳር- ዘማ ወንዝ- ፈለገ ብርሃን የአስፓልት ኮንክሪት መንገድ የጥራት ችግሮች እንዳሉበት የክልሉ የስራ ሃላፊዎች በቢቸና ከህዝብ ጋር ባደረጉት ውይይት ወቅት ተገልጿል።የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን በነዋሪዎች የቀረበውን ቅሬታ ተቀብሎ መንገዱ ላይ ያሉ ጉድለቶችን እንደሚርም አስታውቋል፡፡ዛሬ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት የሆነው መንገድ ከባሕር ዳር – አዲስ አበባ በደብረ ማርቆስ በኩል የሚደረገውን ጉዞ በ80 ኪሎ ሜትር የሚያሳጥር መሆኑ የተነገረ ሲሆን፤ መንገዱ በኢኮኖሚ እና በማኅበራዊ ትስስር ረገድ ከፍተኛ ፋይዳ እንደሚኖረው ታስቦ የተገነባና 175 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው መሆኑ ታውቋል፡፡ የአማራ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገበው፤ አጠቃላይ የግንባታ ወጭውም 2 ቢሊዮን ብር ነው፡፡በጎንጃ ሲሶ እነሴ ወረዳ የግንደ ወይን ከተማ ነዋሪው አቶ ጌትነት አየለ ‹‹የመንገዱ መጠናቀቅ የረዥም ጊዜ ጥያቄያችን ነበር፤ ወረዳው በስፋት የስንዴ እና የአትክልትና ፍራፍሬ አምራች በመሆኑ በሁልም አቅጣጫ ከገበያ ጋር እንዲተሳሰር ያደርገዋል›› ብለዋል። | https://waltainfo.com/am/23970/ | 141 | 3ቢዝነስ
|
አረጋውያንን መንከባከብ የሁሉም ኃላፊነት ሊሆን እንደሚገባ ተገለጸ | ሀገር አቀፍ ዜና | September 19, 2019 | Unknown | አረጋውያንን መንከባከብና መርዳት በችሮታ የሚደረግ ሳይሆን የሁሉም ዜጎች ኃላፊነት መሆን እንደሚገባው የኢፌዴሪ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ዴኤታ ወ/ሮ አየለች እሸቴ በዓሉን አስመልክተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በዓሉ ኢትዮጵያዊን ቀድሞ የነበራቸዉን ፍቅር፣ መቻቻል፣ መከባበርና መደጋገፍን ለማጎልበት የላቀ ድርሻ እንደሚኖረው ተናግረዋል፡፡ቀኑ "የዕድሜ ባለጸጎችን በመደገፍ እንመረቅ" በሚል መሪ ቃል ከመስከረም 18–20/ 2012 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል፡፡ የአረጋውያን ቀን በሚከበርባቸው ቀናት በተለይ በአዲስ አበባ ለአረጋውያኑ የተለያዩ ድጋፎችን በማሰባሰብ ከ10ሺህ በላይ አረጋውያንን ተጠቃሚ ለማድረግ መታቀዱን ሚኒስትር ዴኤታዋ ተናግረዋል፡፡ ከማኅበረሰቡ ባሻገር የበጎ አድራጎት ማኅበራትን በማሳተፍ ንቅናቄውን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራትም ይከናወናሉ ተብሏል፡፡ | https://waltainfo.com/am/32742/ | 92 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የዩኒቨርሲቲዎች የመማር ማስተማር ስራ ሰላማዊና ውጤታማ ለማድረግ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታወቀ | ሀገር አቀፍ ዜና | September 20, 2019 | Unknown | የዩኒቨርሲቲዎች የ2012 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ስራ ሰላማዊ እና ውጤታማ ለማድረግ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም ከሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ፕሬዝዳንቶችና ምክትል ፕሬዝዳንቶች፣ ከተማሪዎች አገልግሎት ሃላፊዎች፣ እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው የስራ ሃላፊዎች ጋር በ2012 የትምህርት ዘመን የዝግጅት ምዕራፍ አፈጻጸም ላይ የቀጥታ ቪዲዮ ኮንፈረንሲንግ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ውይይት አካሂደዋል፡፡የተማሪዎች ቅበላና የቅበላ ዝግጅቶችን፣ የቅበላ አይነቶችን፣ የተማሪዎች ምደባና ዝውውርን፣ ስልጠናዊ ውይይትን፣ የአዳዲስ የትምህርት ፕሮግራሞች አካሄድን፣ ልዩ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ዳሰሳ፣ የተለያዩ በ2012 ተግባራዊ የሚደረጉ ህጎች እና እንዲሁም የአሰራር ድጋፍና ክትትሎችን አጀንዳ ዎች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡በውይይታቸው ላይም ዩኒቨርስቲዎች የ2012 የትምህርት ዘመን የዝግጅት ምዕራፍን በማጠናቀቅ ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጁ መሆናቸው ተገልጾላቸዋል፡፡የመማር መስተማር ስራውን ሰላማዊና ውጤታማ ለማድረግ ሁሉም ተቋማት ሃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ሚኒስትሯ አሳስበዋል፡፡ (ምንጭ:- የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር) | https://waltainfo.com/am/32743/ | 119 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ተመድ ለላሙ ፕሮጀክት ስኬት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተገለጸ | ቢዝነስ | September 20, 2019 | Unknown | የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ጽህፈት ቤት የላሙ ፕሮጀክት እውን እንዲሆን አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገለፀ።በላሙ ወደብ ፕሮጀክት የአዲስ አጋርነት ለአፍሪካ ልማት (ኔፓድ)፣ ፅህፈት ቤት የኬንያ መንግስት ተወካዮች፣ በኬንያ ኤምባሲ እና የመንግስታቱ ድርጀት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ፅህፈት ቤት ተወካዮች ውይይት አካሂደዋል፡፡በትናንትናው እለት በናይሮቢ በተካሄደው በዚህ ውይይት የላሙ ፕሮጀክት በአፍሪካ መሪዎች የአህጉሩን ውህደት ያፋጥናሉ ተብለው ከሚጠበቁ አስር ግዙፍ ቀጠናዊ ፕሮጀክቶች መካከል አንደኛው መሆኑ ተገልጿል።የመንግስታቱ ድርጅት የኢኮኖሚክ ኮሚሽን ተወካይ አዴይንካ አዴዬሚ ፕሮጀክቱ ኢኮኖሚያዊ ልማትን ከማረጋገጥ ባሻገር ቀጠናዊ ሰላምን ለማምጣት እንደሚያግዝ ተናግረዋል።የፕሮጀክቱ ባለቤቶች የሆኑት ኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ደቡብ ሱዳን ለስራዎቹ መጠናቀቅ ተቋማዊ አቅማቸውን ማጠናከር እና ከልማት አጋሮች ጋር በጋራ መስራት እንደሚጠበቅባቸው አንስተዋል።በኬንያ የኢፌዴሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር መለስ ዓለም በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ የተጎራባች ሕዝቦችን በማስተሳሰር የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ለማምጣት የሚዘረጋውን የላሙ ፕሮጀክት እውን እንዲሆን ከኬንያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኔፓድ እና የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽንን ከመሳሰሉ ድጋፍ ሰጪ ተቋማት ጋር ተባብራ ትሰራለች ብለዋል።የላሙ ወደብ ብሮጀክት የቀጠናውን ብቻ ሳይሆን የአህጉሩ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ትስስሮሽ ላይ አዎንታዊ ለውጥ ማምጣትን ራዕዩ አድርጎ የሚገነባ ፕሮጀክት መሆኑንም ጠቅሰዋል።ፕሮጀክቱ የአካባቢውን አጎራባች አርብቶ አደር ማህበረሰብ ኑሮ በዘላቂነት የሚለውጥ በመሆኑ ግጭቶችን ለማስወገድ እንደሚረዳ መግለፃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡የላሙ ፕሮጀክት አካል የሆነው አንደኛው የመርከቦች ማቆያ በቅርቡ ይመረቃል ተብሎ ይጠበቃል። | https://waltainfo.com/am/23971/ | 188 | 3ቢዝነስ
|
የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤ ምክክር በባሕር ዳር እየተካሄደ ነው | ሀገር አቀፍ ዜና | September 20, 2019 | Unknown | የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤ በክልሉ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሚመክር ዓለም አቀፍ የምክክር መድረክ በባሕር ዳር ማካሄድ ጀምሯል፡፡ጉባኤው የአማራ ሕዝብ የፍትሕ፣ የሠላም እና የነፃነት ተጠቃሚነት ለኢትዮጵያ አንድነት በሚፈጥርባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው፡፡የአማራ ሕዝብ በሚያነሳቸው ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ምክክሩ ትኩረት እንደሚያደርግ የታወቀ ሲሆን፤ ለሁለት ቀናትም ይቆያል፡፡በውይይቱ 1 ሺህ 800 ምሁራንና ከ700 በላይ ተጋባዥ እንግዶች እንደሚገኙ ታውቋል፡፡ለውይይቱ መነሻ የሚሆኑ አራት ጥናታዊ ጽሑፎችም ቀርበው ውይይት እየተካሄደባቸው ይገኛል፡፡በውይይቱ የተለዩ ችግሮችን ለመፍታት በቀጣይ እስከ ቀበሌ ድረስ ከሚገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት እንደሚደረግ አብመድ ነው የዘገበው፡፡ | https://waltainfo.com/am/32744/ | 83 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ግማሽ ቢሊዮን ብር ወጭ የሚደረግበት የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ግንባታ በባሕር ዳር ተጀመረ | ቢዝነስ | September 19, 2019 | Unknown | ግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ወጭ የሚደረግበት የንጹሕ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ግንባታ ዛሬ በባሕር ዳር ከተማ ተጀምሯል፡፡በዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ ክፍለ ከተማ የሚገነባው የንጹሕ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት 23 ሺህ ሜትር ኩብ /ከ30 ሺህ ሊትር/ በላይ የንጹሕ መጠጥ ውኃ በቀን ያመነጫል፡፡ፕሮጀክቱ የከተማውን የንጹሕ መጠጥ ውኃ አቅርቦት ሽፋን አሁን ካለበት 60 በመቶ ወደ 80 በመቶ ያሳድጋል የተባለው ሲሆን ፤ የከርሰ ምድር ውኃ ማበልጸግን፣ የውኃ ማጠራቀሚያ ታንከሮችን መገንባትንና ማስተላለፊያ መስመሮችን መዘርጋትን ያካትታል፡፡የግንባታ ወጪው ከጃፓን መንግሥት በተገኘ ድጋፍ ነው የሚሸፈነው፡፡ የጃፓኑ ‹ኮኖኬ› ተቋራጭ ግንባታውን ያከናውናል፡፡የአማራ ክልል ውኃ መስኖና ኢነርጂ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ይመር ሀብቴ ግንባታው በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት እንደሚጠናቀቅ ተናግረዋል፡፡ለጋሽ ሀገራት የንጹሕ መጠጥ ውኃ ተደራሽነትን እያገዙ መሆኑን ያመለከቱት ምክትል ቢሮ ኃላፊው፤ 20 ከተሞችን እና 90 ወረዳዎችን ሊያግዝ የሚችል የአምስት ዓመት መርሀ ግብር ከዚህ ወር ጀምሮ ወደ ሥራ እንደሚገባም ነው ያስታወቁት፡፡መርሀ ግብሩም በዓለም ባንክ፣ በአፍሪካ ልማት ባንክ፣ በዩኒሴፍ፣ በኮሪያ እና በፊንላንድ መንግሥት ትብብር የሚደገፍ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ዓለምነህ ታደሰ በበኩላቸው ፤ በሁለተኛው የዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዘመን ማብቂያ አንድ ሰው በቀን 80 ሊትር ውኃ እንዲቀርብለት ቢታቀድም በቅርቡ በተሠራው ጥናት መሠረት 50 ሊትር ብቻ ነው እየቀረበ ያለው፡፡ ይህም የውኃ አቅርቦት ችግር እንዳለ አመላካች ነው ብለዋል፡፡ዛሬ በይፋ ሥራው የተጀመረው የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር የንጹሕ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት የከተማውን የመጠጥ ውኃ አቅርቦት እንደሚያሻሽለው የገለጹት ምክትል ከንቲባው ፤ ከተማ አስተዳድሩ በግንባታ ሂደቱ የሚያስፈልጉ ነገሮችን ለማሟላት ዝግጁ መሆኑን አንስተዋል፡፡በኢትዮጵያ የጃፓን ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጄንሲ ተወካይ ሃሩካ ናካጋዋ ኤጄንሲው ኢትዮጵያን በግብርናው ዘርፍ፣ በግል ኢንቨስትመንት፣ በመሠረተ ልማት፣ በንጹሕ የመጠጥ ውኃ እና የኃይል አቅርቦት ዘርፎች ሀገራቸው እያገዘች መሆኑን መናገራቸውን አብመድ ዘግቧል፡፡ | https://waltainfo.com/am/23969/ | 241 | 3ቢዝነስ
|
ምክር ቤቱ የክልሉን የኢንቨስትመንት መተዳደሪያ ደንብን ለማሻሻል የቀረበውን አዋጅ አፀደቀ | ቢዝነስ | September 19, 2019 | Unknown | የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት በትላንትናው ዕለት ባካሄደው አምስተኛ የሥራ ዘመን አምስተኛ መደበኛ ጉባዔ የክልሉ የኢንቨስትመንት መተዳደሪያ ደንብን ለማሻሻል በቀረበው አዋጅ ላይ በመምከር አፀደቀ።ደንቡን ማሻሻል ያስፈለገበት ምክንያት ኢንቨስትመንትን የክልሉን ልማት መደገፍ እና ሕዝቡን ተጠቃሚ ማድረግ የሚችልበት ደረጃ ላይ ለማድረስ እንዲሁም ኢንቨስትመንት በክልሉ ኢኮኖሚ ውስጥ ያለውን ሚና ለማሳደግ እንደሆነ ተገልጿል።ተሻሽሎ የሚቀርበው ደንብ በተለይ አርሶ አደሩ በኢንቨስትመንት ምክንያት ካሳ ተከፍሎት ከመሬቱ ላይ የሚሸኝበት ብቻ ሳይሆን በመሬቱ ላይ የሚካሄድ ኢንቨስትመንት ውስጥ ድርሻ ኖሮት ተጠቃሚ እንዲሆን ሁኔታዎችን የሚያመቻች ነው ተብሏል።ግንባር ቀደም የሆኑ አርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች እንዲሁም የጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት ወደ ኢንቨስትመንት ልማት እንዲገቡ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ላይ ያተኮረ መሆኑም ተነግሯል።ደንቡ በክልሉ ውስጥ የሚካሄድ ኢንቨስትመንት የሥራ ዕድል በመፍጠር የኅብረተሰቡን ተጠቃሚነት በማረጋገጡ ረገድ የራሱን ሚና እንዲኖረውም ያደርጋል።በሌላ በኩል ከዚህ በፊት በነበረው የኢንቨስትመንት መተዳደሪያ ደንብ ላይ ሲታዩ የነበሩትን ጉድለቶች ከመሠረቱ በመቅረፍ ለኢንቨስትመንት የሚውሉ መሬቶች ውጤታማ በሆነ መልኩ ጥቅም ላይ እንዲውሉ በማድረግ ላይም ትኩረት ተሰጥቷል።ጎታታ የነበረውን የኢንቨስትመንት ፈቃድ አሰጣጥ ሂደትን በመሻሻል እና ፈጣን የሆነ አገልግሎት በመስጠትም ኢንቨስትመንትን ወደ ክልሉ የመሳብ እና ኅብረተሰቡ በኢንቨስትመንት ውስጥ ያለው ተሳትፎን እንዲያሻሽል ለማድረግም ደንቡን ማሻሻል ማስፈለጉ ነው የተጠቆመው።በዚሁ መሠረት የክልሉን የኢንቨስትመንት መተዳደሪያ ደንብ ለማሻሻል የቀረበው አዋጅ፣ አዋጅ ቁ. 208/2012 ሆኖ እንዲፀድቅ ምክር ቤቱ በሙሉ ድምፅ ወስኗል። (ምንጭ፦ የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት) | https://waltainfo.com/am/23966/ | 190 | 3ቢዝነስ
|
ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ከፈረንሳዩ የባህል ሚንስትር ፍራንክ ራይስተር ጋር ተወያዩ | ሀገር አቀፍ ዜና | September 19, 2019 | Unknown | ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ከፈረንሳዩ የባህል ሚንስትር ፍራንክ ራይስተር ተወያዩጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ በፈረንሳይ መንግስት ድጋፍ እየተካሄዱ ያሉት የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትና የኢዩቤልዩ ቤተመንግስት እድሳት ዙሪያ ከፈረንሳዩ የባህል ሚንስትር ፍራንክ ራይስተር ጋር ተገናኝተው ተወያዩ::የኢትዮጵያና የፈረንሳይን ጠንካራ ግንኙነትና የፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮንን ጥልቅ የትብብር ፍቃደኝነት ያነሱት ጠ/ሚር ዐቢይ እድሳቱን ማፋጠን እንዲቻል አበረታትተዋል::ራይስተር በበኩላቸው የዛሬው ጉብኝታቸው ፕሬዝዳንት ማክሮን ለሁለቱም ሀገራት የሚበጅ የቅርስ ጥበቃ ላይ ለመተባበር ያላቸውን ፍቃደኝነት ማሳያ ነው በማለት የቴክኒክና የልምድ ልውውጥም ለማድረግ ይረዳልም ብለዋል::የኢዩቤልዩ ቤተመንግስትን እድሳት በተመለከተ አስፈላጊው ጥናት እየተጠናቀቀ ሲሆን፤ እድሳቱ በጥቂት ወራት ውስጥ ተጀምሮ በፍጥነት ለቱሪስት ጉብኝት የሚከፈት ይሆናል ተብሏል::የቱሪዝም ዘርፍን ማጎልበት የኢትዮጵያ መንግሥት ለሥራ ፈጠራና ኢንቨስትመንት ለመሳብ ከሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ዋነኛው መሆኑንና ለዚህም የቅርስ ጥበቃና ክብካቤ ቅድሚያ የሚሰጠው የዘርፉ አካል መደረጉን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። | https://waltainfo.com/am/32740/ | 116 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ አካላትና ተቋማት ላይ እርምጃ ተወሰደ | ቢዝነስ | September 19, 2019 | Unknown | በመሰረታዊ ሸቀጦች ላይ ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ አካላትና ተቋማት ላይ እርምጃ መውሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ገለፀ፡፡ቢሮው ጉዳዩን አስመልክቶ በዛሬው ዕለት በሰጠው መግለጫ በከተማዋ የተለያዩ ህገወጥ አሰራሮችን በመጠቀም የመሰረታዊ ሸቀጦች ዋጋ እንዲጨምር ባደረጉ የንግድ ተቋማት ላይ ፍተሻ ማድረጉን አስታውቋል። የኮንትሮባንድ ንግድ ፣ ህጋዊ መስመርን ሳይከተሉና ደረሰኝ ሳይቆርጡ ግብይት መፈፀም ፣የአቅርቦትና ፍላጎት አለመጣጣም ፣ጥራት የሌላቸው ምርቶች ወደ ገበያው ማስገባት አና የህገ ወጥ ደላሎች መበራከት ለሸቀጦች ዋጋ መናር መንስኤ መሆናቸውን ነው የከተማዋ የንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሃላፊና የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ ኢንጂነር እንዳወቅ አብቴ የተናገሩት።ቢሮው ይህን ተከትሎ በመሰረታዊ ሸቀጦች ላይ ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ የኑሮ ውድነት እንዲባባስ ባደረጉ አካላትና ተቋማት ላይ እርምጃ መውሰዱን ገልጿል፡፡በአጠቃላይ በ5 ሺህ 700 የንግድ ተቋማት ላይ ፍተሻ ተካሂዶ ከእነዚህ ውስጥ 609ኙ ሲታሸጉ ከ2 ሺህ በላይ ለሚሆኑትም ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል፡፡እርምጃ ከተወሰደባቸው መካከል 91 ወፍጮ ቤቶች፣ 93 ዳቦ ቤቶች፣ 56 አትክልት ቤቶችና 63 ስጋ ቤቶች ይገኙበታል፡፡በቀጣይም ህጋዊ መስመር ተከትሎ የሚሰራውን ነጋዴ ማበረታታት እና ህጉን ጠብቆ እንዲሰራ ማድረግ ላይ በትኩረት ይሰራል ብሏል፡፡የአቅርቦትና ፍላጎት ክፍተቱን ለመሙላትም ቢሮው ከሌሎች ተቋማት ጋር በቅንጅት እየሠራ እንደሚገኝም ነው የተገለፀው፡፡ለአብነትም የአቅርቦት ማሻሻያ ከማድረግ ጀምሮ 30 ሺህ ኩንታል የጤፍ ምርትን ለማዳረስ እየተሰራ እንደሚገኝ ተነስቷል፡፡ቀደም ሲል በሀገሪቱ ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪን ለመቆጣጠር የተቋቋመው ኮሚቴ ስራውን በባለቤትነት እየሰራ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፤ በቀጣይም ህጋዊ እርምጃዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ተብሏል፡፡ | https://waltainfo.com/am/23967/ | 200 | 3ቢዝነስ
|
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ርዕሰ መስተዳድሩ ከብቸና ነዋሪዎች ጋር እየተወያዩ ነው | ቢዝነስ | September 19, 2019 | Unknown | የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተመስገን ጥሩነህ እንዲሁም ሌሎች የፌዴራል እና የክልል የሥራ ኃላፊዎች ብቸና ከተማ ላይ ከሕዝቡ ጋር እየተወያዩ ነው፡፡በወቅታዊ ጉዳዮች እና ዛሬ የሚመረቀውን መንገድ በተመለከተ እየተወያዩ ሲሆን፣ በውይይታቸውም ኅብረተሰቡ መንገዱ የጥራት ችግር እንዳለበት ጥያቄ አቅርቧል፡፡የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የጥራት ችግሩን በተመለከተ የቀረበውን ሀሳብ ተቀብሎ በሥራ ተቋራጩ ወይም በሌላ መንገድ እንዲስተካከል እንደሚደረግም አስታውቋል፡፡ከባሕር ዳር- ዘማ ወንዝ- ፈለገ ብርሃን የሚዘልቀው የአስፓልት ኮንክሪት መንገድ ከደጀን- ሞጣ- ባሕር ዳር ያለውን አካባቢ ያስተሳስራል፡፡ ከባሕር ዳር – አዲስ አበባ በደብረ ማርቆስ በኩል የሚደረገውን ጉዞ በ80 ኪሎ ሜትር እንደሚያሳጥርም ባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡መንገዱ በኢኮኖሚ እና በማኅበራዊ ትስስር ከፍተኛ ፋይዳ እንደሚኖረው ታስቦ እንደተገነባ ተገልጿል፡፡265 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው መንገዱ ከውይይቱ በኋላ እንደሚመረቅ ይጠበቃል፡፡ ለሥራው 2 ቢሊዮን ብር አካባቢ ወጪ እንደተደረገበት በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ወንድሙ ለአብመድ ገልጸዋል፡፡የመንገዱ ግንባታ በ2005 ዓ.ም የተጀመረና የዲዛይን እና የጥራት ችግር ጥያቄዎች ይነሱበት ስለነበረም ማስተካከያ ለማድረግ በሚል በሥራው ላይ መጓተት ታይቶ ነበር፡፡
ዋና ዋና ሥራዎች መጠናቀቃቸውን፤ ሞጣ ከተማ ላይ 500 ሜትር የሚሆን የመንገዱ ግንባታ ክፍል እንደሚቀርና ይህንን ጨምሮ ሌሎች ማስተካከያዎች እንደሚከናወኑ አቶ ሳምሶን ተናግረዋል፡፡ቀሪ የግንባታ እና የማስተካከያ ሥራዎች በባለሥልጣኑ እንደሚጠናቀቁ ታሳቢ ተደርጎ ከባሕር ዳር- ዘማ ወንዝ- ፈለገ ብርሃን የሚዘልቀው የአስፓልት ኮንክሪት መንገድ ዛሬ እንደሚመረቅ ይጠበቃል፡፡ | https://waltainfo.com/am/23968/ | 187 | 3ቢዝነስ
|
ግምቱ ከ19 ሚሊዮን ብር በላይ የሚሆን አደንዛዥ ዕፅ ተያዘ | ሀገር አቀፍ ዜና | September 19, 2019 | Unknown | ግምቱ ከ19 ሚሊየን ብር በላይ የሚሆን አደንዛዥ ዕፅ ተያዘ።
በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ጉምሩክ በኩል ሊያልፍ ሲል ግምቱ ከ19 ሚሊየን ብር በላይ የሚሆን አደንዛዥ ዕፅ መያዙን የገቢዎች ሚኒስትር አስታወቀ።በቦልቪያናዊዉ ናማኒ ቺንቼ ኢቬሊን የፓስፖርት ቁጥር AE57255 ከብራዚል ሳዖ ፖሎ አዲስ አበባ የገባዉ 8 ኪሎ ግራም የኮኬይን አደንዛዥ ዕፅ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የጉምሩክ ፈታሾች በቁጥጥር ስር እንዲውል መደረጉ ተነግሯል።አደንዛዥ እጹ የተያዘው ከብራዚል ሳኦ ፖሎ ጀምሮ በጉምሩክ ኮሚሽን ኢንተለጀንስ ቡድን ባደረገዉ የተቀናጀና ጠንካራ ክትትል መሆኑ የተነገረ ሲሆን፤ ባለፈዉ ሳምንትም 20 ሚሊየን ብር የሚገመት 10.8ኪ.ግ የሚመዝን አደንዛዥ ዕፅ መያዙ የሚታወስ ነዉ፡፡ | https://waltainfo.com/am/32741/ | 90 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
3 የከፍተኛ ደረጃ የማዕድን ማምረት ፈቃዶች ተሰጡ | ቢዝነስ | September 18, 2019 | Unknown | የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር በተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች የማዕድናት ፍለጋ ለማካሄድ ፈቃድ ለጠየቀውና የፈቃድ መውሰጃ መስፈርቶችን አሟልቶ ለቀረበው አባይ ኢንደስትሪ ልማት አክሲዮን ማኅበር 3 የከፍተኛ ደረጃ ማዕድን ማምረት ፈቃድ ሰጥቷል፡፡ስምምነቱን በፈቃድ ሰጪው መስሪያ ቤት በኩል የፈረሙት ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ሚኒስትር ሲሆኑ፤ በባለፈቃዶቹ በኩል ደግሞ የፈቃድ ወሳጅ ኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ናቸው፡፡ኩባንያው ፈቃድ ያገኘው በአማራ ክልላዊ መንግስት የተለያዩ አካባቢዎች ሲሆን የከፍተኛ ደረጃ ሸክላ አፈር፣ የከፍተኛ ደረጃ ላይም ስቶን ማዕድን እንዲሁም የከፍተኛ ደረጃ የጅፕሰም ማዕድን ያመርታል፡፡ኩባንያው ለኢንቨስትመንት ወጪ በአጠቃላይ 140,712,881.00 ( አንድ መቶ አርባ ሚሊዮን ሰባት መቶ አስራ ሁለት ሽህ ስምንት መቶ ሰማኒያ አንድ) ብር መድቧል ተብሏል፡፡ ባለፈቃዱ በምርት ወቅት በድምሩ ለ114 ኢትዮጵያዊያን የስራ ዕድልእንደሚፈጥር የተገለጸ ሲሆን፤ በውጭ ምንዛሪ ግኝትና ማዳንም አስተዋፅኦ ያበረክታል፡፡የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ኢትዮጵያ ለወጠነችው የኢንዱስትሪያዊነት መዋቅራዊ ሽግግር የኢንዱስትሪ ዘርፉ የሚፈልገውን የማዕድናት ግብዓት ለሟሟላት በሁሉም ዓይነት የዘርፉ ሃብቶቻችን ላይ በስፋት እየሰራ ይገኛል፡፡የሃገር ውስጥ ባለሃብቶች በዘርፉ እንዲሰማሩ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ሲሆን ፍላጎቱ ያላችሁ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን መዋዕለ ነዋያችሁን እያደገ በመጣው የማዕድኑ ዘርፍ ላይ እንድታውሉ እንጋብዛለን፡፡የማዕድን ዘርፉ የሚጠበቅበትን ሚና እንዲወጣም ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትብብር እንዲሰሩና ኩባንያዎች ፈቃድ ወስደው በሚሰራባቸው አካባቢዎች የአካባቢው ህብረተሰብ እና መንግስት አስፈላጊውን ትብርርና ድጋፍ ሁሉ እንዲያደረጉላቸው ጥሪያችን እናቀርባለን፡፡የአካካቢ ጥበቃን በተመለከተ የሠራተኞቹን፣ የአካባቢውን ማህበረሰብ ጤንነትና ደህንነት በማይጎዳና ብክለት በማያስከትል መልኩ የምርት ስራውን ለማከናወን ኩባንያው ውል የፈፀመ ሲሆን ሥራውን ሲያቋርጥ በተፈጥሮ አካባቢ ላይ፣ በሰው ህይወትና ንብረት እንዲሁም ዕፅዋት ላይ ጉዳት ሊያስከትሉ የሚችሉ ማናቸውም ቅሪቶችና ግንባታዎችን ያስወግዳል። (ምንጭ፡-የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር) | https://waltainfo.com/am/23965/ | 219 | 3ቢዝነስ
|
የዘንድሮ ኢሬቻ በዓልን ለማክበር ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለጸ | ሀገር አቀፍ ዜና | September 18, 2019 | Unknown | የ2012 ዓ.ም የኢሬቻ በዓልን ለማክበር ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የኦሮሚያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ፡፡ቢሮ በዛሬው ዕለት ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው; በመስከረም 24፤ 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከአንድ ምዕተ አመት በኋላ የሚከበረውን የሆራ ፊንፊኔ እና በማግስቱ መስከረም 25 በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ የሚከበረው የኢሬቻ በዓል ባህላዊና ትክክለኛ እሴቱን ጠብቆ እንደሚከበርተገልጿልl፡፡በተለይም በመስከረም 24፤2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ የሚከበረው ኢሬቻ ፊንፊኔ ለከተማው ነዋሪዎች ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ የሚሰጥና ኢሬቻን እንደ ገዳ ስርዓት ሁሉ በዩኒስኮ ለማስመዝገብ የሚደረገው ጥረት ስኬታማ እንዲሆን ትክክለኛና ባህላዊ እሴቱ ተጠብቆ እንዲከበር ይደረጋልም ተብሏል፡፡በበዓሉ አከባበርም ኢሬቻን ለሰላም የሚል ታላቅ ሩጫን ጨምሮ የኢሬቻ ፎረም፣ እግዝቪሽንና የኦሮሞ ህዝብ የተለያዩ ባህላዊ ትርዕቶች ለማቅረብ ዝግጅት መጠናቀቁ በመግለጫው ተገልጿል፡፡በበዓሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ እንደሚሆኑ ይጠበቃል፡፡ | https://waltainfo.com/am/32738/ | 109 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጽሕፈት ቤት የተገነቡ ስድስት ት/ቤቶች በ2012 ዓ.ም ስራ ይጀምራሉ | ሀገር አቀፍ ዜና | September 19, 2019 | Unknown | በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጽሕፈት ቤት አማካኝነት ከሚገነቡት ትምህርት ቤቶች ስድስቱ ለ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ዝግጁ እንደሆኑ ታውቋል፡፡የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን ፈንታ ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት እንደገለጹት፤ ከትምህርት ቤቶቹ መካከል አራቱ ለማስተማር ዝግጁ ሆነዋል፡፡ከአራቱ ትምህርት ቤቶች በተጨማሪ አዲስ አበባ ላይ ቁስቋም ትምህርት ቤት በሚል የተሠራው ፕሮጀክት ግንባታው መጠናቀቁን እና ትምህርት ቤቱ ተቀይሮ ለሕጻናት ማሳደጊያ እንዲሆን መወሰኑን አቶ ሙሉቀን ተናግረዋል፡፡ ሰበታ ላይ የሚታደሰው የዐይነ ስውራን ትምህርት ቤትም ሥራው ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆኗል ፡፡ለማስተማር ዝግጁ ከሆኑት መካከል በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ አስተዳድር ላይ የሚገኘው የሎዛ ማርያም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንደሚገኝበት አቶ ሙሉቀን ተናግረዋል፡፡ ከሎዛ ማርያም ትምህርት ቤት በተጨማሪ በኦሮሚያ ክልል የሚገኙት የሊበን ጭቋላ፣ የጉጂ እና የጃኮ ትምህርት ቤቶችም ለማስተማር ዝግጁ የተደረጉ ናቸው፡፡ የሎዛ ማርያም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመንገድ ችግር ምክንያት ሙሉ ለሙሉ ሥራው ባይጠናቀቅም ለሥራ ዝግጁ እንደሆነ ነው የገለፁት፡፡ ለመማር ማስተማር ሥራው ምቹ ክፍሎች እንደተዘጋጁ እና ቀሪ ሥራዎች ከትምህርቱ ጎን ለጎን እንደሚሠሩም ገልፀዋል፡፡በመሆኑም በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጽሕፈት ቤት ከሚገነቡት አዳዲስ 19 ትምህርት ቤቶች እና አንድ የዐይነ ስውራን ትምህርት ቤት እድሳት ውስጥ ስድስቱ ወደ ሥራ ይገባሉ፡፡ቀሪዎቹ ደግሞ በ2012 ዓ.ም ሙሉ ለሙሉ ግንባታቸው ተጠናቅቆ በ2013 የትምህርት ዘመን ወደ ሥራ እንደሚገቡ ተገልጿል፡፡
| https://waltainfo.com/am/32739/ | 183 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ግብፅ በህዳሴዉ ግድብ ዙሪያ ያቀረበችዉን ሃሳብ ኢትዮጵያ ዉድቅ አደረገች | ፖለቲካ | September 19, 2019 | Unknown | የዉኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚንስትሩ ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ግብፅ በግድቡ ዙሪያ ከበፊቱ የሶስትዮሽ ስምምነት ያፈነገጠ ሀሳብ ማቅረቧንና ሀሳቡ በኢትዮጵያ በኩል ዉድቅ መደረጉን አመልክተዋል፡፡ኢትዮጵያ ሰሞኑን በጉዳዩ ዙሪያ በካይሮ በተገረገዉ ውይይት ምክክር ሀሳቡን እንዳልተቀበለችዉ ያስታወሱት ሚንስትሩ ሌላ ድርድር እንደሚካሄድ ጠቁመዋል፡፡ኢትዮጵያ ሱዳንና ግብፅ በጉዳዩ ዙሪያ ከመስከረም 19-22፣ 2012 ይመክራሉ ተብሏል፡፡ስምምነት ያልተፈጠረባቸው ግብጽ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ከተሞላ በኋላ በየዓመቱ ከ45ሚሊየን ሜትር ኩብ ውሃ ሊደርሰኝ ይገባል፤ እና የአስዋን ግድብ ከ167 ሜትር ከፍታ በታች እንዳይወር ኢትዮጵያ ሃላፊነቱን ልትወስ ይገባል በሚል በማቅረቧ ነው ተብሏል።ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ግብፅ ይህንና በህዳሴዉ ግድብ ዙሪያ ያቀረበችዉን ሃሳብ ኢትዮጵያ ዉድቅ ማድረጓን ዶ/ር ኢነርጂ ሚንስትሩ ስለሺ በቀለ አስታውቃል።ሚንስትሩ እንዳሉት ጉዳዩን ከሶስቱ ሀገሮች የተዉጣጣ ገለልተኛ የሳይንስና ምርምር ብሔራዊ ኮሚቴ ያጠናዋል ፡፡ | https://waltainfo.com/am/31355/ | 111 | 5ፖለቲካ
|
ጥቅም ላይ የዋሉት መሣሪዎች ኢራን ተጠያቂ መሆኗን ያረጋግጣሉ- ሳዑዲ | ፖለቲካ | September 19, 2019 | Unknown | በአገሪቱ የነዳጅ ማቀነባበሪያ ተቋማት ላይ በደረሰው ጥቃት ጥቅም ላይ የዋሉት መሣሪዎች ኢራን ተጠያቂ መሆኗን ያረጋግጣሉ ስትል ሳዑዲ ገለጸች፡፡የሳዑዲ መከላከያ ሚኒስትር፤ በአገሪቱ የነዳጅ ማቀነባበሪያ ተቋማት ላይ ከደረሰው ጥቃት የተሰበሰቡ ናቸው ያላቸውን የድሮን እና የሚሳዔል ስብርባሪዎች አሳይተዋል።መከላከያ ሚኒስተሩ ስብርባሪዎቹ ጥቃቱን ያደረሰችው ኢራን ስለመሆኗ ማሳያ ናቸው ብሏል።"18 ድሮኖች እና ሰባት ሚሳዔሎች ወደ ሳዑዲ ተተኩሰዋል" ያለው የሳዑዲ መከላከያ፤ የጥቃቶቹ መነሻ የመን አይደለችም ብሏል።በኢራን ድጋፍ የሚደረግላቸው እና በየመን የሚንቀሳቀሱት የሁቲ አማጽያን "ጥቃቱን ያደርስነው እኛ ነን" ቢሉም ሰሚ አላገኙም።ሳዑዲ ላይ ለተቃጣው ጥቃት፤ የአሜሪካ ባለስልጣናት ኢራንን ተጠያቂ ለማድረግ ጊዜ አልወሰደባቸውም ነበር። ኢራን በበኩሏ ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ እጇ እንደሌለባት በተደጋጋሚ ስትከራከር ቆይታለች።የአሜሪካ ባለስልጣናት፤ የሳዑዲ አረቢያ ነዳጅ ማቀነባበሪያ ተቋማትን ዒላማ አድርገው ከፍተኛ ጉዳት ያደረሱት ጥቃቶች መነሻቸው ከደቡባዊ ኢራን ነው በማለት የሳተላይት ምስሎችን እንደማሳያ አድርገው አቅርበው ነበር።ከዚህ በተጨማሪም የአሜሪካ ባለስልጣናት፤ የሳዑዲን ነዳጅ ማቀነባበሪያ ለመምታት ጥቅም ላይ የዋሉት የድሮን እና የሚሳዔል አይነቶችን ለይተናል ብለዋል።''የድሮን ጥቃቱ ከየመን ስለመነሳቱ የሚያሳይ ምንም አይነት ማስረጃ የለም'' ብለው የነበሩት የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ማይክ ፖምፔዮ፤ ትናንት ሳዑዲ አረቢያ ከደረሱ በኋላ ሁኔታውን "የጦርነት ትንኮሳ" ሲሉ ገልጸውታል።የሳዑዲ መከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኮለኔል ቱርኪ አል-ማልለኪ፤ ጥቃቱ የተፈጸመው "በኢራን ድጋፍ ሰጪነት ስለመሆኑ አጠያያቂ አይደለም" ብለዋል።ቃል አቀባዩ ጨምረው እንደተናገሩት፤ በትክክል ድሮን እና ሚሳዔሎች ጥቃት ከየት እንደተሰነዘሩ ለማወቅ እየሠራን ነው ብለዋል።ጥቃቱን ለመሰንዘር ጥቅም ላይ ከዋሉት የጦር መሣሪያ ስብርባሪዎች በተገኘው መረጃ መሰረት፤ ቢያንስ አንዱ መሣሪያ የኢራን ጦር የሚጠቀምበት ነው ተብሏል። (ምንጭ፡-ቢቢሲ) | https://waltainfo.com/am/34002/ | 209 | 5ፖለቲካ
