headline
stringlengths
2
1.42k
category
stringclasses
6 values
date
stringlengths
9
35
views
stringlengths
1
7
article
stringlengths
63
36.2k
link
stringlengths
28
740
word_len
int64
16
6.74k
label
class label
6 classes
የደቡብ ክልል ም/ቤት መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ
ፖለቲካ
August 31, 2019
Unknown
የደቡብ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር አራተኛ አመት 9ኛ መደበኛ ጉባኤውን መካሄድ ጀምሯል።ምክር ቤቱ በቆይታው የ2011 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም እና የ2012 በጀት ዓመት የስራ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ እንደሚፀድቅ ይጠበቃል።በተጨማሪምም የክልሉን የጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ዋና ኦዲት መስሪያ ቤትን ሪፖርትና እቅድን በማድመጥ ያጸድቃል ተብሏል።በሌላ በኩል የምክር ቤቱ አባላት ከመደበኛ ጉባኤው አስቀድሞ በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ በሀዋሳ ከተማ መክረዋል።ምክክሩ በሀገሪቷ ወቅታዊ ሁኔታና ክልላዊ ጉዳዮች ምን ደረጃ ላይ ናቸው የሚለውንና በክልሉ እየተነሱ ያሉት የአደረጃጀት ጥያቄዎችን በሚመለከት የተደረገ እንደሆነም ነው የተገለፀው፡፡
https://waltainfo.com/am/31322/
79
5ፖለቲካ
የደቡብ ክልል ምክር ቤት ለ2012 በጀት አመት 40 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት አጸደቀ
ቢዝነስ
August 31, 2019
Unknown
የደቡብ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ማካሄድ በጀመረው 5ኛ ዙር 4ኛ አመት 9ኛ መደበኛ ጉባኤ የ2012 በጀት አመት 40 ቢሊዮን 56 ሚሊዮን 938 ሺህ ብር በጀት አጸደቀ፡፡የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሄለን ደበበ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የምክር ቤቱ ጉባኤው ለመዘግየቱ ይቅርታ ጠይቀዋል።በዋናነት በ3 አጀንዳዎች ላይ እየመከረ የሚገኘው ምክር ቤቱ የተለያዩ ሹመቶችንም ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
https://waltainfo.com/am/23936/
53
3ቢዝነስ
ከተማ አስተዳደሩ በክረምት የበጎ ፈቃድ መርሃ ግብር እድሳት የተደረገላቸውን ቤቶች ለአረጋዊያን እና አቅመ ደካሞች እያስረከበ መሆኑን አስታወቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 31, 2019
Unknown
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በክረምት የበጎ ፈቃድ መርሃ ግብር እድሳት የተደረገላቸውን ቤቶች ለአረጋዊያን እና አቅመ ደካሞች እያስረከበ መሆኑን አስታውቋል፡፡የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በክረምት የበጎ ፈቃድ መርሃ ግብር እድሳት የተደረገላቸውን ቤቶች ለአረጋዊያን እና አቅመ ደካሞች በማስረከብ ላይ ይገኛሉ።በዛሬው ዕለትም mክትል ከንቲባው እድሳቱን ያስጀመሩትን በጉለሌ ክፍለ ከተማ ቃኘው ሻለቃ ተብሎ በሚጠራው አደባባይ አከባቢ የሚኖሩ እናት መኖሪያ ቤት ስራው ሙሉ በሙሉ በመጠናቀቁ ለባለንብረቷ ቤታቸውን ማስረከባቸወን የከንቲባ ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡የከተማ አስተዳደሩ በክረምት የበጎ ፈቃድ መርሃ ግብር 1 ሺህ ለሚሆኑ አረጋዊያን ቤት ለማደስ ወደ ስራ የገባ ሲሆን፣እስከ አሁን 1 ሺህ 573 ለሚሆኑ በከተማው ውስጥ ለሚገኙ አረጋዊያን የመኖሪያ ቤት እድሳት እየተከናወነ ይገኛል ተብሏል፡፡ከዚህም ውስጥ 1 ሺህ 111 ቤቶች እድሳት ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቆ ለባለንብረቶቹ መተላፉን ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
https://waltainfo.com/am/32690/
116
0ሀገር አቀፍ ዜና
በዋልያ፣ ቀይ ቀበሮና ጭላዳ ዝንጀሮዎች ላይ በመጪው መስከረም ወር ቆጠራ ሊካሄድ መሆኑ ተገለጸ
ቢዝነስ
August 30, 2019
Unknown
የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ብርቅዬ የዱር እንስሳት በሆኑት ዋልያ፣ ቀይ ቀበሮና ጭላዳ ዝንጀሮዎች ላይ በመጪው መስከረም ወር ወቅታዊ የቆጠራ ሥራ እንደሚካሄድ የፓርኩ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡የፓርኩ ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው በመጪው መስከረም ወር ላይ የሚካሄደው ወቅታዊ ቆጠራ ሁለተኛ ዙር ነው።የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ አበባው አዛናው ለኢዜአ እንደተናገሩት ቆጠራው የሚካሄደው ዋልያ፣ ጭላዳ ዝንጀሮና የቀይ ቀበሮ ብርቅዬ የዱር እንስሳት ያሉበትን ሁኔታ አውቆ ክትትል ለማድረግ ነው።የቆጠራ ሥራው በፓርኩ ክልልና አዋሳኝ በሚገኙ አምስት ወረዳዎች የሚካሄድ ሲሆን ይህም በተጨባጭ መረጃ ተመስርቶ ለጎብኚዎች መረጃ ለመስጠት እንደሚያስችል ገልጸዋል።“ቆጠራው በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በፓርኩ ላይ ደርሶ በነበረው የእሳት አደጋ በዱር እንስሳቱ ላይ ጉዳት መድረሱንና አለመድረሱን በተጨባጭ ለማረጋገጥም ያግዛል” ተብሏል።የዱር እንስሳቱን የውልደትና የሞት መጠን፣ የአመጋጋብ፣ የመኖሪያ አካባቢና ስርጭትን ለማወቅ እንዲሁም የሚደርሱ አደጋዎችን በመለየት ለቀጣይ ግብዓት ለመሰብሰብ እንደሚያስችልም ኃላፊው አስረድተዋል፡፡እንደ አቶ አበባው ገለጻ ቆጠራውን ለማካሄድ የሚያስችሉ የቆጠራ ቦታዎች ልየታ የተካሄደ ሲሆን በእዚህም ከ130 በላይ የቆጠራ ቦታዎችም ተዘጋጅተዋል፡፡ለቆጠራ ሥራው በዘርፉ ልምድ ያላቸው 150 ግለሰቦች መመልመላቸውንና ቆጠራውን በትክክል ማካሄድ እንዲችሉም በባለሙያዎች ስልጠና መሰጠቱን ጠቁመዋል፡፡ የቆጠራ ስራው ለ15 ተከታታይ ቀናት የሚካሄድ ሲሆን ጂ.ፒ.ኤስ በተባለው አቅጣጫ ጠቋሚ መሳሪያ በመታገዝ ጭምር የሚከናወን መሆኑም ተመልክቷል፡፡ለቆጠራው ስራው ከ380 ሺህ ብር በላይ በጀት እንደሚያስፈልግ ኃላፊው ጠቁመው “አፍሪካን ዋይልድ ፋውንዴሽን” የተባለ መግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በጀቱን ለመሸፈን ቃል መግባቱን ነው የተናገሩት፡፡ባለፈው መጋቢት ወር የበጋ ወራት የዱር እንስሳት ቆጠራ በፓርኩ ውስጥ መካሄዱን ያስታወሱት ኃላፊው በቆጠራው ቀይ ቀበሮ 73፣ ዋልያ 619፣ ጭላዳ ዝንጀሮ ደግሞ 18ሺህ 500 መገኘቱን ገልጸዋል፡፡
https://waltainfo.com/am/23935/
213
3ቢዝነስ
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ እስራኤልን ሊጎበኙ ነው
ፖለቲካ
August 30, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ በመጪው እሁድ እስራኤልን ይጎበኛሉ፡፡የእስራኤል ኤምባሲ እንዳስታወቀው፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከእስራኤል አቻቸው ቤንያሚን ኔትኒያሁ በቀረበላቸው ግብዣ መሰረት ነው ሀገሪቱን የሚጎበኙት፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ በቆይታቸው የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔትኒያሁን ጨምሮ ፕሬዚዳንት ሪውቨን ሪቭሊኒን ጋር እንደሚወያዩ ተገልጿል፡፡የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ጉብኝት በኢትዮጵያና እስራኤል መካከል ለረጅም ጊዜ የቆየውን ሁለንተናዊ ግንኙነት እንደሚጠናክረውኢምባሲው ለዋልታ ቴልቭዥን በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡ከዚህ በተጨማሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ እንደ ያድ ቫሼም ያሉትን ታሪካዊ ሃውልቶችን ጨምሮ  የእስራኤል ብሄራዊ የሳበር መከላከያ ተቋምን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ያድ ቫሼም በናዚ በግፍ የተጨፈጨፉ አይሁዶች መታሰቢያ ሃውልት ሲሆን፤ በየዓመቱ በመቶ ሺህዎች የሚጎበኝ ታሪካዊ መካነ መቃብር ስፍራ ነው፡፡የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ጉብኝት የአፍሪካ እና እስራኤል ትብብርን የሚያጠናክር፣ እስራኤልም ፊቷን ወደ አፍሪካ ማዞሯን የሚያመላክት እንደሆነ መግለጫው ጠቅሷል፡፡  
https://waltainfo.com/am/31320/
113
5ፖለቲካ
ጠንካራ እና ውጤታማ የፋይናንስ አስተዳደር ስርዓት እንዲኖር የማሻሻያ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ
ቢዝነስ
August 30, 2019
Unknown
የገንዘብ ሚኒስቴር በሀገሪቱ ውስጥ ጠንካራ እና ውጤታማ የፋይናንስ አስተዳደር ስርዓት እንዲኖር የማሻሻያ ስራዎች እያከናወነ መሆኑን አስታወቀ።28ኛው ዙር የፌደራልና የብሔራዊ ክልላዊ መንግስታት የፋይናንስና ገቢ ዘርፍ ምክክር መድረክ በገንዘብ ሚኒስቴር እየተካሄደ ነው።የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ በምክክር መድረኩ ላይ በሀገሪቱ ውስጥ ጠንካራ እና ውጤታማ የፋይናንስ አስተዳደር እንዲኖር በፌደራል እና በክልሎች የሚገኙ የፋይናንስና ገቢ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ አካላት በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው ተናግረዋል።የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደርን ለማዘመን በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰበሰበው ገቢ ማደግ ይኖርበታልም ብለዋል፡፡የተሰበሰበው ገቢ ለታለመለት ዓላማ እንዲውልም የተጠያቂነት ስርዓት እንዲሰፍን እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።የገቢዎች ሚኒስትር ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው፣ እንደ ሀገር ተከታታይነትና ዘላቂነት ያለው ኢኮኖሚያዊ እድገት ለማረጋገጥ የገቢ ማደግ ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።ሚኒስትሯ በ2012 በጀት ዓመት ለግብር ከፋዩ ምቹና ቀልጣፋ የግብር አከፋፈል ስርአት እንዲኖር ለማስቻል እንደሚሰሩም ጠቁመዋል።የምክክር መድረኩ የኮንትሮባንድ ንግድን መከላከልና ህገ-ወጥ ንግድን ከመቆጣጠር አንፃር እያጋጠሙ ያሉ ተግዳሮቶች ላይ ተወያይቶ ጠንካራ የአሰራር ስልቶችን መንደፍ በሚቻልበት አግባብ ላይ በስፋት እንደሚወያይ ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
https://waltainfo.com/am/23932/
139
3ቢዝነስ
መንግስት የግብርና ዘርፉን በምርምር የበለጠ እንደሚደግፍ አስታወቀ
ቢዝነስ
August 30, 2019
Unknown
መንግስት የግብርና ስራዉን በምርምር ስራዎች የበለጠ እንደሚደግፍ የግብርና ሚንስቴር አስታወቀ፡፡ባለፉት ዓመታት በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በትግራይና በደቡብ ክልሎች በክላስተር የግብርና ስራ ላይ ሲደረግ የነበረዉ ጥናት ይፋ ተደረገ፡፡የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ኡመር ሁሴን ለዋልታ እንደገለጹት፤ ምርምሩ ምን አይነት ማዳበሪያ ለምን አይነት ዘር፣ ምን አይነት መሬት ለምን አይነት ዘርና ከገበያ ጋር የተያያዙ ዝርዝር ሁኔታዎችን የለየ ነዉ ብለዋል፡፡ በክላስተር ግብርና እንደ ሀገር ባለዉ ስራ ላይ ያሉ ክፍተቶችን ማሳየት የቻለ ጥናት መሆኑንም ሚንስቴሩ አክለዉ ገልጸዋል፡፡አቶ ኡመር እንዳሉት ከሆነ መንግስት የምርምር ስራን የግብርና ስራዉ አካል ካደረገ  የበለጠ ዉጤታማ መሆን ይቻላል ብለዋል፡፡ከመንግስት ጋር ላለፉት 6 ዓመታት በጋራ ሲሰራ የቆየዉ “SYNERGOS” የኢትዮጵያ ዳይሬክተር አቶ አበራ ቶላ በበኩላቸዉ፤ ለጥናቱ ስራ ስኬት ከፌዴራል እስከ ክልል ድረስ የነበሩ ድጋፎች አስተዋጽኦ እንደነበራቸዉ ተናግረዋል፡፡ለጥናቱ ዓላማ የሚዉል ቢል ኤንዲ ሚልንዳ ጌትስ ፋዉንዴሽን አንድ ሚልዮን ዶላር ድጋፍ አድርጓል፡፡
https://waltainfo.com/am/23933/
121
3ቢዝነስ
በ2011 ዓ.ም ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከ970 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢተሰበሰበ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 30, 2019
Unknown
በ2011 ዓ.ም ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከ970 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢተሰበሰበ።በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከ970 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የግድቡ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ፅህፈት ቤት አስታወቀ፡፡የግድቡ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ፅህፈት ቤት ለዋልታ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ ለግድቡ ግንባታ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከህዝብ በተደረገ ድጋፍ ከ970 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታውቋል።በ2011 በጀት ዓመት ሁለት ሺህ የሚጠጉ ኢትዮጵያዊያን እና የውጭ ዜጎች ግድቡን መጎብኘታቸውንና የተለያዩ ተቋማትም የጉብኝት ጥያቄ እያቀረቡ መሆኑንም ጽቤቱ በላከው መግለጫ ጠቅሷል። ፅህፈት ቤቱ ከግድቡ ግንባታ ጋር በተያያዘ መረጃዎችን በስፋት ለህብረተሰቡ በማድረስና በቦንድ ዙሪያ የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመፍታት እየሰራሁ መሆኑን አስታውቆ፤ ከሚመለከታቸው የገንዘብ ተቋማት ጋር ግንኙነት በመፍጠር በቦንድ አሻሻጥና አመላለስ ዙሪያ የሚፈጠሩ ችግሮችን በመፍታት ላይ መሆኑን ገልጿል።በቀጣይ በጀት ዓመትም ህዝቡ ለግድቡ ግንባታ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ብሔራዊ መግባባትን የሚያጎለብቱ ተግባራትን ለማከናወን ማቀዱን ጠቁሟል፡፡ነዋሪዎች፣ መገናኛ ብዙሃንና የተለያዩ ተቋማት በገንዘባቸው፣ በዕውቀታቸውና በሞራል ለግድቡ ግንባታ ድጋፍ ማድረጋቸውን በአዲሱ ዓመት የበለጠ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ሲልም ጽህፈት ቤቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡
https://waltainfo.com/am/32688/
154
0ሀገር አቀፍ ዜና
ኢትዮ-ቴለኮም የደንበኞቹን ፍላጎት የለማሻሻል የሚያስችል የሶስት ዓመት ስትራቴጅክ ዕቅድ ማዘጋጀቱን አስታወቀ
ቢዝነስ
August 30, 2019
Unknown
ኢትዮ-ቴለኮም የደንበኞቹን ፍላጎት የለማሻሻል የሚያስችል የሶስት ዓመት ስትራቴጅክ ዕቅድ ማዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡የስትራቴጅክ ዕቅዱ ኩባንያው ወደ ግል ይዞታ እንደሚዞር ታሳቢ ያደረገና ከሀምሌ 2011 ዓ.ም እስከ 2014 ዓ.ም ያለውን ጊዜ እንደሚሸፍን ተገልጿል፡፡ኢትዮ-ቴሌኮም ለ125 አመታት በኢትዮጵያ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን፣ የቴሌኮም ዘርፉን ለማሳደግና የደንበኞችን ፍላጎት ለማሻሻል የሚረዳ ስትራቴጅክ ዕቅድ ማዘጋጀቱንም ነው ያስታወቀው፡፡የሶስት አመታት ስትራቴጅካዊ ዕቅዱ የፋይናንስ አቅሙን ማሳደግ፣ ምርጥ የደንበኞች ሁለንተናዊ ተሞክሮ መፍጠር፣ የአገልግሎትና ቴክኖሎጂ ልህቀት፣ የኦፕሬሽን ልህቀትና ተቋማዊ ገፅታ ማጠናከርን የትኩረት አቅጣጫ እንዳደረገ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራአስፈፃሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት አያለው ገልጸዋል፡፡ተቋሙ በ2012 በጀት ዓመት የአገልግሎት ጥራትን ለማሻሻል በአዲስ አበባና በክልሎች የ4G ኔትወርክ ግንባታ እንደሚያከናውንም ወይዘሪት ፍሬህይወት ተናግረዋል፡፡በበጀት አመቱ የደንበኛ ብዛቱን በ16 በመቶ በመጨመር 50 ነጥብ 4 ሚሊየን ለማድረስ ማቀዱንም አስታውቀዋል፡፡በተጨማሪም በተያዘው በጀት አመት ከ45 ነጥብ 4 ብሊየን የሚደርስ ገቢ ለመሰብሰብ ተቋሙ አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ሲሆን፣ የህም የሀገሪቱ የማክሮ ኢኮኖሚና የዋጋ ግሽበት ታሳቢ ተደርጎ የታቀደ ነው ተብሏል፡፡
https://waltainfo.com/am/23934/
132
3ቢዝነስ
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድና ልኡካቸው ከተለያዩ የልማት አጋሮች ጋር ተወያዩ
ቢዝነስ
August 30, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና ልኡካቸው የኢንቨስትመንት እድሎችንና ጅማሮዎችን ማበረታታትን በተመለከተ ከተለያዩ የልማት አጋሮች ጋር ፡፡የመጀመሪያው ውይይት ከጃፓን የውጪ ንግድ ድርጅት (ጄትሮ) ሊቀመንበር ጋር ያካሄዱ ሲሆን፣  ጄትሮ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት እያደረገች ላለው የኢኮኖሚ ማሻሻያ ከፍተኛ ሚና ሊጫወት እንደሚችል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴያቸውን ለማስፋፋትና ቀጣናዊ ውህደትን በሚያበረታታው የመደመር እሳቤ መሰረት የአፍሪካ ቀንድ ሀገሮችን ለመርዳት እንዲነሱም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በጎአድራጊና በሳሳካዋ አፍሪካ ስር የኢትጵያን የግብርና ዘርፍ ድጋፍን የሚመራውን የኒፖን ፋውንዴሽን ሊቀመንበር የሆኑትን ዮሄ ሳሳካዋን አነጋግረዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለይም ጃፓን ካላት የተፋሰስ ወንዞችን ማጽዳት ስኬት በመነሳት የአዲስ አበባ ወንዞችን የማጽዳትና የከተማ ግብርና ልማት ዙሪያ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡እንዲሁም የጃፓን አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (ጃይካ) ፕሬዝዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር  ዐቢይ ሰላምን ለማምጣት የሚያደርጉትን ጥረት በነበራቸው ውይይት ወቅት አድንቀዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በኢኮኖሚ ማሻሻያው ቅድሚያ የሚሳጣቸውን በማጉላት ጃይካ እነዚህኑ የትኩረት አቅጣጫዎች በማሳካት፣ በሰው ኃብትና ኢንዱስትሪ ልማት ዙሪያ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ መረጃው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ነው፡፡
https://waltainfo.com/am/23931/
140
3ቢዝነስ
አፍሪካ የሩዝ ምርቷን በእጥፍ ለማሳደግ እንድትችል ጃፓን ድጋፍ እንደምታደርግ ገለፀች
ቢዝነስ
August 29, 2019
Unknown
በጃፓን ዮኮሃማ ከተማ የአፍሪካ መሪዎች በተሳተፉበት ኮንፈረንስ ላይ አፍሪካ እ.ኤ.አ. በ2030 የሩዝ ምርቷን በእጥፍ ማሳደግ እንድትችል ጃፓን ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብታለች፡፡የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ በአፍሪካ ልማት ላይ በሚመክረው የቶኪዮ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ላይ ባደረጉት ንግግር የጃፓን ቴክኖሎጂና ፈጠራ ይህን ግብ ለማሳካት ቁልፍ ሚና ይጫወታል ብለዋል፡፡ዕቅዱ አፍሪካ በ11 ዓመታት ጊዜ ውስጥ 50 ሚሊዮን ቶን ስንዴ እንድታመርት መርዳት ነው፡፡የአፍሪካ ልማት ባንክም እቅዱ ተግባራዊ እንዲሆን ድጋፍ እንደሚያደርግ ነው የተገለጸው፡፡"የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት አኪንውሚ አዴሲና በበኩላቸው፣ ምንም እንኳን በግብርናው መስክ የተገኙ ውጤቶች ቢኖሩም፣ ዓለም አቀፉን የፀረ-ርሃብ ትግል በአሸናፊነት እየተወጣ አይደለም። ሁላችንም በአንድነት መነሳት እና በዓለም አቀፍ ርሃብን ደረጃ ማጥፋት አለብን ፡፡ ይህንን እውን ለማድረግ ደግሞ በአፍሪካም ርሀብን ማጥፋት አለብን" ብለዋል፡፡ጃፓን ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር በመተባበር የእርሻ ምርታማነትን ለማሻሻል እንደ አንድ አካል በመሆን አነስተኛ የአፍሪካ ገበሬዎች አምርተው ከመመገብ ባለፈ ምርት እስከ መሸጥ ደረጃ እንዲደርሱ ለመቀየር ተስፋ ታደርጋለች ነው የተባለው፡፡ናይጄሪያ እ.ኤ.አ. ከ2015 ጀምሮ የሩዝ ምርቷን ለማሳደግ ጥረት እያደረገች እንደሆነ በጉባኤው ላይ ተገልጿል፡፡ (ምንጭ፡-ቢቢሲ)
https://waltainfo.com/am/32903/
148
3ቢዝነስ
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ የቶሺባ ኩባንያን ጎበኙ
ቢዝነስ
August 29, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር  ዐብይ አህመድ የቶሺባ ኩባንያን ጎብኝተዋል፡፡ኩባንያው በዋናነት የኤሌክትሮኒክስ አምራች ሲሆን ፤በሀይልና በማህበራዊ መሰረተ ልማት ዘርፎች ላይ በመስራት ላይ ነው፡፡ቶሺባ እ.አ.አ በ1939 ሲመሰረት በ1978 ደግሞ መጠሪያውን ወደ ቶሺባ ኮርፖሬሽን ቀይሯል፡፡ኮርፖሬሽኑ  በርካታ ንዑስ ኩባንያዎችን ያቀፈ ሲሆን  የተለያዩ ምርቶች ላይ የተሰማሩ አራት  ግዙፍ ፋብሪካዎች አሉት፡፡ ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር  ዐብይ የተጎበኘው በሃይል ዘርፍ ስር ያለው የቴክኖሎጂ አምራች ኩባንያው ነው።የኢፌዴሪ መንግስት ለቴክኖሎጂ ዘርፍ ቅድሚያ ሰጥቶ እየስራ እንደሚገኝ ያነሱት  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ  ኩባንያው በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋዩን እንዲያፈስ ጠይቀዋል።የቶሺባ ኩባንያ እ.አ.አ በ2017 ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ጋር የመግባቢያ ስምምነት መፈራረሙ ይታወሳል፡፡
https://waltainfo.com/am/23930/
84
3ቢዝነስ
ቻይና ከ8 ሺህ በላይ አዳዲስ ወታደሮችን ወደ ሆንግኮንግ መላኳ ተገለጸ
ፖለቲካ
August 29, 2019
Unknown
ቻይና ከስምንት ሺህ እስከ 10 ሺህ የሚገመት አዳዲስ ወታደሮቿን ወደ ሆንግኮንግ መላኳ ተገልጿል፡፡አዳዲሶቹ ወታደሮች የተላኩት የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር ነው ተብሏል፡፡ሆንግ ኮንግ ከብሪታንያ ቅኝ ግዛት ተላቃ ለቻይና ከተመለሰች ሃያኛ ዓመት ብታስቆጥርም የምትተዳደረው ግን በ«አንድ ሃገር፤ ሁለት ሥርዓቶች» ፖሊሲ ነው፡፡የኋላ ኋላ ግዛቲቱ ሙሉ በሙሉ ለቻይና ተላልፋ ተሰጥታ በቻይና እንድትተዳደር ውሳኔ ከተሰጠ ሀኋላ ግን አደባባዮቿ በመንግስት ተቃዋሚዎች ተሞልተው ወራትን አስቆጥረዋል፡፡ከዚህ ቀደም በተቃውሞ ሰልፈኞቹ ከፖሊሶች ጋር ግጭቶች መፈጠራቸው ይታወሳል፡፡ የግዛቲቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለሁለት ቀናት በተካሄደው የተቃውሞ ስልፍም 1,000 የሚጠጉ የአውሮፕላን በረራዎች ተሰርዘው ነበር።የሆንግኮንግ ተቃውሞ መጠኑ እየሰፋ መምጣቱን ተከትሎም ቻይና ከስምንት ሺህ እስከ አስር ሺህ የሚጠጉ አዳዲስ ሰራዊቶችን ዛሬ ከሰዓታት በፊት ወደ ሆንግ ኮንግ መላኳን አልጀዚራ ሮይተርስን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ቻይና ሆንግኮንግ ውጥረት እየተባባሰ ሲመጣ ቁጭ ብየ አልመለከትም ማለቷን የዘገበው አልጀዚራ ባለፈው ዓመት ሃገሪቱ የወታደሮቿን ቁጥር እንዳልጨመረች ይፋ ማድረጓን ጠቁሟል፡፡ቻይና ዛሬ ባወጣችው መግለጫ ደግሞ የወታደሮቿን ቁጥር ይበልጥ ልትጨምር እንደምትችል የሚያሳይ ነው ተብሏል፡፡
https://waltainfo.com/am/33992/
137
5ፖለቲካ
የሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄ የህዝበ ዉሳኔ ድምፅ መስጫ ቀን ህዳር 3/2012 እንዲሆን መወሰኑን ምርጫ ቦርድ አስታወቀ
ፖለቲካ
August 29, 2019
Unknown
የሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄ የህዝበ ዉሳኔ ድምፅ መስጫ ቀን ህዳር 3/2012 እንዲሆን መወሰኑን ምርጫ ቦርድ ዛሬ ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣዉ መግለጫ አስታወቀ፡፡ቦርዱ ከነሃሴ 20፤ 2011 እስከ ህዳር 10፤ 2012 ድረስ የሚቆይ የህዝበ ዉሳኔዉን የድርጊት መርሃግብር እና በጀት አዘጋጅቶ ለደቡብ ክልል ምክር ቤትና ሌሎች የሚመለከታቸዉ አካላት መላኩንም አመልክቷል፡፡በድርጊት መርሃግብረሩ መሰረትም የባለድርሻ አካላትን ማስተባበርና የአፈፃፀም ዉይይት የማድረግ ስራ ከነሃሴ 30 ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ሳምንታት የሚከናወን ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ የ8460 ምርጫ አስፈፃሚዎች ምልመላና 1692 የምርጫ ጣቢያዎችን የማደራጀት ስራ እንዲሁም የህዝበ ዉሳኔ መመሪያዎችን የማውጣትና የድምጽ መስጫ ወረቀቶች ህትመትና የመሳሰሉት ስራዎች እንደሚከናወኑ የቦርዱ መግለጫ አዉስቷል፡፡ቦርዱ በተጨማሪም ከመስከረም 07 ቀን 2012 አ.ም ጀምሮ የህዝበ ውሳኔውን ጸጥታና ደህንነት ጥበቃ የእቅድ ዝግጅት ለማከናወን ከፌደራል፣ ከክልል እና ከዞን የጸጥታ አካላት ጋር የጋራ እቅድ የማውጣት ውይይቶችን ያደርጋል፡፡የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የሀዋሳን ከተማ የወደፊት ሁኔታ ፤የሀብት ክፍፍል እና የሌሎች ብሄረሰብ አባላትን የመብቶች ጥበቃ አስመልክቶ ህጋዊ እና አስተዳደራዊ ማእቀፎችን ማውጣት ስራ እስከ መስከረም 22 ድረስ እንዲያጠናቅቅ መታቀዱንም የቦርዱ መግለጫ ያሳያል፡፡ቦርዱ የቴክኒክ ጉዳዮች በቀሪው ጊዜ ሲያጠናቅቅ ባለድርሻ አካላትም በተሰናዳው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት በመወጣት ሕዝበ ውሳኔው በታቀደለት ጊዜ መሰረት እንዲከናወን የበኩላቸውን ሃላፊነት እንዲወጡ አስታውቋል፡፡     
https://waltainfo.com/am/31319/
174
5ፖለቲካ
ቤተክርስቲያኗ ከፍተኛ ውጤት ኖሯቸው ከፍለው መማር ለማይችሉ ተማሪዎች ነፃ የትምህርት እድል ልትሰጥ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
August 30, 2019
Unknown
የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ ውጤት ከ8ኛ ወደ ዘጠነኛ ለሚያልፉና ከፍለው መማር ለማይችሉ በከተማዋ ለሚገኙ ተማሪዎች በነፃ የመማር እድልን ለመስጠት ቃል ገባች።የነፃ የትምህርት እድሉ በቤተክርስያኒቷ ስር በሚተዳደሩ ት/ቤቶች የሚሰጥ ይሆናል።ኢ/ር ታከለ ኡማ ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ካርዲናል ብርሀነእየሱስ ሱራፌል ጋር ቆይታ አድርገዋል።የከተማ አስተዳደሩ በትምህርት ላይ እየሰራ ያለውን ስራ የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን እንደምትደግፈው ካርዲናል ብርሀነ እየሱስ ሱራፌል ተናግረዋል።የአለም የካቶሊክ ቤተክርስቲያናት ሊቀ-ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ ኢ/ር ታከለ ኡማ ቫቲካንን እንዲጎበኙ የላኩትን ጥሪ ካርዲናል ብርሀነእየሱስ ለከንቲባው አቅርበዋል።ኢ/ር ታከለ በፖፕ ፍራንሲስ የቀረበላቸውን የቫቲካን ጉብኝት ጥሪ በደስታ መቀበላቸውን ተናግረዋል።በመጨረሻም ካርዲናሉ ከከተማ ልማት ጋር የተገናኙ መፅሐፍትን በስጦታ ለኢ/ር ታከለ ኡማ አበርክተዋል፡፡(ምንጭ፦ ከንቲባ ፅ/ቤት)
https://waltainfo.com/am/32687/
94
0ሀገር አቀፍ ዜና
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እንዲመጣ የምታደርገው ጥረት ተጨባጭ ለውጥ እያሳየ መሆኑ ተገለጸ
ፖለቲካ
August 29, 2019
Unknown
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እንዲመጣ የምታደርገው ጥረት ተጨባጭ ለውጥ እያሳየ መሆኑ ተገለጸ።ከ7ኛው ቶኪዮ ለአፍሪካ ልማት ጎን ለጎን በአፍሪካ ቀንድ ቀጠና ትኩረቱን አድርጎ እየተካሄደ ባለው ውይይት ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ፤ ኢትዮጵያ በአካባቢው ሰላምና ብልፅግና  እንዲሰፍን ቁርጠኛ ተግባር እያሳየች መሆኑን ገልጸዋል።አካባቢው በርካታ ቁጥር ያለው ወጣት መገኛ መሆኑን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ለወጣቶች የስራ ዕድል መፍጠር የመሪዎች የቀጣይ ተግባር ሊሆን ይገባል ብለዋል። በአካባቢው ዘላቂ ሰላምና የኢኮኖሚ ዕድገት እንዲመጣ በመደመር እሳቤ ልንሰራ ይገባልም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ።የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢትዮጵያ በቀጠናው ሰላም እንዲሰፍን በተግባር እያሳየች ያለው ሚና የሚደነቅ መሆኑን በመጥቀስ፤  በቅርቡ በሱዳን የተደረሰው ስምምነት የኢትዮጵያን ሚና በአብነት አንስተዋል።የአካባቢውን ሰላም እና ልማት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የጃፓን ድጋፍ እንደማይለይም አረጋግጠዋል። የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሙሀመድ አብዱላሂ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ በአካባቢው አንድነት እና ሰላም እንዲመጣ በሚደረገው ጥረት ሚናዋ ልቆ ይታያል ነው ያሉት።
https://waltainfo.com/am/31318/
124
5ፖለቲካ
ሀገራዊ የሪፎርም ስራዎች በጠንካራ ማክሮ ኢኮኖሚ ሊደገፍ እንደሚገባ ተገለፀ
ቢዝነስ
August 28, 2019
Unknown
ሀገራዊ የሪፎርም ስራዎች ዘላቂና ጤናማ እንዲሆኑ በጠንካራ ማክሮ ኢኮኖሚ ሊደገፍ እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገለፁ።ሀገራዊ የሪፎርም ስራዎች ዘላቂና ጤናማ እንዲሆኑ በጠንካራ ማክሮ ኢኮኖሚ ሊደገፍ እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገለፁ።ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ የውይይት መድረክ መክፈቻ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት አቶ ደመቀ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያውን ሁሉም ሊሳተፍበት እንደሚገባ ተናግረዋል።ውይይቱ የሀገሪቱን ፈጣን እድገት ዘላቂ እንዲሆን ማስቻልና ለወጣቶች ሰፊ የስራ ዕድል ለመፍጠር ያለመ ነው።የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራሙን ይዘት ለማበልፀግና አተገባበሩን ለማሳለጥ ሁሉም ገንቢ አስተዋጽኦ ማድረግ እንደሚገባቸው ነው አቶ ደመቀ የገለፁት።በገንዘብ ሚኒስቴር በኩል የተዘጋጀው "ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻአያ" መድረክ ላይ የተለያዩ ምሁራን፣ የግል ዘርፍ ተዎካዮች፣ የተፎካካሪ ፓርቲ ተወካዮች እና የዘርፉ ተዋንያን ተካፍለዋል።ምንጭ፦ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት 
https://waltainfo.com/am/23928/
108
3ቢዝነስ
ጠ/ሚ ቦሪስ ጆንሰን የእንግሊዝን የህዝብ እንደራሴዎች ከስራ ለማገድ ማቀዳቸው ቁጣ ቀሰቀሰ
ፖለቲካ
August 28, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን የእንግሊዝን የህዝብ እንደራሴዎች ከስራ ለማገድ ማቀዳቸው በሀገሪቱ ቁጣ ቀስቅሷል፡፡የሀገሪቱ ንግስት ኤልዛቤት ሁለተኛ ውሳኔውን እንዲያጸድቁት ጥያቄው ይቀርብላቸዋል ተብሎ እየተጠበቀ ስለመሆኑ ተነግሯል፡፡የጠቅላይ ሚኒስትሩ ውሳኔ  በንግስቲቱ ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ጥቅምት ላይ ሀገሪቱን ከአውሮፓ ህብረት ያለምንም ድርድር ለመነጠል የተያዘው የጆንሰን እቅድ ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ ከባድ ፈተና የሚደቅን መሆኑ በበርካታ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች፣ ፖለቲከኞችና ሌሎች ባለሙያዎች እየተተቸ ቢሆንም ቦሪስ ጆንሰን እቅዳቸውን ከማስፈጸም ወደኋላ እንደማይሉ እየተናገሩ ነው፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ የያዙት ፓርላማውን ከስራ የማገድ እቅድ ከፓርላማው አባላት ጋር ውዝግብ ውስጥ ከቷቸዋል፡፡ዘገባው የአልጀዚራ ነው፡፡
https://waltainfo.com/am/33991/
79
5ፖለቲካ
በ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት ፕሮጀክት በኢትዮጵያ ሊተገበር ነው
ቢዝነስ
August 28, 2019
Unknown
ኢትዮጵያ በ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት ስራ ተግባራዊ ልታደርግ ነው፡፡የአረንጓዴ ልማት ስራው “ስዊች  አፍሪካ ግሪን” ከተባለ ተቋም ጋር በትብብር የሚሰራ  ሲሆን የገንዘቡ ምንጭ የአውሮፓ ህብረት ነው፡፡ከዚህ ቀደም በስድስት የአፍሪካ ሀገራት የአረንጓዴ ልማት ኢኮኖሚ ሲያከናውን መቆየቱን ነው ‘ስዊች አፍሪካን ግሪን’ የተባለው ተቋም ያስታወቀው፡፡ተቋሙ በአውሮፓ ህብረት የገንዘብ ድጋፍ በግብርና፣ በቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ፣ በኢንዱስትሪ እንዱሁም ቱሪዝም ዘርፎች  የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት ስራዎች እያከናወነ ይገኛል።ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደምም የአረንጓዴ ልማት ስራን በሰፊው ስታከናውን መቆየቷ ያስታወሱት የአካባቢ፣ የደን እና የአየር ለውጥ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፕሮፌሰር ፍቃዱ በየነ፤ ከመሰል ተቋማት ጋር በቅንጅት መስራት አረንጓዴ ኢኮኖሚን በመገንባት  የአየር ንብረት ለውጥን በመከላከል ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል፡፡የአውሮፓ ህብረት ተወካይ የሆኑት ኤሪክ ሐበርስ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የጀመረችው የአረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት ለሌሎች ሀገራት በምሳሌነት የሚጠቀስ እንደሆነ ነው የገለፁት፡፡‘ስዊች አፍሪካን ግሪን’ የተባለው ተቋም ከሁለት አመታት በፊት በጋና የተመሰረተ ሲሆን፤  ጋና፣ ሞሪሺየስ፣ ኬንያና ዩጋንዳ ፕሮጀክቱን በመተግበር ላይ ይገኛሉ፡፡በታሪኳ መንግስተአብ 
https://waltainfo.com/am/23929/
135
3ቢዝነስ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ከጃፖን ጠቅላይ ሚኒስትር ሽንዞ አቤ ጋር ተወያዪ።
ፖለቲካ
August 29, 2019
Unknown
ሁለቱ መሪዎች የሀገራቱን ግንኙነት ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ነው የተወያዩት።ጠ/ሚ/ር ዐብይ በውይይቱ በኢትዮጵያ እየተከናወነ ስላለው ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ተምረውና ሰልጥነው የሚገኙ ወጣቶች በጃፓን ገብተው ስራ የሚሰሩበት ሁኔታ እንዲመቻች መጠየቃቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት የውጭ ቋንቋና ዲጅታል ሚዲያ ሃላፊ ቢልለኔ ስዮም ገልፀዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በኢትዮጵያ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን በመተግበር ኢትዮጵያን በአፍሪካ ከአምስት በኢኮኖሚ እድገት ቀዳሚ ሀገር ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።ይህንኑ እውን ለማድረግና የጃፖን የንግዱ ማኅበረሰብም በግብርና: ቱሪዝም: አይሲቲና በማእድን ማውጣት ሥራ እንዲሰማሩ ጥሪ አቅርበዋል::ሽንዞ አቤ የዐቢይን የሀገር ውስጥ የለውጥ አጀንዳ እንደሚደግፉ ገልፀዋል:: እንዲሁም ኢትዮጵያ በኤርትራ የምታደርገውን የሰላም ድጋፍ: በደቡብ ሱዳን ያለውን የሰላም ውይይትና በሱዳን ስምምነት የጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድን ሚና ተደናቂ እንደነበር አንስተዋል::ለጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድና ለኢትዮጵያ በተለይም ለጅማ ጭዳ መንገድ ግንባታ ጃፓን የምታደርገውን እርዳታ እንደምትቀጥል ጠ/ሚር ሺንዞ አቤ ተናግረዋል:: ጃፓን አሁን በሀገሪቱ እየተካሄደ ያለውን ሪፎርም እንደሚደግፉም ገልጸዋል።በቅርቡ ለሀገራዊ ምርጫ ማስፈፀሚያ ድጋፍ ያደረገችው ጃፓን በቀጣይም ድጋፏን በምትቀጥልበት ሁኔታ መወያየታቸውንም የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት የውጭ ቋንቋና ዲጅታል ሚዲያ ሃላፊ ቢልለኔ ስዮም ገልፀዋል።እንዲሁም በመሰረተ ልማትም በኩል ጃፓን የምታደርገውን ድጋፍ ትቀጥላለች ተብሏል።
https://waltainfo.com/am/31317/
160
5ፖለቲካ
በህገ-ወጥ መንገድ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ የገቡ 30 ሺህ ኢትዮጵያዊያን ሕጋዊ የሥራ ፈቃድ አገኙ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 29, 2019
Unknown
የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ መንግሥት በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ አገሩ ለገቡ 30 ሺህ ኢትዮጵያዊያን ሕጋዊ የሥራ ፈቃድ ሰጠ።የኢትዮጵያ መንግሥት ከተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ጋር ጥር 30 ቀን 2011 ዓ.ም የሁለትዮሽ የሥራ ሥምሪት ሥምምነት ተፈራርሟል።በሥምምነቱም መሰረት የኢትዮጵያ መንግሥት ከቤት ሠራተኝነት በተጨማሪ በሌሎች ሙያዎች ግለሰቦችን በማብቃት ወደ ተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ለመላክ ውጥን አለው።ይህንንም ተከትሎ ከሥምምነቱ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከተባበሩት አረብ ኢሚሬተስ የመጡ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ግለሰቦቹ የሚሰለጥኑበትን ሥፍራዎች ለመጎብኘት አዲስ አበባ ገብተዋል።ሃላፊዎቹ የህክምና ኮሌጆች፣ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ተቋማት፣ ሆቴልና ቱሪዝም እንዲሁም ሌሎች የሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ይጎበኛሉ ተብሏል።ይህንን በተመለከተ በተዘጋጀው መርኃ ግብር ላይ የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ወይዘሮ ኤርጌጎ ተስፋዬ ሥምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል።ከሥምምነቱ አስቀድሞ ወደ ተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ በሕገ-ወጥ መንገድ የገቡ 30 ሺህ ዜጎች ህጋዊ የሥራ ፍቃድ መሰጠቱን ጠቁመዋል።ለዚህም የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ መንግሥት አመስግነው ከዚህ በኋላ እንዲህ ያለው ምህረት እንዳማይደረግ አስረግጠው ተናግረዋል።የተባበሩት አረበ ኢሚሬትስ ከዚህ ቀደም በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ የሚታይባትን ክፍተት ጥብቅ ማድረጓን ገልጸው ኢትዮጵያም ተመሳሳይ አቋም አላት ነው ያሉት።ለአብነትም በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ በሕገ-ወጥ መልኩ ይንቀሳቀሱ ከነበሩ 130 ኤጀንሲዎች መካከል 94ቱ ሕጋዊ እርምጃ ተወስዶባቸው 36 ብቻ እንዲሰሩ ተደርጓል።በኢትዮጵያም በአሁኑ ወቅት 549 ኤጀንሲዎች መኖራቸውን ገልጸው በሦስት ማኅበራት እንዲታቀፉ በማድረግ የቁጥጥር ሥርዓቱ ጥብቅ መሆኑን አስረድተዋል።ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስን ጨምሮ ከአራት የመካከለኛው ምስራቅ አገራት ጋር የሥራ ሥምሪት ሥመመነት ተፈራርማለች።(ምንጭ፦ኢዜአ)
https://waltainfo.com/am/32686/
195
0ሀገር አቀፍ ዜና
ቻይና የአሜሪካ የጦር መርከብ የወደብ ጉብኝት ጥያቄን ውድቅ አደረገች
ፖለቲካ
August 28, 2019
Unknown
የአሜሪካ ባህር ኃይል ንብረት የሆነው የጦር መርከብ  ኪንግዳኦ የተሰኘችውን የቻይና የወደብ ከተማ ለመጎብኘት ያቀረበው ጥያቄ በቻይና ውድቅ ተደርጓል፡፡እንደ አሜሪካ መከላከያ ባለስልጣናት ከሆነ ሀገሪቱ በወር ለሁለተኛ ጊዜ ነው የጉብኝት ጥያቄውን ውድቅ ያደረገችው፡፡ከዚህ በፊት ሁለት የአሜሪካ ባህር ኃይል መርከቦች ወደ ሆንግ ኮንግ ለማቅናት አቅርበውት የነበረውን ጥያቄ ቻይና ሳትቀበለው መቅረቷን የአልጀዚራ ዘገባ አስታውሷል፡፡ይህን ተከትሎ በንግድ ጦርነት የሚታወቀው የሁለቱ የዓለማችን ሀያላን ሀገራት ፍጥጫ  መልኩን ቀይሮ ወደለየለት ግጭት እንዳያመራ ስጋትን ከደቀነም ዋል አደር ብሏል፡፡በተጨማሪም አሜሪካ በታይዋን ላይ የምታደርገው ጣልቃ ገብነትም  በቻይና እና አሜሪካ መካከል እሰጥ አገባው እንዲካረር አድርጓል፡፡ይህ በእንዲህ እንዳለ  ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቅርቡ ከቻይና ጋር ለመወያየት ዝግጁ መሆናቸውን ማስታወቃቸው ውጥረቱ እንዳይባበስ ይረዳል የሚል ግምት በብዙዎች ዘንድ አሳድሯል፡፡
https://waltainfo.com/am/33990/
103
5ፖለቲካ
በእነ ጀነራል ተፈራ ማሞ የተጠየቀው ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ይሰጠኝ ይግባኝ ውድቅ ተደረገ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 28, 2019
Unknown
በእነ ጀነራል ተፈራ ማሞ መዝገብ የተጠየቀው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ይሰጠኝ ይግባኝ በባሕር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውድቅ ተደርጓል፡፡የባህርዳር እና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በቂ የምርመራ ጊዜ መሰጠት አለመሰጠቱን ለማጣራት በዳኞች አብላጫ ድምፅ ይግባኝ ቀርቧል፡፡ዐቃቤ ህግ በአራት እና አምስት ጊዜ ቀጠሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ባለማቅረቡ ነው የተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ ይሰጠኝ ይግባኙ ውድቅ የተደረገው፡፡ዐቃቤ ህግ ይግባኝ የማለት መብቱ የተጠበቀ መሆኑን ፍርድ ቤቱ አስታውቋል፡፡ፍርድ ቤቱ በትናትናው ዕለት የእነ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የቀዳሚው ምርመራ መዝገብ ለማየት ለዛሬ ቀጠሮ መስጠቱ የሚታወስ ነው፡፡(ዘገባው የአብመድ ነው፡፡)
https://waltainfo.com/am/32684/
80
0ሀገር አቀፍ ዜና
የካንሰር ህመምን ለመከላከል በሚከናወነው ስራ የአፍሪካ ሀገራት ትኩረት እንዲሰጡ ተጠየቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 28, 2019
Unknown
የካንሰር ህመምን ለመከላከል በሚከናወነው ስራ የአፍሪካ ሀገራት ትኩረት እንዲሰጡ ተጠየቀ፡፡በአፍሪካ የካንሰር ህመም ላይ የሚመክር አህጉራዊ ስብሰባ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡በአፍሪካ የካንሰር ህመም ከግንባር ቀደም ገዳይ በሽታዎች ተርታ መሆኑ በወርክሾፑ ላይ የተጠቀሰ ሲሆን፣ ችግሩን ለመከላከል ሀገራቱ የበለጠ ትኩረት ሊሰጡ ይገባል ተብሏል፡፡ኢትዮጵያን ጨምሮ በአንዳንድ ሀገራት ለውጦች እየታዩ ቢሆንም አሁንም ተጨማሪ ስራዎችን በትኩረት መስራት እንደሚገባና ስራውንም በቴክኖሎጂ ማገዝ እንደሚገባ ተገልጿል፡፡በስብሰባው ላይ የተሳተፉት የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን ኢትዮጵያ ድምፅ አልባ ለሆነው የካንሰር ህመም ትኩረት ሰጥታ እየሰራች እንደሆነ ተናግረው፣ ኢትዮጵያ በትንባሆና በአልኮል መጠጦች ላይ ያወጣቻቸውንና የጣለቻቸውን ገደብ ጠቁመዋል፡፡በተያዘው በጀት ዓመትም ተጨማሪ መሰል ገደቦችን የሚጥሉ መሰል ህጎች ይወጣሉ ብለዋል፡፡በሌላ በኩል ስራውን በቴክኖሎጂ የማገዝና ቅድመ መከላከል ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል ፡፡
https://waltainfo.com/am/32685/
106
0ሀገር አቀፍ ዜና
የጃፓን ባለሃብቶች በአፍሪካ ባለፉት ሦስት ዓመታት ከ 20 ቢሊዮን ዶላር በላይ ኢንቨስት አድርገዋል-ሽንዞ  አቤ
ቢዝነስ
August 28, 2019
Unknown
የጃፓን ባለሃብቶች በአፍሪካ ባለፉት ሦስት ዓመታት ከ 20 ቢሊዮን ዶላር በላይ  ኢንቨስት አድርገዋል-ሽንዞ  አቤ፣7ኛው የቶኪዮ ለአፍሪካ ልማት /ቲካድ/ ጉባኤ በጃፓን ዮኮሃማ ከተማ እየተካሄደ ሲሆን፤ በጉባኤው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ፣ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሽንዞ  አቤ፣ የተመድ ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጎቴሬዝ፣ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሳ ፋኪ መሃማት፣ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር አብዱል ፈታህ አልሲሲ ከታደሙት መካከል ናቸው ።እየተካሄደ ባለው 7ኛው የቶኪዮ ለአፍሪካ ልማት /ቲካድ/ ጉባኤ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሽንዞ አቤ ባደረጉት ንግግ፤ ባለፉት ዓመታት የጃፓን የግሉ ዘርፍ ባለሃብቶች በአፍሪካ ኢኮኖሚ ውስጥ 25 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ መዋዕለንዋያቸውን አፍስሰዋል ብለዋል፡፡የጃፓን ባለሀብቶች በአፍሪካ ሁለንተናዊ ተሳትፎ እያደረጉ መሆናቸውን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ባለሃብቶቹ በባለፉት ሶስት ዓመታ ብቻ እንኳ ወደ 20 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ኢንቨስት እንዳደረጉ ገልጸዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም በኢትዮጵያ እና ኤርትራ፣ በሱዳን እንዲሁም በደቡብ ሱዳን የታየውን ሰላም የሚደነቅ ነው ብለዋል።የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር የግብጽ ፕሬዘዳንት አብዱል ፈታ አልሲሲ በበኩላቸው፣ የዘንድሮው የቲካድ መሪ ቃል አፍሪካ በቴክኖሎጂ እና ሰው ሀይል በኩል ያሉባትን ክፍተቶች የለየ መሆኑ ለቀጣይ ስራ መልካም አጋጣሚ የፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል።ጃፓን በአፍሪካ 3 ሚሊየን የሚደርሱ ህፃናት መደበኛ ትምህርት እንዲያገኙ ማስቻሏንና ይህም የጃፓን መንግስት በአህጉሩ ላይ የልማት ውጤት እንዲመጣ ያሳየ ተነሳሽነት ነው ብለዋል፡፡ጃፖንን ጨምሮ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ እና ቴክኖሎጂ ኩባንያዎች በአፍሪካ በስፋት ሊሰማሩ ይገባል ብለዋል።የተባበሩት መንግስት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬስ በበኩላቸው በአፍሪካ ሀገራት የተፈረመው ነጻ የንግድ ቀጠና ስምምነት የንግድ ኢንቨስትመንትን ለማሳለጥ እንደሚያግዝ ገልጸው፣ ጃፓን በአፍሪካ ላይ እያደረገች ያለውን ፍላጎት ለማሳደግ ትልቅ ሚና ይኖረዋል ብለዋል፡፡ኮንፈረንሱ በ3 ቀናት ቆይታው የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች የተወያዩበትን የዮካሃማ 2019 ስምምነት መሪዎችም ተወያይተው ያጸድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።ጉባኤው በህዝብ አስተዳደር፣ በኢኖቬሽን እና የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በአፍሪካ ልማት ላይ ሚና እንዲኖራቸው በማድረግ ላይ ትኩረት አድሮጎ የሚወያይ ሲሆን፤ በአፍሪካና በጃፓን የንግድ ግንኙነት ምን መሆን ባለበት ሁኔታም ይመክራል ተብሏል። 
