headline
stringlengths
2
1.42k
category
stringclasses
6 values
date
stringlengths
9
35
views
stringlengths
1
7
article
stringlengths
63
36.2k
link
stringlengths
28
740
word_len
int64
16
6.74k
label
class label
6 classes
የከተማ አስተዳደሩ ም/ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ በከተማዋ እየታደሱ የሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤቶችን ጎበኙ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 18, 2019
Unknown
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ በከተማ አስተዳደሩና በባለሀብቱ እየታደሱ የሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤቶችን ጎበኙ፡፡በከተማ አስተዳደሩ 488 የመንግስት ትምህርት ቤቶች እየታደሱ የሚገኙ ሲሆን፣ አሁን ወደ መጠናቀቅ ምዕራፍ ላይ ደርሰዋል ነው የተባለው፡፡የትምህርት ቤቶቹ እድሳት ለተሻለ መማር ማስተማር እንዲኖር ከማድረግ ባሻገር ለተማሪዎችም ሆነ ለአስተማሪዎች የትምህርት ፍላጎት ማደግ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ተናግረዋል፡፡ከእድሳት እና ጥገና ስራዎች በተጨማሪ የከተማ አስተዳደሩ በየትምህርት ቤቶቹ ቅጥር ጊቢ ውስጥ ለተማሪዎች የአረንጓዴ ቦታ እና ምቹ የመመገቢያ አዳራሾች በአዲስ መልክ የሚደራጁ ይሆናልም ነው የተባለው፡፡ምክትል ከንቲባው በጉብኝታቸው ወቅት በየትምህርት ቤቶቹ በዩኒቨርሲቲ መግቢያ ከፍተኛ ውጤት ካመጡ ተማሪዎች ጋርም ቆይታ አድርገዋል፡፡ከንቲባው በዛሬ ጉብኝታቸው በአስሩ ክፍለ ከተሞች የሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤቶች እድሳት ሂዴትን ይጎበኛሉ ተብሏል፡፡
https://waltainfo.com/am/32657/
108
0ሀገር አቀፍ ዜና
በካቡል ከተማ አንድ ሠርግ ላይ የፈነዳ ቦንብ 63 ሰዎችን ሲገድል 180 ሰዎችን አቁስሏል
ሀገር አቀፍ ዜና
August 18, 2019
Unknown
በአፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል አንድ ሠርግ ላይ የፈነዳ ቦንብ 63 ሰዎችን ሲገድል 180 ሰዎችን አቁስሏል፡፡የዓይን እማኞች አንድ አጥፍቶ ጠፊ ቦንቡን ተሸክሞ መጥቶ እንዳፈነዳው የተናገሩት፡፡ቦንቡ የፈነዳው ቅዳሜ ምሽት 4፡40 ገደማ ሲሆን ሥፍራው ደግሞ የሺያ ሙስሊሞች የሚያዘውትሩት የካቡል ምዕራባዊ ክፍል ነው ተብሏል።ታሊባን 'እኔ እጄ የበለትም' ሲል አስተባብሏል። እስካሁን ለጥፋቱ ኃላፊነት የወሰደ ቡድን የለም። ራሳቸውን ከሱኒ ሙስሊሞች ጋር የሚያቆራኙት ታሊባን እና አይ ኤስ ከዚህ በፊት የሺያ ሙስሊሞች ላይ ጥቃት መፈፀማቸው ይታወሳል።የአፍጋኒስታን ሃገር ውስጥ ሚኒስትር አደጋው ከደረሰ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ የሟቾችን እና የተጎጂዎችን ቁጥር ይፋ አድርገዋል።ወንዶች እና ሴቶች ለየብቻ ሆነው የሚስተናገዱበት የአፍጋኒስታን የሠርግ ሥነ-ሥርዓት በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ይታደሙበታል።'አጋጣሚ ሆኖ ቦንቡ ሲፈነዳ እኔ ከሴቶች ጎራ ነበርኩ' የሚለው ሞሐመድ ፋርሃግ 'ከፍንዳታው በኋላ ሰዎች ሁላ እግሬ አውጭኝ እያሉ ሲወጡ ተመልክቻለሁ' ሲሉ ኤኤፍፒ ለተሰኘው የዜና ወኪል ተናግሯል።ከ10 ቀናት በፊት ካቡል ውስጥ በሚገኝ አንድ ፖሊስ ጣብያ የፈንዳ ቦንብ የ14 ሰዎችን ሕይወት መቅጠፉ አይዘነጋም። ታሊባን ጥፋቱን የፈፀምኩት እኔ ነኝ ሲል ኃላፊነቱን ወስዷል።ባለፈው አርብ ደግሞ የታሊባን አለቃ ወንድም የሆነው ሂባቱላህ አኩንደዛዳ መስጅድ ውስጥ ሳለ በተመጠደ ቦንብ ሕይወቱ አልፏል።አፍጋኒስታን ውስጥ በርካታ ወታደሮች ያሏት አሜሪካ ከታሊባን ጋር ድርድር ውስጥ እንዳለች እና በጎ ጅማሬዎች እንደታዩ ዕለት አርብ ፕሬዝደንቷ ትራምፕ በትዊተር ገፃቸው ማወጃቸው አይዘነጋም። (ምንጭ፡-ቢቢሲ)
https://waltainfo.com/am/34128/
180
0ሀገር አቀፍ ዜና
የመንግስታቱ ድርጅት ለሱዳን ህዝብ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላለፈ
ፖለቲካ
August 18, 2019
Unknown
በሱዳን ህዝባዊ መንግስት እንዲመሰረት መደላድል የሚፈጥር ስምምነት መፈረሙን ተከትሎ የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጽሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ለአገሪቱ ህዝብ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሱዳን የሽግግር መንግስት እንዲመሰረት ያደረገ ስምምነት መፈረሙን አስመልክቶ የድጋፍ መግለጫ አውጥቷል፡፡በዚህም የሱዳን ህዝብን የቆየ የዲሞክራሲና የሰላም ምኞት ለማሳካት ብሎም የአገሪቱን የሽግግር ጊዜ ለመደገፍ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቁርጠኛ መሆኑን የተቋሙ ዋና ጽሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ተናግረዋል፡፡አያይዘውም የአገሪቱን ኢኮኖሚ እንዲያገግም በማድረግ ዘላቂ ልማት ለማምጣት ምቹ ሁኔታ መፍጠር እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡በሱዳን ወታደራዊ ምክር ቤትና በተቃዋሚ ሀይሎች መካል የተፈረመው የስምምነት ሰነድ ሁለቱ ኃይሎች ስልጣን በመጋራት የሽግግር መንግስት መመስረት የሚያስችላቸው ነው፡፡ስምምነቱ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድና የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ በተገኙበት ትላንት በካርቱም መፈረሙ ይታወቃል፡፡ (ምንጭ፦ ሽንዋ)
https://waltainfo.com/am/33324/
105
5ፖለቲካ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከሳዑዲ  አልጋወራሽ ሞሃመድ ቢን ሳልማን ጋር በስልክ ተወያዩ
ፖለቲካ
August 19, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከሳዑዲ አረቢያ አልጋወራሽ ሞሃመድ ቢን ሳልማን ቢን አብዱላዚዝ ጋር በስልክ ተወያይተዋል፡፡በዚህን ወቅት የሳዑዲው አልጋወራሽ ኢትዮጵያ የሱዳን የፖለቲካ ፓርቲዎች ስምምነት እንዲፈፅሙ  የነበራትን የሸምጋይነት ሚና አድንቀዋል።በተጨማሪም ኢትዮጵያ በቀጠናው ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን የምታደርገውን ጥረት ሳዑዲ  እንደምትደግፍ መናገራቸውን የዘገበው የሳዑዲ ፕሬስ ኤጀንሲ ነው።የሱዳን ተቃዋሚዎችና ወታደራዊ ሃይል ስልጣን መጋራት የሚያስችላቸውን የመጨረሻ ስምምነት ከቀናት በፊት መፈራረማቸው ይታወሳል።
https://waltainfo.com/am/31294/
56
5ፖለቲካ
ሦስት ዓመት የነበረው የዩኒቨርሲቲ የዲግሪ መርሀ ግብር ቆይታ ወደ 4 ዓመት ከፍ እንዲል ተወሰነ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 19, 2019
Unknown
ሦስት ዓመት የነበረው የዩኒቨርሲቲ የዲግሪ መርሀ ግብር ቆይታ ወደ 4 አመት ከፍ እንዲል ተወሰነ፡፡በ2012 ዓ.ም ወደ መንግሥትም ሆነ የግል ዩኒቨርሲቲዎች የሚገቡ አዲስ የመጀመሪያ ዓመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ትምህርት የሚጀምሩት በ15 አዳዲስ ትምህርቶች መሆኑን የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ አስታውቋል።በሦስት ዓመታት ይጠናቀቅ የነበረው የዲግሪ መርሀ ግብርም ወደ አራት ዓመት ከፍ እንደሚል ነው የገለጸው።በዚህ ሂደት እንዲያልፉ የሚደረጉትም በ2012 ዓ.ም ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚገቡ ተማሪዎች እንደሆኑ ነው የተገለጸው፡፡ዩኒቨርሲቲዎቹ በ2012 ዓ.ም ለመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች የሚሰጡት የትምህር ዓይነቶች ለሁሉም የትምህርት ክፍሎች የጋራ እንደሚሆኑ ታውቋል፡፡ትምህርቶቹም ተማሪዎች በአስተሳሰብ ምጡቅ እንዲሆኑ፣ ብዝሀነትን፣ የሀገርን ባህል፣ ሀገር በቀል ዕውቀቶችንና ታሪክ እንዲያውቁ የሚያደርጉ ናቸው ብሏል ኤጀንሲው፡፡የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርት ጥራት፣ ስነምግባር እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን በሚመለከት የሀገሪቱ የትምህርት ስርዓት እንዴት ይቃኝ? በሚል ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ በምሁራን ሰፊ ጥናት ሲደረግና ሕዝብም ሲወያይበት መቆየቱን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አንዱአለም አድማሴ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ አስረድተዋል፡፡ በሂደቱም ማሻሻያ እና ለውጦች ተደርገዋል።በዚሁ መሰረትም በ2012 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ዩኒቨርሲቲ ለሚገቡ ተማሪዎች አዳዲስ የትምህርት ዓይነቶችን መስጠት እንዲችሉ ስምምነት ላይ ተደርሶ ለዚሁ ዝግጅት መደረጉን፣ አሁን ያለው ሁኔታም ትምህርቱን ለመጀመር የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል፡፡
https://waltainfo.com/am/32654/
164
0ሀገር አቀፍ ዜና
ጳጉሜ ‘ጳጉሜን በመደመር’ በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ይታሰባል
ፖለቲካ
August 21, 2019
Unknown
‘ጳጉሜን በመደመር’ በሚል መሪ ሀሳብ ሀገራዊ የመርሐ ግብር ቅድመ ዝግጅት እየተካሄደ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አስታውቋል፡፡ የመደመር ስድስት ምሰሶዎችን ባማከለ መልኩ  ጳጉሜን በመደመር ሀገር አቀፍ መርሃ ግብር መዘጋጀቱን ነው ፅህፈት ቤቱ ያስታወቀው፡፡ የተለያዩ የመንግስት አካላት የየዕለት እንቅስቃሴዎቹን ለማቀድ ፣ ለመምራት፣ ለማስተባበርና ለማስፈፀም ሀላፊነት ወስደው እየተንቀሳቀሱ መሆኑንም ጨምሮ ገልጿል እየፈፀሙ፡፡ በዚህም መሰረት  የጳጉሜን ስድስቱ ቀናት ስያሜ እና አስተባባሪዎች ይፋ የሆኑ ሲሆን ጳጉሜን 1 ብልፅግናን የወከለ ሲሆን በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አስተባባሪነት፣ ጳጉሜን 2 ደግሞ የሰላም ቀን ሲሰኝ በሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፊሪያት ካሚል እንደሚመራ ነው የተገለፀው፡፡ ጳጉሜን 3 ሀገራዊ ኩራት የሚል ስያሜን ሲሰጠው በማስተባበር በኩል የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ሀላፊነቱን ወስደዋል፡፡ ጳጉሜን 4 ዲሞክራሲ የሚል ስያሜን በትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ የተሰጠ ሲሆን ዕለቱን በአስተባባሪነት የሚመሩት ይሆናል፡፡ ጳጉሜን 5 የፍትህ ቀን ሆኖ እንዲታሰብና  የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ እንደሚያስተባብሩት ተመልክቷል፡፡ የመጨረሻው እና የአዲስ አመት ዋዜማው ጳጉሜን 6 ደግሞ የሀገራዊ አንድነት ቀን ሆኖ ታስቦ እንዲውል ውሳኔ ተላልፏል፡፡ ህብረተሰቡም በእነዚህ ቀናት ሰፊ ተሳትፎ በማድረግ ወደ መጪው አዲስ አመት ተስፋን ሰንቆ ለመሻገር እንዲሰናዳ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ጥሪ አቅርቧል፡፡  
https://waltainfo.com/am/31302/
171
5ፖለቲካ
ጠ/ሚ ዐቢይ በሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ሸንጎና የነፃነትና ለውጥ ኃይሎች መካከል በተደረገው የመጨረሻ የስምምነት ፊርማ ላይ ተገኙ
ፖለቲካ
August 18, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ነሐሴ 11 ቀን 2011 ወደ ሱዳን ካርቱም በመጓዝ በወታደራዊ የሽግግር ሸንጎና በነፃነትና ለውጥ ኃይሎች መካከል የተደረገውን የመጨረሻውን የስምምነት ፊርማ ተከታተሉ::ይህ የመጨረሻው ስምምነት ወታደራዊ ያልሆነ መንግስት ለመመስረት መንገድ ከፋች ነው ተብሏል::ከስምምነት ፊርማው ቀደም ብሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከነፃነትና ለውጥ ኃይሎች አባላት ጋር ተወያይተዋል:: አባላቱ  ለዚህ ስምምነት መፈረም የተጫወተችውን ሚና በማድነቅ እነዚህ ሕገ መንግስታዊና ፖለቲካዊ ስምምነቶች ለዘላቂ ዴሞክራሲያዊና ልማት መሰረት ይጥላል ብለዋል::ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በበኩላቸው፣ ይቅርታንና አንድነትን በመንከባከብ እንዲተጉ በማበረታታት ስኬታማ ውይይት መልካም መነሻ እንጂ ብዙ ስራ የሚጠይቀው መንገድ ከዚህ ቀጣዩ ነው ብለዋል::ሴቶች በፖለቲካ አመራር ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ ለዚህም አካታች እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በተያያዘም የኢትዮጵያን ልምድ በማንሳት የነፃነትና የለውጥ ኃይሉ ይህንን 50-50 የፆታ አካታች ካቢኔ እንዲተገብሩ አስታውሰዋል::በሱዳን ስምምነት ፊርማው ስነስርዓት በማስከተል ባደረጉት ንግግር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሀገሪቱ በሚደረገው የዴሞክራሲ ግንባታ ሂደት ወቅት የሱዳን ህዝቦች የሰላማቸውና የክብራቸው ተንከባካቢዎች እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል::በሱዳን ጉዞአቸው ማብቂያም ከመቶ በላይ በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ወደሌላ ሀገር ለመሻገር ሱዳን የቀሩ ኢትዮጵያውያን ሴቶችን ይዘው ተመልሰዋል:: ከነዚህም ውስጥ በተለያየ ጥፋት እስር ቤት የነበሩም ይገኙበታል ነው የተባለው፡፡ መረጃው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ነው፡፡
https://waltainfo.com/am/31293/
166
5ፖለቲካ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ በሱዳን የሽግግር መንግሥትን ምስረታ ስነ ስርዓት ላይ ለመታደም ካርቱም ገቡ
ፖለቲካ
August 17, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ  የሚመሩት ልዑክ በሱዳን የሽግግር መንግሥትን ምስረታ ስነ ስርዓት ላይ ለመታደም  ካርቱም ገብቷል።በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በማኅበራዊ ገጹ እንዳስነበበው፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመሩት ልዑክ ዛሬ ወደ ሱዳን ያቀናው በሱዳን የሽግግር መንግሥትን በይፋ ለመመሥረት በሚከናወነው ሥነ-ሥርዓት ለመታደም ነው፡፡ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ሐሰን ኦማር አልበሽር መንግሥት የሦስት አስርት ዓመታት ቆይታው በሕዝባዊ ተቃውሞ ተናግቶ ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት ሲመሠረት ሱዳን ወደ ቀውስ እንደምትገባ ብዙዎች ገምተው ነበር፡፡ነገር ግን ኢትዮጵያና የአፍሪካ ሕብረት ባደረጉት ተከታታይ ጥረት ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤቱና ሲቪል የፖለቲካ ፓርቲዎች የተሳተፉበት የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ በዚህም ሱዳን ወደ መረጋጋት እንደምትገባ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡ የሽግግር መንግሥቱ ምሥረታ ላይ ለመገኘትም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ  የሚመሩት ልዑክ ዛሬ ጠዋት ካርቱም ገብቷል፤ ደማቅ አቀባበልም ተደርጎለታል ሲል የአማራ መገናኛ ብዙሃን ነው፡፡
https://waltainfo.com/am/31292/
116
5ፖለቲካ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ የ2019 የዓለም የቱሪዝም ሽልማት አሸናፊ ሆኑ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 17, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ በሀገሪቱ ቱሪዝም ዘርፍ ባበረከቱት ከፍተኛ አስተዋፅኦ የ2019 የዓለም የቱሪዝም ሽልማት አሸናፊ መሆናቸውን በብሪታኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።ሽልማቱንም የፊታችን ህዳር ወር ላይ በለንደን ከተማ በሚካሄደው የዓለም የቱሪዝም ሽልማት ስነ ስርዓት ላይ የሚቀበሉ ይሆናል።የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ሀምሌ ወር መጨረሻ ላይ ከአለም የቱሪዝም ፎረም ፕሬዚዳንት ቡሉት ማግቺ ጋር መወያየታቸው ይታወቃል።በውይይታቸውም ተቋማቸው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2020 የሚካሄደውን የአለም የቱሪዝም ፎረም በአዲስ አበባ ለማዘጋጀት ፍላጎት እንዳለው በሉት ማግቺ መናገራቸው በማስታወስ ኤፍ ቢሲ ዘግቧል።
https://waltainfo.com/am/32652/
76
0ሀገር አቀፍ ዜና
የፅዳት ዘመቻ ተግባር ባህል ሆኖ እንዲቀጥልና ህብረተሰቡ ለሀገራዊ ጥሪ የሚያሳየው ምላሽ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገለፀ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 18, 2019
Unknown
የፅዳት ዘመቻ ተግባር ባህል ሆኖ እንዲቀጥል እና ህብረተሰቡ ለሀገራዊ ጥሪ የሚያሳየው ምላሽ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገለፀ፡፡አራተኛው ዙር ሀገር አቀፍ የጽዳት ዘመቻ ፕሮግራም በዛሬው ዕለት ተከናውኗል፡፡በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ይፋ በተደረገው እና ወር በገባ የመጀመሪያው እሁድ በመላ ሀገሪቱ  የሚከናወነው የጽዳት ዘመቻ በአዲስ አበባ ከተማ ስቴድየም እና የኦሮሞ ባህል ማከል አካባቢ ተከናውኗል፡፡የኦሮሚያ ክልል የተለያዩ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች የተሳተፉበት የፅዳት ዘመቻ በአዲስ አበባ ኦሮሞ ባህል ማእከልና አካባቢው የተካሄደ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ ስቴድየም ደግሞ የከተማው ነዋሪዎች፣ የመንግስት ባለስልጣናትና የተለያዩ ተቋማት የጽዳት ስራውን አከናውኗል፡፡የኦሮሚያ ክልል ርአሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ሴፈዲን መሀዲ ንጽህናው በተጠበቀ አካባቢ የሚኖርና  በጥሩ አስተሳሰብ የተገነባ ማህበረሰብ መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡በጽዳት መረኃግብሩ የተሳተፉ አካላትም አካባቢን ከቆሻሻ ጽዱ በማድረግ ጥላቻና መጥፎ አመለካከቶችን ማስወገድ እንደሚገባ አንስተዋል፡፡
https://waltainfo.com/am/32655/
116
0ሀገር አቀፍ ዜና
የኬንያው ፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታ በአዲስ አበባ በሚካሄደው የሰላም ፌስቲቫል ላይ ይሳተፋሉ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 18, 2019
Unknown
ፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታ ከሀገር አቀፍ የአንድነት፣ ይቅርታና ሰላም ኮሚቴ የበላይ ጠባቂ የቀድሞ የኢፌዲሪ ፕሬዚደንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ እና የኮሚቴው አባላት ጋር ባደረጉት ውይይት፤ ኢትዮጵያውያን በምንም ሁኔታ ውስጥ ሆነው የማይለወጡ እና ለድርድር የማይቀርቡ የኬንያውያን ወዳጆች ናቸው ብለዋል።ኢትዮጵያ ከቅድመ-ነጻነት ጊዜ ጀምሮ የኬንያ የቁርጥ ቀን ወዳጅ እንደሆነች ያስታወሱት ፕሬዝዳንት ኡሁሩ፤ በኢትዮጵያ በጳጉሜን 2 እና 3፣ 2011 ዓ.ም በሚካሄደው ሀገር አቀፍ የአንድነት፣ ይቅርታና ሰላም ፌስቲቫል ላይ "እንደ እንደራሳችሁ፤ እንደ ኢትዮጵያውያን ሆኜ እገኛለሁ" ብለዋል።መሪዎች ለሕዝቦቻቸው ሰላም እና ብልፅግናን እንጂ ውድቀትና ጥፋትን ማውረስ አይገባም ሲሉም ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።የሀገር አቀፍ የአንድነት፣ ይቅርታና ሰላም ፌስቲቫሉን ያዘጋጀው እና በበጎ ፈቃድ የተቋቋመው የሀገር አቀፍ የአንድነት፣ ይቅርታና ሰላም ኮሚቴ አባላት ፕሬዚደንትዶ/ር ሙላቱ ተሾመ፤ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ በኢትዮጵያ በሚካሄደው የሰላም ፌስቲባል ላይ እንዲታደሙ ጋብዘዋቸዋል።ኬንያ የኢትዮጵያ ወዳጅ ሀገር መሆኗን ያወሱት ዶ/ር ሙላቱ፤ ከኬንያ ግጭትን የማስወገድ ተሞክሮ እንዲያጋሩም ጠይቀዋል። ከፕሬዚደንቱ በተጨማሪ ለቀድሞ የኬንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ራኢላ ኦዲንጋ በፌስቲቫሉ ላይ እንዲሳተፉ ግብዣ የቀረበላቸው ሲሆን፤ ለመሳተፍ ቃል ገብተዋል።ሀገር አቀፍ የአንድነት፣ ይቅርታና ሰላም ኮሚቴ ሰላሟ እና ልማቷ የተረጋገጠ ኢትዮጵያን ለመፍጠር በሚል ዓላማ ከንግዱ ማህበረሰብ፣ ከኃይማኖት ተቋማት፣ ከስነ-ጥበብ ባለሙያዎች፣ ከወጣቶች እና ከሲቪል ማህበረሰብ አባላት የተዋቀረ ኮሚቴ ነው።
https://waltainfo.com/am/32653/
167
0ሀገር አቀፍ ዜና
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የተሳተፉበት የጽዳት ዘመቻ በአርሲ ዞን ኢተያ ከተማ ተካሄደ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 18, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ባህል ሆኖ እንዲቀጥል ታስቦ የሚካሄደውን አገር አቀፍ የጽዳት ዘመቻ ዛሬ በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ኢተያ ከተማ በመገኘት አከናውነዋል፡፡የጽዳት ዘመቻው የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳና የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ እንዲሁም ሌሎች የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ነው የተካሄደው።ከጽዳት ዘመቻው ቀጥሎም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከልዑካናቸው ጋር በመሆን በአርሲ ዞን ዲገሉና ጢጆ ወረዳ ሙኔሳ አካባቢዎች የኩታ ገጠም ግብርናን በመጎብኘት ላይ ይገኛሉ፡፡አገር አቀፍ የጽዳት ዘመቻው ዛሬ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ  አካባቢዎች ተካሂደዋል፡፡ (ምንጭ:-ኢዜአ)
https://waltainfo.com/am/32656/
78
0ሀገር አቀፍ ዜና
አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የደቡብ ሱዳን የፖለቲካ ፓርቲዎች ከዚህ ቀደም የደረሱትን የሰላም ስምምነት ተግባራዊ እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረቡ
ፖለቲካ
August 21, 2019
Unknown
የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የደቡብ ሱዳን የፖለቲካ ፓርቲዎች ከዚህ ቀደም የደረሱትን የሰላም ስምምነት ተግባራዊ በማድረግ ወደ ተጨባጭ እንቅስቃሴ እንዲገቡ ጥሪ አቅርበዋል።ሚኒስትሩ ጥሪያቸውን ያቀረቡት የደቡብ ሱዳን የፖለቲካ ፓርቲዎቸ ከዚህ ቀደም የደረሱትን የቅድመ ሽግግር የሰላም ስምምነት አፈፃፀም ሂደት ለመገመገም የተጠራው ስብሰባ ዛሬ አዲሰ አበባ በሚገኘው ኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል በተጀመረበት ወቅት ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ነው።የቅድመ ሽግግር ጊዜው የደቡብ ሱዳን ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች በተገኙበት እኤአ ሜይ 12 ቀን 2019 ዓም በአዲስ አበባ ባደረጉት ውይይት በደረሱት ስምምነት መሰረት እስከ ኖቬምበር 2019 ዓም ድረስ ለ6 ወራት ያህል መራዘሙ ይታወቃል።ስምምነቱ እንዲራዘም መግባባት ላይ ከተደረሰ ጊዜ አንስቶ ወደ ሌላ አገር የተሰደዱ የደቡብ ሱዳን ህዝቦች እና ተቃዋሚ ሃይሎች ወደ ጁባ በመመለስ መኖር መጀመራቸው በፓርቲዎች መካከል መተማመን የፈጠረ መሆኑን እንዲሁም በደቡብ ሱዳን ያለው ግድያ እና ተኩስ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ በደቡብ ሱዳን ሰላምን ለማስፈን አበረታች ጅምር መሆኑን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው ገልጸዋል።ይሁን እንጂ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ተግባራዊ መደረግ ያለባቸው ዋና ዋና ጉዳዮች ማለትም የጋራ የፀጥታ ሃይል ምስረታ፣ የሰው ሃይል ስልጠናና ስምሪት፣ የክልላዊ መንግስታትን ቁጥር የመወሰንና መስል ስራዎች አፈፃፀም አዝጋሚና ዝቅተኛ መሆኑን በማስታወስ ሁሉም ፓርቲዎች ለደቡብ ሱዳን ህዝብ ጥቅም ሲሉ ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ ቁርጠኛ እንዲሆኑ ክቡር ሚኒስትሩ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።በዛሬው ውይይት የደቡብ ሱዳን የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የኢጋድ አባል አገራት፣ የኢጋድ ባለድርሻ አካለት ፎረም፣ የትሮይካ፣ የቻይና፣ የውሮፓ ህብረት፣ የአፍሪካ ህብረት፣ የተባበሩት መንግስታት እና ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካለት ተወካዮች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።ስብሰባው በደቡብ ሱዳን የፖለቲካ ፓርቲዎች የተደረሰውን ስምምነት ተግባራዊ ለማደረግ የተሰሩ ስራዎችን ሪፖርት በማዳመጥ እና ቀጣይ አቅጣጫዎችን በማመላከት በዛሬው እለት እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል። መረጃው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ጽ/ቤት ነው፡፡