|
ግብፅ ከሱዳን ጋር ያላትን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ለማጠናከር እንደምትፈልግ ፕሬዚዳንት አል ሲሲ ገለጹ | ፖለቲካ | September 19, 2019 | Unknown | ግብፅ ከሱዳን ጋር ያላትን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ለማጠናከር እንደምትፈልግ ፕሬዚዳንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ ገለጹ፡፡የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት በትናንትናው ዕለት ግብፅ ካይሮ የገቡ ሲሆን፣ ከግብጹ ፕሬዚዳንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ ጋር በሀገራቱ የሁለትዮሽና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።በውይይታቸውም ሀገራቱ በተለያዩ ዘርፎች ዙሪያ ያላቸውን ግንኙነት በተጠናከረ መልኩ ለማስቀጠል መስማማታቸውን የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስማን አብደላህ አስታውቀዋል።በተጨማሪም መሪዎቹ በቀጠናው ስላለው የጸጥታ ሁኔታ፣ ሱዳን አሸባሪዎችን ከሚደግፉ ሀገራት ዝርዝር ውስጥ በምትወጣበት ሁኔታ እና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር አድርገዋል።ፕሬዚዳንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ ግብፅ የቅርብ ጎረቤት ሀገር ከሆነቸው ሱዳን ጋር ያላትን ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ቃል ገብተዋል።በዚህም በአሁኑ ወቅት በሱዳን ያለውን ሰላም በዘላቂነት ለማስቀጠልና በቀጠናው የሚስተዋለውን የሽብር ጥቃት በጋራ ለመከላከል ከሱዳን ጋር በቅንጅት እንደሚሰሩም ገልጸዋል።ሀገራቱ በግብርና፣ በኤሌክትሪክ ሃይል፣ በመሰረት ልማት ግንባታ እና በሌሎች ዘርፎች ዙሪያ በጋራ ለመስራት ያላቸውን ስምምነት ወደ ተግባር ለመቀየርም ቀጣይ ውይይቶች የሚደረጉ እንደሆነ የሱዳን ትሪቡን ዘገባ ያመለክታል፡፡ | https://waltainfo.com/am/33338/ | 139 | 5ፖለቲካ
|
የኢሬቻ የጎዳና ሩጫ የፊታችን እሁድ ይካሄዳል | ሀገር አቀፍ ዜና | September 18, 2019 | Unknown | “የሆራ ፊንፊኔ” የኢሬቻ ሩጫ እሁድ መስከረም 11 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ።ሩጫው መስከረም 24 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ የሚከበረውን የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ የሚካሄድ እንደሆነ ተገልጿል፡፡በዚህ የሩጫ ውድድር ላይ ከ50 ሺህ በላይ ሰዎች ይሳተፉበታል ተብሎ እንደሚጠበቅ የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አድማሱ ዋቅጋሪ ለኢዜአ ተናግረዋል። እንደ አቶ አድማሱ ገለጻ የሩጫው ቲ-ሸርት በፌዴራልና በክልሉ በመሰራጨት ላይ ያለ ሲሆን፣ ሽያጩም አንዱ ቲ-ሸርት በ250 ብር እየተካሄደ ይገኛል።የቲ-ሸርቱ የመሸጫ ቦታዎች በፌዴራልና በክልሉ መስሪያ ቤቶች የሚገኙ ሰራተኞች እንዲሁም በፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞንና በአዲስ አበባ የሚገኙ ነዋሪዎች ከኦሮሞ ባህል ማዕከል ማግኘት እንደሚችሉ ተናግረዋል።በክልሉ ሌሎች ዞኖች የሚገኙ ነዋሪዎች ደግሞ በዞን እና በወረዳ እንዲሁም በሁሉም ከተሞች ባሉት የባህልና ቱሪዝም ቢሮዎች ማግኘት ይችላሉ ብለዋል። | https://waltainfo.com/am/32737/ | 115 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
በባሕር ዳር ከተማ በርካታ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ በቁጥጥር ሥር ዋለ | ፖለቲካ | September 18, 2019 | Unknown | የአማራ ክልል አድማ ብተና 2ኛ ሻለቃ 1ኛ ሻምበል ምክትል ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ታለማ ዳኛ ለአብመድ እንደተናሩት፤ በ20 ጆንያዎች የተቋጠረ 497 ሽጉጥ እና ወደ 46 ሺህ የሚገመት ጥይት በባሕር ዳር ከተማ በቁጥጥር ሥር ውሏል፡፡ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነትና ከኅብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሠረት ከነዳጅ ጋር ተቀላቅሎ ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ በገባ የነዳጅ ማመላለሻ ቦቴ ውስጥ ሲጓጓዝ ነው ሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያው በቁጥጥር ስር የዋለው፡፡ከትናንት ምሽት ጀምሮ በተደረገ ክትትል ነው ባሕር ዳር ከተማ ጣና ክፍለ ከተማ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያው በቁጥጥር ስር የዋለው፡፡አሽከርካሪው ለማምለጥ ሙከራ አድርጎ በቁጥጥር ሥር መዋሉን ያስታወቁት ምክትል ኢንስፔክተር ታለማ ነዳጁ ከባሕር ዳር አልፎ የሚሄድ እንደነበርና ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያውን ከቦቴው ለማውጣት የሚያገለግል ብረት ከተሽከርካሪው መገኘቱን አመልክተዋል፡፡ | https://waltainfo.com/am/31352/ | 103 | 5ፖለቲካ
|
2ኛው የኢጋድ የሚኒስትሮች ስብሰባ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው | ፖለቲካ | September 18, 2019 | Unknown | ሁለተኛው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት/ኢጋድ/ የሚኒስትሮች ስብሰባ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡ስብሰባውም በዋናነት በቀጠናው አገራት ያለውን የስደተኞች ጉዳይ በተመለከተ በተደረሰው የናይሮቢ ስምምነት አፈፃፀም ላይ ያተኮረ ነው፡፡ስምምነቱ የቀጠናው አገራት ስደተኞችን መንከባከብ፣ ስደተኞች ላይ የሚደርሱ ችግሮችን በማስቀረትና ወደ ነበሩበት እንዲመለሱ የሚያደርግ ነው ተብሏል፡፡ስደተኞች የሚሄዱባቸው አገሮችን ጫና ለመቀነስም የሚሰሩ የጋራ ስራዎች መኖራቸው ተነግሯል፡፡የሚኒስትሮቹ ስብሰባ ሰደተኞች ወደ ነበሩበት ከመመለስ ጀምሮ በዘላቂነት እንዲቋቋሙ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ያለመ እንደሆነም ተመልክቷል፡፡በኢትዮጵያ ከተለያዩ የጎረቤት አገራት የተወጣጡ 1 ሚሊዮን ስደተኞች እንደሚገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ | https://waltainfo.com/am/31354/ | 75 | 5ፖለቲካ
|
ቬንዙዌላ ቀንደኛ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪን ፈታች | ፖለቲካ | September 18, 2019 | Unknown | ቬንዙዌላ ቀንደኛ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ የነበሩትን ኤድጋር ዛምብራኖን ከእስር መፍታቷን አስታውቃለች፡፡ኤድጋር ከሌላው የተቃዋሚ መሪ ሁዓን ጉአይዶ ጋር በመሆን የቬንዙዌላ መንግስትን ለመገልበጥ ወታደራዊ አመፅን ቀስቅሰዋል በሚል ላለፉት አራት ወራት በእስር ቆይተዋል፡፡የሀገሪቱ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ታሬክ ዊሊያም ሳዓብ ከብሄራዊ ተቃዋሚ ፓርቲ ጋር በተወሰኑ ነጥቦች ዙሪያ ከስምምነት መደረሱን ተከትሎ መንግስት ግለሰቡ እንዲፈቱ መወሰኑን ተናግረዋል፡፡ይሁንና የኤድጋር ዛምብራኖን የክስ መዝገብ አለመዘጋቱንና ከሀገር እንዳይወጡ የተቀመጠው ክልከላ አለመነሳቱን ነው የቢቢሲ ዘገባ ያመለከተው፡፡ዛምብራኖ መፈታቱን ተከትሎ ከእርሱ ጋር የነበሩ አራት ጓደኞቹን ጨምሮ ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ጠይቋል፡፡ሁዓን ጉአይዶ በበኩሉ የዛምብራኖ ከእስር መፈታት የአለምአቀፉ ማህበረሰብ የፈጠረው ጫና ውጤት እንደሆነ በትዊተር ገፁ አስፍሯል፡፡እ.አ.አ በ2018 ወርሃ ግንቦት በቬንዝዌላ የተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ተዓማኒነት የጎደለው ነው የሚል ዘመቻ መጀመሩን ተከትሎ ሀገሪቱ የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ ገብታ ቆይታለች፡፡
ምንጭ፦ አልጀዚራ | https://waltainfo.com/am/34001/ | 114 | 5ፖለቲካ
|
3ኛው የሰላም ጉዞ በድሬዳዋ ከተማ ይደረጋል | ፖለቲካ | September 18, 2019 | Unknown | ሶስተኛው የሰላም ጉዞ በድሬዳዋ ከተማ እንደሚደረግ ተገለጸ፡፡ ስለ ሰላም፣ መቻቻል፣ ፍቅር እና አንድነት የሚሰብክ የሰላም ጉዞ ለሶስተኛ ጊዜ ወደ ድሬዳወ የሚደረግ ሲሆን፤ በጉዞው አንጋፋ የኪነጥበብ ሰዎች የሚሳተፉበት ይሆናል ተብሏል።መስከረም 17 ቀን 2012 ዓ.ም በሚካሄደው የሰላም ጉዞ መርሃግብር የእግር ጉዞ፣ የደም ልገሳ፣ ችግኝ የመንከባከብ እና የኪነጥበባት ስራዎች የሚቀርቡ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ ከዚህ በተጨማሪም የሃገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች እና የኃይማኖት አባቶች የሚሳተፉበት ውይይት ይደረጋል ተብሏል፡፡በተለያዩ ጊዜያት የሚካሄደው የሰላም ጉዞው የህብረተሰቡን ፍቅር እና ሰላም እንዲሁም አብሮነቱን ለማጠናከር የሚደረግ መርሃግብር እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡ደም በመለገስ ወገኖችን ከሞት ለመታደግና አንድነትን ለማጠናከር፣ ችግኞችን በመትከል በተፈጥሮ ፀጋ ለሌሎች መትረፍ እና ሌሎች የህብረተሰቡን አብሮነት ሊያጠናክሩ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ስለሰላም የሚሰበክበት መድረክ ስለመሆኑ ጉዞዉን የሚመሩ አርቲስቶች ተናግረዋል፡፡ አርቲስቶቹ ሁሉም የህብረሰተብ ክፍል ለሰላም እና ለአንድነትን በመረዳዳትና በመነጋገር መስራት እንዳለበት ተናግረዋል፡ይህ የሰላም ጉዞ ከዚህ ቀደም በቡታጅራ እና ሚዛን ቴፒ ከተሞች ተካሂዶ ውጤታማ እንደነበርም ተጠቁሟል፡፡ በቀጣይም አስራ አራት የሀገር ውስጥ እና አስር ከሀገር ውጭ ተመሳሳይ ጉዞዎች ይደረጋሉም ተብሏል፡፡ | https://waltainfo.com/am/31353/ | 144 | 5ፖለቲካ
|
ጠ/ሚ ዐብይ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት እና መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ጋር ተወያዩ | ሀገር አቀፍ ዜና | September 18, 2019 | Unknown | ጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ተወካዮችና ከኢትዮጵያ እስልምና መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ጋር በዛሬው ዕለት ተወያይተዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ከሁለቱም ወገኖች ጋር መወያየታቸው ተገልጿል፡፡አባላቱ የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታይ እህትና ወንድሞቻቸውን ለማክበር ከመስቀል በዓል በፊት በሚደረግ ጽዳት ላይ ለመሳተፍ ያላቸውን ፍላጎት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡ምንጭ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት | https://waltainfo.com/am/32736/ | 51 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የንግድ ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ እሴት መጨመር ላይ ትኩረት ይደረጋል ተባለ | ቢዝነስ | September 17, 2019 | Unknown | የኢንቨስትመንት ዘርፉን ዉጤታማ ለማድረግና የዉጭ ባለሃብቶችን ለመሳብ የሚያስችል ስራዎችን በጋራ ለመስራት የሚያሥችል የቢዝነስ ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነዉ፡፡የዱባይ የዲስፖራ ቢዝነስ ልዑክ ከኢትዮጵያ ባለሃብቶች ጋር እያካሄደ ያለው ምክክር የኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች የንግድ ትስስርን በማጠናከር በጋራ ለመስራት እንደሚያስችላቸዉ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ምስጋኑ አረጋ ገልፀዋል፡፡በተጨማሪም ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንትን ለማጠናከርና በሀገራቱ የሚገኙ ባለሃብቶች የልምድ ልውውጥ እንዲያካሂዱ በር የሚከፍት ነው ብለዋል፡፡ሚኒስቴር ዲኤታዉ አክለዉም በኢትዮጵያ በኩል የንግድ ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ ምርትን እሴት ጨምሮ ለመላክ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራም ነው የገለፁት፡፡ምርቶችን በአይነትና በጥራት ማሳደግና እሴት መጨመርም የተሻለ ገቢን ከማስገኘት ባለፈ በርካታ ባለሃብቶች በኢንቨስትመንት ሂደቱ ላይ እንዲሳተፉ እገዛው ላቅ ያለ መሆኑን ሚኒስትር ድኤታው አንስተዋል፡፡በዚህ ረገድ ከተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ሀገሪቱ ልምድ ልምድ ለመቅሰም ዝግጁ ናት ብለዋል፡፡በኢትዮጵያ የኢትዮጵያና የተባበሩት አራብ ኢምሬቶች አምባሳደር ሙሃመድ ሳሌም አል ረሺድ በበኩላቸው ፤ የቢዝነስ ፎረሙ የንግድ ትስስር ይበልጥ ለማጠናከርና ልምድና ተሞክሮዎችን ለመውሰድ ጥሩ አማራጭ ነው ብለዋል፡፡“ወደ ብልፅግና የሚያመራውን ድልድይ መገንባት” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ የሚገኘው ይህ ፎረም ፤ የሃገራቱ ባለሃብቶች እንዲተዋወቁና ልምድ እንዲለዋወጡ በማድረግ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለማስተዋወቅ ይረዳል ተብሏል፡፡
| https://waltainfo.com/am/23962/ | 155 | 3ቢዝነስ
|
11 ባለኮከብ ሆቴሎች በመዲናዋ ሊገነቡ ነው | ቢዝነስ | September 17, 2019 | Unknown | አዲስ አበባ ከእቅድ በላይ የኢንቨስትመንት ፍስት እየታየባት መሆኗን እና በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ያስቀመጣቸውን ግቦች ማሳካት መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንቨስትመንት ከሚሽን አስታወቀ።የ11 ባለኮከብ ሆቴሎች ግንባታ ወደ ትግበራ እንዲገባ የከተማዋ ካቢኔ ውሳኔ ማሳለፉንም ገልጿል።ሆቴሎቹን የሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ከውጭ ባለሀብቶች ጋር በሽርክና የሚገነቧቸው እንደሆነም ኮሚሽነር አቶ አብዱልፈታ የሱፍ በተለይ ለአዲስ ዘመን ገልፀዋል፡፡የእነዚህ ሆቴሎች ግንባታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ትግበራ እንዲገባ ካቢኔው ውሳኔ ማሳለፉንና የካፒታል መጠናቸውም በጣም ብዙ መሆኑን አመልክተዋል።ለአንድ ሆቴል ብቻ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ የካፒታል መጠን የቀረበበት ሁኔታ እንዳለም የጠቀሱት ኮሚሽነሩ፤ ይህም የሆቴል ኢንዱስትሪውን በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሳድገው ይጠበቃል ብለዋል፡፡በአጠቃላይ ባለፈው ዓመት ብቻ ከ2 ሺህ 500 በላይ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መውሰዳቸውን ኮሚሽነሩ ጠቅሰው ፤ ወደ 40 ሺህ ኢንቨስተሮች በኢንቨስትመንቱ ዘርፍ እየሰሩ መሆናቸውንም አስታውቀዋል። | https://waltainfo.com/am/23963/ | 113 | 3ቢዝነስ
|
ም/ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን የቀድሞ የኢትዮጵያ ባህር ሃይል ማህበር ተወካዮችን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ | ቢዝነስ | September 18, 2019 | Unknown | የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የቀድሞ የኢትዮጵያ ባህር ሃይል ማህበር ተዎካዮችን በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።የቀድሞ የኢትዮጵያ ባህር ሃይል ማህበር አባላት ካካበቱት ሙያ እና ልምድ አንፃር በቀጣይ በዘርፉ ሃገራዊ አቅም መሆን በሚችሉበት ጉዳዮች ዙሪያ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ ጋር ተወያይተዋል። መረጃው የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ነው፡፡ | https://waltainfo.com/am/23964/ | 49 | 3ቢዝነስ
|
