headline
stringlengths 2
1.42k
| category
stringclasses 6
values | date
stringlengths 9
35
| views
stringlengths 1
7
| article
stringlengths 63
36.2k
| link
stringlengths 28
740
| word_len
int64 16
6.74k
| label
class label 6
classes |
---|---|---|---|---|---|---|---|
የዓለም ምርጥ ሴት አትሌቶች የመጨረሻ እጩዎች ታወቁ | ስፖርት | November 14, 2019 | 40 | ከተያዘው ሳምንት ጀምሮ ስሙን የዓለም አትሌቲክስ በሚል የቀየረው የስፖርቱ የበላይ አካል ዓመታዊው የምርጥ አትሌቶች ምርጫውን ሊያካሂድ ቀናት ብቻ ቀርተውታል፡፡ ስፖርት ወዳዱ ህብረተሰብ እንዲሁም የአትሌቶቹ የቅርብ ሰዎች በኢሜይል እንዲሁም በማህበራዊ ድረገጾች በተዘጋጁት ድምጽ መስጫዎች ይገባዋል ለሚሉት አትሌት ይሁንታቸውን ሰጥተዋል፡፡ በእስካሁኑ 25 ከመቶ ድርሻ ባለው የህዝብ ድምጽ እና ባለሙያዎች ባደረጉት ምርጫ መሰረትም የመጨረሻዎቹ አምስት እጩዎች ታውቀዋል፡፡በዚህም መሰረት ባለፈው የውድድር ዓመት ብቃታቸው እንዲሁም በቅርቡ በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ባገኙት ውጤት መሰረት ከአምስት ሃገራት አምስት የተለያዩ ሴት አትሌቶች ለመጨረሻው ዙር በቅተዋል፡፡ በመካከለኛ ርቀት ኔዘርላንዳዊቷ ሲፈን ሃሰን ከዓመቱ ምርጥ አትሌቶች መካከል ተገኝታለች፡፡ አትሌቷ በአበረታች ቅመሞች ምክንያት በምርመራ ላይ ከሚገኙት አሰልጣኟ አልቤርቶ ሳላዛር ጋር በተያያዘ በጥርጣሬ ትታይ እንጂ በዶሃው የዓለም ቻምፒዮና በ1ሺ500 እና10ሺ ሜትር አሸናፊ መሆኗ በእጩነት ሊያስመርጣት ችሏል። ይህም ብቻ ሳይሆን የ 1ሺ500 እና 5ሺ ሜትር የዳይመንድ ሊግ የድርብ ድል ባለቤቷ ሲፈን በማይል ውድድርም 4:12.33 የሆነ የዓለም ክብረወሰንን በሞናኮ አስመዝግባለች። ይህ በአመቱ ያስመዘገበችው ስኬትም አትሌቷን ከዘጠኝ ቀናት በኋላ በሞናኮ በሚኖረው ስነስርዓት የዓለም ምርጥ ሴት አትሌት በመባል የክብሩ ባለቤት እንድትሆን ይረዳታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የአጭር ርቀት ተወዳዳሪዋ ጃማይካዊት አትሌት ሼሊ-አን ፍራዘር-ፕረይሲም በዓመቱ በተካፈለችባቸው ውድድሮች ያስመዘገበቻቸው ውጤቶች ለሽልማቱ አሳጭቷታል። አትሌቷ በዶሃው ቻምፒዮና በተካፈለችባቸው የ100 ሜትር እና 4በ400 ሜትር ውድድሮች 10 ሰከንድ ከ71 ማይክሮ ሰከንድ እና 41 ሰከንድ ከ44 ማይክሮ ሰከንድ የሆነ ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ነበረች። የ32 ዓመቷ ፕረይሲ በአሜሪካ አህጉር በሚዘጋጀው ውድድር የ200 ሜትር አሸናፊም ነበረች፡፡ የዓለም ፈጣኗ ሴት አትሌት በአመቱ ከተሳተፈችባቸው አስር ውድድሮች በሰባቱ ቀድማ በመግባት ብርቱ አትሌትነቷን አስመስክራለች፡፡ የሰው ልጅ ማራቶንን ከአንድ ሰዓት በታች መግባት እንደሚችል የሃገራ ልጅ በሙከራ ውድድር ባስመሰከረበት ማግስት የዓለም ሴቶች የማራቶን ክብረወሰንን የሰበረችው ኬንያዊት አትሌት ብርጊድ ኮስጊም ከመጨረሻዎቹ አምስት እጩዎች መካከል ተገኝታለች፡፡ በቺካጎ ማራቶን ለ16 ዓመታት የቆየውን ክብረወሰን 2:14:04 በሆነ ሰዓት በመግባት የሰባበረችው አትሌቷ የለንደን ማራቶን አሸናፊም ነበረች፡፡ ወጣቷ አትሌት በዓመቱ በተሳተፈችበት የግማሽ ማራቶን ውድድርም 1:04:28 የሆነ ፈጣን ሰዓት አላት። ሌላኛዋ እጩ አሜሪካዊቷ ደሊላ ሙሃመድ በዓመቱ በ400 ሜትር ያሳየችው አቋም ሊያስመርጣት ችሏል፡፡ አትሌቷ በሃገር አቀፍ ቻምፒዮና 52 ሰከንድ ከ20 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ቀዳሚዋ ስትሆን፤ በ400 ሜትር መሰናክል በራሷ የተያዘውን ክብረወሰን 52 ሰከንድ ከ16 ማይክሮ ሰከንድ በማሻሻል ብቃቷን አስመስክራለች፡፡ በ4 በ400 ሜትርም በተመሳሳይ የዓለም ቻምፒዮን ናት፡፡ በርዝመት ዝላይ ቬንዙዌላዊቷ ዩሊማር ሮጃስ ለመጨረሻው ዙር መብቃት ችላለች፡፡ አትሌቷ 15.37 ሜትር በመዝለል የዓለም ቻምፒዮን ስትሆን፤ ከዚህ ቀደም የዘለለችው 15.41 ሜትር ደግሞ ከዓለም የምንጊዜም ቀዳሚዎቹ መካከል ሊሰፍርላት ችሏል፡፡ ሮጃስ አህጉር አቀፍ ውድድርን ጨምሮ ከተካፈለችባቸው 12 ውድድሮች ዘጠኝ በሚሆኑት ላይ አሸናፊ መሆኗ ከዓለም ምርጦች ተርታ ያሰልፋታል የሚል ግምት አግኝታለች፡፡አዲስ ዘመን ጥቅም4/2012 ብርሃን ፈይሳ | https://www.press.et/Ama/?p=22486 | 378 | 2ስፖርት
|
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በታላቅ የስኬት ጎዳና | ስፖርት | November 16, 2019 | 71 | ኢትዮጵያ በአትሌቲክሱ ዓለም በተለይም በረጅም ርቀት ውድድሮች ገናና ስም በማትረፍ ትታወቃለች።በረጅም ርቀት ውድድሮች ቁጥር ስፍር የሌላቸው ብርቅዬ አትሌቶቿ ከሰሩት ዘመን የማይሽረው ታሪክ ጎን ለጎን በአትሌቲክሱ ዓለም አንድ የሚጠቀስ ታላቅ ስኬትም እያስመዘገበች ትገኛለች።ይህ ስኬትም በጀግናው አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ መስራችነት የተጀመረው ‹‹ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ›› የተሰኘው ታላቅ የጎዳና ላይ ውድድር ነው።ኢትዮጵያ ስፖርትን እንደቱሪዝም በመጠቀም ረገድ ብዙ ባልተጓዘችበት ዘመን ከሁለት አሥርት ዓመታት በፊት የተጠነሰሰው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዛሬ ላይ ከስፖርታዊ ኩነቱ አይሎ የስፖርት ቱሪዝም ጥያቄን እስከ መመለስ ደርሷል።ከዓለም ምርጥ አሥር ተወዳጅና ሳቢ የጎዳና ላይ ሩጫዎች መካከል አንዱ የሆነው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በተወዳጅነት እንደዘለቀ ከሚያገኘው ገቢ ለሰብዓዊ እርዳታ እያዋለ ኢትዮጵያን በበጎ እያስጠራ ይገኛል።ይህም የዓለም አትሌቲክስ አፍቃሪዎችን ከየአቅጣጫው እየሳበ የተሳታፊዎቹን ቁጥር ከዓመት ዓመት እንዲመነደግ አስችሎታል።ከወር በፊትም “በሌትስ ዱ ዚስ” የሚታገዘውና በእውቁ የሩጫ መጽሔት “ረነርስ ወርልድ” የሚቀርበው “ዘ ቻሌንጅስ አዋርድ” የተሰኘ ውድድር በጎዳና ላይ ውድድር ዝግጅት ዘርፍ ትልቁን ዓለም አቀፍ ሽልማት ማሸነፍ ችሏል።ይህም ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያን ከዓለማችን ስኬታማ የውድድር አዘጋጆች ጎራ ሲያሰልፈው የሀገራችንን ስም በበጎ የሚያስነሳ ሌላ ትልቅ ብሔራዊ ሀብት አድርጎታል።ደማቁና ተናፋቂው ዓመታዊ የአስር ኪሎ ሜትር ውድድርም ነገ ለ19 ጊዜ 45ሺ ተሳታፊዎችን ሊያወዳድር ዝግጅቱን አጠናቆ እየተጠባበቀ ይገኛል።ይህንን በማስመልከትም አዲስ ዘመን ቅዳሜ በውድድሩ ዋዜማ ላይ ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ኤርሚያስ አየለ ጋር ያደረገው ቃለ ምልልስ የሚከተለውን ይመስላል፡፡አዲስ ዘመን፡- ነገ በጉጉት
ስለሚጠበቀው ውድድር ምን ማለት ይቻላል?አቶ ኤርሚያስ፡- ይህንን ውድድር በ1993 ዓም የጀመርነው በ10ሺ ሰው ብቻ ነበር፤ በየዓመቱ ሳይቋረጥ ሲካሄድ ቆይቶም ዘንድሮ ለ19ኛ ጊዜ ሲካሄድ 45ሺ ሰዎችን በማሳተፍ ነው።በእርግጥ ፍላጎቱ ከዚያም የበለጠ ነው፤ ነገር ግን ለውድድሩ ጥራት በማሰብ እንዲሁም ከመወዳደሪያ ቦታ ጥበት ጋር በተያያዘ ቁጥሩን ገድበነዋል።ሩጫው እንደሚታወቀው ሁሉንም የሚያሳትፍ በመሆኑ ተሳታፊዎችን የሚያዝናና የሚያስደስት ይሆናል፡፡አዲስ ዘመን፡- ዘንድሮ ካለፉት
19 ዓመታት የተለየ ምን አዲስ ነገር እንጠብቅ? አቶ ኤርሚያስ፡- ቁጥሩ ላይ ጭማሪ አድርገናል፣ አብዛኛው ተሳታፊ ርቀቱን የሚጨርሰው በእርምጃ ከመሆኑ ጋር ተያይዞም ከአንድ ሰዓት በታች የሚገቡ ሯጮችን ቀድመው እንዲነሱ የሚያደርግ የተለየ ቀለም ያለው ከነቴራ (አረንጓዴ ማዕበል) እንዲለብሱ በማድረግ ላለፉት ዓመታት ተሞክሯል፤ ነገር ግን እንደሚፈለገው አልሆነልንም ነበር።በመሆኑም በሰዓት በመከፋፈልና ተሳታፊዎች እንደ ከነቴራቸው ቀለም በየመካከሉ አካላዊ እንቅስቃሴ እያደረጉ በመቆየት ከጥቁር አንበሳ አካባቢ የሚጀምሩትን የአትሌቶችን እና ሌሎቹን በመለያየት የምናካሂድ ይሆናል።እንደተለመደው ውድድሩ ስድስት ሳምንት ሲቀረው ጀምሮ ተሳታፊው ለሩጫው ዝግጅት እንዲያደርግ ቅስቀሳ ስናደርግ ነበር።የመጀመሪያው ሳምንት ዱብ ዱብ ሲሆን፤ ተሳታፊዎች እንቅስቃሴ ከጀመሩ በኋላ ጤናቸውን እንዲመለከቱ ለማድረግ ሁለተኛውን ሳምንት ጤና ብለንዋል።እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሄራዊ ቡድን አረንጓዴ ጎርፍ በሚል ስያሜ ነው የሚጠራው፤ ነገር ግን ጎርፍ ከመሆኑ አስቀድሞ ምንጭ ነውና እኛም የአዳዲስ ስፖርተኞች መታያ እንደመሆናችን ምንጭ ስንል ሰይመነዋል።በነገራችን ላይ ከዚህ ቀደም ለመሳተፍ የሚፈልጉ አትሌቶች ሁሉ ጥያቄ ያቀርቡ ነበር አሁን ግን ይህ እንዳይፈጠር አስቀድመን የማጣሪያ ውድድር አዘጋጅተን ነበር።ቀጣዩን ሳምንት የበጎ ፈቃደኞች ሳምንት ያልነው ሲሆን ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመሆን ልምድ የማካፈል ስራ አከናውነናል።አምስተኛው ሳምንት ደግሞ የጽዳት በማድረግ ውድድሩ የሚካሄድበትን ስፍራ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ከመነሻ እስከ መድረሻ ያለውን አጽድተናል። የመጨረሻውን ሳምንትም የስፖርት ኤክስፖ ሆኖ ነው ያለፈው።አዲስ ዘመን፡- ሌሎች ከሩጫው
ጋር የተያያዙ መርሐ ግብሮችስ ይኖራሉ?አቶ ኤርሚያስ፡- በተለየ የምንሰራው የበጎ አድራጎት ስራ ላይ የመሮጫ ከነቴራዎቹን ለበጎ አድራጎት ለማዋል በ900ብር እንዲሸጥ የማድረግ አንዱ መርሐ ግብር ነው።በዚህም ዘንድሮ በዋግህምራ ዞን አንድ ትምህርት ቤት ለማስገንባት የሚውል ይሆናል። ዛሬ የሚካሄደው የህጻናት ሩጫ እና ምሽት ላይ ደግሞ ከውጪ ሀገራት የሚመጡ ተሳታፊዎቻችንን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት አቀባበል የምናደርግበትም መርሐ ግብር አለን፡፡አዲስ ዘመን፡- ታላቁ ሩጫ
ከሩጫነቱ በዘለለ የሃገር ገጽታ መገንቢያም ሆኗልና በዚህ የረጅም ጊዜ ቆይታው እንደሃገርም ሆነ እንደ ተቋም ያሳካችሁት ምንድነው?አቶ ኤርሚያስ፡- ያሳካነው በርካታ ቢሆንም በዋናነት ግን አራት ጉዳዮችን ማንሳት ይቻላል፤ የመጀመሪያው ከዓመት ዓመት የሃገራችንን በጎ ገጽታ ማሳየት መቻላችን ነው።ወቅታዊ ሁኔታዎች ባይፈትኑን ደግሞ እጅግ በርካታ የውጪ ሃገራት ዜጎች በሩጫው ለመካፈል ወደ እዚህ ይመጣሉ።ያልተቋረጠ የውጪ ሃገራት መገናኛ ብዙሃን ሽፋን ማግኘትም ለሃገሪቷ መልካም ገጽታ ግንባታ ከፍተኛ ሚና አለው።ሁለተኛው ስኬት በሃገር ውስጥ የማስ ስፖርት እንቅስቃሴ እንዲለመድ አድርገናል።ሌላኛው ለአትሌቶች ምቹ የመታያ መድረክ መሆናችን ነው።ማናጀሮች አትሌቶችን ለመመልከት የሚታደሙ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ በአብዛኛው ከአንድ እስከ አስር የሚወጡት አትሌቶች ማናጀር የማግኘት እድላቸው የሰፋ ነው።ይህም ለአትሌቶች ምቹ መድረክ ይፈጥራል።ሌላኛው ጉዳይ ደግሞ የበጎ አድራጎት ስራ ሲሆን፤ ባለፉት ስድስትና አምስት ዓመታት ብቻ ያሰባሰብነው ገንዘብ ወደ ዘጠኝ ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ነው፤ በዚህም በርካታ ድርጅቶችን መርዳት ችለናል፡፡አዲስ ዘመን፡- ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ እንደ ሌሎች ሃገራት ውድድሮች በዓለም አትሌቲክ ደረጃ ተሰጥቶት ለምን አይካሄድም የሚለውም የብዙዎች ጥያቄ ነውና ውድድሩ ደረጃ እንዲያገኝ ያሰባችሁት ነገር አለ?አቶ ኤርሚያስ፡- እኛ የኤይምስ አባል ነን ይህም የዓለም አትሌቲክስ ከሚሰጠው ደረጃ በእኩል መቀመጥ የሚችል ነው።እንደ እኛ ሁሉ ከ400 በላይ የሚሆኑ ሩጫዎችም የዚህ አባል ሲሆኑ የእኛ የጎዳና ላይ ሩጫም ከእነዚህ መካከል አንዱና ታዋቂ ከሆኑት ሩጫዎች መካከል ነው።በመሆኑም ብዙም አስፈላጊ መስሎ አልታየንም።አዲስ ዘመን፡- ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ እዚህ ደረጃ ሲደርስ ብዙ ፈተናዎችን አልፎ ነው፣ አሁንም ፈተናዎች አሉበትና ብትጠቅሳቸው፡፡አቶ ኤርሚያስ፡- ባለፉት ጊዜያት ውድድሩን በየክልሉ ለማስፋት እቅድ ነበረን፤ ይሁንና ሃገሪቷ ውስጥ የነበረው ሁኔታ ብዙ ህዝብ ለመሰብሰብም ሆነ እንዲህ አይነት ዝግጅት ለማድረግ ምቹ አልነበረም።ይህም ብዙ ፍላጎቶቻችንን ነው የገታብን።ሌላው ሁሌም ውድድሩ ሲደርስ አሳሳቢ የሚሆንብን የውድድር ስፍራ ጉዳይ ነው።ቦታውን ቀድሞ አለማወቅ በስራችን ላይ ትልቅ ተጽእኖ እያደረሰብን ሲሆን፤ የመወዳደሪያ ቦታውን ሩጫው ሲደርስ ነው የምናውቀው።በመሆኑም ሩጫው የሃገሪቱ ጭምር በመሆኑ በከተማ አስተዳደሩና በሚመለከታቸው ሁሉ ትኩረት ቢሰጥበትና ቋሚ ቦታ ቢሰጠን መልካም ነው። በመጨረሻም ለተሳታፊዎች ይህ ሩጫ ኢትዮጵያዊነትን የሚያጎላ በመሆኑ በተለመደ ጨዋነቱ ሩጫው ላይ እንዲሳተፍና በኃላፊነት ስሜት የከተማዋን ንጽህና እንዲጠብቅም መልዕክቴን አስተላልፋለሁ።አዲስ ዘመን፡- አቶ ኤርሚያስ
አየለ ለሰጠኸኝ ጊዜ ከልብ አመሰግናለሁ፡፡አቶ ኤርሚያስ፡- እኔም አመሰግናለሁ፡፡አዲስ ዘመን ጥቅም6/2012 ብርሃን ፈይሳ | https://www.press.et/Ama/?p=22603 | 781 | 2ስፖርት
|
ፕሪሚየር ሊጉ እንዲጀመር ክልሎች የጸጥታ ማረጋገጫ አልሰጡም | ስፖርት | November 16, 2019 | 10 | ክልሎች ከጸጥታ ጋር በተያያዘ ማረጋገጫ አለመስጠታቸው የፕሪምየር ሊጉን መካሄድ አሳሳቢ እንዳደረገው አብይ ኮሚቴው ለብሄራዊ ስፖርት ምክር ቤት ገለጸ።ምክር ቤቱም የስፖርቱ ተዋናዮች ኃላፊነታቸውን መወጣት እንደሚገባቸው ጠቁሟል። በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ይመራ የነበረው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከዚህ ዓመት ጀምሮ አዲስ በተቋቋመው አቢይ ኮሚቴ የበላይነት እንደሚካሄድ መወሰኑ ይታወቃል።የውድድር ዓመቱን ህዳር 13 እና 14 ለማስጀመር ዕቅድ የያዘ ሲሆን፤ ትናንት በተቀመጠው መርሐ ግብር መሰረት በአዳማ ከተማ እጣ የማውጣት ስነስርዓት አካሂዷል።ይሁን እንጂ የክልል ጸጥታ አካላት በደህንነት ዙሪያ አስተማማኝ ማረጋገጫ እንዲሰጡ በደብዳቤ ቢጠየቁም ምላሽ አለመስጠታቸውን የኮሚቴው ሰብሳቢ መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ ከትናንት በስቲያ በተካሄደው የብሄራዊ ስፖርት ምክር ቤት ማቋቋሚያ ጉባኤ ላይ ገልጸዋል፡፡ኮሚቴው ምላሽ አለመስጠቱን ተከትሎ በድጋሚ ደብዳቤ ወደ ክልል ጸጥታ አካላት ቢልክም ማረጋገጫውን አስካሁን ማግኘት አልተቻለም።አንዳንድ ክልሎች በበኩላቸው በከተማ ደረጃ ብቻ ምላሽ መስጠታቸው ግራ አጋቢና የውድድር ዓመቱን ለማስጀመር አስተማማኝ እንዳልሆነም በሰብሳቢው ተጠቁ ሟል። በመሆኑም ምክር ቤቱ ሁኔታውን አመዛዝኖ ውሳኔ እንዲሰጥበት ጥያቄያቸውን አቅርበዋል።የብሄራዊ ስፖርት ምክር ቤቱ ሰብሳቢ የሆኑት የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በበኩላቸው ሁሉም የስፖርቱ ተዋናዮች ኃላፊነታቸውን መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል።ኮሚቴው በደብዳቤ ከመጠየቅም ባለፈ ምናልባትም ኃላፊዎቹ ስራ ሊበዛባቸው ስለሚችል ትኩረት ካልሰጡት በአካል ክልሎች ድረስ በመሄድ መወያየት እንዳለባቸውም ምክረ ሃሳባቸውን ሰጥተዋል።ከዚህም ባሻገር ምቹ ሁኔታዎችን ተመልክቶ ሊግ ማስጀመሪያውን ጊዜ ማመቻቸት እንደሚገባ በማንሳት መንግስት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እንደሚነጋገሩና ጊዜ ወስደው እንደሚሰሩም ጠቁመዋል። አዲስ ዘመን ጥቅም6/2012 ብርሃን ፈይሳ | https://www.press.et/Ama/?p=22608 | 198 | 2ስፖርት
|
በኒውዮርክ ማራቶን ኢትዮጵያውያን ለድል ይጠበቃሉ | ስፖርት | November 3, 2019 | 15 | ከዓለማችን ታላላቅ የማራቶን ውድድሮች አንዱ የሆነው የኒውዮርክ ማራቶን ዛሬ ይካሄዳል፡፡ ከሦስት ሳምንት በፊት በዶሃ የዓለም ቻምፒዮና በማራቶን የተሳተፉ በርካታ አትሌቶች በዚህ ውድድር እንደሚሳተፉ ቢጠበቅም ከዓለም ቻምፒዮናው ወዲህ እነዚህ አትሌቶች ለሦስት ወራት ማራቶን እንዳይሮጡ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ማስጠንቀቁን ተከትሎ ጠንካራ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አይሮጡም፡፡ በዓለም ቻምፒዮናው የወርቅ ሜዳሊያ ያጠለቀው ሌሊሳ ዴሲሳ ያለፈው ዓመት የኒውዮርክ ማራቶን አሸናፊ ሲሆን ይህን ድል ለመድገም ከፍተኛ ግምት የተሰጠው በውድድሩ የማይካፈል አትሌት ነው፡፡ ሌሎች ጠንካራ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ግን ከኬንያውያን ጋር ብርቱ ፉክክር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡ በሴቶች መካከል በሚካሄደው ውድድር የ2018 ቻምፒዮኗ ኬንያዊት ማሪ ኪታኒ ትልቅ የአሸናፊነት ግምት አግኝታለች፡፡ 2፡22፡48 በሆነ ሰዓት ሁለተኛውን የውድድር ክብረወሰን ማስመዝገብ የቻለችው ኪታኒ በኒውዮርክ ማራቶን ለአምስተኛ ጊዜ ለማሸነፍ ተዘጋጅታለች፡፡ ኪታኒ ካለፉት አምስት ውድድሮች አራቱን ማሸነፍ ብትችልም ከአስራ ስድስት ዓመት በፊት በማርጋሬት ኦካዮ ተይዞ የቆየውን 2፡22፡31 የሆነ የቦታውን ክብረወሰን ማሻሻል አልቻለችም፡፡ ዘንድሮ ግን ይህን ክብረወሰን ለማሻሻል እንደምትሮጥ አሳውቃለች፡፡ ባለፉት አራት ውድድሮች ሁለተኛ ሆና ማጠናቀቅ የቻለችው ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሩቲ አጋ ኪታኒን የማሸነፍ ግምት ቢሰጣትም በዶሃው የዓለም ቻምፒዮና በመሳተፏ ኒውዮርክ ላይ ተፎካካሪ ላትሆን ትችላለች፡፡ ያም ሆኖ ባለፈው ሁስተን ማራቶን ሁለተኛ ደረጃን ይዛ ያጠናቀቀችው በላይነሽ ፍቃዱ ጠንካራ ፉክክር ታደርጋለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በላይነሽ በማራቶን 2፡26፡41 የሆነ የግሏ ፈጣን ሰዓት አላት፡፡ 2፡28፡06 ሰዓት ያላት ቡዜ ድሪባ ጠንካራ ተፎካካሪ ይሆናሉ ተብለው ከሚጠበቁ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች መካከል አንዷ ነች፡፡ በወንዶች መካከል በሚካሄደው ውድድር የዓለም ቻምፒዮኑ ሌሊሳ ዴሲሳ ተሳታፊ ባይሆንም ባለፈው ዓመት በኒውዮርክ ማራቶን ሁለተኛ ሆኖ ያጠናቀቀው ሹራ ቂጣታ ከፍተኛ የአሸናፊነት ግምት ተሰጥቶታል፡፡ እስካሁን አስራ አንድ የማራቶን ውድድሮችን ያደረገው ሹራ ብዙ የአሸናፊነት ታሪክ ባይኖረውም ገና ሃያ ሦስተኛ ዓመቱ ላይ የሚገኝ መሆኑ ወደ አሸናፊነት ሊመጣ እንደሚችል ይጠበቃል፡፡ ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ታምራት ቶላ የዚህ ውድድር አሸናፊ የመሆን አቅም እንዳለው እየተነገረ ነው፡፡ የዓለም ቻምፒዮና የብር ሜዳሊያ አሸናፊው ታምራት 2017 ላይ በዱባይ ማራቶን ካሸነፈ ወዲህ በጥሩ አቋም ላይ ባይገኝም በማራቶን ጥሩ አቅም ያለው አትሌት ነው፡፡ ባለፈው ሚያዝያ በለንደን ማራቶን ስድስተኛ ሆኖ ያጠናቀቀው ታምራት ባለፈው ቦጎታ ማራቶን አሸናፊ መሆኑ ይታወሳል፡፡ኬንያዊው አትሌት ጂኦፍሪ ኮምዎረር በዛሬው ውድድር ትኩረት የሚሰጠው ነው፡፡ በርካታ የግማሽ ማራቶን ድሎችን በማጣጣም የሚታወቀው ኮምዎረር በማራቶን ትልቅ ስም ባይኖረውም ዛሬ ለኢትዮጵያውያኑ ፈተና እንደሚሆን እምነት ተጥሎበታል፡፡አዲስ ዘመን ጥቅምት23/2012 ቦጋለ አበበ | https://www.press.et/Ama/?p=21918 | 319 | 2ስፖርት
|
ጁንታው የህግ ታራሚዎችን በመቀሌ ከተማ ውስጥ በመልቀቅ ዝርፊያ እንዲፈጸም ማድረጉን የከተማዋ ከንቲባ አስተወቁ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 17, 2020 | 34 | መሀመድ ሁሴን አዲስ
አበባ፡-
የህወሓት ጁንታ በትግራይ ክልል ባሉ ማረሚያ ቤቶች ውስጥ የነበሩ የህግ ታራሚዎችን ሰብስቦ በመቀሌ ከተማ ውስጥ በመልቀቅ ዝርፊያ እንዲፈጸም ማድረጉን የከተማዋ ከንቲባ አስታወቁ።የመቀሌ ከተማ ጊዜያዊ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አታክልቲ ኃይለስላሴ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ በመንግሥት የተወሰደውን የህግ ማስከበር ዕርምጃ ተከትሎ የጁንታው አባላት በክልሉ የተለያዩ ማረሚያ ቤቶች ውስጥ በተለያዩ ወንጀሎች ተይዘው የእስር ጊዜያቸውን እየፈጸሙ የነበሩ ታራሚዎችን መቀሌ ከተማ ለቀዋቸዋል። በዚህም በከተማዋ ውስጥ የዝርፊያ ወንጀል እንዲፈጽሙና ህዝቡ በስጋት ውስጥ እንዲወድቅ አድርገዋል።“በበርካታ ወንጀሎች ተይዘው የነበሩ ሰዎች መቀሌ ላይ ተሰብስበው እንዲለቀቁ ስለተደረገ የግለሰቦች ሱቅ ጭምር እንዲዘረፉ ተደርጓል” ያሉት ከንቲባው፤ ይሄን ያደረጉትም አንድም ተቋማትን በመዝረፍ ሰነዶችን ለማጥፋት፣ ሁለተኛም ሕዝቡ ወደ ስጋት እንዲገባና እንዲጠራጠር በማድረግ በመከላከያ ሠራዊቱ እና በአዲሱ አስተዳደር ላይ እምነት እንዲያጣ ለማድረግ መሆኑንም አስረድተዋል። በዚህ ረገድ መከላከያ ሠራዊት ወደ መቀሌ ከተማ ሲገባ ህዝቡ በደስታ የተቀበለው መሆኑን የሚናገሩት አቶ አታክልቲ፤ ጁንታው በከተማዋ በለቀቃቸው ሰዎች አማካኝነት የሚፈጠሩ የዝርፊያና ስርቆት ተግባራት መበራከት ግን ህዝቡ የደህንነት ስጋት እንዲያድርበት የሚያደርጉ ችግሮችን ፈጥረው እንደነበር ያስታውሳሉ። እነዚህ ችግሮች ደግሞ ሆን ተብለው በጁንታው የተቀነባበሩ መሆናቸውንም ነው ከንቲባው የተናገሩት። “ዝርፊያዎቹን በባህሪያቸው በሁለት ተለይተው መታየት የሚችሉ፤ ብዙ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ሆን ብሎ እንዲዘረፉ የተደረገበትም ነው” ያሉት ከንቲባው፤ ይህ የተደረገውም በተቋማቱ ውስጥ የሚገኙ ሰነዶችን ለማጥፋት አሊያም ለመውሰድ ታስቦ የተቀነባበረም ሆነ ዝርፊያ የተፈጸመበት እንደሆነም አብራርተዋል።በከተማዋ የታየው ዝርፊያ በጁንታው ትዕዛዝ የተፈጸሙ መሆናቸውን በመግለጽም፤ በተለይ በዋና ዋና መስሪያ ቤቶች ላይ ራሳቸው እዚያ ይሠሩ የነበሩ ሰዎች አንዳንድ ሰነዶችን ያጠፉበት መሆኑንም ገልጸዋል። በዚህ ረገድ የከተማ አስተዳደሩ የከንቲባ ጽሕፈት ቤት አስተዳደር ሙሉ ለሙሉ መዘረፉን ተናግረዋል። በተጨማሪም የሕዝብ አገልግሎት መስጫዎች የሆኑት የፍትህ ተቋማት፣ ማዘጋጃ ቤት፣ ፍርድ ቤቶች ውስጥ የሚገኙ ሰነዶች ተዘርፈዋል ያሉት አቶ አታክልቲ፤ በእነዚህ ተቋማት ውስጥ ሆን ተብሎ የተቀናጀ ዝርፊያ ከተፈጸመ በኋላ ተሰርቆ ነው ለማለት ተቋማቱን ክፍት አድርገው መተዋቸውንም አስረድተዋል። ይህንን አጋጣሚ የተጠቀሙ ሌሎች ዘራፊዎችም የተለያዩ ቁሳቁሶችን መዝረፋቸውንም ጠቁመዋል።አሁን ከተማው ወደ ነበረበት የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴዎች እየተመለሰ መሆኑን የሚያሳዩ ጥሩ እንቅስቃሴዎች አሉ ያሉት አቶ አታክልቲ፤ ህብረተሰቡን ያማከለ ሥራ ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በመሆን እየተሠራ ስለሆነ በአጭር ቀናት ውስጥ መቀሌ ወደነበረችበት መደበኛ እንቅስቃሴ እንደምትመለስ አረጋግጠዋል።ለዚህም “በከተማ ደረጃ በምናቋቁመው ምክር ቤት ሕዝቡ በቀጥታ የሚመርጣቸው የየትኛውም ፖለቲካ ፓርቲዎች አባል የሆኑና ለውጡን ደግፈው ሕዝቡን ወደ ተሻለ ደረጃ ሊያሸጋግሩ የሚችሉ አካላት ወደኃለፊነት ይመጣሉ” ያሉት ከንቲባው፤ አሁን የተፈጠረውን ጊዜያዊ ምስቅልቅል በመቆጣጠርና በመምራት ኃለፊነት ወስደው የሚሠሩ፣ ሕዝቡም የተቀበላቸው እና ጥሩ ስነምግባር ኖሯቸው በሕብረተሰቡ አካባቢ ያለውንና የሚነሱትን የፍትህ፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ በፍቃደኝነት መሥራት የሚችሉ ሰዎች በሙሉ የሚካተቱበት ዕድል እነዳለ አስታውቀዋል፡ አዲስ ዘመን ታህሳስ8/2013 ዓ.ም | https://www.press.et/Ama/?p=37507 | 368 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
በኮሮና ዙሪያ የሚስተዋለውን መዘናጋት ለመቅረፍ የማንቂያ መርሃ ግብር ተጀመረ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 16, 2020 | 21 | በኃይሉ አበራአዲስ አበባ፡- በሀገራችን በኮቪድ-19 ዙሪያ በህብረ ተሰቡ መካከል ሰፊ መዘናጋቶች እየታየ በመሆኑ በርካቶች በቫይረሱ እየተያዙ እና ለሞት እየተዳረጉ በመሆኑ መዘናጋቱን ለመቅርፍ የሚያስችል ለአንድ ወር የሚቆይ የማንቂያ መርሃግብር መጀመሩን የአራዳ ክፍለ ከተማ የወጣቶች አደረጃጀት አባላት ገለጹ። የአራዳ ክፍለ ከተማ የበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች አምባሳደር ረሂማ ዋበላ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ በሰጠችው አስተያየት በክፍለ ከተማው 20 የሚሆኑ የተለያዩ የወጣት አደረጃጀት በጎ ፈቃደኛ አምባሳደሮች ኮቪድ-19 መከላከልን ጨምሮ በትምህርት ቤቶች፣ በአረጋውያን ቤት እድሳት እና በመሳሰሉት የበጎ ፍቃድ ስራዎች እየሰሩ ይገኛሉ። በተለይ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላል በሚደረገው ጥረት ውስጥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከፍተኛ መዘናጋት እየተስተዋለ በመሆኑ ህብረተሰቡ ካለበት ሰፊ መዘናጋት እንዲነቃ እና ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲወስድ ለማንቃት ሰፊ ስራ እየተሰራ ይገኛል ብላለች።የንቅናቄው ዓላማ ህብረተሰቡ ግንዛቤ ቢኖረውም እንኳ ባለው መዘናጋት የተነሳ ለኮቪድ-19 እየተጋለጠ በመሆኑ እያንዳንዱ ሰው በሁሉም አካባቢ ርቀቱን እንዲጠብቅ፣ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማስኮችን በአግባቡ እንዲጠቀም፣ እጅን በውሃና በሳሙና ደጋግሞ እንዲታጠብ እና አልኮል ወይም ሳኒታይዘር እንዲጠቀም የማስታወስ ስራ እየሰሩ መሆናቸውን ወጣት ረሂማ ተናግራለች። የአራዳ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ሰብሳቢ አቶ ተካ ደመቀ በበኩሉ እንደገለጸው በኮቪድ-19 ዙሪያ አስፈላጊ ጥንቃቄ ማድረግን እየዘነጋ የመጣውን ማህበረሰባችንን ለማንቃት በሚል በትናንትናው እለት በተጀመረው የማንቂያ መርሃ ግብር ለቀጣይ አንድ ወር የሚቆይ ሰፊ ንቅናቄ ይሰራል።በአንድ ወር ቆይታውም በጎ ፈቃደኛ ወጣት አምባሳደሮችንና ሌሎች ወጣት አደረጃጀቶችን በየቦታው በማስተባበር፣ ህብረተሰቡ ርቀቱን እንዲጠብቅ፣ ማስክ በአግባቡ እንዲያደርግ ከመዘናጋቱ እንዲነቃ እና ሌሎችንም እንዲያስተምር ተደጋጋሚ ንቅናቄ ይደረጋል ብሏል።ከዚህ በፊት በአራዳ ክፍለ ከተማ ደረጃ ሰፊ የማንቂያ ንቅናቄ ሲሰራ መቆየቱን ያስታወሰው አቶ ተካ በዚህ ሁለተኛ ዙር የማንቂያ መርሃ ግብር ህብረተሰቡ መዘናጋቱን በመስበር እና ከራሱ ጀምሮ ኃላፊነቱን በመወጣት ኮሮናን በመከላከሉ ረገድ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ አሳስቧል። በማንቂያ መርሃ ግብሩ ላይ የክፍለ ከተማው የበጎ ፍቃደኛ አምባሳደሮችን ጨምሮ የተለያዩ ወጣት አደረጃጀቶች ከአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በመነሳት በአራት ኪሎና በስድስት ኪሎ በኩል በመጓዝ ሰዎች በሚበዙበት አካባቢዎች የማንቃት ስራዎችን ሰርተዋል።በዓለም ዙሪያ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከተከሰተ ወዲህ ከ73 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውንና ከአንድ ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ደግሞ በዚሁ የተነሳ ለሞት መዳረጋቸውን የዓለም ጤና ድርጅት መረጃዎች ያሳያሉ።አዲስ ዘመን ታህሳስ 7/2013 | https://www.press.et/Ama/?p=37472 | 301 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
አፍሪካውያን ኢትዮጵያ ውስጥ በሚፈለገው ደረጃ ኢንቨስት እንዳላደረጉ ተገለጸ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 16, 2020 | 10 | ፋንታነሽ ክንዴአዲስ አበባ፡- በኢትዮጵያ ኢንቨስት የሚያደርጉ አፍሪካውያን ባለሀብቶች ቁጥር በሚፈለገው ደረጃ አለማደጉን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ። ኮሚሽኑ ከአፍሪካ አገሮች ለመጡ ባለሀብቶችና ሚሽን አባላት በተሻሻለው የኢንቨስትመንት ህግ ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥቷል።የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ፣ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፤ የመጀመሪያው ኢንቨስትመንት ወደ ኢትዮጵያ የመጣው ከአፍሪካ በተለይም ከሱዳን ነበር። በአሁኑ ወቅትም ኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ አፍሪካውያን ባለሀብቶች ቁጥር ቀላል የሚባል አይደለም። ሆኖም ተሳትፏቸው የሚፈለገው ደረጃ ላይ አልደረሰም።እንደ ኮሚሽነር ለሊሴ ገለጻ፤ አፍሪካውያን በኢትዮጵያ በከፍተኛ ደረጃ ኢንቨስት እንዲያደርጉና ጠንካራ የእርስ በርስ ግንኙነት እንዲፈጠር ይፈልጋል። ከዚህ አንጻር የተመዘገቡ የኢንቨስትመንት ቁጥሮች ግን ዝቅ ብለው እንደሚገኙ ነው። ይሄን ችግር ከማቃለል አኳያም የኢንቨስትመንት ህጉ መሻሻሉን ተከትሎ ኮሚሽኑ ከኤምባሲዎች፣ ከኢንቨስትመንት ጋር ግንኙነት ካላቸው የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች፣ ከልማት አጋሮች እና ከተለያዩ አገሮች ከመጡ ኢንቨስተሮች ጋር ተከታታይ ውይይቶች አካሂዷል። አዲሱን የኢንቨስትመንት ህግ ለማስረዳትም ጥረት ተደርጓል። በተደረጉ ተከታታይ ውይይቶች ባለሀብቶች ያሉባቸውን ችግሮች በተሻለ ደረጃ ለመገንዘብ ዕድል መፍጠሩን ያስታወቁት ኮሚሽነሯ፤ ይህም በቀጣይ ኮሚሽኑ ምን ዝግጅት ማድረግ እንዳለበት ለመረዳት ማስቻሉን ገልጸዋል። ተሳታፊዎችም በውይይቱ ደስተኞች እንደሆኑና በ2021 ላይ የተሻለ ውጤት እንደሚጠብቁ ገልጸውላቸዋል።ኮሚሽኑ ከትናንት በስቲያ ከአፍሪካ አገሮች ለመጡ ባለሀብቶችና ሚሽን አባላት በተሻሻለው የኢንቨስትመንት ህግ ዙሪያ ማብራሪያ የሰጠ ሲሆን፤ ከማብራሪያው በኋላ ከተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስተው በሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል። ከተለያዩ የአፍሪካ አገሮች ለመጡ ባለሀብቶችና ሚሽን አባላት ጋር የተደረገው ምክክር ህጉ ከተሻሻለ በኋላ የተካሄደ ስድስተኛ መድረክ መሆኑ ተጠቁሟል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 7/2013 | https://www.press.et/Ama/?p=37459 | 203 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶችን ለመጀመር ብቻ ሳይሆን ለመጨረስ ታስቦ ወደሥራ እንደሚገባ ተገለጸ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 17, 2020 | 7 | አዲሱ ገረመውአዲስ
አበባ፡-
የገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች እንደ ሸገር ፕሮጀክቶች ሁሉ መጀመርን ሳይሆን መጨረስን ታሳቢ በማድረግ ወደ ሥራ እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተናገሩ። ክልሎችም ሆኑ በፕሮጀክቱ ላይ የሚመደቡ አመራሮችና ባለሙያዎች ይህንኑ ታሳቢ አድርገው እንዲሠሩም አሳስበዋል። የሦስቱም የገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች (ወንጪ፣ ጎርጎራና ኮይሻ) አስተባባሪዎች የፕሮጀክቶቹን አጠቃላይ ገጽታ አስመልክተው ትላንት ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ በተገኙበት ማብራሪያ ሰጥተዋል። በዚህ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ሊጀመሩ በታቀዱ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች ላይ ሰፊ የልማት ፍላጎት መታዩትን ገልጸው፤ ነገር ግን ፍላጎትን ከአቅም ጋር ማጣጣም እንደሚገባ እና ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ እንደተከናወነው ከተማን የማስዋብ ሥራ ሁሉ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶችም መጀመርን ሳይሆን መጨረስን ታሳቢ አድርገው ሊሠሩ እንደሚገባ ገልጸዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደገለጹት፤ ሁል ጊዜ ሥራን ከትንሽ በመጀመር በፍጥነት በማሳደግ የሚፈለገውን ትልቁን ነገር ማግኘት እንጂ የመሠረት ድንጋይ በማስቀመጥ ያልተፈጸመበትን ምክንያት ማቅረብ አይደለም። በዚህም መሠረት የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት በሦስቱ ክልሎች (በኦሮሚያ፣ አማራና ደቡብ) እንደሚከናወኑ ተወስኗል። ፕሮጀክቶቹ ለሌሎች ልማቶች ሳቢ በሆነ መንገድ የሚሠሩ ይሆናሉ።በሦስቱም አካባቢዎች የፕሮጀክቶቹን ዓላማ በትክክል ያለመገንዘብና የማስፋት ፍላጎት ይታያል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይሄ ፕሮጀክት በክልልም ይሁን በፌዴራል መንግሥት በጀት ሳይሆን ህዝብን በማስተባበር እንደሚሠራ አመልክተዋል። የፕሮጀክቱ ዋነኛ ዓላማም በአዲስ አበባ የተከናወነውን ከተማን የማስዋብ ሥራ በየክልሉ በተመረጡ ቦታዎች ላይ ማዳረስ ሲሆን፤ አስተባበሪዎች ጊዜያቸውን፣ ጉልበታቸውንና ሃሳባቸውን ሰውተው በመሥራት የግሉ ሴክተር እንዲስፋፋ የበኩላቸውን እንዲወጡም አሳስበዋል።እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ፤ ፕሮጀክቶቹ ተጀምረው እስከሚያልቁ የፌዴራል መንግሥት ፕሮጀክቶች እንጂ የክልሎች ፕሮጀክቶች አይደሉም። ሥራውን በማስኬድ ሂደት የክልል ጣልቃ ገብነትም አይፈልግም። ነገር ግን ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። የፌዴራል መንግሥት ሥራውን ሲጨርስም ያስረክባቸዋል። ይህን ከወዲሁ ለሙያተኞች ማስገንዘብም ከአመራሮች ይጠበቃል። በገንዘብ አሰባሰብ ሂደቱ ከፌዴራል መንግሥት የመጠበቅ ዝንባሌዎች እንዳሉና ነገር ግን በፌዴራል መንግሥት የተለየ የገንዘብ ምንጭ ስለሌለ በዚህ ፕሮጀክት እሳቤ መሠረት ህዝብን የማስተባበር ሥራ እንደሚሠራ ከግምት ውስጥ ማስገባት እንደሚያስፈልግም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል። በተጨማሪም ገንዘብ ሲሰበሰብ አንዳንድ ቦታ የተሳካ፣ አንዳንድ ቦታ ላይ ደግሞ ያነሰ ሊሆን ስለሚችል ገንዘቡ ሌላውንም ፕሮጅክት የልማት አካል አድርጎ ማሰብ ያስፈልጋል ብለዋል። በዚህም አጠቃላይ ገቢው ወደ ማዕከል ከገባ በኋላ የሚከፋፈል እንጂ አንዱ ክልል ያዋጣው ለክልሉ ብቻ እንደማይሆንም ጠቅሰዋል። የፕሮጀክቱ ሥራ መጀመርን ሳይሆን መጨረስን ታሳቢ ያደረገ እንዲሆንም በዚህ ሥራ ውስጥ በፌዴራል በተመደቡ የፕሮጀክት ኃላፊዎች ውጪ ክልሎች መመደብ እንደማይችሉ አሳስበዋል። የገበታ ለሀገር ሦስቱ ፕሮጀክቶች የዲዛይንና የደረሱበት ሂደት በአስተባ ባሪዎች ገለጻ ተደርጎ ውይይት ተካሂዶበታል። በውይይቱ ላይ የገበታ ለሀገር ሦስቱ ፕሮጀክቶች የሚከናወኑባቸው ክልሎች ርዕሰ መስተዳድሮች፣ ሚኒስትሮች እና የሚመለከታቸው አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።አዲስ
ዘመን ታህሳስ 8/2013 ዓ.ም | https://www.press.et/Ama/?p=37508 | 348 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
በኢትዮጵያ የተስተካከለ የግብርና ልማት ፖሊሲ ባለመቀረፁ ዘርፉ ስኬታማ ሳይሆን መቆየቱ ተገለጸ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 17, 2020 | 9 | አብርሃም ተወልደ አዲስ
አበባ፡-
የተስተካከለ የግብርና ልማት ፖሊሲ ባለመነደፉ እና ዕድገትን ከማፋጠን ይልቅ የማደናቀፍ ሚና የሚጫወቱ ፖሊሲዎች ሥራ ላይ በመዋላቸው በኢትዮጵያ ግብርናው ውጤታማ እንዳይሆን መደረጉ ተገለጸ።በኢትዮጵያ
ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የተፈጥሮ ሀብት አያያዝ ምርምር ዳይሬክተር ዶክተር ተመስገን ደሳለኝ ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጹት፤ የግብርና ምርትና ምርታማነት ባለማደጉ የተነሳ በምግብ ራሳችንን መቻል አቅቶን በየዓመቱ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ወገኖቻችን የምግብ ዕርዳታ ለመጠየቅ ተገድደናል።ለዚህ
ደግሞ በዘርፉ የነበረው የእድገት ውስንነት አንዱ ምክንያት ሲሆን፤ በዚህም እንደማነቆ ከነበሩ ጉዳዮች ውስጥ የበጀት ማነስ፣ የሰው ኃይልንና መሬትን አቀናጅቶ አለመጠቀም እና አርሶ አደሩ የሚጠቀምባውን የተሻሻሉ የግብርና ቴክኖሎጂዎችና ግብዓቶች በቀላሉ አለመገኘት ዋና ዋናዎቹ መሆናውንም ዶክተር ተመስገን ጠቁመዋል።የባለሙያው
እውቀት ማነስ አንዱ ተግዳሮት መሆኑን የሚገልጹት ዳይሬክተሩ፤ አሁን ላይ ከዩኒቨርሲቲ ከሚወጣው ባለሞያ ይልቅ የአርሶ አደሩ እውቀት ልቆ ሄዷል ብለዋል። ይህም ለግብርናው የተሰጠውን ትኩረት ያክል ለዘርፉ ትምህርት እንዳልተሰጠ ማሳያ ነው ሲሉ ጠቁመዋል።እንደ
ዶክተር ተመስገን ማብራሪያ፤ ተማሪውም የግብርናን ትምህርት የሚመርጠው መጨረሻ ላይ ነው። ሥራም ስለማያገኝ ግብርናን የሚመርጠው ተማሪ በአቅሙ አነስ ያለ ነው። በዚህም ምክንያት አርሶ አደሩን የመደገፍ አቅሙ እያነሰ መጥቷል። ስለዚህ መንግሥት እዚህ ላይ ትኩረት መደረግ አለበት። ከዚህ
በተጓዳኝ ሊታረስ ከሚችለው መሬት አርባ በመቶ ወይም ሦስት ሚሊዮን ሄክታር መሬት አሲዳማ አፈር መሆኑን የሚናገሩት ዶክተር ተመስገን፤ ከዚህ ውስጥ 10 በመቶውን እንኳ ማከም አልተቻለም ብለዋል። ነገር ግን ከዚህ ውስጥ ስንዴ የሚበቅልባቸውን ቦታዎች ብቻ እንኳን በኖራ ብናክም ከውጭ የምናስገባውን ስንዴ በ50 በመቶ
መቀነስ እንደሚቻል ዶክተር ተመስገን ጠቁመዋል።ዶክተር
ተመስገን ጨምረው እንደገለጹት፤ በአሁኑ ጊዜ በመንግሥታዊ የምርጥ ዘር ድርጅቶች ብቻ በዓመት ከአንድ ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ኩንታል በላይ የተለያዩ ዝርያ ያላቸው ምርጥ ዘሮች ለአርሶ አደሩ እየቀረቡ ይገኛል። ማህበራትና አርሶ አደሩ እርስ በእርስ የሚለዋወጡት ሲጨመር መጠኑ ከሁለት ሚሊዮን ኩንታል በላይ ይሆናል። ይህም ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው እና መንግሥት ዘርፉን ውጤታማ ለማድረግ ከሚወስዳቸው ዕርምጃዎች አንዱ ማሳያ ቢሆንም፤ ግብዓት በሚፈለግበት ሰዓት የማይደርሰበት ሁኔታ አለ።ዶክተር
ተመስገን እንደሚሉት፤ በርካታ ጥናቶች በመስኖ፣ በእንስሳት እርባታ እና መኖ በመሳሰሉት ተሠርተዋል። አብዛኞቹ ደግሞ ችግር ፈቺዎች ቢሆኑም ተግባር ላይ አልዋሉም። ስለዚህ ባለሀብቱም ይሁን መንግሥት መዋለ ነዋይ በማፍሰስ እነዚህን ጥቅም ላይ ማዋል ቢቻል ብዙ ችግሮችን ማቃለል ይቻላል።በሌላ በኩል
ኢትዮጵያ ለመስኖ
ልማት የሰጠችው
ትኩረት አናሳ
በመሆኑ በዚህ
ዘርፍ ግብርናውን
ለማሳደግ እንዳልተቻል
ዶክተር ተመስገን
ይገልጻሉ። በኢትዮጵያ
ውስጥ የከርሰ
ምድር ውሃን
ሳይጨምር ወደ
123 ቢሊየን ኪዩቢክ
ሜትር የሚጠጋ
የውሃ ሀብትና
ከ36 ሚሊየን
ሄክታር በላይ
ሊለማ የሚችል
መሬት አለ
የሚሉት ዶክተር
ተመስገን፤ በሰብል
የለማው የአገሪቱ
መሬት ደግሞ
16 ሚሊየን ሄክታር
ብቻ እንደሆነና
ከዚህ ውስጥም
በመስኖ ልማት
የለማው መሬት
1 ነጥብ 1 ሚሊየን
ሄክታሩ ብቻ
እንደሆነ ጠቁመዋል። | https://www.press.et/Ama/?p=37512 | 371 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የትግራይ ህዝብ አሁን ላይ የሚያስፈልገው ሰላሙን የሚያረጋግጥለትና ልማት የሚሠራለት መንግሥት ነው ሲሉ የትግራይ ተወላጅ ወጣቶች ተናገሩ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 17, 2020 | 10 | • የህወሓት ጁንታ እና የትግራይ ህዝብም አንድ እንዳልነበሩ ገልጸዋል ዋለልኝ አየለአዲስ አበባ፡- ከአሁን በኋላ የትግራይ ህዝብ የሚያስፈልገው ሰላሙን የሚያረጋግጥለት እና ልማት የሚሠራለት መንግሥት ነው ሲሉ የትግራይ ተወላጅ ወጣቶች ተናገሩ። የህወሓት ጁንታ ቡድን የትግራይ ህዝብ ከህወሓት ጋር አንድ መስሎ እንዲታይ የሚያደርግ የሀሰት ትርክቱን ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ጀምሮ ላለፉት 40 ዓመታት ሲሠራ ቢቆይም፤ በተግባር ግን የትግራይ ህዝብና ህወሓት አንድ እንዳልነበሩም ገልጸዋል።የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ከትግራይ ተወላጆች ጋር ትናንት በጌት ፋም ሆቴል የተወያየ ሲሆን፤ የህወሓት ጁንታ ቡድን ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሕፃናት ጀምሮ በሁሉም ደረጃ በሠራው የሀሰት ትርክት በሌላው ህዝብ ዘንድ ህወሓትና የትግራይ ህዝብ አንድ ናቸው የሚል አረዳድ እንዲፈጠር ማድረጉን አስተያየታቸውን ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ የሰጡ የትግራይ ተወላጅ ወጣቶች ገልጸዋል። ይሁን እንጂ ህወሓት እና የትግራይ ህዝብ አንድ እንዳልነበሩ፤ አሁንም የትግራይ ህዝብ የሚያስፈልገው ሰላሙን የሚያረጋግጥለትና ልማት የሚሠራለት መንግሥት መሆኑን ተናግረዋል። ወጣት ዳንኤል ኪዳነ በተለይም ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጸው፤ የህወሓት ጁንታ ቡድን የትግራይ ህዝብ ከህወሓት ጋር አንድ መስሎ እንዲታይ የሚያደርግ የሀሰት ትርክቱን ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ጀምሮ ላለፉት 40 ዓመታት በመሥራቱ ምክንያት ህወሓትና የትግራይ ህዝብ አንድ ናቸው የሚለው አስተሳሰብ እንዲንጸባረቅ አድርጓል። ይሁን እንጂ ህወሓትና የትግራይ ህዝብ አንድ ሊሆን አይገባውም። ምክንያቱም ህወሓት ፓርቲ ነው፤ ፓርቲ ደግሞ ይመጣል፣ ይሄዳል። የትግራይ ህዝብ ደግሞ የሚፈልገው የተሻለ ነገር የሚያስገኝለትንና ሰላሙን የሚያስጠብቅለትን ነው። ህወሓት ሲያስተዳድር በቆየባቸው ዓመታት ደግሞ የትግራይ ህዝብ ከማንም የተለየ አልተጠቀመም።ይልቁንም ሥራ ወዳድና ሰላም ፈላጊ የሆነው የትግራይ ህዝብ ግን የራሱን ጥቅም ብቻ በሚያስጠብቀው የህወሓት ጁንታ ምክንያት ተጠቃሚ ሳይሆን ቆይቷል። እናም አሁን ላይ የትግራይ ህዝብ የሚያስፈልገው ሰላሙን የሚያረጋግጥለትና ልማት የሚሠራለት መንግሥት ነው። ‹‹በትግራይ ክልል ውስጥ እየተመረጡ ያሉት አዳዲስ አመራሮች የትግራይን ህዝብ ስነ ልቦና መቀየር አለባቸው›› የሚለው ሌላው አስተያየት ሰጪ ወጣት ኃይለሚካኤል ፍስሐ በበኩሉ፤ የህወሓት ጁንታ ቡድን ሲያስተዳድር በቆየባቸው ዓመታት የትግራይ ህዝብ ተጠቃሚ እንዳልነበር ይናገራል። በሀሰት ትርክት ግን የትግራይ ህዝብና ህወሓት አንድ እንደሆኑና ህዝቡን ተጠቃሚ አድርጌያለሁ እያለ የህዝቡን ስነ ልቦና ሠርቶበታል።በመሆኑም አዲስ የተመረጡ አመራሮች በህወሓት ዘመን ሳይሠራባቸው የቆዩ የመሰረተ ልማቶችን በመሥራት የህዝቡን ስነ ልቦና መቀየር አለባቸው። ምክንያቱም፣ በትግራይ ክልል ውስጥ ህወሓት ሲያስተዳድር በቆየባቸው ዓመታት ሁሉ ከፍተኛ የሆነ የውሃ ችግር ነበር። አዲስ አስተዳደር ለማስተዳደር እየተዘጋጀ ያለው፣ እንደ ጤና ጣቢያ ያሉ ወሳኝ ማህበራዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን እንኳን መጠቀም ሳይችል የቆየ ህዝብ ያለበት ክልልን ነው። የዩኒቨርሲቲ ተማሪ እያለሁ ከሌላ አካባቢ የሚመጡ ጓደኞቹ ሁሉ ‹‹እናንተማ የቤታችሁ በር ድረስ አስፋልት አላችሁ ይሉኛል፤ ይሄ አስተሳሰብ ደግሞ በጁንታው ተደጋጋሚ የሀሰት ትርክት ብዛት የተቀረጸ ነው›› የሚለው ኃይለሚካኤል፤ እውነታው ግን ለተሽከርካሪ መግቢያ እንኳን የሚሆን መንገድ ጠፍቶ ረጅም ርቀት በእግሩ ይሄድ የነበረ መሆኑን ይናገራል። ህዝቡም ቢሆን የጓድጓድ ውሃ ነው እየጠጣ የቆየው ሲልም ያስረዳል። ‹‹ህወሓትና የትግራይ ህዝብ አንድ የነበረው የበረሃ ትግል ውስጥ እያሉ ነው›› የሚለው ወጣት ኃይለሚካኤል፤ ህወሓት ትግል ላይ በነበረበት ወቅት ሙሉ ህዝባዊ ድጋፍ እንደነበረው ይናገራል። ይሁን እንጂ ከ1983 ዓ.ም በኋላ የተጠበቀው ሳይሆን ቀርቶ ህዝቡ የታገለለትን ዓላማ መነጠቁን እና ፓርቲውና ህዝቡ መለያየታቸውን ይገልጻል። በዚህም የትግራይ ህዝብ ‹‹ፍትሕ ጫካ ቀረ›› እስከማለት ምሬቱን ሲገልጽ መቆየቱን በመጠቆም፤ ህዝቡ በጁንታው የተነጠቀውን የትግል ፍሬ ለማጣጣም እንዲችል አሁን ከተመረጡት አመራሮች ጋር ወጣቱ በትብብር መሥራት እንዳለበት አሳስቧል። ሌላኛው አስተያየት ሰጪ ወጣት ኤሊያስ መድህን እንደሚለው፤ ህወሓትና የትግራይ ህዝብ አንድ ቢሆን ኖሮ ዛሬ ላይ የህወሓት ጁንታ በህዝቡ ላይ ጦርነት አያውጅም ነበር። ያን ሁሉ ንብረትና የመሰረተ ልማት አውታሮች አያወድምም ነበር። ይህ ደግሞ ጁንታውና ጁንታው የሚመራው ፓርቲው ከህዝቡ ጋር አንድ እንዳልሆነ ጉልህ ማሳያ ሲሆን፤ አሁን የተመረጡት አመራሮችም ነገሩን እልባት በመስጠት ህዝቡ ወደሚወደው ሰላምና ልማት እንዲመለስ ተግተው መሥራት ይጠበቅባቸዋል።አዲስ
ዘመን ታህሳስ 8/2013 ዓ.ም | https://www.press.et/Ama/?p=37506 | 510 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
በ782 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ላይ ዕርምጃ መወሰዱ ተገለጸ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 17, 2020 | 11 | በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ፡- በኦሮሚያ ክልል ከሕወሓት ቡድን ጋር በመቀናጀት ግጭቶች ሲያስነሱ፣ ግድያ እና ዝርፊያ ሲፈጽሙ የነበሩ 782 የኦነግ ሸኔ የጥፋት ኃይሎች ላይ ዕርምጃ መወሰዱን የኦሮሚያ ክልል መንግሥት አስታወቀ፡፡የክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ትላንት በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት መንግሥት የክልሉን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ እየሠራ ይገኛል፡፡ሰሞኑን በሆሮ ጉዱሩ ወለጋና በሌሎች ዞኖች ብሄርን መሰረት ያደረጉ ግጭቶች እንዲቀሰቀሱ በማድረግ ግድያ በፈጸሙ የህወሓት ጁንታ ተላላኪዎች ላይ ዕርምጃ መወሰዱንም ገልጸዋል፡፡ከወረዳ እስከ ቀበሌ ድረስ ህግን ማስከበር ባቃታቸውና ከኦነግ ሸኔ ቡድን ጋር በመሆን በንጹሐን ዜጎች ላይ የጥፋት ተግባር ሲፈጽሙ በነበሩ የመንግሥት አመራሮች ላይም ዕርምጃ መወሰዱንም አስታውቀዋል፡፡ይህም የክልሉ መንግሥት ሰላምና መረጋጋትን ማረጋገጥ አልቻለም በሚል በተለያዩ ወገኖች ለሚቀርበው ወቀሳ መልስ ሊሆን ይችላልም ነው ያሉት፡፡ህግ ለማስከበር በተሠራው ሥራ ከከባድ እስከ ቀላል የጦር መሳሪያዎች መያዛቸውንም ነው ያስታወቁት፡፡ ከዚህ በኋላም ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ብሄርን መሰረት ያደረጉ ግጭቶችን ለመቀስቀስ የሚንቀሳቀሱ የጥፋት ኃይሎችን የክልሉ መንግሥት እንደማይታገስም አስረድተዋል ሲል የዘገበው ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ነው፡፡ | https://www.press.et/Ama/?p=37515 | 141 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የአትሌቲክሱ ዓለም የተወዛገበበት የመሮጫ ጫማ | ስፖርት | November 4, 2019 | 33 | ያለፈው የፈረንጆች መስከረም ወር የአትሌቲክሱ ዓለም በርካታ አነጋጋሪና ታሪካዊ ክስተቶችን ያስተናገደ ነበር። በተለይም በማራቶን ውድድር ኬንያዊው አትሌት ኢሉድ ኪፕቾጌ በቬና ማራቶን ከሦስት ሳምንት በፊት ለማመን የሚከብደውን አርባ ሁለት ኪሎ ሜትር ከ2፡00 በታች ሮጦ ማጠናቀቅ እንደሚቻል ያሳየበት ውድድር አሁንም ድረስ መነጋገሪያነቱ ቀጥሏል፡፡ በሃያ አራት ሰዓት ልዩነት ውስጥ ሌላኛዋ ኬንያዊት ብሪጊድ ኮስጌ ቺካጎ ማራቶን ላይ ለአስራ ሰባት ዓመታት ሳይሰበር የቆየውን የዓለም ክብረወሰን ማሻሻሏ ታሪካዊና አነጋጋሪ ከመሆን አልፎ የውዝግቦች መነሻ ሆኗል፡፡ የውዝግቡ መነሻ ሁለቱ አትሌቶች የሰሩት ታሪክ ሳይሆን ታሪክ የሰሩበት የመሮጫ ጫማ ነው፡፡ ግዙፉ የስፖርት ትጥቅ አምራች ኩባንያ ናይኪ ማራቶንን ከ2፡00 በታች መሮጥ ይቻል ዘንድ ባለፉት ዓመታት ትልቅ ፕሮጀክት ቀርፆ ከኬንያዊው አትሌት ኪፕቾጌ ጋር በጋራ ሲሰራ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ ይህም እንዲሳካ ፍጥነትን የሚጨምር ልዩ የመሮጫ ጫማ ከማዘጋጀት ጀምሮ ያልቆፈረው ጉድጓድ አልነበረም፡፡ ይህ ፕሮጀክቱ ተሳክቶም ኪፕቾጌ በአርባ አንድ አሯሯጮችና በዘመናዊው ጫማ ታግዞ አርባ ሁለት ኪሎ ሜትሩን 1፡59፡40 በሆነ ሰዓት ማጠናቀቅ ችሏል፡፡ ሌላኛዋ ኬንያዊት ኮስጌም በቺካጎ ማራቶን በቅርብ ዓመታት ይሰበራል ተብሎ ያልተጠበቀውን የፓውላ ራድክሊፍ 2፡15፡25 የሆነ የዓለም ክብረወሰን በዘመናዊው የናይኪ ጫማ ሮጣ በሰማንያ አንድ ሰከንድ አንክታዋለች፡፡ ኪፕቾጌ ይህን ታሪክ ለመስራት ከሦስት ዓመት በፊት ሲነሳም ከተለያዩ የስፖርት ቤተሰቦች ተቃውሞ ማስተናገዱ አልቀረም። ማራቶንን የሰው ልጅ በተፈጥሯዊ መንገድ ከ2፡00 በታች ማጠናቀቅ እየቻለ በቴክኖሎጂ መታገዙ በበርካቶች ዘንድ አልተዋጠም ነበር፡፡ ኢትዮጵያውያኑ ጀግኖች አትሌቶች ኃይሌ ገብረስላሴና ቀነኒሳ በቀለን ጨምሮ ማራቶንን በቴክኖሎጂ ታግዞ ከ2፡00 በታች መሮጥ እንደማይዋጥላቸው ይልቁንም በተፈጥሯዊ መንገድ ጠንካራ ዝግጅት ተደርጎ ሃሳቡን ማሳካት እንደሚቻል ገና ከውጥኑ ሲናገሩ ነበር፡፡ ኪፕቾጌ ያሳካው ፕሮጀክት በስፖርቱ ትልቅ መነቃቃትን ከመፍጠር ባሻገር የሰው ልጅ የብቃት ጥግ ወሰን እንደሌለው ግንዛቤ ፈጥሯል፡፡ ይሁን እንጂ ይህን ስኬት በርካቶች ከስፖርታዊ ኩነቱ ነጥለው በመመልከት አትሌቱ ተጫምቶት የሮጠበትን የናይኪ ጫማ የማስተዋወቅ የንግድ ስራ አድርገው ተመልክተውታል፡፡ በንግዱ ዓለም ፍልስፍና ብዙ የሚዋጥ ባይሆንም ናይኪ የስፖርት ትጥቅ አምራች ኩባንያ በመላው ዓለም ትልቅ ስም እያለው በዚህ መንገድ ስፖርቱን ተጠቅሞ ምርቱን ለማስተዋወቅ መሞከሩ ሌሎች ተፎካካሪዎቹን ለመዋጥ ያደረገው ስግብግብነት እንደሆነ ያስቀመጡ ወገኖችም ጥቂት አይደሉም፡፡ የሰው ልጅ በተፈጥሯዊ መንገድ ሮጦ ማራቶንን ከ2 ሰዓት በታች ማጠናቀቅ እየቻለ ኪፕቾጌ በምቹ የውድድር ቦታ ላይ በረቀቀ ቴክኖሎጂ ታግዞ ማሳካቱ ከስፖርት መርህ ጋር ተቃራኒ እንደሆነ የሚያነሱም አሉ፡፡ በአርቴፊሽያል ነገሮች በአትሌቲክሱ መግባት ከጀመሩ ወደ ፊት ስፖርቱ አሁን ያለውን የፉክክር ለዛ ይዞ አይቀጥልም የሚል ስጋት ያላቸው የስፖርት ቤተሰቦች ከዚህም ከዚያም አትሌቲክሱ ላይ ጠንከራ ጥያቄና ትችት ሲሰነዝሩ ሰንብተዋል፡፡ ዛሬም ድረስ በበርካታ የቀድሞ የዓለማችን አትሌቶች ተቃውሞ እየገጠመውም ይገኛል፡፡ ዘ ታይምስ እንደ ዘገበው በርካታ አትሌቶች ናይኪ ባሰናዳው ዘመናዊ የመሮጫ ጫማ ላይ የተቃውሞ ድምፅ እያሰሙ ይገኛሉ። የቀድሞው ጣሊያናዊ የማራቶን ቻምፒዮን ጂያኒ ዲማዶናን ጨምሮ ሃያ አትሌቶች ተሰባስበው ለዓለም አትሌቲክስ የናይኪን ዘመናዊ ጫማ ተቃውመው ደብዳቤ አስገብተዋል፡፡ የዓለም አትሌቲክስ ህግ ‹‹የመሮጫ ጫማዎች አትሌቶች እግራቸው ላይ ጉዳት እንዳይደርስባቸውና በምቾት እንዲሮጡ እንጂ ተገቢ ያልሆነ ጥቅምና ድጋፍ እንዲያገኙ አይደለም›› ይላል፡፡ ኪፕቾጌ ማራቶንን ከ2፡00 በታች ሲያጠናቅቅ የተጫማው ጫማ ግን ናይኪ በቴክኖሎጂ የተጠበበትና ገና ለገበያ ያልዋለ እንደመሆኑ ልዩ ትቅም ወይም ድጋፍ አላገኘበትም ማለት አይቻልም፡፡ ኮስጌ በእንግሊዛዊቷ አትሌት ፓውላ ራድክሊፍ ለአስራ ስድስት ዓመታት ተይዞ የቆየውን 2፡15፡25 ክብረወሰን በሰማንያ አንድ ሰከንድ ስታሻሽልም ይሄንኑ ጫማ አጥልቃ ነው የሮጠችው፡፡ ይህም መሮጫ ጫማ ፓውላ ራድክሊፍ ክብረወሰን ስትሰብር ከተጫመችው ከ60 እስከ 90 ሰከንድ አትሌቷን የማፍጠን ጥቅም ስላለው ያሻሻለችውን 81 ሰከንድ ላይ ጉልህ ተፅዕኖ እንደነበረው የተለያዩ ትንታኔዎች ወጥተዋል፡፡ ይህንንም ተከትሎ ዓለም አትሌቲክስ ዘመን አመጣሽ ቴክኖሎጂዎች በተለይም ከመሮጫ ጫማው ጋር ተያይዞ ለአትሌቶች እገዛ ማድረግ አለባቸው የለባቸውም የሚለው ሃሳብ አከራካሪ መሆኑን ገልፃል፡፡ ስለዚህም ጫማው በአትሌቶች ፍጥነት ላይ የሚኖረውን ተፅዕኖ ለመመርመር አንድ የጥናት ቡድን ለማቋቋም ተገዷል፡፡ አትሌቶች በተለያዩ ጊዜዎች በሚመረቱ ጫማዎች ሮጠው የተለያዩ ክብረወሰኖችን ሲሰብሩ ቆይተዋል፡፡ ይህ የናይኪ አዲስ ጫማ ከገበያ አኳያ ብዙ ስለተወራለት እንጂ ከዚህ ቀደም የሌለ ነገር እንዳልሆነ የሚሞግቱ የአትሌቲክስ ቤተሰቦች ቁጥርም ቀላል አይደለም፡፡ እንደ ዘ ታይምስ ትንታኔ ከሆነ ናይኪ አዲስ ያመረተው ጫማ ለአንድ አንድ አትሌቶች ይፋ የተደረገው ከ2016 በፊት ነው፡፡ 2014 ላይ ዴኒስ ኪሜቶ በበርሊን ማራቶን 2፡2፡57 የሆነ የዓለም ክብረወሰን ሲያስመዘግብ ይህን ጫማ ተጫምቷል፡፡ ከዚያ በኋም አምስት ጊዜ ይህን ጫማ ያጠለቁ አትሌቶች ክብረወሰን አሻሽለዋል። ይህን ልብ ያሉት የፕሮፌሽናል አትሌቶች የብቃት አሰልጣኝ ስቲቭ ማግኔስ ‹‹ጥናቶችን ካስተዋልን ጫማው በአትሌቶች ፍጥነት ላይ ትልቅ ተፅዕኖ አለው›› በማለት ለዋሺንግተን ፖስት አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ አዲስ ዘመን ጥቅምት24/2012ቦጋለ አበበ | https://www.press.et/Ama/?p=21977 | 605 | 2ስፖርት
|
ኮሚሽኑ ለ500 ሺህ ወጣቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር አቅዷል | ሀገር አቀፍ ዜና | December 17, 2020 | 9 | ግርማ መንግሥቴአዲስ
አበባ፡-
በኦሮሚያ ክልል የቱሪዝም ዘርፍ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ውስጥ ለ500 ሺህ
ወጣቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ማቀዱን የክልሉ ቱሪዝም ኮሚሽን አስታወቀ። የክልሉ
የቱሪዝም ኮሚሽነር ወ/ሮ
ሌሊሴ ዱጋ ትናንት በጽህፈት ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት መንግሥት ለቱሪዝም ሴክተሩ የሰጠውን ልዩ ትኩረት ተከትሎ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የክልሉን ቱሪዝም ዘርፍ ማሳደግ ያስችላል በሚል ያቋቋመው የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን ሥራውን በይፋ ጀምሯል።ኮሚሽኑ
ከዘርፉ የሚገኙትን ጥቅሞች ይበልጥ ለማሳደግ፣ አገርና ክልሉን የበለጠ ተጠቃሚ ለማድረግ፣ ዜጎችን በተለይም ወጣቱን በማሳተፍ ዘርፉን ለማበልጸግና የባለሀብቱን ቀልብ ለመሳብ ይቻል ዘንድ ታስቦ የተቋቋመ መሆኑን የጠቀሱት ወይዘሮ ሌሊሴ፤ በአጭር ጊዜ ውስጥም ውጤታማ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል። “ክልሉን ለጎብኚዎች ቀዳሚና ተመራጭ መዳረሻ ሆኖ ማየትን” ራእዩ
ያደረገው ኮሚሽኑ ለሀገሪቱ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ለማድረግ፤ በአገሪቱ እየተካሄደ ያለውን ልማት ለማፋጠን፣ ለማገዝና ሌሎች ተግባራትንም ለማከናወን በሚያስችል ደረጃ የተቋቋመው “የኦሮሚያ
ቱሪዝም ኮሚሽን” ክልሉ
የሚታወቅበትንና ያለውን ሰው ሠራሽና የተፈጥሮ ሀብት በአግባቡና ለዜጎች በሚጠቅም መልኩ ለማከናወን እንደሚያስችልም ኮሚሽነሯ ተናግረዋል። እንደ
ኮሚሽነር ሌሊሴ ዱጋ መግለጫ በተለይ የቱሪዝም ኢንቨስትመንትን ከመሳብ፣ ከማስፋፋትና በዘርፉ መሳተፍ የሚፈልጉ ባለሀብቶች እንዲሰማሩ ከማድረግ አኳያ ሰፊ ሥራ የሚሠራ ሲሆን፤ ይህም ሴክተሩ ለሀገር ልማት የሚጠበቅበትን ጉልህ ሚና እንዲወጣና የራሱን ሚና እንዲጫወት ማድረግ የኮሚሽኑ ዋንኛ ትኩረት ሆኖ ተቀምጧል። የክልሉ
ቱሪዝም ልማት ሙሉ ለሙሉ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ማዕከል ባደረገና ወጣት መር በሆነ መልኩ እንደሚሠራ የተናገሩት ወ/ሮ
ሌሊሴ ይህ መርህ አገራችን ከዘርፉ ማግኘት እየተገባት እስከ ዛሬ ያጣችውን ጥቅም እንድታገኝ ከማስቻሉም በላይ ዘርፉ ከራሳችንም አልፎ በቅርብ ጊዜ ውስጥ አገራችንን ከአፍሪካም ቀዳሚ እንደሚያደርጋት ገልጸዋል። በክልሉ
ዘላቂ የቱሪዝም ልማትን ለማረጋገጥ የቱሪዝም ፈንድ በማቋቋም ሴክተሩንም በስፋት ለማጠናከር በእቅድ ተይዞ እንደሚሠራ የተናገሩት ኮሚሽነሯ ለዚህም ፍላጎቱና ሀብቱ ካላቸው ከማናቸውም ወገኖች ጋር ለመሥራት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል። በክልሉ በከፍተኛ
ደረጃ የሥራ
ዕድል ፈላጊ
ወጣቶች መኖራቸውን
የሚናገሩት ኮሚሽነር
ሌሊሴ ይህን
ችግር በመሰረታዊነት
ለመቅረፍና የተለያዩ
የሥራ ዕድሎችን
በመፍጠር በሚቀጥሉት
አምስት ዓመታት
ውስጥ ከ500,000 በላይ ለሚሆኑ
ወጣቶች የሥራ
ዕድል በመፍጠር
ተጠቃሚ ለማድረግ
እቅድ ተይዟል
ሲሉም ተናግረዋል። አዲስ ዘመን ታህሳስ 8/2013 ዓ.ም | https://www.press.et/Ama/?p=37524 | 287 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
“ከለውጡ በፊት ጀምሮ በነበረኝ የሃሳብ ልዩነት በጁንታው አባላትና ደጋፊዎች ማስፈራሪያና ዛቻ ይደርስብኝ ነበር”-የተከበሩ ወይዘሮ ያየሽ ተስፋሁነኝ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ብቸኛዋ የትግራይ ክልል ተወካይ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 17, 2020 | 144 | ማህሌት አብዱልአዲስ
አበባ፡-
የህወሓት ጁንታ በአገሪቱ ህዝብ ላይ ያደርስ የነበረውን ጭቆና እና ግፍ በመቃወማቸውና የሃሳብ ልዩነት በማንጸባረቃቸው በጁንታው አባላትና ደጋፊዎች ከፍተኛ ማስፈራሪያና ዛቻ ሲደርስባቸው እንደነበር በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ብቸኛዋ የትግራይ ክልል ተወካይ ገለጹ። ተወካዩዋ
የተከበሩ ወይዘሮ ያየሽ ተስፋሁነኝ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጹት ድርጅቱን ከተቀላቀሉበት ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ
ጁንታው የህወሓት ቡድን በአገሪቱም ሆነ በመላዉ የትግራይ ህዝብ ላይ ያደርስ የነበረው ጭቆና እና ኢ-ሰብዓዊ
ድርጊት ከፍተኛ በመሆኑ ይህንን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ሲቃወሙና ሲታገሉ ቆይተዋል። በተለይም
በምክር ቤቱ በነበራቸው ቆይታ ሚዛኑን ያልጠበቀና እውነትን መሰረት ያላደረጉ ውሳኔዎች ላይ የሚያምኑበትን ሃሳብ በግልጽ በመናገራቸው ምክንያት በድርጅቱ አመራሮች የተመደቡ ግለሰቦች በስልክና በማሕበራዊ ሚዲያ ዛቻና ማስፈራሪያ ያደርሱባቸው እንደነበር ወይዘሮ ያየሽ ተናግረዋል። ‹‹በፌስቡክና