https://waltainfo.com/am/23926/
260
3ቢዝነስ
ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ቁልፍ ተቋማትን ወደ ግሉ ዘርፍ ለማዞር እየሰራች ነው- ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ
ቢዝነስ
August 28, 2019
Unknown
መንግስት የውጭ ኢንቨስትመንትና ባለሃብቶችን መሳብ በሚያስችል መልኩ ቁልፍ የሆኑ ተቋማትን ወደ ግሉ ዘርፍ ለማዞር እየሰራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ገለጹ፡፡በጃፓን እየተካሄደ ባለው 7ኛው የቶኪዮ ለአፍሪካ ልማት (ቲካድ) ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ፤ ስለ ግሉ ዘርፍ ተሳትፎ፣ ስለ ቀጠናዊ ውህደት እና በሃገሪቱ የተካሄዱ ማሻሻያዎችን በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል። በንግግራቸውም በሁሉም ዘርፍ ተከታታይነት ያለው ኢኮኖሚያዊ እድገት ማስመዝገብ ቅድሚያ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን በመጠቆም፤ በሁሉም ዘርፍ ተሳትፎ ማሳደግ ወሳኝ መሆኑን አውስተዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚዋን ለግሉ ዘርፍ ክፍት ማድረጓን በመጥቀስ፤ የግሉ ዘርፍም ምርታማነትን በሚያሳድጉና ለስራ እድል ፈጠራ ወሳኝ በሆኑ ዘርፎች የሚኖረው ተሳትፎ እንደሚቀጥልም አንስተው በዘርፉ የተደረገው ማሻሻያም ኢንቨስትመንትን ለማሳደግ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸዋል።አሁን ላይም በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ለማሳደግ ይስተዋሉ የነበሩ ተግዳሮቶች ማሻሻያ የተደረገባቸው መሆኑን ገልጸው፤ ለባለሃብቶች ተሳትፎ በሚያመች መልኩ የተንዛዙ አሰራሮችን ሙሉ በሙሉ ለመቅረፍ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።የማክሮ ኢኮኖሚውን ሚዛን ለመጠበቅና ተከታታይነት ያለው እድገት ማስመዝገብ በሚያስችል መልኩ መንግስት ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያዎች ማድረጉን አስረድተዋል።ማሻሻያዎቹ ፈጠራን እና የአፈጻጸም ብቃትን ማሳደግ የሚያስችሉ መሆናቸውንም አስረድተዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።ቀጠናዊ እና ኢኮኖሚያዊ ውህደት ለእድገት በተለይም ተከታታይነት ያለውና ዘላቂ እድገት ለማስመዝገብ አስፈላጊ መሆኑንም ጠቁመዋል።ኢኮኖሚያዊ ውህደት በቀጠናው ለሚኖረው የሰላም ግንባታ ከፍ ያለ ሚና እንዳለው እንረዳለንም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።ከዚህ አንጻርም ኢትዮጵያም የአፍሪካ ነጻ የንግድ ገበያን በመጠቀም ለቀጠናው ብሎም ለአፍሪካ ኢኮኖሚያዊ ውህደት በግንባር ቀደምትነት ትሰራለችም ነው ያሉት።መድረኩን በንግግር የከፈቱት የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ጃፓን የአፍሪካን እድገት የምታደርገውን ድጋፍ ትቀጥላለች ብለዋል፤ የትብብሩ ትኩረትም በኢንቨስትመንት እና ፈጠራ ላይ መሆኑን በመጥቀስ።ባለፉት ሶስት አመታት የጃፓን ኢንቨስትመንት በአፍሪካ ከ20 ቢሊየን ዶላር በላይ መድረሱን ጠቅሰው፥ ቶኪዮ አሁን ላይ  በአህጉሪቱ በሠላም ሂደት እየሠራች መሆኑን አስታውሰዋል።በጃፓኗ ዮኮሃማ መካሄድ የጀመረው ፎረሙ “የአፍሪካን ልማት በሰው ሃብት፣ በቴክኖሎጂ፣ በፈጠራ ማራመድ” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ይገኛል።
https://waltainfo.com/am/23927/
248
3ቢዝነስ
ታንዛኒያ ከ200 ሺህ በላይ የብሩንዲ ስደተኞችን ልታስወጣ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
August 28, 2019
Unknown
በታንዛንያ የሚገኙ ከ200 ሺህ በላይ የብሩንዲ ስደተኞች እስከመጭው ጥቅምት ወር ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ካልሆነ ግን በግድ እንደሚመለሱ የታንዛኒያ የውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጹ።ሚንስትሩ ካንጊ ሉጎላ "አሁን በብሩንዲ ሰላም አለ፤ በመሆኑም እስከ መጭው ጥቅምት ወር ድረስ ስደተኞቹ ወደ አገራቸው መመለስ አለባቸው፤ ከዚያ በኋላ ግን ፈለጉም አልፈለጉም እንመልሳቸዋለን " ብለዋል።ከአራት ዓመታት በፊት በብሩንዲው ፕሬዚደንት ፒዌሬ ንክሩንዚዛ ለሦስተኛ ጊዜ በምርጫ ማሸነፋቸውና የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራን ተከትሎ በነበረው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት በርካታ ብሩንዲያዊያን ወደ ጎረቤት ሃገራት ተሰደዋል።ስደተኞቹ በታንዛኒያ ደቡብ ምዕራብ ግዛት ኪጎማ፤ ኒያሩጉሱ፣ ንዱታ እና ምቴንደሊ የስደተኛ ማቆያ መጠለያ ተጠልለው ይገኛሉ።ታንዛኒያ ስደተኞችን ወደ መጡበት አገር አስገድዶ መላክን በሚከለክለው የተባበሩት መንግሥታት ስምምነት አባል ናት።ይሁን እንጂ የውስጥ ጉዳይ ሚንስትሩ ሉጎላ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኤጀንሲ ባለፈው ዓመት በየቀኑ 2 ሺህ ስደተኞች ለመመለስ በታንዛኒያና በብሩንዲ መካከል የተደረገውን ስምምነት አላከበረም ሲል ወቅሰዋል።ባሳለፍነው አርብ ሉጎላ ከብሩንዲ አቻቸው ፓስካል ባራንዳጊየ፤ በነዱታ የሚገኘውን የስደተኞች መጠለያን የጎበኙ ሲሆን ስደተኞቹ ወደ ሃገራቸው የማይመለሱ ከሆነ ከበድ ያለ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው አስጠንቅቀዋል።አንድ ስሙ እንዳይገለፅ የጠየቀ ስደተኛ ለቢቢሲ እንደተናገረው ወደ ብሩንዲ ለመመለስ ደህንነት እንደማይሰማው ተናግሯል።"ውሳኔው ያልተጠበቀ ነው፤ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ወይም ታንዛኒያ የኒክሩንዚዛ መንግሥት በዜጎቹ ላይ እስር እንዳይፈፅም ምን ሰራ ? ግድያ አለ፤ ጠለፋ አለ፤ አስክሬን ይገኛል፤ የሚመልሱን እንድንገደል ነው" ሲል ስጋቱን ገልጿል።የዓለም አቀፉ ስደተኞች መርጃ ድርጅት (UNHCR) ቃል አቀባይ ዳና ሁግሄስ፤ ሁለቱ ሃገራት ዓለም አቀፉን ስምምነት እንዲያከብሩና የስደተኞችን መብት እንዲጠብቁ አሳስበዋል።ቃል አቀባይዋ እንዳሉት ድርጅቱ በታንዛኒያ የብሩንዲ ስደተኞች በፈቃደኝነት ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ በሚደረገው ሂደት ተሳትፈው እንደነበር አስታውሰው በእያንዳንዱ ቀን 100 አዲስ ስደተኞች ከብሩንዲ ወደ ታንዛኒያ እንደሚገቡም አክለዋል።
https://waltainfo.com/am/33467/
228
0ሀገር አቀፍ ዜና
የጃፓን ባለሃብቶች በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ቢሰማሩ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግላቸው አስታወቀ
ቢዝነስ
August 28, 2019
Unknown
የጃፓን ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ቢሰማሩ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግላቸው አስታወቀ።በደቡብ ኮሪያው እና በጃፓኑ የስራ ጉብኝት የተሳተፉት የሚኒስትሮች ልዑካን ከ7ኛው የቶኪዮ ለአፍሪካ ልማት መድረክ ጎን ለጎን ከጃፖኑ ማሪቦኒ ድርጅት ጋር የቢዝነስ ውይይቶችን አካሂደዋል።በውይይቱ የማሪቦኒ ድርጅት በኢትዮጵያ መሰማራት በሚፈልግባቸው ዘርፎች ዙሪያ ገለፃ የተደረገ ሲሆን፣ በሀገሪቱ በኢነርጂ፣ በማዕድንና በቡና ምርት ላይ እሴት በመጨመር ላይ ፍላጎት እንዳለው የድርጅቱ ስራ አስፈፃሚ ማሳሜ ካሱካኪ አስረድተዋል።ከኢትዮያ በኩል በሀገሪቱ በአሁኑ ወቅት የውጭ ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት የሚያስችሉ የማሻሻያ እና የአሰራር ማስተካከያ መደረጉ ተመልክቷል።ባለሀብቶች በማዕድን፣ በኢነርጂ፣ በኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች ኪራይ እንዲሁም፣ በቡና ዘርፍ ቢሰማሩ ውጤታማ እንደሚሆኑ በማስረዳት በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ለመሰማራት ፍላጎት ያላቸው መሆኑን አስታውቀዋል።መንግስት ለባለሀብቶቹ አስፈላጊውን ድጋፍ እና ማበረታቻ እንደሚሰጥም ልኡካኑ ለባለሃብቶቹ ገልጸውላቸዋል። 
https://waltainfo.com/am/23925/
103
3ቢዝነስ
ባለፉት ሶስት ዓመታት የጤና አገልግሎት ተደራሽነት መሻሻል ማሳየቱ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 27, 2019
Unknown
በጤና ሚኒስቴር ፣ በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትና አጋር ድርጅቶች ሲካሄድ የቆየ ጥናት ዛሬ ይፋ በሆነበት መድረክ፤ ባለፉት ሶስት ዓመታት የጤና አገልግሎት ተደራሽነት መሻሻል ማሳየቱ ተገልጿል።የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ደረጃ የሕብረተሰቡ የጤና አገልግሎት በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ለማወቅና የተሻለ የጤና አገልግሎት የሚሰጥበትን ሁኔታ ለመቀየስ በሚል ከመጋቢት 2011 ዓ.ም ጀምሮ ለ3 ወራት  ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡ጥናቱ ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ በአገር-አቀፍ ደረጃ በተመረጡ 305 የቆጠራ ጣቢያዎች መካሄዱ ተገልጿል፡፡በዚህም መሰረት እድሜያቸው ከ15 እስከ 49 ዓመት ማለትም በመዉለድ የዕድሜ ክልል ዉስጥ የሚገኙ 8 ሺህ 885 ሴቶች  የጥናቱን መረጃ መሰብሰብ ተችሏል፡፡ ለክትባት መረጃም ዕድሜያቸው ከ2 እስከ 3 ዓመት የሆናቸው 1 ሺህ 28 ህጻናት እንዲሁም ለቁመትና ክብደት ልኬት ዕድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች የሆኑ 4 ሺህ 990 ልጆች በጥናቱ ተካተዋል፡፡በዚህም የቤተሰብ ዕቅድ አጠቃቀም በ2008 ዓ.ም ከነበረበት 31 በመቶ  ወደ 41 በመቶ ከፍ እንዲል ማድረግ የተቻለ ሲሆን በጤና ተቋማት የሚወልዱ እናቶች ቁጥርም 50 በመቶ መሻሻል እንዳሳየ ተመልክቷል፡፡በቀጣይ ዕቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ የጤና  ሚኒስቴር  አዳዲስ የጤና አገልግሎት ሥርዓቶችን ተግባራዊ እንደሚያደርግ ሚኒስትሩ ዶክተር አሚር አማን ገልፀዋል።ከ5 ዓመት በታች የሕፃናት ሞት አሁን ላይ ከ1ሺህ ሕፃናት ውስጥ 55 ህፃናቶች እንደሚሞቱ  ጥናቱ ያመለከተ ሲሆን፤ ይህም በ2008 ዓ.ምት ከነበረው 65 በመቶ ጋር ሲነፃፀር ለውጥ መምጣቱንአሳይቷል ተብሏል፡፡ ዋና ዋና የጥናቱ ጠቋሚ መረጃዎች ላይ ሰፋ ያለ ውይይት የተካሄደበት  ሲሆን፤ ከውይይቱ የተገኙ ነጥቦችም በቀጣይ በዘርፉ ለሚሰሩ ስራዎች በግብዓትነት ያገለግላሉ ነው የተባለው።ጥናቱ እውን እንዲሆን የዓለም ባንክ ፣ የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት እና ዩኒሴፍ የቴክኒክና የበጀት ድጋፍ አድርገዋል፡፡  
https://waltainfo.com/am/32682/
215
0ሀገር አቀፍ ዜና
ጠ/ር ዐብይ አህመድ በ7ኛው የቶኪዮ ለአፍሪካ ልማት ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ጃፓን ዮኮሀማ ገቡ
ፖለቲካ
August 27, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ በ7ኛው የቶኪዮ ለአፍሪካ ልማት /TICAD/ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ጃፓን ዮኮሀማ ገቡ። ሰባተኛው የቶኪዮ ለአፍሪካ ልማት መድረክ ዘንድሮ ለ7ኛ ጊዜ በመካሄድ ላይ ሲሆን፤  ቀደም ብሎ በሚኒስትሮች ደረጃ የጀመረው መድረኩ ቀጥሎ በመሪዎች ደረጃ ይካሄዳል።በጃፓን ዮኮሃማ በሚካሄደው በዚሁ ጉባኤ የአፍሪካና የጃፓን መሪዎች እንዲሁም የጃፓን ባለሃብቶችና የንግድ ሰዎች ይሳተፉበታል ተብሎ ይጠበቃል።የቶኪዮ ለአፍሪካ ልማት ጉባኤ በ1993 እ.ኤ.አ አፍሪካን ከጃፓን ጋር በልማት ለማስተሳሰር የተጀመረ ነው።በዘንድሮው ጉባኤ መድረክ ቴክኖሎጂን እና ኢኖቬሽንን በማጣመር ለአፍሪካ ልማት በሚውልበት ሁኔታ ላይ እና በአፍሪካና በጃፓን የንግድ ትስስር ላይ ትኩረቱን ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።
https://waltainfo.com/am/31315/
85
5ፖለቲካ
በምዕራብ ሸዋ ዞን የአዋሽ ወንዝ ያስከተለው ጎርፍ የተዘራ ሰብል ላይ ጉዳት አደረሰ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 27, 2019
Unknown
በምዕራብ ሸዋ ዞን እየጣለ ያለው ከባድ ዝናብ ተከትሎ የአዋሽ ወንዝ ሞልቶ በመፍሰስ ያስከተለው ጎርፍ 3ሺህ 500 ሄክታር የእርሻ ማሳ ላይ የተዘራ ሰብልን ከጥቅም ውጪ ማድረጉን የዞኑ ኮሙዩኔኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታወቀ።የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ጉታ ቡልቻ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ጎርፉ ያደረሰው ጉዳት ኤጀርሳለፎ እና ኤጄሬ በተባሉ ወረዳዎች በሚገኙ 12 ቀበሌዎች ውስጥ ነው።በዚህም በ3ሺህ 500 ሄክታር ማሳ በመጥለቀለቁ ተዘርቶ የነበረ የስንዴ፣ የበቆሎ፣የማሽላና ሌላም ሰብል ከጥቅም ውጭ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ከጥቅም ውጪ የሆነው ሰብል ከ12 ሺህ በላይ አባወራ አርሶ አደሮች የዘሩት እንደነበር ጠቁመው፤ እየጣለ ያለው ከባድ ዝናብ በመቀጠሉ በጎርፍ የሚጥለቀለቅ ማሳ ሊጨምር እንደሚችል ተናግረዋል፡፡የዞኑ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተሾመ መርዳሳ በበኩላቸው፤ ለተጎጂዎቹ  መፍትሄ  ለመስጠት ጥናት የሚያካሂድ ቡድን መቋቋሙንና ድጋፍ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡እየጣለ ያለው ከባድ ዝናብ ተከትሎ በቀጣይ ሊመጣ የሚችለውን ጎርፍ ለመከላከል የአካባቢው ህብረተሰብ ከወዲሁ ጥንቃቄ እንዲያደረግም ማሳሰባቸው ተጠቁሟል።  
https://waltainfo.com/am/32683/
129
0ሀገር አቀፍ ዜና
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሄስያን የሰላም ሽልማት አሸናፊ ሆኑ
ፖለቲካ
August 28, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የአውሮፓውያኑ የ2019 የሄስያን የሰላም ሽልማት አሸናፊ መሆናቸውን በጀርመን የፍራንክፈርት ከተማ የሚገኘው የፍራንክፈርት የሰላም ጥናት ማዕከል ገለጸ፡፡የጥናት ማዕከሉ እንዳስነበበው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ታሪካዊውን የሰላም ስምምነት መፈጸም በመቻላቸው የሄስያን የሰላም ሽልማት አሸናፊ መሆን ችለዋል ብሏል።ሽልማቱም መስከረም 12 ቀን 2012 ዓ.ም. እንደሚበረከትላቸው የፍራንክፈርት የሰላም ጥናት ማዕከል አሳውቋል።ዶክተር ዐቢይ አህመድ በአፍሪካ ተስፋ ከሚጣልባቸው መሪዎች አንዱ መሆናቸውንም ተቋሙ ገልጿል፡፡የፍራንክፈርት የሰላም ጥናት ማዕከል በቀድሞው የሔሰን ግዛት ጠቅላይ ምኒስትር አልበርት ኦስዋልድ የተመሰረተ ሲሆን፣ ላለፉት 26 አመታት ለዓለም አቀፍ መግባባት እና ሰላም የላቀ ሚና ላበረከቱ ግለሰቦች ሽልማት ሲያበረክት ቆይቷል።
https://waltainfo.com/am/31316/
91
5ፖለቲካ
የዝሆን ግልገሎች ለዓለም አቀፍ ንግድ እንዳይቀርቡ እገዳ ተጣለ
ቢዝነስ
August 28, 2019
Unknown
የዝሆን ግልገሎች ለዓለም አቀፍ ንግድ እንዳይቀርቡ በዓለም አቀፍ ደረጃ መታገዳቸው ተገለጸ፡፡በስዊዘርላንድ ጀኔቫ በተካሄደው ጉባዔ ከአፍሪካ የዝሆን ግልገሎችን በመያዝ ለእንስሳት ማቆያ እንዳይሸጡ የሚከለክለው ሕግ ፀድቋል።አደጋ ላይ በሚገኙ የእንስሳት ዝርያዎች ዓለም አቀፍ ንግድ ላይ የሚያተኩረው ጉባዔ ተሳታፊዎች በጉዳዩ ላይ ለቀናት ከተከራከሩበት በኋላ ሕጉን ለማጥበቅ ስምምነት ላይ መድረሳቸው ታውቋል።እግዱ በ87 አብላጫ ድምፅ ድጋፍ እና በ29 ተቃውሞ ካገኘ በኋላ እግዱ እንዲፀድቅ ተወስኗል። ይሁን እንጂ ዝሆኖችን ወደ ውጭ በመላክ የምትታወቀው አፍሪካዊት ሃገር ዚምባብዌ ልክ እንደ አሜሪካ ሁሉ እግዱን ተቃውማለች።ዚምባብዌ እንቅስቃሴውን አጥበቃ በዘመቻ ስትቃወም የነበረ ሲሆን፣ የአውሮፓ ሕብረትም በዓለም ላይ ያለውን የእንስሳት ዝርያ ስብጥር እንዳይኖረው ያደርጋል ሲሉ መጀመሪያ አካባቢ ተቃውመውት ነበር።ከሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ዝሆን በብዛት የሚገኝባቸው ዚምባብዌና ቦትስዋና 'ተቀባይነት ላላቸውና ትክክለኛ ለሆኑ' ተቀባይ ሃገራት ዝሆኖችን ወደ ውጭ ለመላክ ይፈቅዱ ነበር።በዓለም ላይ ከፍተኛ ቁጥር ዝሆኖች የሚገኙባት ቦትስዋና በዚህ በያዝነው ዓመት ዝሆኖችን ማደን የሚከለክለው ሕግ፣ ገበሬዎችንና ከዚህ በፊት በማደን ገቢ ያገኙ የነበሩ ግለሰቦችን እየጎዳ ነው በሚል መፍቀዷ ይታወሳል።እነዚህ ሃገራት ከጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር 2012 ጀምሮ ከ100 በላይ የሚሆኑ የዝሆን ግልገሎችን በመያዝ ለቻይና የእንስሳት ማቆያ መላካቸውን ሁዩማን ሶሳይቲ ኢንተርናሽናል አስታውቋል።በመሆኑም ትናንት የተላለፈው ውሳኔ የዝሆን ንግድን ቁጥጥር እንዲጠብቅ ያደርጋል ተብሏል።በአዲሱ ሕግ መሠረት ዝሆኖች ከዱር ተይዘው በእንክብካቤ በሚቆዩበት በየትኛውም የዓለማችን አካባቢ መቆየት የሚችሉ ሲሆን ይህ ግን የሚቻለው በከተማዋ የኮሚቴ አባላት ሲፀድቅ ይሆናል።ይሁን እንጅ የአውሮፓ ህብረት በልዩ ሁኔታ መላክ እንደሚቻልና በእንስሳት ማቆያ ያሉ ዝሆኖችን ማዛወር እንደሚቻል ሕጉ የተወሰነ መሻሻል ከተደረገበት በኋላ ሃሳቡን ቀይሯል።"ይህ ማለት አንድም ዝሆን ከዱር ተይዞ በውጭ አገር ለእንስሳት ምቹ በሆኑ ማቆያዎች አይገቡም ማለት አይደለም" ሲሉ የቦርን ፍሪ ፋውንዴሽን ፕሬዚደንት ዊል ትሬቨርስ ተናግረዋል።አክለውም እግዱ በተለይ በወደ ሩቅ ምስራቅ በጅምላ ያለ አግባብ የሚላኩ ዝሆኖችን ለመቆጣጠር ሕጉን ማጥበቅ አስፈላጊ እንደሆነም ገልፀዋል። (ምንጭ፡-ቢቢሲ)
https://waltainfo.com/am/33559/
248
3ቢዝነስ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የደቡብ ኮሪያ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደ ጃፓን አቀኑ
ፖለቲካ
August 27, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የደቡብ ኮሪያ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደ ጃፓን አቅንተዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ የ42 አገራት መሪዎች በሚሳተፉበት የቲካድ የመሪዎች ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ነው ወደ ጃፓን ያቀኑት፡፡በዮኮሃማ ጃፓን ለሶስት ቀናት ለሚካሄደው የቲካድ የመሪዎች ስብሰባ በሚኒስትሮች ደረጃ የሚመክረው የአፍሪካ የሚኒስትሮች ጉባዔ ላይ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የሚመራ ልዑክ እየተሳተፈ ይገኛል ፡፡በአፍሪካ ልማት ዙሪያ ምክክር የሚያደርገው የቶኪዮ አለም አቀፍ ኮንፈረንስ/ ቲካድ/ እ.አ.አ ከ1993 ጀምሮ አፍሪካ ከድህነት ለመውጣት የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ በጃፓን ጠንሳሽነትና አመራርነት የሚካሄድ ነው።በጥምር አዘጋጅነትም የአለም ባንክ፣ የተመድ ልማት ድርጅት እንዲሁም የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን እየተሳተፉ ይገኛል፡፡
https://waltainfo.com/am/31313/
86
5ፖለቲካ
አቶ በቀለ ሙለታ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾሙ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 26, 2019
Unknown
አቶ በቀለ ሙለታ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾሙ።የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትን ለአምስት ዓመታት የመሩት አቶ በቀለ ሙለታ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾሙ።የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አክሲዮን ማህበር የቀድሞው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ወልዱ ይመሰል ከዚህ በፊት የጀመሩትን የሶስተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ለመቀጠል የስራ አመራር ቦርዱን ጠይቀው በተፈቀደላቸው መሰረት ነው አዲስ ኃላፊ የተሾመው።በአክሲዮን ማህበሩ ስራቸውን የጀመሩት አዲሱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ በቀለ ቀደም ብሎ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ከሪፖርተርነት እስከ ዋና አዘጋጅነት ያገለገሉ ሲሆን፤ በጋዜጠኝነትና በአመራር የካበተ ልምድ አላቸው።አቶ በቀለ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ትምህርት ዘርፍ የያዙ ሲሆን፤ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን አግኝተዋል።የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ባገለገሉበት ወቅት ተቋሙ ከተጠሪነት ወጥቶ ራሱን ችሎ እንዲንቀሳቀስ ለማድረግ የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን የመሪነት ሚናቸውን ተጫውተዋል።በዚህም ኢዜአ ከቀድሞው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ተጠሪነት ተላቆ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተጠሪ ለመሆን ችሏል።የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን አክሲዮን ማህበር የቀድሞው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዱ ይመሰል በተቋሙ ከጋዜጠኝነት እስከ ዋና ስራ አስፈፃሚነት ከምስረታው ጀምሮ ሲያገለግሉ መቆየታቸው የሚታወቅ ነው። 
https://waltainfo.com/am/32680/
158
0ሀገር አቀፍ ዜና
ኮሪያውያን ባለሀብቶች በኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለዉ ለውጥ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጠየቁ
ቢዝነስ
August 27, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በደቡብ ኮሪያ ዋና ከተማ ሴዑል የኮሪያ ኢትዮጵያ የቢዝነስ ፎረምን የከፈቱ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቀት በርካታ የሪፎርም ስራዎች እየተካሄደ መሆኑን አስረድተዋል።በዚህ ሂደት የውጭ ባለሀብቶች በሀገሪቱ ገብተው መስራት እንዲችሉ የኢንቨስትመንት ህጉን ቀላል መደረጉን በመጠቆም፤ይህንን አጋጣሚ ኮሪያዊውያን ባለሀብቶች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።ዛሬ የተጀመረው የኢትዮጵያ ኮሪያ ቢዝነስ ፎረም በኮሪያ አፍሪካ ንግድ ማህበርና ፋዉንዴሽን በትብብር የተዘጋጀ ነው።የኮሪያ አፍሪካ ፋውንዴሽን ኘሬዚዳንት በበኩላቸው፤ ኮሪያ የኢትዮጵያን ውለታ እንደማትዘነጋ ጠቅሰው ትብብራቸውን እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።በተመሳሳይ ጠቅላይ ሚኒሰትር ዐብይ ከሀዩንዳይ ስራ አስፈፃሚ ሊ ወን ሂ ጋር የተወያዩ ሲሆን፤ ከኤል ጂ የኢኖቬሽን ጋለሪ ስራ አስፈፃሚ ስኮት አን ጋርም ተወያይተዋል።ጋለሪውን የጎበኙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድርጅቱ በኢትዮጵያ እያከናወነ ያለውን ማህበራዊ ሀላፊነት የመወጣት ተግባር አድንቀዋል። 
https://waltainfo.com/am/23924/
104
3ቢዝነስ
አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በቲካድ የሚኒስትሮች ጉባዔ  እየተሳተፉ ነው
ፖለቲካ
August 27, 2019
Unknown
