headline
stringlengths
2
1.42k
category
stringclasses
6 values
date
stringlengths
9
35
views
stringlengths
1
7
article
stringlengths
63
36.2k
link
stringlengths
28
740
word_len
int64
16
6.74k
label
class label
6 classes
የመጀመሪያው የወርቅ ሜዳሊያ ተስፋዎች
ስፖርት
September 30, 2019
49
 ኢትዮጵያ በአትሌቲክስ ስፖርት በተለይ ከምትታወቅባቸውና ውጤታማም ከሆነችባቸው ርቀቶች መካከል ይጠቀሳል፤ 5ሺ ሜትር። ከሁለት ዓመታት በፊት በለንደን በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ኢትዮጵያ በአትሌት ሙክታር እንድሪስ አማካኝነት የርቀቱ ቻምፒዮን መሆኗ ይታወሳል። በቅርቡ በተጠናቀቀው የዳይመንድ ሊግ ውድድር ላይም በተመሳሳይ የዓለም ፈጣኑ ሰዓት የተመዘገበው በኢትዮጵያዊ አትሌት መሆኑ ይታወቃል። ይህም ከተጀመረ ዛሬ አራተኛ ቀኑን ባስቆጠረው የዶሃ ዓለም ቻምፒዮና ላይ የርቀቱን ቀዳሚ የአሸናፊነት ግምት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች እንዲያገኙ አድርጓል። በዚህ ውድድር ተጋባዥ ከሆነው ቻምፒዮኑ ሙክታር ባሻገር፤ ጥላሁን ኃይሌ፣ ሰለሞን ባረጋ፣ እንዲሁም አባዲ ሃዲስ አገራቸውን የሚወክሉ አትሌቶች ናቸው። ይሁን እንጂ አባዲ ሃዲስ ማጣሪያውን ማለፍ አልቻለም። ቀሪዎቹ አትሌቶች በግላቸው ያስመዘገቧቸው ሰዓቶች በርቀቱ ከሚሳተፉት አትሌቶች ሁሉ ፈጣን መሆኑ፤ የርቀቱ ክብር ዘንድሮም ከምሥራቅ አፍሪካውያኑ እጅ እንደማይወጣ ያመላከተ ሆኗል። በሦስት ቻምፒዮናዎች ላይ በተከታታይ መንገስ የቻለው እንግሊዛዊው አትሌት ሞ ፋራህ ዘመን ከማብቃቱ ጋር በተያያዘም ሜዳሊያው የኢትዮጵያውያን ስለመሆኑ ግምታቸውን የሚያስቀምጡም በርካታዎች ናቸው። ኢትዮጵያ በቻምፒዮናው እስካሁን ድረስ ወርቅ አለማስመዝገቧን ተከትሎም እነዚህ ወጣት አትሌቶች የመጀመሪያው የወርቅ ሜዳሊያ ተስፋ ሆነዋል። ሞ ፋራህን በመጨረሻው የመም ውድድሩ የረታው የዓለም ቻምፒዮኑ ሙክታር እድሪስ በዚህ ቻምፒዮና ላይ ተጋባዥ ቢሆንም በጉዳት ምክንያት በዛሬው ውድድር ተሳታፊ ላይሆን እንደሚችል ተገምቶ ነበር። ይሁን እንጂ ሙክታር ማጣሪያውን አልፎ ዛሬ በፍፃሜ ተፋላሚ እንደሚሆን አረጋግጧል። የሁለት ጀግና አትሌቶችን ስም አጣምሮ የያዘው ወጣቱ አትሌት ጥላሁን ኃይሌ በቀለ ለአሸናፊነት ከሚጠበቁት መካከል አንዱ ሲሆን፣ በሮም ዳይመንድ ሊግ ያስመዘገበው 12:52.98 የሆነ ሰዓት በዛሬው ውድድር ላይ የሚካፈሉት አትሌቶች ሁሉ ፈጣኑ ነው። በለንደኑ ቻምፒዮና በርቀቱ አምስተኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቀው ሌላኛው ወጣት አትሌት ሰለሞን ባረጋም በዚህ ውድድር የአሸናፊነት ቅድመ ግምት ያገኘ አትሌት ነው። አትሌቱ እአአ በ2018 ያስመዘገበው ፈጣን ሰዓት 12:43.02 ከርቀቱ ተሳታፊዎች ሁለተኛው ምርጥ ሰዓት ነው። ሰለሞን የዓለም ቻምፒዮና ተሳትፎው ይህ ሁለተኛው መሆኑ የተሻለ ልምድ እንደሚያስገኝለት የሚታመን ሲሆን፤ ለፈጣኑ ሰዓት ያለው ቅርበትም የወርቅ ሜዳሊያውን ለማጥለቅ የሚሮጥ ያሰኘዋል። ባህሬናዊው ብርሃኑ ባለው 12:56.26 ሰዓት በማስመዝገብ ኢትዮጵያውያኑን አትሌቶች የሚከተል ከመሆኑ ባሻገር ለኢትዮጵያውያኑ ፈተና እንደሚሆንባቸውም ይጠበቃል። ኮማንደር ቶሌራ ዲንቃ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የ5ሺ እና 10ሺ ሜትር አሰልጣኝ፤ ርቀቱ በዓለም ላይ ፈጣን ሰዓት ባላቸው አትሌቶች የተዋቀረ መሆኑን ይጠቁማሉ። አዳዲስና ጥሩ ሰዓት ያላቸው ወጣት አትሌቶች ተሳታፊ የሚሆኑበትም ነው። በተጨማሪም ሁሉም አትሌቶቹ በዓመቱ ዳይመንድ ሊግ ላይ ርቀቱን በደንብ የሸፈኑ አትሌቶች መሆናቸው ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ እንደሚረዳቸው በዝግጅታቸው ወቅት ለአዲስ ዘመን ገልጸዋል። በዓለም ቻምፒዮና በ5ሺ ሜትር የኢትዮጵያ ታሪክ እ.አ.አ 1991 ቶኪዮ ላይ ይጀምራል፤ በወቅቱ ፊጣ ባይሳ ኬንያዊውን አትሌት ተከትሎ በመግባት የብር ሜዳሊያ ነበር ያገኘው። ከሁለት ዓመታት በኋላም በስቱትጋርት ኃይሌ ገብረስላሴ እና ፊጣ ባይሳ ተከታትለው በመግባት የብርና የነሐስ ሜዳሊያ ተሸላሚዎች ሆነዋል። እ.አ.አ 2001 ኤድመንተን ላይ በተካሄደው ቻምፒዮና ሚሊዮን ወልዴ ሦስተኛውን የብር ሜዳሊያ እስካስመዘገበበት ጊዜ ድረስም ኢትዮጵያ በሦስት መድረኮች ከሜዳሊያ ሰንጠረዥ መግባት አልቻለችም ነበር። እ.አ.አ 2003 ቀነኒሳ በቀለ የነሐስ፣ ሄልሲንኪ በስለሺ ስህን የብር፣ በርሊን በቀነኒሳ የወርቅ፣ ዴጉ በደጀን ገብረመስቀል የነሐስ፣ ሞስኮ እና ቤጂንግ ሐጎስ ገብረሕይወት ብርና ነሐስ እንዲሁም ለንደን ላይ ሙክታር እድሪስ የወርቅ ሜዳሊያ ያጠለቁ አትሌቶች ናቸው። በርቀቱ ምሥራቅ አፍሪካዊቷ አገር ኬንያ በርካታ ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ ቀዳሚ ስትሆን፤ 14ሜዳሊያዎችን ወደ ካዝናዋ አስገብታለች። አምስት ሜዳሊያዎች ያሏት እንግሊዝ ደግሞ በወርቅ ሜዳሊያ ብዛት ሁለተኛ ስትሆን፤ በተከታይነት ኢትዮጵያ 2የወርቅ፣ 5የብር እና 4የነሐስ በጥቅሉ 11ሜዳሊያዎችን በወንድ አትሌቶች በማግኘት ሦስተኛ ስፍራ ላይ ተቀምጣለች። በዓለም ቻምፒዮናው የርቀቱ ክብረወሰን እ.አ.አ በ2003 የተመዘገበው 12:52.79 ሲሆን፤ ኬንያዊው አትሌት ኢሉድ ኪፕቾጌ ደግሞ የሰዓቱ ባለቤት ነው። ሌላው ዛሬ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚካፈሉበት ርቀት የ3ሺ ሜትር መሰናክል ሴቶች ምድብ ነው። ኢትዮጵያ በዚህ ውድድር እ.አ.አ 2013ቱ የሞስኮ ቻምፒዮና ነበር የነሐስ ሜዳሊያ በአትሌት ሶፊያ አሰፋ ያስመዘገበችው። ሶፊያ በዚህ ርቀት በ2012ቱ የለንደን ኦሊምፒክም ሦስተኛ የወጣች ቢሆንም፤ ቀድማት የገባችው አትሌት የአበረታች ቅመም ተጠቃሚነቷ በመረጋገጡ የብር ሜዳሊያውን ሶፊያ እንድትወስድ ተደርጓል። በዘንድሮው ቻምፒዮና ላይ አትሌት መቅደስ አበበ፣ ሎሚ ተፈራ፣ ዘርፌ ወንድምአገኝ እና አገሬ በላቸው ኢትዮጵያን ይወክላሉ። የ3ሺ ሜትር መሰናክል አሰልጣኝ ተሾመ ከበደ፤ አትሌቶቹ በራባት የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ላይ ተሳታፊ በመሆናቸው ረዘም ላለ ጊዜ በሳምንት ስድስት ቀን በቀን ደግሞ ለሁለት ጊዜ በዝግጅት ላይ መቆየታቸውን ተናግሯል። በሄንግሎ በተካሄደው የሰዓት ማሟያ ውድድር ላይ የተመዘገበው ጥሩ ሰዓት መሆኑን የጠቆሙት አሰልጣኙ፤ በርቀቱ ያለውን ታሪክ ለመቀየር ቡድኑ ወደ ዶሃ ያመራ መሆኑንም አስረድተዋል። በዚህ ርቀት ኬንያውያን አትሌቶች ስኬታማ ሲሆኑ ባትሬክ ቼፕኮች ደግሞ በለንደን ቻምፒዮን መሆኗ አይዘነጋም። አትሌቷ ከ2018 ጀምሮ በተሳተፈችባቸው 17 ውድድሮች 15ቱን ያሸነፈች ጠንካራ አትሌት ስትሆን፤ በተያዘው ዓመት ያስመዘገበችው 8:55.58 የሆነ ሰዓት ደግሞ ፈጣኑ ነው። 9:03.71ሰዓት ያላት ኖራህ ጀሩቶ በ3ሺ ሜትር መሰናክል የአሸናፊነት ግምት እንዲሁም ፈጣን ሰዓት ያላቸው ኬንያውያን አትሌቶች ሁለተኛዋ ናት። እ.አ.አ የ2015 ቻመፒዮኗ ሃይቪን ኪያንግ 9:03.83 በሆነ ሰዓት ሦስተኛዋ ፈጣን አትሌት ናት። ለንደን ላይ ቻምፒዮን የነበረችው አሜሪካዊቷ ኤማ ኮቡርን አራተኛው ፈጣን ሰዓት ያላት ስትሆን፤ ከኬንያውያኑ አትሌቶች ጋር ብርቱ ፉክክር እንደምታደርግም ይጠበቃል።አዲስ ዘመን  መስከረም 19/2012 ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=19713
675
2ስፖርት
የትግራይ ክልልን መልሶ ለመገንባት የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሲቪክ ማህበራት የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 9, 2020
5
በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ ፦ የትግራይ ክልልን መልሶ ለመገንባት በሚደረገው እንቅስቃሴ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ሲቪክ ማህበራት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ።ራሱን ተጋሩ የኢትዮጵያውያን ድርጅት ብሎ የሚጠራው የሲቪክ ተቋም፣ በትግራይ ወቅታዊና መጻኢ ጉዳዮች ዙሪያ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና የሲቪክ ማህበራት ጋር ትናንት ውይይት ባደረገበት ወቅት ፣የድርጅቱ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ዮሐንስ ጎይቶም በክልሉ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ግልፅ እና አሳታፊ ለማድረግ በማሰብ ውይይት ማድረግ ማስፈለጉን ገልጸዋል።ለውጡን ተከትሎ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮች እንዲፈቱ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትና ከማህበረሰቡ ጋር በመተባበር ችግሮቹ እንዲፈቱ እና አፋጣኝ መፍትሄ እንዲያገኙ ለማድረግ መሆኑንም አመልክተዋል።ከሃይማኖት አባቶች፣ ከሃገር ሽማግሌዎች፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች እና ዜጎችን ያካተተ የመማክርት ጉባኤ መቋቋም ስላለበት ለባለድርሻ አካላት ለማስገንዘብ መድረኩ መዘጋጀቱን ጠቁመዋል።የትግራይ ህዝብ በተጀመረው የለውጥ ጉዞ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ፍትህ እንዲቀዳጅ ተባብረን መስራት አለብን ብለዋል ።በውይይቱ ላይ የተገኙት የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ነብዩ ስሁል ሚካኤል በበኩላቸው፣ በትግራይ በሚደረገው መልሶ የማቋቋም ተግባር በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲ እና የሲቪክ ማህበራት የበኩላቸውን ለመወጣት እያደረጉ ያሉት እንቅስቃሴ የሚያበረታታ መሆኑን አስታውቀዋል።የሲቪክ ማህበራትም በቀጣይ በክልሉ በሚደረጉ የለውጥ ጎዞዎች የበኩላቸውን መወጣት እንዳለባቸው ገልፀው ፣ፓርቲውም ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ዶክተር አረጋዊ በርሄ በበኩላቸው፣ የህወሓት ጁንታ በትግራይ ክልል ለሶስት አስርት አመታት ያደረሰውን ችግር መፍታት የሚቻለው ተቀራርቦ በመነጋገር መሆኑን ጠቁመዋል።የትግራይን ህዝብ ችግር መፍታት የሚቻለው የፖለቲካ ፓርቲ በማቋቋም ብቻ ሳይሆን የሲቪክ ማህበራትንም በማደራጀት እንደሆነ አመልክተዋል።አዲስ ዘመን ህዳር 30/2013
https://www.press.et/Ama/?p=36994
202
0ሀገር አቀፍ ዜና
የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት 23 የጸረ-ሰላም ኃይሎች ላይ እርምጃ ወሰደ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 9, 2020
14
በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ ፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን 23 የጸረ ሠላም ኃይሎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የዞኑ ኮማንድ ፖስት አስታወቀ።የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ኮሎኔል አያሌው በየነኝ ጠቅሶ እንዳስታወቀው ፣ በዞኑ ዳንጉር ወረዳ ልዩ ስሙ ቁጥር 3 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሠላምን ሲያውኩ በነበሩ ኃይሎች ላይ በተወሰደው እርምጃ 23 ጸረ-ሠላም ኃይሎች ተደምስሰዋል ።የመከላከያ ሠራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስና የክልሉ የጸጥታ አካላት በወሰዱት እርምጃ ከተደመሰሱት የጸረ-ሠላም ኃይሎች በተጨማሪ ለጥፋት ሲጠቀሙበት የነበረ ሶስት የጦር መሣሪያ በቁጥጥር ስር ውሏል።በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው የጥፋት ቡድን በሠላማዊ መንገድ እጅ እንዲሰጥ በክልሉ መንግሥት ጥሪ መቅረቡን ያስታወሱት ኮሎኔል አያሌው ፣ በተሰጣቸው እድል መጠቀም ካልቻሉ በዋናው ጁንታ ላይ የተወሰደው አይነት የማያዳግም እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።ህብረተሰቡም እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ የአካባቢውን ሠላም በተደራጀ መንገድ በመጠበቅ ረገድ የጀመረውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል ።አዲስ ዘመን ህዳር 30/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37000
130
0ሀገር አቀፍ ዜና
የኤሊዳአር በልሆ የመካከለኛ መስመር የኤሌክትሪክ ዝርጋታ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 9, 2020
14
በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ ፦ የኤሊዳአር በልሆ ወረዳ የመካከለኛ መስመር የኤሌክትሪክ ዝርጋታ ተጠናቆ ተመረቀ፡፡ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ፣ የኤሊዳአር በልሆ ወረዳ የመካከለኛ መስመር የኤሌክትሪክ ዝርጋታ ተጠናቆ ተመርቋል ፤በቅርቡ ስራ ይጀምራል ፡፡የጋላፊ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ አብዱ አሊ በምረቃው ወቅት ፣ፕሮጀክቱ ተጠናቆ አገልግሎት ላይ መዋሉ ለጉምሩክና ኢሚግሬሽን አገልግሎት የላቀ ጥቅም ይሰጣል ብለዋል። ከዚህ በፊት የጉምሩክና ኢሚግሬሽን አገልግሎት ሥራዎች በጄኔሬተር ይሰጥ እንደነበር አስታውሰው ÷ ስራዎችን በተያዘለት ጊዜና በተገቢው መንገድ ለማከናወን ይቸገሩ እንደነበር አመልክተዋል፡፡የፕሮጀክቱ መጠናቀቁ ስራዎቻቸውን በተቀላጠፈ መልኩ ለማከናወን እንደሚረዳቸውም ጠቁመዋል፡፡የኤሊዳአር ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የአቅም ግንባታ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብደላ ሱሌ በበኩላቸው አገልግሎቱ በወረዳዋ የኢኮኖሚ መነቃቃት እና ለወጣቶችም የስራ እድል እንደሚፈጥር አስታውቀዋል፡፡በምርቃቱ ላይ የተገኙት የአፋር ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ስራ አስፈፃሚ አቶ ያሲን አሊ ፣ ፕሮጀክቱ በተያዘለት በጀትና በሚፈለገው ጊዜ መጠናቀቁ ለስራው መቀላጠፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው አስታውቀዋል።የኤሌክትሪክ መስመሩ ኢትዮጵያ በጅቡቲ ድንበር ከምትጠቀምባቸው ወደቦች አንዱ የሆነው የታጁራ ወደብ ምስረታ ጋር ተያይዞ የተዘረጋ ነው ፡፡አዲስ ዘመን ህዳር 30/2013
https://www.press.et/Ama/?p=36987
148
0ሀገር አቀፍ ዜና
በመከላከያ የተጋድሎ ጀብድ፤ በጋዜጠኞች የጦር ሜዳ ምስክርነት የደመቀው መድረክ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 9, 2020
35
ግርማ መንግሥቴአዲስ አበባ፡- በእብሪተኛው የህወሓት ጁንታ ቡድን ምክንያት ተገድዶ ወደ ሕግ ማስከበር እርምጃ የገባው የመከላከያ ሰራዊት ያስመዘገበው ድል እና የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች በየግንባሩ በመሰለፍ ላበረከቱት አስተዋፅኦ የተዘጋጀ መድረክ በመከላከያ የተጋድሎ ጀብድ፤ በጋዜጠኞች የጦር ሜዳ ምስክርነት የደመቀ ሆኖ አልፏል።የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት 80ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በማስመልከት “በሕግ ማስከበር ዘመቻ በግንባር ለተሰለፉ የሚዲያ ባለሙያዎች የተዘጋጀ የእውቅናና የውይይት መድረክ” በሚል መሪ ሀሳብ በትናንትናው ዕለት በካፒታል የእውቅናና ውይይት መርሐ ግብር አካሂዷል፡፡ በመርሃ ግብሩ ላይ እንደተገለፀው፤ ከመከላከያ ሰራዊታችን ጎን በመሰለፍ ወቅታዊ መረጃን ለሕዝብ በማድረስ በኩል ከፍተኛ ሙያዊ ኃላፊነታቸውን ሲወጡ ለቆዩ የተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት ጋዜጠኞች የእውቅናና የምስክር ወረቀት ሽልማት የተሰጠ ሲሆን፤ የመከላከያ ሰራዊቱም የሕግ ማስከበርና ህልውናንና ሉዓላዊነትን የማስቀጠል ኃላፊነቱን በብቃት የመወጣቱ ተግባር የልእልናው እና የአገራችን ከፍታ ማሳያ መሆኑ በመርሃ ግብሩ ላይ ተገልጿል፡፡በመርሐግብሩ ላይ በመገኘት ሽልማቱን የሰጡት የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ቃል አቀባይ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እንደ ተናገሩት፤ መከላከያ ሰራዊቱ ተገዶ ወደ እዚህ አይነቱ ውጊያ የገባ ቢሆንም አስፈላጊውን መስዋዕትነት ሁሉ ከፍሎ የሕግ የበላይነትን አስከብሯል፤ የአገር ሉዓላዊነትንና ማንነትን አስጠብቋል። በዚህም ሊኮራና ሊመሰገን ይገባዋል፡፡መከላከያ ሰራዊታችን በከፈለው ከፍተኛ መስዋዕትነት የሰራዊታችን ብቻ ሳይሆን የአገራችንና ሕዝባችን ሞራልና ክብር በከፍተኛ ደረጃ ከፍ ብሏል ያሉት አምባሳደር ሬድዋን፤ ከመከላከያ ጋር በመሰለፍ መረጃን በፍጥነት ተደራሽ ሲያደርጉ የነበሩና በመድረኩ እውቅናና ሽልማትን ላገኙ ጋዜጠኞችንም እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።በጁንታው ላይ የተገኘው ድል ከፍተኛ ቢሆንም በዚህ ብቻ ልንዘናጋ አይገባም የሚሉት አምባሳደሩ፤ ወደ ፊት ገና ብዙ የሚቀሩን ስራዎች አሉና ለእነሱም እንደዚሁ ከወዲሁ ልንዘጋጅ እንደሚገባም ተናግረዋል።ሌላውና በመድረኩ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡት ሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ሲሆኑ፤ በወቅቱም፣ “ይህ ድል ከህፃናት ጀምሮ እስከ አዋቂዎች ድረስ ከፍተኛ ስሜትንና አንድነትን የፈጠረ፤ የሰራዊታችን፣ ህዝባችንና አገራችን የድምቀትና ልእልና ጫፍ ላይ ያደረሰ ስለሆነ ከዚህ እንዳይወርድ፤ ፖለቲከኞቻችንም፣ አክቲቪስቶቻችን ሁሉም ከዚህ በኋላ ወደ መንደር፣ ወደ ጠባብ አስተሳሰብ እንዳታወርዱን አደራ” በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። በእውቅናና ውይይት መድረኩ ላይ ጋዜጠኞችና የመከላከያ ሰራዊት አባላት ተወካዮች ያጋጠሟቸውን የጦር ሜዳ አሳዛኝ፣ አስደናቂ፣ አስደማሚ፣ አሳፋሪ የጁንታውን ተግባራትን ያቀረቡ ሲሆን፤ መድረኩ እጅግ አሳዛኝ፣ አስተማሪና ታሪካዊ ሆኖ ለማለፍ በቅቷል።የመርሐ ግብሩ አዘጋጅ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጌትነት ታደሰ በበኩላቸው እንደገለጹት፤ ይህን መድረክ ማዘጋጀት ያስፈለገው የጥፋት ኃይሉ ባደረሰው አገር የማፍረስና ሉዓላዊነትን የማጥፋት ተግባርን የመከተውን ሰራዊታችንና ከጎኑ የተሰለፉ ጋዜጠኞችን በማመስገን እውቅናና የምስክር ወረቀት ለመስጠት በማሰብ ሲሆን፤ ይህም የድርጅቱን 80ኛ ዓመት በምናከብርበት በዚህ ወቅት እንደመሆኑ መሰል መርሀ ግብሮች የሚቀጥሉ ይሆናል።በፕሮግራሙ ላይ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን፤ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት በጦር ሜዳ ለተሰው ጋዜጠኞች፤ ፎቶ ጋዜጠኛ ዘውዱ ጥላሁን ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት፣ ሀይሉ ለገሰ እና ዋሲሁን ገብረ ሚካኤል ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ታውሰዋል።አዲስ ዘመን ህዳር 30/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37004
385
0ሀገር አቀፍ ዜና
«የጥፋት ኃይሉ ዕድሜ ልኩን ሽብር ሲሰራ፣ ጥሩ ጥሩ ነገሮችን ሲያወድም የኖረ ነው » ረዳት ፕሮፌሰር አንተነህ ሙሉ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 10, 2020
20
ግርማ መንግሥቴ አዲስ አበባ፡- የህወሓት የጥፋት ኃይል ዕድሜ ልኩን ሽብር ሲሰራ፣ ጥሩ ጥሩ ነገሮችን ሲያወድም የኖረ መሆኑን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ምሁር የሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር አንተነህ ሙሉ አስታወቁ። ረዳት ፕሮፌሰር አንተነህ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለፁት፣ የጥፋት ኃይሉ ዕድሜ ልኩን ሽብር ሲሰራ፣ ጥሩ ጥሩ ነገሮችን ሲያወድም የኖረ ቡድን በመሆኑ ሕግና ሕጋዊ አካሄዶች በሙሉ አይጥሙትም። እሱ እየተመራ ያለው ባረጀና ባፈጀ አስተሳሰብ በመሆኑ ለአዳዲስ አስተሳሰብና አሠራር ፍፁም ዝግ ነው። በዚህም ነው ወደ እንደዚህ ዓይነት ጥፋት ውስጥ ሁሉ ሊገባ የቻለው። ቡድኑ ከጠ/ሚ አብይ ወደ ስልጣን መምጣት ወቅት ጀምሮ ምንም ዓይነት ምቾት ተሰምቶት አያውቅም የሚሉት ረዳት ፕሮፌሰር አንተነህ፣ እሳቸው ወደ ስልጣን ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ የጥፋት ኃይሉ ሲሰራ የቆየው የሽብር ተግባር ብቻ መሆኑንም አመልክተዋል። እንደ ረዳት ፕሮፌሰር አንተነህ ከሆነ፣ ቡድኑ ወደ መቀሌ ሄዶ ከመሸገ ወዲህ ሲያከናውናቸው የነበሩ ተግባራት ሁሉ ሕገወጥና ከፌዴራል ሥርዓቱ ያፈነገጡ ናቸው። ከእነዚህ ተግባራት እንዲቆጠብ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ጀምሮ በሁሉም አካል ቢመከርና የተለያዩ ዕድሎች ቢሰጡትም በፍፁም የሚገባው እና ወደ ትክክለኛና ሕጋዊ መስመር ለመግባት ፈቃደኛ አይደለም። ቡድኑ ለራሱ ባለው እጅግ የገዘፈና እኔ ብቻ ነኝ አዋቂ የሚል ስሜት እራሱን ችግር ውስጥ መክተቱን ጠቁመው፣ ይህ ለራሱ የነበረው የተሳሳተ አመለካከት የተሰጡትን ብዙ ዕድሎች እንዳይጠቀምባቸው አድርጎታል ብለዋል። ጁንታው በዶክተር አብይ የሚመራው የፌዴራል መንግሥት የሚሰራቸውን ጥሩ ጥሩ ሥራዎች ሁሉ በማደናቀፍ፣ በማጣጣልና በማንኳሰስ ሥራ ላይ ተጠምዶ ነው የቆየው የሚሉት ረዳት ፕሮፌሰር አንተነህ፤ ሕግና ሕግን ተከትሎ ወደ መስመር መግባት የሚፈልግ ቡድን እንዳልሆነና ወደ መስመር እንዲገባም መንግሥት እየወሰደ ያለው የሕግ የበላይነትን የማስከበር እርምጃ ተገቢ መሆኑንም ተናግረዋል። ሕጋዊ ያልሆነ ምርጫ፣ ሕጋዊ ያልሆነ ካቢኔ ምስረታ እና ሌሎች ሕጋዊ ያልሆኑ ሥራዎችን ሁሉ ሲሰራ በሂደት ወደ ሕጋዊነት ይመለሳል ተብሎ ቢጠበቅም ጭራሽ እያበላሸና እየባሰበት መሄዱን፤ አሰቃቂና ዘግናኝ ተግባሩም መከላከያ ሰራዊቱን እስከ ማጥቃት መዝለቁን የሚናገሩት ረዳት ፕሮፌሰሩ፤ ይህም ሊሆን የቻለው ቡድኑ ለራሱ ሰጥቶት ከነበረው ሁሉ አወቅነት ደረጃና ይህም በፈጠረው እብሪቱ ምክንያት እንደሆነም አስታውቀዋል። የውጭ ጣልቃ ገብነትን በተመለከተም ቡድኑ የአንድ ክልል አስተዳደር ነው፤ ያ ክልል ደግሞ በፌዴራል መንግሥት ስር ነው። በመሆኑም ሊተዳደርም ሆነ ወደ ሕጋዊ መስመር ሊመጣ የሚገባው በፌዴራል መንግሥቱ አማካኝነት ነው እንጂ በሌላ ጣልቃ ገብ አካል ባለመሆኑ መንግሥት በዚህ በኩል የወሰደው አቋም የሚደነቅ እንደሆነ አስታውቀዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 1/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37041
319
0ሀገር አቀፍ ዜና
ብርጋዴር ጀኔራል አዳምነህ መንግስቴን ጨምሮ 1 ሺ ያህል የሰሜንእዝ መስመራዊና ከፍተኛ መኮንኖች ተለቀቁ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 10, 2020
16
 አዲስ አበባ (ኢዜአ)፡- የህወሓት ጁንታ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ለግብዣ በሚል ጠርቶ አግቷቸው ከነበሩት የሰሜን ዕዝ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽን ብርጋዴር ጀኔራል አዳምነህ መንግስቴን ጨምሮ 1 ሺ ያህል የሰሜን ዕዝ መስመራዊና ከፍተኛ መኮንኖችን የአገር መከላከያ ሰራዊትና የፌዴራል ፖሊስ አባላት በሰሩት የጋራ አሰሳ አስለቀቁ። የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር መሐመድ ተሰማ ትናንት እንደገለጹት፤ የህወሓት ጁንታ ጥቅምት 24 ቀን ምሽት ላይ የእራት ግብዣ ብሎ ከጠራ በኋላ አፍኖ በመውሰድ አግቷቸው ቆይቷል።የጁንታው ኃይል መስመራዊና ከፍተኛ መኮንኖቹን በሸሸበት ቦታ ሁሉ ይዟቸው ሲጓዝ ቆይቶ በቀድሞው የትጥቅ ትግል ወቅት የማዘዣ ቤዝ በነበረው አዴት በሚባል ቦታ አግቷቸው እንደነበር አመልክተው፣ የጁንታው ታጣቂ ኃይል መስመራዊና ከፍተኛ መኮንኖቹን በዚያ አካባቢ መደበቁ በአሰሳና በጥናት እንደተደረሰበት አስታውቀዋል።የአገር መከላከያ ሰራዊትና የፌዴራል ፖሊስ ባደረጉት የጋራ አሰሳ እና እርምጃ መስመራዊና ከፍተኛ መኮንኖቹ ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው ከጁንታው ማስለቀቅ መቻላቸውን ገልጸዋል።ሰራዊቱ ያስለቀቃቸው 1 ሺህ ያክል የመስመራዊና ከፍተኛ መኮንኖች አሁን ላይ ሰራዊቱን መቀላቀላቸውን ሜጀር ጀኔራል መሀመድ ጠቁመዋል። ሰራዊቱ ከጁንታው ካስለቀቃቸው መካከል የሰሜን ዕዝ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽን ብርጋዴር ጀኔራል አዳምነህ መንግስቴም አመልክተዋል።የጁንታውን አባላት የማደን ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን የገለጹት ሜጀር ጀኔራል መሀመድ፣ የመጨረሻ ምዕራፍ በሆነው ወንጀለኞችን የማደንና የመልሶ ግንባታ ምዕራፍ የተደበቀውን ጁንታ አስሶ የመያዙ ሥራ በመከላከያ ሰራዊትና በፌዴራል ፖሊስ የጋራ ቅንጅት ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል። ወደፊትም የጁንታውን ቡድንና ወንጀለኞቸን ለሕግ የማቅረብና የማደን ሥራ ውጤት በየጊዜው ለሕዝብ እንደሚገለፅ አስታውቀዋል፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 1/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37040
198
0ሀገር አቀፍ ዜና
ሕዝቦች ትናንት በአንድነት ለአንድ ሀገር መሰረት መጣላቸው ዛሬ ሀገር አፍራሽ የሆነን ቡድን መመከት እንዳስቻላቸው ተጠቆመ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 9, 2020
6
 ሞገስ ጸጋዬአዲስ አበባ፡- ሕዝቦች ትናንት በአንድነት ለአንድ ሀገር መሰረት መጣላቸው ዛሬ ሀገር አፍራሽ የሆነ ቡድንን መመከት እንዳስቻላቸው አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች አስታወቁ::መንግስት ሕግ ለማስከበር በወሰደው ስኬታማ እርምጃ ዙሪያ ያነጋገርናቸው በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ነዋሪ የሆኑት አቶ አያሌው አስናቀ፤ በሌሎች ሀገራት ታጥቀው ጫካ የገቡ ቡድኖችን ትጥቅ ለማስፈታት ብዙ እየደከሙ እንደማይሳካላቸው ገልጸው፣ በአገራችን ግን ለሀያ ሰባት ዓመታት ያክል መንግስት ሆኖ በሕዝብ ሀብት ጡንቻውን ያፈረጠመውን የህዋሓት ጁንታ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በሕዝቦች አንድነት መደምሰሱ እጅግ የሚያኮራ ተግባር መሆኑን አስታውቀዋል::በአድዋ ላይ ትናንት የታየው ሀገራዊ አንድነት ጀግንነት ዛሬም ጁንታው በሀገር አንድነትና በሀገር ህልውና ላይ የደቀነውን አደጋ በመቀልበስ ዳግም መታየቱን ጠቁመው፣ ምንም እንኳ ጥቃቅን የውስጥ ችግሮች ቢኖሩብንም እነዚህ ችግሮች ከሀገር በላይ የሚሆኑ እንዳልሆኑ አመልክተዋል:: ጁንታው ሀገር ለማፍረስ ኃይል እና መሳሪያ አደራጅቶ እንደመነሳቱ ፣ ችግሩ ብዙ ኪሳራ ሳይደርስብን መመከት መቻሉ እድለኞች ነን ብለዋል ። የትግራይን ሕዝብ ጨምሮ መላው ሕዝብ የጁንታውን ድርጊት በማውገዝ ለሰራዊቱ ያሳየው ድጋፍ ቡድኑ እንዳሰበው ግጭቱ ወደ ሕዝብ እንዳይወርድ አድርጎታል ፤እንዳሰበው ቢሆንለት ኖሮ ችግሩ ለሀገሪቱ ከባድ ፈተና ሆኖ እንደነበር አመልክተዋል::አቶ አያሌው እንዳሉት፣ጁንታው በተሳሳተ ግንዛቤ የሕዝቡ አንድነት እንዲሸረሸር እና መንግሥት ላይ እምነት እንዳይኖረው ለማድረግ ብዙ ሰርቷል ።የለውጥ ኃይሉ ለብሔር ብሔረሰቦች ስጋት ነው በማለት ሆን ብሎ የብሔር ግጭት ለመፍጠር ሲሰራ ቆይተዋል። እውነታው ግን እሱ እንደሚለው ሳይሆን ሕዝቦች ይበልጥ ወንድማማችነታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ የሚያግዝ ነው ::ሌላኛው አስተያየት ሰጭ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የግዥ ባለሙያ የሆነው ወጣት አብነት ነጋ በበኩሉ ፣ የህወሓት ጁንታ ጊዜ ወስዶ እንደመደራጀቱ ሕዝቡ በአንድነት ባይቆም ኑሮ ያሰበው ይሳካለት ነበር ብለዋል ::‹‹በርግጥ ሀገራችን በርካታ ጊዜ ብዙ ፈተናዎች አጋጥመዋት በሕዝቦችዋ የተባበረ ክንድ ፈተናዎችን መመከት መሻገር ችላለች›› ያለው አስተያየት ሰጭው፣ ሕዝቡ ከሰፈሬ ውጣልኝ ማለቱን ትቶ የችግሮቻችን ሁሉ ምንጭ የሆነውን የህወሓትን ጁንታ በተባበረ ክንዱ ማስወገድ እንዳለበት አመልክቷል ::ዜጎች ወደፊትም በጋራ በመቆም ከመሰል ችግሮች ሀገሩን መጠበቅ እንዳለበት ያስታወቀው ወጣት አብነት ፣ መንግሥትም እንደ ሀገር የተዛቡ ነገሮችን በማስተካከል የሕዝቡ አንድነት የሚጠናከርበትን መንገድ ለማምጣት በርካታ ስራዎችን ሊሰራ ይገባል ብሏል::በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ የወረዳ ስምንት ነዋሪ ምስላቸውን ለመስጠት ፍቃደኛ ያልሆኑት አስተያየት ሰጭ ወይዘሮ በለጡ አሞኘ በበኩላቸው፣ሕዝቡ አሁንም ወደፊትም አንድ ነው::በጋራ በመቆሙ ሀገራችንን ከጠላትና ከአፍራሽ ቡድን ታድጓታል::ወደፊትም አንድነቱን አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል::የተማረውም ያልተማረውም ከመከፋፈል አስተሳሰብ ተላቆ በጋራ በመቆም ሀገራችንን ወደ ምትለማበት ጎዳና መምራት ያስፈልጋል ብለዋል::አዲስ ዘመን ህዳር 30/2013
https://www.press.et/Ama/?p=36993
332
0ሀገር አቀፍ ዜና
ብሶት የወለደው መፍትሄ በሌላ ፈተና
ስፖርት
September 17, 2019
31
 ትውልዷ በደቡብ አፍሪካ ሊምፖፖ ግዛት ውስጥ በምትገኝ አነስተኛ መንደር ውስጥ ነው። በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ በሚገኙት ቤተሰቦቿ ውስጥ አራተኛ ልጅ በመሆን እኤአ በ1991 ይህቺን ዓለም ተቀላቀለች፣ ካስተር ሰሜንያ፤ በዓለማችን በ800 ሜትር ንግስት ናት።የዓለማችን ትልቁ መድረክ በሚባለው በኦሎምፒክ ከአንድም ሁለት ጊዜ አሸናፊ ሆናለች። ከበርሊን ከጀመረ ድል አንስቶ በዓለም ሻምፒዮና ላይ ለሶስት ጊዜያት በርቀቱ ማሸነፏ ስሟን በጀግኖች ሰገነት ላይ ከፍ ብሎ እንዲጻፍ አድርጋለች። በውድድር መድረኮች ላይ የምታስመዘግበው ድል በርቀቱ ከፍ ያለ ቦታ፣ አክብሮት፣ አድናቆትና ተወዳጅነት እንድትጎናጸፍ አስችሏታል። በትምህርት ቤት እግር ኳስን ከወንዶች ጋር በመጫወት ወደ አትሌቲክሱ የገባችው ሰሜንያ፣ በእግር ኳስ ሜዳ የምታሳየው ብቃት በተለይ ፈጣን ሩጫ ወደ አትሌቲክስ ስፖርት አቅጣጫዋን እንድትቀይር ምክንያት እንደሆናትም ይነገራል። የተፈጥሮ ልግስና ሆነና ተባእታዊ የሰውነት አቋም ያላት አትሌቷ የሚወዷትና የሚያደንቋት ‹‹ኮብራ›› በሚል ቅጽል ስም የሚጠራት በርካታ ናቸው። በእያንዳንዱ መድረክ ለተወዳዳሪዎቿ በእጅጉ አደገኛና ፈታኝ መሆኗ ይሄንኑ ስያሜ እንዲሰጣት ምክንያት ስለመሆኑ ይመሰክራል።በተለይ በ2009ኙ የዓለም ሻምፒዮና በ800 ሜትር ወርቅ ሜዳልያ መውሰዷን ተከትሎ አነጋጋሪ ሆና ከመቅረቧ በላይ ጾታዋን መሰረት ያደረጉ ጥያቄዎች እንዲነሱ ምክንያት ሆኗል። በዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ተቀናቃኞቿ መሸነፍ ሲሰለቻቸው፣ አትሌቷ እንደ ሴት መቆጠር እንደሌለባት በመጥቀስ ሙገት ሲገጥሟት እና ድሏን ሲያራክሱ ቆይተዋል። በእርግጥ የሰሜንያ ፆታ መለያ ይህን ዓለም ከተቀላቀለች አነስቶ ሴት ስለመሆኗ ይመሰክራል። በህግ የሚታወቀው ይህ ነው። ይሁንና የአትሌቷ የ‹‹ቴስቶስትሮን›› መጠን አንድ ሴት ሊኖራት ከሚችለው ከፍ ያለ ስለመሆኑ ይታመናል። ይህ መሆኑ ደግሞ ለዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን /አይኤኤፍ/ አልተዋጠለትም። እንደ ፌዴሬሽኑ እምነት ‹‹ቴስቶስትሮን›› ለሴት ሯጮች ከፍተኛ ጉልበት ስለሚሆን ይህ ሆርሞን በከፍተኛ መጠን ያላቸው እንደ ሰሜንያ ያሉ ሴት ሯጮች በውድድር ፍትሃዊ ያልሆነ ብልጫ ያሳያሉ። በመሆኑም በሴት ሯጮች የቴስቶስትሮን መጠን በመድኃኒት መገደብ አለበት። እናም እርሷንና ሌሎቹ አትሌቶች በውስጣቸው ያለው የቴስቴስትሮን ሆርሞን መጠን በሕክምና እንዲቀነስ ተደርጎ እንዲወዳደሩ ወይም ወደ ሌላ ርቀት እንዲቀይሩ የሚያዘውን ህግ አውጥቷል። ይህን ተከትሎም ሰሜንያ ሕጉን ተገቢነት የለውም እንደ ተፈጥሮዬ እንዳልሆን የሚያደርግ ነው ስትልም ተከራክራለች። ጉዳዩን ወደ ዓለም አቀፉ የስፖርት የግልግል ዳኝነት (ካስ) ወስዳዋለች። ፍርድ ቤቱ ውሳኔው አድሏዊነት ያለው ነው ቢልም የፌዴሬሽኑን ውሳኔ ግን ለሌሎች ሴት ሯጮች ውድድሮች ፍትሃዊ እንዲሆኑ ከማድረግ አንፃር አስፈላጊ፤ ምክንያታዊና ሚዛናዊ ነው ሲል ገልጾታል። ይህን ውሳኔ ተከትሎ ሰሜንያ በሰጠችው አስተያየት «በመስኩ በጣም ምርጧ ነኝ፣ የዓለም ምርጥ ሆነህ ስትገኝ ሰዎች የምታደርገውን ነገር ሁሉ ይከታተላሉ፣» እኔ ችግር የሆንኩትም ስኬታማና ልሸንፍላቸው ስላልቻልኩ ነው፣ ዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ላለፉት አስር ዓመታት ፍጥነቴን ለመግታት ሞክሯል፣ ተግባሩ ግን እንዲያውም ጠንካራ አደረገኝ›› ስትል ተደምጣለች። በእራሷ ላይ የተላለፈው ፍርድ ውሳኔም እንደማያንበረክካት አስረግጣ ተናግራለች። በፍርድ ቤቱ የተሰጠው ውሳኔ እርሷንና አድናቂዎቿን በእጅጉ ያሳዘነና የተፈጥሮን ልግስና በእጅጉ የካደ መሆኑን በስፋት ተነግሯል። የስፖርት ባለሙያዎችም መድሃኒቱን በመውሰድ የሚከሰቱ ጉዳቶች አሉ። ከእነዚህም አንዱ ቅጥ ያጣ ያልተፈለገ ውፍረት እንዲሁም፣ ራስ ምታትና፣ በሆድ አካባቢ የሚከሰት ህመም ሊከሰት ይችላል›› ሲሉ ተደምጠዋል። ይህን የባለሙያዎች አስተያየት ከግምት የምታስገባው አትሌት ሰሜንያ ደግሞ መሰል የጎንዮሽ ጉዳት እንዳለው የሚታመነው አዲሱ ህግ ከስኬቷ ለማስቆም የተረቀቀ እንደሆነ በማስረገጥ ትናገራለች። የቴስቴስትሮን ሆርሞን ለመቀነስ ፈፅሚ የተባለችውን እምቢ በማለቷ በታላላቅ የአትሌቲክስ መድረኮች እንዳትሳተፍ እግድ ተላልፎባታል። በ800 ሜትር ለሃገሯ ደቡብ አፍሪካ ሶስት ጊዜ ወርቅ ያመጣችው ሰሜኒያ፣ በዚህ ወር ዶሃ ላይ በሚካሄደው ውድድር ላይ አለመሳተፏ እርግጥ ሆኗል። በዚህ መልክ ‹‹ለሴት አትሌቶች ከሚፈቀደው በላይ የቴስቴስትሮን ሆርሞን በውስጧ አለ›› በመባሉ ከአትሌቲክሱ የተገለለችውና በስፖርቱ ብዙ ርቀት የመጓዝ አቅም የነበራት የ28 ዓመቷ ሰሜኒያ፣ ፍርዱን በመቀልበስ የደቡብ አፍሪካን እንዲሁም ለዓለም ወጣት ሴቶችና ሯጮች ምሳሌ እንደምትሆን ቢጠበቅም፣ ከሰሞኑ ከሩጫው ዓለም ወደ እግር ኳሱ ዘርፍ ጎራ ማለቷ ታውቋል። ተቀማጭነቱን ደቡብ አፍሪካ ጓተንግ ያደረገውን ጄቪደብሊው /JVW/ የተሰኘ የሴቶች እግር ኳስ ቡድንን በመቀላቀል ሥልጠና እየወሰደች ስለመሆኑም ተሰምቷል። ቡድኑ ከስድስት ዓመታት በፊት በደቡብ አፍሪካ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን አምበል ጃናይን ቫን ውይክ የተቋቋመ ሲሆን፤ ዓላማው ሴት እግር ኳስ ተጨዋቾችን መመልመል፣ ማጎልበት እና ብቃት ያላቸውን ተጨዋቾች ማፍራት ነው። ሰማኒያ ቡድኑን ከተቀላቀለች በኋላ ቡድኑ በድረ ገፅ ላይ፤ “በአዲሱ ጉዞዬ እቀጥላለሁ፤ ቡድኑ ያሳየኝን ፍቅርና ያደረገልኝን ድጋፍ አደንቃለሁ” የሚለውን አስተያየቷን አስፍሮታል። የቡድኑ መስራች ጃናይን ቫን ውይክ፤ “ሰሜኒያ በሩጫው ፈፅሞ ተስፋ አልቆረጠችም” ብለዋል። አሁን ላይ እረፍት ላይ መሆኗንም በመግለፅ፤ በዚህ የእረፍት ጊዜዋ የተለየ ነገር ማድረግ ስለፈለገች ቡድኑን እንደተቀላቀለች ለቢቢሲ ተናግረዋል። እንደ ቡድኑ መሪ ከሆነ ሰሜኒያ እስካሁን ሁለት የሥልጠና ዙሮች ላይ ተካፍላለች፤ ነገር ግን የሩጫ ዓለምና የእግር ኳስ ሜዳ ስለሚለያዩ ተጨማሪ ሥልጠናዎች ያስፈልጋታል። “የእሷ ወደ እግር ኳሱ መምጣት ለቡድኑ በጣም ጠቃሚ ነው፤ በደቡብ አፍሪካ ለእግር ኳስ የሚሰጠው ክብር ከፍ እንዲል ያደርገዋል” ሲሉም ሰሜኒያ እግር ኳስ ስትጫወት ለቡድኑ አባላትና ለሌሎች ወጣት ሴቶች ተነሳሽነትን መፍጠር ትችላለች በማለት በእሷ ላይ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል። በቀጣዩ ክረምት ቶክዮ ላይ በሚካሄደው የኦሎምፒክ ውድድር በ800 መቶ ሜትር መሳተፍና ማሸነፍ ከቻለች በሶስት ተከታታይ ኦሎምፒኮች ወርቅ በማምጣት ታሪክ የምትሰራው አትሌት፣ ለዚህ ገድል ከመትጋት ይልቅ ወደ እግር ኳሱ ለመግባት መወሰኗ ሁለት አይነት እሳቤዎችን ይዞ መጥቷል። አንዳንዶች ይህን ውሳኔዋን ከተስፋ መቁረጥ ጋር ያዛምዱትና የመም ሩጫዬን ጨርሻለሁ ስለማለቷ ምስክር የሚሰጥ ነው›› ብለውታል። ከዚህ በአንፃሩ፣ ምንም እንኳን አትሌቷ ወደ እግር ኳሱ ዓለም ብትገባም ከአትሌቲክሱ ስፖርት አትርቅም ይህንንም በራሷ በአንደበት አረጋግጣለች›› ሲል ፎክስ ስፖርት እሲያ አስነብቧል። እንደ ዘገባው ከሆነም እግር ኳስ ተጫዋች ሆንኩ ማለት ወደ አትሌቲክሱ የመም ውድድር አልመለስም ማለት አይደለም ስትል ጽፋለች። አትሌቷ በእግር ኳሱ ብትቀጥልም ተመሳሳይ እግድን መጋፈጥ ግድ እንደሚላትም ተጠቁሟል። ከአሁን በኋላም በአትሌቲክስ መስክ አትሌቷን ሲሞግት የነበረው ዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን በዓለም አቀፉ እግር ኳስ የበላይ አካል ፊፋ እንደሚተካ ታውቋል። ፊፋ በውድድር የሚታይን ፍትሃዊ ያልሆነ ብልጫ ለመከላከል በስፖርቱ ተካፋይ የሆኑ ተጫዋቾች ሊያሟሉት ስለሚገባ ህገ ደንብ ከስምንት ዓመት በፊት ይፋ ማድረጉም ለሰሜንያ ራስ ምታት እንደሚሆን ታውቋል። ተገቢነትን ታሳቢ ባደረገው በዚህ የፊፋ ህግም ምርመራን መስጠት ግድ የሚል ሲሆን ይህን ለመከወን ፍቃደኛ ያልሆነ ስፖርተኛም እግድ እንደሚጠብቀው ሰፍሯል። በእርግጥ የደቡብ አፍሪካ የሴቶች ሊግ ብዙ ስምና ፕሮፌሽናል ተጫዋቾች ስብስብ የሚደምቅ አይደለም። አብዛኞቹ ስመጥር የአገሪቱ እንስት እግር ኳስ ተጫዋቾችም ባሕር አቋርጠው ለተለያዩ ታላላቅ ሊጎች የሚጫወቱ ናቸው። ይህ መሆኑም የሰሜንያ ጉዳይ እንደ አትሌቲክሱ ጎልቶ እንዳይሰማ ሊያደርገው ይችላል። ከዚህ ባለፈ ግን ደቡብ አፍሪካ እእአ በ2023 የሚካሄደውን የሴቶች ዓለም ዋንጫ ለማዘጋጀት ከታጩት አገራት አንዷ መሆኗ የካስተር ሰሜንያን የፊፋ ግንኙነት ይበልጥ ቅርብ ያደርጋዋል። ይህ ከሆነም ብሶት የወለደው የካስተር ሰሜንያ መፍትሄ ሌላ ፈተና መጋፈጥ ግድ ይለዋል።አዲስ ዘመን መስከረም 6 / 2012
https://www.press.et/Ama/?p=18151
885
2ስፖርት
በትግራይ ክልል የብሔራዊ አደጋ ስጋት ምላሽ ሥራዎች በተገቢው መንገድ እየተከናወኑ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
December 10, 2020
15
ጽጌረዳ ጫንያለውአዲስ አበባ፡- በትግራይ ክልል የብሔራዊ አደጋ ስጋት ምላሽ ሥራዎች በተገቢው መንገድ እየተከናወኑ መሆናቸውን የብሔራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ። ወደ ሱዳን የተሰደዱ ዜጎችን ለመቀበል የሚያስችል ሥራ እየሰራ መሆኑንና ለተመላሾቹ መጠለያ ካምፕ እየተገነባ መሆኑን ገለጸ::የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳስታወቁት፤ በትግራይ ክልል የብሔራዊ አደጋ ስጋት ምላሽ ሥራዎች በተገቢው መንገድ እየተከናወኑ ነው። በደቡብ ትግራይ ለ24 ሺ፤ በምዕራብ ትግራይ ለ10 ሺ ዜጎች መድረስ ተችሏል።በክልሉ ቀደም ሲልም በሴፍትኔት የሚረዱ አንድ ነጥብ አንድ ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎች እንደነበሩ የጠቆሙት አቶ ምትኩ ፣ እነርሱን ጨምሮ አሁን በተፈጠረው ችግር ሰላም በተገኘባቸው አካባቢዎች ላይ ድጋፉ ተጠናክሮ መቀጠሉንና ከ20 እስከ 30 በመቶ የሚደርሱ የከተማ የቀን ሠራተኞችም ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ አስታውቀዋል:: ኮሚሽኑ የሚመራው የሁሉም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ባለሙያዎችን ያካተተ የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከል መኖሩን ያመለከቱት ኃላፊው፣ የማዕከሉ መመስረት ችግሮች በቀላሉ መፍትሄ እንዲያገኙ እያደረገ ነው ብለዋል። በተመሳሳይ በሰላም ሚኒስቴር የሚመራ የብሔራዊ አደጋ ምላሽ ሰጪ ቡድን መኖሩን ጠቁመው፣ ቡድኑ ለሚያጋጥሙ ችግሮች አፋጣኝ ምላሾች በመስጠት ሥራዎች እንዲቀሉ እያደረገ መሆኑን አመልክተዋል:: በየጊዜው የሚፈጠሩ ችግሮች አገሪቱን ልማት ላይ እንዳታተኩር አድርገዋታል የሚሉት ኮሚሽነሩ፤ መንግሥት ከሰው ነብስ የሚበልጥ የለም ብሎ ልማቱን ይዞ ለሚከሰቱ ችግሮች ምላሽ እየሰጠ ያለበት ሁኔታ የሚያስመሰገን ነው ብለዋል:: በተለይ በተለያዩ ምክንያቶች አዳዲስ ተፈናቃዮች ሲከሰቱ መልሶ ወደ መደበኛ ኑሯቸው ለማስገባት የሚያደርገው ርብርብና ቁርጠኝነት በየትኛውም አገር ላይ ይሆናል ተብሎ የማይታሰብ እንደሆነ አመልክተዋል::እንደ አቶ ምትኩ ገለጻ፣ በእስካሁኑ ችግሮቻችን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ተፈናቅለዋል::ሆኖም ብዙ አደጋ ሳይደርስባቸው ከተፈናቀሉት 94 በመቶ የሚሆኑን ወደ መደበኛ ሕይወታቸው መመለስ መቻላቸውን አስታውቀዋል::ቀሪው ስድስት በመቶ (እስከ ሦስት መቶ ሺ) የሚደርሱት በመጠለያና በየዘመድ ቤት ተጠልለው የሚገኙ መሆናቸውን አመልክተው፤ ለነሱም የሚሰጠው ድጋፍ ባሉበት የቀጠለ መሆኑን ገልጸዋል:: አሁን በትግራይ ክልል የተፈጠረው ችግር ቀደም ሲል አጋጥሞን በስኬት ከተወጣነው አንጻር ሲታይ ብዙ ይፈትነናል የሚል ግምት የለም ብለዋል:: እስከ አሁን የነበሩት ክስተቶች በ50 ዓመት ታሪክ ውስጥ ሆነው የማያውቁ ናቸው ያሉት አቶ ምትኩ፣ በቅርቡ የተከሰተውን የአፋር አካባቢ የጎርፍ ችግር ብናይ በ30 ዓመት ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያ እንደሆነ የሚነገርለት ነው::ነገር ግን ሁሉም የከፋ አደጋ ሳያደርሱ አልፈዋል፡፡ በተለይም ከሰው ሕይወት መጥፋት ጋር ተያይዞ ኢሊኖ ያደረሰው ድርቅ እንደ ከ1977 ዓ.ም 750 ሺ ሰው አልነጠቀንም:: እንደ 1966 ዓ.ም 250 ሺ ሰውም አልሞተብንም::እንዲያውም በተቃራኒው የአንድም ሰው ሕይወት ሳያልፍ ችግሩ እልባት አግኝቷል ብለዋል:: ለዚህ ደግሞ መሠረቱ የመንግሥት አደጋን መከላከልና ምላሽ መስጠት አቅም ከጊዜ ወደጊዜ እየጠነከረ መምጣት እንደሆነ አመልክተዋል:: ወደ ሱዳን የተሰደዱ ዜጎችን ጉዳይ በዋናነት የሚመለከተው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ቢሆንም ሲመለሱ መቀበሉና ተገቢውን ድጋፍ የማድረግ ሥራ የኮሚሽኑ በመሆኑ ድንበር አካባቢ የመጠለያ ካምፕ እየተሰራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል::አዲስ ዘመን ታህሳስ 1/2013
https://www.press.et/Ama/?p=37039
376
0ሀገር አቀፍ ዜና
የእግር ኳሱ የአዲስ ዓመት አሮጌ ፈተናዎች
ስፖርት
September 19, 2019
37
አሮጌው 2011 ዓም በአዲሱ 2012 ዓም ተተክቶ ቀናት ተቆጥረዋል።ዘወትር ንትርክ የማያጣው የኢትዮጵያ እግር ኳስም ካሮጌው ዓመት ሲንከባለሉ የመጡ ፈተናዎችን ተሸክሞ ወደ አዲሱ ዓመት ተሸጋግሯል። ባሮጌው ዓመት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ውዝግቦችና አለመግባባቶች ነግሰውበት ታይቷል። መሬት ያልነኩ ፣ በእውቀት ያልተዋጁ ውሳኔዎች ሰላማዊውን መድረክ የብጥብጥ ቀጠና አድርገውት ሊጉ የሚቀጥልበት አቅም እስከማጣት ደርሶ በተደጋጋሚ ለመቋረጥ ተገዷል። በዘመን ቅብብሎሽ ሂደት ውስጥ የአሮጌው ዓመት መጥፎ ክስተቶች በአዲሱ ዓመት ታድሰው ካልተሻገሩ ፈተና መሆናቸው አይቀርም። ያም ሆኖ እነዚህን ፈተናዎች ለማረም ሌላ አዲስ ዓመት እስኪመጣ መጠበቅ አይገባምና ከወዲሁ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ያስፈልጋል። ለዚህም በአሮጌው ዓመት የነበሩትን አንኳር ፈተናዎች ለይቶ ማስቀመጥ የግድ ይላል። ዘመን የተሻገሩ ፈተናዎች የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ትናንት በትኩሱ ሁነኛ መላ ያልዘየደላቸው የስፖርቱ ነቀርሳዎች ነገ ከነገ ወዲያ ተመሳሳይ አደጋ አንዣበው ከተፍ እንደሚሉ ጥርጥር የለውም። በተለይም ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ በባለቤትነት በሚመራው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የነበሩትን ፈተናዎች ለማረም የሄደበት መንገድና ያሳለፋቸው አወዛጋቢ የመፍትሄ ውሳኔዎች፣ ለትክክለኛ ጥያቄ የተመለሱ የተሳሳቱ ምላሾች አዲሱን የውድድር ዓመትም ከውዝግብ በፀዳ መልኩ የሚያሻግሩት አይሆኑም። በተለይ ከስፖርታዊ ጨዋነት ፣የሊግ አደረጃጀትና የተጫዋቾች ወርሃዊ ደመወዝ ክፍያ ጋር በተያያዘ መፍትሄ ይሆናሉ ተብለው የተላለፉ የተዛቡ ውሳኔዎች በአሮጌው ዓመት መባቻም ዛሬም የውዝግብ መነሻ መሆናቸው አልቀረም። ለችግሮቹ መፍትሄ ለማበጀት ያስችል ዘንድ ቤሔራዊ ፌዴሬሽኑ ያደረገው ጥረት የሚበረታታ መሆኑ ባይካድም በስሌት ሳይሆን በስሜት በአንድ ጀምበር የተላለፉ ውሳኔዎች ትዝብት ላይ መውደቃቸው እየታየ ነው። መፍትሄ የሚሹ ችግሮች ተከድነው ይብሰሉ በሚል መታለፋቸውንም ልብ ይሏል። በ2011 ዓ.ም የስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል ፣የክለቦች አደረጃጀት ውዝግብ እና የተጫዋቾች ወርሃዊ ደመወዝ ክፍያ ጋር ተያይዞ የነበሩት ችግሮች በአዲሱ ዓመት ብሄራዊ ፌዴሬሽኑን ላይ የፈተና ግንብ እንደሚፈጥሩ አንድ በአንድ የኋላ ታሪካቸውን መለስ ብሎ መመልከት ያስፈልጋል።በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እራስ ምታት በመሆን ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ ካልተሻገረው የስፖርታዊ ጨዋነት ጉዳይ በመነሳት የእያንዳንዱን የፈተና ሰበዝ በመምዘዝ እንመልከት። በብሔር የተቃኙ ክለቦችና ሰላም የራቃቸው ስቴድየሞች የኢትዮጵያ እግር ኳስ ዋነኛ ችግር በመሆን የስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል በተለየ መልኩ መጠቀስ ከጀመረ ሁለትና ሦስት ዓመታት አስቆጥሯል።በብሄራዊ ፌዴሬሽኑ አዘጋጅነት በሚካሄደው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ላይ ነጸብራቁን አጉልቶ በማሳየት አሳሳቢነቱ ከጊዜ ወደጊዜ ከፍ እያለ ሲመጣም ለመታዘብ ተችሏል። እግር ኳሱ 2011 ዓም ከፖለቲካም በላይ ጦዞ ለፀጥታ አስከባሪዎች ፈተና ከመሆን አልፎ እንደ አገር ስጋት የሆነበት ደረጃ ላይ ደርሷል። ሰላም በራቃቸው የስፖርት ማዘውተሪያዎች መደበኛ የውድድር መርሐ ግብሮች መተማመኛ ማግኘት እየቻሉ እንዳልሆነ ተመልክተናል።በክልል የሚካሄዱ ጨዋታዎች በፖለቲካ ትኩሳት ሳቢያ ተጨማሪ ራስ ምታት እየሆኑ መምጣታቸውን በተለይም በ2011 የውድድር ዓመት ለመታዘብ ተችሏል። የችግሩ አሳሳቢነት ደረጃ ጎልቶ ከመውጣቱ ጀርባ ደግሞ ስፖርትና ፖለቲካ ወዳጅነት በመፍጠራቸው ነበር።የክለቦች ማንነት ከብሄርና ከጎሳ አኳያ አይቶ የመደገፍ ዝንባሌ ጎልቶ መውጣቱ የውድድር ዓመቱ አስከፊና አሳሳቢ እንዲሆን አድርጎታል።የውድድር ዓመቱ እግር ኳሱን በበላይነት ለሚመራው ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ 2011 ዓ.ም የምጥ ግዜ ያሳለፈበት ዓመት ነበር ማለት ያስደፍራል።የችግሩ ስፋትና ክብደት ክለቦች ተከባብረውና ታፍረው ለሚኖሩባት ሃገር የሰላም ስጋት እስከመሆን ደርሷል።የእግር ኳስ ክለቦች እግር ኳስን ሳይሆን ብሄርን እንዲሸከሙ በመሆኑ፤በስታዲየሞች ሜዳ ላይ ተጫዋቾች ሳይሆን የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚያንከባልሉበት ሁኔታ መኖሩ እግር ኳሱ ከጨዋነት ርቆ የፀብና ድብድብ ዓመትን ለማሳለፍ ተገዷል። በፕሪሚየር ሊጉ ብሄርን እንጂ ኳስን ማንከባለያ የመሆኑ እውነታ የትግራይና የአማራ ክልል ክለቦች መካከል የነበረውን መፋጠጥ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው። በወቅቱ መፍትሄ ለማምጣት በተለያዩ አቅጣጫዎች ሙከራ ቢደረጉም ፤መፍትሄ ሳይገኝ የውድድር ዘመኑ በሁከት ተጀምሮ በሁከት ተጠናቋል። የብሄር መገለጫ በመሆን ለነበረው ምስቅልቅል ማሳያ ከነበሩት የትግራይና የአማራ ክልል ክለቦች አንዱ የሆነው ፋሲል በ2012 ዓ.ም ወደ ትግራይ ክልል ሄዶ እንደማይጫወት በማሳወቅ ነበር ዓመቱን የጨረሰው።በውድድር ዓመቱ የስፖርታዊ ጨዋነት ፈተና የሆነበት ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ እንደ ፋሲል ሁሉ በሌሎች ክለቦች በኩል ጉርምርምታዎች ባሉበት ሁናቴ ነበር ከዘመን ዘመን የተሸጋገረው። ይህ አሳሳቢ ፈተና በአጭሩ ካልተቀጨ በአዲሱ የውድድር ዓመት አሳሳቢነቱ ጎልቶ እንደሚመጣ ግልፅ ነው። ለዚህ ደግሞ መፍትሄ ለመስጠት የሊጉን ፎርማት መቀየር እንደ አንድ መፍትሄ ሊሆን እንደሚችል ሲወራ ከርሟል። ፌዴሬሽኑም ይህን አሳሳቢ ጉዳይ ፈር ለማስያዝ በጥናት ተደግፏል ያለውን ውሳኔ ከቀናት በፊት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። ይህም ሃያ አራት ክለቦች በሁለት ምድብ ተከፍለው እንዲጫወቱ ማድረግ ነው። ይህ ውሳኔ እነማን ክለቦች፣በየትኛው መስፈርትና ሌሎች ምክኒያታዊ ጥያቄዎችን ትተን የስፖርታዊ ጨዋነትን በስቴድየሞች ይመልሳል ወይ? ብለን ከጠየቅን አዎንታዊ ምላሽ የሚሰጥ ሆኖ አልተገኘም። ፌዴሬሽኑ የአማራ ክልል ክለቦች ከትግራይ ክልል ክለቦች ጋር እንዳይገናኙ፣ሲዳማ ቡናና ወላይታ ድቻ እንዲሁም ቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ቡናም በተመሳሳይ እንዳይጫወቱ የሚደርግ ውሳኔ አሳልፏል። ይህ ግን በብዙ የስፖርት ቤተሰቦች ዘንድ የስቴድየሞች ሰላምን የሚመልስ ውሳኔ ነው ተብሎ አልታመነበትም። እንዳይገናኙ ከተደረጉት ክለቦች ባሻገር የሚገናኙት ክለቦች ተመሳሳይ ግጭት ላለመፍጠራቸው ምንም ማስተማመኛ የለም የሚለው ምክኒያት ከብዙዎቹ አንዱ ነው። በፕሪሚየር ሊጉ ህልውና ላይ የቆመው የሊግ አደረጃጀት «የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በአዲስ መልኩ መደራጀት ይገባዋል» የሚለው አጀንዳ በሁለቱ የሸገር ደርቢዎች በስፋት ሲቀነቀን የቆየ አጀንዳ ነበር።በብሄራዊ እግር ኳስ ፌዴሬሽኑ የሚመራው ፕሪሚየር ሊጉ «የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ»በሚል አደረጃጀት ብቅ ያለው ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ ነበር።የኢትዮጵያ ቻምፒዮና ተብሎ ከዛ በፊት ሲካሄድ የነበረው ውድድሩ ፤ከሁለት አስርት ዓመት ቆይታ በኋላ ወደ ቀድሞው አደረጃጀቱ ለመመለስ ከጫፍ ደርሷል።የኢትዮጵያ እግር ኳስ ዓርማና ድምቀት በመሆን ግንባር ቀደም ተጠቃሾቹ ቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ቡና አሁን ያለውን የሊግ አደረጃጀት መታደስ እንደሚገባው አቋማቸውን አንፀባርቀዋል።እግር ኳሱ «የፖለቲካ መገለጫ፣የብሄርተኞች ማላገጫ ፣የደጋፊዎች ቡጢ መወጫ ከመሆን መፍትሄ አለን»ሲሉ በሸገር ክለቦች በኩል ለችግሩ ማጣፊያ የሊግ አደረጃጀት መቀየር እንደሚገባ ሙግት ገጥመው ነበር።ብሄራዊ ፌዴሬሽኑም ሆነ በሌሎች ክለቦች ቅቡል እንዲሆን ሀሳባቸውን በተለያዩ አጋጣሚዎች ሲገልጹ ቆይተዋል።በ2011 ዓ.ም በተጠናከረና ልዩ አቋም የያዘ ነበር።የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከክለቦቹ ጎን በመቆም የአቋማቸውን ጽናት ወደ ውሳኔ እንዲሻገር አድርጎታል።የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በኢትዮጵያ እግር ኳስ የሚታየውን የሊግ ውድድር የአደረጃጀት ችግሮች በመለየትና የመፍትሔ ሀሳቦች በማስቀመጥ ላይ ያተኮረ የአውደ ጥናት መድረክ አዘጋጅቷል ።አጀንዳውን በስፋት ሲያራምዱት የነበሩትን ጊዮርጊስና ቡናን ጨምሮ 22 የሸገር ክለቦች በተገኙበት ጥናቶች ቀርበዋል። በመድረኩ መጨረሻ መዲናዋ የራሷን የውድድር አደረጃጀት እንዲኖራት የሚያስችል የጋራ የስምምነት ሰነድ በመፈራረም መድረኩ እንዲጠናቀቅ ነበር የሆነው ።በመድረኩ ከተሳተፉት 22 ክለቦች የፌዴራል ፖሊስ ክለብ በስተቀር ሁሉም ክለቦች የተስማሙበት ነበር።ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስር በመሆን ለመወዳደር በጋራ ተስማምተውና ውሳኔ አሳልፈው ነበር የተለያዩት።ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ በወቅቱ ሚዲያ ሰብስቦ ማንም መግለጫ ስላወጣ የሚቀየር ነገር እንደሌለ ተናግሯል።የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን ህልውና ለሁለት የፈነከተ የሸገር ክለቦች ውሳኔን አወዛጋቢና አነጋጋሪ በመሆን ከ2011 ዓ.ም ወደ 2012 ዓ.ም ተሸጋግሯል።ይህ የሸገር ክለቦች ሃሳብ በአዲሱ ዓመት እውን የሚሆን አይመስልም። ያም ሆኖ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ሰፊ የደጋፊ መሰረት ያላቸው የሸገር ደርቢዎች ኢትዮጵያ ቡናና ቅዱስ ጊዮርጊስ በማይገናኙበት የአዲሱ ዓመት ፕሪሚየር ሊግ ፌዴሬሽኑ ከጫና ይወጣል የሚል ግምት በብዙዎች ዘንድ የለም። ገና ሳይጀመር እየተነቀፈ የሚገኘው አዲሱ የፕሪሚየር ሊግ አደረጃጀት ነገም የሸገር ክለቦችን ጥያቄ መልሶ እጃቸውን ሰብስበው እንዲቀመጡ ያደርጋቸዋል ተብሎ አይታሰብም። በቅጡ ሳይበጅ ያፈሰሰው የደመወዝ ጣሪያ በሸገር ክለቦች በኩለ የሊግ አደረጃጀት መሻሻሉ ዘርፈ ብዙ ጥቅም እንዳለው በመግለጽ ፣«ስፖርታዊ ጨዋነት ከማስፈን በተጨማሪ የክለቦችን ወጪ ለመቀነስ ያስችላል »ሲሉ ምክረ ሀሳባቸውን ቢያቀርቡም ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ በጄ ሳይል ቀርቷል።ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ ይሄንን ምክረ ሃሳብ ወደ ጎን ትቶ ክለቦችን ጣሪያ ከነካ የፋይናንስ ወጪ ለመታደግ ለተጫዋቾች የደመወዝ ጣሪያ ወሰን ማበጀቱን መፍትሄ አድርጎ ወስዷል።የተጫዋቾች ወርሃዊ የደመወዝ ጣሪያ ከ50 ሺህ መብለጥ የለበትም የሚለው ውሳኔው ይሄው መፍትሄ የ2012 ዓ.ም የብሄራዊ ፌዴሬሽኑ አሮጌ ፈተና እንደሚሆን ከወዲሁ ምልክቶች መታየት ጀምረዋል። የስፖርት ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ የክልል ስፖርት ቢሮ ኃላፊዎችና 14 የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች አመራሮች በተገኙበት ነሐሴ 3 ቀን 2011 ዓ.ም.ቢሾፍቱ በተደረገው ጉባዔ ላይ ነበር ውሳኔው የተላለፈው። በውሳኔው ላይ ሁለቱ የአዲስ አበባ ክለቦች ቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ቡና ያልተገኙ ሲሆን ፤በብሄራዊ ፌዴሬሽኑ ወጪን ለመከላከል ከቀረበው መፍትሄ በላይ ውጤታማ ሊሆን የሚያስችለው የሊግ አደረጃጀት ማሻሻል እንደሆነ በማመን ሳይሆን እንዳልቀረ ግምቶች ቀርበዋል።በብሄራዊ ፌዴሬሽኑ ውሳኔውን ባሰማበት ማግስት ውዝግቦች ከየአቅጣጫው ሲነሱ ለመታዘብ ተችሏል።በተለይ የተጨዋቾችና የአሠልጣኞች ማኅበር በኩል የተሰማው ተቃውሞ ጫን ያለ ነበር። ማኅበሩ ውሳኔው ከፌዴሬሽኑ ደንብና መመሪያ አኳያ ታይቶ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትን ያላሳተፈ መሆኑን ጭምር በመግለጽ ነበር በወቅቱ ቅሬታውን ለፌዴሬሽኑ ያስገባው። ‹‹የኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል ፉትቦለር አሶሴሽን›› በሚል በቅርቡ ሕጋዊ ዕውቅና ያገኘው የተጨዋቾችና አሠልጣኞች ማኅበር 08/12/2011 ዓ.ም. በጻፈው ደብዳቤ ተቃውሞውን ያስገባ ሲሆን ፤ማኅበሩ ተቃውሞውን ያቀረበው መስከረም 27 ቀን 2004 ዓ.ም. በወጣው የፌዴሬሽኑ መተዳደሪያ ደንብ በአንቀጽ 5 የአባላት የጋራ ጥቅም እንዲሁም በአንቀጽ 11፣ 46 እና 47 የአባላት መብቶችና የዓለም አቀፍ የስፖርት ግልግል ፍርድ ቤት ከሚከተሉት ሕጋዊ አሠራር ባፈነገጠ መልኩ የተላለፈ ውሳኔ እንደሆነ ጠቅሶ ውሳኔውን እንደማይቀበለው ነበር ያብራራው ።ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ ከተጫዋቾች ፣ከክለቦች፣ከአሰልጣኞች በኩል በሚወረወሩ የቅሬታ አስተያየቶች ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ አቋም በመያዝ ነበር ከዓመት ዓመት የተሻገረው። የውሳኔውን ህጋዊ መሰረት አልባነት በሞገቱት የሙያው ማህበራትና ያኮረፉትን ተጫዋቾች ልብ ሳያዳምጥ ወደ አዲስ የውድድር ዓመት ለማቅናት ሽር ጉድ እያለ ይገኛል።ከዚህ አኳያ በአሮጌው ዓመት ቅሬታ ሆኖ ያለፈው የደመወዝ ጣሪያ ውሳኔው አንድ ቦታ ባልቆመበት ሁኔታ የሚጀመረው አዲሱ የውድድር ዓመት ፈተና እንደሚሆን ይጠበቃል። በሌላ በኩል የተጫዋቾች የደመወዝ ጣሪያ ሃምሳ ሺ ብር ተብሎ ይወሰን እንጂ በእጅ አዙር ክለቦች ተጫዋቾችን በጥቅማ ጥቅሞችና በፊርማ ገንዘብ ካለፈው የባሰ እንጂ የተሻለ ወጪ እያወጡ እንደማይገኙ መረጃዎች መውጣት ጀምረዋል። ይህ ደግሞ ካለፈውም የደመወዝ አከፋፈል የባሰ መንግሥት ተገቢውን ታክስና ቀረጥ እንዳያገኝ ከማድረግ ባሻገር በህዝብ ገንዘብ የሚንቀሳቀሱትን ክለቦች በፍጥነት ወደ ገደል እንደሚመራቸው ግልፅ ይመስላል። ማጠቃለያ የ2011 ዓም ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ጥሩ ዓመት አልነበረም። አዲሱም ዓመት ካለፈው የተሻገሩ ግዙፍ ችግሮችን ተሸክሞ ለመሄድ ተገዷል። ያም ሆኖ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ችግሮቹን ዓመቱን ሙሉ ይዞ የመዝለቅ ግዴታ የለበትም። እነዚህን ችግሮች ቁርጠኝነቱ ካለ ጊዜ ወስዶ የማሻሻል ሰፊ እድል አለው። በእያንዳንዱ ውሳኔ ላይ የሚደረጉ ጥናቶችን ተዓማኒነት ወይም ተቀባይነት መመርመር የመጀመሪያው እርምጃ ነው። በጥናት የተደገፉ የተባሉ ውሳኔዎች ምን ያህል ውዝግብ እያስነሱ እንደሚገኙ እየታየ ነው። ከልብ በባለሙያ የተጠኑ ጥናቶች፣ ስፖርቱን የሚያውቁ ሃሳብ ያላቸው ግለሰቦችን አዲሱን ዓመት ከውዝግብ ለመሻገር መጠቀም ከተቻለ ዛሬም፣ነገም ነገሮችን መለወጥ የሚቻልበት እድል ይኖራል።አዲስ ዘመን  መስከረም  8 / 2012ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=18335
1,351
2ስፖርት
ዋልያዎቹ ዛሬ መቐለ ላይ ሩዋንዳን ያስተናግዳሉ
ስፖርት
September 22, 2019
45
እ.ኤ.አ በ2019 በምዕራብ አፍሪካዊቷ ካሜሩን አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ አገሮች ዋንጫ (ቻን)የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋልያዎቹ ዛሬ ከሩዋንዳ ጋር የመጀመሪያ የማጣሪያ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። በኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ የሚሠለጥነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለውድድሩ 24 ተጫዋቾችን በመምረጥ ከመስከረም 2 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ በመቐለ ከተማ ዝግጅታቸውን እያደረጉ ይገኛሉ። በአገር ውስጥ ሊጎች ብቻ የሚጫወቱ ተጫዋቾች በሚሳተፉበት የቻን አፍሪካ ዋንጫ አስልጣኝ አብረሃም መብራቱ ከሁለት ሳምንት በፊት በዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ከተጠቀሙት ቡድን ብዙም ልዩነት የሌለው ስብስብ ይዘው ወደ ሜዳ እንደሚገቡ ይጠበቃል። አሠልጣኙ በዓለም ዋንጫው ማጣሪያ ጨዋታ የነበሩትን በስዊድን ሁለተኛ ሊግ የሚጫወተውን ቢኒያም በላይና በግብፅ ሊግ የሚጫወቱትን ሽመልስ በቀለ፣ ጋቶች ፓኖምና ኡመድ ኡኩሪን በማስቀረት ለሩዋንዳው ግጥሚያ ተዘጋጅተዋል። በቡድኑ ስብስብ አብዛኞቹ ተጫዋቾች ለኳታሩ የዓለም ዋንጫ ከሌሶቶ ጋር በነበራቸው የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ የተመረጡት መሆናቸው ለቡድኑ ቅንጅትም ጠቃሚ እንደሆነ እየተነገረ ይገኛል። ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር ዝግጅታቸውን እያደረጉ የሚገኙት ግብ ጠባቂዎች ጀማል ጣሰው፣ ለዓለም ብርሃኑ እና ምንተስኖት አሎ ይገኙበታል። በተከላካይ ክፍል ደግሞ አስቻለው ታመነ፣ ያሬድ ባየ፣ አህመድ ረሺድ፣ አንተነህ ተስፋዬ፣ ረመዳን የሱፍ፣ ደስታ ደሙ፣ ጌቱ ሃይለማርያም እና መሳይ ጳውሎስን አካቷል። አማካዮ ክፍል ደግሞ ከነዓን ማርክነህ፣ ዮናስ በርታ፣ ሃይደር ሸረፋ፣ ፉአድ ፈረጃ፣ ፍጹም አለሙ፣ አማኑኤል ዮሃንስ እና ሱራፌል ዳኛቸው ይገኙበታል። አጥቂዎች አስቻለው ግርማ፣ ሙጂብ ቃሲም፣ አማኑኤል ገብረሚካኤል፣ መስፍን ታደሰ፣ አዲስ ግደይ እና ፍቃዱ አለሙ በመያዝ ዝግጅቱን አድርጓል። ሩዋንዳን የሚገጥሙት ዋልያዎቹ በዛሬው ጨዋታ ቀደም ሲል የነበረባቸውን ችግሮች ማረም ካልቻሉ ከፍተኛ ፈተና ሊገጥማቸው እንደሚችል ይጠበቃል። ዋልያዎቹ ከሌሴቶም ሆነ ከጅቡቲ ጋር በነበራቸው ጨዋታ ጥሩ የሚባል እንቅስቃሴ ቢያሳዩም ኳስን ከመረብ የማዋሃድ ውስንነቶች በተደጋጋሚ ተስተውሎባቸዋል። በሜዳ ላይ እንቅስቃሴ የተሻሉ ነገሮች ቢታዩም ተጫዋቾቹ ያገኟቸው የጎል አጋጣሚዎች የመጠቀም ክህሎታቸው ደካማ መሆን ብሔራዊ ቡድኑን ዋጋ እያስከፈሉት እንደሚገኙ ለመታዘብ ተችሏል። ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ በጨዋታ ዝግጅት ዙሪያ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት አስተያየት፤ ብሔራዊ ቡድኑ ከሩዋንዳ ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ በድል ለመወጣት የስነ ልቦናና የአካል ብቃት ዝግጅት ማድረጉን ገልጸዋል። ቡድኑ ውድድሩን በድል ለመወጣት በትግራይ አለም አቀፍ ስቴድዮም ልምምዳቸውን በተሟላ መንገድ እያካሄዱ መሆናቸውን ገልጸዋል። የብሔራዊ ቡድኑ አባላት ጤንነት፣ በአካልና በስነ ልቦና ዝግጅት በመልካም ሁኔታ እንደሚገኙ አስታውቀዋል። ተጫዋቾቹ መቀሌ ከተማ ሲደርሱ በአካባቢው ነዋሪዎች፣ በክልሉ መንግስትና በፕሪሜየር ሊግ አሰልጣኞች ደማቅ አቀባበል እንዳደረጉላቸውም አስታውሰዋል። እንደ አቀባበሉ ሁሉ በጨዋታው ወቅት የሕዝቡ ድጋፍ በደመቀ መልኩ እንዲደገምም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ የሚደረግበት የመቐለ ስታድየም፣ አኅጉራዊ ውድድሮቸችን ሲያስተናግድ የሩዋንዳው ቡድን የመጀመርያው ቢሆንም፣ የመቐለና አካባቢዋ ነዋሪዎች ለስታድየሙ ድምቀት ከመሆንም ባሻገር፣ ለኢትዮጵያ ቡድን ሥነ ልቦና የሚሰጡት ድጋፍ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ይታመናል። መስከረም 11 ቀን 2012 ዓ.ም በመቐለ ከተማ ትግራይ አለም ዓቀፍ ስታዲየም የሚደረገውን የኢትዮጵያና የሩዋንዳ ብሔራዊ ቡድን ጨዋታውን ሱዳን በኮሚሽነርነት፣ ኬንያ በዋና ዳኝነት ይመሩታል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድኑ ዋልያዎቹ የመጀመሪያ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታውን ከጅቡቲ ጋር በማድረግ ጅቡቲን በደርሶ መልስ 5 ለ 3 በሆነ ውጤት ማሸነፋቸው ይታወሳል።ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=18556
401
2ስፖርት
ጥቂት ስለ ዶሃው ዓለም ቻምፒዮና
ስፖርት
September 22, 2019
25
በሩጫ፣ ዝላይ እና ውርወራ ስፖርቶች የዓለምን ምርጥ አትሌቶች ለመመልከት የአትሌቲክስ ቤተሰቡ በሳምንቱ መጨረሻ በምዕራብ እስያዊቷ ሃገር ኳታር ይከትማል። የተወዳጁን አትሌቲክስ ስፖርት ታላቅ ድግስ የተረከበችው ዶሃም መሰናዶዋን አጠናቃ እንግዶቿን በመቀበል ላይ ትገኛለች። ሃገራትም በዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮናው ስማቸውን ለማስጠራት የሚያደርጉትን ዝግጅት በማጠቃለል ላይ ናቸው። ዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ከሰሞኑ እንዳስታወቀው ከሆነም 209 ሃገራት 1 ሺ 900 አትሌቶቻቸውን በቻምፒዮናው እንደሚያሳትፉ ማረጋገጫቸውን ሰጥተዋል። ከእነዚህ ስመጥርና ጠንካራ አትሌቶች መካከልም ከሳምንታት በፊት በተጠናቀቀው ዳይመንድ ሊግ አሸናፊ የሆኑት 30 አትሌቶች ተካፋይ በመሆን በዓለም ታላቁ ውድድር ላይም ታሪክ ለማስመዝገብ መዘጋጀታቸውን ድረ ገጹ ጠቁሟል። በዚህ ቻምፒዮና የታሪክ መዝገብ በደማቅ ቀለም የሰፈረችው ውጤታማዋ አሜሪካዊት የአጭር ርቀት አትሌት አሊሰን ፍሊክስም የክብረ ወሰኗን ቁጥር ለመጨመር በዶሃ ትገኛለች። አትሌቷ 11 የወርቅ፣ 3 የብር እና ሁለት የነሃስ በድምሩ 16 ሜዳሊያዎችን በእስካሁኑ የዓለም ቻምፒዮና ተሳትፎዋ ሰብስባለች። እ.አ.አ በ2005ቱ የሄልሲንኪ ቻምፒዮና ለመጀመሪያ ጊዜ የተካፈለችው ፍሊክስ፤ የዶሃው ዓለም ቻምፒዮና ሰባተኛ ተሳትፎዋ ነው። በዚህ ቻምፒዮና ከሚሳተፉት አትሌቶች ሁሉ በእድሜ ትልቁ በሚል የተመዘገበው አትሌት ደግሞ ስፔናዊው የርምጃ ተወዳዳሪ ጀሱስ አንጌል ጋርሲያ ነው። እ.አ.አ የ1993ቱ የስቱትጋርት ዓለም ቻምፒዮና ለመጀመሪያ ጊዜ የታየው የ49 ዓመቱ አንጋፋ አትሌት 13ኛ ተሳትፎውን በዶሃ ያደርጋል። የፊታችን አርብ የሚጀመረው 17 ኛው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና በኳታር ዋና ከተማ በሚገኘው ከሊፋ ስታዲየም የመክፈቻ መርሃ ግብሩን ያደርጋል። ውድድሩ በመልካም ሁኔታ እንዲካሄድም ከዓለም ዙሪያ 4 ሺ የሚሆኑ በጎ ፈቃደኛ ሰራተኞች ተሰባስበዋል። ስዊድናዊው የ2004 ኦሊምፒክ የከፍታ ዝላይ ቻምፒዮን ስቴፈን ሆልምም የዚህ ቻምፒዮና የክብር አምባሳደር መሆኑን ዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር አስታውቋል። ሃገራት ብሔራዊ ቡድኖቻቸውን በማሳወቅ ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ ሁሉም በቻምፒዮናው ቁንጮ ለመሆን የሚያደርገው ፉክክርም የዓለም ህዝብ በጉጉት የሚጠብቀው ነው። ኢትዮጵያም ቡድኗን ያሳወቀች ሃገር ስትሆን የ5 ሺ ሜትር ወንዶች እና የ10 ሜትር ሴቶች ቻምፒዮናዎቹ ሙክታር እድሪስ እና አልማዝ አያና በቡድኑ መካተት ርቀቶቹን ከወዲሁ ተጠባቂ ያደርገዋል። በዘንድሮው ዳይመንድ ሊግ የ3 ሺ ሜትር መሰናክል አሸናፊው ጌትነት ዋለ እንዲሁም በውጤታማነታቸው ዓለምን ያስደነቁት ወጣቶቹ ሳሙኤል ተፈራ፣ ዮሚፍ ቀጄልቻ፣ ሰለሞን ባረጋ፣ ጥላሁን ኃይሌ፣ ሃጎስ ገብረህይወት፣ ለተሰንበት ግደይና ሌሎችም አዲስ ታሪክ ያስመዘግባሉ የሚል ግምት አግኝተዋል። ከዚህ በተጨማሪ የተጠባቂዋ አትሌት ገንዘቤ ዲባባ ከውድድሩ መገለልም ሌላኛው መነጋገሪያ ሆኗል።  ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=18548
310
2ስፖርት
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ የሚለይበት መንገድ ይፋ ሆኗል
ስፖርት
September 17, 2019
16
 የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዘንድሮውን የፕሪሚየር ሊግ ውድድር አሸናፊ የሚለይበትን መንገድ ይፋ አድርጓል። ፌዴሬሽኑ በዛሬው እለት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኩባንያ ምስረታን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል። በዘንድሮው ፕሪሚየር ሊግ 24 ቡድኖች በሁለት ምድብ ተከፍለው ውድድራቸውን የሚያካሂዱ ይሆናል። በውድድሩም ከምድባቸው በአንደኝነት የሚያጠናቅቁ ሁለት ቡድኖች ለዋንጫ በገለልተኛ ሜዳ ሁለት ዙር ተጫውተው የጨዋታው አሸናፊ የሊጉን ዋንጫ የሚያነሳ ይሆናል። አሸናፊው ቡድን በአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ሲሳተፍ ሁለተኛ ሆኖ የሚያጠናቅቀው ቡድን ደግሞ ኢትዮጵያን በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ይወክላል። የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ ቡድን ደግሞ ኢትዮጵያን በሴካፋ ወክሎ እንደሚወዳደር ከሶከር ኢትዮጵያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። በሀገር ውስጥ ያሉ የእግር ኳስ ውድድሮችን ለመምራት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኩባንያን ለመመሥረት እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑንም ፌዴሬሽኑ በዚህ ወቅት ገልጿል። አሁን ላይም የክለቦችን ገቢ ለማሳደግ፣ ከደጋፊ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ፣ ዘመናዊ የትኬት ሽያጭ ለመጀመርና የክለቦችንና ደጋፊዎችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑንም ጠቅሷል። አዲስ ዘመን መስከረም 6 / 2012
https://www.press.et/Ama/?p=18148
128
2ስፖርት
‹‹አሰልጣኞች ከእኛ ጋር ራሱ ለመገናኘት አይፈልጉም››-አሰልጣኝ ሻምበል ቶሎሳ ቆቱ
ስፖርት
September 21, 2019
53