በተለያዩ ማሕበራዊ ሚዲያዎች አርፈሽ ካልተቀመጥሽ እንዲህና እንዲያ እናደርግሻለን ከማለትም በተጨማሪ ገንዘብ ተሰጥቶሽ ነው፤ የሚሉ ማስፈራሪያዎች፣ ስድብና ዛቻ ይደርስብኝ ነበር›› ያሉት ወይዘሮ ያየሽ፤ አንዳንዳቹም ለእሳቸው በማሰብና በመስጋት ፊትለፊት መጋፈጥ እንደሌለባቸው ይመክሯቸው እንደነበር ጠቁመዋል። በተለይም መስከረም 25 ቀን 2013 ዓ.ም
የትግራይ ተወካዮች ምክር ቤት እንዳይገቡ በጁንታው የተላለፈውን ጥሪ ባለመቀበላቸው ምክንያት የቅርብ በሚሏቸው አባላት መገለል ያጋጠማቸው መሆኑንና ይህም ቡድኑ የሃሳብ ልዩነትን የማይቀበልና ፅንፈኛ ድርጅት መሆኑን ማሳያ ነው ብለዋል። ከዚህም ባሻገር ይህ ድርጊታቸው አባላቱ በስነልቦናዊ ጫና ውስጥ ተሸብበው እንዲኖሩ ያደረገ አሸባሪ ቡድን መሆኑንም በግልጽ እንደሚያስረዳ ወይዘሮ ያየሽ ተናግረዋል። እንደርሳቸው ማብራሪያ አገር ሲመራ የነበረው ይህ ህገወጥ ቡድን ህገመንግሥቱንና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔን በመተላለፍ ምርጫ ማካሄዱ አልበቃ ብሎ ከመስከረም 25 ጀምሮ መንግሥት የለም በሚል አገር ለማፍረስና ህገመንግሥቱን ለመናድ ያደረገው ሙከራ ምንም እንኳን ባይሳካለትም በታሪክም ሆነ በህግ ተጠያቂ ከመሆን አያግደውም ብለዋል። በተለይም የኮሮና ቫይረስ በዓለም ደረጃ በተስፋፋበት ጊዜ ምርጫ ማካሄዱ ድርጅቱ ከራሱ ጥቅም ውጪ ለህዝቡ የማያስብ መሆኑን አመላካች መሆኑን ወይዘሮ ያየሽ ጠቁመው፤ ‹‹ምርጫው መራዘም እንዳለበት በባለሙዎች ዓይናችን እያየ፣ አሳማኝ ጭብጥ በዝርዝር እየቀረበ መክረንበት የተወሰነ መሆኑ እየታወቀ›› በጁንታው የተላለፈው ምክር ቤት አትግቡ የሚል ትዕዛዝ ፈፅሞ አሳማኝ እንዳልነበረ ያሳያል ብለዋል። በወቅቱም እሳቸው ውሳኔውን በግልጽ ከመቃወም አልፈው ሌሎች አባላትም ውሳኔያቸውን እንዲያስተካክሉ እና ለወከላቸው ህዝብ ታማኝ እንዲሆኑ መምከራቸዉንም አመልክተዋል። “ጁንታው ህወሓትና የትግራይ ህዝብ አንድ ነው ይላል በመሰረቱ ህወሓትና የትግራይ ህዝብ አንድ ከሆነ ምርጫ ለምን ያስፈልጋል? ለምን ሀብትና ጊዜስ ይባክናል?” ሲሉም የተካሄደው ምርጫ ከአሳማኝነቱ ይልቅ ከመስመር የወጣ ተግባርና ለማንም የማያስተምር እንደነበር አንስተዋል። ብዙሃኑ የትግራይ ህዝብ አሁንም በከፍተኛ ድህነት ውስጥ ነው እየኖረ ያለው የሚሉት ወይዘሮ ያየሽ፤ ከጁንታው ጋር ጥገኛ የሆኑ ጥቂት ሰዎች ካልሆኑ በስተቀር የክልሉ ህዝብ አሁንም በርካታ ችግሮችን እየተጋፈጠ እንደሆነ ጠቁመዋል። ለአብነትም በክልሉ አሁንም ከፍተኛ የውሃ እጥረት አለ፤ ተማሪዎች አሁንም በዳስ ነው እየተማሩ ያሉት፤ በክፍተኛ መጠን እየጨመረ የመጣውን አዲስ ትውልድ በአግባቡ ሊቀርፅ የሚችል ተቋም አልተገነባም ሲሉም አስረድተዋል።‹‹ለምርጫ የሚያባክኑት ገንዘብ ለእነዚህ ሥራዎች ቢውል ኖሮ፤ ጠቃሚ እንደነበር የጠቆሙት ወይዘሮ ያየሽ፤ ቡድኑ የራሱን ጥቅምና ፍላጎት ብቻ የሚያስቀድም እንደነበረና የጁንታው አባላትም በገዢነት መደብ ቁጭ ብለው አድራጊና ፈጣሪ ሆነው የሚቀጥሉበትን ዕድል ሲያመቻቹ መቆየታቸውን ጠቁመዋል። አዲስ ዘመን ታህሳስ 8 /2013 ዓ.ም | https://www.press.et/Ama/?p=37517 | 420 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
አንጋፋው የኪነ ጥበብ ባለሙያ ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሰሰ አረፉ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 17, 2020 | 9 | በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- ደራሲ እና ተዋናይ አንጋፋው የኪነ ጥበብ ባለሙያ ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሰሰ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሰሰ፣ በህክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ84 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩትተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ የተለያዩ መፅሐፍትን የደረሱ ሲሆን፤ በተለያዩ ፊልሞች እና ድራማዎች ላይም በተዋናይነት ተሳትፈዋል። በርካታ ተውኔቶች ላይም የትወና ችሎታቸውን ያስመሰከሩ ሲሆን፤ በአጫጭር ልቦለዶችና ግጥሞቻቸው በሩሲያኛ ተተርጉመው ሩሲያ ውስጥ ታትመዋል። ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ መተከዣ (ግጥምና ቅኔ)፣ ጥላሁን ግዛው፣ ዕቃው፣ የሺ፣ አባትና ልጆች፣ ላቀችና ደስታ፣ ተሐድሶ የተሰኙ ተውኔቶችንም ደርሰዋል። እንዲሁም የዑመር ኻያምን ልቦለዳዊ የሕይወት ታሪኩና ሩብ አያቶቹ የትርጉም መፅሐፍ ለአንባቢያን አድርሰዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴዓትር እና ጥበባት ኮሌጅም ለበርካታ ዓመታት በመምህርነት አገልግለዋል። በቀድሞው ሐረርጌ ክፍለ ሀገር ጎሮጉቱ በሚባል አካባቢ ከአባታቸው ከአቶ ገሰሰ ቆለጭ እና ከእናታቸው ወይዘሮ በለጥሻቸው ያየህይራድ መስከረም 17 ቀን 1929 ዓ.ም የተወለዱት ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ፤ በትናንትናው ዕለት በተወለዱ በ84 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። አንጋፋው የጥበብ ሰው ብሄራዊ ቴዓትር ቤት የሽኝት ፕሮግራም እንደሚያዘጋጅ የተገለጸ ሲሆን፤ ቀብራቸው በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን እንደሚፈፀም ተጠቁሟል።የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትም በአንጋፋው የኪነ ጥበብ ባለሙያ ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሰሰ ዜና ዕረፍት የተሰማውን ኀዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቻቸውና ወዳጆቻቸው መጽናናትን ይመኛል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 8/2013 ዓ.ም | https://www.press.et/Ama/?p=37532 | 175 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ሩጫ በባዶ እግ | ስፖርት | November 4, 2019 | 34 | ብስራቱን ለመንገር የመጀመሪያውን ማራቶን ከአቴንስ እስከ ስፓርታ የሮጠው ወታደሩ ፊዲፒደስ ከ30 ሰዓታት በላይ ፈጅቶበታል። ከዘመናት በኋላ ደግሞ 42 ኪሎ ሜትሩ በሁለት ሰዓት ውስጥ የሚጠናቀቅ ሆኗል፡፡ ነገር ግን በቅርቡ ከዚህም በታች በሆነ ሰዓት መግባት እንደሚቻል ኬንያዊው አትሌት አረጋግጧል። ይህንን ሃሳብ በመያዝ ሲንቀሳቀስ የቆየው ናይኪ የተባለው የስፖርት ትጥቅ አምራችም በጫማዎቹ አማካኝነት ርቀቱ እስካሁን በሰው ልጅ ታሪክ ታይቶ በማይታወቅበት ሁኔታ ከሁለት ሰዓት በታች መግባት እንደሚቻል አሳይቷል። ነገር ግን የማራቶን ሰዓት እዚህ ከመድረሱ ናይኪም በዘመን አመጣሽ ጫማዎቹ ሳይራቀቅ በፊት ፊዲፒደስ ርቀቱን በምን ሸፈነው በማለት የታሪክ ማህደርን ማገላበጥ አስፈላጊ ይሆናል። ሩጫ መለያዋ የሆነው ኢትዮጵያም የተከበረውን የኦሊምፒክ መንደር አሃዱ ያለችው በምን መልኩ ነው ለሚለውም ታሪክን መለስ ብሎ ማስታወስ በቂ ነው። ባለሙያዎች «ተፈጥሮአዊ ሩጫ» ሲሉ የሚጠሩትና በተለምዶ በባዶ እግር መሮጥ ለማራቶን ስፖርት መሰረት ነው ለማለት ይቻላል። በዘመነው ዓለም የማይታሰበው የባዶ እግር ሩጫ በአፍሪካ እና በደቡባዊው አሜሪካ ግን እስካሁንም በስፋት ይስተዋላል። በኢትዮጵያም ይህ አሯሯጥ የተለመደ ቢሆንም ምርጫ በማጣት (ከድህነት ጋር በተያያዘ ምክንያት) አሊያም በአስገዳጅ ሁኔታ የሚከወን ስለመሆኑ ዋቢ መጥቀስ አያሻም። በአንጻሩ ከሃብት ማማ ላይ በሚገኙት ምዕራባዊያን ዘንድ ይህ ዓይነቱ ሩጫ ጥቅሙን በመረዳት ይዘወተራል። ከጊዜ ወደ ጊዜም እየታወቀና እየተስፋፋ የመጣ የአሯሯጥ ዓይነት ሆኗል። በተለይ በሃይቅና ውቅያኖስ ዳርቻዎች እንዲሁም በሳር በተሸፈኑ መስኮች ላይ ባዶ እግርን መሮጥ እያደገ ያለ ተግባር ነው። በዚህ የሩጫ ዓይነት ስሙ ጎልቶ የሚነሳው ኢትዮጵያዊው ታላቅ አትሌት አበበ ቢቂላ ቢሆንም ከእርሱ አስቀድመውም ሆነ በዚያው ዘመን በርካቶች ባዶ እግራቸውን በውድድሮች ላይ ይካፈሉ ነበር። ከታዋቂዎቹ መካከልም ደቡብ አፍሪካዊቷ የሁለት ጊዜ የሃገር አቋራጭ ሻምፒዮና ዞላ ቡድ፣ አውስትራሊያዊው የ1ሺ500 ሜትር እና 800 ሜትር አትሌት ኸርብ ኤሎት እንዲሁም እንግሊዛዊው የ3 ማይል ሻምፒዮን ብሩች ቱሎህ ጥቂቶቹ ናቸው። ጀግናውን አትሌት ከሌሎቹ ልዩ የሚያደርገውም በባዶ እግር ቀርቶ በጫማም የማይደፈረውንና እህል ውሃ የማያሰኘውን ማራቶንን በመሮጡ ነው። እርግጥ ነው ከረጅም ዓመታት በኋላም ሌላ ኢትዮጵያዊ አትሌት በዚህ መልክ 42 ኪሎ ሜትሮችን በማቋረጥ ዓለምን አጀብ ማሰኘት ችሏል። ከሰው ልጅ ስልጣኔ እና የአኗኗር ሁኔታ ጋር በተያያዘ የሰው ልጅ ሩጫን በባዶ እግሩ አሊያም ከድብ እና ከሌሎች እንስሳት ቆዳ በሚሰራ ጫማ ሲከውነው እንደነበረ ጥንታዊያን ታሪኮች ያስረዳሉ። ግሪካዊያንም በጥንታዊው ኦሊምፒክ ጭምር በሩጫ ብቻም ሳይሆን በተለያዩ ስፖርቶች የሚካፈሉ ተወዳዳሪዎች ባዶ እግራቸውን ነበር የሚቀርቡት። እንደሌላው ዘርፍ ሁሉ የስፖርት ቁሳቁሶችም ከዘመን ጋር እየዘመኑና በረቀቁ ቴክኖሎጂዎች ታግዘው እየተካሄዱ ይገኛሉ። ለዚህም በቅርቡ ኬንያዊው አትሌት ኢሉድ ኪፕቾጌ በ1ሰዓት ከ59 ደቂቃ ከ40ሰከንድ በሆነ ሰዓት ማራቶንን የሮጠበትን ጫማ ማንሳት ይቻላል። ናይኪ ቫፖርፍላይ የተባለው ይህ የመሮጫ ጫማ ከተፈጥሮአዊው አቅም ባሻገር አትሌቶችን ወደፊት በማፈናጠር ተጨማሪ ፍጥነት የሚሰጥ ነው። በርካቶች ግን 250 ዶላር ዋጋ የተተመነለት ናይኪ ቫፖርፍላይን በህግ ከሚያስቀጣው የአበረታች ቅመሞች ተጠቃሚነት ለይተው አያዩትም። ይህ ከዘመናዊው ዓለም ጋር ከመራመድ እና ከተፈጥሯዊው ልማድ ጋር የመቀጠል እሳቤም የአትሌቲክስ ቤተሰቡን ከሁለት የከፈለ አድርጎታል። በተፈጥሯዊ መንገድ በባዶ እግር መሮጥ ግን ላለንበት ወቅት የማይመጥን ተግባር ተደርጎ ይወሰድ እንጂ የጤና ባለሙያዎች እንዲተገበር የሚመክሩት የአሯሯጥ ዓይነት ነው። ሳይንስም በባዶ እግር መሮጥን ከጉዳት ማገገምን ጨምሮ በርካታ ጥቅሞችን እንደሚያስገኝ ያረጋግጣል። ነገር ግን ተግብሮት ለማያውቅ ሰው በመጀመሪያ ፈታኝ እንደሚሆን እና የሚሮጡበትን ስፍራ ደህንነትም አስቀድሞ ማረጋገጥ እንደሚገባም ያሳስባል። የመጫሚያዎች ምቾት ከሳምባ፣ ከአእምሮ፣ ከደም ዝውውር እንዲሁም ከነርቭ ጋር ይያያዛል። በመሆኑም ከባድ፣ ጠባብ፣ ከተረከዛቸው ከፍ ያሉ፣… ጫማዎች ያደረገውን ሰው ምቾት ከመንሳት ባሻገር ጤናም ላይ ተያያዥ እክሎችን ማድረሱ አይቀርም። በመሆኑም አልፎ አልፎም ቢሆን ባዶ እግርን መጓዝ እና መሮጥን መለማመድ ጠቃሚ ይሆናል። የደም ዝውውርን ለማስተካከል ተመራጭ መንገድ ሲሆን፤ በተለይ ለልብ ህመም እንዲሁም በደም ውስጥ የሚኖሩ መርዘኛ ንጥረ ነገሮችን ለማስወገድ እንደሚረዳ ተመራማሪዎች በሳይንስ ጆርናሎች ያሳተሟቸው ጽሁፎች ያስነብባሉ። በሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር ዳንኤል ሊበርማን እንደሚገልጹት ከሆነ፤ (cushioned
shoes) በመባል የሚታወቁትን የስፖርት ጫማዎች የሚያዘወትሩ አትሌቶች ተረከዛቸው በመዶሻ የመቀጥቀጥን ያህል ጉዳት ይደርስባቸዋል። በመሆኑም አሰልጣኞች አንዳንዴም አትሌቶቻቸውን ባዶ እግራቸውን በሳር ላይ እንዲሮጡ ቢያደርጉ፤ የእግራቸውን ጤንነት ከመንከባከብም በላይ ከደረሰባቸውም ጉዳት እንዲያገግሙ እንደሚረዳቸው ያስረዳሉ። በጫማ መሮጥ በባዶ እግር ከመሮጥ ይልቅ የኦክስጅን ፍጆታን በሁለት እጅ ይጨምራል፤ ይህም አትሌቱ (ሯጩ ግለሰብ) ከሚያወጣው ጉልበት የሚያያዝ በመሆኑ በሚሸፍነው ርቀት ላይ የራሱን ተጽእኖ ማሳረፉ አይቀርም። በእግር ጤንነት፣ ሚዛን፣ ነርቮችን በማነቃቃት፣ የእግር ቅርጽ እና እድገት ላይም በጫማ እና ያለጫማ እንቅስቃሴ ማድረግ ሚናው ይለያያል። በተለይ ደግሞ በሽንጥ፣ ባት፣ ተረከዝ፣ ቁርጭምጭሚት፣ ጅማት፣ አጥንት እና ጡንቻዎች ጤና ላይ የራሱን አሻራ ያሳርፋል። ከዚህ ባሻገር ሰው ከተፈጥሮ ጋር ያለውን ቁርኝትም በማስፋትና ተፈጥሮን በመንከባከብ ረገድ የራሱን ስነ-ልቦናዊ በረከት ያስገኛል።አዲስ ዘመን ጥቅምት24/2012 ብርሃን ፈይሳ | https://www.press.et/Ama/?p=21980 | 625 | 2ስፖርት
|
የኦሊምፒክ ኮሚቴና የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን አለመግባባት ቀጥሏል | ስፖርት | November 7, 2019 | 9 | የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አሁንም አለመግባባት ውስጥ ይገኛሉ። በተለይም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉና የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ መካከል አለመግባባት መፈጠር ከጀመረ የሰነበተ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አለመግባባቱ ከግለሰቦቹ አልፎ ተቋማዊ እየሆነ መጥቷል፡፡ ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ፣ ኦሊምፒክ ኮሚቴው የሚጓዝበት መስመር እና ውሳኔዎች የሚተላለፉባቸው መንገዶች ግልጽ የሆነ አሠራርን የማይከተሉ ከመሆናቸው ባሻገር መመሪያ እና አሠራርን ሳይሆን የግለሰቦች ፍላጎትን ብቻ መሠረት አድርገው የሚካሄዱ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ «ስፖርቱ እውነተኛ ተቆርቋሪ አጥቷል» ሲሉ ቅሬታቸውን ለኦሊምፒክ ኮሚቴው ከትናንት በስቲያ በፃፉት ደብዳቤ አብራርተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ በበኩላቸው «ምንም የተፈፀመ ስህተት የለም» በማለት ትናንት ረፋድ ላይ ለሸገር ስፖርት ተናግረዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ አክለውም ትናንት በአምባሳደር ሆቴል አዲሱ የኦሊምፒክ ኮሚቴ መተዳደሪያ ደንብ ውይይት ሲደረግበት ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር በተያያዘ የሚነሳውን ቅሬታ እንደሚመክሩበት አብራርተዋል፡፡ በአምባሳደር ሆቴል እንደሚካሄድ ቀጠሮ የተያዘለት አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ወይም ስብሰባ ላይ ተሰብሳቢዎቹ የተጠሩበት ሂደት እና የጉባኤው አጀንዳዎች በግልጽ ምን ምን እንደሆኑ ቀደም ብለው አለመታወቃቸው፡ ከኮሚቴው መተዳደሪያ ደንብ እና አሠራር ጋር አብሮ የሚሄድ እንዳልሆነ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ቢልልኝ መቆያ ለልዩ ስፖርት ገልጸዋል፡፡ ደራርቱ ቱሉ ከኦሊምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈፃሚነት ራሷን ለማግለል ውሳኔ ላይ ደርሳ የነበረች ቢሆንም ሃሳቧን መቀየሯ ይታወሳል፡፡ ደራርቱ በኦሊምፒክ ኮሚቴ የውሳኔ አሰጣጥ ረገድ የምትመለከታቸውን ሕጸጾች ከዚህ በኋላ የማይታረሙ ከሆነ ከኦሊምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈፃሚነት ራሷን እንደምታገል ማስጠንቀቋ ይታወሳል፡፡ ደራርቱ ባለፈው ነሐሴ በደብረ ብርሃን ከተማ በተደረገው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ከሥራ አስፈፃሚነት ለመልቀቅ መወሰኗን የተናገረች ቢሆንም በጠቅላላ ጉባኤው በርካታ ሰዎች ውሳኔዋን እንድታጥፍ ግፊት በማሳደራቸው ሃሳቧን ልትቀይር ችላለች፡፡አዲስ ዘመን ጥቅምት27/2012 ቦጋለ አበበ | https://www.press.et/Ama/?p=22111 | 239 | 2ስፖርት
|
በመላ አፍሪካ የተሳተፉ ፌዴሬሽኖች ገንዘብ አላወራረዱም | ስፖርት | November 5, 2019 | 19 | ከሁለት ወር በፊት በሞሮኮ አስተናጋጅነት በተካሄደው አስራ ሁለተኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ላይ የተሳተፉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ስፖርት ፌዴሬሽኖች ለውድድሩ የወሰዱትን ገንዘብ እስካሁን በሕጋዊ ደረሰኝ እንዳላወራረዱ ተገለጸ።የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ትናንት በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ሪፖርትን ባቀረበበት ወቅት እንደተገለፀው በውድድሩ አስራ ሦስት ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች ተሳትፈዋል።ለመላ አፍሪካ ጨዋታዎች በአጠቃላይ ሃያ ሁለት ሚሊዮን ብር ገደማ ወጪ መደረጉ በሪፖርቱ የተገለፀ ሲሆን መንግሥት ለውድድሩ ስልሳ ሚሊዮን ብር መመደቡ ተጠቁሟል።መንግሥት በቂ በጀት የመደበ ቢሆንም የበጀት ክፍፍሉና አጠቃቀሙ ኦሊምፒክ ኮሚቴው ታምኖበት እንዳልተሰጠው ተጠቅሷል።ይህም በጀቱ የዕዝ ሰንሰለቱን በጠበቀ መልኩ እንዳይፈፀም ማድረጉ ተብራርቷል።መንግሥት ለውድድሩ የበጀተው ገንዘብ በቀጥታ ውድድሩን ለሚመራው ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሳይሆን በፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን በኩል ለፌዴሬሽኖች እንዲከፋፈል መደረጉ ቀደም ሲልም ሲነገር ቆይቷል።ወደ ውድድሩ ስፍራ በአጠቃላይ ሁለት መቶ ሰባ ሰው የተጓዘ ሲሆን አላግባብ የተጓዘ ልዑካን ቡድን እንደሌለ በሪፖርቱ ተጠቅሷል።ወደ ውድድሩ አቅንቶ ሳይሳተፍ የተመለሰው የክብደት ማንሳት ልዑካን ቡድን ጉዳይ አነጋጋሪ እንደነበር የሚታወስ ነው።ኢትዮጵያን ወክለው በክብደት ማንሳት ስፖርት ለመሳተፍ ወደ ስፍራው ያቀኑት ስፖርተኞች ሳይሳተፉ የተመለሱት በፀረ አበረታች መድኃኒት ቁጥጥር ከውድድሩ በፊት ምዝገባ ባለማድረጋቸው መሆኑ ታውቋል።ያም ሆኖ ስፖርተኞች ወደ ስፍራው ከመሄዳቸው አስቀድሞ ማሟላት ያለባቸውን አስፈላጊ ነገር ሳያሟሉ በመቅረታቸው ለተፈጠረው ችግር ኃላፊነቱን የትኛው አካል መውሰድ አለበት የሚለው ጉዳይ አነጋጋሪ ሆኖ ቆይቷል።ለዚህ ችግር መፈጠር የውድድሩ አዘጋጆች የመረጃ ክፍተት አንዱ ምክንያት ከመሆኑ ባሻገር «የእኛም ክፍተት አለበት» በማለት በሪፖርቱ ቀርቧል።በውድድሩ ወቅት ችግር ተብለው ከተነሱ ጉዳዮች አንዱ የዳኝነት ችግር በጉልህ ተጠቅሷል።በአንዳንድ ውድድሮች ዓለምአቀፍ የውድድር ልምድ ማነስ ሌላኛው ችግር እንደነበር ተነስቷል።በተለይም በጅምናስቲክ ስፖርት በአገራችን ዘመናዊ መሣሪያዎች አለመኖር ተወዳዳሪዎች እዚያ ሲሄዱ ያጋጠማቸው አዳዲስ መሣሪያ ግራ እንዳጋባቸውና ሳይወዳደሩ እንደቀሩ ጭምር ተገልጿል።ትልቅ ብቃት ያላቸውና ታዋቂ የሆኑ አትሌቶች በውድድሩ አለመሳተፋቸው የተሻለ ውጤት እንዳይመዘገብ ማድረጉ ተብራርቷል።በዝግጅት ወቅት የተለያዩ ስፖርቶች የተዘጋጁበት ወቅት መለያየትም አንድ ችግር ሆኖ ተነስቷል።በዚህ ረገድ ቦክስ፣ ወርልድ ቴኳንዶና አትሌቲክስን በመሳሰሉ ስፖርቶች ዘጠና ያህል ቀናት የተዘጋጁ ሲሆን ሌሎች ስፖርቶች ከአርባ አምስት እስከ ስልሳ ቀናት ብቻ ነው ዝግጅት ያደረጉት።በውድድሩ የገጠሙትን የተለያዩ ችግሮች ለመፍታት የተሞከረ ሲሆን አሰልጣኞች ከዘመኑ ጋር አብረው መጓዝ የሚችሉ መሆን እንዳለባቸውና ከዚህ በኋላ በልምድ ብቻ መጓዝ እንደማይቻል የትኩረት አቅጣጫ ተቀምጧል።ስፖርተኞች የዓለም አቀፍ ውድድሮች ልምድ ቀደም ብለው ማግኘት እንዳለባቸውም ተብራርቷል።በመላ አፍሪካ ጨዋታ አመርቂ ውጤት ያስመዘገቡ ስፖርተኞች እስካሁን ድረስ እውቅናም ይሁን ሽልማት አለማግኘታቸው አነጋጋሪ መሆኑ አልቀረም።ኦሊምፒክ ኮሚቴም ከውድድሮች በኋላ በወቅቱ የእውቅናና ሽልማት ፕሮግራሞች በማዘጋጀት ማበረታታት እንደሚገባ በሪፖርቱ ተመልክቷል።ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በአስራ ሦስት የስፖርት ዓይነቶች መላ አፍሪካ ጨዋታ ላይ በመሳተፍ በቦክስ፣ አትሌቲክስ፣ ወርልድ ቴኳንዶና ብስክሌት ስፖርቶች ባስመዘገበቻቸው ሜዳሊያዎች ዘጠነኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።ከተመዘገቡት ሜዳሊያዎች መካከል ስድስት የወርቅ፣ አምስት የብርና አስራ ሁለት የነሐስ መሆናቸው ይታወሳል።በውድድሩ በአትሌቲክስ አምስት የወርቅ፣ አምስት የብርና ስምንት የነሐስ ሜዳሊያ የተመዘገበ ሲሆን በወርልድ ቴኳንዶ አንድ የወርቅና ሁለት የነሐስ ሜዳሊያዎች ተመዝግበዋል።በቦክስ ስፖርት አንድ የነሐስ ሜዳሊያ ሲመዘገብም ቀሪው በብስክሌት ስፖርት የተመዘገበ ሆኗል።ይህም በበርካታ ስፖርት ተሳታፊ በመሆን የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚቻል የታየበት ነው ተብሏል።የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ሪፖርት እስካሁን ያልቀረበው ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች በወቅቱ ሪፖርታቸውን ባለማቅረባቸውና እንደ አትሌቲክስ ያሉ ፌዴሬሽኖች በዓለም አቀፍ ውድድሮች ተጠምደው በመክረማቸው መሆኑ ታውቋል።አዲስ ዘመን ጥቅምት25/2012 ቦጋለ አበበ | https://www.press.et/Ama/?p=22004 | 432 | 2ስፖርት
|
ሦስት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለታላቅ ሽልማት ታጭተዋል | ስፖርት | November 6, 2019 | 40 | የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር በየዓመቱ በሚያዘጋጀው የምርጥ አትሌቶች ሽልማት ከዚህ ቀደም በርካታ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸናፊ ቢሆኑም አምናና ዘንድሮ በሁለቱም ፆታ ከምርጥ አስር እጩዎች ውስጥ እንኳን ሳይካተቱ መቅረታቸው ይታወቃል። ይሁን እንጂ ዓለም አቀፍ ማህበሩ በሚያዘጋጀው ተመሳሳይ የሽልማት ዘርፍ ወጣትና ወደፊት ትልቅ ተስፋ ባላቸው አትሌቶች ሽልማት ዘርፍ ሦስት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከመጨረሻዎቹ ምርጥ አምስት እጩዎች ውስጥ መካተት ችለዋል። ከሃያ ዓመት በታች የሆኑ አትሌቶች በሚሸለሙበት ዘርፍ ባለፉት ሁለት ዓመታት በመካከለኛና ረጅም ርቀቶች ድንቅ ብቃት እያሳየ የሚገኘው አትሌት ሰለሞን ባረጋ ከመጨረሻዎቹ አምስት እጩዎች ስም ዝርዝር ውስጥ መካተቱ ታውቋል።ሰለሞን ባለፈው ዓመትም በተመሳሳይ ሽልማት እጩ መሆን እንደቻለ ይታወሳል። የደቡብ ፖሊሱ ክለብ አትሌት የሆነው ሰለሞን ባረጋ ከእድሜው ከፍ ብሎ ከታላላቆቹ ጋር በመወዳደር እያስመዘገበ ላለው ስኬት ባለፈው ዓመት ክለቡ የኢንስፔክተርነት ማዕረግ የሰጠው ሲሆን ባለፉት ሦስት ዓመታት እያሳየ ያለው አስደናቂ ብቃት ወደ ፊት ተስፋ እንዲጣልበት አድርጓል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ወደ ታላላቅ የውድድር መድረኮች መጥቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ የስፖርት ቤተሰቡ አይን ማረፊያ የሆነው ወጣት አትሌት ሰለሞን ባረጋ ውጤቱና አስደናቂ ብቃቱ ኢትዮጵያ በቅርቡ በታላላቅ መድረኮች አረንጓዴውን ጎርፍ ዳግም የማየት ብሩህ ተስፋ እንዳላት ማሳያ መሆኑን በርካቶች ይመሰክሩለታል። ድንቅ የሩጫ ተሰጥኦው በመካከለኛና ረጅም ርቀቶች በቅርብ ጊዜ ውስጥ ዙፋን ላይ እንደሚወጣ የስፖርቱ ባለሙያዎች በተደጋጋሚ መስክረውለታል። ከ18 እና ከ2o ዓመት በታች የዓለም ወጣቶች ቻምፒዮና አሸናፊ መሆን የቻለው ሰለሞን የለንደን የዓለም ቻምፒዮና በቀጥታ ወደ ትልቅ ደረጃ ተሸጋግሮ የኢትዮጵያውያንን የአምስት ሺ ሜትር ስብስብ ምን ያህል አስፈሪ እንዳደረው ይታወሳል። ዘንድሮም ይህን አቋም በመድገም በዶሃው የዓለም ቻምፒዮና የብር ሜዳሊያ ወደ ማስመዝገብ ተሸጋግሯል። በ2018 የውድድር ዓመት የአምስት ሺ ሜትር አጠቃላይ የዳይመንድ ሊግ አሸናፊ መሆን የቻለው ሰለሞን ባረጋ በርቀቱ ከሃያ ዓመት በታች የዓለም ክብረወሰንን 12፡ 43፡02 በሆነ ሰዓት ከመጨበጡ ባሻገር እኤአ 2005 ላይ ቀነኒሳ በቀለ በርቀቱ ካስመዘገበው ሰዓት ወዲህ ፈጣን ሰዓት ሆኖ መመዝገቡ ይታወሳል። ሰለሞን በዓለም ከሃያ ዓመት በታች ቻምፒዮናና በአፍሪካ አትሌቲክስ ቻምፒዮናም በርቀቱ አራተኛ ደረጃን ይዞ በመፈፀም በውድድር ዓመቱ በርካታ ስኬቶችን አግኝቷል። ዘንድሮም በዓለም ቻምፒዮና የብር ሜዳሊያ ከማጥለቁ ባሻገር በአምስት ሺ ሜትር 12፡53፡04 በመሮጥ ከሃያ ዓመት በታች አትሌቶች ሁሉ ፈጣን መሆን ችሏል። በአስር ሺ ሜትርም ከሃያ ዓመት በታች የዓመቱን መሪ ሰዓት 26፡ 49፡46 በሆነ ሰዓት ማስመዝገቡ ይታወሳል። አርሁስ ላይ ተካሂዶ በነበረው የዓለም አገር አቋራጭ ቻምፒዮና በአዋቂዎች ምድብ አምስተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁም ለሽልማቱ እጩ አድርጎታል። በዶሃው የዓለም ቻምፒዮና ኢትዮጵያ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በሦስት ሺ ሜትር መሰናክል የብር ሜዳሊያ እንድታገኝ ያስቻለው አትሌት ለሜቻ ግርማ ከአምስቱ ተስፈኛ እጩዎች መካከል አንዱ መሆን ችሏል። ለሜቻ በውድድር ዓመቱ በርቀቱ ከሃያ ዓመት በታች መሪ የሆነውን ሰዓት በ8፡01፡36 ያስመዘገበ ሲሆን የኢትዮጵያን ክብረወሰንም የግሉ ማድረግ ችሏል። በዓለም ቻምፒዮናውም የወርቅ ሜዳሊያ ያመለጠው በ0ነጥብ01 ማይክሮ ሰከንድ ተቀድሞ እንደነበረ አይዘነጋም። ከሁለቱ ኢትዮጵያን እጩዎች ጎን ለጎን ብራዚላዊው የአራት መቶ ሜትር መሰናክል ተወዳዳሪ አሊሰን ዶስ ሳንቶስ እጩ መሆን የቻለ ሲሆን በዶሃው የዓለም ቻምፒዮና ሰባተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል። ይህ አትሌት የፓን አሜሪካን ቻምፒዮን መሆኑ ይታወሳል። ኖርዌያዊው አትሌት ጃኮብ ኢንግብሪትሰን ሌላኛው እጩ ሲሆን የአውሮፓ የሦስት ሺ ሜትር ቻምፒዮን ነው። ይህ አትሌት የዓለም ከሃያ ዓመት በታች የ1500 ሜትር መሪ ሰዓት ያለው ሲሆን የአውሮፓ ከሃያ ዓመት በታች ክብረወሰን ማሻሻሉ በውድድር ዓመቱ የሚጠቀስለት ስኬት ነው። ዩክሬናዊው መዶሻ ወርዋሪ ማይክሃይሎ ኮክሃን ከሃያ ዓመት በታች የመዶሻ ውርወራን 77ነጥብ 39 በመወርወር በውድድር ዓመቱ መሪ ሲሆን በዶሃው የዓለም ቻምፒዮና አምስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል። በሴቶች በኩል አፍሪካን የወከለችው ብቸኛዋ አትሌት ኢትዮጵያዊቷ ለምለም ኃይሉ ሆናለች። በዓለም ከ20 ዓመት በታች ቻምፒዮና በ 1ሺ500 ሜትር 4:02.97 የገባችው ለምለም የርቀቱ ቀጣይ ተስፋ እንደምትሆን እምነት ተጥሎባታል። በመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ላይ በዚሁ ርቀት ነሃስ ሜዳሊያ ባለቤት እንዲሁም በዶሃው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ላይ አገሯን ለመወከል በቅታለች። ለምለም በቻምዮናው ላይ ውጤት ባታስመዘግብም እስከ ግማሽ ፍጻሜ በመጓዝ ያሳየችው አስደናቂ ብቃት እጩ አድርጓታል። በወጣቶች ዓለም ቻምፒዮናው ላይ በ100 ሜትር መሰናክል 12.71 በሆነ ሰዓት በመግባት ዓለም ክብረ ወሰንን የሰበረችው ጃማይካዊቷ ብሪታኒ አንደርሰንም ከእጩዎቹ መካከል ትገኛለች። ዩክሬናዊታ ያሮስላቫ ማሁቺክ ሌላኛዋ እጩ ስትሆን በከፍታ ዝላይ ስፖርት የተሻለ አቅም ያላት አትሌት ናት። አትሌቷ በቻምፒዮናው 2 ሜትር ከ04 ሳንቲ ሜትር በመዝለል የክብረ ወሰን ባለቤት ናት። በዶሃው የዓለም ቻምፒዮናም የብር ሜዳሊያ አግኝታለች። ከዚህም ባሻገር አውሮፓ ቻምፒን መሆን የቻለች ጠንካራ አትሌትም ናት። የኢኳዶሯ እርምጃ ተወዳዳሪ ግሌንዳ ሞርጆን በወጣቶች ቻምፒዮና ያስመዘገበችው ውጤት እጩ አድርጓታል። ያስመዘገበችው 1:25:29 የሆነ ሰዓት ደግሞ ከዓለም ምርጦች ተርታ ሲሰለፍ በደቡብ አምሪካ ደግሞ ቀዳሚው ሆኖላታል። አትሌቷ በአህጉር አቀፍ 10 ኪሎ ሜትር ውድድር ላይ የገባችበት 43:04 ሆነ ሰዓትም ክብረወሰን ነው። አምሪካዊቷ 100 ሜትር የወጣቶች ባለክብረወሰን ሻካሪ ሪቻርድሰንም ከአምስቱ እጩ አትሌቶች መካከል አንዷ ናት። በወጣቶች ዓለም ቻምፒና 100 ሜትሩን በ 10.75 ስታጠናቅቅ 200 ሜትሩን ደግሞ በ 22.17 ገብታለች። ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ሽልማት ኢትዮጵያዊቷ ወጣት አትሌት መሰረት በለጠ ከመጨረሻዎቹ አምስት እጩዎች አንዷ በመሆን መመረጧ ይታወሳል። መሰረት ባለፈው የውድድር ዓመት ግማሽ ማራቶን ውድድር ከዓለም ከሃያ ዓመት በታች ምርጥ የተባለውን 1፡07፡ 51 ሰዓት ማስመዝገቧ ይታወሳል። ከዚህ በተጨማሪ በስፔን ቫሌንሲያ ተካሂዶ በነበረው የዓለም ግማሽ ማራቶን ቻምፒዮና ላይ ስድስተኛ ደረጃን ይዛ ያጠናቀቀች ቢሆንም በቡድን የወርቅ ተሸላሚ ነበረች። በጉተንበርግ ግማሽ ማራቶንም አሸናፊ ሆና ማጠናቀቋ አይዘነጋም። ሌላኛዋ ወጣት ኢትዮጵያዊት አትሌት መስከረም ማሞም አምና ከእጩዎቹ መካከል የተካተተች ሲሆን በውድድር ዓመቱ በዓለም ከሃያ ዓመት በታች የሦስት ሺ ሜትር ውድድር በ8፡33፡63 ሰዓት ፈጣን ተብላ ነበር። የ2018 ምርጥ ታዳጊ አትሌት ሽልማት አሸናፊ በፈረንጆቹ ህዳር 23 ቀን በፈረንሳይ ሞናኮ በሚደረገው የዓለም የዓመቱ ምርጥ የአትሌቶች ሽልማት ይፋ እንደሚሆን የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር አሳውቋል።አዲስ ዘመን ጥቅምት26/2012 ብርሃን ፈይሳ | https://www.press.et/Ama/?p=22051 | 784 | 2ስፖርት
|
አካዳሚው ባለፉት አምስት ዓመታት | ስፖርት | October 27, 2019 | 18 | አካዳሚዎች የሁሉም ስፖርቶች መሠረት ለመሆናቸው ዓለም አቀፍ ልምዶችን መመልከት በቂ ነው። በስፖርቱ መሠረት ያላቸውን ታዳጊዎች ሰብሳቢ የሆኑት አካዳሚዎች ድንቅ የእግር ኳስ፣ አትሌቲክስ፣ ብስክሌት፣ ቦክስ ወዘተ…ጥበበኞች በማፍራት ረገድ ስኬታማ መሆናቸው የአደባባይ ምስጢር ነው። በአካዳሚዎች ገና ከሕፃንነታቸው እንዲሰለጥኑ መንገድ በመክፈት፤ ወደ ታዳጊነት በማሸጋገር ራዕያቸውን እንዲያሳኩ በማንደርደርና ወደ ታላቅነት ስፍራ በማድረስ ይሄንኑ አስመስክረዋል። በዓለም አቀፍ የስፖርት መድረኮች ስኬታማ መሆን የቻሉ ስፖርተኞች መነሻቸው ሲፈተሽ በዚህ መንገድ የተጓዙ ሆነው እናገኛለን። የአካዳሚውን መሠረታዊ ጥቅም የተረዱ እንደነ እንግሊዝ፣ ስፔን ወዘተ… በተለይ በእግር ኳሱ ላይ ትኩረት አድርገው ሰርተዋል። ውጤታማ ለመሆንም መብቃታቸው በዘርፉ የተደረጉ ጥናቶች ምስክር ሆነው ይቀርባሉ። ከዚህ አኳያ አካዳሚዎችን ወደ አገራችን ማምጣቱ ለስፖርቱ ትንሳኤ ዋነኛው መድህን እንደሚሆን በስፖርት አዋቂዎች በኩል ሲንጸባረቅ ቆይቷል። ምክረ ሃሳብ ተደጋግሞ በስፋት ተነግሯል። በተለይ ደግሞ፤ ኢትዮጵያ በዓለም ታላላቅ መድረኮች የታወቀችበትን አትሌቲክስ ስፖርት በመጥቀስ፤ ከዓለም በ5 ሺ ፣10 ሺ ሜትር እንዲሁም በማራቶን ስሟ በቀዳሚነት ትጠራለች።ከዚህ ጥሪ ፊት ለፊት ሞገስ ሆነው የሚቀርቡት ደግሞ ጀግኖች አትሌቶቻችን ናቸው። የአትሌቶቹ ስኬታማነት በግላቸው የሚያደርጉት ጥረትና ከአሰልጣኞቻቸው የሚቸራቸውን ሙያዊ እገዛ ምርኩዝ በማድረግ ነበር። የተፈጥሮ ችሎታቸውን መሠረት ባደረገ ሁኔታ በሳይንሳዊ ሥልጠና ባልታገዙበት በዚያን ዘመን፤ በፍላጎትና በአገር ፍቅር ለድል በቅተዋል። የትናንት ጀግኖች አትሌቶቻችን ከተፈጥሯዊ ችሮታቸው ጋር ሳይንሳዊ ሥልጠናው ቢደመር ምናልባትም ከሰሩት ታሪክ የበለጠ እንደሚሰሩ ጥርጥር የለውም። በአካዳሚዎች መሠረት ባለው ሁኔታ በአትሌቲክሱ ያለውን የተፈጥሮ ችሮታ ደግፎና አሳድጎ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚገባ በስፖርት አዋቂዎች በኩል ተደጋግሞ ሃሳብ ሲቀርብ ቆይቷል። መንግሥት ምክረ ሃሳቡን «ጆሮ ዳባ ልበስ» በሚል አንጥሮ በመመለስ ዓመታትን ተጉዟል። አትሌቲክስን ጨምሮ በተለያዩ የስፖርቱ ዓይነቶች እየተስተዋለ ያለው የውጤት መዋዠቅ ብሎም፤ አንጋፋዎቹን የሚተኩ ታዳጊዎች አለመኖር አካዳሚዎችን ማቋቋሙ መሠረታዊ መፍትሄ እንደሆነ አቋም እንዲያዝ አድርጓል።ስፖርቱን በሚመራው ኮሚሽን ዘንድ ሃሳቡን በመግዛት ወደ ትግበራ ለመቀየር በቅቷል። በዚህም መሠረት ከፍተኛ ገንዘብ ወጪ በማድረግ በወጣቶች ተስፋ ሰንቆ የኢትዮጵያ ወጣቶችና ስፖርት አካዳሚ ተቋቋመ። መንግሥት የአካዳሚው መቋቋም ፋይዳው ዘግይቶ ቢገባውም፤ ወደ ትግበራው መግባቱ እንደመልካም የተቆጠረለት ነበር። ይሄንን መስመር በማለፍ አካዳሚው በ2005 ተመርቆ በ2006 ዓ.ም ስፖርተኞችን መልምሎ ሥራውን ጀምሯል። በአትሌቲክስ፣ በፓራሊምፒክ፣ በቮሊቦል፣ በእግር ኳስ፣ በውኃ ዋና፣ በወርልድ ቴኳንዶ፣ በቅርጫት ኳስ፣ በጠረጴዛ ቴኒስ፣ በቦክስና በብስክሌት የስፖርት ዓይነቶች ሥልጠና በመስጠት ጉዞውን ሊጀምር በቅቷል። አካዳሚው የሥልጠና አቅሙን ከፍ ለማድረግ በ2002 ዓ᎐ም ሥራ ከጀመረው የጥሩነሽ ዲባባ ማሰልጠኛ ማዕከልን በመጠቅለል ትግበራውን አጠነከረ። የኢትዮጵያ ወጣቶችና ስፖርት አካዳሚ በአዲስ አበባ ካምፓስ በሀገሪቱ ስፖርት የሚስተዋለውን የተተኪ ችግርን ሳይንሳዊ በሆነ ሥልጠና ታግዞ ለመቅረፍ ወደ ትግበራ ከገባ አምስት ዓመታትን አስቆጥሯል። አካዳሚው በአምስት ዓመት ቆይታው ያስመዘገበውን ውጤት፣ የነበሩበትን ተግዳሮቶችንና ቀጣይ ለመጓዝ ያሰበውን አቅጣጫ በተመለከተ በጥቅምት 14 ቀን 2012 ዓ.ም በአካዳሚው መሰብሰቢያ አዳራሽ ለጋዜጠኞች ሰፊ ማብራሪያ ሰጥቷል። የአካዳሚው ዋና ዳይሬክተር አቶ አንበሳው እንየው እንደገለፁት፤ የአካዳሚው አላማ የታዳጊዎችና ወጣቶች ሥልጠና አደረጃጀት እና አሠራር ከልማዳዊ አሠራር በማላቀቅ ሳይንሳዊ ዘዴ ላይ እንዲመሰረት ማድረግ ነው። ስፖርቱን ወደ ተሻለ አድማስ ለማድረስ ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ ባለፉት አምስት ዓመታት በርካታ ታዳጊዎችን በ10 የስፖርት ዓይነቶች በመመልመል አሰልጥኖ ማስመርቁን ይገልጻሉ። አካዳሚው ምርጥ ስፖርተኞች የማፍራት ተልዕኮውን በመያዝ ከአምስት ዓመት በፊት መቋቋሙን አስታውሰውም፣ ከ2009 ዓ.ም እስከ 2011 ዓ.ም በሦስት ዙር ያሰለጠናቸው 181 ስፖርተኞች 140
የተለያዩ ክለቦችን እንደተቀላቀሉ አብራርተዋል። በዚህም አካዳሚው ተልዕኮው ከማሳካት አኳያ እየተሳካለት እንደሚገኝ ይናገራሉ።እንደ ዋና ዳይሬክተሩ ገለጻ ፤አካዳሚው ባለፉት አምስት ዓመታት በነበረው ጉዞ በጥንካሬ በርካታ ነጥቦችን አንስቷል። የመጀመሪያው ሰልጣኞች በአካዳሚው በሥልጠና ላይ እያሉ በክለቦች መመረጣቸው ነው። በተናጠልም በቡድን አገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ውጤቶች ማስመዝገባቸው ሌላኛው ጥንካሬ ነው። ሰልጣኞች በስፖርት ሥልጠና የተለያዩ ክህሎቶች እንዲሁም በአካዳሚክ እና ተጨማሪ የቋንቋ እና የመሠረታዊ ኮምፒዩተር ክህሎት እንዲይዙ መደረጉ እና በተለያዩ ምክንያት በውድድር ስፖርት መቀጠል ያልቻሉ በተጓዳኝ ሙያዎች (በአሰልጣኝነት አልያም በዳኝነት መቀጠራቸው) እንደ ጥንካሬ ተነስቷል።ሰልጣኞቹ ከተመረቁ በኋላ እያደረጉ የሚገኘውን እንቅስቃሴና ያመጡትን ውጤት ምን እንደሚመስል ዳሰሳ ማድረግ እንደተቻለ የተገለፀ ሲሆን እንደ ጥንካሬም ተወስዷል። የአካዳሚው ቆይታቸውን የጨረሱ ሰልጣኞች የሙያ ብቃት ምዘና ሲኦሲ እንዲወስዱ የሚደረግ መሆኑ ሰልጣኞቹ በአቅም፣ ችሎታና እውቀት ምልኡ በመሆን እንዲወጡ ማድረጉም ተቀምጧል። በሦስት ዙር ተመርቀው ከወጡ ስፖርተኞች የሙያ ብቃት ምዘናውን ከወሰዱት 99 በመቶ ያህሉ ያለፉ ናቸው። ይህም በአካዳሚው የሚሰጠው ሥልጠና ፍሬያማ መሆኑን ያስገነዘበ ጭምር መሆኑን በጥንካሬ ታይቷል። በተጨማሪም ሰልጣኞች የመደበኛ ትምህርት ፍላጎት እያደገ መምጣቱ በመልካም ጎኑ የተገለጸ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከአካዳሚው የሚወጡ ስፖርተኞቸ በስፖርተኞቹ ብቻም ሳይሆን በመደበኛውም ትምህርት የተሻሉ እንዲሆኑ የሚያግዝ ተሞክሮ መሆኑን ነው ያብራሩት። የአካዳሚው ትምህርትና ሥልጠና ውድድር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አብዮት ተስፋዬ፤ የአካዳሚው ፍሬዎች በ2011 ዓ.ም በነበሩ አህጉር አቀፍና ዓለም አቀፍ የውድድር መድረኮች በመሳተፍ የነበራቸውን ውጤታማነት ለአካዳሚው ስኬት እንደማሳያ አንስተዋል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያ ውጤታማ ያልነበረችበት ርቀት ሦስት ሺ ሜትር መሰናክል ቢሆንም አሁን ታሪክ ተቀይሯል። በራባት ሞሮኮ በተካሄደው የመላ አፍሪካ ጨዋታና የዳይመንድ ሊግ አጠቃላይ አሸናፊ የሆነው የኢትዮጵያ የርቀቱ ባለ ክብረ ወሰን ጌትነት ዋለ አካዳሚው ካፈራቸው ስኬታማ አትሌቶች ዋነኛው መሆኑን ነው ያመላከቱት። ቦነስ አይረስ ላይ በተካሄደው የዓለም የታዳጊዎች ኦሊምፒክ የወርቅ ባለቤት የሆነው አብርሃም ስሜ፣ በማራካሽ ሞሮኮ በተካሄደው 4ኛው ኢንተርናሽናል ፓራሊምፒክ አትሌቲክስ ውድድር በ1 ሺ500 ሜትር ወርቅ፣ በ800 ሜትር ነሐስ ሜዳሊያ ማስመዝገብ የቻለው ገመቹ አመኑ እንዲሁም በተመሳሳይ መድረክ በ200 ሜትር እና በ400 ሜትር ወርቅ ያስመዘገበችው ዝናሽ አሰፋ የአካዳሚው ስኬታማነት ማሳያ መሆናቸው ይገልጻሉ። በዓለም አቀፍና በአህጉር አቀፍ መድረኮች የአካዳሚው ፍሬ የሆኑ ስፖርተኞች እያስመዘገቡ የሚገኙት ውጤት አካዳሚው ከተቋቋመበት አላማና ራዕይ እኩል እየተጓዘ እንደሚገኝ ዳይሬክተሩ አስቀምጠዋል:: አካዳሚው የቆመለትን ዓላማ አጠናክሮ ለማስቀጠል ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ የሁለተኛ ዘመን ስትራቴጂክ እቅድ ዝግጅት ትግበራ በሕዝብ እና አጋሮች ተሳትፎ እንዲከናወን የሚያስችል ሥራ የሚሰራ መሆኑንም ነው ያብራሩት። አዲስ ዘመን ጥቅምት 16/2012 ዳንኤል ዘነበ | https://www.press.et/Ama/?p=21516 | 772 | 2ስፖርት
|
ዓብይ ኮሚቴው የእስካሁን ክንውኖቹን አስታውቋል | ስፖርት | October 27, 2019 | 30 | የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዘንድሮ ውድድር ዓመት በቅርቡ በተዋቀረው ዓብይ ኮሚቴ እንዲመራ መደረጉ ይታወቃል። ይህ ኮሚቴም እስካሁን ድረስ የተለያዩ ሥራዎችን ሲያከናውን የቆየ ሲሆን፤ ከትናንት በስቲያም ኮሚቴው በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ተገኝቶ በክንውኖቹ ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥቷል።የዚህ ዓመት ውድድር የሚጀመረው ኅዳር 13 እና 14/2012 ዓ.ም መሆኑ ይታወቃል። የሊጉ ዕጣ አወጣጥ ሥነሥርዓትም ኅዳር አምስት የሚደረግ መሆኑን የሶከር ኢትዮጵያ ዘገባ ጠቁሟል። በዕለቱ በውድድር ደንቡ ላይ ውይይት የሚደረግ ሲሆን፤ ደንቡ ቀደም ብሎ ለሁሉም የሊጉ ተሳታፊዎች እንዲደርስ በማድረግ አስተያየት ከተሰጠበት በኋላ ይጸድቃል። ዓብይ ኮሚቴው ለዚህ የሚሆነውን የውድድር ሥነ-ሥርዓት ኮሚቴ አባላትን የመረጠ መሆኑም አስታውቋል። ሰባቱ አባላትም፤ አቶ ሃብታሙ ኃይለሚካኤል፣ ዶክተር ወገኔ ዋልተንጉስ፣ አቶ ወንድአወቅ አበዜ፣ አቶ አብርሃም ተክለሃይማኖት፣ ኮማንደር ጌታቸው ኤጀርሶ፣ አቶ ዮናስ ገብረሚካኤል እና አቶ ሞገስ በሪሁን ናቸው። የኮሚቴ አባላቱ ምርጫም በመስፈርትነት የትምህርት ማስረጃ በትንሹ ዲግሪ ያለው ዕድሜው ከ60 ያልበለጠ፣ ባለፉት ሁለት ዓመታት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን በውድድር ታዛቢነት እና በኮሚሽነርነት ያልሰራ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል። ይህ የተደረገበት ምክንያትም ሁለቱ ዓመታት በተለይ በእግር ኳሱ ጥሩ የሚባል ጊዜ እንዳልነበረ ታሳቢ በማድረግ ነው። በዚህም ትክክለኛ ባልሆነ ፍርድ ተሳታፊ የነበሩ አካላት በኮሚቴው አልተካተቱም። የኮሚቴው አባላትም በቅርቡ ተሰባስበው የሥራ ክፍፍል የሚያደርጉ ሲሆን፤ ያለ ማንም ጣልቃ ገብነት ሥራቸውን እንደሚያከናውኑም ነው የተጠቆመው። ከዚህ ቀደም የነበረው የውድድር ሥርዓት ኮሚቴ አሠራርን ፌዴሬሽኑ ማሻሻያ ሊያደርግበት አስቦ ነበር። ይህንን ተከትሎም ዓብይ ኮሚቴው መመሪያዎችን በማዘጋጀት ለሥነሥርዓት ኮሚቴው የሚሰጥ ይሆናል። ኮሚቴው የተለያዩ ሜዳዎችን ተዘዋወሮ የተመለከተ ሲሆን፤ ለውድድሩ የማይመጥኑትን በመለየትም ማስተካከያ እንዲደረግባቸው ከዚህ ቀደም ማሳሰቡ ይታወቃል። በዚህም የድሬዳዋ፣ ሰበታ እና ወልቂጤ ሜዳዎች ለውድድር ብቁ ባለመሆናቸው ሌላ ሜዳ መፈለግ እንደሚገባ ተገልጾላቸዋል። የሆሳዕና፣ ወላይታ ሶዶ እና ጅማ ስታዲየሞች ደግሞ ማስተካከያ ማድረግ የሚገባቸው ናቸው። በዓብይ ኮሚቴው ምልከታ መሠረት አጥር የሌላቸውና የተመልካችን ደህንነት ለማረጋገጥ ከዓለም አቀፉ መስፈርት ቢያንስ ትንሹን ማሟላት እንደሚገባቸውም አመልክቷል።አዲስ ዘመን ጥቅምት 16/2012 ብርሃን ፈይሳ | https://www.press.et/Ama/?p=21519 | 262 | 2ስፖርት
|
ጁንታው በጠለምት ሕዝብ ላይ ያደረሰው በደል ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 15, 2020 | 14 | ሞገስ ተስፋአዲስ አበባ፡- ጁንታው እስካሁን ድረስ በሀገር አቀፍ ደረጃ ካደረሳቸው በደሎች በጠለምት ህዝብ ላይ ያደረሰው ጉዳት ከፍተኛ መሆኑን የጠለምት ወረዳ ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ መርሻ ወረታ ተናገሩ፡፡ አቶ መርሻ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለፁት፣ የትህነግ ጁንታ ቡድን በጠለምትና አካባቢው ማህበረሰብ የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተጠቃሚ እንዳይሆን ዘርፈ ብዙ ጭቆና አድርሶበት ቆይቷል፡፡ የጥፋት ቡድኑ ገና ከጥንስሱ ጀምሮ እስካሁን ድረስ በሀገር አቀፍ ደረጃ ካደረሳቸው በደሎች በጠለምት ህዝብ ላይ ያደረሰውና ያሳደረው ጭቆና ዘርፈ ብዙ ነው፡፡አቶ መርሻ፣ ጠለምት ወረዳ በተፈጥሮ ፀጋዎች የታደለ ቢሆንም ተፈጥሮ ከቸረው የበዛ ፀጋ ውስጥ ግን ህዝቡ ተጠቃሚ እንዳይሆን ተደርጓል፤ የጁንታው ቡድን ተጽዕኖም የበይ ተመልካች አድርጎታል፤ በህዝቡ ላይ ተጭኖት የነበረው የአምባገነን ቀንበር ልኩም በቃላት መግለጽ ከሚቻለው በላይ መሆኑን ገልፀዋል፡፡እንደ አቶ መርሻ ገለፃ፤ ጁንታው ወረዳውን ከመሰረተ ልማት ውጭ አድርጎት ቆይቷል፡፡ ለራሱ የጥፋት ዓላማ የሚመቹትን ስትራቴጂካዊ ቦታዎችን እየቀየሰ የአስፓልት መንገድና ኮንክሬት ምሽግ እየሠራ ሲደራጅና መደበቂያ ዋሻ ሲያዘጋጅ ነው የኖረው። ማህበረሰቡን ግን በተጎሳቆለ ሁኔታ በድህነት እንዲማቅቅ አድርጎት ቆይቷል፡፡ጁንታው በሀገር ላይ ካደረሰው ጥፋት በጠለምት ወረዳ ላይ ያደረሰው ጉዳት የተለየ መሆኑን የሚናገሩት አቶ መርሻ፤ ጁንታው የህዝቡን ሁለንተናዊ ማንነት ብቻ ሳይሆን ገና ሮጠው ያልጠገቡ ታዳጊ ወጣቶችን የበላ ቡድን መሆኑን ይናገራሉ፡፡ ይህ ደግሞ የጠለምትን ህዝብ ህይወት በመቅጠፍ ያልተገደበ፣ ይልቁንም የህብረተሰቡን ሥነ ልቦና እና የመኖር ዋስትናውን ነጥቆት የቆ በመሆኑ የጁንታውን ጥፋት ልዩ እንደሚያደርገው አብራርተዋል፡፡ እንደ አቶ መርሻ ገለፃ፤ የጥፋት ቡድኑ ለበርካታ ዓመታት በሀገር ያስከተለው ኪሳራ ሳያንሰው ጥቅምት 24 በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ ያደረሰው ጥቃት የራሱን ግብአተ መሬት አፋጥኖታል፡፡ በተለይም የጠለምት ወረዳ ከትግራይ ክልል ጋር በሚዋሰኑባቸው 12 በሚደርሱ ቀበሌዎች ዙሪያ ዳግም ሥልጣንን እቆናጠጥባቸዋለሁ ብሎ የተመካባቸው የሠራቸው ምሽጎች በሀገር መከላከያ ሠራዊትና በአማራ ልዩ ኃይል ድባቅ ተመቶ ከለቀቀ በኋላ ህብረተሰቡ ደስታውን የገለፀበት መንገድ ልክ ለሌለው የግፍ ሥራው አንዱ ማሳያ ነው፡፡ እንደሀገር አሁን ላይ የሕግ ማስከበር ሂደቱ የተጠናቀቀ ቢሆንም የተወሰኑ ኃይሎች የመሸጉበት በጠለምት ወረዳ አዋሳኝ አካባቢ ስለሚገኝ አስፈላጊውን እርምጃ በመስጠት የማጽዳት ሥራ ይሠራል፡፡ በጁንታው ኃይል ታፍነው የቆዩ 1ሺ845 በላይ የሚሆኑ የሀገር መከላከያ የሠራዊት አባላትን በሁለት ዙር ተቀብለው ተንከባክበው እንዳሳለፏቸው የሚናገሩት አቶ መርሻ፤ በዚህ ልክ የፌዴራል መንግሥትም በከፍተኛ ሁኔታ ሕግ የማስከበር እርምጃውን አጠናክሮ የሚቀጥልበትን ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ከፍተኛ ሥራ ተሠርቷል፡፡ አሁን ላይ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ሲታይ ማህበረሰቡ ከዚህ አረመኔ ጁንታ ሙሉ ለሙሉ ተላቆ ያለምንም ሥጋት እንደማንኛውም ማህበረሰብ የልማት ተቋዳሽ ሆኖ ለመኖር በጉጉት እየጠበቀ እንደሆነ ነው ምክትል ዋና አስተዳዳሪው የገለፁት፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 6/2013 | https://www.press.et/Ama/?p=37386 | 346 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
በዘንድሮው የመኸር እርሻ እስካሁን በ10 ሚሊዮን ሄክታር ላይ ያለው ሰብል መሰብሰቡ ተገለጸ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 15, 2020 | 24 | እፀገነት አክሊሉ አዲስ አበባ፦ ከክልሎች በተሰበሰበው መረጃ መሰረት የዘንድሮው የመኸር ወቅት በዘር ከተሸፈነው 13 ነጥብ 4 ሚሊዮን ሄክታር ውስጥ እስካሁን 10 ሚሊዮን የሚጠጋ መሬት ላይ ያለው ሰብል መሰብሰቡን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የእርሻ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ማንደፍሮ ንጉሴ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳስታወቁት የዘንድሮው የመኸር እርሻ በምርትና ምርታማነት በኩል እጅግ ጥሩና ተስፋ ሰጪ ነው፡፡እንደ ዶክተር ማንደፍሮ ገለፃ በዘር የተሸፈነው መሬት 13 ነጥብ 4 ሚሊዮን ሄክታር ሲሆን ከዚህ ውስጥ ደግሞ ሁሉም መረጃ ተጠናቅቆ ባይገባም 10 ሚሊዮን የሚጠጋ ሄክታር መሬት ላይ ያለው ሰብል ተሰብስቧል፡፡ ከዚህ ጋር ታያይዞም አሁን ያለው የሰብል ይዞታ የምርታማነት መጠን በጣም ጥሩ በሚባል ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ያሳያል፡፡ ለዚህ የመኸር ወቅት ውጤታማ መሆን የነበረው የዝናብ መጠን ለሰብል ምርታነማነት የሚመች መሆኑ ተጠቃሽ ነው ያሉት ዶክተር ማንደፍሮ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በኩልም ለግብርና ሥራው አጋዥ ሊሆኑ የሚችሉ ግብዓቶችን በማቅረብ ረገድ ሰፊ ሥራ መሠራቱን አብራርተዋል፡፡በመኸር የሥራ ወቅት በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍሎች የጎርፍ አደጋዎች መብዛትና የአምበጣ መከሰት በአገሪቱ በተለይም በግብርና ሥራው ላይ ከፍተኛ የሆነ መደናገጥን ፈጥሮ የነበረ ቢሆንም ተጽዕኗቸው ግን የተፈሩትን ያህል አልነበሩም ብለዋል ዶክተር ማንደፍሮ፡፡እንደ ዶክተር ማንደፍሮ ገለፃ ማሳቸው በጎርፍ የተወሰደባቸው። በአምበጣ የተወረረባቸው አርሶ አደሮች ነበሩ በግለሰብ ደረጃም ከፍተኛ የሆነ ጉዳት አድርሷል፡፡ ነገር ግን እንደ አገር በመኸሩ እርሻ ይገኛል ተብሎ ከታሰበው ውጤት አንፃር ሲገመገም ግን ያን ያህል ከባድ ተጽዕኖ አድርሷል ለማለት እንደማይቻል አብራርተዋል፡፡ ይህ የሆነው ደግሞ የወቅቱ የግብርና ሥራ በተቀናጀና ጥሩ በሆነ ሁኔታ ዝግጅት ተደርጎበት አስፈላጊው ግብዓት ተሟልቶለት ወደ ሥራ በመገባቱ ነው ያሉት ዶክተር ማንደፍሮ፤ ከዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ በክረምቱ ወቅት የጣለው ዝናብ እጅግ ለሰብል የሚመችና የተመጣጠነ በመሆኑ ብዙ ምርት ተመርቷል ብለዋል፡፡ በዚህም ምርትና ምርታማነት ከምን ጊዜውም በላይ የጨመረበት ወቅት በመሆኑ ይህንን በጎርፍ እንዲሁም በአምበጣ የተጎዳውን ሰብል ለማካካስ ከባድ እንደማይሆንም አብራርተዋል፡፡ የዘንድሮው የግብርና ሥራ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ለእርሻ ሥራው የዋለው መሬት ስፋት የተጠቀምነው የዘር። የማዳበሪያ መጠንና የነበረው የዝናብ ሥርጭት ከፍተኛ ነው፤ በዚህም ካለፈው ዓመት በተሻለ ሁኔታ ምርትና ምርታማነት የጨመረበት የተከሰቱት የተፈጥሮ አደጋዎች እንኳን ያልበገሩት እንደሆነም አብራርተዋል፡፡ ዶክተር ማንደፍሮ እንደገለፁት፤ የግብርና ሥራ ዓመቱን በሙሉ የሚሠራ ሥራ ነው ያሉት ዶክተር ማንደፍሮ ከዚህ የተነሳም ለቀጣይ የሥራ ጊዜ በተለይም ለመስኖ ምርት ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሠራ ነው፤ በመስኖ ለማረስ መሬት ዝግጅት ያስፈልጋል፤ ዘር ውሃ እንዲሁም ሌሎች ግብዓቶች ያስፈልጋሉ፤ ይህንን አቀናጅቶ አቀናብሮ ከማዕከል እስከ ቀበሌ ድረስ ማጓጓዝም ሌላው ሥራ ነው ፤ ይህንን ለማድረግ ደግሞ በተለይም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን በመከላከል እንዲሆን ከፍተኛ ጥንቃቄ ተደርጓል፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 6/2013 | https://www.press.et/Ama/?p=37393 | 362 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የጁንታው ቡድን ለወንጀሉ ተገቢውን ቅጣት እስኪያገኝ እርምጃው ሊቀጥል እንደሚገባ ተገለጸ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 15, 2020 | 13 | ሞገስ ፀጋዬ አዲስ አበባ፡- የህወሓት ጁንታ ቡድን በሠራዊቱ ላይ የፈፀመው ጥቃት እና ንፁሃንን የገደለበት መንገድ በጦር ወንጀል የሚያስጠይቀው እንደመሆኑ ለሠራው ወንጀል ተገቢውን ቅጣት እስከሚያገኝ ድረስ የሕግ ማስከበር ተግባሩ ሊቀጥል እንደሚገባው በሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ክፍል ኃላፊ ረዳት ፕሮፌሰር ዘላለም ተስፋዬ አስታወቁ፡፡ረዳት ፕሮፌሰር ዘላለም፣ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለፁት፤ የህወሓት ጁንታ ቡድን ከባድ ወንጀል በመፈፀሙ መደበኛ ፍርድ ቤት ጉዳዩን ላያየው ይችላል፡፡ ተግባሩም በጦር ወንጀል የሚያስጠይቀው ነው፡፡ በመሆኑም ይህ ወንጀለኛ ቡድን ለሕግ እስከሚቀርብ ድረስ የሕግ ማስከበር እርምጃው ሊቀጥል የሚገባው ነው፡፡ እንደ ረዳት ፕሮፌሰር ዘላለም ገለፃ፤ የጁንታውን እኩይ ሥራዎቹን በሦስት ከፋፍሎ ማየት ተገቢ ነው፡፡ ይሄውም አንደኛ፣ አገር ሲመራ በነበረበት ጊዜ፣ ሁለተኛ፣ ከለውጡ በኋላ እና ሦስተኛ ማይካድራ ላይ የፈፀሙት ወንጀል ነው።፡ በዚህ ረገድ ለምሳሌ፣ በማይካድራ የፈፀሙት ወንጀል የሚዳኘው በጦር ወንጀል ሲሆን፤ ቀደም ብሎ የፈፀማቸው በመደበኛ ወንጀል የሚያስከስሳቸው ነው፡፡ የወንጀል ሕግ ደግሞ በባህሪው ያጠፋውን ወገን ወደ ፍትህ በማቅረብ ዜጎች ሰላማዊና የተረጋጋ ህይወትን እንዲመሩ ማስቻል ነው፡፡ “አሸንፋለሁ ብለህ ጦርነት አውጀህ በዜጎች ላይ ጭፍጨፋ ማካሄድና የሰላማዊ ዜጎችን ህይወትን ማጥፋት በጦር ወንጀል ያስጠይቃል፤” ያሉት ረዳት ፕሮፌሰር ዘላለም፤ በተመሳሳይ በመከላከያ ሠራዊቱ ላይ ጥቃት መፈፀም እና ያገቱትንም የመከላከያ ሃይል በጅምላ ረሽኖ መቅበር ሌላው በጦር ወንጀልን የሚያስጠይቃቸው እኩይ ሥራቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡ረዳት ፕሮፌሰር ዘላለም እንደሚሉት፤ ከላይ የተጠቀሱት ድርጊቶቻቸው ብቻ በጦር ወንጀል ለመጠየቅ በቂ ነው፡፡ ምክንያቱም በንፁሃን ዜጎች የወሰዱት እርምጃ በየትኛውም መንገድ ሲገመገም አግባብነት የለውም፡፡ ብሔር ተኮር የሆነ ጥቃት አድርሶና በጅምላ ጨፍጭፎ አስከሬን በየጥሻውና በየገደሉ መጣልም ሌላው ተጨማሪ እኩይ ተግባራቸው ነው፡፡ እንደ አጠቃላይ ሲወሰድም ይህ ሁሉ ወንጀላቸው ተደምሮ የጁንታውን አባላት በጦር ወንጀል ለመከሰስ በቂ ማስረጃ ነው፡፡መንግሥት ሀገርን የመጠበቅ ሃላፊነትና ግዴታ ስላለበት የሕግ ማስከበር ዘመቻው አግባብ መሆኑን የሚናገሩት ረዳት ፕሮፌሰር ዘላለም፤ መንግሥት ሕግ ማስከበርና የዜጎችን ዋስትና የመጠበቅ ግዴታ ስላለበት የተጀመረው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባውም ገልፀዋል፡፡ የሕግ የበላይነት ልዕልና ተከበረ የሚባለውም መጨረሻ ላይ ፍትህ ሲሰፍን ብቻ እንደመሆኑም ለተፈፀሙ ጥፋቶች ተገቢው ቅጣት እስኪወሰን ድረስ በጥሩ መልኩ የቀጠለው የድል ጉዞ መቀጠል እንዳለበት መክረዋል፡፡እንደ ረዳት ፕሮፌሰር ዘላለም ገለፃ፣ ፍትህ ሰፈነ የሚባለው አጥፍተው በየቦታው ያሉ ግለሰቦች ተለቅመው ለሕግ ሲቀርቡና ውሳኔ ሲሰጥ ብቻ ነው፡፡ በመሆኑም ሕግን ከማስከበር ባለፈ ፍትህን ከማስፈን አንፃር በቀጣይ የሚሠሩ በርካታ ሥራዎች አሉ፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን ህዝቡን ማረጋጋት፣ የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ መደበኛ ኑሯቸው መመለስና ክልሉን የመልሶ ግንባታ ሥራን እንዲሁም የክልሉን የመንግሥት መዋቅር መዘርጋት ያስፈልጋል፡፡በዚህ ዘገድ የመንግሥት ሥራ ብዙ ነው፡፡ የሕግ ማስከበር ዘመቻውም በዚህ መልኩ መጠናቀቅ አለበት።፡ ሰላም የማምጣት ሂደት ተቋማትን የመገንባት ጉዳይ ስለሆነ ተቋማትን በአዲስ መልኩ ማደራጀት ከሁሉም በላይ በፍጥነት ሊሠራበት የሚገባ ጉዳይ መሆኑንም ነው ያስረዱት፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 6/2013 | https://www.press.et/Ama/?p=37397 | 374 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ሽሬ ያፈራችው ዳግማዊው ሓየሎም | ሀገር አቀፍ ዜና | December 16, 2020 | 97 | ጌትነት ተስፋማርያምየአገርንና ህዝብን ጡት ከነከሱና ካስለቀሱ ጁንታዎች በተቃራኒ የትግራይ ምድር ለአገርና ለህዝብ የታመኑና ህይወታቸውን ሳይሳሱ የሚሰጡ ጀግኖችን ማፍራት ታውቅበታለች። ለኢትዮጵያና ለክብሯ ሲሉ ውድ ህይወታቸውን የሰዉና የእነአሉላ አባነጋን ፈለግ የተከተሉ ብዙ ጀግኖችም ከትግራይ ማህጸን ፈልቀዋል፤ አሁንም በመፍለቅ ላይ ናቸው።ይህን ጉዳይ ስናነሳ በቅድሚያ ወደ አዕምሯችን ከሚመጡት አንዱና ቀዳሚው በጁንታው ሴራ ህይወቱን የተነጠቀው ሜጀር ጀኔራል ሓየሎም አርአያ ነው። ለዴሞክራሲና ለህዝቦች አኩልነት በተደረገ ትግል አኩሪ ገድል የፈጸመውና በብዙዎች ልብ ውስጥ በጀግነንት ታሪኩ የተጻፈው የሽሬው ሜጄር ጀኔራል ሓየሎም አርአያ፤ የሃሳብ ልዩነት ስላንጸባረቀ ብቻ ግፍና ሴራ ኑሯቸው ባደረጉት የጁንታው አባላት በግፍ ህይወቱን እንደተነጠቀ ብዙዎች የሚናገሩት ሀቅ ነው።ይህን በቅርበት ከሚያውቁት እና ጉዳዩን አስመልክቶ ሃሳባቸውን ለአዲስ ዘመን ከተናገሩት መካከል አቶ ሊላይ ኃይለማርያም አንዱ ናቸው። አቶ ሊላይ በአንድ ወቅት ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ ስለ ግድያው ሲያስረዱ፣ “ሓየሎምን ጁንታው እንደገደለው እርግጠኛ ነኝ። ሓየሎም በሰራዊቱ በጣም ተወዳጅ ከመሆኑም በላይ በአንዳንድ ጉዳዮች ከእነሱ ጋር አይስማማም ነበር። በትጥቅ ትግሉ ወቅት በረሃ ላይ እንዳይገድሉት ከአጠገቡ ሰው ስለማይጠፋ አልተመቻቸውም። በተገደለበት ወቅት ከእሱ በታች ያሉ ጄኔራሎች እንኳን በጥበቃ ነበር የሚሄዱት። እሱ ግን ጥበቃ አልነበረውም። እናም እነዚህን ሁሉ ስታይ እና ማን ገደለው ብለህ ስትጠይቅ እነሱ እንደሆኑ ትረዳለህ” ብለው ነበር።አገራችን ኢትዮጵያ ጀግኖችን
ለመውለድ ማህጸነ ለምለም
ናትና ዛሬም የሓየሎምን
የጽናት ታሪክ የደገመ
አንድ ጀግና ከሽሬ
አፍርታለች። ይህ ጀግና
ሃምሳ አለቃ ሓየሎም
ነጋ ይባላል። ሽሬ
ዞን አዲዳዕሮ በተባለ
የትግራይ አካባቢ የተወለደው
ሃምሳ አለቃ ሓየሎም፣
የመከላከያ ሰራዊት የ23ኛ
ክፍለጦር አባል ነው።
ጥቅምት 24 ቀን
2013 ዓ.ም ሓየሎምና
ጓደኞቹ በሱዳን ጠረፍ
ሁመራ አካባቢ የሀገር
ድንበር በመጠበቅ ላይ
እንደነበሩያስታውሳል። ሀገር አማን ብለው አረፍ ባሉበት ምሽት ግን ጁንታውና ተላላኪዎቹ ጥቃት በመፈጸም እርሱንና ሌሎች የሰራዊቱ አባላትን አፍነው ወሰዱ። ከሁመራ ሉግዲ ወደ ሽሬ እና አክሱም ከተሞች ታፍነው በሚወሰዱበት ወቅት ሓየሎምና ሌሎች የሰራዊቱ አባላት መከራቸውን ሲያዩ እንደነበር አይዘነጋውም። ምግብና መኝታ እንኳን ሳይመቻች በአድዋ እና በጉዊሃ አካባቢዎች በአንድ ክፍል ታጉረው ቆይተዋል። ከዚህ ባለፈ ከቦታ ወደቦታ በተሽከርካሪ ሲያንቀሳቅሷቸው ሰው በሰው ላይ አነባብረው ያጓጉዙ እንደነበር ሓየሎም በኀዘን ያስታውሰዋል። ለ21 ቀናት በተለያዩ አካባቢዎች ታፍነው ሲቆዩ በየቀኑ አንድ አንድ የማታጠግብ ዳቦ እና አልፎ አልፎ ገንፎ እየበሉ ህይወታቸውን ለማትረፍ መታገላቸውንም ነግሮናል። የጁንታው ቡድን አባላት የትግራይ ተወላጆችን አስገድደው በመውሰድ ለራሳቸውም እኩይ ዓላማ እንደሚያሰልፉ ሓየሎም አጫውቶናል።እርሱ ግን አገሩን መክዳት ስለማይፈልግና በኢትዮጵዊነት ላይ ጽኑ አቋም ስለነበረው ከጁንታው ታጣቂዎች ጋር ላለመሰለፍ የትውልድ ቦታውን ቀይሮ የደቡብ ተወላጅ ነኝ በማለት ለአፋኙ ቡድን ታጣቂዎች ተናገረ። ይህን ዘዴ የተጠቀመውም ከመከላከያ ሰራዊት ጓዶቹ ጋር አብሮ ለመቆየት መሆኑን ይናገራል። ሓየሎም የትግራይ ተወላጅ መሆኑን በማሳወቅ ብቻ ከታፈኑት መካከል መውጣት እንደሚችል ቢያውቅም፤ አብረውኝ ከበሉ እና ከጠጡ ጓደኞቼ የሰራዊት አባላት አልለይም ብሎና አብሯችው እንደሚሆኑ እሆናለው የሚል ውሳኔ ላይ መድረሱን ይናገራል። በሌላ ጎኑም ታላቅ ክቡር ነውና ሀገር መክዳትን ፈጽሞ አልመረጠም።በአፈናው ወቅት ጓዶቹን
አይዟችሁ ከሞትንም አብረን
ነው የምንሞተው እያለ
ያበረታታ እንደነበር አይዘነጋውም።
በወቅቱ የጁንታው ታጣቂዎች
አብረህ ከእኛ ጋር
ሂድ ቢሉኝ እንኳን
ዓላማ ስለነበረኝ ግደሉኝ
እንጂ አይሆንም እንደምላቸው
እርግጠኛ ነበርኩም ይላል። እንደሌሎች አይደለሁም ክደው የሄዱ ቢኖሩም እኔ ሰራዊቱን ክጄ አልሄድም፤ ሁለት መለዮ አልለብስም ብዬ ነው ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጋር የቆየሁት ማለቱን ሓየሎም ነገሮናል። ጓደኞቼንና አገሬን አልዋጋም የሚል የጸና አቋም እንዳለው የነገረን ሃምሳ አለቃ ሐየሎም፤ እኔ ሀገሬ ኢትዮጵያ ነችና ለሀገሬ ክብር ብዬ ነው የተነሳሁት፤ ለብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቆምኩ እንጂ፤ ለአንድ የጁንታ ቡድን ፍላጎት ብቻ አይደለም የሚል የጸና ሃሳብ በአዕምሮው መያዙንም ነግሮናል። በመጨረሻም የመከላከያ ሰራዊት ደርሶ የጁንታው ታጣቂዎች ላይ እርምጃ ሲወስድ አፋኞቹ ሓየሎምን እና ሌሎች የሰራዊት አባላትን ከተከዜ ወንዝ ድንበር አካባቢ ወስደው ለቀቋቸው። ሓየሎምም ከጓደኞቹ ጋር ወደአማራ ክልል በእግሩ ተሻገረ። በአማራ ክልል የነበረው አቀባበል ጥሩ ነበር፤ ምግብ፣ አልባሳት እና የሞራል ድጋፉም አስደሳች እንደነበር ሓየሎም በኩራት ይነገራል። በአስቸጋው ቆይታ ወቅት የሰራዊቱ አባላት ሓየሎም ንጹህና ከእኛ ጋር አብሮ ሲታገል የቆየ ታማኝ ወታደር ነው በማለት በሙሉ ልብ አብረውት እንደተሰለፉ ያስታውሳል። በጁንታው ቡድን አማካኝነት ታፍነው የቆዩ የሰራዊቱ አባላት ጎንደር ላይ ተመልሰው ከተደራጁ በኋላ፤ ዳግም ወደግዳጅ ሲሰማሩ ሓየሎምም በትልቅ የሀገራዊ ስሜት አብሮ ወደትግራይ ክልል ተመለሰ። ጓደኞቹ አድናቆታቸውን በመግለጽ ያንተ ታማኝነት እና ተወዳጅነት ከፍተኛ ነውና፤ የያዝከውን መስመር ቀጥልበት ብለው በምላሹ ማበረታቻ ሰጥተውታል። “እኔ ህዝብን
ወክዬ ቃለመሃላ የገባሁለት
ጉዳይ አለኝ፤ ብሔር
ብሔረሰቦችን በአጠቃላይም ኢትዮጵያን
መጠበቅ አለብኝ ብዬ
ነው ቃለመሃላ የገባሁት።
በማንም ይሁን በማን