አሜሪካ ሳዑዲ ላይ የተቃጡት ጥቃቶች መነሻቸው ከኢራን መሆናቸውን ገለጸች | ፖለቲካ | September 18, 2019 | Unknown | አሜሪካ ሳዑዲ ላይ የተቃጡት የድሮን እና የሚሳኤል ጥቃቶች መነሻቸው ከኢራን ስለመሆኑ ደርሼበታለው ማለቷ ተገለጸ፡፡አንድ ከፍተኛ የአሜሪካ መንግሥት ባለስልጣን ለመገናኛ ብዙሃን እንደተናገሩት የሳዑዲ አረቢያ ነዳጅ ማቀነባበሪያ ተቋማትን ዒላማ አድርገው ከፍተኛ ጉዳት ያደረሱት ጥቃቶች መነሻቸው ከደቡባዊ ኢራን ነው።ኢራን በበኩሏ ከጥቃቶቹ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለኝም ስትል ቆይታለች።በየመን የሚንቀሳቀሱት እና በኢራን ድጋፍ የሚደረግላቸው የሁቲ አማጽያን በሳዑዲ ጥቃቱን ያደረስነው እኛ ነን ቢሉም ሰሚ አላገኙም።የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ማይክ ፖምፔዮ ''የድሮን ጥቃቱ ከየመን ስለመነሳቱ የሚያሳይ ምንም አይነት ማስረጃ የለም። ሁሉም መንግሥታት ኢራን በዓለም የኢኔርጂ ምንጭ ላይ የሰነዘረችውን ጥቃት ማውገዝ አለባቸው'' ለማለት ጊዜ አልወሰደባቸውም ነበር።ስማቸው ያልተጠቀሰ አንድ ከፍተኛ የአሜሪካ መንግሥት ባለስልጣን ለመገናኛ ብዙሃን እንደተናገሩት፤ ጥቃቱ የተሰነዘረበት አቅጣጫ እና ስፋት ከግምት ውስጥ ሲገባ የሁቲ አማጽያን ፈጽመውታል ብሎ ለማሰብ ይከብዳል።የሁቲ አማጽያን ከዚህ ቀደም ወደ ሳዑዲ የድሮን ጥቃቶችን አድርሰዋል፤ ሚሳዔሎችንም አስወንጭፈዋል። የአሜሪካ ባለስልጣናት ይህን ጥቃት ግን የሁቲ አማጽያን መፈጸም የሚያስችል ቁመና የላቸውም፤ እንዲሁም ጥቃቶቹ የተሰነዘሩት በየመን የሁቲ አማጽያን ከሚቆጣጠሩት ስፍራም አይደለም።በሳዑዲ ላይ ጥቃቱ ከተሰነዘረ በኋላ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ጨማሪ ማሳየቱ ይታወሳል።የሳዑዲ አረቢያ ኢነርጂ ሚኒስትር ትናንት በነዳጅ ማቀነባበሪያ ተቋማቱ ላይ የደረሰው ጉዳት ተጠግነው ወደ ቀደመ የማምረት አቅማቸው በዚህ ወር መጨረሻ ላይ ይመለሳሉ ብለዋል። | https://waltainfo.com/am/34000/ | 174 | 5ፖለቲካ
|
ደቡብ አፍሪካ ናይጄሪያን ይቅርታ ጠየቀች | ሀገር አቀፍ ዜና | September 18, 2019 | Unknown | ደቡብ አፍሪካ በውጭ አገራት ዜጎች ላይ ከደረሰው ጥቃት ጋር በተያያዘ ናይጄሪያን ይቅርታ መጠየቋ ተነግሯል፡፡በደቡብ አፍሪካ ናይጄሪያውያንን ጨምሮ በውጭ አገራት ዜጎች ላይ በተሰነዘረ ጥቃት ህይወት ጠፍቷል፤ በርካታ ንብረትም ተዘርፏል፡፡በዚህ ሳቢያ ሁለቱ አገራት ግንኙነታቸው ሻክሮ ከቆየ በኋላ አሁን ደቡብ አፍሪካ ናይጄሪያን ይቅርታ ጠይቃለች፡፡የደቡብ አፍሪካ ልዮ መልዕክተኛ ጄፍ ራዴቤ የፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳን የይቅርታ ደብዳቤ ለናይጄሪያው መሪ ሙሐመዱ ቡሐሪ አድርሰዋል፡፡ደቡብ አፍሪካ ናይጄሪያውያንን ጨምሮ በውጭ አገራት ዜጎች ላይ ጥቃቱን በሰነዘሩ ሰዎች ላይ እርምጃ መውሰዷን ልዮ መልዕክተኛው ተናግረዋል፡፡በአገሪቱ በተከሰተው ግጭት የ10 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በርካቶች ተፈናቅለዋል፤ ንብረታቸውም ተዘርፏል ነው የተባለው፡፡ሁለቱ አገራት በተፈጠረው ችግር የሻገረ ግንኙነታቸውን ለማሻሻል እየሰሩ ቢሆንም ናይጄሪያ ዜጎቿን ከደቡብ አፍሪካ እያስወጣች ትገኛለች፡፡(ምንጭ፦ ቢቢሲ) | https://waltainfo.com/am/33475/ | 99 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ የዲሞክራሲ ሽልማትን አሸነፉ | ፖለቲካ | September 18, 2019 | Unknown | ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ የአፍሪካ ዴሞክራሲ ሽልማትን አሸንፈዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስተሩ ለሽልማቱ የበቁት ዴሞክራሲን እና መልካም አስተዳደርን በአፍሪካ ለማረጋገጥ ባደረጉት ጥረት ምክንያት መሆኑ ተገልጿል፡፡ሽልማቱ በአዲስ አበባ በተካሄደው በአራተኛው የአፍሪካ የፖለቲካ የምክክር መድረክ ላይ ነው የተበረከተላቸው፡፡ከመላው አፍሪካ የተውጣጡ ከፍተኛ የፖለቲካ አማካሪዎች የሽልማቱ አዘጋጆች መሆናቸውን መረጃው አመልክቷል፡፡የአዘጋጅ ኮሚቴው ፕሬዚዳንት ኪንዴ ባሚግበታን ሽልማቱ በአህጉሪቱ ዴሞክራሲንና መልካም አስተዳደርን በማስፋፋት ተምሳሌታዊ ተግባር ላከናወኑ ሰዎች እውቅናን የሚቸርና ቀጣይነት ባለው ሁኔታ የሚሰጥ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ በተጨማሪ ናይጄሪያዊው ቦላ ቲኒቡ የዚህ ሽልማት አሸናፊ ሆነዋል፡፡ምንጭ ፦ፖለቲክስ ናይጄሪያ | https://waltainfo.com/am/31351/ | 80 | 5ፖለቲካ
|
ቱኒዚያዊያን ለሁለተኛ ጊዜ ነጻ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫቸውን አከናወኑ | ፖለቲካ | September 16, 2019 | Unknown | በቱኒዚያ እ.አ.አ. በ2011 በተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ ፕሬዝዳንት ቤን አሊ ከስልጣናቸው ከተነሱ በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ ነጻ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ተካሂዷል።በምርጫው 26 ተፎካካሪዎች የተሳተፉ ሲሆን፣ ሁለቱ ደግሞ ሴቶች መሆናቸው ታውቋል።ምርጫው ከተጠናቀቀ በኋላ በግላቸው የሚወዳደሩት ካይስ ሳይድ በመጀመሪያው ዙር ምርጫ የተሻለ ድምጽ ሳያገኙ እንዳልቀረ ተገምቷል። የመራጮች ቁጥር ግን በእጅጉ ዝቅተኛ መሆኑም ተገልጿል።ከአጠቃላይ የቱኒዚያ ህዝብ 45 በመቶ ብቻ የሚሆነው ለምርጫው የወጣ ሲሆን፤ ምንም እንኳን ወጣቶች በምርጫው እንዲሳተፉ ቅስቀሳዎች ሲደረጉ ቢቆዩም አብዛኛዎቹ ጎልማሶችና እድሜያቸው የገፋ ዜጎች መሆናቸው ታውቋል።በቱኒዚያ ታሪክ ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ከአምስት ዓመት በፊት የተመረጡት የቀድሞው ፕሬዝዳንት ቤጂ ኬይድ ኢሴብሲ ባሳለፍነው ሰኔ ወር ላይ ህይወታቸው ማለፉን ተከትሎ ነው ሃገሪቱ ምርጫ ለማካሄድ ደፋ ቀና ስትል የነበረው።ቤጂ ኬይድ ኢሴብሲ በ92 ዓመታቸው የሞቱ ሲሆን፣ ህይወታቸው ያለፈው የዓለማችን በእድሜ የገፉ በስልጣን ያሉ ፕሬዝዳንት ነበሩ።ነገር ግን ወጣቱ ማህበረሰብ በምርጫው ላይ በብዛት አለመሳተፉ ሌላ ፈተና ሊሆን እንደሚችል እየተገለጸ ነው።"ወጣቶቹ የት ሄደው ነው? ሃገሪቱ እኮ የእነሱ ናት። የወደፊቱ ተረካቢዎች እነሱ ናቸው'' ሲል አንድ ለምርጫ የወጡ የ60 ዓመት አዛውንት ለኤኤፍፒ ዜና ወኪል ተናግረዋል።ይፋዊ የሆነው የምርጫ ውጤት ማክሰኞ ዕለት እንደሚገለጽ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ማን ያሸንፋል የሚለው ጥያቄ እጅግ ከባድና ለመገመት አስቸጋሪ መሆኑ እየተዘገበ ነው።በምርጫው አብላጫ ድምጽ ያገኘ ተወዳዳሪ የሚያሸንፍ ይሆናል። ነገር ግን የትኛውም ተወዳዳሪ አብላጫ ድምጽ ማግኘት ካልቻለ ካሉት ተወዳዳሪዎች ከፍተኛውን ድምጽ ማግኘት የቻሉት ሁለት ተወዳዳሪዎች በቀጣዩ ዙር ይፎካከራሉ።አሸናፊው ተወዳዳሪ ደግሞ ለአምስት ዓመታት ሃገሪቱን የሚያስተዳድር ይሆናል። (ምንጭ፡-ቢቢሲ) | https://waltainfo.com/am/33337/ | 202 | 5ፖለቲካ
|
ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ በኢትዮጵያ የሳዑዲ ዓረቢያ አምባሳደር ሳሚ ጀሚል አብዱላህ ጋር ተወያዩ | ሀገር አቀፍ ዜና | September 16, 2019 | Unknown | የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ በኢትዮጵያ የሳዑዲ ዓረቢያ አምባሳደር ሳሚ ጀሚል አብዱላህ ጋር ተወያዩ።ሚኒስትሯ ከአምባሳደሩ ጋር በሁለትዮሽና ለስራ ወደ ሳዑዲ በሚሄዱ ሰራተኞች ዙሪያ የደረሷቸውን ስምምነቶች ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መወያየታቸው ነው የተገለጸው።በዚህ ወቅትም አምባሳደሩ ተቋርጦ የነበረው የውጭ ሃገር የስራ ስምሪት ዳግም እንዲጀመር ላደረጉት ጥረት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።አምባሳደር ሳሚ ጀሚል በበኩላቸው፣ ሚኒስቴሩ ህገ ወጥ የስራ ስምሪትን በመከላከል ህጋዊ የስራ ስምሪት እንዲኖር ያደረገውን ጥረት አድንቀዋል።አያይዘውም ሀገራቸው ኢትዮጵያውያን ዜጎች በሳዑዲ ህጋዊ ሆነውና ደህንነታቸው ተጠብቆ እንዲሰሩ ድጋፍ ማድረጓን አብራርተዋል።ከውይይቱ በኋላም ሀገራቱ ለስራ ወደ ሳዑዲ በሚሄዱ ዜጎች አጠቃላይ ሁኔታ በጋራ ለመስራትና መረጃ ለመለዋወጥ መስማማታቸውን ከሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። | https://waltainfo.com/am/32734/ | 98 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
40 ሺህ ቬንዙዌላውያን ወደ ትሬኔዳድ እና ቶቤጎ ተሰደው አስቸጋሪ ህይወት እየመሩ ነው- ቢቢሲ | ሀገር አቀፍ ዜና | September 16, 2019 | Unknown | 4 ሚሊየን ቬንዙዌላውያን ሀገሪቱ በገጠማት የኢኮኖሚ እና ፖለቲካዊ ቀውስ ሀገራቸውን ጥለው መሰዳዳቸው ተነገረ፡፡40 ሺህ የሚሆኑት ትሬኔዳድ እና ቶቤጎ ወደተባሉት የካሪቢያን ደሴቶች ተሰደው አስቸጋሪ ህይወት እየመሩ እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡የአከባቢው ማህበረሰብ ተሳዶቹን በክፉ አይን ማየታቸው ሀገራቸውን ጥለው ለወጡት የቬንዙዌላ ዜጎች አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንዲወድቁ ማድረጉን በስፍራው ቅኝት ያደረገችው የቢቢሲ ዘጋቢ ተናግራለች፡፡ከመከራ ወደ መከራ ነው የተሸጋገርነው የሚሉት ስደተኞቹ፤ ምግብ ለማብሰል አልጋቸውን እስከመማገድ መድረሳቸውን ገልጸዋል፡፡በሌሎቹም ወሳኝ የማህበራዊ ግልጋሎቶች በሚኖሩባቸው የካሪቢያን ደሴቶች እየተገለሉ መሆኑን ስደተኞቹ ገልፀዋል፡፡ቬንዙዌላ ከአለም የመጀመሪያዋ ነዳጅ ላኪ ለመሆን ስታደርገው የነበረው ጥረት ከሀያ አመት ወዲህ በመንግስት አባክኝነት የተነሳ ወደ ኢኮኖሚው ቀውስ ገብታለች፡፡ከዚህ ባለፈ በሀገሪቱ የተንሰራፋው ከፍተኛ የሙስና ቅሌት አሁን ላይ 94 በመቶ የሀገሪቱን ህዝብ በድህነት እንዲኖር አስገድዷል፡፡ | https://waltainfo.com/am/34134/ | 103 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የኖርዌይ የውጭ እና የመከላከያ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጋር ተወያዩ | ፖለቲካ | September 16, 2019 | Unknown | የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ዛሬ መስከረም 5 ቀን 2011 ዓም የኖርዌይ የውጭ ጉዳይ እና የመከላከያ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አኒከን ሁይትፈልድት እና ልኡካቸውን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።ሁለቱ ወገኖች በሁለትዮሽ፣ በቀጠናዊ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት አድርገዋል።ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት አንደገለጹት ኢትዮጵያ እና ኖርዌይ ረጅም ዘመናትን የስቆጠረ የሁለትዮሽ ግንኙነት እንዳላቸው ገልጸው፤ ግንኙነቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እየተሰራ ነው ብለዋል።በኖርዌይ የልማት ትብብር አማካኝነት ኖርዌይ በኢትዮጵያ በማህበራዊና በኢኮኖሚው ዘርፍ እያደረገች ያለውን ጉልህ እንቅስቃሴ በተመለከተ አቶ ገዱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን አጠቃላይ ሪፎርም በተመለከተ ገለጻ በማድረግ ኖርዌ ለሪፎርሙ መሳካት ድጋፏን አጠናክራ እንድትቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል።ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ እና በቀጣናው ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍንና ኢኮኖሚያዊ ውህደት እንዲመሰረት እየተጫወተች ያለውን ሚና በተመለከተም ሚኒስትሩ ሰፊ ገለጻ አድርገዋል። ኢትዮጵያ እና ኖርዌይ በዓለም አቀፍ መድረኮች በአየር ንብረት ለውጥ እና ተያያዥ ጉዳዮች ጠንካራ ግንኙነት እንደላቸውና በትብብር እየሰሩ መሆኑንም ሚኒስትሩ አብራርተዋል።የኖርዌይ የውጭ ጉዳይ እና የመከላከያ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አኒከን ሁይትፈልድት በበኩላቸው በኢትዮጵያ እተካሄደ ያለውን አጠቃላይ ሪፎርም ኖርዌ እንደምታደንቅ ገልጸዋል።ኢትዮጵያ ለሴቶች እኩልነት በሰጠችው ትኩረት በርካታ ሴቶች ተጠቃሚ መሆናቸውን እንደተገነዘቡም ገልጸዋል። በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል የተደረሰው የሰላም ስምምነት ለቀጠናው ሰላምና መረጋጋት ገልህ ሚና እንደሚጫወት እምነታቸው መሆኑንም አብራርተዋል።ከዚህ በተጨማሪ ኢትዮጵያ በቀጠናው እየተጫወተች ያለውን አጠቃላይ እንቅስቃሴም አድንቀዋል። ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረኮችም ጉልህ ሚና የምትጫወት አገር መሆኗን በማንሳት በዚህ በኩል ከኖርዌይ ጋር ያላትን ግንኙነት አጠናክራ እንድምትቀጥል እምነታቸው መሆኑንም አኒከን ሁይትፈልድት በንግግርቸው አንስተዋል።የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖንን ለመቋቋም ኢትዮጵያ በደን ተከላ እያደረገች ያለውን ከፍተኛ አንቅስቃሴም አድንቀዋል።በኢትዮጵያ ጉብኝት በማደረግ ላይ የሚገኙው የኖርዌይ የውጭ ጉዳይ እና የመከላከያ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በኖርዌይ ፓርላማ ውስጥ መቀመጫ ካላቸው የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተወከሉ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፓርላማ የውጭ እና የመከላከያ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጋር በመወየት የልምድ ልውውጥ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።ኢትዮጵያ እና ኖርዌይ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የመሰረቱት በ1939 ዓም ሲሆን፤ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ኢትዮጵያ ስቶክሆልም በሚገኘው ኤምባሲዋ በኩል ከኖርዌይ ጋር ያላትን ግንኙነት አጠናክራ በመቀጠል ላይ ትገኛለች።በተመሰሰይ ኖርዌይ በ1984 ዓም በአዲስ አበባ ኤምባሲዋን በመክፈት ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግኑኝነት አጠናክራ በማስቀጠል ላይ እንደሚትገኝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። | https://waltainfo.com/am/31350/ | 310 | 5ፖለቲካ
|
የኢጋድ አባል አገራት የሚጠቀሙበት የካንሰር ህክምና ማዕከል በአዲስ አበባ ሊገነባ ነው | ሀገር አቀፍ ዜና | September 16, 2019 | Unknown | የምስራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግስታት /ኢጋድ/ የተወሰነዉ የካንሰር ህክምና ማእከል በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ለሚኖሩ 260 ሚሊዮን ሰዎችን ማእከሉ ተጠቃሚ እንደሚያደርግም ታዉቋል፡፡ማእከሉ በአዉሮፓዉያኑ ዘመን አቆጣጠር 2020 ጥር ወር ላይ የመሰረት ድንጋይ እንደሚጣልና ግንባታዉም በ450 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ወጪ እንደሚከናወን ተገልጿል፡፡ለማእከሉ ግንባታ በከተማ አስተዳደሩ መሬት የተዘጋጀ እንደሆነና በኢትዮጵያ መንግስት በኩል አስፈላጊዉን ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኗን የጤና ሚኒስትሩ ዶክተር አሚር አማን ገልፀዋል፡፡ዶ/ር አሚር በአዲስ አበባ ሂልተን ሆቴል እየተደረገ ባለዉ የገቢ ማሰባሰቢያ መድረክ ተገኝተዉ ማእከል ግንባታ እዉን ከማድረግ አኳያ ለቀጣናዉ አባል ሃገራት ከፍተኛ መሪዎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጥሪ አቅርበዋል፡፡ግንባታው በሁለት አመት ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ የቀጠናዉ አባል ሃገራት መሪዎችና ኢጋድ እንዲሁም የአዉስትራሊያ፣ የጀርመን እና ሌሎች ሃገራት የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋሉ ተብሏል፡፡ለማእከሉ ግንባታ የሚያስፈልገዉ ወጪ በማሰባሰብ ጊዜ እንዳይፈጅና ግንባታዉ ተጠናቆ ቶሎ ወደ ስራ እንዲገባ ለማስቻል የኢትዮጵያ መንግስትም የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋል፡፡በዚህ የገቢ ማሰባሰቢያ መድረክ የተገኙት የሳዉዲ አረቢያ አምባሳደር በኢትዮጵያ አምባሳደር ሳሚ አብዱላሂ በበኩላቸዉ፣ ለማእከል ግንባታው አስፈላጊዉን ድጋፍ ለማድረግ በመንግስታቸዉ በኩል በሙሉ ፍቃደኝነት ድጋፋቸዉን እንደሚያደርጉ ገልፀዋል፡፡የካንሰር በሽታ በአሁኑ ወቅት በአለምአቀፍ ደረጃ በገዳይነቱ ቁጥር አንድ ከሚባሉ ተላላፊ ካልሆኑ በሽታዎች ግንባር ቀደም መሆኑ ይገለፃል፡፡በዚህም በኢትዮጵያ በአሁን ወቅት የካንሰር በሽታ በሁሉም የእድሜ ክልል እና ፆታ በሽታዉ ቁጥሩ ከፍ እያለ እንደመጣ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ | https://waltainfo.com/am/32735/ | 182 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