አንጋፋ ከሆኑ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች መካከል ሻምበል ቶሎሳ ቆቱ አንዱ ናቸው። ሻምበል ቶሎሳ በአትሌትነት ዘመናቸው እ.ኤ.አ በ1980 የሞስኮ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያን ወክለው በ10 ሺ ሜትር ከምሩፅ ይፍጠር፣ ካርሎ ማኒንካና መሐመድ ከድር ቀጥለው በማጠናቀቅ የዲፕሎማ ደረጃ ያገኙ ሲሆን በወቅቱ ‹‹ትራክ ኤንድ ፊልድ ኒውስ›› በርቀቱ የዓለማችን ሰባተኛው አትሌት አድርጎ ሰይሟቸዋል። ሻምበል ቶሎሳ የዓለም ቻምፒዮናን ጨምሮ በበርካታ ዓለም አቀፍ ውድድሮች አገራቸውን ካኮሩ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች መካከል ቢጠቀሱም ወደ አሰልጣኝነት ከመጡ ወዲህ ትልቅ ዝናና ክብር አግኝተዋል። በአሰልጣኝነት ዘመናቸው ከብሔራዊ ቡድን የረጅም ርቀት አሰልጣኝነት ባሻገር በኢትዮጵያ ቡና፣ በመቻልና በሙገር ሲሚንቶ ክለቦች በሰሩባቸው ዘመናት ቀነኒሳ በቀለ፣ ገዛኸኝ አበራ፣ ተስፋዬ ቶላ ሌሎችም ስኬታማ አትሌቶችን በማፍራት ትልቅ ስም ገንብተዋል። ከኢትዮጵያ ባሻገር የባህሬን አትሌቲክስ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ በመሆን ለአምስት ዓመታት ሰርተዋል። ከዚያም ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው በብሔራዊ ቡድን የ5ና 10 ሺ ሜትር አሰልጣኝ ሆነው በማገልገል በርካታ ድሎችን ማስመዝገብ ችለዋል። ሻምበል ቶሎሳ ዛሬ ላይ በአሰልጣኝነት የብሔራዊ ቡድን ስራ ላይ አይገኙም። ይሁን እንጂ የዓለም ቻምፒዮና በተቃረበበት በዚህ ወቅት ስለ ኢትዮጵያ ስብስብና ሌሎች ጉዳዮች እይታቸውን እንደሚከተለው አካፍለውናል።አዲስ ዘመን፡- አሰልጣኝ ቶሎሳ ቆቱ ለረጅም ዓመታት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሔራዊ ቡድን የረጅም ርቀት አሰልጣኝ ሆነው አገልግለዋል፣ በተለይም ባለፈው የዓለም ቻምፒዮና ሙክታር ኢድሪስ ሞ ፋራህን በ5ሺ ሜትር ሲያሸንፍ እርሶ ዋና አሰልጣኝ በመሆን ትልቅ የታክቲክ ስራ ሰርተዋል፣ ዘንድሮ ወደ ኳታር የዓለም ቻምፒዮና ኢትዮጵያን ወክሎ በሚጓዘው ቡድን ውስጥ በአሰልጣኝነት አልተካተቱም፣ ምክንያቱ ምንድነው?አሰልጣኝ ቶሎሳ፡- ባለፉት በርካታ ዓመታት ለብሔራዊ አትሌቲክስ ቡድን አትሌቶችን ከክልልም ከተለያዩ ክለቦችም መልምለን በማምጣት እያሰለጠንን ነው የአረንጓዴው ጎርፍ ታሪክ ጨምሮ ብዙ ውጤቶች የተመዘገቡት፣ አሰልጣኞች ከንጉሴ ሮባ ጀምሮ እነ ዶክተር ወልደመስቀል ኮስትሬ፣ ዶክተር ይልማ በርታና ሌሎችም በብሔራዊ ቡድን ውስጥ ሰርተን ነው በኦሊምፒክም በዓለም ቻምፒዮናም ጥሩ ውጤት ያመጣነው። አሁን ብሔራዊ ቡድን የሚባል ነገር የለም፣ ፈርሷል፣ ብሔራዊ ቡድን ሲፈርስ ተጠንቶ ነበር መሆን የሚገባው፣ ከዚህ በፊት ያመጣነው ውጤትና ወደ ፊት የምናመጣው ውጤት እንዴት ነው ተብሎ መታሰብ ነበረበት፣ ሰዎች ይፍረስ ስላሉ መፍረስ አልነበረበትም፣ ብሔራዊ ቡድን ከቀረ አሁን አንድ ዓመቱ ነው፣ ውጤቱ ይታያል፣ ውጤቱ ታይቶ ጥሩ ከሆነ ይቀጥላል፣ ውጤታማ ካልሆነ ደግሞ ፌዴሬሽኑ የሚያየው ይመስለኛል።አዲስ ዘመን፡- የዓለም ቻምፒዮና ከቀናት በኋላ ይጀመራል፣ ኢትዮጵያም ወደ ኳታር ይዛ የምትጓዘውን ቡድን አሳውቃለች፣ የተመረጡትን አብዛኞችን አትሌቶች እርሶ ያውቋቸዋል፣ የአትሌቶቹን ምልመላና አጠቃላይ የቡድኑን ስብስብ እንዴት ተመለከቱት?አሰልጣኝ ቶሎሳ፡- አትሌቶቹ የተመለመሉት ባመጡት ሰዓት መሰረት ነው፣ ይህ ድሮም የምንሰራበት ስለሆነ ችግር አለበት ብየ አላስብም፣ በረጅም ርቀት እንዳየነው ሄንግሎ በተደረገው የማጣሪያ ውድድር ነው የተመረጡት፣ ያሉን አትሌቶች ናቸው የተመረጡት፣ እነ ሁሴን ሼቦ ናቸው ከእኔ ጋር ረጅም ዓመት የሰሩ አሰልጣኞች ቡድኑን የሚመሩት፣ ስልጠናውን ካላየው ግን የቡድኑን ጥንካሬና ድክመት ይሄ ነው ማለት አልችልም፣ ምክንያቱም ስትሰራ ነው ይሄ ጠንካራ ይሄ ደግሞ ደካማ ነው የምትለው፣ ይሁን እንጂ ዳር ላይ ሆነህ በምትመለከተው ነገር በተለይም ወንዶቹ 5ና 10 ሺ ሜትር ጠንካራ ናቸው ማለት እችላለሁ፣ ውጤታማ ለመሆን ግን የታክቲክ ስራዎች ያስፈልጋቸዋል፣ ምክንያቱም እንደነሱ ጠንካራ የሆኑ የሌሎች አገራት ተፎካካሪ አትሌቶች አሉ፣ ለምሳሌ ባለፈው ዳይመንድ ሊግ 5 ሺ ሜትር ፍፃሜ ላይ በአሯሯጮች ተጠቅሞ ያሸነፋቸው አትሌትን መጥቀስ ይቻላል፣ ጥንቃቄ ያስፈልጋል፣ የዓለም ቻምፒዮና የገንዘብም ውድድር ስለሆነ ለማሸነፍ ብቻ ተጠባብቀው ስለሚሄዱ ጥንቃቄ ያስፈልጋል፣ በዚህ መሰረት ጥሩ ውጤት ሊያመጡ ይችላሉ፣ ጠንካራ ሴቶችም አሉ ነገር ግን ይሄን ያህል ወርቅ ያመጣሉ ብሎ ከዚህ ቀደም እንደነ ጥሩነሽና መሰረት ሙሉ ተስፋ የምትሰጣቸው አይነት አይደለም፣ እኔ በማሰለጥንበት ዘመን እንደነበረው እንደነ ቀነኒሳ፣ ስለሺ፣ ጥሩነሽና መሰረት በነበሩበት ደረጃ ያሉ አትሌቶች አሁን የሉም፣ ያም ሆኖ የአሁኖቹ አትሌቶች ጥሩ ውጤት ቢያመጡ ደስ ይለኛል። አዲስ ዘመን፡- 5ና 10ሺ ሜትር ላይ የተመረጡ አትሌቶች በድንቅ አቋም ላይ እንደሚገኙ ጥርጥር የለውም፣ ቀደም ሲል በምርጫው ዙሪያ ያነሳሁት ጥያቄም ከዚሁ ጋር የተያያዘ ነው፣ አንድ አትሌት 5ና 10 ሺ ሜትር በወንድም በሴትም እንዲወዳደር የተመረጠበት አጋጣሚ አለ፣ ይህ ደግሞ የውድድሩ ስፍራ ኳታር ከፍተኛ ሙቀት በመኖሩ ውጤታቸው ላይ ተፅዕኖ ያሳድራል የሚል ስጋት አለ፣ ምናልባት አንድ አትሌት በሁለት ርቀቶች ተወዳድሮ ከሁለት አንድ ያጣ ከሚሆን ይልቅ በአንዱ ውጤታማ እንዲሆን ማድረግ አይሻልም?አሰልጣኝ ቶሎሳ፡- በትክክል እኔም አላምንበትም፣ ምክንያቱም በሁለት ርቀት ውጤታማ የሚሆኑ አትሌቶች ቅድም እንደጠቀስኩት እንደ ቀነኒሳና ጥሩነሽ ያሉ አትሌቶች ናቸው፣ የአሁኖቹ አትሌቶች የብቃታቸው ጥግ የእነ ቀነኒሳና ጥሩነሽ ላይ ደርሷል ወይ?፣ አንድ አትሌት በሁለት ርቀቶች እንዲሮጡ የተመረጡት በአሰልጣኞች አማካኝነት መሆኑን ሰምቻለሁ፣ እኔ ግን በአንድ ርቀት ቢወዳደሩ መርጣለሁ፣ ለምሳሌ 5 ሺ ሜትር የራሱ ማጣሪያ ውድድር አለው፣ 10 ሺ ሜትር ከሮጡ በኋላ 5 ሺ ማጣሪያና ፍፃሜ መሮጥ በአጠቃላይ 20 ሺ ሜትር መሮጥን ስለሚጠይቅ ከባድ ይሆናል። በሴቶችም ቢሆን ጠንካራ የሆኑ እንደ ኬንያዊቷ ሔለን ኦቢሪ አይነት አትሌቶች በሁለቱም ርቀት ብቃት ያላቸው ስላሉ እኔ ብሆን የእኛን አትሌቶች በሁለት ርቀት እንዲሮጡ አልመርጥም፣ አትሌቶቹና አሰልጣኞቹ ተነጋግረው በአንዱ ላይ ወስነው መስራት አለባቸው።አዲስ ዘመን፡- በሁለቱም ርቀቶች እንዲወዳደሩ ከተመረጡት አትሌቶች መካከል ሐጎስ ገብረሕይወትና ሰለሞን ባረጋ ይገኙበታል፣ በእርግጥ ሰለሞን 10 ሺ ሜትር ላይ በአራተኛ ወይም በተጠባባቂ ነው የተያዘው፣ ሰለሞን እድሜው ለጋ እንደመሆኑ መጠን በሁለቱም ርቀቶች ብዙ ልምድ ሳያካብት ቢወዳደር ከሁለት አንድ ያጣ ሊያደርገው ይችላል፣ በለመደው 5 ሺ ብቻ ቢሮጥ ግን ሊያሸንፍ የሚችልበት አቅም አለው የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች ስህተት ናቸው ማለት ይቻላል?አሰልጣኝ ቶሎሳ፡- እኔ የምመርጠው ሰለሞን በአንድ ርቀት ብቻ ቢሮጥ ነው፣ ሰለሞን ገና ታዳጊ ስለሆነ አልበሰለም፣ አጥንቱም አልጠነከረም፣ 10 ሺ ሮጦ 5 ሺ መድገም ሊከብደው ይችላል፣ አትሌቶቹ ራሱ ሰዓት ስላላቸው ብቻ እሮጣለሁ የሚል አቋም ያላቸው ይመስለኛል፣ ይሄን ደግሞ አሰልጣኞች ትክክል አይደለም ብለው ማስቆም ነበረባቸው፣ አትሌቶቹም አሰልጣኞቹን መስማት ነበረባቸው፣ ሰለሞን 10 ሺ ሜትር ላይ ተጠባባቂ ስለሆነ የሚሮጥ አይመስለኝም፣ በ5 ሺ ሜትር ግን ውጤታማ የሚሆን ይመስለኛል፣ ሐጎስም በተመሳሳይ ሊከብደው ይችላል፣ ነገር ግን 5ሺ ሜትር የሚሮጠው 10 ሺ መጀመሪያ ላይ ከሮጠ በኋላ ከሆነ ጥሩ ሊሆን ይችላል። እነዚህ ልጆች የውድድር ዓመቱን በተደጋጋሚ ዳይመንድ ሊግ ላይ ሲወዳደሩ ነበር፣ የሌሎች አገራት አትሌቶች ደግሞ ለዚህ የዓለም ቻምፒዮና ብቻ ድምፃቸውን አጥፍተው ሲዘጋጁ የቆዩ አሉ፣ ከነዚህ አትሌቶች ጋር ሲፎካከሩ የእኛ አትሌቶች አቅም ሊያንሳቸው ይችላል ብዬ እሰጋለሁ። አዲስ ዘመን፡- በወንዶች 5ና10 ሺ ሜትር ላይ የተመረጡ አትሌቶች አብዛኞቹ ባለፈው ዙሪች የዳይመንድ ሊግ ፍፃሜ ውድድር ላይ በዩጋንዳዊ አትሌት የተሸነፉበት አጋጣሚ አይዘነጋም። እነዚህ አትሌቶች የተሻለ አቅምና ብቃት እያላቸው ዩጋንዳዊውን አትሌት ለቀውት እንደርስበታለን የሚል ከልክ ያለፈ የራስ መተማመን ነበራቸው፣ ይህ ደግሞ ዋጋ አስከፍሏቸዋል። ዩጋንዳዊው አትሌት ይህን ታክቲክ የዓለም ቻምፒዮናው ላይ እንደሚጠቀመው ገልዷል፣ ተመሳሳይ ነገር በዓለም ቻምፒዮናው አይፈጠርም ማለት ይቻላል?አሰልጣኝ ቶሎሳ፡- እንደ ዳይመንድ ሊጉ ውድድር ይለቁታል ብዬ አላስብም፣ ዩጋንዳዎቹ ጠንካራ ናቸው ያንን ታክቲክ አሁንም ሊጠቀሙበት ይችላሉ፣ እንደ ዳይመንድ ሊጉ አሯሯጭ ባይኖርም አንዱን የራሳቸውን አትሌት ከፊት እንዲወጣ በማድረግ ሊጠቀሙበት ይችላሉ፣ የእኛ አትሌቶች አብረው መሄድ መቻል አለባቸው።አዲስ ዘመን፡- 5ሺ ሜትር ላይ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የተሻለ አቅም ብቻም ሳይሆን ቻምፒዮኑን ሙክታር ኢድሪስን ጨምሮ አራት ሆነው መሰለፋቸው የተሻለ እድል አላቸው። ይሁን እንጂ እነዚህ አትሌቶች በተመሳሳይ አቅምና ብቃት ላይ በመኖራቸው በመካከላቸው ኦጎ ሊፈጠር ይችላል፣ ይህንንም በግል ውድድሮቻቸው ላይ አላስፈላጊ ፉክክር ውስጥ ሲገቡ አስተውለናል፣ በዓለም ቻምፒዮናው እነዚህን አትሌቶች እንደ ቡድን እንዲንቀሳቀሱ ማድረግ ለአሰልጣኞች ከባድ አይሆንም?አሰልጣኝ ቶሎሳ፡- እኔ በቦታው ብሆን አትሌቶቹን ቁጭ አድርጌ ለምን ይሄን አይነት ስህተት እንደሰሩ ጠይቃለሁ፣ ከዚያም ለአገራቸው ሲሉ መተጋገዝ እንዳለባቸው፣ አንዱ ቢሄድ ሌላኛው መጠበቅ እንዳለበት መተማመን ላይ እንደርሳለን። ከእነሱ ባሻገር ሌላ ጠንካራ ተፎካካሪ መኖሩን መዘንጋት እንደሌለባቸውም ማወቅ ያስፈልጋል፣ ስለዚህ ወይ ተፎካካሪዎችን መቁረጥ አልያም ፍጥነት ጠብቆ መጓዝ የግድ ነው፣ ይሄን ከተነጋገሩ ነገሮችን መቀየር ይችላሉ የሚል እምነት አለኝ። አዲስ ዘመን፡- የቡድኑን ዝግጅት ስቴድየም አካባቢ የመመልከት አጋጣሚው ይኖሮታልና የአትሌቶቹን ልምምድ ተመልክተው የታዘቡት ነገር ይኖራል?አሰልጣኝ ቶሎሳ፡- ብዙ ጊዜ አያለሁ፣ በተለይም 5ና 10 ሺ ላይ ያሉ አትሌቶች በአንድ ላይ ሲሰሩ እመለከታለሁ፣ አንዳንዴ ልምምድ ላይም ስመለከታቸው እንደ ውድድር ነው የሚሰሩት፣ ይሄን መቆጣጠር ያስፈልጋል፣ ወደ ቡድን መንፈስ መምጣትና አቅም መቆጠብ አለባቸው።አዲስ ዘመን፡- ዘንድሮ ዓለም ላይ በ10 ሺ ሜትር ጎልቶ የታየ አትሌት አለ ማለት አይቻልም፣ ኢትዮጵያውያን የርቀቱን የተለመደ ክብር ለመረከብ ጊዜው አሁን ነው ማለት ይቻላል?አሰልጣኝ ቶሎሳ፡- አንድ ጠንካራ ኬንያዊ አትሌት አለ፣ ዩጋንዳዎችም ቀላል አይደሉም፣ ብዙ ጊዜ እነዚህ ዳይመንድ ሊግ ላይ አይታዩም፣ በደንብ ተዘጋጅተው እንደሚመጡ እርግጠኛ ነኝ፣ የእኛን አትሌቶች ዳይመንድ ሊግ ላይ ብቻ ነው ያየናቸው፣ የሌሎቹ አገራት አቅምና ብቃት ምን ላይ እንደደረሰ አናውቅም፣ ስለዚህ ጥንቃቄ ያስፈልጋል። አዲስ ዘመን፡- ከረጅም ርቀት በተጨማሪ ሌሎችን የመመልከት አጋጣሚ ነበሮት?አሰልጣኝ ቶሎሳ፡- ማራቶን ላይ ምን እንዳለ አላወኩም፣ ማራቶን ላይ ኬንያውያን በጣም ጠንካራ ናቸው፣ ማጣሪያ አድርገው በሰዓታቸው መሰረት ወደ ካምፕ ይገባሉ የትም መንቀሳቀስ የለም፣ እንደኛ ወደዚህ ወደዚያ የለም፣ ካምፓቸው ከከተማ ውጪ ነው በስርዓት ነው የሚጠበቁት፣ የእኛ አትሌቶች በማኔጀሮቻቸው በየግላቸው ነው የሚሰሩት፣ ይሄ በራሱ አንድ ችግር ነው፣ አትሌቶቹ ሳይተዋወቁ ነው ውድድር ላይ የሚገናኙት፣ ይሄ ማኔጀሮቹ ራሳቸው የሰሩት ስራ እንጂ ፌዴሬሽኑ አይደለም፣ በእኛ ዘመን ከተማ ውስጥ ልምምድ ስንሰራ ተሽከርካሪ የለም፣ የአየር ብክለትም የለም፣ አሁን ከአዲስ አበባ ሃያ ኪሎ ሜትር ወጥቶ የልምምድ ቦታ ማግኘት አይቻልም፣ ይሄ ነገር ትክክል አይደለም ብለን እንደ አማራጭ እኔና ሁሴን ሴቦ አሰላ ሄደን የጥሩነሽ ዲባባን አካዳሚ አይተን፣ ጥናትም አቀረብን፣ ፌዴሬሽኑና አካዳሚው ግን መስማማት አልቻሉም፣ አሰልጣኙም ይሁን አትሌቶቹ ከከተማ መውጣት አለባቸው፣ የኬንያ አትሌቶች ናይሮቢ ውስጥ የሉም፣ የተለያየ ገጠር ውስጥ ነው የሚሰሩት፣ ይሄ ራሱ የእኛ አትሌቶች ላይ ተፅዕኖ አለው፣ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከኬንያ ይበልጣሉ፣ አሰራራችንን መቀየር አልቻልንም፣ ጥናቶችን አልተጠቀምንም፣ አንድ ነገር ይደረጋል ተብሎ በዛው ይቀራል፣ ለውጥ እንዴት ይመጣል?፣ ፌዴሬሽን አካባቢ ያሉ ሰዎች ይሄን መስራት አለባቸው፣ የውጪ ጉዞ ላይ መሯሯት ምንድነው?፣ መሰረት ያለው ነገር አገር ውስጥ መስራት አለባቸው።ፕሮጀክቶች ላይ ምን እንደሚሰራ አይታወቅም፣ ገንዘብና ትጥቅ መላክ ብቻ ዋጋ የለውም፣ ወርዶ የሚሰራና የሚያይ ሙያተኛ የለም፣ ሁላችንም ሙያተኞች እዚህ ከተማ ውስጥ ነው የምንሻማው፣ እኔ በፊት ሙገር ክለብ ውስጥ እሰራለሁ ብሔራዊ ቡድንም አሰለጥናለሁ፣ ስለዚህ ገጠር ድረስ ወርጄ ነው አትሌቶችን የምመለምለው፣ አሁን ይሄን የሚሰራ የለም፣ ተመረቀ እዚሁ አዲስ አበባ ነው፣ ወይ ክለብ ይይዛል ወይም ማኔጀር ጋር ይጠጋል እንጂ ወጣ ብሎ አይሰራም፣ የምንሄደው ወደ ላይ ነው ወደ ታች?፣ መንግስትም ይሄን ማስተካከል አለበት። አንዱ አንዱን ፈርቶ ነው የሚኖረው። አዲስ ዘመን፡- በዘንድሮው የዓለም ቻምፒዮና ኢትዮጵያ ምን አይነት ተስፋ ይኖራታል፣ ስጋትስ? አሰልጣኝ ቶሎሳ፡- በእርግጥ በእኛም መካከል ችግር አለ፣ አንዱ አንዱን የማቅረብ ችግር፣ እኔ አሁን የአሰልጣኞች ማህበር ሰብሳቢ ነኝ፣ አሰልጣኞች ከእኛ ጋር ራሱ ለመገናኘት አይፈልጉም፣ ብሔራዊ ቡድን ላይ ያሉ አሰልጣኞች፣ የእኛው ጓደኞች እኛ ሄደን እንድናናግራቸው እንኳን አይፈልጉም፣ ይሄ ደግሞ ግለኝነትን የሚገልፀው፣ አንዱ ካንዱ እውቀቱን ቢካፈል ለአገር ይጠቅማል እንጂ አይጎዳም፣ እኔ ከሌሎች ሰዎች ጋር እሰራ ነበር፣ ዶክተር ወልደመስቀል፣ ንጉሴ ሮባ ጋር አትሌት ሆኜም አሰልጣኝ ሆኜም ስንት ዓመት ሰራሁ፣ ከእነሱ ብዙ ነገር ተምሬ ነው ብርቅዬ አትሌቶች ያፈራሁት፣ አሁን እንደዚህ አይነት ነገር አይፈለግም፣ እዚያው ፌዴሬሽኑ ጋር ጥገኛ ሆኖ መተማማት ነው ያለው፣ አንድ ሰው ሄዶ ሃሳብ ለማካፈል ቢሞክር ሊያበላሽብን ነው ይላሉ፣ ስለዚህ ዝም ብሎ ማየት ነው፣ ከውድድር በኋላ መነጋገራችን አይቀርም፣ ይቅናችሁ ነው የምንለው።አዲስ ዘመን፡- አሰልጣኝ ሻምበል ቶሎሳ ቆቱ ለሰጡን ጊዜ ከልብ አመሰግናለሁ።አሰልጣኝ ቶሎሳ፡- እኔም አመሰግናለሁ።አዲስ ዘመን ቅዳሜ መስከረም 10/2012ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=18505
1,521
2ስፖርት
«መከላከያ ሰራዊታችን ያሳየን የኢትዮጵያዊነትን ልክ ነው» – ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት የዓለም አቀፍና ሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 8, 2020
24
አስቴር ኤልያስአዲስ አበባ፡- መከላከያ ሰራዊታችን በሶስት ሳምንት ውስጥ በታላቅ ጀብዱ የኢትዮጵያዊነታችንን ልክ እንዳሳየን የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት የዓለም አቀፍና ሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ አስታወቁ ፡፡ዶክተር ቢቂላ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳስታወቁት ፤ በትግራይ ክልል ተሸሽጎ የከረመው ጽንፈኛው የህወሓት ስግብግቡ ጁንታ በአገር   መከላከያ ሰራዊት ላይ የፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ መንግስት የሕግ ማስከበሩን ተግባር ባከናወነበት ወቅት የአገር መከላከያ ሰራዊት ትልቅ ጀብድ በመፈጸም የኢትዮጵያዊነትን ልክ አሳይቶናል ።መከላከያ ሰራዊቱ በሶስት ሳምንት ውስጥ በሰራው ጀብዱ በእርግጥም ታላቅነቱንም አስመስክሯል ፡፡ መከላከያ ሰራዊቱ፤ ‹በአገሬ ከመጣህማ እኔን ታርዳለህ እንጂ ትጥቄን አትፈታም፤ በኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና በአገሬ ማንነት ከመጣህ ትጨርሰኛለህ እንጂ በዘር አትከፋፍለንም የሚል የጀግንነት ጥግ አሳይቷል “ ያሉት ዶክተር ቢቂላ ፤ በተለይም ውስጥ ያሉ አመራሮች ትጥቃቸውን ፈተው ላለመስጠት ያደረጉት ተጋድሎ ታላቅ ነው ብለዋል።ሌላ ኃይል እስኪደርስላቸው ድረስ አንገት ለአንገት ተናንቀው የታገሉ መሆናቸውንም አስታውቀዋል ። ከድሉ ጀርባ ያለው የአገር አንድነት መለከያ ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን እንደሆነም ጠቁመዋል ። እንደ ዶክተር ቢቂላ ገለጻ፤ በዚህም ብቻም ሳይሆን ወደ ፊትም ትልልቅ አገራዊ ፈተናዎች ቢከሰቱ እንኳ መከላከያ ሰራዊቱ ያልቃታል እንጂ አገሩን እንደማያስደፍር ማረጋገጥ ተችሏል።ይህን ጀግንነቱንም በማየት ከኋላው 115 ሚሊዮን ሕዝብ ተገልብጦ ኢትዮጵያ ተነካች በማለት ለመከላከያው ያለውን ድጋፍ ገልጿል፡፡ የአገር መከላከያ ሰራዊትን ኢትዮጵያውያን ከዳር እስከዳር መጥተው ያቋቋሙትና ከየትኛው ብሔርና ኃይማኖት ነህ ሳይል አብሮ የሚኖር የኢትዮጵያዊነት መገለጫ ነው ያሉት ዶክተር ቢቂላ፣ ጁንታው ፤ ዜጎች እንደ አይናቸው ብሌን የሚያዩዋትን ኢትዮጵያን ለማጠልሸት ፤ የኢትዮጵያዊነት መገለጫ፣ የአገራዊ አንድነት ምልክት በሆነው መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት መሰንዘሩን አመልክተዋል ፡፡ ከኢትዮጵያዊነት መገለጫዎች አንዱ መከላከያ ሰራዊታችን ነው ያሉት ኃላፊው ፣ በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ የማይታይ ኢትዮጵያ የለም ያሉት ዶክተር ቢቂላ፣ ይህንን ሰራዊት በዘር ለይተው ማጥቃታቸውንም አመልክተዋል።ይህም የተንኮልና የክፋት ሥራቸው ለታሪክ የሚቀመጥ ነው ብለዋል፡፡ ዩኒቨርስቲን፣ ፌዴራል መንግስትን፣ መከላከያን መንካት ኢትዮጵያ መንካት ነው። የአይንን ብሌን መንካት እንደሆነ ያመለከቱት ዶክተር ቢቂላ፣ ከዚህ ድል ጀርባ ያለውን መከላከያ መንካት ማለት የኢትዮጵያውያን አንድነትና መስተጋብርን መንካት እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡ ከዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ ጋር ያደረገውን ቃለ ምልልስ ሙሉ ቃል ገጽ 6 ይመልከቱ ፡፡አዲስ ዘመን ህዳር 29/2012 ዓ.ም
https://www.press.et/Ama/?p=36927
297
0ሀገር አቀፍ ዜና
ባህልና ስፖርት በኢሬቻ ሩጫ
ስፖርት
September 23, 2019
31
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ስፖርት ሲታሰብ አንዱ አቅጣጫ ያመዝናል። የአበበ ቢቂላ፤ እሸቱ ቱራ፣ ቶለሳ ቆቱ፣ ፊጣ ባይሳ፣ ኃይሌ ገብረስላሴ፣ ደራርቱ ቱሉ፣ ጌጤ ዋሚ፣ ገዛኸኝ አበራ፣ ቀነኒሳ በቀለ፣ ስለሺ ስህን፣ ጥሩነሽ ዲባባና ቤተሰቧ እንዲሁም የበርካቶች መገኛ፤ የኦሮሚያ ክልል። ክልሉ የረጅም ዓመታት የኢትዮጵያ የአትሌቲክስ ስፖርት የጀርባ አጥንት ስለመሆኑም አያጠያይቅም። አሁንም የኦሊምፒክ፣ የዓለም ሻምፒዮና እንዲሁም የበርካታ ውድድሮች ድምቀት እንደሚሆኑ ተስፋ የሚጣልባቸው አትሌቶች በመፍራት ላይ ይገኛሉ። አትሌቲክስና ክልሉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ ናቸው ለማለት የሚያስደፍረውም ለስፖርቱ ምንጭ በመሆኑ ነው። በህዝቡም ዘንድ እንደ ባህል የሚታየው ስፖርቱ፤ አንድ የኢኮኖሚ ምንጭ እስከመሆን ደርሷል። ይህ ከህዝቡ ጋር ከፍተኛ ትስስር ያለው ስፖርት ለባህላዊ ሁነት ማድመቂያ እንዲሁም መልዕክት ለማስተላለፍ ተመራጭ ነው። በኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አድማሱ ዋጋሪ፤ የኢሬቻ በዓል አከባበር ወቅት ወጣቶች የሩጫ፣ የፈረስ ጉግስ እና ሌሎች ውድድሮችን የማድረግ ባህል እንዳላቸው ያስታውሳሉ። ይህም የሚያሳየው ሩጫ የበዓሉ አንድ አካል እንዲሁም የሩጫ ስፖርት ለኦሮሚያ ህዝብም ባህል መሆኑን ነው። በተለይ በዚህ የሽግግር ወቅት በህዝቦች መካከል ጥርጣሬ የበዛበት እንደመሆኑ፤ በሩጫው የሰላምና አንድነትን መልዕክት ለማስተላለፍ እንዳስፈለገ ያስረዳሉ። ትናንት «እሬቻ የሰላምና የአንድነት ተምሳሌት» በሚል መሪ ሀሳብ የተካሄደው የሩጫ ውድድርም የዚህ ማሳያ ነው። ከ150 ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ የሚከበረውን የኢሬቻ በዓል ምክንያት በማድረግ እንዲሁም ስለ እሬቻ በዓል ህዝቡ እንዲያውቅና ባህሉን እንዲረዳ ለማድረግ በአዲስ አበባ በተካሄደው የእሬቻ የሰላም ሩጫ ላይ በሺዎች የሚቆጠር ህዝብ ተገኝቷል። መነሻና መድረሻውን በመስቀል አደባባይ ያደረገው የጎዳና ላይ ሩጫው፤ 10 ኪሎ ሜትር የሸፈነ ነበር። በሩጫው ላይ እንዲሳተፉ ለሁሉም የአትሌቲክስ ክለቦች ጥሪ የቀረበ ሲሆን፤ ከ500 በላይ የሚሆኑ አትሌቶች ከኦሮሚያ፣ ድሬዳዋ፣ አዲስ አበባ፣ ከደቡብ እንዲሁም ከአማራ ክልል ተካፋይ ሆነዋል። በወንዶች መካከል በተካሄደው ውድድር የስሁር ኮንስትራክሽን አትሌቱ በሪሁን አረጋዊ አሸነፊ በመሆን የወርቅ ሜዳሊያ እንዲሁም የ50ሺ ብር ሽልማቱን ወስዷል። ያለፈውን ዓመት በጉዳት ከወድድር ርቆ የቆየው አትሌቱ፤ ብርቱ ተፎካካሪ አለመኖሩ ለአሸናፊነቱ እንደረዳውም ገልጿል። ኃይለማሪያም ኪሮስ እና ደጀኔ ደበላ ደግሞ ከመብራት ኃይል እና ኦሮሚያ ውሃ ስራዎች ስፖርት ክለብ ሁለተኛ እና ሦስተኛ በመሆን ውድድራቸውን አጠናቀዋል። በሴት አትሌቶች በኩልም ኦብሴ አብደታ ከለገጣፎ ለገዳዲ ክለብ አሸናፊ ሆናለች። በግሏ የተሳተፈችው አትሌት መስታወት ፍቅሩ ሁለተኛ ስትሆን፤ የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲዋ አንቻለም ሃይማኖት ሦስተኛ በመሆን የነሃስ ሜዳሊያቸውን አጥልቃለች። ከአንድ እስከ ሦስት ያለውን ደረጃ በመያዝ ውድድራቸውን ያጠናቀቁ አትሌቶችም ከሜዳሊያው ባሻገር፤ የ50ሺ፣ 30 እና 20ሺ ብር ማበረታቻ ተበርክቶላቸዋል። የኦሮሚያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊና የሩጫው ኦርጋናይዘር አቶ ነጋ ቱጂባ፤ ሩጫው ከታሰበው ሰዓት ዘግይቶ ቢጀመርም በመልካም ሁኔታ መጠናቀቁን ይገልጻሉ። የኢትዮጵያን መልካም ገጽታ በዓለም ደረጃ የገነባው የአትሌቲክስ ስፖርት፤ ከአበበ ቢቂላ ጀምሮ ያለው ታሪክ በርካታ አትሌቶች የወጡት ከኦሮሚያ ክልል መሆኑን ያሳያል። አትሌቲክስ ከኦሮሞ እሴት ጋር ሊያያዝ የሚችል በመሆኑም፤ ኢሬቻና አትሌቲክስን በማገናኘት ህዝቡ በእኔነት ስሜት እንዲደግፈውና እንዲያሳድገው ያደርጋል። በየዓመቱ ለሚከበረው የኢሬቻ በዓልም ስፖርታዊ ውድድሩ ይበልጥ ውበት የሚሰጠው ይሆናል። የኦሮሚያ ክልል የኢትዮጵያ አትሌቶች ምንጭ ቢሆንም በዚህ ወቅት ግን ውጤቱ እየቀነሰ መምጣቱ ይታያል። የዚህን ምክንያትም በመገምገም ወደ ቀድሞ ስፍራው ለመመለስ ህዝባዊ መሰረት ማስያዝ የግድ ይሆናል። መሰል ውድድሮች በየዞኑ እና ወረዳው ማካሄድ ቢቻል፤ ህዝቡ ስፖርቱንና አትሌቶችን በባለቤትነት ስሜት በመደገፍ ወደ ምንጭነቱ መመለስ እንደሚቻልም ኃላፊው ይጠቁማሉ። በዓሉም በሰላምና በፍቅር ያለ ኃይማኖትና መሰል ልዩነት የሚያከብር በመሆኑ ይህንን አጠናክሮ መቀጠል ለስፖርቱ የራሱን ሚና የሚጫወት ይሆናል። አሁን በ50ሺ ሰው የተጀመረው ውድድር ወደፊትም ተጠናክሮ ለማስቀጠልና ቁጥሩንም ለማሳደግ ጥረት ይደረጋል። ሩጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት እንዲሁም ለተሳታፊዎችም ኃላፊው ምስጋናቸውን አቅርበዋል። አዲስ ዘመን መስከረም 12/2012 ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=18983
486
2ስፖርት
“ባለፉት 27 ዓመታት በንግዱ ዘርፍ እኩል የሆነ የተሳትፎ ዕድል አልነበረም ” አቶ ክቡር ገና የአፍሪካ ንግድ ምክር ቤት ሥራ አስኪያጅ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 8, 2020
36
ለምለም መንግሥቱአዲስ አበባ፦ ባለፉት 27 ዓመት በነበረው የንግድ ሥርዓት እኩል የሆነ የተሳትፎ እድል እንዳልነበረ የአፍሪካ ንግድ ምክር ቤት ሥራ አስኪያጅ አስታወቁ።የህወሓት ጁንታው ንብረት የሆኑ ድርጅቶች ባልተገባ መልኩ ተወዳዳሪ የሚያደርጋቸውን ድጋፍ ያገኙ እንደነበር ጠቁመዋል ።ሥራ አስኪያጁ አቶ ክቡር ገና በተለይ ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት ፣ ባለፉት 27 ዓመታት የነበረው ሀገራዊ የኢኮኖሚ ሥርዓት ፍትሐዊ ተሳትፎ ያላቸው የንግድ ድርጅቶች እንዲፈጠሩ ምቹ ሁኔታ አልነበረም ። ጉዳዩ ዛሬ እንደ አዲስ ይነሳ እንጂ በጉዳዩ ላይ ብዙ ተብሏል፡፡ለሕዝብም አዲስ ነው ብለው እንደማያምኑና እርሳቸው ቀድሞ የንግድ ምክር ቤት በአሁኑ ደግሞ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ተብሎ የሚጠራው ፕሬዚዳንት ሆነው ሲያገለግሉ በማህበራቸውም ሆነ በተለያየ አጋጣሚ ሁሉ ለግሉ ዘርፍ ከአድሎ ነጻ የሆነ አሰራር እንዲኖር ክፍተቶችን በማሳየት ብዙ ርቀት መሄዳቸውን አስታውሰዋል። ሰሚ ባለመኖሩ እኩል ተሳትፎ ሳይፈጠር አሁን ላይ መደረሱን አመልክተዋል ፡፡ለንግድ ድርጅቶች መቋቋም ዋና መሰረቱ አድሎ የሌለበት ምቹ አሰራር መዘርጋት እንደሆነ የጠቆሙት አቶ ክቡር፤ የህዝባዊ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ጁንታ ቡድን የሆኑ አካላት ንብረት የሆኑ ድርጅቶች ባልተገባ መልኩ ተወዳዳሪ የሚያደርጋቸውን ድጋፍ ያገኙ እንደነበር አመልክተዋል። በቦርድ ስም የሚሰየሙ የመንግሥት ኃላፊዎች እነዚህ የንግድ ድርጅቶች፣ መረጃ እንዲያገኙ ፣ከባንክ በፈለጉ ጊዜ መበደር እንዲችሉ፣ ብድር በወቅቱ ለመመለስ እንዳይገደዱ የሚያደርግ አሰራር የተዘረጋበት ሥርዓት እንደነበር ገልጸዋል። ይህ አይነቱ አሰራር ለብዙዎች አዲስ እንዳልሆነና ሲተችም እንደነበር ያመለከቱት አቶ ክቡር ፣ ይህም የግሉን ዘርፍ ክፉኛ እንደጎዳውና ከውድድር እንዳወጣው አስታውቀዋል ። የንግዱ ማህበረሰብ ከራሱ አልፎ ለሀገርም ሚናውን እንዲወጣ አድርጎታል ከተፈለገ ፍትሐዊ አሰራርን ማስፈን እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡መንግሥታት የሕዝብን ጥቅም እናስቀድማለን ቢሉም ይህንን ቃላቸውን በተግባር ሲያውሉት አለማየታቸውን የጠቆሙት አቶ ክቡር፤የራሳቸው ጥቅም የሚያሸንፋቸው መንግሥታትን ማስተዋላቸውን ተናግረዋል፡፡ችግሩ ዓለምአቀፋዊ ቢሆንም አፍሪካ ላይ ባለው የአቅም ውሱንነት ችግሩ የከፋ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡በችግሮች ዙሪያ በተለያዩ ወቅቶች በሚመቻቹ መድረኮች ማህበሩ የሚሰጣቸው ምክረ ሀሳቦች ተቀባይነት እንደሌላቸውና የሚደመጥም እንዳልነበር ያመለከቱት አቶ ክቡር ፣ አንዳንዶች ከሚፈልጉት ጋር ተነጋግረው በሚፈልጉት መንገድ ጉዳያቸውን ማስጨረስ የሚችሉበት እንደነበር አስታውሰዋል፡፡ማህበራትም ሆኑ መንግሥታት ሚናቸው የንግዱ ማህበረሰብ ፍትሀዊ በሆነ መንገድ ለክፍተቶች መፍትሄ መስጠት እንደሆነ የጠቆሙት አቶ ክቡር ፣ ባለፉት 27 ዓመታት ይህ ሲሆን አልታየም ፤ የንግድ ድርጅቶች ባልተገባ መንገድ ከውድድር ውጪ መሆናቸውን አስታውቀዋል። የንግድ ድርጅቶች ከማነቆ የተላቀቁ አለመሆናቸውንም አመልክተዋል፡፡አዲስ ዘመን ህዳር 29/2012 ዓ.ም
https://www.press.et/Ama/?p=36939
307
0ሀገር አቀፍ ዜና
የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዚት አገልግሎት በኃይል ገመድና ኬብል ስርቆት መቸገሩን አስታወቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 8, 2020
28
በኃይሉ አበራአዲስ አበባ:- የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዚት አገልግሎት የኃይል ገመዶች እና ኬብሎች ስርቆት መቸገሩን አስታወቀ። በዚህም ተገልጋዮቹ መንገላታቸውና ኮርፖሬሽኑም ለተደጋጋሚ ኪሳራ መዳረጉን ገለጸ።የአገልግሎት ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ሙሉቀን አሰፋ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት ፣የኃይል ገመዶች እና ኬብሎች በሌቦች ተቆርጠው በመወሰዳቸው ምክንያት ሰሞኑን ከመሿለኪያ ሚኒሊክ አደባባይ እና ከጦርኃይሎች ስቴዲየም ያለው መስመር በከፊል አገልግሎቱ ተቋርጧል። በዚህም ደንበኞቹ ለችግር ተጋልጠዋል።እስካሁን 750 የሚደርሱ የኃይል ኬብሎች እና 15 የኃይል ማሰራጫ ገመዶች ስርቆት እንዳጋጠመ የገለጹት ኢንጂነር ሙሉቀን ፣ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ ማበጀት ባለመቻሉ አገልግሎቱ ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደሚገኝ ገልጸዋል።የኃይል ገመዱን ያገኙ የሚመስላቸው ሌቦች የፋይበር ኦፕቲክስ ገመዶችን ጭምር ስለሚቆርጡ ፣ እነዚህን መልሶ ለማግኘትና ለመጠገን ቢያንስ አንድ ሙሉ ቀን የሚፈልግ መሆኑ የጥገና ስራውን አስቸጋሪ አድርጎታል ብለዋል። በዚህም የተነሳ አገልግሎቱን በከፊል ለማቋረጥ መገደዱን አስታውቀዋል። የህብረተሰቡ እንግልትና ችግር ሳይጨምር በቀን እስከ 200 ሺ ብር የሚገመት ኪሳራ እየደረሰበት መሆኑንም ጠቁመዋል።ባለፉት ሶስት ቀናት ከቃሊቲ እስከ ስታዲየምና ከሀያት እስከ ስቴዲየም ብቻ አገልግሎት ለመስጠት መገደዱን ያመለከቱት ኃላፊው፣ አሁን ላይ በቀን ሳይቀር የመሰረቅ ችግር እያጋጠመው እንደሚገኝም ገልጸዋል። ከዚህም ውጭ ጥገና የተደረገለትን ሆነ ብለው አላቀው የሚሄዱበት ሁኔታ መኖሩንም አመልክተዋል ።ችግሩን ለመፍታት በቅንጅት ለመስራት እስከ ፖሊስ ኮሚሽን ድረስ የተሄደበት ርቀት ቢኖርም ዘላቂ መፍትሄ ባለመገኘቱ ችግሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ መሄዱን አስታውቀዋል ።የባቡር መስመሮቹ አስፈላጊው ጥገና ተደርጎላቸው ከዛሬ ጀምሮ ሙሉ አገልግሎት እንደሚሰጡ ገልጸዋል።ከወቅታዊው የጸጥታ ሁኔታ አንጻር የ24 ሰአት ጥበቃ ለማድረግ ኮርፖሬሽኑ ተጨማሪ የጥበቃ ኤጀንቶችን በተመረጡ ቦታዎች መመደብ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እየመከረ ይገኛል ብለዋል።አዲስ ዘመን ህዳር 29/2012 ዓ.ም
https://www.press.et/Ama/?p=36934
219
0ሀገር አቀፍ ዜና
አርሶ አደሮቹ ወደ መደበኛ የስራ እንቅስቃሴያቸው መመለሳቸውን ገለጹ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 8, 2020
18
ኢያሱ መሰለ ኦፍላ፡- በደቡባዊ ዞን ኦፍላ ወረዳ ሀየሎ ቀበሌ የሚኖሩ አርሶ አደሮች ሰላም በመስፈኑ ወደ መደበኛ ህይወታቸው መመለሳቸውን ገለጹ ።የጁንታው ታጣቂዎች መንደራቸው ውስጥ በመመሸጋቸው ከአካባቢያቸው ርቀው ለመሄድ ተገደው እንደነበር አመለከቱ ።ከሁለት ሳምንት ቆይታ በኋላም የሕግ ማስከበር ሥራው በአጭር ጊዜ በመጠናቀቁ ወደ መንደራቸው ተመልሰው ምርታቸውን በመሰብሰብ ላይ ያገኘናቸው የኦፍላ ወረዳ ሃየሎ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ቄስ መላከ ብርሃን ከበደ ግርማይ እንዳስታወቁት ፣ የጁንታው ታጣቂዎች በግራካሶና አካባቢው በመመሸጋቸው ቤተሰቦቻቸውንና ያሏቸውን እንሰሳት ይዘው ለመሸሽ ተገደው ነበር ።ሕግ የማስከበር እርምጃው በአጭር ጊዜ ውስጥ የተጠናቀቀ በመሆኑ አዝመራ በመሰብሰቡ ላይ እንደሚገኙ የጠቆሙት ቄስ መላከ ብርሃን ከበደ፣ እስካሁን ሰብል በመሰብሰብ ያጋጠማቸው ችግር እንደሌለ አስታውቀዋል ፡፡አርሶ አደሩ አምርቶና ለፍቶ ከመብላት ውጭ ሌላ ዓላማ የለውም ያሉት ቄስ መላከ ብርሃን ፣ የተለመደ ስራን ለማከናወን ሰላም ያስፈልገዋል ፤ በኣካባቢው ሰላም በመኖሩም ተጋግዘው ምርታቸውን በማስገባት ላይ ነን ብለዋል ።ሌላው በስራ ላይ ያገኘናቸው የኦፍላ ወረዳ ሃየሎ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ሃይሌ አበራ አርሶ አደሩ ሰርቶ ለመኖርም ይሁን አምርቶ ለሌሎች ለመትረፍ ሰላም ያስፈልጋል ብለዋል።በሰላም እጦት ምክንያት ለሁለት ሳምንት አካባቢውን ለቀው መሄዳቸውን ተናግረዋል።የሀገር መከላከያ ሰራዊት የአካባቢውን ሰላም በማረጋጋት ወደ ቀደመ ህይወታችን መልሶናል ያሉት አርሶ አደሩ ፣ አዝመራቸውን ምንም አይነት ጉዳት ሳይደርስበት በወቅቱ ለመሰብሰብ መቻላቸውንም ገልጸዋል።በደርግ ሥርዓተ መንግሥት በአካባቢው በነበረው ጦርነት እናታቸውን ፣ ወንድማቸውን፣ ባለቤታቸውንና በርካታ ንብረታቸውን እንዳሳጣቸው የተናገሩት አስተያየት ሰጪው ጦርነቱ መጥፎ ጠባሳ ጥሎባቸው ያለፈ በመሆኑ ዳግም በአካባቢያቸው እንዲከሰት የማይፈልጉ መሆናቸውን ገልጸዋል።የትግራይ ሕዝብ ዘመኑን ሙሉ በጦርነት እንዳሳለፈ የተናገሩት አርሶ አደሩ፣ ይህም ለተለያዩ ችግሮች ዳርጎታል ብለዋል።መንግሥት ሕግ ከማስከበር አንጻር እየወሰደ ያለው እርምጃም ተገቢ እንደሆነና በተለይም የአርሶ አደሩን እንግልት እንደሚቀንስ ገልጸዋል።ገበሬ አርሶ የሚያበላና ፣ ለመንግስት የሚገብር እንደሆነ የተናገሩት አቶ ሃይሌ በስራ የሚደክመው ሳያንሰው ጽንፈኞች በሚፈጥሩት ችግር ምክንያት ሊጉላላ አይገባም ብለዋል።የጥፋት ቡድኑ በሰላማዊ መንገድ እጁን መስጠት እንዳለበትና የቡድኑ ታጣቂ የሆኑ የአርሶ አደር ልጆችም ከወላጆቻቸው ጋር ሆነው አምርተው እንዲኖሩ መክረዋል፡፡አዲስ ዘመን ህዳር 29/2012 ዓ.ም
https://www.press.et/Ama/?p=36940
274
0ሀገር አቀፍ ዜና
“አገራዊ ለውጡ ከተጀመረ አንስቶ ሕዝቦችን ያራራቁ ግንቦች እየፈረሱ ናቸው” ደመቀ መኮንን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
ሀገር አቀፍ ዜና
December 9, 2020
8
በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ፦ አገራዊ ለውጡ ከተጀመረ አንስቶ ሕዝቦችን ያራራቁ ግንቦች እየፈረሱ መሆናቸውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን አስታወቁ ። ኢትዮጵያ ሁሉም ዜጋ በእኩልነት የሚንቀሳቀስባትና የዜጎች ክብር የሰፈነባት፤ ሁሉም የየራሱን ማንነት በነጻነት የሚያንጸባርቅባት እንድትሆን ተግቶ መስራት እንደሚያስፈልግ አመለከቱ ። በአገር አቀፍ ደረጃ 15ኛውን የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ምክንያት በማድረግ ትናንት በአዲስ አበባ በተካሄደ ውይይት ፣ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እንዳስታወቁት ፣የለውጥ ጉዞው የኢትዮጵያ ሕዝቦች በአብሮነትና በአንድነት ወደ ብልጽግና ጎዳና እንዲሻገሩ የሚያስችል ነው። ሁሉም ዜጋ በእኩልነት የሚንቀሳቀስባት፣ የዜጎች ክብር የሰፈነባት የተሻለች አገር እንድትሆን ተግቶ መስራት እንደሚያስፈልግ ያመለከቱት አቶ ደመቀ ፣ እያንዳንዱ ብሔር ፣ብሔረሰብ የየራሱ ቋንቋ፣ ባህልና ትውፊትና ታሪክ በነጻነት የሚስተናገዱባት ስልጡን ምድር እንድትሆን ጠንክሮ መስራት ተገቢ መሆኑን ጠቁመዋል። ሁሉም በወንድማማችነት፣ በመተሳሰብና አንዱ ለሌላው ጠበቃና ዋስትና በመሆን ለሕብረ ብሔራዊ አንድነቱ ዘብ እንዲቆምም ጠይቀዋል።የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አደም ፋራህ በበኩላቸው ፣ከለውጡ በኋላ በአገሪቷ በብዙ ዘርፎች እመርታዊ ለውጦች መመዝገባቸውን ገልጸዋል። ከለውጡ በፊት ከፍተኛ የዴሞክራሲ እጦት፣ ሥራ አጥነትና የሰብዓዊ መብት በሰፊው ይስተዋል እንደነበር ጠቁመዋል።ይህ ሁሉ ችግር ተደምሮ ብሔር፣ ብሔረሰቦች ለውጥ እንዲመጣ መታገላቸውንና የለውጡ አመራርም የተሻሉ ሥራዎችን በመሥራት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል። የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሓመድም፤ ከለውጡ በኋላ የተሻሉ ሁኔታዎች መምጣታቸውን ፤ ሌላው ቢቀር በዚህ ወቅት ሕዝቦችን የሚያቀራረቡ ትርክቶች መጀመራቸውንና ከፋፋይ አስተሳሰቦች እየቀነሱ መምጣታቸውን አስታውቀዋል።በተጨማሪም ሚዛናዊ የፖለቲካ ውክልና እየመጣ መሆኑን አመልክተው ፣ ከዚህ በፊት አጋር ተብለው እንደ ሁለተኛ ዜጋ የሚታዩ ክልሎች ከሌሎች ጋር እኩል በመሆን አንድ ላይ ተቀምጠው በሀገር ጉዳይ ላይ መምከርና መወሰን መቻላቸውን ጠቁመዋል ።የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ፤በተለያዩ ሁኔታዎች አመቺ ያልሆኑ ሕጎች መሻሻላቸውን አንስተዋል።ከተሻሻሉት ሕጎች መካከል ጥቅል የሆነውን የሕገ መንግሥት ድንጋጌ ለአተገባበር በሚያመች መልኩ መሻሻሉን ጠቅሰዋል።የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ የአሜሪካን ሕገ መንግሥት ዋቢ አድርገው የሕገ መንግሥት መሻሻል ያለውን ጥቅም አብራርተዋል።አዲስ ዘመን ህዳር 30/2013
https://www.press.et/Ama/?p=36979
277
0ሀገር አቀፍ ዜና
«ጁንታውና ኦነግ ሸኔን የሚያመሳስላቸው ዓላማቸውን በኃይል ለማስፈጸም የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ነው» – አቶ ቶሌራ አደባ የኦነግ ቃል አቀባይ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 8, 2020
76
አስቴር ኤልያስአዲስ አበባ፡- የህወሓት ጁንታው እና ኦነግ ሸኔ የሚያመሳስላቸው ዓላማቸውን በኃይል ለማስፈጸም የሚያደርጉት እንቅስቃሴ መሆኑን የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ አደባ አስታወቁ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በንጹኃን ኢትዮጵያውያን ላይ እየተወሰዱ ያሉ እኩይ ተግባሮች ከባህላችንም ከባህሪያችንም ውጭ የሆኑ እንደሆኑ አመለከቱ ።የኦነግ ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ፣ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቁት፤ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ለረጅም ዓመታት ተጋብተውና ተዋልደው እንዲሁም ልዩነት ቢኖራቸውም ተቻችለውና ተከባብረው የኖሩ ሕዝቦች ናቸው። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን እየታዩ ያሉ እንቅስቃዎችና እየተወሰዱ ያሉ እኩይ ድርጊቶች ከአሁን በፊት ያልተለመዱ ናቸው። የዚህ አኩይ ተግባር ዋና አራማጅ የህወሓት ጁንታ ነው ፣ ኦነግ ሸኔም በተመሳሳይ መልኩ ዓላማውን በዜጎች ላይ በኃይል ለመጫን እየታተረ ነው ።ሁለቱም ቡድኖች የእኔን መንገድና ሐሳብ ተቀበል፤ ካልተቀበልክ መኖር አትችልም እንደሚሉ አቶ ቶሌራ አመልክተው፣ በመጀመሪያም ቢሆን በኃይል የመጣው ወያኔ፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተጋጋለው የሕዝቦች አመጽ ከያዘው ስልጣን በኃይል ሲያስወግደው ያጣውን ስልጣን አሁንም በድጋሚ በኃይል ለመያዝ ትግል ሲያደርግ መቆየቱን ጠቁመዋል። ኦነግ ሸኔ የሚባለው ቡድን ደግሞ ኦነግ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ወደ አገር ቤት ሲገባ አፈንግጦ የቀረ ቡድን ነው ፤ ያፈነገጠበትም ምክንያት ሰላማዊው መንገድ አያዋጣኝምና የትጥቅ ትግሉን እቀጥልበታለሁ በሚል አዲስ ዘመን ህዳር 29/2012 ዓ.ም  አቋም እንደሆነ ገልጸዋል። ቃል አቀባዩ፣ ኦነግ ሸኔ ዓላማዬንና የፈለኩትን ነገር በጠበመንጃ አፈሙዝ አስገኛለሁ፤ ሕዝቡም ደግሞ በግዴታ እኔን መደገፍ አለበት ብሎ የሚደግፉትን እየተውና ሌሎቹን እያስፈራራ እንዲሁም እያስገደደ በኃይል ወደስልጣን ለመምጣት የሚሰራ ቡድን መሆኑ ከህወሓት ጁንታ ጋር ያመሳስላቸዋል ብለዋል። በሌላ በኩል ደግሞ የበለጠ ሊያቀራርባቸው የሚችለው ጉዳይ በሕዝቦች መካከል መቃቃር እና ቅራኔ ሲኖር ዓላማ ጭነን ለማሳካት ምቹ ሁኔታን ይፈጥርልናል ማለታቸው እንደሆነም አስታውቀዋል። በመሰረቱ እየተካሄደ ባለው የሕግ ማስከበር ዋናው ሰንኮፉ ከተነቀለ የኦነግ ሸኔ ጉዳይ ያን ያህል ስጋት እንደማይሆን ያመለከቱት ቃል አቀባዩ ፣ የሕዝቦች ንቃተ ህሊና ከትናትናው ይልቅ ዛሬ የተሻለ ነው ። ነገ ደግሞ ይበልጥ ይጎለብታል ። በተለይ ደግሞ ሕዝቡ ጥቅሙንና መብቱን በአግባቡ እያወቀ ሲመጣ የትኛውም ኃይል ከአሁን በኋላ በኃይልና በጠመንጃ አፈሙዝ አስገድዶ ሐሳቤን ተቀበል ቢል ተቀባይነት እንደማይኖረው አመልክተዋል። የጁንታው ለአብነት መውሰድ ከተቻለ የትግራይ ሕዝብና ህወሓት አንድ ነው፤ መለየት አይቻልም በማለት ሲናገሩ ነበር ያሉት ቃል አቀባዩ፣ እሱ ደግሞ ትክክል እንዳልሆነ ባለፈው አንድ ወር ውስጥ በተጨባጭ በተግባር ለማየት ተችሏል ብለዋል። የጁንታውን ቡድን ዓላማ በማስፈጸም ላይ ያሉት አንድም በጥቅም የተሳሰሩ ሁለትም ተገድው እንዲዋጉ የተደረጉና መሄጃ እና አማራጭ ያጡ እንደሆኑ ጠቁመዋል ። ጁንታው ለአገራችንም ሆነ ለሕዝባችን ጠቃሚ ነው ብለው አምነውበት የሚታለሉ አሉ ብሎ መገመት እንደሚከብድ አስታውቀዋል። በዚህ አይነት ወደሥልጣን መምጣትም ሆነ ተቀባይነትን ለማግኘት የሚደረግ ሙከራ ከአሁን በኋላ ቦታ እንደሌለው የጠቆሙት አቶ ቶሌራ፣ እነዚሕ ኃይሎች ከዚህ በኋላ የኢትዮጵያ ስጋት ናቸው የሚል ነገር ጨርሶ እንደማይታየው ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ሕዝቦች ለረጅም ዓመታት ተጋብተውና ተዋልደው እንዲሁም ልዩነት ቢኖራቸውም ተቻችለውና ተከባብረው የኖሩ ሕዝቦች ናቸው ፤ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን እየታዩ ያሉ እንቅስቃዎችና እየተወሰዱ ያሉ እኩይ ድርጊቶች ከአሁን በፊት ያልተለመዱ እንደሆኑ ጠቅሰዋል። በተለይም ደግሞ የኦሮሚያ ሁኔታን በሚመለከት በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሕዝቦች ሁሉ ኦሮሚያ ውስጥ ያሉ ሕዝቦች ናቸው ማለት ይቻላል ብለዋል። እንደ አቶ ቶሌራ ከሆነ ፤ በመሰረቱ የዚህ አይነት ዓላማ አራማጆች እነማን ናቸው በሚባልበት ጊዜ ዋነኛ ተጠያቂ የሚሆነው የህወሓት ጁንታ ነው። ቡድኑ ከመጀመሪያውኑ ጀምሮ ሕዝቦች በእኩልነትና በመፈቃቀር ላይ ተመስርተው እንዲኖሩ የሚፈልግ አልነበረም። ጥላቻና ቅሬታ ተባብሶ በቅሬታዎች መሃል እሱ እድሜውን ለማራዘም የሚተጋ ቡድን ነው።አሁንም ቢሆን በቅርቡ በማይካድራ የተፈጸመው ሁኔታ በሕዝቦች መካከል ጥላቻና ጥርጣሬ እንዲሁም መገዳደል ሰፍኖ ሕዝቦች ተፋጅተው ወደ እርስ በእርስ ጦርነት አምርተው አገሪቱ እንድትፈርስ አስበው ያደረጉት ነው ብለዋል። በአንድ ቀን ተነስተው የፈጸሙት ነገር ሳይሆን ረጅም ጊዜ አቅደው የሰሩበት እንደሆነም አመልክተዋል። በዛ አካባቢ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም ክልሎች የዚያን አይነት ሁኔታዎች እንዲፈጠሩና ዓላማቸውንም በኃይል ለመጫን እንደሚሰሩ የታየ ጉዳይ ነው። የጠነከረችና ሕዝቦች በእኩልነት ተቻችለው የሚኖሩባት የበለጸገች አገር እንድትገነባ ፍላጎታቸው ስላልሆነም ያንን ለማስቀጠል በማሰብ ከባህላችንም ፤ ከባህሪያችንም ውጭ የሆኑ የጭካኔ እርምጃዎችን ወስደዋል ብለዋል። አዲስ ዘመን ህዳር 29/2012 ዓ.ም
https://www.press.et/Ama/?p=36933
547
0ሀገር አቀፍ ዜና
የትግራይ ክልል ወደቀደመው መረጋጋትና ሰላም እየተመለሰ መሆኑ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 9, 2020
39
ፋንታነሽ ክንዴ አዲስ አበባ፡- የትግራይ ክልል ወደቀደመ ሰላሙና መረጋጋት እየተመለሰ መሆኑን የትግራይ ብልጽግና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ነብዩ ስሁልሚካኤል አስታወቁ::በክልሉ የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማስጀመር የትምህርት ሚኒስቴር ተጨማሪ 50 ሚሊዮን ብር መመደቡን ገለጹ:: አቶ ነብዩ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቁት፤ በህወሓት ጁንታ ወደ አለመረጋጋት ገብቶ የነበረው የትግራይ ክልል አሁን ላይ ወደቀደመ ሰላምና መረጋጋቱ እየተመለሰ ይገኛል:: ችግሩ ከተፈጠረበት ዕለት ጀምሮ ጉዳዩ ሀገራዊ ጉዳይ ተደርጎ ከፍተኛ ርብርብ እንደተደረገበት እንደሚገኝ ያስታወቁት አቶ ነብዩ ፣ የተገኘው ውጤት ነገሮች በጋራ ሲሰሩ ምን ያህል አመርቂ ውጤት ማግኘት እንደሚቻል ያሳየ ነው ብለዋል ::አሁን ላይ በክልሉ መደበኛ ሕይወት እየተጀመረ ነው፤ የፈረሰው አስተዳደር በጊዜያዊ አስተዳደር እየተተካ ነው ፤ ሕዝቡም እየተወያየ ይምራኝ የሚለው እና ራሱ የመረጠው አካል እንዲመራው እየተደረገ መሆኑን አመልክተዋል::በአክሱም፣ በሽሬ ፣ በአላማጣ በአጠቃላይ ምዕራብ ትግራይና ደቡብ ትግራይ መቀሌ ጨምሮ በሌሎች አካባቢዎች ላይም ሕዝቡ እየተወያየ መሪውን እየመረጠና ወደመረጋጋት እየተመለሰ መሆኑን አብራርተዋል::አገልግሎት ሰጭ የመንግሥት ተቋማትን ወደ ስራ እየተመለሱ መሆኑንም ገልጸዋል::ከመሰረታዊ አገልግሎትና ከሰብዓዊ ድጋፍ ጋር ተያይዞ ተቋርጠው የነበሩ አገልግሎቶች ቶሎ ወደ ሥራቸው እንዲገቡ ለማድረግ የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት እርብርብ እያደረጉ መሆኑን የገለጹት አቶ ነብዩ፤ ከዚህ ጋር በተያያዘ የትምህርት ሚኒስቴር ተጨማሪ 50 ሚሊዮን ብር በመመደብ የመማር ማስተማር ሂደቱን ወደመደበኛ እንቅስቃሴ ለመመለስ እየተሰራ እንደሆነም አስታውቀዋል::ኮቪድን ከመከላከል አንጻርም ወደ 700ሺ የሚሆን የፊት መሸፈኛ ጭምብል በነጻ ለተማሪዎች እንዲታደል ተወስኖ እንቅስቃሴ መጀመሩን ጠቁመዋል። እንደ አቶ ነብዩ ማብራሪያ፤ ክልሉን ወደነበረበት ለመመለስ ሁሉም አካላት የተቀናጀ ሥራ እየሰሩ ነው፤ የትግራይ ብልጽግናም የሚጠበቅበትን እየተወጣ ይገኛል::በዚህም መሰረታዊ አገልግሎቶች ስራ እንዲጀምሩ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል ። ጉዳት የደረሰባቸውን እንደ መንገድና ድልድይ የመሳሰሉ የልማት አውታሮች እንዲጠገኑና ለሕዝቡ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል::በዚህ ረገድ መንግስት በዋናነት የፈረሰውን የቀድሞ አስተዳደር በአዲሱ አስተዳደር በመተካት ሕዝቡ ተገቢውን አገልግሎት እንዲያገኝ እና ቀጣይ ልማቶቹን እንዲያረጋግጥ ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል ::የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ሰሞኑን ባካሄደው ስብሰባ በትግራይ ክልል የተከሰተው ችግር እንዴት እንደተፈጠረና እንዴት እንደተቀለበሰ ትኩረት ሰጥቶ መገምገሙን ያስታወቁት አቶ ነብዩ፤ ትግራይን መልሶ ለማልማትና ለመገንባት ጠንካራ ሥራ መሰራት እንዳለበት አቅጣጫ መቀመጡንም አስታውቀዋል::ከዚህ ባሻገር የትግራይ ህዝብ ከጁንታው ጎን ባለመሆኑና ሊደብቀው ስላልፈቀደ የሕግ ማስከበር ስራው በአጭር ጊዜ እንዲጠናቀቅና መከላከያው ድል እንዲቀዳጅ የማይተካ ድጋፍ በማድረግ እንዲሁም የተፈጠረውን ችግር ለመቀልበስ በተከናወኑ እልህ አስጨራሽ ስራዎች ውስጥ ለነበረው ሚና ሥራ አሥፈጻሚው ለትግራይ ሕዝብ እውቅና መስጠቱን ገልጸዋል::የጁንታው ውድቀት ማለት የትግራይ ሕዝብና ወጣት ውድቀት ማለት እንዳልሆነ ያስታወቁት አቶ ነብዩ ፣ ወጣቱ ለውጡ የራሱ መሆኑን ተገንዝቦ በቁርጠኝነት መንቀሳቀስ እንዳለበት አመልክተዋል ::ወንጀለኞችን በአጭር ጊዜ ለሕግ ለማቅረብና የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ሕዝቡ በተለይም የትግራይ ወጣት ቀደም ሲል ሲያደርግ እንደነበረው የራሱን የማይተካ ሚና መወጣት እንደሚኖርበት አስታውቀዋል ።አዲስ ዘመን ህዳር 30/2013
https://www.press.et/Ama/?p=36977
381
0ሀገር አቀፍ ዜና
በሃገር ክህደት እና በሰብአዊ መብት ጥሰት ወንጀል የተጠረጠሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ነባር አመራሮች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ ወጣ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 9, 2020
8
በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ ፦በሃገር ክህደት እና በሰብአዊ መብት ጥሰት ወንጀል የተጠረጠሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በነበሩ አመራሮች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ መውጣቱን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ::ከኮሚሽኑ ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ፣ተጠርጣሪዎቹ መንግስት እና ሕዝብ የጣለባቸውን ከባድ ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው መቀመጫቸውን ትግራይ ክልል በማድረግ የህወሓት ፀረ-ሰላም እና ፀረ-ሕዝብ ከሆኑ ከፍተኛ አመራሮች ተልዕኮ ተቀብለው ሲንቀሳቀሱ ነበር ::ከዚህ ባለፈም በጽንፈኝነት አስተሳሰብ በመነሣት በኃይል ወደ ስልጣን የመምጣት ፍላጎትን ካነገቡ ፀረ-ሰላም ኃይሎች ተልዕኮ በመቀበል በሀገር ውስጥ ሌሎችን በማደራጀት ሀገር የመበተን፣ ሁከትና ብጥብጥ እንዲፈጠር እና ሕገ-መንግስታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የሚጥል ተግባር ውስጥ በቀጥታ እና በተዘዋዋሪ መንገድ በመሳተፍ ሕዝብ በመንግሥት ላይ አመኔታ እንዳይኖረው በማድረግ በሃገር ክህደት እና በሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል የተጠረጠሩ በተለያዩ የአመራር ደረጃ ላይ የነበሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮች የመያዣ ትዕዛዝ እንደ ወጣባቸው አስታውቋል::የመያዣ ትዕዛዝ የወጣባቸው ተጠርጣሪዎች1. ኮማንደር ሰለሞን አብርሃ ብስራት2. ኮማንደር ኃይለማርያም ብርሃኔ ገብረማርያም3. ምክትል ኢንስፔክተር ክብሮም ገብሩ ገብረእግዚአብሄር4. ምክትል ኢንስፔክተር አረጋዊ ገብረሂወት አስፋው5. ረዳት ኢንስፔክተር ገዛኢ ገብረሂወት ገብረስላሴ6. ረዳት ኢንስፔክተር ተስፋ ኪሮስ ግደይ7. ረዳት ኢንስፔክተር አርአያ ገብረአናንያ ኪዳኑ8. ረዳት ኢንስፔክተር ሰለሞን ወላይ ወልደአብዝጊ9. ዋና ሳጅን ሀይላይ ወልዱ ገብረማርያም10. ዋና ሳጅን ሀፍቱ ካህሳይ አብርሃ ናቸው።በመሆኑም መላው ህዝብ በተለይም ሰላም ወዳዱ የትግራይ ሕዝብ፣ እንዲሁም የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የፖሊስ ሰራዊትና የደህንነት ተቋማት እነዚህን የጁንታው የህዋሓት የጥፋት ቡድን ተፈላጊዎች አባላትን አድኖ ለህግ ለማቅረብ እየተደረገ ባለው ተግባር በያሉበት የድርሻቸውን እንዲወጡ ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል::በቀጣይም የጁንታው ርዝራዥ ቡድን ተጠርጣሪዎችን ተከታትሎ በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ የማድረግ ስራውን አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን በመግለጽ በጉዳዩ ዙሪያ ተከታታይ መረጃዎችን በመገናኛ ብዙሃን በኩል ለህብረተሰቡ ይፋ እንደሚያደርግ ኮሚሽኑ አስታውቋል::አዲስ ዘመን ህዳር 30/2013
https://www.press.et/Ama/?p=36978
235
0ሀገር አቀፍ ዜና
የሰብዓዊ መብት አከባበር ላይ የነበረውን ችግር ለመቅረፍ በህግ ማዕቀፎች ላይ ማሻሻያዎች እንደሚደረጉ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 9, 2020
10
ዋለልኝ አየለአዲስ አበባ፡- በሰብዓዊ መብት አከባበር ላይ የነበረውን ችግር ለመቅረፍ በሕግ ማእቀፎች ላይ ማሻሻያዎች እንደሚደረጉ በፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የብሔራዊ የሰብዓዊ መብት የድርጊት መርሐ ግብር ጽሕፈት ቤት ገለጸ::በፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የብሔራዊ የሰብዓዊ መብት የድርጊት መርሐ ግብር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ይበቃል ግዛው በተለይም ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ የሰብዓዊ መብት የሕግ ማዕቀፎችን ለማሻሻል ረቂቅ ሰነድ ተዘጋጅቷል። ሰነዱ በክልሎች የሚታዩ የሰብዓዊ መብት ጉዳዮችን በአግባቡ የሚለይ ነው::የድርጊት መርሐ ግብሩ ሦስተኛው ሲሆን ከዚህ በፊት ከነበሩት የተሻለ ለማድረግ እየተሰራ ነው:: ከለውጡ በፊት የነበሩት የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ሰፊ ፈተና የነበረባቸው ናቸው ያሉት አቶ ይበቃል ፣ አንደኛውና ሁለተኛው የሰብዓዊ መብት የድርጊት መርሐ ግብሮች አፈጻጸም በነበረው ፖለቲካዊ ዓውድ አመርቂ አልነበረም ብለዋል ። የአፈፃፀም ውስንነቶች እንደነበሩበትም አስታውቀዋል ::ከለውጡ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀው ሦስተኛው ረቂቅ ሰነድ ብዙ ማሻሻያዎችን መያዙን ያመለከቱት ኃላፊው ፣ ለውጡ ሰብዓዊ መብቶችን ለማስከበር ምቹ ሁኔታ የፈጠረ በመሆኑ የረቂቅ ሰነዱ ይዘት በለውጡ ዓውድ የተቃኘ ነው ብለዋል:: እንደ አቶ ይበቃል ገለጻ፤ ከሕግ አንፃር ሰብዓዊ መብቶችን ይበልጥ ለማስከበር እንዲያስችሉ አዳዲስ የህግ ማዕቀፎች ይወጣሉ::መንግስት በዓለም አቀፍ ግዴታዎች ውስጥ ሊፈጽማቸው የሚችል ኃላፊነቶች ይኖሩታል::በፖለቲካዊና የሲቪል መብቶች፣ በሴቶችና ህጻናት፣ በአረጋውያን መብቶች ላይ አዳዲስ የአሰራር ሥርዓቶች ይዘረጋሉ::ሰብዓዊ መብት ሲባል በብዙዎች አዕምሮ የሚመጣው የፍትሕ ተቋማት ላይ ቢሆንም ሰብዓዊ መብት በሁሉም ቦታ ያለ ነው የሚሉት አቶ ይበቃል ፣ ይህን ለማስፈጸም በተዘጋጀው ረቂቅ የድርጊት መርሐ ግብር ላይ በርካታ ተቋማት እንዲካተቱ ተደርጓል::የመሰረተ ልማት ሥራዎች ሁሉ የሰብዓዊ መብት ጉዳይ ያለባቸው ናቸው:: ሰብዓዊ መብት የማይመለከተው የመንግስት ተቋም ስለሌለ ለሁሉም ኃላፊነት እንደሚሰጥ አስታውቀዋል፡ ‹‹ከዚህ በፊት ነበረው አሰራር የፖለቲካ ቁርጠኝነት ከፍተት ይታይ ነበር›› ያሉት አቶ ይበቃል፤ በማዘጋጀትና በመወሰን ሂደት የመንግስት መፍቀድ አለመፍቀድም መሰናክል ሆኖ እንደነበር አመልክተዋል::በዚህም ምክንያት ከዚህ በፊት የነበሩትን መርሐ ግብሮች በታሰበላቸው ዓላማ ለማስኬድ አልተቻለም::ከለውጡ ወዲህ የፖለቲካ ቁርጠኝነት በመታየት የድርጊት መርሐ ግብሩ በሰፊው እንዲሻሻል ተደርጓል ብለዋል::ለድርጊት መርሐ ግብሩ በቂ መዋዕለ ንዋይ እንደሚመደብ በውይይቱ ላይ የተገለጸ ሲሆን፤ የድርጊት መርሐ ግብሩ ግብዓቶች፤ የኢፌዴሪ ሕገ መንግስት፣ ኢትዮጵያ የተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ስምምነቶች፣ የመንግስት ፖሊሲና ስትራቴጂዎች፣ አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎች እና የመንግስት ተቋማት ዓመታዊ ሪፖርቶች ይሆናሉ::አዲስ ዘመን ህዳር 30/2013
https://www.press.et/Ama/?p=36986
304
0ሀገር አቀፍ ዜና
የፍቺው ጥቁር ጥላ በተወዳጁ ሊግ ላይ
ስፖርት
September 10, 2019
23
 በርካታ እግር ኳስ አፍቃሪያን የዓለማችን ምርጡ ሊግ ሲጠቁሙ ‹‹የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን በማስቀደም የሚስተካከለው የለም›› በማለት ሽንጣቸውን ይዘው ይሞግታሉ። ምንም እንኳን የግል የምርጫ ልዩነት እንደተጠበቀ ቢሆንም አንዱን በመለየት ሂደት በመላው ዓለም የሚገኙ የእግር ኳስ አፍቃሪያንን ቀልብ በመሳብ፣ አንድም የገቢ ምንጭ አንድም የመዝናኛ አማራጭ ሆኖ ብዙዎችን እያዝናና ስለመሆኑ ምስክር በማቅረብ ሊጉን ከማንኛውም ሊግ ያስበልጡታል። ባሳለፍነው አመት በአውሮፓ ታላቅ የእግር ኳስ መድረኮች በሻምፒንስ ሊጉና የዮሮፓ ዋንጫም የፍፃሜ ተፋላሚዎች ከእንግሊዝ መሆናቸው ዋቢ በማድረግም ሊጉ የጠንካራ ክለቦች ባለቤትና የአለማችን ምርጡ ስለመሆኑም ያሰምሩበታል። በተጫዋቾች የአልሸነፍ ባይነት የታጋይነት ስሜት ፈጣን፤ መከላከልንና በአብዛኛው አካላዊ ጥንካሬን መሰረት ያደረገው ሊግ፣ በእያንዳንዱ ውድድር አመት አስቀድሞ ከማይገመቱና በደረጃ ግርጌ ያሉ ክለቦች በደረጃው አናት የሚገኙ ከለቦችን ሲያሸንፉ የሚታይበት መሆኑም የደጋፊዎቹን ቀልብም ለመግዛቱና ዓለምዓቀፍ ትኩረት ለመሳቡ ዋነኛው ምክንያት ሆኖ ይጠቀሳል። በተለይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው የቴሌቪዥን ስርጭት ተደራሽነትና ጨዋታዎች የሚተላለፍበት ሰዓትም ይበልጥ ምቹ መሆንም የብዙዎች ምርጫ እንዲሆንና በርካታ የስፖንሰር አድራጊ ተቋማትን ቀልብ እንዲስብ ስለማድረጉም ይታመናል። ብሪታኒያ እኤአ በ2016 ‹‹ከአንድነት ይልቅ ልዩነቱ ይበጀኛል›› በሚል በህዝበ ውሳኔ ከአውሮፓ ህብረት ጋር ለመፋታት ከወሰነች ማግስት አንስቶ ታዲያ የፍቺው አጀንዳ በአገሪቱ እግር ኳስ በተለይ በተወዳጁ ፕሪሚር ሊጉ ውድድር እጣ ፈንታ ላይ ከፍተኛ ስጋትን አጭሯል። በእርግጥ አገሪቱ ባለፉት ሶስት ዓመታት በብሬግዚት ጣጣ ስትቃወስ ብትቆይም ከህብረቱ የመፋታት ፍላጎትን ግን እንዳቀለለችው አልቀለላትም። በአገሪቱ ታሪክ ሁለተኛ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር የሆኑት ቴሪሳ ሜይም የፍቺ አጀንዳ ማስፈፀም አልሆነላቸውም።በጉዳዩ ላይ ከፓርላማ አባላት ጋር ከስምምነት መድረስ ተስኗቸው በገዛ ፈቃዳቸው ስልጣናቸውን ለመልቀቅም ተገደዋል። ስልጣናቸውንም ለሃምሳ አምስት አመቱ ቦሪስ ጆንሰን አስረክበዋል። የብሬግዚት አቀንቃኙ የቀድሞ የለንደን ከተማ ከንቲባና የብሪታንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰንም የለንደንን ከህብረቱ የመፋታት ውጥን እንደሚያሳኩና የሀገሪቷን አንድነት እንደሚያስጠብቁም ቃል ገብተዋል። ካለስምምነት ከህብረቱ መፋታትን አዋጭ አድርገው የሚመለከቱት ጆንሰን፣ በመጪው የፈረንጆቹ ጥቅምት መጨረሻ አገራቸውን ከህብረቱ ለማፋታት ቆርጠው ተነስተዋል። ጉዳዩንም የሞት ሽረት አድርገው ገፍተውበታል። ምንም እንኳን የፍቺውን ፍላጎት የሚደግፉት ቢኖሩም፤ ‹‹ያለምንም ስምምነት ፍቺውን የመፈፀም አደጋ ከባድ ነው፤ ይሕን ለማስቀረትም አማራጮችን መቃኘት ያስፈልጋል›› በሚል ስጋታቸውን የሚያስቀመጡ በርካቶች ሆነዋል። በአለም ኢኮኖሚ እድገት አምስተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠቸውን አገር ኢኮኖሚ በእጅጉ እንደሚጎዳ የሚያሳስቡም አልጠፉም። ገና ከወዲሁ የፓውንድ አቅም መዳከምና ታላላቅ ኩባንዎችም በፍቺው ጣጣ መተማመኛ ማጣታቸውን ሲገልፁ መደምጣቸውም ለዋቢነት ይነሳል። የብሬዚዳት ቀውስ የአገሪቱን በርካታ ኢንዱስትሪዎች እንደመነካካቱ ተወዳጁ የአለማችን ፕሪሚየር ሊጉም ከሰለባዎቹ መካከል ዋነኛው ስለመሆኑ የሚያስገነዝቡ ባለሙያዎች ቁጥርም ከፍተኛ ነው። በተለይ የፍቺው ቀነ ቀጠሮ እየቀረበ በመጣ ቁጥር ስጋቶችም አብረው ከፍ ሲሉ እየተስተዋለ ይገኛል። አገሪቱ በመጪው የፈረንጆቹ ጥቅምት መጨረሻ ከህብረቱ ከተፋታች በተወዳጁ የአለማችን ፕሪሚየር ሊግ ላይ ከሚስተዋሉ ጥቁር ጥላዎች መካከል አንዳንዶቹ ከወዲሁ ተገምተዋል።፡ የሊጉ ተሳታፊ ክለቦችና የተጫዋቾች ዝውውር ላይ የሚያደርሰው ጫናም ከሁሉ ቀድሞ ተጠቅሷል። በተለይ ‹‹በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ከወገብ በላይ ሆነው የሚያጠናቀቁና በተጫዋቾች ዝውውር ገበያው ቀንደኛ ተዋናይ በመሆን ስኬታማ የሚሏቸውን ተጫዋቾች በማስፈረም የሚታወቁ ክለቦች፣ ከፍቺው በኋላ ፍላጎታቸውን በቀላሉ ለማሳካት ይቸግራቸዋል››ተብሏል።በሰዎች ላይ የሚደረጉ ማናቸውም በነፃነት ተንቀሳቅሶ የመስራት ገደቦችም የክለቦቹ ዋነኛ ፈተና እንደሚሆኑም ተመላክቷል። ከብሬግዚት በኋላ ማንችስተር ዩናይትድና አርሰናልን የመሳሰሉ ክለቦች ምርጫ የሆኑት የጀርመን፣ ፈረንሳይና ስፔን ተጫዋቾች እንግሊዝ ምድር እግር ኳስን ለመጫወት የስራ ፈቃድ ማግኘትና መስፈርቶችን ማሟላት ግድ እንደሚላቸውም ታውቋል።ይሕም በተጫዋቾች ብቻ የማይወሰንና አሰልጣኖችንም የሚመለከት ይሆናል። በአለም በኢኮኖሚ እድገት አምስተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠቸው አገር ኢኮኖሚ በእጅጉ ተንገጫግጮ በተለይ የፓውንድ የመግዛት አቅም የሚዳከም ከሆነ ደግሞ ክለቦች የሚፈልጓቸውን ተጫዋቾች ፊርማ ለማግኘት እንዲቸገሩ ማድረጉ አይቀሬ ነው። የመገበያያ ገንዘቡ አቅም ማጣትን ተከትሎም ተጫዋቾች ልፋታቸውን የሚመጥን አቅም ያለው ገንዘብ አለማግኘታቸውን ታሳቢ በማድረግ በእንግሊዝ ምድር እግር ኳስን ለመጫወት ፍላጎት እንዳይኖራቸው ያደርጋል። ለመጫወት እንዲወስኑ ለማግባባት ደግሞ የፕሪሚር ሊጉ ክለቦች ተጨማሪ ገንዘብን ለመክፈል ኪሳቸው መግባት ግድ ይሆንባቸዋል። ተጫዋቾች ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ለመምጣትና ለመቆየት ዳተኛ ከሆኑ ደግሞ በአልሸነፍ ባይነት ተጋድሎ በሚታወቁት ክለቦች መካከል የተፎካካሪነት ስሜት እንዲቀንስ በማድረግ የሊጉን ተወዳጅነት ያደበዝዘዋል። ምርጥነቱን ሊያስነጥቀውም ይችላል። ይሕም በተለይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው የቴሌቪዥን ስርጭት ተደራሽነት ምክንያት የሰበሰባቸውን በርካታ የስፖንሰር አድራጊ ተቋማት ቀልብ በማስነፈግ፣ አስተማማኛና ከፍተኛ የገንዘብ አቅሙን በእጅጉ ያዳክመዋል። ዋጋውንም ዝቅ ያደርገዋል። የብሬግዚት ጣጣ ክለቦች የውጭ አገር ተጫዋቾች ለማስፈረም እንዲቸገሩና ሂደቱንም ውስብስብ በማድረግ በተጓዳኝ የውጭ አገራት ተጫዋቾች ቁጥር ለመቀነስ ሊያስገድዳቸውም ይችላል።መረጃዎች እንደሚያሳዩት፤ እኤአ በ1992 በፕሪሚር ሊጉ ከሚጫወቱ ተጫዋቾች መካከል 70 በመቶ እንግሊዛውያን ነበሩ።ይሕ አሃዝ እያደር አሽቆልቁሎ ባሳለፍነው ውድድር አመት ከ26 እስከ 27 በመቶ ደርሶም ታይቷል። የእንግሊዝ እግር ኳስ ማህበር (ኤፍ.ኤ) በአንድ ክለብ ከ25 ቡድን አባላት ውስጥ የሚገኙ አገር በቀል ተጫዋቾች ቁጥር ከፍ እንዲል ሲተጋ ቆይቷል።የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦችም 12 አገር በቀል ተጫዋቾችን ማስመዝገብ እንዳለባቸውም በፖሊሲው ያስቀምጣል። ይሕ ህግ በተቀመጠበት የሊጉ ክለቦች በፍቺው ጥቁር ጥላ ምክንያት እንደቀድሞው የውጭ ተጫዋቾችን በቀላሉ ለማስፈረም ካልቻሉም ወደ አገር በቀል ተጫዋቾ ማተኮሩና ለታዳጊዎች ልማት ትኩረት መስጠታቸው አይቀሬ ነው። ይሕ ደግሞ በሊጉ የሚጫወቱ እንግሊዛውያን ተጫዋቾችን ቁጥር ከፍ እንዲልለት ፍላጎት ላለው ማህበር ዋነኛ ፍላጎት ነው። አዲሱ የማህበሩ የቴክኒክ ዳይሬክተር ለስ ሪድም የብሬግዚት ጣጣ በርካታ እንግሊዛውያን ተጫዋቾች በተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪሚር ሊግ የመጫወት እድልን እንደሚሰጥ እምነት አላቸው። በአሁን ወቅት በሊጉ የሚጫወቱ እንግሊዛውያን ተጫዋቾች ቁጥር ከ32 እስከ 34 በመቶ ከፍ ማለቱን የሚጠቁሙት ዳይሬክተሩ፣ ማህበሩ ይሕ አሃዝ ይበልጥ እንዲጎለበት ፍላጎት እንዳለውም ያስምሩበታል። ‹‹ጠንካራ ፕሪሚየር ሊግ ያስፈልገናል፤ ይሕ እንዲሆን የምንፈልገውም ለአገሪቱ እግር ኳስ ሁለንተናዊ እድገት ወሳኝ ስለሆነ ነው›› የሚሉት ዳይሬክተሩ፣ ሊጉ የአለማችን ጠንካራና ምርጡ ሆኖ እንዲቀጥል፣ ሳቢና ማራኪ ከመሆኑ ባሻገር በምጥጥንም የተሻለ እንዲሆን ፍላጎታቸው ስለመሆኑም አፅኖት ሰጥተውታል። ለዚሕ ውጥን እውን መሆን ደግሞ ሊጉ ለወጣት እንግሊዛውያን ተጫዋቾች እድል መስጠቱ ግድ መሆኑን አስ ምረውበታል። በአሁን ወቅትም ክለቦች ታዳጊዎችን ለማፍራት እየታተሩ ሰለመሆኑና በቼልሲ ክለብ ላይ ለአንድ አመት የተወሰነው የተጫዋቾች ዝውውር ቅጣት በእስታንፎርድ ብሪጅ የነበረውን ባህል በእጅጉ እንደቀረው የሚጠቁሙት ዳይሬክተሩ፣በአሁኑ የፍራንክ ላምፓርድ የቼልሲ ቡድን አባላት ውስጥ ታሚ አብረሃም ማሶን ማውንትን የመሳሰሉ ወጣቶችን መተዋወቃቸውም አንድ ጅምር ሰለመሆኑ ነው ያስገነዘቡት። በአጠቃላይ በብሬግዚት ጣጣ ክለቦች የውጭ ተጫዋቾችን በቀላሉ ማግኘት ሊያስቸግራቸው ቢችልም፤ በተቃራኒው ትኩረታቸውን ወደ አገርው ውስጥ እንዲመልሱ ስለሚያደርጋቸው በርካታ እንግሊዛውያን ተጫዋቾች በሊግ የመጫወት እድልን እንደሚያገኙም ተማምነዋል። በርካታ የእግር ኳስ ሳይንስ ባለሙያዎች በአንፃሩ በአገር ውስጥ ተጫዋቾች ብቻ የሚካሄድ ሊግን መናፈቅ አግባብ አለመሆኑንና ለተወዳጁ ሊግ ተወዳጅ ሆኖ መዘልቅ አዋጭ አለመሆኑን አስገንዝበዋል።የሊጉ አስተዳዳሪ አካላትም ከዚህ የተሳሳተ እሳቤ መውጣት እንዳለባቸው አፅኖት ሰጥተውታል። ምንም እንኳን በአሁን ወቅት የብሬግዚት አጀንዳ ያልተመለሱ ጥያቄዎች ከፊት ቢደቀኑበትን በርካቶች ግን ከወዲሁ ከፍቺው በኋላ የሚሆነው አስግቷቸዋል። ተወዳጁ የአለማችን ሊግም ዕጣ ፈንታውን የሚወስንለት የፍቺው ቀነ ቀጠሮ እስኪደርስ ተወዳጅ ሆኖ ይዘልቃል።አዲስ ዘመን  ጳጉሜን 5 /2011 ታምራት ተስፋዬ
https://www.press.et/Ama/?p=17599
903
2ስፖርት
የማንጎ ምርት “ኋይት ስኬል “ በተባለው ነፍሳት ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰበት መሆኑ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 9, 2020
12
ሞገስ ጸጋዬአዲስ አበባ፡- የማንጎ ምርት “ኋይት ስኬል” በተባለ ነፍሳት በመጠቃቱ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰበት መሆኑን በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የግብርና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ ተመራማሪና መምህር ዶክተር አዳነ ተስፋዬ አስታወቁ::ከችግሩ የተነሳ አርሶ አደሮች ማንጎ ለማምረት ያላቸው ፍላጎት እንደቀነሰ መሆኑን ጠቆሙ ።ዶክተር አዳነ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት በርካታ የተክል አይነቶች መነሻቸው በማይታወቁ በሽታዎች በመጠቃታቸው የተነሳ ምርታቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ ነው::በተለይ ማንጎ በሀገራችን የተለያዩ ቦታዎች በስፋት የሚመረት ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ምርቱ በተባይ በመጠቃቱ አርሶ አደሮች ከማምረት እየተቆጠቡ ነው ::ማንጎ በበሽታ ከተጎዳና ምርታማነቱ ከቀነስ ቢቆይም ሊታደገው የሚችል መፍትሔ አልተበጀለትም የሚሉት ተመራማሪው፣ በግብርና ሚኒስቴር በኩልም ችግሩ ተገቢውን ትኩረት እንዳላገኘ አመልክተዋል ። በፍጥነት ከመድረስ አኳያ ማንጎ ተመራጭ የገበያ ምርት መሆኑን የጠቆሙት ተመራማሪው ፣ የተሻሻለ ዝርያ ባለመዘጋጀቱ የተነሳ በርካታ አርሶ አደሮች በማንጎ ፈንታ ሌላ ዝርያዎች ወደ ማምረት እየተሸጋገሩ ነው ብለዋል::በርካታ አርሶ አደር ባለበት ሀገር ለግብርናው ዘርፍ ትኩረት ባለመስጠቱ አርሶ አደሮች ከማምረት እየተቆጠቡ ነው::በዘርፉ የሰለጠኑ ባለሙያዎች ቢሆን ወደ ሌላ የስራ መስክ እየሄዱ ነው ፤ይህ ደግሞ ለበሽታው ጥሩ አጋጣሚ እንደፈጠረለትም አስታውቀዋል:: በዘርፉ ለሚደረጉ ጥናቶች የሚበጀተው በጀት በጣም አነስተኛ መሆኑን ያመለከቱት ተመራማሪው ፣ በዚህ የተነሳ በዘርፉ ተገቢው ጥናት ባለመደረጉ በቀላሉ መከላከል የሚቻሉ በሽታዎች ስር ሰድደው ሰፊ ችግር እያስከተሉ መሆኑን ገልጸዋል::አርሶ አደሩ በራሱ አቅም በሽታዎችን ለመከላከል በርካታ ጥረቶችን ቢያደርግም ችግሩን መቋቋም እንዳልቻለ አመልክተዋል::ከውጭ ሀገር የሚመጡ ተመራማሪዎችንና ኢንቨስተሮችን መርምሮ ማስገባት ያስፈልጋል የሚሉት ዶክተር አዳነ፣ በርካታ በሽታዎች የሚመጡት ከውጭ ሀገር መሆኑ ገልጸዋል። የበሽታውን ስርጭት እንዳይስፋፋ ከክልል ወደ ክልል ያለውን የችግኝ ዝውውር መቆጣጠር እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል::ጉዳዩን በተደጋጋሚ ለመንግስት ቢያሳውቁም ትኩረት ከመነፈጉ በላይ የማንጎ ምርት ቀደም ካለው ጊዜ ጋር ሲወዳደር በግማሽ ቀንሷል ፤ በጥራት ደረጃም የወረደና በገበያም ተፈላጊነቱ እየቀነሰ መጥቷል፤ እንዲሁም ወደ ውጭ ይላክ የነበረው ምርት አሁን ሙሉ በሙሉ ቆሟል ብለዋል ::አዲስ ዘመን ህዳር 30/2013
https://www.press.et/Ama/?p=36988
259
0ሀገር አቀፍ ዜና
ዋልያው ወደ ቀጣዩ ዙር አ
ስፖርት
September 10, 2019
27
 የኢትዮጵያ ወንዶች ብሄራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) በ2022 የኳታሩ የዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፋቸውን አረጋግጠዋል። ለ2022 የኳታር የዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታውን ከቀናት በፊት ባህርዳር ላይ ከሌሴቶ ጋር የተጫወተው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን፣ በጨዋታው ከተጋጣሚው የተሻለ የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ማሳየት ቢችልም እድሎች በመፍጠርና የተፈጠረውን እድልም በአግባቡ መጠቀም ባለመቻሉ ያለ ምንም ግብ ማጠናቀቁ ይታወሳል። ብሔራዊ ቡድኑ በሜዳውና ደጋፊው ፊት ነጥብ መጣሉ በቀጣይ መልስ ጨዋታ አጣብቂኝ ውስጥ እንዲገባ ያስገደደው ቢሆንም፤ ወደ ሌሴቶ አቅንቶ በሳምንቱ መጨረሻ ከሌሴቶ አቻው ጋር ያደረገው ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ማጠናቀቅ ችሏል። ከባህር ዳሩ ጨዋታ በተለየ ሶስት ተጫዋቾችን በመቀየር ወደ ሜዳ የገቡት ዋልዎቹ፣ ‹በጨዋታው ኳስን ከኋላ መስርተው በመልሶ ማጥቃት በቁጥር በዝተው በመሄድ እድሎችን ለመፍጠር ለመጫወት ሲሞክሩ ታይተዋል። መከላከልን ምርጫቸው አድርገው ወደ ሜዳ የገቡት የሌሴቶ አዞዎች በአንፃሩ አልፎ አልፎ ከመሃል ሜዳ በረጅሙ በሚላኩ ኳሶች እድሎችን ለመፍጠር ቢሞክሩም የዋልያውን ተከላካይ ክፍል ጥሰው መግባት አልሆነላቸውም። ሁለቱም ቡድኖች ይሕ ነው የሚባል ጠንካራ የግብ ማግባት እድሎችን መፍጠር ሣይችሉ፤ የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቋል። በሁለተኛው አጋማሽ በአንፃሩ ሁለቱም ብሄራዊ ቡድኖች ወደ ተጋጣሚያቸው ሜዳ ክልል በመዝለቅ ተጭነው ለመጫወት ሞክረዋል። ሁለተኛው አጋማሽ ከተጀመረ ከአምስት ደቂቃ በኋላ ቢኒያም በላይ ከቀኝ መስመር በኩል ያሻገራት ኳስ በሌሴቶው ተከላካይ ንካይ ኔትሪሊ ተጨርፋ አዞዎቹ በራሳቸው ላይ ግብ እንዲያስቆጥሩ ምክንያት ሆናለች። ግብ ከተቆጠረባቸው በኋላም የአጨዋወት ዘይቤያቸውን በመለወጥ ተጭነው ለመጫወት የሞከሩትና በተደጋጋሚ ወደ ዋልያው ግብ ክልል የተመላለሱት ሌሴቶዎች፣ ግብ ለማስቆጠር ብዙም ደቂቃ አልፈጀበቸውም። ግብ ከተቆጠረባቸው ከአምስት ደቂቃ በኋላ ያገኙትን ቅጣት ምት ሴፖ ሴትሩማንግ ወደ ግብ አክርሮ የመታት ኳስ የመስፍን ታፈሰን እግር በመጭረፍ ከዋልያው መረብ ላይ አርፋለች። ጨዋታው አንድ አቻ መሆኑን ተከትሎ ዋልያዎቹ ይበልጥ ወደ መከላከሉ ፊታቸውን ያዞሩት ሲሆን፣ አዞዎቹ በአንፃሩ ተጨማሪ ግብ ለማግኘት ይበልጥ ተጨነው ለመጫወት ሞከረዋል። ከአንድም ሁለት ጊዜ ለግብ ቀርበው የግቡ አግዳሚ የመለሰባቸው አጋጣሚም ተስተውሏል። ሰዓት እየገፋ በሄደ ቁጥር ጫና እየበዛባቸው የመጡት በተለይ በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ላይ መረጋጋት የተሳናቸው ሌሴቶዎች፣ ኢትፒሰን ብሄራዊ ቡድን መከላከል ጥመረት በማፍረስ ግብ ማስቆጠር ባለመቻላቸው ጨዋታው በአንድ አቻ ውጤት ሊጠናቀቅ ግድ ብሎታል። ይህንን ተከትሎም ዋልያው ከሜዳው ውጪ ባስቆጠረ በሚል የሌሴቶ አቻውን በመርታት በ2022 የኳታሩ የዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፉን አረጋግጧል። የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ምድብ ድልድል ውስጥ መግባቱንም አውቋል። ዋልያዎቹ ምንም እንኳን ከጨዋታው ነጥብ በማግኘት ወደ ምድብ ድልድሉ መግባት የሚስችላቸውን ውጤት ማግኘት ቢችሉም፤ በተጋጣሚያቸው ሜዳ የሚያሳዩት አለመናበብና የፈጠራ ብቃት እጥረት ግን ዋነኛ ክፍተታቸው መሆኑ ሳይጠቁም አይታለፍም። በዓለም ዋንጫ የማጣሪያ ማጣሪያ የደርሶ መልስ ጨዋታዎች አሸናፊ የሆኑ 14 ቡድኖች ለዋናው የማጣሪያ ጨዋታ ከተመደቡት 26 ቡድኖች ጋር ተቀላልቀለው ይፋለማሉ። እነዚህ የ40 ሀገራትም እያንዳንዳቸው በአራት ቡድኖችን በያዙ 10 ምድቦች ተደልድለው ይጫወታሉ። የየቡድኖቹ አላፊ 10 ቡድኖች የመጨረሻውን ማጣሪያ ያከናውናሉ። ከ10 ቡድኖች አሸናፊ የሚሆኑት አምስቱ የ2022 የኳታር የዓለም ዋንጫ ላይ አፍሪካን ወክለው የሚሳተፉ ይሆናሉ።አዲስ ዘመን  ጳጉሜን 5 /2011 ታምራት ተስፋዬ