ላይ በሀገሬ ኢትዮጵያ
ጉዳይ ህግን የማስከበር
ተግባር ሲያጋጥመኝ ወደኋላ
አልልም። አሁንም ቢሆን
ከጓደኞቼ ጋር ግዳጄን
ለመወጣት ዝግጁ ነኝ
ሀገራችንን የበለጠ ሰላም
እንደምናደርግም ተስፋ አለኝ”
በማለት ለሀገሩ ያለውን
ታማኝነት በገሃድ አሳይቷል። ከምንም ነገር ቅድሚያ ለአገር የሚለው የሽሬ ዞን ተወላጁ ሓየሎም ነጋ፤ ከአጥፊው ቡድን የሴራ ፖለቲካ ይልቅ ለህዝብ መወገኑ ብቻ ሳይሆን ለህይወቱ ሳይሳሳ ሀገሩን ያስቀደመ የሰራዊቱ አባል መሆኑንንም ጭምር በዳግማዊ ሓየሎምነቱ ሥራው ሲያስታውሰው ይኖራል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 7/2013 | https://www.press.et/Ama/?p=37451 | 669 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ የመዲናዋ ነዋሪዎች እያደረጉት ላለው ድጋፍ ምስጋና አቀረቡ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 15, 2020 | 12 | በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ፡-
የአዲስ አበባ ከተማ
ነዋሪዎች በመዲናዋ ለሚከናወኑ
ሁሉን አቀፍ ሥራዎች
ለሚያደርጉት ድጋፍ የከተማዋ
ምክትል ከንቲባ ምስጋና
አቀረቡ፡፡ ነዋሪዎቹ ድጋፋቸውን
አጠናክረው እንዲቀጥሉም ምክትል
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ጠይቀዋል። ጃን ሜዳን
ለሃይማኖታዊ በዓል በሚመጥን
መልኩ የማዘጋጀት ስራ
እየተከናወነ እንደሆነም ገልፀዋል። ኢዜኣ እንደዘገበው፤ ምክትል ከንቲባዋ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳሉት የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የከተማ አስተዳደሩን የተለያዩ ሥራዎች ሲያግዙ ቆይተዋል። በተለይም መከላከያ ሠራዊት ለህዝብ ሰላም፣ ደህንነት አብሮነት ለከፈለው መስዋዕትነት የደረሰበት ጥቃት የከተማዋን ነዋሪዎች ያስቆጣና በጋራ ያቆመ መሆኑን ገልጸዋል። ምክትል ከንቲባዋ፣ መከላከያ ሠራዊት “ራሱ እየሞተ እኛን ያኖረ ሠራዊት ነው” ያሉት ምክትል ከንቲባዋ የተፈጸመበት ጥቃት “እጅግ በጣም አሳፋሪና አስነዋሪ ተግባር ነው” ብለዋል። የከተማ አስተዳደሩ ያደረገውን ጥሪ ተከትሎ የመዲናዋ ነዋሪዎች ካደረጉት የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ በላይ ለመከላከያ ሠራዊት ያላቸውን አክብሮት አሳይተዋል ነው ያሉት። ለአብነትም በአንድ ሳምንት ውስጥ ለመከላከያ ሠራዊት ከ 1ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ማሰባሰብ መቻሉ የከተማ አስተዳደሩ በአድናቆት የሚመለከተው መሆኑን አንስተዋል። ከዚህ ጎን ለጎንም ኅብረተሰቡ አካባቢውን ነቅቶ በመጠበቅ አጋር እንደነበር ገልጸው በየቀኑ ከሚደርሱት ጥቆማዎችም 98 በመቶዎቹ ትክክለኛ ጥቆማዎች እንደነበሩ አስታውሰዋል። የአዲስ አበባ ነዋሪ ኮቪድ 19ን መከላከል፣ ለተማሪዎች ምገባ፣ ለታላቁ ህዳሴ ግድብና ለሌሎችም በጎ ተግባራት በጥቂት ወራት ውስጥ በድምሩ ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን ጠቁመዋል። “የአዲስ አበባ ነዋሪ በጣም ተባባሪና አስተዋይ ነው” ያሉት ምክትል ከንቲባዋ ድጋፉን ይበልጥ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል። ጃን ሜዳ የጥምቀት በዓል ብቻ የሚከበርበት ሳይሆን ሌሎችም በርካታ ማኅበራዊ ኩነቶች የሚካሄዱበት በመሆኑ በዚህ ደረጃ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቁመዋል። አሁንም የጥምቀት በዓል እየተቃረበ በመሆኑ ሥፍራውን ለሃይማኖታዊ በዓሉ በሚመጥን መልኩ ለማዘጋጀት የሚያስችሉ ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሆነ ገልጸዋል።በስፍራው በጊዜያዊነት ተዘዋውረው የቆዩ ነጋዴዎች በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሃይሌ ጋርመንት አካባቢ የሚሰሩበት የገበያ ማዕከል ተገንብቶ እየተጠናቀቀ መሆኑን ጠቁመዋል። ስፍራው ሁሉንም የገበያ ተዋናይ፤ የግብዓት አቅራቢንም ጭምር ማዕከል ያደረገና ደረጃውን የጠበቀ ዘመናዊ የገበያ ማዕከል መሆኑን አስረድተዋል። የአትክልት ተራ ነጋዴዎችም ማፍረስና ማጽዳት ይጀመራል ከተባለበት ቀናት በፊት ሥራዎችን ከወዲሁ እያጠናቀቁ መሆኑን አንስተው፤ ለነጋዴዎቹ ምስጋና አቅርበዋል።በሌላ በኩል ከ 1 ሺህ 400 በላይ ተሽከርካሪዎች ማቆሚያ፣ ሱቆችና ሌሎች አገልግሎቶችን መስጠት የሚችለው የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት በመጠናቀቅ ላይ ነው ብለዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 6/2013 | https://www.press.et/Ama/?p=37398 | 306 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ባለፉት አራት ወራት ከ624 ሚሊዮን ብር በላይ በህዳሴ ግድብ አካውንት ገቢ መደረጉ ተገለጸ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 16, 2020 | 8 | ሞገስ ጸጋዬአዲስ አበባ፡- በወቅታዊ አገራዊ ሁኔታዎች ያልተገ ታው የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ድጋፍ ከምን ጊዜውም በላይ ተጠናክሮ መቀጠሉ እና ባለፉት አራት ወራት ብቻ ከ624 ሚሊዮን ብር በላይ በልማት ባንክ የተረጋገጠ በህዳሴው ግድብ አካውንት ገቢ መደረጉ ተገለጸ።በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልድ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ቀላል የማይባል የህዝብ ለህዝብ የዲፕሎማሲ ሥራ እየሠሩ መሆኑንም ነው የታላቁ የህዳሴ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ያስታወቀው።የጽህፈት ቤቱ የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ኃይሉ አብርሃም በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ የህዝብ ተሳትፎ ከወቅታዊ የህግ ማስከበር ሂደት ጋር በተያያዘ የሚዲያው ትኩረት ቢቀንስም አሁንም ድጋፉ ሳይቋረጥ ተጠናክሮ ቀጥሏል። በዚህም ከመላ ሀገሪቱ ባለፉት አራት ወራት ብቻ በልማት ባንክ የተረጋገጠ ከ624 ሚሊዮን ብር በላይ በህዳሴ ግድብ አካውንት ገብቷልእንደ አቶ ኃይሉ ገለጻ፤ ላለፉት አራት ወራት የነበረው የህዝብ ተሳትፎ እጅጉን ከፍ ያለ ሆኖ ተስተውሏል። ለአብነትም የመጀመሪያው የውሃ ሙሌት ከተጠናቀቀ በኋላ በሀምሌ ወር 119 ነጥብ 9 ሚሊዮን፣ በነሐሴ ወር 152 ሚሊዮን፣ በመስከረም ወር 197 ሚሊዮን እና በጥቅምት ወር 155 ሚሊዮን ብር የተጣራ ገቢ መሰብሰብ ተችሏል።የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ገቢ በዋናነት ቦንድ በመሆኑ ህብረተሰቡ የቦንድ ግዥን አጠናክሮ እንዲቀጥል እየተሠራ ነው ያሉት አቶ ኃይሉ፤ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በተለያየ መልኩ እያገዙ መሆኑንም ተናግረዋል። በዚህም ዲያስፖራው በግድቡ የሚነሱ ጉዳዮች ላይ በኢትዮጵያ ላይ ተፅዕኖ ለማድረግ የሚሞክሩ ሥራዎችን በመቃወም ከፍ ያለ ኃላፊነት እየተወጡ መሆኑንም ገልጸዋል።‹‹ድምፃችን ለግድባችን›› በማለት በዓለም የሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያውያን ዲያስፖራዎች ከኢትዮጵያውያን ፕሮጀክት ጎን በመሆን ድጋፋቸውን አሳይተዋል። ለዚህም በተለያዩ ክፍላተ ዓለማት 72 ያህል የታላቁ የህዳሴ ግድብ ምክር ቤቶች ያሉ ሲሆን፤ ምክር ቤቶቹም በያሉበት የኢትዮጵያ ማህበረሰቦች በመሰባሰብ ዕርዳታ የሚያሰባስቡባቸው ናቸው። በዚህ ረገድ ዘንድሮ አስረኛ ዓመቱን አስመልክቶ በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ ኢትዮጵያ በውጭ ጉዳይ፣ በዲያስፖራ ኤጅንሲና በምክር ቤቶች አማካኝነት በየሀገራቱ እንደሚከበር እና የቦንድ ግዥም እንደሚካሄድ ነው አቶ ኃይሉ የገለጹት።እንደ አቶ ኃይሉ
ገለጻ፤ በውጭ ሀገር
ያሉ ኢትዮጵያውን ቦንድ
ለመግዛት ቢፈልጉም የብር
ማስኮብለል ተደርጎ ስለሚቆጠር
ምቹ አልነበረም። ነገር
ግን የተለያዩ ዘዴዎችን
በመጠቀም ድጋፋቸውን አጠናክረው
እየሄዱ ነው። በዚህ
ዓመት ለመምህር ግርማ ወንድሙ ወደ 450 ሺህ ብር በስጦታ መልክ በመላክ የቦንድ ግዥ ፈጽመዋል። ከገንዘብ ድጋፍ በላይ ለሀገራቸው ጠበቃ በመሆን ለማስረዳትም በተለያዩ ጆርናሎች ላይ በመሳተፍ ስለ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ጠቀሜታ በማሳወቅ ላይ ናቸው። በማህበራዊ ሚዲያ ላይም ቀላል የማይባል ሥራ እየሠሩ ይገኛሉ።ሁሉም ኢትዮጵያውያን ወቅታዊ ጉዳይ ሳያዘናጋቸው ዓይናቸውን ከግድቡ ማንሳት እንደሌለባቸው የሚናገሩት አቶ ኃይሉ፤ በዘንድሮው ዓመት የሙከራ የኃይል ማመንጨት እንደሚጀምር፣ ለዚህም አጠቃላይ የቴክኒካል ሥራዎች እያለቁ ስለሆነ በቀጣይ ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት እና አሁን ባለው ሁኔታ የግድቡ አፈጻጸም ወደ 77 በመቶ መድረሱን በመጠቆም፤ እስከ ግድቡ ፍጻሜ ሁሉም በሚችለው ሁሉ ድጋፎችን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 7/2013 | https://www.press.et/Ama/?p=37447 | 389 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
“የጁንታውን አባላት በሕግ ተጠያቂ ማድረግ እና ሕዝብንም ከጁንታው መርዘኛ አስተሳሰብ ለማላቀቅ መሥራት ያስፈልጋል”አቶ ውብሸት ሙላት የሕግ ባለሙያ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 16, 2020 | 11 | ወርቁ ማሩ አዲስ አበባ፡- መንግሥት የወንጀለኛውን ጁንታ አባላት ነጥሎ በማውጣት ተጠያቂ ማድረግ፤ ህዝቡንም ከጁንታው የተሳሳተና መርዘኛ አስተሳሰብ እንዲላቀቅ መሥራት እንዳለበት የሕግ ምሁር አሳሰቡ። እንዲህ አይነት ሥራዎች ህዝብንም ከእንደዚህ አይነት አስተሳሰብ ለመነጠልና ፓርቲው የሚፈጽማቸውን መጥፎ ነገሮች በሙሉ ለማሳወቅ እንደሚረዳም ጠቁመዋል። የሕግ ባለሙያው አቶ ውብሸት ሙላት ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደገለጹት፤ ወንጀለኛው ጁንታ በኢትዮጵያ ከፖለቲካ እና ኢኮኖሚያዊ ምዝበራና ዘረፋ ባሻገር አስተሳሰብን ለማዛነፍ የሄደባቸው መንገዶች በሀገሪቱ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድረዋል። እንዲህ አይነት አስተሳሰቦች ደግሞ ቶሎ ካልታረሙ ትውልዱን በማበላሸት ዘመን ተሻጋሪ ጉዳት እንደሚሚ ያስከትሉ የተናገሩት አቶ ውብሸት፤ ይህ በመሆኑም ከዚህ በፊት እንዲህ አይነት ችግሮች ሲከሰቱ መንግሥታት የፈቱባቸው ተሞክሮዎች እንደነበሩ አስታውሰዋል። ለአብነትም በጀርመን የናዚ አስተሳሰብ ያላቸውን ሰዎች ለማንፃት “ዲ-ናዚፊኬሽን” የሚባል ሕግ በማውጣት ትውልዱን የማንፃት ሥራ መሰራቱንና በኢራቅም ከሳዳም ሁሴን ህልፈት በኋላ ሀገሪቱን ከባዝ ፓርቲ አስተሳሰብ የማንፃት ሥራ መሰራቱን ጠቁመዋል። አቶ ውብሸት እንደገለጹት፤ ወንጀለኛው ጁንታ ለ27 ዓመታት መንግሥትን ብቻ ሳይሆን ሁሉንም ተቋማት ተቆጣጥሮ እና በትግል ወቅት የነበረውን ልምድ ጨምሮ ሀገሪቱን ለማተራመስ ወይም የብጥብጥ ማዕከል ለማድረግ በሰፊው የሰራበት ወቅት ነበር። በዚህ የተነሳ በህዝብ እና በሀገር ላይ በርካታ ጉዳቶች ደርሰዋል። ያንንም መንግሥት ሙሉ ለሙሉ ለመቆጣጠር ተቸግሮ ነበር። ይህ ቡድን ከአራት ኪሎ ከወጣ በኋላ ያደርሳቸው የነበሩ በርካታ ጥፋቶች ነበሩ ያሉት አቶ ውብሸት፤ እነዚያ ጥፋቶች ደግሞ ከጊዜ ወደጊዜ እየጠነከሩ እና እየጨመሩ በመሄዳቸው በመጨረሻ ለውድቀቱ መፋጠን መንስኤ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። ከነዚህም ውስጥ በመከላከያ ላይ የሰነዘረው ጥቃት እንደተጠበቀ ሆኖ ምርጫ ማካሄዱ የውድቀቱ ማፋጠኛ እንደነበር አንስተዋል። አቶ ውብሸት እንዳሉት፤ ሕገ መንግሥቱ ሲፀነስ ጀምሮ ዋና አጋፋሪው የነበረው ይህ ቡድን ነው። ከዚያ ጊዜ ጀምሮም ሕገ መንግሥቱ እስከሚፀድቅበት ጊዜ ድረስ ሁሉንም ነገር በቁጥጥሩ ሥር አድርጎ ነው ሲሰራ የነበረው። ሕገ መንግሥቱ ከፀደቀ በኋላም በትልቁ ያላከበረውና የጣሰው ራሱ ይኸው ጁንታ ነው። መጨረሻ ላይ በዚህ ሕገ መንግሥት አልገዛም ያለውም ይኸው ቡድን ነው። አቶ ውብሸት ስለጁንታው የጥላቻ ጉዞ ሲያስረዱ፣ “ይህ ቡድን ኢትዮጵያን ጠልቶ ትግል ጀመረ፤ ኢትዮጵያን ጠልቶ ሲታገል ኖረ። ሥልጣን ይዞም ኢትዮጵያን እንደጠላ ኖረ። ከአራት ኪሎን ከለቀቀም በኋላ ያንኑ ጥላቻውን የበለጠ አጠናክሮ ቀጠለ። የመጨረሻ የጥላቻ ቦምቡንም መከላከያ ሠራዊት ላይ ወረወረ፤” በማለት ነው። ጁንታው በመጨረሻው ይሄን ሲያደርግ የርስ በርስ ጦርነት እንዲከፈት ጭምር ለማድረግ አስቦ የተሰራው ደባ እንደነበርም ተናግረዋል። ትንሽ የሚይዝ የሞራል፣ የሕግና የሥነ ምግባር መሰረት ከሌለ የሰው ልጅ አውሬ ነው የሚሆነው የሚሉት አቶ ውብሸት፤ ለዚህም በማይካድራ ላይ የፈፀመው ዘግናኝ ተግባር ማሳያ ነው ብለዋል። እነዚህ ሰዎች ደግሞ ከትግል ወቅት ጀምረው ሕግ አለማክበራቸው፣ መሰረታዊ የሆኑ እና ሰው የሚተዳደርባቸው፣ መርሆዎችን አለማክበራቸው እንደዚህ አይነት ወንጀሎችና የጭካኔ ተግባሮችን የስግብግብነት ባህርይዎችን እየተላበሱና እያሳደጉ መሄዳቸው ዋነኛ ባህርያቸውና መገለጫቸው እንዲሆን እንዳደረጋቸውም ጠቅሰዋል። ወልቃይት አካባቢ ከ1972 ዓ.ም ጀምሮ የተገደለው የህዝብ ቁጥር ብቻውን አንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ብዙ ጊዜ በጅምላ ጭፍጨፋ የሚያስከስስ ነው የሚሉት አቶ ውብሸት፤ የጠፋው እና የተሰወረው ህዝብ ቁጥር በንግግር ብቻ ስንገልፀው ስሜት አይሰጥም እንጂ እጅግ በጣም የጭካኔ ሥራ ነው ብለዋል። ከዚህ ጋር ተያይዞ
አንዳንድ የውጭ ሃይሎች
ይህንን ሕግ የማስከበር
ሥራ በተዛባ መንገድ
ለዓለም ማበረሰብ ለማሳየት
ይሞክራሉ የሚሉት አቶ
ውብሸት፣ ይህ ደግሞ
ብዙዎቹ ከዚህ ቀደምም
የተካኑበት የሴራ ተግባራቸው
አካል እንደነበር አንስተዋል። አቶ ውብሸት እንደሚሉት፤ ከግጭት እንጀራቸውን የሚጋግሩ ሃይሎች አሉ። ብዙዎቹ ተቋማት ኮሮጆአቸውን ይዘው የሚዞሩት ግጭት በመፍጠር እንጀራቸውን ለመጋገር ነው። ለምሳሌ፣ ሽምግልና ብሎ ለማስታረቅ፣ መልሶ ለማቋቋም፣ አንዳንዶቹም በሞቱት ሰዎች ስም በርካታ ገንዘብ ለመሰብሰብ ግጭትን ይጠቀማሉ። በዚህ ረገድም የውጭው ጩኸት የሚታወቅ ነው። የጁንታው አባላት የስግብግብነት
ምንጭ ደግሞ አንዳንዶቹ
የከፋ የድህነት የስልቦና
ጫና የነበረባቸው በመሆናቸው
ናቸው። በልጅነታቸው በአብዛኛው
በረሃ በማሳለፋቸው እና
የልጅነት ጊዜያቸውን በዚህ
ልክ ማሳለፍ ባለመቻላቸው
አሁን ላይ ህጋዊ
ባልሆነ መንገድ ገንዘብ
ሲገኝ ያዩትን ሁሉየመመኘት አባዜ ውስጥ ገቡ። ያዩት ነገር ሁሉ አጓጓቸው። በዚህም ያዩትን ሁሉ የማድረግ እና ያዩትን ሁሉ የመውሰድ አባዜ ተጠናወታቸው። እነዚህ ሰዎች ለህልውናቸው ሲሉ ህፃናትን ለጦርነት ይማግዳሉ። ለዚህ ደግሞ አደንዛዥ እጽ ሊጠቀሙ ይችላሉ። ከአንድም ሁለት ጊዜ የተያዘው በርከት ያለ የአደንዛዥ እጽ ይህንን እንድንጠራጠር የሚያደርግ ነው። ይህ ደግሞ እነዚህ ሰዎች ይሄን ነገር በአንድ በኩል እንደ ንግድ ውስጥ ተሰማርተውበት፤ በሌላ በኩል ደግሞ ይህን ለተልዕኮአቸው ማስፈፀሚያነት እየተጠቀሙበት ሊሆን ይችላል። ብዙ የአሸባሪ ድርጅቶች
ህፃናትን በሽብር ተግባራት
ሲያሰማሩ በዋናነት የሚጠቀሙት
በአደንዛዥ እጽ ነው
ያሉት አቶ ውብሸት፣
የጁንታው አባላትም ይህን
ተጠቅመው እነዚ ህን
ህፃናት ወደጦርነት ውስጥ
አስገብተው ሊሆኑ እንደሚችሉ
ጠቁመዋል። አቶ ውብሸት እንደገለፁት፤ ይህ ቡድን ከነአልቃይዳ፣ ከነአይኤስ ኤስ እና ከአልሸባብ የበለጠ እንጂ የሚያንስ አይደለም። ስለዚህ ይህ ቡድን ሲሰራ የነበራቸው ነገሮች በሙሉ የሽብር ተግባራት ናቸው። የራሱን አስተሳሰብ በሃይል በሌሎች ላይ ለመጫን እና ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ በሰዎች ላይ፣ በመሰረተ ልማቶች ላይ፣ በመንግሥት ተቋማት ላይ ትልቅ ጉዳት ሲያደርስ ነበር።ይህንን የሚጠቀመው ደግሞ ፕሮፓጋዳዎችን በመንዛት ነው። ለዚህ ደግሞ የተለያዩ ሚዲያዎች ያስፈልጋሉ። ስለዚህ ይህንን ድርጅት አሸባሪ ለማለት ምንም ያልተሟላ መስፈርት የለም። በመሆኑም ቡድኑን በአሸባሪነት እንዲፈረጅ በማድረግ ህብረተሰቡንም ከዚህ አስተሳሰብ ማንፃት እንደሚገባ ተናግረዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 7/2013 | https://www.press.et/Ama/?p=37446 | 685 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ወንጀለኞች ቴክኖሎጂን በመጠቀም ፖሊስን እየተገዳደሩ መሆኑ ተገለጸ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 16, 2020 | 23 | ክፍለዮሐንስ አንበርብርአዲስ አበባ፡- ወንጀለኞች የተወሳሰበ እና ዘመናዊ ቴክሎጂዎችን በመጠቀም ፖሊስን እየተገዳደሩ መሆኑን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። ፖሊስ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ቀድሞ መታጠቅና ወንጀልን ቀድሞ መከላከል ላይ ማተኮር አለበት በሚል ታቅዶ እየተሠራ መሆኑም ተገልጿልየፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል እና የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ፕሬዚዳንት አቶ መስፍን አበበ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለፁት፤ በዓለምም ሆነ በኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ወቅት ቴክኖሎጂን ተገን አድርገው በርካታ ወንጀሎች እየተፈፀሙ መሆናቸውን ጠቁመዋል። ይህም የፖሊስን ሥራ ፈታኝ እና በእጅጉ ጥንቃቄ በታከለበት ሁኔታ እንደሚሠራ እያስገደደ መሆኑን አብራርተዋል። በኢትዮጵያ ውስጥ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመታጠቅ ብዙ ጥረቶች እየተደረጉ ቢሆንም አሁንም ያለው በጣም ኋላቋር ነው ያሉት ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መስፍን፤ ‹‹ወንጀለኞች ቴክኖሎጂ በመታጠቅ በንፅፅር ይቀድማሉ። በሳይበር እና በሶሻል ሚዲያ የሚፈፀም ወንጀልም እየረቀቀ ነው። ለአብነት በቴሌ ላይ እየተሰሩ ያሉ ወንጀሎችን በሚሊዮኖች እና በቢሊዮኖች ኪሳራ አደረሱ ሲባል ይሰማል። ይህን ከወንጀለኞች ሰምተን እንጂ ቀድመን አውቀን የማስቀረት አቅም የለንም›› ብለዋል። በመሆኑም እንደ ፖሊስ ቴክኖሎጂን ቀድሞ መታጠቅና ወንጀልን ቀድሞ መከላከል አለብን በሚል ታቅዶ እየተሠራ ነው ያሉት ኮሚሽነር ጄኔራል መስፍን፤ ወንጀል ቢፈፀም እንኳን በፍጥነት ማወቅ አለብን ብለዋል። በቀጣይም በቴክኖሎጂ የትምህርት ክፍል የቴክኖሎጂ ፖሊሲንግ የመከፈት ውጥን ያለ ሲሆን በዚህም ምርምር ማድረግ፣ ባለሙያ የማፍራት እና ቴክኖሎጂን የመታጠቅ አስፈላጊነት ታምኖበት እየተሠራ ነው ብለዋል። እንደ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መስፍን ገለፃ፤ ‹‹መጪው ጊዜ የቴክኖሎጂ ዘመን ነው። እንደባለፈው ዘመን በጥንት የፖሊስ አሠራር መቀጠል አያዋጣም። አሁን የምንከተለው ዕድገት አገርን ወደ ኢንዱስትሪ የማሸጋገር ወቅት በመሆኑ ዘመናዊ ቴክሎጂን የመታጠቅ ሁኔታ ግድ እየሆነ ነው። በመሆኑም የፖሊስ አሠራር ይህን መከተል አለበት። አገር አዘምኖ ፖሊስን ኋላቀር አድርጎ መጓዝ አይቻልም›› ብለዋል። ዘመናዊ ከተሞች በተሠሩ ቁጥር ዘመናዊ የፖሊስ ሥራ መታከል አለበት ያሉት ኮሚሽነሩ፤ እጅግ የረቀቁ የዘመኑን የፖሊስ ቴክኖሎጂ በሁሉም ቦታ ማግኘት ተገቢ መሆኑ ታምኖበታል። ይህን የመታጠቅ፣ የመጠቀም ብሎም በቴክኖሎጂ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ቀድሞ አውቆ ማስቀረትን ታሳቢ በማድረግ መሥራት ለነገ የማይባል ጉዳይ መሆኑን አስገንዝበዋል።ከተቋሙ የተገኘው መረጃ እንደሚያስረዳው፤ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በአገሪቱ ዘመናዊ ፖሊስ ማደራጀት ከተጀመረ አራት ዓመት በኋላ ከ1939 ዓ.ም የተቋቋመ አንጋፋ ተቋም ሲሆን በእውቀት እና በክህሎት የበቃ ሠራዊትና ተልዕኮውን በአግባቡ የሚወጣ የፖሊስ አመራር ማሟላት ዋንኛ ዓላማው ነው። ይህ ተቋም ለ34 ዓመታት በ42 ዙር ለአገር ትልቅ ውለታ ያበረከቱና በማበርከት ላይ ያሉ የአገር ባለውለታና አይረሴ የፖሊስ ዕጩ መኮንኖችን ማሰልጠኑም ይታወቃል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 7/2013 | https://www.press.et/Ama/?p=37448 | 327 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
አፍሪካውያን በዶፒንግ ስጋት ከዓለም ቀዳሚ ናቸው | ስፖርት | October 28, 2019 | 20 | ጎረቤታሞቹ የምስራቅ አፍሪካ የረጅም ርቀት ፈርጦች ኬንያና ኢትዮጵያ በአትሌቲክሱ ያላቸውን መልካም ስም ያህል በስፖርቱ ትልቅ አደጋ እያንዣበበባቸው ይገኛል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአትሌቲክሱ አበረታች መድሃኒት ወይም ንጥረ ነገሮች ተጠቃሚነት ጋር በተያያዘ ሩሲያንን የመሳሰሉ ታላላቅ አገራት ከታላላቅ ውድድሮች እስከመታገድ ደርሰዋል። እነዚህ አገራት አትሌቶቻቸው በብዛት አበረታች መድሃኒት ተጠቃሚ ሆነው ከመገኘታቸው ጋር ተያይዞ በመንግስት ጭምር ይደገፋሉ በሚል ከውድድሮች መታገዳቸው ይታወቃል። የዓለም አቀፉ ፀረ አበረታች መድሃኒቶች ኤጀንሲ እነ ሩሲያን በቀጣበት ወቅት ኢትዮጵያና ኬንያ አደጋው በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያሰጋቸው በማሳወቅ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ምክረሃሳብ ሰጥቷቸው ነበር። ሁለቱ አገራት በተለይም ኢትዮጵያ ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥታ በመስራት አበረታች ውጤት ማስመዝገቧም በኤጀንሲው ጭምር ተመስክሮላታል። ያም ሆኖ ስጋቱ ሙሉ ለሙሉ ተቀርፏል ለማለት አይቻልም። ባለፈው ዓመት የዓለም አትሌቲክስ ኢትዮጵያና ኬንያን በአበረታች መድሃኒት(ዶፒንግ) ምክንያት ስጋት ካለባቸው አገራት ቀዳሚውን ደረጃ እንደሚይዙ ማሳወቁ ይታወሳል። ዘንድሮም ሁለቱ አገራት በአበረታች መድሃኒት ስጋት ቁንጮውን ደረጃ መያዛቸው እንደማይቀር እየወጡ ያሉ መረጃዎች ጠቋሚ ናቸው። ለዚህም ባለፉት ጥቂት ወራት ብቻ አምስት የአፍሪካ አገራት አትሌቶች አበረታች መድሃኒት ተጠቃሚ ሆነው መገኘታቸው ማሳያ ተደርጓል። ቤላሩስና ዩክሬን ሁለቱን የአፍሪካ አገራት ተከትሎ ስማቸው ከቁንጮዎቹ ተርታ ተፅፏል። የአስራ ስምንት ዓመቷ ኬንያዊት አትሌት አንጌላ ሙንጉቲ ከቀናት በፊት አበረታች መድሃኒት ተጠቅማ በመገኘቷ እገዳ ተጥሎባታል። በመላ አፍሪካ ጨዋታዎች የስምንት መቶ ሜትር የብር ሜዳሊያ አሸናፊ የሆነችው ይህች አትሌት በዚህ ወንጀል የተያዘች አርባ አራተኛዋ ኬንያዊት አትሌት ሆናለች። አትሌቷ ባለፈው ዓመት አርጀንቲና ቦነስ አይረስ በተካሄደው የወጣቶች ኦሊምፒክም በስምንት መቶ ሜትር አገሯን ወክላ መወዳደር ችላለች። የዓለም አቀፉ ፀረ አበረታች መድሃኒት አዋጅ የትኛውም አትሌት በውስጡ ለተገኘ አበረቻች ንጥረ ነገር ሃላፊነቱን ይወሳዳል። ይህችም አትሌት ኖራንድሮስቴሮን የተባለ አበረታች ንጥረነገር ተጠቅማ መገኘቷ ተረጋግጣል። ሙንጉቲ በስምንት መቶ ሜትር 2፡06፡21 የሆነ የራሷ ፈጣን ሰዓት ያላት ሲሆን ባለፈው ዓመት በኬንያ ከሃያ ዓመት ቻምፒዮና ሦስተኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቅ ችላለች። ፊሊፕ ሳንጋ ኪሙታይ የተባለው የሰላሳ ስድስት ዓመት ኬንያዊ አትሌት ቴስቴስትሮን የተባለ አበረታች ንጥረነገር ተጠቅሞ የተገኘ አርባ ሦስተኛው ኬንያዊ አትሌት ነው። የዚህ አትሌት ምርመራ በሂደት ላይ ሲሆን ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ ከስፖርቱ ለአራት ዓመታት ሊታገድ እንደሚችል ታውቋል። ኪሙታይ በማራቶን 2፡06፡07 ሰዓት ያለው ሲሆን እኤአ 2011 ላይ በፍራንክፈርት ማራቶን ያስመዘገበው ይህ ሰዓት በውድድር ዓመቱ አስራ ሦስተኛው ፈጣን አትሌት አድርጎት ነበር። ይህ አትሌት ባለፈው ዓመት በጎልድ ኮስት ማራቶን አምስተኛ ደረጃን ይዞ ሲያጠናቅቅ 2፡11፡44 ሰዓት ማስመዝገብ ችሏል። በሆንግኮንግ ማራቶንም አስረኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ 2፡15፡31 ሰዓት ተመዝግቦለታል። በዚህ ወር በአበረታች መድሃኒት ተጠቃሚነት ቅጣት የተላለፈበት ወይንም የተገኘበት አርባ ሁለተኛው ኬንያዊ አትሌት ቪንሰንት ኪፕሴጊች ነው። ይህ የሰላሳ ዓመት አትሌት ቀደም ሲል የተጠቀሰው ኬንያዊ አትሌት ኪሙታይ በጎልድ ኮስት ማራቶን አምስተኛ ሲያጠናቅቅ አራተኛ ሆኖ ማጠናቀቅ ችሏል። 2፡09፡59 የሆነ የራሱ ፈጣን ሰዓትም አለው። ሚያዝያ ወር ላይም በቬና ማራቶን ሰባተኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ 2፡10፡02 አስመዝግቧል። በተመሳሳይ ከዓመት በፊት በሆኖሉሉ ማራቶን ሦስተኛ ሆኖ ጨርሷል። ኢትዮጵውያን አትሌቶች በተለይም በግል ውድድሮች ብቻ የሚታወቁት አልፎ አልፎ በአበረታች መድሃኒት ሲቀጡ ይታያል። ይሁን እንጂ አገርን ወክለው በሚወዳደሩ አትሌቶች ይህ ቅሌት አይታይም ማለት ይቻላል። ባለፈው ክረምት በሞሮኮ ራባት በተካሄደው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ኢትዮጵያን ወክሎ በአስር ሺ ሜትር ወርቅ ማጥለቅ የቻለው ብርሃኑ ፀጉ ኢፒኦ የተባለ ንጥረ ነገር ተገኝቶበት ላልተወሰነ ጊዜ ከስፖርቱ ታግዷል። ይህ የሃያ ዓመት አትሌት ባለፈው ወር በኮፐንሃገን ግማሽ ማራቶን ላይ ሁለተኛ ሆኖ ማጠናቀቁ ይታወሳል። ብርሃኑ ሔንግሎ በተካሄደው የዓለም ቻምፒዮና የኢትዮጵያውያን ማጣሪያ ውድድር ላይ 10ሺ ሜትሩን 27፡00፡73 በሆነ ሰዓት ማጠናቀቅ ችሏል። ብርሃኑ በመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ሲያሸንፍ ኤርትራዊው አሮን ክፍሌና ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ጀማል ይመር ተከትለውት መግባታቸው ይታወሳል። ብርሃኑ የወርቅ ሜዳሊያውን ተነጥቆ ለኤርትራዊው አትሌት፣ የብር ሜዳሊያው ደግሞ ለጀማል ይመር የሚሰጥ ሲሆን አራተኛ ሆኖ ያጠናቀቀው ኬንያዊው ኤድዊን ሦይ የነሐስ ሜዳሊያ ሊያገኝ እንደሚችል መረጃዎች እየወጡ ነው። በአዲስ አበባ አበረታች መድሃኒቶች በስቴድየም አካባቢ ካለ ሃኪም ማዘዣ ጭምር እንደሚሸጡ የእንግሊዝ ሚዲያዎች መዘገባቸውን ተከትሎ የዓለም አትሌቲክስ ኢትዮጵያን ማስጠንቀቁ ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያ ፀረ አበረታች መድሃኒቶች ፅሕፈት ቤትና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለአትሌቶች የተለያዩ ትምህርቶችን እየሰጡ ይገኛሉ። በቅርብ ወራት አበረታች መድሃኒት ተጠቃሚ ሆኖ በመገኘት ስማቸው ከተዘረዘሩ አፍሪካውያን መካከል ሞሮኳዊው ሙስጠፋ ኤል አዚዝ አንዱ ነው። ይህ አትሌት ለአራት ዓመታት ከስፖርቱ እንዲርቅ ቅጣት የተጣለበት ሲሆን 2014 የአፍሪካ ቻምፒዮና ላይ በአስር ሺ ሜትር የብር ሜዳሊያ በማጥለቁ ይታወቃል። ይህ የሰላሳ ሦስት ዓመት አትሌት ባለፈው ሰኔ ክሮሽያ ውስጥ በተካሄደ የጎዳና ላይ ውድድር አበረታች ንጥረነገር ተጠቅሞ በመገኘቱ እገዳው እንደተላለፈበት ተነግሯል። ሞሮኮ በአበረታች መድሃኒት አደጋ ውስጥ ከሚገኙ አገራት መካከል ትጠቀሳለች። ይሁን እንጂ በዚህ አደጋ እጅግ ችግር ውስጥ ካሉ አገራት ተርታ በ2017 የወጣች ቢሆንም አሁን ተመልሳ ገብታበታለች።አዲስ ዘመን ጥቅምት 17/2012 ቦጋለ አበበ | https://www.press.et/Ama/?p=21537 | 639 | 2ስፖርት
|
የወታደሩ ህይወት – ከመጋረጃው ጀርባ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 16, 2020 | 43 | ጌትነት ተስፋማርያምየሰራዊቱ አኗኗር ከግንባር መልስ በተለይም በእረፍት ሰዓት ላይ አዝናኝ ገጽታ አለው። አንዳንዶች ቢጫ ጀሪካኖችን በመጉረድ የቡና ማቅረቢያ ረከቦት ሲያዘጋጁ ሌሎች ደግሞ የውሃ ማሸጊያ ፕላስቲኮችን በመቁረጥ ቡና እና ሻይ መጠጫዎችን ያዘጋጃሉ።በየአካባቢው የተገኘው ቡና ተቆልቶ በተከፈተ ጣሳ ላይ ሊወቀጥም ይችላል። ምክንያቱም ጁንታው ቡድን የሰራዊቱን ንብረት ዘርፎ ሲሄድ ያልሰባበረው እና ያላወደመው አይነት እቃ የለም ማለት በሚያስደፍር ሁናቴ በየማዘዣ ጣቢያዎቹ ከኤሌክትሪክ እቃ አንስቶ እስከ ቢሮ መሳሪያዎች ድረስ የነበሩ ንብረቶች ተበላሽተዋል፤ አሊያም ጠፍተዋል።በሚያሳዝን ሁናቴ የሰራዊት አባላት በገንዘባቸው የገዟቸው አነስተኛ ቡና እና ሻይ ማፍያዎች እንኳን በአካባቢው እንደሌሉ ከጁንታው ጥቃት በኋላ አካባቢውን የተቆጣጠሩ የሰራዊት አባላት ሲናገሩ ይደመጣል።የሰባተኛ ወጋገን ሜካናይዝድ ክፍለጦር አባል የሆነችው ወታደር እታገኝ ሞላ፣ ሰራዊቱ በእረፍት ሰዓቱ የሚያሳልፍባቸው የካምፕ ውስጥ ካፌዎችና ሬስቶራንቶች በመውደማቸው ጓደኞቿ ድብርት (ድበታ) እንዳይገባቸው የበኩሏን ጥረት እንደምታደርግ ነገረችን።ለቀረጻ ሙያው ልዩ ፍቅር ያላት እና በካሜራ ቀረጻ ሙያ ለአንድ ዓመት በሰራዊቱ ያገለገለችው እንስት፤ በህግ ማስከበር ዘመቻ ደግሞ በተለያዩ ግንባሮች ተሰልፋ ተተኳሾችን እና መሳሪያዎችን በማቀበል በኦርዲናንስ ሙያ አገልግላለች።ከህግ ማስከበሩ ዘመቻ መልስ በሚኖራት የእረፍት ጊዜ ደግሞ፣ ሰራዊቱ አረፍ በሚልባቸው አካባቢዎች ሻይ እና ቡና በማፍላት ጊዜያቸውን እንዲያሳልፉ ታደርጋለች። በአካባቢዋ የምታገኛቸውን ምግብ ማዘጋጃ ቁሶች በማሰባሰብ አምባሻ በመጋገርም ተወዳጅ ባለሙያ መሆኗን አስመስክራለች።በተለይ ኮቾሮ ብስኩት በሚበላባቸው አብዛኛው የግንባር ቦታዎች ላይ፣ ስቃጥላ የተሰኘውን የታሸገ የሰራዊቱ ምግብ በልዩ ሁኔታ በማብሰል በፍቃደኝነት ለሰራዊት አባላት ታቀርባለች። “ይህን ማድረጌ ሰራዊቱ በእረፍት ጊዜው ድብርት ውስጥ እንዳይገባ እና ዘመቻውን ዓላማ እንዳይዘነጋ በማሰቤ ነው” የምትለው ወታደር እታገኝ፤ በማንኛውም ሙያ ላይ በመተጋገዝ ለመስራት መምረጧን ነግራናለች።ከግዳጅ መልስ በሚኖረው ቆይታ የእታገኝ ቡና እየተፈላ ስለውሏቸው እና ስለጓዶቻቸው ጀግንነት እየተወራ ሳቅ እና ጨዋታው ይደራል። ከተለያዩ ቦታዎች የመጡትና የተለያየ ቋንቋ የሚናገሩት የሰራዊት አባላትም አንድነታቸውን በሚያሳይ ሁኔታ የተጋገረውን አምባሻም ሆነ የተፈላውን ቡና አንተ ትብስ አንቺ ትብስ ተባብለው በጋራ በመቋደስ ቀናቸውን በደስታ ያሳልፋሉ።ሃምሳ አለቃ ሄኖክ ከተማ፣ እንደ ወታደር እታገኝ ሁሉ ሰራዊቱ አረፍ በሚልባቸው ቦታዎች አምባሻ መጋገሩን እና ቡና ማፍላቱ የሚያዘወትር የአውራምባ ማህበረሰብ የስራ ባህልን የተላበሰ ወታደር መሆኑን በርካቶች ይመሰክራሉ። እሱም ቢሆን፣ በልጅነቱ ቤት ውስጥ እንጀራም ሆነ ሌሎች ስራዎችን በመከወን ወላጆቹን ያግዝ እንደነበር ነው የነገረን። ያ የልጅነት ልምዱ ደግሞ ሰራዊቱ ውስጥም እንዳገዘውና በእረፍት ጊዜው የተለያዩ ደረቅ ምግቦችን እያዘጋጀ ለጓደኞቹ ለማቅረብ እንዳላስቸገረው ገልጾልናል።ሽሬ ከተማ ላይ የማረጋጋት ስራ ከማከናወን እና ከእጀባ ስራው በተጨማሪነት ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ቡና እና ሻይ በማፍላት መረጃ እየተለዋወጠ አረፍ ለማለት ይሞክራል። ዱቄት በተገኘ ወቅትም እርሱ ለማቡካት ሲነሳ ጓደኞቹ የልብስ እጀታቸውን ሰብስበው በጉልበታቸው ተንበርክከው ያግዙታል። እርሱ ደግሞ እንጨት እንድዶ በምጣድ አምባሻውን ይጋግራል። ከህዝብ የተገኘው የሰንጋ አቅርቦትም ካለ በጋራ ታርዶ ለሰራዊቱ ይከፋፈላል። በዚህ ሂደት ታዲያ ሁሉም የሚችለውን ለማድረግ ግን ወደኋላ አይልም።እንደ ሃምሳ አለቃ ሄኖክ ከሆነ፤ በምግብ ዝግጅቱ ላይም ሆነ በማንኛውም ስራ ላይ ያለው የሰራዊቱ ህብረት ይበል የሚያሰኝ ነው። አንድም ቀን ጊዜውን በሰላም እና በፍቅር እያሳለፈ በየቦታው ሆኖ ሰራዊቱ ያበሰለውን ምግብ በጋራ ይመገባል፤ በጋራ እየተጫወተ የእረፍት ጊዜውን ያሳልፋል እንጂ፤ ጸብና ክርክርን አያውቁም። እናም ይህ ህብረት ብዙዎችን የሚስብ በመሆኑ ሊጠናከር የሚገባው እሴት ነው።አዲስ ዘመን ታህሳስ 7/2013 | https://www.press.et/Ama/?p=37458 | 427 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
በመጪዎቹ 10 ዓመታት የነፍስ ወከፍ ገቢን ከ2 ሺህ ዶላር በላይ ለማድረስ ታቅዷል | ሀገር አቀፍ ዜና | December 16, 2020 | 10 | በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- በመጪዎቹ አስር ዓመታት የነፍስ ወከፍ ገቢን ከሁለት ሺህ ዶላር በላይ ለማድረስ መታቀዱን የፕላን ኮሚሽን አስታወቀ። ኮሚሽኑ መሪ እቅዱን በተመለከተ በኢትዮጵያ ከሚገኙ የመገናኛ ብዙኃን ጋር ምክክር አድርጓል።የፕላንና ልማት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዶክተር ነመራ ገበየሁ የ10 ዓመቱ እቅድ የጋራ እቅድ እንደመሆኑ መጠን የሚዲያ ባለሙያዎች መሳተፋቸው አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።በልማት እቅዱ ላይ ከ12 በላይ የመነሻ ጥናቶች፣ የሀገር ውስጥና የውጭ ተቋማት፣ የሙያ ማኅበራት፣ ገለልተኛ ባለሙያዎች እና የመንግሥት ተቋማት ተሳትፎ እንደነበራቸው የተጠቆመ ሲሆን፣ የሌሎች ሀገራት ልምድ ተወስዶ ኮሚሽኑ ምን እና እንዴት እንደሚሠራ የመነሻ ሃሳብ ቀርቦ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መቅረቡንም ዶክተር ነመራ አስታውሰዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድም እያንዳንዱ አስፈጻሚ ተቋም የራሱን እቅድ እንዲያዘጋጅ እንደጠቆሙ ገልጸዋል።በልማት እቅዱ መሠረት ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ከ2013 እስከ 2022 ባለው ጊዜ በአማካይ 10 በመቶ እንደሚያድግ አመልክተዋል።በዚሁ የልማት እቅድ በ10 ዓመት የነፍስ ወከፍ ገቢ በአማካይ በ8 በመቶ እንደሚያድግ፣ በ2022 የኢትዮጵያ የነፍስ ወከፍ ገቢ 2 ሺህ 201 የአሜሪካ ዶላር እንደሚደርስ የታቀደ ሲሆን እንዲሁም የድህነት ምጣኔውንም ከግማሽ በላይ ለመቀነስ እቅድ አለ ብለዋል ምክትል ኮሚሽነሩ።በተጨማሪም ሀገራዊ የከተማ ሥራ አጥነት ምጣኔ በ2012 ከነበረበት 18 ነጥብ 7 በመቶ በ2022 ወደ 9 በመቶ ለመቀነስ እቅድ ተይዟልም ነው ያሉት።በልማት እቅዱ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት፣ የመጠጥ ውሃ፣ የጤና አገልግሎት እና ትምህርትም ዋና ዋና አቅጣጫዎች መሆናቸው ተጠቁሟል።በጤና እቅዱ መሠረት አማካይ የመኖር እድሜ ጣሪያን በ2012 ከደረሰበት 65 ነጥብ 5 በመቶ ዓመት በ2022 ወደ 68 በመቶ ከፍ የማድረግ ግብ መጣሉም ተመላክቷል ሲል ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዘግቧል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 7/2013 | https://www.press.et/Ama/?p=37460 | 217 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በድል የደመቁበት ሳምንት | ስፖርት | October 29, 2019 | 18 | በሳምንቱ የዕረፍት ቀናት በተካሄዱ በርካታ ዓለም አቀፍ የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድሮች ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች እንደተለመደው የድል ባለቤቶች ሆነዋል። በዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር የወርቅ ደረጃ በተሰጠው የፍራንክፈርት ማራቶን ፍቅሬ ተፈራ አሸናፊ ሆኗል። አትሌቱ የበላይነቱን የያዘው 2:07:08 በሆነ ሰዓት ሲሆን፤ በሁለት ሰከንዶች የዘገየው ዳዊት ወልዴ ደግሞ ሁለተኛ ሆኗል። ለባህሬን የሚሮጠው ትውልደ ኢትዮጵያዊው አወቀ ይመር በሦስተኛነት ማጠናቀቅ ችሏል። በሴቶች በኩልም የቦታው ክብረወሰን በኬንያዊቷ አትሌት ተሻሽሏል፤ ቫለሪ አያቢ ያጠናቀቀችበት ይህ 2:19:10 የሆነ ሰዓት በዓለም የምንጊዜም 12ኛው ፈጣን ሰዓት ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ ኢትዮጵያዊያኑ መገርቱ ከበደ እና መስከረም አሰፋ ደግሞ በጠባብ ደቂቃዎች ልዩነት ሁለተኛና ሶስተኛ በመሆን ውድድራቸውን አጠናቀዋል። ቫሌንሲያ ግማሽ ማራቶን የወርቅ ደረጃ ባለው በዚህ ውድድርም ኢትዮጵያዊያኑ አትሌቶች በሁለቱም ጾታ አሸናፊዎች ሆነዋል። በዓለም የቤት ውስጥ ቻምፒዮና በ3ሺ ሜትር የክብረወሰን ባለቤቱ የሆነው ዮሚፍ ቀጄልቻ 59:05 በሆነ ሰዓት የመጨረሻዋን መስመር አቋርጧል። ዮሚፍ በቅርቡ በተጠናቀቀው የዶሃው የዓለም ቻምፒዮና በ10ሺ ሜትር የብር ሜዳሊያ አሸናፊ እንደነበረ ይታወሳል፡፡ በሁለት ሰከንድ የዘገየው ኬንያዊው በናርድ ኔጌኖ ሁለተኛ ሲሆን፤ ጀማል ይመር ሶስተኛ በመሆን አጠናቋል፡፡ በሴቶች በኩል አሸናፊዋ አትሌት ሰምበሬ ተፈሪ 1:05:32 የሆነ ሰዓት ስታስመዘግብ ሰዓቷ የኢትዮጵያ ክብረወሰን ሆኗል፡፡ በዶሃው የዓለም ቻምፒዮና የ10ሺና 1500 ሜትር ቻምፒዮን የሆነችው ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ
የኔዘርላንድስ አትሌት ሲፋን ሃሰን በ21 ሰኮንዶች ዘግይታ በመግባት
ሁለተኛ ሁናለች።ኬንያዊቷ ጆዋን ቼሊሞ ደግሞ እነርሱን በመከተል በሶስተኝነት ያጠናቀቀች አትሌት ናት። ስሎቫንያ ማራቶን በዚህ ማራቶን ከልክሌ ገዛኸኝ ኬንያዊያኑን አትሌቶች በማስከተል አሸናፊ ሆኗል። አትሌቱ የገባበት ሰዓት 2:07:29 ሲሆን፤ አንቶኒ ኪፕላጋት ማርቲም እና ቪንሰንት ሮኖ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል። በሴቶች መካከል በተከናወነው ውድድርም ኬንያዊቷ ቦርነስ ቺፕኪሩይ ኪቱር 2:21:26 በሆነ ሰዓት የቦታውን ክብረወሰን አሻሽላለች። በዚህ ውድድር አምስት ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ከአራተኛ እስከ አስረኛ ባሉት ደረጃዎች ውድድራቸውን ጨርሰዋል። ሃዋይ ማራቶን በዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር የነሃስ ደረጃ በተሰጠው በዚህ ውድድር ሌንጮ አንበሳ፣ ሄነሪ ኪፕሮፕ እና አንድሬው ኪሚታይ እንደ ቅደም ተከተላቸው ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል፡፡ በሴቶች በኩልም ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ዋቄ መቃ ሁለት ኬንያዊያን አትሌቶች ተከትላ በመግባት በሶስተኛነት ውድድሩን ፈፅማለች፡፡ ቻንግሻ ኢንተርናሽናል ማራቶን
የነሃስ ደረጃ ባለውና በብርዳማ የአየር ሁኔታ በተካሄደው በዚህ ውድድር አብዲ ከበደ፤ በቦታው የተያዘውን ክብረወሰን በ50 ሰከንድ በማሻሻል 2:10:23 በሆነ ሰዓት ገብቷል። ኬንያዊው ዴቪድ ኪፕሮኖ እና ኢትዮጵያዊው ወርቅነህ ተስፋም ከቀደመው ክብረወሰን በፈጠነ ሰዓት ውድድራቸውን አጠናቀዋል። ማርሴል 20 ኪሎ ሜትር በፈረንሳይ ማርሴል ሃያ ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ውድድር ኢትዮጵያዊው ኦሊካ አዱኛ አሸናፊ ሆኗል፡ ፡ ከአስር ዓመታት ወዲህም በውድድሩ በተከታታይ ሁለት ዓመታት ማሸነፍ የቻለ አትሌት ሆኗል፡፡ ኦሊካ ውድድሩን በ1:01:10, 41 ሲፈፅም ኬንያዊው ኪፕሮኖ ሜንጆ 1:01:50 በሆነ ሰዓት ሁለተኛ፣ ኮሪር ኪፕየጎን በ1:02:13 ሦስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል፡፡ ሰንበሬ ተፈሪ የኢትዮጵያን የግማሽ ማራቶን ክብረወሰን በ1:05:32
ሰዓት አስመዝግባለች፣አዲስ ዘመን ጥቅምት 18/2012 ብርሃን
ፈይሳ | https://www.press.et/Ama/?p=21580 | 387 | 2ስፖርት
|
‘‘ለአፍሪካ ዋንጫ ጠንካራ ቡድን መፍጠር እንችላለን’’ – ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ | ስፖርት | October 30, 2019 | 17 | ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝነት መስራት ከጀመሩ ከ 1 ዓመት በላይ ሆኗቸዋል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ሲሾማቸው የአራት ዓመት ኮንትራት በመስጠት ነበር። አሰልጣኙ ብሄራዊ ቡድኑን ለ2020 የቻን አፍሪካ ዋንጫ ለማሳለፍ፤ እኤአ ለ2019 የግብጽ የአፍሪካ ዋንጫ ብሄራዊ ቡድኑን ለማሳለፍ ቃል በመግባት ነበር ኃላፊነታቸውን የተረከቡት። አሰልጣኙ ከአንድ ዓመት በላይ ባስቆጠረው ጉዟቸው በርካታ ጨዋታዎችን አድርገዋል። ፌዴሬሽኑ የብሄራዊ ቡድኑን ውጤት ግምገማ እስካሁን ይፋ ባያደርግም የአሰልጣኙ ጉዞ አመርቂ እንዳልሆነ ይነሳል። አሰልጣኙ ከፌዴሬሽኑ ጋር ውል ሲያስሩ ከገቡት ቃል መካከል አንዱ የሆነው ‹‹ኢትዮጵያን በቻን ተሳታፊ ማድረግ›› የሚለው ነው። ይህ የቻን ዋንጫ ተስፋ ከሳምንት በፊት በሩዋንዳ ብሄራዊ ቡድን ተደናቅፏል። በካሜሩን አስተናጋጅነት ለሚዘጋጀው 2020 ቻን ውድድር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሩዋንዳ ብሄራዊ ቡድን በአጠቃላይ ውጤት 2 ለ1 ተሸንፎ ከተሳትፎ ወጥቷል። አሰልጣኙ ብሄራዊ ቡድኑን ለአፍሪካ ዋንጫ የማብቃት ቃልም አልተፈፀመም። አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ ስለ ብሄራዊ ቡድኑ አቋም ፣የቻን ማጣሪያ ጨዋታን፣ የብሄራዊ ቡድኑን ቀጣይ አቅጣጫና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ከትናንት በስቲያ ለመገናኛ ብዙሃን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። የዋልያዎቹና አሰልጣኙ ጉዞ አሰልጣኝ አብረሃም ከዋልያዎቹ ጋር በአሰልጣኝነት በቆዩባቸው ጊዜያት ቡድኑ ከውጤት አንጻር ሲመዘን ደስተኛ እንዳልሆኑ ተናግረዋል። ነገር ግን ውጤቶች በተናጥል የቡድን መሻሻል አይጠቁሙም ብለዋል ።‹‹በግሌ ደስተኛ የምሆንባቸው ጉዳዮች አሉ። በተለይ ብሄራዊ ቡድኑ በወጣቶች እየተገነባ መሆኑና ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻል ማሳየቱ ስሜት ይሰጠኛል። በዚሁ የምንቀጥል ከሆነ በመጪው የአፍሪካ ዋንጫ ጥሩና ጠንካራ ብሄራዊ ቡድን መፍጠር እንችላለን›› የሚል ተስፋ በቡድኑ ማደሩ እንደሚያስደስታቸው አስረድተዋል። የቡድኑ ጥንካሬን ሲመዘን ጠንካራና የተረጋጋ ሊግ በሌለበት ጠንካራ ብሄራዊ ቡድን መገንባት ከባድ መሆኑን የጠቆሙት አሰልጣኙ ይህን ችግር ለመቅረፍ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተወጣጡ የሥነ ልቦና ባለሙያዎች ለተጫዋቾች ክፍተቶችን ለመድፈን ስልጠና እንዲያገኙ መደረጉን ተናግረዋል። በዚህም የተነሳ ከሀገር ውጪ ባደረጉት ጨዋታዎች የተሻለ የስነልቦና ዝግጅቶች ማሳየታቸውን ገልጸዋል። በሌላ በኩል ከጉዳት ጋር በተያያዘ ያጣቸው ተጫዋቾች እንዳሉ አንስተዋል። ነገር ግን አንድ ቡድን ተቀየረ የሚባለው ከግማሽ በላይ ተጫዋቾች ሲለወጡ ነው ይላሉ። አሁን ላይ ያለው ቡድን 90 በመቶ ያህሉ ነባር ተጫዋቾች ናቸው። ስለዚህ አሁንም በሂደት የተወሰኑ ልምድ ያላቸው ተጫዋቾችን በመጨመር ጠንካራ ቡድን ለመገንባት እንደሚጥሩ አብራርተዋል። የቡድኑ ጨዋታ እንቅስቃሴ ብሄራዊ ቡድኑ በአፍሪካ ዋንጫ፣ በቻን ውድድር ማጣሪያ፣ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ፣ በወዳጅነት ጨዋታ የነበሩትን እንቅስቃሴዎች ትንተና እንዳልተሰራ ተናግረዋል። አሰልጣኙ ሙሉ ለሙሉ ኃላፊነት ወስደው መስራት ከጀመሩበት የቻን የመጀመሪያ ማጣሪያ ጨዋታ ጀምሮ ያደረጉትን የጅቡቲውን የደርሶ መልስ ጨዋታ ለመገምገም እንደሞከሩ አብራርተዋል። የሩዋንዳውንም ጨዋታ በቅርቡ ከቴክኒክ ኮሚቴ ጋር በመሆን በጋራ እንደሚገመግሙ ጠቁመዋል። ከዘንድሮ ጀምሮ የአሰልጣኞች ቡድን አባላትና ሌሎች እምነት ከሚጣልባቸው ባለሙያዎች ጋር በመሆን የጨዋታ ምስል ትንተና መስራት መጀመራቸውን አንስተዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፐርፎርማንስ ትራከር በመጠቀም የእያንዳንዱ የብሄራዊ ቡድን ተጫዋቾች የአካል ብቃት መረጃ ከክለቦች ጋር መረጃ በመለዋወጥ ለመስራት እንቅስቃሴ መጀመሩም ተገልጿል። በብሄራዊ ቡድንና በፕሪሚየር ሊግ ክለቦች መካከል ያለው ስልጠና መናበብ ካልቻለ ብሄራዊ ቡድኑም ሆነ ሊጉ መረጋጋት እንደማይችል አሰልጣኙ ተናግረዋል። ከሌሴቶ ጋር በነበረው ጨዋታ በሜዳው የተገኘውን ተመልካች ለማስደሰት ከመነጨ ጉጉት ከተፈለገው አጨዋወት ውጪ የመወጣት ሁኔታ እንደነበር የገለፁት አሰልጣኙ፣ በባህር ዳር የነበረውን ጨዋታ እንደማሳያ በማንሳት በ41 አጋጣሚዎች ረጃጅም ኳሶች ወደ ተቃራኒ የሜዳ ክልል በመውሰድ 39 ኳሶች ስኬታማ እንዳልነበሩ አስታውሰዋል። ይህንንም እንዲህ ገልፀውታል ‹‹በሜዳችን ስንጫወት ተጫዋቾች በደጋፊዎቻቸው ስሜት ውስጥ ገብተው ከጨዋታ እቅድ የመወጣት ነገር ይስተዋላል። በተቃራኒው ከሀገር ውጭ በምንወጣበት ወቅት ከተመልካቾች ከጫና ውጭ ሆነን በመጫወት በእቅዳችን መሠረተ ለመጫወት መሞከራችን የተሻለ ብልጫ መውሰድ አስችሎናል››። በቻን ውድድር ማጣሪያ መርሃ ግብሩ በድንገት የወጣ እንደነበር ያስታወሱት አሰልጣኙ ዝግጅታቸው አጭር እንደነበር አብራርተዋል። በመጀመሪያው የጅቡቲ ጨዋታ ከሜዳ ውጪ ቢሆንም የተሻለ ስነልቦና በመያዝ አሸንፈው ወጥተዋል። በመልሱ ጨዋታ ግን በውጤት ቢያሸንፉም በቡድኑ እንቅስቃሴ ደስተኛ እንዳልነበሩ ተናግረዋል። ከዚያ ጨዋታ በመነሳት የነበሩ ችግሮችን ለማረም በተለይም በአካል ብቃት የነበሩብን ክፍተቶች አርመው ለሩዋንዳ ጨዋታ መዘጋጀታቸውን ያስረዳሉ። ከሩዋንዳ ጋር በመቐለ በተደረገው ጨዋታ ከመጀመሪያው የማጣሪያ ጨዋታ በብዙ መልኩ የተሻለ ቡድን እንደነበረና ሙሉ ለሙሉ ጨዋታውን ተቆጣጥሮ መጫወት እንደተቻለ ይናገራሉ። ያም ሆኖ የተጫዋቾች ልምድ ማነስ፤ በመጠነኛ የተከላካዮች ትኩረት ማነስ ማጣሪያውን እንዳያልፉ ማድረጉን አስቀምጠዋል። በቻን ማጣሪያ ወቅት በያዙት የቡድን ስብስብ ላይ የተወሰኑ ልምድ ያላቸው ተጫዋቾች አካተው ለቀጣይ ጨዋታዎች ልምምድ እንደሚጀምሩም ጠቁመዋል። ‹‹በዕቅዳችን መሠረት ዓርብ ለመጀመር ነበር። ነገር ግን በአዲስ አበባ ሲቲ ካፕና በአሸናፊዎች አሸናፊዎች ዋንጫ የተነሳ ቀኑ ወደ መጪው ሰኞ ሊዘዋወር ችሏል። ዝግጅታችን ሰኞ በመቐለ ከተማ የምንጀመር ይሆናል›› ያሉት አሰልጣኝ አብረሃም ቡድኑ ከፊት ለፊቱ ያሉበት ሁለት የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ጥንቃቄ እንደሚፈልጉ አብራርተዋል።አዲስ ዘመን ጥቅምት 19/2012 ዳንኤል ዘነበ | https://www.press.et/Ama/?p=21680 | 620 | 2ስፖርት
|
ሉሲዎቹ | ስፖርት | October 30, 2019 | 14 | በታዛኒያ አዘጋጅነት ለሚካሄደው የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ የሴቶች ዋንጫ(ሴካፋ) እንዲሁም ለ2020 የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ በርካታ ውድድሮች የሚያደርጉት ሉሲዎቹ አሰልጣኝ ተቀጥሮላቸዋል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛውን በዋና አሰልጣኝነት የቀጠረ ሲሆን በበጀት እጥረት ሴካፋ ላይ ላይወዳደሩ ይችላሉ የተባሉት ሉሲዎቹ በቅርቡ ዝግጅታቸውን እንደሚጀምሩ ተረጋግጧል ። አሰልጣኝ ብርሃኑ እኤአ በ2012 ኢኳቶሪያል ጊኒ ባዘጋጀችው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ሉሲዎቹን ማብቃት የቻለ ሲሆን በፕሪሜር ሊጉ ለሶስት ተከታታይ ዓመት ኮከብ አሰልጣኝ ሆኖ መሸለሙ ይታወሳል። የኢትዮጵያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ በመሆን ውጤታማ ጉዞ ላይ የነበረችው አሰልጣኝ ሠላም ዘርዓይ ካፍ ባቀረበላት ጥያቄ መሰረት የሴቶች የኤሊት ኢንስትራክተር ኮርስ ለመውሰድ ወደ ግብጽ ሰሞኑን ከመጓዟ ጋር ተያይዞ ነው ፌዴሬሽኑ የአሰልጣኝ ለውጥ ያደረገው። አሰልጣኝ ሰላም ከጥቅምት 23 እስከ 27 በሚቆየው የሴት አሰልጣኞች የኤሊት ኢንስትራክተርነት በማግኘት የመጀመሪያዋ ሴት አሰልጣኝ ትሆናለች ተብሎም ይጠበቃል። የተለያዩ ክለብ ደጋፊዎች በአዲስ አበባ መከሩ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ክለብ የደጋፊዎች ማህበር ለመመስረት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በአዲስ አበባ ስታድየም ጥሪ የተደረገላቸው የተለያዩ ክለብ ደጋፊዎች የምክክር መድረክ አድርገዋል። ከተለያዩ ክለብ የተወጣጡ ደጋፊዎች የተገኙ ሲሆን በመድረኩም ስለ ስፖርታዊ ጨዋነትና የክለብ ደጋፊዎች ኃላፊነት፣ በቀጣይ የኢትዮጵያ ክለብ ደጋፊዎች ማሕበር አንድነት በሚቋቋምበት ሁኔታ፣ የዓመቱ የመክፈቻ ጨዋታ በሆነው የመቀለ እና ፋሲል ከነማ የአሸናፊዎች አሸናፊ ጨዋታ ዙርያ ውይይቶች ተደርገዋል። በውይይቱም በምስረታው ዙርያ መነሻ ፅሁፍ የሚያዘጋጁ ደጋፊዎች ተመርጠው ኃላፊነት የተሰጣቸው ሲሆን። ፋሲል ከመቀለ የሚያደርጉት ጨዋታ በሠላም በሚጠናቀቅበት ሁኔታ ላይ ምክክር በማድረግ አስተባባሪዎች ከተለያዩ ክለቦች ተመርጠዋል። የደብሊን ማራቶን የሎተሪ ሲስተም በ2020 የደብሊን ማራቶን ለመሳተፍ የሎተሪ ሲስተም መዘርጋቱን አዘጋጆቹ አሳወቁ። ቀደም ሲል በውድድሩ ለመሳተፍ በኤሌክትሮኒክስ የመመዝገቢያ ዘዴ ቀድሞ ያመለከተ ቅድሚያ የሚሰጠው ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በውድድሩ ለመሳተፍ የአመልካቾች ቁጥር ማየሉን ተከትሎ የሎተሪ ሲስተም ማስፈለጉ ተነግሯል። ይህም አመልካቾችን ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ለማገልገል ታስቦ መሆኑን የውድድሩ ዳይሬክተር ጂም ኦሕኔይ ለመገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል። በውድድሩ ለመሳተፍ አመልካቾች ከመጪው የፈረንጆች ሕዳር አንድ አንስቶ ለሰላሳ ቀናት መመዝገብ የሚችሉ ሲሆን ጥር ላይ ሎተሪውን ያሸነፉ ተሳታፊዎች በአጭር የፅሁፍ መልዕክትና በኢ ሜይል እንደሚገለፅላቸው ታውቋል።አዲስ ዘመን ጥቅምት 19/2012 | https://www.press.et/Ama/?p=21683 | 287 | 2ስፖርት
|
የቮሊቦል ፌዴሬሽን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫ ተራዘመ | ስፖርት | October 22, 2019 | 18 | የኢትዮጵያ ቮሊቦል ፌዴሬሽን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫ እንዲራዘም ፌዴሬሽኑ በ20ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤው ላይ ውሳኔ አስተላለፈ። የኢትዮጵያ የቮሊቦል ፌዴሬሽን መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን ባለፈው ቅዳሜ አዲስ አበባ ላይ ሲያካሂድ፤የኢትዮጵያ ቮሊቦል ፌዴሬሽንን ለ4 ዓመት ሲያገለግል የነበረው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የስራ ዘመኑ የካቲት ወር 2012 ዓ.ም የሚጠናቀቅ ቢሆንም የጀመረውን ስራ ማጠናቀቅ አለበት በሚል እስከ ሰኔ 30 ቀን 2012 መቆየት እንዳለበት ወስኗል። በብሔራዊ የስፖርት ፌዴሬሽኖች የመተዳደሪያ ደንብ መሰረት የፌዴሬሽኖች የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የስልጣን ጊዜ እንዳለቀ አዲስ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት መመረጥ እንዳለባቸው ያስቀምጣል። በዚህ መሰረት አሁን ያለው የቮሊቦል ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከአራት ወራት በኋላ የስራ ዘመኑ የሚጠናቀቅ በመሆኑ የስራ አስፈጻሚውን ቆይታ በተመለከተ የጉባኤው ተሳታፊ ሃሳብ እንዲሰጥበት አጀንዳ ቀርቧል። የጠቅላላ ጉባኤው አባላት በጉዳዩ ላይ ውይይት ካደረጉ በኋላ አዲሱ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ምርጫ ለአራት ወራት እንዲራዘም ወስነዋል። የጠቅላላ ጉባኤው አባላት ከውሳኔው በኋላ በሰጡት አስተያየት፤ አሁን በስልጣን ላይ ያለው የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በ2012 ዓ.ም በጀት ዓመት የጀመረውን ስራ መጨረስ እንዲያስችለው በማሰብ ውሳኔ ላይ እንደደረሱ ተናግረዋል። በዚህ መሰረትም በቀጣዩ በጀት ዓመት ምርጫው በሐምሌ ወር 2012 ዓ.ም እንዲካሄድ ያላቸውን ፍላጎት አንጸባርቀዋል። የኢትዮጵያ ቮሊቦል ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ መስፍን አበራ፣ በጠቅላላ ጉባኤው በኩል ውይይት ተደርጎ በአሁኑ ወቅት ሥራ ላይ የሚገኘው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የቆይታ ጊዜ ለአራት ወራት እንዲራዘም ያሳለፈውን ውሳኔ እንደሚያከብሩት ገልጸዋል። ያም ሆኖ የጠቅላላ ጉባኤውን ውሳኔ የመቀበልና ያለመቀበል ስልጣን የፌዴሬሽኑ ሳይሆን የስፖርት ኮሚሽን መሆኑን ጠቁመዋል። ይህም ውሳኔ ለስፖርት ኮሚሽን እንደሚቀርብ አመልክተዋል። በጉባኤው ላይ የነበሩት የስፖርት ኮሚሽን ተወካይ በሰጡት አስተያየት፤ የፌዴራል የስፖርት ኮሚሽን የጉባኤውን ውሳኔ የሚያከብር ቢሆንም ደንቡ በሚለው መሰረት ምርጫ መሄድ ያለበት በመጋቢት ወር 2012 ዓ.ም እንደሆነ ገልፀዋል። ያም ቢሆን የስፖርት ኮሚሽኑ አመራር በጉዳዩ ላይ ተወያይቶ አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥ አመልክተዋል ።አዲስ ዘመን ጥቅምት 11/2012 ዳንኤል ዘነበ | https://www.press.et/Ama/?p=21210 | 257 | 2ስፖርት
|
54 ቋንቋዎች ለማስተማሪያነት ቢውሉም፣ ለመጥፋት የተቃረቡ መኖራቸውም ተገለፀ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 14, 2020 | 22 | ክፍለዮሐንስ አንበርብርአዲስ አበባ፡- በኢትዮጵያ 54 ቋንቋዎች ለሥርዓተ ትምህርት ማስተማሪያ የዋሉ ቢሆንም በአደገኛ ሁኔታ ውስጥ ያሉ እና ለመጥፋት የተቃረቡ ቋንቋዎች መኖራቸውን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ::በሚኒስቴሩ የትርጉም ሥራ ልማት ቡድን መሪ አቶ ዓለማየሁ ጌታቸው በተለይም ለአዲስ ዘመን ዝግጅት ክፍል እንደገለፁት፤ የአገሪቱ ሕገ መንግሥት ለሁሉም ቋንቋዎች እውቅና የሰጠ ቢሆንም የቋንቋ ልማት የሚመራበት የራሱ የሆነ እውቅና አለመኖር፣ ቅደም ተከተል በሥርዓቱ አለመበጀቱና በብቁ ባለሙያዎች ባለመመራቱ ቋንቋዎች በሚገባው ደረጃ ለምተው ለህብረተሰቡ በሚጠበቀው ደረጃ እየደረሱ አይደለም:: በዚህም የተነሳ የተወሰኑ ቋንቋ ተናጋሪዎች ቁጥር እየቀነሰ ሲሆን ለመጥፋት የተቃረቡ እና የጠፉም መኖራቸውን አስረድተዋል::እንደ አቶ ጌታቸው ገለፃ ቀደም ሲል ጋፋትኛ ቋንቋ የጠፋ ሲሆን፣ አሁን ለመጥፋት የተቃረቡ እና አደገኛ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ቋንቋዎች ይገኛሉ:: በአሁኑ ወቅት ሱዳን የሚነገረው የሙርሌ ቋንቋ በኢትዮጵያ ጠፍቷል ብለዋል:: ደቡብ ኦሞ አካባቢ ይግባቡበት የነበረው ኦንጎታ የሚባለው ቋንቋም ከአስር ዓመት በፊት ከስድስት የማይበልጡ ተናጋሪዎች እንደነበሩ አስታውሰው፤ የመጥፋት አደጋ እንደተደቀነበት አሊያም ሳይጠፋም እንዳልቀረ ገልፀዋል:: የወይጦ ቋንቋ የሚባለውም በዚሁ ደረጃ የጠፋ መሆኑን ገልፀዋል:: በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ
80 በላይ ቋንቋዎች እንደሚነገሩ
ግንዛቤ መኖሩን የጠቆሙት
አቶ ጌታቸው፤ በሥርዓተ
ትምህርት የተካተቱት ግን
54 ብቻ መሆናቸውን ገልፀዋል::እነዚህ
ቋንቋዎች በአገሪቱ ሥርዓተ
ትምህርት ውስጥ ተካተው ግልጋሎት እየሰጡ ቢሆንም፣ በተፈለገው ደረጃ የትምህርት ጥራት ላይ ለውጥ አለመምጣቱንም አብራርተዋል:: ከዚህ በተጨማሪም በአገሪቱ ከሚነገሩ ቋንቋዎች አኳያ በበቂ ደረጃ አለመልማቱን ማሳያ መሆኑን አስገንዝበዋል::የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማሪም በበኩላቸው፤ ልሳነ-ብዙነትን በማበረታታት ሕብረ-ብሔራዊነትን በማጎልበት ቋንቋ ትልቅ ሚና እንዳለውና ለመግባቢያ የሚሆኑ ቋንቋዎች ማዳበር እንደሚገባ ተናግረዋል:: ኢትዮጵያ ከሌላ አገር የተለየ የምልክት ቋንቋ ያላት ሲሆን፤ ይህም በባለሙያዎችና ሳይንቲስቶች በመታገዝ ማደግ አለበት:: አሁን ባለው ሁኔታ በኢትዮጵያ ምን ያክል ቋንቋ በአግባቡ ሥራ ላይ እየዋለ ነው፣ ችግር የተጋረጠባቸው የትኞቹ ናቸው የሚለውን በሚገባ መለየት ይገባል:: የዓደባባይ ቋንቋ አጠቃቀም ጭምር ሕግ እንደሚያስፈልግና ለዚህም መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን አረጋግጠዋል::ጀርመን፣ ካናዳ እና አሜሪካ የግዕዝ ኢንስቲትዩትን እንዳላቸው የተናገሩት ፕሮፌሰር ሂሩት፤ የቋንቋው ባለቤት የሆነችው ኢትዮጵያ በዚህ ደረጃ አለመሥራቷን ጠቁመዋል:: የጥንታዊ ቋንቋ ላይ ጥናትና ምርምር ማድረጉም ጠቀሜታው የበዛ መሆኑን ጠቁመው፤ ይህን ለማስፈፀም ፖሊሲ ብቻውን ጠቃሚ አለመሆኑንና ቴክኒካዊ ሥራዎችን መሰረት በማድረግና ከቴክኖሎጂ ጋር አስተሳስሮ መሥራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል::ልሳነ-ብዝሃነትን ለማበረታታት ሕብረ-ብሔራዊነትን ለማጎልበት በማሰብ የካቲት 2012 ዓ.ም በሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ መሰረት አማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ፣ ሶማልኛ፣ አፋርኛ እና ትግርኛ ቋንቋዎች በፌዴራል ደረጃ የሥራ ቋንቋ እንዲሆኑ መወሰኑ ይታወሳል::አዲስ ዘመን ታህሳስ 5/2013 | https://www.press.et/Ama/?p=37316 | 333 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የጋዜጠኞች የሌላውን ሆድ ከሚያሻክር ዘገባ መቆጠብ የሚፈለገውን አገራዊ ስዕል ለማምጣት እንደሚያስችል ተገለፀ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 14, 2020 | 16 | በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- እያንዳንዱ ጋዜጠኛ የሌላውን ሆድ ሊያሻክር የሚችል ዘገባ ላለመሥራት ለራሱ ቃል ከገባ ድምሩ እንደ አገር የሚፈለገውን ትልቁን ስዕል ለማምጣት የሚያስችል መሆኑ ተገለፀ:: ኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ህዳር 2 ቀን 2013 ዓ.ም ከአዲስ አበባና ከክልል ለተውጣጡ የመንግሥትና የግል መገናኛ ብዙሃን ጋዜጠኞች የግጭት አዘጋገብ ላይ ያተኮረ ስልጠና ሰጥቷል::በስልጠናው ላይ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ወይዘሮ ጽዮን ተክሉ እና የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጌታቸው ድንቁ የተገኙ ሲሆን፤ ስልጠናው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና ከሌሎች ሚዲያ ተቋማት በተውጣጡ ባለሙያዎች ተሰጥቷል ::በስልጠናው ወቅት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጌታቸው ድንቁ እንደገለፁት፤ የመገናኛ ብዙሃን ኢትዮጵያን አሁን ካለችበት ሁኔታ አውጥቶ ወደ ሰላም በመመለስ ያላቸው ሚና እና ኃይል ከፍተኛ በመሆኑ አዎንታዊና አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ የግጭት አዘጋገብ ዘይቤዎችን ተገንዝቦ መሥራት ያስፈልጋል:: ስልጠናው በዚህ ላይ እንዲያተኩር መደረጉም ጋዜጠኞች በዚሁ አግባብ እንዲሰሩ የሚያስችላቸውን ግንዛቤ ለመፍጠር ነው::የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሚኒስቴር ደኤታ ወይዘሮ ጽዮን ተክሉ በበኩላቸው እንዳሉት፤ ከመገናኛ ብዙሃን የሚሰሙ አስደንጋጭና በሰላም ማስፈን ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ዘገባዎች እየተበራከቱ መጥተዋል:: ስለሆነም ህዝብን እኩል ማገልገልና ተገቢ ያልሆኑ አዘጋገቦችን አርሞ ለሀገር ሰላምና ገጽታ ግንባታ የሚውል በጎ መርህ ላይ የተመሰረተ መረጃ አሰጣጥ ሊኖር ይገባል::በስልጠናው ወቅት በቅድመ ግጭት፤ ግጭትና ድህረ ግጭት ላይ መገናኛ ብዙሃን ያላቸው ሚና፣ በዲጂታልና ማህበራዊ ድረ ገጽ የግጭት አዘጋገብ እንዲሁም ሥርዓተ ፆታን ያገናዘበ የግጭት አዘጋገብ ላይ ያተኮሩ ጥናቶች ቀርበዋል:: የጥናት አቅራቢዎቹ እንደገለፁት ደግሞ፣ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ሕግን የማክበርና የማስፈን ሂደቱ ላይ የጎላ አስተዋፅኦ ነበራቸው:: በጊዜ ሂደት ግን እያደጉ ሄደው መጥፎ አሻራ ሊጥሉ የሚችሉ አንዳንድ መርህ አልባ አዘጋገቦች ተስተውለዋል::በዚህም ከቃላት አጠቃቀም ጀምሮ ህዝብን የማበላለጥ አንድምታ ያላቸው የአዘጋገብ ቅኝቶችን መከተል እና በማህበራዊ ሚዲያ መረጃ ተጽዕኖ ሥር መውደቅ ይታይባቸዋል::የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንደሰን አዷለም በበኩላቸው እንደተናገሩት፤ ስልጠናው ግቡን የሚመታው ተሳታፊ ጋዜጠኞች ቢያንስ የሌላውን ወገን ሆድ ሊያሻክር የሚችል ነገር በዘገባ ውስጥ ላለመሥራት በተቻለ መጠን እጠነቀቃለሁ ብለው ለራሳቸው ቃል መግባት ሲችሉ ነው::“እያንዳንዱ ጋዜጠኛ የሌላውን ሆድ ሊያሻክር የሚችል ዘገባ ላለመሥራት ለራሱ ቃል ከገባ፤ ድምሩ የምንፈልገውን ትልቁን ስዕል ይሰጠናል” ያሉት አቶ ወንደሰን፤ አሁን የሚታየው ችግርም የብሔር ሚዲያ በመብዛቱ ወይም መኖሩ ሳይሆን “የአንድን ማህበረሰብ ቋንቋ ባህልና ትውፊትን ለማሳደግ ሚዲያ አቋቁመን ስናበቃ ለሌላው ወገን የሚኖር የአመለካከት ብልሹነት በመኖሩ ነው” ብለዋል::የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው፣