3 ሚሊየን የሶሪያ ስደተኞች ወደ ሀገራቸው ሊመለሱ ነው | ፖለቲካ | September 17, 2019 | Unknown | 3 ሚሊየን የሶሪያ ስደተኞች ደህንነታቸው በተሻለ ሁኔታ እንዲጠበቅ ያስችላል ወደ ተባለ ሰሜናዊ የሃገሪቱ ክፍል ሊመለሱ እንደሚችሉ የቱርኩ ፕሬዝዳንት አስታወቁ።የቱርኩ ፕሬዚዳንት ራሲፕ ጣይፕ ኤርዶሃን እንዳሉት ከማንኛውም አይነት አደጋ ነጻ የሆነው አካባቢ ከአሜሪካመንግስት ጋር በመተባባር የተዘጋጀ መዘጋጀቱንና ደህንነቱን አስተማማኝ ለማድረግ ጊዜ መውሰዱን ገልጸዋል፡፡በአሜሪካ የሚደገፉት የኩርድ ተዋጊዎች ቀደም ብሎ በቱርክ ድንበር በኩል ካለው የሶሪያ ሰርጥ ለቅቀው መሄዳቸው የሚታወስ ነው። ቱርክ ደግሞ የኩርድ ተዋጊዎችን በአሸባሪነት ፈርጃቸዋለች።የፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ዕቅድ ይፋ የሆነው አንካራ ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና ከኢራኑ ፕሬዝዳንት ሃሳን ሮሃኒ ጋር ውይይት ካደረገች በኋላ መሆኑ ታውቋል።ምንም እንኳን የኩርድ ተዋጊዎች ስለፕሬዝዳንቱ አስተያየት ያሉት ነገር ባይኖርም አምርረው እንደሚቃወሙት ግልጽ ነው ብሏል የቢቢሲው የሶሪያ ዘጋቢ አላን ጆንስተን፡፡በያዝነው ወር መጀመሪያ ላይ ቱርክ ስደተኞቹን ወደ ሃገራቸው ለመመለስ በምታደርገው ጥረት ዓለማ አቀፍ ድጋፍ የማታገኝ ከሆነ ስደተኞቹ ወደ አውሮፓ አልፈው እንዲሄዱ ድንበሯን ክፍት እንደምታደርግ ገልጻ ነበር።ቱርክ በድንበሯ በኩል ስደተኞች ወደ አውሮፓ ለመግባት እንዳይሞክሩ ጠበቅ ያለ ጥበቃ ማድረግ እንዳለባት እ.አ.አ በ2016 ከአውሮፓ ህብረት ጋር በተደረሰ ስምምነት መሰረት ስምምነት ተደርሷል፡፡ቱርክ ይህንን በማድረጓና ከሶሪያ የሚመጡ ስደተኞችን በማስተናገዷ ከአውሮፓ ህብረት 6.6 ቢሊየን ዶላር እንደምታገኝ ቃል ተገብቶላት ነበር። ነገር ግን ፕሬዝዳንት ኤርዶአን ቃል ከተገባው ገንዘብ ግማሽ የሚሆነው ብቻ ነው የደረሰን ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።የአውሮፓ ህብረት በበኩሉ 6 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር የሚሆነውን ገንዘብ ለቱርክ አስረክቢያለሁ ብሏል።ቱርክ በ2011 የተጀመረውን የእርስ በእርስ ጦርነት ሸሽተው የወጡ ከ3 ነጥብ 6 ሚሊየን በላይ ስደተኞችን በተለያዩ ማቆያዎች ይዛለች።በቱርክ ድንበር በኩል የምትገኘው ኢድሊብ ግዛት በአማጺያን እና ኢስላማዊ ጂሃዲስቶች ቁጥጥር ስር በመሆኗ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን ዜጎች ከቅያቸው ወደ ሰሜናዊ ሶሪያ ተሰድደዋል። | https://waltainfo.com/am/33999/ | 227 | 5ፖለቲካ
|
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ከቦንጋ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ተወያያዩ | ሀገር አቀፍ ዜና | September 15, 2019 | Unknown | ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ በዛሬው ዕለት ከካፋ ዞን ነዋሪዎች ጋር በቦንጋ ከተማ ተወያይተዋል ።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጋር ለስራ ጉብኝት ካፋ ዞን፣ ቦንጋ ከተማ ሲገቡ በከተማዋ ስታዲየም ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡መንግስት ዜጎች ተከባብረው የሚኖሩባት ታላቋን ኢትዮጵያን ለመፍጠር የሚያደርገውን ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በውይይቱ ወቅት አረጋግጠዋል፡፡የካፋ ህዝብ እንደ ህዝብ ከሰው ብቻ ሳይሆን ከተፈጥሮ ጋር ተስማምቶ የኖረ አስተዋይ ህዝብ እንደሆነ ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ ከቂም፣ ተንኮልና ባለፈ ታሪክ መነታረክ ከድህነት ውጪ የሚያሥገኘው ጥቅም አይኖርም ብለዋል፡፡በትብብርና በመደመር በመሥራት ኢትዮጵያን ለማበልጸግ ጊዜው አሁን መሆኑን በንግግራቸው አፅንዎት የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ መንግስት አቅም በፈቀደ መጠን የተነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል፡፡የክልል አደረጃጀት ለውጥ የሁሉም ጥያቄ መልስ አይሆንም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ተያያዥነት ያላቸው አማራጭ አሰራሮች መፈተሽ እንደሚያስፈልግ አንስተዋል።በውይይቱ ነዋሪዎቹ በክልል ከመሰረተ ልማት፣ ከጤና ተቋም ግንባታ እንዲሁም ከመደራጀት መብት ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን ያነሱ ሲሆን፤ ዞኑ ባለው እምቅ የተፈጥሮ ሀብት ተጠቃሚ እንዲሆን ኢንቨስትመንት እንዲመቻች ጠይቀዋል።ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ለማ መገርሳም እና የደቡብ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው በውይይቱ ተሳትፈዋል። | https://waltainfo.com/am/734/ | 164 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የብሔራዊ አንድነት ቀን በመላ ሀገሪቱ እየተከበረ ነው | ሀገር አቀፍ ዜና | September 15, 2019 | Unknown | የብሔራዊ አንድነት ቀን በመላ ሀገሪቱ እየተከበረ ነው ፡፡መደመር ለብሔራዊ አንድነት በሚል መርህ ቃል ዛሬ በመላው ሀገሪቱ የብሔራዊ አንድነት ቀን እየተከበረ ይገኛል፡፡በአዲሱ አመት በአንድነትና በአብሮነት መንፈስ የምንፈልጋትን ኢትዮጵያ አብረን እንገንባ የሚል መልዕክት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በፌስቡክ ገጹ ላይ አስፍሯል።የዘንድሮ ጳጉሜን ቀናት በተለያዩ ዝግጅቶችና ርዕሰ ጉዳዮች እየተከበሩ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ | https://waltainfo.com/am/737/ | 48 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የሀይማኖት አባቶች ለዘመን መለወጫ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላ | ሀገር አቀፍ ዜና | September 15, 2019 | Unknown | አዲስ የዘመን መለወጫ ተብሎ የሚነገርለት ዕለት አዲስ ሊሆን የሚችለው በዋናነት ልቦና ሲታደስ ነው ያሉት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁእ አቡነ ማትያስ፤ በአስተሳሰብ፣ በስራና በአኗኗር ሁሉ ከልብ የሆነ መታደስ ከሁሉም ይጠበቃል ብለዋል፡፡“የኢትዮጵያን ህዳሴን እናበስራለን” የሚለው መልካም ምኞት ከቃላት ባለፈ በይቅርታና እውነተኛ መግባባት በሁሉም ወገኖች መከናወን እንዳለበት በመጥቀስ፤ በሃሳብ መቀራረብና በሰጥቶ መቀበል መርህ እየተቻቻሉ መሄድን እንደአዋጭ ባህል አድርገን መጓዝ ይኖርብናል ብለዋል፡፡ይህ ታላቅና ባለታሪክ ህዝብ ለዘመናት ተንከባክቦ ያቆየው ሃይማኖቱን፣ ታሪኩን፣ ባህሉንና አንድነቱን አሁንም ፣ነገም ሆነ ከነገ በኋላ ጠብቆ እንዲጓዝ መሰናክል አናብዛ ያሉት ብፁዕነታቸው፤ ይህን በማድረግ በእግዚአብሄርና በታሪክ ፊት በደል ከመፈፀም እንጠንቀቅ ብለዋል፡፡አዲሱ ዓመት የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የአንድነት፣ የስምምነትና የይቅርታ ዘመን ማድረግ የምንችለው ከእግዚአብሄር በታች እኛው በመሆናችን ልዩነቶችን ወደ መቀራረብ ብሎም ወደ ፍፁም መተማመን በማምጣት ሀገሪቱንና ህዝቦቿን ወደ ላቀ ህዳሴ እናሸጋግር ሲሉ አባታዊ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡በአዲሱ 2012 ዓመት መልካም ነገርን ለማቀድና ለመስራት ልባችንን ከፍተን በፍቅር፣ በይቅርታ፣ በአንድነትና በህብረት መንፈስ ልንጀምረው ያስፈልጋል ያሉት ደግሞ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀዻዻሳት ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ ናቸው፡፡ | https://waltainfo.com/am/740/ | 148 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
በሳዑዲ ላይ ጥቃት ከተሰነዘረ በኋላ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አሳየ | ቢዝነስ | September 16, 2019 | Unknown | በሳዑዲ አረቢያ የነዳጅ ማቀነባበሪያ ተቋማት ላይ ጥቃት ከተሰነዘረ በኋላ በየዓለም የነዳጅ ዘይት ዋጋ ጭማሪ ማሳየቱ ተገለጸ።ቅዳሜ ዕለት በሁለት የሳዑዲ አረቢያ ነዳጅ ማቀነባበሪያ ቦታዎች ላይ ጥቃት ከተሰነዘረ በኋላ ለዓለም የሚቀርበው የነዳጅ መጠን አምስት በመቶ ቀንሷል።በዚህም ድፍድፍ የነዳጅ ዘይት ዋጋ ከ15 እስከ 19 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። በድሮን ጥቃት ጉዳት የደረሰባቸው የሳዑዲ ነዳጅ ማቀነባበሪያ ተቋማት ወደ ቀደመ ስራቸው ለመመለስ ሳምንታት ያስፈልጋል ተብሏል።ቅዳሜ ዕለት ጥቃት የተሰነዘረባቸው የሳዑዲ ነዳጅ ማቀነባበሪያ ተቋማት በዓለማችን እጅግ ዘመናዊ እና ከፍተኛ ጥበቃ ከሚደረግላቸው የነዳጅ ማቀነባበሪያዎች መካከል ተጠቃሽ ናቸው።በኢራን ድጋፍ የሚደረግላቸው የሁቲ አማጽያን የድሮን ጥቃቱን የፈጸምነው እኛ ነን ቢሉም አሜሪካ ግን ሳዑዲ ላይ ለደረሰው ጥቃት ኢራንን ተጠያቂ አድርጋለች።የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ማይክ ፖምፔዮ ቅዳሜ ዕለት የሳዑዲ ነዳጅ ማውጫ ተቋማት ላይ ለተሰነዘረው የድሮን ጥቃት ኢራንን ተጠያቂ አድርገዋል።ከምዕራባውያን መንግሥታት ድጋፍ የሚያገኘው ሳዑዲ መራሹ ኃይል በየመን እየተደረገ ባለው ጦርነት ለየመን መንግሥት ድጋፍ የሚያደርግ ሲሆን፤ ኢራን ደግሞ ለሁቲ አማጽያን ድጋፍ ታደርጋለች።የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊው ማይክ ፖምፔዮ ''የድሮን ጥቃቱ ከየመን ስለመነሳቱ የሚያሳይ ምንም አይነት ማስረጃ የለም። ሁሉም መንግሥታት ኢራን በዓለም የኢኔርጂ ምንጭ ላይ የሰነዘረችውን ጥቃት ማውገዝ አለባቸው'' ብለዋል።ፕሬዝዳንት ትራምፕ በበኩላቸው ለጥፋቱ ማን ተጠያቂ እንደሆነ ስለምናውቅ "አቀባብለን" የሳዑዲ መንግሥት ምክረ ሃሰብ ምን እንደሆነ እየጠበቅን ነው ብለዋል።የሳዑዲ ባለስልጣናት ጥቃቱ በሰው ላይ ያደረሰው ጉዳት የለም በማለት የድሮን ጥቃቱ ስላደረሰው ጉዳት ዝርዝር መረጃ ሳይሰጡ ቀርተዋል። የተሰነዘረው ጥቃት የሳዑዲ አረቢያን የድፍድፍ ነዳጅ የማምረት አቅም በግማሽ መቀነሱ ግን ተረጋግጧል።ሳዑዲ አረቢያ የዓለማችን ቁጥር አንድ ነዳጅ አምራች ስትሆን፣ በየቀኑ ወደ 7 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ ወደ ውጪ ሃገራት ትልካለች። (ምንጭ፡-ቢቢሲ) | https://waltainfo.com/am/33561/ | 227 | 3ቢዝነስ
|
በዴሞክራቲክ ኮንጎው ጀልባ ሰጥሞ 34 ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ | ሀገር አቀፍ ዜና | September 16, 2019 | Unknown | በዴሞክራቲክ ኮንጎ፤ በኮንጎ ወንዝ ላይ መንገደኞችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ጀልባ ሰጥሞ ቢያንስ የ34 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ተገለጸ።ፖሊስ እንዳስታወቀው ከአደጋው 76 ተሳፋሪዎች በህይወት መትረፍ የቻሉ ሲሆን፣ በወቅቱ ጀልባው ከአቅሙ በላይ በጣም ብዙ ሰው ሳይጭን እንዳልቀረ ተገምቷል።ጀልባው ከሀገሪቱ ዋና ከተማ ኪንሻሳ በመነሳት ማይ ንዶምቤ ወደተባለችው ሰሜናዊ ግዛት እየተጓዘ ነበር።የአደጋው መንስኤ እስካሁን እንዳልታወቀ የገለጸው ፖሊስ ተሳፋሪዎቹ የውሃ ላይ መንሳፈፊያ ጃኬቶችን አድርገው ነበር ብሎ ለማሰብ እጅግ አስቸጋሪ ነው ብሏል።በዴሞክራቲክ ኮንጎ የውሃ ላይ ጉዞ በጣም የሚዘወተር ሲሆን፣ ጀልባዎች የተለያዩ ጭነቶችና ተሳፋሪዎች ከአቅም በላይ ጨነው ሲጓዙ መመልከት የተለመደ ነው።እስከ 40 ሜትር የሚደርስ ከፍታ ያላቸውና አንዳንዴም ባለሁለት ክፍል ትልልቅ ጀልባዎች ግልጋሎት ላይ ሲውሉ ይስተዋላል። ሁሉም ተሳፋሪዎች ደግሞ ውሃ ዋና ይችላሉ ብሎ ማሰብ ከባድ ነው።የዴሞክራቲክ ኮንጎ የአስፋልት መንገዶች በጣም የተበላሹና ከጥቅም ውጪ በመሆናቸው ብዙ የሀገሬው ሰዎች በጀልባ የሚደረጉ ጉዞዎችን ምርጫቸው ያደርጋሉ። (ምንጭ፡-ቢቢሲ) | https://waltainfo.com/am/33474/ | 126 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የሶስትዮሽ የሚኒስትሮች ስብሰባ በካይሮ እየተካሄደ ነው | ቢዝነስ | September 16, 2019 | Unknown | የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ የኢትዮጵያ፣ የግብጽ እና የሱዳን የሶስትዮሽ የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ በግብጽ ካይሮ መስከረም 4 ቀን 2012 ዓ.ም በመካሄድ ላይ ነው።ስብሰባው በዋናነት የሶስቱ ሀገራት የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች ባለፈው ዓመት መስከረም እና የካቲት 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ካደረጉት እና የግድቡን የውሃ አሞላል እና አለቃቅ በተመለከተ ከተደረገው ውይይት የቀጠለ ነው።በስብሰባው መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢፌዲሪ የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ስለሺ በቀለ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መገንባት ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ኢትዮጵያ በቅን ልቦና እና በመተባበር ፍላጎት ያደረገችውን ጥረት ገልጸዋል።የዚህ ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል በጉዳዩ ላይ የሚደርሰው መግባባት የሶስቱንም ሀገራት እኩል ጥቅም ለማስከበር ወሳኝ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።ሚኒስትሩ በዚህ ስብሰባ ሶስቱ ሀገራት በቀሪ ቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ በሶስቱ ሀገራት ሳይንቲስቶች ቡድን የቀረቡለትን ሪፖርት እና ምክረ-ሃሳቦች ተመልክቶ የወደፊት አቅጣጫ ለማስቀመጥ እንደሆነ አመላክተዋል።በዚህም ረገድ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሚደረጉ ትብብሮች እና የሚቀርቡ ሃሳቦች በሶስቱ ሀገራት የተቋቋሙትን የትብብር ማዕቀፎች ጠብቀው መሄድ እንዳለባቸው አስገንዝበው ሶስቱ አገራት በተናጠል የሚያቀርቧቸው የመፍትሄ ሃሳቦችም ይህንኑ መስመር ተከትለው መቅረብ እንዳለባቸው ገልጸዋል።የአባይ ወንዝ ዋነኛው የኢትዮጵያ የውሃ ምንጭ እንደመሆኑ የውሃው አጠቃቀም የአገሪቱ የህልውና ጉዳይ መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትሩ፣ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ላይ የምትከተለው አቅጣጫ የራሷን መብት እንዲሁም የጎረቤት አገራትን ህዝቦች ጥቅም የጠበቀ እንዲሆን ከፍተኛ ትኩረት ሰጥታለች ብለዋል፡፡የህዳሴው ግድብን አስመልክቶ በሱዳን፣ ግብጽ እና ኢትዮጵያ መካከል የሚደረገው የሶስትዮሽ ምክክር የተፋሰሱን ሀገራት በውሃው የመልማት እና የመጠቀም መብትም የሚያረጋገጥ እና ትብብርንም የሚያጎለብት መሆኑን ሚኒስትሩ አብራርተዋል።ሚኒስትሩ የህዳሴ ግድብ ከተጀመረ ጀምሮ ሶስቱ ሀገራት የመጡበት መንገድ ስኬት የተመዘገበበትና በሀገራቱ መካከል ይበልጥ መቀራረብን እንደፈጠረ ገልጸዋል።የግብጹ የውሃ ሚኒስትር ዶ/ር ሞሐመድ አብድል አቲ በበኩላቸው ባደረጉት ንግግር፣ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ የሚደረገው ትብብር ለሌሎች አገራትም አርአያ እንደሚሆን ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል፡፡ሚኒስትሩ በህዳሴው ግድብ አሞላል እና የውሃ አለቃቀቅ ላይ የሚደረግ ውይይት የሶስቱንም አገራት ጥቅም መሰረት ያደረገ እንዲሁም ሶስቱም ወገኖች አሸናፊ የሚሆኑበት እንዲሆን መስራት እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡ሚኒስትሩ ባለፉት ስምንት አመታት በህዳሴው ግድብ ላይ የተደረጉት ውይይቶች የሚጠበቀውን ያህል ውጤት እንዳላመጡ ገልጸው አዲስ ሃሰቦችን ማስተናገድ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡የሱዳኑ የውሃ እና መስኖ ሚኒስትር ፕሮፌሰር ያሲር ሞሐመድ አባስ በበኩላቸው፣ በሱዳን እና ኢትዮጵያ ባልደረቦቻቸው ስለቀረበላቸው የእንኳን ደህና መጡ መልዕክት ምስጋና አቅርበው ከሚኒስትርነት ሹመታቸው በፊት ያከናውኗቸው የነበሩ የድንበር ተሻጋሪ የውሃ ሃብቶች አስተዳደር ስራዎች በሶስቱ እህትማማች አገራት ውይይት ላይ ገንቢ አስተዋጽኦ ለማድረግ እንደሚያግዛቸው ተናግረዋል፡፡ሚኒስትሩ በተግባር ከሚያውቋቸው የሌሎች የድንበር ተሻጋሪ ወንዝ አገራት ትብብር ጋር ሲነጻጸር የኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ የጀመሩት ትብብር ስኬታማ ስራዎችን ማከናወኑን ገልጸዋል፡፡ሚኒስትሩ ይህ የሶስቱንም አገራት ጥቅም የሚያስጠብቅ ስኬታማ የትብብር ማዕቀፍ በተጀመረው መልኩ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ እንዲቀጥል አገራቸው የሚጠበቅባትን እንደምትወጣ ገልጸዋል፡፡ (ምንጭ:- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር) | https://waltainfo.com/am/23961/ | 375 | 3ቢዝነስ