https://www.press.et/Ama/?p=17596
410
2ስፖርት
«በአዲሱ ዓመት አዲስ አበባ የስፖርት ማዕከልነቷን እንድትመልስ እናደርጋለን» አቶ ዮናስ አረጋይ፤ የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር
ስፖርት
September 13, 2019
43
ለአንድ አገር ስፖርት ውጤታማነት ማንሰራሪያና የትንሳኤ ማብሰሪያ መላና ምክንያት ከሆኑት ውስጥ በተለይ በዋና ከተሞች የሚካሄዱ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ተጠቃሾች ናቸው። የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን በአዲሱ ዓመት – የዓመታት ቁጭቴን በእርካታና በተስፋ ለመሙላት እንዲሁም ለስፖርቱ ትንሳኤ የምችለውን ለማከናወን ቆርጬ ተነስቻለሁ” ብሏል፡፡ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ጋር ቆይታ ያደረጉት አቶ ዮናስ አረጋይም የኮሚሽኑን ተግባራትና መፃኢ ተስፋ አብራርተዋል፡፡ አዲስ ዘመን፡- የከተማ አስተዳደሩ በ2011 ዓ.ም በስፖርቱ ዘርፍ ካከናውናቸው ተግባራት መካከል እንደ ስኬት ያስመዘጋባቸው ምን ምን ጉዳዮች ነበሩ? አቶ ዮናስ፡- በስኬት ደረጃ ያስቀመጥናቸው አምስት ጉዳዮች ናቸው፡፡ የመጀመሪያው አጠቃላይ መዋቅሩን ከታች እስከ ላይ እንዲለወጥ አድርገነዋል፡፡ የማያስፈልጉ መዋቅሮችን አስነስተናል፡፡ የተሻሉ መዋቅሮችን ደግሞ ወደፊት እንዲሄዱ አድርገናል፡፡ ለምሳሌ፤ የማያስፈልገው አንዱ የኮንስትራክሽን ዘርፉ ነው፡፡ እሱን አንስተን ኮንስትራክሽን ቢሮ ይመለከተዋል ብለን ሰጥተነዋል፡፡ ስፖርት ኮሚሽኑ የማዘውተሪያ ስፍራ ያስፈልገናል የሚል ጥያቄ ማቅረብ እንጂ፤ መሐንዲስ በሌለበት የማዘውተሪያ ግንባታ ማካሄድ አይደለም፡፡ ኮሚሽኑ በስፋት የስፖርት ከፍተኛ ባለሙያዎች አልነበሩትም፡፡ ስለዚህ ከሚሽኑ በሚያስተዳድራቸው እንደ ራስ ኃይሉ፤ አበበ ቢቂላ፤ ጃንሜዳ፤ አራት ኪሎ ሥልጠና ማዕከላት ሁለት ሁለት ከፍተኛ ባለሙያዎች እንዲመደቡ አድርገናል፡፡ እነዚህ ማዕከላትም አብዛኞቹ ስፖርትንና የስፖርትን ሥራ ትኩረት አድርገው እንዲሰሩ ሆኗል፡፡ ይህም በተሻለ ደረጃ ተተግብሯል፡፡ የማያሰሩ ማነቆዎች የተባሉትን በጠቅላላ በባለሙያ በተደገፈ ጥናት ፈትሸን ለማየት ጥረት አድርገናል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ለውጥ ባደረግንበት ልክ የሰው ሃይላችንን የመደልደል ሥራም ሠርተናል፡፡ የዚህ ውጤትም የስፖርት ኮሚሽን ከዚህ በፊት የነበረውን እንደ ልብ እንዳይሠራ ያደረገውን አሠራር ለማረምና አዲስ አበባ ያጣቸውን የስፖርት ማዕከልነቷን ለመመለስ ነው፡፡ ይህንን ትኩረት አድርገን ስንሰራም በመዋቅሩ ዙሪያ ምን መደረግ አለበት ብለን ከፍተኛ ግምገማ አድርገናል፡፡ ሌላኛው፤ እንደ መንግሥትም ሊበራታታ የሚገባው ጉዳይ በቀደመው አደረጃጀት የወጣቶች ጉዳይና ስፖርት በጋራ የነበረ ሲሆን፤ ስፖርት ራሱን ችሎ ይሂድ የሚል መዋቅር የመጣውም በዚህ ዓመት ነው፡፡ ሁለተኛው፤ የስኬት ተግባር የማዘውተሪያ ሥፍራን የተመለከተ ነው፡፡ ምንም እንኳን የአዲስ አበባን ጥያቄ በሚመጥን መልኩ ተመልሷል ባይባልም ትናንት የነበሩትንና ያደሩትን ውዝፍ ሥራች ግን ማገባደድ ችለናል፡፡ ለምሳሌ፤ የአበበ ቢቂላ ስታዲየም የረጅም ጊዜ የግንባታ ችግር ነበረበት፡፡ የማስፋፊያ ችግር ነበረበት፡፡ ከተማዋንም የሚመጥን አልነበረም፡፡ አሁን ግን ከተማዋን በሚመጥን መልኩ የወንበር፤ የትራክና የጣራ ሥራዎች ተጠናቅቀው አጠቃላይ ሥራው ወደ 95 በመቶ ያህል አልቋል፡፡ ከ105 ሚሊዮን ብር በላይም ወጭ ተደርጎበታል፡፡ ከህዳሴ ግድብ እኩል የተጀመረው የሜዳ ቴኒስና የዓለም አቀፍ መዋኛ ገንዳውም በአጭር ጊዜ ውስጥ ቀንና ሌሊት እየተሠራ እንዲጠናቀቅ ተደርጓል፡፡ የቀረን ውሃ መሙላትና መሞኮር ብቻ ነው፡፡ ሁለቱም የመዋኛ ስፍራዎች፤ ማለትም የህፃናቱም የአዋቂውም ተጠናቅቀዋል፡፡ ይህም ከ500 ሚሊዮን በላይ ወጭ ተደርጎበታል፡፡ ከዚህ በፊት የተጀመሩትን ሥራዎች በፍጥነት እንዲጠናቀቁ ከማድረግ አኳያ በርካታ ሥራዎች የተሰሩበት ወቅት ነበር፡፡ እዚህ ላይ ሊታሰብ የሚገባው ቁምነገር ግዙፍ የሆኑ ሜጋ ፕሮጀክቶችን መሥራት አይደለም ትልቁ ነገር፤ ዋናው ነገር ተደራሽ በሆነ ሁኔታ አነስ አነስ ያሉ ማዘውተሪያ ቦታዎችን መሥራት ነው የሚያዋጣው፤ በመሆኑም፤ በ2012 ዓ.ም የምንሰራቸው እንዳሉ ሆነው በአፈጣኝ ግን በ117ቱም ወረዳዎች የጥርጊያ ሜዳ መሥራት አለብን ብለን ተነስተን 61 ቦታዎች ተሳክተውልናል፡፡ አዲስ አበባ የነበራትን ነባር ሜዳ በማጣት ነው እንጂ የምናሳልፈው አዲስ ሜዳዎች ሲጨመሩ ብዙም የተለመደ አልነበረም። ይህ በሁለተኛው የዕቅድና ትራንስፎርሜሽን ዘመን ያልሠራነውን ነው በዚህ ዓመት ማሳካት የቻልነው፡፡ ከዚህ ውጭ 63 ቦታዎች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታም አስወጥተናል፡፡ አንዳንዱ ቦታ ካርታ ስለሌለው ማንም ባዶ ቦታ ሲያይ መጥቶ ይገነባል፡፡ ይህ እንዲቀርም ተደርጓል፡፡ ሦስተኛው፤ የታዳጊዎችን ፕሮጀክቶች ከአዲስ አበባና ከኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በዝርዝር እንዲገመገሙ አድርገናል፡ ፡ ገልለተኛ አካላቱ ፕሮጀክቱን ሲያጠኑ እስከዛሬ በነበረው አሠራራችን ላይ ችግር እንደነበር አመላክተዋል፡፡ በእርግጥ የተወሰኑ ፕሮጀክቶች የተሻሉ መሆናቸውም ታይቷል፡፡ በድምር ውጤቱ ግን በአዲስ መንገድ መሄድ እንዳለብን ያመላከቱ ናቸው፡፡ ወደ 132 የሚሆኑ ጣቢያዎች ላይ በነበሩ እንቅስቃሴዎች ከአራት ሺህ አምስት መቶ  በላይ ልጆች የታቀፉበት ሥራ ግን በስኬት የሚታይ ነው፡፡ እነዚህም አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡ ስለዚህ ታዳጊዎች ላይ በአዲስ ዓመት አዲስ ሐሳቦች ተግባራዊ ይደረጋሉ፡፡ በተመረጡ ቦታዎች ላይ ብቻ ለመስራት ነው ዕቅድ የተያዘው፤ በዚህ ዓመት በዘጠኝ የስፖርት ዓይነቶች እስከ ሦስት ዓመት ድረስ ካልሰራን መወዳደሩ አይጠቅምም የሚል አቋም ላይ ነን፡፡ በነገራችን ላይ፤ አዲስ አበባ ላለፉት ስድስት ዓመታት ከስፖርት ማዕከልነቷ ወጥታ በአገር አቀፍ ውድድሮች ስድስተኛና ሰባተኛ ደረጃ ነበር ይዛ የምታጠናቅቀው፤ ስህተታችንን ስላወቅን በትክክል በሰራነው ላይ ብቻ በመሳተፍ ያልሰራነውን በመተው ጥራት ላይ ት ኩረት ማድረግ ጀምረናል፡፡ በአራተኛ ደረጃ፤ ለአጠቃላይ ባለሙያዎች ሠፋፊ ዓለም አቀፍ ይዘታቸውን የጠበቁ ሥልጠናዎች ተሰጥተዋል፡፡ የመጨረሻና ትልቁ ሥራ ደግሞ የማስ ስፖርትን የማጠናከሩ ተግባር ነው፡፡ ስፖርት መሰረቱ ማስ ስፖርት ነው። ይህም በኢትዮጵያ የስፖርት ፖሊሲ ላይ በግልጽ ተቀምጧል፡፡ ማስ ስፖርት ባህል ሆኖ እንዲቀጥልም የተሻለ ሥራ ተሠርቷል፡፡ አዲስ ዘመን፡- እነዚህን ስኬታማ ተግባራት ስታከናውኑ ምንም ሳንካ አልነበረም ማለት ነው? አቶ ዮናስ፡- ቀላል የማይባሉ ችግሮች ነበሩብን፡፡ መዋቅር ሲስተካከል በክፍለ ከተማ ላይ በስፖርት የሰለጠኑ ብቻ ናቸው የስፖርት ዘርፍ ዳይሬክተር መሆን ያለባቸው ስንል በማኔጅመንትና በኢኮኖሚክስ የጨረሱ ነበሩ የተመደቡት፤ ይህንን ለማስተካከል ችግር ፈጥሮ ነበር፡፡ በሌላ በኩል፤ ታዳጊዎች ላይ አሁንም ቀላል የማይባሉ ማነቆዎች አሉ፡፡ ለምሳሌ፦ አንዱ ችግር የእድሜ ማጭበርበር ነው፡፡ አሾልኮ የሚያስገባውም የሚገባውም ትስስር ያላቸው ናቸው፡፡ ልምምድ በአግባቡ ያለመስራት፤ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን በተሻለ ፍጥነት የፍፃሜ ሥራዎችን አለማከናወን፣ በቢሮ በኩል ደግሞ ትጥቅ አለማድረስ፤ አበልና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞችን ማዘግየት፤ እልፍ ሲል ደግሞ የጥራት ጉድለቶችም እንዳሉ አስተውለናል፡፡ በፈፃሚዎች መካከል ያሉ ድክመቶችም ተስተውለዋል፡፡ ከዚህ ውጭ አዲስ አበባ ላይ የማዘውተሪያ ሥፍራ ችግር ቀላል አይደለም፡፡ በተለይ በልማት ምክንያት ተነሽ በሆኑ አካባቢዎች አንድ ስንዝር መሬት እንኳን ማግኘት ችግር ነበር፡፡ ማስ ስፖርቱን ቁልፍ ጉዳይ አድርጎ አለመግምገም እንዲሁ እንደ ክፍተት የሚታይ ነው፡፡ እንደ ካርኒቫልና ፌስቲቫል ከማየት በዘለለ በእያንዳንዱ ወረዳ ላይ እንዲተገበር በማድረግ ረገድ ችግር አለ፡፡ የመጨረሻው አንዱ ችግር የአዲስ አበባ ስታዲየም ጉዳይ ነው፡፡ እንደሚታወቀው ሁሉም ክልሎች ስታዲየም አላቸው፡፡ በፌዴራል የሚተዳደር ስታዲየም የላቸውም፡፡ የፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን መሥራት ያለበት በስትራቴጂክ ጉዳዮች ላይ ነው እንጂ ክልሎች በሚሰሩት ጉዳዮች ላይ መካተቱ ስፖርቱን ያዳክመዋል የሚል እምነት ነው ያለኝ፤ እኛም የአዲስ አበባ ስታዲየም ሜዳው ይሰጠን ብለን አመልክተናል፡፡ ይህንን እየጠበቅን ነው፡፡ በተለይ በስታዲየሙ ዙሪያ ያለው የአልኮል መጠጥ ንግድ ቤቶች በስፖርቱ ላይ ከፍተኛ ማነቆ እንዲፈጠር አድርገዋል፡፡ በመሆኑም ስታዲየሙን ተረክበን አልምተን ለከተማዋ ማህበረሰብ አገልግሎት እንዲሰጥ እናደርጋለን፡፡ ይህ ሲሆን ደግሞ የሚገጥመውን የፋይናንስ ችግር ለመቅረፍ ያግዛል፡፡ አዲስ ዘመን፡- ወርሐዊው የማስ ስፖርት ተሳትፎ ለፖለቲካ ፍጆታ እንጂ ስፖርታዊ መሠረት የለውም የሚሉ አካላት አሉ። አርስዎ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን ይላሉ? ስፖርታዊ ክንዋኔውስ ከታለመለት ዓላማ አንፃር ምን ያህል ውጤታማ ነበር? አቶ ዮናስ፡- በመሰረቱ ስፖርት ከዘር፤ ከሃይማኖትና ከፖለቲካ የፀዳ ነው፡፡ የኦሊምፒክ ውድድሮችን ብዙ ጊዜ በከተማችን ውስጥ ስናካሄድ ቆይተናል፡፡ ስፖርትን የሚያጠናክረው ሠላም ነው፤ የሚያፈርሰውም የሰላም እጦት ነው። አገራችን ውስጥ በሚፈጠር ችግር የስፖርቱ ቤተሰብ ለሰላሙ አቅም ካልሆነ ስፖርት ምንም አይጠቅመንም፡፡ ስፖርት ለአገራችን አንድነትና ፍቅር ጠንካራ የሆነ መሠረት መፍጠሪያ ነው፡፡ ኦሊምፒክን የመሰረተው እኮ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት የፈጠራቸው ችግሮች ናቸው፡፡ በነገራችን ላይ ኦሊምፒክ ውድድር አይደለም። አሁን አሁን የውድድር መልክ ያዘ እንጂ አንድነትና ፍቅር የሚገለፅበት መድረክ ነበር፡፡ ስለዚህ የማስ ስፖርቱ በህዝባችን ውስጥ እንዲሰርፅ ማድረግ አንድነትን ማጠናከሪያ እንጂ በሌላ እይታ የሚታይ አይደለም፡፡ ስፖርቱ ያቀራርባል እንጂ የፖለቲካ ተልዕኮ አይደለም፡፡ በአሁን ወቅት በስፖርት ቤት የገባው አንዱ ነገር ዘረኝነት ነው፡፡ ለዚህ ነው “ዘረኝነት ይብቃ” የሚል መሪ ቃል/ሞቶ እየተጠቀምን ያለነው፤ ስፖርት የፖለቲካው ትኩሳት ጥሩ ሲሆን ጥሩ የምንሆንበት፤ መጥፎ ሲሆን መጥፎ የምንሆንበት አካሄድ አይደለም፡፡ ፖለቲካው ጥሩም ሳይሆን ወደ ሠለም መመለሻ አቅም መሆን አለበት፡፡ ስፖርት ሠላም ነው ካልን ሰላም የሚያደፈርሱ ሃይሎችንም ከእኩይ ተግባራቸው የሚያወጣ ነው፡፡ ትኩሳትን የሚያበርድ እንጂ ለመንግሥትና ለህዝብ ራስ ምታት መሆን የለበትም፡፡ ከዚህ አንፃር፤ ምንም የፖለቲካ አጀንዳ የለውም። የፖለቲካ አመራሮች በማስ ስፖርት ላይ ተገኙ ማለት አጀንዳው ፖለቲካ ነው ማለት አይደለም። መቀራረብና መፈቃቀር ግን አጀንዳው ነው፡፡ ሁሉም ተጋግዘው ነው እየሠሩ ያሉት፤ የሚተላለፈው መልዕክት እንዴት መሥራት እንዳለብን የሚጠቁም ነው፡፡ የስፖርት ቤተሰቡም የመገኘትም ያለመገኘትም መብት አለው፡፡ የማስ ስፖርት መርሐ ግብር ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ዓላማውን እያሳካ ነው፡፡ በማህበረሰቡ ዘንድ መቀራረብ ፈጥሯል፡፡ ሰዎች በጉጉት እንዲጠብቁት ሆኗል፡፡ የተሳታፊዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል። ከጤና አኳያም ብዙ ሰው ባህል አድርጎት እየተሳተፈበት ነው፡፡ የማስ ስፖርት ከጀመርን በኋላ 21 ወረዳዎች በተጠናከረ መልኩ እየሠሩ ይገኛሉ፡፡ አዲስ ዘመን፡- በመዋቅር ለውጡ ስፖርት ኮሚሽን ራሱን ችሎ እንዲቆም ቢደረግም ተጠሪነቱ ግን ለወጣቶችና በጎ ፈቃድ ማስተባሪያ ቢሮ መሆኑ አሉታዊ ተጽዕኖ አይኖረውም? አቶ ዮናስ፡- ክልሎች የተለያየ አደረጃጀት ይኖራቸዋል፡፡ አዲስ አበባ ላይ አሁን ባለው ሁኔታ ለስፖርቱ ትልቅ ትኩረት ከተሰጠው ተጠሪነቱ ለከንቲባው መሆን አለበት የሚል እምነት አለኝ። ይህንንም ምክትል ከንቲባው በተገኙበት በዓመታዊ ግምገማ ላይ ተናግሬያለሁ፡፡ አሁንም ራሱን ችሎ እየሄደ ነው ለማለት ግን የሚጎድለን ነገር የለም፡፡ ቡድን መሪ፣ ዳይሬክተሮችና አመራሩ ነው ወሳኙ፡፡ ሥራውን አጠናቅቆ የመሥራት አቅም ካለ የተጠሪነቱ ጉዳይ አያሳስብም፡፡ ስለዚህ በአሁኑ ወቅት ራሱን የቻለ ተቋም ነው ብለን እየመራን ነው፡፡ ከድጋፍ ጋር በተያያዘ ግን ከከንቲባው ጽህፈት ቤት ጋር መሠራት አለበት የሚል አቋም ነው ያለኝ፤ ይህም የሚወሰነው እንደ አመራር ሚና ይሆናል ብዬ አስባለሁ፡፡ አዲስ ዘመን፡- ኮሚሽኑ በአዲሱ ዓመት በዋናነት ምን ምን ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ ሊሠራ አቀደ? አቶ ዮናስ፡- ከሚሽኑ የራሱ ስትራቴጂክ ዕቅድ አለው፡፡ ዋና ፍኖተ ካርታውም መነሻው ከዚህ ነው። የስትራቴጂክ ዕቅዱ ዋና ራዕይ “አዲስ አበባ ላይ ያለው ትውልድ በተክለ ሰውነትም ሆነ በአዕምሮው የዳበረ፤ በአስተሳሰቡ የተሻለ ጠንካራ ዜጋ በስፖርት ዘርፉ መገንባት” ነው፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን ደግሞ በአገራዊ ጥሪዎች ላይ ከዓለም የጎላ ተወዳዳሪነት መንፈስን ተግባራዊ ማድረግ ነው፡፡ በዚህ አዲስ ዓመት የጥርጊያ ሜዳዎቻችንን ማስፋፋት፣ ጥርጊያ ሆነው የተሰሩትን ደግሞ ወደ ሣር ማሸጋገርና ወጣቶችን አደራጅተን የተሻለ ሥራ ለመሥራት አቅደናል፡፡ 32 ሦስት በአንድ የሆኑ ሜዳዎችን መስራትም አንዱ ዕቅድ ነው። የተጀመሩትን ፕሮጀክቶች ሙሉ ለሙሉ እንዲጠናቀቁ ማድረግም ሌላኛው ሥራ ነው፡፡ ሌለኛው ደግሞ የተለዩ የማዘውተሪያ ሥፍራዎችን የመረከብና የማከል ሥራ ነው፡፡ የማስ ስፖርቱን በተጠናከረ መልኩ በማስቀጠል በሁሉም ወረዳ ተግባራዊ ማድረግ የኮሚሽኑ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ነው፡፡ የታዳጊ ፕሮጀክቶችን በተመረጡ ክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች ላይ በሚታይና በሚቆጠር ሥራ ላይ ትኩረት እናደርጋለን፡፡ ለዚህም ለትምህርት ቤቶች በር እንከፍታለን፡፡ ዋናው ነገር በተመረጡ ስፖርቶች ብቻ ውድድር እያደረግን በአዲሱ ዓመት አዲስ አበባ የስፖርት ማዕከልነቷን እንድትመልስ ማድረግ ነው፡፡ ለዚህም የስፖርቱን ቤተሰብ አቅም ከመገንባት አኳያም የተጀመሩትን ተግባራት እናስቀጥላለን፡፡ አዲስ ዘመን፡- የከተማ አስተዳሩ በስፖርቱ ዘርፍ ከሌሎች ዓለም አቀፍ እህት ከተሞች ጋር ተሞክሮ የመቅሰም ልምድ ካለው ቢጠቅሱልኝ፤ አቶ ዮናስ፡- እስካሁን አለነበረም፡፡ ከአሁን በኋላ ለመጀመር ግን ከተለያዩ አገራት አምባሳደሮች ጋር ተናጋግረናል፡፡ የአርጀንቲና፣ የጃፓን፣ የፈረንሳይና የኮሪያ ተጠቃሾች ናቸው። ስለዚህ በ2012 ዓ.ም ከእህት ከተሞች ጋር በከተማ አስተዳደሩ አማካኝነት ትስስር ፈጥረን በማስ ስፖርትና በታዳጊዎች ላይ እንሠራለን፡፡ ከሚበልጡን ለማማር ዕቅድ ይዘናል፡፡ አዲስ ዘመን፡- አዲስ አበባ የአገሪቷ ርዕሰ መዲና ሆና ሳለች ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም ማጣቷ ለምንድነው? ወደፊትስ ምን ታስቧል? አቶ ዮናስ፡- ስታንዳርዱ በምን ደረጃ ነው መሆን ያለበት የሚለው ነገር እንዳለ ሆኖ፤ በአጠቃላይ ግን ባዳ መሆናችንን ያሳያል፡፡ ምክንያቱም “የአዲስ አበባ ስታዲየም ለምንድነው ደረጃውን ያላሟላው?” የሚለውን ነገር አናውቀውም፡፡ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር አብረን ሆነን በምክክር እንዳንሠራ ችግር አለ፡፡ በግብረ መልሶች ላይ ከኮሚሽነሮች ጋር ተቀምጠን አልተወያየንም፡፡ ነግር ግን፤ በዚህ ዙሪያ በርከታ ሥራ መሥራት እንዳለብን እረዳለሁ፡፡ ችግሩ እንዳይደገምም እየሠራን ነው፡፡ አዲስ ዘመን፡- የባህል ስፖርቶችን በከተማዋ እንዲስፋፉ ለማድረግስ ምን እየተሠራ ነው? አቶ ዮናስ፡- በቅርቡ አምቦ ላይ በተደረገው የባህል ስፖርት ውድድሮች በከተማ ደረጃ የተሻለ አፈፃፀም ታይቷል፡፡ በቀጣይም ከባህልና ቱሪዝም ጋር በመተባበር ሥልጠና እንዲሰጥና የባህል ስፖርቱን አጠናክረን መሄድ እንዳለብን ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ በአዲሱ ዓመት ከምንሠራቸው ተግባራትም አንዱ ትውልዱ አገሩን እንዲወድ በባህል ስፖርት ላይ ትኩረት ማድረግ ነው፡፡ ነባር የሆኑ የባህል ስፖርቶች እንዳይጠፉ ግን በከተማዋ ላይ በርካታ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ነው፡፡ አዲስ ዘመን፡- ለሰጡኝ ሰፊ ማብራሪያ አመሰግናለሁ! አቶ ዮናስ፡- እኔም በጣም አመሰግናለሁ!አዲስ ዘመን መስከረም 2/2011አዲሱ ገረመው
https://www.press.et/Ama/?p=17893
1,590
2ስፖርት
የማህበሩ ቅሬታ ከመግለጫ እስከ ፍርድ ቤት
ስፖርት
September 11, 2019
27
የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን «በኢትዮጵያ አሁን ያለው የሊግ አደረጃጀት በፋይናንስ ረገድ ክለቦች ላይ ያለው ተጽዕኖ ምንድነው?» በሚል ርዕስ አንድ ጥናት አስጠንቶ ነበር። የፌዴሬሽኑ ጥናት እንዳመለከተው፤ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሚገኙት አጠቃላይ ክለቦች በየዓመቱ ሁለት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር ወጪ ያደርጋሉ። ክለቦቹ ይህንን ገንዘብም ለተጫዋቾች ወርሃዊ ደመወዝ፣ ለምግብ፣ ለመኝታ፣ ተዟዙሮ ለመጫወትና ለትራንስፖርት ወጪ እንደሚያወጡም ገልጿል። ከህዝብ፣ ከግብር ከተሰበሰበ ገንዘብ፣ ከክልል መስተዳድሮች በሚሰጥ በጀት ያለ ተጠያቂና ውጤት ተኮር ዓላማ ለተጫዋቾች የሚወጣው በሚሊየኖች የሚቆጠር ገንዘብ እጅጉን ያስደነግጣል። የክለቦቹ ገደብ አልባ ወጪ በብዙ መልኩ አነጋጋሪ በመሆን ለዓመታት የተሻገረ ሲሆን፤ ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ ለዚህ ጉዳይ ልጓም ይሆናል ያለውን መፍትሄ አመላክቷል። ባሳለፍነው ነሐሴ 3 ቀን 2011 ዓ.ም የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ የክልል ስፖርት ቢሮ ኃላፊዎችና የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች አመራሮች በተገኙበት ቢሾፍቱ በተደረገው ጉባዔ ለዚሁ ችግር መፍትሄ የሚያመጣ ውሳኔ መተላለፉ ይታወሳል። ፌዴሬሽኑ በዚህ ውሳኔው የተጫዋቾች ደመወዝ ከ50 ሺህ ብር በላይ እንዳይሆን ህግ አውጥቷል። ይህ መመሪያ ጸድቆ ተግባር ላይ ቢውልም ከወዲሁ የተቃውሞ ድምጾች እየተሰሙበት ይገኛሉ። የኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል ፉት ቦለር አሶሴሽን በውሳኔው ተገቢነት ላይ ጥያቄን ካነሱት አካላት መካከል ይጠቀሳል። ማህበሩ ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ ውሳኔውን ባስተላለፈ ማግስት ውሳኔው ተገቢነት እንደሌለው በመግለጽ ቅሬታውን ሲያሰማ ቆይቷል። ከሰሞኑ መመሪያው የተጫዋቾችን ሰብአዊ መብት የሚነካ በመሆኑ ብሄራዊ ፌዴሬሽኑን ፍርድ ቤት ለማቆም መሰናዶ መጀመሩን አስታውቋል። የኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል ፉት ቦለር አሶሴሽን ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ግርማ እንደነገሩን ፤ ማህበሩ ለዚህ ውሳኔ የበቃው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በተደጋጋሚ ደብዳቤዎች ቢላኩለትም ምላሽ ባለመስጠቱ ነው። የኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል ፉት ቦለር አሶሴሽን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በጉዳዩ ላይ ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ ምን መሰረት ይዞ ውሳኔ እንዳሳለፈ አቶ ግርማ አስረድተዋል። «ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ በመጀመሪያ ደረጃ የተጫዋቾች የደመወዝ ጣሪያ መመሪያ ሲያወጣ የራሱን መመሪያና የፊፋን መተዳደሪያ ደንብ የጣሰ እንደሆነ ያምናል ። መስከረም 27 ቀን 2004 ዓ.ም. በወጣው የፌዴሬሽኑ መተዳደሪያ ደንብ በአንቀጽ አምስት የአባላት የጋራ ጥቅም እንዲሁም በአንቀጽ 11፣ 46 እና 47 የአባላት መብቶችና የዓለም አቀፍ የስፖርት ግልግል ፍርድ ቤት ከሚከተሉት ሕጋዊ አሠራር ያፈነገጠ ነው» ብለዋል።ፕሬዚዳንቱ ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ ውሳኔውን ያስተላለፈው ከስፖርት ኮሚሽን ጋራ በአብሮነት መሆኑን አንስተዋል። ስፖርት ኮሚሽን በብሄራዊ ፌዴሬሽኑ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት የፌዴሬሽኑ አባል አለመሆኑ፣ በፌዴሬሽኑ ደንብ ላይ የተገለጸው የተጫዋቾች መብት አለመጠበቁ፣ አንቀጽ 47 ላይ የተደነገገው የስፖርት ግልግል ጉባኤ አለመተግበሩ ህጋዊ መሰረት የሚያሳጠው መሆኑን በመግለጽ ሞግተዋል። ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ በተጫዋቾች የደመወዝ ጣሪያ መመሪያ ሃገር አቀፍና አለም ዓቀፍን መተዳደሪያ ደንብ ከመጣስ ባሻገር፤ የኢትዮጵያን የፍትሐብሄር ህግ የጣሰ ድርጊት እንደሆነም አመልክተዋል።የፌዴሬሽኑ ውሳኔ ላይ ተቃውሞ እንዳለው የተናገረው የማህበሩ ስራ አስፈጻሚ አባል አቶ ዳዊት እስጢፋኖስ ፤ ፌዴሬሽኑ በግለሰብ ላይ እንዲህ ዓይነት ውሳኔ የማሳለፍ መብት እንደሌለው ገልጿል፡፡ ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ የፈፀመው ድርጊት ህጋዊ መሰረት እንደሌለውና መተዳደሪያ ደንቡን የሚጥስ እንደሆነ በተደጋጋሚ በደብዳቤም ጥያቄ አቅርበው በአፋጣኝ መልስ ሊሰጥ እንዳልቻለ ያስታውሳል። ማህበሩ ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ ለጥያቄያቸው እስከ መስከረም አንድ ቀን 2012 ድረስ መልስ ካልሰጠ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ለመውሰድ ከውሳኔ ላይ መድረሱን አስታውቋል። ዳዊት እስጢፋኖስ፤ ለብሄራዊ ፌዴሬሽኑ ጥያቄያቸውን አስገብተው ምላሽ እየጠበቁ እንደሚገኙ፣ ከፌዴሬሽኑ ጋር አብሮ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸውና አብሮ መስራት ሲባል ግን በዚህ መልኩ አለመሆኑን ጠቅሷል። የፌዴሬሽኑ ዋናው ክፍሎች ተጫዋቾች በመሆናቸውም የተጫዋቾች መብት ማስጠበቅ ይኖርበታል። የተጫዋቾችን መብት ባላከበረና ባልጠበቀ ሁኔታ፣ ሳያማክርና መግለጫ ሳይሰጥ ውሳኔ ማሳለፍ አግባብነት የሌለውና ትክክል እንደሆነ በመግለጽ የብሄራዊ ፌዴሬሽኑን ድርጊት ኮንኗል።የማህበሩ ስራ አስፈጻሚ ሌላው አባል አቶ ኤፍሬም ወንድወሰን በበኩሉ‹‹ማህበሩ አላማው የተጫዋቾችን መብት ማስከበር ነው ፤ በተጫዋቾች ላይ ቀደም ሲል ሲደርሱ የነበሩ የተለያዩ የመብት ጥሰቶች ነበሩ ፤ አሁን ግን ከመንግስት የተሰጠን ፍቃድ በመጠቀም በተጫዋቾች ላይ የሚደርሱ የመብት ጥሰቶችን ለመከላከል እንሰራለን›› ካሉ በኋላ፤ ማህበሩ ፍቃድ ካገኘ በኋላ እርሱን ያላማከለ ውሳኔ ተወስኖ የሞራል ጉዳት መድረሱን አብራርተዋል።አቶ ኤፍሬም «በተደጋጋሚ ለፌዴሬሽኑ ጥያቄዎች ቢቀርቡለትም ከዝምታ ውጪ ምላሽ አልሰጠም። ማህበሩ ካሉት የህግ ሰዎች ጋር ተመካክሮ ቀጣይ መንገዶችን መጓዝ እንዳለበት ከውሳኔ ደርሷል። በመሆኑም ሁላችንም ወደምንዳኝበት ፍርድ ቤት ጉዳዩን ይዘን የምንሄድ ይሆናል። ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ ለመነጋገር በሩ ክፍት ነው። እስከ መስከረም አንድ ቀን 2012 ዓ.ም በዚሁ ፍላጎቱ የሚፀና መሆኑንና ምላሽ ከሌለ ወደ ህግ የሚጓዝ ይሆናል» ሲል ሃሳቡን ቋጭቷል።ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ መመሪያውን ተግባራዊ ለማድረግ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ከመግለጽ በስቀር የማህበሩን እንቅስቃሴ በተመለከተ ምንም አይነት ማብራሪያም ሆነ መግለጫ ሲሰጥ አልተደመጠም።አዲስ ዘመን  ረቡዕ ጳጉሜ 6/2011ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=17791
594
2ስፖርት
በእግር ኳሱ ያየነው ፈተና በ2012 እንዳይደገም
ስፖርት
September 12, 2019
33
አሮጌውን 2011ዓ.ም ሸኝተን አዲሱን 2012 ዓ.ም ዛሬ አንድ ብለን ተቀብለናል። ባለፉት ሦስት መቶ ስልሳ አምስት ቀናት በኢትዮጵያ ስፖርት ውስጥ መልካም ነገሮችና ተስፋዎች የታዩትን ያህል በእግር ኳሱ ዙሪያ ሊጠቀስ የሚችል አንድም መልካም ነገር አልታየም ማለት መዳፈር ሳይሆን ሀቅ ነው። ስለዚህ 2011 ዓ.ም ለኢትዮጵያ እግር ኳስ የጨለማ ዘመን ሆኖ አልፏል ቢባል ማጋነን አይሆንም። ይህን ዘመን ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ጨለማ ነው ለማለት የተለያዩ ማሳያዎችን ማስቀመጥ እና በአዲሱ ዓመት እንዳይደገሙ ሀሳብ እናቀርባለን፤ ይህ ደግሞ ተገቢ ነው። የስቴድየም ሁከትና ግጭት በ2009 ዓ.ም በርካታ ቁጥር ያለው የስቴዲየም ሁከት በተለይም በፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ቢከሰቱም ከብጥብጦቹ ጀርባ እግር ኳስን የሚሻገሩ ገፊ ምክንያቶች እምብዛም እንዳልነበሩ ይጠቀሳል። ከ2009 ወዲህ ግን በልዩ ልዩ ምክንያቶች የሚለኮሱ የስቴድየም ግጭቶችና ረብሻዎች ቁጥር አይሏል። በ2010 የውድድር ዓመት ሐዋሳ፣ ድሬዳዋ፣ አዲግራት፣ ጅማና ወልዲያ ከተሞች ውስጥ የስቴድየም ሁከትና ግጭቶች ተበራክተው እንደነበር ይታወሳል። በተለይም በውድድር ዓመቱ በወልዲያ ስፖርት ክለብና በመቀሌ ከተማ መካከል ሊደረግ የነበረው የእግር ኳስ ጨዋታ ከመጀመሩ ከሰዓታት በፊት በሁለቱ ቡድኖች ደጋፊዎች መካከል በተቀሰቀሰው ግጭት ህይወት የጠፋ ሲሆን ንብረት ላይ ዘረፋና ወድመት ተከስቷል። በዕለቱም ማገባደጃ ላይ በመቀሌ ከተማ መንገዶች ላይ ክስተቱን ለመቃወም በርካታ ሰዎች ወጥተው እንደነበር አይዘነጋም። ጨዋታው ካለመካሄዱ በተጨማሪም የግጭቱ አሻራ እስከ ቀጣይ ቀናት ሲሻገርና ከእግር ኳሳዊ ምክንያት ይልቅ ፖለቲካዊ አንደምታው ሚዛን ሲደፋ ታይቷል። የ2010 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሃ ግብር ከረብሻዎች ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በተለያዩ ክለቦች ላይ የጣለው ቅጣት ግማሽ ሚሊዮን ብር ገደማ መሰብሰብ መቻሉ ግጭቶች በምን ያህል ደረጃ እንደተበራከቱ ማሳያ ነው። ‹‹በእንቁላሉ ጊዜ›› ያልተቀጣው እግር ኳስ 2011 ላይ ከፖለቲካም በላይ ጦዞ ለፀጥታ አስከባሪዎች ፈተና ከመሆን አልፎ እንደ አገር ስጋት የሆነበት ደረጃ ላይ ደርሷል። ሰላም በራቃቸው የስፖርት ማዘውተሪያዎች መደበኛ የውድድር መርሐ ግብሮች መተማመኛ ማግኘት እየቻሉ እንዳልሆነ ተመልክተናል። በክልል የሚካሄዱ ጨዋታዎች በፖለቲካ ትኩሳት ሳቢያ ተጨማሪ ራስ ምታት እየሆኑ መምጣታቸውን በተለይም በ2011 የውድድር ዓመት ለመታዘብ ተችሏል። በአገሪቱ የደፈረሰው ሰላም ለስፖርቱም ዋናው እርሾ እየሆነ በመታየቱ በተለይ በክልል እግር ኳስ ክለቦች መካከል የሚከናወኑ ጨዋታዎች ከእግር ኳሳዊ ትንቅንቁ ይልቅ የሥጋት ምንጭነታቸው ሲያይል ከማየት የበለጠ ለአገሪቱ እግር ኳስ የጨለማ ዘመን ማስረጃ ማቅረብ አይቻልም። በዚህም የብሔራዊ ፌዴሬሽኑ መደበኛ ውድድሮች በተያዘላቸው ቀንና ጊዜ እንዳይከናወኑ ምክንያት ሆኗል። በክልል የሚካሄዱ ጨዋታዎች በፖለቲካ ትኩሳት ሳቢያ ተጨማሪ ራስ ምታት እየሆኑ መምጣታቸውን በዚሁ የውድድር ዓመት ለመታዘብ ተችሏል። ለታኅሣሥ 17 ቀን 2011 ዓ.ም. የታሰበው የወላይታ ድቻና የሲዳማ ቡና ጨዋታ አንዱ ማሳያ ሲሆን፣ ሌላው በዚሁ የፖለቲካ ትኩሳት በይደር የቆየው መቐለ 70 እንደርታ ከፋሲል ከተማ፣ እንዲሁም ባህር ዳር ከተማ ከሽረ እንደስላሴና ሌሎችም ይጠቀሳሉ። ክለቦች በክልሉ በተዟዙሮ የሚያደርጉት ጨዋታ ከወጪውም አኳያ ቀድሞውንም ባይደግፉትም ፖለቲካው ባመጣው ጣጣ አንዳንዶቹ እየተዟዟሩ ለመጫወት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቆይተዋል። ቀደም ሲል የወላይታ ድቻና የሲዳማ ቡና የጨዋታ መርሐ ግብር ሲወጣ አንዳችም ተቃውሞ አልነበረም። ይሁንና የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሠረት እንደሚካሄድ ሲጠበቅ፣ ከሲዳማ ቡና ለፌዴሬሽኑ በተላከ ደብዳቤ ጨዋታውን ወላይታ ድቻ ላይ ሄዶ መጫወት የሚያስችል ሁኔታ ባለመኖሩ ጨዋታው እንዲራዘም ተደርጓል። የመቐለ ከተማና የፋሲል ከተማን ጨዋታ በተመለከተም ፋሲሎች ከሜዳቸው ውጪ ለሚያደርጉት ጨዋታ ዝግጅታቸውን አጠናቀው እንደነበረ፣ ሆኖም ባህር ዳር ከተማ ላይ የሚደረገው የባህር ዳርና የሽረ እንደስላሴ ጨዋታ ፀጥታውን የበለጠ አስተማማኝ ለማድረግ በሚል ከክልሉ የፀጥታ ኃላፊዎች ለፌዴሬሽኑ በቀረበ ጥያቄ መሠረት እንደሆነም በወቅቱ መነገሩ ያታወሳል። በዚሁ ሳቢያ የፋሲል ቡድን ወደ መቐለ የሚያደርገውን ጉዞ ለመሰረዝ መገደዱ ይታወቃል። በእነዚህና በሌሎችም ተያያዥ ምክንያቶች አጣብቂኝ ውስጥ የገባው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የክልል አመራሮችን ማነጋገር የጀመረው ቀደም ሲል ጀምሮ መሆኑ ይታወሳል። ያም ሆኖ ጨዋታዎች መሰረዛቸውና የፀጥታ ስጋት መኖሩ አልቀረም። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ፌዴሬሽኑ በካፍ መርሃግብር መሰረት የአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግና ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ኢትዮጵያን የሚወክሉ ክለቦችን ለማሳወቅ ምን ያህል ጥድፊያ ውስጥ እንደገባ በቅርቡ የምናስታውሰው ነው። በስፖርቱ ዓለም የተመልካቾች ነውጠኝነት ምክንያቶች ብዙ መሆናቸውን በስፖርቱ ጥልቅ እውቀት ያላቸው ባለሙያዎች ሲናገሩ ይደመጣል። ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ ወይንም ምጣኔ ሀብታዊ ብሶቶች ስቴዲየም ላይ ሊያጠሉ እንደሚችሉም ይታመናል። በኢትዮጵያ እግር ኳስን የታከከ ግጭትና ሁከት ሲከሰት የመጀመሪያው ባይሆንም 2011 ላይ ቀይ መስመር አልፎ ታይቷል። የቅርብ ጊዜ ክስተቶችን ስናጤን ደግሞ ከእግር ኳስ ባሻገር ከነዚህ ምክንያቶች ሁሉ ለስፖርት ጠንቅ የሆነ የፖለቲካ አጀንዳ መኖሩን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ራሳቸው አስተውለውታል። እግር ኳስ ማኅበረሰባዊ መሰረት ከሌለው በስተቀር የጠነከረ የእኔነት ስሜት ሊፈጥር አይቻለውም የሚሉ ተንታኞች ፤ ክለቦች ከማኅበረሰባዊ መሰረታቸው በዘለለ ብሔር ተኮር መልክን እየተላበሱ የመምጣታቸው አዝማሚያ አደገኛ መሆኑን አይክዱትም። ክለቦች ሲቋቋሙ ወይንም ሲዋቀሩ አካባቢያዊ መገለጫ ወይንም ከተማዊ ስያሜ ሊኖራቸው ቢችልም ከብሔር፣ ከዘር ወይንም ከኃይማኖት ጋር በተቆራኘ መልኩ መደራጀት ክልክል መሆኑን የስፖርት ኮሚሽን የስፖርት ማኅበራት ማደራጃ መመሪያ አንቀፅ 50 ቁጥር 2 ይገልፃል። ነገር ግን ባለፉት ዓመታት ብቻ ፌዴሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው ሊጎች የብሔር ስም የተቀጠላላቸው በርካታ ክለቦች ውድድር እያደረጉ ይገኛሉ። እግር ኳሱ ከአንዳንድ ሁከቶች አልፎ እጅግ ወደተደራጀ ነውጠኛነት እያመራ ስለመሆኑ የ2011 ዓ.ም መርሃግብሮች ቁልጭ አድርገው አሳይተውናል። ቀስ በቀስም ወደመቧደን እየተሄደ ራሳችንን መከላከልና ማዘጋጀት አለብን በሚል ደጋፊዎች ራሳቸውን ማደራጀት ከጀመሩ የሚያሰጋ ዓይነት እውነታ ሊፈጠር እንደሚችል በ2011 የውድድር ዓመት ተመልክተናል። በደጋፊዎች መካከል የእኔነቱ መንፈስ ከሮ ከኳስ ወዳጅነት አፈንግጦ በብሔርተኝነት ጎዳና መጓዝ ተጀምሯል። ከዚህ ቀደም ብጥብጡ ተጀምሮ የሚያልቀው ስቴዲየም ነው፤ ከዚያ አያልፍም። አሁን አሁን እየታየ ያለውን ግን ማብራሪያ የማይፈልግ የአደባባይ ሃቅ ነው። ክለቦች የማንነት ማግነኛና የራስ ኩራት መገለጫ መድረኮች እየሆኑ የመምጣታቸውን ሃቅ በየአካባቢው እየጎመራ ከመጣው የዘውግ ብሔርተኛነት ጋር የሚያስተሳስሩትም ጥቂት አይደሉም። ክለቦች መጠሪያው ባይኖራቸውም ከሚመጡበት ክልል ጋር ተያይዞ የእገሌ ብሔር ነው የሚል እምነት አሳድረዋል። ከዚህም በተጨማሪ ክለቦች የተለያዩ የአገሪቱን ክልሎች እንደሚወክሉ መታሰቡ፤ ክልሎች ብሔርን መሰረት አድርገው እንደመዋቀራቸው ብሄርን እንደሚወክሉ ወደመታሰብ አድጓል። ፌዴሬሽኑ ከውይይት የዘለለ ፋይዳ ያለው ነገር እየሰራ እንዳልሆነ የሚጠቁሙ የስፖርት ቤተሰቦች ከዚህም በኋላ ችግሩን ይቀርፋል የሚል እምነት ማሳደር ተቸግረውበታል። ይህንንም በውድድር ዓመቱ በጉልህ ተመልክተነዋል። ሳይጠናቀቅ የተጠናቀቀው ፕሪሚየር ሊግ አሁን አሁን በአዲስ አበባም ሆነ የክልል ስታደዬሞች ገብቶ ኳስ መታደም የራስን ደህንነት አደጋ ላይ ከመጣል ጋር ይነፃፀር ጀምሯል። ጨዋነት የጎደላቸው ደጋፊዎች፣ ከዳኛ ጋር ቡጢ የሚገጥሙ ተጫዋቾችና የቡድን አባላት፣ እንዲሁም ኢ-ፍትሐዊ የሆኑ ውሳኔዎች የሊጉ መገለጫ ከሆኑ ሰነባብተዋል። የ2011 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከስቴድየም ግጭትና ከፌዴሬሽኑ አወዛጋቢ ውሳኔዎች ጋር ተያይዞ ክለቦች የውድድር ዘመኑን ሳይቋጩ ራሳቸውን ከውድድር ያገለሉበት ሆኖም ይታወሳል። ውዝግቦችና አለመግባባቶች በኢትዮጵያ እግር ኳስ ነግሰዋል። መሬት ያልነኩ፣ በእውቀት ያልተዋጁ ውሳኔዎች ሰላማዊውን መድረክ የብጥብጥ ቀጠና አድርገውታል። ሊጉ የሚቀጥልበት አቅም ባለማግኘቱም በተደጋጋሚ ለመቋረጥ ተገዷል። ለዚህም የአገሪቱ ታላላቅ ክለቦች የሆኑት ቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ቡና በውድድር ዓመቱ መጨረሻ ላይ ከፌዴሬሽኑ ጋር የገቡበት ውዝግብ የአዲስ አበባ ክለቦች የራሳቸውን ሊግ ለማቋቋም ውሳኔ ላይ እስከመድረስ ገፍተው እንዲሄዱ አድርጓቸዋል። ያም ሆኖ የአዲስ አበባ ክለቦች የራሳቸውን ሊግ በማቋቋም የጀመርነውን አዲስ ዓመት ይገፉበታል ወይም በተለመደው ፕሪሚየር ሊግ ይቀጥላሉ የሚለው ሃሳብ ጥርት ያለ ድምዳሜ ላይ ሳይደረስበት ወደ አዲሱ የውድድር ዓመት ተሸጋግረናል። ብሔራዊ ቡድኑ (ዋልያዎቹ) 2011 ዓም የአንድ አገር ሊግ ድክመትና ጥንካሬ የብሔራዊ ቡድኑ መገለጫ እንደሚሆን አሳይቶን አልፏል ማለት ይቻላል። የአገሪቱ ሊግ በግጭትና ፍትሃዊ ባልሆኑ ውሳኔዎች እየታመሰ አይደለም ለወትሮውም ጥሩ ስም የለውም። የሊጉ ደካማነት ብሔራዊ ቡድኑ (ዋልያዎቹ) ላይ ተንፀባርቆ ያለፈበት ዓመት ለመሆኑ ጥቂት ውድድሮችን ለአብነት ማንሳት ይቻላል። ከሁለትና ሦስት ዓመታት በፊት እንደ ጅቡቲ ያሉ የእግር ኳስ ደረጃቸው ከኢትዮጵያ ያልተሻሉ አገራትን በቀላሉ ግማሽ ደርዘን ግብ አስቆጥረን ማሸነፍ እንችል ነበር። አሁን አሁን ይሄም እየከበደን ከአንድ ግብ በላይ ማስቆጠር እየተሳነን እንደመጣ በውድድር ዓመቱ ተመልክተናል። ቀደም ሲል በቻን የምናደርገውን ተሳትፎ አሁን ማድረግ አልቻልንም፣ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳታፊ አገራት ከአስራ ስድስት ወደ ሃያ አራት ከፍ ብሎ እንኳን ተሳታፊ መሆን አልቻልንም። ለኳታሩ የዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ እንኳን ሌሴቶን ባህር ዳር ላይ ገጥመን ግብ ማስቆጠር አልቻልንም፣ የመልሱም ጨዋታ ቢሆን አንድ ለአንድ ተለያይተን ወደ ምድብ ድልድል የገባንበት አጋጣሚ ደረት የሚያስነፋ አይደለም። በመጨረሻም እግር ኳሱ በ2011 የውድድር ዓመት በዚህ ደረጃ ዘቅጦ ፌዴሬሽኑ አዲሱን ዓመት በምን መልኩ መጀመር እንዳለበት በግልፅ ያስቀመጠው ስትራቴጂክ እቅድ የለም። ፕሪሚየር ሊጉ እንዳለፈው ዓመት ተዟዙሮ የመጫወት መንገድ ይቀጥል አይቀጥል ማንም አያውቅም። ከፌዴሬሽኑ ዝምታ ተነስቶ ግን ሊጉ በነበረበት እንዲቀጥል ፍላጎት መኖሩን መገመት ከባድ አይደለም። ይህ ደግሞ ካለፈው ስህተት አለመማር ብቻም ሳይሆን የአገር ንብረትና የዜጎች ሕይወት የሚጠፋበትን መንገድ መፍቀድ ጭምር ነው። ፌዴሬሽኑ ከዚህ ጉዳይ ይልቅ የተጫዋቾች የደመወዝ ጣሪያ ጉዳይ አስጨንቆት ከርሟል። ለዚህም አበጀሁለት ያለው መላ መልካም ጎን እንዳለው ሁሉ በርካቶችን ያስማማና ከትችት ያመለጠ አልሆነም።አዲስ ዘመን   መስከረም 1 /2012 ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=17852
1,167
2ስፖርት
መንግሥት የወሰደውን ሕግ የማስከበር እርምጃ በመደገፍ በቴልአቪቭ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 6, 2020
11
በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ፡- በእስራኤል የሚኖሩ የቤተ እስራኤል ማኅበረሰብ አባላት፣ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮ ጵያውያን መንግሥት በህወሓት ጁንታ ላይ የወሰደውን ሕግ የማስከበር እርምጃ እና የመከላከያ ሠራዊት ያደረገውን ተጋድሎ በመደገፍ በቴልአቪቭ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ።በእስራኤል የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ የድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊዎች ከቴል አቪቭ፣ ከኢየሩሳሌም፣ ከቤርሼባ እና ከሌሎችም የእስራኤል ከተሞች የመጡ ናቸው ።ሰልፉን ያዘጋጁት ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ባለፉት ሁለት ሳምንታት ጁንታውን በመደገፍ እና በመንግሥት የተወሰደውን የሕግ ማስከ በር እርምጃ በመቃወም ሰልፍ ያደረጉ ሰዎች ጥያቄ እንዳስቆጣቸው አስታውቀዋል።በእስራኤል የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር እና ልዩ መልእክተኛ አምባሳደር ረታ ዓለሙ ለሰልፈኞች ባስተላለፉት መልዕክት “መንግሥታችን የወሰደውን ሕግ የማስከበር እርምጃ እና ለመከላከያ ሠራዊታችን ያላቸውን አክብሮት ለመግለጽ ድጋፍ ስላደረጋችሁ በመንግሥት ስም አመሰግናለሁ” ብለዋል።ሕግ የማስከበር ዘመቻው በድል መጠናቀቁ ትልቅ ስኬት መሆኑን ጠቅሰው፣ በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት መሰረት በሕግ የሚፈለጉትን የጁንታው አባላት ለሕግ ለማቅረብ መንግሥት የሚያከናውነው ወንጀለኞችን የማደንና የመልሶ ግንባታ ምዕራፍ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።በቀጣይ የመንግሥት ዋና ትኩረት የትግራይ ሕዝብ አሁን ካለበት ሁኔታ እንዲወጣ የመልሶ ግንባታ ማከናወን፣ ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ የተሰደዱ ዜጎችን ወደነበሩበት ቀዬ መመለስ መሆኑን አስታውቀዋል ። እነዚህን ተግባራት በመደገፍ ከመንግሥት ጎን እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል።የድጋፉ ተሳታፊዎች ባወጡት የአቋም መግለጫ፣ በሰሜን እዝ ላይ በተፈጸመው ከባድ ክህደት እና ጥቃት ልባችን አዝኗል፤ የጁንታውን ቡድን ለፍትህ ከማቅረብ በተጨማሪ ቡድኑ በሕግ ሊታገድ እንደሚገባ ጠይቀዋል።  ሰልፈኞቹ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት በወቅቱ ያሰባሰቡትን 17 ሺህ 200 የአሜሪካ ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ለኤምባሲው አስረክበዋል።አዲስ ዘመን ህዳር 27/2013 ዓ. ም
https://www.press.et/Ama/?p=36809
209
0ሀገር አቀፍ ዜና
የወታደሯ የሶስት ቀናት የከርሰ ምድር ውስጥ ቆይታ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 6, 2020
23
አዲስ አበባ፦ መ/ወ/ር ተስፋነሽ ጋቢሳ ትባላለች። የመከላከያ ሠራዊታችን ልዩ ኃይል አባል ናት። ጁንታው በከፈተው ውጊያ ለመፋለም በራያ ግንባር ከክፍሏ አባላት ጋር ተሰልፋ በርካታ ግዳጆችን በድል ተወጥታለች።ጠላት ለዓመታት ያዋጋኛል ብሎ እንዳዘጋጀው በወታደራዊ ጠበብቶቹ በግንባሩ መሪ ሌ/ጄ ባጫ ደበሌ እና ሌሎች አመራሮች የተመሰከረለት ልዩ ቦታው አዲ ቀይህ የተባለው ቦታ ላይ ለ3 ቀናት በተደረገው ፍልሚያ በጀግንነት እየተዋጋች ሳለ ያልጠበቀችው ገጠማት። በዚህ ቦታ ላይ ጠላት ሙሉ ኃይሉን ተጠቅሞ መዋጋት በመጀመሩ እንደ ሌሎች ምሽጎች በቀላሉ መስበር ካለመቻሉም ባሻገር፣ ጠላትን ለመደምሰስ የገባውን የወገን ጦር ለመቁረጥ መልሶ ማጥቃት በማድረጉ፣ ወገን የኃይል ሚዛኑን ለማመጣጠንና ሌሎች ወታደራዊ ጥበቦችን ለመጠቀም ሲባል ከጠላት ከበባ ሰብረው እንዲወጡ ሲደረግ ፣ መ/ወ/ር ተስፋነሽ በጠላት ቀጣና ተቆርጣ ትቀራለች። ወ/ር ተስፋነሽ ወገን አሸንፎ ሞሽጉን እንደሚሰብር ሙሉ እምነት ስለነበራት ፣ የታጠቀችውን ስናይፐር ጨምሮ መሬቱን ቆፍራ ራሷን ጉድጓድ ውስጥ ትቀብራለች። አፈሩን በእጆቿ በላይዋ ላይ በመመለስ ከመሬቱ ጋር በሚገባ ትመሳሰላለች። በዚህ ሁኔታ ላይ እያለች ብዙ የጁንታው ታጣቂዎች በላይዋ ላይ እየተረማመዱ ከወዲያ ወዲህ ይመላለሱባታል። መማረክን ከሞት በላይ የምትፈራውና ድሉን ሳታይ መሞት የማትፈልገው ጀግናዋ መ/ወ/ር ተስፋነሽ ያላት አማራጭ ሁሉንም ችላ ዝም ማለት ብቻ ነበር።በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያለች ጁንታው ከአጠገቧ ላይ ዲሽቃውን ጠመደ ፣ አንዱ የዲሽቃው ዎሳ እግር ከተቀበረችበት አቅራቢያ ላይ አረፈ።በቃ ድሽቃው ቦታውን ሳይለቅ ከአቅራቢያዋ እየተኮሰ 3 ቀናት አስቆጠረ ። በነዚህ ቀናት ራሷን እንደሙት ያለምንም እንቅስቃሴ ትንፋሿን አምቃ በከርሰ ምድር ሳለች ከፍተኛ ውጊያ ከተካሄደ በኋላ ሰራዊታችን ሞሽጉን ሰብሮ ድል ማድረጉን የዲሽቃው ዎሳ እግርም እሷ ካለችበት ጉድጓድ  አካባቢ መነሳቱን አወቀች። ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ራሷን ከቀበረችበት በማስነሳት አካባቢውን ስትመለከት ጀግኖች ጓዶቿ ጁንታውን አባረው ቦታውን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥረውታል። እሷ ብታውቃቸውም እነሱ ግን ሙሉ ሰውነቷ ከአፈር ስለተመሳሰለ አላወቋትም ነበርና ‘ እጅ ወደ ላይ ‘ የሚል ድምፅ ሰማች። እሷም እጆቿን አንስታ ‘ ወገን ነኝ ‘ የሚል ድምፅ በደስታ ብዛት ተውጣ አሰማች። እነሱም ወደ ኋላ በመውሰድ ከ 3 ቀናት በኋላ እህልና ውሃ እንድትቀምስ አድርገው ተመልሳ ጁንታውን ለደምሰስ እየተፋለመች ትገኛለች።አዲስ ዘመን ህዳር 27/2013 ዓ. ም
https://www.press.et/Ama/?p=36810
287
0ሀገር አቀፍ ዜና
“ጁንታው የትግራይን ህዝብ መውጪያ መግቢያ ከማሳጣት ባለፈ የጠቀመው ነገር እንደሌለ ጠንቅቆ ያውቃል” – ዶክተር አረጋዊ በርሄ የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር
ሀገር አቀፍ ዜና
December 7, 2020
34
እፀገነት አክሊሉአዲስ አበባ፦ ጁንታው የትግራይን ህዝብ እግር በእግር እየተከታተለ መውጪያ መግቢያ ከማሳጣት ባለፈ የጠቀመው ነገር እንደሌለ ጠንቅቆ እንደሚያውቅ የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አስታወቁ።ሊቀመንበሩ ዶክተር አረጋዊ በርሄ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳስታወቁት ፣ ጁንታው እስከ አሁን ህዝቡ በድርጅቱ ቁጥጥር ስር አድርጎ እያንዳንዷን እንቅስቃሴውን እየተቆጣጠረ መውጪያ መግቢያ አሳጥቶ ነው የኖረው ። አሁን ግን የተጎናጸፈውን ድል በመጠቀምና ነጻነቱን በአግባቡ በማጣጣም የመንግሥትን እገዛ ተጠቅሞ እራሱን ወደልማት ያስገባል።የትግራይ ህዝብን በኢኮኖሚ በፖለቲካ ተጠቃሚ አደርጋለሁ ሲባል መጀመሪያ ሊመጣ የሚገባው ነገር ህዝቡን ማስቻል፤ መብቱን መጠበቅ፤ ተደራጅቶ እንዲንቀሳቀስ ማመቻቸት ነው ያሉት ዶክተር አረጋዊ ፣ ይህ ከሆነለት በአጭር ጊዜ ውስጥ በራሱ መንገድ ኑሮውን በማሻሻል መሰረታዊ ለውጥ ማምጣጥ እንደሚችል አስታውቀዋል።መንግሥት መሰረተ ልማቶችን በማሟላት፤ ለወጣቱ የሥራ እድል በመፍጠር በተለይም ደግሞ የጀመረውን ህግን የማስከበር ሥራ በመላ አገሪቱ በማድረግ የትግራይም ወጣት ሌላ ክልል ሄዶ በነጻነት እንዲሰራ በማመቻቸት በኩል ሚናውን ሊወጣ እንደሚገባ አመልክተዋል።ጁንታው ለትግራይ ህዝብ የማያስብ መሆኑን በዚህ ጦርነት እንኳን እራሱን ለማትረፍ ሲል በህዝብና በመንግሥት መሰረተ ልምቶች ላይ ያደረሰውን ውድመትን ማየት ይቻላል ያሉት ዶክተር አረጋዊ፣ የአክሱም የአየር ማረፊያን ጨምሮ ሌሎች በርካታ መሰረተ ልማቶችን አውድሞ መሄዱን አመልክተዋል ።ጊዜያዊ አስተዳደሩም እነዚህን የወደሙ መሰረተ ልማቶችን ከሚመለከታቸው ጋር በመሆኑ ወደቦታቸው መመለስ ይጠበቅበታል፤ እኛም ማህበራዊ መሰረታችን ትግራይ ክልል የሆንን ፓርቲዎች ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ጋር በጋራ ለመስራት ባለን አቅም ሁሉ ተዘጋጅተናል ብለዋል ።በክልሉ ሥራውን የጀመረው ጊዜያዊ አስተዳደር የህዝቡን አስከፊ ህይወት ለመለወጥ እንደሚሰራ ተስፋ አለኝ ያሉት ዶክተር አረጋዊ፣ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ክልሉን እንደገና ለመገንባትና ከዚህ በፊትም አጥቶት የነበረውን መሰረተ ልምት ለማሟላት እንደ ፓርቲ ህዝቡን በማስተባበር ሌሎች አስፈላጊ ድጋፎችንም በማድረግ እንደሚሳተፉም አስታውቀዋል።የትግራይ ክልል ከዛሬ 46 ዓመት በፊት ጀምሮ በጦርነት እጅግ የተጎዳ አካባቢ ነው፤ ህዝቡም በእርዳታ ስንዴ የሚኖር የተስተካከለ የመጠጥ ውሃ እንኳን ያላገኘ ነው ያሉት ዳክተሩ፣ ጁንታው በስሙ እየነገደ የሚያጋብሰውን ሃብት ስለተመቸውና እራሱን አንደላቆ እንዲሁም ልጆቻቸውን እጅግ በተቀናጣ ምቾት ውስጥ ማኖር ስለቻሉ ብቻ ስለ ህዝቡ ደንታ ቢስ ሆነው መቆየታቸውን ጠቁመዋል።ይህ መሆኑ ደግሞ ሌላውም የአገሪቱ ህዝብ የእነሱን መንደላቀቅ ሲያይ ህዝቡም በዛው ልክ ተመችቶት የሚኖር እየመሰለው መቆየቱን ጠቁመው፣ ነገሩ ሁሉ የተገላቢጦሽ ነው። የገዢዎቹና የህዝቡ ኑሮ ሰማይና ምድር ነው ። ይህንን ማስተካከል ደግሞ የቀጣይ የቤት ሥራችን ይሆናል ብለዋል።የህግ ማስከበሩ ጉዳይ ተጠናክሮ እየቀጠለ ነው ያለው ያሉት ዶክተር አረጋዊ ፣ ጁንታው ሁሉም በሚባል መልኩ ከአዲስ አበባ ሸሽተው እንደሄዱት ሁሉ መቀሌ ላይም ሴራ ሲጠነስሱ ከርመው በአሁኑ ወቅት እዛም ስላልሆነላቸው በመሸሸና የሚደበቁበትን ጥግ በመፈለግ ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል።የመከላከያ ኃይላችንም ከህዝቡ ጋር እየተባበረ እነሱን ይዞ ለፍርድ ለማቅረብ አደን ላይ ነው ። የእነሱ ቡድን አባል የሆነችው ሴትም እጇን ሰጥታለች፤ በቀጣይም ሁሉም እጅ ይሰጣሉ ፤ አንሰጥምም ቢሉ ከመሞት ሌላ አሁን ላይ ምንም አማራጭ እንደሌላቸው ጠቁመዋል።“ የጁንታው ቀንደኛ አባላት በቁጥር ትንሽ ቢሆኑም በርካታ የጥቅም ተጋሪዎች፣ አገልጋዮች፣ ተባባሪዎች እንዲሁም ቤተሰቦችና ታማኞች በትግራይ ክልል ብቻ ሳይሆን በመላ አገሪቱ አሉ፤ ይሁን እንጂ ህዝቡ ማን ምን እንደሆነ ጠንቅቆ ስለሚያውቅ የባሰበትን ለጸጥታ አስከባሪ አሳልፎ በመስጠት ሌላውን ደግሞ በራሱ መንገድ አርፎ እንዲቀመጥ በማድረግ የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል። እኛም እንደ ፓርቲ በተለይም ሌቦቹና ዘራፊዎቹ ህግ ፊት እንዲቀርቡ ለማድረግ ከፍተኛ የሆነ ትብብርን ለማድረግ ተዘጋጅ ተናል” ብለዋል።አዲስ ዘመን ህዳር 28/2013
https://www.press.et/Ama/?p=36856
448
0ሀገር አቀፍ ዜና
የጁንታው የጭካኔ ጥግ – በወታደሮችና በፖሊስ አባላቱ አንደበት
ሀገር አቀፍ ዜና
December 7, 2020
18
ኢያሱ መሰለአስር አለቃ ቤቴልሄም በዛ ትባላለች። የ11ኛ ክፍለ ጦር 2ኛ ብርጌድ 1ኛ ሻለቃ አባል ነች። የከሀዲው ህወሓት ጁንታ ታጣቂዎች በሰሜን እዝ መከላከያ ሰራዊት አባላት  ደርሶባታልም፤ የጁንታው ጭካኔ እንኳንስ በወገን ላይ ቀርቶ በሰው ልጅ ላይ ሊታሰብ የማይችል መሆኑን ትናገራለች።‹‹ሁኔታው ከመፈጸሙ በፊት በሰራዊቱ ውስጥ የጁንታው ተላላኪዎች የሆኑ የሻለቃው አባላት እየተደበቁ በየቀኑ ይሰበሰቡ ነበር። የዋርዲያ ተራቸውን ጠብቀው ስለማይሰሩም የተቀረው ወታደር ያለእረፍት የእነርሱንም ጭምር ሲሸፍን ቆይቷል። የተቀረው ሰራዊት ቀን ቀን አንበጣ እንዲያባርር ይደረጋል። ደምም ሰጥተናል። በብዙ ሌሎች ነገሮችም ማህበረሰቡን እንደግፋለን” ትላለች አስር አለቃ ቤቴልሄም።ጥቃቱ በተፈጸመበት እለትም ቀኑን በሙሉ አንበጣ ሲያባርሩ ውለው ጎናቸውን ለማሳረፍ ጋደም ባሉበት ቅፅበት ነው አብረዋቸው በኖሩ በሰራዊቱ ውስጥ በነበሩ ከሀዲ የጁንታው ተላላኪዎች ከጀርባ የተወጉት::አስር አለቃ ቤቴልሄም ትናገራለች፤ “በዕለቱ ከሌሊቱ አምስት ሰዓት ተኩል ከውጭ ወደ ውስጥ የጥይት ሩምታ ተከፈተብን። ከውስጥ ደግሞ እነዛ አስቀድመው ሲሰበሰቡና ሲያሴሩ የቆዩት የጁንታው እኩይ አላማ ፍፃሚ የሰራዊቱ አባላት የገዛ ጓደኞቻቸው የሆኑ የሌላ ብሄር ተወላጆችን እየመረጡ በተኙበት በጥይት መምታት ጀመሩ።ከተኛንበት እየተጣደፍን ወደ ውጭ ወጣን፤ ትጥቃችን ወዳለበት መጋዘን ሄድን። የመሳሪያ ግምጃ ቤቱ ግን ተቆልፏል። የመጋዘኑን ቁልፍ የያዘውን ወታደር አስቀድመው ገድለውታል” ትላለች አስር አለቃ ቤቴልሄም።በእለቱ ዋርድያ ላይ የነበሩ የሰራዊቱ አባላት በኮሎኔል ሀጎስ መገደላቸውን የምትናገረው አስር አለቃ ቤቴልሄም፤ “ባዶ እጃችንን ስለሆንን እራሳችንንለመከላከል አልቻልንም። ጥቂት ሰዎች ብቻ ነበሩ የሚከላከሉት። ብዙዎችን ገደሉ። እጅ የሰጡትንም ጭምር ገደሏቸው” ትላለች።የጁንታው ታጣቂዎች ግፍና ጭካኔ የትየለሌ መሆኑን የምተናገረው አስር አለቃዋ፤ “አንድ የአራተኛ ክፍለ ጦር አባል የነበረ ወታደር እጁን ከሰጠ በኋላ በታንክ ደፈጠጡት። መትረፍ የሚችሉ ቁስለኞችን ሳይቀር ገደሏቸው። ሬሳቸውን ሳይቀብሩ የራሳቸውን ሰዎች ሬሳ ብቻ አንስተው ሄዱ” ስትል ነው የጓዶቿ በከሀዲ የሰራዊቱ አባላትና በጁንታው ታጣቂዎች የተፈጸመባቸውን ግፍ የምትናገረው።ከዚህ ሁሉ ግፍና ጭካኔ በኋላ የተረፉትን እንድነ አስር አለቃ ቤቴልሄም ያሉ የሰራዊቱ አባላትን የጁንታው ታጣቂና ከሀዲ የሰራዊቱ አባላት በሲኖትራክ ጭነው አጉላ ወደተባለ ትምህርት ቤት ወስደው እንዳጎሯቸው ትናገራለች፤ “በህይወት የተረፉና ከሻምበል በላይ የነበሩ የኦሮሞና የአማራ ተወላጅ የሆኑ የጦር መኮንኖችን ለብቻቸው አስቀመጧቸው። ትኩረታቸው በነሱ ላይ ነበር። እስከ አሁንም የት እንዳደረሷቸው አላውቅም።ሴቶችን ለብቻችን በአንድ ክፍል ውስጥ አጎሩን። ሞባይላችንን፣ ልብሳችንንና ያለንን ዶክመንት፣ ገንዘባችንን ሁሉ ዘረፉን። ያለምግብና ውሃ ለሶስት ቀን ወንበር ላይ እየተኛን አሳለፍን። አንዳንድ የወታደር ሚስት የሆኑ ነዋሪዎች ምግብ ሊሰጡን ሲሞክሩ ይከለክሏቸው ነበር። በረሀብ የተነሳ በጣም ተዳከምን። በመጨረሻ ጥሬ እየቆነጠሩ ይሰጡን ጀመር”እፍኝ ቆሎ እየሰጡ አጉረው ለሁለት ሳምንት ያቆይዋቸውን የሰራዊት አባላት እጃቸውን ጠርንፈው አስረው ወደ መቀሌ እንዳመጧቸው ትናገራለች፤ “መቀሌ የእንስሳት ጤና ኮሌጅ ውስጥ አስቀመጡን። ስድብ፣ እርግጫና ማንጓጠጥ ይደርስብን ነበር።ሌላ አካባቢ የሴቶችን ጡት እንደቆረጡም ሰምተናል። በእኛም ላይ ተመሳሳይ ድርጊት ለመፈጸም መዘጋጀታቸውን እጃቸውን ለመከላከያ ሰራዊቱ የሰጡ የጁንታው ታጣቂዎች ተናግረዋል። ህዳር 21 እቅዳቸውን ለመፈጸም ሲዘጋጁ ህዳር 20 የመከላከያ ኮማንዶዎች ደርሰው ነጻ አውጥተውናል” ስትል በሰራዊቱና በፈጣሪ ታምር መትረፋቸውን ተናግራለች።ጁንታው ለእኩይ አላማው ያልተባብረውን ሁሉ ከማጥፋት የማይመለስ ጨካኝና ከሀዲ ነው ያለችው አስር አለቃ ቤቴልሄም፣ በትግራይ የኩያ ተወላጁን ወታደር ተጋድሎም ታስታውሳለች “የአራተኛ መካናይዝድ አባል የሆነ የኩያ አካባቢ ተወላጅ ከእኛ ወገን ቆሞ ያደረገውን ተጋድሎ ማንሳት ያስፈልጋል። ልጁ ታንከኛ ነው፤ ታንክ ውስጥ እንዳለ እጅህን ስጥ ይሉታል። እኔ የቆምኩት ለኢትዮጵያ ስለሆነ እጄን አልሰጥም ብሎ በታንክ መዋጋት ጀመረ። ታንክ ከታንክ ጋር ገጠሙና ተረባርበው ገደሉት”።ሌላዋ የአይን ምስክር ኮንስታብል አለምነሽ ገመዳ የሰባት ወር እመጫት ናት። የፌዴራል ፖሊስ አባል ስትሆን የጁንታው ታጣቂዎችና የሰራዊቱ ከሀዲ አባላት ለእሷና መሰል እመጫቶች እንኳን እንዳልራሩላቸው ትናገራለች።ኮንስታብል አለምነሽ ምድብ የጥበቃ ሥራዋ አክሱም አየር መንገድ ውስጥ ነው። ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት አካባቢ አየር መንገዱ ውስጥ በጥበቃ ሥራ ላይ ባሉ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ላይ የተፈጸመውን ክህደት ስታነሳ እንባዋን መቆጣጠር አትችልም።“እኔ የሰባት ወር እመጫት ስለነበርኩ መሳሪያዬን ለሌሎች ሰጥቼ ማረፊያ ቤት ውስጥ አራስ ልጄን ይዤ ተቀምጬ ነበር። ጋንታ አመራሩ የጁንታው ተላላኪ ነው። ላካስ ከታጣቂዎች ጋር ተመካክሮ ጨርሷል። በጫካው በኩል አድርገው ወደ ጊቢው ገቡና እጅ ስጡ አሉ። እርሱ ቶሎ ብሎ መሳሪያውን ሰጣቸው። ሌሎቹአንሰጥም ብለው አፈገፈጉ። ከዚያም ተኩስ ተጀመረ። አንድ ኃይል አመራር ከማማው ላይ ሆኖ ለመከላከል ሞከረ። መጨረሻም እጁን እንዲሰጥ አደረጉት። እጁን ከሰጠ በኋላ ግን በረንዳው ላይ እጁን በሰንሰለት አስረው በዱላ ጨፈጨፉት›› ትላለች ኮንስታብል አለምነሽ።ኮንስታብል አለምነሽ በከሀዲዎች የተፈጸመው ግፍ ዛሬም ድረስ ከአይኗ አልጠፋ ብሎ አይኖቿ በእንባ እንደተሞሉ ሳግ እየተናነቃት ነበር ሁኔታውን የነገረችን። “ከዚያ ወደ እኔ መጡ ቤቴን ዘግቼ እንደተቀመጥኩ የጥይት እሩምታ አወረዱብኝ፤ ውጪ አሉኝ ህጻን ልጅ ስለያዝኩ አልወጣም አልኳቸው። ጨካኝ ናቸው ለአራስ ልጄ እንኳን አልራሩም::አስገድደው ገቡና ቤቱን ፈተሹ ፤ አንድም ነገር ሳልይዝ ባዶ እጄን አስወጡኝና ልጄን እንዳቀፍኩኝ በሶምሶማ ሩጪ አሉኝ፤ ከእኔ ጋር ሌላም አንድ ልጅ የያዘች ሴት ነበረች። እርሷ ግን ጭንቅላቷ አካባቢ ተመታ ደሟን እያፈሰሰች ሩጪ ተባለች። ሁለታችንም ህጻን ልጅ ይዘናል፤ እሩጡ እያሉ አስሮጡን።ስላሴ ወደሚባል ቤተክርስቲን ጫካ ውስጥ ወሰዱንና የሞቱ የነሱን ታጣቂዎች ተሸከሙ አሉን። ልብሳችንን ጫማችንም አስወልቀው በባዶ እግራችን አስኬዱን፤ እንደዚ አድርገው ወደ ሽሬ አመጡን፤ እጅ የሰጡ አመራሮቻችንንም ገደሏቸው። በተለይ ኦሮሞና አማራን እየለዩ አስቀሯቸው። የደቡብ ተወላጆች ላይም አይናቸው ላይ በርበሬ እየጨመሩ ያሰቃይዋቸው ነበር። በረሀብም የሞቱ አሉ። የሞቱትን አስፋልት ላይ ሲጎትቷቸው ነበር፤ አንዳንዶቹን አፍነው የት እንደወሰዷቸው አናውቅም።ከባለቤቴ ጋር እስከ ሽሬ ድረስ አብረን ከመጣን በኋላ እርሱን እዛው አስቀሩት፤ አሁን በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ አላውቅም” ከዚህ በላይ ኮንስታብል አለምነሽ መናገር አልቻለችም፤ እንባዋንም መግታት ተሳናት።አዲስ ዘመን ህዳር 28/2013
https://www.press.et/Ama/?p=36859
728
0ሀገር አቀፍ ዜና
«ኢትዮጵያውያን ለመከላከያ ያሳዩት ድጋፍ በሀገር ሉዓላዊነት ላይ የማይደራደሩ መሆኑን ያረጋገጠ ነው» – አቶ ብናልፍ አንዷለም የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የፓርቲው ዋና ጽ/ቤት ኃላፊ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 7, 2020
19
አዲስ አበባ፡- የህወሓት ጁንታ በመከላከያ ሰራዊት ላይ የፈጸመውን ክህደት ተከትሎ ኢትዮጵያውያን ከጫፍ እስከ ጫፍ በነቂስ በመውጣት ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ያሳዩት ድጋፍ በሀገር ሉዓላዊነት ላይ የማይደራደሩ መሆኑን ያረጋገጠ መሆኑን የብልጽግና ሥራ አስፈጻሚ አስታወቀ፡፡የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከህዳር 25 እስከ 26/ 2013 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው በተወያየባቸው አጀንዳዎች እና ባስተላለፋቸው ውሳኔዎች ዙሪያ የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ብናልፍ አንዷለም ትናንት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፤ የህወሓት ጁንታ በሀገር መከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ ላይ ድንገተኛ ጥቃት በመሰንዘር የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት አደጋ ውስጥ የሚከት የክህደት ተግባር ፈጽሟል ፡፡የቡድኑን የክህደት ተግባር ተከትሎ መንግሥት ሀገር የማዳንና ህግ የማስከበር ዘመቻ ማካሄዱን ያመለከቱት አቶ ብናልፍ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ በመከላከያ ላይ የተፈጸመውን የክህደት ተግባር በነቂስ ወጥቶ ከማውገዝ ጀምሮ ለመከላከያ ሰራዊቱ የተለያዩ ድጋፎች በማድረግ ከጎኑ መቆሙን ያረጋገጠበት መንገድ እጅግ የሚያኮራ ነው ብለዋል፡፡ህዝቡ ከጫፍ እስከ ጫፍ ያሳየው መነቃነቅ የሀገር ሉዓላዊነትን ለማፍረስ ለሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ምንም አይነት ትዕግስት የሌለው መሆኑን ያረጋገጡበት መሆኑን የጠቆሙት አቶ ብናልፍ፤ ህዝቡ ያሳየው አኩሪ ድጋፍ ለመከላከያና ህግ ለማስከበር ለተንቀሳቀሱት ለሌሎች ኃይሎች ትልቅ ስንቅና ትጥቅ የሆነ እንደነበር የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መገምገሙን አብራርተዋል፡፡ከመከላከያ ጎን በመሆን የጥፋት ቡድኑን ጥቃት በመከላከልና መልሶ በማጥቃት የጥፋት ቡድኑ ውርደትና ሽንፈት እንዲከናነብ ላደረጉ የአማራ ክልል ልዩ ኃይልና ሚሊሻ ፣ ለአፋር ልዩ ኃይል ፤ እንዲሁም መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እና የትግራይ ህዝብ ከመከላከያ ጎን በመሆን ላሳየው ድጋፍ ሥራ አስፈጻሚው ያለውን አድናቆት ገልጸዋል፡፡የህወሓት ጁንታ በአገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የፈጸመውን ክህደት ተከትሎ የፌዴራል መንግሥት የወሰደው ህግ የማስከበር እርምጃና ኢትዮጵያውያን ከጫፍ ጫፍ በመነቃነቅ ያሳዩት ድጋፍ በሉዓላዊነታቸው ላይ ለሚመጣ ማንኛውም ጉዳይ መቼም እንደማይደራደሩ ያስመሰከሩበት እንደሆነም አመልክተዋል ፡፡ህግ የማስከበር ዘመቻው እና ህዝቡ ከጫፍ እስከ ጫፍ በመውጣት ያሳየው መነቃነቅ የሀገሪቷ ሉዓላዊነት እንዲጠበቅ፤ የአገር መከላከያ ሰራዊት አገር ከመፈራረስ እንዲድን፤ ኢትዮጵያዊነትም ጎልቶ እንዲወጣ ማድረግ ችሏል ያሉት አቶ ብናልፍ ፣ ይህ ህግ የማስከበር ዘመቻም ኢትዮጵያዊነት አሸንፎ የወጣበት ዘመቻ ነው ብለዋል፡፡እንደ አቶ ብናልፍ ማብራሪያ፤ የህግ ማስከበር ሥራውእየተጠናቀቀ ነው፡፡ የጥፋት ቡድኑን የሚያስተባብሩ በህግ የሚፈለጉ አካላትን ከጉድጓድ በማውጣት ለፍርድ እንዲቀርብ የፓርቲያቸው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡ ከዚህ ጎን ለጎንም በግጭቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀዬአቸው እንዲመለሱ እና የተቋረጡ አገልግሎቶች እንዲጀምሩ፣ የወደሙ መሰረተ ልማቶች እንዲገነቡ የሥራ አስፈጻሚው ኮሚቴው አቅጣጫ ማስቀመጡን አመልክተዋል፡፡በየአካባቢው የሚካሄዱ የልማት፣ የዴሞክራሲ እና የሰላም ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸውም ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው አቅጣጫ ማስቀመጡንም አቶ ብናልፍ ገልፀዋል።ሀገራዊ እና ዓለምአቀፋዊ ጉዳዮችን በተመለከተም ብሄረ መንግስት እና ሀገረ መንግስት በመገንባት ሂደት ውስጥ ፅንፍ የወጡ አስተሳሰቦች እንደሚስተዋሉ የተመ ለከተው ሥራ አስፈፃሚው፤ ይህንን ለማስተካከል ህዝቡ ፖለቲካዊ ንቃት እንዲኖረው መሰራት እንዳለበት መገምገሙንም አስታውቀዋል።ከዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች አንፃር በተለይም የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም ከማስጠበቅ አኳያ፣ ከአባይ ፖለቲካ ጋር በተያያዘ የህዳሴ ግድብ እንዳይጠናቀቅ እና የሚፈለገው ደረጃ ላይ እንዳይደርስ የሚከፈቱ ፕሮፖጋንዳዎች ላይ በዝርዝር ውይይት ተደርጎ ግልፅ አቅጣጫ መቀመጡንም ጠቁመዋል።ምርጫን በተመለከተም የ2013 ምርጫ ሰላማዊ፣ ነፃ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ በኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድም ሆነ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ተቀባይነት ያገኘ እንዲሆን አቅጣጫ መቀመጡን አመልክተዋል።የብልጽግና ፓርቲ የሚጠበቅበትን ሁሉ አሟልቶ በዚህ ሂደት ውስጥ ለማለፍ ዝግጅት ማድረጉንም አስታውቀዋል።የብልጽግና ፓርቲ ምርጫውን ለማሸነፍ ማኒፌስቶ አዘጋጅቶ ወደ ምርጫ ቅስቀሳ የሚገባ መሆኑንም በመግለጫው አብራርተዋል።አዲስ ዘመን ሕዳር 28/2013
https://www.press.et/Ama/?p=36858
447
0ሀገር አቀፍ ዜና
የወንጀለኛው ጁንታ የንግድ ድርጅቶች የአገሪቱን ኢኮኖሚ ክፉኛ መጉዳታቸው ተገለፀ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 7, 2020
91
ተገኝ ብሩአዲስ አበባ፡- ወንጀለኛው የህወሓት ጁንታ የንግድ ድርጅቶች በህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴ የአገሪቱን ኢኮኖሚ ክፉኛ መጉዳታቸውን ምጣኔ ሀብት ባለሙያው አቶ አዲሱ እጥፉ አስታወቁ። የሀገሪቱን ሀብት ከመበዝበር ወደ ውጭ ለማሸሽ መሳሪያ እንደነበሩም ጠቆሙ።አቶ አዲሱ እጥፉ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገ ለጹት፦ የህወሓት ጁንታው የንግድ ድርጅቶች በሀገ ሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ያሳደሩት አሉታዊ ተፅዕኖ እጅግ የከበደ ነው።ተቋማቱ የአገሪቱን ኢኮኖሚ በበላይነት በመቆጣጠርና በህገወጥ መንገድ በመዝረፍ የአገሪቱን ሀብት ወደውጭ ሲያሸሹ ነበር።የንግድ ተቋማት አሰራራቸው ብቻ ሳይሆን አጀማ መራቸውም ህገ ወጥ እንደነበሩ የገለፁት የምጣኔ ሀብት ባለሙያው፣ ተቋማቱ ላለፉት በርካታ ዓመታት በማናለብኝነት ሀገሪቱን ሲመዘብሩ መቆየታቸውና የአገሪቱን ኢኮኖሚ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደራቸውን አስታውቀዋል።ጁንታው የፖለቲካ የበላይነት ለመያዝ የኢኮኖሚ የበላይነት ማረጋገጥ አለብኝ ብሎ የሚያምን ድርጅት መሆኑን የተናገሩት ባለሙያው፣ በህገወጥ ተቋማቱ አማካኝነት ይህንን እምነቱን ተጨባጭ ለማድረግ የሄደበት መንገድ በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን አመልክተዋል።ተቋማቱ በተጠና መልክ የተሳሰሩና በሰንሰለት መልክ የተደራጁ ሁሉም ለአንድ አላማ የተቋቋሙ እንደሆኑ የሚናገሩት ባለሙያው፣ አንዱ ተቋም የአንደኛው ግብዓት አቅራቢ በመሆን ለሌላው በመሸጥና ኢኮኖሚውን በተለያየ መልኩ በመቆጣጠር የበላይነቱን ተቆጣጥረውት ቆይተዋል ብለዋል።የህወሓት ጁንታ በነበረው የፖለቲካ የበላይነት ተጠቅሞ የአገሪቱ የወጪና የገቢ ንግድ ሆን ተብሎ ከእነዚህ ድርጅቶች ጋር የተያያዙ እንዲሆኑ ማድረጉን ያመለከቱት ባለሙያው፣ ተቋማቱ ያለገደብ የባንክ ብድ ርና የውጭ ምንዛሪ ያገኙ እንደነበር ገልፀው” ይህ ደግሞ ከሌላ ህጋዊ ድርጅቶች በተለየ መልኩ ኢኮኖሚውን እንዲቆጣጠሩ እድል እንዲሰጣቸው አስታውቀዋል ።የድርጅቱ ባለስልጣን የሆኑት አቶ ስብሀት ነጋ በ2003 ዓ.ም ለአሜሪካ ድምፅ “የህወሓት ተቋም የሆነው ኤፈርት የአገሪቱ ቁጥር አንድ ሀብታም ድርጅት ነው” ማለታቸውን በማሳያነት ጠቅሰዋል።ተቋማቱ ከልማት ባንክና ከንግድ ባንኮች በብድር መልክ የወሰዷቸው ገንዘቦች እንደማይመልሱና የተበላሸ ብድር እየተባለ እንደሚመክን ያስረዱት አቶ አዲሱ፣ እነዚህ ተቋማት አትራፊ መሆናቸውና እጅግ ትልልቅ ገንዘቦች ማዘዋወራቸው እየታወቀ ተቋማቱ ኪሳራ ላይ ናቸው በሚል የተበደሩትን ገንዘብ ሳይመልሱ እንዲቀሩና የመንግሥት ገንዘብ እንዲመዘበር ሆን ተብሎ ሲሰራ መቆየቱን አስታውቀዋል።በህጉ መሰረት አንድ ተቋም መክሰሩ ታውቆ የተበ ደረው ብድር መመለስ እንደማይችል ሲረጋገጥ ብድሩ ተበላሸ እንደሚሰኝ ገልፀው ፣የህወሓት ጁንታው ተቋማት ግን አትራፊ መሆናቸው እየታወቀ የተበደሩትን ገንዘብ እንዳይመልሱ የተለያዩ ምክንያቶች ያቀርቡ እንደነበር ጠቁመዋል።ጤነኛ የንግድ ህግ ተከትለው ይሰሩ የነበሩ ተቋማት በቡድኑ ህገወጥ ድርጅቶች በደረሰባቸው ጫና ከገበያ እንደወጡና በአንፃሩ ደግሞ በቡድኑ የሚተዳደሩ ተቋ ማት በአገሪቱ ግዙፍ የገንዘብ ዝውውር የሚያደርጉና በህገወጥ መንገድ የከበሩ እንደነበሩ አስታውቀዋል። ተቋማቱ ከአገሪቱ በተለያየ መንገድ የዘረፉት ገንዘብ ወደውጭ በማሸሽ ሀገሪቱን የውጭ ምንዛሪ እጥረት እንዲገጥማትና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዋ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንዲፈጠር ምክንያት እንደነበሩ ገልጸዋል።ከአመሰራረታቸው ጀምሮ ህገወጥ በሆነ መልኩ የተቋቋሙት የህወሓት ጁንታው የንግድ ተቋማት በአገሪቱ ላይ የፈጠሩት ኢኮኖሚያዊ ጫና ከፍተኛ መሆኑንም ገልፀዋል። ማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት የንግድ ሥራ ውስጥ መሳተፍ የለበትም ያሉት አቶ አዲሱ ተቋማቱ በ1952 ዓ.ም የወጣውን አገራዊ ህግ በሚፃረር መልኩ የተቋቋሙና በህገወጥ መልኩ ሲሰሩ የቆዩ ናቸው ብለዋል።በመንግሥት ቁጥራቸው 34 የሚሆኑ የንግድ ቋማት ተለይተው የተገለፁ መሆኑንና ጉዳያቸው በህግ ሂደት ላይ ቢሆንም የድርጅቱ የንግድ ተቋማት ግን ቁጥራቸው ከዚያ እጅግ እንደሚበልጥና በመንግሥት በኩል በትክክል ተለይተው ከህገወጥ ተግባራቸው ሊገቱ እንደሚገባም አመልክተዋል ።ተቋማቱ ለመንግሥት ግብር በስርዓት የማይከፍሉና በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች መሬቶችን በመውሰድ እና መልሶ በመሸጥ ለህገወጥ ተግባራቸው መጠቀሚያ ያደርጉ እንደነበር ጠቁመዋል።ዓለምአቀፉ የፋይናንስ ሀቀኝነት ድርጅት በፈረ ንጆች በ2010 ይፋ ባደረገው ሪፖርት መሰረት የጁን ታው ድርጅቶች ከአገሪቱ ከ17 ቢሊዮብ ብር በላይ በማሸሽ በውጭ ሀገር በሚገኙ የተለያዩ ባንኮች ላይ አስቀምጠዋል። ይህ ቁጥር ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ መምጣቱንና እስካሁን ይፋ የተደረገ ሪፖርት ብቻ መሰረት በማድረግ ከአገሪቱ በተለያየ መንገድ የዘረፉት ከ36 ቢሊዮን ዶላር ወይም ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ በተለያዩ አገራት ባንኮች ላይ ማስቀመጣቸውን አስታውቀዋል።ተቋማቱ የአገሪቱ ገንዘብ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ባህላዊና ታሪካዊ ቅርሶችን በመሸጥና ወደውጭ በማሸሽ ታሪክ ይቅር የማይለው ወንጀል ሲፈጽሙ መቆየታቸውንም የገለጹት አቶ አዲሱ፣ ተቋማቱ ገለልተኛ በሆነ መልኩ ተጣርተው አገሪቱ ላይ ያደረሱትን ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖ በመመርመር ተጠያቂ ሊደረጉ እንደሚገባ አመልክተዋል።አዲስ ዘመን ህዳር 28/2013
https://www.press.et/Ama/?p=36864
524
0ሀገር አቀፍ ዜና
«ጁንታው ሕጋዊ የንግድ ውድድርን ማዛባት ብቻ ሳይሆን ተፎካካሪዎችን የማጥፋት አካሄድ ይከተል ነበር » – አቶ ውብሸት ሙላት የህግ ባለሙያ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 8, 2020
105