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በቲካድ የሚኒስትሮች ጉባዔ ላይ እየተሳተፉ ነው።በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የሚመራ የልዑካን ቡድን እ.አ.አ ከነሃሴ 28 እስከ 30 ቀን 2019 በዮኮሃማ (ጃፓን) ለሚካሄደው የቲካድ የመሪዎች ስብሰባ በሚኒስትሮች ደረጃ በሚመክረው የአፍሪካ የሚኒስትሮች ጉባዔ ላይ ይሳተፋል።ከዚሁ ጉባዔ አስቀድሞ የከፍተኛ ባለሙያዎች ስብሰባ ከነሃሴ 25 እስከ 26 ቀን 2019 የተካሄደ ሲሆን፤ በሚኒስትሮች ጉባዔ የሚዳብረውንና በመሪዎች ደረጃ በሚጸድቀው የዮኮሃማ ረቂቅ ሠነድ ላይ ውይይት ተደርጓል።የዘንድሮው ጉባዔ መሪ ቃልም “የአፍሪካን ልማት በሰው ሃብት፣ በቴክኖሎጂ፣ በፈጠራ ማራመድ” የሚል መሆኑ ተገልጿል።ከዚሁ የቲካድ ስብሰባ ጎን ለጎን ነሃሴ 30 በሚካሄደው ኢትዬ-ጃፓን ቢዝነስ ፎረምና ኤግዚቢሽን 180 የጃፓን ባለሃብቶች ይገኛሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፥ 43 የኢትዮጵያ የንግድ ማህበረሰብ አባላትም ይሳተፋሉ።በአፍሪካ ልማት ዙሪያ ምክክር የሚያደርገው የቶኪዮ አለም አቀፍ ኮንፈረንስ/ ቲካድ/ እ.አ.አ ከ1993 ጀምሮ አፍሪካ ከድህነት ለመውጣት የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ በጃፓን ጠንሳሽነትና አመራርነት የሚካሄድ ነው።በጥምር አዘጋጅነትም የአለም ባንክ፣ የተመድ ልማት ድርጅት እንዲሁም የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን እየተሳተፉ መሆኑን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
https://waltainfo.com/am/31312/
144
5ፖለቲካ
ቄራ ጎፋ ማዞሪያ አካባቢ በሁለት የፖሊስ አባላት የተፈፀመውን ድርጊት እያጣራሁ ነው -የአዲስ አበባ ፖሊሰ ኮሚሽን
ሀገር አቀፍ ዜና
August 27, 2019
Unknown
ነሃሴ 20 ቀን 2011 ዓ/ም ከረፋዱ 5 ሰዓት ባለው ጊዜ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ቄራ ጎፋ ማዙሪያ አካባቢ በድለላ ስራ ላይ በተሰማሩ ሁለት ቡድኖች መካከል አለመግባባት ተፈጥሮ እንደነበር ኮሚሽኑ አስታውሷል፡፡የተፈጠረውን አለመግባበት ለመዳኘት ወደ ቦታው ያቀኑ ሁለት የፖሊስ አባለት ያለመግባባቱን ለማብረድ የሁለቱም ቡድን አባለት ወደ ፖሊስ ጣቢያ እንዲሄዱ በሚጠይቁበት ወቅት አለመግባባቱ ተካሮ የፖሊስ አባላቱ ጥይት መተኮሳቸውና በሰዎች ላይ ድብደባ መፈፀማቸውን ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡  የፖሊስ አባለቱ አዲስ እና በቅርቡ ሰራዊቱን የተቀላቀሉ መሆናቸውን ኮሚሽኑ አስታውሶ ነግር ግን የፈፀሙት ድርጊት ተገቢነትና ተቀባይነት የሌለው ስለሆነ ጉዳያቸው በወንጀልና በመተዳደሪያ ደንቡ መሰረት እየተጣራ መሆኑን አስታውቋል፡፡   ጉዳዩን አጣርቶ የደረሰበትን ውጤት ለህዝብ የሚያሳውቅ መሆኑ የገለፀው ኮሚሽኑ ፤ ህብረተሰቡ መሰል ጉዳዮች ሲያጋጥሙ በየደረጃው ለሚገኙ የስራ ኃላፊዎች የማሳወቅ ልምዱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪውን አስተላልፏል፡፡(ምንጭ ፦የአዲስ አበባ ፖሊሰ ኮሚሽን)
https://waltainfo.com/am/32681/
120
0ሀገር አቀፍ ዜና
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከኮይካ ፕሬዝዳንት ጋር ተወያዩ
ፖለቲካ
August 27, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከኮይካ ፕሬዝዳንት ጋር ተወያዩ። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከኮርያ ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (ኮይካ) ፕሬዝዳንት ጋር ለኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ድጋፍ የበለጠ በሚጠናከርበት ዙሪያ ተወያዩ።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኮይካ በኢትዮጵያ በተለይም በትምህርት፣ በውሃና ግብርና ዘርፎች ላይ የሚያደርገውን የልማት ድጋፍ አድንቀዋል።ኮይካ በተለያዩ የልማት ዘርፎች ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ ለማጠናከር ፍላጎት እንዳለው ኃላፊዎቹ መገግለፀፃቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
https://waltainfo.com/am/31314/
56
5ፖለቲካ
በሱዳን የጎርፍ መጥለቅለቅ ተከስቶ ከ60 ሰዎች በላይ መሞታቸው ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 26, 2019
Unknown
በሱዳን የጎርፍ መጥለቅለቅ ተከስቶ ከ60 ሰዎች በላይ መሞታቸው ተገለጸ፡፡የሀገሪቱ ይፋዊ መግለጫ እንደሚያሳየው ሱዳን በከፍተኛ ጎርፍ ተመትታለች።በአደጋው ምክንያትም 62 ሰዎች ሕይወታቸውን እንዳጡ ይፋ የተደረገ ሲሆን፣ በሕዝባዊ ተቃውሞ ስትናጥ የከረመችው ሱዳን ከሃምሌ ወር መግቢያ ጀምሮ ደግሞ ከፍተኛ ዝናብ የሃገሪቱ ሌላኛው ፈተና ሆኖ ቆይቷል።ከባድ ዝናቡ ባስከተለው ጎርፍ 15 የሱዳን ግዛቶች የከፋ ጉዳት ደርሶባቸዋል። በደቡባዊ የሃገሪቱ ክፍል የምትገኘው የነጭ አባይ ግዛት ደግሞ ከፍተኛውን ጉዳት በማስተናገድ ቀዳሚ ነች ተብሏል።በእነዚህ 15 ግዛቶች 200 ሺህ የሚጠጋ ህዝብ በተፈጠረው የጎርፍ መጥለቅለቅ ጉዳት ደርሶበታል ነው የተባለው።በጉዳዩ ላይ ሃሳቡን የሰነዘረው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 37 ሺህ ቤቶች በተፈጠረው የጎርፍ መጥለቅለቅ ከመውደማቸው በተጨማሪ በቀጣዮቹ ጊዜያትም የጎርፍ አደጋ ሊከሰት እንደሚችል ስጋቱን ገልጿል።የሱዳን ዝናባማው ወቅት እስከ ጥቅምት ወር የሚቀጥል መሆኑ ደግሞ ሌላኛው ስጋት ነው።ካለፈው ታህሳስ ወር ጀምሮ በሕዝባዊ ተቃውሞ ስትናጥ የቆየችው ሱዳን አንጻራዊ ሰላም ያመጣ ሽግግር ብታደርግም የወደቀውን ምጣኔ ኃብቷን ለመታደግ ከ8 ቢሊዮን ዶላር በላይ ድጋፍ ያሰፈልጋታል ተብሏል።እንደዚህ አይነት የተፈጥሮ አደጋዎች መከሰታቸው ደግሞ ለሃገሪቱ ተጨማሪ ችግር በመውለድ ሱዳን ከችግር የምትወጣበትን ጊዜ ያራዝመዋል የሚሉ አስተያየቶች በብዛት እንዲስተናገዱ አድርጓል። (ምንጭ፡-ቢቢሲ)
https://waltainfo.com/am/33466/
154
0ሀገር አቀፍ ዜና
ሱዳን የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ አወጀች
ፖለቲካ
August 26, 2019
Unknown
በሱዳን ቀይ ባህር ግዛት በተከሰተ የጎሳ ግጭት 16 ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ በግዛቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጇል፡፡የሱዳን አዲሱ ጊዜያዊ የሽግግር መንግስት አስተዳደር የምስራቃዊ ግዛት አስተዳዳሪ እና የፀጥታ ሀላፊን ከስራ ማሰናበቱም ተገልጿል፡፡በፖርት ሱዳን አካባቢ በባኒ አሚርና ኑባ ቡድን መካከል የተነሳው ግጭት ከረቡዕ እስከ ቅዳሜ ለአራት ተከታታይ ቀናት የቆየው ሲሆን የግጭቱ መንስኤ ምን እስካሁን አልተገለፀም፡፡ለ16 ሰዎች ህልፈት ምክንያት የሆነው ይህ ግጭት ውስጣዊ እና ውጫዊ ምክንያት እንዳለው መንግስት አስታውቋል፡፡ፖርት ሱዳን የቀይ ባህር ግዛት ዋና ከተማ ስትሆን በጣም አስፈላጊ የመርከብ መተላለፊያ መስመር እንደሆነች ይታወቃል፡፡(ምንጭ፦ ቢቢሲ)
https://waltainfo.com/am/33330/
80
5ፖለቲካ
የአሸንዳ በዓል የማጠቃለያ ፕሮግራም በመጪው እሁድ ይካሄዳል
ሀገር አቀፍ ዜና
August 26, 2019
Unknown
ለአሸንዳ በዓል የማጠቃለያ ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን በአዲስ አበባ የትግራይ ሴቶች ማህበር አስታውቋል፡፡የማጠቃለያ ዝግጅቱ  በሚሊኒየም አዳራሽ ነሃሴ 26፣ 2011 ዓ.ም. ይካሄዳል፡፡በዝግጅቱ ላይ አምባሳደሮች ፣ከመላው ብሄር፣ ብሄረሰቦች የተወከሉ ግለሰቦችና አመራሮችን ጨምሮ  ከ30 ሺህ በላይ ሴቶች ይታደማሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ተገልጿል፡፡አዘጋጆቹ የአሸንዳ ዓመታዊ ክብረ በዓል በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኒስኮ) እንዲመዘገብ ለማስቻል እየተሰራ መሆኑን  ለዋልታ ቴሌቭዥን ገልፀዋል፡፡የአሸንዳ በዓል ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ ከትውልድ  ትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግም  ይሰራል ብለዋል፡፡ 
https://waltainfo.com/am/32678/
65
0ሀገር አቀፍ ዜና
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትና የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የሴት ሰራተኞች ተሳትፎ ለማሳደግ ስምምነት ተፈራረሙ
ቢዝነስ
August 26, 2019
Unknown
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በዓለም ባንክ ድጋፍ የሴት ሰራተኞች ተሳትፎን ለመጨመር ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል፡፡ድጋፉ በተቋሙ የሚገኙ ሴት ሰራተኞች በቴክኒክና ሙያ፣ በኢንጂነሪንግና ሌሎች መስኮች ላይ ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያግዝ ነው ተብሏል፡፡በ2025 ዓ.ም. የኤሌክትሪክ አገልግሎትን በመላው ኢትዮጵያ ተደራሽ ለማድረግ ሃገራዊ ፕሮግራም ተግባራዊ በመደረግ ላይ ነው፡፡ለዚሁ ፕሮግራም ስኬታማነት ፣የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የድርጅቱ ሴት ሰራተኞችን አቅም እና ተጠቃሚነትን ለማጎልበት እየሰራ እንደሆነ አስታውቋል፡፡በድርጅቱ ከሚገኙ ሰራተኞች ውስጥ 20 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ሲሆኑ የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ለማጎልበት የሚረዳ ድጋፍ ከአለም ባንክ ያገኘ ሲሆን ለ5 ተከታታይ ዓመታት ተግባራዊ የሚደረግ ነው፡፡የሴቶችን አቅም ለማጎልበትም የዓለም ባንክ በየአመቱ የ500 ሺህ ዶላር ድጋፍ ያደርጋል፡፡ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በኩል ስምምነቱን የፈረሙት ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ሴቶችን ማብቃት የአንድ ሴክተር ስራ መሆን ብቻ እንደማይገባው ገልፀዋል፡፡ለተከታታይ አራት ዓመታት በየዓመቱ 40 ሴት ሰራተኞችን በቋሚነት በመቅጠር ድጋፉን እንደሚያጠናክር የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡
https://waltainfo.com/am/23923/
146
3ቢዝነስ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከደቡብ ኮርያ ፕሬዝዳንት ሙን ጃ-ኢን ጋር ተገናኝተው ተወያዩ
ፖለቲካ
August 26, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከደቡብ ኮርያ ፕሬዝዳንት ሙን ጃ-ኢን ጋር ተገናኝተው ተወያዩ::በውይይታቸው ወቅት ፕሬዝዳንት ሙን ጃ-ኢን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እየወሰዱ ያሉትን መልካም እርምጃዎች በማድነቅ መላው አለም እየተመለከተ እንዳለ አንስተዋል::መሪዎቹ  በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት የበለጠ ለማሳደግ የተስማሙ ሲሆን ከውይይቱም በተጨማሪ ሁለቱ ወገኖች የተለያዩ ስምምነቶችና የመግባቢያ ሰነዶች ተፈራርመዋል::በዚህም መሰረት በአምስት የተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ የመግባቢያ ሰነዶችን ነው የፈረሙት፡፡1. የሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማቲክ ፖስፖርት ይዘው ለሚጓዙ ዜጎች ያለ ቪዛ የሚገቡበት ስምምነት:2.በሁለቱ ሀገራት መካከል የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ለማቋቋም የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ:3. በደረጃ፣ ብቃት ማረጋገጫ፣ ተስማሚነት ምዘናና የቴክኒክ ቁጥጥር ዙሪያ በትብብር ለመስራት የሚያስችል የስምምነት ሰነድ፣ 4. የአካባቢ ጥበቃ ትብብር የስምምነት ሰነድ እና5. በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ውስጥ የልህቀት ማዕከልን ለማቋቋም የብድር ስምምነት ናቸው::ማምሻውን ፕሬዝዳንት ሙን ጃ-ኢን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለማክበር የእራት ግብዣ ያደረጉላቸው ሲሆን፣ ሁለቱም መሪዎች የኢትዮጵያና የኮርያን ህዝቦች ረጅም ታሪካዊ ግንኙነቶች ዙሪያ ንግግር አድርገዋል:: መረጃው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ነው፡፡
https://waltainfo.com/am/31311/
136
5ፖለቲካ
የሰላም ሚኒስትሯ ከብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ጋር በእምነት ተቋማት ላይ እያጋጠሙ ባሉ ችግሮች ዙሪያ መከሩ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 26, 2019
Unknown
የሰላም ሚኒስትሯ ከኢትዮጵያ ከብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ጋር በእምነት ተቋማት ላይ እያጋጠሙ ባሉ ችግሮች ዙሪያ መከሩ።የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እና የሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ አልማዝ መኮንን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ እና ከብጹአን ሊቃነጳጳሳት ጋር በሀገር ደረጃ እና በእምነት ተቋማት ላይ እያጋጠሙ ባሉ ችግሮች ዙሪያ መከሩ፡፡በውይይቱ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከተመሰረተችበት ጊዜ አንስቶ ለሀገር አንድነትና ሰላም የበኩሏን አስተዋጽኦ ስታበረክት መቆየቷን አስታውሰዋል፡፡በአገሪቷ በተለያዩ ጊዜያት በቤተክርስቲያኒቱ ላይ የተለያዩ ጥቃቶች ሲፈጸሙ መቆየታቸውንና ቤተክርስቲያኗም ተልዕኮዋን ለመፈጸም እንቅፋት እየገጠማት መሆኑን ጭምር ለሚንስትሯ አስረድተዋል፡፡በእምነት ተቋማት ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችም ከጊዜ ወደጊዜ እየገዘፉ በመምጣታቸው መንግስት በወንጀል ፈጻሚዎች ላይ ህጋዊና አስተማሪ እርምጃ በመውሰድ ድርጊቶቹ እንዳይበራከቱ ሊያደርግ ይገባዋልም ብለዋል፡፡የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በሀገር ሰላም ግንባታ ላይ ላበረከተችው አስተዋጽኦ በማመስገን፤ቤተክርስቲያኗ ችግሮች ባጋጠሟት ጊዜ ሁሉ በአስተዋይነትና በአርቆ አሳቢነት ላለፈችበት መንገድም መንግስት ትልቅ አክብሮት እንዳለው ገልጸዋል፡፡በእምነት ተቋማት ላይ እየተፈጸሙ ያሉ ጥቃቶች እና የእምነት ተቋማቱን በተለያዩ መንገዶች የማወክ እንቅስቃሴዎች በአንድ ወይም በሁለት ተቋማት ላይ ብቻ የሚፈጸም ሳይሆን ሁሉንም እምነቶች ኢላማ ያደረጉ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሯ፣ የእምነት ተቋማት በሀገር ግንባታ ላይ የሚታይና የሚነበብ ታሪክ ያላቸው በመሆኑ በተቋማቱ ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችም ሀገርን የማፍረስ ተልዕኮ ያነገቡ ሀይሎች የሚፈጽሙት በመሆኑ መንግስትና የሀይማኖት ተቋማት በቅንጅት መከላከል ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡መንግስትም በሀገር ደረጃ ዴሞክራሲን ከማስፋት ጎን ለጎን የህግ የበላይነትን የማረጋገጥ ተግባርን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም የሰላም ሚኒስትሯ ጨምረው ገልጸዋል፡፡ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ እንዳስገነዘቡትም አዲሱን ዓመት ያሉብንን በርካታ ሀገራዊ ችግሮች አራግፈን ወደ ሰላም ዓመት እንድናመራ መላው ኢትዮጵያውያን፣ የእምነት ተቋማት፣ መንግስት እና የሚመለከታቸው ሁሉ ለሰላም መስፈን በጋራ መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡ 
https://waltainfo.com/am/32679/
245
0ሀገር አቀፍ ዜና
ዲሞክራቲክ ኮንጎ ከሰባት ወራት በኋላ አዲስ ካቢኔ አቋቋመች
ፖለቲካ
August 26, 2019
Unknown
ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ አዲሷን ፕሬዝዳንት ፌሊክስ ሲሼኬዲ ወደ ስልጣን ካመጣች ከሰባት ወራት በኋላ የጥምር መንግስት ካቢኔ አቋቁማለች፡፡ሀገሪቷ በ1960 ከቤልጅየም ነፃነቷን ካገኘች ወዲህ በታሪኳ የመጀመሪያ የሆነውን ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ህዳር ወር ላይ በተካሄደው ምርጫ ለማድረግ በቅታለች።አዲሱ ፕሬዝዳንት ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ ከቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ካቢላ ፓርቲ ጋር በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሰዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር ሲልቪስተር ኢሉንጋ ለኤኤፍፒ፣ በመጨረሻም መንግስት እዚህ ተገኝቷል፤ ፕሬዝዳንቱ በስምምነቱ ላይ ፊርማቸውን አኑረዋል፣ በቅርቡም ስራው ይጀመራል ሲሉ ተናግረዋል።(ምንጭ፡-ቢቢሲ)
https://waltainfo.com/am/33329/
69
5ፖለቲካ
በ67 ሚልዮን ብር ወጪ የተገነባው ሰንዳፋ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 25, 2019
Unknown
​​​​በ67 ሚልዮን ብር ወጪ የተገነባው ሰንዳፋ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ ለዋልታ እንዳሉት፤ ክልሉ ለጤናው ዘርፍ ቅድሚያ በመስጠት የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ ነው።በመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሉ ከአምስት ወራት በፊት ግንባታው ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቆ እስካሁን ከ5ሺህ በላይ ታካሚዎች መገልገላቸውን ነግረዉናል።በሆስፒታሉ ውስጥ ህክምናውን ሲከታተል ያገኘናቸው ታካሚ  እንደሚገልጹት፤ የህክምና አገልግሎት አሰጣጡ ጥሩ መሆኑን የተሻለ መሆኑን አስታውቀዋል።ሆስፒታሉ በአቅራቢያው በመገንባቱ ቀድሞ አዲስ አበባ እየሄደ ሲታከም ያወጡት የነበረውን ወጪም እንዳስቀረላቸው ተናግረዋል።በሆስፒታሉ የመድሃኒት እጥረት መኖረን የጠቆሙት ታካሚው፤ በቀጣይም እጥረቱ ተቃሎ ሙሉ አገልግሎት በመስጠት የታማሚዎችን ጤና እንደሚመልስ ተስፋ ማድረጋቸውን ነግረውናል።በሰንዳፋ በኬ አገልግሎት እየሰጠ ያለው ሆስፒታሉ 100 የጤና ባለሙያዎች እንዳሉት እና ለ450ሺህ ሰዎች አገልግሎት እንደሚሰጥ የክልሉ ጤና ቢሮ ሃላፊ ተናግረዋል።በኦሮሚያ ክልል 85 ሆስፒታሎች እና 1450 ጤና ጣቢያዎች መኖሩን ያመለከቱት የክልሉ ጤና ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ደረጄ፤ በቀጣይ በተለይ በጥራት ላይ አተኩረው  እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
https://waltainfo.com/am/32676/
129
0ሀገር አቀፍ ዜና
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ደቡብ ኮሪያ ገቡ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 25, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ደቡብ ኮሪያ ገብተዋል። የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ( ዶክተር) ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ደቡብ ኮሪያ ሴዑል ገብተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ልዑካቸው ሴዑል አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በደቡብ ኮሪያ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ ወዳጆችና በዚያው በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አቀባበል ተደርጎላቸዋል። በሴዑል በሚኖራቸው ቆይታም ከደቡብ ኮሪያው ፕሬዝዳንት ሙን ጃይ ኢን ጋር በሀገራቱ መካከል ስላለው ዘርፈ ብዙ ግንኙነት ዙሪያ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ታላላቅ የሀገሪቱን ኩባንያዎችንም ይጎበኛሉ። 
https://waltainfo.com/am/32675/
70
0ሀገር አቀፍ ዜና
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በኮሪያ የኢትዮጵያ ሰማዕታት ሀውልት ላይ የአበባ ጉንጉን አስቀመጡ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 26, 2019
Unknown
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በኮሪያ የኢትዮጵያ ሰማዕታት ሀውልት ላይ የአበባ ጉንጉን አስቀመጡ።ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ልዑካቸው የደቡብ ኮርያ ይፋዊ ጉብኝታቸውን በኮርያ ጦርነት ወቅት ለወደቁ የኢትዮጵያ ሰማዕታት መታሰቢያ በሆነው በሴውል ብሄራዊ የመቃብር ቦታ ጉንጉን አበባ በማስቀመጥ ነው የጀመሩት፡፡በኮሪያ ጦርነት ኢትዮጵያ ከ6 ሺህ በላይ ሰራዊት ተሳትፎ የነበራቸው ሲሆን፣ ለሁለቱ ሀገራት ግንኙነትም መሰረት የጣለ ክስተት ነወ ተብሏል።የኢትዮጵያና የኮርያ ግንኙነት በ1940ዎቹ ንጉሠ ነገሥታት ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የክቡር ዘበኛ ሰራዊታቸውን ወደ ኮርያ የተባበሩት መንግሥታት ኃይልን እንዲቀላቀሉ በላኩ ወቅት የተጀመረ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚነስትር ዐብይ የኮሪያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዪኒቨርሲቲን ጎብኝተዋል።በጉብኝታቸው ወቅት ከዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራር ጋርም የተወያዩ ሲሆን፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲው ኢትዮጵያውያንን በማስተማር እና በማሰልጠን ሀገሪቱ ወደ ብልጽግና በምታደርገውን ሽግግር የድርሻቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትላንትናው ዕለት በደቡብ ኮርያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባዘጋጀው የእራት ግብዣ ላይ ከኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት ጋር መወያየታቸው ይታወቃል።
https://waltainfo.com/am/32677/
127
0ሀገር አቀፍ ዜና
እስራኤል፤ ሶሪያ ውስጥ የሚገኝ የኢራን ሰው አልባ አውሮፕላኖች ጣቢያ ላይ ወታደራዊ ጥቃት መፈፀሟን አስታወቀች
ፖለቲካ
August 26, 2019
Unknown
እስራኤል፤ ሶሪያ ውስጥ የሚገኝ አንድ የኢራን ሰው አልባ አውሮፕላኖች ጣቢያ ላይ ወታደራዊ ጥቃት መፈፀሟን አስታውቃለች።በሶሪያ ስላላት ተሳትፎ ብዙም መረጃ የማትሰጠው እስራኤል 'ሰው አልባ አውሮፕላን ጣቢያው የቴል-አቪቭ መንግሥት ላይ ጥቃት ለመፈፀም እየተዘጋጀ ነበር' ብላለች።የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ የወታደራዊ ኃይላቸውን እርምጃ 'አብይ እና ስኬታማ ኦፕሬሽን' ሲሉ ገልፀውታል።የሶሪያ የእርስ በርስ ግጭት ከተቀሰቀሰበት እ.አ.አ 2011 ጀምሮ እስራኤል በርካታ ወታደራዊ እርምጃዎችን ስትወስድ ነበር። ዋነኛ ዓላማዋም ኢራን በሶሪያ ያላትን ቦታ መጋፋት ነው።የእስራኤል ወታደራዊ ኃይል ቃል-አቀባይ የሆኑ ሰው ቅዳሜ ዕለት የተካሄደው ኦፕሬሽን፤ ደቡብ ምስራቅ ደማስቆ የከተሙት በኢራን የሚደገፉት ኩርድስ የተሰኙ ታጣቂዎችን ዒላማ ያደረገ ነው።'ሰንዓ ኒውስ ኤጀንሲ' የተባለ አንድ የሶሪያ ዜና ወኪል የእስራኤል ፀረ-አየር ኃይል አባላት የጠላት ይዞታን ዒላማ አድርገዋል ሲል ዘግቧል። ነገር ግን የእስራኤል ሚሳዔሎች ዒላማቸውን ከመምታቸው በፊት ከጥቅም ውጭ ሆነዋል ሲል ነው ወኪሉ ያተተው።ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታኒያሁ ግን በትዊተር ገፃቸው ድል ማስመዝገባቸውን የሚናገር መልዕክት ነው ያስተላለፉት፤ 'ኢራን ሁሉም ቦታ መከላከያ የላትም። የኛ ኃይሎች የኢራንን ወረራ ለመመከት ሁሉም ቦታ ይገኛሉ። አንድ ኃይል ሊገልህ ከተነሳ ቀድመህ ግድለው' ሲሉ።ሌላኛው በኢራን የሚደገፈው 'ሄዝቦላህ' ሁለት የሌባኖስ ዜጎች በእስራኤል ጥቃት መሞታቸውን ይፋ አድርጓል። ድርጅቱ የእስራኤል ንብረት ናቸው ያላቸውን ሁለት ሰው አልባ አውሮፕላኖች መትቶ መጣሉንም አስታውቋል።ምንም እንኳ ስለጥቃቱ ጥርት ያለ መረጃ ሊገኝ ባይቻልም እስራኤል ጥቃት ፈፅሜያለሁ ከማለት አልቦዘነችም፤ ኢራን በጉዳዩ ላይ እስካሁን መግለጫ አልሰጠችም። (ምንጭ፡-ቢቢሲ)