https://waltainfo.com/am/31301/
236
5ፖለቲካ
ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የኳታር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሀመድ ቢን አብዱልራህማን አል-ታኒን ጋር ተወያዩ
ፖለቲካ
August 20, 2019
Unknown
ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የኳታር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሀመድ ቢን አብዱልራህማን አል-ታኒን ጋር ተወያዩ፡፡ኢትዮጵያ ከኳታር ጋር ያላትን ሁለንተናዊ ግንኙነት ለማሳደግ በትምህርት፣ የመካከለኛ አመራር ደረጃን የማሳደግ ስልጠና እና የሴቶችን ሁለንተናዊ አቅም በማጎልበት ረገድ በትብብር መስራት እንደምትፈልግ ፕሬዝዳንቷ በውይይቱ ወቅት ተናግረዋል፡፡የኳታር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሀመድ ቢን አብዱልራህማን አል-ታኒ በበኩላቸው፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ግንኙነት ዘርፈ ብዙ መሆኑን አንስተው ይህንን ለማጠናከር በትምህርት፣ በጤና እና በልዩ ልዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር ለመስራት ሀገራቸው ፍላጎት እንዳላት ገልፀዋል፡፡ሚኒስትሩ አያይዘውም ኢትዮጵያ ለቀጠናው ሰላም መረጋገጥ እያደረገች ያለውን እንቅስቃሴ አድንቀው በተለይ በቅርቡ በሱዳን መረጋጋትና በሰላማዊ የስልጣን ክፍፍሉ ላይ የነበራትን ሚና ልዩ ቦታ የሚሰጠው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ መረጃው የፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ነው፡፡
https://waltainfo.com/am/31299/
107
5ፖለቲካ
በኬንያ ሠርግ ከታደሙ መካከል አንድ ሰው በኮሌራ ሲሞት 40 ሰዎች ሆስፒታል መግባታቸው ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 16, 2019
Unknown
በኬንያ መዲና ናይሮቢ ባለፈው ቅዳሜ በተከናወነ የሠርግ ሥነ ሥርዓት ላይ ከታደሙት መካከል አንድ ተጋባዥ በኮሌራ ሳቢያ ሕይወቱ ሲያልፍ ሌሎች 40 የሚሆኑት ለሕክምና ሆስፒታል መግባታቸውን ዘ ስታር የተባለው ጋዜጣ ዘገበ።ጋዜጣው ጭምሮ እንደገለፀው የሠርጉ ተጋባዦች የሕክምና ምርመራ ውጤት እንደሚያሳየው ተጋባዥ እንግዶቹ ሠርጉን ከታደሙ በኋላ ለኮሌራና የምግብ መመረዝ እንደተዳረጉ ያሳያል።አዲስ ተጋቢ ጥንዶቹ ግን ምንም ዓይነት የጤና መቃወስ ያልገጠማቸው ሲሆን፣ በሠርጋቸው ዕለትም ለጫጉላ ሽርሽር ወደ ዱባይ በረዋል።ይሁን እንጂ የሙሽራው አያት በዚሁ ምክንያት ባሳለፍነው ማክሰኞ ሕይወታቸው ማለፉ ተሰምቷል።በሠርግ ሥነ ሥርዓቱ ላይ 450 የሚሆኑ እንግዶች ተጋብዘው እንደነበር ጋዜጣው አስፍሯል።የሠርግ ሥነ ሥርዓቱ አሠናጅ ይህ ችግር እንዴት ሊከሰት እንደቻለ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል።ኮሌራ በዲያሪያ ኢንፌክሽን የሚመጣ ሲሆን ባክቴሪየም ቫይብሪኦ ኮሌራ በተባለ በሽታ አምጭ ተህዋስ ምግብና ውሃ ሲመረዝ ይከሰታል።በኬንያ የኮሌራ በሽታ መከሰት የተለመደ ባይሆንም ከሁለት ዓመታት በፊት ግን በመዲናዋ በአንድ ሆቴል በተካሄደ ዓለም አቀፍ የጤና ኮንፈረንስ ተሳታፊዎች ላይ ወረርሽኙ ተከስቶ እንደነበር ተነግሯል ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው።
https://waltainfo.com/am/33464/
136
0ሀገር አቀፍ ዜና
የተመድ ዋና ጸሐፊ እና ስምንት የአፍሪካ ሀገራት ርእሳነ መንግሥታት በሱዳን የለውጥ ስምምነት ላይ ይገኛሉ
ፖለቲካ
August 16, 2019
Unknown
የተባበሩት መንግሥታት ድርጀት (ተመድ) ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ፣ ስምንት የአፍሪካ ሀገራት ርእሳነ መንግሥታት፣ የአውሮፓ ኅብረት ፕሬዚዳንት እንዲሁም የአረብ እና የምዕራባውያን ሀገራት መሪዎች ቅዳሜ ዕለት በሱዳን በሚደረገው የፖለቲካ ለውጥ እና ሕገ-መንግሥት የማፅደቅ ስምምነት ላይ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።የሱዳን የነፃነት እና የለውጥ ኃይሎች እና የወታደራዊ ሽግግር ምክር ቤት ታሪካዊ የተባለውን ስምምነት ለማድረግ መስማማታቸው ይታወሳል።በስምምነት ፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ይገኛሉ ተብለው የሚጠበቁት የወቅቱ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር የሆኑት የግብጹ ፕሬዚዳንት አብደል ፋታህ ኤል-ሲሲ፣ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፣ የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ፣ የዩጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ፣ የቻድ ፕሬዚዳንት ኢድሪስ ዴቢ እና የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ሞሳ ፋቂ ናቸው።በዚህ ታሪካዊ ስምምነት ላይ የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካዮች፣ ስድስት ሀገራትን ያከተተው የገልፍ ኅብረት ምክር ቤት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና ሌሎች የባሕረ-ሰላጤ ሀገራት መሪዎች እንደሚገኙም ይጠበቃል።ቅዳሜ ዕለት ለሚደረገው ሕገ-መንግሥት የማፅደቅ ስምምነት ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል፤ ስምምነቱ የወታደራዊ ሽግግር ምክር ቤት ሊቀበንበር አብዴል ፋታህ አል-ቡርሃንን የመጀመሪያው የሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ያደርጋቸዋል ተብሏል።(ምንጭ፦አልሸርቅ አል-አውሳጥ)
https://waltainfo.com/am/33323/
143
5ፖለቲካ
የፌዴራል ፖሊስ፣ ፀረ ሙስና ኮሚሽንና ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ
ቢዝነስ
August 16, 2019
Unknown
የፌዴራል ፖሊስ፣ ፀረ ሙስና ኮሚሽንና ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ሙስና ጨርሶ እንዳይፈፀም በጋራ ለመከላከልና ተፈፅሞም ሲገኝ ለመመርመር የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ስምምነቱ በዋናነት የተደራጀ የፀረ ሙስና ዘመቻ ለማድረግ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡በተለይም በአገሪቱ የሚስተዋለውን ከፍተኛ የሆነ የሙስና ተጋላጭነት ለመቀነስ የሚያስችል ስምምነት መሆኑም ተገልጿል፡፡ሙስናን የሚፀየፍ ትውልድ ለመፍጠር በሚደረገው አገራዊ ጥረት ሶስቱም ተቋማት ተጠናክረው ተግባሩን በጋራ ለመከላከል በቅንጅት እንደሚሰሩ ተገልጿል፡፡የምርመራውን ስራ ፌዴራል ፖሊስ፣ የመክሰሱን ስራ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ እንዲሁም ሙስናን የመከላከሉንና የማስተማሩን ስራ ፀረ ሙስና ኮሚሽን እንደሚሰሩ የሚታወቅ ሲሆን፣ ይህንኑ በቅንጅት ለመስራት ነው ስምምነቱ የተፈረመው፡፡ፀረ ሙስና ኮሚሽን ሙስናን ለመከላከል ደክሟል በሚል በህብረተሰቡ ዘንድ የሚነሳውን ቅሬታ በማስተካከል በቀጣይ ሙስናን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመከላከል የሚያስችል ስራ እያከናወነ መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡
https://waltainfo.com/am/23910/
102
3ቢዝነስ
የደቡብ ክልል አደረጃጀት ጥናት የምክክር መድረክ ማጠቃለያ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው
ፖለቲካ
August 16, 2019
Unknown
የደቡብ ክልል አደረጃጀት ጥናት የምክክር መድረክ ማጠቃለያ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) በአዲስ አበባ እና በአዳማ ሲያካህድ የቆየውን የክልል አደረጃጀት ጥናት ምክክር መድረክ ማጠቃለያ በአዲስ አበባ እያካሄደ ይገኛል።በውይይት መድረኩ ላይ በፌደራል ደረጃ የሚገኙ አመራሮች እና የቀድሞ ነባር አባላት ከሰሞኑ በአዲስ አበባ ሲያካሄዱት የነበረው ውይይት እንዲሁም የአዳማው የአዲስ አበባ ከተማ የደኢህዴን አመራር መድረክ ሪፖርት ቀርቧል፡፡በዚሁም በውይይቱ ላይ የተንሸራሸሩ ሀሳቦች በየቡድን መሪዎች በሪፖርት መልክ ቀርበው ውይይት እየተካሄደባቸው ይገኛል፡፡መድረኩን እየመሩ የሚገኙ የደኢህዴን ሊቀ መንበርና የሰላም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈርያት ካሚል፣ ውይይቶቹ አመራሮቹን በአንድነት ውስጥ ያለውን ሀይል እንዲገነዘቡ ያስቻለ ነው ብለዋል፡፡በዛሬው ውይይት ላይ በደቡብ ክልል የአደረጃጀት ጥናትና በመጨረሻው ምክረ-ሃሳብ ላይ የተስተዋሉ ክፍተቶች መኖራቸውንና ሌሎች የተለያዩ ወቅታዊ ጥያቄዎች ከተሳታፊዎች ተነስተዋል፡፡ሰሞኑ ከክልል ውጭ ባሉ የደኢህዴን አመራሮች ደረጃ የደቡብ ክልል የአደረጃጀት ጥናት ዙሪያ ውይይት ሲካሄድ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡
https://waltainfo.com/am/31291/
124
5ፖለቲካ
በሀገሪቱ የሚፈጠሩ ግጭቶችንና አለመረጋጋትን ለመፍታት የሴቶችን ከፍተኛ ሚና መጠቀም እንደሚገባ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 16, 2019
Unknown
በሀገሪቱ የሚፈጠረውን ግጭትና አለመረጋጋት ከመፍታት ረገድ ሴቶች ያላቸውን ሚና በሚመለከት ውይይት ተደረገ፡፡በኢትዮጵያ ሴቶች ፌደሬሽንና ሰላም ሚኒስቴር ባዘጋጀው በዚህ መድረክ ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ሴቶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡በውይይት መድረኩ ግጭቶችና አለመረጋጋቶች ሲፈጠሩ የመጀመሪያ ተጎጂዎች ሴቶች የመሆናቸውን ያህል ችግሮችን ለመፍታት ደግሞ ሴቶች ከየትኛውም የህብረተሰብ ክፍል በላይ ቅርበት አላቸው ተብሏል፡፡ሴቶች ልጆቻቸውን፣ ባሎቻቸውና ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎችን በቅርበት የማግኘት ዕድሉ ስላላቸው ችግሮችን መፍታት እንደሚችሉም ተገልጿል፡፡በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች የተፈጠሩ ችግሮችን ከመቅረፍ ረገድና ሰላም እንዲሰፍን ሴቶች ጉልህ ሚና እንደነበራቸውም ተጠቁሟል፡፡በውይይቱ ላይ የተገኙት የእርቀ ሰላም ኮሚሽን ምክትል ሰብሳቢ ሎሬት የትነበርሽ ንጉሴ፤ ቀደም ባሉት ጊዜያት በሀገሪቱ በነበረው አለመረጋጋት ሴቶች የሚጠበቅባቸውን ያህል ሚናቸውን አልተወጡም ብለዋል፡፡በመሆኑም ይህንን ታሳቢ በማድረግ በቀጣይ በሀገሪቱ ሰላን በማስጠበቅ በኩል ሴቶች ተፈጥሯዊ ፀጋዎችን በመጠቀምና ማህበራዊ ኃላፊነትን በመወጣት ድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡
https://waltainfo.com/am/32651/
114
0ሀገር አቀፍ ዜና
የኬንያው ፕሬዚደንት ጳጉሜ 2 እና 3 በአዲስ አበባ በሚካሄደው የሰላም ፌስቲቫል ላይ እንደሚሳተፉ አስታወቁ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 17, 2019
Unknown
የኬንያው ፕሬዚደንት ጳጉሜ 2 እና 3 በአዲስ አበባ በሚካሄደው የሰላም ፌስቲቫል ላይ እንደሚሳተፉ አስታወቁፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታ ከሀገር አቀፍ የአንድነት፣ ይቅርታና ሰላም ኮሚቴ የበላይ ጠባቂ የቀድሞ የኢፌዲሪ ፕሬዚደንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ እና የኮሚቴው አባላት ጋር ባደረጉት ውይይት፤ ኢትዮጵያውያን በምንም ሁኔታ ውስጥ ሆነው የማይለወጡ እና ለድርድር የማይቀርቡ የኬንያውያን ወዳጆች ናቸው ብለዋል።ኢትዮጵያ ከቅድመ-ነጻነት ጊዜ ጀምሮ የኬንያ የቁርጥ ቀን ወዳጅ እንደሆነች አስታውሰው፤ በጳጉሜን 2 እና 3፣ 2011 ዓ.ም. በሚካሄደው ሀገር አቀፍ የአንድነት፣ ይቅርታና ሰላም ፌስቲቫል ላይ እንደ ኢትዮጵያውያን ሆኜ እገኛለሁ ብለዋል።መሪዎች ለሕዝቦቻቸው ሰላም እና ብልፅግናን እንጂ ውድቀትና ጥፋትን ማውረስ አይገባም ሲሉም ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።የሀገር አቀፍ የአንድነት፣ ይቅርታና ሰላም ፌስቲቫሉን ያዘጋጀው እና በበጎ ፈቃድ የተቋቋመው የሀገር አቀፍ የአንድነት፣ ይቅርታና ሰላም ኮሚቴ አባላት ፕሬዚደንትዶ/ር ሙላቱ ተሾመ፤ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ በኢትዮጵያ በሚካሄደው የሰላም ፌስቲባል ላይ እንዲታደሙ ጋብዘዋቸዋል።ኬንያ የኢትዮጵያ ወዳጅ ሀገር መሆኗን ያወሱት ዶ/ር ሙላቱ፤ ከኬንያ ግጭትን የማስወገድ ተሞክሮ እንዲያጋሩም ጠይቀዋል።ከፕሬዚደንቱ በተጨማሪ ለቀድሞ የኬንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ራኢላ ኦዲንጋ በፌስቲቫሉ ላይ እንዲሳተፉ ግብዣ የቀረበላቸው ሲሆን፤ ለመሳተፍ ቃል ገብተዋል።ሀገር አቀፍ የአንድነት፣ ይቅርታና ሰላም ኮሚቴ ሰላሟ እና ልማቷ የተረጋገጠ ኢትዮጵያን ለመፍጠር በሚል ዓላማ ከንግዱ ማህበረሰብ፣ ከኃይማኖት ተቋማት፣ ከስነ-ጥበብ ባለሙያዎች፣ ከወጣቶች እና ከሲቪል ማህበረሰብ አባላት የተዋቀረ ኮሚቴ ነው።
https://waltainfo.com/am/33465/
174
0ሀገር አቀፍ ዜና
በ2045 ሁለቱ ኮሪያዎች የመዋሃድ እድል እንዳላቸው የደቡብ ኮሪያው ፕሬዚዳንት ሙን ጃ-ኢን ተናገሩ
ፖለቲካ
August 15, 2019
Unknown
የሁለተኛው የዓለም ጦርነት 100ኛ ዓመት በሚከበርበት እ.አ.አ 2045 ላይ ሁለቱ ኮሪያዎች የመዋሃድ እድል እንዳላቸው የደቡብ ኮሪያው ፕሬዚዳንት ሙን ጃ-ኢን ተናገሩ፡፡ፕሬዚዳንት ሙን ይህንን ያሉት ኮሪያ እ.አ.አ ከ1910-1945 ባሉት ዓመታት ውስጥ ከነበረችበት የጃፓን አገዛዝ ነፃ የወጣችበትን 74ኛ ዓመት ክብረ በዓል አስመልክቶ ነው።ሙን በሰሜን ኮሪያው ኪም ጆንግ ኡን እና በአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ መካከል ከኒዩክሌር ነፃ መሆን በተመለከተ በአጭር ጊዜ ውስጥ አራተኛ ውይይት እንዲካሔድ እየገፋፉ ይገኛሉ።ከኒዩክሌር ነፃ መሆን እና ከሰሜን ኮሪያ ጋር ጠንካራ ኢኮኖሚያዊ ትብብር ማድረግ በሰላጤው ዘላቂ ሰላም ለማምጣት የሚያስችል መሠረት ለመጣል ወሳኝ ነው ብለዋል።ሙን፣ ሴኡል እና ፒዮንግያንግ እ.አ.አ በ2032 በጋራ ኦሎምፒክን እንዲያዘጋጁ ለማድረግ እና እ.አ.አ በ2045 የሁለቱን ኮሪያዎች ውሕደት እውን ለማድረግ ቃል ገብተዋል።በመጨረሻም፣ “ለራሷ፣ ለምሥራቅ እስያ እና ለዓለም ሰላም እና ብልጽግና የምታመጣ አዲሲቷን የኮሪያ ሰላጤ እየጠበቅን ነው” በማለት ሐሳባቸውን ደምድመዋል። (ምንጭ:-ዘጋርዲያን)
https://waltainfo.com/am/33985/
120
5ፖለቲካ
በአዳማ ሲካሄድ የቆየው የደኢህዴን ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች መድረክ ተጠናቀቀ
ፖለቲካ
August 15, 2019
Unknown
በአዲስ አበባ የሚገኙ የደኢህዴን ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በአዳማ ያካሄዱት መድረክ ተጠናቋል፡፡አመራሮቹ በደቡብ ክልል የክልል አደረጃጀት አስመልክቶ ይፋ በተደረገው ጥናት ላይ ተወያይተዋል፡፡በደቡብ ክልል የክልል አደረጃጀት ጥያቄዎችን ለመመለስ የተጠናዉ ጥናት የዜጎችን ህገ መንግስታዊ መብት የሚጥስ አለመሆኑም ተብራርቷል፡፡ የደኢህዴንና የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ተስፋዬ በልጅጌ፤ ደኢህዴን የህዝቦችን ጥያቄ በግምት ሳይሆን በእውቀት ላይ ተመስርቶ በጥናት ለመመለስ በ10ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ በመነሳት በሀገር ደረጃ አዲስ ልምድ ይዞ የመጣና አማራጭ ሃሳቦችን እያበረከተ የሚገኝ መሆኑን ገልፀዋል፡፡የክልሉ 2011 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም የተገመገመ ሲሆን፤መድረኩ ብሄራዊና ሀገራዊ ማንነትን አጣጥሞ ለመሄድ መግባባት የተፈጠረበት መሆኑ ተገልጿል፡፡ለአራት ቀናት በቆየው በዚህ መድረክ ከክልል አደረጃጀት ጥያቄ በተጨማሪ በወቅታዊ፣ አገራዊ፣ ክልላዊ እና በከተማው የፖለቲካዊና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር  አድርገዋል፡፡በምክክር መድረኩ ከ1 ሺህ በላይ በአዲስ አበባ የሚገኙ የድርጅቱ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ 
https://waltainfo.com/am/31290/
119
5ፖለቲካ
ሰሜን ኮሪያ ከደቡብ ኮሪያ ጋር እንደማትደራደር አሳወቀች
ፖለቲካ
August 16, 2019
Unknown
ሰሜን ኮሪያ "በደቡብ ኮሪያ ያልተገባ ድርጊት ምክንያት" በሚል ሰበብ ከደቡብ ኮሪያ ጋር ልታደርግ የነበረውን ቀጣይ ድርድር እንደማታካሂድ አሳወቀች።ሰሜን ኮሪያ እዚህ ውሳኔ ላይ መድረሷን ያሳወቀችው የደቡብ ኮሪያው ፕሬዝዳንት ሙን ጃኢን ትናንት ሐሙስ ያደረጉትን ንግግር ተከትሎ ነው።ይህ በእንዲህ እንዳለ ዛሬ አርብ ሰሜን ኮሪያ ሁለት ሚሳኤሎችን ወደ ምሥራቃዊ የባሕር ዳርቻዋ በመተኮስ ሙከራ ማድረጓን የደቡብ ኮሪያ ሠራዊት አሳውቋል። ይህም ሙከራ ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ ለስድስተኛ ጊዜ መሆኑ ታውቋል።ይህ ተከታታይ የሰሜን ኮሪያ የሚሳኤል ሙከራ የተደረገው ባለፈው ሰኔ ወር ላይ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ከሰሜን ኮሪያው መሪ ጋር ባደረጉት ውይይት የኒዩክሌር ጦር መሳሪያዎችን ለማስወገድ ውይይት ለመጀመር ከተስማሙ በኋላ ነው።የደቡብ ኮሪያው ፕሬዝዳንት ሃገራቸው ከጃፓን ነጻነቷን ያገኘችበትን ቀን በተከበረበት ወቅት ሁለቱ ኮሪያዎች በአውሮፓዊያኑ 2045 እንደሚዋሃዱ በመናገራቸው ነው ሰሜን ኮሪያ ቁጣዋ የተቀሰቀሰው።በቴሌቪዥን በተላለፈው ንግግር "ለራሱና ለምሥራቅ እስያ ብሎም ለዓለም ሰላምና ብልጽግናን የሚያመጣው አዲሱ የኮሪያ ልሳነ ምድር ከፊታችን እየጠበቀን ነው" ሲሉም ተናግረዋል- ፕሬዝዳንቱ።ሰሜን ኮሪያ፣ ደቡብ ኮሪያና አሜሪካ እያካሄዱት ባለው የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ላይ ተቃውሞዋን ያሰማች ሲሆን፣ ይህም ከፕሬዝዳንት ትራምፕና ከሙን ጃኢን ጋር ቀደም ሲል ያደረጉትን ስምምነት የሚጥስ መሆኑን በመግለጫዋ ላይ ጨምራ ገልጻለች።የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት በጻፉት ደብዳቤ ላይ ከፍተኛ ወጪ ስለሚወጣበት የደቡብ ኮሪያና የአሜሪካ የጦር ልምምድ ቅሬታቸውን ገልጸው ነበር።የሰሜን ኮሪያ የውህደት ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እንደተናገሩት፣ አካባቢውን ከኒዩክሌር ጦር መሳሪያ ነጻ ለማድረግ የተጀመረው ንግግር መቋጫ እንዳያገኝ ደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ልምምዱን ማድረጓ ዋኛው ምክንያት ነው ሲሉ ተናግረዋል። (ምንጭ፡-ቢቢሲ)
https://waltainfo.com/am/33986/
209
5ፖለቲካ
ህንድ ግዛቶቿን ወደ ነበረበት ለመመለስ በቁርጠኝነት እንደምትሰራ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ገለጹ
ፖለቲካ
August 15, 2019
Unknown
ህንድ ግዛቶቿን በተመለከተ ወደ ነበረበት ታሪክ ለመመለስ በቁርጠኝነት እንደምትሰራ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ገለጹ፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ የካሽሚር ጉዳይ በተለየ መልኩ የሚታይ እና ለሀገራቸው የህልውና ጉዳይ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡የካሽሚር ግዛት ህንድ በኢንግለዝ ቅኝ ግዛት ከመገዛቷ በፊት የህንድ እንደነበረች የሚነገር ሲሆን፣ ሀገሪቱ በቅኝ ግዛት ስር መውደቋን ተከትሎ በቀጠናው ላይ መበጣጠስ ሲመጣ ጊዛቲቱ በተለያዩ ሀገራት ማለትም በፓኪስታን እና በህንድ ስር ተከፋፍላለች፡፡ታዲያ ህንድ የካሽሚርን ግዛት በተመለከተ በተለያዩ ጊዜያቶች የተለያዩ እርምጃዎችን ስትወስድ የቆየች ብትሆንም በዘላቂነት ችግሩን ለመፍታት አልቻለችም፡፡ በዚህ ጉዳይ የካሽሚር ነዋሪዎች ለሚያነሱት ጥያቄ ህንድ መልስ ለመመለስ መጣር ብቻ ሳይሆን ከጎሮቤቷ ፓኪስታን ጋርም እሰጣ ገባ ውስጥ እንድትገባ አድርጓታል፡፡የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በሰጡት ጋዜጣዊ መግልጫ ሀገራቸው ህንድ ወደ ነበረችበት የቀድሞ ታሪክ መመለስ አለባት፤ ለዚህም መንግስታቸው በቁርጠኝነት ይሰራል ሲሉ መናገራቸው ተገልጸዋል፡፡ህንድ ከኢንግሊዝ ነፃ የወጣችብትን 70ኛ እና ከፓኪስታን የተለያየችበትን የነፃነት ዓመት ስታከብር ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የካሽሚር ግዛት በህንድ ሉዓላዊነት እና ለእድገቷ ወሳኝ ሚና የምትጫወት ነች፤ ስለዚህም ሀገራቸው ከዚህ በኋላ ያለማመንታት ካሽሚር ወደ ቀድሞ ማንነቷ ትመለሳለች ማለታቸዉን የወጡት ዘገባዎች አስነብበዋል፡፡ናሬንደራ ሞዲ ሀገራቸው ሁሉን በልኩ ሊስተካክል የሚያስችል ህገ መንግስት እንዳላት ተናግረው ነገሮች ሁሉ በዛ ይስተካከላል ብለዋል፡፡ በጉዳዩ ከህንድ ጋር እሰጣ ገባ ውስጥ ያለችው ፓኪስታን ህንድ ለመውሰድ ለምተዘጋጀው እርምጃ አፀፋዊ መልስ ለመስጠት ዝግጁ ነኝ ብላለች፡፡የፓኪስታኑ ጠቅላይ ሚንስትር ኢምራን ካሃን እስከ መጨረሻው እስትንፋስ ድረስ ለመፋለም ተዘጋጅተናል ማለታቸዉን ቢቢሲ አስንበቧል፡፡የዓለም ሁሉ ዓይን በካሽሚር እና በፓኪስታን ላይ ነው፡፡ ህንድ ስለምታደርገው ነገር ሃይ ባይ ባጣችበት ውቅት ላይ እኛ ለእርምጃ ተዘጋጅተናል፡፡ ነገር ግን ለሚሆነው ሁሉ ኃላፊነቱን የዓለም ማህበረስብ ራሱ ይወስዳል ብለዋል ጠቅላይ መኒስትር ኢምራን ከሃን፡፡ በዚህ መልስ ግን ናሬንድራ ሞዲ ያሉት ነገር የለም ነው የተባው፡፡(ምንጭ፡-አልጀዚራ፣ ቢቢሲ እና ኢንዲያን ቱደይ)
https://waltainfo.com/am/33984/
245
5ፖለቲካ
ሩዋንዳ በትምህርት የወጣቶችን ስብዕና በመገንባት ውጤታማ ሆናለች -ተመድ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 15, 2019
Unknown
በሩዋንዳ የተዘረጋው የትምህርት መርሀ ግብር የወጣቶችን ስብዕና በመገንባት ውጤታማ እየሆነ ስለመሆኑ ተነግሯል፡፡የዓለም ወጣቶች ቀን በዚህ ሳምንት በመላው አለም እየተከበረ ይገኛል፡፡ወጣቶችን በትምህርት በማብቃት ማህበራዊ ለውጡን ማገዝ በሚለው መርህ መሰረት ሩዋናዳ  ይበል የሚያሰኝ ለውጥ ስለማስመዝገቧ ተዘግቧል፡፡የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ በማህበራዊ፤ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ረገድ ማስፋት ዓለም እየገጠማት ላለው ችግር ሁነኛ መፍትሄ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ትምህርት ዋነኛ የአመለካከት ለውጥ መሳሪያ መሆኑን ተከትሎም ሩዋንዳውያን ወጣቶች የለውጡን ፈር እየተከተሉ ስለመሆናቸው  ነው የሀገሪቱ መንግስት ይፋ ያደረገው፡፡በዓለም አቀፍ ደረጃ 1 ነጥብ 8 ቢሊዮን ዜጎች እድሜያቸው ከ10 እስከ 24 ውስጥ እንደሚገኝ መረጃዎች የሚያመላክቱ ሲሆን፤ ከዚህ ውሰጥ 226 ሚሊየኑ በአፍሪካ  ይገኛሉ፡፡ሩዋንዳም 60 በመቶ ዜጎቿ እድሜያቸው ከ 25 በታች መሆኑን ተከትሎ በትምህርት እንዲዘልቁ በማድረግ በኩል አበክራ በመስራቷ የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ተቋም ዪኒስኮ እውቅና ችሯታል፡፡ባሁኑ ሰዓት ከዓለማችን 262 ሚሊዮን ህጻናትና ወጣቶች ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጥናት ማመላከቱን ተከትሎ ሩዋንዳ ፍታዊ የትምህርት ተደራሽነትን ማሰካቷ ወደኋላ ለቀሩት ሀገራት ተምሳሌት እንድትሆን አሰችሏታል፡፡ከሁለት አመታት አስቀድሞ ይፋ ያደረገቸው የሰባት አመት የትምህርት ማሻሻያ ስትራቴጂ ለውጤቱ እንዳበቃት በመረጃው ተጠቅሷል፡፡ እየተመዘገብ ባለው ውጤት መሰረትም ተመድ አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ ነው ሲል ዘ ኒው ታይምስ ድረ ገጽ ዘግቧል፡፡
https://waltainfo.com/am/33463/
167
0ሀገር አቀፍ ዜና
ሰላሟ የተረጋገጠ ሀገር ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የወጣቱ ሚና የጎላ ሊሆን ይገባል ተባለ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 15, 2019
Unknown
በኢትዮጵያ የአብሮነት እሴት ተጠብቆ እንዲቀጥልና ሰላሟ የተረጋገጠ ሀገር ለመገንባት በሚደረገው ጥረት 70 በመቶውን የሚሸፍነው ወጣት ሚና የጎላ ሊሆን ይገባል ተባለ፡፡ከሁሉም ክልሎችና ከሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የተወጣጡ 1 ሺህ 400 ወጣቶች የተሳተፉበት አገር አቀፍ የወጣቶች የሰላምና የአንድነት ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ነው፡፡የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ አልማዝ መኮንንእንዳሉት፤ ወጣቱ በሰላም፣ ሀገር ግንባታ እና ዴሞክራሲ ያለውን ሚና በአግባቡ መወጣት አለበት ብለዋል፡፡ሰላምን እውን ለማድረግ ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ ሊቀመጥ አይገባም ያሉት ሚኒስትር ድኤታዋ፤ ሁሉም ጥያቄ በሰላም ማዕቀፍ ውስጥ ምላሽ ሊያገኝም እንደሚገባ ነው የገለጹት።የኢትዮጵያ ወጣቶች ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ታረቀኝ አብዱልጀባር በበኩላቸው፤ ወጣቱ ሰላምን ለማስጠበቅ በሚደረገው ስራ ግንባር ቀደም መሆን ይኖርበታል ብለዋል።የሰላም እጦት ዋነኛ ሰለባ ወጣቱ እንደመሆኑ ለሰላም ዘብ ሊቆም እንደሚገባም  የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ገልጸዋል፡፡ “ወንድማማችነትን በማጎልበት ዘላቂ ሰላምን እናረጋግጣለን” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው መድረክ በሰላም ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ ወጣቶች ፌዴሬሽን  ትብብር በጋራ የተዘጋጀ ነው፡፡መድረኩ በውይይት የሚያምንና ጥያቄውን በሰላማዊ መንገድ የሚያቀርብ ትውልድ መፍጠርን ትኩረት አድርጎ መዘጋጀቱም ተገልጿል።  