ወርቁ ማሩአዲስ አበባ ፦ ወንጀለኛው የህውሓት ጁንታ ሁሉንም የቢዝነስ ተቋማት በቁጥጥሩ ስር ለማድረግ ካለው ከፍተኛ ፍላጎት የተነሳ ማንኛውም የንግድ ውድድር እንዳይኖር ከማድረግ በዘለለ ተፎካካሪ ሊሆኑ የሚችሉ የግልና የመንግስት የንግድ ተቋማትን እስከማጥፋት መሄዱን የሕግ ምሑሩ አቶ ውብሸት ሙላት አስታወቁ ።አቶ ውብሸት በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደገለጹት፣ ይህ ቡድን ወደ ስልጣን ከመጣ ጊዜ ጀምሮ በፖለቲካውም ሆነ በኢኮኖሚው መስክ አግላይ ብቻ ሳይሆን ሌላውንና ከሱ ውጭ የሆነውን የሚያስወግድ እና አፋኝ ነበር ። በኢኮኖሚውም መስክ በኢትዮጵያ ትልቁ ኢንቨስተር ይህ ቡድን ነበር ፤ከፌደራል መንግሥት በላይ የኢኮኖሚ አቅም የፈጠረ ነው ።አንድ ቡድን በፖለቲካውም ሆነ በኢኮኖሚው የበላይ ከሆነ እና በዚያ ላይ ያለው አስተሳሰብ አግላይ ከሆነ አገርን አደጋ ላይ ይጥላል የሚሉት አቶ ውብሸት፤ አገር ማፍረስን ጨምሮ የፈለገውን እንዲያደርግ እድል ይሰጠዋል፤ በወንጀለኛው ጁንታ የሆነው ይኸው ነው ብለዋል ። ትልቅ ገንዘብ ለማግኘት ሲታሰብ አንዱ አባላቸው ይነገረውና እንዲዘጋጅ ይደረጋል። ዝግጅቱን ሲጨርስ እሱን የሚያበረታታ ሕግ እንዲወጣ ይደረጋል የሚሉት አቶ ውብሸት ፣ለምሳሌ ከውጭ ያለቀረጥ ተሽከርካሪ ማስገባትና የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት የሚሰራ ድርጅት ፈቃድ ለመስጠት አስበው እንደሆነ። ይህ ቀድሞ ባሰቡት መሰረት የነሱ ሰው እራሱን እንዲያዘጋጅ ይደረጋል ።ዝግጅቱን ከጨረሰ በኋላ የጊዜ ገደብ የተቀመጠለት መመሪያው እንዲወጣ ይደረጋል። በዚህ ጊዜ ውስጥ ያዘጋጁት ሰው ቀድሞ የሚፈለውን ነገር ከውጭ ያዛል በተቀመጠው ቀነ ገደብ ውስጥ ተጠቃሚ ያሆናል። ይህን መንገድ በተደጋጋሚ ሲሰሩበት የነበረ እንደሆነ ጠቁመዋል። በአንድ ወቅት የልማት ባንክ ገንዘብ ተበድረው ሲያልቅ ሁሉም ባንኮች ለልማት ባንክ 27 ከመቶ ብድር እንዲሰጥ እንደተደረገ አቶ ውብሸት ያስታውሳሉ። በዚህ ወቅት ልማት ባንክ ያበደራቸው በሙሉ የጁንታው ቡድን አባላት መሆናቸውንም ይናገራሉ። ቡድኑ በርካታ የጭካኔ መገለጫዎች አሉት ያሉት አቶ ውብሸት፤ ከነዚህም ውስጥ አንዱ በድርቅ ከተጎዱና በሞት አፋፍ ላይ ከነበሩ ሰዎች መንጋጋ ላይ ፈልቅቆ ምግብ እስከመውሰድ የደረሰ ወንጀሉ አንዱ ነው ብለዋል ። ይህም ቡድኑ ቅንጣት ታክል ሰብዓዊነት የሌለው ለመሆኑ ትልቁ መገለጫ እንደሆነም አመልክተዋል ። ለዚህም በ1977 ዓ.ም በተከሰተው ድርቅ ለሰብዓዊ እርዳታ የመጣውን ድጋፍ መዝረፉን ጠቁመዋል።ከዚህም አልፎ በሴፍቲኔትና በተለያዩ ምክንያቶች ለእርዳታ የሚሰጡትን ሁሉ ያለ ይሉኝታ እንደሚወስድም ተናግረዋል። እንደ አቶ ውብሸት ገለጻ፣ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ወደግል ሲዞሩም ከፍተኛ ደባ ተፈጽሟል። በደርግ ጊዜ የተወረሱ፣ ወይም ደርግ በራሱ የገነባቸውም ተመሳሳይ ሸፍጥ ነው የተፈጸመባቸው፤ ሰዎች ባዶኣቸውን ይመጡና ከዚያ ይህንን ለሚገዛ ሰው የባንክ ብድር ይመቻቻል፤ ከዚያ የጨረታ አሸናፊ ይሆናሉ። ከዚያ የሆነ ባንክ እዲከፍልላቸው ይደረጋል። ከሆነ አመት በኋላ የግላቸው ይሆናል። በዚህ መሰረት ከዜሮ የትልቅ ሆቴል እና ፋብሪካ ባለቤት፣ ከዜሮ ሚሊየነር የሆኑ በርካታ የጁንታው ቡድን አባላት አሉ ። የቀደሙ ፋብሪካዎችንም ዘርፈው በመውሰድ ለራሳቸው ድርጅት ማቋቋሚያ እስከማድረግ የዘለቁበትም ሂደት ነበር። ለአብነትም መስፍን ኢንጂነሪንግ የተመሰረተው ከፓዌ በተዘረፈ ሃብት ነው። ደርግ ፓዌ ላይ የገነባው ትልቅ ፋብሪካ ነበር። ይህ ቡድን ኢትዮጵያን መቆጣጠር ሲጀምር እንዳለ ነቃቅሎ ሁሉንም ወስዷል። ከዚያ በኋላ ደግሞ መስፍን ኢንጂነሪንግን ለማጠናከር እነማሩ ብረታ ብረት፣ አምቼ የመሳሰሉትንና አቅም የነበራቸውን ድርጅቶችን ማክሰሩን ጠቁመዋል ። በሌላም በኩል በከፍተኛ ሁኔታ የንግድ ሥርዓቱ ውስጥ ገብተው ውጤታማ የነበሩትን የስታር ቢዝነስ ግሩፕ እና ሌሎች በርካታ የመከኑ የንግድ ድርጅቶችን ማንሳት እንደሚቻል የጠቆሙት አቶ ውብሸት ፣ በፋይናንስ ሴክተሩ አቢሲኒያ ባንክን ጭምር በርካታ ተቋማት የነሱ አባላት አክሲዮን እንዲገዙ በማድረግ በነሱ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ማድረጋቸውን አመልክተዋል። በተቋሙ ውስጥ የነበሩ ሰዎችንም የተለያዩ ምክንያት እየፈለጉ ስምንት እና ዘጠኝ ጊዜ አስረዋቸዋል። አያት ሪል ስቴትንም ማንሳት ለዚህ ትክክለኛ ማሳያ እንደሆነም አስታውቀዋል ። አንዳንድ ድርጅቶቻቸው ሕገወጥ ስራ ላይም ተሰማርተው እንደነበር አቶ ውብሸት ጠቁመው፣ ለአብነትም ሱር ኮንስትራክሽን በአማራ ክልል ከሰራው መንገድ ይልቅ የሰራው ምሽግ ይበልጣል ብለዋል።  በቅማንትና በአማራ ክልል መካከል በተፈጠረው ግጭት በርካታ ድርጅቶች ነዳጅ የሚያመላልሱ መስለው መሳሪያ ሲያመላልሱ እንደቆዩና በየቦታው በነዚህ ድርጅቶች ውስጥ የተገኘው የጦር መሳሪያም የዚህ ማሳያ እንደሆነ ጠቁመዋል። የሽብር ድርጊትን ፋይናንስ የሚያደርጉት እነዚህ ድርጅቶች እንደነበሩ በርካታ ማሳያዎች እንዳሉ አስታውቀዋል። የወንጀለኛው ቡድን አባላት ህይወት እርሻ መካናይዜሽን በሚል ሁመራ አካባቢ እርሻም እንደነበራቸው የጠቆሙት አቶ ውብሸት፤ ይህንን ስንመለከት እነዚህ ሰዎች በእርሻ ስም አደንዛዥ እጽ ሲያለሙ እንደነበርም መገመት ይቻላል ብለዋል። በተለይ ሰሞኑን ወንጀለኛው ጁንታ ሲባረር የተያዘው በርካታ አደንዛዥ ዕፅ ከዚህ ሊሆን ስለሚችል ይህ በአግባቡ መፈተሽ እንዳለበትም አሳስበዋል። በአገራችን የተፈጠሩት በርካታ ግጭቶችን ስንመለከት የፋይናንስ አቅም ይፈልጋሉ ያሉት አቶ ውብሸት ፣ ይህ ገንዘብ ከየት ነው የሚገኘው ካልን ከነዚህ ድርጅቶች ለመሆኑ ግልፅ ነው ብለዋል ። የጁንታው ድርጅቶች በደምብ መታየት ፤ እስከዛሬ ለፈፀሙትም መጠየቅ አለባቸው ብለዋል ። አቶ ውብሸት እንደገለጹት፣ ከተወሰነ ዓመታት በፊት ፓናማ ፔፐርስ በሚል የወጣ አንድ ማስረጃ አንዳንድ የዚህ ቡድን ድርጅቶች በመሳሪያ ዝውውር ስራ ላይ መሰማራታቸውን መጠቆሙን ተናግረዋል። ይህ ደግሞ ቡድኑ ድርጅቶቹን ከሃገር አልፎ ጎረቤት ሃገራትን ለማበጣበጥ ሲጠቀምባቸው እንደነበረ የሚጠቁም እንደሆነ አስታውቀዋል። በአገራችንን የጦር ሕግጋት ያልወጣው ለዚህ ነበር የሚሉት አቶ ውብሸት፤ በኢትዮጵያ ውስጥ የጦር መሳርያ በገፍ ነበር የሚሸጠው፤ ይህንን ግን ማነው የሚሸጠው፤ እንዴት ነው ወደ ኢትዮጵያ የሚገባው የሚለው እስካሁን በቂ ምላሽ ያላገኘ ጥያቄ እንደሆነ ገልጸዋል ። ይህ ቡድን ከሃገሪቷ አልፎ ለቀጠናው ሰላምና መረጋጋትም ካንሰር እንደነበር ያስታወቁት አቶ ውብሸት፤ይህንን በአግባቡ በማጥናት ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ ቀንድንም ከዚህ ቡድን ማንፃት ያስፈልጋል ብለዋል ። አንድ ድርጅት ሕገወጥ ተግባር ውስጥ ተሰማርቶ ከተገኘ ይከሰሳል። እንደሁኔታውም ንብረቱ በመንግስት ሊወረስ ይችላል፤ ካልሆነም በገንዘብ ቅጣት ሊቀጣ ይችላል። እነዚህ ድርጅቶችም የፈፀሙት ወንጀል በጣም ከፍተኛ በመሆኑ ሊወረሱ ይገባል።አመራሩን በመቀየርና ዓላማውን በማስተካከል ወደጤናማ የንግድ ስርዓት ውስጥ እንዲገቡ ማድረግ እንደሚያስፈልግም አመልክተዋል። በቀጣይም ተመሳሳይ ችግሮች እንዳይከሰቱ እያንዳንዱን ሥራ ሕግን መሰረት አድርጎ መስራት እንደሚገባም አሳስበዋል። ፋይናሽያል ኢንተለጀንስ፣ ሽብርን ፋይናንስ የማድረግ እንቅስቃሴ መኖር አለመኖሩን መከታተል፤ እነዚህ አይነት የንግድ ድርጅቶች ሕግን ተከትለው በውድድር መንፈስ እየሰሩ መሆን አለመሆናቸውን መከታተል፤ ይህንንም ሊቆጣጠሩና ሊከታተሉ የሚችሉ ጠንካራ አቅም ያላቸው ተቋማትን መገንባት፣ እንደዚህ አይነት ሁኔታ ሲፈጠርም እግር በእግር እየተከታተሉ ወደ ሕግ ማምጣት እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል ። ይህ ሲሆን አጠቃላይ ሀገራዊ ሥርዓቱን ጤናማ እንደሚሆን አስታውቀዋል ።አዲስ ዘመን ህዳር 29/2012 ዓ.ም
https://www.press.et/Ama/?p=36925
810
0ሀገር አቀፍ ዜና
በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የመመስረትና መልሶ የማደራጀት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 7, 2020
19
ኢያሱ መሰለመቀሌ፡- በትግራይ ክልል ህግን የማስከበር ሶስተኛው ምእራፍ ከተጠናቀቀ በኋላ ጊዜያዊ አስተዳደር የመመስረትና መልሶ የማደራጀት ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑ ተገለጸ።የትግራይ ብሄራዊ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ እንደገለጹት ፣ ህግን የማስከበር እርምጃውን በጥንቃቄ በማከናወን ወደ ቀጣዩ ምእራፍ መሸጋገር ተችሏል። ጊዜያዊ አስተዳደር የመመስረትና መልሶ የማደራጀት ሥራ መጀመሩን በመግለጽም በሽሬ ፣ እና በአክሱም የተለያዩ ቀበሌዎችንና ወረዳ አስተዳደሮችን መልሶ የማደራጀት ሥራ መሰራቱን ገልጸዋል።ለጊዜያዊ አስተዳደሩ የተመረጡ ሥራ አስፈጻሚዎች ሥራ መጀመራቸውን ያስታወቁት ዶክተር ሙሉ ፣ በመቀሌ ከተማ ህዝቡ ወደ መደበኛው ሥራው እንዲመለስ፣ የመንግሥት ተቋማት ሥራቸውን እንዲያከናውኑና የንግድ ተቋማትም ሥራቸውን እንዲጀምሩ የማድረግ ሥራ እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል።ወጣቶች ተደራጅተው ከመከላከያ ጎን እንዲቆሙ የልዩ ኃይልና የሚሊሻ አባላት እጃቸውን በሰላማዊ መንገድ እንዲሰጡም እየተሰራ መሆኑን የገለጹ ትዶክተር ሙሉ፣የሀገር ሽማግሌዎችና የአካባቢው ነዋሪዎች የመንግሥትን እገዛ ሲጠባበቁ እንደነበር ጠቁመዋል።በከተሞች አልፎ አልፎ የሚታየውን ዘረፋ ለማስቆም ከጸጥታ ኃይሉ ጋር እየተሰራ ነው ፤ በጸጥታ ስጋት ምክንያት ከመኖሪያ አካባቢያቸው ሸሽተው የሄዱ ሰዎችን ወደ ነበሩበት የመመለስ እና የማረጋጋት ሥራ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳዩ እንደሆነ ገልጸዋል።መከላከያ ሰራዊት መቀሌንና ሌሎች ከተሞችን የተቆጣጠረ በመሆኑ ህብረተሰቡ ያለምንም ስጋት ወደሚኖርበት አካባቢ በመምጣት ሰላማዊ ኑሮውን እንዲኖር ምቹ ሁኔታዎች እየተፈጠሩ መሆኑን አመልክተዋል።የህግ ማስከበሩ ሥራ ለትግራይ ህዝብ ከፍተኛ ጥቅም ይዞ የሚመጣ እንደሆነ የገለጹት ዶክተር ሙሉ ፣ህዝቡ ከነበረበት ጫና ወጥቶ በነጻነት እንዲንቀሳቀስ ያስችለዋል ብለዋል።የክልሉን የካቢኔ አባላት የማዋቀር ሥራ እንደሚሰራና እንደ ባንክ ፣ቴሎኮም፣ መብራት የመሳሰሉት አገልግሎት ሰጪ ቋማትን ከፌዴራል መንግሥት ጋር በመተባበር የማስጀመሩ ሥራ ትኩረት ተሰጥጦታል ብለዋል።የሥራ እንቅስቃሴ ከመቋረጡ ጋር ተያይዞ የምግብ እጥረት ሊፈጠር ስለሚችል እርዳታዎችን የማስተባበር ሥራዎች እንደሚከናወኑ አስታውቀዋል።አዲስ ዘመን ህዳር 28/2013  ዓ.ም
https://www.press.et/Ama/?p=36880
226
0ሀገር አቀፍ ዜና
ባለ ከዘራው ኮሎኔል
ሀገር አቀፍ ዜና
December 7, 2020
531
ጌትነት ተስፋማርያምፊታቸው ላይ የአልበገርም ባይነት ስሜት ጎልቶ ይነበባል፤ እያነከሱም ቢሆን ከቦታ ቦታ ይንቀሳቀሳሉ። መገናኛ ራዲዮናቸውን እና የምርኩዝ ከዘራቸውን ይዘው የጁንታው ቡድን አመራር ያለበት ቆላ ተንቤን አቅራቢያ በምትገኝ ሰዋራማ ስፍራ ላይ ጦሩን እየመሩ ይገኛል።ኮሎኔል ሻምበል በየነ ይባላሉ። በቆሙበት የውጊያ ትዕዛዝ እየሰጡ ኮስታራ ፊታቸውን ወደእኛ ዘወር አደረጉ። ቆስለው አልታከምም በማለት በወኔ እየመሩ የሚገኙ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አመራር መሆናቸውን ሰማንና ታሪካቸውን እንዲያካፍሉን ጠየቅናቸው።ድንገተኛ ፈገግታ እያሳዩ ቀድሞም የጁንታው አባላት ውጊያ ሰራዊቱ ላይ ሊከፍቱ እንደሆነ ጥርጣሬ ነበረኝ በማለት በተረጋጋ ስሜት ትውስታቸውን ማጋራት ጀመሩ። እኔ የ31ኛ ክፍለጦር ምክትል የኦፕሬሽን አዛዥ ነበርኩ ዋና አዛዡ ከጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ቀደም ብሎ የተወሰኑ አባላትን ሽሬ ድረስ ወስዶ ሲሰበስብ የሆነ ነገር ሊፈጥር እንደሚችል አስበው እንደነበር።ማታውኑ ችግር ሊኖር እንደሚችል በማመን በግሌ ዝግጅት አደረግኩ። ስዘጋጅ በባንክ አካውንቴ የነበረውን ጥቂት ገንዘብ በቤተሰብ አዞርኩ። ከዚያም ጥቃት ለማድረስ ከበባ ሲፈጽሙብኝ ተከብቤያለሁ በሚል ለበላይ አካላት ሪፖርት አደረኩ ።በመከላከያ ላይ ጥቃት ሲፈጸምም የክፍለጦሩ አዛዡ ከድቶ የጁንታውን ቡድን ተቀላቀለ። በዚህ ጊዜ የክፍለጦር ኮሚቴ ወይም ከበታች አዛዦች አባላት ጋር በመሆን ግብግብ ፈጸምን። እኔም ከፊቴ ያለውን በጥይት መትቼ ጣልኩ። እኔ ጋር የተጀመረች የመከላከል ተኩስ እስከታችኛው የሻለቃ አመራር ድረስ እየተደማመጠ የመከላከል እርምጃውን ወሰደ።በኋላም የካምፑን ከበባ አጠናቅቄ ስወጣ ደግሞ የልዩ ኃይል ከውጭ ጠበቀኝ የሚሉት ኮሎኔል፤ እነሱንም ጥሼ በመውጣት ከስምንተኛ ሜካናይዝድ ጦር ጋር ተቀላቀልኩ ሲሉ የነበረውን ሁኔታ ያስታውሱታል።በወቅቱ እግራቸው ላይ በጥይት መመታታቸው እምብዛም ቁብ አልሰጡትም። በዚያ ሁኔታ ላይ እያሉ ወደኤርትራ በማፈግፈግ በዚያ ከሚገኘው እና በጁንታው ታጣቂ ጥቃት ደርሶበት ከሚገኘው ጦራቸው ጋር ተገናኙ። ጦሩን አደራጅተው በመመለስ ሽራሮ ፣ሽሬ፣ አዲ አደራይ፣ አዲነብሪ እና በርካታ ቦታዎች በማስለቀቅ የህግ ማስከበር እርምጃቸውን በብቃት መወጣትም ቻሉ።ይህ ሁሉ ሲሆን ግን ከታፋቸው የሚፈስ ደም እንደ ነበር በቅርበት የሚያውቋቸው ወታደሮች ይናገራሉ። ቁስሉን በየሶስት ቀኑ በጦር ሜዳ አካባቢ እየታከምኩ አንዷ ጥይት ወጣች የሚሉት ኮሎኔል ሻምበል፤ ምርኩዝ ይዘው ግዳጃቸውን መወጣታቸውን ነግረውናል። ዋና አዛዡ ግን የጁንታውን ቡድን በመቀላቀል ለጁንታው አመራር ሽፋን ለመስጠት ጥረት እያደረገ መሆኑን አስረድተዋል።አሁን ላይ ቆላ ተንቤን ላይ ወንጀለኛ ለማስመለጥ እና ወንጀለኛ ለመያዝ ዋናው እና ምክትል አዛዡ ፊት ለፊት ተፋጠዋል። ምክትል አዛዥ ዋናውን ከነጀሌዎቹ እያባረረ እርምጃ እየወሰደበት ይገኛል። ከሚመሩት ጦር ጋር በርካታ ሀገር የከዱ ጄኔራሎችን እያባረሩ ቆላ ተምቤን ላይ ያደረሱት ኮሎኔል ሻምበል፤ እዚህ በመድረሴ ትልቅ ደስታ ይሰማኛል ሲሉ በኩራት ይናገራሉ።ቆላ ተምቤን ላይ የመሸገውን የከሃዲው ቡድን አመራር አባላት ለህግ ሲቀርቡ በተሻለ ህክምና በጥይት የተመታውን እግራቸውን ሊታከሙት እንደሚችሉ እንደተወርዋሪ ኮኮብ መሳይ ብልጭታ ባለው ፈገግታቸው ታጅበው በለሆሳስ ነገረውናል። ቦታው ላይ ቆስለውም ቢሆን ጦሩን እየመሩ መገኘታቸው ለሰራዊቱም ብርታት መሆኑን አልሸሸጉንም።በእጃቸው ከዘራቸውን ጨብጠው የሚንቀሳቀሱት የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ፤ በጉዳት እያሉም ቢሆን በህግ ማስከበር እርምጃ የጁንታውን አመራሮችን ለመያዝ ፀሐይ ውርጭ ሳይሉ በመታገል ላይ ናቸው። ይህም ኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆችን በየጊዜው አታጣም የሚባለው ብሂል እውነት መሆኑን ያረጋገጠ ነው። አዲስ ዘመን ህዳር 28/2013  ዓ.ም
https://www.press.et/Ama/?p=36881
404
0ሀገር አቀፍ ዜና
የእግር ኳስ ውጤታማ የአጨዋወት መንገድ
ስፖርት
September 15, 2019
104
አሁን አሁን እግር ኳስን ከመዝናኛነት በዘለለ የማወቅ እና የብስለት መመዘኛ አድርገን እየቆጠርን የመጣንበት ዘመን ሆኗል። አንድ ወዳጃችን የእግር ኳስ ጨዋታን የሚወድ ከሆነ እና እኛ በሱ ተቃራኒ ከሆንን ለትችት ሁላ እስከመጋለጥ እንደርሳለን። እርሱም አብሮን ቁጭ ብሎ እግር ኳስን እየተመለከተ «እኔ የምልህ! አየህው ይሄ እኮ የአሰልጣኙ ችግር ነው። «እንትናን» እዚህ ቦታ ላይ ማሰለፍ አልነበረበትም?። በዚያ ላይ ደግሞ አጠቃላይ የሚከተለው ስልት በዚህ መንገድ መሆን አልነበረበትም?» በማለት ምላሽ ከእኛ ሲጠብቅ፤ እንደገባን በማስመሰል እራሳችንን ልናነቃንቅ እንችላለን። በእርግጥ ለራሳችን ስሜት የማይሰጠን ከሆነ ማንም በፍላጎታችን ገብቶ ሊያስገድደንም ሆነ ሊመዝነን አይችልም። ከዚህም በዘለለ ግን ጨዋታውን እየወደድነው በሜዳ ውስጥ እየሆነ ያለው ላይገባን ይችላል። በዚህ ጊዜ እውቀታችንን እንዴት እንደምናሰፋ ልናስብ እንችል ይሆናል። ታዲያ መፍትሄው ምን ይሆን? የዝግጅት ክፍላችን ለዛሬ ከጊዜ ወደ ጊዜ ተወዳጅነትን እያተረፈ የመጣውን የእግር ኳስ ስፖርት በእውቀት መመልከት ከሚያስችሉን መንገዶች ውስጥ «አሰላለፍ» በመምረጥ መሠረታዊ የእግር ኳስ አጨዋወት ፍልስፍናን ይዞላችሁ ቀርቧል። ይህ ጨዋታ በአፍሪካ በተለይ በአገራችን ኢትዮጵያ በበርካታ ሰዎች ተወዳጅነት ያተረፈ ቢሆንም ስፖርቱ ግን በሚፈለገው ደረጃ ሊያድግ አልቻለም። ለስፖርቱ ማደግ እንቅፋት ናቸው ተብሎ ከሚገመቱ ምክንያቶች መካከል ደግሞ የአጨዋወት ፍልስፍናውን በሳይንሳዊ መንገድ በአግባቡ አለመተግበር ሲሆን፤ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ እና እየረቀቀ ከመጣው ከዚህ ፍልስፍና ጋር በቶሎ አለመዋሀድ ደግሞ ለመጓተቱ ሰፊውን ድርሻ እንደሚወስድ በባለሙያዎች ይነገራል። ተመልካቹ ይህን እንደ ምክንያት በማድረግ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ጫፍ የደረሰውን የሌሎች አገራት እግር ኳስ በመውደድ ዓይኖቹ ወደ ውጭ እንዲያማትሩ ሆነዋል። የዛሬ ርእሰ ጉዳያችን ዋና ማጠንጠኛ ባይሆንም በአጭሩ ጠቅሰን ለማለፍ ያክል፤ ከላይ ላነሳነው ችግር መፍትሄ ሊሆን የሚችለው ዘመኑ የደረሰበትን የእግር ኳስ ደረጃ ከአገራችን እና ከአህጉራችን ነባራዊ ሁኔታ ማጣጣም ነው። የአገራችንን እግር ኳስ የሚመሩ በርካታ አሰልጣኞች እግር ኳሱን አንድ ደረጃ ወደ ፊት ሊወስዱት አልቻሉም። ከሚተቹበት ዋንኛ ምክንያቶች ደግሞ መሠረታዊውን የአጨዋወት ሂደት ከራሳቸው እና ከአገራቸው ተጫዋቾች አንፃር ስለማይቃኙት እና የግላቸው የሆነ ፍልስፍናም ስለሌላቸው ጭምር መሆኑ ይነሳል። እንደ በጎ ጅምር ከሚጠቀሱ የአገራችን አሰልጣኞች መካከል የራሱን የእግር ኳስ አጨዋወት ፍልስፍና እና የአገሪቷን ተጫዋቾች ተክለሰውነት ታሳቢ ያደረገ ሂደት በመከተል፤ እግር ኳስን በጥሩ ሁኔታ እንዲጫወቱ ያስቻለው በኢትዮጵያ ቡና አሰልጣኝነት ለዓመታት ሲሰራ የነበረው ካሳዬ አራጌ ነበር። ሆኖም ግን ይህ እንቅስቃሴው በስፖርቱ ላይ ዘለቄታዊ ለውጥ ሊያመጣ አልቻለም። ወደ ዋናው ጉዳያችን ስንመለስ ተመልካቹ እግር ኳስን ከመዝናኛነት ባለፈ በደንብ ተረድቶ እንደ 12ተኛ ተጫዋች ተሳታፊ እንዲሆን አሰልጣኞች እና ተጫዋቾች በሜዳ ላይ በምን ዓይነት መልኩ ለመጫወት እና አሸናፊ ለመሆን እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ ሊረዳ ይገባል። ያ ማለት ግን እግር ኳስን ለመመልከት በስፖርቱ ኤክስፐርት መሆን ግዴታ ነው የሚል ድምዳሜ ለማንሳት እንዳልሆነ ልብ ሊባል ይገባል። እስቲ ዛሬ ጨዋታውን በቀላሉ ለመረዳት ከሚያስችሉ መንገዶች መካከል ከላይ ለመዳሰስ ወደመረጥነው የ«አሰላለፍ ቅርፅ» እንሻገር። ቦታን መሠረት አድርጎ መጫወት መቼ ተጀመረ? ወቅቱ 1872 ዓ.ም ነበር። በጊዜው በእግር ኳስ ታሪክ የመጀመሪያው ኢንተርናሽናል ጨዋታ በሁለት አገራት መካከል ተደረገ። ጨዋታውን ያደረጉት እንግሊዝ እና ስኮትላንድ ነበሩ። በዚያን ጊዜ ነበር «አሰላለፍ» ወይም ቦታን መሠረት አድርጎ ቡድንን ማዋቀር እንደ ሕግ ሆኖ የተጀመረው። ተጫዋቾች በአሰኛቸው ቦታ እና መንገድ ወደ ተጋጣሚያቸው ግብ በመድረስ እና የግብ ክልላቸው እንዳይደፈር በመከላከል ይጫወቱ ነበር። የመጀመሪያው የእግር ኳስ ማህበር ዋና ጸሐፊ ቻርልስ አልኮክ በጽሑፉ እንዳሰፈረው «በወቅቱ ሰባት አጥቂዎች የባላጋራ ክልል ላይ ጎልን ያነፈንፉ ነበር። ሦስቱ ደግሞ ግብ እንዳይቆጠርባቸው በተቃራኒው ይጠብቁ ነበር። በእርግጥም የመጀመሪያው መስመር ላይ የሚኖረው በረኛው ብቻ ነው» በማለት ለመጀመሪያ ጊዜ የእግር ኳስ ሕግ እና ፍልስፍናን ተከትሎ ጨዋታዎችን ማድረግ እንደተጀመረ፤ እንግሊዝም ባላጋራዋን ስትገጥም 1-2-7 አሰላለፍ ይዛ እንደቀረበች፤ ስኮትላንድ በአንፃሩ 2-2-6 አሰላለፍን እንደመረጠች ይናገራል። በወቅቱ የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ምንም ግብ ሳይቆጠርበት ነበር የተጠናቀቀው። ከሁለቱ አገራት ጨዋታ በኋላ አሰላለፍን መሠረት አድርጎ መጫወት አዋጪ እንደሆነ የእግር ኳስ ባለሙያዎች መገንዘብ ጀመሩ። በሌላ በኩል የእንግሊዙ ካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ እና ኖቲንግሀም ፎረስት በጊዜው የ2-3-5 አሰላለፍን በእግር ኳሱ ላይ ለማስረፅ ጥረት እያደረጉ ነበር። ከዚህም ሌላ ቀስ በቀስ በባላጋራ ክልል ላይ ግብ ለማግባት የሚራኮቱ አጥቂዎችን የመቀነሱ ተግባር ፋሽን ሆነ። እ.አ.አ በ1960 በዩክሬኑ የዳይናሞ ኬቭ የእግር ኳስ ክለብ ተደናቂ ታሪክ ያለው አሰልጣኝ «ቪክቶር ማስሎቭ» እግር ኳስን እንደ «አውሮፕላን» መስሎ በማቅረብ አዲስ የጨዋታ ፍልስፍናን አስተዋወቀ። ባላጋራን ለመርታት አጥቂዎችን መቀነስ፣ የተከላካይ ክፍሉን እና የመሀል ክፍሉን ማጠናከር ተገቢ መሆኑን ገለፀ። በዚህም 5 የነበሩት አጥቂዎች ወደ 4 ከዚያም ወደ3 እያለ መቀነስ ተለመደ። ከዚያም አልፎ በእግር ኳስ «ዝግመተ ለውጥ» የፊት መስመር ተጫዋችን እንደዋና የማሸነፊያ ስልት አድርጎ መቁጠር ያረጀና ያፈጀ እንደሆነ ይታሰብ ጀመር። ሀሰተኛ አጥቂ ማለትም ከመሀል እየተነሱ ግብ የሚያስቆጥሩ ተጫዋቾች በጊዜው ተፈጠሩ። «ዘ ፈርስት ግሬት ሴንተር ፎረዋርድ» እየተባለ በሀሰተኛ የፊት መስመር ተጫዋችነት የሚጠራው ለኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ እና ለኮረንቲያስ የእግር ኳስ ቡድኖች ለበርካታ ዓመታት የተሰለፈው ጂ ኦ ስሚዝ አንዱ ነበር። ኳስን እርስ በእርስ እየተሻሙ ግብ ለማስቆጠር ከመሞከር በዘለለ በእውቀት ላይ የተመሰረተ ጨዋታ እንዲሆን በርካታ የስፖርቱ ቤተሰቦች አስተዋጽዖ አበርክተዋል። ከጊዜ ወደ ጊዜ ስፖርቱ ተወዳጅነትን እንዲያተርፍ ካደረጉት ነገሮች መካከልም፤ ኳስን ተቆጣጥሮ ማራኪ እንቅስቃሴ እና ቅብብል ማድረግ በመቻሉ ነበር። በሌላ መልኩ እግር ኳስ እንዲያድግ እና አዳዲስ የሜዳ ላይ እንቅስቃሴዎች እንዲታዩ ያደረገው የአሰላለፍ ፍልስፍናው በየጊዜው እየተሻሻለ በመምጣቱም ጭምር ነው። «ፎርሜሽን» ተጫዋቾች እራሳቸውን በሜዳ ውስጥ አቀናጅተው የሚጫወቱበት መንገድ ነው። አሰልጣኙ ሜዳ ላይ ተጫዋቾቹን ከማስገባቱ በፊት የሚከተለውን አሰላለፍ የመምረጥ ግዴታ ይኖርበታል። ይህ ካልሆነ ግን በባላጋራው ብልጫ እንደሚወሰድበት ምንም ጥርጥር አይኖርም። አንድ ዓይነት የአሰላለፍ ስልት በሜዳ ውስጥ ይዞ መግባት የተለመደ ቢሆንም በጨዋታው ሂደት ላይ ለውጥ የማይመጣ ሲሆን እንዲሁም በባላጋራ ብልጫ መውሰዱ ከታመነበት በድጋሚ አሰልጣኙ አሰላለፉን ሊቀይር ይችላል። እስቲ ከዚህ ቀጥሎ በእግር ኳስ ጨዋታ ላይ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያገኙ እና በጊዜ ሂደት ለስፖርቱ ማራኪነት አስተዋጽዖ ያበረከቱ መሠረታዊ የ«ፎርሜሽን» ዓይነቶችን እንመልከት። አራት-አራት-ሁለት ይህ ፎርሜሽን እ.አ.አ በ1990ዎቹ ብሎም በ2000 መጀመሪያ ላይ በበርካታ ብሔራዊ ቡድኖች እና ክለቦች ተቀባይነትን ያገኘ የአሰላለፍ ፍልስፍና ነበር። አሰልጣኞች ቡድናቸውን በ4-4-2 አሰላለፍ በማቀናጀት በተጋጣሚያቸው ላይ ብልጫ ለመውሰድ ይሞክሩ ነበር። አሁን ላይም አብዛኞቹ የአሰላለፍ ታክቲኮች ይህንን መሠረት አድርገው የተዋቀሩ ናቸው። በዚህ የእግር ኳስ ፍልስፍና ላይ የመሀል ተጫዋቾቹ ከፍተኛ ሚና ይኖራቸዋል። ማለትም የአጥቂውንና የተከላካዩን ክፍል የመርዳት ኃላፊነት በነሱ ላይ የተጣለ ነው። ከአራቱ የመሀል ክፍል ተጫዋቾች ውስጥ አንደኛው «Attacking midfielder» የግዴታ ወደ ፊት በመሳብ የአጥቂውን ክፍል በተለየ መልኩ ሊረዳ ይገባል። ይህን ሚና የሚወስደው ተጫዋች የመሀል ክፍሉን ሚዛን ከመጠበቅ ባሻገር ባገኘው አጋጣሚ ግብ ለማስቆጠር መጣር ይኖርበታል ማለት ነው። በአጥቂ መስመር ላይ የሚገኙት ሁለቱ ተጫዋቾችም አስፈላጊ በሆነ ሰዓት የተከላካይ ክፍሉን ለማገዝ ወደ ኋላ ተስበው ይጫወታሉ። ይህም በባላጋራቸው ብልጫ እንዳይወሰድባቸው እና በፍጥነት ኳሱን እንዲቆጣጠሩ ያስችላል። በዚህ የአሰላለፍ ፍልስፍና በስፋት በመመራት ከሚታወቁ አሰልጣኞች መካከል ጣሊያናዊው «ፋቢዮ ካፔሎ» ይጠቀሳሉ። አራት-አራት-አንድ-አንድ ይህኛው አሰላለፍ መጀመሪያ ላይ ካነሳነው ፎርሜሽን ብዙም ልዩነት የለውም። ነገር ግን አንድ አጥቂ ሲኖር ከእርሱ በስተጀርባ የሚቆም አንድ ተጨማሪ አጥቂ ወይም «ተደራቢ» አጥቂን ያካትታል። ይህ ተደራቢ አጥቂ ሚናው ግብ ማስቆጠር ቢሆንም የእግር ኳስ ክህሎቱ ላቅ ያለ ሊሆን ይገባል። ከመሀል ክፍሉ ጋር ተናቦ ኳስ መቀበል እና ወደ ግብ ክልል ማምራት ይኖርበታል∷ በተጨማሪም ከሁለተኛው አጥቂ ጋር የሚያደርገው የኳስ ልውውጥ ጥሩ የማጥቃት እንቅስቃሴን ይፈጥራል። አራት-ሦስት-ሦስት ይህ የአሰላለፍ ስልት ከቀድሞው የ4-2-4 የቡድን አወቃቀር የተወሰደ ነው። በዚህ ፎርሜሽን ሕግ መሠረት ሦስቱ የመሀል ተጫዋቾች በአብዛኛው ጊዜ ተጠጋግተው በመጫወት የመከላከሉንም ሆነ የማጥቃቱን ሚና ያቀጣጥላሉ። ሦስቱ የፊት መስመር ተጫዋቾች ደግሞ በተለያዩ አቅጣጫዎች የማጥቃቱን እንቅስቃሴውን በማስፋት ግብ ለማስቆጠር ሙከራ ያደርጋሉ። ከዋናው ግብ የማስቆጠር ኃላፊነታቸው ባሻገር የባላጋራን የመስመር ተከላካዮች ኳስ የመንጠቅ ተጨማሪ ግዴታ ይጣልባቸዋል። እ.አ.አ በ2005/6 ፍራንክ ራይካርድ ባርሴሎናን በሚያሰለጥንበት ወቅት የኢኒዬስታ ሚና በቡድኑ ውስጥ ከፍ እንዲል የእርሱ 4-3-3 አሰላለፈን መምረጥ ከፍ ያለ አስተዋጽኦ ተጫዋቹ በነፃነት በመሀል ሜዳው ላይ ኳስን የማቀጣጠል ሚናውን ከፍ እንዲል ፎርሜሽኑ ትልቅ እገዛ አድርጎለታል። አራት-አምስት-አንድ በአሁኑ ሰዓት ትልቅ ተቀባይነትን እያገኘ የመጣ አሰላለፍ ነው። በዋናነት መከላከልን መሠረት ያደረገ የአጨዋወት ስልት ቢመስልም የባላጋራ የግብ ክልል ለመፈተሽ ጥሩ አጋጣሚንም ይፈጥራል። ሦስቱ የመሀል ክፍል ተከላካዮች እና ከፊት መስመር በተመላላሽነት የኳስ ቁጥጥር ሚዛኑን ለመጠበቅ የሚያግዙት አጥቂዎች፤ የተቃራኒ ቡድን ላይ ብልጫ ለመውሰድ የሚያስችል እንቅስቃሴ ያደርጋሉ። የመሀል ክፍሉ በጣም የተጠጋጋ እና ኳስን መሠረት አድርጎ የሚጫወት በመሆኑ ተቃራኒ ቡድን በቀላሉ ኳስን እንዳያገኝ እና እንዲራብ የሚያደርግ የአጨዋወት መንገድ ነው። ሞሪኖ ሞናኮን እና ቼልሲን በሚያሰለጥንበት ወቅት በዚህ አሰላለፍ ስኬታማ መሆን ቢችልም ወደ ስፔኑ ሪያል ማድሪድ ሲያቀና ግን በዚህ ሂደት ውጤትን ማምጣት ተስኖት ነበር። በዚህ የተነሳም ሌላ ፎርሜሽን ለመቀየር ግዴታ ውስጥ ነበር። አራት-አንድ-ሁለት-አንድ-ሁለት ይህን አሰላለፍ «ዳይመንድ ፎርሜሽን» በማለት የእግር ኳስ ጠበብቶች ይጠሩታል። የአጨዋወት ባህሪው የሚያተኩረውም የአማካኝ አጥቂዎች ላይ ይሆናል። ነገር ግን ኳሱን የማጨናገፍ፣ ቦታ የመሸፈን እና ጠንካራ ተክለሰውነትን በመያዝ የሚታወቀው የመሀል ተከላካይን ያቀፈ ነው። የአማካኝ አጥቂ ተጫዋቾቹ ግብ ለማስቆጠር ሙከራ ሲያደርጉ ብዙም ቦታቸውን በመልቀቅ አይደለም። ያገኙትን ክፍተት ተጠቅመው የማጥቃት እንቅስቃሴ ውስጥ በመሳተፍ በፍጥነት ወደ ቦታቸው ላይ ይመላለሳሉ። በግራና በቀኝ የሚሆኑን የመሀል ተጫዋቾችም ኳስ የማጨናገፍ ሚና ያለውን ተጫዋች የማገዝ ኃላፊነት ይኖራቸዋል። የዳይመንድ ፎርሜሽንን በመጠቀም አስገራሚ ውጤት ማግኘት እንደሚቻል ካስመሰከሩ አሰልጣኞች መካከል ካርሎ አንችሎቲ አንዱ ናቸው። በእርሳቸው ሲሰለጥን የነበረው ኤሲ ሚላን ስኬታማ እንቅስቃሴን ማድረግ ችሎ ነበር። አራት-ስድስት-ዜሮ እግር ኳስ ከጊዜ ወደ ጊዜ በአዳዲስ የአጨዋወት ፍልስፍናዎችን እየዳበረ ይመጣል። ለዓመታት በአንድ መንገድ የሚጓዝ አይደለም። በስፖርቱ ፍቅር አቅላቸውን የሳቱ እና በህልማቸውም ጭምር ከኳስ ጋር የሚያድሩ ባለሙያዎች እግር ኳስን ለማሻሻል ይጠበባሉ። በአንዱ ዘመን የመጣው ፋሽን ትንሽ ሲቆይ ያልፍበታል። ደግሞ አዲስ ይፈጠራል። በእግር ኳስ ዝግመተ ለውጥ በአሁን ሰዓት የባለሙያውን እና የኳስ አፍቃሪውን ቀልብ የሳበው «ፎርሜሽን» 4-6-0 ነው። በክፍለ ዘመኑ ከምርጥ አሰልጣኝ ጎራ የሚመደቡት ቪሴንት ዴልቦስኬ የዚህ አጨዋወት አፍቃሪ ነበሩ። እ.አ.አ በ2012 የስፔን ብሔራዊ ቡድንን በመምራት በአውሮፓ ዋንጫ በዚህ አሰላለፍ ጣፋጭ ድል አጣጥመውበታል። የአጨዋወት ስልቱ ከመሀል በመነሳት አራቱ የፊት መስመር ተጫዋቾች የማጥቃት እንቅስቃሴ ያደርጋሉ። የተቃራኒ ቡድን ተከላካዮች ቀለበት ውስጥ ሊያስገቡት የሚችሉት አጥቂ ስለማይኖር በቀላሉ ባላጋራ ላይ ድልን ለማስመዝገብ ምቹ አጋጣሚን ይፈጥራል። በማጥቃት እንቀስቃሴ ከሁሉም አቅጣጫ «out-and-out striker» ይደረጋል። ከዚህም ባለፈ በማንኛውም ደቂቃ፣በሁሉም መንገድ እንዲሁም ከየትኛውም አቅጣጫ የባላጋራን የተከላካይ ክፍል መፈተን የፍልስፍናው መሠረታዊ ሕግ ነው። ይህ ፎርሜሽን ፍጥነትን፣ የግል ክህሎትን እንዲሁም ጠንካራ ተክለ ሰውነትን ስለሚጠይቅ፤ ሙሉ 90 ደቂቃ ኳስን ሳይደክሙ መጫወት ስለሚፈልግ፤ በብዛት አሰላለፉን የሚከተሉ ቡድኖች የሉም። የተወሰኑ የኳስ ክለቦች እና የብሔራዊ ቡድኖች አጨዋወቱን ቢከተሉትም ቀጣይነት ባለው መልኩ የቡድናቸው ቋሚ አሰላለፍ አያደርጉትም። ይህ ፎርሜሽን ፍጥነትን፣ የግል ክህሎትን እንዲሁም ጠንካራ ተክለ ሰውነትን ስለሚጠይቅ፤ ሙሉ 90 ደቂቃ ኳስን ሳይደክሙ መጫወት ስለሚፈልግ፤ በብዛት አሰላለፉን የሚከተሉ ቡድኖች የሉም። የተወሰኑ የኳስ ክለቦች እና የብሔራዊ ቡድኖች አጨዋወቱን ቢከተሉትም ቀጣይነት ባለው መልኩ የቡድናቸው ቋሚ አሰላለፍ አያደርጉትም። ያም ሆነ ይህ በርካታ የእግር ኳስ ባለሙያዎች እንደሚገምቱት 4-6-0 የወደፊቱ ተመራጭ ፎርሜሽን ይሆናል። በአሁኑ ወቅት አጥቂዎችን በቀላሉ ለመያዝ «ኢዚ ቱ ማርክ» ተከላካዮች አይፈተኑም። በመሆኑም ይህን አሰላለፍ በመከተል አጥቂዎችን ከእይታ ውጪ ማድረግ እና በአንድ ተጫዋች ላይ አለመወሰን ለጊዜው አማራጭ የማይገኝለት ውጤታማ የአጨዋወት መንገድ ይሆናል።አዲስ ዘመን መስከረም 4/2012ዳግም ከበደ
https://www.press.et/Ama/?p=18068
1,508
2ስፖርት
ወደ ሕዝብ ባለመተኮስ የተገለጸ ቃል ኪዳንና ጽናት!
ሀገር አቀፍ ዜና
December 8, 2020
211
ኢያሱ መሰለ ሻለቃ ዘላለም ብዙነህ በሰሜን አየር ምድብ የአየር መከላከል እቅድና ስልጠና ቡድን መሪ ነው።ዋናው የስራ ድርሻው ጠላት የአየር ጥቃት እንዳያደርስ መከላከል እና የምድር ኃይሉ እንዳይጎዳ ድጋፍ መስጠት ነው።ሰሜን አየር ምድብ ከመጣም ከ17 ዓመት በላይ ሆኖታል።ሻለቃ ቡዙነህ እንደሚያስረዳው ዶክተር አብይ ወደ ስልጣን ከመጡ ከ2010 ዓ.ም በኋላ ለውጡ ያልጣማቸው ኃይሎች አዳዲስ ባህሪ አምጥተዋል።ከፌደራል መንግስት የሚተላለፉ መመሪያዎችን ያለመቀበልና ሰራዊቱን ከፋፍሎ የመመልከት ሁኔታዎችም ይስተዋሉ ነበር። የእነሱን ሀሳብ የማይቀበለውን የአየር ኃይል አባል የብልጽግና ፓርቲ  ደጋፊ ነው በማለት ያጥላላሉ።በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያሉም ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ከምሽቱ አምስት ሰዓት ላይ ምንም ባላሰቡት ሁኔታ መቀሌ በሚገኘው የሰሜን አየር ምድብ መኖሪያ ቤት የተኩስ ሩምታ ተከፈተ፤ ምንድ ነው ብለው ሲጠይቁም የሴራው ተባባሪ የሆኑና ጉዳዩን የሚያውቁ አባላት ልምምድ ነው እያሉ ያዘናጓቸው እንደነበር ያስታውሳል።‹‹ሌሊቱን ሙሉ ሳንተኛ አድረን ልክ አስራ ሁለት ሰዓት ሲደርስ ልዩ ኃይሎች ወደ ግቢው መግባት ጀመሩ።በተለይም የአማራና የኦሮሞ ተወላጅ አባላትን ከቤታችን እያወጡ እያመናጨቁና እየገረፉ ወሰዱን።ወደ ማጎሪያ ቤት ከወሰዱን በኋላ በብሔር ከፋፈሉን።ደቡብን ለብቻ ፤ አማራና ኦሮሞን በአንድ ላይ አድርገው አጎሩን።ሚሳኤል የመተኮስ ልምድና እውቀቱ እንዳለኝ  ስለሚያውቁ እኔን ለብቻዬ ወሰዱኝና እንድተኩስላቸውና ከእነርሱ ወገን እንድቆም ጠየቁኝ።እኔ ከምንም በላይ ቃል የገባሁት የሀገሬን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ሕዝቤን ለመጠበቅ ነው፤ ከሀገር በላይ ክብር የለም ፤ ስለዚህ መልሼ ሀገሬን አልወጋም አልኳቸውና 20 ዓመት የታገልኩበትን የትግል ዓላማ በአንድ ቀን እንደማላፈርሰው ነገርኳቸው።ሙያዊ እገዛ አድርግልን ፤ ተኩስልን፤ አሉኝ።እምቢ ስላቸውም በዚህና በዚያ መሳሪያ ደቅነውብኝ አስፈራሩኝ፤ ሰደቡኝም።ከፈለጋችሁ ግደሉኝ አልኳቸው።ከመሃላቸው አንዱ በጥፊ መታኝና ውጣ አለኝ።ከወጣሁ በኋላ ለሚሊሺያዎች አስረከቡኝ።ሚሊሺያዎቹ እግሬን በዱላ ሰባብረው ጣሉኝ፡፡እረ ባካችሁ ተውኝ እያልኩ ብማጸናቸውም ትንሽ እንኳን ሊራሩልኝ አልፈለጉም።ቀጥቅጠው ጥለውኝ ሲሔዱ በዳዴ እየተሳብኩ ቤቴ ገባሁ።ቤት ከገባሁ በኋላም እንደገና መጥተው እንድተኩስላቸው ጠየቁኝ እግሬ መጎዳቱን አሳየኋቸውና እንደማልችል፤ ቃል ኪዳኔንም እንደማላፈርስ ደግሜ ነገርኳቸው።ኮሌኔል በላይ የሚባል ሰው ፈቃደኛ ከሆንኩና ከተኮስኩ እንደሚያሳክመኝ ነገረኝ።እኔ ግን ከፈለግህ ግደለኝ አልኩት።ሚሳኤል ማስወንጨፊያው ሶስት ቦታ ላይ ማለትም መሶቦ፣ አዲግራትና አክሱም ነው ያለው።የሚሳኤሉ ዋና ታርጌት ተዋጊ አውሮፕላኖችን መጣል ነው፤ እስከ 25 ኪሎሜትር ይጓዛል።ወደ ባህር ዳር ይተኩሱት የነበረው ግን ሚሳኤል ሳይሆን ሮኬት ነው።ሮኬቱን ተሽከርካሪ ላይ አጥምደው ቦታ እየቀያየሩ ነበር የሚተኩሱት።ለምሳሌ መሶቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ አካባቢም እየመጡ ይተኩሱ ነበር።አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ወደ ሌላ ቦታ ወስደው ሲተኩሱት ይሰማል።ጦርነቱ እየተባባሰ ሲመጣ ወደ ግንባር ሄዱ።ከዚያም መከላከያ ሰራዊት ከተማውን ሲቆጣጠረው መረጋጋት ጀመርኩ።ምንም አይነት ህክምና ሳላገኝ ማታ ማታ እየታሸሁ አሁን ትንሽ ተሽሎኛል።አድራጎታቸው በጣም ያማል ፤እስከአሁንም አዕምሮዬ ትክክል አይደለም።እህል በማጨድ፣ አንበጣ በማባረር ፣ ኮሮናን በመከላከልና በተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ድጋፍ ሲያደርግ የነበረን ሰራዊት ክብሩ ተገፎ ውርደት ደርሶበታል።በተፈጸመብን የጭካኔ ተግባር ምክንያት እስከ አሁን ራሴን እያመመኝ ነው ፤ ጤነኛ አይደለሁም።መከላከያ ሰራዊት ለሀገሩ የገባው ቃል ኪዳን አለ።ሕዝብና መንግስት የሰጠውን ኃላፊነት የመፈጸም አደራ አለበት።ትግል ውስጥ ስገባ ልንሞትም ነው።እኛ እንደሻማ ቀልጠን ሌሎች ብርሃን እንዲወጣላቸው ቃል ገብተናል።በዚህ ቃል ኪዳናችን እንጸናለን፡፡አዲስ ዘመን ህዳር 29/2012 ዓ.ም
https://www.press.et/Ama/?p=36926
396
0ሀገር አቀፍ ዜና
የሳምንቱ እግር ኳስ ወሬዎች
ስፖርት
September 1, 2019
23
 ባሳለፍነው ሳምንት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ዙሪያ የሚያጠነጥኑ በርካታ መረጃዎች ወጥተዋል። በተለይ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዓመት ፋሲል ከተማን በመያዝ ስኬታማ ጊዜያትን ያሳለፈው አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በይፋ ሰበታ ከነማን ለማሰልጠን የመስማማቱ ዜና ጆሮ ገብ ሆኖ በርካታ የስፖርት ቤተሰብን ሲያነጋግር መቆየቱ ይታወሳል። ዛሬ የአሰልጣኝ የዝውውር ዘገባን ጨምሮ ትኩረት የሳቡ የስፖርት ዘገባዎችን የምናስነብብ ሲሆን ዘገባዎቹን ለማዘጋጀት የተለያዩ ዋቢዎችንና በዋናነት የሶከር ኢትዮጵያ ድረ ገፅ ተጠቅመናል። ባህር ዳር ከተማ በኢትዮጵያ እግር ኳስ የዝውውር መስኮት ላይ በንቃት እየተሳተፈ የሚገኘው ባህር ዳር ከተማ ሰለሞን ወዴሳን ስድስተኛ ፈራሚ ማድረጉ ተሰምቷል። ከሀዋሳ ከተማ ወጣት ቡድን ከተገኘ በኋላ በወጣት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ጊዜ ተጠርቶ መጫወት የቻለው እና በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በመድን የአማካይ ተከላካይ ሥፍራ ጥሩ ግልጋሎት ሲሰጥ የነበረው ሰለሞን ወዴሳ የጣና ሞገዶቹን በሁለት ዓመት ውል ተቀላቅሏል። ከተከላካይ አማካይነት በተጨማሪ በተከላካይ ስፍራ የሚጫወተው ይህ ተጫዋች ከሃያ ቀናት በፊት በወላይታ ድቻ ለመጫወት የተስማማ ቢሆንም ዝውውሩን ሳያጠናቅቅ በመቅረት ወደ ባህር ዳር ማምራቱ ታውቋል። አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ሰበታ ከተማ ውበቱ አባተን አዲሱ አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙን አስታውቋል። የውድድር ዓመቱን በፋሲል ከነማ ያሳለፉትና ከቡድኑ ጋርም የኢትዮጵያ ዋንጫን ያነሱት አሰልጣኝ ውበቱ ከፋሲል ጋር ከተለያዩ በኋላ ከበርካታ ክለቦች ጋር ስማቸው ሲያያዝ ቢቆይም ወደ ሰበታ ለማምራት መስማማታቸው የሚታወስ ነው። በዚህም መሠረት ነሐሴ 25 በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰበታ ከተማ አሰልጣኝ ሆነው መሾማቸው በይፋ ተነግሯል። ዓለምገና በሚገኘው ዓለም ሆቴል ከጠዋቱ 3:00 የቡድኑ አመራሮች በተገኙበት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ከሰበታ ከተማ ጋር ስለሚኖራቸው ቆይታ እና ስምምነት ዝርዝር እንዲሁም ቀጣይ እቅድ ዙሪያ ማብራሪያ ተሰጥቷል። የሴካፋ ከ15 ዓመት በታች ላለፉት ሳምንታት በኤርትራ አዘጋጅነት ሲካሄድ የቆየው የሴካፋ ከ15 ዓመት በታች ውድድር ሲጠናቀቅ ዩጋንዳ የዋንጫ አሸናፊ ሆናለች። ሩዋንዳ ደግሞ ሦስተኛ ደረጃ ይዛለች። ከትናንት በስቲያ 7 ሰዓት 30 የተካሄደው የብሩንዲ እና ሩዋንዳ የደረጃ ጨዋታ ሲሆን መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ አንድ ለአንድ ተጠናቆ ወደ መለያ ምት በማምራት ሩዋንዳ 4ለ2 በማሸነፍ ሦስተኛ ደረጃ ይዛ ማጠናቀቅ ችላለች። ቀጥሎ የተካሄደውና 10 ሰዓት የተጀመረው የፍፃሜው ጨዋታ በዩጋንዳ እና ኬንያ መካከል ተከናውኖ ዩጋንዳ ከፍፁም ብልጫ ጋር 4ለ0 በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀው ዋንጫ ተሸላሚ ሆናለች። የዩጋንዳ ጎሎች የተቆጠሩት በኦግዋ ዴቪስ፣ ትራቪስ ሙታይባ እና ኬዩኔ አባስ ነው። የኤርትራው ተመስገን ተስፋይ ግምት አግኝቶ ከነበረው የዩጋንዳው ትራቪስ ሙታይባ በመብለጥ የውድድሩ ኮከብ ተጫዋች ሆኖ ተሸልሟል። የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በፕሪሚየር ሊጉ ለሚጫወት ማንኛውም ተጫዋች ከነሐሴ 3 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ የደመወዙ ጣሪያ ታክስን ጨምሮ ብር ሃምሳ ሺ ብር እንዲሆን 15 የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ቢሾፍቱ ላይ መወሰናቸው ይታወቃል። ፌዴሬሽኑ ውሳኔውን እንዲያስፈጽም ክለቦች በወሰኑት መሠረት ፌዴሬሽኑ በቁጥር 2/ኢ.እ.ፌ አ-4/1069 ነሐሴ 08/12/2011 ዓ.ም በጻፈው የሰርኩላር ደብዳቤ ክለቦች በዚህ ውሳኔ መሠረት የተጫዋቾችን ውል እንዲፈጽሙ መግለጹ ይታወቃል። ሆኖም ግን የተወሰነውን ውሳኔ በአግባቡ ከመፈፀም ይልቅ የተወሰኑ ክለቦች በተጠቀሰው የገንዘብ መጠን ውል እየተዋዋሉ እና እያፀደቁ በተቃራኒው ግብር የማይከፈልበት ገንዘብ በሕገ ወጥ መንገድ ለተጫዋቾች ክፍያ እየፈጸሙ እንደሆነ ከተለያዩ ጠቋሚ የመረጃ ምንጮች ጥቆማዎች ደርሰውናል። በመሆኑም ፌዴሬሽኑ ይህንን ሕገ ወጥ ድርጊት ከተጫዋቾች ጋር በመመሳጠር በታክስ ስወራና ሕገ ወጥ በሆነ ተግባር ላይ የተሰማራችሁ ካላችሁ ከድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ እያሳሰብን፤ መንግሥት በራሱ የሚወስደው እርምጃ እንደተጠበቀ ሆኖ ፌዴሬሽኑም በዚህ ሕገ ወጥ ተግባር ላይ ተሰማርቶ በተገኘ ክለብ፤ የክለብ አመራርና ተጫዋቾች ላይ ከስፖርቱ ዓለም እስከማገድ የሚደርስ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን ለክለቦች በላከው ደብዳቤ አሳውቋል። (መረጃው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ነው )አዲስ ዘመን ነሐሴ 26/ 2011
https://www.press.et/Ama/?p=17119
480
2ስፖርት
ለእግር ኳሱ ውበት የደረቡ ሕጎች
ስፖርት
September 1, 2019
52
 በ1983 በእንግሊዟ ለንደን ከተማ ውስጥ የመጀመሪያው አጨዋወት ሕግ እስኪረቀቅ የእግር ኳስ ወዳጆች ባሻቸው መንገድ ፍልሚያቸውን ያደርጉ ነበር። ታሪክ በመዝገቡ ያሰፈራት ይህቺ ቀን ግን ለእግር ኳስ አጨዋወት የሥነ ሥርዓት ፈር አበጀች። ሁሉም ነገር ሥርዓት ሲኖረው ውበት ይጨምራል። ተወዳጅነቱም የጎላ ይሆናል። ጨዋታም ይሁን የሰው ልጆች እያንዳንዱ የማህበራዊ ሕይወት እንቅስቃሴ፤ ሕግ ሲበጅለት ነው ይበልጥ እያደገ እና አዳዲስ የሕይወት መስመሮችን እያበጀ የሚጓዘው። በዚህ ደረጃ ስፖርቱን እንዲወደድ ካደረጉት ነገሮች መካከል ሕጉ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱ ነው። አይደለም «የእግር ኳስ» ጨዋታ በዓለማችን ላይ አስከፊ የሆነው የሰው ልጅ ጦርነት እንኳን የራሱ ሕግ አለው። ጦረኛው ተማራኪውን በሥነ ሥርዓቱ ይይዛል። ማሸነፍም በወጉ ሲሆን አይደል የሚያምረው? የዛሬው የእሁድ የስፖርት አምዳችን የእግር ኳስ ሕግ እና ሥርዓት ላይ ያተኩራል። ወደ ኋላ መለስ ብለን ጨዋታው አሁን ላይ የደረሰበትን ደረጃ፣ የአጨዋወት ሥርዓት እንዲሁም የረቀቁ ስልቶችን እና ማራኪ የአጨዋወት መንገዶችን እንዳስሳለን። እ.አ.አ በ1840 የካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ ምሩቆች መሠረታዊ እና ወጥ የሆነ የእግር ኳስ አጨዋወት ሕጎችን ለማውጣት ሙከራ ያደረጉበት ጊዜ ነበር። ሆኖም ግን የጨዋታውን ሥርዓት በሚፈልጉት መንገድ አላሻሻሉትም ነበር። በወቅቱ ኳስን በእጅ ማንኛውም ተጫዋች እንዲይዝ ይፈቀድለት ነበር። ይህ ደግሞ ውበቱን ቅጥ እንዲያጣ ያደርገው ነበር። ተወዳጁን የእግር ኳስ ጨዋታ ይበልጥ ማራኪ እንዲሆን በጊዜው በእንግሊዝ ውስጥ ያሉ ባለሙያዎች እና የስፖርቱ ወዳጆች የራሳቸውን ድርሻ አበርክተዋል። ከነዚህ ሰዎች መካከል ደግሞ ኢቢኔዘር ኮቢ ሞርሊ አንዱ ነበር። በለንዶን ከተማ በሚገኘው «ፍሪሜሲን ታቨርን» (ይህ ቦታ በርካታ ተቋማት እና በተለያየ ሙያ ላይ የተሰማሩ ሰዎች በመሰባሰብ የሚወያዩበት፤ ሕግና ደንብ የሚያረቁበት ስፍራ ነው) 12 እግር ኳስን የሚጫወቱ ቡድኖች ተሰባስበው ሕጎችን ለማውጣት እየተወያዩ ነበር። ዋናው አጀንዳቸው የነበረው ደግሞ ጨዋታው አሁን ካለበት ደረጃ እንዴት ከፍ ማድረግ እንደሚቻል ነበር። ይህ ውይይታቸው በጨዋታው ላይ 14 መሠረታዊ ሕጎችን በማርቀቅ ተቋጨ። ሆኖም ግን ውይይታቸው አልጋ ባልጋ ሆኖ አልተጠናቀቀም ነበር። በደቡብ ምሥራቅ ለንደን በምትገኘው «ብላክ ሂዝ» የምትባልን አነስተኛ ከተማ ወክሎ የመጣው የእግር ኳስ ቡድን ከወጡት ሕጎች መካከል በጥቂቶቹ ሳይስማማ ቀረ። በተለይ በጨዋታ ወቅት «ከእግር በታች የተቃራኒ ቡድን ተጫዋች መጥለፍ» እንደ ጥፋት ይቆጠራል ተብሎ የወጣውን ሕግ እንደማይቀበል አስታውቆ ውይይቱን ረግጦ ወጣ (ይህ ክለብ እግር ኳሱን ትቶ የራግቢ ህብረት በዚያው ወቅት ከሌሎች አጋሮቹ ጋር መስርቷል)። ሌሎቹ 11 ክለቦች በፕላኔታችን ላይ በቀዳሚነት ተወዳጅነትን ያተረፈውን፤ በተመልካች እና ተጫዋቾች ቁጥር ብዛት ቀዳሚ የሆነውን የእግር ኳስ ጨዋታ ሕግ ለመጀመሪያ ጊዜ ማርቀቅ ቻሉ። «ኦፍሳይት» ከጨዋታ ውጪ አሁን ላይ በእግር ኳስ ውስጥ ከሚታወቁ መሠረታዊ ሕጎች መካከል ተፋላሚዎችን ከጨዋታ ውጪ በማድረግ ለተቃራኒ ቡድን የቅጣት ምት የሚያሰጠው የ«ኦፍሳይት» ሕግ ነው። ይህ ሕግ ከላይ እንዳነሳነው በ1863 ከወጡት የአጨዋወት መሠረታዊ መርሆች መካከል አንዱ ነበር። በወቅቱ እግር ኳስን ለመጫወት ወደ ሜዳ የሚገቡት የሁለቱም ባላጋራ ቡድን ቢያንስ ስምንት የሚደርሱ አጥቂዎች ይኖራቸው ነበር። ይህ ደግሞ በተቃራኒ ቡድን ሜዳ ውስጥ (ሁለቱንም ያካትታል) የሚጣልን ኳስ በመሻማት ግብ ለማስቆጠር ማራኪ ያልሆነ ሽኩቻ እንዲያደርጉ ያስገድድ ነበር። በዚህ የኦፍሳይት ሕግን ማውጣት አስፈለገ። ከጨዋታ ውጪ ወይም «ኦፍሳይት» የምንለው አጨዋወት ኳስ ወደ ተቃራኒ ቡድን የግብ ክልል አሊያም ሜዳ ውስጥ፤ ለቡድን አጋር ግብ እንዲያስቆጥር ሲመታ፤ ተጫዋቹ ኳሷ ከመሬት ከመነሳቷ በፊት እና ከባላጋራው ቀድሞ፤ ሜዳው ውስጥ የሚገኝ ከሆነ በጨዋታው ተቆጣጣሪ «ዳኛ» እንቅስቃሴው እንዲቆም ይገደዳል። ለተቃራኒ ቡድንም የመልስ ምት ይሰጣል። ታዲያ ይህ ሕግ መውጣቱ እና ተጫዋቾች በተቃራኒ ቡድንም ሜዳ ውስጥ በፈለጉት መንገድ እንዳይንቀሳቀሱ መገደባቸው፤ አዲስ የሆነ ማራኪ የኳስ ቅብብል እንዲኖር እና ፍሰት ያለው ውብ አጨዋወት እንዲፈጠር ዕድሉን ከፈተ። እግር ኳስም ሜዳ ላይ ገብቶ ሁሉም እንደፈለገ የማይጫወተው ሆነ።ሕጎቹ ከረቀቁበት ዓመት ጀምሮ የእግር ኳስ ጨዋታ ይበልጥ በብዙኃን ዘንድ ተወዳጅነትን እያተረፈ መጣ። የእግር ኳስ ማህበራትም በአገራቶች መመስረት ጀመሩ። ቀጣዩ ለውጥ የነበረው የእንግሊዙ ክለብ «ሼፊልድ» ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ማህበር እንዲመሰረት የጠነሰሰው ሀሳብ ነበር። ይህ ሀሳብም ኢንግላንድ፣ አየርላንድ፣ ስኮትላንድ እንዲሁም ዌልስን አስማማ። ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ማህበር ተመሰረተ። ይህ ደግሞ 1886 የእግር ኳስ ሕግን «Laws of the Game» ላይ ለመወያየት በጋራ እንዲገናኙ እና ስፖርቱን የሚያሻሽሉ እርምጃዎች እንዲወስዱ አስቻላቸው። መሠረታዊ ለውጦች መሠረታዊ ለውጦች በመጡበት በዚያን ወቅት የእግር ኳስ ሕጎች እየተፀነሱ መወለድ ጀመሩ። ለውጡ እና አዳዲስ ፋሽኖቹ ደግሞ አንዲት ሴት ልጅ ፊቷ ላይ ሜካፕ ተጠቅማ በውበት ላይ ውበት እንደምትደርበው ዓይነት ነበር። በጨዋታው ቋንቋ «ጎል ኪክ» ወይም የመልስ ምት የምንለው ሕግ እ.አ.አ በ1969 ተዋወቀ። ይህን ድርጊት ወይም ኳሷን ለቡድን አጋሮቹ የሚያቀብለው ተጫዋች፤ የግቡን ግርግዳ የሚጠብቀው በረኛ ነው። በመልስ ምት በግብ ክልሉ ውስጥ ኳስ ተመትቶ ከወጣ የመልስ ምት ይሰጣል። 1872 ደግሞ ሌላ ተጫማሪ የአጨዋወት ሕግ ወጣ። በአንደኛው ቡድን ሜዳ ውስጥ ኳስ በራሱ በተጫዋቹ ተመትታ ወደ ውጪ የምትወጣ ከሆነ፤ ለተቃራኒ ቡድን አሁን ላይ ኮርና ወይም «ኮርና ኪክ» የምንለው ዕድል እንዲሰጥ ተወሰነ። በ1878 ደግሞ ሁለቱን ቡድኖች ሀይ የሚል እና ሕግን የሚያስከብረው «ዳኛ» ከርቀት ሊሰማ የሚችል እና ጨዋታው እንዲቆም አሊያም እንዲቀጥል የሚያዝ «ፊሽካ» እንዲይዝ ተደረገ። እስከ 1891 ባለው የእግር ኳስ ታሪክ የፍፁም ቅጣት ምት አሊያም «ፔናሊቲ» አልነበረም። ምክንያቱ ደግሞ ትንሽ አስገራሚ ቢጤ ነበር። አንድ እግር ኳስ ተጫዋች ሆን ብሎ በተቃራኒ ቡድን ተጫዋች ላይ ጥፋት አይሰራም የሚል እሳቤ ነበር። ሆኖም እግር ኳስ ተወዳጅነቱ እየበረታ፤ አሸናፊነት የሚያሰጠው ክብር እና ዝና እየናረ በመጣ ቁጥር በስፖርቱ የበላይነትን ለመውሰድ የሚደረገው ፍጥጫ የተጋጣሚ ቡድን ተጫዋችን ፈጥፍጦ ሜዳ ላይ እስከመዘረር ደረሰ። ጉዳዩ አሳሳቢ እየሆነ ሲመጣም ሕግ አርቃቂዎቹ በዚህ ዓመት በተለዋጭ ስሙ «the kick of death» ወይም ፍፁም ቅጣት ምትን አስተዋወቁ። ይህ ሕግ አንድ ተጫዋች ጎል ለማግባት በግብ ክልል ውስጥ ሙከራ ሲያደርግ በተከላካይ አሊያም በበረኛ ከተጠለፈ ቅጣቱ ይሰጠዋል። በረኛው እና ቅጣት መቺው ለብቻ የሚፋጠጡበት በመሆኑ ጎሉን ለመሳት የሚከብድ አጋጣሚ ነው። ረዳት ዳኞች እና የሕጎች መጠንከር በእግር ኳስ ጨዋታ ሁለቱን ባላጋራዎች ለመዳኘት አንድ ሰው አስፈላጊ ነበር። ይህም ከ1891 በፊት ተግባራዊ ተደርጎ ነበር። ሆኖም ግን ሌላ ተጨማሪ ዳኞ አስፈላጊ ሆነ። የመሀል ዳኛው በማይደርስባቸው አካባቢዎች የሚሰሩ ጥፋቶችን ለማስቆም እና ትክክለኛ ውሳኔዎችን ለማሳለፍ በግራ እና በቀኝ መስመር በሚገኘው የሜዳው ቦታ ላይ በተለምዶ «አራጋቢ» የምንላቸው ሁለት ዳኞች ተዋወቁ። አሁን ላይ እነዚህ ዳኞች «አሲስታንት ሬፈሪ» ወይም ረዳት ዳኛ በመባል ይታወቃሉ። ይህ መሆኑ እና ከላይ ያነሳናቸው ሕጎች በ«ሎው ኦፍ ዘጌም» መካተታቸው አሁን ላይ ያለውን አዲስ የእግር ኳስ ዘመን አስተዋወቀ። ቡድኖች ጨዋታ ሲጀምሩ፣ ግብ ከተቆጠረ በኋላ እንዲሁም ከእረፍት መልስ ኳሱን የሚያስጀምሩት መሀል ላይ ነበር። ሕጉ ደግሞ ጨዋታውን የማይጀምረው ቡድን ቢያንስ በ8 ሜትር እንዲርቅ ያስገድዳል። በሌላ መልኩ የፍፁም ቅጣት ምት ለመምታትም በበረኛው እና በመቺው መካከል የ11 ሜትር ርቀት ያስፈልጋል። ፍፁም ቅጣት ምት ክልል ውስጥ አንድ ተጫዋች ተጠልፏል እንዲባል ደግሞ ቢያንስ የወደቀበት ስፍራ ከግብ ክልሉ የ16 ሜትር ርቀት ውስጥ ሊሆን ይገባል። እነዚህ ቦታዎችን ለመለየት እና ዳኛቹ ውሳኔዎችን ሲሰጡ እንዳይቸገሩ ሜዳውን በነጭ መስመር መከፋፈል አስፈለገ። ይህ ደግሞ ሜዳ ላይ ያለውን እንቅስቃሴ እና ሥርዓት ብሎም በግምት የሚሰራውን ሥራ አስቀረ። በ1904 እግር ኳስ ከምን ጊዜውም በተለየ ፍጥነት ተቀባይነቱ እና ተወዳጅነቱ እየጨመረ መጣ። የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር «ፊፋ» እና የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር ቦርድ «አይ ኤፍ ኤ ቢ» አንድ ላይ ለመስራት ወሰኑ። ፊፋ የተመሰረተው በፈረንሳይ ከተማ ፓሪስ በቤልጄም፣ዴንማርክ፣ስዊድን፣ሲውዘርላንድ፣ ኔዘርላንድ፣እና በሪያል ማድሪድ ክለብ በተወከለችው ስፔን እና በፈረንሳይ ነው። የቀድሞው የእግር ኳስ ማህበር አባል «ዳንኤል በርሊ ውልፎል» ፈረንሳዊውን «ሮበርት ጉሪንን» ተክተው በ1906 የፊፋ ፕሬዚዳንት ሆኑ። ፊፋም «አይ ኤፍ ኤ ቢ» አባል ሆኖ በእግር ኳስ ጨዋታ ላይ የሚወጡ ሕጎች በጠንካራ ውይይት እና በድምፅ ብልጫ እንዲወሰን ተደረገ። አባል አገራቱ እና ፊፋ ባላቸው መቀመጫ የየራሳቸው የምርጫ ድምፅ ይኖራቸዋል። ከዚህም በኋላ ሕጎች መውጣታቸው አላቆመም። ምክንያቱም ስፖርቱ ሁልጊዜም በጠንካራ ለውጥ ላይ ስለሆነ። በ1912 በረኞችን ከፍፁም ቅጣት ምት ውጪ ኳስን በእጃቸው እንዳይዙ የሚከለክል ሕግ ወጣ። ከዚህም ሌላ ቀድሞ የእጅ ውርወራ ሲሰጥ አንድ ተጫዋች ከጨዋታ ውጪ አቋቋም ላይ «ኦፍሳይት» ከሆነ የመልስ ምት በዳኛው ይሰጥ ነበር። ይህ እንዲቀር ውሳኔ ተላልፎ፤ የእጅ ውርወራ ሲሰጥ ማንኛውም ተጫዋች ከጨዋታ ውጪ እንዳይሆን ተደረገ። በየጊዜው አዳዲስ የእግር ኳስ ሕጎች ወጥተዋል። ሆኖም እነዚህ ሕጎች የስፖርቱን ውበት እንዳያበላሹ። የፉክክር መንፈስን እንዳያጠፉ ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረግባቸዋል። እንደዚያም ሆኖ ግን ተግባራዊ እንዲደረጉ የሚወጡት አዳዲስ ሕጎች ክርክርን ማስነሳታቸው እና መተቸታቸው የማይቀር ነው። ሕጎቹ መርቀቃቸው በሜዳ ላይ ያለው እንቅስቃሴ ከተቆጣጣሪዎቹ ብቃት እና ፍፁም ካለመሆን ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ ስህተቶችን ለመቀነስ አስችሏል። አንድ ከነበረው ዳኛ ወደ ሦስት ከሦስት ወደ አራት እያለ፤ በጨዋታው ላይ ያለውን ስህተቶች እና ጥፋቶች እንዲሁም ፍሰት ለመቆጣጠር ዕድል ፈጥሯል። እንዲያም ሆኖ ግን እግር ኳስ ጨዋታ ሙሉ ለሙሉ ከሚያስቆጩ ስህተቶች እና መታለፍ የሌለባቸው ጥፋቶችን ከማስተናገድ አልዳነም። እንዲያውም እነዚህ ሾልከው የሚፈጠሩ ስህተቶች ለጨዋታው ውበት የሚሆኑበት አጋጣሚ አለ። ከላይ ያነሳናቸው ሕጎች ለእግር ኳሱ ውበት ጃኖ ደርበውለታል። ከሥርዓት አልባ እግር ኳስ ወደ ማራኪ እና ሥነ ሥርዓትን ወደ ተላበሰ ጨዋታ ተሸጋግሯል። አሁን ያለበት ለመድረስ ግን አንድ ምእተ ዓመት ጠይቋል። የጊዜው መርዘም ደግሞ በዓለም ላይ በተወዳጅነቱ ወደር የማይገኝለትን እግር ኳስ ይበልጥ እንዲስብ አድርጎታል።አዲስ ዘመን ነሐሴ 26/ 2011  ዳግም ከበደ
https://www.press.et/Ama/?p=17116
1,243
2ስፖርት
‹‹ሰዎችን በጅምላ መግደል ሃይማኖታዊ ተጠያቂነቱ ከፍ ያለ ነው›› ሸህ ሱልጣን ሃጂ አማን የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት
ሀገር አቀፍ ዜና
December 5, 2020
37
እስማኤል አረቦአዲስ አበባ፦ ሰዎችን በብሄራቸው ወይም በሃይማኖታቸው ምክንያት በጅምላ መግደል የኢትዮጵያውያን ወግና ባህል ካለመሆኑም በላይ ከፍ ያለ ሃይማኖታዊ ተጠያቂነት እንደሚያስከትል የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ሸህ ሱልጣን አማን አስታወቁ።ሸህ ሱልጣን በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፣ ሰላም በእስልምና ከፍተኛ ቦታ አለው። የሃይማኖት ሰዎች ሲገናኙ ‹‹አሰላም አለይኩም›› ወይም ሰላም ለአንተ ይሁን የሚል ሰላምታ ተለዋውጠው ነው ወደቀሪ ጉዳያቸው የሚገቡት። ይህ ከሰላም በፊት የሚቀድም ጉዳይ እንደሌለ የሚያመላክት ከመሆኑም ባሻገር ሰላም ከሌለ ሀገር የለም፤ ልማት የለም፤ በአግባቡ አምልኮንም ማከናወን አይቻልም የሚልም መልዕክት አለው።“ነፍስን ማጥፋት በእስልምና በጣም የተወገዘ ነው። አንድን ነፍስ ማጥፋት ዓለምን እንደማጥፋት ነው። እንኳን የሰው ነፍስን ቀርቶ ያለ አግባብ የነፍሳትን ነፍስ ማጥፋት በእስልምና በጣም የተወገዘ ነው። ይሁን እንጂ አሁን በኢትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎች የሚታዩ ሰዎችን በጅምላ የመግደል ተግባሮች እንደሃይማኖት አባት በጣም የሚወገዝ ነው” ብለዋል።‹‹እኛ ኢትዮጵያውያን ተባብረን፤ ተቃቅፈን ፤ ተዋደን ብሄርና ሃይማኖት ሳይለየን በሰላም ስንኖር የቆየን ህዝቦች ነን። አሁን ግን በተለያዩ ቦታዎች ዘግናኝ የሆኑ ግድያዎችና ጭፍጨፋዎችን እያየን ነው ያሉት ሸህ ሱልጣን ሃጂ አማን፣ ይህ ከኢትዮጵያውያን አማኝነትና ባህልና እሴት አንጻር በጣም የሚያሳፍርና እኛን የማይገልጽ እንደሆነ አመልክተዋል። ፖለቲከኞች ሃይማኖትንና ብሄርን ሽፋን አድርገው በሳለም ለዘመናት የኖረውን ህዝብ ሲያባሉትና ሲያጫርሱት እየተመለከትን ነው›› ያሉት ፕሬዝደንቱ ፣ በየቦታው የሚታዩ ግጭቶችና ግድያዎች መንስኤያቸው ከሃይማኖትና ብሄር ይልቅ ፖለቲካ መሆኑን ጠቁመዋል። ሸህ ሱልጣን እንደሚሉት ፖለቲከኞች የራሳቸውን አጀንዳ ለማስፈጸም ሲሉ አንድን ብሄር ከሌላው ጋር ወይም ሃይማኖትን ከሃይማኖት ጋር እያጋጩ የሚፈጽሙት ድርጊት እንጂ ኢትዮጵያውያን እንደዚህ አይነት ታሪክም ሆነ ስነልቦና የላቸውም። “ኢትዮጵያን መዋደድ ፤ መፋቀር ፤ መከባበርና መተሳሰብ እንጂ የእልቂትና የጭፍጨፋ ስነልቦና የላቸውም። ይህ በሁሉም ሃይማኖት የተወገዘና በወዲያኛውም ዓለም የሚያስጠይቅ ነው። አሁን በማይካድራም ሆነ በሌሎች አካባቢዎች እየሰማነው ያለው ዘርን መሰረት ያደደረገ ጥቃትና ጭፍጨፋ እንደሃይማኖትም ፤ አንደ ኢትዮጵያን ወግና ልማድ በጣም የሚያሳፍርና አንገት የሚያስደፋ ነው። ይህ ጸያፍ ድርጊት ሃይማኖት አለኝ የሚል የሰው ፍጡር የሚፈጽመው አይደለም” ብለዋል ። ብሄርን ወይም ሃይማኖትን መሰረት አድርገው የሚፈጸሙ ጅምላ ግድያዎች አረመኔያዊና ጸያፍ ድርጊት በመሆኑ ሊወገዝ የሚገባው ነው ያሉት ሸህ ሱልጣን፣ ሰው ካጠፋ በበህላዊ ሽምግልና ወይም ሀገሪቱ በምትመራበት ህግ መዳኘት እንጂ ዘርን መሰረት አድርጎ በሚወሰዱ የጅምላ ግድያዎች ፍትህን አረጋግጣለሁ ወይም አንድን አካል እጎዳለሁ ብሎ መነሳት ከጤናማ አእምሮ የሚመነጭ እንዳልሆነ ገልጸዋል። ይህን ድርጊት የሚፈጽሙ ግለሰቦች ወይም ቡድኖች  ኢትዮጵያውያን ናቸው ብሎ ለመናገርም አያስደፍርም ያሉት ሸህ ሱልጣን፣ ይህ ኢትዮጵያውያንን የሚገልጽ አለመሆኑን፤ ሰዎችን በጅምላ መግደል የሚያስከትለው ሃይማኖታዊ ተጠያቂነት ከፍ ያለ መሆኑንም ጠቁመዋል። ‹‹እኔ ከልጅነቴ ጀምሮ ኢትዮጵያን ተዘዋውሬ አይቻታለሁ። ከሶማሌ እስከ አፋር፤ ደቡብ ፤አማራን፤ ኦሮሞን ፤ጋምቤላና ቤኒሻንጉልን ሁሉንም ተዘዋውሬ ተመልክቻለሁ። በዞርኩባቸው አካባቢዎች በሙሉ ሁሉም ኢትዮጵያውያን እንግዳ ተቀባይ፤ አዛኝና ተከባብሮ የሚኖር ነው” ብለዋል። አሁን፤ አሁን ፖለቲከኞች በሚፈጥሩት ውዥንብር ሰዎች በሃይማኖትና በብሄር በመከፋፈል አንዱ አንዱን ውጣልኝ ሲል ይሰማል። አልፎም ግድያ ሲፈጸም እናያለን። ስለዚህም ፖለቲከኞች የሚፈጽሙት ተግባር ከኢትዮጵያውያን ወግና ባህል ውጭ በመሆኑ ህዝቡ ተባብሮ በቃችሁ ሊላቸው እንደሚገባም አመልክተዋል። ስር እየሰደደ የመጣውን ዘረኝነትና በእሱም የተነሳ እየተስፋፋ ያለውን ግጭት፤ መፈናቀልና ግድያ ለዘለቄታው ለማስወገድ የሃይማኖት አባቶች ከፍተኛ ድርሻ እንዳላቸውና የሃይማኖት አባቶች ተከታዮቻቸውን ከሃይማኖታዊ ትምህርት ጎን ለጎን የኢትዮጵያውያንን የቆየ የመተሳሰብ፤ የመተጋገዝና የአብሮነት እሴቶችን በማስተማር ህዝቡ እሴቶቹን ጠብቆ እንዲጓዝ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸውም አስታውቀዋል። በተለይ ለወጣቶች ልዩ ትኩረት በመስጠት ወጣቱ ሃይማኖቱን እንዲከተል፤ ወግና ባህሉን እንዲያከብርና ሀገሩን እንዲወድ ማድረግ ከሃይማኖት አባቶች የሚጠበቁ ተግባራት ናቸው። ብሄርተኝነት ወደ ጥፋት እንጂ ወደ ሰላም እንዳልወሰደ፤ ወደ ድህነት እንጂ ወደ ልማት እንዳላሻገረ፤ እርስ በእርስ ወደ መተላለቅ እንጂ ወደ ትብብርና አንድነት እንዳላመጣና፤ እንደማያመጣም የሃይማኖት አባቶች በስፋት ማስተማር እንዳለባቸው አሳስበዋል።አዲስ ዘመን ህዳር 26 ቀን 2013 ዓ.ም
https://www.press.et/Ama/?p=36736
501
0ሀገር አቀፍ ዜና
ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ከተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ድጋፍ ድርጅት ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 5, 2020
8
በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ፦ የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ከተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ድጋፍ ድርጅት ኃላፊዎች ጋር የበይነ መረብ ውይይት አካሂደዋል። ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ እንዳመለከተው፣ በውይይቱ ላይ ሬና ገላኒ፣ በተባበሩት መንግስታት ዋና መስሪያ ቤት የሰብዓዊ ድጋፍ ዳይሬክተር፣ ዶክተር ካትሪን ሶዚ፣ በተባበሩት መንግስታት አስተባባሪና የሰብዓዊ ድጋፍ የኢትዮጵያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ድጋፍ የኢትዮጵያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ተካፍለዋል። ሚኒስትሯ በሰሜናዊ የኢትዮጵያ ክፍል በተካሄደው የህግ ማስከበር ሂደት እንዲሁም ከወታደራዊ ህግ የማስከበር ሂደት ቀድሞ ሰላምን በሰለጠነ መልኩ በውይይት ለማምጣት ስለተሄደው ረጅም ርቀት ሰፊ ገለጻ አድርገዋል። በሰላም ማስከበር ሂደቱም ንጹሃን እንዳይጎዱና መሰረተ ልማት እንዳይፈርስ ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ የተሞላበት ዘመቻ እንደተካሄደ አስረድተዋል። ሬና ገላኒ በበኩላቸው ስለተደረገላቸው ገለጻ አመስግነው በኢትዮጵያ መንግስት ንጹሃን ዜጎች ላይ የሚደርሰውን አደጋ ለመቀነስ የተደረገውን ጥረት አድንቀዋል። በመጨረሻም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንደሁልጊዜውም ሰብዓዊና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ ድጋፎችን ከመንግስት ጋር በገባው የሁለትዮሽ ስምምነት መሰረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።አዲስ ዘመን ህዳር 26 ቀን 2013 ዓ.ም
https://www.press.et/Ama/?p=36744
141
0ሀገር አቀፍ ዜና
የህግ ማስከበሩን ተግባር ዓላማ ለዓለም አቀፉ ህብረተሰብ ለማስረዳት የተከናወነው የዲፕሎማሲ ስራ ውጤታማ እንደነበር ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 5, 2020
9
በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ፦ ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል የነበረውን የህግ ማስከበር ዘመቻ ዓላማ ለዓለም ለማሳወቅ የሰራችው ዲፕሎማሲ ስኬታማ እንደነበር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። ወደ ሱዳን የተሰደዱ ዜጎችን ወደ አገራቸው ለመመለስ እየተሰራ መሆኑንም ገለጸ፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በትግራይ ክልል የነበረውን የህግ ማስከበር ዘመቻ ዓላማ ለዓለም ለማሳወቅ የተሰራውን የዲፕሎማሲ ስራ አስመልክቶ ትናንት በሰጡት መግለጫ ፣ የፌዴራል መንግስት ሲያከናውን የነበረውን ህግ የማስከበር ተግባር ዓላማ ለዓለም መሪዎች ለማስረዳት የተሰሩ የዲፕሎማሲ ስራዎች ስኬታማ እንደነበሩ አስታውቀዋል። በአፍሪካና አውሮፓ በአካል፣ በበይነ መረብ፣ በስልክና ሌሎች የመገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም የህግ ማስከበሩን ዘመቻ አላማ ለዓለም አቀፉ ህብረተሰብ የማስረዳት ስራ መከናወኑን ያመለከቱት ቃል አቀባዩ፣ በተለይም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በጎረቤትና በአውሮፓ አገሮች ባደረጉት ጉብኝት ውጤታማ ነበር ብለዋል። በዲፕሎማሲ ስራው ባለፉት ሁለት ዓመታት ተኩል በፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፍ የመጡ ለውጦችን ለዓለም አቀፉ ህብረተሰብ ማስረዳት መቻሉን ጠቁመው ፣ የህወሓት ጁንታው አመራሮች ለውጡን መጻረራቸውንና ወደ ለውጡ እንዲመለስ የፌዴራል መንግስት የሰጣቸውን ሰፊ እድል ማሳየት መቻሉን ገልጸዋል። የጁንታው አባላት የተሠጣቸውን እድል ከመጠቀም ይልቅ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በገንዘብና በአደረጃጀት የሽብር ስራዎችን ሲደግፉ እንደነበር ማስረዳት መቻሉን ጠቁመው ፣ ህገ ወጥ ቡድኑ በሰሜን እዝ ላይ በፈጸመው ጥቃት ህግ ለማስከበር የተወሰደው እርምጃ የውስጥ ጉዳይ መሆኑን በማስረዳት ውጤታማ የዲፕሎማሲ ስራ መከናወኑን አብራርተዋል። ህግ የማስከበር ተግባሩ ንጹሃን ዜጎችን ሳይጎዳ መጠናቀቁን ከሩሲያ፣ ዴንማርክ፣ ኖርዌይና ሌሎች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር በስልክ ውይይቶች መደረጋቸውን አንስተዋል። በውይይቱም ድርድር ማድረግን በተመለከተ ህጋዊ ከሆነው ጊዜያዊ አስተዳደሩ ጋር እየተደረገ መሆኑንና ሌሎች ጉዳዮች ላይ የማስረዳት ስራ መከናወኑን ገልጸዋል። ወደ ሱዳን የተሰደዱ ዜጎችን ወደ አገራቸው ለመመለስ ከአገሪቱ መንግስት ጋር እየተሰራ መሆኑንም ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው አስታውቀዋል።አዲስ ዘመን ህዳር 26 ቀን 2013 ዓ.ም
https://www.press.et/Ama/?p=36749
249
0ሀገር አቀፍ ዜና
ለተመራቂ ሥራ ፈላጊዎች የበይነ መረብ የሥራ ዓውደ ርዕይ ሊካሄድ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
December 5, 2020
7
ዋለልኝ አየለ አዲስ አበባ፦ ከተለያዩ የትምህርት ተቋማት ለሚመረቁ ሥራ ፈላጊዎች የበይነ መረብ የሥራ ዓውደ ርዕይ እንደሚካሄድ የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን አስታወቀ። ዓውደ ርዕዩ አካላዊ ቅርርብን በማስቀረት ኮቪድ-19 ወረርሽኝን የሚከላከልና ሥራ ፈላጊዎችን ከቀጣሪ ድርጅቶች ጋር የሚያገናኝ እንደሆነም ገልጿል። በሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን የኮምኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት አማካሪ ወይዘሮ ተወዳጅ እሸቱ በተለይም ለአዲስ ዘመን ትናንት እንደገለጹት፤ የንግድ ሥራ ክፍል የሆነው ደረጃ ዶት ኮም ከኢፌዴሪ የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ጋር በመተባበር ከህዳር 29 እስከ ታህሳስ 9 ቀን 2013 ዓ.ም የበይነ መረብ የሥራ ዓውደ ርዕይ ይካሄዳል። በዓውደ ርዕዩም የጅማ፣ የባህርዳር፣ የአዲስ አበባ እና ሌሎች አንጋፋ ዩኒቨርሲቲዎች ይሳተፋሉ። እንዲህ አይነት የሥራ ዕድል ዓውደ ርዕይ በሌላው ዓለም ብዙ የሥራ ዕድል ለመፍጠር እንደሚረዳ ያመለከቱት አማካሪዋ ፣ በኢትዮጵያም የተሻለ የስራ አድል ለመፍጠር ያስችላል በሚል ተግባራዊ መደረግ መጀመሩን አስታውቀዋል። በደረጃ ዶት ኮም አነሳሽነት ከዚህ በፊት በየከተሞች እየተዞረ በአካላዊ ቅርርብ የስራ እድል ለመፍጠር ይሰራ እንደነበር ጠቁመው ፤ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ብዙ ሰዎችን ማሰባሰብ ባለመቻሉ ስራውን በበይነ መረብ ዓውደ ርዕይ እየተካሄደ መሆኑን አመልክተዋል። አገልግሎቱን በበይነ መረብ መሰጠቱ የአገልግሎቱን ተደራሽነት እንዳሰፋው የገለጹት አማካሪዋ፣ በበይነ መረብ አገልግሎት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ እንደገባ ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎችን ማሳተፍ ተችሏል ብለዋል። ‹‹የሥራ ዕድል ፈጠራ አጀንዳው የመንግስት ኃላፊነት ብቻ አይደለም›› ያሉት ወይዘሮ ተወዳጅ፤ የግል ባለሀብቶችና ሌሎች ቀጣሪዎች ኃላፊነት እንዳለባቸው ጠቁመዋል። መንግስት በግል አስቀጣሪዎች የሚሰሩ የስራ ፈጠራ ስራዎችን እንደሚደግፍም ተናግረዋል። የደረጃ ዶት ኮም ፕሮግራም ዳይሬክተር ወይዘሪት ሲሃም አየለ በበኩላቸው እንደገለጹት፤ ደረጃ ዶት ኮም ከማስተር ካርድ ፋንውዴሽን በሚያገኘው ድጋፍ ከሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ጋር በመተባበር አዲስ ተመራቂዎችን ከቀጣሪ ድርጅቶች ጋር ያገናኛል፤ ያስቀጥራል። ከተቀጣሪዎች ምንም አይነት ክፍያ አይቀበልም። ደረጃ ዶት ኮም ከአንድ ሺህ በላይ ተመራቂዎችን ከ80 ቀጣሪ ድርጅቶች ጋር ማገናኘቱን የገለጹት ወይዘሪት ሲሃን፣ ህዳር 29 በሚከፈተው ዓውደ ርዕይ ከአራት ሺህ በላይ ተመራቂዎች እንደሚሳተፉም አስታውቀዋል ። እንደ ወይዘሪት ሲሃን ገለጻ፤ ደረጃ ዶት ኮም ከቀጣሪ ድርጅቶች እና ከተመራቂዎች ጋር ማገናኘቱ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሥርዓተ ትምህርት ቀረጻ ግብዓት የሚሆኑ መረጃዎችን ማግኘት ማስቻሉን ጠቁመዋል። እንደ አሰራር ቀጣሪ ተቋማቱ ከተመራቂ ተማሪዎች ላይ ያጡትን ክህሎት ለደረጃ ዶት ኮም ያሳውቃሉ ያሉት ወይዘሪት ሲሃም ፣ ደረጃ ዶት ኮም በበኩሉ ተመራቂ ተማሪዎች በተመረቁበት ሙያ አጡት የተባለውን ክህሎት ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያሳውቃል ብለዋል። ደረጃ ዶት ኮም ከ25 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ተመራቂዎች የሥራ ዕድል ፈጠራ ክህሎትን በተመለከተ ሥልጠና መስጠቱን አስታውቀው ፣ በመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት 14 የሙያ ማበልጸጊያ ማዕከላት ማቋቀሙን ገልተጸዋል። ለስድስት ሺህ ተመራቂዎች የሥራ ዕድል ማስገኘቱን አመልክተዋል። የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን በ2012 ዓ.ም በጀት ዓመት ለሦስት ሚሊዮን ወጣቶች የሥር ዕድል የመፍጠር እቅድ እንደነበረው ይታወሳል።አዲስ ዘመን ህዳር 26 ቀን 2013 ዓ.ም
https://www.press.et/Ama/?p=36756
378
0ሀገር አቀፍ ዜና
አሁንም አፍላ ወጣቶቻችንን እየነጠቀን ያለው የኤች አይ ቪ ቫይረስ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 5, 2020
16
አስመረት ብስራት የተለያዩ ተስፋ የሚሰንቁበት፤ ነገን በብሩህ መንፈስ የሚመለከቱበት፤ ሁሉንም ነገር ማየት መሞከር በሚያስደስትበት የእድሜ ክልል ላይ የሚገኙ ወጣቶች ናቸው። በዘወዲቱ ሆስፒታል የማህበራዊና ስነ ልቦናዊ ድጋፍ በሚሰጥበት ክፍል ውስጥ ከኤች አይቪ ቫይረስ ጋር ግብ ግብ መገጠም ግድ ሆኖባቸዋል። ገሚሱ እድሜያቸው ለአካለ መጠን ሳይደርሱ የጀመሩት ግንኙነት ለዚህ ቫይረስ ሰለባ የዳረጋቸው፣ ገሚሱ ደግሞ ከወላጆቻቸው የተላለፈባቸው ናቸው። እነዚህ ህፃናትና ወጣቶች አፍላነታቸው በእድሜ ልክ በሽታ መጠቃታቸው እጅግ ልብ የሚነካ ነው። የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከፌዴራል ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽህፈት ቤትና ሌሎች አጋር ድርጅቶች የ2013 ዓ.ም የዓለም ኤድስ ቀን አከባበር አካል የነበረውን የሆስፒታሉ ጉብኝት ላይ የተመለከትናቸው ህፃናትና ወጣቶች ምንም ያህል በሽታውን ተቀብለውት በጥንካሬ ቢኖሩም የበሽታው ስርጭት ግን ምን ያህል አስከፊ እንደነበር ለመመልከት ያስቻለ ነው። በአዲስ አበባ የስርጭት መጠኑ ከሶስት በመቶ በላይ መሆኑን በፕሮግራሙ ላይ አግኝተን ያናገርናቸው በዘውዲቱ ሆስፒታል የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር አስቴር ሸዋአማረ፣ ዛሬም በከፍተኛ ሁኔታ በቫይረሱ ከተያዙ መካከል ሴቶችና አፍላ ወጣቶች ከፍተኛውን ቁጥር ይይዛሉ ብለዋል። በከተማዋ ኤች አይቪ በደማቸው የሚገኙ ግለሰቦች 109 ሺ በላይ መሆናቸውን ያስታወሱት ዶክተሯ፣ ከእነዚህ መካከል እድሜያቸው ከ 15-24 የሚሆን ወጣቶች ከፍተኛ ቁጥር መያዛቸውን ጥናቶች እንደሚያሳዩ ተናግረዋል። በሀገራችን 76 በመቶ የሚሆኑ ወጣት ሴቶች ስለ ኤች አይ ቪ እውቀት የሌላቸው መሆኑን ነው ያስረዱት። በዝግጅቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስቴር ዴኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ እንደሚሉት አዲስ አበባ ከጋምቤላ ቀጥሎ በከፍተኛ ሁኔታ የኤች አይቪ ስርጭት የሚታይባት ከተማ ናት። በጋምቤላ የኤች አይቪ የስርጭት መጠን ወደ አምስት በመቶ የሚጠጋ መሆኑን አስታውሰው፣ አንዳንድ የሀገሪቱ ከተሞች ላይም የስርጭት መጠኑ ከፍ ማለቱን ጠቅሰዋል። ዶክተር ደረጀ እንደሚሉት በከተማዋ በአፍላ ወጣቶች ያለው የኤች አይቪ የስርጭት መጠን ከፍ ማለት ምክንያት መዘናጋት ነው። የተለያዩ አካላት ኤች አይቪ ላይ የሚሰጡት የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርቶች መቀዛቀዛቸው በአዲሱ ትውልድ የስርጭት ምጣኔው ከፍ እንዲል ምክንያት መሆኑን ነው የሚያስረዱት። የኤችአይቪ መከላከያና መቆጣጠያ ጽ/ቤት ኃላፊ ዶክተር ፅጌረዳ ክፍሌ እንደሚሉት በከተማዋ ያለውን የኤች አይቪ የስርጭት መጠን አሳሳቢ የሚያደርገው በአፍላ ወጣቶች መካከል ያለው የስርጭት መጠን ከፍተኛ መሆኑ ነው። ለዚህም ኃላፊዋ እንደ ምክንያትነት የጠቀሱት ከስራ አጥነት ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮችን ነው። “ስራ አጥነት ለኤች አይቪ የሚያጋልጡ ስፍራዎች እንዲውሉ ገፊ ምክንያት ነው” የሚሉት ዶክተሯ በከተማዋ ያሉ የኢንዱስትሪና የሆቴሎች መስፋፋት ሌላው እንደምክንያት ያነሱት ነው። በከተማዋ የመጤ ባህሎች መስፋፋትም እንደሚታይ የገለጹት ሲስተር ብርዛፍ የራቁት ዳንስ ቤት፣ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት፣ ጫት፣ ሺሻና ቡና ቤቶች መበራከታቸው ለኤች አይቪ መስፋፋት አስተዋጽኦ ማድረጉን ገልጸዋል። በአዲስ አበባ ከተማ የሚታየው የኮንስትራክሽን ስራዎች ላይ ለመሰማራት ከተለያዩ ከተሞች የሚመጡ ወጣቶች ቁጥር ከፍ ማለትም የስርጭቱ መጠን ከፍ እንዲል እንዳደረገው አብራርተዋል። ጽህፈት ቤታቸው በከተማዋ ለኤች አይቪ ተጋላጭ ብሎ የለያቸውን የከተማዋ የህብረተሰብ ክፍሎችን ሲዘረዝሩ በትምህርት ቤትም ሆነ ውጭ ያሉ ወጣቶች፣ የቀን ሰራተኞች፣ የከባድ መኪና የረዥም ርቀት አሽከርካሪዎች፣ በወህኒ ቤት የሚገኙ ታራሚዎች፣ በወሲብ ንግድ የተሰማሩ ግለሰቦች፣ እና በቅርቡ በተደረጉ ጥናቶች እንደታየው ደግሞ ባሎቻቸውን በፈቱ ሴቶች የስርጭት ምጣኔው ከፍ ያለ ነው። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶቹ በብዛት በሚገኙባቸው አካባቢዎች የትምህርት ስራውን ሊያውኩና ወጣቶቹን ለኤች አይቪ ሊያጋልጡ የሚችሉ መዝናኛዎችን ከትምህርት ቤት መራቅ አለባቸው የሚል አቋም ይዞ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ለመስራት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ተናግረዋል። የዓለም ጤና ድርጅት እኤአ በ2030 አዲስ በቫይረሱ የሚያዝ ግለሰብ መኖር የለበትም የሚል ራዕይ አስቀምጧል። በኢትዮጵያ የኤች አይቪ የስርጭት መጠኑ 0.9 በመቶ ነው።አዲስ ዘመን ህዳር 26 ቀን 2013 ዓ.ም