https://waltainfo.com/am/33989/
192
5ፖለቲካ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኮሪያው ኤግዚም ባንክ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ
ቢዝነስ
August 26, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኮሪያው ኤግዚም ባንክ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ::በውይይታቸው ለኢትዮጵያ ሲደረጉ በነበሩና በአዳዲስ ድጋፎች ዙሪያ መክረዋል::በአሁኑ ወቅት በኤግዚም ባንክ ድጋፍ ከ600 ሚልዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ የሚፈጁ ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ 300 ሚሊዮን ዶላሩ በ2011-2012 በኮርያ ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ልማት ትብብር ፈንድ ማእቀፍ ስር የተፈረመ ነው ተብሏል፡፡መረጃው የጠቅላይ ሚኒስትረት ጽ/ቤት ነው፡፡
https://waltainfo.com/am/23922/
51
3ቢዝነስ
ብራዚል የአማዞን እሳትን ለማጥፋት ወታደር ልትልክ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
August 24, 2019
Unknown
የብራዚል ፕሬዘዳንት ጃዬር ቦልሶናሮ፤ በአማዞን ደን የተነሳውን እሳት ለማጥፋት በሚደረገው ጥረት የአገሪቱ ወታደራዊ ኃይል ድጋፍ እንዲሰጥ ትዕዛዝ አስተላለፉ።በፕሬዘዳንቱ ውሳኔ መሰረት በጥብቅ ተፈጥሯዊ ሥፍራና በድንበር አካባቢ ወታደሮች ይሰማራሉ። ውሳኔው ይፋ ከመደረጉ አስቀድሞ የአውሮፓ መሪዎች ብራዚል ላይ ከፍተኛ ጫና እያደረጉ ነበር።"ወታደር እንደመሆኔ የአማዞን ጫካን እወደዋለሁ፤ ልታደገውም እፈልጋለሁ" ሲሉ ፕሬዘዳንቱ ንግግር አድርገዋል።ወታደሮቹ ይሠማራሉ የተባለው ለአንድ ወር ሲሆን፤ የመከላከያ ሚኒስትሩ ፈርናንዶ አዜቬዶ ኤ ሲልቫ ሂደቱን ያስፈጽማሉ ተብሏል።ብራዚል በአማዞን ጫካ የተከሰተውን እሳት ለማጥፋት ያላሰለሰ ጥረት ካላደረገች ፈረንሳይና አየርላንድ ከሰሜን አሜሪካ ጋር ሊያደርጉት የነበረውን የንግድ ስምምነት እንደማያጸድቁ ተናግረዋል።የብራዚል ፕሬዘዳንት በበኩላቸው መሪዎቹ "በአማዞን ደን የተነሳውን እሳት አስታከው ማዕቀብ መጣል አይችሉም" ሲሉ ተችተዋል።በአሁን ወቅት የአውሮፓ ሕብረት ካውንስል መሪ የሆነችው ፊንላንድ የገንዘብ ሚኒስትር፤ የአውሮፓ ሕብረት የብራዚል የሥጋ ምርት ላይ ማዕቀብ እንዲጥል ጠይቀዋል።የተፈጥሮ ጥበቃ ላይ የሚሠሩ ቡድኖች ባሳለፍነው አርብ በመላው ብራዚል ሰላማዊ ሰልፍ አድርገው ነበር። በተለያዩ አገሮች የሚኖሩ ብራዚላዊያንም ተቃውሟቸውን እያሰሙ ይገኛሉ።የዓለም ግዙፉ ደን እንዲሁም "የዓለም ሳምባ" እየተባለ የሚሞካሸው አማዞን የሙቀት መጠን መጨመር ጋብ እንዲል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል።አማዞን የአንድ ሚሊየን ሰዎች መኖሪያ ከመሆኑ በተጨማሪ ከሦስት ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ እጽዋትና እንስሳት መገኛም ነው።የጀመርኗ መራሔተ መንግሥት አንግላ መርኬል፣ የፈረንሳዩ ፕሬዘዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እና የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን እሳቱን "ዓለም አቀፍ ቀውስ" ብለውታል።አንግላ እና ኢማኑኤል በ ጂ-7 ውይይት ላይ የአማዞን ደን እሳት ለውይይት መቅረብ እንዳለበትም ገልጸዋል።የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሀፊ አንቶንዮ ጉቴሬዝ በትዊት ገጻቸው ላይ "ዓለም በአየር ንብረት ለውጥ ቀውስ ውስጥ በምትገኝበት በዚህ ወቅት፤ ቀዳሚ የኦክስጅን ምንጫችን የሆነው የአማዞን ደን አደጋ ውስጥ መውደቅ አይገባውም" የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።የብራዚሉ ፕሬዘዳንት ጃዬር በበኩላቸው፤ የፈንሳዩ ፕሬዘዳንት ኢማኑኤልን ጨምሮ በርካታ መሪዎች በአማዞን ጉዳይ ጣልቃ የሚገቡት "ለፖለቲካ ጥቅም ነው" በማለት ትችት ሰንዝረዋል።ብራዚል የአማዞን ደንን ለመጠበቅ በቂ ጥረት እያደረገች አይደለም የሚለውን አስተያየት "መሰረተ ቢስ ወሬ" በማለት ፕሬዘዳንቱ አጣጥለዋል። አገሪቱ ጫካውን ለመጠበቅ "አዳዲስ ሕጎች አውጥታለች" ሲሉም ተደምጠዋል።አገሪቱ ሞቃታማ የአየር ሁኔታ በምታስተናግድበት ወቅት ሁሉ እሳት እንደሚነሳም ተናግረዋል።ከብሔራዊ የህዋ ምርምር የወጣ የሳተላይት መረጃ እንዳመለከተው የእሳት ቃጠሎው 85 በመቶ ጨምሯል። ፕሬዘዳንቱ ግን "ወቅቱ አርሶ አደሮች አዲስ ሰብል ለመትከል መሬት የሚያቃጥሉበት ወቅት ስለሆነ ነው" ብለው ቁጥሩን አልተቀበሉም።የተፈጥሮ ጥበቃ ባለሙያዎች እንደሚሉት፤ የብራዚል ፕሬዘዳንት አርሶ አደሮች የአማዞንን ደን እንዲመነጥሩ ያበረታታሉ። የምረጡኝ ቅስቀሳ ባካሄዱበት ወቅት፤ ደኑ ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ግለሰቦች የሚጣልባቸውን ቅጣት እንደሚያለዝቡ ተናግረው ነበር። የአገሪቱን የአካባቢ ጥበቃ ተቋም ለማዳከምም ቃል ገብተው ነበር። (ምንጭ፡-ቢቢሲ)
https://waltainfo.com/am/34130/
336
0ሀገር አቀፍ ዜና
ብራዚል የአማዞን ደን ቃጠሎን ለመከላከል የእሳት አደጋ ሰራተኞቿን  ወደ ስፍራው ላከች
ሀገር አቀፍ ዜና
August 24, 2019
Unknown
ብራዚል የአማዞን ደንን ከሰደድ እሳት ቃጠሎ ለመታደግ ወደ ስፍራው ወታደራዊ ሀይሏንና የእሳት አደጋ ሰራተኞቿን  መላኳ ተገለፀ፡፡የአማዞን ደን ያጋጠመውን ሰደድ እሳት ተከትሎ የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አደጋው ዓለማቀፍ መቅሰፍት  ስለሆነ  ክስተቱ በቡድን ሰባት ስብሰባ ላይ መነጋገሪያችን ሊሆን ይገባል ከማለት በተጨማሪ በቲዊተር ገጻቸው ላይ "ቤታችን እየነደደ ነው" ሲሉ አስፍረዋል።የብራዚሉ ርዕሰ ብሔር ጃይር ቦልሶናሮ የማክሮንን አስተያየት ጉዳዩን ፖለቲካዊ ገጽታ ማላበስ ነው ሲሉ ወርፈዋል።ብራዚል በሌለችበት ሰባቱ የበለጸጉ ሀገራት በአማዞን ሰደድ እሳት ጉዳይ ስብሳባ ለማድረግ መሞከር ምዕራባዊያን አሁንም ከቅኝ ግዛት አስተሳሰብ አለመላቀቃቸውን የሚያሳይ ነው ሲሉም ፕሬዝዳን ቦልሶናሮ አክለዋል።የብራዚሉን ፕሬዝዳንት አሰተያየት እንደዋዛ ያላዩትት የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የብራዚሉ አቻቸው የሰደድ እሳቱን ለመቆጣጠር አስፈለጊውን እርምጃ የማይወስዱ ከሆነ የደቡብ አሜሪካ ሀገራት ከአውሮፓ ህብረት ጋር ከሃያ ዓመታት ድርድር በኋላ የተደረሰውን የንግድ ስምምነት ተግባራዊ እንዳይሆን አደርጋለሁ ብለዋል፡፡ይህን የማክሮን አስተያየት ተከትሎ ብራዚል ዛሬ የእሳት ቃጠሎውን ለመቆጣጠር የእሳት አደጋ ሰራተኞችን ወደ ቦታው መላኳን አስታውቃለች፡፡ብራዚል ይህንን ያደረገችው ከአውሮፓ ሀያላን ሀገሮች የመጣውን ተደጋጋሚ ጫና ተከትሎ እንደሆነም ነው የተነገረው፡፡እናም ብራዚል የአማዞን ቃጠሎን ለመታደግ ወታደሮቿንና የእሳት አደጋ ሰራተኞቿን የአንድ ወር የዘመቻ ጊዜ ሰጥታቸዋለች፡፡የአማዞን ጥቅጥቅ ደን ከፍተኛ የሆነ ኦክስጅን ለዓለም ከባቢ አየር እንደሚያበረክት ሲሆን፤ የዓለማችን ትልቁ ደን አማዞን ከ3 ሚሊየን በላይ የእንስሳትና እፅዋት ዝርያዎች እንዲሁም ከ1 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን በውስጡ አቅፎ ይዟል፡፡አሁን ግን  አማዞን እየተቃጠለ ነው ብራዚሊያዊያን ደግሞ ጩኸታቸውን ወደ ፕሬዝዳንት ቦሎሶናሬ አድርገዋል ተብሏል፡፡ብራዚል የአማዞን ደንን ከቃጠሎ ለመታደግ በምታደርገው ጥረት የአሜሪካ እና እስራኤልን ድጋፍም መጠየቋ የተነገረ ቢሆንም፤የዓለም መሪዎች የዓለም ሳምባ በመባል የሚታወቀውን የዓማዞን ደን  ለመታደግ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ከማድረግ ይልቅ ዝምታን መምረጣቸው አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ዘገባው የቢቢሲ እና አልጀዚራ ነው፡፡ 
https://waltainfo.com/am/34131/
230
0ሀገር አቀፍ ዜና
የ4 ቢሊየን የችግን መርሃ ግብር ሙሉ ለሙሉ ተሳክቷል- ብሄራዊ የቴክኒክ ኮሚቴ
ቢዝነስ
August 24, 2019
Unknown
የ4 ቢሊየን የችግኝ መርሃ ግብር ሙሉ ለሙሉ መሳካቱን በሀገር አቀፍ ደረጃ የችግኝ መርሃ ግብሩ አስተባባሪ ብሄራዊ የቴክኒክ ኮሚቴ አስታወቀ፡፡በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የችግኝ ተከላ ማሳረጊያ መርሃ ግብር ተከናውኗል፡፡በዚህ ወቅት የ4 ቢሊየን ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ የተተከሉ የችግኝ አይነቶች እና ብዛት የማጣራት ስራ እንደሚካሄድ ነው የተነገረው፡፡በክረምቱ በተካሄደው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ 60 በመቶ የሚሆኑት ለጥምር ግብርና የሚያገለግሉ ሲሆን 40 በመቶዎቹ ደግሞ ለደን የሚሆኑ ችግኞች መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡በቀጣይነትም ችግኞችን የመንከባከብ ስራ በተቀናጀ ሁኔታ እንደሚከናወን ነው የተገለፀው፡፡እንደ ኤፍቢሲ ዘገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ብሄራዊ የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት ጋር በመሆን በቤተ መንግስት የችግኝ ተክለዋል፡፡ኢትዮጵያውያን ከዚህ በመቀጠል ለችግኞች እንክብካቤ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል::
https://waltainfo.com/am/23920/
103
3ቢዝነስ
አዲሱ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ ምግባር ረቂቅ አዋጅ በሙሉ ድምፅ ፀደቀ
ፖለቲካ
August 24, 2019
Unknown
ተሻሽሎ የቀረበውን የኢትዮጰያ የምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ ምግባር ረቂቅ አዋጅን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሙሉ ድምፅ አፀደቀው፡፡ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በረቂቅ አዋጁ ላይ ሰፊ ክርክር ካደረገ በኋላ ነው በሙሉ ድምፅ ያፀደቀው፡፡ይሁን እንጂ ወንድ እና ሴት ተወዳዳሪዎች እኩል ድምጽ ቢያገኙ ሴት ተወዳዳሪዋ እንደምታሸንፍ በረቂቅ አዋጁ ላይ ቢቀመጥም ም/ቤቱ በአብላጫ ድምጽ ውድቅ አድርጎታል።ምክንያቱ ደግሞ የፆታ እኩልነትን መርህ የሚፃረር የሚል ነው፡፡ዛሬ በፀደቀው ረቂቅ አዋጅ የመንግስት ሰራተኛ የፖለቲካ ፓርቲ አባል ሆኖ በምርጫ ቅስቀሳና በውድድር ቢሳተፍ ያለ ደመወዝ ፈቃድ ማግኘት እንደሚችል ይደነግጋል፡፡የፖለቲካ ፓርቲዎች አባሎቻቸውን በተለያዩ ምክንያቶች ከአባልነት ለመሰረዝ ቢፈልጉም ያለ ፍርድ ቤት ፈቃድ ማሰናበት እንዲችሉም ፈቃድ የሚሰጥ ተብሏል፡፡በፀደቀው ረቂቅ አዋጅ መሰረት ለግል ለተወዳዳሪዎች መንግስት ድጋፍ እንደሚሰጥም ተደንግጓል፡፡ምንጭ ፡ ኢቢሲ 
https://waltainfo.com/am/31309/
108
5ፖለቲካ
ከተማ አስተዳደሩ ጳጉሜ 3 ቀን ለሚከበረዉ “የሀገራዊ የኩራት ቀን” ዝግጅት ማጠናቀቁን ገለፀ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 23, 2019
Unknown
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጳጉሜ 3 ቀን የሚከበረዉን  "የሀገራዊ የኩራት ቀን" ለማስተባበር ዝግጅት ማጠናቀቁን ተናገረ፡፡የከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ፌቨን ተሾመ አንደተናገሩት  መርሀ-ግብሩ የተለያዩ ሀገራዊ እሴቶችን ይበልጥ በሚያጎሉ ዝግጅቶች እንደሚከበር ገልፀዋል፡፡በመርሀ ግብሩ 250 ሺህ ሰዎች የሚታደሙ ሲሆን በዕለቱ የመከላከያ ሰራዊት አየር ኃይል ወታደራዊ ትርኢት ያደርጋል ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞችም የተለያዩ ትርኢቶችን እንደሚያሳዩ የገለፁት ፕሬስ ሴክሬታሪዋ የኢትዮጵያን የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሰችን የማስተዋወቅ ስራም ይኖራል ብለዋል፡፡በዕለቱ “አዲስ አበባ ቤቴ፤ ኢትዮጵያዊነት ኩራቴ” የሚል ፁሁፍ የተፃፈበት 100 ሺህ ቲሸርት በነፃ ለታዳሚዎች ይከፋፈላል፡፡ዝግጅቱ በመስቀል አደባባይና በሚለኒየም አዳራሽ ይከበራል ተብሏል፡፡
https://waltainfo.com/am/32673/
83
0ሀገር አቀፍ ዜና
ከኢንዱስትሪዎች የሚወጣዉን ዝቃጭ በአግባቡ ለማስወገድ የሚያስችል መመሪያ ይፋ ተደረገ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 23, 2019
Unknown
ኢትዮጵያ ከኢንዱስትሪዎቿ የሚወጣዉን በካይ ፈሳሽ ወይም ዝቃጭ በአግባቡ ለማስወገድ የሚያስችል መመሪያ ዛሬ ይፋ አደረገች፡፡መመሪያዉ ለ3 ዓመታት ጥናት ሲደረግበት የቆየ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡መመሪያዉን ይፋ ለማድረግ በተዘጋጀዉ ስነ ስርአት ላይ የተገኙት የአካባቢ፣ ደንና አየር ንብረት ለዉጥ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፕሮፌሰር ፈቃዱ በየነ እንደገለፁት ከሆነ ይህ መመሪያ ሀገሪቱ እስከዛሬ በዘርፉ ያወጣቻቸዉን ፖሊሰዎች በአግባቡ ለመፈፀም ያስችላል፡፡ኮሚሽነሩ አክለም በዘርፉ የሚከናወነዉ ስራ ባለቤትንና ተጠያቂነትን  በግልፅ ያስቀምጣል ብለዋል፡፡የኢንዱስትሪ ፓርኮች ኮርፖሬሽን በበኩሉ ከዚህ በፊት የነበሩ ኢንዱስትሪዎችም ሆኑ እንደ አዲስ የሚቋቋሙት እየለቀቁት ያለዉ ዝቃጭ በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩን ገልፆ ይህ መመሪያ በዘርፉ የሚከናዉኑትን ስራ ዉጤታማ በሆነ መልኩ ለማከናወን እንደሚያስችል ተናግሯል፡፡የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ለሊሴ ነሜ መመሪያዉ ከቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ በመጀመር በሀሉም ኢንዱስትሪ ፓርኮች ተግባራዊ ይደረጋል ብለዋል፡፡ 
https://waltainfo.com/am/32672/
105
0ሀገር አቀፍ ዜና
በአማራ ክልል ከአምደወርቅ- ተኬዜ-እብናት የገጠር መንገድ ፕሮጀክት ተመረቀ
ቢዝነስ
August 24, 2019
Unknown
በአማራ ክልል የተገነባው አምደወርቅ-ተኬዜ-እብናት የገጠር መንገድ ፕሮጀክት በዛሬው ዕለት ተመርቆ ለትራፊክ ክፍት ሆነ፡፡በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ፤ የተለያዩ የክልሉ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡የ124 ኪ.ሜ የሚሸፍነው መንገዱ በአካባቢው ያለውን የእንስሳትና የተለያዩ የግብርና ምርቶችን ወደ ገበያ ለማቅረብ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡በአካባው በኢኮኖሚ መነቃቃት ረገድ ጉልህ ሚና ከመጫወቱም ባሻገር የሁለቱን ዞኖች ህዝቦች ማህበራዊ ግንኙነት እንደሚያጠናክርም ተገልጿል፡፡
https://waltainfo.com/am/23921/
56
3ቢዝነስ
ኢትዮጵያ እና ብሪታንያ የ120 ሚሊየን ፓውንድ የድጋፍ ስምምነት ተፈራራሙ
ቢዝነስ
August 23, 2019
Unknown
ኢትዮጵያ እና ብሪታንያ የ120 ሚሊየን ፓውንድ የድጋፍ ስምምነት ተፈራራሙ፡፡ስምምነቱን የኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ አድማሱ ነበበ እና የብሪታኒያ ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ሚኒስትር አሎክ ሻርማ በዛሬው እለት ተፈራርመውታል፡፡ከድጋፉ 95 ሚሊየን ፓውንዱ የፋይናንስ ተቋማትን ለማጠናከር፣ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ እና ለንጹህ ውሃ አቅርቦት እንደሚውል ተገልጿል፡፡ቀሪው 25 ሚሊየን ፓውንድ ለአራተኛው ዙር የሴፍቲኔት ልማት ፕሮግራም ማስፈጸሚያ የሚውል ነው ተብሏል፡፡የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ እና የውሃ ንጽህና አገልግሎት ድጋፉ ዓላማ በኢትዮጵያ በድርቅ በሚጠቁ አካባቢዎች የ1 ነጥብ 2 ሚሊየን ያህል ዜጎችን የንጽህና እና የንጽህና አጠባበቅ ልምድ ለማሻሻል ያለመ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡ቀሪው 25 ሚሊየን ፓውንድ የሴፍቲኔት ድጋፍ በገጠር አካባቢዎች የምግብ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የምግብ ድጋፍ እና አደጋ ቅነሳ ስራ ለማከናወን የሚውል መሆኑም ተገልጿል፡፡ (ምንጭ፡-የገንዘብ ሚኒስቴር)
https://waltainfo.com/am/23919/
106
3ቢዝነስ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከእንግሊዝ ዓለም አቀፍ ልማት ትብብር ሚኒስትር አሎክ ሻርማ ጋር ተወያዩ
ፖለቲካ
August 23, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከእንግሊዝ ዓለም አቀፍ ልማት ትብብር ሚኒስትር አሎክ ሻርማና ልዑካቸው ጋር ዛሬ ተወያይተዋል፡፡ሁለቱ ወገኖች እንግሊዝ ለኢትዮጵያ የልማት እንቅስቃሴዎች በምታደርገው ድጋፍ ዙሪያ ውይይት አድረገዋል፡፡የእንግሊዝ ዓለም አቀፍ ልማት ትብብር ሚኒስትር አሎክ ሸርማ፣ በኢትዮጵያ ያለው አገር በቀል ሪፎርምን አድንቀው፣ አገራቸው ለኢትዮጵያ ልማት የምታደርገውን ድጋፍ እንደምትቀጥል ተናግረዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እንግሊዝ ለኢትዮጵያ ለምታደርገው ድጋፍ አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡(ምንጭ:-የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት)
https://waltainfo.com/am/31307/
59
5ፖለቲካ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን ካውንስል አባላት ጋር ተወያዩ
ፖለቲካ
August 24, 2019
Unknown
የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን የካውንስል አባላት ጋር በትናንትናው እለት ተወያይተዋል።በውይይቱ ወቅት ሚኒስትሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ባደረጉት ንግግር፥ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ በሌሎች ሀገራት ተሰርቶበት ለገፅታ ግንባታና ለመልካም ወዳጅነት በጎ ሚና መጫወቱን ጠቅሰዋል።በኢትዮጵያ ካለው አቅም ጋር ሲነፃፀር ግን ቨፐብሊክ ዲፕሎማሲ ዘፍር ብዙ እንዳልተሰራ ያመላክተዋል ሲሉም ተናግረዋል።ስለሆነም ያለውን አቅም በተሻለ ለመጠቀም ቀደም ብሎ በነበረው የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን ላይ አዳዲስ አባላት በመጨመርና መመሪያ በማዘጋጀት እንዲሁም ድጋፍ ሰጪ ተቃማትን በማስፋት ለአዲስ የዲፕሎማሲ ስራ ዝግጅቶች መጠናቀቁን አስታውቀዋል።የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን ካውንስል አባላቱ በበኩላቸው መመርያው ላይ ቢሻሻል የበለጠ ውጤት ያመጣል ያሉትን እንዲካተቱ ሃሳበ አቅርበዋል።ከበፊቱ የላቀ ስኬታማ ተግባራትን ማከናወን እንደሚችሉ ለዚህም ተግባር በመመረጣቸው ደስተኛ መሆናቸውን መግለፃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን 75 አባላትን ያቀፈ ሲሆን፥ ከታዋቂ ሰዎች፣ ከሀይማኖት አባቶችና ተፅእኖ ፈጣሪ ግለስቦችን በማካተት ከስምንት አመት በፊት መዋቀሩ ይታወቃል።
https://waltainfo.com/am/31308/
131
5ፖለቲካ
ኢትዮጵያዊያን ሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ መርኃግብር ላይ ያሳዩትን ህብረት በሁሉም መስክ እንዲደግሙ ተጠየቀ
ቢዝነስ
August 23, 2019
Unknown
ኢትዮጵያዊያን ሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ መርኃግብር ላይ ያሳዩትን ህብረት በሁሉም መስክ እንዲደግሙ ተጠየቀ፡፡የ2011 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የችግኝ ተከላ መርሃግብር የማጠቃለያ ፕሮግራም በዛሬው ዕለት በብሔራዊ ቤተመንግስት ተካሂዷል፡፡  በማጠቃለያ ፕሮግራሙ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በችግኝ ተከላ መርሃግብሩ ላይ የታየዉ ኢትዮጵያዊ ህብረትና ተሳትፎ ኢትዮጵያዊያን በሁሉም መስክ ላይ ከተባበሩ የማያስመዘግቡት ድል ላለመኖሩ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡ሀገር አቀፍ የችግኝ ተከላ መረሃግብር ከታቀደለት በላይ ስኬታማ እንደነበርም ፕሬዝዳንቷ ጠቁመዋል፡፡በብሔራዊ ቤተመንግስት በተካሄደው የ2011 የችግኝ ተከላ መርሃግብር የማጠቃለያ ፕሮግራም ላይ በርካታ አርቲስቶች ችግኝ በመትከል አሻራቸውን አኑረዋል፡፡እንዲሁም ብሔራዊ አንድነት ጎልቶ በተስተዋለበት በአንድ ጀንበር ከ350 ሚሊየን በላይ ችግኞች በተተከሉበት የሐምሌ 22ቱ ሀገር አቀፍ የችግኝ ተከላ መርሃግብር በየክልሉ ተሰማርተው የነበሩ የአርቲስቶች ቡድን ከየክልሉ ይዘው የመጡትን ምልዕክት በማስተላለፍ ዘጠኙን ክልሎችንና ሁለት ከተማ አስተዳደሮችን የሚወክሉ አንዳንድ ችግኝ በቤተመንግስት ውስጥ ተክለዋል፡፡ክልሎቹንና ከተማ አስተዳደሮቹን ወክለው ከተተከሉ 11 ችግኞች በተጨማሪ በመሃከላቸው የኢትዮጵያ አንድነትን የሚወክል 12ኛው ችግኝ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን በመወከል ተተክሎ የመርሃግብሩ ማጠቃለያ ተደርጓል፡፡
https://waltainfo.com/am/23916/
138
3ቢዝነስ
ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ በዋግ ኽምራ ያስገነባው ትምህርት ቤት ተመረቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 23, 2019
Unknown
ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ስላሴ የቀድሞውን የዳስ ትምህርት ቤት ደረጃውን በጠበቀ መልኩ አስገንብቶ አስመርቋል፡፡አትሌቱ በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ፃግብጂ ወረዳ ላይ ያስገነባው ገልኩ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነው ለምረቃ የበቃው፡፡ትምህርት ቤቱ ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ስላሴ አጠቃላይ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተሰኝቷል፡፡ሁለት ብሎኮችና ስምንት የመማሪያ ክፍሎች ያሉትን ይህን ት/ቤት ኃይሌ በሦስት ወራት በማስገንባት ነው ለቀጣዩ የትምህርት ዘመን ማስተማሪያ ዝግጁ ያደረገው፡፡በምረቃ ሥነ ስርዓቱ  ነዋሪነታቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ አንድ ግለሰብ 8 ሺህ 500 የማጣቀሻ መጻህፍትን ለትምህርት ቤቱ መለገሳቸው ተገልጿል፡፡
https://waltainfo.com/am/32670/
77
0ሀገር አቀፍ ዜና
ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያ የለውጥ ዙሪያ የሚወያይ ኮንፈረንስ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ አስጀመሩ
ፖለቲካ
August 23, 2019
Unknown
ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያ የለውጥ ሂደት፣ ወቅታዊ ሁኔታ፣ መፃኢ እድል እና ስጋቶች ዙሪያ የሚወያይ ኮንፈረንስ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ አስጀመሩ፡፡ፕሬዝዳንቷ ኢትዮጵያ በታሪኳ ወሳኝ የሚባል የለውጥ መንደርደሪያ ላይ እንደምትገኝ ገልፀዋል፡፡ይህ ወቅት ኢትዮጵያ የህዝቦቿን መሰረታዊ ጥያቄዎች ለመመለስና ፍላጎታቸውን ለማርካት ከፍተኛ የለውጥ እንቅስቃሴ ጅማሮ ላይ እንደምትገኝም አብራርተዋል፡፡በዚህ ሂደት ላይ የህዝቡን አንድነትና ተነሳሽነት ለማጠናከር ከቃላት ባለፈ በተግባር የሚገለፁ በርካታ መሰራት ያለባቸው ተግባራት ከፊት እንደሚጠብቁ ተናግረዋል፡፡እስካሁን ድረስ የታዩት ተስፋዎችን አጠናክሮ በመቀጠል ለሚፈለገው ድል ለመድረስ ከህዝቡ አቅም በላይ እንደማይሆን አምናለሁ ያሉት ፕሬዝዳንቷ ለዚህ ሂደት አቅጣጫ የሚያመላክት ፍሬያማ ውይይት ከኮንፈረንሱ እንደሚጠብቁ አብራርተዋል፡፡ መረጃው የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ነው፡፡