https://waltainfo.com/am/32650/
140
0ሀገር አቀፍ ዜና
የሚኒስትሮች ም/ቤት በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ተዘጋጅተው በቀረቡ ልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳለፈ
ቢዝነስ
August 15, 2019
Unknown
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባካሄደው 16ኛ አስቸኳይ ስብሰባ በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ተዘጋጅተው በቀረቡ ልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡በዚህም መሠረት የመንግስት ሠራተኞች የሥራ መደቦች ምዘና፣ ደረጃዎች ምደባና የደመወዝ ስኬል ረቂቅ ደንብ፣ ወደ ነጥብ የሥራ ምዘና ሥርዓት ለማሸጋገር በቀረበ ውሳኔ የመንግስት ሠራተኞች የደመወዝ ስኬል ጥናትና የውሳኔ ሃሳብ እና የጡረታ አበል ተመን በተመለከተ ለሚኒስትሮቸ ምክር ቤት በቀረቡ ጉዳዮች ላይ በዝርዝር ከተወያየ በኋላ አንዳንድ ማሻሻዎችን በማከል ከሀምሌ 1 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ በሥራ ላይ እንዲውሉ ወስኗል፡፡(ምንጭ፡-ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት)
https://waltainfo.com/am/23908/
76
3ቢዝነስ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ መልዕክተኛ ጋር ተወያዩ
ፖለቲካ
August 14, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሽንዞ አቤ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ዮሽፉሚ ኦካሙራ ጋር ዛሬ ተወያይተዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩና ልዩ መልዕክተኛው የሁለቱ አገራት ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከርና በአፍሪካ የአከባቢ ሰላም ጉዳዮች ላይ አብሮ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡(ምንጭ:-ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት)
https://waltainfo.com/am/31289/
39
5ፖለቲካ
የሴት ልጅ ግርዛትና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ሙሉ ለሙሉ ለማስቆም የተዘጋጀው ፍኖተ ካርታ ይፋ ሆነ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 14, 2019
Unknown
ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የሴት ልጅ ግርዛትና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ሙሉ ለሙሉ ለማስቆም የተዘጋጀውን ፍኖተ ካርታ ይፋ አደረጉ፡፡ፕሬዝዳንቷ ኢትዮጵያ በ2025 የሴት ልጅ ግርዛትንና ያለ ዕድሜ ጋብቻን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የያዘችውን ዕቅድ ለማሳካት ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።ባለፉት አምስት አመታት ሲዘጋጅ የቆየውና በቀጣዮቹ አምስት አመታት የሚተገበር ሀገራዊ  የጸረ ሴት ልጅ ግርዛትና ያለዕድሜ ጋብቻ ፍኖተ ካርታ በዛሬው ዕለት ይፋ ሆኗል፡፡በስነሥርዓቱ ላይ የተገኙት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የሴት ልጅ ግርዛትና ያለዕድሜ ጋብቻ ሴቶችን ለዕድሜ ልክ ችግር የሚዳርግ በመሆኑ፤ አሁን የተዘጋጀው ፍኖተ ካርታ ኢትዮጵያ ችግሩን ለመፍታት ያላትን ቁርጠኝኘት ያሳያል ብለዋል፡፡ባለድርሻ አካትና ህብረተሰቡ ለፍኖተ ካርታው ስራ ስኬት የበኩላቸውን እንዲያበረክቱም ጥሪ አቅርበዋል፡፡የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስትር ወ/ሮ ያለም ፀጋይ በበኩላቸው፤ የሴት ልጅ ግርዛትና ያለዕድሜ ጋብቻ በመላው ሀገሪቱ ያለ ችግር መሆኑን አንስተዋል። ፍኖተ ካርታውን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለማከናወን  ሰፊ ማህበራዊ ንቅናቄ እንደሚደረግና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋርም በጋራ እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡ፍኖተ ካርታውን ለማስፈጸም ሶስት ቢሊየን ብር እንደሚያስፈልግም በመድረኩ ላይ ተጠቁሟል፡፡
https://waltainfo.com/am/32649/
141
0ሀገር አቀፍ ዜና
በግንባታ ላይ የሚደርስ አደጋን ለመከላከል የወጡ ህጎች ባለመተግበራቸው ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰ መሆኑ ተገለጸ
ቢዝነስ
August 14, 2019
Unknown
በአዲስ አበባ በግንባታ ላይ የሚደርስ አደጋን ለመከላከል የወጡ ህጎች አለመተግበራቸው በሰራተኛው ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ከፍተኛ አድርጎታል ተብሏል፡፡የህጎቹ በትክክል አለመተግበርም የግንባታ ባለቤቶች ለሰራተኛው ደህንነት መጠበቅ ትኩረት እንዳይሰጡ አድርጓቸዋል ነው የተባለው፡፡ይህ የተባለው በአዲስ አበባ በተለይ በየካ፣ ቂርቆስ እና ቦሌ እንዲሁም የ20/80 እና የ40/60 የኮንዶሚኒየም መኖሪያ ቤቶች ግንባታ በስፋት በሚከናወኑባቸው አካባቢዎች የጤና እና ግንባታ ደህንነት ላይ የተሰራ የህዝብ አስተያየት እና ጥናት ይፋ በተደረገበት ወቅት ነው፡፡የግንባታ ባለቤቶች የደህንነት ቁሳቁሶችን አለመጠቀማቸው እና የሚጠቀሙትም ቢሆኑ ርካሽ ዋጋን ፍለጋ ጥራታቸውን እና ደረጃቸውን ያልጠበቁ መሳሪያዎችን ከውጭ አገር እያስገቡ ሰራተኛው እንዲጠቀምባቸው ማድረጋቸው በአዲስ አበባ ውስጥ በግንባታ ዘርፉ ላይ በየጊዜው የሚደርሰውን ጉዳት ከፍተኛ እንዲሆን አድርጎታል፡፡እንደ ኢቲቪ ዘገባ ዘርፉ በኢትዮጵያ ውስጥ ከ850 ሺህ በላይ የስራ ዕድል የሚፈጥር ቢሆንም፤ ለዘርፉ በቂ ትኩረት ባለመሰጠቱና እና ደህንነቱን እንዲጠብቅ ባለመደረጉ በሰራተኛው ምርታማነት ላይ ጉዳት እያስከተለ መሆኑ ተነግሯል፡፡
https://waltainfo.com/am/23907/
122
3ቢዝነስ
በሩሲያ በሮኬት ፍንዳታ የተከሰተ የጨረር መጠን ከመደበኛው በ16 እጥፍ ይልቃል ተባለ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 14, 2019
Unknown
በሩሲያ ለአምስት ሰው ሞት መንስኤ የሆነው የሮኬት ፍንዳታ በአከባቢ ያለውን የጨረር መጠን ከመደበኛው በ16 እጥፍ ከፍ እንዳደረገው ተገልጿል።የሩሲያ የኒውክሌር ኤጀንሲ በወደብ ከተማዋ ሴቬሮድቪንስክ የሮኬት ፍንዳታ ከተከሰተ በኋላ በአካባቢው ያለውን የጨረር መጠን በመለካት ይፋ አድርጓል።180 ሺህ ህዝብ በሚኖርባት ሴቬሮድቪንስክ ከተማ በሚገኙ ስድስት የሙከራ ጣቢያዎች የጨረር መጠኑ የተለካ ሲሆን፥ በዚህም የጨረር መጠኑ ከመደበኛው ከአራት እስከ 16 እጥፍ መጨመሩ ተነግሯል።መደበኛው የጨረር መጠን በሰዓት 0 ነጥብ 11 ማይክሮ ሲኤቨርት ሲሆን በአንድ ጣቢያ በሰዓት 1 ነጥብ 78 ማይክሮሲኤቨርት መመዝገቡ ተነግሯል።ይህ መጠን አደጋኛ ከሚባለው ደረጃ በታች መሆኑ የተገለፀ ቢሆንም፥ በሰው ላይ መጠነኛ ችግር ሊፈጥር እንደሚችል የኒውክሌር ባለሙያዎች ገልፀዋል፡፡ፍንዳታውን ተከትሎ የጨረር መጠኑ ከመደበኛው ከፍ ያለ እንደነበረ እና ከቆይታ በኋላ ግን ወደ መደበኛ ደረጃ መመለሱን የሴቬሮድቪንስክ ከተማ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።ባለስልጣናት ፍንዳታው በተከሰተበት አከባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች አካባውን  ለቀው እንዲወጡ ማሳሰቢያ ቢሰጡም ሌሎች የሩሲያ ባለስልጣናት ግን ውሳኔውን መቃወማቸውን የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡
https://waltainfo.com/am/34127/
130
0ሀገር አቀፍ ዜና
ሀምሌ 22 የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብ ስራ በይፋ ተጀመረ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 13, 2019
Unknown
ሀምሌ 22 የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብ ስራ በይፋ መጀመሩን የአካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡የኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት ዘገባ እንደሚያመለክተው ኮሚሽኑ በአረንጓዴ አሻራ ቀን የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብና የመተካካት ስራን ዛሬ በምስራቅ ሸዋ ዞን አደአ ወረዳ የረር የመትከያ ጣቢያ አስጀምሯል፡፡የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ፕሮፌሰር ፍቃዱ በየነ ለችግኞቹ እንክብካቤ በተደረገበት ወቅት በኮሚሽኑ ሰራተኞች የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብ ስራን አስጀምረዋል፡፡በስነስርዓቱ ላይ 100 የሚሆኑ ሰራተኞች ተሳታፊየሆኑ ሲሆን ሀገራችን ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ሀሳብ አመንጪነት አረንጓዴ አሻራ ቀን በሚል ሀምሌ 22 ቀን 2011 ዓ.ም በአንድ ጀምበር ከ 350 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል በአለም አቀፍ ደረጃ የተያዘውን ክብረወሰን መረከቧ ይታወሳል፡፡
https://waltainfo.com/am/32647/
92
0ሀገር አቀፍ ዜና
“የክልል እንሁን” ጥያቄዎችን ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ ለመፍታት እየሰራ እንደሆነ ደኢህዴን አስታወቀ
ፖለቲካ
August 14, 2019
Unknown
የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) በደቡብ ክልል የሚነሱ “የክልል እንሁን” ጥያቄዎችን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ እንደሚፈታ በአዲስ አበባ የሚገኙትን የድርጅቱን ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በአዳማ ከተማ አባ ገዳ አዳራሽ ሰብስቦ እያወያየ ባለበት ወቅት አስታዉቋል፡፡በስብሰባዉ ላይ ንግግር ያደረጉት የደኢህዴን ስራ አስፈፃሚ አባልና የአዲስ አበባ የኢህአዴግ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተበራከተ የመጣዉን “የክልል እንሁን” ጥያቄ ለመፍታት 7 ወራት የፈጀ ጥናት መካሄዱን አስታዉሰዋል፡፡አቶ ተስፋዬ እንደተናገሩት 20 አባላት ባሉት ቡድን የተካሄደዉ ጥናት ይፋ መደረጉን ተከትሎ በየደረጃዉ የሚገኙ አካላት እንዲወያዩበት ተደርጓል፡፡የዛሬዉ ዉይይት የዚሁ አካል መሆኑን የተናገሩት ኃላፊዉ በጥናቱ ላይ ግብረ-ሀሳብ ዉይይት ማድረግ፣ በክልልና ሀገርአቀፍ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ዉይይት ማድረግና የአዲስ አበባ ደህዴን ቅርንጫፍ 2011ዓ.ም አፈፃፀም ግምገማ አጀንዳዎች ናቸዉ፡፡የዉይይቱ መድረኩ ከስሜት የፀዳ፣ እዉቀትን መሰረት ያደረገና ሀገራዊና ብሄራዊ ማንነትን ባገናዘበ መልኩ እየተካሄደ መሆኑን አቶ ተስፋየ ገልፀዋል፡፡ዉይይቱ ለ 3 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ከ1005 በላይ በአዲስ አበባ የሚገኙትን የድርጅቱን ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች እየተሳተፉ ነዉ ተብሏል፡፡  
https://waltainfo.com/am/31287/
140
5ፖለቲካ
በኦሮሚያ ከልል ከ80 ሺህ በላይ ለሚሆኑ አመራሮች ስልጠና ተሰጠ
ፖለቲካ
August 14, 2019
Unknown
በስልጠናው 20 ሺህ ለሚሆኑ ከፍተኛ አመራሮች በአዳማና ጅማ ለአስራ አምስት ቀናት እነደተሰጠ የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሀላፊ አቶ አድማሱ ዳምጠው አስታዉቀዋል፡፡  በ20 ዞኖች በተመረጡ አስራ ዘጠኝ ከተሞችና በሶስት መቶ ሀያ ሶስት  ወረዳዎች በሰባት ሺ ስልሳ ስድሰት ቀበሌዎች ለሚገኑ ስልሳ ሺ አመራሮች በአጠቃላይ ከሰማንያ ሺ በላይ  ለሚሆኑ አመራሮች ስልጠናው መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡የስልጠናው ዋና አላማም በፈጣንን በተቀላጠፈ መልኩ  እየሄደ ያለውን  ለውጥ ለማስቀጠል የአመለካከትና የአገልጋይነት ስሜት ተፈጥሮ የህበረተሰቡን የመልካም አስተዳደርና መሰረታዊ ችግሮችን ለመቅረፍ ታስቦ የተዛጋጀ ነው ተብሏል፡፡በአስተሳሰብና በአመራር ሂደት ወጥ የሆነ መዋቅር መፍጠር ለውጡን ታች ድረስ በማድረስ ለክልሉም ሆነ ለሀገር የሚሰሩ በጎ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል ያስፈልጋል፡፡ለዚህ ደግሞ በእውቀትና በክህሎት የዳበረ አመራር መፈጠር ያስፈልጋል ያሉት ሃላፊው ስልጠናው እጅጉን መጥቀሙን ጠቅሰዋል፡፡ከስልጠናው በኃላም በተገኘው ግብረ መልስና በተጨባጭ  በመጣው ለውጥ ስልጠናው አመርቂ መሆኑም ተነግሯል፡፡ 
https://waltainfo.com/am/31288/
116
5ፖለቲካ
በታንዛኒያ ያላገቡ ሴቶችን ከመታለል ለመታደግ ያገቡ ወንዶች የመረጃ ቋት እንዲቋቋም ሃሳብ ቀረበ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 14, 2019
Unknown
በታንዛኒያ የዳሬሰላም ገዢ ያላገቡ ሴቶችን ከመታለል ለመታደግ ያገቡ ወንዶች የመረጃ ቋት እንዲቋቋም ሃሳብ አቅርበዋል፡፡በአጭበርባሪ ባለትዳር ወንዶች የሚሠቃዩ ሴቶችን ጉዳት መቀነስን ዓላማ ያደረገ እንደሆነ  ገዢው ፖል ማኮንዳ ተናግረዋል፡፡ባለፈው ዓመትበርካታ ያላገቡ ሴቶች ወደ ቢሯቸው በመጡበት ወቅት የችግሩን ስፋት በመረዳት  ሀሳቡ እንደመጣላቸው ፖል ማኮንዳ ገልጸዋል፡፡ሚስተር ማኮንዳ ስለ አዲሱ የመፍትሄ እቅድ  ሂደት ምንም ዓይነት ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ግን ተቆጥበዋል፡፡ገዢው አወዛጋቢ መግለጫዎችን በመስጠት እንደሚታወቁ በዘገባው ያስታወሰው ቢቢሲ ነው፡፡
https://waltainfo.com/am/33462/
63
0ሀገር አቀፍ ዜና
የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ዉጤት ከ 11፡ 30 ጀምሮ ይፋ ይሆናል
ሀገር አቀፍ ዜና
August 14, 2019
Unknown
የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ዉጤት ከ 11፡ 30 ጀምሮ ይፋ እንደሚሆን የሀገር አቀፍ የፈተናዎች ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡በዘንድሮዉ ፈተና የተቀመጡት ተማሪዎች ቁጥር በአጠቃላይ 319ሺህ 264 ሲሆን ፤ከነዚህ ዉስጥ 180ሺህ625 ወንደችና ቀሪዎቹ ደግሞ ሴቶች መሆናቸዉን ኤጀንሲ አስታዉቋል፡፡3453 ተማሪዎች በተለያየ ምክንያት ፈተናዉን አለመዉሰዳቸዉ ታዉቋል፡፡ከአጠቃላይ ተፈታኞች 48.59 ፐርሰንት የሚሆኑት ፈተናዉን ከግማሽ በላይ ያመጡ ሲሆን፤ አንድ ተማሪ ከአማራ ክልል 645 ነጥብ በማምጣት ከፍተኛ ዉጤት አስመዝግቧል፡፡
https://waltainfo.com/am/32648/
59
0ሀገር አቀፍ ዜና
የተባበሩት መንስታት ድርጅት ተጠሪ ተቋማት ለኢትዮጵያዉያን ስራ ፈላጊዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አዘጋጁ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 13, 2019
Unknown
የተባበሩት መንስታት ድርጅት ተጠሪ ተቋማት ከ1800 በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያዉያን   ስራ ፈላጊዎች ወደ ስራዉ አለም መቀላቀል በሚችሉበት ሁኔታ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አዘጋጅተዋል፡፡በመድረኩ የተገኙ ከ26ቱ የመንግስታቱ ድርጅት ተጠሪ ተቋማት የመጡ ተወካዮችም ስራ ፈላጊዎች እንዴት ስራዉን አለም መቀላቀል እንደሚችሉና በቀጣይ በየተቋማቱ የስራ እድል ማግኘት በሚችሉባቸዉ ጉዳዮች ዙሪያ ገለፃ አድርገዉላቸዋል፡፡የኢትዮጵያ የህዝብ ቁጥር ከ100 ሚልዮን በላይ እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ። ከዚህ ዉስጥም 11 ሚሊዮን የሚጠጋዉ የሀገሪቱ ዜጋ ስራ ፈላጊ እንደሆነ ይነገራል፡፡ ይህ ሳይበቃ በየዓመቱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ስራ ፈላጊዉን ማሕበረሰብ እንደሚቀላቀሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ታዲያ ይህንን የስራ አጥነት ችግር ለመቅረፍ መንግስት ጉዳዩን የሚከታተል የስራ ፈጠራ ኮሚሽን እስከማቋቋም ደርሷል፡፡ በተጨማሪ እስከሚቀጥለው ዓመት መጨረሻ ድረስ ለ3 ሚሊዮን ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ መግለፃቸዉም ይታወሳል፡፡
https://waltainfo.com/am/32646/
111
0ሀገር አቀፍ ዜና
የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ወደ መምህርነት ሙያ የሚገቡ ተማሪዎች ብቁ መሆን እንዳለባቸው ተገለፀ
ቢዝነስ
August 12, 2019
Unknown
የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገቡና በመምርነት ሙያ የሚሰለጥኑ ተማሪዎችን ውጤት መሰረት በማድረግ መመልመል እንደሚገባ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ሰልጣኖች ለመምህርነት ለመመልመል ከፍተኛ ውጤትና ፍላጎት ሊኖራቸው እንደሚያስፈልግ ነው የትምህርት ሚኒስቴር የ2011 በጀት ዓመት ሪፖርቱን ባቀረበበት ወቅት ያስታወቀው፡፡በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የቅድመ መደበኛ ትምህርትና የጎልማሶች ትምህርት ላይ በቂ ስራ አለመሰራቱም ተጠቁሟል፡፡በተለይም በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ምክንያቶች ወደ 1 ነጥብ 6 ሚሊዮን የሚሆኑ ተማሪዎች ትምህርት ማቋረጣቸው የተገለጸ ሲሆን፤ በቀጣይ መፍትሄ እንደሚበጅለት የትምህርት ሚኒስትር ዶ/ር ጥላዬ ጌቴ ገልጸዋል፡፡በ2012 በጀት ዓመት መምህራን የሚያነሷቸውን ጥያቄዎች ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ለመመለስ እንደሚሰራ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል፡፡በተለይም የመምህራንን ጉዳይ በተመለከተ ከመምህራን ማህበር ጋር በመተባበር ጥናት እየተካሄደ መሆኑንና ጥናቱ እንዳለቀ ውጤቱ ይፋ እንደሚደረግ መገለፁን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
https://waltainfo.com/am/23903/
107
3ቢዝነስ
ኢትዮጵያ እና ቻይና በ300 ሚሊየን ዶላር አዲስ የኢንዱስትሪ ፓርክ ሊገነቡ ነው
ቢዝነስ
August 13, 2019
Unknown
ኢትዮጵያ እና ቻይና በ300 ሚሊየን ዶላር የጋራ ወጭ በአዳማ የኢንዱስትሪ ፓርክ ሊገነቡ ነው።በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ የኢኮኖሚ እና ንግድ ጉዳዮች ተጠሪ ሊው ዩ፣ በአዳማ የሚገነባው አዲሱ የኢንዱስትሪ ፓርክ በያዝነው የፈረንጆች 2019 ዓመት ከመጠናቀቁ አስቀድሞ ሊጀመር ይችላል ሲሉ ተናግረዋል።85 በመቶ የኢንዱስትሪ ፓርኩ ግንባታ ወጭ ከቻይና መንግሥት በሚገኝ ዝቅተኛና በተራዘመ ጊዜ በሚከፈል የብድር ወለድ የሚሸፈን መሆኑን ተናግረዋል። ቀሪው 15 በመቶ ደግሞ በኢትዮጵያ መንግሥት እንደሚሸፈን ተገልጿል።የሚገነባው ፓርክ በዋናነት መሣሪያዎችን የሚያመርቱ ኢንዱስትሪዎችን ታሳቢ ያደረገ ነው ያሉት ሊው፣ በአሁኑ ወቅት መሬት እና ገንዘብ ማግኘት ጋር የተያያዙ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው ብለዋል።በቻይና ድጋፍ እና ሞያዊ እገዛ የሚገነባው አዲሱ ፓርክ ለአዳማ ከተማ ሁለተኛው ይሆናል።የቻይና እና የኢትዮጵያ መንግሥት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታ ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ውጤታማ የሆነ ጠንካራ ግንኙነት አላቸው ሲሉም ሊው ተናግረዋል። (ምንጭ:-ሽንዋ)
https://waltainfo.com/am/23905/
113
3ቢዝነስ
በአዲስ አበባ ከመስመር ጥገና ጋር ሳምንቱን ሃይል የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች ይፋ ተደረጉ
ቢዝነስ
August 12, 2019
Unknown
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በዚህ ሳምንት በመዲናዋ ከመስመር ጥገና ጋር በተያያዘ ሃይል የሚቋረጥባቸውን አካባቢዎች ይፋ አደርጓል፡፡በዚህም መሰረት ረቡዕ ነሃሴ 8 ቀን 2011 ዓ.ም በቸራልያ ፋብሪካ፣ በገነት መናፈሻ ኮንደሚኒየም፣ በማሩ ብረታ ብረት፣ በወህኒ ቤት ጀርባ፣ በቂሊንጦ ማረሚያ፣ በሳሪስ አቦ ቤተክርስቲያን፣ በቦሌ ቡልቡል ኮንዶሚኒየም፣ በቡልቡላ ማርያም ማዞሪያ፣ በክሬሸር፣ በባሌስትራ ፋብሪካ፣ በጎፋ ካምፕ ኮንደሚኒየም፣ በመካኒሳ፣ በከፍያለው መድሀኒት ማከፋፈያ፣ በቫቲካን ኤምባሲ፣ በመካኒሳ አቦ ቤተ ክርስቲያን፣ በቄራ ይመስገን ጋራዥ እና በአካባቢዎቻቸው ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከ ቀኑ 6 ሰዓት ድረስ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ይቋረጣል፡፡በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከ ቀኑ 9 ሰዓት ድረስ በቡና ቦርድ፣ በምርጫ ቦርድ፣ በዳችያ፣ በጎፋ መብራት ኃይል፣ በአየር መንገድ፣ በቦሌ ሚካኤል፣ በቦሌ ካርጎ፣ በማዕድን ማሕበር እና በአካባቢዎቻቸው ሃይል እንደሚቋረጥ ተገልጿል፡፡በማግስቱ ሐሙስ ነሃሴ 9 ቀን 2011 ዓ.ም በእሕል በረንዳ፣ በአውቶብስ ተራ፣ በአዲስ ከተማ ትምህርት ቤት፣ በገነሜ ትምህርት ቤት፣ በአማኑኤል ቤተ ክርስቲያን፣ በሻወል ደማ ትምህርት ቤት፣ በሰባተኛ ትራፊክ መብራት፣ በዶሮ ተራ፣ በጦር ሀይሎች፣ በመኮንኖች ክበብ፣ በቶሎሳ ሰፈር፣ በገዳመ እየሱስ፣ በወንድማማቾች፣ በሜክሲኮ፣ በፍሬህይወት ትምህርት ቤትና አካባቢዎቻቸው ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከ ቀኑ 10 ሰዓት ድረስ ሃይል አይኖርም፡፡አርብ ነሃሴ 10 ቀን 2011 ዓ.ም ደግሞ በለቡ፣ በጆሞ 1 በከፊልና አካባቢዎቻቸው ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከ ቀኑ 9 ሰዓት ድረስ በከፍተኛ የኤሌክትሪክ መስመር የማሻሻያ ስራ ለማከናወን ሲባል የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት የሚቋረጥ በመሆኑ ደንበኞች ከወዲሁ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ተቋሙ አሳስቧል።
https://waltainfo.com/am/23904/
198
3ቢዝነስ
ትራምፕ ሕጋዊ ስደተኞች የሚያገኙትን የምግብ ድጋፍ ለማስቀረት አልመዋል ተባለ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 13, 2019
Unknown
የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ሕጋዊ ስደተኞች የሚያገኙትን የምግብ ድጋፍ ለማስቀረት አልመዋል ተባለ፡፡አስተዳደሩ ያጡ የነጡ ሕጋዊ ስደተኞች ቪዛቸውን ለማራዘም አልያም ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ (ግሪን ካርድ) ለማግኘት የሚያደርጉትን ጥረት ከባድ ለማድረግ እየሠራ መሆኑ ነው የተገለጸው።መመሪያው ታላሚ ያደረገው የምግብ፣ የመኖሪያ ቤት ድጋፍ ከአንድ ዓመት በላይ እያገኙ የሚቆዩ ሕጋዊ ስደተኞችን ነው።መንግሥት ከዚህ በኋላ እነዚህን ድጋፎች ማግኘት አትችሉም ብሎ ከወሰነ ማመልከቻቸው ውድቅ እንዲሆን ይደረጋል ተብሏል።ባለስልጣናት መመሪያው "ራስን መቻልን" ያበረታታል ሲሉ ተናግረዋል።ይህ አዲሱ መመሪያው "ፐብሊክ ቻርጅ ሩል" የሚሰኝ ሲሆን፣ በጥቅምት ወር አጋማሽ ሥራ ላይ መዋል ይጀምራል ነው የተባለው።በዚህ ሕግ በአሜሪካ በቋሚነት እየኖሩ ያሉ ስደተኞች ላይጎዱ ይችላሉ፤ እንዲሁም ጥገኝነትና መጠለያ የጠየቁትን አይመለከትም ተብሏል።ነገር ግን ቪዛቸው እንዲራዘምላቸው የጠየቁ፣ ግሪን ካርድ ወይንም የአሜሪካ ዜግነት ለማግኘት ያመለከቱ ላይ ተፈፃሚ የመሆን እድል አለው።የገቢ ደረጃቸው ከሚጠበቀው በታች የሆነ ወይንም እንደ መኖሪያ ቤትና ሕክምና የመሳሰሉ ጥቅማ ጥቅሞች ላይ ሕይወታቸውን የመሰረቱ ወደፊት ወደ ሀገሪቱ እንዳይገቡ ሊታገዱ ይችላሉ።በአሜሪካ ውስጥም ያሉ ግለሰቦች ማመልከቻቸው ውድቅ ሊደረግ እንደሚችልም ተገልጿል።በአሜሪካ 22 ሚሊየን ይሆናሉ ተብለው የተገመቱ ሕጋዊ ስደተኞች ያለ ዜግነት የሚኖሩ ሲሆን፣ ከእነዚህ አብዛኞቹ በዚህ መመሪያ መሰረት ሊጎዱ ይችላሉ ተብሏል።የመብት ተሟጋቾች መመሪያው ያጡ የነጡ ስደተኞች ላይ ፍትሀዊ ባልሆነ መልኩ ትኩረት ተደርጎባቸዋል ሲሉ ተናግረዋል።የብሔራዊ ስደተኞች የሕግ ማዕከል የተሰኘ ተቋም ይህ መመሪያ ስራ ላይ እንዳይውል የትራምፕ አስተዳደርን ከስሼ ሕግ ፊት አቆማቸዋለሁ ሲል ተናግሯል።ነገር ግን ዋይት ሐውስ ይህ ስርዓት "ራሳቸውን በገቢ የቻሉና የመንግሥትን ድጋፍ ከማይጠብቁ ይልቅ" አሜሪካ ቤተሰብ ያላቸው ስደተኞችን የሚደግፍ ነው ሲል ተናግሯል። (ምንጭ፡-ቢቢሲ)
https://waltainfo.com/am/34126/
211
0ሀገር አቀፍ ዜና
ተቋማት ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምር በማካሄድ አምራች ኢንዱስትሪውን መደገፍ እንዳለባቸው ተገለፀ
ቢዝነስ
August 13, 2019
Unknown