|
ብራዚል የአማዞን እሳትን ለማጥፋት ወታደር ልትልክ ነው | ዓለም አቀፍ ዜና | September 15, 2019 | Unknown | የብራዚል ፕሬዘዳንት ጃዬር ቦልሶናሮ፤ በአማዞን ደን የተነሳውን እሳት ለማጥፋት በሚደረገው ጥረት የአገሪቱ ወታደራዊ ኃይል ድጋፍ እንዲሰጥ ትዕዛዝ አስተላለፉ።በፕሬዘዳንቱ ውሳኔ መሰረት በጥብቅ ተፈጥሯዊ ሥፍራና በድንበር አካባቢ ወታደሮች ይሰማራሉ። ውሳኔው ይፋ ከመደረጉ አስቀድሞ የአውሮፓ መሪዎች ብራዚል ላይ ከፍተኛ ጫና እያደረጉ ነበር።“ወታደር እንደመሆኔ የአማዞን ጫካን እወደዋለሁ፤ ልታደገውም እፈልጋለሁ” ሲሉ ፕሬዘዳንቱ ንግግር አድርገዋል።ወታደሮቹ ይሠማራሉ የተባለው ለአንድ ወር ሲሆን፤ የመከላከያ ሚኒስትሩ ፈርናንዶ አዜቬዶ ኤ ሲልቫ ሂደቱን ያስፈጽማሉ ተብሏል።ብራዚል በአማዞን ጫካ የተከሰተውን እሳት ለማጥፋት ያላሰለሰ ጥረት ካላደረገች ፈረንሳይና አየርላንድ ከሰሜን አሜሪካ ጋር ሊያደርጉት የነበረውን የንግድ ስምምነት እንደማያጸድቁ ተናግረዋል።የብራዚል ፕሬዘዳንት በበኩላቸው መሪዎቹ “በአማዞን ደን የተነሳውን እሳት አስታከው ማዕቀብ መጣል አይችሉም” ሲሉ ተችተዋል።በአሁን ወቅት የአውሮፓ ሕብረት ካውንስል መሪ የሆነችው ፊንላንድ የገንዘብ ሚኒስትር፤ የአውሮፓ ሕብረት የብራዚል የሥጋ ምርት ላይ ማዕቀብ እንዲጥል ጠይቀዋል።የተፈጥሮ ጥበቃ ላይ የሚሠሩ ቡድኖች ባሳለፍነው አርብ በመላው ብራዚል ሰላማዊ ሰልፍ አድርገው ነበር። በተለያዩ አገሮች የሚኖሩ ብራዚላዊያንም ተቃውሟቸውን እያሰሙ ይገኛሉ።የዓለም ግዙፉ ደን እንዲሁም “የዓለም ሳምባ” እየተባለ የሚሞካሸው አማዞን የሙቀት መጠን መጨመር ጋብ እንዲል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል።አማዞን የአንድ ሚሊየን ሰዎች መኖሪያ ከመሆኑ በተጨማሪ ከሦስት ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ እጽዋትና እንስሳት መገኛም ነው።የጀመርኗ መራሔተ መንግሥት አንግላ መርኬል፣ የፈረንሳዩ ፕሬዘዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እና የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን እሳቱን “ዓለም አቀፍ ቀውስ” ብለውታል።አንግላ እና ኢማኑኤል በ ጂ-7 ውይይት ላይ የአማዞን ደን እሳት ለውይይት መቅረብ እንዳለበትም ገልጸዋል።የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሀፊ አንቶንዮ ጉቴሬዝ በትዊት ገጻቸው ላይ “ዓለም በአየር ንብረት ለውጥ ቀውስ ውስጥ በምትገኝበት በዚህ ወቅት፤ ቀዳሚ የኦክስጅን ምንጫችን የሆነው የአማዞን ደን አደጋ ውስጥ መውደቅ አይገባውም” የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል። | https://waltainfo.com/am/706/ | 224 | 4ዓለም አቀፍ ዜና
|
ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በቀድሞው የዚምባብዌ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ የስንብት ፕሮግራም ላይ ተሳተፉ | ሀገር አቀፍ ዜና | September 15, 2019 | Unknown | ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ባለፈው ሳምንት ከዚህ ዓለም በሞት በተለዩት በቀድሞው የዚምባብዌ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ የስንብት ፕሮግራም ላይ ተሳትፈዋል፡፡በሀራሬ በሚገኘው ብሄራዊ የስፖርት ስታዲየም በተካሄደው ስነ ስርዓት ላይ የሀገራትና የመንግስታት መሪዎች እንዲሁም የቀድሞ ፕሬዝዳንቶችና በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ተገኝተዋል፡፡ኢትዮጵያ በሺዎች የሚቆጠሩ የነጻነት ታጋዮችን በማሰልጠን ዚምባብዌ ከቅኝ ግዛት እንድትላቀቅ የራሷን ሚና መጫወቷ ይታወቃል፡፡ይህ ሁኔታ ሮበርት ሙጋቤ ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸው ቁርኝት ጥብቅ እንዲሆን የራሱን አስተዋፅዖ አድርጓል፡፡ምንጭ፡- የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት | https://waltainfo.com/am/32733/ | 64 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ከቦንጋ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ተወያያዩ | ሀገር አቀፍ ዜና | September 15, 2019 | Unknown | ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ በዛሬው ዕለት ከካፋ ዞን ነዋሪዎች ጋር በቦንጋ ከተማ ተወያይተዋል ።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጋር ለስራ ጉብኝት ካፋ ዞን፣ ቦንጋ ከተማ ሲገቡ በከተማዋ ስታዲየም ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡መንግስት ዜጎች ተከባብረው የሚኖሩባት ታላቋን ኢትዮጵያን ለመፍጠር የሚያደርገውን ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በውይይቱ ወቅት አረጋግጠዋል፡፡የካፋ ህዝብ እንደ ህዝብ ከሰው ብቻ ሳይሆን ከተፈጥሮ ጋር ተስማምቶ የኖረ አስተዋይ ህዝብ እንደሆነ ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ ከቂም፣ ተንኮልና ባለፈ ታሪክ መነታረክ ከድህነት ውጪ የሚያሥገኘው ጥቅም አይኖርም ብለዋል፡፡በትብብርና በመደመር በመሥራት ኢትዮጵያን ለማበልጸግ ጊዜው አሁን መሆኑን በንግግራቸው አፅንዎት የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ መንግስት አቅም በፈቀደ መጠን የተነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል፡፡የክልል አደረጃጀት ለውጥ የሁሉም ጥያቄ መልስ አይሆንም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ተያያዥነት ያላቸው አማራጭ አሰራሮች መፈተሽ እንደሚያስፈልግ አንስተዋል።በውይይቱ ነዋሪዎቹ በክልል ከመሰረተ ልማት፣ ከጤና ተቋም ግንባታ እንዲሁም ከመደራጀት መብት ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን ያነሱ ሲሆን፤ ዞኑ ባለው እምቅ የተፈጥሮ ሀብት ተጠቃሚ እንዲሆን ኢንቨስትመንት እንዲመቻች ጠይቀዋል።ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ለማ መገርሳም እና የደቡብ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው በውይይቱ ተሳትፈዋል። | https://waltainfo.com/am/32732/ | 164 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ናይጄሪያ በደቡብ አፍሪካ ለሚገኙ የሀገሪቱ ዜጎች ነፃ የአውሮፕላን ትኬት አቀረበች | ዓለም አቀፍ ዜና | September 15, 2019 | Unknown | በደቡብ አፍሪካ በውጭ ሀገራት ዜጎች ላይ ያተኮረ ጥቃት መቀስቀሱን ተክትሎ ናይጀሪያ በሀገሪቱ በመኖርና በመስራት ላይ የሚገኙ ዜጎች ወደ ናይጄሪያ ይመለሱ ዘንድ ነፃ የአውሮፕላን ትኬት አቅርባለች ፡፡የናይጄሪያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በትዊተር ገፁ እንዳስታወቀው ፤ከደቡብ አፍሪካ ወደ ሀገራቸው መመለስ የሚፈልጉ ዜጎች የነፃ የአውሮፕላን ጉዞ ትኬትን ተዘጋጅቶላቸዋል፡፡የሰላም አየርመንገድ ሃላፊ አለን ኦኦንይማ ከነገ ዓርብ ጀምሮ ከደቡብ አፍሪካ ወደ ናይጄሪያ መመለስ ለሚሹ ዜጎች በነፃ ዜጎችን የሚያመላልስ አውሮፕላን ደቡብ አፍሪካ እንደሚላክና ፈቃደኛ ለሆኑ ናይጄሪያውያን የነፃ የአየር ትራንስፖርት ግልጋሎት እንደሚሰጥ አስታውቀዋል፡፡ወደ ሀገራቸው የመመለስ ፍላጎቱ ያላቸው ዜጎች በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶርያ የናይጀሪያ ከፍተኛ ኮሚሽን መረጃዎችን መውሰድ እንዳለባቸውም ተገልጿል፡፡ከዚህ አስቀድሞ የናይጄሪያ ልዩ መልዕክተኛ ቡድን በዛሬው ዕለት በወቅታዊ የደቡብ አፍሪካ ሁኔታ ዙሪያ ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎዛ ጋር እንደሚወያይም ነው የሲጂቲኤን ዘገባ ያመለከተው፡፡በደቡብ አፍሪካ በውጭ ሀገራት ዜጎች ላይ ያተኮረ ጥቃት መቀስቀሱን ተከትሎ በርካታ ሀገራት ዜጎቻቸው አስፈላጊውን የደህንነት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማስጠንቀቂያዎችን ሲሰጡ ቆይተዋል፡፡ | https://waltainfo.com/am/725/ | 132 | 4ዓለም አቀፍ ዜና
|
የአለም ባንክ ለኬንያ የ75 ቢሊዮን ሽልንግ ብድር ፈቀደ | ዓለም አቀፍ ዜና | September 15, 2019 | Unknown | የአለም ባንክ ኬንያ የጠየቀችውን የ75 ቢሊዮን ሽልንግ ብድር ፈቀዷል፡፡ባለፈው የፈረንጆቹ መጋቢት ወር ኬኒያ ለአለም ባንክ በጻፈችው ደብዳቤ በጀቷን ለመደጎም አስቸኳይ ብድር እንዲሰጣት በጠየቀችው መሰረት ነው ይህ ብድር የተፈቀደላት፡፡ገንዘቡ በኬንያ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውል ሲሆን በተለይም የአርሶ አደሮችን ምርታማነት እና ገቢ ለማሳደግ ስራ እንደሚውል አበዳሪው ተቋም ገልጿል፡፡በተጨማሪም በግብርናው ዘርፍ የሚስተዋለውን ስር የሰደደ ሙስና ለመዋጋትም ይውላልም ነው የተባለው፡፡እንደ የአለም ባንክ ገለጻ ከሆነ ገንዘቡ በሃገሪቱ ግልጽ የሆነ የግብይት ስርዓት እንዲፈጠር እንዲሁም የመንግስት መስሪያ ቤቶች የግዢ ሂደትን ለማሻሻል ይውላል፡፡ከዚህም ባሻገር ይህ ብድር በኬንያ ያለውን የኢንተርኔት አጠቃቀም ለማሳደግና የኢንተርኔት አገልግሎትን ለመላው ኬንያዊያን ተደራሽ ለማድረግ ያግዛል፡፡/ሲጂቲኤን/ | https://waltainfo.com/am/728/ | 89 | 4ዓለም አቀፍ ዜና
|
የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ደቡብ አፍሪካን ሊጎበኙ ነው | ዓለም አቀፍ ዜና | September 15, 2019 | Unknown | በቀጣዩ ወር የሚደረገው የፕሬዚዳንቱ ይፋዊ ጉብኝት የሀገራቱን ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ ስለመሆኑ የሲጂቲኤን ዘገባ ያመለክታል፡፡ ቀደም ሲል የናይጄሪያ ልዩ ልዑክ ከደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ጋር በሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ የመከረ ሲሆን፤ የፕሬዚዳንት ቡሃሪ ጉብኝትም የተጀመረውን የሁለትዮሽ ምክክር ይበልጥ መስመር ለማስያዝ እንደሚያስችል ይጠበቃል፡፡ ይሁንና የደቡብ አፍሪካው ኤምቲኤን ግሩፕ እና በሱፐርማርኬት የሚታወቀው ሾፕራይት በናይጄሪያ የሚገኙ ቅርንጫፎቻቸውን ዘግተዋል፡፡ ተቋማቱ በናይጄሪያ ቢሮዎቻቸው የሚሰሩ ሰራተኞች ላይ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ ነው ከዚህ እርምጃ ላይ የደረሱት ተብሏል፡፡ስጋት ላይ ናቸው በሚል ናይጄሪያ ነፃ የአውሮፕላን ትኬት ማቅረቧ ይታወሳል፡፡ በደቡብ አፍሪካ በውጪ ሀገራት ዜጎች ላይ እየተፈፀመ ያለውን ጥቃት በርካታ ሀገራት ማውገዛቸውም አይዘነጋም፡፡ | https://waltainfo.com/am/731/ | 89 | 4ዓለም አቀፍ ዜና
|
27 ሚሊዮን ብር የሚገመት አደንዛዥ ዕፅ ወደ አገር ውስጥ ሊገባ ሲል ተያዘ | ቢዝነስ | September 15, 2019 | Unknown | የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን በቦሌ አለም አቀፍ አየርመንገድ በኩል ወደ አገር ሊገባ የነበረ 27 ሚሊዮን ብር የሚገመት 10 ነጥብ 8 ኪሎ ግራም የሚመዝን አደንዛዥ ዕፅ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል።የጉምሩክ ተቆጣጣሪዎች ባደረጉት ክትትል በቁጥጥር ስር ያዋሉት ሄሮይን እና ኮኬን የተባሉ አደንዛዥ እፆችን ነው፡፡አደንዛዥ እፆቹን አንድ ናይጄሪያዊ ዜጋ በያዘው ቀላል ሻንጣ ውስጥ ደብቆ ለማለፍ ሲሞክር በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት እንደሚገኝ የቦሌ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ተገኔ ደረሰ በተለይ ለኢቢሲ ገልፀዋል፡፡ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ህገ ወጥ ንግድን ለመከላከል እየሰራው ባለው ስራ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎች በመያዝ ላይ ይገኛሉ። | https://waltainfo.com/am/23959/ | 86 | 3ቢዝነስ
|
17 የምግብ ዘይት ምርቶች መሰረታዊ ችግር ስላለባቸው ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው ተገለጸ | ቢዝነስ | September 15, 2019 | Unknown | የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን በአዲስ አበባና ሌሎች አካባቢዎች ባደረገው የገበያ ጥናት 17 የምግብ ዘይት ምርቶች ላይ መሰረታዊ ችግር በመስተዋሉ ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው አሳስቧል፡፡ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ባደረገው የገበያ ጥናት የዘይት ምርቶቹ የሚመረቱበት ቦታና የተመረተበት ሃገር ፣የምርት መለያ ቁጥር ፣የአምራች አድራሻ የሌላቸው፣የገላጭ ጽሁፍ ችግርና ለጤና ጠቀሜታ እንዳለው ተደርጎ የተቀመጠ፣የመጠቀሚያ ጊዜና ማብቂያ ቀን የሌላቸው እንዲሁም የሀገሪቱን የደረጃ ምልክት ያለጠፉና ደረጃውንም የማያሟሉ መሆናቸው በተደረገው ጥናት መረጋገጡን አስታውቋል፡፡ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው የተባሉት የምግብ ዘይት ምርቶችም ሉሉ ዘይት፣ አርሲ ዘይት፣አሃዱ ዘይት፣ድሬ ንጹህ የምግብ ዘይ፣አሚን ንጹህ የምግብ ዘይት፣ሮያል የምግብ ዘይት፣ዳግም የተጣራ የኑግ ዘይት፣ጄጃን የምግብ ዘይት፣ውብ የተጣራ የኑግ ዘይት፣ለማ የኑግ ዘይት፣ኑድ ንጹህ የምግብ ዘይት፣ገበታ የምግብ ዘይት፣ዘመን ዘይት፣አጋር ዘይት፣አናጅና ዘይት ናቸው፡፡በመሆኑ ህብረተሰቡ የትኛውንም የምግብ ምርት ከገበያ ሲገዛ የተመረተበትና የመጠቀሚያ የአገልግሎት ጊዜው ትክክለኛነት ፣ያልተፋቀና ያልተሰረዘ መሆኑን ፤የአምራች ድረጀቱ ስምና ሙሉ አድረሻ፣የምርት መለያ ቁጥር ያለው መሆኑን በማረጋገጥ እንዲገዛ የተጠየቀ ሲሆን ፤የምርት ገላጭ ጹሁፍ ይዘቶችን ያላሟላ ምርት ህብተሰቡ መግዛት እንደሌለበት ተገልጿል፡፡ተመሳሳይ ምርቶች በሌሎች አካባቢ የመገበያያ ስፍራዎች ሊኖሩ ስለሚችሉም ህብረተሰቡ በአቅራቢያው ለሚገኝ የጤና ተቆጣጣሪ ፣ለፖሊስ አካላት ወይም በፌደራል ደረጃ ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በነጻ ስልክ መስመር በ8482 በመጠቆም እንዲያሳውቅ ጠይቋል፡፡በማያያዝም የክልል ተቆጣጣሪዎችና በየደረጃው የሚገኙ የቁጥጥር አካላት ምርቶቹን ከገበያ ላይ በአፋጣኝ የመሰብሰብ ስራውን እንዲሰሩ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጥሪውን አቅርቧል፡፡ | https://waltainfo.com/am/23960/ | 182 | 3ቢዝነስ
|