https://waltainfo.com/am/31306/
89
5ፖለቲካ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከእንግሊዝ ዓለም አቀፍ ልማት ትብብር ሚኒስትር አሎክ ሻርማ ጋር ተወያዩ
ቢዝነስ
August 23, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከእንግሊዝ ዓለም አቀፍ ልማት ትብብር ሚኒስትር አሎክ ሻርማና ልዑካቸው ጋር ዛሬ ተወያይተዋል፡፡ሁለቱ ወገኖች እንግሊዝ ለኢትዮጵያ የልማት እንቅስቃሴዎች በምታደርገው ድጋፍ ዙሪያ ውይይት አድረገዋል፡፡የእንግሊዝ ዓለም አቀፍ ልማት ትብብር ሚኒስትር አሎክ ሸርማ፣ በኢትዮጵያ ያለው አገር በቀል ሪፎርምን አድንቀው፣ አገራቸው ለኢትዮጵያ ልማት የምታደርገውን ድጋፍ እንደምትቀጥል ተናግረዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እንግሊዝ ለኢትዮጵያ ለምታደርገው ድጋፍ አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡(ምንጭ:-የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት)
https://waltainfo.com/am/23917/
59
3ቢዝነስ
የእነ ብርጋዲየር ጄነራል ተፈራ ማሞን የክስ መዝገብ ለመመርመር ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 23, 2019
Unknown
የባሕር ዳር እና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የእነ ብርጋዲየር ጄነራል ተፈራ ማሞ የምርመራን መዝገብ ለመመርመር ለነሐሴ 21 ቀን 2011 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ።ፍርድ ቤቱ በእነ ጄነራል ተፈራ ማሞ የክስ መዝገብ መርማሪ ፖሊስ በጠየቀው የጊዜ ቀጠሮ ይግባኝ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለመመርመር በማስፈለጉ ነው ቀጠሮ የሰጠው።ብርጋዲየር ጄነራል ተፈራ ማሞ የብዙዎቻችን ተጠርጣሪዎች የባንክ ደብተሮች በመርማሪ ቡድኑ ስለተያዙብን፣ በቤት ኪራይ የሚኖሩ ቤተሰቦቻችን ለችግር ተዳርገዋል ሲሉ ለችሎቱ አቤት ብለዋል።የመርማሪ ቡድኑ በበኩሉ ከወንጀሉ ጋር የሚያያዝ ከሆነ የባንክ አካውንት የሚታገድበት እንጂ የባንክ ደብተሩ የሚያዝበት አግባብ እንደሌለ ለችሎቱ አስረድቷል።የተጠርጣሪዎቹ የባንክ ደብተር እና አልባሳት በቁጥጥር ስር በዋሉባቸው ፖሊስ ጣቢያዎች ሊኖሩ እንደሚችሉም መርማሪ ቡድኑ ጠቁሟል።ፍርድ ቤቱም ተጠርጣሪዎቹ በምርመራ ሒደት በቁጥጥር ስር ሲውሉ ከሕግ አግባብ ውጭ የተያዙባቸው ንብረቶች እንዲመለሱላቸው ትእዛዝ ሰጥቷል።እንደ ኢቢሲ ዘገባ የተጠርጣሪ ጠበቆች በበኩላቸው ተጠርጣሪዎቹ በመታሰራቸው ምክንያት የሚያስተዳድሯቸው ቤተሰቦች ችግር ላይ ወድቀዋል በሚል ለችሎት ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት፣ ለችግር የተጋለጡ የተጠርጣሪ ቤተሰቦች ቀለብ እንዲሰጣቸው ትእዛዝ አስተላልፏል።
https://waltainfo.com/am/32671/
136
0ሀገር አቀፍ ዜና
የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ መሠረት ማስፋት የሚያስችል የሦስት ዓመት ፕሮጀክት ይፋ ሆነ
ቢዝነስ
August 23, 2019
Unknown
የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ መሠረት ማስፋት የሚያስችል ለሶስት ዓመታት የሚተገበር በአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ተራድኦ (ዩኤስ ኤይድ) የሚደገፍ እና በሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ጥናት የሚመራ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ።ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያ የጀመረችውን የኢኮኖሚ ሪፎርም ይደግፋል ሲሉ የብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶ/ር ይናገር ደሴ ተናግረዋል፡፡ፕሮጀክቱን ለማስፈፀምም መንግስት በሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ጥናት ታግዞ እንደሚሰራ የገለፁት ገዢው፤ በኢንቨስትመንት ማስፋፊያ፣ በስራ አጥነት ቅነሳ እና ጥናትን መሠረት ባደረጉ ፕሮጀክቶች ላይ ይሰራልም ብለዋል፡፡ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ በተጀመረው የኢኮኖሚ ሪፎርም የፖሊሲ ምክረ ሐሳብ በማፍለቅ በኩል እገዛ እንደሚያደርግ የብሔራዊ ባንክ ዋና ገዥ ዶ/ር ይናገር ደሴ ተናግረዋል።ኢትዮጵያ የወሰደችውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ የአሜሪካ መንግስት እንደሚደግፍ የገለፁት በኢትዮጵያ የዐሜሪካ አምባሳደር ማይክ ራይነር ለማሻሻያው ተግባራዊነት እና ተፈፃሚነት መንግስታቸው ያላሰለሰ ድጋፍ እንደሚያደርግም ተናግረዋል፡፡አሜሪካ ላላፉት ሦስት ዓመታት በትምህርት፣ በጤና እና በኃይል ልማት ዘርፎች ከሦስት ቢሊየን ዶላር በላይ ኢንቨስት ማድረጓንም አምባሳደሩ ተናግረዋል።ፕሮጀክቱን  ዩኤ ኤይድ በገንዘብ የሚደግፈው መሆኑም ተገልጿል።
https://waltainfo.com/am/23918/
122
3ቢዝነስ
የሻዳይ፣አሸንድዬ እና ሶለል ባህል ዓመታዊ ክብረ በዓል በባሕር ዳር ከተማ በድምቀት ተከበረ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 25, 2019
Unknown
የሻዳይ፣አሸንድዬ እና ሶለል ባህል ዓመታዊ ክብረ በዓል በባሕር ዳር ከተማ በድምቀት ተከበረ፡፡በዋግ ሹሞች መዲና ሰቆጣና አካባቢዋ ሻደይ፣ በቆቦ አካባቢ ሶለል እና በላስታ እና በአብዛኛው የክልሉ አካባቢዎች አሸንድዬ በሚል የሚከበረው የልጅ አገረዶች ጨዋታ በዓል ዛሬ በባህርዳር ከተማ በድምቀት ተከብሯል።በዚሁ በክልላዊው የሻደይ፣ አሸንድዬ እና ሶለል በዓል አከባበር ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ የፌዴራል ባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ኂሩት ካሳው እና የተለያዩ የክልል እና የፌዴራል የስራ ሃላፊዎች ታድመዋል፡፡በስነ ስርዓቱ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ከመገፋፋትና ከመጠላላት ወጥተን አንድ ስንሆን የጥበብ አውድማ እና የፍቅር ተምሳሌት እንሆናለን ብለዋል፡፡ዘመን ባልከለሰው አብሮነታችሁ አምራችሁና ደምቃችሁ ስትታዩ በእርግጥም ‘የአማራ ሕዝብ ታላቅ ነው’ ስንል ያለምክንያት አለመሆኑን ከመግለፁም ባሻገር ጥበብ፣ ኩራት፣ አብሮነትና ጀግንነት የክልሉ ህዝብ መገለጫዎች ማሳያ ጭምር እንደሆኑ ያሳያልም ብለዋል።የአብሮነታችን አሻራ፣ የአንድነታችን ተምሳሌት እና የፍቅራችን መገለጫ የሆነው የሻደይ፣ አሸንድየ እና ሶለል በዓል በዩኔስኮ በማይዳሰ ወካይ ቅርስነት ለማስመዝገብ ስራ መጀመሩንም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል፡፡የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ “ታላቅ ነን ስንል ራሳችንን አክብረንና አስከብረን ሌሎችንም የምናከብር ህዝቦች ነን ማለታችን ነው፤ ታላቅ ነን ስንል ችግር በገጠመን ጊዜ አንድ ሆነንና ተባብረን ከችግር የምንወጣ ብርቱ ህዝቦች ነን ማለታችን ነው፤ ታላቅ ነን ስንል በችግር አረንቋ ውስጥ ያሉ ሌሎች ህዝቦችን የምንታደግ ህዝቦች ነን ማለታችን ነው›› በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።የሻዳይ፣አሸንድዬ እና ሶለል ባህል በዩኔስኮ በማይዳሰ ወካይ ቅርስነት ለማስመዝገብ ስራ መጀመሩንም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል፡፡የአማራ ክልል ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ግዛት አብዩ በበኩላቸው የሻደይ፣ አሸንድዬ እና ሶለል በዓል ራሱን የቻለ የቱሪስት መስህብ እንዲሆን እንደሚሰራ ገልጸዋል።በአማራ ክልል በርካታ ዘመን ተሻጋሪ ባህላዊ ሁነቶች እንዳሉ የገለጹት አቶ ግዛት፤ የሻደይ፣ አሸንድዬ እና ሶለል ባህላዊ ክዋኔዎቹ ሳይበረዙ እና ሳይከለሱ የባህሉ ባለቤት በሆነው ሕዝብ ተጠብቀው፣ ተናፍቀው እና ተወዳጅነታቸውን አጎልብተው እንዲዘልቁም ይደረጋል ብለዋል።
https://waltainfo.com/am/32674/
256
0ሀገር አቀፍ ዜና
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ ለአዳዲሶቹ የሱዳን መሪዎች የመልካም ምኞት መግለጫ አስተላለፉ
ፖለቲካ
August 22, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለአዳዲሶቹ የሱዳን መሪዎች የመልካም ምኞት መግለጫ አስተላልፈዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዛሬው እለት ባስተላለፉት መልእክት፥ ጀነራል አብዱል ፈታህ ቡርሀን 11 አባላት ያሉት ሉዓላዊ ምክር ቤት መሪ ሆነው በመመረጣቸው እንኳን ደስ አለዎት ብለዋል።እንዲሁም የነሐሴ 11 የሽግግር መንግስት ስምምነት ፊርማን ተከትሎ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው ለተመረጡት አብደላ ሀምዶክ የመልካም ምኞት መግለጫ ማስተላለፋቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።ጄኔራል አብድል ፈታ ቡርሃን አዲስ የተቋቋመው እና 11 አባላት ያሉት የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት መሪ ሆነው በትናንትናው እለት ነው የተመረጡት።11 አባላት ያሉት የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ሸንጎ ኦማር ሀሰን አል በሽር ከስልጣን ከወረዱበት ሚያዚያ 2019 ጀምሮ ሀገሪቱን ሲመራ የቆየውን ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤትን ተክቶ ትናንት ነው በይፋ ስራውን የጀመረው።ሌተናል ጄነራል አብደል ፈታህ አብደልራህማን ቡርሃን አዲስ የተቋቋመው የሱዳን ሉአላዊ ምክር ቤት መሪ በመሆን በትናንትናው እለት ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።ጀኔራል ቡርሃን ከሶስት ዓመት በላይ የሽግግር ጊዜ ውስጥ የሉዓላዊ ሸንጎውን ለ21 ወራት በበላይነት የሚመሩት ሲሆን፥ የሲቪል ተወካዮች ደግሞ ቀጣዮቹን 18 ወራትን ይመራሉ።11 አባላት ያሉት ሉዓላዊ ምክር ቤት በትናንትናው እለት በይፋ ስራውን መጀመሩን ተከትሎም አብደላ ሀምዶክ የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን በትናንትናው እለት ቃለመሃላ ፈፅመዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚነታቸውን የለቀቁት ባለፈው ዓመት ነበር።አብደላ ሃምዶክ በኢኮኖሚ ተንታኝነት ከ30 ዓመት በላይ ልምድ ያላቸው ሲሆን፥ ከካርቱም ዩንቨርሲቲና ከታወቁ የእንግሊዝ ትምህርት ተቋሞት ዲግሪያቸውን አግኝተዋል።ወታደራዊ ምክር ቤቱና የነጻነትና የለውጥ ኃይሎች ጥምረት የአገሪቱን የሽግግር መንግሥት ለመጀመር ባለፈው ቅዳሜ መፈራረማቸው የሚታወስ ነው።(ምንጭ፦ ኤፍቢሲ)
https://waltainfo.com/am/31304/
216
5ፖለቲካ
በተያዘው ክረምት ወራት በጎርፍ አደጋ ከ1.3 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሊጠቁ እንደሚችሉ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 22, 2019
Unknown
በክረምት ወራት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በሚከሰተው የጎርፍ አደጋ ከ1.3 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሊጠቁ እንደሚችሉ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን፣ ብሄራዊ ሜትዎሮሎጂ እና የተፋሰሶች ልማት ባለስልጣን በጋራ በመሆን በሀገሪቷ የክረምት ወቅት ሊፈጠር ይችላል ተብሎ በሚታሰበው ቅጽበታዊ ጎርፍ አደጋ እና ሊደረግ የሚገባውን ጥንቃቄ አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል፡፡በኢትዮጵያ በአጭር ጊዜ በሚዘንብ ዝናብ፣ በወንዞች እና ግድቦች መሙላት ምክንያት በተለያዩ የሃገሪቷ አካባቢዎች የጎርፍ አደጋዎች እየተስተዋሉ ነው፡፡ በዚህም የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የጎርፍ አደጋው የሚያስከትለውን አደጋ ለመቀነስ እና ለመከላከል በፌደራል እና በክልል ደረጃ ግብረ ሃይል ተቋቁሞ እየተሰራ መሆኑን የገለጸ ሲሆን፣ ለቅድመ ጎርፍ መከላከል እና በጎርፍ ወቅት 1.3 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በጎርፍ ሊጠቁ እንደሚችሉ የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ዳመና ዳሮታ ተናግረዋል፡፡በደቡብ፣ አማራ፣ ኦሮሚያ እና አፋር ክልሎች በሚገኙ ሰባት ወረዳዎች ከ23 ሺህ 900 በላይ ሰዎች ላይ በጎርፍ አደጋ ጉዳት እንደደረሰም ምክትል ኮሚሽነሩ ገልጸዋል፡፡የብሄራዊ ሜትዎሮሎጂ ኤጀንሲ የ2011 የክረምት የአየር ፀባይ አዝማሚያን በተመለከተ በግንቦት ወር መረጃውን ለህዝብ ተደራሽ ማድረጉን አስታውቀዋል፡፡ በዚህም ባለፉት ሁለት የክረምት ወራት በአብዛኛው ሃገሪቷ ክፍል ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደነበር መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡በሚቀጥሉት የክረምት ወራት ደግሞ መደበኛ እና ከመደበኛ በላይ ዝናብ እንደሚከሰት እና በአንዳንድ አካባቢዎች ቅጽበታዊ ጎርፍ ያጋጥማል ተብሎ እንደሚጠበቅ የብሄራዊ ሜትዎሮሎጂ ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ክንፈ ሃ/ማርያም ገልጸዋል፡፡በሀገሪቷ በተለያዩ አካባቢዎች በተለይ ቆቃ፣ መልከዋከና፣ ግልገል ጊቤ፣ ተከዘ እና ሌሎች ግድቦች ላይ እየተከሰተ ባለው የውሃ መሙላት ሳቢያ የጎርፍ አደጋ እንሚያጋጥማቸው ተገልጿል፡፡ግድቦቹ በመሙላታቸው በሰው እና በንብረት ላይ ከፍተኛ አደጋ እያስከተሉ እንደሚገኙ የገለጹት የተፋሰሶች ልማት ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ግዛው በግድቦቹ አካባቢ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ሊያጋጥም የሚችለውን የጎርፍ አደጋ ለመከላከል የጎርፍ ስጋት ወደሌለባቸው አካባቢዎች መሄድ እንደሚገባቸው ጠቁመዋል፡፡
https://waltainfo.com/am/32669/
242
0ሀገር አቀፍ ዜና
33 የምግብ አምራችና አስመጭዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ
ቢዝነስ
August 23, 2019
Unknown
በ33 የምግብ አምራችና አስመጪ ድርጅቶች ላይ እርምጃ መውሰዱን የኢትዮጵያ የምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ፡፡ባለስልጣኑ የተቋሙን የ2011 እቅድ አፈፃፀም እና የ2012 እቅድ አስመልክቶ ትናንት መግለጫ ሰጥቷል።የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተሩ አቶ ሳምሶን አብርሃም እንደተናገሩት ህገ ወጥ ተግባራት ሲያከናውኑ በተገኙ ተቋማት ላይ እርምጃ ተወስዷል፡፡“ህገወጥ ተግባራትን በፈፀሙ አካላት ላይ ምርቶችን ከማስወገድ አንስቶ ተቋማቱን እስከ ማስዘጋት ደርሰናል” ያሉት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው ከዘርፉ የማስወጣት እና በህግ የመጠየቅ ሥራ መሰራቱንም ተናግረዋል፡፡ተቋሙ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚሰጡ ጥቆማዎችን መሠረት በማድረግ መድሃኒት እና ምግብ አስመጪዎች ላይ ፍተሻዎችን በማድረግ እርምጃ እየተወሰደ እንደሆነ ነው ያስታወቁት፡፡የታሸጉ ምግቦች በብዛት በበረሃማ አካባቢዎች ስለሚገቡ ወደ አደገኛ ኬሚካልነት እንደሚቀየሩና በኅብረተሰቡ ላይም ከፍተኛ የጤና ጉዳት፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እንደሚያስከትሉ ተመላክቷል።እንደ አዲስ ዘመን ዘገባ በበጀት ዓመቱ በኅብረተሰቡ ጥቆማ እንዲሁም ድንገት በተደረገ ፍተሻ ከ4 ሺህ 763 ቶን በላይ ምግብ መያዙን አቶ ሳምሶን አስታውቀዋል።
https://waltainfo.com/am/23915/
123
3ቢዝነስ
የኦሮሚያ ክልል የዜግነት አገልግሎት ምክር ቤት ምስረታ እየተካሄደ ነው
ፖለቲካ
August 23, 2019
Unknown
የኦሮሚያ ክልል የዜግነት አገልግሎት ምክር ቤት ምስረታ መድረክ በአዲስ አበባ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት አዳራሽ እየተካሄደ ነው፡፡ጨፌ ኦሮሚያ በ4ኛ ዓመት 5ኛ የስራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባኤው የዜግነት አገልግሎት አዋጁን በማጽደቅ የክልሉ መንግስት ስራ ላይ ያዋለው መሆኑ ይታወቃል፡፡በመድረኩ ላይ የኦሮሚያ ክልል ም/ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ አባገዳዎች፣ አርቲስቶችና ሌሎች ተሳታፊዎች መገኘታቸውን ከኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
https://waltainfo.com/am/31305/
58
5ፖለቲካ
ሞቃዲሾ አዲስ ከንቲባ አገኘች
ፖለቲካ
August 23, 2019
Unknown
የሶማሊያው ፕሬዚዳንት መሐመድ አብዱላሂ ፋርማጆ የቀድሞውን የጦር አበጋዝና የመንግሥት ሚኒስትር የነበሩት ኦማር መሐመድን  የሞቃዲሾ ከንቲባና የባዲር ግዛት አስተዳደሪ አድርገው ሾመዋል።ሹመቱ ባለፈው ወር በአጥፍቶ ጠፊዎች ህይወታቸው ያለፈውን የቀድሞ ከንቲባ አብዱራህማን ኦማር ኦስማንን ለመተካት መሆኑ ተገልጿል፡፡አዲሱ ከንቲባ ኦማር መሐሙድ መሐመድ እ.አ.አ 2004 ላይ በተመሠረተው የሽግግር መንግሥት ውስጥ የሃይማኖት ጉዳዮች ሚኒስትር ከመሆናቸው አስቀድሞ ሞቃዲሾ ውስጥ የጦር አበጋዝ ነበሩ።እ.አ.አ እስከ 2009 ድረስም በሚኒስትርነት አገልግለዋል።ኦማር መሐመድ ለሞቃዲሾ ከንቲባነት የተመረጡት በመንግሥት ውስጥ ባላቸው ልምድ እንዲሁም የልማት ፕሮጀክቶችን ተግባራዊነት ማስቀጠል የሚያስችሉ በመሆናቸው ነው መባሉን የዘገበው ቢቢሲ ነው።
https://waltainfo.com/am/33328/
80
5ፖለቲካ
ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በመቐለ እየተከበረ በሚገኘው የአሸንዳ በዓል ላይ ተገኙ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 22, 2019
Unknown
ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የአሸንዳ ክብረ በዓል ላይ ለመገኘት በዛሬው ዕለት  መቐለ ገብተዋል፡፡ፕሬዝዳንቷ አሉላ አባነጋ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በትግራይ ክልል ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤልና በሌሎች የክልሉ አመራሮች አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡የአሸንዳ   በዓል በትግራይ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የሰላም፣ አንድነትና ልማት ተምሳሌት” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል፡፡በትግራይ ክልል በነሃሴ ወር የሚከበረው የአሸንዳ፣ ማሪያ እና ዓይኒ-ዋሪ በዓላት የክልሉን ባህል፣ ትውፊትና የቱሪዝም መስህቦች በማስተዋወቅ ረገድ የላቀ ሚና እንዳለው ይነገራል፡፡
https://waltainfo.com/am/32668/
62
0ሀገር አቀፍ ዜና
የሻደይ፣ አሸንድዬ እና ሶለል የልጃገረዶች ጨዋታዎች ከዛሬ ጀምሮ ይከበራሉ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 22, 2019
Unknown
የሻደይ፣ አሸንድዬ እና ሶለል ጨዋታዎች በዋግ ኽምራ፣ በላል ይበላ እና በቆቦ ከዛሬ ነሐሴ 16 እስከ 21/2011 ዓ.ም ይከበራሉ።በበዓሉ ለመታደም በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ተመስገን ጥሩነህ የተመራ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ልዑክ ትናንት ማምሻውን ሰቆጣ ከተማ ገብቷል።ለልኡካኑ የሰቆጣ ከተማና እና አካባቢዋ ነዋሪዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል። የየወረዳዎቹ ሻደይ ባህላዊ ተጫዋች ቡድኖችም በባህሉ ዜማና ጨዋታዎች ታጅበው ነው የአቀባበል ያደረጉላቸው። ሰቆጣም ከዋዜማው ጀምሮ የሻደይ ጨዋታን መከወን ጀምራለች።የዘንድሮው የሻደይ በዓል "ሻደይ ባህላችን ለዘላቂ ልማትና ሰላማችን" በሚል መሪ ሀሳብ ነው የሚከበረው።የሻደይ፣ አሸንድዬ እና ሶለል የልጃገረዶች ጨዋታዎች ባለፈው ዓመት በክልል ደረጃ ባሕር ዳር ላይ መከበሩ ይታወሳል። በዚህ ዓመት ደግሞ ከክልል ባለፈ አዲስ አበባ ላይም እየተከበረ ነው። በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎችም እንደሚከበር ታውቋል።በአዲስ አበባ በፓናል ውይይት በየክፍለ ከተሞች ሲከበር የቆየው በዓሉ የፊታችን ነሐሴ 19/2011 ዓ.ም በሚሊኒዬም አዳራሽ ይከበራል፤ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በማይዳሰሱ ቅርሶች መዝገብ ለማስፈርም ጥረቱ ቀጥሏል።
https://waltainfo.com/am/32666/
135
0ሀገር አቀፍ ዜና
ኢትዮጵያ በኢንዶኔዢያ- አፍሪካ የመሰረተ ልማት ዓለም አቀፍ ጉባኤ እየተሳተፈች ነው
ቢዝነስ
August 22, 2019
Unknown
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የከተማ ልማትና ኮንስራክሽን ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ በባሊ ኢንዶኔዢያ በመካሄድ ላይ ባለው የኢንዶኔዢያ- አፍሪካ የመሰረተ ልማት ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡በጉባዔው  በተካሄደው የፓናል ውይይት ማብራሪያ የሰጡት  ኢንጂነር አይሻ ባለፉት አስርት ዓመታት ኢትዮጵያ ጠንካራ የኢከኖሚ ዕድገት ማሰመዝገቧን ተናግረዋል፡፡በተለይም በመሰረተ ልማት ልማት ያላትን ተሳትፎ ይበልጥ ውጤታማና ተወዳዳሪ ለማድረግ እየሰራች መሆኗንም ገልፀዋል፡፡በመንገድ መሰረተ ልማት ፣ በባቡር ሐዲድ ፣ በብሔራዊ ሎጅስቲክስ ልማት ፣ በትራንስፖርት ዘርፍና በአየር ትራንስፖርት ዘርፎች የተመዘገቡት ውጤቶች አስደናቂ መሆናቸውን ሚኒስትሯ ለጉባኤው ተሳታፊዎች  አብራርተዋል፡፡በተለይም  የኢትዮጵያ የባቡር ኮርፖሬሽኑ ዋና ከተማዋን ከጂቡቲ ወደብ ጋር የሚያገናኝ የ 656 ኪሎ ሜትር የባቡር መስመር መዘርጋቱንና ይህም ወደ ጅቡቲ ወደብ ለመድረስ ይፈጅ የነበረውን የ 84 ሰዓታት ቆይታ ጊዜ ወደ 10 ሰዓታት ድረስ ለመቀነስ መቻሉንም አንስተዋል፡፡የኢትዮጵያ መንግስት የግንኙነት ትስስርን እና መሠረተ ልማቶችን ለማጎልበት ብሎም የአካባቢያዊ ና የአለም አቀፍ የንግድ እንቅስቃሴዎችን ለማሳደግ የኢትዮ-ቴሌኮም ፣ የኢትዮጵያ የመርከብና የሎጂስቲክስ አገልግሎት እንዲሁም የኢትዮጵያ አየር መንገድን የመሳሰሉ በመንግስት የተያዙ ኩባንያዎችን በከፊል በግል ለማዞር የሚያችል ዕቅድ መዘርጋቱን ገልጸዋል ፡፡የኢትዮጵያ መንግስት ከኢንዶኔዥያና ከህዝቧ ጋር በመሰረተ ልማትና በሌሎች ዘርፎች ለጋራ ብልፅግናና ልማት እንደምትሰራ መናገራቸውን ከኢፌዴሪ የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡የኢንዶኔዢያ- አፍሪካ የመሰረተ ልማት ጉባኤ በየዓመቱ ኤንዶኔዢያ ከአፍሪካ ጋር ያላትን ትስሰስር ለማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳየች ላይ የሚመክር ጉባኤ ነው፡፡
https://waltainfo.com/am/23913/
183
3ቢዝነስ
የአሸንዳ /አውርስ በዓል በትግራይ ክልል እየተከበረ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
August 22, 2019
Unknown