ኢንስቲትዩቶች ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምር በማካሄድ አምራች ኢንዱስትሪውን መደገፍ አለባቸው ሲል ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ሚኒስቴር በመስሪያ ቤቱ የ2011 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸሙን በስሩ ካሉ 15 ተጠሪ ተቋማት አመራሮች ጋር በቢሾፍቱ ከተማ እየገመገመ ይገኛል፡፡የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚአብሔር ኢንስቲትዩቶች ኢንዱስትሪውን በሚፈለገው ደረጃ እየደገፉ አይደለም ብለዋል፡፡ኢንስቲትዩቶች ሲቋቋሙ ዋና ተልኳቸው ጥናት በማካሄድ ኢንዱስትሪውን ማሳደግ ስለሆነ ወደዚህ መደበኛ ስራቸው ገብተው ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምር ማካሄድ እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡የወጪ ንግድ ችግሮችን በመለየት የአገራትን የገበያ ፍላጎት እንዲሁም የአገር ውስጥ ምርቶች ገበያ የሚያገኙበትን አገራት መለየት የሚሉትን በማጥናት ለኢንዱስትሪው የመፍትሄ ምንጭ መሆን አለባቸው ብለዋል ሚኒስትሯ፡፡በሌላ በኩል ኢንስቲትዩቶች የራሳቸው ቢሮና የጥናትና ምርምር ቦታ እንዲኖራቸው ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ድጋፍ ያደርጋል ተብሏል፡፡በተጨማሪም የአገሪቷን አጠቃላይ ትራንስፎርሜሽን እውን ለማድረግ በአምራች ኢንዱስትሪው ሴክተር ለውጥ ማምጣት ይገባል የተባለ ሲሆን ለዚህም በዘርፉ ያላውን የስራ ባህል መቀየር እንደሚያስፈልግ ተነግሯል፡፡ምንጭ፦ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር
https://waltainfo.com/am/23906/
124
3ቢዝነስ
የሱዳን የቀድሞ የመረጃና ደህንነት ኃላፊ ሳላህ ጎሽ ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ታገዱ
ፖለቲካ
August 15, 2019
Unknown
የሱዳን የቀድሞ የመረጃና ደህንነት ኃላፊ ሳላህ ጎሽ ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ መታገዳቸው ተገለፀ።የቀድሞ ኃላፊው ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ የታገዱት በሰብአዊ መብት ጥሰት እጃቸው አለበት በሚል ሲሆን፣ እርሳቸው ብቻም ሳይሆኑ ቤተሰባቸውም ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ እገዳው ተጥሎባቸዋል ነው የተባለው።የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያወጣው መግለጫ እንደሚያትተው የቀድሞ ኃላፊው ሳላህ፤ የሱዳን ብሔራዊ የፀጥታና ደህንነት ኃላፊ በነበሩበት ወቅት ሰዎችን በማሰቃየት እጃቸው እንዳለበት ተጨባጭ ማስረጃ አለኝ ብሏል።የቀድሞ የአገሪቷ ፕሬዝዳንት ኦማር አል በሽር ከሥልጣን እስከተወገዱበት ሚያዚያ ወር ድረስ ከመረጃና ደህንነት ኃላፊው ሳላህ ጋር ጥብቅ ግንኙነት እንደነበራቸው ተገልጿል።እርሳቸው ከሥልጣን ከወረዱ በኋላ በተቃዋሚዎች ግፊት ምክንያት ኃላፊነታቸውን ለቀዋልም ነው የተባለው።የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማይክ ፖምፔዮ፤ ሱዳን በሲቪል የሚመራ መንግሥት እንዲኖራት ድጋፋቸውን እንደሚያደርጉ በትዊተር ገፃቸው ላይ መልእክታቸውን አስፍረዋል።አሁን ሃገሪቷን እያስተዳደረ ያለው ምክር ቤት እና የተቃዋሚዎች ጥምረት በሦስት ዓመታት የሽግግር ጊዜ ስለሚኖራቸው ኃላፊነት ከአስር ቀናት በፊት መፈራረማቸው የሚታወስ ነው።በሚኖራቸው የሥልጣን ክፍፍል ላይም ለመጨረሻ ጊዜ በመጭው ቅዳሜ እንደሚፈራረሙ ይጠበቃል። (ምንጭ፡-ቢቢሲ)
https://waltainfo.com/am/33322/
137
5ፖለቲካ
የመከላከያ አባላት ያላቸውን የላቀ ስብዕና እና የአገር ፍቅር ለተተኪ ማስተላለፍ እንደሚገባቸው ተገለፀ
ፖለቲካ
August 11, 2019
Unknown
የመከላከያ አባላት ያላቸውን የላቀ ስብዕና እና የሀገር ፍቅር ለተተኪ ማስተላለፍ እንደሚገባቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ገለፁ።የመከላከያ አዛዥነት ስታፍ ኮሌጅ ለ13ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን 100 የሚሆኑ ከፍተኛ መኮንኖች ዛሬ በታላቁ ቤተ መንግስት አስመርቋል።የመከላከያ አዛዥነት ስታፍ ኮሌጅ ዛሬ ካስመረቃቸው 100 ከፍተኛ መኮንኖች ውስጥ 92 ፖስት ስታፍ እና ስምንት የሁለተኛ ዲግሪያቸውን የተከታተሉ ሲሆኑ 21 ተመራቂዎች ከጎረቤት አገሮች መሆናቸው ተገልጿል።ኮሌጁ ዛሬ ካስመረቃቸው ተመራቂዎች የጎረቤት አገራት ጅቡቲ፣ ሶማሊያ እና ደቡብ ሱዳን የተውጣጡ ከፍተኛ መኮንኖች መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።በምርቃት ሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገኝተው የሥራ መመሪያ የሰጡት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዶክተር አብይ አህመድ የወታደር መኮንን መሆን ድርብ ኃላፊነት መሆኑን ተናግረዋል።በተለይም ለተመራቂ የኢትዮጵያ መኮንኖች የአገሪቱን ታሪክ የህዝቦችን ባህል፣ ማንነትና ድንበር ጠንቅቀው በማወቅ የላቀ ስብዕናን በመገንባት ለተተኪ ትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።የመከላከያ አባላት ያላቸውን የላቀ ስብዕና እና የአገር ፍቅር ስሜት ለተተኪ ማስተላለፍ እንደሚገባቸውም አክለዋል።አባላቱ የፖለቲከኞች ሽኩቻ ሳይወስዳቸው ከወረዱ ዘረኞችና ደካሞች ጋር ሳይወርዱ ለኢትዮጵያ አንድነት እና ለህዝቦች እኩልነትና ደህንነት እንደሚሰሩ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።በመጨረሻም መከላከያን የማዘመን ሥራ በሁሉም ተቋማቶች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ለአብነትም ዘመናዊ ጀቶችና ሄሊኮፕተሮች፣ ሰው አልባ ሚሳኤል እና የሳይበር ስራዎች ላይ የማዘመን ስራ በፍጥነት እንደሚሰራ ጠቁመዋል።ለመከላከያ አባላት የሚሰጠው ከስልጠና እስከ ትጥቅ የማዘመን ሥራ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ተመራቂዎች ተረድተው ለቀጣይ አዳዲስ ስልጠና እና ትምህርት ራሳቸውን ዝግጁ እንዲያደርጉም ጠይቀዋል።የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል አደም መሀመድ በበኩላቸው መከላከያ የሰራዊቱን ተልዕኮ የመፈፀም አቅም እና ብቃት ለማሳደግ የሚያስችለው የሪፎርም ሥራ ላይ እንደሚገኝ አንስተዋል።ከዚህ ውስጥ የመከላከያ አዛዥነት ስታፍ ኮሌጅ አንዱ በመሆኑ ዛሬ የተመረቁ ከፍተኛ መኮንኖች የተጀመረውን ተቋማዊ ሪፎርም ከግብ ለማድረስ ሚናቸው የጎላ መሆኑን አንስተዋል።ተመራቂ ከፍተኛ መኮንኖች በበኩላቸው የተሰጣቸውን ህገ መንግስታዊ ተልዕኮ ለመወጣት ከፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ ሆነው ለህገ መንግስቱና ህገ መንግስታዊ ሥርዓቱ ዘብ እንደሚቆሙ አረጋግጠዋል።ተመራቂ ከፍተኛ መኮንኖቹ በኮሌጁ ያገኙትን የወታደራዊ ሳይንስና አመራር ተጠቅመው ህገ መንግስታዊ ግዳጆችን በስኬት ለማጠናቀቅ ያላቸውን ዝግጁነት ገልፀዋል።/ኢዜአ
https://waltainfo.com/am/31286/
271
5ፖለቲካ
የሊቢያ ተዋጊዎች የኢድ በአልን በማስመልከት ጊዜያዊ የእርቅ ስምምነት አደረጉ
ፖለቲካ
August 12, 2019
Unknown
የሊቢያ ዋነኛ ተቀናቃኝ ተዋጊ ቡድኖች ለሶስት ቀናት የሚከበረው የኢድ አል አድሃ በዓልን በማስመልከት ጊዜያዊ ስምምነት ማድረጋቸውን አስታውቀዋል።ይህንንም ውሳኔ የተባበሩት መንግሥታት ይበል የሚያሰኝ ነው ብሎታል።ቅዳሜ እለት ቤንጋዚ ላይ በደረሰ የቦምብ ጥቃት ሶስት ሰራተኞቹን ያጣው የተባበሩት መንግሥት ድርጅት በዚህ የሰላም ስምምነትም እንደ አንድ አደራዳሪ ሆኖ ቀርቧል።በዚህ ስምምነት ላይ በሊቢያ መዲና ትሪፖሊ ከፍተኛ ጥቃትን ሲፈፅም የነበረው ወታደራዊ ኃይል ኃላፊ ጄኔራል ካሊፋ ሃፍተር ዋነኛ ተደራዳሪ ናቸው።የአለም ጤና ድርጅት እንደዘገበው ከሚያዝያ ጀምሮ በነበረው ጥቃት አንድ ሺ ሰዎች ተገድለዋል።"ጄኔራሉ ለእርቁ የተስማሙት ሊቢያውያን የኢድን በአል በሰላም እንዲያከብሩ ነው" በማለት ቃል አቀባያቸው አህመድ አል ሜስማሪ ገልጿል።እርቁ ቅዳሜ ከ9 ሰአት የጀመረ ሲሆን፣ ሰኞ እስከ ከሰአትም እንደሚቀጥል ቃል አቀባዩ አክለው ተናግረዋል።ኢድ አል አድሐ በመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ አምላክ ለአብርሃም በህልም ተገልፆ አንድ ልጁን እንዲሰዋ ትእዛዝ ካስተላለፈለት በኋላ፤ መስዋእቱን ለማድረግ በሚዘጋጅበት ወቅት በግ የላከበትን ቀን የሚታወስበት ነው።በመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ 1 ሺህ 440ኛው ዓመተ ሒጅራ የኢድ አል አድሐ አረፋ በዓል በትላንትናው ዕለት ተከብሮ ውሏል፡፡ (ምንጭ፡-ቢቢሲ) 
https://waltainfo.com/am/33321/
146
5ፖለቲካ
በመዲናዋ 98 ሺ ለሚልቁ ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
August 12, 2019
Unknown
በአዲስ አበባ ከተማ በጎ ፈቃደኞች የማጠናከሪያ ትምህርትና በስፖርት፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂና በስነ ጥበብ ዙሪያ ላይ ያተኮሩ ስልጠናዎችን ከ98 ሺህ በላይ ለሆኑ ተማሪዎች እየሰጡ መሆኑን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ አስታወቀ።የቢሮ የበጎ ፈቃድ ዳይሬክተር አቶ አክሊሉ ትዕዛዙ እንደገለጹት÷ በ114 ትምህርት ቤቶች ከ5ኛ ክፍል እስከ 10 ክፍል ላሉ 62 ሺህ 700 ተማሪዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ይገኛል።በተጨማሪም በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ በኪነ ጥበብ፣ በስፖርትና ኢትዮጵያዊነት ዙሪያም ለ36 ሺህ ተማሪዎች ለሁለት ወራት ስልጠና እየተሰጠ ነው።ወጣቱ ትውልድ የኢትዮጵያ ታሪክና ባህላዊ እሴቶችን የሚያትቱ መፅሀፎችን ከማንበብ ይልቅ በማህበራዊ ሚዲያዎች ተጠምዶ የሚውል መሆኑን ዳይሬክተሩ አመልክተው ስለ ኢትዮጵያዊነት የሚሰጠው ስልጠናም ወጣቱ በስሜት የሚነዳ ሳይሆን ምክንያታዊ ትውልድ ለመፍጠር እንደሚረዳ አመልክተዋል።የበጎ ፈቃድ ትምህርትና ስልጠና ከሚሰጥባቸው ትምህርት ቤቶች መካከልም ዳግማዊ ምኒልክ፣ ጥቁር አንበሳ፣ ኮከበ ጽባህ እንደሚገኙባቸው ጠቅሰዋል።ትምህርቱ እስከ ነሀሴ 30 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ የሚሰጥ መሆኑ መገለፁን የኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅ ዘገባ ያመለክታል፡፡
https://waltainfo.com/am/32645/
134
0ሀገር አቀፍ ዜና
ሚኒስትሯ በአዲስ አበባ እየተሰሩ ያሉ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ
ቢዝነስ
August 12, 2019
Unknown
የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ፣ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሙሉ ገ/እግዚአብሔር እንዲሁም የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባና የትራንስፖርት የቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰለሞን ኪዳነ እና ሌሎችም በመዲናዋ የትራንስፖርት ቢሮ እየተሰሩ ያሉ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።በጉብኝቱ የመርካቶ አውቶብስ ተርሚናል በአንድ ጊዜ 20 አውቶብሶችን በማስተናገድ እስከ 2 ሺህ ሰው የመጫን አቅም ያለው መሆኑ ተገልጿል።ተርሚናሉ ለአካል ጉዳተኞች የሊፍት አገልግሎት እንዲሰጥ ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑም በጉብኝቱ ወቅት ተብራርቷል፡፡ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅም በሰዓት 6 ሺህ ተጠቃሚዎችን ማስተናገድ እንደሚችልም ነው የተገለፀው።የሸጎሌ እና የቃሊቲ አውቶብስ ተርሚናሎችም በጥሩ አፈፃፀም ላይ እንደሚገኙና የአውቶብስ ዴፖዎቹ የራሳቸው የጥገና ማዕከል፣የነዳጅ ማደያ፣ ዘመናዊ የመኪና የማጠቢያ ቦታና ሰፊ የማቆሚያ ቦታ እንዳላቸው ተገልጿል፡፡ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ የከተማ አስተዳደሩ የትራንስፖርት ቢሮ ኘሮጀክቶችን በቅርበት በመከታተል በወቅቱ ተጠናቀው ለህብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሰጡ ላደረጉት ከፍተኛ ጥረት ምስጋና አቅርበዋል።ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሙሉ ገ/እግዚአብሔርም በበኩላቸው ይህ ትልቅ ውጤትና ጅማሮ በሌሎች የሀገራችን ክፍሎችም ሊስፋፋና ህብረተሰቡም እንዲያውቀዉ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ ሊሰራ ይገባል ማለታቸውን ከትራንስፖርት ሚኒስቴር የተገኘነው መረጃ ያመለክታል።
https://waltainfo.com/am/23901/
137
3ቢዝነስ
በእስያ የደረሰው የጎርፍ አደጋ የበርካቶችን ህይወት ቀጥፏል ተባለ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 12, 2019
Unknown
በእስያ የደረሰው የጎርፍ አደጋ የበርካቶችን ህይወት መቅጠፉ ተገለጸ፡፡በ10ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችም በጊዜያዊ መቆያ ጣቢያዎች ኑሮአቸውን ለመመስረት ተገደዋል ነው የተባለው፡፡ምንም እንኳን ቻይና በጎርጎሮሳውኑ 2019 ብቻ 9 አውሎ ንፋስ ብታስተናግድም የቻይናው የዜና አውታር ሽንዋ ይዞት በወጣው መረጃ መሰረት ሊኪማ የተሰኘው የአሁኑ አውሎ ንፋስ ግን በሀገሪቱ ታሪክ በአመታት የታየው ከባዱ አውሎ ንፋስ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በገንግ ዡ ከተማ ዤጀንግ ግዛት በአውሎንፋሱ ሳቢያ ተፈጥረው እንዳሻቸው የሚተሙ ወንዞች ያገኙትን እየጠራረጉ መውሰዳቸውን ቀጥለዋል፡፡በግዛቲቷ የተሰማሩ የነፍስ አድን ሰራተኞችም ሰዎችን ከጎርፍ አደጋው ለመታደግ ህይወትን እሰከማጣት የሚያደርስ ተግባር በጀግንነት ሲከውኑ ተስተውለዋል፡፡በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎችም ቤታቸውን ለቀው እንዲወጡ ተደርገዋልም የተባለው፡፡ምንም እንኳን ማእበሉ የመቀነስ አዝማሚያ ቢታይበትም ወደ ቻይናዋ ቅንጡ ከተማ ሻንጋይ ግን መገስገሱን አሁንም አላቆመም ተብሏል፡፡አስቸጋሪው የአየር ጸባይ በቻይና ብቻ ሳይገታ ጉዞውን ወደ ሌሎችም የእስያ ክፍሎች በማድረግ በፓኪስታኗ ካራቺም መዳረሻውን አድርጓል፡፡ጥቂት የማይባሉ ሰዎችም በሀገራቸው መንግስት ላይ ቁጣቸውን እየገለጹ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡በቻይና ሊኪሚያ በተሰኘው አውሎ ንፋሰአዝ ሳቢያ በትንሹ 36 ሰዎች ሲሞቱ፣ በፓኪስታን እና ህንድ ደግሞ መነሻውን ከውቂያኖስ ያደረገ ነፋስ ባስከተለው ከባድ ዝናብ ምክኒያት ከ160 በላይ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡165ሺ የሚጠጉት ሰዎች ደግሞ ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለው መጠለያ ጣቢያ ውስጥ ለመጠለል መገደዳቸውን አልጀዚራ በዘገባው አመላክቷል፡፡
https://waltainfo.com/am/34125/
166
0ሀገር አቀፍ ዜና
1 ሺህ 440ኛው የአረፋ በዓል በመላ ሀገሪቱ ተከበረ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 11, 2019
Unknown
የ1440ኛው የዒድ አልአድሀ (አረፋ) በዓል በመላ አገሪቱ  በደማቅ ስነ ስርዓት ተከበረ፡፡የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተወካይ ሼህ ሰዒድ አህመድ ሙስጠፋ በበዓሉ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ለአገራችን አንድነትና ለሰላም፣ ለአብሮነት በጉልበታችን፣ በእውቀታችንና በገንዘባችን የሚፈለግብንን ሁሉ ማበርከት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡በበዓሉ ላይ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ሱልጣን አማን ኤባ በበኩላቸው፣ የአረፋ በዓል ለመላው የሙስሊም ማህበረሰብ የሰላም፣ የፍቅርና የመተሳሳብ እንዲሆን ተመኝተዋል፡፡ሼህ ሱልጣን አማን ኤባ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ አስተዳደር የሙስሊሙን ጥያቄ ለመመለስ የሚያደርገው ጥረት የሚያበረታታ መሆኑን ገልጸው፤ ይህም በዘላቂነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡የአዲስ አበባ ከተማ ም/ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ተወካይ አቶ ዮሃንስ ምትኩ በዓሉ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የዘንድሮን የዒድ አልአድሀ በዓል ልዩ የሚያደርገው የሙስሊሙ አንድነት ከወትሮው በተለየ መልኩ የተጠናከረበት፣ በተለይም በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድና በሃይማኖት አባቶች ያጋራ ጥረት በሰላማዊ መንገድ ልዩነቶች የጠበቡበትና መቻቻል በታየበት ወቅት በድምቀት መከበሩ ነው ብለዋል፡፡(ኢቢሲ) 
https://waltainfo.com/am/32644/
130
0ሀገር አቀፍ ዜና
ወደ አብሮነትና ሠላም ፣ወደ አንድነትና ብልፅግና የሚመሩንን  ተግባራት ተግተን መፈፀም ይኖርብናል- ጠ/ሚ አብይ አህመድ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 10, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ ለ1 ሺህ 440ኛው ዓመተ ሒጅራ የኢድ-አል አድሐ (ዓረፋ) በዓልን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡በመላው ዓለም በሚገኙ ሙስሊሞች በታላቅ ድምቀት በየዓመቱ ከሚከበሩ ሀይማኖታዊ በዓሎች መካከል ኢድ – አል አድሃ አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ ኢድ አል አድሃ የመስዕዋት (የእርድ) በዓልም በመባል ይታወቃል፡፡በእስልምና የዘመን አቆጣጠር መሠረት የኢድ-አል ፍጡር በዓልን ተከትሎ ከአስር ሳምንታት ቦኋላ ወይም በአስራ ሁለተኛው የዙል ሂድጃ ወር ውስጥ የሚከበረው የዒድ-አል አድሃ በዓል የሐጅ ሥርዓት በሚከናወንባቸው አምስት ተከታታይ ቀናት ውስጥ የሚካተት ታላቅ ሃይማኖታዊ ሥርዓት ነው፡፡የኢድ አል አድሃ በዓል የተካተተበት የሐጅ ሥርዓት ታላላቅ ተምሳሌታዊ ዕሴቶችን ያቀፉ በርካታ ኩነቶችን አጣምሮ ከመያዙም ባሻገር ከአምስቱ የእስልምና መሠረቶች መካከል አንዱ የሆነውና ማንኛውም ሙስሊም የገንዘብና የጉልበት አቅሙ እስከፈቀደ ድረስ በሕይወት ዘመኑ ቢያንስ አንድ ጊዜ ሊያከናውነው የሚገባውን የሀጅ ሥርዓትም ይፈፀምበታል፡፡በዚህ አኳያ ኢድ አል አድሐ በዓል የተካተተበት የሀጅ ሥርዓት ዘርና ቀለም፣ ሃብታምና ደሀ፣ ሴትና ወንድ ተብሎ መለያየት ሳይኖር ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የተሰባሰቡ ሙስሊሞች በአንድ ሥፍራ፣ በአንድነት ፈጣሪያቸው ፊት በመቆም መራራቅን ሳይሆን መቻቻልን፣ ጠላትነትን ሳይሆን ዓለም አቀፍ ወንድማማችነትን፣ ፀብና ሁከትን ሳይሆን ሠላምና ፍቅርን ከፍ በማድረግ መታዘዝንና መስዋዕትን በእምነትና በተግባር፣ በስሜትና በምግባር ከራሳችን ጋር የምናቆራኝበት ታላቅ የመታሰቢያ በዓል ተደርጎም ይወሰዳል፡፡ ኢድ ሙባረክ!በእስልምና የዘመናት ታሪክ ውስጥ ከነቢዩ ላህ ኢብራሂም እስከ ነቢዩ መሐመድ (ሠ.ዓ.ወ)፣ ከአደም እና ሐዋ እስከ አጀርና እስማኤል፣ በሕይወት እና ሞት፣ በሥጋዊ እና መንፈሳዊ ተምሳሌቶች እምነት እና ተስፋ፣ ፈተና እና ደስታ ጎልቶ የተገለፀበት ሀይማኖታዊ ሥርዓት ነው – ሐጅ፡፡ይህን እውነታ የነቢያት ሁሉ ቀደምት አባት የሆኑት ነቢዩ ላህ ኢብራሂም (አላሂሰ ሠላም) በእርጅና እድሜ የታደሉት ልጃቸው እስማኤልን መስዋዕት አድርገው እንዲያቀርቡ በፈጣሪ መታዘዛቸው፣ በፈጣሪ ትዕዛዝ ቅስማቸው ቢሰበርም በእምነታቸው ጸንተው ትዕዛዙን ለመፈፀም መፍቀዳቸው በዚህም የተነሳ ፈጣሪ በልጃቸው ምትክ የሚታረድ በግ ያቀረበላቸው መሆኑ፣ በዚህም ከሀዘን ወደ ደስታ መሻገራቸውን አሳይቶናል፡፡በመካ ዙሪያ ቀበሌዎች በሚገኙት በሳፋና በማርዋህ አነስተኛ ኮረብታዎች ሠባት ጊዜ በመመላለስ የሚከናወነው በፀሎት እና ዝክር የነቢዩላህ ኢብራሂም (አላሂሰ ሠላም) ሚስት ግብፃዊቷ አጃር ወይም አጋር ጡት ከሚጠባ ልጇ እስማኤል ጋር በብቸኝነት መሸሿ፣ በዚያ ምድረ-በዳ የሚላስ እህል የሚቀመስ ጠል አጥታ በሠፈያና በመርዋ ኮረብቶች መካከል መባዘኗ በምድረበዳ የዘምዘም ውኋ ምንጭ የፈለቀላት መሆኑ፣ ሌላም ሳይሆን ያንኑ እምነት እና ተስፋ፣ ፈተና እና ደስታ ማሳያ ተምሳሌት ነው፡፡ዛሬም በሀገራዊው የለውጥ ጉዞና እርምጃ ተስፋ ማድረግን ሀብትና እምነቱ ያደረገ ሕዝብ በዚያው መጠን በሚያጋጥሙ ፈተናዎች ተስፋ መቁረጥ ቢጫነው አይገርምም፡፡ ተስፋ መቁረጥ ግን ከፈተና አያድንም፡፡ወገንንም ወደ ድል አያሻግርም፡፡ በእምነታቸው በፀኑ ዜጎች እንጂ በተስፋ ቆራጮች ሀገርና ሕዝብ ፈተናቸውን አልፈው መሠናክሉን ተሻግረው ለድልና ደስታ አይበቁም፡፡ በእንዲህ አይነቱ ወቅት ሀገርና ሕዝብ አሻጋሪና ሩቅ ተመልካች ባለራዕይ መሪ ያስፈልጋቸዋል፡፡ለሠላም እና ለፍትህ መስዋዕትነትን ለመክፈል ዝግጁ የሆነ መሪ፡፡ ይህ ሲሆን በድካም ተሸንፈው በጉዞ መሐል የወደቁት እና በስብሰው አፈር ወደ መሆን ሊሸጋገሩ የተቃረቡት አፈራቸውን ከላያቸው በማራገፍ ቀጥ ብለው ዳግም አብረውን መጓዝ ይጀምራሉ፡፡ሠላም ረዥሙ የታሪክ ጊዜ ነው። ችግሮቻችን ሁሉ በአንድ ጀንበር ሊፈቱ እንደማይችሉ ተገንዝበን፣ የጋራ ችግራችንን በጋራ ለመፍታት ቆርጠን ከተነሳን እንደ ነቢዩላህ ኢብራሂም እንደ አጋርና ኢስማኤል ዘመን ተሸጋሪ ሠላምና ብልፅግናን ማረጋገጥ ለእኛ ለኢትዮጵያውያን እጅግም ከባድ አይሆንብንም፡፡ውድ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች!በላቀ ደረጃ ሕብረትን፣ በልዩነት ምትክ አንድነት ከመነሻው አንስቶ እስከ መድረሻው የሚዘልቀው የኢድ አል አድሃ በዓል እና የሐጅ ሥርዓት ለእኛ ለዚህ ዘመን ኢትዮጵያውያን የመልካም ዕሴት መማሪያ ሊሆን ይችላል፡፡ በርግጥም ግለኝነትና ስግብግብነት፣ ጽንፈኝነትና ግትርነት፣ ሠፍቶ በተንሰራፋበት ወቅትና ዘመን መራራቅን ሳይሆን መቻቻልን፣ ጠላትነትን ሳይሆን ዓለም አቀፍ ወንድማማችነትን፣ ፀብና ሁከትን ሳይሆን ሠላምና ፍቅርን ከፍ በማድረግ በእምነትና በተግባር፣ በስሜትና በምግባር ከእኛነታችን ጋር የሚያቆራኝ ሥርዓት እጅግ ሲበዛ አስፈላጊ ነው፡፡በዚህ ረገድ፣ በሐጅ ሥርዓት ሶስተኛ ምዕራፍ የተካተተው የአረፋ ሥርዓት በአንድ በኩል ነቢዩ መሀመድ (ሠለላህ አላይህ ወሰላም) ምድርን ተሰናብተው ወደ ዘላለማዊ መኖሪያቸው ከማምራታቸው በፊት የመጨረሻውን የቁርዓን አንቀፅ በአረፋ ኮረብታ ማውረዳቸው ሲዘከርበት በሌላ በኩል ደግሞ የፍርድ ቀን መኖሩን እና በዚያም ወቅት ገላችንን ከምንሸፍንበት ጨርቅ ባሻገር አንድም ሀብት ንብረት እንደማይከተለን ማስታወሻ ነው፡፡የአረፋ ሥርዓት ከዚህም በተጨማሪ አባታችን አደም እና እናታችን ሀዋ የፈጣሪያቸውን ትዕዛዝ በማጉደላቸው የተነሳ ከገነት ቤታቸው ወደ ምድራዊ ዓለም ተባረው ተለያይተው ሲኖሩ ከቆዩ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አርዱል አረፋ ተብሎ በሚጠራው የአረፋ ኮረብታ ላይ መገናኘታቸው ‹አረፍኪኒ›‹አረፍቲኒ› መባባላቸው ይዘከርበታል፡፡በትናንትና ጥፋት እና ስህተት ሳቢያ የሠው ልጅ በሕይወት ከተሳሰረው አካሉ ጋር ለዘለዓለሙ ተለያይቶና ተራርቆ መኖር እንደሌለበት ይልቁንም በንሰሃ፣ በይቅርታ፣ በምህረትና በእርቅ አብሮነትንና አንድነትን ማስቀጠል መልካም መሆኑን የሠው ልጅ መማር እንዲችል በአባታችን አደም እና በእናታችን ሀዋ (የየአርዱል አረፋ) በአረፋ ተራራ መገናኘት የተገለፀ ታላቅ ተምሳሌታዊ አስተምሮት ተደርጎም ይቆጠራል፡፡እኛ ኢትዮጵያውያን በትናንት አብሮነታችን ያስመዘገበናቸው በርካታ አኩሪ የጋራ ገድሎች እንዳሉን ሁሉ በትናንት ግንኙነታችን ውስጥ ፍቅርን፣ ፍትህና ርትዕን አጉድለንና ጎድሎብንም ሊሆን ይችላል፡፡ ግን ደግሞ በትናንት ታሪክ ውስጥ እድሜ ዘላለማችንን ተኝተን በማማረር ማሳለፍ መፍትሄ አይሆንም፡፡ በዛሬ ሕይወቱ ዳገት መውጣትን የሚፈራ ትውልድ በነገ ሕይወቱ ቁልቁለት መውረድ ሊጠብቀው አለመቻሉ ግልፅ ነው፡፡ነገን በዛሬ ቀና ራዕይና መልካም ተግባር እንጂ በምንም መልኩ ብርሃን ማላበስ አይቻልም፡፡ ችግራችን ውስብስብ ቢሆንም መፍትሄም ያለው፣ እዚሁ የአብሮነት ባህላችን ውስጥ ነው፡፡ አብረን ከሆንን አንሰበርም፡፡ አብረን ከሆንን የማንፈታው ችግር አይኖርም፡፡ የእድገትና የብልጽግናችን ዋስትና ደግሞ እየተቋሰልንም ቢሆን አብረን ተዋደን እና ተከባብረን መኖራችን ነው፡፡ለዓመታት ተከፋፍሎ የቆየው የሙስሊም ማኀበረሰብ ለውጡ የፈጠረለትን መልካም አጋጣሚ ተጠቅሞ አንድነቱን ለማጠናከር በጋራ መንቀሳቀስ በጀመረበት ማግስት የምናከብረው ይህ በዓል ደስታችንን እጥፍ ድርብ የሚያደርግልን ብቻ ሳይሆን ተስፋችንንም የሚያለመልም ነው፡፡ የእስልምና እምነት ተከታይ በሆነው ኀብረተሰባችን መካከል የሚፈጠር አንድነት ለሙስሊሙ ወገናችን ብቻ ሳይሆን ለሀገራችንም አንድነትና ጥንካሬ ምንጭ መሆኑን መንግስት እንደትናት ሁሉ ዛሬም አበክሮ ይገነዘባል፡፡ይህም ሆኖ ግን ዛሬም ድረስ ውስብብስብ እና ፋታ የማይሰጡ ችግሮች ባለቤቶች መሆናችን ከቶውንም ሊዘነጋን አይገባም፡፡ እነዚህ ችግሮቻችን እንኳንስ፣ ተለያይተንና ተከፋፍለን ቀርቶ፣ ተባብረን እና ተዋደንም ቢሆን ለመፍታት ዘመናት ያስፈልጉናል፡፡ያን የመፍትሄ ዘመን በአዲሱ የለውጥ መንገድ ከዓመት በፊት አንድ ብለን እንደጀመርነው ሁሉ ከዚህ በኋላም የአብሮነትንና የአንድነትን ዋጋ በልኩ በመረዳትና በመገንዘብ ከቀድሞው በላይ የሚያራርቁንና የሚያቃቅሩንን፣ የሚያጠፋፉንን የሚያለያዩንን ተግባራት ሳይሆን በፍቅር፣ በይቅር ባይነት ወደ አብሮነትና ሠላም ፣ወደ አንድነትና ብልፅግና የሚመሩንን የመደመር ዕሳቤና ተግባራት ተግተን መፈፀም ይኖርብናል፡፡የአሁኑ ትውልድ ከትናንት ታሪኩ ትምህርት ወስዶ ከሚገኝበት ሀገራዊ የማንነት የቀውስ አዙሪት የሚወጣበትና ወደ እድገትና ወደ ብልፅግና ጎዳና መግባት የሚያስችለውን የቁጭት ስንቅ መሠነቂያ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ በእጃችን ውስጥ ባለው ዛሬ ተጠቅመን በመለያየት ሳይሆን በአርዱል አረፋ እንደተቀጠለው የአዳምና ሄዋን መገናኘት በአብሮነትና አንድነት ዘላለማዊ የድል ታሪክ የምንሰራ ትውልዶች ለመሆን እንድንተጋ ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡ክቡራትና ክቡራን ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች!በላቀ መደጋገፍ ታጅቦ ከጅማሮ እስከ ማክተሚያ የሚጓዘው በዓል ጠንካሮች ደካሞችን ፣ ባለፀጎች ምስኪኖችን፣ ወጣቶች አዛውንቶችና ሕጻናትን በዓሉ ላይ በሕብረት በመቆም፣ ከበዓሉ ቦኋላም መጠያየቅ፣ አብሮ ማሳለፍ ትልቅ ቦታም ይሰጠዋል፡፡ከእኛ በዓቅም ያነሱ ወገኖቻችን በዓሉ ለእኛም ሆነ ለእነርሱ እኩል ቢመጣም በማጣታቸው ፣ጠያቂ በማጣታቸው የተነሳ በዓሉን በባዶ ሆድ እንዳያሳልፉ ከሱም በላይ ሳቅና ወግ ርቋቸው መተከዛቸውና ማዘናቸው ሊሰማንና ሊያሳዝነን ይገባል፡፡ከዚሁ በተጓዳኝ ነቢዩ መሀመድ (ሠለላህ አለይህ ወሠለም) በተለያዩ ሀዲሶቻቸው አረንጓዴ አሻራን አትሞ ማለፍ ያለው ምንዳ ከሰደቃ ሊስተካከል እንደሚችል ከመግለፃቸው ባሻገር፣ “የመጨረሻው የፍርድ ቀን ሊዘረጋ ሠዓቱ የተቃረበ ቢሆን እንኳ እርሱ በእጁ የዛፍ ችግኝ የጨበጠ ሠው ቀሪዋ አንድ ሠከንድ እንኳ ብትሆን እርሷን ተጠቅሞ ችግኙን ይትከል” በማለት አስተምረዋል፡፡እኛ ኢትዮጵያውያን እንደሀገርና ሕዝብ በውዲቷ የሀገራችን ምድርና አፈር የአረንጓዴ አሻራችንን አሳርፈን ለማለፍ ቃል ተገባብተን በችግኝ መትከል እና መንከባከብ የጅማሮ ጉዞ ማድረጋችን ብዙም ያልደበዘዘ የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው፡፡ ሐምሌ 22 ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ የተከልነው የችግኝ ብዛት በራሳችን ብቻ ሳይሆን በዓለም ደረጃ ሀገራዊ ስማችንን ከፍ ያደረገና በዓለም የላቀ ክንውን ክብረ ወሰን መዝገብ ማስፈርም ያስቻለን ታላቅ ታሪካዊ ዕለት ሆኖ አልፏል፡፡ኢትዮጵያውያኖች ዛሬም እንደትናንቱ ከወሰኑና ከቆረጡ በአንድ ጀንበር በሚሊዮኖች በመትመም ያስቀመጡትን ዓላማና ግብ ከዳር ለማድረስ የማይሰንፉ ሕዝቦች መሆናችንን ዳግም ለዓለም ሕዝብ ያረጋገጥንበት እና ያስመሰከርንበት ትዕይንት መሆኑ ባይካድም በሀገር ደረጃ ካለብን የተከማቸ እና የዞረ ዕዳ አንፃር የአረንጓዴ አሻራ የማኖር ሥራችንን መጀመርን እንጂ መጨረስን የሚያሳይ አይደለም፡፡ በመሆኑም መልካም ጅምራችንን አጠናክረን በመቀጠል የችግኝ ተከላ እንቅስቃሴያችንን፣ በውኋ ማጠጣት፣ አረምን በማስወገድና መንከባከብ አጠናክረን እንቀጥል፡፡ለዚህም ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በታሪካዊው ሐምሌ 22 ቀን ከተቀረው የሀገራችን የሌሎች እምነት ተከታዮችና ቤተሰቦች ጋር ጎን ለጎን በመቆም እና እጅ ለእጅ በመያያዝ እንደፈፀማችሁት የላቀ ገድል ሁሉ በቀጣዮቹ ጊዚያትም የጀመርነውን ሀገርን የማስዋብ ስራ አጠናክሮ በመቀጠል፣ ሀገራችሁን ከምድረ-በዳነት እና ከዙሪያ መለስ ብክለት ለመታደግ አረንጓዴ አሻራችሁን ደጋግማችሁ በማኖር የዜግነት ኋላፊነታችሁን እንድትወጡ ዳግም ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡ተፈፃሚ እንደምታደርጉትም እተማመናለሁ፡፡በመጨረሻም እንኳን ለኢድ አል – አድሃ በዓል በሠላም አደረሳችሁ በማለት በዓሉ ለመላው ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የደስታ የሠላም፣ የይቅርታ፣ የፍቅር እና የአንድነት እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቴን እገልጻለሁ፡፡ኢድ ሙባረክ