በተለይ የቃላት አጠቃቀም
ላይ ያሉ ችግሮች
ቶሎ ካላስተካከሉ የቅርብ
መዘዛቸውና በቀጣይ ትውልድ
ላይ የሚፈጥሩት የመራራቅ
መንፈስ ከፍተኛ ሊሆን
ይችላል ሲሉ ሃሳባቸውን
ገልጠዋል:: ዘገባውን ያደረሰን
የባለሥልጣኑ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
ነው::አዲስ ዘመን ታህሳስ 5/2013 ዓ.ም | https://www.press.et/Ama/?p=37317 | 351 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ኢትዮጵያዊያን በድል ያንፀባረቁበት ሳምንት | ስፖርት | October 22, 2019 | 1023 | ጥቅምት ወር በአትሌቲክሱ ዓለም በተለይም የጎዳና ላይ ሩጫዎች በስፋት የሚካሄዱበት ነው። ባለፈው ሳምንት መጨረሻም በመላው ዓለም ዙሪያ በርካታ የማራቶን ውድድሮች ተካሄደዋል። በዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር እውቅና ኖሯቸው ከተካሄዱት ውድድሮች መካከልም ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች እንደተለመደው የሳምንቱን መጨረሻ ቀናት በድል አንፀባርቀዋል፡፡ አምስተርዳም ማራቶን በዓለም አቀፉ ማህበር የወርቅ ደረጃ በተሰጠው በዚህ ውድድር በተለይ በሴቶቹ ምድብ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ደጊቱ አዝመራው የቦታውን ክብረወሰንም ያስመዘገበችበት ነበር። አትሌቷ 2:19:26 የሆነ ሰዓት ያስመዘገበች ሲሆን ንፋስ አልባው አየር ለውድድሩ ምቹ እንደነበረም ተጠቁሟል። በሰከንዶች የዘገየችው ትዕግስት ግርማ ሁለተኛ ስትሆን
2:19:52 ደግሞ የገባችበት ሰዓት ነው። አዝመራ ገብሩ እና በሱ ሳዶ ደግሞ ሦስተኛ እና አራተኛ በመሆን ውድድራቸውን ፈጽመዋል። በወንዶች መካከል በተካሄደው ውድድር ኬንያዊው ቪንሰንት ኪፕቹምባ ቀዳሚውን ስፍራ ሲይዝ፤ ሰለሞን ዲክሲሳ እና በተስፋ ጌታሁን ደግሞ ሁለተኛ እና ሦስተኛ በመሆን የብርና ነሐስ ሜዳሊያ ባለቤቶች ሆነዋል። ዴልሂ ግማሽ ማራቶን በዚህ ውድድርም 1:06:00 በሆነ ሰዓት የገባችው ኢትዮጵያዊት አትሌት ፀሐይ ገመቹ ናት፡፡ ያለምዘርፍ የኃላው ፀሐይን ተከትላ ሁለተኛ ስትሆን፤ ዘይነባ ይመርም የአገሯን ልጆች ተከትላ በሦስተኝነት አጠናቃለች። በወንዶች በኩል አንዱአምላክ በልሁ አሸናፊ ሲሆን፤ የገባበት 59:10 የሆነ ሰዓት ደግሞ የግሉ ምርጥ ሰዓት ሆኗል። ሰለሞን በሪሁ በሁለተኛነት ሲገባ ኬንያዊው ኪቢዎት ካንዴ በሰከንዶች ልዩነት ሦስተኛ በመሆን ውድድሩን ደምድሟል። ቶሮንቶ ማራቶን እስከ 30ኛው ኪሎ ሜትር በርካታ አትሌቶች አንገት ለአንገት ተናንቀው በሮጡበት በዚህ ውድድር አሸናፊ የሆነችው ኬንያዊቷ ማግዴልይኔ ማሳይ ናት። በጤና መታውክ ምክንያት ውድድሩን ልታቋርጥ ትችላልች የሚል ስጋት ያሳደረችው ኢትዮጵያዊቷ ብሩክታይት እሸቱ ደግሞ ሌላኛዋን ኬንያዊት ቤትሲ ሴናን በማስከተል ሁለተኛ ሆናለች። በወንዶች ምድብ ኬንያዊው ፊሊሞን ሮኖ ለሦስተኛ ጊዜ አሸናፊ መሆን ችሏል። ኢትዮጵያዊው ለሚ ብርሃኑ እና ኡጋንዳዊው ፍሊክስ ቼሞንገስ ደግሞ እርሱን ተከትለው እጅግ በተቀራረበ ሰዓት የገቡ አትሌቶች ሆነዋል። ሊዝበን ማራቶን በጥሩ የአየር ሁኔታ ታጅቦ በተካሄደው በዚህ ውድድር በሁለቱም ጾታ ኢትዮጵያዊያን አሸንፈዋል። በሴቶቹ በኩል ሲጫሌ ደላሳ ስታሸንፍ፤ ኬንያዊቷ ሄለን ጄፕኩራጋት እና ኢትዮጵያዊቷ ሱሌ ኡቱራ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ሆነዋል። በወንዶች፤ አንዱዓለም ሽፈራው ኬንያዊያኑን ሳሙኤል ዋንጂኩ እና ስቴፈን ቼምላኒን አስከትሎ በመግባት አሸናፊ ሆኗል።አዲስ ዘመን ጥቅምት 11/2012 ብርሃን
ፈይሳ | https://www.press.et/Ama/?p=21214 | 289 | 2ስፖርት
|
በአዲስ አበባ የአማራ ባለሀብቶች የክልሉን ልማት ለማስቀጠልና የፀጥታ መዋቅሩን ለመደገፍ ከመንግሥት ጎን እንደሚቆሙ አረጋገጡ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 14, 2020 | 21 | በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- በአዲስ አበባ የአማራ ባለሀብቶች በክልሉ ያለውን ልማት ለማስቀጠልና የፀጥታ መዋቅሩን ለመደገፍ ከክልሉ ህዝብና መንግሥት ጎን እንደሚቆሙ አረጋገጡ:: በሀገሪቱ እና በክልሉ ወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አገኘሁ ተሻገርን ጨምሮ ሌሎች የክልልና የፌዴራል ከፍተኛ መሪዎች በተገኙበት በአዲስ አበባ ከአማራ ባለሀብቶች ጋር ምክክር ተደርጓል።የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት እንደዘገበው፤ የጁንታው አጥፊ ቡድን በኢትዮጵያ ህዝቦች ላይ በፈፀመው ክህደት በመንግሥት በኩል በተወሰደው ሕግ የማስከበር ሥራ ይህ የጥፋት ኃይል በሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ በአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚኒሻና ሌሎችም የፀጥታ ሃይሎች ከፍተኛ ተጋድሎ ላይመለስ ተቀብሯል። ይህን ታላቅ ገድልም ትውልድ ሲዘክረው ይኖራል:: ይሄን ተከትሎም በአዲስ አበባ የአማራ ባለሀብቶች በክልሉ ያለውን ልማት ለማስቀጠልና የፀጥታ መዋቅሩን ለመደገፍ ከክልሉ ህዝብና መንግሥት ጎን እንደሚቆሙ አረጋግጠዋል::መረጃው እንዳመለከተው፤ መድረኩን የመሩት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር በሕግ ማስከበር ሂደቱ የነበሩ እውነታዎችን ለባለሀብቶች ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል::ሀገር ችግር ውስጥ በሆነችበት ጊዜ መደጋገፍ እና አብሮ መቆም ከአባቶቻችን የወረስነው ነው ብለዋል:: በዚህ ሕግ የማስከበር ሥራ ክልሉ ያለውን ሁሉ አድርጓል፤ በቀጣይ የጀመረውን ሰላምና ልማት ለማስቀል ባለሀብቶች እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ፋንታ ማንደፍሮ በአማራ ህዝብ ላይ ሲደርስ የቆየው አማራን አጥፊና በዳይ አድርጎ በጠላትነት የመፈረጅ የሴራ እሳቤ እና ጥላቻ እውነታው መጋለጡን ጠቅሰዋል:: ወራሪው፣ ተስፋፊውና አሸባሪው የትህነግ አጥፊ ቡድን በመከላከያ፣ በጀግናው የአማራ ልዩ ኃይልና ሚኒሻ እንዲሁም በአማራ ህዝብ ሽንፈት መከናነቡን ገልፀዋል፤ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ “ቀጣዩ ምዕራፍ በጋራ ቆመን የኛን የቤት ሥራ የምንሰራበት ጊዜ ነው” ብለዋል::የክልሉ መንግሥት ሕግ በማስከበር ሂደቱ የተለያዩ ወጪዎችን ማውጣቱን የጠቀሱት ዶክተር ፋንታ፤ ባለሀብቶች የክልሉን ነባራዊ ሁኔታ በመገንዘብም አለኝታነታቸውን በተግባር አሳይተዋል ብለዋል::በውይይቱ የተሳተፉ ባለሀብቶች በበኩላቸው፣ “ይህን ማድረግ ለኛ ክብር ነው፤ እኛ የምንከበረው የሚከበር ሀገር እና የዘመነ የፀጥታ ኃይል ሲኖር ነው፤ እናም የክልሉ መንግሥት እየሠራቸው ያሉ ሥራወችን ወደፊትም ለማገዝ ዝግጁ ነን” ብለዋል:: በዕለቱም ከ3 መቶ 76 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ ቃል የተገባ ሲሆን፤ በእውቀትና በቁሳቁስ ድጋፍ ማድረግም ሌላው በመድረኩ ቃል ከተገባው ውስጥ ነው::በመጨረሻም፣ “ከ40 ዓመታት በላይ በዘራፊውና የጥፋት ኃይሉ ትህነግ የአማራ ህዝብ መዋቅራዊ በሆነ መልኩ አጥፊና በዳይ በሚል ትርክት ጥቃቶች ሲፈፀሙበት ኖሯል፤ ዛሬ ልጆቹ በከፈሉት ዋጋ ነፃ ወጥቷል፤ ቀጣዩ ዘመን ድሉ ለአማራ ህዝብ ትንሳኤ መሆኑን በመገንዘብም በአብሮነት ቆመን ልንሠራ ይገባል፤” ሲሉ የአዲስ አበባ አማራ ባላሀብቶች ጥሪ አቅርበዋል::“ነፃነታችን አውጀን መሥራት እና ሀገርን መደገፍ በምንችልበት ልክ እኛም ከህዝብና ከመንግሥት ጎን እንቆማለን፤” ሲሉም አረጋግጠዋል:: “ጎጠኝነት የህዝባችን ሥነ ልቦና የማይፈቅደው፣ አባቶቻችን ያላወረሱን እኩይ ተግባር ነው” ያሉት የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል በበኩላቸው፤ ከዚህ በኋላ አብረን በመቆም የሚመጣውን መታገል እንጅ በጎጥ እና በሰፈር በመከፋፈል እንቅፋት መሆን ሊቆም እንደሚገባም አሳስበዋል::አዲስ ዘመን ታህሳስ 5/2013 | https://www.press.et/Ama/?p=37326 | 373 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
በመተከል አካባቢ ከአንድ ሺህ በላይ ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር በማዋል ጉዳያቸው በሕግ እየታየ ነው | ሀገር አቀፍ ዜና | December 14, 2020 | 12 | በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- በመተከል አካባቢ እና ቀጠናውን ለማረጋጋት በተደረገው ሕግን የማስከበር ሥራ 1 ሺህ 1 የሚሆኑ ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር በማዋል ጉዳያቸው በሕግ እየታየ መሆኑን የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት አስታወቀ።ፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት እንደዘገበው፤ በዞኑ በተፈጠረው የሰዎች ሞት እና መፈናቀል ምክንያት የሆኑ 284 ፀረ ሰላም ሃይሎች መደምሰሳቸውን ኮማንድ ፖስቱ ገልጿል። መንግሥት የሰጣቸውን ሃላፊነት ወደ ጎን በመተው ለፀረ ሰላም ሃይሉ መረጃ በመስጠት የተጠረጠሩ ከክልል እስከ ወረዳ በሚገኙ 66 አመራሮች ላይም እርምጃ መወሰዱን ኮማንድ ፖስቱ አስታውቋል::በተጨማሪም፣ ኮማንድ ፖስቱ እያከናወነ ባለው ኦፕሬሽን 50 ሰዎች የተማረኩ ሲሆን፤ 43 የሚሆኑት ደግሞ በመግባባት እጅ ሰጥተዋል። በተደጋጋሚ ግጭቱ እንዳይቆም ህዝባዊ ሃላፊነት ባልተወጡ 32 የፖሊስ አባላትና 35 የፀረ ሽምቅ አባላትን በቁጥጥር ሥር በማዋል ጉዳዩም በሕግ እየታየ ይገኛል ነው የተባለው። ቀጠናውን ለማረጋጋት በሚደረገው ሕግን የማስከበር ሥራ 119 ዘመናዊ የጦር መሣሪያ፣ 108 ኋላ ቀር መሣሪያ በአጠቃላይ 227 የጦር መሣሪያ እና የተለያዩ የወታደር ልብሶችም ተይዘዋል።በዘገባው እንደተመላከተው፤ በቀጠናው በተፈጠረው አለመረጋጋት እስካሁን 22 ሺህ 768 የህብረተሰብ ክፍሎች ከቀያቸው የተፈናቀሉ ሲሆን፤ ለእነዚህ ወገኖች ሰብዓዊ ድጋፍ በማድረግ እና ወደ ነበሩበት ለመመለስ ርብርብ እየተደረገ እንደሆነም ተገልጿል። በመተከል ዞን የተከሰተውን አለመረጋጋት በዘላቂነት ለመፍታት 2 ሺህ 679 አዲስ የሚኒሻ አባላት በማሰልጠን ከህብረተሰቡ ጋር ቀጠናውን እንዲጠብቁ ተደርጓል::አዲስ ዘመን ታህሳስ 5/2013 | https://www.press.et/Ama/?p=37325 | 179 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከሱዳኑ አቻቸው አብደላ ሀምዶክ ጋር ተወያዩ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 14, 2020 | 14 | በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ (ኢዜአ)፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከሱዳኑ አቻቸው አብደላ ሀምዶክ ጋር ሀገራቱን በሚያስተሳስሯቸው የሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል። የሱዳኑ ጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሀምዶክ ለሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት ትናንት አዲስ አበባ ገብተዋል::ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ
ሀምዶክ፣ በሁለት ቀን
ቆይታቸው በሁለቱ አገራት
የጋራ ጉዳዮች በተለይም
የሀገራቱን የሁለትዮሽና የኢኮኖሚ
ትብብር በሚያጠናክሩ ጉዳዮች
ዙሪያ ላይ የሚመክሩ
ሲሆን፤ ትናንትናም ከጠቅላይ
ሚኒስትር አብይ ጋር
ተወያይተዋል። በቆይታቸው፣ ሁለቱ መሪዎች ከሁለትዮሽ ትብብር በተጨማሪ በአካባቢያዊና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩም ይጠበቃል።ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ቀደም ሲል በሱዳን ባደረጉት የሥራ ጉብኝት ከሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር አብዱልፈታህ አልቡርሃን እንዲሁም ከጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ጋር መወያየታቸው ይታወሳል።ኢትዮጵያና ሱዳን የሁለትዮሽ እና የኢኮኖሚ ትብብራቸውን ከማጠናከር በተጨማሪ በአካባቢው ሰላምና መረጋጋት እንዲኖር በጋራ እየሠሩ መሆኑ ይታወቃል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 5/2013 | https://www.press.et/Ama/?p=37324 | 115 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
በመቀሌና በማይጨው የሞባይል ድምጽ አገልግሎት መጀመሩ ተገለፀ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 14, 2020 | 9 | በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- ከጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ከሌሊቱ 6፡37 ሰዓት ጅምሮ በመቀሌ ከተማና በማይጨው የተቋረጠው የስልክ አገልግሎት ዳግም ሥራ መጀመሩን ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ::ኢትዮ ቴሌኮም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ የሰሜን ሪጅን የቴሌኮም አገልግሎትን ለማስጀመር ሰፊ ሥራዎችና ከፍተኛ ርብርብ ሲካድ መቆየቱን አስታውሶ፤ በአሁኑ ወቅትም በመቀሌና በማይጨው የሞባይል ድምጽ አገልግሎት ማስጀመር ተችሏል ብሏል::የመቀሌ የሞባይል ድምጽ
አገልግሎት የተጀመረው አማራጭ
ሃይል በመጠቀም ከመሆኑ
አንፃር የአገልግሎት መቆራረጥ
ሊያጋጥም ስለሚችል ደንበኞች
ይህንኑ እንዲገነዘቡም ኢትዮ
ቴሌኮም አሳስቧል:: የጥገናና የመሰረተ ልማቶችን መልሶ የማቋቋም ሥራዎችን በማከናወንና ከሃይል አቅርቦት ጋር የተገናኘ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር በመሥራት የተሟላ የቴሌኮም አገልግሎት ለመስጠት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑን ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል::ከዚህ ቀደም በዳንሻ፣ በተርካን፣ በሑመራ፣ በሽራሮ፣ በማይፀብሪና፣ ማይካድራ እና በኮረም አካባቢዎች በከፊል እንዲሁም በአላማጣ ሙሉ ለሙሉ የቴሌኮም አገልግሎት የተጀመረ መሆኑን ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል::ድርጅቱ በሰሜን ሪጅን አገልግሎቱ መቼና እንዴት እንደተቋረጠ እንዲሁም ያቋረጡ አካላት በሚመለከት ታህሳስ 1 ቀን 2013 ዓ.ም ዝርዝር መረጃና ማስረጃ ማቅረቡን አስታውቆ፤ አገልግሎቱን መልሶ ለማስጀመር ከዋና ሞባይል ጣቢያ የሚያገናኙና ሁሉም አማራጭ መስመሮች መቆረጣቸውንና የሃይል አቅርቦት መቋረጡ ዋነኛ ተግዳሮት መሆናቸውን መጥቀሱ ይታወሳል::አዲስ ዘመን ታህሳስ 5/2013 | https://www.press.et/Ama/?p=37334 | 163 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የጁንታው ግፍ ባገታቸው መኮንኖች አንደበት | ሀገር አቀፍ ዜና | December 15, 2020 | 12 | ጌትነት ተስፋማርያም ጁንታው በሀገር መከላከያ ሰራዊት በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ካደረሰ በኋላ ከአንድ ሺህ በላይ የመከላከያ ሰራዊት አመራሮችን እና መኮንኖችን አፍኖ ወደ መቀሌ ነበር የወሰዳቸው። መቀሌ በመከላከያ ሰራዊት ኮማንዶዎች ስትያዝ እግሬ አውጭኝ ብሎ ሲሸሽ ብቻውን አልነበረም የሸሸው፤ እነዚህኑ ያገታቸውን የሀገር ባለውለታ ሰራዊቶችንም ይዞ እንጂ። ታጋቾቹን በእግር ከቦታ ቦታ እያጓጓዘ አድክሟቸዋል። ምግብና ውሃ ከልክሎ አሰቃይቷቸዋል። በዚህም ምክንያት አብዛኛው ታጋች የሰራዊቱ አመራሮች ተጎሳቁለዋል፤ የታመሙም አሉ። ህዳር 30 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ ስምንት ሰዓት አካባቢ ግን ወገን ለወገኑ ደረሰ። በሄሊኮፕተር እና በድሮን ጭምር የታገዘው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ለቀናት ሲከታተል ቆይቶ አመቺ ቦታ ሲያገኝ በጁንታው አመራርና ታጣቂዎች ላይ እርምጃ ወሰደ። መከላከያ ሰራዊቱ በምድር የሚያደርገውን ጥንቃቄ የተሞላበትን ኦፕሬሽን አጠናከረ። ይህንን የተቀናጀ እርምጃ መቋቋም ያልቻቸው የጁንታው ታጣቂ ግን ተሽከርካሪዎቹን እና ጠብመንጃውን እየጣለ በየጢሻውና ጉራንጉሩ አፈተለከ። በወቅቱ ታፍነው የነበሩ የሰራዊቱ አመራሮች ከደረሰላቸው ሰራዊት ጋር ታጅበው አዴትን ለቀው ወጡ። ከታፋኞቹ መካከል አንዱ የነበሩት የሰሜን ዕዝ ኢንዶክትሪኔሽን ኃላፊ ኮሎኔል አበባው መንግስቱ እንባ እና ሲቃ በተቀላቀለበት ድምጸት ባሳለፏቸው አስከፊ ቀናት የሆነውን ሁሉ አጋርተውናል። ‹‹በመጀመሪያ ደረጃ አፍነው በጦር አውድማ ለምን ሲያንቀሳቅሱን ከረሙ የሚለው ጥያቄ አልተመለሰልኝም። ወይ ሊደራደሩብን አሊያም አማራጭ ሲያጡ ሊጨርሱን አስበው ይሆናል። በወቅቱ ትልቁ ችግር የነበረው ግን ታፋኞችን በምግብ ለመጉዳት የተሸረበው ሴራ ነው›› ይላሉ። በቀን አንድ ዳቦ ይሰጣቸው እንደነበረ በማስታወስ በመጨረሻዎቹ ቀናት ግን እሷም ቀርታ ውሃ እና ማብሰያ በሌለበት በረሃ ጥቂት ዱቄት ብቻ እንደቀረበላቸው ያስታውሳሉ። ዱቄቱን የሚያገነፉበት አንድ ድስት ከሺ በላይ ለሆኑ ሰዎች ቀርቧል። ጨው እና ማባያ በሌለበት ሁናቴ ገንፎው በትግል ተሰርቶ ሲያበቃ ማቅረቢያ እቃ ግን በቦታው አልነበረም። “በወቅቱ ህይወታቸውን ለማዳን በድንጋይ ጥራቢ እና በእንጨት ቅርፊት ባዶውን ገንፎ ለሁለት እና ለሶስት ተቃምሰን ህይወታችንን ለማትረፍ ታግለናል” ሲሉ የነበረውን አስከፊ ሁናቴ በጉንጫቸው እየወረደ ባለው እንባ ታጅበው አስረዱን።ከምግቡ ባሻገር ግን በቆላ በደጋ በግዳጅ በእግር እንዲጓጓዙ መደረጉን አስታውሰው፤ በእግር ጉዞ ብቻ እግራቸው መላላጡን እና ያገኙትን ብትር ለምርኩዝነት እየተጠቀሙ ፍዳ ማየታቸውን ነግረውናል። አንድ ቀን ሙሉ ትልቅ ተራራ ሲወጡ መዋላቸውን አጫውተውናል። ‹‹ብዙ ጊዜ በውትድርና ኑረናልና ብዙ ጊዜ ችግር ሊያጋጥም ይችላል፤ በጁንታው ስር የገጠመን ችግር ግን ከየትኛውም ወቅት ጋር ሊነጻጸር የሚችል አይደለም>> ያሉት ኮሎኔል አበባው መንግስቱ፤ የእራሳቸው ጓደኞች እና የቀድሞ የስራ ባልደረቦች ጭምር ግፉን መፈጸማቸው ደግሞ የበለጠ እንደሚያሳዝናቸው አልሸሸጉም። በመጨረሻ ግን ጁንታው በመከላከያ ሰራዊት እርምጃ አማካኝነት መፈናፈኛ በማጣቱ ንብረቱን ትቶ በየአቅጣጫው መበታተኑን ታዝበዋል። አንዳንድ ባለስልጣናትም ሽርጥ ቢጤ ፊታቸው ላይ በመከናነብ እና ጥቁር መነጽር በማድረግ በዘመናዊ ተሽከርካሪ አብረው ሲከታተሏቸው እንደነበረ የታዘቡት ኮሎኔል አበባው፤ በመጨረሻዋ ሰዓት ግን ሁሉም ከየመኪናው እየዘለለ በየገደላገደሉ ሲያፈተልክ መመልከታቸውን ይገልጻሉ። የጁንታው ቡድን አፍኖ ከወሰዳቸው የመከላከያ ሰራዊት አመራሮች መካከል አንዱ የሰሜን ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል አዛዥ ኮሎኔል ተሾመ ይመር ናቸው። በጁንታው ቡድን ታጣቂዎች ስር የቆዩባቸው ከአንድ ወር በላይ የሆኑ ቀናት መራርነት ከባድ መሆኑን ነግረውናል። በአንድ በኩል በምግብ የሚቀጡበት መንገድ ለአብዛኛው መኮንኖች ጤና መቃወስ ጉልህ ሚና ነበረው። “የጁንታው ታጣቂዎች በመከላከያ ሰራዊት ጥንቃቄ የተሞላበት እርምጃ በሚወሰድበት ወቅት ታፋኞችን ይዘው በጦር ቀጠና ውስጥ በእግር እንድንጓዝ ፈረዱብን። አብዛኛው ሰው በምግብና ውሃ ጥም ከመዳከሙ የተነሳ በቅጡ መራመድ እንኳን ቢያቅተውም ነብሱን ለማዳን ግን እየተደጋገፈ እና አፈሩንም ቢሆን እየቧጠጠ ተራራማ ስፍራዎችን ጭምር ሊጓዝ ችሏል” ብለዋል። ከተንቤን ተራራማ ስፍራዎች አንስቶ እዳጋ ሃሙስ እና አዴት ድረስ ብቻ ለአራት ቀናት ታፋኞች በእግር እንዲንቀሳቀሱ የተደረገበትን መንገድ መመልከት ቢቻል ጁንታው ምን ያህል ለሰብአዊነት የማይራራ አረመኔ መሆኑን ያሳያል። በየመንገዱ መጓዝ አቅቷቸው ወደኋላ የሚቀሩትን በዱላ እና በመሳሪያ በመምታት አሳፋሪ ተግባር ፈጽሟል። በተለይ ግን በህግ ማስከበር የጦር ግንባሮች የጁንታው ታጣቂዎች ያፈኗቸውን የሰራዊት አባላት እንደሽፋን በመጠቀም ለማስጨረስ ቆረጠው ነበር። ዶዘር ጭምር በማሰማራትም ለታፋኞች መቀበሪያ የሚሆን ጉድጓድ ሲዘጋጅ እንደነበርም ተመልክተናል። ሰራዊቱ ባይደርስ ምናልባት ከደቂቃዎች በኋላ በህይወት ላይኖሩ የሚችሉበት አጋጣሚ ሊፈጠር እንደሚችል ግምታቸውን ያስቀምጣሉ። የወገን ጦር በየጊዜው እኛ ወዳለንበት እየተጠጋ መሆኑን ግን በተለያዩ አጋጣሚዎች እየሰማን በመሆኑ እንደሚደርሱ ተስፋ አድርገናል። የታሰበውም አዴት ላይ ሆነ። በመጨረሻም መከላከያ ሰራዊትም ሆነ አየር ሃይል ሁኔታውን በመገንዘብ ለቀናት ታግሶ በመጨረሻ አመቺ ጊዜ ሲያገኝ በወሰደው ወገን የማዳን እርምጃ የጁንታው ኃይል እግሬ አውጭኝ ብሎ ተበታትኗል በማለት ሁናቴውን ነግረውናል። በወቅቱ በርካታ የጁንታው አመራሮች ግን በዘመናዊ ተሽከርካሪዎች ሲንቀሳቀሱ እንደነበር እና በመጨረሻም የያዙትን ንብረት እና ፋይሎች እያንጠባጠቡ በየአቅጣጫው መበታተናቸውን አስተውለዋል። “መከላከያ ህዝባዊ ሰራዊት መሆኑን እናውቃለን፤ እንደሚደርስልንም እምነት ነበረን፤ ሌት ተቀን ብሎ የሚከፈለውን መስዋዕት እየከፈለ ደርሶልናል። ለተቋማችንም ሆነ ለመንግስት እኛን በሰላም ከአፈናው ለማውጣት የተደረገው ጥረት ከፍተኛ ዋጋ የተከፈለበት ስለሆነ ምስጋና አቀርባለሁ” ብለዋል። ታጋቾችን ለማዳን የተደረገውን ጥንቃቄ የተሞላበት ጥረት ያደነቁት መኮንኖች፤ በቀጣይ የጁንታውን አመራሮች አድኖ ለመያዝ የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ እና የሙያ ግዴታቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 6/2013 | https://www.press.et/Ama/?p=37379 | 651 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
በትግራይ እየተዋቀረ ባለው የመንግስት አስተዳደር ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች እየተካተቱ መሆኑ ተገለጸ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 15, 2020 | 42 | በጋዜጣው ሪፖርተሮች አዲስ አበባ:- ከጁንታው መደምሰስ በኋላ በትግራይ ክልል እየተዋቀረ ባለው የመንግስት አስተዳደር ውስጥ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችም እየተካተቱ እንደሆነ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አስታወቁ። ዋና ሥራ አስፈጻሚው ዶ/ር ሙሉ ነጋ እንደገለጹት፤ እየተዋቀሩ በሚገኙ አስተዳደሮች ብዙ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች እየተሳተፉ ነው። መሳተፍም ብቻ ሳይሆን የሽግግሩ መንግስቱ አካል ሆነው እስከ ቢሮ ሃላፊነት ድረስ ይመራሉ። እንደ ዶክተር ሙሉ
ገለጻ፤ አረና፣ ትዴፓ
እና አሲምባ የመሳሰሉ
ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ
አመራሮችና አባላት በክልሉ
ካቢኔ ውስጥ እንዲገቡ
ተወስኗል። ከዚህ በፊት
በነበረው የክልሉ ነበራዊ
ሁኔታ እነዚህ አካላት
በፖለቲካ አመለካከታቸው የተነሳ
ሲታሰሩ፣ ሲገደሉና ሲሳደዱ
ቆይተዋል። የትግራይ ክልል ሕዝብ በአፈና ውስጥ የኖረ ሕዝብ ነው ያሉት ዶ/ር ሙሉ፤ “በአሁኑ ወቅት ግን ህዝቡ ከታች ጀምሮ እየተሳተፈ ነው፡፡ይህ ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ እየሆነ ያለ ነው። ቀበሌ፣ ክፍለ ከተማ እና ሌሎቹንም የአስተዳደር እርከኖች ጭምር ሕዝቡ ነጻ ሆኖ ራሱ እንዲመርጥ ይደረጋል” ብለዋል፡፡ በጁንታው ላይ የተወሰደው ሕግ የማስከበር እርምጃ ለትግራይ ክልል ሕዝብ እንደመልካም አጋጣሚ የሚወሰድ እንደሆነ ያነሱት ዶ/ር ሙሉ፤ በክልሉ የነበረው የዴሞክራሲ ምህዋር ዝግና ጭላንጭል ያልነበረው በመሆኑ በመንግስት የተወሰደው ሕግ የማስከበር እርምጃ ለትግራይ ክልል ሕዝብ ወደ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲሸጋገር የሚያደርግ መልካም አጋጣሚ ተደርጎ የሚወሰድ ነው ብለዋል፡፡ “ከመጀመሪያው ጀምሮ የሕዝቡ አስተያየትና ተሳትፎ የሚደነቅ መሆኑን ያነሱት ዶክተር ሙሉ ፤ “ይሄን ሁኔታ ይበልጥ አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡በትግራይ በአጭር ጊዜ የፖለቲካ ተሳትፎ ምህዳሩ መስፋት አለበት፡፡የሐሳብ ብዝሃነት በነጻት መስተናገድ አለበት፡፡ይሄ ራሱ ትልቅ አጋጣሚ ነው፡፡ከአሁን በኋላ በትግራይ ‘እኔ አውቅልሃለሁ፤ እኔ ብቻ’ የሚል አስተሳሰብ አይኖርም፡፡የመጫወቻ ሜዳውን እና የመጫወቻውን ሕግ እኩል እናደርጋለን” ነው ያሉት፡፡ እንደ ዶ/ር ሙሉ ገለጻ፤ በመከላከያ ሰራዊት ላይ የተፈጸመውን ክህደት የትግራይ ሕዝብ እየተገነዘበ መምጣት ጀምሯል፡፡በተደረጉ ውይይቶች እውነታውን ማወቅ እየቻለ ነው፡፡በመሆኑም ጁንታው የፈጸመውን ግፍና በደል እንዲሁም ኢሰብዓዊ ድርጊት ህብረተሰቡ በትክክል እየተገነዘበ መጥቷል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የትግራይ ብልጽግና ከፍተኛ አመራር የሆኑት ዶ/ር አብረሃም በላይ በበኩላቸው፤ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ለህዝብ ያለው ተቆርቋሪነት አሁንም ከህግ ማስከበር ዘመቻው በኋላ እያደረገ ባለው ድጋፍ ማየት ይቻላል ብለዋል። ሰራዊቱ ለህዝብ ያለው ተቆርቋሪነት አሁንም ከህግ ማስከበር ስራው በኋላ የትግራይ ህዝብ እንዳይቸገር ነዳጅ ሳይቀር ከራሱ ቀንሶ ለህዝብ እየሰጠ መሆኑን ነው ዶ/ር አብረሃም ያስታወቁት፡፡ “ህዝቡ የሀገር መከላከያ ሰራዊቱን ሲያገኝ የሚያሳየው ስሜት የተለየ ነው” ያሉት ዶ/ር አብረሃም፤ ይህ የሰራዊቱና የህዝቡ ወዳጅነት በዚሁ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡ መንግስትም በፍጥነት ምላሽ በመስጠት ለትግራይ ህዝብ የምግብና የመድሃኒት ድጋፍ በማድረግ ላይ ነው ያሉት ዶ/ር አብረሃም፤ የትግራይ ህዝብም በፍጥነት ወደ ነበረበት በመመለስ ትግራይን ማልማት አለበት ብለዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 6/2013 | https://www.press.et/Ama/?p=37378 | 350 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
በትግራይ ክልል ሙሉ በሙሉ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመስጠት እየተሰራ ነው | ሀገር አቀፍ ዜና | December 15, 2020 | 8 | የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ የደረሰው ከፍተኛ ጉዳት ጥገናውን ፈታኝ አድርጎታል ዋለልኝ አየለ አዲስ አበባ፡- በትግራይ ክልል በሁሉም አካባቢዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑ ተገለጸ፡፡የህወሓት የጥፋት ቡድን በከፍተኛ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ ያደረሰው ጉዳት የከፋ መሆኑ የጥገና ሥራውን ፈታኝ እንዳደረገውም ተጠቁሟል፡፡የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ በትግራይ ክልል ተቋርጦ የቆየውን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ዳግም ለማስጀመር በተደረገው ሰፊ ጥረት የክልሉን ዋና ከተማ መቀሌን ጨምሮ በአንዳንድ ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት ጀምሯል፡፡በቀጣይም ወደ ሽሬ ያሉ አካባቢዎችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ እና ከመቀሌ ወደ ዓድዋ ያሉ አካባቢዎችንም የማገናኘት ሥራ እየተሰራ ነው፡፡በኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ የደረሰው ጉዳት ከፍተኛ መሆኑን የገለጹት አቶ ሞገስ፤ መቀሌ ከተማ ላይ እንኳን መስመሮችን ለማገናኘት ያልተቻለበት ሁኔታ ተፈጥሮ እንደነበር ተናግረዋል፡፡አሁን ላይ በክልሉ መቀሌን ጨምሮ አንዳንድ ከተሞች ላይ የኤሌክትሪክ አገልግሎት መስጠት የተቻለ ቢሆንም፤ በቀጣይ ሙሉ መስመሩን ከማገናኘት በተጨማሪ ከዋናው መስመር ወጪ መስመሮችም መሰራት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡በወጪ መስመሮችም ላይ ጉዳት ስለደረሰ እንደገና እየተሰሩ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡እንደ አቶ ሞገስ ገለጻ፤ የጥገና ሥራው በሌሎች አካባቢዎች እንደሚደረገው አይደለም፡፡ምክንያቱም የማስተላለፊያ መስመሮች በቦምብ የተመቱና በከፍተኛ ሁኔታ የተጎዱ ከመሆናቸው በተጨማሪ በፈንጅ የታጠሩ አካባቢዎችም አሉ፡፡በዚህም የኤሌክትሪክ ጥገና ሥራው እየተሰራ ያለው በኤሌክትሪክ ባለሙያዎች ብቻ ሳይሆን ከፀጥታ ኃይል ጋር በመሆን ነው፡፡በዚህም የፀጥታ ኃይሉ ከፈንጅ ነፃ የሆኑ አካባቢዎችን እየለየ ለኤሌክትሪክ ባለሙያዎች ይሰጣል፡፡ሂደቱም ለኤሌክትሪክ ባለሙያዎች ፈታኝና ስጋት ያለበት ነው፡፡ምክንያቱም የኤሌክትሪክ ባለሙያዎች
በስነ ልቦና ጫና
ውስጥ ሆነው ነው
ቀን ከሌሊት እየሰሩ
ያሉት፡፡የኤሌክትሪክ ምሰሶዎችን ለመትከል
ተራራማና ገደላማ ቦታዎ
ውስጥ መግባትን ይጠይቃል፡፡የሰዓት
እላፊ የታወጀባቸው አካባቢዎች
ስላሉም በቂ ጊዜ
ያለማግኘት ችግርም አለ፡፡ሆኖም
በፈታኝ ሁኔታ ውስጥ
በመሆንም ክልሉ የአሌክትሪክ
አገልግሎት እንዲያገኝ እየተሰራ
መሆኑን፣ አቶ ሞገስ
ተናግረዋል፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 6/2013 | https://www.press.et/Ama/?p=37387 | 244 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ጁንታው ከመከላከያ ዘርፎ ለጥፋት ዓላማ ይጠቀምባቸው የነበሩ መሳሪያዎች ተጠግነው ወደ አገልግሎት እየተመለሱ ናቸው | ሀገር አቀፍ ዜና | December 15, 2020 | 47 | ጌትነት ተስፋማርያምጁንታው ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ዘርፎ ለጥፋት ዓላማው ሲጠቀምባቸው የነበሩ የተለያዩ መሳሪያዎች ተጠግነው ወደ አገልግሎት በመመለስ ላይ መሆናቸው ተገለጸ። የምዕራብ ግንባር የጥገና ኃላፊ ሌተናል ኮሎኔል አባተ ተስፋዬ እንደገለጹት፤ ጁንታው ከመከላከያ ሰራዊት ዘርፎ ለጥፋት ዓላማው ሲጠቀምባቸው የነበሩ በርካታ የሀገር ሀብቶች ከየመንገዱ እየተሰበሰቡ ተጠግነው ወደ አገልግሎት በመመለስ ላይ ናቸው። እንደ ሌተናል ኮሎኔል አባተ ገለጻ፤ ጁንታው ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም መከላከያ ሰራዊቱ ላይ ጥቃት ሲከፍት ታንኮች፣ መድፎች እና በርካታ ከባድ መሳሪያዎችን ዘርፏል። ከባድ መሳሪያዎቹን ከዘረፈ በኋላ ይዞ ለመዋጋት ቢያስብም በመከላከያ ሰራዊቱ ጥንቃቄ የተሞላበት እርምጃ እና በአየር ኃይል ኢላማቸውን የጠበቁ እርምጃዎች ምክንያት መሳሪያዎቹን እየጣለ ሊፈረጥጥ ግድ ሆኖበታል። አንዳንድ መሳሪያዎቹን በከፊል ሲያወድም የተቀሩትን ግን በየአስፓልት ዳሩ እና በየጫካው አስቀምጦ እግሬ አውጪኝ ብሏል። ከሃዲው ቡድን ከመከላከያ ሰራዊቱ የደረሰበትን እርምጃ መቋቋም ባለመቻሉ ከሽሬ አንስቶ እስከ ሽራሮ እና ተንቤን ድረስ በየመንገዱ ያንጠባጠባቸው ከባድ ተሽከርካሪዎች፣ የተለያየ አቅም ያላቸው መድፎች፣ ሎቤዶች እና ቢኤም መሳሪያዎች ተጓጉዘው ወደሽሬ የጥገና ማዕከል እየገቡ ይገኛሉ ያሉት ሌተናል ኮሎኔል አባተ፣ የጥገና ባለሙያዎችም መሳሪያዎቹን በመፈተሽ ዳግም ወደስራ ለማስገባት በመረባረብ ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል። በርካታ ከባድ መሳሪያዎች እና ተሽከርካሪዎችም ከጥገናቸው በኋላ የተሳካ ሙከራ ተደርጎባቸው ወደስራ መመለሳቸውን ሌተናል ኮሎኔል አባተ ተስፋዬ ተናግረዋል። ለመሳሪያዎቹ ጥገና አስፈላጊው ዝግጅት እና የመለዋወጫ አቅርቦት በሀገር ውስጥ መኖሩን የገለጹት ሌተናል ኮሎኔል አባተ፤ የመከላከያ ሰራዊቱ ንብረቶችን አጠቃላይ የጥገና ስራ ሙሉ በሙሉ በኀገር ውስጥ ባለሙያዎች እየተከናወነ እንደሚገኝ አስረድተዋል። ጁንታው አስቀድሞ ለጥፋት ዓላማው ዝግጅት በማድረጉ ከባድ መሳሪያዎችን የሚጠግኑ ባለሙያዎችንም ከሰራዊቱ ጋር አፍኖ መውሰዱን አስታውሰው፤ መከላከያ ሰራዊት ባደረገው ጥንቃቄ የተሞላበት እርምጃ ባለሙያዎቹን ከጁንታው ቡድን ነጻ ማውጣት መቻሉንም ገልጸዋል። አሁን ላይ ከተለያዩ ከተሞች የተሰባሰቡ የሰራዊቱ ባለሙያዎች አገልግሎቱን በተሳካ ሁኔታ በመስጠት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል። እንደ ሌተናል ኮሎኔል
አባተ ገለጻ፤ ጁንታው
ጥቅምት 24 ቀን
2013 ዓ.ም ላይ
በመከላከያ ሰራዊቱ ላይ
ጥቃት ከፈጸመ የሰሜን
እዝ የሰራዊቱ ንብረት
የሆኑ በርካታ ከባድ
መሳሪያዎችን ዘርፎ መውሰዱ ይታወሳል። ከባድ መሳሪያዎቹንም ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ለጥቂት ቀናት ህዝብ እና ሀገር ለማሸበር ሲጠቀምባቸው ቆይቷል። በመከላከያ ሰራዊት በቅንጅተ በወሰዱት እርምጃ መሳሪያዎቹ ተጠግነው ዳግም ለአገልግሎት መብቃታቸው የመልሶ ግንባታ እና የማደራጀት ስራዎች በተሳካ ሁኔታ በመከናወን ላይ ናቸው። ሌተናል
ኮሎኔል አባተ እንደገለጹት፤
ጁንታው በሀገር ሀብትና
ጉልበት የተሰሩ መንገዶችን
ሲቆፍርባቸው የነበሩ ዶዘሮች
እና የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች
እንዳይበላሹ የጥበቃ ስራ
እየተከናወነ ይገኛል። በጁንታው
የተበላሹ መንገዶችም ጊዜያዊ
ጥገና ተደርጎላቸው ከባድ
ተሽከርካሪዎች የሚፈለግባቸው ግዳጅ
እየተወጡ ይገኛል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 6/2013 | https://www.press.et/Ama/?p=37380 | 340 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ከዶሃው ቻምፒዮና ተምሮ ለቶኪዮ ኦሊምፒክ መዘጋጀት እንደሚያስፈልግ ተገለጸ | ስፖርት | October 23, 2019 | 8 | ከአንድ ዓመት ያነሰ ጊዜ ለቀረው የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ከወዲሁ ዝግጅት እንደሚደረግ ተገለጸ። በዶሃ የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ተሳታፊ ለሆነው ብሄራዊ ቡድንም ገንዘብ ሽልማት ተበርክቶለታል። የቶኪዮ ኦሊምፒክ በመጪው ሐምሌ ወር እንደሚካሄድ ይታወቃል። ለዚህ ውድድር ከወዲሁ ትልቅ ዝግጅት ማድረግ እንደሚያስፈልግ የዶሃው የዓለም ቻምፒዮና አመላካች እንደሆነ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አስታውቋል። ከትናንት በስቲያ ምሽት በዶሃ ለተሳተፈው ልዑክ በተደረገው የሽልማት ስነስርዓት፣ አትሌቶቹ በኳታር ከፍተኛ የሙቀት መጠን ተወዳድረው ያስመዘገቡት ውጤት የሚያስመሰግናቸው መሆኑ ተገልጿል። ይሁን እንጂ ከተስተዋሉት ጥቃቅን ስህተቶች ከፍተኛ ትምህርት በመውሰድ ከወዲሁ ቅድመ ዝግጅት ማድረግ እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ
ፌዴሬሽን ተቀዳሚ
ምክትል ፕሬዚዳንት
ኮማንደር አትሌት
ደራርቱ ቱሉ በሽልማት
ስነስርዓቱ እንደተናገረችው፣
በዶሃ የዓለም
አትሌቲክስ ቻምፒዮና
የተመዘገበው ውጤት ጥሩ
ቢሆንም የሚያኩራራ
ሳይሆን ለቶኪዮ
ኦሊምፒክ መንግስት፣
የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ
ኮሚቴ እንዲሁም
ፌዴሬሽኑ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተው ሊረባረቡበት እንደሚገባ አመላካች ነው። በ17ኛው የዶሃ የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ኢትዮጵያን በመወከል የተሳተፈው ቡድን፤ ሁለት የወርቅ፣ አምስት የብር እና አንድ የነሃስ በድምሩ ስምንት ሜዳልያዎች በመሰብሰብ ከዓለም አምስተኛ ከአፍሪካ ደግሞ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቁ ይታወሳል። በዕውቅና እና ሽልማት መርሃ ግብሩም ላይ የወርቅ ሜዳሊያ ያስመዘገቡ አትሌቶች 40 ሺ ብር፣ የብር ሜዳሊያ ያስመዘገቡ አትሌቶች 30ሺ ብር ተሸላሚዎች ሆነዋል። የነሐስ ሜዳሊያ ያስመዘገበችው ብቸኛዋ አትሌት ጉዳፍ ፀጋየ 20 ሺ ብር እንዲሁም ዲፕሎማ ላገኙና ተሳታፊ ለነበሩ አትሌቶች ማበረታቻ ገንዘብ ተበርክቷል። ለመርሃ ግብሩም በአጠቃላይ ከ2 ነጥብ 25 ሚሊየን ብር በላይ መውጣቱ ታውቋል። በሽልማት ስነስርዓቱ ላይ የኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የስፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀብታሙ ሲሳይ፣ የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ጌታቸው ባልቻ፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ፣ እንዲሁም የፌዴሬሽኑና የኦሊምፒክ ኮሚቴው ሥራ አስፈፃሚ አባላት ተገኝተዋል። ከሽልማቱ ባሻገር ኢትዮጵያውያን የአትሌቲክስ ባለሙያዎች በዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ዕውቅና ማግኘታቸውም ተጠቁሟል። በዚህም ፈር ቀዳጅ እና ውጤታማ የአትሌቲክስ አሰልጣኝ በሚል ዶክተር ወልደመስቀል ኮስትሬ ሲመረጡ፤ በርካታ አትሌቶችን ያፈራችው በቆጂ የስመጥር አትሌቶች መፍለቂያ በመባል ተወድሳለች። በተለየ መርሃ ግብር ደግሞ የቴክኒክ ዳይሬክተሩ አቶ ዱቤ ጅሎ በተሳለጠ የአትሌቲክስ አሰራር የዓለም አቀፍ ቬተራን ደረት ፒን እና የምስክር ወረቀት ከዓለም አትሌቲክስ ፕሬዚዳንት ሰባስቲያን ኮ እንደተበረከተላቸው ይታወሳል። አዲስ ዘመን ጥቅምት 12/2012 ብርሃን ፈይሳ | https://www.press.et/Ama/?p=21257 | 305 | 2ስፖርት
|
ቀዩ ትንቅንቅ ድሮም ዘንድሮም ወደ ፊትም አንድ ነው | ስፖርት | October 22, 2019 | 30 | ሁለቱን ከተሞች ከአንድ ሰዓት ያነሰ መንገድ ብቻ ያለያያቸዋል። ማህበራዊና ታሪካዊ ዳራዎች ያጠሉበት የማንቸስተርና ሊቨርፑል ከተሞች እግር ኳስ የዘላለም ተቀናቃኝ አድርጓቸዋል። የሰሜን ምዕራብ እንግሊዝን የበላይነት ለመቆጣጠር ሁለቱ ከተሞች ፍልሚያ ያደርጉ ነበር። ማንቸስተር በማኑፋክቸሪንግ ኢንደስትሪ ትመራለች፤ ሊቨርፑል በወደብ ከተማነት ትንቅንቅ ውስጥ ይገባሉ። ድንገት ግን የማንቸስተር የመርከብ መተላለፊያ መንገድ ታናል ተሠራና መርከቦቹ በቀጥታ ሊቨርፑል ከተማን ዘለው ዕቃዎችን ወደ ማንቸስተር ማጓጓዝ ቻሉ። የሊቨርፑል ነጋዴዎችና ህብረተሰቡ ኑሮው ቀነሰ፤ ሥራ አጦች በረከቱ፤ ቁጣም ተፈጠረ። ያ ክስተት በሁለቱ ከተማ ነዋሪዎች መካከል ልዩነትን ፈጠረ። ያም የከተማ ተቀናቃኝነት የኢኮኖሚ ሽኩቻ በቀላሉ ወደ እግር ኳስ ሜዳዎች ሰተት ብሎ ገባ። ሁለቱ ክለቦች «የእንግሊዝ ሀያሉ ክለብ እኔ ነኝ» በማለት ዛሬም ድረስ ይቆራቆዛሉ።ማንቸስተር ዩናይትድና ሊቨርፑል በጋራ 124 ዋንጫዎችን ጥርግርግ አርገው የመደርደሪያቸው ማድመቂያ አድርገዋል። ሊቨርፑል እኤአ ከ1975 እስከ 1990 11 የሊግ ዋንጫዎችን ያነሳባቸውን ዓመታት በኩራት ያነሳል። ማንቸስተር እኤአ ከ1993 እስከ 2013 ፍፁም በነገሠባቸውና 13 የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችን ባነሳባቸው ዓመታት በመኩራራት «የእንግሊዝ ሀያሉ ክለብ እኔ ነኝ»ይላል። ዩናይትድ 20 የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችን ሊቨርፑል 18 ዋንጫዎችን በማንሳት በታሪክ ተከታትለው ይጠራሉ። ዛሬም ድረስ ግን ሁለቱ ክለቦች የማይበርድ ውዝግብ ያደርጋሉ። ቀዩ ትንቅንቅ ድሮም ዘንድሮም ወደ ፊትም ተመሳሳይ ነው። እግር ኳስ ለሁለት የሰነጠቃቸው ሁለት ከተሞች ጉምቱ አሰልጣኞች ስድብ ያመርቱበታል፤ ገናና ተጫዋቾች ሁሌም ይተናነቁበታል። ኮከቦቻቸው አንጨባበጥም ያሉበት የእግር ኳስ ጦርነት ከሁለቱም አቅጣጫ እሳት በየዘመኑ ይወረወራል። ጨዋታው የ90 ደቂቃ ብቻ አይደለም። ከዚያ የዘለለ ትርጉም ይሸከማል። በተቀናቃኞቻቸው የሞት ክስተት ላይ እንኳን ሹፈትን ለመፍጠር የማይመለሱ ነውጠኛ ደጋፊዎች የሚታዩበት፤ ታሪክም ወቅታዊ ሁኔታም ጋዝ ሆነው የሚያቀጣጥሉት፤ አሰልጣኞችም ተጨዋቾችም ከስሜት የማይፀዱበት፤ ልጅም አዋቂም እኩል ጎራ ከፍለው የሚሻኮቱበት፣ የፖለቲካም የኢኮኖሚም የስፖርት የበላይነት ጥያቄም ያልተለየው የእግር ኳስ ጦርነት። «ቀዩ ትንቅንቅ።» ሁለቱ ቀያይ ለባሾች
አንዱ አንዱን አምርሮ
ከመጥላቱ ባሻገር በተራ
ጨዋታ መሸናነፍ እንደሞት
ይቆጥሩታል። ዋንጫ በሌለበት
እንኳን ማሸነፋቸው እንደ
ዋንጫ ማንሳት ይቆጠርላቸዋል።
«የኔ ፈተና አንድ
ብቻ ነው ሊቨርፑልን
ሁሌም በሚኩራሩበት ሜዳ
መደቆስ፤ ከዛ ቀሪውን
እናንተ ትፅፉታላችሁ» በማለት
ታላቁ የዩናይትድ አሰልጣኝ
ሰር አሌክስ ፈርጉሰን
በአንድ ወቅት ለጋዜጠኞች
የሰጡት አስተያየት የክለቦቹን
ሽኩቻ ቁልጭ አድርጎ
ያሳያል። «እኔ ስለ
ሊቨርፑሎች ምን አገባኝ?፤
ደጋፊያቸው፤ ስታዲየማቸው ምናቸውም
ደስ አይለኝም፤ እነሱን
ስናሸንፍ የሚሰማኝን ደስታ
እኔ ብቻ ነኝ
የማውቀው» ያለበት የዩናይትዱ
ታሪካዊ ተጫዋች ጋሪ
ኔቭል ንግግርም የሚዘነጋ
አይደለም። የቅርቡ ኮከባቸው
ዋይኒ ማርክ ሩኒም
ቢሆን «ያደግኩት ሊቨርፑልን እየጠላሁ ነው» ማለቱ እስከአሁን ክለቡን ለቆ እንኳን ጥርስ አስነክሶበታል። ወደ አንፊልድ መንደርም ይህ መሪር ጥላቻ ተመሳሳይ ነው። በአንድ ወቅት ታሪካዊው ኮከባቸው ስቴቭን ጀራርድ ወደ መኖሪያ ቤቱ አንድ የቀረፃ ቡድን ይዞ ሄደ። «እነዚህ የምትመለከቷቸው መለያዎች በርካታ የተቃራኒ ክለብ መለያዎች ሲሆኑ ከጨዋታ በኋላ የተቀያየርኳቸው መለያዎች ናቸው፤ ግን አንድም የዩናይትድ መለያ አታገኙም፤ አንድም የዩናይትድ መለያ ቤቴ አይገባም» ያለበት አጋጣሚ ጥላቻው ከእግር ኳሳዊ ጉዳይ የዘለለ ምክኒያት ያለው አስመስሎት ነበር። ሉዊስ ሱዋሬዝ ፓትሪስ
ኤቭራን ያልጨበጠበት፤ ሪዮ
ፈርዲናንድና ዳኒ ዌልቤክ
ሱዋሬዝን አንተ አትጨብጠንም
በማለት አፀፋ የሰጡበት
ክስተት የቅርብ ጊዜ
ትውስታ ነው። ተጫዋቾች
በቀዩ ትንቅንቅ ስሜታቸውን
የሚገልጹበት መንገድ የተለየ
ነው። ኳስና መረብ
ሲያገናኙ ደስታቸውን ለመግለጽ
ሜዳው አይበቃቸውም። ሲበለጡ
ሽንፈትን በፀጋ የመቀበል
ክህሎታቸው ይከዳቸዋል። ሁሌም ከሜዳ ውጪ የሚጫወተውን ክለብ ለመደገፍ ትኬት ማግኘት ከባድ ነው። ቀድሞ ትኬት ይጠናቀቃል። በጠላት ድንበር ገብተህ እንደመዘመርና እንደ መቦረቅ ምን የሚያስደስት ነገር አለ የሚሉ ደጋፊዎች ብዙ ናቸው። ኦልድ ትራፎርድን ህልም እውን የሚሆኑበት፤ አንፊልድን የታማኝ ደጋፊዎች ህብረ ድምፅ ሌላ ዓለም የሚያስመስላቸው ያኔ ነው። በቀዩ ትንቅንቅ በጨዋታ ወቅት በሚፈጠሩ ነገሮች ሁሉ በብስጭት የተገኘ ነገር ሁሉ ይወረወራል። ፈርጉሰን በሊቨርፑል ደጋፊዎች በእንቁላል ተደብድበዋል። በ2011 የታዳጊዎች ኤፍ ኤ ጨዋታ ተቋርጧል፣ ብዙ ብዙም ነገር ተከስቷል። የሁለቱን ክለቦች የመረረ ጥላቻ የሚያሳይ ሌላም መገለጫ አለ። እኤአ በ1964 ፊል ቼዝናል የተባለ ተጫዋች ከዩናይትድ ወደ ሊቨርፑል ከተዛወረ በኋላ ባለፉት ከሃምሳ አራት ዓመታት በላይ በሁለቱ ክለቦች መካከል አንድም የተጫዋቾች ዝውውር በቀጥታ ተፈፅሞ አያውቅም። ሊቨርፑል በአሰልጣኝ የርገን
ክሎፕ እየተመራ የቻምፒዮንስ
ሊግ ዋንጫን አምና በማንሳት ወደ ኃያልነቱን ለመመለስ መንገድ ጀምሯል። ከሃያ ስምንት ዓመታት በኋላ ፕሪሚየርሊጉ ላይ መንገሥም ወደ ኃያልነቱ ለመመለስ ትልቅ ዋጋ አለው። ከስምንት ጨዋታዎች ሙሉ ሃያ አራት ነጥብ በመሰብሰብ የመጡበት ወጥ አቋም በታሪካዊው ተቀናቃኛቸው እንደማይገታ የብዙዎች እምነት ነበር። በተለይም ዩናይትድ ከስምንት ጨዋታ ዘጠኝ ነጥብ ብቻ ይዞ እጅግ በደከመ አቋም መገኘቱ ብዙዎች ከትናንት በስቲያ በተደረገው ቀዩ ትንቅንቅ በርካታ ግብ እንዳያስተናግዱ ስጋት ፈጥሮባቸው ነበር። ያምሆኖ ቀዩ ትንቅንቅ ትናንትም፣ ዛሬም፣ ነገም አንድ ነውና ዩናይትዶች እንደተፈራው የግብ ናዳ ሳይወርድባቸው አንድ ለአንድ በሆነ ውጤት የሊቨርፑልን መቶ በመቶ የአሸናፊነት ጉዞ መግታት ችለዋል። ባለፉት ስምንት ሳምንታት ለትናንሽ ክለቦች እንኳን ሲያንቀላፉ የነበሩት ዩናይትዶች ለታሪካዊ ተቀናቃኛቸው እንደማይተኙ አሳይተዋል። ይህም የተነቃነቀው አሰልጣኛቸው ሶልሻየር ወንበር ለጊዜውም ቢሆን ረግቶ የሚቆይ አስመስሎታል።አዲስ ዘመን ጥቅምት 11/2012 ቦጋለ
አበበ | https://www.press.et/Ama/?p=21221 | 656 | 2ስፖርት
|
ጫማ ሰቅለው ጓንት ያነሱ፤ ከሩጫም ወደ ኳስ ያቀኑ ኮከቦች | ስፖርት | October 14, 2019 | 39 | ልምምድን አድምቶ በመስራትና በጥንካሬ በመቆየት የመጨረሻዋን መስመር በቀዳሚነት መርገጥ ዋጋው ከደስታም ይልቃል። ሃገርን ማስጠራት እንዲሁም ክብርን መቀዳጀት ደግሞ የስኬታማነት ክፍያው ነው። እንደ አትሌቶቹ ሁሉ፤ ልምምድን በትጋት መልሶ መላልሶ መስራት የግድ ነው፤ በየትኛውም ስፖርት ከውጤት ማድረሱም እውነት ነው። ባሉበት ስፖርት በታማኝነት ጊዜን፣ ጉልበትንና አቅምን አሟጦ መጠቀምም አስፈላጊ ነው። ነገር ግን ስኬትን ከተቀዳጁበት አንድ ስፖርት ወደ ሌላ በመሸጋገር በድጋሚ ውጤታማ መሆን ይቻላል? ከተጫዋችነት አሊያም ከአትሌትነት ወደ አሰልጣኝነት እንዲሁም ወደ አማካሪነትና ሌሎች ስራዎች መሸጋገር የተለመደ ነው። ጫማ ሰቅሎ የቦክስ ጓንት ማጥለቅ፣ ከመም ወደ እግር ኳስ ሜዳ መሸጋገር እንዲሁም ጓንት ሰቅሎ የበረዶ ላይ ገና ጨዋታ ዱላን ማንሳት ግን አደናጋሪ ነው። ዋናው ጥያቄም እውን እጅግ በተለያዩ ሁለት ስፖርቶች በቀላሉ ስኬታማነትን ማግኘት ይቻላል? የሚለው ይሆናል። ለዚህ ጥያቄ ምላሽ ለማግኘት ጥናት ማድረግን ቢጠይቅም፤ ለዛሬ ከአንዱ ወደ ሌላኛው ስፖርት የተሸጋገሩ ስፖርተኞችን እናንሳ። «በርካታ ዋንጫዎችን አንስቻለሁ፤ አሁን ግን ቀበቶ ማግኘት እፈልጋለሁ» በሚል ነበር የተነሳው። ይህ የሁለት ክብሮች ናፋቂ የእንግሊዝን ብሄራዊ ቡድንን ለ14ዓመታት በተለይ የታወቀበትን ክለብ ማንቸስተር ዩናይትድን ደግሞ ለ12ዓመታት ያገለገለው ሪዮ ጋቪን ፈርዲናንድ ነው። በአራት ክለቦች ሁለት አስርት ዓመታትን በተጫዋችነት ያሳለፈው ፈርዲናንድ፤ በእንግሊዛውያን ዘንድ የምንጊዜም ተወዳጅነትን ካተረፉ ተጫዋቾች መካከል ተጠቃሽ ነው። ስድስት የፕሪምየር ሊግ፣ አንድ የቻምፒዮንስ ሊግ፣ አንድ የፊፋ የክለቦች እንዲሁም ሌሎች ዋንጫዎችን ጨምሮ በርካታ ክብሮችንም በግሉ እና በቡድን አግኝቷል። በ39ዓመቱ የእግር ኳስ ሜዳን ሲሰናበት ግን የቦክስ መፋለሚያ ሪንግን እያሰበ ነበር። በሰቀለው ጫማ ምትክም ጓንት ማጥለቁ መነጋገሪያ አድርጎታል፡፡ በፕሮፌሽናል ቦክሰኛነት በከባድ ሚዛን ለመሳተፍ በሳምንት ከ4-5 ቀናት ልምምድ እንደሚያደርግም አስታወቀ። ነገር ግን በፕሮፌሽናል የቦክስ ማህበር በኩል «ብቁ ነህ» የሚል ማረጋገጫ ማግኘት ሳይችል ቀረ። በዚህ ምክንያትም ማዘኑን «ቦክስ ሰውነት ብቻም ሳይሆን ጠንካራ ልብ ነው የሚፈልገው» ሲል ነበር የገለጸው። የእግር ኳስ ተንታኝ የሆነው አንጋፋው ተጫዋች እንዲያም ቢሆን ፈቃዱን ለማግኘት ጥረቱን እንደማይተውና ጠንክሮ እንደሚሰራ አረጋግጧል። ጃማይካዊው የዓለም ፈጣኑ ሰው ደግሞ ከመም በቀጥታ ወደ እግር ኳስ ማንከባለል የገባ ስፖርተኛ ነው። የሰው ልጅ በዚህን ልክ ይፈጥናል ተብሎ ባይጠበቅም በአጭር ርቀት አትሌቲክስ አዲስ ታሪክ ያስመዘገበው ቁመተ መለሎውና ቀልደኛው ዩሲያን ቦልት ስምንት የኦሊምፒክ ሜዳሊያዎችን ጠራርጎ በመውሰድ ስኬታማ ነው። ቦልት 100 ሜትርን በ9ሰከንድ ከ58 ማይክሮ ሰከንድ፣ 200ሜትርን ደግሞ 19ሰከንድ ከ19ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት በመግባት የዓለምን ክብረወሰን አርቆ የሰቀለ አስደናቂ አትሌት ነው። ቦልት ከታወቀበት አትሌቲክስ ባሻገር እግር ኳስን እጅግ የሚወድ እንዲሁም የሚመኘውም ስፖርት ነው። የእንግሊዙ ማንቺስተር ዩናይትድ ክለብ ደጋፊ የሆነው አትሌቱ የቀያዮቹ ሴጣን ተጫዋች የመሆን ህልም እንዳለውም ይናገር ነገር። እአአ ከ2017ቱ የለንደን የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና በኋላም ከአትሌቲክስ ስፖርት ወጥቶ ወደ እግር ኳስ መግባቱን አሳወቀ። የእግር ኳስ ልምምዱን በቅድሚያ የጀመረው በኖርዌይ ክለብ ሲሆን፤ የዓለምን ክብረወሰን ያስመዘገበበትን 9.58 የሚያስታውስ ማሊያ ይለብስ ነበር። ከቆይታ በኋላም የአውስትራሊያውን ሴንትራል ኮስት ማሬነርስ የተባለውን ክለብ ተቀላቀለ፤ በመጀመሪያው የወዳጅነት ጨዋታም ሁለት ግቦችን ማስቆጠር ቻለ። ነገር ግን ብዙም ሳይቆይ ከስፖርት ህይወት ሙሉ ለሙሉ ወጥቶ ወደ ንግድ መግባቱን ይፋ አደረገ። ለበርካታ ጊዜያት ጾታዊ ጥርጣሬ ውስጥ በመግባት አስቸጋሪ ጊዜን መግፋት የግድ የሆነባት ደቡብ አፍሪካዊቷ አትሌት ካስተር ሰመኒያም በቅርቡ ከአትሌቲክስ ስፖርት እግር ኳስን እንደመረጠች አስታውቃለች። በተክለ ቁመናዋ ምክንያት በርካታ ፈተናዎችን ለመጋፈጥ የተገደደችው የ800 ሜትር የኦሊምፒክ ቻምፒዮናዋ ሰመኒያ ዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ያወጣውን ደንብ ተከትሎ በክስ ሂደት መቆየቷ ይታወሳል። ነገር ግን እሰጣ አገባው እንዳሰበችው ሆኖ ባለመጠናቀቁ፤ በልጅነቷ ታንከባልል እንደነበር ወደ ገለጸችው ኳስ ገብታለች። በሃገሯ የሚገኝን ክለብ የተቀላቀለችው ተጫዋቿ አዲሱ የጨዋታ ዘመን እስኪጀመር በልምምድ ላይ የምትቆይ መሆኗን ተከትሎ «ይሻላል» ባለችው እግር ኳስ ያላትን ብቃት ማስመስከር አልቻለችም። ከሰሞኑ በተሰማ ሌላ ዜና ደግሞ የቀድሞው ግብ ጠባቂ ፒተር ቼክ በጓንቱ ፋንታ የበረዶ ላይ ገና ጨዋታ ዱላ ወደ ማንሳት መሸጋገሩን አስታውቋል። በተለይ በሰማያዊዎቹ እና በመድፈኞቹ ቤት ቆይታው የሚታወቀው ግብ ጠባቂው ጓንቱን ከሰቀለ በኋላ በቀድሞ ክለቡ ቼልሲ የቴክኒክ አማካሪ በመሆን እያገለገለ ይገኛል። ከዚህ ስራው ጎን ለጎንም በልጅነቱ የተጫወተውንና የሚወደውን ይህንን ስፖርት ተቀላቅሏል። እንደ ግብ ደጀንነቱ ሁሉ በዚህ ስፖርትም ስኬታማ መሆን አለመሆኑም ጊዜ ምላሽ ይሰጥበታል።አዲስ ዘመን ጥቅምት 3/2012ብርሃን ፈይሳ | https://www.press.et/Ama/?p=20763 | 561 | 2ስፖርት
|
የሲቲ ካፕ ጨዋታዎች በቅርቡ ይጀመራሉ | ስፖርት | October 18, 2019 | 18 | የ2012 ዓም ፕሪሚየር ሊግ ቅድመ አቋም መለኪያ ውድድሮች በተያዘው ወር አጋማሽ ይጀመራሉ። የአዲስ አበባ እና የደቡብ ክልል የቅድመ ውድድር ዘመን ጨዋታዎች ዝግጅትም ተጠናክሮ ቀጥሏል። ክለቦች የውድድር ዘመኑ ከመጀመሩ አስቀድሞ
የአቋም መለኪያ ጨዋታዎችን እንደሚያደርጉ ይታወቃል። በኢትዮጵያም የተለያዩ ክለቦችን በማሳተፍ ከተማ አቀፍ (ሲቲ ካፕ) ጨዋታዎችን
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከመጀመሩ አስቀድሞ ማካሄድ የተለመደ ነው። ረጅም ዓመታትን ካስቆጠሩት ውድድሮች መካከል በአዲስ አበባ
እግር ኳስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት የሚካሄደው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ቀዳሚው ሲሆን፤ ዘንድሮም ለ14ኛ ጊዜ ይካሄዳል። በዚህም መሰረት ውድድሩ በተያዘለት መርሐ ግብር ከጥቅምት 22 እስከ ህዳር 7/2012ዓ.ም እንደሚካሄድ
ሶከር ኢትዮጵያ በዘገባው ጠቁሟል። በውድድሩም ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ መከላከያ፣ ኤሌክትሪክ፣ ወልቂጤ እና ሰበታ
ከተማ ተሳታፊነታቸው ተረጋግጧል። የኢኮስኮ እና የኢትዮጵያ መድን ተሳታፊነት አጠራጣሪ ሲሆን፤ ሲዳማ ቡና እና ባህርዳር ከተማ ተሳታፊ
ሊሆኑ እንደሚችሉ ይጠበቃል። የዚህን ዓመት ውድድር ልዩ የሚያደርገውም በሽልማት እንዲሁም በተለያዩ ነገሮች ላይ ማሻሻያ በማድረጉ
እንደሆነም በዘገባው ተመላክቷል። አሸናፊ በመሆን ዋንጫውን ለሚያነሳው ክለብ ብቻም ሳይሆን በደረጃ ለሚያጠናቅቁት ክለቦችም ከፍተኛ
የገንዘብ ሽልማት የሚበረከትላቸው ሲሆን፤ ሌሎች ክለቦችም በተሳታፊነታቸው ብቻ በስጦታ መልክ ገንዘብ የሚበረከትላቸው ይሆናል። የስታዲየም
መግቢያ ትኬቶችን እንዲሁም ሌሎች ሥራዎችንም በዘመናዊ መልኩ ለማከናወን ጥረት በመደረግም ላይ ይገኛል። ከዚህም ባሻገር ውድድሩ የመገናኛ ብዙሃን የቀጥታ ሽፋን እንደሚያገኝ ታውቋል፡፡ በከተማ አስተዳደሩ
ስር የሚገኘው ቴሌቪዥን ጣቢያ ከእጣ አወጣጡ ጀምሮ የተመረጡ ጨዋታዎችን ሽፋን በመስጠት ለህዝቡ የሚያደርስም ይሆናል። ሌላኛው የደቡብ ሪጅናል ካስቴል ዋንጫ ሲሆን፤ ከጥቅምት 15 ጀምሮ በሃላባ ቁሊቶ ከተማ የሚካሄድ
መሆኑን የሶከር ኢትዮጵያ ዘገባ ጠቁሟል። ዘንድሮ ለሰባተኛ ጊዜ የሚካሄደው ይህ ውድድር አስር ክለቦችን እንደሚያሳትፍ የክልሉ እግር
ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። የፕሪምየር ሊጉ ተሳታፊ የሆኑት የክልሉ ክለቦች፤ ሃዋሳ ከተማ፣ ሲዳማ ቡና፣ ወልቂጤ ከተማ እና ሃዲያ
ሆሳዕና ተሳታፊ ናቸው። ከከፍተኛ ሊግ ደግሞ ደቡብ ፖሊስ እና አርባ ምንጭ ከተማ ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ጅማ አባጅፋር፣
አዳማ ከተማ እና ሰበታ ከተማ በተጋባዥነት እንዲሳተፉ ጥሪ ተደርጎላቸዋል። በከፍተኛ
ሊግ ክለቦች መካከል የሚካሄደው ውድድር ደግሞ በቀጣዩ ህዳር ወር የሚካሄድ ይሆናል። በቢጂአይ ኢትዮጵያ ስፖንሰርነት የሚካሄደውን
ይህንን ውድድር፤ በሆሳዕና ከተማ ለማድረግ ቢታቀድም ሜዳው በዕድሳት ላይ በመሆኑ ለውጥ ተደርጎበታል። ውድድሩን በተሻለ መልኩ ለማስኬድም
ፌዴሬሽኑ ቅድመ ዝግጅቱን አጠናክሮ ቀጥሏል። አዲስ ዘመን ጥቅምት 7/2012 ብርሃን ፈይሳ | https://www.press.et/Ama/?p=20994 | 312 | 2ስፖርት
|