https://www.press.et/Ama/?p=36743
477
0ሀገር አቀፍ ዜና
ለዓመታት የክልሉ ኢንቨስትመንት ላይ ማነቆ የነበረው የመሬት ካሳ አዋጅ ተሻሽሎ ሊተገበር ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
December 5, 2020
20
ክፍለዮሐንስ አንበርብር አዲስ አበባ፡- የክልሉን ኢንቨስትመንት ለማፋጠን የወጣው የመሬት ካሳ አዋጅ ተሻሽሎ ሊተገበር ከመጨረሻው ምዕራፍ ላይ መድረሱን የአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨትመንት ቢሮ አስታወቀ፡፡ በአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨትመንት ቢሮ የአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ያየህ አዲስ ለዝግጅት ክፍሉ እንደገለጹት፤ ቀደም ሲል የነበረው የመሬት ካሳ አዋጅ የክልሉን ኢንቨስትመንት ላይ ማነቆ ሆኖ መቆየቱን ጠቁመው በአሁኑ ወቅት ቀደም ሲል የነበረው የመሬት ካሳ አዋጅ ተሻሽሎ ሊተገበር ከመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሷል፡፡ ለአርሶ አደር የሚከፈል ካሳን አስመልክቶ እንዲወጣ የታሰበው አዋጅ በፌዴራል መንግስት ዘንድ አንድ ዓመት ቆይቷል፡፡ ወደ ክልል ከመጣ በኋላ ደግሞ ወራት ተቆጥረዋል የሚሉት አቶ ያየህ ፣ የአዋጁ ተግባራዊ አለመሆን ባለሀብቶችን በፍጥነት ለማስተናገድ እንቅፋት ሆኗል ብለዋል፡፡ እንደ ኃላፊው ገለፃ፤ ክልሉ በፍጥነት መመሪያ አውጥቶ ከሚመለከታቸው አካላትን ጋር ባለመወያየቱና ወደ ሥራ ባለመግባቱ ከተማ አስተዳደሮችና የልማት ኮሪደሮች ባለሀብቶችን ለማስተናገድ ተቸግረዋል፡፡ ይህ አሰራር በአሁኑ ወቅት መፍትሄ ሊሰጠው ተቃርቧል። አዋጁ ተግባራዊ ሲሆን በሳምንታት የኢንቨስተሩን ጥያቄ መመለስ ይቻላል፡፡ አርሶ አደሩም በአሁኑ ወቅ ምርት እየሰበሰበ ሲሆን በወቅቱ ካሳ ካልተከፈለው ወደ መሬት ማረስ እና ማለስለስ ብሎም ዘር መዝራት ስለሚገባ በሚቀጥለው ዓመትም ተመሳሳይ ችግር የሚፈጥር መሆኑን የጠቀሱት ሃላፊው፤ በመሆኑም በፍጥነት አዲሱን አዋጅ ታሳቢ ባደረገ መልኩ ወደ ሥራ መግባት እንደሚገባ በከፍተኛ አመራሮች መግባባት ላይ መደረሱን ገልጸዋል፡፡ ለዓመታት የክልሉ ኢንቨስትመንት ላይ ማነቆ የነበረ የመሬት ካሣ አዋጅ ተሻሽሎ ወደ ሥራ ሲገባም በክልሉ ከፍተኛ መዋዕዋለ ንዋይ የሚያፈሱ ባለሀብቶች እንደሚኖሩና ከፍተኛ የሆነ የኢንቨስትመንት ፍሰት እንደሚኖርም እምነታቸው እንደሆነ አስታውቀዋል ፡፡ የደብረብረሃን ከተማ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ብርሃን ገብረሕይወት በበኩላቸው፤ የአዋጁ መዘግየት በከተማው እና በአካባቢው በሚካሄደው ኢንቨስትመንት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩን ጠቁመዋል፡፡ በተለይም በአሁኑ ወቅት ወደ ከተማዋ የሚጎርፉ የአገር ውስጥ እና የውጭ አገር ባለሀብቶችን ለማስተናገድ እና የሚፈልጉትን አገልግሎት በወቅቱ ለመስጠት ፈታኝ ሆኖ መቆየቱን ጠቁመው፤ በተደጋጋሚ ከዞን እስከ ክልል ችግሩ እንዲፈታና ለሚመለከታቸው ጥያቄ ሲያቀርቡ መቆየታቸውን አስታውሰዋል፡፡ አዋጁ በመዘግየቱ ባለሀብቶች በፈለጉት መንገድ ኢንቨስትመንት እንዳያካሂዱ ያደረጋቸው ሲሆን ከወረዳ እስከ ዞን ለሚገኙ አስተዳደሮችም ፈተና እንደነበርና አርሶ አደሩን ካሳ ከፍሎ መሬት እንዲለቅ የሚደረገው ጥረት በእጅጉ አስቸጋሪ ሆኖ መቆየቱንም ኃላፊው ገልጸዋል፡፡አዲስ ዘመን ህዳር 26 ቀን 2013 ዓ.ም
https://www.press.et/Ama/?p=36750
303
0ሀገር አቀፍ ዜና
የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 6, 2020
71
ጌትነት ምህረቴ ”አንድ በሬ ሸጬ ስድስት ዓመት በመቀሌ የታሰረውን የልጅ ልጄን በደከመ አቅሜ ሄጄ አስፈትቻለሁ። ከተፈታ በኋላም አፋኙ የህወሓት ጁንታ በሚደረግበት ጫናና ክትትል ተማሮ ወደ ሳውዲ አረቢያ ሄዷል። የልጅ ልጄ ያለበትን ቦታና ምን እንዳጋጠመው ስለማላውቅ የበረሃ ራት ሆኖ ይሆን ብዬ እየተጨነኩ ነበር። አምና ግን ሳውዲ መግባቱን ስለሰማሁ ደስታዬ ወደር የለውም” የሚሉት ወይዘሮ ከፍያለች በላይ ናቸው። ንት ሁኗታል። ከተማዋ ነጻነቷን በመቀናጀቷ እፎይታ ከተሰማቸው ነዋሪዎች መካከል አንዷ ወይዘሮ ከፍያለች በላይ ናቸው። አፋኙ ቡድኑ በማንነታቸው ምክንያት በእኚህ አዛውንት ላይ ከፍተኛ ማንገላታት፣ ሰቆቃና ግፍ ፈጽሞባቸዋል። ማንነቴን አልሸጥም እኔ የወልቃይት አማራ ነኝ አባቴ፣ አጎቶቼ ይግባኝ ሲኖራቸው መቀሌ ሳይሆን ደባርቅና ዳባት ሄደው ሲያስፈጽሙ ነበር ብዬ በአደባባይ በመናገሬ እያረስኩና እያሳረስኩ ልጆቼን ያሳደኩበትን መሬቴን ተነጥቄያለሁ ይላሉ ። ሁለት ልጆችና አንድ የልጅ ልጃቸውን በግብርና ሥራ ያስተዳድራሉ። ልጆቼም ብዙ መከራና መገፋት ደርሶባቸዋል። በተለይ ቃፍታ ከተማ የመንግሥት ሥራ ሲሰራ የነበረው የልጄ ልጄ 600 ብር አጥፍተሃል ተብሎ ስድስት ዓመት መቀሌ ወስደው አስረውታል። ይኸው በዚህ ደካማ አቅሜ የማሳርስበትን በሬ ሸጬ 10ሺ ብር ዋስትና ከፍለው ማስፈታታቸውን ያስታውሳሉ። የምንኖርበት ቃፍታ ሁለት ህግ ነው ያለው የሚሉት ወይዘሮ ከፍያለች፣ የወልቃይት አማራ ከፍተኛ ልዩነትና ጫና ይደረግበት ነበር። ለዚህም ብር ያጠፋና ነብስ ያጠፋ ሰው እኩል ፍርድ የሚሰጥበት ሁኔታ እንዳስተዋሉ ገልጸዋል። የእሳቸው የልጅ ልጅ የመንግሥት ሥራ በሚሰራበት የወረዳው የፋይናንስ መስሪያ ቤት 600 ብር አሳስተሃል ተብሎ 6 ዓመት የተፈረደበት ሲሆን ሌላው የትግራይ ተወላጅ ደግሞ የሰው ህይወት አጥፍቶ 6 ዓመት የተፈረደበት መሆኑን በመግለጽ የዳኝነት ልዩነቱን በአብነት ጠቅሰዋል። ከሀዲው ቡድን አማራን ይጠላል፤ በግልጽም የወልቃይት መሬቱን እንጂ እናንተን አንፈልጋቸውም ይል ነበር የሚሉት ወይዘሮ ከፍያለች ፤ በርካታ የወልቃይት አማራ ወጣቶች በሚደርስባቸው በደል፣አፈና፣መገለልና ጫና ምክንያት አገር ጥለው ለስደት መዳረጋቸውን ነግረውናል። ታስሮ የተፈታውም ሆነ ሁለት ልጆቻቸው በከ ሀዲው ህወሓት ይደርስባቸው የነበረውን ጫናና በደል አንገፍግፏቸው አገር ጥለው መኮብለላቸውን ያወሳሉ። ላለፉት 30 ዓመታት በወልቃይት አማራዎች ላይ የሚደ ርሰው ጫና፣ በደል፤ ልዩነት አይጣል የሚያስብል መሆኑን የሚገልጹት ከፍ ባለ ምሬት ነው። ለልጆቻቸው ብቻ ሳይሆን ለእሳቸውም ጭምር ጆሮ ጠቢ ይመደብባቸው እንደነበርም ይናገራሉ። ላለፉት 30 ዓመታት ምን አወራን ፣ ዛሬ ደግሞ ምን ሊያደርጉን ነው ብለን እንደነግጣለን እንጂ እንደጉም ይጠፋሉ ብለን አስበን አናውቅም የሚሉት አዛውንቷ፤ የከሀዲው የህወሓት ጁንታ በውስጡ እንጥፍጣፊ ርህራሄ የሌለው መሆኑ ንጹሀን ሰዎችን ብቻ ሳይሆን ከእነሱ ጋር አብረዋቸው የሚሰሩ ሰዎችን ጭምር ሳይቀር ገድለዋቸው ነው የፈረጠጡት፤ ይህ የሚያሳየው ዞሮ ዞሮ ግፍ የሚሰራ ሰው የእጁን እንደሚያገኝ ነው ብለዋል። አሁን ነጻ ወጥተናል፤ ከሀዲውና አፋኙ የህወሓት ጁንታን ተገላግለናል። ይህን ነጻነትና እፎይታ በዘላቂነት ለማስቀጠል የከተማው ነዋሪም ሆነ መንግሥት እጅና ጓንት ሆነው መስራት ይኖርባቸዋል። እኔም በጸሎት አግዛለሁ ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተውናል። አደራጀው ጫሉ የሚባለውን ትንሽ ወንድማቸው በአፋኙ የህወሓት ጁንታ የተገደለባቸው መሆኑን የሚገልጹት የጸገዴ ወረዳ ከተማ ንጉስ ከተማ ነዋሪ ወይዘሮ አዲሲ ቀለብ ፤ የአማራ ነጋዴና ገበሬ እሱ ቤት ተሰብስበው ነው የአማራ ማንነትን የሚጠይቁት በሚል ደብድበው ገድለው ወደ ገደል እንደጣሉት በቁጭት ይናገራሉ። “የወንድሜን ሞት ሲያረዱኝ ሴት ልጄ አራስ ነበረች፤ ገደል ገብቶ ሞተ ብለው አስከሬኑን ደጃፌ ላይ ጥለውት ሄዱ፤ በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ወቅት አደራጀው ወንድሜ አንተ ነህ የማትተካ እንጂ ነገ የአማራን መብት የሚያስጠብቅ ትንታግ ትንታጉን እንተካዋለን ብለሽ አልቀሰሻል ተብዬም በትግራይ ልዩ ሃይል በሰደፍ መመታታቸውን ይናገራሉ ። ከአንድ ወር በላይም ታስሬያለሁ፤ የሚሉት ወይዘሮዋ፣ ከዚያ አስከፊ አስተዳደርና አገዛዝ በመከላከያ ሰራዊትና በአማራ ልዩ ኃይል ነጻ በመውጣታቸው ደስታቸው እጅግ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸውልናል። “ ድቅድቁ ጨለማ አልፏል ፤አሁን ጸሐይ ወጥቶልናል፤ ይህን የተገኘውን ነጻነት ተንከባክቦ መጠበቅና ማስቀጠል ከጸገዴ ወረዳ ህዝብ ይጠበቃል። እኔም በማንኛውም መልኩ ለማገዝና ለመተባበር ሙሉ ፈቃደኛና ደስተኛ ነኝ” ሲሉም አስተያየታቸውን ሰጥተውናል።አዲስ ዘመን ህዳር 27 ቀን 2013 ዓ ም
https://www.press.et/Ama/?p=36795
512
0ሀገር አቀፍ ዜና
በቆላ ተንቤን የሚገኘው የጁንታው የመጨረሻ ምሽግ ተከቦ እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል
ሀገር አቀፍ ዜና
December 6, 2020
519
የጁንታው የአመራር ቡድን የታየባቸው ቦታዎች ላይ ጥቃት እየተፈጸመ ነው ጌትነት ተስፋማርያም ተንቤን:- በቆላ ተንቤን የሚገኘው የጁንታው የመ ጨረሻ ምሽግ በሀገር መከላከያ ሰራዊት በሶስት አቅጣጫ ተከቦ እርምጃ እየተወሰደበት እንደሚገኝ ተገለጸ። በቆላ ተምቤን የጁንታውን አመራር ለመያዝ የሚ ደረገውን ዘመቻ እየመሩ ያሉት በመከላከያ ሰራዊት የ31ኛ ክፍለ ጦር ምክትል ኦፕሬሽን አዛዥ ኮሎኔል ሻምበል በየነ እንደገለጹት፤ ከመቀሌ ቢሮው ለቆ የሸሸው የጁንታው አመራር በቆላ ተንቤን የመጨረሻ ምሽጉ ላይ ይገኛል። የመከላከያ ሰራዊትን የጁንታውን የመጨረሻ ምሽግ በተለያዩ አቅጣጫዎች ከቦ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል። ቆላተምቤን ወርቅ አምባ ከተማ ላይ የመጨረሻ ምሽጉን ያደረገውን የጁንታውን አመራር ለመያዝ አሊያም ለመደምሰስ መከላከያ ሰራዊት በመረጃ የተደገፈ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል ያሉት ኮሎኔል ሻምበል፤ ከአድዋ መስመር የመጣው ሰራዊት አካባቢውን ለመቆጣጠር እየገሰገሰ እንደሆነ እና ከሃውዜን እና መቀሌ መስመር ያለውም ወደ ቦታው በከፍተኛ ወኔ እየተጠጋ እንደሚገኝ ገልጸዋል። መከላከያ ሰራዊቱ ወርህ የሚባል ትልቅ ወንዝ መሻገር አይችልም በሚል አካባቢ የጁንታው ታጣቂዎች ማጥቃት ቢፈጽምም ሰራዊቱ ወደ አካባቢው ተጠግቶ ከወርቅ አምባ 10 ኪሎ ሜትር ላይ እንደሚገኝ አመልክተዋል። እንደ ኮሎኔል ሻምበል ከሆነ፤ በቆላ ተምቤን ወርቅ አምባ አካባቢ የመሸገው ጁንታው በምድር ከሚወሰድበት እርምጃ ባለፈ በአየር ጭምር እርምጃ ተወስዷል። በአየርና በድሮን አውሮፕላኖች በተወሰደ እርምጃ ወርቅ አምባ አካባቢ ሲንቀሳቀሱ ከነበሩ ሰባት የጁንታው ዘመናዊ ተሽከርካሪዎች ወድመዋል። በአካባቢው የነበሩ የጁንታው የቀድሞ ባለስልጣናትም በየአቅጣጫው ተበታትነዋል። <<ከአጥፊው ቡድን ጋር በርካታ ሀገር የከዱ ጄኔራሎች፤ የፖለቲካ እና የአስተዳደር አመራሮች እንደሚገኙም በቂ መረጃ ተገኝቷል>> ያሉት ኮሎኔል ሻምበል፤ ከተገኘው መረጃም ከጁንታው አመራር ከዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል አንስቶ እነ ጌታቸው ረዳ፣ ስዩም መስፍን፤ አቦይ ስብሃት እና በርካታ የአጥፊው ቡድን አባላት በአካባቢው እንደሚገኙ እንደታወቀ ገልጸዋል። ከመከላከያ የከዱ ጄኔራል ከበደ እና ጄኔራል ጆን የሚባሉ ተፈላጊዎች የጁንታውን አመራር ሽፋን በመስጠት ላይ መሆናቸውን አመልክተው፣ሰራዊቱ የጁንታው ዋና አመራርና አጃቢዎችን እንዲሁም የኮማንዶ አባላቱን በብረት ለበስ ከቦ እንደሚገኙም ገልጸዋል።የጁንታው ቡድን ከአመራር እስከ ደጋፊ ሃይሉን አሰባስቦ ቆላ ተምቤን መገኘቱን የገለጹት የግንባሩ አዛዥ፤ በአካባቢው ኮማንዶዎቹን በማሰማራት አይደፈርም በሚል ሲኩራራበት የነበሩ 10 ዙር ምሽጎች በመከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር ከመግባታቸውም በላይ በአካባቢውም በቀንና ማታ ጭምር እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን አስታውቀዋል። የመከላከያ ሰራዊቱም የጁንታውን አመራር ከተቻለ ለመያዝ አሊያም ለመደምሰስ የሚያስችለውን እርምጃ በማካሄድ ላይ መሆኑን የተናገሩት ኮሎኔል ሻምበል፤ <<የጁንታው አመራር እና የመጨረሻ ቡድን ቀለብ፣ ውሃ እና ነዳጅ አልቆበታል። ስለሆነም በቅርብ ጊዜ በዝርዝር የተያዙ የጁንታው አመራር አባላትን እና ተበታተኖ የሚገኘውን ወንጀለኛ የመልቀም ሥራ ይከናወናል>> ብለዋል። የጁንታው አመራር የሚፈልጋቸው ከተሞችን ውጊያ እንዳይካሄድባቸው እየለቀቀ ከሄደ በኋላ ለምን ቆላ ተምቤን ላይ መሽጎ ተቀመጠ የሚለው ግልጽ እንዳልሆነ የተናገሩት ኮሎኔል ሻምበል፤ አድዋን አክሱምን እና መቀሌ ከተማ የህግ ማስከበር እርምጃ እንዳይካሄድባቸው እየለቀቀ መሬት ይዞ እንኳን ሳይተኩስ መውጣቱን ገልጸዋል። ሽሬ ላይ ደግሞ ውጊያ ገጥሞ ህዝብ ለማስጨረስ ቢፎክርም አልተሳካለትም። አሁን ላይ በተንቤን ውጊያ እንዲካሄድ የፈለገው ጁንታው ስልጣን ላይ በነበረበት ወቅት የተንቤን ህዝብ መብራት እንዳያገኝ እና በመሰረተ ልማት እንዳይጠቀም ሲያደርግ በመቆየቱና ህዝቡም ይህንን በተደጋጋሚ በግልጽ ይቃወም ስለነበር ህዝቡን ለጥቃት ለማጋለጥ ሊሆን እንደሚችል ማብራሪያ ሰጥተዋል። እንደ ኮሎኔል ሻምበል ከሆነ፤ የጁንታው አመራር አሁን ላይ በተንቤን በመመሸግ ፣ውጊያ እንዲካሄድ እና የተንቤን ህዝብ እንዲያልቅ ያለውን ፍላጎት በግልጽ አሳይቷል። መከላከያ ሰራዊቱ ግን ለይቶ በሚወስደው እርምጃ ህዝብን ከጥቃት በመከላከል የጁንታው መገኛዎችና መዳረሻን ዒላማ ባደረገ ሁኔታ በመረጃ የተደገፈ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል። ሰራዊቱ በሚወስደው እርምጃ የጁንታው ታጣቂ የነበሩ ወጣቶች ተይዘዋል። ከተያዙ ሰዎችም የሚገኙ ተጨማሪ መረጃዎችን በመያዝ የህግ ማስከበሩ ሥራ በተጠናከረ መንገድ እየተከናወነ ይገኛል ፤ የጁንታ አመራር በቅርቡ ለህግ ቀርቦ ፍርዱን እንዲያገኝ ይደረጋል ብለዋል።አዲስ ዘመን ህዳር 27/2013 ዓ. ም
https://www.press.et/Ama/?p=36796
489
0ሀገር አቀፍ ዜና
የኦነግ ሸኔ አባላትን ዕድሜ ለማሳጠር የጂ ፒ ኤስ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ እየዋለ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
December 6, 2020
73
ክፍለዮሐንስ አንበርብር ፊንፊኔ፡- በኦሮሚያ በየጊዜው እያጋጠመ ለሚ ገኘው የህይወትና ንብረት ውድመት በህወሓት ጁንታ እና ተላላኪዎቹ የሚፈፀም መሆኑንና ይህንንም ለማስወገድ ብሎም የቡድንን ዕድሜውን ለማሳጠር በ‹ጂ ፒ ኤስ› ቴክኖሎጂ የታገዘ ሥራ እያከናወነ መሆኑን የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ፖሊስ ኢንዶክተሬሽን መምሪያ አስታወቀ።የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ፖሊስ ኢንዶክተሬሽን መም ሪያ ኃላፊ ምክትል ኮማንደር እንዳለ ቁምላቸው ለበሪሳ ጋዜጣ እንደገለፁት፤ የህወሓት ጁንታ እና የኦነግ ሸኔን ሴራ ለማክሸፍና ዕድሜ ለማሳጠር ‹‹ጂ ፒ ኤስ›› ቴክኖሎጂ እየተጠቀመ መሆኑን አብራርተዋል። እነዚህ አካላት ዜጎችን ለምን እንደሚገድሉ እን ደማያውቁ በመጠቆም በህግ ቁጥጥር ሥር ለማዋልም በቴክኖሎጂ የተደገፈ ሥራ መጀመሩን ጠቁመዋል። ቴክኖሎጂው እነዚህ አካላት ያሉበትን ቦታ ለመከታተል የሚያስችል እንደሆነም አመልክተዋል።በዚህ ቴክኖሎጂ በመታገዝ የኦነግ ሸኔ አባላት በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆናቸውን የተናገሩት ኃላ ፊው፤ በሠላማዊ መንገድ እጅ ለማይሰጡና የኃይል አማራጭ ለመጠቀም የሚሞክሩት ላይ ደግሞ እርምጃ እየተወሰደባቸው እንደሆነ አስታውቀዋል ። እነዚህ ጸረ ሠላም አካላት አባ ቶርቤ በሚል ስያሜ የሚንቀሳቀሱ መሆኑን አመልክተው ፣ ኦሮሚያ ክልልን የግጭትና ጦር አውድማ ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ መቆየታቸውን ገልጸዋል። ሠላማዊ ዜጎችን መግደል ሥራቸው አድርገው መቆየታቸውንም አመልክተዋል። ማንኛውንም የፖለቲካ አመለካከት ያለው አካል በዴሞክራሲያዊ መንገድ የፖለቲካ አስተሳሰቡን ለህዝብ መሸጥ ይጠበቅበታል ያሉት ኮማንደር እንዳለ፤ ከዚህ ውጪ ሰላም በማደፍረስና ሠላማዊ ዜጎችን በመግደል ስኬታማ መሆን እንደማይቻል አስረድተዋል። የኦሮሚያ ፖሊስም ከፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ የሆነና የዜጎችን ሠላም ለመጠበቅ የተቋቋመ ነው ያሉት ምክትል ኮማንደር ፣ በየትኘውም ሁኔታ የዜጎችን ሰላም ችግር ውስጥ የሚከቱ ተግባራትን አይታገስም ብለዋል። መንግሥትም ለዜጎች ሠላምና ደህንነት መቃወስ ምክንያት የሆኑ እንደ የህወሓት ጁንታና ፣ አባ ቶርቤ፣ ሸኔ እና ሌሎችንም ወደ ህግ ለማቅረብ ከመቼውም በላይ ጠንካራ ሥራ እየሰራ መሆኑን አረጋግጠዋል።ቀደም ሲል እነዚህን አካላት በህግ ጥላ ሥር ሆነው እንዲዳኙ የተለያዩ ሥራዎች ቢሰሩም አሁንም ዜጎችን እየገደሉ በመሆኑ በቴክኖሎጂ በመታገዝ የማጽዳት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል። በአሁኑ ወቅት የክልሉ የፖሊስ ኃይል በቴክኖ ሎጂው በመታገዝ የተላላኪዎችን ሁኔታ በማወቅ ብሎም የሚንቀሳቀሱበት አካባቢ በመከታተል ወደ ህግ ለማቅረብ አስፈላጊውን ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል። እነዚህ አካላት ዜጎችን ከመግደል በዘለለ የንግድ እንቅስቃሴ በማስተጓጎል ሽብር ለመፍጠር እየተሯሯጡ መሆኑን ጠቁመው፣ የነዚህን አካላት ዕድሜ ለማሳጠር በትጋት እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል ። ዜጎችም ከኦሮሚያ ልዩ ኃይል ፖሊስ ጎን በመቆም እነዚህን ፀረ ሰላም አካላት እንዲፋለም ጥሪ አቅርበዋል፤ ፖሊስ ከመቼውም በላይ ሰላም ለማስከበር ዝግጁ መሆኑን ምክትል ኮማንደር እንዳለ አረጋግጠዋል።አዲስ ዘመን ህዳር 27/2013 ዓ. ም
https://www.press.et/Ama/?p=36804
323
0ሀገር አቀፍ ዜና
“የህወሓት ጁንታ ደቡብ ሱዳን የተረጋጋች ሀገር እንዳትሆን ሲሰራ ነበር” – አምባሳደር ጀምስ ፒታ ሞርጋን በኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን አምባሳደር
ሀገር አቀፍ ዜና
December 6, 2020
15
በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፦ የህወሓት ጁንታ ደቡብ ሱዳን የተረጋጋች ሀገር እንዳትሆን ሲሰራ መቆየቱን በኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን አምባሳደር ጀምስ ፒታ ሞርጋን አስታወቁ ።በኢትዮጵያ እና በደቡብ ሱዳን መካከል በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ እንዲሁም በህዝብ ለህዝብ ያለው ግንኙነት ጠንካራ ደረጃ ላይ መድረሱንም ገለጹ።አምባሳደር ጀምስ ፒታ ሞርጋን በተለይ ለኢትዮያን ሄራልድ እንደገለፁት፣ የህወሓት ጁንታ አባል አንዱ በሆኑት አምባሳደር ስዩም መስፍን ዋና አደራዳሪነት ሲካሄድ የነበረው የደቡብ ሱዳን የሰላም ድርድር የጁንታው ቡድን ለሀገሪቱ ፖለቲካ ፓርቲዎች በነበረው አድሏዊ አቋም የሚጠበቀውን ውጤት ማምጣት አልቻ ለም።በፈረንጆቹ 2015 የተፈረመው የሰላም ስምምነት ተግባራዊ መሆን አለመቻሉን ያስታወሱት አምባሳደሩ፣ ለዚህ አምባሳደር ስዩም በወቅቱ ያሳዩት ወገንተኝነት ምክንያት እንደነበር አመልክተዋል።በህወሓት ጁንታ አባል ዋና አደራዳሪነት ሲካሄድ የነበረው የደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነትም አስፈላጊውን ውጤት ሳያመጣ ቀርቷልም ብለዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ባሳለፍነው ሰኞ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረጉትንግግር የህወሓት ጁንታ በደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት ሂደት ላይ የነበረውን አሉታዊ ሚና ይፋ ማድረጋቸው እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል።ቡድኑ በሰላም ድርድሩ ላይ የነበረው የተዛባ አመለካከት ረጅም ጊዜ ያስቆጠረውን የሁለቱን ወዳጅ ሀገራት ግንኙነት የጎዳ መሆኑንም ጠቁመዋል።አሁን ላይ ደቡብ ሱዳን በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አስተዳደር ትተማመናለች ያሉት አምባሳደሩ፣ ኢትዮጵያ የውስጥ ችግሯን በራሷ መንገድ በመፍታት ወደ ልማት ሥራዎች እንደምትመለስ እምነታቸውን ገልፀዋል።በኢትዮጵያ እና በደቡብ ሱዳን መካከል በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ እንዲሁም በህዝብ ለህዝብ ያለው ግንኙነት ጠንካራ ደረጃ ላይ መድረሱንም አስታውቀዋል።“ኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን ዲፕሎማቶች ከሀገሯ እንዲወጡ አዘዘች”በሚል በማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ የተሰራጨውን መረጃ፣ በደቡብ ሱዳን ውስጥ በሚንቀሳቀሱ ተቀናቃኝ የፖለቲካ ሀይሎች የተፈበረከ መሆኑን አመልክተዋል። በሀገራት መካከል ውጥረት እንዲነግስ ካላቸው ፍላጎት የመነጨ እንደሆነም ገልጸዋል።አዲስ ዘመን ህዳር 27/2013 ዓ. ም
https://www.press.et/Ama/?p=36802
222
0ሀገር አቀፍ ዜና
አረንጓዴው ጎርፍ በሌላ የታሪክ ምዕራፍ
ስፖርት
September 4, 2019
35
ኢትዮጵያ እግራቸው እንደ አቦሸማኔ የሚወረወር፣ እንደ ንሥር የሚበሩ፣ ጽናትንና ብርታትን ከአልሸነፍም ባይነት እልህ ጋር ያዋደዱ፣ ተስማምተው እየተማከሩ ከኋላና ከፊት አገርና ህዝብን አስከትለው የሚሮጡ፣ የርቀት መጠን ለክተው ሳይጠበቅ የሚፈተለኩ፣ ለሰንደቅ ዓላማና ለሕዝብ ፍቅር የተገዙ አትሌቶች እናት ናት። ከአገሩ አልፎ ለመላው አፍሪካ ህዝቦች የአሸናፊነት ተምሳሌት ሆኖ በታሪክ የሚዘከረው ሻምበል አበበ ቢቂላና ማሞ ወልዴን ጨምሮ ሌሎችም አትሌቶች፣ በአህጉራዊና ዓለም ዓቀፋዊ የአትሌቲክስ ውድድሮች ላይ ውጤታማ በመሆን ከወርቅ እስከ ነሐስ በማምጣት፣ ለሚወዷት አገራቸውና ሕዝባቸው ልዕልና እና ክብር የአሸናፊነት ዓርማ ሆነዋል። ሰንደቅ አላማዋንም በዓለም አደባባይ በተደጋጋሚ ከፍ አድርገው አውለብልበዋል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ታሪክ ሲዘከርም በርካታ አይረሴ፣ ደማቅና ወርቃማ ዘመናትን ማስታወስ አይከብድም። ከሁሉ በላይ ግን ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች የማንኛውንም አገር አትሌት ጣልቃ ሳያስገቡ በሚያሳዩት የአጨራረስ ብቃትና ውጤት ያገኙት ‹‹አረንጓዴው ጎርፍ›› (ዘ ግሪን ፍለድ) መጠሪያና ታሪክ ቀድሞ የሚታወስና በአብዛኞች ዘንድ መቼም የማይዘነጋ ነው። ይህን ሁነት የተመለከቱ ታላላቅ የዓለም መገናኛ ብዙኃንም በአረንጓዴው መለያ መላውን ዓለም ያስደመሙት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች እውነትም ‹‹አረንጓዴው ጎርፍ›› እንጂ ለገድላቸው ሌላ ተቀጽላ እንደማይገልጻቸው ሲናገሩም ተደምጠዋል። ከግል ይልቅ የቡድን ሥራ በትልቁ የሚንፀባረቅበት፣ አንዱ በሌላው ተንኮልና ሸፍጥ የማይሰራበት፣ እውነተኛ ወንድማማችነትና አጋርነት የሚስተዋልበት የአገሪቱ አትሌቶች ‹‹አረንጓዴው ጎርፍ›› የሚል ስያሜ ከ1970 እስከ 1980ዎቹ መጀመሪያ በነበሩት የውድድር ዓመታት ውስጥ መነሻውን አሃዱ ስለማለቱም መረጃዎች ይጠቁማሉ። በዋናነት ለአረንጓዴው ጎርፍ ስያሜ ትልቁን ውለታ ከዋሉት መካከልም የሞስኮ ኦሊምፒክ በአምስትና አስር ሺ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ የድርብ ድል ባለቤቱ ማርሽ ቀያሪው ‹‹ይፍጠር ዘ ሺፍተር›› ሻምበል ምሩፅ ይፍጠር፣ በዚሁ የሞስኮ ኦሊምፒክ በአስር ሺ ሜትር የነሐስ ሜዳሊያ ያስመዘገበው መሐመድ ከድር፣ ሻምበል እሸቱ ቱራ፣ ከበደ ባልቻ፣ ደረጀ ነዲ፣ ዮሐንስ መሐመድ፣ ብርሃኑ ግርማ፣ ግርማ ወለደሃናን ጨምሮ ሌሎችም ድንቅ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የጎላውን ስፍራ እንደሚዙ አንዳንድ ባለሙያዎች መረጃዎችን ጠቅሰው ይጠቁማሉ። የአረንጓዴው ጎርፍ ይበልጡን ጎሎቶ የወጣው ግን በታላላቅ አትሌቲክስ መድረክ እ.ኤ.አ በ2003 በፈረንሳይ ፓሪስ በተካሄደው ሻምፒዮና ላይ ነው። በዚህ መድረክ በአስር ሺ ሜትር ወንዶች ቀነኒሳ በቀለ፣ ኃይሌ ገብረ ስላሴ እና ስለሺ ስህን በድንቅ የቡድን ሥራ ዓለምን ባስደመመ መከባበርና የወንድማማች ፍቅር የማንኛውንም አገር አትሌት ጣልቃ ሳያስገቡ ተከታትለው በመግባት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ የአረጓዴው ጎርፍ ታሪክን ይበልጥ ማጉላታቸው ይታወሳል። እ.ኤ.አ በ2005ቱ ሄልሲንኪ በተካሄደው ሻምፒዮና ደግሞ አረንጓዴ ጎርፉ በወንዶች ብቻ ሳይሆን በሴቶችም ቢሆን ቀጣይ ስለመሆኑ ያስመሰከረና የኢትዮጵያም አትሌቲክስ ስፖርት ሥምና ታሪክ እንዲታወስ የላቀ ሚና ተጫውቷል። በዚሁ መድረክ በሴቶች አምስት ሺ ሜትር በጥሩነሽ ዲባባ፣ መሰረት ደፋር እና እጅጋየሁ ዲባባ አማካኝነት የአረንጓዴው ጎርፍ ስም ይበልጡን ደምቋል። ከዚህ የብርቅ እንስት አትሌቶቻችን አኩሪ ታሪካ በኋላ የአረንጓዴው ጎርፍ ገድል መልሶ ለማግኘት አምስት ሻምፒዮናዎች መጠበቅ ግድ ያለው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ከዓመታት በኋላም በቤጅንጉ ሻምፒዮና በአልማዝ አያና፣ ሰንበሬ ተፈሪ እና ገንዘቤ ዲባባ አማካኝነት ዳግም አሳክቶታል። በቤጂንግ 15ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ማጠናቀቂያ ላይ በተካሄደው የአምስት ሺ ሜትር ሴቶች ፍጻሜ አልማዝ አያና 14 ደቂቃ:26:83 የሆነ ሰዓት የወርቅ፣ ሰንበሬ ተፈሪ 14:44:07 በሆነ ሰዓት፣ የብር እንዲሁም ገንዘቤ ዲባባ 14:44:14 በሆነ ሰዓት የነሐስ ሜዳሊያ ለሀገራቸው አስገኝተዋል። በጥሩነሽ ዲባባ፣ መሰረት ደፋር እና እጅጋየሁ ዲባባ አሃዱ የተባለው ‹‹አረንጓዴው ጎርፍ››ን የእንስት አትልቶቻችን ታሪክ በማስቀጠል አገሪቱ በድንቅ ክህሎትና አቅም የካበቱ በድላቸውም የሰንደቅ ዓላማቸውንና የሕዝባቸውን ልዕልና ከፍ ያደረጉ አትሌቶች ሃብታም ስለመሆኗ አስመስከረዋል። በዚሁ መድረክ አልማዝ ያስመዘገበችው ሰዓት የሻምፒዮናው ክብረ ወሰን ሆኖ መመዝገቡ ደግም ድሉን ይበልጥ ጣፋጭ ያደርገዋል። ባለፉት ሳምንት በሞሮኮ ራባት በተካሄደው የ12ኛው በመላ አፍሪካ ጨዋታዎች አትሌቶች የማንኛውንም አገር አትሌት ጣልቃ ሳያስገቡ በድንቅ የአጨራረስ ብቃትና ውጤት ‹‹አረንጓዴው ጎርፍ›› (ዘ ግሪን ፍለድ) ታሪክ በአፍሪካ ምድር ላይ ደግመውታል። በዚህ መድረክ በሴቶች አስር ሺ ሜትር ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ ሶስት ተከታትለው በመግባት በበላይነት አጠናቀዋል። አትሌት ፀሐይ ገመቹ 31 ደቂቃ ከ56 ሰከንድ ከ92 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ለሀገሯ የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝታለች። አትሌት ዘይነባ ይመር 31 ደቂቃ ከ57 ሰከንድ ከ95 ማይክሮ ሰከንድ ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ ስታስገኝ፤ አትሌት ደራ ዲዳ 31 ደቂቃ ከ58 ሰከንድ ከ78 ማይክሮ ሰከንድ ሶስተኛ ሆና በመግባት የነሐስ ሜዳሊያ አስገኝታለች። በዚህ መድረክ የአረንጓዴውን ጎርፍ ታሪክ በአንድ የውድድር ርቀት ብቻም አልተገደበም። እንደ አስር ሺ ሜትር ሁሉ በሴቶቹ ግማሽ ማራቶን ውድድር ከአንድ እስከ ሶስት ተከታትለው ገብተዋል። አትሌቶቹ ፍልሚያውን በበላይነት ከማጠናቀቅ በላይ በአንድ መድረክ በሁለት የርቀት አይነቶች የአረንጓዴውን ጎርፍ እንዲፈስ በማድረግ አዲስ ታሪክን ሰርተዋል። አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው 1ሰአት፡10 ሰከንድ.26ማይክሮ ሰከንድ ወርቅ፣ አትሌት ደጊቱ አዝመራው 1ሰአት፡ 10 ሰከንድ 31ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ ስታስገኝ፣ አትሌት መሠረት በለጠ 1ሰአት፡12 ሰከንድ.08 ማይክሮ ሰከንድ ሶስተኛ ሆና በመግባት የነሐስ ሜዳሊያ አስገኝታለች። ‹‹አረንጓዴው ጎርፍ›› ከአሸናፊነትም በላይ ለአሁኑ የአትሌቲክስ ተዋንያን በአስተማሪነቱ ትልቅ ታሪክ ያለው ሆኖ የዘለቀ ሲሆን፣ ተተኪዎችም በተለያዩ ታላላቅ አትሌቲክስ መድረኮች እያስቀጠሉት ስያሜውም ለኢትዮጵያውያን አትሌቶች ልዩ መጠሪያቸው ሆኖ እንደትናንቱ ዛሬም ቀጥሏል።አዲስ ዘመን ነሐሴ 28/2011 ታምራት ተስፋዬ
https://www.press.et/Ama/?p=17298
660
2ስፖርት
የልኡካን ቡድን አቀባበል ተደረገለት
ስፖርት
September 4, 2019
28
በሞሮኮ አስተናጋጅነት በተካሄደው 12ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች በ13 የስፖርት ዓይነቶች የተሳተፈው የኢትዮጵያ የስፖርት ልኡካን ቡድን በአዲስ አበባ ስታዲየም ይፋዊ አቀባበል ተደረገለት። ከትናንት በስቲያ አዲስ አበባ የገባው የልዑካን ቡድኑ ትናንት ይፋዊ አቀባበል በተደረገለት ወቅት በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ስፖርት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ጌታቸው ባልቻ፣ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ እና ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተውጣጡ አካላት ተገኝተዋል። 250 አባላትን የያዘው የስፖርት ልኡካን ቡድኑ በሞሮኮው መድረክ ስድስት የወርቅ፣ አምስት የብር እና 12 የነሐስ ሜዳሊያዎች በማስመዝገብ ከአፍሪካ ዘጠነኛ ደረጃ ይዞ ማጠናቀቁ ይታወሳል። በዚህ መድረክ በሴቶች አስር ሺ ሜትር ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ ሶስት ተከታትለው በመግባት በበላይነት አጠናቀዋል። አትሌት ፀሐይ ገመቹ 31 ደቂቃ ከ56 ሰከንድ ከ92 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ለሀገሯ የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝታለች። አትሌት ዘይነባ ይመር 31 ደቂቃ ከ57 ሰከንድ ከ95 ማይክሮ ሰከንድ ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ ስታስገኝ፤ አትሌት ደራ ዲዳ 31 ደቂቃ ከ58 ሰከንድ ከ78 ማይክሮ ሰከንድ ሶስተኛ ሆና በመግባት የነሐስ ሜዳሊያ አስገኝታለች። በሴቶች ግማሽ ማራቶን ውድድር አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው 1፡10.26 በመግባት የወርቅ፣ አትሌት ደጊቱ አዝመራው 1፡10.31 የብር ሜዳሊያ፣ አትሌት መሰረት በለጠ 1፡12.08 የነሀስ ሜዳሊያ በማምጣት አረንጓዴውን ጎርፍ አሳይተዋል። በ800 ሜትር ርቀትም አትሌት ሂሩት መሸሻ 2፡ 03:16 በሆነ ጊዜ የወርቅ ሜዳሊያ፣ በ10 ሺ ሜትር ውድድር አትሌት ብርሃኑ ወንድሙ 27፡56.81 በመግባት የወርቅ ሜዳሊያ ፣አትሌት ጀማል ይመር 27፡59.02 በመግባት የነሐስ ሜዳሊያ አስገኝተዋል በ3000 ሜትር መሰናክል የሴቶች ሩጫ አትሌት መቅደስ አበበ 9፡35.18 በሆነ ጊዜ በመግባት 1ኛ በመሆን ወርቅ ሜዳሊያ፣ አትሌት ወይንሸት አንሳ 9፡38.56 በሆነ ጊዜ በመግባት የነሐስ ሜዳሊያ አግኝታለች።በሴቶች 10ሺሜትር ውድድር አትሌት ጸሐይ ገመቹ 31፡56.92 በመግባት የወርቅ ሜዳሊያ ፣በአትሌት ዘይነባ ይመር 31፡57.95 በሆነ ጊዜ በመግባት የብር ሜዳሊያ፣በአትሌት ደራ ዲዳ በ31፡ 58.78 በሆነ ጊዜ በመግባት የነሐስ ሜዳሊያ፣ ለአገራቸው አምጥተዋል። በወንዶች በ3000 ሜትር ውድድር አትሌት ጌትነት ዋሌ 8፡14.06 በመግባት የብር ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆኗል። በ5000 ሜ የሴቶች ውድድር ደግሞ በአትሌት ሃዊ ፈይሳ የብር ሜዳሊያ ፣በአትሌት አለሚቱ ታሪኩ የነሐስ ሜዳሊያ ተገኝቷል።በወንዶች የ20 ኪሎ ሜትር የእርምጃ ውድድር በአትሌት ዮሐንስ አልጋው 1፡22.50 የብር ሜዳሊያ አሁንም በሴቶች የ20ኪሎ ሜትር እርምጃ ውድድር አትሌት የኋልዬ በለጠው የነሐስ ሜዳሊያ ስታመጣ፣ በ1ሺ500 የሴቶች ውድድር አትሌት ለምለም_ሀይሉ በተመሳሳይ የነሐስ ሜዳሊያ አግኝታለች።በሴቶች ከፍታ ዝላይ አትሌት አርያት ዲቦ 1ነጥብ81 ሜትር በመዝለል የነሐስ ሜዳሊያ ማግኘት ችላለች። የወርልድ ቴኳንዶ ስፖርት ውድድርን በተመለከተ በወንዶች ውድድር በ63 ኪሎ ግራም በአትሌት ታሪኩ ግርማ ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች። በ54 ኪሎ ግራም በአትሌት ሰለሞን ቱፋ የነሐስ ሜዳሊያ፣ በ53 ኪሎ ግራም በአትሌት ጸባኦት ጎሳዬ የነሐስ ሜዳሊያ ማግኘት ተችሏል። በብስክሌት ስፖርት ውድድር በሴቶች ቡድን የነሐስ ሜዳሊያ ተገኝቷል። በቦክስ ስፖርትም በ52 ኪሎ ግራም አትሌት ዳዊት በቀለ የነሐስ ሜዳሊያ አስገኝታለች። በ12ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች 54 ሀገሮች በ26 የስፖርት አይነት 6ሺ አትሌቶች ተሳትፈውበታል።አዲስ ዘመን ነሐሴ 28/2011
https://www.press.et/Ama/?p=17306
397
2ስፖርት
ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ አዲስ የካፍ ማዕረግን አገኙ
ስፖርት
August 22, 2019
26
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ የካፍ ኤሊት ኮንቲኔንታል ኢንስትራክተር ማዕረግን አገኙ። ኢንስትራክተር አብርሃም የአፍሪካ እግር ኳስ ማህበር ካፍ ከሶስት ወር በፊት በሞሮኮ ራባት አዘጋጅቶት በነበረው የኤሊት ኢንስትራክተሮች ስልጠና ላይ መሳተፋቸው ተገልጿል። በካፍ ሲሰጣቸው የነበረውን ስልጠና እና ምዘና በውጤታማነት በማጠናቀቃቸው ካፍ ኤሊት ኮንቲኔንታል ኢንስትራክተር የሚል ማዕረግ ሊሰጣቸው መቻሉን ተቋሙ በላከው ደብዳቤ ማረጋገጡን ታውቋል። ካፍ ኢንስትራክተሮችን በሶስት ደረጃ የሚከፍል ሲሆን እነዚሁም ሎካል፣ሪጅናል እና ኤሊት በሚል የሚመድባቸው መሆኑ ተገልጿል። በዚህ መሰረት ኢንስትራክተር አብርሃም የመጨረሻውን የካፍ የኢንስትራክተሮችን ማዕረግ ነው ያገኙት ተብሏል። ኤሊት ኮንቲኔንታል ኢንስትራክተር ማዕረግ የሚሰጣቸው ኢንስትራክተሮች ማዕረጉን ለሁለት ዓመታት የሚቆይ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤በዚህ ጊዜ በአህጉር ደረጃ የተለያዩ ስልጠናዎቸን እንዲሰጡ የሚያደርግ መሆኑ ታውቋል። አሰልጣኞቹ ቢያንስ ለሶስት ጊዜያት ካፍ በሚያዘጋጃቸው ስልጠናዎች ላይ ተሳታፊ ሆነው ማሰልጠን ይጠበቅባቸዋል። በመቀጠል ከሁለት ዓመት በኋላ ጊዜው የሚጠናቀቅ መሆኑን ተከትሎ ሌላ ምዘና መውሰድ እንደሚገባቸው ካፍ በደብዳቤው ላይ አስረድቷል። ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ ስልጠናዎችን እንዲሰጡ በካፍ በተመደቡበት ማንኛውም ወቅት የጉዞ የሆቴል እና ሌሎች አስፈላጊ ወጪዎችን ካፍ እንደሚሸፍን በላከው ደብዳቤ አረጋግጧል። ካፍ ከዘመኑ እግር ኳስ አሰለጣጠን ጋር እንዲጓዙ ብሎም በስልጠና ተሳታፊ እንዲሆኑ በየትኛውም ጊዜ እና ወቅት ስልጠና እንዲሰጡ ምደባ ሊያካሂድ እንደሚችል ገልጾ፤ ዝግጁ መሆን እንደሚገባቸውም ማስገንዘቡን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በፌስቡክ ገጹ አስነብቧል። ኢንስትራክተር አብርሃም በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ የታደሙት፣ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ከጨዋታው አስቀድሞ አሥራ አምስት አባላትን ባካተተው የ2019ኙ የአፍሪካ ዋንጫ የቴክኒክ ጥናት ቡድን ሆነው መካተታቸው ይታወቃል፡ ፡ ኢንስትራክተር አብርሃምን ጨምሮ ለአፍሪካ አገሮች የብሔራዊ ቡድኖች ዋና አሠልጣኞች፣ የቴክኒክ ቡድኑን ቢቀላቀሉ ‹‹ይመጥናሉ አይመጥኑም›› የሚለውን መለየት የኦንላይን ፈተና ከወሰዱ ባለሙያዎች መካከል ብቁ ናቸው በማለት ስለመረጣቸው የዋሊያዎቹ ዋና አሠልጣኝ በግብፁ የአፍሪካ ዋንጫ ለመሳተፍ እንደበቁ ይታወሳል፡፡አዲስ ዘመን ነሀሴ 16/2011 ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=16516
247
2ስፖርት
አትሌቱ ቀዳሚ ሆኖ የገባበት ሰአት በዓለም ክብረ ወሰንነት ተመዘገበ
ስፖርት
August 20, 2019
20
ኢትዮጵያዊው አትሌት ሳሙኤል ተፈራ የካቲት 9 ቀን 2011 ዓ.ም በእንግሊዝ በርሚንግሃም ከተማ በተካሄደ የቤት ውስጥ የአትሌቲክስ ውድድር በ1 ሺህ 500 ሜትር ውድድር ቀዳሚ ሆኖ የገባበት 3 ደቂቃ ከ31 ሴኮንድ ከ4 ማይክሮ ሴኮንድ የዓለም ክብረ ወሰን በመሆን በዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ተመዘገበ። የ1500 ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር ክብረ ወሰን በሞሮኳዊው አትሌት ሂሻም አልገሩሽ እአአ ከ1997 አንስቶ ተይዞ የቆየ ሲሆን፣ ይህን 3 ደቂቃ፡ 31 ሴኮንድ፡18 ማይክሮ ሴኮንድ ክብረ ወሰን 19 አመቱ ኢትዮጵያዊ አትሌት በ14 ማይክሮ ሴኮንዶች ማሻሻል ችሏል። ዮሚፍ በዚህ ውድድር 3 ደቂቃ 31 ሴኮንድ፡ 58 ማይክሮ ሴኮንድ በመግባት የግሉን ምርጥ ሰዓት ማስመዝገብ ችሏል። አትሌት ሳሙኤል ውድድሩን ሲያሸንፍ የገባበት ጊዜም በርቀቱ የዓለም ክብረ ወሰንን እንዲጨብጥ አድርጎታል። ውድድሩን በማሸኘፉም 3 ሺህ ዶላር እንዲሁም ሪከርድ በመስበሩ 30 ሺህ ዶላር ተሸላሚ ለመሆን በቅቷል። አሸናፊነቱን ከተቀዳጀ በኋላም አትሌቱ በሰጠው አስተያት ‹‹በጣም ደስተኛ ነኝ፤ ደስታዬ ይሄ ነው ለማለት ይከብደኛል፤ ወደዚህ ውድድር የገባሁት በግፊት እንጂ የራሴ ሃሳብ ኖሮኝ አይደለም፤ የፈጣሪ እርዳታ ነው›› በማለት ለመገናኛ ብዙሃን ተናግሯል። በተመሳሳይ ኢትዮጵያዊቷና ለኔዘርላንድስ የምትሮጠው ሲፋን ሃሰን በአይኤኤፍ የዳይመንድ ሊግ አንዱን ማይል ውድድር ሞናኮ ላይ 4 ደቂቃ፡ 12 ሴኮንድ፡ 33 ማይክሮ ሴኮንድ በማጠናቀቅ ለ23 ዓመታት ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን የሰበረችበት ሰአትም መመዝገቡ ታውቋል። ይህ ክብረ ወሰንም እ.ኤ.አ. 1996 የኦሊምፒክ 800 ሜትር እና 1 ሺ 500 ሜትር ሻምፒዮን በሆነችው ሩሲያዊት ሲቪትላና ማስተርኮቫ ተይዞ የቆየ ነበር።አዲስ ዘመን ነሀሴ 14/2011
https://www.press.et/Ama/?p=16422
205
2ስፖርት
በመላ አፍሪካ ጨዋታዎች የመጀመሪያው ሜዳሊያ
ስፖርት
August 23, 2019
21
አስራ ሁለተኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች በሞሮኮ አስተናጋጅነት ከተጀመረ ቀናቶችን አስቆጥሯል። ውድድሩ ማክሰኞ እለት በይፋ ከተጀመረ አንስቶ በተለያዩ ስፖርቶች የማጣሪያ ፍልሚያዎች የተከናወኑ ሲሆን፤ በርካታ አገራት ሜዳሊያ እየሰበሰቡ ይገኛሉ፡፡ ኢትዮጵያም ከትናንት በስቲያ ምሽት በሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ መግባት የቻለችበትን ውጤት በወርልድ ቴኳንዶ ስፖርት አስመዝግባለች፡፡ የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ሰልጣኝ የነበረችው ጸባዖት ጎሳዬ በወርልድ ቴኳንዶ ከ51- 53 ኪሎ ግራም ተወዳድራ የመጀመሪያውን የነሐስ ሜዳልያ ለአገሯ ማስመዝገብ ችላለች፡፡ ጸባዖት ነሐሴ 15 ቀን 2011 ዓ.ም. በውድድሩ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዋን ያደረገችው ከዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኦፍ ኮንጎ አቻዋ ሙካ ማሴሌ ግሎዲ ጋር ሲሆን፤ ጨዋታውን በሰፊ ብልጫ 29 ለ 9 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ማለፍ ችላለች፡፡ በግማሽ ፍፃሜው ውድድር በናይጄሪያዋ ቺናዙም ሩት 14 ለ 10 ተሸንፋ ወደ ሩብ ፍፃሜው ሳታልፍ የቀረች ቢሆንም፤ የቱኒዚያዋን ራህማ ቤን አሊን በማሸነፍ የነሀስ ሜዳልያ ተሸላሚ ሆናለች፡፡ ጸባዖት ጎሳዬ የተወለደችው እ.ኤ.አ. በ2002 ቁመቷ 1 ሜትር ከ71 ሴንቲ ሜትር፤ ክብደቷ ደግሞ 53 ኪሎ ግራም መሆኑን በስፍራው የሚገኙ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡ ኢትዮጵያ በዚህ ብቸኛ የነሐስ ሜዳሊያ እስከ ትናንት ድረስ በሃያ አራተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችላለች፡፡ በሴቶች 3 ለ 3 ቅርጫት ኳስ ውድድር ኢትዮጵያን ወክሎ ወደ ስፍራው ያቀናው ቡድን የመጀመሪያ የማጣሪያ ውድድሩን ማለፍ ያልቻለ ሲሆን፤ በውሃ ዋና ወንዶች የቀረቡ ተወዳዳሪዎችም ወደ ቀጣዩ ዙር ሳያልፉ መቅረታቸው ታውቋል፡፡ ኢትዮጵያ በውድድሩ በርካታ ሜዳሊያዎችን እንደምትሰበስብ የምትጠበቅበት የአትሌቲክስ ውድድር የፊታችን ሰኞ የሚጀመር ሲሆን፤ የአትሌቲክስ ልዑካኑ ቡድን ከትናንት በስቲያ ወደ ስፍራው አምርቷል፡፡ እስከ ትናንት በተካሄዱ ውድድሮች ግብፅ በተለያዩ ስፖርቶች በሰበሰበቻቸው ሰላሳ ሜዳሊያዎች ሰንጠረዡን በአንደኝነት እየመራች ሲሆን፤ አልጄሪያ በሃያ አንድ ሜዳሊያ ተከታዩን ደረጃ ይዛለች፡፡አዲስ ዘመን ነሀሴ 17/2011 ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=16589
234
2ስፖርት
ፋሲል ከነማ እና መቐለ ሰባ እንደርታ ለመልስ ጨዋታ ዝግጅታቸውን አጠናቅቀዋል
ስፖርት
August 23, 2019
27
 የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ልዑካን ቡድን በሀገር ውስጥ ዝግጅቱን አጠናቅቆ ትናንት ታንዛኒያ ዳሬ ሰላም ገብቷል። በትናንትናው እለትም በአዛም ኮምፕሌክስ ሜዳ ተመሳሳይነት ባለው የሰው ሰራሽ ሜዳ አንድ ሰዓት ከ30 ደቂቃ የቆየ ልምምዳቸውን በመስራት በተሳካ ሁኔታ ማጠናቀቃቸው ታውቋል። የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ በመሆን በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ውድድር ተሳታፊ ሆኖ የመጀመሪያውን የማጣሪያ ጨዋታ በሜዳው የባህርዳር አለም አቀፍ ስታዲየም አዛምን 1ለ0 ማሸነፉ ይታወሳል። ክለቡ የፊታችን እሁድ ነሃሴ 18 ቀን በአዛም ኮምፕሌክስ ስታዲየም የመልሱን ጨዋታ ለማከናወን በባህርዳር እና በአዲስ አበባ ለተከታታይ ሰባት ቀናት ዝግጅት በማድረግ በሀገር ውስጥ የመጨረሻ ልምምዳቸውን በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ከትናንት በስቲያ በመስራት ነበር በተሳካ ሁኔታ ማጠናቀቃቸው የተገለጸው። በአፄዎቹ የቡድን ስብስብ ቀደም ብሎ ጉዳት የደረሰበት አብዱራህማን ሙባረክ (ግሪዳው) በህክምና ላይ የሚገኝ ሲሆን ከአዛም ጋር የማሸነፊያዋን አንድ ጎል ያስቆጠረው በዛብህ መለዮ በጉዳት ሁለት ቀን ልምምዱን ያልሰራ ሲሆን በጨዋታው ላይ ጉዳት አጋጥሞት ከሜዳ የወጣው ሚካኤል ሳማኪ ከጉዳቱ አገግሞ ልምምዱን በመስራት ላይ ይገኛል። “ክለባችንን አዲስ የተቀላቀሉት እንየው ካሳሁን እና ኪሩቤል ሃይሉን ጨምሮ ሌሎች ሁሉም ተጫዋቾች በሙሉ ጤንነት ላይ ይገኛሉ” ሲል ክለቡ በመረጃው አስታውቋል። አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከክለቡ ጋር መለያየታቸውን ተከትሎ አዲሱ አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ከምክትል አሰልጣኞቻቸው እና ከሙሉ የኮችንግ ስታፉቸው ጋር በመሆን በታንዛኒያ ዳሬ ሰላም ከአዛም ጋር ለሚደረገው የመልስ ጨዋታ ትኩረት በማድረግ ክለቡ አሸንፎ ወደ ቀጣይ ዙር እንዲያልፍ የተሳካ ዝግጅት ማድረጋቸውም ተገልጿል። የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ልዑካን በትናንትናው እለት ማለትም ነሃሴ 15 ቀን 2011 ዓ.ም ከጠዋቱ 2 ሰዓት ከአዲስ አበባ ቦሌ አለምአቀፍ ኤርፖርት ወደ ታንዛኒያ ዳሬ ሰላም መጓዙም ለማወቅ ተችሏል ። በተመሳሳይ በርካታ ደጋፊዎች አርብ ነሃሴ 17 ቀን ክለባቸውን ለመደገፍ ወደ ስፍራው እንደሚጓዙ ክለቡ በመረጃው አስፍሯል። በተመሳሳይ በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ኢትዮጵያን ወክሎ የሚሳተፈው መቐለ ሰብዓ እንደርታ የማጣሪያ የመልስ ጨዋታውን እሁድ ነሐሴ 19 ቀን 2011 ዓ.ም በመቐለ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ከኢኳቶሪያል ጊኒው ክለብ ካኖ ስፖርት አካዳሚ ጋር ያደርጋል። ነሐሴ 4 ቀን ዓ.ም በተደረገው የመጀመሪያ ጨዋታ ካኖ ስፖርት አካዳሚ በጆሴ ፔድሮ ኦቢያንግና ጆሴ ፊደል ሲፒ ጎሎች መቐለ ሰብዓ እንደርታን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ማሸነፉ የሚታወስ ነው። የ2011 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊው መቐለ 70 እንደርታ በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ኢትዮጵያን የወከለ ክለብ እንደመሆኑ፤ በሜዳው ለሚያደርገው ጨዋታ ትልቅ ግምት ሰጥቶ እንደሚጫወት ይጠበቃል። በአሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ የሚመራው መቐለ 70 እንደርታ ከ15 ቀናት በፊት 2 ለ 1 በሆነ በጠባብ የግብ ክፍያ የደረሰበትን ሽንፈት በማካካስ ውጤቱን ለመቀልበስ ትኩረት ሰጥቶ ሲሰራ መቆየቱ ተገልጿል። በአሁኑ ወቅት ያሬድ ከበደ በጉዳት ምክንያት ከጨዋታ ውጪ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ፤ ከያሬድ በስተቀር ሁሉም ተጫዋቾች በመልካም ጤንነትና አቋም ላይ እንደሚገኙ ተነግሯል። ሁለገብ ተጫዋች እንደሆነ የሚነገርለት ያሬድ በተለይ በመጀመሪያው ጨዋታ ወቅት ጥሩ እንቅስቃሴ በማድረግ ረገድ አይነ ገብ እንደነበር በመጥቀስ የተጫዋቹ መጎዳት ክለቡን ሊጎዳው እንደሚችል በስጋት እየተነሳ ይገኛል።አዲስ ዘመን ነሀሴ 17/2011 ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=16574
404
2ስፖርት
አሰልጣኙ ለዛማሊክ ክለብ ፈረሙ
ስፖርት
August 20, 2019
16
ስማቸውን ከፈረሰኞቹ ጋር ሲያያዙ የቆዩት ሰርቢያዊው የኦርላንዶ ፓይሬትስ አሰልጣኝ ሰርዮቪች ሚሉቲን ሚቾ ለግብፁ ዛማሊክ መፈረማቸው ታወቀ። የደቡብ አፍሪካውያን ክለብ ኦርላንዶ ፓይሬትስ ላለፉት ሁለት ዓመታት ያሰለጠኑት ሰርዮቪች ሚሉቲን ሚቾ ባሳለፍነው ሳምንት በገዛ ፈቃዳቸው ከሃላፊነታቸው ማንሳታቸው ይታወሳል። ፖርቱጋላዊው ቫዝ ፒንቶን ተክተው የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብን የተረከቡት አሰልጣኝ ስቴዋርት ሀል ባሳለፍነው በግንቦት ወር በገዛ ፈቃዳቸው ስራ መልቀቃቸውን ተክትሎ ያለ ዋና አሰልጣኝ ወራትን ያስቆጠሩት ፈረሰኞቹም ሚቾን ዳግም በመቅጠር ፍላጎት እንዳላቸው ሲነገር ቆይቷል። በቅዱስ ጊዮርጊስ ቆይታቸው ለአምስት ዓመታት የሊጉን ዋንጫ ማንሳት የቻሉት አሰልጣኙ በሱዳኑ አል ሂላል ኦምዱርማን፣ በቱኒዚያው ያንግ አፍሪካ፣ በዩጋንዳው ቪላ እንዲሁም በዩጋንዳ ብሔራዊ ቡድን ጥሩ ጊዜያት አሳልፈዋል። ኡጋንዳ በጋቦኑ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ ከምድብ ሳታልፍ ብትመለስም በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ለታላቁ አፍሪካ መድረከ ለመብቃት የአሰልጣኙ ሚና የገዘፈ ነው። እኤአ ከ2011 እስከ 2013 የሩዋዳን ብሄራዊ ቡድን እንዲሁም የዩጎዝላቪውን ከ20 አመት በታች ዋና አሰልጣኝ ሆነውም ሰርተዋል። የዘንድሮውን የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ያነሳው ዛማሊክ ሲዊዘርላዳዊውን ክርሲቲን ክሮስ ካሰናበተ በኋላ አዲስ አስልጣኝ ለመቅጠር ሁነኛ የሚለውን ሰው ሲፈልግ ቆይታል። በአወዛጋቢ አስተያየታቸውና አስገራሚ ውሳኔዎቻቸው የሚታወቁትና እእአ በ2014 የክለቡ ፕሬዚዳንት ሆነው የተሾሙት ሞርታዳ መንሱር አዲስ አሰልጣኝ መሾማቸውን አሳውቀዋል። አሰልጣኙን ከአንድ አመት በፊት ለመቅጠር አቅደው እንደነበር ጠቁመው፣ በመጨረሻ ፊርማውን ለማግኘት መቻላቸውን ተናግረዋል። ለሰርዮቪች ሚሉቲን ሚቾ መልካም የስራ ዘመን ተመኝተዋል። ሰርቪያዊው የኦርላንዶ ፓይሬትስ አሰልጣኝ ሰርዮቪች ሚሉቲን ሚቾ የአንድ አመት ውል ለመፈረም በሳምንቱ መጨረሻ ግብፅ ላይ ታይተዋል። የ49 አመቱ አሰልጣኝ ለግብፁ ክለብ መፈረማቸውን ተከትሎም ‹‹አፍሪካ ውስጥ ለ19 አመታት ሰርቻለሁ፣ በሰባት አገራት አሰልጥኛለሁ፣ ከ54ቱ አገራት መካከልም በ50ኛው ጉብኝት አድርጌያለሁ፣,አሁን ደግሞ ዛማሊክን ለማሰልጠን ሃላፊነቱን ወስጃለሁ፣ ሕልሜም እውን ሆኖልኛል›› ሲሉ ተናግረዋል። የደጋፊውን ፍላጎት እውን ለማድረግም ጠንክረው እንደሚሰሩ አስታውቀዋል። ሚቾ የቅዱስ ጊዮርጊሱ አሰልጣኝ በነበሩበት ወቅት በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ታሪክ ኮከብ አሰልጣኝ በመሆን የመጀመሪያው የውጭ አገር ዜጋ ተሸላሚ ለመሆን በቅተዋል። ሰርዲዮቪች ሚቾ የመጀመሪያው የውጭ አገር ዜጋ ተሸላሚ ብቻም ሳይሆኑ ለአምስት ጊዜ በተደጋጋሚ ኮከብ ሆነው በመመረጥ ቀዳሚው አሰልጣኝ ናቸው። አሰልጣኙ በ1997 ዓ.ም ኮከብ ተብለው መመረጥ የጀመሩ ሲሆን፣ በ1998፣ በ2000፣ በ2201 እና በ2002 ዓ.ም ኮከብ አሰልጣኝ መሆን ችለዋል። ዘገባው የስፖርት 24 እና የቢቢሲ ነው። አዲስ ዘመን ነሀሴ 14/2011ታምራት ተስፋዬ
https://www.press.et/Ama/?p=16418
305
2ስፖርት
ኢትዮጵያ – የግማሽ ምዕተ ዓመት የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ጉዞ
ስፖርት
August 24, 2019
75
ዓለማችን ከምታስተናግዳቸው ታላላቅ ስፖርታዊ ክንውኖች ከኦሊምፒክና የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ቀጥሎ በግዝፈቱ ሦስተኛ ደረጃ ላይ እንደሚቀመጥ የሚነገርለት የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ነው። የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና በመሰረቱ የኦሊምፒክ ውድድር አካል ቢሆንም እኤአ በ1976 የሞንትሪያል ኦሊምፒክ 50 ኪሎ ሜትር የርምጃ ውድድር ከኦሊምፒክ መቀነሱን ተከትሎ የአትሌቲክስ ቻምፒዮና ራሱን ከኦሊምፒክ ነጥሎ ውድድሮችን ለማዘጋጀት ችሏል። የመጀመሪያው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና በውስን የውድድር አይነቶች እኤአ 1980 ላይ የተካሄደ ቢሆንም ከ1983 አንስቶ በይፋ መካሄድ እንደጀመረ የስፖርቱ የታሪክ ሰነዶች ይነግሩናል። እኤአ ከ1983 እስከ 1991 ድረስ በአራት ዓመት አንድ ጊዜ ከተካሄደ በኋላም አሁን ያለውን ቅርፅ ይዞ በሁለት ዓመት አንድ ጊዜ በመካሄድ ላይ ይገኛል። ኢትዮጵያም ግማሽ ምዕተ ዓመት ሊሞላው ጥቂት በቀረው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ታሪክ ተሳታፊ ከመሆን ባለፈ በውጤት ካሸበረቁ አገራት መካከል አንዷ ሆና ዛሬ ላይ ደርሳለች። ባለፉት አስራ ሰባት ያህል ቻምፒዮናዎችም አንዴ ውጤት ሲቀናት አልፎ አልፎም ሲከዳት ታይቷል። 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና በመካከለኛው ምስራቅ ኳታር ዶሃ ላይ ሊካሄድ የአንድ ወር ጊዜ ብቻ በቀረው በዚህ ወቅት አዲስ ዘመን ቅዳሜ ኢትዮጵያ በቻምፒዮናው ያሳለፈችውን ታሪክና ውጤት እንደሚከተለው ቃኝቶታል። ሔልሲንኪ-1983በዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና የመጀመሪያው ሜዳሊያ የሚጀምረው እኤአ በ1983 በፊንላንድ ሔልሲንኪ ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደው ቻምፒዮና ነው። የአትሌቲክስ ታሪካችን በሮም ኦሊምፒክ በአበበ ቢቂላ የማራቶን ድል እንደሚጀምረው ሁሉ በዓለም ቻምፒዮናም የሜዳሊያ ታሪካችን በማራቶን ነው የጀመረው። እንደ አበበ ቢቂላ የወርቅ ሜዳሊያ ባይሆንም ከበደ ባልቻ ያስመዘገበው የብር ሜዳሊያ በታሪክ የኢትዮጵያ የመጀመሪያው የዓለም ቻምፒዮና ሜዳሊያ ሆኖ በታሪክ ይነሳል። ይህ ሜዳሊያ ኢትዮጵያ በእዚያ ቻምፒዮና ያስመዘገበችው ብቸኛ ሜዳሊያና አስራ አምስተኛ ደረጃን ይዛ ያጠናቀቀችበት ጭምር ነው። ቶኪዮ-1991ከአራት ዓመት በኋላ በጣሊያን ሮም 1987 ላይ በተካሄደው ቻምፒዮና ኢትዮጵያ የተመዘገበላት ሜዳሊያ አልነበረምና ቀጣዩን የቶኪዮ ቻምፒዮና መመልከቱ የተሻለ ይሆናል። የ1991 የቶኪዮ ቻምፒዮናም ኢትዮጵያ በፊጣ ባይሳ የአምስት ሺ ሜትር የብር ሜዳሊያ ከዓለም ሃያ አንደኛ ደረጃን ይዛ ነው የተመለሰችው።ስቱትጋርት-1993 የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ለሦስት ጊዜ ያህል በአራት ዓመት አንድ ጊዜ ተካሂዶ ከቶኪዮው ቻምፒዮና በኋላ በሁለት ዓመት አንድ ጊዜ መካሄድ ከጀመረ ወዲህ ግን ኢትዮጵያ በቻምፒዮናው የሜዳሊያ ቁጥሯን ከፍ በማድረግ በሦስቱ ቻምፒዮናዎች በብር ሜዳሊያ ብቻ ተወስኖ የነበረውን ታሪኳን መቀየር ጀመረች። የጀርመኗ ስቱትጋርት ከተማ እኤአ የ1993 ወይንም አራተኛውን የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና የደገሰች ከተማ ነበረች። የረጅም ርቀት ጀግናው ኃይሌ ገብረስላሴም በትልቅ ደረጃ ብቅ ያለበት ውድድር ይህ ነበር። ኢትዮጵያ በእዚህ ቻምፒዮና አንድ የወርቅ፤ አንድ የብርና አንድ የነሐስ ሜዳሊያ በማስመዝገብ አስራ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ ስታጠናቅቅ ኃይሌ በአምስት ሺ ሜትር የብርና በአስር ሺ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ ያጠለቀ አትሌት ነበር። ፊጣ ባይሳ በአምስት ሺ ሜትር ኃይሌን ተከትሎ በመግባት የነሐሱ ባለቤት ነው። ኃይሌ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ የአሸናፊነት ተምሳሌትና የስፖርት ጀግናም ብቻ ሳይሆን በዓለም በወርቅ ሜዳሊያ ፈርቀዳጅና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ወርቃማ ዘመን ጎህ ቀዳጅ ነው። ለእዚህም ከስቱትጋርት በኋላ ኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ ተፎካካሪ እየሆነች የመጣችበትን ታሪክ መመልከት በቂ ነው። ጉተንበርግ-1995አምስተኛውን ቻምፒዮና ያስተናገደችው የስዊድኗ ከተማ ጉተንበርግ ናት። ኢትዮጵያም በአንድ ወርቅና አንድ ብር ሜዳሊያ አስራ ስድስተኛ ሆና ተመልሳለች። ኃይሌ ለሁለተኛ ጊዜ የነገሰበት አስር ሺ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ በሴቶች ደራርቱ ቱሉ በተመሳሳይ ርቀት ብቸኛውን ብር ይዘው የመጡ አትሌቶች ናቸው።አቴንስ-1997በቀጣዩ የአቴንስ ቻምፒዮና ኢትዮጵያ ከአንድ በላይ ሜዳሊያ ማግኘት አልቻለችም። ይህም ሜዳሊያ ኃይሌ ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ በአስር ሺ ሜትር የነገሰበት የወርቅ ሜዳሊያ ነው። ኢትዮጵያ በእዚህ ቻምፒዮና በአንድ ሜዳሊያ ብትመለስም የወርቃማ አትሌቲክስ ዘመኗ ሊጎመራ ከሁለት ዓመት በላይ ጊዜ አልወሰደበትም። ሴቪሊ-1999እኤአ 1999 ስፔን ሴቪሊ የቻምፒዮናው አስተናጋጅ ነች። ኢትዮጵያ ሁለት የወርቅና ሦስት የነሐስ ሜዳሊያ ተሸልማ ዘጠነኛ ደረጃን ይዛ ያጠናቀቀችበት የመጀመሪያው አጋጣሚ። ኃይሌ በአስር ሺ ሜትር በታሪክ ላይ ታሪክ፤ በአሸናፊት ክብረወሰን ላይ ሌላ ክብረወሰን በማኖር ለአራተኛ ጊዜ በአስር ሺ ሜትር ላይ ነግሷል። በተመሳሳይ ርቀት ጌጤ ዋሚ በቻምፒዮናው ለኢትዮጵያ በርቀቱ የመጀመሪያ የወርቅ ባለቤት ያደረጋትን ታሪክ ሰርታለች። አሰፋ መዝገቡ በአስር ሺ ሜትር፤ ቁጥሬ ዱለቻ በአንድ ሺ አምስት መቶ ሜትርና አየለች ወርቁ በአምስት ሺ ሜትር የነሐስ ሜዳሊያ ባለቤቶች ናቸው።ኤድመንተን-2001እኤአ የ2001 ካናዳ ኤድመንተን ቻምፒዮና ኃይሌና አሰፋ መዝገቡ ወርቅ ለማጥለቅ ሲጠባበቁ በኬንያዊው የማይረሳው ጥርሰ ወላቃ አትሌት ቻርልስ ካማቲ የአስር ሺ ሜትር ወርቅ ከእጃቸው የወጣበት አጋጣሚ በብዙ ስፖርት ቤተሰቦች ዘንድ ይታወሳል። በእዚህ ቻምፒዮና አሰፋ የብር፤ ኃይሌ የነሐሰ ሜዳሊያ ቢያጠልቁም ኢትዮጵያ ወርቅ ሳትይዝ አልተመለሰችም። የመጀመሪያው የአረንጓዴ ጎርፍ ባለታሪኮች ደራርቱ ቱሉ፤ ብርሃኔ አደሬና ጌጤ ዋሚ በአስር ሺ ሜትር ሦስቱንም ሜዳሊያዎች ጠራርገው ሲወስዱ በማራቶን ገዛኸኝ አበራ የመጀመሪያውን ወርቅ አጥልቋል። ሚሊዮን ወልዴ በአምስት ሺ ሜትር ብር፤ በተመሳሳይ ርቀት አየለች ወርቁ ነሐስ በማጥለቅ ኢትዮጵያ በሁለት ወርቅ፤ ሦስት ብርና ሦስት ነሐስ ሰባተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።ሴንትዴኒስ-2003 ቀጣዩ የሴንት ዴኒስ ፈረንሳይ ቻምፒዮና የኢትዮጵያውያን የረጅም ርቀት የበላይነት የነገሰበት ነበር። ቀደም ሲል በሴቶች አስር ሺ ሜትር የታየው አረንጓዴ ጎርፍ በወንዶች የተደገመበት አጋጣሚ ይታወሳል። ኢትዮጵያ በሦስት ወርቅ፤ ሁለት ብርና ሁለት ነሐስ አራተኛ ሆና ያጠናቀቀችበት ትልቅ ውጤትም ነበር። ጀግና በጀግና የተተካበት ታሪካዊ ውድድር። ቀነኒሳ በቀለ ኃይሌንና ስለሺ ስህንን አስከትሎ የአስር ሺ ሜትር ዘውዱን የተረከበበት ታሪካዊ አጋጣሚ። በተመሳሳይ ርቀት የብርሃኔ አደሬ ወርቅና በጥሩነሽ ዲባባ የአምስት ሺ ሜትር ጣፋጭ ድል ኢትዮጵያ አጊጣለች። ኃይሌና ወርቅነሽ ኪዳኔ በአስር ሺ ሜትር ብር፤ ቀነኒሳ ከአስር ሺ ሜትር ወርቁ በተጨማሪ በአምስት ሺ ሜትር ነሐስና የስለሺ ስህን የአስር ሺ ሜትር ነሐስ የኢትዮጵያ ሜዳሊያዎች ናቸው።ሔልሲንኪ-2005 አረንጓዴው ጎርፍ በ2005 ሔልሲንኪ ዳግም ባዘጋጀችው ቻምፒዮናም በሴቶች አስር ሺ ሜትር ለሦስት ተከታታይ ቻምፒዮናዎች ኢትዮጵያን አድምቋል። ኢትዮጵያ በታሪኳ ሦስት ወርቅ፤ አራት ብርና ሁለት ነሐስ በመሰብሰብ ሦስተኛ ሆና ያጠናቀቀችበት ትልቅ ውጤትም ይህ ነው። ጥሩነሽ ዲባባ በአምስትና አስር ሺ የጥምር ድል ባለቤት ስትሆን ቀነኒሳ የአስር ሺ ሜትር ድሉን ደግሟል። ስለሺ ስህን በአምስትና አስር ሺ ሜትር ሁለት ብሮችን ሲያጠልቅ መሰረት ደፋር በአምስት ሺ ሜትር ጥሩነሽን ተከትላ ተመሳሳይ ሜዳሊያ አጥልቃለች። ጥሩነሽ በአስር ሺ ሜትር ድሏ ብርሃኔ አደሬንና ታላቅ እህቷን እጅጋየሁ ዲባባን አስከትላ የገባችበት ታሪካዊ ድልም ይህ ነበር።ኦሳካ-2007 ቀጣዩ ጃፓን ኦሳካ ላይ የተካሄደው ቻምፒዮና ነው። በእዚህ ቻምፒዮና ኢትዮጵያ እንደተለመደው በብርቅዬና በወርቃማው የአትሌቲክስ ትውልዷ ሦስት የወርቅና አንድ የብር ሜዳሊያ ይዛ በአራተኛ ደረጃ አጠናቃለች። ቀነኒሳ በቀለ ለሦስተኛ ተከታታይ ቻምፒዮናዎች አስር ሺ ሜትር ላይ ሲነግስ ጥሩነሽም በተመሳሳይ ርቀት ንግስት ነበረች። መሠረት ደፋርም ወደ አምስት ሺ ሜትር ድል የመጣችው በእዚሁ ቻምፒዮና ነው። ቀሪው አንድ ብር የስለሺ ስህን የአስር ሺ ሜትር ነው።በርሊን-2009ከቤጂንግ ኦሊምፒክ ማግስት እኤአ 2009 ላይ በርሊን ባዘጋጀችው ቻምፒዮና ጥሩነሽ ዲባባና መሰረት ደፋርን የመሳሰሉ የወርቃማው ዘመን አትሌቶች መጎዳታቸውን ተከትሎ የኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ እጣ ፋንታ በቀነኒሳ በቀለ ትከሻ ላይ ወድቆ ነበር። እሱም በአምስትና አስር ሺ ሜትር ጥምር ወርቆችን በማጥለቅ ከባዱን ሃላፊነት ተወጥቷል። ደረሰ መኮንን በአንድ ሺ አምስት መቶ ሜትርና መሰለች መልካሙ በአስር ሺ ሜትር ያስመዘገቧቸው የብር ሜዳሊያዎች ኢትዮጵያ ሰባተኛ ደረጃን ይዛ እንድታጠናቅቅ አስችለዋል። ዴጉ-2011ኢትዮጵያ ከስድስት ቻምፒዮናዎች ወይንም ከአስራ ሁለት ዓመት በኋላ በአንድ የወርቅ ሜዳሊያ የተመለሰችው በ2011 የደቡብ ኮሪያ ዴጉ ቻምፒዮና ነው። ኢብራሒም ጄይላን በድንቅ አጨራረስ ብቃት በአስር ሺ ሜትር ያስመዘገበው ብቸኛ ወርቅ ከመሰረት ደፋር የአምስት ሺ ሜትር ነሐስ፤ ከፈይሳ ሌሊሳ የማራቶን ነሐስ፤ ኢማና መርጋ የአስር ሺ ሜትር ነሐስና የደጀን ገብረመስቀል የአምስት ሺ ሜትር ጋር ተደምረው ኢትዮጵያ ዘጠነኛ ሆና አጠናቃለች። ሞስኮ-2013በ2013 የሞስኮው ቻምፒዮና የወርቃማው ትውልድ አትሌቶች የተወሰኑት ከጉዳታቸው አገግመው ወደ ድል የመጡበት ነበር። ጥሩነሽ ዲባባ በኬንያውያን ለሁለት ተከታታይ ቻምፒዮናዎች የተነጠቅነውን የአስር ሺ ሜትር ወርቅ ስታጠልቅ መሰረት ደፋር በሁለት ቻምፒዮናዎች ያልተሳካላትን የአምስት ሺ ሜትር ወርቅ አጥልቃለች። መሐመድ አማን በታሪክ የመጀመሪያውን የስምንት መቶ ሜትር ድል ያጣጣመውም በእዚሁ ቻምፒዮና ነው። ከእዚህ በዘለለ ሃጎስ ገብረህይወት በአምስት ሺ፤ ኢብራሂም ጀይላን በአስር ሺና ሌሊሳ ዴሲሳ በማራቶን የብር ሜዳሊያ አጥልቀዋል። ታደሰ ቶላ በማራቶን፤ አልማዝ አያና በአምስት ሺ ሜትር፤ በላይነሽ ኦልጂራ በአስር ሺ ሜትር፤ ሶፊያ አሰፋ በሦስት ሺ ሜትር መሰናክል የነሐስ ሜዳሊያዎችን በማጥለቅ ኢትዮጵያ ስድስተኛ ሆና እንድታጠናቅቅ አስችለዋል። ቤጂንግ-2015ከአራት ዓመት በፊት ቤጂንግ የደገሰችው ቻምፒዮና ገንዘቤ ዲባባና ማሬ ዲባባ በታሪክ የመጀመሪያውን የአንድ ሺ አምስት መቶና የማራቶን ወርቅ ሲያጠልቁ አልማዝ አያና የአምስት ሺ ሜትር ድል አጣጥማለች። ገለቴ ቡርቃ በአስር ሺ ሜትር፤ ሰንበሬ ተፈሪ በአምስት ሺ ሜትርና የማነ ፀጋዬ በማራቶን የብር ሜዳሊያ አጥልቀዋል፤ ገንዘቤ በአምስት ሺ ሜትር የነሐስ ሜዳሊያ ስትደግም ሃጎስ ገብረህይወት በአምስት ሺ ሜትር ያስመዘገበው ነሐስ ኢትዮጵያን በአምስተኛ ደረጃ እንድታጠናቅቅ ረድቷታል።ሎንደን-2017ያለፈው የሎንደን ቻምፒዮና አልማዝ አያና በአስር ሺ ሜትር የደመቀችበት ከመሆኑ ባሻገር ለሦስት ተከታታይ ቻምፒዮናዎች ከእጃችን ወጥቶ የቆየውን የአምስት ሺ ሜትር የወንዶች ድል በሙክታር ኢድሪስ አማካኝነት ወደ ቤቱ ተመልሷል። አልማዝ ከ10ሺ ሜትር ድሏ ባሻገር በ5ሺ ሜትር የብር ሜዳሊያ ስታስመዘግብ ጥሩነሽ ዲባባ በ10ሺ ሜትርና ታምራት ቶላ በማራቶን የብር ሜዳሊያዎችን ማሸነፍ ችለዋል። ይህም ኢትዮጵያን ከዓለም ሰባተኛ ደረጃን ይዛ እንድታጠናቅቅ አስችሏታል።አዲስ ዘመን ቅዳሜ ነሀሴ 18/2011 ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=16669
1,195
2ስፖርት
ቻምፒዮንስ ሊግ እና ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ክለቦችን ይፈትናሉ
ስፖርት
August 25, 2019
37
 ባሳለፍነው ሳምንት በርካታ አነጋጋሪ የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ዘገባዎች ተደምጠዋል፡፡ የአሰልጣኝ ቅጥር እና የኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል ስፖርት የመጀመሪያ ጉባኤ ትኩረት ስበው ካለፉ ዘገባዎች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ከዚህ ባለፈ ዛሬ በአገር ውስጥ እና በውጪ የአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ማጣሪያ እና ኮንፌዴሬሽን ካፕ ማጣሪያ ጨዋታ ፋሲል ከተማ እና መቀሌ ከተማ ተጋጣሚዎቻቸውን ይፋለማሉ፡፡ እኛም ከነዚህ ስፖርታዊ ወሬዎች ውስጥ ጆሮ ገብ የሆኑትን መራርጠን አቅርበናል፡፡ የሶከር ኢትዮጵያ ድረ ገፅንም በዋናነት ዋቢ አድርገን ተጠቅመናል፡፡ ሴካፋ ከ15 ዓመት በታች ከዚህ ሳምንት አነጋጋሪ ዘገባዎች መካከል በሴካፋ ከ15 ዓመት በታች ውድድር ሶማሊያ እና ኬንያ ተጋጣሚዎቻቸውን ማሸነፋቸውን እና ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፋቸውን የሚያወሳው ዘገባ ነው። አዘጋጇ ኤርትራም ከምድብዋ ሳታልፍ መቅረቷ የስፖርት ቤተሰቡን ቀልብ የሳበ ነበር። የሶማሊያ እና ሱዳን ጨዋታን ሶማሊያ ከጨዋታ ብልጫ ጋር 2ለ0 አሸንፋለች። በጨዋታው የብዙዎች አድናቆት ለጎረፈላቸው ሶማሊያዎች ጎሎቹን ያስቆጠሩት ሞሐመድ ዓብዱልቃድር እና አብዱላሂ ዑመር ነበሩ። ሁለተኛ የነበረው ጨዋታ የኤርትራ እና የውድድሩ ጠንካራ ቡድን ኬንያ ሲሆን ኬንያ አዘጋጅዋን 2 ለ 1 በማሸነፍ ምድቡን መርታ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏን አረጋግጣለች። ኤርትራም በደጋፊዎችዋ ፊት ከምድቧ በመውደቅ አሳዛኝ ተሳናባች ሆናለች። ውድድሩም ቀጥሎ ታንዛኒያ እና ሩዋንዳ ተፋልመዋል፡፡ በዚህም ሩዋንዳ ተጋጣሚዋን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፋ ወደ ቀጣይ ዙር ለማለፍ ችላለች። ዩጋንዳ እና ደቡብ ሱዳን ባደረጉት ጨዋታም እስከ እረፍት ድረስ በዩጋንዳ አምስት ለባዶ መሪነት ቢጓዝም በደቡብ ሱዳን ተጫዋቾች ጉዳት ምክንያት ጨዋታው ተቋርጦ በኡጋንዳ አሸናፊነት ውጤቱ ተደምድሟል፡፡ በዚህ ውድደር ላይ አስቀድማ ተሰናባች መሆኗን ያረጋገጠችው ኢትዮጵያ ናት። ፋሲል ከተማ እና መቀሌ ከተማ ፋሲል ከተማ በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የመልስ ጨዋታውን ከአዛም ጋር ዛሬ በታንዛኒያ ዳሬ ሰላም የሚያደርግ ይሆናል፡፡ በአዲሱ አሰልጣኝ ስዩም ከበደ በመመራት ከሶስት ቀን በፊት 19 ተጫዋቾችን ይዞ ወደ ዳሬ ሰላም ያቀናው ፋሲል ከተማ በሜዳው በጠባብ ውጤት በበዛብህ መለዩ ብቸኛ ጎል 1ለ 0 በማሸነፍ ነው የዛሬውን ጨዋታ የሚያካሂደው፡፡ አዲሱ አሰልጣኝም በካፍ ኮንፌዴሬሽን ልምድ ያካበቱ ሲሆን መከላከያን በሚያሰለጥኑበት ወቅት ከናይጄሪያው ክለብ ሬንጀርስ ኢንተርናሽናል በምድብ ውጤት ተሸንፈው ከውድድሩ ተሰናብተዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በቻምፒየንስ ሊግ ቅድመ ማጣርያ የመልስ ጨዋታ የመቐለ 70 እንደርታ ተጋጣሚ የሆኑት ካኖ ስፖርት አካዳሚዎች ከሶስት ቀን በፊት አዲስ አበባ ገብተው ወደ መቀሌ በማምራት ትናንት የመጨረሻ ልምምዳቸውን በመቀሌ ኢንተርናሽናል ስታዲየም በማድረግ ዛሬ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡ በውድድሩ እንደ መቀሌ ሁሉ የመጀመርያ ተሳትፏቸውን እያደረጉ የሚገኙት ካኖዎች ለኢኳቶርያል ጊኒ ብሔራዊ ቡድን ያስመረጧቸው የቡድኑ ወሳኝ ተከላካይ ቪሴንቴ አሲሙ እና አጥቂው ልዊስ ሚግዌል ኔቮን ጨምሮ የመጀመርያው ዙር ጨዋታ ያካሄደው ሙሉ የቡድን አባላት ይዘው ነው ኢትዮጵያ የገቡት። ክለቡ በአበበ ቢቂላ ልምምድ ያደረገ ሲሆን ትናንት ጠዋት ጨዋታው ወደሚያካሂድበት መቀሌ በማምራት የመጨረሻ ልምምዱን አከናውኖ የመልሱን ጨዋታውን ለማድረግ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል። ማላቦ በተካሄደው የመጀመርያው ዙር የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ካኖ ስፖርት አካዳሚዎች መቀሌን በጠባብ ውጤት 2ለ1 አሸንፈዋል። አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ ያለፈውን አንድ ዓመት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ረዳት አሰልጣኝ በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩት አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ የባህር ዳር ከተማ ዋና አሰልጣኝ ሆነው መሾማቸውን ተከትሎ አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ ማንን ቀጣይ ረዳታቸው እንደሚያደርጉ አነጋጋሪ መሆኑን ሶከር ኢትዮጵያ ድረ ገፅ አስነብቧል። የብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ የፋሲል ተካልኝን ምትክ ለመተካት እየተንቀሳቀሱ መሆናቸው እየተነገረ ባለበት በአሁኑ ወቅት ሁለት ምክረ ሀሳቦች እንደቀረበላቸው ይህ ድረ ገፅ ይፋ አድርጓል። የመጀመርያው ረጅም ዓመት በአሰልጣኝነት የቆዩ ቢሆኑ ካላቸው ልምድ በመነሳት ብሔራዊ ቡድኑን ሊጠቅሙ ይችላሉ በማለት እንደ አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም፣ ወርቁ ደርገባ፣ ዻውሎስ ጌታቸው፣ አጥናፉ ዓለሙ እና ግርማ ሐብተዮሐንስን ምክትል አሰልጣኝ ቢያደርጉ መልካም ነው የሚለው ምክረ ሀሳብ ተጠቃሽ ነው። በሁለተኛ ደረጃ የቀረበው ደግሞ ወደ ፊት ረጅም ዓመት ብሔራዊ ቡድኑን ሊያገለግሉ የሚችሉ፣ አቅማቸውን የሚያሳድጉ እና ልምድ እያገኙ ሲሄዱ ብሔራዊ ቡድኑን ማጠናከር የሚችሉ ወጣት አሰልጣኞችን ማድረጉ የተሻለ ነው በሚል እንደ አንዋር ያሲን፣ ዕድሉ ደረጄ፣ እስማኤል አቡበከር እና ካሊድ መሐመድን ቢመለከቱ የሚል ሀሳብ ቀርቦላቸዋል። እስካሁን አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር ለመለያየት የመልቀቂያ ደብዳቤ ለፌዴሬሽኑ ያላስገቡ በመሆናቸው ከአሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ ጋር አብረው በቀጣይ ጨዋታዎች ሊቀጥሉ እንደሚችሉ ሲገመት የመልቀቂያ ደብዳቤ ካስገቡ በኋላ በሂደት ተተኪ ምክትል አሰልጣኝ ሊያሳውቁ እንደሚችሉ እየተነገረ ይገኛል። ይህም ቢሆን አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ በምክትል አሰልጣኝ አድርጎ ለመሾም ቀዳሚ ምርጫቸው የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዕውቁ ተጫዋች በአሁኑ ወቅት የኤሌክትሪክ ዋና አሰልጣኝ በመሆን እያገለገለ የሚገኘውን አንዋር ያሲን እንዲሆን ፍላጎት እንዳላቸው ሰምተናል። የኢትዮጵያን ፕሮፌሽናል ፉትቦለርስ አሶሴሽን ከተመሠረተ አጭር ጊዜ የሆነው ኢትዮጵያን ፕሮፌሽናል ፉትቦለርስ አሶሴሽን በወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ ሰሞኑን በዋቢ ሸበሌ ሆቴል ከአባላቶቹ ጋር ረጅም ሰዓት የፈጀ ውይይት በማድረግ የአቋም መግለጫ ማውጣቱ ተገለፀ። እንደ ሶከርኢትዮጵያ ድረ ገፅ ዘገባ በጉባኤው ላይ የማኅበሩ መስራች እና ሰብሳቢ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ማኅበሩ ከተመሰረተ አጭር ጊዜ ቢሆንም የባለሙያውን መብት ለማስከበር ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ መቆየቱን በመግለፅ ዓላማውን ለተሳታፊዎች በዝርዝር አስረድተዋል። ‹‹እናንተ አሉ የምትሉትን ችግሮች በግልፅ ተነጋግረን አንድ አቅጣጫ መያዝ ይገባናል›› በማለት የሚሰማቸውን ስሜት እንዲገልፁ መድረኩን ለተሳታፊ አባላት ክፍት አድርገዋል። ተሳታፊዎቹ ‹‹እስከዛሬ ብዙ በደሎች ሲደርሱብን መብታችንን የሚያስከብርልን ማኅበር ባለመኖሩ ብዙ ችግሮችን በዝምታ አልፈናል። ከፌዴሬሽኑም ሆነ ከክለቦች ጋር ለመካሰስ አቅም አልነበረንም። አሁን ግን ለእኛ የሚቆረቆር ማኅበር በመቋቋሙ ደስተኞች ነን። ይህን ኃላፊነት በመውሰድ እንዲቋቋም ላደረጋችሁ የቀድሞ ተጫዋቾች እና አሁን እየተጫወታችሁ ለምትገኙ መስራቾች ከፍተኛ ምስጋና እናቀርባለን›› በማለት አሉ የሚሉትን ችግሮችን በዝርዝር ተናግረዋል። በዋናነት ካነሷቸው ነጥቦች መካከል ከዚህ ቀደም ተጫዋቾቹን ሳያማክሩ የፊርማ ገንዘብ ይቅር በደመወዝ ይሁን መባሉን በዝምታ ማለፋቸውን ከፍተኛ ችግር እንደፈጠረባቸው፤ የውል ዘመናቸው ሳይጠናቀቅ ክለቦች እንደፈለጉ እያሰናብቱን መብታችንን ማስከበር አቅቷቸው ለከፋ ጉዳት መዳረጋቸው፤ ባላጠፉት ጥፋት ፌዴሬሽኑም ሆነ ክለቦች በማን አለብኝነት ከፍተኛ የሆነ ቅጣት ሲጥሉባቸው በዝምታ ማለፋቸውን፤ በሚጫወቱባቸው አንዳንድ ክለቦች የአራት እና የሁለት ወር ደመወዝ እየተከፈላቸው ባለመሆኑ ችግር ውስጥ እንደገቡ፤ እነዚህን እና መሰል ችግሮችን በትዕግስት እያለፉ ባሉበት በአሁኑ ወቅት የተጫዋች የደመወዝ ጣሪያ ከ50 ሺህ ብር በላይ እንዳይሆን መወሰን ተገቢ አይደለም ብለዋል። ይህን ውሳኔም የማይቀበሉት እና የማያምኑበት በመሆኑ ለማህበሩ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል። አመራሮቹም በሚችሉት ሁሉ የተጫዋቾችን መብት ለማስከበር እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የማኅበሩ አመራሮችም የተወሰነውን ውሳኔ ከዚህ ጉባዔ አስቀድሞ በተለያዩ መገናኛ ብዙኀን ሲቃወሙት እንደቆዩ ገልፀው በጋራ በተጠናከረ ሁኔታ አቋማቸውን መግለፅ እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።አዲስ ዘመን ነሐሴ 19 / 2011   ዳግም ከበደ