ኢትዮጵያ በተጠናቀቀው 2011 ቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንትን በመሳብ ከምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ሆነች | ሀገር አቀፍ ዜና | September 15, 2019 | Unknown | በተጠናቀቀው ዓመት 2011 ኢትዮጵያ ቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንትን በመሳብ ከምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ሆናለች፡፡ኢዋይ የተሰኘ አለምአቀፍ የፋይናንስ አማካሪ ተቋም ይፋ ያደረገው ጥናት እንዳመለከተው፤ ሀገሪቱ በዚህ ዓመት ከ258 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ የሆነ ቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንትን መሳብ ችላለች፡፡ይህ አሀዝም ከምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚዋ ሀገር አድርጓታል ነው ያለው፡፡ኢትዮጵያን ተከትሎ ኬንያ 74 ሚሊየን ዶላር ቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንትን መሳብ የቻለች ሀገር ሆናለች፡፡ታንዛኒያ በበኩሏ ቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንትን የመሳብ አቅሟ 36 ሚሊየን ዶላር በላይ በመድረሱ ከቃጣናው የሶስተኝነት ደረጃን አሰጥቷታል፡፡ኢትዮጵያ በተጠቀሰው ዓመት በ29 ፕሮጀክቶች ከ16 ሺህ ለሚልቁ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር የቻለች ሲሆን በአንፃሩ ኬንያ ከ64 ፕሮጀክቶች መፍጠር የቻለችው የስራ ዕድል 6 ሺህ ነው፡፡ታንዛኒያ በምታንቀሳቅሳቸው 19 ፕሮጀክቶች ከ3 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር ችላለች፡፡ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት አመቺ አካባቢዎችን ማዘጋጀት መቻሏ እና ተወዳዳሪ የገበያ እድል መኖሩ ተመራጭ እንዳደረጋት ነው በሪፖርቱ የተመለከተው፡፡በተለይም የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ለውጪ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማመቻቸት በሩን ለኢንቨስትመንት ክፍት መድረጋቸው ለሀገሪቱ ቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት ፍሰት መጨመር በምክንያትነት ተጠቅሷል፡፡ | https://waltainfo.com/am/693/ | 141 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የሮበርት ሙጋቤ አስከሬን ከሲንጋፖር ወደ ዚምባቡዌ ተሸኘ | ዓለም አቀፍ ዜና | September 15, 2019 | Unknown | ከቀናት በፊት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የቀድሞው የዚምባቡዌ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ አስከሬን ከሲንጋፖር ወደ ሀገሩ ዚምባቡዌ በአውሮፕላን ተሸኝቷል።ላለፉት ወራት በሲንጋፖር ሕክምናቸውን ሲከታተሉ የቆዩት ፕሬዚዳንቱ በ95 ዓመታቸው ነበር ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት፡፡የቀብር ስነስርዓታቸውም የፊታችን እሁድ የሚፈፀም ሲሆን፤ ከዚህ አስቀድሞ 60 ሺህ ተመልካቾችን ያስተናግዳል በተባለ ስታዲየም ይፋዊ የስንብት ይከናወናል ተብሏል፡፡የቀብሩ ቦታን በተመለከተ ግን እስካሁን ከስምምነት አለመደረሱም ነው ቢቢሲ በዘገባው ያመለከተው፡፡በወቅቱ የዚምባቡዌ ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ አስተዳደር እና በሙጋብዌ ቤተሰቦች መካከል ቀብሩ የት ይፈፀም በሚለው ጉዳይ ላይ ከመግባባት አልተደረሰም ተብሏል፡፡ | https://waltainfo.com/am/696/ | 76 | 4ዓለም አቀፍ ዜና
|
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከታሊባን ጋር የነበረውን የሰላም ስምምነት መሰረዛቸውን አስታወቁ | ዓለም አቀፍ ዜና | September 15, 2019 | Unknown | የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከታሊባን ጋር የነበረውን የሰላም ስምምነት መሰረዛቸውን አስታወቁ።ትራምፕ በትዊተር ገጻቸው ላይ የአፍጋኒስታኑን ፕሬዝዳንት አሽራፍ ጋህኒ እና የታሊባን መሪዎችን ለማግኘት ቀጠሮ ይዘው እንደነበር አስታውቀዋል።ይሁን እንጂ ሐሙስ ዕለት በአፍጋኒስታን መዲና ካቡል በተፈጸመው እና ታሊባን ኃላፊነቱን በወሰደው ጥቃት አንድ የአሜሪካ ወታደር መገደሉን ተከትሎ ትራምፕ የሰላም ስምምነቱን ሰርዘዋል።ሁለቱ አካላት ከሰላም ስምምነት እንዲደርሱ የአሜሪካ መንግሥት እና የታሊባን ተወካዮች በኳታር ዶሃ ከዘጠኝ ጊዜ በላይ ተገናኝተው መክረዋል። የሰላም ስምምነቱ አደራዳሪዎች ከቀናት በፊት አሜሪካ እና ታሊባን ‘በመርህ ደረጃ’ ከሰላም ስምምነት ደርሰዋል ብለው ነበር።ታሊባን ፈጽሜዋለሁ ባለው ጥቃት አንድ የአሜሪካ ወታደር ከተገደለ በኋላ፤ ትራምፕ በትዊተር ገጻቸው ላይ “በአስቸኳይ ውይይቶቹ እና የሰላም ድርድሩ እንዲቆም አዝዣለሁ” ብለዋል።የሰላም ስምምነቱ ተፈጻሚ ቢሆን ኖሮ አሜሪካ ወደ አፍጋኒስታን ካዘመተቻቸው ወታደሮች መካከል 5400 የሚሆኑት በ20 ሳምንታት ውስጥ ልታስወጣ ነበር።በአሁኑ ሰዓት አሜሪካ በአፍጋኒስታን ከ14 ሺህ በላይ ወታደሮች አሏት። ሐሙስ ዕለት በካቡል መኪና ላይ የተጠመደ ቦምብ ፈንድቶ አሜሪካዊውን ወታደር ጨምሮ 12 ሰዎች ተገድለዋል።ታሊባን በምፈጽማቸው ጥቃቶች ዒላማ የማደርገው የውጪ ሀገር ኃይሎችን ነው ይበል እንጂ በጥቃቶቹ ለከፍተኛ ጉዳት የሚዳረጉት ንጹሐን የአፍጋኒስታን ዜጎች ናቸው።አሜሪካ እ.አ.አ. 2001 ላይ አፍጋኒስታንን ከወረረች ወዲህ ከ3500 በላይ የውጪ ሀገራት ጥምር ኃይሎች ተገድለዋል። ከእነዚህም መካከል 2300 የሚሆኑት አሜሪካውያን ናቸው።ባለፉት 18 ዓመታት ምን ያክል የአፍጋኒስታን ሲቪሎች፣ የመንግሥት ወታደሮች እና ታጣቂ ሚሊሻዎች ህይወታቸውን እንዳጡ በውል አይታወቅም።ከወራት በፊት የተባበሩት መንግሥታት ባወጣው ሪፖርት መሰረት ከ32 ሺህ በላይ ሲቪሎች የተገደሉ ሲሆን፣ ሌሎች ተቋማት በበኩላቸው የውጪ ኃይሎችን ሲፋለሙ የነበሩ ከ42 ሺህ በላይ ሚሊሻዎች መገደላቸውን ይጠቁማሉ። (ምንጭ፡-ቢቢሲ) | https://waltainfo.com/am/699/ | 215 | 4ዓለም አቀፍ ዜና
|
በግማሽ አመት የኦንላይን ግብይት የቻይና ኢኮኖሚ እምርታ ማሳየቱ ተገለጸ | ዓለም አቀፍ ዜና | September 15, 2019 | Unknown | በግማሽ አመት የኦንላይን ግብይት የቻይና ኢኮኖሚ እምርታ ማሳየቱ ተገለጸ፡፡የኦንላይን ግብይት ለሀገሪቱ ምጣኔ ሃብታዊ ዕድገት ከፍተኛ ድርሻ እየተጫወተ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡ባለፉት ሁለት ተከታታይ ሳምንታት የኦንላይን ግብይት የግማሽ አመት የቻይና ኢኮኖሚ እድገት አስተዋፅኦ እንደነበር የሲጂቲኤን ዘገባ አመላክቷል፡፡የአለም ሁለተኛዋ ባለ ግዙፍ ምጣኔ ሃብት ባለቤት ቻይና ለኢኮኖሚዋ እድገት የሃገሪቱ ግዙፍ የማኑፋክቸሪንግ አምራች ሴክተሮች ድርሻ ከፍተኛ እንደሆነም ተነግሯል፡፡ አሁን ደግሞ በሃሪቱ ያሉት የኦላንይን የኢ-ኮሜርስ ኩባንያዎች ለሃገሪቱ የምጣኔ ሃብት እድገት ከፍተኛ ድርሻ እንዳበረከቱ መረጃዎች አሳይተዋል፡፡ከእነዚህ የኢ-ኮሜርስ ወይም የድረገፅ መገበያያ ተቋማት ዉስጥ ግዙፉ የአሊባባ ኩባንያ ተጠቃሽ ነዉ፡፡ የአሊባባ ኦንላይን ግብይት ቸርቻሪ የሆነዉ ቲ ሞል የ150 ሚሊዮን ሸማቾች ትእዛዝ ተቀብሏል፡፡የስታስቲክስ መረጃ እንደሚያመላክተዉ ከ8 ኦንላይን የግብይት ጥያቄዎች አንዱ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች ሲሆን ሽያጩም ከ40 የተለያዩ መለያ ያላቸዉ ምርቶች ከ100 ሚሊየን በላይ የቻይና ዩአን ገቢ አስገኝተዋል፡፡በባለፉት ዓመታት በፍጥነት በማደግ ላይ የነበረው የቻይና ኢኮኖሚ በዚህ በኢንተርኔት ኦንላይን መገበያያ ተመራጭ የግብይት ዘዴ መደገፉም ይነገራል፡፡እንደ አፕል ያሉ ታዋቂ መለያ ያላቸዉ ምርቶች 170 በመቶ ዓመታዊ እድገት እያሳዩ መምጣታቸዉ ለሃገሪቱ ምጣኔ ሀብት ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክተዋል፡፡ የሃገሪቱ ንግድ ሚኒስቴር ባወጣዉ የግማሽ አመት ኢ ኮሜርስ መረጃ ገጠራማ የቻይና አካባቢዎች የታየዉ የንግድ እንቅስቃሴ 1.3 ትሪሊዮን ዩአን የደረሰ ሲሆን በየአመቱ የ30.4 በመቶ እድገት እያስመዘገበ መጥቷልም፡፡በቻይና ያሉ የኢ ኮሜርስ ኩባንያዎች በአጠቃላይ ባሳለፍነዉ ግማሽ አመት 31.36 ትሪሊዮን ዩአን ገቢ አስገኝተው፤ 8.5 በመቶ የእድገት መጠንም አሳይተዋል፡፡በ2019 መጨረሻ በተያዘዉ ግብ ቢያንስ 10 ሚሊዮን ዜጎችን ከድህነት ለማላቀቅ ሃገሪቱ አቅዳ እየሰራች እንደሆነም የ ሲ ጂቲኤን ዘገባ ያሳያል፡፡ | https://waltainfo.com/am/702/ | 210 | 4ዓለም አቀፍ ዜና
|
ፕሬዝደንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የልብ ማዕከልን ጎበኙ | ሀገር አቀፍ ዜና | September 13, 2019 | Unknown | ፕሬዝደንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ግቢ ውስጥ የሚገኘውን የልብ ማዕከል ጎበኙ፡፡በማዕከሉ ህክምናቸውን በመከታተል ላይ ያሉ ልጆችንም ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡ፕሬዝዳንቷ አዲሱን አመት ምክንያት በማድረግም ለልጀቹ ስጦታ አበርክተዋል፡፡ከተመሰረተ አስር አመታት ገደማ የሆነው ማዕከል እስካሁን ድረስ ከ4 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ልጆች ነጻ የልብ ቀዶ ህክምና አገልግሎት ሰጥቷል፡፡ማዕከሉ የሚያደርጋቸው የስራ እንቅስቃሴዎች የሚያስደስቱ መሆናቸውን ያመለከቱት ፕሬዝደንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ኢትዮጵያውያን ከተባበርን ምን አይነት ታላቅ ስራ መስራት እንደምንችል ያየንበት ነው ብለዋል፡፡ምንጭ:- የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት | https://waltainfo.com/am/32728/ | 66 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ኢትዮጵያና የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት የቲቢ በሽታን ለመከላከል የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ | ሀገር አቀፍ ዜና | September 13, 2019 | Unknown | ኢትዮጵያና የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት/ዩኤስ አይ ዲ/ የቲቢ በሽታን ለመከላከል የሚያደርጉትን ጥረት ለማደስ የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡የጤና ሚኒስቴር ለቀጣይ 5 ዓመት የሚቆየውን አዲስ ስምምነትን በዩኤስ አይ ዲ በኩል ነው የተፈራረመው ።ስምምነቱን የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ሊያ ታደሰ እና በኢትዮጵያ የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (ዩ ኤስ አይ ዲ) ዳይሬክተር ሲን ጆንስ ተፈራርመዋል፡፡ስምምነቱ ዩ ኤስ አይ ዲ ዓለም ላይ የቲቢ በሽታን ለማጥፋት የሚተገብረው ፕሮግራም አካል ሲሆን በ2035 የቲቢ በሸታን ለመጥፋት "ግሎባል አክስሌተር ቱ ኢንድ ቲቢ" በሚል መርህ እየተሰራ ይገኛል ።በተጨማሪም ስምምነቱ እ.አ.አ በ2022 ዓለም ላይ ለ40 ሚሊየን የበሽታው ተጠቂዎች ህክምና ለማድረስ የሚያደርገውን ጥረት ለማገዝ ያለመ ነው ተብሏል፡፡የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ላይ የቲቢ በሽታን ለማጥፋት በትብብር እየሰራ ከሚገኝባቸው 30 ሃገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡ | https://waltainfo.com/am/32729/ | 112 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ የፈተና ውጤት ይፋ ሆነ | ሀገር አቀፍ ዜና | September 13, 2019 | Unknown | ሀገር አቀፉ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤትን በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል።ይፋ በተደረገው ውጤት መሰረት ከተፈታኞቹ መካከል ከ10 ሺህ በላይ ተማሪዎች አራት ነጥብ ማምጣታቸው ታውቋል።75 ነጥብ 5 በመቶ ያህል ተፈታኞች ደግሞ ሁለት ነጥብ እና ከዚያ በላይ እንዳመጡ ነው የተገለጸው።ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች የዘንድሮውን የ10ኛ ክፍል ፈተና መፈተናቸውን ኤጀንሲው አስታውቋል።ተማሪዎች ውጤታቸውን በኤጀንሲው ድረ ገጽ ወይም እንዲሁም በአጭር የጽሁፍ መልዕክት 8181 ላይ ID- ብለው የአድሚሽን ቁጥራቸውን በማስገባት መመልከት ይችላሉ። | https://waltainfo.com/am/32730/ | 73 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
መስከረም 4 ቀን ሊካሄድ የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ተራዘመ | ሀገር አቀፍ ዜና | September 13, 2019 | Unknown | በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ ጥቃት እየደረሰ ነው በሚል መስከረም 4፣ 2012 ዓ.ም ሊካሄድ ታስቦ የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ወደ ጥቅምት 30 ተራዘመ።የሰልፉ አስተባባሪዎች ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡ ሲሆን፤ መንግስት በጉዳዩ ዙሪያ ከተለያዩ ተቋማት ጋር ተጨማሪ ውይይቶችን ለማድረግ ሲባል ሰልፉ ወደ ጥቅምት 30 ቀን 2012 ዓ.ም መዘዋወሩን አስታውቀዋል።አስተባባሪዎቹ ከድሬዳዋና ሐረሪ ክልሎች ውጪ የፌደራል መንግስትን ጨምሮ ከቀሪዎቹ ክልሎች ጋር መወያየታቸውን አስታውሰው፤ የተለያዩ የመንግስት ተቋማትና ሃላፊዎች ሰልፉ እንዲራዘም በመጠየቃቸው ሰልፉን ሊራዘም መቻሉን ተናግረዋል።አስተባባሪዎቹ አክለውም በየጊዜው ከመንግስት ጋር የሚደረጉ ውይይቶችን በየ15 ቀኑ ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል። | https://waltainfo.com/am/32731/ | 82 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የደቡብ ሱዳን አቻቸውን አነጋገሩ | ፖለቲካ | September 15, 2019 | Unknown | የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የደቡብ ሱዳን አቻቸው አዉት ዴንግ አኩዊልን ትናንት ማምሻውን ተቀብለው አነጋግረዋል።በውይይታቸው በደቡብ ሱዳን ጁባ በቅርቡ በፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር እና በዶክተር ሪክ ማቻር መካከል ውይይት መካሄዱ ለደቡብ ሱዳን ብሎም ለአካባቢው ሠላም ያለው ፋይዳ እጅግ የላቀ መሆኑን አቶ ገዱ ገልጸዋል።የሁለቱ መሪዎች ፊት ለፊት ተገናኝቶ መወያየትም በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን በተቀናቃኝ ወገኖች የተቀመጠውን የሰላም ፍኖተ ካርታ ለመተግበር ወሣኝ ምዕራፍ መሆኑንመም ነው የተናገሩት።የደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አዉት ዴንግ አኩዊል በበኩላቸው በደቡብ ሱዳን እየታየ ያለው ፈጣን የፖለቲካ ለውጥ በአፍሪካ ቀንድ እየነፈሰ ካለው የተስፋና የሰላም አየር ጋር አብሮ የሚሄድ መሆኑን አንስተው፥ በለውጡ የደቡብ ሱዳን ህዝብ እጅግ ደስተኛ መሆኑን ገልፀዋል።የሁለቱ መሪዎች ውይይትም በደቡብ ሱዳን የደህንነትና የፖለቲካ ሁኔታዎች ዙሪያ ለመመካከር መልካም አጋጣሚን መፍጠሩን ነው ያመለከቱት።ለቀጣዩ ሂደትም ጎረቤት ሃገሮችና ኢጋድ የድጋፍ ሚናቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ ማቅረባቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት አስታውቋል። | https://waltainfo.com/am/31349/ | 132 | 5ፖለቲካ
|
ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የአልባሳት ስጦታና የምሳ ግብዣ አደረጉ | ሀገር አቀፍ ዜና | September 11, 2019 | Unknown | ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው አዲሱን ዓመት 2012 ምክንያት በማድረግ ከተለያዩ የህፃናት ማሳደጊያዎች ለተውጣጡ ታዳጊዎች የአልባሳት ስጦታ እና የምሳ ግብዣ አደረጉ፡፡ቀዳማዊት እመቤቷ ከ18 የህፃናት ማሳደጊያዎች ለመጡ 650 ለሚሆኑ ታዳጊዎች የአልባሳት ድጋፍ በማድረግ ታዳጊዎቹ መተሳሰብ፣ መረዳዳት እና አብሮነትን እንዲላመዱ ለማስቻል በቤተ-መንግስት አዲስ ዓመት ዋዜማን በሚኒሊክ አዳራሽ አክብረዋል፡፡ታዳጊዎቹም በቤተመንግስት ቅጥር ግቢ ውስጥ እየተሰራ ያለውን የእድሳት ስራና ታሪካዊ አሻራዎችን ጎብኝተዋል፡፡በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በተዘጋጀው ክብረ በዓል ላይ የቁርስ እና የምሳ ግብዣ ለህፃናቱ የተደረገ ሲሆን ህፃናቱም የተለያዩ ትዕይንቶችን አቅርበዋል።ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ከዚህ በፊት ከ400 በላይ ለሚሆኑ ህፃናት በተመሳይ ድጋፍ አድርገው በዓሉን በጋራ አክብረዋል፡፡ | https://waltainfo.com/am/32725/ | 88 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