የአሸንዳ /አውርስ በዓል በትግራይ ክልል በመከበር ላይ ይገኛል፡፡በዓሉ “አሸንዳ/አውርስ የሰላም፣ አንድነትና ልማት ተምሳሌት” በሚል መሪ ቃል በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በመከበር ላይ ነው የሚገኘው።በዓሉ በክልሉ በሚገኙ ከተሞች እና የገጠር ወረዳዎች በሙሉ በመከበር ላይ የሚገኝ ሲሆን፥ በአሁኑ ሰዓትም በክልል ደረጃ በዓቢይ ዓዲ ከተማ እየተከበረ ነው።በበዓሉ ላይም የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ደኤታ ወይዘሮ ብዙነሽ መሰረት፣ በትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ማእረግ የከተማ ልማት፣ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሃላፊ ዶክተር አብረሃም ተኸስተን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የክልል እና የፌደራል የስራ ሃላፊዎች እና የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።በዓቢይ ዓዲ ከተማ በመከበር ላይ በሚገኘው በዓል ላይም ከሰቆጣ የመጡ ልኡካንም በመሳተፍ ላይ እንደሚገኙ ታውቋል።አሸንዳ/አውርስ በዓል ከ8 ሰዓት ጀምሮ በክልል ደረጃ ከፍተኛ የፌደራል እና የክልል አመራሮች በተገኙበት በመቐለ ከተማ በደማቅ ሁኔታ እንደሚከበርም ይጠበቃል።በትግራይ ክልል በነሃሴ ወር የሚከበረው የአሸንዳ፣ ማሪያ እና ዓይኒ-ዋሪ በዓላት የክልሉን ባህል፣ ትውፊትና የቱሪዝም መስህቦች በማስተዋወቅ ረገድ የላቀ ስራ የሚሰራበት ፕሮግራም ነው።አሸንዳ እና ማሪያ ከነሃሴ 16 ጀምሮ የሚከበር ሲሆን፥ ዓይኒ-ዋሪ ደግሞ ነሃሴ 24 2011 ዓ.ም በአክሱም ከተማ እና አካባቢው የሚከበር የልጃ ገረዶች በዓል ነው።በዓሉ በህዝቦች መካከል ሰላም፣ አንድነት እና ፍቅር እንዲኖር ከሚሰጠው ጠቀሜታ በተጨማሪ ለቱሪዝም መስህብነት በማገልገል ለኢኮኖሚው አስተዋዕኦ እንዳለው ይታወቃል።እንደ ኤፍቢሲ ዘገባ አሸንዳ/አውርስ በዓል የፊታችን ነሃሴ 26 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ የሚከበር ይሆናል።
https://waltainfo.com/am/32667/
185
0ሀገር አቀፍ ዜና
አምስት የአውሮፓ ሕብረት ሀገራት ስደተኞችን ሊቀበሉ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
August 22, 2019
Unknown
አምስት የሚሆኑ የአውሮፓ ሕብረት አባል ሃገራት፤ ስፔን፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ሉክዘምበርግ እና ፖርቹጋል በጣሊያን ደሴት ላምፔሱዳ የደረሱ ስደተኞችን ሊቀበሉ መሆናቸው ተገለፀ።ስደተኞቹን የጫነችው የእርዳታ መርከብ ተቀባይ በማጣቷ ለሳምንታት በሜዲትራኒያን ባህር ላይ ስትዋልል ቆይታ ጣሊያን ላምፔሱዳ የደረሰችው ባለፈው ማክሰኞ እንደነበር ተገልጿል።የአገሪቷ አቃቤ ሕግ መርከቧ እንድትለቀቅ ትዕዛዝ ማስተላለፈቻውን ተከትሎ ቁጥራቸው ወደ አንድ መቶ የሚጠጉ ስደተኞችን ያሳፈረችውና 'ባለሽበት ቆይ' የተባለችው መርከብ እንድትንቀሳቀስ ተፈቅዶላታል።ምንም እንኳን ከስደተኞቹ መካከል ህፃናትና በጠና የታመሙ ሰዎች ቢኖሩም የአገር ውስጥ ሚንስትሩ ማቴዎ ሳልቪኒ "ከዚህ በኋላ ወደቦቻችን ለስደተኞች ዝግ ናቸው።" በማለት ስደተኞቹ ከመርከቧ እንዳይወርዱ ለሦስት ሳምንታት ያህል ተከልክለው ቆይተዋል።ቀደም ሲል 10 ስደተኞች ደሴቷ ጋር በዋና እንደርሳለን በሚል ተስፋ ከመርከቧ ዘለው ባህር ውስጥ መግባታቸው ተጠቅሷል።በሥፍራው የሚገኙት ስደተኞችም ቆስለውና በፋሻ ተጥቅልለው ይታዩ እንደነበር ኤ ኤፍ ፒ የዜና ወኪል ዘግቧል።ከስደተኞቹ መካከል አንዱ "ልቀውስ ትንሽ ቀርቶኝ ነበር" ሲል የነበረበትን ሁኔታ ለዜና ወኪሉ ገልጿል።እንደ ሮይተርስ የዜና ወኪል ከሆነ የአውሮፓ ሕብረት ኮሚሽን እነዚህን ስደተኞችን የሚቀበሉ ሃገራትን ሲያፈላልግ ቆይቷል።በመጨረሻም ስደተኞችን የጫነችው ሁለተኛዋ የእርዳታ መርከብ፤ ለ13 ቀናት በሜዲትራኒያን ባህር ላይ ከቆየች በኋላ ሃገራቱ ከአደጋው የተረፉትን ከ100 በላይ ስደተኞች ለመቀበል ፈቅደዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
https://waltainfo.com/am/34129/
162
0ሀገር አቀፍ ዜና
ሊድ አሲድ ለአካባቢ አየር ንብረት ለዉጥ የሚያበረክተዉን አስተዋፅኦ ለመቀነስ የሚያስችል ፍኖተ ካርታ ለማዘጋጀት ዉይይት ተካሄደ
ቢዝነስ
August 22, 2019
Unknown
ባገለገሉ ባትሪዎች ዉስጥ የሚገኘዉ ሊድ አሲድ ለአካባቢ አየር ንብረት የሚያበረክተዉን አስተዋፅኦ ለመቀነስ የሚያስችል ፍኖተ ካርታ ለማዘጋጀት ዉይይት ተካሄደ፡፡በአካባቢ ደንና አየር ንብረት ለዉጥ ኮሚሽን የፖሊሲ ፤ ደረጃዎች ጥናትና ዝግጅት ጀነራል ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር አየለ ሄገና በዉይይት መድረኩ ላይ እንዳሉት ኢትዮጵያ ባለፉት 30 አመታት የአየር ንብረት ለዉጥን ተፅዕኖ ለመከላከል የተለያዩ ተግባራትን ስታከናዉን ቆይታለች፡፡ባለፉት 2 አመታትም የተለያዩ ከጉዳዩ ጋር የተያያዙ አዋጆችና ደንቦች ማሻሻያ እንዲደረግባዉ መደረጉን አዉስተዉ በቀጣይ ወደተግባር ለሚገባዉ የፍኖተ ካርታ ዝግጅት መንግስት የበኩሉን እንደሚወጣ ገልፀዋል፡፡የሊድ አሲድ በአለም አቀፍ ደረጃ 977 ቢሊየን ዶላር በማሳጣት ተፅዕኖ እንደሚያደርስ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ በአፍሪካም 134.7 ቢሊየን ዶላር የሚገመት ጉዳት ማድረሱንና ይህም በአህጉሩ 4 በመቶ ለሚሆነዉ የምርት መቀነስ ምክኒያት መሆኑ ተመልክቷል፡፡ይህ አሲድ በኢትዮጵያም 4 በመቶ ሃገራዊ ምርት እንዲቀንስ የበኩሉን አስተዋጾ ማበርከቱ ተነግሯል፡፡ፍኖተ ካርታዉ በመጀመሪያ ዙር 1.1 ሚሊየን ዩሮ ከባለድርሻ አካላት ተመድቦለት ወደተግባር እንደሚገባ ተገለፀ፡፡በዉይይቱ ላይ የአዉሮፓ ህብረት፤ በሃይል አቅርቦት ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ባለሃብቶችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡ 
https://waltainfo.com/am/23914/
138
3ቢዝነስ
ም/ቤቱ ባካሄደው 73ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ
ፖለቲካ
August 24, 2019
Unknown
ም/ቤቱ ባካሄደው 73ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈምክር ቤት በቅድሚያ በማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ተዘጋጅተው በቀረቡ ከፍተኛ ደረጃ የድንጋይ ከሰል ማዕድን እና አነስተኛ ደረጃ የክሮማይት ማዕድን ማምረት ፈቃድ ስምምነቶች ላይ የተወያየ ሲሆን፤ ስምምነቶቹ በህጉ መሰረት መሟላት የሚገባቸው ጉዳዮች ከተሟሉ በኋላ እንደተዘጋጁ ተገልጿል፡፡ምክር ቤቱም በቀረቡት የከፍተኛ እና የአነስተኛ ደረጃ የማዕድን ማምረቻ ፈቃድ ስምምነቶች ላይ ከተወያየ በኋላ በስራ ላይ እንዲውሉ መወሰኑ ተመልክቷል፡፡በመቀጠልም ምክር ቤቱ በሰው የመነገድና ሰውን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት የተደረገበት ሲሆን፤ በዚህ ዙሪያ የሚደርሱ ወንጀሎች በዜጎች ላይ የከፋ ጉዳት እንዳያስከትሉ ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ወንጀሎቹን ለመከላከል የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ አዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ለውሳኔ አቅርቧል፡፡ምክር ቤቱም በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ በዝርዝር ከተወያየ በኋላ ማሻሻያዎችን በማዕከል ይፀድቅ ዘንድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ ወስኗል፡፡እንዲሁም የማሪታይም ጉዳይ ባለስልጣን የተለያዩ የማሪታይም አገልግሎቶችን ለመስጠት የሚያወጣውን ወጪ ተመጣጣኝ በሆነ መልኩ የአገልግሎቱ ቀጥተኛ ተጠቃሚ የሆነው ተገልጋይ እንዲሸፍን ለማድረግ የሚያስችል የህግ መሰረት መኖሩ አስፈላጊ መሆኑን በመግለፅ፤ የገንዘብ ሚኒስቴር የአገልግሎት ክፍያውን ለመወሰን የሚያስችል ረቂቅ ደንብ አዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ ያቀረበ ሲሆን፤ ምክር ቤቱም ደንቡ ላይ ተወያይቶ በስራ ላይ እንዲውል መወሰኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
https://waltainfo.com/am/31310/
179
5ፖለቲካ
የኦሮሚያ ክልል ም/ፕሬዝዳንትና የእንግሊዝ የዓለም አቀፍ ልማት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዩኒሌቨር ኩባንያን ጎበኙ
ቢዝነስ
August 22, 2019
Unknown
የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ የእንግሊዝ ዓለም አቀፍ ልማት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሎክ ሸርማ በኢስተርን እንደስትሪ ዞን የሚገኘውን የዩኒሌቨር ኩባንያን ጎብኝተዋል፡፡አቶ ሽመልስ አብዲሳና የብሪታኒያ የዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ሚኒስትር አሎክ ሻርማ በኢንዱስትሪ ዞኑ ባደረጉት ጉብኝትም የዩኒሊቨር ኩባንያ ስራዎችን ተዘዋውረው መመልከታቸውን የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል።ዓለም አቀፍ ተቋም የሆነው ዩኒሊቨር ኩባንያ በዱከም በሚገኘው ኢስተርን ኢንደስትሪያል ዞን ውስጥ ለምግብነት እና ለመዋብያነት የሚያገለግሎ ምርቶችን እያመረተ ለገበያ በማቅረብ ላይ ይገኛል።ኩባንያ ኢስተርን ኢንደስትሪያል ዞን ባለው ፋብሪካም ከዚህ ቀደም ክኖር የምግብ ማጣፈጫ፣ ላይፍ ቦይ የንፅህና መጠበቂያ ሳሙና እና ቫዝሊን ሎሽን እያመረተ ይገኛል። (ምንጭ:-የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ0
https://waltainfo.com/am/23912/
93
3ቢዝነስ
የአዲሱ የትምህርት መዋቅር 6-2-4 በሚል ማሻሻያ መደረጉን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 21, 2019
Unknown
አዲሱ የትምህርት መዋቅር 6 ዓመት የአንደኛ ደረጃ፣ 2 ዓመት የመለስተኛ ትምህርት እንዲሁም 4 ዓመት የ2ኛ ደረጃ ትምህርት እንዲሆን መወሰኑን የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡የትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ጥላዬ ጌቴ በዛሬው ዕለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ከዚህ በፊት የነበረው የትምህርት ፖሊሲ የውጭ ናፋቂና ሀገር በቀል እውቀቶችን ከመስጠት አንፃር ውንነቶች እንዳሉ በመረዳት የትምህርት ስርዓቱ የሃገሪቱን አንድነት የሚያስቀጥል፣ ከማህበረሰቡና ከተማሪው ጋር የተጣጣመ እንዲሁም ሃገር በቀል እውቀቶችን መሰረት ባደረገ መልኩ እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡ሚኒስትሩ በመግለጫቸው አዲሱ የትምህርት መዋቅር በሶስት ክፍሎች ተመድቦ እንደሚሰራ ጠቅሰው፥ 6 ዓመት የአንደኛ ደረጃ ትምህርት፣ 2 ዓመት የመለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት እንዲሁም 4 ዓመት ደግሞ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት እንዲሆን ተወስኗል ብለዋል።ተማሪዎች 6ኛ ክፍልን ሲያጠናቅቁ ክልላዊ ፈተናን የሚፈተኑ ሲሆን፥ ከዚህ በፊት ክልላዊ ፈተና የነበረው 8ኛ ክፍል ደግሞ ሃገራዊ ፈተና ይሆናልም ተብሏል።ከዚህ ጋር ተያይዞ ከዚህ በፊት በግል ዘርፍ ተይዞ የቆየው የቅድመ መደበኛ ትምህርት (የህጻናት ማቆያን ጨምሮ እስከ ኬጂ) በግልና በመንግስት እንዲያዝ ይደረጋል ነው የተባለው፡፡ከዚህ ቀደም ሲሰጥ የቆየው የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና አይኖርም የተባለ ሲሆን፥ የ12ኛ ክፍል ፈተና ለከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ሊሆንም ላይሆንም እንደሚችል ተጠቁሟል። በተጨማሪም የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠናዎች ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ትምህርታቸውን ከጨረሱ በኋላ እንደሚጀምሩ ተገልጿል።በዚህም ተማሪዎች በቴክኒክና ሙያ ትምህርት መርሃ ግብር ከደረጃ 1 እስከ ደረጃ 8 (እስከ ሶስተኛ ዲግሪ) ደረጃ ድረስ መማር እንደሚችሉም በመግለጫው ወቅት ተነስቷል።የመምህራን ድልድልን በተመለከተም መምህራኑ ያላቸውን የትምህርት ደረጃ መሰረት ባደረገ መልኩ ይተገበራልም ነው የተባለው።ለአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው መምህራን፣ ለሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ሁለተኛ ዲግሪ (ማስተርስ) እንዲሁም ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሁለተኛ ዲግሪና ከዚያ በላይ ያላቸው መምህራን የሚመደቡ ይሆናል።ፍኖተ ካርታው ከ3 እስከ 5 አመታት የሚፈጅ በሆንም መሰረታዊ ተብሎ የተለዩ ጉዳዮች በቀጣይ አንድ ወር በመጨርስ ወደ ትምህርት ማዕቀፉ በእቅድ ደረጃ እንዲገባ ይደረጋል በ2012 አጠቃላይ ስራው አልቆ በ2013 ወደ ትግበራ ይገባል፡፡ፍኖተ ካርታው ከትምህርት ጋር በተያያዘ የሚነሱ ቅሬታዎችንና  ያልተካተቱ ጠቃሚ ጉዳዮች ከማከተቱም በሻገር ትውልዱን ኢትዮጵያዊ  አውቀት እንዲኖረው ያደርጋል ተብሎም ይታሰባል፡፡ለሀያ አራት ዓመታት አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ እንዲሁም እስትራቴጂ ያመጣቸው በጎ ለውጦች ቢበዙም  ዘመኑን  ያላማከለ እንዲሁም  ከፍተቶች ያሉበት በመሆኑ ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ በትምህርትና ስልጠናው ፍኖተ ካርታ ሲዘጋጅ ቆይቷል፡፡ፍኖተ ካርታውን የሚመለከታቸው አካላት ካዘጋጁት በኋላ ከአምስት አመት በፊት ለህዝብ ይፋ ሆኖ  ምክክር ተደረጎበታል፡፡ከምክክሩና  በኋላም ከ357 በላይ ቢሻሻሉ የተባሉ የመፍትሔ ሀሳቦች የተሰበሰቡ ሲሆን፣ በዋናነት  36ቱ መሰረታዊ ሆነው ተገኝተዋል፡፡ ከእነዚህም ባሻገር በትምህርትና ስልጠናው ፍኖተ ካርታ ከተቀመጡት 37 የመፍትሄ አቅጣጫዎች መካከል ከቀጣዩ የትምህርት ዘመን ጀምሮ በተመረጡት 13 የርብርብ መስኮች ላይ በትኩረት እንደሚሰራ የትምህርት ሚኒስቴሩ ዶ/ር ጥላዬ ጌቴ  ገልፀዋል።የትምህርት ሚኒስትሩ መግለጫቸው ከቀጣዩ የትምህርት ዘመን ጀምሮ መንግስት በመልካም እሴት፣ ስነ ምግባርና በብቃት የታነጸ ዜጋን ለማፍራት እንደሚሰራ ተናግረዋል።
https://waltainfo.com/am/32664/
375
0ሀገር አቀፍ ዜና
ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የስራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን የአየርላንድ አምባሳደር ሚስ ሶንጃ ሃይላንድን አሰናበቱ
ፖለቲካ
August 21, 2019
Unknown
ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የስራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን የአየርላንድ አምባሳደር ሚስ ሶንጃ ሃይላንድን አሰናበቱ፡፡አምባሳደሯ ባለፉት ሁለት ዓመታት ቆይታቸው በኢትዮጵያና በአየርላንድ መካከል የነበረው ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ላደረጉት አሳተዋፅኦ ፕሬዝዳንቷ አመስግነዋል፡፡ በቀጣይ ለሚኖረው ግንኙነትም በተግባር ካዩት እውነታ ተነስተው በኢትዮጵያ ያለውን የሀገር ግንባታ እንቅስቃሴ እንዲደግፉ ጠይቀዋል፡፡ተሰናባቿ የአይርላንድ አምባሳደር ሚስ ሶንጃ ሃይላንድ በበኩላቸው፣ በቆይታቸው በኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ለተደረገላቸው ሁለንተናዊ ድጋፍ አመስግነው በጤና፣ በትምህርት፣ በኢንቨስትመንትና ሌሎች ዓለም አቀፍ የጋራ ጉዳዮች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የበኩላቸውን ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል፡፡ መረጃው የፕሬዝዳንት ጽጽቤት ነው፡፡
https://waltainfo.com/am/31303/
74
5ፖለቲካ
ሱዳን ለሦስት ዓመታት ለሚቆየው የሽግግር መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር ሾመች
ፖለቲካ
August 22, 2019
Unknown
ሱዳን ለሦስት ዓመታት ለሚቆየው የሽግግር መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር ሾመች።አዲስ የተሾሙት ጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሃምዶክ የሽግግር መንግሥቱ መሪ በመሆን ቃለ መሃላ የፈፀሙ ሲሆን፣ በቃለ መሃላቸው በአገሪቱ ያለውን ሰላም ማረጋገጥ እና ለምጣኔ ሐብታዊ ቀውሶች እልባት መስጠት ቅድሚያ የሚሰጡት ጉዳይ እንደሆነ ገልፀዋል።ሌተናንት ጄነራል አብደል ፈታህ አብደልራህማን ቡርሃን ለሉዓላዊ ምክርቤቱ መሪ ሆነው መምራት ከጀመሩ በኋላ የተሾሙት ጠቅላይ ሚንስትሩ እስከ ቀጣዩ የአገሪቷ ምርጫ ድረስ እንደሚያስተዳድሩ ተገልጿል።የሉዓላዊ ምክር ቤቱና ሃምዶክ በቃለ መሃላ ሥነስርዓቱ ላይ ሱዳን ኦማር አል በሽር ሥልጣን በኋላ ከወታደራዊ አገዛዝ ሥርዓት የተላቀቀችበት የመጀመሪያው ጊዜ ብለውታል።ተቃዋሚ ፓርቲዎችም በበኩላቸው አሁን የተመሰረተው መንግሥት በአገሪቷ የነበረውን የወታደራዊ አገዛዝ ሥርዓት እንዲያከትም ያደርገዋል በማለት ተስፋ ሰንቀዋል።ጠቅላይ ሚንስትር ሃምዶክ ከአውሮፓዊያኑ 2011 ጀምሮ በተባበሩት መንግሥታት ከፍተኛ የምጣኔ ሐብት ባለሙያ ሆነው አገልግለዋል።መንግሥት ቅድሚያ ሰጥቶ ከሚሰራቸው ተግባራት መካከል፤ ጦርነትን ማስቆም፣ ዘላቂነት ያለው ሰላም መገንባት፣ የምጣኔ ሐብት ቀውስን መፍታት እና ሚዛናዊነቱን የጠበቀ የውጭ ፖሊሲ መገንባት እንደሆኑ ሃምዶክ ለሮይተርስ ዜና ወኪል አስታውቀዋል።ባለፈው ዓመት ሃምዶክ የአገሪቷ የገንዘብ ሚኒስቴር እንዲሆኑ ከሥልጣን በተወገዱት ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽር የታጩ ሲሆን ጥያቄው ሳይቀበሉት መቅረታቸውን ኤ ኤፍ ፒ የዜና ወኪል ዘግቧል።በሱዳን የተፈጠረው ቀውስ የጀመረው ባለፈው ዓመት መጨረሻ አካባቢ ሲሆን አገሪቷን ለ30 ዓመታት ያስተዳደሩት ኦማር አል በሽር ከሥልጣን እንዲወርዱ በመጠየቅ ነበር።የሲቪል መንግሥት እንሻለን የሚሉ የአገሪቷ ዜጎች ለወራት ተቃውሟቸውን ያሰሙ ሲሆን በእነዚህ ጊዜያትም የበርካቶች ሕይወት ማለፉ ይታወሳል ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው።
https://waltainfo.com/am/33327/
196
5ፖለቲካ
ቻይና እና ሩሲያ የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት በአሜሪካ ሚሳኤል ሙከራ ዙሪያ ስብሰባ እንዲጠራ ጠየቁ
ፖለቲካ
August 22, 2019
Unknown
ቻይና እና ሩሲያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጸጥታው ምክር ቤት በአሜሪካ ሚሳኤል ሙከራ ዙሪያ ስብሰባ እንዲጠራ መጠየቃቸው ተገለጸ፡፡ አሜሪካ ባሳላፍነው ሰኞ የመካከለኛ ርቀት ሚሳኤሎችን የማልማትና የመጠቀም ፍላጎት እንዳላት መግለጫ መስጠቷ ይታወሳል፡፡ ቤጅንግ እና ሞስኮ ጉዳዩ ለዓለም አቀፉ ሰላምና መረጋጋት ስጋት በመሆኑ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ እንዲመክር ጥያቄ ማቅረባቸው ተገልጿል፡፡ በሳለፍነው ሰኞ የአሜሪካ መከላከያ በሰጠው መግለጫ የመካከለኛ ርቀት ሚሳኤል ሙከራ ማድረጉን አስታውቋል፡፡ ሙከራው ከ500 ኪሎ ሜትር ርቀት በላይ ኢላማውን መምታት መቻሉም ነው በመግለጫው የተመላከተው፡፡ የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስትር ማርክ ኢስፐር ለፎክስ ኒውስ በሰጡት ቃለ ምልልስም የሚሳኤል ሙከራው ለቻይና እና ሩሲያ ብሎም ለሰሜን ኮሪያ መልዕክት የሚያስተላልፍ ነው ማለታቸውን ዘገባው አስታውሷል፡፡ አሜሪካ በቀዝቃዛው ጦርነት ከተፈራረመችው የመካከለኛው ርቀት ሚሳኤል መጠቀም ከሚከለክለው ስምምነት መውጣቷን ይፋ ካደረገች በኋላ ሙከራው የመጀመሪያው መሆኑምን ዘገባው ያስረዳል፡፡ (ምንጭ፡-አልጀዚራ)
https://waltainfo.com/am/33988/
120
5ፖለቲካ
ወ/ሮ ሂሩት ዘመነ አዲስ አበባ ከሚኖሩ የኢጋድ አባል አገራት አምባሳደሮች ጋር ተወያዩ
ፖለቲካ
August 20, 2019
Unknown
የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሂሩት ዘመነ ዛሬ ነሀሴ 14 ቀን 2011 ዓም አዲስ አበባ ከሚኖሩ የኢጋድ አባል አገራት አምባሳደሮች ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።የኢጋድ አባል አገራት አምባሳደሮች በቀጠናው ሰላምን በማስፈን ዘላቂ ልማት ለማስመዝገብ በሚደረገው እንቅሰቃሴ የሚያደርጉትን ጥረት አጠናክረው እንዲቀጥሉ ሚኒስትር ዴኤታዋ አሳስበዋል።አምባሳደሮቹ በበኩላቸዉ በቀጠናው በተለይም በደቡብ ሱዳን ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፈን እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ ከግብ እንዲደርስ የሚያደርጉትን ጥረት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡ሚኒስትር ዴኤታዋ  ውይይቱ በዋናነት የደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት ፈራሚ አካላት በነገው እለት በአዲስ አበባ ከሚያደርጉት ስብሰባ ጋር በተያያዘ ያለውን ቅድመ ዝግጅት ስራ በተመለከተ መረጃ መለዋወጥ ላይ ያተኮረ መሆኑን ነው የገለፁት።በውይይቱ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የሱዳን፣ የሶማሊያ፣ የጅቡቲ፣ የኬንያ እና የኡጋንዳ አምባሳደሮች መሣተፋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
https://waltainfo.com/am/31300/
111
5ፖለቲካ
በአቶ አብዲ መሐመድ ዑመር የክስ መዝገብ  የተከሰሱ ሰዎች ጉዳያቸው በሌሉበት እንዲታይ ተወሰነ 
ፖለቲካ
August 20, 2019
Unknown
የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት 4ኛ የወንጀል ችሎት በቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አብዲ መሐመድ ዑመር የክስ መዝገብ ተጠቅሰው ያልተገኙ 11 ተከሳሾች ጉዳያቸው በሌሉበት እንዲታይ ብይን ሰጠ።በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጥሪ ተደርጎላቸው ሳይቀርቡ በሌሉበት ጉዳያቸው እንዲታይ ከተበየነባቸው ተከሳሾች የክልሉ ልዩ ኃይል አዛዥ የነበሩት ጄኔራል አብዱራህማን አብዱላሂ፣ ሻለቃ ሼክ ሙክታር እና ሄጎ የተሰኘውን የአመፅ ቡድንን በምክትልነት ሲመሩ ነበር የተባሉት የወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ መሐመድ አህመድ ይገኙበታል።ችሎቱ ከነዚህ በተጨማሪ በክስ መዝገቡ የመኖሪያ አድራሻ ተፈልገው ያልተገኙ ሌሎች 7 ተከሳሾችም እንዲቀርቡ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጥሪ እንዲደርሷቸው ትዕዛዝ ሰጥቷል።በተሻሻለው ክስ ላይ 1ኛው ተከሳሽ የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አብዲ ዑመር ከጠበቆች ጋር ተማክሬ የክስ መቃወሚያ አቀርላሁ ብለዋል።ጉዳያቸውን በአካል እየተከታተሉ ከሚገኙ 14 ተከሳሾች የተፋጠነ ፍትሕ ተጠቃሚ መሆን አልቻልንም፤ ጉዳያችንን ፍርድ ቤቱ በትኩረት ይመልከትልን በማለት አመልክተዋል።ችሎቱ የክስ መዝገቡ በጋራ የሚታይ በመሆኑ የተከሳሾች የግል አቤቱታ የክስ መቃወሚያ እና ከሌሎች መሰል ጉዳዮች ጋር በተያያዘ የተጠቀሰውን ጊዜ ሊቆጠር ችሏል ብሏል፡፡ 
https://waltainfo.com/am/31296/
137
5ፖለቲካ
የመቐለ ከተማ ሴቶች የአሸንዳ በዓልን ምክንያት በማድረግ ችግኝ ተከሉ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 20, 2019
Unknown
የመቐለ ከተማ ሴቶች የአሸንዳ በዓልን ምክንያት በማድረግ ዛሬ በሰማዕታት ሐውልት ግቢ ችግኝ ተከሉ። ሴቶቹ ችግኞቹን የተከሉት በዓሉን ከማድመቅ በተጨማሪ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የአረንጓዴ ልማት ፕሮግራምን ለማሳካት እንደሆነም ተገልጿል።ሴቶቹ ችግኞቹን ተንከባክበው ለማጽደቅ እንደሚሰሩም ተገልጿል።በተከላው ከተሳተፉት ሴቶች መካከል ወይዘሮ ፅጌ አብርሃ የሴቶች የነጻነት መገለጫ የሆነውን በዓል ለማድመቅና መነሳሳትን ለመፍጠር ያስችላል ብለዋል።እንዲሁም የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር የጀመሩትን የአረንጓዴ ልማት ፕሮግራም ከዳር እንደሚያደርሱ ተናግረዋል።ሌላዋ አስተያየት ሰጪ ኮማንደር አበባ ነጋሽ በበኩላቸው በችግኝ ተከላው የተሳተፉት በአረንጓዴ ልማት መርሐ ግብር  ስኬት ተሳትፏቸውን  ለማረጋገጥ መሆኑን ገልጸዋል።ሴቶች በሁሉም መስኮች ከተሰማሩ የማያሳኩት ሥራ እንደሌለ ለማሳየትና በዓሉን ለማድመቅ ነው ብለዋል።የትግራይ ክልል ሴቶች ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር የትምወርቅ ገብረመስቀል እንዳሉትም ችግኝ ተከላው የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ለአረንጓዴ ልማት ፕሮግራም ስኬት የነበራቸውን ታላቅ አስተዋጽኦ ለማስታወስ የተዘጋጀ ነው። 