https://www.press.et/Ama/?p=16705
853
2ስፖርት
በትምህርት ዘርፉ ህገ ወጥ አሰራሮችን የሚያጋልጥ የመረጃ አያያዝ ስርዓት ይፋ ሆነ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 5, 2020
10
 አዲስ አበባ:- በትምህርት ዘርፉ የአሰራር ስርዓትን በማዘመን፣ መልካም አስተዳደርን የሚያሰፍኑ ብልሹ አሰራሮችን የሚቀርፍና ተጠያቂነትን መፍጠር የሚያስችል፣ ህገ ወጥ አሰራሮችንም የሚያጋልጥ የመረጃ አያያዝ ስርዓት ይፋ ሆነ፡፡ በከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲና በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ትብብር የተዘጋጀ ‹‹የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ የመረጃ አስተዳደር ሥርዓት›› ትናንት በተመረቀበት ወቅት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም፤ ግልጸኝነት የተላበሰ አሰራርና የዘመነ የመረጃ አስተዳደር ስርዓት መተግበሩ ህገ ወጥ አሰራሮች ተጋልጠው እንዲታረሙ፣ በትምህርት ዘርፉ መተማመንን እንደሚፈጥርና የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ እንደሚያስችል ተናግረዋል።መንግስት በትምህርት ዘርፉ የሚታየውን ህገ ወጥነት ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያደርገውን ጥረት ለማረጋገጥ እንደሚያግዝ በመግለጽ፤ ተቋማት ባሉበት ሆነው በአጭር ጊዜና በቀላሉ የእውቅና ፍቃዳቸውን የሚያወጡበት፣ የሚያድሱበትና መሰል አገልግሎቶችን ያለ ውጣ ውረድ የሚያገኙበትን ዕድል እንደሚፈጥር ፕሮፌሰር ሂሩት ጠቁመዋል። ሚኒስትሯ፤ የከፍተኛ ትምህርት ለማስፋት ከቅበላ እስከ ምረቃ ድረስ የሚያስኬድ የበይነ መረብ ትምህርት አቅርቦት መመሪያ ተዘጋጅቶ ወደ ተግባር መገባቱን፤ የተለያዩ አማራጮችን ተግባራዊ በማድረግ ትምህርትን ማስፋት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል። ሚኒስትሯ ወቅታዊ፣ የተሟላ ይዘት ያለው፣ ግልጸኝነትን የተላበሰ፣ ከትክክለኛ ምንጭ የተገኘና የተረጋገጠ መረጃ ጥራት ያለው ውሳኔ ለመስጠት እንደሚያግዝ፣ ተቋማዊ ተልእኮን በውጤታማነት ለመወጣት እንደሚያስችል ፣ ተፈላጊ መረጃዎችን በማደራጀትና በመተንተን ለሚመለከተው ባለድርሻ አካል ወቅታዊ መረጃና ግብረ መልስ ለማቅረብ የሚያስችል የዘመነ የመረጃ አስተዳደር ስርዓት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ሚናው ከፍተኛ መሆኑንም አስረድተዋል። እስካሁን ተቋማት የት እንዳሉ፣ ምን ያህል የማስተማሪያ ጊቢ እንዳላቸው፣ በምን መርሀ ግብር ትምህርት እየሰጡ እንደሚገኙ፣ ምን ያህል ተማሪና መምህራን እንዳላቸው የተሟላ መረጃ እንዳልነበረም ፕሮፌሰር ሂሩት ገልጸው፤ የቀደመው አሰራር በትምህርት ጥራትና አግባብነት ላይ ትልቅ ጫና የፈጠረና ህገወጥነትን የፈቀደ እንደነበር ጠቁመዋል። የግል ከፍተኛ ተቋማትን የሚመለከቱ አስፈላጊና ወቅታዊ መረጃዎችን ተደራሽ ማድረግ የተጠቃሚ ባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ ለማጎልበት እንደሚያስችል፣ የትምህርት ጥራት እንዲሻሻልና የአሰራር ስርዓቱ እንዲጎለብቱ ግብዓት ለመስጠት ሚናው የጎላ እንደሚሆንም አክለዋል። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶክተር)፤ የመረጃ አስተዳደር ስርዓቱ የከፍተኛ ትምህርትን ለማዘመን እንደሚያግዝ ፣ ከቴክኖሎጂ ጋር ለማስተሳሰር መንግስት እያደረገ ያለው ጥረት አካል መሆኑን ፣ ቴክኖሎጂው ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጊዜ ቆጣቢና ቀላል አሰራርን የሚተገበርበት እንደሆነና በትምህርት ዘርፉ የሚታየውን ህገወጥነት ለመከላከል እንደሚጠቅም ጠቁመው፤ ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያለው የመረጃ አስተዳደር ስርዓት በመሆኑ አሰራርን ለማዘመን እንደሚያስችልም ገልጸዋል። የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ዳይሬክተር አንዱዓለም አድማሴ (ዶክተር)፤ ተቋሙ ቁጥጥር እንዲያካሂድና የትምህርት ጥራትን እንዲከታተል የተቋቋመ ቢሆንም፤ ባለፉት ዓመታት በዘርፉ ከፍተኛ የህግ ጥሰቶችና ከፍተኛ የጥራት መጓደል መታየቱን ጠቅሰው፤ ይህንን ችግር ለመቅረፍ የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት በነጻ ሙያ ድጋፍ አበልጽጎ ወደ ትግበራ ማስገባቱን ተናግረዋል። ዳይሬክተሩ፤ ስራው በእጅ በታገዘ ልማዳዊ አሰራር ሲተገበር መቆየቱን ፣ የተማሪዎችንና የመምህራንን ቁጥር ለመለየትም አዳጋች እንደነበር ጠቁመው፤ አዲሱ አሰራር ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እውቅና መስጠት፣ እድሳት ማድረግና ክትትል ማካሄድ እንደሚገኝበት፣ የትምህርት ጥራትን እንደሚከታተልና የትምህርት ማስረጃን የማረጋገጥ ስራ እንደሚተገብር ተናግረዋል።ወደ ዘመናዊ አሰራር መገባቱ በአገር ውስጥ የሚገኙ ተመራቂዎችን በሙሉ በዳታ ቤዝ መያዝ እንደሚያስችል፣ ቀጣሪ መስሪያ ቤቶች በቀጥታ ማረጋገጥ እንደሚያስችላቸው፣ በመማር ላይ የሚገኙ ተማሪዎችን በቀጥታ በቴክኖሎጂው ለማግኘት፣ ለመከታተልና ለመቆጣጠር የሚያስችል አሰራር መዘርጋቱን ዳይሬክተሩ አስረድተዋል። በተያያዘ ዜና ከቅበላ እስከ ምርቃት ድረስ በበይነ መረብ ትምህርት አቅርቦት (on line learning) ለማስተግበር የሚያስችለው እና የተዘጋጀው መመሪያ ወደ ተግባር መግባቱ ለትምህርት ዘርፉ አማራጭ እንደሚሆን የትምህርት ሚኒስርሯ ተናግረዋል። ሚኒስትሯ በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ላለፉት 18 ወራት ከ20 ባለሙያዎች በላይ የተሳተፉበት በቴክኖሎጂ የተደገፈ የመረጃ አስተዳደር ስርዓት መዘጋጀቱን ጠቁመዋል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 29/2012  ዘላለም ግዛው
https://www.press.et/Ama/?p=36639
462
0ሀገር አቀፍ ዜና
ግብጽ የአባይ ውሃ የህልውናዬ ጉዳይ ነው ብትልም ሰፊ የውሃ አማራጮች እንዳሏት ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 5, 2020
23
 አዲስ አበባ ፦ ግብጽ የአባይ ውሃ የህልውናችን ጉዳይ ነው ብትልም በተጨባጭ ግን ሰፊ የውሃ አማራጮች እንዳሏት በውሃ ጉዳይ ተመራማሪው ዶክተር ኢንጂነር ጸጋ ጥበቡ አስታወቁ ። ግብጻውያኑን ከዕንቅልፍ መቀስቀስ እና ለአማራጮቻቸው ትኩረት እንዲሰጡ ማነቃቃት እንደሚያስፈልግም አመለከቱ ።በውሃ ዘርፍ ሰፊ ጥናቶችን በማካሄድ በዘርፉ የረጅም ጊዜ ልምድ ያላቸው ዶክተር ኢንጂነር ጸጋ ጥበቡ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳመለከቱት፤ ግብጽ ከአባይ ውጪ ሌላ የውሃ አማራጭ እንደሌላት አድርጋ ለዘመናት የሄደችበት መንገድ የተሳሳተና አለምንም ያሳሳተ ነው። ‹‹ግብጽ ከአባይ ውሃ ውጪ በጠጣሩ የኑብያ አሸዋማ ከርሰ ምድር የተከማቸው ውሃ አላት›› ያሉት ተመራማሪው ፤ ከዚህም ውጪ የቀይ ባሕርንና የሜዲትራንያንን ባሕር ከጨው በማላቀቅ አማራጭ የውሃ ምንጭ አድርጋ ልትጠቀም እንደምትችል፤ ለዚህም የሚሆን በቂ እና ርካሽ ቴክኖሎጂ በገበያ ላይ እንዳለ አመልክተዋል ። በአፍሪካዊ የመተባበር መንፈስ መንቀሳቀስ ከተቻለ ከላይኛው የዓባይ ተፋሰስ በጆንግላይ ቦይ አማካይነት ወደ ግብጽ በቀላሉ ሊቀለበስ የሚችል ሰፊ የውሃ ሀብት እንዳለ የጠቆሙት ተመራማሪው ፤ ከታላቁ ኮንጎ ወንዝ ወደ ግብጽ ሊቀዳ የሚችል ሰፊ የውሃ ሀብት መኖሩን አስታውቀዋል ። ከሀገሪቱ ከቤት፣ ከኢንዱስትሪ እና ከመስኖ አገልግሎት የሚወጣውን ውሃ እንደገና አጣርቶ ጥቅም ላይ በመዋልም ሰፊ ውሃ ማግኘት እንደምትችል ገልጸዋል። የኑብያ ጠጣር አሻዋማ ስነምድር ውስጥ የሚገኝ የከርሰ ምድር ውሃ በመላው ግብጽ፤ ምስራቃዊ ሊቢያ ፤ሰሜን ቻድ እና ሰሜን ሱዳን ውስጥ ተከማችቶ ይገኛል ያሉት ተመራማሪው፤ በቅርቡ በተደረገ ጥናት ወደ 450,000 (አራት መቶ ሀምሳ ሺ) ኪዊቢክ ሜትር ውሃ እንደሚገኝ መረጋገጡን ተናግረዋል ።የኑብያ የከርሰ ምድር ውሃ ክምችትን ስናስብ ሊቢያን በምሳሌነት ልንጠቅስ እንችላለን ያሉት ዶ/ር ጸጋ፣ ያቺ አገር የከርሰ ምደሩን ውሃ አውጥታ፤ ሰው ሠራሽ የተባለውን ወንዝ ፈጥራ ጥቅም ላይ በማዋል የአረቡን ዓለም በእርሻ ምርት በሥጋና በፍራፍሬ በማጥለቅለቋ ሊቢያውያን ከፍተኛ የኑሮ እርከን ላይ መድረሳቸውን አመልክተዋል ።ግብጻውያን ይህንን ፈር በመከተል ከጥቁር ዓባይ ጥገኝነት እራሳቸውን ነጻ ማውጣት እንዳለባቸው፤ ከቁጥጥር ውጪ የሆነ አስቸጋሪ ሁኔታ ሲያጋጥም ሁሉም የተፋሰሱ አገሮች በጋራ የሚቆሙበትን ስርዓት መፍጠር ተገቢ መሆኑንም አመልክተዋል ። ለዚሁ የሚሆን መርህ ማዘጋጀት እንደሚያስፈልግም አስታውቀዋል።ግብጽ የቀይ ባሕር እና የሜዲትራንያንን ውሃ ተጋሪ ከመሆኗ አንጻር ይህን የውሃ ሀብት ከጨው በማላቀቅ እንደ አንድ አማራጭ የውሃ አቅም አድርጋ ልትወስድ እንደሚገባ ያመለከቱት ተመራማሪው ፤ አሁን ባለንበት ክፍለ ዘመን የባሕርን ውሃ ከጨው የማላቀቁ ሂደት በጣም እየቀለለና በዋጋም እየረከሰ መምጣቱን ጠቁመዋል። ወደፊትም ይበልጥ ዋጋው እየቀነሰ እንደሚሄድ ይገመታል ብለዋል ። ግብጻውያን ጨዋማን ውሃ የማጣራት በቂ ልምድ ስላላቸው፤ በዚህ ምንም የሚቸግራቸው ነገር እንደሌላ ጠቁመው ፤ የውቂያኖስ ውሃን በማጣራት ከበቂ በላይ ውሃ ማግኘት እንደሚችሉም አመልክተዋል ። በተፋሰሱ ሀገሮች መካከል በቂ መተማመን መፍጠር ከተቻለ የላይኛው ዓባይ ላይ ውሃ አጠራቅሞ የዓባይን ፍሰት ማጎልበት ሌላኛው አማራጭ እንደሆነ የጠቆሙት ተመራማሪው፤ ይህ አማራጭ ቀደም ብሎ ግብጽና ሱዳን በታላቋ ብሪታንያ አስተዳደር በነበሩበት ወቅት ተጀምሮ ደቡብ ሱዳን ውስጥ ተነሰቶ በነበረው የእርስ በርስ ጦርነት መቋረጡን ጠቁመዋል ።መሠረተ ሃሳቡም ቪክቶሪያ ሀይቅ ላይ ግደብ ሠርቶ ውሃ በማጠራቀም፤ ውሃው ወደ ነጭ ዓባይ እንዲፈስ በማድረግ ሱድ የተበለውን 8000 (ስምንት ሺ) ኪሎ ሜትር ካሬ የሚሸፍነውን ረግረጋማ መሬት በካናል በማሳለፍ ነጭ ዓባይ ውስጥ እንዲገባ በማድረግ ወደ ሱዳንና እና ግብጽ የጎለበተ ውሃ እንዲወርድ ማድረግ እንደነበረ አስታውቀዋል ። ከኮንጎ ወንዝ ውሃ በመጨለፍ የነጭ ዓባይን ፍሰት ማጎልበት ተጨማሪ አማራጭ እንደሆነ ያስታወቁት ዶ/ር ጸጋ ፤ የታላቁ የኮንጎ ወንዝ በሴኮንድ 40,000 ( አርባ ሺ) ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ወደ አትላንቲክ ውቅያኖስ ያፈሳል። ዓባይ በ 6750 ኪሎ ሜትር ርዝመት ቢጓዝም ኮንጎ በፍሰት መጠን ዐባይን 7 ጊዜ ይበልጣል ። ይህንን የአፍሪካውያን አኩሪ ኃብት ለጋራ ጥቅም ማልማት ይቻላል ብለዋል ። ግብጽ ከፍተኛ መጠን ያለው ውሃ ለቤት ውስጥ አገልግሎት፣ ለኢንዱስትሪ እና ለመስኖ እርሻ እንደምትጠቀም ፤ አገልግሎቱን ጨርሶ የሚባክን ከፍተኛ መጠን ያለው ውሃ መኖሩን ፤ ይህንን ውሃ አጣርቶ በመጠቀም ተጨማሪ የውሃ አቅም መፍጠር እንደምትችል ጠቁመዋል ።ዶ/ር ጸጋ አህጉራዊ ራዕይ በማዳበር አማራጮች ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ያስፈልጋል ያሉት ተመራማሪው፤ አማራጮች ላይ ትኩረት መስጠት የብስለትና የአርቆ አስተዋይነት መገለጫ መሆኑንና ግብጻውያኑን ከዕንቅልፍ መቀስቀስ እና ለአማራጮቻቸው ትኩረት እንዲሰጡ ማነቃቃት እንደሚያስፈልግ ጠቁመው በሦስቱ አገሮች መካከል እየተደረገ ባለው ድርድርም አማራጭ የውሃ ግኝት አንደ አንድ የመደራደሪያ ርዕሰ ጉዳይ ሆኖ ሊነሳ እንደሚገባ አስታውቀዋል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 29/2012  በጋዜጣው ሪፖርተር
https://www.press.et/Ama/?p=36642
579
0ሀገር አቀፍ ዜና
የወታደሮቹ ሚስቶች የስቃይ ትውስታ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 4, 2020
9
በእያሱ መሰለ እምባባ ታረቀኝና ባለቤቷ የተዋወቁት እንደሃዋርያት በሚባል ቦታ ነው የተዋወቁት። እርሷ የወታደሮች ምግብ አብሳይ ሆና፤ ባለቤቷ ደግሞ በሰሜን እዝ መከላካያ ሠራዊት ውስጥ ዳር ድንበርን የመጠበቅ ተልእኮውን በመፈጸም ላይ በነበረበት ወቅት። እምባባ የትግራይ ተወላጅ ስትሆን ባለቤቷ ደግሞ የኦሮሞ ተወላጅ ነው። ከቋንቋ ልዩነቱ በላይ ኢትዮጵያዊነት አስተሳስሯቸው ትወደዋለች፤ ይወዳታል። ትዳር መስርተው መኖር ከጀመሩም ጥቂት ዓመታትን አሳልፈዋል። አሁን የዘጠኝ ወር ነፍሰጡር መሆኗን ነግራናለች። በሰሜን እዝ መከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት መከፈቱን ተከትሎ እምባባ ያሳለፈችው ፈተና ብዙ ነው። ‹‹ ሠራዊቱ ላይ በድንገት ጥቃት ሲፈጸም እኔና ባለቤቴ አብረን አልነበርንም፣ አርሱ ምሽግ ውስጥ ነበር፤ አኔ ደግሞ መኖሪያ ሰፈር አካባቢ ነኝ፤ ምሽግ አካባቢ የነበሩ ወታደሮች በራሳቸው ወገን በድንገት የተከፈተባቸውን ጥቃት እየተከላከሉ ወደ ኤርትራ መሻገራቸውን ሰማሁ። እኔም የባለቤቴን ዱካ ተከትዬ መጓዝ ጀመርኩኝ ፤ ብዙ ካፈላለኩ በኋላ በህይወት መኖሩን ሳረጋግጥ ተረጋጋሁ። በኋላም ባለቤቴ በሌላ ግንባር ከሠራዊቱ ጋር ተደራጅቶ ህግ ወደ ማስከበር ሥራ መግባቱን ስሰማ ወዳለበት ግንባር ሄድኩኝ። ከሠራዊቱ ኋላ ኋላ እየከተልኩና በሚያስለቅቋቸው ከተሞች እያረፍኩ ሠራዊቱን እየተከተልኩ መጓዜን ቀጠልኩ። በእግርና በተሽከርካሪ አድካሚ ጉዞ እየተጓዝኩ ባለቤቴ ከፊት እኔ ከኋላ ሆነን መቀሌ መግባት ቻልን ትላለች። መከላከያ ሠራዊትና የትግራይ ህዝብ በማህበራዊ ህይወት የተሳሰሩ ናቸው የምትለው እምባባ፣ ከዚያም አልፎ በርካታ የትግራይ ተወላጆች ልክ እንደእርሷው ሁሉ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የመጡ የሠራዊቱን አባላት አግብተው መውለዳቸው፣ ይህም ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በደም እንድንተሳሰር ያደረገ መልካም አጋጣሚ ነው ትላለች። በመከላከያ ሠራዊቱ ላይ የተፈጸመው ጥቃት በጣም እንዳሳዘናት እና ድርጊቱ የትግራይን ህዝብ የማይወክል፣ በጥቃቱ የትግራይ ተወላጆችም ተጎጂ መሆናቸውን የእርሷ ህይወት በቂ ምስክር እንደሚሆንም ገልጻለች። ባለቤቷን ለመግደል የመጣ አካል የእርሷም ገዳይ እንጂ ወዳጅ አለመሆኑን እማባባ ትናገራለች።አበባ በየነ የአክሱም አካባቢ ተወላጅ ነች። አበባ የአማራ ተወላጅ የሆነ የመከላከያ ሠራዊት አባል አግብታ እንደምትኖር ትናገራለች። ከባለቤቷ ጋር የስድስት ዓመት ቆይታ አላት፤ አንድ ልጅም አፍርተዋል። ባለቤቷ አዲግራት አካባቢ ሲኖር እርሷ ደግሞ እንደሃዋሪያት አካባቢ ልጇን እያሳደገች ትኖራለች። በሰሜን እዝ መከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ የባለቤቷ ጉዳይ እንቅልፍ ነስቷት ነበር። የባለቤቷ ነገር ሰላምና እረፍት ሲነሳት ልጇን ይዛ በኤርትራ አቆራርጣ ጾረና ከወታደሮች ምሽግ አቅራቢያ ትደርሳለች። የባሏ ዕጣ ፈንታ ምን እንደሆነ ያላወቀችው ይቺ የወታደር ሚስት ባሏን በህይወት ስታገኘው የነበራት ደስታ በቋንቋ ለመግለጽ እንደሚከብዳት ስትናገር ያ ስሜት አሁንም ከውስጧ እንዳልጠፋ ያሳብቅባታል። ባሏን በህይወት ካገኘችው በኋላ እርሱ ህግ ወደ ማስከበር ሥራው ገባ፤ እርሷም የእርሱን ዱካ እየተከተለች ተያይዘው መቀሌ መግባታቸውን ትገልጻለች። ባሌን ሊገድል የመጣ የእኔ ወዳጅም ተቆርቋሪም ሊሆን እይችልም ትላለች።የትግራይ ነፃ አውጪ ነን እያሉ ወንጀል የሚሠሩ አካላት ትግራይን አይወክሉም። የትግራይ ህዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ወንድሞቹ ጋር እሴቱን ጠብቆ በፍቅር የሚኖር ማህበረሰብ ነው የምትለው አበባ፣ ባልን ከሚስቱና ከልጆቹ እየለዩና እየገደሉ በትግራይ ህዝብ ስም መነገድ ተገቢ አይደለም፤ተቀባይነት የለውም ትላለች። ወታደር የኢትዮጵያ ህዝብ ልጅ ነው፤ እኔም እንደባለቤቴ ኢትዮጵያዊነትን የማስቀድም የወታደር ሚስት ነኝ። ምንም ባልጠረጠሩበት ሁኔታ ድንገተኛ ጥቃት ሲፈጸምባቸው ማየቴ እጅግ አስከፍቶኛል፤ በጣም አዝኛለሁ። መንግሥት ህግን ለማስከበር ዕርምጃ እየወሰደ መሆኑ ደግሞ አስደስቶኛል። አጥፊዎችና ነፍሰ ገዳዮች ለህግ መቅረብ ይኖርባቸዋልም ትላለች።
https://www.press.et/Ama/?p=36672
421
0ሀገር አቀፍ ዜና
ኢንጂነር ታከለ ኡማ የዕውቅና ሽልማት ተበረከተላቸው
ሀገር አቀፍ ዜና
August 5, 2020
13
 አዲስ አበባ ፦ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ወደ ኃላፊነት ከመጡበት ጊዜ አንስቶ ላከናወኗቸው ውጤታማ ስራዎች የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የዕውቅና ሽልማት አበረከተ ።ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለከክተው ምክር ቤቱ ለኢንጂነር ታከለ የዕውቅና ሽልማቱን ያበረከተው የሚሰሩ ስራዎች የከተማዋ ነዋሪዎችን ያማከለ እንዲሆን በማድረግ በኩል ውጤታማ ስራዎችን በማከናወናቸው ፣ አስታዋሽ አጥተው ለዘመናት የተዘነጉ የማህበረሰብ ክፍሎችን ማዕከል ያደረጉ ስራዎችን በመስራት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ነው።በተጨማሪም የከተማዋን ታሪካዊና የቱሪዝም መስህብነት የሚያጎሉ እንዲሁም የነዋሪዎችን ችግር የሚፈቱና ኢኮኖሚያዊ ሚና ያላቸው ታላላቅ ፕሮጀክችን ማስጀመራቸው በታሰበላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቅ በማስቻላቸው መሆኑም ተገልጿል።በከተማዋ ለሚገኙ ተማሪዎች ምግብ፣ የትምህርት ቁሳቁስ እና ዩኒፎርም እንዲቀርብ አመራር መስጠታቸው፣ ስራውንም ተቋማዊ እንዲሆን ማድረጋቸው ለሽልማቱ በምክንያትነት ተጠቅሷል።በኢኮኖሚው ዘርፍ የከተማ ግብርና በስፋት ከተማዋ ባህል እንዲሆን ሀሳብ በማመንጨትና አመራር በመስጠት፣ እንዲሁም የእደጥበብ ዘርፎች ኢኮኖሚያዊ ፋይዳቸው እንዲጨምር እየሰሩ ባሉት ስራ ስኬታማ መሆናቸው ጭምር ነው ።በአጠቃላይም ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከመሀል ከተማ ነዋሪ ጀምሮ አዋሳኝ ቦታ ላይ የሚገኙ አርሶ አደሮች ድረስ የባለቤትነት ስሜት በመፍጠር፣ የከተማዋ እድገት ሁሉንም ያካተተ እንዲሆን በማድረግ በኩል ባለፋት ሁለት ዓመታት ላደረጉት ስኬታማ ስራ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የእውቅና ሽልማት ማበርከቱን ተጠቁሟል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 29/2012  በጋዜጣው ሪፖርተር
https://www.press.et/Ama/?p=36636
167
0ሀገር አቀፍ ዜና
‹‹በትምክህት የደነደነ ልብ ሳይሆን በስልጠና የፈረጠመ ጡንቻ ሁሌም ያሸንፋል›› – ብርጋዴር ጀኔራል ካሳዬ ጨመዳ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 4, 2020
15
በአስመረት ብስራት በትምክህት የደነደነ ልብ ሳይሆን በጦረነት እውቀትና በስልጠና የፈረጠመ ጡንቻ ያለው ኢትዮጵያዊነት የገባው ወታደር ሁልጊዜም የድል ባለቤት መሆኑን ብርጋዴር ጀኔራል ካሳዬ ጨመዳ አስታወቁ።ብርጋዴር ጀኔራሉ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደተናገሩት፣ የህውሓት ጁንታ ቀደም ሲል ከ15 ዓመታት በላይ ሲዋጉ ጠንካራ የሚገዳደራቸው ወታደር ነበር፤ አሁንም ለሀገሩ የሚዋጋ ጠንካራ አቅም ያለው የመከላከያ ሠራዊታችን የቀደመ ታሪካቸውን እንዲያስታውሱ አድርጓቸዋል።ድሮም ምንም አቅም ምንም እውቀት ኖራቸው አያውቅም ነበር ያሉት ብርጋዴር ጀኔራል ከሳዬ፣ ባዶ ውሸትና ትምክህት ብቻ በሞላው ልባቸው ወደጦርነት በመግባታቸው የሽንፈትን ፅዋ ለመጨለጥ ተገደዋል ብለዋል። ድሮም ወደ ስልጣን መምጣት የቻሉት የተዋጊነት አቅም ኖሯቸው ሳይሆን በደርግ መንግሥት ስህተትና ድክመት ህዝቡ መሰላቸት እና የሀያላን ሀገር ጣልቃ ገብነት በመጨመሩ እንደነበር ጠቁመዋል። በህውሓት ጁንታ አሁን በጠላትነት የተፈረጀው የኢትዮጵያ ህዝብ እያበላ፥ እያጠጣ፥ መንገድ እየመራ ደጀን መሆን ደግፎ ወደስልጣን አወጣው እንጂ በፊትም ወታደራዊ ብቃት እንዳልነበራቸው አስታውቀዋል። ለዚህ ውለታው ህዝቡን በዘር በመከፋፈል ከማጫረስ በስተቀር ምንም ሳይጠቅሙት መኖራቸውን ገልጸዋል።የህዝብ ዕንባ የመከላከያ ሠራዊቱ ጥንካሬ ከዚህ ቡድን ነፃ ስላወጣን ምስጋና ሊቸረው ይገባል ብለዋል።በባዶ ጉራ ሙሉ የመከላከያ ሠራዊቱን በቁጥጥራቸው ስር አውለው፤ በጦር መሳሪያና በሹመት ብዛት የሚያሸንፉ መስሏቸው ሲፎክሩ ቆዩ እንጅ ወታደራዊ ብቃት ያለነበራቸው ቡድኖች መሆናቸውን መከላከያ ሠራዊታችን በገልፅ አሳይቷል ያሉት ብርጋዴር ጀኔራል ካሳዬ፣ ለሁሉም ደባና ተንኮል የሚያስከፈለውን ዋጋ በአግባቡ ለመመልከት እንደቻሉ ጠቁመዋል።የተዋጊያቸውን አቅም ያላገናዘቡት እነዚህ ተንኳሽ ቡድኖች ዘመኑ የቴክኖሎጂ መሆኑን ሳያስተውሉ በቴክኖሎጂ የተደገፈው ጦር ሠራዊታችን ባሳየው የኃይልና የእውቀት ብልጫ ትምክህተኛውን ለማሸነፍ መቻሉ የሚያኮራ ይበል የሚባል ተግባር መሆኑን አመልክተዋል።የትግራይ ህዝብ ኢትዮጵያዊነቱን የሚያከብር ህዝብ መሆኑን እዚህ በተገኘሁበት ወቅት ተመልክቻለሁ የሚሉት ብርጋዴር ጀኔራል ካሳዬ፣ እንግዳ የሚቀበል ሰው አክባሪ የሆነ ጠንከራ ህዝብ መሆኑን ገልጸዋል። ሀገርን እኛ ካላስተዳደርን ይፍረስ ብሎ መዝለል ተገቢ እንዳልሆነም ጠቁመዋል። ከአንድ መቶ ሚሊዮን ህዝብ በላይ ያለባት ሀገር ሁሉም ህዝብ ወንበር መያዝ ቢፈልግ የማይችል መሆኑን አስረድቶ ሁሉም በያለበት ሀገርን የማሳደግ ኃላፊነትን ከመወጣት ባለፈ የግድ ልምራ ማለት ፍትሐዊ ያልሆነ ጥያቄ እንደሆነ ገልጸዋል።የትግራይ ህዝብ ከዚህ በፊትም ታፍኖ የኖረ አሁንም ታፍኖ ነው ያለው ህዝቡ ፤ ህዝቡ በስሙ ተነገደበት እንጂ ምንም ያልተሠራለት ዛሬም ይህ ህዝብ የተራበ የተጠማ እንደሆነ አመልክተዋል። ልጆቹ ድንጋይ ላይ ተቀምጠው የሚማሩ ናቸው። የህውሓት ጁንታ ለፕሮፖጋንዳ የሚያሳዩትን ያህል ሳይሆን በጥልቀት ሲታይ በችግር እንዲኖር ያደረጉት ይህን የተጎዳ ህዝብ በመካስ ይህን ጨዋ ህዝብ ወደ እውነተኛ ማንነቱ መመለስ ከሁሉም ኢትዮጵያዊ ይጠበቃል ብለዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=36673
329
0ሀገር አቀፍ ዜና
‹‹ቀጣይ ሀገራዊ የፖለቲካ ድባቡ በብዝሃነት ውስጥ የደመቀ ጠንካራ ኢትዮጵያዊ አንድነት የሚመጣበት ነው›› – ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት የዓለም አቀፍና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ሃላፊ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 4, 2020
11
በአስቴር ኤሊያስ ቀጣይ ሀገራዊ የፖለቲካ ድባቡ በብዝሃነት ውስጥ የደመቀ ጠንካራ ኢትዮጵያዊ አንድነት የሚመጣበት ፍልስፍናን የያዘ እንደሆነ የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት የዓለም አቀፍና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ሃላፊ ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ ገለጹ። ዘርፎም ሆነ በኮንትሮባንድ እስከ አፍንጫው የታጠቀውን ጁንታ በ25 ቀናት ውስጥ የዛሬ 47 ዓመት ወደነበረበት ዋሻ ተመልሶ እንዲገባ መደረጉን አስታወቁ። ዶክተር ቢቂላ በተለይ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳስታወቁት፤ መከላከያ ሠራዊት የዓይኑ ብሌን በሆነች በኢትዮጵያዊነት የማይደራደር ነው። በግራም ይሁን በቀኝ ዘርፎም ሆነ በኮንትሮባድ አግበስብሶ እስከአፍንጫው የታጠቀውን የጁንታውን ቡድን በ25 ቀን ውስጥ የዛሬ 47 ዓመት ከነበረበት ዋሻ ውስጥ መልሶ ከቶታል። ይህም የኢትዮጵያዊነት መገለጫ የሆነው የመከላከያ ሠራዊታችን ጥንካሬና ጀግንነት ነው ያሉት ኃላፊው፣ ይህ ጀግንነት ደግሞ ህዝቡም ውስጥ ያለ እና የኖረ እንደሆነ የጠቆሙት ኃላፉው፣ የህዝቡ ጀግንነት መከላከያ ሠራዊታችን ውስጥ በተግባር የተረጋገጠ መሆኑንም አመልክተዋል። እንደ ዶክተር ቢቂላ ገለጻ፤ ይህ መሰሪና አጥፊ ቡድን የዛሬ 47 ዓመት አካባቢ ዋሻ ውስጥ ነበር፤ በአሁኑ ሰዓትም 47 ዓመታት ወደኋላ ተንፏቆ ቀድሞ በነበረበት ዋሻ ውስጥ ይገኛል። ይሁንና ከዚያ አፈር ውስጥ ተለቅሞ ይወጣል። ወደነበረበት ጉድጓድ እንዲገባ ያደረገው የኢትዮጵያውያን አንድነት ምልክት የሆነው መከላከያ ሠራዊት ሲሆን፣ የህዝቡም ጥምረት ውጤት ነው። ጁንታው በተንኮልና ክፋት የተወረሰ ነው ያሉት ዶክተር ቢቂላ፣ ተንኮልና ክፋት ደግሞ የፈለገውን ያህል አንገቱን ቀና ቢያደርግ አንድ ቀን ተንኮሉና ክፋቱ ራሱን መልሶ መብላቱ አይቅርም ብለዋል። ስለዚህ መነሻ የምናደርው እውነት ሁልጊዜ ታሸንፋለች፤ ተንኮልና ክፋት ሁልጊዜ ይሸነፋል የሚለውን ነው ብለዋል። ሁሌም የአሸናፊነት ምስጢር እውነት እንደሆነችም አስታውቀዋል። ከዚህ ከእውነት ጋር የታገለ ማንኛውም ኃይል እንደሚወድቅ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ህዝብ ሁልጊዜ የሚቆመው ከእውነትና ከሐቅ ጋር መሆኑን ጠቅሰው፤ ትልቁ አቅምና ጉልበት የነበረው ይኸው እንደሆነ አመልክተዋል። ላለፉት ሁለት ዓመታት ያህል ተንኮለኛው ቡድን መቀሌ ሲኮለኮል፤ ኢትዮጵያውያኑ ደግሞ አንድ ወደሚያደርጋቸው ነገር ሲሳቡ ቆይተዋል። በመጨረሻ ግን ቡድኑ የኢትዮጵያዊነት መገለጫ፤ የአገራዊ አንድነት ምልክት በሆነው ላይ እና ኢትዮጵያውያን እንደ ዓይናቸው ብሌን በሚያይዋት ኢትዮጵያ ላይ እጁን በማንሳቱ እውነት መነካቱን አስታውቀዋል። መከላከያ ሠራዊቱም ጥቃትን መቋቋም ስላልሆነለት የኢትዮጵያዊነትን ልክ ማሳየት ችሏል ብለዋል። እንዲህ ዓይነት ፈተና ቀርቶ ወደ ፊትም ትልልቅ አገራዊ ፈተናዎች ቢከሰቱ እንኳ ያልቃታል እንጂ አገሩን እንደማያስደፍር ማረጋገጡን አስረድተዋል። ከኋላው ያለው 115 ሚሊዮኑም ህዝብ የኢትዮጵያን መጠቃት ከመቃወም በተጨማሪ በሁለንተናው ድጋፍ እንዳበረከተ አመልክተዋል። ስለዚህ የፖለቲካው ድባብ በብዝሃነት ውስጥ የደመቀ ጠንካራ ኢትዮጵያዊ አንድነትን እናመጣለን የሚል ፍልስፍና ነው የያዘነው ያሉት ዶክተር ቢቂላ፣ ፖለቲካው በግራም በቀኝም ማጠንጠኛው ይህ ነው ብለዋል። ስለዚህ ይህ የጁንታው ቡድን ሲነቀል የፖለቲካ ድባቡ ከዘር ነጋዴነት እየተላቀቀ ይመጣል ሲሉም አብራርተዋል። ኃላፊው እንደተናገሩት፤ ብዝሃነትን ማቀፍና የዘር ነጋዴ መሆን ይለያያል። ቡድኑ ባለፉት 27 ዓመታት ብዝሃነትን የሚያቅፍ ሳይሆን የዘር ነጋዴ ነበር። ጁንታው የብሄር ነጋዴ ነው። በየቦታውም ሄዶ ግጭትን ሲያነሳ ሰንብቷል። ከዚህ በኋላ የብሄር ንግድ አክሳሪ ነው የሚሆነው፤ ነጋዴዎችም ከስረው ከገበያ ይወጣሉ። ብዝሃነትን ያቀፈ፣ ኢትዮጵያን የሚመስል፣ ሁሉንም ቋንቋም ሆነ ማንነት ወደመሃል ያመጣ፣ የሚያቅፍና የሚያሳትፍ፣ ተጠቃሚ የሚያደርግ፣ በኢትዮጵያዊነቱ ላይ ግን የማይደራደር ኢትዮጵያዊ አንድነት ይገነባል ብለዋል። ስለዚህ ቀስ በቀስ ከአክሳሪው፣ ከመሰሪውና ከተንኮለኛው የብሄር ንግድ እየተወጣ ወደ ብዝሃነትን ወደአቀፈች ጠንካራ ኢትዮጵያ ይመጣል ብለዋል። ፖለቲካ እየተቃኘ ያለው ወደዚህ ነው ሲሉም አስታውቀዋል።
https://www.press.et/Ama/?p=36680
438
0ሀገር አቀፍ ዜና
የብሄር ብሄረሰቦች ቀን በሰላም አምባሳደሮች ዓመቱን ሙሉ እንደሚከበር ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 4, 2020
22
 ዋለልኝ አየለ አዲስ አበባ፡- በየዓመቱ ህዳር 29 ይከበር የነበረው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ሰላምና አንድነትን በሚሰብኩ የሰላም አምባሳደሮች ዓመቱን ሙሉ እንደሚከበር ተገለጸ። በጭፈራ ብቻ ሲከበር የቆየው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ሰላምና አንድነትን ሊያመጣ በሚችል መንገድ መከበር እንደሚኖርበት ተጠቆመ ። ኢስት አፍሪካ ኢንተርቴይመንት ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ጋር በመተባበር በዓሉን አስመልክተው ከትናንትበስቲያ በሰጡት መግለጫ ፣ የኢስት አፍሪካ ኢንተርቴይመንት የሁነቶች አደራጅ አቶ ቢኒያም ፈቃዱ እንደገለጹት፤ በዚህ ዓመት በሚከበረው 15ኛው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ‹‹ቆንጂት አንድነት›› የተሰኘ የቁንጅና ውድድር ይካሄዳል። ከሁሉም ክልሎች እና ከሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች ሦስት ሦስት ቆነጃጅት ተወዳድረው አሸናፊዎች በየክልላቸው የሰላም አምባሳደር ይሆናሉ ብለዋል። የሚመረጡት የሰላም አምባሳደሮች ሰላምና አንድነትን በመስበክ ብሄራዊ አንድነትን የሚያጠናክሩ ሥራዎችን ይሠራሉ።የማጠቃለያ ዝግጅቱም የፊታችን ዕሁድ ህዳር 27 ቀን በሸገር ፓርክ እንደሚካሄድ ጠቁመው፣ የሚመረጡት ቆነጃጅት የመጡባቸውን አካባቢዎችና የወከሏቸውን ብሄሮች ባህልና ትውፊት እንደሚያስተዋውቁ አስታውቀዋል። በአምባሳደርነታቸውም እስከሚቀጥለው ዓመት ድረስ በየአካባቢያቸው ከሚገኙ ወጣቶች ጋር በሰላም ዙሪያ ይሠራሉ። ይህም በአገሪቱ ሲሸረሸር የቆየውን ህብረ ብሔራዊ አንድነት እንዲስተካከል ይረዳል ብለዋል። ለ15ኛው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን የየክልል ተወካዮች ወደ አዲስ አበባ እየመጡ መሆኑን የገለጹት አቶ ቢኒያም፤ ብሄሮቻቸውን ወክለው የሚመጡት ቆነጃጅት የአገር አንድነት ላይ የሚያተኩር ሥልጠና እንደሚሰጣቸው ተናግረዋል። የኢስት አፍሪካ ኢንተርቴይመንት ባለቤት አቶ ሞቲ ሞሮዳ በበኩላቸው፤ ‹‹ቆንጂት አንድነት›› በሚል የሰላም አምባሳደር መሰየም ያስፈለገው በሰላም ጉዳይ በአብዛኛው ወጣቶች ላይ መሥራት ስለሚያስፈልግ ነው ብለዋል። የአገሪቱን ሰላም የማይፈልጉ ቡድኖች ለጥፋት የሚጠቀሙት ወጣቶችን ነው። ወጣቶች ላይ ስለሰላምና አንድነት በቂ ግንዛቤ ለመፍጠር የተሻለ እንደሚሆን አጋጣሚ እንደሚፈጥር ጠቁመዋል። በመድረኩ ላይ የተገኘው አርቲስት ቀመር የሱፍ በሰጠው አስተያየት፤ እስከዛሬ የነበረው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን የሚታወቀው በዘፈንና ጭፈራ ነው፤ የዘንድሮውን ልዩ የሚያደርገው የኢትዮጵያን ውጫዊና ውስጣዊ ውበት በሚያሳይ መልኩ ለማክበር መታሰቡ ነው ብሏል። የኢትዮጵያን ውስጣዊ ውበት ማስተዋወቅ ያስፈልጋል። አንድ ሰው ዓመቱን ሙሉ የኢትዮጵያን ብሄር ብሄረሰቦች ቢዞር አንድም ቀን ተመሳሳይ ምግብ ሳይደግም የተለያየ ምግብ ሊመገብ የሚችልበትን ዕድል የሚፈጥር እንደሆነ ገልጿል። ይህን ደግሞ የኢትዮጵያ ድንቅ መገለጫ እንደሆነ አመልክቷል። ‹‹እኔ ኦሮሞ ነኝ፣ ኦሮምኛ ነው የምዘፍነው፤ ይሄንን ባህሌን የኢትዮጵያ ሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች እንዲወዱልኝና እንዲያከብሩልኝ ከፈለኩኝ ወደ እነርሱ መቅረብ አለብኝ›› ያለው አርቲስት ቀመር፤ የየትኛውም ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ባህልና ወግ የሚከበረውና የሚጠበቀው የሌላውን ሲያከብርና ወደሌላው ሲቀርብ መሆኑን ገልጿል። በቆንጂት አንድነት የቁንጅና ውድድር ላይ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት የደም ልገሳ እንደሚደረግ። ቆነጃጅቱ የሰላም አምባሳደር በሚሆኑበት ዓመት ሌሎች የበጎ አድራጎት ሥራዎችን እንደሚሠሩ በመግለጫው ተጠቅሷል።አዲስ ዘመን ህዳር 25 ቀን 2013 ዓ.ም
https://www.press.et/Ama/?p=36686
341
0ሀገር አቀፍ ዜና
ጁንታው ላለፉት 27 ዓመታት የራሱን ድርጅቶች አላግባብ እንዲፈረጥሙ፤ ሌሎች ደግሞ እንዲቀጭጩ ማድረጉ ተጠቆመ
ሀገር አቀፍ ዜና
December 4, 2020
24
ሞገስ ፀጋዬ አዲስ አበባ፡- የህዋሓት ጁንታ ላለፉት 27 ዓመታት የራሱን ድርጅቶች አላግባብ እንዲፈረጥሙ፤ ሌሎችን ደግሞ አላግባብ እንዲቀጭጩ ሲያደርግ እንደነበር የኢኮኖሚክስ ባለሙያው ዶክተር ዳዊት ሀየሶ አስታወቁ። በዚህም በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ የከፋ የሚባል ችግር መፍጠሩን ጠቆሙ።በዲላ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህር የሆኑት ዶክተር ዳዊት ሀየሶ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፣ ባለፉት 27 ዓመታት የሀገሪቷን ሀብት ከመጠቀም አንጻር ፍትሐዊነት አልነበረም። ጁንታው ባልተገባ መልኩ የራሱን ድርጅቶች ፈርጣማ እንዲሆኑ አድርጓል። ፍትሐዊ ባለሆነ የገበያ ውድድር የግል ድርጅቶች ከንግድ ስርዓቱ እንዲወጡና ጤናማ ያልሆነ ገበያ ስርዓት እንዲፈጠር አድርጓል።በጁንታው የንግድ ስርዓቱም እድገቱም ፍትሐዊ እንዳይሆን ተደርጓል የሚሉት ዶክተሩ፣ የሀገሪቱን ሀብት አጠቃቀም ለቡድኑ ያጋደለ ስለነበር ፍትሐዊ አልነበረም ብለዋል። ይህም ከባድ የሚባል ኪሳራን በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ማድረሱን አመልክተዋል። በፖለቲካ ድርጅት የተያዙ የንግድ ተቋማት መኖራቸው የግል ድርጅቶች ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንዳለው ያመለከቱት ዶክተሩ ፣ ይህ ደግሞ ሀገሪቷን ከእድገት ብዙ ዕርምጃ ወደ ኋላ እንደጎተታት ገልጸዋል። በተለይ የግል ሴክተሩን እንደገደለው ጠቁመዋል። ለማንኛውም ከውጭ ለሚመጣ እቃ ለጁንታው የፓርቲ ድርጅቶች ኃላፊነት በመስጠትና እንዲያሰራጭ በማድረግ ኢፍትሐዊ በሆነ መንገድ ሀብት ሲያካብቱ ቆይተዋል። የግል ድርጅቶች ተወዳድረው አትራፊ እንዳይሆኑ፣ እንዳይጠቀሙና ፍትሐዊነት እንዳይኖር በማድረግ የሀገር ኢኮኖሚን ክፉኛ ሲጎዱት መቆየታቸውን ገልጸዋል። ጁንታው ለራሱ ድርጅቶች የተሻለ የመጫወቻ ሜዳ በማመቻቸት ራሱ ተጫዋችና ዳኛ ሆኖ የንግዱን ስርዓት ጤናማ እንዳይሆን ማድረጉን ያመለከቱት ዶክተር ዳዊት፣ በዚህ ምክንትም ከነጋዴው ባልተናነሰ ደሃውን ህዝብ ሲጎዳው ነበር ብለዋል።መንግሥት አገልግሎት በማቅረብ አምራቹንና ሸማቹን ማገናኘት ሲገባው ጣልቃ በመግባት የንግድ ስርዓቱን ሲረብሽ ነበር የሚሉት ባለሙያው፣ የንግድ ስርዓቱ ቅርቃር ውስጥ ገብቶ መውጣት እንዲያቅተው የሆነው መንግሥት በአንድ በኩል ነጋዴ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ለንግዱ ማህበረሰብ ምቹ ሁኔታን የማያመቻች አካል በመሆኑ እንደሆነ ጠቁመዋል። ይህ ሁኔታ ደግሞ ጤናማ የሆነ የኢኮኖሚ ስርዓት ከመገንባት አንጻር ሲታይ መንግሥት ነጋዴ መሆን የለበትም ብለዋል። ባለፉት 27 ዓመታት ጁንታው የሚያወጣቸው ህጎች ሁሉ የራሱን ድርጅቶች ብቻ ተጠቃሚ የሚያደርግ ነበር። በቀኝ እጅ እየነገደ በግራ እጁ ህግ የሚያወጣ ስለነበረ ተወዳዳሪነትን የሚያበረታታም አልነበረም ብለዋል። ጁንታው እንደ መንግሥት ራሱ አበዳሪ ራሱ ተበዳሪ በመሆን የራሱ ድርጅቶች ብድር አላግባብ እንዲያገኙ በማድረግ ከልክ በላይ የፈረጠሙ የራሱን ድርጅቶች ፈጥሯል ሲሉ ገልጸዋል።አዲስ ዘመን ህዳር 25 ቀን 2013 ዓ.ም
https://www.press.et/Ama/?p=36692
299
0ሀገር አቀፍ ዜና
ባለቤት አልባዎቹ ቆሞ ቀር ስታዲየሞች
ስፖርት
August 14, 2019
58
የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) በቅርቡ ባደረኩት ግምገማ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ሜዳዎች ዓለም አቀፍ ውድድሮችን የማስተናገድ አቅም የላቸውም ሲል ከሰሞኑ ይፋ አድርጓል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን «ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ሜዳዎች አንዳንቸውም የካፍን መመዘኛ አያሟሉም ተብለናል» ሲል ለዚሁ ማረጋገጫ ሰጥቷል። የካፍ የግምገማ ውጤት ሰሞነኛ ጉዳይ በመሆንም ሰንብቷል። በሀገሪቱ የተለያዩ ክልሎች ስታድየሞች እየተገነቡ ባሉበት ወቅት እንዴት አንዱ እንኳን የካፍን መመዘኛ ማሟላት አቃተው? ሲሉም በርካቶች እየተጠየቁ ይገኛል። ጥያቄው ተገቢና መሰረታዊ መሆኑ የሚያሻማ አይደለም። የካፍ ግምገማን ተከትሎ ብዙ ብዙ የተባለላቸው ስታዲየሞቻችን አሁናዊ ቁመናን መፈተሽ ደግሞ ለዚህ ምላሽ ይሰጣል።በኢትዮጵያ በየዓመቱ ሲከበር የቆየውን የብሔር ብሔረሰቦችን በዓልን መሰረት በማድረግ በመላ ሀገሪቱ ግዙፍ የሚባሉ ስታዲየሞች በመገንባት ላይ ቢሆኑም አንዳቸውም ሙሉ ለሙሉ አልተጠናቀቁም። ለአብነትም በአዲስ አበባ ከሚገኘውና የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታው እየተጠናቀቀ ካለው ብሔራዊ ስታድየም አንስቶ በባህርዳር፣ ሐዋሳ፣ መቐለ ላይ ያሉት በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ። ከተመልካቾች መቀመጫና ውጫዊ ገጽታ ባሻገር የመጫወቻ ሜዳ ጥራት፣ አስፈላጊ ውስጣዊ ግንባታዎች ላይ የሚሰጠው ትኩረት አናሳ መሆኑም ዋጋ እያስከፈለ መጥቷል። ብሄር ብሄረሰቦች የወለዷቸው ስታዲየሞችበብሔር ብሔረሰቦች ቀን አማካኝነት ግንባታቸው ከተጀመሩ ታድየሞች መካከል በጋምቤላ ፣አፋር ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝና ሐረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስታት የሚገነቡት ዋነኞቹ ናቸው፡፡ የስታዲየሞቹ ግንባታ ትልቅ ቁም ነገር ያለው ቢሆንም ፤ፕሮጀክቶቹ ሲታቀዱ “ማን ከማን ያንሳል” በሚል ስሜታዊነት በመሆኑ ፍጻሜያቸው እንዳጀማመራቸው ሳይሆን ቀርቷል። አንዳንዶቹ ባሉበት ቁመና የአገር ውስጥ ውድድሮች በማስተናገድ ላይ ይገኛሉ፡፡ ጥቂቶቹ ደግሞ መሠረታቸው ተጥሎ ግንባታቸው ከተጀመረ ሁለት አስርታት ዓመታት ሊሞላቸው ተቃርቧል።የስታዲየሞቹ ግንባታ መሰረት የተደረገው ስፖርትን ሳይሆን ፖለቲካን በመሆኑ ክብረ በዓሉ እንዳለፈ አስታዋሽ በማጣታቸው ምክንያት ቆመው ቀርተዋል። ለምሳሌ በጋምቤላ ክልል ብሄር ብሄረሰቦች በዓልን ምክንያት በማድረግ የተጀመረው ስታዲየም ግንባታው የካቲት 12 ቀን 2007 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን በሁለት ዓመታት ውስጥ ተገንብቶ በ 2009 ዓ.ም ላይ ይጠናቀቃል ተብሎ ነበር፡፡ ለግንባታውም 648 ሚሊዮን 776 ሺ አምስት መቶ ዘጠና ብር ተበጅቶለትም ነበር፡፡ ምን ዋጋ አለው አሁን ላይ አርባ ዘጠኝ በመቶ ብቻ ተሰርቶ በፋይናነስ እጥረትና ተጓዳኝ ምክንያቶች ቆሞ ይገኛል። ሌላው የብሄር ብሄረሰቦችን ቀንን መሰረት አድርገው መሰረታቸውን ከጣሉት ግዙፍ ስታዲየሞች አንዱ ደግሞ «አሕመድ ነስር» መታሰቢያ ስታዲየም ነው። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እየተገነባ የሚገኘው ይህ ስታዲየም ግንባታ የካቲት 23 ቀን 2006 ዓ.ም ነበር የተጀመረው። ጥቅምት 2011 ዓ.ም ይጠናቀቃል ተብሎ ነበር፡፡ አሁን ላይ የግንባታው ሂደቱ ሃምሳ በመቶ ላይ ነው የቆመው። የግንባታው ሂደት ከመጓተቱ ባሻገር የፋይናንስ አፈጻጸሙም ደግሞ ሌላ ተጨማሪ ጥያቄን የሚያስነሳም ሆኗል። በ 460 ሚሊዮን ብር ወጪ ይገነባል የተባለው ይህ ስታዲየም ፤ እስከ አሁን 50 በመቶ ላይ ይገኝ እንጂ 340 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበታል፡፡ ይህ ገንዘብ የሙሉ ግንባታ ወጪን የሚስተካከል በመሆኑ ከስራው መጓተት ባሻገር የፋይናንስ አፈጻጸሙም ምርመራን የሚሻ መሆኑን ጠቁመን ወደ ሐረር ተሻገርን ።በሐረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሚገነባው አባድር ስታዲየም ሚያዝያ 2008 ዓ.ም ነው የተጀመረው፤ ጥቅምት 2011 ዓ.ም ይጠናቀቃል ተብሎ ነበር፡፡ ግንባታውን በታሰበበት ጊዜ እንዲጠናቀቅ በ2010 ዓ.ም ሦስት መቶ ስልሳ ሚሊዮን ብር ተመድቦ የነበረ ቢሆንም አሁንም 600 ሚሊዮን ብር አስወጥቶ ከ65 በመቶ ላይ ግን ፈቅ ማለት አልቻለም ተብሏል። በአሁኑ ወቅት ግንባታው እንደቆመ የሚነገርለት ስታዲየሙ ሙሉ በሙሉ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ 1 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር እንደሚፈጅ ታውቋል። የግንባታው መቋረጥ መንግስትን ለተጨማሪ ወጪ መዳረጉ የማይቀር መሆኑም ሊሰመርበት ይገባል።የብሄር ብሄርሰብ በዓልን መሰረት አድርገው ከተገነቡና ክብረ በዓሉ ሲያልፍ ከተዘነጉ ከፍተኛ ወጪ ከወጣባቸው ስታዲየሞች አንዱ የሆነው የሰመራ ስታዲየም ሌላው የትኩረታችን አቅጣጫ ነው። ግንባታው ሐምሌ 18 ቀን 2009 ዓ.ም ነበር የተጀመረው በአራት ዓመት ውስጥ ለማጠናቀቅም እቅድ ተይዞለት ነበር። አንድ ቢሊዮን ብር የሚጠጋ በጀት የተያዘለት ስታዲየሙ፤ በሶስት ዓመት ለማጠናቀቅ ውል ተገብቶ ቢጀመርም ፤ በአሁኑ ወቅት 44 በመቶ ላይ ደርሶ ቆሟል። ይህም ስታዲየምም እንደሌሎቹ ሁሉ መጀመርን እንጂ መጨረስን መሰረት ያደረገ አልነበረም። ከላይ በማሳያነት የቀረቡትም ሆነ ይሄንኑ ዓላማ ማነጣጠሪያ አድርገው የተጀመሩት ሁሉ ግንባታቸው ከክብረ በዓሉ ማግስት ጀምሮ ተረስቷል። ምክንያቱ ደግሞ አነሳሱም ስፖርቱን ሳይሆን ፖለቲካውን የያዘ ከዛ ባለፈ ደግሞ የእርስ በእርስ ፉክክር የወለዳቸው ስለነበሩ ጣሪያ አልባ ሆነው የህዝብና መንግስትን ሀብት አላግባብ ሲባክንባቸው ቆይቷል። መቋጫ አልባው ጅማሮ በሀዋሳ ፣መቐለ፣ ባህርዳርና አዲስ አበባ የሚገኙ ስታዲየሞች የግንባታ ሂደት ምንም እንኳን ከላይ እንዳልነው ፖለቲካዊ አጀንዳን መሰረት አድርገው መጀመራቸው ለመጓተታቸው ምክንያት ቢሆንም ስፖርቱን ታሳቢ በማድረግ ግንባታቸው የተጀመሩቱም የችግሩ ሰለባ ከመሆን ካለመዳናቸውም በላይ ሙሉ ለሙሉ አለመጠናቀቃቸው ከካፍ መስፈርት ውጪ አድርጓቸዋል። ለዚህ ማሳያ ይሆን ዘንድ በባህር ዳርና መቐለ ከተማ እየተገነቡ የሚገኙት ስታዲየሞች የግንባታ ሂደት ዘርዘር አድርጎ መመልከቱ አስፈላጊ ይሆናል። ማቱ ሳላህ ትግራይ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታ በ2003 ዓ.ም ነበር የተጀመረው። የስታዲየሙን ግንባታ ውጥን ከአስር ዓመት በፊት ቢጀመርም ቅሉ ዛሬም ግንባታው አልተጠናቀቀም። ህብረተሰቡ የግንባታው ሂደት መጓተቱን አስመልክቶ «ማቱሳላ» የሚል መጠሪያ ሰጥቶታል፡፡ በእርግጥ ከህዝብና መንግስት በተገኘ ገንዘብ የሚሰራ ግንባታ በዚህን ያህል ጊዜ ሲቆይ ስሙ ከዚህም በላይ ቢባል ያንሰዋል።የትግራይ ክልል ስፖርትና ወጣቶች ጽህፈት ቤት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ገብረማርያም ዘሚካኤል ከወራት በፊት ለአዲስ ዘመን የሰጡት መረጃ እንደሚያመለክተው ፤ስታዲየሙን በ530 ሚሊዮን ብር ገንብቶ ለማጠናቀቅ ታስቦ ነበር ፤ የተለያዩ ችግሮች በማጋጠማቸው ግንባታው ተጓቷል ወጪውም ከታሰበው ከፍ ብሏል። በአሁኑ ወቅት የግንባታው የመጀመሪያው ምዕራፍ 90 በመቶ መድረሱንና ስድስት መቶ 57 ሚሊዮን ብር ወጪ መደረጉን ነበር የነገሩን። የግንባታው የመጀመሪያው ምዕራፍ አስር በመቶ የቀረው ቢሆንም ፤ ከ127 ሚሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ ወጪ አስወጥቷል። አቶ ገብረማርያም ፤የግንባታው ቀሪ 10 በመቶ ስራ «የፊኒሺንግ» ስራ ነው። ይሄውም የወንበር ገጠማና የሼድ ስራ ይቀራል፣ የመብራትና የድምጽ ሥርዓት፣ የካሜራ ሲስተም ዝርጋታና ጣሪያ የመግጠም ስራን ያጠቃልላል። ለዚህ ደግሞ የሚያስፈልገው ገንዘብ ግን ከ600 ሚሊዮን ብር ያላነሰ ነው። የግንባታው ሂደት መጓተት በህዝብና መንግስት ሀብት ላይ ጎትቶ ያመጣው ብክነት ግን ለትውልድ እዳ ይሆናል። የትግራይ ስታዲየምን መቋጫ አልባ የግንባታ ሂደት ተመለከትን እስቲ ወደ ባህር ዳር እንውረድ። ጣሪያ አልባው ስታዲየም የባህር ዳር ስታዲየም ግንባታ ታህሳስ 2 ቀን 2002 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን ፤የግንባታ ሂደቱ እንደሌሎቹ ሁሉ መጓተት ተስተውሎበታል። የባህርዳር ሁለገብ ስታዲየምን ለመገንባት በአማራ ክልል የቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር አቶ አያሌው ጎበዜና በሚድሮክ ኢትዮጵያ ባለቤት በሼህ መሃመድ አላሙዲን አማካኝነት የውል ስምምነት ተፈርሞ በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ይጠናቀቃል ቢባልም ይኸው እስከ አሁን አለ፡፡ 60ሺ ተመልካቾችን የመያዝ አቅም እንደሚኖረውም የተነገረለትና በሁለት ምዕራፍ ተከፍሎ በ700 ሚሊዮን ብር ሊገነባ ጉዞው የጀመረው ስታዲየሙ የመጀመሪያውን ምዕራፍ በ380 ሚሊዮን ብር ወጪም ነበር የተጀመረው።ስታዲየሙ ለክልሉ ብቻ ሳይሆን ሀገሪቱ ዓለም አቀፍና አህጉር አቀፍ ውድድሮችን ለማዘጋጀት የሚያስችል መሆኑ ብዙዎች እንዲናፈቁት ያደረገ ቢሆንም ከስድስት ዓመት በላይ ሳይጠናቀቅ አስቆጠረ። የአማራ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ጉዳይ ቢሮ የግንባታው ሂደት መዘግየቱን አምኖ ሁኔታው ግንባታው ሲጀምር በዕቅዱ ያልተካተቱ ተጨማሪ ማሻሻያዎች በመኖራቸው ነው ሲል ምላሽ ሰጠ። ያልተጠናቀቁ ሥራዎች ላይ ብቻ ሳይሆን በተጨማሪም ሁለት የእግር ኳስ ሜዳዎችን ሊገነቡ መታቀዳቸው ተናገረ፡፡በመሆኑም ከተቋራጮች ጋር የነበረው የስምምነት ዕድሳት እና ከስድስት ዓመታት በፊት የነበረው የግንባታ ግብዓት ወጪ ተመጣጣኝ ያለመሆኑ እንዲዘገይ አድርጎታል። ቢሮው ይሄንን ሲል መጓተቱን ተከትሎ የደረሰውን ያለ አግባብ ወጪ ሳይሸሽግ ተናገረ 2003 ዓ.ም የስታዲየሙ ግንባታ ሲጀመር በ380 ሚሊዮን ብር ቢሆንም አሁን ላይ 589 ሚሊዮን ብር ደርሷል። እንደምንም ብሎም ስታዲየሙ በ2009 ዓ.ም 86 በመቶ ላይ መድረስ ቻለ። በዚሁ ዓመት ደግሞ የስታዲየም ዋና አካል የሆነው የጣራና የወንበር ተከላ ሳይጠናቀቅ የአማራ ክልላዊ መንግስት ርክክብ መፈጸሙ ተሰማ። የአማራ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ጉዳይ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙሉአዳም ጌታነህ በወቅቱ፤ የተመልካች ወንበር ዝርጋታ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2009 ዓ.ም. ድረስ እንደሚጠናቀቅና በ2010 ዓ.ም የሽፋን ግንባታ በሚድሮክ ኢትዮጵያ ለማከናወንም ስምምነት መደረሱንና በቀሪው ግንባታ ተጨማሪ 400 ሚሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ ተናግረው ነበር። የጣሪያውም ሆነ የተመልካች ወንበር በተባለው ጊዜው ሳይጀመር ይኸው ሁለት ዓመት ተቆጠረ። የባህር ዳር ስታዲየም ግንባታ በከፊል ከተጠናቀቀ በኋላ ከሰባት ያላነሱ ዓለም አቀፍ ውድድሮችን ሲያከናውን ቆይቷል። ኢትዮጵያ ለምታስተናግደው እግር ኳሳዊ ውድድሮች ከዓለም አቀፍም ሆነ ከአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ዕውቅናና ተቀባይነት በማግኘት እነዚህ ጨዋታዎችን ማድረግ ቢቻልም፤ቀጣይ ጨዋታዎችን ለማድረግ ማሟላት የሚገባው መስፈርት መኖሩን ካፍ ከሰሞኑ በደብዳቤ አስታውቋል። የትግራይ ስታዲየምም በተመሳሳይ እጣ ፈንታ ላይ ተቀምጧል። ትኩረት ይሰጥ ዘንድ በአጠቃላይ በመላው አገሪቱ የሚገነቡት ስታዲየሞች አንዳቸውም ሙሉ ለሙሉ አልተጠናቀቁም። ከተመልካቾች መቀመጫና ውጫዊ ገጽታ ባሻገር የመጫወቻ ሜዳ ጥራት፣ አስፈላጊ ውስጣዊ ግንባታዎች አለመጠናቀቅ ዋጋ እያስከፈለ መጥቷል። በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች ተገንብተዋል የሚባሉትንና በግንባታ ሂደት ላይ የሚገኙት በአጭር ጊዜ ማጠናቀቅ ከተቻለ ለስጋቱ ምላሽ የሚሰጥ ይሆናል። በተለይ ደግሞ ዋነኛ አማራጭ ሆነው የቀረቡትን የትግራይና ባህር ዳር ስታዲየሞች ቀሪ ስራዎቹን በከፍተኛ ትኩረትና ርብርብ መስራትን የግድ ይላል ። ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ እስካሁን ለዚህ ችግር ዘላቂ የሆነ መፍትሄ ለማምጣት ያሰበው ነገር ከመናገር ይልቅ ትግራይና ባህርዳር ስታዲየም ጊዜያዊ ፍቃድ ማግኘታቸውን አጉልቶ ማውራትን ነው የመረጠው። ሆኖም ሀገሪቱ ከገባችበት ምጥ ለመውጣት የሚቻለው ዘለቄታዊ መፍትሄ ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት ነው የሚያስፈልገው::በሌላ በኩል ከወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ጋር በመቀናጀት ለመፍትሄው በአብሮነት መስራቱ በይደር መተው የለበትም። በየክልሉ ግንባታቸው ተጀምረው በትኩረት እጦት ቆመው የቀሩትን ስታዲየሞች በማስቀጠል በአጭር ጊዜ እንዲጠናቀቁ መስራት ያስፈልጋል። አዲስ ዘመን ረቡዕ ነሐሴ 8 / 2011 ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=16047
1,234
2ስፖርት
ካልተጠበቀው የአርሰናሎች እጅ መፈታት ጀርባ
ስፖርት
August 13, 2019
25
ላለፉት ሁለት ወራት በእንግሊዝ ክፍት ሆኖ የቆየው የተጫዋቾች ዝውውር መስኮት መቋጫቸውን አግኝቶ ከመዘጋቱ በፊት የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች ለ2019/20 የውድድር አመት ተጠናክረው ለመምጣትና የሊጉን ዋንጫ ማንሳት እንዲቻላቸው ውጤታማ ያደርጉናል ብለው የሚያስቧቸውን ምርጥ ተጫዋቾች የግላቸው ለማድረግ ሲለፉ ሰንበተዋል። ከወትሮው በተለየ ዘንድሮ በደራው የተጫዋቾች ዝውውር ከአንድ ነጥብ አራት ቢሊየን ፓውንድ በላይ ወጪ ሆኗል። ከዚህ ገንዘብ መካከልም በተለይ የሊጉ ዋነኛ ተፎካካሪዎቻቸው ከፍተኛ ገንዘብ ፈሰስ አድርገዋል። በአርሰን ቬንገር የአሰልጣኝነት ዘመን ተጫዋች ለማስፈረም የሚሰስተው አርሰናልም ዘንድሮ ባልተጠበቀና በርካቶችን ባስገረመ መልኩ እጁ ተፈትቷል። የታክቲክ ቀማሪው የሰሜን ለንደኑ ክለብ አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሪም በዝውውር መስኮት ሞቅ ደመቅ ያለና ሚዛን የሚደፋ የዝውውር ተሳትፎ አድርገዋል። የዝውውር መስኮቱ ሲከፈት የአርሰናል የክረምቱ በጀት 45 ሚሊየን ፓውንድ እንደሆነ ሁሉም ሚዲያዎች ያስታወቁ ሲሆን፣ይህም በርካቶችን ተስፋ ቢያስቆርጥም በኋላ የሆነው ግን መድፈኞቹን ያስደሰተ ሆኗል። በዝውውር መስኮቱ ብራዚላዊው ወጣት ጋብሪኤል_መርቲኔሊ፣ዊሊያም_ሳሊባ፣ የማድሪድ ኮከብ ዳኒ_ሴባዮስ በውሰት፣ የሴልቲኩን የግራ ተከላካይ ኬይራን ቴርኔይን በ25 ሚሊየን ፓውንድ እንዲሁም የ32 ዓመቱን ብራዚላዊ የመሀል ተከላካይ ዴቪድ ሊውዝን ከቼልሲ በ8 ሚሊየን ፖውንድ አስፈርመዋል። አርሰናሎችን ከሁሉም በላይ ያስደንቃቸው ግን ኮትዲቫራዊውን የሊል ኮከብ ኒኮላስ ፔፔን ወደ ኤመሬትስ ማምጣት መቻላቸው ነው።ለፔፔ የተፈታው እጃቸው ወጪ ያደረገው 72 ሚሊዮን ፓውንድ የዝውውር ሂሳብም ተጫዋቹን በእንግሊዝ ፕሪሚር ሊግ ታሪክ አራተኛው ውዱ ተጫዋች አድርጎታል። ተጫዋቹ ከአፍሪካ ተጫዋች መካከልም በከፍተኛ ወጪ በመዘዋወር ክብረ ወሰኑን እንዲረከብ አስቻሎታል። በእርግጥም በዘንድሮው የተጫዋቾች የዝውውር ገበያ ኡናይ ኤምሪ የሚፈልጉትን ያገኙ ይመስላሉ። መድፈኞቹ አስፈሪ የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቾችን ይዘዋል። የመሃል ሜዳ ክፍሉም በድንቅ ብቃት በተካኑ ተጫዋቾች የተዋቀረ ነው። ምንም እንኳን ማንችስተር ሲቲ እና ሊቨርፑልን ከመሳሰሉ ክለቦች ጋር ሲነፃጸር ምርጥ ነው ባይባልም ከአምናው በተሻለ የተከላካይ ሥፍራ ተጫዋቾችንም አዋቅረዋል። የዘንድሮው የውድድር አመት ለአርሰናሎች እጅግ አስደሳች እንዲሆን፣ ድንቅ ወጣት ተጫዋቾችን በማስፈረምና ሪከርድ መስበር እና ለእዚህም ከአርሰናሎች እጅ መፈታት ጀርባ ደግሞ አንድ ሰው አለ፤ የክለቡ የእግር ኳስ ጉዳዮች ሃላፊ ራውል ሳንለሂ። ራውል ሳንለሂ፡ ከእግር ካስ ስራ ጋር የተዋወቀው እአአ በ2003 ነው። የገበያ ማኔጅመንት ስራውን አሃዱ ያለው ደግሞ በስፔኑ ሃያል ክለብ ባርሴሎና ሲሆን ፣ከአምስት አመታት በኋላም የኑካም የእግር ኳስ ዳይሬክተር ለመሆን ችሏል። ሳንለሂ በባርሴሎና ቤት የ10 አመታት ቆይታውም እአአ በ2013 ኔይማር ጁኒየርን ከብራዚሉ ሳንቶስ፣ ሉዊስ ሱዋሬዝን ከሊቨርፑል፣ ሴስክ ፋብሪጋዝን ከአርሰናል እንዲሁም በርካታ ታላላቅ ተጫዋቾችን ለካታላኑ ክለብ አበርክቷል። እነዚህን ተጫዋቾች የሰበሰበው የካታላኑ ክለብ ሶስት ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊ መሆን ችሏል። ሰውየው በስፔን ቆይታው ያስመዘገበው ስኬቶችም ከማንም ቀደመው የታዩት ደግሞ በአርሰናል ነበር። ጥሩ ተጫዋቾችን በጥሩ ዋጋ የማግኘት ብቃት ያለው ራውል ሳንለሂ፣አርሰናልን የተቀላቀለው በ2018 ላይ የክለቡ የእግር ኳስ ጉዳዮች መሪ በመሆን ነው። መድፈኖች በወቅቱ ለለውጥ የሚንደረደሩበትና የክለቡ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢቫን ጋዚዲዝም ከወራት በኋላ ወደ ኤሲ ሚላን ማቅናታቸው ራውል የክለቡ የእግር ኳስ ጉዳዮች ሃላፊ እንዲሆን አስችሎታል። በእርግጥ ሳንለሂ በአርሰናል አዲሱን የስራ ሃላፊነት ከተረከበ በኋላ ነገሮች ጥሩ አልነበሩም። በተለይ የክለቡ በፋይናንስ አቅሙ መንገዳገዱ፣ የራምሴ በነፃ መልቀቅና አስተዳደሩም ክፉኛ አሰልችቶታል።ይሁንና የንግዱ ሰው በዘንድሮው የዝውውር መስኮት ያሳየው ብልጠትና የቢዝነስ ብቃቱን ሁሉን አስረስቶታል። ምንም እንኳን አርሰናል ለሁለት አመታት ከታላቁ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ መራቁን ተከትሎ በደረሰበት የፋይናንስ ቀውስ ምክንያት በተገደበ በጀት ለመንቀሳቀስ ቢገደድም፣ በራውል ተፅእኖ ተጠቃሚ ተጫዋቾች ወደ ክለቡ መጥተዋል።፡ ስድስት ተጫዋቾች ወደ መድፈኛው ሲቀላቅሉ የፔፔ ዝውውር የክለቡን ሪከርድ ሰብሯል። የ50 አመቱ ሰው እነዚህን የመሳሰሉ ዝውውሮች ሲፈፀም፣ የተጋነነ ወጪ አለማውጣቱና የክለቡን ወጪና ገቢ በማመጣጠን 91 ሚሊየን ፓወንድ ብቻ ነው ወጪ ያደረገው። አልክስ ኢዎቢ፣ሎረን ኮሲዬልኑ፣ ጃንኪነሰን የመሳሰሉ ተጫዋቾችን በመሸጥ 60 ሚሊየን ፓውንድ ገቢ በማስገኘቱም የበርካቶችን አድናቆት አትርፏል። የመድፈኖቹ ደጋፊዎች እንደ ከዚህ ቀደሙ የዘንድሮውን የውድድር አመት በጭንቀት እንዳያሳልፉ ምርጥ ተጫዋቾችን ወደ ኤመርትስ በማምጣት እፎይታን ሰጥተዋልና ከሁሉም ቀድመው ራውል ሳንለሂ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።አዲስ ዘመን ነሀሴ 7/2011 ታምራት ተስፋዬ
https://www.press.et/Ama/?p=15999
520
2ስፖርት
የዶሃ የሞቀ ድግስና የኳታር ጥሪ
ስፖርት
August 17, 2019
21
የዓለማችን ትልቁ የአትሌቲክስ ውድድር ከአንድ ወር በኋላ በኳታር መዲና ዶሃ ይካሄዳል። ለአንድ ሳምንት ያህል የሚካሄደውን ትልቅ የአትሌቲክስ ድግስ ለመጀመሪያ ጊዜ በመካከለኛው ምሥራቅ ለማሰናዳት ዶሃ ፍላጎቷን የገለጸችው እኤአ 2014 ላይ ሲሆን የአሜሪካዋን ዩጂንና የስፔኗን ባርሴሎና ከተማ በልጣ ውድድሩን የማዘጋጀት ይሁንታን አግኝታለች። ባለፈው 2017 የለንደን አትሌቲክስ ቻምፒዮና ሲቋጭም ዶሃ ውድድሩን የማዘጋጀት ዓርማ ተረክባ ባለፉት ሁለት ዓመታት ስትዘጋጅ ቆይታለች። ዶሃ በቀጣይ ሳምንታት የሞቀ ድግሷ ላይ እንዲታደሙ ከ205 አገራት እንግዶችን ስትቀበል፣ 3,500 የዓለማችን ድንቅ ድንቅ አትሌቶች የድግሷ አድማቂዎች እንደሚሆኑ ይጠበቃል። በተለያዩ ርቀቶች በተለይም በረጅም ርቀት ለውጤት የምትጠበቀው ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ አገራትም ወደ ዶሃ ለመብረር ሻንጣቸውን እያዘጋጁ ይገኛሉ። ከ10 ሺ በላይ ዓለም አቀፍ እንግዶችና ከ30 ሺ በላይ ተመልካቾች ከተለያዩ አገራት በስፍራው ይገኛሉ ተብሎም ይጠበቃል። ከኦሊምፒክና የዓለም ዋንጫ ቀጥሎ ትልቁ የዓለማችን የስፖርት መድረክ በሆነው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ከ 2 ሺ በላይ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን በስፍራው ተገኝተው ለተቀረው ዓለም ዘገባዎችን ለማድረስ ጓዛቸውን ሸክፈው ወደ መካከለኛው ምሥራቋ ቅንጡ ከተማ ለማቅናት አኮብኩበዋል። በዚህም ውድድሩን በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት ከ2 መቶ በላይ አገራት የሚገኙ ከ7 ሚሊየን በላይ ዜጎች ይከታተሉታል ተብሎ ይጠበቃል። አዲስ ዘመን ቅዳሜ የኳታርን ዝግጅትና በውድድሩ ዙሪያ ያልተሰሙ አዳዲስና አስገራሚ እውነታዎችን እንደሚከተለው ተመልክቷቸዋል። ከሊፋ ዓለምአቀፍ ስቴድየምየኳታር ዝግጅት ሲነሳ ውድድሩን የሚያስተናግደው የከሊፋ ዓለም አቀፍ ስቴድየም ሳይዳሰስ የሚታለፍ አይደለም። ይህ እጅግ በረቀቁ ቴክኖሎጂዎች የተደራጀው ስቴድየም በመካከለኛው ምሥራቅ በርካታ ታላላቅ ውድድሮችን ያስተናገደ ሲሆን ታሪካዊና በኳታር ሕዝቦች ዘንድ ልዩ ስፍራ የሚሰጠው ነው። እኤአ በ1976 የተገነባው ከሊፋ ስቴድየም 40 ሺ ተመልካቾች የመያዝ አቅም ያለው ሲሆን ባለፉት ሦስት ዓመታት የተደረገለት እድሳት በዓለማችን እጅግ ዘመናዊ ከሆኑ ስቴድየሞች አንዱ አድርጎታል። ስቴድየሙ እውን ካደረጋቸው ቴክኖሎጂዎች መካከል የአየር ፀባይ መቆጣጠሪያ አንዱ ሲሆን ሙቀትና ቅዝቃዜን እንደየአስፈላጊነቱ መጥኖ ያቀርባል። ይህም 40 ዲግሪ ሴልሺየስ የሆነውን የሙቀት መጠን ወደ 21 እንዲወርድ ያደርገዋል። ቀልብ መማረክ የሚችሉ ዘመን አፈራሽ መብራቶችን ማፍለቅ የሚችለው ይህ ስቴድየም ተመልካቾች ውድድሮችን አንድ ቦታ ተቀምጠው ከየትኛውም ማዕዘን በምቾት እንዲመለከቱ ያስችላቸዋል። ስቴድየሙ ለትራንስፖርት ምቹ በሆነው ማራኪ ስፍራ አል ዋብ አካባቢ የተገነባ ሲሆን ከዋና ከተማዋ ዶሃ በአስራ አራት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል። የትኛውም ሰው በቀላሉ በተለያዩ የትራንስፖርት አማራጮች ወደ ፈለገው ስፍራ መንቀሳቀስ እንዲችልም ያደርጋል። ከ2014 ጀምሮ እድሳት ሲደረግለት ተመልካች የመያዝ አቅሙ ወደ 48 ሺ ከፍ እንዲል ተደርጓል፣ በዙሪያውም 6 ሺ መኪኖችንና 2,300 የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶችን ማቆም እንዲችል ተደርጎ ተገንብቷል። ዋና ዋናዎቹ የስቴድየሙ መግቢያ በሮች ከዘመናዊ የባቡር ትራስፖርት ጋር የተገናኙ ሲሆን አካል ጉዳተኞች ከትራንስፖርት ወርደው ሳይንገላቱ በዘመናዊ አሳንሰሮች ታግዘው በምቾት ወደ መቀመጫቸው በቀላሉ መድረስ ይችላሉ። የስቴድየሙ የኳስ መጫወቻ ሜዳ ከአሜሪካው ኦክላሆማ ዩኒቨርሲቲና ከሌሎች የጥናት ቡድኖች ጋር በመሆን በተገኘው የምርምር ውጤት መሰረት ሙሉ በሙሉ በተፈጥሮ ሳር ተሸፍኗል። ይህ የአገሪቱን ከፍተኛ የሙቀት መጠን እንዲቋቋም ተደርጎ የተነጠፈው የተፈጥሮ ሳር በ13 ነጥብ 5 ሰዓት ውስጥ የተተከለ ሲሆን አውሮፓ ውስጥ 18 ሰዓት ይፈጅ የነበረውን የመትከል ክብረወሰን ያሻሻለ ነው። ለዚህም ከሰማንያ በላይ ማሽኖችና ከዘጠና በላይ ሰዎች በተከላው ሥራ ላይ መሰማራታቸው ተነግሯል። የማራቶን ውድድር ኳታር በረሃማ የአየር ፀባይ ያላት አገር እንደመሆኗ ከፍተኛ የሙቀት መጠን በየትኛውም ጊዜ ተጠባቂ ነው። በዓመት የምታገኘው የዝናብ መጠን በአማካኝ 70 ሚሊ ሜትር ሲሆን ይህንንም የዝናብ መጠን በብዛት የምታገኘው ከጥቅምት እስከ መጋቢት ባሉት ወራት ነው። የዓለም ቻምፒዮናውን በምታስተናግድበት ወቅት ከመስከረም እስከ ጥቅምት ባለው ጊዜ ውስጥ አገሪቱ ምሽት ላይ የሚኖራት የሙቀት መጠን ከሃያ አምስት ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሲሆን እኩለ ቀን ላይ ይህ የሙቀት መጠን ከሠላሳ ዲግሪ ሴልሺየስ ከፍ የሚልበት ዕድል ሰፊ ነው። ይህ የተፈጥሮ ፈተና በተፈጥሮ ሀብቷ የተመለሰ ይመስላል። ምስጋና ለተፈጥሮ ሀብቷ ነዳጅ ይሁንና ተዝቆ በማያልቀው የነዳጅ ገንዘቧ የአየር ፀባይን የሚቆጣጠር ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ስቴድየም ውስጥ አስገጥማ የብዙዎች ስጋት የሆነውን ጉዳይ መልስ ሰጥታበታለች። ይሁን እንጂ ተፈጥሮን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ማዋል የማይታሰብ ነውና ከስቴድየም ውጪ የሚደረጉ ውድድሮችን ኳታር ምን ታደርጋቸዋለች? የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀርም። በዓለም ቻምፒዮናው ከስቴድየም ውጪ ሊካሄድ የሚችለው ውድድር ደግሞ ማራቶን ነው። ዶሃ ለዚህም ጥያቄ ከዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ጋር በመሆን መፍትሔ አበጅታለች። ይህም ዓለማችን በታሪክ የመጀመሪያ የሆነ የእኩለ ሌሊት የማራቶን ውድድር እንድትመለከት ማድረግ ነው። የማራቶን ውድድሩ በእኩለ ሌሊት መካሄዱ አትሌቶችን ከከፍተኛ የሙቀት መጠን ከመገላገል ባለፈ በዘመናዊና ማራኪ መብራቶች የተሸቆጠቆጡት ግዙፍ ሕንፃዎቿ ዓይነ ግቡ እንዲሆኑ ያስችላቸዋል። ‹‹ይህ የፈጠራ ውጤት ነው፣ የተለየ ነገር ከመሆኑ ባሻገር የዓለማችን ታላላቅ የማራቶን ውድድሮች ገበያን የመሳብ አቅም ይኖረዋል›› በማለት የዓለም አቀፉ አትሌቲክ ፕሬዚዳንት ሴባስቲያን ኮ የምሽቱን ማራቶን ከወዲሁ አሞግሰውታል። በርካታ አትሌቶችም ይህን ሃሳብ ደግፈውታል። አካል ጉዳተኞችኳታር የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮናውን በማስተናገዷ ብቻም ሳይሆን በሌሎች ጊዜያትም ለአካል ጉዳተኞች ምቹ ከሆኑ አገራት መካከል ትጠቀሳለች። ሆቴሎች፣የአየር መንገዶች፣የንግድ ማዕከላት፣ትላልቅ ባንኮች፣የመንግሥት ሕንፃዎች ለአካል ጉዳተኞች ዊልቼርና መፀዳጃዎችን ለማቅረብ ተዘጋጅተው ይጠብቃሉ። አለባበስሁሉም የአረብ አገራት ማለት ይቻላል ከአለባበስ ጋር በተያያዘ ያላቸው ጥብቅ አቋም በብዙዎች ዘንድ ይታወቃል። በዓለም ቻምፒዮናው ወቅት ግን ማንኛውም ሰው የአካባቢውን ባህልና ስነ ስርዓት በማይፃረር መልኩ ቀላል ልብሶችን መጠቀም ይችላል። ጎብኚዎችም በሆቴሎችና በመዋኛ ገንዳዎች አካባቢ አጭርና ገላን ሊያሳይ የሚችል ልብስ ሊያደርጉ ይችላሉ። እነዚህ ልብሶች ግን ሕዝብ በሚሰበሰብበት አካባቢ እንዲለበሱ አይመከርም። በተለይም ሴቶች በአረብ አገራት ከአለባበስ ጀምሮ የሚጣልባቸው ገደብ በኳታር በተለየ መልኩ የሚታይ ከመሆኑ ባሻገር ሴቶች ለብቻቸውም ይሁን በቡድን የመንቀሳቀስ መብታቸው የተከበረና በሚኖራቸው ባህሪ ላይም ገደብ እንዳልተቀመጠ በመጥቀስ አገሪቱ ታበረታታለች። ቋንቋእንደ አለባበስ ሁሉ በአብዛኞች አረብ አገራት ጎብኚዎች ከቋንቋ ጋር በተያያዘ የሚቸገሩበት አጋጣሚ ትንሽ አይደለም። ኳታር ግን የቋንቋ ጉዳይ አያሳስባችሁ ትላለች። የአገሪቱ ብሔራዊ ቋንቋ አረብኛ ቢሆንም እንግሊዝኛ በስፋት ይነገራል ወይም ለመግባቢያነት ይውላል። በተለይም አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ በርካታ የአውሮፓ ቋንቋዎች በሥራ ላይ እንደሚውሉ ታውቋል።በከተማዋ ዶሃ መድሃኒቶችን ጠይቆ የማይታጣባቸው የተደራጁ በርካታ መድሃኒት መደብሮች ሃያ አራት ሰዓት በእንግሊዝኛ ቋንቋ ለማገልገል ዝግጁ ናቸው። ከዚሁ ከጤና ጋር በተያያዘ ኳታር በጤናው ዘርፍ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ከሚቀመጡ አገራት መካከል አንዷ ስትሆን በርካታ ቁጥር ያላቸው ክሊኒኮችን ከማዘጋጀት ባለፈ ጎብኚዎች በአደጋ ጊዜ የመንግሥት ሆስፒታሎችን መጠቀም እንዲችሉ ስርዓቶችን ዘርግታለች። ፀጥታና ደህንነት11,500 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ስፋት ያላት ኳታር ሉአላዊ አገር የሆነችው እኤአ 1971 ላይ ሲሆን ባለፈው ዓመት የሕዝብ ቁጥሯ 2 ነጥብ 56 ሚሊዮን እንደ ደረሰ መረጃዎች ይጠቁማሉ። እጅግ ሀብታም ከሚባሉ የዓለማችን አገራት አንዷ የሆችው ኳታር የሕዝቧ የነብስ ወከፍ ገቢ መቶ ሺ ዶላር ደርሷል። በዓለማችን ዝቅተኛ ወንጀል ከሚፈፀምባቸው አገራት አንዷ ስትሆንም የሐይማኖትም ይሁን የፖለቲካ ቀውስ የሌለባት ፍፁም የተረጋጋች አገር ናት። በወታደራዊና በመንግሥት ተቋማት፣በፖሊስና አየር ማረፊያዎች አካባቢ ካለ ፍቃድ ፎቶ ግራፍ ማንሳት ይከለከላል። የአገሪቱን ዜጎች ካለፍቃዳቸው ፎቶ ግራፍ ማንሳትም አይፈቀድም። ከሐይማኖት ጋር በተያያዘ የአገሪቱ ሕዝቦች እስልምና የሕይወታቸው መሰረት ቢሆንም ሌሎች ሐይማኖቶችን አቅፈው ለመያዝ አይቸገሩም። ለዚህም የሒንዱ የእምነት ስፍራዎችና ቤተክርስቲያናት በአገሪቱ መኖራቸው ማሳያ ነው። ስጋቶችኳታር ታላቁን የዓለም ዋንጫ ከማስተናገዷ ከሦስት ዓመታት አስቀድሞ የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮናን ማዘጋጀቷ ለወደፊቱ ድግሷ ገፅታን በመገንባት ረገድ ፋይዳ ቢኖረውም የቅርቡ ጥሪዋን ሊያደበዝዝ የሚችል አንድ ስጋት ሊገጥማት እንደሚችል ይታመናል። ይህም ስጋት የአትሌቲክስ ቻምፒዮናው ቀድሞ ከሚካሄድበት ወቅት ገፋ ተደርጎ መስከረም ወር ላይ መደረጉ ነው። የመስከረም ወር አብዛኞቹ ተወዳጅ የአውሮፓ ሊጎች ውድድር የሚጀምሩበት መሆኑ በርካታ የስፖርት ቤተሰብ ቀልቡ ወደ እግር ኳሱ ሊሸፍት ይችላል የሚል ስጋት አለ። ከዚህ በተጨማሪ የዓለም ቻምፒዮናው በሚካሄድበት ወቅት ጃፓን የምታዘጋጀው የዓለም ራግቢ ቻምፒዮና የመገናኛ ብዙሃንና የስፖርቱን ቤተሰብ ትኩረት በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ይሻማባታል የሚል ምክኒያታዊ ስጋት አለ።አዲስ ዘመን ነሀሴ 11/2011 ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=16266
1,022
2ስፖርት
ኢትዮጵያ በመላ አፍሪካ ጨዋታ በ13 ስፖርት ትሳተፋለች
ስፖርት
August 15, 2019
55