https://waltainfo.com/am/32639/
1,166
0ሀገር አቀፍ ዜና
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ለመቄዶንያ የ155 ሚሊየን ብር የአደጋ ስጋት የመድህን ሽፋን ሰጠ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 10, 2019
Unknown
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ለመቄዶንያ አረጋዊያንና አዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል የ155 ሚሊየን ብር የአደጋ ስጋት የመድህን ሽፋን ሰጥቷል፡፡የድርጅቱ አመራሮችና ሰራተኞች የአረጋዊያኑን መርጃ ማዕከል  በጎብኙበት ወቅት የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ነፃነት ለሜሳ እንዳሉት መርጃ ማዕከሉ ቀጣይነት ያለው አገልግሎት መስጠት እንዲችል ዘላቂ የመድህን ዋስትና ሽፋን እንዲያገኝ ጥረት እየተደረገ ነው ፡፡ማዕከሉ ለሚያስገነባው ሆስፒታል፣ ሰራተኞች እንዲሁም ተሽከርካሪዎች የሚሆን 155 ሚሊየን ብር የሚደርስ የአደጋ ስጋት የመድህን ሽፋን መስጠቱን አቶ ነፃነት ገልፀዋል፡፡የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ከዚህ በፊትም ለመቄዶኒያ የአረጋዊያንና አዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል የተለያዩ ድጋፎችንና የመድህን ሽፋን መስጠቱ ይታወሳል፡፡  
https://waltainfo.com/am/32641/
82
0ሀገር አቀፍ ዜና
አዲስ ወግ ውይይት በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት እየተካሄደ ነው
ቢዝነስ
August 12, 2019
Unknown
አዲስ ወግ የውይይት መድረክ “አንድ ጉዳይ የምጣኔ ሃብት ሪፎርም መነሻና አቅጣጫ” በሚል ርዕስ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡በመድረኩ ባለፉት 17 ወራት የተተገበሩ አንኳር የማሻሻያ ስራዎችን በተመለከተ   የፋይናንስ ሚኒስትሩ ከፍተኛ አማካሪ ብሩክ ታዬ ማብራሪያ ሰጥተዋል።ዘላቂ መፍትሄ የሚሹት እንደ የዋጋ ግሽበት፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረትና የብድር አከፋፈል ችግሮችንና ልሎችንም ለመፍታት የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ወደ ግል ለማዞር እንቅስቃሴዎች መደረጋቸውን አስታውሰዋል።ለዚህም ሲባል ከአበዳሪዎች ጋር በመደራደር እፎይታ ለማግኘት የሚያስችሉ ስልቶችን ተግባራዊ ማድረግ፣ ያላለቁ የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ማጠናቀቅ እንዲሁም ሕጎችን የማብላላትና የመከለስ ስራዎች መሰራታቸውን አንስተዋል።በወጭ ንግድ ላይ አለም አቀፍ አሰራርን የመረዳት ክፍተት ችግሮች ባጋጠሙ ወቅት ሙሉ በሙሉ መርምሮ የመረዳት አቅም ማዳበር አለመቻሉን ያነሱት የንግድ እንደራሴው  አቶ ብሩክ ፍቅሩ÷የሕግና የአሰራር ማዕቀፎች ባለሃብቶችንና የተወሰኑ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ብቻ ሳይሆን ግለሰቦችንም መሰረት ያደረጉ እንዲሆኑ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡አዲስ ወግ የውይይት መድረክ  ከአዲስ አበባ ውጭ ለመጀመሪያ ጊዜ በድሬዳዋ ከተማ በቅርቡ መካሄዱ ይታወሳል፡፡
https://waltainfo.com/am/23902/
131
3ቢዝነስ
የወሳን ኩነት ምዝገባ የዜጎችን ህገ መንግስታዊ፣  ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ነው- ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 10, 2019
Unknown
ሁለተኛው ሃገር አቀፍ የወሳኝ ኩነት ምዝገባና ስታቲስቲክስ ቀን ከተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ሃላፊዎች እና የሚመለከታቻው አካላት በተገኙበት ተከብሯል፡፡“የልደት ምስክር ወረቀት ለሰብዓዊ መብቶች መከበርና አድሏዊ አሰራርን ለማስወገድ መሰረት ነው” በሚል መሪ ቃል ነው የተዘጋጀው፡፡በዝግጅቱ ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ የወሳን ኩነት ምዝገባ  ዜጎች ህገ መንግስታዊ መብታቸውንና  ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን የሚረጋግጥ ነው ብለዋል፡፡የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ዘይኑ ጀማል በበኩላቸው ከልደት እና ሞት ጋብቻ እና ፍቺ ምዝገባ የሚገኘው መረጃ ለሃገሪቱ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ተግባራት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልፀዋል፡፡የኢሚግሬሽን፣ ዜግነት እና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙጂብ ጀማል በዓለም ከ1 ቢሊየን ሰዎች በላይ የማንነት መታወቂያ ሰርተፊኬት እንደሌላቸው በመግለፅ÷ በኢትዮጵያም 65 በመቶዎቹ ህጋዊ መታወቂያ እንደሌላቸው ነው የገለፁት፡፡ለሚቀጥለው የትምህርት ዘመን የሚመዘገቡ ተማሪዎችም ምዝገባቸው ያለምንም ክፍያ የሆኑ በልደት የምስክር ወረቀት እንዲመዘገቡ እንደሚደረግም አክለዋል፡፡በ2063 የተያዘው ዘላቂ የልማት ግቡን ለማሳካት በህብረተሰቡ ዘንድ ግንዛቤ መፍጠር እንደሚያስፈልግም ነው የገለፁት፡፡በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የህፃናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ ዳይሬክተር አደል ሆደር በኢትዮጵያ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ከመጀመሩ በፊት የተወለዱ ጨቅላ ህፃናትን የማስመዝገብ ባህሉ 3 በመቶ ብቻ የነበረ ሲሆን÷ የወሳን ኩነት ምዝገባ ከተጀመረበት በሶስት ዓመታት ውስጥ ቁጥሩ ወደ 20 በመቶ ከፍ ማለቱን አንስተዋል፡፡በዝግጅቱልጆቻቸውን ለልደት ሰርተፊኬትያስመዘገቡ ወላጆችና አዲስ ጋብቻቸውን በወሳኝ ኩነት ያስመዘገቡ ጥንዶች ከፕሬዚዳንት ወ/ሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ የምስክር ወረቀት ተቀብለዋል፡፡
https://waltainfo.com/am/32643/
190
0ሀገር አቀፍ ዜና
ኢንጅነር ታከለ ኡማ ለቡ ቫርኔሮ አከባቢ ሰሞኑን በፈረሰው አሊፍ መስጅድ በመገኘት የሀይማኖት አባቶችን አነጋገሩ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 10, 2019
Unknown
የአዲስ አበባ ከተማ አስተደዳር ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ለቡ ቫርኔሮ አከባቢ ሰሞኑን በፈረሰው አሊፍ መስጅድ በመገኘት የሀይማኖት አባቶችን አነጋግረዋል፡፡ኢንጅነር ታከለ ኡማ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከከተማ አስተዳደሩ እውቅና ውጪ የፈረሰውን የአሊፍ መስጅድ ጎብኝተዋል፡፡በዚሁ ጉብኝታቸውም ጥቂቶች በተንኮል ከሙስሊሙ ማህበረሰብ ጋር ሊያጋጩ እና በሴራ ሊበትኑ ቢያስቡም እኛ ግን ችግሮችን በተሻለ መንገድ እናልፋቸዋለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የማምለኪያ ቦታዎችን ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ ከሁሉም የእምነት ተቋማት ጋር በትብብር እየሰራ እንደሆነም ነው የተናገሩት፡፡መስጅዱን በማፍረስ የተሳተፉ አካላትን ተጠያቂ ከማድረግ ጎን ለጎንም መስጅዱን በተሻለ ሁኔታ ለመገንባትም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ 4 ሺህ ካሬ ሜትር ተለዋጭ ቦታም ለአዲስ አበባ መጅሊስ መተላለፉም ነው የተገለጸው፡፡ከተጀመረው የለውጥ ጉዞ የሚያስተጋጉሉንን ለመግታት አሁንም የጋራ ጥረታችን ሊቀጥል ይገባል ሲሉም መልዕክታቸውን ማስተላለፋቸውን ከከንቲባው ጽ/ቤት የተኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
https://waltainfo.com/am/32640/
118
0ሀገር አቀፍ ዜና
የግብርና ሚኒስቴር በ2011 በጀት ዓመት ለ1.3 ሚሊየን ዜጎች የገጠር ስራ ዕድል መፍጠሩን አስታወቀ
ቢዝነስ
August 9, 2019
Unknown
የግብርና ሚኒስቴር በ2011 በጀት ዓመት ለ1.3 ሚሊየን የገጠር ስራ ዕድል መፍጠሩን አስታወቀ፡፡ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በ2011 በጀት ዓመት በግብርና፣ በማዕድን ማናፋክቸሪንግ እና በሌሎች አገልግሎት ሰጪ መስኮች ላይ 1.8 ሚሊየን የገጠር ስራ ዕድል ለመፍጠር አቅዶ 1.3 ሚሊየኑን ማሳካቱን አስታውቋል፡፡ሚኒስቴሩ በስራ እድል ፈጠራ ዙሪያ የ2011 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀምና የ2012 ዓ.ም የትኩረት አቅጣጫ ላይ በቢሾፍቱ ከተማ እየተወያየ ሲሆን፣ በባለፈው በጀት ዓመት በገጠር የስራአጥነት ችግርን ለመቅረፍ በተሰራው ስራ የእቅዱን 73 በመቶ ማሳካት አሳክቻለሁ ብሏል፡፡በዞን፣ ወረዳና ቀበሌ የአደረጃጀት እርከኖች ላይ የገጠር የስራ ዕድል ፈጠራ ባለቤት ማጣት በዘርፉ የሚታይ ዋነኛ ተግዳሮት እንደነበር  በውይይቱ ላይ የተገለጸ ሲሆን፤ የአቅም ማነስ፣ ተደራሽ የሆነ የመረጃ አያያዝ ችግር፣ የገበያ ትስስር ማጣት እንዲሁም የባለድርሻ አካላት በቅንጅት አለመስራት በማነቆነት ተለይቷል፡፡በ2011 በጀት ዓመት የኦሮሚያ ክልል የዕቅዱን 83 በመቶ፣ የአማራ ክልል ደግሞ 81 በመቶ በማሳካት የተሻለ ውጤት በማስመዝገብ ቀዳሚ ነበሩ ተብሏል።ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በተግዳሮትነት የተመዘገቡ ማነቆዎችን በማቃለል በ2012 በጀት ዓመት በመላ ሀገሪቱ 1.7 ሚሊየን የገጠር ስራ ዕድል ለመፍጠር እንደሚሰራም አስታውቋል፡፡የግብርና ሚኒስቴር ከ2008 እስከ 2010 ዓ.ም በገጠር የስራ እድል ፈጠራ ዙሪያ ባደረገው የዳሰሳ ጥናት ስራ ፈላጊዎች በፍላጎታቸው ወደ ስራ ከመግባት ይልቅ መንግስት ባስቀመጣቸው አማራጮች መሳተፋቸው በውጤታማነታቸው ላይ ትልቅ ተጽዕኖ እንደፈጠረባቸውም ገልጿል፡፡በጥናቱ ከ2000 እስከ 2010 ዓ.ም በገጠር የስራ እድል ፈጠራ ከ3.8 ሚሊዮን በላይ የስራ እድል እንደተፈጠረም ተመላክቷል፡፡
https://waltainfo.com/am/23899/
193
3ቢዝነስ
የአረፋ በዓል ሲከበር አቅመ ደካሞችን በማሰብና በመደገፍ ሊሆን ይገባል- ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጅ ዑመር
ሀገር አቀፍ ዜና
August 9, 2019
Unknown
የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል እምነቱ በሚያዘው መሰረት አቅመ ደካሞችን በማሰብና ያለው ለሌለው በማካፈል እንዲያከበር ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጅ ዑመር ኢድሪስ አሳሰቡ።የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጅ ዑመር ኢድሪስ 1 ሺህ 440ኛውን የአረፋ በዓል አስመልክተው ለሕዝበ ሙስሊሙ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።ኢድ አል አድሃ አረፋ አላህ የነብዩ ኢብራሂምን ፍቅርና እምነት ለመፈተን ልጃቸውን ለመስዋዕትነት እንዲያቀርቡ ያዘዘበትን ዕለት ለማሰብ የሚከበር ሃይማኖታዊ በዓል ነው።ይህን ታሪክ ለመዘከር በዓሉ “የመስዋዕትነት በዓል” ተብሎ እንደሚጠራ የእምነቱ ሊቃውንት ያስረዳሉ፤ የእምነቱ ተከታዮችም የነብዩ መሃመድን ፈለግ ተከትለው በዕለቱ እርድ ይፈጽማሉ።ምዕመኑ በዓሉን ሲያከብርም እምነቱ በሚያዘው መሰረት አቅመ ደካሞችን በማሰብ፣ ያለውን በማካፈልና በማስደሰት መሆን እንዳለበት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።በአሁኑ ወቅት አንገብጋቢው ጉዳይ አንድነትና ሠላምን ማስጠበቅ መሆኑን የጠቀሱት ሃጅ ኡመር እድሪስ “በአገርም ሆነ በውጭ ያለን ሁሉ አንድነታችንንና ሠላማችንን ልንጠብቅ ይገባል” ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። (ምንጭ፡-ኢዜአ)
https://waltainfo.com/am/32638/
121
0ሀገር አቀፍ ዜና
የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሲያካሂድ የነበረውን ስብሰባ አጠናቀቀ
ፖለቲካ
August 10, 2019
Unknown
የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሲያካሂድ የነበረውን ስብሰባ የተለያዩ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ አጠናቀቀ።የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው አባልና በኢህአዴግ ፅህፈት ቤት የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሲቪክ ጉዳዮች ሀላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ ለኢቢሲ እንደተናገሩት፥ ኮሚቴው በወቅታዊ የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የድርጅት ስራዎች እና የአመራር ቁመና ላይ ሀላፊነት በተሞላው መንገድ ህዝብና መንግስትን በሚያስቀጥል መልኩ ዝርዝርና ጥልቅ ግምገማዎችን አካሂዷል።በዚህ ድክመት ነው ያላቸውን በመለየት በዝርዝር መፍትሄዎችን ያስቀመጠው ኮሚቴው፥ ከሀገራዊ ለውጡ ጋር የመጡ በድክመት ያነሳቸውን ዝንባሌዎችን መመልከቱን ነው ያነሱት።ለውጡ ህዝቡ በሚፈልገው ደረጃ ወደፊት እንዲሄድ ህዝቡና ሀገሪቱ ወደሚፈለገው የከፍታ ደረጃ እንዲደርሱ የሚታትሩ እንዳሉ ሁሉ በለውጡ የቀድሞውን ይዞ የመቆዘም፣ ህዝበኝነት እና ወላዋይነት በአመረራር ደረጃ እንዳሉና ይህም የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች አንድ ሆነው በአንድ አቅጣጫና እና በተመሳሳይ ፍጥነት እንዳይሄዱ ማድረጉን በድክመት እንደገመገመ ገልፀዋል።በዚህ ላይም የጋራ ስምምነት መደረሱን በመጠቆም ከድርጅት በላይ ኢትዮጵያና ህዝቦቿ መቀጠል እንዳለባቸው በማንሳት ለውጡን በመምራት ሂደት በተሸለ መረጋጋት፣ መደማመጥ እና ሀላፊነት በሚሰማ አግባብ ግምገማውን መካሄዱን ነው አቶ ፍቃዱ የተናገሩት።በሀገር ደረጃ የሚስተዋለው የብሄር ፅንፈኝነት ለሀገራዊ አንድነት እና ለፌደራላዊትና ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ችግርና ተግዳሮት እንደሆነ በማንሳት መታገል እንደሚገባ ኮሚቴው ተመልክቷል።ማንነቶች መከበር ያለባቸው ቢሆንም ኢትዮጵያዊ ማንነትን አስታርቆና አቻችሎ ማስኬድ እንደሚገባ መነሳቱንና በማህበራዊ ሚዲያው ከሚንፀባረቁትና አመራሩም ከሚገዛቸው ፅንፈኝነት በመውጣት መታገል እንደሚገባ ዝርዝር ግምገማ ተካሂዷል ብለዋል።የህግ የበላይነትን ከማስከበር አንፃር ባለፉት ጊዜያቶች ህግና ስርዓትን ለማስከበር የህዝቡ የሰብዓዊ እና ዴሞክራሲያው መብቶች ተገድበው እንደነበር ከዚህም ለመውጣት በህዝቡ ገፊነት ኢህአዴግ ለውጡን እዚህ ደረጃ ማድረሱን ተመልክቷል።ነገር ግን ህዝቡ ነፃነቱን አጠቃቀም ላይ ክፍተቶች መታየታቸውን በማንሳት ኮሚቴው በነፃነት እና በደህንነት መካከል ሚዛኑ መጠበቅ እንዳለበት በማንሳት ማንኛውም ጥያቄ በሰለጠነ እና በሰከነ መልኩ ለሀገር ያለውን ፋይዳ በመመልት የተሰጠውን መብት መጠቀም እንደሚገባ መገምገሙን ነው አቶ ፍቃዱ ያነሱት።ከዚህ ውጪ የሚሄዱ ህገውጥ፣ ስርዓት አልበኝነት እና በሀይል ማንኛውንም ለመፈፀም የሚደረጉ ነገሮች ዋጋ የሚያስከፍሉ በመሆናቸው እና ነፃነቱን የሚፈታተኑ በመሆናቸው እነዚህን ክፍተቶች ከህዝቡ ጋር በመሆን በውስጡም ያሉትን ጉድለቶች በማረም የህግ የበላይነትን ሳይደራደር ማስከበር አለበት የሚል ድምዳሜ በግምገማው መደረሱን አስታውቀዋል።በለውጡ ላይ ያለውን ብዥታ የተመለከተው ኮሚቴው ለውጡ በህዝብ ግፊት ኢህአዴግ በውስጡ በወሰዳቸው እርምጃዎች የመጣ መሆኑን በማስመር ሁሉም በለውጡ ውስጥ ድርሻ እንዳለው ተመልክቷል።ኮሚቴው በግምገማው የደረሰባቸውን ድምዳሜዎች ያብራሩት አቶ ፍቃዱ፥ አንዱ ድምዳሜ እንድነትን የሚንዱ ነገሮች መታረም እንዳለባቸው የሚመለከተው ነው ብለዋል።በብሄራዊ ድርጅቶች መካከል በጋራ ያሳለፏቸው መልካም ነገሮች በጋራ የከፈሏቸው መስዋእቶች እና ትግሎች እንዳሉ ያነሱት አቶ ፍቃዱ፥ ዛሬ ላይ አነስተኛ እና ስትራቴጂክ ያለሆኑ ጉዳዮች አይደለም መታየት ያለባቸው ብለዋል።ይህንንም ታሳቢ በማድረግ ኮሚቴው አንድነትን የሚጎዱ ነገሮችን በግልጽ በመገምገም አንዱ ድርጅት ሌላው ላይ ጣት መቀሰር ሳይሆን ራሱን ከለውጡ አንፃር እንዲመለከት ድምዳሜ ላይ ተደርሷል ብለዋል።በጋራ በመስማማት ድምዳሜ የተደረሰባቸውን ነገሮችን በሁሉም ደረጃ መተግበር ላይ ክፍተቶች እንዳሉ ኮሚቴው ተመልክቷል።ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው የደረሰባቸውን ድምዳሜዎች መሰረት በማድረግም ቀጣይ አቅጣጫዎችን እንዳስቀመጠ አቶ ፍቃዱተናገርዋል።በሁሉም የሀገሪተ አከባቢዎች የዜጎች የመዘዋወር እና ንብረት የማፍራት ህገ መንግስታዊ መብት መከበር እንዳለበት በመመለክት የደህንነት እና ነፃነት ሚዛን በተጠበቀ መለኩ የህግ የበላይነት እንዲከበር አቅጣጫ አስቀምጧል።የለውጡ ስራዎች ተቋማዊ እንዲሆኑ ከማድረግ አንፃር የሚያስፈልጉ ህጎች እና ደንቦችን በማውጣት ህዝቡን ባሳተፈ ሁኔታ እንዲተገበሩም የሚል አቅጣጫ ተቀምጧል።የለውጡን ትክክለኛ ምን ማለት እና ዓላማው ምንድነው በሚለው ላይ ግልፅነት መፍጠር ሌላው አቅጣጫ መሆኑን አንሰተዋል።መገናኛ ብዙሃን በህዝብ አብሮነትና መቻቻል እንዲሁም አንድነት እና የህግ የበላይነት ላይ እንዲሰሩ ለማስቻልም እንዲሰራ ኮሚቴው አቅጣጫ ማስቀመጡ ነው የተናገሩት።ቀጣዩ ሀገር አቀፍ ምርጫም ህገመንግስቱ ባስቀመጠው መሰረት 2012 ላይ መካሄዱ አስፈላጊነት ላይ አቋም በመያዝ እንደ ድርጅትም እንደ መንግስትም ዝግጅት እንዲደረግ ነው አቅጣጫ ያስቀመጠው።በደቡብ ክልል እየተነሱ ባሉት የክልልነት ጥያቄ በተመለከተ ኮሚቴው መምከሩን የተናገሩት አቶ ፍቃዱ፥ ደኢህዴን በክልሉ እየተነሱ ላሉት ጥያቄዎች ሳይንሳዊ መፍትሄ ለመስጠት ያከናወነውን ጥናት ተመልክቷል።በጥናቱ መሰረት ደኢህዴን ያቀረበውን የክልልነት መዋቅር የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በአወንታ መመልከቱን እና ለተግባራዊነቱም ድጋፍ ለማድረግ መስማማቱን ገልፀዋል።ከኢህአዴግ ውህደት አንጻር በሀዋሳው ድርጅታዊ ጉባኤ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ የተካሄደ ጥናት አልቆ ውይይት እየተደረገ መሆኑን እና ሁሉም ብሄራዊ ድርጅቶች መክረውበት ለስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው እንዲያቀርቡ አቅጣጫ መቀመጡን ተናግረዋል።
https://waltainfo.com/am/31285/
545
5ፖለቲካ
በሆንግ ኮንግ አዉሮፕላን ጣቢያ ለሶስት ቀናት የሚዘልቅ አዲስ ተቃዉሞ መቀስቀሱ ተሰማ
ፖለቲካ
August 10, 2019
Unknown
በቻይናዋ እራስ ገዝ አስተዳደር ሆንግ ኮንግ አዉሮፕላን ጣቢያ ለሶስት ቀናት የሚዘልቅ አዲስ ተቃዉሞ መቀሳቀሱ ተሰማ፡፡በቻይናዋ እራስ ገዝ አስተዳደር ሆንግ ኮንግ ወንጀል ፈፅመዉ ጥፋተኛ የሚባሉ ዜጎች ለፈጸሙት ወንጀል ከቻይና መንግስት ፍርድ እንዲሰጣቸዉ የሚያስችል ህግ መዉጣቱን ተከትሎ የግዛቲቱ ነዋሪዎች ህጉን በመቃወማቸዉ ሆንግ ኮንግ ለወራት በህዝባዊ አመፅ ስትናወጥ ቆይታለች።ለሶስት ወራት የዘለቀዉ ህዝባዊ ተቃዉሞ ማብቂያዉ መች እንደሆነ ዛሬም በዉል የታቀወ ነገር የለም።  አልጀዚራ ባስነበበዉ መረጃ በግዛቲቱ አዉሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ ለሶስት ቀናት የሚዘልቅ አዲስ ተቃዉሞ ተቀስቅሷል። ተቃዋሚዎቹ በአዉሮፕላን ጣቢያዉ ድምፃቸዉን ያሰሙት በአዉሮፕላን ጣቢያዉ የሚመላለሱ አለም አቀፍ ተጓዦች የችግሩን መጠን እንዲረዱና አለም አቀፉ ማህበረሰብም በጉዳዩ ላይ የበኩሉን ተፅእኖ እንዲያሳድር በማሰብ ነዉ ተብሏል።የተቃዉሞዉ ዳግም መቀስቀስን ተከትሎ የሆንግ ኮንጓ ዋና አስተዳዳሪ ካሪ ላም መንግስታቸዉ ተቃዋሚዎችን የሚለማመጥበት ትዕግስት እንደሌለዉና አስፈላጊዉን እርምጃ ለመዉሰድ መሰናዳቱን አስታዉቀዋል።በቼክ ላፕ ኮክ አዉሮፕላን ጣቢያ የተሰባሰቡት ተቃዋሚዎቹ ጥቁር ቲሸርቶችን የለበሱና ቁጥራቸዉም በመቶዎች የሚቆጠር ስለመሆኑ ተነግሯል። ተቃዋሚዎቹ ከዚህ ቀደምም በተመሳሳይ ተቃዉሟቸዉን ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማድረስ መሰል ተቃዉሞ ያካሄዱ ሲሆን፣ የአሁኑም ለሁለተኛ ጊዜ ስለመሆኑ ተነግሯል።ተቃዉሞዉን ተከትሎም የአዉሮፕላን ማረፊያ ጣቢያዉ ኃላፊዎች በአከባቢዉ ያለዉ የፀጥታ ኃይል እንዲጠናከርና የአዉሮፕላን መሳፈሪያ ቅፅ ያልያዙ ሰዎች ወደ ቅጥር ግቢዉ እንዳይገቡ እግድ ጥለዋል።የአሁኑ ተቃዉሞ ከመንግስት አካላት እዉቅና የሌለዉ ቢሆንም ከዚህ ቀደም በአዉሮፕለን ጣቢያዉ የተደረጉ የተቃዉሞ ሰልፎች ግን በሰላማዊ መንገድ መጠናቀቃቸዉ ነዉ የተሰማዉ። በመሆኑም ምንም እንኳን ተቃዉሞዉ ቢኖርም የአዉሮፕላን ጣቢያዉ መደበኛ ስራዉን እያከናወነ ስለመሆኑ ተገልጿል።የአልጀዚራዉ ሰዉ ሮብ ማክብራይድ ከስፍራዉ እንደዘገበዉ የአዉሮፕላን ጣቢያዉ ተቃዉሞ ይልቅ የግዛቲቱን ባለስልጣናት ስጋት ዉስጥ የከተታቸዉ በቀጣይ ቀናት ሀመላዉ ሆንግ ኮንግ ይካሄዳል ተብሎ የተሰጋዉ የተቃዉሞ ሰልፍ ነዉ።በሆንግ ኮንግ የተቀሰቀሰዉ ተቃዉሞ ካስከተለዉ የፀጥታ መደፍረስ ባለፈ የግዛቲቱን ምጣኔ ሀብትም ክፉኛ እየጎዳዉ ስለመሆኑ መረጃዎች አመላክተዋል። በግዛቲቱ ኃላፊዎች ይፋ የተደረገ መረጃ እንዳመላከተዉ ባለፈዉ ወር መጨረሻ ላይ የነበረዉ የቱሪስት ፍሰት ከባለፈዉ አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ26 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል።   ይህ ደግሞ በግዛቲቱ ነዋሪወፖች ላይ የሚያስከትለዉ ምጣኔ ሀብታዊ ቀዉስ የከፋ እንደሚሆን ነዉ የሚጠበቀው። በሆንግ ኮንግ ለ250ሺ ሰዎች የስራ እድል የፈጠረዉ የቱሪዝም ዘርፉ 4.5 በመቶ የሚሆነዉን የግዛቲቱን ምጣኔ ሀብት ዘርፍም ይሸፍናል።የግዛቲቱ አስተዳዳሪ ካሪ ላምም ለወራት የዘለቀዉ ህዝባዊ ተቃዉሞ ያስከተለዉን ምጣኔ ሀብታዊ ቀዉስ ሱናሚ ሲሉ ከአስከፊዉ የአዉሎ ንፋስ ወጀብ ጋር አመሳስለዉታል።የሆንግ ኮንጉ ተቃዉሞ ግዛቲቱ በፈረንጆቹ 1997 ከእንግሊዝ ለቻይና ተላልፋ ከተሰጠች ወዲህ ከፍተኛዉ ስለመሆኑ አልጀዚራ በዘገባዉ አስታዉሷል።
https://waltainfo.com/am/33982/
326
5ፖለቲካ
ሰሜን ኮሪያ የአጭር ርቀት የባልስቲክ ሚሳኤል ሙከራ አደረገች
ፖለቲካ
August 10, 2019
Unknown