ጅት ኩን ዶ- የገሃዱ ዓለም ፍልሚያ | ስፖርት | October 14, 2019 | 60 | ተወዳጅ ከሆኑ የፍልሚያ ስፖርቶች መካከል ጅት ኩን ዶ በቀዳሚነት ይጠቀሳል፡፡ በኢትዮጵያ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የተለያዩ የፍልሚያ ስፖርቶች በርካታ ተከታዮችን በተለይም ወጣቶችን ከማፍራት አልፈው በዓለም አቀፍና አገር አቀፍ ደረጃ ውጤት ማስመዝገብ ችለዋል፡፡ ወርልድ ቴኳንዶና ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ በዚህ ረገድ ረጅም ርቀት የተጓዙ የፍልሚያ ስፖርቶች ሆነው ይገኛሉ፡፡ በፍልስፍና እንዲሁም በእንቅስቃሴ ደረጃ የተለየና የገሃዱ ዓለም ፍልሚያን መሬት ማውረድ የቻለው ጅት ኩን ዶ በዝነኛው የማርሻል አርት ንጉስና ተዋናይ ብሩስ ሊ እንደተፈለሰፈ ይነገራል፡፡ ይህ እንቅስቃሴ እንደሌሎቹ የፍልሚያ ስፖርቶች በኢትዮጵያ በስፋት ሲዘወተርና ሲወራለት አይታይም፡፡ ማስተር ኤርሚያስ ገሰሰ ጅት ኩን ዶ ከሌሎች የማርሻል አርት እንቅስቃሴዎች የሚለየው በሳይንሳዊ ፍልስፍናው መሆኑን ይናገራል፡፡ ጅት ኩን ዶ በገሃዱ ዓለም ፍልሚያ ላይ እንደሚያተኩር የሚያብራራው ማስተር ኤርሚያስ፤ ሰዎች ራሳቸውን እንዲሆኑና ራሳቸውን እንዲገልፁ ያስችላቸዋል ይላል፡፡ በስፖርቱ ከሃያ አምስት ዓመታት በላይ ያሳለፈው ማስተር ኤርሚያስ ገርጂና መገናኛ አካባቢ በሁለት ቅርንጫፎች በከፈተው የጅት ኩን ዶ ስፖርት ክለብ በርካታ ወጣቶችን እያፈራ ይገኛል፡፡ በአሁኑ ወቅትም ከሁለት መቶ በላይ ወጣቶችን እያሰለጠነ ይገኛል። ጅት ኩን ዶ እንደሌሎች የፍልሚያ ስፖርቶች በአገራችን እንዳልተሰራበት ይናገራል፡፡ በስፖርቱ ሙያተኞች ቢኖሩም ፍላጎት ከማጣትም ሊሆን ይችላል በሌሎች መሰናክሎች በአገራችን ስፖርቱን ለማስፋፋት ሲሰሩበት አይስተዋልም፡፡ ጥቂት እንደ ማስተር ኤርሚያስ ያሉ ባለሙያዎች ግን ስፖርቱን ለማስፋፋት ጠንክረው እየሰሩ መሆኑን መካድ አይቻልም፡፡ ጅት ኩን ዶ እንደሌሎቹ የማርሻል አርት ስፖርቶች ሁሉ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚያንቀሳቅሰው ፌዴሬሽን አለው፡፡ የዚህ ስፖርት መታሰቢያነቱ የማርሻል አርት ንጉሱ ቻይናዊው ብሩስ ሊ መሆኑን ማስተር ኤርሚያስ ይናገራል፡፡ በዚህ እንቅስቃሴ ዋናው ትምህርት ፍልሚያ ላይ የሚያተኩር ሲሆን ሰዎች የሚመዘኑትም በፍልሚያ ነው፡፡ሰዎች ምን ያህል ተጋጣሚያቸውን ማጥቃት ይችላሉ፣ ምን ያህልስ ራሳቸውን መከላከል ይችላሉ? የስፖርቱ ዋና መመዘኛ መሆኑን ማስተር ኤርሚያስ ያብራራል፡፡ በዚህ ስፖርት እንቅስቃሴ ውስጥ የነጠላ ወይም አንድ ለአንድ ፍልሚያ፣ ሁለትና ሦስት ለአንድ ፍልሚያ እንዲሁም የቡድን ፍልሚያ የሚታወቁ ሲሆን እንቅስቃሴዎች በባዶ እጅ፣በመሳሪያና ሌሎችም በገሃዱ ዓለም ያሉ ፍልሚያዎችን ያካተተ ነው፡፡ ፍልስፍናውም በጥልቀት የሚሰራው እዚሁ ላይ ነው፡፡ በአገራችን ጅት ኩን ዶ በፌዴሬሽን ደረጃ በጥምር ማርሻል አርት ፌዴሬሽኖች ውስጥ ተካቶ ውድድሮችንም እያካሄደ ይገኛል፡፡ ጅት ኩን ዶ በአገራችን ከጥምር ማርሻል አርት ፌዴሬሽን ተነጥሎ ራሱን ችሎ ለመቋቋም የሰዎች አለማግባባትና የአሰልጣኞች አለመትጋትና የሚጠየቁ መስፈርቶች ውስብስብ መሆን እንቅፋት እንደሆነ ማስተር ኤርሚያስ ያስረዳል፡፡ ጅት ኩን ዶ ራሱን ችሎ በፌዴሬሽን ደረጃ ለመውጣት በተለይም የሚጠየቀው መስፈርት ከባድ መሆኑን ይናገራል፡፡ በአንድ ክፍለ ከተማ ሦስትና ከዚያ በላይ ክለቦችን የሚጠይቅ መስፈርት ከባለሙያ እጥረት ጋር ትልቁ ችግር መሆኑንም ያስቀምጣል፡፡ የስፖርቱ ባህሪ በራሱ አስቸጋሪና ውስጡ መቆየትን የሚጠይቅ መሆኑን የሚያስቀምጠው ማስተር ኤርሚያስ የኑሮ ውጣውረድና ሌሎችም ፈተናዎች ወጣቱን በሚፈለገው መጠን በስፖርቱ እንዲያልፍ አላስቻለውም ባይ ነው፡፡ ይህም ስፖርቱን እንዳይስፋፋ አድርጎታል፡፡ ወርልድ ቴኳንዶን በመሳሰሉ ስፖርቶች በርካታ ወጣቶች በዓለም አቀፍና አህጉር አቀፍ ውድድሮች አገራቸውን ወክለው ትልቅ ውጤት ከማስመዝገብ ባሻገር ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን መጥቀም እየቻሉ ነው፡፡ ጅት ኩን ዶ ለሚያዘወትሩት ወጣቶች እንደ ወርልድ ቴኳንዶ ሁሉ አገርን በመወከልና ጥቅም በማግኘት ረገድ ያለውን ተስፋ ማስተር ኤርሚያስ ሲናገሩ ‹‹በፊት ለፊት የሚታይ ነገር የለም፣ነገር ግን የእኛ ጥረት ይሄን ይለውጠዋል፣ አሁን በአገራችን ጥሩ መነሳሳት አለ፤በተለይ በከተማችንና በክፍለ ከተሞች ደረጃ በስፖርቱ ተነሳሽነት አለ፤ ማንኛውንም ስፖርት ለማስፋፋት ባለሙያዎች እየተጠሩና እያወያዩ ነው፣ ይሄን ማሳደግና በፌዴሬሽን ደረጃ ራሱን እንዲችል ማድረግ ከተቻለ ዓለም አቀፍ ግንኙነቶችንም መፍጠር ይቻላል፣ይህም ወጣቶች በዓለም አቀፍ ውድድሮች ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል›› በማለት ስፖርቱ ያለውን ተስፋ ያብራራል፡፡ ኤርሚያስ ገሰሰ ጂምና ማርሻል አርት ማዕከል ወጣቶችን በጅት ኩን ዶ እንቅስቃሴ ከማብቃት ጎንለጎን የበጎ አድራጎት ስራዎችን እንደሚሰራም ማዕከላቱ በሚገኙበት አካባቢ ይታወቃል፡፡ የበጎ አድራጎት ስራ ከማርሻል አርት ስፖርት ጋር አብሮ እንደሚሄድ የሚናገረው ማስተር ኤርሚያስ፤ ወጣቶች ማርሻል አርትን ሲማሩ የስነምግባር ትምህርትም አብሮ እንደሚሰጣቸው ያብራራል፡፡ ይህ የስነ ምግባር ትምህርት መገለጫው በጎ ተግባር ነው፡፡ 1995 ዓ.ም አካባቢ የተማሪ ቤተሰቦች፣በጎ ፍቃደኞችና ሌሎችም በጋራ ሆነው የስፖርቱን እንቅስቃሴ ሲጀምሩ ገንዘብ በማዋጣት ጎዳና ላይ ያሉ ወገኖችን በምግብ፣በአልባሳት ድጋፍ ከማድረግ ባሻገር በዘላቂነት በማቋቋም መደበኛ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ እየተደረገ ይገኛል፡፡ የበጎ አድራጎት ስራውን ከስፖርቱ ባሻገር ለማስፋት በቅርቡ ‹‹ጳጉሜን 5 የበጎ አድራጎት ድርጅት›› በሚል ስያሜ በማሳደግ እውቅና አግኝቶ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ በየዓመቱም የትንሳዔን በዓል ምክንያት በማድረግ በጎዳና ላይ ያሉ ወገኖችን የመመገብ፣አልባሳትንና ገንዘብ የመስጠት መርሃግብሮችን ያካሂዳል፡፡ መማር የሚችሉ እንዲማሩ፣መስራት የሚችሉ እንዲሰሩ ማድረግም አንዱ ተግባር ነው፡፡ በዚህም የበርካታ ወጣቶችን ሕይወት መለወጥ ተችሏል፡፡አዲስ ዘመን ጥቅምት 3/2012 ቦጋለ አበበ | https://www.press.et/Ama/?p=20759 | 593 | 2ስፖርት
|
የኮርፖሬሽኑ ተምሳሌታዊ የስፖርት ፖሊሲ ትግበራ | ስፖርት | October 17, 2019 | 19 | በ1990 ዓ.ም. በአገር አቀፍ ደረጃ የወጣው የስፖርት ፖሊሲ ሕዝቡ በሚኖርበት፣ በሚማርበትና በሚሰራበት አካባቢ ስፖርት እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚገባው ይደነግጋል። ህብረተሰቡ በሚኖርበት፣ በሚማርበትና በሚሠራበት አካባቢ በስፖርት እንቅስቃሴ ተሳታፊ የሚሆንበት መንገድ መመቻቸት እንዳለበት ያስቀምጣል። ከመንግሥት ተቋማት እስከ ታችኛው የኅብረተሰብ ክፍል በየደረጃው ኅብረተሰቡ ለሚሳተፍባቸው መድረኮች ትኩረት በማድረግ ልሂቃን (ኤሊቶች) የሚፈጠሩበት ዕድል እንዳለም ፖሊስው ያመለክታል። በሌላ በኩል አምራች ዜጋ ለመፍጠር፣ የኅብረተሰቡ ማኅበራዊ ግንኙነት የሚዳብርበት፣ ከዚያም ሲያልፍ ዜጎች ጤንነታቸውን ለመጠበቅና ለመዝናናት እንዲሁም አካላቸውን ለማጎልበትና አዕምሯዋቸውን ለማበልጸግ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ታምኖበታል። የስፖርት ፖሊሲውን መሰረት በማድረግ የሕብረተሰቡን ተሳትፎ በማስፋት ረገድ እየተሄደበት ያለው መንገድ አጥጋቢ አለመሆኑ ተደጋግሞ ይነሳል። በመንግስትም ሆነ በህብረተሰቡ በኩል እንደሚነሳው «ሕዝቡ በሚኖርበት፣ በሚማርበትና በሚሰራበት አካባቢ የስፖርት እንቅስቃሴ ማድረግ አለበት»በሚል በፖሊሲ ደረጃ ቢቀመጥም ወደ ተግባር ከመለወጥ አንጻር ከፍተኛ ክፍተት መኖሩ ይታመናል። በተለይ በመንግስትና በግል ተቋማት ህብረተሰቡ በሚሰራበት ቦታ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ እንዲያደርግ እድል በመፍጠር ረገድ የፍላጎትም ሆነ የግንዛቤ ክፍተቶች እንዳሉ በስፖርቱ አዋቂዎች በኩል ይነገራል። በተቋማት የስፖርቱን ማህበራዊም ሆነ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳን በመረዳት ስፖርታዊ ክንውኖችን የማዘጋጀት ባህሉ በእጅጉ አናሳ መሆኑም አብሮ ይነሳል። መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት በኩል የስፖርቱን ዘርፈ ብዙ ፋይዳ በመረዳት የስፖርት ፌስቲቫል የማዘጋጀት ልምድ ባለቤት የሆኑ ተቋማት በጣት የሚቆጠሩ ናቸው። ከእነዚህ ተቋማት መካከል የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በግንባር ቀደምነት ይጠቀሳል። የቤተሰብ ስፖርት ፌስቲቫሉ ዘንድሮ ለ5ኛ ጊዜ ከመስከረም 26 ጀምሮ ለአስር ቀናት ያክል «የኋላውን እያደስን የወደፊቱን ለመገንባት እንተጋለን »በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ይገኛል። የኮርፖሬሽኑ የቤተሰብ ስፖርት ፌስቲቫል በ2002 ዓ.ም እንደተጀመረ መረጃዎች ያመላከታሉ ። ኮርፖሬሽኑ በሚያከናውነው የስፖርት ፌስቲቫል፤ አገር አቀፍ የስፖርት ፖሊሲውን ተግባራዊ ከማድረግ ባሻገር በሰራተኞች መካከል መቀራረብን እንደሚፈጥር ታምኖበታል። የስፖርት ፌስቲቫሉ ጤናው የተጠበቀና አምራች ዜጋን በማፍራት ውጤታማ መሆን እንደሚቻል ማሳያ መሆኑም ተጠቁሟል። የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የቤተሰብ ስፖርት ፌስቲቫል አስተባባሪ አብይ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ጥንፉ ሙጬ፤ የስፖርት ፌስቲቫሉ በአገር አቀፍ ደረጃ የወጣውን የስፖርት ፖሊሲ መሰረት በማድረግ የተጀመረ መሆኑን ይናገራሉ። ህዝቡ በሚኖርበትና በሚሰራበት አካባቢ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነቱን ማጉላት እንደሚችል መሰረት ባደረገ መልኩ ተቋሙ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑንም ይገልጻሉ። እንደ አቶ ጥንፍ ገለጻ፣ ስፖርት በተለይ ደግሞ በሰራተኞች መካከል እርስ በእርስ እንዲተዋወቁ፣ ጤናው የተጠበቀና አምራች ዜጋን ለማፍራት እንዲቻል፣ የሰራተኞችን አንድነት ለማጠናከር ፋይዳው ግዙፍ መሆኑን ያብራራሉ። በመሆኑም ኮርፖሬሽኑ የቤተሰብ ስፖርት ፌስቲቫሉን እነዚህን ውጤቶች መሰረት በማድረግ ትኩረት ሰጥቶ እንደጀመረ ይናገራሉ። «ፌስቲቫሉ በየሁለት ዓመቱ ቢደረግ የበለጠ ዝግጅት ተደርጎ በጠንካራና ባማረ ሁኔታ ማከናወን ይቻላል »በሚል አስተዳደሩ ወስኖ በየሁለት ዓመቱ ሊካሄድ እንደቻለም ያስታውሳሉ። የኮርፖሬሽኑ የቤተሰብ ስፖርት በዚህ መልኩ በመቋቋም ባለፉት አስር ዓመታትን መጓዝ ችሏል። በስፖርት ክንውኑ ተቋሙ ውጤታማ መሆን ችሏል? ስንል ጥያቄ ሰንዝረናል። አቶ ጥንፍ ባለፉት አስር ዓመታት በነበረው ስፖርታዊ ክንዋኔ ተቋሙ ውጤታማ መሆኑን ይገልጻሉ። በመጀመሪያ ደረጃ አመራሩና ሰራተኛው መልካም የሆነ ግንኙነት እንዲፈጥሩ አድርጓል። እያደረገም ይገኛል። በአካልም፣ በአዕምሮም የበለፀገ ሰራተኛና አመራር እንዲኖር አስችሏል። ጤናማ ሰራተኛ በመፍጠር ረገድ ውጤት ማምጣት ተችሏል። መታወቅ ያለበት ያለ ጤናማ ሰራተኛ የኮንስትራክሽን ስራ የሚታሰብ እንዳልሆነም ያብራራሉ። የስፖርት ፌስቲቫሉ ሠራተኛውም ሆነ አመራሩን የበለጠ የሚያቀራርብ፣ ሠራተኛው ትርፍ ጊዜውን አዕምሮውንና አካላዊ ብቃቱን የሚያዳብርበት፣ ለተቋሙ ያለውን ወገናዊነት የሚያሳይበት፣ በሌሎች ፕሮጀክቶች ከሚገኙ ሠራተኞች ጋር ለመቀራረብና ለመተዋወቅ መንገድ እየከፈተ እንደሚገኝ ይገልጻሉ። እንደ አቶ ጥንፍ ማብራሪያ፤ የዘንድሮ መድረክ ከእስከ ዛሬው ለየት የሚያደርገው የተሳታፊነቱን ኮታ ለአመራሩ አንድ ሶስተኛውን በመስጠት ዋና ሥራ አስፈጻሚውን ሳይቀር ተሳታፊ ማድረጉ ነው። ስፖርት ፌስቲቫሉ ለአመራሩና ለሰራተኛው እኩል እድል ከመስጠት ባሻገር፤ በሁለቱ አካላት መካከል መቀራረብ እንዲፈጠርና የበለጠ ቀረቤታን መፍጠር እንዲያስችል ነው። ይህን በተግባርም ለመመልከት ተችሏል። የዘንድሮው ውድድር ሴቶችን የበለጠ ተሳታፊ እንዲሆኑ አድርጓል። በመድረኩ ያለፉት ዓመታት ጉዞ ሴቶች ቡድን አልነበራቸውም፤ ዘንድሮ ሁለት ቡድኖች ተቋቁመው በመረብ ኳስና በጠረጴዛ ቴኒስ ስፖርቶች ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ተደርጓል። «የዘንድሮው ፌስቲቫል ልዩ ገጽታው የለውጥ አስተሳሰቦችን ለማስረጽ ጥረት መደረጉ ነው። በውድድሩ ያሉትን ቡድኖች ስያሜን በዚህ ሁኔታ እንዲቃኙ የተደረገ ሲሆን ስያሜዎቹም አሸናፊ፣ ብቁ፣ ታዋቂ፣ ድንቅ፣ ባለራዕይ እና ተስፋ በሚል እንዲሰየሙ ተደርጓል›› ያሉት አስተባባሪው ከዚህ በተጨማሪም ቀደም ሲል ዘርፎች በቡድን ተደራጅተው እርስ በዕርስ የሚያደርጉት ውድድር እንደነበር ተናግረዋል። አደረጃጀቱ እንደ ኮርፖሬሽን ውህደት ባለማምጣቱ አዲስ አደረጃጀት በመፍጠር ወድድሩ እየተካሄደ ሲሆን፤ በመድረኩ የበለጠ መቀራረብና ተቋማዊ ስሜት መፍጠር እንደተቻለ በውድድሩ የአምስትና ስድስት ቀናት ቆይታ ወቅት ለመታዘብ ተችሏል። የስፖርት ፌስቲቫሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ ተቋማዊ ፋይዳውን እያሳደገ መምጣቱን የ5ኛው የቤተሰብ ስፖርት ውድድር እያሳየም ይገኛል። አቶ ጥንፍ ኮርፖሬሽኑ ግዙፍና በርካታ ፕሮጀክቶች ያቀፈ እንደመሆኑ በስፖርት ፌስቲቫሉ ሁሉም ፕሮጀክቶች ተሳታፊ እንዲሆኑ በመስራት የስፖርቱን ግዙፍ ፋይዳ በተቋሙ ምሉእ እንዲሆን ለማድረግ በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራም አስቀምጠዋል። በ5ኛው የኮርፖሬሽኑ የቤተሰብ ስፖርት ሲሳተፍ ያገኘናቸው በኮርፖሬሽኑ የፋሲሊቲ ሰራተኛ የሆኑት አቶ ዜናው ደነቀው በበኩላቸው፤ የስፖርት ክንውኑን እንደ ኮርፖሬሽኑ ሁሉ ሌሎች ተቋማት ተግባራዊ ማድረግ ቢችሉ ያለውን ፋይዳ ይናገራሉ። «በእኛ ተቋም ያለውን ተሞክሮ በሌሎች የመንግስትና የግል መስሪያ ቤቶች ተግባራዊ ማድረግ ቢቻል፤ በአገር አቀፍ ደረጃ ተጠቃሚ መሆን ይቻላል። ከስፖርቱ የሚገኘውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ማግኘት ይቻላል። በተጨማሪም ኢሊት ስፖርተኞች የሚፈሩበትን አጋጣሚ በማስፋት ረገድ የራሱ የሆነ ድርሻ ይኖረዋል። የአገራችንን ስፖርት በማሳደግ ረገድም የመንግስት ተቋማት ድርሻቸውን እንዲወጡ አጋጣሚውን መፍጠር ይቻላል» ሲል ያብራራል። በኮርፖሬሽኑ የቤተሰብ ስፖርት ፌስቲቫል ላይ ከአሰልጣኝነት እስከ ዳኝነት የተሻገረ ተሳትፎን ከመጀመሪያው ጀምሮ ሲያደርጉ እንደነበረ የገለፁልን የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ሰራተኛ የሆኑት አቶ አለማየሁ ገብሬ፤ የኮርፖሬሽኑ ተሞክሮን ሌሎች ተቋማት መውሰድ ቢችሉ ያለውን ነጥብ በማሳት ተመሳሳይ ሃሳብ ይጋራሉ። የቤተሰብ ስፖርቱን ከመጠንሰስ እና ቀጣይነት እንዲኖረው ከማድረግ አካያ በተቋሙ የነበሩና ያሉ አመራሮች ትልቅ ድርሻ እንደነበራቸውም ይናገራሉ። የኮርፖሬሽኑ አመራሮች የስፖርት ፌስቲቫሉ ሳይቋረጥ እንዲቀጥል ከማደርግ አኳያ ያሳዩት ቁርጠኝነት በተለይ ደግሞ የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ዮናስ አያሌው ትልቅ ስራን መስራታቸውን ያስረዳሉ። አቶ አለማየሁ ዋና ስራ አስፈፃሚው ስፖርታዊ ክንውኑ ቀጣይነት ኖሮት በጠንካራ መስመር እንዲጓዝ ከመስራት ባሻገር፤ በውድድሩ ተጫዋች በመሆን የስፖርቱ ተሳታፊ መሆናቸው የሚያስመሰግናቸው መሆኑን ይገለጻሉ። ስፖርቱ ትኩረት እንዲያገኝ ከማድረግ አኳያም አመራሩ ያሳየው ቁርጠኝነት በሌሎች ተቋማት እንደ አርዓያ ሊወስዱት ይገባል ባይናቸው። ኮርፖሬሽኑም በየሁለት ዓመቱ ይህ የስፖርት ባህል ተጠናክሮ እንዲቀጥል ማድረግ እንደሚገባው ያስቀምጣሉ። በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የቤተሰብ ስፖርት ፌስቲቫል ተሞክሮ በሌሎች መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት መውሰድ ቢቻል ዘርፈ ብዙ ውጤቶች እንደ አገር ማትረፍ እንደሚቻል መመስከር ይቻላል። ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በህብረተሰቡ ዘንድ ትኩረት እንዲሰጠው ፖሊሲ ከመቅረጽ ባሻገር ተግባራዊ እንዲሆን እንደ ኮርፖሬሽኑ ሌሎች ተቋማት መስራት አለባቸው።አዲስ ዘመን ረቡዕ ጥቅምት 5/2012ዳንኤል ዘነበ | https://www.press.et/Ama/?p=20928 | 874 | 2ስፖርት
|
የኦሊምፒክ ማራቶን የሚካሄድበት ከተማ ሊቀየር ነው | ስፖርት | October 18, 2019 | 9 | በቅርቡ በተጠናቀቀው የዶሃ ዓለም ቻምፒዮና በሴቶች በተካሄደው የማራቶን ውድድር ከተሳተፉት 68 አትሌቶች
መካከል 28ቱ ውድድሩን ማቋረጣቸው የሚታወስ ነው። ለዚህ ምክንያት የሆነውም በዶሃ የነበረው ከፍተኛ ሙቀትና ወበቅ መሆኑ ተነግሯል።
ከአንድ ዓመት ያነሰ ጊዜ የሚቀረው የቶኪዮ ኦሊምፒክም ከፍተኛ ሙቀት እክል ሊሆንበት እንደሚችል ስጋት ተፈጥሯል፡፡ ይህንን ተከትሎም
ዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ የማራቶን እና የእርምጃ ውድድር ቀደም ብሎ ሊካሄድበት ከታሰበው ከተማ ለውጥ ለማድረግ ማሰቡን አስታውቋል።
በከባድ ሙቀት ምክንያት በውድድሩ ላይ የሚደርሰውን ተጽእኖ ለመቀነስ ሲባልም በተሻለ መጠን ነፋሻማ
የአየር ሁኔታ ያለው አካባቢ አስፈልጓል። በመሆኑም ቀድሞ ከታሰበው የኦሊምፒኩ ዋና መዳረሻ ቶኪዮ ወደ አገሪቷ ሰሜናዊ ክፍል ለማሸጋገር
መታሰቡን የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር በድረ-ገጹ አስነብቧል። በ800ኪሎ ሜትር ርቀት በሆካኢዶ ተራራማ አካባቢዎች
የሚገኘው ሳፖሮ የተባለው ይህ ስፍራ ውድድሩ በሚካሄድበት ወቅት የአየር ሁኔታው በተሻለ መጠን የሚቀዘቅዝ መሆኑ አትሌቶችን እንደሚረዳቸው
ይታሰባል። ስፍራው እ.አ.አ 1972 የክረምት ኦሊምፒክ የተካሄደበትም ነው። የውድድሩ አዘጋጅ ኮሚቴ፣ የኦሊምፒክ ኮሚቴ እንዲሁም የማህበሩ የጤና ባለሙያዎችና አማካሪዎች እንዳስታወቁት
ኦሊምፒኩ የሚካሄደው በበጋው ወቅት በመሆኑ የቶኪዮ ከተማ የሙቀት መጠን በከፍተኛ መጠን ይጨምራል። ይህም በአትሌቶች ላይ እንዲሁም
በውድድሩ ላይ ተጽእኖ ማሳደሩ እንደማይቀር አጽንኦት መስጠታቸውን ተከትሎ የቦታ ለውጥ ለማድረግ መታቀዱ ታውቋል፡፡ ሙቀቱ ከማራቶን
እና እርምጃ ውድድሮች ባሻገር የ5ሺ ሜትር እና 10ሺ ሜትር ውድድሮች እንደተለመደው በቀኑ ክፍለ ጊዜ ሳይሆን ሌሊት ላይ ለማካሄድ
ሊያስገድድ እንደሚችልም ተነግሯል፡፡ ከረጃጅም ርቀት አትሌቲክስ
ባሻገር ላሉ ሌሎች ስፖርቶችም በተመሳሳይ ሙቀቱ አስቸጋሪ ሊሆን ስለሚችል የተለያዩ እገዛዎች እንደሚደረጉም ተጠቁሟል። ይህም መጠለያዎችን
በማበራከት እንዲሁም የውሃ ማቀዝቀዣ፣ ከፍተኛ የውሃ አቅርቦት እንዲኖርና አትሌቶች ዝግጅት በሚያደርጉበት ወቅት በመረዳት ነው።
ከዚህ ባሻገር በተያዘው የፈረንጆቹ ወር መጨረሻ በሚደረገው ስብሰባ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን በውድድሩ ስፍራ ለውጥ
እንዲሁም በኦሊምፒኩ ዙሪያ ሰፊ ውይይት ለማድረግ ቀጠሮ ተይዟል። የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ
ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ቶማስ ባች ባደረጉት ገለጻም «የአትሌቶች ጤና እና ደህንነት ቀዳሚው ጉዳይ ነው። አትሌቶችን ከጉዳት ለመታደግም
በርካታ ኪሎ ሜትሮችን በመጓዝ ለውጥ ከማድረግ ላይ ደርሰናል፤ ይህም ምን ያህል ትኩረት እንደምንሰጥ የሚያሳይ ነው። ኦሊምፒክ ማለት
አትሌቶች በህይወት ዘመናቸው የሚያሳኩት ሁነት ነው፤ በመሆኑም ብቃታቸውን ማሳየት አለባቸው። ለዚህ ሥራም እየተባበረን ያለውን ማህበር
ማመስገን ይገባል» ብለዋል። የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ፕሬዚዳንት ሰባስቲያን ኮ
በበኩላቸው «ከዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እና ከ2020 የቶኪዮ ኦሊምፒክ አዘጋጆች ጋር በቅርበት ስንሰራ ቆይተናል። አትሌቶች
ብቃታቸውን ያሳዩ ዘንድ አስፈላጊውን ሁሉ ልናመቻችላቸው ይገባል፤ በመሆኑም ለማራቶን እና እርምጃ ተወዳዳሪዎች የሚሻል የአየር ሁኔታ
ወዳለው ስፍራ ለውጥ ማድረግ አስፈልጓል» ሲሉ አብራርተዋል። አዲስ
ዘመን ጥቅምት 7/2012 ብርሃን ፈይሳ | https://www.press.et/Ama/?p=20999 | 352 | 2ስፖርት
|
ኢትዮጵያዊያን ለ2 ዓመታት የምርጥ አትሌቶች ሽልማት አልታጩም | ስፖርት | October 17, 2019 | 39 | የጽናት ምልክቱና በ10ሺ ሜትር ጀግናው አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ኢትዮጵያን ወክሎ የዓለም ምርጡ አትሌት ሲሰኝ የመጀመሪያው ነው። በአቴንሱ የዓለም ቻምፒዮና 10ሺ ሜትር እንዲሁም በፈረንሳይ የቤት ውስጥ ቻምፒዮና 3ሺ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ በማጥለቅ አገሩን ባስጠራ ማግስት፣ የጎልደን ሊጉ አሸናፊም በሆነበት ዓመት እአአ 1998 የዓመቱ የዓለም ምርጥ አትሌት በሚል ለመሸለም በቃ። በኃይሌ እግር የተተካው ቀነኒሳ በቀለ ደግሞ ይህንን ክብር በማግኘት ሁለተኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ለመሰኘት ቻለ። የ5ሺ፣ 10ሺ እና የአገር አቋራጭ ንጉሱ በተከታታይ እአአ በ2004 እና 2005 በወንዶች የዓለም ምርጥ አትሌት በመሆንም ታሪካዊ አትሌትነቱን አስመስክሯል። በወንዶች በኩል ከቀነኒሳ ቀጥሎ ይህንን ክብር ያገኘ ኢትዮጵያዊ አትሌት ባይኖርም በሴቶች በኩል ግን እስከ ቅርብ ዓመታት ለማሸነፍ የቻሉ አትሌቶች ታይተዋል። አትሌት መሰረት ደፋር እአአ በ2007 ይህንን ሽልማት ያሳካች አትሌት ናት። ከዚያ በኋላ ባሉት ዓመታት ባይቆጠርም እአአ በ2015 ገንዘቤ ዲባባ ሁለተኛውን ክብር እንዲሁም በረጅም ርቀት የዓለም እና የኦሊምፒክ ቻምፒዮናዋ አልማዝ አያና በ2016 የዓመቱ ምርጥ አትሌት በመባል ለመሸለም በቅተዋል። በዓለም ላይ በተለይ በረጅም ርቀት አትሌቲክስ ተጽእኖ ፈጣሪ ከሚባሉ አገራት መካከል አንዷ ኢትዮጵያናት። በዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ዕውቅና በተሰጣቸው ውድድሮች ላይ በግላቸው ከሚሳተፉት አትሌቶች ባሻገር በዳይመንድ ሊግ፣ ዓለም ቻምፒዮና አንዲሁም በኦሊምፒክ መድረክም ሜዳሊያ ያጠለቁ የዝነኛ አትሌቶች ምድርም ናት፤ ኢትዮጵያ። አሸንፎ ሜዳሊያውን ማጥለቅ ብቻም ሳይሆን ሰዓት በማሻሻልና የዓለም ክብረወሰንን በመስበር ጭምር በርካታ ስኬታማ አትሌቶችን ለዓለም አበርክታለች። ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በዓለም ምርጥ አትሌቶች ሽልማት ማሸነፍ ባይችሉ እንኳን ከመጀመሪያዎቹ አስር እጩዎች በሁለቱም ፆታ መካተታቸው ብርቅ አልነበረም። ባለፈው ዓመትና ዘንድሮ ግን በተከታታይ ከአስሩ እጩዎች ዝርዝር ውስጥ ሳይካተቱ ቀርተዋል። የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባለሙያዎች እንዲሁም ከሁሉም አህጉራት በተወጣጡ ተወካዮች በሁለቱም ጾታ በዓመቱ ጥሩ ብቃት ያሳዩ 20 አትሌቶች ቀርበዋል። ዕጩዎቹም በዳይመንድ ሊግ፣ በዓለም አገር አቋራጭ ቻምፒዮና፣ በዶሃው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና እንዲሁም ማህበሩ በሚያዘጋጃቸው ውድድሮች ላይ በሩጫ፣ ዝላይ እና ውርወራ የተሻለ ብቃት ያሳዩ ሲሆኑ ከነዚህ መካከል ለተከታታይ ሁለት ዓመታት አንድም ኢትዮጵያዊ አትሌት ሳይካተት መቅረቱ አስገራሚ ሆኗል። ዘንድሮ እጩ ሆነው ከቀረቡት አትሌቶች መካከል አሜሪካ በርካታ አትሌቶችን በማስመረጥ ቀዳሚዋ አገር ሆናለች። በዓመቱ ከተካፈለባቸው አምስት የ800 ሜትር ውድድሮች አራቱን ያሸነፈው ዶናቫን ብራዜር በእጩነት ከቀረቡት መካከል ይገኛል። አሜሪካዊው አትሌት በቻምፒዮናው ላይ በ800 ሜትር 1:42.34 የዓለም ክብረወሰን የሆነ ሰዓት ከማስመዝገቡም ባሻገር የዳይመንድ ሊጉ አሸናፊ ነው። በዓመቱ በ100 ሜትር ውድድር ተዕእኖ ፈጣሪ የነበረውና የዶሃ ርቀቱን 9 ሰከንድ ከ76 ማይክሮ የገባው ክርስቲያን ኮለመንም ሌላኛው እጩ ነው። የከፍታ ዝላይ አሸናፊው ሳም ኬንድሪክስ፣ የ200 ሜትር ሯጩ ናህ ላይለስ እንዲሁም የርዝመት ዘላዩ ክርስቲያን ቴይለር በእጩነት የቀረቡ አሜሪካዊያን አትሌቶች ናቸው። ባለፈው ሳምንት ማራቶንን ለመጀመሪያ ጊዜ ከሁለት ሰዓት በታች በመግባት ታሪክ ያጻፈው ኬንያዊው ኢሉድ ኪፕቾጌም በእጩነቱ ተካቷል። አትሌቱ ዕውቅና የሌለውን የስፖርት ትጥቅ አምራቹን ኩባንያ ናይኪ ፕሮጀክት የሆነውን ማራቶንን ከ2 ሰዓት በታች የማጠናቀቅ ህልም ከማሳካቱም ባለፈ በለንደን ማራቶን
2:02:37 በመግባት የራሱን ፈጣን ሰዓት በማሻሻል የዓለም ክብረወሰኑን አለማስነጠቁ የሚታወቅ ነው። የአገሩ ልጅ የሆነው ቲሞዚ ቺሩዪት ሌላኛው እጩ ሲሆን፤ በ1ሺ500ሜትር የዳይመንድ ሊግ እንዲሁም የዓለም ቻምፒዮን ነው። በአውሩስ በተካሄደው የዓለም አገር አቋራጭ ቻምፒዮን የሆነው ኡጋንዳዊው ጆሹዋ ቼፕቴጊም ከእጩዎቹ ተካቷል። አትሌቱ በ10ሺ ሜትር ቀዳሚ የሆነውን
26:48.36 ሰዓት ሲያስመዘግብ በ500ሜትር የዳይመንድ ሊጉ ቻምፒዮን ነው። የ400ሜትር አትሌቱ ባህሬናዊ ስቲቭ ጋርድነር፣ በዲስከስ ውርወራ የዓለም ቻምፒዮኑ ስዊድናዊ ዳንኤል ስታል እንዲሁም ኖርዌያዊው ካርስቴን ዋርሆልም በምርጫው የተካተቱ ሌሎች እጩዎች ናቸው። ለምርጫው የዓለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ባለሙያዎች 50 በመቶ የሚሆነውን ድምጽ የሚሰጡ ሲሆን 25 በመቶ የሚሆነውን ደግሞ ሌላው ህዝብ በድረገጾች ድምጹን የሚሰጥ ይሆናል። እጩዎቹን አሸናፊ ለማድረግም በየትኛውም የህዝብ መገናኛ እንዲሁም የማህበራዊ ገጾች ማስተዋወቅ የሚረዳቸው ሲሆን፤ ከወር በኋላ የመጨረሻዎቹ አምስት እጩዎች ይታወቃሉ። አሸናፊው እትሌትም በሞናኮ በሚኖረው ስነስርዓት ላይ ይፋ እንደሚደረግ ይታወቃል። አዲስ ዘመን ረቡዕ ጥቅምት 5/2012ብርሃን ፈይሳ | https://www.press.et/Ama/?p=20932 | 523 | 2ስፖርት
|
“ዋናው ነገር የሀገር ጉዳይ ነው፤ እኛ ብንሞትም ብንኖርም ለሀገር ስለሆነ ችግር የለውም፤ ጓደኞቻችን ግን ነፃ አውጥተውናል” – ከታጋቾች መካከል አንዱ የነበሩት ብርጋዴር ጄኔራል ኑሩ ሙዘይን የመከላከያ ሠራዊት 20ኛ ክፍለጦር አዛዥ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 13, 2020 | 15 | በጋዜጣው ሪፖርተርብርጋዴር ጄኔራል ኑሩ ሙዘይን፣ በጁንታው ቡድን ታግተው ከቆዩ የመከላከያ ሠራዊት አመራሮች መካከል አንዱ ናቸው። ብርጋዴር ጄኔራል ኑሩ፣ በወቅቱ የጁንታው ታጣቂዎች የሠራዊቱ አባላት ትጥቃቸውን እንዲፈቱ መልዕክት በግዳጅ እንዲያስተላልፍ ሲደረግ “እኔ ትጥቄን ፈትቻለሁ እናንተም ፍቱ፤ እኔን ግን ከዚህ በኋላ አታገኙኝም” ብለው ውስጠ ወይራ መልዕክት አስተላለፉ። አክለውም በኦሮምኛ ለሠራዊቱ ትጥቅ እንዳይፈታ የሚያግዝ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ያስታውሳሉ። መከላከያ ሠራዊቱም ጥቃቱ
ከተፈፀመ ማግስት ጀምሮ
በመከላከልና የሕግ ማስከበር
እርምጃ በመፈፀም ህይወት
የማዳን እና አጥፊዎቹን
የመቅጣት እርምጃውን ገፋበት።
በርካታ የሠራዊቱ አባላት
እና አመራሮችም ከብዙ
እንግልት በኋላ ከጁንታው
እጅ ነፃ ወጡ።
ከታጋቾች መካከል አንዱ
የነበሩት ብርጋዴር ጄኔራል
ኑሩም በዚህ ወቅት
ነው ነፃ የወጡት፡፡
እናም ነፃ ከወጡ
በኋላ ሲቃ በተሞላበት
ንግግራቸው የነበረውን ሁኔታ
አስረድተዋል። “ከሁሉ
በፊት ለመላው የኢትዮጵያ
ህዝብ ለመከላከያ ሠራዊትም
እንኳን ለዚህ ድል
አበቃን፤ እኛንም ከአንድ
ወር ልፋትና እንግልት
በኋላ እንኳን በሰላም
አገናኘን። ዋናው ነገር
የሀገር ጉዳይ ነው፤
እኛ ብንሞትም ብንኖርም ለሀገር ስለሆነ ችግር የለውም በሚል ተስፋ ቆርጠን ነበር። ጓደኞቻችን ግን ህዳር 30 ቀን 2013 ዓ.ም ላይ ኦፕሬሽናቸውን በመፈፀም ነፃ አውጥተውናል።የተለያዩ ቀናትን ያለምግብ እና ውሃ ሳንጠጣ በርካታ የመሬት ገፆች ላይ ተንገላተናል። በርካታ የሠራዊት አባላትም ይህን እንግልት ተቋቁመን አሁን የደረስንበት ደረጃ በመድረሳችን በታጋቾች እና በራሴ ስም ለመከላከያ ሠራዊትም ሆነ ለኢትዮጵያ ህዝብ ምስጋና ማቅረብ እፈልጋለሁ።በአጠቃላይ በሠራዊታችንም ሆነ በህዝባችን ሲከናወን የነበረውን ነገር በተለያየ መንገድ የሰማነው ስለሆነ እኛም ደስ ብሎናል። ለመከላከያ ሠራዊትም ሆነ ለኢትዮጵያ ህዝብ ለድል ያበቃችሁን አንድነታችሁን በማጠናከር የቀሩትን ሥራዎችም እንድታጠናቅቁ አደራ ማለት እፈልጋለሁ>> ብለዋል። ለአንድ ወር ከስድስት ቀን በጁንታው ታጣቂዎች ጥቃት ከተፈፀመባቸው በኋላ ታግተው በረሃብና በእንግልት የቆዩት የመከላከያ ሠራዊት መኮንኖች በሠራዊቱ አማካኘነት ነፃ ከወጡ በኋላ ህይወታቸውን ለማትረፍ ለተደረገው ጥንቃቄ የተሞላበት ጥረት ምስጋና አቅርበዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 4/2013 | https://www.press.et/Ama/?p=37237 | 246 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
እንስቶቹ የሠራዊቱ ፈርጦች | ሀገር አቀፍ ዜና | December 13, 2020 | 18 | ጌትነት ተስፋማርያም ፊታቸው ላይ
ሊፒስቲክ፣
ኩል
እና
የውበት
መጠበቂያ
ክሬሞች
ፈጽሞ
አይታዩም።
ከዚህ
ይልቅ
ፊታቸው
ላይ
የሚታየው
የአልበገር
ባይነት
ወኔ
እና
ተፈጥሯዊ
ውበት
ነው።
ፀጉራቸውንም
ቢሆን
እንደወጉ
ይሠሩት
እንደሆን
እንጂ
ዛሬም
ነገም
መተኮስ
እና
ባማሩ
ጌጦች
ማስዋብ
የሚያስችል
ጊዜም
ሆነ
ዕድሉ
የላቸውም።
ምክንያቱም
ዓላማቸው
የሀገር
ህልውና
ማስከበር
እና
ወንጀለኞችን
ሥርዓት
ማስያዝ
ነውና፡፡ገደላገደሉን ሲዘሉ፤ ጢሻውን ሲያቋርጡ ነው አብዛኛውን ጊዜያቸውን በግዳጅ ላይ የሚያሳልፉት። ሕብረ- ብሔራዊነትን በአግባቡ በተላበሰው የመከላከያ ሠራዊት ውስጥ የፆታ ልዩነት ሳይገድባቸው በጽናት የቆሙ እንስቶች የሠራዊቱ ብርቱ ክንድ ስለመሆናቸው ደግሞ የሚያውቋቸው ይመሰክራሉ።ወታደር አስደሳች ታከለ እና ወታደር ታሪኬ ኤርሚያስ የመከላከያ ሠራዊትን የተቀላቀሉት ከሐዲያ እና ጋሞ ዞኖች ነው። ሁለቱም እንስቶች የ20 ዓመት የወጣትነት እድሜ ላይ የሚገኙ የ24ኛ ክፍለጦር አባላት ናቸው። በትግራይ ክልል በተደረገው የሕግ ማስከበር ዘመቻ አቧራ ለብሰው ኮቾሮ ቀምሰው አፈር ላይም ጋደም ብለው ያሳለፏቸው በርካታ ቀናት መኖራቸውን አጫወቱን እና ታሪካቸውን በይበልጥ ለመስማት ጓጓን። ግርማ ሞገስ ባለው አረማመዷ ታጅባ ታሪኳን ያወጋችን ሴት ወታደር አስደሳች ታከለ፤ የሕግ ማስከበር ዘመቻው ከጅማሮው አንስቶ ላይ መሳተፏን ነገረችን። በተለይ በአከርና በአካባቢው የነበሩ የጁንታው ቡድን ታጣቂዎችን ለይቶ ለሕግ በማቅረብ እና የአካባቢው ኗሪ ሳይጎዳ ግዳጁን ለማጠናቀቅ ጥረት መደረጉን ታስታውሳለች። በወቅቱ ግን ከበአከር አለፍ ብላ ባለች አንድ ተራራማ ቦታ ላይ ስትደርስ ባጋጠማት የመንሸራተት አደጋ ወድቃ ቀኝ እጇ ላይ ስብራት አጋጠማት።አደጋው የማያላውስ እና ጥዝጣዜውም ከባድ ህመም ያለው ቢሆንም ግን “መሣሪያዬን ለማንም አልሰጥም” ብላ የሚመጣውን ሃይል ለመመከት ዝግጅት ማድረጓ አልቀረም። በመጨረሻም አካባቢውን መከላከያ ሠራዊት ሙሉ በሙሉ ሲቆጣጠረው እርሷም ለህክምና ተወሰደች። እስከ ባህር ዳር
ከተማ ድረስ ተጉዛ
አስፈላጊውን ህክምና ስትከታተል
ግን ትጥቄን ስጡኝ
በማለት ከአጠገቧ ሳትነጥል
ማቆየቷን አትዘነጋውም። ዓላማዋ
ቶሎ ተመልሳ የሕግ
ማስከበር እርምጃው ላይ
ለመሳተፍ እንደነበር ነግራናለች።
አሁን ላይ በመልካም
ጤንነት ላይ መገኘቷን
በማሳወቅ ልቧ እንደፈቀደው
ዳግም ወደግዳጅ ለመመለስ
ጥያቄ አቅርባለች። በሠራዊቱ ውስጥ ያለው የሴቶች ተሳትፎ የሚያኮራ ነው የምትለው ወታደር አስደሳች፤ 150 ጥይት ታጥቀው ከወንድ እኩል የሚሮጡ እና የተሰጣቸውን ግዳጅ በብቃት የሚፈጽሙ አባላት እና አመራሮችም ለሌሎች እንስቶች ሁሉ የጽናት ተምሳሌት መሆናቸውን ትገልፃለች። ወታደር ታሪኬ ኤርሚያስ በበኩሏ “በከተማ አካባቢ መኖርና መመለስ ሃሳቤ አይደለም። ዓላማዬ ሁሉ ለሀገሬ መታገል እና ለእናት ሀገሬ መኖር ነው” ትላለች። በሠራዊቱ ውስጥ ያለውን የሴቶች ተሳትፎ ስትገልጽም “ሴት ነኝ ብሎ ወደኋላ የሚሸሽ የለም። ሴቶች በውጊያ መሳተፍ ብቻ ሳይሆን ሠራዊቱንም በማበረታታት ጭምር ጥንካሬያቸውን አሳይተዋል፤ ሴቶች ከባድ መሣሪያ ጭምር ይዘው ለሀገር ህልውና ለህይወታቸውን ሳይሳሱ ተሰልፈዋል” ብላለች። ለሀገሯ አይደለም ደሟን ማፍሰስ ህይወቷንም ልታጣ የምትችልበት አጋጣሚ እንደሚኖር የምትናገረው ወታደር ታሪኬ እርሷም በአከር አካባቢ በነበረ የሕግ ማስከበር ዘመቻ ብሽሽቷ አካባቢ በጥይት ተመታ ቆስላለች። በቆሰለችበት አጋጣሚ ደም ፈሷት ህመም ቢበረታባትም ግና ወኔዋ ሁሉ መሣሪያዋን ይዛ ግዳጇን ለመቀጠል እንደነበር አትረሳውም።መከላከያ ሠራዊት የህክምና ባለሙያዎች በአካባቢው የመጀመሪያ ዕርዳታ አድርገውላት ለተጨማሪ ህክምና ወደባህርዳር እና ሌሎች ከተሞች የተወሰደችው ወታደር ታሪኬ፤ ህክምናዋን ስታጠናቅቅ ግን፤ ስለዚህ አሁኑኑ ወደ ዘመቻ ልሂድ” ብላ መነሳቷን ነግራናለች። ይሁንና ኢትዮጵያ በርካታ ልጆች ስላሏት ተጨማሪ ሥራ ሲያስፈልግ እንደምትጠራ ተገልፆላት ዝግጅት በማድረግ ላይ ነች። ሠራዊቱ ውስጥ ያሉ በርካታ እንስቶች ዛሬም በድንበር እና በተለያዩ የግዳጅ አካባቢዎቸ የጁንታው ቡድን አመራሮችን ለመያዝ ደፋ ቀና ይላሉ። የሠራዊቱ ፈርጦች መሆናቸውንም በተግባር አሳይተዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 4/2013 | https://www.press.et/Ama/?p=37235 | 448 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብዓት አምራቾች ወደአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጣና ለመግባት መዘጋጀት አለባቸው ተባለ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 13, 2020 | 12 | ፋንታነሽ ክንዴአዲስ አበባ፡- በኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብዓት አምራችነት የተሰማሩ ኢንዱስትሪዎች ወደ አፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ለመግባት መዘጋጀት እንዳለባቸው ተገለፀ፡፡ኤክስፖርትን ማበረታታት ዓላማው ያደረገ የኤክስፖ ንቅናቄ ከትናንት በስቲያ ተካሂዷል፡፡የኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብዓቶች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ባዘጋጀው በዚህ መድረክ ላይ የተገኙት የኢ.ፌዴ.ሪ. ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የውጭ ንግድ ማስፋፊያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋናው አረጋ እንደገለፁት፤ ኢትዮጵያ በቅርቡ ሙሉ በሙሉ የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጣና አባል ሆናለች፡፡በመሆኑም በኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብዓት አምራችነት የተሰማሩ ኢንዱስትሪዎች ወደ አፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ለመግባት መዘጋጀት ይኖርባቸዋል፡፡እንደ አምባሳደር ምስጋናው ገለፃ፤ ኢትዮጵያ ወደ ነፃ ንግድ ቀጣና ስትገባ ውድድሩ ከአገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎች ጋር ብቻ ሳይሆን ከጎረቤት ብሎም በአፍሪካ ደረጃ ካሉ አምራቾች ጋር ነው፡፡ስለሆነም በዘርፉ የተሰማሩ አምራቾች አቅማቸውን በአፍሪካ ያሉ ዕድሎችንም ለመጠቀም በሚያስችል ደረጃ ማሳደግ ይኖርባቸዋል፡፡በኬሚካልና ኮንስትራክሽን ዘርፍ ኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጡ ምርቶችን እንደምታስገባ ጠቁመው፤ ይህንን በአገር ውስጥ ምርት መተካት ከተቻለ ትልቅ የውጭ ምንዛሬን የሚቀንስ በመሆኑ ከውጭ የሚገቡ ምርቶች በአገር ውስጥ ምርት መተካት ላይ በስፋት መሥራት እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡ባለፉት አምስት ዓመታት ብቻ ከ8 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጡ ምርቶች እንዲገቡ መደረጉን የጠቀሱት አምባሳደር ምስጋናው፤ ይህንን ወጪ ማስቀረት መቻል በራሱ ትልቅ ሥራ በመሆኑ አቅምን አጎልብቶ ለኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብዓቶችንና ምርቶችን በማምረት የአፍሪካን ገበያ ለመጠቀም መሥራት እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡በዚህ ረገድ በኬሚካልና ኮንስትራክሽን ዘርፍ ያሉ ችግሮችን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ማጥናቱን ተናግረው፤ በተለይ ዘርፉን አንቀው የያዙትን ችግሮች ለመፍታት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡በመድረኩ ላይ የውይይት መነሻ ጽሑፍ ያቀረቡት በኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብዓቶች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የጎማና ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ ልማት ዳይሬክተር ኢንጅነር ዮናስ አባተ በበኩላቸው እንደገለፁት፤ በዘርፉ ውስጥ ከፍተኛ ወጪ ከሚወጣባቸው ምርቶችና ግብዓቶች መካከል ማዳበሪያ፣ ጎማና ፕላስቲክ ለመሥራት እንዲሁም ለሳሙናና ቀለም የሚሆኑ ግብዓቶች ይገኙበታል፡፡በዚህ ረገድ ባለፉት አምስት ዓመታት ከውጭ ግብዓቶችና ምርቶችን ለማስገባት በኬሚካል ዘርፍ ከ8 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር በላይ፣ በኮንስትራክስን ዘርፍ ደግሞ ከ1 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር በላይ በአጠቃላይ ከ 9 ነጥብ 8 ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ ተደርጓል፡፡የኬሚካልና ኮንስትራክሽን ኢንስቲትዩት የተቋቋመው ደግሞ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ለመተካት እንደመሆኑ ምርቶችን ወደ ውጭ መላክ እንዲችሉ ለማለማመድ ሲሠራ ቆይቷል፡፡ይህንንም ተከትሎ ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ በየዓመቱ 20 ሚሊዮን ዶላር የሚሆኑ ምርቶች ወደ ውጭ ሲላኩ ነበር፡፡በአሁኑ ወቅት ባደጉ አገሮች ካሉ ኢንዱስትሪዎች ጋር ሊወዳደሩ የሚችሉ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ይዘው የመጡ ኢንዱስትሪዎች መኖራቸውን የገለፁት ኢንጅነር ዮናስ፤ ከባጃጅ እስከ ትራክተር ድረስ ያሉ ጎማዎችን በአገር ውስጥ ማምረት መቻሉንም አስረድተዋል፡፡በኬሚካል ዘርፍ በከፍተኛ ደረጃ ለማደግ ጥረት እየተደረገ እንደሆነም አብራርተዋል፡፡ከተፈጥሮ ጋዝ የፔትሮ ኬሚካል ውጤቶችን አገር ውስጥ ለማምረት እየተሠራ እንዳለም ገልፀው፤ ይህም ከአገር ፍጆታ አልፎ በዓመት እስከ 2 ቢሊዮን ዶላር ያህል የውጭ ምንዛሬ ማግኘት የሚያስችል ምርት ወደ ውጭ መላክ እንደሚያስችል ጠቅሰዋል፡፡“ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ኢንዱስትሪዎችን እንፍጠር” በሚል መሪ ሃሳብ የተካሄደው ንቅናቄ መድረክ ዘርፉን ለማነቃቃት፣ እስካሁን የተሄደበትን እርቀት ለማየትና ዘርፉ ላይ ያለውን እምቅ አቅም ለመረዳት የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 4/2013 | https://www.press.et/Ama/?p=37247 | 403 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
“ሠራዊቱ የታፈኑትን ነፃ ሲያወጣ ጠላትና ወገንን የለየ ምርጥ ኦፕሬሽን አከናውኗል” – ብርጋዴር ጄኔራል አዳምነህ መንግስቴ፣ የሰሜን ዕዝ ምክትል ኦፕሬሽን አዛዥ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 13, 2020 | 15 | ጌትነት ተስፋማርያምሽሬ:- “መከላከያ ሠራዊት በጁንታው ታጣቂዎች አማካኝነት የታፈኑትን የሠራዊቱ አመራርና አባላትን ነፃ ሲያወጣ ጠላትና ወገንን የለየ ምርጥ ኦፕሬሽን አከናውኗል” ሲሉ ከታጋቾቹ መካከል አንዱ የነበሩት የሰሜን ዕዝ ምክትል ኦፕሬሽን አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል አዳምነህ መንግስቴ ተናገሩ። የሰሜን ዕዝ ምክትል ኦፕሬሽን አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል አዳምነህ መንግስቴ እንደገለፁት፤ መከላከያ ሠራዊቱ ታጋቾችን እና የጁንታውን ታጣቂ ለመለየት የተጠቀመው እርምጃ የሚደነቅ ነው። በዚህም የሠራዊቱ አመራርና አባላትን በማይጎዳ መልኩ ጥንቃቄ የተሞላበት ኦፕሬሽን በተሳካ ሁኔታ ተፈፅሟል። “መከላከያ ሠራዊታችን እኛ የታፈንነውን አመራርና አባላት ላይ አደጋ እንዳይደርስ ጥንቃቄ በተሞላው መንገድ እርምጃ ወስዷል። በተለይ የጁንታው አመራሮች በቅርበት ይከታተሉን ስለነበር እነርሱን በሚነጥል ሁኔታ በአየር ከፊት ጠባብ መንገድ ላይ ተሽከርካሪዎቻቸውን አቃጥሏል። መከላከያ ሠራዊቱ የጁንታው አመራሮች ወደኋላ ሊመለሱ ሲሄዱ በኋላ በኩልም ተሽከርካሪዎቻቸው ተመተው መንገዱ እንዲዘጋባቸው አድርጓል። በዚህ ወቅት የጁንታው አመራሮች መሄጃ በማጣታቸው የነበራቸውን ተሽከረካሪዎች እና ንብረት እየጣሉና እያንጠባጠቡ ሲበታተኑ መከላከያ ሠራዊታችን ደርሶ አብረውኝ የነበሩትን ሁሉ ታጋቾችን ነፃ አውጥቷል” በማለት የሠራዊቱን እርምጃ አወድሰዋል። ሠራዊቱ የታፈኑትን ነፃ ሲያወጣ ጠላትና ወገንን የለየ ምርጥ ኦፕሬሽን አከናውኗል ያሉት ብርጋዴር ጄኔራል አዳምነህ፤ እርምጃው መላው የኢትዮጵያ ህዝብም ደስተኛ የሆነበት እና ጥሩ ሥራ የተከናወነበት እንደሆነም ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። “መከላከያ ሠራዊታችንን በግሌም ሆነ አብረውኝ በነበሩ አመራሮች ስም ላመሰግን እወዳለሁ። በመከላከያ ሠራዊታችን ኮርተንበታል” ብለዋል። በአፈናው ወቅት ስለነበረው ሁናቴ ሲያስረዱም፣ “ስሜቱን መግለጽ ያጥረኝ ይሆናል፤ እናትና አባትህ ይክዱኛል ብለህ በማትጠብቅበት ሰዓት በሠራዊቲ ላይ ክህደት ተፈጽሟል። ቤታችን ነው ሰላም ነው ባልንበት ቦታ በተደራጀ ሃይል የአፈና ሥርዓት ተካሂዷል።የአፈናው ጊዜ በሙሉ በርካታ ውጣ ውረዶች ያሉት ነው፤ ረጅም የእግር ጉዞዎች በቀንም በሌሊትም ያለዕረፍት ነበረው። ዞሮ ዞሮ ህይወታችንን ካተረፉን የመከላከያ ሠራዊት ወንድሞቻችን ጋር ሆነን ታሪኩን በጽሁፍ በሰፊው የምናቀርበው ይሆናል” በማለት ሁኔታውን በአጭሩ አስረድተዋል። ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ላይ በጁንታው ቡድን ታጣቂዎች ጥቃት ተፈጽሞባቸው የታፈኑት የሰሜን ዕዝ መከላከያ ሠራዊት አመራሮች ሽሬ ከተማ ሲደርሱ በሠራዊቱ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። በርካታ የሠራዊቱ አባላት ታፍነው የሰነበቱ አመራሮቹን እና ጓደኞቻቸውን ሲያገኙም ወደ ሰማይ በሚተኮስ የጥይት ድምጽ እና በጭፈራ ደስታቸውን ገልፀዋል።ህዳር 30 ቀን ከሰዓት በኋላ የጁንታው ቡድን አጋቾች አዴት በተባለ አካባቢ በእግር ሲያጓጉዟቸው የነበሩትን ከ1 ሺህ በላይ የሠራዊቱን መኮንኖች በመልቀቅ በየአቅጣጫው መበታተኑ ታውቋል። ታፍነው የሰነበቱ የሠራዊቱ አመራሮች መንግሥት ላደረገው የህይወት አድን ጥረት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 4/2013 | https://www.press.et/Ama/?p=37240 | 318 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ለምዕራብ ትግራይ ተፈናቃዮች 31 ሺህ 500 ኩንታል የስንዴና የታሸጉ ምግቦች ድጋፍ ቀረበ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 13, 2020 | 7 | ጌትነት ተ/ማርያም ሽሬ:- ከምዕራብ ትግራይ አካባቢዎች ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውል 31 ሺህ 500 ኩንታል ስንዴ እና የታሸጉ ምግቦች ድጋፍ መቅረቡን የብሔራዊ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ። የብሔራዊ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አደጋ ምላሽና ክትትል ቡድን መሪ እና በትግራይ ክልል ለሚቀርበው ድጋፍ አስተባባሪ አቶ ታዬ ጌታቸው እንደገለፁት፤ በምዕራብ ትግራይ አካባቢዎች አፋጣኝ የምግብ ዕርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ስንዴ እና ለህፃናት፣ እናቶችና አረጋውያን የሚሆኑ ፓስታ፣ ሩዝ፣ ዘይት፣ አልሚ ምግብ እና የማብሰያ ቁሳቁሶች ቀርቧል። እንደ አቶ ታዬ
ገለፃ፤ መንግሥት ያቀረበውን
ድጋፍ ለተፈናቃይ ዜጎች
ለማከፋፈል በትግራይ ክልል
ከተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር
ጋር በጋራ እየተሠራ
ይገኛል። በተለያዩ ማዕከላት
ተጠልለው የሚገኙ ተፈናቃዮች
አፋጣኝ ድጋፍ እንዲደረግላቸው
ተለይተዋል። ማምረት እና
መሥራት የማይችሉ ዜጎች
ጭምር ቤት ለቤት
የምግብ ድጋፉ ይቀርብላቸዋል። አስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ ያስፈልጋቸዋል ተብለው የተለዩ 13 ሺህ ዜጎች ቅድሚያ ድጋፉ እየቀረበላቸው ይገኛል። የሽሬ እንዳሥላሴ ከተማ ጊዜያዊ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሃጎስ በርሄ በበኩላቸው እንደገለፁት፤ ከምዕራብ ትግራይ ተፈናቅለው በሽሬ ከተማዋ የሚገኙ ዜጎች በዩኒቨርሲቲ እና በትምህርት ቤቶች ተጠልለው ይገኛሉ። እንደ አቶ ሃጎስ ከሆነ፤ መንግሥት ችግሩን ተገንዝቦ ለተፈናቃዮች ዕርዳታውን በተጠየቀ ጊዜ ቶሎ በማድረሱ ምስጋና ይገባዋል። ድጋፉን በፍትሃዊነት ለማከፋፈል እንዲቻል በጊዜያዊ አስተዳደሩ ከቀበሌ አንስቶ እስከ ከተማ አስተዳደር ጀምሮ የሰዎች ምደባ ተደርጓል። በከተማ ደረጃ ህብረተሰቡን ለማረጋጋት እና ድጋፎችን ለማከፋፈል አምስት የካቢኔ አካላት እና 25 የወረዳ ምክር ቤት አባላት ተመርጠዋል። በየቀበሌው አምስት አመራር እና 15 ጊዜያዊ የምክር ቤት አባላት አሉ። በተጨማሪ የድጋፍ ክፍፍሉን የሚያስተባብሩ አካላት ከኅብረተሰቡ ተመርጠው በተቻለ መጠን ድጋፉ ለታለመለት ዓላማ እንዲውል ጥረት እየተደረገ ይገኛል። አሁን ላይ ሀብታሙም ድሃውም ሕብረተሰብ የባንክ አገልግሎት ባለመኖሩ ምክንያት እኩል የሆኑበት አጋጣሚ አለ የሚሉት አቶ ሃጎስ፤ ይሁንና ችግሩን ቀስ በቀስ ለመፍታት ጥረት በማድረግ በቅድሚያ ግን ህፃናት፣ ጧሪ የሌላቸው አረጋውያን እና በልመና የሚተዳደሩ ዜጎች አስቸኳይ ድጋፉ እንደሚሰጣቸው አስረድተዋል። ድጋፉ ሲዳረስም የመንግሥት ሠራተኞችን ጨምሮ ደመወዛቸው በባንክ ያሉ ነዋሪዎች እና ለሌሎች ዜጎች ድጋፍ ማቅረብ እንደሚቻል ገልፀዋል። ከተለያዩ የፌዴራል ተቋማት የተላኩ ተወካዮች በትግራይ ክልል የሚኖሩ ዜጎች ያሉባቸውን የሰብአዊ ድጋፍ እና አስቸኳይ የመሰረተ ልማት አቅርቦቶች እንዲሁም ተያያዥ ችግሮች በቀጣይነት የሚፈቱበት ሁኔታ ላይ በትግራይ ከተቋቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር ተወያይተዋል። ህብረተሰቡ በውሃ በኩል ያለበትን ችግር መፍትሄ እንዲያገኝ ከውሃ መስኖ ሚኒስቴር የመጡ ተወካዮች እንደሚያስተባብሩ ታውቋል። የህፃናት፣ እናቶችን እና አረጋውያን ጉዳዮችን ደግሞ የሴቶችና ህፃናት ሚኒስቴር ተወካዮች ያስተባብራሉ። ቀድሞ በሴፍቲኔት ታግዘው ድጋፍ ሲያገኙ የነበሩ ሥር የሰደደ የምግብ አቅርቦት ችግር ያለባቸውን ዜጎችን ጉዳይ ደግሞ የግብርና ሚኒስቴር እንደሚያስተባብር ታውቋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 4/2013 | https://www.press.et/Ama/?p=37250 | 349 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ከጀግኖቹ አንደበት | ስፖርት | October 10, 2019 | 32 | ከቀናት በፊት የኢትዮጵያን ተስፋዎች አስከትላ በ17ኛው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ላይ የተሳተፈችው የባርሴሎና ኦሊምፒኳ ንግስት፤ ድል ቀንቷት በሜዳሊያ የታጀበ ቡድኗን ይዛ ወደ አገሯ ተመልሳለች። በኤድመንተንና ጉተምበርግ ቻምፒዮናዎች በወርቅ እና የብር ሜዳሊያዎቿ ኢትዮጵያውያንን ያስፈነደቀችው ኮሎኔል ደራርቱ ቱሉ ቦታዋን ቀይራለች። የአገሯን ብሔራዊ መዝሙር ስትሰማ በሃሴት የምታነባው ብዙዎች የእናትነት ተምሳሌት የሚሏት የቀድሞዋ አትሌት፤ አሁን ሌሎችን ለውጤታማነት መትጋቱን ተያይዛለች። የእርሷን ዱካ የተከተሉትን በዝግጅትና ውድድራቸው እያበረታታች ሲያሸንፉም እቅፍ አበባ እያበረከተች መምራቱንም አጠናክራለች። በአትሌቲክስ ስፖርት ታላቁ ውድድር የመራቻቸው በወጣትና አዳዲስ አትሌቶች የተዋቀረው ቡድን በተሳተፈባቸው ሰባት ርቀቶች ሁለት የወርቅ፣ አራት የብር እና አንድ የነሐስ በጥቅሉ ሰባት ሜዳሊያዎችን አስመዝግቧል። ይህም በአገራት የደረጃ ሰንጠረዥ ከዓለም አምስተኛ ከአፍሪካ ደግሞ ኬንያን ተከትላ በሁለተኛነት እንዲያጠናቅቅ አድርጓል። የብሔራዊ ቡድን አባላቱም በዶሃ የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው ትናንት ማለዳ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳ፣ የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ጌታቸው ባልቻ፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት አትሌት ገብረእግዚአብሔር ገብረማርያም፣ የአትሌቶች ማህበር ፕሬዚዳንት አትሌት ማርቆስ ገነቴ እንዲሁም ሌሎች የሙያ ማህበራት እና የክለብ አመራሮች ተገኝተው የአበባ ጉንጉን አበርክተውላቸዋል። ሜዳሊያ ያስመዘገቡ በርካታ አትሌቶች በተለያዩ አገራት ውድድሮች ስላሉባቸው ከልዑካን ቡድኑ ጋር አልተመለሱም። አዲስ ዘመን በስፍራው ተገኝቶ የተወሰኑትን የሜዳሊያ ባለቤቶች እንደሚከተለው አነጋግሯል። ሙክታር ኢድሪስ በአምስት ሺ ሜትር ለሁለተኛ ጊዜ የዓለም ቻምፒዮን የሆነው አትሌት ሙክታር እድሪስ በዶሃ የነበረው የአየር ሁኔታ ለቡድኑ ከባድ ቢሆንም ጥሩ ውድድር በማድረግ በድል መመለሳቸውን ገልጿል። ለረጅም ጊዜ በጉዳት ላይ የቆየው ሙክታር ለቡድኑ ሞራል በሚል ወደ ዶሃ ቢያቀናም የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት መሆኑ ደስታውን እጥፍ አድርጎለታል። እንደ ቡድንም ጥሩ ቆይታ በማድረግ መልካም የሚባል ውጤት መመዝገቡን ተናግሯል። በውድድሩ ወቅት የነበረውን ሁኔታ ሲያስረዳም «ወደ ውድድር ከመግባታችን በፊት አብረውኝ ከሮጡት ሰለሞን ባረጋ እና ጥላሁን ኃይሌ ጋር እግሬን ሊያመኝ ስለሚችል እኔ ላግዛቸው እነርሱ ደግሞ ሊሮጡ ተነጋግረን ነበር። የመጀመሪያውን ሁለት ዙር እኔ በመምራት ከዚያ በኋላ ያሉትን ደግሞ እነርሱ አክርረው በመሮጥ ከፍጻሜ ለመድረስም ነበር ያቀድነው። በዚህ መሠረት ነበር እየተጠባበቅን የሄድነው፤ ነገር ግን የኖርዌይና የአሜሪካ አትሌቶች ሰለሞንን እንደያዙት ስመለከት ለአገሬ ካልሆነ እግሬ ይቆረጥ ብዬ ወደፊት በመውጣት አሸናፊ ሆንኩ። በዚህ በጣም ደስተኛ ነኝ»
ብሏል። በአቀባበሉ ላይም «እኛ በመም ላይ እንታይ እንጂ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከእኛ እኩል እንደሚሮጥ እናውቃለን፤ እኔ እንዳሸንፍ ያደረገኝም የሕዝቡ ጸሎት ነው። ምክንያቱም በህመም ላይ ነበር የቆየሁት፤ ለመቅረትም አስቤ ነበር። ከሐኪሜ ጋር በመነጋገር ለሙከራ ሄድኩ እንጂ እንደሌላው ጊዜ ልምምድ ሰርቼ አልነበረም። የሕዝቡ ጸሎት ነው የደረሰልኝና ለዚህ ድጋፍም በጣም እናመሰግናለሁ። ከአንድ ዓመት ያነሰ ጊዜ ለቀረው ኦሊምፒክም እንደዚሁ ላለመደፈር እንታገላለን» በማለት ምስጋናውን ከማቅረብ ባሻገር ለቀጣዩ ኦሊምፒክ ቃል ገብቷል። ሌሊሳ ዴሲሳ በዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ታሪክ ከ18ዓመታት በኋላ በማራቶን ሁለተኛው የወርቅ ሜዳሊያ በዶሃ ተመዝግቧል። የሜዳሊያው ባለቤት ሌሊሳ ዴሲሳ «ውድድሩ የተካሄደው በእኩለ ሌሊት መሆኑና የቦታው ከፍተኛ ሙቀት ተዳምሮ ሰውነትን የማድቀቅና የእንቅልፍ ስሜት መጫጫን ስለሚሰማ ለሰውነት ነፃነት አይሰጥም ነበር። ቢሆንም ለእኛ ተሳክቶልናል፤ በዚህም ደስተኛ ነኝ» በማለት በውድድሩ የነበረው ቆይታ ይናገራል። ሙቀቱ ጫና የሚያሳድር በመሆኑ ምክንያት በሰውነታቸው ድርቀት እንዳይከሰት እርሱና አጋሮቹ ቶሎ ቶሎ ውሃ በማንሳት እየተቀባበሉ መሄዳቸውም ለውጤቱ መገኘት ሚና እንደነበረውም ያስታውሳል። አትሌቱ በዚህ ቻምፒዮና አሸናፊ በመሆን የአገሩን እንዲሁም የራሱን ስም ለማስጠራትም ጠንካራ ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን ያስታውሳል፤ «የአየር ሁኔታውን ለመላመድ በስቲምና ሳውና ባዝ እንዲሁም ወደ ሶደሬ፣ አዳማ እና ቢሾፍቱ በመጓዝ ጭምር ተዘጋጅቻለሁ። ከዚህ ውጪም የፀሐይ ግለት በሚጨምርበት ጊዜ ልምምድ አደርግም ነበር» በማለት የስኬቱን ምስጢር ይናገራል። በዶሃ ቆይታው በተለይ ኢትዮጵያውያን ያደርጉላቸው የነበረው ድጋፍ ከፍተኛ እንደነበረም ሌሊሳ ተናግሯል። ለሜቻ ግርማ ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም በማትታወቅበትና ኬንያውያን አትሌቶች በነገሱበት የ3ሺ ሜትር መሰናክልም አዲስ ታሪክ በወጣቱ አትሌት ለሜቻ ግርማ ተመዝግቧል። ብሔራዊ ቡድኑን በቅርቡ የተቀላቀለው ወጣቱ አትሌት «ጥሩ ውድድር ነበረ፤ ውጤት በማስመዝገቤም ተደስቻለሁ። ወደ ውድድሩ ከመግባቴ አስቀድሞ አሸናፊ ለመሆን ነበር ዝግጅት ሳደርግ የቆየሁት፤ በዚህም ስኬታማ ሆኛለሁ። እስካሁን በሦስት ዓለም አቀፍ ውድድሮች ተሳትፎዬ መልካም የሚባል ውጤት አለኝ» ሲልም ይገልጻል። ጉዳፍ ጸጋዬ በቻምፒዮናው ላይ በሴቶች
ምድብ ከተመዘገቡት ሁለት
ሜዳሊያዎች መካከል አንዱ
በ1ሺ500 ሜትር
የተገኘ ነው። በዚህ
ውድድር የነሐስ ሜዳሊያውን
ያጠለቀችው ደግሞ አትሌት
ጉዳፍ ጸጋዬ፤ በቻምፒዮናው
አሸናፊ ለመሆን ዝግጅት
ስታደርግ መቆየቷን ታስታውሳለች።
ብዙም ባልተለመደው በዚህ
ርቀት ታሪክ ሁለተኛዋ
ባለሜዳሊያ አትሌት ከመሆኗም
ባሻገር ያስመዘገበችው 3፡54.38
የሆነ ፈጣን ሰዓት
እንዳስደሰታትም ገልጻለች። በኢትዮጵያውያን
ድጋፍ እንዲሁም አቀባበሉ
ያስደሰታት አትሌቷ «ያገኘሁት
ውጤት ለቀጣይ የሚያበረታታኝ
በመሆኑ ለኦሊምፒኩም ውጤታማ
ለመሆን ጠንክሬ እሰራለሁ» በማለት ቀጣይ
እቅዷን ገልጻለች። አዲስ ዘመን መስከረም
29/2012 ብርሃን ፈይሳ | https://www.press.et/Ama/?p=20446 | 626 | 2ስፖርት
|
መንግሥት በትግራይ ክልል የሚያካሂደውን ሁለንተናዊ ሰብዓዊ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለፀ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 14, 2020 | 16 | በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ፡- መንግሥት በትግራይ ክልል የሚያካ ሂደውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለፀ:: ይህ የተገለፀው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ኬንያ እና ማላዊ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በተወያዩበት ወቅት ነው::እንደ ፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት ዘገባ፤ ውይይቱ ቅዳሜ ህዳር 3 ቀን 2013 ዓ.ም በበይነ መረብ (ቨርቹዋል) የተካሄደ ሲሆን፤ በወቅቱም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኬንያ እና ማላዊ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በዚህ ፈታኝ ጊዜ ላሳዩት ሀገራዊ ስሜት እና ላደረጉት ድጋፍ አመስግነው መንግሥት በአሁኑ ወቅት በትግራይ ክልል የሚያካሂደውን ሁለንተናዊ ሰብዓዊ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ለተሳታፊዎቹ ገልፀውላቸዋል።ሀገራችን ከውስጧ በተነሱ ከሃዲዎች ሉዓላዊነታችንን አደጋ ላይ የጣለውን፣ ጭካኔና አሳፋሪ ድርጊት የተፈፀ መበትን ሁኔታ ለመለወጥ፣ ሕግን ለማስከበር፣ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ መንግሥታችን ያካደሄው ፈጣንና ውጤታማ ተልዕኮ በሕዝባችን ድጋፍና አብሮነት፣ በቁርጠኛው መከላከያ ሠራዊታችን እና ልዩ ልዩ የፀጥታ አካላት አብሮ በመዋደቅ የተገኘው ድል የሁላችንም ድልና ኩራት ነው ብለዋል።በዚህ ኢ-ሰብዓዊና ጭካኔ በተሞላበት ተግባር የተሰማሩ ግለሰቦች ለሕግ እንዲቀርቡም መንግሥት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እንሚሠራም ተናግረዋል። በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያ መንግሥትና አቋሞች በማስረዳት፣ ለመልሶ ማቋቋሙ እና ዳግም ግንባታው አስተዋጽኦ በማድረግ መንግሥት በሚያደገርው ጥረት እንዲደግፉም ጥሪ አቅርበዋል።በኬንያ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር መለስ ዓለም በበኩላቸው፣ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት አገራችን በህወሓት አፍራሽ ሃይል ተገዳ ወደ ሕግ ማስከበር መግባቷን ተከትሎ በኬንያ እና ማላዊ የሚኖሩ ወገኖቻችን ላሳዩት የጋለ ብሔራዊ ስሜት እና ላደረጉት ድጋፍ አመስግነዋል። መንግሥት እያካሄደ ያለውን የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ፣ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን የመጠበቅ እና የዜጐችን ደህንነት የማስከበር ዘመቻ እንዲሳካ በኬንያና ማላዊ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሙያተኞች እና ነጋዴዎች ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ጠቅሰው፤ በገንዘባቸው፣ በእውቀታቸው ባላቸው ግንኙነት የህዝብ አምባሳደር ሆነው ስለአገራቸው አቋምና ፍላጐት ዘብ መቆማቸውን ተናግረዋል። በቀጣይም ወንጀለኞችን ለሕግ ለማቅረብ፣ የተፈናቀሉትን ለማቋቋም እና የፈረሰውን ለመገንባት መንግሥት በሚያደርገው ዲያስፖራው የሚጠበቅበትን ሁሉ እንደሚያደርግ ሚሲዮኑ ሙሉ እምነት እንዳለውም አምባሳደር መለስ ገልፀዋል::አዲስ ዘመን ታህሳስ 5/2013 | https://www.press.et/Ama/?p=37305 | 278 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
መከላከያ ሰራዊት የታደገው የአሲምባው ወጣት | ሀገር አቀፍ ዜና | December 13, 2020 | 51 | ክብሮም መሰለ ይባላል፡፡ ትውልዱና እድገቱ ትግራይ ክልል አሲምባ አካባቢ ነው፡፡ የ17 ዓመት ታዳጊና የዘጠነኛ ክፍል ተማሪ ነው፡፡ አላማውና ምኞቱ ተምሮ እራሱንና ቤተሰቡን መለወጥ ነው፡፡ “በጥባጭ ካለ ማን ጥሩ ይጠጣል” እንዲሉ የጁንታው
ታጣቂዎች አንድ ቀን ሌሊት መጥተው እርሱንና ጓደኞቹን በመኪና ጭነውን ወደ ራያ ግንባር ወሰዷቸው፡፡ ለጁንታው ታጣቂ ቡድን ጥይት እንዲያቀብሉና እግረመንገዳቸውን ውጊያ እንዲለማመዱ ተነገራቸው። ሸሽተው የሚሄዱ ከሆነ ደግሞ ተይዘው እንደሚረሸኑ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው፡፡ ክብሮም በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ እንዲህ ያስረዳል፤ ‹‹የህወሓት ታጣቂዎች ሌሊት መጥተው እኔና ጓደኞቼን ከተኛንበት ቀስቅሰው ተሳቢ መኪና ጭነው ወሰዱን፡፡ ከአንድ ቀን ጉዞ በኋላ ራያ ግንባር መኾኔ ከተማ አጠገብ ካለው የታጣቂዎቹ ምሽግ ደረስን፤ ሃይለኛ የተኩስ ልውውጥ እየተደረገ ነበር፤ ለታጣቂዎቹ ጥይት ይዤ ወደ ተኩሱ መሃል እንደገባ አዘዙኝ፡፡ በሰላም ከምኖርበት ቦታና ከቤተሰቦቼ በድንገት ተለይቼ እሳት ውስጥ ስገባ ግራ ገባኝ፡፡ ከፊታችን መከላከያ ሰራዊት ወደእኛ ይተኩሳል፤ ከኋላም የታጣቂው አመራሮች በአይናቸው ይጠብቁናል፤
ሊተኩሱብን ተዘጋጅተዋል፡፡ ወደየትም ማምለጥ አይቻልም”“ያለህ አማራጭ ሳትወድ በግድ ባለህበት መሆን ነው፡፡ የመከላከያ ሰራዊት ጥቃት እየከፋ ሲመጣ በጣም ከመደንገጤ የተነሳ ቦታዬን ለቅቄ ወደ ኋላ ማፈግፈግ ጀመርኩ፡፡ እኔ የሰለጠንኩ ወታደር አይደለሁም፤ የጦርነት ልምድም የለኝም፤ ወጊያ አይቼ አላውቅም ብላቸውም ሊሰሙኝ አልቻሉም፤ ከኋላ ያለው አዛዥ ወደ ኋላ እንዳልመለስ ያስፈራራኛል፡፡ ዝም ብዬው ወደ ኋላ ሸሸሁ፤ አስቀድሞ ማስጠንቀቂያ ቢሰጥም ወገኑ ነኝና ጨክኖ የሚመታኝ አልመሰለኝም ነበር፡፡ ግን ሽጉጡን አውጥቶ ተኮሰብኝ፡፡ የቀኝ ታፋዬ ላይ መታኝ ፤ እዛው ወደቅኩኝ፤ አንድ ሙሉቀን እዛው ተኛሁ፤ ብዙ ደም ፈሰሰኝ፤ ተኩሶ የመታኝ ሰው ኮለኔል ግርማይ በርሄ ይባላል፡፡ ሀሳቡ ሊገድለኝ ነበር እግዚአብሄር ግን ጠበቀኝ”ወጣቱ እንደሚናገረው፤
ህዳር 9 ከቤቱ ወደ ግንባሩ ወሰደውት
ህዳር 11 በጥይት መትተው ጫካ ውስጥ ጥለውት ሄዱ፡፡ መከላከያ ሰራዊት ቦታውን ሲቆጣጠረው ከወደቀበት
አንስቶ የመጀመሪያ እርዳታ አደረጉለት።
“በልጅነቴ አይጋ አካባቢ ስማር ደብተር እና አስኪብሪቶ እየገዙ፣