በአዲሱ ዘመን በኢትዮጵያ የታላቅነት የጉዞ ብስራት የሚታወጅበት ይሆናል- ም/ጠ/ ሚ ደመቀ መኮንን | ሀገር አቀፍ ዜና | September 12, 2019 | Unknown | የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን አዲሱ ዘመን በኢትዮጵያ የታላቅነት ጉዞ ብስራት የሚታወጅበት እና የብልፅግና መሰረት በጋራ የሚጣልበት እንደሚሆን በአዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ገለጹ።ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የ2012 ዓ. የዘመን መለወጫ በዓልን አስመልክተው ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።በመልክታቸው በአዲሱ ዘመን በሃገራችን የታላቅነት ጉዞ ብስራት የሚታወጅበት እና የብልጽግና መሰረት በጋራ የምንጥልበት ይሆናልም ብለዋል።በአሮጌው ዓመት ከድህነት የሚመነጩ እና ወደ ፊት የማያራምዱ እኩይ አስተሳሰቦችን አራግፈን መሻገር ይኖርብናል በማለት የብሩህ ተስፋ መልዕክት የሰነቀ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።“ማቅ አውልቀን ግምጃ እንልበስ!” በሚል ቅን እሳቤ ለኢትዮጵያ ስኬት እጅ ለእጅ ተያይዘን መረባረብ እንደሚገባም አመልክተዋል።ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲሱ ዘመን ለሁላችንም የሰላም፥ የስራ፥ የአንድነት፥ የትብብርና የብልጽግና እንዲሆን ተመኝተዋል።የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጽህፈት ቤትም አዲስ ዓመትን አስመልክቶ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል።ዘመኑ የሰላም የደስታና የብልጽግና እንዲሆንም ተመኝቷል።በ2011 ዓ.ም በኢኮኖሚ፣ፖለቲካ፣ ማህበራዊና የውጭ ግንኙነት መስኮች ጉልህና ወሳኝ ስኬቶች የተመዘገቡበትና አገራዊ ፈተናዎች የተመዘገቡበት መሆኑም ፅህፈት ቤቱ አስታውሷል።ያለፈውን ዓመት መለስ ብሎ በመቃኘት ለመጪው ዘመን ለኢትዮጵያ ብልጽግና ከመላው ኢትዮጵያውን ጋር በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኑንም ፅህፈት ቤቱ አረጋግጧል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም የ2012 ዓ.ም የዘመን መለወጫን አስመልክቶ በአገር ውስጥም በውጭም ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፈ ሲሆን ዘመኑ የሰላምና የስኬት እንዲሆን ተመኝቷል።የተለያዩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች፣ የመንግስት ድርጅቶችና ተቋማት፣ የግል ድርጅቶችና ታዋቂ ግለሰቦች የአዲስ ዓመት የመልካም ምኞት መግለጫቸውን ማስየተላለፋቸውን ጠቅሶ የዘገበው ኢዜአ ነው። | https://waltainfo.com/am/32727/ | 196 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ኢትዮጵያ በተጠናቀቀው 2011 ቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንትን በመሳብ ከምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ሆነች | ቢዝነስ | September 13, 2019 | Unknown | በተጠናቀቀው ዓመት 2011 ኢትዮጵያ ቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንትን በመሳብ ከምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ሆናለች፡፡ኢዋይ የተሰኘ አለምአቀፍ የፋይናንስ አማካሪ ተቋም ይፋ ያደረገው ጥናት እንዳመለከተው፤ ሀገሪቱ በዚህ ዓመት ከ258 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ የሆነ ቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንትን መሳብ ችላለች፡፡ይህ አሀዝም ከምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚዋ ሀገር አድርጓታል ነው ያለው፡፡ኢትዮጵያን ተከትሎ ኬንያ 74 ሚሊየን ዶላር ቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንትን መሳብ የቻለች ሀገር ሆናለች፡፡ታንዛኒያ በበኩሏ ቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንትን የመሳብ አቅሟ 36 ሚሊየን ዶላር በላይ በመድረሱ ከቃጣናው የሶስተኝነት ደረጃን አሰጥቷታል፡፡ኢትዮጵያ በተጠቀሰው ዓመት በ29 ፕሮጀክቶች ከ16 ሺህ ለሚልቁ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር የቻለች ሲሆን በአንፃሩ ኬንያ ከ64 ፕሮጀክቶች መፍጠር የቻለችው የስራ ዕድል 6 ሺህ ነው፡፡ታንዛኒያ በምታንቀሳቅሳቸው 19 ፕሮጀክቶች ከ3 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር ችላለች፡፡ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት አመቺ አካባቢዎችን ማዘጋጀት መቻሏ እና ተወዳዳሪ የገበያ እድል መኖሩ ተመራጭ እንዳደረጋት ነው በሪፖርቱ የተመለከተው፡፡በተለይም የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ለውጪ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማመቻቸት በሩን ለኢንቨስትመንት ክፍት መድረጋቸው ለሀገሪቱ ቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት ፍሰት መጨመር በምክንያትነት ተጠቅሷል፡፡(ምንጭ፦ ዘ ሞኒተር) | https://waltainfo.com/am/23958/ | 143 | 3ቢዝነስ
|
በሶማሊያ 2 ሚሊየን ሰዎች ለርሃብ መጋለጣቸውን ተመድ አስታወቀ | ሀገር አቀፍ ዜና | September 13, 2019 | Unknown | በሶማሊያ 2 ሚሊየን ሰዎች ለርሃብ አደጋ መጋለጣቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ፡፡የተባበሩት መንግስታት የዓለም አቀፍ ሰብዓዊ ጉዳዮች ምክትል ዋና ፀሃፊ ማርክ ሎውኮክ ከሶማሊያ የሁለት ቀናት ጉብኝት በኋላ 2 ሚሊየን ሰዎች ለርሃብ አደጋ መጋለጣቸውን አስውቀዋል፡፡ባለፉት ተከታታይ አመታት ድርቅ ክፉኛ በተደጋጋሚ በጎበኛት ሶማሊያ በሚቀጥለው ወር 6 ሚሊየን ሰዎች የምግብ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ገልጸዋል፡፡ከዚህ አሃዝ አንድ ሶስተኛ ያህሉ ለከፋ የምግብ እጥረት ችግር የሚጋለጥ እንደሆነም ነው ያስጠነቀቁት፡፡ምንጭ፦ አልጀዚራ | https://waltainfo.com/am/33473/ | 62 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር እስራኤል ኋይት ኃውስን ትሰልላለች የሚለውን ዘገባ አስተባበሉ | ፖለቲካ | September 13, 2019 | Unknown | የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ፤ አገራቸው አሜሪካን ትሰልላለች ተብሎ የወጣውን ዘገባ አስተባብለዋል።እስራኤልን አሜሪካን በመሰለል የሚወነጅለው ዘገባ በአሜሪካ በሚገኝ 'ፖለቲኮ' በተሰኘ የዜና ድረ ገፅ ላይ የወጣው ሐሙስ ዕለት ነበር።'ፖለቲኮ' የተሰኘው ይህ የዜና ድረ ገፅ፤ ሦስት የቀድሞ የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣናትን ጠቅሶ፤ ዋይት ኃውስ አቅራቢያ ተገኘ ካለው የመከታተያ መሣሪያ ጀርባ እስራኤል ትኖርበታለች ሲል ዘግቧል።ነገር ግን ከጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ቢሮ የወጣው መግለጫ እንደሚያስረዳው ውንጀላው ነጭ ውሸት ነው።በአሜሪካ በየትኛውም የስለላ ተግባር ላለመሳተፍ ረዥም ጊዜ ፀንቶ የቆየ መግባባት አሠራር አለ ይላል መግለጫው ።ሐሙስ ዕለት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በጋዜጠኞች ስለ ሪፖርቱ ሲጠየቁ፤ እስራኤል አሜሪካን ትሰልላለች ብለው እንደማያምኑ ተናግረው ነበር።እጅጉን ለማመን ተቸግሬያለሁ፤ ከእስራኤል ጋር ያለኝ ግንኙነት በጣም ጥሩ የሚባል ነው ያሉት ፕሬዝዳንት ትራምፕ፤ ከኢራን ጋር ያለው የኒውክሌር ስምምነት ማብቃቱንና አሜሪካ በእስራኤል የሚገኘውን ኢምባሲዋን ወደ እየሩሳሌም ለማዞር የወሰነችበትን አወዛጋቢ ውሳኔ በአስረጅነት ጠቅሰዋል።ይህንን ወሬ አላምነውም፤ አይሆንም ማለት ፤ ግን አልችልም ብለዋል።ምንጭ፦ ቢቢሲ | https://waltainfo.com/am/33998/ | 132 | 5ፖለቲካ
|
በቡራዩ ከተማ በፖሊስ ካምፕ ላይ ጥቃት በማድረስ የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ | ፖለቲካ | September 13, 2019 | Unknown | ትናንት ምሽት 1:30 ገደማ በቡራዩ ከተማ በኦሮሚያ ፖሊስ ማረፊያ ቦታ ላይ በደረሰ የቦምብ ጥቃት 9 ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት መድረሱ ተገልጿል፡፡ጥቃት ከደረሰባቸው 9 ሰዎች መካከል አንዱ ሕክምና ተደርጎለት ወደ ቤት የተመለሰ ሲሆን፣ ስምንቱ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ሆስፒታል ተልከው ሕክምና እያገኙ ነው ተብሏል፡፡ጥቃት ከደረሰባቸው ሰዎች ውስጥ አንዷ ለፖሊሶች ምግብ የምታዘጋጅ እንደሆነች ተገልጿል፡፡በቡራዩ ጥቃት ጋር ተያይዞ የሸኔ ሽፍታ አባላትና ሌሎች ከእነሱ ጋር ትስስር ያላቸው 22 ሰዎች በቁጥጥር ስር
ውለዋል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ማንነታቸውን ከሚገልጹ መረጃዎች ጋር እንደተያዙ ነው ከኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ የሚያመለክተው፡፡ | https://waltainfo.com/am/31348/ | 81 | 5ፖለቲካ
|
የሀይማኖት አባቶች ለዘመን መለወጫ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላለፉ | ሀገር አቀፍ ዜና | September 11, 2019 | Unknown | የ2012 የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ የሀይማኖት አባቶች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡አዲስ የዘመን መለወጫ ተብሎ የሚነገርለት ዕለት አዲስ ሊሆን የሚችለው በዋናነት ልቦና ሲታደስ ነው ያሉት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁእ አቡነ ማትያስ፤ በአስተሳሰብ፣ በስራና በአኗኗር ሁሉ ከልብ የሆነ መታደስ ከሁሉም ይጠበቃል ብለዋል፡፡“የኢትዮጵያን ህዳሴን እናበስራለን” የሚለው መልካም ምኞት ከቃላት ባለፈ በይቅርታና እውነተኛ መግባባት በሁሉም ወገኖች መከናወን እንዳለበት በመጥቀስ፤ በሃሳብ መቀራረብና በሰጥቶ መቀበል መርህ እየተቻቻሉ መሄድን እንደአዋጭ ባህል አድርገን መጓዝ ይኖርብናል ብለዋል፡፡ይህ ታላቅና ባለታሪክ ህዝብ ለዘመናት ተንከባክቦ ያቆየው ሃይማኖቱን፣ ታሪኩን፣ ባህሉንና አንድነቱን አሁንም ፣ነገም ሆነ ከነገ በኋላ ጠብቆ እንዲጓዝ መሰናክል አናብዛ ያሉት ብፁዕነታቸው፤ ይህን በማድረግ በእግዚአብሄርና በታሪክ ፊት በደል ከመፈፀም እንጠንቀቅ ብለዋል፡፡አዲሱ ዓመት የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የአንድነት፣ የስምምነትና የይቅርታ ዘመን ማድረግ የምንችለው ከእግዚአብሄር በታች እኛው በመሆናችን ልዩነቶችን ወደ መቀራረብ ብሎም ወደ ፍፁም መተማመን በማምጣት ሀገሪቱንና ህዝቦቿን ወደ ላቀ ህዳሴ እናሸጋግር ሲሉ አባታዊ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡በአዲሱ 2012 ዓመት መልካም ነገርን ለማቀድና ለመስራት ልባችንን ከፍተን በፍቅር፣ በይቅርታ፣ በአንድነትና በህብረት መንፈስ ልንጀምረው ያስፈልጋል ያሉት ደግሞ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀዻዻሳት ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ ናቸው፡፡በዚህ ርዕሰ ዐውደ ዓመት ሁሉም ባለው አቅም ከየአካባቢው የተፈናቀሉትን የተቸገሩትንና አቅመ ደካሞችን በመርዳት በጎ ነገሮችን ሁሉ በፍቅር እንዲያደርግና በዓሉን በጋራና በአንድነት እንዲያከብር ጥሪ አቅርበዋል፡፡አዲሱ ዓመትም የሰላ ፣ የፍቅር የትዕግስትና የመግባባት ዘመን እንዲሆን ተመኝተዋል፡፡የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ እየሱስ ፕሬዚዳንት ቄስ ዩናስ ይገዙ በበኩላቸው ፤ ጊዜ የሰው ልጅ ለኑሮ የሚበጀውን እንዲያከናውን ከእግዚአብሄር የተሰጠ ስጦታ እንደመሆኑ ለተሰጠን የጊዜ ስጦታ ታማኝ ባለአደራ በመሆን ለበጎ ተግባር ብቻ ልንጠቀመው ይገባል ብለዋል፡፡በዚህ የበዓል ወቅትም ሆነ በሌሎች ጊዜያት በመካከላችን ያሉና ድጋፍ የሚያሻቸውን ወገኖች በቸርነት ማሰብ እንደሚገባ ያሳሰቡት ቄስ ዮናስ ፤ አዲሱ ዓመት የደስታ ፣ የህብረትና የበረከት ይሆን ዘንድ ተመኝተዋል፡፡ | https://waltainfo.com/am/32721/ | 249 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
አቶ ሽመልስ አብዲሳ ለአዲሱ ዓመት የእንኳን ደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ | ሀገር አቀፍ ዜና | September 11, 2019 | Unknown | የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ም/ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ አዲሱን ዓመት በማስመልከት ባስተላለፉት መልዕክት 2012 ዓ.ም የህዝባችንን ተጠቃሚነት በይበልጥ የምናረጋግጥበት ዘመን ይሆናል ብለዋል፡፡የኦሮሞ ህዝብ የክረምቱ ዝናብና ጨለማ አልፎ ወደ ጸደይ ብርሃን ሲገባ፣ ጨለማውን አሳልፎ ብርሃኑን ላሳየው ዋቃ ምስጋናን ያቀርባል፣ ለሰራው መልካም ሥራዎች ምስጋና ያደርሳል፣ የጎደለውን ለመሙላት ወደፊት ያልማል ብለዋል አቶ ሽመልስ ባስተላለፉት መልዕክት፡፡አዲሱ ዘመን እንደ ብረት በጠነከረው አንድነት የህዝቡን ሕይወት ለመቀየር ሌት ተቀን በመትጋት የህዝቡ ፍላጎት የሚሟላበት ዘመን ይሆን ዘንድም ተመኝተዋል፡፡አቶ ሽመልስ “አዲሱ አመት በጎ በጎውን አስበንና ሰርተን የህዝባችንን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ህይወት የምንለዉጥበትና ብሩህ ተስፋን የምንሰንቅበት ዘመን ይሁንልን” በማለት መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡ | https://waltainfo.com/am/32722/ | 91 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
በሶማሌ ክልል የተጀመሩ የልማት ስራዎች በአዲሱ ዓመትም ለማጠናከር በትኩረት ይሰራል- አቶ ሙስጠፌ ሙሃመድ | ሀገር አቀፍ ዜና | September 11, 2019 | Unknown | በሶማሌ ክልል የተጀመሩ የህግ የበላይነት ማስከበርና የልማት ስራዎች በአዲሱ ዓመትም ተጠናክረው ህዝቡ ባገኘው ነፃነት እንዲጠቀም በትኩረት እንደሚሰራ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ አስታወቁ።የዘመን መለወጫን በዓልን አስመልክተው ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ እንደገለጹት በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በክልሉን ሆነ በሀገሪቱ የተለያዩ አከባቢዎች ግጭትና የዜጎች አለመረጋጋት የተከሰተበት ጊዜ ነበር።ችግሩን በመንግስትና ህዝቡ ጥረት በፍጥነት ማስተካክል መቻሉን ተናግረዋል።“ዓመቱ በሀገሪቱ የዴሞክራሲ ተቋማት መገንባት የተቻለበት ዓመት ነበር ፤በዚህም ክልሉም ሆነ ሀገሪቱ በለውጥ ጎዳና ላይ ይገኛሉ፤ የህግ የበላይነት የበለጠ የሚጠናክሮበት ዓመት ይሆናል ብለን እንጠብቃልን” ብለዋል።አቶ ሙስጠፌ እንዳሉት ባለፈው ዓመት መጀመሪያ አከባቢ በጅግጅጋ የነበረው ችግር ተወግዶ አሁን ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በአንድነት በፍቅር የሚኖርበት ከተማ መሆኗንና ይሀው በቀጣይ አጠናክሮ ለማስቀጠል በትኩረት ይሰራል።“አዲሱ ዓመት የህብረተሰቡን የልማት እና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት የተያዙ እቅዶች የምንተገበርበትና ህዝቡ ያገኘውን ነፃነት የበለጠ የሚጠቀሚበት ይሆናል” ብለዋል።የክልሉ መንግስት ሰላምና አንድነት እንዲጠናክር እንደሚሰራ አመልክተው ህዝቡም የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።አቶ ሙስተፌ ሙሁመድ ለክልሉና ለሌሎችም ኢትዮጵያዊያን አዲሱ ዓመት የጤና፣ የብልጽግና የስኬት ዘመን እንዲሆን ምኞታቸውን ገልጸዋል።ምንጭ ፦ኢዜአ | https://waltainfo.com/am/32723/ | 146 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የብሔራዊ አንድነት ቀን በመላ ሀገሪቱ እየተከበረ ነው | ፖለቲካ | September 11, 2019 | Unknown | የብሔራዊ አንድነት ቀን በመላ ሀገሪቱ እየተከበረ ነው ፡፡መደመር ለብሔራዊ አንድነት በሚል መርህ ቃል ዛሬ በመላው ሀገሪቱ የብሔራዊ አንድነት ቀን እየተከበረ ይገኛል፡፡በአዲሱ አመት በአንድነትና በአብሮነት መንፈስ የምንፈልጋትን ኢትዮጵያ አብረን እንገንባ የሚል መልዕክት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በፌስቡክ ገጹ ላይ አስፍሯል።የዘንድሮ ጳጉሜን ቀናት በተለያዩ ዝግጅቶችና ርዕሰ ጉዳዮች እየተከበሩ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ | https://waltainfo.com/am/31346/ | 48 | 5ፖለቲካ
|