በሞሮኮ ራባት ከተማ በሚካሄደው 12ኛው መላ አፍሪካ ጨዋታ ኢትዮጵያ በ13 የስፖርት አይነቶች ተሳታፊ ለመሆን ልዑካን ቡድኗን ወደ ስፍራው ልካለች። ከዚህ ቀደም በነበረው የመላ አፍሪካ ጨዋታ ኢትዮጵያ በአስር የስፖርት አይነት ተሳታፊ እንደነበረች የሚታወስ ሲሆን ዘንድሮ በቼዝ ፣ ካራቴና 3 በ 3 ቅርጫት ኳስ ውድድር በአዲስ የምትሳተፍባቸው የስፖርት ዓይነቶች ሆነው ተካተዋል። ውድድሩ ከመጪው ማክሰኞ አንስቶ ለተከታታይ ሁለት ሳምንታት የሚካሄድ ሲሆን ኢትዮጵያን በተለያዩ ስፖርቶች የወከሏት መቶ ሰማንያ ስምንት አትሌቶችና የልዑካን ቡድኑ ከትናንት በስቲያ ምሽት በሂልተን ሆቴል አሸኛኘት ተደርጎለታል። የአሸኛኘት ፕሮግራሙ ላይ የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ እርስቱ ይርዳ ፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደ ጊወርጊስ እንዲሁም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ሱፐር ኢንቴደንት ኮረኔል ደራርቱ ቱሉ በመገኘት የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፈዋል ። ኮሚሽነሩ አቶ እርስቱ ይርዳ 12ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታ ከዚህ በፊት ከነበረው በተሻለ መልኩ ጊዜ ተወስዶ ዝግጅት እንደተደረገበት ገልፀዋል። አትሌቶች የተሻለ የቴክኒክ፣ የታክቲክ እና ስነ ልቦና ዝግጅት ያደረጉበት፤ አሠልጣኞች በቂ ጊዜ ወስደው ሠልጣኞችን ለማብቃት እና ውጤታማ ለማድረግ ተግተው የሰሩበት መሆኑን የተናገሩት ኮሚሽነሩ ኢትዮጵያ በዘንድሮው መላ አፍሪካ ጨዋታ ተሳትፎዋን ከፍ በማድረግ በአስራ ሦስት የስፖርት አይነቶች ተፎካካሪ እንደምትሆን አብራርተዋል። ‹‹ በ12ኛው መላ አፍሪካ ጨዋታ ስትሳተፋ ሀገርን ነው የምትወክሉት፣ የቡድን መንፈስን በማጠንከር፣ ኢትዮጵያዊ ዲሲፕሊን ጠብቃችሁ፣ በብቃት እና በውጤት የተሻላችሁ በመሆን ሀገራችን በአፍሪካ መድረክ ደምቃ እና ሰንደቋ ከፍ ብሎ የሚታይበት ሊሆን ይገባል›› በማለትም ኮሚሽነሩ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል። የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊወርጊስ በበኩላቸው ስፖርት መቻቻልና መደጋገፍን የሚጠይቅ መሆኑን ጠቁመው፤ ኢትዮጵያ በአፍሪካ በሁሉም ነገር የመሪነት ሚና እንዳላት አብራርተዋል። በመሆኑም ስፖርተኞች በቆይታቸው በኢትዮጵያዊ ስነምግባር እና በአስተማሪነት መሪ በመሆን ፤ ከሁሉ በላይ ህዝቡ የሚጠብቀውን ውጤት በማስመዝገብ ተልዕኳቸውን አሳክተው መመለስ እንደሚገባቸው ተናረዋል። ለዚህም ኮሚሽኑ እና ኦሊምፒክ ኮሚቴ አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረጉን አብራርተዋል። ከሁሉም ዘግየት ብላ ወደ ስፍራው የደረሳቸው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ሱፐር ኢንቴደንት ኮረኔል ደራርቱ ቱሉ ወደ አዳራሹ ስትገባ በስነስርዓቱ እየታደሙ የሚገኙ አትሌቶች በሙሉ ከመቀመጫቸው በመነሳት በደማቅ ጭብጨባ ተቀብለዋታል። ደራርቱ በአስተላለፈችው መልዕክት ‹‹ሀገርን መወከል ከባድ ነው፤ ስፖርት ጨዋነት ነው፣ ፍቅር ነው፣ ማሸነፍ ሌላ ጉዳይ ነው፤ በመሆኑም ሀገራችሁን በጥሩ ስነመግባር እና ስፖርታዊ ጨዋነት ልታስጠሩ ይገባል›› ብላለች ። ‹‹ኢትዮጵያን መወከል መታደል ነው እና ክብር እና ኩራት ሊሰማችሁ ይገባል። እኔም ከ20 ዓመታት በፊት ይህ እድል ገጥሞኝ ስሜቱ ምን እንደሆነ አውቀዋለሁና›› በማለትም ደራርቱ ተናግራለች። በአሸኛኘት ስነ ስርዓቱ ላይ የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ጌታቸው ባልቻ የልዑካን ቡድኑ በድል እንዲመለስ ምኞታቸውን የገለፁ ሲሆን፣ የተሳፊ ልዑካን ቡድን አባላት ተወካዮች በውድድሩ የተሻለ ውጤት ለማስመ ዝገብ በቂ ዝግጅት ማድረጋቸውን በመድረኩ ገልፀዋል ። አዲስ ዘመን ነሀሴ 9/2011ቦጋለ አበበ
https://www.press.et/Ama/?p=16126
377
2ስፖርት
«የአዲስ አበባ ስታዲየምን አድሰን ለውድድር ብቁ እናደርገዋለን»
ስፖርት
August 19, 2019
28
– አቶ ዮናስ አረጋይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽነር ከዓመታት በፊት በሃገር አቀፍ ስፖርታዊ ውድድሮች በውጤታማነት አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተጠቃሽ ነበር። ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ግን የከተማዋ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ እያሽቆለቆለ በመሆኑ ይህ እውነታ በቦታው የለም። ከወራት ወዲህም ባልተለመደ መልኩ ህዝባዊ የስፖርት እንቅስቃሴ እየተስፋፋ ይገኛል፤ በከተማዋ። ይህም ስፖርቱ ዳግም የሚያንሰራራበት ይሆናል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል። አዲስ ዘመን ጋዜጣም ከከተማ አስተዳደሩ ስፖርት ኮሚሽነር አቶ ዮናስ አረጋይ ጋር በክንውናቸው ዙሪያ እንደሚከተለው ቆይታ አድርጓል። እኔም አመሰግናለሁ። የመጀመሪያ ሥራችንን ያደረግነው ከወረዳ እስከ ከተማ ያለውንና ስፖርቱን የሚመራውን አካል መፈተሽ ነው። በዚህም የማስፈጸም አቅም ማነስ፣ ስልጠናዎችን አለማግኘት እንዲሁም አላስፈላጊ ተቋማት እንደነበሩ በጥናት ለይተናል። ከዚህም በኋላ ሙያተኞች በተማሩባቸውና በሚፈልጓቸው ሥራዎች ላይ እንዲሰማሩ አድርገናል። ለአመራሮችም የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን ሰጥተናል። ቢሮው ብዙውን ጊዜ ውድድሮች ላይ ነው ያሳለፈው፤ ውድድር ካለ ደግሞ ሁሌም አበል አለ። ይህ ደግሞ ከፍተኛ ወጪን ያስከትላል። ከዚህ ይልቅ ታዳጊዎች ላይ ትኩረት አድርገን ብንሠራ የተሻለ እንደሚሆን በማመንም በተለያዩ ስፖርቶች ጸጋ ያለባቸውን ቦታዎች ለይተን መሄድ እንዳለብን ከስምምነት ደርሰናል። በመሆኑም ጥቂት ውድድሮችን አዘግይተናል፤ ስፖርት ለሁሉም መሆኑን ካመንን ደግሞ አዳራሽ ውስጥ በመሰብሰብ አይደለም። ስፖርት እንቅስቃሴ በመሆኑ ወደ ማስ ስፖርት እንቅስቃሴ ገብተናል። እንደሚታወቀው ትውልዱ ተላላፊ ባለሆኑ በሽታዎች ተጠቂ እየሆነ ነው፤ በአካል ብቃት ረገድም ጥንካሬ አይታይበትም። በመሆኑም በአካልና በአዕምሮ ጠንካራ የሆነ ትውልድ ለማፍራት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ አስፈላጊ ነው። የማስ ስፖርትን የጀመርነው በዚህ ሲሆን፤ በመጀመሪያው ዙር 21ሺ፣ በሁለተኛው 35ሺ እንዲሁም በሦስተኛው ዙር 55ሺ ሰዎች ተሳትፈዋል። በቀጣይ ደግሞ 250ሺ ሰዎች ተሳታፊ ይሆናሉ ብለን እንጠብቃለን። በእርግጥ በወር አንዴ እየተገናኙ እንቅስቃሴ ማድረግ ውጤታማ ያደርጋል ተብሎ አይጠበቅም፤ ነገር ግን ህዝቡን በአንድ ማሰባሰብ እንዲሁም መልዕክት ማስተላለፍ ይቻላል። ከዚህ ባሻገር የውጤታማ ስፖርተኞች ምንጭም ይሆናል፤ ለአብነት ያህል ታዳጊዎች በአካላዊ እንቅስቃሴዎች ተሳታፊ ሲሆኑ ፍላጎታቸው ወዳዘነበለበት ስፖርት ሊገቡ ይችላሉ። ባለሙያዎችም እንደየተሰጥኦአቸው ታዳጊዎችን ለመለየት ያስችላቸዋል። በመሆኑም ይህ እንቅስቃሴ እንደ ፌስቲቫል ብቻም ሳይሆን ከስፖርት ተልእኮ አኳያም ስትራቴጂ ነው። ከክረምቱ ጋር በተያያዘ የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ስልጠና እየተሰጠ ነው። በአርባ ምንጭ በተጀመረው የፕሮጀክቶች ሻምፒዮና ላይም እየተሳተፍን ነው። ከዚህ ባሻገር በአዲስ አበባ እና ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ስናስጠና ፕሮጀክቱ በሚፈለገው መልኩ እየሄደ አለመሆኑ ታውቋል። በከተማዋ ከ200 በላይ ጣቢያዎች ቢኖሩም ቆም ብለን ማየት ያሉብን ነገሮች አሉ። ጥሩ የተያዙ ቢኖሩም፤ ሱፐርቫይዘሮችን በቅጡ እንዳልያዝናቸው፣ አሰልጣኞችን በትክክል እንዳልመራናቸው እንዲሁም የትጥቅ እጥረት መኖሩን ተመልክተናል። ስልጠናው ላይም ችግር እንዳለ ታውቋል፤ ለምሳሌ ፕሮጀክቶች ላይ መሰጠት ያለበት በስልጠና ማዕከላት ይሰጣል፤ በማዕከላት የሚሰጠው ደግሞ በፕሮጀክቶች። ይህንንም ለማስተካከል ሰነድ በማዘጋጀት ላይ ነን። የማያስፈልጉ ተቋማት መካከል አንዱ ግንባታን የሚመለከት ነው። የተለያዩ የማዘውተሪያ ስፍራዎችን ለመገንባት ከተያዘው የጊዜ ገደብ በላይ ረጅም ዓመታትን የቆዩ አሉ። ከእኛ መካከል ደግሞ የግንባታ ባለሙያ የለም፤ ታዲያ እንዴት አድርገን ልንመራው እንችላለን? ታላቁ የህዳሴ ግድብ ከመገንባቱ በፊት የተጀመሩ ግንባታዎች እስከአሁን መጠናቀቅ አልቻሉም፤ በመሆኑም ከዚህ በኋላ ሜዳዎችና ስታዲየሞች እንደሚያስፈልጉን ለኮንስትራሽን ቢሮ ሃሳብ እናነሳለን እንጂ ግንባታዎችን አንመራም። ሌላው የትምህርትና ስልጠና ማዕከላት በሚል የሚጠሩት ተቋማት፤ እንደ ስማቸው ስልጠና እየሰጡ አይደለም። እንዲያውም አንዳንዶቹ ሆቴል ይመስል አልጋ ያከራያሉ፤ ይህንን ከለየን ኋላም ወደ እርምጃ ገብተናል። በከተማዋ ስንዝር መሬት ማግኘት አስቸጋሪ ቢሆንም፤ በሁሉም ወረዳዎች አንድ ጥርጊያ ሜዳ ለማሠራት አስበን እስከአሁን 61 አሠርተናል። ሌሎችንም ሳር በማልበስና በማጠር ወጣቶች ተደራጅተው ገቢ እንዲያገኙ ለማድረግ እየሠራን ነው። ከዚህ ጎን ለጎን ነባር ማዘውተሪያዎችን የይዞታ ማረጋገጫ እንዲያገኙ እያደረግን ነው። በተደጋጋሚ ቅሬታ በሚነሳባቸው ኮንዶሚኒየሞች አካባቢ ባደረግነው ምልክታም ለማዘውተሪያ የተተው ስፍራዎች ኮብል ስቶን ተነጥፎባቸው የመኪና ማቆያ ሆነዋል። በመሆኑም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን እየሠራን ነው። በከተማዋ ምን ያህል የማዘውተሪያ ስፍራዎች አሉ የሚለውም እየተጠና ነው። በእርግጥ በየአካባቢው ምን ያህል የማዘውተሪያ ስፍራዎች አሉ የሚለው ስታንዳርድ የለም፤ በመሆኑም ይህንን በምሁራን ለማስጠናት አስበናል። ነገር ግን ይህ በቂ አይደለም ተጨማሪ ሥራ ያስፈልገናል። በሜጋ ፕሮጀክቶቻችን ላይ የነበሩትን ችግሮች እየተሻገርን ነው። ለአብነት ያህል 56 ሚሊዮን ብር የወጣበት የራስ ኃይሉ የመዋኛ ገንዳ በሁለት ዓመት ያልቃል ተብሎ ሰባት ዓመት ሆኖታል። በዚህ አጭር ጊዜም እየገነባ ካለው ተቋም ጋር በመነጋገርና አቋም በመውሰዳችን «ተረከቡን» የሚል ደብዳቤ ደርሶናል። ከዚህ በኋላ የሚቀረን ውሃ ተሞልቶበት መሞከር ነው። ለዚህ ደግሞ ትልቁ ገንዳ ከ6ሚሊዮን ሊትር በላይ ትንሹ ደግሞ 300 ሺ ሊትር ውሃ ያስፈልጋል። በመሆኑም ከውሃ ልማት ጋር ተነጋግረን ከአዲስ ዓመት በፊት ገንዳው ተሞክሮ ለመረከብ አስበናል። አሁን የአጥር እና ሌሎች የፅዳት ሥራዎች ላይ ነን። የአበበ ቢቂላ ስታዲየምም አብዛኛው የእድሳት ሥራው ተጠናቆ ጣራው እየተገጠመ ነው። ይህም በዓመት ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ ለምክር ቤቱ ማስገባት ይችላል። ይህ ብርም በየአካባቢው ላሉ ታዳጊዎች ድጋፍ ይውላል። የአቃቂ ስታዲየምም በአሁኑ ወቅት 56 ከመቶ ሥራው ተጠናቋል። ወወክማ ከዚህ ቀደም የነበረው አልጋ ማከራየት ቀርቶ ታዳጊዎችና የአካባቢው ነዋሪ በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲገለገልበት ተደርጓል። በቀጣይም ባለ ሰባት ፎቅ ሕንፃ የመገንባት ዕቅድ አለን። ሌላው ጃንሜዳ ነው፤ እኔ እዚያ ያሉ ግንባታዎች ትክክል ናቸው ብዬ አላምንም። ቦታው የሃይማኖት ተቋም እንደመሆኑ ሌሎች ግንባታዎችን ማከናወን በከተማዋ ያለንን አንድ ሰፊ ቦታ ማጥፋት ነው። ለረጅም ዓመታት ሲንከባለል የቆየው የጂምናዚየም ግንባታም ውሉ እንዲቋረጥና ጉዳዩም ወደ ፍርድ ቤት እንዲሄድ አድርገናል። በእኔ እምነት ከዚህ በኋላ ጃንሜዳን ከ10 በላይ ትንንሽ ሜዳዎች የሚወጣው በመሆኑ ሳር አስተክለን ለእንቅስቃሴ ማካሄጃ እንዲሁም ቱሪስቶችን የሚስብ ቦታ መሆን አለበት። በመሆኑም ይህንን ጉዳይ ለኮንስትራክሽን ቢሮ ሃሳብ አንስተናል። አንዳንድ ሱቆችም በህግ ውላቸው እንዲቋረጥ አድርገናል። ሌላው አዲስ ነገር የአዲስ አበባ ስታዲየም እንዲመለስልን ጥያቄ አቅርበናል። የአዲስ አበባ ስታዲየም እንደ ስሙ የአዲስ አበባ ከሆነ አድሰን ለውድድር ብቁ እናደርገዋለን። በዙሪያው የሚሸጠው የአልኮል መጠጥም እንዲቀር እናደርጋለን። ለከተማዋ ክለቦች ከከንቲባው ጀምሮ ከፍተኛ ድጋፍ በማድረግ ላይ እንገኛለን። ከንቲባው በተደጋጋሚ ከክለቦቹ ቦርዶችና ደጋፊዎች ጋር ተነጋግረዋል፤ በችግኝ ተከላውም አብረው ነበሩ። ለረጅም ዓመታት የቆየው የስታዲየም ማስፋፊያ ጥያቄያቸውም ተመልሶላቸዋል። በቅርቡ በተደረገ ሌላ መድረክም ሁለቱ ክለቦች የፋይናንስ ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ቃል ተገብቶላቸዋል። ከዚህ ባሻገር ለስታዲየም ብጥብጥ ምክንያት የሚሆነው በዙሪያው ያለው የአልኮል መጠጥ በመሆኑ፤ ከሁለቱ ክለቦች 250 በድምሩ 500 ወጣት ደጋፊዎችን በመለየት በጥቃቅን እና አነስተኛ ተደራጅተው እንዲሠሩ በሂደት ላይ እንገኛለን። ወጣቶቹ ሥራ አጥ መሆናቸውን በመለየት የተደራጁ ሲሆን፤ ስልጠናም ሰጥተናቸዋል። የስም ዝርዝራቸውንም ለአነስተኛና ጥቃቅን አስተላልፈናል። ለስታዲየም ሰላም ወጣቶቹ ሥራ እንዲኖራቸውና ስፖርቱን መዝናኛ እንዲያደርጉት ነው። ይህንንም ከንቲባው በልዩ ሁኔታ እየተከታተሉት ነው። ጳጉሜ 3 ቀን በአዲስ አበባ የብሄራዊ ኩራት ቀን ይከበራል። በዚህም ላይ አራተኛው የህብረተሰብ አቀፍ የስፖርት እንቅስቃሴ የሚካሄድ ነው የሚሆነው። ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት እስከ 2፡00 ሰዓት ድረስም ህብረተሰቡ አካላዊ እንቅስቃሴ ያደርጋል። ለዚህም ከ100 ሺ በላይ ቲሸርቶች በስፖንሰር አማካኝነት እየታተሙ ይገኛሉ።አዲስ ዘመን ነሐሴ 13/2011 ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=16338
897
2ስፖርት
የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ዛሬ ይጀመራል
ስፖርት
August 19, 2019
30
እአአ 1965 መነሻውን በኮንጎ ብራዛቪል አደረገ፤ ለግማሽ ምዕተ ዓመትም ሃገራት እየተቀባበሉት ከዛሬ ደርሷል። ተረኛ አዘጋጅ የሆነችው የሞሮኮዋ ራባትም ከዛሬ ጀምሮ ከ54ቱ የአፍሪካ ሃገራት የተወጣጡትን 6ሺ አትሌቶች በ26 የስፖርት ዓይነቶች ለ12 ቀናት ታፋልማለች ። የመክፈቻ መርሐ ግብሩም በንጉሥ መሃመድ ስድስተኛ ስታዲየም ይካሄዳል። ሞሮኮ ውድድሮቹን በሰባት ከተሞቿ ያሰናዳች ሲሆን፤ ራባት፣ ካሳብላንካ፣ ሳሌ፣ ቴማራ፣ ኬህሚሴት፣ ሞሃመዲያ እና ኤል ጃዲድ ደግሞ ከተሞቹ ናቸው። የውሃ ዳር ቮሊቦል እና እግር ኳስ ውድድራቸውን ቀድመው ሲጀምሩ፤ የጁዶ ስፖርት ግን ከትናንት በስቲያ እና ትናንት በተካሄዱ ውድድሮች ማጠቃለያውን አግኝቷል። ከነገ ጀምሮም ሌሎች ስ ፖርቶች መካሄድ ይጀምራሉ። ኦሊምፒክ ከመካሄዱ ከአንድ ዓመት በፊት የሚካሄደው ይህ ውድድር የአህጉራት ኦሊምፒክ በመባል የሚታወቅ ሲሆን፤ ለታላቁ ውድድር እንደ አንድ የመምረጫ መስፈርት ያገለግላል። እአአ በ2020 የጃፓኗ ቶኪዮ በምታካሂደው ኦሊምፒክ ከመወዳደሪያ ስፖርቶች መካከል 18 በሚሆኑት የሚሳተፉ ስፖርተኞች በመላ አፍሪካ ጨዋታ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ይጠበቅባቸዋል። ኢትዮጵያም በዚህ ውድድር ተሳታፊ ከሆኑት ሃገራት መካከል ስትገኝ፤ ልዑካን ቡድኗን ባሳለፍነው ሳምንት አጋማሽ ወደ ቦታው ሸኝታለች። በውድድሩ የምትካፈልባቸው ስፖርቶችም 13 ሲሆኑ፤ አትሌቲክስ፣ ብስክሌት፣ ቦክስ፣ ካራቴ፣ ወርልድ ቴኳንዶ፣ ቼስ፣ ክብደት ማንሳት፣ የውሃ ስፖርቶች፣ ጂምናስቲክ፣ ቅርጫት ኳስ፣ ባድሜንተን፣ ጠረጴዛ ቴኒስ እና ሜዳ ቴኒስ ናቸው፡፡ የብሄራዊ ቡድን አባላትም በእነዚህ መስኮች ዝግጅታቸውን አጠናቀው ለውጤት ተዘጋጅተዋል። ከእነዚህ ስፖርቶች መካከል ቼስ፣ ካራቴ እና ሦስት በሦስት ቅርጫት ኳስ ደግሞ ሃገሪቷ ለመጀመሪያ ጊዜ በመድረኩ የምትሳተፍባቸው ስፖርቶች ናቸው። ኢትዮጵያ በዚህ ውድድር የደረጃ ሰንጠረዥ በ122 ሜዳሊያዎች ስምንተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። ከእነዚህ መካከልም 39ኙ የወርቅ፣ 39ኙ የብር እንዲሁም 52 ቱ የነሐስ ሜዳሊያዎች ናቸው። ከአራት ዓመታት በፊት በኮንጎ ብራዛቪል በተካሄደው መላ አፍሪካ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ ኬንያን በመከተል ስምንተኛ ሆና ያጠናቀቀች ሲሆን፤ 6 የወርቅ፣ 5 የብር እና 6 የነሐስ በጥቅሉ 17 ሜዳሊያዎችን ነበር ያስመዘገበችው።አዲስ ዘመን ነሐሴ 13/2011 ብርሃን ፈይሳ
https://www.press.et/Ama/?p=16341
251
2ስፖርት
ሉሲዎቹ ለቶኪዮ ኦሎምፒክ እየተዘጋጁ ነው
ስፖርት
August 15, 2019
24
የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ለቶኪዮ ኦሎምፒክ ማጣሪያ ሁለተኛ ዙር የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ነሃሴ 19 ቀን 2011 ዓ.ም በባህር ዳር ስታዲየም ከካሜሩን ያደርጋሉ።ሉሲዎቹ በአሰልጣኝ ሰላም ዘርዓይ እየተመሩ አዳማ ከተማ ቅድመ ዝግጅታቸውን እያደረጉ ይገኛል። ሉሲዎቹ ከካሜሩን የሚያደርጉት ጨዋታ ወደ ቶኪዮ ለማቅናት ወሳኝ መሆኑን ተከትሎ ክብደት በሰጠ መልኩ ዝግጅት እያደረጉ ይገኛል ተብሏል። ብሄራዊ ቡድኑ ፌዴሬሽኑ ከአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን(ካፍ) ባገኘው የአካል ብቃት መሳሪያ (ካታ ፑልት ጂፒኤስ ሲስተም) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር ዶክተር ዘሩ በቀለ ተግባራዊ እየተደረገ ልምምድ በመስራት ላይ የሚገኙ መሆኑ ተከትሎ ፤በቡድኑ ለጨዋታው እየተደረገ ያለውን ዝግጅት ክብደት የተሰጠው እንደሆነ እየተገለጸ ይገኛል። አሰልጣኝ ሰላም ጥሪ ያደረገችላቸውን 23 ተጫዋቾች በመያዝ ላለፋት ሰባት ቀናት ይሄንኑ ጠንካራ ልምምዶችን እያሰራቻቸው ሲሆን፤ከእነዚህ ተጫዋቾች መካከል ግብ ጠባቂዋ ማርታ በቀለ በጉዳት ምክንያት ከብሄራዊ ቡድን ስብስብ ውጭ እንደሆነች ለማወቅ ተችሏል ።በተጎዳችው ግብ ጠባቂ ምትክ የቅዱስ ጊዮርጊሷ ከንባቴ ከተሌ ቡድኑን ተቀላቅላ የዝግጅቱ አካል ሆናለች ተብሏል። ሉሲዎቹ ለቀናት ያህል የነበራቸውን ዝግጅት ለመፈተን ከትናንት በስቲያ ከ17 ዓመት በታች የወንዶች ቡድን ጋር የአቋም መፈተሻ ጨዋታ አድርገዋል።ተጨማሪ የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ለማድረግ በዛሬው እለት ወደ ኬኒያ እንደሚጓዙ ታውቋል።ከኬኒያ ሴት ብሄራዊ ቡድን ጋር የፊታችን ቅዳሜ አቋማቸውን ፈትሸው የሚመለሱ መሆኑን የሶከር ኢትዮጵያ ዘገባ አመላክቷል ። በባህር ዳር ስታዲየም ሁለተኛ ዙር የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ከካሜሩን የሚያደርጉት ሉሲዎቹ፤ በመጀመሪያውን ዙር ማጣሪያ ከኡጋንዳ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ጋር የተጫወቱት ሉሲዎች በድምር ውጤት 4ለ2 በማሸነፍ ነበር ወደ ቀጣዩ ዙር ያለፍት። በጨዋታው በአዲስ አበባ ስታዲዮም 3 ለ2 በሆነ ውጤት በማሸነፉ፤በመልሱ ወደ ካምፓላ በማቅናት 1ለ 0 ነበር የረቱት ። አዲስ ዘመን ነሀሴ 9/2011ዳንኤል ዘነበ
https://www.press.et/Ama/?p=16129
226
2ስፖርት
በስሪንጅ እጥረት የተቋረጠው የክትባትአገልግሎት መስተካከሉ ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 4, 2020
6
አዲስ አበባ፦ በንፋስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ ወረዳ አንድ ጤና ጣቢያ ውስጥ የወሊድ አገልግሎት ያገኙት የወረዳው አንዲት ነዋሪ በ72 ሰዓት ጊዜ ውስጥ ልጃቸው ማግኘት የሚገባትን ክትባት ባለማግኘቷ ለአምስት ቀናት ለመቆየት መገደዳቸውን ገለጹ። በስሪንጅ እጥረት ለሕፃናት የሚሰጠው የሳምባ በሽታ መከላከያ ክትባት ከአንድ ወር በፊት በአንዳንድ ጤና ጣቢያዎች አገልግሎቱ ተቋርጦ እንደነበርና አሁን መስተካከሉን የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ ገለጸ።በንፋስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ መንበረ ጌታቸው ለአዲስዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፣ በሚኖሩበት ወረዳ ውስጥ በሚገኝ አንድ ጤና ጣቢያ ሐምሌ 11 ቀን 2012 ዓ.ም የወሊድ አገልግሎት ያገኙ ሲሆን፣ ልጃቸው በ72 ሰዓት ክትባት ማግኘት ሲገባት በወቅቱ አገልግሎቱ ባለመኖሩ ከሦስት ቀናት በኋላ እንዲመለሱ በተሰጣቸው ቀጠሮ ቢመለሱም አገልግሎቱን አላገኙም። ተመላልሰው እንዲጠይቁ በጤና ጣቢያው መልስ እንደተሰጣቸውም ገልጸዋል። በግላቸው ፈልገው ከአምስት ቀናት በኋላ ማስከተብ ቢችሉም በጊዜው ባለማስከተባቸው በልጃቸው ጤና ላይ ችግር እንዳይፈጠር እንዳሰጋቸው ተናግረዋል።የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ በሽታ መከላከል ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሙሉጌታ እንዳለ በኮቪድ 19 ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት ምክንያት ስሪንጁን በወቅቱ አጓጉዞ ለማስመጣት ባለመቻሉ መከተቢያው ስሪንጅ (መርፌ) ከአንድ ወር በፊት እጥረት በማጋጠሙ በአንዳንድ ጤና ጣቢያዎች አገልግሎቱ መቋረጡን ገልጸዋል። ክምችት በነበራቸው ጤና ተቋማት ግን አገልግሎቱ ሲሰጥ እንደነበር አመልክተዋል። እጥረቱ በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ያጋጠመ አለመሆኑንም ጠቁመዋል።ስሪንጁ ከሁለት ሳምንት በፊት መግባቱንና ለጤና ጣቢያዎች መሰራጨት መጀመሩንም ገልጸዋል። በስርጭቱ ያልተዳረሰባቸው ጤና ጣቢያዎች ካሉ እንደሚያጣሩ አመልክተዋል። ክትባቱ ዘግይቶ ቢወሰድም ስጋት እንደሌለው ተናግረዋል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 28/2012  ለምለም መንግሥቱ
https://www.press.et/Ama/?p=36566
204
0ሀገር አቀፍ ዜና
በአውሮፕላንና በመሬት ላይ የመድኃኒት ርጭት የታገዘ የአንበጣ መከላከል ስራ እየተካሄደ ነው
ሀገር አቀፍ ዜና
August 4, 2020
7
 አዲስ አበባ፡- በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ የተከሰተው ሰፊ የአንበጣ መንጋ ወረርሽኝ ለመከላከል በአየር በአውሮፕላንና በመሬት ላይ የመድኃኒት ርጭት የታገዘ መጠነ ሰፊ ስራ እየተካሄደ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ። በግብርና ሚኒስቴር የእፀዋት ጤናና ቁጥጥር ዳይሬክተር ጄነራል አቶ ወልደሃዋርያት አሰፋ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለፁት፤በ2011 ዓ.ም ሰኔ አጋማሽ በመጀመሪያ በምስራቁ የሀገሪቱ ክፍል በመቀጠልም በሰሜን ምስራቅ ሶማሊያ አዋሳኝ አካባቢዎች፣ በአፋር፣ ትግራይና አማራ አዋሳኝ ቦታዎች የአንበጣ መንጋ ተከስቷል። የአንበጣ መንጋው በስፋት የተከሰተው በምስራቁ የሃገሪቱ ክፍል በተለይም በሶማሌ ክልል፣ በኦሮሚያ ምስራቅና ምእራብ ሀረርጌ፣ምስራቅ ባሌ፣ አርሲ፣ በደቡብ ኦሮሚያ ጉጂና ቦረና፣ በደቡብ ብሄር ብሄሮችና ህዝቦች ክልል ኮንሶና ኦሞ መሆኑንና በእነዚህ አካባቢዎች ሰፊ የመከላከል ስራዎች ተሰርተው መንጋው መቀነሱን ዳይሬክተር ጄነራሉ አስታውቀዋል። በአሁኑ ወቅት የአንበጣ መንጋው በሶማሌ፣ አፋርና አማራ ክልሎች እንዲሁም በትግራይ አዋሳኝ አካባቢዎች የተወሰኑ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ እንደሚገኝም ዳይሬክተር ጄኔራሉ ጠቅሰው፤ በአውሮፕላን፣ መሬት ለመሬት በሰው ሃይል የመርጫ መሳሪያዎች በመታገዝ ለመከላከል ጥረት መደረጉን ተናግረዋል። የመድኃኒት መርጨቱ ስራ በፌዴራል መንግስትና በክልሎች በቅንጅት እየተካሄደ መሆኑን ጠቅሰው፤ ለዚሁ የመድኃኒት ርጭት የሚያገለግሉ ስድስት አውሮፕላኖች በየክላስተሩ መሰማራታቸውንም አመልክተዋል። መረጃ ከመሰብሰብና አሰሳ ከማካሄድ አኳያም በሁሉም አካባቢዎች ላይ ተደራሽ ለመሆን መሬት ለመሬት የሚደረገው አሰሳ እንዳለ ሆኖ በአየር ላይም የታገዘ አሰሳ እንዲኖር ሶስት የአሰሳ ሄሊኮፕተሮች በየክላስተሩ መሰማራታቸውንም ዳይሬክተር ጀነራሉ ገልፀዋል። በእጅ የሚረጩና በጀርባ የሚታዘሉ ብዛት ያላቸው የመርጫ መሳሪያዎችና የፀረ ተባይ መድኃኒቶችም የአንበጣ መንጋው በተከሰተባቸውና መንጋው በስፋት በታየባቸው አካባቢዎች ላይ መሰራጨታቸውንና በክልሎችና በፌዴራል መንግስት ቅንጅት መጠነ ሰፊ የመከላከል ስራ እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል። በቀጣዮቹ ወራትም የአንበጣ መንጋው ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚችል ትንበያዎች ማሳየታቸውን የጠቆሙት ዳይሬክተር ጄኔራሉ፤ በመከላከል ሂደት የሚቀረው የአንበጣ ርዝራዥ ዳግም የሚራባበት እድል እንዳለና ከየመን ወደ ኢትዮጵያ ሊሻገር እንደሚችል ትንበያው ማመላከቱንም ገልፀዋል። በሰሜን ኬንያ አካባቢዎች በሚፈለፈለው አንበጣ ላይ ጠንካራ የመከላከል ስራ ካልተሰራ ከዛ አምልጦ ወደ ሰሜንና ደቡብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ሊሰራጭ እንደሚችልም ትንበያው ማሳየቱንም ገልፀው፤ ከዚህ አኳያ መንጋውን ለመከላከል ጠንካራ ስራዎች መሰራት እንደሚገባቸው አመልክተዋል። ቀደም ሲል የአንበጣ መንጋውን ለመከላከል ጠንካራ የመከላከል ስራዎች በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በኩል መሰራታቸውንም ያስታወሱት ጄኔራል ዳይሬክተሩ፤ አሁንም መንጋው ዳግም የሚከሰትበት እድል በመኖሩና የከፋ ጉዳትም ሊያስከትል የሚችል በመሆኑ ቀደም ሲል የተሰራውን የመከላከል ስራ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም አሳስበዋል። በሰባት ክልሎች፣ በአንድ የከተማ አስተዳደርና በ178 ወረዳዎች በ2011 ዓ.ም በኢትዮጵያ የተከሰተው የአንበጣ መንጋ እስካሁን ድረስ 397 ሺ ሄክታር መሬት መሸፈኑን ከግብርና ሚኒስቴር የወጡ መረጃዎች ያሳያሉ።አዲስ ዘመን ሐምሌ 28/2012  አስናቀ ፀጋዬ
https://www.press.et/Ama/?p=36571
338
0ሀገር አቀፍ ዜና
ኮርፖሬሽኑ የሚያስገነባቸው ቤቶች አፈጻጸም በጥሩ ደረጃ ላይ መሆኑን ገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 4, 2020
15
 አዲስ አበባ፡- የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ ከተማ አምስት ሳይቶች የሚያካሂደው የቤቶች ግንባታ አፈጻጸም በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ አስታወቀ። የኮርፖሬሽኑ ኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ክብሮም ገብረ መድህን በተለይ ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት፤ የቤቶቹ ግንባታ በአቧሬ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ ፋብሪካ አካባቢ፣ በመካኒሳ፣ ብሪቲሽ ካውንስልና ቦሌ ላይ እየተካሄደ ነው፤ ህንጻዎቹም እስከ 10 ፎቅ የሚደርሱና ለቅይጥ አገልግሎት (ለንግድ እና ለመኖሪያ) በሚል እየተገነቡ ያሉ ናቸው።ግንባታዎቹ እንደየቦታው ስፋት የተለያዩ አይነቶች መሆናቸውን ጠቅሰው፤ መንታ /ትዊን/ ተደርገው የሚገነቡም እንዳሉ ጠቁመዋል።የመካኒሳው፣ የጊዮርጊስ ቢራ ፋብሪካ አካባቢውና የብሪቲሽ ካውንስሉ ፕሮጀክቶች ባለሁለት መንታ ግዙፍ ህንጻዎች መሆናቸውን አስታውቀው፤ የቦሌው አንድ ግዙፍ ህንጻ መሆኑን ጠቁመዋል።እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ፤አንዳንዶቹ ህንጻዎች ባለሰባት፣ አንዳንዶቹ ደግሞ ባለ 10 ወለሎች ሲሆን፤ እየተገነቡ ያሉት በከተማ አስተዳደሩ የየአካባቢው ፕላን መሰረት ነው። በአጠቃላይ ግን የንግድ ተቋማቱ ብዛት በካሬ ሆኖ ወደፊት የሚለይ ሲሆን፤ የተቀሩት ግን ለቀቅ ባለ /ሌግዠርየስ/ በሆነ መልኩ ወደ አንድ ሺ ሰዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ቤቶች እየተገነቡ ነው። በግንባታው ላይ ተደጋጋሚ ጉብኝት በማድረግ ክትትል እንደሚደረግ ጠቅሰው፤ የተቋሙ ማኔጅመንት ካውንስል /የስራ አመራር ኮሚቴው/ ፣ የተቋሙ ቦርድም ክትትልና ድጋፍ እያደረጉ መሆናቸውን አስታውቀዋል። የፓርላማው የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽንና ትራንስፖርት ቋሚ ኮሚቴም ክትትል እንደሚያደርግ ተናግረው፤ ሰራተኛውም፣ ተቋራጮቹም፣ መሀንዲሶቹም እንዲሁ ሁሉም በጋራ በመረዳዳት መንፈስ እየተሰራ በመሆኑ አፈጻጸሙ ስኬታማ መሆን መቻሉን ተናግረዋል። የፓርላማ አባላት ፕሮጀክቶቹን እንደጎበኙትና በአፈጻጸሙም አድናቆቱ እንዳላቸው መግለጻቸውንም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።‹‹በቀጣይ ደግሞ ሰፋፊ ፕሮጀክቶች እንደሚኖሩ ይጠበቃል›› ያሉት ዳይሬክተሩ፤ የአሁኖቹ ፕሮጀክቶች ልምድ የሚቀሰምባቸው፣ አቅም እና ካፒታል የሚሰባሰብባቸው መሆናቸውን አስታውቀዋል። ኮርፖሬሽኑ ማኅበራዊ ኃላፊነቱንም እየተወጣ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከኮቪድ ጋር በተያያዘ ለንግዱ ማህበረሰብ 50 በመቶ የኪራይ ቅናሽ ማድረጉን አስታውሰዋል። ባለፉት አራት ወራት በኮቪድ ምክንያት በየወሩ ከኪራይ መሰብሰብ የሚገባውን 60 ሚሊየን ብር ከተከራዮች አለመሰብሰቡን ተናግረዋል።ዳይሬክተሩ በዚህ ፈተና ውስጥ እንዴት ከማህበረሰቡ ጎን መቆም አለብኝ ብሎ በማሰብ ኮርፖሬሽኑ ኪራይ ለመቀነስ ውሳኔ ላይ መድረሱን አስታውሰዋል። በኪራይ ዋጋ ቅነሳም በየወሩ ከአጠቃላይ ገቢው 50 በመቶውን እያጣ መሆኑን ጠቅሰው፤ በወር ከሚያገኘው 120 ሚሊየን ብር ገቢ እየሰበሰበ ያለው 60 ሚሊየን ብር ብቻ መሆኑን አስታውቀዋል። እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ፤ ኮሮና ቫይረስ ወደ ሀገራችን ከገባ አንስቶ ባሉት አራት ወራት ኮርፖሬሽኑ ማግኘት ከነበረበት 480 ሚሊየን ብር የሰብሰበው ግማሹን ብቻ መሆኑን ጠቁመዋል። ኮርፖሬሽኑ በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ብሄራዊ ንቅናቄ ሲቋቋም ድጋፍ ካደረጉት የመጀመሪያ አንዱ መሆኑን ጠቅሰው፤ በወቅቱም 10 ሚሊየን ብር መስጠቱንም ጠቅሰዋል። ኮርፖሬሽኑ በአዲስ አበባና በድሬዳዋ 18ሺ153 ቤቶች እንዳሉት ከኮርፖሬሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ከእነዚህ መካከል ወደ 6ሺ 500 አካባቢ የንግድና የድርጅት ሲሆኑ፤ የተቀሩት ደግሞ የመኖሪያ ቤቶች ናቸው።አዲስ ዘመን ሐምሌ 28/2012  ኃይሉ ሣህለድንግል
https://www.press.et/Ama/?p=36578
355
0ሀገር አቀፍ ዜና
የኦን ላይን ትምህርቱን ለከርሞም
ሀገር አቀፍ ዜና
August 4, 2020
18
 እንኳን ደስ ያላችሁ…እንኳን ደስ ያላችሁ… የምትለዋ ዜማ በምርቃ ወቅት የብዙዎች ትዝታና ከአንድ ምዕራፍ ወደሌላ ምዕራፍ መሻገራቸውን አመላካች ናት። አብዛኛው ተማሪ የልፋቱን ውጤት የሚያይበት ወቅት በመሆኑ የምርቃ ቀን እንደ ልዩ ቀን ትቆጠራለች። በዚህ ዓመት ግን የኮሮና ወረርሽኝ በመከሰቱ የዘንድሮ ተመራቂዎችን የምርቃ ቀን አደብዝዞታል። ለምን ከተባለ ከመጋቢት በኋላ ያለው የትምህርት አሰጣጥ፣ የምርምር ስራና የምርቃ ስነስርዓት የገጽ ለገጽ መሆኑ ቀርቶ በኦላይን እንዲካሄድ በመደረጉ ነው። ተማሪ ልዑል ሰለሞን በማርኬቲንግ ማኔጅመንት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሁለተኛ ዲግሪ ዘንድሮ ተመርቋል። ተማሪ ልዑል እንደሚናገረው፤ የዘንድሮ የትምህርት አሰጣጥና የምርቃ ስነስርዓት በኦን ላይን እንዲሆን በመደረጉ ከምርቃው ጋር በተያያዘ ያሰባቸውን ፕሮግራሞች እንዲሰርዝ አድርጎታል። የመመረቂያ ፅሁፉን በሚሰራበት ወቅት መረጃ ለማግኘትና ከአማካሪው ጋር ለመገናኘት የኢንተርኔት መጥፋት ተስፋ አስቆርጦት እንደነበር ያስታውሳል። የኮሮና ቫይረስ ድንገት የተከሰተ በመሆኑ እሱ የተማረበት ዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን ለማስቀጠል ምንም ዝግጅት አለመደረጉን ያስታውሳል። ኋላ ላይ ግን የኦን ላይን ትምህርት በመጀመሩ ከአማካሪው ጋር በፍጥነት እየተገናኘ መመረቂያ ፅሁፉን ማጠናቀቁን ይገልፃል።በኦን ላይን የትምህርት አሰጣጡን ለማስቀጠል ለተማሪዎች የኢንተርኔት አገልግሎት ሊመቻች ይገባል፤ ላፕቶፕ ሊኖራቸውም ያስፈልጋል ይላል። በተለይ በገጠራማ ቦታዎች ለሚገኙ ተማሪዎች ይበልጥ ትኩረት ተሰጥቶ ሊታይ እንደሚገባ ያሳስባል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፖለቲካል ሳይንስና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ትምህርት ክፍል መምህርና በዩኒቨርሲቲው የውጭ ግንኙነት ቢሮ ዳይሬክተር ዶክተር ደመቀ አጭሶ እንደሚናገሩት፤ የኮቪድ ወረርሽኝ ከተከሰተ በኋላ በተለይ የሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ የትምህርት አሰጣጥ በኦን ላይን እንዲሆን መወሰኑ ይታወሳል። ነገር ግን የኢንተርኔት አገልግሎት ዜጎች በስፋት በማያገኙበት ሁኔታ መሆኑ ችግር ነበር። በአገሪቱ አብዛኛው ተማሪ ኢንተርኔት የመጠቀም እድሉ አነስተኛ ነው። ሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ ተማሪዎች በስራም በትምህርትም ከተማ አካባቢ የሚኖሩ በመሆናቸው የኦን ላይን ትምህርቱ እንዲሰጣቸው ተደርጓል። ለትምህርት አሰጣጡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ብቻ ሳይሆን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በርካታ እገዛዎችን ማድረጉን ይናገራሉ። ሚኒስቴሩ ለማስተማሪያ የሚሆኑ ማቴሪያሎችን ከመምህራን ተቀብሎ እንዲጫኑ በማድረግና ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመነጋገር ለተማሪዎች የዋጋ ቅናሽ እንዲደረግ ጥሩ ስራዎች ማከናወኑን ያመለክታሉ። ቀደም ብሎ በዩኒቨርሲቲው የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርት ሲሰጥ የነበረው በሞጁል እንደነበር አስታውሰው፤ የኮቪድ ወረርሽኝ ከመግባቱ በፊት የተጠናቀቁ ትምህርቶች እንደነበሩም ያስረዳሉ። ነገር ግን ትምህርታቸው ሰፊ የሆኑ መምህራን የማስተማሪያ ማቴሪያሎችን ለተማሪዎች ምቹ በሆነ መንገድ እንዲቀመጥ በማድረጋቸው ያለምንም ችግር በኦን ላይን ተማሪዎቹ እንዲማሩ መደረጉን ይጠቅሳሉ። እንደ ዶክተር ደመቀ ገለጻ፤ እነዚህ ስራዎች ከተከናወኑ በኋላ ሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ ተማሪዎችን ለማስመረቅ ተችሏል። ነገር ግን የተመረቁት አብዛኛዎቹ የክፍል ትምህርት ካጠናቀቁ በኋላ የኮቪድ ወረርሽኝ የገባ በመሆኑ በኦን ላይን የማማከር ስራ ብቻ ነው የተከናወነው። በቀጣይ የኮቪድ ወረርሽኝ በዚሁ ከቀጠለ በመማር ማስተማሩ ላይ በኦን ላይ ለማካሄድ ፈተናዎች ሊያጋጥሙ እንደሚችሉ ዶክተር ደመቀ ያስገነዝባሉ። ምክንያቱም ኮርሱን በኦን ላይን ተምረው የምርምር ስራቸውንም በኦን ላይን የሚያደርጉ ከሆነ ለተማሪዎቹ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል ነው የሚሉት። በተጠናቀቀው ዓመት ግን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ውጤታማ ስራ አከናውኗል ያሉት ዶክተር ደመቀ፤ በማታው መርሃ ግብር ለሚገኙ ተማሪዎች በቴሌግራም አስተማሪዎች ትምህርቱን በድምፅ በማዘጋጀት ለተማሪዎች ይልኩ እንደነበር ይገልጻሉ። በመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች የክፍል ክለሳ ያስፈልጋቸዋል በመባሉ እንጂ ዩኒቨርሲቲው በኦንላይን ለማስተማር ዝግጅት ማጠናቀቁንም ጠቁመዋል። በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ካሳሁን ተገኘ በበኩላቸው እንደተናገሩት፤ የኮቪድ ወረርሽኝ ከተከሰተ በኋላ የፊት ለፊት ትምህርት አስቸጋሪ በመሆኑ የኦን ላይን ትምህርት እንዲጀመር ተደርጓል። በዚህም ጥሩ ውጤት ተገኝቷል። ይህን ለማስቀጠል የመምህራንና የማቴሪል ዝግጅት ተደርጓል። ከዛም በኦን ላይን ትምህርቱ እንዲሰጥ ተደርጎ ተማሪዎቹ ተመርቀዋል። የኦላይን ትምህርቱን ውጤታማ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎች መከናወናቸውን የጠቀሱት ዶክተር ካሳሁን፤ ቴክኖሎጂውን በማስተዋወቅ ረገድም ውጤታማ ስራ መከናወኑን ይገልጻሉ፤ በቀጣይም በዚሁ ለመቀጠል ዝግጅት መደረጉን ያመለክታሉ።እንደ ዶክተር ካሳሁን አባባል፤ በኦን ላይን ትምህርት አሰጣጥ የሰዎች አቀባበል ችግር፣ የመሰረተ ልማት ማለትም የኢንተርኔት መቆራረጥ እንዲሁም ተማሪዎች የላፕቶፕ እጥረቶች እንደ ችግር ማጋጠማቸውን ይጠቁማሉ። የኦን ላይን ትምህርቱን ተማሪዎቹ እየለመዱት ሲመጡ የትምህርት አሰጣጡ መሻሻሉን ያመለክታሉ። በሌላ በኩል ዩኒቨርሲቲው በራሱ ስም የኢሜል አገልግሎት በመክፈት በቀላሉ ተማሪዎች መረጃ እንዲያገኙ መደረጉንም ጠቁመዋል። በተጠናቀቀው የትምህርት ዘመን የተመረቁት አምስት ሺህ 315 ተማሪዎች መሆናቸውን በመጥቀስ፤ የተመረቁት ሁሉም በኦን ላይን ተምረው ሳይሆን ቀድመው የምርምር ስራቸውን ያጠናቀቁም እንደተካተቱበት ይናገራሉ። በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርት የተከታተሉ እንደሚበዙ፣ የማታም ተማሪዎች በኦን ላይን ተምረው እንዲመረቁ መደረጉን ይገልፃሉ። በቀጣይ ዓመት በኦን ላይ ትምህርት ለመስጠት ዝግጅት እንደተደረገና ከቀደመው ትም ህርት ተወስዶ የመምህራን ዝግጅት፣ መሰረተ ልማቶች እንዲሁም የትምህርት ማቴሪያሎች መዘጋጀታቸውን ያብራራሉ።አዲስ ዘመን ሐምሌ 28/2012  መርድ ክፍሉ
https://www.press.et/Ama/?p=36575
584
0ሀገር አቀፍ ዜና
በወንዞች ላይ ለሚከናወኑ የልማት ስራዎች ቅድመ ዝግጅት
ሀገር አቀፍ ዜና
August 5, 2020
5
አዲስ አበባ፡- ኢትዮጵያ በቀጣይ ጊዜያት በዓባይና በሌሎች ወንዞች ላይ የምታከናውናቸውን የልማት ፕሮጀክቶች ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመፈፀም ሁለገብ ቅድመ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባት ምሁራን አሳሰቡ። በዲላ ዩኒቨርሲቲ የታሪክና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች መምህርና ተመራማሪ ዶክተር አብዱ መሐመድ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ በኅዳሴው ግድብ ግንባታ ሂደት የተገኙ ልምዶችን በመቀመር በቀጣይ ጊዜያት በዓባይና በሌሎች ወንዞች ላይ የሚከናወኑ የልማት ፕሮጀክቶችን ውጤታማ ማድረግ ይገባል። ወደፊት በዓባይም ሆነ በሌሎች ወንዞች ላይ የሚከናወኑ የልማት ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያን ጥቅም የሚያስጠብቁ፣ ዓለም አቀፍ ተቀባይነትና ተሰሚነትን የሚጨምሩ ሆነው እንዲጠናቀቁ በሁለንተናዊ ጥንካሬ የተገነባ ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ያስፈልጋል። ዶክተር አብዱ ‹‹ሁለንተናዊ ጥንካሬ ሲባል የቅስቀሳና ንቅናቄ፣ የሕዝብ ግንኙነት፣ የሳይበር፣ ወታደራዊ፣ ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ጥንካሬን ያካተተ ቅድመ ዝግጅት ማድረግን ያካትታል። ኢትዮጵያ በቀጣይ ጊዜያት በዓባይም ሆነ በሌሎች ወንዞቿ ላይ የልማት ፕሮጀክቶችን ለመስራት ስትዘጋጅ መሃንዲስና ፖለቲከኛ ብቻ ሳይሆን፤ ስራውን የሚያሳልጥ ብቁ የመገናኛ ብዙኃንና የሳይበር ኃይል ማዘጋጀት ይጠበቅባታል። የ21ኛው ክፍለ ዘመን ጦርነት ከጦር መሳሪያም በላይ የኮምፒውተር ጦርነት ሊሆን ስለሚችል የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኃይል ያስፈልጋል›› ብለዋል።እንደርሳቸው ገለፃ፤ ውጤታማ የልማት ፕሮጀክቶችን ለማከናወን የውስጥ አንድነትን ማጠንከርም ያስፈልጋል። ውስጣዊ ልዩነቶችን በድርድር በመፍታት ክፍተቶችን መዝጋት ይገባል። የውስጥ ክፍተቶችን በብሔራዊ እርቅ መዝጋት ከተቻለ አገሪቱ በውሃ ሀብቷ እንዳትጠቀም ሴራ የሚሸርቡ የውጭ ኃይሎችን መመከት ይቻላል። ለውጤታማ ዓለም አቀፍ ድርድሮችና ዲፕሎማሲ መሰረት የሆኑ ጠንካራ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ተግባራትን በማከናወን ከዚህ ቀደም የታዩ ክፍተቶች እንዳይደገሙ መስራት ያስፈልጋል። ዶክተር አብዱ በወታደራዊ ኃይል ጠንካራ ሆኖ መገኘት እንደሚያስፈልግ ፤ ለዚህም በወታደራዊ ኃይላቸው ጠንካራ የሆኑት እንደ ቻይና፣ እስራኤልና ሕንድ ያሉ አገራት የውሃ ሀብታቸውን በመጠቀም ምጣኔ ሀብታቸውን እንዳሳደጉ በማሳያነት ጠቅሰዋል። ግብፅ አንዲትም ኩባያ ውሃ ሳታዋጣ ላለፉት በርካታ ዓመታት የዓባይ በወንዝ የበላይ ተጠቃሚ ሆና የቆየችው ወታደራዊ ኃይሏን እንደመሳሪያ በመጠቀም ጭምር መሆኑን ጠቁመው፤ ሌሎች አገራትን በማይጎዳ መልኩ ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን የማስፈን መርህ የምትከተለው ኢትዮጵያም በወታደራዊ ዘርፍም ጠንካራ ሆና መገኘት እንደሚኖርባት ዶክተር አብዱ አስረድተዋል።‹‹ከዓባይ በተጨማሪ በሌሎቹ ወንዞችም የመጠቀም እድል አለን፤ የዓባይ ጉዳይም ቢሆን ገና ያላለቀለት ጉዳይ በመሆኑ ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ትግል የሚያስፈልገን ከዚህ በኋላ ነው›› ያሉት ዶክተር አብዱ፤ ኢትዮጵያ በቀጣይ ጊዜያት ሌሎች ድንበር ተሻጋሪ ወንዞቿን ለመጠቀም ስትነሳ ከኅዳሴው ግድብ ግንባታ ሂደት የተገኙትን ልምዶች ግምት ውስጥ አስገብታ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ሊሆን እንደሚገባ አስገንዝበዋል።በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የውሃ ምህንድስና መምህር ዶክተር አሰግደው ጋሻው በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ በቀጣይ ጊዜያት በዓባይና በሌሎች ወንዞች ላይ ለምታከናውናቸው የልማት ፕሮጀክቶች የዲፕሎማሲና የሕዝብ ግንኙነት ስራዎችን ከፕሮጀክቶቹ ግንባታ ጎን ለጎን ማስኬድ እንዳለባት አስረድተዋል። ‹‹ፈተናው የተጀመረው ከትልቁና ከከባዱ ነው›› የሚሉት ዶክተር አሰግደው፤ ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ እየገነባች ያለው የኅዳሴ ግድብ ከሌሎቹ ግዙፍና ከዓለም አቀፍ ጉዳዮች አንፃር ትርጉሙ ከበድ ያለ ስለሆነ በቀጣይ ጊዜያት በወንዞቿ ላይ የምታከናውናቸው የልማት ፕሮጀክቶች እንደኅዳሴው ግድብ ከባድ እንደማይሆኑባት ተናግረዋል። የልማት ስራዎቹን ውጤታማ ለማድረግ የተፋሰሱ አገራትን የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ማጠናከርና ምሁራንም በጋራ እንዲሰሩ ማድረግ እንደሚስፈልግ የጠቆሙት ዶክተር አሰግደው፤ ‹‹አሁን ካለው የዓለም ነባራዊ ሁኔታ አንፃር ሦስተኛው የዓለም ጦርነት የውሃ ጦርነት ሊሆን ስለሚችል ከፊታችን ከባድ ፈተና ይገጥመናል ፤የኢትዮጵያን ጥቅም የሚያስጠብቅ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ‹የምስራቅ አፍሪካ የውሃ ማማ› እየተባለች ውሃ የምትጠማ ሆና የኖረችውን ኢትዮጵያን የቀጣናው የዳቦ ቅርጫትና የምጣኔ ሀብት ማዕከል ማድረግ ይገባል›› ብለዋል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 29/2012 አንተነህ ቸሬ
https://www.press.et/Ama/?p=36619
443
0ሀገር አቀፍ ዜና
ቢሮው ከ855 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው ሀሰተኛ ደረሰኞችን ውድቅ ማድረጉን አስታወቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 5, 2020
11
 አዲስ አበባ:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በበጀት ዓመቱ በአጠራጣሪ ደረሰኞች ላይ ባካሄደው የማጣራት ተግባር ከ855 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው ሀሰተኛ ደረሰኞችን ውድቅ ማድረጉን አስታወቀ።በቢሮው የህግ ተገዥነት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ታምራት ንጉሴ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ በበጀት ዓመቱ በአንድ ሺ 944 ግብር ከፋዮች የቀረቡ ስምንት ሺ 825 አጠራጣሪ ደረሰኞች ላይ በተካሄደ የማጣራት ተግባር በ514 ግብር ከፋዮች የቀረቡ 855 ሚሊዮን 995ሺ 663 ብር ግምት ያላቸው ሁለት ሺ 623 ሃሰተኛ ደረሰኞችን ውድቅ በማድረግ ግብር ከፋዮቹ የሚጠበቅባቸውን የግብር ግዴታ እንዲወጡ ከማድረግ ባሻገር በህግ ተጠያቂ የማድረግ ስራ ተሰርቷል። እንደርሳቸው ገለጻ፤ አንዳንድ ግብር ከፋዮች የግብር ወይም የታክስ ማሳወቂያ ደረሰኞችን በሚያቀርቡበት ጊዜ ትክክለኛውን ግብር ላለመክፈል ወጪ በማናርና የግብዓት ታክስን በማሳደግ ተከፋይ የዕሴት ታክስን ለማሳነስ እንዲሁም ተመላሽ ታክስ በመጠየቅ ከመንግስት ካዝና ያለአግባብ ገንዘብ ለመውሰድ ታሳቢ በማድረግ የተለያዩ ሃሰተኛ ደረሰኞችን በማዘጋጀት የሚያቀርቡ አሉ። በሃሰተኛ ደረሰኝ የተደገፈ የሂሳብ መዝገብ በማዘጋጀት የሚቀርቡ የግብር ማሳወቂያ ደረሰኞች ትክክለኛ ግብርን አያሳዩም ያሉት ሃላፊው፤ የተቋሙን የታክስ አወሳሰን የተሳሳተ ከማድረግ ባሻገር መንግስት መሰብሰብ የሚገባውን ገቢ በአግባቡ እንዳይሰበስብ የሚያደርግ የታክስ አስተዳደር ዋነኛ ተግዳሮት መሆኑን ያስረዳሉ። ግብር ከፋዮች የግብር ማሳወቂያ ደረሰኞችን በሚያቀርቡበት ጊዜ በተለይ በወጪ ማስረጃነትና በታክስ ግብዓት ማቀናነሻነት የሚቀርቡ ሰነዶች አጠራጣሪ ሆነው ሲገኙ በትኩረት የማጣራት ስራ እንደሚሰራ ምክትል ቢሮ ኃላፊው ጠቁመው፤ በበጀት ዓመቱ በሁለት ሺ 723 ግብር ከፋዮች የቀረቡ 14ሺ 160 አጠራጣሪ ደረሰኞች ውስጥ በአንድ ሺ 944 ግብር ከፋዮች የቀረቡ ስምንት ሺ 825 አጠራጣሪ ደረሰኞችን ማጣራት መቻሉን ገልጸዋል። አቶ ታምራት ከተጣሩት 8ሺ 825 ደረሰኞች ውስጥ በ514 ግብር ከፋዮች የቀረቡ 855 ሚሊዮን 995ሺ 663 ብር ግምት ያላቸው ሁለት ሺ 623 ሃሰተኛ ደረሰኞችን ውድቅ በማድረግ ግብር ከፋዮቹ የሚጠበቅባቸውን የግብር ግዴታ እንዲወጡ ከማድረግ ባሻገር በህግ ተጠያቂ የማድረግ ስራ ተሰርቷል ብለዋል። ቢሮው በበጀት ዓመቱ በአጠራጣሪ ደረሰኞች ላይ ባካሄደው የማጣራት ተግባር መንግስት በሃሰተኛ ደረሰኝ ሳቢያ ሊያጣው የነበረውን 855 ሚሊዮን 995ሺ 663 ብር ገቢ ማዳን መቻሉን ምክትል ቢሮ ኃላፊው ገልጸው፤ ግብር ከፋዮቹ የሚጠበቅባቸውን የግብር ግዴታ እንዲወጡ ከማድረግ ባሻገር 208 ግብር ከፋዮች ያቀረቧቸው 723 ሃሰተኛ ደረሰኞች ተደራጅተው ፖሊስ ምርመራ እንዲያደርግባቸው ተላልፈዋል። ፖሊስም መዝገቡን አደራጅቶ ለአቃቢህግ አቅርቦ ክስ መስርቶባቸዋል ብለዋል። ቢሮው በበጀት ዓመቱ ባደረገው ቁጥጥር የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያዎችን በአግባቡ ባልተጠቀሙና ያለደረሰኝ ግብይት ሲፈጽሙ በተገኙ ሰባት ሺ 782 ግብር ከፋዮች ላይ 244 ሚሊዮን 565 ሺ ብር አስተዳደራዊ ቅጣት መጣሉ ታውቋል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 29/2012 ሶሎሞን በየነ
https://www.press.et/Ama/?p=36622
345
0ሀገር አቀፍ ዜና
ፖሊስ በአቶ በቀለ ገርባ ላይ ሲያካሂድ የነበረውን ምርመራ ማጠናቀቁን ገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 5, 2020
11
  አዲስ አበባ፦ የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ በወንጀል ድርጊት በተጠረጠሩት አቶ በቀለ ገርባ ላይ ሲያካሂድ የነበረውን ምርመራ ማጠናቀቁን ገለጸ።የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን ባለፉት ስምንት ቀናት አከናወንኩ ያላቸውን ተግባራት በዝርዝር ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት የአራዳ ተረኛ ወንጀል ችሎት ትናንት አቅርቧል ።መርማሪ ፖሊስ በተጠርጣሪው ላይ ባደረገው ማጣራት በተፈጠረው ሁከት በትራንስፖርት ዘርፍ ግምቱ ከ37 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ ጉዳት መድረሱን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ማሰባሰቡን ፣ሰባት ሽጉጦች ላይ ባደረገው የፎረንሲክ ምርመራ ሁሉም ህጋዊ እንዳልሆኑና የፋብሪካ ቁጥራቸው የተለወጠ መሆኑን፣ እንዲሁም ከተጠርጣሪው ቤት የተገኙ ሁለት ሽጉጦች ህጋዊነት የሌላቸው መሆኑን እንዳረጋገጠ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል።‹‹በስልጣን ላይ ያለውን መንግስት መጣል አለብን›› ብለው ባስተላለፉት መልዕክት የተነሳ በተፈጠረ ሁከት በተለያዩ አካባቢዎች የሰው ህይወት ማለፉንና ሰዎች መፈናቀላቸውን የገለጸው መርማሪ ፖሊስ፤ መኖሪያ ቤት፣ ሆቴል፣ ሱቅ፣ ፋብሪካ፣ የመንግስት ተቋማት እና የሃይማኖት ተቋም መዘረፉንና መቃጠሉን በማስረጃ እንዳረጋገጠ አስረድቷል። ከተጠርጣሪው መኖሪያ ቤት የተገኙ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን ውጤት ከመዝገብ ጋር ማያያዙንና የምስክሮች ቃል መስማቱን ፣በተሰማው የምስክርነት ቃል ተጠርጣሪው ከግብረ አበሮቻቸው ጋር የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ አስከሬን ከቡራዩ ተመልሶ ወደ ኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት እንዲገባ፣ አስከሬኑ ለ10 ቀናት በአዲስ አበባ እንዲቆይ ተደርጎ የምኒሊክ ሃውልት እንዲፈርስ እንዲሁም ወደ ቤተ-መንግስት የመግባት ዕቅድ እንዳላቸው ማወቁን ገልጿል።ፖሊስ ባካሄደው ምርመራ በተጠርጣሪው ላይ ሲያደርግ የነበረውን ማጣራት ማጠናቀቁን ገልጾ፤ ቀዳሚ ምርመራ ለማሰማት ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ እንዲሰጥ ጠይቋል።የተጠርጣሪ ጠበቆች በበኩላቸው ‹‹ መዝገቡ መነሻ ያደረገው የአርቲስት ሃጫሉ አስከሬን እንዲመለስ ማድረግና ስልክ ደውለው ሁከት ቀስቅሰዋል የሚል ነበር›› በማለት ገልጸው፤ ሁከት ማስነሳት ዋስትና የማያስከለክል በመሆኑ የደንበኛቸው የዋስትና መብት እንዲፈቀድ ጠይቀው፤ ደረሰ የተባለው ጉዳት የደንበኛቸውን ድርሻ አመላካች ሆኖ እንዳልቀረበ በመግለጽ ተከራክረዋል።የተጠርጣሪ ጠበቆች ቀዳሚ ምርመራ ከመጀመሪያው ጀምሮ መደረግ እንደነበረበት በመግለጽ አሁን ፖሊስ የጠየቀው ቀዳሚ ምርመራ ደንበኛቸውን ከፍርድ ውጪ አስሮ ለማቆየት እንደሆነ በመግለጽ የዋስትና መብት እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል።ተጠርጣሪው አቶ በቀለ ገርባ ‹‹ እኔ የፓርቲ መሪ እንጂ የሰራዊት መሪ ስላልሆንኩ ህዝብ ያደረሰውን ጉዳት እኔ ላይ መጫን አይገባም፤ መንግስት በምርጫ አልመጣምና ምርጫ ተካሂዶ ህዝብ የመረጠው ፓርቲ ማስተዳደር አለበት በማለት ምርጫው መራዘም የለበትም የሚል አቋም አለኝ፤ ይህ በደጋፊዎቼና በእኔ ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር የተደረገ ነው፤ ሁከት መቀስቀስ የዋስ መብት አያስከለክልምና የዋስትና መብቴ ሊጠበቅ ይገባል›› ብለዋል። ዐቃቤ ህግ በበኩሉ ችሎቱ ማስረጃ መስማት ባለመሆኑ የማስረጃ ምዘና ውስጥ መግባት እንደማያስፈልግ አስረድቶ፤ ተጠርጣሪው የቀረበባቸው ማስረጃ የእርስ በርስ ግጭት ማስነሳት እና የሰው ህይወት ያለፈበት፤ ክሱ ከ15 ዓመት በላይ ሊያስቀጣ የሚችል በመሆኑ ዋስትና ሊፈቀድ እንደማይገባ በመግለጽ ተከራክሯል።ግራ ቀኙን ያዳመጠው ፍርድ ቤቱ የምርመራ መዝገቡን በማየት ዋስትናን በተመለከተ ውሳኔ ለማሳለፍ ለሐምሌ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ የቀዳሚ ምርመራ ማሰማትን በተመለከተ ‹‹በመዝገቡ ክርክር ማቅረብ ይቻላል›› ብሏል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 29/2012  በጋዜጣው ሪፖርተር
https://www.press.et/Ama/?p=36631
381
0ሀገር አቀፍ ዜና
በአማራ ክልል ከ1 ነጥብ 3 ቢሊዮን በላይ ችግኞች መተከላቸው ተገለጸ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 5, 2020
7
አዲስ አበባ:- የዘንድሮው የአምስት ቢሊዮን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በአገሪቱ በይፋ ከተጀመረ አንስቶ በአማራ ክልል ከአንድ ቢሊዮን 398 ሚሊዮን በላይ ችግኞች መተከላቸውን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።በቢሮው የተፈጥሮ ሃብት ልማት ጥበቃና አጠቃቀም ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው እንግዳየሁ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ በዘንድሮው የአምስት ቢሊዮን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በክልሉ አንድ ነጥብ 58 ቢሊዮን የደረሱ ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ ወደ ስራ የተገባ ሲሆን፤ መርሃ ግብሩ በይፋ ከተጀመረ አንስቶ በክልሉ ከአንድ ቢሊዮን 398 ሚሊዮን 600ሺ በላይ ችግኞችን በመትከል ከወዲሁ የዕቅዱን 88 በመቶ ማሳካት ተችሏል።እንደ ዳይሬክተሩ ማብራሪያ፤ የዘንድሮው አገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በይፋ ከመጀመሩ አስቀድሞ በክልሉ የደን ልማት ስራ ላይ የሚስተዋሉ ደካማና ጠንካራ ጎኖች ተለይተው፤ ጥንካሬዎቹን በሁሉም አካባቢዎች ተደራሽ ለማድረግና ድክመቶቹን ለመቅረፍ የዳሰሳ ጥናቶች ተካሂደው ስትራቴጂክ ዶክመንት በማዘጋጀት አርሶ አደሩና ባለሙያው የጋራ መግባባት ላይ እንዲደረስ ውይይቶች ተካሂደዋል። በውይይቱ በደን ልማቱ እንደ ቁልፍ ችግር የተነሱት ከመጠን፣ ከመጽደቅ፣ የተተከሉ ችግኞች ባለቤት አልባ መሆን፣ የተተከሉ ችግኞችን ተከታትሎ መንከባከቡ ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለመሙላት፤ የተከላ ቦታዎች ተለይተው ተስማሚ የችግኝ ዝርያዎችን የማዘጋጀትና የችግኞቹን ባለቤት የመለየት ስራ ከመሰራቱ ባሻገር የተከላ ቦታዎች ምናባዊ እንዳይሆኑ በጂፒኤስ ድንበራቸው ተለይቶ በጂአይኤስ ፕሮግራም በአጠቃላይ የአጠቃቀም ካርታ እንዲዘጋጅላቸው መደረጉን ተናግረዋል።አቶ ጌታቸው ከነዚህ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በተጨማሪ የተለያዩ ግብዓቶችን በማሟላት በክልሉ ከአንድ ነጥብ 75 ቢሊዮን ችግኞች በላይ ማፍላት መቻሉን ጠቁመው፤ ከዚህ ውስጥ በዘንድሮው የአምስት ቢሊዮን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በክልሉ አንድ ነጥብ 58 ቢሊዮን ለተከላ የደረሱ ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ ወደ ስራ የተገባ ሲሆን፤ በአገሪቱ መርሃ ግብሩ በይፋ ከተጀመረ አንስቶ በክልሉ ከአንድ ቢሊዮን 398 ሚሊዮን 600ሺ በላይ ችግኞችን በመትከል ከወዲሁ የዕቅዱን 88 በመቶ ማሳካት መቻሉን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።አቶ ጌታቸው በክልሉ አንድ ነጥብ 58 ቢሊዮን ለተከላ የደረሱ ችግኞችን እስከ ነሃሴ 5 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ተክሎ ለማጠናቀቅ እቅድ ተይዞ የነበረ ቢሆንም፤ በአብዛኛው አካባቢ በተሳካ ሁኔታ የችግኝ ተከላው ከወዲሁ መጠናቀቁን ጠቁመው፤ በዚህም በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በክልሉ 156ሺ 574 ሄክታር መሬት በችግኝ መሸፈኑን ተናግረዋል። በመጀመሪያው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በክልሉ ከተተከሉት ችግኞች ውስጥ 75 በመቶው መጽደቃቸውን ዳይሬክተሩ ጠቁመው፤ ዘንድሮ በአገር አቀፍ ደረጃ ለመትከል ከታቀደው ችግኝ አንጻር ክልሉ ለመትከል ያቀደው ቁጥር ያነሰው ችግኞችን ከመትከል ባሻገር መጽደቁ ላይ በትኩረት በመስራት ከተተከሉት ችግኞች 90 በመቶውን ለማጽደቅ ግልጽ የተጠያቂነት የአሰራር ስርዓት መዘርጋቱ መሆኑን ገልጸዋል። በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በክልሉ በአንድ ጀንበር ሃምሌ 9 ቀን 2012 ዓ.ም 190 ሚሊዮን 643 ሺ ችግኞች ሲተከሉ፤ ችግኝ በማፍላትና ችግኙን ከቦታ ቦታ በማጓጓዝ 24 ሺ ሰዎች የስራ እድል እንደተፈጠረላቸው ለማወቅ ተችሏል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 29/2012  ሶሎሞን በየነ
https://www.press.et/Ama/?p=36618
368
0ሀገር አቀፍ ዜና
የአረንጓዴ አሻራ ለተፋሰሶች ልማት የማይተካ ሚና እንዳለው ተጠቆመ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 4, 2020
12
አዲስ አበባ:- አገራችን የተያያዘችውን የአረንጓዴ ልማት ተፋሰሶች የውሃ ሀብት መገኛ ሆነው በዘላቂነት እንዲቀጥሉ ለማድረግ ፤ ስነ-ምህዳሩን ከተለያዩ ጉዳቶች በመጠበቅ ፤ የተፋሰሶቹን ደህንነት ከመጠበቅ አንጻር የሚኖረው ፋይዳ የማይተካ መሆኑ ተገለጸ።የተፋሰስ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የብሔራዊ የችግኝ ተከላ አስተባባሪ የቴክኒክ ኮሚቴ አባል አቶ ጌታቸው ግዛው ለአዲስ ዘመን እንደተናገሩት፤ የአረንጓዴ ልማት ተፋሰሶች የውሃ ሀብት መገኛ ሆነው በዘላቂነት እንዲቀጥሉ በማድረግ ስነ-ምህዳሩን ከተለያዩ ጉዳቶች በመጠበቅ የሚኖረው አስተዋፅኦ ከፍተኛ ሲሆን ፤ የተፋሰሶቹን ደህንነት ከመጠበቅ አንጻር የሚኖረው ፋይዳ የማይተካ ነው። የአረንጓዴ ልማት ሥራው ተፋሰሱን በመጠበቅ የውሃ ሀብቱን አስተማማኝ በማድረግ ጥራቱም የተጠበቀ ፤የድርቅንም ሆነ የጎርፍ አደጋ መቋቋም ከማስቻሉም ባሻገር፤ መሠረተ ልማቶች የሚጠበቅባቸውን አገልግሎቶች መስጠት እንዲችሉ በማድረግ ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ነው አቶ ጌታቸው የሚናገሩት።የአረንጓዴ ልማት ለተፋሰሱ ልማት መሠረት ነው የሚሉት አቶ ጌታቸው፤ ችግኞቹ የሚተከሉት ጥናትን መሠረት ባደረገ መልኩ ቅድሚያ ሊሰጣቸው ይገባል ተብለው በተለዩ በጣም ተጋላጭ በሆኑ ንዑስ ተፋሰሶችና የውሃ መሠረተ ልማት ማዕከል አካባቢዎች ላይ መሆኑን ይገልጻሉ። በተጠበቁ አካባቢዎች የሚደረገው የችግኝ ተከላ የጽድቀት መጠኑ የተሻለ እንደሚያደርገው የሚናገሩት ኃላፊው፤ ከዚህም በተጨማሪ ተፋሰሶች ቶሎ እንዲያገግሙ ዕድል የሚሰጥ መሆኑን ጠቁመው፤ ለተከላ የተዘጋጁት ችግኞች ዘርፈ ብዙ አገልግሎት የሚሰጡ የእጽዋት ዓይነቶች መሆናቸውንም አመልክተዋል።የዘንድሮ አምስት ቢሊዮን ችግኝ የመትከል መርሐ ግብር በእነዚህ የተፋሰስ ልማት ላይ የሚሠራ መሆኑን ጠቁመው፤ በተለይ የውሃ መሠረተ ልማቶች አካባቢዎችና በሁሉም ተፋሰሶች ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን አመልክተዋል።“ክረምቱ ቀደም ብሎ መግባቱን ምቹ ሁኔታን በመፈጠሩ ምክንያት ብዙ ቦታዎች ላይ የችግኝ ተከላ ለማካሄድ አልተቸገርንም” የሚሉት ኃላፊው፤ ይህም ለችግኞች ጽድቀት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ጠቆመዋል። አክለውም እስከአሁን 4 ነጥብ 1 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን መተከላቸውን አመልክተዋል።በዚህ ዓመት ሰፊ ዝግጅት ተደርጎ ችግኞችን የመትከል ሥራ የተጀመረ መሆኑን የሚገለጹት አቶ ጌታቸው ፤ እንክብካቤ በማድረግም ደረጃ ሰፊ ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ አመልክተዋል። ‹‹የተክልናቸውን ችግኞች ተመልስን በማየት ፤በመንከባከብ ፤ በውሃ ማጠጣት ፤ በማረም ፤ በመኮትኮት ፤ ከንክኪ በመጠበቅ ኃላፊነታችንን የማንወጣ ከሆነ የለፋንበት ልፋት የታለመውን ጥቅም ሊያስገኝ አይችልም ›› የሚሉት አቶ ጌታቸው፤ ለዚህም ተካዩን ህብረተሰብ የተከለው ችግኝ እንክብካቤ እንደሚፈልግ ታሳቢ አድርገን ተመልስን በማየት መኮትኮት፤ ማረም፤ መንከባከብና መጠበቅ እንደሚገባ አመልክተዋል። የልማቱ ውጤት ተብሎ የሚወሰደውም እነዚህ ችግኞች ተተክለው የሀብት ምንጭ በማድረግ ሲችል መሆኑን ጠቁመው፤ ሁሉም ህብረተሰብ በተከላው ላይ እንደተረባረበ ሁሉ፤ በዚሁ ልክ ትኩረት ተሰጥቶ እንክብካቤ ላይ እንዲቀጥል ማድረግ እንደሚጠበቅበት አመልክተዋል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 28/2012  ወርቅነሽ ደምሰው
https://www.press.et/Ama/?p=36584
327
0ሀገር አቀፍ ዜና
የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አደረገ
ስፖርት
August 9, 2019
73
– ለ2020 የቶኪዮ ኦሎምፒክ የኢትዮጵያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ተካፋይ ለመሆን በአፍሪካ ዞን የማጣሪያ ጨዋታ ሉሲዎቹ ነሐሴ 20/ 2011 ዓ.ም ከካሜሮን ጋር ለሚያደርጉት ፍልሚያ ብሔራዊ ቡድኑ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አደረገ። ሶከር ኢትዮጵያ በድረ ገጹ እንዳስነበበው፤ የኢትዮጵያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሰላም ዘርዓይ ለ2020 የቶኪዮ ኦሎምፒክ የኢትዮጵያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ተካፋይ ለመሆን በአፍሪካ ዞን ማጣሪያ ሉሲዎቹ ነሐሴ 20/ 2011 ዓ.ም ከካሜሮን ጋር ለሚያደርጉት ፍልሚያ ቀድሞ ለመዘጋጀት ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ ያደረገች ሲሆን፤ በግብ ጠባቂነት ጥሪ ከተደረገላቸው ተጫዋቾች መካከል ማርታ በቀለ ከመከላከያ፣ ታሪኳ በርገና ከጥረት ኮርፖሬትና ዓባይነሽ ኤርቄሎ ከሃዋሳ ከተማ ይገኙበታል። እንዲሁም በተከላካይ መስመር በብሔራዊ ቡድኑ ጥሪ ከተደረገላቸው ተጫዋቾች መካከል፤ መስከረም ካንኮ፣ ነጻነት ጸጋዬ፣ እፀገነት ቡዙነህና ናርዶስ ጌትነት ከአዳማ ከተማ፣ ገነሜ ወርቁና ብዙዓየሁ ታደሰ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ መሠሉ አበራ ከመከላከያ፣ ቅድስት ዘለቀ ከሃዋሳ ከተማ እንዲሁም ዓለምነሽ ገረመው ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ተካተዋል። በአማካይ መስመር በአሰልጣኝ ጥሪ የተደረገላቸው፤ ሕይወት ደንጌሶና ብርቱካን ገ/ክርስቶስ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ እመቤት አዲሱና አረጋሽ ከልሳ ከመከላከያ እና ሰናይት ቦጋለ ከአዳማ ከተማ ጥሪ ተደርጎላቸዋል። በተጨማሪ በአጥቂ መስመር ጥሪ ከተደረገ ላቸው ተጫዋቾች መካከል፤ ምርቃት ፈለቀና መዲና ጀማል ከሃዋሳ ከተማ፣ ሎዛ አበራ፣ ሰርካዲስ ጉታና ሴናፍ ዋቁማ ከአዳማ ከተማ እንዲሁም ሔለን እሸቱ ከመከላከያ ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች ናቸው። የዩጋንዳን ብሔራዊ ቡድን አሸንፈው ወደ ቀጣዩ ዙር ያለፉት ሉሲዎቹ ነሐሴ 20/2011 ዓ.ም ከካሜሮን ጋር ለሚያደርጉት ለ2020 የቶኪዮ ኦሎምፒክ የአፍሪካ ዞን የማጣሪያ ጨዋታ ከነሐሴ 1/2011 ዓ.ም ጀምሮ ዝግጅታቸውን ማከናወን የጀመሩ ሲሆን፤ ነሐሴ 11/2011 ዓ.ም ከኬኒያ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።አዲስ ዘመን ነሃሴ 3/2011ሶሎሞን በየነ
https://www.press.et/Ama/?p=15763
224
2ስፖርት
የስፖርት አካዳሚው የ2012 ዓ.ም ዕጩ ስፖርተኞችን ሊመለምል ነው
ስፖርት
August 8, 2019
44
የኢትዮጲያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ የ2012 ዓ.ም የስልጠና ዘመን ዕጩ ስፖርተኞችን ምልመላ ሊያካሂድ መሆኑን በይፋዊ የማህበራዊ ገጹ አስታውቋል ። አካዳሚው በዚሁ መረጃ ላይ እንዳሰፈረው፤ የ2012 ዓ.ም የስልጠና ዘመን ዕጩ ስፖርተኞችን ምልመላ ሊያካሂድ መሆኑን ገልጾ፤ በአስር የስፖርት አይነቶች በርካታ ቁጥር ያላቸውን ስፖርተኞችን በአስር የስፖርት አይነቶች ተቀብሎ ለማሰልጠን እቅድ ይዞ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። በዚህ መሰረት በእግርኳስ፣ አትሌቲክስ፣ ቮሊቮል፣ ቅርጫት ኳስ፣ ብስክሌት፣ ቦክስ፣ ወርልድ ቴኳንዶ፣ ዉሃ ዋና፣ ፓራሊምፒክ፣ ጠረጴዛ ቴኒስ ስፖርት ነው ብሏል። የስልጠና መስፈርት ማስቀመጡን የገለጸው አካዳሚ፤ ከ15 በታች እና ከ17 ዓመት በታች ታዳጊዎች በማንኛውም የትምህርት ደረጃ የሚገኙ ፍላጎት ያላችው ታዳጊዎች ለመመልመል ማቀዱን ይፋ አድርጓል። አካዳሚው ምልመላውን ከነሐሴ 1 እስከ 15 ቀን 2011 ዓ.ም እንደሚያካሂድ የገለጸው አካዳሚው የሰልጣኝ ምልመላ የሚደረግባቸው አካባቢዎች በአራቱም የሃገሪቱ አቅጣጫዎች በሰባት ቡድን በመዋቀር ወደ ተለያዩ ክልሎች ከትናንት ጀምሮ መንቀሳቀስ መጀመሩን አስታውቋል። በዚህ መሰረትም ወልቂጤ፣ ጅማ፣ መቱ፣ ጋምቤላ ደምቢዶሎ፣ ግምቢ፣ ቤኒሻንጉል፣ መቀለ፣ ሽሬ፣ አክሱም፣ አዲግራት፣ አብአላ፣ ሰመራ፣ አዋሽ አርባ፣ ጅግጅጋ፣ ሀረር፣ ምስራቅ ሀረርጌ፣ ድሬዳዋ፣ ጭሮ፣ መተሀራ፣ሀዋሳ፣ ሻሸመኔ፣ ሀላባ፣ ወላይታ፣ አርባምንጭ፣ ጂንካ፣ ሆሳእና፣ ወራቤ፣ዲላ፣ ጉጂ፣ ቦረና፣ በባሌ ፣ አርሲ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ደብርማርቆስ፣ ኮሶበር፣ ባህርዳር፣ ጎንደር፣ ወልዲያ፣ ደሴ፣ ደብረ ብርሀን መሆኑን አስታወቋል። አካዳሚው ሰልጣኞችን የሚመለምል በትን መንገድ በተደጋጋሚ ጥያቄን ሲያስነሳ የነበረ እንደመሆኑ በቀጣይ ወር ለማከናወን የጀመረው ጉዞ ከዚሁ ትችት የሚያወጣው መሆኑ ተገልጿል። በአራቱም የሃገሪቱ አቅጣጫዎች የሚገኙ ክህሎት ያላቸውን ታዳጊ ስፖርተኞችን በጥራትና በብዛት ማግኘት የሚያስችለው እንደሚሆን ተጠብቋል። የኢትዮጲያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ በ2005 ተመርቆ በ2006 ዓ.ም ስፖርተኞችን መልምሎ ስራውን የጀመረ ሲሆን ፤በ2011 ዓ.ም ዘንድሮ በጥሩነሽ ዲባባ ማሰልጠኛ ማዕከል ለሰባተኛ ጊዜ፣ የአዲስ አበባ ካምፓስ ደግሞ ለሶስተኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን 105 ስፖርተኞች ማስመረቁ የሚታወስ ነው።አዲስ ዘመን ነሃሴ 2/2011
https://www.press.et/Ama/?p=15709
240
2ስፖርት
የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ዛሬ ምሽት ይጀመራል
ስፖርት
August 9, 2019
311
የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ በ20 ክለቦች መካከል የሚደረግ የ38 ሳምንታት እልህ አስጨራሽ ትግል የአንድ ክለብ የዋንጫ አሸናፊነት ክብር የሚታወጅበት፤ ክለቦች በቻምፒዮንስ ሊጉ ተሳታፊ ለመሆን የሚያበቃቸውን ከአንድ እስከ አራት ያለውን ደረጃ ለመቆናጠጥ አንገት ለአንገት የሚተናነቁበት ሊግ ነው። በአንጻሩ ደግሞ ሶስት ክለቦች ወደ ቻምፒዮን ሺፑ ላለመውረድ በሚያደርጉት እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ አንዱ ክለብ ለአንዱ በቀላሉ እጅ የማይሰጥበትና ይሄ ክለብ በቀላሉ ያሸንፋል ብሎ ለመገመት አዳጋች በመሆኑ፤ ሚሊየኖች የሚያብዱለትና እንባ የሚራጩበት በዓለም እግር ኳስ አፍቃሪያን ዘንድ በጉጉት የሚጠበቅ፤ የሁሉንም ስፖርት አፍቃሪ ቀልብና ስሜት የገዛ፤ ሃያላን ክለቦች የሚፋለሙበት ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የ2019/20 የውድድር ዓመት ዛሬ ምሽት አራት ሰዓት የመርሲ ሳይዱ ሊቨርፑል በአንፊልድ ከኖርዊች ሲቲ በሚያደርጉት ፍልሚያ አሃዱ ብሎ ይጀምራል፡፡ አዲሱን የውድድር ዓመት በአዲስ የቡድን መንፈስና ጥንካሬ ለመጀመር ቡድኖች ራሳቸ ውን በቅድመ ውድድር የወዳጅነት ጨዋ ታዎች ሲያዘጋጁና ትናንት በተጠናቀቀው የክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት አዳ ዲስ ተጫዋቾችን ወደ ክለባቸው በማዘዋወር ክለባ ቸውን ሲያጠናክሩ ቆይተዋል። በመሆኑም የ2019/20 የእንግሊዝ ፕር ሚየር ሊግ የውድድር ዘመን ዛሬ ምሽት ሊቨርፑል ከኖርዊች ሲቲ በሚያደርጉት ፍልሚያ ሲጀምር፤ ነገ ሊጉ ቀጥሎ ሲውል ስድስት ጨዋታዎች የሚካሄዱ ይሆናል። ከነዚህ መካከል በምሳ ስዓት ጨዋታ ዌስት ሃም ዩናይትድ ከሊጉ ቻምፒዮና ማንቸስተር ሲቲ፣ ምሽት 11 ስዓት ክሪስታል ፓላስ ከኤቨርተን እና ምሽት አንድ ሰዓት ተኩል ቶተነሃም ሆትስፐር ከቻምፒዮን ሺፑ ከአደገው ከአስቶን ቪላ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታዎች በጉጉት ይጠበቃሉ። እሁድ እለት ቀጥሎ በሚውለው የሊጉ መርሐ ግብር ሶስት ጨዋታዎች የሚካሄዱ ሲሆን፤ ቀያይ ሰይጣኖቹ ማንቸስተር ዩናይትድ በኦልድትራፎርድ ቲያትር ኦፍ ድሪምስ ስታዲየም ከሰማያዊዎቹ ቼልሲ ጋር የሚያደርጉት የሳምንቱ ትልቁ ጨዋታ በዚሁ እለት የሚካሄድ ይሆናል። ባሳለፍነው የውድድር ዓመት በቀያይ ሰይጣኖቹ ቤት ስኬታማውን አሰልጣኝ ጆሴ ሞሪንሆን ተክተው ኦልትራፎርድ የደረሱት የቀድ ሞው የቀያይ ሰይጣኖቹ የፊት መስመር ተጫዋች የነበረውና አሁን ላይ የክለቡ ዋና አሰልጣኝ የሆነው ኦሌ ገነር ሶልሻየር የዘንድሮውን የሊጉን ዋንጫ ከክለቡ ጋር ከፍ አድርጎ ለመሳምና በቻምፒዮንስ ሊጉ ተሳታፊ የሚያደርጋቸውን ውጤት ለማስመዝገብ በክረምቱ የዝውውር መስኮት በንቃት በመሳተፍ ክለቡን በወጣት ተጫዋቾች ያጠናከሩ በመሆኑ፤ ቀያይ ሰይጣኖቹ ከወዲሁ ይሄንን ትልማቸውን ለማሳካት የሚያ ስችላቸውን ስንቅ ለመሰነቅ ከሰማያዊዎቹ ጋር የሚያደርጉት ትንቅንቅ ጨዋታውን ተጠባቂ አድርጎታል። ቀያይ ሰይጣኖቹ ባሳለፍነው የውድድር ዓመት በሊጉ ስድስተኛ ደረጃን ይዘው ያጠናቀቁ ሲሆን፤ በክለቡ በተከላካይ መስመር ላይ የሚታየውን ክፍተት ለመሙላት እንግሊዛዊውን የሌስተር ሲቲ ተከላካይ ሃሪ ማጉዌርን የዓለማችን ውዱ ተከላካይ በማድረግ በ80 ሚሊዮን ፓውንድ አስፈርሟል። ተጫዋቹም በቀያዮቹ ቤት ቪዲችና ሪዮ ፈርዲናንድ ያሳዩትን ጥምረት ዳግም በኦል ትራ ፎርድ ለመድገም እንደሚጥር ከወዲሁ የተናገረ ሲሆን፤ በዚህ ጨዋታ የዓለማችን ውዱ የቀያዮቹ የተከላካይ ክፍል በሰማያዊዎቹ ቼልሲ ይደፈር ይሆን? የሚለው ጨዋታውን ተጠባቂ ካደረጉት ምክንያቶች አንዱ ነው። በአንጻሩ ባሳለፍነው የውድድር ዘመን ሰማያዊዎቹ ቼልሲ በጣሊያናዊው ማውሪዚዮ ሳሪ እየተመራ በቻምፒዮንስ ሊጉ መሳተፍ የሚያስችለውን የሶስተኛ ደረጃን ይዞ ከማጠ ናቀቁ ባሻገር የዩሮፓ ሊግ ዋንጫን ማንሳት የቻለ ቢሆንም፤ አሰልጣኙ ወደ ጣሊያን ማቅናታቸውን ተከትሎ በቻምፒዮን ሺፑ ደርቢ ካውንቲን በአሰልጣኝነት ይዞ ድንቅ ብቃቱን ያሳየው የሰማያዊዎቹ የቀድሞው የመሃል ሜዳ ፈርጥ ፍራንክ ላምፓርድ የክለቡን ዋና አሰልጣኝነት ዙፋኑን ከማውሪዚዮ ሳሪ ተቀብሏል። በመሆኑም አሰልጣኙ ስታምፎርድ ብሪጅን በአሰልጣኝነት በተቀላቀለ ማግስት ሰማያዊዎቹ በሊጉ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ከቀያዮቹ ጋር በሚያደርጉት ፍልሚያ አሃዱ ብለው ይጀምራሉ። ላምፓርድም ይሄን ጨዋታ በበላ ይነት በማሸነፍ ለቦታው እንደሚመጥን እራሱን የሚያሳይበት በመሆኑ፤ ጨዋታውን ከመቼውም ግዜ በላይ ተጠባቂ ያደርገዋል። እንዲሁም ሰማያዊዎቹ ቼልሲ በቁርጥ ቀን ልጃቸው በፍራንክ ላምፓርድ እየተመራ በቅድመ የውድድር የወዳጅነት ጨዋታዎች ላይ ክለቡ ድንቅ ብቃቱን አሳይቷል። በተለይ ቼልሲ ከባርሴሎና ባደረጉት የወዳጅነት ጨዋታ ላይ ሰማያዊዎቹ በፍጹም የጨዋታና የጎል የበላይነት የዓለማችንን ሀያል ክልብ ባርሴሎናን አምበርክከዋል። ስለዚህ ሰማያዊዎቹ በቅድመ ወድድር የወዳጅነት ጨዋታ በባርሴሎና ላይ የፈጸሙትን ጀብድ ዳግም በኦልትራፎርድ ቲያትር ኦፍ ድሪ ምስ ስታዲየም ሊደግሙት ይችላሉ የሚል መላምት ከወዲሁ በስፖርት ቤተሰቡ እየተሰጠ በመሆኑ፤ በጨዋታው ማን ያሸንፋል የሚለውን በጉጉት እንዲጠበቅ አድርጎታል። ሁለቱ ክለቦች ባለፈው በተገናኙበት ስድስት ጨዋታዎች ሁለት ሁለት ጊዜ ሲሸናነፉ፤ ሁለት ጊዜ ደግሞ አቻ ወጥተዋል። በጥቅሉ ሁለቱ ክለቦች በፕርሚየር ሊጉ በተገናኙበት ጨዋታዎች 78 ጊዜ ቀያይ ሰይጣኖቹ ሲያሸንፉ፤ በአንጻሩ ሰማያዊዎቹ ደግሞ 54 ጊዜ ረትተዋል። በ51 ጨዋታዎች ደግሞ አቻ ወጥተዋል። በአጠቃላይ በዚህ የውድድር ዓመት የፕሪሚየር ሊጉ ቻምፒዮና ማንቸስተር ሲቲ የሊጉን ዋንጫ ሶስት ጊዜ በተከታታይ በማንሳት ‹‹ሀትሪክ›› ለመስራት ይፋለማል፤ ሊጉ እንዳዲስ ከተቋቋመ ጀምሮ የሊጉን ዋንጫ ማሳካት የተሳነው የቻምፒዮን ሊጉ አሸናፊ የመርሲ ሳይዱ ሊቨርፑል ባሳለፍነው የውድድር ዓመት በአንድ ነጥብ ልዩነት የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ በውሃ ሰማያዊዎቹ ማንቸስተር ሲቲ በመነጠቁ፤ በዚህ የውድድር አመት ቀያዮቹ ከስተታቸው በመማር የሊጉን ዋንጫ ለማንሳት ይፋለማሉ። እንዲሁም የእግር ኳስ ጠበብቱ አርሴን ቬንገር ከ22 ዓመታት የኤምሬትስ ቆይታ ከተሸኙ በኋላ መድፈኞቹ አርሴናል በኡና ኤምሬይ እየተመሩ ሁለተኛ የውድድር አመታቸውን የሚያካሂዱ ሲሆን፤ አሰልጣኙ በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት በንቃት በመሳተፍ የሊጉን ዋንጫ ለማንሳት ከወዲሁ ቆርጠው ተነስተዋል። ስለዚህ የ2019/20 የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የውድድር ዘመን የሊጉ ሃያላን ክለቦች የሊጉን ዋንጫ ለማንሳት ከመቼውም ጊዜ በላይ ቆርጠው የተነሱበት በመሆኑ፤ የስፖርት ቤተሰቡ አስደሳች የውድድር አመት የሚያሳልፍበትና ታላላቅ የእግር ኳስ ትዕይንት የሚታይበት የውድድር ዓመት እንደሚሆን ከወዲሁ እየተ ተነበየ ይገኛል። ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ እንደ አዲስ ከተጀመረ እ.አ.አ ከ1992 ወዲህ 28ኛ የውድድር ዘመኑን ዛሬ ምሽት በይፋ ሲጀመር፤ ባሳለፍነው የውድድር አመት በኮከቡ አሰልጣኝ ጋርዲኦላ የሚመራው ማንቸስተር ሲቲ 98 ነጥቦችን ሰብስቦ ቻምፒዮን ሆኖ ሲያጠናቅቅ፤ በአንፃሩ ደግሞ ካርዲፍ ሲቲ፣ ፉልሃምና ሁደር ስፊል ታውን ከፕርሚየር ሊጉ ወደ ቻምፒዮንስ ሺፑ ተሰናብተዋል። በነዚህ ክለቦች ምትክ በ2018/19 የውድድር ዓመት ሶስት አዳዲስ ቡድኖች ከሻምፒዮን ሺፑ ፕሪሚየር ሊጉን የተቀላቀሉ ሲሆን፤ ክለቦቹም ኖርዊች ሲቲ፣ ሼፍልድ ዩናይትድና አስቶን ቪላ ናቸው። እነዚህ ክለቦችም ወደ ቻምፒዮን ሺፑ ተመልሰው ላለመውረድ በሚያደርጉት እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ የ2019/20 የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የውድድር ዘመን ድምቀት ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡አዲስ ዘመን ነሃሴ 3/2011ሶሎሞን በየነ