ምግብ እያበሉኝ፣ ልብስ እያለበሱኝ፣ ጫማቸውን አውልቀው እየሰጡኝ ያስተማሩኝ የምወዳቸው ባለውለታዎቼ የመከላከያ ሰራዊት አባለት አሉ፡፡ አንዱ ገቢሳ ይባላል አንዱም መለሰ ይባላል አልረሳቸውም፡፡ አብረን እንማር ነበር፡፡ ሁልጊዜ በትምህርቴ እንድጎብዝ ይመክሩኝ ነበር፡፡ ያሳደጉኝ ቤተሰቦቼ ሳይሆኑ እነርሱ ናቸው፡፡ እወዳቸዋለሁ ፤ ይናፍቁኛል፡፡ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ይደውሉልኝ ነበር” ይላል
ወጣቱ፡፡ መከላከያ ሰራዊት ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለትግራይ ህዝብ ባለውለታ ነው” የሚለው
ወጣቱ፤ “ሁሉም ሰው በሰላም ተኝቶ የሚያድረው በመከላከያ ሰራዊት ነው፡፡ ከጠላት ይጠብቁታል፤ በጉልበትና በገንዘብ ያግዙታል፡፡ ያሁሉ ውለታው ተረስቶ መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት በመፈጸሙ በጣም አዝናለሁ፡፡ ይህንን ድርጊት የፈጸሙ አካላት ተይዘው ፍርድ እንዲሰጣቸው እፈልጋለሁ”
ሲልም ነው ስሜቱን የገለጸው።“አሁን እኔ ቆስዬ እያነከስኩ በህይወት አለሁ። እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፡፡ ብዙ ጓደኞቼ ሞተዋል፡፡ ከወደቅኩበት አንስተው ያሳከሙኝን የመከላከያ ሰራዊትንም አመሰግናለሁ፡፡ አሁንም እያሳከመኝ ያለውን የቆቦ ወረዳ አመሰግናለሁ፡፡ የትግራይ ወጣቶች ሰላማዊ መንገድን እንዲከተሉ እመክራቸዋለሁ፤ አትሞኙ የቻላችሁትን መንገድ ተጠቅማችሁ ወደ ቤታችሁ ግቡ ማለት እፈልጋለሁ”“የራሳቸውን ልጆች ውጭ እያስተማሩ የደሃ ልጆችን ለሚያስገድሉ አመራሮች ታዛዥ አትሁኑ እላቸዋለው፡፡ ህይወታችሁን አትርፉ እላቸዋለሁ፡፡ የትግራይ ወጣት ከዚህ በኋላ ሰርቶ የሚበላበትና የሚድገግበት ጊዜ ስለመጣ መንግስትን ሊደግፍ ይገባል፡፡ እነዚህ ትግራይን የሚበጠብጡ አመራሮች የመንግስትን በጀት ለራሳቸው የሚጠቀሙ ሌቦች ናቸው፡፡ የትግራይ ህዝብ ፈርቶ ነው እንጂ ሁሉንም ያውቃል፡፡ አነዚህ ሌቦች የትግራይን ህዝብ ከኢትዮጵያ ህዝብ ለመለየት ነው የሚጥሩት፡፡ ይህ ደግሞ አይሳካም፤ በምንማረው ትምህርት ውስጥ ሳይቀር ልዩነትን ያስተምራሉ፡፡ አንዱ ብሄር በሌላው ላይ ጥላቻ እንዲኖረው ያደርጋሉ፤ በተለይ በታሪክ ትምህርት ውስጥ የሚቀርበው ነገር ችግር የሚፈጥር ነበር፡፡ ለምሳሌ አጼ ቴዎድሮስ እከሌን ገድሎ ስልጣን ያዘ፤ አጼ ሚኒልክ የእከሌን ብሄር አጠቃ የሚል ትምህርት ማስተማር ተገቢነት የሌለው ነው”፡፡ “እንዲህ አይነቱ ትምህርት እውቀትን የሚያስጨብጥ ሳይሆን ክፋትን የሚያስተምር ነው፡፡ ኢትዮጵያ ህዝቦች አንድነታቸውንና ፍቅራቸውን ጠብቀው ሊሄዱ ይገባል፡፡ የሰዎች ቋንቋ፣ ሃይማኖት ባህል ተጠብቆ በሰላም መኖር ይኖርባቸዋል፡፡ እነዚህ የትግራይ አመራሮች የትግራይን ህዝብ አዋርደውታል፤ አቀርቅሮ እንዲሄድ አድርገውታል፤ ግን ህዝቡን አይወክሉም፤ ነገ የተሻለ ጊዜ ይመጣል ብዬ አስባለሁ፡፡ የትግራይ ህዝብ እነዚህን ሰዎች እንደማይደግፋቸው የኢትዮጵያ ህዝብ ማወቅ አለበት ›› ሲል ነው ሀሳቡን የቋጨው፤ ክብሮም መሰለ። በኢያሱ መሰለ | https://www.press.et/Ama/?p=37298 | 529 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የአትሌት ደምሰው ፀጋ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፀመ | ስፖርት | October 11, 2019 | 17 | የአትሌት ደምሰው ፀጋ የቀብር ስነስርዓት በትውልድ መንደሩ ጫጫ ክርስቶስ ሳምራ ቤተክርስቲያን ትናንት ስምንት ሰዓት ላይ ተፈፅሟል፡፡ በቀብር ስነስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፅሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ቢልልኝ መቆያን ጨምሮ ፣ ወዳጅ ጓጀኞቹ ፣የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ኃላፊዎች ፣ የተለያዩ አትሌቶች፣ ማናጀሮች፣ አሰልጣኞች ተገኝተዋል፡፡ አትሌት ደምሰው_ፀጋ በ1980 ዓ.ም በሰሜን ሸዋ ዞን በአንጎለላ ጠራ ወረዳ በጫጫ ቀበሌ በጦጦሴ መንደር የተወለደ ሲሆን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን ከ1988—1991 ዓ.ም በጦጦሴ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ከ1992—1995 ዓ.ም በጫጫ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከታተለ። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ደግሞ በ1996 ዓ.ም በደብረብርሃን አጠቃላይ 2ኛደረጃ ትምህርት ቤት ተከታትሏል፡፡ አትሌት ደምሰው ትምህርቱን እየተከታተለ በመረብ ኳስ፣ በቅርጫት ኳስ እና በገና ጨዋታ የተዋጣለት ስፖርተኛ እንደነበረ የሕይወት ታሪኩ ያስረዳል፡፡ በኋላም በስፖርት መምህሩ ምክር ወደ አትሌቲክስ ስፖርት አመራ፡፡ በ1997 ዓ.ም በዞንና በወረዳ ደረጃ በሚካሄዱ የ3፣5ና 10ሺ ሜትር ውድድሮች ውጤታማ መሆኑን ተከትሎ ወደ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ሊመጣ ችሏል፡፡ አትሌት ደምሰው ዓለም አቀፍ ውድድሮችን እኤአ በ2006 ማድረግ የጀመረ ሲሆን ከ2006 እስከ 2015 ድረስ በ9 አመት ውስጥ በህመም ምክንያት ወጣ ገባ እያለ 24 ውድድሮችን አድርጓል። ከነዚህ ውድድሮች ውስጥ ሶስቱ ሀገሩን ኢትዮጵያን የወከለባቸው ውድድሮች ናቸው። በኬንያ ሞምባሳ፣ በጃፓን በቶኪዮ በ5ሺ እና በ10 ሺ ሜትሮች እንዲሁም በማራቶን ተሳትፎ ሜዳሊያ አግኝቷል። አትሌት ደምሰው የአንደኛ ደረጃ የአሰልጣኝነት ኮርስን የወሰደ ሲሆን፤ የሩጫ ሕይወቱ በፈለገው ደረጃ እንዳያድግ እንቅፋት የሆነበት ሕመም ሲሰማው ወደ ትውልድ መንደሩ እያመራ በርካታ አትሌቶችን በማሰልጠን ማፍራት ችሏል፡፡ አትሌት ደምሰው የአንድ ወንድና የአንዲት ሴት ልጅ አባት ሲሆን ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ ኑሮውን በአሜሪካ አድርጓል፡፡ ባደረበት ፅኑ ህመም ምክንያት ህክምናውን በአሜሪካ ሚሪላንድ ግዛት ሲከታተል ቆይቶ መስከረም 24 ቀን 2012 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል። አዲስ ዘመን ለአትሌቱ ቤተሰቦች፣ጓደኞችና የስፖርት ቤተሰቦች የተሰማውን ሃዘን ይገልፃል፡፡አዲስ ዘመን መስከረም 30/2012 ቦጋለ አበበ | https://www.press.et/Ama/?p=20471 | 254 | 2ስፖርት
|
የፌዴሬሽንና የክለቦች ውረድ አትውረድ ድራማ | ስፖርት | October 11, 2019 | 16 | አጨቃጫቂና አሰልቺ ከነበረው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የፕሬዚዳንትነትና ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነት የምርጫ ሂደት በኋላ አፋር ሰመራ ላይ ግንቦት 26 ቀን 2010 ዓ.ም አዲሱ አመራር ወደ ኃላፊነት መምጣቱ ይታወሳል፡፡ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት አቶ ኢሳያስ ጅራና ሥራ አስፈጻሚው በሚፋጀው ወንበር ላይ በኃላፊነት ከተቀመጡ ከአንድ ዓመት በላይ እስቆጥረዋል፡፡ ፌዴሬሽኑን ለመምራት ብዙ ውጣ ውረዶችን ተሻግሮ የመጣው ቡድን የፈተናዎች መደራረብ ወደፊት አላስኬድ እንዳሉት ለመታዘብ እየተቻለ ይገኛል። ፌዴሬሽኑን አጣብቂኝ ውስጥ እንዲገባ በይበልጥ እንቅፋት ከሆኑት ጉዳዮች መካከል የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጉዳይ አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ በእግር ኳሱ ላይ ፖለቲካዊ ጥላ ማጥላቱ ፌዴሬሽኑ የሚያሳልፋቸውን ውሳኔዎች ይበልጥ በርካታ ፈተናዎችን እንዲጋፈጥ ምክንያት ሲሆን ለመታዘብ ተችሏል፡፡ በኢትዮጵያ ኳስና ፖለቲካው በተደበላለቁበት ሁኔታ ፕሪሚየር ሊጉን መሰረት አስይዞ ለመምራት ዳገት ሆኗል። ክለቦች ተዘዋውረው የመጨዋወት ህልውናቸውን እስኪያጡ ደርሰዋል፡፡ ፌዴሬሽኑ መስመር ለማስያዝ በተለያዩ ጉዳዮች የሚያስተላልፋቸው ውሳኔዎች በተደጋጋሚ መሬት ለመውረድ እግር ሲያጥራቸው ይስተዋላሉ።ፌዴሬሽኑ በፕሪሚየር ሊጉ የሚስተዋለውን የስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል መፍትሄ ለማምጣት አዲስ የሊግ የውድድር ሥርዓትን (ፎርማት) ተግባራዊ ለማድረግ ያሳለፈው ውሳኔም ተቀባይነት ማግኘት አልቻለም፡፡ ተግባራዊ ለማድረግ የታሰበው የሊግ ውድድር ሥርዓት በፕሪሚየር ሊጉ የሚሳተፍ ክለቦችን ቁጥር ከ16 ወደ 24 ከፍ የሚያደርግ መሆኑ ብዙ ውዝግብ ፈጥሯል፡፡ ፌዴሬሽኑ በ2011 የውድድር ዘመን ከፕሪሚየር ሊጉ የወረዱትን መከላከያ፣ደቡብ ፖሊስና ደደቢትን በነሀሴ ወር ይፋ ባደረገው የሊግ አደረጃጀት ለውጥ ምክንያት በሊጉ እንደሚቆዩ ከውሳኔ ደርሶ ነበር።በተጨማሪም ስምንት ከከፍተኛ ሊግ የሚገኙ ክለቦች አካል አድርጓል። የፌዴሬሽኑን ውሳኔ ተከትሎ ክለቦቹ ዝግጅታቸውን ፕሪሚየር ሊጉን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ሲያደርጉ ቆይተዋል።የክለቦቹ የተጫዋቾች ዝውውርም ይሄንኑ ታሳቢ በማድረግ ዝግጅት ሲያደርጉበት ቆይተዋል። ፌዴሬሽኑ በ24 ቡድኖች አደርገዋል ያለው ውድድር ብዙም ሳይቆይ መሻሩን ተከትሎ ፌዴሬሽኑን አምነው ለፕሪሚየር ሊግ ሲያዘጋጁ የከረሙትን ክለቦች ውሃ በልቷቸዋል፡፡ የፌዴሬሽኑን የውሳኔ ዥዋዥዌ ተከትሎ ቅሬታቸውን በአደባባይ ከገለጹት ክለቦች መካከል አንዱ የሆነው መከላከያ እግር ኳስ ክለብ ይጠቀሳል። የመከላከያ ክለብ ፕሬዚዳንት ኮሎኔል ደረጀ መንግስቱ ክለቡ ከመሰረቱ ጀምሮ ቅሬታ ውስጥ እንደነበረ በማስረዳት ይናገራሉ። በ2011 የውድድር ዘመን መከላከያ 14ኛ ደረጃን በመያዝ ከፕሪሚየር ሊጉ ቢሰናበትም በወልዋሎና ሽረ እንዳስላሴ ጨዋታ ቅሬታን በወቅቱ ለፌዴሬሽኑ አስገብቶ እንደነበር ያስታውሳሉ። ከፌዴሬሽኑ ምላሽ ሳይሰጠው እንደቆየ የሚናገሩት ኃላፊው፤ ክለቡ የፌዴሬሽኑን ውሳኔ በመጠባበቅ እያለ ነሃሴ ወር መጀመሪያ መመሪያ እንደተሰጣቸው ያብራራሉ። ክለቡ በዚህም መመሪያ መሠረት በፕሪሚየር ሊጉ ለመወዳደር ሲዘጋጅ ቆይቶ አዲሱ ፎርማት ዳግም መቀየሩ እርግጥ ሆኗል፡፡ በአዲሱ ፎርማት መሠረት በፕሪሚየር ሊጉ ትሳተፋላችሁ በተባለው መሰረት በፕሪሚየር ሊጉ ለመሳተፍ ክለቡ ዝግጅት እያደረገ ባለበት ወቅት ይህን አይነት ውሳኔ መሰማቱ ክለቡን በከፍተኛ ሁኔታ ቀውስ ውስጥ የሚያስገባው መሆኑን ያስረዳሉ ።«በ24 ክለቦች መካከል እንዲካሄድ የተወሰነው ውሳኔ ስለመታጠፍ አልያም ፤የተወሰነው ውሳኔ ይሄ ነው በሚል የተገለጸልን ነገር የለም» ሲሉ ፕሬዚዳንቱ ከፌዴሬሽኑ በኩል ስለ ውሳኔው መቀየር እስካሁን አንዳችም ነገር የተባሉት ነገር እንደሌለና በደብዳቤም እንዳላሳወቃቸው ያመላከቱት። ህጋዊ ሆኖ የመጣ ውሳኔ ባይኖርም የሚለወጥ ነገር ከመጣ ግን ክለቡ የራሱን ውሳኔ የሚወስን መሆኑንም ነው ያሳሰቡት። ክለቡ በሚወስደው እርምጃ ዙሪያ ከመናገር የተቆጠቡት ፕሬዚዳንቱ ክለቡ ከፌዴሬሽኑ በኩል ይፋዊ ደብዳቤ ሲደርሰው አቋማቸውን እንደሚያሳውቁ ነው ያስገነዘቡት። የፌዴሬሽኑን የውሳኔ ተለዋዋጭነት ተከትሎ ቅሬታን ካሰሙት ክለቦች መካከል የደቡብ ፖሊስ እግር ኳስ ክለብ ይጠቀሳል። ክለቡ በሊግ አደረጃጀቱ ላይ ለውጥ ተደርጎ ሊጉ በ16 ክለቦች እንዲቀጥል መወሰኑ አግባብ እንዳልሆነ በመግለጽ በብሄራዊ ፌዴሬሽኑ ላይ ቅሬታውን እያሰማ ይገኛል። የክለቡ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኢንስፔክተር እታገኝ ዜና ለሶከር ኢትዮጵያ በሰጡት አስተያየት ‹‹ለፕሪሚየር ሊጉ ዝግጅት በማድረግ ላይ እያሉ የውሳኔ ለውጥ መደረጉ ያሳዝናል›› ብለዋል፡፡ ‹‹ፌዴሬሽኑ እየበጠበጠን ነው›› ያሉት ኢንስፔክተር እታገኝ በ2012 ዓ.ም በፕሪሚየር ሊጉ ተሳታፊ በመሆናቸው ዝግጅት እንዲያደርጉ ደብዳቤ ደርሷቸው ነበር፡፡ የፌዴሬሽኑን ደብዳቤ መሰረት በማድረግ ለፕሪሚየር ሊጉ ዝግጅት ሲያደርጉ በመቆየትም ፕሪሚየር ሊጉ ላይ ተሳታፊ መሆንን ታሳቢ በማድረግ በጀት እንደተያዘ ያብራራሉ፡፡ ‹‹አሰልጣኝም ሆነ ተጫዋቾችን ያስፈረምነው ይሄንኑ ታሳቢ በማድረግ ነው።የፌዴሬሽኑ ውሳኔ እንደ ክለብ ጎድቶናል፣ለምሳሌ የፌዴሬሽኑን ውሳኔ የሰሙ ተጫዋቾች ዛሬ ልምምድ ላይ ሳይገኙ ቀርተዋል። የእነሱም ዝግጅት ለፕሪሚየር ሊጉ እንጂ ለሌላ አልነበረም። በአጠቃላይ ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ እኛ ላይ ችግር እየፈጠረ ነው። በተለይ ደግሞ በየጊዜው እያሳየ የሚገኘው የሃሳብ መለዋወጥ አሳዝኖናል›› ይላሉ። በፌዴሬሽኑ የውሳኔ መለዋወጥ ቅሬታ የተሰማቸው ክለቦች ከተጠቀሱት ክለቦች በተጨማሪ እንደሌሉ መጥቀስ ይቻላል፡፡ ፌዴሬሽኑ በእውቀት ሳይሆን በይሆናል መንገድ፤ በስሌት ሳይሆን በስሜት የሚወስናቸው ውሳኔዎች ዋጋ እንዳስከፈላቸው እየተናገሩም ይገኛሉ። በአዲሱ የሊግ አደረጃጀት መሰረት ለፕሪሚየር ሊጉ ዝግጅታቸውን እያደረጉ ባሉበት ሁኔታ እንዲህ አይነት የውሳኔ መዋለል መታየቱ በርካታ ክለቦችን ጎድቷል። ፌዴሬሽኑ የወሰነው ውሳኔ ከመሰረቱ ጥናት ያልተደረገበት መሆኑ ደግሞ የፌዴሬሽኑን ተጠያቂነት ይበልጥ ያጎላዋል። ፌዴሬሽኑ ተጠያቂነትን ባልወሰደበት ሁኔታ ብሎም የፕሪሚየር ሊጉ መጨረሻ ሳይለይለት የ2012 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን በወርሃ ጥቅምት መጨረሻ እንደሚጀምር በአቋሙ እንደፀና ይገኛል። የውድድር መርሃ ግብሩን በ24 ክለቦች መካከል ለማድረግ ውሳኔ ካስተላለፈ ከቀናት በኋላ ሃሳቡን ቀይሮ በ16 ቡድኖች እንደሚወዳደሩ እርግጥ ሆኗል፡፡ የፌዴሬሽኑን መወላወል ተከትሎ ቅሬታዎች መሰማታቸው ፕሪሚየር ሊጉ በወርሃ ጥቅምት መካሄዱ ብቻም ሳይሆን ፤በዚህ ዓመት ሊጉ ራሱ ስለመካሄዱ ጥርጣሬ እንዳለ ጭምር እየተነገረ ይገኛል። ፌዴሬሽኑ ፕሪሚየር ሊጉን ማካሄድ ይችል ይሆን? የሚለውን ጥያቄ የስፖርት ቤተሰቡ በከፍተኛ ጉጉት እየተጠባበቀ ይገኛል። ይፋዊ ያልሆኑ ሰሞኑን እየተሰሙ የሚገኙ አንዳንድ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ግን መከላከያ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ለማደግ 99% እድል አለው። ለዚህም መከላከያ ከወረደ ቅዱስ ጊዮርጊስና ሽሬ እንዳስላሴ ይወርዳሉ የሚሉ መላ ምቶች ገፍተው እየወጡ ነው፡፡ ለዚህም በቂ ማስረጃዎች አሉ። ይህ ከሚሆን መከላከያን ማሳደግ ቀላሉ መፍትሄ ነው። መከላከያ የሰራዊት ክለብና በአገሩ ተጫዋቾች ብቻ የሚኮራ ወይም የሚያምን ቡድን ስለሆነ ‹‹ቢያድግ›› የሚቃወም አይኖርም የሚሉ ስፖርት ቤተሰቦች በርካታ ናቸው። ጥያቄው ግን አምና ወደ ፕሪሚየር ሊግ አድጎ የወረደው የደቡብ ፖሊስ ጉዳይስ ይሆናል? መልሱ ቀላል ይመስላል፣ ለመከላከያ የሚወሰነው ለደቡብ ፖሊስም ይሰራል። ከከፍተኛ ሊግ አደጉ ለተባሉት ክለቦች ወደመጡበት እንዲወርዱ ደብዳቤ መላኩ ደግሞ ይሄን ሃሳብ ውሃ እንዲያነሳ ያደርጋል::አዲስ ዘመን መስከረም 30/2012 ዳንኤል ዘነበ | https://www.press.et/Ama/?p=20468 | 779 | 2ስፖርት
|
ኮሚሽኑ የማዘውተሪያ ስፍራዎችን ቁጥር 40ሺ ለማድረስ አቅዷል | ስፖርት | October 12, 2019 | 15 | የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን በአገሪቷ የሚገኙ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን በዓይነት፣ በመጠንና በቦታ በተጨባጭ መኖራቸውን የሚያረጋግጥ ቆጠራማድረጉን አስታወቀ። ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ደረጃ ለሚገኙ ማዘውተሪያዎች አቅጣጫ መጠቆሚያ (ማፒንግ) በማዘጋጀት ላይም ይገኛል። ኮሚሽኑ ለአገሪቷ ስፖርት እድገት እንደ
ምክንያት የሚነሳውን የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እጥረት የመፍታት እንዲሁም ሕጋዊ ይዞታ እንዲያገኙ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ላይ ይገኛል። በዚህም መሠረት በ2007 ዓ.ም 12ሺ428 የነበሩትን የማዘውተሪያ ስፍራዎች፤ በተያዘው ዓመት መጨረሻ ወደ 40ሺ ለማሳደግ አቅዶ
እየሰራ ነው። በ2011 የበጀት ዓመት
በተደረገው ቆጠራም 21ሺ ማዘውተሪያዎች በአገሪቷ እንዳሉ ታውቋል። እነዚህ ማዘውተሪያዎች የይዞታ ማረጋገጫ እንዲሁም የደረጃ የመለየት ሥራ
የተደረገባቸው ሲሆኑ፤ ያሉበትን ቦታ የሚያሳዩ የአቅጣጫ መጠቆሚያ በማዘጋጀት ላይ ይገኛል። ከጠቅላላው የማዘውተሪያ ስፍራዎች መካከል መንግሥት በከፍተኛ ወጪ የሚገነባቸው ግዙፍ ስታዲየሞችም ይገኙበታል። ከእነዚህ መካከል ብሔራዊ ስታዲየም አንዱ ሲሆን፤ ወደ ሁለተኛው ዙር ግንባታው ለመግባት በጨረታ ሂደት ላይ እንደሚገኝም ነው ኮሚሽኑ ትናንት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ያስታወቀው። በተለያዩ ክልሎች እየተገነቡ ያሉ ስታዲየሞች የቁጥጥርና ክትትል ሥራ እያከናወነ እንደሚገኝም ተመልክቷል። ኮሚሽኑ ከማዘውተሪያዎች ባለፈ በማስፈጸም አቅም ግንባታ፣ የተተኪ ስፖርተኞችን ችግር በመቅረፍ፣ በማዘውተሪያ ስፍራዎች እንዲሁም ኅብረተሰቡን በስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ተሳታፊ በማድረግ ረገድ ባለፈው ዓመት ዓበይት ተግባራት ማከናወኑንም ገልጿል። ከተግባራቱ መካከል አንዱ የማስፈጸም አቅም ግንባታን የሚመለከት ሲሆን፤ ከዚህም ጋር በተያያዘ ከአገር አቀፍ የስፖርት ማህበራት ጋር በጋራ እየራ ይገኛል። የስፖርት ማህበራቱ ዓመታዊ ጉባኤያቸውን በወቅቱ እንዲያደርጉ በመከታተል፣ እንዲሁም የሚወጡ ደንቦች ከአገሪቷ፣ አህጉር እንዲሁም ዓለም አቀፍ የስፖርት ማህበራት ጋር የተናበቡ መሆናቸውንም ያረጋግጣል። የማህበረሰብ አቀፍ ስፖርት ኮሚቴዎች እንዲደራጁና እንዲጠናከሩም አድርጓል። የስፖርታዊ ጨዋነት ጥሰትን በተመለከተም መንስኤውን በጥናት በመለየት የፖለቲካ ችግሩን በከፍተኛ አመራሮች ግንኙነት በተወሰነ ደረጃ መፈታቱ ተጠቁሟል። በጥናቱ የተለዩ ሌሎች ችግሮችንም ከባለድርሻ አካላት ጋር መግባባት ላይ ለመድረስ የሚያስችሉ መድረኮች ተዘጋጅተዋል። የተሰጡ የመፍትሄ አቅጣጫዎችንም በሚመለከተው አካል ተግባራዊ እንዲሆን የማስተግበር፣ የመከታተልና የመገምገም ሥራዎች ተከናውነዋል። ኮሚሽኑ አገር አቀፍ የስፖርት ማህበራት ዕቅዳቸውን በብቃት እንዲያሳኩ ድጋፍ ማድረጉም በሪፖርቱ ተጠቁሟል። 27ቱም ማህበራት የተደረገው የበጀት ድጋፍም ከስምንት ሚሊዮን ብር በላይ ነው። በዓመቱ በተካሄዱት የታዳጊ ወጣቶች ምዘና እና የተማሪዎች ውድድር፣ በባህርዳር በተካሄደው የአፍሪካ ብስክሌት ቻምፒዮና፣ የሴቶች ጨዋታ እንዲሁም ለፓራሊምፒክና ዴፍሊምፒክ ስፖርቶች በድምሩ ከ45 ሚሊየን ብር
በላይ ድጋፍ ተደርጓል። ለ12ኛው
የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ዝግጅት እንዲሁም ተሳትፎ 38 ሚሊዮን ብር ጥቅም ላይ ውሏል። ከዚህም ባሻገር ኮሚሽኑ በአፍሪካና በዓለም አቀፍ የወጣቶች ኦሊምፒክ፣ ከ16 እና
18ዓመት በታች ውድድሮች ላይ ኢትዮጵያም ተካፋይ በመሆን ሜዳሊያዎችን እንድታስመዘግብ ድጋፍ አድርጓል። በአገሪቷ የሚታየውን የተተኪ ስፖርተኞች ችግር በመቅረፍ በኩልም የተለያዩ ተግባራት ተከናውነዋል። ታዳጊዎች በ17 የስፖርት ዓይነት በ2ሺ የሥልጠና ጣቢያዎች፣ ከአምስት በላይ በሚሆኑ የስፖርት ማሰልጠኛ ማዕከላት እንዲሁም በሁለት አካዳሚዎች ላይ ሥልጠናቸውን በመከታተል ላይ ይገኛሉ። ይሁን እንጂ የሥልጠና ፕሮግራሙ ከታለመለት ዓላማ አንጻር ውጤታማ ባለመሆኑ ያለበትን ደረጃ እና ያስገኘውን ውጤት የማረጋገጥ ሥራ ተከናውኗል። ዓመታዊው የታዳጊ ወጣቶች የምዘና ውድድርም በአርባምንጭ ከተማ ተካሂዷል። ኅብረተሰቡ በሚኖርበት፣ በሚሰራበትና በሚማርበት አካባቢ በስፖርት ተሳታፊ በማድረግ ረገድም ባለፈው ዓመታት የተሻሉ ጅምሮች ታይተዋል። በአገር አቀፍ ደረጃ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በቅንጅት የእግር ጉዞ እንዲሁም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መርሃ ግብሮችን ማዘጋጀት ተችሏል። በዚህም ከአንድ ሚሊዮን በላይ ቁጥር ያለውን ሕዝብ ማሳተፍ መቻሉን በሪፖርቱ ተጠቁሟል።በተያዘው በጀት ዓመትም የስፖርት ችግሮችን በጥናት ለመለየት፣ የፌዴራል ስፖርት ምክር ቤት ጉባኤን ለማካሄድ፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን ቁጥር ለማሳደግ እንዲሁም ሕጋዊነታቸውን ማረጋገጥ፣ በስፖርት ለሁሉም መርሃ ግብሮች ኅብረተሰቡን በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለማሳተፍ፣ ስፖርታዊ ጨዋነትን በዘላቂነት ለማስፋት፣ የታዳጊ ወጣቶች ሥልጠናን በጥናቱ መሠረት ለመምራት እንዲሁም የሽልማትና ዕውቅና መድረኮችን ለማዘጋጀት ታቅዷል። አዲስ ዘመን ጥቅምት 1/2012 ብርሃን ፈይሳ | https://www.press.et/Ama/?p=20621 | 481 | 2ስፖርት
|
የአትሌት ደምሰው ፀጋ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፀመ | ስፖርት | October 11, 2019 | 10 | የአትሌት ደምሰው ፀጋ የቀብር ስነስርዓት በትውልድ መንደሩ ጫጫ ክርስቶስ ሳምራ ቤተክርስቲያን ትናንት ስምንት ሰዓት ላይ ተፈፅሟል፡፡ በቀብር ስነስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፅሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ቢልልኝ መቆያን ጨምሮ ፣ ወዳጅ ጓጀኞቹ ፣የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ኃላፊዎች ፣ የተለያዩ አትሌቶች፣ ማናጀሮች፣ አሰልጣኞች ተገኝተዋል፡፡ አትሌት ደምሰው_ፀጋ በ1980 ዓ.ም በሰሜን ሸዋ ዞን በአንጎለላ ጠራ ወረዳ በጫጫ ቀበሌ በጦጦሴ መንደር የተወለደ ሲሆን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን ከ1988—1991 ዓ.ም በጦጦሴ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ከ1992—1995 ዓ.ም በጫጫ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከታተለ። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ደግሞ በ1996 ዓ.ም በደብረብርሃን አጠቃላይ 2ኛደረጃ ትምህርት ቤት ተከታትሏል፡፡ አትሌት ደምሰው ትምህርቱን እየተከታተለ በመረብ ኳስ፣ በቅርጫት ኳስ እና በገና ጨዋታ የተዋጣለት ስፖርተኛ እንደነበረ የሕይወት ታሪኩ ያስረዳል፡፡ በኋላም በስፖርት መምህሩ ምክር ወደ አትሌቲክስ ስፖርት አመራ፡፡ በ1997 ዓ.ም በዞንና በወረዳ ደረጃ በሚካሄዱ የ3፣5ና 10ሺ ሜትር ውድድሮች ውጤታማ መሆኑን ተከትሎ ወደ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ሊመጣ ችሏል፡፡ አትሌት ደምሰው ዓለም አቀፍ ውድድሮችን እኤአ በ2006 ማድረግ የጀመረ ሲሆን ከ2006 እስከ 2015 ድረስ በ9 አመት ውስጥ በህመም ምክንያት ወጣ ገባ እያለ 24 ውድድሮችን አድርጓል። ከነዚህ ውድድሮች ውስጥ ሶስቱ ሀገሩን ኢትዮጵያን የወከለባቸው ውድድሮች ናቸው። በኬንያ ሞምባሳ፣ በጃፓን በቶኪዮ በ5ሺ እና በ10 ሺ ሜትሮች እንዲሁም በማራቶን ተሳትፎ ሜዳሊያ አግኝቷል። አትሌት ደምሰው የአንደኛ ደረጃ የአሰልጣኝነት ኮርስን የወሰደ ሲሆን፤ የሩጫ ሕይወቱ በፈለገው ደረጃ እንዳያድግ እንቅፋት የሆነበት ሕመም ሲሰማው ወደ ትውልድ መንደሩ እያመራ በርካታ አትሌቶችን በማሰልጠን ማፍራት ችሏል፡፡ አትሌት ደምሰው የአንድ ወንድና የአንዲት ሴት ልጅ አባት ሲሆን ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ ኑሮውን በአሜሪካ አድርጓል፡፡ ባደረበት ፅኑ ህመም ምክንያት ህክምናውን በአሜሪካ ሚሪላንድ ግዛት ሲከታተል ቆይቶ መስከረም 24 ቀን 2012 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል። አዲስ ዘመን ለአትሌቱ ቤተሰቦች፣ጓደኞችና የስፖርት ቤተሰቦች የተሰማውን ሃዘን ይገልፃል፡፡አዲስ ዘመን መስከረም 30/2012 ቦጋለ አበበ | https://www.press.et/Ama/?p=20478 | 254 | 2ስፖርት
|
ቀንም ሌትም ከሠራዊቱ ጎን ያልተለዩት ሐኪሞች | ሀገር አቀፍ ዜና | December 14, 2020 | 14 | ጌትነት ተስፋማርያም ኮሎኔል ዶክተር ተረፈ ንጉሴ በትግራይ ክልል የሕግ ማስከበር ዘመቻ የጤና አገልግሎት እንዲሰጥ ከአዲስ አበባ በተላከው የህክምና ቡድን ውስጥ አባል ናቸው። በመከላከያ ሠራዊት ምዕራብ ዕዝ የፈውስና ክብካቤ ኃላፊ ሆነው እየሠሩ ይገኛል። ከህዳር 1 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምረው መከላከያ ሠራዊቱ በሚንቀሳቀስባቸው እና ግዳጅ በሚፈፅምባቸው አካባቢዎች በመንቀሳቀስ የህክምና አገልግሎት በመስጠት ላይ ናቸው።በጁንታው አማካኝነት በመከላከያ ሠራዊቱ ላይ የተፈፀመው ጥቃት የህክምና ባለሙያውን አስቆጭቶታል፤ ቁጭቱን ለመግለፅም በሙያው ለማገልገል በወኔ ተነስቷል። ሐኪሙም ከሠራዊቱ ጋር ቢዋጋ ደስ ይለዋል፤ ይሁንና ህይወት ማዳኑም ትልቅ ሥራ ነውና ሙያውን እያሳለጠ እንቅልፍ ሳይበግረው ለሠራዊቱ አጋር በመሆን ላይ እንደሚገኝ ነገረውናል። ያሉበት ቦታ ኔትወርክ የሌለበት ቢሆንም የተገኘው ቤተሰብ ናፈቀኝ አሊያም ገንዘብ አስፈለገኝ ብሎ ሲያማርር አይስተዋልም። ለግዳጅ የወጣው የህክምና ባለሙያ ተንቀሳቃሽ ሆኖ በየቦታው መሪ ሳይፈልግ ምን እናድርግ ብሎ ለመፍትሄው ይሮጣል፤ ለማስተባበርም ቀላል የሆነ እና በወኔ የሚሠራ ባለሙያ ነው የታየው። የህክምና ባለሙያው የሚተኛባቸውን አነስተኛ ፍራሾች እንኳን ለታካሚዎች አውጥቶ በመስጠት ጭምር እያገለገለ መሆኑን ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።ተረኛ ነኝ የሚባል ንግግር በሐኪሙ ዘንድ የለም። በተለያየ ምክንያት ወደ ማዕከላት መጥተው የህክምና ዕርዳታ የሚፈልጉ ወታደሮችን ቀን ብቻ ሳይሆን ምሽት ላይም አገልግሎት በመስጠት ሐኪሞች ሌሊቱን ጭምር ቆመው በሥራ ያሳለፉባቸው ጊዜያት በርካታ መሆናቸውን አውግተውናል። ሁሉም በትብብር ለመጣበት ሀገራዊ ዘመቻ በጋራ ተሰልፏል የሚሉት ኮሎኔል ዶክተር ተረፈ፤ ረጅም ሰዓት ቆመው በማገልገላቸው ድካም የሚታይባቸውን ሐኪሞች በግድ ጎትተው ያሳረፉበት ወቅት መኖሩን ይናገራሉ። የህክምና ባለሙያዎቹ ስሜት ግን ለሀገሩ ክብር ሲል ሲዋደቅ ለሚውለው ወታደር 24 ሰዓት ሙሉ የህክምና አገልግሎት መስጠት ነውና እረፉ ሲባል እንኳን የማይስማሙ በርካታ ባለሙያዎች መኖራቸውን ነው የነገሩን። ቆስለው እንኳን የሕግ ማስከበር እርምጃውን ሳናጠናቅቅ አንመለስም የሚሉ የጦር መሪዎች እና የሠራዊት አባላት መኖራቸውን ያስታወሱት ኮሎኔል ዶክተር ተረፈ፤ ከፍተኛ የህክምና ዕርዳታ እያስፈለጋቸው የህክምና ባለሙያዎችን የሚያበረታቱ ሰዎች መኖራቸውን ማየታቸው ከትውስታዎቻቸው መካከል ዋነኞቹ መሆናቸውን ነው ያስረዱን።<<አሁን ላይ ዋናው የሕግ ማስከበር እርምጃ ቢጠናቀቅም የማጥራት ሥራ ነው እየተከናወነ የሚገኘው፤ ይሁንና ዋናውን የጁንታ አመራር ለማግኘት የተወሰነ ጊዜ ሊወስድ ይችላል። እኛ የህክምና ባለሙያዎች በትግራይ ክልል አዲሱ መስተዳደር ተረክቦ እራሱን እስኪችልና መረጋጋት እስኪፈጠር የሚሰጠንን ግዳጅ በአግባቡ ለመወጣት ሁሌም ዝግጁ ነን። ብዙ ጊዜ ይወስዳል ብዬ ባላስብም ሁኔታው እስከፈቀደ ድረስ በሙያዬ ለማገለገል ዝግጁ ነኝ>> ብለዋል። የህክምና ባለሙያው ሌተናል ኮሎኔል በላይነህ በሪሁን የምዕራብ ዕዝ ቀዶ ጥገና ክፍል ኃላፊ ናቸው። የሠራዊቱ አጋር ለመሆንና በሙያቸው ለመደገፍ ጥቅምት 27 ቀን 2013 ዓ.ም መነሻቸውን ከባህር ዳር ከተማ ማድረጋቸውን ያስታውሳሉ። ሠራዊቱ በተንቀሳቀሰባቸው አካባቢዎች ሁሉ ከጎንደር ጀምሮ እስከ ዳንሻ፣ ሑመራ እስከ ሽራሮ፣ አዲሃገራይ እና ሽሬ እንዲሁም ሽሬ ከተሞች እየተንቀሳቀሱ የህክምና ባለሙያዎችን በማስተባበር አገልግሎት በመስጠት ላይ ናቸው። የሕግ ማስከበር እርምጃው የጦር መሣሪያ ልውውጥ ያለው ነውና ቁስለኛ መኖሩ አይቀርም። እርሳቸውና የሥራ ባልደረቦቻቸው ቁስለኞችን በማከም ህይወት የማስቀጠል ሙያ ተግባራቸውን ወደውና ፈቅደው እየተወጡ እንደሚገኝ ነግረውናል። በሁለት ቡድን ተከፍሎ የህክምና ዕርዳታ እየሰጠ የሚገኘው ቡድን ባረፈባቸው ቦታዎች ሁሉ ግዳጁን በብቃት እየፈፀመ ይገኛል። የጁንታው ቡድን የጥፋት ተልዕኮ የተደራጀ እንደነበር ያስታወሱት ሌተናል ኮሎኔል በላይነህ፤ ሽራሮ አካባቢ የነበረን ትልቅ ሆስፒታል ንብረት በሙሉ ዘርፎ መውወሰዱን ነግረውናል። ንብረቱን ብቻ ሳይሆን ሰዎችንም በመጫን በቦታው የነበሩ የህክምና ባለሙያዎችን ጭምር አፍነው መውሰዳቸውን ነግረውናል። አካባቢውን መከላከያ ሲቆጣጠረው አንድ ባዶ የአስክሬን ሳጥን ብቻ መገኘቱን በትዝብት መልክ አጋርተውናል። የህክምና ባለሙያው ሠራዊቱ ላይ የተፈፀመው ጥቃት እና የደረሰው በደል ሲያይ ማንም ሳይቀሰቅሰው በቁጭት እና በሞራል የህክምና አገልግሎት እንዲሰጥ አድርጓል። ሐኪሙም የራሱን መኝታ ብቻ ሳይሆን የዝናብ ልብሱንም ጭምር ለሠራዊቱ በመስጠት ታካሚው አረፍ የሚልበትን መንገድ ሁሉ እያመቻቸ መሆኑን ይናገራሉ። ቀንም ማታም በሥራ ላይ ከማሳለፍ ባለፈ የምግብ ሰዓቱን የሚያስታውስ የህክምና ባለሙያ አለመኖሩን ነው ያጫወቱን። በህክምና ማዕከላቱ የጽዳትም ሠራተኞች አለመኖራቸው ቢታወቅም ሐኪሞች የጤና አገልግሎት ከመስጠት ባለፈ ክብሬ ተነካ ሳይሉ የህክምና ማዕከላቸውን ወለል እና ግድግዳ በማጽዳት ጭምር ግዳጃቸው በውጤት እንዲጠናቀቅ እየተጉ መሆናቸውን ያስረዳሉ። ምንም እንኳን የመብራት አገልግሎት ባይኖርም <<የህክምና ባለሙያው ግን ይህ ችግር አለብኝ ብሎ ሳይማረርና እና ሥራውን ሳያስተጓጉል በሻማና በእጅ ባትሪ አገልገሎት እየሰጠ ይገኛል፤ እንደ ህክምና ባለሙያ በግንባር ተገኝቼ በሰጠሁት አገልግሎት እጅግ ደስተኛ ነኝ >> ብለዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 5/2013 | https://www.press.et/Ama/?p=37306 | 561 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ናይኪ የኦሪገን ፕሮጀክቱን ዘጋ | ስፖርት | October 12, 2019 | 11 | ግዙፉ የስፖርት ትጥቅ አምራች ኩባንያ ናይኪ በአሜሪካ ፖርትላንድ ኦሪገን ያለውን የአትሌቲክስ ፕሮጀክት መዝጋቱን አስታወቀ። የፕሮጀክቱ አሰልጣኝ የሆነው አልቤርቶ ሳላዛር ከአበረታች መድኃኒት ዓለምአቀፍ ሕግጋቶች መጣስ ጋር ተያይዞ ከሳምንት በፊት ከማንኛውም ስፖርት ለአራት ዓመታት መታገዱ ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ ናይኪ ፕሮጀክቱን ለመዝጋት እንደወሰነ ረነርስ ወርልድ ከትናንት በስቲያ ምሽት ዘግቧል። አሰልጣኝ አልቤርቶ ሳላዛር በፕሮጀክቱ የሚያሰለጥናቸውን አትሌቶች አውቀውም ይሁን ሳያውቁ አበረታች መድኃኒት እንዲጠቀሙ ያደርጋቸዋል በሚል ከስፖርቱ መታገዱን ተከትሎ በፕሮጀክቱ የታቀፉ አትሌቶች ጥያቄ ውስጥ መግባታቸው አልቀረም። የናይኪ ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ማርክ ፓርከር ለረነርስ ወርልድ እንደገለፁት፣ የፕሮጀክቱ አትሌቶች ባልተረጋገጠ አሉባልታ ከአበረታች መድኃኒትተጠቃሚነት ጋር ስማቸው መነሳቱ ያላቸውን እምቅ አቅም ተጠቅመው በልምምድና ውድድሮች ላይ ትኩረት እንዳያደርጉ ተፅዕኖ ስለሚፈጥርባቸው ፕሮጀክቱን መዝጋት አስፈላጊ ሆኗል። ስለዚህም ናይኪ ኩባንያ የፕሮጀክቱን አትሌቶች በሚፈልጉትና ትክክል ነው ብለው በሚያምኑት አሰልጣኝና የሥልጠና ሂደት እንዲከታተሉ በማድረግ ድጋፉን ከውጪ ሆኖ እንደሚቀጥልበት ሥራ አስፈፃሚው ተናግረዋል። የፕሮጀክቱን በርካታ አትሌቶች የሚያሰለጥኑት ፒት ጁሊያን ከአበረታች መድኃኒት ጋር በተያያዘ ስማቸው የማይነሳ ከመሆኑም ባሻገር የዓለም አትሌቲክስ ጋር ጥሩ ግንኙነት እንዳላቸው ይነገራል። የናይኪ ኦሪገን ፕሮጀክት ሲዘጋ የእኚህ አሰልጣኝ ዕጣፈንታ ምን እንደሚሆን የተገለፀ ነገር የለም። በቅርቡ በተጠናቀቀው የዶሃ የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና በአስር ሺ ሜትር የብር ሜዳሊያ ማሸነፍ የቻለው ኢትዮጵያዊው አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻን ጨምሮ የአስርና አንድ ሺ አምስት መቶ ሜትር ቻምፒዮኗ ትውልደ ኢትዮጵያዊት የኔዘርላንድስ አትሌት ሲፈን ሃሰን የናይኪ ኦሪገን አትሌቲክስ ፕሮጀክት ሰልጣኞች ናቸው። ነገ በሚካሄደው የቺካጎ ማራቶን የሚወዳደሩት አሜሪካውያኑ ጋለን ሩፕና ጆርዳን ሃሴይም የዚሁ ፕሮጀክት ፍሬዎች ናቸው። የሦስት የዓለም ቻምፒዮናዎችና የሁለት ኦሊምፒኮች የአስርና አምስት ሺ ሜትር ቻምፒዮኑ እንግሊዛዊው አትሌት ሞ ፋራህን በነገው የቺካጎ ማራቶን ለአሸናፊነት የሚጠበቅ የቀድሞ የናይኪ ኦሪገን አትሌቲክስ ፕሮጀክት ውጤት መሆኑ ይታወቃል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ የሆነው የአትሌቲክስ ስፖርት አሠልጣኝ አልቤርቶ ሳላዛር የተከለከሉ አበረታች ቅመሞችን ከቦታ ቦታ ማዘዋወርን
(Trafficking) ጨምሮ የፀረ-ዶፒንግ እንቅስቃሴውን በማወክ
(Tampering) እና በተለያዩ የፀረ-ዶፒንግ የሕግ ጥሰቶች ተጠርጥሮ ጉዳዩ በአሜሪካ የፀረ-ዶፒንግ ኤጀንሲ (USADA) ሲጣራ ቆይቷል። በዚህም መሠረት ግለሰቡ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ ለአራት ዓመታት በስፖርቱ ውስጥ እንዳይሳተፍ እገዳ ተጥሎበታል። ኢትዮጵያውያን አትሌቶችና የስፖርት ባለሞያዎችም ካሳለፍነው ሳምንት ጀምሮ ከአሰልጣኝ አልቤርቶ ሳላዛር ጋር የሚኖራቸውን ቀጥተኛም ይሁን ቀጥተኛ ያልሆነ ግንኙነት ማቋረጥ እንዳለባቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽሕፈት ቤት ማሳሰቡ ይታወሳል።አዲስ ዘመን ጥቅምት 1/2012ቦጋለ አበበ | https://www.press.et/Ama/?p=20624 | 316 | 2ስፖርት
|
ማራቶንን ከ2 ሰዓት በታች የማጠናቀቅ ተስፋ | ስፖርት | October 12, 2019 | 17 | በማራቶን የዓለም የሁለት ጊዜ ቻምፒዮኑ ኬንያዊ ኢሉድ ኪፕቾጌ በሳምንቱ መጨረሻ ማራቶንን ከ2ሰዓት በታች የመግባት ሙከራውን በኦስትሪያ ቬና ያደርጋል። ኪፕቾጌ እ.አ.አ በ2018 የበርሊንን ማራቶን የገባበት 2፡01.39 የሆነ ሰዓት የዓለም ክብረወሰን ሲሆን፤ ይህንን በማሻሻል 1ሰዓት ከ59 ደቂቃ የመግባት ሙከራ ያደርጋል። አትሌቱ ለሙከራው እንዲሁም «የሰው ልጅ ዓቅም አይወሰንም» የሚለውን አባባል በተግባር ለማሳየት የሚችልበት አቋም ላይ እንደሚገኝም ተገልጿል። ናይኪ የተባለው የስፖርት ትጥቅ አምራች የተያዘው ይህ ፕሮጀክት ሙከራውን ከዓመታት በፊት የጀመረ ሲሆን፤ ዛሬ በቬና በያዘው ቀጠሮም ይሳካል የሚል እምነት አሳድሯል። አትሌቱ ለሩጫው ያመቸው ዘንድ ልዩ የመሮጫ ጫማ የተዘጋጀለት ሲሆን፤ ከተማዋም በዛፍ የተከበበችና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ያላት በመሆኑ አትሌቱ ያሰበውን ለማሳካት ይረዳዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ከሁለት ዓመት በፊት አትሌቱ በጣሊያኗ ሞንዛ ከተማ ባደረገው ሙከራ በ26 ሰከንዶች ዘግይቶ ዓላማውን ማሳካት አልቻለም ነበር፤ አሁን ግን የከተማዋ የቦታ አቀማመጥ እንዲሁም አሯሯጮች የተዘጋጁ በመሆኑ ሰዓቱን እንደሚያሻሽል ተስፋ ተጥሎበታል። ኢሉድ ኪፕቾጌ ሙከራውን በተመለከተ በሰጠው አስተያየትም «ከሁለት ሰዓት በታች የመግባት ሙከራውን ለማድረግ ተዘጋጅቻለሁ። ዝጅግቴም ጥሩ ነበር፤ ይህንንም በተግባር አሳይቼ የሰው ልጅ አቅም ገደብ እንደሌለው አስመሰክራለሁ» ሲል ለኒውስ 24 ገልጿል። ከአትሌቱ ጋር በአሯሯጭነት
በሙከራው ላይ የሚሳተፉት
41አትሌቶች የታወቁ ሲሆን
ዘ ዋሽንግተን ፖስትም
ታዋቂዎቹን በስም ጠቅሷል።
በ1ሺ500 ሜትር
የዓለም ቻምፒዮን የሆነው
አሜሪካዊው ማቲው ሴንትሮዊትዝ፣
በዶሃው የዓለም ቻምፒዮና
የ5ሺ ሜትር
የብር ሜዳሊያ ተሸላሚው
ሰለሞን ባረጋ፣ በ3ሺ
ሜትር የዓለም ቀዳሚው
ሰዓት ባለቤት ኡጋንዳዊው
ሮናልድ ሙሳጋላ እንዲሁም
ሌሎች ጠንካራ አትሌቶች
ተካፋይ ይሆናሉ።አዲስ ዘመን ጥቅምት 1/2012 ብርሃን ፈይሳ | https://www.press.et/Ama/?p=20630 | 209 | 2ስፖርት
|
‹‹በሐዋርያት መካከል ራስ ወዳድ ሆኖ አምላኩን የሸጠ እንዳለ ሁሉ በሕዝብ መካከልም ይሁዳዎች ይጠፋሉ ብሎ ማሰብ ትክክል አይደለም››ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 12, 2020 | 12 | ጽጌረዳ ጫንያለው አዲስ አበባ፡- በ12ቱ ሐዋርያት ራስ ወዳድ ሆኖ አምላኩን የሸጠ እንዳለ ሁሉ በሕዝብ መካከልም
ዳግማዊ ይሁዳዎች ይጠፋሉ ብሎ ማሰብ ትክክል እንዳልሆነ
የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ አስታወቁ። ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቁት፤ በ12ቱ ሐዋርያት
መካከል ሐዋርያዊ ተልዕኮ ተሰጥቶት ከተላከበት
ሥራ ይልቅ ራሱን ወዶ አምላኩን
የሸጠ ይሁዳ እንዳለ ሁሉ በሕዝብ መካከል፣ የተዘሩ የዲያቢሎስ የግብር ልጅ የሆኑ ዳግማዊ ይሁዳዎች
መኖራቸው የማይቀር ነው።ለዚህም
ማሳያው ብሔርንና የአገር ባለውለታን እየነጠሉ በጅምላ የጨፈጨፉት የህወሓት ጁንታዎች ተጠቃሽ ናቸው። ግን እነዚህ አካላት ትግሬ በመሆናቸው የትግራይ ሕዝብን ይወክላሉ ብሎ ማሰብ የተሳሳተ ምልከታ ነው። የትግራይ ሕዝብ አማኝና ኢትዮጵያዊነቱን አጥብቆ የሚወድ እንደሆነ በርካታ እናቶች ምስክር እንደሚሆኑ የተናገሩት ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ፣ በቤተ እምነት ውስጥ ሳይቀር ምሽጉን አድርጎ ሕዝብ ለማስፈጀት ሲጥር የነበረው ደግሞ ሌላው ጎራ ነው ብለዋል። እነዚህ አካላት እምነት አልባና ክፉ ሀሳብ ያላቸው ይሁዳዎች ናቸው። ምክንያቱም በሕዝብ ውስጥ መሸሸግና እርስ በርስ ማጠላላት ዋነኛ ተግባራቸው መሆኑን ገልጸዋል። የትግራይ ሕዝብ ይህንን አደረገ ብሎ ከአማራው ጋር ለማጋጨት ብዙ እኩይ ተግባራትን ሲፈጽሙ እንደነበር አመልክተው፣ ሕዝቡ ይህንን ተረድቶ ከሥራቸው ታውቋቸዋላችሁ እንደተባለው ሊያውቃቸው ይገባል ብለዋል። ምንም በማያውቁት በጁንታው ቡድን ለሞቱት ሁሉ እግዚአብሔር ነብሳቸውን በአጸደ ገነት እንዲያኖረው የተመኙት ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ፤ ሁኔታው የተደረገው ለኢትዮጵያውያን አስባለሁ ከሚል ለኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲ እታገላለሁ ከሚል ቢሆንም ተግባሩ ይህ እንዳልሆነ በግልጽ ታይቷል። ይህን እኩይ ተግባሩም ጥቁር ጠባሳ ሆኖ ሲዘከር ይኖራል። አስተማሪ ሆኖ እንዲያልፍ ግን ሁሉም የበኩሉን ማድረግ እንደሚጠበቅበት አስታውቀዋል። ጁንታው ሃይማኖታዊ መሰረት የሌላቸው፣ ሰብዓዊ ርህራሄ ያልፈጠረባቸው ከግል አልፎ ለቡድን ጥቅምና ሥልጣን የሚስገበገቡና የሚጥሩ አካላት የሞሉበት እንደሆነ የሚያነሱት ጠቅላይ ጸሐፊው፤ 98 በመቶ ሃይማኖተኛ የሆነባት አገር ውስጥ ይህ ለምን ይሆናል የሚለውን እንደማይቀበሉትና እንደ ጁንታው ዓይነት ሃይማኖት አልባ ክፉ ቡድኖች መኖራቸውን ሁሉም ማሰብ እንደሚገባው ጠቁመዋል። እነዚህ አካላትም ሃይማኖትን እንደ ምሽግ እንደዋሻ የሚጠቀሙ ስለሆኑ እነርሱን ከሃይማኖት ጋር አስተሳስሮ ማንሳት ተገቢነት የሌለው ነውም ብለዋል። በማንኛውም ሃይማኖት አስተምሮ መግደል ሀጥያት ቢሆንም እነዚህ አካላት ግን ከመግደል ያለፈ ተግባር ፈጽመዋል ያሉት ሊቀትጉሃን ቀሲስ ታጋይ፤ ጉራፈርዳ ላይ በሄዱበት ጊዜ በንጹሀን ጭፍጨፋ የህወሓት ጁንታ እጅ እንዳለበት ነዋሪዎቹ እንዳስረዷቸው አስታውቀዋል። ይህ ዓይነት ተግባር በየቦታው እየፈነዳ ያለው ሰላም ከማይወዱ፣ ሁልጊዜ ሥልጣን ላይ ብቻቸውን መቀመጥ ከሚፈልጉ፤ ሌላው ሲሰራና ሲለወጥ የሚያማቸው፤ ከእነርሱ ውጭ በአገር ብቻ ሳይሆን በዓለም ላይ እንዲኖር የማይፈልጉ በመሆናቸው እንደሆነ አስረድተዋል። እንደ ሊቀትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ገለጻ፤ እነዚህ ሰዎች ኢትዮጵያ ላይ ቢሳካላቸው ተረጋግተው የሚቀመጡ አይደሉም። አፍሪካ ብሎም ዓለምን በእኛ ሥር አድርገን ካልገዛን ከእኛ ውጪ መሆን የለበትም የሚሉና ጦርነት ለማንሳት የሚቃጣቸው ናቸው። በዚህም አሁን እንደ አገር የተሰራው ሥራ የአገርን ክብር ከመመለስም በላይ ነው። በተለይ ኢትዮጵያ የሚለውን ስም ከማስጠበቅ አኳያ ትልቅ ፋይዳ አለው። የጭፍጨፋው ምንጭ አላማው ከሥልጣን እኔ ለምን ገሸሽ ተደረኩ የሚል ነው። ከዚያ ውጪም በሥልጣን ላይ እያሉ ብዙ የተለመዱ ክፉ ተግባራትን ሲሰሩ መኖራቸው ሊያመጣባቸው የሚችለውን ተጠያቂነት ፍርሀትም ሌላው ምክንያት እንደሆነ ጠቁመዋል። ለአብነት ከሕግ ውጪ ፈላጭ ቆራጭ ነበሩ፤ በሕገወጥ መንገድ ሀብት ሲያከማቹ እንደነበር አስታውቀዋል። የእነርሱ ልብ በዲያቢሎስ እጅ የገባና የእርሱን አመራር የተከተለ ነው። የዲያቢሎስ የግብር ልጅ መሆን ደግሞ ፈሪሀ እግዚአብሔርን ከማስነጠቅም በላይ ሰብዓዊነት የሚባለው ነገር ትዝ እንዳይል ያደርጋል። ከጠንካራው ይልቅ ደካማውን እየመረጡ እንዲያጠቁና እናቶች እንዲያዝኑ አድርገዋል። ከዚያ ከፍ ሲልም በክፋት መንፈስ የተደፈነ ልብ ስለያዙ በአስከሬን ቀልደዋል እንደ ጀግና ፎክረዋል። ከተረዱት ተግባሩ የወራዳና ወራዳነት ምግባር ነው ብለዋል። እንደ ሊቀትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ማብራሪያ፤ እነዚህ አካላት አገር ከሀዲነት ብቻ አይገልጻቸውም። ከዚያ በላይ አገር የገደሉ ናቸው። ነጭ የደም ሴልን ገሎ አለሁ ማለት ከመሞት አይተናነስምና። ስለዚህም ሕዝቡ ከእነዚህ ተኩላዎች በሁለት ነገር መጠንቀቅ ይኖርበታል። የመጀመሪያው እነዚያ ክፉ ሰዎች የሰሩትን ተግባር ሕዝብ ለሕዝብ ጦርነት እንዲያውጅ በመፈለግ የተደረገ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል። ይህንን ዘግናኝ ተግባርም ሁሉም ማህበረሰብ በነቂስ ወጥቶ ማውገዝና እነርሱን እንደማይገልጽ ማስገንዘብ ይኖርባቸዋል። ሌላው እያንዳንዱ ሰው የእነርሱ ሽንፈት ማስፈጸሚያ እንዳይሆን መጠንቀቅ ይኖርበታል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 3/213 | https://www.press.et/Ama/?p=37168 | 551 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
“የማይካድራውን የዘር ጭፍጨፋ የፈጸሙ ኃይሎች በምድራዊ ፍትህ ተመጣጣኝ ቅጣት አይገኝላቸውም”-ኡስታዝ አብዱልገፋር ሸሪፍ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 12, 2020 | 13 | ሶሎሞን በየነ አዲስ አበባ:- በማይካድራ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ወንጀል የፈጸሙና ያስፈጸሙ ኃይሎች ተይዘው ለፍርድ ቢቀርቡ እንኳን በምድራዊ ፍትህ ተመጣጣኝ ቅጣት እንደማይገኝላቸው ኡስታዝ አብዱልገፋር ሸሪፍ አስታወቁ።ኡስታዝ አብዱልገፋር ሸሪፍ የማይካድራ ጭፍጨፋን አስመልክተው በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ በማይካድራ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ወንጀል የፈጸሙና ያስፈጸሙ ኃይሎች ተይዘው ለፍርድ ቀርበው ተገቢውን ፍትህ ማግኘት እንደሚገባቸው ጠቁመው፤ ያም ቢሆን ግን እነዚህ ኃይሎች በንፁሃን ዜጎች ላይ የፈፀሙት የጅምላ ጭፍጨፋ በድርጊት አፈጻጸምም ሆነ በተጎዱ ሰዎች ብዛት፣ እስካሁን በኢትዮጵያ ውስጥ ከተፈፀሙ አሰቃቂ ኢ-ሰብአዊ ድርጊቶች ሁሉ በእጅጉ የከፋ አረመኔያዊ ተግባር ነው።ፈጣሪ በሰማይ ቤት ዋጋቸውን ይከፍላቸው ካልሆነ በስተቀር ተይዘው ለፍርድ ቢቀርቡ እንኳን በምድራዊ ፍትህ ተመጣጣኝ ቅጣት አይገኝላቸውም ያሉት ኡስታዝ አብዱልገፋር፣ የእስልምና ሃይማኖት አስተምሮ አላህ! “አንተ ሰላም ነህ፤ ሰላምም ከአንተ ነው” በሚል እንደሚጀምር አስታውቀዋል።በአንድ ፈጣሪ ስር ያሉ ሁሉም ፍጡራን የእርሱን ህግና ስርዓት ተከትለው ተናበውና ተሳስበው በሰላም እንዲኖሩ እምነቱ ያዛል ያሉት ኡስታዝ አብዱልገፋር፤ በመሆኑም አይደለም ክቡር የሆነውን የሰውን ልጅ ቀርቶ አዕዋፍን፣ እንስሳትን፣ ነፍሳትን ወዘተ በምድር ላይ ህይወት ያለውን ሁሉ ያለምንም ምክንያት መንካት፣ ማሰቃየት፣ ማንገላታት፣ መምታት፣ መግደል በእስልምና አስተምሮ የተወገዘ መሆኑን አመልክተዋል።ከዚህ አንጻር በማይካድራ ከተማ የተፈጸመው የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ወንጀል ጠንካራ እምነት እና ፈጣሪያቸውን ይፈራሉ ከሚባሉት ኢትዮጵያዊያን ቀርቶ ከኢ-አማንያን የማይጠበቅ አረመኔያዊ ተግባር መሆኑን ኡስታዝ አብዱልገፋር ገልጸው፤ በማይካድራ የተፈጸመው ጥቃት “ክስተቱ እጅግ አስደንጋጭ ይሆናል ተብሎ የማይገመትና በሰው ዘር ላይ የተፈጸመ አረመኔያዊ ድርጊት ነው” ብለዋል። “አይደለም በጅምላ ሰዎችን መግደል ቀርቶ የአንድን ሰው ህይወት በምንም አይነት ምክንያት ተነሳስቶ ማጥፋት በአላህ ዘንድ ዓለም ከተፈጠረች ጀምሮ ከዚህ በፊት የሞቱትን፣ በህይወት ያሉትንና ለወደፊትም የሚፈጠሩትን የሰው ልጆች ሁሉ እንዳጠፋ ተደርጎ የሚቆጠር ነው” ያሉት ኡስታዝ አብዱልገፋር፤ “ጭፍጨፋው ዘርንና ማንነትን መሰረት ያደረገ፤ በገመድ በማነቅ፣በስለት በመውጋትና በሌሎች መሰል አሰቃቂ መንገዶች መፈጸሙ ባለፉት አመታት አገሪቱ የተገነባችበትን የጥላቻና የቂምበቀል ፖለቲካ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ እንደሆነ አመልክተዋል። ድርጊቱ ከሞራልም፣ ከሰብአዊነትም፣ ከምድራዊም ሆነ ከሰማያዊ ህግ አንጻር የተወገዘ ነው ያሉት ኡስታዝ አብዱልገፋር፤ ይህንን አረመኔያዊ ድርጊት በንጹሃን ላይ የፈጸሙ ኃይሎች ከምስረታቸው ጀምሮ ውስጣቸው በክፋት የተጠነሰሰ፣ ሃይማኖት የሌላቸው፣ ሰብዓዊነት የማይሰማቸው፣ በጥላቻ፣ በቂም፣ በምቀኝነት፣ በክፋት መንፈስ የሰከሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል። በንጹሃን ዜጎች ላይ ይህን አሰቃቂ ድርጊት የፈጸሙ ኃይሎች ተይዘው ለፍርድ ቀርበው ተገቢውን ፍትህ ማግኘት እንደሚገባቸው ቢያምኑም፤ እነዚህን ኃይሎች ዓላህ በሰማይ ቤት ዋጋቸውን ይከፍላቸው ካልሆነ በስተቀር ተይዘው ለፍርድ ቢቀርቡ እንኳን በምድራዊ ፍትህ ተመጣጣኝ ቅጣት እንደማይገኝላቸው ገልጸዋል። የድርጊቱ መንስኤ ባለፉት ዓመታት እንደዋዛ የተረጩ የጥላቻና የቂም በቀል አስተምሮዎች፣ የትምህርት ፖሊሲው፣ ወጣቱ በስነ ምግባር አለመቀረጹ የመሳሰሉት ዋና ዋናዎቹ እንደሆኑ ጠቅሰው፤ ይህን አሰቃቂ ወንጀል የፈጸሙ ኃይሎችን አድኖ ህግ ፊት የማቅረብ ሂደቱ እንደተጠበቀ ሆኖ ጥፋቱ እንዳይደገም የአገሪቱ አንድነትና የህዝብ ደህንነት ያገባኛል የሚል ማንኛውም የማህበረሰብ ክፍል በችግሩ መንስኤና መፍትሄው ላይ ፍርጥርጡን አውጥቶ ተወያይቶ ዘላቂ መፍትሄ ማስቀመጥ፣ የትምህርት ፖሊሲውን መፈተሽ፣ ወጣቱን በስነ ምግባር ማስተማርና ማረቅ፣ ህብረተሰቡን ከቂምና ከጥላቻ ፖለቲካ አላቆ በአዲስ መልክ መገንባት እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 3/213 | https://www.press.et/Ama/?p=37169 | 406 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
በአማራ ክልል በመኸር ወቅት 65 በመቶ ምርት መሰብሰቡ ተገለጸ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 12, 2020 | 2 | ወርቅነሽ ደምሰው አዲስ አበባ፡- በዘንድሮ ዓመት በአማራ ክልል በመኸር ወቅት በሰብል ከተሸፈነው 4ሚሊየን 282
ሺህ 517 ሄክታር መሬት እስካሁን 65 በመቶ ያህሉ ምርት መሰብሰቡን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ተስፋሁን መንግሥቴ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ በክልሉ በዘንድሮ ዓመት በመኸር ወቅት 4ሚሊየን 282ሺህ 517 ሄክታር መሬት በሰብል የተሸፈነ ሲሆን፤ በአሁኑ ሰዓት ወደ 2ሚሊየን 800 ሺህ156 ሄክታር መሬት (65 በመቶው) የደረሰ ምርት መሰብሰብ ተችሏል።በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ የሆነ የሰብል አሰባሰብ የሚካሄድበት ወቅት እንደመሆኑ፤ በተለይም ለዘር የሚሆኑ የጤፍ፣ የስንዴና የበቆሎ ምርጥ ምርቶች ስብሰባ እየተካሄደ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ተስፋሁን፤ ለዚህም የደረሱ ሰብሎች ለመሰብሰብ የሚረዱ 104
የሚሆኑ ኮምባይነሮችን በመጠቀም ሰብል እየተሰበሰበ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም በኮምባይነሮች ከ19ሺህ 481 ሄክታር በላይ ማሳ ላይ ያለ ሰብል የታጨደ ሲሆን፤ ከዚህም 715 ሺህ 698 ኩንታል ምርት ተሰብስቧል። ኮቪድ ጋር ተያይዞ ሰብል አሰባሰብ ሂደት በርካታ የሰው ኃይል ለመጠቀም አስቸጋሪ መሆኑ ኮምባይነሮቹ እጅግ ጠቃሚ ናቸው የሚሉት ምክትል ኃላፊው፤ በተለይ በኩታ ገጠም በሆኑ ማሳዎች ላይ የተዘሩ ሰብሎችን ለመሰብሰብ ኮምባይነሮቹ ጥቅም ላይ እየዋሉ መሆኑን ተናግረዋል።ይሄም በሰው ጉልበት ከ10 እስከ 20 ቀናት የሚወስድ የምርት አሰባሰብ ሂደት ከአንድ እስከ ሁለት ባሉት ቀናት ውስጥ እንዲሰበሰብ ማድረግ ማስቻሉን ተናግረዋል። ክልሉ ዘንድሮ በኮቪድ ወረርሽኝ፣ በአንበጣ መንጋ፣ በጎርፍ ክስተት፣ በመሬት መንሸራተትና በጦርነት ውጥረት ውስጥ ከመቆየቱ አኳያ የሰብል አሰባሰብ ሂደቱ በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኝ መሆኑን የገለጹት አቶ ተስፋሁን፤ ደጋማ የሆኑ አካባቢዎች ያሉ ሰብሎች ገና ያልደረሱ በመሆናቸውም አጠቃላይ የሰብል ስብሰባውን ውጤታማ ማድረግ የሚያስችሉ ሥራዎች በልማት ግንባር እየተሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።ሂደቱም በየቀኑ እየተገመገመ ስለሆነ አፈጻጸሙ ጥሩ መሆኑን ተናግረዋል።እንደ አቶ ተስፋሁን ገለጻ፤ በወቅታዊ የሀገራዊ ጉዳይ ከክልሉ ለህግ ማስከበር ዘመቻ የተሰማሩ አርሶ አደሮች ሰብል ለመሰብሰብ በተደረገ ጥረት 24ሺህ 845 ተሳታፊዎች በማሳተፍ 84 ሺህ ሦስት መቶ 97 ሄክታር መሬት ምርት ተሰብስቧል።ለአብነትም፣ ሰሜን ጎንደር፣ ደቡብ ጎንደርና ምዕራብ ጎጃም ሰብል ከመሰብሰብ አልፎ እስከ መውቃት ድረስ ባለ ቁርጠኝነት እየተሰበሰበ ሲሆን፤ አሁን ላይ ለህግ ማስከበር ዘመቻው ከሄዱት ውስጥ አንዳንዶቹ እየተመለሱ መሆኑንም ጠቁመዋል።በዘንድሮ የምርት አሰባሰቡ ላይ ከኮቪድ ቫይረስ ጋር ተያይዞ የታየውን ችግር መነሻ በማድረግ አልፎ አልፎ የጣለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በመኖሩ የደረሱ ሰብሎች እንዳይበላሹ ቀደሞ ለመሰብሰብ እንዲቻል ከግብርና ባለሙያዎች ጋር በመወያየት መሰራቱን አቶ ተስፋሁን ተናግረዋል። ዋና ዋና የደረሱ ሰብሎችን ቀድሞ መሰብሰብ እንጂ እንደድሮ ከምሮ ማስቀመጥ እንደማያዋጣ ጠቁመው፤ የተሰበሰበው ሰብል እንደደረቀ ወቅቶ ምርቱን መሰብሰብ በአውድማ ቦታ የሚፈጠሩ ችግሮችን ስለሚቀንስ ከድሮ በተለየ መልኩ ሰብሉን ቶሎ ለማስገባት በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።እንደ አቶ ተስፋሁን ገለጻ፤ አርሶ አደሩ ሰብሉን ሲሰበስብ ድግስ በማብዛት ወይም ተረጋግቶ ከመሰብሰብ አልፎ ያለንበትን ሁኔታ ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ካጨደ በኋላ በፍጥነት ወቅቶ ሰብሉን በእጁ መያዝ አለበት። ምክንያቱም ይሄን ሲያደርግ በምርቱ ላይ ሊደርሱ የሚችሉ በተባይ መበላት፤ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ መታደግ ይችላል። ይህ እንዲሆን ደግሞ በየደረጃው ያለ የግብርና ተቋምና ባለሙያዎች እገዛ ማድረግ እንዳለባቸው ነው አቶ ተስፋሁን ያሳሰቡት።አዲስ ዘመን ታህሳስ 3/213 | https://www.press.et/Ama/?p=37175 | 410 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
በትግራይ ክልል የመድኃኒትና የሕክምና መገልገያዎች ስርጭት እንደሚካሄድ ተገለጸ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 12, 2020 | 24 | አንድ ሚሊየን ለሚጠጉ ስደተኞችም ድጋፍ እየተደረገላቸው ነው በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ፡- ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት መድኃኒትና የሕክምና መገልገያ ቁሳቁስ ወደ ትግራይ ክልል እየተጓጓዘ ሲሆን፤ ከዛሬ ጀምሮም ይሰራጫል ተብሏል። በተያያዘም አንድ ሚሊየን ለሚሆኑ ስደተኞች አስፈላጊው ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሆነ ተገልጿል።መድኃኒቱና የሕክምና መገልገያው ከትናንት በስቲያ ጀምሮ ወደ መቀሌ፣ አዲግራትና ሽሬ ከተሞች በመጓጓዝ ላይ መሆኑ ታውቋል። በስፍራው እንደደረሰም በተለያዩ ሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች የሚሰራጭ ይሆናል። ወደ ስፍራው በመጓጓዝ ላይ ካሉት መድኃኒቶች መካከል ለስኳር ሕሙማን እንዲሁም ለእናቶችና ህጻናት ጤና አገልግሎት የሚውሉ መድኃኒቶች ይገኙበታል።የመድኃኒትና የሕክምና መገልገያዎቹ ስርጭት በኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ በኩል በመጓጓዝ ላይ መሆኑ ታውቋል። ከዚህ ቀደም ለምዕራብና ደቡባዊ የትግራይ ዞኖች በአማራና አፋር የኤጀንሲው ቅርንጫፎች በኩል መድኃኒት መሰራጨቱ ይታወቃል።በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የእለት ደራሽ ምግብና የተለያዩ ቁሳቁሶች በመዳረስ ላይ ሲሆኑ፤ የዕለት ደራሽ እርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት ከ12ሺ በላይ ኩንታል ስንዴ በ30 የጭነት መኪናዎች አማካኝነት ወደ መቀሌ የተጓጓዘ መሆኑ ይታወቃል።የመሰረተ ልማት ተቋማት መልሶ ግንባታ እየተካሄደ ከመሆኑ ጋር ተያይዞም የኤሌክትሪክና የቴሌኮም አገልግሎት ወደ ስራ እየገቡ መሆኑም ታውቋል።በተያያዘ ዜና፣ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የስደተኛ መጠለያ ውስጥ ለሚገኙ ከተለያዩ አገራት ማለትም ከደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ኤርትራና ከሱዳን ተሰደው ለመጡ ሰዎች በ26 የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ወደ አንድ ሚሊየን ለሚጠጉ ስደተኞች አስፈላጊው ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሆነ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ማጣሪያ አስታወቀ።ኢትዮጵያ በምትከተለው ፖሊሲ አንጻር ስደተኞች ከስደተኞች መጠለያ ወጥተው ህግን በተከተለ አሰራር በፈቀዱት ቦታ እንዲኖሩ እያደረገች በመሆኗ በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ከአንድ ሚሊየን በላይ ስደተኞች ተጠልለው እንደሚገኙ መረጃው አመላክቷል።ሆኖም የተሳሳተ መረጃ በመያዝ ኤርትራውያን ስደተኞች ከማይ ዓይኒ እና ሀሩሽ የስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎች ህጋዊ አሰራርን ሳይከተሉ ወደ አዲስ አበባ መግባታቸውን ነው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማጣሪያው የገለጸው። በአሁኑ ወቅት የህግ ማስከበር ዘመቻው በተጠናቀቀበት ትግራይ ክልልም ሆነ በሌሎች አካባቢዎች የስደተኛ ማቆያዎች ውስጥ የሚገኙ ሰዎች በሰላማዊ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ አመልክቷል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 3/213 | https://www.press.et/Ama/?p=37181 | 263 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ኤጀንሲው ኑሯቸውን በጎዳና ላይ ላደረጉ 22ሺ ዜጎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር አስታወቀ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 12, 2020 | 7 | ሞገስ ተስፋአዲስ አበባ፡- በተያዘው በጀት ዓመት ኑሯቸውን በጎዳና ላይ ላደረጉ 22ሺ ዜጎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር የፌዴራል ከተሞች የሥራ ዕድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ገለጸ።የፌዴራል ከተሞች የሥራ ዕድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን
ዳይሬክተር የሆኑት ወይዘሮ አቦዘነች ነጋሽ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለፁት፤ በ2013
ዓ.ም በጀት ዓመት ኑሯቸውን ጎዳና ላይ አድርገው ሕይወታቸውን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚገፉ 22ሺ ዜጎች የሥራ ዕድል ይፈጠራል።የፌዴራል ከተሞች የሥራ ዕድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ በከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔትና በፓይለት ፕሮጀክት ለዜጎች የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር ሰፊ ሥራ እየሰራ መሆኑን አመልክተው፤ ከዚህም ጎን ለጎን ኑሯቸውን ጎዳና ላይ ላደረጉ ዜጎች አስፈላጊ የሚባሉ ሥልጠናዎች እንደሚሰጡ አስታውቀዋል። ባለፈው ዓመት ስድስት ሺ ለሚሆኑ ኑሯቸውን በጎዳና ላይ ላደረጉ ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠሩን የገለጹት ኃላፊዋ፤ ዘንድሮ ግን ክፍተቶች በጥናት ተለይተው ከሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ፣ ከሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን፣ ከመንግሥትና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የጋራ አቅጣጫ በማስቀመጥ ለዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል ለመፍጠር ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።በተለይ በሥራ ዕድል ፈጠራ ትግበራው
ላይ ችግሮች እንዳይፈጠሩ
የሚከታተል ኮሚቴ የሚመለከታቸውን አካላት በማካተት መቋቋሙን
የጠቆሙት ወይዘሮ
አቦዘነች፤ ፕሮጀክቱን
በበላይነት የሠራተኛና ማህበራዊ
ጉዳይ ሚኒስቴር እንደሚመራው