ሰሜን ኮሪያ ሁለት የባልሰቲክ ሚሳኤሎችን ወደ ባህር ማስወንጨፏ ተነግሯል፡፡ይህም ሀገሪቱ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ያደረገቻችውን የሚሳኤል ሙከራዎች  አምስት አድርሶታል፡፡ከደቡብ ሃምግዮንግ ግዛት ሃምሁን ከተማ እንደተተኮሱ የተነገረላቸው  ሁለቱ ሚሳኤሎች በጃፓን ባህር የኮሪያ ባህረ ሰላጤ አካባቢ ማረፋቸው ተነግሯል፡፡የባሊስቲክ ሚሳኤሎቹ  የመካከለኛ ርቀት ተወንጫፊዎች ሊሆኑ እንደሚችልም የደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከሰሜን ኮሪያ ሰላማዊ መልዕክት እንደደረሳቸው ከገለጹ በኋላ ሰሜን ኮሪያ ወደ ባልስቲክ ሚሳኤል ሙከራ ተመልሳ ገብጻለች፡፡የሰሜን ኮሪያው አቻቸው ኪም ጆንግ ኡን በበኩላቸው የደቡብ ኮሪያና አሜሪካ የጋራ ወታደረዊ ልምምድ እንዳልተዋጠላቸው ገልጸው እንደነበረም ቢቢሲ በዘገባው አስታውሷል፡፡
https://waltainfo.com/am/33983/
79
5ፖለቲካ
መቀንጨርን ዜሮ ለማድረግ መንግሥትና ባለድርሻ አካላት በቁርጠኝነት ሊሰሩ እንደሚገባ ም/ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን አሳሰቡ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 9, 2019
Unknown
መቀንጨርን ዜሮ ለማድረግ የመንግሥት እና የባለድርሻ አካላት ቁርጠኝነት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን አሳሰቡ።የሰቆጣ ቃል ኪዳን የሙከራ ምዕራፍ ትግበራን አስመልክቶ የተዘጋጀ ከፍተኛ የምክክር መድረክ በሸራተን ሆቴል ተካሂዷል።በመድረኩ ላይ የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡ተሳታፊዎቹ የመቀንጨር ችግርን በሚፈለገው ደረጃ ለመፍታት በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል፡፡በቀጣይ የሰቆጣ ቃልኪዳን አፈፃፀም ላይ የሚታዩ የበጀት፣ የግብዓት እና ተያያዥ ችግሮችን በመፍታት በተያዘው በጀት ዓመት ውጤታማ ስራ መስራት እንደሚገባ የጋራ አቅጣጫ ተቀምጧል። (ምንጭ፡-የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት)
https://waltainfo.com/am/32635/
75
0ሀገር አቀፍ ዜና
ፓኪስታን ከህንድ የካሽሚር ውሳኔ ጋር በተያያዘ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯን ወደ ቻይና ላከች
ፖለቲካ
August 9, 2019
Unknown
የፓኪስታኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሻህ ሙሀሙድ  ህንድ በካሽሚር ግዛት ያሳለፍችውን ውሳኔ እንድትቀለብስ ለመድረግ ያለመ ጉዞ ወደ ቻይና አድርገዋል፡፡በቻይና ቆይታቸውም ከሀገሪቱ ባለስልጣናት ጋር በጉዳዩ ላይ ውይይት እንደሚያደርጉም ነው የሚጠበቀው።የአሁኑ  የህንድ ውሳኔ ከፍተኛ  የፖለቲካ ትኩሳት በነገሰበት አካባቢ ባለፉት ሰባት አስርት ዓመታት ከተላለፉ ውሳኔዎች መካከል ጠንካራው እንደሆነም ፖለቲከኞች ይናገራሉ፡፡ይህን ተከትሎም ፓኪስታን ጉዳዩን ወደ ዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ለመውሰድ መዘጋጀቷን ገልጻለች።ህንድ በቅርቡ የሻረችው አንቀፅ 370 የካሽሚር ግዛት የነበረውን የራስ ገዝ አስተዳደር እና ህግ የሚያግድ ሲሆን፤ ውሳኔውን ተከትሎ ህንድ በርካታ ወታደሮችን ወደ አካባቢው በማሰማራት ፖለቲከኞችን አስራለች፣ የኢንተርኔት እና  የስልክ ግንኙነትም እንዲቋረጥ አድርጋለች፡፡ይህ ውሳኔ ወትሮም ሻክሮ የቆየውን የሁለቱን  ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ ወደ ውጥረት  ከቶታል፡፡ ህንድ ለካሽሚር ግዛት ልዩ መብት የሚሰጠውን ህገ መንግስታዊ ውሳኔ እንዲሻር ማድረጓ የሚታወስ ነው፡፡ምንጭ፦ አልጀዚራ
https://waltainfo.com/am/33981/
112
5ፖለቲካ
በደቡብ አፍሪካ የታሰሩ ኢትዮጵያውያን እንዲለቀቁ የማድረጉ ስራ መጀመሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 9, 2019
Unknown
በደቡብ አፍሪካ ጆሀንስበርግ የታሰሩ ኢትዮጵያውያን እንዲለቀቁ የማድረጉ ስራ መጀመሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡በደቡብ አፍሪካ ጆሀንስበርግ ከተማ ኢትዮጵያውያን እና ሌሎች የውጭ አገራት ዜጎች በሚነግዱበት የቢዝነስ ሴንተር ተብሎ በሚታወቅ አካባቢ የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴ አለ በሚል አለመግባባት በአገሪቱ ህግ አካላት መታሰራቸው ይታወሳል፡፡ኢትዮጵያውያኑን ለማስለቀቅ በፕሪቶሪያ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና በዚያው በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ የአትዮጵያ ኤምባሲ ማህረሰብ ከአመራሮች ጋር ንግግር እየተደረገ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነብያት ጌታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጸዋል፡፡ከዚህ በተጨማሪም ኢትዮጵያውያኑ የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው እና በህጋዊ መንገድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩትን ከእስሩ እንዲፈቱ የማድረጉ ስራ መኖሩን ገልጸዋል፡፡በሌላ በኩል በሱዳን በኩል ተከስቶ የነበረውን አለመግባባት ኢትዮጵያ እና እና የአፍሪካ ህብረት ለመፍታት ላሳዩት ቁርጠኝነት እውቅና መገኘቱን አውስተዋል፡፡በተጨማሪም ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲም እየተሰራበት እንደሆነ ገልጸው፣ በመካከለኛው ምስራቅ ስራ ሰርተው ደሞዝ የተከለከሉ ዜጎች ደሞዝ እንዲከፈላቸው የማድረግ ስራ ተሰርቷል ብለዋል፡፡በእስር ቤት የነበሩ ዜጎች ከከእስር ተለቀው እንዲመለሱ የኢትዮጵያ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስራቱን ገልጸው፣ በኬንያ ታስረው የነበሩ 64 ኢትዮጵያውያን በኢፌዴሪ በኬንያ ኤምባሲ በኩል መፈታታቸው አስታውሰዋል፡፡ 
https://waltainfo.com/am/32636/
144
0ሀገር አቀፍ ዜና
የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ እየተካሄደ ነው
ፖለቲካ
August 9, 2019
Unknown
የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ዛሬም ቀጥሎ እየተካሄደ ነው፡፡የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከትናንት ነሓሴ 2 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል፡፡ኮሚቴው የድርጅት ስራዎች አፈጻጸምና በሌሎች ሀገራዊ ወቅታዊ ጉዳች ላይ ውይይት እያደረገ ነው፡፡ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው የድርጅት ስራዎችና ወቅታዊ ሁኔታዎችን በጥልቀት ከገመገመ በኃላ ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
https://waltainfo.com/am/31284/
52
5ፖለቲካ
የኢትዮጵያና ኬንያ ተጎራባች ማህበረሶች የባህል እና ቱሪዝም ፌስቲቫል ሊካሄድ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
August 9, 2019
Unknown
በኢትዮጵያ የኛንጋቶም እና በኬንያ የቱርካና እና ሌሎች ማህበረሰቦች የባህል እና ቱረዝም ፌስቲቫል በኬንያ ሊካሄድ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።ተጎራባች ማህበረሰቦቸን ከባህል ባለፈ በጋራ ልማት፣ ሰላም እና ጸጥታ የሚጫወቱትን ፈርጀ-ብዙ ሚና ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ዓላማውን ያደረገው ፌስቲቫሉ በኬንያ የቱርካና ክልል ዋና ከተማ ሎድዋር ከነሐሴ 8 እስከ 11 ቀን 2011 ዓ.ም. ድረስ ይካሄዳል ተብሏል፡፡በኬንያ የኢፌዲሪ አምባሳደር መለስ ዓለም በፌስቲቫሉ ዙሪያ የቱርካና ክልል አስተዳዳሪ ጆስፋት ናኖክ ጋር በትናንትናው ዕለት በጽ/ቤታቸው ተወያይተዋል።አምባሳደር መለስ ዓለም በውይይቱ ወቅት፤ሚሲዮኑ በኢትዮጵያ እና ኬንያ የጋራ ድንበር አካባቢ የሚገኙ አጎራባች እና በባህል እና ቋንቋ የሚወራረሱ ማህበረሶቦች ዘንድ ያለውን ትስስር ለማጠናከር እንደሚሰራ ገልጸዋል።የቱርካና ክልል አስተዳዳሪ ጆስፋት ናኖክ በበኩላቸው፤ በኢትዮጵያ እና ኬንያ አጎራባች አካባቢዎች የሚገኙ ማህበረሰቦች ግንኙነት ለዘመናት የዘለቀ እና በባህል እና ቋንቋ መወራረስ ጠንካራ መሰረት ላይ የተገበነባ መሆኑን ተናግረዋል።የባህል መድረኩ ግጭቶችን ለማስወገድ፣ መግባባትን ለመፍጠር እና ልማትን ለማረጋጥ ይጠቅማልም ብለዋል።የቱርካና የባህል ፌስቲቫል በሰሜን ምዕራብ ኬንያ በሚገኘው የቱርካና ካውንቲ አስተዳደር አዘጋጅነት በየዓመቱ የሚካሄድ ከኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ዩጋንዳ በሚውጣጡ የአተከር ወይም የኛቴኬሪን ቋንቋ ተነጋሪ በሆኑት የኛንጋቶም፣ የቱርካና፣ የቶፖሳ፣የካራሞጆንግ፣ የጂ እና የቴሶ ህዝቦች ክበረ በዓል ሲሆን፤ በዕለቱ የሁለቱ ሀገሮች ባህሎች እና ሌሎች እሴቶች ለእይታ ይቀርቡበታል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ባደረሰን መረጃ መሰረት ኤምባሲው በሚያዚያ 2011 ዓ.ም. በቦማስ ኦፍ ኬንያ የቱሪስት መንደር በተደረገው የቦረና ዓመታዊ የባህል ምሽት ላይ ኢትዮጵያን ወክሎ መታደሙን አስታውሷል። 
https://waltainfo.com/am/32637/
200
0ሀገር አቀፍ ዜና
በኬንያ በተከሰተው ድርቅ ከአንድ ሚልዮን በላይ ዜጎች ለረሃብ ተጋልጠዋል ተባለ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 9, 2019
Unknown
በኬንያ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ከአንድ ሚልዮን በላይ ዜጎች ለረሃብ ተጋልጠዋል ተባለ፡፡በተለይም በሰሜናዊ የኬንያ ክፍል የሚኖሩ አርብቶአደሮች በድርቁ ምክንያት ለስደት እና ለግጭት መዳጋቸው ተገልጿል፡፡አና ሊሳንጅሬ በሰሜን ኬንያ በአርብቶ አደርነት የሚተዳደሩ ኬንያዊት ሲሆኑ፣ በአካባቢያቸው በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ግጦሽ እና ውሃ በመጥፋቱ  ከነቤተሰባቸው ለመሰደድ ተገደናል ብለዋል፡፡ለሚያረቧቸው እንስሳት የሚሆን ግጦሽና ዉሃ ለማግኘትም የአንድ ቀን ጉዞ እንደሚያደርጉ ነው የገለጹት፡፡በሰሜናዊው ኬንያ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ እረኞች ለከብቶቻቸው የሚሆን ግጦሽና ዉሃን ለማግኘት ማራላል ወደተባለች አካባቢ እና ወደ ሌሉችም ስፍራዎች ይሰደዳሉ፡፡በሀገሪቱ እየተከሰተ ባለው ተደጋጋሚ ድርቅ ምክንያትም በእረኞች እና በአካባቢው ተወላጆች መካከል ግጭቶች ይነሳሉ ተብሏል፡፡እንደ የአልጀዚራዋ ካትሪን ሶል መረጃ በአካባቢው የሚነሱ ግጭቶች መንስኤያቸው ቀላል ቢሆንም የበርካቶችን ህይወት እስከመቅጠፍ ይደርሳል፡፡እነዚህ በኬንያ ሳምቡሩ በተባለች ቦታ የሚኖሩ ሽማግሌዎችና የጎሳ አባላት ናቸው፡፡ የዛሬ 10 ዓመት በተከሰተው ችግር ምክንያት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በተገደሉበት ፀብ እና መፍትሔ ላይ እየተወያዩ ነው፡፡በኬንያ እንዲህ ዓይነቱ ድርቅ ተከስቶ ሚልየኖችን ለርሃብ ሲያጋልጥ ይህ የመጀመሪያው አይደለም፡፡ ሀገሪቱ የዛሬ ሁለት ዓመት በገጠማት ድርቅ ምክንያት ብሔራዊ የአደጋ ጊዜ ማወጇ አይዘነጋም፡፡ (ምንጭ፡-አልጀዚራ)
https://waltainfo.com/am/33461/
147
0ሀገር አቀፍ ዜና
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር የጎዳና ኑሮና ልመናን በህግ እስከመከልከል የሚደርስ እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 10, 2019
Unknown
የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ታከለ ኡማ በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካደ ባለው “ያገባኛል ይመለከተኛል” በሚል መሪ ሀሳብ በተካሄደው የገቢ ማሰባሰቢያ የመዝሙር ኮንሰርት ላይ ነው ይህን ያሉት፡፡ምክትል ከንቲባው በአዲስ አበባ ከየትኛውም የአገሪቱ ክፍል መጥቶ ሰርቶ መኖር ይቻላል፣ ጎዳና ግን መኖርም ሆነ መለመን የማይቻልበት ሁኔታ እንዲፈጠር ለመስራት እንገደዳለን ብለዋል፡፡በተናጠል ከምንሰጥ መንግስት በዘረጋው አሰራር ስር በመስጠት ጎዳና ላይ የወጡ ወገኖችን በዘላቂነት መቀየር እንደሚገባም ነው የገለፁት፡፡የኮንሰርቱ አዘጋጅ የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን ሊደርስ ፌሎውሺፕ በበኩሉ 100 ሚሊየን ብር አሰባስቦ ለትረስት ፈንዱ ገቢ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡የፌሎውሺፑ ሊቀመንበር ሐዋሪያው ጳውሎስ ዜጎችን ከጎዳና ላይ ለማንሳት በሚደረገው ጥረት ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል፡፡የመዝሙር ኮንሰርቱ ገቢ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ጎዳና ላይ የወጡ ዜጎችን ለማንሳት የተመሰረተውን ማህበራዊ ትረስት ፈንድ ለመደገፍ ይውላል ተብሏል፡፡በስነ ስርዓቱ ከመግቢያ ክፍያ በተጨማሪ በ6400 የአጭር ፅሁፍ መልዕክት የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር መካሄዱን ከአዲስ አበባ ከንቲባ ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
https://waltainfo.com/am/32642/
126
0ሀገር አቀፍ ዜና
የመከላከያ ሰራዊትን ወታደራዊ እውቀት ለማሳደግ መንግስት በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ጠ/ሚኒስትር  ዐብይ አህመድ ገለፁ፡፡
ቢዝነስ
August 10, 2019
Unknown
የመከላከያ ሰራዊትን ወታደራዊ እውቀት ለማሳደግ መንግስት ከመቼውም ጊዜ በላይ እየሰራ እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ገልፀዋል፡፡የመከላከያ አዛዥነት ስታፍ ኮሌጅ ለ13ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን 100 ከፍተኛ መኮንኖች ባስመረቀበት ወቅት ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት፡፡በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ከተመረቁት 100 ከፍተኛ መኮንኖች ውስጥ 92 ፖስት ስታፍ ሲሆኑ ስምንት ያህሉ የሁለተኛ ድግሪያቸውን የተከታተሉ ናቸው።ከእነዚህ ውስጥም 21ዱ ከጅቡቲ፣ ሶማሊያ እና ደቡብ ሱዳንን የመጡ መሆናቸውም ነው በምረቃ ስነ ስርዓቱ ወቅት የተገለፀው።የጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዶክተር አብይ አህመድ ለተመራቂዎች ዲፕሎማ በሰጡት ወቅት ሰልጣኞች በስነ ምግባር፣ በወታደራዊ ጥበብ፣ በሙያዊ ብቃትና በላቀ ዝግጅት የሰራዊት አባላትን ለመምራት የሚያስችላቸውን እውቀትና ከህሎት መከታተላቸውን ገልፀዋል።በመሆኑም የቀሰሙትን ትምህርት ከዚህ በፊት ካገኙት ልምድና በተፈጥሮ ከያዙት  እውቀት ጋር በማዋሃድ በትጋት ሀገራቸውን እንዲያገለግሉ አሳስበዋል፡፡የመከላከያ ሰራዊትን ወታደራዊ እውቀት ለማሳደግ መንግስት ከመቼውም ጊዜ በላይ እየሰራ እንደሚገኝም ነው የገለፁት፡፡ወታደራዊ ተቋማት በሳይንስና በቴክኖሎጂ ፣ በስነ ምግባር አርዓያዎች፣ ሀገርን እና ወገንን በመጠበቅ አኩሪዎች፣ ህግና ስርዓትን በማክበር እና በማስከበር ተምሳሌት መሆን ይገባቸዋል ብለዋል።  
https://waltainfo.com/am/23900/
141
3ቢዝነስ
በክልሉ የሚገኙ ተፈጥሯዊ፣ ታሪካዊና ባህላዊ ሀብቶችን በተቀናጀ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ስራ በጋራ ለመስራት ውይይት ተደረገ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 8, 2019
Unknown
የደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል እና ዋልታ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ኮርፖሬት የተቀናጀ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ስራዎችን በጋራ ለመስራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ተወያዩ።በዚህ ወቅት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ ሰብለጸጋ አየለ እንደተናገሩት፤ የክልሉ መንግስት በክልሉ የሚገኙ የባህል እና የቱሪዝም መስህቦችን ለማጎልበትና ለማሳደግ ከዋልታ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ኮርፖሬት ጋር በጋራ ለመስራት ፍላጎት አለው።በክልሉ የሚገኙ ተፈጥሯዊ፣ ታሪካዊና ባህላዊ ሀብቶችን ለተቀረው ዓለም በማስተዋወቅ ክልሉን የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ እየሰሩ መሆኑን የገለጹት ቢሮ ሃላፊዋ፤ በዚህ ዙሪያም በቀጣይ በቂ ግንዛቤ እንዲፈጠር ከዋልታ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ኮርፖሬት ጋር በጋራ እንሰራለን ብለዋል።ቢሮ ሃላፊዋ የዋልታ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ኮርፖሬት የተለያዩ የስራ ክፍሎችም ከኮርፖሬቱ ማኔጅመንት አባላት ጋር በመሆን ጎብኝተዋል።የዋልታ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ኮርፖሬት ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ንጉሴ መሸሻ በበኩላቸው፤ ኮርፖሬቱ ከክልሉ መንግስት ጋር በጋራ ለመስራ በመመረጡ ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።ኮርፖሬቱ ከዚህ ቀደም በተለያዩ ዶክመንታሪዎችና ፕሮግራሞች የክልሉን የባህል ስራዎች በተለያዩ ዶክመንታሪ ፊልሞችና ፕሮግራሞች በማስተዋወቅ በቅንጂት ሲሰራ መቆየቱን አስታውሰው፤ አሁንም የክልሉ ባህል እና እሴቶች ላይ ግንዛቤ የሚያጎለብቱ ስራዎችን እንሰራለን ብለዋል።
https://waltainfo.com/am/32634/
147
0ሀገር አቀፍ ዜና
ኢትዮጵያን ደቡብ ኮሪያ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ለመቀነስና አረንጓዴ ኢኮኖሚን ለማሳደግ በጋራ እንደሚሰሩ ገለፁ
ቢዝነስ
August 8, 2019
Unknown
ሁለቱ አገራት የአየር ንብረት ለውጥ ተፅእኖን ለመቀነስና  አካባቢ ጥበቃ ስራን ለማጠናከር የተለያዩ ልምዶች የሚገኙበት የጋራ መድረክ አዘጋጅተዋል::በመድረኩ ላይ የተገኙት የአካባቢ ደንና አየር ንብረት ለዉጥ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ፍቃዱ በየነ ኢትዮጵያ እየገነባች ላለዉ አረንጓዴ ኢኮኖሚ የካርበን ልቀትን መቀነስ አንዱ አጀንዳ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ በዚህም ኮሪያ የቴክኖሎጂና የፋይናንስ ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል፡፡በኢትዮጵያ የኮሪያ አምባሳደር ሆን ሚን ሊም የአየር ንብረት ለዉጥን ለመቋቋም አለምአቀፍ ትብብር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያና ኮሪያም በጋራ እንደሚሰሩና የኮሪያ ተሞክሮም ለኢትዮጵያ እንደሚቀርብ ተናግረዋል፡፡በኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለዉጥ ላይ ያተኮረ የኮሪያ ተሞክሮ በኮሪያ ዩኒቨርሲቲ በኩል ለኢትዮጵያ የአቅም ግንባታና የቴክኖሎጂ ድጋፍ እየተሰጠ ነዉ፡፡ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለዉጥን ለመቋቋም ከኮሪያ አለምአቀፍ ትብብር ኤጀንሲ ጋር በመተባበር እየሰራች ትገኛለች፡፡የአየር ንብረት ለዉጥ እያስከተለ ያለዉን ዘርፈ ብዙ ተፅዕኖ ለመቋቋም የሚያስችል የተሞከሮና ልምድ ልዉዉጥ በኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያ መካከል እየተደረገ ነዉ፡፡ በዚህም ኢትዮጵያ የአቅም ግንባታና የቴክኖሎጂ ድጋፍ ታገኛለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡ኢትዮጵያ የፓሪሱን የአየር ንብረት ለዉጥ ስምምነት ከፈረሙ አገሮች አንዷ ናት፡፡ በዚህም ስምምነቱን በማክበር ለሌሎች አገራት ምሳሌ ለመሆን የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ እያከናወነች ትገኛለች ተብሏል፡፡ 
https://waltainfo.com/am/23897/
148
3ቢዝነስ
የዓለምን ሙቀት መጨመር ለመግታት የአስተራረስ እና የአመጋገብ ዘዬ ሊለወጥ እንደሚገባ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 8, 2019
Unknown
የዓለምን ሙቀት መጨመር ለመግታት የአስተራረስ እና የአመጋገብ ዘዬ ሊለወጥ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡የሙቀት መጨመርን ወይም የምግብ ዋስትና፣ ጤና እና ብዝሀ ሕይወት ችግርን ለመግታት የዓለም ሕዝብ የመሬት አጠቃቀም፣ አመራረት እና አመጋገብ ላይ ለውጥ ማምጣት አለበት ነው የተባለው።የመንግስታቱ ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ቦርድ ዛሬ ይፋ ባደረገው ሪፖርት፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ እየጨመረ የመጣው የሕዝብ ቁጥር እና የምግብ ፍጆታ አጠቃቀም በመሬት እና ውሃ አጠቃቀም ላይ ያልተጠበቀ ተፅዕኖ አሳድሯል ብሏል።የአመጋገብ ሥርዓት ለውጥ ማድረግ፣ ተክሎችን መሠረት ያደረጉ እና ሚዛናዊ የሆነ ከእንስሳት ተዋጽኦ የተገኙ ምግቦችን መጠቀም እ.አ.አ በ2050 ላይ በሚሊየኖች የሚቆጠር መሬት ነፃ እንዲሆን ብሎም በየዓመቱ ከ0.7 እስከ 8.0 ጊጋ ቶን የሚደርስ በካይ ጋዝ ማስቀረት ይቻላል ብሏል።ነገር ግን የተጠቀሱትን ተግባራት ከማድረግ መዘግየት በተወሰኑ ሥነ ምህዳሮች ላይ የማይካካስ ተፅዕኖ በማሳደር የዓለም ሙቀት መጨመርን ያባብሳል ሲል አትቷል።የመንግስታቱ ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ቦርድ ይህንኑ ሪፖርት ለማጠናቀቅ እና በያዝነው የፈረንጆች 2019 መጨረሻ አካባቢ በቺሊ ለሚካሄደው የዓለም ሙቀት መጨመር የተመለከተ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ግብዓት ለመስጠት በያዝነው ሳምንት ውስጥ ጄኔቫ ውስጥ ይገናኛል። (ምንጭ:-ሮይተርስ)
https://waltainfo.com/am/34124/
148
0ሀገር አቀፍ ዜና
የዴሞክራሲ እሴቶችን በማስረጽ የሚዲያ ተቋማት ሚና ዝቅተኛ ነበር ተባለ
ፖለቲካ
August 8, 2019
Unknown
ባለፉት 20 አመታት ዴሞክራሲን በማስረፅ ረገድ የህዝቦችን ተሳትፎ የቃኘ ጥናት ይፋ በሆነበት ወቅት እንደተገለፀው፤ በርካታ የሚዲያ ተቋማት የዴሞክራሲ እሴቶችን አጉልቶ በማውጣት ረገድ ሰፊ ውስንነቶች ታተውባቸዋል፡፡ባለፉት ዓመታት በርካታዎቹ  የስነ-ምግባር መርሆዎችን ሳይጠብቁ  የመዘገብ ዝንባሌ ነበራቸው ተብሏል፡፡በኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢኒስቲትዩት በተካሄደውና ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተወከሉ ዜጎች በተሳተፉበት አውደ ጥናት በዋናነት በዴሞክራሲ ስርፀት ዙሪያ የዜጎችን ምልከታ፣ አተገባበርና ተፅእኖን በመገምገም መፍትሄን ማመላከት እንደሆነ ተገልጿል፡፡ሙሉ በሙሉ በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ትኩረቱን ባደረገው በዚህ ጥናት ፖለቲከኞች ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ በማተኮር ሀሳብ ከማመንጨት ይልቅ በግላዊ ጥቅሞቻቸው ላይ ማተኮራቸው ሀላፊነታቸውን በአግባቡ እንዳይወጡ ማድረጉ ተነስቷል፡፡ዜጎችም ቢሆኑ  ነገሮችን በሰከነ ሁኔታ ከማጤን ይልቅ በስሜታዊነት ወደ አላስፈላጊ ግጭቶች የማምራት ሁኔታ ሲስተዋልባቸው እንደነበር ያመላከተው ጥናቱ፤ ይህም ዴሞክራሲ ስር እንዳይሰድ የራሱን ተፅዕኖ ማሳደሩን ተነስቷል፡፡በመንግስት በኩል የታዩ ክፍተቶችንም ጥናቱ ያመላከተ ሲሆን፤ በተለይም ለአሰራር ምቹ ያልሆኑ አደረጃጀቶችን ያለመተቸት ችግር፣ በፓርቲዎች የግል አቋም ጣልቃ መግባትን ጨምሮ የዴሞክራሲ ተቋማትን ተናበውና ተቀናጅተው እንዲሰሩ ያለማድረግ ችግሮች ተስተውለዋል፡፡በመሆኑም ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለዴሞክራሲ ስርፀጥ ሚናውን በአግባቡ እንዲወጣ በመድረኩ ጥሪ ቀርቧል፡፡
https://waltainfo.com/am/31282/
147
5ፖለቲካ
በአዲስ አበባ የሞተር ብስክሌት ተሽከርካሪዎች ዳግም ወደ አገልግሎት ለማስገባት ምክክር ተካሄደ
ቢዝነስ
August 8, 2019
Unknown
በአዲስ አበባ ከተማ በከፊል የታገደውን የሞተር ብስክሌት ተሽከርካሪዎች አገልግሎት ዳግም ወደ ስራ እንዲገቡ የሚያሥችል ረቂቅ ላይ ውይይት ተካሂዷል።ለውይይት የቀረበው ረቂቅ መመሪያ በአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የተዘጋጀ ነው፡፡ረቂቁ ህግና ስርዓትን በማበጀትና ሞተረኞች በተሻለ ሁኔታ በማህበር እንዲደራጁ በማድረግ በከተማዋ የትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችል እንደሆነ ተብራርቷል፡፡መመሪያው ሞተረኞች ከቦታ ቦታ በመንቀሳቀስ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡ፣ ዕቃ ማመላለስን ጨምሮ ለግል ትራንስፖርት አገልግሎት መጠቀምን የሚፈቅድ ነው።አገልግሎቱን ለመስጠት ከባለስልጣኑ ፈቃድ የሚወስዱት ሞተረኞችም በኮድ 3 የተመዘገቡት ብቻ ሲሆኑ በኦሮሚያና አማራ ክልል ሰሌዳ የሚጠቀሙ ሞተረኞች ግን በአዲስ አበባ አገልግሎት መስጠት አይችሉም ተብሏል።መመሪያው የመከታተያና የመቆጣጠሪያ ስርዓት ቴክኖሎጂ /ጂ ፒ ኤስ/ በማስገጠም  አንድ ሞተረኛ አንድ አገልግሎት ብቻ እንዲሰጥ የሚፈቅድ መሆኑ ተገልጿል፡፡
https://waltainfo.com/am/23898/
101
3ቢዝነስ
ለኢትዮጵያና ጃፓን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የመታሰቢያ ስነ ስርአት በቤተመንግስት ተከናወነ
ፖለቲካ
August 8, 2019
Unknown