https://www.press.et/Ama/?p=15766
781
2ስፖርት
የኢትዮጵያ ካራቴ ብሄራዊ ቡድን ዝግጅት
ስፖርት
August 8, 2019
106
12 ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታ ከነሐሴ 13 እስከ 25 ቀን 2011 ዓ.ም በሞሮኮ ራባት ከተማ የሚካሄድ ሲሆን ኢትዮጵያም ተሳታፊ ከምትሆንባቸው 13 የስፖርት አይነቶች አንዱ ካራቴ ነው። በውድድሩ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ካራቴ ብሄራዊ ቡድን ልኡክ ከወዲሁ ቅድመ ዝግጅቱን እያደረጉ እንደሚገኙና በውድድሩም ጥሩ ውጤት ያስመዘግባሉ የሚል እምነት መያዙ ተጠቁሟል። ተሳታፊ ስፖርተኞችም ውጤታማ ለመሆን እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ካራቴ ፌዴሬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሠፋ አንጀሎ ዝግጅቱን አስመልክተው እንደተናገሩት ፤ ለውድድሩ ትኩረት በመስጠት ከግንቦት ወር ጀምሮ ዝግጅት መጀመሩንና ሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተሳተፉበት ሻምፒዮና በማካሄድ ውጤታማ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሎ የታመነባቸው 25 ወጣት ስፖርተኞች ዕጩ የብሔራዊ ቡድን አባል የማድረግ ስራ መከናወኑን ተናግረዋል፡፡ ከተመለመሉት ዕጩ የብሔራዊ ቡድን አባላት ውስጥም አስፈላጊውን ማጣሪያ በማድረግ 3 ሴትና 6 ወንድ ስፖርተኞች ለውድድሩ ተመርጠዋልⵆ ስፖርተኞቹም በቀን 2 ጊዜ የስልጠና መርሃ ግብር ወጥቶላቸው ዝግጅታቸውን በማድረግ ላይ ሲሆኑ መንግስትም በቂ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ በውድድሩ የተሻለ ውጤት እንደሚመዘገብ ፍላጎት ማሳየቱን ተናግረዋል። እገዛው ጥሩ ቢሆንም ብሄራዊ ቡድኑ በተወሰነ መልኩ ውስንነቶች እንዳሉበት ጠቁመዋል። ከውስንነቶቹ መካከል ዓለም አቀፉ የካራቴ ፌዴሬሽን ያረጋገጠው የመወዳደሪያ ልብስ “ቲሞኖ” በሀገር ውስጥ አለመኖሩ ነው ያሉት አቶ አሰፋ ይህን ችግር ለመፍታትና ለውድድሩ ሙሉ ሆኖ ለመገኘት ከአንዳንድ ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በመጻጻፍ ላይ ነን ብለዋል፤ ጥረቱ ተሳክቶም ለውድድሩ እንደሚደርስ ያላቸውን እምነት ጠቁመዋል። የብሄራዊ ቡድኑ ዋና አሠልጣኝ ኢንስትራክተር ዮሴፍ ተበጀ በበኩላቸው ዝግጅቱ ጥሩ መሆኑን ተናግረው ተወዳዳሪ ስፖርተኞች የሚሰጣቸውን ስልጠና በአግባቡ እየተቀበሉ መሆኑን እና በስነ ልቦና ፣ በታክቲክ እና በቴክኒክ በመዘጋጀት ሙሉ የማሸነፍ አቅምም መፍጠራቸውን ተናግረዋል ፡፡ ኢንስትራክተር ዮሴፍ እንደሚሉት ቡድኑ እየተደረገለት ያለው ድጋፍ ከወትሮው የተለየ ነው ተወዳዳሪዎችም በድጋፉ ልክ ውጤት ለማስመዝገብ ጥረት እያደረጉ መሆኑን ገልፀዋል ፡፡ በዝግጅቱ ዙሪያ አስተያየቱን የሰጡት የነጠላ ካታና የቡድን ካታ ተወዳዳሪ የሆኑት ሄዋን እና ሰለሞን እንደገለፁት ፤ በፌዴሬሽኑ እየተደረገ ያለው ድጋፍ እና በአሠልጣኙ እየተሰጣቸው ባለው ስልጠና ደስተኞች መሆናቸውን በመግለጽ ለሀገራቸው ውጤት በማስመዝገብ አዲስ ታሪክ ለመስራት መዘጋጀታቸውን አብራርተዋል፡፡ በሞሮኮ ራባት በሚካሄደው 12ኛው መላ አፍሪካ ጨዋታ በካራቴ ስፖርት ኢትዮጵያ በ 3 ሴት በ 6 ወንድ ስፖርተኞች ተወክላ የምትሳተፍ ሲሆን በነጠላ ካታ እና ኩምቴ (fight) በወንድ እና በሴት እንዲሁም በቡድን ካታ በወንድ ትካፈላለች ፡፡አዲስ ዘመን ነሃሴ 2/2011
https://www.press.et/Ama/?p=15706
312
2ስፖርት
የኢትዮጵያዊውና ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ወግ በኦሪገን
ስፖርት
August 10, 2019
39
ከአንድ ወር በኋላ በኳታር ዶሃ በሚካሄደው 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ለውጤት ከሚጠበቁ የዓለማችን አትሌቶች መካከል ኢትዮጵያዊው ዮሚፍ ቀጄልቻና ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ የሆላንድ አትሌት ሲፈን ሃሰን ግንባር ቀደሞቹ ስለመሆናቸው ጥርጥር የለውም። በዘንድሮው የውድድር ዓመት በተለያዩ ርቀቶች አስደናቂ ብቃት እያሳዩ የሚገኙት እነዚህ አትሌቶች የዓለም ቻምፒዮናው ላይ ለተለያዩ ሁለት አገራት የሚሮጡ ቢሆንም አሁን ላይ የሚያመሳስላቸውና የሚጋሩት በርካታ ነገሮች እንዳሉ የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ድረ ገፅ ፀሐፊው ስቲቭ ላንዴልስ ሰሞኑን ያስነበበው ሰፊ ሐተታ ይነግረናል። ሁለቱ ኮከቦች በደም ኢትዮጵያውያን መሆናቸው መጀመሪያ የሚጋሩት እውነታ ሲሆን የሕይወት እጣ ፋንታቸው መንገዳቸውን ለየቅል አድርጎት ዓለም አቀፍ ውድድሮችን አንዱ ለትውልድ አገሩ ሲሮጥ ሌላኛው መጠጊያ ለሆነችው አገር ሰንደቅ አላማ ሲሮጡ እንመለከታቸዋለን። ይህን እውነታ የሚጋሩ በርካታ አትሌቶች በየአህጉሩ የሚገኙ ቢሆንም በአሜሪካ ፖርትላንድ ኦሪገን ግዛት ያለው የናይኪ (የስፖርት ትጥቅ አምራች ኩባንያ) የአትሌቲክስ ፕሮጀክት ሲፈንና ዮሚፍን በአንድ ካፕ አምጥቶ በርካታ ጉዳዮችን እንዲጋሩ አስችሏቸዋል። ዮሚፍና ሲፈን በኢትዮጵያ ተወልደው ያደጉ ሲሆን አሁን ላይ በናይኪ ኦሪገን ፕሮጀክት አማካኝነት ኑሯቸውን አሜሪካን አገር ካደረጉ ሰንብተዋል። በአንድ አሰልጣኝ፣ በአንድ የልምምድ ቡድንና በአንድ ካፕ ውስጥ እየኖሩም ዘንድሮ የዓለም የማይል ክብረወሰንን ለመጨበጥ በቅተዋል። በአስራ አምስት ዓመቷ ኢትዮጵያን ተሰናብታ ወደ ሆላንድ ሃገር ያቀናችው ሲፈን በሂደት የአትሌቲክስ ሕይወትን አዳብራ 2014 ላይ የአውሮፓ ቻምፒዮን ስትሆን በ2016 የዓለም የቤት ውስጥ ቻምፒዮና የ1500 ሜትር አሸናፊ እስከ መሆን ደርሳለች። በ2016 ሪዮ ኦሊምፒክ በ1500 ሜትር አምስተኛ ሆና ካጠናቀቀች ወዲህ በሃያ ሦስት ዓመቷ የናይኪን ፕሮጀክት ተቀላቅላ ነበር ወደ ኦሪገን ያመራችው። ድንቅ የሩጫ ተሰጥኦና ቁመናን የታደለው ወጣት ኢትዮጵያዊ አትሌት 2013 ላይ ገና በአስራ አምስት ዓመቱ የዓለም ከሃያ ዓመት በታች ቻምፒዮና አሸናፊ ከመሆን ባሻገር በቀጣይ ጥቂት ዓመታት የዓለም ከሃያ ዓመት በታች የ5ሺ ሜትር ቻምፒዮንና የወጣቶች ኦሊምፒክ የ3ሺ ሜትር ቻምፒዮን ለመሆን በቅቷል። 2016 ላይ በዓለም የቤት ውስጥ ቻምፒዮና አሸናፊ መሆኑን ተከትሎ የውድድሩ አዘጋጅና የአሁን መኖሪያው የሆነችውን ፖርትላንድን ተዋወቀ። የናይኪን ፕሮጀክት ተቀላቅሎም ኑሮውን እዚያው ለማድረግ ወሰነ። ዮሚፍ ከወጣቶች ጎራ ወጥቶ ወደ አዋቂዎች የውድድር ጎራ ያደረገው ሽግግር እንደታሰበው በውጤት የታጀበ አልነበረም። 2016 ሪዮ ኦሊምፒክ ላይ አገሩን ሳይወክል ከመቅረቱ ባሻገር በ2017 የዓለም ቻምፒዮና ለንደን ላይ በ5ሺ ሜትር አራተኛ ሆኖ ማጠናቀቁ ምቾት አልሰጠውም ነበር። ‹‹ለንደን ላይ አራተኛ ማጠናቀቄ አላስደሰተኝም ነበር፣ ይህም ከመም ውድድር ወጥቼ ወደ ጎዳና ላይ ውድድሮች እንዳተኩር ውሳኔ ላይ እስከመድረስ አድርሶኝ ነበር፣ ማኔጀሬ ግን ቢያንስ አንድ ዓመት በመም ውድድሮች ላይ እንድቆይ ነበር ምክር የለገሰኝ›› በማለት ዮሚፍ ከሁለት ዓመት በፊት የነበረውን ያስታውሳል። ያኔ የኦሪገንን ፕሮጀክት ሲቀላቀል የእንግሊዘኛ ቋንቋ ይቸግረው የነበረው ዮሚፍ አሁን ላይ የቋንቋ ችሎታውን እያሻሻለ ይገኛል። ለዚህ ደግሞ ፕሮጀክቱን ሲቀላቀል ያገኛት ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሲፈን ሃሰን እሱ የሚናገረውን የአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ተናጋሪ መሆኗ በእጅጉ ነገሮችን አቅልሎለታል።‹‹መጀመሪያ ላይ አሜሪካን አገር ለመኖር ተቸግሬ ነበር፣ እንግሊዝኛ ቋንቋ መናገር ስለማልችል የምትረዳኝ ሲፈን ነበረች፣ ከሁለት ሳምንታት በኋላ ግን እንግሊዝኛ ለማውራት ራሴን ማስገደድ ጀመርኩኝ›› ይላል ዮሚፍ።ከትውልድ አገሯ ለረጅም ዓመታት የራቀችው ሲፈን አብዛኛውን የወጣትነት ዘመኗን በአውሮፓውያን ባህል ውስጥ እንደማሳለፏ የዮሚፍን የቋንቋ ክፍተት ለመድፈን የምትቸገር አይደለችም። ‹‹ዮሚፍ ወደ ፕሮጀክቱ ለመምጣት የወሰነው እኔ እዚህ እንዳለሁ ስለሚያውቅ ነበር፣ ይህም አስተርጓሚው ሆኜ በፕሮጀክቱ የሚኖረውን ሕይወትና የአሜሪካን አገር ቆይታውን ቀላል አድርጎለታል›› በማለት ሲፈን በተለመደ ፈገግታዋ ታጅባ ትናገራለች። ይሁን እንጂ ለወጣቱ አትሌት ከቋንቋ ጀምሮ የአካባቢውን ባህልና አዲስ አካባቢ መላመድ ቀላል አልነበረም። በእውቁ አሰልጣኝ አልቤርቶ ሳላዛር የሚሰጠውን የልምምድ ጫናም መቋቋም በቀላሉ የሚለመድ አልሆነለትም። ‹‹ከስድስት እስከ ስምንት ባሉት የመጀመሪያ ወራት ብዙ መሰዋዕትነት መክፈል ነበረብኝ፣ በነዚህ ጊዜያት ወደ አገሬ ለመመለስ ያሰብኩበበት አጋጣሚ ሁሉ ነበር፣ ያም ሆኖ በነዚያ ጊዜያት ያመጣሁትን ለውጦች ዞር ብዬ እመለከት ነበር፣ ስለዚህ እዚሁ መቆየት ትክክለኛ ውሳኔ መሆኑን አመንኩኝ›› ይላል ዮሚፍ አስቸጋሪውን ጊዜ ሲያስታውስ።ሲፈን በበኩሏ‹‹ እኔ ልክ እንደ እህቱ ነኝ፣ የትም ቦታ ቢሆን ይዤው እሄዳለሁ›› ትላለች። ሁለቱ አትሌቶች አንድ ካምፕ ውስጥ ከመኖር በዘለለ ፊልሞችን የሚመለከቱትና የሚመገቡት ጭምር አንድ ላይ ነው። ሲፈን የዮሚፍ አብሯት መኖር እሷን የበለጠ ተጠቃሚ እንዳደረጋት ትናገራለች። በተለይም በለጋ እድሜዋ ከተለየቻት አገሯ ኢትዮጵያ ጋር የበለጠ እንድትቀራረብ በማድረግ ረገድ በእጅጉ መጠቀሟን ታብራራለች። ከኢትዮጵያ ማርና ቅቤ አንስቶ በርካታ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች እስከሚያዘወትሩት የገብስ በሶ ድረስ እንዳስታረቃትም ታወሳለች። ‹‹ባለፈው ዓመት ሁለት ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ሄጃለሁ፣ ወደ ኢትዮጵያ ባህል በመጠኑም ቢሆን መጠጋቴ ጥሩ ነው›› ስትልም ሲፈን የትውልድ አገሯን ታስታውሳለች። ዮሚፍ አዲሱን ኑሮ ለመላመድ እንደተቸገረው ሁሉ ሲፈንም በፕሮጀክቱ የሚሰጣትን የልምምድ ጫና ለመቋቋም ተቸግራ ነበር። በተለይም ልምምዷን ከዮሚፍ ጋር መስራት በጀመረችባቸው ሳምንታት የበለጠ ጫናና ድካም እንደነበረባት ታስታውሳለች። ሆላንድ በነበረችበት ወቅት ከምትሰራው ልምምድ በበለጠ ከዮሚፍ ጋር ጠንካራ ልምምድ እንደምታደርግም ትናገራለች። ‹‹በአንድ ማለዳ አራት መቶና ሁለት መቶ ሜትርን በተደጋጋሚ ልምምድ ስንሰራ ከአቅሜ በላይ ሆኖ ነበር፣ መሞቴ ነው እንዲህ አይነት ልምምድ ከምሰራ በጥይት ብትገድሉኝ ይሻለኛል አልኩ፣ ለምን ያህል ድግግሞሽ ልምምዱን እንዳረኩኝ ባላስታውስም ልምምዱን ከጨረስኩኝ በኋላ ሰውነቴ ዝሎ መንቀሳቀስ እንዳልቻልኩኝ አስታውሳለሁ›› በማለት ሲፈን በፕሮጀክቱ ስለሚያደርጉት ጠንካራ ልምምድ ታብራራለች።በአጭር ጊዜ ውስጥ ሁለቱ አትሌቶች የልምምዱን ጫና እየተላመዱ አካል ብቃታቸው እያደገ መምጣቱ አልቀረም። ይህም ባለፈው ዓመት በብቃታቸውና በውጤታቸው ላይ ለውጥ አምጥቶላቸዋል። ዮሚፍ በርሚንግሃም ላይ በዓለም የቤት ውስጥ ቻምፒዮና የ1500 ሜትር ክብሩን ከማስጠበቅ ባለፈ በተመሳሳይ ርቀት ከቤት ውጪ 3፡32፡59 የሆነ የራሱ ፈጣን ሰዓት ማስመዝገብ አስችሎታል። በ3ሺ ሜትር 7፡28፡00 የሆነ የዓመቱ ፈጣን ሰዓት ሲያስመዘግብም በ5ሺ ሜትር 12፡46፡79 የሆነ ፈጣን ሰዓት ባለቤት መሆን ችሏል። በኮፐንሃገን ግማሽ ማራቶን ለመጀመሪያ ጊዜ በርቀቱ ተወዳድሮ ያስመዘገበው 59፡17 ሰዓትም አይን ውስጥ የሚገባ ነበር።በተመሳሳይ ሲፈን 2018 የውድድር ዓመት ላይ የአውሮፓ የ5ሺ ሜትር ቻምፒዮን ስትሆን በአንድ ማይል ውድድር 4፡14፡71፣ በ3ሺ ሜትር 8፡27፡50፣ በ5ሺ ሜትር ደግሞ 14፡22፡34 የሆነ ሰዓት በማስመዝገብ የሆላንድን ክብረወሰኖች መጨበጥ ችላለች። ዮሚፍ ለመጀመሪያ ጊዜ በተወዳደረበት የኮፐንሃገን ግማሽ ማራቶን ሲፈንም ለመጀመሪያ ጊዜ በርቀቱ ተወዳድራ 1፡05፡15 በሆነ ሰዓት የአውሮፓን ክብረወሰን ከማስመዝገብ ባለፈ በርቀቱ ያላትን እምቅ አቅም አሳይታበታለች። ሲፈን የ 8 መቶና የ1500 ሜትር ሯጭ በነበረችበት ወቅት የ5ሺ ሜትር ሯጭ ብትሆን የተሻለ እንደሚሆን ሃሳብ ነበራት። ይሁን እንጂ አሰልጣኟ ግማሽ ማራቶንን በ68ና 69 ደቂቃ ማጠናቀቅ እንደምትችል ምክር ከለገሳት በኋላ ኮፐንሃገን ላይ እንደተወዳደረች ትናገራለች። በዚህ ውድድር ከጠበቀችው በላይ ግማሽ ማራቶንን በ65 ደቂቃ ማጠናቀቅ በመቻሏ መደነቋን አልሸሸገችም። ሁለቱ አትሌቶች ከ2018 በተሻለ በ2019 የውድድር ዓመት በዓለም አትሌቲክስ ላይ የሚያሳድሩት ተፅዕኖ እየጨመረ መጥቷል። ባለፈው የካቲት ሲፈን ሞናኮ ከተማ በጎዳና ላይ 5 ኪሎ ሜትር ውድድር 14፡14 የሆነ የዓለም ክብረወሰን መስበር ስትችል፣ ዮሚፍ ቦስተን ላይ 3፡47፡01 የሆነ የአንድ ማይል የዓለም ክብረወሰን አሻሽሏል። ዮሚፍ በዘንድሮ የውድድር ዓመት በተለይም በ5ሺ ሜትር የዳይመንድ ሊግ ውድድሮች አስደናቂ ብቃቱን እያሳየ ይገኛል። ስታንፎርድ፣ ሻንጋይና ሉዛን ከተሞች ላይ በርቀቱ የተካሄዱ የዳይመንድ ሊግ ውድድሮችን ማሸነፉ የሚታወስ ሲሆን ከሦስት ሳምንት በፊት ሄንግሎ ላይ በተካሄደው የኢትዮጵያውያን የማጣሪያ ውድድር በ10ሺ ሜትር ለመጀመሪያ ጊዜ ተሳትፎ 26:49.99 ሰዓት በማስመዝገብ ሦስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል። ይህም በዶሃው የዓለም ቻምፒዮና ኢትዮጵያን በ10 ሺ ሜትር ከሚወክሉ አትሌቶች መካከል አንዱ አድርጎታል። ሲፈን በበኩሏ በ3ሺ ሜትር 8፡18፡49ና በ5ሺ ሜትር 14፡22፡12 የሆነ የአውሮፓ ክብረወሰን ማስመዝገብ የቻለች ሲሆን ስታንፎርድ ዳይመንድ ሊግ ላይ 10ሺ ሜትርን 31፡18፡12 በሆነ ሰዓት ማጠናቀቅ ችላለች። እነዚህ ስኬቶች ሁለቱ የአንድ አገር አትሌቶች በዜግነት ቢለያዩም የአትሌቲክስ ሕይወታቸው በኦሪገን ፕሮጀክት ውስጥ እያበበ የብቃታቸው ጥግ ላይ እየደረሱ እንደሚገኙ ነው።.በናይኪ ኦሪገን ፕሮጀክት ውስጥ አሰልጣኝ የሆነው ቲም ሮውበሪ ሁለቱ አትሌቶች ፕሮጀክቱን ከተቀላቀሉ ወዲህ እያሳዩ የሚገኘውን ለውጥ ሲናገር፣ ዮሚፍና ሲፈን ጠንካራ ሰራተኛ ለመሆን ያላቸውን ከፍተኛ ፍላጎት ብቻም ሳይሆን አዳዲስ ፈተናዎችን ለመጋፈጥ ያላቸውን ቁርጠኝነት ሳያደንቅ አያልፍም። ሁለቱ አትሌቶች የአትሌቲክሱን ስልጠና ያግዛቸው ዘንድ የውሃ ዋና እንዲደፍሩ በየጊዜው እንደሚያበረታታቸው የሚናገረው አሰልጣኙ፣ አትሌቶች የመዋኘት ልምድ ባይኖራቸውም ለመልመድ ደስተኛ ሆነው እየሰሩ እንደሚገኙ ያብራራል። በተለይም ዮሚፍ ከጥቂት ወራት በፊት ምንም አይነት የመዋኘት ልምድ የሌለው አትሌት እንደመሆኑ በፍጥነት እየለመደ መምጣቱ አስገራሚ መሆኑን ይናገራሉ። ሁለቱ አትሌቶች በዶሃው የዓለም ቻምፒዮና ትኩረት የሚሰጣቸው እንደመሆኑ በናይኪ ኦሪገን ፕሮጀክት መታቀፋቸው አሰልጣኙን ደስተኛ እንዳደረገው ይናገራል። ሁለቱ አትሌቶች በፕሮጀክቱ ውስጥ መኖራቸው ለሌሎች የፕሮጀክቱ አትሌቶች የሚጨምርላቸው ነገር እንደሚኖር እምነቱ ነው። ዮሚፍና ሲፈን አስደናቂ የሩጫ ተሰጥኦ ያላቸው ከመሆኑ ባሻገር አዲስ ነገሮችን በፍጥነት የመላመድ ችሎታቸውን አሰልጣኙ ያደንቃል።‹‹ ከዚህ በፊት እንደነዚህ አይነት አትሌቶች አሰልጥኜ አላውቅም፣ሁለቱም የተለዩ አትሌቶች ናቸው›› ሲልም አሰልጣኙ ይመሰክርላቸዋል። አዲስ ዘመን ቅዳሜ 4/12/11 
https://www.press.et/Ama/?p=15791
1,134
2ስፖርት
ሌላኛው የማሸነፍ ምስጢር
ስፖርት
August 11, 2019
69
ከጊዜ ወደ ጊዜ የእግር ኳስ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው በእጅጉ እየጨመረ ነው። ከሁለት ባላጋራዎች የሜዳ ላይ ፉክክር አልፎ እያንዳንዳችን ቤት ገብቷል። ከሌሎች ስፖርታዊ ክንውኖች ባሻገር ዓለም አቀፍ ተፅእኖውም በጣም ከፍተኛ ነው። ክለቦች፣ ብሄራዊ ቡድኖች እንዲሁም የእግር ኳስ አካዳሚዎች ረብጣ ገንዘብ በስፖርቱ ላይ በማፍሰስ የድል ማማ ላይ ለመንጠልጠል ይፎካከራሉ። ማንኛውንም ነገር ስኬት ላይ የሚያደርሳቸው ከሆነ ያለማቅማማት ይተገብሩታል። ድሮ ድሮ የእግር ኳስ ቡድኖች ተጫዋቾቻ ቸውን በታክቲክ እና በአካል ብቃት እንዲሁም በተለያዩ የተግባር ልምምዶች ይገነቡ ነበር። በዚህ ዘመን ግን በውድድሮች ሁሉ አሸናፊ ለመሆን እርሱ ብቻ በቂ ሆኖ አልተገኘም። የተጫዋቾች የስነ ልቦና ይዘት እና ያሉበት ሁኔታ ለአንድ ቡድን ማሸነፍ ከምንም ነገር በላይ አስፈላጊ ነው። በመሆኑም ያላቸውን አቅም እና ክህሎት በሚገባ እንዲጠቀሙበት፤ በራስ መተማመናቸው እና የስነ ልቦና ይዘታቸው ጥሩ ሁኔታ ላይ መገኘት ይኖርበታል። ምንም እንኳን አንድ እግር ኳስ ተጫዋች የአካል እና የታክቲክ ብቃቱ ጥሩ ሁኔታ ላይ ቢገኝም፤ በተለያየ ምክንያት የስነ ልቦና ይዞታው ጥሩ ካልሆነ በሚፈለገው ደረጃ የሚጫወትበትን ቡድን ሊጠቅም አይችልም። ይህ በመሆኑን የእግር ኳስ ብሄራዊ ቡድኖች፣ ክለቦች እንዲሁም አካዳሚዎች የተጫዋቾቻቸውን የስነ ልቦና ደረጃ በመልካም ሁኔታ ለማሳደግ በዘርፉ ጠበብት የሆኑ ባለሙያዎቻቸውን በቡድናቸው ውስጥ ያካትታሉ። ለዛሬ የዝግጅት ክፍላችን «ስነ ልቦና በእግር ኳስ መድረክ ላይ ያለውን ጠቀሜታ» ለመዳሰስ ይሞክራል። በተለይም ለአገራችን የእግር ኳስ እድገት የስፖርቱ ቤተሰቦች ይህንን ተግባራዊ እንዲያደርጉ አንዳንድ ነጥቦችን ለመጠቆም ይሞክራል። በዚህ ወቅት ብሄራዊ ቡድናችን እንዲሁም በአገሪቷ የሚገኙ ክለቦች፤ የስነ ልቦና ሳይንሱን በሚገባ ተረድተው ከጥቅሞቹ ለመቋደስ መሄድ የሚገባቸውን ርቀት እንዳልተጓዙ የሚያመለክቱ በርካታ ጉዳዮችን ማንሳት ይቻላል። ሆኖም ለምን ተግባራዊ አላደረጉም የሚል ትችት ከመሰንዘር ባለፈ ዘርፉ ያለውን ጠቀሜታ ለመዳሰስ እና ጉልህ ሚናውን ለነዚህ የስፖርት ቤተሰቦች ለማሳየት እንሞክራለን። ይህ ዳሰሳ ስነ ልቦናን ከእግር ኳስ አንፃር ቢቃኝም ቅሉ ሳይንሱ ለሌሎች ስፖርቶች አይሰራም ማለት እንዳልሆነ ከግምት ውስጥ መግባት ይኖርበታል። የእግር ኳስ ደረጃቸው ጫፍ ላይ የደረሱ ብሄራዊ ቡድኖች እና ክለቦች በስብስባቸው ላይ የተጫዋቾቻቸውን ስነ ልቦና ደረጃ ከፍ ለማድረግ፤ በሳይንሱ ብቁ ቦታ ላይ የሚገኙ ባለሙያዎችን በቡድናቸው ውስጥ ያካትታሉ። የስነ ልቦና ህክምና ወይም ድጋፍ በአውሮፓ የእግር ኳስ ቡድኖች ውስጥ የሚካተት ቢሆንም በስፋት ግን የመገናኛ ብዙሀንን ትኩረት አያገኝም። ምክንያቱም በባህሪው ለተጫዋቾች የሚደረገው የስነ ልቦና ድጋፍ ሚስጥራዊ ይዘት ስለሚኖረው ነው። ሆኖም ግን ተጫዋቾች ከተለመደው ልምምዳቸው እኩል የስነ ልቦና ድጋፍ ሲያስፈልጋቸው ጎን ለጎን መውሰዳቸው አዲስ አይደለም። ዶክተር ቲም ኦብሪን በዘርፉ ከፍተኛ ዝናና አድናቆትን ያተረፉ የስነ ልቦና ባለሙያ ናቸው። በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በርካታ ደጋፊ እና አስደናቂ ክብረ ወሰኖች ባለቤት ከሆነው አርሰናል ክለብ ጋር ከ10 ዓመት በላይ አብረው ሰርተዋል። እኚህ አንጋፋ የዘርፉ ጠቢብ በአርሰናል ቤት አሻራቸውን ጥለው ላለፉት ዴኒስ ቤርካምፕ፣ሮበርት ፒሬዝ፣ቴሪ ዳንኤል ሄንሪ እና ሌሎች ተጫዋቾች እርዳታ ባስፈለጋቸው ቁጥር ከጎናቸው ነበሩ። ዶክተሩ «የስነ ልቦና ህክምና» ለእግር ኳስ ያለውን ከፍተኛ ጠቀሜታ ይናገራሉ። ዶክተር ቲም በስነ ልቦናው ሳይንስ «እሳቤ፣ስሜት እና ባህሪ» ያላቸውን የተወሳሰበ ግንኙነት ትኩረት በማድረግ ይሰራሉ። እነዚህ ሶስት አስፈላጊ ነገሮች ሲሆኑ በተጫዋቾች ብቃት ላይ በአሉታዊ እና አወንታዊ መልኩ ተፅእኖ ያሳድራሉ። ባለሙያው ተጫዋቾቹ ያላቸውን ትክክለኛ አቅም አውጥተው እንዲጠቀሙ፤ ስሜት፣ባህሪ እና እሳቤያቸው ጤናማ ግንኙነት እንዲያደርጉ እርዳታቸውን ይለግሷቸዋል። በእግር ኳስ ክለቦች የስነ ልቦና ባለሙያ ቀጥሮ ድጋፍ ማድረግ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ አስቆጥሯል። እንደ ዶክተር ቲም ገለፃ ግን በእግር ኳስ ላይ ብቻ ሳይሆን በሁሉም የሰው ልጅ እሳቤ የዚህ ሳይንስ ድጋፍ ጠቀሜታ የት የለሌ ነው። «እኔ በስፖርት ውስጥ የምሰራ የስነ ልቦና ባለሙያ እንጂ፤ የእግር ኳስ ስነ ልቦና ባለሙያ አይደለሁም። እኛ እያወራን ያለነው ስለ ሰው ልጆች ነው። ስለዚህ ሁሉም እሳቤውን እና አእምሮውን በጥልቅ እንዲገነዘብ ማድረግ ተገቢ ነው። በጥልቅ አእምሯችን ውስጥ ያለው ታሪክ እሳቤያችንን፣ስሜታችንን እና ድርጊታችንን ይመራዋል። ሁላችንም በአእምሯችን ውስጥ የተለያየ ጥልቅ ታሪክ አለን። ስለዚህ ይህ ታሪካችን እኛነታችንን እንዴት እንደሚገድበን እና እንደሚቀይረን መረዳት መቻል ይኖርብናል። አብዛኛው የስፖርት ቤተሰብ ተጫዋቾችን እንደ ቲያትረኛ ይመለከታቸዋል። ነገር ግን የእግር ኳስ ቲያትረኛ ከመሆናቸው በፊት ሰዎች ነበሩ» በማለት ዶክተር ቲም የተጫዋቾችን ጥልቅ ስሜት፣እሳቤ እና ባህሪ በመረዳት ውጤታማ እንዲሆኑ እንደሚረዷቸው ይናገራሉ። የብቃታቸው ጫፍ ላይ የደረሱ ተጫዋቾች ቢኖሩ እንኳን የስነ ልቦና ጥንካሬያቸው በዚያን ወቅት ጥሩ ካልሆነ በፈለጉት ደረጃ ቡድናቸውን መጥቀም አይችሉም። የአጠቃላይ ቡድኑ ጥንካሬ በእነርሱ ወቅታዊ ብቃት ላይ የተመሰረተ ነው። በማለት በተለያዩ ጉዳዮች የእግር ኳስ ተጫዋቾች የስነ ልቦና ችግር ሊያጋጥማቸው እንደሚችል ይናገራሉ። በዚህ ጊዜም ከባለሙያ ድጋፍ ማግኘት እንደሚኖርባቸው ይጠቁማሉ። አንድ እግር ኳስ ተጫዋች 90 ደቂቃ ሊጫወት ይችላል። እግር ኳስ የታክቲክ፣ የሰውነት ንክኪ እና የፈጠራ ብቃት ላይ የተመሰረተ ጨዋታ ነው። ነገር ግን ይህ ጨዋታ የስነ ልቦና ቁማርንም «psychological game» እንደሚጨምር መረዳት ይኖርብናል። ወደ አገራችን ስንመለስ በተለያዩ ክለቦች እና ፕሮጀክቶች በርካታ ተጫዋቾች አሉ። አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ የአገራችንን ክለቦች ስንመለከት ለቡድናቸው አስፈላጊውን ሁሉ በማሟላት ቡድናቸውን ውጤታማ ለማድረግ ሙሉ አቅም ላይኖራቸው ይችላል። ነገር ግን ለስኬታቸው ቁልፍ የውጤታማነት መሰረት የሆኑ ጉዳዮችን መረዳት እና መተግበር ይኖርባቸዋል። ከእነዚህ መካከል ደግሞ ተጫዋቾቻቸውን በስነ ልቦና ሳይንስ የተሻለ ደረጃ ላይ እንዲደርሱ ባለሙያዎችን በቡድናቸው ውስጥ ማካተት ቀዳሚው ተግባር ነው። ዶክተር ቲም ከላይ ያነሳነውን ጉዳይ የሚያጠናክር ሀሳብ ያነሳሉ «ለምሳሌ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ላይ ያሉ ተጫዋቾችን እንመልከት። ሊጉ በጣም ፍጥነት የተቀላቀለበት ነው። ተጫዋቾቹ በዚያ ሁኔታ ላይ ሆነው እንኳን በጣም አስደናቂ ነገሮችን በሰከንድ ውስጥ ሲወስኑ እና ሲተገብሩ እንመለከታለን። ከቡድናቸው ጋር በቀላሉ መናበብ ይችላሉ። በሙሉ የራስ መተማመን እና ጥንካሬ ከተፋላሚያቸው ጋር ይፋጠጣሉ። ይህ እንዲሆን ከተፈለገ አንድ የእግር ኳስ ቡድን ተጫዋቾቹን የሚደግፍ፣የሚያበረታታ እንዲሁም ጭንቀታ ቸውን እና የአእምሮ ውጥረታቸውን የሚያስ ወግድ የስነ ልቦና ባለሙያ ያስፈልገዋል» ሲሉ አስተያየታቸውን ያስቀምጣሉ። እግር ኳስ በጣም በርካታ ተመልካች ባለበት ሜዳ ላይ ለ90 ደቂቃዎች የሚደረግ ፍልሚያ ነው። ከዛም ባለፈ በመገናኛ ብዙሀን ላይ ሰፊ ሽፋን ያገኛል። በተለይ አሁን የማህበራዊ ድረ ገፆች መስፋፋትን ተከትሎ በእያንዳንዷ ሰከንድ ከተጫዋቾች እና ከክለቦች ጋር የተያያዙ መረጃዎች ይወጣሉ። በበጎም ሆነ በመልካም ነገር የሚዛመት የተጫዋቾች መረጃ ለስነ ልቦና ጫና ያጋልጣሉ። ይህ ደግሞ የተጫዋቾቹን የግል ህይወት ሲጨምር ጫናው እንዲበረታ ያደርገዋል። በዚህ ጊዜ ነው እንግዲህ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው። የስነ ልቦና «ጫና» እና «ውጥረት» የየራሳቸው ባህሪ አላቸው። በእግር ኳስ አምጥተን ከተመለከትናቸው ደግሞ አንዳንዶቹ ተጫዋቾች በጫና ውስጥ ሆነው ጥሩ ብቃታቸውን ሊያሳዩ ይችላሉ። ጫናውን ይወዱታል። ምክንያቱም በእያንዳንዷ ጨዋታ ላይ ያዳበሩት ልምድ እንዲቋቋሙት አስችሏቸዋል። ዶክተር ቲም ሲናገሩ «በህይወት ውስጥ ጫና ወደ ውጥረት ሲቀየር፤ ነገሮችን ለመቋቋም የሚያስችል የስነ ልቦና ብቃት እንደሌለህ ልታስብ ትችላለህ። ይህ በስፖርቱ ዘርፍ ላይ ተመሳሳይ ነው። በዚህ ጊዜ እርዳታ ያስፈልግሀል። የባለሙያ እርዳታ ደግሞ በጫና ውስጥ ሆነህ እንዴት ስኬታማ እንቅስቃሴ እንደምታደርግ መንገዱን ያመላክትሀል» በማለት በእግር ኳስ ህይወት ላይ ምን ያህል ህክምናው ጠቀሜታ እንዳለው ለማስረዳት ይሞክራሉ። የሰው ልጅ አእምሮ ውስብስብ እና በጣም ሚስጢራዊ አሰራር ያለው ነው። ይህ በመሆኑ በስነ ልቦና ህክምና ላይ ብቁ የሆኑ ባለሙያዎችን በስራዎቻችን ላይ ማሳተፍ ለውጤታማነታችን አሌ የማይባል አስተዋጽኦ ያበረክታል። በእግር ኳስ ዘርፉ ላይ የስነ ልቦና ባለሙያዎችን በቡድናቸው ውስጥ ከሚያካትቱት ውስጥ እንደ ምሳሌ ከላይ ያነሳነው የእንግሊዙን አርሰናል ክለብ ነው። በአሁኑ ሰዓት ክለቡ በቦርዱ ውስጥ ዶክተር ሴሪ ኢቫንስን አካቷል። እርሳቸው የስነ አእምሮ ባለሙያ ናቸው። በስኬታማነት ከሚጠቀስላቸው ስራ መካከል የሲውዘርላንድ የራግቢ ብሄራዊ ቡድንን በሙያቸው እየረዱ የዓለም ዋንጫ ማንሳት መቻላቸው ነው። ከዚህም ሌላ በዋናው ቡድን ላይ የስነ ልቦና እና የስነ አዕምሮ ማበልፀጊያ ክፍል ሃላፊው ዴቪድ ፕሪስትሊ ይገኛሉ። የእግር ኳስ ቡድኖች የሙሉ ጊዜ የስነ ልቦና ባለሙያ ለመቅጠር የሚገደዱት ስፖርቱ በተጫዋቾች ላይ ይዞት የሚመጣው ውስብስብ ተፅእኖ ስላለ ነው። ነገር ግን የእግር ኳስ ቡድን ስንል ምን ማለታችን ነው? የእግር ኳስ ቡድን በአንድ መንደር ውስጥ እንደሚኖሩ እና በጥብቅ ማህበራዊ ግንኙነት እንደተሳሰሩ ማህበረሰቦች ይመሰላል። ዝም ብሎ 11 ተጫዋቾች ከሌላ ባላጋራቸው ጋር በሜዳ ላይ የሚያደርጉት ፍልሚያ አይደለም። በጨዋታው ለማሸነፍ በሜዳ ላይ ብቻ አብሮ መግባት በቂ አይደለም። ከዚህ ሌላ ቡድኑ አሸናፊ ለመሆን የአይበገሬነት እና በጣም የጠነከረ አንድነት ሊኖረው ይገባል። ይህ ሲሆን የሚፈለገው ውጤት ይመጣል። አንድ ተጫዋች የራሱ ማንነት እና ጥንካሬ ሊኖረው ይችላል። አንድ ቡድንም እንዲሁ በተመሳሳይ የራሱ ማንነት ፣ ጥንካሬ እንዲሁም ድክመት ይኖረዋል። በአንድ ቡድን ውስጥ ያሉ ተጫዋቾች ደግሞ የተለያየ ማንነት፣ባህል፣ ብቃት እንዲሁም የስነ ልቦና ጥንካሬ ላይ የሚገኙ ሊሆኑ ይችላሉ። እነዚህን ሁሉ የተሟላ እና ጥሩ በሆነ የራስ መተማመን አሸናፊነትን እንዲላበሱ እንደ እነ ዶክተር ቲም ያለ የስነ ልቦና ሳይንስን ጠንቅቆ የሚያውቅ ባለሙያ ቡድኑ ሊኖረው ይገባል። ዶክተር ቲም መጀመሪያ ከእግር ኳስ ተጫዋቾች ጋር መስራት ሲጀምሩ ያጋጠማቸውን ነገር ሲገልፁ እንዲህ ይላሉ «ልክ ስራዬን ስጀምር በአብዛኛው እግር ኳስ ተጫዋቾች ላይ አንድ ድምዳሜ ነበር። ይሄም አንዳንድ ተጫዋቾች በስነ ልቦና ደካማ አንዳንዶቹ ደግሞ ጠንካራ አድርጎ የመውሰድ የተሳሳተ አመለካከት ነበር። በስነ ልቦና ባለሙያ የሚረዱ ተጫዋቾች በደፈናው ደካማ እንደሆኑ ይቆጠር ነበር። ይህ ግን ፍፁም የተሳሳተ ነው። የስነ ልቦና ባለሙያ ከነበረህ ጥሩ አቋም የተሻለ ጥንካሬ እና ብቃት እንድትጨምር ያግዛል እንጂ፤ ችግር ያለባቸውን ሰዎች ብቻ ህክምና አያደርግም» በማለት የአእምሮ ደካማነት «mental weak­ness» እንዲሁም የአእምሮ ጥንካሬ «men­tal strength» ፤ በምርምር ላይ ተመስርቶ በሚገኝ ውጤት የሚረጋገጥ እንጂ በደፈናው አንድ ተጫዋች በስነ ልቦና ባለሙያ ስለተደገፈ እና ስላልተደገፈ የሚታወቅ አለመሆኑን ያስረዳሉ። ባለሙያው በቡድን ውስጥ በዋናነት የሚያስፈልገውም ቀለል ያሉ ማህበራዊ እና ግላዊ ችግሮችን በመቅረፍ ውጤታማነትን ስለሚያጎናፅፍ መሆኑን ይገልፃሉ። በቅርቡ የእግር ኳስ ተጫዋቾች የስነ አእምሮ ይዞታ መሰረት አድርጎ የወጣ «ፊፍ ፕሮፕ» የተባለ ጥናት እንደጠቆመው በአሁን ሰዓት በዓለም ዙሪያ ላይ እየተጫወቱ ከሚገኙ 607 ተጫዋቾች (ጥናቱን ለመስራት ከተመረጡት) ውስጥ 38 በመቶ ( 219 ተጫዋቾች ) በጭንቀት፣ ጥልቅ በሆነ ድብርት እንዲሁም ውጥረት የተጠቁ መሆኑን አረጋግጧል። ሌላ ተጨማሪ ማረጋገጫ እና አስተያየት ሳንጠብቅ የጥናቱ ውጤት ላይ ብቻ ተመስርተን ምን ያህል የስነ ልቦና ባለሙያ በእግር ኳስ ቡድን ውስጥ አስፈላጊ መሆኑን መገመት አያዳግተንም። ዶክተር ቲም «ስሜትህ ሁል ጊዜ ዓለምን በምትረዳበት ልክ ነው የሚሆነው። ለምትሰራው ስራ ዋጋ የምትሰጥ ከሆነ ያ በእርግጠኝነት ደስተኛ ያደርግሀል። ይህን ለመረዳት ደግሞ የባለሙያ እገዛ ያስፈልግሀል። ምንም ስራ ምን፤ የመጨረሻ ግብ ሊኖርህ ይገባል። የእግር ኳስ ደረጃቸው በጣም ከፍተኛ በሆነ አገር ውስጥ ረብጣ ገንዘብ እየተከፈለህ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ፍላጎትህን፣ ስሜትህን እንዲሁም አስተሳሰብህን ሊከፋፍል የሚችል ጉዳይ ከገጠመህ ደስታህን ይነጥቀዋል። ይሄ ደግሞ በአቋምህ እና ወቅታዊ ብቃትህ ላይ ተፅእኖ ይፈጥራል» በማለት ይናገራሉ። ይህ በሚሆንበት ሰዓት ደግሞ ቡድኑን ለመርዳት አብረው የሚገኙ የስነ ልቦና ባለሙያዎች ትልቁን ሚና ይጫወታሉ በማለት ያስረዳሉ። የኢትዮጵያ እግር ኳስ በጣም ዝቅተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ለማወቅ ሰፊ ርቀት መጓዝ አይጠይቅም። ለእድገቱ መጓተት ብሎም ባለበት ደረጃ ላይ መቆም፤ በርካታ ምክንያቶች ይነሳሉ። ከነዚህ ውስጥ ደግሞ በዋናነት እግር ኳሱ ዘመኑ ከፈቀደው የስልጣኔ እና ቴክኖሎጂ ትሩፋት ለመቋደስ ባለመቻሉ መሆኑን የተለያዩ ባለሙያዎች በየፊናቸው ይናገራሉ። እኛም ይህንኑ መነሻ በማድረግ ነው የዛሬውን ዘገባችንን ከአካላዊ እንቅስቃሴ ውጪ ባለው የእግር ኳስ ስነ አእምሮ ላይ ማተኮር የፈለግነው። በመሆኑም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሁሉ ዳሰሳውን በያዘው የመረጃ ልክ ተገንዝበውት ወደዚህ አሰራር ቢገቡ አንድ እርምጃ ወደፊት መጓዝ ይችላሉ የሚል እሳቤ አለን። ሰላም!አዲስ ዘመን ነሐሴ 5 /2011 
https://www.press.et/Ama/?p=15863
1,501
2ስፖርት
የኮቪድ 19 የማህበረሰብ አቀፍ ልየታና የምርመራ ዘመቻ ዛሬ ይጀመራል
ሀገር አቀፍ ዜና
August 2, 2020
14
አዲስ አበባ ፡-የኮቪድ 19 የማህበረሰብ አቀፍ ልየታና የምርመራ የመጀመሪያ ዙር ዘመቻ ዛሬ እንደሚጀመር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስታወቁ። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ትናንት በጽህፈት ቤታቸው ከሚኒስትሪያል ኮሚቴው አባላት ጋር በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ በተወያዩበት ወቅት እንዳስታወቁት የማህበረሰብ አቀፍ ልየታና የምርመራ ዘመቻው የሚደረገው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን አውቆ የበሽታውን ስርጭት ለመግታት እንዲያስችል እንዲሁም በነሀሴ ወር የተሳካ ስራ ተሰርቶ በሚቀጥለው ዓመት አብዛኛውን እንቅስቃሴ ወደ መደበኛነቱ ለመመለስ ነው። ከዛሬ ጀምሮ የሚደረገው ማህበረሰብ አቀፍ ምርመራ የልየታ ስራ በሚቀጥለው ዓመት ለምንሰራቸው ሁሉም ስራዎች ወሳኝ መነሻ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ሌሎችንም መንግስታዊ የሆኑ አሰራሮች እንዴት ይቀጥሉ የሚለውንም ለመወሰን ያስችላል። የልየታ ስራውን ለመስራት በመንግስት በኩል በቂ ዝግጅት ተደርጓል፤ በቂ መመርመሪያ አለ። የህክምና ተቋሞች ከፍተኛ የሆነ ልምድ አዳብረዋል። ነሀሴ ላይ የስርጭቱን ሂደት መቀነስ ከተቻለ መስከረም ላይ ለሚሰሩ ስራዎች ቀላል ይሆናል። በመሆኑም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ለመጀመር ዋነኛ ስራቸው ዘመቻውን ማሳካት መሆኑን ገልጸዋል። በሀገሪቱ በነበረው ግጭት ምክንያት የስርጭቱ መጠን መጨመሩን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል በሁለትና በሶስት እጥፍ ምርመራ ማድረግ አስፈላጊ ነው ብለዋል። ኮሮናን በመከላከል ጥሩ ውጤት ካስመዘገቡ ሀገራት መካከል አንዷ ኢትዮጵያ ናት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ከመስከረም በኋላ በጥቂት ወራት ውስጥ ቴስት ኪት ኢትዮጵ ውስጥ በማምረት ስርጭቱን ለመግታት እንደሚሰራ ገልጸዋል። እስካሁን ጥሩ ስራ በመሰራቱ ቀድሞ ከተተነበየው ጋር ሲነፃፀር የሚያዙ ሰዎች በ85 በመቶ፣ የሞት ምጣኔ ደግሞ በ95 በመቶ መቀነሱን አስታውቀዋል። ይህን ቁጥር ማስቀጠል ከተቻለ ትልቅ ድል ነው ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ እንዳሉት ምርመራ ካልተደረገና ምን ያህል ሰው እንደተያዘ ካልታወቀ አንድ ሰው ሶስት ሰዎችን ያስይዛል። ይህ ደግሞ ስርጭቱን ያስፋፋል፤ ከቁጥጥር ውጭ እንዲወጣም ያደርገዋል። የማህበረሰብ አቀፍ ምርመራ እስካሁን ያለውን ስራ የሚያጠናክርና ለወደፊትም አጋዥ መሆኑን ጠቅሰው በተያዘው ዓመት ክረምት ውስጥ ኮሮናን መቆጣጠር ካልተቻለ ጥሩ ስራ እየሰሩ ያሉትን አርሶ አደሮች ስራ ያስተጓጉላል። ሌሎች የልማት ስራዎችም እንቅፋት ይፈጥራል። ስለዚህ የዘመቻ ስራው ውጤታማ እንዲሆን ማህበረሰቡም የበኩሉን ተሳትፎ ማድረግ አለበት ብለዋል። የሃይማኖት ተቋማት በከፍተኛ የሃላፊነት ስሜት ምዕመናንን የማዳን ስራ መስራት ከቻሉ፣ የትምህርት ተቋማት መምህራንንና ተማሪዎችን አስተባብረው ጥሩ ውጤት ማምጣት ከቻሉ፣ የመንግስት አመራሮችና ሰራተኞች በደንብ ስራቸውን ከሰሩና የሚዲያ ተቋማት ደግሞ ምርመራ መስፋፋቱ አጠቃላይ የሀገር ህልውናንና ዜጎችን ለመታደግ መሆኑን ለህብረተሰቡ ካስተማሩ በዚህ ወር የተሳካ ስራ ሰርተን በሚቀጥለው ዓመት አብዛኛው ነገር ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ መመለስ የሚያስችል እድል እንደሚፈጠር ተናግረዋል። የዘጋነውን ትምህርት ዘሎ መክፈት ስለማይቻል የተጀመረው የኦንላይን ትምህርት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ማድረግ አስፈላጊ ነው። በኦሮሚያ ክልል በየትምህርት ቤቶች ተጨማሪ ክፍሎችን መገንባት፣ በመላ ሀገሪቱ ማስፋፋት አንዱ የቅድመ ዝግጅት አካል መሆን እንዳለበት ጠቅሰው በቅድሚያ የሚከፈተው አንደኛ ደረጃ በመሆኑ በአጭር ጊዜ ውስጥ ዝግጅት መደረግ እንዳለበት አሳስበዋል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 26/2012 ሞገስ ጸጋዬ
https://www.press.et/Ama/?p=36507
382
0ሀገር አቀፍ ዜና
በህግ የበላይነት አለማመን ከፈጣሪ መለየትና ከሰው ልጆች መስተጋብሯዊ ሂደት መውጣት ነው” – ሊቀትጉኀን ቀሲስ ታጋይ ታደለ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 2, 2020
25
አዲስ አበባ፦ በህግ የበላይነት አለማመን ከፈጣሪ መለየት ብቻ ሳይሆን፤ ከሰው ልጆች መስተጋብሯዊ ሂደት ውስጥ መውጣት ጭምር እንደሆነ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ፀሐፊ ሊቀትጉኀን ቀሲስ ታጋይ ታደለ አስታወቁ። ከህግ በላይ መሆን በማንኛውም መልኩ ዋጋ እንደሚያስከፍልም ገለጹ። ቀሲስ ታጋይ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ፣ በህግ የበላይነት አለማመን ከፈጣሪ መለየት ብቻ ሳይሆን፤ ከሰው ልጆች መስተጋብራዊ ሂደት መውጣት ጭምር ነው ብለዋል። ከህግ በላይ መሆንም በማንኛውም መልኩ ዋጋ ያስከፍላል። ህግ እንጂ ሰው የበላይ እንዳልሆነ ማመን እንደሚያስፈልግ ሃይማኖት እንደሚያስተምር አመልክተዋል። ህግ ሲከበር ዘርቶ የመልቀም፣ ወጥቶ የመግባትና ሠርቶ የመልማት አቅም ይፈጠራል፤ ተጠያቂነትም ይሰፍናል። ሰላምና መረጋጋትም ይመጣል ያሉት ቀሲስ ታጋይ ፣ ከዚህ ውጪ ግን መሪም፣ ተመሪም፣ ገዳይም ተገዳይም ሳይታወቅ መር የለቀቀ ሁኔታ በአገሪቱ ላይ ይንሰራፋል። ይህም ሰው እና አገር አልባ መሆንን ያስከትላል ብለዋል።ህግ ማለት የእግዚአብሄር ቃል ነው፤ እግዚአብሔርን የማያከብር ደግሞ ቤተእምነት ላይ ምንም ዋጋ ሊኖረው እንደማይችል አመልክተው ፣ የህግ የበላይነት አስተምሮ ከዚህ አንጻር እንዲቃኝም እየሠራን ነው ብለዋል። መንግሥት አሁን የጀመረው የህግ ማስከበር ሥራ ከእኛ አስተምህሮ ጋር ተመጋጋቢ ስለሆነ በሃይማኖት በኩል የሚመጣውን የህግ ጥሰት እናስቆማለን የሚል እምነት እንዳላቸው አስታውቀዋል። መጽሐፋዊ አስተምህሮ ሰውን በአግባቡ የሚመራና ወደፊት እንዲጓዝ አቅም የሚፈጥር እንደሆነ ጠቁመው፣ ከመጽሐፉ ውጪ በራስ አስተሳሰብ የመጽሐፉን ቃል እያጣመሙ በመተርጎም መሄዱ ብዙዎችን ዋጋ እያስከፈለ መሆኑን ገልጸዋል። በተለይም ከፖለቲካዊ አስተምሮ አንጻር ሰባክያንና መምህራን የእምነቱን መሰረት ባልጠበቀ መልኩ ትምህርት መስጠታቸው አገር ብዙ ዋጋ እንድትከፍል እያደረጋት መሆኑንም ጠቁመዋል። የሃይማኖት ተቋማት የሃይማኖት ሜዳ እንጂ የፖለቲካ ጨዋታ የሚካሄድበት መድረክ አይደሉም። የተቸገሩ መጠለያ እንጂ የጠገቡ መሸሸጊያም ሊሆን አይገባም ያሉት ቀሲስ ታጋይ ፣ ሃይማኖትና መንግሥት የሚገናኘው በፖለቲካው ሳይሆን በሰላምና በልማት ነው። ስለዚህም ሃይማኖተኛ ነኝ የሚለው አካል አውዱን መለየት አለበት ብለዋል። ማህበራዊ ቀውሶች ሲመጡ እንድ ላይ ሆኖ መሥራትም ግዴታ መሆኑን ሊቀበል እንደሚገባ አመልክተዋል። እኛንም መንግሥትንም የሚጠቀም ህዝብ ስለሆነ በህጉ መሰረት ህዝብን በጋራ ማገልገል ጥያቄ የማይነሳበት ጉዳይ መሆኑን አምነን እየሠራን ነው ያሉት ቀሲስ ታጋይ ፣ በአስተምሯችን መሰረት ህዝብን ለማገልገል ሃይማኖት ተገን ሳናደርግ፣ መንግሥትም ፖለቲካውን ሳይወግን መሥራት ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባም ጠቁመዋል። በትውልዱ ላይ እየታየ ላለው የሥነ ምግባር ችግር በዋነኛነት ተጠያቂው ወላጅ መሆኑን አመልክተው፣ ወላጅ ግብረገብነትን ከቤት ጀምሮ አላስተማረም። ዱላ ይዞ ሲወጣ አልተቆጣም፤ ራሱን ሰድቦ ሳያበቃ ሌሎችን ሲደበድብ አላስቆመውም። ስለ አገሩ እንኳን መጥፎ ነገር ሲናገር አላስተወውም። አንድነትና ሰብዓዊ ክብር የሚለውን በአግባቡ እየተረዳ እንዲያድግ አልኮተኮተውም ብለዋል። የእምነት ተቋማት ሌላኞቹ ተጠያቂዎች መሆናቸውን ጠቁመው፤ እነዚህ ተቋማት ከቤተሰብ ልጅን ተረክበው በሃይማኖትና በምግባር የተሻለ ማድረግ ይጠበቅባቸው እንደነበር ገልጸዋል። ይህን ሥራቸውን ባለመሥራታቸው አንዱ በሌላው ሃይማኖት ተከታይ ሰው ላይ ዱላ ይዞ በመውጣት አትግደል የተባለውን በመጣስ ይገላል፤ ወንድምህን እንደራስህ አድርገህ ውደድ ቢባልም መውደዱን ትቶ ያሳድደዋል። እናት አባትህን አክብር የሚለውም ትዕዛዝ ለእርሱ መመሪያውና ግዴታው እንደሆነ ባለመረዳትም ሲደበድባቸው እንደሚስተዋል አመልክተዋል። “ትውልዱ የአገሩን ንብረት እያጠፋ የሚገኘው ስላልተማረና በሥነምግባር ስላልታነጸ ነው። በተለይ የሚያሳዝነው የስላሴን ፍጡር ሲያፈርስ ምንም ዓይነት ርህራሄ ሳይሰማው ማድረጉ ነው። እናም ይህ ውጤት የሃይማኖት ተቋማት በሚገባ ማስተማር ባለመቻላቸው መጥቷል” ብለዋል። መንግሥትም ቢሆን በትምህርት ተቋማቱ ቀለም እንጂ ሥነምግባር እያስተማረ ትውልዱን አላስቀጠለም። በዚያ ላይ እስከአሁን ባሉት ተግባራት የትውልድ ልማት የሚባለው ነገር እንደ ሀገር በምንም መልኩ አልተሠራበትም ያሉት ቀሲስ ታጋይ ፣ በዚህ የተነሳ ትውልዱ መረን ለቋል። የማልጠቅም ሰው ነኝ በማለት ራሱን ስለሚፈርጅም ወደተሻለ ነገር እንዳያመራ ሆኗል። አገሩ ለእርሱ የአዕምሮ ልማት ስላልሠራችለት ሌላ አገር ብቻ የሚያስብ እንደሆነ አስታውቀዋል። “የሰው ክቡርነትንና ራሱም እንደሚሞት ሳይረዳ ዩኒቨርሲቲ እና ከዚያ በላይ እየተሰጠ ተዛውሯል። ይህ ደግሞ ቀጣይ አገር ተረካቢን ከሚያፈራው ዩኒቨርሲቲ አገር የሚገነባ ሳይሆን ከፎቅ ላይ ሰው እየወረወረ አስከሬን የሚልክ ትውልድ ሆኗል። ስለዚህ አስተምሬያለሁ፤ ቀርጼያለሁ የሚል ሞራል እንደመንግሥት የለም ማለት ይቻላል ብለዋል። ዛሬ ያለመሥራታችንን ውጤት እያጨድን የምንገኝበት ጊዜ ነው። ስለዚህ ነገም ሌሎችን በዚህ መስመር ውስጥ እንዳናስጉዛቸው ትውልድ መሥራት ላይ መረባረብ አለብን ብለዋል። እንደዛሬው ተነስቶ እንኳን እንዲቀመጡ ዕድል የማይሰጥ፤ አባትና እናቱን የሚገድልና የሚመታ፤ የራሱን መኖሪያና የቀጣይ ሕይወቱን ማበልጸጊያ ሳይቀር የሚያወድም እንዳንፈጥር ሦሶስቱም አካላት ኃላፊነት ሊወጡ እንደሚገባ አመልክተዋል። “ችግር እንደሚያጠነክር አምኖ ችግር ፈጣሪዎችን በህግ እየጠየቁ በዚያው ልክ ስለ እውነት የሚቆም ትውልድ እየፈጠረ ነገን መሥራት ይገባል። አላማኞች በህግ መጠየቅና ወደ አማኝነት ማምጣት ላይ መሥራትም ይጠበቃል። እንክርዳዱን ወደ ስንዴነት ለመቀየር የማይቻል ከሆነ ደግሞ ስንዴውን በስንዴነት ማስቀጠል ላይ መበርታት ግድ ነው” ብለዋል። አሁን የነብር ጅራት ተይዟል። ይህ ደግሞ ህጉ ሲሆን፤ ከለቀቅነው መጀመሪያ የሚበላን እኛን ነውና ማጥበቃችን ሊቀጥል ይገባል። ጎን ለጎንም ትውልዱን የመገንባት ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አመልክተዋል። የዚህ አገር ችግር ድሮ ዳቦ ሲሆን፤ አሁን ግን ሁለት ጉዳዮች ጠያቄያችን ሆነዋል። ብሔርና ሃይማኖት። ይህ ደግሞ መቀማትን አምጥቷል። ሳይሠሩ የሌሎችን መመኘትን፤ ቢያገኙም አለመርካትን አላብሶናል ሲሉን ተናግረዋል። “አስከሬን ላይ ሰልፊ መነሳት፣ እየጎተቱ መግረፍ የትም ያልታየ ሰብዓዊነት የሌለው ተግባር መተግበራችን አላሸማቀቀንም። ሰው ሲገደል እያየንም መቃወም አልቻልንም። ስለዚህም ይህንን የተረገምንበትን ሁኔታ ለይተን ካላወጣን አሁንም ሰው መሆናችን መልስ አይኖረውም” ይላሉ። ለዚህ ያበቃቸው ደግሞ አገራዊ እሳቤ የሌላቸው መሪዎችና አመራሮች የመሪነትን ቦታ እንዲይዙ መደረጋቸው ነው። ቀበሌያዊና ጎጣዊ አስተሳሰባቸውን በአገሪቱ ላይ እንዲሰፍን አድርገው ሰው ሊያደርገው የማይገቡ ተግባራትን እንድናይ ሆነናል። ለዚህ በአብነት የሚነሳው ደግሞ ሻሸመኔ ላይ የተሠራው ግፍ ነው። ስለዚህም ኢትዮጵያዊነት መተባበር፣ መተጋገዝ፣ ሰውን መርዳትና ከፍ እንዲል መትጋት ቢሆንም ዛሬ መልኩን ቀይሮ አለመተማመንና መቀማማት ሆኗል ብለዋል። ሌላው ኢትዮጵያዊ መልክን የቀየረው የመሪው አስተምሮ ነው፤ እርሱ እየተነገረው ያደገው በጎውን ሳይሆን መጥፎውን ስለነበር በመምራት ሂደት ይኸው በስፋት ተንጸባርቋል። ቀደም ሲል የሚነገረን ትርክት በብሔር እንድናስብ ሆነን ስላሳደገን እንዳንተማመን ጭምር አድርጎናል። መጥፎ ትርክቶችን ብቻ ይዘን መቀጠላችንም እንዲሁ መልካሙን ሳይሆን መጥፎውን ብቻ እንድንመለከትና በመጥፎው መንገድ እንድንጓዝም አድርጎናል። ስለዚህ አሁን መፍትሔው ክፉ ታሪኮችን ለአስተማሪነት በማወቅና በመተው ወደፊት መገስገስ ላይ መሥራት ነው ሲሉ ተናግረዋል። በቅርቡ የተከሰተውን ብቻ ብንመለከት ችግሩ ሁለት መልክ እንዲይዝ ተደረገ እንጂ ሁለቱም ትክክል አልነበረም። ሃይማኖትን ብናነሳ ጥያቄው የእምነት ቢሆን ኖሮ ሃጫሉ የሌላ እምነት ተከታይ መሆን ነበረበት። ሃጫሉ ግን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ ነው። ስለዚህም በእርሱ መሞት መቆጨትና በግፍ ሊገደል እንደማይገባ መጠየቅ የነበረባትም፤ ውግዘትም ማድረግ ያለባት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ነች። ግን ጩኸቴን ቀሙኝ ይመስል በቤተክርስቲያኗ ላይ አደጋ አደረሱ። ምዕመናኖቿንም ቀሟት። ስለዚህም ጉዳዩ የሃይማኖት እንዳልሆነ በደንብ ያሳያል ብለዋል። በተመሳሳይ ብሔር ነው ለማለትም ብዙ የኦሮሞ ልጆች በዚያው ተወልደው ባደጉበት ቦታ የችግሩ ሰለባ ሆነዋል። እናም ምክንያቱ ብሔርም ሆነ ሃይማኖት ሳይሆን ልዩ የፖለቲካ ፍላጎት ነው። እናም ይህንን መጠቀሚያ ያደረጉትን መለየት የሃይማኖት አባቶችና የመንግሥት ጉዳይ መሆን አለበት። ሁልጊዜ የእምነት ተቋማት የፖለቲካ ምንጭ መሆን እንዳይኖርባቸው ከመቼውም በበለጠ ይህንን መነሻ አድርጎም የማያዳግም የህግ ማስከበር ሥራ መከወን ይኖርበታል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 26/2012  ጽጌረዳ ጫንያለው
https://www.press.et/Ama/?p=36511
916
0ሀገር አቀፍ ዜና
የትግራይ ክልል ለምርጫ የጀመረውን ኢ-ህገ መንግስታዊ እንቅስቃሴ እንዲያቆም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አሳሰበ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 2, 2020
14
አዲስ አበባ፦ የትግራይ ክልል መንግስት ምርጫ ለማካሄድ የጀመረውን ኢ-ህገ መንግስታዊ እንቅስቃሴ በአፋጣኝ እንዲያቆም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አሳሰበ። ምክር ቤቱ ለትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት በላከው ደብዳቤ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ስድስተኛውን ሀገራዊ ምርጫ ማካሄድ እንደማይችል ያቀረበውን ሪፖርት መነሻ በማድረግ የሕገ መንግስት ትርጉም እንደተሰጠበት አስታውሷል። በዚህም የኢፌዴሪ ሕገ መንግስት ምርጫን በወቅቱ ለማካሄድ ከአቅም በላይ የሆነ እክል ሲያጋጥም ምን መደረግ እንዳለበት በግልጽ ባለመደንገጉ እና ህገ መንግስቱ በሚፈቅደው መሰረት ክፍተቱን በህገ መንግስት ትርጉም መሙላት ተገቢ መሆኑን በማመን ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ እንዲራዘም መወሰኑንም አስታውሷል። ይሁንና የትግራይ ክልል መንግስት ይህን ውሳኔ ወደ ጎን በመተው በክልሉ ምርጫ ለማካሄድ ወስኖ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን አረጋግጠናል ያለው ምክር ቤቱ፣ በህገ መንግስቱ አንቀጽ 102 መሰረት በፌዴራልና በክልል ነጻና ትክክለኛ ምርጫ በገለልተኛነት ማካሄድ የሚችለው የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ብቻ እንደሆነና በክልል ደረጃ የሚቋቋም ምርጫ ቦርድ አለመኖሩን ጠቅሷል። በመሆኑም የትግራይ ክልል ምርጫን በሚመለከት የወሰነው ውሳኔና የራሱን የምርጫ ኮሚሽን በማቋቋም ጭምር እያካሄደ ያለው እንቅስቃሴ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ስድስተኛውን ሀገራዊ ምርጫ በተመለከተ ሰኔ 3 ቀን 2012 ዓመተ ምህረት ያሳለፈውን ውሳኔ ያላከበረ ከመሆም ባሻገር ግልጽ የሆነ የህገ መንግስት ጥሰት መሆኑን አመልክቷል። በተጨማሪም በህገ መንግስቱ አንቀጽ 62(9) መነሻ በማድረግ ማንኛውም ክልል ህገ መንግስቱን በመጣስ ህገ መንግስዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የጣለ እንደሆነ የፌዴራሉ መንግስት ጣልቃ የሚገባበትን ሥርዓት ለመደንገግ በወጣው አዋጅ ቁጥር 359/1995 አንቀጽ 12 መሰረት በአንድ የክልል መንግስት ተሳትፎ ወይም እውቅና ህገ መንግስቱን ወይም ህገ መንግስታዊ ሥርዓቱን ባለማክበር የሚደረግ እንቅስቃሴ ወይም ድርጊት ህገ መንግስታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የጣለ እንቅስቃሴ ወይም ድርጊት እንደሆነ በግልጽ መደንገጉን አስታውቋል። በመሆኑም የትግራይ ክልል ምርጫን ለማካሄድ የጀመረው እንቅስቃሴ ህገ መንግስቱን የሚቃረን፣ ህገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የሚጥልና የኢትዮጵያን የፌዴራል ሥርዓት የሚጎዳ አካሄድ እንደሆነ ጠቁሟል። በተጨማሪም በህገ መንግስቱ አንቀጽ 50(8) መሰረት ለፌዴራል መንግስት የተሰጠው ሥልጣን በክልሎች መከበር ያለበት መሆኑና የህገ መንግስት የበላይነት በሚደነግገው የህገ መንግስቱ አንቀጽ 9 (1) መሰረት፣ ማንኛውም ህግ ወይም የመንግስት አካል ውሳኔ ከህገ መንግስቱ ጋር የሚቃረን ከሆነ ተፈጻሚነት እንደማይኖረው ታውቆ የክልሉ መንግስት ህገ መንግስቱንና የፌዴሬሽን ምክር ቤትን ውሳኔ እንዲያከብርና የጀመረውን ኢ-ህገ መንግስታዊ እንቅስቃሴ በአፋጣኝ እንዲያቆም ምክር ቤቱ አሳስቧል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 26/2012  በጋዜጣው ሪፖርተር
https://www.press.et/Ama/?p=36508
316
0ሀገር አቀፍ ዜና
ዛሬ ከቀኑ 10፡00 ጀምሮ ኢትዮጵያውያን ለሶስት ደቂቃ ደስታቸውን ያበስራሉ
ሀገር አቀፍ ዜና
August 2, 2020
25
አዲስ አበባ፡- ዛሬ ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም የኢትዮጵያ ወዳጆች ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የደረሰበትን ደረጃ አስመልክቶ በያሉበት ሆነው ለሶስት ደቂቃ ደስታቸውን የሚያበስሩ መሆኑ ተገለጸ። የሁነቱ አዘጋጆች “ድምጻችን ለግድባችን” በሚል መሪ ቃል የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት እና ሊፍት ኢትዮጵያ የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት በጋራ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ይህ ዓለም አቀፍ ሁነት ኢትዮጵያውያን ግድቡ አሁን የደረሰበት ደረጃ በመድረሱ የተሰማቸውን ደስታ እንዲገልጹ የተዘጋጀ ነው። የሊፍት ኢትዮጵያ መስራችና የቦርድ አባል አቶ አብርሃም ስዩም እንደተናገሩት፤ የግድቡ የመጀመሪያ ዙሪያ የውሃ ሙሌት መጠናቀቅ እንደ ቀላል ነገር መታየት የለበትም። የዓለም ዐይንና ጆሮ የሚከታተለው እጅግ ትልቅ ስኬት ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ በከፈለው መስዋዕትነት እና በመሪዎች ቆራጥ አመራር እዚህ መድረሱ እጅግ የሚያስደስት ነው። ህዝቡ ከጫፍ እስከ ጫፍ ደስታውን የሚገልጽበት መንገድ እየፈለገ ኮሮናን በመፍራት ሊያደርገው ስላልቻለ የህዝቡን ፍላጎት ለማሳካት ከጽህፈት ቤቱ ጋር በመሆን ሁነቱ መዘጋጀቱን ያብራሩት አቶ አብርሃም፤ በቤታቸው ያሉ ሰዎች በራፍ ላይ በመቆም፣ መኪና የሚነዱ ሰዎች መኪናቸውን ጥግ አስይዘው በማቆም፣ መንገድ ላይ የሚሄዱ ሰዎች ባሉበት ቆመው፣ ለሶስት ደቂቃ ደስታቸውን እንዲገልጹ ታስቦ መዘጋጀቱን አብራርተዋል። ለኮሮና ወረርሽኝ በማያጋልጥ መልኩ ኢትዮጵያውያን በያሉበት ድምጻችን ለግድባችን በማለት፣ እጃቸውንና የኢትዮጵያን ሰንደቅ በማውለብለብ እንዲሁም በብሄር ብሄረሰቦች አልባሳት ተውበውና አምረው ደስታቸውን መግለጽ እንደሚችሉ ጠቁመዋል። እስከ ግድቡ ፍጻሜ ድረስ ኢትዮጵያውያን የሚያደርጉት ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ኢትዮጵያ የምትከተለውን የልማት አቅጣጫ ማህበረሰቡ የሚደግፈው መሆኑን ለዓለም ማህበረሰብ መልዕክት የሚተላለፍበት ነው። የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሀይሉ አብርሃም እንደተናገሩት፤ የመጀመሪያ የውሃ ሙሌት መጠናቀቁ ለኢትዮጵያውያን ትልቅ ስኬት ነው። የውሃ ሙሌቱ ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን በሚዲያዎች በተሰራጨው የሀሰት መረጃ ምክንያት ስጋት ውስጥ ወድቀው ለነበሩ የታችኞቹ ተፋሰስ ሀገራት ህዝቦችም ትልቅ ብስራት ነው። ግድቡ ጉዳት እንደማያደርስባቸው በተጨባጭ ያረጋገጡበት ነው ። በዚህም መላው ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ደስ ብሏቸዋል። ኢትዮጵያውያን ዛሬ ድምጻቸውን የሚያሰሙት ግድቡን እየተገነበ ያለው ማንንም ለመጉዳት ሳይሆን ለፍትሃዊ ተጠቃሚነትና ከድህነት ለመውጣት መሆኑን ዓለም እንዲያውቅ ነው ያሉት አቶ ሀይሉ፤ ከዚያ በተጨማሪ ኢትዮጵያውያን ግድቡን እንደጀመሩት እንዲጨርሱት መልዕክት ለማስተላላፍ ያለመ ነው። በተለይም ዲያስፖራው ካለው አቅም አንጻር የሚጠበቅበትን ስላልተወጣ ለማነቃቃት ጭምር መሆኑን ገልጸዋል። እንደ አቶ ሀይሉ ማብራሪያ፤ ኢትዮጵያ ግድብ የምትገነባው በታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ላይ ጉዳት በማያደርስ መልኩ በፍትሃዊነት ለመጠቀም እንደሆነ የውሃ ሙሌቱ ያረጋገጠ ነው። የውሃ ሙሌቱ ዓለም የኢትዮጵያን ፍላጎት እንዲረዳ እድል የፈጠረ ነው። ይህም ለኢትዮጵያ ትልቅ ድል ነው። የውሃ ሙሌት ቀጣይ ድርድር በመተማመን ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል። ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትና የህዳሴ ግድብ ምክር ቤት አባላት በተገኙበት ከሸራተን አዲስ በቀጥታ ስርጭት የሚተላለፍ መርሃ ግብር እንደሚኖርም ተጠቁሟል። አዲስ ዘመን ሐምሌ 26/2012  መላኩ ኤሮሴ
https://www.press.et/Ama/?p=36519
390
0ሀገር አቀፍ ዜና
ሰሚ የሚፈልጉ ድምጾች
ሀገር አቀፍ ዜና
August 2, 2020
25
ከወር በፊት የተወጋው ልባቸው ፤ ያልታከመው ቁስላቸው አልጠገገም ። ዛሬም ትናንትን እያሰቡ ያዝናሉ። በግፍ የተገደሉ ቤተሰቦቻቸውን እያስታወሱ ያነባሉ። በሞት የተነጠቁ ቤተሰቦቻቸውን ሃዘን እርም ሳያወጡ ሌላ ሃዘን ተጨምሮባቸዋል። በቁስል ላይ ቁስል ሆኖብናል ሲሉም ይናገራሉ። ቦርቀው ያልጠገቡ ህፃናት በወላጆቻቸው እቅፍ ይታያሉ። ማረፊያ ያጡ ሰዎች በችግር ውስጥ ተጠልለው ይጣራሉ። ይህ ትዕይት የአርቲስ ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ ከተፈፀመባቸው ጥቃት የዳኑ የዴራ ነዋሪዎች ነው። ሰቆቃ የሚስተዋልበት የዴራ ደብረ መድሃኒት መድሃኒያለም ቤተክርስቲያን ቅጥር ጊቢ 400 ብሶተኞች ተጠግተዋል። ከእነዚህም መካከል ልጃቸው በግፍ የተገደለባቸው አቶ ደረጃ በቀለ አንዱ ናቸው። ግለሰቡ ጥቃት ፈፃሚዎቹ አቅደውና ተዘጋጅተው የፈፀሙት መሆኑን ይጠቁማሉ። የጥቃት ሰለባ የሚሆኑ ሰዎችን ስም ዝርዝር በመያዝ ሃይማኖታዊ መልክ በማላበስ ግድያ አካል ማጉደልና ንብረት የማውደም ጥፋት መፈፀማቸውን ይገልፃሉ። ንብረታቸው ሙሉ ለሙሉ መውደሙን የሚጠ ቁሙት አቶ ደረጃ በቤተክርስቲያን ተጠልለው በቆዩ ባቸው ጊዜም ሰባካ ጉባኤውንም በማስፋራራት ከተጠ ሉለበት እንዲወጡ ተፅእኖ እያሳደሩባቸው መሆኑንም ያመለክታሉ። በመሆኑም መንግስት በፍጥነት እንዲታደ ጋቸው ነው የጠየቁት። በየዘመዶቻቸው ቤት ተበታትነው የሚገኙ ልጆቻቸውንም ማሰበሳብ እንዲችሉና ዳግም የሚቋቋሙበትን ሁኔታ እንዲፈጠርላ ቸው ይጠይቃሉ። የአርቲስቱን ሞት ተከትሎ ሌት የክርስትና እምነት ተከታይ የሆኑ ነዋሪዎች ቤቶች ተለይተው በዴራ ከተማ ከፍተኛ ጥቃት መፈፀሙን የሚናገሩት ደግሞ ወይዘሮ አበበች ፈለቀ ናቸው። ግድያው በተፈፀመ ሌሊት ጩኸት መስማታቸውን አስታውሰው፤ ስለሃጩሉ መገደል መስማታቸውና ወደ ቤታቸው በፍጥነት እንዲገቡ መደረጉን ይጠቁማሉ። ጥቂት ቆይቶም የተኩስ ድምፅ በመስማታቸው የመከላከያ ሰራዊት ሁኔታውን ያረጋጋዋል ብለው መረጋጋት መጀመራቸውን ይገልፃሉ። «እኔ እንዳሰብኩት ግን ተኩስ የከፈቱት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሳይሆኑ ጥቃት አድራሾቹ መሆናቸውን የተገነዘብኩት ጥቃቱ መባበሱን ባወቅሁኝ ጊዜ ነው» ይላሉ። ጥቃቱን ተከትሎ በቤተክርስቲያኒቱ ከተጠለሉ አንድ ወር እንደሞላቸው የሚነሱት ነዋሪዋ ‹‹ህፃናትን ይዘን ስለምንገኝ የሚመለከተው አካል ችግራችንን አይቶ ፈጣን ምላሽ ሊሰጠን ይገባል» ሲሉ ይናገራሉ። በሌላ በኩል ጥቂት ወንጀል ፈፃሚዎች ቢያዙም ጥቃቱን በገንዘብ የደገፉ ግለሰቦችና ሆን ብለው ችግሩ እንዲባበስና በቸልተኝነት ያሳለፉ አመራሮችን በማስመለጥ የተባበሩ የፖሊስ አባላት በህግ ሊጠየቁ እንደሚገባም ይጠይቃሉ። አሁንም ቢሆን ማስፈራሪያና ዛቸው የቀጠለ በመሆኑ መንግስት በአካባቢው የህግ የበላይነት እንዲከበር ማድረግ ይገባዋል ሲሉም ያስገነዝባሉ። የአርሲ አገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ ሊቀህሩያን ታምራት ሁንዴ የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ መነሻ በማድረግ ከወር በፊት ከፍተኛ ችግር በአካባቢው ነዋሪ ላይ መድረሱ ያነሳሉ። ይሁንና ጥቅምት 12 ቀን 2012 ዓ.ም ሆነም ከዚያ በፊት ተመሳሳይ ችግሮች አጋጥመው እንደነበር ያመለክታሉ። ቤቶች ተለይተው መውደማቸውን ፤ ሰዎች በስም ዝርዝር ተይዘው ህይወታቸው በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲጠፋ መደረጉን ይጠቁማሉ። መኖሪያ ቤቶች ፣ ሆቴል ቤቶች፣ ወፍጮ ቤቶች፣ ዱቄትና የእጨት መሰንጠቂያ ፋብሪካዎች እንዲሁም ግምታቸው ያልታወቀ ንብረት መውደሙን ይጠቁማሉ። «ፈጥኖ እርምጃ ቢወሰድ ኖሮ ይህንን ያህል የከፋ አደጋ አይከሰትም ነበር» ሲሉም በቁጭት ያነሳሉ። ፖሊስ ህግ ማስከበር ዋናው ስራው መሆኑን በመጠቆም «ትዕዛዝ አልደረሰንም» በሚል ወንጀለኞች ጥፋት ሲያደርሱ በዝምታ መመልከት ተገቢ እንዳልነበርም ያመለክታሉ። መንግስት የህግ ማስከበር ስራን ካልሰራ በሃላፊነት እያሉ በዝምታ ያሳለፉ ሰዎች የማይጠየቁ ከሆነ የከፋ አደጋ ሊያስከትል ስለሚችልም የህግ ማስገበሩ ስራ በትኩረት እንዲተገበርም ነው የጠየቁት።አዲስ ዘመን ሐምሌ 26/2012  ዘላለም ግዛው
https://www.press.et/Ama/?p=36514
407
0ሀገር አቀፍ ዜና
ቋንቋ ሊገልጸው ያልቻለ የህዝብ አጋርነት !
ሀገር አቀፍ ዜና
August 3, 2020
10
አዲስ አበባ ፦ እኔ ያየሁትን የአዲስ አበባን አውድ ላስቃኛችሁ እንጂ በድፍን ኢትዮጵያ ፤ ብሎም በድፍን ዓለም ባሉ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ተመሳሳይ ስሜት  ስለመኖሩ አልጠራጠርም። ጉዳዩ የታላቁ ህዳሴ ግድባችን ጉዳይ ነውና። አሁድ ሃምሌ 26 /2012 ዓ.ም ለወትሮው በክረምቱ ጭጋግና ዝናብ ጨለምለም የምትለው አዲስ አበባ ትናንት ያለወትሮ ባህሪዋ ፈክታለች። የአዲስ አበባ ጎዳናዎች በሰንደቅ ዓላማ ተሞሽረው መብራት በሚያበሩና የጡርንባ ድምጽ በሚያሰሙ ተሸካርካሪዎች ተጨናንቀዋል። እግረኞች ግራና ቀኝ ሆነው ፤ ሌሎችም በየበራፋቸው ላይ ቆመው የሀገርን ፍቅርና አንድነት በሚገልጹ ዘፈኖች ደስታቸውን ይገልጻሉ። አንዳንዶች ይጨፍራሉ። አንዳንዶችም ያለቅሳሉ። ብዙዎች ስሜታቸውን መቆጣጠር የቻሉ አይመስልም። ብቻ የተደበላለቁ ሰዎች ፤ የተደበላለቁ ስሜቶች ይታያሉ። እኚህ ሰዎች የጋራ ጉዳያቸው አንድ ነው። የህዳሴው ግድብ የመጀመሪያ ዙር የውሃ ሙሌት ይፋዊ የብስራት ቀን ፤ እና የመጨረሻን ምዕራፍ የማጠናቀቅ የቃል ኪዳን ቀን ። ይህ የዘመናት ቁጭት መልስ ያገኘበት የመጀመሪያው ምዕራፍ ብዙዎችን በደስታ አስክሯል፤ አስፈንጥዟል ፤ ቀልብ ነስቷል። መኪኖቻቸውን በባንዲራ አሸብርቀው የተለያዩ ዜማዎችን አያዜሙ ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ያላቸውን አጋርነት የሚገልጹ የከተማዋ ነዋሪዎች ስሜት በቋንቋ ለመተረክ የሚመች አይደለም። ዕልልታው ፣ፌሻታው በያንዳንዱ ሰው ላይ የሚታየው ፈገግታ ፤ ፈገግታ ውስጥ ያለው ተስፋ ውብ ነው። የግንባታው አሁን ያለበት ደረጃና እውነታ ለከተማዋ ነዋሪ ከደስታ በላይ ሆኖ አምሽቷል። አብዛኛው የከተማዋ ነዋሪ ስሜቱን ለመግለጽ ቋንቋ ያገኘ አይመስልም ። ስሜቱ ተደበላልቆበታል ፤ በአንዳንዶች አይን ስር የሚታይ የእምባ እንክብል እና ሲቃ የያዘው ድምጽ ብዙ ይናገራል። በርግጥም የታላቁ የህዳሴ ግድብ ጉዳይ በያንዳንዱ ዜጋ ስጋና ደም ውስጥ ስለመግባቱ ትይንቱን በማስተዋል ለሚመለከት ተጨማሪ ትርክት አያስፈልገውም ። ለኢትዮጵያውያን የአባይ ጉዳይ ሌላው ዓለም ከሚረዳው በላይ ስለመሆኑ ተጨባጭ ማሳያ ነው።ግድቡን ከኑሮው ላይ ቆጥቦ የገነባው ከመሆኑ በላይ የዘመናት የአይቻልምን ተግዳሮት ሰብሮ ይቻላል በሚል መንፈስና ቁርጠኝነት እየገነባው መሆኑ ፣ ከዛም በላይ ከብዙ አሉባልታ ቦኋላ እዚህ ደረጃ ላይ መድረሱ ታላቅ እልልታው ነው። አደባባይ ወጥቶ እልል ፤ ቋንቋ አውጥቶ ኡኡ ቢል ለተመልካች እና ለሰሚ ግር የሚል አይደለም። አቶ ተመስገን ዝናቡ በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስድስት ነዋሪ ናቸው። ዕድሜያቸው ከ60 እስከ 70 ዓመት ይሆናል። ሙሉ ልብስና ከረባት አስረዋል። በላዩ ላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ተጎናጽፈው ከፒያሳ ወደ አራት ኪሎ በሚወስደው ጎዳና ላይ በእግራቸው እየተጓዙ ድምጻቸውን ጮክ አድርገው ደስታቸውን ይገልጻሉ። አዲስ ዘመን ስለደስታቸው ምንጭ ሲጠይቃቸው ሲቃ በተናቀቀውና በተቆራረጠ ድምጽ እንዲህ አሉ ‹‹መጀመሪያ ይችን ቀን እንዳይ ያደረገኝ እግዚአብሔር ይመስገን ፤ በእኔ ዘመን አባይ መገደቡና የአባቶቻችንን ቁጭት በእኛ በልጆቻቸው መልስ ማግኘቱ እጅግ ደስታ ፈጥሮብኛል፤ ዛሬ ውስጤ የሚንቀለቀለው የድል አድራጊነት ስሜት ነው። የመጪው ትውልድ ተስፋና የኢትዮጵያ ትንሳኤ ያየሁት ዛሬ ነው። ከምንም በላይ በዚህ በፈተና ወቅት ሀገሬ እንዲህ ዓይነት ድል ማግኘቷ ክብርና ኩራት ነው። ይህ ክስተት በቀሪው የህዳሴው ግድብ ግንባታ ላይ አዲስ ተነሳሽነት የሚፈጥር ነው። ግብጽም ግድቡ ለእኛ ምን ማለት እንደሆነ የምትረዳው ዛሬ ነው። የኢትዮጵያ ልጆች አሁንም ከመንግስት ጎን ቆመን ግድባችንን አንጨርሰዋለን። ብልጽግናችንንም እናረጋግጣለን ሲሉ ነበር ስሜታቸውን የገለጹት አቶ ተመስገን። አሁንም ክንዳችንን አጠናክረን ግድቡን ከመጨረስ የሚከለክለን አንዳችም ነገር ሊኖር አይችልም፤ ከተባበርንና ከተደማመጥንና በሀገራችን ጉዳይ ለማንም ቀዳዳ ካልከፈትን አንሸንፋለን። ቀጣዩንም በድል እናጠናቅቃለን። ለዚህ ደግሞ ኢትዮጵያዊነት ስሜት እና ወኔያችንን አጠናክረን መቀጠል ይጠበቅብናል። ይላል ወታደር ፍቃዱ በስሜትና በተጋጋለ ወኔ ተሞልቶ። ወጣት ሄኖክ ወርቁ መኪናቸውን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ አልብሰው ደስታቸውን ሲገልጹ ከነበሩ የጨርቆስ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች አንዱ ነው ። ህዳሴው ግድብ ወደ ቀደመው ማንነታችን እና ክብራችን የመለሰን የስራችን ውጤት ነው ይላል። ተባብረን ከሰራን ድህነትን ታሪክ ማድረግ እንደምንችል ያሳየንበትና ተቀናቀኞቻችንን ተስፋ ያስቆረጥንበት ልዩ ክስተት ነው ። ይህ ግድብ የዚህ ትውል አሻራ ያረፈበት እንደመሆኑ አሁንም አንድነትን በማጠናከር ሌሎች ድሎችን ማስመዝገብ ይኖርብናል። አንድነታችን የህዳሴውን ግድብ ከዳር ለማድረስ እንደረዳን ሁሉ አሁንም ያሉብንን ችግሮች በድል መወጣት የምንችለው ትልቁ አቅማችን እንደሆነም ስሜት አውርቶናል። አሁንም እስከ መጨረሻው ለማድረስ በእውቀታችን፣ በጉልበታችን ፣ በገንዘባችን ድጋፍ ማድረግ ይኖርብናል። እኔ ዛሬ ቃል ገብቻለሁ ለዚህም ነው በአደባባ ደስታዬን እየገለጽኩ ያለሁት ብሎናል። የህዳሴውን ግድብ በአንድነት አምረንና ደምቀን እንደጀመር ነው እንዲሁ እንዳማረብንና እንደደመቅን እንጨርሰዋለን ያሉት ደግሞ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ናቸው፤ ቀኑን አስመልክቶ በሸራተን አዲስ በተዘጋጀ መድረክ ላይ ባስተላለፉት መልእክት። ለዚህ የመጀመሪያው ዙር የውሃ ሙሌት እንኳን ደስ ያላችሁ በማለትም ቀሪውን የግድቡን ስራ አጠናቀን ወደ ናፈቅነው ስራ ለመግባት ሁሉም የተለመደው ድጋፉን ማድረግ እንደሚገባውም አመልክተዋል። ገና የቤት ስራችን አላለቀም ፤ አብረን የምንዘምትባቸው ሌሎችም ጉዳዮች አሉን ፤ ኮቪድ 19ኝን መዋጋት፣ ኢኮኖሚን እንዲያገግም በጋራ መስራት ፣ ውስጣዊ ችግሮቻችንንና ሰላማችንን ማስጠበቅ ሲሉም ለመላው ህዝብ ለቀጣይ ስራና ድል እንዲዘጋጅ ጠይቀዋል። የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሮማን ገብረስላሴ እንዲሁ እለቱን አስመልክተው ባስተላለፉት መልእክት ፣ ሁሉንም ኢትዮጵያ ውያን ሀገር ውስጥ ያለነውና በውጭ የምንኖር ያለምንም ልዩነት አንድ ሆነን በሞራል፣ በጉልበት፣ በእውቀት የዚህ ድል ባለቤት ሆነናል ብለዋል። በዲፕሎማሲ በተለይም በተለያዩ ሀገራት ያሉ ምሁራንና የአረብኛ ቋንቋ ተናጋሪ ዜጎች እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን አረቡን ዓለም በመሞገትና በማስረዳት ፤ ባለፉት ዓመታት ከልጅ እስከ አዋቂ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ይህንን ውጤት አግኝተናል ሲሉም ተናግረዋል። አይጀምሩትም ተብለን ጀምረናል፤ አይችሉትም ተብለን ችለናል፤ አይቀጥሉም ተብለን ቀጥለናል ፤ ውሃ አትሞሉም ተብለንም ሞልተን አሳይተናል በዚህም እንደምንችል ለዓለም እያሳየን ያለን ህዞቦች ነን ብለዋል። መላው ህዝብ ድጋፉን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጥሪ አስተላልፈዋል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 27/2012 እያሱ መሰለ
https://www.press.et/Ama/?p=36525
734
0ሀገር አቀፍ ዜና
ህዝቡ ለግድቡ 13 ቢሊዮን 680 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል
ሀገር አቀፍ ዜና
August 4, 2020
7
 አዲስ አበባ፡- የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ህዝቡ 13 ቢሊዮን 680 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን የግድቡ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት አስታወቀ። ዘንድሮ ከ745 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ መሰብሰቡም ተጠቁሟል።የጽህፈት ቤቱ የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሀይሉ አብርሃም እንደተናገሩት፤ ከ13 ቢሊዮን 680 ሚሊዮን ውስጥ 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ድጋፍ ከዲያስፖራ የተገኘ ሲሆን ቀሪው ከሀገር ውስጥ በስጦታ፣ በቦንድ ግዥና በ8100 አጭር መልዕክት የተገኘ ነው።የመንግስት ሰራተ|ኞች የገቡትን ቃል በመፈጸም ግንባር ቀደም ናቸው ያሉት አቶ ሀይሉ መከላከያና ፖሊስ የግድቡንና የአካባቢውን ሰላም በመጠበቅ ረገድ እየተወጡት ካለው የላቀ አስተዋጽኦ ባሻገር እስከ ስምንት ዙር ቦንድ በመግዛት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ገልጻዋል።ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ለግድቡ በተለያየ መንገድ አስተዋጽኦ ሲያበረክት መቆየቱን ጠቅሰው ከቅድመ መደበኛ ተማሪዎች ጀምሮ እስከ ጡረተኛ ድረስ ድጋፍ አድርጓል። በሞት አፋፍ ላይ ያሉ ሰዎች ጭምር በኑዛዜ ከሀብታቸው የተወሰነ እጅ ለግድቡ አበርክተዋል። በቀን ስራ የሚተዳደሩና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው እንዲሁም የህግ ታራሚዎች ጭምር ለግድቡ አበርክተዋል።ዘንድሮ ብቻ ከ745 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን የተናገሩት አቶ ሀይሉ፤ ከመጋቢት ጀምሮ ባሉት አራት ወራት በ8100 አጭር የጽሁፍ መልዕክት 29 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡን አብራርተዋል።የውሃ ሙሌቱ ከተጀመረ በኋላ የህዝቡ ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉን ያብራሩት አቶ ሀይሉ፤ የውሃ ሙሌቱ ከተካሄደ በኋላ ባለው ሁለት ሳምንት ውስጥ 22 ሚሊዮን ብር የቦንድ ግዥ መፈጸሙን አብራርተዋል። እንደ አቶ ሀይሉ ማብራሪያ ለግድቡ ግንባታ የተለያዩ ተቋማትና ግለሰቦች የሚያደርጉት ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል። የጋብቻ 50ኛ ዓመት፣ የልደት በዓል ወዘተ አስመልከቶ በርካታ የቦንድ ግዥ እና ስጦታ እያበረከቱ ናቸው።የግድቡ የመጨረሻ መጀመሪያ መድረሱንና ኢትዮጵያውያን የላባቸውን ፍሬ የሚቀምሱበት ጊዜ መቃረቡን ጠቅሰው አሁንም ህዝቡ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል። አዲስ ዘመን ሐምሌ 28/2012  መላኩ ኤሮሴ
https://www.press.et/Ama/?p=36555
242
0ሀገር አቀፍ ዜና