አስታውቀዋል።ባለፉት አምስት ዓመታት በአጠቃላይ ለ604ሺ ዜጎች የሥራ ዕድል እንደተፈጠረላቸው ገልፀው፤ በተያዘው በጀት ዓመትም በሀገሪቱ ባሉ 83 ከተሞች የከተማ ሴፍቲኔት ፕሮግራም በመዘርጋት 480 ሺ 880 ዜጎች በከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እንደሚሆኑ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተሯ ገልፀዋል። | https://www.press.et/Ama/?p=37186 | 201 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የአማራ ባንክ አክሲዮን ማህበር ከአክሲዮን ሽያጩ ቃል ከተገባለት ውስጥ ስድስት ቢሊዮን ብር መከፈሉን ገለጸ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 12, 2020 | 13 | ፍሬህይወት አወቀ አዲስ አበባ፡- በምስረታ ላይ ያለው የአማራ ባንክ አክሲዮን ማህበር ከአክሲዮን ሽያጩ ቃል ከተገባለት ስምንት ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር ውስጥ ስድስት ቢሊዮን ብር መከፈሉን ገለጸ።ማህበሩ ባለ አክሲዮኖች ውክልና እንዲሰጡ ጥሪ አቅርቧል። የአማራ ባንክ አክሲዮን ማህበር አደራጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ መላኩ ፈንታ፣ የማህበሩ የአክሲዮን ሽያጭ መጠናቀቁን አስመልክተው እንደተናገሩት፤ የአክሲዮን ሽያጩ ኅዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም የተጠናቀቀ ሲሆን፤ ከአክሲዮን ሽያጩ ቃል የተገባለት ስምንት ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር እንደሆነና ከዚህ ውስጥም ስድስት ቢሊዮን ብር መከፈሉን ተናግሯል። ከአገልግሎት ክፍያ ጋር በተያያዘም አራት መቶ ሁለት ሚሊዮን ብር መገኘቱን አስታውቋል።በአክሲዮን ሽያጩ ላይ መንግሥት አስተዋጽኦ እንደነበረው የጠቀሱት አቶ መላኩ፤ ባንኩ የሕዝብ እንደመሆኑ በአክሲዮን ግዥው ሁሉም ብሔር ብሔረሰብ ተሳታፊ እንደነበር አመልክተዋል። ኅብረተሰቡን ጨምሮ በሽያጩ ላይ ተሳታፊ ለነበሩ አስር ባንኮችም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።ይሁን እንጂ የባለአክሲዮኖች ውክልና አሰጣጥን በተመለከተ
ከኅዳር አንድ እስከ ኅዳር 30 ቀን
2013 ዓ.ም የውክልና
አሰጣጡ በሰነዶች ማረጋገጫ
ኤጀንሲ መሰጠቱን ያነሱት አቶ መላኩ፤ ከ185 ሺ ባለአክሲዮኖች መካከል
75 ሺ ወይም 41 በመቶ የሚሆኑ ሰዎች ብቻ ውክልናቸውን
የሰጡ መሆናቸውንም አመልክተዋል። ለዚህ ደግሞ ባለአክሲዮኖች ወይም ወኪሎች በአካል ተገኝተው ውክልና የሚሰጡበት የንግድ ሕግ ቢኖርም ወቅታዊ ሁኔታው ለዚህ ምቹ አለመሆኑን ገልፀዋል።ሆኖም በተቀመጠው የአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ባለአከሲዮኖች ሙሉ በሙሉ ውክልና መስጠት ያልቻሉና ይህም ምስረታውን ወደ ኋላ እየጎተተው እንደሆነ ያነሱት አቶ መላኩ፤ ባለአክሲዮኖች እስከ ታኅሣሥ 15 ቀን 2013 ዓ.ም ውክልናቸውን እንዲሰጡ ጥሪያቸውን አቅርበዋል። የባንኩ አደራጅ ጊዜውን ሰውቶ እያገለገለ እንደመሆኑ፣ ባለአክሲዮኖችም የአንድ ቀን ጊዜ ወስደው በተሰጠው ተጨማሪ ጊዜ በሰነዶች ማረጋገጫ ኤጀንሲ በመገኘት ውክልናቸውን እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል። የውክልናውን ሂደት ተከትሎም ጉባኤው የሚካሄድበትን ጊዜ የሚያሳውቁ መሆኑን ጠቁመዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 3/213 | https://www.press.et/Ama/?p=37180 | 235 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአሠልጣኝ ሳላዛር እንዲርቁ ተጠየቀ | ስፖርት | October 3, 2019 | 24 | እኤአ 2015 የቢቢሲ ፓናሮማ የተሰኘው ፕሮግራም በአሜሪካ የሚገኘው የናይኪ ኦሪገን የአትሌቲክስ ማሰልጠኛን በተመለከተ ያቀረበው ዘገባ የብዙዎችን ቀልብ የሳበ ነበር። ከአሜሪካው ፕሮፑብሊካ ድረ ገፅ ጋር በጋራ በመሆን በተሰራው በዚህ ፕሮግራም ላይ በአትሌቲክስ ማሰልጠኛው በከፍተኛ ሁኔታ የአበረታች መድሃኒት እንደሚሰጥ በተደረገው ምርመራ እንደተደረሰበት አጋልጧል። በማሰልጠኛው ተገቢነት ያልሆኑ ተግባራት እንደሚካሄዱም ዘገባው በወቅቱ ይፋ ማድረጉ አይዘነጋም። እኤአ ከ2011 ጀምሮ የፕሮጀክቱ አስተዳዳሪ የነበሩት አሰልጣኝ አልቤርቶ ሳላዛር የመጀመሪያ ተጠያቂ አድርጎ ዘገባው አቅርቧቸዋል። አራት የኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳሊያዎችን
አሸናፊ የሆነው እንግሊዛዊው አትሌት ሞ ፋራህ የዚህ ማዕከል ፍሬ መሆኑን የምርመራ ዘገባው መጠቆሙን ተከትሎ ጉዳዩ ከስፖርትም በዘለለ
ሊጦዝ ችሏል። የፓናሮማ ዘገባን ተከትሎ የአሜሪካው የፀረ አበረታች መድሃኒት ኤጀንሲ ጉዳዩን በመያዝ የ61 ዓመቱ ሳላዛር ፍርድ
ቤት ሳይውል ሳያድር እንዲቆም አድርጓል። ኤጀንሲው ሰውዬውን ተጠያቂ ለማድረግም መረጃዎችን በማሰባሰብ ዓመታትን ተሻግሯል። የተለያዩ
መረጃና ማስረጃዎችንም ሲያሰባስብ ቆይቷል። የአሰልጣኙ ጉዳይ በተለይ ከ ሞፋራህ ጋር የተያያዘ መሆኑ በብዙ መልኩ አነጋጋሪ መሆን
የቻለ ሲሆን ከትናነት በስቲያ በኤጀንሲው ይፋ የተደረገው መረጃ ጉዳዩን እንደ አዲስ መነጋገሪያ አድርጎታል። ቢቢሲ የኤጀንሲውን
መረጃ ዋቢ አድርጎ አሰልጣኝ አልቤርቶ ሳላዛር ከአራት ዓመት ምርመራና ከሁለት ዓመት የፍርድ ቤት ክርክር በኋላ ጥፋተኛ ሆኖ መገኘቱን
ዘግቧል። አሰልጣኙ የተከለከሉ አበረታች ቅመሞችን
ከቦታ ቦታ ማዘዋወርን ጨምሮ የፀረ-ዶፒንግ እንቅስቃሴውን በማወክ እና በተለያዩ የፀረ-ዶፒንግ የህግ ጥሠቶች እንደፈጸመ መረጋገጡን
አስታውቋል። የዩኬ ስፖርቶችን የሚቆጣጠረው ዩኬ አትሌቲክስ፣ የራሱን ምርመራ ማካሄዱን የጠቀሰው ዘገባው፤ በናይክ እየተከፈላቸው
በርካታ የሳላዛር አትሌቶችን የሚያክሙት ዶክተር ጄፍሪ ብራውን ደግሞ ለአራት ዓመት መታገዳቸውን ዘግቧል። ቢቢሲ የሞ ፋራህ ቀድሞ አሠልጣኝ፣ አልቤርቶ ሳላዛር፣ ከአበረታች መድሀኒት ጋር በተያያዘ ከስፖርት
ለአራት ዓመት መታገዱን ባስነበበው በዚህ ዘገባው፤ ፋራህ ከሳላዛር ጋር የተለያየው በ2017 መሆኑን ጠቅሶ ከአበረታች መድሃኒት
ጋር በተያያዘ አለመሆኑን ገልጿል ከማለት ውጪ፤ ፋራህ ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ ጥፋተኛ ይሁን አይሁን ምንም ያለው ነገር የለም። ከተለያዩ አገራት አትሌቶች ጋር በቅርበት እንደሚሰራ የሚነገርለት አሰልጣኝ ሳላዛር ጥፋተኝነትን ተከትሎ
አገራት አትሌቶቻቸውን ከአሰልጣኙ እንዲርቁ እያስገነዘቡ መሆኑም ተሰምቷል። ኢትዮጵያዊያን አሰልጣኞችና የስፖርት ባለሙያዎችም ከአሠልጣኙ
ሊርቁ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ፅህፈት ቤት በላከው መግለጫ አስታውቋል። «ኢትዮጵያውያን አትሌቶችና
የስፖርት ባለሞያዎች ከአሰልጣኝ አልቤርቶ ሳላዛር ጋር የሚኖራቸውን ቀጥተኛም ይሁን ቀጥተኛ ያልሆነ ግንኙነት ማቋረጥ አለባቸው»
ሲልም አሳስቧል። በአለም ዓቀፉ የፀረ-ዶፒንግ ህግና በአገራችን የፀረ- ዶፒንግ መመሪያ አንቀፅ 2 ነጥብ 10 መሠረት
በህግ ጥሰት ቅጣት ከተላለፈባቸው ግለሰቦች ጋር ያልተገባ ግንኙት መፍጠር በጥብቅ የተከለከለ ሲሆን እስከ ሁለት ዓመት የሚደርስ
የእስር ቅጣትን እንደሚያስከትል አስገንዝቧል። የአገራችን አትሌቶች በተለያየ መልኩ ከአሠልጣኝ አልቤርቶ ሳላዛር ጋር እንደሚሠሩ
የገለጸው ጽህፈት ቤቱ፤ በግለሰቡ ላይ የተጣለው ይህ የቅጣት ውሳኔ ይፋ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ ያላቸውን ቀጥተኛም ይሁን ቀጥተኛ
ያልሆነ ግንኙነት እንዲያቋርጡ ጥሪውን አስተላልፏል። ከዚህ ባሻገር
የስፖርት ባለሞያዎችም ይሁን ሌሎች አካላት ከዚህ ግለሠብ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ማቋረጥ እንደሚኖርባቸው አስገንዝባል። «ስፖርተኞችም
ይሁን ሌሎች ባለሞያዎች የተቀመጠውን ህግ በመተላለፍ ቀደም ሲል የነበራቸውን ግንኙነት ለማስቀጠልና አዳዲስ ግንኙነቶችን ለመፍጠር
እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ከሆነ ፅህፈት ቤታችን ጉዳዩን በማጣራት አስፈላጊውን የህግ እርምጃ ለመውሰድ ይገደዳል» በማለት ፅህፈት ቤቱ
ሁሉም አካላት የፀረ-ዶፒንግ ህጎችን በማክበርና በማስከበር ንፁህ ስፖርትን ለማስፋፋት ጥረት ማድረግ እንደሚገባም አብራርቷል።አዲስ ዘመን መስከረም 22/2012ዳንኤል ዘነበ | https://www.press.et/Ama/?p=19910 | 431 | 2ስፖርት
|
«ወንጀለኛው ጁንታ ዋናው ዓላማው ኢትዮጵያን ማፈራረስና ለዓመታት ይዞ የቆየውን የዝርፊያ ፍላጎቱን ማስቀጠል ነበር» አቶ ብናልፍ አንዷለም የብልጽግና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 12, 2020 | 32 | ማህሌት አብዱልአዲስ አበባ፡- ወንጀለኛው ጁንታ ዋነኛ ዓላማውና የሴራው ማጠንጠኛ ኢትዮጵያን በማፈራረስ የራሱን የአገዛዝ ሥርዓት በማስቀጠል ይዞ የቆየውን የአፈናና የዝርፊያ ፍላጎት ማስቀጠል እንደነበር የብልጽግና ጽሐፈት ቤት ኃላፊ አቶ ብናልፍ አንዷለም ገለፁ። አቶ ብናልፍ ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጹት፤ ወንጀለኛው ጁንታ ከዝርፊያ ውጪ ሌሎች መንገዶችን ማየት የማይችልና የራሱንም ሃሳብ መልሶ የሚክድ የማፍያ ቡድን ነው። ለምሳሌ ቀደም ሲል በኢህአዴግ ውስጥ በጋራ አንድ አጀንዳ ላይ ተወያይቶና ውሳኔ ካሳለፈና የውሳኔዎቹ ሃሳብ በመግለጫ ከወጣ በኋላ፣ ለብቻው ወጥቶ እንደገና ሌላ መግለጫ ያወጣል።በወቅቱ የሚያወጣው መግለጫ ደግሞ የኢህአዴግን ውሳኔ የተቃረነ ነበር። በጋራ መድረክ ተስማምቶ ሲያበቃ ለብቻው መግለጫ ካወጣባቸው ጉዳዮች መካከል የኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ውዝግብ ወደ እልባት እናምጣው የሚለው አጀንዳ ይጠቀሳል። የፕራይቬታይዜሽን ጉዳይም ሌላው አወዛጋቢ ጉዳይ ሲሆን፤ የልማት ድርጅቶችን ደረጃ በደረጃ አዋጭነታቸው እየታየ አንዳንድ ተቋማት ወደ ግል ሴክተር እንዲዛወሩ የተወሰኑ ውሳኔዎችንም አብሮ ነበር የወሰነው። ይህንንም በጋራ ከወሰነ በኋላ በሚቀጥለው ቀን በመቃወም እንደገና መግለጫ አውጥቷል።ከዚህም ውጪ በሀገሪቱ የተካሄደውን የፖለቲካ ሪፎርም ለማደናቀፍ ጁንታው በከፍተኛ ሁኔታ ሲንቀሳቀስ እንደነበርም አቶ ብናልፍ ተናግረዋል። ለአብነትም፣ ኢህአዴግ የሚመራበት አብዮታዊ ዴሞክራሲ በሚል ፍልስፍና ርዕዮተ ዓለም ደግሞ ጠላትና ወዳጅ ብሎ የሚለይ ነው። ሰዎችን በአመለካከታቸው ብቻ ይሄኛው ጠላቴ ነው፤ ሌላኛው ደግሞ ወዳጄ ብሎ የሚያስቀምጥ መሆኑ በሕዝቦች መካከል የጥላቻ ግድግዳ ፈጥሮ ኖሯል። ይህ አስተሳሰብ እንዲስተካከል ግን ፈጽሞ ፍላጎት አልነበረውም።የሚገርመው ግን ጠላት ወይም ወዳጅ ከሚለው ውጪ ሌላ ሦስተኛ መንገድ አለ ብሎ አለማመኑ እንደሆነ የገለፁት አቶ ብናልፍ፤ በዚህ ርዕዮተ ዓለም አንድ ዜጋ ምንም ዓይነት አስተሳሰብ ይኑረው ገለልተኛ ሆኖ መኖር አይፈቀድለትም ብለዋል። ይህም አሁን ባለው የኢትዮጵያ ሕዝብ የፖለቲካ ንቃት፤ የአገሪቱ የዓለምአቀፍ ሁኔታ በፍፁም አያስኬድም የሚል አቋም በአብዛኛዎቹ የለውጡ ኃይሎች ዘንድ ተይዞ እንደነበር እና ጁንታው ግን ይህ ሊዋጥለት እንዳልቻለ ተናግረዋል።እንደ አቶ ብናልፍ ገለጻ፤ ጁንታው በኢኮኖሚ ረገድ በመላ አገሪቱ በሚባል ደረጃ ኢፍትሃዊ የሆነ አሠራር ነበር ሲከተል የነበረው።
ይሄ ቡድን በሁለት ዓይነት መንገድ ነበር ኢ-ፍትሃዊነቱን ሲያስፋፋ
የነበረው። አንደኛው ሕጋዊ የሆኑትን የመንግሥት
ተቋማት በመጠቀም ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ በልማት ድርጅቶች
አማካኝነት የሚደረግ ዘረፋ ነው። ለምሳሌ በአማራ ክልል የመንገድ ፕሮጀክቶችን የሚመሩት የጁንታው አካላት ስለነበሩ እንዲህ ዓይነት ፕሮጀክቶች በሚያዙበት ጊዜ ኢ-ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ይካሄድ እንደነበር አቶ ብናልፍ ጠቅሰዋል።በኢንቨስትመንት ሰፋፊ የእርሻ ቦታ ባላቸው አካባቢዎች ላይ የእነሱ ተላላኪ፣
የእነሱ ዘመድ፣ የእነሱ የቅርብ አስፈፃሚ
የሆኑ ሰዎችን የኢንቨስትመንት ፍቃድ እንዲያወጡ አድርገው በኢንቨስትመንት ስም እርሻ እንዲወስዱ ሲያደርጉ እንደነበር በመጥቀስ፤ ቤኒሻንጉልና ጋምቤላ ክልሎች ላይ የፈፀሙት ምዝበራ ለዚህ አብነት የሚሆን ማሳያ ነው ብለዋል።አቶ ብናልፍ እንዳሉት፤
ይህ ቡድን በወልቃይት፣
በጠገዴ፣ በራያና በመሳሰሉት
አካባቢዎች ያሉ ሕዝቦች ድምጽ እንዳይሰማ
አጀንዳ እያስቀየረ ነው የኖረው። አሁን የተፈጠረው አዲሱ ነገር ጥያቄው ከዚህ በኋላ መታፈን አይችልም የሚለው ነው። ይሄ አፋኝ ቡድን ላይመለስ ወደመቃብሩ ወርዷል፤ ስለዚህ የመጨረሻ የሞት ሞት ያደረጉት ትግል ይህንን የሕግ ማስከበርና አገር የማዳን ዘመቻ የመሬት ማስመለስ ዘመቻ ነው በሚል አገናኝተው ቀላል የማይባል መደነጋገሪያ ፈጥረዋል። ሆኖም ሃቁና እውነቱ ተደብቆ አይቆይም።ሆኖም የእነዚህ ሰዎች ጥያቄ የመብት ጥያቄ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል። እዚያ አካባቢ ያለ የእርሻ መሬትም በተግባር ሄዶ ሲታይ አማራም ሆነ ትግሬ ሄዶ ሊያርስ ይችላል፤ ዋናው ነገር እሱ አይደለም፤ ዋናው ነገር የሰው ልጆች ክብር ነው፣ ብለዋል አቶ ብናልፍ።የኢትዮጵያን ብሔር ብሔረሰቦች በመከፋፈልና በጠላትነት እንዲተያዩ በማድረግ በጋራ የመሰረቱትን የአንድነት እሴታቸውን እያፈረሰ በልዩነቶቻቸው ላይ ሲሰራ እንደኖረና የልዩነቶቻቸው አንኳር አድርጎ የወሰደው ደግሞ አማራ የሚባል ጨቋኝ ብሔር አለ የሚል ትርክት ላይ ተመስርቶ እንደሆነም አቶ ብናልፍ ጠቅሰዋል።አቶ ብናልፍ እንደገለጹት፤ ከነዚህ ሁሉ ሴራዎች ጀርባ የነበረው ደግሞ የደህንነት መዋቅሩ ነው። ይህ መዋቅር ወንጀለኛው ጁንታ ባስቀመጣቸው ሰዎች የሚመራ ስለነበር ሁሉም ነገር በምስጢር ነው የሚደረገው። አብዛኛው የፖለቲካ አመራር አያውቀውም ነበር። ለምሳሌ፣ ድብቅ እስር ቤቶች አሏቸው፤ ግን ሌላው አመራር አያውቃቸውም ነበር። እናም የሚፈልጉትን ሰው በድብቅ እስር ቤት ውስጥ አስገብተው ከፍተኛ የሆነ ኢሰብዓዊ ድርጊት ይፈፅሙባቸው ነበር።እንደሚታወቀው፣ ደግሞ በአብዛኛው እስር ቤት የአማራና የኦሮሞ ተወላጆች በብዛት ነበሩ፤ የኦሮሞ ተወላጆችን ከኦነግ ጋር አብረው የሽብር ተግባር ሲፈፅሙ ነው የያዝኳቸው ይላል፤ በአማራ ክልል በኩል ያሉትን ደግሞ የግንቦት ሰባት ተላላኪዎች ናቸው እያለ ነበር መከራና ግፍ ሲያደርስባቸው የነበረው። አቶ ብናልፍ እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ አገር መከላከያ ሰራዊት የተሰጠውን ግዳጅ በጥንቃቄና በብቃት በመወጣቱ ሂደት ንፁሃን እንዳይጎዱ በማድረግ ረገድ ጥፋተኛውን ኃይል ብቻ ነጥሎ በመምታት ሕግን ለማስከበር የወሰደው እርምጃ ትልቅ አድናቆት ሊሰጠው የሚገባ ነው። በታሪክ መዝገብ ሊመዘገብ የሚገባ ትልቅ ክስተትም ነው።ከሃዲው ቡድን ሽንፈቱ አይቀሬ መሆኑን እየተገነዘበ ሲሄድ የያዛቸውንና ምሽግ የሰራባቸውን ቦታዎች እየለቀቀ በሚሄድበት ጊዜ የተለያዩ መሠረተ ልማቶችን እያፈረሰ እንደሄደ የጠቆሙት አቶ ብናልፍ፤ ለምሳሌ መከላከያ ሰራዊት አልፎና ተሻግሮ እንዳይሄድ መንገድ ሲቆርጥና ሲያፈርስ ነበር፤ አየር ማረፊያዎችን ከጥቅም ውጪ አድርጓል፤ ስልክና ኤሌክትሪክ የመሳሰሉትን መሠረተ ልማቶች ቆራርጧል፤ ብለዋል። እነዚህን መሠረተ ልማቶችም ተጠግነው ቶሎ አገልግሎት የሚሰጡበትን መንገድ ለመፍጠር እየተሰራ እንደሆነ ጠቁመዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 3/213 | https://www.press.et/Ama/?p=37187 | 658 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የሚኒስትሮች ምክር ቤት የሀገሪቱን የአሥር ዓመት ብሔራዊ ዕቅድ አጸደቀ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 12, 2020 | 12 | – የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት ረቂቅ አዋጅንም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መርቷል በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ92ኛው መደበኛ ስብሰባው የተለያዩ ውሳኔዎችን ያሳለፈ ሲሆን፤ በዚህ ውሳኔውም ኢትዮጵያን ወደ ዕድገት ማማ በማስፈንጠር አፍሪካዊት የብልጽግና ተምሳሌት እንድትሆን የሚያስችላት የኢትዮጵያ የአሥር ዓመት ብሔራዊ ዕቅድ ማጽደቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስታወቁ።ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገጻቸው እንደገለጹት፤ ዕቅዱ በተለይም በሰላም ግንባታ እና ተቋማዊ ሕዳሴ ላይ የሚያተኩሩ አሥር ምሰሶዎች አሉት። በተጨማሪም፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኅትመት እና የብሮድካስት መገናኛ ብዙኃን መተዳደሪያ ሆኖ የሚያገለግለውን እና ለበይነ መረብ ሚዲያ የሕግ ማዕቀፍ ሆኖ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚተገበረውን የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት ረቂቅ አዋጅ አጽድቋል። የዘርፉን ግዴታዎች እና ኃላፊነቶች የሚተነትነው አዋጅ፣ የመረጃ እና የፕሬስ ነጻነት ተግባራዊነትን በከፍተኛ ሁኔታ የሚደግፍ ነው።የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በበኩሉ በፌስቡክ ገጹ እንዳመለከተው፤ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በትናንትናው ዕለት በሁለት ጉዳዮች ላይ የተወያየ ሲሆን፤ የመጀመሪያው የልማት እቅድ ፍኖተ ካርታ ብልጽግና 2013 – 2022 ሰነድ ላይ ነው። የልማት መሪ እቅዱ አገር በቀል የልማት አቅጣጫን የተከተለ፣ በዘርፎች መካከል ሊኖር የሚገባውን ትስስር የሚያጎለብት፣ የቀጣይ አስር ዓመታት የሚያተኩርባቸውን የልማት ምሰሶዎች እና የትኩረት መስኮች የለየ ነው።ይህ ሰነድ፣ የዜጎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ፣ ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ የሚያስችል ብሎም የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግና እውን ለማድረግና የአፍሪካ ብልጽግና ተምሳሌት እንድትሆን የሚያስችል እቅድ ነው። ይሄው እቅድ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት መቅረቡን ተከትሎ በእቅዱ ላይ በመወያየትና ግብዓቶችን በማከል ስራ ላይ እንዲውል ወስኗል።በተመሳሳይ ምክር ቤቱ የመገናኛ ብዙኃን ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል። ይህ ረቂቅ አዋጅ የዜጎችን ሃሳብ በነጻነት የመግለጽ መብት የሚያረጋግጥ፣ የመገናኛ ብዙሃን በተቋምነታቸው የአሰራር ነጻነት እንዲኖራቸው እና የሃሳብ ብዝሃነት የማስተናገድ አቅም እንዲያጎለብቱ የሚያስችል ነው። ከዚህ ባለፈ የቴክኖሎጂ እድገት የደረሰበትን የሚዲያና ብሮድካስት ቴክኖሎጂ እውቅና የሚሰጥ፣ በገለልተኝነት ዘርፉን የሚመራ ተጠሪነቱ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሆነ ተቋማዊ ስርዓት ማጎልበት የሚያስችል ነው። ምክር ቤቱም ረቂቅ አዋጁ ላይ በጥልቀት ተወያይቶ ይጸድቅ ዘንድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ ወስኗል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 3/213 | https://www.press.et/Ama/?p=37174 | 275 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ፌዴሬሽኑ በአራት ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አሳለፈ | ስፖርት | October 3, 2019 | 25 | የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ከትናንት በስቲያ በተቋሙ መሰብሰቢያ አዳራሽ ከጠዋቱ አራት ሰዓት እስከ ምሽት አንድ ሰዓት የቆየ ስብሰባ አድርጓል። በ2011 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የመጣው አመራር በቆይታው ምን ምን ጉዳዮችን ሰራ፣ ምንስ ሳይሰራ ቀረ እንዲሁም ሥራዎችን በምን ደረጃ ሲከታተል ቆየ በሚል አጠቃላይ ውይይት መደረጉን ፌዴሬሽኑ ገልጿል። ከዚህ ቀደም በተቋሙ የታዩ ክፍተቶች በምን ደረጃ መስተካከል ይኖርባቸዋል፣ በሥራ አስፈጻሚው መካከል የነበረው አለመናበብ እና በቀጣይ ሊሻሻሉ የሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ጥልቅ ውይይት እንዲሁም የግል ግምገማ በማድረግ በአራት ጉዳዮች ላይ ውሳኔ መተላለፉን አስታውቋል። ፌዴሬሽኑ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን የተሳታፊ ክለቦችን ቁጥር በተመለከተም ውሳኔ አስተላልፏል። ፌዴሬሽኑ
መስከረም 05 ቀን 2012 ዓ.ም የውድድር ዓመቱ በሁለት ምድብ ተከፍሎ 24 ክለቦች እንደሚሳተፍ ያስተላለፈውን ውሳኔ በመሻር፤
በ16 ቡድኖች መካከል ውድድሩ እንዲካሄድና በምን አግባብ መመራት እንዳለበት ከክለቦች ጋር በቅርብ ውይይት እንዲካሄድ ውሳኔ መተላለፉን
አስታውቋል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዲሲፕሊን መመሪያ ሌላው በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ውሳኔ የተላለፈበት መሆኑን የገለጸው
ፌዴሬሽኑ፤ በአንድ የውድድር ዘመን ሁለት ጊዜ ፎርፌ ለተጋጣሚ ቡድኖች የሰጠ ቡድን ከውድድር እንደሚሰረዝ አስታውቋል። ቅዱስ ጊዮርጊስ
እግር ኳስ ክለብ ባለፈው የውድድር ዓመት ሁለት ጊዜ በወጣለት መርሃ ግብር መሰረት ጨዋታዎች ላይ አለመገኘቱን ፌዴሬሽኑ ከታዛቢዎች
ሪፖርት ተመልክቷል። በዚህም የሊግ ኮሚቴ ውጤቱን ለመወሰን የውድድር ክፍል በወቅቱ ባለማሳወቁ ውሳኔው ሂደት ያልጠበቀ እንዲሆን
አድርጎታል ተብሏል። ስህተቱን በፈጠረው ሰራተኛ ላይ የዲሲፕሊን ቅጣት እንዲተላለፍበትም ተወስኗል። ቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብም
በፕሪሚየር ሊጉ እንዲቆይ እና በ2012 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እንዲወዳደር ውሳኔ ላይ መደረሱን በመግለጫው ተጠቅሷል። በአንደኛ ሊግ ተሳታፊ የነበረው ቦሌ ገርጂ እግር ኳስ ክለብ በፀጥታ ችግር ቡድኑ ወደ ጨዋታ ስፍራ
መጓዝ ባለመቻሉ የተሰጠው ፎርፌ ቡድኑ እንዲሰረዝ ምክንያት እንደነበር ይታወሳል። ሆኖም ውድድር ክፍል ላይ በነበረው የአሰራር ክፍተት
ቡድኑ አለመጓዙ ሥራ አስፈጻሚው ስለተረዳ ቡድኑ ላይ የተሰጠው ውሳኔ እንዲሰረዝ እና በአንደኛ ሊግ እንዲወዳደር መወሰኑን ፌዴሬሽኑ
አስታውቋል። ሥራ አስፈፃሚው
በእለቱ ውሳኔ የሰጠበት ሌላው ጉዳይ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን ይመለከታል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለኳታር የአለም ዋንጫ ማጣሪያ
ወደ ሌሴቶ ሲያቀና ላጋጠመው እንግልት ምክንያት የሆኑ ሰራተኞች በጽህፈት ቤቱ በኩል በሰራተኞች አስተዳደር በዲሲፕሊን እንዲጠየቁ
እንዲሁም በጽህፈት ቤት ኃላፊው የመጀመሪያ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ እንዲሰጣቸው መደረጉ ታውቋል።አዲስ ዘመን መስከረም 22/2012ዳንኤል ዘነበ | https://www.press.et/Ama/?p=19916 | 314 | 2ስፖርት
|
አንጋፋው ክለብ በፌዴሬሽኑ አሰራር ግራ ተጋብቷል | ስፖርት | October 6, 2019 | 36 | በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ወጥነት የሌለው አሰራር ምክንያት በርካታ ቅሬታ ከእግር ኳስ ቤተሰቡ ሲነሳ ይስተዋላል። ፌዴሬሽኑ ችግሮች ሲገጥሙትም በአሰራር እንዲሁም በአስተዳደራዊ ሁኔታ መፍታት አለመቻሉም ክለቦችን ለቅሬታ ብቻም ሳይሆን ወደሌላ ችግር እየከተታቸው ነው። ከእነዚህ ክለቦች መካከል አንዱ የመከላከያ እግር ኳስ ቡድን ሲሆን፤ አንጋፋው ክለብ ከምስረታው እስከ አሁን ያሳለፋቸውን ሁኔታዎች የክለቡ ኃላፊ ኮሎኔል ደሱ ታደሰ ለአዲስ ዘመን ገልጸዋል። ምስረታ የመከላከያ ስፖርት
ቡድን
የተመሰረተው
በ1938
ሲሆን፤
የእግር
ኳስ
ቡድኑ
ግን
መቻል
በሚል
መጠሪያ
በ1984ዓም ነው የተቋቋመው። በወቅቱ በአዲስ አበባ አንደኛ ዲቪዚዮን ሲጫወት ቢቆይም ወደ ሁለተኛ ዲቪዚዮን መውረድ እጣ ፈንታው ሆነ። ይሁን እንጂ ከአንድ ዓመት ቆይታ በኋላ በድጋሚ በ1986 ዓ.ም
ወደ
አንደኛ
ዲቪዚዮን
ሊያድግ
ችሏል።
በዚህ
ሁኔታ
እስከ
1987 ዓ.ም መጨረሻ ቢቆይም
ቡድኑ
የመበተን
አደጋ
ሊገጥመው
እንደቻለ
የቡድኑ
ኃላፊ
ይገልጻሉ።
በ1989 ዓ.ም የኢትዮጵያ ጦር
ኃይሎች
ፌስቲቫል
መካሄዱን
ተከትሎ
ተጫዋቾችን
በማሰባሰብ
በ1990
ዓ.ም መከላከያ በሚል
ስያሜ
በድጋሚ
ተዋቀረ።
በአዲስ
መልክ
ሁለተኛ
ዲቪዝዮን
ላይ
ቢጫወትም
በዚያው
ዓመት
ቻምፒዮን
በመሆኑ
ወደ
አንደኛ
ዲቪዚዮን
ሊያድግ
ችሏል።
እስከ
1993 ዓ.ም ባለው ጊዜም
ፋና
እና
ጸሃይ
ግባት
በሚል
ስያሜ
በድጋሚ
ተከፍሎ
በብሄራዊ
እና
ከፍተኛ
ሊግ
ሲጫወቱም
ቆዩ።
በ1996
ዓ.ም ድጋሚ ክለቦቹ
መከላከያ
በሚል
ተዋህዶ
በኢትዮጵያ
ፕሪምየር
ሊግ
ተሳትፎውን
ጀመረ።
የፕሪምየር ሊግ ቆይታ መከላከያ እግር
ኳስ
ክለብ
እስከ
2011 ዓ.ም ድረስም በኢትዮጵያ
ፕሪምየር
ሊግ
ለረጅም
ዓመታት
ከቆዩት
ክለቦች
መካከል
አንዱ
ሊሆን
ችሏል።
በእነዚህ
ዓመታትም
ሶስተኛ
ሆኖ
የጨረሰበት
ውጤት
ከፍተኛው
ቢሆንም
በደረጃ
ሰንጠረዡ
መካከለኛ
ስፍራ
ላይ
የሚቀመጥ
ክለብ
ነው።
በተለይ
ከሊጉ
ተሳታፊዎች
ክለቡን
ለየት
የሚያደርገው
አንድም
የውጪ
ተጫዋች
ባለማስፈረምና
በአገር
ውስጥ
ተጫዋቾች
ብቻ
በመገልገሉ
ነው።
የግብ
ጠባቂ
እጥረት
ያለበት
የኢትዮጵያ
ወንዶች
ብሄራዊ
ቡድን
ለዓለም
አቀፍ
ውድድሮች
የሚያማትረው
ወደ
ክለቡ
መሆኑም
ይታወቃል።
ለአራት
ጊዜያት
ያህልም
የኢትዮጵያ
ጥሎ
ማለፍ
ቻምፒዮን
በመሆን
ለአራት
ጊዜ
በአፍሪካ
ኮንፌዴሬሽን
ዋንጫ
ተሳታፊ
መሆኑ
እንደ
ስኬት
ሊነሳለት
ይችላል።
የስፖርታዊ ጨዋነት
ችግር
ለዓመታት
በነገሰበት
የኢትዮጵያ
ፕሪምየር
ሊግ
ስሙ
ሳይነሳ
የቆየው
የመከላከያ
እግር
ኳስ
ክለብ
መሆኑም
የሚታወቅ
ነው።
እንዲያውም
ስፖርታዊ
ጨዋነትን
በማስፈን
ረገድ
ተጫዋቾች
የሚወጡት
ሚና
ያስመሰገናቸውም
ነበር።
ምክንያቱ
ደግሞ
ክለቡ
ተጫዋቾችን
በወታደር
ስነ-ስርዓት ማስተዳደሩ ነው። ባልተፈቀደ ሜዳ ኃይልና ጉልበት መጠቀም እንደማያስፈልግ ክለቡ ያስገነዝባል፤ ተጫዋች ይህንን ተላልፎ ክለቡ በፌዴሬሽኑ ቅጣት ቢጣልበት እንኳ ተጫዋቹ እንዲከፍል እንዲሁም በክለቡ ደንብ መሰረት እንዲቀጣ የሚደረግ መሆኑንም ኮሎኔል ደሱ ይገልጻሉ። በርካታ ክስተቶችን
ያስተናገደው
ያለፈው
የውድድር
ዓመት
ግን
ለክለቡ
ጥሩ
የሚባል
አልሆነም።
በዓመቱ
መጀመሪያ
አካባቢ
ክለቡ
ጥሩ
ጅማሬ
ቢያደርግም
ከአዳማ
ከተማ
ጋር
ባደረገው
ጨዋታ፤
ከቀይ
ካርድ
ጋር
ተያይዞ
መንገዳገድ
እንደጀመረ
ኃላፊው
ያስታውሳሉ።
ከዚህ
ባሻገር
ክለቡ
ከአዲስ
አበባ
ወጥቶ
በሚያደርጋቸው
ጨዋታዎች
ላይ
የስፖርታዊ
ጨዋነት
ሰለባ
በመሆን
በጫና
ውስጥ
ዓመቱን
አሳልፏል።
በዳኞች
ፍትህ
ማጉደል
እንዲሁም
በሪፖርት
ጸሃፊዎች
ችግር
ሲደርስበት
ቆይቷል።
በኋላም
በነበሩት
ውስጣዊና
ውጫዊ
ጉዳዮች
ክለቡ
አሁን
ካለበት
አድርሶታል።
ቅሬታመከላከያ እግር
ኳስ
ክለብ
ከኢትዮጵያ
ፕሪምየር
ሊግ
ስለመውረዱ
ከፌዴሬሽኑ
የተሰጠው
አንዳችም
ማረጋገጫ
አለመኖሩን
ኃላፊው
ኮሎኔል
ደሱ
ያረጋግጣሉ።
በውድድር
ዓመቱ
ክለቡ
የነበሩበትን
ስጋቶች
ለበርካታ
ጊዜያት
በጽሁፍ
ለፌዴሬሽኑ
ቢያቀርብም
ወደጎን
የተተውበት
መሆኑንም
የሚጠቁሙት።
የውድድር
ዓመቱ
ከተጠናቀቀ
በኋላም
ውድድሩ
ፍትሃዊነት
ይጎድለዋል
በሚል
በተደጋጋሚ
ደብዳቤ
ቢያስገባም
ምላሽ
አልተሰጠውም።
ይህም
ክለቡ
ከፕሪምየር
ሊግ
መውረድ
አለመውረዳቸውን
የሚጠቁም
ባለመሆኑ
ክረምቱን
ለሊግ
መደረግ
ባለበት
ደረጃ
በዝግጅት
ላይ
ቆይቷል።
ከሰሞኑ ሶከር
ኢትዮጵያ
በሰራው
ዘገባም
በአዲሱ
የውድድር
ዓመት
ፕሪምየር
ሊጉ
በ24
ክለቦች
እንደሚቀጥልና
ዝግጅታቸውንም
በዚህ
መንገድ
እንዲቀጥሉ
ፌዴሬሽኑ
በደብዳቤ
ማሳወቁን
አስነብቧል።
ነገር
ግን
ሊጉ
በቀደመው
መልኩ
በ16
ክለቦች
መካከል
ይቀጥላል
መባሉን
በመረጃ
ደረጃ
እንጂ
ከፌዴሬሽኑ
በህጋዊ
መንገድ
የደረሰው
ነገር
አለመኖሩን
የክለቡ
ፕሬዚዳንት
ኮሎኔል
ደረጃ
መንግስቱ
ገልጸዋል።
ክለቡ
የተጫዋቾችን
ውል
በፕሪምየር
ሊጉ
መሰረት
እያጸደቀ
ሲሆን፤
ተለዋጭ
ሃሳብ
የሚመጣ
ከሆነ
ግን
ክለቡ
የራሱን
እርምጃ
እንደሚወስድና
አቋሙንም
ከፌዴሬሽኑ
ይፋዊ
ደብዳቤ
ሲደርሰው
የሚያሳውቅ
መሆኑን
በዘገባው
ተመልክቷል።
ብርሃን ፈይሳ አዲስ ዘመን መስከረም
25/2012 | https://www.press.et/Ama/?p=20095 | 536 | 2ስፖርት
|
በቻምፒዮናው ፍፃሜ የሚጠበቁ ሜዳሊያዎች | ስፖርት | October 6, 2019 | 9 | አትሌቶች አቅማቸውን የሚፈታትሹበት፣ አገራትም በአትሌቲክስ ስፖርት ያሉበትን ደረጃ የሚገመግሙበት እንዲሁም አዘጋጅ አገር የሆነችው ኳታር ለቀጣዩ የዓለም ዋንጫ ጭምር ያላትን አቅም የምታስመሰክርበት የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ዛሬ ይጠናቀቃል። የዓለም ምርጥ እና ብቃት ያላቸው አትሌቶችን የሚያገናኘው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮናን ያስተናገደችው ዶሃ በከሊፋ ስታዲየም በሚደረገው የመዝጊያ ስነ-ስርዓት ተራውን ለቀጣዩ አዘጋጅ ታስረክባለች። ለአስር ቀናት
በሜዳ
ተግባራት
እንዲሁም
በአጭርና
ረጅም
ርቀት
ሲከናወን
የቆየው
ውድድር
በተመልካች
ማነስ
ቢታማም
ዛሬ
ፍጻሜውን
ያገኛል።
በመጨረሻ
ከሚካሄዱት
ውድድሮች
መካከልም
ኢትዮጵያውያን
አትሌቶች
የሚሳተፉባቸው
ሁለት
ርቀቶች
ተጠባቂ
ናቸው።
1ሺ500
ሜትር
የወንዶች
ውድድር
በቅድሚያ
የሚካሄድ
ሲሆን፤
ኢትዮጵያውያን
በድል
የሚታወቁበት
10ሺ
ሜትር
የወንዶች
ውድድር
ይካሄዳል።
በ1ሺ500
ሜትር
ማጣሪያ
ከየምድቡ
ከአንድ
እስከ
ስድስት
የወጡ
በቀጥታ
እንዲሁም
ሌሎች
የተሻለ
ውጤት
ያላቸው
ስድስት
አትሌቶች
ለዛሬው
የፍጻሜ
ውድድር
በቅተዋል።
ኢትዮጵያን
በዚህ
ርቀት
የወከሉት
ሁለቱ
አትሌቶችም
ለማጣሪያው
ማለፋቸው
ታውቋል።
ወጣቱ
አትሌት
ሳሙኤል
ተፈራ
በተካፈለበት
ምድብ
3፡37.82
በሆነ
ሰዓት
ሰባተኛ
ሆኖ
ነው
ያጠናቀቀው።
አትሌቱ
በተያዘው
የፈረንጆቹ
ዓመት
የዓለም
የቤት
ውስጥ
ቻምፒዮና
ለረጅም
ጊዜ
በሞሮኳዊው
አትሌት
ተይዞ
የቆየውን
የዓለም
ክብረወሰን
ማሻሻሉ
የሚታወስ
ነው።
ሳሙኤል
ያስመዘገበው
3፡31.04
የሆነው
ይህ
ሰዓት
ደግሞ
የግሉ
ፈጣን
ነው።
በማጣሪያ
ውድድሩ
ተጠልፎ
በመውደቅ
11 ደረጃን
ይዞ
ያጠናቀቀው
አትሌት
ታደሰ
ለሚ፤
በቡድኑ
ቴክኒክ
መሪ
አቶ
ዱቤ
ጂሎ
ቅሬታ
ማቅረባቸውን
ተከትሎ
ወደ
ፍጻሜው
እንዲገባ
ተደርጓል።
አትሌቱ
3፡35.09
የሆነ
ሰዓት
ደግሞ
ከዚህ
ቀደም
ያስመዘገበው
ፈጣን
ነው።
ኢትዮጵያውያኑ
አትሌቶች
በዚህ
ውድድር
ብርቱ
ተፎካካሪ
ከመሆን
ባለፈ
ለአሸናፊነት
የሚያበቃ
ቅድመ
ግምት
አግኝተዋል።
ሌላኛውና ኢትዮጵያ
ተጨማሪ
ሜዳሊያዎችን
ልታገኝ
ትችላለች
በሚል
የሚጠበቀው
የ10ሺ ሜትር ውድድር
በመዝጊያው
የሚደረግ
የረጅም
ርቀት
ውድድር
ነው።
በዚህ
ርቀት
በተለይ
ስኬታማዎቹ
የምስራቅ
አፍሪካ
አትሌቶች
የበላይነቱን
ይወስዳሉ
በሚልም
ይጠበቃሉ።
በዚህ
ውድድር
ልምድ
ያለው
ሐጎስ
ገብረህይወት
በኢትዮጵያውያን
ምድብ
ባለፈጣን
ሰዓት
ሲሆን፤
በሄንግሎ
በተደረገው
የሰዓት
ማሟያ
ላይ
26፡48.95
የሆነ
ውጤት
አስመዝግቧል።
ያለፈውን
ዓመት
ስኬታማ
በሆነ
መልኩ
ያሳለፈው
ወጣቱ
አትሌት
ዮሚፍ
ቀጄልቻ
ደግሞ
26፡49.99
ፈጣን
ሰዓቱ
ነው።
ሌላኛው
አትሌት
አንዱአምላክ
በልሁ
26፡53.15
በሆነ
ሰዓት
ሶስተኛው
ኢትዮጵያን
የሚወክል
አትሌት
ነው።
ከቀናት
በፊት
በ5ሺ ሜትር የብር
ሜዳሊያ
ባለቤት
የነበረው
ሰለሞን
ባረጋ
26፡49.46
የሆነ
ሰዓት
ቢኖረውም
በውድድሩ
ይካፈላል
ተብሎ
አይጠበቅም።
አዲስ ዘመን መስከረም 25/2012ብርሃን ፈይሳ | https://www.press.et/Ama/?p=20098 | 306 | 2ስፖርት
|
የ10ሺ ሜትር ድልና ኢትዮጵያ ለ10 ዓመታት ተለያይተዋል | ስፖርት | October 8, 2019 | 29 | በዓለም አትሌቲክስ ታሪክ አስር ሺ ሜትር ውድድር ለኢትዮጵውያን የተለየ ቦታ አለው። የዓለም ሕዝብም ይህን ርቀት የኢትዮጵያውያን የባህል ስፖርት አድርጎ እስከ መቁጠር ደርሷል። ማርሽ ቀያሪው ምሩፅ ይፍጠር በሞስኮ ኦሊምፒክ በርቀቱ ካስመዘገበው ድል አንስቶ ኃይሌ ገብረሥላሴና ቀነኒሳ በቀለ በኦሊምፒክም ይሁን በዓለም ቻምፒዮና ደጋግመው ድል በማድረግ ኢትዮጵያ የርቀቱ ንጉሥ መሆኗን አስመስክረዋል። ከምሩፅ ይፍጠር በኋላ ኢትዮጵያ በርቀቱ ንጉሥ ለማግኘት በርካታ ዓመታትን መጠበቋ ባይዘነጋም ከኃይሌ ገብረሥላሴ ጀምሮ የመጣው የአትሌቲክስ ትውልድ የርቀቱን የኢትዮጵያ የበላይነት አስጠብቆ ቆይቷል። እ.ኤ.አ 2011 ደቡብ ኮሪያ ዴጉ ካስተናገደችው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ወዲህ ግን ኢትዮጵያውያን ካለፉት ስምንት ዓመታት በላይ የርቀቱን ዙፋን ለሌላ አገር አትሌቶች ለማስረከብ የተገደዱበት ሁኔታ ተፈጥሯል። በዴጉው የዓለም ቻምፒዮና አትሌት ኢብራሒም ጀይላን እንግሊዛዊው ሞ ፋራህን መቼም በማይረሳ ሁኔታ ካሸነፈ ወዲህ ኢትዮጵያ በርቀቱ እንደቀድሞዎቹ ጀግኖች አልሸነፍ ባይና እስከ መጨረሻ ታጋይ አትሌት ለዓለም ማሳየት አልቻለችም። ይህም ሞ ፋራህ በርቀቱ በሦስት የዓለም ቻምፒዮናዎችና በሁለት ኦሊምፒኮች እንዲነግሥ ምክኒያት ሆኖታል። በነዚህ ዓመታት ኢትዮጵያ ትልቅ ተስፋ የጣለችባቸው ወጣትና ባለተሰጥኦ አትሌቶች በብዛት መፈጠር ቢችሉም የፋራህ ተከታይ ሆነው የብርና የነሐስ ሜዳሊያ ከማጥለቅ በዘለለ የርቀቱን ክብር ወደ ቤቱ መመለስ አልተቻላቸውም። ፋራህ ካለፈው የለንደን
የዓለም ቻምፒዮና በኋላ
ከህመም ውድድሮች ራሱን
ማግለሉን ተከትሎ ዓለማችን
በአስር ሺ ሜትር
ውድድር አዲስ ንጉሥ
ስትጠብቅ ቆይታለች። ከለንደን
ቻምፒዮና በፊትና በኋላ
በርቀቱ ትልቅ ተሰጥኦ
ያላቸው ኢትዮጵያውያን ወጣት
አትሌቶች በብዛት መፈጠራቸውን
ተከትሎ አስር ሺ
ሜትር ዳግም የኢትዮጵያውያን
አትሌቶች ዙፋን የመሆኛው
ትክክለኛ ጊዜ እንደደረሰ
በርካቶች ተስፋ አድርገው
ነበር። ከትናንት በስቲያ
በተጠናቀቀው የዶሃው የዓለም
ቻምፒዮናም የትኛው ኢትዮጵያዊ
አትሌት የርቀቱን ዘውድ
እንደሚደፋ በጉጉት ሲጠበቅ
ነበር። ኢትዮጵያ በዚህ
ርቀት ፈጣን ሰዓት
ያላቸው ወጣትና ልምድ
ያካበቱ አትሌቶችን ከማሰለፏም
በላይ በርቀቱ ያላት
ታሪክ ዳግም ወደ
ድል የምትመለስበት ጊዜ
አሁን እንደሆነ ብዙዎች እምነት አሳድረው ነበር። ልምድና ብቃት ከድንቅ የሩጫ ክህሎት ጋር የተላበሰው ሐጎስ ገብረሕይወት፣ ቁመተ መለሎው ባለተሰጥኦ አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ እንዲሁም ጠንካራው አትሌት አንዱዓምላክ በልሁ የርቀቱን ድል የመመለስ ተስፋ የተጣለባቸው አትሌቶች ናቸው። እነዚህ አትሌቶች እንዳላቸው ብቃት ተባብረው የቡድን ሥራ ሠርተው ድሉን ወደ ቤቱ ማምጣት ግን ሳይችሉ ቀርተዋል። ኢትዮጵያም የአስር ሺ ሜትር ድል ከእጇ ከወጣ ይህ አራተኛ የዓለም ቻምፒዮና ሊሆን ችሏል። ለአስር ዓመታት ከእጃችን ለመውጣት የተገደደው የአስር ሺ ሜትር ከዚህ በኋላ ለመመለስ ስንት ዓመት እንደሚፈጅ መገመት አይቻልም። ምክኒያቱም ዶሃ መልካምና የተሻለ አጋጣሚ ነበርና። በርቀቱ ተፎካካሪና ተመሳሳይ ታሪክ ያላት ኬንያም አልተሳካላትም። ያልተጠበቀውና ትኩረት ያልተሰጠው ዩጋንዳዊው አትሌት ጆሹዋ ቺፕቴጌ በዓለም ቻምፒዮና ታሪክ ሁለተኛውን ፈጣን ሰዓት በ26:48.37 አስመዝግቦ ለአገሩ አዲስ ታሪክ ፅፏል። ወጣቱና ወደ ፊት ባይባል እንኳን በቅርቡ ትልቅ ተስፋ እንዳለው ያስመሰከረው ዮሚፍ ቀጄልቻ በርቀቱ ገና ለሁለተኛ ጊዜ ቢወዳደርም 26:49.34 በሆነ ሰዓት የብር ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ ማስመዝገብ ችሏል። ይህም ኢትዮጵያ በቻምፒዮናው በሁለት ወርቅ፣አራት ብርና አንድ ነሐስ ሜዳሊያ ከዓለም አምስተኛ ከአፍሪካ ደግሞ ሁለተኛ ሆና እንድታጠናቅቅ አስችሏታል። ባለፈው መጋቢት በዓለም አገር አቋራጭ ቻምፒዮና በወጣቶች ምድብ ወርቅ ማጥለቅ የቻለው ዩጋንዳዊ ኮከብ ሆኖ ባመሸበት የዓለም ቻምፒዮና የመዝጊያ ውድድር ኬንያዊው ሮኔክስ ኪፕሩቶ 26:50.32 በሆነ ሰዓት የነሐስ ሜዳሊያ ሲያጠልቅ ለድል ሲጠበቅ የነበረው ሐጎስ ገብረሕይወት በ27:11.37 ሰዓት ዘጠነኛ ደረጃን ይዞ መፈፀሙ አስደንጋጭ ነበር። በአንፃሩ የርቀቱን ድል ለመመለስና የቡድን ሥራ ለመሥራት ጥረት ሲያደርግ የነበረው አንዱዓምላክ በልሁ 26:56.71 በሆነ ሰዓት አምስተኛ ደረጃን ይዞ ፈፅሟል።አዲስ ዘመን መስከረም 27/2012 ቦጋለ
አበበ | https://www.press.et/Ama/?p=20279 | 460 | 2ስፖርት
|
«ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ» | ስፖርት | October 6, 2019 | 17 | ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ «ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ» በሚል መርሃ ግብሩ በሚያሰባስበው ገንዘብ ትምህርት ቤት ለማሰራት ማቀዱን አስታወቀ። ትምህርት ቤቱ በዳስ ትምህርት በሚሰጥበት አካባቢ የሚገነባም ይሆናል። በህዳር ወር
የሚካሄደው
ዓመታዊው
ታላቁ
ሩጫ
በኢትዮጵያ
ብዙዎችን
ከሚያሳትፍበት
የሩጫ
መርሃ
ግብር
ጎን
ለጎን
«ሌሎችን
ለመርዳት
እሮጣለሁ»
በሚል
የእርዳታ
ማሰባሰቢያ
ስራ
ያከናውናል።
ዘንድሮም
ከሩጫው
ተሳታፊዎች
መካከል
ለበጎ
አድራጎት
የሚውሉ
ቦታዎች
የተዘጋጁ
ሲሆን፤
በዚህም
1ነጥብ
9 ሚሊዮን
ብር
ለማሰባሰብ
ታቅዷል።
ገንዘቡም
ታዳጊዎች
በዳስ
በሚማሩበት
በዋግህምራ
ዞን
ትምህርት
ቤት
ለማስገንባት
የሚውል
ይሆናል።
የመነሻ
ሃሳቡም
ሻለቃ
ኃይሌ
ገብረስላሴ
በቅርቡ
በአካባቢው
አንድ
ትምህርት
ቤት
ማሰራቱን
ተከትሎ
የተነሳ
መሆኑም
ጋዜጣዊ
መግለጫው
በተሰጠበት
ወቅት
ተጠቁሟል።
ታላቁ ሩጫ
በኢትዮጵያ
ከ1998
ዓ.ም ጀምሮ ከሩጫው
በተጓዳኝ
የእርዳታ
ማሰባሰቢያዎችን
የሚያካሂድ
መሆኑ
ይታወቃል።
በዚህም
ባለፉት
13ዓመታት
ከ13ነጥብ5 ሚሊዮን ብር በላይ በማሰባሰብ ሰላሳ ለሚሆኑ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ሲያከፋፍል ቆይቷል። ከእዚህ መካከል ዘጠኝ ሚሊዮን የሚሆነው ገንዘብ ባለፉት ስድስት ዓመታት ብቻ የተሰባሰበ ነው። በዚህ የበጎ አድራጎት ሩጫ ላይ መካፈል የሚፈልግ ሰውም ቲሸርቱን በ600 ብር በአሞሌ
የመገበያያ
ቴክኖሎጂ
ወይም
ከዳሸን
ባንክ
መግዛት
ይችላል።
ውድድሩ
ከመካሄዱ
ከአንድ
ሳምንት
ቀደም
ብሎም
በአዲስ
አበባ
ኤግዚቢሽን
ማዕከል
የታላቁ
ሩጫ
ኤክስፖ
ላይ
ማግኘት
ይቻላል።
በቅርቡ የዓለም
ምርጡ
የሩጫ
ውድድር
የሚል
እውቅና
ያገኘው
ታላቁ
ሩጫ
በኢትዮጵያ
ዘንድሮ
ህዳር
ሰባት
የሚካሄድ
ይሆናል።
45ሺ
ሰዎችን
የሚያሳትፈው
ሩጫው
ባለፈው
ሰኔ
ወር
2011ዓም
በተጀመረው
ምዝገባ
42ሺ
ሰዎች
ተመዝግበዋል።
ከአዋቂዎች
ውድድር
ባሻገር
ህጻናት
በስፖርታዊ
እንቅስቃሴ
ተሳታፊ
እንዲሆኑ
የሚያግዘው
የህጻናት
የሩጫ
ውድድር
በዋዜማው
በ3ሺ500 ልጆች መካከል
ይደረጋል።
«ሴቶች
ልጆች
በእኩል
ሚዛን
መታየት፤
መደመጥና
ተቀባይነት
ሊኖራቸው
ይገባል»
በሚል
መሪ
ሃሳብ
የሚደረግም
ይሆናል።
አዲስ ዘመን መስከረም 25/2012ብርሃን ፈይሳ | https://www.press.et/Ama/?p=20100 | 233 | 2ስፖርት
|
‹‹ኅብረተሰቡ ከጸጥታ ኃይሎች ጋር ትብብሩን ካጠናከረ የኦነግ ሸኔ መጥፊያው ሰዓት አጭር ይሆናል›› – ኮሚሽነር ጀኔራል አራርሳ መርዳሳ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር | ሀገር አቀፍ ዜና | December 11, 2020 | 4 | አስቴር ኤልያስአዲስ አበባ፡- በኦሮሚያ ክልል የሚገኘው የኅብረተሰብ ክፍል ከክልሉ ጸጥታ ኃይል ጋር የመስራት ትብብሩን አጠናክሮ ከቀጠለ በክልሉ እየተንቀሳቀሰ ሽብር የሚፈጥረው ኦነግ ሸኔ መጥፊያው ሰዓት አጭር እንደሚሆን የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀኔራል አራርሳ መርዳሳ ገለጹ። ኮሚሽነር ጀኔራል አራርሳ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳስታወቁት፤ እንደ ኦነግ ሸኔ ያሉ አሸባሪ ኃይሎች በጂ.ፒ.ኤስ በሚወሰድ ርምጃ ብቻ ሙሉ ለሙሉ ለማስወገድ የሚያስችል ለውጥ ይመጣል ተብሎ የሚጠበቅ አይደለም። ትልቁ ነገር እነዚህን ኃይሎች የማስወገድ እና ዕድሜያቸውን የማሳጠር ሥራ ነው። ይህ ደግሞ በዋናነት ስኬታማ የሚሆነው የየኅብረተሰቡ ተሳትፎ ሲታከልበት ነው። ኅብረተሰቡ ከክልሉ ጸጥታ ኃይል ጋር በመሆን የጀመረውን ትብብር አጠናክሮ የሚቀጥል ከሆነ ሽብር ፈጣሪው ኦነግ ሸኔ መጥፊያው ሰዓት አጭር ይሆናል። የኅብረተሰቡ አንዱ ሥራ እነዚህን ቡድኖች የጥፋት ኃይሎች መሆናቸውን ተገንዝቦ ሴረኞቹን የማጋለጥ ሥራ መስራት ነው ያሉት ኮሚሽነር ጀኔራል አራርሳ፣ ሁለተኛው ደግሞ ኅብረተሰቡ ራሱ ተደራጅቶ እነዚህን ኃይሎች የመመከት ሥራ ማከናወን መሆኑን ተናግረዋል። ኅብረተሰቡ በእነዚህ ሥራዎች ከጸጥታ ኃይሎች ጋር ተባብሮና አብሮ ርምጃ በመውሰዱ ላይ ከተሳተፈ የኦነግ ሸኔ ዕድሜ እንደሚያጥር አመልክተዋል። እንደ ኮሚሽነር ጀኔራል አራርሳ ገለጻ፤ ኅብረተሰቡ በዚህ ሥራው ያለማቅማማት ከተባበረ ኦነግ ሸኔ ሊወገድ ይችላል። በአሁኑ ወቅት ኅብረተሰቡ የጀመረው እንቅስቃሴ አበረታች ነው። ካለውም የጸጥታ ኃይል ጋር ያለውም ትብብር ጥሩ የሚባል ነውና ይህ እገዛው በዚሁ ከቀጠለ ኦነግ ሸኔን የማስወገድ ሥራ መስራት ብዙም የሚከብድ አይደለም። አሁን የጀመርነው ርምጃ የመውሰዱን ሥራ ሕዝቡ በሎጂስቲክ እንዲሁም እውነታውን በመናገሩ በኩል ከሰራ የተሻለ ውጤት ይኖራል ያሉት ኮሚሽነር ጀኔራሉ፣ ጸረሰላም ኃይሉ ኦነግ ሸኔ ከኅብረተሰቡ የሚያገኘው ድጋፍ ሙሉ ለሙሉ የሚቋረጥ ይሆናልና ከዚህ በኋላ ብዙ እንደማይቆይ አስረድተዋል። ስለሆነም ኅብረተሰቡ አሁን የጀመረውን ትብብርና ለሰላም መስፈን እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቀርባለሁ ብለዋል። የኦሮሞ ብሔርም ይሁን በክልሉ የሚኖሩ ብሔር ብሔረሰቦች በትብብር በመሆን ለማንምና ለምንም የማይበጁትን ጸረ ሰላም ኃይሎች ለማስወገድ በቅንጅት እና በጋራ መስራት እንደሚጠበቅባቸውም ገልጸዋል። ስለዚህም ማህበረሰቡ የማጋለጡን ሥራ ያለምንም ርህራሄ አጠናክሮ እንዲቀጥል እና ከጸጥታ ኃይሉ ጋርም በመሆን ተባብሮ እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ
2/2013 | https://www.press.et/Ama/?p=37098 | 283 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
በትምህርት ቤቶች በኮቪድ 19 ዙሪያ እየተደረጉ ያሉ ጥንቃቄዎች | ሀገር አቀፍ ዜና | December 10, 2020 | 14 | ሞገስ ተስፋ ጭር ብለው ለስምንት ወራት የቆዩት ትምህርት ቤቶች ውበትን ተላብሰዋል፡፡ ከአምስተኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች ትምህርት ተጀምሯል፡፡ እኛም በሁለት ትምህርት ቤቶች ቅኝት አድርገናል፡፡ አፄ ናኦድ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ስንዘልቅ ገና ከበሩ የሙቀት መከሊያ፣ የእጅ ንፅሀና መጠበቂያና ሳኒታይዘር በተገቢው ቦታ ላይ ተቀምጠዋል፡፡ ተማሪዎች የአፍና የአፍንጫ ጭንብላቸውን አድርገው ዕውቀት ወደሚገበዩበት ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ይገባሉ፡፡ መምህራን ነጭ ጋዋናቸውን አድርገው የቀለም ልጆቻቸውን በዕውቀት፣ በክህሎትና በአመለካከት ለመቅረፅ ዝግጅታቸውን አጠናቀው አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሳቸውን ይዘው እያስተማሩ ነው፡፡ እኛም ይህንኑ ሁነት የስድስተኛ ክፍል ተማሪዎች ወደሚማሩበት ክፍል ዘልቀን ተመልክተናል፡፡ ተማሪ አማኑኤል ማሬ የስድስተኛ ክፍል ተማሪ ነው። የ2013 ዓመተ ምህረት ትምህርት መጀመሩን በጉጉት ሲጠብቅ እንደነበረ ገልፆልናል፡፡ ተማሪ አማኑኤል እንደሚለው ለሥምንት ወራት ከትምህርት ገበታ ርቆ በመቆየቱ ከፍተኛ ተፅዕኖ አሳድሮብኝ ነበር፣ አሁን ላይ ሁሉም ተማሪ የትምህርትን መጀመር በጉጉት ሲጠብቀው ስለነበር ዕውቀት ወደምንገበይበት ቤት መመለሳችን በጣም ደስታ ተሰምቶናል ይላል፡፡ ወደትምህርት ቤት ሲገቡ የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል የሚያስችሉ ማለትም የአፍና የአፍንጫ ጭንብል በማድረግ እጅን በመታጠብ ወደ መማሪያ ክፍላቸው ከገቡ በኋላም እያንዳንዱ ተማሪ ሳኒታይዘረት እና አልኮል እንደሚጠቀሙ አማኑኤል ይናገራል፡፡ ተማሪዎች እንዳይዘናጉ በትምህርት ቤቱ ሚኒ ሚዲያ አማካኝነት የተለያዩ መልዕክቶችን በማዘጋጀት ሁሉም በንቃት ራሱን ከቫይረሱ እንዲጠብቅ ከሰልፍ ሥነ ሥርዓት ጀምሮ በእረፍትና ምሳ ሰዓት እንደሚተላለፉ የገለፀልን ተማሪ አማኑኤል አስተማሪዎቻቸው የሚሰጧቸውን መመሪዎች በመቀበል ራሳቸውን ከኮሮና ቫይረስ በመከላከል ትምህርታቸውን በአግባቡ እየተከታተሉ እንደሆነ እኛም ክፍል ውስጥ በመዘለቅ ታዝበናል፡፡የአፄ ናኦድ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህርት የሆኑት ወይዘሮ ፀሐይ ካሳ እንደገለፁልን፣ የትምህርት አጀማመራቸው ቀድመው የትምህርት ቤቱን ግቢ ለተማሪዎች ምቹና ተስማሚ እንዲሆን የግቢ ማስዋብ ሥራ ሰርተዋል፡፡ ከዚያም ለኮሮና ቫይረስ መከላከል አስፈላጊ የሆኑ የእጅ ማስታጠቢያ እስከ መፀዳጃ ቤት ደረጃቸውን የጠበቁ በማድረግ ዝግጅት እንዳደረጉ ይገልፃሉ፡፡ ይህ ሲሆን ሳሙና፣ ሳኒታይዘርና አልኮል ምቹ በሆኑ ቦታዎች በማስቀመጥ ሲሆን ተማሪዎችም ሳይዘናጉ ራሳቸውን እንዲጠብቁ ሁሉም መምህራን በኃላፊነት ስሜት እየሰሩ ነው ሲሉ ገልፀውልናል፡፡ እንደ ርዕሰ መምህሯ ገለፃ፣ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ለሥምንት ወራት ርቀው ስለቆዩ ወደትምህርት ቤት በሚመጡበት ወቅት አምሯቸው ብሩህና ንቁ ሆነው እንዲማሩ ለማድረግ ሰፊ ቅድመ ዝግጅት አድርገው ስለተቀበልናቸው ለትምህርታቸው የሰጡት ትኩረት ከፍተኛ ነው፡፡ ከወረዳ ስድስት ጤና ጽሕፈት ቤት ጋር በጋራ በመሆን የጤና ባለሙያዎች ተመድበው ሙቀት በመለካት ለተማሪዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ሰፊ ሥራ እየተሰራ መሆኑን ነግረውናል። ወደ ትምህርት ያልተመለሱ ተማሪዎችን በመለየት እና ወደወላጆቻቸው በመደወል ትምህርት እንዲጀምሩ ለማስቻል የሚረዱ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው። ለዚህም ማህበራዊ ድረ ገጾችን ጭምር እየተጠቀሙ ነው፡፡በተመሳሳይ መልኩ በምኒልክ ሁለተኛና መሰናዶ ትምህርት ቤት ተገኝተን በትምህርት ቤቱ ያለውን እውነታ ለመታዘብ ችለናል። ሳሙኤል መንግሥቱ የ11ኛ ክፍል ተማሪ ነው። ‹‹ትምህርት በመጀመሩ ደስተኛ ነኝ፤ ምክንያቱም ለሥምንት ወራት ከትምህርት ገበታችን ስላራቀን አላስፈላጊ ቦታ እንድንውል በማድረግ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድሮብን ነበር፡፡ ስለሆነም አሁን ላይ ትምህርታችን በፈረቃም ቢሆን መጀመራችን ትልቅ እፎይታን ሰጥቶናል›› ሲል ስሜቱን አጋርቶናል፡፡ በምኒልክ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር የሆኑት አቶ ሲሳይ አለሙ በበኩላቸው፣ የመማር ማስተማሩ ሂደት ከሁለት ቀናት በፊት ከዘጠነኛ እስከ 12ኛ ክፍል የሚገኙ ተማሪዎችን ተቀብለው ጀምረዋል። ኮሮናን ለመከላከል ሲባል 12ኛ ክፍል በአንድ ክፍል 24 ተማሪዎች በ24 ወንበር ምደባ በ44 ክፍል ተደልድለው በአንድ ፈረቃ ሰኞ፣ ረቡዕና አርብ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ነው፡፡ በሁለተኛው ፈረቃ ደግሞ ዘጠነኛ፣ አስረኛና አስራ አንደኛ ክፍል ተማሪዎች ተደልድለው ትምህርት ጀምረዋል፤ የክፍል ጥምርታውም በክፍል 24 ሲሆን በ46 ክፍሎች ማክሰኞ፣ ሐሙስና ቅዳሜ ጥንቃቄ በተሞላበት ማስተማር መጀመራቸውን ገልፀዋል፡፡ በትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ተገኝተን ባደረግነው ምልከታ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚረዱ የእጅ ማስታጠቢያ ገንዳ፣ ሳሙና፣ ሳኒታይዘርና የመሳሰሉት ቁሳቁሶች ለአጠቃቀም ምቹ በሆነ ቦታ ተቀምጠዋል፡፡ በተጨማሪም ሁሉም ተማሪ በርቀት ሆኖ ስለቫይረሱ መተላለፊያ መንገዶችና ሊወስዱት ስለሚገባቸው ጥንቃቄ የሚያስገነዝቡ መልዕክት የያዙ ማስታወቂያዎች መኖራቸው ተገቢ መሆኑን ታዝበናል፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 1/2013 | https://www.press.et/Ama/?p=37051 | 509 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ወታደሮችን በሲኖ ትራክ እስከመጨፍለቅ የዘለቀው የጁንታው የክፋት ጥግ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 11, 2020 | 11 | ኢያሱ መሰለሃምሳ አለቃ ደረጀ አንበሳ በመከላከያ ሰራዊት የሰሜን ዕዝ የጥገና ባለሙያ ናቸው። በሙያቸው አገራቸውን ሌት ተቀን ከማገልገላቸውም በላይ እንደማንኛውም የመከላከያ አባል ለትግራይ ሕዝብ በችግሩ ጊዜ ከጎኑ በመቆም አጋርነታቸውን ሲገልጹ ኖረዋል። የሕዝብና የአገር ከለላና መከታ የሆነው የኢፌዴሪ መከላከያ አባል እንደመሆናቸው አንድም ቀን በአገር ልጅ የባንዳነት ተግባር ይፈጸምብኛል ብለው አስበውም አያውቁም። ይሁንና በእናት ጡት ነካሾች ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ከምሽቱ አራት ሰዓት ያልታሰበ ጥቃት ተፈጸመባቸውና ያለምንም ጥፋታቸው ተይዘው ለእስር መዳረጋቸውንና ቀላሚኖ እስርቤት መታሰራቸውን ይገልጻሉ። «ከቀላሚኖ እስር ቤት ወደ አግቤ በመቀጠልም ከትንሽ ቀን በኋላ ወደ ተንቤን መምህራን ኮሌጅ ወሰዱን። የመከላከያ ሠራዊትን የከባድ መሳሪያ ድምፅ ሲሰሙ የ90 ኪሎ ሜትር የእግር ጉዞ አስጀመሩን። ልክ 40 ኪሎ ሜትር እንደተጓዝን ከምሽቱ 2 ሰዓት አካባቢ ሲኖ ትራክ መኪና ከኋላችን መጣ። ተጓዡ ወደ 1,200 ሰው ነበር። ከአስፋልት እንድንወጣ ካለመፈቀዱም በላይ ከአስፋልቱ መሀል ከወጣን ልዩ ኃይል ተኩሶ ይመታን ነበር። ከግራና ከቀኝ ገደላማ የሆነ ጠባብ ቦታ ላይ ስንደርስ ሲኖ ትራክ መኪና ልከው ከኋላችን ነዱብንና የሚገድለውን እየገደለ፣ ያቆሰለውን እያቆሰለ ሄደብን። እኔንም አንድ እግሬን አገኘኝና እግሬ ከተሰበረ በኋላ ተንከባልዬ ጉድጓድ ውስጥ ገባሁ። እዚያው ጉድጓዱ ውስጥ ከተጎዱ ጓደኞቼ ጋር ተኝቼ አደርኩ። ሲኖ ትራኩ ቢያንስ እስከ 50 ሜትር የተጓዘው በሰዎች ላይ ነበር። በዚህም ግማሹ ሞተ፣ ግማሹ ቆሰለ የቀረውም ወደገደል ገባ። እንግዲህ የራሳችን ወገን ነው እንዲህ ዓይነት በደል የፈፀመብን። ይህ ደግሞ በጣም የሚያሳዝን ድርጊት ነው። ስንት ዓመት ሙሉ አብረናቸው ኖረን በመኪና ሲጨፈልቁን በጣም ነው የተሰማኝ፤ በጥይት ቢገድሉኝ ይሻል ነበር» ይላል:: በወቅቱ ሴቶችም ሕፃናትም አብረውን ነበሩ ማን እንደሞተ ማን እንደተረፈ አንኳን አላውቅም ያለው ወታደሩ «በወቅቱ በሕይወት የተረፉትም ተበታተኑ፤ አንዳንዶቹም ቆስለው ወደጫካው ገቡ፤ የሞቱትም እዚያው ቀሩ አምስት የምንሆን ሰዎች እዚያው አድረን ከሞቱት ሰዎች መሀል በሕይወት ወጣን። የሞቱ ልጆችን እንኳን ለመለየት አልቻልኩም፤አጠገቤ ነው እየጮሁ የሞቱት፤ ምንም ልረዳቸው አልቻልኩም። በወቅቱ እኔም በሁለት እግሬ መቆም አልችልም ነበርና በጉልበቴ ዳዴ እያልኩ ነው የወጣሁት» ሲል የወቅቱን አሳዛኝ ሁኔታ ይገልፃል:: «እኛኮ ከሌሊቱ 11 ሰዓት እየተነሳን አጨዳ የምናጭድ፤ ኮሮና ገባ ሲባል ብር እያዋጣን የምንደግፍና ከደመወዛችን እየቆረጥን የልማት ሥራዎችን የምንሰራ ነን። እኛ ለትግራይ ሕዝብ ልማት ወደኋላ ብለን አናውቅም። ይሁንና ጁንታውና የእሱ ተላላኪዎች በሰው ላይ የማይፈፀም ድርጊት ነው የፈፀሙብን። ሰብስበው በቦምብ ቢያቃጥሉን ወይም በጥይት ቢገድሉን ይሻል ነበር። የውጭ ጠላት እንኳን በመኪና ሰውን ደፍጥጦ አይገድልም። ድርጊቱ ከተፈፀመብን በኋላ በመኪና መንገድ ላይ ስንሄድ እየተሸማቀቅን ነው። ጭንቅላታችን ራሱ ተጎድቷል::» ሌላው ተመሳሳይ ድርጊት የተፈፀመበት አምሣ አለቃ ወንድማገኝ ወልደገብርኤል ነው። እሱ እንደሚገልፀው በልዩ ኃይል እና በሚሊሻ ታጅበን በእግር እየተጓዝን ሳለ ከአስፓልቱ እንዳትወጡ አሉን እኛም ፈንጂ ያለ መስሎን የአስፋልቱን መሀል ይዘን መጓዝ ጀመርን። ጨለምለም ሲል ከኋላችን ሲኖትራክ መኪና መጣ፤ ከፊት ለፊት ተኩስ ተከፈተብን፤ እንዳንመታ ብለን ሁላችንም ተኛን፤ በዚህ ወቅት ሲኖ ትራኩ እየጨፈለቀን ሄደ። ግማሹ እየተንከባለለ ወደገደል ገባ፤ ተገጭተን የተረፍነው በማግስቱ ተነሳን፤ ብዙዎች ግን በሚያሳዝን ሁኔታ ሞቱ፤ አንዳንዶቹም ቆሰሉ፤ አሽከርካሪው ለመትረፍ የሚሞክሩ ሰዎችንም ዚግዛግ እየነዳ ነበር ሲጨፈልቃቸው የነበረው። በእግራችን መሄድ አቅቶን ጅብ ይብላን ብለን እዚያው ከተኛን በኋላ ታፍነው በመከላከያ ሰራዊት እርዳታ የተለቀቁ እስረኞች እየረዱን የተወሰነ ርቀት ከተጓዝን በኋላ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ደርሰው ወደዚህ አመጡን። ሲሉ የደረሰባቸውን ግፍ አስረድተዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ
2/2013 | https://www.press.et/Ama/?p=37097 | 446 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የጁንታው ግፍ የማንነት ጥያቄ ባነሱ ዜጎች አንደበት | ሀገር አቀፍ ዜና | December 11, 2020 | 17 | ኢያሱ መሰለ ወጣት
ሞገስ
ዳርጌ
የራያ
አላማጣ
ተወላጅ
ሲሆን
የማንነት
ጥያቄ
በማንሳቱ
ብቻ
ከሥራ
ቦታው
ታፍኖ
በማይጨው
ገጠራማ
አካባቢ
በሚገኝ
ዋሻ
ውስጥ
ለሦስት
ወር
ከቆየ
በኋላ
ወደ
መቀሌ
እስር
ቤት
መዛወሩን
ይናገራል።
በማይጨው
ቆይታው
የደረሰበትን
አካላዊና
ሞራላዊ
ጥቃት
እንዲህ
ያስረዳል። በእስር ቤቱ ውስጥ እጅና እግሬ ታስሮ ነው የተወረወርኩት፤ በተለይ እግሬ የታሰረበት እስከ አሁን ምልክቱ አለ፤ ቀንና ሌሊቱን አላውቀውም፤ አንዳንዴ ከዋሻው እያወጡ አንድ ትልቅ የወይራ ዛፍ ላይ አስረው ያሰቃዩኛል፤ ሲፈልጉ ሽንታቸውን ይሸኑብኛል፤ ስለራያ ማንነት የሚከራከሩ ሰዎችን ጠቁመን ይሉኛል፤ እነርሱ ሊያስሯቸው በሚፈልጉ ሰዎች ላይ መስክር ይሉኛል፤ ከመሰከርክባቸው ሃምሳ ሺ ብር እና ቦታ እንሰጥሃለንም ይሉኝ ነበር። እነዚህ ሰዎች ያልሰሩኝ ሥራ የለም፤ አሪዎስ እንኳን እንደነሱ የክፋት ሥራ አልሰራም። በምድር ላይ ያለውን የክፋት ሥራ ሁሉ በእኔ ላይ ፈጽመዋል፤ ያልደረሰብኝ ነገር የለም፤ ሽንት ቤት ውስጥ አስረውኛል፤ ሲፈልጋቸው አንገቴ ላይ ሰንሰለት አስገብተው ዛፍ ላይ አስረው ወደ ላይ ይጎትቱኝና ልሞት ስል ይለቁኛል፤ እንደገና ደግሞ አስረው ይጎትቱኛል፤ ጉድጓድ ቆፍር ይሉኛል፤ መቆፈር ሲያቅተኝ ይመቱኛል፤ ይሰድቡኛል፤ እስከ አንገቴ ድረስ በቁመቴ ልክ ጉድጓድ ውስጥ ቀብረውኝ እንገድልሃለንም ይሉኛል። ይህ አልበቃ ብሏቸው ማይጨው ማረሚያ ቤት ወሰዱኝ፤ ቀጥለውም መቀሌ ማረሚያ ቤት አስገቡኝ፤ በኋላም መንግሥት ሕግ የማስከበር ርምጃ ሲወስድና መቀሌ አቅራቢያ ሲደርስ ወደ ተንቤን ወሰዱን፤ በዚህ ወቅት ምግብም ውሃም አልነበረም። አንድ ጊዜ አንድ እንጀራ ለአራት ከሰጡን በኋላ እስከ ሁለት ቀን ሳንበላ እንቆያለን፤ መከላከያ ሰራዊቱ አሁንም ተንቤን ሲደርስ ሊረሽኑን አሰቡ። ጌታቸው ረዳ፣ አለም ገብረዋህድ እና የክልሉ የጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ተክኤ ምትኩ በወልቃይት፣ በራያ፣ በትግራይ ደምሒት አባላት ላይ ሞት ፈርደውብን ሄዱ። ከዚህ በኋላ ስልሳ ሰዎች ተመርጠን፤ የሁለት ሰዎች እጅ አንድ ላይ እየታሰረ ወደ በረሃ ተወሰድን። ከዚያም አንድ ሸጥ ውስጥ አስገብተውን ካስቀመጡን በኋላ ውሳኔ የተላለፈበት ወረቀት እንዲመጣ ሰዎችን ላኩ፤ በወቅቱ የአላማጣ ተወላጅ የሆኑና የታጣቂ ቡድኑ አባል የነበሩ የማውቃቸው ሰዎች ነበሩ። እነዚህ ሰዎች አመራር ስለነበሩ በዚህ ባለቀ ሰዓት ለምን ይገደላሉ ብለው ሲከራከሩ ነበር። ግድያው የዘገየውም በዚሁ ምክንያት ይመስለኛል። ይሁንና የውሳኔ ወረቀቱን እንዲያመጡ የተላኩ ሰዎች ወረቀቱን ይዘው ሲመለሱ በመከላከያ ሰራዊት ተያዙ። ያገቱን ታጣቂዎችም መከበባቸውን ሲያውቁ ትተውን ሸሹ። ሌላው የጁንታውን እኩይ ተግባር ከደረሰበት አንጻር የሚያስረዳው፣ አቶ ጥጋቤ እሸቴ፤ የወልቃይት ጠገዴ ሳንጃ ወረዳ ነዋሪ ሲሆን፤ ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት ነው። የማንነት ጥያቄ ከሚያቀርቡ የወልቃይት ተወላጆች አንዱ በመሆኑም በ1998 ዓ.ም በህወሓት ጁንታ ታጣቂዎች ተይዞ መቀሌ ከተማ መታሰሩን ይናራል። ከዚያም ወደ ማይጨው እስር ቤት ተዛወረ። ከማይጨው እንደገና ወደ መቀሌ ማረሚያ ቤት ተወስዶ እያለ የጁንታው ታጣቂዎች በመከላከያ ሰራዊት ላይ የፈጸሙትን ጥቃት ተከትሎ መንግሥት ሕግ የማስከበር ርምጃ ሲወስድ የጁንታው ታጣቂዎች መቀሌ ማረሚያ ቤት ያሉትንና በፖለቲካ ጉዳይ የሚፈልጓቸውን እስረኞች ወደ ተንቤን ይዘዋቸው እንደሸሹ ይናገራል። ከአስራ አምስት ዓመት የአፈና ቆይታ በኋላ በመከላከያ ሰራዊት አማካኝነት ነፃ የወጣው አቶ ጥጋቤ፣ የእስር ቤት ቆይታውን እንዲህ ያስረዳል። በእስር ቤት ውስጥ የደረሰብኝ አሰቃቂ በደል መቼም ከህሊናዬ አይጠፋም፤ እንዳልሞት ብቻ ትንሽ ምግብ ይሠጡኛል፤ አንገቴን ያንቁኛል፤ ልሞት ስል ይለቁኛል፤ ይገርፉኛል፤ እስከ አንገቴ ድረስ አፈር ውስጥ ቀብረውኝ ሳንገድልህ የምንጠይቅህን ንገረን ይሉኛል፤ ያሰቃዩኛል ይሰድቡኛል። አንዳንድ ጓደኞቻችንን ማታ ወስደው ባዶ ቤት ውስጥ ካስገቧቸው በኋላ ጧት ራሳቸውን አንቀው ገደሉ እያሉ አስክሬናቸውን ያሳዩናል። ብዙ ሰዎችን እንዲህ እያደረጉ ገድለዋቸዋል። በመጨረሻም የመከላከያ ሰራዊት ጥቃት ሲበረታባቸው ደርግ በዚህ በኩል እየመጣባችሁ ስለሆነ በዚህ በኩል ሂዱ ብለው መንገድ አመላከቱን። እኛ ግን እነርሱ ያሳዩንን መንገድ ትተን በተቃራኒው ሄድን። በመኪና ተገጭተውና ገደል ተወርውረው እግራቸውና ጭንቅላታቸው የቆሰሉ አስራ አንድ ሰዎችንም አገኘን። እነርሱን ተራ በተራ እየተሸከምን ወደ ኋላ ስናፈገፍግ መከላከያ ሰራዊቱ ከሞት አፋፍ አትርፎን ወደ መቀሌ ይዞን መጣ፤ ብለዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ
2/2013 | https://www.press.et/Ama/?p=37101 | 502 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