በብሄራዊ ቤተመንገስት ውስጥ በሚገኘውና በዋነኝነት በጃፓን መንግስት በልዩ ሁኔታ ጥበቃ በሚደረግልት የአትክልት ስፍራ የኢትዮጵያና ጃፓንን ረጅም ዕድሜ ያስቆጠረ ዲፕሎማሲዊ ግንኙነት ለማስታወስ የሻይ ማፍላት ስነስርአት ተከናወነ፡፡እ.ኤ.አ 1956 ቀዳማዊ ሀይለስላሴ በጃፓን ያደረጉት ጉብኝት ተከትሎ ከአመታት በኋላ የጃፓና ልኡል አዲስ ካገባት ባለቤቱ ጋር በመሆን የጫጉላ ሽርሽራቸውን በአዲስ አበባ በማድረግ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ወደ ህዝብ ለህዝብ ቀረቤታ አሳድገውታል፡፡በወቅቱ ቀዳማዊ ሀይለስላሴ ሁለቱን ሙሽሮች ተቀብለው ከማስተናገድ ባሻገር በብሄራዊ ቤተመንገስት ለጃፓን ህዝብ መታሰቢያ የሚሆን የአትክልት ቦታ በመስጠት ቋሚ ማስታወሻ አስቀምጠዋል፡፡በተለይም ቀዳማዊ ሀይለስላሴ እ.ኤ.አ 1956 በጃፓን ያደረጉት ይፋዊ ጉብኝት ለሁለቱ ሀገራት አዲስ የግንኙነት ምእራፍ በመክፈት ግንኙነቱም ወደ ህዝብ ለህዝብና የባህል ቅርርብ እንዲያመራ አድርጎታል፡፡የሁለቱን ሀገራት ታሪካዊ ወዳጅነት በመዘከር የዲፕሎማሲ ድልድይ ሆኖ እያገለገለ በሚገኘው በዚህ የአትክልት ስፍራ የመንግስት ከፍተኛ ሀላፊዎችና  አምባሳደሮች በተገኙበት የጃፓን የሻይ ማፍላት ስነ ስርአት ተካሂዷል፡፡ይህ ስነስርአት የኢትዮጵያ እና የጃፓንን የዘማናት ወዳጅነት በማስታወስ ግንኙነቱን ለማደስ የሚያስችል መነቃቃት ለመፍጠር የሚያግዝ ስለመሆኑ ተገልጧል፡፡ጃፓን  ለኢትዮጵያ ንካራ የልማት አጋር ስትሆን በተለይም በትምህርት እና ስልጠና ዘረፍ የሰው ሀይል ልማት ላይ ከፍተኛ እገዛ እያደረገች ትገኛለች፡፡የከፍተኛ ትምህረት ሚኔስቴር ሚኒስትር ዲኤታ የሆኑት ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ትምህርተቻወን በጃፓን  የተከታተሉ ሲሆን  ከጃፓን ማህበረሰብ ጋርም ጠንካራ ቀረቤታ አላቸው፡፡ጃፓኖች ከኢትዮጵያ ጋር የሚያመሳስላቸው በርካታ ጎዳዮች እንዳሉ የሚጠቅሱት ፕሮፌሰር አፈወርቅ ያም ሆኖ ኢትዮጵያውያን ከጃፓኖች ልንማራቸው የሚገቡ የእድገት እና የባህል መሰረቶች መኖራቸውን ያነሳሉ፡፡በብሄራዊ ቤተ መንገስት በሚገነው የጃፓን የአትክልት ስፍራ በተካሄደው  መርህ ግብር ላይ የኢትዮጵያ ቡና እና የጃፓን ሻይ ማፍላት ስነ ስርአት ተካሂዷል፡፡ሁለቱ ሀገራት ከሻይና ቡና ስነስረአት  ባሻገር በተለያዩ ባህሎች የሚያመሳስላቸው እሴት ያላቸው ሀገራት በመሆናቸው አጋጣሚው የባህል መቀራረቡን ወደ ህዝብ ለህዝብ ትስስር ለማሳግ መልካም አጋጣሚ መሆኑ ተገልቷል፡፡የኢትዮጵያና የጃፓን ግንኙነት እ.ኤ.አ ከ1930ቹ ጀምሮ በተለያዩ የእድገት ምእራፎች ውስጥ ያለፈ ቢሆነም ይህ የሁለትዮሽ ግንኙነቱ ወደ ላቀ የዲፕሎማሲ ግንኙት ምእራፍ የተሸጋረው ግን 1950ዎቹ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡     
https://waltainfo.com/am/31283/
258
5ፖለቲካ
በአልሸባብ ቁጥጥር ስር የነበረችውን አውዴግል ከተማ ነጻ ወጣች
ፖለቲካ
August 8, 2019
Unknown
በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ሀይል አሚሶምና የሶማሊያ የደህንነት ሀይል በታችኛው ሸበሌ ቀጠና በአልሸባብ ቁጥጥር ስር የነበረችውን አውዴግል ከተማን ነጻ አውጥተዋል፡፡አሸባሪ ቡድኑ አልሸባብ በሶማሊያ በሚሰነዝራቸው የሽብር ጥቃቶች በርካታ ዜጎች ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡ ሀገሪቱም የጸጥታ ስጋቷን መቅረፍ ተስኗት ቆይታለች፡፡ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን የሀገሪቱ የጸጥታ ሀይሎችና የሰላም አስከባሪ ሀይሎች የቡድኑን ጠንካራ ይዞታዎች በመገርሰስ ላይ ይገኛሉ፡፡በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ሀይል አሚሶምና የሶማሊያ የደህንነት ሀይል ባካሄዱት የጋራ ወታደራዊ  ዘመቻ በታችኛው ሸበሌ ቀጠና በአሸባሪው ቡድን አልሸባብ ቁጥጥር ስር የነበረችውን አውዴግል ከተማን ነጻ አውጥተዋል ተብሏል፡፡ከተማይቱ ላለፉት ዓመታት የሽብር ቡድኑ መናሀሪያና የጥቃት ሴራ ማቀነባበሪያ ሆና መቆየቷን ያስታወሰው ዘገባው፤ በተደራጀው ወታደራዊ ዘመቻ ከሽብር ቡድኑ ይዞታ ነጻ መውጣቷን አመላክቷል፡፡የከተማዋን ነጻ መውጣት ተከትሎ  በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ሀይል አሚሶም ዋና አዛዥ አምባሳደር ፍራንሲስኮ ማዴራ፤ ወታደራዊ ተልዕኮውየሶማሊያ የደህንነት ሀይል ከዚህም በላይ ውስብስብ የሆኑ ግዳጆችን መወጣት የሚችል መሆኑን ያሳየ ነው ብለዋል፡፡በአልሸባብ ይዞታ ስር የቆዩ ቦታዎችን ነጻ ማውጣት የሽብር ቡድኑ የጥቃት ሰለባ ሆነው ለቆዩና ስቃይና እንግልት ሲደርስባቸው ለነበሩ የሶማሊያ ዜጎች ፍትህን እንደማጎናጸፍ ይቆጠራል ብለዋል፡፡በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ሀይል አሚሶምና የሶማሊያ የደህንነት ሀይል የሶማሊያን ህዝብ ክብር ለማስመለስና ለዜጎች የተሻለ ሕይወት በአልሸባብ ይዞታ ስራ ያሉ ሌሎች ቦታዎችን ነጻ ለማውጣት ስራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ዋና አዛዡ ገልጸዋል፡፡ካሳለፍነው የፈረንጆቹ ሚያዚያ ወር ጀምሮ በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ሀይል አሚሶምና የሶማሊያ የደህንነት ሀይል የአልሸባብ ጠንካራ ይዞታ የነበሩ ቦታዎችን ማስለቀቃቸውን አስታውሶ ኬ ኤም ኤ የዜና ወኪል ዘግቧል፡፡
https://waltainfo.com/am/33320/
209
5ፖለቲካ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ልዩ መልዕክተኛ ጋር ተወያዩ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 7, 2019
Unknown
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ልዩ መልዕክተኛ ጋር ተወያዩየኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የተባበሩት መንግስታት ሴክሬታሪ ጄነራል የአፍሪካ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ  ሚስ ሀና ሰርዋ ቴቴን ዛሬ በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።ሚኒስትሩ አቶ ገዱ በዚህ ወቅት ባደረጉት ንግግር የመንግስታቱ ድርጅት ለአፍሪካ ጸጥታና ሰላም መረጋጋት ትልቅ አስተዋጽኦ እያደረገ እንደሚገኝ በማስታወስ፤ ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የጸጥታ ምክር ቤት  እና የአፍሪካ ሕብረት የጸጥታ ምክር ቤት በአዲስ አበባ የሚያደርጉት የምክክር መድረክ በስኬት እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ትብብር እንደምታደርግ አስታውቀዋል።ሀገሪቱ በኢጋድ ሊቀ መንበርነት ባላት ሚና በቀጠናዋ ሰላም ለማስፈን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እንደምትሰራም ሚኒስትሩ አክለው ገልጸዋል።የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ልዩ መልዕክተኛ  ሚስ ሀና ሰርዋ ቴቴ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ በሱዳን የነበረው አለመረጋጋት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ላደረገቸው ትልቅ ሚና አመስግነዋል።ልዩ መልዕክተኛዋ  የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኢትዮጵያ የምታደርጋቸው የሰላም ማስከበርና ተዛማጅ ሥራዎች ለመደገፍ ቁርጠኛ እንደሆነም አስታውቀዋል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/በት ለጣቢያችን ባደረሰው መረጃ መሰረት ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ መስከረም 23 ቀን 2019 ኒው ዮርክ በሚካሄደው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ተሳታፊ እንድትሆን  ልዩ መልዕክተኛዋ ጥሪ አቅርበዋል።በተመሳሳይ  አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የተባበሩት መንግስታት ኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (UNIDO) ተወካይና የክልላዊ ቅርንጫፍ ዳይሬክተር ሚስ አውረሊያ ካላብሮን ዛሬ  በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ  በዚህ ወቅት ባደረጉት ንግግር የተባበሩት መንግስታት ኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ኢትዮጵያ  የጀመረችውን የኢንዳስትሪያላይዜሽን ጉዞ  እውን ለማድረግ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ በመግለጽ ለድርጅቱ ምስጋና አቅርበዋል።የኢትዮጵያ መንግስት ድርጅቱ የሚያስተባብራቸውን የልማት ሥራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ አስፈላጊውን ትብብር እንደሚያደርግም ሚኒስትሩ ገልጸዋል።የተባበሩት መንግስታት ኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ተወካይና የክልላዊ ቅርንጫፍ ዳይሬክተር ሚስ አውረሊያ ካላብሮ   በበኩላቸው፤ በኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ለውጥ በማድነቅ፤ድርጅቱ በሀገሪቱ ለሚገኙ የቆዳ፣ጨርቃ ጨርቅ፣ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርኮች እንዲሁም ሌሎች ፕሮጀክቶች ድጋፍ እያደረገ እንደሆነ ለክቡር ሚኒስትሩ አስረድተዋል።በተጨማሪ ድርጅቱ ለሸገር ማስዋብ ፕሮጀክት ድጋፍ እንደሚያደርግ በመግለጽ፤ ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ ከኖቬምበር 3 እስከ 7 ቀን 2019 አቡ ዳቢ በሚካሄደው UNIDO(United Nations Industrial Development Organization) ኮንፈረንስ ተሳታፊ እንድትሆን ክብርት ዳይሬክተሯ ጥሪ አቅርበዋል። 
https://waltainfo.com/am/32630/
273
0ሀገር አቀፍ ዜና
በጋምቤላ ከተማ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት ያደረሰ የፖሊስ አባል ተያዘ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 7, 2019
Unknown
በጋምቤላ ከተማ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት የፈጸመ የፖሊስ አባል በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ።የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ቱት ኮር እና የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አቶው ኡኮት ጥቃቱን አስመልክቶ በጋራ በሰጡት መግለጫ እንዳመለከቱት አባሉ ጉዳቱን ያደረሰው ከተመደበበት ቦታ በመልቀቅ መናኸሪያ አካባቢ ሄዶ ተኩስ በመክፈት ነው።ዛሬ ከቀኑ ስምንት ሰዓት ላይ በደረሰው ጥቃት ዘጠኝ ሰዎች ላይ የመቁሰል አደጋ መድርሱም ተገልጿል።ይሔን ተከትሎ ከተፈጠረው ግርግር ጋር ተያይዞም ሌሎች አራት ሰዎች በድንጋይ ውርወራ ጉዳት ሲደርስባቸው የፖሊስ አባሉ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት መሆኑንም ኃላፊዎቹ ተናግረዋል።ጉዳት የደረሰባቸው ግለሰቦች በጋምቤላ ሆስፒታል አስፈላጊው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን ጠቁመው በወቅቱ በአካባቢው ተፈጥሮ የነበረው ግርግርም በፀጥታ አካላት ጥረት ወደ ነበረበት መረጋጋት መመለሱን አስታውቀዋል።በደረሰው ጉዳት ማዘናቸውን የገለጹት ኃላፊዎቹ ጉዳዩ የአንድ ግለሰብ መሆኑን በመገንዘብ ህብረተሰቡ በተረጋጋ መልኩ የተለመደውን የዕለት ተዕለት ተግባሩን ያለስጋት ማከናወን እንዳለበትም አሳስበዋል።በተጨማሪም ህብረተሰቡ የአካባቢውን ሰላም ለማስጠበቅ እያደረገ ያለውን ተሳትፎ እንዲያጠናክር የጠየቁት ኃላፊዎቹ በጥቃቱ ያለፈ የሰው ህይወት እንደሌለም አመልክተዋል። (ምንጭ፡-ኢዜአ)
https://waltainfo.com/am/32631/
141
0ሀገር አቀፍ ዜና
ምክትል ከንቲባው የመሬት ልማት ማኔጅመንትን ጨምሮ በአራት ተቋማት ድንገተኛ ጉብኝት አደረጉ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 8, 2019
Unknown
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ በአንድ ህንፃ ላይ አገልግሎት እየሰጡ ባሉ የመሬት ልማት ማኔጅመንትን ጨምሮ በፕላን ኮሚሽን፣ ግንባታ ፈቃድ እና ቅሬታ ሰሚ ጽ/ቤቶች ድንገተኛ ጉብኝት አድርገዋል፡፡አዲስ አበባን ተመራጭ የኢንቨስትመንትና የቢዝነስ ማዕከል ለማድረግ አስተዳደሩ ላስቀመጠው ግብ ስኬታማነት የአንድ ማዕከል አገልግሎትና የአገልግሎት ጥራት ደረጃን ማሳደግ የላቀ ትኩረት ተሰጥቶታል፡፡በዚህ እንቅስቃሴ በከተማው ተቀራራቢና ተመሳሳይ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትን በአንድ ማዕከል በማሰባሰብ የአገልግሎት ቅልጥፍናንና ጥራትን የማሳደግ ስራ ከተጀመረባቸው ተቋማት መካከል የመሬት ልማት ማኔጅመንትን ጨምሮ በፕላን ኮሚሽን፣ ግንባታ ፈቃድ እና ቅሬታ ቢሮዎች ኢ/ር ታከለ ኡማ ትናንት ማምሻውን ድንገተኛ ጉብኝት አድርገዋል፡፡ለተገልጋዮች ደረጃውን የጠበቀ ፍትሃዊና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት በአንድ ማእከል አገልግሎት እንዲሰጡ ከተደረጉ ማዕከላት አመራሮች ጋርም በስራ እንቅስቃሴያቸውና የተገልጋዩን እርካታ ማሳድግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በመነጋገርም የስራ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡በዋነኛነት እነዚህን ተቋማት በአንድ ህንፃ ላይ አገልግሎት እንዲሰጡ የተደረገው አገልግሎት ፈላጊው እንዳይጉላላ እና ኢንቨስት ለሚያደርጉ ግለሰቦች የሚሰጠው አገልግሎት ፈጣን እና የተሳለጠ እንዲሆን መሆኑን በመገንዘብ ከታች እስከላይ ያለው ሰራተኛና አመራር በትልቅ የኃላፊነት ስሜት ለስኬታማነቱ እንዲሰራ ማሳሰባቸውን ከአዲስ አበባ ከንቲባ ፅ/ቤት  ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
https://waltainfo.com/am/32632/
154
0ሀገር አቀፍ ዜና
22 የቱርክ ስሪት ሽጉጥ በጉምሩክ ፈታሾች ተያዘ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 8, 2019
Unknown
በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 22 የቱሪክ ስሪት ሽጉጥ ቶጎጫሌ የመቆጣጠሪያ ጣቢያ ላይ ዛሬ ጠዋት 1፡00 ላይ የጉምሩክ ሰራተኞች ባደረጉት ፍተሻ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ከሶማሌ ላንድ ተነስቶ በቶጎጫሌ በኩል ወደ ጅግጅጋ ሲጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ 44696 በሆነ አይሱዙ ተሸክራካሪ ደብቆ ለማሳለፍ ሲሞከር በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡በወቅቱ ተሸከርካሪው ውስጥ የነበረ አንድ ግለሰብ በድርጊቱ እጁ ሊኖርበት ይችላል በሚል ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጓል፡፡ህብረተሰቡ የሰላምና ደህንነት ፀር የሆኑ የኮንትሮባንድ ድርጊቶችን ለመከላከል በባለቤትነት ከጉምሩክ ኮሚሽን ጋር ተባብሮ እንዲሰራ የጅግጅጋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጥሪ አቅርቧል፡፡ምንጭ፡- የገቢዎች ሚኒስቴር
https://waltainfo.com/am/32633/
79
0ሀገር አቀፍ ዜና
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነ የፍጥነት መቆጣጠሪያ መሳሪያ በተሽከርካሪዎች ላይ ተግባራዊ ተደረገ
ቢዝነስ
August 7, 2019
Unknown
የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን በኢትዮጵያ መጀመሪያ የሆነውን የፍጥነት መቆጣጠሪያ መሳሪያ በተሽከርካሪዎች ላይ ተግባራዊ ማድረጉን አስታወቀ፡፡በባለስልጣኑ የመንገድ ትራፍክ ደህንነት ዳይሬክተር አቶ ያዕቆብ በላይ በሰጠት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ አዲሱ ቴክኖሎጂ በየጊዜው እየጨመረ የመጣውን የትራፍክ አደጋ ለመቆጣጠር እንደሚያስችል አስታውቀዋል፡፡በተሽከርካሪዎች ለይ የሚገጠመው የፍጥነት መቆጣጠሪያ መሳሪያው የተለያዩ ሀገራ ተሞክሮ ተወስዶ ተግባራዊ የተደረገ መሆኑንና የትራፍክ አደጋን ለመቀነስ እንደሚያስችል ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል፡፡ለሶስት ዓመታት ጥናት ተደርጎ ተግባራዊ የሆነው  ቴክኖሎጂ አቅጣጫ ጠቋሚ (GPS)፣ ብሉቱዝ እንዲሁም ዩኤስቢን በመጠቀም ተቆጣጣሪውን በቀላሉ አሽከርካሪው በምን ያህል ፍጥነት እየተጓዘ እንዳለ የሚያሳይ በመሆኑ ለቁጥጥርና ክትትል አመቺ ነው ብለዋል፤ ዳይሬክተሩ፡፡በመላ ሀገሪቱ ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ተሸከርካሪዎች ይኖራሉ ተብሎ የሚገመት ሲሆን፣ በቀጣይ በሀገር ውስጥ ያሉት እንደሚገጠምላቸውና ከውጭ የሚገቡ ተሽከርካሪዎች ደግሞ የፍጥነት መቆጣጠሪያ መሳሪያው ተገጥሞላቸው እንዲገቡ ይደረጋል ብለዋል፡፡የባለስልጣኑ 10 ተሸከርካሪዎች ላይ ቴክኖሎጂው የተገጠመ ሲሆን፣ በቀጣይ በሲኖትራክና የንግድ ተሸከርካሪዎች፣ የመንግስት መኪኖች እና የቤት መኪኖች ላይ በሶስት ደረጃዎች ተከፍሎ እንደሚገጠምም ተገልጿል፡፡ቴክኖሎጂውን ተግባራዊ ከማድረጉ በፊት ሰፊ የሆነ የግንዛቤ ስራ መሰራቱንም አቶ ያዕቆብ አስረድተዋል፡፡
https://waltainfo.com/am/23896/
139
3ቢዝነስ
የድሬዳዋ ከተማ የ2012 በጀት ከ2 ቢሊየን 834 ሚሊየን ብር በላይ ሆኖ ፀደቀ
ፖለቲካ
August 7, 2019
Unknown
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት የከተማዋን የ2012 በጀት 2 ቢሊየን 834 ሚሊየን 440 ሺህ ብር አድርጎ አፀደቀ፡፡የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ለሁለት ቀናት ሲያካሂድ የቆየውን 2ኛ የስራ ዘመን 42ኛ መደበኛ ጉባኤ በትናንትናው ዕለት አጠናቋል፡፡መደበኛ ጉባኤው በአስተዳደሩ የ2011 በጀት አመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ውይይት ማድረጉ ነው የተነገረው፡፡በጉባኤው ማጠናቀቂያ ላይም ምክር ቤቱ ለሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ቢሮ ሃላፊነት በእጩነት የቀረቡት የወይዘሮ ከሪማ አሊን ሹመት አፅድቋል፡፡
https://waltainfo.com/am/31280/
62
5ፖለቲካ
የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ በእምነት ተቋማት ዉስጥ ስላለዉ የመልካም አስተዳደር ችግር  ምክክር አደረገ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 7, 2019
Unknown
የኢትዮጵያ የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የሀይማኖት ተቋማት መልካም አስተዳደርን በማስፈን ረገድ ስለሚኖራቸው አስተዋፅኦ ምክክር አድርጓል፡፡በምክክሩ ላይ የኢ/ያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያን ህብረት፣ የኢ/ያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነየሱስ እና የኢትዮጵያ ቃለሕይወት ቤተክርስቲያናት ተሳትፈዋል፡፡ተገቢ ያልሆነ የጥቅም ትስስር፣ ሙስና፣ እና ሌሎች ጉዳዮች የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲከሰቱ ምክንያት እነደሆኑ ነው የሃይማኖት መሪዎቹ ገለጹት፡፡በመድረኩም ተቋሙን ያቋቋሙት ሰባቱ የሃይማኖት ተቋማት በውስጣቸወ ስላለው የመልካም አስተዳደር ችግሮች ውይይት አድርገዋል፡፡ሰኞ ሐምሌ 30 የጀመረው መድረኩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን የተመለከተ ሲሆን ነሐሴ 1 ደግሞ የኢ/ያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያን ህብረትን፣ የኢ/ያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነየሱስ እና የኢትዮፕያ ቃለሕይወት ቤተክርስቲያናት ውስጥ የመልካም አስተዳደር ችግርን በተመለከተ ውይይት አድርገዋል፡፡በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በሰላም ሚኒስትር የሃይማኖት እና የእምነት ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ጌታዋ ደስታ መንግስት የዜጎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ እንደሆነ በመግለፅ የሃይማኖት ተቋማትም በውስጣቸው ያለውን የመልካም አስተዳደር ችግር በመቅረፍ የበኩላቸውን ሊወጡ እንሚገባ ገልፀዋል፡፡የኢ/ያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲን ህብረት፣ የኢ/ያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነየሱስ እና የኢትዮጵያ ቃለሕይወት ቤተክርስቲያናት መሪዎች እንደገለጹት ተገቢ ያልሆነ የጥቅም ትስስር፣ ሙስና፣ እና ሌሎች ጉዳዮች የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲከሰቱ ምክንያት እነደሆኑ ነው የገለጹት፡፡በቀጣይም የሚታዩትን ችግሮችን ለማስወገድ የቀረበው ጥናታዊ ጽሁፍ አመላካች መሆኑን የገለጹት የሃይማኖት መሪዎቹ ትልልቅ የሃይማኖት መሪዎች ምእመናንን በሚያስተምሩት ልክ መሆን እነደሚገባቸው ነው የገለፁት፡፡መድረኩ እስከ ነሐሴ 3 ድረስ ሚቆይ ሲሆን  ነሐሴ 2 ቀን የእስልምና ጉዳዮች፣ ነሐሴ 3 ደግሞ የኢ/ያ ካቶሊካት ቤተክርስቲየን እና የኢ/ያ 7 ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን የውስጥ የመልካም አስተዳደር ይዞታቸውን የሚገመግሙ ይሆናል፡፡
https://waltainfo.com/am/32628/
209
0ሀገር አቀፍ ዜና
የቀድሞ አሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን “ትራምፕ የነጭ የበላይነትን ያበረታታሉ” አሉ
ፖለቲካ
August 8, 2019
Unknown
የቀድሞ አሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን “ትራምፕ የነጭ የበላይነትን ያበረታታሉ” አሉ፡፡የዴሞክራት እጩ ሆነው የቀረቡት ጆ ባይደን “እኚህ ፕሬዚዳንት አሜሪካ ውስጥ የነጮች የበላይነት እንዲስፋፋ ነዳጅ እያርከፈከፉ ነው”ብለዋል።ትራምፕ አሜሪካ ውስጥ ነባርና መጤ የሚል ከፋፋይ ትርክቶችን እያንጸባረቁ መሆኑንም ባይደን ተናግረዋል። “አሜሪካ የነጭ የበላይነት ማቆጥቆጥ ችግር ሰለባ ሆናለች፤ ትራምፕ ይህን አጉልተው በማንጸባረቅ የችግሩ ተጠያቂ ናቸው” ብለዋል።ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከባይደን ለተሰነዘረባቸው ትችት በሰጡት ምላሽ “አሰልቺ” ሲሉ ተናግረዋል። ትራምፕ ሰሞኑን በአንድ የ21 ዓመት ወጣት በጠመንጃ የ22 ሰዎች ህይወት የተቀጠፈባትን ኤል ፓሶን ትናንት ጎብኝተዋል።ግድያው ከመፈፀሙ ከደቂቃዎች በፊት “የቴክሳስ ወራሪዎች በሆኑት ስፓንኛ ተናጋሪዎች ላይ እርምጃ እንወስዳለን” የሚል የጥላቻ ፅንፈኛ መልዕክት በድረ-ገፅ ተሰራጭቶ ነበር ተብሏል። (ምንጭ፡-አናዶሉ)
https://waltainfo.com/am/33980/
97
5ፖለቲካ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ማርቆስ ተክሌ የዴንማርክ የልማት ትብብር ሚኒስትርን አነጋገሩ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 7, 2019
Unknown
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ማርቆስ ተክሌ የዴንማርክ የልማት ትብብር ሚኒስትር ራስሙስ ፕረህንን በዛሬው ዕለት በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡ሚኒስትር ዴኤታው በውይይታቸው ወቅት  ኢትዮጵያና ደንማርክ በሁሉም ዘርፍ መልካም የዲፕሎማሲ ወዳጅነት ያላቸው መሆኑን ገልጸው፤ የዴንማርክ መንግስት ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ፣ በድህነት ቅነሳ፣ ምርታማነትን በማሳደግ እና  የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በመደገፍ ላበረከተው አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡የዴንማርክ የልማት ትብብር ሚኒስትሩ ራስሙስ ፕረህን በበኩላቸው፤ በኢትዮጵያ እየተከናወነ ያለውን የለውጥ ሂደት እንደሚያደንቁ ገልጸዋል።ቀደም ሲል ሁለቱ ሀገራት በተፈራረሙት የሁለትዮሽ ኢኮኖሚ ትብብር ማዕቀፍና የፖለቲካ ምክክር መግባቢያ ሰነድ መሰረት ሀገራቸው ለኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ለመስጠት ቁርጠኛ መሆኗንም ገልጸዋል፡፡ኢኮኖሚውን ለማነቃቃት መንግስት የወሰዳቸውን አርምጃዎች ምቹ ሁኔታዎችን የፈጠሩ በመሆናቸው ዴኒሽ ባለሃብቶች ወደ ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት እንዲመጡ እንደሚሰሩም ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡ የአየር ንብረት ለውጥን በተመለከተ ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ መድረኮች የአፍሪካን ድምጽ በማሰማት እየተጫወተች ያለችው ሚና የሚያስመሰግን መሆኑን ጠቅሰው፤ በዚህ ዘርፍ ያለውን ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል፡፡ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት መረጃ መሰረትኢትዮጵያና ዴንማርክ ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ ሁለትዮሽ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን፤ ኢትዮጵያ ስቶክሆልም በሚገኘው ኤምባሲዋ ዴንማርክን ሸፍና ትሰራለች፡፡
https://waltainfo.com/am/32629/
152
0ሀገር አቀፍ ዜና
የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከነገ ጀምሮ ስብሰባውን ያካሂዳል
ፖለቲካ
August 7, 2019
Unknown
የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከነገ ጀምሮ ስብሰባውን ያካሂዳልየኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር(ኢህአዴግ) ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከነገ ነሓሴ 2 ቀን 2011 ም ጀምሮ ስብሰባውን የሚካሂድ ሲሆን፤ በተለያዩ አጀንዳዎች እንደሚመክር ይጠብቃል፡፡ኮሚቴ የድርጅት ስራዎች አፈጻጸም እና በሌሎች ሀገራዊ ወቅታዊ አጀንዳዎች ላይ ውይይት እንደሚያካሄድ የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው የድርጅት ስራዎችና ወቅታዊ ሁኔታዎችን በጥልቀት ከገመገመ በኃላ ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል::
https://waltainfo.com/am/31281/
60
5ፖለቲካ
የ2012 ዕድገት የሚለካው ሰውን ሥራ በማስያዝ መሆን እንደሚገባው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሳሰቡ
ቢዝነስ
August 7, 2019
Unknown
የ2012 ዕድገት የሚለካው ሰውን ሥራ በማስያዝ መሆን እንደሚገባው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሳሰቡ።ጠቅላይ ሚኒስትር  ዶር ዐብይ አህመድ  ከዚ በኋላ የሚፈጠሩ ሥራዎችን በስም ሳይቀር በመዘርዘር ለምክር ቤቱ ተጨባጭ ሪፖርት እንደሚያቀርቡ ተናገሩ፡፡ለሥራ ዕድል ፈጠራውም 3 ቢሊዮን ብር ድጋፍ ከውጭ መገኘቱን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡ለዚሁ ሥራም በሀገር አቀፍ ደረጃ በ2012 ዓ.ም 3 ሚሊዮን የሥራ ዕድል የሚፈጥር የሠራተኛ እና ኢንቨስትመንት ኮሚቴ ተቋቁሟል፡፡ኮሚቴው ተጨባጭ የሆኑ ሥራዎችን በመፍጠር የሀገሪቱን ችግሮች እንደሚያቃልል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡ ከ10 ሚኒስትሮች ፣ ከ9 ርዕሳነ መስተዳድሮች እንዲሁም ከሁለቱ የከተማ መስተዳድሮች ከንቲባዎች ጋር ውይይት ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ለኢንቨስትመንቱ ፈተና የሆነውን ሙስና፣ ቢሮክራሲ እና የኢንቨስተሮች አጋዥ ማጣት መፍታት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ በሀገሪቱ በአሁኑ ወቅት 11 ሚሊዮን ሥራ ፈላጊ ወጣቶች የሚገኙ ሲሆን፤ በየዓመቱ ከ2 እስከ 3 ሚሊዮን የሥራ ፈላጊው ቁጥር እንደሚጨምር ተጠቁሟል፡፡በ2012 ዓ.ም ብቻ ሊፈጠር ከታሰበው 3 ሚሊዮን ሥራ ውስጥ 1 ነጥብ 4 በጊዜያዊነት እና 1 ነጥብ 6 ደግሞ በቋሚነት ይፈጠራል ተብሏል።ጠቅላይ ሚኒስተሩ ከዚህ በኋላ የሚፈጠሩ ሥራዎችን በስም ሳይቀር በመዘርዘር ለምክር ቤቱ ሪፖርት እንደሚያቀርቡም የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የ2012 በጀት ዓመት ዕድገት የሚለካው ሰውን ሥራ በማስያዝ እንደሆነ ሲል የአማራ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል።
https://waltainfo.com/am/23895/
163
3ቢዝነስ
የአፍሪካ ልማት ባንክ ለኢትዮ-ጅቡቲ የመንገድ ፕሮጀክት የ98 ሚሊዮን ዶላር ፈንድ አፀደቀ
ቢዝነስ
August 7, 2019
Unknown
የአፍሪካ ልማት ባንክ ኢትዮጵያን ከጎረቤት ሀገር ጅቡቲ ጋር ለሚያገናኘውና በአዲስ መልክ ለሚሰራው የመንገድ ትራንስፖርት ኮሪደር ፕሮጀክት የሚውል የ98 ሚሊዮን ዶላር ፈንድ በትላንትናው ዕለት ማፅደቁን አስታውቋል።የድጋፍ ስምምነቱን በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ እና በአፍሪካ ልማት ባንክ የኢትዮጵያ ተጠሪ አብዱል ካማራ ተፈራርመዋል።ፕሮጀክቱ በአጠቃላይ የ255 ሚሊዮን ዶላር ወጪን የሚጠይቅ ነው ። 98 ሚሊዮን ዶላሩ የአፍሪካ ልማት ባንክ ለኢትዮጵያ መንግሥት የሚሰጠው ድጎማ ሲሆን ፣5.3 ሚሊዮን ዶላሩ ባንኩ ለጅቡቲ መንግሥት በሚሰጠው ድጎማ ለመንገዱ ፕሮጀክት የሚውል ነው። የመንገዱ ቀሪ 151 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ደግሞ የኢትዮጵያ መንግሥት በሚያደርገው አስተዋፅኦ የሚሸፈን ይሆናል።ፕሮጀክቱ ከአዳማ እስከ አዋሽ የሚዘረጋውን የ126 ኪ.ሜ መንገድ ያቀፈ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 60 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው ባለ አራት መስመር የፍጥነት መንገድ ግንባታ የያዘ ነው።የመንገድ ፕሮጀክቱ ስራ በቀጣይ ዓመት ይጀመራል።ፕሮጀክቱ የትራንስፖርት ወጪን በእጅጉ በመቀነስ ንግድን እንደሚያጠናክር እና የሁለቱን ሀገሮች የኢኮኖሚ ዕድገት እንደሚያሳላጥ ባንኩ በመግለጫው አትቷል።(ምንጭ፦የአፍሪካ ልማት ባንክ)
https://waltainfo.com/am/23894/
132
3ቢዝነስ
የድሬዳዋ ከተማ የ2012 በጀት ከ2 ቢሊየን 834 ሚሊየን ብር በላይ ሆኖ ፀደቀ
ቢዝነስ
August 7, 2019
Unknown
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት የከተማዋን የ2012 በጀት 2 ቢሊየን 834 ሚሊየን 440 ሺህ ብር አድርጎ አፀደቀ፡፡የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ለሁለት ቀናት ሲያካሂድ የቆየውን 2ኛ የስራ ዘመን 42ኛ መደበኛ ጉባኤ በትናንትናው ዕለት አጠናቋል፡፡መደበኛ ጉባኤው በአስተዳደሩ የ2011 በጀት አመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ውይይት ማድረጉ ነው የተነገረው፡፡በጉባኤው ማጠናቀቂያ ላይም ምክር ቤቱ ለሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ቢሮ ሃላፊነት በእጩነት የቀረቡት የወይዘሮ ከሪማ አሊን ሹመት አፅድቋል፡፡
https://waltainfo.com/am/23893/
62
3ቢዝነስ
የኢንቨስትመንትና የስራ ፈጠራ ብሔራዊ ኮሚቴ አባላት ይፋ ሆኑ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 7, 2019
Unknown
የኢንቨስትመንትና የስራ ፈጠራ ብሔራዊ ኮሚቴን አባላት ይፋ ሆኑ፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የኢንቨስትመንትና የስራ ፈጠራ ብሔራዊ ኮሚቴን ዛሬ ይፋ አድርገዋል፡፡ኮሚቴው በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራ ሲሆን፣ በውስጡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ፣ የዘጠኙ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድሮች፣ የአዲስ አበባና የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች፣ ሁለት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ተወካዮችና 10 የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችን ያቀፈ ነው፡፡ የዘገበው ኢቢሲ ነው፡፡
https://waltainfo.com/am/32626/
53
0ሀገር አቀፍ ዜና
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ከዴንማርክ የልማት ትብብር ሚኒስትር ጋር ተወያዩ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 7, 2019
Unknown
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ከዴንማርክ የልማት ትብብር ሚኒስትር ጋር ተወያዩ።ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከዴንማርክ የልማት ትብብር ሚኒስትር ራስመስ ፕሬህን ጋር ዛሬ በጽ/ቤታቸው ተወያይተዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩና የልማት ትብብር ሚኒስትሩ በኢነርጂ ፖሊሲ፣ ስራ ፈጠራ፣ ኢንቨስትመንት፣ ዴሞክራሲ፣ የአየር ለውጥና አከባቢ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በተገኘው መረጃ መሰረት።
https://waltainfo.com/am/32627/
46
0ሀገር አቀፍ ዜና
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ለ50 ቀናት በከፊል ዝግ እንደሚሆኑ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 7, 2019
Unknown
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ለ50 ቀናት በከፊል ዝግ ይሆናሉ።የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ከነሃሴ 1 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 20 ቀን 2012 ዓ.ም በከፊል ዝግ ሆነው እንደሚቆዩ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡ፍርድ ቤቶቹ በከፊል ዝግ ሆነው በሚቆዩባቸው 50 ቀናት አስቸኳይና ጊዜ የማይሰጡ፣ ከዜጎች መሰረታዊ መብቶች እንዲሁም ከአገር ሰላምና ፀጥታ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ጉዳዮች ግን እንደሚመለከቱ ተገልጿል፡፡የጊዜ ቀጠሮ፣ የዋስትናና የዕግድ ጥያቄዎች፣ የመያዣና የብርበራ ትዕዛዞች፣ በተፋጠነ ስነ-ስርዓት የሚታዩ የእጅ ከፍንጅ ወንጀሎች ፍርድ ቤቶቹ ዝግ ቢሆኑም ይታያሉ ነው የተባለው።ከቤተሰብና ከሕፃናት ቀለብና አስተዳደግ ጋር የተያያዙ አጣዳፊ መሰረታዊ ጉዳዮችም በተረኛ ችሎቶች የሚስተናገዱ እንደሆነ ነው የተገለፀው፡፡ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በላከው መረጃ መሰረት።
https://waltainfo.com/am/32623/
96
0ሀገር አቀፍ ዜና
ሰሜን ኮሪያ “የሳይበር ጥቃትን በመጠቀም ሁለት ቢሊዮን ዶላር መስረቋ” ተገለጸ
ፖለቲካ
August 7, 2019
Unknown
ሰሜን ኮሪያ የጦር መሣሪያ መርሃ ግብሯን ለመደጎም “2 ቢሊዮን ዶላር በሳይበር ጥቃት መስረቋን” ሾልኮ የወጣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሪፖርት ይፋ አደርጓል።ፒዮንግያንግ ገንዘቡን ለመሰብሰብ ባንኮችን እና በኢንተርኔት ሲስተም የሚደረጉ የገንዘብ ልውውጦችን ዒላማ ማድረጓን ነው ምሥጢራዊ ሪፖርቱ የጠቆመው።የተመድ የዘርፉ ጠበብቶች የ'ሳይበር ማይኒንግ' ድርጊቶችን ማለትም እጅግ የረቀቁ ኮምፒዩተሮችን በመጠቀም የሚደረጉ የውጭ ገንዘብ የመመንተፍ ድርጊቶች ላይ ምርመራ እያካሄዱ ይገኛሉ።ሪፖርቱ ለተባበሩት መንግስታት ደርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በሰሜን ኮሪያ ላይ ማዕቀብ ለመጣል ምርመራ ለሚያደርገው ኮሚቴ የተዘጋጀ ነው።ከሳይበር ጥቃቱ ባሻገርም ከዚህ በፊት ሰሜን ኮሪያ ተጥሎባት የነበረውን ከመርከብ መርከብ የእቃዎች ሽግግር መፈፀሟን የሚገልፁ መረጃዎችም በሪፖርቱ ተካተዋል።ሰሜን ኮሪያ ከአሜሪካ ጋር የጀመረችው ድፕሎማሲ ጥረት አልሳካ ሲላት የተለያዩ ርቀት ያላቸው ሚሳኤሎችን ማስወንጨፏን ተከትሎ ዳግም ቀጠናው ወደ ውጥረት ተመልሷል።(ምንጭ፦ ቢቢሲ)
https://waltainfo.com/am/33979/
108
5ፖለቲካ
ረሃብን ከአፍሪካ ለማስወገድ የተቀናጀ ጥረት ያስፈልጋል- ፕሬዚዳንትፖል ካጋሚ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 6, 2019
Unknown
ረሃብን ከአፍሪካ ለማስወገድ የተቀናጀ ጥረት እንደሚያስፈልግ የሩዋንዳ ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሚ ገለፁ፡፡ፕሬዚዳንቱ ይህን ያሉት በሩዋንዳ እስተናጋጅነት እየተካሄደ ባለውና የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ ላይ ባተኮረው የመሪዎች ጉባኤ ላይ ነው፡፡በአውሮፓውያኑ 2025 አፍሪካ ረሃብን ለማስወገድ በማላቡ ስምምነት ላይ የገባችውን ቃል እየጠበቀች አትገኝም፣ይህን በማሳካት በኩልም ከመስመር ወጥታለች ብለዋል ፖል ካጋሚ፡፡ይህ ችግር በትብብር ፣ በተቀናጀ ጥረት እና ተገቢውን ቴክኖሎጂ ሁሉ በመጠቀም ብቻ ሊቀረፍ እንደሚችልም ነው አፅንዎት የሰጡት፡፡የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ፈተና እዚህ ሩዋንዳም ተደቅኖብናል ያሉት ፕሬዚዳንቱ ይሁንና ተገቢውን እውቀት በተገቢው የሰው ሃይልና ቴክኖሎጂ በማቀናጀት እንሰራለን፣ በትብብር ከተንቀሳቀስን ደግሞ ችግሩ የማይቀረፍ አይደለም ብለዋል፡፡ይህን አለምአቀፍ የምክክር መድረክ የሩዋንዳ መንግስት ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን፣አለም ባንክ እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት የምግብ እና እርሻ ድርጅትና ሌሎችም በትብብር እንዳሰናዱት ሲጂቲኤን በዘገባው አመልክቷል፡፡
https://waltainfo.com/am/33460/
106
0ሀገር አቀፍ ዜና
የናይሮቢ ኤምባሲ 64 ያህል ዜጎችን ወደ ሃገር ቤት መለሰ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 6, 2019
Unknown
በናይሮቢ የሚገኘው የኢፌዴሪ ኤምባሲ አስፈላጊ የጉዞ ሰነድ ሳይዙ በሰዎች አዘዋዋሪዎች አማካኝነት ድንበር አቋርጠው ወደ ኬንያ በመግባታቸው በተለያዩ ማረምያ ቤቶች ታስረው የነበሩ 64 ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት መለሰ።ኤምባሲው ወደ ኢትዮጵያ መመለስ ቢችልም በህገወጥ አዘዋዋሪዎች አማካኝነት አቆራርጠው ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመሄድ ሲሉ በኬንያ የፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ናቸው ተብሏል።በኬንያ የፖሊስ ኃይል በቁጥጥር ስር ውለው ካዮሌ ፖሊስ ጣቢያ ከነበሩት ኢትዮጵያውያን መካከል 54 ያህል፤ እንዲሁም ሞያሌ የነበሩት 10 ኢትዮጵያውያንን ኤምባሲው ከኬንያ መንግስት ጋር ባደረገው ድርድርና ማግባባት ክሳቸው ተቋርጦ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ አድርጓል፤ በናይሮቢ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለጣቢያችን በላከው መረጃ።በአገሪቱ አምስት ኢትዮጵያውያን ከህገወጥ አዘዋዋሪዎች ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል ፖሊስ ለተጨማሪ ምርመራ ያስፈልጋቸዋል በማለቱ ኤምባሲው የቅርብ ክትትል እየተደረገባቸው እንደሚገኝ አስታውቋል።በኬንያ የኢፌዲሪ ኤምባሲ በኬንያ እና ሌሎች በተወከለባቸው ሀገራት (ኮሞሮስ፣ ማላዊ እና ሲሼልስ) የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ወገኖቻችንን መብት ለማስከበርና ክብራቸውን ለማስጠበቅ ከሀገሪቱ የኢሚግሬሽን ኃላፊዎች ጋር በቅርበት ተባብሮ እየሰራ የሚገኝ መሆኑን አስታውቋል።በኬኒያ ናይሮቢ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በግንቦት 2011 ዓ.ም ኤምባሲው 500 ያህል ዜጎቸን ወደ ሀገር ቤት መመለሱንም ኤምባሲው አስታውቋል ።
https://waltainfo.com/am/32624/
151
0ሀገር አቀፍ ዜና
የአሲዳማ አፈርን ለማከም የሚያስችል ኖራ እንዲቀርብላቸው አርሶአደሮች ጠየቁ
ቢዝነስ
August 6, 2019
Unknown
በኢትዮጵያ አሲዳማ አፈር ከሚገኝባቸው አንዱ በሆነው የስልጤ ዞን የአሲዳማ አፈር ለማከም የሚያስችለውን የኖራ እጥረት እንዲቃለልላቸው የዞኑ አርሶአደሮቹ ጠየቁ፡፡የአሲዳማ አፈርን ለማከም የሚያስችላቸው የኖራ አቅርቦት በሚፈልጉት ደረጃ አለማግኘቱ በምርታቸው ላይ ተፅዕኖ መፍጠሩን ለዋልታ አስተያየታቸውን የሰጡ አርሶአደሮች ተናግረዋል፡፡የዞኑ አስተዳደር በበኩሉ በዞኑ የኖራ እጥረት ከመኖሩም ባሻገር ለማጓጓዝ የሚፈለገው እንቅስቃሴ ወጪውን በእጥፍ እያናረ በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡ችግሩን ለመቅረፍም ከክልሉ መንግስት ጋር በጋራ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ክልሉ ግብርና ቢሮ በበኩሉ ከክልሉ አፈር 43 በመቶ አሲዳማ በመሆኑ ኖራ የሚገኝባቸውን አካባቢዎችን በጥናት በመለየታቸው በቅርቡ ኖራውን የሚፈጩ ወፍጮች ይተከላሉ ብለዋል፡፡የኖራውን እጥረት ለመፍታት ሌሎች አማራጮችንም በመጠቀም እንደሚሰሩም ጭምር ነው ያስታወቀው፡፡የግብርና ሚኒስቴርም እንዲሁ ለመፍትሔው ከክሉ ጋር በጋራ እሰራለው ብለዋል፡፡
https://waltainfo.com/am/23892/
96
3ቢዝነስ
ኢ/ር ታከለ ኡማ ከዓለም የቱሪዝም ፎረም ፕሬዝዳንት ቡሉት ማግቺ ጋር ተወያዩ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 6, 2019
Unknown
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ከዓለም የቱሪዝም ፎረም ፕሬዝዳንት ቡሉት ማግቺ ጋር ተወያዩ፡፡በውይይታቸውም ተቋማቸው እ.አ.አ በ2020 የሚካሄደውን የዓለም የቱሪዝም ፎረም በአዲስ አበባ ለማዘጋጀት ፍላጎት እንዳለው ተናግረዋል፡፡ፕሬዝዳንቱ አዲስ አበባን የቱሪዝም መዳረሻ እና ለጎብኚዎች ምቹ ለማድረግ በከተማዋ የሚሰራውን ሸገርን የማስዋብ ፕሮጀክት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ እና በከተማዋ ውስጥ ላሉ ታሪካዊ ቅርሶች ለሚደረገው እንክብካቤ ድጋፍ እንደሚያደርጉም ተናግረዋል፡፡ተቋሙ አዲስ አበባን የMICE ማዕከል ለማድረግ በከተማዋ አዲስ ከተቋቋመው የኮንቬሽን ቢሮ ጋር በቅርበት እንደሚሰራ እና ከተማዋን የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ እየሰራ እንደሆነም ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡ኢ/ር ታከለ ኡማ በበኩላቸው ከተማዋ እ.አ.አ በ 2020 የሚዘጋጀውን የዓለም የቱሪዝም ፎረም ብታዘጋጅ ተጠቃሚ እንደምትሆን ተናግረዋል፡፡አለም አቀፍ የቱሪዝም ፎረም የመሠሉ መድረኮችን በከተማዋ ውስጥ ማስተናገድ ከሚሰጠው ዘርፈ ብዙ ጥቅም በተጨማሪ ከተማዋን የቱሪስት መዳረሻ እንድትሆን እንደሚያደርጋትም ኢ/ር ታከለ ኡማ ተናግረዋል፡፡በውይይቱ ላይም በቅርብ የተቋቋመው የአዲስ አበባ የኮንቬንሽን ቢሮ ዳይሬክተር አቶ ቁምነገር ተከተል መገኘታቸውን ከከንቲባ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡
https://waltainfo.com/am/32625/
133
0ሀገር አቀፍ ዜና
ህዝበ ክርስቲያኑ በፍልሰታ ፆም ለሃገር ሰላምና ፍትህ እንዲፀልይና የተቸገሩትንም እንዲረዳ ጥሪ ቀረበ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 5, 2019
Unknown
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ አቡነ ማቲያስ የፍልሰታ ፆም መግቢያን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ፓትሪያርክ ብፁዕ አቡነ ማቲያስ ሰው ሠራሽ በሆነ ምክንያት በከፋ ድህነት ውስጥ የሚገኙና ከቅያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን ማሰብና መደገፍ ይገባል ብለዋል፡፡ምዕመኑ በፍልሰታ ፆም ወቅት የተቸገሩትን ባለው አቅም ሁሉ እንዲደግፍ እና ለሀገር ሰላም የድርሻውን እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ፆመ ፍልሰታ ነሃሴ 1፣2011 ዓ.ም ይጀምራል፡፡አረጋዊ ሰለሞን
https://waltainfo.com/am/32620/
53
0ሀገር አቀፍ ዜና
የቀድሞው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ከጃፓን መንግስት የክብር ሽልማት ተበረከተላቸው
ሀገር አቀፍ ዜና
August 3, 2019
Unknown
የቀድሞው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከጃፓን መንግስት የክብር ሽልማት ተበረከተላቸው፡፡ሽልማቱ የ2019 ስፕሪንግ ኢምፔርያል ሽልማት ሲሰኝ በጃፓን መንግስት በኩል የተለየ ተግባር ላከናወኑ የውጭ ሀገራት መሪዎች የሚሰጥ ነው፡፡ሽልማቱን የሰጡት በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ዳይሱኬ ማትሱናጋ ናቸው፡፡በተለይም አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በስልጣን ዘመናቸው በኢትዮጵያ ተፈጥሮ የነበረውን ማህበራዊ ቀውስ እልባት ለመስጠት ላበረከቱት አስተዋፅኦ፣ በጤናው ዘርፍ እና የካይዘን ፍልስፍናን በማስረፅ እንዲሁም በሌሎች ጉዳዮች ለነበራቸውን አስተዋፅኦ የተበርከተ እንደሆነም ነው የተገለጸው፡፡በሀገሪቱ ተፈጥሮ የነበረውን ውጥረት ለማርገብ በሰላማዊ መንገድ የስልጣን ሽግግር በማድረጋቸው ደስተኛ መሆናቸውን አቶ ኃለማርያም ከሽልማቱ በኋላ ተናግረዋል፡፡
https://waltainfo.com/am/32616/
79
0ሀገር አቀፍ ዜና
አሜሪካ በሩስያ ላይ አዲስ ማዕቀብ መጣሏን አስታወቀች
ፖለቲካ
August 3, 2019
Unknown
አሜሪካ በሩስያ ላይ አዲስ ማዕቀብ መጣሏን አስታወቀች።ዋሺንግተን ማዕቀቡን የጣለችዉ ሩስያ በ2018 ሰርጌ እስክሪፓል የተባለን የእንግሊዝ ሰላይ በኬሚካል ንጥረ ነገር መርዛለች በሚል ምክንያት ነዉ ተብሏል።የቀድሞዉ የሩስያ ወታደራዊ የስለላ ሰዉ ሰርጌ እስክሪፓል ሀገሩ ሩስያን ክዶ ለእንግሊዝ የስለላ ስራን ሲያከናዉን በነበረበት በፈረንጆቹ 2018 በእንግሊዟ ሳሊስበሪ ከተማ ከሴት ልጁ ሁሊያ ስክሪፓል ጋር በአንድ የገበያ ማዕከል አካባቢ ተመርዞ አደጋ ላይ መውደቁ ይታወሳል።በወቅቱ ሴት ልጁን በሞት ያጣው ሰርጌ እስክሪፓል ሩስያ ሰራሽ በሆነና ነርቭን በሚያጠቃዉ ኖቪቾክ የተሰኘ ንጥረ ነገር በመመረዙ ነበር፤ በድርጊቱ የሩሲያ የረዘመ የሩስያ እጅ እንዳለበት አሜሪካና እንግሊዝ የጸና እምነት አሳድረው ቆይተዋል።ሩስያ አሁንም ድረስ ክሱን መሰረተ ቢስ ስትል በተደጋጋሚ ብታጣጥለዉም፤ በወቅቱ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በበሩስያ ላይ ማዕቀብ የጣለችው አሜሪካ፤ አሁን ላይ ደግሞ ከሰርጌ እስክሪፓል መመረዝ ጋር በተያያዘ በሞስኮ ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ ስለመጣሏ ተሰምቷል።የአሜሪካ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ባወጣዉ መግለጫ፤ ከዚህ በኋላ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ለሩስያ የሚያደርጉትን የገንዘብ ድጋፍ አሜሪካ በፅኑ እንደምትቃወም አመላክቷል ተብሏል።አሜሪካ ወደ ሩስያ የምትልካቸዉን የቴክኖሎጂ መሳሪያዎችና ሌሎች ለኬሚካል ቅመማ፣ ለጦር መሳሪያ ምርት የሚያገለግሉ ቁሳቁሶችን መጠን በከፍተኛ መጠን እንደምትቀንስ የአሜሪካ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ ሞርጋን ኦርታገስ አስታዉቀዋል።ማዕቀቡ ሞስኮ ከዋሺንግተን ጋር በነበራት የሁለትዮሽ የንግድ ትስስር የምታገኘዉን ቢሊዮን ዶላሮች የሚያሳጣት ይሆናልም ተብሏል።ማዕቀቡ ከቀጣዩ የፈረንጆቹ ነሃሴ 19 ጀምሮ ለ15 ቀናት ከሚዘልቀዉ የኮንግረንስ አባላት ምክክር በኋላ ወደ ትግበራ ይገባል የተባለ ሲሆን፤ የ12 ወራት ቆይታ እንደሚኖረዉም ይጠበቃል ተብሏል።ከአሁኑ የአሜሪካ ማዕቀብ አስቀድሞም የአዉሮፓ ህብረትም ባለፈዉ የፈረንጆቹ ጥር ወር ላይ በዘጠኝ የሩስያና የሶርያ ባለስልጣናት ላይ የኬሚካል ጦር መሳሪያ ማዕቀብ መጣሉ ይታወሳል።ዘገባው የኤ.ኤፍ.ፒ ነው። 
https://waltainfo.com/am/33977/
225
5ፖለቲካ
በኳታር ዶሃ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለሕዳሴ ግድብ ግንባታ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናገሩ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 3, 2019
Unknown
በኳታር ዶሃ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለሕዳሴ ግድብ ግንባታ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናገሩ።በኳታር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስለ ግድቡ ግንባታ ወቅታዊ መረጃ እንዲያገኙ የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ትናንት ተካሂዷል፡፡በኳታር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የግድቡ ግንባታ ከተጀመረ አንስቶ ሌሎች ድጋፎችን ሳይጨምር ከ35 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጋቸው ታውቋል፡፡ይሁን እንጅ በግድቡ ላይ ተከስቶ በነበረው የቴክኒክ፣ የአስተዳደርና ሌሎች ችግሮች ምክንያት ድጋፋቸው ተቀዛቅዞ መቆየቱ ተገልጿል፡፡ የማስተካከያ እርምጃ መወሰዱን ተከትሎ ደግሞ ድጋፋቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል፡፡በኳታር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስለ ግድቡ ግንባታ ወቅታዊ መረጃ እንዲያገኙ የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ትናንት ሐምሌ 26/2011 ዓ.ም በኢትዮጵያ ኢምባሲ አዘጋጅነት ተካሂዷል።ተሳታፊዎችም ሁሉም ዜጋ ምንም ዓይነት ቅድመ ሁኔታ ሳያስቀምጥ በአዲስ ሞራል የአገራዊ አንድነት ምልክት የሆነውን የሕዳሴ ግድብ ተረባርቦ ከፍጻሜ ማድረስ እንደሚገባ ስምምነት ላይ መድረሳቸው ታውቋል፡፡ኢትዮጵያውያኑ ለግድቡ ግንባታ የሚያደርጉትን ድጋፍም አጠናክረው እንደሚቀጥሉ መናገራቸወኘ ከኳታር የኢትዮጵያ ኢምባሲ ያገኘውን መረጃ ጠቅሶ የዘገበው የአማራ መገናኛ ብዙሃን ነው።
https://waltainfo.com/am/32617/
124
0ሀገር አቀፍ ዜና
የኦሮሞና የሱማሌ ሕዝቦች የምክክር መድረክ ተጀመረ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 4, 2019
Unknown
የኦሮሞና የሱማሌ ህዝቦች የወንድማማችነት የምክክር መድረክ ዛሬ በጅግጅጋ ከተማ ተጀምሯል፡፡በመድረኩ ላይ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የሱማሌ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፌ መሐመድ ዑመር፣ የሁለቱ ክልሎች ከፍተኛ አመራሮች፣ አባገዳዎች እና የሃይማኖት አባቶች እንዲሁም የሁለቱ ክልል ህዝቦች ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡በተመሳሳይ በሚያዚያ ወር ላይ በአዳማ ከተማ የሁለቱ ክልሎች የህዝብ ለህዝብ መድረክ መካሄዱ ይታወሳል።(ምንጭ፡-  ኢቢሲ)
https://waltainfo.com/am/32618/
53
0ሀገር አቀፍ ዜና