https://waltainfo.com/am/32662/
116
0ሀገር አቀፍ ዜና
ኮሚሽኑ የተሰጠውን ተልእኮ በብቃት ማስፈም እንዲችል አዋጅና ደንቦችን የሚያሻሽል ረቂቅ አዘጋጀ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 20, 2019
Unknown
የፌዴራል የስነምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን የተሰጠውን ተልእኮ በብቃት ማስፈም እንዲችል አዋጅና ደንቦችን የሚያሻሽል ረቂቅ አዘጋጅቷል፡፡አዲስ በመዘጋጀት ላይ ካለው የከፍተኛ መንግሥት ባለስልጣናት የስነ ምግባር ደንብ በተጨማሪ በሀብት ማሳወቅና ማስመዝገቢያ እንዲሁም የስነምግባር መኮንኖች አሰራርን ለመወሰን በወጣው ደንብ ላይ ረቂቅ ማሻሻያዎች መዘጋጀታቸውን ኮሚሽኑ ገልጿል።ኮሚሽኑ የባለፈውና የቀጣይ በጀት አመቱን እቅድና አፈጻጸም አስመልክቶ በጋራ ከሚሰሩ የጸረሙስና ጥምረት አካላት ጋር ውይይት አድርጓል፡፡በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ሀብት ማስመዝገብ ላይ ያለው አፈጻጸም ደካማ መሆኑ በመድረኩ ተነስቶ ተገምግሟል።ኮሚሽኑ በስሩ የምርመራና አቃቤ ህግ ስራን አቀናጅቶ አለመስራቱ  ውጤታማ እንዳይሆን  አድርጎታል ተብሏል፡፡በሌላ በኩል ሙስና በሃገሪቱ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ ያስችላል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት 3ኛው ሃገር አቀፍ የሙስና ቅኝት  ጥናት መጀመሩን  ኮሚሽኑ አስታውቋል።ከዚህ በተጨማሪም ሀገራዊ የፀረ ሙስና ፖሊሲና ስትራቴጂ የዝግጅት ሂደት መጀመሩንም ነው ኮሚሽኑ የገለፀው።የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አየልኝ ሙሉዓለም እንዳሉት የኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅን ጨምሮ ተቋማዊ የውስጥ አሠራርን የተመለከቱ መመሪያዎች ተዘጋጅተው ውይይት እየተደረገባቸው ነው።ብልሹ ስነ ምግባርንና ሙስናን የመዋጋቱ ስራ በተቋማዊ አደረጃጀት ብቻ የሚሳካ ባለመሆኑ የህብረተሰቡንና የሚመለከታቸው አካላትን የተቀናጀ ተሳትፎ ለማሳደግ እየተሠራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡ 
https://waltainfo.com/am/32663/
150
0ሀገር አቀፍ ዜና
የግብርና ሚኒስቴር ከቻይና አቻው 4 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የግብርና መሳሪያዎች ተበረከቱለት
ቢዝነስ
August 20, 2019
Unknown
የቻይናው ግብርናና ገጠር ጉዳዮች ሚኒስቴር ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የግብርና መሳሪያዎችና ቁሳቁስ ለግብርና ሚኒስቴር አበርክቷል፡፡ርክክቡ ሲካሄድ የቻይናው አምባሳደር ሚስተር ታን ጄይን እንዲሁም በኢትዮጵያ በኩል የግብርናው ሚኒስትር አቶ ዑመር ሁሴን ተገኝተዋል፡፡ርክክብ ከተደረገባቸው መሳሪያዎች መካል ትራክተር፣ ዘር መዝሪያ ማሽን፣ የአፈር መከስከሻ ማሽን፣ የሩዝና ስንዴ መውቂያ ማሽን፣ የጥጥ ዘር መፈልፈያ፣ ጀነሬተሮች እና የቢሮ መገልገያ እቃዎች ይገኙባቸዋል፡፡መሳሪያዎቹ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ለማስተዋወቅና ግብርናን ለማዘመን ከፍተኛ ሚና ያላቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡የቻይና መንግስት ለኢትዮጵያ ግብርና እድገት እያደረገ ላለው ድጋፍ የግብርናው ሚኒስትር አቶ ዑመር ሁሴን ከፍተኛ ምስጋና ማቅረባቸውን ከግብርና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
https://waltainfo.com/am/23911/
84
3ቢዝነስ
ኢትዮጵያና አሜሪካ የሕግ ማስከበር እና የወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ስምምነት ተፈራረሙ
ፖለቲካ
August 20, 2019
Unknown
የሰላም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪሀት ካሚልና በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክል ሬይኖር መንግሥቶቻቸውን ወክለው የሕግ ማስከበር እና የወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ስምምነት ተፈራርመዋል።ስምምነቱም ለሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱና ለፌደራል ፖሊስ እንዲሁም ለፍትህና ሕግ ማስከበር አካላት ድጋፍ በመስጠት የሕግ ማስፈጸም እና የፍትሕ ዘርፉን ለማሻሻል ያለመ መሆኑን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
https://waltainfo.com/am/31298/
45
5ፖለቲካ
ዛምቢያ ቀረጥ ያልከፈሉ ተሽከርካሪዎችን በድሮን እያደነች ነው ተባለ
ቢዝነስ
August 20, 2019
Unknown
የዛምቢያ ግብር ባለሥልጣናት ቀረጥ ያልከፈሉ ተሽከርካሪዎችን በድሮን እያደነች ነው ተባለ፡፡ባለሥልጣናቱ ቀረጥ ሳይከፍሉ እቃዎችን የሚያዘዋውሩ ከባድ መኪናዎችን ለመቆጣጠር ድሮኖችን መጠቀም መጀመራቸው ነው የተገለጸው፡፡ባሳለፍነው ቅዳሜና እሁድ የዛምቢያ ገቢዎች ባለሥልጣን በድሮኖች በመታገዝ ከዋናው መንገድ በመውጣት ተደብቀው የነበሩ ሰባት ተሽከርካሪዎች መያዛቸውን አስታውቀዋል።"ድሮኖቹ የፍተሻ ሠራተኞች በማይደርሱባቸው እንዲሁም አደጋ ባለባቸውና ጥንቃቄን በሚጠይቁ ቦታዎች ድረስ በመግባት አሰሳ ያደርጋሉ" ሲሉ የዛምቢያ ገቢዎች ባለስልጣን የኮሚዩኒኬሽን ሥራ አስኪያጅ ቶፕሲይ ሲካሊንዳ ለቢቢሲ ተናግረዋል።በዚህ ሰባት ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ሥር በዋሉበት ፍተሻ ድሮኖቹ 'ካፒሪ ስርነጅ' በተባለ መንገድ በመግባት ማሰስ የጀመሩ ሲሆን፣ ዋናው የተሽከርካሪ መንገድ ባዶ ሆኖ አግኝተውታል፤ ከዚያም ከዋናው መስመር 14 ኪሎሜትር በሚርቅ ጥሻ ውስጥ አመላክተዋል።በዛምቢያ ወደ ደቡብ አቅጣጫ የሚጓዙ ተሽከርካሪዎች በአብዛኛው ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ማላዊ፣ ወይም ታንዛኒያ የሚመጡ ናቸው።ኃላፊው ሲካሊንዳ እንዳስታወቁት አብዛኞቹ ተሽከርካሪዎች በጣም በርካታ እቃዎችን ይጭኑና ወደ ፍተሻ ጣቢያው ሲቃረቡ በትንንሽ መኪና ቀንሰው ይጭናሉ ይህም ባለሙያዎቹ ጥርጣሬ ውስጥ እንዳይገቡ ምክንያት ሆኗል።የዛምቢያ የገቢዎች መሥሪያ ቤት ቴክኖሎጂን በመጠቀም ገቢውን ለማሳደግ ተስፋ እንዳለው የቀረጥ ባለሥልጣናት ጨምረው ተናግረዋል። (ምንጭ፡-ቢቢሲ)
https://waltainfo.com/am/32902/
143
3ቢዝነስ
የጦር መሳሪያ በተሽከርካሪ ሲያዘዋውር የተያዘው ተከሳሽ በ2 ዓመት ጽኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጣ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 20, 2019
Unknown
ተከሳሽ አብዱራህማን ዩኑስ ከሚመከለተው የመንግስት ፈቃድ ውጪ ወደ ሀገር እንዳይገቡ ገደብ የተደረገባቸው የጦር መሳሪያዎችን በተሸከርካሪ ደብቆ ወደ ሀገር ሊያስገባ ሲል ተይዞ ዐቃቤ ሕግ በመሰረተው ክስ በእስራት ተቀጥቷል፡፡ተከሳሽ 53 ቱርክ ስሪት ሽጉጦችንና 35 ሺህ 766 ጥይቶችን የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-A50931 አ.አ በሆነ ላንድክሩዘር መኪና ደብቆ ወደ ሀገር ሊያስገባ ሲሞከር በተደረገው ክትትል በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ክልል ልዩ ቦታው ጣፎ አደባባይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በተሸከርካሪው ላይ በተደረገ ፍተሻ ተይዟል፡፡ተከሳሽ ክሱ በችሎት ተነቦለት እንዲረዳ ከተደረገ በኃላ ድርጊቱን ክዶ በመከራከሩ ዐቃቤ ሕግ እንደ ክሱ አቀራረብ ምስክሮች አሰምቷል፡፡ፍርድ ቤቱም መዝገቡን መርምሮ ተከሳሽ ሽጉጥና ጥይት በመኪና ደብቆ በፍተሻ ስለመያዙ በመረጋገጡና መከላከልም ባለመቻሉ በተከሰሰበት ድንጋጌ ጥፋተኛ መሆኑን በይኗል፡፡የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 8ኛ ወንጀል ችሎት መዝገቡን መርምሮ የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት በመመልከት ተከሳሽ በ2 ዓመት ጽኑ እስራት እና በ5 ሺህ ብር መቀጮ እንዲቀጣ ወስኗል፡፡ምንጭ፡- ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
https://waltainfo.com/am/32661/
135
0ሀገር አቀፍ ዜና
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኳታር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ተወያዩ
ፖለቲካ
August 19, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኳታር ምክትል ጠ/ሚርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ተወያዩጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ከኳታር ምክትል ጠ/ሚርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሼክ መሐመድ ቢን አብዱልራሕማን ቢን ጃሲም አል ታኒ ጋር ተወያዩ፡፡ሁለቱ ወገኖች ጠ/ሚሩ በመጋቢት ወር 2011 በኳታር ይፋዊ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት የተጀምረውን ውይይት በማስቀጠል በቁልፍ የሁለትዮሽ ትብብር ጉዳዮች ላይ ተነጋግረዋል፡፡ሼክ መሐመድ ከዚህ ቀደም ስምምነት ላይ የተደረሰባቸው የኢንቨስትመንት ዘርፎች በተለይም በሆቴል፣ ስኳር ፋብሪካ፣ በቱሪዝም ልማትና አዳዲስ የኩላሊት ሕክምና ማዕከላት ግንባታን ለማስጀመር ዝግጁነት እንዳለ መግለጻቸውን ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያስረዳል።
https://waltainfo.com/am/31297/
78
5ፖለቲካ
በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ የለውጥ ስራዎችን ማስጀመሪያ መድረክ እየተካሄደ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
August 19, 2019
Unknown
በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ የለውጥ ስራዎችን ማስጀመሪያ መድረክ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማርያም በተገኙበት በአዲስ አበባ ሸራተን ሆቴል እየተካሄደ ነው፡፡የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በሀገራችን የመጀመሪያውን የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታ ከሶስት አመታት በላይ ከፈጀ የዝግጅት ምዕራፍ በኋላ ከ 2012 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ያደርጋል፡፡ፍኖተ ካርታው እስከ 2022 ዓ.ም የሚተገበር ሲሆን፣ 2012 ዓ.ም የመጀመሪያው የትግበራ አመት ይሆናል፡፡ ፍኖተ ካርታው በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያሉ ችግሮችን ለይቶ መፍትሄዎችን አስቀምጧል፡፡የስርዐት ትምህርት አዘገጃጀት ይዘትና ትግበራ ችግር፣ የዩኒቨርሲቲዎች በተልእኮ አለመለየት፣ የትምህርት አደረጃጀት ችግር እና ሌሎችም አራት ችግሮች የተለዩ ሲሆን፣ በእነዚህ ችግሮች ምክንያትም የስነምግባርና የሞራል ውድቀት፣ ስርአት አልበኝነትና ምክንያታዊ አለመሆን፣ የስራ ጠባቂነትና ጥገኝነትን የመሳሰሉ ችግሮች በተማሪዎች ዘንድ ተስተውለዋል ተብሏል፡፡የአንደኛ አመት ተማሪዎችን የታሪክ፣ ጂኦግራፊና አንትሮፖሎጂ፣ የኮምፒውቴሽናል ክህሎት፣ የስነምግባር፣ የቋንቋ፣ የስነ ተግባቦት፣ ምክንያታዊነት፣ ቴክኖሎጂና አለምአቀፋዊ እውቀት ሊያስጨብጡ የሚችሉ ትምህርቶችን መስጠት፣ ዩኒቨርሲቲዎችን እንደ ተልዕኳቸው ትኩረት ማደራጀት ማለትም የምርምር፣ የአፕላይድ ሳይንስ እና ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲዎች አድርጎ ማደራጀት እና የዩኒቨርሲቲ ቆይታን አራት አመት እንዲሆን ማድረግ ለምህንድስና አምስት ለህክምና ስድስት አመት ለማስተርስ ዲግሪ ሁለት አመት እንዲሁም ለፒኤችዲ ዲግሪ ደግሞ አራት አመት ማድረግ ችግሮችን ከስር መሰረታቸው ለመፍታት በፍኖተ ካርታው የተቀመጡ የመፍትሄ ምክረ ሀሳቦች ናቸው ተብሏል፡፡ መረጃው የፕሬስ ኤጄንሲ ነው፡፡
https://waltainfo.com/am/32658/
173
0ሀገር አቀፍ ዜና
በምዕራብ ኢትዮጵያ የሚገኙ ክልሎች የጋራ መድረክ እየተካሄደ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
August 19, 2019
Unknown
የምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ መድረክ በአሶሳ እየተካሄደ ነው::የቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ የአማራ፣የኦሮሚያና የጋምቤላ ክልሎች የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ መድረክ ሲሆን፤ የክልሎቹ አፈ ጉባኤዎች፣ የቢሮዎች ሀላፊዎች፣ እንዲሁም የአራቱ ክልሎች ተጎራባች ዞኖችና ወረዳዎች አመራሮች በመታደም ላይ ናቸው፡፡የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከኦሮሚያ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የጋራ የሰላምና ልማት ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ጋር በትብብር መድረኩን አዘጋጅተዋል፡፡ፕሬስ ድርጅት እንደዘገበው የምዕራብ ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ህዝቦች ሁለንተናዊ ሁኔታ፤ ፌዴራሊዝምና የሰላም እሴት ግንባታ፤ የቤኒሻንጉል ጉሙዝና የኦሮሚያ ዞኖችና ወረዳዎች የጋራ ልማትና ሰላም ስምምነት ይፈረማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
https://waltainfo.com/am/32659/
78
0ሀገር አቀፍ ዜና
በነብርጋዴር ጄነራል ተፈራ ማሞ የክስ መዝገብ ላይ ብይን ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ
ፖለቲካ
August 19, 2019
Unknown
በእነ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የክስ መዝገብ ላይ የምርመራ ቡድኑ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ በጠየቀው ይግባኝ ላይ የባሕር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ ለመስጠት ለነሐሴ 16/2011 አ.ም የጊዜ ቀጠሮ ሰጠ።በእነ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የክስ መዝገብ ላይ ሐምሌ 29/ 2011 ዓ.ም በነበረው የጊዜ ቀጠሮ የባህር ዳር ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ውድቅ ማድረጉ ይታወሳል ። ይህን ተከትሎም የምርመራ ቡድኑ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው የባህር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤትን ዛሬ ጠይቋል።የምርመራ ቡድኑ “አዳዲስ ተከሳሾች ተይዘዋል። ቃል እየተቀበልን ነው። በድርጊቱ ዋና ተከሳሾች ካልተያዙ ክስ መመስረት አንችልም። በህክምና ላይ ያሉትን ምስክሮች ቃል የመቀበል ስራ እየተከናወነ ነው። በፌዴራል ከሚካሄደው ምርመራም ጋር የሚያያዙ ጉዳዮች አሉ። የቀዳሚ ምርመራ የሚሰሙ ብዙ ምስክሮች እያሉን የቀረቡት ጥቂቶቹ ናቸው” በሚሉ ምክንያቶች ተጨማሪ የይግባኝ ጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል።የተከሳሾቹ ጠበቆች በበኩላቸው የጊዜ ቀጠሮው ይግባኝ የሚቀርብበት እንዳልሆነ እና ለምርመራ የተሰጠው የጊዜ ቀጠሮ በቂ መሆኑን በመግለጽ ይግባኙን ተቃውመዋል።ከፍተኛ ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን ካደመጠ በኋላ በይግባኝ ክርክሩ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለነሐሴ 16/2011 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ቀጠሮ ሰጥቷል።(ዘገባው የአብመድ ነው)
https://waltainfo.com/am/31295/
160
5ፖለቲካ
በግማሽ አመት የኦንላይን ግብይት የቻይና ኢኮኖሚ እምርታ ማሳየቱ ተገለጸ
ቢዝነስ
August 19, 2019
Unknown
በግማሽ አመት የኦንላይን ግብይት የቻይና ኢኮኖሚ እምርታ ማሳየቱ  ተገለጸ፡፡የኦንላይን ግብይት ለሀገሪቱ ምጣኔ ሃብታዊ ዕድገት ከፍተኛ ድርሻ እየተጫወተ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡ባለፉት ሁለት ተከታታይ ሳምንታት የኦንላይን ግብይት የግማሽ አመት የቻይና ኢኮኖሚ እድገት አስተዋፅኦ እንደነበር የሲጂቲኤን ዘገባ አመላክቷል፡፡የአለም ሁለተኛዋ ባለ ግዙፍ ምጣኔ ሃብት ባለቤት ቻይና ለኢኮኖሚዋ እድገት የሃገሪቱ ግዙፍ የማኑፋክቸሪንግ አምራች ሴክተሮች ድርሻ ከፍተኛ እንደሆነም ተነግሯል፡፡ አሁን ደግሞ በሃሪቱ ያሉት የኦላንይን የኢ-ኮሜርስ ኩባንያዎች ለሃገሪቱ የምጣኔ ሃብት እድገት ከፍተኛ ድርሻ እንዳበረከቱ መረጃዎች አሳይተዋል፡፡ከእነዚህ የኢ-ኮሜርስ ወይም የድረገፅ መገበያያ ተቋማት ዉስጥ ግዙፉ የአሊባባ ኩባንያ ተጠቃሽ ነዉ፡፡ የአሊባባ ኦንላይን ግብይት ቸርቻሪ የሆነዉ ቲ ሞል የ150 ሚሊዮን ሸማቾች ትእዛዝ ተቀብሏል፡፡የስታስቲክስ መረጃ እንደሚያመላክተዉ ከ8 ኦንላይን የግብይት ጥያቄዎች አንዱ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች ሲሆን ሽያጩም ከ40 የተለያዩ መለያ ያላቸዉ ምርቶች ከ100 ሚሊየን በላይ የቻይና ዩአን ገቢ አስገኝተዋል፡፡በባለፉት ዓመታት በፍጥነት በማደግ ላይ የነበረው የቻይና ኢኮኖሚ በዚህ በኢንተርኔት ኦንላይን መገበያያ ተመራጭ የግብይት ዘዴ መደገፉም ይነገራል፡፡እንደ አፕል ያሉ ታዋቂ መለያ ያላቸዉ ምርቶች 170 በመቶ ዓመታዊ እድገት እያሳዩ መምጣታቸዉ ለሃገሪቱ ምጣኔ ሀብት ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክተዋል፡፡ የሃገሪቱ ንግድ ሚኒስቴር ባወጣዉ የግማሽ አመት ኢ ኮሜርስ መረጃ ገጠራማ የቻይና አካባቢዎች የታየዉ የንግድ እንቅስቃሴ 1.3 ትሪሊዮን ዩአን የደረሰ ሲሆን በየአመቱ የ30.4 በመቶ እድገት እያስመዘገበ መጥቷልም፡፡በቻይና ያሉ የኢ ኮሜርስ ኩባንያዎች በአጠቃላይ ባሳለፍነዉ ግማሽ አመት 31.36 ትሪሊዮን ዩአን ገቢ አስገኝተው፤ 8.5 በመቶ የእድገት መጠንም አሳይተዋል፡፡በ2019 መጨረሻ በተያዘዉ ግብ ቢያንስ 10 ሚሊዮን ዜጎችን ከድህነት ለማላቀቅ ሃገሪቱ አቅዳ እየሰራች እንደሆነም የ ሲ ጂቲኤን ዘገባ ያሳያል፡፡
https://waltainfo.com/am/33558/
210
3ቢዝነስ
በእናቶችና ሕፃናት ጤና ላይ ያተኮረ ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
August 19, 2019
Unknown
በእናቶችና ሕፃናት ጤና ላይ ያተኮረ ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው::በጤና ሚኒስቴር አዘጋጅነት በአዲስ አበባ  እየተካሄደ ባለው በዚህ ኮንፈረንስ በእናቶች ፣ህፃናትና ወጣቶች ፣ በስነ ተወልዶና በቤተሰብ እቅድ እንዲሁም ከስርዓተ ምግብ ጋር በተያያዘ ጥራት ያለው የጤና አግልግሎት መስጠት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ምክክር ይደረጋል፡፡በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያሉ የምርምር ባለሞያዎች  በተለይም በእናቶች፣ በጨቅላ ሕፃናት፣ በሥርዓተ ምግብ እና በክትባት ዙሪያ የሚሰሩ ጥናቶች በጤናው ዘርፍ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለመሙላት እንዲያግዙ ማድረክ የኮንፈረንሱ ዋና ዓላማ ነው፡፡በኮንፈረንሱ በአጠቃላይ ከ41 በላይ የጥናት ሥራዎች እንደሚቀርቡ ይጠበቃል፡፡ጥናቶቹ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የእናቶች እና ሕፃናት ጤናን ለመጠበቅ እና ለማረጋገጥ በሚያደርገው ጥረት ውስጥ ለሚያወጣቸው ፖሊሲዎች እንደ ግብዓት የሚጠቅሙ መሆናቸው ተገልጿል።ለውይይት የቀረቡት ጥናቶችም የመቀንጨር ችግር ለመቅረፍ ለሚሠራው የሰቆጣ ቃል ኪዳን ፕሮግራም በግብዓትነት  የሚያገለግሉ  የምርምር ሥራዎች መሆናቸውን የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሳህረላ አብዱላሂ ተናግረዋል፡፡እነዚህን የጥናት ውጤቶች መነሻ በማድረግም በቀጣይ በእናቶች፣ ሕፃናት እና በአፍላ ወጣቶች ላይ ያተኮሩ ሥራዎች ላይ በትኩረት ይሰራል ነው ያሉት፡፡                                 
https://waltainfo.com/am/32660/
136
0ሀገር አቀፍ ዜና
የሱዳን ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አምስት የሉዓላዊ ምክር ቤት አባላትን ሰየሙ
ፖለቲካ
August 19, 2019
Unknown
የሱዳን ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አምስት የሉዓላዊ ምክር ቤት አባላትን ሰየሙ፡፡አባላቱ ዛሬ ቃለ መሀላ እንደሚፈፅሙ የተገለጸ ሲሆን፣ ከመሃላው በፊት ሀገሪቷን እያስተዳደረ የሚገኘው ወታደራዊው መንግስት ከሲቪል ተወካዮች በሁለት በልጦ አባል መርጦ አዘጋጅቷል፡፡አባላቱም በምክር ቤቱ ውስጥ ከፍተኛ ስልጣን የሚኖራቸው ይሆናሉ ነው የተባለው፡፡ሱዳን ሰላም አጥታ ለበርካታ ወራት ስትታመስ ከቆየች በኋላ ለህዝቡ ጥያቄ የመጨረሻ እልባት መፍትሄ ሰጭ የተባለለት የስምምነት ደረጃ ላይ ተደርሷል፡፡የሀገሪቷ የአስተዳደር አካል ከወታደራዊው አገዛዝ ይልቅ ህዝባዊ አካል ሀገሪቱን ሊያስተዳድር ይገባል የሚል ሀሳብ በተቃዋሚ የፖለቲካ አመራሮች ሲመራና ሲራመድ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡በዚህ ሀሳብ በገዥው ወታደራዊው መንግስት እና በህዝብ መካከል ከፍተኛ መተራመስ በመፈጠሩ ከ127 በላይ ሱዳናዊያንም ሞት እና ለባርካቶች አካላቸው ጉዳት ምክንያት ሆኗል፡፡ ሱዳን ሰላም እንድታገኝ እና በገዢው አካል መካከል ሰላም እንዲወርድ ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ ሀገራት እንዲሁም የአፍሪካ ህብረት ጥረት ሲያደርጉም ቆይተዋል፡፡በስተመጨረሻም ሁለቱ አካላት ስምምነት ላይ ደርሰው ዛሬ መቋጫዉን ሊያገኝ ስልጣን ላይ ያለው ወታደራዊው መንግስት እና የሱዳን ተቃዋሚ የፖለቲካ አባላት የስልጣን ክፍፍል ሊያደርጉ የሉዓላዊ ምክር ቤት አባሎቻቸዉን መርጠው አዘጋጅተዋል፡፡ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አምስት ወታደራዊው መንግስት ከሲቪሊያኑ በሁለት ከፍ ብሎ ሰባት በምክር ቤቱ ውስጥ ከፍተኛ ስልጣን የሚኖራቸዉን አባሎቻቸዉን መርጠዋል፡፡በዘመነ አልበሽር ሱዳን በከፍተኛ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ የሴቶች ተሳትፎ ያን ያህል ነበር፡፡ ከዚህ አካሄድ ለየት ባለ መልኩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በመረጧቸው አባላቶቻቸው ውስጥ ሴቶችን አካተዋል ነው የተባለው፡፡ሁለቱ አካላት ሰልጣን መጋራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ቅዳሜ ስምምነት ላይ የደረሱ ሲሆን፣ ዛሬ ደግሞ የመጨረሻ መሃላ ሊፈፅሙ የምክር ቤቱ አባላቶቻቸዉን አዘጋጅተዋል፡፡አባላቶቹ በምክር ቤቱ ከፍተኛ ስልጣን የሚኖራቸው ቢሆንም ትልቁ ኃላፊነታቸው ለካቢኒው የሚሰሩ ነው የሚሆነው፡፡ ሱዳን አጥታ ለነበረው ሰላም እና ህዝቡ ሲያነሳ ለነበረው ጥያቄ መልስ የሚሰጥ ነው የተባለው ይህ ስምምነት ዛሬ ላይ በርካታ ሱዳናዊያን በካርቱም እና በሌሎች ከተሞች ጎዳና እንዲወጡ ምክኒያት ሆኗቸዋል፡፡ ደስታቸዉን ለመግለጽ እና የፊርማ ስምምነቱን ለማክበር ሲባል፡፡ሁለቱ አካላት ዛሬ የመጨረሻ ቃለ መሃላ የሚፈጽሙ ሲሆን፣ በስምምነታቸውም መሰረት ወታደራዊው ሽግግር መንግስት ለ21 ወራት ስልጣን ላይ የሚቆይ ሲሆን የሲቪሉ አካል ደግሞ ለሚቀጥሉት 18 ወራት ስልጣን በመጋራት በጋራ ሱዳንን ያስተዳድራሉ፡፡(ምንጭ፡-ሚድል ኢስት እና አልጄዚራ)
https://waltainfo.com/am/33325/
284
5ፖለቲካ