«ጁንታው ከአፈጣጠሩ ጀምሮ ዴሞክራሲያዊ አልነበረም» -አቶ ቶሎሳ ተስፋዬ የኦሮሞ ብሔራዊ ኮንግረስ ፓርቲ ሊቀመንበርና በፌዴራሊስት ኃይሎች የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 11, 2020 | 3 | ዳግማዊት ግርማአዲስ አበባ፡- የህወሓት ጁንታ ከአፈጣጠሩ ጀምሮ ዴሞክራሲያዊ ያልነበረ፤ ዴሞክራሲን የማያውቅ መሆኑን የኦሮሞ ብሔራዊ ኮንግረስ ፓርቲ ሊቀመንበርና በፌዴራሊስት ኃይሎች የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ቶሎሳ ተስፋዬ ገለጹ። አቶ ቶሎሳ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቁት፣ የህወሓት ጁንታ ከመጀመሪያውኑ በአገሪቱ ዴሞክራሲ እንዲሰፍን ዝግጅት፣ ዓላማ እና ፍላጎት አልነበረውም። በባህሪውም የዴሞክራሲያዊ እሴቶች አይታይበትም ነበር። ቡድኑ ጠመንጃ አንግቦ ጫካ እንደገባ ሁሉ ወደ ሥልጣን ከመጣ ወዲህም እንደ መፈክር ይዞት የመጣውን የዴሞክራሲ ሥርዓት ወደ ጎን በመተው ሕግና ሕገ መንግሥቱን በመጨፍለቅ ስለዴሞክራሲ የሚያቀነቅኑ ቡድኖችን ሆነ ግለሰቦች በማፈን፣ ከአገር እንዲሰደዱ በማድረግ እንዲሁም በመግደል በጫካ አስተሳሰቡ አምባገነናዊ ሥርዓት እንዲሰፍን ማድረጉን አስታውቀዋል። ጁንታው በ1983 ዓ.ም አምባገነኑን የደርግ ሥርዓት ገርስሶ በትረ ሥልጣኑን በጨበጠበት የመጀመሪያ ሰሞን ላይ መልካም አስተዳደር እገነባለሁ፣ ዴሞክራሲ አሰፍናለሁ፣ ሕዝባዊ መንግሥትን እመሰርታለሁ ብሎ ሲምልና ሲገዘት እንደነበር አስታውሰው፤ በሥልጣን ዘመኑ በተጨባጭ ቃሉን ማክበር እንዳልቻለ አመልክተዋል። በሚፈለገው ደረጃ ዴሞክራሲያዊ ባይሆንም በ1987 ዓ.ም ሕገመንግሥት መርቀቁና ተግባራዊ መደረጉ፣ የፌዴራል አደረጃጀቶች፣ የክልሎች የራስ አስተዳደር አስተዳደሮች መመስረታቸውን የጠቆሙት አቶ ቶሎሳ፣ በወቅቱ ከደርግ አምባገነናዊ ሥርሥት የተሻለ የሚመስል ጭላንጭል ጅምሮች ቢታዩም፤ ሳይቆይ ግን ቡድኑ ሕግና ሕገ መንግሥቱን በመጨፍለቅ አምባገነን መሆኑን ገልጸዋል። የህወሓት ጁንታው ሕዝቡ ከስጋትና ከፍርሃት ቀጣና ወጥቶ መብቱን እንዳይጠይቅ ሥልጣኑን ለማራዘም እሱ ከሌለ ኢትዮጵያ አንድነቷን ይዛ እንደማትቀጥል፤ የብሔርና የሃይማኖት ግጭቶች እንደሚስፋፉ ኢትዮጵያም የሱማሌ ዕጣ እንደሚገጥማት ይሰብክ እንደነበር አስታውሰው፣ ይህ ደግሞ መቼም ሥልጣን ለመልቀቅ ዝግጁ አለመሆኑና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን ጠል መሆኑን እንደሚያሳይ አመልክተዋል። እንደ ኃላፊው ማብራሪያ በአገራችን ባለፉት ዓመታት በተደረጉ ምርጫዎች ቡድኑ በሀገሪቱ ዴሞክራሲን የማስፈን ፍላጎት ስላልነበረው በ1987 ዓ.ም ጥሩ የሚመስል ጅምር ቢታይም ጅምሩ የ1997 ዓ.ም በድምፅ ዝርፊያ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን አስታውቀዋል። በዚህ ምርጫ ሕዝቡ ጁንታው ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ደንታ እንደሌለውና የራሱን አምባገነናዊ ሥርዓት እንደዘረጋ በግልጽ የተረዳበት ወቅት ነበር ብለዋል። ጁንታው በመጀመሪያ በማዕከል የታጠረ የይስሙላ ዴሞክራሲን የማከፋፈል ባህሪ እንደነበረ ጠቁመው፣ ክልሎች የዴሞክራሲ መብታቸውን በነፃነት እንዳይተገብሩ የአፈና መዋቅር እስከ ቀበሌ ድረስ በመዘርጋት ብቻውን ያሻውን ሲያደርግ መቆየቱን አስታውቀዋል። ከሀብት ብዝበዛ በተጨማሪ አስነዋሪ ኢ-ሰብአዊ ድርጊቶችን ሲፈጽምና ሲያስፈጽም እንደነበረ አመልክተዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ
2/2013 | https://www.press.et/Ama/?p=37107 | 289 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ለአገራዊና ክልላዊ ለውጡ ከፍተኛ ድርሻ እንደነበረው ተገለጸ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 10, 2020 | 21 | ዋለልኝ አየለአዲስ አበባ፡-
የአማራ ብዙኃን መገናኛ
ድርጅት (አብመድ) በ2010
ዓ.ም በአገሪቱ
እና በአማራ ክልልውስጥ ለመጣው ለውጥ ከፍተኛ ድርሻ እንደነበረው ተገለጸ::ድርጅቱ በአዲስ አበባ ያስገነባውን ስቱዲዮ አስመረቀ::ድርጅቱ ትናንት ስቱዲዮውን
ባስመረቀበት ወቅት በክብር
እንግድነት የተገኘኑት የገቢዎች
ሚኒስትር አቶ ላቀ
አያሌው እንደገለጹት፤ አብመድ
ከ2008 ዓ.ም
ጀምሮ በወቅቱ የክልሉ
አመራሮች ያደርሱት የነበረውን
በደል እየዘገበ የሕዝብ
ዓይንና ጆሮ ሆኗል:: ‹‹እኛ እንዳይጋለጡ የምንፈልጋቸውን ነገሮች በማጋለጥ ትህነግ በጎንደርና ባህርዳር ላይ ያደርስ የነበረውን ግፍ ለሕዝብ አድርሷል›› ያሉት አቶ ላቀ፤ በወቅቱ ሁለት ፈተናዎችን ተቋቁሞ ይሰራ እንደነበር አመልክተዋል::ህወሓት ያኔ ሙሉ ጥርስ የነበረው በመሆኑ ከሱ የሚመጣው ጫና አንደኛው ፈተና ነበር ያሉት አቶ ላቀ፣ ሌላው ደግሞ በራሱ በክልሉ አመራሮች ይደርስበት የነበረው ጫና እንደነበር አስታውሰዋል:: የአብመድ ጋዜጠኞች እነዚህን ጫናዎች ተቋቁመው በክልሉ ሕዝብ ላይ ይደርስ የነበረውን ግፍና ኢፍትሀዊነት ለሕዝብ ማድረሳቸውን ገልጸው፤ ዛሬ ወያኔ ከወደቀ በኋላ ብዙዎች ስለዚህ ጉዳይ ብዙ ማለት ቢችሉም፤ አብመድ ግን ከነሙሉ ጥርሳቸው በነበሩበት ጊዜ ፊት ለፊት ሲታገላቸው እንደነበር አስታውቀዋል::ድርጅቱ ላለፉት 40 ያህል ዓመታት አማራን እንደ ጠላት ተደርጎ የተሳለበትን ትርክት የሚያስተካክል ሰፊ ሥራ መሥራት እንደሚጠበቅበት ያመለከቱት አቶ ላቀ፣ የአማራ ሕዝብ እና የአማርኛ ቋንቋ ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ሕዝቦች ቋንቋዎች ጋር ሆኖ ለኢትዮጵያ ያበረከተውን አስተዋጽኦም ማስተዋወቅ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል::አማራ ከሌላው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የተለየ ዕጣ ፈንታ እንደሌለው፤ የአማራ አርሶ አደር ከተበደለም ከተጠቀመም ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጋር እኩል እንጂ ለብቻው የሚሆን ነገር እንደሌለ ተናግረዋል::በምረቃው ሥነ ሥርዓት ላይ የተገኙት የመላው ኢትዮጵያውያን አንድነት ድርጅት ፕሬዚዳንት አቶ ማሙሸት አማረ በበኩላቸው፤ አብመድ እየተደረገ ባለው የሕግ ማስከበር ሂደት ውስጥ ለሰራው ትልቅ ሥራ አመስግነዋል::በጦርነቱ ቦታ ላይ ተገኝቶ የሕዝብ ልሳን ሆኗል::በአገሪቱ ላይ ሲሰራ የነበረውን ግፍ ለሕዝብ አሳይቷል ብለዋል::የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር በበኩላቸው፤ አብመድ በአዲስ አበባ የቀጥታ ማሰራጫ ስቱዲዮ መገንባቱ ከክልሉ ውጪ ላሉ ሕዝቦች ልሳን ለመሆን እንደሚያግዘው አስታውቀዋል::በቀጣይም በአዲስ አበባ የራሱ የሚዲያ ኮምፕሌክስ እንደሚኖረው ጠቁመዋል። ድርጅቱ በቀጣይ በሁሉም ክልሎች የዘገባ ወኪሎች እንደሚኖሩት ያመለከቱት አቶ አገኘሁ፣ በአዲስ አበባ ጨምሮ የአማራ ክልል አዋሳኝ በሆኑ ክልሎች የኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያዎች እንደሚጀመሩ አመልክተዋል::ድርጅቱ ወደ ኮርፖሬት እንደሚያድግም ተናግረዋል::አዲስ ዘመን ታህሳስ 1/2013 | https://www.press.et/Ama/?p=37042 | 294 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የዘንድሮ ምርጫ በሕዝብ ዘንድ ሊኖረው የሚችለውን ተቀባይነት የሚያጎሉ ምልክቶች እየታዩ መሆኑ ተገለጸ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 11, 2020 | 7 | ዋለልኝ አየለአዲስ አበባ፡- የዘንድሮ ምርጫ ከዚህ በፊት ከነበሩት ምርጫዎች በተሻለ በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት ሊኖር እንደሚችል የሚጠቁሙ የነፃነት ምልክቶች እየታዩ መሆኑን አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየት ገለጹ። የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ በቀጣዩ ምርጫ ዙሪያ የደረሰበትን የውሳኔ ሀሳብ አስመልክቶ ያነጋገርናቸው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ በኃይሉ ተሰማ እንደገለጹት፤ ከዚህ በፊት በነበሩት ምርጫዎች ግልጽ የሆኑ ጫናዎች ይደረጉ ነበር። ይሄን ነው መምረጥ ያለብህ የሚሉ አስገዳጅ ትዕዛዞች ይሰጡ ነበር። ነገር ግን አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ሰዎች የሚፈልጉትን የፖለቲካ አመለካከት ማራመድ እንዲሁም ያለምንም መሸማቀቅ ሀሳባቸውን በነፃነት የመግለጽ ሁኔታ እየታየ ነው ።በተጨማሪ መንግሥትም በተደጋጋሚ የዘንድሮ ምርጫ ከዚህ በፊት ከነበሩት ምርጫዎች በተሻለ በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረው በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ተናግሯል። በአገሪቱ ውስጥ ጥቃት በመፈጸምና በማስፈጸም የአገሪቱን ሰላም ሲያውኩ የነበሩት በህወሓት ጁንታ እና በኦነግ ሸኔ ላይ እየተወሰደ ያለው የሕግ ማስከበር እርምጃ ለምርጫው የተሻለ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል። ምርጫው በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነትና ታማኝነት ያለው እንዲሆንም እንዲህ ዓይነት የጥፋት ቡድኖችን ሥርዓት ማስያዝ ተገቢ እርምጃ ከመሆኑ በላይ የዜጎችን ሥጋት በማስወገድ ሰላማዊ ምርጫ ለማካሄድ ያስችላል ብለዋል። ‹‹በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ምርጫ ማድረግ የሚቻለው መንግሥት ከዚህ በፊት ይደረግ ከነበረው ትምህርት ከወሰደ ነው›› የሚሉት ደግሞ ሌላኛው አስተያየት ሰጪ መምህር ዮሐንስ ግሩም ናቸው። ከዚህ በፊት በተደረጉ ምርጫዎች በሃይማኖት ተቋማት ሁሉ ግፊት ይደረግ ነበር። ከላይ እስከ ታች ያሉ አመራሮች አንድ ፓርቲ ብቻ እንዲመረጥ ጫና አድርገዋል። ምርጫ በሚደረግ ቀን እዚህ አስገቡ እየተባለ ነፃነት አልነበረም፤ መንግሥት ለእነዚህ ችግሮች በበለጠ ትኩረት ስጥቶ ከሰራ በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ምርጫ ማድረግ ይቻላል ብለው እንደሚያምኑ ገልጸዋል። ከዚህ በፊት በተደረገው ምርጫ የታዩ ጥፋቶች ከተቀረፉ በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ምርጫ ማድረግ ይቻላል። በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ምርጫ ለማካሄድ ፍትሐዊ የሆነ የመገናኛ ብዙኃን የሰዓት ድልድል ማድረግ እንደሚገባ መንግሥት ቀደም ብሎ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ከጀመረው የምክክር መድረክ መገንዘብ ይቻላል ብለዋል። የመገናኛ ብዙኃን እንደየ ፖለቲካዊ ፍላጎታቸው ለፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳ ለሕዝብ በወቅቱ ማድረስ እንዳለባቸውና መንግሥትም ፍትሐዊ የአየር ሰዓት ድልድል ማድረግ እንዳለበት አሳስበዋል። ከዚህ በፊት የነበረው ወቀሳ ከአየር ሰዓት ድልድል ጀምሮ ለሁሉም ሕዝብ ግልጽ የሆነ አድሎ ይደረግ ስለነበር ነው። ‹‹በመገናኛ ብዙኃን ድልድል ብቻ ሳይሆን የታዛቢዎችና የአስመራጮችም ገለልተኝነት መኖር አለበት፤ ይህ ከሆነ ምርጫው በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያለው መሆኑን ሕዝቡ ራሱ ያምናል›› ብለዋል። የብልጽግና ፓርቲ ሥራ
አስፈጻሚ ኮሚቴ ከኅዳር
25 እስከ 26 ቀን
2013 ዓ.ም ባካሄደው
መደበኛ ስብሰባው፤ የ2013
ምርጫ ሰላማዊ፣ ነፃ፣
ዴሞክራሲያዊ፣ በዓለም አቀፉ
ማህበረሰብ ዘንድ እና
በኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ
ተቀባይነት ያለው እንደሚሆን
የፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ
ኮሚቴ አባልና ዋና
ጽሕፈት ቤት ኃላፊ
አቶ ብናልፍ አንዱዓለም
መግለጻቸው ይታወሳል።አዲስ ዘመን ታህሳስ
2/2013 | https://www.press.et/Ama/?p=37106 | 374 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
የክለቦች ስያሜና ውዝግብ ያስነሳው የፌዴሬሽን ማሳሰቢያ | ስፖርት | September 26, 2019 | 45 | በኢትዮጵያ እግር ኳስ በተለይም በፕሪሚየር ሊግና ከፍተኛ ሊግ ክለቦች መካከል በሚካሄዱ ውድድሮች ስታዲየሞች ስፖርት ለሰላም፣ ለጤንነት ከሚለው መርህ አፈንግጠው የሁከት መናኸሪያ መሆንን ፋሽን አድርገውታል።ካለፉት ሁለትና ሦስት ዓመት ወዲህ እግር ኳሱ በብሔርተኝነት ጥላስር ወድቆ ስታዲየሞች ኳስ ሳይሆን የፖለቲካ አጀንዳ ማንከባለያ ሲሆኑ ታዝበናል። መንግሥትም ሆነ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ በአደገኛ ሃዲድ ላይ እየተጓዘ ለሚገኘው የስፖርታዊ ጨዋነት ጉዳይ ጥናትን መሠረት ባደረገ መልኩ መፍትሄ ማበጀት በይደር ሊተዉት የማይገባ ጉዳይ እንዳልሆነ እውን ነው። በተለይ እግር ኳሱን በሚመራው ብሔራዊ ፌዴሬሽን መሠረታዊ ለውጥ ማምጣት የሚያስችል የማያሻማ የመፍትሄ እርምጃዎችን አምጥቶ ወደመሬት ማውረድ አንገብጋቢ ጉዳይ ነው።ፌዴሬሽኑ ለስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል ብርቱ ችግር ናቸው ብሎ የለያቸው ምክንያቶችና ያቀረባቸው የመፍትሄ አቅጣጫዎች ግን ሌላ ችግር እየመዘዙ ይገኛሉ። ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ለስፖርታዊ ጨዋነት ችግር ብሎ ከጠቀሳቸው ምክንያቶች ውስጥ የክለቦች ስያሜ አንዱ መሆኑም ለውዝግቦች መነሻ እየሆነ ይገኛል፡፡ፌዴሬሽኑ በ2012 ዓ.ም ስያሜያቸው ብሔር ተኮር የሆኑ የእግር ኳስ ክለቦች የስም ለውጥ ማድረግ እንዳለባቸው ማሳሰቡ ይታወሳል።ፌዴሬሽኑ የስያሜ ለውጥ በአምስት ክለቦች ላይ ተግባራዊ እንደሚደረግ መረጃዎች መውጣታቸውን ተከትሎ፤ ከወዲሁ ቅሬታዎች በርትተዋል። ፌዴሬሽኑ ለስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል ምክንያት ናቸው በሚል አምስት ክለቦች ስያሜያቸውን እንዲቀይሩ ማሳሰቢያ ማውጣቱን ተከትሎ በክለቦቹ ተቃውሞ ገጥሞታል።መቐለ 70 እንደርታ ወደ መቐለ ከተማ፣ ፋሲል ከተማ ወደ ጎንደር ከተማ፣ ጅማ አባጅፋር ወደ ጅማ ከተማ፣ ስሁል ሽረ ወደ ሽረ ከተማ እንዲሁም ሀዲያ ሆሳዕና ወደ ሆሳዕና ከተማ ስማቸው እንዲቀየር የተሰጠውን ማሳሰቢያ ክለቦቹ ውድቅ በማድረግ ማሳሰቢያውን እንደማይቀበሉት የተለያዩ የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።ፖለቲካዊ ይዘት ያለው የፋሲል ከነማ ስያሜ ሳይሆን የፌዴሬሽኑ ጥያቄ እንደሆነ ክለቡ በማህበራዊ ገፁ አቋሙን አስታውቋል። ‹‹ፋሲል ከነማ ለጎንደር ሕዝብ መገለጫው ነው፣ የዛሬ 52 ዓመት የነበረን ስያሜ ዛሬ ቀይሩ ማለት መልዕክቱ ሌላ ነው›› በማለትም የፌዴሬሽኑን ማሳሰቢያ ክለቡ እንደማይቀበለው አረጋግጠዋል።ከተመሰረተ ከግማሽ ምዕተዓመት በላይ ያስቆጠረው ፋሲል ከነማ የተጫዋቾቹ መለያ ስም አፄዎቹ ይባላል፤ በተመሳሳይ የደጋፊዎች መለያ ስም አፄያውያን ይባላል። ስለዚህ ፌዴሬሽኑ ውሳኔውን መለስ ብሎ ሊመለከት ይገባል በማለት ክለቡ ያለውን አቋም አሳውቋል።በጉዳዩ ዙሪያ ለዝግጅት ክፍላችን አስተያየታቸውን የሰጡት የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ቡድን መሪ አቶ ሀብታሙ ዘዋሉ ይሄንኑ አቋሙን እንዲህ ሲሉ አረጋግጠዋል። ‹‹የፋሲል ከነማ ራዕዩ፣ ሕልም እና አቋሙ ስፖርት ብቻ ነው። ስያሜውም የጎንደር ከተማ መገለጫ በሆነው በዩኔስኮ በተመዘገበውና የኢትዮጵያ ቅርስ በሆነው የፋሲል ግንብ አሰሪ እና የኢትዮጵያ ንጉስ በሆኑት በአፄ ፋሲለደስ የተሰየመ እንጂ ሌላ ፖለቲካዊ አጀንዳ የሌለው ፍፁም ኢትዮጵያዊ ክለብ ነው››።ፋሲል ከነማ የጎንደር ከተማ ሕዝብና የክለቡ ደጋፊዎችም ይህንን የፌዴሬሽን ውሳኔ እንደማይቀበሉት ፌዴሬሽኑ እንደሚያውቀውም ቡድን መሪው ተናግረዋል። ጉዳዩ የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብን በእንደዚህ ዓይነት ነገሮች ችግር ውስጥ በማስገባት የስፖርት ክለቡን አንገት ለማስደፋት የሚደረግ ፖለቲካዊ አንድምታ ያለው ውሳኔ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ፖለቲካዊ ይዘት ያለው የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ስያሜ ሳይሆን የፌዴሬሽኑ ድፍረት የተሞላበት ‹‹ስም ቀይሩ›› የሚል ውሳኔ መላውን ኢትዮጵያዊ ስፖርት ወዳጅ እና የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች በፅኑ የሚቃወሙት መሆኑን ተናግረዋል።በመሆኑም ክለቡ የስያሜ ለውጥ ለማድረግ በምንም መልኩ ፈቃደኛ እንዳልሆነ አብራርተዋል።የክለቡ የቦርድ አመራሮች በቅርቡ ስብሰባ እንዳላቸው የጠቆሙት ቡድን መሪው ፌዴሬሽኑ ጥቅምት መጀመሪያ ላይ በሚያደርገው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ይሄንኑ አቋም ይዘው እንደሚመጡም እምነት አላቸው፡፡በተመሳሳይ የስያሜ ለውጥ እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ እንደተሰጣቸው ከተነገረው ክለቦች መካከል አንዱ የሆነው የጅማ አባጅፋር ክለብ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሱልጣን ዛኪር፣ ከብሔራዊ ፌዴሬሽኑ በኩል በጉዳዩ ዙሪያ ምንም ዓይነት የደረሳቸው ደብዳቤ እንደሌለ ተናግረዋል።‹‹እኛም የሰማነው በጭምጭምታ ነው። ይፋዊ የሆነ ነገር አልሰማንም። ክለቡ ከስያሜ ጋር ተያይዞ የስፖርታዊ ጨዋነት ችግር አለበት የሚል እምነት የለንም›› ያሉት ሥራ አስኪያጁ የስያሜው ባለቤት ሕዝብ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡ክለቦች ከስያሜያቸው ጀምሮ ምንም ዓይነት የብሔርተኝነትና የስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል ምክንያት ባለመሆናቸው ፌዴሬሽኑ ውሳኔውን ሊቀይር እንደሚገባ በመግለፅም በጉዳዩ ማዘናቸውን ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል።ከተለያዩ አቅጣጫዎች እየተሰጡ የሚገኙ አስተያየቶች የአንዱ ክለብ ደጋፊ ከሌላው ደጋፊ ሲጋጭ፣ ሲቋሰል፣ ሲጨካከን የነበረው ወቅታዊ የአገሪቱን ፖለቲካ በተከተለ መልኩ እንደነበር ይዘረዝራሉ።ክለቦች ከመጡበት ክልል አኳያ የሚሰነዘሩ ጥቃቶችና የሚፈጠሩ መፋጠጦች፤ በተቃራኒው ደግሞ የወንድማዊነት፣ የወገንተኝነት አዝማሚያዎች በዚህ መልክ የተቃኙ እንደነበረ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነበር። ለዚህም እንደማሳያ የሚቀመጠው ቻምፒዮኑ መቐለ 70 እንደርታ፣ ከስሁል ሽረ፣ ከደደቢት ብሎም ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ክለቦች ጋር እርስ በእርስ ሲገናኙ የሚስተዋለው የስታዲየም ድባብ የአንድነትና የወንድማማችነት መሆኑ ነው።በተመሳሳይ በፋሲል ከነማ፣ ባህርዳር ከነማ፣ ወልዲያ ከነማ ደጋፊዎች መካከል ያለውን ወንድማዊ ስሜት መጥቀስ ይቻላል።በ2011 የውድድር ዓመት በትግራይ ክልል እና በአማራ ክልል ክለቦች መካከል በሚካሄዱ ጨዋታዎች የነበረው ሁኔታ ተቃራኒ መሆኑን መመልከት ይቻላል።ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የስፖርታዊ ጨዋነት ምንጩ የክለቦች ብሔር ተኮር ስያሜ ከመያዛቸው መሆኑን ጠቅሶ «ብሔር ተኮር የሆኑ የእግር ኳስ ክለቦች ከቀጣዩ ዓመት ጀምሮ ስያሜያቸውን እንዲያስተካክሉ ይደረጋል» የሚለውን ውሳኔ ከዚህ አንጻር መልሶ ሊመለከት ይገባል የሚሉ የስፖርት ቤተሰቦች በርካታ ናቸው። ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ካንሰር የሆነው ብሔር ተኮር ስያሜ ሳይሆን ብሔር ተኮር እሳቤ መሆኑን ሊሰመርበት እንደሚገባ በተደጋጋሚ ይነሳል።ብሔር ተኮር ስያሜን የያዙ ክለቦች ያውም በሌሉበት ስያሜው ተቀይሮ አመለካከት ሳይቀየር ለውጥ ማምጣት እንደማይቻልም የሚያሰምሩበት ወገኖች አሉ። ፌዴሬሽኑ መሬት ያለውን እውነት ተቀብሎ አመለካከት ላይ መስራቱ አንዱና ዋነኛው መፍትሄ ሊሆን ይገባል። ሌላው በጎሰኝነት፣ ብሔርተኝነት በሽታ ውስጥ የሚገኘውን እግር ኳስ ለመታደግ በተለያዩ መድረኮች ሲነሱ የነበሩ የመፍትሄ ሃሳቦችን ዞር ብሎ መመልከቱም ጠቃሚ ይመስላል፡፡የኢትዮጵያ ስፖርት እንቅስቃሴ ውስጥ የዘር ልዩነት እንዲጠፋ የኦሊምፒክና የዓለም አቀፍ የስፖርት ማኅበራት ደንብና መመሪያዎች እንዲከበሩ ማድረግ አንዱና ዋነኛው መፍትሄ ሊሆን እንደሚችል ይታመናል።አዲስ ዘመን ረቡዕ መስከረም
14 / 2012 ዳንኤል
ዘነበ | https://www.press.et/Ama/?p=19256 | 724 | 2ስፖርት
|
ከጀግናው አንደበት፣ ለአዲሶቹ ጀግኖች | ስፖርት | September 27, 2019 | 19 | በ25 ዓመታት የውድድር ዘመኑ፤ በርካታ የኦሊምፒክና የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ሜዳሊያዎችን እንዲሁም 27 የዓለም ክብረወሰኖችን በእጁ አስገብቷል። በረጅም ርቀት የመም ተወዳዳሪዎችም ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል፤ ከገጹ ፈገግታ የማይነጥፈው ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ። በስድስት ዓለም ቻምፒዮናዎች ተሳትፎው አራት የወርቅ፣ ሁለት የብርና አንድ የነሃስ በጥቅሉ ሰባት ሜዳሊያዎችን ለሃገሩ አበርክቷል። እአአ 1993 የስቱትጋርት ቻምፒዮና የመጀመሪያ ተሳትፎው ሲሆን፤ በ10ሺ ሜትር የወርቅ በ5ሺ ሜትር ደግሞ የብር ሜዳሊያ ነበር ያጠለቀው። ከሁለት ዓመታት በኋላም ጉተንበርግ በተዘጋጀው ቻምፒዮና በ10ሺ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያውን መድገም ችሏል። በአቴንስ እና ሴቪላ በተካሄዱት ውድድሮችም በተመሳሳይ የወርቅ ሜዳሊያውን የግሉ አድርጓል። እአአ የ2001 የኤድመንተን ቻምፒዮና የመጀመሪያውን የነሃስ ሜዳሊያ ሲወስድ፤ በመድረኩ የመጨረሻ ተሳትፎውን ያደረገበት የፓሪሱ ቻምፒዮናም አትሌቱን በብር ሜዳሊያ ነው ያሰናበተው። አሁን ኃይሌ ራሱን ከውድድሮች ካገለለ ዓመታትን አስቆጥሯል። ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንትነት መንበሩን በቃኝ ብሎ ቢያስረክብም አገራቸውን ወክለው ለመሮጥ ከተዘጋጁ አትሌቶች ጎን አይጠፋም። በስድስት ጊዜ የዓለም ቻምፒዮና ተሞክሮውን ነገ በሚጀምረው የኳታር የዓለም ቻምፒዮና ኢትዮጵያን ለሚወክሉ አትሌቶች እንደሚከተለው ያካፍላል። «ዓለም ቻምፒዮናን፤ በዓለም ላይ ያሉ ምርጥ አትሌቶች የሚሳተፉበት መሆኑ ለየት ያደርገዋል። በዳይመንድ ሊግ እና ሌሎች ውድድሮች ላይ የሚገኙት ጥቂቶች ሊሆኑ ይችላሉ፤ በዓለም ቻምፒዮና ግን በዓለም ላይ ‘አሉ’ የተባሉ አትሌቶች የሚሰባሰቡበት ነው»። ጠንካራ አትሌቶች
የሚገናኙበትና የምርጦች
ምርጥ የሚመረጥበትም
ይኸው ውድድር
በመሆኑ በአትሌቶች
ዘንድ በልዩነት
ይታያል። አትሌቶች
ሃገራቸውን የሚወክሉበት
እንዲሁም ሃገራት
ባስመዘገቡት ውጤት በዓለም
አቀፉ የአትሌቲክስ
ፌዴሬሽኖች ማህበር
ደረጃ የሚያገኙበት
በመሆኑም፤ ስፖንሰር
አድራጊ ተቋማትም
ጭምር ከፍተኛ
ትኩረት እንደሚሰጡት አንጋፋው አትሌት ይጠቁማል። ሃገሩን ወክሎ
በጥረቱ ውጤት ካስመዘገበባቸው
ቻምፒዮናዎች ሁሉ እስካሁንም
ከትውስታው ያልተሰረዙ
ገጠመኞችም አሉት።
«ከተካፈልኩባቸው ቻምፒዮናዎች
ሁሉ እስካሁንም
የማዝንበት አጋጣሚ
የደረሰው በስቱትጋርት
ነው። እአአ የ1993ቱ
ቻምፒዮና በ5ሺ
ሜትር አሸናፊነት
አምልጦን የብር ሜዳሊያ
ነበር ያገኘነው»
ሲል ቁጭቱን
ይናገራል። ገጠመኞቹ
እነዚህ ብቻም አይደሉም
ኃይሌ ይቀጥላል፤
«እአአ 2001 ኤድመንተን
ላይ እኔና አሰፋ
መዝገቡ ማሸነፍ
በምንችለው ውድድር
ላይ የፈጸምነው
ስህተት ነው። በተለይ
እኔ ለአምስተኛ
ጊዜ አሸናፊ
እንደምሆን በማመኔ
መዘናጋት አሳይቼ
ነበር፤ ባልተጠበቀ
ሁኔታ ግን አንድ
ኬንያዊ አትሌት
አሸነፈን። ይህም እስካሁን
እንደ እግር እሳት
ነው የሚለበልበኝ»
በማለት በድንገት
ከመሃላቸው ፈትልኮ
ወርቁን ስላጠለቀው
ጥርሰ ፍንጭቱ
ኬንያዊ አትሌት
ቻርልስ ካማቲ ያስታውሳል። ከተካፈለባቸው ቻምፒዮናዎች ሁሉ አንጋፋውን አትሌት በተለየ የሚያስደስተው እአአ 1995 በስዊድን ጉተንበርግ የነበረው ተሳትፎ ነው። በዚህ ውድድር ላይ የመጨረሻውን 200ሜትር፤ የወቅቱ ጠንካራ አትሌቶች ከነበሩት፤ ፖል ቴርጋት፣ ካሊድ ካህ እና ሳላ ኢሱ ለማምለጥ ያደረገው ጥረት ያስደስተዋል። አጨራረሱን ሲያስታውስም ምናልባት ከ800ሜትር ሯጮች በላይ የፈጠነ እንደነበር ነው የሚገልጸው። ከትውስታው መልስም
ነገ በዶሃ በሚጀመረው
ቻምፒዮና ስለሚሳተፈው
የኢትዮጵያ ብሄራዊ
ቡድን አስተያየት
ሰጥቷል። ከዳይመንድ
ሊግ ውድደሮች
በመነሳት በወንድም
በሴትም በተለይ
በ10ሺ ሜትር
ጥሩ ጥሩ አትሌቶች
አሉ። በዚህ ውድድር
ላይ ግን ብልጠት
በጣም አስፈላጊ
ነገር ነው። በተለይ
የመጨረሻዎቹ ሜትሮች
ላይ የተለየ
ነገር ካላደረጉ
ልፋታቸው ሁሉ ገደል
ነው የሚገባው።
የመጨረሻው 100ሜትር
ቀላል አይደለም
በጣም ብዙ ነገር
ነው የሚያበላሸው፤ በመሆኑም እዚህ ላይ አእምሯቸውንና ሰውነታቸውን መጠቀም አለባቸው። ብልጠት ካልታከለበት ሰውነት ብቻውን አሸናፊ አያደርግም፤ ብልጥ ከሆኑ ግን ሰውነትም ቢደክም ማሸነፍ ይቻላል በማለት የይቻላል ተምሳሌቱን ይናገራል። ቡድኑ ወደ ዶሃ ከመጓዙ ከሁለት ቀናት አስቀድሞም የብዙዎች ተምሳሌት የሆነው አትሌቱ ልምምድ በሚያደርጉበት አዲስ አበባ ስታዲየም ተገኝቶ ምክርና ተሞክሮውን አካፍሏል። «ውድድር ‘እንዲህ ነው፤ እንዲያ ነው’ አይባልም ሁሉም የሰራውን ነው የሚያመጣው። ስታዲየሙ የሚያቀዘቅዝ መሳሪያ ስለተገጠመለት እዚህ ካለው አየር የተለየ አይሆንም። ከዚህ ባለፈ በአትሌቶችም ሆነ አሰልጣኞች መካከል አብሮነት አስፈላጊ ነው፤ የእናንተ አብሮ መሆን ብዙ ነገር ይቀይራል። የእናንተ በጋራ መስራት ከውጤትም በላይ ነው፤ ህዝቡም የሚፈልገው ይሄንኑ ነው። ሁሌም ሩጫ ስትሮጡ መጠንቀቅ ያለባችሁ የመጨረሻዎቹን 500 እና 600ሜትሮች ነው። ሌላውን ርቀት ሳትጨናነቁና ሳትፈሩ ዘና ብላችሁ ሸፍኑ። በመካከለኛ ርቀትም ቢሆን ሩጫውን ማንበብ የግድ ነው፤ መዘናጋት አያስፈልግም» ሲልም አስገንዝቧል። ቀጥሎም፤ «አንዳችሁ ለሌላችሁ ውጤት አስፈላጊ እንደሆናችሁ እንዳትዘነጉ። ልብ አድርጉ፤ አሰልጣኞችም ሆናችሁ አትሌቶች ‘እኔ ውጤት ላምጣ እንጂ ስለሌላው አያገባኝም’ ማለት የለባችሁም። ሌላው ማስታወስ ያለባችሁ እናንተን የሚመለከቱ ብዙ ሺ ታዳጊዎች አሉ፤ ውጤት ሁለተኛ ነገር ነው ዋናው እርስ በእርሳችሁ የምታሳዩት ስነ-ምግባር ነው። እናንተ ውጤት ስላመጣችሁ ብቻ መደሰት ሳይሆን ሌላውንም መደገፍ በተመሳሳይ አስፈላጊ ነገር ነው። አሰልጣኞች፣ የቡድን መሪዎችና ቴራፒስቶችም ከልምምዱ ባሻገር ስነ-ምግባር ላይም ማተኮር አለባችሁ»ም ብሏል። በመጨረሻም ለብሄራዊ ቡድኑ መልካም ውድድር እንዲሆን ተመኝቷል።አዲስ ዘመን መስከረም 15/2012 ብርሃን ፈይሳ | https://www.press.et/Ama/?p=19334 | 589 | 2ስፖርት
|
በትግራይ ክልል ለተስተጓጎለው የቴሌኮም አገልግሎት የክልሉ ልዩ ኃይል ተሳታፊ እንደነበር ተገለጸ | ሀገር አቀፍ ዜና | December 11, 2020 | 30 | ክፍለዮሐንስ አንበርብርአዲስ አበባ፡- ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ከሌሊቱ 6 ሰዓት ከ37 ደቂቃ ላይ በሰሜን ሪጅን ትግራይ ክልል ለተቋረጠው የቴሌኮም አገልግሎት የክልሉ ልዩ ኃይል ተሳታፊ እንደነበር ተገለፀ። የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ፣ በሰሜን ሪጅን የቴሌኮም አገልግሎት ላይ የደረሰውን የአገልግሎት መቋረጥ አስመልከተው ትናንት በስካይ ላይት ሆቴል ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ፤ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በሰሜን ሪጅን አገልግሎት ተቋርጧል። ይህም በመቀሌና በሽሬ የሚገኙ ዋና ጣቢያዎችን አማራጭ የመገናኛ መስመሮች በሙሉ በመቁረጥና የኮመርሻል ኃይል አቅርቦት ከጥቅም ውጪ በማድረግ የተፈፀመ ነው። የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት እንዲቋረጥም ሲደረግ በዕለቱ የግቢ ጥበቃ ላይ የነበሩትን የቴሌኮም ሠራተኞችን በኃይል ከግቢ እንዲወጡ በማድረግና አካባቢው በልዩ ኃይል በመጠበቅ የተከናወነ እንደነበር አስታውሰዋል። በዕለቱ በሰሜን ሪጅን ላይ የቴሌኮም አገልግሎት መቋረጡን የሚያሳይ መረጃ በማዕከል ከሚገኘው የኔትወርክ መቆጣጠሪያ ሲስተም ለቴክኒክ ቡድንና ለከፍተኛ አመራሩ መድረሱን ያስታወሱት ሥራ አስፈጻሚዋ፤ በወቅቱ ግን ችግሩን ይህ ነው ብሎ በቅጽበት መናገር እንዳልተቻለ አስረድተዋል። ሆኖም በሂደት በተደረገ ምርመራና በተንቀሳቃሽ ምስል በተደገፈ መረጃ መረዳት የተቻለው አገልግሎቱን ሆን ተብሎ እንዲቋረጥ ተደርጓል። ችግሩ ከታወቀ በኋላም ሁኔታዎችን የመከታተልና ተጨማሪ አገራዊ አደጋ እንዳይከተልም አስፈላጊው እርምጃ ተወስዷል። እንደ ሥራ አስፈፃሚዋ ገለፃ፤ በአሁኑ ወቅት የተስተጓጎለውን የቴሌኮም አገልግሎት እንደገና እንዲጀምር ጥረት እየተደረገ ሲሆን በዳንሻ፣ ተርካን፣ ሁመራ፣ ሽራሮ፣ ማይፀብሪ፣ ማይካድራ፣ ኮረም በከፊል አገልግሎት የጀመረ ሲሆን በአላማጣ ሙሉ ለሙሉ አገልግሎቱ ተጀምሯል። ሆኖም በመላ ክልሉ የቴሌኮም አገልግሎት ለማስጀመር በሚደረገው ጥረት የኃይል መቋረጥ፣ የቴሌኮም መሠረተ ልማቶች መቆራረጥና የሰው ኃይል ለማሰማራት ምቹ ሁኔታ አለመኖር አገልግሎቱን ወደቀድሞ ሁኔታ ለመመለስ ፈታኝ ሆኗል። አገልግሎቱን ማቋረጥ የሚችሉ ግለሰቦች የተሳተፉበት መሆኑንና የክልሉ ልዩ ኃይልም በዚህ እኩይ ተግባር ተሳታፊ መሆኑን ከሥፍራው የደህንነት ካሜራዎች በተቀረፀ ተንቀሳቃሽ ምስል መረዳት የተቻለ መሆኑን የገለፁት ሥራ አስፈፃሚዋ፤ ከድርጊቱ ጋር የተያያዙ በርካታ ጉዳዮች በምርመራ ላይ መሆናቸውን ጠቁመው በቀጣይ ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረጉ አረጋግጠዋል። ከኢትዮ ቴሌኮም የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፤ በመላ አገሪቱ ከ16ሺ በላይ ቋሚ ሠራተኞች ያሉት ተቋም ሲሆን ዘርፈ ብዙ አገራዊ ፋይዳ ያላቸውን የቴክኖሎጂ ሥራዎችን በማከናወን አገራዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሚተጋ ተቋም ነው።አዲስ ዘመን ታህሳስ
2/2013 | https://www.press.et/Ama/?p=37110 | 288 | 0ሀገር አቀፍ ዜና
|
ለሁሉም ክፍት የሆነ የወርልድ ቴኳንዶ ውድድር ተጠናቀቀ | ስፖርት | September 27, 2019 | 52 | ከሁለት መቶ በላይ ስፖርተኞች የተሳተፉበት ለሁሉም ክፍት የሆነ የወርልድ ቴኳንዶ ውድድር ተጠናቀቀ፡፡ በብሔራዊ ስፖርት ፌዴሬሽን አዳራሸ በተካሄደው ውድድር ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ስፖርተኞች ተሳታፊ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ወርልድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ያደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ ጥር 2012 ዓ.ም ሞሮኮ ላይ የሚካሄደውን የኦሊምፒክ ማጣሪያ የቴኳንዶ ውድድር ኢትዮጵያን ወክለው የሚሳተፋ ስፖርቶችን መምረጥና በተለያየ ጊዜ በቴኳንዶ ውድድር ዕድል ያላገኙ ስፖርተኞችን በማሳተፋ ብቃታቸውን እንዲያሳድጉ ማድረግ የውድድሩ ዓላማ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከውድድሩ ጎን
ለጎን ከ300 በላይ
የወርልድ የቴኳንዶ
ስፖርተኞች ከ1ኛ
እስከ 4ኛ የዳን
ዕድገት ፈተና የተሰጣቸው
መሆኑንም ፌዴሬሽኑ
አሳውቋል፡ ፡ ውድድሩ
በሁለቱም ፆታ የተካሄደ
ሲሆን በወንዶች ከ58 ኪሎ ግራም በታች፣ ከ68 ኪሎ ግራም በታች እና ከ80 ኪሎ ግራም በታች ተከፍሎ ተካሂዷል፡፡ በሴቶች ደግሞ ከ49 ኪሎ ግራም በታች፣ ከ67 ኪሎ ግራም በታች እና ከ67 ኪሎ ግራም በታች መካሄዱ ተገልጿል፡፡ በዚህም መሠረት በውድድሩ ፍጻሜ በወንዶች ከ68 ኪሎ ግራም በታች ጀማል ሀጂ ከኦሮሚያ ክልል የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ሲሆን ገመቺስ ኤፍሬም ከአዲስ አበባ ብር ሜዳሊያ ማጥለቅ ችሏል፡፡ ዮሐንስ ለማ ከኦሮሚያ ክልልና አብዱል ፈታ ሠፋ ከአዲስ አበባ የነሐስ ሜዳሊያ አግኝተዋል፡፡ በወንዶች ከ58 ኪሎ ግራም በታች ፍጹም ዘውዴ ከአዲስ አበባ የወርቅ ሜዳሊያ ሲያሸንፍ፣ ባስልኤል ደረጄ ከደቡብ ክልል የብር ሜዳሊያ፣ አብዱራህማን ሰፋ ከአዲስ አበባ እና ሁሴን ሀጂ ከኦሮሚያ የነሐስ ሜዳሊያ አግኝተዋል፡፡ በወንዶች ከ80 ኪሎ ግራም በታች በተካሄደው ውድድር ሲያንሰው ዘኪ ከደቡብ ክልል የወርቅ ሜዳሊያ ወስዷል፡፡ በረሳ አብዲሳ ከኦሮሚያ ክልል የብር ሲያሸንፍ፣ ስንታየው ዘመድኩን ከኦሮሚያ እና ቁምላቸው ፈንቴ ከአማራ የነሐስ ሜዳሊያ ማጥለቅ ችለዋል፡፡ በሴቶች ከ49 ኪሎ ግራም በታች ውድድር ሰብለ ፈለቀ ከአማራ ክልል የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ስትሆን ሶፊያ በለጠ ከኦሮሚያ ክልል የብር ሜዳሊያ ማጥለቅ ችላለች፡፡በዚሁ ውድድር አጸደ አድማሱ ከኦሮሚያ እና ማስተዋል ታረቀኝ ከአማራ የነሐስ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ በሴቶች ከ57 ኪሎ ግራም በታች መቅደስ አስማረው ከአዲስ አበባ የወርቅ ሜዳሊያው ባለቤት ስትሆን ምህረት ሞላ በተመሳሳይ ከአዲስ አበባ የብር ሜዳሊያውን አጥልቃለች፡፡አሜን ሚኤሴ እና አያንቱ ሚኤሴ ከኦሮሚያ የነሐስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ በሴቶች ከ67 ኪሎ ግራም በታች አያና አሠፋ ከደቡብ የወርቅ፣ መስከረም ሽፈራው በተመሳሳይ ከኦሮሚያ የወርቅ ሜዳሊያ ሲያሸንፉ፣ ረድኤት ጌታቸው ከአዲስ አበባ እና ወርቄ ሚልኬሳ ከኦሮሚያ የነሐስ ተሸላሚ በመሆን ውድድራቸውን አጠናቀዋል::አዲስ ዘመን መስከረም 16/2012 ቦጋለ አበበ | https://www.press.et/Ama/?p=19535 | 315 | 2ስፖርት
|
ኮ ዳግም የዓለም አትሌቲክስ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ | ስፖርት | September 27, 2019 | 27 | የዓለም አትሌቲክስ ፕሬዚዳንት ሆነው ባለፉት አራት ዓመታት የቆዩት እንግሊዛዊው ሴባስቲያን ሎርድ ኮ በድጋሚ ተመርጠዋል። የኦሊምፒክ የቀድሞ የ1ሺ500 ሜትር ቻምፒዮኑ ኮ በዶሃ በተጀመረው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና በተካሄደው የአባል አገራት ጉባኤ ለአንድ የኦሊምፒክ ዓመት በመሪነት እንዲቀጥሉ ዕድል እንደተሰጣቸው ታውቋል፡፡ ኮ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ስልጣን የመጡት እአአ በ2015 ሲሆን፤ በስልጣን ላይ በቆዩባቸው ጊዜያትም በሩሲያ የአበረታች ቅመሞች ጉዳይ እንዲሁም በቅርቡ ከደቡብ አፍሪካዊቷ አትሌት ካስተር ሰመኒያ ጋር በገቡት እሰጣ ገባና በጠንካራ ውሳኔ ሰጪነታቸው ይታወቃሉ። በተለይ ከአበረታች ቅመሞች ጋር በተያያዘ የሰሯቸው ስራዎች እንደሚያስደስታቸውም ነው የሚናገሩት። በዚህ ምርጫ ላይም 203ቱም አባል አገራት ያለ አንዳች ማቅማማት ሙሉ ድምጻቸውን እንደሰጧቸው የሮይተርስ ዘገባ ያሳያል። የሁለት ጊዜያት የኦሊምፒክ ወርቅ ሜዳሊያ ባለቤቱ ኮ ዳግም መመረጣቸውን ተከትሎም «ቀላል የሚባል ቆይታ አልነበረም፤ አራቱ ዓመታት ከባድ ነበሩ። ማሰብ ያለብን ስፖርቱን ስለማሳደግና የስፖርት ቤተሰቡን ስለማርካት ነው። አሁን ስፖርቱ ባለበት የአንድነት ስሜት እኮራለሁ፤ አሁንም ጥሩ የምንሰራበት ጊዜ ላይ እንገኛለን» ሲሉም ገልጸዋል ። ኮ የማህበሩን የመሪነት ስፍራ የተቆናጠጡት እአአ በ2015 በቤጂንግ የዓለም ቻምፒዮና ሲሆን፤ ዩክሬናዊውን የቀድሞ ምርኩዝ ዝላይ ባለክብረወሰን ሰርጄ ቡቡካን ሰፊ በሆነ ድምጽ በመርታት ነበር። ከእርሳቸው በፊት ቦታውን ለ16ዓመታት የያዙት ካሜሩናዊው ላሚን ዲያክ ለሩሲያ አትሌቶች ሽፋን ይሰጣሉ በሚል ምክንያት በፈረንሳይ ፖሊሶች ክስ ተከፍቶባቸው እንደነበር ይታወሳል፡፡ የዓለም አትሌቲክስ
የስራ አስፈጻሚ
አባላት 13 ወንበር
ያለው ሲሆን፤
በደንቡ መሰረትም
ከእነዚህ ውስጥ ቢያንስ
ስድስት የሚሆኑት
ሴት መሆን ይገባቸዋል።
በዚህም መሰረት
ጉባኤው አዲስ ሴት
ምክትል ፕሬዚዳንት
መርጧል። የምክትልነት
መንበሩን የተቆናጠጡት ኮሎምቢያዊቷ አንጋፋ አትሌት ዚሜና ሬስትሬፖ ናቸው። የ50ዓመቷ ሬስትሬፖ እአአ 1992ቱ የባርሴሎና ኦሊምፒክ በ400ሜትር ነሃስ በማጥለቅ የመጀመሪያዋ ሴት ኮሎምቢያዊት አትሌት ናቸው። መመረጣቸውን ተከትሎ ባደረጉት ንግግር ላይም «ይህ ለእኔ እና ለአገሬ ትልቅ አጋጣሚ ነው። እንደማስበው ከሆነ ከበፊቱ ይልቅ አሁን እኛ ሴቶች የተሻለ ዕድል እያገኘን ነው፤ በምክር ቤቱ ሰባት ሴቶች አለን። ይህ በጣም ትልቅ ቁጥር ነው፤ በዚህ ደግሞ ደስተኛ ነኝ» ማለታቸውን ዘገባው አስነብቧል። ፕሬዚዳንት ኮ የምክትላቸውን መመረጥ ተከትሎም « የቀድሞዋ አትሌት ዚሜና ስፖርቱን ለማሳደግ በምናደርገው ጥረት ጥሩ ይረዱናል። ለመጀመሪያ ጊዜ ሴት ምክትል ፕሬዚዳንት እንዲሁም ተጨማሪ የምክር ቤት አባል በማግኘታችን ደስተኛ ነኝ፤ ይህ ታሪካዊ አጋጣሚ ነው» ብለዋል።አዲስ ዘመን መስከረም 16/2012 ብርሃን ፈይሳ | https://www.press.et/Ama/?p=19544 | 306 | 2ስፖርት
|
አወዛጋቢው መዋቅር በተሻረበት ዝግ ስብሰባ ምን ተባለ? | ስፖርት | September 27, 2019 | 35 | የ2011 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከወትሮው በተለየ በአጨቃጫቂ ሁኔታ፣ በተደጋጋሚ መቆራረጥ እንዲሁም በአሰልቺ የውድድር መርሐ ግብር ሳይጠናቀቅ ተጠናቋል። የ2012 ፕሪሚየር ሊግን ችግር የጸዳ ለማድረግ በእንቅስቃሴ ላይ እንደሆነ የሚናገረው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፤ መስከረም 5 ቀን 2012 ዓ.ም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ፕሪሚየር ሊጉን በተወሰነ ደረጃ ከስፖርታዊ ጨዋነት ጉድለቶች የፀዳ ለማድረግ አዲስ የውድድር ሥርዐት ወይም መዋቅር መዘርጋቱን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። ፌዴሬሽኑ በወቅቱ እንዳስታወቀው ፤ በ2012 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 24 ቡድኖች በሁለት ምድብ ተከፍለው ውድድራቸውን የሚያካሂዱ ይሆናል።የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ኮሎኔል አወል አብዱራሂም፤ ሊጉ በሁለት እንዲከፈል የተደረገበት ምክንያት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣውን የስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል መፍትሄ እንዲሰጥ በማሰብ መሆኑን ነበር በጋዜጣዊ መግለጫው የተናገሩት። በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተግባራዊ የሚደረገው አዲሱ የሊግ አደረጃጀት ወቅታዊ የአገሪቱን ሁኔታ መሰረት ያደረገ መሆኑን አስቀምጠዋል። በዋናነት የሊግ አደረጃጀት መለወጥ ምክንያት የሆነው በክለቦች መካከል የተፈጠረ አለመግባባት ሲሆን፤ ለጊዜው መገናኘት የሌለባቸውን ክለቦች በተቻለ መጠን አለማገናኘት እንደ መፍትሄ ተወስዷል። በዚህም ባለፈው ዓመት በፕሪሚየር ሊጉ ውድድር ሲገናኙ በስፖርታዊ ጨዋነት ችግር ተስተውሎባቸዋል የተባሉ ቡድኖች ለአብነትም ወላይታ ድቻ፣ ሲዳማ ቡና እንዲሁም የአማራ ክልል ከትግራይ ክልል ክለቦች ጋር እንዳይገናኙ ለማድረግ ነበር የታሰበው። ፌዴሬሽኑ በውድድር ዓመቱ ተግባራዊ ሊያደርገው የነበረው አዲሱ የሊግ አደረጃጀት ከተለያዩ አቅጣጫዎች ጥያቄዎች ማስነሳቱ አልቀረም። በተለይ እግር ኳስ የሠላም መፍጠሪያና አንድነትን ማጠናከሪያ መድረክ ሆኖ ሳለ አዲሱ የሊግ አደረጃጀት ህዝብን ከህዝብ የሚያራርቅ እንደሆነ ትችቶች ሲሰነዘሩበት ሰንብቷል።በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ቡናና ቅዱስ ጊዮርጊስ የመሳሰሉ አንጋፋ የአዲስ አበባ ክለቦች የፌዴሬሽኑን ሃሳብ በፅኑ ሲቃወሙ ታይቷል። እነዚህ ክለቦች ጉዳዩን ወደ መንግስት እስከ መውሰድ ደርሰውም ማስቆም ችለዋል። በጉዳዩ ላይ በሸምጋይነት ጣልቃ የገባው የፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን ከትናነት በስቲያ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ተመካክሮ ፌዴሬሽኑ ተግባራዊ ለማድረግ ያሰበውን የሃያ አራት ክለቦች ሊግ መዋቅር ማገዱ ተሰምቷል። ከክልል እና ከከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽነሮች ጋር ምክክር ያካሄደው ስፖርት ኮሚሽን ፌዴሬሽኑ ያሰበው አዲሱ መዋቅር እንዲታገድ ሲወስን በዋናነት ምክንያት ተደርጎ የቀረበው አዲሱ መዋቅር ጥናት ሳይደረግበት ወደ ተግባር እንዲለወጥ በመደረጉ መሆኑ ታውቋል። ስፖርት ኮሚሽን ያዘጋጀውን ስብሰባ የኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ዶክተር ሒሩት ካሳው በሰብሳቢነት፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ፣ የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር፣ የዘጠኙ ክልሎችና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የስፖርት ኮሚሽን አመራሮች እንዲሁም የእግር ኳስ ፌዴሬሽን አመራሮች ተሳታፊ ያደረገ ነበር። በመድረኩ ላይ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጂራ በ2011 ዓ.ም በእግር ኳሱ እየተፈጠሩ ያሉ ችግሮች ምን እንደሆኑ በዝርዝር አስረድተዋል ።አቶ ኢሳያስ ሁኔታውን በማስረዳት እየተፈጠሩ ያሉ አለመግባባቶችን ለመቀነስ እንደመፍትሄ በጊዜያዊነት በሁለት ምድብ የተከፈለ 24 ቡድኖች የሚካፈሉበት ውድድር ማዘጋጀት እንዳስፈለገ ተናግረዋል። በስብሰባው ታዳሚ የነበሩት አንዳንድ የፌዴሬሽን የሥራ አስፈጻሚ አባላት መካከል አቶ አሊሚራና አቶ አበበ ገላጋይ «በፌዴሬሽኑ የተላለፈው ውሳኔ ክለቦች ሳይማከሩበት እና ጥናትን መሠረት ያላደረገ መሆኑን በወቅቱም በሥራ አስፈጻሚ ስብሰባ ወቅት አጽንኦት ሰጥተን ተናግረን ነበር። ሆኖም እኛም በማናውቀው መልኩ የተወሰነ ውሳኔ ነው» በማለት ተቃውሞ አሰምተዋል። ይህም በፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚዎች መካከል መግባባት እንደሌለ ያሳበቀና ትዝብት ላይ የጣላቸው ጉዳይ ሆኗል። በክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን አመራሮች በኩል በተለይ የአማራና የትግራይ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን አመራሮች ፣ የፌዴሬሽኑ ውሳኔ በእጅጉ ተኮንኗል። በውድድሩ የሚሳተፉት ቡድኖች ሆነው የአማራና ትግራይ ክልል ክለቦች እንዳይገናኙ የተወሰነው ውሳኔን እንደማይቀበሉትም አበክረው ሲገልጹ ተደምጠዋል።እግር ኳስ የሠላም እና የማቀራረቢያ መድረክ መሆኑን አስረግጠው በመናገርም የፌዴሬሽኑን ውሳኔ እንደማይቀበሉት አሳስበዋል። የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጥናት በማስጠናት በውስጥ ውድድር ተካሂዶ በኋላም በኢትዮጵያ ሻምፒዮና ውድድሩ ይጠናቀቅ በማለት ያቀረበው ሃሳብ የሚያስመሰግን ሆኖም ተነስቷል። ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ግን እንደ መፍትሄ ከመቀበል ይልቅ የራሱን መንገድ መከተሉ ስህተት መሆኑ ተጠቁሟል። በተጨማሪም ፌዴሬሽኑ ከክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ጋር ተቀራርቦ የመስራት ችግሮች እንዳሉበት ተነግሯል። የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ በበኩላቸው ፤በፕሪሚየር ሊጉ 24 ቡድኖች መሳተፋቸውን እንደማይደግፍ እና ከኦሊምፒክ መርህ አንጻር ክልሎች እና ህዝቦች እንዳይገናኙ ማድረግ ተገቢ አለመሆኑን ገልጸዋል። የኢፌዴሪ ባህል፣ ቱሪዝም እና ስፖርት ሚኒስቴር ዶክተር ሒሩት ካሳው፤አለም ዓቀፍ የእግር ኳስ ማህበር ፊፋ ላስቀመጠው ደንብ እና ህግ ተገዥ በመሆን አባል አገራቱም ለተቀመጠው መመሪያ ተገዥ እንዲሆኑ በማድረግ እያስተዳደረ በመገኘቱ ተፈሪና ተቀባይነት ያለው ተቋም መሆን እንደቻለ አስታውሰዋል። በመሆኑም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፊፋ ላወጣው ደንብና መመሪያ ተገዥ በመሆን እግር ኳሱን መምራት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል። በብሄራዊ ፌዴሬሽኑ አመራሮች መካከል የተፈጠረውን የሃሳብ ልዩነት በውስጥ እንዲፈታና፤ 24 ቡድኖች በሁለት ምድብ ተከፍለው የሚጫወቱበት መዋቅር ለጊዜው እንዲቆም በስተመጨረሻ ውሳኔ ላይ ተደርሷል። በቀጣይም ክለቦች በተገኙበት ውይይት በማድረግ ዘላቂ መፍትሄ እንዲቀርብ ተወስኗል። ስፖርት ኮሚሽኑም ጉዳዩን በጥንቃቄ እንደሚከታተለው በማስታወቅ ስብሰባው ተጠቃሏል።አዲስ ዘመን መስከረም 15/2012 ዳንኤል ዘነበ | https://www.press.et/Ama/?p=19340 | 638 | 2ስፖርት
|
‹‹የእነ ቶሎ ቶሎ ቤት›› ቀጣዩ የውዝግብ ምዕራፍ | ስፖርት | September 28, 2019 | 96 | የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በጥድፊያ ውሳኔ ላይ በመድረስ የሚስተካከለው የለም ቢባል አልተጋነነም። በአጭሩ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ‹‹የእነ ቶሎ ቶሎ ቤት›› እንደሚባለው ዛሬ በጥድፊያ ይወስናል ነገ ይሽረዋል። እሱ ባይሽረው እንኳን ሌሎች በተቃውሞ እንዲሽረው ያደርጉታል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እንደ አዲስ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ካለፉት ሃያ ዓመታት በላይ የተወዳዳሪ ክለቦችን ቁጥር ሲቀያይር ታይቷል። የተወዳዳሪ ክለቦች ብዛት በሚቀያየርበት ወቅት በጥናት አለመደገፉም ዘወትር ከተቃውሞ ነፃ ሆኖ አያውቅም። ዘንድሮም ከስፖርታዊ ጨዋነትና ከስቴድየም ግጭቶች ጋር በተያያዘ ለጊዜውም ቢሆን መፍትሄ ይሆናል በሚል ፌዴሬሽኑ የተሳታፊ ክለቦችን ቁጥር ወደ ሃያ አራት አሳድጎ በሁለት ምድብ ለማካሄድ ማሰቡ ከዚህም ከዚያም ተቃውሞ አስነስቶበት በመንግሥት ጣልቃ ገብነት ከመታገድ አልዳነም። በቀጣይም ክለቦች ተወያይተው አዲስ መዋቅር እንደሚሰራ ይጠበቃል። ያም ሆኖ የውድድር ዓመቱ ከመጀመሩ በፊት ባለው ጥቂት ጊዜ ምን ዓይነት ጥናት ተጠንቶ ወደ ተግባር እንደሚገባ የሚያውቁት የእግር ኳሱ አመራሮች ብቻ ናቸው። ይህም ቀጣይ ሌላ የውዝግብ ምዕራፍ እንደሚከፍት ስጋት ያላቸው የስፖርት ቤተሰቦች ከወዲሁ በጉዳዩ ላይ ትኩረት እንዲሰጡ አድርጓል። ወትሮውንም ቢሆን የተሳታፊ ክለቦች ብዛት ከ12 ወደ 14፣ ከ14 ወደ 16 ያደገበት አሳማኝ ምክንያት አልነበረውም። የሊጉ ክለቦች ቁጥር 16 መሆኑ የአገሪቱን አቅም ያገናዘበ እንዳልሆነ ብዙዎች ይስማማሉ በምክንያትም ይሞግታሉ። ፊፋም ከ16 ይልቅ 14 ክለቦች ያሉት ፕሪሚየር ሊግ ቢሆን መልካም ነው ሲል ምክረሃሳብ እንደሰጠን ይሰማል። የሊጉ ክለቦች ቁጥር 14 በነበረበት በ2004 ዓ.ም. መቀመጫቸውን ሸገር ላይ ያደረጉ ክለቦች ብዛት ሰባት ነበር። የሊጉን እኩሌታ ቁጥር መያዛቸው በሌሎች የክልል ክለቦች ላይ የማይገባ የፉክክር ጥቅም ያስገኝላቸው ነበር። በሰንጠረዡ ግርጌ የጨረሰው ፊንጫ ስኳር በመኪና እየተዟዟረ ተዳክሞ ሲጫወት፣ ሰባቱ ክለቦች ብዙሃኑን የሊግ ጨዋታዎች ያለጉዞ ድካም በአዲስ አበባ ያካሂዱ ነበር። በዚያ ዓመት በሰንጠረዡ እስከ አራተኛ የነበረውን ቦታ ይዘው ያጠናቀቁት የአዲስ አበባ ክለቦች መሆናቸው አያስገርምም። በሊጉ በጨዋታ የሚቆጠረው አማካይ የጎል መጠን 2.34 የነበረ ሲሆን እስካለፈው 2011 ድረስ ይህን ያህል ጎል በአማካይ የተመዘገበበት ዓመት ከዚያ ወዲህ አልታየም።አምና ደደቢት በደረሰበት ከባድ የፋይናንስ ችግር ምክንያት ስብስቡን በማሳሳቱ የሊጉ እጅግ ደካማው ቡድን በመሆን በዘጠኝ ዓመታት ከታየው ሁሉ መጥፎውን የጎል ዕዳ ይዞ ወርዷል። ይህም የሊጉን የጎል ብዛት ያለምክንያት አሳድጎታል።የ14 ክለቦች ሊግ ከ16 ክለቦች ሊግ የተሻለ ንጻሬ እንዳለው በርካታ ምክንያቶችን መደርደር ይቻላል። በጨዋታዎች መካከል በቂ የማገገሚያ ጊዜ የሚሰጥ መርሐግብር ስለነበር በንጽጽር ያልተዳከሙ ተጫዋቾች በየጨዋታው የመገኘታቸው ዕድል ከፍ ያለ ስለነበር የጨዋታውም ግለት የተሻለ እንደሚሆን ጥርጥር አይኖርም። ‹‹የሊግ ክለቦች ቁጥር የሚጨመርበትና የሚቀነስበት በጥናት የጎለበተ ስፖርታዊ ምክንያት መኖር ነበረበት›› የሚሉ የስፖርት ቤተሰቦች ሌላው ቢቀር በዓመት የ58 ጨዋታ ልዩነት ስለፈጠረ፣ የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ዋንጫ ከሊጉ መርሃግብር ጋር ተጣጥሞ የመከናወኛ ጊዜ በማጣቱ ለዛ ቢስ እንዲሆን ምክንያት ሆኗል።የሊጉ ተወዳዳሪዎች ብዛት በመደበኛነት 16 ሲደረግ የሊጉ አማካይ የጎል መጠን እያሽቆለቆለ መምጣቱን ባለሙያዎች በስታትስቲካዊ መረጃ አስደግፈው ያስቀምጡታል። በሊጉ የአዲስ አበባ ክለቦች ብዛት በቀነሰ ቁጥር የቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ቡና ግብ የማስቆጠር አቅም እየወረደ ሊሄድ መገደዱን እዚህ ጋር ያነሳሉ።በስምንት ዓመት ውስጥ የቅዱስ ጊዮርጊስ የዓመቱ መጨረሻ የግብ ክፍያ ከ39 ወደ 10 አሽቆልቁሏል። የሊጉ የጨዋታ አማካይ ጎል መጠንም ከ2004 እስከ 2010 ባለው የጊዜ ርቀት በጨዋታ በአማካይ በ0.48 ጎል ቀንሷል። ያለግብ የሚጠናቀቁ ጨዋታዎች ብዛት እየጨመረ፣ የሊጉ አዝናኝነት እየቀነሰ ሲመጣ ግን ያስተዋለው የለም።ኢትዮጵያ ቡና የሊጉ ቻምፒዮን ከሆነበት ከ2003 ዓ.ም ወዲህ በየጨዋታው የሚሰበስበው አማካይ ነጥብ ከ2.1 ወደ 1.3 አሽቆልቁሏል። በሊጉ ላይ ሰባት የአዲስ አበባ ክለቦች በነበሩበት 2003 እና ሦስት ብቻ በቀሩበት በ2011 መካከል ቡና በአማካይ በየጨዋታው የ0.8 ነጥብ ማሽቆልቆል አሳይቷል። በተመሳሳይ በጎል መጠንም ቢሆን በሁለቱ ዘመናት መካከል በጨዋታ 0.8 ጎል ቀንሷል። ሊጉ በዚሁ መልኩ ከቀጠለ፣ ሁለት የሸገር ክለቦች ብቻ በቀሩበት በ2012 የኢትዮጵያ ቡና ዕጣ ምን ይሆናል?የአስራ አራት ጊዜ ቻምፒዮኑ ቅዱስ ጊዮርጊስም ቢሆን ከፍተኛ ጎል ካስቆጠረበት ከ2006 ወዲህ በአምስቱ ዓመታት ‹‹የጎል ምርቱ›› ቀንሶበታል። ቢያንስ የ27 ጎሎች ልዩነት አሳይቷል። ይህ የሆነው በአምናው ውድድር ‹‹ፈረሰኞቹ ሦስት ጨዋታዎችን ባለመጫወታቸው ነው›› የሚል ሙግት ሊነሳ ይችላል። ነገር ግን ሦስቱን ጨዋታዎች ቢጫወቱና በእያንዳንዳቸው ስምንት፣ ስምንት ጎሎችን ቢያስቆጥሩ እንኳን ልዩነቱ የሚጠብ አይሆንም። በ2006 አንድ ክለብ 26 ጨዋታዎች ሲጫወት፣ 30 ጨዋታዎች ከሚያደርግበት 2011 ጋር በአራት ጨዋታ እንደሚያንስም ልብ ይሏል። የጨዋታዎች ቁጥር በዝቶ የጎሉ መጠን ይህን ያህል ዝቅ የሚልበት አንድ አንገብጋቢ ምክንያት ከሌለ በስተቀር በጤና እንዳልሆነ ግልጽ ነው።በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በደርሶ መልስ የሚደረገው ውድድር ከ22 ዓመት በፊት በ1990 ዓ.ም ሲጀመር ይገመት የነበረው አደጋ ማለትም ሕዝቡን በጎሳ አደራጅቶ እርስ በርስ ያባላል የሚለው አደጋ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በተግባር እየታየ ነው። አዲስ መዋቅር በተግባር ላይ ይዋል ከተባለ ይህንን አደጋ የሚያስወግድ መሆን አለበት እንጂ ያንኑ አጠናክሮ የሚያስቀጥል መሆን የለበትም። በተለይ በ2010 ዓ.ም እና በ2011 ዓ.ም የታዩትን ዓይነት ሁከቶች እንዲቀጥሉ ዕድል መክፈት የጤነኝነት ሊሆን አይችልም። የሊግ ጥራት የሚለካዉ የክለቦችን ቁጥር በመጨመር አይደለም። አካባቢያዊ እና ተቋማዊ የሆኑ መሠረታዊ ጥያቄዎችን የሊግ ውድድርን ችግር ሳያጠኑ ክለቦችን ወደ ፕሪሚየር ሊግ በማሳደግ ማምለጥ አይቻልም። ይህ ውሳኔ የፉክክር መርህን የሚጣረስ ፣ ክለቦች ለተዋረዳዊ ውድድር ያላቸውን ክብር እንዲዘነጉ የሚያስገድድም በመሆኑ ጊዜ ወስዶ ማየት ተገቢ ነው።አዲስ ዘመን መስከረም 17/2012 ቦጋለ አበበ | https://www.press.et/Ama/?p=19619 | 696 | 2ስፖርት
|
ቀነኒሳ በ2 ሰከንድ የማራቶን ክብረወሰን አመለጠው | ስፖርት | September 30, 2019 | 38 | የረጅም ርቀትና የአገር አቋራጭ ንጉሱ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ከረጅም ጊዜ ጉዳት ተመልሶ የማራቶን የዓለም ክብረወሰንን ለመስበር ተቃርቧል። ትናንት በተካሄደው የበርሊን ማራቶን ቀነኒሳ ርቀቱን 2፡01፡41 በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ በጀርመኗ መዲና ለሁለተኛ ጊዜ ነግሷል። ቀነኒሳ እ.አ.አ በ2016 የበርሊን ማራቶን ሲያሸንፍም የዓለም ሁለተኛውን ፈጣን ሰዓት አስመዝግቦ እንደነበረ ይታወሳል። ቀነኒሳ እ.አ.አ ለመጀመሪያ ጊዜ 2015 የፓሪስ ማራቶንን የቦታውን ክብረወሰን በማሻሻል ጭምር ካሸነፈ ወዲህ በርቀቱ ትልቅ ተስፋ የተጣለበት አትሌት ቢሆንም በተደጋጋሚ በሚገጥመው ጉዳት ውድድሮችን አቋርጦ ለመውጣት ሲገደድ ታይቷል። ለረጅም ጊዜ ከጉዳቱ ለማገገም ሲጥርም በርካታ ውድድሮች አምልጠውታል። ያምሆኖ ትናንት ከወደቀበት ተነስቶ ታሪክ መስራት እንደሚችል በማሳየቱ የዓለም መገናኛ ብዙኃንን ቀልብ ስቧል። በኳታር ዶሃ እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ኢትዮጵያ እስከ ትናንት ድረስ የጠበቀችውን ውጤት ማምጣት ባለመቻሏ ቅር የተሰኙ የስፖርት ቤተሰቦችም በቀነኒሳ ድል ተፅናንተዋል። በኬንያዊው ድንቅ አትሌት ኢሉድ ኪፕቾጌ ተይዞ የሚገኘው የዓለም የማራቶን ክብረወሰን 2፡01፡39 ሲሆን ይህን ክብረወሰን ሌላ አትሌት እንደማይደፍረው ሲነገር ቆይቷል። ቀነኒሳ በትናንቱ ውድድር ምናልባትም ውሃ አንስቶ ለመጠጣት ያባከናት ሽርፍራፊ ሰከንድ ዋጋ አስከፈለችው እንጂ ይህን ክብረወሰን ማሻሻል እንደሚችል አስመስክሯል። ከቀነኒሳ ጎን ለጎን የዘንድሮው የበርሊን ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የነገሱበት ሆኗል። ቀነኒሳን ተከትሎ ብርሃኑ ለገሰ 2:02:48 በሆነ የራሱ ምርጥ ሰዓት ሁለተኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ ሲሳይ ለማ በ2:03:36 ሰዓት ሦስተኛ ሆኗል። በሴቶች መካከል በተካሄደው ውድድርም ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል። እሸቴ በክሪ የኢትዮጵያን ክብረወሰን 2:20:14 በሆነ ሰዓት በማሻሻል ጭምር ቀዳሚ ሆና ስታጠናቅቅ የቀድሞ የዓለም ቻምፒዮኗ ማሬ ዲባባ 2:20:21 በሆነ ሰዓት ሁለተኛ ሆናለች። ኬንያዊቷ ሳሊ ቺፕየጎ 2:21:06 ሰዓት ሦስተኛ፣ ሔለን ቶላ በ2:21:36 ሰዓት አራተኛ ሆነው ውድድሩን ጨርሰዋል። በውድድሩ ትልቅ የአሸናፊነት ግምት ተሰጥቷት የነበረችው የቀድሞ የኦሊምፒክና የዓለም ቻምፒዮኗ አትሌት መሠረት ደፋር እስከ ሰላሳ ኪሎ ሜትር ገደማ ከመሪዎቹ ተርታ ሆና ብትታገልም ደረጃ ውስጥ ገብታ ማጠናቀቅ አልቻለችም።አዲስ ዘመን መስከረም 19/2012 ቦጋለ
አበበ | https://www.press.et/Ama/?p=19710 | 256 | 2ስፖርት
|
ከአስቆጪ ውጤት ጋር የተገኘች መፅናኛ | ስፖርት | September 30, 2019 | 35 | የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ከተጀመረ ዛሬ ሦስተኛ ቀኑን ይዟል። ኢትዮጵያ ትልቅ ውጤት የምትጠብቅበት የሴቶች አስር ሺ ሜትር ውድድር ከትናንት በስቲያ ምሽት ተካሂዶም በአትሌት ለተሰንበት ግደይ አማካኝነት የብር ሜዳሊያ ሊመዘገብ ችሏል። ቻምፒዮኗ አልማዝ አያና በመጨረሻ ሰዓት በጉዳት ምክንያት በውድድሩ መሳተፍ አለመቻሏን ተከትሎ ዓለማችን የርቀቱን አዲስ ቻምፒዮን በጉጉት ስትጠብቅ ነበር። ኢትዮጵያ በርቀቱ ብዙ ልምድ በሌላቸው አትሌቶች ለተሰንበት ግደይ፣ሰንበሬ ተፈሪና ነፃነት ጉደታ የተወከለች ቢሆንም የተለመደው የወርቅ ሜዳሊያ መመዝገብ አልቻለም። ይሁን እንጂ ወጣቷ አትሌት ለተሰንበት የወርቅ ሜዳሊያውን ለማጥለቅ ያደረገችው የአልሸነፍ ባይነት ትግል መፅናኛ የሆነውን የብር ሜዳሊያ ማምጣት ችሏል። በውድድሩ ከኢትዮጵያውያንና ከኬንያውያን አንፃር ብዙም የአሸናፊነት ግምት ያልተሰጣት ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ የኔዘርላንድስ አትሌት ሲፈን ሃሰን 30:17.33 በሆነ ሰዓት ማሸነፍ ችላለች። ከሦስቱ ኢትዮጵያውያን መካከል አንዷ የሆነችው ነፃነት ጉደታ ውድድሩን ባቋረጠችበት አጋጣሚ ሰንበሬ ተፈሪና ለተሰንበት ሌሎቹን ተፎካካሪዎች ለመቁረጥ ትልቅ ጥረት አድርገዋል። ሆኖም ሰንበሬ ወደ ኋላ በመቅረቷ ለተሰንበት በጊዜ ለመምራት ጥረት አድርጋለች። ይህም በውድድሩ መጨረሻ ዋጋ አስከፍሏት በሲፈን ሃሰን የወርቅ ሜዳሊያውን እንድትነጠቅ ምክንያት ሆኗል። ለተሰንበት ወርቁን ላለመነጠቅ ያደረገችው ጥረት አድናቆት ሳይቸረው የሚታለፍ አይደለም። ርቀቱን 30:21.23 በሆነ የራሷ ምርጥ ሰዓት ሁለተኛ በመሆን አጠናቃ ለአገሯ ያስመዘገበችው የብር ሜዳሊያም በቻምፒዮናው የመጀመሪያና ትልቅ ክብር የሚሰጠው ነው። በውድድሩ ትልቅ የአሸናፊነት ግምት አግኝታ የነበረችው ኬንያዊት ሔለን ኦቢሪ ጭምር ጠንካራ ተፎካካሪ መሆን ሲሳናት ታይቷል። ሆኖም የአገሯ ልጅ አግኒስ ቲሮፕ 30:25.20 በሆነ ሰዓት ሦስተኛ በማጠናቀቅ የነሐስ ሜዳሊያውን አጥልቃለች። ሰንበሬ ተፈሪ በስድስተኛነት ውድድሩን ፈፅማለች። ኔዘርላንድስ ለበርካታ ዓመታት ገንዘቧን በማፍሰስ ከሥልጠና ጀምሮ በተለያዩ መንገዶች ስታዘጋጃት የቆየችው አትሌቷ ሲፈን ሃሰን አሁን ፍሬ ማፍራት ችላለች። በአሰልጣኝና ሥልጠና ጋር በተያያዘ ሰፊ ክፍተቶች በኢትዮጵያውያን ዘንድ መኖሩንም ከውድድሩ ለመታዘብ ተችሏል። በርካታ የስፖርት ቤተሰቦችም የለተሰንበትን ጥረትና ያስመዘገበችውን የብር ሜዳሊያ በማድነቅ በርቀቱ የተለመደው የወርቅ ሜዳሊያ አልማዝና ጥሩነሽ ከሌሉ የለም ማለት ነው? በሚል ቅሬታቸውን በተለያዩ ማህበራዊ መገናኛ መረቦች ሲገልፁ ለመታዘብ ተችሏል። ከዚሁ ከዓለም ቻምፒዮና ጋር በተያያዘ በመጀመሪያው ቀን በተካሄደው የሴቶች የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያን የወከሉት ሹሬ ደምሴ፣ ሩቲ አጋና ሮዛ ደረጄ ሦስቱም ውድድሩን አቋርጠው መውጣታቸው ይታወሳል። በዶሃ ያለውን ከፍተኛ የሙቀት መጠንና ወበቅ ለመቀነስ ታስቦ ለመጀመሪያ ጊዜ በእኩለ ሌሊት የተካሄደው የማራቶን ውድድር ላይ ኢትዮጵያውያኑን ጨምሮ ሃያ ስምንት አትሌቶች አቋርጠው ለመውጣት ተገደዋል። ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ውድድሩን ማቋረጥ ብቻም ሳይሆን በመኪና ተጭነው እስከመሄድና ሆስፒታል እስከ መግባት እንደደረሱ በስፍራው ያሉ ታዛቢዎች ተመልክተዋል። ሆኖም ኬንያዊቷ ሩዝ ቺፕጌቲች አስቸጋሪውን ሙቀት ተቋቁማ የወርቅ ሜዳሊያ ማጥለቅ ችላለች። ያለፈው ቻምፒዮና አሸናፊዋ በትውልድ ኬንያዊ የሆነችው የባህሬን አትሌት ሩዝ ቺሌሞ ሁለተኛ ስትሆን ናሚቢያዊቷ ሄሌሊያ ጆሃንስ ሦስተኛ ሆና ጨርሳለች። ከኬንያውያን አትሌቶች ጋር ተፎካካሪና ተመጣጣኝ ብቃት እንዲሁም ፈጣን ሰዓቶችን ይዘው ወደ ውድድር የገቡት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የነበረውን ጫና ተቋቁመው እስከ ውድድሩ ግማሽ እንኳን መሄድ አለመቻላቸው በስፖርት ቤተሰቡ ዘንድ በርካታ ጥያቄዎችን እያስነሳ ይገኛል። ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከኬንያውያን ጋር ተመሳሳይ አቅም ያላቸው እንደመሆኑ ከሥልጠና ጋር ተያይዞ የሚመጣ ችግር ውድድሩን ለማቋረጥ እንዳስገደዳቸው የሚናገሩም በርካታ ናቸው። የአየር ፀባዩ ለሁሉም አትሌቶች እኩል እንደመሆኑ በሥልጠና ወቅት ውድድር ላይ ከሚኖረው የአየር ፀባይ ጋር ተመሳሳይ ወይም ተቀራራቢ ስፍራን መርጦ ዝግጅት ቢደረግ ይህ ሁሉ እንደማይከሰት ምክንያታዊ አስተያየት ያላቸውም የስፖርት ቤተሰቦች ጥቂት አይደሉም። አዲስ ዘመን መስከረም 19/2012 ቦጋለ
አበበ | https://www.press.et/Ama/?p=19706 | 443 | 2ስፖርት
|